Language: Amharic

Book: Matthew

Matthew

ምዕራፍ 1

1 የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ መጽሐፍ፡፡ 2 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና የይሁዳን ወንድሞች ወለደ፤ 3 ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ 4 አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ 5 ሰልሞንም ከረዐብ ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፡፡ 6 ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤ 7 ሰሎሞንም ሮበዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አብያን ወለደ፤ አብያም አሳፍን ወለደ፤ 8 አሳፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤ 9 ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤ 10 ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞጽን ወለደ፤ አሞጽም ኢዮስያስን ወለደ፤ 11 ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ፡፡ 12 ከባቢሎን ምርኮ በኋላም፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤ 13 ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤ 14 አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤ 15 ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤ 16 ያዕቆብም ክርስቶስ ተብሎ የሚጠራውን ኢየሱስን የወለደችውን፣ የማርያምን ባል ዮሴፍን ወለደ፡፡ 17 ከአብርሃም እስከ ዳዊት፣ የነበሩት ትውልዶች ሁሉ ዐሥራ አራት፤ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ድረስም እንደዚሁ ዐሥራ አራት፤ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ድረስ የነበሩትም ዐሥራ አራት ትውልዶች ናቸው፡፡ 18 የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሚከተለው መንገድ ተፈጸመ፡- እናቱ ማርያም ዮሴፍን ልታገባው ታጭታ ነበር፤ ነገር ግን ሳይጋቡ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች፡፡ 19 ዮሴፍ ጻድቅ ነበረ፤ በመሆኑም እርሷን በሕዝብ ፊት ሊያዋርዳት አልፈለገም፡፡ ስለዚህ ከእርሷ ጋር የነበረውን የዕጮኛነቱን ግንኙነት በምስጢር ለማቋረጥ ወሰነ፡፡ 20 ዮሴፍ ስለ እነዚህ ነገሮች እያሰበ ሳለ፣ የጌታ መልአክ፣ "የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፣ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ፤ ምክንያቱም እርሷ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነው። 21 እርሷ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ ሕዝቡንም ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ" በማለት ተገለጠለት። 22-23 ይህ ሁሉ የሆነው፣ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ብለው ይጠሩታል፤ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው" ብሎ ጌታ በነቢይ የተናገረው እንዲፈጸም ነው። 24 ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቃ፣ የጌታ መልአክ አዝዞት እንደ ነበረውም አደረገ፡- ማርያምን እን ደሚስቱ ወሰዳት፡፡ 25 (ይሁን እንጂ፣ ልጅ እስከምትወልድ ድረስ ከእርሷ ጋር ግንኙነት አላደረገም፡፡) የሕፃኑንም ስም ኢየሱስ አለው፡፡



Matthew 1:1

ማቴዎስ 1፡1-3

አጠቃላይ መረጃ ጸሐፊው ኢየሱስ ከዳዊት እና ከአብርሃም ዘር እንደመጣ ለማሳየት ጽሑፉን የጀመረው ከኢየሱስ የዘር ሀረግ ነው። ይህ የዘር ሀረግ ዝርዝር እስክ ዲረስ ይቀጥላል MAT 1:17 የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ መጽሐፍ ይህ የኢየሱስ ትውልድ ዝርዝር ነው። የዳዊት ልጅ፥ የአብርሃም ልጅ በኢየሱስ፥ በዳዊት እና በአብረሃም መካከል ብዙ ትውልዶች አሉ። በዚህ ሥፍራ "ልጅ" ማለት "ዘር' ማለት ነው። "የዳዊት ልጅ የሆነው እርሱ የአብርሃምም ልጅ ነው።" የዳዊት ልጅ አንዳንድ ጊዜ "የዳዊት ልጅ" የሚልው ሀረግ እንደ ስያሜ ሆኖ ያገልግላል ነገር ግን በዚህ ሥፍራ ላይ የኢየሱስን ቅድመ አያቶች ለማሳየት የገባ ቃል ነው። አብርሃም የይሳቅ አባት ነው። ይህንን በተለያዩ መንገዶች መተርጎም ይቻላል። በዬትኛውም መንገድ ተርጉሙት በዘር ሀርግ ዝርዝር ውስጥ ተመሳሳ በሆነ መልኩ መተርጎሙ ጥሩ ነው። ትርጉም፡ "አብርሃም የይሳቅ አባት ሆነ" ወይም "አብርሃም ይሳቅ የሚባል ልጅ ነበረው፨" ፋሬስንና ዛራን . . . ኤስሮምን . . . አራም እነዚህ የሰዎች ስም ። ፋሬስን . . . አባት ነው ኤስሮም . . . ነው።

Matthew 1:4

ማቴዎስ 1፥4-6

ሰልሞንም የቦኤዝ አባት ነው "ሰልሞን የቦኤዝ አባት ነው፤ የቦኤዝ እናት ደግሞ ረአብ ናት" ወይም "ሰልሞን እና ረአብ የቦኤዝ ወላጆች ናቸው።" ቦኤዝ የኢዮቤድ አባት ነው፤ የኢዮቤድም እናት ሩት ናቴ" ወይም "ቦኤዝ እና ሩት የኢዮቤድ ወላጆች ናቸው። ዳዊትን የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ምስቱ ሰሎሞንን ወልዶ አባቱ ሆን ወይም "ዳዊት እና የኦርዮ ሚስት የነበረችው ምስቱ የሰለሞን ወላጆች ናቸው። የኦርዮ ሚስት የነበረችው ሰለሞን የተወለደው ኦርዩ ከሞተ በኃላ ነው።

Matthew 1:7

ማቴዎስ 1፥ 7-8

አሳ አንዳንድ ጊዜ "አሳፍ" ተብሎ ይተረጎማል። የዖዝያን ትክክለኛ ስሙ ሮብዓም፥ ስለዚህም "አባት" የሚለው ቃል "የዘር ሀረግ" ተብሎ መተርጎም ይችላል። ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ፤ (UDB).

Matthew 1:9

ማቴዎስ 1፥ 9-11

አሞን አሞን አንዳንድ ጊዜ "አሞፅ" ተብሎ ይተረጎማል። ኢዮስያስ የኢኮንያንን አባት ነው እውነታው ኢዮስያስ የኢኮንያንን አያት ነው። በባቢሎንም ምርኮ ጊዜ "ወደ ባቢሎን በምርኮ ተገደው እንዲሄዱ ሲድረግ" ወይም "ባቢሎናዊያን ቁጥጥር በሆኑ ጊዜና ወደ ባቢሎን እንዲሄዱ ስያስገድዷቸው።" በቋንቋችሁ ማን ወደ ባቢሎን እንደሄደ መግለጽ አስፈላጊ ከሆነ እንዲህ ማለት ትችላላችሁ "እስራኤላዊያን" ወይም "በይሁዳ ይኖሩ የነበሩ እስራኤላዊያን" ባቢሎን በዚህ ሥፍራ ላይ ባቢሎን የሚለው ቃል የሚያመለክተው ባቢሎን የተሰኘችውን ሀገር እንጂ የባቢሎን ከተማን ብቻ አይደለም።

Matthew 1:12

ማቴዎስ 1፥ 12-14

ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ MAT 1:11. ላይ ከተጠቀምከው ቃል ጋር ተመሳሳይ ቃልን ተጠቀም። ሰላትያል የዘሩባቤል አባት ነው እውነታው ሰላትያል የዘሩባቤል አያት ነው፨

Matthew 1:15

ማቴዎስ 1፥ 15-17

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ጸሐፊው በ MAT 1:1. ላይ የጀመረውን የኢየሱስን የትውልድ ሀርግ ያጠናቅቃል። ኢየሱስን የወለደችው ማሪያም ኤቲ፡ "ኢየሱስን የወለደችው ማሪያም" ( ይመልከቱ) ክርስቶስ የተባለው ይህ እንዲህ ልተረጎም ይችላል፡ ኤቲ፡ "ሰዎች ክርስቶስ ብለው የሚጠሩት።" ( ተመልከቱ) ዐሥራት አራት "14" ( ተመልከቱ) የባቢሎን ምርኮ MAT 1:11. ላይ ከተጠቀምከው ቃል ጋር ተመሳሳይ ቃልን ተጠቀም።

Matthew 1:18

ማቴዎስ 1፥ 18-19

አጠቃላይ መረጃ ይህ ክፍል ጸሐፊው ለኢየሱስ መወለድ ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎችን የገለጸበት የታርኩ አዲሱ ጅማሬ ነው። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ነበር "እናቱ ማርያም ዮሴፍን ልታገባ ነበር።" ብዘመኑ ወላጆች ለልጆቻቸው ትዳር አጋር ያዘጋጁ ነበር። ኤቲ፡ "የኢየሱስ እናት የሆነችው ሪያም ወላጆቿ ለዮሴፍ እርሷን ለመዳር ተስማምተዋል።" ( ተመልከት) እናቱ ማርያም ታጭታ ነበር ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ በነበረበት ወቅት ኢየሱስ አለመወለዱን በሚያሳይ መንገድ ተርጉሙት። ኤቲ፡ "ኋላ ላይ ኢየሱስን የወለደችው ማሪያም ታጭታ ነበር" ሳይገናኙ "ከመጋባታቸው በፊት።" ይህ ዮሴፍ እና ማሪያም አብረው ከመተኛታቸው በፊት" የሚለውን የሚያመልክት ይሆናል። ኤቲ፡ "አብረው ከመተኛታቸው በፊት"። ( ተመልከት) አርግዛ ተገኘች ይህ እንዲህ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ልጅ ልትወልድ እንደሆነ አወቁ” ወይም “አረገዘች፡፡” ( ተመልከት) በመንፈስ ቅዱስ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ማሪያም ከሰው ጋር ሳትተኛ ማርገዝ እንድትችል አደረጋት፡፡ ባሏ ዮሴፍ ዮሴፍ ማሪያምን ገና አላገባትም ነበር ይሁን እንጂ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ትዳር ለመጋባት ቃል ከተገባቡ ምንም እንኳ አብረው መኖር ባይጀምሩም አይሁዶች ባል እና ምስት አድርገው ይቆጥሯቸው ነበር፡፡ ከእርሷ ጋር የተነበረውን እጮኝነት ለማቆም “ለመጋባት የነበራቸውን እቅድ ለመሰረዝ”

Matthew 1:20

ማቴዎስ 1፡ 2-22

እንዳሰበው “ዳዊት እንዳሰበው” በሕልም ተገለጠለት “ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦለት” የዳዊት ልጅ በዚህ ሥፍራ “ልጅ” ማለት “የልጅ ልጅ” ማለት ነው፡፡ በማሕጸኗ ውስጥ የተሸከመችው ልጅ የተጸነሰው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “መንፈስ ቅዱስ ማሪያም እንዲትጸንስ አደረገ፡፡” ( ተመልከት) ወንድ ልጅ ትወልዳለች እግዚአብሔር መልአክን ስላዘዘ መልአኩ የተወለደው ወንድ ልጅ እንደሆነ ያውቅ ነበር፡፡ እንዲህ ብለሽ ትጠሪዋለሽ ይህ ትዕዛዝ ነው፡፡ ኤቲ፡ “እንዲህ ብለሽ ጥሪው” ወይም “እንዲህ የሚል ስም ልትሰጪው ይገባል፡፡ ያድናልና በዚህ ሥፍራ ላይ ተርጓሚዎች እንዲህ የሚል የግሪጌ ማስታወሻ መጨመር ይችላሉ፡ “ኢየሱስ የሚለው ስም ጌታ ያድናል ማለት ነው፡፡ ሕዝቡን ይህ የሚያመለክተው አይሁዳዊያንን ነው

Matthew 1:22

ማቴዎስ 1፡22-23

አጠቃላይ መረጃ ጸሐፊው የኢየሱስ አወላለድ በቅዱሳት መጽሐፍት አስቀድሞ በተነገረው መሠረት መሆኑን ለማሳየት ከነብይ ኢሳያስ መጽሐፍ ጠቅሶዋል፡፡ ( ተመልከት) ይህ ሁሉ ሆነ መልአኩ መናገር አቁሟል፡፡ አሁን ማቴዎስ መልአኩ የተናገረው ነገር ምን ያኽል አስፈላጊ እንደሆነ እያብራራ ነው፡፡ ጌታ በመላዕክቱ አማካኝነት የተናገረው ነገር ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡ ኤቲ፡ “ጌታ ለነብይ ኢሳያስ ከብዙ ዘመናት በፊት የተናገረው እንዲጽፍ የነገረው ነገር፡፡” ( ተመልከት) እነሆ . . . አማኑኤል በዚህ ሥፍራ ላይ ማቴዎስ ከነብዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ጠቅሷል፡፡ እነሆ ይህ ቃል ሰዎች ከዚህ በኋላ ለሚነገረው ነገር አጽኖት እንዲሰጡ የሚጨመር ቃል ነው፡ ኤቲ፡ “ተመልከቱ” ወይም “አድምጡ” ወይም “አሁን ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ”:: አማኑኤል ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው ይህ በኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ የለም፡፡ ማቴዎስ የስሙን ትርጉም እያብራራ ነው፡፡ ይህን ለብቻው በአንድ ዐረፍተ ነገር መተርጎም ትችላላችሁ፡፡ ኤቲ፡ “የዚህ ስም ትርጉም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው፡፡

Matthew 1:24

ማቴዎስ 1፡24-25

አያያዥ ዐረፍተ ነገር ጸሐፊው የኢየሱስ አወላለድን ምን ይመስል እንደነበር የሰጠውን ገለጻ አጠናቀቀ፡፡ የጌታ መልአክ ባዘዘው መሠረት መልአኩ ዮሴፍን ማሪያምን ምስቱ አድርጎ እንዲወስዳት እና የልጁንም ስም ኢየሱስ እንዲለው አዘዘው፡፡ እርሱም እርሷን ምስቱ አድርጎ ወሰዳት “አገባት” ለልጁ ዮሴፍ እውነተኛ አባቱ አለመሆኑን ግልጽ መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ኤቲ፡ “ወንድ ልጅ” ወይም “ለልጇ” እና ኢየሱስ ብሎ ስም ጠራው “ዮሴፍ ሕጻኑን ኢየሱስ የሚል ስም አወጣለት”


Translation Questions

Matthew 1:1

በኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ የትውልድ ሐረግ ውስጥ የትኞቹ ሁለት የትውልድ ሐረጎች ናቸው ጠቀሜታቸውን በሚያሳይ መልኩ መጀመሪያ ላይ የተዘረዘሩት?

መጀመሪያ ላይ የተዘረዘሩት ሁለቱ አባቶች ዳዊት እና አብርሃም ናቸው። [1:1]

Matthew 1:15

በትውልድ ሐረግ ዝርዝር መጨረሻ ላይ ስሟ የተጠቀሰችው ሚስት ማን ናት፣ ደግሞስ ለምንድን ነው ስሟ የተዘረዘረው?

ማርያም የተባለችው የዮሴፍ ሚስት ተጽፏል፣ ምክንያቱም ኢየሱስ በእርሷ በኩል ተወልዷል። [1:16]

Matthew 1:18

ማርያም ከዮሴፍ ጋር ከመጋባቷ በፊት ምን ሆነባት?

ማርያም ከዮሴፍ ጋር ከመጋባቷ በፊት በመንፈስ ቅዱስ ፀነሰች። [1:18]

ዮሴፍ ምን ዓይነት ሰው ነበር?

ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ነበር። [1:19]

ማርያም እርጉዝ መሆኗን ሲያውቅ ዮሴፍ ምን ለማድረግ ወሰነ?

ዮሴፍ ከማርያም ጋር ያለውን እጮኝነት በድብቅ ለማቆም ወሰነ። [1:19]

Matthew 1:20

ለማርያም እንደታጨ እንዲቆይ ዮሴፍ ይወስን ዘንድ ምን ገጠመው?

አንድ መልአክ በህልሙ ተገልጦ ሕጻኑ በመንፈስ ቅዱስ ስለተፀነሰ ማርያምን ሚስቱ አድርጎ እንዲወስድ ነገረው [1:20]

ለሕጻኑ ኢየሱስን በማለት ስም እንዲሰጠው ለዮሴፍ የተነገረው ለምን ነበር?

ዮሴፍ ህፃኑን ኢየሱስን እንዲለው የተነገረው ህዝቡን ከኃጢአታቸው ስለሚያድናቸው ነው። [1:21]

Matthew 1:22

በእነዚህ ክስተቶች የተፈጸመው የብሉይ ኪዳን ትንቢት ምን ይላል?

የብሉይ ኪዳን ትንቢት “ድንግል ወንድ ልጅ እንደምትወልድ እና ስሙንም አማኑኤል እንደሚሉት፣ የስሙም ትርጉም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት እንደሆነ ነው። [1:23]

Matthew 1:24

ማርያም ኢየሱስን እስክትወልድ ድረስ ዮሴፍ እንዳያደርገው መጠንቀቅ የነበረበት ምን ነበር?

ኢየሱስን እስክትወልድ ድረስ ከማርያም ጋር እንዳይተኛ መጠንቀቅ ነበረበት። [1:25]


ምዕራፍ 2

1 በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ኢየሱስ በቤተ ልሔም ይሁዳ ከተወለደ በኋላ፣ ጠቢባን ሰዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ እንደዚህም በማለት ጠየቁ፤ 2 ‹‹የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት ነው? የእርሱን ኮከብ በምሥራቅ አየን፣ ልንሰግድለትም መጥተናል፡፡›› 3 ንጉሡ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ ተረበሸ፤ መላው ኢየሩሳሌምም ከእርሱ ጋር ታወከ፡፡ 4 ሄሮድስ የካህናቱን አለቆችና የሕዝቡን የሕግ መምህራን ሰብስቦ፣ ‹‹ክርስቶስ የሚወለደው የት ነው?›› በማለት ጠየቀ፡፡ 5 ‹‹በቤተ ልሔም ይሁዳ›› አሉት፤ በነቢዩ የተጻፈው ይህ ነውና፡ 6 በይሁዳ ምድር የምትገኚ አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፣ ሕዝቡን እስራኤልን የሚጠብቅ ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልና፡፡ 7 ከዚያም በኋላ ሄሮድስ ኮከቡ በትክክል በምን ሰዓት ታይቶ እንደ ነበር ሊጠይቃቸው ጠቢባኑን በምስጢር ጠራቸው፡፡ 8 ወደ ቤተ ልሔምም ላካቸው፤ ‹‹ሂዱና ሕፃኑን በጥንቃቄ ፈልጉ፡፡ ስታገኙት እኔም ደግሞ እንድመጣና እንድሰግድለት ንገሩኝ›› አላቸው፡፡ 9 ንጉሡ የተናገረውን ከሰሙ በኋላ ሄዱ፤ በምሥራቅ አይተውት የነበረውም ኮከብ ሕፃኑ በነበረበት ላይ እስኪደርስና እስኪቆም ድረስ በፊታቸው ይሄድ ነበር፡፡ 10 ጠቢባኑ ኮከቡን ባዩት ጊዜ፣ እጅግ በጣም ተደሰቱ፡፡ 11 ወደ ቤት ገብተው ሕፃኑንም ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት፡፡ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፣ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት፡፡ 12 እግዚአብሔር ጠቢባኑን ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ በሕልም አስጠነቀቃቸው፤ ስለዚህም በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ፡፡ 13 ጠበባኑ ከሄዱ በኋላ፣ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣ "ተነሥ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፡፡ እኔ እስክነግርም ድረስ እዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልጋልና" አለው፡፡ 14 በዚያ ሌሊት ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ ግብፅ ሄደ፡፡ 15 ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ እዚያው ቈየ፡፡ በዚህም ጌታ፣ ‹‹ልጄን ከግብፅ ጠራሁት›› ብሎ በነቢዩ የተናገረው ቃል ተፈጸመ፡፡ 16 ከዚያም ሄሮድስ ጠቢባኑ እንደ ተሣለቁበት ሲገነዘብ በጣም ተናደደ፡፡ በቤተ ልሔምና በዚያ አውራጃ የነበሩ ወንድ ሕፃናትን፣ እንደዚሁም ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን ሁሉ ከጠቢባኑ በትክክል በተረዳው ጊዜ መሠረት ልኮ አስፈጀ፡፡ 17 በዚያም በነቢዩ ኤርምያስ ተነግሮ የነበረው፡- 18 ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፣ ልቅሶና መሪር ዋይታ፣ ራሔል ስለ ልጆቿ በማልቀስ፣ ለመጽናናትም እምቢ አለች፣ በሕይወት የተረፈ የለምና›› የሚለው ተፈጸመ፡፡ 19 ሄሮድስ ሲሞት፣ እነሆ፣ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣ 20 ‹‹ሕፃኑን ሊገድሉት የፈለጉት ስለ ሞቱ፣ ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ›› አለው፡፡ 21 ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል አገር ሄደ፡፡ 22 አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ስፍራ ተተክቶ ይሁዳን ይገዛ እንደ ነበረ ሲሰማ ግን ወደዚያ ለመሄድ ፈራ፡፡ እግዚአብሔር በሕልም ካስጠነቀቀው በኋላ፣ ወደ ገሊላ አውራጃ ሄደ፤ 23 ናዝሬት በምትባል ከተማ ውስጥም ኖረ፡፡ ይህ በነቢዩ ተነግሮ የነበረውን፣ ናዝራዊ ተብሎ ይጠራል የሚለውን እንዲፈጸም አደረገ፡፡



Matthew 2:1

ማቴዎስ 2፡1-3

አጠቃላይ መረጃ የታሪኩ አዲስ ክፍል የሚጀምረው በዚህ ሥፍራ ላይ ነው፡፡ ከዚያም እስከ ምዕራፉ መጨረሻ ድረስ ይሄዳል፡፡ ጸሐፊው ሄሮዶስ አዲሱን የአይሁድ ንጉሥ ለመግደል ስላደረገው ሙከራ ይነግረናል፡፡ ቤተልሔም ይሁዳ “በይሁዳ ግዛት ውስጥ የሚትገኝ የቤተልሔም ከተማ” ሄሮዶስ ንጉሥ በነበረበት ዘመን “በዚያ ሄሮዶስ ንጉሥ ሆኖ ሳለ” ሄሮዶስ ሄሮዶስ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ታላቁን ሄሮዶስን ነው፡፡ የተማሩ ሰዎች “ክዋክብትን ያጠኑ ሰዎች” (UDB) ከምስራቅ የመጡ “ከይሁዳ በስተምስራቅ በኩል ከሚገኝ ሀገር የመጡ” የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ዬት አለ? ሰዎቹ ከክዋክብት ጥናታቸው የአይሁድ ንጉሥ ለመሆን የተወለደ ልጅ እንዳለ አውቀዋል፡፡ በዬት ሥፍራ እንዳለ ለማወቅ ፈልገዋል፡፡ ኤቲ፡ “የአይሁድ ንጉሥ ለመሆን አንድ ልጅ ተወልዷል፡፡ ዬት ነው ያለው?” የእርሱ ኮከብ ኮከቧ ትክክለኛ ባለቤት ልጁ ነው እያሉ አይደለም፡፡ ኤቲ፡ “ስለ እርሱ የሚትናገረው ኮከብ” ወይም “ከእርሱ መወለድ ጋር የተያያዘችው ኮከብ” በምስራቅ “በምስራቅ በወጣች ጊዜ” ወይም “በሀገራችን ሳለን” ማምለክ አማራጭ ትርጉሞች 1) ልጁ መለኮት እንደሆነ ተገንዝበወ ለማምለክ ፈልገዋል ወይምመ 2) እንደ አንድ ንጉሥ ልያከብሩት ፈልገዋል፡፡ ቋንቀዋችሁ ሁለቱንም ትርጉሞች መያዝ የሚችል ቃል ካለው በዚህ ሥፍራ ላይ ይህንን ቃል መጠቀምንን ከግንዛቤ ውስጥ አስገቡ፡፡ ተጨነቀ “ፈራ”፡፡ ይህ ልጅ ንግሥናዬን ይቀማኛል ብሎ በመፍራት ተጨነቀ፡፡ ኢየሩሳሌም በሙሉ በዚህ ሥፍራ ላይ “ኢየሩሳሌም” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎችን ነው፡፡ እንዲሁም “ሁሉም” ማለት “ብዙ” ማለት ነው፡፡ ማቴዎስ በዚህ ሥፍራ ላይ ብዙ ሰዎች በዚህ ጉዳይ መጨነቃቸውን ለማመልከት ግነት ተጠቅሟል፡፡ ኤቲ፡ “በኢየሩሳሌም ያሉ ብዙ ሰዎች፡፡” (UDB) ( and ተመልከት)

Matthew 2:4

ማቴዎስ 2፡4-6

አጠቃላይ መረጃ በቁጥር 6 ላይ ካህናት አለቆች እና ጸሐፊት ክርስቶስ በቤተልሔም ከተማ እንደሚወል ከሚልክያስ መጽሐፍ በመጥቀስ አሳይተዋል፡፡ በቤተልሔም ይሁዳ “በይሁዳ ግዛት የሚትገኘው ቤተልሔም ውስጥ” ይህ በነብያት የተነገረው ነገር ነው ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡ ኤቲ፡ “ይህ ነቢያት ከብዙ ዘመናት በፊት የጻፉት ነገር ነው፡፡” (፡ ተመልከት) እና አንች፣ ቤተልሔም . . . ኢስራኤል ከሚልክያስ መጽሐፍ ላይ እየጠቀሱ ነው፡፡ አንች፣ ቤተልሔም . . . ከይሁዳ መሪዎች መካከል መጨረሻ አይደለሽም ሚልክያስ በቤተልሔም ይኖሩ ለነበሩ ሰዎች ከእርሱ ጋር እንደሆኑ አድርጎ ይነግራቸው ነበር ነገር ግን እነርሱ ጋር ከእርሱ ጋር አልነበሩም፡፡ በተጨማሪም “የመጨረሻ አልነበሩም” ይህ አዎንታዊ በሆነ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እናንተ የቤተልሔም ሰዎች . . . ከተማችሁ በይሁዳ ግዛት ውስጥ ከሚገኙ ከተሞች መካል ትልቁ ነው፡፡” ( እና ተመልከቱ) ሕዝቤን ኢስራኤል የሚጠብቅ ማን ነው ሚልክያስ እነዚህን ገዥዎችን እንደ እርኛ አድርጎ ይናገራቸዋል፡፡ ይህ ማለት ሕዝቡን የሚመሩ እና የሚንከባከቡ፡፡ ኤቲ፡ “እረኛ በጎቹን እንደሚመራ ሁሉ ሕዝቤን የሚመራ ማን ነው” ( ተመልከት)

Matthew 2:7

ማቴዎስ 2፡ 7-8

ሄሮዶስ በሚስጥር የተማሩ ሰዎችን ጠራቸው ይህ ማለት ሄሮዶስ የተማሩ ሰዎችን ሌሎች ሰዎች ሳያውቁ በድብቅ አስጠርቶ አናገራቸው ማለት ነው፡፡ ኮከቡ የታየው በትክክል መቼ እንደሆነ ጠያቃቸው ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ከዚያም እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፣ “ኮከቡ በትክክል የታየው መቼ ነበር?” ( ተመልከት) ኮከቡ የታየው መቼ ነበር ይህ የተማሩት ሰዎች ከኮቡን መቼ እንደተመለከቱት በተዘዋዋር መንገድ እንደነገሩት ያሳያል፡፡ የተማሩትም ሰዎች ለሄሮዶስ ኮከቡን መቼ እንደተመለከቱ ነገሩት፡፡ ( ተመልከት) ጨቅላው ሕጻን ይህ ኢየሱስ የሚያመለክት ነው፡፡ ቃል አምጡልኝ ኤቲ፡ “አሳውቁኝ” ወይም “ንገሩኝ”( ተመልከት) እንዳመልከው ይህንን በ MAT 2:2 ላይ በተረጎምከው መሠረት ተርጉመው፡፡

Matthew 2:9

ማቴዎስ 2፡ 9-10

ከእነርሱ በኋላ “ከተማሩተ ሰዎች በኋላ” በምስራቅ ተመለከቱ “በምስራቅ በኩል ስወጣ አዩት” ወይም “በሀገራቸው አዩት” ከፊት ፊታቸው ይሄድ ነበር “ይመራቸው ነበር” ወይም “መንገድ ያሳያቸው ነበር” ቀጥ ብሎ ቆመ “ቆመ” ጨቅላው ሕጻን ያለበት “ጨቅላው ሕጻን ያለበት ሥፍራ ስደረስ”

Matthew 2:11

ማቴዎስ 2፡11-12

አያያዥ ዐረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ላይ የታሪኩ ፍሰት ወደ ማሪያም፣ ዮሴፍ እና ትንሹ ኢየሱስ ወደ ሚኖሩበት ቦታ ተለውጧል፡፡ ሄዱ “የተማሩት ሰዎች ሄዱ” አምልኮ ይህንን በ MAT 1:2 ላይ በተረጎምከው መሠረት ተርጉመው፡፡ ንብረታቸው በዚህ ሥፍራ ላይ “ንብረታቸው” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ንብረታቸውን ብዙ ጊዜ የሚይዙበት ሳጥን ወይም ሻንጣን ነው፡፡ ኤቲ፡ “ንብረታቸውን የሚይዙበት ሻንጣ፡፡” ." ( ተመልከት) እግዚአብሔር አስጠነቀቃቸው “ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር አስጠነቀቃቸው፡፡ ሄሮዶስ ልጁን ሊገድለው እንደሚፈልግ እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ወደ ሄሮዶስ እንዳይመለሱ ይህ በትምህረተ ጥቅስ ውስጥ ተደርጎ መተርጎም ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እንዲህ በማለት “ወደ ንጉሥ ሄሮዶስ ተመልሳችሁ እንዳትሄዱ፡፡” ( ተመልከቱ)

Matthew 2:13

ማቴዎስ 2፡13-15

አጠቃላይ መረጃ በቁጥር 15 ላይ ጸሐፊው ክርስቶስ በግብጽ ምድር እንደሚቆይ ከነብዩ ሆሴን ይጠቅሳል፡፡ ሄዱ “የተማሩት ሰዎች ሄዱ” ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለት “ዮሴፍ ሕልም እያለመ ሳለ ወደ እርሱ መጣ” ተነስ፣ ያዝ . . . ሽሽ . . . ቆይ . . . አንተ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ተናገረው፡፡ ስለዚህ ሁሉም በነጠላ ቁጥር ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡ . ( ተመልከት) እስክነግርህ ድረስ የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም በግልጽ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ ኤቲ፡ “መመለስህ ሰላም እንደሆነ እኔ እስክነገር ድረስ” ( ተመልከት) ቆየ ይህ ዮሴፍ፣ ማሪያም እና ኢየሱስ በግብጽ ምድር ውስጥ መቆየታቸውን ያሳያል፡፡፡፡ ኤቲ፡ “በዚያ ቆዩ” ( ተመልከት) ሄሮዶስ እስኪሞት ድረስ ሄሮዶስ MAT 2:19. ድረስ አልመተም፡፡ ይህ ዓረፍተ ነገር በግብጽ ምድር ውስጥ ለምን ያኽል ጊዜ እንደቆዩ ያሳያል እንዲሁም በእነዚህ ጊዜያት ሄሮዶስ እንደሞተ አይናገረም፡፡ ልጄን ከግብጽ ምድር ጠራሁት “ልሄን ከግብጽ ጠራት” ልጄ በሆሴ ውስጥ ይህ እስራኤላዊያንን የሚያመለክት ቃል ነው፡፡ ማቴዎስ ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለመናገር ይህንን ክፍል ጠቅሶታል፡፡ ይህንን ብቸኛ ልጅ ወይም የመጀመሪያ ልጅን በሚያሳይ ቃል ተርጉሙት፡፡

Matthew 2:16

ማቴዎስ 2፡16-16

አያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ላይ የታርኩ ፍሰት ወደ ሄሮዶስ ይመለሳልና የተማሩት ሰዎች እንዳታለሉት ሄሮዶስ ባወቀ ጊዜ ያደረገውን ይነግረናል፡፡ አጠቃላይ መረጃ ይህ ሁኔታ የተከሰተው ጸሐፊው MAT 2:15. ላይ የጠቀሰው እና ሄሮዶስ ከመሞቱ በፊት ነው፡፡ ( ተመልከት) የተማሩት ሰዎች ቀለዱበት ይህ እንዲህ ባለ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡ ኤቲ፡ “የተማሩት ሰዎች ሸውደውት ሄደው አዋረዱት”፡፡ ( ተመልከት) ሰዎችን ልኮ ሁሉንም ልጆች አስገደላቸው ሄሮዶስ ልጆቹን እርሱ ራሱ አልገደላቸውም፡፡ ኤቲ፡ “ሁሉንም ወንድ ልጆችን ይገድሉ ዘንድ ግን ትዕዛዝ ሰጣቸው” ወይም “ሁሉንም ወንድ ሕጻናትን ይገድሉ ዘንድ ወታደሮቹን ላካቸወ፡፡” ( ተመልከት) ሁለት እና ከሁለት ዓመት በታች የሆኑትን “2 ዓመት እና ከዚያ በታች ያሉትን” (UDB) ( ተመልከት) እንደግዜው “በጊዜው መሠረት”

Matthew 2:17

ማቴዎስ 2፡17-18

አጠቃላይ መረጃ በይሁዳ ግዛት ውስጥ የነበሩት ወንድ ልጆች ሁሉ መገደላቸው በቅዱሳት መጽሐፍት በተነገረው መሠረት መሆኑን ጸሐፊው ነብዩ ኤርሚያስን በመጥቀስ ጽፏል፡፡ ይህም ተፈጸመ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ይህ ተፈጸመ” ወይም “የሄሮዶስ ተግባር ተፈጸመ፡፡” ( ተመልከት) የተፈጸመው ነገር በነብይ ኤርሚያስ አስቀድሞ ተነግሮ ነበር ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ገታ በነብይ ኤርሚያስ አማካኝነት ከብዙ ዘመናት በፊት እንደተናገረው፡፡” ( ተመልከት) ድምፅ ተሰማ . . . ከእንግዲህ የሉም ማቴዎስ ነብዩን ኤርሚያስን እየጠቀሰ ነው ድምፅ ተሰማ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡ ኤቲ፡ “ሰዎች ድምፅ ሰሙ” ወይም “ከፍተኛ ድምፅ ነበር፡፡ ( ተመልከት) ራሔል ስለልጆቿ አለቀሰች ራሔል ይህ ነገር ከመሆኑ ብዙ ዓመታት በፊት ነው የኖረችው፡፡ ይህ ትንቢት የሚያሳያው ከብዙ ዓመታት በፊት የሞተችው ራሔል ስለ ልጆቿ ማልቀሷን ነው፡፡ መጽናናትንም እንቢ አለች ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ማንም ሊያጽናናት አልቻለም፡፡” ( ተመልከት) የሉምና “ልጆቿ ጠፍተዋል እንዲሁም እንደገና ፈጽመው አይመለሱም፡፡ በዚህ ሥፍራ “የሉም” የሚለው ቃል ለዘብ ባለ ቃል መሞታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ስለሞቱ”፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 2:19

ማቴዎስ 2፡19-21

አያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ የታርኩ ፍሰት ዮሴፍ፣ ማሪያም እና ጨቅላው ኢየሱስ ወደሚኖሩበት ወደ ግብጽ ተቀይሯል፡፡ እነሆ ይህ በትልቁ ታርክ ውስጥ አንድ ሌላ ሁኔታ የመጀመሩ ምልክት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ካሉት ሁኔታዎች ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ተጨማሪ ሰዎችን ሊጨምር ይችላል፡፡ በቋንቋችሁ ይህንን የሚትገልጹበት መንገድ ሊኖራችሁ ይችላል፡፡ የሕጻኑን ሕይወት የሚፈልጉት ሰዎች ኤቲ፡ “ሕጻኑን ለመግደል የሚፈልጉት ሰዎች”፡፡ ( ተመልከት) የሚፈልጉት ሰዎች ይህ ንጉሥ ሄሮዶስን እና አማካሪዎቹን የሚያመለክት ነው፡፡

Matthew 2:22

ማቴዎስ 2፡22-23

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ በ MAT 2:1 የተጀመረው ታርክ ሄሮዶስ የአይሁድ አዲሱን ንጉሥ ለመግደል ያደረገው ሙከራ የመጨረሻው ክፍል ነው፡፡ ይህንን በሰማ ጊዜ “ዮሴፍ ይህንን ስሰማ ግን” አርኬላዎስ ይህ የሄሮዶስ ልጅ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) ፈራ “ዮሴፍ ፈራ” በነቢያቱ የተነገረው ነገር ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ከብዙ ዘመናት በፊት ጊዜ በነቢያቱ አማካኝት እንደተናገረው፡፡” ( ተመልከት) ናዝራዊ ተብሎ ይጠራል በዚህ ሥፍራ “እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሱስን ነው፡፡ ከእርሱ በፊት ይኖሩ የነሩ ነቢያት ስለ እርሱ ስባገሩ መስሑ ወይም ክርስቶስ ብለው ይጠሩታል፡፡ ኤቲ፡ “ሰዎች ክርስቶስ ናዝራዊ ነው ይላሉ፡፡” ( ተመልከት)


Translation Questions

Matthew 2:1

ኢየሱስ የተወለደው የት ነው?

ኢየሱስ የተወለደው በይሁዳ ቤተልሔም ነው። [2:1]

ከምሥራቅ የመጡት ጠቢባን ለኢየሱስ የሰጡት መጠሪያ ምንድነው?

ከምሥራቅ የመጡት ጠቢባን ለኢየሱስ “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል መጠሪያ ሰጡ። [2:2]

ጠቢባኑ የአይሁድ ንጉሥ እንደተወለደ እንዴት አወቁ?

ጠቢባኑ በምሥራቅ የአይሁድን ንጉሥ ኮከብ አይተው ነበር። [2:2]

ንጉሥ ሄሮድስ ከጠቢባን ለሰማው ነገር ምላሽ የሰጠው እንዴት ነበር?

ንጉሡ ሄሮድስ ወሬውን ከጠቢባኑ ሲሰማ ተጨነቀ። [2:3]

Matthew 2:4

የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ክርስቶስ የሚወለደው የት እንደ ሆነ እንዴት ዐወቊ?

ክርስቶስ በቤተ ልሔም እንደሚወለድ የተነገረውን ትንቢት ያውቁ ነበር። [2:5]

የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ክርስቶስ የሚወለደው የት እንደ ሆነ እንዴት ዐወቊ?

ክርስቶስ በቤተ ልሔም እንደሚወለድ የተነገረውን ትንቢት ያውቁ ነበር። [2:6]

Matthew 2:9

ኢየሱስ በትክክል የት እንደሚወለድ ጠቢባን የተረዱት እንዴት ነበር?

በምሥራቅ የነበረው ኮከብ ኢየሱስ ወደ ነበረበት ቦታ እስከሚቆም ድረስ ከፊታቸው ይሄድ ነበር። [2:9]

Matthew 2:11

ጠቢባኑ ሊያዩት ሲሄዱ ኢየሱስ ዕድሜው ስንት ነበር?

ጠቢባን ሲመጡ ኢየሱስ ትንሽ ልጅ ነበር። [2:11]

ጠቢባን ለኢየሱስ የሰጡት ስጦታ ምን ነበር?

ጠቢባን ለኢየሱስ ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ ሰጡ። [2:11]

ጠቢባኑ ወደ አገራቸው የተመለሱት በየትኛው መንገድ ነው? በዚህስ መንገድ የሄዱት ለምንድነው?

ተመልሰው ወደ ሄሮድስ እንዳይሄዱ እግዚአብሔር በሕልም ስላስጠነቀቃቸው ጠቢባኑ በሌላ መንገድ ተመለሱ። [2:12]

Matthew 2:13

ዮሴፍ በሕልሙ ምን መመሪያዎችን ተቀበለ?

ሔሮድስ ኢየሱስን ለመግደል እየሞከረ ስለነበር፣ ዮሴፍ ኢየሱስን እና ማርያምን ይዞ ወደ ግብጽ እንዲሸሽ ተነገረው። [2:13]

ኢየሱስ ከዚያ በኋላ ከግብጽ በመመለሱ የተፈጸመው የትኛው ትንቢት ነው?

ኢየሱስ ኋላ ላይ ከግብጽ ሲመለስ "ልጄን ከግብጽ ጠራሁት" የሚለው ትንቢት ፍጻሜውን አገኘ። [2:15]

Matthew 2:16

ጠቢባኑ ወደ እርሱ ባለመመለሳቸው ሄሮድስ ምን አደረገ?

ሄሮድስ ሁለት ዓመት ወይም ከዚያ በታች የነበሩ በቤተልሔም የሚገኙ ወንድ ልጆችን በሙሉ አስገደላቸው። [2:16]

Matthew 2:19

ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ጆሴፍ በሕልሙ ምን መመሪያዎችን ተቀበለ?

ዮሴፍ ወደ እስራኤል ምድር እንዲመለስ በሕልም ታዝዞ ነበር። [2:19]

ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ዮሴፍ በሕልሙ ምን መመሪያዎችን ተቀበለ?

ዮሴፍ ወደ እስራኤል ምድር እንዲመለስ በሕልም ታዝዞ ነበር። [2:20]

Matthew 2:22

ዮሴፍ ከማርያምና ከኢየሱስ ጋር ለመኖር የሠፈረው የት ነበር?

ዮሴፍ በገሊላ ናዝሬት ከማርያምና ከኢየሱስ ጋር ለመኖር ሠፈረ። [2:22]

ዮሴፍ ከማርያምና ከኢየሱስ ጋር ለመኖር የሠፈረው የት ነበር?

ዮሴፍ በገሊላ ናዝሬት ከማርያምና ከኢየሱስ ጋር ለመኖር ሠፈረ። [2:23]

ዮሴፍ ወደ አዲሱ ቦታ ሲዘዋወር የተፈጸመው ትንቢት የትኛው ነው?

ክርስቶስ ናዝራዊ ይባላል ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ። [2:23]


ምዕራፍ 3

1 በእነዚያ ቀኖች መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ ፤ 2 "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ እየሰበከ መጣ። 3 በነቢዩ ኢሳይያስ፦ "ምድረ በዳ ውስጥ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፣ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናዎቹንም አስተካክሉ" ተብሎ የተነገረለት ይህ ነውና። 4 ዮሐንስ ይለብስ የነበረው የግመል ጠጕር፣ በወገቡ የሚታጠቀውም የቆዳ ጠፍር ነው፤ ምግቡም አንበጣና የዱር ማር ነበረ። 5 በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌም፣ መላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር። 6 ሕዝቡ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ እጅ ተጠመቁ። 7 ነገር ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፣ "እናንተ የመርዛማ እባቦች ልጆች ከሚመጣው ቊጣ ለማምለጥ ማን አስጠነቀቃችሁ? 8 ለንስሐ የሚጠቅም ፍሬ ይኑራችሁ። 9 ለራሳችሁም አብርሃም አባታችን አለን" ብላችሁ አታስቡ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች እንኳ ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና። 10 አሁን መጥረቢያው በዛፎቹ ሥር ተቀምጦአል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል በእሳት ውስጥም ይጣላል። 11 እኔ ለንስሐ የማጠምቃችሁ በውሃ ነው፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቃል፤ ጫማውን መሸከምም እንኳ አይገባኝም። እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል። 12 ዐውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን በጎተራ ውስጥ ለመክተት መንሹ በእጁ ነው። ገለባውን ግን ፈጽሞ በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል። 13 ከዚያም ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ። 14 ነገር ግን "እኔ አንተ እንድታጠምቀኝ ሲገባ፣ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?" በማለት ሊያስቆመው ሞከረ። 15 ኢየሱስም መልሶ፣ "አሁን ይህን ፍቀድ፤ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ለእኛ ተገቢ ነውና" አለው። ከዚያም በኋላ ዮሐንስ ፈቀደለት። 16 ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ፣ ወዲያውኑ ከውሃ ውስጥ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ። የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ መልክ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲቀመጥ አየ። 17 እነሆ፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው። "በእርሱ እጅግ ደስ ይለኛል" የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።



Matthew 3:1

ማቴዎስ 3፡ 1-3

አጠቃላይ መረጃ፡ ይህ ጸሐፊው የመጥመቁ ዮሐንስን ታሪክ የተነናገረበት አዲስ የታሪኩ አካል መጀመሪያ ነው፡፡ በቁ. 3 ላይ ጸሐፊው የኢየሱስ አገልግሎት መንገድን ያዘጋጅ ዘንድ መጥመቁ ዮሐንስ በእግዚብሔር የተመረጠ መሆኑን ከነብዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ጠቅሶ ጽፏል፡፡ በእነዚህ ቀናት ይህ ዮሴፍ እና የእርሱ ቤተሰብ ከግብጽ ምድር ወደ ናዝሬት ከተመሰሉ ብዙ ዓመታት በኋላ የሆነ ነው፡፡ ይህ ምናልባትም ኢየሱስ አገልግሎቱን ለመጀመር በተቃረበበት ጊዜ የተፈጸመ ነገር ይሆናል፡፡ ኤቲ፡ “ከዚያ በኋላ” ወይም “ከጥቂት ዓመታት በኋላ” ንሰሓ ግቡ ይህ በቅርጹ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ ዮሐንስ ይህንን ለሕዝቡ እየተናገረ ነው፡፡ ( ተመልከት) የእግዚአብሔር መንግስት ቀርባለች “የእግዚአብሔር መንግስት ቀርባለች” የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር ንጉሥ ሆነ መግዛቱን ያሳያል፡፡ ይህ ሀረግ በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ይገኛል፡፡ ከተቻለ በትርጉምህ ውስጥ “ሰማይ” የሚል ቃልን ተጠቀም፡፡ ኤቲ፡ “በሰማይ የሚኖር አባታችን ራሱን እንደ ንጉሥ አድርጎ በቅርቡ ያሳያል፡፡” ( ተመልከት) በነብዩ ኢሳያስ አስቀድሞ ስለ እርሱ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ይህ ስለሆነ ነው ይህ እንዲህ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡፡ “ነብዩ ኢሳያስ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡፡” ( ተመልከት) የአንድ ሰው ድምፅ በዚህ ሥፍራ ላይ “ድምፅ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሉ ሰውን ነው፡፡ ኤቲ፡ “አንድ ሰው አለ፡፡” ( ተመልከት) የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ መንገዱንም አቅኑ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ መንገዱንም አቅኑ”፡፡ ይህ በዮሐንስ ሰዎችን ለኢየሱስ መምጣት ሰዎችን በንሰሓ የሚያዘጋጅ ምሳሌያዊ መልዕክት ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 3:4

ማቴዎስ 3፡4-6

አሁን . . . የበረሃ ማር “አሁን” የሚለው ቃል በታሪኩ ፍሰት ውስጥ በዚህ ሥፍራ ለአንባቢው ምልክት እንዲሰጥ ተብሎ ጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ ማቴዎስ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ የኋላ ታሪክ መረጃን ይሰጣል፡፡ ( ተመልከት) የግመል ጠጉር ይለብስ ነበር እንዲሁም ጠፍርንም ይታጠቅ ነበር ይህ የዮሐንስ አለባበስ ከእርሱ በፊት ይኖሩ እንደነበሩ ነብያት በተለይም እንደ ለነብዩ ኤልሳ ትንብታዊ መልዕክት ነበረው፡፡ ( እና ተመልከት) ኢየሩሳሌም፣ ይሁዳ ሁሉ እና በአከባቢው ያሉ ሁሉ ይህ በዚህ አከባቢ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን የሚያመለክት ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ “ሁሉም” የሚለው ቃ “ብዙ” ማለት ነው፡፡ ማቴወዎስ ወደ መጥመቁ ዮሐንስ የመጡት ብዙ ሰዎች መሆናቸውን አጽኖት ይሰጠቃል፡፡ ( እና ተመልከት) በእርሱ ተጠመቁ ይህ እንዲህ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ዮሐንስ አጠመቃቸው፡፡” ( ተመልከቱ) እነርሱ ይህ ማለት ከኢየሩሳሌም፣ ከይዳ እና ከዮርዳኖስ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች መምጣታቸውን ያመለክታል፡፡

Matthew 3:7

ማቴዎስ 3፡7-9

አጠቃላይ መረጃ መጥመቁ ዮሐንስ ፈርሳዊያንን እና ሳዱቃዊያንን ይገስጻቸው ጀመረ፡፡ እናንተ የመርዛማ እባብ ልጆች ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር ነው፡፡ መርዛማ እባቦች አደገኛ ናቸው እንደሁም ክፋትን ይወክላሉ፡፡ ኤቲ፡ “እናንተ መርዛማ እባቦች!” ወይም “ልክ እንደ መርዝማ እባቦች ክፉዎች ናችሁ፡፡” ( ተመልከት ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ ዮሐንስ ፈርሳዊያንን እና ሳዱቃዊያንን ለማስጠንቀቅ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዳይቀጣቸው ዮሐንስ ያጠምቃቸው ዘንድ ይጠይቁት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ኃጢአት ማድረጋቸውን ማቆም አይፈልጉም ነበር፡፡ ኤቲ፡ “በዚህ ዓይነት መንገድ ከእግዚአብሔር ፍርድ ማምለጥ አይቻልም፡፡” ወይም “እኔ ስላጠመኳችሁ ከእግዚአብሔር ፍርድ የሚታመልጡ አይመስላችሁ፡፡” ( ተመልከት) ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ “ቁጣ” የሚለው ቃል በዚህ ሥፍራ ጥቅም ላይ የዋለው የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማመለከት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ይህ ከእግዚአብሔር ቅጣት ቀድሞ የሚመጣ ስለሆነ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ከሚመጣው ቅጣት ለማምለጥ” ወይም “ከእግዚአብሔር ቅጣት ለማምለጥ፡፡” ( ተመልከት) የንሰሓን ፍሬ አፍሩ “አፍሩ” የሚለው ቃል ምሳሌያዊ አነጋገር ሲሆን የሰውዬውን ተግበባራት ያሳያል፡፡ ኤቲ፡ “ተግባራችሁ በእውነት ንሰሓ እንደገባችሁ ያሳይ፡፡” ( ተመልከት) አባታችን አብረሃም አለልን “አብረሃም አባታችን ነው” ወይም “እኛ የአብረሃም ዘሮች ነን፡፡” የአይሁድ መሪዎች የአብረሃም ዘሮች በመሆናቸው ምክንያት እግዚአብሔር እንደማይቀጣቸው ያስቡ ነበር፡፡” ( ተመልከት) እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ ይህ ዮሐንስ ቀጥሎ ስለሚናር ነገር አጽኖት እንድሰጠ ያሳያል፡፡ ከእነዚህ ድንጋዮች እግዚአብሔር ልጆችን ማስነሳት ይችላል “ከእነዚህ ድንጋዮች ሳይቅር እግዚአብሔር ለአብረሃም ለልጆችን አበጅቶ ለአብረሃም መስጠጥ ይችላል፡፡”

Matthew 3:10

ማቴዎስ 3፡ 10-12

አያያዥ ዓረፍተ ነገር መጥመቁ ዮሐንስ ፈርሳዊያንን እና ሳዱቃዊያንን መገሰጹን ቀጥሏል፡፡ በዛፉ ሥር ላይ መሳሩ ተቀምጦዋል፡፡ መልካምን ፍሬ የማያፈራ ዘፍ ሁሉ ተቆርጦ ወደ እሳት ይጣላል፡፡ ይህ ምሳሌ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ለመቅጣት ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ በዚህ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚብሔር ምሳሩን አንስቷል፡፡ መጥፎ ፍሬ የሚያፈሩ ዛፎችን ለመቁረጥ እና ለማቃጠል ተዘጋጅቷል” ወይም “አንድ ሰው መጥፎ ፍሬ የሚያፈራን ዘፍ ለመቁረጥ እና ለማቃጠል ምሳሩን እንደሚያዘጋጅ ሁሉ እግዚአብሔርም ስለኃጢአታችሁ ሊቀጣችሁ ተዘጋጅቷል፡፡ ( እና ተመልከት) ለንሰሓ “ንሰሓ እንደገባችሁ የሚያሳይ ነገር” ነገር ግን ከእኔ በኋላ የሚመጣው ኢየሱስ ከዮሐንስ በኋላ የሚመጣው ነው፡፡ ከእኔ ይልቅ ኃይለኛ ነው “ከእኔ ይልቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡” በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ያጠምቃችኋል ይህ ምሳሌ የዮሐንስን ጥምቀት ለወደፊት ከሚሆነው በእሳት መጠመቅ ጋር ያነጻጽራል፡፡ ይህ ማለት የዮሐንስ ጥምቀት ሰዎች ከኃጢአታቸው መንጻታቸው ውጫዊ ምሳሌ ሆኖ የሚያገለግል ብቻ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት መጠመቅ ግን ሰዎችን በእውነት ከኃጢአታቸው ያነጻል፡፡ ከዮሐንስ ጥምቀት ጋር ለማነጻጸር ይረዳ ዘንድ በትርጉማችሁ ውስጥ ከተቻለ “መጠመቅ” የሚለውን ቃል ጥቅም ላይ አውሉት፡፡ ( ተመልከት) ስንዴውን ከገለባው መለየት እንዲችል መንሹ በእጁ ላይ ነው ይህ ምሳሌ ስንዴ ከገለባ እንደሚለይ ሁሉ ክርስቶስ ጻድቅ የሆኑ ሰዎችን ኃጢአተኞች ከሆኑን ይለያል፡፡ ኤቲ፡ “ክርስቶስ በእጁ መንሽን እንደያዘ ሰው ነው፡፡” ( ተመልከት) መንሽ በእጁ ላይ ነው በዚህ ሥፍራ “በእጁ ላይ ነው” የሚለው ሀረግ ሰውየው ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ያሳያል፡፡ ኤቲ፡ “ክርስቶስም መንሹን በእጁ ይዟል ምክንያቱም ዝግጁ ነው፡፡” መንሽ ይህ የስንዴ ነዶን ወደ ሰማይ በመወርወር በንፋስ አማካኝነት ገለባውን ከፍሬው ለመለየት የሚረዳ መሣሪያ ነው፡፡ ክብደት ያለው ፍሬው መደመሬት ስወድቅ የማይፈለገው ገለባው ግን በንፋስ ይወሰዳል፡፡ ከሹካ ጋር ተመሳሳይ ቅርጽ ያለው ሲሆን መንሽ ግን የሚሠራው ከእንጨት ነው፡፡ ( ተመልከት) አውድማ “እህል የሚወቃበት ሜዳ” ወይም “ፍሬው እና ገለባው የሚለይበት ሥፍራ” ምርቱንም ወደ ጎተራው ይከተዋል . . . ገለባውን ግን ወደ ማይጠፋ እሳት ውስጥ ይጨምረዋል፡፡

ይህ እግዚአብሔር እንዴት ጻድቃንን ከኃጢአትን እንደሚለይ የሚያሳይ ምሳሌ ነው፡፡ ገበሬ ስንዴውን ወደ ጎተራው እንደሚያስገባ ሁሉ ጻድቃንም ወደ ሰማይ ይሄዳሉ እንዲሁም እንደ ገለባው ያሉትን ሰዎች እግገዚአብሔር ወደ ማይጠፋ እሳት ውስጥ ይጨምራቸዋል፡፡ ( ተመልከት) ወደማይጠፋ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላለል፡፡ ኤቲ፡ “ነዶ ወደማያልቅ፡፡” ( ማይጠፋ እሳት ውስጥ ይጨምራቸዋል፡፡ ( ተመልከት))

Matthew 3:13

ማቴዎስ 3፡13-15

አያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ጸሐፊው ታርኩ በኋላ ላይ ዮሐንስን ኢየሱስን ወደ አጠመቀበት ይቀይረዋል፡፡ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ

ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ዮሐንስ ያጠምቀው ዘንድ፡፡” ( ተመልከት) አንተ ወደ እኔ ትመጣለህ? እኔ በአንተ እጅ መጠመቅ ያስፈልገኛል፡፡

ኢየሱስ ለጠየቀው ጥያቄ ዮሐንስ በአግራሞት በጥያቄ መልክ ስመልስ እናያለን፡፡ ኤቲ፡ “አንተ ከእኔ ይልቅ አስፈላጊ ነህ፡፡ እኔ አንተን ማጥመቅ የለብኝም፡፡ አንተ እኔ ማጥመቅ አለብህ፡፡” ( ተመልከት) ለእኛ በዚህ ሥፍራ “እኛ” የሚለው ቃል ኢየሱስን እና ዮሐንስን የሚታመለክት ናት፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 3:16

ማቴዎስ 3፡16-17

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ የተነገረው ታርክ መጨረሻ እና ኢየሱስን ካጠመቀ በኋላ ምን እንደሆነ የተገለጸበት ክፍል ነው፡፡ ከተጠመቀ በኋላ ይህ በቀጥታ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ዮሐንስ ኢየሱስን ካጠመቀ በኋላ፡፡” ( ተመልከት) እነሆ “እነሆ” የሚለው ከዚህ ቀጥሎ ያለው ማስረጃ አስገራሚ ስለሆነ አጽኖት ለመስጠት ነው፡፡ ሰማያት ለእርሱ ተከፈቱ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ኢየሱስ ሰማያት ተከፍቶ ተመለከተ” ወይም “እግዚአብሔር ሰማያትን ለኢየሱስ ከፈተ”፡፡ ( ተመልከት) በእርግም አምሳሌ ወረደ አማራጭ ትርጉሞች እነዚህ ናቸው 1) መንፈስ በእርግም አምሳሌ መውረዱን የሚያመለክት ቀጥተኛ ትርጉም ወይም 2) እርግም በቀስታ እንደሚትወርድ ሁሉ ልክ እንደዚሁ መንፈስ ቅዱስ በቀስታ በኢየሱስ ላይ መውረዱን የሚያመለክት ምሳሌ ነው፡፡ ( ተመልከት) እንዲህ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ “ኢየሱስ ድምፅ ከሰማይ ሰማ፡፡” (UDB) ( ተመልከት) ልጅ ይህ የኢየሱስ በጣም አስፈላጉ የማዕረግ ስም ነው፣ የእግዚአብሔር ልጅ፡፡ ( ተመልከት)


Translation Questions

Matthew 3:1

መጥምቁ ዮሐንስ በምድረ በዳ የሰበከው መልእክት ምን ነበር?

ዮሐንስ "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" በማለት ሰበከ። [3:2]

መጥምቁ ዮሐንስ ምን ለማድረግ እንደሚመጣ ነው የኢሳይያስ ትንቢት የሚናገረው?

ትንቢቱ የሚናገረው መጥምቁ ዮሐንስ የጌታን መንገድ እንደሚያዘጋጅ ይናገራል። [3:3]

Matthew 3:4

ሕዝቡ በዮሐንስ ሲጠመቁ ምን አደረጉ?

ሲጠመቁ፣ ኃጢአታቸውን ተናዘዙ። [3:6]

Matthew 3:7

ፈሪሳውያንንና ሰዱቃውያን ምን እንዲያደርጉ መጥምቁ ዮሐንስ ነገራቸው?

ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ለንስሐ የሚገባውን ፍሬ እንዲያፈሩ መጥምቁ ዮሐንስ ነገራቸው። [3:8]

መጥምቁ ዮሐንስ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ለራሳቸው እንዳያስቡ ያስጠነቀቃቸው ምንድነው?

ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን አብርሃም አባት እንዳላቸው እንዳያስቡ አስጠንቅቋል። [3:9]

Matthew 3:10

ዮሐንስ እንደሚለው፣ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ምን ይሆናል?

መልካም ፍሬ የማያፈራው ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ ወደ እሳት እንደሚጣል ዮሐንስ ተናገረ። [3:10]

ከዮሐንስ በኋላ የሚመጣው እንዴት ነው የሚያጠምቀው?

ከዮሐንስ በኋላ የሚመጣው በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ያጠምቃል። [3:11]

Matthew 3:13

እንዲያጠምቀው ዮሐንስን ለማሳመን ኢየሱስ ምን ተናገረ?

ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም ሲባል ዮሐንስ ኢየሱስን ማጥመቊ ትክክል እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ። [3:15]

Matthew 3:16

ኢየሱስ ከውኃ ሲወጣ ያየው ምን ነበር?

ከውኃው ሲወጣ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድበት አየ። [3:16]

ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ከሰማይ የተናገረው ድምፅ ምን የሚል ነበር?

ከሰማይ የተሰማው ድምፅ "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው" የሚል ነበር። [3:17]


ምዕራፍ 4

1 ከዚያም በኋላ በዲያብሎስ ሊፈተን መንፈስ ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ መራው፡፡ 2 ኢየሱስ ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ፡፡ 3 ፈታኙ ወደ እርሱ መጣና፣ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እንጀራ እንዲሆኑ እነዚህን ድንጋዮች እዘዛቸው›› አለው፡፡ 4 ኢየሱስ ግን መለሰና፣ ‹‹ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል" አለው፡፡ 5 ከዚያም ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ወሰደው፤ በቤተ መቅደስ ሕንጻ ዐናት ላይም አቁሞ፣ 6 የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ ‹እንዲጠብቁህ መላእክቱን ይልካል፣› እና ‹‹እግርህ ድንጋይ እንዳይመታው፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል›› ተብሎ ተጽፎአል አለው፡፡ 7 ኢየሱስም፣ ‹‹‹ጌታ አምላክህን አትፈታተን› ተብሎም ተጽፎአል›› አለው፡፡ 8 እንደ ገናም ዲያብሎስ ወደ አንድ ተራራ ወሰደውና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ከሙሉ ክብራቸው ጋር አሳየው፡፡ 9 ‹‹ብትወድቅና ብትሰግድልኝ፣ እነዚህን ሁሉ እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡ 10 ከዚያም ኢየሱስ፣ አንተ ሰይጣን ከዚህ ሂድ! ‹ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፣ እርሱንም ብቻ አምልክ››› ተብሎ ተጽፎአልና አለው፡፡ 11 ከዚያ በኋላ ዲያብሎስ ተወው፤ እነሆም፣ መላእክት መጡና ኢየሱስን አገለገሉት፡፡ 12 ኢየሱስ የዮሐንስን መያዝ ሲሰማ፣ ወደ ገሊላ ሄደ፡፡ 13 ናዝሬትን ትቶ በመሄድ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በገሊላ ባሕር አጠገብ ባለው በቅፍርናሆም ኖረ፡፡ 14 ይህ የሆነው፣ በነቢዩ ኢሳይያስ ተነግሮ የነበረው እንዲፈጸም ነው፤ ይኸውም፡- 15 ‹‹የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፣ በባሕሩ አቅጣጫ፣ ከዮርዳኖስ ማዶ፣ የአሕዛብ ገሊላ! 16 በጨለማ ውስጥ የኖረ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፣ በሞት ጥላና ምድር ውስጥ ለሚኖሩትም፣ ብርሃን ወጣላቸው›› የሚለው ነው፡፡ 17 ኢየሱስ ከዚያ ጊዜ አንሥቶ፣ ‹‹መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ 18 ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ እየሄደ ሳለ፣ ሁለት ወንድማማቾችን አየ፤ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ ዓሣ አጥማጆች ስለ ነበሩ፣ ወደ ባሕሩ መረብ እየጣሉ ነበር፡፡ 19 ኢየሱስ፣ ‹‹ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ›› አላቸው፡፡ 20 እነርሱም ወዲያውኑ መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡ 21 ኢየሱስ ከዚያ ዐለፍ እንዳለም ሁለት ሌሎች ወንድማማቾችን፣ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን አየ፤ ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ውስጥ መረቦቻቸውን ያበጃጁ ነበር፡፡ ኢየሱስም ጠራቸው፡፡ 22 ወዲያውኑ ጀልባዋንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት፡፡ 23 ኢየሱስ በምኵራቦቻቸው ውስጥ እያስተማረ፣ የመንግሥትን ወንጌልም እየሰበከና በሕዝቡ መካከል ያሉ በሁሉም የደዌና የበሽታ ዐይነት የሚሠቃዩትን እየፈወሰ በመላው ገሊላ ተዘዋወረ፡፡ 24 ስለ እርሱ በሶርያ ምድር ሁሉ ተወራ፤ ሕዝቡም የታመሙትን ሁሉ፣ በልዩ ልዩ ደዌና ሕመም የሚሠቃዩትን፣ በአጋንንት የተያዙትንና የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡ 25 ከገሊላ፣ ከዐሥሩ ከተሞች፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፡፡



Matthew 4:1

ማቴዎስ 4፡1-4

አጠቃላይ መረጃ በዚህ ሥፍራ ላይ ጸሐፊው ኢየሱስ በምድረ በዳ 40 ቀናትን ያሳለፈበትን፣ በሴጣን የተፈተነበትን የታሪኩን አዲስ ክፍል ይጀምራል፡፡ በቁጥር 4 ላይ ኢየሱስ ከዘዳግም መጽሐፍ በተወሰዱ ጥቅሶች አማካኝነት ሴጣንን ስገስጸው እንመለከታለን፡፡ ኢየሱስ በመንፈስ ተመርቶ

ይህ በቀጥታ በዚህ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “መንፈስ ኢየሱስን መራው፡፡” ( ተመልከት) በዳብሎስ ይፈተን ዘንድ ይህ በቀጥታ በዚህ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ዳብሎስ እርሱን መፈተን ይችል ዘንድ፡፡” ( ተመልከት) ዳቢሎስ . . . ፈታኙ እነዚህ ሁለት ቃላት የሚያመለክቱት አንድ ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱን ለመተርጎም አንድ ቃል መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ጾመ . . . ተራበ ይህ ስለኢየሱስ የተባለ ነው፡፡ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እዘዝ የዚህ ሀረግ አማራጭ ትርጓሜዎች 1) ይህ ፈተና ኢየሱስ ለራሱ ጥቅም ተዓምራትን ይሠራ ዘንድ የቀረበ ፈተና ነው፡፡ ኤቲ፡ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ስለዚህ ማዘዝ ትችላለህ፡፡” 2) ይህ የሚያመለክተው በኢየሱስ ላይ የቀረበውን ክስ ነው፡፡ ኤቲ፡ “የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህ ትዕዛዝ በመስጠት አረጋግጥ፡፡” ሴጣን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እንደሚያውቅ ማሰቡ ይበልጥ ተመራጭ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልጅ ይህ በኢየሱስ እና በእግዚአብሔር መካከሎ ያለውን ግንኙነት የሚገልጽ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) ድንጋዩ ዳቦ እዲሆን እዘዝ ይህንን በቀጥጣ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ለእነዚህ ድንጋዮች እንዲህ ብለህ ተናገር፣ ዳቦ ሁኑ!” ( ተመልከት)

ዳቦ ኤቲ፡ “ምግብ” ( ተመልከት)

እንዲህ ተብሎ ተጽፏል ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ሙሴ ከብዙ ዘመናት በፊት እንዲህ በማለት ጽፏል፡፡” ( ተመልከት)

የሰው ልጅ በዳቦ ብቻ አይኖርም ይህ በቀላሉ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ከምግብ በላይ ሌላ በጣም አስፈላጊ ነገር አለ ማለት ነው፡፡

ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ማንኛውም ቃ እንጂ በዚህ ሥፍራ “ቃል” እና “አፍ” የሚሉ ቃላት እግዚአብሔር የተናገራቸውን ነገሮችን ያመለክታሉ፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ነገሮች በማድመጥ እንጂ፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 4:5

ማቴዎስ 4፡5-6

አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 6 ላይ ሴጣን ከመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ውስጥ ኢየሱስን ለመፈተን ሲል የሆነ ሀሳብ ስወስድ እናያለን፡፡

አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ራስህን ወደታች ወርውር የዚህ ሀረግ አማራጭ ትርጉሞች 1) 1) ይህ ፈተና ኢየሱስ ለራሱ ጥቅም ተዓምራትን ይሠራ ዘንድ የቀረበ ፈተና ነው፡፡ ኤቲ፡ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆንህ ራስህን ወደታች መወርወር ትችላለህ፡፡” ወይም 2) ይህ የሚያመለክተው በኢየሱስ ላይ የቀረበውን ክስ ነው፡፡ ኤቲ፡ “አንተ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆንህ ራስህን ወደታች በመወርወር አረጋግጥ፡፡” (UDB) ሴጣን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እንደሚያውቅ ማሰቡ ይበልጥ ተመራጭ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልጅ ይህ በኢየሱስ እና በእግዚአብሔር መካከሎ ያለውን ግንኙነት የሚገልጽ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)

ራስህን ወደታች ወርውር “ወደታች ራስህን ወርውረህ ውደቅ” ወይም “ወደታች ዝለል”

እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና ይህ በዚህ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “መዝሙረኛው በመመጽሐፉ ውስጥ አንዲህ ብሎ ጽፏልና” ወይም “በቅዱሳት መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ተብሏልና፡፡” ( ተመልከት)

ይጠብቁህ ዘንድ መልአክቱን ስለአንተ ያዛልና “አንተን እንዲጠብቁህ እግዚአብሔር መልአክቱን ስለአንተ ያዛል፡፡” ይህ እንዲህ ተብሎ በትምህረተ ጥቅስ ውስጥ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ለመልአክቱ እንዲህ ይላቸዋል፣ “ጠብቁት፡፡” ( ተመልከት)

ያነሱሃል “መልአክቱ ይይዙሃል”

Matthew 4:7

ማቴዎስ 4፡7-9

አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 7 ላይ ኢየሱስ ሴጣንን የገሰጸው ከዘዳግም መጽሐፍ ውስጥ በተወሰደ ጥቅ አማካኝነት ነው፡፡

እንደገና እንዲህ ተብሎ ተጽፏል ኢየሱስ እንዲህ ማለቱ እንደገና ከመጽሐፍ ቅዱስ መጥቀሱን የሚያመለክት ነው፡፡ ኤቲ፡ “እንደገና ሙሴ በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ የጻፈውን ነገር እነግርሃለሁ፡፡” ( እና ተመልከት)

አትፈታተኑት በዚህ ሥፍራ ላይ “እናንተ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ማንኛውንም ሰው ነው፡፡ ኤቲ፡ “ማንም እርሱን መፈታተን የለበትም” ወይም “ማንኛውም ሰው እርሱን መፈታተን የለበትም፡፡”

እንደገና ዳቢሎስ “በመቀጠልም ዳቢሎስ”

እንዲህ አለው “ዳቢሎስ ኢየሱስን እንዲህ አለው፡፡”

እነዚህን ነገሮች ሁሉ እሰጥሃለሁ፡፡ “እነዚህ ነገሮች ሁሉ እሰጥሃለሁ፡፡” ፈታኙ አንዳንዶቹን ሳይሆን “ሁሉንም ነገሮች” እንደሚሰጠው አጽኖት ሰጥቶዋል፡፡”

Matthew 4:10

ማቴዎስ 4፡10-11

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ይህ ሴጣን ኢየሱስን እንዴት እንደፈተነው የሚያወሳው ታሪክ የመጨረሻው ክፍል ነው፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 10 ላይ ኢየሱስ ከዘዳግም መጽሐፍ ውስጥ በመውሰድ ሴጣንን ገስጾታል፡፡

እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና ይህ በዚህ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “መዝሙረኛው በመመጽሐፉ ውስጥ አንዲህ ብሎ ጽፏልና” ወይም “በቅዱሳት መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ተብሏልና፡፡” ( ተመልከት)

አንተ አለብህ በዚህ ሥፍራ “አንተ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ማንኛውንም ሰው ነው፡፡ ( ተመልከት)

እነሆ “እነሆ” የሚለው ቃል ከዚህ በመቀጠል የሚሰጠው መረጃ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡

Matthew 4:12

ማቴዎስ 4፡12-13

አጠቃላይ መረጃዎች፡ ይህ ኢየሱስ በገሊላ አገልግሎቱን የጀመረበትን መንገድ ጸሐፊው የገለጸበት አዲሱ የታሪኩክፍል ጅማሬ ነው፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ እንዴት ወደ ገሊላ እንደመጣ ያብራራሉ፡፡ ( ተመልከት)

አሁን ይህ ቃል በታሪኩ ፍሰት ውስጥ ያለውን ክፍተት ለማሳየት ጥቅም ላይ የዋሉ ናቸው፡፡ ማቴዎስ በዚህ ሥፍራ ላይ የታሪኩን አንዲስ ጅማሬ ክፍል ይናገራል፡፡ ዮሐንስ ተሠረ ይህ በቀጥታ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ንጉሡ ዮሐንስን አሠረው፡፡” ( ተመልከት)

በዛብሎን እና ንፍታሌን አገር እነዚህ ከብዙ ዓመታት በፊት ከሌላ ሀገር የመጡ ሰዎች ቦታወን ከመቆጣጠራቸው በፊት በእነዚህ ሥፍራዎች ይኖሩ የነበሩ ጎሣዎች ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 4:14

ማቴዎስ 4፡14-16

አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 15 እና 16 ላይ ኢየሱስ በገሊላ የነበረው አገልግሎት ከዚህ በፊት ተነግሮ የነበረ ትንቢት ፍጻሜ መሆኑን ለማሳየት ጸሐፊው ከነብዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ይጠቅሳል፡፡

እንዲህም ሆነ ይህ ኢየሱስ ቅፍርናሆም ወደ ተሰኘው መንደር ለመኖር መምጣቱን ያመለክታል፡፡

ከዚህ በፊት እንደተነገረው ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር እንደተናገረው፡፡” ( ተመልከት)

የዛብሎን እና የንፍታሌን አገር . . . የአሕዛብ ገሊላ እነዚህ ሁሉ ስሞች አንድን አከባቢ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ይህ በአንድ ዓረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “በዛብሎን እና ንፍታሌን አገር . . . ብዙ አሕዛብ የሚኖሩበት የገሊላ መንድ፡፡”

በባሕር መንገድ ይህ የገሊላን ባሕርን ያመለክታል፡፡

በጨለማ የተቀመጠ ሕዝብ ታላቅ ብርሃንን አየ በዚህ ሥፍራ “ብርሃን” የሚለው ቃል ግብረገባዊ ጨለማን ወይም ሰዎችን ከእግዚአብሔር የለየውን ኃጢአትን የሚያመለክት ነው፡፡ ይህ አሁን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተስፋን ያገኙ ነገር ግን አስቀድሞ ምንም ተስፋ ያልነበራቸውን ሕዝቦች ያሳያል፡፡ ( ተመልከት)

በዚያ አከባቢ የሚኖሩ እና በሞት ጥላ ሥር ላሉ ሕዝቦች ብርሃን ወጣላቸው ይህ ከመጀመሪያው የዓረፍተ ነገሩ ክፍል ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ “አከባቢ እና በሞት ጥላ ሥር” የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው መንፈሳዊ ሞት ወይም ከእግዚአብሔር መለየት ነው፡፡ ( እና ተመልከት)

Matthew 4:17

ማቴዎስ 4፡ 17-17

መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንሰሓ ግቡ ይህን በ MAT 3:2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡

Matthew 4:18

ማቴዎስ 4፡18-20

አጠቃላይ መረጃ ይህ በታሪኩ ውስጥ ኢየሱስ በገሊላ ስለነበረው አገልግሎት አስመልክቶ አዲስ ታሪክ የተጀመረበት ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ ሰዎች የእርሱ ደቀ መዛሙርት ይሆኑ ዘንድ መሰብሰብ ጀመረ፡፡

መረባቸውን ወደ ባሕሩ ይጥሉ ነበር ኤቲ፡ “ዓሳ ለማጥመድ መረባቸውን ወደ ውሃው ውሰጥ ይጨምሩ” ( ተመልከት)

ተከተሉኝ ኢየሱስ ጴጥሮስ እና እንድርያስን ይከተሉት፣ ከእርሱ ጋር ይኖሩ እና የእርሱ ደቀ መዛሙርት ይሆኑ ዘንድ ጠራቸው፡፡ ኤቲ፡ “ደቀ መዛሙርቴ ሁኑ፡፡” ሰዎችን የሚታጠምዱ አደርጋችኋለሁ ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ጴጥሮስ እና እንድርያስ እውነተኛውን መልዕክት ለእግዚአብሔርን ሕዝብ በማስተማሪ ሌሎችም ደግሞ ኢየሱስን እንዲከተሉ ያደርጋሉ፡፡ ኤቲ፡ “ዓሳ ታጠምዱ በነበረበት መንገድ እናንተም ሰዎችን እንዴት መሰብሰብ እንደሚትችል አስተምራችኋለሁ፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 4:21

ማቴዎስ 4፡21-22

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ይሆኑ ዘንድ ተጨማሪ ሰዎችን ጠራ፡፡

ጠራቸው “ኢየሱስ ዮሐንስ እና ያዕቆብን ጠራቸው፡፡” ይህ ሀረግም ኢየሱስ ይከተሉት፣ ከእርሱ ጋር ይኖሩ እና የእርሱ ደቀ መዛሙርት ይሆኑ ዘነድ ጠራቸው ማለት ነው፡፡

ወዲያውኑ “በዚያኑ ጊዜ”

ታንኳቸውን ትተው . . እና ተከተሉት ይህ የሕይወት ዘይቤ ለውጥ መሆኑን መግለጽ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ወደ ዓሳ አጥማጅነታቸው እና የቤተሰባቸውን ሥራ ከዚያን ጊዜ ጀምረው በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ኢየሱስን ለመከተል ትተዋለል፡፡

Matthew 4:23

ማቴዎስ 4፡23-25

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ይህ ኢየሱስ በገሊላ የጀመረው አገክግሎት ታሪክ የመጨረሻው ክፍል ነው፡፡ እነዚህ ቁጥሮች ምን እንዳደረገ እና ሰዎች የሰጡት ምላሽ ምን እንደሆነ ጠቅለል አድርጎ ያሳየናል፡፡ ([[End of Story]] ተመልከት)

በምኩራቦቻቸው እያስተማረ “በገሊላ ውስጥ በሚገኙ ምኩራቦች ውስጥ እያስተማረ” ወይም “በእነዚህ ሰዎች ምኩራብ ውስጥ እያስተማረ፡፡”

የመንግስቱን ወንጌል እየሰበከ በዚህ ሥፍራ ላይ “መንግስት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚብሔር ንጉሥ ሆኖ መንገሡን ነው፡፡ ኤቲ፡ “ወንጌልን ማለትም እግዚአብሔር እንዴት ራሱን ንጉሥ አድርጎ እንደገለጠ እየሰበከ” (UDB) ( ተመልከት)

ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች እና ደዌዎች “ማንኛውንም በሽታ እና ደዌ፡፡” “በሽታ” እና “ደዌ” የሚሉት ቃላት በጣም የተቀራረቡ ናቸው ነገር ግን ከተቻለ በሁለት የተያዩ ቃላት አማካኝነት ቢተረጎሙ መልካም ነው፡፡ “በሽታ” አንድ ሰው አንዲታመም የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ “ደዌ” አካላዊ ድክመት ወይም በሽተኛ በመሆን በአካል ላይ የሚሆን ህመም ነው፡፡

በዳቢሎስ የተያዙ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “በዳቢሎስ የተያዘ” ወይም “ዳቢሎስ የተቆጣጠራቸው፡፡” ( ተመልከት) የሚጥል በሽታ “የሚጥል በሽታ ያለባቸው” ወይም “ካለባቸው በሽታ የተነሳ የሚወድቁትን”

ሽባዎችን “መራመድ የማይችሉትን” ከዐሥሩም ከተሞች ይህ “ዐሥር ከተማዎች” ስም ነው፡፡ ." (UDB) ይህ ከገሊላ ባሕር በደቡብ ምስራቅ በኩሉ የሚገኘውን አከባቢ መጠሪያ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)


Translation Questions

Matthew 4:1

በዲያቢሎስ እንዲፈተን ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ የመራው ማን ነው?

በዲያቢሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ወደ ምድረበዳ መራው። [4:1]

ኢየሱስ በምድረ በዳ ለምን ያክል ጊዜ ጾመ?

ኢየሱስ በምድረ በዳ ለአርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ። [4:2]

ዲያቢሎስ ለኢየሱስ ያቀረበው የመጀመሪያው ፈተና ምን ነበር?

ዲያቢሎስ ኢየሱስ ድንጋዩን ወደ ዳቦ እንዲቀይር ፈተነው። [4:3]

ኢየሱስ ለመጀመሪያው ፈተና ምን መልስ ሰጠ?

ኢየሱስ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም አለ። [4:4]

Matthew 4:5

ሰይጣን ለኢየሱስ ያቀረበው ሁለተኛው ፈተና ምንድነው?

ኢየሱስ ከቤተ መቅደሱ ራሱን ወደ ታች እንዲጥል ዲያቢሎስ ፈተነው። [4:5]

ሰይጣን ለኢየሱስ ያቀረበው ሁለተኛው ፈተና ምንድነው?

ኢየሱስ ከቤተ መቅደሱ ራሱን ወደ ታች እንዲጥል ዲያቢሎስ ፈተነው። [4:6]

Matthew 4:7

ለሁለተኛው ፈተና ኢየሱስ ምን መልስ ሰጠው?

ኢየሱስ ጌታ አምላክህን አትፈታተነው ሲል መለሰለት። [4:7]

ሰይጣን ለኢየሱስ ያቀረበው ሦስተኛው ፈተና ምን ነበር?

ኢየሱስ የዓለም መንግሥታት ሁሉ እንዲሰጡት ወድቆ ያመልከው ዘንድ ዲያቢሎስ ፈተነው። [4:8]

ሰይጣን ለኢየሱስ ያቀረበው ሦስተኛው ፈተና ምን ነበር?

ኢየሱስ የዓለም መንግሥታት ሁሉ እንዲሰጡት ወድቆ ያመልከው ዘንድ ዲያቢሎስ ፈተነው። [4:9]

Matthew 4:10

ኢየሱስ ለሦስተኛው ፈተና ምን መልስ ሰጠ?

ኢየሱስ ጌታ አምላክህን አምልክ፣ እርሱንም ብቻ አገልግል ሲል ኢየሱስ ተናገረ። [4:10]

Matthew 4:14

ኢየሱስ ወደ ገሊላ ቅፍርናሆም በመሄዱ የተፈጸው ምን ነበር?

በገሊላ ያሉ ሰዎች ታላቅ ብርሃን እንደሚያዩ የተነገረው የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጸመ። [4:15]

ኢየሱስ ወደ ገሊላ ቅፍርናሆም በመሄዱ የተፈጸው ምን ነበር?

በገሊላ ያሉ ሰዎች ታላቅ ብርሃን እንደሚያዩ የተነገረው የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጸመ። [4:16]

Matthew 4:17

ኢየሱስ ከዚያ በኋላ ምን ስብከት መስበክ ጀመረ?

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ ኢየሱስ ሰበከ። [4:17]

Matthew 4:18

ጴጥሮስና እንድርያስ መተዳደሪያቸው ምን ነበር?

ጴጥሮስና እንድርያስ አሣ አጥማጆች ነበሩ። [4:18]

ኢየሱስ ጴጥሮስንና እንድርያስን ምን እንደሚያደርጋቸው ተናገረ?

ጴጥሮስንና እንድርያስን ሰዎችን አጥማጆች እንደሚያደርጋቸው ኢየሱስ ተናገረ። [4:19]

Matthew 4:21

ያዕቆብና ዮሐንስ መተዳደሪያቸው ምን ነበር?

ያዕቆብና ዮሐንስ አሣ አጥማጆች ነበሩ። [4:21]

Matthew 4:23

በዚህ ጊዜ፣ ለማስተማር ኢየሱስ የሄደው ወደ የት ነበር?

ኢየሱስ በገሊላ ምኩራብ አስተማረ። [4:23]

ወደ ኢየሱስ ያመጧቸው ምን ዓይነት ሰዎችን ነበር፣ ደግሞስ ኢየሱስ ምን አደረገላቸው?

ታመው እና በአጋንንት የተያዙ ሁሉ ወደ ኢየሱስ መጥተው ነበር፣ ኢየሱስም ፈወሳቸው። [4:24]

በዚህ ጊዜ ኢየሱስን ይከተሉ የነበሩት ስንት ሰዎች ነበሩ?

በዚህ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስን እየተከተሉት ነበር። [4:25]


ምዕራፍ 5

1 ኢየሱስ ሕዝቡን ሲያይ፣ ወደ ተራራ ወጣ፤ እዚያም ሲቀመጥ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ መጡ። 2 እንደዚህ እያለም አስተማራቸው፤ 3 በመንፈስ የደኸዩ የተባረኩ ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና። 4 የሚያዝኑ የተባረኩ ናቸው፤ ይጽናናሉና። 5 የዋሆች የተባረኩ ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና። 6 ለጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ የተባረኩ ናቸው፤ ይጠግባሉና። 7 የሚምሩ የተባረኩ ናቸው፤ ይማራሉና። 8 ልበ ንጹሖች የተባረኩ ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና። 9 የሚያስታርቁ የተባረኩ ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና። 10 ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ የተባረኩ ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና። 11 ሰዎች ሲሰድቧችሁና ሲያሳድዷችሁ፣ ወይም በእኔ የተነሣ ክፉውን ሁሉ በእናንተ ላይ በሐሰት ሲናገሩ ብፁዓን ናችሁ። 12 በሰማይ ዋጋችሁ ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፣ ሐሤትም አድርጉ። ሰዎች ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት በዚህ መንገድ አሳድደዋቸዋልና። 13 እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ካጣ፣ እንደ ገና ጨው እንዴት መሆን ይችላል? ወደ ውጭ ተጥሎ በእግር ከመረገጥ በቀር ፈጽሞ ለምንም አይጠቅምም። 14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ የተመሠረተች ከተማ ልትሰወር አትችልም። 15 ሰዎች መብራት አብርተው ቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ በቅርጫት ሥር አያስቀምጡትም። 16 መልካሙን ሥራችሁን እንዲያዩና በሰማይ ያለ አባታችሁን እንዲያከብሩት መብራታችሁ እንዲሁ በሰዎች ፊት ይብራ። 17 ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ የመጣሁት ልሽራቸው ሳይሆን ልፈጽማቸው ነው። 18 ምክንያቱም፣ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ፣ ሁሉ እስኪፈጸምም ድረስ፣ ከሕግ እንዷ ፊደል ወይም ቅንጣት ከቶ አታልፍም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ። 19 እንግዲህ ከእነዚህ ትእዛዞች ትንሿን የሚሽርና ለሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ የሚያስተምር፣ በመንግሥተ ሰማይ ታናሽ ይባላል። የሚጠብቃቸውና የሚያስተምራቸው ግን በመንግሥተ ሰማይ ታላቅ ይባላል። 20 ምክንያቱም፣ ጽድቃችሁ ከሕግ መምህራንና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ልቆ ካልተገኘ መንግሥተ ሰማይ ከቶ አትገቡም እላችኋለሁ። 21 ለቀደሙት፣ 'አትግደል፣ የገደለ ይፈረድበታል' እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 22 እኔ ግን፣ 'ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ይፈረድበታል፣ ወንድሙን፣ 'አንተ የማትረባ!' የሚለው የሸንጎ ፍርድ፣ 'ቂል' የሚለውም የገሃነመ እሳት ፍርድ ይፈረድበታል። 23 እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ልታቀርብ ከሆነና ወንድምህ አንዳች ነገር በአንተ ላይ እንዳለው ካስታወስህ፣ 24 መባህን በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ፣ በቅድሚያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ፣ ከዚያም ተመልሰህ መጥተህ መባህን አቅርብ። 25 ባላጋራህ ለዳኛው፣ ዳኛውም ለአሳሪው አሳልፎ እንዳይሰጥህና በወህኒ ውስጥ እንዳትጣል፣ ወደ ፍርድ ቤት ዐብረኸው እየሄድህ ሳለ ከሚከስስህ ባላጋራህ ጋር በፍጥነት ተስማማ። 26 እውነት እነግርሃለሁ፣ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ ፈጽሞ አትወጣም። 27 "አታመንዝር" እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ 28 እኔ ግን፣ ሴትን ተመኝቷት የሚመለከት ሁሉ በልቡ አመንዝሯል እላችኋለሁ። 29 የቀኝ ዐይንህ ቢያሰናክህል አውጥተህ ጣለው፤ መላ ሰውነትህ በገሃነም ከሚቃጠል፣ ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱ ቢጠፋ ይሻልሃልና። 30 የቀኝ እጅህም ቢያሰናክልህ ቆርጠህ ጣለው፤ መላ ሰውነትህ ገሃነም ውስጥ ከሚገባ ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱ ቢጠፋ ይሻልሃል። 31 'ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ የፍቺ ማረጋገጫ ይስጣት' ተብሎአል። 32 እኔ ግን፣ 'በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ እንድታመንዝር ያደርጋታል፤ ከተፈታች በኋላ የሚያገባትም ምንዝርና ይፈጽማል። 33 ደግሞም ለቀደሙት፣ በሐሰት አትማል፣ መሐላዎችህንም ለጌታ ስጥ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 34 እኔ ግን ከቶ አትማሉ፤ በሰማይም፣ የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤ 35 በምድርም፣ እግሩ የሚያርፍባት ናትና፤ በኢየሩሳሌምም፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና። 36 በራሳችሁም አትማሉ፤ አንዷን ጠጕር ነጭ ወይም ጥቍር ማድረግ አትችሉምና። 37 ነገር ግን ንግግራችሁ 'አዎ፣ አዎ'፣ ወይም 'አይደለም፣ አይደለም' ይሁን። ከዚህ የወጣ ሁሉ ከክፉው ነው። 38 ዐይን ስለ ዐይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፣ 39 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ 'ክፉውን ሰው አትቃወሙት፣ ይልቁን የቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውንም አዙርለት። 40 ማንም ሰው ሊከስስህና ኮትህን ሊወስድ ቢመኝ፣ ካባህንም ይውሰድ። 41 አንድ ምዕራፍ እንድትሄድ ማንም ሰው ቢያስገድድህ፣ ዐብረኸው ሁለት ምዕራፍ ሂድ። 42 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፣ ከአንተ መበደር ከሚፈልገውም ፊትህን አታዙር። 43 ባልንጀራህን ውደድ፣ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 44 እኔ ግን ጠላቶችህን ውደድ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ ብዬ እነግራችኋለሁ። 45 ይኸውም በሰማያት ያለ አባታችሁ ልጆች እንድትሆኑ ነው። እርሱ ፀሐይን በክፉዎችና በደጎች ላይ ያወጣል፤ ዝናብም በጻድቃንና በኅጥኣን ላይ ያዘንባል። 46 የሚወድዷችሁን ብትወዱ፣ ምን ዋጋ ታገኛላችሁ? ቀራጮች እንኳ እንደዚህ ያደርጉ የለምን? 47 ለወንድሞቻችሁ ብቻ ሰላምታ ብታቀርቡ፣ ከሌሎች የበለጠ የምታደርጉት ምንድን ነው? አሕዛብስ እንኳ ይህንኑ ያደርጉ የለምን? 48 እንግዲህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።



Matthew 5:1

ማቴዎስ 5፡1-4

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ይህ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ማስመተማር የጀመረበት አዲስ ታሪክ ጅማሬ ክፍል ነው፡፡ ይህ ክፍል እስከ ምዕራፍ 7 ድረስ ይቀጥላል እንዲሁም ብዙ ጊዜም የተራራው ስብከት ተብሎ ይጠራል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 3 ላይ ኢየሱስ የተባረኩ ሰዎች ባሕርያት ምን ምን እንደሆኑ መግለጽ ይጀምራል፡፡

አፉን ከፍቶ ኤቲ፡ “ኢየሱስ መናገር ጀመረ” ( ተመልከት)

አስተማራቸው “እነርሱን” የሚለው ቃል ደቀ መዛሙርቱን የሚያመለክት ነው፡፡

በመንፈሰስ ድሆች ይህ ማለት ትሁት የሆነ ማለት ነው፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር እንደሚያስፈልጋቸው ያወቁ፡፡” ( ተመልከት)

መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና በዚህ ሥፍራ ላይ “መንግስተ ሰማየት” የሚያመለክተው እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ መግዛቱን፡፡ ይህ ሀረግ በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ነው የሚገኘው፡፡ ከተቻለ በትርጉማችሁ ውስጥ “ሰማይ” የሚለው ቃል እንዲኖር አድርጉ፡፡ ኤቲ፡ “በሰማይ ያለው እግዚአብሔር ንጉሣቸው ይሆናልና፡፡” ( ተመልከት)

የሚያለቅሱ ያዘኑበት ምክንያት ሊሆን የሚችለው 1) በዚህ ዓለም ኃጢአት ወይም 2) በራሳቸው ኃጢአት ወይም 3) በሌላ ሰው ሞት ምክንያት፡፡ ቋንቋችሁ ካላስገደዳችሁ በስቀተር ምክንያቱን አትግለጹ፡፡

ይጽናናሉና ይህ እንዲህ በቀጥታ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ያጽናናቸዋል፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 5:5

ማቴዎስ 5፡5-8

የዋሆች “ትሁታን” ወይም “በራሳቸው ኃይል የማይታመኑት”

ምድርን ይወርሳሉ “እግዚአብሔር ምድርን ሁሉ ይሰጣቸዋል”

ጽድቅን የሚራቡ እና የሚጠሙ ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ከልቡ የሚሻ ሰው ማለት ነው፡፡ ኤቲ፡ “ውሃ እና ምግብን ሰው እንደሚሻ ሁሉ በጽድቅ ለመኖር የሚሹ” ( ተመልከት)

ይሞላሉ ይህ እንዲህ ተብሎ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ይሞላቸዋ” ወይም “እግዚብሔር ያረካቸዋል፡፡” : ( ተመልከት)

ልበ ንጹሖች

“ልባቸው ንጹሕ የሆኑ ሰዎች፡፡” በዚህ ሥፍራ “ልብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የአንድ ሰውን ፍላጎት ነው፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔርን ለማገልገል የሚፈልጉ ሰዎች፡፡” ( ተመልከት)

እግዚአብሔርን ያዩታል በዚህ ሥፍራ ላይ “ማየት” የሚለው ቃል በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ መኖር መቻልን የሚያመለክት ነው፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መኖር እንዲችሉ ይፈቅድላቸዋል፡፡”

Matthew 5:9

ማቴዎስ 5፡9-10

አስታራቂዎች እነዚህ ሌሎች ሰዎች እርስ በእርሳቸው ሰላም እንዲሆኑየሚያግዙ ሰዎችን ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና ይህ በእንዲህ ዓይነት መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ልጆቼ ብሎ ይጠራቸዋልና” ወይም “የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉና፡፡” (: ተመልከት)

የእግዚአብሔር ልጅ “ልጆች” የሚለውን ቃል በእናንተ ቋንቋ ለሰው ልጅ ወይም ሕጻናት በተለምዶ የሚትጠቀምበትን ተመሳሳይ ቃላት መጠቀሙ ጥሩ ነው፡፡

የሚሰደዱ ይህ በቀጥታ በዚህ ዓይነት መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ሌሎእ ሰዎች በተገቢው መንገድ ያልያዟቸው ሰዎች፡፡” ( ተመልከት)

ስለጽድቅ “እግዚአብሔር እንዲያደርጉ የሚፈልገውን ነገር በማድረጋቸው ምክንያት”

መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና ይህንን በ MAT 5:3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡

Matthew 5:11

ማቴዎስ 5፡11-12

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ኢየሱስ የተባረኩ ሰዎች ባሕርያትን ማብራሩትን ጨርሷል፡፡

የተባረካቹ ናቸሁ “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው፡፡ ( ተመልከት)

ስለ አንተ በውሸት ክፉ ነገሮችን ሁሉ ይናገራሉ፡፡ “ስለ አንተ ሁሉንም ዓይነት ክፉ ውሸትን ይናገራሉ” ወይም “እውነት ያልሆነ መጥፎ መጥፎ ነገሮችን ይናገራሉ”

ስለ እኔ ሲባል “እኔን በመከተልህ ምክንያት” ወይም “በእኔ በማመንህ ምክንያት”

ደስ ይበላችሁ እንዲሁም ሐሴትም አድርጉ “ደስ ይበላችሁ” እና “ሐሴት አድርጉ” የሚሉት ሁለቱ ቃላት ተመሳሳይ መልዕክቶችን የሚያስተልፉ ናቸው፡፡ ኢየሱስ አድማጮቹ ደስ ይበላችሁ ብቻ አላላቸው ነገር ግን ከተቻለ ከመደሰት በላይ እንዲያደርጉ ነግሮዋቸዋል፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 5:13

ማቴዎስ 5፡13-14

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንደ ጨው እና ብርሃን ይሆኑ ዘንድ ማስተማር ጀመረ፡፡

እናንተ የምድር ጨው ናቸው አማራጭ ትርጓሜዎች 1) ጨው ለምግብት ጣእም እንደሚሰጥ ሁሉ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በዓለም ውስጥ ያሉ ሰዎች መልካም ይሆኑ ዘንድ ተጽእኖ ፈጣሪዎች መሆን ይኖርባቸዋል ወይም 2) ልክ ጨው ምግብ ለረጅም ጊዜ ሳይበላሽ እንዲቆይ እንደሚያደረግ ሁሉ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሰዎች ሙሉ ለሙሉ እንዳይበላሹ የሚያደርጉ ሊሆኑ ይባል፡፡ ኤቲ፡ “ለዓለም ሕዝቦች እናንተ ልክ እንደ ጨው ናችሁ” ወይም “ጨው ለምግብ እንደሆነ ሁሉ እናንተም ለዓለም እንደዚሁ ናችሁ፡፡” ( ተመልከት)

ጨው ጣእሙን ካጣ አማራጭ ትርጉሞች 1) “ጨው ጨው የሚሠራውን ነገር መሠርት የሚያስችለውን ኃይሉን ካጣ” ((UDB) ወይም 2) “ጨው ጣዕሙን ካጣ፡፡” ( ተመልከት)

እንዴት ጨው የሚሰጠውን ጥቅም ሊሰጥ ይችላል? “እንደገና እንዴት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል?” ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለማስተማር ጥያቄን ይጠቀማል፡፡ ኤቲ፡ “አንደገና ጠቃሚ መሆን የሚችልበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም፡፡” ( እና ተመልከት)

ወደ ውጪ ከመጣል እና በሰዎች ከመረገጥ በስቀር ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡ ኤቲ፡ “በመንገድ ዳር ይጥሉታል፤ ሰዎችም ይረጋግጡታል፡፡” (See: ተመልከት)

እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ይህም ማለት የኢየሱስ ተከታዮች የእግዚአበብሔር እውነት ያለበትን መልዕክት እግዚብሔርን ወደ ማያውቁት ሰዎች ሁሉ ድረስ የሚያደርሱ ናቸው፡፡ ኤቲ፡ “እናንተ በዓለም ውስጥ ላሉ ሰዎች ልክ እንደ ብርሃን ናችሁ፡፡” (See: ተመልከት)

በተራራ ላይ ያለች ከተማ ፈጽሞ ልትደበቅ አትችልም ይህ ሰዎች የከተማዋን ብርሃን በምሽት መመልከት ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ይህ በቀጥታ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “በምሽት በተራራ ላይ ያለች ከተማን ብርሃን ማንም ሰው ሊከልል አይችልም፡፡ ( እና ተመልከት)

Matthew 5:15

ማቴዎስ 5፡15-16

መብራት የሚያበራ ሰውም እንዲሁ “ሰዎች መብራትን እንዲሁ አብርቶ

ከእንቅብ በታች አያኖረውም “መብራቱን ከቅርጫት በታች አያኖረውምለለ”፡፡ ይህ ማለት መብራን አብርቶ ሰዎች እንዳያዩት መደበቅ ሞኝነት ነው የሚል ነግግር ነው፡፡

ብርሃናችሁ በሰዎች ሁሉ ፊት ያብራ ይህ ማለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሌሎች ሰዎች የእግዚአብሔር እውነት ከእነርሱ መማር በሚችሉበት መንገድ መኖር አለባቸው ማለት ነው፡፡ ኤቲ፡ “ሕይወታችሁ ልክ እንደ መብራት በሰዎች ፊት ይብራ፡፡” ( ተመልከት)

በሰማይ የሚኖረው አባታችሁ “አባት” የሚለውን ቃል በጥሩ ሁኔታ ለመተርጎም በቋንቋችሁ ውስጥ አንድን አባት ለመጥራት የሚትጠቀሙትን ቃል ተጠቀሙ፡፡

