1እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። 2ምድርም ቅርፅ የሌላትና ባዶ ነበረች። ጥልቅ የሆነው ስፍራዋም በጨለማ ተውጦ ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ሰፍፎ ነበር።3እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። 4እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ ብርሃንኑም ከጨለማ ለየው። 5እግዚአብሔርም ብርሃኑን ‘ቀን’ ጨለማውን ደግሞ ‘ሌሊት’ ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ ሌሊቱም ነጋ አንድ ቀን ሆነ።6እግዚአብሔርም፦ “በውሆች መካከል ጠፈር ይሁን፣ ውሆችንም ይለያዩ” አለ። 7እግዚአብሔር ጠፈርን አደረገና ከጠፈር በላይና ከጠፈር በታች ያሉትን ውሆች ለየ። እንደዚያም ሆነ። 8እግዚአብሔር ጠፈሩን ‘ሰማይ’ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ ሌሊቱም ነጋ ሁለተኛ ቀን።9እግዚአብሔር፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ወደ አንድ ስፍራ ይሰብሰብ፣ ምድሩም ይገለጥ” አለ። እንደዚያም ሆነ። 10እግዚአብሔርም ምድሩን ‘የብስ’፣ ወደአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ ‘ባሕር’ ብሎ ጠራው። ይህም መልካም መሆኑን ተመለከተ።11እግዚአብሔር፦ እንደ ዓይነታቸው ዘርን የሚያፈሩ ተክሎችን፣ በውስጣቸው ዘርን ያዘሉ የፍራፍሬ ዛፎችን እንደዓይነታቸው የሚያፈሩ አዝርዕትን ታብቅል” አለ። እንደዚያም ሆነ። 12ምድር እንደአይነታቸው የሚያፈሩ አዝርዕትን አበቀለች። ይህም መልካም እንደሆነ እግዚአብሔር ተመለከተ። 13ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ ሶስተኛ ቀን ሆነ።14እግዚአብሔር፦ “ቀኑን ከሌሊቱ ይለዩ ዘንድ በሰማይ ብርሃናት ይሁኑ። እነዚህ ብርሃናት የዓመት ወቅቶችን፣ ቀናትንና ዓመታትን የሚለዩ ምልክቶች ይሁኑ። 15ለምድርም ብርሃን ይሰጡ ዘንድ በሰማይ ላይ የሚገኙ ብርሃናት ይሁኑ” አለ። እንደዚያም ሆነ።16እግዚአብሔር ታላቁ ብርሃን በቀን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት ይሠለጥኑ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ። ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። 17ለምድርም ብርሃን ይሰጡ ዘንድና 18በቀንና በሌሊት ላይ እንዲሠለጥኑ እንደዚሁም ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ በሰማይ አኖራቸው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደሆነ ተመለከተ። 19ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ አራተኛ ቀን ሆነ።20እግዚአብሔር፦ “ውሆች በሕያዋን ፍጡራን የተሞሉ ይሁኑ፣ ወፎችም ከምድር በላይ ባለው በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። 21እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር ፍጥረታትን እንደዚሁም በምድር የሚንቀሳቀሱ፣ በውሆች ውስጥ የሚርመሰመሱና በክንፎቻቸው የሚበሩ ወፎችን እንደዓይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደሆነ ተመለከተ።22እግዚአብሔርም፦ “ብዙ ተባዙ የባሕርን ውሆች ሙሉአቸው፣ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። 23ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ አምስተኛ ቀን ሆነ።24እግዚአብሔርም፦ “ምድር እንደወገናቸው ሕያው ፍጥረታትን ማለትም ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡትንና የምድር አራዊትን ታስገኝ” አለ። እንደዚያም ሆነ። 25እግዚአብሔር በየዓይነታቸው የምድር አራዊትን፣ በየዓይነታቸው ማናቸውንም በምድር የሚሳቡትን ፈጠረ።26እግዚአብሔርም፦ “ሰውን በመልካችን እንደ አምሳላችን እንፍጠር፣ ሰዎችም በባሕር ዓሣዎች፣ በሰማይ በሚበሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚሳቡ ማናቸውም ተሳቢ ፍጥረቶች ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ። 27እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ፣ በራሱም አምሳል ፈጠረው። ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።28እግዚአብሔር ባረካቸው እንደዚህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሉአት ግዟትም። በባሕር ውስጥ ባሉት ዓሣዎች፣ በሰማይ ላይ በሚበሩት ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱት ማናቸውም ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ” 29እግዚአብሔርም፦ “እነሆ፣ ምግብ ይሆኑላችሁ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ በውስጣቸው ዘርን ያዘሉ ማናቸውንም ተክሎችና በውስጣቸው ፍሬ ያላቸውን ማናቸውንም የፍራፍሬ ዛፎች ሰጥቻችኋለሁ።30በምድር ላይ ለሚገኙ እንስሳት ሁሉ፣ በሰማይ ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፣ እንዲሁም በምድር ላይ ለሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ማለትም የሕይወት እስትንፋስ ላለበት ማንኛውም ፍጡር ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ። እንደዚሁም ሆነ። 31እግዚአብሔር የፈጠረውን ማንኛውንም ነገር ተመለከተ። እነሆ፣ እጅግ መልካም ነበረ። ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ ስድስተኛ ቀን ሆነ።
1የምድር በውስጣቸው ያሉትም ሕያዋን ፍጡራን አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ። 2እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጽሞ በዚሁ ቀን ከሥራው ሁሉ አረፈ። 3እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ ያረፈው በዚህ ቀን ስለሆነ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም።4እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረበት ወቅት የሰማይና የምድር የአፈጣጠራቸው ታሪክ እንደዚህ ነበር። 5እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ ዝናብ እንዲዘንብ ስላደረገና ምድርንም የሚያለማ ሰው ባለመኖሩ በምድር ላይ ምንም ቡቃያ አልነበረም፣ በምድር ላይ የሚበቅል ተክልም ገና አልበቀለም። 6ነገር ግን ውሃ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር።7እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ። 8እግዚአብሔር አምላክም በስተምሥራቅ በኩል በዔደን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፣ የአበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው።9ከምድር ውስጥም እግዚአብሔር አምላክ ለዓይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ። በአትክልት ስፍራው መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበር፣ መልካሙንና ክፉውን የሚያሳውቀውም ዛፍ በዚያ ነበር። 10የአትክልት ስፍራውንም የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ይፈስ ነበር። ወንዙም ከኤደን ከወጣ በኋላ አራት ወንዞች ሆኖ ይከፋፈል ነበር።11የመጀመሪያው ፊሶን የተባለው ወንዝ ነበር፣ ይህም ወርቅ ይገኝበት የነበረውን መላውን የሐዊላ ምድር አቋርጦ የሚፈስው ወንዝ ነበር። 12የዚያ አገር ወርቅ የጠራ ወርቅ ነበር፤ በተጨማሪም በዚያ አገር ሽቶና የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ።13የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ይባል ነበር፣ እርሱም መላውን የኢትዮጵያ ምድር አቋርጦ ይፈስ ነበር። 14የሶስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ ይባል ነበር፣ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈሳል። አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ነበር።15እግዚአብሔር አምላክም የኤደንን የአትክልት ስፍራ ያለማና ይንከባከብ ዘንድ ሰውን ወስዶ በዚያ አኖረው። 16እግዚአብሔር አምላክም እንዲህ በማለት አዘዘው፣ “በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም የፍሬ ዛፍ መብላት ትችላልህ። 17ነገር ግን መልካሙንና ክፉውን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፣ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።”18ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም። ስለዚህ የምትመቸውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” አለ። 19እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር የምድር እንስሶችንና የሰማይ ወፎችን አበጀ። ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ይመለከት ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው። ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር አዳም ያወጣለት ስም ያ ስሙ ሆነ። 20አዳም ለሁሉም ከብቶች፣ ለሁሉም የሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው። ነገር ግን ለአዳም ለራሱ የምትመች ረዳት አልተገኘለትም።21እግዚአብሔር አምላክ በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፣ ስለሆነም አዳም አንቀላፋ። እግዚአብሔር አምላክ አዳም አንቀላፍቶ ሳለ ከጎድን አጥንቶቹ አንዱን ወስዶ አጥንቱን የወሰደበትን ስፍራ በሥጋ ዘጋው። 22እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም ከወሰደው የጎድን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት። ወደ አዳምም አመጣት። 23አዳምም፦ “አሁን ይህቺ ከአጥንቴ የተገኘች አጥንት ከሥጋዬ የተገኘች ሥጋ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል” አለ።24ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። 25አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።
1እግዚአብሔር በምድር ላይ ከፈጠራቸው ማናቸውም ሌሎች አራዊቶች ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኮለኛ ነበር። እርሱም ሴቲቱን፦ “በእርግጥ እግዚአብሔር ‘በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም ዛፍ አትብሉ’ ብሎአልን?” ብሎ ጠየቃት። 2ሴቲቱም ለእባቡ፦ “በአትክልቱ ስፍራ ካሉት የዛፎች ፍሬዎች መብላት እንችላለን፤ 3ነገር ግን በአትክልቱ ስፍራ መካከል ስለሚገኘው ዛፍ እግዚአብሔር “እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም” ብሎአል።4እባብም ለሴቲቱ፦ “በፍጹም አትሞቱም። 5ከእርሱ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንደሚከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካሙንና ክፉውን የምታውቁ እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው አላት።” 6ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት መልካም፣ ሲያዩት ደስ የሚያሰኝና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደሆነ ተመልክታ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከእርሷ ጋር ለነበረውም ለባሏ ከፍሬው ሰጠችው፣ እርሱም በላ።7የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፣ ራቁታቸውን እንደነበሩም አወቁ። የበለስ ቅጠሎችንም በማጋጠም ከሰፉ በኋላ ለራሳቸው መሸፈኛ ግልድም ሠሩ። 8ቀኑ ወደ ምሽት ሲቃረብ በአትክልት ስፍራው ሲመላለስ የእግዚአብሔር አምላክን ድምፅ ሰሙ፤ ስለዚህ አዳምና ሚስቱ ከእግዚአብሔር አምላክ ፊት በመሸሽ በአትክልቱ ስፍራ በነበሩት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።9እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ጠራውና፣ “የት ነህ?” አለው። 10አዳምም፣ “በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ድምፅህን ሰማሁና ራቁቴን ስለነበርሁ ፈራሁ፤ በዚህም ምክንያት ተሸሸግሁ።” 11እግዚአብሔርም፦ “ራቁትህን እንደሆንክ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ብዬ ካዘዝኩህ ከዛፉ ፍሬ በላህን?” አለው።12አዳምም፦ “አብራኝ እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝ፣ እኔም በላሁት” አለ። 13እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ “ምንድነው ያደረግሽው?” አላት። ሴቲቱም፦ “እባቡ አታለለኝና በላሁ” አለች።14እግዚአብሔር አምላክም ለእባቡ፦ “ይህንን በማድረግህ ከእንስሳት ሁሉና ከምድር አራዊት ሁሉ ተለይተህ የተረገምህ ትሆናለህ። በደረትህ እየተሳብክ ትሄዳለህ፣ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ አፈር ትበላለህ። 15በአንተና በሴቲቱ፣ በዘርህና በዘሯ መካካል ጠላትነትን አደርጋለሁ። የእርሷ ዘር ራስህን ይቀጠቅጣል፣ አንተም ተረከዙን ትነክሳለህ” አለው።16ለሴቲቱም እንዲህ አላት፦ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በስቃይም ትወልጃለሽ። ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፣ እርሱም ገዢሽ ይሆናል።”17ለአዳምም እንደዚህ አለው፦ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘ከእርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ከዛፉ ፍሬ ስለበላህ ከአንተ የተነሳ ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ በከባድ ድካም ምግብህን ከእርሷ ታገኛለህ። 18ምድር እሾህና አሜኬላ ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። 19ከተገኘህበት አፈር እስክትመለስ ድረስ በላብህ እንጀራን ትበላለህ። አፈር ነህና ወደ አፈር ተመልሰህ ትሄዳለህ”።20የሕያዋን ሁሉ እናት በመሆኗ አዳም ለሚስቱ ‘ሔዋን’ የሚል ስም አወጣላት። 21እግዚአብሔር አምላክ ከቆዳ ልብስ አዘጋጅቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።22እግዚአብሔር አምላክ፦ “መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማውቅ ረገድ አሁን ሰው ከእኛ እንደ አንዱ ሆኖአል። ስለዚህ አሁን እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ቀጥፎ እንዳይበላ ለዘላለምም እንዳይኖር ሊፈቀድለት አይገባም” አለ። 23በዚህም ምክንያት የተገኘባትን ምድር እንዲያለማ እግዚአብሔር አዳምን ከኤደን የአትክልት ስፍራ አስወጣው። 24ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ከአትክልት ስፍራው አባረረው፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ከኤደን የአትክልት ስፍራ በስተቀኝ በኩል ኪሩቤልን እንደዚሁም በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ አኖረ።
1አዳምም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ። እርሷም ፀነሰች። ቃየንንም ወለደች። “በእግዚአብሔር ዕርዳታ ወንድ ልጅ ወለድሁ” አለች። 2ከዚያ በኋላም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤል የበግ እረኛ ሲሆን ቃየን ግን ገበሬ ሆነ።3ከዕለታት አንድ ቀን ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መባ አቀረበ። 4አቤል ደግሞ መጀመሪያ ከተወለዱ በጎች መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር በአቤልና በመሥዋዕቱ ደስ ተሰኘ፣ 5በቃየንና በመሥዋዕቱ ግን ደስ አልተሰኘም። ስለዚህ ቃየን በጣም ተቆጣ፣ ፊቱም ተኮሳተረ።6እግዚአብሔር አምላክ ቃየንን፦ “ለምን ተቆጣህ፣ ፊትህስ ለምን ተኮሳተረ? 7መልካም ብታደርግ ፊትህ ያበራ አልነበረምን? ያደረግኸው መልካም ካልሆን ግን ኃጢአት በደጅህ እያደባች ናት፣ ልትቆጣጠርህም ትፈልጋለች፣ አንተ ግን በቁጥጥርህ ሥር አድርጋት” አለው።8ቃየን ወንድሙን አቤልን፦ “ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው፣ በዚያም ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ በቁጣ ተነሳበት፣ ገደለውም። 9ከዚያ በኋላም እግዚአብሔር ቃየንን፦ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” አለው። እርሱም፦ “አላውቅም፣ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” አለ።10እግዚአብሔርም፦ “ያደረግኸው ምንድን ነው? የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል” አለው። 11“አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ። 12ምድርንም በምታርስበት ጊዜ ፍሬዋን በሙላት አትሰጥህም። በምድር ላይ ኮብላይና ተንከራታች ትሆናለህ” አለው።13ቃየንም ለእግዚአብሔር፦ ቅጣቴ ከምችለው በላይ ነው። 14በእርግጥም ዛሬ ከምድሪቱ አባርረኸኛል፣ እኔም ከፊትህ እሸሸጋለሁ። በምድር ላይ ኮብላይና ተንከራታች እሆናለሁ፣ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል” አለው። 15እግዚአብሔርም፦ “ቃየንን የሚገድል ማንኛውም ሰው ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ ይወሰድበታል” አለ። ከዚያ በኋላም የሚያገኘው ማንኛውም ሰው እንዳይገድለው እግዚአብሔር በቃየን ላይ ምልክት አደረገበት።16ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፣ ከኤደን በስተምሥራቅ በነበረው ኖድ በተባለው ምድር ኖረ። 17ቃየንም ከሚስቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ፣ እርሷም ፀነሰች፣ ሄኖክንም ወለደች። ቃየን ከተማን መሠረተ፣ የመሠረታትንም ከተማ በልጁ ስም ሄኖክ ብሎ ጠራት።18ሄኖክም አራድን ወለደ። አራድም መሑያኤልን ወለደ። መሑያኤልም መቱሳኤልን ወለደ። መቱሳኤልም ላሜክን ወለደ። 19ላሜክም ዓዳና ጺላ የተባሉ ሁለት ሚስቶችን አገባ።20ዓዳ ያባልን ወለደች፣ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ለከብት አርቢዎች አባት ነበር። 21የእርሱ ወንድም ዩባልም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበር። 22ጺላም ከነሐስና ከብረት መሣሪያዎችን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች። የቱባልቃይንም እህት ናዕማ ትባል ነበር።23ላሜክ ለሚስቶቹ፦ “አዳና ጺላ ስሙኝ፣ እናንተ የላሜክ ሚስቶች የምላችሁን ስሙኝ ስለጎዳኝና ስላቆሰለኝ አንድ ሰው ገድያለሁ። 24ቃየንን የሚገድል ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ የሚወሰድበት ከሆነ የላሜክ ገዳይማ ሰባ ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ ይወሰድበታል” አላቸው።25አዳም ከሚስቱ ጋር እንደገና የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ፣ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ምትክ ሰጠኝ” በማለት ስሙን ሤት ብላ ጠራችው። 26ለሤትም ወንድ ልጅ ተወለደለት፣ ስሙንም ሄኖስ አለው። በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ጀመሩ።
1የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረው ጊዜ በራሱ አምሳያ ፈጠራቸው፤ 2ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፣ ባረካቸውም። በተፈጠሩም ጊዜ ‘ሰው’ ብሎ ጠራቸው።3አዳም ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፣ ስሙንም ‘ሤት’ ብሎ ጠራው። 4አዳም ሤትን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ 5930 ዓመት ሲሆነውም ሞተ።6ሤት ዕድሜው 105 ሲሆን ሄኖስን ወለደ። 7ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሤት 807 ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 8ሤት 912 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።9ሄኖስ 90 ዓመት ሲሆነው ቃይናንን ወለደ። 10ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 11ሄኖስ 905 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።12ቃይናን 70 ዓመት ሲሆነው መላልኤልን ወለደ። 13ቃይናን መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 14ቃይናን 910 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።15መላልኤል 65 ዓመት ሲሆነው ያሬድን ወለደ። 16መላልኤል ያሬድን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 17መላልኤል 895 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።18ያሬድ 162 ዓመት ሲሆነው ሄሮክን ወለደ። 19ያሬድ ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 20ያሬድ 962 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።21ሄኖክ 65 ዓመት ሲሆነው ማቱሳላን ወለደ። 22ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል 300 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 23ሄኖክ 365 ዓመታት ኖረ። 24ሄኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል ኖረ፣ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ስለወሰደው አልተገኘም።25ማቱሳላ 187 ዓመት ሲሆነው ላሜሕን ወለደ። 26ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ 782 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 27ማቱሳላ 969 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።28ላሜሕ 182 ዓመት ሲሆነው አንድ ወንድ ልጅ ወለደ። 29“ይህ ልጅ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከብርቱ ሥራችን ያሳርፈናል” ሲል ስሙን ‘ኖህ’ ብሎ ጠራው።30ላሜሕ ኖህን ከወለደ በኋላ 595 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 31ላሜሕ 777 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።32ኖህ 500 ዓመታት ሲሆነው ሴም፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።
1የሰው ልጆች በምድር ላይ እየበዙ ሲሄዱ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። 2የእግዚአብሔር ልጆችም የሰዎች ሴቶች ልጆች የሚስብ ውበት እንዳላቸው ተመለከቱ። ከእነርሱ መካከልም የመረጧቸውን ሚስቶች አድርገው ወሰዱ። 3እግዚአብሔርም፦ “እርሱ ሥጋ ስለሆነ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜውም 120 ዓመት ይሆናል” አለ።4የእግዚአብሔር ልጆች ከሰዎች ሴቶች ልጆች ጋብቻ በፈጸሙና ልጆችን በወለዱበት በዚያን ጊዜ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ግዙፍ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንት ዘመን ዝናን ያተረፉ ኅያላን ነበሩ።5እግዚአብሔር የሰው ልጆች ክፋት በምድር ላይ እየበዛ እንደሆነና የልቡም ሃሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ። 6እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ ልቡም አዘነ።7በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር፦ “የፈጠርሁትን የሰው ልጅ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ፤ ስለፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና ከእነርሱም ጋር እንስሳትን፣ በደረታቸው የሚሳቡትን ፍጥረታትና የሰማይ ወፎችን ሁሉ አጠፋለሁ” አለ። 8ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አገኘ።9የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው። ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፤ የእግዚአብሔርንም መንገድ የሚከተል ሰው ነበር። 10ኖኅ ሴም፣ ካምና ያፌት የተባሉትን ሶስት ወንዶች ልጆች ወለደ።11በእግዚአብሔር ፊት በክፉ ሥራ ረከሰች በዓመፅም ተሞላች። 12እግዚአብሔር ምድርን ተመለከተ፣ የተበላሸች እንደሆነችና በምድር የሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ በክፋት እንደሚኖሩ አየ።13እግዚአብሔርም ኖኅን፦ “ሥጋን የለበሰ ሁሉ ፍጻሜ ደርሶአል፣ ከእነርሱ የተነሳ ምድር በግፍ ተሞልታለችና። እኔም በእርግጥ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ። 14አንተ ግን ከጥሩ እንጨት መርከብ ሥራ፤ መርከቧም ክፍሎች እንዲኖራት አድርግ፤ ውስጧንና ውጭዋንም በቅጥራን ለቅልቀው። 15እንደዚህ አድርገህ ሥራት፦ ርዝመቷ 140 ሜትር፣ ወርዷ 23 ሜትር፣ ከፍታዋ 13. 5 ሜትር ይሁን።16ለመርከቧ ጣራ አብጅላት፣ ጣራና ግድግዳው በሚጋጠምበት ቦታ ግማሽ ሜትር ክፍተት ተው፤ ከጎኗ በር አውጣላት፤ ባለ ሦስት ፎቅ አድርገህ ሥራት። 17እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባችውን ፍጡራን ሁሉ ለማጥፋት እነሆ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል።18ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋር ወደ መርከቧ ትገባላችሁ። 19ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲቆዩ ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ወንድና ሴት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ።20ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቆዩ ዘንድ ወደ አንተ ይምጡ። 21ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።” 22ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።
1እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ። 2ከንፁህ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ወንድና ሴት፣ ንፁሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት ከአንተ ጋር አስገባ። 3እንዲሁም ከሰማይ ወፎች ወገን ሰባት ወንዶችና ሰባት ሴቶች በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋር ታስገባለህ።4ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ላይ አጠፋለሁ።” 5ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።6የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የ600 ዓመት ሰው ነበር። 7ኖኅና ወንዶች ልጆቹ ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ።8ንፁሕ ከሆኑትና ንፁሕ ካልሆኑት እንስሳት ከወፎችና በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጡራን ሁሉ 9ጥንድ ጥንድ ወንድና ሴት ሆነው ወደ ኖኅ መጡ፤ እግዚአብሄር ኖኅን ባዘዘው መሠረትም ወደ መርከቧ ገቡ። 10ከሰባት ቀንም በኋላ የጠፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ።11ኖኅ በተወለደ በ600ኛው ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ። 12ዝናቡም መዝነብ ጀመረ፣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ባለማቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ።13ዝናቡ መዝነብ በጀመረበት ቀን ኖኅና ሚስቱ ከልጆቻቸው ጋር ከሴም ከካም ከያፌትና ከሶስቱም ልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገቡ። 14ከአራዊት ከእንስሳት በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዓይነት አብረዋቸው ገቡ።15የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸው ፍጡራን በሙሉ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ከኖኅ ጋር ወደ መርከቡ ገቡ። 16ከሕያዋንም ፍጡራን ሁሉ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘው መሠረት ወንድና ሴት እየሆኑ ገቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር የመርከቡን በር ከውጭ ዘጋ።17የጥፋት ውሃም ለአርባ ቀናት ያለመቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ ውሃው እየጨመረ በሄድ መጠን መርከቧን ከምድር ወደ ላይ አነሳት። 18ውሃው በምድር ላይ በጣም እየጨመረና ከፍ እያለ ሲሄድ፣ መርከቧ በውሃ ላይ ተንሳፈፈች።19ውሃው በጣም ከፍ በማለቱ፣ ከሰማይ በታች ያሉትን ታላላቅ ተራሮች ሁሉ ሸፈናቸው። 20ውሃው ከተራሮች ጫፍ በላይ 7ሜትር ያህል ከፍ አለ።21በምድር ላይ የነበሩ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ፦ ወፎች፣ የቤት እንስሳት፣ አራዊት፣ በምድር የሚርመሰመሱ ፍጡራን ሰዎችም በሙሉ ጠፉ። 22የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው በምድር የነበሩ ፍጡራን ሁሉ ሞቱ።23ሕይወት ያላቸው ፍጡራን ሁሉ ከሰዎች ጀምሮ እንስሳት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራንና የሰማይ ወፎች ሁሉም ከምድር ገጽ ጠፉ። ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቧ ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ። 24ውሃውም ምድርን ሸፍኖ መቶ አምሳ ቀን ቆየ።
1እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቧ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሳት ሁሉ አሰበ። በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ ውሃውም ጎደለ። 2የጥልቁ ምንጮችና የሰማይ መስኮቶች ተዘጉ፣ ዝናቡም መዝነቡን አቆመ። 3ውሃው ከምድር ላይ ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣ፤ ከመቶ ሃምሳ ቀን በኋላም የውሃው ከፍታ እጅግ ቀነሰ።4በሰባተኛው ወር፤ በአሥራ ሰባተኛው ቀን መርከቧ በአራራት ተራሮች ላይ አረፈች። 5ውሃው እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ቀስ በቀስ እየጎደለ ሄደ። በአሥረኛው ወር መጀመሪያው ቀን የተራሮች ጫፎች ታዩ።6ከአርባ ቀን በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቧን መስኮት ከፍቶ፣ 7ቁራን ወደ ውጭ ላከ፤ ቁራውም ውሃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር።8ከዚያም በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ ገጽ ጎድሎ እንደሆነ ለማወቅ ርግብን ላከ፤ 9ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ መርከቡ ውስጥ አስገባት።10ሰባት ቀን ከቆየ በኋላ ኖኅ ርግቧን እንደገና ላካት። 11እርሷም ወደ ማታ ተመለሰች፤ እነሆም የለመለመ የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጉደሉን አወቀ። 12ደግሞም ሰባት ቀን ከቆየ በኋላ ኖኅ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ በዚህ ጊዜ ግን ርግቢቱ ወደ እርሱ አልተመለሰችም።13ኖኅ በተወለደ 601ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውሃው ከምድር ላይ ደረቀ። ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ዙሪያውን ተመለከተ፣ ምድሪቱም እንደደረቀች አየ። 14በሁለተኛው ወር፣ በሃያ ሰባተኛው ቀን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ደረቀች።15ከዚያም እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው። 16“አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከመርከቧ ውጡ። 17እንዲዋለዱ፣ እንዲራቡና በምድር ላይ እንዲበዙ ከአንተ ጋር ያሉትን ወፎች፣ እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ይዘሃቸው ውጣ።”18ስለዚህ ኖኅ ከልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር ወጣ። 19እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር የሚሳቡት፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ።20ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ። ንፁሕ ከሆኑት እንስሳትና ንፁሕ ከሆኑት ወፎች አንዳንዶቹን ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ። 21እግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን መዓዛ አሸተተ፣ በልቡም እንዲህ አለ፦ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በእርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጡራንን ዳግመኛ አላጠፋም። 22ምድር እስካለች ድረስ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ፣ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት አይቋረጡም።”
1ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን እንዲህ ሲል ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት፤ 2አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በእንስሳት፣ በሰማይ ወፎች፣ በደረት በሚሳቡ ተንቀሳቃሽ ፍጡሮችና በባሕር ዓሦች፣ በምድር ላይ በሚገኙ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ላይ ይሁን። ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ።3ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፣ ለምለሙን ዕፅዋት እንደሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ። 4ነገር ግን ሕይወቱ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።5ሰውን የገደለ ሁሉ ስለሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፤ የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ። 6የሰውን ደም የሚያፈስ ሁሉ ደሙ በሰው እጅ ይፈሳል፤ በእግዚአብሔር አምሳል እግዚአብሔር ሰውን ሠርቶታልና። 7እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፣ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ ይንሠራፋም።”8ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ አላቸው፦ 9“እነሆ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጣው ዘራችሁ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ 10እንዲሁም ከእናንተ ጋር ከነበሩት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ከወፎች፣ ከእንስሳት ከእናንተ ጋር ከመርከቧ ከወጡት በምድር ላይ ካሉት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር ኪዳን እገባለሁ።11ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋር ኪዳን እገባለሁ።” 12እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “በእኔና በእናንተ መካከል ከእናንተም ጋር ካሉ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ፣ ከሚመጣው ትውልድ ሁሉ ጋር፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤ 13ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አድርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል።14ደመናን በምድር ላይ በጋረድሁና ቀስቴም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ 15ከእናንተና ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር የገባሁትን ኪዳን አስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም።16ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ በእኔና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጡራን መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን አስባለሁ።” 17ከዚያ በኋላም እግዚአብሔር ለኖኅ፦ “ይህ በእኔና በምድር ላይ በሚኖሩ ሕያዋን ሁሉ መካከል የገባሁት ኪዳን ምልክት ነው።” አለው።18ከመርከቧ የወጡትም የኖኅ ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ነበር፤ ካም የከነዓን አባት ነው። 19እነዚህ ሶስቱ የኖኅ ልጆች ሲሆኑ፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከነዚሁ ነው።20ኖኅ ገበሬ መሆን ጀመረ፣ ወይንንም ተከለ። 21ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ እርቃኑን ተኛ።22የከንዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። 23ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በትከሻቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ።24ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ። 25ከዚህም የተነሣ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም አገልጋይ ይሁን።” አለ።26ደግሞም፦ “የሴም አምላክ የሆነው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣ ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን። 27እግዚአብሔር የያፌትን ግዛት ያስፋ፤ ያፌት በሴም ድንኳኖች ይኑር፤ ከነዓን የያፌት አገልጋይ ይሁን።” አለ።28ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ። 29ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖሮ ሞተ።
1የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ዝርያዎች የሚከተሉት ናቸው። ከጥፋት ውሃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው።2የያፌት ልጆች፦ ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕና ቴራስ ነበሩ። 3የጋሜር ልጆች፦ አስከናዝ፣ ሪፋትና ቴርጋማ ነበሩ። 4የያዋን ልጆች፦ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲምና ሮዳኢ ነበሩ። 5ከእነዚህም በየነገዳቸው በየጎሳቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።6የካም ልጆች፦ ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥና ከነዓን ነበሩ። 7የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማና ሰበቀታ ነበሩ። የራዕማ ልጆች፦ ሳባና ድዳን ነበሩ።8ኩሽ በምድር ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ጦረኛ የነበረው የናምሩድ አባት ነበር። 9እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ አዳኝ ነበር። ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር። 10የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች በሰናዖር ምድር የነበሩት፡- ባቢሎን፣ አሬክ፣ አርካድና ካልኔ ነበሩ።11ከዚያም ወደ አሦር ምድር ሄደና ነነዌን፣ ርሆቦትን፣ ካላሕን 12እንዲሁም በነነዌና በካላሕ መካከል የነበረውን ታላቅ ከተማ ሬሴን የተባሉትን ከተሞች መሠረተ። 13ምጽራይም የሎዳማውያን፣የዐናሚማውያን፣ የላህሚማውያን፣ የነፍታሌማውያን፣ 14የፈተሩሲማውያንና ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የካስሎሂማውያንና የቀፍቶርማውያን አባት ነበር።15የከነዓንም የበኩር ልጅ ሲዶን ተከታዩም ሔት ይባሉ ነበር። 16ሌሎቹም የከነዓን ዝርያዎች ኢያቡሳውያን፣ አሞራውያን፣ ጌርጌሳውያን፣ 17ኤውያውያንን፣ ዓርቃውያን፣ ሲናውያን፣ 18ኤርዋዳውያን፣ አርዋዳውያን፣ ደማራውያን፣ ሐማታውያን የሚባሉ ነበሩ። ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጎሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ።19የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል ገሞራን አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል። 20እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ነበሩ።21ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅድመ አያት ነበር። 22የሴም ልጆች ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ነበሩ። 23የአራም ልጆች ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ ነበሩ።24አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ኤቦርን ወለደ። 25ዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለነበር የአንደኛው ልጅ ስም ፍሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።26ዮቅጣንም የአልሞዳድ፣ የሼሌፍ፥ የሐጸርማዌት፣ የዮራሕ፣ 27የዐዶራም፣ የኢዛል፣ የዲቅላ፣ 28የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣ 29የኦፊር፣ የሐዊላና የዮባብ አባት ነበር። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዝርያዎች ነበሩ።30መኖርያ ስፍራቸውም በስተምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ስፋር ይደርስ ነበር። 31እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ነበሩ።32የኖኅ ወንዶች ልጆች ጎሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነበር።
1በዚያ ዘመን መላው ዓለም የሚናገረውና የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር። 2ወደ ምሥራቅ ሲጓዙ፣ በሰናዖር አንድ ሜዳማ ቦታ አግኝተው በዚያ ሰፈሩ።3እርስ በርሳቸውም፣ “ኑ፣ ጡብ እንሥራና እስከበቃው ድረስ በእሳት እንተኩሰው” ተባባሉ። በድንጋይ ፈንታ ጡብ ተጠቀሙ፤ ጡቡን እርስ በርስ ለማያያዝም ቅጥራን ተጠቀሙ። 4ከዚያም፣ “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆን ጫፉ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ። ያንን ካላደረግን በምድር ሁሉ ፊት መበታተናችን ነው” አሉ።5የአዳም ልጆች የሠሩትን ለማየት ያህዌ ወደ ከተማውና ወደ ግንቡ ወረደ። 6ያህዌም፣ “አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ በመሆናቸው ይህን ማድረግ ችለዋል! ከእንግዲህ ማድረግ የፈለጉትን ለማድረግ ምንም የሚያቅታቸው አይኖርም። 7ኑ እንውረድ፤ አርስ በርስ እንዳይግባቡም ቋንቋቸውን እንደበላልቀው” አለ።8ስለዚህ ያህዌ ከዚያ ቦታ ወደ መላው ዓለም በታተናቸው፣ እነርሱም ከተማዋን መሥራት አቋረጡ። 9በዚያ የዓለምን ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዋ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም ያህዌ በመላው ዓለም በተናቸው።10የሴም ትውልድ ይህ ነው። የጥፋት ውሃ ከመጣ ሁለት ዓመት በኋላ ሴም መቶ ዓመት ሲሆነው አርፋድሰድን ወለደ። 11አርፋድሰድን ከወለደ በኋላ ሴም አምስት መቶ ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።12አርፋክሰድ በሰለሣ አምስት ዓመቱ ሰላን ወለደ፤ 13ሰላን ከወለደ በኋላ አርፋክሰድ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ እርሱም ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።14ሳላ ሰላሣ ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤ 15ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።16ዔቦር አራት ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤ 17ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር አራት መቶ ሰላሣ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።18ፋሌቅ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ራግውን ወለደ፤ 19ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።20ራግው ሰለሣ ሁለት ዓመት ሲሆነው፣ ሴሮሕን ወለደ፤ 21ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው ሁለት ሞት ሰባት ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።22ሴሮሕ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ናኮርን ወለደ፤ 23ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።24ናኮር ሃያ ዘጠኝ ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤ 25ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር አንድ መቶ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ። 26ታራ ሰባ ዓመት ሲሆነው አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።27የታራ ትውልድ ይህ ነው። ታራ፣ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራን ወለደ። ሐራን ሎጥን ወለደ። 28ሐራን አባቱ ታራ በሕይወት እያለ በተወለደበት ከተማ በከለዳውያን ዑር ሞተ።29አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ። የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካ የሐራን ልጅ ስትሆን፣ ሐራን የሚልካና የዮሳካ አባት ነበር። 30ሦራ ምንም ልጅ ያልነበራት መካን ነበረች።31ታራ ልጁ አብራምን፣ የልጅ ልጁን ሎጥንና የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ዑር አብረው ወጡ። ሆኖም፣ ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ። 32ታራ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖሮ በካራን ሞተ።
1በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን፣ ወገንህንና የአባትህን ቤተ ሰብ ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ፤ 2ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት አደርግሃለሁ። 3የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግሙህንና የሚያዋርዱህን እረግማለሁ። በአንተ አማካይነት በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይባረካሉ።”4ስለዚህ አብራም ያህዌ እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ተነሥቶ ሲሄድ፣ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበር። 5አብራም ሚስቱ ሦራን፣ የውንድሙ ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዞ በመጓዝ፣ ከነዓን ምድር ገቡ።6አብራም በሞሬ ያለው ግዙፍ የወርካ ዛፍ እስካለበት እስከ ሴኬም ዘልቆ ሄደ። በዚያ ዘመን ከነሻናውያን በዚህ ምድር ይኖሩ ነበር። 7ያህዌ ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። ስለዚህ አብራም ለተገለጠለት ለያህዌ በዚያ መሠዊያ ሠራ።8ከዚያ በመነሣት ከቤቴል በስተ ምሥራቅ ወዳለው ተራራማ አገር ሄደ፤ ቤቴል በስተ ምዕራብ፣ ጋይ በስተ ምዕራብ ባለችበት ቦታ ድንኳኑን ተከለ። እዚያ ለያህዌ መሠዊያ ሠራ፤ የያህዌንም ስም ጠርቶ ጸለየ። 9አብራም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ መጓዙን ቀጠለ።10በዚያ ምድር ጽኑ ራብ ስለ ነበር አብራም እዚያ ጥቂት ጊዜ ለመቆየት ወደ ግብፅ ሄደ። 11ግብፅ በመግባት ላይ እያለ አብራም ሚስቱ ሦራን እንዲህ አላት፤ “መቼም አንቺ ቆንጆ ሴት መሆንሽን አውቃለሁ። 12ግብፃውያን ሲያዩሽ ‘ይህች ሚስቱ ናት’ ይላሉ፤ እኔን ይገድሉኛል፤ አንቺን ግን ይተዉሻል። 13ስለዚህ በአንቺ ምክንያት ለእኔ መልካም እንዲሆልኝ ሕይወቴም እንዲተርፍ እኅቱ ነኝ’ በዪ አላት።14አብራም ወደ ግብፅ ሲገባ፣ ሦራ ምን ያህል ቆንጆ እንደ ሆነች ግብፃውያኑ አዩ። 15የፈርሾን ሹማምንት ባዩአት ጊዜ እርሷን እያደነቁ ለፈርዖን ነገሩት፤ ወደ ቤተ መንግሥትም ተወሰደች። 16በእርሷ ምክንያት ፈርኦን አብራምን በክብር አስተናገደው፤ በጎች፣ በሬዎች፣ ወንድ አህዮች ወንድና ሴት ባሪያዎች፣ ሴት አህዮችና ግመሎች ሰጠው።17በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ያህዌ ፈርዖንና ቤተ ሰቡን በታላቅ መቅሠፍት መታ። 18ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ለመሆኑ ምን እያደረግህብኝ ነው? ሚስትህ መሆንዋን ለምን አልነገርከኝም? 19ለምን እኅቴ ናት አልከኝ? እኅቴ ናት ስላልከኝ ሚስቴ ላደርጋት ነበር። አሁንም ሚስትህ እቻት፤ ይዘሃት ሂድ” 20ከዚያም ፈርዖን አብራምን በተመለከተ ለባለሟሎቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋር አሰናበቱት።
1ስለዚህ አብራም ሚስቱንና ያለውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከግብፅ ወደ ኔጌብ ሄደ። ሎጥም ከእነርሱ ጋር ነበረ። 2በዚህ ጊዜ አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ በልጽጎ ነበር።3ከኔጌብ ተነሥቶ እስከ ቤቴል ተጓዘ፤ ቀድሞ ድንኳን ተክሎበት ወደ ነበረው በቤቴልና በጋይ መካከል ወደ ነበረው ቦታ ደረሰ። 4ይህ ቀድሞ መሠዊያ የሠራበት ቦታ ሲሆን በዚያ ያህዌን ጠራ።5ከአብራም ጋር ይጓዝ የነበረው ሎጥ የራሱ በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት። 6ሁለቱ አንድ ላይ ይኖሩ ስለ ነበር ስፍራው አልበቃቸውም፤ በዚህ ላይ ንብረታቸውም በጣም ብዙ ስለ ነበር አብረው መኖር አልቻሉም። 7ይህም በመሆኑ በአብራምና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተፈጠረ። በዚያ ዘመን ከነኣናውያንና ፌርዛውያን በዚያው አገር ይኖሩ ነበር።8አብራም ሎጥን እንዲህ አልው፤ “በእኔና በአንተ፣ በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ግጭት መኖር የለበትም፤ በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ ሰብ ነን። 9ይኸው እንደምታየው ምድሩ ሰፊ ነው፤ ብንለያይ ይሻላል። አንተ ግራውን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ቀኙን ብትመርጥ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።10ስለዚህ ሎጥ ዙሪያውን ሲመለከት እስከ ዞዓር ድረስ ያለው የዮርዳኖስ ረባዳ ሜዳ ሁሉ እንደ ያህዌ ገነት እንደ የግብፅ ምድር በጣም ለም ሆኖ አገኘው። እንዲህ የነበረው እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን ከማጥፋቱ በፊት ነበር። 11ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ ሁሉ መርቶ ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ በዚህ ሁኔታ ዘመዳሞቹ ተለያዩ።12አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ባሉት ከተሞች መካከል ኖረ። እስከ ሰዶም ድረስ ባለው ቦታ ድንኳኖቹን ተከለ። 13የሰዶም ሰዎች በጣም ዐመፀኞችና በያህዌም ፊት እጅግ ኀጢአተኞች ነበሩ።14ሎጥ ከእርሱ ከተለየው በኋላ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ቦታ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት። 15ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁ።16ዘርህን እንደ ምድር ትቢያ አበዛዋለሁ፤ የምድር ትቢያ ሊቆጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር ሊቆጠር አይችልም። 17እንግዲህ ምድሪቱን ስለምስጥህ ተነሣና በርዝመትና በስፋቱ ተመላለሰባት።” 18ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቀለና በኬብሮን ወዳሉት የመምሬ ወርካ ዛፎች መጥቶ ኖረ፤ እዚያም ለያህዌ መሠዊያ ሠራ።
1አምራፌል የሰናዖር ንጉሥ፣ አርዮክ የአላሳር ንጉሥ፣ ከሎደጎምር የኤላም ንጉሥ፣ ተድዓል የጎይም ንጉሥ፣ 2በነበሩበት ዘመን፤ ከሰዶም ንጉሥ በላ፣ ከጎሞራ ንጉሥ ከብርሳ፣ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፣ ከሰቦይ ንጉሥ ከሰሜበር፣ እንዲሁም ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ወጡ።3እነዚህ የኋለኞቹ አምስት ነገሥታት የጨው ባሕር እየተባለች በምትጠራው በሲዶም ሸለቆ ተሰበሰቡ። 4እነርሱም አሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ተገዙ፤ በአሥራ ሦስተኛው ዓመት ግን ዐመፁ። 5በአሥራ አራተኛው ዓመት ከሎዶጎምርና ከእርሱም ጋር የነበሩት ነገሥታት መጥተው ራፋይምን፣ በአስታሮት ቃርናይምን፣ በካም ዙዚምን፣ በሴዊ ኑሚምን፣ በሸቮት ኢምንን፣ 6የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይ በረሐማ አጠገብ እስካለው እስከ አልፋራን ድረስ ድል አደረጋቸው።7ከዚያም ተመልሰው ዓይንሚስፓጥ ወደሚባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌዋውያንና በሐሴስ ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ። 8ከዚያም የሶዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የሰቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት ወደ ሲዶም ሸለቆ ሄደው ለጦርነት ተዘጋጁ። 9እነዚህ አምስቱ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉስ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በአላሶር ንጉሥ በአርዮክ በእነዚህ ላይ ዘመቱባቸው።10በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጉድጓዶች ነበሩ፤ የሰዶምና የጎመራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጉድጓዶች ውስጥ ወደቁ። የተረፉትም ወደ ተራሮች ሸሹ። 11አራቱ ነገሥታትም በሰዶምና በጎሞራ ያገኙትን ሀብትና ምግብ ሁሉ ዘርፈው ሄዱ። 12በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብርሃምን ወንድም ልጅ ሎጥንና የነበረውን ንብረት ሁሉ ይዘው ሄዱ።13ከዚያ ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው። በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው የአስኮና የእውናን ወንድም በነበረው በአሞራዊው መምሬ ዋርካ ዛፎች አጠገብ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የአብራም አጋሮች ነበር። 14ጠላት ዘመዶቹን ማርኮ መውሰዱን አብራም ሲሰማ በቤቱ ተወልደው ያደጉ ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ሰዎች ይዞ እስከ ዳን ድረስ ተከታተሏቸው።15አብራም ጠላቶቹን ለማጥቃት ሰራዊቱን ሌሊቱን በቡድን በቡድን ከፋፍሎ ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው። 16ጠላት የማረከውን በሙሉ አስጣለ፤ ዘመዱ ሎጥንና ንብረቱን፣ እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎች ሰዎችን አስመለሰ።17አብራም የኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩ ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ ተብሎ በሚጠራው በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ። 18የሰሌም ንጉሥ መልከጼዴቅ እንጀራና ወይን ጠጅ ይዞ መጣ። እርሱ የልዑል አምላክ ካህን ነበር።19አብራምም እንዲህ በማለት ባረከው፣ “ሰማይና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ።20ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠ ልዑል እግዚአብሔር ይባረክ።” አብራምም ይዞት ከነበረው ሁሉ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።21የሰዶም ንጉሥ አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው። 22አብራምም ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ቢሆን፣ 23ደግሞም ‘አብራምን ባለጸጋ አደረግሁት’ እንዳትል የአንተ ከሆነ ምንም ነገር እንዳልወስድ ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ አምላክ ወደ ያህዌ እጄን አንሥቻለሁ። 24አብረውኝ ያሉት ሰዎች ከበሉትና የእነርሱ ድርሻ ከሆነው በቀር ምንም ነገር አልወስድም። አውናን፣ ኤስኩልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”
1ከዚህ በኋላ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፣ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ሽልማትህም እኔው ነን።” 2አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ እኔ ልጅ የለኝም፤ የቤት ወራሽ የሚሆነው የደማስቆው ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ አንተ ለእኔ የምትሰጠኝ ምንድን ነው?” አለ። 3በመቀጠልም አብራም “አንተ ልጅ እስካልሰጠኸኝ ድረስ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም” አለ።4በዚህ ጊዜ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ይልቁንም ወራሽህ የሚሆነው ከአብራክህ የሚከፈል የራስህ ልጅ ይሆናል።” 5ከዚያም ወደ ውጭ አወጣውና እንዲህ አለው፤ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ መቍጠር ከቻልህ ከዋክብቱን ቍጠር። ዘርህም እንዲሁ ይበዛል።”6አብራም ያህዌን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት። 7እንዲህም አለው፤ “ይህችን ምድር እንድትወርስ ልሰጥህ ከከለዳውያን ምድር ከዑር ያወጣሁህ እኔ ያህዌ ነኝ።” 8አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ ይህችን ምድር እንደምወርስ እንዴት አውቃለሁ?” አለ።9በዚህ ጊዜ፣ “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንዲት ፍየልና አንድ በግ እንዲሁም ዋኖስና አንድ ርግብ አቅርብልኝ” አለው። 10እርሱም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቆርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጣቸው፤ ወፎቹን ግን አልከፈላቸውም። 11አሞሮች ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራምም አባረራቸው።12ፀሓይ ልትጠልቅ ስትል አብራም ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማም መጣበት። 13በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ዘሮችህ የራሳቸው ባልሆነ ምድር ባዕድ እንደሚሆኑና እዚያ ለአራቶ መቶ ዓመት በባርነት እንደሚኖሩ በእርግጥ ዕወቅ።14እኔም ባሪያዎች ባደረጓቸው ሕዝብ እፈርዳለሁ፤ በኋላም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ። 15አንተ ግን በሰላም ወደ አባቶችህ ትሄዳለህ፤ ዕድሜም ጠግበህ ትቀበራለህ። 16በአራተኛውም ትውልድ እንደ ገና ወደዚህ ይመጣሉ፤ ምክንያቱም የአሞራውያን ኀጢአት ጽዋው ገና አልሞላም።”17ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና በተቆራረጡት ሥጋዎች መካከል አለፈ። 18በዚያን ቀን ያህዌ እንዲህ በማለት ከአብራም ጋር ኪዳን አደረገ፤ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤ 19የምሰጣቸውም የቄናውያንን፣ የቄንፌዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣ 20የኬጢያውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የራፋይምን፣ 21የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያን፣ የጌርሳውያንንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው።”
1የአብራም ሚስት ሦራ ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ነገር ግን አጋር የምትባል ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። 2አብራምንም፣ "ያህዌ ልጅ እንዳልወደልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጅ አገኝ ይሆናልና ክአገልጋዬ ጋር ተኛ" አለችው። አብራም ሦራ በነገረችው ተስማማ። 3የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋ ሚስት እንድትሆነው ለአብራም የሰጠችው አብራም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ነበር። 4አብራም ክአጋር ግን'ኡንት አደረገ እርሷም ፀነሰች። አጋር መፅነሷን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን በንቀት ማየት ጀመረች።5በዚህ ጊዜ ሦራ አብራምን፣ "ይህ በደል የደረሰብኝ በአንተ ምክንያት ነው። ኅቅፍህ ውስጥ እንድትሆን አገልጋዬን ሰጠሁ፤ እርሷ ግን መፅነሷን ስታውቅ እኔን መናቅ ጀመረች። ያህዌ በእኔና በአንተ መካከ ይፍረድ" አለችው። 6አብራምም መልሶ ሦራን፣ "አገልጋይሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ ናት እርሷ ላይ የፈለግሽውን ማድረግ ትችያልለሽ" አላት። ስለዚህ ሦራ ስላሠቃየቻት፣ አጋር ከቤት ጠፍታ ሄደች።7የያህዌ መልአክ አጋርን ምድረ በዳ ውስጥ በነበረ አንድ ምንጭ አጠገብ አገኛት፤ ያ ምንጭ ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ላይ ነበር። 8መልአኩም፣ "የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፣ ከየት መጣሽ ወዴትስ እየሄድሽ ነው?" አላት። እርሷም፣ "ከእመቤቴ ከሦራ ኮብልዬ እየሄድሁ ነው" አለችው።9የያህዌ መልአክ፣ "ወደ እመቤትሽ ተመለዒ፤ ራስሽንም ለሥልጣንዋ አስገዢ" አላት። 10ከዚያም የያህዌ መልአክ፣ "ዘርሽን እጅግ አበዛዋለሁ፤ ከበምዛቱም የተነሣ ሊቆጠር አይቻልም" አላት።11የያህዌም መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤ "እነሆ ፀንሰሻል ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ያህዌ ችግርሽን ሰምቷልና ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ። 12እርሱ እንደ ዱር አህያ ይሆናል። ከሰው ሁሉ ጋር ይጣላል፤ ሰው ሁሉም ከእርሱ ጋር ይጣላል፤ ከወንድሞቹ ሁሉ ተነጥሎ ይኖራል።"13እርሷም ይሚያናግራትን ያህዌን፣ "አንተኮ እኔን የምታይ አምላክ ነህ"በማለት ጠራችው፤ ምክንያቱም፥ "እርሱ እኔን እንዳየ ሁሉ እኔም እርሱን አየው ይሆን?" ብላ ነበር። 14ስለዚህ ያ ምንጭ ብኤርልያህሮኢ ተባለ፤ የሚገኘው በቃዴስና በባሬድ መካከ ልነው።15አጋር ለአብራም ወድን ልጅ ወለደችለው፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን ልጅ እስማኤል ብሎ ጠራው። 16አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ አብራም ሰማንያ ስድስት ዓመት ሆኖት ነበር።
1አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው እያለ ያህዌ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፤ "እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ ነቀፋም አይኑርብህ። 2በእኔና በአንተ መካከል የተደረገውን ኪዳን አጸናለሁ፤ አንተንም እጅግ አበዛሃለሁ።"3አብራም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እግዚአበሔርም እንዲ አለው፤ 4"እነሆ ኪዳኔ ክአንተ ጋር ነው። የብዙ ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ። 5ከእንግዲህ ስምህ አብራም መባል የለበትም፤ ስምህ አብርሃም መባል እለበት፤ ምክንያቱም የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ። 6እጅግ አበዛሃለሁ፣ ሕዝቦች ክአንተ ይገኛሉ፤ ነገሥታትም ክአንተ ይወጣሉ።7በእኔና በአንተ፣ ክአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በዘላለም ኪዳን አምላክ እሆናችኋለሁ። 8ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ይህች አሁን የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣላለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።"9ከዚያም እግዚአብሔር አብርሃምን፣ "በአንተም በኩል፣ አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ። 10በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ በእኔና በዘርህ መካከል መጠበቅ ያለባችሁ ኪዳኔ ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። 11እናንተ ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእናንተ መካከል ያለው ኪዳን ምልክት ይሆናል።12በመካከላችሁ ያለው ማንኛውም ስምንት ዓመት የሞላው ወንድ የሚመጣው ትውልድ ሁሉ ይገረዝ። ይህ በቤትህ የተወለደውን በገንዘብህ የተገዛውን ሁሉ ይጨምራል። 13ቤትህ ውስጥ የተወለደና በገንዘብህ የገዛኸው መገረዝ አለባቸው። ስለሆነም ኪዳኔ በዘላለም ኪዳን ሥጋችሁ ላይ ይሆናል። 14ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን አፍርሷልና ከወገኖቹ ይወገድ።"15እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ሚስትህ ሦራን ክአንግዲህ ሥራ እንጂ ሦራ ብለህ አትጥራት። 16እባርክሃለሁ፤ ከእርሷ ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ። እባርካታለሁ። እርሷም የብዙ ሕዝብ እናት ትሆናልች፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ክአርሷ ይወጣሉ።17በዚህ ጊዜ አብርሃም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ እየሳቀ በሉ እንዲህ አለ፤ "ለመሆኑ የመቶ ዓመት ሽማግሌ ልጅ መውልደድ ይችላል? የዘጠና ዓመቷ አሮጊት ሥራስ ብትሆን ልጅ መውለድ ይሆንላታል?" 18አብርሃም እግዚአብሔርን፣ "ይልቅ፣ እስማኤልን ብቻ ባኖርህልኝ!" አለ።19እግዚአብሔርም፣ "እንደዚያ አይደለም፤ ሚስትህ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ። የዘላለም ኪዳኔን ከእርሱ ጋር፣ ከእርሱም በኋላ ከዘሩ ጋር እመጸርታለሁ። 20እስማኤልን በተመለከተም ልምናህን ሰምቻለሁ። እነሆ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ። የአሥራ ሁለት ነገዶች አባት ይሆናል፤ ታላቅ ሕዝብ እንዲሆንም አደርጋለሁ። 21ኪዳኔን ግን፣ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ሣራ ከምትወልድህል ከይስሐቅ ጋር እመሠርታለሁ።"22ከእርሱ ጋር መነጋገሩን ከጨረሰ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ላይ ወጣ። 23በዚያኑ ዕለት አብርሃም ልጁ ይስሐቅን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትን በሙሉ፣ በገንዘቡ የገዛቸውን ሁሉ፣ ቤቱ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድ ሁሉ እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ገረዛቸው።24አብርሃም በተገረዘ ጊዜ እድሜው ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ነበር። 25ልጁም እስማኤል በተገረዘ ጊዜ እድሜው አሥራ ሦስት ነበር።26በዚያው ቀን አብርሃምና ልጁ እስማኤልም ተገረዙ። 27ቤቱ ውስጥ የተወለዱትን፣ ከውጭ በገንዘብ የተገዙትን ጨምሮ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ወንዶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ተገረዙ።
1ቀኑ በጣም ሞቃት በሆነ ጊዜ አብርሃም በመምሬ ወርካ ዛፎች አቅራቢይ ኣድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ እያለ ያህዌ ተገለጥለት። 2እርሱም ቀና ብሎ ሦስት ሰዎች ፊት ለፊቱ ቆመው አየ። ባያቸውም ጊዜ ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ፈጥኖ ወደ እነርሱ ሄዶ፣ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ።3አብርሃም እንዲህ አለ፤ "ጌታዬ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ባሪያህን አልፈህ አትሂድ። 4ጥቂት ውሃ ትምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚያም ዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ። 5ወደ እኔ ወዳገልጋያችሁ ከመጣችሁ የደከመ ሰውነታችሁ እንዲበረታ እስቲ ጥቂት እህል ላምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም. "እንዳልኸው አድርግ" አሉት።6ያኔውኑ አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወደ ነበረችበት ድንኳን ገብቶ፣ "ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ" አላት። 7ከዚያም ወደ መንጋው በፍጥነት ሄዶ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ግን ገር የሆነ ጥጃ መረጠና ለአገልጋዩ ሰጠው፤ እርሱም በአስቸኳይ አደረሰው። 8አብርሃምም እግሮ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀበላቸው፤ እነርሱ እየበሉ እያለ እርሱ ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር።9እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "ሚስትህ ሥራ የታለች?" እርሱም፣ "ድንኳን ውስጥ ናት" አለ። 10እነርሱም፣ "የዛሬ ዓመት በፀደይ ወቅት ልክ በዚሁ ጊዜ በእርግጥ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሥራ ልጅ ትወልዳለች" አለ። ሥራ ከጀርባ በነበረው ድንኳን ደጃፍ ሆና ታዳምጥ ነበር።11በዚህ ጊዜ አብርሃምና ሥራ በጣም አርጅተው ነበር፤ ሥራማ ልጅ የመውለጃ ጊዜ አልፎባት ነበር። 12ስለዚህ ሣራ በልቧ፣ "ይህን ያህል ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛልን?" ብላ ሳቀች።13ያህዌ አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ካረጀሁ በኋላ እንዴት አድርጌ ልጅ እወልዳለሁ ስትል ሣራ የሳቀችው ለምንድን ነው? 14ለመሆኑ ለያህዌ የሚሳነው ነገር አለ? እኔ በወሰንሁት የፀደይ ወቅት ወደ እናንተ እመለሳለህ፤ በሚመጣው ዓመት በዚህ ጊዜ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች።" 15ሣራ ግን ፈርታ ስል ነበር፣ "ኧረ እልሳቅሁም" በማለት ካደች። እርሱም፣ "የለም፤ ስቀሻል እንጂ" አላት።16ሰዎቹ ለመሄድ ሲነሡ ቁልቁል ወደ ሰዶም ተመለከቱ። አብርሃምም ሊሸኛቸው ከእነርሱ ጋር ሄደ። 17በዚህ ጊዜ ያህዌ እንዲህ አለ፤ "እኔ የማደርገውን ክአብርሃም መደበቅ አለብኝን? 18አብርሃም በእርግጥ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይህሆናል፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ። 19ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የያህዌን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቡን እንዲያስተምር እኔ አብርሃምን መርጬዋለሁ፤ ይኸውም ለአብርሃም የነገረውን ሁሉ ያህዌ እንዲፈጽምለት ነው።"20ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ "በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ክስ በጣም ስለ በዛ፣ ኀጢአታቸውም በጣም ትልቅ ስል ሆነ፤ 21ወደ እኔ የመጡ ክሶች ምን ያህል እውነት መሆናቸውን ለማየት ወደዚያ እወርዳለሁ፤ እንደዚይ ካልሆነም አውቃለሁ።"22ሰዎቹም ፊታቸውን ወደ ሰዶም አቅንተው ሄዱ፤ አብርሃም ግን ያህዌ ፊት እንደ ቆመ ነበር። 23አብርሃም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ፣ "በእርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር ታጠፋለህን?24ምናልባት በከተማዋ ሃምሳ ጻድቃን ቢገኙስ? እዚያ ባሉ ጻድቃን ስትል ከተማዋን ሳታድን ታጠፋታለህን? 25ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር በመግደል፣ ኀጢአተኛ ላይ የደረሰው በእርሱም እንዲደርስ ማድረግን የመሰለ ንገር ከአንተ ይራቅ! እንዲህ ያለው ከአንተ ይራቅ! የምድር ሁሉ ዳኛ እውነተኛ ጻድቅ የሆነውን አያደርግምን? 26ያህዌም እንዲህ አለ፤ "በሰዶም ከተማ ውስጥ ሃምሳ ጻድቃን ካገኘሁ ፣ ለእነርሱ ስል ያንን ቦታ እምራለሁ።"27አብርሃምም መልሶ እንዲህ አለ፤ "እኔ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታዬ ጋር ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤ 28ለመሆኑ ከአምሳዎቹ ጻድቃን አምስት ቢጎድሉ፣ በጎደሉት አምስቱ ምክንያት ከተማዋን በሙሉ ታጠፋለህን?" እርሱም፣ "እዚያ አርባ አምስ ጻድቃንካገኘሁ አላጠፋትም" አለ።29አብርሃምም እንደ ገና፣ "ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?" እለ፤ እርሱም፣ "ለአርባዎቹ ስል አላደርገውም" እለ። 30አብርሃምም፣ "እባክህን ጌታዬ ይህን ያህል በመናገሬ አትቆጣኝ። እንደው ምናልባት ሰለሣ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፣ "ሰላሣ ጻድቃን ካገኘሁ አላደርገውም" በማለት መለሰ። 31አብርሃምም፣ "መቼም አንዴ ከጌታዬ ጋር መናገር ጀምሬአለሁ! እንደው ምናልባት ሃያ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፥ "ለሃያዎቹ ስል አላደርገውም" አለ።32በመጨረሻም እንዲህ አለ፤ "እባክህ ጌታዬ አትቆጣኝ፤ አንዴ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት አሥር ቢገኙስ። እርሱም፣ "ለአሥሩ፣ ሲል አላጠፋትም" አለ። 33ከአብርሃም ጋር መነጋገሩን እንደ ጨረሰ ያህዌ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።
1ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ወደ ሰዶም መጡ፤ በሰዶም ከተማ መግቢያበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ሎጥ ሲያያቸው ሊቀበላቸው ተነሣ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ። 2እርሱም፣ "እባካችሁ ጌቶቼ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ሌሊቱንም ከእኛ ጋር አሳልፉ፤ ከዚያ ጧት በማለዳ ተነሥታችሁ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም፣ "የለም፤ እዚሁ አደባባዩ ላይ እናድራለን" አሉት። 3ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው እርሱ ቤት ለማደር አብረውት ገቡ። ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ።4ሆኖም፣ ገና ከመተኛታቸው በፊት የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት። 5ሎጥን በመጣራት፣ "በዚህ ምሽት ወደ ቤትህ የመጡ ሰዎች የታሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን" አሉት።6ሎጥ ሊያነጋግራቸው ወደ ውጭ ወጣ መዝጊያውን ከበስተ ኋላው ዘጋ። 7እንዲህም አለ፤ "ወንድሞቼ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ እለምናችሏለሁ። 8ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁና የወደዳችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን ምንም ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ተብተዋልና።"9እነርሱ ግን፣ "ዞር በል!" ይኸ ሰውዬ ስደተኛ ሆኖ እዚህ ለመኖር መጣ፤ ደግሞ ዳኛ ሆነብን! ይልቁ በእነርሱ ላይ ካሰብነው የከፋ እንዳይደርስብህ ዘወር በልልን" አሉት ሎጥንም እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተቃርበው ነበር።10ሰዎቹ እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ ቤት አስገቡትና በሩን ዘጉ። 11ከቤቱ ውጪ የነበሩትን ውጣቶችንም ሆን ሽማግሌዎችን ግን የሎጥ እንግዶች ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ እነርሱም በሩን ለማግኘት ይደነባበሩ ጀመር።12ከዚያም ሰዎቹ ሎጥን እንዲህ አሉት፤ "በከተማዋ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን፣ የወንዶች ልጆችህን ሚስቶች፣ የሴቶች ልጆችህን ባሎችና ሌሎች ዘመዶችህን ሁሉ ከዚህ አውጣ። 13ምክንያቱም ይህን ቦታ ልናጠፋ ነው፤ በያህዌ ፊት ከተማዋ ላይ የሚቀርቡ ክሶች በጣም እየጮኹ በመሆናቸው እንድናጠፋት እርሱ ልኮናል።"14ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹን ባሎች፣ የሴት ልጆቹን እጮኞች፣ "ቶሎ ከዚህ ቦታ ውጡ፤ ያህዌ ከተማዋን ሊያጠፋ ነው" አላቸው። የሴት ልጆቹ ባሎች ግን የሚቀልድ መሰላቸው። 15ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥኝ፣ "ከተተማዋ ላይ በሚመጣው ቅጣት አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱ ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ" እያሉ አቻኮሉት።16ሎጥ አመነታ፤ ያህዌ ምሕረት ስላደረገላቸው ሰዎቹ የእርሱ፣ የሚስቱንና የሁለት ሴት ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዋ አወጣቸው። 17ከከተማው ካወጧቸው በኋላ ከሰዎቹ አንዱ፣ "ሕይወታችሁን ለማዳን ሩጡ! ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ወይም ረባዳው ስፍራ ላይ አትቆዩ። ወደ ተራሮች ሽሹ፤ አለበለዚያ ትጠፋላችሁ።"18ሎጥም እንዲህ አላቸው፤ "ጌቶቼ ሆይ፣ 19እኔ ባሪያችሁ በፊታችሁ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርጋችሁልኛል፤ እኔ እንደ ሆንኩ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል። 20ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ቦታ ያለች ትንሽ ከተማ አለች ሸሽቼ ወደዚያ ብሄድ ሕይወቴን ማዳን እችላለሁ።"21እርሱም፣ "ይሁን እሺ፤ ልመናህን ተቀብብያለሁ፤ ያክካትንም ከተማ አላጠፋትም። 22አንተ እዚያ እስክትደርስ ምንም ማድረግ ስለማልችል በል ቶሎ ፍጠንና ወደዚያ ሽሽ" አለው። ስለዚህ ያቺ ከተማ ዞዓር ተባለች።23ሎጥ ዞዓር ሲደርስ ፀሓይ በምድሩ ወጥታ ነበር። 24ከዚያ ያህዌ ሰዶምና ጎሞራ ላይ ድኝና እሳት አዘነበ። 25እነዚያን ከተሞችና ረባዳ ቦታዎቹን፣ የከተሞቹ ነዋሪዎችንና እዚይ ኣያሉ ለምለም ነገሮችን ሁሉ አጠፋ።26ከኋላው የነበረችው የሎጥሚስት ግን ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች። 27አብርሃም ጠዋት ማለዳ ተነሥቶ ያህዌ ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ። 28ቁልቁል ሰዶምና ጎሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የነበረውን ምድር ተመለከተ። ከምድጃ የሚወጣ የመሰለ ጢስ ከምድሩ እየወጣ ነበር።29እግዚአብሔር በረባዳው ቦታ የነበሩ ከተሞችን ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው። ሎጥ የነበረበትን ከተሞች ቢያጠፋም፣ እርሱ ግን ከጥፋት መሐል አወጣው።30ሎጥ ግን በዞዓር መኖር ስለ ፈራ ከሁለት ሴቶች ልጆቹ ጋር ተራሮቹ ላይ ለመኖር ከዞዓር ወደ ላይ ወጣ። ስለዚህ እርሱና ሁለት ሴቶች ልጆቹ ዋሻ ውስጥኖሩ።31ታላቋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፣ "አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ከእኛ ጋር የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም። 32ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር እናትርፍ።" 33ስለዚህ በዚያ ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት። ታላቂቱ ልጅ ሄዳ ክአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቅም።34በሚቀጥለው ቀን ታላቂቱ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ "ትናንት ሌሊት እኔ ከእባቴ ጋር ተኛሁ። ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፣ ከዚያ አንቺ ሄደሽ ከእርሱ ጋር ትተኛለሽ፣ የአባታችንንም ዘር እናተርፋለን።" 35ስለዚህ በዚያም ምሽት አባታቸውን ወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታናሺቱ ልጅ ሄዳ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።36ሁለቱ የሎጥ ልጆች ክአባታቸው አረገዙ። 37ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት ሞዓባውያን አባት ሆነ። 38ታናሺቱም እንዲሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት አሞናውያን አባት ሆነ።
1አብርሃም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ አካብቢ ሄደ፤ በቃዴስና በሱር መካከልም መኖር ጀመረ። ለጥቂት ጊዜ በጌራራ ተቀመጠ። 2አብርሃም ሚስቱ ሥራራን፣ "እኅቴ ናት" ይል ነበር፤ ስለዚህ ይጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ሰዎች ልኮ ሣራን ወሰዳት። 3እግዚአብሔር ግን በሕልም ወደ እቢሜሌክ መጥቶ፣ "እነሆ በወሰድካት ሴት ምክንያት አንተ ምውት ነህ፤ ምክንያቱም እርሷ ባለ ባል ናት" አለው።4አቢሜሌክ ገና አልሰረሰባትም ነበርና እንዲህ አለ፤ "ጌታ ሆይ፣ በደል ያልተገኘበትን ሕዝብ ልታጠፋ ነውን? 5'እኅቴ ናት' ያለኝ እርሱ ራሱ አይደለምን? እርሷም ብትሆን 'ወንድሜ ነው' ብላኛለች። እኔ እንዲህ ያደረግሁት በቅን ልቦናና በንጹሕ እጅ ነው።"6በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም እንዲህ አለው፤ "አዎን፣ ይህን ያደረግኸው በልብ ቅንነት እንደ ነበር እኔም አውቃለሁ፤ እኔ ላይ ኀጢአት እንዳትፈጽም የጠበቅሁህና እንዳትነካትም ያደረግሁት በዚህ ምክንያት ነው፤ 7ስለዚህ የሰውየውን ሚስት መልስለት፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ ይጸልይልሃል አንትም ትድናለህ። እርሷን ካልመለስህ፣ እንተና የአንተ የሆነው ሁሉ በእርግጥ እንደምትጠፉ ዐውቃለሁ።"8አቤሜሊክ ጧት በማለዳ ተነሥቶ ሹማምንቶቹን ሁሉ ጠራ። የሆነውን ሁሉ ሲነግራቸው በጣም ፈሩ። 9ከዚያም አቤሜሌ አብርሃምን አስጠርቶ፣ "ለመሆኑ፣ ምን እያደረግህብን ነው? በእኔና በግዛቴ ላይ እንዲህ ያለውን ትልቅ መዘዝ ያመጣህብኝ ምን ብበድልህ ነው? መደረግ ያልነበረትን አድርገህብኛል" አለው።10በመቀጠልም፣ አብርሃምን፣ "እንዲህ እንድታደርግ ያነሣሣህ ምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው። 11አብርሃምም፣ "በዚህ ቦታ እግዚአብሔርን መፍራት የለም፤ ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል በማለት ስላሰብሁ ነው። 12በዚህ ላይ ደግሞ ከእናቴ ባትወለድም የአባቴ ልጅ እኅቴ ናት፤ በኋላም ሚስቴ ሆነች።13የአባቴን ቤት ትቼ በየአገሩ እንድዞር እግዚአብሔር ሲያዝዘኝ፣ "ለእኔ ለባልሽ ያለሽን ታማኝነት በዚህ አሳዪኝ፤ በምንሄድበት ቦታ ሁሉ 'ወንድሜ ነው' በዪ አልኳት።" 14ከዚያ አቤሜሊክ በጎችና በሬዎች፣ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ለአብርሃም ሰጠው። ሚስቱ ሣራንም ለአብርሃም መለሰለት።15አቤሜሌክ እንዲህ አለ፤ "አገሬ አገርህ ነው፤ ደስ በሚያሰኝህ ቦታ ተቀመጥ።" 16ሣራንም፣ "ለወንድምሽ አንድ ሺህ ጥሬ ብር እሰጠዋለሁ። ይህም፣ በአንቺ ላይ ለተፈጸመው በደል ካሣ እንዲሆንና አብረውሽ ያሉ ሁሉ አንቺ ንጹሕ ሴት መሆንሽን እንዲያውቁ ነው።"17ከዚያም አብርሃም ለአቤሜሌክ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ ልጅ ለመውለድም በቁ። 18ከአብርሃም ሚስት ከሣራ የተነሣ በአቢሜሌክ ቤት የሚገኙ ሴቶችን ሁሉ ያህዌ ማኅፀናቸውን ዘግቶ ነበር።
1ለአብርሃም በሰጠው የተስፋ ቃል መሰረት እግዚአብሔር ሳራን አሰባት፤ እንደገባላት የተስፋ ቃልም አደረገ ፤ 2ስለዚህም ሳራ አርግዛ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው «በዚህ ጊዜ ይወለዳል» ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው። 3አብርሃም ሚስቱ ሳራ የወለደችለትን ልጅ «ይስሐቅ» ብሎ ስም አወጣለት። 4ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሰረት አብርሃም ገረዘው።5ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ አብርሃም መቶ ዓመት ሆኖት ነበር። 6ሳራም «እግዚአብሔር ሳቅ አደረገልኝ ስለዚህ ይህንን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል»አለች። 7ቀጥላም «ሳራ ለአብርሃም ልጆችን ወልዳ ታጠባለች» ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድሁለት» አለች።8ልጇም አድጎ ጡት መጥባት ተወ፤ ጡት ባስጣሉበትም ቀን አብርሃም ታላቅ ግብዣ አደረገ። 9ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል ከዕለታት አንድ ቀን በሳራ ልጅ በይስሐቅ ላይ ሲያሾፍበት ሳራ አየች።10ስለዚህ ሳራ አብርሃምን«ይህችን አገልጋይ ከነ ልጅዋ ወዲያ አባርልኝ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም» አለችው። 11እስማኤልም ልጁ ስለሆነ ይህ ጉዳይ አብርሃምን በብርቱ አስጨነቀው12እግዚአብሔር ግን አብርሃምን «ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ። ዘር የሚወጣልህ በይስሃቅ በኩል ስለሆን እርሳ የምትልህን ሁሉ አድርግ። 13የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ዘርያ ስልሆን ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ» አለው14አብርሃም በማለዳ ተነሳ ጥቂት ምግብ ውሃም በአቁማዳ ለአጋር በትከሻዋ አደረገላት። ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም በቤርሳቤህ በረሃ ትንከራተት ጀመር። 15በአቁማዳ የነበረው ውሃ ባለቀ ጊዜ ልጁን በቁጥቋጦ ስር አስቀምችጠችው። 16እርስዋም «ልጄ ሲሞት ማየት አልፈልግም» በማለት ጥቂት ከልጅዋ ርቃ ተቀመጠች፤ እዚያም ሆና ድምጻን ከፍ አድርጋ ታለቅስ ጀመር።17እግዚአብሔሬም ልሉ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን «አጋር ሆይ የምትጨነቂበት ነገር ምንድር ነው? እግዚአብሔር የልጂን ለቅሶ ሰምቶአልና አትፍሪ። 18ተነሺ ሂንና ልጁን አንስተስ አባብይው፤ የእርሱንም ዘር አበዛለሁ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ።19በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ዓይኖችዋን ከፈተላትና አንድ የውኃ ጉድጋድ አየች፤ ሄዳም በአቁማዳ ውሃ ሞላች ለልጅዋም አጠጣችው። 20ልጁ እያደገ በሚሄድበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር። 21በፋራንም በረሓ ኖረ፤ ቀስት በመወርወርም የታወቀ አዳኝ ሆነ። እናቱም ከአንዲት ግብጻዊት ጋር አጋባችው።22በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ከሰራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር ሄደና አብርሃምን «በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ 23እኔንም ሆነ ልጆቼን ወይም ዝርያዎቼን እንዳትዋሸኝ አሁን በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ። እኔ ለአንተ ታማኝነትን አሳይቻለሁ፤ አንተም ለእኔና ለዚህች ለምትኖርባትአገር ታማኝንትን እንደምታሳይ ማልልኝ» አለው። 24አብርሃምም «እሺ እምላለሁ» አለ።25አብርሃም የአቢሜሌክ አገልጋዮች ስለ ወሰዱበት የውሃ ጉድጋድ ለአቤሜሌክ አቤቱታ አቀረበ፤ 26አቤሜሌክም «ይህን ያደረገ ማን እንደሆን አላውቅም። አንተም አልነገርኸኝም ይህንን ነገር ገና ዛሬ መስማቴ ነው» አለው። 27ከዚህ በኋላ አብርሃም ብዙ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ በዚያን ቀን ሁለቱም የስምምነት መሀላ አደረጉ።28በዚያን ጊዜ አብርሃም ሰባት እንስት የበግ ጠቦቶችን ከመንጋው ለየ፤ 29አቤሜሌክም «እንዚህን ሰባት ጠቦቶች ለይተህ ያቆምሃቸው ለምንድር ነው?» አለው። 30አብርሃምም «እነዚህን ሰባት እንስት ጠቦቶች ተቀበለኝ እነርሱን ከተቀበልከኝ ይህን ጉድጋድ የቆፈርሁ እኔ መሆኔን ምስክር እንዲሆን ነው» አለው፤31ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ የዚያ ቦታ ስም ቤርሳቤህ ተባል፤ 32ይህን ስምምንት በቤርሳቤህ ተስማምተው ካደረጉ በኋላ አቤሜሌክና የሰራዊቱ አለቃ ፊኮል ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ33ከዚህ ብኃላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከልና የዘላለም አምላክ ለሆነው ሰገደ፤ 34አብርሃም በፍልስጥኤም ምድር በእንግድነት ለረዥም ጊዜ ኖረ።
1ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም «አብርሃም»ብሎ ጠራው፤ «እነሆ አለሁኝ» ብሎ መለሰ። 2እግዚአብሔርም «የምትወደውን አንድ ልጅህን ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ። እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን የሚቃጠል መስዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ» አለው፤ 3አብርሃም በማለዳ ተነስቶ ለመስዋዕት የሚሆን እንጨት ቆረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅን ና ሁለት ወጣት ሰዎችን ይዞ እግዚአብሔር ወደ ነገረው ቦታ ለመሄድ ጉዞ ጀመረ።4በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ። 5ከዚህ በኃላ አብርሃም የርሱን ወጣቶች «እናንተ ከአህያው ጋር በዚህ ቆዩ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ከሰገድን በኃላ እንመለሳለን፤ 6አብርሃምም የሚቃጠለውን መስዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንስቶ ለልጁ ለይስአቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢላዋውንና እሳቱን ያዘ ሁለቱም አብረው ሄዱ።7ይስሐቅ አብርሃምን «አባባ» አለው፤ እርሱም «እነሆ አለሁ ልጄ» አለው፤ ይስሐቅም «እነሆ እሳትና እንጨት ይዘናል ታዲያ ለመስዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?» በማለት አብርሃምን ጠየቀው። 8አብርሃምም «ልጄ ሆይ ለመስዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር እራሱ ያዘጋጃል» አለው። ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ።9እግዚአብሔር ነገረው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሰዊያ ሰርቶ እንጨቱን ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሰዊያው ላይ አጋደመው። 10ልጁን ለማረድ ቢላዋ አንስቶ እጁን ዘረጋ።11ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ «አብርሃም! አብርሃም!» ብሎ ጠራው። እርሱም «እነሆኝ አለሁኝ» አለ። 12እርሱም «በልጁ ላይ እጅህን አትጫንበት፣ ምንም ዓይነት ጉዳትም አታድርስበት፣ እነሆ እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቻለሁ፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት አልተቆጠብህም» አለው።13አብርሃም ዙሪያውን በተመለከት ጊዜ ከበስተጀርባው ቀንዶቹ በቁጥቋጥ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ አቀረበው። 14አብርሃምም ያን ቦታ «እግዚአብሔር ያዘጋጃል» ብሎ ጠራው። ዛሬም ቢሆን ሠዎች «እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል» ይላሉ።15የእግዚአብሔር መልአክ ለሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ከሰማይ ጠራውና፤ 16እንዲህ አለው፤ «እግዚአብሔር ብዙ በረከት እንድምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ» ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቆጠብህ፤ 17እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባህር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዝርያዎችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነስተው፤ ከተሞቻቸውን ይይዛሉ።18ትዕዛዜን ስለ ፈጸምህ የዓለም ህዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ»፤ 19ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ ወጣቶችሁ ተመለሰና በአንድነት ሆነው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ።20ከዚህ ሁሉ በኋላ እንዲህ ተብሎ ለአብርሃም ተነገረው «ሚልካ ልጆችን ለወንድምህ ለናኮር ወልዳለች፤ 21እነርሱም የመጀመሪያው ልጅ ዑፅ ወንድሙም ቡዝ የአራም አባት ቀሙኤል፤ 22ኬሰድ፣ ሐዞ፣ ፊልዳሽ፤ ይድላፍና በቱኤል ናቸው።23በቱኤል ርብቃን ወለደ። ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለንኮር ወለደችለት፤ 24ረኡማ የተባለች የናኮር ቁባት ደግሞ ጤባሕን፣ ገሐምን፣ ተሐሽና ማዕካን ወለደችለት።
1ሣራ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ኖረች። እነዚህን ዓመታት ነበር ሳራ የኖረችው። 2በከነዓን ምድር ባለችው ቂርያት አርባ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃም በሣራ ሞት ምክንያት እጅግ ሃዘነ አለቀሰም።3ከዚያም አብርሃም ከተቀመጠበት ከሚስቱ ሬሳ አጠገብ ተነሳ፣ ኬጢያውያንን እንዲህ አላቸው፤ 4«እኔ በመካከላችሁ በእንግድነት የምኖር ነኝ። እባካችሁ የመቃብር ቦታ ስጡኝ፤ የሚስቴንም ሬሳ ልቅበርበት።»5የኬጢ ልጆችም ለአብርሃም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ 6«ጌታ ሆይ ስማን፣ አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ። ከመቃብር ቦታችን በመረጥከው ስፍራ ሬሳህን መቅበር ትችላለህ፣ ማናችንም ብንሆን የሞተብህን ሰው እንዳትቀብርበት የምቃብር ቦታችንን አንከለክልህም።»7አብርሃም ተነሣ በኬጢያውያን ልጆች ፊት እጅ ነስቶ እንዲህ አለ። 8የሚስቴን አስከሬን እዚህ እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ የጾሐር ልጅ ዔፍሮምን ስለ እኔ ሆናችሁ ልምኑልኝ፤ 9በእርሻው ዳር ያለችውን መክፈል የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፣ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንት ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።»10ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ የኬጢም ሰው ኤፍሮንም የኪጥ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሲስሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ 11«አይደለም ጌታዬ፣ ስማኝ። እርሻውን፣ በርሱም ዳር ያለውን ዋሻ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼአለሁ። ሬሳህን ቅበር።»12አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ። 13የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፤ «እባክህ ፈቃደኛ ብትሆን አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ። አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፤ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ14ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ 15«ጌታዬ ሆይ እኔን ስማኝ፤ የመሬቱ ዋጋ እራት መቶ ሰቅል ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይሄ በእኔና በአንተ መካከል ምንድር ነው? ሬሳህንም ቅበር» 16አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ፤ አብርሃምም በኬት ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው፤ ብሩንም በወቅቱ የንግድ መለኪያ መሰረት መዘነለት።17በዚህም ሁኔታ በመምሬ አጠገብ በመክፈላ ያለውን የኤፍሮንን እርሻ ቦታ ከነዋሻው በከልሉ ካሉት ዛፎች ሁሉ ጭምር ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈ፤ 18እርሻው በእርሱ ያለውን ዋሻው በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው እንጨት ሁሉ በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ ሆነ።19ከዚያም በኋላ ኬብሮን በምትባል በምምሬ ፊት በከነአን ፊት ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍሌ በሆነው ዋሻ ውስጥ ሚስቱን ሳራን ቀበረ። 20እርሻውና በርሱ ያለው ዋሻው በኪጥ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።