Matthew 5:17

ማቴዎስ 5፡17-18

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን መጽሕፍት ውስጥ የተጻፉትን ሕግጋት ለመፈጸም እንደመጣ ማስተማሪ ጀመረ፡፡ ነቢያት ይህ ነቢያት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የጻፏቸውን መጽሐፍትን ያመለክታል፡፡ ( ተመልከት) እውነት እላችኋለሁ “እውነት እላችኋለሁ፡፡” ይህ ሀረግ ኢየሱስ ቀጥሎሊናገረው ያለው ሀሳብ አጽኖት ልሰጥበት የሚገባ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር የፈጠራቸው ነገሮች ሁሉ ያልፋሉ፡፡” ( ተመልከት) አንድት ነጥብ “ከፊደል ትንሸዋ እንኳ ሳትቀር፡፡ ይህ ከቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ በሰዎች ይህንን ያኸለ አስፈላጊ አይደሉም ተብሎ የሚቆጠሩት እንኳ ሳይቀሩ የሚለውን ለማሳየት የቀረበበ ምሳሌያዊ ንግግር ነው፡፡ ኤቲ፡ “አስፈላጊ የማይመስሉ ሕግጋት እንኳ ሳይቀሩ”፡፡ ( ተመልከት) ሁሉ ነገር ይፈጸማል ይህ በግልጽ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር በሕግ ውስጥ የተጻፉትን ነገሮች ሁሉ ፈጽሟል፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 5:19

ማቴዎስ 5፡19-20

የተላለፈ ማንኛውም ሰው “የማይታዘዝ ማንኛውም ሰው” ወይም “ሳይታዘዝ የቀረ ማንኛውም ሰው” ከእነዚህ ትዕዛዛት መካከል ትንሹን “ከእነዝህ ትዕዛዛት መካከል፣ ጥቅሟ በጣም ትንሽ የሆነችውን ትዕዛዛ እንኳ ሳይቀር” ተብሎ ይጠራል ይህ እንዲህ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ያንን ሰው አግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ይጠራዋል፡፡” ( ተመልከት) በመንግስተ ሰማይ ውስጥ ትንሽ “መንግስተ ሰማይ” ሚለው ሀረግ የእግዚአብሔር አገዛዝ ያመለክታል፡፡ ይህ ሀረግ የሚገኘው በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የሚቻል ከሆነ “በትርጉማችሁ ውሰጥ “ሰማይ” የሚለው ቃል ተጠቀሙ፡፡ ኤቲ፡ “በመንግስተ ሰማይ ውስጥ አስፈላጊነቱ ትንሽ ይሆናል” ወይም “በሰማይ የእግዚአብሔ አገዛዝ ውስጥ ያለው ጠቀሜታ በጣም ትንሽ ይሆናል፡፡” ( ተመልከት) ጠብቋቸው እንዲሁም አስተምሯቸው “እነዚህ ትዕዛዛት ሁሉ ታዘዙ እንዲሁም ሌሎችም ይህንኑ ያደርጉ ዘንድ አስተምሯቸው፡፡” ታላቅ “በጣም አስፈላጊ” እንዲህ ብዬአችኋለሁ ይህ ኢየሱስ ከዚህ በመቀጠል ስለሚናገረው ነገር አጽኖት ይሰጣል፡፡ አንተ . . . እናንተ . . . አንተ ይህ ብዙ ቁጥርን ያመለክታል፡፡ ( ጽድቃችሁ ካልበለጥ . . . ልትገቡ አትችሉም ይህ በአዎንታዊ መንገድ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ጽድቃችሁ መብለጥ አለበት . . . ለመግባት፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 5:21

ማቴዎስ 5፡21-22

አያያዥ ዓረፍ ነገር ኢሰየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን ለመፈጸም መምጣቱን ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሥፍራ ስለ ነፍስ ማጥፋት እና ንዴት ተናግሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንደ ግለሰብ እያንዳንዳቸው ምን ሊያጋጥማቸው እንደሚችል እየተናገረ ነው፡፡ “ሰምታችኋል” የሚለው ሀረግ ውስጥ ያለው “እናንተ” የሚለው ቃል እና “እላችኋለሁ” ሀረግ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ “አትግደል” የሚለው ሀረግነጠላ ቁጥር ነው ይሁን እንጂ በብዙ ቁጥር ሊተረጎም ይችላል፡፡ በጥት ዘመን እንዲህ ተብሎ ተነግሯቸዋል ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ከብዙ ዘመናት በፊት እግዚአብሔር ተናግሮ ነበር፡፡ ( ተመልከት) ነፈስ ያጠፋ ማንኛውም ሰው ፍርድ አለበት በዚህ ሥፍራ “ፍርድ” የሚለው ቃል ይህ ሰው እንዲገደል የሚያዘውን ሕግ የሚያሳይ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ሌላ ሰው የገደለ ማንኛው ሰው ላይ ዳጃው ይፈርዳል፡፡” ( ተመልከት) ግዲያ. . . ግድያዎች ይህ የሚያመለክተው ቃል ሆኖ ነፍስ ማጥፋት እንጂ ሁሉንም ዓይነት የግዲያ አይነቶችን አይደለም፡፡ ነገር ግን እኔ እንዲህ እላችኋለሁ “እኔ” የሚትለው ቃ አጽኖታዊ ናት፡፡ ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ የተናገረው ነገር እግዚአብሐየር በመጀመሪያ ከሰጠው ትዕዛዝ ጋር የሚስተካከል ነው፡፡ ስትተረጉም ይህንን አጽኖት በሚያሳይ ሀረግ ለመተርጎም ሞከር፡፡ ወንድም ይህ አማኝን እንጂ በሥጋ ወንድምን ወይም ጎረበትን የሚያመለክት አይደለም፡፡ ፍርድ ይገባዋል በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ስለ ሰው ፍርድ ሳይሆን በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሰውን እግዚአብሔር የሚያመጣውን ፍርድ ነው፡፡ ( ተመልከት) እርባና የሌለው . . . ሞኝ ይህ በትክክል ማሰብ የማይችሉ ሰዎች የሚሰደቡትን ስድብ የሚያመለክት ነው፡፡ “እርባና ያሌለው” የሚለው ቃል “አእምሮ የሌለው” ከሚለው ቃል ጋር ተቀራራቢ ሲሆን “ሞኝ የሚለው ደግሞ እግዚአብሔርን አለመታዘዝ ጋር ተያያዥነት ያለው ሀሳብ ነው፡፡ ሸንጎ ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው የሸንጎ ሳይሆን በአከባቢው ያለው ሸንጎ ነው፡፡

Matthew 5:23

ማቴዎስ 5፡23-24

እንተ ኢየሱስ በቡድን ላሉ ሰዎች እያንዳንዳቸው ምን እንደሚያጋጥማቸው እየተናገረ ነው፡፡ “አንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው፡፡ እናንተ ግን በቋንቋች በብዙ ቁጥር ሊትተረጉሙት ትችላላችሁ፡፡ ( ተመልከት) መባህን “ስጦታ ስትሰጥ” ወይም “ስጦታህ ስታቀርብ” በመሠዊያው ላይ ይህ በኢየሩሳሌሚ ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገኘውን የእግዚአብሄርን መሠዊያ የሚያመለክት ነው፡፡ ኤቲ፡ “በቤተ መቅዲስ ውስጥ በሚገኘው የእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ፡፡” ( ተመልከት) በዚያ ሳለህ ቢታስታውስ “በመሠዊያው ፊት ቆመህ ሳለ ቢታስታውስ” ወንድምህ አንዳች ነገር ከአንተ ጋር እንዳለው “አንተ ባደረከው አንድ ነገር የተነሳ ወንድም በአንተ የተቆጣ መሆኑን ካስታወስክ” በመጀመሪያ ሂድና ከወንድምህ ጋር ታረቅ ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ከሰውዬው ጋር ሰላምን ፍጠር፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 5:25

ማቴዎስ 5፡ 25-26

ከአንተ . . . ጋር ተስማማ ኢየሱስ በቡድን ላሉ ሰዎች እያንዳንዳቸው ምን እንደሚያጋጥማቸው እየተናገረ ነው፡፡ “አንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው፡፡ እናንተ ግን በቋንቋች በብዙ ቁጥር ሊትተረጉሙት ትችላላችሁ፡፡ ( ተመልከት) ከከሳሽ ጋር ይህ ሰው ሌላኛውን ሰው በደል እየነቀሰ የሚወቅስ ሰው ነው፡፡ በዳኛ ፊት ሆኖ ሌላኛው ሰው የበደለውን በደል በመናገር ይከሳል፡፡ ለዳኛ አሳልፎ ይሰጥሃል በዚህ ሥፍራ ላይ “አሳልፎ ይሰጥሃል” የሚለው ሀረግ ትርጉሙ አንድን ሰው በሌላ ሰው ቁጥጥር ሥር እንዲሆን መስጠትን ያመለክታል፡፡ ኤቲ፡ “ዳኛው በሕጉ መሠረት እንዲፈርድብህ ያደርጋል፡፡” ( ተመልከት) ዳኛውም ለወህኒ ጠባቂዎች አሳልፎ ይሰጥሃል በዚህ ሥፍራ ላይ “አሳልፎ ይሰጥሃል” የሚለው ሀረግ ትርጉሙ አንድን ሰው በሌላ ሰው ቁጥጥር ሥር እንዲሆን መስጠትን ያመለክታል፡፡ ኤቲ፡ “ዳኛውም ለወህኒ ጠበቂ አሳልፎ ይሰጥሃል፡፡” ( ተመልከት) የወህኒ ጠባቂ ይህ ሰው ሰው በዳኛው የተሰጠውን ውሳኔ የሚያስፈጽም ግለሰብ ነው፡፡ ወደ ወህኒ ትጣላለህ ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “የወህኒ ጠባቂው በወህኒ ቤት ውስጥ እንዲትታሠር ያደርጋል፡፡” ( ተመልከት) እውነት እውነት እላችኋለሁ “እውነት እውነት እላችኋለሁ”፡፡ ይህ ሀረግ ኢየሱስ ቀጥሎ ለሚናገረው ነገር አጽኖት እንዲንሰጥ ያደርገናል፡፡ ከዚያ ሥፍራም “ከወህኒ ቤት”

Matthew 5:27

ማቴዎስ 5፡27-28

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን ለመፈጸም መምጣቱን ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሥፍራ ስለዝሙት እና ምኞች ማስተማር ጀምሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “ሰምታችኋል” በሚለው ሀረግ ውስጥ የሚገኘው “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው፡፡ “አታመንዝር” የሚለው ትዕዛዝ “አንተ” የሚለውን ቃ በውስጡ ይዞዋል ይሁን እንጂ “አንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር መተርጎም ትችላለህ፡፡ ( ተመልከት) እንዲህ እንደተባለ ሰምታችኋል ይህ በቀጥታ እንዲህ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል፡፡” ( ተመልከት) መፈጸም ይህ ቃል አንድን ነገር ማድረግን ያመለክታል፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ ይህንን በ MAT 5:22 እንደ ተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ ሴትን ተመልክቶ በልቡ የተመኛት ማንኛውም ሰው አመንዝሯል ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ሴትን ተመልክቶ በልቡ የተመኛት ማንኛውም ሰው ካመነዘረ ሰው እኩሉ ጥፋተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡ ( ተመልከት) የተመኛት “እንዲሁም የተመኛት” ወይም “ከእርሷ ጋር ለመተኛት የተመኘ ሰው” በልቡ በዚህ ሥፍራ “ልብ” የሚያመለክተው የአንድን ሰው ሀሳብ ነው፡፡ ኤቲ፡ “በአእምሮው” ወይም “በሀሳቡ”፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 5:29

ማቴዎስ 5፡29-30

የአንተ . . . ከ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “አንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው ይሁን እንጂ በብዙ ቁጥር መተርጎም የግድ ሊሆንብህ ይችላል፡፡ ( ተመልከት) የቀኝ ዐይንህ ካሰናከለችህ በዚህ ሥፍራ “ዐይን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድ ሰው የሚያየውን ነው፡፡ እንዲሁም “መሰናከል” ምሳሌያዊ ንግግር ሲሆን “ኃጢአት” ማለት ነው፡፡ ኤቲ፡ “የሚትመለከተው ነገር እንድትሰናከል የሚያደርግ ከሆነ” ወይም “ከሚታየው ነገር የተነሳ ኃጢአት ማድረግ የሚትሻ ከሆነ፡፡” ( እና ተመልከት) ቀኝ ዐይን . . . ቀኝ እጅ ከግራ ዐይን ወይም እጅ በተቃራኒው በጣም ጠቃሚው ዐይን ወይም እጅ፡፡ “ቀኝ” የሚለው ቃል “አስፈላጊ የሆነ” ወይም “ብቸኛ” በሚሉ ቃላት ለትተረጉማቸው ትችላለህ፡፡ ( ተመልከት) አውጥተህ “በኃይል ማስወገድ” ወይም “ማጥፋት”፡፡ ቀኝ ዐይን የሚለው በቀጥታ ካልተጠቀሰ “ዐይንህ አጥፋ” ብለህ ልትተረጉም ትችላል፡፡ ዐይን የተጠቀሰ ከሆነ “አጥፋቸው” ብለህ ልትተረጉም ትችላለህ፡፡ አውጣው . . . ቁረጠው ኢየሱስ የኃጢአትን አደገኝነት ላይ አጽኖት በመስጠት ለዚህ ሰዎች መስጠት ስላለባቸው ምላሽ ግነት የተሞላት መልኩ ተናገግሯል፡፡ ( ተመልከት) አውጥተህ ጣለው “አስወግደው” ከሰውነት ክፍለህ አንዱ ይጥፋ “ከሰውነት ክፍልህ አንዱን ማጣት ይሻላል፡፡” መላ አካልህ ወደ ሲኦል ከሚጣል ይልቅ ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊገለጽ ይችላለል፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር መላ አካልህን ወደ ሲኦል ከሚጨምረው ይልቅ፡፡” ( ተመልከት) ቀኝ እጂህ ካሰናከለችህ ይህ ምሳሌያዊ ንግግር የአንድ ሰው ሁለተናዊ ተግባርን ከእጁ ጋር ታያይዛለች፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 5:31

ማቴዎስ 5፡31-32

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን እንዴት ለመፈጸም እንደመጣ ማስተማሩ ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ስለፍች ማስተማር ጀምሯል፡፡ እንዲህም ተብሏል “የተናገረው” እግዚአብሔር ነው፡፡ ኢየሱስ የእርሱ ተቃርኖ ከእግዚብሔር ወይም ከእግዚብሔር ቃል ጋር አለመሆኑን ለመግለጽ ነው ይህን ዓይነት ንግግር የተናገረው፡፡ ይልቁንም ፍች የተፈቀደው ለትክክለኛ ምክንያት ብቻ ነው፡፡ ወንዱ ምንም እንኳ በትዕዛዛቱ መሠረት የፍች ወረቀቷን ለሚስቱ ቢሰጣትም እንኳ ፍትሓዊ አይደለም፡፡ ( ተመልከት) ሚስቱን የሚሰዳት ይህ ፍችን የሚያመለክት ምሳሌያዊ አነጋገር ነው፡፡ ( ተመልከት) ይስጣት “ልሰጣት ይገባል” እኔ ግን እንዲህ እላለሁ ይህንን በ MAT 5:22 በምን ዓይነት መንገድ እንደተረጎማችሁ ተመልከቱ፡፡ አመንዝራ ያደርጋታል ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ሚስቱን የፈታት ሰው “እንድታመነዝር ያደርጋል”፡፡ በብዙ ባሕሎች ውስጥ እንደገና ማግባት ትችላለች ነገር ግን የተፋታችው ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ከሆነ ግን እንዲህ አይነቱ ትዳር ዝሙት ነው፡፡ ከተፋታች በኋላ ይህ በቀጥታ እንዲህ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ባሏ ከፈታት በኋላ” ወይም “ፍች የፈጸመችው ሴት”፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 5:33

ማቴዎስ 5፡33-35

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን እንዴት ለመፈጸም እንደመጣ ማስተማሩ ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ስለመሃላ ማስተማር ጀምሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “ሰምታችኋል በሚለው ሀረግ ውስጥ ያለው “እናንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ ይሁን እንጂ “አትማል” እና “ፈጽማቸው” በሚለው ውስጥ ያለው “አንተ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ እንደገና አንተ “አንተም ደግሞ” ወይም “ሌላ ምሳሌ ይኼው፡፡ አንተ” እንዲህ ሲባል ሰምታችኋል . . . በውሸት አትማሉ በዚህ ሥፍራ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር እና ከቃሉ ጋር በግልጽ የሚስማማ ነገር ስናገር ትመለከታላችሁ፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎችን ለማሳመን የእነርሱ ያልሆነ ነገር እንዳይናገሩ ያሳስባቸዋል፡፡ ኤቲ፡ “የሃይማኖት መሪዎቻችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለው ነግረዋችኋል . . . አትማሉ፡፡” ( ተመልከት) በውሸት አትማሉ መኃላችሁን ፈጽሙ እንጂ አማራጭ ትርጉሞች 1) የማትፈጽሙትን ነገር አደርጋለሁ ብላችሁ በእግዚአብሔር ፊት አትማሉ ወይም 2) አንድ ነገር ውሸት መሆኑን እያወቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት እውነት ነው ብላችሁ አትማሉ፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ በ MAT 5:22 የሚገኘውን በምን መንገድ እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ ፈጽሞ አትማሉ . . . የታላቁ ንጉሥ ከተማ በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ የተናገረው ማንም ሰው ፈጽሞ መማል እንዳሌለበት ነው፡፡ አንዳንዶች አንድ ሰው የማለው ከእግዚአብሔር ውጪ በሆነ ነገር ማለትም በሰማይ፣ በምድር ዌም በኢየሩሳም የማለ ከሆነ መሃላውን ሳይፈጽም ቢቀር ይህን ያኽል ጉዳት የለውም ብለው ሳያስተምሩ አልቀሩም፡፡ ኢየሱስ ይህም ቢሆን እንደ ማንኛውም መሃላ መጥፎ ነው ምክንያቱም ሁሉ ነገር የእግዚአብሔር ስለሆነ ነው፡፡ ፈጽሞ አትማሉ ለዚህ ትዕዛዝ የሚሆን ቃል በቋንቋችሁ በብዙ ቁጥር የሚገኝ ከሆነ በዚህ ሥፍራ ይህንን ቃል ተጠቀሙ፡፡ “በውሸት አትማሉ” የሚለው ሀረግ አድማጮች መማል እንደሚቻል ነገር ግን በውሸት መማል የማይቻል እንደሆነ ያሳያል፡፡ “ፈጽሞ አትማሉ” የሚለው ሀረግ ግን ሁሉንም ዓይነት መሃላዎችን ይከለክላል፡፡ የእግዚአብሔር ዚፋን ነው በዚህ ሥፍራ ላይ “ዙፋን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ መግዛቱን ነው፡፡ ኤቲ፡ “የእግዚአብሔር አገዛዝ”፡፡ ( ተመልከት) የእግሩ መረገጫ ናት ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር ምድርም ቢትሆን የእግዚአብሔር መሆኗን ያሳያል፡፡ ኤቲ፡ “ንጉሥ እግሩን የሚያሳርፍበት የእግሩ መርገጫ ሥፍራ ዓይነት ናት፡፡ ( ተመልከት) የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና “ይህች ከተማ የታላቁ ንጉሥ የእግዚአብሔር ከተማ ናትና፡፡”

Matthew 5:36

ማቴዎስ 5፡37-38

አጠቃላይ መረጃ፡ ከዚህ በፊት በነበረው ክፍል ውስጥ ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር ዙፋን፣ የእግሩ መረገጫ እና ምድራዊ ቤተ ጭምር ሊምሉበት የሚገባ የእርሱ ንብረት አለመሆኑን ገልጾዋል፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ደግሞ በራሳቸው ላይ ባለው ጸጉር እንኳ መማል እንደማይገባቸው ይናገራል፡፡ እናንተ . . . አንተ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “አትማል” እና “አትችልም” በሚሉ ሀረጋት ውስጥ ያለው “አንተ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ ይሁን እንጁ በምትተረጉሙበት ጊዜ በብዙ ቁጥር ልትተረጉሙ ትችላላችሁ፡፡ ( ተመልከት) መሃላ በ MAT 5:34እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡ ንግግርህ “አዎ፣ አዎ ወይም አይ ፣ አይ” ይሁን” “አዎ ማለት ከፈለግህ “አዎ” በል እንዲሁም “አይ” ማለት ከፈለግህ “አይ” በል፡፡

Matthew 5:38

ማቴዎስ 5፡38-39

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን እንዴት ለመፈጸም እንደመጣ ማስተማሩ ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ጠላትን ስለመበቀል ማስተማር ጀምሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “ሰምታችኋል” እና “እኔ እንዲህ እላችኋለሁ” በሚለው ሀረግ ውስጥ የሚገኘው “እናንተ” የሚለው ቃል የተገለጸው በብዙ ቁጥር ነው፡፡ “ማንም ቢመታህ” የሚለው ሀረግ ውስጥ የሚገኘው “አንተ” የሚለው ቃል ግን በብዙ ቁጥር መተርጎም ትችላላችሁ፡፡ ( ተመልከት) እንዲህ መባሉን ሰምታችኋል ይህንን በ MAT 5:33 እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከት፡፡ ዐይን ለዐይን ጥርስ ለጥርስ የሙሴ ሕግ የጎዳንን ሰው በተመሳሳይ መንገድ እንዲጎዳ ያዛል ይሁን እንጂ ከዚያ በላይ እንዲጎዳ አያደርግም፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላለሁ ይህንን በ MAT 5:22.እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከት፡፡ ክፉውን “ክፉ የሆነ ሰው” ወይም “የጎዳችሁ ሰው” (UDB) ቀኝ ጉንጫችሁን የመታችሁ ኢየሱስ በኖረበት ባሕል ውስጥ የአንድን ሰው ቀኝ ጉንጭ በጥፊ መምታት ስድብ ነው፡፡ ልክ እንደ ዐይን እና እጅ ሁሉ ቀኝ ጉንጭም በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ ጉንጭን በጥፊ መምታት ትልቅ ስድብ ነው፡፡ መምታት “በጥፊ መምታት”፡፡ ይህ ማለት በቃሪያ ጥፉ አንድን ሰው መምታት ማለት ነው፡፡ ሌላኛውንም ፊት አዙሩለት “ሌላኛውን ፊታችሁን የሚታችሁ ዘንድ አዙሩለት”

Matthew 5:40

ማቴዎስ 5፡40-42

አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “ፍቀድ”፣ “ሂድ”፣ “ስጥ” እና “አትመለስ” በሚሉ ቃላት ውስጥ ያለው “አንተ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ ( ተመልከት) ኮትህ . . . መጎናጸፊያ “ኮት” በሰዉነት ላይ እንደ ቲሸረት የሚጠለቅ ነው፡፡ “መጎናጸፊያ” ከእነዚህ ይልቅ ውድ የሆነ “ከኮት” ላይ ለሙቀት የሚደረብ እንዲሁም በሽት ለሙቀት የሚለበስ ነገር ነው፡፡ ይወስድ ዘንድ ፍቀድለት “ለዚያ ሰው ስጠው” ማንምን ሰው “እንዲሁም ይህ ሰው”፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ በተዘዋዋር መንገድ የተጠቀሰው የሮማዊያን ወታደር ነው፡፡ ( ተመልከት) አንድ ምዕራፍ አንድ የሮም ወታደር በዚያ ዘመን አንድን ሰው አንድ ዕቃ ተሸክሞ እንዲሄድ በሕግ ማስገደድ የሚችለው አንድ ሺህ እርምጃዎች ያኽል ነው፡፡ “ማይል” የሚለው ቃል የሚያምታታ ከሆነ “አንድ ኪሎ ሜትር” ወይም “ረጅም ርቀት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ከእርሱ ጋር አብረኸው እንዲትሄድ ያስገደደ ሰውን ያመለክታል፡፡ ከእርሱ ጋር እጥፍ መንገድ ሂደት “አስገድዶህ እንዲትሄድ ያደረግህን ምዕራፍ ያኸል ሂደት ከዚያም ሌላ አንድ ማዕራፍ ጨምርለት፡፡” “ማይል” የሚለው ቃል የሚያምታታ ከሆነ “ሁለት ኪሎ ሜትር” ወይም “እጥፍ ርቀት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አትከልክል “እንዲሁም ሊበደርህ የሚፈልግ ሰውን አትከልክል፡፡” ይህ በአውንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይገባል፡፡ ኤቲ፡ “አበድር”፡፡

Matthew 5:43

ማቴዎስ 5፡43-45

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን እንዴት ለመፈጸም እንደመጣ ማስተማሩ ቀጥሏል፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ጠላትን ስለመውደድ ማስተማር ጀምሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “የሚወድሁን ውደድ . . . የሚጠሉህ ጥላ” የሚለው ብቻ በነጠላ ቁጥ የተጻፈ ሲሆን እነዚህም ቢሆን በብዙ ቁጥር መተርጎም ትችላህ፡፡ ለሌሎች “እናንተ” የሚል ቃል ባለባቸው ሥፍራዎች ሁሉ እና “ፍቅር”እና “ጸሎት” ቦታዎች በብዙ ቁጥር የተገለጹ ናቸው፡፡ ( ተመልከት) እንዲህ እንደተባለ ሰምታችኋል ይህንን በ MAT 5:33. እንደተረጎማችሁት ተመልከት፡፡ ባለንጀራህን “ባለንጀራ” የሚለው ቃል አንድ ሰው በመልካም መንገድ ማስተናገድ የሚሻውን የተመሳሳይ ማህበረሰብ ወይም ቡድን አባላትን የሚያመለክት እንጂ በአከባቢያችን የሚኖሩ ሰዎችን ሁሉ አያመለክትም፡፡ ይህንን የብዙ ቁጥርን በሚያመለክት ቃል ልትተረጉሙት ትችላላችሁ፡፡ እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ ይህንን በ MAT 5:22. እንደተረጎማችሁት ተመልከት፡፡ የአባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ “ልጆች” የሚለው ቃል በጥሩ ሁኔታ ለመተርጎም በቋንቋችሁ ለሰው ልጆችን ወይም ሕጻናት የሚትጠቀሙትን ቃል ተጠቀሙ፡፡ አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 5:46

ማቴዎስ 5፡46-48

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ሕግጋትን እንዴት ለመፈጸም እንደመጣ ያስተማረውን ትምህርት በዚህ ከፍል ውስጥ ያጠናቅቃል፡፡ ይህ ክፍል የሚጀምረው በ MAT 5:17 ላይ ነው፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ ያኽል “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር አመልካች ነው፡፡ በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ የሚገኘው ጥያቄ መጠይቃዊ ነው፡፡ ( እና ተመልከት) ታላቅ ይህ አድማጮቹ መልካምነት ያለውን መሻት የሚያሳይ አጠቃላይ ቃል ነው፡፡አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)


Translation Questions

Matthew 5:1

በመንፈስ ድሃ የሆኑት ብፁዓን የሆኑት ለምንድነው?

በመንፈስ ድሃ የሆኑት ብፁዓን የሆኑት መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ስለሆነች ነው። [5:3]

የሚያለቅሱ ብፁዓን የሆኑት ለምንድነው?

የሚያለቅሱ ብፁዓን የሆኑት ስለሚጽናኑ ነው። [5:4]

Matthew 5:5

የዋሆች ብፁዓን የሆኑት ለምንድነው?

የዋሆች ብፁዓን የሆኑት ምድርን ስለሚወርሱ ነው። [5:5]

ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን የሆኑት ለምንድነው?

ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙት ብፁዓን የሆኑት ስለሚጠግቡ ነው። [5:6]

Matthew 5:11

ስለ ኢየሱስ ሲሉ የሚሰደቡና የሚሰደዱ ብፁዓን የሆኑት ለምንድነው?

ስለ ኢየሱስ የሚሰደቡና የሚሰደዱ ብፁዓን የሚሆኑት ዋጋቸው በሰማይ ታላቅ ስለሆነ ነው። [5:11]

ስለ ኢየሱስ ሲሉ የሚሰደቡና የሚሰደዱ ብፁዓን የሆኑት ለምንድነው?

ስለ ኢየሱስ የሚሰደቡና የሚሰደዱ ብፁዓን የሚሆኑት ዋጋቸው በሰማይ ታላቅ ስለሆነ ነው። [5:12]

Matthew 5:15

አማኞች ብርሃናቸው በሰው ፊት እንዲበራ የሚያደርጉት እንዴት ነው?

መልካምን ሥራ በማድረግ አማኞች ብርሃናቸው በሰው ፊት እንዲበራ ያደርጋሉ። [5:15]

አማኞች ብርሃናቸው በሰው ፊት እንዲበራ የሚያደርጉት እንዴት ነው?

መልካምን ሥራ በማድረግ አማኞች ብርሃናቸው በሰው ፊት እንዲበራ ያደርጋሉ። [5:16]

Matthew 5:17

ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ህግ እና ነብያት ላይ ምን ለማድረግ መጣ?

ኢየሱስ የመጣው የብሉይ ኪዳን ህግ እና ነብያትን ለመፈጸም ነው። [5:17]

Matthew 5:19

በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ የሚባለው ማን ነው?

ትእዛዛቱን የሚጠብቁና ለሌሎች የሚያስተምሩ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላሉ። [5:19]

Matthew 5:21

የሚገድሉ ብቻ ሳይሆን ምን የሚያደርጉት ጭምር ናቸው በፍርድ አደጋ ውስጥ እንደሆኑ ኢየሱስ ያስተማረው?

የሚገድሉ ብቻ ሳይሆን፣ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ በፍርድ አደጋ ውስጥ እንደሆነ ኢየሱስ አስተማረ ። [5:21]

የሚገድሉ ብቻ ሳይሆን ምን የሚያደርጉት ጭምር ናቸው በፍርድ አደጋ ውስጥ እንደሆኑ ኢየሱስ ያስተማረው?

የሚገድሉ ብቻ ሳይሆን፣ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ በፍርድ አደጋ ውስጥ እንደሆነ ኢየሱስ አስተማረ ። [5:22]

Matthew 5:23

ወንድማችን በእኛ ላይ የተቀየመው የትኛውም ነገር ቢኖረው ምን እንድናደርግ ኢየሱስ አስተማረ?

ሄደን ከወንድማችን ጋር እንድንታረቅ ኢየሱስ አስተማረ። [5:23]

ወንድማችን በእኛ ላይ የተቀየመው የትኛውም ነገር ቢኖረው ምን እንድናደርግ ኢየሱስ አስተማረ?

ሄደን ከወንድማችን ጋር እንድንታረቅ ኢየሱስ አስተማረ። [5:24]

Matthew 5:25

ከሳሻችን ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት ምን እንድናደርግ ኢየሱስ አስተማረ?

ወደ ፍርድ ቤት ከመድረሱ በፊት ከከሳሻችን ጋር እንድንስማማ ኢየሱስ አስተማረ። [5:25]

Matthew 5:27

ዝሙትን መፈጸም ብቻ ሳይሆን ሌላ ምን ማድረግ ጭምር ስህተት እንደሆነ ኢየሱስ አስተማረ?

ዝሙትን መፈጸም ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ሴትን አይቶ መመኘትም ስህተት እንደሆነ ኢየሱስ አስተማረ። [5:27]

ዝሙትን መፈጸም ብቻ ሳይሆን ሌላ ምን ማድረግ ጭምር ስህተት እንደሆነ ኢየሱስ አስተማረ?

ዝሙትን መፈጸም ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ሴትን አይቶ መመኘትም ስህተት እንደሆነ ኢየሱስ አስተማረ። [5:28]

Matthew 5:29

ኃጢአት እንድናደርግ በሚያነሣሣን የትኛውም ነገር ላይ ምን እንድናደርግ ኢየሱስ ተናገረ?

ኃጢአት እንድናደርግ የሚያደርገን የትኛውንም ነገር ልናስወግድ እንደሚገባ ኢየሱስ ተናገረ። [5:29]

ኃጢአት እንድናደርግ በሚያነሣሣን የትኛውም ነገር ላይ ምን እንድናደርግ ኢየሱስ ተናገረ?

ኃጢአት እንድናደርግ የሚያደርገን የትኛውንም ነገር ልናስወግድ እንደሚገባ ኢየሱስ ተናገረ። [5:30]

Matthew 5:31

ኢየሱስ ፍቺን የፈቀደው በምን ጉዳይ ሲሆን ነው?

ኢየሱስ ፍቺን የፈቀደው በዝሙት ጉዳይ ሲሆን ነው። [5:32]

ያላግባብ ከፈታት እና መልሳ ካገባች ባል ሚስቱን ምን እንድትሆን ያደርጋታል?

ያላግባብ ከፈታትና እርሷም መልሳ ካገባች ባል ሚስቱን አመንዝራ ያደርጋታል። [5:32]

Matthew 5:36

ለተለያዩ ምድራዊ ነገሮች መሃላ ከማድረግ ይልቅ ንግግራችን ምን ሊሆን እንደሚገባ ኢየሱስ ተናገረ?

በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ከመማል ይልቅ ንግግራችን “አዎን፣ አዎን፣” ወይም “አይደለም፣ አይደለም” ሊሆን እንደሚገባ ኢየሱስ ተናገረ። [5:37]

Matthew 5:38

ክፉ ለሚሆንብን ምን እንድናደርግ ኢየሱስ አስተማረ?

ክፉ የሚያደርግብንን እንዳንቃወም ኢየሱስ አስተማረ። [5:38]

ክፉ ለሚሆንብን ምን እንድናደርግ ኢየሱስ አስተማረ?

ክፉ የሚያደርግብንን እንዳንቃወም ኢየሱስ አስተማረ። [5:39]

Matthew 5:43

በጠላቶቻችን እና የሚያሳድዱን ላይ ምን እንድናደርግ ኢየሱስ አስተማረ?

ጠላቶቻችን እና የሚያሳድዱንን እንድንወድድ እና እንድንጸልይላቸው ኢየሱስ አስተማረ። [5:43]

በጠላቶቻችን እና የሚያሳድዱን ላይ ምን እንድናደርግ ኢየሱስ አስተማረ?

ጠላቶቻችን እና የሚያሳድዱንን እንድንወድድ እና እንድንጸልይላቸው ኢየሱስ አስተማረ። [5:44]

Matthew 5:46

የሚወድዱንን ብቻ ሳይሆን ጠላቶቻችንን ጭምር ልንወድድ እንደሚገባን ኢየሱስ የተናገረው ለምንድነው?

የሚወድዱንን ብቻ ብንወድድ፣ አሕዛብ የሚያደርጉትን ብቻ ማድረጋችን ስለሆነ ዋጋ እንደማናገኝ ኢየሱስ ተናገረ። [5:46]

የሚወድዱንን ብቻ ሳይሆን ጠላቶቻችንን ጭምር ልንወድድ እንደሚገባን ኢየሱስ የተናገረው ለምንድነው?

የሚወድዱንን ብቻ ብንወድድ፣ አሕዛብ የሚያደርጉትን ብቻ ማድረጋችን ስለሆነ ዋጋ እንደማናገኝ ኢየሱስ ተናገረ። [5:47]


ምዕራፍ 6

1 ሰዎች እንዲያዩአችሁ የጽድቅ ተግባሮቻችሁን በፊታቸው ከማከናወን ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ከሰማይ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም፡፡ 2 ስለዚህ አንተ ምጽዋት ስትሰጥ ግብዞች የሰዎችን ከበሬታ ለማግኘት በምኵራቦችና በጐዳና ላይ እንደሚያደርጉት፣ በፊትህ ጥሩንባ አታስነፋ፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡ 3 አንተ ግን ምጽዋት ስትሰጥ፣ የቀኝ እጅህ የሚያደርገውን የግራ እጅህ እንዲያውቅ አታድርግ፤ 4 ይኸውም ምጽዋትህ በስውር የሚሰጥ እንዲሆንና ከዚያም በስውር የሚያይ አባትህ ዋጋህን እንዲከፍልህ ነው፡፡ 5 ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ግብዞች ሕዝብ እንዲያያቸው በምኵራቦችና በጐዳና ማእዘኖች ላይ ቆመው መጸለይ ይወዳሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡ 6 አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ጓዳህ ገብተህ በር ዝጋና በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡ 7 ስትጸልይም አሕዛብ እንደሚያደርጉት ረብ የለሽ ድግግሞሽ አታድርግ፤ አሕዛብ በንግግራቸው ብዛት ምክንያት የሚሰሙ ይመስላቸዋልና፡፡ 8 ስለዚህ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤ እናንተ ከመለመናችሁ በፊት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ አባታችሁ ያውቃልና፡፡ 9 እንግዲህ እንደዚህ ጸልዩ፡- ‹በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ፡ 10 መንግሥትህ ትምጣ፡፡ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን፡፡ 11 የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፡፡ 12 በደላችንን ይቅር በለን፣ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፡፡ 13 ወደ ፈተና አታግባን፣ ከክፉው አድነን እንጂ፡፡› [መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም የአንተ ነውና፣ ለዘላለም፣ አሜን፡፡] 14 የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ብትሉ፣ የሰማይ አባታችሁ እናንተንም ይቅር ይላችኋል፡፡ 15 የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ካላላችሁ ግን፣ የሰማይ አባታችሁ የእናንተን ኀጢአት ይቅር አይልም፡፡ 16 ስትጾሙም ግብዞች እንደሚያደርጉት ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ እንደ ጾመኛ ለመታየት ግብዞች ፊታቸውን ያጠወልጋሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡ 17 አንተ ግን ስትጾም ራስህን ተቀባ፣ ፊትሀንም ታጠብ፣ 18 ይኸውም፣ በስውር ላለው የሰማይ አባትህ ብቻ እንጂ ለሰዎች ጾመኛ መስለህ እንዳትታይ ነው፡፡ በስውር የሚያይ የሰማይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡ 19 ብልና ዝገት በሚበላውና ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት በምድር ላይ ሀብትን ለራሳችሁ አታከማቹ፡፡ 20 ይልቁን ብልም ሆነ ዝገት በማያጠፋበት፣ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብትን ለራሳችሁ አከማቹ፡፡ 21 ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛልና፡፡ 22 ዐይን የሰውነት መብራት ነው፡፡ ስለሆነም ዐይንህ ጤናማ ከሆነ፣ መላ ሰውነትህ በብርሃን ይሞላል፡፡ 23 ዐይንህ ጤናማ ካልሆነ ግን፣ መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል፡፡ እንግዲህ በውስጥህ ያለው መብራት በእውነት ጨለማ ከሆነ፣ ጨለማው እንዴት ከባድ ይሆን 24 ! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡ 25 ስለዚህ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ ወይም ምን እንደምትጠጡ፡- ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን? 26 አየር ላይ የሚበርሩ ወፎችን ተመልከቱ! እነርሱ እህል አይዘሩም ወይም አያጭዱም፣ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ፣ የሰማይ አባታችሁ ይመግባቸዋል፡፡ ከወፎች ይልቅ እናንተ እጅግ የሚበልጥ ዋጋ ያላችሁ አይደላችሁምን? 27 ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ቀን መጨመር የሚችል ይገኛልን? 28 ስለ ልብስስ የምትጨነቁት ለምንድን ነው? 29 ነገር ግን እነግራችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ክብሩ ሁሉ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡ 30 እግዚአብሔር ዛሬ የሚታየውንና ነገ እሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንደዚህ ካለበሰ፣ እናንት እምነት የጐደላችሁ! እናንተንማ እንዴት እጅግ የበለጠ አያለብሳችሁም? 31 እንግዲህ ‹ምን እንበላለን?› ወይም ‹ምን እንጠጣለን?› ወይም ‹ምን እንለብሳለን?› ብላችሁ አትጨነቁ፡፡ 32 አሕዛብ እነዚህን ሁሉ ይፈልጋሉና፤ የሰማይ አባታችሁ እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል፡፡ 33 ነገር ግን በመጀመሪያ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ፤ ከዚያም እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡ 34 ስለዚህ ለነገ አትጨነቁ፤ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና፡፡ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል፡፡



Matthew 6:1

ማቴዎስ 6፡1-2

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ በ MAT 5:3ላይ የተጀመረውን የተራራው ስብከቱን ማስተማር ቀጥሏል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “የጽድቅን ተግባራት” የሆኑትን አስራት ማውጣት፣ ጸሎት እና ጾምን አስመልክቶ አስምሯል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “እናንተ” የሚለው ቃል ሁሉም በብዙ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ በሰዎች ለመታየት ለሰዎች ብለው የሚያደርጉ ሰዎች እርሱን እያከበሩት እንዳልሆነ በተዘዋዋር መልኩ ያመለክታል፡፡ ይህ እንዲህ ባለ መልኩ በቀጥታ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ስላደጋችሁት ነገር ሰዎች ያመሰግናችሁ ዘንድ በሰዎች ፊት የሚታደርጉት ከሆነ፡፡” ( እና ተመልከት) አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) ለራስህ መለከት አታስነፋ ይህ ምሳሌ የሚያሳየው የሰዎችን ትኩረት ሆን ብለህ ለመሳብ የተለያዩ ነገሮችን ማድረግ ነው፡፡ ኤቲ፡ “በብዙ ሰዎች መካከል መለከት በታላቅ ድምፅ እንደሚነፋ ሰው ወደ ራሰህ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ጥረት አታድረግ፡፡” ( ተመልከት) እውነት እልሃለሁ “እውነቱን እነግርሃለሁ”፡፡ ይህ ሀረግ ኢየሱስ በመቀጠል ስለሚናገረው ነገር አጽኖት የሚሰጥ ሀረግ ነው፡፡

Matthew 6:3

ማቴዎስ 6፡3-4

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ ኢየሱስ ስመ ስጦታ መስተማሩን ቀጥሏል፡፡ አጠቃላያ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር አመልከች ነው፡፡ ግራ እጅህ ቀኝ እጅህ የሚሰጠውን አይወቅ ይህ የሚታደርገው ነገር ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ምስጥር መሆን እንዳለበት የሚያሳይ ምሳሌ ነው፡፡ ምንም እንኳ ሁለቱም እጆች ብዙ ጊዜ ነገሮችን በጋራ የሚያከናውኑ ቢሆንም እንኳ፣ አንዱ የሚያደርገውን ሌላኛው “የሚያውቅ” ቢሆንም እንኳ ለድሆች በሚትሰጥበት ጊዜ እነዚህ በጣም የሚቀራረቡ እጆች እንኳ አንደኛው የሌላኛውን ማወቅ የለበትም፡፡ ( ተመልከት) ስጦታችሁ በድብቅ ይሁን ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ሌሎች ሰዎች መስጠትህ ሳያውቁ ለድሆች ልትሰጥ ትችላለህ፡፡” ( ተመልከት) ይሸልምሃል “ሽልማት ይሰጥሃል፡፡” (UDB)

Matthew 6:5

ማቴዎስ 6፡5-7

አያያዥ ዓረፍተ ነገሮች ኢየሱስ ስለ ጸሎት እንዲህ በማለት ማስተማር ጀመረ፡፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ በቁጥር 5 እና 7 ላይ “እናንተ” የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር አመልካች ቃል ሲሆን በቁጥር 6 ላይ ግን በነጠላ ቁጥር ተገልጾዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን በብዙ ቁጥር ልትተረጉመው ትችላለህ፡፡ ( ተመልከት) ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን ያዩላቸው ዘንድ በዚህ ሀረግ ውስጥ ተመልካቾቹ ድርጊቱን ተመልክተው ክብር እንደሚሰጧቸው በተዘዋዋር መንገድ ያሳያል፡፡ ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ሰዎች ያዮዋቸው እና ክብር ይሰጧቸው ዘንድ፡፡” ( እና ተመልከት) እውነት እውነት እላችኋለሁ “እውነቱን እነግራቿለሁ”፡፡ ይህ ሀረግ ኢየሱስ በመቀጠል ለመናገረው ነገረ ትኩርት እንዲንሰጥ ያደርገናል፡፡ ወደ እልፍኝህ ግባ፡፡ በርህንም ዝጋ “ለብቻ ወደምትሆንበት ሥፍራ ግባ” ወይም “ለብቻ መሆን ወደምትችልበት ሥፍራ ሂድ” በውስር ያለው አባት ለዚህ አማራጭ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔርን ማንም ሰው ማየት አይችልም ወይም 2) እግዚአብሔር በዚያ ለብቻው ከሚጸልየው ሰው ጋር አለ፡፡ አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) በስውር የሚታደርገውን የሚያይ አባት “አባትህ በስውር የሚታደርገውን ያያል” በከንቱ አትድገም “ትርጉም የሌሽ ቃላትን አትደጋግም” ይሰማል ይህ እንዲህ በቀላሉ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “የሐሰት አማልክቶች ይሰሟቸዋል፡፡” ( ተመልከት) ብዙ በመናገራቸው “በረጃጅም ጸሎቶቻቸው” ወይም “ በብዙ ቃሎቶቻቸው፡፡”

Matthew 6:8

ማቴዎስ 6፡8-10

አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “እንዲህ ጸልዩ” እስከሚለው ድረስ ለቡድን ተናግሯል፡፡ “እናንተ” ከሚለው ቀጥሎ ያለው “ሰማያዊ አባታችሁ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር ነው የተቀመጠው፡፡ (See: ተመልከት) አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) ስምህን ይቀደስ በዚህ ሥፍራ ላይ “ስም” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን የሚያመለክት ነው፡፡ ኤቲ፡ “ቅዱስ እንደሆንክ ሁሉም ሰው ይወቅት፡፡” ( ተመልከት) መንግስትህ ትምጣ በዚህ ሥፍራ “መንግስት” የሚለው ቃል እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ ሆኖ የሚገዛበትን የሚያመለክት ቃል ነው፡፡ ኤቲ፡ “በሁሉም ላይ ገዥ ሁን እና ሙሉ ለሙሉ ሁሉን ግዛ፡፡” ( ተመልከት) ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እዲሁም በምድር ላይ ትሁን ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “በሰማይ ያሉት ሁሉም እንደሚታዘዙህ ሁሉ በምድር ላይ ያሉት ሁሉ ይታዘዙህ፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 6:11

ማቴዎስ 6፡11-13

አጠቃላይ መረጃ “እኛ” እና “የእኛ” የሚሉት ቃላት ኢየሱስ እየተናገራቸው ያለውን የተሰበሰበውን ሕዝብ ያመለክታል፡፡ ( ተመልከት) የእለት እንጀራችንን በዚህ ሥፍራ ይ “እንጀራ” የሚለው ቃል በአጠቃላይ ምግብን ያመለክታል፡፡ ( ተመልከት) ብድር ብድር አንድ ሰው ያለበት ዕዳ ነው፡፡ ይህ ኃጢአትን በምሳሌ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነው፡፡ ( ተመልከት) ባለዕዳ ባለዕዳለ ከሌላ ሰው የተበደረ ሰው ነው፡፡ ይህ ኃጢአትን በምሳሌ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነው፡፡ ( ተመልከት) ወደ ፈተና አታግባን “ፈተና” የሚለው ቃል በግሥ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ምንም ነገር እንድፈትነን አትፍቀድለት” ወይም “ኃጢአትን እንድንመኝ የሚያደረግ ማንኛውንም ነገር ሕይወታችን ውስጥ አትፍቀድ፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 6:14

ማቴዎስ 6፡14-15

አጠቃላይ መረጃ “እናንተ” የሚለው ቃል የሚገኝበት ሥፍራ ሁሉ በብዙ ቁጥር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ሌሎች ሰዎችን ይቅር ካላሉ በግል ምን እንደሚደርስባቸው እየነገራቸው ነው፡፡ ተመልከት) መተላለፍ “ስህተት” ወይም “ኃጢአት” አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 6:16

ማቴዎስ 6፡16-18

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ስለ ጾም ማስተማር ጀመረ፡፡ አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ በቁጥር 17 አና 18 ላይ “አንተ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር የተገለጸ ሲሆን በቁጥር 16 ላይ ካለው ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን በብዙ ቁጥር ልትተረጉመው ትፈልግ ይሆናል፡፡ ( ተመልከት) በተጨማሪ “እንዲሁም” ፊታቸውን ያጎሳቁላሉ ግብዞች ፍታቸውን አይታጠቡም ወይም ጸጉራቸውን አያበጥሩም፡፡ ይህንን የሚያደርጉት ሆን ብለው እየጾሙ መሆናቸውን ለማሳየት የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ እና ከእነርሱ ክብር ለማግኘት ሲሉ ይህንን ያደርጋሉ፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፡፡” ይህ ሀረግ ኢየሱስ በመቀጠል ለሚናገረው ነገር ትኩረት መስጠቱን ያመለክታል፡፡ ራስህን ዘይት ተቀባ “ዘይት ተቀባ” ወይም “ጸጉርህን አበጥር”፡፡ ራስህን “ተቀባ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለጸጉር የተለመደውን እንክብካቤ ማድረግ ነው፡፡ “ከክርስቶስ” “የተቀባው” መሆኑ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ኢየሱስ ማለት የፈለገው ሰዎች ጾም እየጾሙም ሆነ ሳይጾሙ ተመሳሳይ መሆን አለባቸው ነው፡፡ በስውር ያለው አባት . . . በስውር የሚያይ ይህንን እንዴት በ MAT 6:6. እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 6:19

ማቴዎስ 6፡19-21

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ስለ ገንዘብ እና ንብረት ማስማር ጀመረ፡፡ አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “አንተ” የሚል ቃል ጥቅም ላይ በዋለባቸው ሥፍራዎች ከቁር 21 በስተቀር ብዙ ቁጥርን ያመለክታል፡፡ ይሁን እንጂ በቁትር 21 ላይ ነጠላ ቁጥር ነው፡፡ ( ተመልከት) ንብረት “ሀብት” ብል እና ዝገት የሚበሉት “ብል እና ዝገት የሚያበላሹት ሀብት” ብል ብል ልብስን የሚያበላሹ በራሪ ነፍሳት ናቸው፡፡ ዝገት ብረት ውሃ ሲነካው የሚፈጠር ቡናማ ቀለም ያለው ነገር ነው፡፡ store up for yourselves treasures in heaven This is a metaphor that means do good things on earth so God will bless you in heaven. በሰማይ ሀብትን አከማቹ ይህ ምሳሌ የሚያሳየው እግዚአብሔር በሰማይ ይበባርካችሁ ዘንድ በምድር ላይ ሳላቹ መልካምን ነገር አድርጉ፡፡ ( ተመልከት) ልብህም ደግሞ በዚያ ይሆናል በዚህ ሥፍራ ላይ “ልብ1 ማለት አሳብ እና ፍላጎት ማለት ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 6:22

ማቴዎስ 6፡22-24

አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “አንተ” የሚል ቃል ጥቅም ላይ በዋለባቸው ሥፍራዎች ውስጥ በነጠላ ቁጥር የተጠቀሰ ሲሆን አንተ ግን በብዙ ቁጥር ለመተርጎም ታስብ ይሆናል፡፡ ( ተመልከት) ዐይን የሰውነት ብርሃን ነች . . . ጨለማው ምን ያኽል ታላቅ ይሆን ይህ ማየት የሚችል ጤናማ ዐይንን አንድን ሰው ዐይነ ሥውር ከሚያደረግ በሽታ ጋር ያነነጻጽራል፡፡ ይህ ምሳሌ የሚያመለክተው መንፈሳዊ ጤንነትን ነው፡፡ ብዙ ጊዜ አይሁዳዊያን “መጥፎ ዐይንን” ከስስት ጋር ያይዙታል፡፡ ትርጉሙም አንድ ሰው ሁለተናውን ለእግዚአብሔር ከሰጠ እንዲሁም ሁሉንም ነገር ከእግዚአብሔር አንጻር መመልከት ከቻለ ትክክለኛውን ነገር ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው ስስታም ከሆነ ክፋትን ያደርጋል፡፡ ( ተመልከት) ዐይን የሰውነት ብርሃን ነው የዚህ ምሳሌያዊ ንግግር ትርጉም ልክ መብራት በጨለማ ውስጥ ሰው አጥርቶ እንዲያይ እንደሚያደርግ ሁሉ ዐይንም አንድ ሰው በደንብ ማየት እንዲችል ያደርገዋ፡፡ ኤቲ፡ “እንደ መብራት ዐይን ነገሮችን በግልጽ ማየት እንድትችል ያደርጋል፡፡” ( ተመልከት) ዐይን ይህንን በብዙ ቁጥር ልትተረጉመው ትችላለህ፤ “ዐይኖች”፡፡ ዐይንህ መጥፎ ቢሆን ይህ ምትሃትን አያመለክትም፡፡ አይሁዶች ብዙ ጊዜ ስስታምነትን በዚህ ምሳሌያዊ አነጋገር ይገልጹታል፡፡ ( ተመልከት) አንዱን ይወዳል ሌላኛውን ይጠላል ወይም ለአንዱ ይገዛል ሌላኛውን ደግሞ ይንቃል ሁለቱም በመሠረታዊ ሀሳባቸው አንድ ናቸው፡፡ አጽኖት የሚሰጡት አንድ ሰው እግዚአብሔር መውደድ እና መገዛት እንዲሁም ገንዘብንም መውደድና ለእርሱ መገዛት በአንድ ጊዜ አይችልመም፡፡ ( ተመልከት) ለሀብት እና ለእግዚአብሔር መገዛት አትችሉም፡፡ “በአንድ ጊዜ እግዚአብሔርን እና ገንዘብን መውደድ አትችሉም፡፡”

Matthew 6:25

ማቴዎስ 6፡25-26

እላችኋለሁ ይህ ኢየሱስ ከዚህ በመቀጠል የሚናገረው ነገር አጽኖት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ያሳያል፡፡ ለእናንተ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “እናንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ ( ተመልከት) ሕይወት ከመብል እንዲሁም ሰውነት ከልብስ አይበልጥምን? በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ ሰዎችን ለማሰተማር ጥያቄን ተጠቅሟል፡፡ ኤቲ፡ “በእርግጥ ሕይወት ከምግብ እንዲሁም አካል ከምንለብሰው ልብስ ይበልጣል፡፡” ( ተመልከት) ጎተራ እህል ማጠራቀሚያ ሥፍራ፡፡ አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) Are not you of much more value than they? Jesus uses a question to teach the people. AT: "Obviously you are more valuable than birds." አንተ ከእነርሱ ይልቅ በጣም ኩቡር አይደለህምን? ኢየሱስ ሰዎችን ለማስተማር ጥያቄን ይጠቀማል፡፡ ኤቲ፡ “ከሰማይ ወፎች ይልቅ አንተ ክቡር ነህ፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 6:27

ማቴዎስ 6፡27-29

አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “እናንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ ( ተመልከት) ከእናንተ መካከል በመጨነቅ በእድሜው ላይ ስንዝር ታኽል የጨመረ ማን ነው? ኢየሱስ ሰዎችን ለማስተማር ጥያቄን ይጠቀማል፡፡ ይህ ማለት ማንም በጭንቀት ረጅም እድሜ መኖር የሚችል የለም፡፡ ( ተመልከት) አንድ ክንድ “አንድ ክንድ” ከከግማሽ ሜትር ትንሽ የሚያንስ ነው፡፡በዚህ ሥፍራ ላይ ጥቅም ላይ የዋለው አንድ ሰው በእድሜው ላይ ምንም መጨመር እንደማይችል በምሳሌ ለመግለጽ ነው፡፡ ( እና ተመልከት) ስለምትለብሱት ነገር ስለምንት ትጨነቃላችሁ? ኢየሱስ ሰዎችን ለማስተማር ጥያቄን ይጠቀም ነበረወ፡፡ ኤቲ፡ “ምን እለብሳለሁ ብላችሁ አትጨነቁ፡፡” ( ተመልከት) ስለአንድ ነገር ማሰብ “መጨነቅ” አበቦች የሜዳ አበቦች ( ተመልከቱ) እላችኋለሁ ይህ ኢየሱስ ከዚህ በመቀጠል የሚናገረው ነገር አጽኖት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ያሳያል፡፡ ማንም እንደነዚህ አግጦ አያውቅም ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እንደነዚህ የሜዳ አበቦች ያጌጠ ልብስ ማንም ለብሶ አያውቅም፡፡”

Matthew 6:30

ማቴዎስ 6፡30-31

አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ “እናንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር የተገለጸ ነው፡፡ እነዚህ ሣሮች እንደዚህ ካለበሳቸው ይህ ምሳሌ እግዚአብሔር አበቦችን እንዲህ ውብ ካደረጋቸው ማለት ነው፡፡ ( ተመልከት) ሣር በቋንቋችሁ ሣር የሚለው ቃል የሚያካትት እና ከከዚህ በፊት የሜዳ አበባዎች ተብሎ የተተረጎመውን የሚያካትት ከተገኘ ያንን ቃል ተጠቀም፡፡ ወደ ማቃጠያ እቶን የሚጣለውን አይሁዳዊያን ምግባቸውን ለማብሰል ሣርን ይጠቀማሉ፡፡ ይህ በቀጥታ እንዲህ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ወደ ማቃጠያ ይጥለዋል” ወይም “አንድ ሰው እንዲቀጣል ያደርገዋል፡፡” ( ተመልከት) እናንተ ምን አያለብሳችሁም . . . እምነት? ኢየሱስ ሰዎችን ለማስተማር ጥያቄን ይጠቀም ነበር፡፡ ኤቲ፡ “በእርግጠኝነት ያለብሳችኋል . . . እምነት፡፡” ( ተመልከት) እናንተ እምነት የጎደላችሁ “እናንተ ትንሽ እምነት ያላችሁ፡፡” በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት በጣም ትንሽ ከመሆኑ የተነሳ ኢየሱስ ሰዎችን ይገስጻቸዋል፡፡ ስለዚህ “እነዚህ ሁሉ ምክንቶች”

Matthew 6:32

ማቴዎስ 6፡32-34

አሕዛብም እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይፈልጋሉ “አሕዛብም ነገ ምን እንደሚበሉ፣ እንደሚጠጡ እና እንደሚለብሱ ይጨነቃሉ፡፡” በሰማይ ያለው አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ያውቃል ኢየሱስ በዚህ ንግግሩ ውስጥ በተዘዋዋር መልኩ የሚያስረግጠው ነገር መሠረታዊ ፍላጎቶቻችሁ በእግዚአብሔር በእርግጠኝነት ይሟላሉ፡፡ አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) በመጀመሪያ መግስቱን እና ጽድቁን ፈልጉ በዚህ ሥፍራ ላይ “መንግስቱ” የሚለው ቃል እግዚብሔር እንደ ንጉሥ መግዛቱን የሚያመለክት ነው፡፡ ኤቲ፡ “ንጉሥ የሆነውን እግዚአብሔርን አገልግል እንዲሁም መልካም የሆነውን ነገር አድርግ፡፡” ( ተመልከት) እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይጨመሩልሃል ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር እነዚህ ነገሮች ያዘጋጅልሃል፡፡” ( ተመልከት) ስለዚህ “በእነዚህ ሁሉ ምክንቶች” tomorrow will be anxious for itself Jesus is describing "tomorrow" as if it is a person that can worry. Jesus means that a person will have enough to worry about when the next day comes. ነገ ስለራሱ ይጨነቅ በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ “ነገን” ልክ እንደ ሰው የሚጨነቅ አድርጎ ያቀርበዋል፡፡ ኢየሱስ አንድ ሰው ነገ ስመጣ በዚያ ቀን በቂ የሚጨነቅበት ነገር አለው ማለቱ ነው፡፡ ( ተመልከት) ለዛሬ የራሱ ክፋት ይበቃዋል “እያንዳንዱ ቀን በውስጡ በቂ የሆነ ክፋትን ይዟል” ወይም “ሁሉም ቀናት በቂ ችግሮች አሏቸው”


Translation Questions

Matthew 6:1

ጽድቃቸው በሰው ፊት እንዲታይላቸው የሚያደርጉ ሰዎች ዋጋ ምንድነው?

ጽድቃቸው በሰው ፊት እንዲታይላቸው የሚያደርጉ ሰዎች የሰዎችን ምስጋና መቀበል ዋጋቸው ይሆናል። [6:2]

Matthew 6:3

አብ ዋጋችንን እንዲሰጠን ጽድቃችን ምን መምሰል አለበት?

ጽድቃችንን በስውር ማድረግ ይኖርብናል። [6:3]

አብ ዋጋችንን እንዲሰጠን ጽድቃችን ምን መምሰል አለበት?

ጽድቃችንን በስውር ማድረግ ይኖርብናል። [6:4]

Matthew 6:5

በሰዎች ለመታየት ሲሉ በግብዝነት የሚጸልዩት ምን ዋጋ ይቀበላሉ?

በሰዎች ለመታየት ሲሉ በግብዝነት የሚጸልዩ ዋጋቸውን ከሰዎች ይቀበላሉ። [6:5]

በስውር የሚጸልዩ ዋጋቸውን የሚቀበሉት ከማን ነው?

በስውር የሚጸልዩ ዋጋቸውን የሚቀበሉት ከአብ ነው። [6:6]

ከንቱ ድግግሞሽን በማድረግ ልንጸልይ የማይገባን ለምን እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ?

ከንቱ ድግግሞሽን በማድረግ ልንጸልይ እንደማይገባን ኢየሱስ የተናገረው አብ የሚያስፈልገንን ሳንጠይቀው ስለሚያውቀው ነው። [6:7]

Matthew 6:8

ፈቃዱ የት እንዲፈጸም ነው አብን ልንጠይቀው የሚገባን?

ፈቃዱ በሰማይ እንደሆነች፣ እንዲሁም በምድር እንድትሆን አብን ልንጠይቅ ይገባናል። [6:10]

Matthew 6:14

የሌሎችን እዳ የማንተው ከሆነ፣ አብ ምን ያደርጋል?

የሌሎችን እዳ የማንተው ከሆነ፣ እግዚአብሔርም የእኛን አይተውልንም። [6:15]

Matthew 6:16

ከአብ ዋጋን እንድንቀበል ልንጾም የሚገባን እንዴት ነው?

እንደምንጾም ለሰዎች ሳንታይ ልንጾም ይገባናል፣ ከዚያም አብ ዋጋ ይከፍለናል። [6:16]

ከአብ ዋጋን እንድንቀበል ልንጾም የሚገባን እንዴት ነው?

እንደምንጾም ለሰዎች ሳንታይ ልንጾም ይገባናል፣ ከዚያም አብ ዋጋ ይከፍለናል። [6:17]

Matthew 6:19

መዝገባችንን እንድናኖር የሚገባን የት ነው፣ ለምን?

ከዚያ ሊጠፋ ወይም ሊሰረቅ ስለማይችል መዝገባችንን በሰማይ ልናኖር ይገባናል። [6:19]

መዝገባችንን እንድናኖር የሚገባን የት ነው፣ ለምን?

ከዚያ ሊጠፋ ወይም ሊሰረቅ ስለማይችል መዝገባችንን በሰማይ ልናኖር ይገባናል። [6:20]

መዝገባችን ባለበት የሚገኘው ነገር ምንድነው?

መዝገባችን ባለበት ልባችን ይኖራል። [6:21]

Matthew 6:22

ከሁለት አንዳቸውን የምንመርጣቸው ሁለት ጌታች ምን እና ምን ናቸው?

ጌታችን ልናደርግ ከሁለት አንዳቸውን የምንመርጣቸው እግዚአብሔር ወይም ብልጥግና ናቸው። [6:24]

Matthew 6:25

ስለምንበላው፣ ስለምንጠጣው እና ስለምንለብሰው ልንጨነቅ የማይገባን ለምንድነው?

ስለ ምግብ፣ መጠጥ እና ልብስ መጨነቅ የሌለብን ለወፎች ግድ የሚለው አብ ከእነርሱ አብልጦ ለእኛ ግድ ስለሚለው ነው። [6:25]

ስለምንበላው፣ ስለምንጠጣው እና ስለምንለብሰው ልንጨነቅ የማይገባን ለምንድነው?

ስለ ምግብ፣ መጠጥ እና ልብስ መጨነቅ የሌለብን ለወፎች ግድ የሚለው አብ ከእነርሱ አብልጦ ለእኛ ግድ ስለሚለው ነው። [6:26]

Matthew 6:27

ተጨንቀን ልናደርግ እንደማንችል ኢየሱስ ያስታወሰን ምንን ነው?

በእድሜያችን ላይ ተጨንቀን አንዲት ሰዓት ልንጨምር እንደማንችል ኢየሱስ አስታውሶናል። [6:27]

Matthew 6:32

አስቀድመን ልንሻው የሚገባን፣ ከዚያም ምድራዊ ፍላጎቶቻችን ሁሉ የሚጨመሩልን ምንድነው?

አስቀድመን የእግዚአብሔርን መንግሥት እና ጽድቅ ስንሻ፣ ከዚያም ምድራዊው ነገር ሁሉ ይጨመርልናል። [6:33]


ምዕራፍ 7

1 አትፍረዱ፥ እናንተም አይፈረድባችሁም። 2 በምትፈርዱበት ፍርድ፥ ይፈረድባችኋል፤በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ፥ ለእናንተም ይሰፈርላችኋል። 3 በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታስተውል፥ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ የምታየው ለምንድን ነው? 4 በአንተ ዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ፣ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ ማለት እንዴት ትችላለህ? 5 አንተ ግብዝ! በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ በደንብ አይተህ ለማውጣት፣ በመጀመሪያ በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ አስወግድ። 6 በእግራቸው እንዳይረግጡትና እናንተንም እንዳይቦጫጭቁዋችሁ፤ ቅዱስ የሆነውን ለውሾች አትስጡ፥ እንቁዎቻችሁንም ለዐሳማዎች አትጣሉ። 7 ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፥ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል። 8 የሚለምን ሰው ሁሉ ይቀበላልና፣ የሚፈልግ ሰውም ያገኛል፥ ለሚያንኳኳም ሰው ይከፈትለታል። 9 ከእናንተ መካከል ልጁ እንጀራ ሲለምነው፣ ድንጋይ የሚሰጠው፣ 10 ዐሣ ሲለምነው፣ እባብ የሚሰጠው? ምን ዐይነት ሰው ነው? 11 እንግዲህ፥ እናንተ ክፉዎች የሆናችሁ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ የሚኖር አባታችሁ ለሚለምኑት አብዝቶ መልካም ስጦታን እንዴት አይስጣቸውም? 12 ስለዚህ፣ ማንኛውንም ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፣ እናንተም ልታደርጉላቸው ይገባል፤ ምክንያቱም ሕጉም ነቢያቱም የሚያስተምሩት ይህንኑ ነው፡፡ 13 በጠባቡ በር ግቡ፣ ምክንያቱም ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ሰፊ፣ የሚሄዱበትም ብዙዎች ናቸው፡፡ 14 በሩ ጠባብ፣ ወደ ሕይወት የሚወስደውም መንገድ ቀጭን ስለ ሆነ፣ የሚያገኙት ጥቂቶች ናቸው፡፡ 15 የበግ ቆዳ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፣ በትክክል ግን ነጣቂ ተኩላዎች ከሆኑ፣ ከሃሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ። 16 በሚያፈሩት ፍሬ ታውቋቸዋላችሁ፡፡ሰው ከእሾኽ የወይን ፍሬ፣ ወይም ከኩርንችት በለስ ሊሰበስብ ይችላልን? 17 እንደዚያው፥ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፣ መጥፎ ዛፍ መጥፎ ፍሬ ያፈራል። 18 መልካም ዛፍ ሆኖ መጥፎ ፍሬ የሚያፈራ፣ ወይም መጥፎ ዛፍ ሆኖ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም። 19 ማንኛውም መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፣ ወደ እሳትም ይጣላል። 20 እንግዲህ በሚያፈሩት ፍሬ ታውቋቸዋላችሁ። 21 በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እንጂ፣" ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣" እያለ የሚጠራኝ ሁሉ፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባ አይደለም፡፡ 22 በዚያ ቀን ብዙዎች፣ "ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣ በስምህ ትንቢት ተናግረን አልነበረም እንዴ፣ በስምህ አጋንንት አስወጥተን አልነበረም እንዴ፣ በስምህስ ብዙ ታላላቅ ነገሮችን አድርገን አልነበረም እንዴ?" ይሉኛል፡፡ 23 እኔም፣ “እናንት ክፉ አድራጊዎች፣ የት ዐውቃችሁና ነው? ከእኔ ራቁ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ” 24 ስለዚህ፣ ቃሎቼን የሚሰማና የሚታዘዛቸው ልክ ቤቱን በድንጋይ ላይ የመሠረተ አስተዋይ ሰውን ይመስላል፡፡ 25 ዝናብ ዘነበ፣ ጎርፍም ጎረፈ፣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት መታው፤ ይሁን እንጂ ቤቱ በዐለት ላይ ስለ ተመሠረተ፣ አልወደቀም፡፡ 26 ሆኖም ቃሌን ሰምቶ የማይታዘዝ፣ ቤቱን በአሸዋ ላይ የመሠረተ ሞኝ ሰውን ይመስላል፡፡ 27 ዝናብ ዘነበ፣ ጎርፍ ጎረፈ፣ ነፋስም ነፈሰ፣ ያንንም ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም ከባድ ሆነ ። 28 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ተናግሮ ሲጨርስ፣ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡ 29 ያስተማረውም እንደ ባለስሥልጣን እንጂ ፣እንደ ጽሐፍት አልነበረም።



Matthew 7:1

ማቴዎስ 7፡1-2

አያያዥ ዓረፍተ ነገር፡ በ in MAT 5:3 በተጀመረው የተራራው ስብከት ውስጥ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “እናንተ” የሚለው ቃል እና የተሰጡት ትዕዛዛት በብዙ ቁጥር ተገልጸዋል፡፡ ( ተመልትከት) አትፍረድ በዚህ ሥፍራ ላይ “አትፍረድ” የሚለው ቃል ጠንከር ያለ “ጠንከር ያለ ማውገዝን” ወይም “ጥፋተኛ አድርጎ መወሰንን” የሚያመለክት ቃል ነው፡፡ ኤቲ፡ “በሰዎችን ላይ አትፍረድ”፡፡ ( ተመልከት) አይፈረድብህም ይህ በግልጽ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “መጥፎ ፍርድ አይፈረድብህም፡፡” ( ተመልከት) Be sure the reader understands the statement in 7:2 is based on what Jesus said in 7:1. ምክንያቱም ኢየሱስ በ7፡2 ላይ የተናገረው ንግግር መሠረቱ በ7፡1ላይ የተናገረው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ፡፡ በፈረዳችሁት ፍርድ እናንተም ላይ እንዲሁ ይፈረዳል ይህ በዚህ መልኩ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “በሌሎች ሰዎች ላይ በፈረዳችሁበት መጥን ልክ እናንተም ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል፡፡” ( ተመልከት) በዚያው ልክ ይፈረዳል ይህ እንዲህ በቀጥታ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር በዚያው ልክ ይፈርዳል፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 7:3

ማቴዎስ 7፡3-5

አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “እንተ” የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር ተገልጸዋል ይን እንጂ በብዙ ቁጥር ልትተረጎማቸው ትችላለህ፡፡ ስለምን ታያለህ . . . እንዴትስ ትለዋለህ ኢየሱስ እነዚህን ሁሉት ጥያቄዎች የተጠቀመው ሰዎችን ለማስተማር እና አመለካከታቸውን እንደገና ይመለከቱት ዘንድ ነው፡፡ የሌሎች ሰዎች ኃጢአት ላይ ጣታቸውን ከመቀሰራቸው በፊት ለራሳቸውን ኃጢአት ትኩረት መስጠት ስለፈለገ ነው፡፡ ( ተመልከት) በጣም ትንሽ ብናኛ “ቆሻሻ”(UDB) ወይም “ብናኝ” ወይም “አፈር”፡፡ ወደ ሰዎች ዐይን ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚገባን ነገር ለመግለጽ የሚትጠቀሙትን ቃል ተጠቀም፡፡ ይህ በሰዎች ውስጥ የሚያጋጥምም በጣም ትንሹን ስህተትን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋ ምሳሌ ነው፡፡ ( ተመልከት) ወንድም ይህ የሥጋ ወንድምን ወይም ጎረቤትን ሳይሆን አማኝን የሚያመለክት ነው፡፡ ምሰሶ አንድ ሰው በቆረጠው ዛፍ ውስጥ የሚገኘው ትልቁ ክፍል ምሰሶ ነው፡፡ ይህ ወደ ሰዎች ዐይን ለመግባት በጣም ትልቅ የሆነ ግንድ ነው፡፡ ይህ በሰው ሕይወት ውስጥ ያለ በጣም ትልቅ ስህተትን ያሳያል፡፡ እና ተመልከት)፡፡

Matthew 7:6

ማቴዎስ 7፡6-6

አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “እናንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር ተገልጸዋል፡፡ ውሾች . . . እሪያዎች አይሁዶች እነዚህ እንስሳት ቆሻሾች አድርገው ይቆጥሯቨዋል እንዲሁም እግዚአብሔርም እነዚህን እንስሳት እንዳይበሉ አዞዋቸዋል፡፡ ይህ ቅዱስ ለሆነው ነገር ዋጋ የማይሰጡ ኃጢአተኛ ሰዎችን ለማመልከት የቀረበ ምሳሌያዊ አነጋገር ነው፡፡ ይህንን ቃል በቁሙ መተርጎሙ ባጣም ጥሩ ነው፡፡ ( ተመልከት)፡፡ እንቁዎች እነዚህ በጣም ትንንሽ፣ ውድ የሆኑ ድንጋዮች ናቸው፡፡ ይህ ስለእግዚአብሔር ወይም ስለውድ ነገሮች በአጠቃላይ ማወቅ ጋር ተያያዥነት ያለው ምሳሌያዊ ንግግር ነው፡፡ ( ተመልከት) በእግሮቻቸው ልረጋግጡት ይችላሉ “እሪያዎቹ ይረጋግጡታል” እናም ወደ ትፋታቸው ይመለሳሉ “እናም ውሾች ወደ ትፋታቸው ይመለሳሉ”

Matthew 7:7

ማቴዎስ 7፡7-10

አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “እንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር ተገልጸዋል፡፡ ( ተመልከት)፡፡ ጠይቁ . . . ፈልጉ . . . አንኳኩ ይህ ወደ እግዚአብሔር መጸለይን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ምሳሌያዊ ንግግር ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ግሥ እግዚአብሔር ምላሽ እስኪሰጠን ድረስ እንዲንጸለይ የሚያደርግ ነው፡፡ በቋንቋችሁ አንድን ነገር መልሳችሁ መልሳችሁ ማድረግ እንዳለባችሁ የሚገልጽ ቃል ካለ ይህንን ቃል ተጠቀሙ፡፡ ( ተመልከት) ጠይቁ ይህ ከእግዚአብሔር የሆነ ነገርን ጠይቁ ማለት ነው፡፡ (UDB) ይሰጣችኋል ይህ እንዲህ ባለ መልኩ በቀጥታ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “የሚያስፈልጋችሁን ነገር እግዚአብሔር ይሰጣችኋል፡፡ ( ተመልከት) ፈልጉ “ስለምትፈልጉትን ነገር የእግዚአብሔርን ፊት ፈልጉ” አንኳኩ በር ማንኳኳት በቤት ውስጥ ያለ ሰው በሩን እንዲከፍትላችሁ በትህትና መጠየቅ ነው፡፡ በእናንት ባሕል ውስጥ በር ማንኳኳት ትህትና ካልሆነ ሰዎች በእናንተ ባሕል ውስጥ በር እነንዲከፈትላቸው በትህትና የሚጠይቁ በምን ዓይነት መንገድ ነው፣ ይህንንም ቃል ተጠቀሙ፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር በሩን እንዲከፍትላችሁ እንደሚትልጉ ንገሩት፡፡” ወይም ከእናንተ መካከል ማን ነው . . . ድንጋይ? ኢየሱስ ሰዎችን ለማስተማር ጥያቄን ይጠቀማል፡፡ ኤቲ፡ “ከእናንተ መካከል ማንም የለም . . . ድንጋይ፡፡” ( ተመልከት) ቁራጭ ዳቦ ይህ በአጠቃላይ ምግብን ያመለክታል፡፡ ኤቲ፡ “የሆነ ምግብ፡፡” ( ተመልከት) ድንጋይ. . . ዓሳ . . . እባብ እነዚህ ስሞች በቁማቸው መተርጎም አለባቸው፡፡ ወይም ኣሳ ጠይቋችሁ እባብ የምትሰጡት? ኢየሱስ ለማስተማር ሌላ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡ በዚህ ሥፍራም ኢየሱስ ስለ ሰውዬው እና ልጁ እየተናገረ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ከእናንተ መካከል ልጁ ዓሳ ጠይቆት እባብ የሚሰጠው ማንንም የለም፡፡” ( እና ተመልከት)

Matthew 7:11

ማቴዎስ 7፡11-12

አጠቃላይ መረጃ ኢየሱስ በቡድን ለሚያደምጡ ሰዎች በግለሰብ ደረጃ ምን እንደሚያጋጥማቸው በመናገር ላይ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “እንተ” የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር ተገልጸዋል፡፡ ( ተመልከት)፡፡ በሰማይ ያለው አባታችሁ አስበልጦ ምን ያኽል አይሰጣችሁ . . . አርሱ? በዚህ ሥፍራ ኢየሱስ ሕዝቡን ለማስተማር ጥየቄን ተጠቀሟል፡፡ ኤቲ፡ “በሰማይ ያለው አባታችሁ በእርግጠኝነት ይሰጠዋል . . . እርሱ፡፡” ( ተመልከት) አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) ሰዎችን እንዲያደርጉላችሁ የሚትፈልጉትን ነገር ሁሉ “ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የሚትልጉትን ነገር ሁሉ” (UDB) ሕግ እና ነቢያት እነዚህ ናቸው በዚህ ሥፍራ ላይ “ሕግ” እና “ነቢያት” የሚለው ቃል ሙሴ እና ነቢያት የጻፏቸወ መጽሐፍትን ያመለክታል፡፡ ኤቲ፡ “ይህ ሙሴ እና ነቢያት የጻፉጽ ስለዚህ ጉዳይ ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 7:13

ማቴዎስ 7፡13-14

አጠቃላይ መረጃ፡ ስለ ሁለቱ በሮች እና መንገዶች አጽኖት መስጠት ያስችለ ዘንድ ስትተረጉም “ሰፍ” የሚለው ቃል “ጠባብ” ከሚለው በተቻለ መጠን የሚለይ መሆኑን አሳይ፡፡ በጠባቢ በር ግቡ . . የሚገኙት ጥቂቶች ናቸው ይህ በመንገድ ላይ የሚሄድ እና ወደ መንግስቱ በበር የሚገባ ሰው ምስል ነው፡፡ ወደ አንደኛው መንግስት መግባት ቀላል ሲሆን ወደሌላኛው መንግስት መግባት ግን ከባድ ነው፡፡ ይህ ሰዎች የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት ሰዎች ከባድ የሆነውን በሕይወታቸው እግዚአብሔርን መታዘዝ መቀበል እንደሚኖርባቸው ለማሳየት የቀረበ ምሳሌ ነው፡፡ እግዚአብሔር የተመታዘዝ ቀላሉን መንገድ ከመረጡ ወደ ስኦል ይገባሉ፡፡ ( ተመልከት) በጠባቢ በር ግቡ ይህንን ወደ ቁጥር 14 መጨረሻ ልትወስዱት ትችላላችሁ፡ “ስለዚህ በጠባቡ በር ግቡ”፡፡ በር . . . መንገድ አማራጭ ትርጉሞች 1) ይህ ወደ መንግስቱ መግቢያ በር እና ወደ በሩ የሚወስድ መንገድን ያመለክታል፡፡ ይህ ከሆነ በUDB ላይ ያለውን ቅደም ተከተል ልታለዋውጠው ትችላለህ፡፡ ወይም 2) “በር” እና “መንገድ” ሁለቱም የመንግስቱ መግቢያነ ናቸው፡፡ ይህ ከሆነ ቅደም ተከተሉን ማለዋወጥ አይኖርብህም፡፡ ( ተመልከት) ወደ ጥፋት . . . ወደ ሕይወት እነዚህ በግስ ልተረጎሙ ይችላሉ፡፡ ኤቲ፡ “ወደምትሞቱበት ሥፍራ . . . በሕይወት ወደሚትኖርቡት ሥፍራ” ( ተመልከት)

Matthew 7:15

ማቴዎስ 7፡ 15-17

ተጠንቀቁ “ራሳችሁን ጠብቁ” የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ ነገር ግን ተኩላዎች ከሆኑ ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር መልካም እና መርዳት የሚፈልጉ መስለው የሚመጡ ነገር ግን ክፉ የሆኑ እና ከሚጎዷችሁ ሐሰተኛ ነቢያት ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ( ተመልከት) በፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ይህ ምሳሌዊ ንግግር የሰውን ተግባር የሚያመለክት ነው፡፡ ኤቲ፡ “ዘፍ በፍሬው እንደሚታወቅ ሁሉ ሐሰተኛ ነቢያት በሥራቸው ይታወቃሉ፡፡” ( ተመልከት) ሰዎች ከኩርንችት. . . ይለቅማሉን ኢየሱስ ጥየቄን ሰዎችን ለማስተማር ተጠቅሟል፡፡ ሰዎች ለዚህ ጥያቄ ምላሱ አይ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡ ኤቲ፡ “ሰዎች ከኩርንችት . . . አይለቅሙም፡፡” ( ተመልከት) መልካም ዛፉ ሁሉ መልካ ፍሬን ያፈራል ኢየሱስ የፍሬን ምሳሌ በመጠቀም ጥሩ ሥራ ወይም ቃል ስለሚያመጡ ስለጥሩ ነቢያት መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ( ተመልከት) የተበላሸ ዘፍ መጥፎ ፍሬ ያፈራል ኢየሱስ የፍሬን ምሳሌ በመጠቀም መጥፎ ሥራ ስለሚሠሩ መጥፎ ነቢያት መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 7:18

ማቴዎስ 7፡18-20

መልካምን ፍሬ የማያፈራውን ዘፍ ይቆረጣል እንዲሁም ወደ እሳት ይጣላል ኢየሱስ የፍሬውን ምሳሌ ሐሰተኛ ነቢያትን ለማመልከት ተጠቅሞዋል፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ በመጥፎ ዛፍ ላይ ምን እንደሚሆን ብቻ ተናግሯል፡፡ ይህ በተዘዋዋር መንገድ የሚያሳየው በሐሰተኛ ነቢያት ላይ ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ( እና ተመልከት) ይቆረጣል፣ ወደ እሳትም ይጣላል ይህ በዚህ መንገድ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ይቆርጡትና ያቃጥሉታል፡፡ “ ( ተመልከት) በፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ “እነርሱን” የሚለው ቃል ነብያቱን ወይም ዛፎቹን ሊያመለክት ይችላል፡፡ የዛፉ ፍሬ እና የነቢያቱ ድርጊት የሁለቱም መልካ ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡ ከተቻለ ከሁለቱ አንዱን በሚያመለክት መልኩ ተርጉሙት፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 7:21

ማቴዎስ 7፡ 21-23

ወደ መንግስተ ሰማያት ይገባል በዚህ ሥፍራ ላይ “መንግስት” የሚለው ቃ እግዚአብሑር እንደ ንጉሥ መግዛቱን ያመለክታል፡፡ “መንግስተ ሰማያት” በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነው፡፡ ከተቻለ “ሰማይ” የሚለውን ቃል በትርጉማችሁ ውስጥ ለማኖር ጥረት አድርጉ፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ራሱን እንደ ንጉሥ በሚገልጥበት ጊዜ በሰማይ ከእግዚአብሔር ጋር ይኖራል፡፡” ( ተመልከት) የአባቴን ፈቃድ የሚያደረግ ማንኛውም ሰው “የአባቴን ፍላጎት የሚፈጽም ማንም ሰው” አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) በዚያ ቀን ኢየሱስ “በዚያ ቀን” በማለት የተናገረው አድማጮቹ በዚያ ቀን የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው የፍርድ ቀንን እንደሆነ እንደሚገባቸው ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡ አንባቢዎቻችሁ በግልጽ በዚያ ቀን የሚለው ሀረግ ትንቢት አልተናገርንምን . . . ሴጣንን አላወጣንምን . . . ብዙ ተዓምራትን አላደረግንምን? ሰዎች እነዚህ ነገሮች ማድረጋቸው ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ኤቲ፡ “ትንቡትን ተናግረናል . . . ሴጣንን አስወጥተናል . . . ታላላቅ ተዓምራን አድርገናል፡፡” ( ተመልከት) እኛ ይህ “እኛ” የሚለው ቃ ኢየሱስን አያካትትም፡፡ ( ተመልከት) በስምህ በዚህ ሥፍራ ላይ “በስምህ” የሚለው ቃል በኢየሱስ ስልጣን እና ስም” ማት ነው፡፡ ( ተመልከት) ታላላቅ ነገሮችን “ተዓምራትን” አላውቃችሁም ይህ ማለት ይህ ሰው የኢየሱስ አይደለም ማለት ነው፡፡ ኤቲ፡ “አንተ የእኔ ተከታይ አይደለህም” ወይም “ከአንተ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 7:24

ማቴዎስ 7፡24-25

ስለዚህ “በዚህ ምክንያት” ቃሎቼ በዚህ ሥፍራ ላይ “ቃሎቼ” የሚለው ቃል ኢየሱስ የተናገራውን ቃላት ያመለክታል፡፡ ( ተመልከት) በዓለት ላይ ቤትን የሠራን ጠቢብ ሰው ይመስላሉ ኢየሱስ የእርሱን ቃል የሚጠብቁ ሰዎችን ምንም ነገር ልጎዳው በማይችል መሠረት ላይ ቤታውን ከሠሩ ሰዎች ጋር ያነጻጽራል፡፡ ( ተመልከት) ዓለት ይህ በመሬት የላይኛው ክፍል ላይ ከመገኘው አፈር እ አሸዋ ቀጥሎ የሚገኝ ነው፡፡ በዚህ ላይ ቤቱን የገነባ ይህ በቀጥታ እንዲህ ልገለጽ ይገባል፡፡ ኤቲ፡ “የገነባው” ( ተመልከት)

Matthew 7:26

ማቴዎስ 7፡26-27

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ በ MAT 5:3. የተጀመረው የኢየሱስ የተራራው ስብከት መጨረሻ ነው፡፡ ሞኝ ሰው ቤቱን በአሸዋ ላይ ይሠራል ኢየሱስ ከዚህ በፊት ያቀረበውን ንጽጽር ቀጥሏል፡፡ ትዕዛዛቱን ያልታዘዙ ሰዎችን ቤታቸውን በአሸዋ ላይ ከሠሩ ሞኝ ሰዎች ጋር አነጻጽሯል፡፡ ቤቱን ዝናብ፣ ጎርፍ እና አውሎ ንፋስ ልያጠፋው በሚችል አሸዋማ መሬት ላይ የሚሠራ ሞኝ ሰው ብቻ ነው፡፡ ( ተመልከት) ወደቀ በቋንቋችሁ አንድ ቤት መውደቁን ለመግለጽ የሚትጠቀሙትን የተለመደ ቃል በዚህ ሥፍራ ላይ ተጠቀሙ፡፡ ጥፋቱ እጅግ በጣም የከፋ ይሆናል ዝናቡ፣ ጎር እና አውሎ ንፋሱ ቤቱን ፈጽሞ ያጠፋዋል፡፡

Matthew 7:28

ማቴዎስ 7፡ 28-29

አጠቃላይ መረጃ እነዚህ ቁጥሮች ኢየሱስ በተራራው ስብከት ውስጥ ስላስተማራቸው ትመህርቶች የሰጠውን ምላሽ ምን ይህንን ከፈጸመ በኋላ ይህ ሀረግ የተራራው ስብከት መጨረሻ ለመሆኑ ምልክት ነው፡፡ ኤቲ፡ በመጨረሻውም” በትምህርቱ እጅግ በጣም ተገረሙ በ7፡29 ላይ ኢየሱስ ባስተማረው ትምህርት ብቻ ሳይሆን ባስተማረበት መንገድም እንደተገረሙ በግልጽ ማየት ይቻላል፡፡ ኤቲ፡ “በማስተማር ዘዴውም እጅግ በጣም ተገረሙ፡፡”


Translation Questions

Matthew 7:3

ወንድማችንን ለመርዳት በግልጽ ከማየታችን በፊት አስቀድመን ልናደርግ የሚገባን ነገር ምንድነው?

ራሳችንን መፈተሽ እና ወንድማችንን ከመርዳታችን በፊት በዐይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ ልናስወግድ ይገባናል። [7:3]

ወንድማችንን ለመርዳት በግልጽ ከማየታችን በፊት አስቀድመን ልናደርግ የሚገባን ነገር ምንድነው?

ራሳችንን መፈተሽ እና ወንድማችንን ከመርዳታችን በፊት በዐይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ ልናስወግድ ይገባናል። [7:4]

ወንድማችንን ለመርዳት በግልጽ ከማየታችን በፊት አስቀድመን ልናደርግ የሚገባን ነገር ምንድነው?

ራሳችንን መፈተሽ እና ወንድማችንን ከመርዳታችን በፊት በዐይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ ልናስወግድ ይገባናል። [7:5]

Matthew 7:6

ቅዱስ የሆነውን ለውሾች ከሰጣችሁ ምን ይሆናል?

ቅዱስ የሆነውን ለውሾች ከሰጣችሁ፣ ሊረግጡት እና ነክሰው ሊቦጫጭቋችሁ ይችላሉ። [7:6]

Matthew 7:7

ከአብ ለመቀበል ምን ልናደርግ ይገባናል?

ከአብ ለመቀበል ልንጠይቅ፣ ልንፈልግ እና ልናንኳኳ ይገባናል። [7:8]

Matthew 7:11

ለሚጠይቊት እግዚአብሔር ምን ይሰጣቸዋል?

እግዚአብሔር ለሚጠይቊት መልካም ነገሮችን ይሰጣቸዋል። [7:11]

ሌሎችን እንዴት እንድንቀርባቸው ነው ህግና ነብያት የሚያስተምሩን?

ሰዎች እንዲያደርጉልን እንደምንፈልግ እኛም እንድናደርግላቸው ህግ እና ነብያት ያስተምራሉ። [7:12]

Matthew 7:13

ሰፊው መንገድ የሚመራው ወደ ምንድነው?

ሰፊው መንገድ ወደ ጥፋት ያመራል። [7:13]

ሰፊው መንገድ የሚመራው ወደ ምንድነው?

ሰፊው መንገድ ወደ ጥፋት ያመራል። [7:14]

ጠባቡ መንገድ ወደ ምን ያመራል?

ጠባቡ መንገድ ወደ ሕይወት ያመራል። [7:14]

Matthew 7:15

ሐሰተኛ ነብያትን የምንለየው እንዴት ነው?

ሐሰተኛ አስተማሪዎችን የምንለያቸው በሕይወታቸው ፍሬ ነው። [7:15]

ሐሰተኛ ነብያትን የምንለየው እንዴት ነው?

ሐሰተኛ አስተማሪዎችን የምንለያቸው በሕይወታቸው ፍሬ ነው። [7:16]

Matthew 7:21

ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባው ማን ነው?

የአብን ፈቃድ የሚያደርጉት ወደ መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ። [7:21]

በስሙ ትንቢት ለተናገሩት፣ አጋንንትን ላወጡት እና ተዓምራትን ላደረጉት ብዙዎች ኢየሱስ ምን ይላቸዋል?

“ከቶ አላወቅኋችሁም! ከፊቴ ዘወር በሉ እናንተ ክፉዎች!” ይላቸዋል። [7:22]

በስሙ ትንቢት ለተናገሩት፣ አጋንንትን ላወጡት እና ተዓምራትን ላደረጉት ብዙዎች ኢየሱስ ምን ይላቸዋል?

“ከቶ አላወቅኋችሁም! ከፊቴ ዘወር በሉ እናንተ ክፉዎች!” ይላቸዋል። [7:23]

Matthew 7:24

ስለ ሁለቱ ቤቶች በተናገረው የኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ ልክ እንደ ብልኅ ሰው የሆነው ማነው?

የኢየሱስን ቃሎች ሰምቶ የሚታዘዛቸው ልክ እንደ ብልኅ ሰው ነው። [7:24]

Matthew 7:26

ስለ ሁለቱ ቤቶች በተናገረው የኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ ልክ እንደ ሰነፍ ሰው የሆነው ማነው?

የኢየሱስን ቃሎች ሰምቶ የማይታዘዛቸው ልክ እንደ ሰነፍ ሰው ነው። [7:26]

Matthew 7:28

ከጸሐፍቶቻቸው ጋር ሲነጻጸር ኢየሱስ ሕዝቡን ያስተማራቸው እንዴት ነበር?

ጸሐፍት እንደሚያስተምሩት ሳይሆን፣ ኢየሱስ ያስተማራቸው እንደ ባለሥልጣን ነበር። [7:29]


ምዕራፍ 8

1 ኢየሱስ ከተራራው በወረደ ጊዜ፣ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። 2 እነሆ፣ አንድ ለምጻም ወደ እርሱ መጣ፣ “ጌታ ሆይ፣ ፈቃደኛ ከሆንህ፣ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት በፊቱ ሰገደለት። 3 ኢየሱስም፣ “ፈቃደኛ ነኝ ንጻ” በማለት እፉን ዘርግቶ ዳሰሰው። ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ። 4 ኢየሱስ፣ “ተጠንቀቅ! ለማንም አትናገር። ዝም ብለህ ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ፣ምስክር እንዲሆናቸውም ሙሴ ያዘዘውን ስጦታ አቅርብ”አለው። 5 ኢየሱስ ወደቅፍርናሆም በገባ ጊዜ፣ አንድ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ መጥቶ፣ 6 ጌታ ሆይ፣ "አገልጋዬ በከባድ ሕመም ሽባ ሆኖ ቤቴ ተኝቷል" በማለት ለመነው። 7 ኢየሱስ፣ "መጥቼ እፈውሰዋለሁ” አለው። 8 የመቶ አለቃውም መልሶ፣“ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፣ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር አገልጋዬም ይፈወሳል” አለው፡፡ 9 እኔ ደግሞ ከሌላው ሥልጣን ሥር ያለሁና በእኔም ሥልጣን ሥር ወታደሮች ያሉኝ ሰው ነኝ። አንዱን “ሂድ” ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም “ና” ብለው ይመጣል፣ አገልጋዬንም 'ይህን አድርግ' ብለው ያደርጋል"፡፡ 10 ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ በጣም ተደነቀ፣ ይከተሉት ለነበሩት ሰዎችም “እውነት ነው የምነግራችሁ፣ በእስራኤል እንኳ እንደዚህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም” አላቸው፡፡ 11 እነግራችኋለሁ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፣ በእግዚአብሔር መንግሥትም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በማዕድ ይቀመጣሉ። 12 የመንግሥት ልጆች ግን ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ ውጪው ጨለማ ይጣላሉ፡፡ 13 ኢየሱስም የመቶ አለቃውን፣ “ሂድ! እንደ እምነትህ ይሁንልህ" አለው። አገልጋዩም በዚያው ሰዓት ተፈወሰ ፡፡ 14 ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ የጴጥሮስን አማት በትኩሳት ታማ ተኝታ አገኛት። 15 ኢየሱስ እጅዋን ነካት፣ ትኩሳቱም ለቀቃት፣ ተነሥታም ታገለግለው ጀመር። 16 በመሸ ጊዜ፣ ሕዝቡ አጋንንት የያዙአቸውን ብዙዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፣ እርሱም በቃሉ፣ መናፍስቱን አስወጣቸው፤ ታመው የነበሩትንም ሁሉ ፈወሳቸው። 17 በዚህ ዐይነት፣ በነቢዩ ኢሳይያስ፣ “እርሱ ሕመማችንን ተቀበለ ደዌዎቻችንን ተሸከመ” ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ። 18 ኢየሱስም በዙሪያው ያሉትን ሕዝብ ባየ ጊዜ፣ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ። 19 ከዚያም አንድ ጸሐፊ ወደ እርሱ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ፣ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው። 20 ኢየሱስም "ቀበሮዎች ጉድጓድ የሰማይ ወፎችም ጎጆዎች አሏቸው። የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያሳርፍበት ምንም ስፍራ የለውም"አለው። 21 ከደቀመዛሙርቱም ሌላው፣ "ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ እንድሄድና አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ አለው።" 22 ኢየሱስ ግን፣ “ተከተለኝ፣ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው” አለው። 23 ኢየሱስ ወደ ጀልባ በገባ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱም ተከትለውት ገቡ። 24 እነሆም፣ በባሕሩ ላይ ታላቅ ማዕበል ተነሥቶ ጀልባዋ በማዕበል ተሸፈነች። ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር። 25 ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ መጥተው፣ "ጌታ ሆ፣ እድነን ልንጠፋ ነው" በማለት ቀሰቀሱት። 26 ኢየሱስ፣ "እናንተ እምነት የጐደላችሁ ስለምን ፈራችሁ?”አላቸው። ከዚያም ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠፀ፣ ከዚያ በኋላ ታላቅ ጸጥታ ሆነ። 27 ሰዎቹም ተገርመው፣ "ይህ ምን ዓይነት ሰው ነው? ነፋሳትና ባሕሩም እንኳ ይታዘዙለታል" አሉ። 28 ኢየሱስም ወደ ማዶ ወደ ጌርጌሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፣ አጋንንት የተቆጣጠራቸው ሁለት ሰዎች ተገናኙት። የመጡትም ከመቃብር ነበርና በዚያ ማንም ማለፍ እስከማይችል ድረስ በጣም ኅይለኞች ነበሩ። 29 እነሆም፣ እየጮኹ፣ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ፣ እኛ ከአንተ ምን ጉዳይ አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?" አሉ። 30 ከዚያ አካባቢ ብዙ ሳይርቅ በግጦሽ ላይ ያሉ ብዙ ዐሳማዎች ነበሩ። 31 አጋንንቱም ኢየሱስን፣ "የምታወጣን ከሆነ ወደዚያ የዐሳማዎች መንጋ ስደደን" ብለው መለመናቸውን ቀጠሉ። 32 ኢየሱስም፣ "ሂዱ!"አላቸው። አጋንንቱም ወጥተው ዐሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ እነሆም፣ የዐሳማዎቹ መንጋ ሁሉ ወደ ታች ቁልቁለቱን እየተጣደፉ ወደ ባሕሩ ወርደው ውሃው ውስጥ ገብተው ጠፉ፡፡ 33 እነዚያም ዐሳማዎቹን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች ሸሽተው ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ሁሉ ፣ በአጋንንት ተይዘው ስለ ነበሩት ሰለ ሁሉቱ ሰዎችም አወሩ። 34 የከተማውም ሕዝብ ሁሉ ኢየሱስን ለማየት መጡ። ባዩትም ጊዜ አካባቢያቸውን ለቆ አንዲሄድ ለመኑት።



Matthew 8:1

ማቴዎስ 8፡1-3

አጠቃላይ መረጃ፡ ይህ በታሪክ ውስጥ ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን የፈወሰበት የአዲሱ ክፍል ጅማሬ ነው፡፡ ይህ ጭብጥ በእነዚህ ውስጥ ይቀጥላል MAT 9:35. ( ተመልከት) ኢየሱስ ከተራራ በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተለው “ኢየሱስ ከተራራ ከወረደ በኋላ ብዙ ሕዝብ ከተለው፡፡” ይህ ሕዝብ በተራራው ከእርሱ ጋር የነበሩትን እንዲሁም ያልነበሩትንም ሊያካትት ይችላል፡፡ እነሆ “እነሆ” የሚለው ቃል በታሪክ ውስጥ አዲስ ሰውን ያስተዋውቀናል፡፡ በቋንቋችሁ ይህንን የሚታደርጉበት ቃል ሊኖራችሁ ይችላል፡፡ ለምጻም “ለምጽ ያለበት ሰው” ወይም “የቆዳ በሽታ ያለበት ሰው፡፡” (UDB) በፊቱ ሰገደ ይህ በኢየሱስ ፊት ያሳየው ትህትና የሞላበት አቀራረብ ምልክት ነው፡፡ ( ተመልከት) ፈቃደኛ ከሆንክ “ከፈለግህ” ወይም “ፍላጎት ካለህ”፡፡ ለምጻሙ ሰው ኢየሱስ እርሱን የመፈወስ ኃይል እንዳለው አውቋል ይሁን እንጂ ኢየሱስ እርሱን ለመንካት ፈቃደኛ ይሁን አይሁን ግን አላወቀም፡፡ ልታነጻኝ ትችላለህ በዚህ ሥፍራ ላይ “ልታነጻኝ” የሚለው ቃል መፈወስን እና በማሀህበረሰቡ ውስጥ እንደገና ተቀላቅሎ መኖርን የሚያመለክት ቃል ነው፡፡ ኤቲ፡ “ልትፈውሰኝ ትችላለህ” ወይም 1እባክህ ፈውሰኝ”፡፡ (UDB) ( ተመልከት) ወዲያው “በዚያን ጊዜ” ከለምጹ ነጻ “ንጻ” የሚለው የኢየሱስ ንግግር ውጤቱ የሰውዬው መፈወስ ነው፡፡ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ጤነኛ ሆነ” ወይም “ለምጹ ለቀቀው” ወይም “ከለምጹ ነጻ”፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 8:4

ማቴዎስ 8፡4-4

ለእርሱ ይህ ኢየሱስ የፈወሰውን ሰው ያመለክታል፡፡ ለማንም አትናገር “ለማንም ምንም አትናገር” ወይም “እኔ እንደፈወስኩህ ለማንም አትናገር” ለካህናት ራስህን አሳይ የአይሁዳዊያን ሕግ የተፈወሰ ሰው ቆዳውን ለካህናት ማሳየት እንዳለበት ይጠይቃል፡፡ እነርሱም ቆዳውን ከተመለከቱ በኋላ ከሕዝቡ ጋር እንዲቀላቀል ይፈቅዱለታል፡፡ ( ተመልከት) ለእርሱ ምስክር ይሆንህ ዘንድ በሙሴ ትዕዛዝ መሠረት መስዋዕትን አቅርብ በሙሴ ሕግ መሠረት ከለምጽ የተፈወሰ ሰው የምስጋና መስዋዕትን ለከካህናት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ካህናቱ ስጦታውን ከተቀበሉ ሕዝቡ ይህ ሰው መፈወሱን ያውቃሉ፡፡ ( ተመልከት) ለእነርሱ ይህ የሚያመለክተው 1) ካህናትን ወይም 2) ሌሎች ሰዎችን ወይም 3) ኢየሱስን የሚተቹ ሰዎችን ሊሆን ይችላል፡፡ ከተቻለ ከእነዚህ ቡድኖች መካከል ዬትኛውንም የሚያመለክትን ስም ተጠቀሙ፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 8:5

ማቴዎስ 8፡5-7

አያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ የታሪኩ ክፍል ውስጥ ጸሐፊው ወደሌላ ጊዜ እና ቦታ በመሄድ ኢየሱስ ሌላ ሰው የፈወሰበትን ሁኔታ ያሳያል፡፡ ወደ እርሱ መጥቶ ጠየቀው “በዚህ ሥፍራ “እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሱስን ነው፡፡ ሽባ “ከበሽታው የተነሳ ከቦታ ቦታ መዘዋወር የማይችል” ኢየሱስም እንዲህ አለው፡፡ “ኢየሱስ ለመቶ አለቃው እንዲህ አለው” መጥቼ እፈውሰዋለሁ “ወደ ቤትህ መጥቼ ባርያህን አድነዋለሁ፡፡”

Matthew 8:8

ማቴዎስ 8፡8-10

ወደ ቤቴ ጣሪያ ሥር ግባ “”የቤቴ ጣሪያ ሥር” የሚለው ሀረግ “ቤቴ” ማለት ነው፡፡ ( ተመልከት) ቃል ተናገር በዚህ ሥፍራ “ቃል” የሚለው ቃል ትዕዛዝ ስጥ ማለት ነው፡፡ ኤቲ፡ “ትዕዛዝ ስጥ”፡፡ ( ተመልከት) ይፈወሳል ይህ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ይድናል፡፡” ( ተመልከት) በስልጣን ሥር ያለ ይህ በዚህ መልኩ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “በሌላ ሰው ሥልጣን ሥር ያለ ማንኛውም ሰው፡፡” ( ተመልከት) በሥልጣን ሥር . . . በእኔ ሥር በአንድ ሰው “ሥር” መሆን ማለት የሌላ ሰው ትዕዛዝ እንደሚበልጥ በማወቅ ትዕዛዙን መቀበል፡፡ ( ተመልከት) ወታደሮች “የሰለጠኑ ተደባዳቢዎች” እውነት እልሃለሁ “እውነት እልሃለሁ፡፡” ይህ ሀረግ ኢየሱስ በቀጣይነት የሚናገረው ነገር ላይ ትኩረት እንዲደረግ ይጋብዛል፡፡ እንዲህ ዓይነት እምነት በእስራኤል እንኳ አላገኘሁም የኢየሱስ አድማጮች የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆኑ የሚያስቡት በእስራኤል ያሉ አይሁዳዊያን ከማንም ይልቅ ታላቅ የሆነ እምነት እንደሚኖራቸው ያስቡ ነበር፡፡ ኢየሱስ ግን ተሳስተዋል በማለት ተናግሯል፡፡ የመቶ አለቃው እምነት ከሁሉ ታላቅ ነበር፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 8:11

ማቴዎስ 8፡11-13

አንተ በዚህ ሥፍራ ላይ “አንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥርን የሚያመለክት ሲሆን “እርሱን የሚከተሉትን ሰዎችን” ነው፡፡ MAT 8:10. (: ተመልከት) ከምስራቅ እና ከምዕራብ ተቃራኒ የሆኑትን “ምቅራቅ” እና “ምዕራብ”ን በመጠቀም “በሁሉም አከባቢ” የሚል መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ኤቲ፡ “በሁሉም አከባቢ” ወይም “በሁሉም አቅጣጫ ከሩቅ ሥፍራ” ( ተመልከት) በማዕድ ይቀመጣሉ በዚያ ባሕል ውስጥ ያሉ ሰዎች ምግብ በሚመገቡበት ወቅት በጠረጴዛ ዙሪያ ይቀመጣሉ፡፡ ይህ ሀረግ የሚያመለክተው በጠረጴዛው ዙሪያ የሚቀመጡት ቤተሰብ እና የቅርብ ጓደኞች ናቸው፡፡ ኤቲ፡ “እንደ ቤተሰብ ከዳኞች ጋር መኖር”፡፡ ( ተመልከት) በመንግስተ ሰማያት በዚህ ሥፍራ “መንግስት” የሚለው ቃል እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ የሚገዛበትን የሚያመለክት ነው፡፡ “መንግስ ሰማያት” የሚለው ሀረግ ጥቅም ላይ የዋለው በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ከተቻለ “ሰማይ” የሚለውን ቃል በትርጉማችሁ ውስጥ ላማስቀመት ሞክሩ፡፡ ኤቲ፡ “በሰማይ ያለው አምላካችን ንጉሥ መሆኑን በሚሳይበት ጊዜ፡፡” ( ተመልከት) የመንግስቱ ለልጆች ይጣላሉ ይህ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር የመንግስቱን ልጆች አውጥቶ ይጥላቸዋል፡፡” ( ተመልከት) የመንግስ ልጆች “የ. . . ልጆች” የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው የእርሱ የሆኑት ፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር መንግስት የሆኑት ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ሥፍረ ምጸታዊ ንግግር አለ ምክንያቱም እንግዶች ወደ መንግስቱ እንዲገቡ ሲደረግ “ልጆች” ወደ ውጪ ይጣላሉ፡፡ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ይገዛቸው ዘንድ የፈቀዱለት”፡፡ ( እና ተመልከት) ወደ ውጭ ጨለማ ይህ እግዚአብሔርን ያልተቀበሉት ዘላለማዊ መዳረሻቸው ምን እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ከእግዚአብሔር የራቀ ጨለማ ሥፍራ” ወይም “ስኦል”፡፡ ( ተመልከት) ለእናንተ ይሆን ዘንድ ይህ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ለእናንተ አደርገዋለሁ፡፡” ( ተመልከት) ባሪያው ተፈወሰ ይህ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ኢየሱስ ባሪያወን ፈወሰ፡፡” ( ተመልከት) በዚያው ሰዓት “ኢየሱስ ባሪያውን እፈውሰዋለሁ ብሎ በተናገረበት ቅጽበት”

Matthew 8:14

ማቴዎስ 8፡14-15

አያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ጸሐፊው ታሪኩን ወደ ሌላ ጊዜ እና ቦታ በመቀየር ኢየሱስ ሌላ ሰው የፈወሰበትን ሁኔታ ያሳየናል፡፡ ኢየሱስ መጥቶ ደቀ መዛሙርቱ ምናባት ከእርሱ ጋር ልሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የታሪኩ ዋና ትኩረት ኢየሱስ ስላደረገው እና ሰስለተናገረው ነገር ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ ደቀ መዛሙርቱን የጠቀሰበት ምክንት የተሳሳተ ትርጉም እንዳይኖር በማለት ነው፡፡ የጴጥሮስ አማች “የጴጥሮስ ምስት እናት” ንዳዱ ትቷት ሄደ በቋንቋችሄ እንዲህ ያለ ሰውኛ የአጻጻፍ ስልት ማለትም ንዳድ በራሱ አስቦ አንድን ነገር እንደሚፈጽ የሚሳይ ሰውኛ የአነጋገር ስልት ካለ “ተሸለት” ወይም “ኢየሱስ ፈወሳት” ተብሎ ልተረጎም ይችላል፡፡ ( ተመልከት) ተነስታ “ከተኛችበት አልጋ ተነስታ”

Matthew 8:16

ማቴዎስ 8፡16-17

አያያዥ ዓረፍተ ነገር› በዚህ ሥፍራ የታሪኩ ፍሰት በዚያው ቀን ምሽት ላይ ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ወደ ፈወሰበት እና ሴጣንን ከብዙ ሰዎች ወደአወጣበት ታርክ ይዞራል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 17 ላይ ጸሐፊው የኢየሱስ የፈውስ አገልግሎቱን በነብያት የተነገው ትንቢት ፍጻሜ መሆኑን ከነብዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ በመጥቀስ ጽፏል፡፡ በመሸም ጊዜ ይህ ከሰንበት በኋላ መሆኑን ያሳያል ምክንያቱም አይሁዳዊየን በሰንበት ቀን ሥራ አይሠሩም ወይም መንገድ አይሄዱም፡፡ እስኪመሽ ድረስ ጠብቀው ሰዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፡፡ የተሳሳተ ትርጉምን ከማስወገድ አንጻር ካልሆነ በስተቀር ሰንበት የሚለው ቃል መጥቀሱ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ( ተመልከት) በዳብሎ የተያዙ ብዙ ሰዎችን ወደ እርሱ አመጡ ይህ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ብዙ በዳብሎስ የተያዙ” (UDB) ወይም “በዳብሎስ ቁጥር ሥር የሆኑ ብዙ ሰዎች” ( ተመልከት) በቃሉ መናፍስቱን አስወጣ በዚህ ሥፍራ “ቃል” የሚለው ቃል ትርጉሙ ትዕዛዝ ነው፡፡ ኤቲ፡ “መንፈሱ እንዲወጣ አዘዘ፡፡” ( ተመልከት) በነብይ ኢሳያስ የተነገረው ትንቢትን ይፈጽም ነበር ይህ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ነብዩ ኢሳያስ ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው የትንቢት ቃልን ኢየሱስ ፈጸመው፡፡ () ተመልከት) ድካማችን ተቀበለ ደዊያችንንም ተሸከመ ማቴዎስ ከነብዩ ኢሳያስ መጽሐፍ በዚህ ሥፍራ ላይ ጠቅሷል፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሀረጋት በመሠረታዊ መልዕክታቸው ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሁለቱም አጽኖት የሚሰጡት እርሱ ሁሉንም በሽታችንን ፈውሷል፡፡ ኤቲ፡ “የታመሙትን ፈውሷል እንዲሁም ደና አድርጓቸዋል፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 8:18

ማቴዎስ 8፡18-20

አያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ላይ ታሪኩ ኢየሱስ ልከተሉት ለሚፈልጉ ሰዎች የሰጠው ምላሽ ምን እንደሆነ ወደማሳየት ይሄዳል፡፡ አሁን በዚህ ሥፍራ ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በዋናው ታርክ ውስጥ አዲስ ታሪክ መጀመሩን ለማሳየት ነው፡፡ ማቴዎስ በዚህ ሥፍራ ላይ የታሪኩን አዲስ ክፍል ይነግረናል፡፡ መመሪያዎች ሰጠ “ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው” ከዚያ ማለትም ኢየሰስ “መመሪያዎችን ከሰጠ በኋላ ነገር ግን ወደ ታንኳይቱ ከመግባቱ በፊት በዬትም ሥፍራ “በዬትኛውም ቦታ” ቀበሮዎች ጉድጓድ አላቸው እንዲሁም የሰማይ ወፎች ጎቾ አላቸው ቀበሮዎች ቀበሮዎች እንደ ውሻ ያሉ እንስሳት ናቸው፡፡ በጎጆዋቸው ውስጥ ያሉትን አእዋፋት እና ሌሎች ትንንሽ እንስሳትን ይበላሉ፡፡ ቀበሮዎች በእናንተ ዙሪያ የማይታወቁ ከሆነ እንደ ውሻ ያለ በማለት አጠቃላይ ቃልን ተጠቀሙ፡፡ ( ተመልከቱ) ጉድጋዶች ቀበሮዎች ለመኖሪያቸው የሚሆን ጉድጓድን ይቆፍራሉ፡፡ ቀበሮወችን ለማመልከት የተጠቀማችኋቸው እንስሳት የሚኖሩበትን ሥፍራ ግለጹ፡፡ የሰው ልጅ ኢየሱስ ስለ ራሱ እየተናገረ ነው፡፡ ( ተመልከት) ራሱን የሚያሳርፍበት ሥፍራ ይህ የመተኛ ሥፍራን ያመለክታል፡፡ ኤቲ፡ “የሚተኛበት የራሱ ሥፍራ የለውም፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 8:21

ማቴዎስ 8፡21-22

በመጀመሪያ አባቴን እንድቀብረው ፍቀድልኝ የሰውዬው አባት መሞቱን እና ወዲያው መቅበር እንዳለበት በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም ወይም አባቱ እስኪሞት እና እስኪቀበር ድረስ ለረጅም ጊዜ መቀየት ይኖርበት አይኖርበት የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ዋናውን ነጥብ ይህ ሰው ኢየሱስን ከመከተሉ በፊት ሌላ አዲስ ነገር ማድረግ ይፈለጋል ማለት ነው፡፡ ሙታን ሙታናቸውን ይቀብሩ ዘንድ ተዋቸው በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ በቀጥታ የሞቲ ሰዎች ሌሎች የሞቱትን ይቅበሩ ማለቱ አይደለም፡፡ “ሙታን” የሚለው ቃል አማራጭ ትርጉሞች 1) በቅርብ ጊዜ ስለሚሞቱ ሰዎች የሚነገር ምሳሌያዊ አነጋገር ወይም 2) ኢየሱስን የማይከተሉ እና መንፈሳዊ ሞት የሞቱ ሰዎችን ለማመልከት የሚውል ሚሳሌያዊ አነጋገር፡፡ ዋናው ነጥብ ማንኛውም ኢየሱስን መከተል ለሚወድ ሰው ምንም ነገር ሊያዘገየው አይገባም፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 8:23

ማቴዎስ 8፡23-25

አያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ላይ የታሪኩ ፍሰት ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙር የገሊላን ባሕር ሽሻገሩ የተነሳውን ማዕበል ኢየሱስ እንዴት ጸጥ እንዳደረገው ወደሚያሳይ ታሪክ ይለወጣል፡፡ ወደ ታንኳይቱ ገቡ “ወደ ተንኳ ገቡ” ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት ለ”ደቀ መዛሙር” እና “ተከተል” ለሚለው ቃል በ(MAT 8:21-22). ላይ የተጠቀምከውን ተመሳሳይ ቃላትን ተጠቀም፡፡ እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይራል፡፡ ኤቲ፡ “በድንገት”(UDB) ወይም “ያለምንም ማስጠንቀቂያ” ባሕሩም በታላቅ ማዕበል ተናወጠ ኤቲ፡ “ታላቅ ማዕበል ባሕሩን አናወጠው” በዚህም ምክንያት ታንኳይቱን ውሃ ሞላት ይህ እንዲህ ልገለጽ ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “ስለዚህም ምክንያት ታንኳይቱን ውሃ ሞላት”፡፡ ( ተመልከት) ተነስ አድነን አሉት የዚህ ሀረግ አማራጭ ትርጓሜዎች 1) በመጀመሪያ ኢየሱስን ከተኛት ቀስቅሰው “አድነን” አሉት ወይም 2)ኢየሱስን እየቀሰቀሱት “አድነን” አሉት፡፡ እኛ . . . እኛ ይህ ቃል ሁሉን የሚያጠቃልል ወይም የማያጠቃልል አድርገን የሚንተረጉመው ከሆነ ሁሉን የሚያጠቃልል ቃልን ብንጠቀም መልካም ይሆናል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ምናልባት ኢየሱስ እነርሱን እና ራሱን ከትንኳይቱ መስጠም እንዲታደግ ያቀረቡት ጥያቄ ሊሆን ይችላል፡፡ ( ተመልከት) መሞታችን ነው “ልንሞት ነው”

Matthew 8:26

ማቴዎስ 8፡ 26-27

ለእነርሱ “ለደቀ መዛሙርቱ” ለምን ፈራችሁ . . . እምነት? ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ጥያቄ በመጠየቅ ይገስጻቸዋል፡፡ ኤቲ፡ “ልትፈሩ አይገባም . . እምነት” ወይም “የምትፈሩበት አንዳች ምክንያት የለም . . . እምነት፡፡” ( ተመልከት) እናንተ ትንሽ እምነት ያላችሁ ይህንን በ MAT 6:30 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ ንፋስን እና ባሕር የሚታዘዙለት ይህ ምን ዓይነት ሰው ነው? “ንፋስና ባሕር ይታዘዙታል! ምን ዓይነስ ሰው ነው? ይህ የደቀ መዛሙርቱን አግራሞት የሚያሳይ ጥያቄ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ይህ ከሌሎች ሰዎች ሁሉ የተለየ ነው! ንፋስ እና ማዕበል ሳይቀር ይታዘዙታል!” ( ተመልከት) ንፋስ እና ባሕር ሳይቀር ይታዘዙታል ሰዎች ወይም እንስሳት ቢታዘዙት ወይም ባይታዘዙት ብዙም አያስደንቅም ነገር ግን ንፋስ እና ውሃ እርሱን መታዘዛቸው በጣም አስደናቂ ነገር ነው፡፡ ይህ በሰውኛ የቀረበው ሀሳብ ተፈጥሮአዊ ነገሮች ልክ እንደ ሰው ሰምተው ምላሽ መስጠጥ ይችላሉ፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 8:28

ማቴዎስ 8፡28-29

አያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ላይ ጸሐፊው ከዚህ በፊት ወደ ጀመረው ኢየሱስ በሽተኞችን ወደሚፈውስበት አገልግሎት ታሪኩ ተመልሶ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ ሁለት በዳብሎስ እስራት ተይዘው የነበሩትን ሰዎች ነጻ ሲያወጣ እንመለከታለን፡፡ በዚያኛው በኩል “ከገሊላ ባሕር ማዶ” የጌርጋሴኖን ሀገር ጌርጋሴኖን የጌርጋ ከተማ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ በጣም አስቸጋሪዎች ነበሩ እነዚህን ሁለት ሰዎችን የያዙት ዳብሎሶች በጣም አደገኞች ከመሆናቸው የተነሳ ማንም ሰው በዚያ በኩል ማለፍ አይችልም ነበር፡፡ እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይራል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ከአንተ ጋር ምን አለን? ይህንን ጥያቄ የጠየቁት በቁጣ ነበር፡፡ ( ተመልከት) የእግዚአብሔር ልጅ ይህ ኢየሱስ ከእግዚብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ የኢየሱስ ወሳኝ የሆነ መጠሪያ ስሙ ነው፡፡ ( ተመልከት) ጊዜው ሳይደርስ ልትሣቅየን ወደዚህ መጣህን? ሁለተኛው ጥያቄም ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ አልነበረም፡፡ ትረጉሙም “እግዚአብሔር እኛን ለመቅጣት የወሰነው ጊዜ ሳይደርስ መጥተህ እኛን በመቅጣት እግዚአብሔርን መታዘዝ መተው የለብህም፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 8:30

ማቴዎስ 8፡28-29

አያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ላይ ጸሐፊው ከዚህ በፊት ወደ ጀመረው ኢየሱስ በሽተኞችን ወደሚፈውስበት አገልግሎት ታሪኩ ተመልሶ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ ሁለት በዳብሎስ እስራት ተይዘው የነበሩትን ሰዎች ነጻ ሲያወጣ እንመለከታለን፡፡ በዚያኛው በኩል “ከገሊላ ባሕር ማዶ” የጌርጋሴኖን ሀገር ጌርጋሴኖን የጌርጋ ከተማ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) እነርሱም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ እስኪሳነው ድረስ በጣም አስቸጋሪዎች ነበሩ እነዚህን ሁለት ሰዎችን የያዙት ዳብሎሶች በጣም አደገኞች ከመሆናቸው የተነሳ ማንም ሰው በዚያ በኩል ማለፍ አይችልም ነበር፡፡ እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይራል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ከአንተ ጋር ምን አለን? ይህንን ጥያቄ የጠየቁት በቁጣ ነበር፡፡ ( ተመልከት) የእግዚአብሔር ልጅ ይህ ኢየሱስ ከእግዚብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ የኢየሱስ ወሳኝ የሆነ መጠሪያ ስሙ ነው፡፡ ( ተመልከት) ጊዜው ሳይደርስ ልትሣቅየን ወደዚህ መጣህን? ሁለተኛው ጥያቄም ሰላማዊ የሆነ ጥያቄ አልነበረም፡፡ ትረጉሙም “እግዚአብሔር እኛን ለመቅጣት የወሰነው ጊዜ ሳይደርስ መጥተህ እኛን በመቅጣት እግዚአብሔርን መታዘዝ መተው የለብህም፡፡” ( ተመልከት)

አሁን ይህ ቃል ጸሐፊው የታሪኩን ቀጣይ ክፍል ከመተረኩ በፊት አንባቢዎቹ ማወቅ ያለባቸውን አንድ መረጃ እንደሚሰጣቸው ያሳያል፡፡ ኢየሱስ ወደዚያ ሥፍራ ከመምጣቱ በፊት አሳማዎች በዚያ ሥፍራ ነበሩ፡፡ ( ተመልከት) ካስወጣኸን ኤቲ፡ “ልታስወጣን ስለሆነ” እኛ ይህ ሁሉን አቀፍ ነው፤ ትርጉሙም ለአሳማዎች ብቻ ነው፡፡ ( ተመልከት) እነርሱ በሰውዬው ውስጥ ያለው እርኩስ መንፈስ እርኩስ መንፈሱም ከሰውዬው ውስጥ ወጥቶ ወደ አሳማዎቹ ገባ ኤቲ፡ “እርኩስ መንፈሱም ከሰውዬው ውስጥ ወጥቶ ወደ አሳማዎቹ ገባ” እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይራል፡፡ ከተራራወ አፋፍ ወደታች ሮጡ ኤቲ፡ “በፍጥነት ከተራራው አናት ወደታች ሮጡ” በውሃ ውስጥ ሞቱ ኤቲ፡ “በውሃ ውስጥ ወድቀው ሰመጡ”

Matthew 8:33

ማቴዎስ 8፡33-34

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ኢየሱስ በእርኩስ መንፈስ የተያዙ ሁለት ሰዎችን ኢየሱስ የፈወሰበት ታሪክ ማጠቃለያ ነው፡፡ አሳማዎች የሚያሰማሩ “አሳማዎችን የሚጠብቁ” በእርኩስ መንፈስ የተያዙት ሰዎች ምን እንደሆኑ ኤቲ፡ “በእርኩስ መንፈስ የተያዙትን እነነዚህ ሰዎች ለማገዝ ኢየሱስ ያደረገው ነገር” እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይራል፡፡ በሁሉም ከተሞች ይህ ማለት ብዙ ወይም አብዛኞቹ ሰዎች ማለት እንጁ ሁሉም ሰዎች ማለት የግድ አይደለም፡፡ ( ተመልከት) አከባቢ ኤቲ፡ “ከተማዋ እና በአካቢው ያሉት”


Translation Questions

Matthew 8:4

የተፈወሰው ለምጻም ወደ ካህን ሄዶ ሙሴ ያዘዘውን መባ እንዲያቀርብ ኢየሱስ የነገረው ለምንድነው?

የተፈወሰው ለምጻም ወደ ካህን እንዲሄድ ኢየሱስ የነገረው ለእነርሱ ምስክርነት እንዲሆን ነበር። [8:4]

Matthew 8:5

መቶ አለቃው ሽባ ስለ ሆነው አገልጋዩ በነገረው ጊዜ ምን እንደሚያደርግ ኢየሱስ ተናገረ?

ወደ መቶ አለቃው ቤት ሄዶ አገልጋዩን እንደሚፈውስ ኢየሱስ ተናገረ። [8:7]

Matthew 8:8

ኢየሱስ ወደ ቤቱ ሊመጣ እንደማያስፈልገው መቶ አለቃው የተናገረው ለምን ነበር?

ኢየሱስ ወደ ቤቱ ይገባ ዘንድ እንደማይገባው፣ ቃል ብቻ መናገር እንደሚችልና አገልጋዩን እንደሚፈውስ ተናገረ። [8:8]

ለመቶ አለቃው ኢየሱስ የሰጠው የድጋፍ ንግግር ምን ነበር?

የመቶ አለቃውን ያክል እምነት ያለውን ሰው በእስራኤል እንኳን ከአንድም ሰው እንዳላገኘ ኢየሱስ ተናገረ። [8:10]

Matthew 8:11

በመንግሥተ ሰማያት መጥተው በገበታ እንደሚቀመጡ ኢየሱስ የተናገረላቸው እነማን ናቸው?

ብዙዎች ከምሥራቅና ከምእራብ መጥተው በመንግሥተ ሰማያት ገበታ ላይ እንደሚቀመጡ ኢየሱስ ተናገረ። [8:11]

ልቅሶ እና የጥርስ ማፏጨት ባለበት ወደ ውጪያዊው ጨለማ እነ ማን ይጣላሉ ብሎ ኢየሱስ ተናገረ?

የመንግሥተ ሰማያት ልጆች ወደ ውጫዊው ጨለማ እንደሚጣሉ ኢየሱስ ተናገረ። [8:12]

Matthew 8:14

ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ ኢየሱስ የፈወሰው ማንን ነበር?

ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ የጴጥሮስን ዐማት ፈወሳት። [8:14]

ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ ኢየሱስ የፈወሰው ማንን ነበር?

ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ የጴጥሮስን ዐማት ፈወሳት። [8:15]

Matthew 8:16

ኢየሱስ በአጋንንት ተይዘው እና ታምመው የነበሩትን ሁሉ በፈወሰ ጊዜ የትኛው የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጸመ?

“እርሱ ደዌያችንን ተሸከመ፣ ሕመማችንንም ተቀበለ” የሚለው የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጸመ። [8:17]

Matthew 8:18

አንደኛው የአይሁድ መምህር እንዲከተለው በጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ ስለሚኖርበት ሁኔታ ምን አለ?

ቋሚ የሆነ ቤት እንደሌለው ኢየሱስ ተናገረ። [8:20]

Matthew 8:21

አንደኛው ደቀመዝሙር ኢየሱስን ከመከተሉ በፊት ሄዶ አባቱን እንዲቀብር በጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ ምን አለ?

ለደቀመዝሙሩ እንዲከተለው፣ ሙታን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ እንዲተዋቸው ኢየሱስ ነገረው። [8:21]

አንደኛው ደቀመዝሙር ኢየሱስን ከመከተሉ በፊት ሄዶ አባቱን እንዲቀብር በጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ ምን አለ?

ለደቀመዝሙሩ እንዲከተለው፣ ሙታን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ እንዲተዋቸው ኢየሱስ ነገረው። [8:22]

Matthew 8:23

ታላቅ ማእበል በባህር ላይ በተነሣ ጊዜ ኢየሱስ በጀልባው ውስጥ ምን እያደረገ ነበር?

ታላቅ ማእበል በባህር ላይ በተነሣ ጊዜ ኢየሱስ ተኝቶ ነበር። [8:24]

Matthew 8:26

እንዳይሞቱ ስለፈሩ ደቀመዛሙርት ኢየሱስን ባነቊት ጊዜ ኢየሱስ ምን አላቸው?

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ “እናንት እምነት የጎደላችሁ ስለምን ትፈራችሁ?” አላቸው [8:26]

ጸጥታ ከሆነ በኋላ ደቀመዛሙርቱ በኢየሱስ የተደነቊት ለምን ነበር?

ደቀመዛሙርቱ በኢየሱስ የተደነቁት ነፋሳት እና ባህር ስለታዘዙት ነበር። [8:27]

Matthew 8:28

ወደ ጌርጌሴኖን አገር በመጣ ጊዜ ምን ዓይነት ሰዎች ወደ ከኢየሱስ ጋር ተገናኙ?

እጅግ ኃይለኞች የነበሩትን ሁለት በአጋንንት የተያዙ ሰዎችን ኢየሱስ አገኛቸው። [8:28]

በሰዎቹ በኩል ለኢየሱስ የሚናገሩት አጋንንት ያሳሰባቸው ነገር ምን ነበር?

ጊዜው ሳይደርስ ኢየሱስ ሊያሰቃያቸው እንደመጣ አጋንንቱ አሳስቧቸው ተናገሩ። [8:29]

Matthew 8:30

ኢየሱስ አጋንንቱን ባወጣቸው ጊዜ ምን ተከሰተ?

ኢየሱስ አጋንንቱን ባስወጣ ጊዜ፣ ወደ እርያ መንጋ ሄደው ገቡ፤ እርያዎቹም ወደ ባሕር ተጣድፈው ገቡ። [8:32]

Matthew 8:33

ሰዎቹ ሊያገኙት ከከተማይቱ በወጡ ጊዜ ኢየሱስ ምን እንዲያደርግላቸው ጠየቊት?

ሰዎቹ አካባቢያቸውን ለቅቆ እንዲወጣ ኢየሱስን ለመኑት። [8:34]


ምዕራፍ 9

1 ኢየሱስ ወደ ጀልባ ገባ፤ ባሕሩንም አቋርጦ ወደ ገዛ ከተማው መጣ። 2 እነሆ፣ በምንጣፍ የተኛ አንድ ሽባ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን በማየት ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፣ አይዞህ፤ ኅጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው፡፡ 3 አንዳንድ ጸሐፍት ግን እርስ በርሳቸው፣ "ይህ ሰው እኮ እየተሳደበ ነው" ተባባሉ ። 4 ኢየሱስም ዐሳባቸውን ዐውቆ፣ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?” 5 ለመሆኑ የሚቀለው፣'ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል' ነው፣ ወይስ 'ተነሣና ሂድ ማለት ነው?' 6 ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ዕወቁ" አለ፡፡ ሽባውንም፣ "ተነሣና፣ምንጣፍህን ይዘህ ወደ ቤት ሂድ" አለው፡፡ 7 ከዚያም ሰውየው ተነሥቶ ወደ ቤቱ ሄደ። 8 ሕዝቡም ይህን ባዩ ጊዜ ተገርመው፣ ለሰው እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ። 9 ኢየሱስም ከዚያ አለፍ እንዳለ፣ ማቴዎስ የሚባለውን ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያ ቦታ ላይ ተቀምጦ አየውና "ተከተለኝ" አለው።እርሱም ተነሥቶ ተከተለው፡፡ 10 ኢየሱስም በቤቱ ውስጥ ለመመገብ በተቀመጠ ጊዜ፣ ቀረጥ የሚሰበስቡ ብዙ ሰዎችና ኃጢአተኞች መጥተው፣ ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርት ጋር አብረው ተመገቡ። 11 ፈሪሳውያንም ይህን ሲያዩ፣ደቀ መዛሙርቱን "ለምንድን ነው መምህራችሁ፣ ከግብር ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላው?" አሏቸው፡፡ 12 ኢየሱስም ይህንን ሲሰማ ፣"ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፡፡ 13 'ሂዱና' ምሕረት እንጂ መሥዋዕትን አልፈልግም' የሚለውን ተማሩ፣ እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኅጥአንን ወደ ንስሓ ለመጥራት" ነው አለ። 14 ከዚያም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣" እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ እንጾማለን ፣የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?" አሉት። 15 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ሰርገኞች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሆኖም ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፣በእነዚያ ቀናት ይጾማሉ። 16 ማንም ሰው በአሮጌ ልብስ ላይ ዐዲስ ቊራጭ ጨርቅ አይለጥፍም፤ ምክንያቱም አሮጌውን ልብስ ይቦጭቀዋል፣ ልብሱም የባሰ ይጐዳል። 17 ሰዎች ዐዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ ውስጥ አያስቀምጡም፤ እንደዚያ ካደረጉ አቁማዳው ይፈነዳል፣ የወይን ጠጁ ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይቀደዳል። ይልቁንም ዐዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ውስጥ ያስቀምጡታል፣ ሁለቱም ይጠበቃሉ፡፡" 18 ኢየሱስ ይህን እየተናገራቸው እያለ፣ አንድ ሹም እየሰገደ ወደ እርሱ መጣ። “ልጄ አሁን ገና ሞተች፣ ነገር ግን ና ና እጅህን ጫንባት በሕይወትም ትኖራለች አለው”። 19 ኢየሱስም ተነሥቶ ተከትሎት ሄደ፤ ደቀ ዛሙርቱም ደግሞ አብረውት ሄዱ። 20 አንዲት ለዐሥራ ሁለት ዓመት ከባድ የደም መፍሰስ የነበረባት ሴት፣ ከኢየሱስ ኋላ መጥታ የልብሱን ጠርዝ ነካች፤ 21 "የልብሱን ጫፍ ብቻ ብነካ ደኅና እሆናለሁ" ብላ ነበርና። 22 ኢየሱስም ዞር ብሎ አያትና፣ “ልጄ ሆይ፣ አይዞሽ እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ሴቲቱም ወዲያውኑ ደኅና ሆነች። 23 ኢየሱስም ወደ ሹሙ ቤት በገባ ጊዜ፣ዋሽንት የሚነፉትንና የሚንጫጩትን አይቶ፣ 24 "ወደዚያ ዞር በሉ፣ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም"አላቸው። እነርሱ ግን በማፌዝ ሳቁበት። 25 ሕዝቡን ወደ ውጭ ባስወጡ ጊዜ፥ ኢየሱስ ወደ ክፍሉ ገብቶ እጅዋን ያዘ፤ልጅቱም ተነሣች። 26 ወሬውም በዚያ አካባቢ ሁሉ ተዳረሰ። 27 ኢየሱስም በዚያ ሲያልፍ፣ ሁለት ዐይነ ስውሮች ተከተሉት፣ ያለ ማቋረጥም፣ "የዳዊት ልጅ ማረን!" እያሉ ይጮኹ ነበር። 28 ኢየሱስም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ፣ ዐይነ ስውሮቹ ወደ እርሱ መጡ። ኢየሱስም፣ "ይህን ለማድረግ እንደምችል ታምናላችሁ?" አላቸው። እነርሱም "አዎን፣ ጌታ ሆይ" አሉት፡፡ 29 ከዚያም ኢየሱስ ዐይኖቻቸውን ዳስሶ፣ "እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ" አላቸው። 30 ዐይኖቻቸውም ተከፈቱ። ከዚያም ኢየሱስ፣"ይህንን ማንም እንዳያውቅ" ብሎ በጥብቅ አዘዛቸው። 31 ሁለቱ ሰዎች ግን ሄደው ወሬውን በየቦታው አዳረሱት። 32 ሁለቱ ሰዎች እየሄዱ እያሉ እነሆ፣ በጋኔን የተያዘ ዲዳ ወደ ኢየሱስ አመጡ። 33 ጋኔኑም ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ። ሕዝቡም ተገርመው፣ "እንዲህ ያለ ከዚህ በፊት በእስራኤል አልታየም" አሉ። 34 ፈሪሳውያን ግን "አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው" ይሉ ነበር። 35 ኢየሱስ ወደ ከተሞችና መንደሮች ሁሉ ሄደ፣ በየምኩኲራቦቻቸውም ማስተማሩን፣ የመንግሥትን ወንጌል መስበኩንና፣ ማንኛውንም ዐይነት በሽታና ደዌ መፈወሱን ቀጠለ። 36 ሕዝቡንም ሲያይ፣ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው ነበርና ራራላቸው። 37 ለደቀ መዛሙርቱም፣ "መከሩ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን ጥቂት ናቸው። 38 ስለዚህ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ፣ ወደ መከሩ ጌታ አጥብቃችሁ ጸልዩ" አላቸው።



Matthew 9:1

ማቴዎስ 9፡1-2

ማቴዎስ 9፡1-2 አያያዥ ዓረፍተ ነገር ጸሐፊው በ MAT 8:1 የጀመረው ኢየሱስ ሰዎችን ከበሽታ የፈወሰበትን ታሪክ እንደገና ወደ መተረክ ተመልሷል፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ኢየሱስ ሽባውን ሰው እንዴት እንደፈወሰው ይተርካል፡፡ ኢየሱስ ወደ ታንኳይቱ ገባ ደቀ መዛሙርቱም ከእርሱ ጋር ሄደው ሊሆን ይችላል፡፡ ታንኳ ይህ ምናልባት በ MAT 8:23 ላይ የተገለጸው ታንኳ ሊሆን ይችላል፡፡ ግራ መጋባትን ለማስወገድ ከፈለግህ ብቻ ይህንን መግለጽ ትችላለህ፡፡ ወደ ገዛ ከተማው መጣ ኤቲ፡ “ወደመከኖርበት ከተማ” (UDB) እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይኖራል፡፡ እነርሱ . . . እነርሱ ይህ ሽባውን ሰው ወደኢየሱስ ያመጡትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ ሽባውንም ሰው ሊያመለክት ይችላል፡፡ ልጅ ይህ ሰው በእርግጥ የኢየሱስ ልጅ አይደለም፡፡ ኢየሱስ በዚህ ሥፍራ ላይ በትህትና እያናገረው ነው፡፡ ይህ ሰዎችን ግራ የሚያጋባ ከሆነ እንዲህ በማለት ሊትተረጉመው ተትችላለህ “ወዳጄ ሆይ” ወይም “አንተ ጎበዝ” ወይም ከተውኑ ልትተው ትችላለህ፡፡ ኃጢአትህ ተሰሪያልሃለች ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ኃጢአትህን ሠሪዮልሃል” ወይም “ኃጢአትን ሠሪዬልሃለሁ” ( ተመልከት)

Matthew 9:3

ማቴዎስ 9፡3-6

እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይኖራል፡፡ ከእነርሱ መካከል ይህ “ለእነርሱ ለራሳቸው” “በመካከላቸው” ወይም “እርስ በእርሳቸው”፣ “በራሳቸው አፍ” እግዚአብሔርን ይሳደባል እግዚአብሔር ብቻ ሊያደርጋቸው የሚችላቸው ነገሮች ኢየሱስ ማድረግ እችላለው እያለ ነው፡፡ የልባቸውን ሀሳብ አውቆ ኢየሱስ ሀሳባቸውን ያወቀው በልዕለ ተፈጥሮ ኃይል አማካኝነት ነው ወይም እርሱ በእርሳቸው ስነጋገሩ ተመልክቶ ነው፡፡ በልባችሁ ስለምን ክፋትን ታስባላችሁ? ኢየሱስ ይህንን የተናገረው ጸሐፊትን ለመገሰጽ ነው፡፡ ( ተመልከት) አንናተ . . . እናንተ እነዚህ ቃላት ብዙ ቁጥር አመልካች ናቸው፡፡ ( ተመልከት) ክፋት ይህ ግብረገባዊ ክፋት እንጂ ዝም ብሎ ስህተት አይደለም፡፡ ዬቱ ይቀላል . . . ተራመድ ኢየሱስ ጸሐፊዎችን ይህንን ጥያቄ በመጠየቅ ማስታወስ የፈለገው ነገር ሰውዬው ሽባ የሆነው በኃጢአቱ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህም ኃጢአቱ ይቅር ከተባለለት ሽባው ሰው መራመድ ይችላል ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ማለት እንደሚችል ጸሐፊት ያውቁ ዘንድ ይህን ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡ ለመናገር ቀላሉ ዬቱ ነው፤ “ኃጢአትህ ተሠረየችልህ” ወይስ “ተነሳና ተራመድ?” ብሎ መናገር ነው ኤቲ፡ ለመናገር ቀላሉ ዬቱ ነው፤ “ኃጢአትህ ተሠረየችልህ” ወይስ “ተነሳና ተራመድ” ብሎ መናገር ነው? Your sins are forgiven This can mean 1) "I forgive your sins" ኃጢአትህ ተሠረየችልህ ይህ ማለት 1) “ኃጢአትን ይቅር ብዬሃለሁ” (UDB) ወይም 2) “እግዚአብሔር ኃጢአትህን ይቅር ብሎልሃል”፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ “አንተ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በነጠላ ቁጥር ነው፡፡ ( ተመልከት) ታውቁ ዘንድ ነው ኤቲ፡ “አረጋግጥላችኋለሁ”፡፡ በዚህ ሥፍራ ለእናንተ የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የብዙ ቁጥርን በሚያመለክት መልኩ ነው፡፡ ( ተመልከት) your...your These are singular. አንተ . . . አንተ ይህ ነጠላ ቁጥር ነው፡፡ ( ተመልከት) ወደ ቤትህ ሂድ ኢየሱስ ሰውዬውን ወደ ሌላ ቦታ እንዳይሄድ አልከለከለውም፡፡ ለሰውዬው ወደ ቤቱ የሜድ ዕድል ሰጠው፡፡

Matthew 9:7

ማቴዎስ 9፡7-9

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ኢየሱስ ሽባውን ሰው የፈወሰበት ታሪክ ማጠቃለያ ነው፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ከቀረጥ ሰብሳቢዎች መካከል አንድ ሰውን የእርሱ ደቀ መዝሙር ይሆን ዘንድ ጠራው፡፡ ምሳጋና በ MAT 5:16 ላይ የተጠቀምከውን ተመሳሳይ ቃል በዚህ ሥፍራም ተጠቀም፡፡ እንዲህ ያለ ስልጣን ኃጢአትን የማስተሰረይ ስልጣን ማቴዎስ . . . እርሱ . . እርሱ የቤተ ክርስቲያን አባቶች በዚህ ሥፍራ ላይ የተጠቀሰው የማቴዎስ ወንጌል ጸሐፊ ማቴዎስ እራሱ ነው ይላሉ፡፡ ይሁን እንጂ በክፍሉ ውስጥ ያለው “እርሱ” የሚለው ቃል “እኔ” ወደሚለው እንዲንለውጥ የሚያደርገን ምንም ምክንያት የለም፡፡ እርሱም እንዲህ አለው “ኢየሱስ ለማቴዎስ እንዲህ አለው” ኢየሱስም በዚያ ስያልፍ ሳለ ይህ ሀረግ እነሆ በሚል ቃል በ MAT 9:8 የተጀመረው ታሪክ መግቢያን የሚያሳይ ነው፡፡ በቋንቋችሁ እንዲህ ማሳየት ከቻላችሁ ተጠቀሙበት፡፡ በዚያ ስያልፍ “መሄድ” የሚለውን ቃል ተጠቀሙ፡፡ ኢየሱስ ወደ ተራራ መውጣቱን ወይም ወደ ሸለቆ መውረዱን ወይም ወደ ቅፍረናሆም መሄዱን ወይም ከዚያ ሪቆ ለመሄድ መነሳቱን የሚገለጽ ምንም ነገር የለም፡፡ ተነሥቶም ተከተለው “ማቴዎስ ተነሣና ኢየሱስን ተከተለው”፡፡ የተከተለው ኢየሱስን እስከሚቀጥለው ሥፍራ ድረስ እንደተከተሉት ሰዎች ሳይሆን እንደ ደቀ መዝሙር ነው፡፡

Matthew 9:10

ማቴዎስ 9፡10-11

አጠቃላይ መረጃ ይህ ታሪክ የተፈጸመው በቀራጩ ማቴዎስ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ቤት ይህ ምናልባትም የማቴዎስ ቤት ይሆናል፤ ነገር ግን የኢየሱስም ቤት ሊሆን ይችላል (“ከኢየሱስ እና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው በሉ”፡፡ ግራ መጋባትን የሚፈጥር ከሆነ ብቻ ምንነቱን በመግለጽ አስቀምጡት፡፡ ፈሪሳዊያን ይህንን በተመለከቱ ጊዜ “ፈሪሳዊያን ኢየሱስ ከቀረጥ ሰብሳቢዎች እና ከኃጢአተኛ ሰዎች ጋር እየበላ እንደሆነ በተመለከቱ ጊዜ”

Matthew 9:12

ማቴዎስ 9፡12-13

አጠቃላይ መረጃ፡ ይህ ታሪክ የተፈጸመው በቀራጩ ማቴዎስ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ኢየሱስም ይህንን በሰማ ጊዜ “ይህንን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ፈሪሳዊያን ኢየሱስ ስለምን ከቀራጮች እና ከኃጢአተኞች ጋር ይበላል ብለው የጠየቁትን ጥያቄን ያመለክታል፡፡ ጤነኞች ኤቲ፡ “ጤናማ የሆኑ ሰዎች” ( ተመልከት) ሐኪም “ዶክተር”(UDB) ታማሚዎች “ዶክተር የሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ናቸው” ይህ ምን ማለት እንደሆነ ሄዳችሁ አጥኑ ኤቲ፡ “የዚህን ትርጉም ምንነት ሄዳችሁ አጥኑ፡” ሂዱ “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥርን ያመለክታል፡፡

Matthew 9:14

ማቴዎስ 9፡14-15

አያያዥ ዓረፈተ ነገር የመጥቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ስለምን እንደማይጾሙ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አይጾሙም ጾም ማለት ምንም ነገር አለመብላት ማለት ነው፡፡ ምንም ዓይነት ጾም ባሌለባቸው አንዳንድ ባሕሎች ውስጥ “በቀጣይነት መብላት መቆም” ተብሎ ልገለጽ ይችላል፡፡ ( ተመልከት) የሠረግ ታዳሚዎች ኃዘንተኞች መሆን ይችላሉ . . . እነርሱ? የሠረግ ታዳሚዎች ሠርገኞቹ ከእነርሱ ጋር እያሉ እንድጾሙ የሚጠብቅባቸው ማንም የለም፡፡ ( ተመልከት) የሠርግ ታዳሚዎች ይህ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሚያመለክት ምሳሌያዊ ንግግር ነው፡፡ ( ተመልከት) ሠርገኛወ ገና ከእርሱ ጋር ነውና . . . ሠርገኛው ከእነርሱ ከተለየ በኋላ “ሠርገኛው” ኢየሱስ ነው፣ እርሱ ደግሙ አሁን ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ ( ተመልከት) ሠርገኛው ከእነርሱ የሚወሰደብት ጊዜ ይመጣል ኤቲ፡ “የሆነ ሰው ሠርገኛውን ይወስደዋል፡፡” ይህ እንደሚገደል በምሰሌያዊ አነጋገር ስገለጽ ነው፡፡ ( ተመልከት) ያዝናሉ “ያለቅሳሉ” ወይም “ያዝናሉ”(UDB)

Matthew 9:16

ማቴዎስ 9፡16-16

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ላነሱት ጥያቄ መልስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ ማንም በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ የሚሰፋ የለም የዚህ ምሳሌያዊ ንግግር ትርጉሙ አሮጌውን ባሕል የሚያው ሰዎች አዲሱን ለመቀበል አይጓጉም፡፡ ( ተመልከት) ልብስ “ልብስ” እራፊ የተቀደደ ልብስን ለመስፋት የሚሆን “አዲስ ቁራጭ ጨርቅ”

Matthew 9:17

ማቴዎስ 9፡17-17

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ለተየቁት ጥያቄ መልስ መስጠቱት ቀጥሏል፡፡ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር ማንም የለም ኢየሱስ ይህንን ምሳሌያዊ አነጋገር የተጠቀመው ለዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ነው፡፡ ጥያቄያቸውም “እኛ እና ፈሪሳዊን እንጾማለን ነገር ነገር የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ስለምን አይጾሙም?” ( ተመልከት) የሚያኖር ማንም የለም ኤቲ፡ “የሚያኖር ማንም የለም” (UDB) ወይም “ሰዎች በጭራሽ አያስቀምጡም” አዲስ ወይን ኤቲ፡ “የወይን ጁስ”፡፡ ይህ ያልፈላ ወይንን ያመለክታል፡፡ ወይን በእናንተ አከባቢ የማይታወቅ ከሆነ ለፍራፍሬ አጠቃላይ ስም የሚውል ቃል ተጠቀሙ፡፡ ( ተመልከት) የአረጀ አቁማዳ ይህ ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለን አቁማዳ ያመለክታል፡፡ (ተመልከት) አቁማዳ ከእንስሳት ቆዳ የሚሠራ ከረጥት ነው፡፡ “የወይን መያዣ” ወይም “የቆዳ ከረጥት” ተብሎም ይጠራል፡፡ (UDB). ( ተመልከት) አቁማዳው ይፈነዳል አዲሱ ወይን ስፈላ አቁማዳው ይፈነዳል ምክንያቱም ከዚህ በላይ መለጠጥ ስለማይችል ነው፡፡ ( ተመልከት) ይጠፋል “ይበላሻል”(UDB) አዲስ አቁማዳ “አዲስ አቁማዳ” ወይም “አዲስ የወይን ከረጥት”፡፡ ይህ ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ውሎ የማያቅን አቆማዳ ያመለክታል፡፡ ( ተመልከቱ)

Matthew 9:18

ማቴዎስ 9፡ 18-19

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ታሪክ የሚጀምረው ኢየሱስ የአይሁድ አለቃነ ሴት ልጅ ከሞት ካስነሳ በበኋላ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ይህ ኢየሱስ ለዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ ጾም የሰጠውን መልስ የሚያመለክት ነው፡፡ እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይኖራል፡፡ ወድቀው ሰገዱለት ይህ በአይሁድ ባሕል መሠረት ለሰዎች አክበሮትን ማሳያ መንገድ ነው፡፡ ና እና እጅህን በእርሷ ላይ ጫን፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራለች ይህ የአይሁድ አለቃ ኢየሱስ ሴት ልጁን ከሞት ለማስነሳት የሚያስችለው ኃይል እንዳለው ያምናል ማለት ነው፡፡

Matthew 9:20

ማቴዎስ 9፡ 20-22

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ኢየሱስ ወደ አይሁድ አለቃው ቤት በመሄድ ላይ ሳለ እንዴት አንዲትን ሴት እንደፈወሳት የሚገልጽ ታሪክ ነው፡፡ እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይኖራል፡፡ ከፍተኛ የደም መፍሰስ ኤቲ፡ “በከፍተኛ ሁኔታ ደም ይፈሳታል፡፡” የወር አበባዋ መምጫው ጊዜ እንኳ ሳይሆን ከማሕጸኗ ውስጥ ድም ይፈሳት ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ ለመግለጽ የሚያስችል ቃል በአንዳንድ ባሕሎች ውስጥ አለ፡፡ ( ተመልከት) ልብሶቹን መንካት ብችል እንኳ ደህና እሆናለሁ ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ፈውሷል፤ ከዚህች ሴት ይበልጥ ከፈተኛ በሽታ ውስጥ የሆኑትን ሰዎች እንኳ ፈውሷል፡፡ ( ተመልከት) ጨርቅ “መቀነት” ነገር ግን “ይልቁንም” ሴትቱ ይሆናል ብላ የጠበቀችው ነገር አልሆነም፡፡ ሴት ልጅ ይህች ልጅ የኢየሱስ ልጅ አይደለችም፡፡ ኢየሱስ በትህትና አናገራት፡፡ ይህ በሰዎች አእምሮ ውስጥ ግራ መገጋባትን የሚፈጥር ከሆነ “አንድ ወጣት” ወይም ሳይተረጎም ሊታለፍ ይችላል፡፡

Matthew 9:23

ማቴዎስ 9፡23-24

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ኢየሱስ የአይሁድ አለቃውን ሴት ልጅ ወደ ሕይወት ወደመለሰበት ታሪክ ይመራናል፡፡ የአለቃው ቤት ይህ የአይሁድ አለቃው ቤት ነው፡፡ እምቢልታ ይህ ረጅም የሆነ በአንድ በኩል እስትፋንስ እየተሰጠው ጥቅም ላይ የሚውል የሙዚቃ መሣሪያ ነው፡፡ የእምቢልታ ጠቻዋቾች “እምቢልታ የሚጫወቱ ሰዎች” ሂዱ በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ ለብዙ ሰዎች እየተናገረ ነው፡፡ ስለዚህ በቋንቋችሁ የብዙ ቁጥር አመልካች ቃልን ተጠቀም፡፡ ልጅቱ አልሞተችም አንቀላፍታለች እንጂ በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ የያዘው የቃላት ጫወታ ነው፡፡ ኢየሱስ በኖረበት ዘመን የሞተ ሰው ተኝቷል ብሎ መጥራት የተለመደ ነው፡፡ ይሁን ዘንጂ በዚህ ሥፍራ ሞታ የነበረችው ልጅ ልክ ተኝቶ እንደነበር ሰው ከሞት ተነሳች፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 9:25

ማቴዎስ 9፡ 25-26

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ኢየሱስ የአይሁድ አለቃውን ሴት ልጅ ወደ ሕይወት የመለሰት ታሪክ ማብቂያ ነው፡፡ አጠቃላይ መረጃ ቁጥር 26 ኢየሱስ ልጅቷን ከሞት የማስነሳቱ ውጤት ምን እንደሆነ ማጠቃለያ ሀሳብ ነው፡፡ ሕዝቡ ውጪ እንዲወጣ ካደረገ በኋላ “ኢየሱስ ሕዝቡን ወደ ውጪ ካስወጣ በኋላ” ወይም “የልጅቱ ቤተሰቦች ሕዝቡን ወደ ወጪ ካስወጣ በኋላ” ተነሽ “ከአልጋሽ ተነሽ”፡፡ በ MAT 8:15 ያለው ትርጉም ተመሳሳይ ነው፡፡ የዚህ ነገር ዜና በሀገሩ ሁሉ ተሰማ ይህ ሰውኛ አገላለጽ የዚህ ነገር ዜና መሰራጨቱን ያሳያል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንተያት አንዱ ለሌላኛው ሰው በመንገሩ ነው፡፡ ኤቲ፡ “በአከባቢው የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ሰለተፈጠረው ነገር ሰሙ” (UDB) ወይም “የልጅቱን በሕይወት መኖር የተመለከቱ ሰዎች በዚያ አለባቢ ላሉ ሰዎች ሁሉ ማናገር ጀመሩ፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 9:27

ማቴዎስ 9፡27-28

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ስለ ሁለት ዐይነ ስውራን ታሪክ የሚጀመርበት ነው፡፡ ኢየሱስ በዚያ ስያልፍ ሳለ ኢየሱስ አከባቢውን ለቆ ሲሄድ ስያልፍ ኢየሱስ ወደ ተራራ እየወጣ ወይም እየወረደ እንደሆነ ምንም ፍንጭ የለም፡፡ ስለዚህ “ሄደ” የሚል ጠቅለል ያለ ቃል መጠቀሙ ጥሩ ነው፡፡ የዳዊት ልጅ ኢየሱስ በቀጥታ የዳዊት ልጅ አይደለም፡፡ ስለዚህም እንዲህ ልተረጎም ይችላል “ከዳዊት ዘር የሆነው” (UDB)፡፡ ይሁን እንጂ “የዳዊት ልጅ” የሚለው የመስሑ የማዕረግ ስም ነው፡፡ see MAT 21:9 ተመልከት) እና እነዚህ ሰዎችም ምናበት ኢየሱስን ይህንኑ የማዕረግ ስሙን ታሳቢ በማድረግ ጠርተውታል፡፡ ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ይህ ኢየሱስ ወደ ገዛ ቤቱ መግባቱን (UDB) ወይም በ MAT 9:10 ላይ የተጠቀሰውን ቤት ልያመለክት ይችላል፡፡ አዎን፥ ጌታ ሆይ ኤቲ፡ “አዎን ጌታዬ አንተ መፈወስ እንደሚትችል እናምናለን፡፡”

Matthew 9:29

ማቴዎስ 9፡ 29-31

ዓይኖቻቸውን ዳሰሰ። ኢየሱስ የሁለቱንም ሰዎች ዐይኖች እንዴት በአንድ ጊዜ መዳሰስ እንደቻለ ግልጽ አይደለም ወይም በቀኝ እጁ የአንዱን ዐይን በሌላኛው እጁ ደግሞ የሌላኛውን ዐይን ዳስሶ ይሆናል፡፡ የግራ እጅ ብዙ ጊዜ ንጹሕ ላልሆነ ነገር እንደመዋሉ መጠን ኢየሱስ እነዚህን ሰዎች የፈወሳቸው ቀኝ እጂን ተጠቅሞ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እየዳሰሳቸው ሳለ ቃል መናገር አለመናገሩ ወይም በመጀመሪያ መዳሰሱን ከዚያመ ቃል መናገሩን የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ዐይኖቻቸው ተከፈቱ ኤቲ፡ “እግዚአብሔር ዐይኖቻቸውን ፈወሰ” ወይም “ሁለቱ ዐይነ ስውራን መመልከት ቻሉ” ( ተመልከት) But "Instead." The men did not do what Jesus told them to do. ነገረ ግን “ይሁን እንጂ” እነዚህ ሰሰዎች ኢየሱስ እንዲያደርጉ የነገራውን ነገር አላደረጉም፡፡ ዜናውን አሰራጩት ኤቲ፡ “ምን እንደተደረገላቸው ለብዙ ሰዎች ተናገሩ”

Matthew 9:32

ማቴዎስ 9፡32-34

አያያዥ ዐረፍተ ነገር ይህ ኢየሱስ በእርኩስ መንፈስ በመያዙ ምክያት መናገር የማይችለውን ሰው የፈወሰበት ታሪክ እና ለዚህ ፈውስ ሰዎች የሰጡት ምላሽ ታሪክ ነው፡፡ እነሆ ይህ በትልቁ ታሪክ ውስጥ የአንድ አዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ ይህንን ማሳየት የሚቻልበት መንገድ ይኖራል፡፡ ዲዳ መናገር የማይችል ዲዳ ሰው ተናገረ ኤቲ፡ “ዲዳው ሰው ማናገር ጀመረ” ወይም “መናገር የማይችለው ሰውዬ መናገር ቻለ” ወይም “ዲዳ የነበረው ሰው መናገር ቻለ” ሕዝቡም ተገረሙ ኤቲ፡ “ሕዝቡም ተደነቀ” እንዲህ ያለ ነገር ታይቶም አይታወቅም “እንዲህ ዓይነት ሀገር ተደርጎ አይታወቅም” ወይም “ይህን ዓይነት ነገር ከዚህ በፊት ማንም ሰው አድርጎ አያውቅም” ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ እርኩሳን መናስፍስት አስወጣ በዚህ ሥፍራ ላጥ “እርሱ” የሚለው የሚያመለክተው ኢየሱስን ነው፡፡

Matthew 9:35

ማቴዎስ 9፡35-36

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ቁጥር 35 በ MAT 8:1 የተጀመረው ኢየሱስ በገሊላ የነረው የፈውስ አገልግሎት ታሪክ ማብቂያ ነው፡፡ (የታሪኩ ማብቂያ) አጠቃላይ መረጃ፡ ከቁጥር 36 ጀምሮ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በማስተማር እርሱ እንዳደረገው ይስብኩና ይፈውሱ ዘንድ የላካቸው ታሪክ አዲስ የታሪኩ ክፍል ጅማሬ ነው፡፡ በሁሉም ከተሞች ኤቲ፡ “በብዙ ከተሞች” ( ተመልከት) ከተሞች . . . መንደሮች ኤቲ፡ “ትልልቅ መንደሮች . . . ትንንሽ መንደሮች” ወይም “ትልልቅ ከተሞች . . . ትንንሽ ከተሞች” ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች እና ሕመሞች ኤቲ፡ “ሁሉንም በሽታዎች እና ሕመሞች”፡፡ “በሽታ” እና “ሕመም” ተቀራራቢ የሆኑ ነገሮች ይሁን እንዲ ከተቻለ በሁለት የተለያዩ ቃላት ቢተረጎሙ የተሸለ ነው፡፡ “በሽታ” አንድ ሰው እንዲታመም የሚያደርጉት ነገሮች ሲሆኑ፡፡ “በሽታ” ደግሞ በዚህ በሽታ ከመያዛችን የተነሳ የሚሰማን አካላዊ ድካም ወይም ሕመም ነው፡፡ እረኞች እንደሌላቸው በጎች ተቅበዝብዘዋል ኤቲ፡ “ሰዎቹ መሪ አልበራቸውም” ( ተመልከት)

Matthew 9:37

ማቴዎስ 9፡37-38

አጠቃላይ መረጃ፡ ኢየሱስ የመከርን ምሳሌ በመጠቀም ከዚህ በፊት ለነበረው የሕዝቡ ፍላጎት ደቀ መዛሙርቱ በምን ዓይነት መንገድ ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው ነገራቸው፡፡ መከሩ ብዙ ነው ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው ይህ ምሰሌያዊ ንግግር በእግዚአብሔር የሚያምኑ እና ወደ መንግስቱ የሚጨመሩ ሰዎች ቁጥር በእርሻ ማሳ ውስጥ በለ ሰብል በመመሰል ስ እግዚአብሔር ለሰዎች የሚናገሩ ሰዎችን በሠራተኞች በመመሰል ያነጻጽራል፡፡ የዚህ ምሳሌያዊ ንግግር ዋናው ነጥብ ስለ እግዚአብሔር የሚናገሩ በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው ነው፡፡ መከር ኤቲ፡ “የደረሰ ሰብል” ሠራተኞች “ሠራተኞች” ለመከሩ ጌታ ጸልዩ ኤቲ፡ “የመከሩ ባለቤት ወደሆነው ጌታ ጸልዩ”


Translation Questions

Matthew 9:3

አንዳንዶቹ ጸሐፍት ኢየሱስ እግዚአብሔርን የሰደበው የመሰላቸው ለምን ነበር?

አንዳንዶቹ ጸሐፍት ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየሰደበ የመሰላቸው ለሽባው ሰው ኃጢአቱ እንደተሰረየለችለት ኢየሱስ ስለነገረው ነው። [9:3]

አንዳንዶቹ ጸሐፍት ኢየሱስ እግዚአብሔርን የሰደበው የመሰላቸው ለምን ነበር?

አንዳንዶቹ ጸሐፍት ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየሰደበ የመሰላቸው ለሽባው ሰው ኃጢአቱ እንደተሰረየለችለት ኢየሱስ ስለነገረው ነው። [9:4]

አንዳንዶቹ ጸሐፍት ኢየሱስ እግዚአብሔርን የሰደበው የመሰላቸው ለምን ነበር?

አንዳንዶቹ ጸሐፍት ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየሰደበ የመሰላቸው ለሽባው ሰው ኃጢአቱ እንደተሰረየለችለት ኢየሱስ ስለነገረው ነው። [9:5]

ሽባ ለነበረው ሰው ተነሥቶ እንዲሄድ ከመንገር ይልቅ፣ ኃጢአቱ እንደተሰረየችለት ኢየሱስ የተናገረው ለምን ነበር?

ለሽባው ሰው ኃጢአቱ እንደተሰረየችለት ኢየሱስ መናገሩ በምድር ላይ ኃጢአትን ለማስተሰረይ ሥልጣን እንዳለው ያሳያል። [9:5]

ሽባ ለነበረው ሰው ተነሥቶ እንዲሄድ ከመንገር ይልቅ፣ ኃጢአቱ እንደተሰረየችለት ኢየሱስ የተናገረው ለምን ነበር?

ለሽባው ሰው ኃጢአቱ እንደተሰረየችለት ኢየሱስ መናገሩ በምድር ላይ ኃጢአትን ለማስተሰረይ ሥልጣን እንዳለው ያሳያል። [9:6]

Matthew 9:7

የሽባው ሰው ኃጢአት ይቅር ተብሎለት እና ሰውነቱም ተፈውሶ ባዩ ጊዜ ሰዎች እግዚአብሔርን ያመሰገኑት ለምን ነበር?

እንዲህ ያለውን ሥልጣን ለሰዎች በመስጠቱ ተደንቀው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። [9:8]

ኢየሱስን ከመከተሉ በፊት የማቴዎስ ሙያ ምን ነበር?

ማቴዎስ ኢየሱስን ከመከተሉ በፊት ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር። [9:9]

Matthew 9:10

ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ የበሉት ከማን ጋር ነበር?

ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ የበሉት ከቀረጥ ሰብሳቢዎች እና ኃጢአተኛ ሰዎች ጋር ነበር። [9:10]

Matthew 9:12

ኢየሱስ እነማንን ወደ ንስሃ ለመጥራት እንደ መጣ ተናገረ?

ኃጢአተኞችን ወደ ንስሃ ለመጥራት እንደመጣ ኢየሱስ ተናገረ። [9:13]

Matthew 9:14

ደቀመዛሙርቱ እንደማይጾሙ ኢየሱስ የተናገረው ለምን ነበር?

ደቀመዛሙርቱ እንደማይጾሙ ኢየሱስ የተናገረው እርሱ ከእነርሱ ጋር ስላለ ነበር። [9:15]

ደቀመዛሙርቱ መቼ እንደሚጾሙ ነው ኢየሱስ የተናገረው?

ከእነርሱ በሚወሰድባቸው ጊዜ ደቀመዛሙርቱ እንደሚጾሙ ኢየሱስ ተናገረ። [9:15]

Matthew 9:20

ብዙ ደም የሚፈስሳት ሴት ያደረገችው ነገር ምን ነበር፣ ለምን እንደዚያ አደረገች?

ብዙ ደም የሚፈስሳት ሴት ልብሱን ብቻ ብነካ እድናለሁ ብላ በማሰብ የኢየሱስን ልብስ ጫፍ ነካች። [9:20]

ብዙ ደም የሚፈስሳት ሴት ያደረገችው ነገር ምን ነበር፣ ለምን እንደዚያ አደረገች?

ብዙ ደም የሚፈስሳት ሴት ልብሱን ብቻ ብነካ እድናለሁ ብላ በማሰብ የኢየሱስን ልብስ ጫፍ ነካች። [9:21]

ብዙ ደም የሚፈስሳትን ሴት ያዳናት ምን እንደሆነ ነው ኢየሱስ የተናገረው?

ብዙ ደም የሚፈስሳት ሴት የዳነችው በእምነቷ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። [9:22]

Matthew 9:23

ኢየሱስ ወደ ምኩራብ አለቃው ቤት በገባ ጊዜ ሰዎቹ በኢየሱስ የሳቁበት ለምን ነበር?

ልጅቷ እንዳልሞተች፣ ነገር ግን እንደተኛች ኢየሱስ በመናገሩ ሰዎቹ በኢየሱስ ላይ ሳቁበት። [9:24]

Matthew 9:25

ኢየሱስ ልጅቱን ከሙታን ካስነሣት በኋላ ምን ተከሰተ?

ልጅቷን ከሙታን የማስነሣቱ ዜና በክልሉ ሁሉ ናኘ። [9:26]

Matthew 9:27

ሁለቱ ማየት የተሣናቸው ሰዎች ወደ ኢየሱስ ምን እያሉ ጮኹ?

“የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን!” እያሉ መጮኻቸውን ቀጠሉ። [9:27]

Matthew 9:29

ኢየሱስ ሁለቱን ማየት የተሣናቸው ሰዎች የፈወሳቸው ምንን መሠረት አድርጎ ነው?

ሁለቱን ማየት የተሣናቸው ሰዎች ኢየሱስ የፈወሳቸው እምነታቸውን መሠረት አድርጎ ነው። [9:29]

Matthew 9:32

ዲዳውን ሰው ኢየሱስ ከፈወሰው በኋላ፣ ፈሪሳውያን ምን ሲሉ ከሰሱት?

ፈሪሳውያን አጋንንትን በአጋንንት አለቃ ያወጣል ሲሉ ከሰሱት። [9:34]

Matthew 9:35

ኢየሱስ ለሕዝቡ ያዘነላቸው ለምን ነበር?

ኢየሱስ ለሕዝቡ ያዘነላቸው ተጨንቀው እና ግራ ተጋብተው ስለነበረ፣ ደግሞም እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለነበሩ ነበር። [9:36]

Matthew 9:37

ስለ ምን ጉዳይ በአስቸኳይ እንዲጸልዩ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው?

የመከሩ ጌታ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ እንዲጸልዩ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው። [9:38]


ምዕራፍ 10

1 ሁለቱን ደቀ መዛሙርት በአንድ ላይ ጠርቶ፣ ርኩሳን መናፍስትን እንዲያወጡ፣ ሁሉንም ዐይነት በሽታና ደዌ እንዲፈውሱ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡ 2 የዐስራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ የመጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣ 3 ፊልጶስና በርተሎሜዎስ፣ ቶማስና ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ፣ 4 ቀነናዊው ስምዖን፣አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ። 5 ኢየሱስ እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን "አሕዛብ ወደሚኖሩበት የትኛውም ቦታ አትሂዱ፤ ወደ የትኛውም የሳምራውያን ከተማ አትግቡ። 6 ከዚያ ይልቅ ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት በጐች ሂዱ። 7 መንግሥተ ሰማይ ቀርባለች፣ ብላችሁ ስበኩ" ብሎ አስተምሮ ላካቸው። 8 ሕሙማንን ፈውሱ፣ ሙታንን አስነሡ፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ አጋንንትንም አስወጡ፣ በነጻ ተቀብላችኋል በነጻ ስጡ። 9 በቦርሳችሁ ወርቅ ብር ወይም ናስ አትያዙ፤ 10 ለሠራተኛ ቀለቡ የሚገባው ስለ ሆነ፣ ለመንገዳችሁ ሻንጣ ወይም ትርፍ ልብስ፣ ወይም ጫማ፣ ወይም በትር አትያዙ። 11 ወደ የትኛውም ከተማ ወይም መንደር ስትገቡ፣ በዚያ ተገቢ የሆነው ሰው ማን እንደሆን እወቁ፤ ለቃችሁ እስከምትሄዱ ድረስ በዚያው ቆዩ። 12 ወደ ቤት ስትገቡ፣ ሰላምታ ስጡ። 13 ቤቱ የሚገባው ከሆነ ሰላማችሁ ይደርሰዋል፤ የማይገባው ከሆነ ግን ሰላማችሁ ይመለስላችኋል። 14 እናንተን የማይቀበላችሁን፣ ወይም ቃላችሁን የማይሰማውን በተመለከተ ግን፣ ከዚያ ቤት ወይም ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን አቧራ አራግፉ። 15 እውነት እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ይቀልላቸዋል። 16 ተመልከቱ፣ እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ። ስለዚህ፣ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። 17 ከሰዎች ተጠበቁ፣ ወደ ፍርድ ሸንጎ ያቅርቧችኋል፣ በምኲራባቸውም ይገርፏችኋል። 18 ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን፣ በእኔም ምክንያት ወደ ገዥዎችና ነገሥታት ፊት ትቀርባላችሁ። 19 ለፍርድም ሲያቀርቧችሁ፣ በዚያች ሰዓት የምትናገሩት ስለሚሰጣችሁ፣ ምን ወይም እንዴት እንደምትናገሩ አትጨነቁ። 20 በእናንተ ውስጥ የሚናገረው የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ የምትናገሩት እናንተ አይደላችሁም። 21 ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን፣ ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ተነሥተው ያስገድሏቸዋል። 22 ከስሜ የተነሣ በሰው ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ ነገር ግን ማንም እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል። 23 በዚህች ከተማ በሚያሳድዷችሁ ጊዜ ወደሚቀጥለው ከተማ ሽሹ። እውነት እላችኋለሁ፣ የሰው ልጅ ከመምጣቱ በፊት፣ የእስራኤልን ከተሞች አታዳርሱም። 24 ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ወይም አገልጋይ ከጌታው በላይ አይደለም። 25 ለደቀ መዝሙር ልክ እንደ መምህሩ፣ ለአገልጋይም ልክ እንደ ጌታው መሆን ይበቃዋል። 26 እንግዲህ አትፍሯቸው፤ የማይገለጥ የተሰወረ፣ የማይታወቅ የተደበቀ ምንም የለም። 27 በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን፣ በሹክሹክታ የምትሰሙትንም በአደባባይ ተናገሩት፡፡ 28 ሥጋን እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ከዚያ ይልቅ ነፍስንም፣ ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ፡፡ 29 ሁለት ድንቢጦች በትንሽ ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ሆኖም አንዷም ብትሆን አባታችሁ ሳያውቅ በመሬት ላይ አትወድቅም፡፡ 30 የእናንተ ግን የራሳችሁ ጠጉር እንኳን ሳይቀር የተቈጠረ ነው፡፡ 31 አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች የበለጠ ዋጋ አላችሁ፡፡ 32 ስለዚህ በሰዎች ፊት ለሚመሰክርልኝ፣ እኔም በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፡፡ 33 በሰው ፊት የሚክደኝን ግን፣ እኔም ደግሞ በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ፡፡ 34 በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ፣ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም፡፡ 35 ሰውን በአባቱ ላይ፣ ሴት ልጅን በእናቷ ላይ፣ ምራትን በአማቷ ላይ ለማነሣሣት መጥቻለሁ፡፡ 36 የሰውም ጠላቶቹ የገዛ ቤተ ሰቦቹ ይሆናሉ፡፡ 37 አባትን ወይም እናትን ከእኔ የበለጠ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም፤ እንዲሁም ወንድ ልጅን፣ ወይም ሴት ልጅን ከእኔ የበለጠ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም። 38 መስቀሉን ተሸክሞ፣ ከኋላዬ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም፡፡ 39 ሕይወቱን የሚያገኛት ያጣታል፤ ስለ እኔ ብሎ ሕይወቱን የሚያጣት ግን ያገኛታል፡፡ 40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፡፡ 41 ነቢይ ስለ ሆነ ነቢይን የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅ ስለ ሆነ ጻድቅን የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል፡፡ 42 እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ታናናሾች ለአንዱ፣ ደቀ መዝሙሬ ስለ ሆነ፣ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ማንም፣ በምንም ዐይነት ዋጋውን አያጣም፡፡



Matthew 10:1

ማቴዎስ 10፡1-1

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ይህ ኢየሱስ ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርቱን የእርሱን ሥራ ይሠሩ ዘንድ የለከበት ታሪክ መጀመሪያ ነው፡፡ የእርሱ የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን በአንድነት ጠርቶ ኤቲ፡ “የእረሱን ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት ጠርቶ” ሥልጣንን ሰጣቸው በዚህ ክፍል ውስጥ የተሰጣቸው ስልጣን 1) እርሰኩስ መንፈስን ማስወጣት እንዲችሉ 2) በሽታን እና ደዌን ይፈውሱ ዘንድ እንደሆነ ክፍሉ በግልጽ እንደሚናገር እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ማስወጣት ኤቲ፡ “እርኩስ መንፈስ እንዲወጣ ማድረግ” ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች እና ሕመሞች ኤቲ፡ “ሁሉንም በሽታዎች እና ሕመሞች”፡፡ “በሽታ” እና “ሕመም” ተቀራራቢ የሆኑ ነገሮች ይሁን እንዲ ከተቻለ በሁለት የተለያዩ ቃላት ቢተረጎሙ የተሸለ ነው፡፡ “በሽታ” አንድ ሰው እንዲታመም የሚያደርጉት ነገሮች ሲሆኑ፡፡ “በሽታ” ደግሞ በዚህ በሽታ ከመያዛችን የተነሳ የሚሰማን አካላዊ ድካም ወይም ሕመም ነው፡፡

Matthew 10:2

ማቴዎስ 10፡2-4

አጠቃላይ መረጃዎች በዚህ ሥፍራ ላይ ጸሐፊው የዐሥራ ሁሉትን ሐዋሪያት ስም በመዘርዝር የኋላ ታሪክ መረጃ ይሰጣል፡፡ ( ተመልከት) መጀመሪያ በቅደም ተከተል እንጂ በደረጃ አይደለም ቀናተኛው የዚህ ቃል አንዱ ትርጉም ሊሆን የሚችለው 1) “ቀናተኛ”፡፡ አይሁዳዊያንን ከሮማዊያን አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የሚፈልጉ ቡድች ውስጥ ያለን ሰው ያመለክታል፡፡ ኤቲ፡ “ታጋይ” ወይም “የሀገር ፍቅር ያለው” ወይም “የነጻነት ታጋይ”፡፡ ሌላኛው የቃሉ ትርጉም ሊሆን የሚችለው 2 “ቀናተኛ የሆነው”፡፡ ይህ እግዚአብሔር ይከብር ዘንድ ይቀና የነበረው እንደ ማለት ነው፡፡ ማቴዎስ ቀረጥ ሰብሳቢው “ቀረጥ ይሰበስብ የነበረው ማቴዎስ” እርሱን የካደው “ኢየሱስን የካደው”

Matthew 10:5

ማቴዎስ 10፡5-7

ዓያያዥ ዓረፍተ ነገር በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ለመስበክ ስሄድ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ምን እንደሚያጋጥማቸው መመሪያ መስጠት መጀመሩን እንመለከታለን፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ ምንም እንኳ ቁጥር 5 የሚጀምረው ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ላካቸው በማለት ቢሆንም ኢየሱስ ይህንን መመሪያ የሰጣቸው እነርሱን ከመላኩ በፊት ነው፡፡ ( ተመልከት) እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን ላካቸው ኤቲ፡ “ኢየሱስ እነዚህ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ላካቸው” ወይም “ኢየሱስ የላካቸው እነዚህን ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ነው” የተላከ ኢየሱስ የላካቸው ለተወሰነ ዓላማ ነው፡፡ “የተላከ” የሚለው ቃል በ MAT 10:2 ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው “አፖስትል” የሚለው ቃል የግሥ ቅርጹ ነው፡፡ አዘዛዘቸው ኤቲ፡ “ምን ማድረግ እንዳለባቸው ነገራው” ወይም “አዘዛቸው” የጠፉት የእስራኤል በጎች ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር አጠቀላይ የእስራኤልን ሕዝብ ከእረኛቸው ከጠፉት በጎች ጋር የሚያነጻጽር ነው፡፡ (UDB) ( ተመልከት) የእስራኤል ቤት ይህ ገለጻ የእስራኤልን ሕዝብ የሚገልጽ ነው፡፡ ኤቲ፡ “የእስራኤል ሕዝብ” ወይም “የእስራኤል ዘር” ( ተመልከት) እንዲሁም ስትሄዱ “እናንተ” የሚለው ተውላጠ ስም ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያትን የሚያመለክት ነው፡፡ (: ተመልከት) የእግዚአብሔር መንግስ ቀርባለች ይህንን በ MAT 3:2 ውስጥ ያለውን ተመሳሳይ ሀሳብ በተረጎምክበት መንገድ መተርጎም ይኖርብሃል፡፡

Matthew 10:8

ማቴዎስ 10፡8-10

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ለመስበክ በሚወጡበት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ምን እንደሚጠብቃቸው ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ትዕዛዝ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ እናንተ ይህ ቃል የሚያመለክተው ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ነው፡፡ ወርቅ፣ ብር ወይም ናስ እነዚህ ሳንትሞች የሚሠሩባቸው ብረታ ብረቶች ናቸው፡፡ እነዚህ የገንዘብ ተለዋጭ ዝርዝሮች ናቸው፡፡ ብረታ ብረቶች በአካቢያችሁ የማዬታወቁ ከሆነ እነዚህ”ገንዝብ” ብለህ መተርጎም ትችላለህ፡፡ ( ተመልከት) ቦርሳ ይህ “ቀበቶ” ወይም “የገንዘብ ቀበቶ” ማለት ነው ነገር ግን ማንኛውንም ገንዘብ ለመያዝ የሚያገለግል ነገርን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ቀበቶ ረጅም የጨርቅ መቀነት ወይም በወገብ ዙሪያ ሰዎች የሚታጠቁት ከቆዳ የሚሠራ ነገር ነወ፡፡ ብዙ ጊዜ ታጥፎ በውስጡ ሳንቲሞችን እና ገንዘብን ለመያዝ የሚያስችለው ስፋት አለው፡፡ የጉዞ ቦርሳ ይህ በጉዞ ወቅት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለመያዝ የሚያገለግል ቦርሳ ወይም በሰዎች ምግብ ወይም ገንዘብ ለመሰበብሰብ የሚሆን ቦርሳን ያመለክታል፡፡ ተጨማሪ ነገሮችን በ MAT 5:40 ውስጥ ተጨማሪ ነገሮችን ብላችሁ የተረጎማችሁትን ቃል በዚህ ሥፍራ ተጠቀሙ፡፡ ሠራተኛ “ሠራተኛ” ምግቡ ኤቲ፡ “የሚያስፈልገው ነገር”

Matthew 10:11

ማቴዎስ 10፡11-13

አያያዥ ዓረፈተ ነገር ለመስበክ በሚወጡበት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ምን እንደሚጠብቃቸው ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ትዕዛዝ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ እናንተ እነዚህ ተውላጠ ስሞች ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያትን ያመለክታሉ፡፡ ወደዬትኛው ከተማ ወይም መንደር ስትገቡ ኤቲ፡ “ወደ አንድ ከተማ ወይም መንድር ስትገቡ” ወይም “ወደዬትኛውም መንደር ወይም ከተማ ስትገቡ” ከተማ ወይም መንደር “ትልቅ መንደር . . . ትንንሽ መንደር” ወይም “ታላላቅ ከተማ . . . ትንንሽ ከተማ፡፡” በ MAT 9:35 ውስጥ የተጠቀምከውን ተመሳሳይ ቃል በዚህም ሥፍራ ተጠቀም፡፡ ከዚያ ከተማ ለቃችሁ እስክትወጡ ድረስ በዚያ ቆዩ ኤቲ፡ “ከተማውን ወይም መንደሩን ለቃችሁ እስኪትወጡ ድረስ በዚያ ሰው ቤት ውስጥ ቆዩ” As you enter into the house, greet it AT: "As you enter into the house, greet the people who live in it." A common greeting in those days was "Peace be to this house!" ወደቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ ኤቲ፡ “ወደቤት ስትገቡ በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ሰላም በሏቸው፡፡” በዚያ ዘመን የተለመደው የሠላምታ ዓይነት “ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን” የሚል ነበር›› ( ተመልከቱ) ቤቱም የሚገባው ቢሆን ኤቲ፡ “በዚያ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከተቀበሏችሁ” (UDB) ወይም “በዚያ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በሚገባ ከተንከባከቧችሁ” ( ተመልከት) ሰላማችሁ ይሁንለት ኤቲ፡ “ሠላም ይሁንለት” ወይም “በዚያ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በሠላም ይኑሩ” ሰላማችሁ ይህ ሐዋርያቱ በዚያ ቤት ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ ይመጣ ዘንድ እግዚአብሔርን የሚጠይቁት ሰላም ነው፡፡ ባይገባው ግን ኤቲ፡ “በደንብ ካልተቀበሏችሁ” (UDB) ወይም “በደንብ ያላስተናገዷችሁ ከሆነ” ሰላማችሁ ይመለስ ይህ ሁለት አማራጭ ትርጓሜዎች ይሩታል፡ 1) ይህ ቤት ያልተገባው ከሆነ እግዚአብሔር ሰላሙን ወይም በረከቱን ከዚያ ቤት ላይ ይይዘዋል ወይም 2) ቤቱ ያልተገባው ከሆነ ሐዋርያቱ አንድ ነገር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ይኸውም እግዚአብሔርን ያቀረቡላቸውን ሰላምታ እንዲያከብር መጠየቅ፡፡ ሰላምታችሁን መልሳችሁ መውሰድ ወይም የዚህ ውጤት አስመልክቶ በቋንቋችሁ ውስጥ ያሉት ቃላት ተመሳሳይ ከሆኑ በዚህ ሥፍራ መጠቀም ያለባችሁም እነዚህኑ ቃላት ነው፡፡

Matthew 10:14

ማቴዎስ 10፡14-15

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ለመስበክ በሚወጡበት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ምን እንደሚጠብቃቸው ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ትዕዛዝ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ ኤቲ፡ “በከተማው ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች መካከል ማንም ሳይበቀላች ቢቀር ወይም ያደመጣችሁ ሰው ባይኖር” እናንተ ይህ ዐሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት ያመለክታል፡፡ ቃላችሁን የማይሰሙ ቢሆን ኤቲ፡ “መልዕክታችሁን ማድመጥ” " (UDB) ወይም “ማለት የፈለጋችሁትን የሚያደምጥ” ከተማ ይህንን በ MAT 10:11 ከተጠቀምከው ቃል ጋር ተመሳሳይ የሆነ ቃልን በመጠቀም ሊትተረጉመው ትችላለህ፡፡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ ኤቲ፡ “ከእግራችሁ ላይ የዚያን ቤት ወይም ከተማ አቧራ አራግፉ፡፡” ይህ እግዚአብሔር በዚያ ቤት ወይም ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን መተውን የሚያመለክት ምልክት ነው፡፡ ይበልጥ ይቀልላቸዋል ኤቲ፡ “መከራቸው ትንሽ ይሆናል፡፡” የሶዶም እና ገሞራ ምድር ኤቲ፡ እግዚአብሔር ከሰማይ በመጣ እሳት ያጠፋቸው በ“ሰዶም እና ገሞራ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች፡፡ ይችህ ከተማ ይህ ሐዋርያትን ወይም መልዕክቶቻቸውን ያልተቀበሉ በከተማይቱ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል፡፡

Matthew 10:16

ማቴዎስ 10፡16-18

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርን ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ በዚህም ሥፍራ ላይ ለመስበክ በሚሄዱበት ወቅት ስለሚያጋጥማቸው ስደት ይነግራቸው ጀምሯል፡፡ ተመልከቱ “ተመልከቱ” የሚለው ቃል በዚህ ሥፍራ ላይ ያለው ጠቀሜታ ከዚህ በታች የተጠቀሰው ሀሳብ ትኩረት እንዲሰጠው ማድረግ ነው፡፡ ኤቲ፡ “ተመልከቱ” ወይም “አዲምጡ” ወይም “ ከዚህ በመቀጠል ለሚናረው ነገር ትኩረት ስጡ”፡፡ እልካችኋለሁ ለተወሰነ ዓላማ ኦየሱስ ልኳቸዋል፡፡ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ እንስሳት በመመሰል ሊያጠቋቸው በሚችሉ የዱር እንስሳት መካከል እንደሚልካቸው ይናገራል፡፡ ( ተመልከት) እንደ በጎች በጎች ራሳቸውን መከላከል አይችሉም፡፡ ( ተመልከት) በተኩላዎች መካከል ኤቲ፡ “እንደ ተኩላ አደገኛ በሆኑ ሰዎች መካከል” ወይም “አደገኛ እንስሳት ከሚያደርጓቸው ነገሮች ጋር የሚመሳሰል ተግባር በሚያደርጉ ሰዎች መካከል” ወይም “ሊያጠቋችሁ በሚችሉ ሰዎች መካከል” ( ተመልከት) እንደ እባብ ብልጦች እና እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ ንጽጽሩን አለመግለጡ የተሻለ ነው፡፡ ኤቲ፡ “በመረዳት እና በጥንቃቄ እንዲሁም በንጹሕ ልብ እና ሥነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ ነገሮችን ፈጽሙ” ( ተመልከቱ) ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጧችኋል ኤቲ፡ “ምክንያቱም ወደ ፍርድ ቤታቸው አሳልፈው ይሰጧኋል” ሸንጎዎች እነዚህ የማህረሰቡን ሰላም የሚጠብቁ የአከባቢው የሃይማኖት መሪዎችን ወይም ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ ኤቲ፡ “ፍርድ ቤቶች” ይገርፏችኋል ኤቲ፡ “በመግረፊያ ይገርፏቸኋል” አሳልፈው ይሰጧኋል “ይወስዷችኋል” ወይም “ይጎትቷችኋል” ( ተመልከት) ስለ እኔ ኤቲ፡ “የእኔ ስለሆናችሁ” (UDB) ወይም “እኔን በመከተላችሁ ምክንያት” ለእነርሱና ለአሕዛብም “ለእነርሱ” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው “ገዥዎች እና ነገሥታት” ነው ወይም አይሁዳዊያን ከሳሾችን ነው (10፡17)

Matthew 10:19

ማቴዎስ 10፡19-20

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለመስበክ ስወጡ ስለሚጋጥማቸው ስደት ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ “ሰዎች ወደ ሸንጎ ስወሰዷችሁ”፡፡ በዚህ ሥፍራ “ሰዎች” ተብሎ የተጠቀሱት በ MAT 10:17 ላይ ሰዎች ተብለው ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ እናንተ “እናንተ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ነው፡፡ አትፍሩ ኤቲ፡ “አትጨነቁ” እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ “እንዴት መናገር እንዳለባችሁ ወይም ምን መናገር እንዳለባችሁ”፡፡ እነዚህ ሁለት ሀሳቦች በአንድነት ሊጣመሩ ይችላሉ፡፡ “ምን ማለት እንዳለባችሁ” ( ተመልከት) በዚያች ሰዓት ኤቲ፡ “በዚያን ጊዜ” (: ተመልከት) የአባታችሁ መንፈስ አስፈላጊ ከሆነ ይህ “የሰማያዊ አበባተታችሁ የእግዚአብሔር መንፈስ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ወይም ይህ የእግዚአብሔርብ መንፈስ የሚያመለክት እንጂ ምድራዊ አባትን የማያመለከት እንደሆነ ለማሳየት የግርጌ ማስታወሻ መጨመረም ይቻላል፡፡ አባት ይህ የእግዚአብሔር ዋና መጠሪያ ነው ( ተመልከት) በእናንተ ውስጥ ኤቲ፡ “በእናንተ በኩል”

Matthew 10:21

ማቴዎስ 10፡21-23

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለመስበክ ስወጡ ስለሚጋጥማቸው ስደት ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ኤቲ፡ “ወንድም ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል እንዲሁም አባቶች ልጆቻቸውን ለሞት አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡” አሳልፎ መስጠት በ MAT 10:17 በተረጎምከው መሠረት ይህንን መተርጎም፡፡ ይነሣሉ ኤቲ፡ “ማመጽ”(UDB) ወይም “መቃወም” ይገድሉአቸውማል ኤቲ፡ “ያስገድሏቿል” ወይም “ ባለስልታናቱ እንዲገድሏቸው ደርጋሉ በሁሉም የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ኤቲ፡ “በሁሉም የተጠላች ትሆናላችሁ” ወይም “ሁሉም ሰዎች ይጠሏችኋል”ተመልከቱ) እናንተ … እናንተ . . . እናንተ ይህ ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያትን የሚያመለክት ነው፡፡ ስለስሜ ኤቲ፡ “በስሜ ምክንያት” ወይም “በእኔ በማመናችሁ ምክንያት” (UDB) እስከ መጨረሻ የሚጸና ኤቲ፡ “እስከ መጨረሻ በታማኝነት የሚቆይ” እርሱ ይድናል ኤቲ፡ “ያን ሰው እግዚአብሔር ያድነዋል” ( ተመልከት) ወደ ቀጣዩ ሽሹ “ወደ ቀጣዩ ከተማ ሽሹ” እስኪመጣ ኤቲ፡ እስኪመጣ

Matthew 10:24

ማቴዎስ 10፡24-25

አያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለመስበክ ስወጡ ስለሚጋጥማቸው ስደት ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም ይህ በአጠቃላይ እውነት የሆነ ነገር ነው፡፡ ይን አንጂ ይህንን ዓረፍተ ነገር ለሁሉም ደቀ መዝሙር እና መምህር ማዋል አንችል፡፡ ደቀ መዝሙር ከመምህሩ “በላይ ጠቃሚ” አይደለም፡፡ ይህ ምልባትም ከመመምህሩ “በላይ ስለማያውቅ” ወይም “ከፍተኛ ደረጃ ስለሌለው” ወይም “የተሸለ ስላልሆነ” ሊሆን ይችላል፡፡ ኤቲ፡ “የደቀ መዝሙሩ አስፈላጊነት ሁል ጊዜ ከመምህሩ ያነሰ ነው” ወይም “መምህሩ አስፈላጊነቱ ከደቀ መዝሙር ሁሉ ጊዜ የተሻለ ነው፡፡ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም “ጌታው ከመምህሩ አይበልጥም”፡፡ ይህ አጠቃላይ መርህ እንጂ ማንኛውንም ባሪያን እና ጌታን አይወክልም፡፡ ባሪያው ከጌታው “አይበልጥም” ወይም “የተሻለ ጠቃሚ” አይደለም፡፡ ኤቲ፡ “ባሪያ ያለው ጠቄታ ሁል ጊዜ ከጌታው ያነሰ ነው፡፡” ወይም “ጌታው ያለው ጠቀሜታ ከባሪያው ሁልጊዜ የበለጠ ነው፡፡” አገልጋይ “ባሪያ” ጌታ “ባለቤት” ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ መሆኑ ይበቃዋል ኤቲ፡ “ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ መሆኑ በቂው ነው” እንደ መምህሩ ኤቲ፡ “መምህሩ የሚያውቀውን ያኽል ቢያውቅ” ወይም “እንደ መምህሩ ቢሆን” እንዲሁም ባሪያውም እንደ ጌታው ኤቲ፡ “ባሪያው እንደ መምህሩ ጠቃሚ መሆኑ ይበቃዋል” ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው ኢየሱስን አንገላተውታል ስለዚህም ደቀ መዛሙርቱም ተመሳሳይ ነገር እንደሚጠብቃቸው ማወቅ አለባቸው፡፡ ካሉት ኤቲ፡ “ሰዎች አንዲህ ብለው ከጠሩት” የቤቱን ባለቤት ኢየሱስ ይህንን ምሳሌያዊ ንግግር የተናገረው ስለራሱ ነው፡፡ ( ተመልከት) ብዔል ዜቡል ይህ ስም 1) እንዳለ “ብዔል ዘቡል” ወይም 2) ጸሐፊው ማስተላለፍ የፈለገው ትርጉም “ሴጣን” በሚለው ሊተረጎም ይችላል፡፡ ቤተሰቦቹ ይህ ምሳሌያዊ ንግግር የሚያመለክተው የኢየሱስን ደቀ መዛሙርት ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 10:26

ማቴዎስ 10፡26-27

አያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለመስበክ ስወጡ ስለሚጋጥማቸው ስደት ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ አትፍሩአቸው በዚህ ሥፍራ ላይ “እነርሱን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የኢየሱ ደቀ መዛሙርትን የሚያንገላቱትን ሰዎች ነው፡፡ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። ኤቲ፡ ሰዎች የደበቋቸውን ነገሮች እግዚአብሔር ይገልጣቸዋል፡፡ ( ተመልከት) በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ። ኤቲ፡ “በጨለማ የነገርኳችሁ ነገር በቀን ለሰዎች ተናገሩ እንዲሁም በጆሮዋችሁ የነገርኳችሁን ነገር ለሰዎች ንገሩ፡፡” ( ተመልከት) በጨለማ የምነግራችሁን ኤቲ፡ “በሚስጥር የሚነግራችሁን” ወይም “በግላችሁ የሚነግራችሁን ነገር” ( ተመልከት) በብርሃን ተናገሩ፤ ኤቲ፡ “በግልጽ ተናገሩ” ወይም “በአደባባይ ተናገሩ” ( ተመልከት) በጆሮም የምትሰሙትን ኤቲ፡ “በጆሮዋችሁ የነገርኳችሁን ነገር” በሰገነት ላይ ስበኩ። ኤቲ፡ “በሚሰማ ድምጽ ሁሉም እንዲሰማ አድርጋችሁ ተናገሩ”፡፡ ሰገነት ኢየሱስ በኖረበት ሥፍራ በከፍታ ላይ ያለ ሥፍራ ሲሆን በከፍተኛ ድምፅ ከዚህ ሥፍራ ሆኖ የሚደረግን ንግግር በሩቅ ሥፍራ ያሉ ሰዎች እንኳ ይሰሙታል፡፡

Matthew 10:28

ማቴዎስ 10፡ 28-31

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለመስበክ ስወጡ ስለሚጋጥማቸው ስደት ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ አጠቃላይ መረጃ በተጨማሪም በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱ ደቀ መዛሙርቱ የሚያጋጥማቸውን ስደት መፍራት ያሌለባቸው ለምን እንደሆነ መናገር የጀመረበት ክፍል ነው፡፡ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ “ሰዎችን አትፍሩ፡፡ ሥጋን መግደል ይችላሉ ነገር ግ ነፍስን ግን መግደል አይችሉም፡፡” ሥጋን መግደል አካላዊ ሞት ማስከተል፡፡ እነዚህ ቃላት ግራ የሚጋቡ ከሆኑ “ልገድሉአችሁ” ወይም “ሌሎች ሰዎችን መግደል” የሚለችሉ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ሥጋ በእጅ ልዳሰስ የሚችል የሰው ክፍል ነፍስ መግደል ሰዎች ከሞቱ በኋላ መጉደት ነፍስ በእጅ ልዳሰስ የማይችል የሰው ክፍል እና ከአካላዊ ሞት በኋላ የሚኖር ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ይህ ጥያቄ እንነዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል “ስለ ድንቢጦች አስቡ፡፡ ያላቸው ዋጋ በጣም ትንሽ ከመሆኑ የተነሳ በአምስት ሳንቲም ሁለቱን ልትገዟቸው ትችለላላችሁ” (UDB). ( ተመልከት) ድንቢጦች እነዚህ በጣም ትንንሽ የሆኑ ጥራጥሬ የሚበሉ ወፎች ሲሆን በዚህ ምሌያዊ ንግግር ውስጥም ሰዎች ምንም ጥቅም የላቸው ብለው ከሚያስባቸው ነገሮች ጋር ተነጻጽሮ ቀርቧል፡፡ አምስት ሳንቲም ይህ ብዙ ጊዜ በሚተረጎምበት ቋንቋ ውስጥ ጥቅም ላይ በዋለው ገንዘብ ውስጥ በሚገኘው ሳንቲም ይተረጎማል፡፡ ይህ የመዳብ ሳንቲም ሲሆን አንድ ሰው በቀን ከሚገኘው ገቢ ውስጥ አንድ ዐሥራ ስድስተኛው ያኸል ነው፡፡ “በጣም ትንሽ ገንዘብ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። ይህ ንግግር እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል “ከእነዚህ መካከል አንዱ እንኳ ወደ ምድር የሚወድቀው አባታችሁ ካወቀው ብቻ ነው” ወይም “አባታችሁ ካወቀው ብቻ ነው ከእነዚህ መካከል አንዱ ወደ ምድር ሊወድቅ የሚችለው”፡፡ (: ተመልከት) አንዱም እንኳ “አንድ ድንቢጥ እንኳ” ወደ ምድረ አይወድቅም “አይሞትም” የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል “በራሳችሁ ላይ እንኳ ስንት ጸጉር እንዳለ እግዚአብሔር ያውቃል” ( ተመልከት) ተቆጥሮአል “ተቆጥሮአል” በዋጋችሁ ከብዙ ድንቢጦች ትበልጣላችሁ “ከብዙ ድንቢጦች ይልቅ እግዚአብሔር ለእናንተ ዋጋ ይሰጣል”

Matthew 10:32

ማቴዎስ 10፡32-33

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለመስበክ ስወጡ ስለሚጋጥማቸው ስደት ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ “ለሌሎች የእኔ ደቀ መዝሙር መሆኑን የሚናገር ማንኛውም ሰው” ወይም “ለእኔ ታማኝ መሆኑን ለማንም ሰው የሚናገር ማንም ሰው” መመስከር “መናገር” በሰዎች ፊት “በሰዎች ፊት” ወይም “በሌሎች ሰዎች ፊት” አባት ይህ የእግዚአብሔር ዋና መጠሪያ ነው ( ተመልከት) በሰዎች ፊት የሚክደኝ ሁሉ “በሰዎች ፊት የሚክደኝ ሁሉ” ወይም “በሰዎች ፊት የማይቀበለኝ ሁሉ” ወይም “በሌሎች ሰዎች ፊት የእኔ ደቀ መዝሙር መሆኑን የማይናር ሁሉ” ወይም “ለእኔ ታማኝ መሆኑን የማይናገር ሁሉ”

Matthew 10:34

ማቴዎስ 10፡34-36

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ስደት መፍራት የሌለባቸው በምን ምክንያት እንደሆነ ማስተማሩን ቀጥሏል አይምሰላችሁ “እንደዚህ አታስቡ” ወይም “እንዲህ አይምሰላችሁ” ሰይፍ ይህ ምሳሌያዊ ንግግር 1)የአመጽ ሞት ("መስቀል" በ MAT 10:38(ተመልከት) ወይም 2) መከፋፈልን የሚያመጣ መከራ ( ተመልከት) ለማምጣት “መመለስ” ወይም "መከፋፈል" ወይም "መለያየት" ሰውን ከአባቱ “ልጅን በአባቱ ላይ” ለሰውም ጠላቶች “የሰው ጠላቶሱ” ወይም “የሰው መጥፎ ጠላቶቹ” ቤተ ሰዎቹ ናቸው “የራሱ ቤተሰብ አባላት ናቸው”

Matthew 10:37

ማቴዎስ 10፡37-39

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ስደት መፍራት የሌለባቸው በምን ምክንያት እንደሆነ ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ የሚወድ . . . ሊሆን አይገባውም፤ ኤቲ፡ “የሚወድ . . . ሊሆን አይገባውም፤” ወይም “የሚትወዱ ከሆነ . . . አትገቡም” የ ይህ “ማንም” ወይም “ይህንን የሚያደረግ” ወይም “ይህንን የሚያደረግ ማንን ሰው” ወይም “ይህንን የሚያደርጉ ሰዎች” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ መውደድ በዚህ ሥፍራ ላይ መውደድ የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው “ወንድማዊ መዋደድን” ወይም “ከጓደኛ የሚገኝ ፍቅርን” የሚያመለክት ነው፡፡ በተጨማሪም “መንከባከብ” ወይም “መሰጠት” ወይም “የሚገኝ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ይህ እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል “የእኔ ሊሆን ፈጽሞ አይገባውም” ወይም “የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይገባውም” ወይም “የእኔ መሆን አይገባውም” የማይዝ . . . አይሆንም አማራጭ ትርጉሞች፡ “የማይዙ . . አይደሉም” ወይም “የማትይዝ ከሆነ . . . አይደለህም” ወይም “የማትይዙ ከሆነ . . . አይደላችሁም፡፡” አንሣ . . . መስቀሉን እና ተከተለኝ ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ለመሞት ፈቃደኛ መሆን ማለት ነው፡፡ ማንሣትን እና ከሌላ ሰው ኋላ መከተልን የሚያመለክቱ የተለመዱ ቃላትን ተጠቀም፡፡ ( ተመልከት) አንሣ “አንሣ” ወይም “አንሣና ተሸከም” የሚያገኝ . . . ያጠፋታል . . የሚያጠፋ . . . ያገኛታል፡፡ እነዚህ ቃላት በተቻለ መጠን በጣም ትንሽ ቃላት አማካኝነት ሊተረጎሙ ይገባል፡፡ አማራጨ ትርጓሜዎች፡ “የሚያገኗት. . . ያጠፏታል . . . የሚያጠፏት . . . ያገኟታል” ወይም “ካገኘሃት . . . ታጠፋታለህ . . . ካጠፋሃት . . . ታገኛታለህ” ማግኘት ይህ “መጠበቅ” ወይም “ደንነቱን መጠበቅ” ከሚለው ቃል ጋር ተቀራራቢ ትርጉም ያለው ነው፡፡ አማራጭ ትርጓሜዎቹ፡ “ለመጠበቅ የሚሞክር” ወይም “ለማዳን የሚሞክር” ( ተመልከት) ያጠፋታል ይህ ሰውዬው ይሞታል ማለት አይደለም፡፡ “እውነተኛ ሕይወት አይኖረውም” ለሚለው ምሳሌያዊ ንግግር ነው፡፡ ( ተመልከት) ነፍሱን የሚያጠፋ ይህ ማለት መሞት ማለት አይደለም፡፡ ይህ ማለት ከራሱ ሕይወት ይልቅ ኢየሱስን መታዘዝ አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ ማለት ነው፡፡ ኤቲ፡ “የራሱን ሕይወት የካደ፡፡” ለእኔ ሲል “በእኔ በማመኑ ምክንያት” ወይም “ለእኔ ሲል” ወይም “በእኔ ምክንያት”፡፡ ይህ በ MAT 10:18. ላይ ካለው “ለእኔ ሲል” ከሚለው ሀረግ ጋር ተመሳሳይ ሀሳብ ያለው ነው፡፡ ያገኛታል ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ትርጉሙ “እውነተኛ ሕይወትን ያገኛል” ማለት ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 10:40

ማቴዎስ 10፡40-41

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ስደት መፍራት የሌለባቸው በምን ምክንያት እንደሆነ ማስተማሩን ቀጥሏል፡፡ የሚ ይህ እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል “ማንም” ወይም “ማንም ሰው” ወይም “ይህን ያደረገ ሰው” የሚቀበል ይህ በ MAT 10:14 ውስጥ “መቀበል” ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ትርጉሙም “እንደ እንግዳ መቀበል ማለት ነው፡፡” እናንተ በዚህ ሥፍራ ላይ “እናንተ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሱስ እያስረማራቸው ያሉትን ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ነው፡፡ የላከኝን ይቀበላል። “የላከኝን እግዚአብሔር አብን ይቀበላል”

Matthew 10:42

ማቴዎስ 10፡42-42

አያያዥ ዓርፈተ ነገር ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለመስበክ ሲወጡ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ምን ምን ነገር እንደሚያጋጥማቸው ማስተማሩን አጠናቀቀ፡፡ የሚሰጥ ሁሉ “የሚሰጥ ማንኛውም ሰው” ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ ይህ እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል “የእኔ ደቀ መዝሙር ስለሆነ ከእነዚህ ከታነናናሺቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ የሚሰጥ ማንም ሰው” ወይም “ከእነዚህ ደቀ መዛሙርቶቼ መካከል ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ እንዲጠጣ የሚሰጥ ማንኛውም ሰው” ዋጋው አይጠፋበትም። “ይህ ሰው በእርግጥ ሽልማቱን ይቀበላል” ( ተመልከት) አያጣም “አይከለከልም”፡፡ ይህ በምንም ዓይነት መንገድ ንብረቱን ከመውሰድ ጋር አይገናኝም፡፡


Translation Questions

Matthew 10:1

ኢየሱስ ለዐሥራ ሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ምን ሥልጣን ሰጣቸው?