1በዚህ ጊዜ አብርሃም ሸመገለ፤ ዕድሜውም ገፋ፤ እግዚአብሔርም አብርሃምን በሁሉ ነገር ባረከው። 2አብርሃምም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ የቤቱ ሁሉ አዛዥ የሆነውን አገልጋይ እንዲህ አለው፤ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ 3እኔም በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናዊያን ለልጄ ሚስት እንዳታጭለት በሰማይና በምድር አምላክ እግዚአብሔር አስምልሃለሁ። 4ነገር ግን ወደ ገዛ ሀገሬ እና ወደ ወገኖቼ ሄደህ ለልጄ ለይስሐቅ ሚስትን ታጭለታለህ።5አገልጋዩም «ምናልባት የምመርጥለት እጮኛ ከእንይ ጋሬ ወደዚህ አገር ለመምጣት እምቢ ብትልስ? ልጅህን ቀድሞ አንተ ወደ ነበርክበት አገር እንዲመለስ ላድርገው?» ብሎ ጠየቀ።6አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ «በምንም ዓይነት ምክንያት ቢሆን ልጄን ወደዚያ አገር መልሰህ እንዳትወስድ ተጠንቀቅ፤ 7የሰማይ አምክክ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤትና ከትውልድ አገሬ አውጥቶ አምጥቶኛል፤ ይህንንም ምድር ለዝርያዎቼ እንደሚሰጥ በመሃላ ቃል ገብቶልኛል፤ ከዚያ ለልጄ ሚስት ማግኘት እንድትችል እግዚአብሔር መልአኩን በፊትህ ይልካል።8ልጅትዋ ከአንተ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንከዚህ መሓላ ነፃ ትሆናለህ፤ ልጄን ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደዚያ አትመልሰው።»9ከዚህ በኋላ አገልጋዩ እጁን በጌታው በአብርሃም ጉልበት ላይ አድርጎ አብርሃም ያዘዘውን ሁሉ እንደሚፈፅም በመሐላ ቃል ገባ።10የአብርሃም ንብረት ኀላፊ የነበረው መጋቢ ከጌታው ቤት ምርጥ የሆኑ የስጦታ ዕቃዎችን በዕሥር ግመሎች ጭኖ በሰሜን መስጴጦምያ ናኮር ወደሚኖርበት ከተማ ሄደ። 11እዚያ በደረሰ ጊዜ ከከተማው ውጭ ባለ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ግመሎቹ ተንበርክከው እንዲያርፉ አደረገ፤ ሰዓቱም ሊመሽ ተቃርቦ፣ ሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚወጡበትን ጊዜ ነበር፤12አገልጋዩ እንዲህ ብሎ ጸለየ፣ "የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ የእኔን አሳብ በመፈፀም ለጌታዬ ለአብርሃም ዘላለምዊ ፍቅርህን ግለጥ። 13እነሆ፣ እኔ በዚህ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ የከተማይቱም ልጃገረዶች ውሃ ሊቀዱ ወደዚህ ይመጣሉ፤ 14ከእነሱም አንድዋ ልጃገረድ 'እንስራሽን ዘንበል አድርገሽ ውሃ አጠጪኝ' እላታለሁ፤ 'አንተም ጠጣ፤ ግመሎችህም እንዲጠጡ ውጃ ቀድቼ አመጣለሁ' ካለችኝ ለአገልጋይህ ለይስሐቅ ፍቅርህን እንዳሳየኸው ዐውቃለሁ።"15ገና ጸሎቱን ሳፅቸርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት ባቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው። 16ርብቃ ገና ወንድ ያልደረሰባት በጣም ቆንጆ ልጃገረድ ነበረች፤ እርስዋ ወደ ውሃው ጉድጓድ ወርዳ በእንስራዋ ውሃ ከቀዳች በኋላ ተመለሰች።17አገልጋዩም ወደ እርስዋ ሮጦ ሄዳና "እባክሽ ከእንስራሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ"አላት። 18እርስዋም "እሺ ጌታዬ ጠጣ" አለችና እንስራዋን ከትከሻዋ አውርዳ ዘንበል አድርጋ ያዘችለት።19ጠጥቶም ከረካ በኋላ "ለግመሎችህም ውሃ እቀዳላቸዋለሁ፤ እስኪበቃቸውም ድረስ ይጠጡ" አለችው። 20ወዲያውኑ፤ በእንስራዋ የያዘችውን ውሃ ግመሎቹ በሚጠጡበት ገዳን ላይ ገልብጣ ግመሎቹ ሁሉ ጠጥተው እስከሚረኩ ድረስ እየተጣደፈች ከጉድጓድ ውሃ መቅዳት ቀጠለች።21ሰውየውም እግዚአብሔር የሄደበትን ተልእኮ አቃንቶለት እንደሆን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ሁሉ ዝም ብሎ ይመለከት ነበር። 22ግመሎቹ ጠጥተው በኋላ ሰውየው አምስት ግራም ያህል የሚመዝን የወርቅ ጎታቻ አውጥቶ በጆሮዋ ላይ አደረገላት፤ መቶ ዐሥር ግራም ያህል የሚመዝን ሁለት የወርቅ አምባሮችንም አውጥቶ በእጆችዋ ላይ አደረገላትና፤ 23"የማን ልጅ ነሽ? እስቲ እባክሽ ንገሪኝ፤ ለእኔና አብረውኝ ቤት ይገኛልን?" ብሎ ጠየቃት።24እርስዋም "የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር፣ እናቱም ሚልካ ይባላሉ፤ 25በቤታችን ብዙ ገለባና ድርቆሽ አለ፤ ለእናንተም ማደሪያ ቦታ ይገኛል" አለችው።26ሰውየምውም በመንበርከክ ለእግዚአብሔር ሰግዶ፣ 27"ለጌታዬ የገባውን ቃል ኪዳንና ዘላለማዊ ፍቅሩን የጠበቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በቀጥታ መርቶ ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት ያመጣኝ እርሱ ነው" አለ።28ልጅትዋ ወደ ቤት ሮጣ ሄደችና የሆነውን ሁሉ ለእናትዋና ለእርስዋ ጋር ላሉት ሁሉ ነገረቻቸው። 29ርብቃ ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፤ እርሱ የአብርሃም አገልጋይ ወዳለበት ውሃ ጉድጓድ እየሮጠ ሄደ። 30ላባ ወደ ሰውየው የሄደው እኅቱ በጆሮዋ ላይ ያደረገችውን ጉትቻና በእጆችዋ ላይ ያደረገቻቸውን አንባሮች ስላየና ርብቃ ሰውየው ጉድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ አገኘው።31ስለዚህ ላባ "አንተ እግዚአብሔር የባረከህ ሰው! ና ወደ ቤት እንሂድ፤ በውጭ የቆምኸው ለምንድን ነው? በቤታችን ለአንተ ማደሪያ የተዘጋጀ ቦታ አለ" አለው። 32ከዚህ በኋላ ሰውየው ወደ ቤት ሄደ፤ ላባም በግመሎቹ ላይ የነበረውን ጭነት አረግፎ ገለባና ድርቆሽ አቀረበላቸው፤ ቀጥሎም የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበትን አመጣላቸው።33ገበታ በቀረበው ጊዜ ጊዜ ሰውየው "የተላክሁበትን ጎዳይ ከመናገሬ በፊት እህል አልቀምስም" አለ። ላባም "ይሁን ተናገር" አለው። 34እርሱም "እኔ የአብርሃም አገልጋይ ነን፤ 35እግዚአብሔር ጌታዬ እጅግ ባርኮል፤ ባለጸጋም አድርጎታል፤ ብዙ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋ፣ ብርና ወርቅ፣ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ግመሎችና አህዮች ሰጥቶታል።36የጌታዬ ሚስት ሣራ በእርጅናዋ ዘምን ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤ ጌታዬም ያለውን ሀብት ሁሉ ለዚሁ ልጅ አውርሶታል። 37ጌታዬ አብርሃም 'እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናዊያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳላጭለት፤ 38ነገር ግን ወደ አባቴ ቤተሰብና ወደ ዘመዶቼ ሄደህ ለልጄ ሚስት እጭለት' ሲል በመሐላ ቃል ኪዳን አስገብቶኛል።'39እኔም ጌታዬን 'ልጅቷ ከእኔ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ ምን ላድርግ?' ብዬ ጠየኩት። 40እርሱም እንዲህ አለኝ 'ዘውትር የማገለግለው እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፤ ጉዞህም የተቃና እንዲሆን ያደርጋል፤ በዚህ ሁኔታ አንተም ከአባትቴ ቤተሰብና ከዘመዶቼ መካከል ለልጄ ሚስት ልታጭለት ትችላለህ፤ 41ከመሐላህ ነፃ የምትሆነው ወደ ዘመዶቼ ሄደህ እነርሱ ልጅትዋን አንሰጥም ብለው የከለከሉህ እንደሆነ ብቻ ነው።'42"ከዚያም በኋላ ዛሬ ወደ ውሃው ጉድጓድ ስመጣ እንዲህ ብዬ ጸለይሁ 'የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ የመጣሁበት ጉዳይ እንዲቃና አድርግልኝ፣ 43እነሆ በዚህ ውሃ ጉድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ አንዲት ልጃገረድን ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ፣ 'እባክሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ' ብዬ እጠይቃታለሁ፤ 44እርስዋም 'እሺ ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳቸዋለሁ'የምትለኝ ብትሆን፣ ለጌታዬ ልጅ ሚስት እንድትሆን አንተ የመረጥሃት እርስዋ ትሁን።45የኅሊና ጸሎትን ገና ሳልጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ ብቅ አለች፤ ወደ ጉድጓዱም ሄዳ ውሃ ቀዳች፤ እኔም 'እባክሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ አልኋት። 46እርስዋም እንስራዋን በፍጥነት ከጀርባዋ አወረደችና ዘንበል አድርጋ 'እሺ ጠጣ፤ ግመሎችህንም አጠጣልሃለሁ' አለችኝ፤ ስለዚህ እኔም ጠጣሁ፤ ግመሎቼንም አጠጣችልኝ።47እኔም 'የማን ልጅ ነሽ?' ብዬ ጠየቅኋት። እርስዋም 'የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር እናቱም ሚልካ ይባላሉ' አለችኝ። ከዚህ በኋላ ጉትቻ በጆሮዋ ላይ፣ አንባሮቹንም በእጅዎችዋ ላይ አደረግሁላት፤ 48ከዚህ በኋላ በጉልበቴ ተንበርክኬ ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ የጌታዬን የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር አመሰገንሁ፤ ምክንያቱም ለጌታዬ ልጅ ሚስት የምትሆነዋን ሴት ወዳገኘሁበት ወደ ጌታዬ ወንድም ቤት በቀና መንገድ የመራኝ እርሱ ነው።49እንግዲህ የጌታዬን ዐደራ በእውነት ተቀብላችሁ እርሱን ደስ ለማሰኘት የምትፈቅዱ እንደሆነ ንገሩኝ፤ የማትፈቅዱም እንደሆነ ቁርጡን ነገሩኝ፤ እኔም እግዚአብሔር ወደሚመራኝ እሄዳለሁ።"50ላባና ባቱኤልም "ይህ ነገር ከእግዚአብሔር የመጣ ስለሆነ፣ መከልከል አልችልም፤ 51ርብቃ ይችውልህ፤ እነሆ ይዘሃት ሂድ፤ እግዚአብሔር ራሱ እንደተናገረው ለጌታዬ ልጅ ሚስት ትሁን" አሉት።52የአብርሃም አገልጋይ ይህን በሰማ ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ 53ከውርቅና ከብር የተሠሩ ጌጣጌጦችን፣ እንዲሁም ልብስ አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ለወንድምዋና ለእናትዋም በጣም ውድ የሆኑ ስጦታዎችን አውጥቶ ሰጣቸው።54ከዚህ በኋላ የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩ ሰዎች በልተው ጠጥተው እዚያው አደሩ፤ ጠዋት በተነሡ ጊዜ የአብርሃም አገልጋይ "እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ ፍቀዱልኝ" አለ። 55ነገር ግን የርብቃ ወንድምና እናትዋ "ልጅትዋ ዐሥር ቀን ያህል ከእኛ ጋር ትቆይ፤ ከዚህ በኋላ ከአንተ ጋር ልትሄድ ትችላለች" አሉት።56እርሱ ግን "እባካችሁ አታቆዩኝ፤ እግዚአብሔር የመጣሁበትን ጉዳይ ስላቃናልኝ ቶሎ ብፄ ወደ ጌታዬ ልመለስ" አላቸው። 57እነርሱም "እስቲ ልጅቷን እንጥራትና እርስዋ የምትለውን እንስማ" አሉ። 58ስለዚህ ርብቃን ጠሩና "ከዚህ ሰው ጋር መሄድ ትፈልጊያለሽ?" ብለው ጠየቅዋት። እርስዋም "አዎ እሄዳለሁ"አለች።59ስለዚህ ርብቃ ሞግዚትዋን አስከትላ፣ ከአብርሃም አገልጋይና ከእርሱ ሰዎች ጋር እንድትሄድ ፈቀዱላት። 60"አንቺ እኅታችን የብዙ ሺ ሕዝብ እናት ሁኚ፤ ዝርያዎችሽም የጠላቶችሽን ከተሞች ይውረሱ" ብለው ርብቃን መረቁአት።61ከዚህ በኋላ ርብቃ ከተከታዮችዋ ጋር ለመሄድ ተነሣች፤ በግመሎቹ ላይ ተቀምጠው ከአብርሃም አገልጋይ ጋር ለመሄድ ተዘጋጁ። በዚህ ዐይነት የአብርሃም አገልጋይ ርብቃን ይዞ ሄደ። 62በዚህ ጊዜ ይስሐቅ "ብኤር ላሐይ ሮኤ ወይም የሚያየኝን ሕያው አምላክ"የተባለው ኩሬ ወዳለበት በረሓ መጥቶ በኔጌብ ተቀምጦ ነበር።63ከለዕታት አንድ ቀን ወደ ማታ ጊዜ እያሰላሰለ በመስክ ውስጥ ሲዘዋወር ሳለ ግመሎች ሲመጡ በሩቅ አየ። 64ርብቃ ይስሐቅ ባየች ጊዜ ከግመሏ ወረደችና፣ 65"ያ በመስክ ውስጥ ወደ እኛ የሚመጣው ሰው ማን ነው?" ስትል የአብርሃምን አገልጋይ ጠየቀችው። አገልጋዩም "እርሱ ጌታዬ ነው!" አላት። ስለዚህ በጥፍነት በሻሽ ፊትዋን ሸፈነች።66አገልጋዩም ያደረገውም ነግር ሁሉ ለይስሐቅ ነገረው። 67ከዚህ በኋላ ይስሐቅ እናቱ ሣራ ትኖርበት ወደነበረው ድንኳን ርብቃን ይዞአት ገባ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ይስሐቅ ርብቃን ወደዳት፤ በእናቱ ሞት ምክንያት ከደረሰበትም ሐዘን በዚህ ሁኔታ ተጽናና።
1አብርሃም ቀጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ፤ 2እርስዋም ዚምራንን፣ ዮቅሻንን፣ መዳንን፣ ምድያምን፣ ዩሽባቅንና ሹሐን ወለደችለት። 3ዮቅሻንም ሳባንና ደዳንን ወለደ፤ የዳደንም ዝርያዎች አሹራውያን፣ ሌጡሻውያንና ሌአማውያን ናቸው። 4የምድያም ልጆች ዔፋ፣ ዔፈር፣ ሐኖክ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚሁ ሁሉ የቁጠራ ዝርያዎች ናቸው።5አብርሃም ያለው ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤ 6ከሌሎች ሴቶች ለተወለዱትም ልጆች ገና በሕይወት ሳለ ስጦታ ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ እነዚህ ሌሎች ልጆች ከይስሐቅ ርቀው ወደ ምሥራቅ አገር እንዲሄዱ አደረጋቸው።7የአብርሃም ዕድሜ በአጠቃላይ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤ 8በዚህም ዐይነት አብርሃም በቂ ዕድሜ አግኝቶ ካረጀ በኋላ ሞተ፤9ልጆቹ ይሰሐቅና እስማኤል ማክጴላ በተባለ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ ከመምሬ በስተምሥራቅ በሒታዊ በጶሐር ልጅ በዔፍሮን እርሻ ውስጥ የሚገኘው ነው። 10እነሱም አብርሃም ከሒታዊያን ላይ የገዛው የመቃብር ቦታ ነው፤ በዚህ ዐይነት አብርሃም ሚስቱ ሣራ በተቀበረችበት ዋሻ ተቀበረ። 11አብርሃም ከሞተ በኋላ ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር ባረከው፤ ይስሐቅ "ብኤርላሐይሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ" ተብሎ በመጠራት ኩሬ አጠገብ ይኖር ነበር።12የሣራ አገልጋይ ግብፃዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን እስማኤል፤13ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፣ ቄዳር፣ አድብኤል፣ ሚብሣም፣ 14ሚሽማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ 15ሐዳድ፣ ቴማ፣ ይጡር፣ ናፊሽና ቄድማ ናቸው። 16እነዚህ የእስማኤል ልጆች ለአሥራ ሁለት ነገዶች ቅድመ አያቶች ነበሩ፤ ስማቸውም በኖሩባቸው ከተሞችና ስፍራዎች ሲጠራ ይኖራል።17እስማኤል መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ሲሆነው ሞተ። 18የእስማኤል ዝርያዎች ከግብፅ በስተምጅራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር። የኖሩበትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዝርያዎች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር።19የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ታሪክ ይህ ነው። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። 20ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሞኖሩ ሶሪያውያን ነበሩ።21ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርስዋ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤ 22የተፀነሱትም መንትያዎች ስለነበሩ እርስ በርሳቸው በማሕፀንዋ ውስጥ ይገፋ ነበር፤ እርስዋም "ይህን ዐይነት በገር ለምን ደረሰብኝ?" በማለት ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ተነሣሣች።23እግዚአብሔርም ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ታናሹ አገልጋይ ይሆናል" አላት።24የመውለጃዋም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ። 25የመጀመሪያው ልጅ መልኩ ቀይ፣ ሰውነቱ ጠጉራም ነበር፤ ስለዚህ ዔሳው ተባለ። 26ሁለተኛው ልጅ ሲወለድ የዔሳውን ተገረዝ ይዞ በመውጣቱ ያዕቆብ ተባለ፤ ልጆቹ በተወለዱ ጊዜ ይስሐቅ ስልሳ ዓመት ሆኖት ነበር።27ሁለቱም ልጆች አደጉ፤ ዔሳው በዱር መዋል የሚወደ ብልኅ አዳኝ ሆነ፤ ያዕቆብ ግን በቤት መዋል የሚወድ ጭምት ሰው ነበር። 28ይስሐቅ ዔሳውን ይወድ ነበር። ምክንያቱም ዔሳው እያደነ ሥጋ ያበላው ነበር።ርብቃ ግን ያዕቆብን ትንን ነበር።29ለዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤ 30ስለዚህም ያዕቆብ "ከዚህ ከቀይ ወጥ ሰጠኝ" አለው። ኤዶም የተባለውም ነዚሁ ምክንያት ነበር።31ያዕቆብም "በመጀመሪያ ብኩርናህን ሽጥልኝ" አለው። 32ዔሳውም "እኔ በረሀብ መሞቴ ነው፤ ታዲያ ብኩርና ምን ያደርግልኛል?" አለው። 33ያዕቆብም "እንግዲያውስ ብኩርናህን እንደምትሸጥልኝ መጀመሪያ ማልልኝ" አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኩርናውን ለያዕቆብ ሸጠ። 34ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኩርናውን በመናቅ አቃለላት።
1በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ረሀብ ሌላ ዳግመኛ ረሀብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማዋን ንጉሥ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤2በዚህም እግዚአብሔር ለይስሐቅ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፣ "ወደ ግብፅ አገር አትሂድ፤ እንድትኖርበትም በምነግርህ በዚህ ምድር ተቀመጥ፤ 3እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ይህም ምድር ለአንተና ለዝርይዎችህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈፅማለሁ፤4ዘርህን አንደ ሰማይ ክዋክብት አበዛዋልለሁ፤ ይህንንም ሁሉ ምድር አወርሳቸዋለሁ፤ ይህንንም ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ። 5አንተን የምባርክበትንም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁት ሕግና ሥርዓት ሁሉ ስለ ጠበወ ነው።6ስለዚህ ይስሐቅ መኖሪያውን በገራር አደረገ፤ 7በዚያ አገር ስሰዎችም ስለ ርብቃ "ምንህናት" ብለው በጠየቁት ጊዜ "እኅቴ ናት" አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቆንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው። 8ይስሐቅ እዚያ አገር ብዙ ጊዜ ከቆያ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት ይስሐቅና ርብቃ እንደባልና ሚስት በመዳራት ሲጫወቱ አየ።9ስለዚህ አቢሜሌክ ይስሐቅን አስጠርቶ "ለካስ ርብቃ ሚስትህ ናት! ታዲያ "እኅቴ ናት' ያልከው ለምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው። እርሱም "ሚስቴ ነች ያልኩ እንደሆን ሰዎች ይገድሉኝል ብዬ አስፈራሁ ነው" ብሎ መለሰ። 10አቢሜሌክ "ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? ከእኛ ሰዎች አንዱ በቀላሉ ሚስትህን ለመድፈር በቻለ ነበር፤" 11ቀጥሎም አቢሜሌክ "ይህን ሰው ወይም ሚስቱን የሚነካ ሰው በሞቱ ይቀጣል"የሚል ማስጠንቀቂያ ለሕዝቡ ሰጠ።12ይስሐቅ በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፤ እግዚአብሔር ስለባረከውም በዚያኑ ዓመት መቶ እጥፍ አመረተ፤ 13ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረበት ዘመን የእርሱ አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን የውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው። 14ብዙ የበግና የከብት መንጋ፤ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት።15ስለዚህ የይስሐቅ አባት አብርሃም በሕይወት በነበረበት ዘመን የእሱን አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን ውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው። 16በዚያን ጊዜ አቢሜሌክ ይስሐቅን "ኅይልህ ከእኛ ይልቅ እየበረታ ስለሄደ፤ አገራችንን ለቀህ ውጣ" አለው። 17በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ያንን ቦታ ለቆ በገራር ሸለቆ ውስጥ ሰፈረ፤ እዚያም ተቀመጠ።18አብርሃም በሕይወት ሳለ አስቆፍሮአቸው የነበሩትን አብርሃም ከሞተ በኋላ ግን ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጉድጓዶች ይስሐቅ እንደገና እንዲቆፍሩ አደረገ፤ አባቱ ባወጣላቸ ስሞችም ጠራቸው።19የይስሐቅ አገልጋዮች በሸለቆው ውስጥ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሩና ጥሩ የምንጭ ውሃ አገኙ፤ 20የገራር እረኞች ግን "ይህ ውሃ የእኛ ነው" በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ተጣሉ።በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ጉድጓዱን "ዔሤቅ" ብሎ ሰየመው።21የይስሐቅ አገልጋዮች ሌላ የውሃ ጉድጓድ ቁፈሩ፤ በዚህኛውም ጉድጓድ ምክንያት ሌላ ጠብ ተነሣ፤ ስለዚህ ይስሐቅ ይህን ጉድጓድ "ስጥና" ብሎ ሰየመው። 22ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተናሳ "እነሆ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል ያንን ቦታ 'ረሖቦት" ብሎ ሰየመው።23ከዚያ በኋላ ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ፤ 24በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና "እኔ የአባትህ አምላክ ነኝ፤እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ! ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ" አለው። 25ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጉድጓድ ቆፈሩ።26አቢሜሌክ ከአማካሪው ከአሑዘትና ከሠራዊቱ ኣዥ ኮፊኮል ጋር ይስሐቅን ለመጎብኘት ከገራር ወት፤ 27ስለዚህ ይስሐቅ "ከዚህ በፊት ጠልታችሁን አገራችሁ እንድወጣ አድርጋችሁኛል፤ ታዲያ አሁን ልትጎበኝ የመጣችሁት ለምንድን ነው?" አላቸው።28እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፣ "እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈፀም አስበናል፤ በዚህም መጀረት ቃል ኮዳን እንድትገባልን የሚንፈለገው፣ 29በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ምክንያቱም እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ አልሠራንም፤ ዘውትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።"30ከዚህ በኋላ፣ ይስሐቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡ። 31በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ።32ከዚያኑ ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቁፈሩት ጉድጓድ ለይስሐቅ ነገሩት፤ "ውሃ አገኘን" ብለውም አበሠሩት። 33እርሱም የውሃን ጉድጓድ "ሳቤህ"ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ "ቤርሳቤህ" እየተባለ ይጠራል።34ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆንው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ። 35ይህም ጋብቻ ይስሐቅንና ርብቃን ሲያዝናቸው ይኖር ነበር።
1ይስሐቅ አርጅቶ ዐይኖቹም ታውረው ነበር፤ ታላቁ ልጁን ዔሳውን፤ "ልጄ ሆይ!" ብሎ ጠራው፤ ልጁም "እነሆ አለሁ" አለ። 2ይስሐቅም እንዲህ አለው፣ "እንደምታየኝ አርጅቻለሁ፤ የምሞትበትንም ቀን አላውቅም፤3ስለዚህ የምታድንበትን ቀስትና ፍላጻ ያዝ፤ ወደ ዱር ሂድና አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤ 4ልክ እንደምወደው አድርገህ ምግብ ሥራልኝ ከበላሁም በኋላ ከመሞቴ በፊት የመጨረሻ ምርቃቴን እሰጥሃለሁ።"5ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው ወደ አደን ከሄደ በኋላ፣ 6ርብቃ ልጅዋን ያዕቆብን "አባትህ ዔሳውን እንዲህ ሲለው ሰማሁ፣ 7አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤ ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሥራልኝ፤ ሳልሞትም በእግዚአብሔር ፊት እነርቅሃለሁ፤8አሁንም ልጄ ሆይ! የምነግርህን አድምጥ፤ የማዝህንም አድርግ፤ 9አባትህ እንደሚወደው አጣፋጩ ጥሩ ምግብ እንድሠራለት፣ ወደ መንጋዎች ሂድና ሁለት የሰቡ የፍየል ጥቦቶች አምጣልኝ፤ 10አንተም ያዘጋጀሁትን ምግብ እንዲበላ ለአባትህ ወስደህ ታቀርብለታለህ፤ በዚህ ዐይነት አባትህ ከመሞቱ በፊት ይመርቅሃል።"11ያዕቆብ ግን እናቱን ርብቃን "የወንድሜ የዔሳው ገላ ጠጉራም ነው፤ የ እኔ ገላ ግን ምንም ጠጉር የሌለው ለስላሳ ነው፤ 12ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝና እንዳታለልኩህ ቢያውቅ በምርቃት ፈንታ እርግማን እንደማተርፍ ታውቂ የለምን?" አላት።13እናቱም "ልጄ ሆይ! የአንተ እርግማን በእኔ ላይ ይሁን፤ አሁንም እንደነገርሁህ አድርግ፤ ሄድህ ጥቦቶቹን አምጣልኝ" አለችው። 14ስለዚህ ሄዶ ጥቦቶቹን አመጣለት እርስዋም ልክ አባቱ እንደሚወደው እድርጋ ጥሩ ወጥ ሠራች፤15የታላቁ ልጅዋን የዔሳውን የክት ልብስ ከተቀመጠበት ቦታ አውጥታ ለያዕቆብ አለበሰችው። 16የፍየሎቹንም ቆዳ በክንዶቹ ላይና ጠጉር በሌለበት በአንገቱ ላይ አለበሰችው። 17ያዘጋጀውንም ጥሩ ወጥ ከጋገረችው እንጀራ ጋር ልልጅዋ ለያዕቆብ ሰጠችው።18ያዕቆብ ወደ አባቱ ሄደና "አባባ!" አለው፤ እርሱም "እነሆ አለሁ! ለመሆኑ አንተ የትኛው ልጄ ነህ!" አለ። 19ያዕቆብም "የበኩር ልጅህ ዔሳው ነኝ፤ እነሆ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ፤ እንድትመርቀኝ እስቲ ቀና በልና ያመጣሁልህን የአደን ሥጋ ተመገብ" አለው።20ይስሐቅም "ልጄ ሆይ! እንዴት ቶሎ ልታገኝ ቻልህ?" አለው። ያዕቆብም "አምላክህ እግዚአብሔር ስለረዳኝ በቶሎ ለማግኘት ቻልሁ" አለው። 21ይስሕቅም "እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በልና ልዳብስህ፤ በእርግጥ አንተ ዔሳው ነህን?" አለው።22ያዕቆብም ወደ አባቱ ተጠጋ፤ አባቱም ዳሰሰውና "ድምፅህ የያዕቆብ ድምፅ ይመስላል፤ ክንድህ ግን የዔሳውን ክንድ ይመስላል" አለው። 23ክንዶቹ እንደ ዔሳው ክንዶች ጠጉራም ስለ ነበሩ ይስሐቅ ያዕቆብን ለይቶ ማውቅ አልቻለም፤ ሊመርቀው ከዝዘጋጀ በኋላ፣24"እርግጥ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?" ሲል እንደገና ጠየቀው፤ እርሱም "አዎ ነን" አለ። 25ይስሐቅም "ልጄ! በል ከአደንከው ሥጋ አቅርብልኝ፤ ከበላሁም በኋላ እመርቅህለሁ" አለው። ያዕቆብም ምግቡን አቀረበለት፤ የወይን ጠጅም እንዲጠጣ አመጣለት።26ከዚህ በኋላ አባቱ ይስሐቅ "ልጄ ሆይ! ቀረብ በልና ሳመኝ" አለው፤ 27ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብ ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፣ "እነሆ የልጄ መልካም ሽታ እግዚአብሔር እንደባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤28እግዚአብሔር ከሰማይ የሚያረሰርሰው ተል ይስጥህ፤ ምድርህን ያለምልምልህ፤ እህልንና የወይን ጠጅህን ያብዛልህ፤29መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችህም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህ የተመረቁ ይሁኑ።"30ይስሐቅ ያዕቆብን መርቆ እንዳበቃና ያዕቆብም አባቱን ፊት እንደወጣ ወዲያውኑ ዔሳው ከአደን ተመልሶ መጣ። 31እርሱም በበኩሉ የጣፈጠ ወጥ ሠርቶ ለአባቱ አቀረበለትና "አባቴ ሆይ እንድትመርቀኝ፣ እስቲ ቀና ብለህ ካመጣሁልህ የአደን ሥጋ ብላ" አለው።32ይስሐቅም 'አንተ ማን ነህ?" አለው፤ እርሱም "እኔ የበኩር ልጅ ዔሳው ነኝ" አለ። 33ይስሐቅም እጅግ ደንግጦ እየተነቀጠቀጠ "ታዲያ አውሬ አድኖ ያመጣልኝ ማን ነበረ? ልክ አንተ ከመምጣትህ በፊት ተመገብሁ የመጨረሻ ምርቃቴንም ሰጠሁት፤ ምርቃቱም ተእርሱ ሆኖ ይኖራል"አለው።34ዔሳው ይህን በሰማ ጊዜ ድምፁን ከፍ በማድረግ ምርር ብሎ እያለቀሰ "አባቴ ሆይ! እኔንም መርቀኝ!" አለ። 35ይስሐቅም "ወንድምህ መጥቶ እኔን በማታለል የአንተን ምርቃት ወስዶብሃል"አለው።36ዔሳውም "እርሱ እኔን ሲያሰናክለኝ ይህ ሁለተኛው ነው፤ ያዕቆብ መባሉ ተገቢ ነው፤ ከዚህ በፊት ብኩርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ፤ ታዲያ ለእኔ ያስቀረከው ምንም ምርቃት የለምን? አለው። 37ይስሐቅም "ቀድሞ ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?" አለው።38ዔሳውም "አባቴ ሆይ! ምርቃትህ እንዲት ብቻ ናትን? እባክህ እኔንም መርቀኝ" እያለ ለማልቀስ አባቱን ነዘነዘው።39ይስሐቅም አንዲህ አለው። "በረከት ከሞላበት ለምለም ምድር ርቀህ ትኖራለህ፤ የሰማይ ጠልም አታገኝም፤ 40በሰይፍም ኅይል ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ፤ በተቃወምከውም ጊዜ ግን ከእርሱ ጭቁና ትላቀቃለህ።"41አባቱ ስለመረቀው ዔሳው ያዕቆብን አጥብቆ ጠላው፤ በልቡም "አባቴ በቅርብ ቀን ይሞታል፤ ከዚህ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ"ብሎ አሰበ። 42ነገር ግን ርብቃ የዔሳውን ዕቅድ ስለ ሰማች፣ ያዕቆብን ጠርታ እንዲህ አለችው፣ "አድምጠኝ፤ ወንድምህ ዔሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ አስቦአል፤43አሁንም ልጄ ሆይ! የምልህን አድርግ፤ ተነሥተህ በካራን ወደሚገኘው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ፤ 44የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እዚያው ቆይ፤ 45ቁጣውም ሲበርድ ያደረግህበትን ነገር ይረሳል፤ ከዚያ በኋላ ሰው ልኬ አስመጣሃለሁ፤ ሁለታችሁም በአንድ ቀን ማጣት አልፈልግም።46ርብቃ ይስሐቅን "ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሖታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱ ከገባ ለመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ"አለችው።
1ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ መረቀው፤ እንዲህም ሲል አዘዘው፣ "ከነዓናዊት ሴት እንድታገባ፤ 2ይልቅስ ተነሥተህ በመስጴጦምያ ወዳለው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጎትህ ከገባ ሴቶች ልጆች አንዷን አግባ፤3ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ብዙ ልጆችም ይስጥህ፤ የብዙ ሕዝቦችም አባት ያድርግህ፤ 4አብርሃምን እንደባረከ አንተንና ዘርህን ይባርክ፤ ይህንንም ለአብርሃም ሰጥቶት የነበረውንና አንተም ደስተኛ ሆነህ የኖርክበት ምድር ርስት አድርጎ ይስጥህ።"5በዚህ ሁኔታ ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ ያዕቆብም በመስጴጦምያ ወደሚያኖረው ወደ ላባ ሄደ፤ ላባ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ነበረ፤ አባቱም ሶርያዊው ባቱኤል6ይስሐቅ ያዕቆብን እንደመረቀና ሚስት እንደሚፈልግ ወደ መስጴጦምያ እንደላከው ዔሳው ተረዳ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ሲመርቀው "ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ" ብሎ ያዘዘው መሆኑንም ሰማ፤ 7ያዕቆብ ለአባቱና ለእናቱ በመታዘዝ ወደ መስጴቶምያ መሄዱንም ተረዳ፤8በዚህም አባቱ ይስሐቅ የከነዓንያውያንን ሴቶች እንደማይወድ ዔሳው ተገነዘበ፤ 9ስለዚህ ከዚህ በፊት ከገባቸው ሌላ በተጨማሪ ወደ አብርሃም ልጅ ወደ እስማኤል ሄዶ ልጁን ማሕላትን አገባ፤ እርስዋም የነባዮት እኅት ናት።10ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤ 11ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ ወደ አንድ ስፍራ መጥቶ ዐፈር፤ በዚያም አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ተኛ፤12በሕልሙም ከመሬት እስከ ሰማይ የሚደርሰው መሰላል አየ፤ በመሰላሉም የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ላይ ይውጡና ወደ ታች ይውረዱ ነበር። 13እግዚአብሔር በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፣ "እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለዝርያዎችህ እንዲሆን ይህን የተገኘበት ምድር እሰጥሃለሁ።14ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ እነርሱ በሁሉ አቅጣጫ ይዞታቸውን ያስፋፋሉ፤ በአንተና በዘርህ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ። 15አይዞህ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚያም ምድር በደህና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈፅምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።"16ያዕቆብም ከእንቅልፉ ነቃና "በእርግጥ እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር"አለ። 17በጣም ፈርቶም ስለነበር "ይህ እንዴት የሚያስፈራ ቦታ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ ወደ ሰማይ የሚያስገባው በር ይህ ነው"አለ።18ያዕቆብ በማግሥቱም ጠዋት በማለዳ ተነሣ፤ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ መታሰቢያ እንዲሆን እንደ ሐውልት አቆመው፤በላዩ ላይም የወይራ ዘይት አፈሰሰበት። 19ይህንንም ስፍራ "ቤትኤል"ብሎ ሰየመው፤ ይህ ስፍራ ከዚያ በኋላ ሎዛ እየተባለ ይጠራ ነበር።20ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ "ከእኔ ጋር ሆነህ በምትሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ፣ የሚያስፈልገኝን ምግብና ልብስ ብትሰጠኝ፣ 21ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብትመልሰኝ፤ አንተ አምላኬ ትሆናለህ፤ 22ይህ ለመታሰቢያነት ያቆምሁት ድንጋይ ወደ ፊት የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሁሉ ከዐሥር አንዱን እጅ ለአንተ እሰጣለሁ።"
1ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በስተ ምሥራቅ ወዳለው አገር ደረሰ፤ 2እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጉድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጉድጓድ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጉድጓድ ነበር፤ ጉድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤ 3መንጋዎቹ ሁሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ ድንጋዩን አንከባለው ከጉድጓዱ ውሃ ያጠቱአቸው ነበር፤ መንጋዎቻቸውን ካጠጡ በኋላ ግን ድንጋዩንም መልሰው በጉድጓዱ አፍ ላይ ይከዱኑታል።4ያዕቆብም እረኞቹን "ወዳጆቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "እኛ የመጣነው ከካራን ነው" አሉት። 5እርሱም "የናኮርን የልጅ ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "አዎ እናውቀዋለን" አሉት። 6እርሱም "ለመሆኑ እርሱ ደኅና ነውን?" አላቸው። እነርሱም "አዎ፣ ደኅና ነው፤ እንዲያውም ልጁ ራሔል ያችውልህ! በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ነች" አሉት።7ያዕቆብም "ጊዜው ገና ቀን ነው፤ መንጋዎቻቸውንም ወደ ቤት የምታስገቡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ታዲያ ለምን ውሃ አጠጥታችሁ አታሰማሩአቸውም? ፤ አለ። 8እነርሱም "እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን" አሉት።9ያዕቆብም ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ወደዚያ መጣች፤ ምክንያቱም እርስዋ የበጎች እረኛ ነበረች። 10ያዕቆብ ያጉቱን የላባን በጎች እየነዳች ስትመጣ ራሔልን አይቶ ወደ ጉድጓድ ሄደ፤ ጉድጓዱ የተከደነበትንም ድንጋይ አንከባሎ በጎቹን አጠጣቸው።11ከዚያ በኋላ ራሔልን ሳማት። ከደስታውም ብዛት የተነሣ አለቀሰ፤ 12"እኔ የአባትሽ እኅት የሆነችው የርብቃ ልጅ ሄደች።13ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ አቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤ 14ላባም "በእርግጥ አንተ ቅርብ የሥጋ ዘመዴ ነህ" አለው፤ ያዕቆብም አንድ ወር ያህል ከአጎቱ ጋር ተቀመጠ።15ላባ ያዕቆብን "ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነፃ ልታገለግለኝ አይገባህም፤ ስለዚህ ምን ያህል ደመወዝ ላስብልህ? አለው። 16ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ታላቂቱ ልያ፤ ታናሽቱ ራሔል ይባሉ ነበር። 17ልያ ዐይነ ልም ስትሆን፣ ራሔል ግን ቁመናዋ የሚያምር የደስ ደስ ያላት ነበረች። 18ያዕቆብ ራሔልን እጅግ ስለወደዳት "ራሔልን ብትድርልኝ ሰባት ዓመት አገለግልሃለሁ" አለ።19ላባም "ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ እሺ ተስማምቼአለሁ፤ እዚሁ ከእኔ ጋር ኑር" አለው። 20ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለነበር የቆየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።21ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ላባን "እነሆ የአገልግሎት ዘመኔ ተፈፅሞአል፤ ሚስት እንድትሆነኝ ልጅህን ስጠኝ" አለው። 22ላባም የሠርግ ድግስ አዘጋጅቶ በአቅራቢያው የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ጠራ።23ነገር ግን ላባ በራሔል ምትክ ልያን ለያዕቆብ ሰጠው፤ ያዕቆብም ከልያ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ። 24ላባ ሴት አገልጋዩን ዚልፋን አገልጋያዋን እንድትሆን ለልጁ ለልያ ሰጣት። 25በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ልያ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ ወደ ላባ ሄዶ "ይህ ያደረግህብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልሁህ ራሔልን ለማግኘት አልነበረም? ታዲያ ለምን አታለልከኝ"አለው።26ላባም "ታላቂቱ ሳትዳር፤ ታናሺቱን መዳር የአገራችን ልማድ አይደለም፤ 27የልያ ሠርግ ሰባት ቀን እስኪሞላው ድረስ ጠብቅ፤ ከእንግዲህ ወዲይ ሰባት ዓመት የምታገለግለኝ ከሆነ ራሔልን እሰጥሃለሁ" አለው።28ያዕቆብም ነገሩ ተስማማ፤ ከልያ ጋር ሰባት ቀን ተሞሽሮ ከቆየ በኋላ፤ ላባ ልጁን ራሔልን ለያዕቆብ ሳረለት። 29ላባ ሴት አገልጋዩን ባላን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለራሔል ሰጣት። 30ያዕቆብ ከራሔልም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ከልያም አብልጦ ወደዳት፤ ከዚያ በኋላ ላባን ሰባት ዓመት አገለገለው።31ልያ የራሔልን ያህል እንዳልተወደደች እግዚአብሔር ባየ ጊዜ መውለድ እንድትችል ማሕፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መኻን ሆነች፤ 32ልያ ርርግዛ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እግዚአብሔር መከራዬን ተመለከተ፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ባሌ ይወደኛል" ስትል ስሙን ሮቤል አለችው።33እንደገና አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወደች፤ "እግዚአብሔር እንዳልተወደድሁ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ' ስትል ስሙን ስምዖን አለችው። 34እንደገና 'አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል" ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤35እንደገና አረገዘችና ውንድ ልጅ ወለደች፤ "አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ" ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች።
1ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ እንዳልወለደችለት ባየች ጊዜ በእኅቷ ቀናች። ያዕቆብንም፣ “ልጅ ስጠኝ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው። 2ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፤ “እኔ የሆድሽን ፍሬ በነሳሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን?” አላት።3እርሷም፣ “እነሆ፣ አገልጋዬ ባላ አለችልህ፣ ልጆች እንድትወልድልኝና እኔም ደግሞ በእርሷ አማካይነት ልጆች እንዳገኝ ከእርሷ ጋር ተኛ” አለችው። 4ስለዚህ ባላን እንደሚስት አድርጋ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ከእርሷ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነት አደረገ።5ባላም አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደችለት። 6ራሔልም፦ “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፣ ልመናዬንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጥቶኛል” አለች። ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው።7የራሔል አገልጋይ ባላ ዳግመኛ አረገዘችና ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደች። 8ከእኅቴ ጋር ብርቱ ትግል ታግዬ አሸነፍኋት” አለች። ስለዚህ ስሙን ንፍታሌም ብላ ጠራችው።9ልያም ልጅ መውለድ ማቆሟን እንደተረዳች፣ አገልጋይዋን ዘለፋን ሚስት እንድትሆነው ለያዕቆብ ሰጠችው። 10የልያ አገልጋይ ዘለፋም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት፣ 11ልያም፣ “እንዴት የታደልሁ ነኝ!” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው።12የልያም አገልጋይ ዘለፋ ለያዕቆብ ሁለተኛ ልጅ ወለደችለት፤ 13ልያም፣ “እጅግ ደስ ብሎኛል፣ ከእንግዲህ ወዲያ ሴቶች ‘ደስተኛዋ’ ይሉኛል አለች፤ ስሙንም ‘አሴር’ ብላ ጠራችው።14በስንዴ መከር ወራት ሮቤል ወደ ዱር ሄዶ እንኮይ አገኘ፤ ለእናቱ ለልያም አመጣላት፤ ራሔልም ልያን፣ “እባክሽን ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት። 15ልያም፦ “ባሌን የቀማሽኝ አነሰና የልጄን እንኮይ ደግሞ ልትወስጂ አማረሽ?” አለቻት። ራሔልም፣ “ስለልጅሽ እንኮይ ዛሬ ያዕቆብ ከአንቺ ጋር ይደር” አለቻት።16በዚያ ምሽት ያዕቆብ ከእርሻ ሲመለስ፣ ልያ ወጥታ ተቀበለችውና፣ “በልጄ እንኮይ ስለተከራየሁህ የዛሬው አዳርህ ከእኔ ጋር ነው” አለችው። ያዕቆብም በዚያች ሌሊት ከእርሷ ጋር አደረ። 17እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፣ ስለዚህ አረገዘችና ለያዕቆብ አምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት። 18ልያም፦ “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ደመወዜን ከፈለኝ” አለች። ስሙንም ይሳኮር አለችው።19ልያ አሁንም ደግማ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች። 20እርሷም፣ “እግዚአብሔር በከበረ ስጦታ አድሎኛል፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለወለድሁለት ከእንግዲህ ባሌ አክብሮ ይይዘኛል” አለች፤ ስሙንም ዛብሎን አለችው። 21ከዚያም በኋላ ሴት ልጅ ወለደች ስምዋንም ዲና አለቻት።22እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፤ ጸሎትዋንም ሰምቶ ልጅ እንድትወልድ አደረጋት፤ 23አርግዛም ወንድ ልጅ ወለደችና፣ “እግዚአብሔር ዕፍረቴን አስወገደልኝ” አለች፤ 24ደግሞም ሌላ ወንድ ልጅ ይጨምርልኝ ስትል ስሙን ዮሴፍ ብላ ጠራችው።25ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ተወለድሁበት አገር እንድመለስ አሰናብተኝ፤ 26አንተን በማገልገል ያገኘኋቸውን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያህል አገልግሎት እንዳበረከትኩልህ ታውቃለህ።”27ላባም፣ “በአንተ ምክንያት እግዚአብሔር እንደባረከኝ በንግርት መረዳቴን ልነግርህ እወዳለሁ፤ 28የምትፈልገውን ደመወዝ ንገረኝና እከፍልሃለሁ” አለው።29ያዕቆብም እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልሁህና የከብትህም መንጋ በእኔ ጠባቂነት እንዴት እንደረባልህ አንተ ታውቃለህ፤ 30እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ በተሰማራሁበት ሁሉ እግዚአብሔር በረከቱን አብዝቶልሃል። ታዲያ፣ ለራሴ ቤት የሚያስፈልገኝን የማቀርበው መቼ ነው?”31ላባም፣ “ታዲያ ምን ያህል ልክፈልህ?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ የምልህን አንድ ነገር ብቻ ብታደርግልኝ መንጋህን ማሰማራቴንና መጠበቄን እቀጥላልሁ፤ 32ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጉርጉርና ነቁጣ ጥቁርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቁጣና ዝንጉርጉር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤33ወደፊት ደመወዜን ለመቆጣጠር በምትመጣበት ጊዜ ታማኝነቴ ይታወቃል፤ ደመወዜን ለመቆጣጠር ስትመጣ ዝንጉርጉር ያልሆነ ወይም ነቁጣ የሌለበት ፍየል ብታገኝ፣ እንዲሁም ጥቁር ያልሆነ በግ ብታገኝ የተሰረቀ መሆኑን መረዳት ትችላልህ” አለው። 34ላባም፣ “እሺ አንተ ባልከው እስማማለሁ” አለ።35ነገር ግን በዚያኑ ዕለት ከተባት ፍየሎች ሽመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቁጣ ያለባቸውን ሁሉ እንዲሁም ከእንስት ፍየሎች ነቁጣ ያለባቸውን ዝንጉርጉር የሆኑትን ሁሉ መረጠ፤ ደግሞም ጥቋቁር የሆኑትንም በጎች ሁሉ ለየና ወንዶች ልጆቹን አስጠበቃቸው። 36ከዚህ በኋላ ላባ መንጋውን ነድቶ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ከያዕቆብ ርቆ ሄደ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጋዎች መጠበቁን ቀጠለ።37ያዕቆብም ልብን፣ ለውዝና ኤርሞን ከሚባሉ ዛፎች እርጥብ በትሮችን ወሰደ፤ በበትሮቹ ያለው ነጭ እንዲታይ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው፤ 38መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ ከፊት ለፊት እንዲያዩአቸው የተላጡትን በትሮች በውሃ ማጠጫዎቹ ውስጥ አደረጋቸው። መንጎቹም ስሜታቸው ሲነሣሣና ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ፣39በትሮቹን ፊት ለፊት እያዩ ይሳረሩ ነበር፤ ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ የጣለባቸውንም ግልገሎች ወለዱ። 40ያዕቆብ እነዚህን ግልገሎች ለብቻ ለየ፤ የቀሩትን ግን ዝንጉርጉርና ጥቁር በሆኑት በላባ መጋዎች ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በዚህ ዓይነት የራሱን መንጋ ከላባ መንጋ ጋር ሳይቀላቅል ለብቻ አቆማቸው።41ያዕቆብም ብርቱ እንስቶች አውራ ፈልገው በሚቅበጠበጡበት ጊዜ በትሮቹ አቅራቢያ እንዲጠቁ በትሮቹን በውሃ ገንዳዎች ውስጥ ፊት ለፊታቸው ያስቀምጥ ነበር፤ 42ደካማ በሆኑት እንስቶች ፊት ግን በትሮቹን አያስቀምጥም ነበር፤ ስለዚህ ደካሞቹ ለላባ ሲሆኑ፣ ብርቱዎቹ ለያዕቆብ ሆኑ።43በዚህም ሁኔታ ያዕቆብ እጅግ ባለጸጋ ሆነ፤ ብዙ መንጋዎች፤ ሴቶችና ወንዶች አገልጋዮች፣ ብዙ ግመሎችና አህዮችም ነበሩት።
1የላባ ወንዶች ልጆች፣ “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት እንዳለ ወስዶታል፤ ይህ ሁሉ እርሱ ያከማቸውም ሀብት ከአባታችን የተገኘ ነው” እያሉ ሲያወሩ ያዕቆብ ሰማ። 2በላባም ዘንድ እንደቀድሞ ተወዳጅ አለመሆኑን ተረዳ። 3እግዚአብሔርም ያዕቆብን፣ “ወደ አባቶችህ ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው።4ስለዚህ ያዕቆብ መንጋዎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤ 5እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ ስለ እኔ ያለው አመለካከት እንደ ቀድሞ አለመሆኑን ተረድቻለሁ፤ ቢሆንም የአባቴ አምላክ አልተለየኝም፤ 6መቼም ባለኝ አቅም አባታችሁን ማገልገሌን እናንተ ታውቃላችሁ።7አባታችሁ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ እየለዋወጠ አታልሎኛል፣ ሆኖም እንዲጎዳኝ እግዚአብሔር አልፈቀደለትም። 8እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጉርጉሮቹ ይሆናሉ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጉርጉር ወለዱ’፤ ደግሞም፣ ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤ 9ስለዚህ እግዚአብሔር የአባታችሁን ከብቶች ወስዶ ለእኔ ሰጠኝ።10እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ መሆናቸውን በሕልም አየሁ። 11በዚያው ሕልም የእግዚአብሔር መልአክ፦ ‘ያዕቆብ’ ብሎ ጠራኝ፣ እኔም ‘እነሆ አለሁ’ አልሁ።12እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘መንጋዎቹን የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸው መሆናቸውን ተመልከት፣ ላባ የፈጸመብህን በደል አይቻለሁ። 13የድንጋይ ሐውልት በማቆም ዘይት ቀብተህ የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ይህን አገር ፈጥነህ ልቀቅ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመልሰህ ሂድ’ አለኝ።”14ራሔልና ልያም እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “ከአባታችን የምንወርሰው ድርሻ አለን? 15እርሱ እኛን የሚያየን እንደ ባዕዳን አይደለምን? ደግሞም እኮ እኛን ሽጦናል፣ የተሸጥንበትንም ዋጋ ራሱ በልቶታል። 16እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የነገረህን ሁሉ አድርግ።”17ከዚያም ያዕቆብ ተነሥቶ ልጆቹንና ሚስቶቹን በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ 18በመስጴጦምያ ካፈራው ሀብት ሁሉ ጋር ከብቶቹን በሙሉ ወደፊት አስቀደመ፣ ወደ አባቱም ወደ ይስሐቅ አገር፣ ወደ ከነዓን ምድር ጉዞውን ቀጠለ።19ላባ በጎቹን ሊሸልት ሄዶ ስለነበር፣ እርሱ በሌለበት ራሔል ከቤት የነበሩትን የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ ሄደች። 20ያዕቆብ መሄዱን ለላባ ሳይገልጥለት አታሎት ሄደ፣ 21የራሱ የሆነውን ሀብት ይዞ በፍጥነት ታጓዘ፤ የኤፍራጥስንም ወንዝ ተሻግሮ ወደ ኮረብታማው አገር ወደ ገለዓድ ሄደ።22ያዕቆብ መኮብለሉን ለላባ በሦስተኛው ቀን ተነገረው። 23ከዘመዶቹ ጋር ሆኖ ያዕቆብን ተከታተለው፤ ሰባት ቀን ከተጓዙ በኋላ ገለዓድ በተባለው ተራራማ አገር ላይ ሊደርስበት ተቃረበ።24በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ለላባ በሕልም ተገለጠለትና “ያዕቆብን ክፉም ሆን ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ” አለው። 25ያዕቆብ ገለዓድ በተባለው ኮረብታማ ስፍራ ድንኳኑን በመትከትል ሰፍሮ ሳለ ላባ ደረሰበት፤ ላባና ዘመዶቹም እዚያው ድንኳናቸውን ተክለው ሰፈሩ።26ከዚህ በኋላ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ስለምን እንዲህ አድርገህ አታለልኸኝ፤ ሴቶች ልጆቼንስ በጦርነት እንደተማረኩ ያህል ይዘሃቸው ለምን ሄድህ? 27ሳትነግረኝ ተሰውረህ በመሄድ ለምን አታለልኽኝ? ነግረኸኝ ቢሆን በከበሮና በመስንቆ እየተዘፈነ በደስታ በሸኘሁህ ነበር። 28ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን በመሳም እንድሰናበታቸው ባለማድረግህ የሞኝነት ተግባር ፈጽመሃል።29ጉዳት ሳደርስብህ እችል ነበር፣ ነገር ግን ባለፈው ሌሊት የአባትህ አምላክ፣ ‘ያዕቆብን ክፉም ሆነ ደግ አንድ ቃል እንዳትናገረው’ ብሎ አስጠነቀቀኝ፣ 30ወደ ትውልድ አገርህ ለመመለስ ባለህ ብርቱ ፍላጎት እንደተለየኸኝ አውቃለሁ፣ ታዲያ የቤቴን ጣዖቶች የሰረቅኽብኝ ለምንድነው?”31ለላባ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ሴቶች ልጆችህን በኃይል ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ ብዬ ስለ ፈራሁ ነው በድብቅ የሄድኩት። 32ነገር ግን ከእኛ መካከል የአንተን የጣዖት ምስል የሰረቀ ሰው ካለ ይሙት። የአንተ የሆነ አንዳች ነገር ከኔ ዘንድ ቢገኝ፣ አንተው ራስህ ዘመዶቻችን ባሉበት ፈልግና ውሰድ።” እንደዚህ ሲል ራሔል የጣዖታቱን ምስል መስረቋን ያዕቆብ አያውቅም ነበር።33ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን እንዲሁም ወደ ሁለቱ ደንገጡሮቹ ድንኳን ገባ፤ ነገር ግን ምንም አላገኘም። ከልያ ድንኳን ከወጣ በኋላ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ።34ራሔል ግን ጣዖቱቹን ወስዳ በግመሉ ኮርቻ ሥር በመሰወር በላያቸው ተቀምጣባቸው ነበር። ላባ በድንኳኑ ውስጥ ያለውን ጓዝ ሁሉ በርብሮ ምንም ነገር አላገኘም። 35ራሔልም አባቷን፦ “በፊትህ ተነሥቼ መቆም ስላልቻልሁ፣ ጌታዬ አትቆጣ የወር አበባዬ መጥቶ ነው” አለችው፤ ስለዚህ በረበረ፤ የጣዖቱን ምስል ግን ማግኘት አልቻለም።36በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ተቆጣ፤ ላባንም እንዲህ ሲል ወቀሰው፦ “እስቲ ወንጀሌ ምንድን ነው? ይህን ያህል የምታሳድደኝ ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው? 37ዕቃዬን አንድ በአንድ በርብረሃል፤ ታዲያ የአንተ ሆኖ ያገኘኸው ዕቃ የትኛው ነው? ካለ፣ እስቲ በአንተም በእኔም ዘመዶች ፊት አቅርብና እነርሱ ያፋርዱን።38ሃያ ዓመት አብሬህ ኖሬአለሁ፤ በጎችህና ፍየሎችህ አልጨነገፉም፤ ከመንጋህም አንድ ጠቦት እንኳ አልበላሁም። 39አውሬ የሰበረውንም ቢሆን እተካ ነበር፣ በቀንም ሆነ በሌሊት የተሰረቁትን ሁሉ ስታስከፍለኝ ኖረሃል። 40ብዙ ጊዜ በቀን ሐሩርና በሌሊት ቁር እሠቃይ ነበር፤ በቂ እንቅልፍ ያገኘሁበት ጊዜ አልነበረም።41ሃያ ዓመት በቤትህ የኖርሁት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ዐሥራ አራት ዓመት ለሁለቱ ልጆችህ ብዬ አገለገልሁ፤ ስድስት ዓመት ስለመንጋዎችህ ስል አገለገልሁ፤ ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋውጠኽብኛል። 42የአባቴ አምላክና እርሱም የሚፈራው የአብርሃም አምላክ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን ሰድደኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መከራዬን ዐይቶ፣ ልፋቴን ትመልክቶ ትናንት ሌሊት ገሠጸህ።”43ላባም ለያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እነዚህ ሴቶች የእኔው ልጆች ናቸው፤ ልጆቻቸውም የእኔ ናቸው፤ እነዚህም መንጋዎች የእኔ ናቸው፤ ይህ የምታየው ሁሉ የራሴ ነው፤ ታዲያ በእነዚህ ሴቶች ልጆቼና በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ዛሬ ምን ማድረግ እችላለሁ? 44በል አሁን ቃል ኪዳን እንጋባ፤ ኪዳኑም በአንተና በእኔ መካከል ምስክር ይሁን።”45ያዕቆብም ድንጋይ ውስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፤ 46ከዚያም ዘመዶቹን “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው። እነርሱም ድንጋይ እያመጡ ከመሩ፤ በክምሩም አጠገብ ምግብ በሉ። 47ላባም ክምር ድንጋዩን ይጋርሠሀዱታ ብሎ ጠራው፤ ያዕቆብ ደግሞ ገለዓድ አለው።48ላባም “ይህ ክምር ድንጋይ በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለው። ገለዓድ ተብሎ የተጠራውም በዚሁ ምክንያት ነው፤ 49ደግሞም ምጽጳ ተባለ ምክንያቱም ላባ እንዲህ ብሎአልና፤ “እንግዲህ ከዚህ በምንለያይበት ጊዜ እግዚአብሔር እኔንና አንተን ይጠብቀን፤ 50ልጆቼን ብትበድላቸው ወይም ሌሎችን በላያቸው ብታገባ፣ ማንም ከእኛ ጋር ባይኖርም እንኳ እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ምስክር መሆኑን አትርሳ።”51ላባም ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ክምር ድንጋዩ እነሆ፤ በአንተና በእኔ መካካል ያቆምሁትም ሐውልት እነሆ፤ 52ይህን ክምር ድንጋይ አልፌ አንተን ለማጥቃት ላልመጣ፣ አንተም ይህን ክምር ድንጋይና ይህን ሐውልት አልፈህ እኔን ለማጥቃት ላትመጣ፤ ይህ ክምር ድንጋይ ምስክር ነው፤ ይህም ሐውልት ምስክር ነው። 53የአብርሃም አምላክ፣ የናኮር አምላክ፣ የአባታቸውም አምላክ በመካከላችን ይፍረድ።” ስለዚህ ያዕቆብ አባቱ ይስሐቅ በሚፈራው በእግዚአብሔር ማለ።54ያዕቆብ በኮረብታማው አገር ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው፤ እነርሱም ከበሉ በኋላ እዚያው አደሩ። 55በማግስቱም ማለዳ ላባ የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆችን ስሞ መረቃቸው፤ ከዚያም ወደ አገሩ ተመለሰ።
1ያዕቆብ በጉዞ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መላእክት በመንገድ ተገናኙት። 2ባያቸውም ጊዜ፤ “ይህ የእግዚአብሔር ሰፈር ነው” አለ፤ የዚያንም ቦት ስም መሃናይም አለው።3ያዕቆብም በኤዶም አገር ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤ 4እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፤ “ጌታዬን ዔሳውን እንዲህ ትሉታላችሁ፤ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ብሎአል በሉት፤ ከላባ ዘንድ ተቀምጬ እስካሁን ድረስ እዚያው ኖርሁ፤ 5ከብቶች፣ አህዮች፣ የበግና የፍየል መንጎች እንደዚሁም የወንድን የሴት አገልጋዮች አሉኝ፤ አሁንም ይህን መልእክት ለጌታዬ መላኬ በአንተ ዘንድ ሞግስ አገኛለሁ በሚል ተስፋ ነው።’”6የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንት ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት። 7በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እጅግ በመፍራት ተጨነቀ፤ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች በሁለት ክፍል መደባቸው፤ እንዲሁም በጎቹን፣ ፍየሎቹን፣ ከብቶቹንና ግመሎቹን በሁለት በሁለት መደባቸው። 8ይህንንም ያደረገው፦ “ዔሳው የመጀመሪያውን ክፍል ቢያጠቃ፣ ሌላው ክፍል ሊያመልጥ ይችላል” ብሎ በማሰብ ነው።9ያዕቆብ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ፣ የአባቴ የይስሐቅ አምላክ ሆይ፣ ‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመልስ፣ እኔም በጎ ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፣ 10እኔ ባሪይህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በስተቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሠራዊት ሆኛለሁ።11ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁኝ፤ 12ነገር ግን አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።”13በዚያችም ሌሊት ያዕቆብ እዚያው አደረ፤ ካለው ሀብት ለወንድሙ ለኤሳው እጅ መንሻ እንዲሆኑ እነዚህን መረጠ፦ 14ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችና ሃያ አውራ ፍየሎች፣ ሁለት መቶ እንስት በጎችና ሃያ አውራ በጎች፣ 15ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፣ አርባ ላሞችና ዐሥር ኮርማዎች፣ ሃያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባት አህዮች። 16እነዚህንም በየመንጋው ለይቶ፣ የሚነዱአቸውን ጠባቂዎች መደበላቸው፤ ጠባቂዎችንም እናንተ ቀድማችሁ ሂዱ፣ መንጋዎቹንም አራርቃችሁ ንዱአቸው” አላቸው።17ቀድሞ የሚሄደውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፤ ዔሳው አግኝቶህ ‘የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ 18‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ከበስተኋላችን እየመጣ ነው’ ብለህ ንገረው19እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎቹን የሚነዱትን ሌሎቹንም ሁሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ ‘ዔሳውን ስታገኙት ይህንኑ ትነግሩታላችሁ፤ 20በተጨማሪም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ በሉት። ይህንንም ያዘዘው፣ ‘ዔሳው ከእኔ ጋር ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል’ ብሎ ስላሰበ ነበር። 21ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከእርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩ ቦታ አደረ።22በዚያኑ ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ ሁለቱን ሚስቶቹን፣ ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና ዐሥራ አንዱን ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ። 23ወንዙን አሻግሮ ከሸኛቸው በኋላ፣ ጓዙን ሁሉ ሰደደ።24ያዕቆብም ብቻውን እዚያ ቀረ፤ አንድ ሰውም እስኪነጋ ድረስ ሲታገለው አደረ። 25ያም ሰው ያዕቆብን ታግሎ ማሸነፍ እንዳቃተው በተረዳ ጊዜ፣ የጭኑን ሹልዳ መታው፣ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤ 26በዚያን ጊዜ ሰውዬው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለሆን ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው።27ሰውዬውም፣ “ስምህ ማን ነው?” አለው። እርሱም፣ “ያዕቆብ ነው” አለ። 28ሰውዬውም፣ “ከእግዚአብሔርም ከሰዎችም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና ከእንግዲህ ስምህ እስራኤል እንጂ ያዕቆብ አይባልም” አለው።29ያዕቆብም፣ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። ሰውዬውም፣ “ስሜን ለማወቅ ለምን ፈለግህ?” አለው፤ በዚያም ስፍራ ባረከው። 30ስለዚህ ያዕቆብ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ዐይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል አለው።31ጵኒኤልንም እንዳለፈ ፀሐይ ወጣችበት፣ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። 32ከዚህም የተነሣ የእስራኤል ልጆች ሹልዳን ከጭኑ ጋር የሚያገናኘውን ሥጋ አይበሉም፤ ምክንያቱም ያዕቆብ ከሰውዬው ጋር ሲታገል ሰውዬው ሹልዳውን መትቶት ስለነበር ነው።
1ያዕቆብ አሻግሮ ተመለከተ፤ እነሆ፣ ዔሳው አራት መቶ ሰዎች አስከትሎ እየመጣ ነበር። ስለዚህ ያዕቆብ ልጆቹን ለልያ ለራሔልና ለሁለቱ አገልጋዮቹ አከፋፈላቸው። 2ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ። 3እርሱ ራሱም ቀድሞአቸው ሄደ፤ ወንድሙም ዘንድ እስኪደርስ ድረስ ሰባት ጊዜ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።4ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጦ ሄዶ አቀፈው፤ በአንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። 5ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን ዐየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ አብረውህ ያሉ እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው።6በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሴት አገልጋዮችና ልጆቻቸው ቀርበው እጅ ነሡ፤ 7ከዚያም ልያና ልጆቿ መጥተው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል መጡ፤ እነርሱም ቀርበው እጅ ነሡ። 8ዔሳውም፣ “ወደ እኔ ተነድቶ የመጣው ይህ ሁሉ መንጋ ምንድነው?” አለው። ያዕቆብም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ በአንተ ዘንድ ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው።9ዔሳው ግን፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እኔ በቂ አለኝ፤ የራስህን ለራስህ አድርገው” አለው። 10ያዕቆብም፣ “የለም፣ እንዲህ አይደለም፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፣ እጅ መንሻዬን ተቀበል፤ በመልካም ሁኔታ ተቀብለኸኝ ፊትህን ማየት መቻሌ ራሱ፣ የእግዚአብሔርን ፊት የማየት ያህል እቆጥረዋለሁ። 11እግዚአብሔር በቸርነቱ አሟልቶ ስለ ሰጠኝ የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝና ያቀረብሁልህን እጅ መንሻ እባክህ ተቀበለኝ” አለው። ያዕቆብ አጥብቆ ስለለመነው፣ ዔሳው እጅ መንሻውን ተቀበለ።12ዔሳውም፣ “እንግዲህ እንሂድ፤ እኔም ከአንተ ቀድሜ እሄዳለሁ” አለው። 13ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ እንደምታየው ልጆቹ ይህን ያህል የጠኑ አይደሉም፣ ለሚያጠቡት በጎችና ጥገቶች እንክብካቤ ማድረግ አለብኝ፤ እንስሳቱ ለአንዲት ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ በሙሉ ያልቃሉ። 14ስለዚህ ጌታዬ፣ አንተ ቀድመኸኝ ሂድ፤ እኔም በምነዳቸው እንስሳትና በልጆቹ ጉዞ አቅም ልክ እያዘገምሁ ሴይር ላይ እንገናኛለን”15ዔሳው፣ “እንግዲያስ ከሰዎቼ ጥቂቶቹን ልተውልህ” አለው። ያዕቆብ ግን፣ “ለምን ብለህ? በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘቴ ይበቃኛል” አለው። 16ስለዚህ ዔሳው በዚሁ ዕለት ወደ ሴይር ለመመለስ ተነሣ። 17ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ።18ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም በሰላም ደረሰ፤ በከተማይቱም ፊት ለፊት ሰፈረ። 19ድንኳኑን የተከለበትንም ቦታ የሴኬም አባት ከነበረው ከኤሞር በመቶ ጥሬ ብር ገዛው፤ 20በዚያም መሠዊያ አቁሞ፤ ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው።
1ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ሴት ልጅ ዲና፤ አንድ ቀን የዚያን አገር ሴቶች ለማየት ወጣች። 2የአገሩ ገዥ የኤዊያዊ የኤሞር ልጅ ሴኬም ባያት ጊዜ ያዛት በማስገደድም ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ። 3ልቡ በያዕቆብ ልጅ በዲና ተማረከ፤ ልጅቷንም በጣም ወደዳት፤ በጣፈጠም አንደበት አናገራት።4ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፣ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው። 5ያዕቆብ የልጁን የዲናን ክብረ-ንጽሕና ሴኬም እንደደፈረ ሰማ፤ ነገር ግን ወንዶች ልጆቹ የከብት መንጋ ይዘው ተሰማርተው ስለነበር፣ እነርሱ እስኪመጡ ዝም ብሎ ቆየ፤6ከዚያም የሴኬም አባት ኤሞር፣ ያዕቆብን ሊያነጋግረው ወጣ። 7የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም የተፈጸመውን ድርጊት እንደሰሙ ወዲያውኑ ከመስክ መጡ፤ ሴኬም መደረግ የማይገባውን አስነዋሪ ነገር በእስራኤል ላይ በመፈጸም የያዕቆብን ልጅ ስለደፈረ አዘኑ እጅግም ተቆጡ።8ኤሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን በጣም ወዶአታል፤ ስለዚህ እንዲያገባት ፍቀዱለት፤ 9በጋብቻ እንተሳሰር፣ ሴት ልጃችህን ስጡን፣ የእኛንም ሴቶች አግቡ። 10አብራችሁንም መኖት ትችላላችሁ፤ አገራችን አገራችሁ ናት፣ ኑሩባት፤ ነግዱባት፣ ሀብት ንብረትም አፍሩባት።11ሴኬም ደግሞ የዲናን አባትን ወንድሞች እንዲህ አላቸው። “በእናንተ ዘንድ ሞገስ ላግኝ እንጂ የተጠየቅሁትን ሁሉ እሰጣለሁ፤ 12ለሙሽራዋም ጥሎሽ የፈለጋችሁትን ያህል ጠይቁኝ፤ እርሷን እንዳገባ ፍቀዱልኝ እንጂ፣ የፈለጋችሁትን ሁሉ ለመጠት ዝግጁ ነኝ።” 13ሴኬም እኅታቸውን ዲናን አስነውሮ ስለነበር የያዕቆብ ልጆች ለእርሱና ለአባቱ በተንኮል እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፣14እንዲህ አሉአቸው፤ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ብንሰጥ ውርደት ስለሚሆንብን፣ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም። 15ሆኖም የምንስማማበት አንድ መንገድ ብቻ አለ፤ ይኸውም አንተና በእናንተ ዘንድ ያሉት ወንዶች ሁሉ እንደኛ የተገረዛችሁ እንደሆነ ነው። 16እንዲህ ከሆነ እናንተ የእኛን ሴቶች ልጆች ታገባላችሁ፣ እኛም የእናንተን ሴቶች ልጆች እናገባለን፣ አንድ ሕዝብ ሆነንም አብረን እንኖራለን። 17ዐሳባችንን ባትቀበሉና ባትገረዙ ግን እኅታችንን ይዘን እንሄዳለን።18ያቀረቡትም ዐሳብ ለኤሞርና ለልጁ ለሴኬም መልካም መስሎ ታያቸው። 19ከአባቱ ቤተሰብ ሁሉ እጅግ የተከበረው ይህ ወጣት የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወዶአት ስለነበር፣ ያሉትን ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም።20ስለዚህ ኤሞርና ልጁ ሴኬም ይህንኑ ለወገኖቻቸው ለመንገር ወደ ከተማቸው በር ሄዱ፤ 21እንዲህም አሏቸው፤ “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር የሚኖሩት በሰላም ነው፣ በምድሪቱ ላይ አብረው ይቀመጡ፣ ተዘዋውረውም እንዲነግዱ እንፍቀድላቸው፤ ምድሪቱ እንደሆን ለእኛም ለእነርሱም ትበቃለች። ሴቶች ልጆቻቸውን እናገባለን፤ እነርሱም የእኛን ሴቶች ልጆች ያገባሉ፤22ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋር እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው አብረውን ለምኖር ፈቃደኞች የሚሆኑት፣ የእኛ ወንዶች እንደ እነርሱ የተገረዙ እንደሆነ ብቻ ነው። 23ታዲያ እንዲህ ብናደርግ ከብታቸው ንብረታቸው፣ እንስሶቻቸውም ሁሉ የእኛው ይሆኑ የለምን? ስለዚህ ባሉት እንስማማ፣ እነርሱም አብረውን ይኑሩ።”24የከተማይቱ ነዋሪዎች ሁሉ ኤሞርና ሴኬም ባቀረቡት ዐሳብ ተስማምተው ወንዶቹ ሁሉ ተገረዙ። 25በሦስተኛውም ቀን የሁሉም ቁስል ገና ትኩስ ሳለ ከያዕቆብ ልጆች ሁለቱ፣ የዲና ወንድሞች ስምዓንና ሌዊ፣ ሰይፋቸውን መዘው ሳይታሰብ ወደ ከተማይቱ ገብተው ወንዶቹን በሙሉ ገደሏቸው። 26ኤሞርንና ሴኬምንም በሰይፍ ገድለው፣ እኅታቸውን ዲናን ከሴኬም ቤት አውጥተው ይዘዋት ተመለሱ።27የቀሩትም የያዕቆብ ልጆች እኅታቸውን ስለደፈሩባቸው ወደ ሞቱት ሰዎች ቤት እየገቡ ከተማይቱን በሙሉ ዘረፉ። 28የበግና የፍየል መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውንና አህዮቻቸውን እንዲሁም በከተማይቱና በአካባቢው የሚገኘውን ንብረታቸውን ሁሉ ወሰዱባቸው፤ 29ሀብታቸውን ሁሉ ዘርፈው ሴቶቻቸውንና ሕፃናቶቻቸውን ሁሉ ማርከው በየቤቱ ያገኙትን ሁሉ ይዘው ሄዱ።30ያዕቆብ ስምዖንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በእኔ ላይ ከባድ ችግር አመጣችሁብኝ፤ እነሆ፣ በዚህ ድርጊት የተነሣ በዚህች ምድር የሚኖሩ ከነዓናውያንና ፌርዛውያን ይጠሉኛል፤ እኛ በቁጥር አነስተኞች ነን፣ እነርሱ ተባብረው ቢያጠቁን እኔና ቤተሰቤ እንጠፋለን።” 31ስምዖንና ሌዊ ግን፣ “ታዲያ ሴኬም እኅታችንን እንደዝሙት አዳሪ ይድፈራትን?” አሉት።
1እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሣና ወደ ቤቴል ሂድ፣ እዚያም ኑር። ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ አለው። 2ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና አብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ። 3ተነሥተን ወደ ቤቴል እንሂድ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።4ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሰብስበው፣ የጆሮ ጉትቾቻቸውን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት። ያዕቆብም ወስዶ ሴኬም አጠገብ ካለው ዋርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። 5ያንንም ቦታ ለቀው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው በነበሩት ከተሞች ሁሉ ላይ ፍርሃትና ድንጋጤ ስለለቀቀባቸው ያሳደዳቸው አልነበረም።6ያዕቆብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በከነዓን ወደምትገኘው፣ ቤቴል ወደተባለችው ወደ ሎዛ ደረሱ። 7ያዕቆብም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ ስሙን ኤል ቤቴል አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ ሸሽቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነበር። 8በዚህ ጊዜ የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ ሞተች፣ ከቤቴል ዝቅ ብሎ በሚገኘው የዋርካ ዛፍ ሥር ተቀበረች። ከዚህ የተነሣም ያ ቦታ አሉንባኩት ተባለ።9ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ዳግመኛ ተገለጠለትና ባረከው። 10እግዚአብሔርም፣ “እስካሁን ስምህ ያዕቆብ ነበር፤ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ነገር ግን ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህም እስራኤል ብሎ ጠራው።11ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉም ማድረግ የሚችል አምላክ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑሩህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ። 12ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ፤ ከአንተም በኋላ ይህችን ምድር ለዘርህ አሰጣለሁ።” 13እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ከዚያ ስፍራ ወደ ላይ ወጣ።14ያዕቆብ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፣ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቁርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት። 15ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው።16ከዚያም ከቤቴል ተነሥተው ሄዱ፤ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፣ ምጡም ጠናባት። 17ምጧ እየበረታ በሄደ ጊዜ አዋላጅቱ፣ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ሌላ ወንድ ልጅ ልትወልጂ ነው” አለቻት። 18እርስዋ ግን ልትሞት ታጣጥር ስለነበር ከመሞቷ በፊት ልጅዋን ‘ቤንኦኒ’ አለችው፤ አባቱ ግን ‘ብንያም’ አለው። 19ራሔል ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ በቤተልሔም ተቀበረች። 20ያዕቆብም በራሔል መቃብር ላይ ሐውልት አቆመ፤ እስከዛሬም የራሔል መቃብር ምልክት ይኸው ሐውልት ነው።21ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በዔዴር ግንብ ባሻገር ድንኳን ተክሎ ሰፈረ። 22ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት፣ እነርሱም፦23የልያ ልጆች፦ የያዕቆብ የበኩር ልጅ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤ 24የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍ፣ ብንያም፤ 25የራሔል አገልጋይ የባላ ልጆች፦ ዳን፣ ንፍታሌም፤26የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦ ጋድ፣ አሴር፣ ናቸው። እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በመስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ናቸው። 27ያዕቆብ በቂርያት አርባቅ (በኬብሮን) አጠገብ መምሬ በምትባል ስፍራ ወደሚኖረው አባቱ ወደ ይስሐቅ ሄደ፤ ይህም ስፍራ አብርሃምና ይስሐቅ የኖሩበት ነው።28ይስሐቅ መቶ ሰማንያ ዓመት ኖረ፤ 29አርጅቶ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።
1ኤዶም የተባለው የዔሳው የትውልድ ታሪክ የሚከተለው ነው፤ 2ዔሳው ከነዓናውያን ሴቶችን አገባ፤ እነርሱም የኬጢያዊው የዔሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤውያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳት አህሊባማ፣ 3እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችውን የእስማኤል ልጅ ቤስሞት ነበሩ።4ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት። 5እንደዚሁም አህሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆቹ ናቸው።6ዔሳው ሚስቶቹንና ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ። 7ብዙ ሀብት ስለነበራቸው አብረው መኖር አልቻሉም፣ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም። 8ስለዚህ ዔዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።9በተራራማው አገር በሴይር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤ 10የዔሳው ልጆች ስም፦ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤ 11የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤ 12የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ትምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።13የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህም ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው። 14የፅብዖን የልጅ ልጅ፤ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት አህሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤15ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኩር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ቄኔዝ 16ቆሬ፣ ጎቶምና አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።17የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሃማና፣ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ነበሩ። 18የዔሳው ሚስት የአሕሊባማ ልጆች፦የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ ከዔሳው ሚስት አሕሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። 19እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።20በኤዶም ምድር ነዋሪዎች የነበሩት የሴይር ልጆች የነበሩ የሖራውያን አለቆች፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣ 21ዲሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ በሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ። 22የሎጣን ልጆች፦ ሖሪና ሔማም የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ትባል ነበር።23የሦባል ልጆች፦ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባልና ስፎና አውናንም፤ 24የፅብዖን ልጆች፦ አያና፣ ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅባዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍልውሃ ምንጮችን በምድረበዳ ያገኘ ሰው ነው።25የዓና ልጆች፦ዲሶንና የዓና የሴት ልጅ አህሊባማ፤ 26የዲሶን ልጆች፦ ሔምዳን፣ ሴስባን፣ ይትራንና ክራን፤ 27የኤድር ልጆች፦ ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤ 28የዲሳን ልጆች፦ዑፅና አራን።29የሖራውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ፅዖን፥ ዓና፣ 30ዶሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።31ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦ 32የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነግሦ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። 33ባላቅ ሲሞት፣ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።34የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ሲሞት የቴማኒው ሑሳም ነገሠ። 35ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር። 36ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።37ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ። 38ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በልሐናን በምትኩ ነገሠ። 39የዓክቦር ልጅ በልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብዔል ሲሆን፣ እርሷም መጥሬድ የወለደቻት የሜዛሃብ ልጅ ነበረች።40ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ፣ ዓለዋ፣ የቴት፣ 41አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፌኖን፣ 42ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣ 43መግዲኤልና ዒራም፣ እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው ከኤዶም የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። ይህም ዔሳው የኤዶማውያን አባት ነበር።
1የዕቆብ አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ። 2የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረ ጊዜ፣ ከአባቱ ሚስቶች ከባላቅና ከዘለፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር። እርሱም ስለወንድሞቹ ድርጊት ለአባቱ መጥፎ ወሬ ይዞለት መጣ።3እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወደው ነበር፣ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም ሰፋለት። 4ወንድሞቹም አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው መሆኑን ሲያዩ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበት ሊያናግሩት አልቻሉም።5ዮሴፍ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት፤ 6እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ”7‘እኛ ሁላችን በእርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ ተነሣና ቀጥ ብሎ ቆመ፤ የእናንተ ነዶዎች ዙሪያውን ተሰብስበው ለእኔ ነዶ ሰገዱለት’” 8ወንድሞቹም፣ “ታዲያ በእኛ ላይ ንጉሥ ሆነህ ልትገዛን ታስባለህን?” ብለው ጠየቁት። ስለ ሕልሙና ስለተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት።9እንደ ገናም ሌላ ሕልም አለመ፤ ለወንድሞቹም እነሆ፣ ሌላ ሕልም አለምሁ፣ ፀሐይና ጨረቃ፣ ዐሥራ አንድ ክዋክብትም ሲሰግዱልኝ ዐየሁ” ብሎ ነገራቸው። 10ይህንኑ ለወንድሞቹ የነገራቸውን ሕልም ለአባቱም በነገረው ጊዜ፣ አባቱ፣ “ይህ ምን ዐይነት ሕልም ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም በፊትህ ወደ ምድር ተጎንብሰን በርግጥ ልንሰግድልህ ነው?” ሲል ገሠጸው። 11ወንድሞቹ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው።12አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን መንጋዎች ይዘው ወደ ሴኬም ተሰማሩ፤ 13እስራኤልም ዮሴፍን፣ “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ” አለው። ዮሴፍም፣ “እሺ እሄዳለሁ” አለ። 14አባቱም፣ “በል እንግዲህ ሄድና የወንድሞችህንና የመንጋዎቹን ደኅንነት አይተህ ንገረኝ” አለው። በዚህ ዓይነት እስራኤል ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣15ሜዳ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲባዝን አንድ ሰው አግኝቶት፣ “ምን እየፈለግህ ነው?” ሲል ጠየቀው። 16ዮሴፍም፣ “ወንድሞቼን እየፈለግኋቸው ነው፤ መንጎቻቸውን የት እንዳሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህ?” አለው። 17ሰውዬውም፣ “ከዚህ ሄደዋል፤ ደግሞም ‘ወደ ዶታይን እንሂድ’ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው። ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ሄደ፣ በዶታይን አቅራቢያም አገኛቸው።18ወንድሞቹም ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቅ ዐዩት፣ ወደ ነበሩበትም ስፍራ ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ። 19እነርሱ እንዲህ ተባባሉ፦ “ያ ሕልም አላሚ መጣ፤ 20ኑ እንግደለውና ከጉድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም፣ ‘ክፉ አውሬ ነጥቆ በላው’ እንላለን፤ እስቲ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን።”21ሮቤል ግን ይህን ምክር ሲሰማ ከእጃቸው ሊያድነው ፈለገ እንዲህም አለ፤ “አንግደለው፤ 22የሰው ደም አታፍስሱ፣ ከምትገድሉት ይልቅ በዚህ በበረሃ ባለው ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት” አላቸው። ሮቤል ይህን ያለው ሕይወቱን ከእጃቸው አትርፎ ወደ አባቱ ሊመልሰው ዐስቦ ነበር።23ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደደረሰ፣ የለበሳትን በኅብረ ቀለማት የጌጠች እጀ ጠባቡን ገፈፉት፤ 24ይዘውም ወደ ጉድጓድ ጣሉት፤ ጉድጓዱም ውሃ የሌለበት ደረቅ ነበር።25ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ፤ አሻግረው ሲመለከቱም ከገለዓድ የሚመጡ እስማኤላውያን ነጋዴዎች ጓዛቸውን በግመሎች ላይ ጭነው ተመለከቱ። ነጋዴዎቹ ሽቶ፣ በለሳን፣ ከርቤ በግመሎቻቸው ጭነው ወደ ግብፅ የሚወርዱ ነበሩ። 26ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “ወንድማችንን መግደልና አሟሟቱን መደበቅ ምን ይጠቅመናል?27ከዚህ ይልቅ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች እንሽጠው፤ እጃችንን ግን በእርሱ ላይ አናንሳ። ምንም ቢሆን የሥጋ ወንድማችን ነው” ወንድሞቹም በሃሳቡ ተስማሙ። 28የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማሴላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጉድጓድ ጎትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፣ እነርሱም ወደ ግብፅ ይዘውት ሄዱ።29ሮቤል ወደ ጉድጓዱ ተመልሶ ሲያይ፣ ዮሴፍን በማጣቱ ልብሱን በሐዘን ቀደደ። 30ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ፣ “እነሆ፣ ልጁ እዚያ የለም! እንግዲህ እኔ ወዴት ብሄድ ይሻለኛል?” አለ።31ከዚህ በኋላ አንድ ፍየል አረዱና የዮሴፍን ልብስ በደም ነከሩት። 32በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስቲ እየው” አሉት። 33እርሱ የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ፣ “ይህማ የልጄ እጀ ጠባብ ነው! ፤ ክፉ አውሬ በልቶታል፣ በእርግጥም ዮሴፍ ተቦጫጭቆአል” አለ።34ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለብሶ ስለ ልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፤ 35ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና አልቻለም፣ “በሐዘን እንደተኮራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ። 36በዚህ ጊዜ የምድያም ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወስደው፣ ከፈርዖን ሹማምንት አንዱ ለነበረው ለዘበኞች አለቃ፣ ለጲጥፋራ ሸጡት።
1በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ሒራ ወደተባለ ዐዱላማዊ ሰው ዘንድ ሄደ፣ መኖሪያውንም 2እዚያም ሳለ፣ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ ዐየ፤ እርሷንም አግብቶ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ።3እርሷም አርግዛ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው። 4እንደገናም አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም አውናን አለችው። 5አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው፣ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር።6ይሁዳ የመጀመሪያ ልጁን ዔርን ትዕማር ከምትባል ልጃገረድ ጋር አጋባው። 7የይሁዳ የበኩር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።8ይሁዳ አውናንን፣ “ዋርሳዋ እንደመሆንህ ከወንድምህ ሚስት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በመፈጸም የወንድምህን ስም የሚያስጠራለት ዘር ተካለት አለው። 9አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የእርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በፈጸመ ቁጥር የወንድሙን ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወለድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስ ነበር። 10ይህም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሆኖ ስለተገኘ፣ እርሱንም እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው።11ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፤ ሴሎም እንደወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለፈራ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።12ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፣ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደተምና ሄደ። 13ሰዎቹም ለትዕማር፣ “አማትሽ የበጎቹን ጠጉር ወደሚሸልቱ ሰዎች ዘንድ ወደተምና እየሄዱ ነው” አሏት። ይህን እንድሰማች 14የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፣ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ በር ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፣ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፣ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።15ፊቷ በሻሽ ተሸፋፍኖ ሲያያት፣ ይሁዳ ዝሙት አዳሪ መሰለችው። 16ምራቱ መሆኗን ባለማወቁ፣ እርሷ ወዳለችበት ወደ መንደሩ ዳር ጠጋ ብሎ፣ “እባክሽን አብሬሽ ልተኛ” አላት። እርሷም፣ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።17“ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርሷም “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ ምን መያዣ ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው። 18“ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፣ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፣ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና አብሯት ተኛ፤ እርሷም አረገዘችለት።19ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሽዋን አውልቃ እንደወትሮዋ የመበለት ለብሷን ለበሰች። 20ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶሎማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፣ እርሱ ግን ሊያገኛት አልቻለም።21“በኤናይም ከተማ መግቢያ ከመንገዱ ዳር የነበረች ያቺ ዝሙት አዳሪ የት ደረሰች?” ብሎ ዓዶሎማዊው ሰውዬ ጠየቀ። ሰዎቹም፣ “በዚህ አካባቢ እንደዚህ ያለች ዝሙት አዳሪ የለችም” አሉት። 22ስለዚህ ወደ ይሁዳ ተመልሶ ሄደና፣ “ላገኛት አልቻልሁም፤ በዚያ የሚኖሩትም ሰዎች፥ ‘እንደዚህ ያለች ዝሙት አዳሪ እዚህ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው። 23ይሁዳም፣ “እንግዲህ መያዣውን እንደያዘች ትቅር አለዚያ መሳቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፣ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።24ከሦስት ወር ያህል በኋላ፣ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፣ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ። 25እርሷም ተይዛ በምትወሰድበት ጊዜ ለአማትዋ፣ “እኔ ያረገዝሁት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” ስትል ላከችበት፤ ደግሞም፣ “የማኅተሙ ቀለበት ከነማንጠልጠያውና በትሩ የማን እንደሆነ እስቲ ተመልከት” አለችው። 26ይሁዳም ዕቃዎቹን አውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም።27የመውለጃዋ ጊዜ እንደደረሰም ፅንሷ መንታ መሆኑ ታወቀ። 28በምትወልድበትም ጊዜ አንደኛው እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም፣ “ይህኛው መጀመሪያ ወጣ” ስትል በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት፤29ነገር ግን፣ እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም፣ “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፣ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ። 30ከዚያ በኋላ እጁ ላይ ቀይ ክር የታሰረለት ወንድሙ ተወለደ፣ ስሙም ዛራ ተባለ።
1ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖንም ሹማምንት አንዱ የነበረውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብፃዊው ጴጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው። 2እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ስለነበረ ኑሮው ተቃናለት፤ እርሱም በግብፃዊው አሳዳሪው ቤት ኖረ።3አሳዳሪው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለና ሥራውንም ሁሉ እንዳከናወነለት ባየ ጊዜ፣ 4ዮሴፍ በእርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፣ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፣ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኃፊነት ሰጠው።5ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር የግብፅዊውን ቤት ባረከ፣ የእግዚአብሔርም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ። 6ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፣ የቀረበለትንም ከመመገብ በስተቀር፣ ማናቸውንም ጉዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ-መልካም ነበር፤7ከጊዜ በኋላ የጌታው ሚስት ዮሴፍን ተመልክታ ስላፈቀረችው፣ “ና ከእኔ ጋር አብረን እንተኛ” አለችው። 8እርሱ ግን ይህን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኃላፊነት ስለሰጠኝ፣ በቤቱ ውስጥ ስላልው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። 9በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኃላፊነት ያለው ማንም የለም፣ ከአንቺ በቀር በእኔ ቁጥጥር ሥር ያላደረገው ምንም ነገር የለም፤ ይኸውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ፣ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እፈጽማለሁ?”10ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር፤ እርሱም ከእርሷ ጋር ይተኛ ዘንድ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም። 11አንድ ቀን ዮሴፍ ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤት ሲገባ በቤት ውስጥ አንድም ሠራተኛ አልነበረም፤ 12እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ፣ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጅዋ ላይ ትቶላት ከቤት ሸሽቶ ወጣ።13እርሷም ልብሱን በእጅዋ ላይ ትቶ ከቤት ሸሽቶ መውጣቱን በተመለከተች ጊዜ፣ 14አገልጋዮችዋን ጠርታ እንዲህ አለቻቸው፣ “እነሆ፣ ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ ሊያዋርደኝ ነበር፤ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፤ እኔ ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ። 15ዕርዳታ ለማግኘትም መጮኼን በሰማ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።”16የዮሴፍ አሳዳሪ እስኪመጣ ድረስ ልብሱን በእርስዋ ዘንድ አቆየችው። 17በመጣም ጊዜ የሆነውን ታሪክ እንዲህ ስትል ዘርዝራ ነገረችው፤ “አንተ ወደዚህ የመጣኸው ዕብራዊ አገልጋይ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊያዋርደኝ ነበር። 18ነገር ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ በጮኽሁ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።”19“የአንተ አገልጋይ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን ታሪክ በሰማ ጊዜ የዮሴፍ አሳዳሪ እጅግ ተቆጣ። 20ዮሴፍንም ወስዶ፣ የንጉሥ እስረኞች ወደታሠሩበት እስር ቤት አስገባው።21እግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍቅሩን ዐሳየው፣ በእስር ቤት አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው። 22ስለዚህ የእስር ቤቱ አዛዥ ዮሴፍን የእስረኞች ሁሉ አለቃ አደረገው፤ በእስር ቤት ላለውም ነገር ሁሉ ኃላፊ ሆነ። 23እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እንዲቃናለት ስላደረገ የእስር ቤት አዛዥ በዮሴፍ ቁጥጥር ሥር በነበረው ነገር ምንም ዐሳብ አልነበረበትም።
1ከዚህም በኋላ የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊውና የእንጀራ ቤት ኃላፊው ንጉሡን የሚያሳዝን በደል ፈጸሙ። 2ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዡ፣ በሁለቱም ሹማምንቱ ላይ እጅግ ተቆጣ፤ 3በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደታሠረበት እስር ቤት አስገባቸው።4የዘበኞቹም አለቃ እስረኞቹን ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ በእስር ቤትም ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። 5ታስረው የነበሩት የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም ዐዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍቺ ነበረው።6በማግስቱ ጥዋት ዮሴፍ እነርሱ ወዳሉበት ክፍል በገባ ጊዜ ተክዘው አገኛቸውና፤ 7“ዛሬ በፊታችሁ ላይ ሐዘን የሚታየው ለምንድን ነው?” አላቸው። 8እነርሱም፣ “ሁለታችንም ሕልም ዐየን፤ ነገር ግን የሚተረጉምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፣ “ሕልም የመተርጎም ችሎታ የሚሰጥ እግዝአብሔር ነው፣ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።9ስለዚህ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፤ “ከፊት ለፊቴ አንዲት የወይን ተክል ዐየሁ፤ 10ተክሏም ሦስት ሐረጎች ነበሯት፤ ወዲያው እቆጥቁጣ አበበች፤ የወይን ዘለላውም ወዲያው በሰለ። 11የፈርዖንንም ጽዋ ይዤ ነበር፣ የወይኑን ፍሬ ለቅሜ በጽዋው ውስጥ ጨምቄ ጽዋውን በእጁ ሰጠሁት።”12ዮሴፍም እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ የሕልሙ ትርጓሜ ይህ ነው፤ ሦስቱ ሐረግ ሦስት ቀን ነው፤ 13በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፣ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል፤ በፊት የመጠጥ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ኡሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።14እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፣ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤ 15ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በአፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።”16የእንጀራ ቤት አዛዡም፣ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም የተሰጠው ፍቺ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፣ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፣ ሦስት መሶቦች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 17በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፣ ነገር ግን ወፎች ምግቡን ከመሶቡ እያነሱ የበሉት ነበር።”18ዮሴፍም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ 19በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ራስህን ካስቆረጠ በኋላ በእንጨት ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን የበሉታል።”20በሦስተኛው ቀን የፈርዖን ልደት በዓል ስለነበር ለመኳንንቱ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ በዚያኑ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምንቱ ካሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው። 21የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር፤ 22የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው ሰቀለው። 23የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው።
1ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለም፤ ሕልሙም በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤ 2እነሆ፣ መልካቸው ያማረ፣ ሥጋቸው የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ይበሉ ጀመር። 3ቀጥሎም መልካቸው የከፋ አጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወጡት ላሞች አጠገብ ቆሙ።4እነዚህ መልካቸው የከፋና አጥንታቸው የወጣ ላሞች፥ እነዚያን ያማሩና የወፈሩ ላሞች ሲውጡአቸው ዐየ፤ ከዚያም ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ። 5ፈርዖንም እንደገና እንቅልፍ ወስዶት ሳለ ሌላ ሕልም ዐየ። በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዐየ፤ 6ቀጥሎም የቀጨጩና ከበረሐ በተነሣ የምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎች ወጡ።7የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፤ ሰባቱን የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጡአቸው፤ በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፣ ነገሩ ሕልም ነበር። 8በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፣ ስለዚህ በግብፅ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፣ ይሁን እንጂ፣ ሕልሞቹን ሊተረጉምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።9በዚያን ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ “የሠራሁት በደል ዛሬ ታወሰኝ። 10ፈርዖን ሆይ! አንተ በእኔና በእንጀራ ቤት ኃላፊው ላይ ተቆጥተህ በዘበኞች አለቃ ቤት እንድንታሰር አድርገህ ነበር፤ 11በዚያ ሳለን በአንድ ሌሊት ሁለታችንም የተለያየ ሕልም ዐየን፤ የእያንዳንዳችንም ሕልም የተለያየ ትርጉም ነበረው።12በዚያን ጊዜ የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የሆን አንድ ዕብራዊ ወጣት ከእኛ ጋር እስር ቤት ነበር። ሕልማችንን በነገርነው ጊዜ፣ ፍቺውን ነገረን፤ ለእያንዳንዳችንም እንደ ሕልማችን ተረጎመልን፤ 13ነገሩም ልክ እርሱ እንደተረጎመልን፤ እኔ ወደ ቀድሞ ሹመቴ ተመለስሁ፤ የእንጀራ ቤት አዛዡም ተሰቀለ።14ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ትዕዛዝ ሰጠ፤ ከእስር ቤትም በጥድፊያ ይዘውት መጡ፤ ጠጉሩንም ከተላጨና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ፈርዖን ፊት ቀረበ 15ፈርዖንም ዮሴፍን፣ “ሕልም ዐይቼ ነበር፣ ሕልሜን ሊተረጉምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፣ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጎም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው። 16ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “ይህ በእኔ አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በበጎነት ይመልስለታል”17ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሕልሜ በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር። 18ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው የማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ ዐየሁ።19ከእነርሱም በኋላ ዐቅመ ደካማ፣ መልካቸው እጅግ የከፋና አጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብፅ ምድር ከቶ ዐይቼ አላውቅም። 20አጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፣ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። 21ከዋጧቸውም በኋላ፣ ያው የበፊቱ መልካቸው ስላልተለወጠ እንደዋጧቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ ከዚያም ከእንቅልፌ ነቃሁ22ደግሞም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዐየሁ፤ 23ቀጥሎም የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ። 24የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ያየኋቸውንም ሕልሞች ለአስማተኞች ነገርሁ፣ ነገር ግን ሕልሞቹን ማንም ሊተረጉምልኝ አልቻለም።”25ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዓይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል። 26ሰባቱ የሚያምሩ ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው።27ከእነርሱም በኋላ አጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው። 28አስቀድሜ ለፈርዖን እንደተናገርሁት እግዚአብሔር ወደፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል። 29በመላው የግብፅ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ።30በዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጎዳት በግብፅ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። 31ከጥጋብ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። 32ሕልሙ ለፈርዖን በድጋሚ መታየቱ፣ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቆረጠ ስለሆነ ነው፤ ይህንንም እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ይፈጽመዋል፤33እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፣ በመላው የግብፅ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም። 34እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፣ አንድ አምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኃላፊዎችን ይሹም።35እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ። 36የሚከማቸው እህል፣ ወደፊት በግብፅ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።37ዕቅዱም ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት። 38ፈርዖንም፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው።39ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፣ “እግዚአብሔር ይህን ሁል ገለጠለህ እንዳንተ ያለ አስተዋይና ብልህ ሰው የለም። 40አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።” 41ከዚያም፣ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “በመላይቱ የግብፅ ምድር ላይ ኃላፊ አድርጌሃለሁ” አለው።42ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት። 43በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፣ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው።44ከዝህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም በመላይቱ ግብፅ ያለ አንተ ፈቃድ ማንም ሰው እጁን ወይም እግሩን ማንቀሳቀስ አይችልም” አለው። 45ፈርዖን ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም አስናት ተብላ የምትጠራውን ኦን ተብሎ የሚጠራው ከተማ ካህን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው።46ዮሴፍ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብፅን ምድር በሙሉ ዞረ። 47በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች።48በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፣ ዮሴፍ በግብፅ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፣ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ። 49ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር።50ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣታቸው በፊት የኦን ከተማ ካህን የጶጢፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንድ ልጆች ወለደችለት። 51ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው። 52እንደዚሁም “መከራ በተቀበልሁበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው።53በግብፅ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን አለፈና 54ዮሴፍ አስቀድሞ እንደተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፣ በመላው የግብፅ ምድር መስፋፋት ሲጀመር፣55ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፍርዖንም ግብፃውያኑን፣ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው። 56ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለሄደ፣ ዮሴፍ ጎተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላይቱ ግብፅ ጸንቶ ነበር። 57ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለነበር፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ምድር መጡ።
1በግብፅ እህል መኖሩን ሲሰማ፣ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ለምን እርስ በርስ ትተያያላችሁ?” 2በግብፅ አገር እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ በራብ ከመሞታችን በፊት ወደዚያ ሂድና እህል ግዙልን” አላቸው። 3ስለዚህ ዐሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ሄዱ። 4ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሃት ከወንድሞቹ ጋር አልላከውም።5ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፣ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ከሄዱት መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ። 6በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዢ ነበር፣ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደደረሱ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው ሰገዱለት።7ዮሴፍም ወንድሞቹን ባየ ጊዜ ዐወቃቸው፣ ነገር ግን የማያውቃቸው በመምሰል በቁጣ ቃል፣ “ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እህል ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን" ብለው መለሱለት። 8ዮሴፍ ወንድሞቹን ቢያውቃቸውም እንኳ እነርሱ ግን አላወቁትም።9በዚህ ጊዜ ስለወንድሞቹ ያየው ሕልም ትዝ አለውና፣ “ሰላዮች ናችሁ፣ የመጣችሁት አገራችን በየትኛው በኩል ለጥቃት የተጋለጠች መሆኗን ለመሰለል ነው” አላቸው። 10እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን ሆይ፣ እንዲህስ አይደለም፤ እኛ አገልጋዮችህ የመጣነው እህል ለመሸመት ነው፤ 11ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ነን፤ አገልጋዮችህም የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።”12እርሱም መልሶ፣ “አይደለም፣ ግብፅ በየት በኩል ለጥቃት የተጋለጠች መሆኗን ለመሰለል ነው” አላቸው። 13እነርሱ ግን መልሰው፣ “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን አገር ከሚኖር ከአንድ ሰው የተወለድን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን። ትንሹ ወንድማችን አባታችን ዘንድ ሲሆን አንዱ ወንድማችን ሞቷል።14ዮሴፍም እንዲህ አላቸው፤ “ነገርኋችሁ እኮ፤ ሰላዮች ናችሁ 15ታናሽ ወንድማችሁ እዚህ እስካልመጣ ድረስ ከዚህ ንቅንቅ እንደማትሉ በፈርዖን ስም እምላልሁ፤ ማንነታችሁ የሚረጋገጠውም በዚህ ነው። 16ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁትም እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስት ቤት ትቆያላችሁ፤” 17ሁሉንም ሦስት ቀን በእስር አቆያቸው።18በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ። 19ታማኝ ሰዎች ከሆናችሁ፣ ከመካከላችሁ እንዱ እዚህ እስር ቤት ሲቆይ፣ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ትወስዱላቸዋላችሁ፤ 20ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።21እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፤ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፣ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ። 22ሮቤልም መልሶ፣ “በዚህ ልጅ ላይ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።23ዮሴፍ የሚያነጋግራቸው በአስተርጓሚ ስለሆነ የሚነጋገሩትን እንደሚሰማባቸው ዐላወቁም ነበር። 24ከፊታቸውም ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ከዚያም ወደእነርሱ ትመልሶ እንደገና አነጋገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ዓይናቸው እያየ አሰረው፤ 25ዮሴፍ ለአገልጋዮቹ በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፤ ብሩንም በያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ተደረገላቸው።26እነርሱም እህላቸውን በአህዮቻቸው ጭነው ጉዞአቸውን ቀጠሉ። 27በመንገድም ለአዳር ሰፍረው ሳለ፣ ከእነርሱ አንዱ ከያዘው እህል ላይ ለአህያው ለመስጠት ስልቻውን ሲፈታ፣ በስልቻው አፍ ላይ ብሩን አገኘ። 28እርሱም ወንድሞቹን፣ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፣ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ።29በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ከደረሱ በኋላ ያጋጠማቸውን ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩት፤ 30“የግብፅ አገር አስተዳዳሪ ‘አገሬን ልትሰልሉ የመጣችሁ ናችሁ’ በማለት በቁጣ ቃል ተናገረን፤ 31እኛ ግን እንዲህ አልነው፤ “እኛ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም። 32እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆንን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፣ አንዱ የለም፣ ታናሽ ወንድማችን ግን ከአባታችን ጋር በከነዓን ይገኛል።’33ከዚህ በኋላ የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው እንዲህ አለን፣ “ታማኝ ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው በዚህ ነው ከእናንተ መካከል አንዱን ወንድማችሁን እዚህ እኔ ዘንድ ትታችሁ የተቀራችሁት ለትራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁላቸው ሂዱ። 34ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያን ጊዜም ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደፈለጋችሁ እየተዘዋወራችሁ መነገድ ትችላላችሁ።35እህሉንም ሲዘረግፉ በየስልቻቸው ውስጥ ብራቸው እንደተቋጠረ ተገኘ፤ የእያንዳንዳቸውን የተቋጠረ ብር ሲያዩም፣ እነርሱም ሆኑ አባታቸው ደነገጡ። 36አባታቸው ያዕቆብም፣ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፣ ዮሴፍ የለም፣ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ” አለ።37በዚህን ጊዜ ሮቤል አባቱን፣ “ብንያምን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣው ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ወስደህ ግደላቸው፣ ስለዚህ በእኔ ኃላፊነት ላከው፤ እኔም መልሼ አመጣዋለሁ” እለው። 38ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፣ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጉዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።
1አሁንም በምድሪቱ ላይ እንደጸና ነበር፤ 2ከግብፅ ያመጡትንም እህል በልተው ከጨረሱ በኋላ፣ አባታቸው፣ “እስቲ እንደገና ወርዳችሁ፣ ጥቂት እህል ሸምቱልን” አላቸው።3ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ ያ ሰው ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤ 4ወንድማችን ከእኛ ጋር እንዲወርድ ከፈቀድህ ወደዚያ ሄደን እህል እንሸምትልሃለን፤ 5እርሱን የማትልከው ከሆነ ግን እኛም ወደዚያ አንወርድም፤ ያም ሰው፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም’ ብሎናል።”6እስራኤልም፣ “ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለዚያ ሰው በመንገር ለምን ይህን ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። 7እነርሱም፣ “ሰውዬው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተ ሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ?’ ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታዲያ፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?” ብለው መለሱለት።8ይሁዳም አባቱን እስራኤልን እንዲህ አለው፣ “ልጁን ከእኔ ጋር ስደደው፤ እኛም በቶሎ እንሂድ፣ ይህ ከሆነ አንተም፣ እኛም፣ ልጆቻችንም አንሞትም፣ እንተርፋለን። 9ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኃላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘላለም በደለኛ እኔ ልሁን። 10ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፣ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።”11ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፣ ምድሪቱ ከምታፈራቸው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና ለውዝ በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው ስጦታ ውሰዱለት። 12በየስልቾቻችሁ አፍ ላይ የተገኘውን ብር መመለስ ስላለባችሁ፣ ዕጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ ያ በየስልቾቻችሁ ውስጥ የተገኘው ብር ምናልባት በስሕተት የመጣ ሊሆን ይችላል።13ወንድማችሁንም ይዛችሁ ወደ ሰውዬው በቶሎ ሂዱ። 14ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ይዛችሁ ለመመለስ እንድትችሉ ሁሉን የሚችል አምላክ በምሕረቱ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እኔ በበኩሌ ልጆቼን ካጣሁ፣ ባዶ እጄን መቅረቴ ነው።” 15ስለዚህ ወንድማማቾቹ ገጸ በረከቱንና ዕጥፍ ገንዘብ ይዘው ከብንያም ጋር ወደ ግብፅ ለመሄድ ጉዞ ጀመሩ፤ እዚያም በደረሱ ጊዜ ዮሴፍ ፊት ቀረቡ።16ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፣ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፣ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ አንድ ከብት እረድና አዘጋጅ” አለው። 17አዛዡም ዮሴፍ የነገረውን አደረገ፣ ሰዎቹንም ወደ ዮሴፍ ቤት ወሰዳቸው።18ሰዎቹም ወደ ዮሴፍ ቤት በመወሰዳቸው ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ወደዚህ የመጣነው ቀደም ሲል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው። ሰውዬው ሊያስረንና ባሪያዎች ሊያደርገን አህዮቻችንንም ሊወስድ ይችላል።” 19ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፣ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤ 20እንዲህም አሉት፤ “ለመጀመሪያ ጊዜ እህል ለመሸመት ወደዚህ መጥተን ነበር፤21ነገር ግን ለአዳር በሰፈርንበት ቦታ የየስልቾቻችንን አፍ ስንከፍት እያንዳንዳችን በስልቾቻችን አፍ ላይ ብራችንን ሙሉውን አገኘነው። ገንዘቡንም ይኸው መልሰን ይዘን መጥተናል። 22አሁንም እህል መሸመት የሚሆነን ተጨማሪ ብር ይዘን መጥተናል፤ በዚያን ጊዜ ገንዘቡን በየስልቾቻቸን ውስጥ ማን መልሶ እንዳስቀመጠው ግን አናውቅም” አሉት። 23የቤቱ አዛዥም፣ “አይዞአችሁ አትፍሩ፣ በየስልቾቻችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ገንዘብ የሰጣችሁ የእናንተም የአባቶቻችሁም አምላክ ነው፤ እኔ እንደሆንሁ ብሩን ተቀብያለሁ” አላቸው። ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ አገናኛቸው።24የቤቱ አዛዥ ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገብቶ እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አቀረበላቸው፤ ለአህዮቻቸውም የሚበሉት ገፈራ ሰጣቸው። 25ምሳ በዚያ እንደሚበሉ ተነገሯቸው ስለነበር፣ ዮሴፍ በቀትር ከመግባቱ በፊት እጅ መንሻዎቻቸውን ለማበርከት ተዘጋጁ።26ዮሴፍም ወደ ቤቱ ሲገባ የመጧቸውን ስጦታዎች አበረከቱለት፤ ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት። 27ዮሴፍም ስለ ደኅንነታቸው ጠየቃቸው፣ ከዚያም፣ “ሽማግሌ አባት እንዳላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ደኅና ነው? አሁንም በሕይወት አለ?” አላቸው።28እነርሱም መልሰው፣ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው እጅ ነሡት። 29ዮሴፍ በዓይኑ ሲቃኝ የእናቱን ልጅ ብንያምን ዐየና፣ “ያ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። ብንያምንም፣ “ልጄ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።30ዮሴፍ ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ በጥልቅ ስለተነካ፣ ፈጥኖ ከፊታቸው ገለል አለ፤ ሰውር ያለ ቦታም ፈልጎ፣ ዕልፍኙ ውስጥ አለቀሰ። 31ፊቱንም ከታጠበ በኋላ ወጣ፤ ስሜቱንም በመቆጣጠር ምሳ እንዲቀርብ አዘዘ።32ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደጸያፍ ይቆጥሩት ነበር። 33ወንድማማቾቹ ከታላቁ አንስቶ እስከታናሹ እንደየዕድሜአቸው በዮሴፍ ፊት በተርታ ተቀምጠው ነበር፤ በመገረምም እርስ በርሳቸው ተያዩ። 34ከዮሴፍ ገበታ ላይ እየተነሣ ለእያንዳንዳቸው ምግብ ሲቀርብ የብንያም ድርሻ ከሌሎቹ አምስት ዕጥፍ ነበር። እነርሱም እንዲህ ባለ ሁኔታ አብረውት ተደሰቱ እስኪረኩም ጠጡ።
1ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ያህል እህል በየስልቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዱንም ገንዘብ በየስልቻው አፍ አስቀምጠው። 2ከዚያም የብር ዋንጫዬን በታናሹ ወንድማቸው ስልቻ አፍ ከእህሉ ዋጋ ጋር ጨምረው።” አዛዡም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ።3ጠዋት በማለዳ ወንድማማቾቹ አህዮቻቸውን ይዘው እንዲሄዱ ተደረገ። 4ከከተማውም ምንም ያህል ርቀው ሳይሄዱ፣ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፤ “እነዚያን ሰዎች ቶሎ ድረስባቸውና፣ ‘በመልካም ፋንታ ክፉ የመለሳችሁት ስለ ምንድን ነው? 5የጌታዬን የብር ዋንጫ የሰረቃችሁት ለምንድነው? ዋንጫው ጌታዬ የሚጠጣበትና ሁሉን ነገር መርምሮ የሚያውቅበት እንደሆነ አታውቁምን? ይህ ያደረሳችሁት በደል እጅግ ከባድ ነው’ ብለህ ነገራቸው።”6የቤቱ አዛዥም እንደደረሰባቸው፣ ልክ እንደተባለው ተናገራቸው። 7እነርሱ ግን እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን እንዲህ ያለ ነገር ለምን ይናገራል? እኛ አገልጋዮችህ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም።8ከዚህ ቀደምም በየስልቾቻችን አፍ የተገኘውን ብር ከከነዓን እንኳ መልሰን አምጥተናል፤ ታዲያ አሁን ብር ወይም ወርቅ ከጌታህ ቤት እንዴት እንሰርቃለን? 9የጠፋው ዕቃ ከአገልጋዮችህ የተገኘበት ይሙት፤ የቀረነው የጌታችን ባሮች እንሁን።” 10አዛዡም መልካም ነው፤ እንዳላችሁት ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው ባሪያዬ ይሆናል፤ የቀራችሁት ግን ከበደል ነጻ ትሆናላችሁ” አላቸው።11ስለዚህ በፍጥነት ስልቻዎቻቸውን አወረዱ፤ እያንዳንዱም የራሱን ስልቻ ከፈተ። 12ከዚያም አዛዡ ፍተሻውን ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ቀጠለ። በመጨረሻም ጽዋው በብንያም ስልቻ ውስጥ ተገኘ። 13በዚህ ጊዜ ልብሶቻቸውን በሐዘን ቀደዱ፤ ሁሉም ስልቾቻቸውን በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማይቱ ተመለሱ።14ይሁዳና ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ሲገቡ፣ ዮሴፍ ገና ከቤቱ አልወጣም ነበር። እነርሱም በፊቱ ተደፍተው ሰገዱ። 15ዮሴፍም፣ “ለምን እንዲህ ያለ ነገር አደረጋችሁ? እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን የሚያውቅበት ልዩ ጥበብ እንዳለው አታውቁምን?” ሲል ጠየቃቸው።16ይሁዳም፣ “ከእንግዲህ ለጌታችን ምን ማለት እንችላለን? ምንስ እንመልሳለን? እንዲህ ካለው በደል ንጹሕ መሆናችንን ማስረዳትስ እንዴት ይቻለናል? ምክንያቱም እግዚአብሔር የሠራነውን በደል ገልጦታል፤ እንግዲህ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሪያዎችህ እንሁን” አለ። 17ዮሴፍም፣ “ይህንስ አላደርገውም፣ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ መሆን አለበት፤ ሌሎቻችሁ በሰላም ወደ አባታችሁ መመለስ ትችላላችሁ” አለ።18ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፣ ምንም እንኳ የፈርዖን ያህል የተከበርክ ብትሆንም እባክህ አትቆጣኝ። 19ጌታዬ፣ ‘አባት ወይም ወንድም አላችሁ?’ ብሎ አገልጋዮቹን ጠይቆ ነበር።20እኛም፣ ‘አዎን ሽማግሌ አባት አለን፤ አባታችንም በስተርጅና የወለደው ትንሽ ልጅ አለው፣ ወንድምዬው ሞቶአል፣ ከአንድ እናት ከተወለዱት ልጆች መካከል የተረፈው እርሱ ብቻ ነው፤ አባቱም በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር። 21ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፣ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን። 22እኛም ለጌታዬ፣ ‘ልጁ ከአባቱ ሊለይ አይችልም፤ ከተለየው ደግሞ አባትዬው ይሞታል’ አልንህ።23አንተ ግን እኛን አገልጋዮችህን፣ ‘ታናሽ ወንድማችሁ አብሮአችሁ ወደዚህ ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም’ አልኸን። 24እኛም ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ በተመለስን ጊዜ አንተ ጌታዬ ያልኸንን ነገርነው። 25ከዚያም አባታችን፣ ‘እስቲ ተመልሳችሁ ጥቂት እህል ሸምቱልን’ ሲለን 26‘መሄድ አንችልም፤ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን አብሮን ሲሄድ ብቻ ነው። ታናሽ ወንድማችንን ይዘን ካልሄድን በስተቀር የሰውዬውን ፊት ማየት አንችልም’ አልነው።27አገልጋይህ አባቴም እንዲህ አለን፤ ‘ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆች እንደወለደችልኝ ታውቃላችሁ፤ 28አንዱ በወጣበት በመቅረቱ በእርግጥ አውሬ በልቶት ይሆናል አልሁ፣ ከዚያ በኋላ ዐላየሁትም። 29አሁን ደግሞ ይህን ልጅ ወስዳችሁ አንዳች ጉዳት ቢደርስበት ሽበቴን በመራር ሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።’30እንግዲህ አሁን ልጁን ሳንይዝ ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ ብመለስ ሕይወቱ ከልጁ ሕይወት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ስለሆነ፣ 31የልጁን ከእኛ ጋር አለመኖር ሲያይ አባቴ ይሞታል። ከዚህም የተነሣ እኛ አገልጋዮችህ የአባታችንን ሽበት በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እናወርደዋለን። 32እኔ አገልጋይህ፣ “ልጅህን መልሼ ሳላመጣ ብቀር ለዘላለም በደለኛ አድርገህ ቁጠረኝ’ በማለት ስለ ልጁ ደህንነት በአባቴ ፊት ራሴን ዋስ አድርጌአለሁ።33ስለዚህ አሁን፣ አገልጋይህ በልጁ ፋንታ የአንተ የጌታዬ ባሪያ ሆኜ እዚሁ ልቅር ልጁ ግን ከወንድሞቹ ጋር ይመለስ። 34ልጁን ሳልይዝ እንዴት ተመልሼ ወደ አባቴ እሄዳለሁ? እባክህ በአባቴ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዳይ አታድርገኝ።”