ኢየሱስ ለዐሥራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት እርኩሳን መናፍስትን እንዲያስወጡ እና ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው። [10:1]

Matthew 10:2

ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጠው ደቀመዝሙር ስም ማን ነው?

ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጠው ደቀመዛሙር ስም የአስቆሮቱ ይሁዳ ነበር። [10:4]

Matthew 10:5

በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ወደ የት ላካቸው?

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን የላከው ከእሥራኤል ቤት ወደ ጠፉት በጎች ብቻ ነበር። [10:6]

Matthew 10:8

ደቀመዛሙርቱ ማንኛውንም ገንዘብ ወይም ትርፍ ልብሶች ከእነርሱ ጋር መያዝ ነበረባቸውን?

በፍጹም፣ ደቀመዛሙርቱ የትኛውንም ልብስ ወይም ተጨማሪ ልብስ መያዝ አይይዙም። [10:9]

ደቀመዛሙርቱ ማንኛውንም ገንዘብ ወይም ትርፍ ልብሶች ከእነርሱ ጋር መያዝ ነበረባቸውን?

በፍጹም፣ ደቀመዛሙርቱ የትኛውንም ልብስ ወይም ተጨማሪ ልብስ መያዝ አይይዙም። [10:10]

Matthew 10:11

ከመንደር ወደ መንደር በሚሄዱ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ የሚቆዩት የት ነበር?

ደቀመዛሙርት በመንደሩ ውስጥ የተገባው የሆነን ሰው አግኝተው ለቅቀው እስኪሄዱ ድረስ በዚያ ይቆያሉ። [10:11]

Matthew 10:14

ደቀመዛሙርቱን ያልተቀበሉ ከተሞች ላይ ወይም ቃሎቻቸውን ባልሰሙት ላይ ምን ይሆናል?

ደቀመዛሙርቱን ባልተቀበሉ ወይም ቃሎቻቸውን ባልሰሙት ከተሞች ላይ የሚኖረው ፍርድ ከሶዶም እና ጎሞራ ፍርድ የባሰ ይሆናል። [10:14]

ደቀመዛሙርቱን ያልተቀበሉ ከተሞች ላይ ወይም ቃሎቻቸውን ባልሰሙት ላይ ምን ይሆናል?

ደቀመዛሙርቱን ባልተቀበሉ ወይም ቃሎቻቸውን ባልሰሙት ከተሞች ላይ የሚኖረው ፍርድ ከሶዶም እና ጎሞራ ፍርድ የባሰ ይሆናል። [10:15]

Matthew 10:16

ሰዎች በደቀመዛሙርት ላይ ምን እንደሚያደርጉ ኢየሱስ ተናገረ?

ሰዎች ደቀመዛሙርትን ወደ ሸንጎዎች አሳልፈው እንደሚሰጡ፣ እንግሚገርፏቸው፣ ወደ መንግሥታትና ገዢዎች እንደሚያመጧቸው ኢየሱስ ተናገረ። [10:17]

ሰዎች በደቀመዛሙርት ላይ ምን እንደሚያደርጉ ኢየሱስ ተናገረ?

ሰዎች ደቀመዛሙርትን ወደ ሸንጎዎች አሳልፈው እንደሚሰጡ፣ እንግሚገርፏቸው፣ ወደ መንግሥታትና ገዢዎች እንደሚያመጧቸው ኢየሱስ ተናገረ። [10:18]

Matthew 10:19

በተወሰዱ ጊዜ በደቀመዛሙርቱ በኩል የሚናገረው ማን ነው?

የአብ መንፈስ ደቀመዛሙርቱ በተወሰዱ ጊዜ በእነርሱ አልፎ ይናገራል። [10:20]

Matthew 10:21

በመጨረሻ የሚድነው ማን እንደሚሆን ነው ኢየሱስ የተናገረው?

እስከ መጨረሻ የሚጸኑት ብቻ እንደሚድኑ ኢየሱስ ተናገረ። [10:22]

Matthew 10:24

ኢየሱስን የሚጠሉት የኢየሱስን ደቀመዛሙርት ምን ያደርጓቸዋል?

ኢየሱስን የሚጠሉት ደቀመዛሙርቱንም ይጠሏቸዋል። [10:24]

ኢየሱስን የሚጠሉት የኢየሱስን ደቀመዛሙርት ምን ያደርጓቸዋል?

ኢየሱስን የሚጠሉት ደቀመዛሙርቱንም ይጠሏቸዋል። [10:25]

Matthew 10:28

እነማንን እንዳንፈራ ነው ኢየሱስ የነገረን?

ሰውነትን ገድለው ነፍስን ግን መግደል የማይችሉትን መፍራት የለብንም። [10:28]

እነማንን እንዳንፈራ ነው ኢየሱስ የነገረን?

ሰውነትን ገድለው ነፍስን ግን መግደል የማይችሉትን መፍራት የለብንም። [10:28]

Matthew 10:32

በሰዎች ፊት ለሚመሰክርለት ኢየሱስ ምን ያደርጋል?

በመንግሥተ ሰማይ በአብ ፊት ኢየሱስ ይመሰክርለታል። [10:32]

በሰዎች ፊት ለሚክደው ኢየሱስ ምን ያደርጋል?

በመንግሥተ ሰማይ በአብ ፊት ኢየሱስ ይክደዋል። [10:33]

Matthew 10:34

ምን ዓይነት መከፋፈልን እንደሚያደርግ ነው ኢየሱስ የተናገረው?

በቤት ውስጥ መከፋፈልን ለማድረግ እንደ መጣ ኢየሱስ ተናገረ። [10:34]

ምን ዓይነት መከፋፈልን እንደሚያደርግ ነው ኢየሱስ የተናገረው?

በቤት ውስጥ መከፋፈልን ለማድረግ እንደ መጣ ኢየሱስ ተናገረ። [10:35]

ምን ዓይነት መከፋፈልን እንደሚያደርግ ነው ኢየሱስ የተናገረው?

በቤት ውስጥ መከፋፈልን ለማድረግ እንደ መጣ ኢየሱስ ተናገረ። [10:36]

Matthew 10:37

ስለ ኢየሱስ ሲል ሕይወቱን የሚያጣ ምን ያገኛል?

ስለ ኢየሱስ ሲል ሕይወቱን የሚያጣ ሕይወቱን ያገኛል። [10:39]

Matthew 10:42

ከደቀመዛሙርቱ ለትንሹ ቀዝቃዛ ውሃ የሚሰጥ ሰው ምን ይቀበላል?

ከደቀመዛሙርቱ ለትንሹ ቀዝቃዛ ውሃ የሚሰጥ ሰው ዋጋውን ይቀበላል። [10:42]


ምዕራፍ 11

1 እንዲህም ሆነ፣ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት አዝዞ ከጨረሰ በኋላ፣ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ ሄደ፡፡ 2 ዮሐንስ በወህኒ ቤት ሆኖ የክርስቶስን ሥራዎች በሰማ ጊዜ፣ በደቀ መዛሙርቱ መልእክት ላከበት፡፡ 3 እንዲህም አለው፣ "የሚመጣው አንተ ነህ፣ ወይስ መጠበቅ ያለብን ሌላ ሰው አለ?" 4 ኢየሱስም መለሰ እንዲህም አላቸው፤ “ሂዱና፣ ለዮሐንስ የምታዩትንና የምትሰሙትን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ 5 ዕውሮች ብርሃናቸውን እያገኙ፣ አንካሶች እየተራመዱ፣ ለምጻሞች እየነጹ፣ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ፣ ሙታን እየተነሡ፣ ድኾችም የምሥራች እየሰሙ ነው፡፡ 6 በማንኛውም ሁኔታ በእኔ የማይሰናከል ሁሉ የተባረከ ነው" ። 7 እነዚህ ሰዎች እንደ ሄዱ፣ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ መናገር ጀመረ፣ እንዲህም አለ፣ "ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆን? 8 ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ? የሚያምር ልብስ የለበሰውን? በርግጥ፣ ጥሩ ልብስ የሚለብሱ የሚኖሩት በቤተ መንግሥት ነው፡፡ 9 ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን ነውን? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጠውን ነው፡፡ 10 እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ስለ እርሱ ነው፦ 'መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡' 11 እውነት እላችኋለሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም። በመንግሥተ ሰማይ ግን፣ ታናሹ ሰው ከእርሱ ይበልጣል፡፡ 12 ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በዐመፅ ትቸገራለች፣ ዐመጸፀኞች ግን በኅይል ይወስዷታል፡፡ 13 እስከ ዮሐንስ ዘመን ድረስ ሕጉም፣ ነቢያቱም ሁሉ ትንቢት ሲናገሩ ነበርና፡፡ 14 እንግዲህ ልትቀበሉት ፈቃደኞች ከሆናችሁ፣ የሚመጣው ኤልያስ እርሱ ነው፡፡ 15 የሚሰማ ጆሮ ያለው፣ ይስማ። 16 ይህን ትውልድ ከምን ጋር ላነጻጽረው? በገበያ ተቀምጠው፣ እየተቀባበሉ እንደሚዘፍኑ ልጆች ነው፡፡ 17 'ዋሽንት ነፋንላችሁ፣ አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወጣንላችሁ እናንተም አላለቀሳችሁም' ይላሉ። 18 ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላና የወይን ጠጅ ሳይጠጣ በመምጣቱ፣'ጋኔን አለበት' አሉት። 19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ በመምጣቱ፣ 'ተመልከቱ ይህ ሰው በላተኛና ጠጪ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና፣ የኃጢአተኞች ወዳጅ ነው!' አሉት ነገር ግን ጥበብ በሥራዋ ትክክል ሆነች፡፡ 20 ኢየሱስም ብዙ ታላላቅ ሥራዎች ያደረገባቸውን ከተማዎች፣ ንስሓ ባለመግባታቸው ይገሥጻቸው ጀመር፡፡ 21 ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ታላላቅ ሥራዎች በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ ማቅ ለብሰውና፥ ዐመድ ነስንሰው ድሮ ንስሓ በገቡ ነበር፡፡ 22 ነገር ግን በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ፣ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል፡፡ 23 አንቺ ቅፍርናሆም፣ እስከ ሰማይ የወጣሽ ይመስልሻልን? በፍጹም፤ ወደ ሲኦል ትወርጂያለሽ፡፡ ለአንቺ እንደተደረጉት ትልልቅ ነገሮች በሰዶም ተደርገው ቢሆን ፣ እስከ አሁን በኖረች ነበር፡፡ 24 ነገር ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን፣ ከእናንተ ይልቅ ለሰዶም ይቀልላታል፡፡ 25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ ይህን ከዐዋቂዎችና ከአስተዋዮች ሰውረህ እንደ ሕፃናት ላልተማሩት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።” 26 አዎ፣ አባት ሆይ፣ በፊትህ እጅግ ደስ የሚያሰኝህ ይህ ሆኖአልና፡፡ 27 ከአባቴ ሁሉ ተሰጥቶኛል፣ ከአባት በቀር ማንም ልጅን የሚያውቀው የለም፤ ከልጅም በቀር፣ ልጁም ሊገልጥለት ከሚፈልገው በቀር፣ አባትን የሚያውቅ ማንም የለም፡፡ 28 እናንተ ደካሞች፣ ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋላሁ፡፡ 29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህና በልቤ ትሁት ነኝ፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡፡ 30 ቀንበሬ ቀላል፣ ሸክሜም የማይከብድ ነው፡፡



Matthew 11:1

ማቴዎስ 11፡1-3

አጠቃላይ መረጃ ይህ በታሪከው ውስጥ ጸሐፊው ኢየሱስ ለመጥመቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ጥያቄ ምን ዓይነት ምላሽ እንደሰጠ የሚተርከው ታሪክ ጅማሬ ነው፡፡ ( ተመልከት) ከዚያ አለፈ ይህ ሀረግ የአዲስ ታሪክ ጅማሬ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የአንድ ታሪክ ጅማሬን ማሳያ መንገድ በቋንቋችሁ ውስጥ ካለ ያንን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ “ከዚያ” ወየም “ከዚያ በኋላ” በሚሉ ቃላት ሊተረጎም ይችላል፡፡ ማዘዙን ይህ ቃል “ማስተማር” ወይም “ትዕዛዝ መስጠት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ዐሥራ ሁለቱ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ይህ በኢየሱስን የተመረጡን ዐሥራ ሁለቱን ያመለክታል፡፡ አሁን “በዚያን ጊዜ”፡፡ ይህንን ሳትተረጉሙት ማለፍ ትችላላችሁ፡፡ ዮሐንስ በእስር ቤት ሆኖ በሰማ ጊዜ አማራጭ ትርጓሜዎች፡ “በእርስ ቤት ያለው ዮሐንስ በሰማ ጊዜ” ወይም “ሌሎች ሰዎች በእርስ ላይ ላለው ለዮሐንስ በነገሩት ጊዜ” በደቀ መዛሙርቱ በኩል መልዕክትን ላከ መጥመቁ ዮሐንስ በራሱ ደቀ መዛሙርት በኩል ወደ ኢየሱስ መልዕክትን ላከ እንዲህም አለው “እርሱን” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው ኢየሱስ ነው፡፡ የሚትመጣው አንተ ነህን “የሚትመጣው” ወይም “ትመጣለህ ተብለህ የሚትጠበቀው” ተብሎ ይተርጎም ይህ የሚያመለክተው መስሑን ወይም ክርስቶስን ነው፡፡ ( ተመልከት) ሌላ እንፈለግ “ሌላ እንጠብቅ”፡፡ “እኛ” የሚለው ተውላጠ ስም ሁሉንም አይሁዳዊንን የሚያመለክታል እንጂ የዮሐንስን ደቀ መዛሙርት ብቻ አይደለም፡፡

Matthew 11:4

ማቴዎስ 11፡4-6

ለዮሐንስ መልሱ ነገሩት “ለዮሐንስ ነገሩት”

Matthew 11:7

ማቴዎስ 11፡7-8

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለመጥመቁ ዮሐንስ መናገር ጀመረ፡፡ ምን ልታዩ ወጣችሁ . . . ንፋስ? ኢየሱስ ሕዝቡ ስለመጥመቁ ዮሐንስ እንዲያስቡ ለማድረግ እነዚህ ሦስት ደረጃዎች ያሉት ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡ እንዲህ ሊተረጎም ይችላል “ንፋስ . . . ለማየት ነው የወጣችሁትን? በእርግጥ አይደለም!” ወይም “በእርግጠኝነት ንፋስን ለማየት አልወጣችሁም!” ( ተመልከት) በንፋስ የሚወዛወዝ ሸንበቆ ይህ እንዲህ ሊሆን ይችላል 1) በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ የሚበቅሉ ተክሎች ወይም 2) አንድን ሰው ለማመልከት የቀረበ ምሳሌያዊ ንግግር፡ “በንፋስ እንደሚዠዋዠው ሸንበቆ ያለ ሰው፡፡” ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ሁለት አማራጭ ትርጓሜዎች ይኖሩታል፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰው 1) በቀላሉ በንፋስ አማካኝነት የሚንቀሳቀስ፣ ይህ ሀሳቡን በቀላሉ የሚለውጥ ሰውን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ምሳሌያዊ አነጋገር ነው፡፡ ወይም 2) ንፋሱ ስነፍስ ድምፅ የሚያሰማ፡፡ ይህ ምሳሌያዊ ገለጻ ብዙ ነገር ይናገራል ይሁን እንጂ ይህን ያኸል ጠቃሚ ነገር አይናገርም፡፡ ( and ተመልከት) ሸንበቆ “ረጅም፣ ሳር መሰል ተክል” ለስላሳ ልብስ የለበሰ “ውድ ልብስ የለበሰ”፡፡ ሀብታሞች ይህንን ዓይነት ልብስ ይለብሱ ነበር፡፡ የምር ይህ ቃል ብዙ ጊዜ “እነሆ” በሚል ቀጥሎ ለሚመጣው ሀሳብ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ በሚያሳስብ ቃል ተተርጉሟል፡፡ ተለዋጭ ትርጉሙለ “በእርግጥ”

Matthew 11:9

ማቴዎስ 11፡9-10

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጥር 10 ላይ ኢየሱስ ከነቢይ ሚልክያስ መጽሐፍ በመጥቀስ የመጥመቁ ዮሐንስ ሕይወት እና አገልግሎት በተነገረው ትንቢት መሠረት መሆኑን አሳይቷል፡፡ ነገር ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ - ነብይ ይህ ስለመጥመቁ ዮሐንስ የተጠየቁ ተከታታይ ጥያቄዎች ቀጣዩ ክፍል ነው፡፡ ( ተመልከት) ነገር ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ - ነብይ? አዎን እላችኋለሁ “እናንተ” የሚለው በብዙ ቁጥር የተገለጸው ተውላጠ ስም በሁለቱም ሁኔታዎች ውስጥ ሕዝቡን የሚያመለክት ነው፡፡ ከነቢይም የሚበልጥ “ተራ ነቢይ ያለሆነ” ወይም “ከተራ ነቢይ በጣም የሚበልጥ” ይህ እርሱ ነው “ይህ” መጥመቁ ዮሐንስ የሚያመለክት ነው፡፡ ስለ እርሱ የተጻፈው እርሱ ነው “እርሱ” የሚው ቃል “በቀጣዩ ሀረግ ውስጥ “መልዕክተኛዬ” የተባለው የሚያመለክት ነው፡፡ መልዕክተኛዬን እልካለሁ “እኔ” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው እግዚአብሔር ነው፡፡ የዚህ የብሉይ ኪዳን ትንቢት ጸሐፊ እግዚአብሔር የተናገረውን በቀጥታ ጽፏል፡፡ በፊትህ “ከፊትህ” ወይም “ከአንተ በፊት ይሄድ ዘንድ፡፡” “አንተ” የሚለው ተውላጠ ስም የነጠላ ቁጥር ነው፡፡ ምክንያቱም በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ መስሑ የተነገረ ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 11:11

ማቴዎስ 11፡11-12

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ከሴቶች ከተወለዱ ሁሉ “ሴቶች ከወለዷቸው ሰዎች መካከል” ወይም “በምድር ላይ ከኖሩ ሰዎች መካከል” ከመጥመቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም ኤቲ፡ “መጥመቁ ዮሐንስ ትልቁ ነው” በመንግስተ ሰማያት እግዚብሔር በሚመሰርተው አገዛዝ ውስጥ፡፡ ኤቲ፡ “ወደ መንግስተ ሰማየት ከሚገቡ ሰዎች መካከል” ከእርሱ የሚበልጥ የለም “ከመጥመቁ ዮሐንስ በላይ ጠቃሚ የለም” ከመጥመቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ “”ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ” መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። አማራጭ ትርጓሜዎቹ 1) ግፈኞች በግፍ ይናጠቁታል ወይም 2) “ሰዎች የመንግስተ ሰማይን ዋና ሀሳብ ያሳድዳሉ እንዲሁም ግፈኞች ልቆጣጠሩት ይሞክራሉ” ወይም 3) “መንግስተ ሰማያት በኃይል ወደፊት ትሄዳለች እንዲሁም ኃይለኛ የሆኑ ሰዎች የዚህ አካል ለመሆን ይፈልጋሉ፡፡”

Matthew 11:13

ማቴዎስ 11፡13-15

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ሕግ “የሙሴ ሕግ” ዮሐንስ “መጥመቁ ዮሐንስ” እና አናንተ ከሆነክ “አናንተ” የሚለው ተውላጠ ስም በሕዝቡ መካከል ያሉ ሰዎችን ነው፡፡ ይህ ኤልያስ ነው “ይህ” መጥመቁ ዮሐንስ የሚያመለክት ነው፡፡ ይህ ሀረግ መጥመቁ ዮሐንስ በብሉይ ኪዳን የተገለጸው የነብዩ ኤልያስ ጋር ተዛምዶ ያለው ነው ይሁን እንጂ መጥመቁ ዮሐንስ ኤልያስ ግን ማለት አይደለም፡፡ ( ተመልከት) የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ ኤቲ፡ “የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ” የሚሰማ ጆሮ ያለው “መስማት የሚችል ጆሮ ያለው” ወይም “የሚሰማኝ ሁሉ” ይስማ በደንብ ይስማ” ወይም “ለተናገርኩት ነገር ትኩረት ይስጥ”

Matthew 11:16

ማቴዎስ 11፡16-17

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ይህን በምን እመስለዋለሁ? ይህ የጥያቄ መጀመሪያ ነው፡፡ይህንን ጥያቄ ኢየሱስ የተጠቀመው በዚያ ዘመን ይኖር የነበረውን ሕዝብ እና ሕጻናት በገቢያ ሥፍራ ከሚያደርት ነገር ጋር በማነጻጸር ነው፡፡ በጥያቄ ጀምሯል፡፡ “ ( ተመልከት) በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፥ እነርሱም በዚያ ተቀምጠው እርስ በእርሳቸው ይጠራራሉ፡፡ ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ትርጉም እንደዚህ ሊሆን ይችላል 1) ኢየሱስ “ዋሽንት ነፋላቸው” እንዲሁም ዮሐንስ “አለቀሰላቸው” ነገር ግን “ይህ ትውልድ” ለመደነስም ሆነ ለማልቀስ አሻፈረኝ አለ፡፡ ይህ የመታዘዝ ምሳሌ ነው፡፡ ወይም 2) ፈሪሳዊያን እና ሌለች ሃይማኖታዊ መሪዎች እነርሱ በሙሴ ሕግ ላይ የጨመሯቸውን ሕጎች አልታዘዝ አለ በማለት ሕዝቡን ይወቅሱታል፡፡ ( ተመልከት) ይህ ተውልድ “በዚህ ዘመን የሚኖሩ ሰዎች” ወይም “እነዚህ ሰዎች” ወይም “እናንተ የዚህ ዘመን ሰዎች” የገቢያ ሥፍራ ይህ ትልቅ የሆነ ሰዎች የተለያዩ ነገሮችን የሚገዙበትን እና የሚሸጡበት ክፍት ሥፍራ ነው፡፡ ዋሽንት ተጫወትንላችሁ “እኛ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በገቢያ ሥፍራ የተቀመጡትን ልጆች ነው፡፡ “እናንተ” የሚለው ቃ የሚያመለክተው “ይህንን ተውልድ” ነው ወይም ሙዝቃ ሰምቶ ምንም ምላሽ ያልሰጠውን ሕዝብ ነው፡፡ ዋሽንት የመሰለ የሙዚቃ መሣሪያ ይህ ረጅም የሆነ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያ ነው፡፡ እንዲሁም አልደነሳችሁም “ይሁን እንጂ በሙዚቃው አልተጫወታችሁም” ወይም አላለቀሳችሁም "ከእኛ ጋርም አላለቀሳችሁም"

Matthew 11:18

ማቴዎስ 11፡18-19

አያያዥ ዓረፍተ ነገር ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ መጥመቁ ዮሐንስ መናገሩን አጠናቀቀ፡፡ ምግብ ሳይበላና ሳይጠጣ "ምግብ ሳይበላ" ይህ ዮሐንስ ምንም ዓይነት ምግብ በልቶ አያውቅም ማለት አይደለም፡፡ ኤቲ፡ “ብዙ ጊዜ ይጾም ነበር” ወይም “ጥሩ ምግብ አይበላም ነበር” (UDB) እንዲህ አሉት፡፡ “እርኩስ መንፈስ አለበት” ኢየሱስ ሰዎች ስለ ዮሐንስ የተናገሩትን በቀጥታ ጠቅሷል፡፡ ይህ በቀጥታ እንዲህ ሊጠቀስ ይችላል ፡ “እነርሱም እርኩስ መንፈስ አለበት አሉት” ወይም “ዳብሎስ አለበት አሉት” ወይም “እርኩስ መንፈስ አለበት ብለው ከሰሱት”( ተመልከት) እነርሱ “እነርሱ” የሚለው ተውላጠ ስም በዚያ ዘመን ይኖሩ የነበረው ሰዎችን ያመለክታል፡፡ የሰው ልጅ በዚያ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ኢየሱስ የሰው ልጅ እንደሆነ መረዳት ይኖርባቸው ብሎ ይጠብቅ ስነበር እንዲህ ተብሎ መተርጎም ይችላል “እኔ የሰው ልጅ እነርሱ ግን እንዲህ አሉት፣ “እነሆ፥ በላተኛው ኢየሱስ እንደ የሰው ልጅነቱ ሰዎች ስለ እርሱ የተናገረውን ጠቅሷል፡፡ ይህንን በትምህርት ጥቅስ ውስጥ ሳናስቀምጥ እንዲህ ሊተረጎም ይችላል፡ “በታለተኛ ነው አሉት” ወይም “ብዙ ይበላል ብለው ከሰሱት”፡፡ የሰው ልጅ የሚለው ሀረግ 1እኔ የሰው ልጅ” ብለህ ከተጎምህ ይህንን ደግሞ “እኔን በታለተኛ ነው አሉኝ” ብለህ መተርም ትችላለህ፡፡ በታለተኛና ነው "እርሱ በላተኛ ነው” ወይም “ሁል ጊዜ ብዙ ምግብ ይበላል” ጠጭ "ጠጭ" ወይም "ብዙ አልኮል ሁል ጊዜ ይጠጠቃል" ይሁን እንጂ ጥበብም በሥራዋ ጸደቀች። ይህ ምናልባትም ኢየሱስ ከሁኔታው ጋር ተስማሚ የሆነ ምሳሌን የተናገረበት ነው፡፡ ምክንያቱም ሕዘቡም እርሱ እና ዮሐንስን ስለ ጥበባቸው አልተቀበሏቸውም፡፡ በ UDB ውስጥ ባለው መሠረት በቀጥታ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ( ተመልከት) ጥበብ ጸደቀች በዚህ ገለጻ መሠረት ኢየሱስ ጥበብን በሴት ይመስላታል፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ ጠበብ ከእግዚአብሔር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሚያደረገን የሚናገር ሳይሆን ጥበብ ራሱ ትክክለኛ እንደሆነች የተገለጸበት ነው ( ተመልከት) በሥራዎቿ “እርሷ” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው “”ኢየሱስ በሴት የመሰላትን ጥበብን ነው፡፡

Matthew 11:20

ማቴዎስ 11፡20-22

አጠቃላይ መረጃ: ኢየሱስ ከዚህ በፊት የተለያዩ ተዓምራትን ባደረገባቸው ሥፍራዎች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን መገሰጽ ጀመረ፡፡ ከተማዎቹን ገሰጸ ኢየሱስ በዚህ ሥፍራ ላይ ምሌን በመጠቀም በከተማዎቹ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ትክክለኛ ስላልሆነው ሥራቸው ገሰጸቻ ( ተመልከት) ከተማዎች "ከተማዎች" ታላላቅ ተዓምራት የተደረጉባቸው ይህ እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡ “ብዙዎቹን ታላላቅ ተዓራትን ያደረገባቸው ሥፍራዎች” ( ተመልከት) ታላላቅ ተዓምራት ኤቲ፡ “ታላላቅ ሥራዎች” ወይም “ታላላቅ ኃይል” ወይም “ተዓምራት” ንሰሓ ስላልገቡ “እነርሱ” የሚለው ተውላጠ ስም በከተማዎቹ ውስጥ የሚኖሩ ንሰሓ ያልገቡትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! ኢየሱስ ኮራዚ እና ቤተ ሳይዳ የተባሉ ከተማዎች የሚደምጡ አድርጎ ነው የተናገረው፡፡ ይሁን እንጂ እነርሱ አይሰሙን፡፡ ( ተመልከት) ኮራዚ . . . ቤተ ሳይዳ . . . ጢሮስ . . . ሲዶና በእነዚያ ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ለማመልከት የዋለ ምሳሌያዊ ንግግር ነው፡፡ ( ተመልከት) እናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ይህ እንዲህ ሊተረጎም ይችላል: "በእናንተ መካከል ያደረኩትን ተዓምራት በጢሮስና በሲሶና ባደረግ ኖሮ” ( ተመልከት) ወዮልሽ . . . በእናንተ መካከል የተደረገው “አንተ” የሚለው ተውላጠ ስም የተገለጸወ በነጣ ቁጥር ነው፡፡ ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና። በዚህ ሥፍራ “እነርሱ” ተብሎ የተገለጸው የጢሮስና ሲዶና ሰዎች ነው፡፡ ንሰሓ "ስለ ኃጢአታቸው ይቅርታን በጠየቁ ነበር" በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። "በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ እግዚብሔር ለጢሮስ እና ለሲዶና የተሻለ መምህረት ያደርግላቸዋል" ወይም "እግዚብሔር ከጢሮስ እና ከሶዶና ሐህዝቦች ይልቅ እግዚአብሔር እናንተን ይቀጣል፡፡” በተዘዋዋር የተገለጸው መረጃ “ምንም እንኳ ያደረኳቸውን ተዓምራትን ቢትመለከቱም ንሰሓ ስላልገባቹ እና በእኔ ስላላመናችሁ፡፡” ( ተመልከት) ከአንተ ይልቅ በዚህ ሥፍራ “አንተ” የሚለው ተውላጠ ስም በነጠላ ቁጥር ሲሆን ኮራዚ ወይም ቤተ ሳይዳን ያመለክታል፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 11:23

ማቴዎስ 11፡23-24

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ኢየሱስ ከዚህ በፊት ተዓምራት ያደረገባቸው ከተማዎች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን መገሰጹን ቀጥሏል፡፡ . እንች ቅፍርናሆም በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ በቅርፍናሆን የሚኖሩ ሰዎች ልክ እንደሚያደምጡ አድርጎ ይናገራል ይሁን እንጂ እነርሱ እየሰዳመጡት አይደለም፡፤ “አንተ” የሚለው ተውላጠ ስም በነጠላ ቁጥር የተገለጸ ሲሆን በእነዚህ ሁለት ጥቅሶች ውስጥ ቅፍርናሆምን የሚያመለክት ነው፡፡ ( and ተመልከት) ቅፍርናሆም . . . ሶዶም የእነዚህ ከተሞች ስም በቅፍርናሆም እና ሶዶም ውስጥ ለሞኖሩ ሰዎች ምሳሌ ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ( ተመልከት) እስከ ሰማይ ከፍ አልኩ ብለስ ታስቢያለሽ? የቅፍርናሆም ሕዝቦች ስላላቸው ትምክት ለመገሰጽ ኢየሱስ የተጠቀመው ጥያቄ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ ሊተረጎም ይችላል “እስከ ሰማይ እሄዳለሁ?" ወይም “እግዚአብሔር ያከብረኛል ብለሽ ታስቢያለሽ?" ( እና ተመልከት) ከፍ ከፍ እላለሁ "እከብራለሁ" ( ተመልከት) ወደ ሲኦል ትወርጂያለሽ "እግዚአብሔር ወደ ሲኦል ያወርድሻ" ( ተመልከት) በአንቺ የተደረገው ተአምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን፥ "በእናንተ ያደረኳቸውን ተዓምራት በሶዶም አድርጌ ቢሆን ኖሮ" ( ተመልከት) ታላላቅ ነገሮች "ታላላቅ ሥራዎች" ወይም "የኃይል ሥራ" ወይን "ተዓምራት" እስከ ዛሬ በኖረች ነበርና። “እርሷ” የሚለው ተውላጠ ስም የሶዶምን ከተማ ያመለክታል፡፡ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም አገር ይቀልላታል። ይህ እንዲህ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል “በፍርድ ቀን እግዚብሔር ከእናንተ ይልቅ ለሶዶም ምድር ይበልይ ምህረት ያደርግላታል” ወይም “በፍርድ ቀን እግገዚአብሔር እናንተ ከሶዶም ይልቅ ይቀጣችኋል”፡፡ ይህ በተዘወዘዋር መልኩ የሚሰጠው መረጃ “ምንም እንኳ እኔ የሠራኋቸውን ተዓምራትን ቢትመለከቱም ንሰሓ ስላልገባቹ እና በእኔ ስላለመናችሁ” ( ተመልከት)

Matthew 11:25

ማቴዎስ 11፡25-27

አጠቃላይ መረጃ: በቁጥር 25 እና 26 ላይ በሕዝቡ መካከል ሆኖ በሰማይ ወደሚኖረው አባቱ ጸለየ፡፡ በቁጥር 27 እንደገና ለሕዝቡ መናገር ጀመረ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጠ ከዚያም እንዲህ አለ ይህ እንዲህ ማለት ሊሆን ይችላል 1) በ MAT 10:5 የተላኩት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከሄዱበት ተመልሰዋል (MAT 12:1 ተመልከት) እንዲሁም አንድ ሰው ስላለው አንድ ነገር ኢየሱስ ምላሽ እየሰጠ ነው ወይም 2) ኢየሱስ ንሰሓ ስላልገቡት ከተሞች የተናገረውን የፍረድ ንግግር አጠቃሏል፡ “ከዚህ በተጨማሪ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡፡” አባት . . . ልጅ በእግዚአብሔር እና ኢየሱስ መካከል ያለውን የአባት እና ልጅ ግንኙነት የሚያሳይ የማዕረግ ስም ነው ( የሰማይ እና የምድር ጌታ ይህንን እንደ ምሳሌ መረደት ይቻላል “በሰማይ እና በምደር ባሉት ነገሮቸ ሁሉ ላይ ጌታ የሆነ” ወይም “የዓለማት ሁሉ ጌታ” ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው “እነዚህን ነገሮች” የሚለው ሀረግ ምንን እንደሚያመለክት ግልጽ ነው፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ ቋንቋ ለመናገር አማራጭ ትርጉም ተመራጭ ይሆናል፡ “ጠብባን እና የተማሩ ሰዎች ለማወቅ ያልተፈቀደላቸውን እውነት ምንም ለማያውቁ ሰዎች ገለጥክላቸው፡፡” ይህንን ነገር ከ . . . ሰወርክ “ይህንን ከ. . . ሰወርክ” ወይም “ይህንን ነገር ለ . . . አልገለጥክም”፡፡ አልገለጥም የሚለው ግሥ “የመገለጥ” ተቃራኒ ነው፡፡ ጠቢባን እና አዋቂዎች "ጠቢባን እናነአዋቂዎች የሆኑ ሰዎች” ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ጠቢባን እና አዋቂዎች እንደሆኑ የሚያስቡ ሰዎች” ( ተመልከት) ገለጥክላቸው “አስታወካቸው”፡፡ “ለእርሱ” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው በዚህ ቁጥር መጀመሪያ አከባቢ የተጠቀሰውን “እነዚህ ነገሮች” የሚለውን ነው፡፡ ላልተማሩ፣ እንደ ትንንሽ ሕጻናት ላሉት ይህ አጠቃላይ ሀረግ “ትንንሽ ልጆች1 እና “ያልተማሩ” ወይም “የማያውቁ” የሚለውን በውስጡ አጠቃሎ በመያዝ የተተረጎመ ነው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ምንም የማያውቁ ትንንሽ ልጆች” ይህ በአንተ ፊት መልካም ፈቃድህ ሆነ በፊትህ መልካም ፈቃድ ሆነ - "ምክንያቱም ይህንን ማድረግ መልካም እንደሆነ ተመለከትህ"

እንደ ትንንሽ ሕጻናት ያሉ ጠብባን ያልሆኑ ወይም በጣም ያልተማሩ ሰዎችን ወይም ጠብባን እና በሚገባ የተማሩ እንዳልሆኑ ለሚያውቁ ሰዎች ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ምሳሌ ነው፡፡ ( ተመለልከት) ይህ በአንተ ፊት መልካም ፈቃድህ ሆነ በፊትህ መልካም ፈቃድ ሆነ - "ምክንያቱም ይህንን ማድረግ መልካም እንደሆነ ተመለከትህ"

ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊተረጎም ይችላል፡ “አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል” ወይም “አባቴ ሁሉን ነገር ለእኔ ሰጥቶኛል”፡፡ እግዚአብሔር አብ ከእግዚአብሔር ወልድ፣ ከኢየሱስ ጋር ዘላለማዊ ግንኙነት ያለው ሲሆን ይም በእግዚአብሐየር አብ እና ወልድ መካከል ባለ የአባት እና ልጅ ግንኙነት ተገልጧል፡፡ “አባት” እና “ልጅ” የሚሉ ቃላት በመጀመሪያዎቹ ቅዱሳት መጽሐፍ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉት ይህንን ግንኙነት ለመግሌ ነው ( እና ተመልከት ከአብ በቀር ልጅን የሚያውቅ የለም "ልጅን የሚያውቅ አብ ብቻ ነው፡፡" አባት እና ልጅ በእርግጠኝነት እርስ በእርስ የእውነት የሚተዋወቁ ናቸው (ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር)፡፡ ልጅን የሚያውቅ ካላቸው ግንኙነተ የተነሳ ልጅን ማወቅ ልጅ በዚህ ሥፍራ ላይ ኢየሱስ ራሱን በሦስተኛ መደብ ይጠራል፡፡ ( ተመልከት) ከልጅ በስተቀር አባትን የሚያውቅ ማንም የለም “ከወልድም በቀር አብን የሚያውቅ የለም።” አብን የሚያውቅ ከግል ግንኙነታች የተነሳ ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር ለተርጓሚዎች ምክር፡ "ሰዎች አብ ማን እንደሆነ ማወቅ የሚችሉት ልህ አብን ልገልጥላቸው ከወደደ ብቻ ነው፡፡”

Matthew 11:28

ማቴዎስ 11፡ 28-30

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ኢየሱስ ለለሕዝቡ ማናገሩን ጨረሰ፡፡ ደካች እና ሸክም የከበደባችሁ ይህ ምሳሌ የአይሁድ ሕግ “ቀንበር” የሚያመለክት ነው፡፡ ( ተመልከት) እኔም አሳርፋችኋለሁ "ከድካማችሁ እና ሸክማችሁ አሳርፋችኋለሁ" ( ተመልከት) ቀንበሬን ተሸከሙ “እናንተ” የሚለው ተውላጠ ስም “ደካሞች እና ሸክም የከበደበባችሁ ሁሉ” የሚለውን የሚያመለክት ነው፡፡ የዚህ ምሳሌ ትርጉሙ “የሰጠኋችሁን ሥራ ተቀበሉ” ወይም “ከእኔ ጋር ተባብራችሁ ሥሩ” ( ተመልከት) ሸክሜ ቀሊል ነው “ቀላል” የሚለው ቃል የከባድ ተቃራኒ እንጂ የጨለማ ተቃራኒ አይደለም


Translation Questions

Matthew 11:1

በከተሞች ለማስተማር እና ለመስበክ ከመሄዱ በፊት ኢየሱስ ምን ማድረግን አጠናቀቀ?

ከመለየቱ በፊት ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ማዘዝ ጨረሰ። [11:1]

መጥምቊ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ የላከው መልእክት ምን ነበር?

መጥምቊ ዮሐንስ የላከው “የምትመጣው አንተ ነህ፣ ወይስ ሌላውን እንጠብቅ” የሚል ነበር፤ [11:3]

Matthew 11:4

የሚመጣው እርሱ ለመሆኑ ማስረጃ አድርጎ እየተከሰተ እንዳለ ኢየሱስ የተናገረው ምን ነበር?

በሽተኞች ይፈወሳሉ፣ ሙታን ይነሣሉ፣ ለድኾችም የምሥራቹ ወንጌል እየተሰበከ ነው። [11:5]

በእርሱ ለማይሰናከሉት ኢየሱስ ምን ቃል ገባ?

በእርሱ ለማይሰናከሉት እንደሚባረኩ ኢየሱስ ቃል ገባ። [11:6]

Matthew 11:9

መጥምቊ ዮሐንስ በእርሱ ሕይወት ምን ሚና እንደተጫወተ ኢየሱስ ተናገረ?

መጥምቊ ዮሐንስ ሊመጣ ካለው በፊት ሆኖ መንገድን የሚያዘጋጅ የተተነበየው መልእክተኛ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። [11:9]

መጥምቊ ዮሐንስ በእርሱ ሕይወት ምን ሚና እንደተጫወተ ኢየሱስ ተናገረ?

መጥምቊ ዮሐንስ ሊመጣ ካለው በፊት ሆኖ መንገድን የሚያዘጋጅ የተተነበየው መልእክተኛ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። [11:10]

Matthew 11:13

መጥምቊ ዮሐንስ ማን እንደነበረ ኢየሱስ ተናገረ?

መጥምቊ ዮሐንስ ኤልያስ እንደነበረ ኢየሱስ ተናገረ። [11:14]

Matthew 11:18

እንጀራ ሳይበላ ወይም ወይንን ሳይጠጣ ስለመጣው መጥምቊ ዮሐንስ ትውልዱ ምን አለ?

መጥምቊ ዮሐንስ አጋንንት እንዳለበት ትውልዱ ተናገረ። [11:18]

እየበላና እየጠጣ ስለመጣው ኢየሱስ ትውልዱ ምን አለ?

ኢየሱስ ስስታምና ጠጪ እንደሆነ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኃጢአተኞች ወዳጅ እንደሆነ ያ ትውልድ ተናገረ። [11:19]

Matthew 11:20

ታላላቅ ተዓምራቱ በተፈጸመባቸው፣ ነገር ግን ንስሃ ያልገቡ ከተሞችን በተመለከተ ኢየሱስ ምን አለ?

ኢየሱስ ታላላቅ ተዓምራት የተፈጸመባቸውን፣ ነገር ግን ንስሃ ያልገቡትን ከተሞች ገሠጻቸው። [11:20]

Matthew 11:25

ኢየሱስ መንግሥቱን ከማን ስለሰወረ ነው አብን ያመሰገነው?

ብልኅ ነን፣ እናውቃለን ለሚሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስለ ሰወረባቸው ኢየሱስ እግዚአብሔርን አመሰገነ። [11:25]

ኢየሱስ መንግሥቱን ከማን ስለሰወረ ነው አብን ያመሰገነው?

ብልኅ ነን፣ እናውቃለን ለሚሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስለ ሰወረባቸው ኢየሱስ እግዚአብሔርን አመሰገነ። [11:25]

አብን ያውቃሉ ብሎ ኢየሱስ የተናገረው እነማንን ነው?

እርሱ እና ሊገልጥለት የሚወድደው ሁሉ አብን እንደሚያውቅ ኢየሱስ ተናገረ። [11:27]

Matthew 11:28

ኢየሱስ እረፍትን ቃል የገባው ለማን ነው?

ኢየሱስ ለማሳረፍ ቃል የገባው ሸክም ለከበደባቸው ሁሉ ነው። [11:28]


ምዕራፍ 12

1 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት በእርሻ መካከል ሄደ። ደቀ መዛሙርቱም ተርበው ስለ ነበር፣ እሸቱን እየቀጠፉ ይበሉ ጀመር፡፡ 2 ፈሪሳውያንም ያንን ባዩ ጊዜ፣ “ኢየሱስን፣ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት የሚያደርጉትን የማይገባ ነገር ተመልከት” አሉት፡፡ 3 ኢየሱስ ግን፣ "ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ከቶ አላነበባችሁምን? 4 ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፣ ለካህናት ብቻ እንጂ ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ያልተፈቀደውን የተቀደሰ እንጀራ እንዴት እንደበላ?" አላቸው። 5 በሰንበት ካህናት በቤተ በመቀደስ ሥራ እንድሚሠሩና፣ ሰንበትን እንደሚያረክሱ፣ በደልም እንደማይሆንባቸው ከሕጉ አላነበባችሁምን? 6 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ከቤተ መቅደስ የሚበልጠው እዚህ አለ፡፡ 7 “መሥዋዕትን ሳይሆን ምሕረትን እፈልጋለሁ” የሚለውን ብታውቁ ኖሮ፣ በደል የሌለባቸውን አትፈርዱባቸውም ነበር፡፡ 8 የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።" 9 ከዚያም ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ፣ ወደ ምኲራባቸው ገባ። 10 እነሆ፣ እጁ ሽባ የሆነ አንድ ሰው ነበረ፡፡ ፈሪሳውያንም ኢየሱስን በኅጢአት ለመክሰስ፣ "ሕጉ በሰንበት መፈወስን ይፈቅዳልን?" ብለው ጠየቁት፡፡ 11 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ከእናንተ መካከል አንድ በግ ብቻ ብትኖረውና፣ ያቺም በግ ጉድጓድ ውስጥ ብትገባበት፣ በሰንበት የማያወጣት ማን ነው? 12 ታዲያ ሰውማ ፣ ከበግ ይልቅ ምን ያህል ዋጋ ይኖረዋል! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዷል ፡፡" 13 ከዚያም ኢየሱስ፣ ሰውየውን፣ “እጅህን ዘርጋ” አለው፡፡ እጁንም ዘረጋ፣ እንደ ሌላውም እጅ ጤነኛ ሆነ፡፡ 14 ነገር ግን ፈሪሳውያን ሄደው አሤሩበት፣ እርሱን የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡ 15 ኢየሱስ ይህን እንዳወቀ፣ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤ እርሱም ሁሉንም ፈወሳቸው፡፡ 16 ሰዎቹን ስለ እርሱ ለሌሎች እንዳይገልጹ አዘዛቸው፣ 17 ይህም የሆነው በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፤ 18 እነሆ፣ እኔ የመረጥኩት አገልጋዬ፤ የምወደው ነፍሴም ደስ የተሰኘችበት። መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ፍትሕን ለአሕዛብ ያውጃል። 19 አይጨቃጨቅም ወይም አይጮህም፤ ወይም ማንም ድምፁን በጐዳናዎች ላይ አይሰማም። 20 ፍርድን ለድል እስኪያበቃ ድረስ፤ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤሰውንም የጧፍ ክር አያጠፋም፣ 21 አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።" 22 ከዚያም በአጋንንት የተያዘን ዐይነ ስውርና ዲዳ ሰው ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም ፈወሰው፤ ዲዳውም ተናገረ፣ አየም። 23 ሕዝቡም በመገረም፣ "ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆን እንዴ?" አሉ፡፡ 24 ነገር ግን ፈሪሳውያን ይህን ተአምር በሰሙ ጊዜ “ይህ ሰው በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል ካልሆነ በቀር አጋንንቱን አያወጣም ነበር" አሉ፡፡ 25 ኢየሱስም ዐሳባቸውን ዐውቆ ፣“እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ይወድቃል፤ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማ ወይም ቤት ሁሉ አይጸናም፡፡ 26 ሰይጣን ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፣ እርስ በርሱ ተከፋፍሏል፣ መንግሥቱስ እንዴት ይቆማል? 27 እኔ አጋንንትን የማወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ተከታዮቻችሁ በማን ሊያወጡ ነው? ከዚህ የተነሣ እነርሱው ይፈርዱባችኋል፡፡ 28 ነገር ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆነ፣ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥታለች፡፡ 29 ማንም ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ቤቱ ገብቶ ንብረቱን እንዴት መዝረፍ ይችላል?፡፡ ካሰረው በኋላ ግን፣ ንብረቱን ይዘርፋል። 30 ከእኔ ጋር ያልሆነ ተቃዋሚዬ ነው፣ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል፡፡ 31 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ማንኛውም ኅጢአትና ስድብ ለሰዎች ይቅር ይባልላቸዋል ፤መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ግን ይቅር አይባልም፡፡ 32 በሰው ልጅ ላይ ማንኛውንም ቃል የሚናገር ይቅር ይባልለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ግን፣ በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ይቅር አይባልም። 33 እንግዲህ ዛፍ የሚታወቀው በፍሬው ስለ ሆነ ዛፉን መልካም አድርጉ፤ ፍሬውም መልካም ይሆናል፣ ወይም ዛፉን መጥፎ አድርጉ ፍሬውም መጥፎ ይሆናል፡፡ 34 እናንተ የእባብ ልጆች ክፉዎች ስለ ሆናችሁ፣ እንዴት መልካም ልትናገሩ ትችላላችሁ? ምክንያቱም በልብ ውስጥ የሞላውን አፍ ይናገረዋል፡፡ 35 . መልካም ሰው በልቡ ውስጥ ካለው መልካም መዝገብ፣ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ልቡ ውስጥ ካለው ክፉ መዝገብ ክፉውን ይወጣል። 36 ለእናንተም እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ሰዎች ስለ ተናገሯቸው ከንቱ ንግግሮች መልስ ይሰጣሉ፡፡ 37 ምትናገሩት ትጸድቃላችሁ፣ በምትናገሩትም ይፈረድባችኋልና፡፡ 38 አንዳንድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን መልሰው ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፣ ምልክት እንድታሳየን እንፈልጋለን" አሉት። 39 ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፣ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምንም አይሰጠውም፡፡ 40 ዮናስ በትልቅ ዐሣ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፣ የሰው ልጅም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ ይሆናል፡፡ 41 የነነዌ ሰዎች በዮናስ ስብከት ንስሓ በመግባታቸው፣ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፡፡ ደግሞም ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ፡፡ 42 የደቡብ ንግሥት፣ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻዎች መጥታለችና፣ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፡፡ደግሞም ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ፡፡ 43 ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ፣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለባቸው ቦታዎች ያልፋል፣ ነገር ግን አያገኝም። 44 ከዚያም፣ 'ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ' ይላል። ሲመለስም ቤቱ ጸድቶ ተዘጋጅቶ ያገኘዋል፡፡ 45 ከዚያም ይሄድና ከእርሱ ይልቅ የከፉትን ሰባት ሌሎች መናፍስትን ይዞ ይመጣል፣ ሁሉም በዚያ ለመኖር ይመጣሉ፡፡ የዚያም ሰው የመጨረሻው ሁኔታ ከመጀመሪያው የከፋ ይሆናል፡፡ በዚህ ክፉ ትውልድ ላይ የሚሆነውም እንደዚሁ ነው፡፡ 46 ኢየሱስም ለሕዝቡ እየተናገረ እያለ፣ እናቱና ወንድሞቹ ሊያናግሩት ፈልገው፣ በውጭ ቆመው ነበር። 47 አንድ ሰውም፣ "እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ሊያነጋግሩህ በውጭ ቆመዋል" አለው። 48 ኢየሱስም መልሶ ለነገረው ሰው፣ "እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?" አለው። 49 ከዚያም እጁን ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፣ "እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው! 50 በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፣ ወንድሜ፣ እኅቴ እናቴም ነውና" አለ።



Matthew 12:1

ማቴዎስ 12፡1-2

አጠቃላይ መረጃ: ይህ አዲስ የታሪኩ አዲስ ክፍል ሲሆን ጸሐፊው በዚህ ክፍል ውስጥ በኢየሱስ አገልግሎት ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ስለመጣው ተቃውሞ ይተርካል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥም ፈርሳዊያን የእርሱን ደቀ መዛሙርት በሰንበት አሸት መቅጠፋቸውን አስመልክቶ ያቀረቡትን ተቃውሞ እንመለከታለን፡፡ የእርሻ ማሳ ሰብል የተዘራበት መሬት፡፡ ስንዴ በአከባቢያችሁ የማይታወቅ ከሆነ “ሰብል”፣ “ዳቦ ለመጋገር የሚሆን እህል ማብቀያ ሥፍራ” በሚል አጠቃላይ መጠሪያን ተጠቀሙ፡፡ እሸት ይቀጥፉ ይበሉም ጀመር . . . በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ በሰዎች ማሳ ውስጥ የሚገኝን እሸት ቀጥፈው መብላት ሌብነት አይደለም፡፡ ጥያቄው በበሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደን ነገር ማድረግ ይቻላል ወይ የሚል ነው፡፡ ይህንን የእሼቱን ጫፍ ቀንጠበው እሸቱን ጫፍ ይህ ረጅም ሳሪ ከሚመስለው የስንዴ ተክል ጫፍ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ ጫፍ የተክሉን ፍሬ በውስጡ ይይዛል፡፡ ተመልከት አማራጭ ትርጉሞች፡ “ተመልከት”ወይም “አድምጥ” ወይም “አሁን ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጥ”

Matthew 12:3

ማቴዎስ 12፡1-2

አጠቃላይ መረጃ: ይህ አዲስ የታሪኩ አዲስ ክፍል ሲሆን ጸሐፊው በዚህ ክፍል ውስጥ በኢየሱስ አገልግሎት ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ስለመጣው ተቃውሞ ይተርካል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥም ፈርሳዊያን የእርሱን ደቀ መዛሙርት በሰንበት አሸት መቅጠፋቸውን አስመልክቶ ያቀረቡትን ተቃውሞ እንመለከታለን፡፡ የእርሻ ማሳ ሰብል የተዘራበት መሬት፡፡ ስንዴ በአከባቢያችሁ የማይታወቅ ከሆነ “ሰብል”፣ “ዳቦ ለመጋገር የሚሆን እህል ማብቀያ ሥፍራ” በሚል አጠቃላይ መጠሪያን ተጠቀሙ፡፡ እሸት ይቀጥፉ ይበሉም ጀመር . . . በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ በሰዎች ማሳ ውስጥ የሚገኝን እሸት ቀጥፈው መብላት ሌብነት አይደለም፡፡ ጥያቄው በበሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደን ነገር ማድረግ ይቻላል ወይ የሚል ነው፡፡ ይህንን የእሼቱን ጫፍ ቀንጠበው እሸቱን ጫፍ ይህ ረጅም ሳሪ ከሚመስለው የስንዴ ተክል ጫፍ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ ጫፍ የተክሉን ፍሬ በውስጡ ይይዛል፡፡ ተመልከት አማራጭ ትርጉሞች፡ “ተመልከት”ወይም “አድምጥ” ወይም “አሁን ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጥ”

Matthew 12:5

ማቴዎስ 12፡5-6

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ኢየሱስ ለፈርሳዊያን ትችት ምላሽ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ አናንተ . . . አናንተ ፈርሳዊያን በ . . . ውስጥ እንዲህ የሚል ቃል አላነበባችሁምን “ሕግ ምን እንደሚል ታውቁ ዘንድ የሕግ መጽሐፍትን አላነበባችሁምን" ( ተመልከት) ሰንበትን አያከብሩም "በሌሎች ቀናት የሚያደርጉትን ነገር በሰንበትም ያደርጋሉ" ጥፋት የለባቸውም "እግዚብሔር አይቀጣቸውም" ከመቅደስ የሚበልጥ በዚህ አለ "ከመቅደሱ ይበልጥ ጠቃሙ የሆነ”፡፡ ኢየሱስ የሚበልጠው ብሎ የተናገረው ስለ ራሱ ነው፡፡

Matthew 12:7

ማቴዎስ 12፡ 7-8

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ኢየሱስ ለፈሪሳዊያን ምላሽ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ አጠቃላይ መረጃ፡ በቁጠር 7 ላይ ኢየሱስ ፈሪሳዊያንን ለመገሰጽ ከነብዩ ሆሴ መጽሐፍ ጠቅሷል፡፡ ብታውቁ ኖሮ "አታውቁም" እናንተ . . . እናንተ ፈሪሳዊያን ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም መሥዋዕት ጥሩ ነገር ነው ነገር ግን ምህረት ግን ይሻላል፡፡ ( ተመልከት) ይህ ማለት ምን ማለት ነው "እግዚአብሔር በቅዱሳት መጽሐፍቱ አማካኝነት ምን አለ" እወዳለሁ “እኔ” የሚለው ተውላጠ ስም እግዚአብሔርን የሚያመለክት ነው፡፡

Matthew 12:9

ማቴዎስ 12፡9-10

አጠቃላይ መረጃ፡ በዚህ ሥፍራ ፈሪሳዊያን ኢየሱስ በሰንበት አንድ ሰውን መፈወሱን ወደተቃወሙበት የታሪኩ አቅጣጫ ይለወጣል፡፡ ኢየሱስ ከዚያ አልፎ ሄደ "ኢየሱስ የእርሻ ማሳውን ለቆ ወጣ" የእነርሱ ኢየሱስ እየተናገራቸው ያሉት ፈሪሳዊያን ምኩራብ እነሆ “እነሆ” የሚለው ቃል በታሪክ ውስጥ አዲስ ሰውን ያስተዋውቀናል፡፡ በቋንቋችሁ እንዲህ ዓይነት ነገር ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ "የሰለለች" ወይም "ያጠረች"

Matthew 12:11

ማቴዎስ 12፡ 11-12

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ኢየሱስ ለፈሪሳዊያን ትችት ምላሽ ሰጠ፡፡ ከእናንተ . . . ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው? አማራጭ ትርጉም፡ “ሁላችሁም . . . ጎትታችሁ ታወጣላችሁ ( ተመልከት) እናንተ . . . እናንተ ፈሪሳዊያን ያለው "ያለው ሰው" በዚያ የሚተወው "በጉን በጉድጓድ ውስጥ የሚተወው" መልካም ማድረግ በሕግ ተፈቅዷል "መልካም የሚያደርጉ ሰዎች ሕጉን እየተላለፉ አይደለም” ወይም “መልካም የሚያደርጉ ሰዎች ሕጉን እየታዘዙ ነው"

Matthew 12:13

ማቴዎስ 12፡ 13-14

ሰው የሰለለች እጅ ያለው ሰው እጅህን ዘርጋ "እጅህን አንሳ" ወይም እጅህን ዘርጋ" እርሱ ሰውዬው እጁ የሰውዬው እጅ ጤናው ተመለሰች "ሙሉ ለሙሉ ተፈወሰ" ወይም "ሙሉ ጤነኛ ሆነ" በእርሱ ላይ ተማከሩበት "እንዲያጠፉት ተማከሩ" እንዴት አድርገው "ዘዴ ፈለጉ" እርሱን ለመግደል ኢየሱስን ለመግደል h

Matthew 12:15

ማቴዎስ 12፡ 15-17

አጠቃላይ መረጃ፡ ይህ ታሪክ እንዴት የኢየሱስ ተግባር የነብዩ ኢሳያስን ፍጻሜ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ይህ "ፈሪሳዊያን እርሱን ለመግደል አቀዱ" ትቷቸው ሄደ "ተዋቸው" እንዳይገልጡትም ነገራቸው "ስለ እርሱ ለሌላ ለማንም ሰው እንዳይናገሩ" በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦ "እግዚአብሔር በነብዩ ኢሳያስ አማካኝነት የተናገረው እና የተጻፈው"

Matthew 12:18

ማቴዎስ 12፡18-18

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: በዚህ ክፍል ውስጥ ጸሐፊው የኢየሱስ አገልግሎት በነብዬ ኢሳያስ የተጻፈው የትንቢት ቃል ፍጻሜ መሆኑን ለማሳየት ጠቅሶታ፡፡

Matthew 12:19

ማቴዎስ 12፡ 19-21

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ጸሐፊው ነብዩ ኢሳያስን መጥቀሱን ቀጥሏል፡፡ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም "ደካማ ሰዎችን አያጠቃም” ( ተመልከት) የተቀጠቀጠ "በግማሽ የተሰበረ ወይም ጉዳት የደረሰበት” የሚጤስን የጥዋፍ ክርም የጥዋፍ ክር አንድ ጊዜ መብራት ከጀመረ በኋላ ጠንካራ አይደለም፤ ይህ ደግሞ ረዳት ያሌላቸው ሰዎችን ያመለክታል ( ተመልከት) እስኪ. . . ይህ ከአዲስ ዓረፍተ ነገር ጋር እንዲህ ሊተረጎም ይችላል፡ “ይህን እስኪያመጣ ድረስ ይህንን ያደርጋል” ወደ ድል የሚያደርስ ፍርድን ያመጣል "እኔ ትክክል እንደሆንኩ ሰዎችን ያሳምናል" በእርሱ ስም ለተርጓሚዎች ምክር: "በእርሱ" ( ተመልከት)

Matthew 12:22

ማቴዎስ 12፡22-23

አንድ ዕውር ዲዳም የሆነ ሰው "ማየት እና መናገር የማይችል አንድ ሰው" ሕብዙም ሁሉ ተገረሙ "ኢየሱስ ሰወዬውን እንደፈወሰው የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ በጣም ተገረሙ"

Matthew 12:24

ማቴዎስ 12፡24-25

ይት ተዓምር የዐይነ ስውሩ፣ ደንቆሮው እና በእርኩስ መንፈስ የተያዘው ሰው የመፈወሱ ተዓምር ይህ ሰው በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም "ይህ ሰው አጋንትን ማውጣት የቻለበት ብቸኛው ምክንያት የብዔል ዜቡል አገልጋይ በመሆኑ ነው" ይህ ሰው ፈሪሳዊያን ኢየሱስን ያለመቀበላቸውን ለማሳየጥ የእርሱን ስም አይጠሩም ነበር፡፡ እናንተ . . . እናንተ ፈሪሳዊያን

Matthew 12:26

ማቴዎስ 12፡26-27

ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ "ሴጣን የራሱን መንግስት ተቃውሞ የሚሠራ ከሆነ" ( ተመልከት) መንግስቱ እንዴት ጸንታ ትቆማለች? "የሴጣን መንግስት ጸንቶ ሊቆም አይችልም" ወይም "የሴጣን መንግስት ይፈራርሳል" ( ተመልከት) ማስወጣት "አስገድዶ ማስወጣት" ወይም "ማበባረር" ወይም "አውጥቶ መወርወር" ወይም "ነቅሎ ማውጣት" ተከታዮቻችሁ በማን ያወጧቸዋል ለተርጓሚዎች ምክር፡ "የእናንተ ተከታዮች አጋንትን የሚያስወጡት በብዔል ዘቡል ኃይል አማካኝነት ነው" (ወይም UDB ተመልከት) ( ተመልከት) እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል ለተርጓሚዎች ምክር፡ "አጋንትን በእግዚአብሔር ኃይል የሚያስወጡት የእናንተ ተከታዮች እኔን በብዔል ዘቡል ኃይል አጋንት ያስወጣል በማለታችሁ በእናንተ ላይ ይፈርዳሉ"

Matthew 12:28

ማቴዎስ 12፡28-30

ወደ እናንተ ደርሳለች በፈሪሳዊያን ላይ መጣለች በመጀመሪያ ኃይለኛውን ሳያስሩ "ኃይለኛውን በመጀመሪያ በቁጥጥር ሥር ሳያደርጉ" ከእኔ ጋር ያልሆነ "እኔን የማይደግፈኝ” ወይም “ከእኔ ጋር የማይሠራ" የእኔ ተቃዋሚ ነው "እኔን ተቃውሞ ይሠራል" ወይም "ሥራዬን ያፈርሳል" መሰብሰብ ይህ ሰብል መሰብሰብ የሚያመለክት የተለመደ ቃል ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 12:31

ማቴዎስ 12፡31-32

ማንኛው ኃጢአት እና በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ስድብ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል "ሰዎች የፈጸሟቸው ኃጢአቶች እና ስድቦችን እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል” ወይም “ኃጢአት የፈጸሙ ሰዎችን ሁሉ እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል፡፡ ወይም “እግዚብሔር ኃጢአት ያደረጉ ወይም የተሳደቡ ሰዎችን ሁሉ ይቅር ይላቸዋል” ( ተመልከት) በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ አይሰረይለትም። "መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብን ግን እገግዚአብሔር ይቅር አይለውም" ( ተመልከት) እንነዲሁም በሰው ልጅ ላይ የሚናገር ኃጢአቱ ይሰረይለታል "የሰው ልጅን በመቃወም የሚነገርን ንግግር እግዚአብሔር ይቅር ይለዋል" በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው ለተርጓሚዎች ምክር፡ "በዚህ ጊዜ . . . በመጪው ጊዜ"

Matthew 12:33

ማቴዎስ 12፡33-35

ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፥ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ። "ፍሬዋ መልካም ከሆነ ዛፏ መልካም እንደሆነች እንዲሁም ፍሬዋ ክፉ ከሆነ ዛፏም ክፉ እንደሆነች ይታወቃል" መልካም . . . ክፉ ይህ ማለት 1) “ጤናማ . . . ጤናማ ያልሆነ” ወይም 2) "የሚበላ . . . የማይበላ" ዘፍ በፍሬው ይታወቃል ይህ እንዲህ ሊሆን ይችላል 1) "ሰዎች አንድ ዘፍ ጤናማ መሆን አለመሆኑን ፍሬውን ተመልክተው ያውቃሉ" ወይም 2) "ሰዎች የዛፉን ፍሬ በመመልከት የዛፉን ዝሪያ ያውቃሉ" ( ተመልከት) እናንተ . . . እናንተ ፈሪሳዊያን በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና። "አንድ ሰው በአንደበቱ የሚናገረው በልቡ ውስጥ ካለው ብቻ ነው” ( ተመልከት) መልካም መዝገብ . . . ክፉ መዝገብ "ትክክለኛ ሀሳቦች. . . ክፉ ሀሳቦች" ( ተመልከት)

Matthew 12:36

ማቴዎስ 12፡ 36-37

እናንተ . . . እናንተ ፈሪሳዊያን ሰዎች ስለሚናገሩት ነገር . . .መልስ ይሰጡበታል፤ "እግዚአብሔር ይጠይቀቸዋል" ወይም "እግዚአብሔር ቃላቸውን ይመዝናል" እርባና የሌለው "ጥቅም የሌለው" ለተርጓሚዎች ምክር: "የሚጎዳ" እነርሱ "ሕዝቡ" ትጸድቃለህ . . . ትኰነናለህ "እግዚአብሔር ያጸድቅሃል . . . እግዚአብሔር ይፈርድብሃል" ( ተመልከት)

Matthew 12:38

ማቴዎስ 12፡38-40

መሻት "ፍላጎት" ክፉና አመንዝራ ትውልድ በዚህ ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ክፉ ማድረግ ይወዳሉ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ታማኞች አይደሉም፡፡ ምንም ዓይነት ምልክት አይሰጣቸውም "ለዚህ ክፉ እና አመንዝራ ትውልድ እግዚአብሔር ምንም ዓይነት ምልክት አይሰጥም" ( ተመልከት) የዮናስ ምልክት ለትርጓሚዎች ምክር፡ "ለዮናስ ምን ሆነ" ወይም "ለዮናስ እግዚአብሔር ያደረገው ተዓምር ምን ነበር” ( ተመልከት) በመሬት ልብ ውስጥ በመቃብር ውስጥ ( ተመልከት)

Matthew 12:41

ማቴዎስ 12፡41-41

የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "የነነዌ ሰዎች ይህንን ትውልድ ይከሳሉ . . . እንዲሁም እግዚአብሔር ክዳቸውን ይሰማል እና በእናንተ ላይም ይፈርዳል” "እግዚአብሔር የነነዌ ሰዎችን እና ይህንን ትውልድ በኃጢአተኛነታቸው ይፈርድባቸዋል ይሁን እንጂ እነርሱ ንሰሓ ገብተዋል፤ እናንተ ግን አልገባችሁም ስለዚህም በእናንተ ላይ ብቻ ይፈርዳል” ( ተመልከት) ይህ ትውልድ ኢየሱስ በኖረበት እና ባገለገለበት ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ( ተመልከት) የሚበልጥ "ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ"

Matthew 12:42

ማቴዎስ 12፡ 42-42

የደቡድ ንግሥተ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ ለተርጓሚዎች ምክር: "የደቡድ ንግሥት በዚህ ትውልድ ላይ ትፈርዳለች . . . እግዚአብሔርም ፍርዷን ይሰማል በእናንተም ላይ ይፈርዳል” ወይም እግዚአብሔር በደቡቧ ንግሥት እና በዚህ ትውልድ ላይ በኃጢአታቸው ይፈርዳል ይሁን እንጂ እርሷ ንጉሥ ሰለሞንን ስለመጣች እናንተ ግን እኔን ስላልሰማችሁ የሚፈረደው በእናንተ ላይ ብቻ ይሆናል፡፡ ( ተመልከት) የደቡቧ ንግሥት ይህ የአሕዛብ መንግስ ንግሥት ሳባን ያመለክታል ( ተመልከት) ከምድር ዳርቻ መጥታለች "በጣም ሩቅ ከሆነ ሥፍራ መጥታለች” ( ተመልከት) ይህ ትውልድ ኢየሱስ ባገለገለበት ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ( ተመልከት) የሚበልጥ "ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ"

Matthew 12:43

ማቴዎስ 12፡43-45

ውሃ የሌለበት ሥፍራ "ደረቅ ቦታ" ወይም "ሰዎች የማይኖሩበት ቦታ" አያገኝም "የሚያርፍበት ቦታ አያገኝም" እንዲህም ይላል "እርኩስ መንፈሱም እንዲህ ይላል" ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ ያገኘዋል። ለተርጓሚዎች ምክር፡ "እርኩስ መንፈሱም ቤቱ ጸድቶ እና ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ያገኘዋል" ( ተመልከት)

Matthew 12:46

ማቴዎስ 12፡46-47

እናቱ የኢየሱስ እናት ወንድሞቹ ይህ እንዲህ ሊሆን ይችላል 1) የእናቱ እና የአባቱ ልጆች ወይም 2) የቅርብ ጓደኞቹ ወይም በእስራኤል ውስጥ ከእርሱ ጋር የሚቀራረቡ

ፍለጋውን "ፈለጉት"

Matthew 12:48

ማቴዎስ 12፡48-50

እርሱ ለነገረው "ለኢየሱስ እናቱ እና ወንድሞቹ ልያናግሩት እንደሚፈለጉ ለነገረወ ሰው" እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እናቴ እና ወንድሞቼ እነማን እንደሆኑ በእርግጥ እነግራችኋለሁ" ( ተመልከት) ማንም "ማንም" አባት ይህ ለእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)


Translation Questions

Matthew 12:1

ለእርሱ ስሞታ እስኪነግሩ ድረስ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ምን እያደረጉ ነበር?

የኢየሱስ ደቀመዛሙርት በሰንበት ቀን ማድረግ ያልተፈቀደ ተብሎ የሚታመነውን እሸት እየቀጠፉ ይበሉ ስለነበረ ፈሪሳውያን ስሞታ አቀረቡ። [12:2]

Matthew 12:5

ከመቅደስ የሚበልጥ ብሎ ኢየሱስ የተናገረው ማንን ነው?

ኢየሱስ እርሱ ከመቅደስ እንደሚበልጥ ተናገረ። [12:6]

Matthew 12:7

ኢየሱስ የሰው ልጅ ምን ሥልጣን አለው?

ኢየሱስ የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው። [12:8]

Matthew 12:9

እጁ የደረቀችበትን ሰው ፊት ለፊት ፈሪሳውያን ምኩራብ ውስጥ ኢየሱስን የጠየቁት ጥያቄ ምንድነው?

ፈሪሳውያን ኢየሱስን የጠየቁት “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዷልን?” በማለት ነው፤ [12:10]

Matthew 12:11

ፈሪሳውያን ኢየሱስን የጠየቁት “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዷልን?” በማለት ነው፤ [12:10]

በሰንበት መልካምን ማድረግ እንደተፈቀደ ኢየሱስ ተናግሯል። [12:12]

Matthew 12:13

ኢየሱስ እጁ የደረቀችበትን ሰው ሲፈውስ ፈሪሳውያን በተመለከቱ ጊዜ፣ ምን አደረጉ?

ፈሪሳውያን ወጥተው እንዴት እንደሚያጠፉት ተማረከሩ። [12:14]

Matthew 12:18

ስለ ኢየሱስ በተነገረው የኢሳይያስ ትንቢት ውስጥ የእግዚአብሔርን ፍርድ ሰምተው በኢየሱስ መተማመን የሚኖራቸው እነማን ናቸው?

አሕዛብ የእግዚአብሔርን ፍርድ ሰምተው በኢየሱስ መተማመን ይኖራቸዋል። [12:18]

Matthew 12:19

አሕዛብ የእግዚአብሔርን ፍርድ ሰምተው በኢየሱስ መተማመን ይኖራቸዋል። [12:18]

ኢየሱስ አይጨቃጨቅም፣ አይጮኽም፣ ድምፁን በአደባባይ አያሰማም፣ የተቀጠቀጠ ሸንበቆን አይሰብርም፣ የሚጤስንም የጧፍ ክር አያጠፋም። [12:19]

ስለ ኢየሱስ በተነገረው የኢሳይያስ ትንቢት፣ ኢየሱስ ምን አያደርግም?

ኢየሱስ አይጨቃጨቅም፣ አይጮኽም፣ ድምፁን በአደባባይ አያሰማም፣ የተቀጠቀጠ ሸንበቆን አይሰብርም፣ የሚጤስንም የጧፍ ክር አያጠፋም። [12፡20]

Matthew 12:26

በብዔልዜቡል አለቃ አጋንንትን እንደሚያስወጣ ሲከሰስ ኢየሱኢ ምን መለሰ?

ሰይጣን ሰይጣንን ቢያስወጣው፣ እንግዲያው የሰይጣን መንግሥት እንዴት ይቆማል? [12:26]

Matthew 12:28

አጋንንት በእግዚአብሔር መንፈስ ቢያስወጣ ምን እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ?

አጋንንትን በእግዚአብሔር መንፈስ ቢያስወጣ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደመጣች ኢየሱስ ተናገረ። [12:28]

Matthew 12:31

የማይሰረየው ኃጢአት ብሎ ኢየሱስ የተናገረው የትኛውን ነው?

መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ይቅር እንደማይባል ኢየሱስ ተናገረ። [12:31]

Matthew 12:33

ዛፍ በምን ይታወቃል?

ዛፍ በፍሬው ይታወቃል። [12:33]

Matthew 12:36

ፈሪሳውያን የሚጸድቊትና የሚኮነኑት በምንድነው ብሎ ኢየሱስ ተናገረ?

ፈሪሳውያን በቃላቸው እንደሚጸድቊ ወይም እንደሚኮነኑ ኢየሱስ ተናገረ። [12:37]

Matthew 12:38

ለትውልዱ ምን ምልክት እንደሚሰጥ ኢየሱስ ተናገረ?

ለትውልዱ የዮናስን ከምድር ልብ በታች ሦስት ቀንና ሦስት ቀናት ያደረበትን ምልክት ነገራቸው። [12:39]

ለትውልዱ ምን ምልክት እንደሚሰጥ ኢየሱስ ተናገረ?

ለትውልዱ የዮናስን ከምድር ልብ በታች ሦስት ቀንና ሦስት ቀናት ያደረበትን ምልክት ነገራቸው። [12:40]

Matthew 12:41

ከዮናስ እንደሚበልጥ ኢየሱስ የተናገረው ማንን ነው?

ኢየሱስ እርሱ ከዮናስ እንደሚበልጥ ተናገረ። [12:41]

የነነዌ ሰዎች በኢየሱስ ዘመን የነበሩትን ትውልድ የሚኮንኑት ለምንድነው?

የነነዌ ሰዎች የኢየሱስን ትውልድ የሚኮንኑት የእግዚአብሔርን ቃል በዮናስ በኩል ስለ ሰሙ፣ ነገር ግን የኢየሱስ ትውልድ ከዮናስ የሚበልጠውን የሰው ልጅ ሰምተው እንኳን ስለማያውቊ ነው። [12:41]

Matthew 12:42

ከሰሎሞን እንደሚበልጥ ኢየሱስ የተናገረው ማንን ነው?

እርሱ ከሰሎሞን እንደሚበልጥ ኢየሱስ ተናገረ። [12:42]

Matthew 12:43

የኢየሱስ ትውልድ እርኩስ መንፈስ እንደለቀቀው ሰው የሚመስሉት እንዴት ነው?

የኢየሱስ ትውልድ እርኩስ መንፈስ ለቅቆት እንደ ሄደበት ሰው ይመስሉ የነበረው እርኩሱ መንፈስ ከሌሎች ሰባት መናፍስት ጋር ስለሚመለሱበት እና የሰውዬው የመጨረሻ ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ስለሚሆን ነው። [12:43]

የኢየሱስ ትውልድ እርኩስ መንፈስ እንደለቀቀው ሰው የሚመስሉት እንዴት ነው?

የኢየሱስ ትውልድ እርኩስ መንፈስ ለቅቆት እንደ ሄደበት ሰው ይመስሉ የነበረው እርኩሱ መንፈስ ከሌሎች ሰባት መናፍስት ጋር ስለሚመለሱበት እና የሰውዬው የመጨረሻ ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ስለሚሆን ነው። [12:44]

የኢየሱስ ትውልድ እርኩስ መንፈስ እንደለቀቀው ሰው የሚመስሉት እንዴት ነው?

የኢየሱስ ትውልድ እርኩስ መንፈስ ለቅቆት እንደ ሄደበት ሰው ይመስሉ የነበረው እርኩሱ መንፈስ ከሌሎች ሰባት መናፍስት ጋር ስለሚመለሱበት እና የሰውዬው የመጨረሻ ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ስለሚሆን ነው። [12:45]

Matthew 12:48

ወንድም፣ እህት እና እናት እንደሆኑት ኢየሱስ የተናገረው እነማንን ነው?

የአብን ፈቃድ የሚያደርጉ ሁሉ ወንድሙ፣ እህቱና እናቱ እንደሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [12:48]

ወንድም፣ እህት እና እናት እንደሆኑት ኢየሱስ የተናገረው እነማንን ነው?

የአብን ፈቃድ የሚያደርጉ ሁሉ ወንድሙ፣ እህቱና እናቱ እንደሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [12:49]

ወንድም፣ እህት እና እናት እንደሆኑት ኢየሱስ የተናገረው እነማንን ነው?

የአብን ፈቃድ የሚያደርጉ ሁሉ ወንድሙ፣ እህቱና እናቱ እንደሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [12:50]


ምዕራፍ 13

1 በዚያ ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕር ዳርቻ ተቀመጠ። 2 በጣም ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ተሰበሰቡ፣ ስለዚህ ጀልባ ውስጥ ገብቶ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ቆመው ነበር። 3 ከዚያም ኢየሱስ በምሳሌ ብዙ ነገር ነገራቸው። እንዲህም አለ፤ "ዘሪ ለመዘራት ወጣ። 4 ሲዘራም፣ አንዳንዱ ዘር በመንገድ አጠገብ ወድቆ፣ ወፎች መጥተው በሉት። 5 ሌላውም ዘር በቂ አፈር በሌለበት በዐለታማ መሬት ላይ ወደቀ። አፈሩም ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ። 6 ፀሐይ ሲወጣ ግን፣ሥር ስላልነበረው ጠውልጎ ደረቀ። 7 ሌላው ዘር ደግሞ በእሾኽማ ቊጥቋጦ መካከል ወደቀ፣ እሾኹም አድጎ አነቀው። 8 ሌላው ዘር በመልካም መሬት ላይ ወድቆ ፍሬ አፈራ፤ አንዳንዱ መቶ፣ አንዳንዱ ሥልሳ፣ አንዳንዱም ሠላሳ ፍሬ አፈራ። 9 ጆሮ ያለው ይሰማ።" 10 ደቀ መዛሙርቱም መጡና ኢየሱስን፣ “ለምንድን ነው ለሕዝቡ በምሳሌ የምትናገረው?" አሉት። 11 ኢየሱስም መልሶ፣ "ለእናንተ የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር ማወቅ ተሰጥቷችኋል፣ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም" አላቸው። 12 ምክንያቱም ላለው ሁሉ የበለጠ ይሰጠዋል፤ ይበዛለትማል። የሌለው ግን ያለው እንኳ ይወሰድበታል። 13 ስለዚህ ለእነርሱ በምሳሌ እነግራቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ቢያዩ እንኳ እያዩ አይደለም፣ ቢሰሙም እየሰሙ አይደለም፣ ወይም አያስተውሉም። 14 በእነርሱ ላይ እንዲህ የሚለው የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጸመ ፦ መስማትን ትሰማላችሁ፣ ነገር ግን በምንም መንገድ አታስተውሉም፣ ማየትን ታያላችሁ፣ ግን ምንም አትገነዘቡትም። 15 በዐይናቸውም እንዳይመለከቱ፣ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ጆሯቸው ለመስማት ተደፍኗል፣ ዐይናቸውም ተጨፍኗል። እንዳይመለሱና እኔም እንዳልፈውሳቸው የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗል። 16 የእናንተ ዐይኖች ግን ስለሚያዩ፣ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ የተባረኩ ናቸው። 17 እውነት እላችኋለሁ፣ ብዙ ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ለማየት ተመኝተው አላዩም፤ የምትሰሙትን ለመስማት ተመኝተው አልሰሙም። 18 እንግዲህ የዘሪውን ምሳሌ ስሙ። 19 ማንም የመንግሥትን ቃል ሰምቶ ባያስተውል፣ ክፉው ይመጣል በልቡም የተዘራውን ይነጥቃል። ይህም በመንገድ ዳር የተዘራውን ይመስላል። 20 በዐለት ላይ የተዘራው ፣ቃሉን የሚሰማና ወዲያውኑ በደሰታ የሚቀበለው ነው፤ 21 ሆኖም በራሱ ሥር ስለሌለው፣ የሚቆየው ለአጭር ጊዜ ነው። በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሚነሣበት ጊዜ፣ ወዲያውኑ ይሰናከላል። 22 በእሾኽ ተክሎች መካከል የተዘራው፣ ቃሉን የሚሰማ ሆኖ የዓለም ዐሳብ፣ የብልጥግናም አሳሳችነት ቃሉን ያንቁታል፣ ፍሬ ቢስም ይሆናል። 23 በመልካም መሬት ላይ የተዘራው፣ ቃሉን የሚሰማና የሚረዳ ነው፤ በርግጥ የሚያድገውና ፍሬ የሚሰጠውም ይህኛው ነው፤ አንዱ መቶ፣ አንዱም ሥልሳ፣ አንዱም ሠላሣ እጥፍ ያፈራል። 24 ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህ አለ፤ “መንግሥተ ሰማይ በዕርሻው ላይ መልካም ዘር የዘራ ሰው ትመስላለች። 25 ሰዎቹ በተኙ ጊዜ ግን፣ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው መካከል እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ። 26 ቅጠሉም በለመለመና ፍሬ ማፍራት በጀመረ ጊዜ፣ እንክርዳዱ ደግሞ አለ። 27 የዕርሻው ባለቤት አገልጋዮች መጥተው፣ "ጌታ ሆይ፣ በዕርሻው ላይ መልካም ዘር ዘርተህ አልነበረምን? ታዲያ እንክርዳድ የበቀለው እንዴት ነው?"አሉት። 28 እርሱም፣ “ጠላት ይህን አደረገ" አላቸው። አገልጋዮቹም መልሰው፣"ስለዚህ ሄደን እንድንነቅለው ትፈልጋለህን?" አሉት። 29 የዕርሻውም ባለቤት፣ 'አይሆንም፣ እንክርዳዱን በምትነቅሉበት ጊዜ ስንዴውንም አብራችሁ ልትነቅሉት ትችላላችሁ 'አላቸው። 30 እስከ መከር ድረስ አብረው ይደጉ። በመከሩ ጊዜ ለኣጫጆቹ፣ "መጀመሪያ እንክርዳዱን ነቅላችሁ እንዲቃጠል አንድ ላይ ሰብስቡ። ስንዴውን ግን ሰብስባችሁ ወደ ጎተራዬ አስገቡት እላቸዋለሁ" አላቸው። 31 ኢየሱስም ሌላ ምሳሌ ነገራቸው። እንዲህም አለ፤ “መንግሥተ ሰማይ ሰው ወስዶ በዕርሻው ላይ የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች። 32 በርግጥ ይህች ዘር ከሌሎች ዘሮች ሁሉ ታንሳለች። በምታድግበት ጊዜ ግን የሰማይ ወፎች በቅርንጫፎቿ እስኪሰፍሩባት ድረስ፣ ከሌሎች ዛፎች ትበልጣለች፡፡ 33 ከዚያም ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ ሴት ወስዳ ኩፍ እስኪል ድረስ ከሦስት እጅ ዱቄት ጋር የደባለቀችውን እርሾ ትመስላለች።” 34 ኢየሱስም ለሕዝቡ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፣ ያለ ምሳሌም ምንም አልነገራቸውም። 35 ይህም ፦ "አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፣ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ የተሰወረውን እገልጣለሁ" ተብሎ በነቢዩ የተነገረው እንዲፈጸም ነው። 36 ኢየሱስ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ መጥተው "በዕርሻው የነበረውን የእንክርዳዱን ምሳሌ አስረዳን" አሉት። 37 ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አለ፤ “መልካሙን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው። 38 ዕርሻው ይህ ዓለም ነው፣ መልካሙ ዘር የመንግሥቱ ልጆች ናቸው። እንክርዳዱ የክፉው ልጆች ናቸው፤ 39 ዘሩን የዘራው ጠላት ዲያብሎስ ነው። መከሩ የዓለም መጨረሻ ሲሆን፣ አጫጆቹም መላእክት ናቸው። 40 ስለዚህ እንክርዳዱ ተሰብስቦ በእሳት እንደሚቃጠል፣ በዓለም መጨረሻም እንዲሁ ይሆናል። 41 የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፣ ከመንግሥቱ ለኅጢአት ምክንያት የሆኑ ነገሮችን ሁሉና፣ ክፉ አድራጊዎችን ይሰበስቧቸዋል፣ 42 ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት፣ ወደ እቶን እሳትም ይጥሏቸዋል። 43 ከዚያም ፃድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ። ጆሮ ያለው ይስማ። 44 መንግሥተ ሰማይ በዕርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት ትመስላለች፣ አንድ ሰውም አግኝቶ ደበቃት፤ ከደስታውም የተነሳ ያለውን ንብረት ሁሉ ሸጦ ያንን ዕርሻ ገዛው። 45 ደግሞም፣ መንግሥተ ሰማይ የከበሩ ዕንቈች የሚፈልግ ነጋዴን ትመስላለች። 46 በጣም ትልቅ ዋጋ ያለው ዕንቊ ባገኘ ጊዜ፣ ሄዶ ያለውን ንበረት ሁሉ ሸጠና ገዛው። 47 እንዲሁም፣መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር የተጣለችና ሁሉም ዓይነት ፍጥረታት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች። 48 መረቡዋ ስትሞላ፣ ዓሣ አጥማጆቹ ወደ ዳር አወጡት። ተቀምጠውም መልካም መልካሙን ሰብስበው በዕቃ አደረጉ፣ የማይጠቅመውን ግን አውጥተው ጣሉት። 49 በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፣ መላእክት መጥተው ከጻድቃን መካከል ክፉዎችን ይለያሉ። 50 ከዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት፣ ወደሚነደው እቶን እሳት ይጥሏቸዋል። 51 ይህን ሁሉ ተረድታችኋል?" አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም፣ “አዎን” አሉት። 52 ከዚያም ኢየሱስ፣ “ ስለዚህ የመንግሥተ ሰማይ ደቀ መዝሙር የሆነ ጸሐፊ ሁሉ፣ ከሀብቱ መካከል አሮጌውንና ዐዲሱን ያወጣ የቤት ጌታን ይመስላል አላቸው"። 53 ከዚያም ኢየሱስ እነዚህን ምሳሌዎች በጨረሰ ጊዜ፣ ከዚያ ስፍራ ሄደ። 54 ኢየሱስ ወደ ራሱ አገር መጥቶ፣ በምኲራቦቻቸው ሕዝቡን አስተማረ፣ ከዚህም የተነሣ ተገርመው፣ "ይህ ሰው ይህን ጥበቡንና እነዚህን ተአምራት ከየት አገኘ? 55 ይህ ሰው የአናጢው ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም አይደለችም ወይ? ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳስ ወንድሞቹ አይደሉም ወይ? 56 እኅቶቹስ ከእኛው ጋር አይደሉም ወይ? ታዲያ ይህ ሰው እነዚህን ነገሮች ሁሉ ከየት አገኛቸው?" አሉ። 57 በእርሱም ተሰናከሉበት። ኢየሱስ ግን፣ "ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤተ ሰቡ በቀር መከበሩ አይቀርም" አላቸው። 58 በአለማናቸውም ምክንያት ፣በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።



Matthew 13:1

ማቴዎስ 13፡1-2

በዚያ ቀን ይህ ነገር የፈጸመው ከዚህ በፊት ባለው ምዕራፍ ውስጥ የተገለጸው ታሪክ በተፈመበት ዕለት ነው፡፡ ከቤት ውጪ ኢየሱስ በማን ቤት ውስጥ በእንግድነት እንደተቀመጠ አልተገለጸም፡፡ ወደ ተንኳይቱ ገብቶ ይህ ምናልባትም ከእንጨት የተሠራ የዓሳ ማጥመጃ ጀልባ ሊሆን ይችላል፡፡

Matthew 13:3

ማቴዎስ 13፡3-6

ኢየሱስ በምሳሌም ብዙ ነገራቸው "ኢየሱስ በምሳሌም ብዙ ነገራቸው " ለእነርሱ ለሕዝቡ to the people in the crowd እነሆ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "ተመልከቱ” ወይም “አድምጡ” ወይም “አሁን ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ” ዘሪ ሊዘራ ወጣ "አንድ ገበሬ በማሳው ላይ ዘርን ለመዝራት ወጣ" እርሱም ሲዘራ "ገበሬው ስዘራ ሳለ" መንገድ ዳር ከማሳው አጠገብ ባለ “መንገድ” ላይ፡፡ ብዙ ሰዎች በዚያ መንገድ ላይ ከመራመዳቸው የተነሳ መንገዱ ጠንክሯል፡፡ ለቀሟቸው "የተዘሩትን ዘሮች ለቀሟቸው" ዓለታማ መሬት በድንጋይ ላይ ብዙ አፈር ያሌለበት ወዲያው በቀለ "የተዘረዘው ዘር ወዲያው በቀለ” ጠወለገ "ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፤ በጣም ይሞቅ ነበር" ( ተመልከት) ደረቀ "ተክሉ ደረቀና ሞተ"

Matthew 13:7

ማቴዎስ 13፡7-9

በእሾህ መካከል ወደቀ "የእሾህ ተክል ባለበት ሥፍራ ወደቀ" አነቀው "አዲሱን ተክል አነቀው፡፡" የተለመዱ አረሞች ሌሎች ተክሎች እንዳያድጉ የሚገልጽን ቃል ተጠቀሙ፡፡ ፍሬ ሰጠ "ፍሬ አፈራ" ወይም "ብዙ ፍሬ አፈራ” የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። ለተርጓሚዎች ምክር፡ "ለመስማት ጆሮ ያላችሁ ስሙ" ጆሮ ያለው "ማስማት የሚችሉ ሁሉ” ወይም “የሚሰማኝ ሁሉ" ያድምጠኝ “በሚገባ ያድምጠኝ" ወይም "አሁን ለሚናገረው ነገር ትኩረት ይስጥ"

Matthew 13:10

ማቴዎስ 13፡10-12

ለእነርሱ ለደቀ መዛሙርቱ ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም። ይህ በቀጥታ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሰጡ መረጃዎችን በማካተት እንዲህ ሊገለጽ ይችላል ፡ እግዚአብሔር የመንግስተ ሰማያትን ምስጢር መረዳት የሚትችሉበትን ዕድል ሰጥቶዋችኋ ይሁን እንጂ ይህ እድል ለሌሎች ሰዎች አልተሰጠም፡፡” ወይም እግዚአብሔር የመንግስተ ሰማያትን ምስጢር መረዳት እንዲትችሉ አድርጓል ይሁን እንጂ ለሌሎች ግን ይህ ችሎታ አልተሰጣቸውም፡፡” (en:ta:vol2:translate: and ተመልከት) አናንተ ደቀ መዛሙርት ምስጢር ለብዙ ጊዜ ተደብቆ የነበረው እውነት አሁን በኢየሱስ ተገጦዋል፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ምስጢር” ወይም “የተደበቀ እውነት”፡፡ ይህ የተሰጠው "ይህንን መረዳት የተሰጠው" ወይም "የማስተምረው ነገርን የተቀበለ ማንም ነው" ለእርሱ ተጨማሪ ይሰጠዋል ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊተረጎም ይችላል፡ “እግዚአብሐየር ተጨማሪ መረዳትን ይሰጠዋ፡፡” ( ተመልከት) ይህንን መረዳት ላለው "በግልጽ መረዳት ይችላል" ይህንን መረዳት ላሌለው "ይህንን መረዳት ላሌለው ሁሉ” ወይም "የማስተምረውን ነገር ያልተቀበለ ሰው ሁሉ" ያለው እንኳ ይወሰድበታል ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊተረጎም ይችላል፡ "ያለውን እንኳ እግዚአብሔር ይወስድበታል፡፡” ( ተመልከት)

Matthew 13:13

ማቴዎስ 13፡13-14

እነግራቸዋለሁ በእነዚህ ሁለት ቁጥሮች ውስጥ “እነርሱ” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው ሕዝቡን ነው፡፡ ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ። ኢየሱስ ይህንን ትይዩዋዊ ንጽትር የጠጠቀመው ሕዝቡ ለመስማት አሻፈረኝ ማለቱን ለደቀ መዛሙርቱ ለመናገር ነው፡፡ ( ተመልከት) ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም። "ምንም እንኳ በዐይናቸው ቢመለከቱም አይረዱትም”፡፡ “መምለከት “ የሚለው ሁለተኛው ቃል ትርጉም መረዳት ነው፡፡ መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ የተሰማው ነገር ምን እንደሆነ በግልጽ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ምንም እንኳ ትምህርቱን ቢሰሙም እውነቱን ግን አይረዱተም፡፡” ( ተመልከት) መስማትን ትሰማላችሁ ነገር ግን አትረዱትም፤ ማየትን ታያላችሁ ነገር ግን አታስተውሉም ይህ ከነብዩ ኢሳያስ የተወሰደው በኢሳያስ ዘመን ይኖሩ ስለነበሩ የማያምኑ ሰዎች የተነገረው ክፍል የሚጀምርበት ነው፡፡ ኢየሱስ ይህንን ክፍል በመውሰድ እያዳመጡ ያሉት ሰዎችን ለመግለጽ ተጠቅሞበታል፡፡ ይህ ሌላኛው ትይዩዋዊ ንጽጽር ነው ( ተመልከት) መስማትን ትሰማላችሁ ነገር ግን በጭራሽ አታስተውሉም "ነገሮችን ተሰማላችሁ ነገር ግን አትረዷቸውም"፡፡ የተሰማው ነገር ምን እንደሆነ በግልጽ እንዲህ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ትምህርቱን ትሰማላችሁ ነገር ግን እውነቱን ግን አትረዱም” ( ተመልቱ) ማየትን ታያላችሁ ነገር ግን በጭራሽ አታስተውሉም "ነገሮችን ትመለከታላችሁ ነገር ግን አትረዷቸውም"

Matthew 13:15

ማቴዎስ 13፡ 15-15

የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና "ይህ ሕዝብ ከእንግዲህ በኋላ አይማርም" ለመስማት አስቸጋሪዎች ሆነዋል "ለመስማት ምንም ፍላጎት የላቸውም" ዐይኖቻቸውን ጨፍነዋል "ለመስማት አሻፈረኝ ብለዋል" በዓይናቸው እንዳያዩ፥ ወይም በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ ወይም በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመሰሉ "በዐይኖቻው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ እና በዚህም ምክንያት እንዳይመለሱ" እንዳይመለሱ “ወደኋላ እንዳይመሰሉ” ወይም "ንሰሓ እንዳይገቡ” እንድፈውሳቸው "እኔ እንዳድናቸው" ለተርጓሚዎች ምክር፤ "እንደገና እንድቀበላቸው" ( ተመልከት)

Matthew 13:16

ማቴዎስ 13፡16-17

እናንተ . . . እናንተ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርት እየተናገር ነው፡፡ እናንተ ስለሚታዩ "ማየት ስለሚችሉ” ወይም “እናንተ ማየት ስለሚችሉ" እናንተ ስለሙትሰሙ "እናንተ መስማት ስለሚትችሉ” ወይም “እናንተ መስማት ስለሚትችሉ” ያያችሁትን ነገር "ሳደረግ ያያችሁኝን ነገሮች" የሰማችሁኝ ነገሮች "ስናገር የሰማችሁኝን ነገሮች

Matthew 13:18

ማቴዎስ 13፡18-19

ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ "ሴጣን የሰማውን የእግዚአብሔርን ቃል እንዲረሣ ያደርገዋል” ይነጥቃል የአንድ ሰውን ንብረት በጉልበት መቀማትን ለመግለጥ የሚያገለግል ቃልን ተጠቀሙ፡፡ በልቡ የተዘራውንም ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊተረጎም ይችላል፡ “የእግዚአብሔር ቃል በልብቡ ውስጥ ተዘርቷል” ( ተመልከት) በልቡም ውስጥ በአድማጩ ልብ ውስጥ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው። የቁም ትርጉሙ ምንም ትርጉም የማይሰጥ ከሆነ አንባቢዎቹ ዘሪው ኢየሱስ፣ ዘሩ መልዕክቱ እና በመንገድ ዳር ያለው አፈር ደግሞ አድማጮቹ መሆናቸው መረዳት በሚችሉበት መንገድ ለመተርጎም ጥረት አድርጉ ( and ተመልከት) በመንገድ ዳር "መንገድ” ወይም "መተላለፊያ" ይህንን በ MAT 13:4 ላይ በተረጎማችሁት መንገድ ተርጉሙት፡፡

Matthew 13:20

ማቴዎስ 13፡20-21

በጭንጫ ላይ የተዘራውም የቁም ትርጉሙ ምንም ትርጉም የማይሰጥ ከሆነ አንባቢዎቹ ዘሪው ኢየሱስ፣ ዘሩ መልዕክቱ እና በመንገድ ዳር ያለው አፈር ደግሞ አድማጮቹ መሆናቸው መረዳት በሚችሉበት መንገድ ለመተርጎም ጥረት አድርጉ ( and ተመልከት) ሥር የለውም "ረጅም ሥር የለውም” ወይም “አዲሱ ተክል ለሥሩ የሚሆን ሥፍራን አያገኝም”( እና ተመልከት) ከቃሉ የተነሣ "ከመልዕክቱ የተነሣ" ወዲያውኑ ይሰናከላል "ወዲያውኑ ወድቃል" ወይም "ወዲያውኑ እምነቱን ይተዋል" ( ተመልከት)

Matthew 13:22

ማቴዎስ 13፡22-23

በእሾህ መካከል የተዘራው . . . በመልካም መሬት የተዘራው የቁም ትርጉሙ ምንም ትርጉም የማይሰጥ ከሆነ አንባቢዎቹ ዘሪው ኢየሱስ፣ ዘሩ መልዕክቱ እና እሾሃማ መሬት ደግሞ አድማጮቹ መሆናቸው መረዳት በሚችሉበት መንገድ ለመተርጎም ጥረት አድርጉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ “በእሾህ መካከል የተዘረው ዘር እንዲህ ሆነ . . . በመልካም መሬት ላይ የተዘራው ዘር እንዲህ ሆነ ( እና ተመልከት) ቃል "መልዕክት" የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል። ለተርጓሚዎች ምክር፡ "አረሞች መልካም ተክል እንዳያድግ እንደሚያደርጉት ሁሉ የዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለልም ይህ ሰው ፍሬያማ እንዳይሆን ያደርጉታል ( ተመልከት) የዓለም አሳብ "በዚህ ዓለም ውስጥ ያሉና ሰዎችን የሚያሳስቡ ነገሮች" ፍሬያማ እንዳይሆኑ ያደርጋል "ውጤታማ እንዳይሆኑ ያደርጋል" ይህ በእውነት ፍሬ የሚያፈራ ነውና ተንከባከቡት "እነዚህ ፈፍሬ የሚያፈሩ እና ውጤታማ የሚሆኑት ናቸው" ወይም "መልካም ፍሬን እንደሚያፈሩት ጤናማ አትክልቶች እነዚህ ሰዎች ውጤታማ ናቸው" ( እና ተመልከት)

Matthew 13:24

ማቴዎስ 13፡24-26

ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው ኢየሱስ ለሕዝቡ ሌላ ምሳሌ ነገራው፡፡ ( ተመልከት) መንግስተ ሰማይት . . . ሰው ትመስላለች ትርጉም መነንግስተ ሰማይን ከሰውዬው ጋር እኩል ማድረግ የለበትም ይልቁንም መንግስተ ሰማያት በምሳሌ ውስጥ ከተገለጸው ሁኔታ ጋር ይመሳሰላል፡፡ *ተመልከት: መልካም ዘር "መልካም ዘሮች" ወይም "መልካም የሰብል ዘሮች”፡፡ ኢየሱስን የሚያደምጡት ሰዎች ኢየሱስ ስለ ስንዴት እየተናገረ እንደሆነ ተገንዝበዋል፡፡ ( ተመልከት) ጠላቱ መጥቶ "ጠላቱ ወደ ማሳው መጥቶ" አረሞች እነዚህ አረሞች ገና በለጋነታቸው የምግብ አትክሎቶችን የሚመስል ቢሆንም ፍሬያቸው ግን መርዛማ ነው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “መጥፎ ዘሮች” ወይም “የአረም ፍሬዎች” (UDB) ስንዴው በበቀለ ጊዜ "የስንዴው ዘር በበቀለ ጊዜ” ወይም “ፍሬው በበቀለ ጊዜ” ፍሬያቸውን ባፈሩ ጊዜ "ፍሬያቸውን ስያፈሩ" ወይም "የስንዴ ፍሬ ባፈራ ጊዜ" አረሞችም አብረው በቀሉ ለተርጓማች ምክር፡ "ከዚያም ሰዎች በማሳው ውስጥ አረሞችም መኖራቸውን ተመለከቱ"

Matthew 13:27

ማቴዎስ 13፡ 27-28

የእርሻው ባለቤት ይህ በእርሻ ማሳው ላይ መልካም ዘርን ከዘራው ሰው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? "መልካም ዘርን በእርሻህ ዘርተህ ነበር”፡፡ የመሬቱ ባለቤት ባሮቹ እንዲዘሩ አድርጋቸው ይሆናል፡፡ ( እና ተመልከት) አንዲህም አላቸው "የመሬቱ ባለቤት ለሎሌዎቹ እንዲህ አላቸው" እኛ . . . ትፈልጋለህን “እኛ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሎሌዎቹን ነው፡፡

Matthew 13:29

ማቴዎስ 13፡29-30

የመሬቱ ባለቤት እንዲህ አለ "የመሬቱ ባለቤት ለሎሌዎቹ እንዲህ አለ" አጫጆችን፦ “እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ” እላለሁ አለ። ይህንን በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ሳትከቱ መተርጎም ትችላላችሁ፡ “ለአጫጆቹ እንዲህ እላቸዋለሁ፤ በመጀመሪያ በእሳት እዲቃጠል እንክርዳዱን ሰብሰቡና በአንድ ላይ እሰሩ ከዚያም ስዴውን ሰብስባችሁ ወደ ጎተራዬ አስገቡ ( ተመልከት) ጎተራዬ ጎተራ በእርሻ ቦታ የሚሠራ የሰብል ምርት ማከማቻ ነው፡፡

Matthew 13:31

ማቴዎስ 13፡31-32

ኢየሱስ እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው "ኢየሱስ ለሕዝቡ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው" ( ተመልከት) መንግስተ ሰማያት . . . ትመስላለች ይህንን በ MAT 13:24 ላይ እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ የሰናፍጭ ፍሬ ትልቅ ዛፍ የሚትሆን በጣም ትን ሽ ዘር ( ተመልከት) ይህ ዘር ከሌሎች ዘሮች ሁሉ ይልቅ በጣም ትንሽ ናት የምሳሌው የመጀመሪያ አድማጮች ከሚያውቋቸው ዘሮ መካከል በጣም ትንሸዋ የሰናፍጭ ፍሬ ናት ( ተመልከት) ይሁን እንጂ ካደገች በኋላ "ይሁን እንጂ ተክሏ ካደገች በኋላ" ዛፍ ይሆናል "በጣም ትልቅ ዛፍ ይሆናል" ( እና እና ተመልከት) የሰማይ ወፎች "ወፎች" ( ተመልከት)

Matthew 13:33

ማቴዎስ 13፡33-33

ከዚያም ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው "ከዚያም ኢየሱስ ለሕዝቡ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው" ( ተመልከት) መንግስተ ሰማየት . . . ትመስላለች በ MAT 13:24 ላይ እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ መንግስቱ እንደ እርሾ አይደለም ይሆኑ እንጂ የመንግስቱ መስፋፋት እንደ እርሾ ነው ተመልከት) ሦስት መሥፈሪያ ዱቄት "ብዙ ዱቄት" ወይም በባሕላችሁ ውስጥ ብዙ መጠን ያለው የዱቄት መሥፈሪያን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ እስኪቦካ ድረስ እስኪቦካ ድረስ፡፡ በዚህ ሥፍራ በተዘዋዋር የተሰጠው መረጃ ዳቦ ለመጋገር በሦስት መሥፈሪያ ዱቄቱ ላይ እርሾ ተጨምሮ መቦካቱ ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 13:34

ማቴዎስ 13፡34-35

ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም። ቅደም ተከተሉ “ተናገረ . . . በምሳሌዎች . . . በምሳሌዎች . . . ተናገረ”፡፡ ይህንን ቅደም ተከተል የተከተለው በምሳሌ እንደተናገራቸው አጽኖት ለመስጠት ነው፡፡ ( ተመልከት) እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይህ ኢየሱስ በ MAT 13:1 መጀመሪያ ላይ ያስተማረውን ያመለክታል፡፡ ያለ ምሳሌ ምንም አልተናገራቸውም "ከምሳሌ ውጪ ምንም አልነገራቸውም" ለተርጓሚዎች መክር፡ "የነገራውን ሁሉ በምሳሌ ነገራቸው" ( እና ተመልከት) በነቢዩምየተባለው ይፈጸም ዘንድ፣ እኔ ስናገር ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ልገለጽ ይችላል፡ “ከብዙ ዘመናት በፊት እግዚአብሔር ለአንድ ነቢይ እንዲጽፍ ያደረገው ነገር እውን እንዲሆን አደረገ” (UDB). ( ተመልከት) የተሰወረ ነገር ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ልገለጽ ይችላል፡ “ለብዙ ጊዜያት ተሰውሮ የነበረው ነገር" ( ተመልከት) ዓለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ "ከፍጠትረታት ጅማሬ አንስቶ" ወይም "እግዚብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጊዜ አንስቶ"

Matthew 13:36

ማቴዎስ 13፡36-39

ወደ ቤት ገባ "ወደ ቤት ውስጥ ገባ" ወይም "ወደሚያርፍበት ቤት ገባ" ዘር የዘራው "ዘሪው" የሰው ልጅ በዚህ ሥፍራ ኢየሱስ ራስን እያመለከተ ነው፡፡ የመንግስቱ ልጆች "የመንግስቱ አካል የሆኑ ሰዎች” የክፉ ልጆች "የክፉ የሆኑት ሰዎች" ጠላት የዘራቸው እንክርዳዱን የዘረው ጠላት የዓለም መጨረሻ "የዘመን መጨረሻ"

Matthew 13:40

ማቴዎስ 13፡ 40-43

ስለዚህ እንክርዳዱ ተሰብስቦ እንዲቃጠል ሲደረግ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ በቀጥታ ሊተረጎም ይችላል፡ “ስለዚህም ሰዎቹ እንክርዳዱን ሰብስበው ስያቃጥሉ" ( ተመልከት) የዓለም መጨረሻ "የዘመን መጨረሻ" የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል በዚህ ሥፍራ ኢየሱስ ስለ ራሱ እየተናገረ ነው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እኔ፣ የሰው ልጅ መላእክት እልካቸዋለሁ”፡፡ ዓመፃን የሚያደርጉት "ክፋትን የሚያደርጉ" ወይም "ክፉ ሰዎች" እቶን እሳት ለተርጓሚዎች ምክር፡ "እቶን እሳት”፡፡ “ማቃጠያ ሥፍራ” የሚለው ቃል በእናንተ አከባቢ የማይታወቅ ከሆነ “እሳት ማንደጃ ሥፍራ” የሚለውን ቃል መውሰድ ይቻላል፡፡ እንደ ጸሐይ ይበራል "ልክ እንደ ፀሐይ የሚትታዩ ሁኑ” ( ተመልከት) የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ። ለተርጓሚዎች ምክር: "ጆሮ ያለው ይስማ” ወይም “ጆሮዎች ያሉት እንገግዲህ ያድምጥ"፡፡

Matthew 13:44

ማቴዎስ 13፡44-46

መንግስተ ሰማያት . . . ትመስላለች በ MAT 13:24 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ (ተመልከት) በእርሻ ውስጥ የተሰወረን መዝገብ ትመስላለች መዝገብ በጣም ጠቃ፣ እና ውድ የሆኑ ነገሮች ስብስብ ነው፡፡ ይህ እንዲህ ባለ መንገድ ሊተረጎም ይችላል፡ “የሆነ ሰው በእርሻ ውስጥ የደበቀው መዝገብ” ( እና ተመልከት) ደበቀው "covered it up" ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ በዚህ ሥፍራ ላይ በተዘዋዋሪ መንገድ የተገለጸው መረጃ የተሰወረ መዝገብ በውስጡ የያዘው የእርሻ ቦት ሰውዬው መግዛቱ ነው፡፡ (ተመልከት ነጋዴ ነጋዴ የተለያዩ ነገሮችን የሚሸጥ፣ ብዙ ጊዜም የሚሸጡ ነገሮችን ከሩቅ ሥፍራ የሚያመጣ ነው፡፡ መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤ በዚህ ሥፍራ ላይ በተዘዋዋር መንድ የተገለጸው መረጃ መሠረት ይህ ሰው መልካም ዕንቁን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ውድ ዕንቁ “ዕንቁ” ለስላሳ፣ ጠንካራ፣ የሚያንጸባርቅ፣ ነጭ ወይም ቀለል ያለ ቀለም ያለው ከውሃ ውስጥ የሚገኝ እና ውድ የሆኑ ጌጣ ጌጦችን ለማዘጋጀት የሚውል ውስድ ነገር ነው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “መልካም ዕንቆዎች” ወይም “የሚያምሩ ዕንቁዎች”፡፡

Matthew 13:47

ማቴዎስ 13፡47-48

መንግስተ ሰማያት . . . ትመስላለች በ MAT 13:24 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ የእግዚአብሔር መንግስት እንደ መረብ አይደለችም ይሁን እንጂ መንግስተ ሰማያት ልክ መረብ የተለያዩ ዓሳዎችን እንደሚይዝ እንዲሁ መንግስተ ሰማይም ሁሉንም ዓይነት ሰዎችን ወደራሱ ይሰበስባል፡፡ ( ተመልከት) ወደ ባሕር እንደሚጣል መረብ ይህ በዚህ ዓይነት መንገድ ሊተረጎም ይችላል፡ “አንዳንድ ዓሳ አጥማጆች ዓሳ ለማጥመድ ወደ ባሕር ውስጥ እንደሚጥሉት መረብ፡፡” ( ተመልከት) ወደ ባሕር ውስጥ የሚጣል ባሕር "ወደ ባሕር ውስጥ የሚጣል መረብ" ሁሉንም ዓይነት ፍጥረታትን እንደሚሰበስብ "ሁሉንም ዓይነት ዓሳዎች እንደሚይዝ" ወደ ወደቡ አወጦአት "መረቡን ወደ ባሕሩ ዳርቻ አወጡት” ወይም “መረቡን ወደ ባሕሩ ዳርቻ ጎትተው አወጡት" መልካም የሆኑ ነገሮችን "ጥሩ ጥሩውን ነገር" ጥቅም ያሌለውን "መጥፎዎቹን ዓሳዎች" ወይም "የማይበሉ የዓሳ ዓይነቶችን ግን" አውጥተው ይጥሉአቸዋል "አያስቀምጡትም"

Matthew 13:49

X

ማቴዎስ 13፡49-50

የዓለም መጨረሻ "የዘመን መጨረሻ" መጣ "ከሌላ ቦታ የመጣ" ወይም "የሚሄድ" ወይም "ከሰማይ የመጣ" ወረወራቸው "ክፉዎቹን ወረወራቸው" ቆሻሻ ማቃጠያ እሳት ይህ የገሃነም እሳት ምሳሌ ነው፡፡ “ቆሻሻ ማቃጠያ” የሚለው የማይታወቅ ከሆነ “ማቃጠያ” የሚል ቃል ልንጠቀም እንችላለን፡፡ ለተርጓማች ምክር፡ "የማቃጠያ ሥፍራ" ( ተመልከት) በዚያ ለቅሶ እና የጥርስ ማፋጨት ይሆናል "ክፉዎች የሚያለቅሱበት እና ጥርሳቸውን የሚያፋጩበት ሥፍራ"

Matthew 13:51

X

ማቴዎስ 13፡51-53

ይህን ሁሉ አስተዋላችሁን? ደቀ መዛሙርቱ “አዎን” አሉት፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይህን በቀጥታ በመጥቀስ ሳይጠቀስ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ “ይህንን ሁሉ በደንብ መረዳታቸውን ኢየሱስ ጠየቃቸው፣ እነርሱን አዎን ተረድተነዋል ( ተመልከት) ደቀ መዝሙር የሆነ "ስለሆነ ነገር ተማረ" መዝገብ መዝገብ በጣም ውድ እና ዋጋ ያላቸው ነገሮች ስብስብ ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ እነዚህ ነገሮች የተከማቹበት ሥፍራን፣ “መጋዝን” ማለት ነው፡:

Matthew 13:54

ማቴዎስ 1፡54-56

ወደ ገዛ አገሩ "የእርሱ ሀገር" ወደ ምኩራቦች በዚህ ሥፍራ ላይ “የእነርሱ” የተጠቀሰው ተውላጠ ስም በዚያ አከባቢ ያሉ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ በጣም ተገረሙ "ተደነቁ" በእነዚህ ተዓምራቶች "እነዚህን ተዓምራት ያደረገበትን ኃይል ከዬት አገኘ” ( ተመልከት) የአናጥዉ ስም አናጢ ከእንጨት ወይም ከድንጋይ የተለያዩ ነገሮችን የሚያበጅ ሰው ነው፡፡ “አናጢ” የሚለው ቃል በእናንተ ዘንድ የማይታወቅ ከሆነ “ግንበኛ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡

Matthew 13:57

ማቴዎስ 13፡ 57-58

ተሰናከሉበት "ኢየሱስ በሚኖርበት መንደር ውስጥ የሚኖሩት ሰዎች በእርሱ ተሰናከሉበት” ወይም “. . . እርሱን አይቀበሉትም” ነብይ አይከበርም "ነብይ በሁሉም ሥፍራ ይከበራል" “ነብይ ክብርን በሁሉም ሥፍራ ያገኛል” ወይ “በሁሉም ሥፍራ ያሉ ሰዎች ነብያትን ያከብራሉ” ( ተመልከት) በገዛ ሀገሩ "በአከባቢው" ወይም "በመንደሩ" የገዛ ቤተሰቦቹ "በራሱ ቤት" በዚያም ብዙ ተዓምራትን አላደረገም “ኢየሱስ በገዛ ሀገሩ ብዙ ተዓምራትን አላደረገም”፡፡


Translation Questions

Matthew 13:3

ስለ ዘሪው በተናገረው የኢየሱስ ምሳሌ ላይ በመንገድ ዳር በወደቀው ዘር ላይ ምን ሆነ?

በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር ወፎች ለቀሙት። [13:4]

ስለ ዘሪው ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ በዐለታማ መሬት ላይ የወደቀው ዘር ላይ ምን ሆነ?

በዐለታማ መሬት ላይ የወደቀው ዘር ወዲያውኑ በቀለ፣ ነገር ግን ፀሐይ አጠወለገውና ደረቀ። [13:5]

ስለ ዘሪው ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ በዐለታማ መሬት ላይ የወደቀው ዘር ላይ ምን ሆነ?

በዐለታማ መሬት ላይ የወደቀው ዘር ወዲያውኑ በቀለ፣ ነገር ግን ፀሐይ አጠወለገውና ደረቀ። [13:6]

Matthew 13:7

ስለ ዘር በተናገረው የኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ በእሾሃማ ቦታ የወደቀው ዘር ላይ ምን ሆነ?

በእሾህ መሃል የወደቀው ዘር በእሾኹ ታነቀ። [13:7]

ስለ ዘር በተናገረው የኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር ምን ሆነበት?

በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር አንዳንዱ መቶ እጥፍ፣ ሌላው ስድሳ፣ ሌላው ሠላሳ አፈራ። [13:8]

Matthew 13:13

የኢሳይያስ ትንቢት ሰዎቹ ይሰማሉ ያያሉ፣ ነገር ግን ምን አያደርጉም?

የኢሳይያስ ትንቢት ሰዎቹ እንደሚሰሙ፣ ነገር ግን እንደማያስተውሉ፣ እንደሚያዩ ግን ልብ እንደማይሉ ይናገራል። [13:14]

Matthew 13:15

ኢየሱስን የሚሰሙ ነገር ግን የማያስተውሉ ሰዎች ችግራቸው ምንድነው?

ኢየሱስን የሚሰሙ ነገር ግን በሙሉ ልባቸው የማያስተውሉ ሰዎች ልባቸው ደንድኖ መስማት ትተዋል፣ ዐይኖቻቸውም ተጨፍኗል። [13:15]

Matthew 13:18

በዘሪው ምሳሌ ውስጥ በመንገድ ዳር እንደተዘራው ዘር የሆነው ምን ዓይነት ሰው ነው?

በመንገድ ዳር እንደተዘራው ዘር የሆነው የመንግሥቱን ቃል ሰምቶ የማያስተውለው ሰው ነው፣ ከዚያም ክፉው መጥቶ በልቡ የተዘራውን ይወስዳል። [13:19]

Matthew 13:20

በዘሪው ምሳሌ ውስጥ፣ በዐለታማ መሬት ላይ የተዘራውን ዘር የሚመስለው ምን ዓይነት ሰው ነው?

በዓለታማ መሬት ላይ የተዘራው ዘር ቃሉን ሰምቶ ወዲያውኑ በደስታ የሚቀበለው፣ ነገር ግን ስደት በተነሣ ጊዜ ወዲያውኑ የሚሰናከል ነው። [13:20]

በዘሪው ምሳሌ ውስጥ፣ በዐለታማ መሬት ላይ የተዘራውን ዘር የሚመስለው ምን ዓይነት ሰው ነው?

በዓለታማ መሬት ላይ የተዘራው ዘር ቃሉን ሰምቶ ወዲያውኑ በደስታ የሚቀበለው፣ ነገር ግን ስደት በተነሣ ጊዜ ወዲያውኑ የሚሰናከል ነው። [13:21]

Matthew 13:22

በዘሪው ምሳሌ ውስጥ በእሾሃማ ተክሎች መካከል የተዘራው ምን ዓይነት ሰውን የሚወክል ነው?

በእሾህ መካከል የተዘራው ዘር ቃሉን የሚሰማ፣ ነገር ግን የዚህ ዓለም ጉዳዮች እና የብልጥግና ማታለል ቃሉን አንቆ የሚያስቀርበት ነው። [13:22]

በዘሪው ምሳሌ ውስጥ በመልካም መሬት ላይ የተዘራው ምን ዓይነት ሰውን የሚወክል ነው?

በመልካም መሬት ላይ የተዘራው ዘር ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውለው፣ ከዚያም ፍሬ የሚያፈራበት ሰው ነው። [13:23]

Matthew 13:27

በእንክርዳዱ ምሳሌ ውስጥ፣ በእርሻው ውስጥ እንክርዳድ የዘራው ማን ነው?

በእርሻው ውስጥ ጠላት እንክርዳዱን ዘራ። [13:28]

Matthew 13:29

የእርሻው ባለቤት ስለ እንክርዳዱ እና ስንዴው ለአገልጋዮቹ የሰጠው መመሪያዎች ምንድናቸው?

የእርሻው ባለቤት ስለ እንክርዳዱ እና ስንዴው ለአገልጋዮቹ የሰጠው መመሪያዎች ምንድናቸው?

Matthew 13:31

ስለ ስናፍጭ ቅንጣቷ ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ፣ በትንሿ የስናፍጭ ቅንጣት ላይ ምን ሆነ?

የስናፍጯ ቅንጣት ከሌሎች አትክልቶች በላይ ትልቅ ዘፍ ሆነችና ከዚያም የተነሣ ወፎች በቅርንጫፎቿ ላይ ተጠለሉ። [13:31]

ስለ ስናፍጭ ቅንጣቷ ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ፣ በትንሿ የስናፍጭ ቅንጣት ላይ ምን ሆነ?

የስናፍጯ ቅንጣት ከሌሎች አትክልቶች በላይ ትልቅ ዘፍ ሆነችና ከዚያም የተነሣ ወፎች በቅርንጫፎቿ ላይ ተጠለሉ። [13:31]

Matthew 13:33

የእግዚአብሔር መንግሥት ልክ እንደ እርሾ ነው በማለት ኢየሱስ የተናገረው እንዴት ነበር?

የእግዚአብሔር መንግሥት ሊጡን ሁሉ እስኪያቦካ ድረስ የተለወሰ ሦስት መስፈሪያ እርሾ ነው በማለት ኢየሱስ ተናገረ። [13:33]

Matthew 13:36

በእንክርዳዶቹ ምሳሌ ውስጥ መልካሙን ዘር የዘራው ማን ነው፣ እርሻው ምንድነው፣ መልካሙ ዘር ማነው፣ እንክርዳዶቹ እነማን ናቸው እንክርዳዱንስ የዘራው ማንነው?

የመልካሙ ዘር ዘሪ የሰው ልጅ ነው፣ እርሻው ዓለም ናት፣ መልካሙ ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፣ እንክርዳዱ የክፉው ልጆች ናቸው፣ የእንክርዳዱ ዘሪ ዲያቢሎስ ነው። [13:37]

በእንክርዳዶቹ ምሳሌ ውስጥ መልካሙን ዘር የዘራው ማን ነው፣ እርሻው ምንድነው፣ መልካሙ ዘር ማነው፣ እንክርዳዶቹ እነማን ናቸው እንክርዳዱንስ የዘራው ማንነው?

የመልካሙ ዘር ዘሪ የሰው ልጅ ነው፣ እርሻው ዓለም ናት፣ መልካሙ ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፣ እንክርዳዱ የክፉው ልጆች ናቸው፣ የእንክርዳዱ ዘሪ ዲያቢሎስ ነው። [13:38]

በእንክርዳዶቹ ምሳሌ ውስጥ መልካሙን ዘር የዘራው ማን ነው፣ እርሻው ምንድነው፣ መልካሙ ዘር ማነው፣ እንክርዳዶቹ እነማን ናቸው እንክርዳዱንስ የዘራው ማንነው?

የመልካሙ ዘር ዘሪ የሰው ልጅ ነው፣ እርሻው ዓለም ናት፣ መልካሙ ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፣ እንክርዳዱ የክፉው ልጆች ናቸው፣ የእንክርዳዱ ዘሪ ዲያቢሎስ ነው። [13:39]

በእንክርዳዱ ምሳሌ ውስጥ፣ አጫጆቹ እነማን ናቸው፣ ደግሞስ መከሩ ምንን ይወክላል?

አጫጆቹ መላእክት ሲሆኑ፣ መከሩ ደግሞ የዓለም ፍጻሜ ነው። [13:39]

Matthew 13:40

በዓለም መጨረሻ ላይ ዓመጻን በሚያደርጉት ላይ ምን ይሆናል?

በዓለም መጨረሻ ላይ ዓመጻን የሚያደርጉት ወደ ሚነድደው እሳት ይጣላሉ። [13:42]

ጻድቃን ለሆኑት በዓለም መጨረሻ ላይ ምን ይሆናል?

በዓለም መጨረሻ ላይ፣ ጻድቃን እንደ ፀሐይ ያበራሉ። [13:43]

Matthew 13:44

በኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚወክለውን ሃብትን በእርሻ ውስጥ ያገኘው ሰው ምን አደረገ?

ሃብትን ያገኘው ሰው ያለውን ሁሉ ሸጦ እርሻውን ገዛ። [13:44]

በኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚወክለውን ታላቅ ዋጋ ያላትን ውብ ዕንቊ ያገኘው ሰው ምን አደረገ?

ታላቅ ዋጋ ያላትን ውብ ዕንቊ ያገኘው ሰው ያለውን ሁሉ ነገር ሸጦ ይገዛዋል። [13:45]

በኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚወክለውን ታላቅ ዋጋ ያላትን ውብ ዕንቊ ያገኘው ሰው ምን አደረገ?

ታላቅ ዋጋ ያላትን ውብ ዕንቊ ያገኘው ሰው ያለውን ሁሉ ነገር ሸጦ ይገዛዋል። [13:46]

Matthew 13:47

አሳ ማጥመጃ መረብን በተመለከተ የተነገረው ምሳሌ በዓለም መጨረሻ የሚሆነውን ነገር የሚመስለው እንዴት ነው?

የማይጠቅሙት ነገሮች ከመልካሞቹ ተለይተው ከመረብ እንደተጣሉ ሁሉ፣ በዓለም መጨረሻ ላይ ክፉዎች ከጻድቃን ተለይተው ወደ እሳት ይጣላሉ። [13:47]

አሳ ማጥመጃ መረብን በተመለከተ የተነገረው ምሳሌ በዓለም መጨረሻ የሚሆነውን ነገር የሚመስለው እንዴት ነው?

የማይጠቅሙት ነገሮች ከመልካሞቹ ተለይተው ከመረብ እንደተጣሉ ሁሉ፣ በዓለም መጨረሻ ላይ ክፉዎች ከጻድቃን ተለይተው ወደ እሳት ይጣላሉ። [13:48]

Matthew 13:54

በትውልድ አካባቢው የነበሩት ሰዎች ኢየሱስ ሲያስተምር በሰሙት ጊዜ ስለ ኢየሱስ የጠየቊት ጥያቄ ምን ነበር?

ሰዎቹ፣ “ይህ ሰው ይህንን ጥበብ እና ተዓምራት ከየት አገኘው” በማለት ጠየቁ። [13:54]

Matthew 13:57

ነብይ በገዛ አገሩ ምን አይሆንም ሲል ኢየሱስ ተናገረ?

ነብይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር ኢየሱስ ተናገረ። [13:57]

ከሰዎቹ አለማመን የተነሣ በኢየሱስ ክልል ውስጥ ምን ሆነ?

ከሰዎቹ አለማመን የተነሣ፣ ኢየሱስ በገዛ ክልሉ ብዙ ተዓምራት ማድረግ አልቻለም። [13:58]


ምዕራፍ 14

1 በዚያን ጊዜ፣ የአራተኛው ክፍል ገዢ የነበረው ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ሰማ። 2 አገልጋዮቹንም፣ "ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው። ስለዚህ ይህ ሁሉ ኅይል በእርሱ የሚሠራው ከሞት ስለ ተነሣ ነው" አላቸው። 3 ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት፣ ይዞ አሳስሮት ነበርና፡፡ 4 ምክንያቱም ዮሐንስ፣ "እርሷን ማግባትህ ተገቢ አይደለም" ይለው ነበር። 5 ሄሮድስ ሊያስገድለው ፈልጎ፣ ሕዝቡን ፈራ፣ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያዩት ነበር። 6 ነገር ግን በሄሮድስ የልደት ቀን፣ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከል ስትጨፍር፣ ሄሮድስን ደስ አሰኘችው። 7 በዚህም ምክንያት፣ የምትጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰጣት በመሓላ ቃል ገባላት። 8 በእናቷም ተመክራ፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ እዚሁ፣ በሳሕን አድርገህ ስጠኝ” አለችው። 9 ንጉሡ በጥያቄዋ በጣም ዐዘነ፣ ነገር ግን በመሓላውና ከእርሱ ጋር እራት ላይ በነበሩት ምክንያት፣ የተናገረው እንዲፈጸም አዘዘ። 10 ሰው ልኮ፣ በወህኒ ቤት የዮሐንስን ራስ አስቈረጠ። 11 ከዚያም ራሱ በሳሕን ተደርጎ ለልጅቱ ተሰጣት፣ እርሷም ለእናቷ ወስዳ ሰጠች። 12 ከዚያም የእርሱ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣ በድኑን ወስደው ቀበሩት። ከዚህ በኋላ ሄደው ለኢየሱስ ነገሩት። 13 ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ በጀልባ ገለል ወዳለ ቦታ ሄደ። ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ፣ ከየከተሞቹ በእግር ተከተሉት። 14 ከዚያም ኢየሱስ ቀድሞአቸው መጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና ራራላቸው፣ ሕመምተኞቻቸውንም ፈወሰ። 15 በመሸም ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ መጡና፣ “ቀኑ መሽቷል ይህም ስፍራ ምድረ በዳ ነው ። ሕዝቡን ወደ መንደሮች እንዲሄዱና፣ ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ አሰናብት" አሉት። 16 ኢየሱስ ግን፣ "መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተው የሚበሉትን ስጧቸው" አላቸው። 17 እነርሱም፣ “ እኛ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዐሣ ብቻ ነው" አሉት። 18 ኢየሱስም፣ "እነርሱኑ ወደ እኔ አምጡአቸው" አለ። 19 ከዚያም ኢየሱስ ሣሩ ላይ እንዲቀምጡ ሕዝቡን አዘዘ። ዐምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዐሣ ወሰደ፣ ወደ ሰማይ አሻቅቦ እያየ፣ አመሰገነ፤ እንጀራውንም ቈርሶ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ። 20 ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚያም የተረፈውን ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ ቊርስራሽ ሰበሰቡ። 21 የበሉትም፣ ከሴቶችና ከልጆች ሌላ፣ ዐምስት ሺ ያህል ወንዶች ነበሩ። 22 እርሱም ሕዝቡን እያሰናበተ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱን ወዲያው ወደ ጀልባ ገብተው፣ ከእርሱ በፊት ወደ ማዶ እንዲሄዱ አዘዛቸው። 23 ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ፣ ብቻውን ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። በመሸ ጊዜ፣ በዚያ እርሱ ብቻውን ነበር። 24 ጀልባዋ በባሕሩ መካከል እያለች፤ ከተቃራኒ አቅጣጫ ይነፍስ ስለ ነበር፣ በማዕበሉ ክፉኛ ትንገላታ ነበር። 25 ከምሽቱ በአራተኛው ክፍል፣ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ እየመጣ ነበር። 26 ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ እየተራመደ ሲያዩት፣ እጅግ ደንግጠው፣ “መንፈስ ነው”ብለው በፍርሀት ጮኹ። 27 ኢየሱስ ግን ወዲያውኑ፣ “አይዟችሁ! እኔ ነኝ! አትፍሩ” ብሎ ተናገራቸው። 28 ጴጥሮስም መልሶ፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተስ ከሆንህ፣ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ" አለው። 29 ኢየሱስም፣ “ና" አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወጥቶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ፣ በውሃው ላይ ተራመደ። 30 ነገር ግን ጴጥሮስ ነፋሱን አይቶ በመፍራት፣ መስጠም በጀመረ ጊዜ ፣ “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ” ብሎ ጮኸ። 31 ኢየሱስም ያኔውኑ እጁን ዘርግቶ ጴጥሮስን ያዘውና፣ “አንተ እምነት የጎደለህ፣ ለምን ትጠራጠራለህ?” አለው። 32 ከዚያም ኢየሱስና ጴጥሮስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ፣ ነፋሱ መንፈሱን አቆመ። 33 በጀልባው ውስጥ የነበሩት ደቀ መዛሙርትም ኢየሱስን፣ “አንተ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት። 34 ከተሻገሩም በኋላ፣ ጌንሳሬጥ ወደ ተባለ አገር መጡ። 35 በዚያም ስፍራ የነበሩ ሰዎች ኢየሱስ መሆኑን ባወቁ ጊዜ፣ በአካባቢው ወዳለ ስፍራ ሁሉ መልእክት ላኩና፣ የታመመውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ። 36 የልብሱን ጫፍ ብቻ ለመንካት ለመኑት፣ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ።



Matthew 14:1

ማቴዎስ 14፡1-2

በዚያ ጊዜ "በዚያ ዘመን" ወይም “ኢየሱስ በገሊላ እያገለገለ ሳለ" የአራተኛው ክፍል ገዥ የሆነው ሄሮዶስ ሄሮድ አንቲፓስ የእስራኤልን አንድ አረተኛ ግዛት ይገዛ ነበር ( ተመልከት) ስለኢየሱስ ዝና ሰማ "ሰዎች ስኢየሱስ የሚሉትን ሰማ" ወይም "ስለ ኢየሱስ ዝና ሰማ" እንዲህም አለ "ሄሮዶስ እንዲህ አለ"

Matthew 14:3

ማቴዎስ 14፡3-5

ሄሮዶስ ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበር ይህ የሚሆነው ሄሮዶስ ሌሎች ሰዎችን በእርሱ ፈንታ ሄደው ዮሐንስን እንዲይዙት በማዘዝ ነው ( ተመልከት) ሄሮዶስ ዮሐንስን አስያዘው "ሄሮዶስ ዮሐንስ እንድታሠሰር አደረገ" ዮሐንስ፦ እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም ይለው ነበርና። “እርሷን ምስትህ አድርገህ መውሰድ ለአንድ አልተፈቀደም ስላለው ነው ( ተመልከት) ዮሐንስ ስላለው ነው "ዮሐንስ ይህንን ደጋግሞ ለሄሮዶስ ይለው ነበር" በሕግ አክተፈቀደም ሄሮዶስ ሄሮዲያስን ስያገባ ፊልፕ በሕይወት ነበር፡፡

Matthew 14:6

ማቴዎስ 14፡6-7

በዚህ መካከል የልደት ክብረ በዓል ለማክበር የመጡ እንግዶች መካከል ( ተመልከት)

Matthew 14:8

ማቴዎስ 14፡8-9

የእናቷን ምክር ተከትላ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እናትየው ከመከረቻት በኋላ" ( ተመልከት) ተምክራ "መመሪያ መሠረት" እንዲህ አለች “እርሷ” የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው የሄሮዲስን ሴት ልጅ ነው፡፡ ሳህን ትልቅ ሳህን ንጉሡ በጥያቄዋ እጅግ በጣም ተበሳጨ "ጥያቄዋ ንጉሡን አበሳጨው" ( ተመልከት) ንጉሥ የአራረተኛ ክፍል ገዥው ሄሮዶስ አንቲፓስ (MAT 14:1).

Matthew 14:10

ማቴዎስ 14፡ 10-12

ጭንቅላቱን በሳህን አድርገው ለልጅቷ ሰጧት "የሆነ ሰው ጭንቅላቱን በሳህን አድርጎ ለልጅቷ ሰጣት" ( ተመልከት) ሳህን ትልቅ ሳህን ሴት ልጅ ያላገባች ልጅን የሚያመለክት ቃልን ተጠቀም፡፡ ደቀ መዛሙርቱ "የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት" ሬሳውን "በድኑን" ወደ ኢየሱስ ሄደው ነገሩት "የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ኢየሱስ ዘንድ ሄደው መጥመቁ ዮሐንስ ላይ ምን እንዳደረጉበት ለኢየሱስ ነገሩት ( ተመልከት

Matthew 14:13

ማቴዎስ 14፡ 13-14

ይህንን ስሰማ "በዮሐንስ ላይ የሆነውን ነገር ስሰማ" ወይም "ስለ ዮሐንስ የተነገረውን ነገር ስሰማ” ( ተመልከት) ፈቀቅ አለ ከሕዝቡ ተለይቶ ሄደ ከዚያ "ከዚያ ሥፍራ" ሕዝቡን ይህንን ስሰሙ “ሕዝቡን ወዴት እንደሄደ በሰሙ ጊዜ” ወይም “እንደሄደ ሕዝቡ በሰሙ ጊዜ” ሕዝቡ "ሕዝቡ" ወይም “የተሰበሰበው ሕዝብ” ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጥቶ የተሰበሰበውን ብዙ ሕዝብ ተመለከተ "ኢየሱስ ወደ ባሕሩ ዳርጃ በመጣ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ ተመለከተ”

Matthew 14:15

ማቴዎስ 14፡15-15

ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ መጥተው "የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ መጥተው"

Matthew 14:16

ማቴዎስ 14፡ 16-18

አያስፈልጋቸውም "ሕዝቡ . . . አያስፈልጋቸውም" እናንተ ስጧቸው “አናንተ” የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር አመልካች ሲሆን የሚያመለክተውም ደቀ መዛሙርቱን ነው፡፡ (en:ta:vol1:translate: ተመልከት) እነርሱም እንዲህ አሉት "ደቀ መዛርቱ ለኢየሱስ እንዲህ አሉት" አምስት ዳቦ እና ሁለት ዓሣ "5 ዳቦዎች እና 2 ዓሣዎች ( ተመልከት) እነርሱን ወደ እኔ አምጧቸው "ዳቦዎቹን እና ዓሣዎቹን ወደ እኔ አምጧቸው"

Matthew 14:19

ማቴዎስ 14፡ 19-21

ተቀመጡ ወይም “ይረፉ”፡፡ በዚህ ሥፍራ ላይ በእናንተ ባሕል ውስጥ ሰዎች ምግብ ለመመገብ የሚቀመጡበትን መንገድ የሚገልጽ ቃልን ተጠቀሙ፡፡ ወሰደ "በእጆቹ ይዞ፡፡" ሰርቋቸው አይደለም፡፡ (en:ta:vol1:translate: ተመልከት) ዳቦዎች "ዳቦዎች” ወይም “ያላቸውን ሁሉ ዳቦ" ወደ ሰማይ ተመለከተ ይህ ማለት 1) “ወደላይ እየተመለከተ” ወይም 2) “ወደላይ ከተመለከተ በኋላ”፡፡ እነርሱም ወደ ላይ ተመለከቱ "ደቀ መዛሙርቱም ደወ እርሱ ተሰበሰቡ " የበሉትም ሰዎች ዳቦውን እና ዓሣውን የበሉት ሰዎች" ( ተመልከት)

Matthew 14:22

ማቴዎስ 14፡ 22-24

ወዲያውም "ኢየሱስ አምስት ሺህ ሰዎችን ከመገበ በኋላ" በመሸም ጊዜ "ወደ ምሽት ላይ” ወይም “በጨለመ ጊዜ”" ከማዕበሉ የተነሳ ልቆጣጠሯት አልቻሉም "ማዕበሉ ታንኳይቱን ያናውጣት ነበር"

Matthew 14:25

ማቴዎስ 14፡ 25-27

በባሕሩ ላይ እየተራመደ "በውሃው ላይ እየተራመደ" በጣም ፈሩ "ደቀ መዛሙርቱ በጣም ፈሩthe disciples were very afraid" ምትሃት የሞተ ሰውን ትቶ የሄደ መንፈስ መሰላቸው

Matthew 14:28

ማቴዎስ 14፡28-30

ጴጥሮስ እንዲህ ሲል መለሰ "ጴጥሮስ ለኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ"

Matthew 14:31

ማቴዎስ 14፡ 31-33

አንተ እምነት የጎደለህ በ MAT 6:30 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ ስለምን ትጠራጠራለህ? "ልትጠራጠር አይገባህም" ( ተመልከት) የእግዚአብሔር ልጅ የይህ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት የሚገልጽ በጣም አስፈላጊ የሆነ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 14:34

ማቴዎስ 14፡34-36

በተሻገሩም ጊዜ "ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ ባሕሩን ከተሸገሩ በኋላ" ጌንሴሬጥ ከገሊላ ባሕር ማዶ በሰሜን ደቡብ በኩል የሚትገኝ ትንሽ መንደር ናት ( ተመልከት) መልዕከት ላኩ "በዚያ አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች መልዕክት ላኩ” ለመኑት "የታመሙት ሰዎች ለመኑት" ልብስ "የለበሰው ልብስ”


Translation Questions

Matthew 14:1

ሔሮድስ ኢየሱስ ማን እንደነበረ ያስብ ነበር?

ኢየሱስ ከሞት የተነሣው መጥምቊ ዮሐንስ እንደሆነ ሔሮድስ አሰበ። [14:2]

Matthew 14:3

ሔሮድስ በህገ-ወጥ መንገድ ያደረገው ነገር እንደሆነ መጥምቊ ዮሐንስ የነገረው ምን ነበር?

ሔሮድስ የወንድሙን ሚሰት አግብቶ ነበር። [14:4]

ሔሮድስ ወዲያውኑ መጥምቊ ዮሐንስን ያላስገደለው ለምን ነበር?

ሔሮድስ መጥምቊ ዮሐንስንስን ወዲያውኑ ያላስገደለው ዮሐንስን እንደ ነበብይ ይቆጥሩ የነበሩትን ሰዎች ስለፈራ ነበር። [14:5]

Matthew 14:6

በልደት ቀኑ ላይ ሔሮድያዳ ከዘፈነችለት በኋላ ሔሮድስ ምን አደረገ?

የምትጠይቀውን ሁሉ ሊሰጣት ሔሮድስ በመሃላ ቃል ገባላት። [14:7]

Matthew 14:8

ሔሮድያዳስ ምን ጠየቀች?

ሔሮድያዳስ ምን ጠየቀች?

ሔሮድያዳስ የጠየቀችውን ሔሮድስ የሰጣት ለምን ነበር?

ሔሮድስ ለሔሮድያዳስ የጠየቀችውን የሰጣት ከመሐላው የተነሣ እና እራት ላይ አብረውት ከነበሩት ሰዎች የተነሣ ነው። [14:9]

Matthew 14:13

ብዙ ሕዝብ ሲከተለው ባየ ጊዜ ኢየሱስ ያደረገው ነገር ምን ነበር?

ብዙ ሕዝብ ሲከተለው ባየ ጊዜ ኢየሱስ ያደረገው ነገር ምን ነበር?

Matthew 14:16

ደቀመዛሙርቱ ለሕዝቡ ምን እንዲያደርጉ ነው ኢየሱስ የጠየቃቸው?

ደቀመዛሙርቱ ለሕዝቡ ምን እንዲያደርጉ ነው ኢየሱስ የጠየቃቸው?

Matthew 14:19

ደቀመዛሙርቱ ለሕዝቡ ምን እንዲያደርጉ ነው ኢየሱስ የጠየቃቸው?

ደቀመዛሙርቱ ለሕዝቡ ምን እንዲያደርጉ ነው ኢየሱስ የጠየቃቸው?

ደቀመዛሙርቱ ለሕዝቡ ምን እንዲያደርጉ ነው ኢየሱስ የጠየቃቸው?

አምስት ሺህ ወንዶች እንዲሁም ሴቶች እና ሕጻናት ተመገቡና ዐሥራ ሁለት ቅርጫት ሙሉ ተረፈ። [14:20]

ምን ያክል ሰዎች ተመገቡ፣ ምን ያክልስ ምግብ ተረፈ?

ምን ያክል ሰዎች ተመገቡ፣ ምን ያክልስ ምግብ ተረፈ?

Matthew 14:22

ኢየሱስ ሕዝቡን ከሸኛቸው በኋላ ምን አደረገ?

ኢየሱስ ሕዝቡን ከሸኛቸው በኋላ ምን አደረገ?

ደቀመዛሙርቱ በባህሩ መካከል ሳሉ ምን ተከሰተ?

የደቀመዛሙርቱ ጀልባ ከንፋሱ እና ከማእበሉ የተነሣ ከሞላ ጎደል ከቊጥጥር ውጪ ሆና ነበር። [14:24]

Matthew 14:25

ኢየሱስ ወደ ደቀመዛሙርቱ የሄደው እንዴት ነበር?

ኢየሱስ በውሃ ላይ እየተራመደ ወደ ደቀመዛሙርቱ ሄደ። [14:25]

ባዩት ጊዜ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ምን ነገራቸው?

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንዳይደነግጡና እንዳይፈሩ ነገራቸው። [14:27]

Matthew 14:28

ኢየሱስ ለጴጥሮስ መጥቶ እንዲያደርግ የነገረው ምን ነበር?

ኢየሱስ ለጴጥሮስ የነገረው መጥቶ በውሃ ላይ እንዲራመድ ነበር። [14:29]

ጴጥሮስ ውሃ ውስጥ የሰጠመው ለምን ነበር?

ጴጥሮስ ውሃ ውስጥ የሰጠመው በፈራ ጊዜ ነበር። [14:30]

Matthew 14:31

ኢየሱስ እና ጴጥሮስ ወደ ጀልባ በሄዱ ጊዜ ምን ተከሰተ?

ጴጥሮስ እና ኢየሱስ ወደ ጀልባው በሄዱ ጊዜ፣ ንፋሱ መንፈሱን ተወ። [14:32]

ይህንን ባዩ ጊዜ ደቀመዛሙርት ምን አደረጉ?

ደቀመዛሙርት ይሄንን ባዩ ጊዜ፣ ኢየሱስን በማምለክ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ተናገረ። [14:33]

Matthew 14:34

ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ከባህሩ ማዶ በደረሱ ጊዜ ሕዝቡ ምን አደረጉ?

ኢየሱስ እና ደቀመዛሙርቱ ወደ ባሕሩ ማዶ በደረጉ ጊዜ፣ ሕዝቡ ታምመው የነበሩትን ሁሉ አመጧቸው። [14:35]


ምዕራፍ 15

1 ከዚያም አንዳንድ ፈሪሳውያንና የአይሁድ የሕግ መምህራን ከኢየሩሳሌም ኢየሱስን ለማነጋገር መጥተው እንዲህ አሉ፤ 2 "ደቀ መዛሙርትህ የሽማግሌዎችን ወግ የሚጥሱት ለምንድነው? ምግብ ከመብላታቸው በፊት እንደ ወጉ እጃቸውን አይታጠቡምና።" 3 ኢየሱስም መለሰና፣ "እናንተስ ስለ ወጋችሁ ስትሉ ለምን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትተላለፋላችሁ?" አላቸው፡፡ 4 እግዚአብሔር፣ ‹አባትህንና እናትህን አክብር፣› ‹ስለ አባቱ ወይም ስለ እናቱ ክፉ የሚናገር በርግጥ ይሞታል› ብሏልና፡፡ 5 እናንተ ግን፣ "አባቱን ወይም እናቱን፣ 'ከእኔ የተቀበላችሁት ማንኛውም እርዳታ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው ትላላችሁ፡፡' 6 ያ ሰው አባቱን ማክበር አያስፈልገውም። ስለ ወጋችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፡፡ 7 እናንተ ግብዞች፣ ኢሳይያስ ስለ እናንተ፣ 8 'ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ 9 የሰዎችን ትእዛዝ እንደ ሕግ በመቊጠር የራሳቸውን ትምህርት ስለሚያስተምሩ፣ እኔን በከንቱ ያመልኩኛል›› ብሎ ትንቢት በመናገሩ መልካም አድርጓል። 10 ከዚያ ሕዝቡን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ "አድምጡ አስተውሉም፡- 11 ወደ አፍ የሚገባ ሰውን ምንም አያረክስም፡፡ ይልቁንም ከአፍ የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ነው" አላቸው፡፡ 12 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ኢየሱስን፣ ‹‹ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሲሰሙ እንደ ተሰናከሉ ዐወቀሃል?›› አሉት፡፡ 13 ኢየሱስም መለሰና፣ ‹‹አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል፤ 14 እነርሱን ተዉአቸው፤ ዐይነ ስውር መሪዎች ናቸው፡፡ አንድ ዐይነ ስውር ሌላውን ዐይነ ስውር ቢመራው ሁለቱም ተያይዘው ጕድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡›› 15 ጴጥሮስ መልሶ ኢየሱስን፣ ‹‹ይህን ምሳሌ አብራራልን›› አለው፡፡ 16 ኢየሱስ፣ ‹‹እናንተ ደግሞ አሁንም አታስተውሉምን? 17 ወደ አፍ የሚገባው ሁሉ ወደ ሆድ እንደሚሄድና ከዚያም ዐይነ ምድር ሆኖ ወደ ውጭ እንደሚጣል አታስተውሉምን? 18 ዳሩ ግን ከአፍ የሚወጣ ከልብ ይወጣል፡፡ እነዚህ ነገሮች ሰውን ያረክሳሉ፡፡ 19 ከልብ ክፉ ዐሳብ፣ ነፍስ መግደል፣ ምንዝርና፣ ዝሙት፣ ስርቆት፣ የሐሰት ምስክርነትና ስድብ ይወጣሉ፤ 20 ሰውን የሚያረክሱት እነዚህ ናቸው፡፡ ነገር ግን ባልታጠበ እጅ መብላት ሰውን አያረክስም፡፡" 21 ቀጥሎም ኢየሱስ ከዚያ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና ከተሞች አካባቢ ሄደ፡፡ 22 እነሆም፣ አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከዚያ አካባቢ ወጣችና ጮኽ ብላ እንዲህ አለች፣ ‹‹የዳዊት ልጅ፣ ጌታ ሆይ፣ ማረኝ፡፡ ልጄ በጋኔን ተይዛ በጣም እየተሠቃየች ነው፡፡›› 23 ኢየሱስ ግን አንድም ቃል አልመለሰላትም፡፡ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው፣ ‹‹ይህች ሴት ትጮኽብናለችና ሸኛት›› ብለው ለመኑት፡፡ 24 ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ፣ ‹‹እንደ በግ ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት ሰዎች ካልሆነ በቀር ወደ ማንም አልተላክሁም›› አለ፡፡ 25 ነገር ግን ሴቲቱ "ጌታ ሆይ፣ እርዳኝ" በማለት መጥታ በፊቱ ሰገደች፡፡ 26 ኢየሱስ መልሶ፣ "የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለቡችሎች መጣል ትክክል አይደለም" አለ፡፡ 27 ሴቲቱ፣ "አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ ከሚወድቀው የተወሰነውን ትርፍራፊ ይበላሉ" አለች፡፡ 28 ከዚያም ኢየሱስ መልሶ፣ "አንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው፤ ልክ እንደ ተመኘሽው ይሁንልሽ" አላት፡፡ ልጇም በዚያች ሰዓት ተፈወሰች፡፡ 29 ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ወደ ገሊላ ባሕር አቅራቢያ ሄደ፡፡ ከዚያም ወደ አንድ ኮረብታ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ፡፡ 30 ብዙ ሕዝብም ወደ እርሱ መጡ፤ አንካሶችን፣ ዐይነ ስውሮችን፣ ዲዳዎችንና ጕንድሾችን፣ እንዲሁም ሌሎች ታመው የነበሩ ብዙዎችን ይዘው መጡ፡፡ በኢየሱስ እግር አጠገብም አስቀመጧቸው፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡ 31 ስለዚህ ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ፣ ጕንድሾች ሲፈወሱ፣ አንካሶች ሲራመዱ፣ ዐይነ ስውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፡፡ የእስራኤልንም አምላክ አመሰገኑ፡፡ 32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ "ለሕዝቡ አዝንላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ከእኔ ጋር ሦስት ቀን ቈይተዋል፣ የሚበሉትም የላቸውም፡፡ በመንገድ ላይ ዝለው እንዳይወድቁ ሳይበሉ ዝም ብዬ አላሰናብታቸውም" አለ፡፡ 33 ደቀ መዛሙርቱ፣ "በዚህ በረሓ ይህን የሚያህል ብዙ ሕዝብ የሚያጠግብ እንጀራ ከየት እናገኛለን?" አሉት፡፡ 34 ኢየሱስ፣ "ስንት እንጀራ አላችሁ?" አላቸው፡፡ "ሰባት እንጀራና ጥቂት ትናንሽ ዐሣ አለ" አሉት፡፡ 35 ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን መሬት ላይ እንዲቀመጡ አዘዛቸው፡፡ 36 ኢየሱስ ሰባቱን እንጀራና ዐሣዎቹን ይዞ ካመሰገነ በኋላ እንጀራውን ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጧቸው፡፡ 37 ሕዝቡ ሁሉ በሉና ጠገቡ፡፡ ትርፍራፊውንም ሰበሰቡ፤ ትርፍራፊውም ሰባት ቅርጫት ሙሉ ነበር፡፡ 38 የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡ 39 ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን አሰናበተና በጀልባም ገብቶ መጌዶን ወደ ተባለ ክፍለ አገር ሄደ፡፡



Matthew 15:1

ማቴዎስ 15፡1-3

የሽማግሌዎችን ወግ ይተላለፋሉ "በትልልቅ የሃይማኖት መሪዎች የተሰጡትን ደንቦች አይጠብቁም" እጃቸውን አይጣጠቡም "በሕጉ መሠረት የተሰጠውን የእጅ መታጠብ ስርዓትን በመከተል እጃቸውን አይታጠቡም ( ተመልከት)

Matthew 15:4

ማቴዎስ 15፡4-6

ማንም "ዬትኛውም ሰው" ወይም "ማንም ቢሆን" አባቱን ሊያከብር የማይወድ አባቱን በመንከባከብ ለእርሱ ያለውን አክብሮት ለማሳየት የማይፈልግ ሰው ለወጋችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ቃል አፍርሳችሁታል ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ።”

Matthew 15:7

ማቴዎስ 15፡ 7-9

ኢሳያስ ስለ እናንተ ምን አለ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "ኢሳያስ በዚህ ትንቢት ላይ የተናገረው እውነት ነው” እንዲህ ሲል ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እግዚአብሔር የተናገረውን ስናገር" ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ኤቲ፡ “ይህ ሕዝብ ስለእኔ ትክክል የሆኑ ነገሮችን ይናገራል” ልቡ ግን ከእኔ ርቋል ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ይሁን እንጂ በእርግጥ አይወዱኝ” (en:ta:vol1:translate: ተመልከት) እንዲሁ በከንቱ ያመልኩኛል ለተርጓሚዎች ምክር፡ “አምልኮአቸው ለእኔ ምንም አይደለም” ወይም “እኔን ያመለኩ ያስመስላሉ” የሰው ስርዓት "ሰዎች በሰሩት ስርዓት"

Matthew 15:10

ማቴዎስ 15፡10-11

ሰሙ አስተዋሉም ኢየሱስ ከዚህ ቀጥሎ ላለው ዓረፍተ ነገር አጽኖት በመስጠት ተናግሯል

Matthew 15:12

ማቴዎስ 15፡12-14

ይህን ቃል የሰሙ ፈሪሳዊያን እንደ ተሰናከሉብህ አወቅህን? ለተሯሚዎች ምክር፡ “ይህ ዓረፍተ ነገር ፈሪሳዊያንን አበሳጭቷቸዋል?" ወይም "ይህ ዓረፍተ ነገር ፈሪሳዊያንን አሰናክለሏልን?" ( ተመልከት)

Matthew 15:15

ማቴዎስ 15፡15-17

ለእኛ "ለእኛ ለደቀ መዛሙርትህ" ያለፋል "ይወጣል" እዳሪ ሰዎች የሆድ እዳሪያቸውን የሚያስወግዱበት ሥፍራን በጨዋ ቋንቋ ለመግለጽ ነው፡፡

Matthew 15:18

ማቴዎስ 15፡18-20

ከአፍ የሚወጣ "አንድ ሰው የሚናገረው ቃል" ከልብ ይወጣል "ከሰውዬው እውነተኛ ስሜት እና ሀሳቦች ውጤት ናቸው” መግደል ንጹሕ ሰውን መግደል ስድብ "ሌላ ሰውን የሚያሰናክል ነገር ማነገር" ያልታጠበ እጅ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ያልታጠበ እጅ

Matthew 15:21

ማቴዎስ 15፡ 21-23

ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ሴትቱ ሀገሯን ትታ ወደ እስራኤል በመምጣት ኢየሱስን አገኘችው ከነናዊት ሴት ከነዓን የሚባል ሀገር አሁን የለም፡፡ “ከነዓን ተባለ ሀገር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች መካከል የሆነች አንዲት ሴት" ሴት ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል "ሴት ልጄን ጋኔን በጣም እያሰቃያት ነው” ( ተመልከት) ምንም ቃል አልመለሰላትም "ዝም አላት"

Matthew 15:24

ማቴዎስ 15፡ 24-26

ወደ እርሱ መጣች "ከነዓናዊቷ ሴት ወደ እርሱ መጣች" የልጆችን እንጀራ ...ለቡችሎች "በትክክለኛው መንገድ ለአይሁዶች የሆነውን ነገር . . . ለአሕዛብ" ( ተመልከት)

Matthew 15:27

ማቴዎስ 15፡27-28

ቡችሎች እንኳ ከጌቶቻቸው ማዕድ የተራረፈውን ይበላሉ አሕዛብ ከአይሁዳዊያን የተራረፈው መልካም ነገር ልያገኙ ይገባል፡፡ ( ተመልከት) ሴት ልጇ ተፈወሰች "ኢየሱስ ሴት ልጇን ፈወሰላት” ወይም "ኢየሱስ የሴት ልጇን ጤና መለሰላት” ( ተመልከት) በዚያን ጊዜ "በተመሳሳይ ሰዓት" ወይም "ወዲያው"

Matthew 15:29

ማቴዎስ 15፡ 29- 31

ሽባ፣ ዐይነ ስውር፣ ዲዳ እና መሄድ የማይችል "መራመድ የማይችሉ ሰዎች፣ ማየት የማይችሉ አንዳንዶች፣ መናገር የማይችሉ፣ እግራው እና እጃቸው የማይሰራ ሰዎች”፡፡ አንዳንድ ጥንታዊያን ቅጅዎች እነዚህን ቃላት በተለያየ ቅደም ተከተል አስቀምጠውታል፡፡ በኢየሱስ እግሪ ፊት አስቀመጡ "ሕዝቡ የታመመውን ሰው በኢየሱስ ፊት አስቀመጡ"

Matthew 15:32

ማቴዎስ 15፡32-35

ዝለው እንዳይወድቁ አማራጭ ትርጉሞች 1) “ራሳቸነውን እንዳይስቱ በመፍራት” ወይም 2) “ሊደክማቸው ይችላል ከሚል ስጋት” ( ተመልከት) ተቀመጡ ጠረጴሳ ባሌለበት ሁኔታ ሰዎች ምግብ ለመመገብ በባሕላችሁ የሚቀመጡበትን መንገድ የሚገልጽ ቃልን ተጠቀም፡፡

Matthew 15:36

ማቴዎስ 15፡36-39

ወሰደ "ኢየሱስ ወስዶ” ፡፡ ይህንን በ MAT 14:19 በተረጎምከው መሠረት ተርጉመው፡፡ ስጧቸው "ዳቦዎቹን እና ዓሳዎቹን ስጧቸው" ለቀሟአቸው "ደቀ መዛሙርቱ ለቀሙ" የተመገቡት "የበሉት ሰዎች" አከባቢ "የአንድ ሀገር አንዱ ክፍል" መጌዶል አንዳንድ ጊዜ “ማጌዳላ” ተብሎ ይጠራል ( ተመልከት)


Translation Questions

Matthew 15:4

ፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን ቃል በትውፊታቸው የሚሽሩት እንዴት እንደሆነ ለማሳየት ኢየሱስ የሰጠው ምሳሌ ምን ነበር?

ፈሪሳውያኑ “ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ” ነው በማለት ገንዘብ እየወሰዱ ልጆች ወላጆቻቸውን እንዳይረዱ ይከለክሏቸው ነበር። [15:4]

ፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን ቃል በትውፊታቸው የሚሽሩት እንዴት እንደሆነ ለማሳየት ኢየሱስ የሰጠው ምሳሌ ምን ነበር?

ፈሪሳውያኑ “ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ” ነው በማለት ገንዘብ እየወሰዱ ልጆች ወላጆቻቸውን እንዳይረዱ ይከለክሏቸው ነበር። [15:4]

ፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን ቃል በትውፊታቸው የሚሽሩት እንዴት እንደሆነ ለማሳየት ኢየሱስ የሰጠው ምሳሌ ምን ነበር?

ፈሪሳውያኑ “ለእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ” ነው በማለት ገንዘብ እየወሰዱ ልጆች ወላጆቻቸውን እንዳይረዱ ይከለክሏቸው ነበር። [15:4]

Matthew 15:7

ስለ ፈሪሳውያን ከንፈሮች እና ልቦች የኢሳይያስ ትንቢት ምን ይላል?

ፈሪሳውያን እግዚአብሔርን በከንፈራቸው ያከብራሉ፣ ልባቸው ግን ከእግዚአብሔር የራቀ እንደሆነ ኢሳይያስ ተነበየ። [15:7]

ስለ ፈሪሳውያን ከንፈሮች እና ልቦች የኢሳይያስ ትንቢት ምን ይላል?

ፈሪሳውያን እግዚአብሔርን በከንፈራቸው ያከብራሉ፣ ልባቸው ግን ከእግዚአብሔር የራቀ እንደሆነ ኢሳይያስ ተነበየ። [15:8]

የእግዚአብሔርን ቃል ከማስተማር ይልቅ ፈሪሳውያን አስተምህሮ አድርገው ያስተምሩት የነበረው ነገር ምን ነበር?

ፈሪሳውያን አስተምህሮ አድርገው ያስተምሩት የነበረው ነገር የሰዎችን ትእዛዛት ነበር። [15:9]

Matthew 15:10

ሰውን እንደማያረክሰው በመግለጽ ኢየሱስ ያስተማረው ምንን ነው?

ሰው የሚበላው ነገር እንደማያረክሰው ኢየሱስ ተናገረ። [15:11]

ሰውን እንደሚያረክሰው ኢየሱስ የተናገረው ምንን ነው?

ከሰው አፍ የሚወጣው ሰውን እንደሚያረክስ ኢየሱስ ተናገረ። [15:11]

Matthew 15:12

ከሰው አፍ የሚወጣው ሰውን እንደሚያረክስ ኢየሱስ ተናገረ። [15:11]

ኢየሱስ ፈሪሳውያንን እውራን መሪዎች አላቸው፣ ደግሞም ወደ ጉድጓድ እንደሚወድቁ ተናገረ። [15:14]

Matthew 15:18

ሰውን የሚያረክሱ ሆነው ከልብ የሚወጡ ነገሮች ምን ዓይነት ነገሮች ናቸው?

ከልብ ክፉ አሳብ፣ መግደል፣ ምንዝርና፣ ወሲባዊ ርኩሰት፣ ስርቆሽ፣ በሃሰት መመስከር እና ስድብ ይወጣሉ። [15:19]

Matthew 15:21

ከነዓናዊቷ ሴት ምሕረት እየለመነች ወደ እርሱ በጮኸች ጊዜ ኢየሱስ መጀመሪያ ላይ ምን አደረገ?

ኢየሱስ ቃል እንኳን አልመለሰላትም ነበር። [15:23]

Matthew 15:24

ከነዓናዊቷን ሴት ላለመርዳቱ የኢየሱስ ምክንያት ማብራሪያ ምን ነበር?

እርሱ የተላከው ከእስራኤል ለጠፉት በጎች ብቻ እንደሆነ ኢየሱስ አስረዳ። [15:24]

Matthew 15:27

ከነዓናዊቷ ሴት ራሷን ስታዋርድ፣ ኢየሱስ ለእርሷ ምን አለ፣ ምንስ አደረገላት?

ከነዓናዊቷ ሴት ራሷን ስታዋርድ፣ ኢየሱስ ለእርሷ ምን አለ፣ ምንስ አደረገላት?

Matthew 15:29

ከነዓናዊቷ ሴት ራሷን ስታዋርድ፣ ኢየሱስ ለእርሷ ምን አለ፣ ምንስ አደረገላት?

ኢየሱስ ድዳዎችን፣ ሽባዎችን፣ መራመድ የማይችሉትንና ማየት የማይችሉትን ፈወሳቸው። [15:30]

ገሊላ ውስጥ ብዙ ሆነው ወደ እርሱ ለመጡት ሕዝብ ኢየሱስ ምን አደረገ?

ኢየሱስ ድዳዎችን፣ ሽባዎችን፣ መራመድ የማይችሉትንና ማየት የማይችሉትን ፈወሳቸው። [15:31]

Matthew 15:32

ሕዝቡን ለመመገብ ደቀመዛሙርት የነበራቸው እንጀራ እና አሳ ምን ያክል ነበር?

ደቀመዛሙርት ሰባት እንጀራ እና ጥቂት ትንንሽ አሳዎች ነበሯቸው። [15:34]

Matthew 15:36

እንጀራዎቹን እና አሳዎቹን ኢየሱስ ምን አደረጋቸው?

እንጀራዎቹን እና አሳዎቹን ኢየሱስ ምን አደረጋቸው?

ሁሉ ከበሉ በኋላ ምን ያክል ምግብ ተረፈ?

ሁሉ ከበሉ በኋላ ሰባት ቅርጫት ሙሉ ተረፈ። [15:37]

ምን ያክል ሰዎች ከእንጀራውና አሳው በልተው ጠገቡ?

አራት ሺህ ወንዶች፣ እንዲሁም ሴቶችና ልጆች በልተው ጠገቡ። [15:38]


ምዕራፍ 16

1 ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም መጥተው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው በመጠየቅ ኢየሱስን ፈተኑት፡፡ 2 ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "በመሸ ጊዜ ሰማዩ ቀልቷልና ዝናብ አይኖርም ትላላችሁ 3 በነጋ ጊዜም፣ ‹ዛሬ ሰማዩ ስለ ጠቈረ ይዘንባል› ትላላችሁ፤ የዘመኑን ምልክት ግን መለየት አትችሉም፡፡ 4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም፡፡" ከዚያም ኢየሱስ ትቶአቸው ሄደ፡፡ 5 ደቀ መዛሙርቱ ወደ ማዶ ተሻገሩ፤ እንጀራ መያዝን ግን ረሱ፡፡ 6 ኢየሱስ፣ "ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም" አላቸው፡፡ 7 ደቀ መዛሙርቱ፣ "እንጀራ ስላልያዝን ነው" ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፡፡ 8 ኢየሱስ ይህን ዐውቆ፣ "እናንተ እምነተ ጎደሎዎች፣ እንጀራ ስላልያዝን ነው ብላችሁ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ?" 9 ዐምስት እንጀራ ለዐምስቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንደ ሰበሰባችሁ አሁንም አታስተውሉም ወይም አታስታውሱም? 10 ወይም ደግሞ ሰባቱ እንጀራ ለአራቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንዳነሣችሁስ አታስታውሱምን? 11 እኔ የነገርኋችሁ ስለ እንጀራ እንዳልነበረ እንዴት ነው የማታስተውሉት? ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያ እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም፡፡" 12 ከዚያም እርሱ ሲነግራቸው የነበረው ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንዲጠበቁ እንጂ፣ ስለ እንጀራ እርሾ እንዳልነበረ ተረዱ፡፡ 13 ኢየሱስም ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ክልል በመጣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፣ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ነው ይላሉ?" በማለት ጠየቃቸው፡፡ 14 እነርሱ፣ እንዲህ አሉ፤ "አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ የቀሩትም ኤርምያስ፣ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ፡፡" 15 "እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?" አላቸው፡፡ 16 ስምዖን ጴጥሮስ፣ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት መልስ ሰጠ፡፡ 17 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለው፣ "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ አንተ የተባረክህ ነህ፤ ይህን የገለጠልህ የሰማዩ አባቴ ነው እንጂ፣ ሥጋና ደም አይደለም፡፡ 18 ደግሞም አንተ ጴጥሮስ ነህም እላለሁ፤ በዚህም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም፡፡ 19 እኔ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፡፡ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈታውም ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡›› 20 ከዚያም ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ለማንም እንዳይናገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፡፡ 21 ከዚያን ጊዜ አንሥቶ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ፣ በሽማግሌዎችና በካህናት አለቆች፣ በፈሪሳውያንና በሕግ መምህራንም እጅ ብዙ መከራ መቀበልና መገደል፣ በሦስተኛውም ቀን መነሣት እንዳለበት ለደቀ መዛሙርቱ ይነግራቸው ጀመር፡፡ 22 ከዚያም ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ገለል አድርጎ፣ "ጌታ ሆይ፣ ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ይህም ከቶ አይሁንብህ" በማለት ገሠጸው፡፡ 23 ኢየሱስ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን፣ "ከፊቴ ዞር በል፣ ሰይጣን! ስለ ሰው እንጂ ስለ እግዚአብሔር ነገር ደንታ የለህምና አንተ ለእኔ እንቅፋት ነህ" አለው፡፡ 24 ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር፣ ራሱን መካድ፣ የራሱን መስቀል መሸከምና እኔን መከተል አለበት፡፡ 25 ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣዋል፤ ስለ እኔ ሕይወቱን የሚያጣ ግን ያገኘዋል፡፡ 26 ሰው ሙሉውን ዓለም የራሱ ቢያደርግ ሕይወቱን ግን ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰው በሕይወቱ ፈንታ ምን መስጠት ይችላል? 27 የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ከመላእክቱ ጋር ይመጣልና፡፡ ከዚያም ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፡፡ 28 እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆማችሁት መካከል የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ፡፡"



Matthew 16:1

ማቴዎስ 16፡ 1-2

ሰማይ . . . ሰማይ የአይሁድ መሪዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትን ይሹ ነበር ይሁን እንጂ ኢየሱስ ማየት ወደሚችሉት ሰማይ ይመለከቱ ዘንድ ነገራቸው፡፡ አንባቢዎቹ የትርጉም ልዩነቱን መረዳት የሚችሉ ከሆነ ብቻ ለእግዚአብሔር ማደሪያም እንዲሁም ለሰማይ ከተቻለ አንድ ቃል ተጠቀም፡፡ ( ተመልከት) በመሸም ጊዜ ፀሐጥ በጠለቀች ጊዜ ጥሩ የአየር ሁኔታ ግልጽ እና ጥርት ያለ ሰማይ ነው ሰማዩ ቀልቷል ሰማዩ ብርሃማ እና ከፀሐይ መትለቅ ጋር ተያይዞ ቀላልቷል

Matthew 16:3

ማቴዎስ 16፡3-4

የአየር ጸባዩ ጥሩ አይደለም "ዳመናማ እና ጭጋጋማ ነው" ጨልሟል "ጨለማ እና የሚያስፈራ ነው" ምንም ዓይነት ምልክት አይሰጣችሁም ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ለእናነት ምንም ምልክት እግዚአብሔር አይሰጣችሁም (en:ta:vol2:translate: እና ተመልከት)

Matthew 16:5

ማቴዎስ 16፡5-8

እርሾ ክፉ ሀሳቦች እና ስህተት ትምህርት ( ተመልከት) ምክንያት "መከራከር" ወይም “መጣላት"

Matthew 16:9

ማቴዎስ 16፡9-10

ለአምስቱ ሺህ አምስቱ እንጀራ፥ ስንት መሶብም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን? ወይስ ለአራቱ ሺህ ሰባቱ እንጀራ፥ ስንት ቅርጫትም እንዳነሣችሁ ትዝ አይላችሁምን? ኢየሱስ እየገሰጻቸው ነው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “በአምስት ዳቦ 5000 ሰዎች የተመገቡበት እና ምን ያህል ቅርጫት እንደሰበሰባችሁ መረዳት እና ማስታወስ ነበረባችሁ! ከዚህ በተጨማሪ በ7 ዳቦዎችን 4000 ሰዎች ስትመግቡ ምን ያህል ሰበሰባችሁ! ( and ተመልከት)

Matthew 16:11

ማቴዎስ 16፡11-12

ስለ እንጀራ እንዳልተናገርኋችሁ እንዴት አታስተውሉምን? "በእርግጥ ስለ እንጀራ እያወራሁ እንዳልሆነ መረዳት ነበረባችሁ፡፡” (UDB) ( ተመልከት) እርሾ ክፉ ሀሳቦች እና የተሳሳቱ ትምህርቶች ( ተመልከት) እነርሱ . . . እነርሱ “ደቀ መዛሙርቱ”

Matthew 16:13

ማቴዎስ 16፡13-16

ነገር ግን እናንተ እኔ ማን እንደሆኑ ትለላላችሁ? "እናንተን ግል ልጠይቃች፡ እኔ ማን እንደሆኑን ትላላችሁ?"

Matthew 16:17

ማቴዎስ 16፡17-18

የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ " (UDB) ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህም "ይህንን ዬትኛው የሰው ልጅ አልገለጠልህም” ( ተመልከት)፡፡ “አንተ ክርስቶስ ፣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” የሚለው የጴጥሮስ ንግግር ወደ ጴጥሮስ የመጣው በማንም ሳይሆን በእግዚአብሔር በራሱ ነው፡ አባት ይህ በኢየሱስ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ግንኙነት በሚገባ የሚገልጽ በጣም ጠቃሚ የሆነ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) የገሃነም ደጆች አይችሏትም አማራጭ ትርጉሞች: 1) "የሞት ኃይል ልቋቋማት አይችልም " ወይም 2) የጦር ሠራዊት አንድን ከተማ ሰብሮ እንደሚገባው ሁሉ የሞትን ኃይል ይሠባብራል፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 16:19

ማቴዎስ 16፡19-20

የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ አገልጋይ ሰዎች ወደቤት ስገቡ ተቀበሎ እንደሚያገልግል ሁሉ ሰዎች የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆን የሚችሉበትን መንገድ የመክፈት ክህሎት ( ተመልከት) በምድር ያሠራችሁት . . . በሰማይ የተፈራ ይሆናል በሰማይ እንደሚሆነው ሁሉ ለሰዎች ይቅርታን መስጠት ወይም በእነርሱ ላይ መፍረድ ( ተመልከት)

Matthew 16:21

ማቴዎስ 16፡21-23

ከዚያ ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ለሌላ ለማንም እንዳይናገሩ ካዘዛቸው በኋላ እግዚአብሔር ለእርሱ ያለው እቅዱን ያካፍላቸው ጀመረ፡፡ anded his disciples not to tell anyone that he was the Christ, he began sharing God's plan for himself. እንደሚሞት ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እንደሚገድሉት” ( ተመልከት) በሦስተኛው ቀን በሕይወት እንደሚነሳ "በሦስተኛው ቀን እግዚአብሔር እንደገና ሕያው እንደሚያደርገው"

Matthew 16:24

ማቴዎስ 16፡24-26

ተከተለኝ "ደቀ መዝሙሬ ሁን" ራስህን ካድ "በራስህ ምኞች አትወሰድ" ወይም "የራስህን መሻት ተው" መስቀሉን ተሸከምና ተከተለኝ "መስቀሉን አንሳ፣ ተሸከም እና ከእኔ በኋላ ተከተል”፣ መከራን ለመቀበል እና ለክርስቶስ ለመሞት ፈቃደኛ ሁን ( ተመልከት) የሚወድ ማንም ቢኖር "የሚፈልግ ማንም ቢኖር" ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ "በዓለም ያለውን ሁሉ ቢያተርፍ" ነፍሱን ግን ቢያጎድል "እርሱን ግን ቢጠፋ”

Matthew 16:27

ማቴዎስ 16፡ 27-28

የሰው ልጅ . . . አባቱ ኢየሱስ እንደ “ሰው ልጅነቱ” እና “የእርሱ” ልጅ መሆኑን ስገልጽ በሥላሴ ውስጥ እንዳለ ሦስተኛ አካል ያሳያል ፡፡ ለተሯሚዎች ምክር፡ "እኔ፣ የሰው ልጅ . . . አባቴ” ( ተመልከት) አባቱ ይህ በኢየሱስ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ግንኙነት በሚገባ የሚገልጽ በጣም ጠቃሚ የሆነ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት) የሰው ልጅ በመንግስቱ እስኪመጣ ድረስ ሞትን አይቀምሱም "ከመሞታቸው በፊት የሰው ልጅ በመንግስቱ ስመጣ ያዩታል” ሞትን አይቀምሱም "ሞትን አያዩም" ወይም “አይሞቱም" የሰው ልጅ በመንግስቱ ሲመጣ ኢየሱስ ራሱን እንደ ሥላሴ ሦተኛ አካል እየጠራ ነው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “በመንግስቴ ሲመጣ እስኪያዩኝ ድረስ” ( ተመልከት)


Translation Questions

Matthew 16:1

ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን እንደ ፈተና አድርገው ከኢየሱስ ማየት የፈለጉት ምን ነበር?

ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ኢየሱስ ከሰማይ የሚያሳያቸውን ምልክት ማየት ፈለጉ። [16:1]

Matthew 16:3

ኢየሱስ ለፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ምን እንደሚሰጣቸው ተናገረ?

ኢየሱስ ለፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን የዮናስን ምልክት እንደሚሰጣቸው ተናገረ። [16:4]

Matthew 16:5

ደቀመዛሙርቱ ከምን እንዲጠበቊ ኢየሱስ ነገራቸው?

ኢየሱስ ከፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን እርሾ እንዲጠበቁ ነገራቸው። [16:6]

Matthew 16:11

ለደቀመዛሙርቱ እንዲጠነቀቁ ሲነግራቸው ኢየሱስ በእርግጥ እያወራ የነበረው ስለ ምን ነበር?

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እየነገራቸው የነበረው ከፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን አስተምህሮ እንዲጠበቁ ነበር። [16:12]

Matthew 16:13

ወደ ቂሳሪያ ፊሊጲስዩስ በመጡ ጊዜ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ የጠየቃቸው ጥያቄ ምን የሚል ነበር?

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ፣ “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ሲል ጠየቃቸው [16:13]

አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስ ማን እንደነበረ ነበር ያስቡ የነበሩት?

አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስ ማለት መጥምቊ ዮሐንስ፣ ወይም ኤልያስ፣ ወይም ኤርምያስ፣ ወይም ከነብያት አንዱ እንደሆነ አስበው ነበር። [16:14]

ጴጥሮስ ለኢየሱስ ጥያቄ የሰጠው ምላሽ ምን ነበር?

ጴጥሮስ ሲመልስ “አንተ ክርስቶስ፣ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” አለ። [16:16]

Matthew 16:17

ጴጥሮስ ለኢየሱስ ጥያቄ መልሱን ያወቀው እንዴት ነበር?

ጴጥሮስ የኢየሱስን ጥያቄ መልስ ያወቀው አብ ስለገለጠለት ነበር። [16:17]

Matthew 16:19

ኢየሱስ በምድር ላይ ለጴጥሮስ የሰጠው ሥልጣን ምን ነበር?

ኢየሱስ ለጴጥሮስ የሰጠው የመንግሥተ ሰማያትን ቊልፍ ሲሆን፣ ያም በምድር ያሉትን እንዲያስር ወይም እንዲፈታ እና በሰማይ ያሉትን እንዲያስር ወይም እንዲፈታ ነው። [16:19]

Matthew 16:21

በዚህ ጊዜ፣ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ በግልጽ የነገራቸው ምን ነበር?

ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ እንደሚያስፈልገው፣ በብዙ መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚገደል እና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነበር። [16:21]

ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ እንደሚያስፈልገው፣ በብዙ መከራ እንደሚቀበል፣ እንደሚገደል እና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነበር። [16:21]

ኢየሱስ ለጴጥሮስ “ዞር በል፣ አንተ ሰይጣን!” አለው [16:23]

Matthew 16:24

ኢየሱስን መከተል የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ሁሉ ምን ማድረግ ይኖርበታል?

ኢየሱስን መከተል የሚፈልግ ሰው ሁሉ ራሱን መካድና መስቀሉን መሸከም ይኖርበታል። [16:24]

ለሰው እንደማይጠቅመው ኢየሱስ የተናገረው ምንድነው?

ሰው ዓለሙን ሁሉ አትርፎ፣ ነፍሱን ቢያጣ ምንም እንደማይጠቅመው ኢየሱስ ተናገረ። [16:26]

Matthew 16:27

የሰው ልጅ የሚመጣው እንዴት ነው ብሎ ኢየሱስ ተናገረ?

የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር እንደሚመጣ ኢየሱስ ተናገረ። [16:27]

የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ ለእያንዳንዱ ሰው የሚከፍለው እንዴት ነው?

የሰው ልጅ በሚመጣ ጊዜ ለእያንዳንዱ ሰው እንደየ ሥራው ይከፍላል። [16:27]

የሰው ልጅ በመንግሥቱ በሚመጣበት ጊዜ ያያሉ በማለት ኢየሱስ የተናገረው እነማንን ነው?

ከእርሱ ጋር እዚያ ከቆሙት አንዳንዶቹ የሰው ልጅ በመንግሥቱ በሚመጣ ጊዜ እንደሚያዩት ኢየሱስ ተናገረ። [16:28]


ምዕራፍ 17

1 ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙን ይዞ ብቻቸውን ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው፡፡ 2 በፊታቸውም መልኩ ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን አንጸባረቀ፡፡ 3 እነሆ፣ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ 4 ጴጥሮስ መልሶ ኢየሱስን፣ "ጌታ ሆይ፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትፈልግ እኔ እዚህ ሦስት ዳሶችን፡- አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እሠራለሁ" አለው፡፡ 5 እርሱ ገና እየተናገረ እያለ፣ እነሆ፣ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም፣ "በእርሱ እጅግ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ ነበረ፡፡ 6 ደቀ መዛሙርቱ ድምፁን በሰሙ ጊዜ ፈሩ፣ በግንባራቸውም ወደቁ፡፡ 7 ከዚያም ኢየሱስ መጥቶ ዳሰሳቸውና፣ ‹‹ተነሡ አትፍሩ›› አላቸው፡፡ 8 ከዚያም እነርሱ ቀና ብለው ተመለከቱ፣ ነገር ግን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡ 9 ከተራራ ሲወርዱም ኢየሱስ፣ "የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ይህን ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ" ብሎ አዘዛቸው፡፡ 10 ደቀ መዛሙርቱ፣ "እንግዲያው የአይሁድ ሕግ መምህራን መጀመሪያ ኤልያስ መምጣት አለበት ለምን ይላሉ?" በማለት ጠየቁት፡፡ 11 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፤ "ኤልያስ በርግጥ ይመጣል፣ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል፡፡ 12 ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ኤልያስ አስቀድሞ መጥቷል፤ ነገር ግን አላወቁትም፡፡ በዚህ ፈንታ የፈለጉትን ነገር ሁሉ አደረጉበት፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የሰው ልጅ በእነርሱ እጅ መከራ ይቀበላል፡፡›› 13 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ የተናገራቸው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነበረ ተረዱ፡፡ 14 ወደ ሕዝቡ በመጡ ጊዜ አንድ ሰው መጥቶ በፊቱ ተንበረከከ፤ እንዲህም አለው፤ 15 "ጌታ ሆይ፣ ልጄን ማረው፣ የሚጥል በሽታ ይዞት በኀይል ይሠቃያል፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ወይም በውሃ ውስጥ ይጥለዋልና፡፡ 16 ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት፤ ነገር ግን እነርሱ ሊፈውሱት አልቻሉም፡፡› 17 ኢየሱስ መልሶ፣ "የማታምኑና ምግባረ ብልሹ ትውልድ፣ እስከ መቼ ድረስ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ? እስከ መቼስ እናንተን መታገሥ አለብኝ? እስቲ ወደ እኔ አምጡት" አለ፡፡ 18 ኢየሱስ ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፤ ልጁም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ፡፡ 19 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "እኛ ልናወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?" አሉ፡፡ 20 ኢየሱስ፣ ‹‹በእምነታችሁ ማነስ ምክንያት፤ እውነት እላችኋለሁና፣ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት እንኳ ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ማዶ ሂድ ብትሉት ይሄዳል፡፡ ማድረግ የሚሳናችሁ ምንም ነገር አይኖርም፡፡ 21[1]22 በገሊላ እያሉ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ "የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፤ 23 እነርሱም ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል" አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በጣም ዐዘኑ፡፡ 24 ወደ ቅፍርናሆም በመጡ ጊዜ ግማሽ ሰቅል ቀረጥ የሰበሰቡ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ መጥተው፣ "መምህራችሁ ግማሽ ሰቅሉን ቀረጥ አይከፍልምን?" አሉ፡፡ 25 እርሱ፣ "አዎ" አለ፡፡ ጴጥሮስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ግን ኢየሱስ መጀመሪያ እርሱን ተናገረው፤ "ስምዖን ሆይ፣ ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥ ወይም ግብር የሚሰበስቡት ከማን ነው? ከዜጎቻቸው ወይስ ከውጭ አገር ሰዎች?" አለው፡፡ 26 ጴጥሮስ፣ "ከውጭ አገር ሰዎች" ባለ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "እንግዲያስ ዜጎቹ ከክፍያ ነጻ ናቸው፡፡ 27 ነገር ግን ቀረጥ ሰብሳቢዎቹን ኃጢአት እንዲሠሩ እንዳናደርጋቸው ወደ ባሕር ሄደህ መንጠቆ ጣል፤ በመጀመሪያ የምታጠምደውን ዐሣ አፍ ስትከፍት አንድ ሰቅል ታገኛለህ፤ ያንን ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ክፈል፡፡››


Footnotes


17:21 [1]አንዳንድ የጥንት ቅጂዎች ቊጥር 21ን ያስቀሩታል፡፡ ነገር ግን የዚህ ዓይነቱ ጋኔን በጾምና በጸሎት ካልሆነ በቀር አይወጣም፡፡


Matthew 17:1

ማቴዎስ 17፡ 1-2

ማቴዎስ 17፡ 1-2

ጴጥሮስ እና ያዕቆብ እንዲሁም ወንድሙ ዮሐንስ "ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና የያዕቆብ ወንድም ዮሐንስ” ተለወጠ "እግዚአብሔር የኢየሱስ መልክ ሙሉ ለሙሉ ለወጠው” ወይም ( ተመልከት) ልብሶች "ልብስ" እንደ ብርሃን ያበሩ ነበር "እንደ ብርሃን ያንጸባርቁ ነበር" ( ተመልከት)

Matthew 17:3

X

ማቴዎስ 17፡3-4

እነሆ ይህ ቃል ሰዎች ከዚህ በኋላ ለሚነገረው ነገር አጽኖት እንዲሰጡ የሚጨመር ቃል ነው፡፡ ለእነረሱ ከኢየሱስ ጋር ለነበሩት ደቀ መዛሙርት እንዲህ ሲል መለሰላቸው "አላቸው” ጴጥሮስ ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ እየሰጠ አይደለም፡፡ በዚህ መሆን ለእኛ ይሻላል አማራጭ ትርጉሞች፡ 1) "እኛ ደቀ መዛሙርት በዚህ ከአንተ፣ ከሙሴ እና ከኤልያስ ጋር መሆናችን መልካም ነው” ወይም “አንተ፣ ሙሴ፣ ኤልያስ እና እኛ ደቀ መዛሙርትህ በአንድነት መሆናችን መልካም ነው፡፡” ( ተመልከት) መጠለያዎች አማራጭ ትርጉሞች 1) ሰዎች ለአምልኮ የሚመጧቸው ሥፍራዎች ወይም 2) ሰዎች በጊዜያዊነት ለመተኛ የሚዘጋጇቸው

Matthew 17:5

ማቴዎስ 17፡ 5-8

እነሆ ይህ ቃል ሰዎች ከዚህ በኋላ ለሚነገረው ነገር አጽኖት እንዲሰጡ የሚጨመር ቃል ነው፡፡ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው "ደቀ መዛሙርተ በግንባራቸው በመሬት ላይ ተደፍተው”

Matthew 17:9

ማቴዎስ 17፡9-10

እነርሱ . . . ሳለ "ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ . . . ሰለ"

Matthew 17:11

ማቴዎስ 17፡11-13

ሁሉን ነገር ያድሳል "ሁሉን ነገር በሥርዓት ያደርጋል" እነርሱ . . . እነርሱ . . . እነርሱ አማራጭ ትርጉሞች: 1) የአይሁድ መሪች ወይም 2) ሁሉም የአይሁድ ሕዝቦች

Matthew 17:14

X

የሚጥል በሽታ ያለበት ራሱን ስቶ የሚያደርገው ነገር የማያውቅ ሰው

Matthew 17:17

ማቴዎስ 17፡17-18

ከእናንተ ጋር እስከ መቼ እቆያለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ኢየሱስ በሕዝቡ ደስተኛ አልነበረም፡፡ የተርጓሚዎች ምክር፡ ከእናንተ ጋር መሆን ደከመኝ! አለማመናችሁ እና ክፋታችሁ ሰለቸኝ!” ( ,ተመልከት)

Matthew 17:19

ማቴዎስ 17፡19-21

እኛ ተናጋሪው እንጂ ሰሚዎቹ አይደሉም ( ተመልከት) እኛ ማውጣት ያቃተን ለምንድ ነው "ጋኔኑ እንዲወጣ ማድረግ ያቃጠን ለምንድ ነው” ማድረግ የማትችሉት ነገር የለለምNothing will be impossible for you to do "ምንም ነገር ማድረግ ትችላላችሁ” ( ተመልከት)

Matthew 17:22

ማቴዎስ 17፡22-23

በዚያም ቆዩ "ደቀ መዛሙር እና ኢየሱስ በዚያ ቆዩ" የሰው ልጅ አሳልፎ ይሰጣል ለተርጓሚዎች ምክር፡ "የሆኑ ሰዎች የሰው ልጅን አሳልፈው ይሰጡታል” ( ተመልከት) ይገድሉታ "ባለስልጣናት የሰወ ልጅን ይገድሉታል” ከሞት ይነሣል "እግዚብሔር ከሞት ያሥነሣዋል” ወይም “እንደገና ወደ ህይወት ይመላሳለር” ( ተመልትከት)

Matthew 17:24

ማቴዎስ 17፡24-25

በ . . . ጊዜ እነርሱ ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ በ . . ጊዜ

Matthew 17:26

ማቴዎስ 17፡26-27

ሥር ያሉ በአጋዘዙ ውስጥ ወይም በንጉሥ ሥር ያሉ አፉ "የዓሣ አፍ" ውሰዱ "አስታተር ውሰድና"


Translation Questions

Matthew 17:1

ከፍ ወዳለው ተራራ ከኢየሱስ ጋር የወጡት እነማን ነበሩ?

ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ከፍ ወዳለው ተራራ ወጡ። [17:1]

በተራራው ላይ የኢየሱስ ገጽታ ምን ሆነ?

ፊቱ እንደ ፀሐይ እስኪያበራ፣ ልብሱም እንደ ብርሃን እስኪሆን ድረስ ኢየሱስ ተለወጠ። [17:2]

Matthew 17:3

ተገልጠው ኢየሱስን ሲያነጋግሩ የነበሩት እነማን ነበሩ?

ሙሴ እና ኤልያስ ተገልጠው ከኢየሱስ ጋር ሲነጋገሩ ነበር። [17:3]

ጴጥሮስ ምን ለማድረግ አሳብ አቀረበ?

ጴጥሮስ ሦስት ድንኳኖችን ለሦስት ሰዎች ለመሥራት ሃሳብ አቀረበ። [17:4]

Matthew 17:5

ከደመና የወጣው ድምፅ ምን አለ?

ከደመና የወጣው ድምፅ “የምወድደው ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት” አለ። [17:5]

Matthew 17:9

ከተራራ በሚወርዱበት ጊዜ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ምን ትእዛዝ ሰጣቸው?

ያዩትን የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ለማንም እንዳይናገሩ ኢየሱስ አዘዛቸው። [17:9]

Matthew 17:11

ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ እንደሚገባው ጸሐፍት ስላስተማሩት ነገር ኢየሱስ ምን አለ?

ኤልያስ በእርግጥም እንደመጣና ሁሉን ነገር እንደ ቀድሞው እንዳደረገ ኢየሱስ ተናገረ። [17:11]

አስቀድሞ የመጣው ኤልያስ እንደሆነ ኢየሱስ የተናገረው ማንን ነው፣ ደግሞስ ምን አደረጉበት?

መጥምቊ ዮሐንስ አስቀድሞ የመጣው ኤልያስ እንደሆነ እና፣ በእርሱ ላይ ማድረግ የፈለጉትን ሁሉ እንዳደረጉበት ኢየሱስ ተናገረ። [17:12]

አስቀድሞ የመጣው ኤልያስ እንደሆነ ኢየሱስ የተናገረው ማንን ነው፣ ደግሞስ ምን አደረጉበት?

መጥምቊ ዮሐንስ አስቀድሞ የመጣው ኤልያስ እንደሆነ እና፣ በእርሱ ላይ ማድረግ የፈለጉትን ሁሉ እንዳደረጉበት ኢየሱስ ተናገረ። [17:13]

Matthew 17:14

ደቀመዛሙርቱ የሚጥል በሽታ ያለው ልጅ ላይ ማድረግ ያልቻሉት ነገር ምንድነው?

ደቀመዛሙርቱ የሚጥል በሽታ ያለበትን ልጅ ሊፈውሱት አልቻሉም ነበር። [17:14]

ደቀመዛሙርቱ የሚጥል በሽታ ያለው ልጅ ላይ ማድረግ ያልቻሉት ነገር ምንድነው?

ደቀመዛሙርቱ የሚጥል በሽታ ያለበትን ልጅ ሊፈውሱት አልቻሉም ነበር። [17:15]

ደቀመዛሙርቱ የሚጥል በሽታ ያለው ልጅ ላይ ማድረግ ያልቻሉት ነገር ምንድነው?

ደቀመዛሙርቱ የሚጥል በሽታ ያለበትን ልጅ ሊፈውሱት አልቻሉም ነበር። [17:16]

Matthew 17:17

የሚጥል በሽታ ላለበት ልጅ ኢየሱስ ምን አደረገ?

ኢየሱስ አጋንንቱን ገሠጸው፣ ልጁም ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ። [17:18]

Matthew 17:19

ደቀመዛሙርት የሚጥል በሽታ ያለበትን ልጅ መፈወስ ያልቻሉት ለምን ነበር?

ከትንሹ እምነታቸው የተነሣ የሚጥል በሽታ ያለበትን ልጅ መፈወስ እንዳልቻሉ ኢየሱስ ተናገረ። [17:20]

Matthew 17:22

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ በጣም እንዲያዝኑ ያደረጋቸውን ምን ነገር ነገራቸው?

ኢየሱስ በሚገድሉት ሰዎች እጅ ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ በሦስተኛውም ቀን እንደሚነሣ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው። [17:22]

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ በጣም እንዲያዝኑ ያደረጋቸውን ምን ነገር ነገራቸው?

ኢየሱስ በሚገድሉት ሰዎች እጅ ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ በሦስተኛውም ቀን እንደሚነሣ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው። [17:23]

Matthew 17:26

ጴጥሮስ እና ኢየሱስ የግማሽ ስቅል ግብር የከፈሉት እንዴት ነበር?

ጴጥሮስ ወደ ባህር እንዲሄድ እና መንጠቆውን በመጣል መጀመሪያ የሚይዘውን አሳ አውጥቶ ለግብር የሚሆነውን ስቅል ከአፉ እንዲያወጣ ነገረው። [17:27]


ምዕራፍ 18

1 በዚያው ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው?" አሉ 2 ኢየሱስ አንድ ትንሽ ልጅ ጠርቶ በመካከላቸው አቆመው፤ 3 እንዲህም አለ፡- "እውነት እላችኋለሁ፤ ንስሐ ካልገባችሁና እንደ ልጆች ካልሆናችሁ በምንም መንገድ ወደ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም፡፡ 4 ስለዚህ እንደዚህ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሰው ሁሉ፣ እንዲሁ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ይበልጣል፡፡ 5 እንደዚህ ያለውን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፡፡ 6 ነገር ግን በእኔ ከሚያምነው ከእነዚህ ልጆች አንዱን ኀጢአት እንዲሠራ የሚያደርግ ማንም፣ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቁ ባሕር ቢሰጥም ይሻለዋል፡፡ 7 የመሰናክል ምክንያት በመሆኗ ለዓለም ወዮላት! መሰናክል መምጣቱ ግድ ነው፤ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣ ሰው ወዮለት! 8 እጅህ ወይም እግርህ ቢያሰናክልህ፣ ቈርጠህ ከአንተ ጣለው፡፡ ሁለት እጆች ወይም እግሮች ኖረውህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል የአካል ጉዳተኛ ወይም አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃል፡፡ 9 ዐይንህ እንድትሰናከል ቢያደርግህ፣ አውጥተህ ከአንተ ጣለው፡፡ ሁለት ዐይኖች ኖረውህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻላል፡፡ 10 ከእነዚህ ከታናናሾች ማንኛውንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክታቸው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ሁልጊዜ ያያሉና፡፡ 11 (2) ብዙ ምንጮች፣ አንዳንድ የጥንት የሆኑ ቊ. 11ን ያስገባሉ፡፡ 11[1]12 ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት፣ ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፣ ዘጠና ዘጠኙን በኮረብታው ጥግ ትቶ የጠፋውን ሊፈልግ አይሄድምን? 13 በሚያገኘውም ጊዜ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል፡፡ 14 በተመሳሳይ መንገድ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ የሰማዩ አባታችሁ ፈቃድ አይደለም፡፡ 15 ወንድምህ ቢበድልህ፣ ሂድና አንተና እርሱ ብቻ ሆናችሁም ጥፋቱን አሳየው፡፡ ቢሰማህ፣ ወንድምህን የራስህ ታደርገዋለህ፡፡ 16 ባይሰማህ ግን፣ ቃል ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ይጸናልና፣ ከአንተ ጋር አንድ ወይም ሁለት ተጨማሪ ወንድሞችን ይዘህ ሂድ፡፡ 17 እነርሱንም አልሰማም ቢል፣ ጉዳዩን ለቤተ ክርስቲያን ንገር፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ደግሞ አልሰማም ቢል፣ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቊጠረው፡፡ 18 እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር የምታስሩት ነገር ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱትም ነገር ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡ 19 በተጨማሪም እላችኋለሁ፣ ከእናንተ ሁለቱ በምድር ስለሚለምኑት ስለ ማንኛውም ነገር ቢስማሙ፣ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላቸዋል፡፡ 20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት ቦታ እዚያ በመካከላቸው እገኛለሁና፡፡ 21 ከዚያም ጴጥሮስ መጥቶ ኢየሱስን፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?›› አለው፡፡ 22 ኢየሱስም፣ ‹‹ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ፣ ሰባት ጊዜ አልልህም›› አለው፡፡ 23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ከአገልጋዮቹ ጋር ሒሳብ ሊተሳሰብ የፈለገ ንጉሥን ትመስላለች፡፡ 24 መተሳሰቡን እንደ ጀመረ፣ የዐሥር ሺህ መክሊት ዕዳ ያለበትን አገልጋይ ወደ እርሱ አመጡ፡፡ 25 ነገር ግን የሚከፍልበት መንገድ ስላልነበረው፣ ጌታው ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ያለውም ሁሉ ተሸጦ ክፍያው እንዲፈጸም አዘዘው፡፡ 26 ስለዚህ አገልጋዩ ወድቆ በፊቱ ተንበረከከ እንዲህም አለ፤ ‹ጌታዬ ሆይ፣ ታገሠኝ፣ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፡፡› 27 ስለዚህ የዚያ አገልጋይ ጌታ ስለ ራራለት፣ ተወው፤ ዕዳውንም ሠረዘለት፡፡ 28 ነገር ግን ያ አገልጋይ ወጥቶ አብረውት ከሚሠሩት አገልጋዮች መቶ ዲናር ያበደረውን አንዱን አገልጋይ አግኝቶ ያዘው፤ ጕሮሮውን አነቀውና፣ ‹‹ያለብህን ዕዳ ክፈለኝ›› አለው፡፡ 29 ነገር ግን የሥራ ባልደረባው፣ ‹‹ታገሠኝ፣ እከፍልሃለሁ›› በማለት ወድቆ ለመነው፡፡ 30 የመጀመሪያው አገልጋይ ግን አሻፈረኝ አለ፤ በዚህ ፈንታ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍለው ድረስ በእስር ቤት ጣለው፡፡ 31 የሥራ ጓደኞቹ የሆኑት አገልጋዮች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ፣ በጣም ተበሳጩ፤ መጥተውም ለጌታቸው የሆነውን ሁሉ ነገሩት፡፡ 32 ከዚያም የዚያ አገልጋይ ጌታ ጠራው፣ እንዲህም አለው፤ 'አንተ ክፉ አገልጋይ፣ ስለ ለመንኸኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውሁልህ፡፡ 33 እኔ አንተን እንደማርሁህ፣ የሥራ ባልደረባህ የሆነውን አገልጋይ ልትምረው አይገባህም ነበርን?' 34 ጌታው ተቈጥቶ ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ለሚያሠቃዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡ 35 ስለዚህም ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልብ ይቅር ባይል የሰማዩ አባቴ እንዲሁ ያደርግበታል፡፡"


Footnotes


18:11 [1]አንዳንዶቹ ጥንታዊ የሆኑ፣ ብዙ ቅጂዎች ቊ11ን የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቷልና፡፡


Matthew 18:1

ማቴዎስ 18፡ 1-3

እንደ ሕጻን መሆን "ሕጻናት እነደሚያስቡት ማሰብ፡፡” (MAT 18:4 እና ተመልከት)

Matthew 18:4

ማቴዎስ 18፡4-6

እንደዚህ ሕጻን ራሱን የሚያዋርድ "ይህ ሕጻን ራሱን በሚያዋርድበት መንገድ ራሱን የሚያዋርድ ማንኛውም ሰው" ( ተመልከት) የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር። "የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ አስረው ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ከተሻለው”( ተመልከት የወፍጮ ድንጋይ ትልቅ፣ ክብ ቅርጽ ያለው ከባድ ድንጋይ ሆኖ እህል ለመፍጨት የሚያገለግል ነው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "ከባድ ድንጋይ"

Matthew 18:7

ማቴዎስ 18፡ 7-8

እጅህ ኢየሱስ አድማጮቹ እንደ አንድ ሰው አድርጎ በነጠላ ቁጥር እየተናገራቸው ነው፡፡

Matthew 18:9

ማቴዎስ 18፡9-9

አውጥተህ ጣለው ይህ ሀረግ የሚያሳየው ተከታታይነት ያለው አለማመንን እና የሚያስከፍለውን ማንኛውንም ዋጋ መሸሽን ነው፡፡ ወደ ሕይወት መግባት "ወደ ዘላለም ሕይወት መግባት"

Matthew 18:10

ማቴዎስ 18፡10-11

አትናቁ "አትናቁ" ወይም "ጠቃሚ አይደሉም ብላችሁ አታስቡ" ለተርጓሚዎች ምክር፡ "አክብሩ" ሁል ጊዜ . . . ፊት ያያሉ "ሁል ጊዜ ቅርብ ናቸው "

Matthew 18:12

ማቴዎስ 18፡12-14

ምን ይመስላችኋል? “ሰዎች ምን እንደሚያደርጉ አስቡ" ( ተመልከት) ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን? "ሁልጊዜ ትቶ ሄዶ የባዘነውን ይፈልጋል፡፡” ዘጠና ዘጠኝ “99” ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም። "በሰማይ ያለው አባታችሁ እነዚህ ትንንሾቹም ሁሉ እንዲኖሩ ፈቃዱ ነው" ( ተመልከት)

Matthew 18:15

ማቴዎስ 18፡15-16

ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው "ከወንድምህ ጋር ያለህን ግንኙነት እንደገና መልካም ታደርጋለህ” አፍ ለምስክሮችህ “አፍ” በሚወጣው ቃል ( ተመልከት)

Matthew 18:17

ማቴዎስ 18፡17-17

እነርሱ መስማት ምስክሮቹን መስማት (MAT 18:16) ለአንተ ልክ እንደ አሕዛብ እና ቀራጭ ይሁንልህ "አሕዛብን እና ቀራጭን እንደሚትመለከተው እንደዚያው ይሁንልህ"

Matthew 18:18

ማቴዎስ 18፡18-20

ያሰራችሁት … የታሰረ . . . -ፈታችሁት . . . የተፈታ ይህህ በ MAT 16:19 ላይ እንዴት እንደተረጎምከተው ተመልከት፡፡ ይታሰራል . . . ይፈታል "እግዚአብሔር ያስረዋል . . . እግዚአብሔር ይፈተዋል" ( ተመልከት) እነርሱ . . . እነርሱ "ሁለት ሆናችሄ" ሁለት ወይም ሦስት "ሁለት ወይም ከዚያ በላይ" ወይም "ቢያንስ ሁለት" ተሰብሰባችሁ "ስበሰባ" አባት ይህ የእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ የማዕረግ ስም ነው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 18:21

ማቴዎስ 18፡21-22

ሰባት እጥፍ "7 እጥፍ" ( ተመልከት ሰባ ጊዜ ሰባት አማራጭ ትርጉሞች: 1) "70 ጊዜ 7" (ULB) ወይም 2) "77 ጊዜ"፡፡ ቁጥርን መጠቀም ግራ የሚያጋባ ከሆነ እንዲህ ማለት ትችላለህ “መቁጠር ከማትችለው ቁጥር በላይ" ( ተመልከት)

Matthew 18:23

ማቴዎስ 18፡23-25

አንድ አገልጋይ አመጡ "አንድ ሰው ከንጉሡ አገልጋዮች መካከል አንድ ሰው አመጣ" ( ተመልከት) ዐስር ሺህ መክልት "10,000 መክልቶች" ወይም "አገልጋዩ መክፍለል ከሚችለው በላይ" ( ተመልከት) አለቃው ተሸጦ ክፍያው እንዲፈጸም አዘዘ "ንጉሡ ይህ ሰው እንዲሸጥና ከሽያጩ ላይ እዳው እንዲከፈል አዘዘ"

Matthew 18:26

ማቴዎስ 18፡ 26-27

በፊቱ ወድቆ በመስገድ "በጉልበቱ ወድቆ አንገቱን ወደ ታች ደፍቶ" በእርሱ ፊት "በንጉሡ ፊት" ለቀቀው "እንዲሄድ ፈቀለትet him"

Matthew 18:28

ማቴዎስ 18፡28-29

አንድ መቶ ዲናር "100 ዲናር" ወይም "የመቶ ቀን የሥራ ክፍያ ( ተመልከት) ያዘው "አሰረው" ወይም “ያዘው" (UDB) በፊቱ ወደቀ . . . ታገሰኝ እና እከፍልሃለሁ ይህንን በ MAT 18:26 ላይ “በፊቱ ወደቀ . . . ታገሰኝ እና እከፍልሃለሁ” በተረጎምከው መሠረት ትርጉመው፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 18:30

ማቴዎስ 18፡30-31

Matthew 18:32

ማቴዎስ 18፡32-33

ከዚያም የአገልጋዩ ጌታ ጠራው "ከዚያ ንጉሡ የመጀመሪያውን አገልጋይ ጠርቶት" አይገባህምን "አይገባህምን” ( ተመልከት)

Matthew 18:34

X

ማቴዎስ 18፡ 34-35


Translation Questions

Matthew 18:1

ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ምን እንድናደርግ እንደሚያስፈልገን ኢየሱስ ተናገረ?

ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ንስሃ ልንገባ እና ልክ እንደ ልጆች ልንሆን እንደሚያስፈልግ ኢየሱስ ተናገረ። [18:3]

Matthew 18:4

በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ የሚሆነው ማን እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ?

ራሱን ልክ እንደ ትንሽ ልጅ የሚያዋርድ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ። [18:4]

በኢየሱስ ያመነውን ታናሽ የሚያስት ሰው ላይ ምን ይሆናል?

በኢየሱስ የሚያምነው ታናሽ እንዲስት የሚያደርግ ሁሉ በአንገቱ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ታስሮ ወደ ባህር ቢጣል ይሻለዋል። [18:6]

Matthew 18:7

እንድንሰናከል በሚያደርገን በማንኛውም ነገር ላይ ምን ልናደርግ እንደሚገባን ኢየሱስ ተናገረ?

እንድንሰናከል የሚያደርገን ማንኛውም ነገርን ልንጠል እንደሚገባን ኢየሱስ ተናገረ። [18:8]

Matthew 18:10

ከታናናሾች ማናቸውንም ልንንቅ እንደማይገባን ኢየሱስ የተናገረው ለምንድነው?

ታናናሾችን ልንንቅ የማይገባን መላእክቶቻቸው የአብን ፊት ሁልጊዜ ስለሚያዩ ነው። [18:10]

Matthew 18:12

አንዱን የጠፋ በግ የሚፈልግ ሰው በሰማይ ያለውን አብ የሚመስለው እንዴት ነው?

ከታናናሾቹ አንዱ ይጠፋ ዘንድ የፈላጊው ሰው ብቻ ሳይሆን የአብም ፈቃድ አይደለም። [18:12]

አንዱን የጠፋ በግ የሚፈልግ ሰው በሰማይ ያለውን አብ የሚመስለው እንዴት ነው?

ከታናናሾቹ አንዱ ይጠፋ ዘንድ የፈላጊው ሰው ብቻ ሳይሆን የአብም ፈቃድ አይደለም። [18:13]

አንዱን የጠፋ በግ የሚፈልግ ሰው በሰማይ ያለውን አብ የሚመስለው እንዴት ነው?

ከታናናሾቹ አንዱ ይጠፋ ዘንድ የፈላጊው ሰው ብቻ ሳይሆን የአብም ፈቃድ አይደለም። [18:14]

Matthew 18:15

ወንድምህ ቢበድል፣ ልታደርግ የሚገባህ የመጀመሪያው ነገር ምንድነው?

በቅድሚያ፣ ልትሄድ እና ጥፋቱን ብቻችሁን ሆናችሁ ልታሳየው ይገባል። [18:15]

ወንድምህ ባይሰማ፣ ልታደርግ የሚገባህ ሁለተኛው ነገር ምንድነው?

በመቀጠል፣ ከአንተ ጋር አንድ ወይም ሁለት ወንድሞችን ምስክር አድርገህ ልትወስድ ይገባል።

Matthew 18:17

ወንድምህ አሁንም የማይሰማ ቢሆን፣ ሦስተኛው ልታደርግ የሚገባው ነገር ምንድነው?

ሦስተኛ፣ ጉዳዩን ለቤተክርስቲያን ልታሳውቅ ይገባል። [18:17]

ወንድምህ አሁንም የማይሰማ ቢሆን፣ ምን መደረግ አለበት?

በስተመጨረሻ፣ ቤተክርስቲያንን የማይሰማ ቢሆን፣ እንደ አረማዊ እና ግብር ሰብሳቢ መቆጠር አለበት። [18:17]

Matthew 18:18

ሁለት ወይም ሦስት በስሙ በሚሰበሰቡበት ኢየሱስ ምን ለማድረግ ቃል ገባ?

ሁለት ወይም ሦስት በስሙ በሚሰበሰቡ መካከል ለመገኘት ኢየሱስ ቃል ገባ። [18:20]

Matthew 18:21

ወንድማችንን ምን ያክል ጊዜ ይቅር ማለት እንዳለብን ኢየሱስ ተናገረ?

ወንድማችንን ሰባ ጊዜ ሰባት ይቅር ማለት እንዳለብን ኢየሱስ ተናገረ። [18:21]

ወንድማችንን ምን ያክል ጊዜ ይቅር ማለት እንዳለብን ኢየሱስ ተናገረ?

ወንድማችንን ሰባ ጊዜ ሰባት ይቅር ማለት እንዳለብን ኢየሱስ ተናገረ። [18:22]

Matthew 18:23

ባርያ ለጌታው ምን እዳ ነበረበት፣ ደግሞስ ለጌታው መልሶ መክፈል ይችላልን?

ባርያው ለጌታው ሊከፍለው ያልቻለው ዐሥር ሺህ ታላንት እዳ ነበረበት። [18:24]

ባርያ ለጌታው ምን እዳ ነበረበት፣ ደግሞስ ለጌታው መልሶ መክፈል ይችላልን?

ባርያው ለጌታው ሊከፍለው ያልቻለው ዐሥር ሺህ ታላንት እዳ ነበረበት። [18:25]

Matthew 18:26

ጌታው ለባርያው እዳውን የተወለት ለምን ነበር?

ጌታው ስለ ራራለት እዳውን ለባርያው ተወለት። [18:27]

Matthew 18:30

ባርያው አብሮት የሚያገለግለውን የመቶ ዲናር እዳ ያለበትን ባርያ ምን አደረገው?

ባርያው መታገስ ባለመፈለግ አብሮት የሚያገለግለውን ባርያ ወደ እስር ቤት ጣለው። [18:30]

Matthew 18:32

አብሮት ለሚያገለግለው ባርያ ማድረግ የነበረበት ምን እንደነበረ ነበር ጌታው ለባርያው የነገረው?

አብሮት ለሚያገለግለው ባርያ ምሕረት ማድረግ እንደነበረበት ጌታው ለባርያው ነገረው። [18:33]

Matthew 18:34

ጌታው በባርያው ላይ ከዚያ በኋላ ምን አደረ?

ጌታው እዳውን ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ለሚያሰቃዩት ባርያዎች አሳልፎ ሰጠው። [18:34]

ወንድማችንን ከልባችን ይቅር የማንል ከሆንን አብ ምን እንደሚያደርግ ኢየሱስ ተናገረ?

ወንድማችንን ከልባችን ይቅር የማንል ከሆነ ጌታው በባርያው ላይ እንዳደረገ አብ እንደሚያደርግብን ኢየሱስ ተናገረ። [18:35]


ምዕራፍ 19

1 እንዲህም ሆነ፤ ኢየሱስ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ገሊላን ትቶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ ጠረፍ መጣ፡፡ 2 ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፤ እዚያም ፈወሳቸው፡፡ 3 ፈሪሳውያን እንዲህ በማለት ሊፈትኑት ወደ እርሱ መጡ፤ "በማንኛውም ምክንያት ሰው ሚስቱን ቢፈታ ሕጋዊ ነውን?" 4 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፣ "ከመጀመሪያው የፈጠራቸው እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸውና 5 ደግሞም፣ 'በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ አንድ ሥጋም ይሆናሉ' የተባለውን አላነበባችሁምን? 6 ስለዚህ እነርሱ ከእንግዲህ አንድ ሥጋ እንጂ ሁለት አይደሉም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር አንድ ላይ ያጣመረውን፣ ማንም አይለየው፡፡›› 7 እነርሱ፣ "ታዲያ የፍቺ የምስክር ወረቀት ሰጥተን ከዚያ በኋላ እንድናባርራት ሙሴ ለምን አዘዘን?" አሉት፡፡ 8 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ "ከልባችሁ ድንዳኔ የተነሣ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ሙሴ ፈቀደላችሁ፤ ነገር ግን ከመጀመሪያው እንደዚያ አልነበረም፡፡ 9 እኔ እላችኋለሁ፣ ከዝሙት በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል፡፡" 10 ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ "የባልና የሚስት ጉዳይ እንዲህ ከሆነ ማግባት ጥሩ አይደለም" አሉት፡፡ 11 ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ "እንዲቀበሉት የተፈቀደላቸው እንጂ፣ ሁሉም ሰው ይህን ትምህርት አይቀበለውም፡፡ 12 በተፈጥሮ ከእናታቸው ማኅፀን ስልብ ሆነው የተወለዱ አሉና፡፡ ሰዎች የሰለቧቸውም ይገኛሉ፡፡ ስለ መንግሥተ ሰማያት ሲሉም ራሳቸውን ስልብ ያደረጉ አሉ፡፡ ይህን ትምህርት መቀበል የሚችል፣ ይቀበለው፡፡›› 13 በዚያን ጊዜ እጁን ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሰዎች ልጆችን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው፡፡ 14 ኢየሱስ ግን፣ "ልጆቹን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም እንዲመጡ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና" አለ፡፡ 15 15 እጁንም በልጆቹ ላይ ጫነባቸው፤ ከዚያም ያን ቦታ ትቶ ሄደ፡፡ 16 እነሆ፣ አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ ‹‹መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ማድረግ አለብኝ?›› አለ፡፡ 17 ኢየሱስ፣ ‹‹ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም አንድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ትእዛዛትን ጠብቅ›› አለው፡፡ 18 ሰውዬው፣ ‹‹የትኞቹን ትእዛዛት? አለ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "አትግደል፤" "አታመንዝር" "አትስረቅ፤" "በሐሰት አትመስክር፤" 19 "አባትህንና እናትህን አክብር፤" እንዲሁም፣ "ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡" 20 ወጣቱ፣ "እነዚህን ነገሮች ሁሉ ፈጽሜአለሁ፣ ሌላስ ምን ያስፈልገኛል?" አለው፡፡ 21 ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "ፍጹም ለመሆን ብትፈልግ፣ ሂድና ያለህን ሽጠህ ለድኾችም ስጠው፤ በሰማይም ሀብት ይኖርሃል፡፡ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ፡፡›› 22 ነገር ግን ወጣቱ ኢየሱስ የተናገረውን በሰማ ጊዜ፣ ብዙ ንብረት ነበረውና ዐዝኖ ሄደ፡፡ 23 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ከባድ ነው፡፡ 24 ደግሜ እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከመግባት፣ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፡፡" 25 ደቀ መዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ተደነቁና፣ "ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?" አሉ፡፡ 26 ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተመልክቶ፣ "ይህ ለሰዎች የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል" አለ፡፡ 27 ከዚያም ጴጥሮስ መልሶ፣ "ተመልከት፣ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ ታዲያ ምን እናገኛለን?" አለ፡፡ 28 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ እኔን የተከተላችሁኝ፣ በዐዲሱ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም በዐሥራ ሁለት ዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶችም ላይ ትፈርዳላችሁ፡፡ 29 ስለ ስሜ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን፣ ወይም ርስትን የተወ ሁሉ፣ መቶ እጥፍ ይቀበላል፣ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል፡፡ 30 ነገር ግን አሁን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች ይሆናሉ፤ ኋለኞች የሆኑ ብዙዎችም ፊተኞች ይሆናሉ፡፡



Matthew 19:1

ማቴዎስ 19፡1-2

ከዚያ በኋላ በቋንቋችሁ የአንድን ታሪክ አዲስ ክፍል ለመጀመር የሚያገለግል ቃል ካለ ይህንን ቃል ተጠቀሙ፡፡ እነዚህ ቃላት የ . . . ቃላት MAT 18:1-35 ተለየ "ከእነርሱ ራቀ” ወይም "ተዋቸው" በዚያው ክልል ውስጥ "በዚያው አከባቢ"

Matthew 19:3

ማቴዎስ 19፡3-4

ወደ እርሱ መጣ "ወደ ኢየሱስ መጣ" አላነበባችሁምን . . . ሴት? ኢየሱስ ፈሪሳዊያኑን ሊያሳፍራቸው ፈልጎሏል፡፡ ( ተመልከት)

Matthew 19:5

ማቴዎስ 19፡5-6

እንዲሁም እንዲህ አለ .. . ሥጋ? በ MAT 19:3 ላይ የተጀመረው ጥያቄ የቀጠለ ነው፡ "በተጨማሪም እንዲህ የሚል ነገር አላነባችሁምን . . . ሥጋ?" ( እና ተመልከት) ከምስቱ ጋር ይጣበቃል "ከምስቱ ጋር ይቀራረባል" አንድ ሥጋ "አንድ ሰው"

Matthew 19:7

ማቴዎስ 19፡7-9

እንዲህ አሉት "ፈሪሳዊያኑ ለኢየሱስ አንዲህ አሉት" አዞናል "አይሁዳዊ እንደመሆናችን እንዲህ ታዘናል" የፊች ወረቀት ጋብቻው ሕጋዊ በሆነ መንገድ መቆሙን የሚሳይ ወረቅት ከመጀመሪያው ግን እንዲህ አልነበረም "እግዚብሔር ወንድን እና ሴትን ሲፈጥር መቼም ቢሆን እንድፋቱ አልነበረም" የተፈታቸችሁንም የሚያገባ ማንኛውም ሰው ያመነዝራል ብዙዎቹ የጥንት ቅጂዎች እነዚህንን ቃላት አይጨምሩትም፡፡

Matthew 19:10

ማቴዎስ 9፡10-12

ራሱን ጃንደረባ ያደረገ አማራጭ ትርጉሞች 1) "የግል አካሉን ቆርጦ የጣለ” ወይም 2) "ላለማግባት እና ምንም ዓይነት ግብረስጋ ግንኙነት ላለማድረግ የወሰነ ሰው” ( ተመልከት) ለመንግስተ ሰማያት ሲል "እግዚአብሔርን ይበልጥ ለማገልገል ይችል ዘንድ" ይህንን ትምህርት ተቀበል . . . ተቀበል “ይህንን ትምህርት ተቀበል . . . ተቀበል” የሚለው በ19፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከተው ተመልከት፡፡

Matthew 19:13

ማቴዎስ 19፡ 13-15

ሕጻናትን ወደ እርሱ አመጡ ለተርጓሚዎች ምክት፡ “አንዳንድ ሰዎች ሕጻናትን ወደ ኢየሱስ አመጡ፡፡” ( ተመልከት) ፈቃድ "ፍቀዱ" ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው "ወደ እኔ እንዳይመጡ አትከልክሏቸው" የመንግስተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና "መንግስተ ሰማየት እንደነዚህ ላሉ ሰዎች ናትና” ወይም “ልክ እንደነዚህ ሕጻናት የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት የሚችሉት"

Matthew 19:16

ማቴዎስ 19፡ 16-17

እነሆ ይህ ቃል ሰዎች ከዚህ በኋላ ለሚነገረው ነገር አጽኖት እንዲሰጡ የሚጨመር ቃል ነው፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ተመልከቱ” ወይም “አድምጡ” ወይም “አሁን ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ”:: መልካም ነገር እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር

Matthew 19:18

ማቴዎስ 19፡18-19

Matthew 19:20

ማቴዎስ 19፡20-22

ምኞት "ፍላጎት"

Matthew 19:23

ማቴዎስ 19፡23-24

ሀብታም ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላል ለሀብታም ወደ እግዚአብሔር መንግስር መግባት በጣም ከባድ ነው ( ተመልከት) የመርፌ ቀዳዳ ለክር ማስገቢያ የሚሆን በመርፌ አናት ላይ የሚገኝ ቀዳዳ

Matthew 19:25

ማቴዎስ 19፡25-27

በጣም ተገረሙ "ደቀ መዛሙርቱ ተደነቁ" ማን ልድን ይችላል? አማራጭ ትርጉሞች: 1) መልስ እየፈለጉ ነው ወይም 2) ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ማንም ሊድን አይችልም!” ( ተመልከት) እኛ ሁሉን ነገር ተውን "ሀብታችንን ሁሉ ተውን" ወይም "ያለንን ነገር ሁሉ ተውን" ታዲያ ምን እናገኛለን? "እግዚአብሔር ለእኛ ምን መልካም ነገር ይሰጠናል?"

Matthew 19:28

ማቴዎስ 19፡28-28

አዲስ ልደት "ሁሉ ነገር አዲስ በሚሆንበት ጊዜ” ወይም "በአዲሱ ዘመን" በዐሥራ ሁለቱ ዙፋናት ላይ ትቀመጣላችሁ፣ ትርዳላችሁ "ነገሥታት እና ፈራጆች ትሆናላችሁ"

Matthew 19:29

ማቴዎስ 19፡ 29-30

መቶ እጥፍ ትቀበላላችሁ "የተዋቿቸውን መልካም ነገሮች ሁሉ በመቶ እጥፍ ትቀበላላችሁ" አሁን መጀመሪያ የነበሩ ብዙዎች መጨረሻ ሆነዋል በሰዎች ዐይን መጀመሪያ የነበሩት ማለትም ሀብታሞች እና ሌሎችን የሚዙ ሰዎች በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ አንድ ቀን መጨረሻ ይናሉ፡፡


Translation Questions

Matthew 19:3

ፈሪሳውያን ኢየሱስን ለመፈተን ምን ጥያቄ ጠየቁት?

ፈሪሳውያን ኢየሱስን “ሰው ሚስቱን በማንኛውም ምክንያት ሊፈታ ተፈቅዷልን?” ብለው ጠየቊት [19:3]

ከፍጥረት መጀመሪያ አንሥቶ እውነት የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ኢየሱስ መለሰላቸው?

ከፍጥረት መጀመሪያ አንሥቶ እግዚአብሔር ወንድ እና ሴት አድርጎ እንደፈጠራቸው ኢየሱስ ተናገረ። [19:4]

Matthew 19:5

እግዚአብሔር ወንድ እና ሴት አድርጎ ስለፈጠራቸው፣ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበት ኢየሱስ ተናገረ?

ሰው አባት እና እናቱን መተው እና ከሚስቱም ጋር መጣበቅ እንዳለበት ኢየሱስ ተናገረ። [19:5]

ባል ከሚስቱ ጋር በሚጣበቅ ጊዜ ምን እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ?

ባል ከሚስቱ ጋር በሚጣበቅበት ጊዜ ሁለቱ አንድ ስጋ እንደሚሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [19:5]

ባል ከሚስቱ ጋር በሚጣበቅ ጊዜ ምን እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ?

ባል ከሚስቱ ጋር በሚጣበቅበት ጊዜ ሁለቱ አንድ ስጋ እንደሚሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [19:6]

እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው ምን ሊያደርግ እንደማይገባ ኢየሱስ ተናገረ?

እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው ሊለየው እንደማይገባ ኢየሱስ ተናገረ። [19:6]

Matthew 19:7

ሙሴ የፍቺዋን ወረቀት እንዲሰጣት ያዘዘው ለምን እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ?

የፍቺ ወረቀት እንዲሰጣት ሙሴ ያዘዘው ከአይሁድ ልቦች ደንዳንነት የተነሣ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። [19:7]

ሙሴ የፍቺዋን ወረቀት እንዲሰጣት ያዘዘው ለምን እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ?

የፍቺ ወረቀት እንዲሰጣት ሙሴ ያዘዘው ከአይሁድ ልቦች ደንዳንነት የተነሣ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። [19:8]

ዝሙት እንደፈጸመ አድርጎ ኢየሱስ የተናገረው ማንን ነው?

ከዝሙት በስተቀር ሚስቱን ሌላኛዋን የሚያገባ ምንዝርናን ይፈጽማል፣ የተፈታችይቱንም ሴት የሚያገባ ምንዝርና ይፈጽማል። [19:9]

Matthew 19:10

ጃንደረባነትን ሊቀበል እንደሚችል ኢየሱስ የተናገረው ማንን ነው?

ሊቀበሉት የተፈቀደላቸው ጃንደረባነትን ሊቀበሉ እንደሚችሉ ኢየሱስ ተናገረ። [19:10]

ጃንደረባነትን ሊቀበል እንደሚችል ኢየሱስ የተናገረው ማንን ነው?

ሊቀበሉት የተፈቀደላቸው ጃንደረባነትን ሊቀበሉ እንደሚችሉ ኢየሱስ ተናገረ። [19:11]

ጃንደረባነትን ሊቀበል እንደሚችል ኢየሱስ የተናገረው ማንን ነው?

ሊቀበሉት የተፈቀደላቸው ጃንደረባነትን ሊቀበሉ እንደሚችሉ ኢየሱስ ተናገረ። [19:12]

Matthew 19:13

ትንንሽ ልጆችን ወደ ኢየሱስ ባመጧቸው ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ምን አደረጉ?

ትንንሽ ልጆች ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ፣ ደቀመዛሙርቱ ገሠጿቸው። [19:13]

ትንንሽ ልጆችን ባያቸው ጊዜ ኢየሱስ ምን አለ?

የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነርሱ ላሉት ስለሆነች፣ ትንንሽ ልጆች እንዲመጡ እንዲፈቅዱላቸው ኢየሱስ ተናገረ። [19:14]

Matthew 19:16

ወጣቱ ሰው ወደ ዘላለም ሕይወት እንዲገባ ምን ማድረግ እንዳለበት ኢየሱስ ተናገረ?

ወደ ዘላለም ሕይወት ለመግባት ትእዛዛትን እንዲጠብቅ ኢሱስ ለወጣቱ ነገረው። [19:16]

ወጣቱ ሰው ወደ ዘላለም ሕይወት እንዲገባ ምን ማድረግ እንዳለበት ኢየሱስ ተናገረ?

ወደ ዘላለም ሕይወት ለመግባት ትእዛዛትን እንዲጠብቅ ኢሱስ ለወጣቱ ነገረው። [19:17]

Matthew 19:20

ትእዛዛትን እንደጠበቀ ሰውዬው በተናገረ ጊዜ፣ ኢየሱስ ምን እንዲያደርግ ነገረው?

ትእዛዛትን እንደጠበቀ ሰውዬው በተናገረ ጊዜ፣ ያለውን ሁሉ ሸጦ ለድሆች እንዲሰጥ ኢየሱስ ነገረው። [19:20]

ትእዛዛትን እንደጠበቀ ሰውዬው በተናገረ ጊዜ፣ ኢየሱስ ምን እንዲያደርግ ነገረው?

ትእዛዛትን እንደጠበቀ ሰውዬው በተናገረ ጊዜ፣ ያለውን ሁሉ ሸጦ ለድሆች እንዲሰጥ ኢየሱስ ነገረው። [19:21]

ወጣቱ ሰው ያለውን እንዲሸጥ ኢየሱስ የሰጠውን ትእዛዝ እንዴት አድርጎ ምላሽ ሰጠበት?

ወጣቱ ሰው ብዙ ሃብት ስለነበረው እያዘነ ሄደ። [19:22]

Matthew 19:25

ሃብታሙ ሰው ወደ መንግሥተ ሰማያት ሊገባ የሚችልበት እድል ኢየሱስ ምን አለ?

ኢየሱስ ሲናገር ለሰው እንደማይቻል፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሁሉ ይቻላል። [19:26]

Matthew 19:28

ለተከተሉት ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ ምን ብድራትን ቃል ገባላቸው?

በአዲሱ ልደት በዐሥራ ሁለቱ ዙፋናት ላይ ተቀምጠው በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ እንደሚፈርዱ ኢየሱስ ተናገረ። [19:28]

Matthew 19:29

አሁን ላይ ፊተኛ ስለሆኑ ቀጥሎ ኋለኛ ስለሚሆኑት ኢየሱስ ምን አለ?

አሁን ላይ ፊተኛ የሆኑት ኋለኛ እንደሚሆኑ፣ አሁን ላይ ኋለኛ የሆኑት ፊተኛ እንደሚሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [19:30]


ምዕራፍ 20

1 መንግሥተ ሰማይ ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤትን ትመስላለች። 2 በቀን አንዳንድ ዲናር ሊከፍላቸው ከሠራተኞቹ ጋር ከተስማማ በኋላ፣ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ላካቸው። 3 ደግሞም በሦስት ሰዓት ገደማ ወጥቶ በገበያ ቦታ ሥራ ፈትተው የቆሙ ሌሎች ሠራተኞችን አየና፣ 4 'እናንተ ደግሞ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሂዱ፤ የሚገባችሁንም እከፍላችኋለሁ' አላቸው። ስለዚህ እነርሱም ሊሠሩ ሄዱ። 5 ደግሞ በስድስት ሰዓትና በዘጠኝ ሰዓት ገደማ ወጥቶ እንደዚሁ አደረገ። 6 አሁንም በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ገደማ ወጥቶ ሥራ ፈትተው የቆሙ ሌሎችን አገኘ። እነርሱንም፣ 'ቀኑን ሙሉ ሥራ ፈትታችሁ እዚህ ለምን ቆማችኋል?' አላቸው። 7 'ማንም ስላልቀጠረን ነው' አሉት። 'እናንተም ደግሞ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሂዱ' አላቸው። 8 ቀኑ በመሸ ጊዜ፣ የወይኑ አትክልት ባለቤት ሥራ አስኪያጁን፣ 'ሠራተኞቹን ጥራ ከኋለኞቹ አንሥተህ እስከ ፊተኞቹ የሠሩበትን ገንዘብ ክፈላቸው' አለው። 9 በዐሥራ አንደኛው ሰዓት የተቀጠሩት ሠራተኞች በመጡ ጊዜ፣ እያንዳንዳቸው አንዳንድ ዲናር ተቀበሉ። 10 ፊተኞቹ ሠራተኞች በመጡ ጊዜ፣ የበለጠ የሚቀበሉ መሰላቸው፤ ነገር ግን እነርሱም ደግም እያንዳንዳቸው አንዳንድ ዲናር ተቀበሉ። 11 ገንዘባቸውን በተቀበሉ ጊዜ፣ በወይኑ አትክልት ባለቤት ላይ አጕረመረሙ። 12 እንዲህም አሉ፤ 'እነዚህ በመጨረሻ የመጡ ሠራተኞች በሥራ ላይ አንድ ሰዓት ብቻ አሳልፈዋል፤ ነገር ግን አንተ የዕለቱን ሸክምና የሚለበልበውን ሙቀት ከተሸከምነው ከእኛ ጋር እኩል አድርገሃቸዋል።' 13 ባለቤቱ ግን መልሶ ከእነርሱ አንዱን እንዲህ አለው፤ "ወዳጄ ሆይ፣ አልበደልኩህም። ከእኔ ጋር በአንድ ዲናር አልተስማማህምን? 14 የሚገባህን ተቀብለህ መንገድህን ሂድ፤ ለእነዚህ በመጨረሻ ለተቀጠሩት ሠራተኞች ልክ እንደ አንተው ልሰጣቸው ደስ ይለኛል። 15 በገዛ ንብረቴ የፈለግሁትን ማድረግ አይገባኝምን? ወይስ እኔ ደግ ስለ ሆንሁ ትመቀኛለህን? 16 ስለዚህ ኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ።" 17 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ስለ ነበር፣ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ወሰደ፤ በመንገድ ላይም እንዲህ አላቸው፦ 18 እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለሕግ መምህራን ተላልፎ ይሰጣል። ሞትም ይፈርዱበታል፤ 19 እንዲዘብቱበት፣ እንዲገርፉት፣ እንዲሰቅሉትም ለአሕዛብ ይሰጡታል። ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ይነሣል።" 20 በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆቿ ጋር ወደ ኢየሱስ መጣች፤ በፊቱ ተንበርክካም ከእርሱ አንድ ነገር ለመነች። 21 ኢየሱስ፣ "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት። እርሷም፣ "በመንግሥትህ እነዚህ ሁለት ልጆቼ አንዱ በቀኝህ፣ አንዱም በግራህ እንዲቀመጡ እዘዝ" አለችው። 22 ኢየሱስ ግን መልሶ፣ "የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?" አለ። እነርሱ፣ "እንችላለን" አሉት። 23 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "በርግጥ ጽዋዬን ትጠጣላችሁ። በቀኜና በግራዬ መቀመጥን የምሰጥ ግን እኔ አይደለሁም፤ ነገር ግን በአባቴ ለተዘጋጀላቸው ለእነርሱ ነው።" 24 ሌሎቹ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ይህን በሰሙ ጊዜ፣ በሁለቱ ወንድማማች ላይ ተቈጡ። 25 ነገር ግን ኢየሱስ ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ "የአሕዛብ አለቆች ሕዝባቸውን ጨቊነው ይገዛሉ፤ የበላዮቻቸውም ይሠለጥኑባቸዋል። 26 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መደረግ የለበትም። ይልቁንም፣ ከእናንተ መካከል ታላቅ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን፤ 27 ከእናንተም ፊተኛ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን። 28 የሰው ልጅ ሊያገለግል፣ ሕይወቱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ እንጂ፣ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" 29 ከኢያሪኮ እንደ ወጡ፣ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስን ተከተሉት። 30 እነሆ፣ ሁለት ዐይነ ስውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው ነበር፤ ኢየሱስ ሲያልፍ በሰሙ ጊዜ ጮኽ ብለው፣ "ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ማረን" አሉ። 31 ሕዝቡ ግን ዝም እንዲሉ በመንገር ገሠጿቸው። ይሁን እንጂ፣ እነርሱ አብዝተው በመጮኽ፣ "ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ ማረን" አሉ። 32 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ቆም ብሎ ጠራቸውና፣ "ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?" አለ። 33 እነርሱም፣ "ጌታ ሆይ፣ ዐይኖቻችን እንዲከፈቱ ነው" አሉት። 34 ከዚያም ኢየሱስ ራርቶ፣ ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ። እነርሱም ወዲያውኑ አይተው ተከተሉት።



Matthew 20:1

ማቴዎስ 20፡1-2

መንግስ ሰማያት የመሬት ባለቤትን ትመስላለች እግዚአብሔር በሁሉም ነገር ላይ ያለው አገዛዝ አንድ ባለመሬት መሬቱን የሚያስተዳድርበትን መንገድ ይመስላል ( ተመልከት) መንግስተ ሰማይ ትመስላለች በ MAT 13:24 ላይ በምን መልኩ እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ ከተስማማ በኋላ "የመሬቱ ባለቤት ከተስማማ በኋላ" በአንድ ዲናር "የአንድ ቀን ገቢ" ( ተመልከት)

Matthew 20:3

ማቴዎስ 20፡3-4

እንደ ገና ወጣና "የመሬቱ ባለቤት እንደገና ወጣና" ያለሥራ የቆሙተን "ምንመ የማይሠሩትን” ወይም “ሥራ ያሌላቸውን"

Matthew 20:5

ማቴዎስ 20፡5-6

እንደ ገና ወጣና "የመሬቱ ባለቤት እንደገና ወጣና" ያለሥራ የቆሙተን "ምንመ የማይሠሩትን” ወይም “ሥራ ያሌላቸውን"

Matthew 20:8

ማቴዎስ 20፡ 8-10

ለእያንዳንዱ "በዐሥራ አንድ ሰዓት መሥራት ለጀመረውም ለእያንዳንዱ" አንድ ዲናር "የአንድ ቀን ገቢ" ( ተመልከት) እነርሱ እነንዲህ አሰቡ "ረጅም ሰዓት የሠሩት ሠራተኞች እንዲህ አሰቡ"

Matthew 20:11

ማቴዎስ 20፡11-12

በተቀበሉ ጊዜ "ረጀም ሰዓት ስሰሩ የነበሩት ሠራተኞች ስቀበሉ" ባለቤቱ "የመሬቱ ባለቤት" ወይም "የወይን እርሻው ባለቤት" የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን "በጠራራ ፀሐይ ቀኑን ሙሉ ሥንሠራ የነበርን"

Matthew 20:13

ማቴዎስ 20፡13-14

ከመካከላቸው አንዱ "ረጅሙን ሰዓት ከሠሩት ሠራተኞች መካከል አንዱ" ወዳጆቼ በዚህ ሥፍራ ላይ አንድ ሰው ሌላኛውን ሰው በትህትና ለመገሰጽ የሚጠቀምበትን ቃል ተጠቀም፡፡ በአንድ ዲናር ለመሥራት ከእኔ ጋር አልተስማማችሁምን? ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ለሥራችሁ ዋጋ አንድ ዲናር ለመክፈል ተስማሚቼያለሁ፡፡ (en:ta:vol1:translate: ተመልከት) አንድ ዲናር "የአንድ ቀን ገቢ" ( ተመልከት) መስጠት እወዳለሁ "መስጠት ያስደስተኛል” ወይም “መስጠት እወዳለሁ”

Matthew 20:15

ማቴዎስ 20: 15-16

በራሴ ሀብት የፈለኩትን የማድረግ መብት የለኝምን? ለተርጓሚዎች ምክር፡ "በራሴ ሀብት የፈለኩትን ማድረግ እችላለሁ” መብት "ሕጋዊ" ወይም "ፍትሐዊ" ወይም "ትክክል" ወይም እኔ መልካም ስለሆንኩ ቀናችሁን? "ለማይገባቸው ሰዎች መልካም በማድረጌ አልተደሰታችሁምን"

Matthew 20:17

ማቴዎስ 20፡17-19

እንሄዳለን ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ የሰው ልጅን አሳልፈው ይሰጡታል "አንድ ሰው የሰው ልጅን አሳልፎ ይሰጠዋል" ይፈርዱበታል. . . እና አሕዛብ ይዘባበቱበት ዘንድ አሳልፎ ይሰጣል የካህናት አለቆች እና ፀሐፍት ይፈርዱበታል እንዲሁም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ አሕዛብም ይዘባበቱበታል ይነሳል "እግዚብሔር ያስነሳዋል”

Matthew 20:20

ማቴዎስ 20፡20-21

በቀኝህ በኩል . . . በግራህ በኩል ሥልጣን ያለው ቦታ

Matthew 20:22

ማቴዎስ 20፡22-24

አናንተ እናት እና ልጆች ትችላለህን...ለመጠጣት? "ለመጠጣት . . . ትችላለህን?" ኢየሱስ ይህን የተናረው ለልጆች ብቻ ነው፡፡ አሁን ልጠጣው ያለሂትን ጽዋ ጠጣ "አሁን ልቀበለው ያለሁትን መከራ ውስጥ እለፍ" እነርሱ ልጆች በአባቴ ለተዘጋጀላቸው ነው "ከአጠገቤ በክብር መቀመጥ ይህንን ክብር አባቴ ላዘጋጀላቸው ነው" መዘጋጀት የተዘጋጀላቸው

Matthew 20:25

ማቴዎስ 20፡25-28

የአሕዛብ ገዥዎች ይገዟቸዋል "የአሕዛብ ገዥዎች ገዥው የፈለገውን ነገር እንዲያደር ሕዝቡን ያዛሉ" እርሱ በጣም አስፈለጊ ሰው ናቸው በገዥዎች ስልጣን የተሰጣቸው ሰዎች በእነርሱ ላይ ስልጣን አላቸው "ይቆጣጠሯቸዋል" ፍላጎት "ፍላጎት" ወይም "መሻት" ሕይወት መስጠት "ለመሞት መፈለግ"

Matthew 20:29

ማቴዎስ 20፡29-31

እንደፈለጉ ለደቀ መዛሙርቱ እና ኢየሱስ ተከተሉት "ኢየሱስን ተከተሉ" እናም ተመለከቱ አንዳንድ ጊዜ “እነሆነ” ተብሎ ተተርጉሟል፡፡ ጸሐፊው ከዚህ በመቀጠል ለሚመጣው ነገር ትኩርት እንዲሰጠው ይፈልጋል፡፡ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ነገር በቋንቋችሁ ውስጥ ይኖራል፡፡ በዚያ ስያልፉ "በዚያ ሥያልፉ" ይበልጥ ድምጻቸው አሰመተው ጮኹ "ዐይነ ሥውራኑ ከበፊቱ ይልቅ አብዝተው ጮኹ” ወይም “ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ጮኹ"

Matthew 20:32

ማቴዎስ 20፡32-34

ጠራቸው ዐይነ ሥውራኑን ጠራቸው ፍላጎት "ፍላጎት" እናይ ዘንድ እንወዳለን ለተርጓማች ምክር፡ “ማየት እንችል ዘንድ ታደርግ ዘንድ እንወዳለን" ወይም "ማየት እንችል ዘንድ እንወዳለን ራራላቸው "ራራላቸው” ወይም "ለእነርሱ ራራ"


Translation Questions

Matthew 20:1

የእርሻው ባለቤት በማለዳ ለቀጠራቸው ሠራተኞች ምን ያክል ሊከፍላቸው ተስማማ?

የእርሻው ባለቤት በማለዳ ለቀጠራቸው ሠራተኞች በቀን አንድ ዲናገር ለመክፈል ተስማምቶ ነበር። [20:1]

የእርሻው ባለቤት በማለዳ ለቀጠራቸው ሠራተኞች ምን ያክል ሊከፍላቸው ተስማማ?

የእርሻው ባለቤት በማለዳ ለቀጠራቸው ሠራተኞች በቀን አንድ ዲናገር ለመክፈል ተስማምቶ ነበር። [20:2]

Matthew 20:3

የእርሻው ባለቤት በሦስተኛው ሰዓት ለቀጠራቸው ሠራተኞች ምን ያክል ሊከፍላቸው ተስማማ?

የእርሻው ባለቤት በሦስተኛው ሰዓት ለቀጠራቸው ሠራተኞች እርሱ የፈለገውን ያክል ለመክፈል ተስማምቶ ነበር። [20:4]

Matthew 20:8

በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ የተቀጠሩት ሠራተኞች ምን ያክል ተቀበሉ?

በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ የተቀጠሩት አንድ ዲናር ተቀበሉ። [20:9]

Matthew 20:11

ገና በማለዳ ተቀጥረው የነበሩት ሠራተኞች የነበራቸው ቅሬታ ምን ነበር?

ሙሉ ቀን ሠርተው፣ ለአንድ ሰዓት ከሠሩት ጋር ተመሳሳይ ክፍያ እንደተቀበሉ አገሩመረሙ። [20:11]

ገና በማለዳ ተቀጥረው የነበሩት ሠራተኞች የነበራቸው ቅሬታ ምን ነበር?

ሙሉ ቀን ሠርተው፣ ለአንድ ሰዓት ከሠሩት ጋር ተመሳሳይ ክፍያ እንደተቀበሉ አገሩመረሙ። [20:12]

Matthew 20:13

የእርሻው ባለቤት ለሠራተኞቹ ቅሬታ ምን ምላሽ ሰጠ?

የእርሻው ባለቤት ምንም እንዳልበደላቸው እና ለእነርሱ የተገባቸውን እንደከፈላቸው ተናገረ። [20:13]

የእርሻው ባለቤት ለሠራተኞቹ ቅሬታ ምን ምላሽ ሰጠ?

የእርሻው ባለቤት ምንም እንዳልበደላቸው እና ለእነርሱ የተገባቸውን እንደከፈላቸው ተናገረ። [20:14]

Matthew 20:17

ወደ ኢየሩሳሌም እየሄዱ በነበሩ ጊዜ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ አስቀድሞ ምን እንደሚከሰት ነገራቸው?

ለሊቀ ካህናት እና ጸሐፍት ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ እስከ ሞት ድረስ እንደሚፈረድበት፣ እንደሚሰቀል፣ እና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው። [20:17]

ወደ ኢየሩሳሌም እየሄዱ በነበሩ ጊዜ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ አስቀድሞ ምን እንደሚከሰት ነገራቸው?

ለሊቀ ካህናት እና ጸሐፍት ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ እስከ ሞት ድረስ እንደሚፈረድበት፣ እንደሚሰቀል፣ እና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው። [20:18]

ወደ ኢየሩሳሌም እየሄዱ በነበሩ ጊዜ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ አስቀድሞ ምን እንደሚከሰት ነገራቸው?

ለሊቀ ካህናት እና ጸሐፍት ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ እስከ ሞት ድረስ እንደሚፈረድበት፣ እንደሚሰቀል፣ እና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው። [20:19]

Matthew 20:20

የዘብዴዎስ ልጆች እናት ለኢየሱስ የነበራት ጥያቄ ምን ነበር?

ሁለቱ ልጆቿ አንደኛው በቀኙ ሌላኛው በግራው እንዲቀመጡ ኢየሱስ እንዲያደርግላት ፈለገች። [20:20]

የዘብዴዎስ ልጆች እናት ለኢየሱስ የነበራት ጥያቄ ምን ነበር?

ሁለቱ ልጆቿ አንደኛው በቀኙ ሌላኛው በግራው እንዲቀመጡ ኢየሱስ እንዲያደርግላት ፈለገች። [20:21]

Matthew 20:22

በመንግሥቱ ውስጥ በእርሱ ቀኝ እና ግራ እንዲቀመጡ የሚወስነው ማን እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ?

እነዚያን ቦታዎች ለመረጣቸው አብ እንዳዘጋጀ ኢየሱስ ተናገረ። [20:23]

Matthew 20:25

አንድ ሰው በደቀመዛሙርቱ መካከል ታላቅ ሊሆን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ?

ታላቅ ሊሆን የሚወድድ ማንም ሰው ቢሆን አገልጋይ መሆን እንዳለበት ኢየሱስ ተናገረ። [20:26]

ኢየሱስ ለምን እንደመጣ ተናገረ?

እርሱ የመጣው ሊያገለግል እና ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ መሆኑን ኢየሱስ ተናገረ። [20:28]

Matthew 20:29

ኢየሱስ ያልፍ በነበረበት መንገድ ላይ ተቀምጠው የነበሩት ሁለቱ ማየት የተሳናቸው ሰዎች ምን አደረገ?

ሁለቱ ማየት የተሳናቸው “ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ማረን” ይሉ ነበር። [20:30]

Matthew 20:32

ኢየሱስ ሁለቱን ማየት የተሳናቸው ሰዎች የፈወሰው ለምን ነበር?

ኢየሱስ ሁለቱን ማየት የተሳናቸውን ሰዎች የፈወሰው ስላዘነላቸው ነበር። [20:34]


ምዕራፍ 21

1 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም እንደቀረቡ፣ በደብረ ዘይት ወዳለው ወደ ቤተ ፋጌ መጡ፤ 2 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ በማለት ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤ “ወደሚቀጥለው መንደር ሂዱ፤ አህያም ከነውርንጫዋ ታስራ ታገኛላችሁ። ፈትታችሁ ወደ እኔ አምጧቸው፤ 3 ማንም ስለዚያ አንዳች ቢናገራችሁ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ፈጥኖ ይሰዳቸዋል።” 4-5 ይህ የሆነው፣ “እነሆ፣ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሯት” ተብሎ በነቢዩ የተተነበየው ይፈጸም ዘንድ ነው። 6 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሄደው ልክ ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ። 7 አህያይቱንና ውርንጫዋን አመጡ፤ ልብሳቸውንም አደረጉባቸውና ኢየሱስ ተቀመጠባቸው። 8 ከሕዝቡ አብዛኞቹ ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፣ ሌሎችም የዘንባባ ዝንጣፊ እየቈረጡ በመንገድ ላይ አደረጉ። 9 ከኢየሱስ ፊት ይሄዱ የነበሩትና የተከተሉትም ሕዝብ፣ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው። ሆሣዕና በአርያም ይሁን!” በማለት ጮኹ። 10 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ከተማይቱ በሞላ ታወከችና፣ “ይህ ማን ነው?” አለች። 11 ሕዝቡ፣ “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የሆነው ነቢዩ ኢየሱስ ነው” ብለው መለሱ። 12 ከዚያም ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደ። በቤተ መቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን አስወጣ። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና ወንበሮች ገለበጠ። 13 እንዲህም አላቸው፤ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል። እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት።" 14 ከዚያም ዐይነ ስውሮችና ሽባዎች ወደ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው። 15 ነገር ግን የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን እርሱ ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች ባዩና በቤተ መቅደስ ልጆች፣ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ” በማለት ሲጮኹ በሰሙ ጊዜ፣ ተቈጡ። 16 “ሕዝቡ የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት። ኢየሱስ፣ “አዎ! ነገር ግን ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው። 17 ከዚያም ኢየሱስ ትቷቸው ከከተማው ወጣና ወደ ቢታንያ ሄዶ በዚያ ዐደረ። 18 ኢየሱስ ጠዋት ወደ ከተማው እንደተመለሰ፣ ተራበ። 19 በመንገድ ዳር አንዲት የበለስስ ተክል አየና ወደ እርሷ ሄደ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። “ሁለተኛ ከቶ ፍሬ አይገኝብሽ” አላት። የበለስ ተክሊቱም ወዲያውኑ ደረቀች። 20 ደቀ መዛሙርቱ ባዩአት ጊዜ ተደንቀው፣ “የበለስ ተክሊቱ እንዴት ወዲያውኑ ደረቀች?” አሉ። 21 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፣ እምነት ቢኖራችሁና ባትጠራጠሩ፣ በዚች የበለስ ተክል የሆነባትን ብቻ ሳይሆን፣ ይህን ኮረብታ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት እንኳ ይሆናል። 22 አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ።” 23 ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ መጥተው፣ “በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉ። 24 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ደግሞ አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ። ያንን ከነገራችሁኝ እኔ ደግሞ በማን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ እነግራችኋለሁ። 25 የዮሐንስ ጥምቀት ከየት መጣ ከሰማይ ነውን ወይስ ከሰዎች?” እርስ በርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋገሩ፤ “ከሰማይ ነው ብንለው፣ ‘ለምን አታምኑትም?’ ይለናል። 26 ነገር ግን ‘ከሰው ነው ብንል፣ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ስለሚያዩት ሕዝቡን እንፈራለን።” 27 ከዚያም መልሰው ኢየሱስን፣ “አናውቅም” አሉት። እርሱ ደግሞ፣ “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው። 28 ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፣ ወደ መጀመሪያው ሄዶ፣ ልጄ ሆይ፣ ዛሬ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሄደህ ሥራ’ አለው። 29 ልጁ መልሶ፣ ‘አልሄድም’ አለ፤ በኋላ ግን ዐሳቡን ለውጦ ሄደ። 30 ሰውዬውም ወደ ሁለተኛው ልጅ ሄዶ ይህንኑ ነገረው። ይህኛው ልጅ መልሶ፣ ‘እሄዳለሁ፣ አባዬ’ አለ። ነገር ግን አልሄደም። 31 ከሁለቱ ልጆች የአባቱን ትእዛዝ የፈጸመው የትኛው ነው? እነርሱ፣ "የመጀመሪያው” አሉ። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ቀድመዋችሁ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባሉ። 32 ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ ወደ እናንተ መጥቶ ነበርና፤ እናንተ ግን አላመናችሁትም፤ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ግን አመኑት። እናንተም ይህ ሲሆን አይታችሁ ታምኑት ዘንድ በኋላ እንኳ ንሰሐ አልገባችሁም። 33 ሌላም ምሳሌ ስሙ። ሰፊ መሬት ያለው አንድ ሰው ነበር። የወይን አትክልት ተከለ፤ ዐጥር አጠረለት፤ የወይን መጥመቂያ ማሰለት፤ መጠበቂያ ማማ ሠራለት፤ ለወይን ገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። 34 የወይን ፍሬ የሚሰበሰብበት ጊዜ እንደ ደረሰ፣ ፍሬውን እንዲቀበሉ ጥቂት አገልጋዮችን ላከ። 35 የወይኑ ገበሬዎች ግን አገልጋዮቹን ያዙ፤ አንዱን ደበደቡት፣ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውንም በድንጋይ ወገሩት። 36 ባለቤቱ እንደ ገና ከፊተኞቹ የበዙ ሌሎች አገልጋዮችን ላከ፤ ነገር ግን የወይን ገበሬዎቹ ያንኑ አደረጉባቸው። 37 ከዚያ በኋላ ባለቤቱ፣ ‘ልጄንስ ያከብሩታል’ በማለት የገዛ ልጁን ላከ። 38 የወይን ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ፣ እርስ በርሳቸው፣ 'ይህ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ። 39 ስለዚህ ያዙትና ከወይኑ አትክልት ስፍራ ወደ ውጭ ጣሉት፤ ገደሉትም። 40 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ባለቤት በሚመጣበት ጊዜ እነዚያን የወይን ገበሬዎች ምን ያደርጋቸዋል?” 41 ሕዝቡ እንዲህ አሉት፤ “እነዚያን ክፉ ሰዎች እጅግ በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ ያጠፋቸዋል፤ ከዚያም የወይኑን አትክልት ስፍራ ወይኑ በሚያፈራበት ጊዜ ገንዘቡን ለሚከፍሉ ለሌሎች የወይን ገበሬዎች ያከራየዋል።” 42 ኢየሱስ እነርሱን፣ “ 'ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነ። ይህ ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው ተብሎ የተጻፈውን ፈጽሞ አላነበባችሁም?’ 43 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰድና ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች። 44 በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይሰባበራል። ድንጋዩ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ይፈጨዋል።” 45 የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ፣ የተናገረው ስለ እነርሱ እንደ ሆነ ተረዱ። 46 ነገር ግን ሊይዙት በፈለጉ ጊዜ ሁሉ፣ ሰዎቹ እንደ ነቢይ ይቈጥሩት ስለ ነበር ሕዝቡን ፈሩ።



Matthew 21:1

ማቴዎስ 21፡1-3

ቤተ ፋጌ መንደር
ውርንጭላ "ትንሽ ወንድ አህያ"

Matthew 21:4

ማቴዎስ 21፡4-5

ይህ በነቢያት የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው "እግዚአብሔር ስለዚህ ጉዳይ ከብዙ ዘመናት በፊት በነቢያ አማካኝነት ምን እንደሚሆን ተናግሮ ነበር” በነቢያት የተነገረው ነገር "ነገሩ ከመፈጸሙ በፊት ነቢያት አስቀድመው የተናገሩት ነገር” የጽዮን ሴት ልጅ እስራኤል አህያ ድሆች የሚጋልቡት እንስሳ ውርንጭላ ትንሽ ወንድ አህያ

Matthew 21:6

ማቴዎስ 21፡6-8

ጨርቅ ከውጪ የሚደረብ ወይም ረጅም ኮት ኢየሱስ በዚያ ተቀመጠ "አህያይቱን ጨርቅ አልብሰው ኢየሱስ በዚያ ላይ እንዲቀመጥ አደረጉ"

Matthew 21:9

ማቴዎስ 21፡9-11

ሆሣዕና ይህ የዕብራይስጥ ቃል ሲሂን ትርጉሙም “አድነን” ማለት ነው ይሁን እንጂ “እግዚአብሔር ይመስገንም” መሆን ይችላል፡፡ ከተማው ሁሉ ተናወጠ "በከተማይቱ ውስጥ ያሉ ሁሌ እርሱን ለማየት ጓግተው ነበር" ከተማው ሁሉ "በከተማይቱ ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች"

Matthew 21:12

ማቴዎስ 21፡12-14

እንዲህ አላቸው "ገንዘብ ለዋጮቹን እና የተለያዩ ነገሮችን የሚገዙትን እና የሚሸጡትን ሰዎች" የጸሎት ቤት "ሰዎች የሚጸልዩበት ሥፍራ" የወንበዴዎች ዋሻ "እንደ ወንበዴዎች መሸሸጊያ ዋሻ” አንካሳ በጣም ከመጎዳታቸው የተነሳ መራመድ የማይችሉ ሰዎች

Matthew 21:15

ማቴዎስ 21፡15-17

ሆሣዕና በ MAT 21:09 ላይ ምን ብለህ እንደተረጎምው ተመልከት፡፡ የዳዊት ልጅ በ MAT 21:09 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ ተቆጡ "ኢየሱስን ጠሉት እንዲሁም በጣም ተበሳጩበት" እነዚህ ሰዎች የሚሉትን አትሰማምን? "ሰዎች ስለአንተ እንዲህ ዓይነት ንግግር እንዲያደርጉ ልትፈቅድላቸው አይገባም!" ይሁን እንጂ ፈጽሞ አላነበባችሁምን . . . ምስጋና'? "አዎ አየሰማኋቸው ነው ይሁን እንጂ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያነበባችሁት ማስታወስ ይገባችሁ ነበር . . . ምሳጋና" ኢየሱስ ትቷቸው ሄደ "ኢየሱስ የካህናት አለቆችንና ጸሐፊትን ትቶ ሄደ"

Matthew 21:18

ማቴዎስ 21፡18-19

ደረቀ "ሞተ" ማቴዎስ 21፡20-21

እምነት ካላችሁና የማትጠራጠሩ ከሆነ እነዚህ ሁለት ሀረጎች የሚስተላልፉት ተመሳሳይ ሀሳብ ነው፡፡ ሁለት ጊዜ የተጻፈው አጽኖት ለመስጠት ነው፡፡ በአንዳንድ ቋንቋዎች ውስጥ አጽኖት መስጫ ሌላ መንገድ አለ፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “በእርግጥ ካመናችሁ” ወዲያው ደረቀ "ደርቆ ሞተ"

Matthew 21:20

ማቴዎስ 21፡20-21

እምነት ካላችሁና የማትጠራጠሩ ከሆነ እነዚህ ሁለት ሀረጎች የሚስተላልፉት ተመሳሳይ ሀሳብ ነው፡፡ ሁለት ጊዜ የተጻፈው አጽኖት ለመስጠት ነው፡፡ በአንዳንድ ቋንቋዎች ውስጥ አጽኖት መስጫ ሌላ መንገድ አለ፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “በእርግጥ ካመናችሁ” ወዲያው ደረቀ "ደርቆ ሞተ"

Matthew 21:23

ማቴዎስ 21፡23-24

Matthew 21:25

ማቴዎስ 21፡28-30

ማቴዎስ 21፡25-27

ከሰማይ "በሰማይ ካለው እግዚአብሔር” እንዲህ ይለናል "ኢየሱስ እንዲህ ይለናል" ሕዝቡን ፈራን "ሕዝቡ ምን እንደሚያስብ ፈራን ወይም ምን እንደሚያደርግብን ፈራን" ዮሐንስን ነብይ አድርገው ይቆጥሩት ነበር "ዮሐንስ ነብይ እንደሆነ ያምኑ ነበር"

Matthew 21:28

ማቴዎስ 21፡28-30

Matthew 21:31

ማቴዎስ 21፡31-32

እንዲህ አሉ "የካህናት አለቆችና ሽምግሌዎች እንዲህ አሉ" ኢየሱስ አንዲህ አላቸው "ኢየሱስ ለካህናት አለቆችና ለሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው" ዮሐንስ ወደ እናንተ መጣ ዮሐንስ ወደ ሃይማኖት መሪዎች እና ሕዘቡ መጥቶ ሰበከ፡፡ በጽድቅን መንገድ ዮሐንስ ሰዎች እንዴት ለእግዚአብሔት ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው እና መኖር እንዳለባቸው አሳየ

Matthew 21:33

ማቴዎስ 21፡33-34

ትልቅ መሬት ያለው አንድ ሰው "ብዙ ሀብት ያለው አንድ ሰው" ለወይን ተካዮች መሬቱን አከራየ "ወይን የሚያመርቱ ሰዎችን በቦታው ላይ ሾመ” የወይን እርሻው ባለቤት ግን አሁንም ቢሆን የመሬቱ ባለቤት ነው፡፡ የወይን ተክል የሚተክሉ ሰዎች ወይንን እንዴት መትከል እና ማሳደግ እንደሚቻል የሚያውቁ ሰዎች

Matthew 21:35

ማቴዎስ 21፡35-37

ሠራተኞችን የመሬቱ ባለቤት ሠራተኞች (MAT 21:33)

Matthew 21:38

ማቴዎስ 21፡ 38-39

Matthew 21:40

ማቴዎስ 21፡40-41

ሰዎች እንዲህ አሉት "ሕዝቡ ለኢየሱስ እንዲህ አሉት"

Matthew 21:42

ማቴዎስ 21፡42-42

ኢየሱስ እንዲህ አላቸው "ኢየሱስ ለሕዝቡ እንዲህ ብሎ ተናገረ" (MAT 21:41) ግንበኞች የናቁት ድንጋጥ የማዕዘን ራስ ሆነ፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "በአናጽዋች የናቁት ድንጋይ በጣም አስፈላጊው ድንጋይ ሆነ፡፡” ባለስልጣናቱ ኢየሱስን ባይቀበሉትም ነገር ግን እግዚአብሔር የመንግስቱ ራስ ያደርገዋል፡፡ “ ይህ ከጌታ ነው "ይህንን ታላቅ ለውጥ ያመጣው ጌታ ነው"

Matthew 21:43

ማቴዎስ 21፡43-44

እላችኋለሁ ኢየሱስ ለካህናት አለቆች እና ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፡፡ ፍሬውን ተንከባቡ "ትክክለኛውን ነገር አድርጉ ፍሬውን "የእግዚአብሔር መንግስ ፍሬ" በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ማንም ሰው "በዚህ ድንጋይ የሚሰናከል ማንም ቢኖር የሚወድቅበት ማንም ሰው "ፍርዱ የሚመጣበት ማንም ሰው

Matthew 21:45

ማቴዎስ 21፡45-46

የእርሱ ምሳሌዎች "የኢየሱስ ምሳሌዎች" እጃቸውን በእርሱ ላይ አኖሩ "አሰሩት"


Translation Questions

Matthew 21:1

በአንጻራቸው ባለው መንደር ውስጥ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ምን እንደሚያገኙ ኢየሱስ ተናገረ?

የታሰረች አህያ ከውርንጫዋ ጋር ሆና እንደሚያገኙ ኢየሱስ ተናገረ። [21:2]

Matthew 21:4

ስለዚህ ክስተት ነብዩ ምን ተንብዮ ነበር?

ንጉሥ በአህያ እና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ እንደሚመጣ ነብዩ ተንብዮ ነበር። [21:4]

ስለዚህ ክስተት ነብዩ ምን ተንብዮ ነበር?

ንጉሥ በአህያ እና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ እንደሚመጣ ነብዩ ተንብዮ ነበር። [21:5]

Matthew 21:6

ኢየሱስ ይጓዝበት በነበረው ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ላይ ሕዝቡ ምን አደረጉ?

ሕዝቡ ከላይ የደረቡትን ልብስ ያነጥፉ፣ የዛፍ ቅርንጫፎችንም በመንገዱ ላይ ያኖሩ ነበር። [21:8]

Matthew 21:9

ኢየሱስ ሲያልፍ ሕዝቡ ምን እያሉ ጮኹ?

ሕዝቡ፣ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም” እያሉ ጮኹ። [21:9]

Matthew 21:12

ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው የእግዚአብሔር መቅደስ በገባ ጊዜ ኢየሱስ ምን አደረገ?

በመቅደስ ውስጥ ይገዙ እና ይሸጡ የነበሩትን ኢየሱስ አስወጣቸው፣ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛ እና የእርግብ ሻጮችን መቀመጫዎች ገለበጠ። [21:12]

ነጋዴዎቹ የእግዚአብሔርን መቅደስ ምን እንዳደረጉት ኢየሱስ ተናገረ?

ነጋዴዎቹ የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ የወንበዴዎች ዋሻ እንዳደረጉት ኢየሱስ ተናገረ። [21:13]

Matthew 21:15

ሊቀ ካህኑ እና ጸሐፍት ልጆቹ ስለ ኢየሱስ ይጮኹ የነበሩትን በተቃወሙ ጊዜ፣ ኢየሱስ ምን አላቸው?

እግዚአብሔር ከሕጻናቱ እና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራሱ እንዳዘጋጀ ነብዩ የተናገረውን ኢየሱስ ጠቀሰ። [21:15]

ሊቀ ካህኑ እና ጸሐፍት ልጆቹ ስለ ኢየሱስ ይጮኹ የነበሩትን በተቃወሙ ጊዜ፣ ኢየሱስ ምን አላቸው?

እግዚአብሔር ከሕጻናቱ እና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራሱ እንዳዘጋጀ ነብዩ የተናገረውን ኢየሱስ ጠቀሰ። [21:16]

Matthew 21:18

ኢየሱስ በበለስ ዛፏ ላይ ምን አደረገ፣ ለምን?

በላዩዋ ላይ ፍሬ ስላልነበራት ኢየሱስ የበለስ ዛፏ እንድትደርቅ አደረገ። [21:18]

ኢየሱስ በበለስ ዛፏ ላይ ምን አደረገ፣ ለምን?

በላዩዋ ላይ ፍሬ ስላልነበራት ኢየሱስ የበለስ ዛፏ እንድትደርቅ አደረገ። [21:19]

Matthew 21:20

ከምትደርቀው የበለስ ዛፍ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ስለ ጸሎት ምን አስተማራቸው?

አምነው በጸሎት ቢጠይቁ እንደሚቀበሉ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ አስተማራቸው። [21:20]

ከምትደርቀው የበለስ ዛፍ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ስለ ጸሎት ምን አስተማራቸው?

አምነው በጸሎት ቢጠይቁ እንደሚቀበሉ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ አስተማራቸው። [21:21]

ከምትደርቀው የበለስ ዛፍ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ስለ ጸሎት ምን አስተማራቸው?

አምነው በጸሎት ቢጠይቁ እንደሚቀበሉ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ አስተማራቸው። [21:22]

Matthew 21:23

ኢየሱስ በሚያስተምርበት ጊዜ፣ ሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ የጠየቁት ስለምን ነበር?

ሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው በምን ሥልጣን እንደሆነ ማወቅ ፈለጉ። [21:23]

Matthew 21:25

በምላሹ ኢየሱስ ለሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ ምን ጥያቄ ጠየቃቸው?

መጥምቁ ዮሐንስ ከሰማይ ወይስ ከሰው እንደሆነ የሚያስቡትን ጠየቃቸው። [21:25]

ሊቀ ካህናቱ እና ጸሐፍት መጥምቊ ዮሐንስ ከሰማይ ነው ብለው መመለስ ያልፈለጉት ለምን ነበር?

ቀጥሎ ለምን በዮሐንስ እንዳላመኑ ኢየሱስ እንደሚጠይቃቸው ያውቁ ነበር። [21:25]

ሊቀ ካህናቱ እና ጸሐፍት የመጥምቊ ዮሐንስ ጥምቀት ከሰው ነው ብለው መመለስ ያልፈለጉት ለምን ነበር?

ዮሐንስ ነብይ ነው ብለው የሚያምኑትን ሕዝብ ፈሩ። [21:26]

Matthew 21:28

ስለ ሁለቱ ልጆች ኢየሱስ በተናገረው ታሪክ ውስጥ በወይኑ እርሻ ውስጥ ሄዶ እንዲሠራ በተነገረው ጊዜ የመጀመሪያው ልጅ ምን አደረገ?

የመጀመሪያው ልጅ እንደማይሄድ ተናገረ፣ ነገር ግን አሳቡን ቀይሮ ሄደ። [21:28]

ስለ ሁለቱ ልጆች ኢየሱስ በተናገረው ታሪክ ውስጥ በወይኑ እርሻ ውስጥ ሄዶ እንዲሠራ በተነገረው ጊዜ የመጀመሪያው ልጅ ምን አደረገ?

የመጀመሪያው ልጅ እንደማይሄድ ተናገረ፣ ነገር ግን አሳቡን ቀይሮ ሄደ። [21:29]

በወይኑ ተክል ውስጥ እንዲሠራ በተነገረው ጊዜ ሁለተኛው ልጅ ምን አደረገ?

ሁለተኛው ልጅ እንደሚሄድ ተናገረ፣ ነገር ግን ሳይሄድ ቀረ። [21:30]

Matthew 21:31

የአባቱን ፈቃድ ያደረገው ከሁለቱ የትኛው ልጅ ነው?

የመጀመሪያው። [21:31]

ከሊቀ ካህናት እና ጸሐፍት በፊት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ግብር ሰብሳቢዎች እና ጋለሞታዎች ይቀድማሉ ሲል ኢየሱስ የተናገረው ለምን ነበር?

እነርሱ ዮሐንስን አምነውበት ስለነበር፣ ነገር ግን ሊቀ ካህናቱ እና ጸሐፍቱ በዮሐንስ ስላላመኑ እነዚያ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንደሚገቡ ኢየሱስ ተናገረ። [21:31]

ከሊቀ ካህናት እና ጸሐፍት በፊት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ግብር ሰብሳቢዎች እና ጋለሞታዎች ይቀድማሉ ሲል ኢየሱስ የተናገረው ለምን ነበር?

እነርሱ ዮሐንስን አምነውበት ስለነበር፣ ነገር ግን ሊቀ ካህናቱ እና ጸሐፍቱ በዮሐንስ ስላላመኑ እነዚያ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንደሚገቡ ኢየሱስ ተናገረ። [21:32]

Matthew 21:35

የወይን ፍሬውን እንዲያመጡለት ባለቤቱ በላካቸው አገልጋዮች ላይ ሠራተኞቹ ምን አደረጉባቸው?

የወይን እርሻ ሠራተኞቹ አገልጋዮቹን መትተው፣ ገደሏቸው፣ ወገሯቸውም። [21:35]

የወይን ፍሬውን እንዲያመጡለት ባለቤቱ በላካቸው አገልጋዮች ላይ ሠራተኞቹ ምን አደረጉባቸው?

የወይን እርሻ ሠራተኞቹ አገልጋዮቹን መትተው፣ ገደሏቸው፣ ወገሯቸውም። [21:36]

የእርሻው ባለቤት በስተመጨረሻ ወደ ወይን እርሻው ሠራተኞች የላከው ማንን ነው?

ባለቤቱ በስተመጨረሻ የገዛ ልጁን ላከ። [21:37]

Matthew 21:38

የወይኑ እርሻ ሠራተኞች ባለቤቱ በስተመጨረሻ በላከው ሰው ላይ ምን አደረጉበት?

የወይን እርሻ ሠራተኞቹ የባለቤቱን ልጅ ገደሉት። [21:38]

የወይኑ እርሻ ሠራተኞች ባለቤቱ በስተመጨረሻ በላከው ሰው ላይ ምን አደረጉበት?

የወይን እርሻ ሠራተኞቹ የባለቤቱን ልጅ ገደሉት። [21:39]

Matthew 21:40

የወይኑ ባለቤት ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለበት ሰዎች ተናገሩ?

ባለቤቱ የመጀመሪያዎቹን የወይኑ እርሻ ቅጥረኞች ማጥፋት እና ከዚያም ለሚከፍሉ ሌሎች የወይን እርሻ ሠራተኞች ማከራየት እንዳለበት ተናገሩ። [21:40]

የወይኑ ባለቤት ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለበት ሰዎች ተናገሩ?

ባለቤቱ የመጀመሪያዎቹን የወይኑ እርሻ ቅጥረኞች ማጥፋት እና ከዚያም ለሚከፍሉ ሌሎች የወይን እርሻ ሠራተኞች ማከራየት እንዳለበት ተናገሩ። [21:41]

Matthew 21:42

ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በጠቀሰው የቅዱሳት መጻሐፍት ክፍል ውስጥ ግንበኞች በናቊት ድንጋይ ላይ ምን ሆነ?

ግንበኞች የናቊት ድንጋይ የማእዘን ራስ ሆነ። [21:42]

Matthew 21:43

ኢየሱስ በጠቀሰው የቅዱሳት መጻሐፍት ክፍል መሠረት፣ ምን እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ?

የእግዚአብሔር መንግሥት ከሊቀ ካህናት እና ፈሪሳውያን እንደሚወሰድ፣ ከዚያም ፍሬ ለሚያፈሩ ሕዝቦች እንደሚሰጥ ኢየሱስ ተናገረ። [21:43]

Matthew 21:45

ሊቀ ካህናት እና ፈሪሳውያን ወዲያውኑ በኢየሱስ ላይ እጃቸውን ያልጫኑት ለምን ነበር?

ሕዝቡ ኢየሱስን እንደ ነብይ ያዩት ስለ ነበረ፣ ሕዝቡን ፈርተው ነበር። [21:46]


ምዕራፍ 22

1 ኢየሱስም ደግሞ እንዲህ በማለት በምሳሌ መለሰላቸው፤ 2 "መንግሥተ ሰማይ ለልጁ የሰርግ ድግስ የደገሰ ንጉሥን ትመስላለች፡፡ 3 ወደ ሰርጉ እንዲመጡ ወደ ጋበዛቸው ሰዎች አገልጋዮቹን ላከ፤ እነርሱ ግን መምጣት አልፈለጉም፡፡ 4 እንደ ገና ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንዲህ በማለት ላከ፤ "እነሆ፣ እራት አዘጋጅቻለሁ፤ በሬዎቼንና የሰቡ ወይፈኖቼን አርጃለሁ፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአልና ወደ ሰርግ ግብዣው ኑ በሏቸው፡፡' " 5 ሰዎቹ ግን ግብዣውን ከልብ አልተቀበሉትም፡፡ አንዳንዶቹ ወደ እርሻዎቻቸው፣ ሌሎች ደግሞ ወደ ሥራ ቦታቸው ሄዱ፡፡ 6 አንዳንዶቹ የንጉሡን አገልጋዮች ደበደቡአቸው፤ አዋረዱአቸው፤ ገደሉአቸው፡፡ 7 ንጉሡ ግን ተቈጣ፤ ወታደሮቹን ላከ፤ እነዚያን ነፍሰ ገዳዮች ገደለ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ፡፡ 8 ከዚያም ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፤ 'ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎች ግን የሚገባቸው ሆነው አልተገኙም፡፡ 9 ስለዚህ ወደ ዐውራ መንገድ ማቋረጫ ሄዳችሁ የምታገኙአቸውን ያህል ሰዎች ወደ ሰርጉ ግብዣ ጥሩ፡፡ 10 ሰዎቹም ወደ ዐውራው መንገድ ሄደው መልካምም ሆኑ መጥፎዎች ያገኙአቸውን ሁሉ አንድ ላይ ሰበሰቡ፡፡ ስለዚህ የግብዣው አዳራሽ በተጋባዦች ተሞላ፡፡ 11 ንጉሡ ተጋባዦቹን ለማየት ሲመጣ ግን፣ የሰርግ ልብስ ያልለበሰ ሰው አየ፡፡ 12 ንጉሡ እንዲህ አለው፤ ‹ወዳጄ፣' የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?› ሰውየውም ዝም አለ፡፡ 13 ከዚያም ንጉሡ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አላቸው፤ እጅና እግሩን አስራችሁ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት፡፡' 14 የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡" 15 ከዚያም ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስን እንዴት በንግግሩ ማጥመድ እንደሚችሉ ዕቅድ አወጡ፡፡ 16 ከዚያም ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ደቀ መዛሙርታቸውን ወደ እርሱ ላኩ፡፡ ኢየሱስንም እንዲህ አሉት፤ "መምህር ሆይ፣ አንተ በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ የምታስተምር እውነተኛ ሰው መሆንህን እናውቃለን፤ ሰውን በመፍራት ዐሳብህን አትለውጥም፤ በሰዎች መካከል አድልዎ አታደርግም፡፡ 17 እስቲ ንገረን ምን ይመስልሃል? ለቄሳር ግብር መስጠት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?" 18 ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ "እናንት ግብዞች የምትፈትኑኝ ለምንድን ነው? 19 እስቲ የግብሩን ገንዘብ አሳዩኝ" አላቸው፡፡ እነርሱም ዲናሩን አመጡለት፡፡ 20 ኢየሱስም፣ "ይህ የማን መልክና ስም ነው?›› አላቸው፡፡ 21 እነርሱም፣ "የቄሣር፣" አሉት፡፡ ከዚያም ኢየሱስ፣ "እንግዲያስ የቄሣር የሆነውን ለቄሣር ስጡ፤ የእግዚአብሔር የሆነውን ለእግዚአብሔር ስጡ" አላቸው፡፡ 22 ያንን ሲሰሙ ተገረሙ፡፡ ትተውትም ሄዱ፡፡ 23 በዚያው ቀን ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ጥቂት ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጡ፡፡ 24 "መምህር ሆይ፣ ‹አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሞተ ሚስቱን ወንድሙ እንዲያገባና ለወንድሙ ልጅ እንዲወልድለት ሙሴ ተናግሮአል› 25 ሰባት ወንድማማች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፡፡ ሚስቱ የወንድምየው ሆነች፡፡ 26 ሁለተኛውና ሦስተኛውም እስከ ሰባተኛው ድረስ ያንኑ አደረጉ፡፡ 27 ከሁሉም በኋላ ደግሞ ሴትየዋ ሞተች፡፡ 28 እንግዲህ ሰባቱም ወንድማማች አግብተዋት ነበርና በትንሣኤ ቀን የማንኛው ሚስት ልትሆን ነው?" በማለት ጠየቁት፡፡ 29 ኢየሱስ ግን እንዲህ በማለት መለሰላቸው፤ "መጻሕፍትንም ሆነ የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታወቁ ተሳስታችኋል፡፡ 30 ምክንያቱም በትንሣኤ ቀን እንደ ሰማይ መላእክት ይሆናሉ እንጂ፣ አያገቡም፣ ደግሞም አይጋቡም፡፡ 31 ትንሣኤ ሙታንን በተመለከተ፣ እግዚአብሔር 32 "እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ" በማለት ለእናንተ የተናገረውን አላነበባችሁምን? እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ እንጂ፣ የሙታን አምላክ አይደለም፡፡" 33 ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡ 34 ኢየሱስ ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው ፈሪሳውያን ሲሰሙ፣ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ 35 ከእነርሱ መካከል ሕግ ዐዋቂ የሆነ አንዱ እርሱን ለመፈተን፣ 36 "መምህር ሆይ፣ ከሕጉ ሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው ነው" ብሎ ጠየቀው፡፡ 37 ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ "እግዚአብሔር አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ ዐሳብህ ውደድ፡፡" 38 ከሁሉም የሚበልጠው የመጀመሪያው ትእዛዝ ይህ ነው፡፡ 39 ሁለተኛውም ትእዛዝ ያንኑ ይመስላል፤ 'ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡' 40 ሕግና ነቢያት ሁሉ የትመሠረቱት በእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ላይ ነው፡፡ 41 ፈሪሳውያን በአንድነት ተሰብስበው እያለ ኢየሱስ አንድ ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡ 42 "ስለ ክርስቶስ ምን ታስባላችሁ? ለመሆኑ የማን ልጅ ነው?" አላቸው፡፡ "የዳዊት ልጅ ነው" አሉት፡፡ 43 ኢየሱስም፣ "ታዲያ፣ ዳዊት፣ በመንፈስ፣ 44 ጌታ ጌታዬን ‹ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ' በማለት እንዴት ጌታ ብሎ ይጠራዋል? 45 ዳዊት ክርስቶስን 'ጌታ' በማለት ከጠራው እንዴት የዳዊት ልጅ ሊሆን ይችላል?" 46 ማንም አንዲት ቃል ሊመልስለት አልቻለም፤ ከዚያ ቀን ጀምሮ ጥያቄ ሊያቀርብለት የደፈረ አልነበረም፡፡



Matthew 22:1

ማቴዎስ 22፡1-3

መንግሰተ ሰማያት . . . ትመስላለችThe kingdom of heaven is like በ MAT 13:24 ላይ ምን ብለህ እንደተረጎምህ ተመልከት የተጋበዙት ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ንጉሡ የጋበዛቸው ሰዎች

Matthew 22:4

ማቴዎስ 22፡4-4

Matthew 22:5

ማቴዎስ 22፡5-7

እነዚህ ሰዎች "የተጋበዙት እንግዶች" (MAT 22:4) ግብዣውን ከቁም ነገር አልቆጠሩትም "የእርሱን ግብዣ ቸል አሉት"

Matthew 22:8

ማቴዎስ 22፡8-10

የማቋረጫ መንገድ "መንገዶች የሚገናኙበት ቦታ" አደራሽ ትልቅ ክፍል

Matthew 22:11

ማቴዎስ 22፡11-12

Matthew 22:13

ማቴዎስ 22፡13-14

Matthew 22:15

ማቴዎስ 22፡15-17

ኢየሱስ በሚናገርበት ወቅት እንዴት ያቋርጡት ነበር "ኢየሱስ አንድ ነገር ስናገር በየመኃሉ እያቋረጡት ለክስ የሚሆናቸውን ነገር ለማግኘት ጥረት ያደርጉ ነበር፡፡” ከሄሮዶስ ወገን ከሮማዊያን አገዛዝ ጋር ጓድኛ የሆነው የአይሁድ ንጉሥ የሆነው የሄሮዶስ ተወካዮች እና ተከታዮች በሰዎች መካከል ልዩነት አታደረግም "ለሰዎች የተለየ አክብሮት አትሰጥም " ወይም "በጣም ጠቃሚ ለሚባሉ ሰዎች ትኩርት አትሰጥም"

Matthew 22:18

ማቴዎስ 22፡18-19

ዲናር የአንድ ቀን ደሞዝ የሆነ የሮማዊን ገንዘብ ነው

Matthew 22:20

ማቴዎስ 22፡20-22

የቄሳርን "የቄሳር የሆነው ነገር የእግዚአብሔርን "የእግዚአብሔር የሆነውን ነገር"

Matthew 22:23

ማቴዎስ 22፡23- 24

መምህር ሙሰተ እንዲህ ብሏል “አንድ ሰው ከሞተ ሙሴ በቅዱሳት መጽሕፍት ውስጥ ስለጻፈው ነገር ጠየቁት፡፡ በቋንቋችሁ ውስጥ በትቅስ ውስጥ ሌላ ትቅስ መጻፍን የማይፈቅድላችሁ ከሆነ በተዘዋዋር መንገድ ሀሳቡን መግለጽ ትችላላችሁለ “ሙሴ አንድ ሰው ከሞት” (ተመልከት ወንድሙ . . . ምስቱ . . ወንድሙ የሞተው ሰው

Matthew 22:25

ማቴዎስ 22፡25-28

ሁሉም አንዱ ከሌላኛው በኋላ "የሰውዬው ወንድሞች ሁሉ እርሷን ካገቡ በኋላ ሞቱ” ወይም “ሁሉም ወንድሞቹ ከሞቱ በኋላ”

Matthew 22:29

X

ማቴዎስ 22፡29-30 የእግዚአብሔርን ኃይል "እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንደሚችል"

Matthew 22:31

ማቴዎስ 22፡31-33

እንዲህ የሚል ነገር አላነበባችሁምን . . . ያዕቆብ? "እንዳነበባችሁ አውቃለሁ ነገር ግን ያዕቆብ . . . የሚለውን የተረዳችሁት ግን አይመስልም” በ . . . ለእናንተ የተነገረው "እገዚአብሔር ለእናንተ የተናገረው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “እኔ . . . ያዕቆብ”? ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ነው፡፡ “እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለው፡፡ እኔ እግዚአብሔር የአብረሃም አምላ፣ የይሳቅ አምላክ እና የያዕቆብ አምላክ ነኝ፡፡”

Matthew 22:34

ማቴዎስ 22፡34-36

የሕግ ባለሞያዎች የሙሴን ሕግ ጠንቅቀው የሚያውቁት ፈሪሳዊያን

Matthew 22:37

ማቴዎስ 22፡37-38

Matthew 22:39

ማቴዎስ 22፡39-40

ወደዱት ሕግጋቱን ወደዱት MAT 22:37.

Matthew 22:41

X

ማቴዎስ 22፡41-42

Matthew 22:43

ማቴዎስ 22፡43-44

ጠላቶችህን የእግር መረገጫ እስካደረግ ድረስ "ጠላቶችን እስካጠፋቸው ድረስ”

Matthew 22:45

ማቴዎስ 22፡45-46

ዳዊት ክርስቶስን “ጌታዬ” ብሎ ከጠራው እንዴት እርሱ የዳዊት ልጅ ሊሆን ይችላል? ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ዳዊት ጌታዬ ብሎ ጠርቶታል ስለዚህ ክርስቶስ ከዳዊት ዘር በላይ ነው ማለት ነው፡፡” ዳዊት ክርስቶስን እንዲህ ብሎ ከጠራው ዳዊት ክርስቶስን “ጌታዬ” ብሎ ከጠራው፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ክርስቶስ የዳዊት ዘር የሆነ ብቻ ሳይን ከዚያም በላይ የሆነ ነው፡፡


Translation Questions

Matthew 22:5

ወደ ንጉሡ ልጅ የሠርግ ድግሥ ተጋብዘው የነበሩት የንጉሡ አገልጋዮች ግብዣውን ባመጡ ጊዜ ምን አደረጉ?

አንዳንዶች ግብዣውን ከልባቸው አልተቀበሉም ነበርና ወደ ገዛ ሥራቸው ሄዱ፣ ሌሎች በንጉሡ አገልጋዮች ላይ እጆቻቸውን በመጫን ገደሏቸው። [22:5]

ወደ ንጉሡ ልጅ የሠርግ ድግሥ ተጋብዘው የነበሩት የንጉሡ አገልጋዮች ግብዣውን ባመጡ ጊዜ ምን አደረጉ?

አንዳንዶች ግብዣውን ከልባቸው አልተቀበሉም ነበርና ወደ ገዛ ሥራቸው ሄዱ፣ ሌሎች በንጉሡ አገልጋዮች ላይ እጆቻቸውን በመጫን ገደሏቸው። [22:6]

ወደ ሠርጉ ድግሥ ለተጋበዙት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ንጉሡ ምን አደረገላቸው?

ንጉሡ ሠራዊቱን ልኮ፣ እነዚያን ነፍሰ-ገዳዮች ገደላቸው፣ ከተሞቻቸውንም አቃጠለ። [22:7]

Matthew 22:8

ከዚያ በኋላ ንጉሡ እነማንን ወደ ሠርጉ ድግሥ ጋበዘ?

ከዚያ በኋላ ንጉሡ የእርሱ አገልጋዮች ሊያገኟቸው የቻሉትን ያክል መጥፎም ሆነ ጥሩ ሰዎችን ጋበዙ። [22:9]

ከዚያ በኋላ ንጉሡ እነማንን ወደ ሠርጉ ድግሥ ጋበዘ?

ከዚያ በኋላ ንጉሡ የእርሱ አገልጋዮች ሊያገኟቸው የቻሉትን ያክል መጥፎም ሆነ ጥሩ ሰዎችን ጋበዙ። [22:10]

Matthew 22:13

የሠርግ ልብስ ሳይለብስ ወደ ድግሡ በመጣው ሰው ላይ ንጉሡ ምን አደረገ?

ንጉሡ እንዲታሠር እና በውጭ ወዳለው ጨለማ እንዲጣል አስደረገ። [22:13]

Matthew 22:15

ፈሪሳውያን በኢየሱስ ላይ ምን ለማድረግ እየሞከሩ ነበር?

ፈሪሳውያኑ ኢየሱስን በገዛ ራሱ ንግግር ለማጥመድ እየሞከሩ ነበር። [22:15]

የፈሪሳውያኑ ደቀመዛሙርት ኢየሱስን የጠየቁት ጥያቄ ምን ነበር?

ለቄሳር ግብር መክፈል ተፈቅዶ እንደሆን ወይም እንዳልሆነ ኢየሱስን ጠየቁት። [22:17]

Matthew 22:20

ከፈሪሳውያን ደቀመዛሙርት የቀረበለትን ጥያቄ ኢየሱስ የመለሰው እንዴት ነበር?

የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር እንዲሰጡ ኢየሱስ ተናገረ። [22:21]

Matthew 22:23

ትንሣኤን በተመለከተ ሰዱቃውያን ምን እምነት ነበራቸው?

ትንሣኤ የሚባል እንደሌለ ሰዱቃውያኑ ያምኑ ነበር። [22:23]

Matthew 22:25

በሰዱቃውያኑ ታሪክ ውስጥ፣ አንዲት ሚስት ስንት ባሎች አሏት?

ሴቲቱ ሰባት ባሎች ነበሯት። [22:26]

በሰዱቃውያኑ ታሪክ ውስጥ፣ አንዲት ሚስት ስንት ባሎች አሏት?

ሴቲቱ ሰባት ባሎች ነበሯት። [22:27]

Matthew 22:29

ሰዱቃውያኑ ያላወቋቸው ሁለት ነገሮች ምን እንደሆኑ ኢየሱስ ተናገረ?

ሰዱቃውያኑ መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል እንደማያውቁ ኢየሱስ ተናገረ። [22:29]

በትንሣኤ ስለሚሆን ጋብቻ ኢየሱስ ምን ተናገረ?

በትንሣኤ ትዳር እንደማይኖር ኢየሱስ ተናገረ። [22:30]

Matthew 22:31

ትንሣኤ እንዳለ ኢየሱስ ከመጽሐፍት ጠቅሶ ያሳየው እንዴት ነበር?

እግዚአብሔር የአብረሃም፣ የይስሃቅ እና የያዕቆብ፣ የሕያዋን አምላክ እንደሆነ የተነጋረበትን ክፍል ኢየሱስ ጠቀሰ። [22:32]

Matthew 22:34

ፈሪሳዊው ህግ ዐዋቂ ኢየሱስን የጠየቀው ጥያቄ ምን ነበር?

ፈሪሳዊው ህግ ዐዋቂ ኢየሱስን የጠየቀው ከህግ ታላቂቱ ትእዛዝ የትኛዋ እንደሆነች ነበር። [22:36]

Matthew 22:37

ታላቂቱ እና የመጀመሪያይቱ ትእዛዝ እንደሆነች ኢየሱስ የተናገረው የትኛዋን ነው?

እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም አሳብህ ውደድ የምትለው ታላቅ እና ፊተኛ ትእዛዝ ነች። [22:37]

ታላቂቱ እና የመጀመሪያይቱ ትእዛዝ እንደሆነች ኢየሱስ የተናገረው የትኛዋን ነው?

እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም አሳብህ ውደድ የምትለው ታላቅ እና ፊተኛ ትእዛዝ ነች። [22:38]

Matthew 22:39

ሁለተኛይቱ ትእዛዝ ምን እንደሆነች ኢየሱስ ተናገረ?

ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ የምትለዋ ሁለተኛይቱ ትእዛዝ ነች። [22:39]

Matthew 22:41

ኢየሱስ ፈሪሳውያንን የጠየቀው ጥያቄ ምን የሚል ነበር?

ክርስቶስ የማን ልጅ እንደሆነ ኢየሱስ ጠየቃቸው። [22:42]

ፈሪሳውያን ለኢየሱስ የመለሱት መልስ ምን ነበር?

ክርስቶስ የዳዊት ልጅ እንደሆነ ፈሪሳውያን ተናገሩ። [22:42]

Matthew 22:45

ኢየሱስ ለፈሪሳውያን የጠየቀው ሁለተኛው ጥያቄ ምን የሚል ነበር?

ኢየሱስ ቀጥሎ የጠየቃቸው ዳዊት ልጁን እንዴት ክርስቶስ፣ ጌታዬ ብሎ ሊጠራው እንደቻለ ነበር። [22:45]

ፈሪሳውያን ለኢየሱስ የሰጡት መልስ ምን የሚል ነበር?

ፈሪሳውያን ለኢየሱስ ቃል ምንም መመለስ አልቻሉም ነበር። [22:46]


ምዕራፍ 23

1 ከዚያም ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ 2 "የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል፡፡ 3 ስለዚህ የሚያዝዙአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ አክብሩትም፡፡ እነርሱ የሚያደርጉትን ግን አታደርጉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው የሚናገሩትን አያደርጉትም፡፡ 4 ለመሸከም የሚያስቸግር ከባድ ሸክም አንሥተው በሰዎች ትከሻ ላይ ይጭናሉ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ግን መሸከም ቀርቶ በጣታቸው ሊያነሡት እንኳ አይፈልጉም፡፡ 5 ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት በሰዎች ለመታየት ነው፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ፡፡ 6 ግብዣ ላይ የከበሬታ ቦታዎችንና በምኵራብ ውስጥ የተለየ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ፤ 7 በገበያ ቦታ ሰዎች የተለየ ክብር እንዲሰጧቸውና፣ 'መምህር ሆይ› በማለት እንዲጠሩአቸው ይፈልጋሉ፡፡ 8 እናንተ ግን ያላችሁ አንድ መምህር ብቻ ስለሆነና ሁላችሁም ወንድማማች ስለሆናችሁ ‹መምህር› ተብላችሁ አትጠሩ፡፡ 9 በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ፤ ምክንያቱም በሰማይ የሚኖር አንድ አባት ብቻ አላችሁ፡፡ 10 ‹ሊቅም› ተብላችሁ አትጠሩ፤ ምክንያቱም ያላችሁ አንድ ሊቅ ብቻ ነው፤ እርሱም ክርስቶስ ነው፡፡ 11 ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነው አገልጋያችሁ ይሁን፡፡ 12 ራሱን ከፍ የሚያደርግ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል፡፡ 13 እናንተ፣ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ግን ወዮላችሁ! በሰዎች ፊት መንግሥተ ሰማይን ትዘጋላችሁ፡፡ እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ፡፡ 14[1] እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ለታይታ ረጅም ጸሎታችሁን በማድረግ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ ወዮላችሁ! ስለዚህ የበለጠውን ፍርድ ትቀበላላችሁ፡፡ እናንተ ግብዞች የአይሁድ ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! 15 አንድን ሰው ተከታያችሁ ለማድረግ በባሕርና በምድር ትሄዳላችሁ፤ ተከታያችሁ ካደረጋችሁት በኋላ፣ ከእናንተ እጥፍ የሚከፋ የገሃነም ልጅ ታደርጉታላችሁ፡፡ 16 እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች ወዮላችሁ፤ አንድ ሰው 'በቤተ መቅደሱ ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ባለው ወርቅ ቢምል ግን፣ በመሐላው ይጠመዳል' ትላላችሁ፡፡ 17 እናንተ የታወራችሁ ሞኞች፣ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ወርቁ ወይስ ወርቁን የሚቀድሰው ቤተ መቅደሱ? 18 አንድ ሰው በመሠዊያው ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ መሠዊያው ላይ ባለው ስጦታ ቢምል ግን በመሐላው ይጠመዳል ትላላችሁ፡፡ 19 እናንተ ዕውሮች፤ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ስጦታው ወይስ ስጦታውን የሚቀድሰው መሠዊያ? 20 ስለዚህ በመሠዊያው የሚምል በመሠዊያውና እርሱ ላይ ባሉ ነገሮች ሁሉ ይምላል፡፡ 21 በቤተ መቅደሱ የሚምል በቤተ መቅደስና እርሱ ውስጥ በሚኖረው ይምላል፡፡ 22 በሰማይ የሚምል በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል፡፡ 23 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፣ ከአዝሙድ፣ ከእንስላልና ከከሙን ዐሥራት ብታወጡም፣ የሕጉን ዋና ዋና ነገሮች ማለትም ፍትሕን፣ ምሕረትንና እምነትን ሥራ ላይ አታውሉም፡፡ ሌላውን ችላ ሳትሉ እነዚህን መፈጸም ነበረባችሁ፡፡ 24 እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች፣ ትንኝን አውጥታችሁ ትጥላላችሁ፤ ግመልን ግን ትውጣላችሁ! 25 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የጽዋውንና የሳሕኑን ውጫዊ ክፍል ታጠራላችህ፤ ውስጡ ግን ቅሚያና ስስት ሞልቶበታል፡፡ 26 አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፣ ውጫዊ አካሉም ንጹሕ እንዲሆን በመጀመሪያ የጽዋውንና የሳሕኑን ውስጥ አጽዳ፡፡ 27 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ከውጭ ሲያዩት እንደሚያምር፣ ውስጡ ግን የሞቱ ሰዎች አጥንትና ርኵሰት እንደ ሞላበት መቃብር ናችሁ፡፡ 28 በተመሳሳይ መንገድ እናንተም ከውጭ ለሰዎች ጻድቃን ትመስላላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ርኲሰት ሞልቶበታል፡፡ 29 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፣ የጻድቃንን መቃብር ስለምታስጌጡ፣ 30 በአባቶቻችን ዘመን ኖረን ቢሆን ኖሮ፣ የነቢያትን ደም በማፍሰስ አንተባበራቸውም ነበር ትላላችሁ፡፡ 31 ስለሆነም የነቢያት ገዳይ ልጆች መሆናችሁን እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡ 32 እናንተ ራሳችሁም አባቶቻችሁ የጀመሩትን ኃጢአት ትፈጽማላችሁ፡፡ 33 እናንተ እባቦች፣ እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ? 34 ስለዚህ ነቢያትን፣ አስተዋይ ሰዎችንና የአይሁድ ሕግ መምህራንን ወደ እናንተ እልካለሁ፡፡ አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፣ ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹን በምኵራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፣ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፡፡ 35 ከጻድቁ ከአቤል አንሥቶ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካካል እስከ ገደላችሁት የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደም ድረስ፣ በምድር ላይ በፈሰሰው ጻድቃን ደም ሁሉ ትጠየቃላችሁ፡፡ 36 እውነት እላችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይሆናሉ፡፡ 37 ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ ወደ አንቺ የተላኩትን በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን መሰብሰበ ብዙ ጊዜ ፈልጌ ነበር፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም! 38 ስለሆነም ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀራል፡፡ 39 'በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው' እስክትሉ ድረስ ከአሁን ጀምሮ አታዩኝም እላችኋለሁ፡፡


Footnotes


23:14 [1]በጣም የታወቁ የጥንት ቅጂዎች ቊጥር 14 የላቸውም፡፡ (አንዳንድ ቅጂዎች ይህን እዚህና ከቊጥር 12 በኋላ አስገብተውታል)፡፡


Matthew 23:1

ማቴዎስ 23፡ 1-3

Matthew 23:4

ማቴዎስ 23፡4-5

ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ "ተግባራዊ ለማድረግ በጣም አስቸጋሪ የሆኑ ደንቦችን በእናንተ ላይ ይጭናሉ" እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም። "ምንም ዓይነት እገዛ ለማድረግ ግን ፈቃደኞች አይደሉም" አሸንክታብ ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉበት ወረቀት መያዥያ ትንሽ የቆዳ ሳጥን

Matthew 23:6

ማቴዎስ 23፡6-7

Matthew 23:8

ማቴዎስ 23፡8-10

በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ "በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ” ወይም “በምድር ላይ ያለን ማንንም ሰው አባቴ ብላችሁ አትጥሩ" በሰማይ ያለ አንድ አባት አላችሁና እግዚአብሔር አባር የአማኞች ሁሉ “አባት” ነው፡፡ አንድ መምህር አላችሁ እርሱም ክርስቶስ ነው ኢየሱስ “ክርስቶስ” ብሎ ስናገር በሦስተኛ መደብ ስለራሱ መናገሩ ነው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክርለ “እኔ ክርስቶስ፣ እኔ ብቻ የእናንተ መምህር ነኝ"

Matthew 23:11

ማቴዎስ 23፡ 11-12

ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደረግ "ራሱን በጣም አስፈላጊ የሚያደረግ" ከፍ ከፍ ያለ "ራሱን በጣም አስፈላጊ ያደረገ"

Matthew 23:13

ማቴዎስ 23፡ 13-15

አትገባም "እግዚአብሔር በአንተ ላይ እንዲገዛ አትፈቅድ" የመበልቶችን ቤት መበዝበዝ "የሚጠብቃቸው ወንድ ያሌላቸው ሴቶች ትዘርፋለህ” የገሃነም ልጅ "ለገሃነም የተገባህ ሰው" ወይም "ወደ ገሃነም መግባት ያለበት ሰው

Matthew 23:16

ማቴዎስ 23፡16-17

የእውር ምሪት . . . ሞኞች ምንም እንኳ መሪዎቹ ዐይነ ሥውራን ባይሆንም እንደ ተሳቱ ማወቅ አይችሉም ነበር በመኃላ ታሥሯል "ለማድረግ በመኋላ የገባውን ቃል መፈጸም አለበት” ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ? ኢየሱስ ይህንን ጥቅስ ፈሪሳዊያንን ለመገሰጽ ተጠቅሞበታል፡፡

Matthew 23:18

ማቴዎስ 23፡18-19

ዐይነ ሥውራን መንፈሳዊ ዐይነ ሥውርነት ያለባቸው ሰዎች መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው? ኢየሱስ ይህንን ጥቅስ እንሱ እሰቀድመው የሚያውቁትን ነገር ለማስታወስ ተጠቅሞበታል ስጦታ/መባ በመሰዊያው ላይ በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርብ የእንስሳት መስዋዕት ወይም እህል መስዋዕት ነው፡፡ አንድ ጊዜ መሰዊያው ላይ ከሆነ ቧላ መስዋእት ይሆናል፡፡

Matthew 23:20

ማቴዎስ 23፡20-22

Matthew 23:23

ማቴዎስ 23፡23-24

ወዮላችሁ በ MAT 23:13 በምን መንገድ እንተረጎምከው ተመልከት መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው? ለምግብ ጥሩ ጣዕም ለመስጠጥ የሚውሉ ቅጠላ ቅጠሎች እና ፍሬዎች ዐይነ ሥውራነት መሪዎች እነዚህ ሰዎች አካላዊ ዐይናቸው አልጠፋም፡፡ ኢየሱስ አካላዊ ዐይነ ሥውርነትን ከመንፈሳዊ ዐይነ ሥውርነት ጋር ያነጻጽራል፡፡ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ። በጣም ትንንሽ የሆኑ ንጹሕ እንስሳትን ላለመዋጥ በመጠንቀቅ የትልቁን ንጹሕ ያልሆነ እንስሳ ሥጋ ግን ሆን ብላችሁ ወይም ሳታውቁ ትበላላችሁ ልክ እንደዚሁ በጣም ትንነሽ የሆኑ ሕግጋትን ለመጠበቅ ጥረት ታደርላችሁ ይሂን እንጂ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሕግጋትን ግን ቸል ትላላችሁ፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "ልክ ትንኝ በምጠጣው ነገር ውስጥ የሚያወጣ ነገር ግን ግመል እንደሚውጥ ሰው ሞኞች ናችሁ፡፡” ትንኝን እንዳይገባ ትንንኝ ወደ አፋቸው እንዳይገባ በጨርቅ አጥልለው ይጠጣሉ ትንኝ ትንንሽ በራሪ ነፍሳት

Matthew 23:25

ማቴዎስ 23፡25-26

ወዮላችሁ በ MAT 23:13 ላይ ምን ብለህ እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ የብርጭቆ እና የሣህኑን ውጪ ታጠራላችሁ “ጸሐፍ” እና “ፈርሳዊያን” ከውጪ በሰዎች ፊት “ንጹሕ መስለው” መታየት ይፈልጋሉ፡፡ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ "ከሚያስፈልጋቸው በላይ እንዲኖራው በጉልበት የሌላ ሰውን ነገር ይወስዳሉ “ ዐይነ ሥውራን ፈሪሳዊያን ፈሪሳዊያን እውነቱን አይረዱትም፡፡ አካላዊ ዐይነሥውነት ግን የለባቸውም፡፡ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ። ልባቸው ከእግዚአብሔር ጋር ትክክል ከሆነ ሕይወታቸውም ይህንኑ ያሳያል፡፡

Matthew 23:27

ማቴዎስ 23፡27-28

Matthew 23:29

ማቴዎስ 23፡29-31

Matthew 23:32

ማቴዎስ 23፡32-33

የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ኃጢአት ሙሉ። "አባቶቻችሁ የጀመሩትን ኃጢአት ፈጽሙ" እናንተ እባቦች፥ የእፉኝት ልጆች "ልክ እንደ አደገኛ እና መርዛማ እባቦች ናችሁ" ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ? "የገሃነም ፍርድን የሚታመልጡበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም!" (ተመልከት:

Matthew 23:34

ማቴዎስ 23፡34-36

ከአቤል . . እስከ ዘካሪያስ አቤል የመጀመሪያው የተገደለ ሰው ነው እንዲሁም ምናልባትም በአይሁዳዊያን ዘንድ በቤተ መቅደስ ውስጥ የተገደለው የመጨረሻው ሰው ነው፡፡ ዘካሪያስ ይህ የመጥመቁ ዮሐንስ አባት አይደለም

Matthew 23:37

ማቴዎስ 23፡ 37-39

እየሩሳሌም፣ እየሩሳሌም ኢየሱስ በእየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችን ልክ ከተማዋን እንደሚናገር ሰው ይናገራቸዋል፡፡ ልጆቻችሁ የሁሉም እስራኤላዊያን ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል። ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እግዚአብሔር ቤታችሁን ትቶ ይሄዳል ባዶም ይሆናል” ቤታችሁ አማራጭ ትርጉሞች፡ 1) የኢየሩሳሌም ከተማ ወይም 2) ቤተ መቅደሱ፡፡


Translation Questions

Matthew 23:1

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ላይ ስለተቀመጡ፣ በአስተምህሯቸው ምን እንዲያደርጉ ኢየሱስ ለሕዝቡ ነገራቸው?

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ከሙሴ ወንበር ሆነው የሚያስተምሯቸውን ነገሮች እንዲያደርጉ እና እንዲፈጽሟቸው ኢየሱስ ለሕዝቡ ተናገረ። [23:2]

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ላይ ስለተቀመጡ፣ በአስተምህሯቸው ምን እንዲያደርጉ ኢየሱስ ለሕዝቡ ነገራቸው?

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ከሙሴ ወንበር ሆነው የሚያስተምሯቸውን ነገሮች እንዲያደርጉ እና እንዲፈጽሟቸው ኢየሱስ ለሕዝቡ ተናገረ።። [23:3]

ሕዝቡ ከጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ተግባር መስለው መገኘት እንደሌለባቸው ኢየሱስ የተናገረው ለምንድነው?

ነገሮችን ስለሚሉ፣ ነገር ግን ስለማያደርጓቸው የእነርሱን ተግባራት መምሰል እንደሌለባቸው ኢየሱስ ተናገረ። [23:3]

Matthew 23:4

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ተግባራቸውን ሁሉ ያከናወኑት ለምን አላማ ነበር?

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ተግባራቸውን የሚያደርጉት በሕዝብ ፊት ለመታየት ብለው ነበር። [23:5]

Matthew 23:8

አንዱ አባታችን እና አንዱ መምህራችን ማን እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ?

አንዱ አባታችን በሰማይ ያለው፣ እንዲሁም አንዱ መምህራችን ክርስቶስ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። [23:8]

አንዱ አባታችን እና አንዱ መምህራችን ማን እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ?

አንዱ አባታችን በሰማይ ያለው፣ እንዲሁም አንዱ መምህራችን ክርስቶስ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። [23:9]

አንዱ አባታችን እና አንዱ መምህራችን ማን እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ?

አንዱ አባታችን በሰማይ ያለው፣ እንዲሁም አንዱ መምህራችን ክርስቶስ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ [23:10]

Matthew 23:11

ራሱን ከፍ ከፍ በሚያደርግ እና ራሱን ዝቅ ዝቅ በሚያደርግ ምን እግዚአብሔር ምን ያደርጋል?

ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገውን እግዚአብሔር ያዋርዳል፣ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርገውን እግዚአብሔር ያከብራል። [23:12]

Matthew 23:13

ባሕርያቸውን የሚገልጽ አድርጎ ኢየሱስ ጸሐፍትን እና ፈሪሳውያንን በተደጋጋሚ የጠራበት ስም ምንድነው?

ኢየሱስ ጸሐፍትንና ፈሪሳውያንን በተደጋጋሚ ግብዞች በማለት ጠርቷቸዋል። [23:13]

ባሕርያቸውን የሚገልጽ አድርጎ ኢየሱስ ጸሐፍትን እና ፈሪሳውያንን በተደጋጋሚ የጠራበት ስም ምንድነው?

ኢየሱስ ጸሐፍትንና ፈሪሳውያንን በተደጋጋሚ ግብዞች በማለት ጠርቷቸዋል። [23:14]

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን አዲስ አማኝ ሲያገኙ የማን ልጅ ይሆናል?

ጸሐፍት እና ፈሪሳዊያን አዲስ አማኝ ሲያገኙ፣ ከእነርሱ እጥፍ ጊዜ የከፋ የሲዖል ልጅ ያደርጉታል። [23:15]

ባሕርያቸውን የሚገልጽ አድርጎ ኢየሱስ ጸሐፍትን እና ፈሪሳውያንን በተደጋጋሚ የጠራበት ስም ምንድነው?

ኢየሱስ ጸሐፍትንና ፈሪሳውያንን በተደጋጋሚ ግብዞች በማለት ጠርቷቸዋል። [23:15]

Matthew 23:16

በመሃላ ስለ መታሰር ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን የሚያስተምሩትን በተመለከተ ኢየሱስ ምን አለ?

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን እውራን መሪዎች እና እውራን ሞኞች እንደሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [23:16]

በመሃላ ስለ መታሰር ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን የሚያስተምሩትን በተመለከተ ኢየሱስ ምን አለ?

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን እውራን መሪዎች እና እውራን ሞኞች እንደሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [23:17]

Matthew 23:23

ከአዝሙድ፣ ከእንስላልና ከከሙን ዐሥራ የሚያወጡ ቢሆንም፣ ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ማድረግ ያቃታቸው ምን ነበር?

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን በሕግ ያሉትን ዋና ነገሮች ማለትም ፍርድን፣ ምህረትን እና ታማኝነትን ማድረግ አቅቷቸው ነበር። [23:23]

Matthew 23:25

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ማጥራት የተሳናቸው ነገር ምን ነበር?

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ማጥራት ያቃታቸው ውጪው ደግሞ ንጹህ እንዲሆን የጽዋቸውን ውስጥ ነበር። [23:25]

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ማጥራት የተሳናቸው ነገር ምን ነበር?

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ማጥራት ያቃታቸው ውጪው ደግሞ ንጹህ እንዲሆን የጽዋቸውን ውስጥ ነበር። [23:26]

Matthew 23:27

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን በውስጣቸው ምን የተሞሉ ነበሩ?

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን በውስጣቸው ግብዝነት እና ዐመፀኝነት ተሞልተው ነበር። [23:28]

Matthew 23:29

የጸሐፍት እና ፈሪሳውያን አባቶች በእግዚአብሔር ነብያት ላይ ምን አድርገው ነበር?

የጸሐፍት እና ፈሪሳውያን አባቶች የእግዚአብሔርን ነብያት ገድለዋቸው ነበር። [23:29]

የጸሐፍት እና ፈሪሳውያን አባቶች በእግዚአብሔር ነብያት ላይ ምን አድርገው ነበር?

የጸሐፍት እና ፈሪሳውያን አባቶች የእግዚአብሔርን ነብያት ገድለዋቸው ነበር። [23:30]

የጸሐፍት እና ፈሪሳውያን አባቶች በእግዚአብሔር ነብያት ላይ ምን አድርገው ነበር?

የጸሐፍት እና ፈሪሳውያን አባቶች የእግዚአብሔርን ነብያት ገድለዋቸው ነበር። [23:31]

Matthew 23:32

ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ምን ዓይነት ፍርድ ይቀበላሉ?

ጸሐፍትና ፈሪሳውያን የሲዖል ፍርድ ይቀበላሉ። [23:33]

Matthew 23:34

ጸሐፍት እና ፈሪሳውያን በነብያት፣ በጢቢባን እና እርሱ በሚልካቸው ጸሐፍት ላይ ምን እንደሚያደርጉ ኢየሱስ ተናገረ?

እንደሚገድሏቸው፣ አንዳንዶቹን እንደሚሰቅሏቸው፣ አንዳንዶቹን እንደሚገርፏቸው፣ ሌሎቹን ከከተማ እንደሚያባርሯቸው ኢየሱስ ተናገረ። [23:34]

ከባሕርያቸው የተነሣ በጸሐፍት እና ፈሪሳውያን ላይ የሚመጣባቸው ውንጀላ ምን ይሆናል?

በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ በጸሐፍትና በፈሪሳውያን ላይ ይመጣል። [23:35]

ኢየሱስ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይሆናሉ ያለው በየትኛው ትውልድ ላይ ነው?

እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዚህኛው ትውልድ ላይ እንደሚሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [23:36]

Matthew 23:37

ለኢየሩሳሌም ልጆች ኢየሱስ የነበረው ምኞት ምን ነበር፣ ደግሞስ ለምን አልተፈጸመም?

ኢየሱስ የኢየሩሳሌምን ልጆች በአንድ ላይ ለማሰባሰብ ተመኝቶ ነበር፣ ነገር ግን እነርሱ አልተስማሙም። [23:37]

የኢየሩሳሌም ቤት አሁን ላይ እንዴት የተተወ ይሆናል?

የኢየሩሳሌም ቤት አሁን ላይ የተተወ እንደሆነ ይቀራል። [23:38]


ምዕራፍ 24

1 ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ እየሄደ ሳለ፤ ደቀ መዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ሕንጻ ሊያሳዩት ወደ እርሱ መጡ፡፡ 2 እርሱ ግን፣ "እነዚህን ሁሉ ነገሮች ታያላችሁ? እውነት እላችኋለሁ፣ ይፈርሳል እንጂ፣ አንድ ድንጋይ እንኳ በሌላ ድንጋይ ላይ እንደ ተነባበረ አይቀርም" በማለት መለሰላቸው፡፡ 3 በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ መጥተው፣ "እስቲ ንገረን፤ ይህ ሁሉ የሚሆነው መቼ ነው? የአንተ መምጣትና የዓለም መጨረሻስ ምልክቱ ምንድን ነው?" አሉት፡፡ 4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ 5 ምክንያቱም ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ፤ 'እኔ ክርስቶስ ነኝ' እያሉ ብዙዎችን ያሳስታሉ 6 ጦርነትንና የጦርነትን ዜና ትሰማላችሁ፤ በፍጹም እንዳትታወኩ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ ግድ ነው፤ ቢሆንም፣ መጨረሻው ገና ነው፡፡ 7 ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፡፡ በተለያየ ቦታ ራብና የምድር መናወጥ ይሆናል፡፡ 8 እነዚሀ ሁሉ ግን የምጥ ጣር መጀመሪያ ብቻ ናቸው፡፡ 9 ከዚያም ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሏችኋልም፡፡ ስለ ስሜ ሕዝቦች ሁሉ ይጠሏችኋል፡፡ 10 ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ ይካካዳሉ፤ እርስ በርስ ይጠላላሉ፡፡ 11 ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፣ ብዙዎችን ያሳስታሉ፡፡ 12 ዐመፅ ስለሚበዛ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል፡፡ 13 እስከ መጨረሻ የሚታገሥ ግን ይድናል፡፡ 14 ለሕዝቦች ሁሉ ምስክር እንዲሆን የመንግሥቱ ወንጌል ለመላው ዓለም ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል፡፡ 15 ስለዚህ በነቢዩ ዳንኤል የተነገረለት የጥፋት ርኲሰት በተቀደሰው ቦታ ቆሞ ስታዩ፣ (ያኔ አንባቢው ያስተውል) 16 በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣ 17 ጣራ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ያለውን ምንም ነገር ከቤቱ ለመውሰድ አይመለስ፣ 18 በእርሻ ያለ ልብሱን ለመውሰድ አይመለስ፡፡ 19 ልጆች ላሉአቸውና ለሚያጠቡ እናቶች ግን ወዮላቸው! 20 ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፡፡ 21 ምክንያቱም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስና ከዚያም በኋላ ፈጽሞ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል፡፡ 22 እነዚያ ቀኖች ባያጥሩ ኖሮ፣ ማንም ሥጋ ለባሽ አይድንም ነበር፤ ለተመረጡት ሲባል ግን እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ፡፡ 23 ስለዚህ ማንም "እነሆ ክርስቶስ፣ እዚህ ነው" ወይም፣ 'ክርስቶስ እዚያ ነው' ቢላችሁ አትመኑ፡፡ 24 ምክንያቱም ብዙዎችን ለማሳሳት ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት መጥተው ታላላቅ ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋሉ፤ ከተቻለም የተመረጡትን እንኳ ያሳስታሉ፡፡ 25 ይህ ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፡፡ 26 ስለዚህ፣ ‹ክርስቶስ በምድረ በዳ ነው› ቢሏችሁ ወደ ምድረ በዳ አትሂዱ ወይም ቤት ውስጥ ነው ቢሏችሁ አትመኑ፡፡ 27 መብረቅ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በአንዴ እንደሚታይ የሰው ልጅ ሲመጣ እንደዚያው ይሆናል፡፡ 28 የሞተ እንስሳ ባለበት ሁሉ፣ በዚያ አሞሮች ይሰበሰባሉ፡፡ 29 ከእነዚህ የመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉ፡፡ 30 ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ የምድር ነገዶች ሁሉ አምርረው ያለቅሳሉ፡፡ የሰው ልጅንም በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፡፡ 31 መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም፣ ከአንድ የሰማይ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ ከአራቱም ነፋሳት ምርጦቹን ይሰበስቧቸዋል፡፡ 32 ከበለስ ዛፍ ተማሩ፡፡ ቅርንጫፎቿ ሲለመልሙና ቅጠሎች ብቅ ብቅ ሲሉ በጋ መቅረቡን ታውቃላችሁ፡፡ 33 እናንተም እነዚህን ሁሉ ስታዩ እርሱ መቅረቡን፣ እንዲያውም በደጅ መሆኑን ዕወቁ፡፡ 34 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም፡፡ 35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም፡፡ 36 ስለዚያች ቀንና ሰዓት ግን ማንም አያውቅም፤ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ አያወቁም፤ አብ ብቻ እንጂ ወልድ እንኳ ቢሆን አያውቅም፡፡ 37 በኖኅ ዘመን እንደ ነበረው፣ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል፡፡ 38 ከጥፋት ውሃ በፊት እንደ ነበረው ዘመን፣ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባ ድረስ ይበሉና ይጠጡ፣ ያገቡና ይጋቡ ነበር። 39 ጐርፉ መጥቶ እስኪያጠፋቸው ድረስ ምንም አላወቁም፣ የሰው ልጅ ሲመጣም እንዲሁ ይሆናል፡፡ 40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሌላው ይቀራል፡፡ 41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች፡፡ 42 ስለዚህ ጌታችሁ በምን ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተጠንቀቁ፡፡ 43 ይህን ግን ዕወቁ፤ ሌባው በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ የቤቱ ባለቤት ቢያውቅ ኖሮ ይጠነቀቅ ነበር፤ ቤቱ አይዘረፍም ነበር፡፡ 44 የሰው ልጅ ባልጠበቃችሁት ሰዓት ስለሚመጣ እናንተም ብትሆኑ ተዘጋጅታችሁ መጠበቅ አለባችሁ፡፡ 45 በተገቢው ጊዜ ለቤተ ሰቦቹ ምግባቸውን ለመስጠት ጌታው በቤቱ ላይ ኀላፊነት የሰጠው ታማኝና አስተዋይ አገልጋይ ማን ነው? 46 ጌታው ሲመጣ ያንን እያደረገ የሚያገኘው አገልጋይ የተባረከ ነው፡፡ 47 እውነት እላችኋለሁ የምላችሁ፣ ጌታው ባለው ነገር ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ይሾመዋል፡፡ 48 ይሁን እንጂ፣ አንድ ክፉ አገልጋይ በልቡ፣ ‹‹ጌታዬ ከመምጣት ዘግይቶአል ብሎ ቢያስብ፣ 49 አገልጋይ ጓደኞቹን መደብደብና ከሰካራሞች ጋር መብላት መጠጣት ቢጀምር 50 የዚያ አገልጋይ ጌታ አገልጋዩ ባልጠበቀው ቀንና በማያውቀው ሰዓት ይመጣበታል፡፡ 51 ጌታው ለሁለት ይሰነጥቀዋል፤ ዕጣ ፈንታውን ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፣ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡



Matthew 24:1

ማቴዎስ 24፡1-2

ይህን ሁሉ ታያላችሁን? አማራጭ ትርጉሞች: ኢየሱስ እየተናገረ ያው 1) ስለ ቤተ መቅደሱ ግንባታ

Matthew 24:3

ማቴዎስ 24፡3-5

ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ "ማንም ስለዚህ ጉዳይ እንዳይዋሻችሁ ተጠንቀቁ"

Matthew 24:6

ማቴዎስ 24፡6-8

አትደናገጡ "እነዚህ ነገሮች አያናውጧችሁ"

Matthew 24:9

ማቴዎስ 24፡9-11

አሳልፈው ይሰጢ,ጡአችዋል

"የእናንተን መሰደድ የሚወዱ ሰዎች አሳልፈው ይሰጡአችዋል" አሳልፎ መሰጠት በ MAT 10:17 ላይ ምን ብለህ እንዴተረጎምከው ተመልከት፡፡

Matthew 24:12

ማቴዎስ 24፡12-14

የብዙዎች ፍቅር እየቀዘቀዘ ይመጣል አማራጭ ትርጉሞች: 1) "ብዙ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን መውደድ ይተዋሉ" ወይም 2) "ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን መውደዳቸውን ይተዋሉ" በዓለም ሁሉ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “በሁሉም ሥፍራ ያሉ ሁሉም ሰዎች"

Matthew 24:15

ማቴዎስ 24፡15-18

በነብዩ ዳንኤል የተነገረው ትንቢት ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ነብዩ ዳንኤል በጻፈው ትንቢት መሠረት”

Matthew 24:19

ማቴዎስ 24፡ 19-22

ነፍሰ ጡር ያረገዘች ሴት ክረምት "ቀዝቃዛ ወራት" ሥጋ ለባሽ ሰዎች

Matthew 24:23

ማቴዎስ 24፡23-25

አትመኑ "የሚነግሯችሁን ውሸት አትመኑ"

Matthew 24:26

ማቴዎስ 24፡26-28

መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና፤ አመጣጡ በፍጥነት እና በቀላሉ ለታይ በሚችል መልኩ ነው፡፡ የሞተ እንስሳ ባለበት በዚያ ጥንብ አንሳዎች ይሰበሰባሉ አማራጭ ትርጉሞች 1) የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ ሁሉም ሰዎች ያዩታል እንዲሁም የእርሱን መምጣት ያውቃሉ ወይም 2) በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የሞቱ ሰዎች ባሉበት ሥፍራ ውሸትን የሚነግሯቸው ሐሰተኛ ነብያት በዚያ አሉ፡፡ ጥንብ አንሳ የሞቱ ወይም ሊሞቱ ያሉ እንስሳትን ሥጋ የሚበሉ አእዋፋት

Matthew 24:29

ማቴዎስ 24፡29-29

ወዲያው "በዚያ ቅጽበት" በእነዚያ ቀናት በ MAT 24:23-28 ላይ የተገለጹት ቀናት አራት ንፈሳት ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ከሰሜን፣ ከደቡበድ፣ ከምስራቅ እና ከምዕራብ” ወይም “ከሁሉም አቅጣጫ" የሰማይ ኃይላት ሁሉ ይናወጣሉ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እግዚአብሔር በሰማይ ያሉትን ነገሮች ሁሉ እና ከሰማይ በላይ ያሉትን ነገሮች ያናውጣል

Matthew 24:30

ማቴዎስ 24፡30-31

ደረታቸውን ይደቃሉ የሚመጣውን ፍርድ በመፍራት ደረታቸውን ይመታሉ ይሰበሰባሉ "መላዕክቶቹ ይሰበስባሉ" ምርጦቹን የሰው ልጅ የመረጣቸውን ሰዎች ከአራቱም ንፋሳት ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ከሰሜን፣ ከደቡበድ፣ ከምስራቅ እና ከምዕራብ” ወይም “ከሁሉም አቅጣጫ"

Matthew 24:32

ማቴዎስ 24፡32-33

በደጅ እንደቀረበ እወቁ ወራሪ ሠራዊት ከተማዋን ሰብሮ ለመግባት ዝግጁ እንደሆነ

Matthew 24:34

ማቴዎስ 24፡34-35

ይህ ተውልድ አያልፍም "ዛሬ የሚኖሩ ሰዎች አይሞቱም" ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እነዚህ ነገሮች እግዚብሔር እንዲሆኑ እስኪደረግ ድረስ" ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ "ሰማይ እና ምድር ሕልውናቸው ያበቃል"

Matthew 24:36

ማቴዎስ 24፡36-36

የሰው ልጅም ቢሆን "የሰው ልጅ እንኳ"

Matthew 24:37

ማቴዎስ 24፡ 37-39

በኖህ ዘመን እንደሆነው የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል "የሰው ልጅ የሚመጣበት ቀን ልክ በኖህ ዘመን እንደሆነው ነው” ምክንያቱም ማንም መጥፎ ነገር ይሆንብና ብሎ አላሰበም፡፡ በዚያ ዘመን እንደሆነው ከጥፋት ውሃ በፊት ይበሉ እና ይጠጡ . . . ጠራርቆ ወሰዳቸው- የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል "ከሰው ልጅ መምጣት በፊት ያለው ጊዜ ልክ የጥፋት ውሃ ሊመጣ ሲል ያለውን ይመስላል፣ ሁሉም ስበሉና ስጠጡ ሳለ - - - ጠራትቆ ወሰዳቸው”

Matthew 24:40

ማቴዎስ 24፡ 40-42

ከዚያ የሰው ልጅ ሲመጣ አንዱ ይወሰዳል ሌላኛው ይቀራል አማራጭ ትርጉሞች: 1) እግዚአብሔር ወደ ሰማይ ይወስደዋል ሌሎቹን ደግሞ ለፍርድ በምድር ላይ ይተዋቸዋ፡፡ ወይም 2) መላእክት አንዱ ልፍርድ ይወስዱታል ሌላኛውን ለበረከት ይተውታል ወይም (ተመልከት), MAT 13:40-43). የድንጋይ ወፍጮ እህል ለመከካት የሚሆን እቃ ስለዚህ "ከነገርኳችሁ ነገር የተነሳ" ጸንታችሁ ቁሙ "በንቃት ተከታተሉ"

Matthew 24:43

ማቴዎስ 24፡ 43-44

ሌባ ኢየሱስ ልክ እንደ ሌባ ሰዎች ባላሰቡት ሰዓት እንደሚመጣ ተናግሯል፤ ይሁን እንጂ ሊሰርቅ አይደለም የሚመጣው፡፡ ነቅቶ ይጠብቅ ነበር ቤቱ እንዳይዘረፍ “ነቅቶ በጠበቀ ነበር” ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር። "ማንም ቤቱ ገብቶ ንረቱን አንድሰርቅ ባላደረገ ነበር"

Matthew 24:45

ማቴዎስ 24፡ 45-47

እንኪያስ በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ . . . ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው? "ታማኝ፣ ልባም ባሪያ ማን ነው? ጌታው በጊዜው . . . እርሱን ነው፡፡” ምግባቸውን ይሰጣቸው ዘንድ "በጌታው ቤት ላሉት ሰዎች ምግባቸውን ይሰጥ ዘንድ"

Matthew 24:48

ማቴዎስ 24፡ 48-51

በለልቡ እንዲህ አለ "በአእምሮው እንዲህ አሰበ" እድል ፈንታወን ለመወሰን "ይቀበሉት ዘንድ"


Translation Questions

Matthew 24:1

በኢየሩሳሌም ስላለው ቤተመቅደስ ኢየሱስ ምን ትንቢት ተነበየ?

አንድም የቤተመቅደሱ ድንጋይ ሳይፈርስ ባለበት እንደማይቀር ኢየሱስ ተነበየ። [24:2]

Matthew 24:3

ስለ ቤተመቅደሱ ትንቢት ከሰሙ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ምን ጠየቁት?

ደቀመዛሙርቱ እነዚህ ነገሮች ሲከሰቱ፣ የመምጣቱና የዓለም መጨረሻ ምልክት ምን እንደሚሆን ኢየሱስን ጠየቁት። [24:3]

ብዙዎችን ያስታሉ ብሎ ኢየሱስ የተናገረው ምን ዓይነት ሰዎችን ነው?

ብዙዎች ክርስቶስ ነን እያሉ እንደሚመጡ እና ብዙዎችንም እንደሚያስቱ ኢየሱስ ተናገረ። [24:5]

Matthew 24:6

የምጥ ጣር መጀመሪያ እንደሆኑ አድርጎ ኢየሱስ የተናገራቸው ክስተቶች ምንድናቸው?

ጦርነት፣ ረሃብ፣ የምድር መናወጥ የምጥ ጣር መጀመሪያ እንደሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [24:6]

የምጥ ጣር መጀመሪያ እንደሆኑ አድርጎ ኢየሱስ የተናገራቸው ክስተቶች ምንድናቸው?

ጦርነት፣ ረሃብ፣ የምድር መናወጥ የምጥ ጣር መጀመሪያ እንደሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [24:7]

የምጥ ጣር መጀመሪያ እንደሆኑ አድርጎ ኢየሱስ የተናገራቸው ክስተቶች ምንድናቸው?

ጦርነት፣ ረሃብ፣ የምድር መናወጥ የምጥ ጣር መጀመሪያ እንደሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [24:8]

Matthew 24:9

በዚያን ጊዜ ባሉ በአማኞች ላይ ምን እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ?

አማኞች በመከራ ይሰቃያሉ አንዳንዶቹም ይሰናከላሉ አንዳቸውም ሌላኛቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ። [24:9]

በዚያን ጊዜ ባሉ በአማኞች ላይ ምን እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ?

አማኞች በመከራ ይሰቃያሉ አንዳንዶቹም ይሰናከላሉ አንዳቸውም ሌላኛቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ። [24:10]

Matthew 24:12

እንደሚድኑ ኢየሱስ የተናገረው እነማን ናቸው?

እስከ መጨረሻ የሚጸና ይድናል ሲል ኢየሱስ ተናገረ። [24:13]

መጨረሻው ከመምጣቱ በፊት ወንጌል ምን ይሆናል?

የመንግሥቱ ወንጌል መጨረሻው ከመምጣቱ በፊት በዓለም ሁሉ ይሰበካል። [24:14]

Matthew 24:15

የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ በሚያዩ ጊዜ አማኞች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናገረ?

አማኞች ወደ ተራሮች መሸሽ እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናገረ። [24:15]

የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ በሚያዩ ጊዜ አማኞች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናገረ?

አማኞች ወደ ተራሮች መሸሽ እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናገረ። [24:16]

የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ በሚያዩ ጊዜ አማኞች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናገረ?

አማኞች ወደ ተራሮች መሸሽ እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናገረ። [24:17]

የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ በሚያዩ ጊዜ አማኞች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናገረ?

አማኞች ወደ ተራሮች መሸሽ እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናገረ። [24:18]

Matthew 24:19

በእነዚያ ቀናት መከራው ምን ያክል ታላቅ ይሆናል?

በእነዚያ ዘመናት፣ መከራው ታላቅ ይሆናል፣ ታላቅነቱም ከዓለም ጅማሬ አንሥቶ ከሆነው ሁሉ በላይ ነው። [24:21]

Matthew 24:23

ሃሰተኛ ክርስቶሶች እና ሃሰተኛ ነብያት ብዙዎችን የሚያስቱት እንዴት ነው?

ሃሰተኛ ክርስቶሶች እና ሃሰተኛ ነብያት ብዙዎችን ለማሳት ታላላቅ ምልክቶች እና ተዓምራትን ያሳያሉ። [24:24]

Matthew 24:26

የሰው ልጅ መምጣት ምን ይመስላል?

የሰው ልጅ መምጣት ከምሥራቅ እስከ ምእራብ እንደሚበርቅ መብረቅ ይሆናል። [24:27]

Matthew 24:29

ከእነዚያ ቀናት መከራ በኋላ በፀሐይ፣ ጨረቃ እና ከዋክብት ላይ ምን ይሆናል?

ፀሐይ እና ጨረቃ ይጨልማሉ፣ ክዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ። [24:29]

Matthew 24:30

የምድር ወገኖች የሰው ልጅ በኃይል እና ታላቅ ክብር ሲመጣ ሲያዩ ምን ያደርጋሉ?

የምድር ወገኖች ደረታቸውን ይደቃሉ። [24:30]

የሰው ልጅ የተመረጡትን እንዲሰበስቡ መላእክቱን በሚልክበት ጊዜ ምን ድምፅ ይሰማል?

መላእክት የተመረጡትን በሚሰበስቡበት ጊዜ ታላቅ የመለከት ድምፅ የሚሰማ ይሆናል። [24:31]

Matthew 24:34

እነዚህ ሁሉ ነገሮች እስኪሆኑ ድረስ እንደማያልፍ ኢየሱስ የተናገረው ምንድነው?

እነዚህ ሁሉ ነገሮች እስኪሆኑ ድረስ ይህ ትውልድ እንደማያልፍ ኢየሱስ ተናገረ። [24:34]

እንደሚያልፍ እና ፈጽሞ እንደማያልፍ ኢየሱስ የተናገረው ምንድነው?

ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ነገር ግን ቃሎቹ ፈጽሞ እንደማያልፉ ኢየሱስ ተናገረ። [24:35]

Matthew 24:36

እነዚህ ነገሮች መቼ እንደሚከሰቱ የሚያውቀው ማን ነው?

እነዚህ ክስተቶች መቼ እንደሚሆኑ የሚያውቀው አብ ብቻ ነው። [24:36]

Matthew 24:37

የሰው ልጅ መምጣት ከጥፋት ውሃ በፊት እንደነበሩት የኖህ ዘመን የሚመስለው እንዴት ነው?

ሰዎች ሊያጠፋቸው ስለሚመጣው ፍርድ ምንም ሳያውቊ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ያገባሉ ይጋባሉ። [24:37]

የሰው ልጅ መምጣት ከጥፋት ውሃ በፊት እንደነበሩት የኖህ ዘመን የሚመስለው እንዴት ነው?

ሰዎች ሊያጠፋቸው ስለሚመጣው ፍርድ ምንም ሳያውቊ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ያገባሉ ይጋባሉ። [24:38]

የሰው ልጅ መምጣት ከጥፋት ውሃ በፊት እንደነበሩት የኖህ ዘመን የሚመስለው እንዴት ነው?

ሰዎች ሊያጠፋቸው ስለሚመጣው ፍርድ ምንም ሳያውቊ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ያገባሉ ይጋባሉ። [24:39]

Matthew 24:40

ስለ መምጣቱ አማኞች ሊኖራቸው የሚገባው አመለካከት ምን መሆን እንዳለበት ኢየሱስ ተናገረ፣ ደግሞስ ለምን?

ጌታ የሚመለስበትን ቀን ስለማያውቁ በእርሱ የሚያምኑት ሁልጊዜ ዝግጁ እንዲሆኑ ኢየሱስ ተናገረ። [24:42]

Matthew 24:45

ጌታው በሌለ ጊዜ ታማኝ እና ብልኅ የሆነው ባርያ ምን ያደርጋል?

ታማኝ እና ብልኅ የሆነው አገልጋይ ጌታው በሌለበት ጊዜ ላይ የጌታውን ቤተሰብ ይንከባከባል። [24:45]

ጌታው በሌለ ጊዜ ታማኝ እና ብልኅ የሆነው ባርያ ምን ያደርጋል?

ታማኝ እና ብልኅ የሆነው አገልጋይ ጌታው በሌለበት ጊዜ ላይ የጌታውን ቤተሰብ ይንከባከባል። [24:46]

ታማኝ እና ብልኅ ለሆነው አገልጋይ ጌታው በሚመለስበት ጊዜ ምን ያደርጋል?

በሚመለስበት ጊዜ፣ ጌታው ታማኝ እና ብልኅ የሆነውን አገልጋይ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል። [24:47]

Matthew 24:48

ጌታው በሌለበት ጊዜ ላይ ክፉ የሆነው ባርያ ምን ያደርጋል?

ክፉ የሆነው ባርያ ጌታው በሌለበት ጊዜ ላይ አብረውት የሚሠሩትን ባርያዎች ይመታል፣ ይበላል ይጠጣል፣ ይሰክርማል። [24:48]

ጌታው በሌለበት ጊዜ ላይ ክፉ የሆነው ባርያ ምን ያደርጋል?

ክፉ የሆነው ባርያ ጌታው በሌለበት ጊዜ ላይ አብረውት የሚሠሩትን ባርያዎች ይመታል፣ ይበላል ይጠጣል፣ ይሰክርማል። [24:49]

በሚመለስበት ጊዜ ጌታው በክፉ ባርያው ላይ ምን ያደርጋል?

በሚመለስበት ጊዜ፣ ጌታው ክፉውን አገልጋይ ከሁለት ይሰነጥቀዋል፣ ለቅሶ እና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ይልከዋል። [24:51]


ምዕራፍ 25

1 መንግሥተ ሰማይ መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ለመቀበል የወጡ ዐሥር ድንግሎችን ትመስላለች። 2 ዐምስቱ ሞኞች፣ ዐምስቱ ልባሞች ነበሩ። 3 ሞኞቹ ድንግሎች መብራታቸውን ይዘው ሲሄዱ ምንም ዘይት አልያዙም ነበር። 4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር ዘይትም ይዘው ነበር። 5 ሙሽራው በዘገየ ጊዜ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ሁሉም ተኙ። 6 ዕኩለ ሌሊት ላይ ግን፣ “ሙሽራው መጥቶአልና ወጥታችሁ ተቀበሉት!” የሚል ሁካታ ሆነ። 7 ያኔ እነዚያ ድንግሎች ሁሉ ተነሥተው መብራታቸውን አዘጋጁ። 8 ሞኞቹም ልባሞቹን፣ “መብራታችን እየጠፋ ስለ ሆነ፣ ከዘይታችሁ ጥቂት ስጡን” አሏቸው። 9 ልባሞቹ ግን፣ “ለእኛና ለእናንተ የሚበቃ ስለሌለን፣ ወደ ሻጮች ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ” በማለት መለሱአቸው። 10 ለመግዛት ሲሄዱ፣ ሙሽራው መጣ፤ ተዘጋጅተው የነበሩት ግብዣው ላይ ለመገኘት ከእርሱ ጋር ሄዱ፤ በሩም ተዘጋ። 11 በኋላ ሌሎቹ ድንግሎች መጥተው፣ “ጌታው፣ በሩን ክፈትልን” አሉ። 12 እርሱ ግን መልሶ፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ አላውቃችሁም” አላቸው። 13 ስለዚህ ቀኑን ወይም ሰዓቱን አታውቁምና ነቅታችሁ ጠብቁ። 14 ነገሩ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ ያሰበ ሰውን ይመስላልና፤ አገልጋዮቹን ጠርቶ በሀብት በንብረቱ ሁሉ ላይ ኀላፊነት ሰጣቸው። 15 እንደ ዐቅማቸው መጠን ለአንዱ ዐምስት መክሊት፣ ለሌላው ሁለት፣ ለሌላው ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸውና ሄደ። 16 ዐምስት መክሊት የተቀበለው ወዲያውኑ ሄዶ ነገደበት፤ ሌላ ዐምስት አተረፈ። 17 ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንደዚያው ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ። 18 አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ግን ሄዶ ጉድጓድ ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። 19 ከብዙ ጊዜ በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ መጣና ተሳሰባቸው። 20 ዐምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ሌላ ዐምስት መክሊት ጨምሮ አመጣና፣ “ጌታ ሆይ፣ ዐምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እኔ ግን ሌላ ዐምስት መክሊት አተረፍሁ” አለ። 21 ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ።' አለው። 22 ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው አገልጋይም መጥቶ፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር። ሌላ ሁለት መክሊት አትርፌአለሁ’ አለ። 23 ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው። 24 ከዚያም አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ መጥቶ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ። 25 ስለዚህ ፈራሁ፤ መክሊትህን መሬት ውስጥ ቀበርሁት። መክሊትህ ይኸውልህ' አለው። 26 ጌታው ግን መልሶ፣ 'አንተ ዐመፀኛና ሰነፍ አገልጋይ፤ ካልዘራሁበት የማጭድ፣ ካልበተንሁበት የምሰበስብ መሆኔን ታውቃለህ። 27 ስለዚህ ገንዘቤን በባንክ ማስቀመጥ ይገባህ ነበር፤ እኔ ስመጣ ከነወለዱ እወስደው ነበር' አለው። 28 ስለዚህ መክሊቱን ከእርሱ ወስዳችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት። 29 ላለው የበለጠ እንዲያውም የተትረፈረፈ ይሰጠዋል። ምንም ከሌለው ግን፣ ያው ያለው ነገር እንኳ ይወሰድበታል። 30 ይህን የማይረባ አገልጋይ አውጡና ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት” አለ። 31 የሰው ልጅ በክብሩ ከመላእክቱ ሁሉ ጋር ሲመጣ፣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል። 32 አሕዛብ ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ ሕዝቡን ይለያቸዋል። 33 በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን በግራው ያደርጋቸዋል። 34 ከዚያም ንጉሡ በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ 'እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። 35 ተርቤ ነበር ምግብ ሰጣችሁኝ፤ ተጠምቼ ነበር የምጠጣው ሰጣችሁኝ፤ እንግዳ ሆኜ ነበር አስተናገዳችሁኝ፤ 36 ተራቊቼ ነበር አለበሳችሁኝ፤ ታምሜ ነበር ተንከባከባችሁኝ፤ ታስሬ ነበር ጠየቃችሁኝ' ይላቸዋል። 37 ከዚያም ጻድቃን እንዲህ ብለው ይመልሱለታል፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ያገኘንህና ያበላንህ ወይስ ተጠምተህ ያጠጣንህ መቼ ነው? 38 38 እንግዳ ሆነህ ያየንህና ያስተናገድንህ መቼ ነው? ወይም ተራቊተህ ያለበስንህ መቼ ነው? 39 ታምመህ የተንከባከብንህ ወይስ ታስረህ የጠየቅንህ መቼ ነው?’ 40 ንጉሡም መልሶ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ለእነዚህ ታናናሽ ወንድሞቼ ያደረጋችሁትን ለእኔ አድርጋችሁታል።’ 41 ከዚያም በግራው ያሉትን፣ ‘እናንተ ርጉማን ከእኔ ራቁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ገሃነም እሳት ሂዱ። 42 ምክንያቱም ‘ተርቤ ነበር አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ ነበር አላጠጣችሁኝም፤ 43 እንግዳ ሆኜ ነበር አልተቀበላችሁኝም፤ ተራቊቼ ነበር አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜ፣ ታስሬ ነበር፣ እናንተ ግን አልተንከባከባችሁኝም’ ይላቸዋል። 44 እነርሱም መልሰው እንዲህ ይሉታል፤ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ወይም ተጠምተህ ወይም እንግዳ ሆነህ ወይም ተራቊተህ ወይም ታምመህ ወይም ታስረህ ያላገለገልንህ መቼ ነው?’ 45 እርሱም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ አለማድረጋችሁ ለእኔ አለማድረጋችሁ ነው’ ይላቸዋል። 46 እነዚህ ወደ ዘላለም ቅጣት፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።"



Matthew 25:1

ማቴዎስ 25፡ 1-4

መብራት ይህ እንዲህ ሊሆን ይችላል 1) መብራት ወይም 2) በእንጨት ጫፍ ላይ ጨርቅ በመጠምጠም ጨርቁን በዘይት በመንከር የሚዘጋጅ ችቦ አምስት ሴቶች "አምስት ልጃገረዶች" ትርፍ ዘይት አልያዙም "በመብራታቸው ውስጥ እንጂ ተጠባባቂ ዘይት አልያዙም"

Matthew 25:5

ማቴዎስ 25፡5-6

እንቅልፍ ወሰዳቸው "ዐሥሩም ልጃገረዶች ተኙ"

Matthew 25:7

ማቴዎስ 25፡7-9

መብራታቸውን አዘጋጁ "በደንብ እንድበራ መብራቸውን አስተካከሉ " ሞኞቹ ለጠቢባኑ እንዲህ አሏቸው "ሞኞቹ ልጃገረዶች ለጠቢባኑ ልጃገረዶች እንዲህ አሏቸው" ዘይታችን ሊያልቅ ነው "በመብራታችን ውስጥ ያለው ዘይት ደምቆ መብረቱን አቁሟል”

Matthew 25:10

ማቴዎስ 25፡10-13

ሄዱ "አምስቱ ሞኝ ልጃገረዶች ሄዱ" ዝግጁዎች የሆኑት ተጠባባቂ ዘይት የነበራቸው ልጃገረዶች በሩ ተዘጋ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ብሩን ተዘጋ" ክፈቱልን "ወደ ውስጥ መግባት እንችል ዘንድ በሩን ክፈቱልን" አላውቃችሁም "ማን እንደሆናችሁ አላውቅም”

Matthew 25:14

ማቴዎስ 25፡ 14-16

ይህንን ይመስላል "መንግስ ሰማያት ይህንን ይመስላል" (ተመልከት MAT 25:1) ለሄድ ስነሳ "ለመሄድ ዝግጁ በሆነ ጊዜ” ወይም “ለመሄድ በተነሳ ጊዜ” ሀብቱን አስረከበ "ሀብቱን ይቆጣጠሩለት ዘንድ ስልጣን ሰጣቸው" ሀብቱ "የእርሱ ሀብት” የእርሱ ሀብት መክሊት “አንድ መክሊት” የሃያ ዓመት ደሞዝ ያክላል፡፡ ይህንን በዘመናዊ የገንዘብ መጠን አትለውጡት፡፡ ምሳሌው በማነጻጸር ላይ ያለው አምስት፣ ሁለት እና አንድ እንዲሁም በጣም ትልቅ ሀብትን ነው፡፡ ለተርጓማች ምክር፡ “አምስት ሻንጣ ሙሉ ወርቅ “ ከዚያም አምስት ጠጨማሪ መክሊቶችን አተረፈ “በመክሊቱ ነግዶ አምስት መክሊቶችን አተረፈ”

Matthew 25:17

ማቴዎስ 25፡ 17-18

ሌላ ሁለት አተረፈ "ሌላ ሁለት መክሊቶችን አተረፈ"

Matthew 25:19

ማቴዎስ 25፡ 19-21

አምስት ተጨማሪ መክሊቶችን አተረፈ "አምስት ተጨማሪ መክሊቶችን አተረፍኩ" መክሊቶች በ MAT 25:15 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፤ ጥሩ አድርገሃል "ጥሩ አድርገሃል” ወይም “መልካም አድርገሃል”፡፡ ባሕላቹ ምናልባት የጌታውን ንግግር ይበልጥ መግለጽ የሚያስችል ቃል ይኖረው ይሆናል፡፡

Matthew 25:22

ማቴዎስ 25፡ 22-23

ተጨማር መክሊቶችን አተረፍኩ በ MAT 25:20 ላይ እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡ ጥሩ አድርገሃል . . . የጌታው ሰላም በ MAT 25:21 ላይ እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡

Matthew 25:24

ማቴዎስ 25፡ 24-25

ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ r እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ሀሳብን የሚያስተላልፉ ናቸው፡፡ አገልጋዩ ጌታውን የእርሱ ያልሆነ ምርትን ይሰበስባል በማለት ይከሰዋል፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ምግብን የአንተ ካልሆነ ማሳ ውሰጥ ትሰበስባለህ” " መዝራት በዚያ ዘመን በመሥመር ከመዝራት ይልቅ በጥቂት በጥቂቱ ይበትኑት ነበር፡፡ ተመልከት የአንተ የሆነውን ይኸው ይዤ መጥቻለሁ "ይኼው፣ የአንተን ይዤ መጥቻለሁ"

Matthew 25:26

ማቴዎስ 25፡26-27

አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ "አንተ መስራት የማትፈልግ ክፉ ባሪያ ነህ" ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ይህንን ሀሳብ በ MAT 25:24 ላይ እንዴት እንተረጎምክ ተመልከት፡፡ ጠራሴን እወሰዳለሁ “የራሴን ወርቅ እወስዳለሁ" ትርፍ ከባንክ በብድር የሚወሰድ ብር ላይ የሚደመር ትርፍ

Matthew 25:28

ማቴዎስ 25፡ 28-30

ከዚያም የሚበልጥ "የሚበዛ" በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። "ሰዎች የሚያለቅሱበት እና ጥርሳቸውን የሚያፋጩበት ቦታ"

Matthew 25:31

X

ማቴዎስ 25፡31-33

አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "በፊቱ ሕዝቦችን ሁሉ ይሰበስባል" በፊቱ "ከእርሱ ፊት" አሕዛብን ሁሉ "ከሁሉም ሀገራት የተውጣጡ ሕዝቦች" ፍየሎች ፍየሎች መካከለኛ መጠን ያላቸው በአራት እግሮቻቸው የሚራመዱ ከበግ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ አጥቢ እንስሳት ናቸው፡፡ ያስቀምጣቸዋል "የሰው ልጅ ያስቀምጣቸዋል"

Matthew 25:34

ማቴዎስ 24፡ 34-36

ንጉሥ ይህ ኢየሱስ በ MAT 25:31 ላይ ስለ ሰው ልጅ የተናገረው ሌላኛው ሥፍራ ነው፡፡ ንጉሥ . . . በቀኙ ኢየሱስ ስለ ራሱ በሦስተኛ መደብ እየጠናገረ ነው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እኔ፣ ንጉሡ . . . በቀኜ” ኑ፣ የአባቴ ብሩካን ለተርጓሚዎች ምክር: "ኑ አባቴ የባረካችሁ" አባት ይህ ለእግዚአብሔር የማዕረግ ስም ነው ለእናንተ የተዘጋጀውን መንግስት ውረሱ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እግዚአብሔር ያዘጋጀላችሁን መንግስት ውረሱ"

Matthew 25:37

ማቴዎስ 25፡ 37-40

ንጉሥ "የሰው ልጅ" (MAT 25:31) እንዲህ አላቸው "በቀኙ ላሉት እንዲህ አላቸው" ወንድሞች በቋንቋችሁ ወንዶችን እና ሴቶችን የሚካትት ቃል ቃለ ያንን ቃል ተጠቀሙ፡፡ ለእኔ አድርጋችኋል "ለእኔ እንዳደረጋችሁት እቆጥረዋለሁ"

Matthew 25:41

ማቴዎስ 25፡ 41-43

እናንተ ርጉማን "እናንተ እግዚአብሔር የረገማችሁ" ወደ ተዘጋጀላቸው ዘላለማው እሳት ለተርጓሚዎች ምክር: "እግዚብሔር ያዘጋቸው ዘላለማዊ እሳት" መላእክቱ የእርሱ አጋዦች ታርዤ አላለበሳችሁኝም "ታርዤ አላለበሳችሁኝምን” ታምሜ እና ታስሬ "ታምሜ እነ ታስሬ"

Matthew 25:44

ማቴዎስ 25፡ 44-46

እነርሱም እንዲህ ብለው ይመልሱለታል "በግራው ያሉት" (MAT 25:41) ይመልሱለታል ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ "ከእነዚህ የእኔ ሕዝብ ከሆኑን ለአንዱም” ስላላደረጋችሁ "ለእኔ እንዳላደረጋችሁት አስባለሁ" ወይም "በእርግጥ ያልረዳችሁት እኔን ነው" ዘላለማዊ ቅጣት "ማብቂያ ያሌለው ቅጣት" ጻድቃን ወደ ዘላለም ሕይወት ይገባሉ "ጻድቅ የሆኑ ሰዎች ወደ ዘላለም ሕይወት ይገባሉ"


Translation Questions

Matthew 25:1

ሙሽራውን ሊቀበሉ በሚሄዱበት ጊዜ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ያላደረጉት ነገር ምንድነው?

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ከመብራታቸው ጋር ምንም ዓይነት ዘይት አልያዙም ነበር። [25:3]

ብልኆቹ ቆነጃጅት ሙሽራወንኢ ሊቀበሉ በሄዱ ጊዜ ም አደረጉ?

ብልኆቹ ቆነጃጅት ከመብራታቸው ጋር ትርፍ ዘይት ይዘው ነበር። [25:4]

Matthew 25:5

ሙሽራው የመጣው መቼ ነበር፣ የመጣው በሚጠበቅበት ጊዜ ላይ ነበር?

ሙሽራው የመጣው ከሚጠበቅበት ጊዜ ዘግይቶ በእኩለ ሌሊት ላይ ነበር። [25:5]

ሙሽራው የመጣው መቼ ነበር፣ የመጣው በሚጠበቅበት ጊዜ ላይ ነበር?

ሙሽራው የመጣው ከሚጠበቅበት ጊዜ ዘግይቶ በእኩለ ሌሊት ላይ ነበር። [25:6]

Matthew 25:10

ሙሽራው በመጣ ጊዜ ብልኆቹ ቆነጃጅት ምን ሆኑ?

ብልኆቹ ቆነጃጅት ከሙሽራው ጋር ወደ ሠርጉ ድግሥ ገቡ። [25:10]

ሙሽራው በመጣ ጊዜ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ምን ሆኑ?

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ዘይት ለመግዛት ሄዱ፣ ሲመለሱ ወደ ድግሡ የሚያስገባው በር ተዘጋባቸው። [25:10]

ሙሽራው በመጣ ጊዜ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ምን ሆኑ?

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ዘይት ለመግዛት ሄዱ፣ ሲመለሱ ወደ ድግሡ የሚያስገባው በር ተዘጋባቸው። [25:11]

ሙሽራው በመጣ ጊዜ ሰነፎቹ ቆነጃጅት ምን ሆኑ?

ሰነፎቹ ቆነጃጅት ዘይት ለመግዛት ሄዱ፣ ሲመለሱ ወደ ድግሡ የሚያስገባው በር ተዘጋባቸው። [25:12]

ከቆነጃጅቱ ምሳሌ አማኞች ምን እንዲማሩ ኢየሱስ እንደሚፈልግ ተናገረ?

ቀኑንና ሰዓቱን ስለማያውቊ አማኞች መጠንቀቅ እንዳለባቸው ኢየሱስ ተናገረ። [25:13]

Matthew 25:14

አምስት እና ሁለት ታላንት ያላቸው አገልጋዮች ጌታቸው በተጓዘ ጊዜ በታላንታቸው ምን አደረጉ?

አምስት ታላንት ያለው ሌላ አምስት ታላንት አተረፈ፣ ሁለት ታላንት ያለው ሌላ ሁለት ታላንት አተረፈ። [25:16]

Matthew 25:17

አንድ ታላንት ያለው ባርያ ጌታው በተጓዘ ጊዜ ታላንቱን ምን አደረገ?

አንድ ታላንት ያለው መሬቱን ቆፍሮ የጌታውን ገንዘብ ቀበረ። [25:18]

Matthew 25:19

ጌታው በጉዞው ለምን ያክል ጊዜ ርቆ ሄዶ ነበር?

ጌታው ለረጅም ጊዜ ርቆ ሄዶ ነበር። [25:19]

በተመለሰ ጊዜ፣ አምስት እና ሁለት ታላንት ለተሰጣቸው ባርያዎች ጌታቸው ምን አደረገ?

ጌታቸው “መልካም አንተ በጎና ታማኝ ባርያ!” አለውና በበርካታ ነገሮች ላይ ሾመው። [25:20]

በተመለሰ ጊዜ፣ አምስት እና ሁለት ታላንት ለተሰጣቸው ባርያዎች ጌታቸው ምን አደረገ?

ጌታቸው “መልካም አንተ በጎና ታማኝ ባርያ!” አለውና በበርካታ ነገሮች ላይ ሾመው። [25:21]

Matthew 25:26

በተመለሰ ጊዜ፣ አንድ ታላንት ተሰጥቶት በነበረው ባርያ ላይ ጌታው ምን አደረገ?

ጌታው “አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባርያ” አለውና አንዱን ታላንቱን ከወሰደበት በኋላ በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣለው። [25:26]

Matthew 25:31

የሰው ልጅ በሚመጣ እና በክብር ዙፋኑ ላይ በሚቀመጥ ጊዜ ምን ያደርጋል?

የሰው ልጅ ሕዝቦችን ሁሉ አከማችቶ ሰዎችን አንዳቸው ከሌላኛቸው ይለያቸዋል። [25:31]

የሰው ልጅ በሚመጣ እና በክብር ዙፋኑ ላይ በሚቀመጥ ጊዜ ምን ያደርጋል?

የሰው ልጅ ሕዝቦችን ሁሉ አከማችቶ ሰዎችን አንዳቸው ከሌላኛቸው ይለያቸዋል። [25:32]

Matthew 25:34

በንጉሡ ቀኝ ያሉት ምን ይቀበላሉ?

በንጉሡ ቀኝ እጅ ያሉት ከዓለም መፈጠር በፊት ጀምሮ ለእነርሱ የተዘጋጀላቸውን መንግሥት ይቀበላሉ። [25:34]

በንጉሡ ቀኝ ያሉት በሕይወታቸው ምን አድርገዋል?

በንጉሡ ቀኝ ያሉት ለተራቡት ምግብ ሰጥተዋል፣ የተጠሙትን አጠጥተዋል፣ እንግዶችን ተቀብለዋል፣ የታረዙትን አልብሰዋል፣ ለታመሙት እንክብካቤ አድርገዋል፣ እስረኞችንም ጎብኝተዋል። [25:35]

በንጉሡ ቀኝ ያሉት በሕይወታቸው ምን አድርገዋል?

በንጉሡ ቀኝ ያሉት ለተራቡት ምግብ ሰጥተዋል፣ የተጠሙትን አጠጥተዋል፣ እንግዶችን ተቀብለዋል፣ የታረዙትን አልብሰዋል፣ ለታመሙት እንክብካቤ አድርገዋል፣ እስረኞችንም ጎብኝተዋል። [25:36]

Matthew 25:41

በንጉሡ ግራ ያሉት ምን ይቀበላሉ?

በንጉሡ ግራ ያሉት ለዲያቢሎስ እና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀው የዘላለም እሳት ይጣላሉ። [25:41]

በንጉሡ ግራ ያሉት በሕይወታቸው ያላደረጓቸው ነገሮች ምንድናቸው?

በንጉሡ ግራ ያሉት ለተራቡት አላበሉም፣ ለተጠሙት አላጠጡም፣ እንግዶችን አልተቀበሉም፣ የታረዙትን አላለበሱም፣ የታመሙትን አልተንከባከቡም፣ እስረኞችንም አልጎበኙም። [25:42]

በንጉሡ ግራ ያሉት በሕይወታቸው ያላደረጓቸው ነገሮች ምንድናቸው?

በንጉሡ ግራ ያሉት ለተራቡት አላበሉም፣ ለተጠሙት አላጠጡም፣ እንግዶችን አልተቀበሉም፣ የታረዙትን አላለበሱም፣ የታመሙትን አልተንከባከቡም፣ እስረኞችንም አልጎበኙም። [25:43]


ምዕራፍ 26

1 ኢየሱስ እነዚህን ቃሎች ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ 2 "ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንደሚሆን ታውቃላችሁ፣ የሰው ልጅም ተሰቅሎ እንዲገደል ተላልፎ ይሰጣል፡፡" 3 ከዚያ የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ቀያፋ በሚሉት ሊቀ ካህናት ግቢ ውስጥ ተሰበሰቡ፤ 4 ኢየሱስን በረቀቀ ዘዴ ለማሰርና ለመግደል ተማከሩ፡፡ 5 ምክንያቱም፣ በሕዝቡ መሓል ረብሻ እንዳይነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም እያሉ ነበር፡፡ 6 ኢየሱስ በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት 7 ማዕድ ላይ ተቀምጦ እያለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ ያለበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣችና ራሱ ላይ አፈሰሰች፡፡ 8 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲያዩ በጣም ተቈጥተው፣ "ይህ ብክነት ምንድን ነው? 9 ይህ እኮ ከፍ ባለ ዋጋ ተሸጦ ገንዘቡን ለድኾች መስጠት ይቻል ነበር" አሉ፡፡ 10 ኢየሱስም ይህን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፣ "ይህችን ሴት ለምን ታስቸግሯታላችሁ? ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች፡፡ 11 ድኾች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልሆንም፡፡ 12 ይህን ሽቱ እኔ ላይ ባፈሰሰች ጊዜ ለቀብሬ አድርጋዋለች፡፡ 13 እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ወንጌል በመላው ዓለም ሲሰበክ ለእርሷ መታሰቢያ እንዲሆን ይህች ሴት ያደረገችውም ይነገርላታል።" 14 ከዚያም የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆቹ ሄዶ፣ 15 "እርሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ለእኔ ምን ትሰጡኛላችሁ?" አላቸው፡፡ እነርሱም ሠላሣ ጥሬ ብር ተመኑለት፡፡ 16 ከዚያ ጊዜ ወዲህ እርሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን ምቹ ጊዜ ይጠባበቅ ጀመር፡፡ 17 በቂጣ በዓል በመጀመሪያው ግን ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "የፋሲካን እራት እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?" አሉት፡፡ 18 እርሱም፣ "ከተማው ውስጥ ወዳለ አንድ ሰው ሂዱና፣ 'መምህሩ "ጊዜዬ ደርሷል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በአንተ ቤት ማክበር እፈልጋለሁ' ይልሃል በሉት'" አላቸው፡፡ 19 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንደ ነገራቸው አደረጉ፤ የፋሲካንም እራት አዘጋጁለት፡ 20 ምሽት ላይ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ለመብላት ተቀመጠ፡፡ 21 በመብላት ላይ እያሉ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል" አላቸው፡፡ 22 እነርሱ በጣም ዐዘኑ፤ እያንዳንዱም፣ "እኔ እሆንን?" በማለት ይጠያየቁ ጀመር፡፡ 23 እርሱም፣ "አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር እጁን ወደ ሳሕኑ የሚሰደው ነው፡፡ 24 የሰው ልጅ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈው ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ግን ወዮለት! ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር" በማለት መለሰላቸው፡፡ 25 አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳ፣ "መምህር ሆይ፣ እኔ ነኝ እንዴ?" አለው፤ እርሱም፣ "አንተው ራስህ ብለኸዋል" አለው፡፡ 26 በመብላት ላይ እያሉ፣ ኢየሱስ እንጀራ አንሥቶ ባርኮ ቈረሰ፡፡ "እንካችሁ ውሰዱ፣ ብሉት፤ ይህ ሥጋዬ ነው" ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ 27 ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነና ሰጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ "ሁላችሁም ጠጡት 28 ይህ ለብዙዎች ኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የኪዳኑ ደሜ ነው፡፡ 29 እንደ ገና በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር እስክጠጣው ድረስ ከእንግዲህ ከዚህ ወይን ፍሬ እንደማልጠጣ ግን እነግራችኋለሁ፡፡" 30 መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ፡፡ 31 ያኔ ኢየሱስ፣ "በዚህ ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ምክንያት ትሰናከላላችሁ፤ ምክንያቱም፣ 'እረኛውን እመታለሁ በጎቹም ይበተናሉ' ተብሎ ተጽፎአል፡፡ 32 ከተነሣሁ በኋላ ግን ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ" አላቸው፡፡ 33 ጴጥሮስ ግን፣ "ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እንኳ እኔ አልሰናከልም" አለው፡፡ 34 ኢየሱስም፣ "እውነት እልሃለሁ ፣ በዚህች ሌሊት ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ" አለው፡፡ 35 ጴጥሮስም፣ "ከአንተ ጋር መሞት ቢኖርብኝ እንኳ አልክድህም" አለ፡፡ ሌሎችም ደቀ መዛሙርት ሁሉ እንደዚያው አሉ፡፡ 36 ከዚያም ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደሚሉት ቦታ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱንም፣ "ወደዚያ ሄጄ እስክጸልይ ድረስ እዚህ ሁኑ" አላቸው፡፡ 37 ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዴዎስ ልጆች ይዞ ሄደ፤ ያዝንና ይጨነቅም ጀመር፡፡ ከዚያም፣ 38 "ነፍሴ፣ እስከ ሞት ድረስ በጣም ዐዝናለች፡፡ እዚህ ሆናችሁ ከእኔ ጋር ትጉ" አላቸው፡፡ 39 ጥቂት ራቅ ብሎ በመሄድ በግንባሩ ወድቆ ጸለየ፤ "አባት ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ፤ ይሁን እንጂ፣ የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን" አለ፡፡ 40 ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም፣ "ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት ያህል እንኳ መትጋት አልቻላችሁምን? 41 ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፡፡ መንፈስ በእርግጥ ፈቃደኛ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው" አለው፡፡ 42 ለሁለተኛ ጊዜ ጥቂት ፈቀቅ ብሎ ጸለየ፤ "አባት ሆይ፣ እኔ ካልጠጣሁት በቀር ይህ የማያልፍ ከሆነ፣ ፈቃድህ ይሁን" አለ፡፡ 43 እንደ ገና ሲመጣ ዐይኖቻቸው ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፡፡ 44 እንደ ገና ትቶአቸው ሄዶ ለሦስተኛ ጊዜ ያንኑ ቃል ጸለየ፡፡ 45 ከዚያም ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፣ "አሁንም ዐርፋችሁ ተኝታችኋል? ጊዜው ደርሷል፤ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፡፡ 46 እንግዲህ ተነሡ እንሂድ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል" አላቸው፡፡ 47 ገና እየተናገረ እያለ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፣ ከእርሱም ጋር ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች የመጡ ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ 48 በዚህ ጊዜ አሳልፎ የሚሰጠው፣ "እኔ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት" የሚል ምልክት ሰጣቸው፡፡ 49 ወዲያውኑ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ "መምህር ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!" ብሎ ሳመው፡፡ 50 ኢየሱስም፣ "ወዳጄ፣ የመጣህበትን ጉዳይ ፈጽም" አለው፡፡ ከዚያም መጡ ኢየሱስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፣ ያዙትም። 51 ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፍ አወጣ፤ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ጆሮ መትቶ ቈረጠ፡፡ 52 ያኔ ኢየሱስ፣ "ሰይፍህን ወደ ቦታው መልስ፤ ሰይፍ የሚያነሡ በሰይፍ ይጠፋሉ፡፡ 53 አባቴን ብጠይቅ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ መላእክት የማይልክልኝ ይመስልሃል? 54 እንደዚያ ከሆነ ይህ እንደሚሆን የሚናገረው መጽሐፉ ቃል እንዴት ይፈጸማል?" አለው፡፡ 55 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡ፣ "ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ መጣችሁ? በየቀኑ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ እያስተማርሁ ነበርሁ፡፡ እናንተም አልያዛችሁኝም ነበር፡፡ 56 የነቢያት መጽሐፍ እንዲፈጸም ይህ ሆኗል" አላቸው፡፡ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ፡፡ 57 ኢየሱስን የያዙ ሰዎች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ሽማግሌዎቹ ተሰብስበው ወደ ነበሩበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ቤት ወሰዱት፡፡ 58 ጴጥሮስ ግን ከሩቅ ሆኖ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ተከተለው፤ ወደ ውስጥ ገብቶም የሚሆነውን ለማየት ከጠባቂዎቹ ጋር ተቀመጠ፡፡ 59 እርሱን ለማስገደል የካህናት አለቆቹና ሸንጎው ሁሉ በኢየሱስ ላይ በሐሰት የሚመሰክሩበትን ሰዎች እየፈለጉ ነበር፡፡ 60 ምንም እንኳ ብዙ የሐሰት ምስክሮች ቢመጡም፤ በቂ ማስረጃ አላገኙም፡፡ በኋላ ግን ሁለት ሰዎች ወደ ፊት መጥተው፣ 61 "ይህ ሰው፣ 'የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ እንደ ገና ልሠራው እችላለሁ' ብሏል" አሉ፡፡ 62 ሊቀ ካህናቱ ተነሥቶ፣ "መልስ የለህም? በአንተ ላይ እየመሰከሩብህ ያለው ምንድን ነው?" አለው፡፡ 63 ኢየሱስ ግን ዝም አለ፡፡ ሊቀ ካህናቱም፣ "በሕያው እግዚአብሔር አዝሃለሁ፤ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን አለመሆንህን ንገረን" አለው፡፡ 64 ኢየሱስም፣ "አንተው ራስህ አልህ፤ ግን ልንገርህ፣ ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያለህ" በማለት መለሰለት፡፡ 65 ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀደደና፣ "እግዚአብሔርን ተሳድቧል፤ ታዲያ፣ ምስክር የምንፈልገው ለምንድን ነው? አሁን ስድቡን ሰምታችኋል 66 ለመሆኑ፣ ምን ታስባላችሁ?" አለ፡፡ እነርሱም መልሰው፣ "ሞት ይገባዋል" አሉ፡፡ 67 ከዚያም ፊቱ ላይ ተፉበት፣ በጡጫና በጥፊ መቱት፤ 68 "አንተ ክርስቶስ እስቲ ትንቢት ተናገር፡፡ ለመሆኑ፣ በጥፊ የመታህ ማን ነው?" አሉት፡፡ 69 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እደጅ ግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት አገልጋይ ልጅ ወደ እርሱ መጥታ፣ "አንተም ደግሞ ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርህ" አለችው፡፡ 70 እርሱ ግን፣ "ምን እየተናገርሽ እንደ ሆነ አላውቅም" በማለት በሁሉም ፊት ካደ፡፡ 71 ከግቢው ወደሚያስወጣው በር እየሄደ እያለ፣ ሌላ አገልጋይ ልጅ አየችውና እዚያ ለነበሩት፣ "ይህኛውም ሰውየ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበረ" አለች፡፡ 72 እርሱም፣ "ሰውየውን አላውቀወም" በማለት በመሐላ ጭምር በድጋሚ ካደ፡፡ 73 ጥቂት ቆየት ብሎ እዚያ ቆመው የነበሩት መጥተው ጴጥሮስን፣ "በርግጥ አንተም ብትሆን ከእነርሱ አንዱ ነህ፤ አነጋገርህ ራሱ ያጋልጥሃል" አሉት፡፡ 74 ከዚያም፣ "ሰውየውን ጨርሶ አላውቀውም" በማለት ይራገምና ይምል ጀመር፤ ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ፡፡ 75 ጴጥሮስ "ዶሮ ሳይጮኽ ሦስቴ ትክደኛለህ" በማለት ኢየሱስ የተናገረውን አስታወሰ፡፡ ከዚያ ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡



Matthew 26:1

ማቴዎስ 26፡1-2

በፈጸመ ጊዜ፥ በቋንቋችሁ አዲስ ታሪክ መጀመሪያን ማሳያ መንገድ ካለ ያንን ተጠቀሙ፡፡ እነዚህ ቃላትን በ MAT 24:4-25:46 ውስጥ ያሉትን ቃላት የሰው ልጅ እንዲሰቀል አሳልፈው ይሰጡታል "አንዳንድ ሰዎች የሰው ልጅን ለሚሰቅሉት አሳልፈው ይሰጡታል"

Matthew 26:3

ማቴዎስ 26፡3-5

ተሰበሰቡ "በምስጥር" በበዓል ቀን ግን አይደለም ለተርጓሚዎች ምክር፡ “በበዓል ቀን ኢየሱን መግደል የለብንም” በዓል ዓመታዊ የፈስካ በዓል

Matthew 26:6

ማቴዎስ 26፡6-9

ምግብ ለመብላት ተቀምጠው ሳለ በጎናቸው ጋደም ብለው፡፡ ሰዎች ምግብ ለመመገብ የሚቀመጡበትን መንገድ የሚገልጽን ቃል መጠቀም ትችላለህ፡፡ አንድት ሴት ወደ እርሱ መጥታ አንድደት ሴት ወደ ኢየሱስ መጥታ የአልባስጥሮስ ጠርሙስ ከለስላሳ ድንጋይ የሚሰራ በጣም ውድ መያዥያ ነው ሽቶ ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት የዚህ ብክነት ምክንያቱ ምንድ ነው? "ይህች ሴት ይህንን ሽቶ በማባከኗ መጥፎ ነገር አድርጋለች!"

Matthew 26:10

ማቴዎስ 26፡ 10-11

ይህችን ሴት ስለምን ታስጨንቋታላችሁ? "ይህችን ሴት ልታስጨንቋት አይገባም!" እናንተ . . . እናንተ . . . አናንተ ደቀ መዛሙርቱ

Matthew 26:12

ማቴዎስ 26፡ 12-13

Matthew 26:14

ማቴዎስ 26፡ 14-16

ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጣቸው ዘንድ “አሳልፌ እንድሰጣችሁ” ወይም "ኢየሱስን መያዝ ትችሉ ዘንድ" ሠላሣ ብር ይህ ቃል በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከሚገኘው የትንቢት መልዕክት ጋር ተመሳሳይ ቃል በመሆኑ የገንዘቡን መጠን በዘመናዊ የገንዘብ መጠን ከመጻፍ ይልቅ እንዳለ ማስቀመጡ ተመራጭ ነው፡፡ ለእነርሱ አሳልፎ ለመስጠት "የካህናት አለቆች ኢየሱስን ይዙት ዘንድ ለማገዝ”

Matthew 26:17

ማቴዎስ 26፡ 17-19

እርሱም፦ ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ፦ መምህር፦ ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ ይላል በሉት አለ።" ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ለሌላ ሰው ሄደው የኢየሱስን መልክት እንድነገሩት ነገራቸው፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ለደቀ መዛሙርቱ ወደ ከተማ እንዲሄዱ፣ ወደ አንድ ሰው ቤትም እንዲሄዱና መምህር እንዲህ ይልሃል ብለው እንድነግሩት ነገራቸው፡፡ “ጊዜዬ ቀርቦአል፡፡ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋስካን በአንተ ቤት ማሳለፍ እፈልጋለሁ” ብሏል ብላችሁ ንገሩት፡፡ ወይም “ ደቀ መዛሙርቱ ወደ አንድ ሰው ዘንድ እንዲሄዱና መምህራቸው ጊዜዬ ቀርቧል፤ ፋስካን በአንተ ቤት ከደቀ መዛሙርተቼ ጋር ማሳለፍ እፈልጋለሁ ብለው ይነግሩት ዘንድ ላካቸው፡፡” ጊዜዬ አማራጭ ትርጉሞች: 1) "የነገርኳችሁ ጊዜ" (UDB) or 2) "እግዚአብሔር ለእኔ አስቀድሞ ያዘጋጀው ጊዜ" ቀርቧል አማራጨ ትርጉሞች: 1) "ቅርብ ነው" ፋስካን ማክበር "የፋስካን መብል መብላት" ወይም "ልዩ የሆነ ምግብ በመብላት ፋስካን ማክበር"

Matthew 26:20

ማቴዎስ 26፡ 20-22

ምግብ ልመገብ ተቀመጠ በባሕላችሁ ሰዎች ምግብ ለመመገብ የሚቀመጡበትን መንግድ የሚገለጽ ቃልን ተጠቀሙ፡፡ ጌታዬ እኔ በእርግጠኝነት አይደለሁም? "በእርግጠኝነት እኔ አይደለሁም፣ ነኝ እንዴ ጌታዬ?"

Matthew 26:23

ማቴዎስ 26፡ 23-25

የሰው ልጅን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው "የሰው ልጅን የሚከዳ ሰው" አንተ ራስህ አልክ "አንተ ራስህ እንዳልከው አንተ ነህ" ወይም "አንተ ራስህ አሁን አመንክ"

Matthew 26:26

ማቴዎስ 26፡ 26-26

ወሰደ . . . ባረከው . . . ሰበረው ይህንን በ MAT 14:19 ላይ በተረጎምከው መሠረት ተርጉመው፡፡

Matthew 26:27

ማቴዎስ 26፡ 27-29

ወሰደ ይህንን በ MAT 14:19. ላይ በተረጎምከው መሠረት ተርጉመው፡፡ ሰጣቸው "ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው" ስለቃል ኪዳኑ የሚፈሰው ደሜ ነው "ኪዳኑ የጸና መሆኑን የሚያሳይ ደም ነው”ወይም “ኪዳን እንዲቻል ደረገ ደም ነው" የሚፈሰው "በሞቱ ጊዜ የሚፈሰው” ወይም “በቅርቡ ከአካሌ የሚፈሰው” ወይም ስሞት ከአካሌ የሚፈስ ደም ነው” የወይንን ፍሬ "ወይን" በአባቴ መንግስት ውስጥ አዲሱን ከእናንተ ጋር እስከሚጠጣት ጊዜ ድረስ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው፣ ደሙ በእርሱ ለሚያምኑት ከአባት ዘንድ የዘላለም የኃጢአት ይቅርታን ያስገኘው ኢየሱስ አባቱ በመስቀል ላይ የቀረበውን መስዋእት መርካቱን የሚያከብርበት ነው፡፡ “አባት” እና “ልጅ” የሚለው ቃል በሥላሴ አካላት መካከል መቀራረብ እና ቤተሰባዊ ህብረት ያለ መሆኑን የሚያሳይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል በመሆኑን እንዳለ በቁሙ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡

Matthew 26:30

ማቴዎስ 26፡ 30-32

መዝሙር ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚስጋና መዝሙር ይወድቃሉ "ትተውኝ ይሄዳሉ" የመንጋውም በጎች ይበተናሉ ለተርጓሚዎች ምክር፡ 1) "ሁሉን የበጎች መንጋዎች ይበተናሉ " (UDB) ወይም 2) "የበጎች መንጋዎቹ በሁሉም አቅጣጫ ይበተናሉ" የበጎች መንጋ ደቀ መዛሙርቱ ከተነሳሁ በኋላ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "እግዚአብሔር ካስነሳኝ በኋላ"

Matthew 26:33

ማቴዎስ 26፡ 33-35

ይበተናሉ ይህንን በ MAT 26:31 ላይ በተረጎምከው መሠረት ትረጉም ዶሮ ሳይጮኽ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "ፀሐይ ከመውጣቱ በፊት" ዶሮ ከመጮኹ rooster ልነጋጋ ሲል ዶሮ የሚያሰማቸው ከፍተኛ ጩኸት የዶሮ ጩኸት ዶሮ የሚያሰማው ጩኸት

Matthew 26:36

ማቴዎስ 26፡ 36-38

ኃዘን በጣም አዘነ

Matthew 26:39

ማቴዎስ 26፡ 39-41

በፊቱ ወድቆ ለመጸለይ ሆን ብሎ ፊቱን በመሬት ላይ መድፋት አባቴ ይህ በእግዚአብሔር እና በኢየሱስ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ የእግዚአብሔር የማዕረግ ስም ነው ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ ከ “ይህ ጽዋ” የሚለው ቃል ኢየሱስ ሊያልፈበት ያለውን መከራ የሚያመለክት ነው፡፡ ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን ይህ በሙሉ ዐዓረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “እኔ የሚፈልገው አታደርግ ነገር ግን አንተ የሚትፈልገውን አድርግ”"

Matthew 26:42

X

ማቴዎስ 26፡ 42-44

ሄደ "ኢየሱስ ሄደ" እኔ ካልጠጣሁት "የዚህ የመከራ ጽዋ የማልጠጣ ከሆነ" አባቴ ይህ በእግዚአብሔር እና በኢየሱስ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ የእግዚአብሔር የማዕረግ ስም ነው ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበር "እንቅልፍ ይዞዋቸው ነበር"

Matthew 26:45

ማቴዎስ 26፡ 45-46

ሰዓቲቱ ቀርባለች "ጊዜው ቀርቧል" በኃጡአተኞች እጅ "ኃጢአተኞች" ተመልከቱ "አሁን ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጡ"

Matthew 26:47

ማቴዎስ 26፡ 47-48

በመናገር ላይ ሳለ "ኢየሱስ እየተናገረ ሳለ" እንዲህ አለ “የሚስመው እርሱ ነውና ያዙት” "እርሱ የሚስመው እርሱ ነውና ያዙት” የሚስመው "አሁን የሚስመው" ወይም "እኔ የሚስመው ሰው" (UDB) መሳም ለአንድ ታላቅ መምህር የሚቀርብ አክብሮት

Matthew 26:49

ማቴዎስ 26፡ 49-50

ወደ ኢየሱስ መጥቶ "ይሁዳ ወደ ኢየሱስ መጥቶ" ሳመው "በመሳም ሰላም አለው" ኢየሱስን ያዙት ኢየሱስን ልጎዱት ያዙት ያዙት እስረኛ አደረጉት

Matthew 26:51

ማቴዎስ 26፡ 51-54

እነሆ ጸሐፊው አዲስ ሰውን በታሪኩ ውስጥ አካቷል፡፡ በቋንቋችሁ ይህንን ለማደረግ የሚያስችል መንገድ ሊኖር ይችላል፡፡ አባቴን እንድለምን እርሱም አሁን ከአሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት እንዲሰድልኝ የማይቻል ይመስልሃልን? ለተርጓሚዎች ምክር፡ "አባቴን መጥራት እንደሚችል፣ እርሱ ደግሞ ከዐሥራ ሁለት ጭፍሮች በላይ መላእክትን ልልክልኝ እንደሚችል ማወቅ ነበረባችሁ፡፡” አባቴ ይህ በእግዚአብሔር እና በኢየሱስ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ የእግዚአብሔር የማዕረግ ስም ነው ከዐሥራ ሁለት ጭፍሮች በላይ መላእክት የመላእክቱ ትክክለኛ ቁጥት ይህን ያኸል አስፈላጊ አይደለም ጭፍሮች የሮማዊያን ሠራዊት አከፋፈል ሆኒ አንዱ ስድት ሺህ ወታደሮችን ይይዛል

Matthew 26:55

ማቴዎስ 26፡ 55-56

ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? ለተርጓማች ምክር፡ “እኔ ወንበዴ እንዳልሆንኩ ታውቃላችሁ ስለዚህ እኔት ለመያዝ ሰይፍ እና ጎመድ ይዛችሁ መምጣታችሁ ስህተት ነው፡፡” ጎመድ ሰዎችን ለመምታት የሚሆን ጠንካራ ደረቅ ዱላ ተውት በቋንቋችሁ ከእርሱ ጋር መሆን ስገባቸው ትተውት መሄዳቸውን ለማመልከት የሚሆን ቃል ካለ ይህንን ቃል ተጠቀሙ፡፡

Matthew 26:57

ማቴዎስ 26፡ 57-58

Matthew 26:59

ማቴዎስ 26፡ 59-61

ሁለት ሰዎች ወደፊት መጥተው "ሁለት ሰዎች ቀርበው” (UDB) ወይም "ሁለት ምስክሮች ቀርበው" “እነዚህ ሰዎች እንዲህ አሉ፣ እኔ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ እንደገና እገነባለሁ” ለተርጓሚዎች ምክር: "የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሶ በሦስት ቀናት ውስጥ መልሶ እንደሚገነባ ስናገር ሰምተናል ብለው መሰከሩበት” ይህ ሰው እንዲህ አለ "ይህ ሰው ኢየሱስ እንዲህ አለ"

Matthew 26:62

ማቴዎስ 26፡ 62-64

በእርሱ ላይ መሰከሩበት "ምስክሮቹ በኢየሱስ ላይ መሰከሩ" የእግዚብሔር ልጅ ይህ በክርስቶስ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ በጣም አስፈላጊ የሆነ ስም ነው፡፡ አንተ ራስህ አልህ ኢየሱስ ራሱ እርሱ “ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ” አረጋግጧል፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “አንተው ራስህ እንዳልከው ነኝ” ወይም “አንተ ራስህ አሁን አመንክ” ነገር ግን እላችኋለሁ፥ እንግዲህ ወዲህ ኢየሱስ ለሊቀ ካህኑ እና በዚያ ላሉት ሰዎች በመመናር ላይ ነው፡፡ እንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ አማራጭ ትርጉሞች ›፡ 1) የሰው ልጅን ወደፊት የሆነ ጊዜ ያዩታል ወይም 2) “አሁን” የሚለው ቃ የሚያመለክተው የሰው ልጅ የሞተበትን፣ ከሞቱ የተነሳበትን እና ወደ ሰማይ ያረገዘበት ጊዜ ነው፡፡ በኃይል ቀኝ "ሁሉን ቻይ በሆነው በእግዚአብሔር ቀኝ” በሰማይም ደመና ሲመጣ "በሰማይ ዳመና ሆኖ ወደ መሬት ሲመጣ"

Matthew 26:65

ማቴዎስ 26፡ 65-66

ሊቀ ካህኑ ልብሱን ቀደደ ልብስ መቅደድ የሚያሳዝን ነገር በመሆኑ የተከሰተ ንዴት ምልክት ማሳያ ነው፡፡ እንዲህ ሲሉ መለሱለት "የአይሁድ መሪዎች እንዲህ ሲሉ መለሱለት"

Matthew 26:67

ማቴዎስ 26፡ 67-68

ከዚያ እነርሱ አማራጭ ትርጉሞች፡ “ከዚያም ከእነርሱ መካከል አንዳንዶቹ” ወይም “ከዚያ ወታደሮቹ” ፊቱ ላይ ተፉበት ይህ ስድብ ነው ትንቢት ንገረን በዚህ ሥፍራ “ትንቢት ንገረን” ማለት “በእግዚአብሔር ኃይል ንገረን” ማለታቸው እንጂ “ወደፊት የሚሆነውን ነገር ንገረን ማለታቸው አይደልም”

Matthew 26:69

ማቴዎስ 26፡ 69-70

እናንተ ስለምትሉት ነገር የማውቀው ነገር የለኝም ጴጥሮስ ይህች ገረድ እያለች ያለው ነገር ገብቶታል፡፡ ከኢየሱስ ጋር የነበረ መሆኑን ለመካድ ይህንን ቃል ተጠቀሟል፡፡

Matthew 26:71

ማቴዎስ 26፡ 71-72

እንዲህ ሲል "ጴጥሮስ እንዲህ ባለ ጊዜ" መግቢያ በግቢው አጥር መግቢያ በር

Matthew 26:73

ማቴዎስ 26፡ 73-75

ከእነርሱ አንዱ "ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ ነው" የንግግር ቅላጼህ ያስታውቃል "ከገሊላ እንደሆንክ ከንግግርህ ቅላጼ ማወቅ እንችላለን ምክንያቱም የሚትናገረው እንደ ገሊላ ሰዎች ነው፡፡" እምላለሁ “ይህን ሰው ፈጽሞ አላውቀውም” ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ይህን ሰው አላውቀውም”


Translation Questions

Matthew 26:1

በሁለት ቀናት ውስጥ እየመጣ እንደሆነ ኢየሱስ የተናገረው የአይሁድ በዓል ምን ነበር?

ፋሲካ በሁለት ቀናት ውስጥ እየመጣ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። [26:2]

Matthew 26:3

በሊቀ ካህናቱ መኖሪያ ውስጥ ሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎች ያሴሩ የነበረው ምን ነበር?

ኢየሱስን በስውር ለመያዝ አንአ ለመግደል እያሴሩ ነበር። [26:4]

ሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ የፈሩት ምን ነበር?

በበዓሉ ሰሞን ኢየሱስን ከገደሉ፣ ሕዝቡ እንዳያምጽ ፈርተው ነበር። [26:5]

Matthew 26:6

ሴቲቱ ውድ የሆነውን ሽቱ በኢየሱስ ራስ ላይ ስታፈስስ የደቀመዛሙርቱ አፀፋ ምን ነበር?

ደቀመዛሙርቱ ተቆጡ ሽቱውም ተሽጦ ገንዘቡ ለድሆች ያልተሰጠው ለምን እንደሆነ ማወቅ ፈለጉ። [26:6]

ሴቲቱ ውድ የሆነውን ሽቱ በኢየሱስ ራስ ላይ ስታፈስስ የደቀመዛሙርቱ አፀፋ ምን ነበር?

ደቀመዛሙርቱ ተቆጡ ሽቱውም ተሽጦ ገንዘቡ ለድሆች ያልተሰጠው ለምን እንደሆነ ማወቅ ፈለጉ። [26:7]

ሴቲቱ ውድ የሆነውን ሽቱ በኢየሱስ ራስ ላይ ስታፈስስ የደቀመዛሙርቱ አፀፋ ምን ነበር?

ደቀመዛሙርቱ ተቆጡ ሽቱውም ተሽጦ ገንዘቡ ለድሆች ያልተሰጠው ለምን እንደሆነ ማወቅ ፈለጉ። [26:8]

ሴቲቱ ውድ የሆነውን ሽቱ በኢየሱስ ራስ ላይ ስታፈስስ የደቀመዛሙርቱ አፀፋ ምን ነበር?

ደቀመዛሙርቱ ተቆጡ ሽቱውም ተሽጦ ገንዘቡ ለድሆች ያልተሰጠው ለምን እንደሆነ ማወቅ ፈለጉ። [26:9]

Matthew 26:12

ሴቲቱ ሽቱውን በእርሱ ላይ ያፈሰሰችው ለምን እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ?

ሴቲቱ ሽቱውን በእርሱ ላይ ያፈሰሰችው ለቀብሩ እንደሆነ ኢየሱስ ተናገረ። [26:12]

Matthew 26:14

የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን በሊቀ ካህናቱ እጅ አሳልፎ ለመስጠት የከፈለው ምን ነበር?

ይሁዳ ኢየሱስን በሊቀ ካህናቱ እጅ አሳልፎ ለመስጠት ሠላሳ የብር ሳንቲሞች ተከፍሎት ነበር። [26:14]

የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስን በሊቀ ካህናቱ እጅ አሳልፎ ለመስጠት የከፈለው ምን ነበር?

ይሁዳ ኢየሱስን በሊቀ ካህናቱ እጅ አሳልፎ ለመስጠት ሠላሳ የብር ሳንቲሞች ተከፍሎት ነበር። [26:15]

Matthew 26:20

ከደቀ መዛሙርቱ ስለ አንደኛው ኢየሱስ በመጨረሻው እራት ወቅት ያለው ምን ነበር?

ከደቀመዛሙርቱ አንደኛው አሳልፎ እንደሚሰጠው ኢየሱስ ተናገረ። [26:21]

Matthew 26:23

እርሱን አሳልፎ የሚሰጠው ሰው የወደፊት እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ?

እርሱን አሳልፎ የሰጠው ባይወለድ ይሻለው እንደነበረ ኢየሱስ ተናገረ። [26:24]

ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሚሆን ይሁዳ በጠየቀ ጊዜ ኢየሱስ እንዴት መለሰለት?

ኢየሱስ “አንተው ራስህ ነህ” ሲል መለሰለት። [26:25]

Matthew 26:26

ኅብስቱን አንስቶ ቆርሶ፣ ባርኮ ለደቀመዛሙርቱ ሲሰጣቸው ኢየሱስ ምን አለ?

ኢየሱስ “ውሰዱ፣ ብሉ፣ ይህ ስጋዬ ነው” አላቸው። [26:26]

Matthew 26:27

ቀጥሎ ለደቀመዛሙርቱ ስለሰጣቸው ጽዋ ኢየሱስ ምን አለ?

ጸዋው ስለ ኃጢአት ይቅርታ ለብዙዎች የሚፈስሰው የአዲስ ኪዳን ደም እንደሚሆን ኢየሱስ ተናገረ። [26:28]

Matthew 26:30

በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ኢየሱስ በዚያች ሌሊት ሁሉም ምን እንደሚያደርጉ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው?

ሁሉም ከእርሱ የተነሣ በዚያች ሌሊት እንደሚሰናከሉ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው። [26:30]

በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ኢየሱስ በዚያች ሌሊት ሁሉም ምን እንደሚያደርጉ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው?

ሁሉም ከእርሱ የተነሣ በዚያች ሌሊት እንደሚሰናከሉ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው። [26:31]

Matthew 26:33

ጴጥሮስ መቼም እንደማይሰናከል ሲናገር፣ በዚያች ሌሊት ምን እንደሚያደርግ ኢየሱስ ነገረው?

ጴጥሮስ ኢየሱስን በዚያች ሌሊት ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ እንደሚክደው ኢየሱስ ተናገረ። [26:33]

ጴጥሮስ መቼም እንደማይሰናከል ሲናገር፣ በዚያች ሌሊት ምን እንደሚያደርግ ኢየሱስ ነገረው?

ጴጥሮስ ኢየሱስን በዚያች ሌሊት ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ እንደሚክደው ኢየሱስ ተናገረ። [26:34]

Matthew 26:36

እርሱ በሚጸልይበት ጊዜ ጴጥሮስ እና ሁለቱ የዘብዴዎስ ልጆች ምን እንዲያደርጉ ኢየሱስ ጠየቃቸው?

በዚያ እንዲቆዩ እና ከእርሱ ጋር ነቅተው እንዲጠብቁ ኢየሱስ ጠየቃቸው። [26:37]

እርሱ በሚጸልይበት ጊዜ ጴጥሮስ እና ሁለቱ የዘብዴዎስ ልጆች ምን እንዲያደርጉ ኢየሱስ ጠየቃቸው?

በዚያ እንዲቆዩ እና ከእርሱ ጋር ነቅተው እንዲጠብቁ ኢየሱስ ጠየቃቸው። [26:38]

Matthew 26:39

በጸሎቱ ኢየሱስ ለአብ ምን ጥያቄ አቀረበ?

ኢየሱስ የጠየቀው የሚቻል ከሆነ፣ ይህ ጽዋ ከእርሱ እንዲያልፍ ነበር። [26:39]

ኢየሱስ ከጸሎት ሲመለስ ደቀመዛሙርቱ ምን እያደርጉ ነበር?

ኢየሱስ ከመጸለይ ሲመለስ ደቀመዛሙርት ተኝተው ነበር። [26:40]

Matthew 26:42

የኢየሱስ ፈቃድ ምንም ቢሆን ምን፣ ኢየሱስ እንዲደረግ የጸለየው ምን ነበር?

የኢየሱስ የራሱ ፈቃድ ምንም ቢሆን ምን፣ የአብ ፈቃድ እንዲደረግ ኢየሱስ ጸለየ። [26:42]

ኢየሱስ ለመሄድና ለመጸለይ ትቷቸው የሄደው ለምን ያክል ጊዜ ነው?

ለመሄድ እና ለመጸለይ ኢየሱስ ሦስት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ትቷቸው ሄደ። [26:42]

ኢየሱስ ለመሄድና ለመጸለይ ትቷቸው የሄደው ለምን ያክል ጊዜ ነው?

ለመሄድ እና ለመጸለይ ኢየሱስ ሦስት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ትቷቸው ሄደ። [26:43]

ኢየሱስ ለመሄድና ለመጸለይ ትቷቸው የሄደው ለምን ያክል ጊዜ ነው?

ለመሄድ እና ለመጸለይ ኢየሱስ ሦስት ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ትቷቸው ሄደ። [26:44]

Matthew 26:47

የሚይዙት ኢየሱስ መሆኑን ለይተው እንዲያውቁ ይሁዳ ለሕዝቡ የሰጣቸው ምልክት ምን ነበር?

የሚይዙት ኢየሱስ መሆኑን በምልክት እንዲያውቊ ይሁዳ ኢየሱስን ሳመው። [26:47]

የሚይዙት ኢየሱስ መሆኑን ለይተው እንዲያውቁ ይሁዳ ለሕዝቡ የሰጣቸው ምልክት ምን ነበር?

የሚይዙት ኢየሱስ መሆኑን በምልክት እንዲያውቊ ይሁዳ ኢየሱስን ሳመው። [26:48]

Matthew 26:51

ኢየሱስ በተያዘ ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ አንደኛው ምን አደረገ?

ከኢየሱስ ደቀመዛሙርት አንደኛው ሰይፉን መዝዞ የሊቀ ካህናቱን ባርያ ጆሮ ቆረጠ። [26:51]

ራሱን መከላከል ቢፈልግ ኖሮ ማድረግ ይችል ስለነበረው ነገር ኢየሱስ ምን አለ?

ዐሥራ ሁለት ጭፍራ ሙሉ መላእክትን ሊልክለት የሚችለውን አብን መጥራት እንደሚችል ኢየሱስ ተናገረ። [26:53]

በእነዚህ ክስተቶች እየተፈጸመ እንዳለ ኢየሱስ የተናገረው ምን ነበር?

በእነዚህ ክስተቶች የቅዱሳት መጻሕፍት ትንቢት እየተፈጸመ እንዳለ ኢየሱስ ተናገረ። [26:54]

Matthew 26:55

ከዚያ በኋላ ደቀመዛሙርት ሁሉ ምን አደረጉ?

ደቀመዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ። [26:56]

Matthew 26:59

ኢየሱስን ለመግደል ሊቀ ካህናቱ እና መላው ጉባዔ ይፈልጉ የነበረው ምን ነበር?

ኢየሱስን ለመግደል በኢየሱስ ላይ በሃሰት የሚመሰክሩትን ይፈልጉ ነበር። [26:59]

Matthew 26:62

ሊቀ ካህናቱ በሕያው እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠው ትእዛዝ ምን ነበር?

ሊቀ ካህናቱ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን አለመሆኑን እንዲነግራቸው ኢየሱስን አዘዘው። [26:63]

ለሊቀ ካህናቱ ትእዛዝ ኢየሱስ የሰጠው ምላሽ ምን የሚል ነበር?

ኢየሱስ “አንተ ራስህ ብለሃል” አለ። [26:64]

ሊቀ ካህናቱ እንደሚያይ ኢየሱስ የተናገረው ምንድነው?

የሰው ልጅ በልዑል ኃይል ቀኝ ሲቀመጥ፣ እንዲሁም በሰማይ ደመና ሲመጣ ሊቀ ካህናቱ እንደሚያይ ኢየሱስ ተናገረ። [26:64]

Matthew 26:65

ከዚያ በኋላ ሊቀ ካህናቱ በኢየሱስ ላይ ያቀረበው ውንጀላ ምን ነበር?

ኢየሱስ እንደተሳደበ አድርጎ ሊቀ ካህናቱ ከሰሰው። [26:65]

Matthew 26:67

እርሱን ከወነጀሉት በኋላ በኢየሱስ ላይ ምን አደረጉበት?

በኢየሱስ ፊት ላይ ተፉበት፣ መቱት፣ በጥፊ መቱት። [26:67]

Matthew 26:73

እርሱ ከኢየሱስ ጋር እንደነበረ አንድ ሰው በጠየቀው ጊዜ ጴጥሮስ ሦስት ጊዜ የመለሰው ምን ነበር?

ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደማያውቅ ሦስት ጊዜ መለሰ። [26:73]

እርሱ ከኢየሱስ ጋር እንደነበረ አንድ ሰው በጠየቀው ጊዜ ጴጥሮስ ሦስት ጊዜ የመለሰው ምን ነበር?

ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደማያውቅ ሦስት ጊዜ መለሰ። [26:74]

ጴጥሮስ ለሦስተኛ ጊዜ ምላሽ እንደሰጠ ምን ተከሰተ?

ጴጥሮስ ለሦስተኛ ጊዜ ምላሽ እንደሰጠ፣ ዶሮ ጮኸ። [26:74]

እርሱ ከኢየሱስ ጋር ለመሆኑ አንድ ሰው በጠየቀው ጊዜ ሦስቱን ጊዜያት ጴጥሮስ ምን ምላሽ ሰጠ?

ኢየሱስን እንደማያውቀው ጴጥሮስ መለሰ። [26:75]

ከሦስተኛው ምላሹ በኋላ ጴጥሮስ ምን አስታወሰ?

ዶሮ ሳይጮኽ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ እንዳለው ጴጥሮስ አስታወሰ። [26:75]


ምዕራፍ 27

1 ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስን ለመግደል ተማከሩ። 2 አስረው ወሰዱትና ለአገሩ ገዢው ለጲላጦስ አስረከቡት። 3 አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ኢየሱስ እንደ ተፈረደበት ባየ ጊዜ ተጸጸተ፣ ሠላሣውን ጥሬ ብር ለካህናት አለቆቹና ለሽማግሌዎቹ መልሶ፣ 4 "ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠት በድያለሁ" አለ። እነርሱ ግን፣ “ታዲያ፣ እኛን ምን አገባን? የራስህ ጉዳይ ነው” አሉት። 5 ከዚያም ጥሬ ብሩን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ወረወረና ወጥቶ ራሱን ሰቀለ። 6 የካህናት አለቆቹ ጥሬ ብሩን ወስደው፣ “ይህ የደም ዋጋ ስለ ሆነ፣ ከቤተ መቅደሱ ገንዘብ ጋር መቀላቀል ተገቢ አይደለም” አሉ። 7 እርስ በርሳቸው ተነጋግረው የእንግዶች መቀበሪያ እንዲሆን የሸክላ ሠሪውን መሬት ገዙበት። 8 ከዚህ የተነሣ ያ መሬት እስከዚህ ጊዜ ድረስ፣ “የደም መሬት” ተባለ። 9 በነቢዩ ኤርምያስ፣ “የእርሱ ዋጋ እንዲሆን የእስራኤል ልጆች የተመኑለትን ሠላሣ ጥሬ ብር ወሰዱ፣ 10 እግዚአብሔር እንደ አዘዘኝ ለሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉት” ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ። 11 ኢየሱስ በአገረ ገዢው ፊት ቆመ፤ አገረ ገዢውም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህ እንዴ?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተ እንዳልኸው ነው” በማለት መለሰለት። 12 የካህናት አለቆችና፣ ሽማግሌዎቹ፣ ሲከሱት ምንም አልመለሰም። 13 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ፣ “በአንተ ላይ የሚያቀርቡትን ክስ ሁሉ አትሰማምን?” አለው። 14 እርሱ ግን አንድ ቃል እንኳ ስላልመለሰለት አገረ ገዡ በጣም ተደነቀ። 15 በዓል ሲመጣ አገረ ገዢው ሕዝቡ የሚፈልጉትን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው። 16 በዚያን ጊዜ በርባን የሚሉት ከባድ ወንጀለኛ በእስር ቤት ውስጥ ነበር። 17 ተሰብስበው እያለ ጲላጦስ፣ “ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ፣ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን?” አላቸው። 18 ምክንያቱም አሳልፈው የሰጡት በቅናት መሆኑን ያውቅ ነበር። 19 በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ እያለ ሚስቱ፣ “በዚያ ንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ፤ እርሱን በተመለከተ በዚህ ሌሊት በሕልሜ ብዙ መከራ ተቀብያለሁ” የሚል ቃል ላከችበት። 20 የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ በርባን እንዲፈታና ኢየሱስ እንዲገደል እንዲጠይቁ ሕዝቡን ቀሰቀሱ። 21 አገረ ገዢው፣ “ከሁለቱ የትኛውን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፣”በርባንን” አሉ። 22 ጲላጦስም፣ “ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስንስ ምን ላድርገው?” አላቸው። ሁሉም፣ “ስቀለው” በማለት መለሱ። 23 እርሱም፣ “ለምን፣ የሠራው ወንጀል ምንድንነው?” አላቸው። እነርሱ ግን፣ “ስቀለው” እያሉ የበለጠ ጮኹ። 24 ስለዚህ ምንም ማድረግ እንዳልቻለና እንዲያውም ዐመፅ እየተነሣ መሆኑን ጲላጦስ ባየ ጊዜ፣ በሕዝቡ ፊት እጁን በውሃ ታጥቦ፣ “እኔ ከዚህ ንጹሕ ሰው ደም ነጻ ነኝ፤ ከእንግዲህ ኀላፊነቱ የእናንተው ነው” አለ። 25 ሕዝቡ ሁሉ፣ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” አሉ። 26 ከዚያም በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቅሉት ሰጣቸው። 27 የአገረ ገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱትና ወታደሮቹን ሁሉ ሰበሰቡ። 28 ልብሱን ገፍፈው ቀይ ልብስ አለበሱት። 29 ከዚያም የእሾኽ አክሊል ሠርተው በራሱ ላይ ደፉ፣ በቀኝ እጁ በትር አስያዙት፤ በፊቱ ተንበርክከውም፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ አሾፉበት። 30 ፊቱ ላይም ተፉበት፤ በትሩን ወስደው ራሱን መቱት። 31 ካፌዙበትም በኋላ ልብሱን አውልቀው የራሱን ልብስ አለበሱትና እንዲሰቀል ወሰዱት። 32 እንደወጡ ስምዖን የሚሉት የቀሬና ሰው አገኙ፤ መስቀሉን እንዲሸከም አስገደዱት። 33 ጎልጎታ ወደሚባል ቦታ መጡ፤ ትርጕሙም “የራስ ቅል” ማለት ነው። 34 ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሰጡት፤ እርሱ ግን ቀምሶ ሊጠጣው አልፈለገም። 35 በሰቀሉት ጊዜ ዕጣ በመጣጣል ልብሶቹን ተከፋፈሉ፤ 36 ተቀምጠው ይጠብቁትም ጀመር። 37 ከራሱ በላይ፣ “ይህ የአይሁድ ንጉሥ ኢየሱስ ነው” የሚል የክስ ጽሕፈት አኖሩ። 38 ሁለት ወንበዴዎች አንዱ በቀኙ ሌላው በግራው በኩል ከእርሱ ጋር ተሰቅለው ነበር። 39 የሚያልፉ ሰዎችም ሰደቡት፤ ራሳቸውን እየነቀነቁም 40 “ቤተ መቅደሱን የምታፈርስና በሦስት ቀን የምትሠራ ራስህን አድን። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ” ይሉት ነበር። 41 በተመሳሳይ መንገድ የካህናት አለቆች፣ ከአይሁድ የሕግ መምህራንና ከሽማግሌዎቹ ጋር አብረው፣ 42 “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አልቻለም። እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ነው፣ ከመስቀል ይውረድ፣ ከዚያም እኛ እናምንበታለን። 43 በእግዚአብሔር ተማምኖአል፤ እርሱ ከወደደ ያድነው፤ ምክንያቱም፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሏል" እያሉ ያፌዙበት ነበር። 44 ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም እንዲሁ ይሰድቡት ነበር። 45 ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ምድሩን ሁሉ የሚሸፍን ጨለማ ሆነ። 46 በዘጠኝ ሰዓት ኢየሱስ፣ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰባቅታኒ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጒሙም፣ “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ” ማለት ነው። 47 እዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ፣ “ኤልያስን እየተጣራ ነው” አሉ። 48 ወዲያውኑ ከእነርሱ አንዱ ሮጦ ሄደና ስፖንጁን የኮመጠጠ ወይን ጠጅ ውስጥ ነክሮ በሸንበቆ በትር አድርጎ እንዲጠጣ ሰጠው። 49 የተቀሩትም፣ "እስቲ ተዉት፤ ኤልያስ መጥቶ ሲያድነው እናያለን” አሉ። 50 ከዚያም ኢየሱስ በድጋሚ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን ሰጠ። 51 የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተከፈለ፤ ምድር ተናወጠ፤ ዐለቶችም ተሰነጠቁ፤ 52 መቃብሮች ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው የነበሩ ብዙ ቅዱሳን ተነሡ። 53 ከትንሣኤው በኋላ ከመቃብር ወጡ፤ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩ። 54 የመቶ አለቃውና ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩ ሰዎች የምድር መናወጡንና የሆኑትን ነገሮች ሲያዩ በጣም ፈርተው፣ "በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው" አሉ። 55 እርሱን ለመርዳት ከገሊላ ጀምሮ ኢየሱስን ተከትለው የነበሩ ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር። 56 ማርያም መግደላዊት፣ የያዕቆብና የዮሴፍ እናት ማርያም፣ እንዲሁም የዘብዲዎስ ልጆች እናት ከእነርሱ ጋር ነበሩ። 57 ምሽት ላይ ዮሴፍ የሚሉት አንድ ሀብታም ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱ ራሱ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር። 58 ወደ ጲላጦስ መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ። ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ። 59 ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ፤ በንጹሕ ናይለን ጨርቅ ጠቀለለውና 60 ለራሱ ከዐለት በሠራው መቃብር ውስጥ አኖረው። ከዚያም ትልቅ ድንጋይ አንከባልሎ መቃብሩ ደጃፍ ላይ አድርጎ ሄደ። 61 ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም መቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው በዚያ ነበሩ። 62 በሚቀጥለው ቀን ከዝግጅት በኋላ የካህናት አለቆቹና ፈሪሳውያን በአንድነት ከጲላጦስ ጋር ተሰበሰቡ። 63 እንዲህም አሉ፣ "ጌታ ሆይ፣ ያ አሳሳች በሕይወት በነበረ ጊዜ፣ 'ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ' ብሎ እንደ ነበር ትዝ አለን። 64 ስለሆነም፣ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ መቃብሩ በጥንቃቄ እንዲጠበቅ እዘዝ፤ አለበለዚያ ግን፣ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ሥጋውን ይሰርቁና ለሕዝቡ፣ ‘ከሞት ተነሣ’ ይላሉ፤ የኋላው ስሕተት ከመጀመሪያው የከፋ ይሆናል” አሉት። 65 ጲላጦስም፣ “ጠባቂ ወስዳችሁ፣ የሚቻላችሁን ያህል በጥንቃቄ እንዲጠበቅ አድርጉ” አላቸው። 66 ስለዚህ ሄደው መቃብሩ በጥንቃቄ እንዲጠበቅ አደረጉ፤ ድንጋዩን አተሙ፤ ጠባቂ አኖሩ።



Matthew 27:1

ማቴዎስ 27፡ 1-2

Matthew 27:3

ማቴዎስ 27፡ 3-5

ከዚያም ይሁዳ ይንን ባደረገ ጊዜ በቋንቋችሁ የተጀመረን አንድ ታሪክ አቋርጦ ሌላ ታሪክ መጀመሩን የሚያመለክት ቃል ካለ ይህንን ቃል በዚህ ሥፍራ ላይ ተጠቀም፡፡ ሠላሳ ብር የካህናት አለቆች ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ ይሰጣቸው ዘንድ ለይዳ የሰጤት ብር ነው (MAT 26:15) ንጹሕ ደም "መሞት የማይገባው ሰው"

Matthew 27:6

ማቴዎስ 27፡6-8

ይህንን ማድረግ ሕጋዊ አይደለም "ሕጋችን ይህንን እዲናደረግ አይፈቅድልንም" እንድናስቀመጥ "ይህንን ብር እንድናስቀመጥ" የደም ዋጋ አንድ ሰው እንዲሞት የሚከፈል ገንዘብ የሸክላ መሬት ይህ መሬት በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ምጻተኛ የሆነ ሰው ቢሞት የሚቀበርበት ቦታ ነው፡፡ እስከዛሬ ድረስ ጸሐፊው መጽሐፉን እስከ ጻፈበት ጊዜ ድረስ

Matthew 27:9

ማቴዎስ 27፡ 9-10

ነብዩ ኤርሚያስ እንዲህ በማለት የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈተመ "ነብዩ ኤርሚያስ ይህንን የትንቢት ቃል ተናገረ፤ እንደተናገውም ሆነ፡፡ ነብዩ ያለው እንዲህ ነው” የእስራኤል ሕዝቦች የእስራኤል የሃይማኖት መሪዎች እንደገመተኝ ነብዩ ኤርሚያስ እንደገመተው

Matthew 27:11

ማቴዎስ 27፡ 11-14

አሁን በቋንቋችሁ ውስጥ የተቋረጠው ታሪክ መቀጠሉን የሚያሳይ ቃል ካለ ይህንን ቃል መጠቀሙ መልካም ይሆናል፡፡ ሀገረ ገዥው ጵላጦስ (MAT 27:1) አንተ አልክ "አንተ ራሰህ ተቀበልከው" ይሁን እንጂ በካህናት ለቆች እና ሽማግሌዎች ክስ በቀረበበት ጊዜ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ነገር ግን የካህናት አለቆች እና ሽምግሌዎች በከሰሰቱት ጊዜ” በእንተ ላይ የሚያቀርቡትን ክስት አትሰማምን? "መጥፎ ነገር አድርጓል ብለው ለሚከሱህ ሰዎች ምንም ምላሽ አለመስጠትህ አስገርሞኛል!” አንዲት ቃል፣ በዚህም ገዥው በጣም ተገረመ፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ "አንዲት ቃል፤ ይህ ነገር ገዥውን እጅግ አስገረመው፡፡"

Matthew 27:15

ማቴዎስ 27፡ 15-16

አሁን ይህ ቃል በታሪኩ ፍሰት ውስጥ የእረፈት ጊዜ መኖሩ የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህም ጸሐፊው በ [MAT 27:17] ክብረ በዓል ፋስካ በዓል የሚከበርበት ጊዜ (MAT 26:2) በሕዝቡ የተመረጠው እስረኛ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ሕዝቡ የመረጠው እስረኛ” ነውጠኛ መጥፎ ነገር በማድረግ በጣም የሚታወቅ ሰው

Matthew 27:17

ማቴዎስ 27፡ 17-19

አሳልፈው ሰጡት ጵላጦስ ይፈርድበት ዘንድ "ኢየሱስን ወደ እርሱ አመጡ” በዚያም ተቀምጦ ሳለ "ጵላጦስ በዚያ ተቀምጦ ሳለ" በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳለ ፍርድን እንደሚሰጥ ሰው በስራው ላይ ሳለ መልዕክት ላከ "መልዕክት ላከ"

Matthew 27:20

ማቴዎስ 27፡ 20-22

ጠየቃቸው "ሕዝቡን ጠየቀ"

Matthew 27:23

ማቴዎስ 27፡ 23-24

ምን አድርጎ ነው "ኢየሱስ ምን አደረገ" በታላቅ ድምፅ ጮኹ "ሕዝቡም በታላቅ ድምፅ ጮኹ" ደሙ "ሞቱ"

Matthew 27:25

ማቴዎስ 27፡ 25-26

ደሙ በእኛ እና በልጆቻችን ላይ ይሁን፡፡ "አዎ! እኛ እና የእኛ ልጆች በደስታ እርሱን እንዲሞት የማድረግ ኃላፊነቱን እንወስዳን!"

Matthew 27:27

ማቴዎስ 27፡ 27-29

የገዥው ግቢ አማራጭ ትርጉሞች: 1) ወታደሮቹ የሚኖሩበት ሥፍራ ወይም 2) የገዥዎቹ መኖሪያ ልብሱን ገፈፉት "ልብሱን ገፈፉት" (UDB) ቀይ ልብስ ደማቅ ቀይ ልብስ ተዘባበቱበት "እናከብርሃን" ወይም "ረጅም እድሜ ኑር"

Matthew 27:30

ማቴዎስ 27፡ 30-31

እነርሱ . . . እነርሱ . . . እነርሱ የጵላጦስ ወታደሮች እርሱ . . . እርሱ . . . እርሱ . . . እርሱ . . . እርሱ ኢየሱስ

Matthew 27:32

ማቴዎስ 27፡ 32-34

ከዚያ በወጡ ጊዜ "ከእየሩሳሌም እየወጡ ሳለ" የእርሱን መስቀል ይሸከም ዘንድ አስገደዱት "ወታደሮቹ የኢየሱስን መስቀል ይሸከም ዘንድ አስገደዱት" ጎልጎታ ወደ ተባለ ሥፍራ "ሰዎች ጎልጎታ ብለው ወደሚጠሩት ሥፍራ" ሐሞት ሰውነታችን ምግብን ለመፍጨት የሚጠቀምበት ብጫ ፈሳሽ ነገር

Matthew 27:35

ማቴዎስ 27፡ 35-37

ልብስ ኢየሱስ ይለብሰው የነበረውን ልብስ

Matthew 27:38

X

ማቴዎስ 27፡ 38-40

ከእርሱ ጋር ሁለት ወንበዴዎች ተሰቅለው ነበር ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ወታደሮቹ ሁለት ወንበዴዎችን ከኢየሱስ ጋር ሰቀሉ”፡፡ ራሳቸውን እየነቀነቁ ይህንን ያደረጉት በኢየሱስ ላይ ለመሳለቅ ነው፡፡ አንተ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ከመስቀል ውረድ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆኑ ስለማያምኑ ይህን እንዲያረጋግጥላቸው ጠየቁት፡፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “አንተ በእርግጥ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ከመስቀል በመውረድ ይህንን አረጋግጥልን አሉት” የእግዚብሔር ልጅ ይህ በክርስቶስ እና በእግዚአብሔር ልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያስረዳ በጣም አስፈላጊ የሆነ ስም ነው፡፡

Matthew 27:41

ማቴዎስ 27፡ 41-42

ሌሎቹን አዳነ ነገር ግን ራሱን ማዳን አልቻለም አማራጭ ትርጓሜዎች፡ 1) የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስ ሌሎችን እንዳዳነ አያምኑም ወይም ራሱንም ማዳን እንደሚችል አያምኑም ወይም 2) ሌሎችን እንዳዳነ ያምናሉ ነገር ግን ራሱን ማዳን ስላልቻለ ሳቁበት፡፡ እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ነው መሪዎቹ የእስራኤል ንጉሥ እንደሆነ አያምኑም ነበር

Matthew 27:43

ማቴዎስ 27፡ 43-44

የእግዚብሔር ልጅ ይህ በክርስቶስ እና በእግዚአብሔር ልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያስረዳ በጣም አስፈላጊ የሆነ ስም ነው፡፡ ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም "ወታደሮቹ ከኢየሱስ ጋር የሰቀሏቸው ወንበዴዎችም

Matthew 27:45

ማቴዎስ 27፡ 45-47

ጮኸ "ተጣራ" ወይም "በታላቅ ድምፅ ጮኸ" ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ተርጓሚዎች ብዙ ጊዜ እነዚህ ቃላት እንዳሉ በዕብራይስጥ ቋንቋዎች ይተዋቸዋል፡፡

Matthew 27:48

ማቴዎስ 27፡ 48-50

ከእነርሱ መካከል አንዱ አማራጭ ትርጉሞች፡ 1) ከወታደሮቹ መካከል አንዱ ወይም 2) ቆመው ከሚመለከቱት መካከል አንዱ እስፖንጅ ከባሕር እንስሳት መካከል የሚሰበሰብ ውሃ ለመያዥያነት የሚገለግል፡፡ ለእርሱ ሰጠው "ለኢየሱስ ሰጠው

Matthew 27:51

ማቴዎስ 27፡ 51-53

እነሆ ይህ ቃል ሰዎች ከዚህ በኋላ ለሚነገረው ነገር አጽኖት እንዲሰጡ የሚጨመር ቃል ነው፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ተመልከቱ” ወይም “አድምጡ” ወይም “አሁን ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ”:: መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤ "እግዚብሔር መቃብሮችን ከፍቶ ከሞቱት መካል ብዙ ቅዱሳንን ከሞት አስነሣ ተኝተው የነበሩ "የሞቱ" መቃብሮችም ተከፍተው . . . ለብዙዎች ታዩ። ሁኔታዎቹ የተፈጸሙበት የጊዜ ቅደም ተከተል ግልጽ አይደለም፡፡ ሊሆነ የሚችሉት የጊዜ ቅደም ተከተሎች፡ ኢየሱስ ሲሞት በተነሳው ከተነሳው የምድር መንቀጥቀጥ በኋላ መቃብሮች ተከፈቱ 1) ቅዱሳን ተነሱ፣ ኢየሱስ ከሞት ተነሣ እና ቅዱሳን ወደ ከተማው ገቡ እና ለብዙዎች ታዩ ወይም 2) ኢየሱስ ከሞት ተነሣ እና ቅዱሳን ከሞት ተነሡ፣ ወደ ከተማ ገቡ እና ለብዙዎች ታዩ፡፡

Matthew 27:54

ማቴዎስ 27፡ 54-56

የእግዚብሔር ልጅ ይህ በክርስቶስ እና በእግዚአብሔር ልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያስረዳ በጣም አስፈላጊ የሆነ ስም ነው፡፡

Matthew 27:57

ማቴዎስ 27፡ 57-58

ከዚያም ጵላጦስ ይሰጠው ዘንድ አዘዘ "ከዚያም ጵላጦስ ወታደሮቹን የኢየሱስ በድን ለዮሴፍ ይሰጠው ዘንድ አዘዘ፡፡”

Matthew 27:59

ማቴዎስ 27፡ 59-61

ለስላሳ ጨርቅ ብዙ ብር የሚያወጣ ጨርቅ ከመቃብሩ ተቃራኒ "ከመቃብሩ ማዶ"

Matthew 27:62

ማቴዎስ 27፡ 62-64

ዝግጅት ለፋስካ በዓል የሚዘጋጁበት ጊዜ ነበር ይህ አሳች በሕይወት እያለ "አሳቹ ኢየሱስ በሕይወት እያለ"

Matthew 27:65

ማቴዎስ 27፡ 65-66

ጠባቂ 4 እስከ 16 የሮማዊያን ወታደሮች ድንጋዩን በማሕተም አትመው አማራጭ ትርጓሜዎች: 1) በድንጋዩ ዙሪያ ገመድ በማድረግ ወደ መቃብሩ ሌላኛው መግቢያ ጋር በማያያዝ አሠሩት ወይም 2) በድንጋዩ ና በግድግዳው መካከል ማሕተም አኖሩ፡፡ ጠባቂዎች በዚያ አኖሩ "ወታደሮቹ ሰዎች መቃብሩን መንካት የማይችሉበት ቦታ እንዲቆሙ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡"


Translation Questions

Matthew 27:1

በማለዳ፣ ሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ ኢየሱስን ወደ የት ወሰዱት?

ሲነጋ ወደ ገዢው ወደ ጲላጦስ ወሰዱት። [27:2]

Matthew 27:3

የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስ እንደተፈረደበት ባየ ጊዜ ምን አደረገ?

ንፁህ ደም አሳልፎ በመስጠቱ ይሁዳ ተጸጸተ፣ ብሩን መልሶ ወጣና ራሱን ሰቅሎ ሞተ። [27:3]

የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስ እንደተፈረደበት ባየ ጊዜ ምን አደረገ?

ንፁህ ደም አሳልፎ በመስጠቱ ይሁዳ ተጸጸተ፣ ብሩን መልሶ ወጣና ራሱን ሰቅሎ ሞተ። [27:4]

የአስቆሮቱ ይሁዳ ኢየሱስ እንደተፈረደበት ባየ ጊዜ ምን አደረገ?

ንፁህ ደም አሳልፎ በመስጠቱ ይሁዳ ተጸጸተ፣ ብሩን መልሶ ወጣና ራሱን ሰቅሎ ሞተ። [27:5]

Matthew 27:6

ሊቀ ካህናቱ በሠላሳው ብር ምን አደረጉበት?

የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቅበሪያ ገዙበት። [27:6]

ሊቀ ካህናቱ በሠላሳው ብር ምን አደረጉበት?

የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቅበሪያ ገዙበት። [27:7]

Matthew 27:9

እነዚህ ክስተቶች የማንን ትንቢት ይፈጽማሉ?

እነዚህ ክስተቶች የኤርምያስን ትንቢት ይፈጽማሉ። [27:9]

እነዚህ ክስተቶች የማንን ትንቢት ይፈጽማሉ?

እነዚህ ክስተቶች የኤርምያስን ትንቢት ይፈጽማሉ። [27:10]

Matthew 27:11

ጲላጦስ ኢየሱስን የጠየቀው ጥያቄ ምን ነበር፣ የኢየሱስስ መልስ ምን ነበር?

ጲላጦስ ኢየሱስን የጠየቀው እርሱ የአይሁድ ንጉሥ እንደሆነ ሲሆን፣ ኢየሱስ የመለሰው “አንተ እንዳልከው ነው” የሚል ነበር። [27:11]

ለሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ ውንጀላዎች ሁሉ ኢየሱስ የሰጠው ምላሽ ምን ነበር?

ኢየሱስ አንዲትም ቃል እንኳን አልመለሰለትም። [27:12]

ለሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ ውንጀላዎች ሁሉ ኢየሱስ የሰጠው ምላሽ ምን ነበር?

ኢየሱስ አንዲትም ቃል እንኳን አልመለሰለትም። [27:13]

ለሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ ውንጀላዎች ሁሉ ኢየሱስ የሰጠው ምላሽ ምን ነበር?

ኢየሱስ አንዲትም ቃል እንኳን አልመለሰለትም። [27:14]

Matthew 27:15

ጲላጦስ እንደ ፋሲካ በዓል ልማድ ለኢየሱስ ምን ማድረግ ፈልጎ ነበር?

ጲላጦስ እንደ ፋሲካ በዓል ልማድ ኢየሱስን ለመልቀቅ ፈልጎ ነበር። [27:15]

ጲላጦስ እንደ ፋሲካ በዓል ልማድ ለኢየሱስ ምን ማድረግ ፈልጎ ነበር?

ጲላጦስ እንደ ፋሲካ በዓል ልማድ ኢየሱስን ለመልቀቅ ፈልጎ ነበር። [27:16]

Matthew 27:17

የጲላጦስ ሚስት እርሱ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳለ ምን መልእክት ላከችበት?

በዚያ ንጹህ ሰው ላይ ምንም እንዳያደርግበት ለጲላጦስ ነገረችው። [27:19]

Matthew 27:20

እንደ አይሁድ ልማድ በርባን እንጂ ኢየሱስ ያልተፈታው ለምን ነበር?

ሊቀ ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ ከኢየሱስ ይልቅ በርባን እንዲፈታላቸው ሕዝቡን አሳምነው ነበር። [27:20]

በኢየሱስ ላይ እንዲደረግበት ሕዝቡ ምን እያለ ጮኸ?

ኢየሱስ እንዲሰቀል እንደሚፈልጉ ሕዝቡ ጮኸ። [27:22]

Matthew 27:23

ጲላጦስ አመፅ እንደተቀሰቀሰ ሲያይ፣ ምን አደረገ?

ጲላጦስ እጆቹን ታጠበ፣ ከዚህ ንፁህ ሰው ደም ንፁህ እንደሆነ ተናገረና ኢየሱስን ለሕዝቡ አሳልፎ ሰጠ። [27:24]

Matthew 27:25

ጲላጦስ ኢየሱስን አሳልፎ በሰጣቸው ጊዜ ሕዝቡ ምን አሉ?

ሕዝቡ “ደሙ በእኛ እና በልጆቻችን ላይ ይሁን” አሉ። [27:25]

Matthew 27:27

የገዢው ወታደሮች በኢየሱስ ላይ ምን አደረጉበት?

ወታደሮቹ ቀይ ልብስ አለበሱትና በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል አደረጉበት። [27:27]

የገዢው ወታደሮች በኢየሱስ ላይ ምን አደረጉበት?

ወታደሮቹ ቀይ ልብስ አለበሱትና በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል አደረጉበት። [27:28]

የገዢው ወታደሮች በኢየሱስ ላይ ምን አደረጉበት?

ወታደሮቹ ቀይ ልብስ አለበሱትና በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል አደረጉበት። [27:29]

Matthew 27:32

የቀሬናው ስምዖን ምን እንዲያደርግ ተገደደ?

ስምዖን የኢየሱስን መስቀል እንዲሸከም ተገደደ። [27:32]

ኢየሱስን ለመስቀል የት ሄዱ?

“የራስ ቅል ስፍራ” ማለት ወደ ሆነው ጎልጎታ ሄዱ። [27:33]

Matthew 27:35

ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ ወታደሮቹ ምን አደረጉ?

ወታደሮቹ የኢየሱስን ልብስ ለመከፋፈል እጣ ተጣጣሉ፣ ከዚያም ተቀምጠው ይጠብቊት ነበር። [27:35]

ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ ወታደሮቹ ምን አደረጉ?

ወታደሮቹ የኢየሱስን ልብስ ለመከፋፈል እጣ ተጣጣሉ፣ ከዚያም ተቀምጠው ይጠብቊት ነበር። [27:36]

ከኢየሱስ ራስ በላይ ያኖሩት ጽሑፍ ምን የሚል ነበር?

“ይህ የአይሁድ ንጉሥ ነው” የሚል ጻፉ። [27:37]

Matthew 27:38

ከኢየሱስ ጋር አብሮ የተሰቀለው ማን ነበር?

ሁለት ወንበዴዎች ከኢየሱስ ጋር ተሰቅለው የነበረ ሲሆን፣ አንደኛው በቀኙ፣ ሌላኛው በግራው ነበሩ። [27:38]

Matthew 27:41

ሕዝቡ፣ ሊቀ ካህናቱ፣ ጸሐፍት እና ሽማግሌዎች ኢየሱስ ምን እንዲያደርግ ሞገቱት?

ሁሉም ራሱን እንዲያድን እና ከመስቀል እንዲወርድ ሞገቱት። [27:42]

Matthew 27:45

ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ምን ተከሰተ?

ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ጨለማ በመላው ምድር ላይ መጥቶ ነበር። [27:45]

በዘጠነኛው ሰዓት ላይ ኢየሱስ ምን ብሎ ጮኸ?

ኢየሱስ “አምላኬ፣ አምላኬ፣ ስለምን ተውኸኝ?” በማለት ጮኸ [27:46]

Matthew 27:48

ኢየሱስ በድጋሚ በታላቅ ድምፅ ከጮኸ በኋላ ምን ተከሰተ?

ኢየሱስ መንፈሱን ተወ። [27:50]

Matthew 27:51

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በቤተመቅስ ውስጥ ምን ተከሰተ?

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ የቤተመቅደሱ መጋረጃ ከጫፍ እስከ ታች ድረስ ለሁለት ተቀደደ። [27:51]

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በመቃብሮች ላይ ምን ተከሰተ?

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ አንቀላፍተው የነበሩት በርካታ ቅዱሳን ተነሥተው ለብዙዎች ታዩ። [27:52]

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ በመቃብሮች ላይ ምን ተከሰተ?

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ አንቀላፍተው የነበሩት በርካታ ቅዱሳን ተነሥተው ለብዙዎች ታዩ። [27:53]

Matthew 27:54

እነዚህን ሁሉ ክስተቶች ካየ በኋላ የመቶ አለቃው ምስክርነት ምን የሚል ነበር?

መቶ አለቃው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር” አለ። [27:54]

Matthew 27:57

ከተሰቀለ በኋላ፣ በኢየሱስ ስጋ ላይ ምን ተከሰተ?

ባለጠጋ የነበረው የኢሱስ ደቀ መዝሙር ዮሴፍ፣ ስጋውን ከጲላጦስ ጠይቆ በበፍታ ጠቀለለውና በአዲስ መቃብር ውስጥ አኖረው። [27:57]

እርሱ ከተሰቀለ በኋላ፣ በኢየሱስ ስጋ ላይ ምን ሆነ?

ባለጠጋ የነበረው የኢሱስ ደቀ መዝሙር ዮሴፍ፣ ስጋውን ከጲላጦስ ጠይቆ በበፍታ ጠቀለለውና በአዲስ መቃብር ውስጥ አኖረው። [27:58]

Matthew 27:59

የኢየሱስ ስጋ አርፎበት ከነበረበት ቦታ በተቃራኒ በበራፉ ምን ተቀምጦ ነበር?

የኢየሱስ ስጋ አርፎበት በነበረበት ቦታ በተቃራኒ በበራፉ ትልቅ ድንጋይ ተቀምጦ ነበር። [27:60]

Matthew 27:62

በቀጣዩ ቀን ሊቀ ካህናት እና ፈሪሳውያን ከጲላጦስ ጋር የተገናኙት ለምን ነበር?

ሊቀ ካህናቱ እና ፈሪሳውያን የኢየሱስ መቃብር በደንብ እየተጠበቀ መሆኑን፣ ከዚያም የተነሣ ማንም ሰውነቱን እንደማይሰርቀው እርግጠኛ መሆን ፈለጉ። [27:62]

በቀጣዩ ቀን ሊቀ ካህናት እና ፈሪሳውያን ከጲላጦስ ጋር የተገናኙት ለምን ነበር?

ሊቀ ካህናቱ እና ፈሪሳውያን የኢየሱስ መቃብር በደንብ እየተጠበቀ መሆኑን፣ ከዚያም የተነሣ ማንም ሰውነቱን እንደማይሰርቀው እርግጠኛ መሆን ፈለጉ። [27:63]

በቀጣዩ ቀን ሊቀ ካህናት እና ፈሪሳውያን ከጲላጦስ ጋር የተገናኙት ለምን ነበር?

ሊቀ ካህናቱ እና ፈሪሳውያን የኢየሱስ መቃብር በደንብ እየተጠበቀ መሆኑን፣ ከዚያም የተነሣ ማንም ሰውነቱን እንደማይሰርቀው እርግጠኛ መሆን ፈለጉ። [27:64]

Matthew 27:65

በመቃብሩ ላይ ምን እንዲያደርጉ ጲላጦስ ፈቀደላቸው?

ጲላጦስ ድንጋዩን እንዲያትሙ እና ጠባቂዎችን በመቃብሩ ላይ እንዲያቆሙ ፈቀደላቸው። [27:65]

በመቃብሩ ላይ ምን እንዲያደርጉ ጲላጦስ ፈቀደላቸው?

ጲላጦስ ድንጋዩን እንዲያትሙ እና ጠባቂዎችን በመቃብሩ ላይ እንዲያቆሙ ፈቀደላቸው። [27:66]


ምዕራፍ 28

1 ሰንበት እንዳለፈ፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ማለዳ፣ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም ወደ መቃብሩ መጡ። 2 የጌታ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ነበርና ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ መጥቶም ድንጋዩን አንከባልሎ በላዩ ተቀመጠ። 3 መልኩ እንደ መብረቅ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር። 4 ጠባቂዎቹ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ እንደ ሞተ ሰውም ሆኑ። 5 መልአኩም እንዲህ በማለት ተናገረ፤ "አትፍሩ፤ ተሰቅሎ የነበረውን ክርስቶስን እንደምትፈልጉ አውቃለሁ። 6 እንደ ተናገረ ተነሥቷል እንጂ፣ እዚህ የለም፤ ኑና የነበረበትን ቦታ እዩ። 7 በፍጥነት ሄዳችሁ፣ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ በማለት ንገሩ፤ 'እርሱ ከሞት ተነሥቷል፤ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል። እዚያ ታዩታላችሁ።' እንግዲህ ነግሬአችኋለሁ።” 8 ሴቶቹ ፈጥነው በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር ከመቃብሩ እየሮጡ ሄዱ። 9 እነሆ ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ሴቶቹም እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት። 10 ከዚያም ኢየሱስ፣ "አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሩ፤ እዚያ ያዩኛል" አላቸው። 11 ሴቶቹ እየሄዱ እያሉ፣ ከጠባቂዎች ጥቂቱ ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ሁሉ ለካህናት አለቆቹ ነገሩ። 12 ካህናቱ ከሽማግሌዎቹ ጋር ተገናኝተው የሆነውን ሁሉ ሲናገሩ፣ ለወታደሮቹ ብዙ ገንዘብ በመስጠት፣ 13 “እኛ ተኝተን እያለ ፣ ሌሊት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መጥተው አስክሬኑን ሰረቁ” ብለው እንዲናገሩ ነገሩዋቸው። 14 ይህ ወሬ ወደ አገረ ገዢው ከደረሰ፤ እኛ እናሳምነዋለን፣ እናንተም ከሥጋት ነጻ ትሆናላችሁ" አሏቸው። 15 ወታደሮቹ ገንዘቡን ተቀብለው ፣ እንደ ተነገራቸው አደረጉ። ይህ ወሬ እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁድ መሐል በሰፊው ተሰራጭቷል። 16 ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ወደ ገሊላ ኢየሱስ ወደ ነገራቸው ተራራ ሄዱ። 17 ባዩት ጊዜ ሰገዱለት፤ አንዳንዶቹ ግን ተጠራጥረው ነበር። 18 ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጥቶ፣ “በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠኝ። 19 ስለዚህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ፣ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስም ስም እያጠመቃችኋቸው፤ 20 እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲያደርጉ እያስተማራችኋቸው፤ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”



Matthew 28:1

ማቴዎስ 28፡ 1-2

በሰንበትም በሳምንቱ መጀመሪያው ቀን መጨረሻ "ሰንበት ካለቀ በኋላ የእሁድ ማለዳ ጸሐይ መውጣት ሲጀምር" ሌላኛዋ ማሪያም "ማሪያም ተብላ የሚትጠራዋ ሌላኛዋ ሴት” የያዕቆብ እና የዮሴፍ እናት የሆነችው ማሪያም (MAT 27:56) እነሆ ይህ ቃል ሰዎች ከዚህ በኋላ ለሚነገረው ነገር አጽኖት እንዲሰጡ የሚጨመር ቃል ነው፡ ለተርጓሚዎች ምክር፡ “ተመልከቱ” ወይም “አድምጡ” ወይም “አሁን ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ”:: የጌታ መላእክት በመውረዳቸው . . . እና ድንጋዩን በማንከባለላቸው ምክንያት ታላቅ የመሬት መናወጥ ሆነ አማራጭ ትርጉሞች: 1) የመሬት መናወጡ የተከሰተበት ምክንያት መላእክት በመውረዳቸው እና ድንጋዩን በማንከባለላቸው ነው (ULB) ወይም 2) እነዚህ ሁሉም ነገሮች የሆኑት በተመሳሳይ ጊዜ ነው (UDB). የመሬት መናወጥ (መንቀጥቀጥ) ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የመሬት መንቀጥቀጥ

Matthew 28:3

ማቴዎስ 28፡ 3-4

የእርሱ መልክ "የመልአክ መልክ" መብረቅ ይመስል ነበር "እንደ መብረቅ ያበራ ነበር" እንደ በረዶ ነጭ ነበር "በከፍተኛ ሁኔታ ያንጸባርቅ ነበር" እንደ ሞተ ሰው "መንቀሳቀስ ያቃተው"

Matthew 28:5

ማቴዎስ 28፡ 5-7

ሴቶቹ "መግደላዊት ማሪያም እና ማሪያም ተብላ የተጠራው ሌላኛዋ ሴት" የተሰቀለው "ሕዝቡ እና ወታደሮቹ የሰቀሉት" ነገር ግን ተነሣ " ገር ግን እግዚአብሔር አስነሣው"

Matthew 28:8

ማቴዎስ 28፡ 8-10

ሴቶቹ "መግደላዊት ማሪያም እና ማሪያም ተብላ የሚትጠራው ሌላኛይቱ ሴት" እነሆ ጸሐፊው አንድ አስደናቂ ነገር ልሆን እንዳለ ለአንባቢዮቹ ያስታውቃቸዋል፡፡ በቋንቋችሁ ይህን ዓይነቱን ነገር ማድረግ የሚችትችሉበት መንገድ ሊኖር ይችላል፡፡ እግሩን ያዙት "በጉልበታቸው ተንበርክከው እግሩን ያዙት" ወንድሞቼ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት

Matthew 28:11

ማቴዎስ 28፡ 11-13

ሴቶቹ መግደላዊት ማሪያም እና ሌላኛዋ ማሪያም ከእነርሱ ጋር ስለሁኔታው ተወያዩ "ስለ አቀዱት እቅድም በጋራ ወሰኑ፡፡” ካህናቱ እና ሽማግሌዎቹ ለወታደሮቹ ብር ለመስጠት ወሰኑ፡፡ ለሌሎች እንዲህ ብላችሁ ንገሩ “በተኛንበት ሰዓት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መጥተው . . .” "ለጠየቃችሁ ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ንገሩ፣ ተኝተን ሳለ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መጥተው"

Matthew 28:14

ማቴዎስ 28፡14-15

ገዥው ጵላጦስ (MAT 27:2) እንደተነገራቸው እንደዚያው አደረጉ "ካህናቱ እንዲያደርጉ እንደ ነገሯቸው እንደዚያው አደረጉ" ዛሬ ማቴዎስ መጽሐፉን በጻፈበት ወቅት

Matthew 28:16

ማቴዎስ 28፡ 16-17

Matthew 28:18

ማቴዎስ 28፡ 18-19

በስሜ "በእኔ ስልጣን" አብ . . . ወልድ ይህ በእግዚአብሔር አብ እና በኢየሱስ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያብራራ ጠቃሚ ስም ነው፡፡


Translation Questions

Matthew 28:1

መቅደላዊት ማርያም እና ሌላኛይቱ ማርያም ወደ ኢየሱስ መቃብር የሄዱት በምን ቀን ነበር?

በሣምንቱ የመጀመሪያ ቀን ሲነጋ ወደ ኢየሱስ መቃብር ሄዱ። [28:1]

ድንጋዩ ከኢየሱስ መቃብር ላይ የተንከባለለው እንዴት ነበር?

የጌታ መልአክ ወረደና ድንጋዩን አንከባለለው። [28:2]

Matthew 28:3

መልአኩን ባዩት ጊዜ ጠባቂዎቹ ምን አደረጉ?

ጠባቂዎቹ በፍርሃት ተንቀጠቀጡና መልአኩን ባዩት ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኑ። [28:4]

Matthew 28:5

መልአኩ ለሁለቱ ሴቶች ስለ ኢየሱስ ምን አላቸው?

ኢየሱስ እንደተነሣ እና ወደ ገሊላ ቀድሟቸው እንደሚሄድ መልአኩ ተናገረ። [28:5]

መልአኩ ለሁለቱ ሴቶች ስለ ኢየሱስ ምን አላቸው?

ኢየሱስ እንደተነሣ እና ወደ ገሊላ ቀድሟቸው እንደሚሄድ መልአኩ ተናገረ። [28:6]

መልአኩ ለሁለቱ ሴቶች ስለ ኢየሱስ ምን አላቸው?

ኢየሱስ እንደተነሣ እና ወደ ገሊላ ቀድሟቸው እንደሚሄድ መልአኩ ተናገረ። [28:7]

Matthew 28:8

ለደቀመዛሙርቱ ለመንገር በሚሄዱበት ጊዜ ሁለቱ ሴቶች ምን አጋጠማቸው?

ሴቶቹ ኢየሱስን አገኙትና እግሩን ይዘው አመለኩት። [28:8]

ለደቀመዛሙርቱ ለመንገር በሚሄዱበት ጊዜ ሁለቱ ሴቶች ምን አጋጠማቸው?

ሴቶቹ ኢየሱስን አገኙትና እግሩን ይዘው አመለኩት። [28:9]

Matthew 28:11

በመቃብሩ ላይ የሆነውን ነገር ጠባቂዎቹ ለሊቀ ካህናቱ በነገሩ ጊዜ፣ ሊቀ ካህናቱ ምን አደረገ?

ሊቀ ካህናቱ ለወታደሮቹ ጠርቀም ያለ ገንዘብ ከፍሏቸው የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ሰውነቱን ሰረቀ እንዲሉ ነገሯቸው። [28:11]

በመቃብሩ ላይ የሆነውን ነገር ጠባቂዎቹ ለሊቀ ካህናቱ በነገሩ ጊዜ፣ ሊቀ ካህናቱ ምን አደረገ?

ሊቀ ካህናቱ ለወታደሮቹ ጠርቀም ያለ ገንዘብ ከፍሏቸው የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ሰውነቱን ሰረቀ እንዲሉ ነገሯቸው። [28:12]

በመቃብሩ ላይ የሆነውን ነገር ጠባቂዎቹ ለሊቀ ካህናቱ በነገሩ ጊዜ፣ ሊቀ ካህናቱ ምን አደረገ?

ሊቀ ካህናቱ ለወታደሮቹ ጠርቀም ያለ ገንዘብ ከፍሏቸው የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ሰውነቱን ሰረቀ እንዲሉ ነገሯቸው። [28:13]

Matthew 28:16

ኢየሱስን በገሊላ ባዩት ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ምን አደረጉ?

ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን አመለከቱት፣ አንዳንዶች ግን ተጠራጠሩ። [28:17]

Matthew 28:18

ምን ዓይነት ሥልጣን እንደተሰጠው ኢየሱስ ተናገረ?

ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር እንደተሰጠው ኢየሱስ ተናገረ። [28:18]

ደቀመዛሙርቱ ምን እንዲያደርጉ ኢየሱስ አዘዛቸው?

ደቀመዛሙርቱ እንዲሄዱና ደቀመዛሙርትን እንዲያደርጉ፣ እንዲያጠምቋቸውም ኢየሱስ አዘዛቸው። [28:19]

በማን ስም እንዲያጠምቊ ነው ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸው?

በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቊ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ነገራቸው። [28:19]

Matthew 28:20

ምን እንዲያስተምሩ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ አዘዛቸው?

ሕዝቦችን ሁሉ እርሱ ያዘዛቸውን ነገሮች መታዘዝን እንዲያስተምሩ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ አዘዛቸው። [28:20]

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ የሰጠው የመጨረሻው ተስፋ ምን ነበር?

ኢየሱስ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ቃል ገባላቸው። [28:20]


Translation Words

ሄሮድያዳ

ሄሮድያዳ መጥምቁ ዮሐንስ ባገለገለበት ዘመን ይሁዳን እየገዛ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ (አንቲጳስ) ሚስት ነበረች።

ልብ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልብ የሰውን ሐሳብ፣ ስሜት፣ ፍላጎት ወም ፈቃድ ለማመልከት ብዙውን ጊዜ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

ልያ

ልያ ከያዕቆብ ሚስቶች አንኳ ነበረች። የዐሥር ወንዶች ልጆች እናት ስትሆን ዐሥሩ ልጆች ከእስራኤል ነገዶች የተወሰኑት ነበሩ።

ሐሤት

ሐሤት በደስታን በፍስሐ መሞላት፣ እጅግ በጣም ደስ መሰኘት ማለት ነው፥

ሕልም

ሕልም ሰዎች ተኝተው እያለ የሚያዩት ወይም አእምሮአቸው ውስጥ የሚለማመዱት ነገር ነው።

ሕዝቅያስ

ሕዝቅያስ 13ኛው የይሁዳ ንጉሥ ነበር። በእግዚአብሔር የሚታመንና ለእርሱ የሚታዘዝ ንጉሥ ነበር።

ሕዝብ

ሕዝብ የሚባለው በአንድ ዐይነት መንግሥታዊ አስተዳደር የሚመራ የሰዎች ስብስብ ነው። ብዙውን ጊዜ በዘር፣ በነገድ፣ በቋንቋና በሌሎችም ባሕርዮች የሚመሳሰሉ ሰዎችን ያካትታል።

ሕጋዊ

ሕጋዊ የሆነ ነገር አሳሪ ከሆነው ደንብ ወይም ሕግ መሠረት የተደረገ ወይም ከእርሱ ጋር የሚስማማ ማለት ነው።

መለከት

“መለከት” ሙዚቃ ለመጫወት ወይም ዐዋጅ ለማሰማት ወይም ሕዝብን ለስብሰባ ለመጥራት ጥቅም ላይ የሚውል መሣሪያ ነው።

መለየት

“መለየት” የሚለው ቃል አንድ ዓላማን ለመፈጸም ከአንድ ነገር ተለይቶ መውጣትን ያመለክታል

መለየት

መለየት አንድን ነገር ወይም ሰው እግዚአብሔርን እንዲያገለግል መመደብ ማለት ነው። በዚህ መልኩ የተለየ ሰው ወይም እቃ ለእግዚአብሔር እንደ ተቀደሰና እንደ ተለየ ይቆጠራል።

መሐላ

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አንዳች ነገር ለማድረግ የሚሰጥ ውል ያለው ተስፋ ቃል ነው። መሐላ የሚያደርግ ሰው የሰጠውን ተስፋ የመፈጸም ግዴታ አለበት።

መሠዊያ

መሠዊያ ለእግዚአብሔር መባ(ስጦታ)እንዲሆን እስራኤላውያን እንስሳትና የእህል ዓይነቶችን የሚያቃጥልበት ከፍ ብሎ የሚሠራ ነገር ነው።

መስቀል

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን መስቀል አንድ ቀጥ ብሎ የወጣ እንጨት ሲሆን ጫፉ አካባቢ አንድ ሌላ ግንድ ይጋደምበት ነበር።

መስቀል

አንድን ነገር መስቀል ያንን ነገር ከመሬት በላይ ማንጠልጠል ማለት ነው።

መስበክ

ስለ እርሱ ለማስተማርና ለእርሱ እንዲታዘዙ ለማሳሰብ ለተወሰኑ ሰዎች መናገር ማለት ነው።

መሸከም

ቃል በቃል ከተወሰደ፣ “መሸከም” አንድን ነገር ራስ ላይ መጫን ማለት ነው። ይህ ቃል በርካታ ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት።

መቀበል

“መቀበል”የሚለው ቃል ለአንድ ሰው ወይም ሁኔታ ተገቢ ዕውቅና ወይም ይሁንታ ሲሰጠው ማለት ነው።

መቀበል

“መቀበል” የተሰጠ ወይም የቀረበ ነገርን ተቀብሎ የራስ ማድረግ ማለት ነው።

መብራት

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሰዎች ይጠቀሙበት የነበረው መብራት በሚነድበት ጊዜ ብርሃን የሚሰጥ ብዙውን ጊዜ እንደ ኀይል ሰጪ የሚያገለግል ዘይት የያዘ ዕቃ ነበር።

መቶ አለቃ

መቶ አለቃ ከእርሱ ሥር 100 ወታደሮች የነበሩት የሮም ሰራዊት ባለ ሥልጣን ነበር።

መና

መና ከግብፅ ከወቱ በኋላ እስራኤል በምድረ በዳ ይንከራተቱ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር የሰጣቸው እንጀራ የመሰለ ስስ ምግብ ነበር።

መንቀጥቀጥ

“መንቀጥቀጥ” ከፍርሃት ወይም ከከባድ ጭንቀት የተነሣ መናወጥ ወይም፣ መንዘፍዘፍ ማለት ነው።

መንጋ

“መንጋ” በጎችንና ፍየሎችን ወይም በሬዎችንና ላሞችን ወይም አሳማዎችን ያመለክታል

መንግሥት

መንግሥት በንጉሥ የሚገዛ የሰዎች ቡድን ነው። ንጉሥ ወይም ሌሎች ገዦች የሚቆጣጠሩትና በሥልጣን የሚያስተዳድሩትንም አካባቢ ወይም ፖለታካዊ አገርንም ያመለክታል።

መከራ

“መከራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው መከራና ጭንቀት ያለበት አዳጋች ጊዜን ነው።

መከር

“መከር” የሚለው ቃል እህል፣ ፍራፍሬ ወይም አትክልት መሰብሰብን ያመለክታል።

መዝሙር

ቅዱስ ዝማሬ፣ ብዙ ጊዜ በሙዚቃ የታጀበ ግጥም ወይም ቅኔ ማለት ነው። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፈ መዝሙር በእስራኤላውያን የተጻፉ የመዝሙሮች ስብስብ ይዟል።

መያዝ

“መያዝ” አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር በኅይል መያዝ ማለት ነው። ማሸነፍ ወይም ከቁጥጥር ሥር ማድረግ ማለትም ይሆናል

መጋረጃ

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን “መጋረጃ” የሚያመለክተው መገናኛው ድንኳንንና ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን ወፍራምና በጣም ከባድ ጨርቅ ነበር።

መግዛት

መግዛት በአንድ አገር ወይም በአንድ መንግሥትና ሕዝቡ ላይ ንጉሥ መሆን ማለት ነው። አንድ ንጉሥ የሚገዛው እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ነበር።

መጠየቅ

“መጠየቅ” መረጃ የሚጠይቅ ማለት ነው።

መጥረቢያ

መጮኽ

“መጮኽ” እንባ አውጥቶ ማልቀስ ወይም ጭንቅ ውስጥ ያለ ሰው የሚያሰማው ጥሪ ሊሆን ይችላል።

መፈጸም

“መፈጸም” አንዳች የሚጠበቅ ነገርን ፈጽሞ ወይም አከናውኖ መገኘት ማለት ነው።

ሙሴ

ሙሴ ለ40 ዓመት የእስራኤል ሕዝብ ነቢይና መሪ ነበር።

ማርያም

ማርያም የአሮንና የሙሴ ታላቅ እኅት ነበረች።

ማርያም መግደላዊት

ማርያም መግደላዊት ኢየሱስን መከተል የጀመረችው ሰባት አጋንንት ከእርሷ ካስወጣ በኋላ ነበር።

ማቅ

ማቅ ከፍየል ወይም ከግመል ጠጉር የሚሠራ ልብስ ነው። ይህ ዐይነቱ ልብስ ሻካራና የሚኮሰኩስ ነበር።

ማክበር

አንድ ሰው ወይም ነገር ምን ያህል ታላቅና አስፈላጊ መሆኑን ማሳየት ወይም መናገር ማለት ነው። ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ክብር መስጠት” ማለት ነው።

ምሳሌ

ምሳሌ ግብረ ገባዊ ወይም ሃይማኖታዊ ትምህርት ለማስተማር የሚቀርብ አጭር ታሪክ ነው።

ምሳሌ

ምሳሌ ጥበብ ወይም እውነት የያዘ አጭር ዐረፍተ ነገር ነው።

ምስጋና

አንድ ሰው ማመስገን ለዚያ ሰው ያለንን አድናቆትና ክብር መግለጥ ማለት ነው።

ምናሴ

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ምናሴ ተብለው የተጠሩ አምስት ሰዎች ነበር።

ምጽዋት

“ምጽዋት” የሚለው ቃል ድኾችን ለመርዳት የሚሰጥ ገንዘብን፣ምግብን ወይም ሌሎች ነገሮችን ያመለክታል።

ሠሪ

አጠቃላይ በሆነ አነጋገር፣ “ሠሪ” ነገሮችን የሚፈጥር ወይም የሚሠራ ማለት ነው።

ሥልጣን

“ሥልጣን” የተሰኘው ቃል አንድ ሰው ሌላው ሰው ላይ ያለውን ተፅዕኖ የማሳደር ወይም የመቆጣጠር ኅይልን ያመለክታል

ሥጋ

መጽሐፍ ቅዱስ ሥጋ ሲል ቃል በቃል የሰውን ወይም የእንስሳን ለስላሳውን የአካል ክፍል ያመለክታል።

ረባት

ረባት በጣም ጠቃሚ የአሞራውያን ከተማ ነበረች።

ሩት

ሩት መሳፍንት እስራኤላውያንን እየመሩ በነበረ ዘመን የነበረች ሞዓባዊት ሴት ናት። ጥንታዊ የኢየሱስ ክርስቶስ መገኛ ነበረች

ራሔል

ራሔል ከያዕቆብ ሚስቶች አንዷ ነበረች። እርሷና እኅቷ ልያ የያዕቆብ አጎት የላባን ልጆች ነበሩ።

ራማ

ራማ ከኢየሩሳሌም በስተ ሰሜን 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ጥንታዊ የእስራኤል ከተማ ነበረች።

ራስ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ራስ” በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞች አሉት።

ሮብዓም

ሮብዓም ከንጉሥ ሰሎሞን ልጆች አንዱ ሲሆን፣ ሰሎሞን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ንጉሥ ሆኗል.

ሰሎሞን

ሰሎሞን ከንጉሥ ዳዊት ልጆች አንዱ ነበር። የእናቱ ስም ቤርሳቤህ ይባል ነበር

ሰንበት

ሰንበት የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ነው፤ ይህ ቀን ምንም ሥራ የማይሠራበት የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አዝዞ ነበር።

ሰዓት

አንድ ነገር የተፈጸመው ምቼና እንዴት እንደ ነበር ከማመልከት በተጨማሪ፣ “ሰዓት” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለቻቸው በርካታ ምሳሌያዊ መንገዶች አሉ።

ሰይፍ

ሰይፍ ለመቁረጥ ወይም ለመውጋት የሚያገለግል ጠፍጣፋ ስለት ያለ የጦር መሣሪያ ነው መያዣና ረጅም፣ ሾጠጥ ያለና ጫፉ ላይ ስለት አለው

ሰዱቃውያን

ሰዱቃውያን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ያላቸው የአይሁድ ካህናት ነበሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ባገለገለ ዘመን የነበረውን የሮም አገዛዝ ይደግፉ ነበር። በሙታን ትንሣኤ አያምኑም

ሰዶም

ሰዶም የአብርሃም ወንድም ልጅ ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ይኖርበት የነበረ ከከነዓን በስተ ደቡብ አካባቢ ያለ ከተማ ነበር

ሳባ

በጥንት ዘመን ሳባ ደቡብ አረቢያ አንድ ቦታ የሚገኝ ሥልጣኔ ወይም አካባቢ ነበር

ሳዶቅ

ሳዶቅ በንጉሥ ዳዊት ዘመን በእስራኤል የነበረ ሁነኛ ሊቀ ካህን ነበር።

ሴም

ሴም ከሦስቱ የኖኅ ወንዶች ልጆች አንዱ ሲሆን፣ ኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ የተለጸው የጥፋት ውሃ በመጣ ጊዜ ከአባቱ ጋር መርከቡ ውስጥ ገብቶ ነበር

ሴት

ሴት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ ሦስተኛው የአዳምና የሔዋን ልጅ ነበር

ስም

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስም በተለያዩ ምሳሌያዊ አነጋገርና ጥቅም ላይ ውሏል።

ስምዖን

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስምዖን የተባሉ ጥቂት ሰዎች ነበሩ

ስንዴ

ስንዴ ሰዎች ለምግብ የሚያመርቱት እህል ነው።

ስጦታ

“ስጦታ” የሚለው ለሌላው ወገን የተሰጠ ማንኛውንም ነገር ያመለክታል። ስጦታ የሚሰጠው በምላሹ ምንም ነገር ባለ መጠበቅ ነው።

ሶርያ

ሶርያ ከእስራኤል ሰሜን ምሥራቅ የሚገኝ አገር ነው። አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን በሮም መንግሥት የሚተዳደር አገር ነው

ሸክም

ሸክም ከባድ ጫና ነው። ቃል በቃል የጥንት እንስሳት የሚሸከሙትን ሸክም ያመልክታል። “ሸክም” የሚለው ቃል በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት።

ሽማግሌ

ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ሕዝብ መሐል መንፈሳዊና ተግባራዊ መሪነት ኀላፊነት ያላቸው መንፈሳዊ ማስተዋል ያላቸው ስሞች ናቸው።

ቀረጥ

“ቀረጥ” ሰዎች እነርሱ ላይ ሥልጣን ላይ ላለው መንግሥት የሚከፍሉት ገንዘብ ወይም ዕቃ ነው

ቀረጥ ሰብሳቢ

የቀረጥ ሰብሳቢ ሥራ ከሰዎች የተቀበለውን ገንዘብ ለመንግሥት ማስተላለፍ ነበር

ቀሬና

ቀሬና ከአፍሪካ ሰሜናዊ ባሕር ዳርቻ ሜዲትራንያን ባሕር ላይ ከቀርጤስ ደሴት ደቡብ ትገኝ የነበረች የግሪክ ከተማ ናት።

ቀኝ እጅ

“ቀኝ እጅ” የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር፣ በአንድ መሪ፣ ወይም ሥልጣን ባለው ሰው ቀኝ ያለውን የክብር ቦታ ያመለክታል።

ቀያፋ

ቀያፋ መጥምቁ ዮሐንስና ኢየሱስ ባገለገሉበት ዘመን የእስራኤል ሊቀ ካህን ነበር።

ቃል

“ቃል” አንድ ሰው የተናገረውን ያመለክታል።

ቃና

ቃና ናዝሬት በስተ ሰሜን ዘጠኝ ማይሎች ያህል ርቃ የምትገኝ ገሊላ አውራጃ ውስጥ ያለች መንደር ወይም ከተማ ነበረች።

ቃየን

ቃየንና ታናሽ ወንድሙ አቤል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የመጀመሪያ የአዳምና የሔዋን ልጆች ናቸው።

ቄሳር

“ቄሳር” የተሰኘው ቃል ብዙዎቹ የሮም ገዦች የሚጠቀሙበት ስም ወይም መጠሪያ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ መጠሪያ ሦስት ገዦችን ያመለክታል።

ቅርጫት

“ቅርጫት” እርስ በርስ ከተጠላለፉ ነገሮች የሚሠራ መያዣን ያመለክታል

ቅዱሳን

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ቅዱሳን” – “ቅዱስ የሆኑ ሰዎች” ማለት ሲሆን፣ በኢየሱስ ያመኑ ወገኖችን የመለክታል

ቅዱስ

“ቅዱሱ” የሚለው መጠሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሌም የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው።

ቅድስት ከተማ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ቅድስት ከተማ” የሚያመለክተው የኢየሩሳሌም ከተማን ነው።

ቅፍርናሆም

ቅፍርናሆም ከገሊላ ባሕር ዳርቻ ሰሜን ምዕራብ የምትገኝ ዓሣ የሚጠመድባት ቦታ ናት።

በለስ

በለስ የበለስ ዛፍ ላይ የሚበቅል ትንሽና ጣፋጭ ፍሬ ነው። ሰዎች ትኩሱን፣ ቀቅለው ወይም አድርቀው በለስ መብላት ይችላሉ፣ ወይም ይከትፏቸውና እንደቂጣ አድርገው ይበሏቸዋል።

በረዶ

“በረዶ” ተራሮችን በመሳሰሉ ከፍታ ቦታዎች ወይም የዓለማችን ሰሜን ወይም ደቡብ ጫፍ ላይ የሚወርድ ውሃ አዘል ጠጣር ነገር ነው

በርባን

በርባን ኢየሱስ በተያዘ ጊዜ ኢየሩሳሌም ውስጥ የነበር እስረኛ ነበር

በትር

በትር ቀጭን፣ ጠንካራና በተለያየ መንገድ ጥቅም ላይ የሚውል ከዘራ መሰል ነገር ነው። ምናልባትም በትንሹ አንድ ሜትር ያህል ሊረዝም ይችላል።

በዓል

በዓል ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው በመመገብ የሚይሳልፉት ሁኔታ ሲሆን፣ እንዲህ የሚደረገው አንድን ሁኔታ አብሮ ለማክበር ሊሆን ይችላል። “በዓል ማድረግ” በልዩ አይነት ሁኔታ የተዘጋጀ ምግብ በብዛት መመገብን ያሳያል።

ቢታንያ

ቢታንያ ከኢየሩሳሌም ምሥራቅ 2ማይል ርቀት ላይ ከደብረ ዘይት ተራራ ምሥራቅ ባለው ተዳፋት ግርጌ የምትገኝ ከተማ ነበረች

ባልንጀራ

“ባልንፈራ” እንደ ጓደኛ ወይም እንደ የትዳር አጋር ከአንድ ሰው ጋር አብሮ መሆንን ወይም ኅብረት ማድረግን ያመለክታል።

ባቤል

ባቤል ከመሰጵጦምያ በስተደቡብ በነበረችው ሰናዖር በምትባል አካባቢ ዋነኛ ከተማ ነበረች በኋላ ላይ ሰናዖር ባቢሎን ተብላለች

ቤተ መቅደስ

ቤተ መቅደስ እስራኤል ለጸሎትና ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሰበሰቡበት ዙሪያውን በተከበበ አደባባይ ውስጥ ያለ ሕንፃ ነው። ቤተ መቅደስ የነበረው ኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ባለው የሞሪያ ተራራ ነበር።

ቤተ መቅደስ

ቤተ መቅደስ እስራኤል ለጸሎትና ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሰበሰቡበት ዙሪያውን በተከበበ አደባባይ ውስጥ ያለ ሕንፃ ነው። ቤተ መቅደስ የነበረው ኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ባለው የሞሪያ ተራራ ነበር።

ቤተ መንግሥት

“ቤተ መንግሥት” ከቤተሰቡና ከአገልጋዮቹ ጋር ንጉሥ የሚኖርበት ሕንፃ ወይም ቤት ማለት ነው።

ቤተ ክርስቲያን

በአዲስ ኪዳን መሠረት ቤተ ክርስቲያን የሚባለው ለመጸለይና የእግዚአብሔር ቃል ሲሰበክ ለመስማት ዘወትር የሚሰበሰቡ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች ስብስብ ነው። “ቤተ ክርስቲያን” ብዙውን ጊዜ፣ ክርስቲያኖችን ሁሉ ያመለክታል።

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ፣ “ቤት” ጥቅም ላይ የዋለው በምሳሌያዊ መልኩ ነው።

ቤዛ

“ቤዛ” የሚለው ቃል በምርኮ የተያዘ ሰውን ለማስለቀቅ እንዲከፈል የተጠየቀ ገንዘብ ወይም ሌላ ነገር ያመለክታል።

ብልጥ

“ብልጥ” በተለይ ተግባራዊ በሆኑ ነገሮች በጣም ብልህና አስተዋይ ሰው ነው

ብር

ብር ሳንቲሞችን፣ ጌጣጌጦችን፣ ዕቃዎችንና ማስዋቢያዎችን ለመሥራት የሚያገለግል አንጸባራቂ ነጭ/ግራጫ መልክ ያለው የከበረ ድንጋይ ነው

ብርሃን

መጽሐፍ ቅዱስ “ብርሃን” የሚለውን ቃል በተለያዩ ምሳሌያዊ ገለጻዎች ይጠቀምበታል። ብዙውን ጊዜ ጻድቃን፣ ቅድስናንና እውነትን ለማመልከት እንደ ተለዋጭ ዘይቤ ያገለግላል።

ብዔልዜቡል

ብዔልዜቡል የአጋንንት አለቃ ሲሆን፥ የሰይጣን ወይም የድያብሎስ ሌላ ስም ነው

ቦዔዝ

በዔዝ የሩት ባል፣ የንጉሥ ዳዊት አያትና ኢየሱስ የተገኘበት ዘር ዋና ግንድ የነበረ እስራኤላዊ ነበር።

ተኩላ

ተኩላ አደገኛ ሥጋ በል አውሬ ሲሆን፣ ከቀበሮ ጋር ይመሳሰላል።

ትንሣኤ

“ትንሣኤ” ከሞት በኋላ ተመልሶ ወደ ሕይወት መምጣት ነው።

ትውልድ

ትውልድ የሚባለው በአንድ ዘመን የተወለደና በአንድ ዘመን የነበረ የሰዎች ስብስብ ነው።

ትዕማር

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ትዕማር ተብለው የተጠሩ በርካታ ሴቶች ነበሩ። ትንቢተ ሕዝቅኤል ውስጥ ትዕማር የተባለ ቦታ ተጠቅሷል

ቶማስ

ቶማስ ደቀ መዛሙርቱ እንዲሆኑ ኢየሱስ ከመረጣቸው ሰዎች አንዱ ነበር (ሐዋርያት ተብለዋል)።

ነጻ

“ነጻ” የሚለው ቃል ወንጀል ከመፈጸም ወይም ከሌሎች በደሎች ነጻ የሆነ ማለት ነው። በጠቅላላው በማንኛውም ክፉ ነገር አለመሳተፉን ያመለክታል።

ነፍስ

ነፍስ የሰው ውስጣዊ፣ የማይታይና ዘላለማዊ ክፍል ነው። የሰውን ቁሳዊ ያልሆነ ነገር ሁሉ ይጨምራል

ናሆም

ናሆም ክፉው ንጉሥ ምናሴ እየገዛ በነበረበት ዘመን ያገለገለ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር።

ንዴት

ንዴት ከቁጥጥር የወጣ ቁጣ ነው። አንድ ሰው ከተናደደ፣ አጥፊ በሆነ ሁኔታ ቁጣውን እየገለጸ ነው ማለት ነው።

ንጉሥ

ንጉሥ የአንድ ነጻ ከተማ፣ መንግሥት ወይም አገር መሪ ነው።

ንፍታሌም

ንፍታሌም ስድስተኛው የያዕቆብ ልጅ ነው። የእርሱ ዘሮች ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ የሆነውን የንፍታሌም ነገድ አስገኝተዋል።

ኖኅ

ኖኅ በዓለም የነበሩ ክፉ ሰዎችን ለማጥፋት እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ የሚያዳርስ ጎርፍ በላከበት ጊዜ ከ4000 ዓመት በፊት ይኖር የነበረ ሰው ነው። ጎርፉ ምድርን በሚሸፍንበት ጊዜ እርሱና ቤተ ሰቡ የሚኖሩበት ግዙፍ መርከብ እንዲሠራ እግዚአብሔር ለኖኅ ነገረው።

አልዓዛር

አልዓዛር ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው ወዳጁ ነበር።

አልዓዛር

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልዓዛር የበርካታ ስሞች ስም ነበር።

አሕዛብ

አሕዛብ የያዕቆብ ወይም የአሥራ ሁለቱ የእርሱ ልጆች ዘር ያልሆነ ሰው ነው። ስለሆነም አሕዛብ አይሁድ አይድለም ማለት ነው።

አሞጽ

የነቢዩ ኢሳይያስ አባት አሞጽ ይባል ነበር።

አሞጽ

አሞጽ በይሁዳ ንጉስ በዕዝያን ዘመን የነበረ እስራኤላዊ ነብይ ነበር፤

አሳ

አሳ ክ913-873 አቅክ ድረስ ለአርባ ዓመት የይሁዳን መንግሥት የገዛ ንጉሥ ነበር

አሳፍ

አሳፍ ሌዋዊ ካህን ሲሆን፥ ለንጉሥ ዳዊት መዝሙሮች ሙዚቃ ያዘጋጀ ጥሩ ስጦታ ያለው ሙዚቀኛ ነበር። አሳፍ የራሱን መዝሙሮችም ጽፎአል

አስቆሮቱ ይሁዳ

የአስቆሮቱ ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር። ለአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠ እርሱ ነበር።

አቤል

አቤል የአዳምና የሔዋን ሁለተኛ ልጅ ነበር። እርሱ የቃየል ታናሽ ወንድም ነበር።

አንበጣ

“አንበጣ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንዳንዴ እጅግ በብዛት የሚመጡ፣ ያገኙትን ሁሉ የሚበሉ በጣም አጥፊ ትልቅ በራሪ ፌንጣዎች ናቸው።

አካል

“አካል” ቃል በቃል የሰው ወይም የእንስሳ ሥጋ ማለት ነው። ይህ ቃል አንድን ነገር ወይም በአንድ ቡድን ውስጥ ያሉ ግለ ሰቦችን ለማመልከትም ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

አካዝ

አካዝ ከ732 ዓቅከ - 716 ዓክከ የይሁዳን መንግሥት የገዛ በጣም ክፉ ንጉሥ ነበር። ይህ ይሆነው በእስራኤልና በይሁዳ የነበሩ ብዙ ሰዎች በምርኮ ወደ ባቢሎን ከመወሰዳቸው 140 ዓመት በፊት ነበር።

አውራጃ

አውራጃ አንድ ወረዳ ወይም የአገር ክፍል ነው።

ኢሳይያስ

ኢሳይያስ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበር።

ኢየሩሳሌም

ኢየሩሳሌም በኋላ እጅግ ተፈላጊ የሆነች በመጀመሪያ የከነዓናውያን የነበረች ጥንታዊት ከተማ ነበረች። አሁንም ኢየሩሳሌም የዘመናዊት ኢየሩሳሌም ዋና ከተማ ነች።

ኢያሪኮ

ኢያሪኮ በተስፋው ምድር በከነዓን የነበረች በጣም ኅያል ከተማ ነበረች።

ኢዮራም

ኢዮራም የእስራኤል ንጉሥና የአክዓብና የኤልዛቤል ልጅ ነበር።

ኢዮራም

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮራም ተብለው የሚጠሩ ሁለት ንጉሦች ነበሩ።

ኢዮስያስ

ኢዮስያስ ለሰላሳ እንደ ዓመት የይሁዳን መግሥት የገዛ እግዚአብሔርን የሚፈራ ንጉሥ ነበር። ሕዝቡ በንስሐ እንዲመለሱና ያህዌን እንዲያመልኩ ለማበረታታት ብዙ ነገሮች አድርጓል።

ኢዮአታም

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ኢዮአታም ተብለው የሚጠሩ ሦስት ሰዎች አሉ።

ኤልያስ

ኤልያስ በጣም ታዋቅ ከሆኑት የያህዌ ነቢያት አንዱ ነበር። ንጉሥ አክዓብን ጨምሮ ኤልያስ በተለያዩ የእስራኤል ወይም የይሁዳ ነገሥታት ዘመን ነበር ያገለገለው።

ኤልያቄም

ኤልያቄም የሁለት የብሉይ ኪዳን ሰዎች ስም ነው።

ኤርምያስ

ኤርምያስ በይሁዳ መንግሥት የእግዚአብሔር ነብይ ነበር።

እህል

ብዙውን ጊዜ፣ “እህል” የሚያመለክተው እንደ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ማሽላ ወይም ሩዝን የመሳሰሉ ለምግብ የሚሆኑ እህል ዘሮችን ነው። አንዳንዴ ዘሩ ራሱን ያመለክታል።

እምነት

በአጠቃላይ ደረጃ “እምነት” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር፣ በሰው ወይም፣ በነገሮች መተማመንን፣ መደገፍን፣ ወይም፣ መመካትን ነው።

እረኛ

እረኛ በጎችንና እነርሱን የመሳሰሉ እንስሳትን የሚጠብቅ ሰው ነው

እሳት

እሳት አንድ ነገር ሲቃጠል የሚገኝ ሙቀት፣ ብርሃንና ነበልባል ነው።

እሴይ

እሴይ የቦዔዝ የልጅ ልጅና የንጉሥ ዳዊት አባት ነው።

እባብ

እባብ የዘንዶ ሌላ ስም ነው። በኤደን አትክልት ቦት ከሔውን ጋር በተናገረ ጊዜ ሰይጣን በዚህ ስም ነበር የተጠራው

እንድርያስ

እግዚአብሔር

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር አጽናፈ ዓለሙን ከምንም ያስገኘው ዘላለማዊ ፈጣሪን ያመለክታል። እግዚአብሔር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በሚባሉ ሦስት አካሎች ተገልጧል። የእግዚአብሔር ተፀውዖ (መጠሪያ) ስም፣ “ያህዌ” ነው።

ከርቤ

ከርቤ ከተለየ ዐይነት ዛፍ ሙጫ የሚዘጋጅ ቅመም ነው።

ካም

ካም ብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተጠቀሱት ሦስቱ የኖኅ ልጆች ሁለተኛው ነው።

ካባ

ካባ ወንዶችም ሆነ ሴቶች የሚለብሱት እጅጌ ረጃጅም ከውጭ የሚደረብ ልብስ ነው። ከኮት ጋር ይመሳሰላል።

ክርስቲያን

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከሄደ ጥቂት ጊዜ በኋላ ስዎች “ክርስቲያን” የሚለውን ስም አወጡ፤ ክርስቲያን የክርቶስ ተከታይ ማለት ነው።

ክብር

“ክብር” የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ከሀብትና መልክ ጋር የሚያያዝ የላቀ ውበትና ግርማ ያመለክታል

ክፉ አድራጊ

“ክፉ አድራጊ” ኀጢአትና ዐመጻን የሚያደርጉ ሰዎች አጠቃላይ መገለጫ ነው።

ወሬ

“ወሬ” አንድን ሁኔታ አስመልክቶ በቃል ወይም በጽሑፍ አንዱ ለሌላው የሚናገረው ነው።

ወርቅ

ወርቅ ቢጫ መልክ ያለው በጣም ውድ ነገር ነው። በጥንት ዘመን ወርቅ ከማንኛውም የበለጠ ውድ ነገር ነበር።

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጣዖቶች፣ ጌጣጌጦች፣ መሠዊያዎች፣ የቃል ኪዳኑ ታቦት የተወሰነ ክፍልና መገናኛው ድንኳን ወይም ቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ነገሮች የሚሠሩት ከወርቅ ነበር። አንዳንዴ፣ “ወርቅ” የሚባለው ወርቅ የተለበጠ እንጂ እውነተኛ ወርቅ ላይሆን ይችላል። በዚህ ጊዜ፣ “ወርቃማ” ወይም፣ “ወርቅ የተለበጠ” በተሰኙ ሐረጎች እንጠቀማለን።

ወንድም

ብዙውን ጊዜ ወንድም የሚባለው ቢያንስ ከወላጆች ከአንዱ የተወለደ ወንድ ልጅ ነው።

ወይን ጠጅ

ወይን ጠጅ ከወይን ፍሬ ጭማቂ የሚሠራ የተብላላ መጠጥ ነው። ያልተብላላው የወይን ፍሬ ጭማቂም በዚሁ ስም ይጠራል።

ወዮ

“ወዮ” ከፍ ያለ ጭንቀትና ሐዘንን ያመለክታል። ስለሚመጣው ከባድ ጥፋት ማስጠንቀቂያም ይሆናል።

ዋሽንት

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ዋሽንት ከአጥንትና ከእንጨት የሚሠራ የሙዚቃ መሣሪያ ሲሆን ድምፅ እንዲያወጣ መተላለፊያዎች ይሠሩለትም ነበር።

ዐመድ

“ዐመድ” የሚለው የሚያመለክተው እንጨት ከተቃጠለ በኋላ የሚቀረውን ግራጫ ዱቄት መሳይ ነገርን ነው። ዋጋ ቢስ ውይም ጥቅም የሌለውን ነገር ለማመልከት ምሳሌያዊ በሆን መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅም ላይ ውሏል።

የትርጉም ሥራው ፕሮጀክት በሚጠቀምበት ቃል ተጠቀሙ

ዓሣ አጥማጆች

ዓሣ አጥማጆች ለመግብ የሚሆናቸውንና ሸጠው ገንዘብ የሚያገኙበትን ዓሣ ከባሕር የሚያጠምዱ ሰዎች ናቸው። አዲስ ኪዳን በተጻፈበት ዘመን ዓሣ አጥማጆች ዓሣ የሚያጠምዱት በመረብ አማካይነት ነበር።

ዕረፍት

“ዕረፍት” የሚለው ቃል ዘና ለማለትና ኀይልን ለማደስ የሚሠሩትን ማቆም ማለት ነው።

ዕጣን

ዕጣን እሳት ላይ በሚደረግበት ጊዜ ደስ የሚል ሽታ የሚሰጥ ጣፋጭ መዓዛ ያላቸው ቅመሞድ ድብልቅ ነው። እነዚህ ቅመሞች ከዕፅዋት ክፍሎች የተገኙ ሲሆኑ፣ በጣም ጥቃቅን እስኪሆኑ ድረስ ይደቅቃሉ።

ዕጣን

ዕጣን ከዛፍ ሙጫ የሚገኝ ጣፋጭ ሽታ ያለው ቅመም ነው። ሽቱኑ ሌላም ጣፋጭ መዓዛ ያለው ነገር ለመሥራት ያገለግላል።

ነጻ መሆን፣ ነጻነት፣ አርነት “ነጻ መሆን” ወይም፣ “ነጻነት” ባርያ አለመሆንን በምንም ዓይነት ቀንበር ሥር አለመሆንን ያመለክታል።

ዘላለም

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዘላለም” የሚያመለክተው ፍጻሜ የሌለውን ጊዜ ነው። አንዳንዴ፣ በታም ረጅም ጊዜን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።

ዘሩባቤል

ብሉይ ኪዳን ውስጥ ዘሩባቤል ተብለው የተጠሩ ሁለት ሰዎች ነበር።

ዘር

ዘር እርሱን የመሳሰሉ ብዙ ዘሮች እንዲገኙ መሬት ላይ የሚዘራ ወይም የሚተከል የአትክልት ክፍል ነው። በርካታ ምሳሌያዊ ትርጉሞችም አሉት

ዘብዴዎስ

ዘብድዎስ ዓሣ አጥማጅ የገሊላ ሰው ነበር። ያዕቆብና ዮሐንስ የተባሉ ሁለት ልጆቹ አብረውት ይሠሩ ነበር። በኋላ ግን ሥራቸውን ትተው ሁለቱም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ።

ዘንባባ

“ዘንባባ” ረጃጅም፣ በቀላሉ የሚተጣጠፍ፣ ከጫፉ ጀምሮ እንደማራገቢያ ዓይነት ቅጠል ያበዛባቸው ቅርንጫፎች ያሉት ረጅም የዛፍ ዘር ነው።

ዘይት

ዘይት ከአንዳንድ ተክሎች ወይም ፍሬዎች ሊገኝ የሚችል ወፈር ያለ ፈሳሽ ነገር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን አብዛኛውን ጊዜ ዘይት የሚገኘው ከወይራ ፍሬዎች ነው።

ዙፋን

ዙፋን አብዛኛውን ጊዜ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ፍርድ ለመስጠት ንጉሥ የሚቀመጥበት የተለየ ወንበር ነው።

ዙፋን

ዙፋን አብዛኛውን ጊዜ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ፍርድ ለመስጠት ንጉሥ የሚቀመጥበት የተለየ ወንበር ነው።

ዛብሎን

ዛብሎን የያዕቆብና የልያ የመጨረሻ ልጅ ሲሆን፣ ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች የአንዱ ስም ነበር።

የምጥ ጣር

“ምጥ” ላይ ያለች ሴት ልጅ ከመውለዷ በፊት ሕመም ይደርስባታል፤ ይህም “የምጥ ጣር” ይባላል።

የራስ ቅል

የራስ ቅል የአንድ ሰው ራስ አጥንት የሆነው ክፍል ነው

የሰው ልጅ

የሰው ልጅ“የሰው ልጅ” የሚለው ሐረግ ብዙ ጊዜ ኢየሱስ ራሱን የሚጠራበት ስም ነበር። ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የሰው ልጅ” ማንኛውም ሰው የሚታወቅበት ስም ነበር

ጥቅሶች እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታሉ

የተቀደሰ

“የተቀደሰ” የሚለው ቃል ቅዱስ የሆነና ለእግዚአብሔር ክብር የተለየ ነገርን ያመለክታል

የተጻፈ

“እንደ ተጻፈ” ወይም፣ “የተጻፈው” የተሰኙት ቃሎች አዲስ ኪዳን ውስጥ ተደጋግመው ጥቅም ላይ ውለዋል፣ ብዙውን ጊዜ የሚያመለክቱት በዕብራውያን ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉ ትእዛዞች ወይም ትንቢቶች ነው።

የአይሁድ ንጉሥ

የእግዚአብሔር ልጆች

“የእግዚአብሔር ልጆች” በርካታ ትርጉሞች ያሉት ምሳሌያዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል

የካህናት አለቆች

ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ የካህናት አለቆች ከፍ ያለ ሥልጣን የነበራቸው የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ነበሩ።

የወይን ፍሬ

ወይን ፍሬ የወይን ሐረጉ እዚህና እዚያ ተበታትነው የሚያድጉ ትናንሽ ክብ ፍሬዎች ናቸው። ወይን ጠጅ የሚሆነው እነዚህ ፍሬዎች ተጨምቀው ነው።

የደም መፍሰስ

“የደም መፍሰስ” በግድያ፣ በጦርነት ወይም በሌላ አደጋ የሰዎችን ሞት ያመለክታል።

ያልተፈቀደ

“ያልተፈቀደ” ነገር የሚያደርግ ሰው ሕግ ያፈርሳል።

ይሁዳ

ይሁዳ የያዕቆብ አራተኛ ልጅ ነው እናቱ ልያ ትባላለች።

ይሁዳ

“ይሁዳ” የሚለው ቃል የመጣው ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ከነበረው ይሁዳ ከሚለው ስም ነው። ጠበብ ባለና ሰፋ ባለ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

ተርጓሚዎቹ ልዩነቱን በጣም ግልጽ ማድረግ ከፈለጉ፣ ሰፋ ባለ መልኩ የቀረበውን ይሁዳ (ለምሳሌ ሉቃስ 1፥5) “የይሁዳ አገር” በማለት መተርጎም ይችላሉ፤ ጠበብ ባለ መልኩ (ለምሳሌ ሉቃስ 1፥39) ጥቅም ላይ ከዋለ፣ ይህ ቦታ መጀመሪያ የይሁዳ ነገድ የነበረበት የጥንቱ የእስራኤል ምድር አካል ስለነበር፣ “የይሁዳ ክፍለ ሀገር” በማለት መተርጎም ይቻላል።

ይስሐቅ

ምንም እንኳ በጣም ያረጁ ቢሆኑም ለእነርሱ እንደሚሰጣቸው እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለሣራ ቃል የገባላቸው ልጅ ነው።

ዮርዳኖስ ወንዝ

ዮርዳኖስ ወንዝ ከሰሜን ወደደቡብ፣ ከነዓን ተብሎ ይጠራ ከነበረው ምድር ምሥራቃዊ ድንበር ይፈስ የነበረ ወንዝ ነው።

ዮናስ

ዮናስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ እስራኤላዊ ነቢይ ነበር።

ደም

“ደም” ጉዳት ወይም ቁስል ሲኖር ከአንድ ሰው ቆዳ የሚወጣ ቀይ ፈሳሽ ነገርን ያመለክታል። ደም ለሰው አካል ሕይወት ሰጪ ምግብን ያመጣል።

ደቀ መዝሙር

“ደቀ መዝሙር” በቃልም ሆነ በሕይወት ምሳሌነት ከመምህሩ ለመማር ሲል ብዙ ጊዜውን ከመምህሩ ጋር የሚያሳልፍ ሰው ነው።

ደብረ ዘይት ተራራ

ደብረ ዘይት ተራራ ከኢየሩሳሌም ከተማ በስተ ምሥራቅ በኩል ያለ ተራራ ወይም ረጅም ኮረብታ ነው። ይህን ስሙን ያገኘው በብዛት እዚያ ከሚገኙት የወይራ ዛፎች ሊሆን ይችላል።

ደጃፍ

“ደጃፍ” የሚባለው የበር ታችኛው ክፍል ነው። ወደ አንድ ቤት ሲገባ ደጃፉን መርገጥ ይገባል።

ዳን

ዳን አምስተኛው የያዕቆብ ልጅ ሲሆን ከአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዱ ነበር። የዳን ነገድ ይኖርበት የነበረው ሰሜናዊው የከነዓን ክፍል በዚህ ስም ይጠራል።

ዳንኤል

ዳንኤል ገና ወጣት እያለ በ600 ዓቅክ በባቢሎን ነጉሥ ናቡከደነፆር በምርኮ የተወሰደ እስራኤላዊ ነቢይ ነበር።

ዳዊት

ዳዊት እግዚአብሔርን በመውደዱና እርሱን በማገልገሉ የታወቀ ሁለተኛው የእስራኤል ንጉሥ ነው። የመዝሙራት መጽሐፍ ዋናው ጸሐፊም እርሱ ነው።

ድምፅ

አንድ ሰው ሲናገር ድምፅ ይጠቀማል፤ ስለዚህም ብዙ ጊዜ “ድምፅ” ንግግርን ወይም ሐሳብ ማስተላለፍን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል።

ድብ

ድብ ጥቁር ቡናማ ጠጉርና ጠንካራ ጥርሶችና ጥፍሮች ያሉት ባለአራት እግር ግዙፍ እንስሳ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ድብ በእስራኤል በብዛት ይገኝ ነበር

ድነት

“ድነት” የሚለው ቃል ከክፉና ከአደጋ መዳንና ማምለጥን ያመለክታል

ድንጋይ

ይህ ቃል የሚያመለክተው ከሰማይ የሚወርድ ጠጣር ነገርን ነው።

ድንግል

ድንግል የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያላደረገች ሴት ናት።

ገለባ

ደረቅ የእህል ዘር መከላከያ ሽፋን ነው። ገለባ ለምግብነት አይጠቅምም፤ ስለዚህም ከእህሉ እንዲለያይ ይደረግና በኋላ ይጣላል።

ጉድጓድ

ጉድጓድ ወደ መሬት በጣም ዝቅ ብሎ የተቆፈረ ድንጋይ ነው።

ጊዜ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ጊዜ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የተወሰኑ ነገሮች የተፈጸሙበትን ወቅት ወይም ዘመን ለማመልከት ነው። “ዕድም” ወይም፣ “ዘመን” ወይም “ወቅት” ጋር የሚመሳሰል ትርጕም አለው።

ጋይ

በብሉይ ኪዳን ዘመን ጋይ ከቤቴል በስተ ደቡብ ከኢያሪኮ ሰሜን ምዕራብ 8 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኝ የከነዓናውያን ከተማ ስም ነበረች።

ጌታ

ጌታ የሚለው ቃል ሰዎች ላይ ባለቤትነት ወይም ሥልጣን ያለውን ሰው ያመለክታል።

ጌቴሴማኒ

ጌቴሴማኒ ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከቄድሮን ሸለቆ ማዶ፣ ደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ያለ የወይራ ዛፎች የነበሩበት አትክልት ቦታ ነው።

ግመል

ግመል ጀርባው ላይ አንድ ወይም ሁለት ሻኛ ያለው ግዙፍ ባለ አራት እግር እንስሳ ነው።

ግብር

ግብር ከለላ ለማግኘትና በሕዝቦቻቸው መካከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር አንድ መንግሥት ወይም ገዢ ለሌላው የሚያቀርበው ስጦታ ነው።

ግብዣ

ብዙውን ጊዜ ግብዣ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች የሚቀርቡበት ታዋቂ ሰፊ ድግስ ነው

ግዛት

ግዛት ሰዎችን፣ እንስሳትንና መሬትን የመቆጣጠር፣ የመግዛት ኃይልና ሥልጣንን ያመለክታል።

ጎልጎታ

“ጎልጎታ” ኢየሱስ የተሰቀለበት ቦታ ስም ነው። ቃሉ የመጣው፣ “የራስ ቅል” ወይም፣ “የራስ ቅል ቦታ” ከተሰኙ የአረማይክ ቃል ነው።

ጎርፍ

ብዙውን ጊዜ ጎርፍ የሚባለው ምድሩን ሁሉ የሚሸፍን ብዛት ያለው ውሃ ነው። የአንድን ነገር ብዛት ወይም በድንገት ነገር ለማመልከትም ምሳሌያው በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።

ጎተራ

“ጎተራ” ምግብ ወይም ሌሎች ነገሮችን ለማከማቸት የሚያገለግል ማስቀመጫ ነው

ጠቢባን

“ጢቢባን” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የተለየ ዕውቀትና ችሎታ ያላችው ሰዎችን ለማመልከት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ እነዚህ ሰዎች በንጉሡ አደባባይ ነበር የሚገኙት።

ጠባቂ

“ጠባቂ” አንድ ነገር በጥንቃቄ የሚመለከት፣ ረጋ ብሎና ቀረብ ብሎ በማስተዋል የሚመረምር ማለት ነው። ቃሉ በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት።

ጠብ

ጠብ በሰዎች መካከል ያለ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ግጭት ማለት ነው

ጢሮስ

ጢሮስ በአሁኑ ዘመን ሊባኖስ በሚባለው ሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ ላይ የነበረች ጥንታዊ የከነዓናውያን ከተማ ናት። የከተማዋ አንድ ክፍል ከባሕሩ ዳርቻ አንድ ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ካለው ደሴት ጋር ይያያዛል።

ጥላ

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ጥላ” ብርሃን ሲጋረድ የሚፈጠረውን ጨለማ ያመለክታል። በርካታ ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት

ጥርስ ማፋጨት

ጥርስ ማፋጨት ማለት ጥርሶችን በማያያዝ ወደ ፊት ወደ ኋላ በማድረግ ወይም ግራና ቀኝ በማድረግ እርስ በርሳቸው እንዲፋጩ ማድረግ ማለት ነው። ይህ ብዙውን ጊዜ የሚያሳየው ከባድ ስቃይን (ሕመምን) ወይም ቊጣን ነው።

ጥፋት

ጥፋት የሚለው ቃል ምንም ይግባኝ ወይም ማምለጫ የሌለው ፍርድና ኩነኔን ያመለክታል።

ጦር

ጦር በአንድ በኩል ሹል ብረት ያለው ሆኖ ጠላት ላይ የሚወረወር ረጅም እጀታ ያለው መሣሪያ ነው

ጨለማ

ቃል በቃል፣ “ጨለማ” የብርሃን አለመኖር ማለት ነው። ይህ ቃል የተለያዩ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት።

ጲላጦስ

ጲላጦስ ኢየሱስ እንዲገደል የፈረደ ሮማዊ ባለ ሥልጣን ነበር።

ጾም

መጾም ምግብን ወይም አንዳንድ የምግብ ዐይነቶችንና መጠጦችን ለተወሰነ ጊዜ ማቆም ነው።

ፈሪሳዊ

ፈሪሳውያን ኢየሱስ በዚህ ምድር በነበረ ዘመን በጣም ታዋቂ የእስራኤል ሃይማኖት መሪዎች ነበር። አብዛኞቹ መካከለኛ ኑሮ ያላቸው ሠራተኞች ሲሆኑ፣ ጥቂቶቹም ካህናት ነበሩ።

ፈተና

“ፈተና” የሚለው ቃል የአንድን ሰው ብርታትና ድካም ለይቶ የሚያሳይ አስቸጋሪ ወይም አዳጋች ሁኔታ ያመለክታል።

ፊት

“ፊት” የሚለው ቃል የአንድ ሰው ራሱ ከፊት በኩል ያለውን ክፍል ነው፤ ቃሉ አያሌ ምሳሌያዊ ትርጉሞች አሉት።

ፍቅር

አንድን ሰው መውደድ ለዚያ ሰው ማሰብና መጠንቀቅ እንዲሁም ለእርሱ የሚጠቅመውን ነገር ማድረግ ነው። “ፍቅር” የተለያዩ ትርጕሞች አሉት፤ አንዳንድ ቋንቋዎች በተለያዩ ቃሎች ይገልጹታል። 1. ከእግዚአብሔር የሚመጣው ፍቅር ምንም እንኳ ራስን የሚጠቅም ባይሆንም ሌሎችን መጥቀም ላይ ያተኩራል። ምንም ያድርጉ ምን ይህ ፍቅር ለሌሎች ያስባል፣ ለሌሎች ይጠነቃቃል። እግዚአብሔር ራሱ ፍቅር ነው፤ የእውነተኛ ፍቅር ምንጭም እርሱ ነው።

ፍጹም

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ፍጹም” የሚለው ቃል በክርስትና ሕይወታችን አስተዋዮችን በሳሎች ሆኖ መገኘትን ነው። አንዳንዴ “ፍጹም” የሚለው ቃል የተሟላና እንከን የሌለበት እስኪሆን ድረስ በክርስትና ሕይወት ማደግ ማለትም ይሆናል።