1በዚያን ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩ ሰዎች ፊት ስሜቱን ሊገታ ባለመቻሉ፣ “እዚህ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፤ ስለዚህም ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት ጊዜ ከእርሱ ጋር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም። 2ዮሴፍም ድምፁን ከፍ አድርጎ በማልቀሱ ግብፃውያን ሰሙት፣ ወሬውም ወደ ፈርዖን ቤተ ሰዎች ደረሰ። 3ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ ለመሆኑ አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” ሲል ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ግን በፊቱ ተደናግጠው ስለነበር መልስ ሊሰጡት አልቻሉም።4ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በሉ” አላቸው፣ ወደ እርሱም በቀረቡ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ 5አሁንም በመሸጣችሁ አትቆጩ፤ በራሳችሁም አትዘኑ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወት ለማዳን ሲል ከእናንተ አስቀድሞ እኔን ወደዚህ ልኮኛል። 6በምድር ላይ ራብ ከገባ ይኸው ሁለት ዓመት ሆነ፣ ከዚህ በኋላም የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና አሉ።7ነገር ግን እግዚአብሔር ሕይወታችሁን በታላቅ ማዳን ለመታደግና ዘራችሁ ከምድር ላይ እንዳይጠፋ በማሰብ ከእናንተ አስቀድሞ ወደዚህ ላከኝ። 8ስለዚህ አሁን ወደዚህ የላከኝ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፣ እርሱም ለፈርዖን እንደ አባት፤ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታ፣ እንዲሁም በግብፅ ምድር ላይ ገዢ አደረገኝ።9አሁንም ‘በፍጥነት ወደ አባቴ ተመልሳችሁ እንዲህ በሉት፤ “ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔር የመላው ግብፅ ጌታ አድርጎኛል፤ ስለዚህ ሳትዘገይ ወደ እኔ ና። 10ልጆችህን የልጅ ልጆችህን በጎችህን፣ ፍየሎችህን ከብቶችህንና ያለህን ሁሉ ይዘህ በአቅራቢያዬ በጌሤም ትኖራለህ። 11ገና ወደ ፊት የሚመጣ የአምስት ዓመት ራብ ስላለ፣ በዚያ የሚያስፈልጋችሁን እኔ እሰጣችኋለሁ፤ ያለበልዚያ ግን አንተና ቤተ ስዎችህ ያንተም የሆነው ሁሉ፣ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።’12ፊታችሁ ሆኜ የማናግራችሁ እኔ ዮሴፍ ራሴ መሆኔን እናንተም ሆናችሁ ወንድሜ ብንያም በዓይናችሁ የምታዩት ነው። 13በግብፅ ስላሏኝ ክብርና ስላያችሁትም ሁሉ ለአባቴ ንገሩት፣ አባቴንም በፍጥነት ይዛችሁት ኑ።14ከዚያም በወንድሙ በብንያም አንገት ላይ ተጠምጥሞ አለቀሰ፤ ብንያምም እያለቀሰ ዮሴፍን አቀፈው። 15የቀሩትምንም ወንድሞቹን አንድ በአንድ እየሳመ አለቀሰ። ከዚያም ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር መጨዋወት ጀመሩ።16የዮሴፍ ወንድሞች መምጣት በፈርዖን ቤተ መንግሥት በተሰማ ጊዜ፣ ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ ደስ አላቸው። 17ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ለወድሞችህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘እንዲህ አድርጉ እህዮቻችሁን ጭናችሁ ወደ ከነዓን ምድር ተመለሱ። 18ከዚያም አባታችሁንና ቤተ ሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብፅ ምድር እሰጣችኋለሁ፤ በምድሪቱ በረከት ደስ ብሎአችሁ ትኖራላችሁ።’19ደግሞም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ይህን አድርጉ፣ ከግብፅ ምድር ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን የምታጓጉዙባቸው ሠረገላዎች ወስዳችሁ፤ አባታችሁን ይዛችሁ ኑ። 20ስለ ንብረታችሁ ምንም አታስቡ፣ ከግብፅ ምድር እጅግ ለም የሆነው የእናንተ ይሆናልና።’”21የእስራኤልም ልጆች ይህንኑ አደረጉ። ዮሴፍም ፈርዖን ባዘዘው መሠረት ሠረገላዎች አቀረበላቸው፤ የመንገድም ስንቅ አስያዛቸው። 22ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የክት ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን ሶስት መቶ ጥሬ ብርና አምስት የክት ልብስ ሰጠው። 23ለአባቱም በግብፅ ምድር ከሚገኘው የተመረጠ ነገር በዐሥር አህዮች፣ እንደዚሁም በዐሥር እንስት አህዮች ዳቦና ሌላ ምግብ አስጭኖ ሰደደለት።24ከዚህ በኋላ ወንድሞቹን አሰናበታቸው፤ ከእርሱም ሲሰናበቱ፣ መንገድ ላይ እንዳትጣሉ” አላቸው። 25እነርሱም ከግብፅ ወጥረው በከነዓን ምድር ወደሚኖረው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ መጡ። 26አባታቸውንም፣ እነሆ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በግብፅ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኖአል” ብለው ነገሩት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።27ነገር ግን ዮሴፍ ያላቸውን ሁሉ በነገሩት ጊዜና እርሱን ወደ ግብፅ የሚወስዱበትን ዮሴፍ የላከለትን ሠረገላ ባየ ጊዜ የአባታቸው የያዕቆብ መንፈስ ታደሰ። 28ከዚያም እስራኤል፣ “ልጄ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ ከመሞቴ በፊት ሄጄ ዐየዋለሁ” አለ።
1እስራኤልም ጓዙን ሁሉ ጠቅልሎ ተነሣ፤ ቤርሳቤህም ሲደርስ፣ ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ መሥዋዕት ሠዋ። 2እግዚአብሔርም ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ፣ “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፣ አለሁ” አለ። 3እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ በዚያ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና፤ 4አብሬህ ወደ ግብፅ እወርዳለሁ፣ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፣ የዮሴፍ የራሱ እጆች በምትሞትበት ጊዜ ዓይኖችህን ይከድናል።5ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን ለያዕቆብ በላከላቸው ሠረገላ ላይ አወጧቸው። 6ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብፅ ወረዱ። 7ወደ ግብፅም የወረደው፤ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን ማለት ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው።8ወድ ግብፅ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ የያዕቆብ ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦ የያዕቆብ የበኩል ልጆ ሮቤል። 9የሮቤል ልጆች፦ ሄኖኅ፣ ፈሉሶ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው። 10የስሞዖን ልጆች፦ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጸሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሳኡል ናቸው። 11ልጆች፦ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው።12የይሁዳ ልጆች፦ ዔር አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። 13የይሳኮር ልጆች፦ ቶላ፣ ፉዋ፣ ዮብና ሺምሮን ናቸው፤ 14የዛብሎን ልጆች፦ ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤ 15እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መሰጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቁጥር ሠላሳ ሦስት ነው።16የጋድ ልጆች፦ ጽፎን፣ ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤ 17የአሴር ልጆች፦ ዩምና፣ የሱዋ፣ የሱዊና በሪዓ ናቸው፤ እኅታቸውም ሤራሕ ናት፤ የበሪዓ ልጆች፦ ሐቤርና መልኪኤል ናቸው፤ 18እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።19የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤ 20በግብፅም የኦን ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት። 21የብንያም ልጆች፦ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ንዕማን፥ አኪ፣ ሮስ፥ ማንፌን፣ ሑፊምና አርድ ናቸው። 22እነዚህ ዐሥራ አራቱ፣ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።23የዳን ልጅ፦ ሑሺም ነው፤ 24የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዮጽርና ሺሌም ናቸው፤ 25እነዚህ ሰባቱ ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።26ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የሄዱት የገዛ ዘሮቹ ብዛት ስድሳ ስድስት ሲሆን የልጆቹን ሚስቶች አይጨምርም። 27ዮሴፍ በግብፅ የወለዳቸውን ሁለት ልጆች ጨምሮ ወደ ግብፅ የወረደው የያዕቆብ ቤተ ሰብ ቁጥር ሰባ ነበር።28ያዕቆብም ወደ ጌሤም ለመሄድ መመሪያ ይቀበል ዘንድ፣ ይሁዳን አስቀድሞ ወደ ዮሴፍ ላከው። እርሱም ጌሤም ሲደርሱ፣ 29ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ። ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደደረሰ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ለረጅም ጊዜ አለቀሰ። 30እስራኤልም ዮሴፍን፣ “በሕይወት መኖርህን ስላየሁ፣ ከእንግዲህ ብሞትም አይቆጨኝም” አለው።31ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ እነግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል። 32ሰዎቹ ከብት የሚጠብቁ ስለሆኑ እረኞች ናቸው፣ ሲመጡም በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውንና ከብቶቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።33ፈርዖን አስጠርቶአችሁ፣ ‘ሥራችሁ ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፤ 34እናንተ፣ ‘እኛ አገልጋዮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከብት አርቢዎች በግብፃውያን ዘንድ እንደ ጸያፍ ስለሚቆጠሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”
1ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው። 2ከወንድሞቹም መካከል አምስቱን መርጦ፣ ፈርዖን ፊት አቀረባቸው።3ፈርዖን የዮሴፍን ወንድሞች፣ “ሥራችሁን ምንድነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ፈርዖንን፣ “እኛ አገልጋዮችህ ልክ እንደአባቶቻችን ከብት አርቢዎች ነን” አሉት። 4ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት።5ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “አባትንህና ወንድሞችህ ወደ አንተ መጥተዋል፤ 6የግብፅ ምድር እንደሆነ በእጅህ ነው፤ አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው ምድር አስፍራቸው፤ በጌሤም ይኑሩ። ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ፣ የከብቶቼ ኅላፊዎች አድርጋቸው።”7ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ቤተ መንግሥት አግብቶ በፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብ ፈርዖንን ከመረቀው በኋላ 8ፈርዖን፣ “ለመሆኑ ዕድሜህ ምን ያህል ነው?” ሲል ያዕቆብን ጠየቀው። 9ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋር ሲነጻጸር አጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት። 10ከዚያም ያዕቆብ ፈርዖንን መርቆ፣ ተሰናብቶት ወጣ።11ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን በግብፅ እንዲኖሩ አደረገ፤ ፈርዖን በሰጠውም ትእዛዝ መሠረት ምርጥ ከሆነው ምድር ራምሴን በርስትነት ሰጣቸው። 12ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተ ሰዎች በልጆቻቸው ቁጥር ልክ ቀለብ እንዲሰፈርላቸው አደረገ።13በመላው ምድር እህል ባለመኖሩ ራቡ እየጸና ሄደ፤ ከዚህ የተነሣም ግብፅና ከነዓን በራብ እጅግ ተጎዱ፤ 14ዮሴፍ የግብፅና የከነዓን ሰዎች እህል በመሸመት የከፈሉትን ገንዘብ ሁሉ ሰብስቦ ወደ ፈርዖን ቤተ መንግሥት አስገባ።15የግብፅና የከነዓን ሕዝቦችም ገንዘባቸው ባለቀ ጊዜ፣ ግብፃውያን ሁሉ ወደ ዮሴፍ ቀርበው፣ “የምንበላው እህል ስጠን፣ ገንዘባችን አልቆብናል፤ ዓይንህ እያየ እንዴት በራብ እንለቅ?” አሉት። 16ዮሴፍም ከብቶቻችሁን አምጡ፣ ገንዘባችሁ ካለቀ በከብቶቻችህ ለውጥ እህል እሰጣችኋለሁ አለ። 17ስለዚህ ከብቶቻቸውን ወደ ዮሴፍ አምጡ፤ እርሱም በፈረሶቻቸው፣ በበጎቻቸው፣ በፍየሎቻቸው፣ በከብቶቻቸውና በአህዮቻቸው ለውጥ እህል ሰጣቸው። በከብቶቻቸው ልዋጭ ባገኙት ምግብ በዚያ ዓመት ሳይራቡ እንዲያልፉ አደረጋቸው።18ያም ዓመት ካለፈ በኋላ ሕዝቡ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዮሴፍ መጥተው እንዲህ አሉት፣ “እንግዲህ ከጌታችን የምንሰውረው ምንም ነገር የለም፤ ገንዘባችን አልቆአል፤ ከብቶቻችንንም አስረክበንሃል፤ እንግዲህ ለጌታችን የምንሰጠው፣ ከሰውነታችንና ከመሬታችን በቀር ሌላ ምንም ነገር የለንም። 19ታዲያ እያየኸን እንዴት እንለቅ? መሬታችንም ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንና መሬታችንን ውሰድና በለውጡ እህል ስጠን፤ እኛ የፈርዓን አገልጋዮች እንሆናለን፤ መሬታችንም የእርሱ ይሁን፣ እኛም እንዳንሞት መሬታችንም ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው ዘር ስጠን።20ስለዚህ ዮሴፍ የግብፅን ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛለት፤ ራቡም እጅግ ስለጸናባቸው ግብፃውያን ሁሉ መሬታቸውን ሸጡ፣ ምድሪቱም የፈርዖን ርስት ሆነች። 21ዮሴፍ በግብፅ አገር ዳር እስከ ዳር ያሉት ሰዎች ሁሉ የንጉሡ አገልጋዮች እንዲሆኑ አደረገ። 22ሆኖም ዮሴፍ የካህናቱን መሬት አልገዛም፤ ምክንያቱም ካህናቱ ከፈርዖን ቋሚ አበል ስለሚያገኙ እርሱም ከሚሰጣቸው አበል ምግብ ያገኙ ስለነበረ መሬታቸውን አልሸጡም።23ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፣ “እነሆ፣ ዛሬ እናንተንም መሬታችሁንም ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁና ይህን ዘር ወስዳችሁ በመሬት ላይ ዝሩ። 24መከሩ በሚሰበሰብበት ጊዜ ግን ከአምስት እጅ አንዱን ለፈርዖን ታስገባላችሁ፣ ከአምስት እጅ አራቱን ደግሞ ለመሬታችሁ ዘር፣ እንዲሁም ለራሳችሁ፣ ለቤተ ሰቦቻችሁና ለልጆቻችሁ ምግብ ታደርጉታላችሁ።”25እነርሱም፣ “እንግዲህ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤ በጌታችን ፊት ሞገስ ካገኘን ለፈርዖን ገባሮች እንሆናለን” አሉት። 26ስለዚህ ዮሴፍ የምርቱ አንድ አምስተኛ ለፈርዖን እንዲገባ የሚያዝ የመሬት ሕግ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ይሠራበታል። በፈርዖን እጅ ያልገባው መሬት የካህናቱ ብቻ ነው።27በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን በግብፅ አገር በጌሤም ይኖሩ ነበር፣ በዚያም ሀብት ንብረት አፈሩ፤ ቁጥራቸውም እጅግ እየበዛ ይሄድ ጀመር። 28ያዕቆብ በግብፅ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ፣ ዕድሜውም አንድ መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነበር።29እስራኤልም የሚሞትበት ጊዜ መቃረቡን እንደተረዳ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ እጅህን በጭኔ ላይ አኑረህ፣ በጎነትንና ታማኝነትን ልታደርግልኝ ቃል ግባልኝ፤ በምሞትበት ጊዜ በግብፅ አትቅበረኝ፤ 30እኔም ከአባቶቼ ጋር ሳንቀላፋ ከግብፅ አውጥተህ እነርሱ በተቀበሩበት ቦት ቅበረኝ” ዮሴፍም፣ “እሺ፣ እንዳልኸኝ አደርጋለሁ” አለ። 31ያዕቆብ፤ “በል ማልልኝ” አለው። ዮሴፍም ማለለት፣ እስራኤልም በአልጋው ራስጌ ላይ ሆኖ ጎንበስ አለ።
1ከጥቂት ጊዜ በኋላም፣ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ስለተነገረው ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ። 2ለያዕቆብ፣ “ልጅህ ዮሴፍ ወደ አንተ መጥቶአል” ተብሎ በተነገረው ጊዜ፣ እስራኤል ተበረታትቶ አልጋው ላይ ተቀመጠ።3ያዕቆብም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር ሎዛ በምትባል ቦታ ተገለጠልኝ፤ ባረከኝም፤ 4እንዲህም አለኝ፤ ‘ፍሬያማ አደርግሃለሁ፣ ዝርያዎችህም ብዙ ሕዝቦች ይሆናሉ፣ ይህችንም ምድር ለዝርያዎችህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ’ አለኝ።”5ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ የወለድሃቸው ሁለቱ ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ሆነው ይቆጠራሉ፤ ሮቤልና ስምዖን ልጆቼ እንደሆኑ ሁሉ፣ ኤፍሬምና ምናሴም ልጆቼ ይሆናሉ። 6ከእነርሱ በኋላ የሚወለዱልህ ልጆች ግን፣ የአንተ ይሁኑ፤ በርስት ድልድላችው ግን በወንድሞቻቸው ስም ይቆጠራሉ። 7ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ስመለስ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረኝ፤ እናትህ ራሔል በከነዓን ምድር ሞታብኝ አዘንሁ። እኔም ወደ ኤፍራታ ማለት ወደ ቤተ ልሔም በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።”8እስራኤልም የዮሴፍን ልጆች ባየ ጊዜ፣ “እነዚህ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤ 9ዮሴፍም፣ “እነዚህ እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ብሎ መለሰለት፤ እስራኤልም “አቅርባቸውና ልመርቃቸው” አለ። 10በዚህ ጊዜ እስራኤል ዓይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ አቀፋቸው።11እስራኤልም ዮሴፍን፣ “ዓይንህን እንደገና ዐያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ልጆችህን ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው። 12ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጉልበት ፈቀቅ በማድረግ አጎንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ። 13ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተቀኝ ከእስራኤል በስተግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተግራ ከእስራኤል በስተቀኝ በኩል አቀረባቸው።14እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፣ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኩሩ በምናሴ ላይ አኖረ። 15ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ መንገዱን በመከተል ያገለገሉትና ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስ በዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ፣ 16ከጉዳትም ሁሉ የታደገኝ ምልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይስሐቅ ስም ይጠሩ፣ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።17ዮሴፍ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ቅር ተሰኘ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንስቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤ 18ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፣ እንዲህ አይደለም በኩሩ ይህኛው ስለሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው።19አባቱ ግን፣ “ዐውቃለሁ፣ ልጄ ዐውቃለሁ፣ እርሱም እኮ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ፣ ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፤ ዘሮቹም ታላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” ብሎ እምቢ አለው። 20በዚያን ዕለት ባረካቸው፣ እንዲህም አላቸው፤ “እስራኤላውያን በሚመርቁበት ጊዜ የእናንተን ስም በማስታወስ፤ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ’ ይላሉ” በዚህ ሁኔታም ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው።21ከዚህ በኋላ እስራኤል ዮሴፍን እንዲህ አለው፣ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ወደ አባቶቻችሁም ምድር መልሶ ያገባችኋል። 22እነሆ በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራውያን እጅ የወሰድኋትን ምድር ከወንድሞችህ ድርሻ አብልጬ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።”
1ያዕቆብ ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአንድነት ተሰብሰቡና ወደፊት የሚገጥማችሁን ነገር ልንገራችሁ፣ 2እናንተ የያዕቆብ ልጆች፣ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፣ አባታችሁ እስራኤል የሚነግራችሁንም አድምጡ።3ሮቤል፣ ኃይልና የጎልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ የወለድሁህ የበኩር ልጄ ነህ። ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኃይል የምትበልጥ አንተ ነህ። 4ይሁን እንጂ እንደ ውሃ የምትዋልል ስለሆንህ የበላይ አለቅነት ለአንተ አይገባም፣ ምክያንቱም የአባትህን መኝታ ደፍረሃል ምንጣፌንም አርክሰሃል።5“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው፣ ዓመፅ ለመፈጸም የጦር መሣሪያዎቻቸውን ያነሳሉ። 6ወደ ሸንጎአቸው አልግባ፣ ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፣ በቁጣ ተነሣስተው ወንዶችን ገድለዋል፣ የበሬዎችንም ቋንጃ እንደፈለጉ ቆራርጠዋል።7እጅግ አስፈሪ የሆነ ቁጣቸው፣ ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤ በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፣ በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።8ይሁዳ ወንድሞችህ ያመሰግኑሃል፣ እጅህም የጠላቶችህን አንገት አንቆ ይይዛል፣ የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይስግዱልሃል።9ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፣ ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣ እንደ አንበሳ ያደፍጣል በምድርም ላይ ይተኛል፤ እንደ እንስት እንበሳም ያደባል፣ ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?10በትረ መንግስሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤ የገዥነት ምርኩዝም ከእግሮቹ መካከል፣ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለት ‘ሴሎ’ እስኪመጣ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙለታል።11አህያውን በወይን ግንድ፣ ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፣ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጎናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል። 12ዓይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣ ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ።13ዛብሎን በባሕር ዳርቻ ይኖራል፣ የመርከቦቹ መጠጊያም ይሆናል፣ ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።14ይሳኮር፣ አጥንተ ብርቱ አህያ በጭነት መካከል የሚተኛ፣ ማረፊያ ቦታው መልካም፣ 15ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ ትከሻውን ለሸክም ዝቅ ያደርጋል ከባድ የጉልበት ሥራም ይሠራል።16ዳን ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል። 17ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣ የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤ ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣ የፈረሱን ሰኮና ይነክሳል። 18እግዚአብሔር ሆይ፣ ማዳንህን እጠባበቃለሁ።19ጋድን ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፣ እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል። 20አሴር ማዕደ ሰፊ ይሆናል፤ ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል። 21ነጻ እንደተለቀቀች ሚዳቋ ነው፣ የሚያማምሩ ግልገሎች ይኖሩታል።22ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣ በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው። ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ። 23ቀስተኞች በብርቱ ያጠቁታል፤ በቀስታቸውም እየነደፉ ያሳድዱታል፤24ነገር ግን በያዕቆብ ኃያል አምላክ ክንድ፣ እረኛም በሆነው በእስራኤል አለት ቀስቱ ጸና ጠንካራ ክንዱም ቀልጣፋ ሆነ።25አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣ በሚባርክህ ሁሉን በሚችል አምላክ፣ ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣ ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣ ከማኅፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል።26ከጥንት ተራሮች በረከት፣ ከዘላለም ኮረብቶች ምርቃት ይልቅ፣ የአባትይ በረከት ይበልጣል፤ ይህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ።27ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው፤ ያደነውን ማለዳ ይበላል፤ የማረከውን ማታ ያከፋፍላል።28እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው። 29ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እኔ የምሞትበትና ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በኬጢያዊው በኤፍሮን እርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤ 30ይህንን በከነዓን ምድር በመምሬ አጠገብ በማክፌል እርሻ ውስጥ ያለውን ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ የገዛው አብርሃም ነው።31በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤ እኔም ልያን የቀበርኋት እዚያው ነው፤ 32እርሻውና ዋሻው የተገዙት ከኬጢያውያን ላይ ነው።” 33ያዕቆብ እነዚህን ቃላት ለልጆቹ ተናግሮ እንዳበቃ እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ የመጨረሻ ትንፋሹን ተንፍሶ ሞተ፣ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።
1ዮሴፍ እጅግ ከማዘኑ የተነሣ በአባቱ ፊት ተደፍቶ አለቀሰ ሳመውም። 2ከዚያም የአባቱ የእስራኤል አስከሬን እንዳይፈርስ ባለ መድኃኒት የሆኑ አገለጋዮች በመድኃኒት እንዲያሹት አዘዘ። ባለ መድኃኒቶቹም አስከሬኑ እንዳይፈርስ በመድኃኒት አሹት። 3በአገሩ ልማድ መሠረት አስከሬኑ እንዳይፈርስ ማሸቱ አርባ ቀን ወሰደባቸው፤ ገብፃውያንም ሰባ ቀን አለቀሱለት።4የለቅሶው ወራት በተፈጸመ ጊዜ ዮሴፍ የፈርዖንን ባለሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፤ “መልካም ፈቃዳችሁ ቢሆን እባካችሁ ለፈርዖን፣ 5‘አባቴ ለመሞት ሲቃረብ በከነዓን ምድር ባዘጋጀው መቃብር እንድቀብረው በመሐላ ቃል አስገብቶኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ቀብሬ እንድመለስ ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቆአል’ ብላችሁ ንገሩልኝ” አላቸው። 6ፈርዖንም፣ “ባስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው።7ስለዚህ ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ሄደ፣ የፈርዖን ሹማምንት በሙሉ፣ የቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንዲሁም የግብፅ ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖች ሁሉ ተከተሉት። 8እንደዚሁም የዮሴፍ ቤተ ሰቦች ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተ ሰቦች ሁሉ ከዮሴር ጋር ሄዱ፣ በጌሤም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፣ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋዎቻቸው ብቻ ነበሩ። 9እንዲሁም ሠረገሎች፣ ፈረሰኞች አብረውት ወጡ፤ አጀቡም እጅግ ብዙ ነበር።10እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ለቅሶ ተቀመጠ። 11በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ ዐውድማ የተደረገውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ለግብፃውያን መራራ ልቅሶአቸው ነው” አሉ። በዮርዳኖስ አጠገብ ያለው የዚያ ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ተብሎ መጠራቱም ከዚሁ የተነሣ ነበር።12በዚህ ሁኔታ የያዕቆብ ልጆች አባታቸው እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ 13አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦት እንዲሆን ከኬጢያዊው ከኤፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው። 14ዮሴፍ አባቱን ከቀበረ በኋላ ከወንድሞቹና ለቀብር አጅበውት ከሄዱት ሰዎች ሁሉ ጋር ሆኖ ወደ ግብፅ ተመለሰ።15የዮሴፍ ወንድሞች ከአባታቸው ሞት በኋላ፣ “ከፈጸምንበት በደል የተነሣ ዮሴፍ ቂም ይዞ በበቀልን ምን እናደርጋለን ተባባሉ። 16ስለዚህ እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ፣ አባትህ ከመሞቱ በፊት፣ 17‘ለዮሴፍ ወንድሞችህ በአንተ ላይ የፈጸሙትን ኃጢአትና ክፉ በደል ይቅር በላቸው’ ብላችሁ ንገሩት የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። አሁንም የአባትህን አምላክ አገልጋዮች ኃጢአት ይቅር በለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ።18ከዚያም ወንድሞቹ መጡና በፊቱ ተደፍተው፣ “እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን” አሉት። 19ዮሴፍ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፣ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የተቀመጥሁ አይደለሁም፣ 20እናንተ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ አድርጋችሁት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደሚታየው ሁሉ የብዙዎችን ሕይወት ለማዳን ለበጎ ነገር አዋለው። 21አሁንም ቢሆን አትፍሩ፤ ለእናንተና ለልጆቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” በማለት በመልካም ንግግር አረጋጋቸው።22ዮሴፍ ከአባቱ ቤተ ሰቦች ጋር በግብፅ ተቀመጠ፤ አንድ መቶ ዐሥር ዓመትም ኖረ፤ 23የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ ዐየ። ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች በጭኑ ላይ አድርጎ አቀፋቸው።24ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጎበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል። 25እግዚአብሔር በሚጎበኛችሁና ወደዚያች ምድር በሚመልሳችሁ ጊዜ ዐጽሜን ከዚህ ይዛችሁ የምትወጡ መሆናችሁን በማረጋገጥ ቃል ግቡልኝ” ብሎ አስማላቸው። 26ዮሴፍም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሞላው ሞተ፣ አስከሬኑንም መድኃኒት ቀብተው በሬሳ ሳጥን ካስገቡት በኋላ በግብፅ ምድር አስቀመጡት።
1እያንዳንዳቸው ቤተ ሰባቸውን በመያዝ፣ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦ 2ሮሜል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ 3ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ብንያም፣ 4ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር። 5ከያዕቆብ ዘር የተገኙት ሰዎች ሰባ ነበር። ዮሴፍ ቀድሞውኑ በግብፅ ውስጥ ነበረ።6ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ፣ ወንድሞቹ ሁሉና ያ ትውልድ በሙሉ ሞቱ። 7ነገር ግን እስራኤላውያን እየተዋለዱ ሄዱ፤ ቊጥራቸውም እጅግ ጨምሮ በጣም ብርቱዎች ሆኑ፤ ምድሪቱንም ሞሏት።8በግብፅ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ ዐዲስ ንጉሥ ተነሣ። 9ለሕዝቡም እንደዚህ አለ፤ “እስራኤላውያንን ተመልከቷቸው፤ ከእኛ ይልቅ በቍጥር በዝተዋል፤ እጅግም በርትተዋል። 10በቍጥር እየበዙ እንዳይሄዱ፣ ጦርነት ቢነሣም ከጠላቶቻችን ጋር ዐብረው እንዳይወጉንና ምድሪቱ ጥለው እንዳይሄዱ ኑ በዘዴ እርምጃ እንውሰድባቸው።”11በከባድ ሥራ የሚያስጨንቋቸው አሠሪ አለቆችን በላያቸው ሾሙ። እስራኤላውያን ለፈርዖን ፊቶምና ራምሴ የተባሉ የንብረት ማከማቻ ከተሞችን ሠሩ። 12ግን ግብፃውያን እስራኤላውያንን ባስጨነቋቸው ቊጥር፣ እስራኤላውያን በቊጥር እየበዙና በምድሪቱ እየተስፋፉ ሄዱ። ስለዚህ ግብፃውያን እስራኤላውያን መፍራት ጀመሩ።13ግብፃውያን እስራኤላውያንን በጥብቅ እንዲሠሩ አደረጓቸው። 14በሸክላ ሥራና ጭቃ በማስቦካት፣ በዕርሻ ውስጥም ሁሉን ዐይነት ከባድ ሥራ በማሠራት አስመረሯቸው (ሕይወታቸውን መራራ አደረጉባቸው) ። የሚጠበቅባቸው ሥራ ሁሉ ከባድ ነበር።15ከዚያም በኋላ የግብፅ ንጉሥ ሲፓራና ፉሐ የሚባሉ ዕብራውያት አዋላጆችን እንዲህ አላቸው፤ 16“ዕብራውያት ሴቶችን በማማጫው ላይ ስታዋልዱ፣ በሚወልዱበት ጊዜ ተመልከቱ። ወንድ ከተወለደ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።” 17ነገር ግን አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ፈሩ፣ ንጉሡ ያዘዛቸውንም አልፈጸኩም፤ ትእዛዙን በመፈጸም ፈንታ ሕፃናት ወንዶችን በሕይወት እንዲኖሩ አደረጉ።18የግብፅ ንጉሥ አዋላጆቹን ጠርቶ፣ “ለምን ይህን አደረጋችሁ፣ ሕፃናት ወንዶችንስ ለምን አልገደላችኋቸውም?” አላቸው። 19አዋላጆቹም ለፈርዖን፣ “ዕብራውያት ሴቶች እንደ ግብፃውያት ሴቶች አይደሉም። እነርሱ ብርቱዎች ናቸው፣ የሚወልዱትም አዋላጅ ወደ እነርሱ ከመምጣቱ በፊት ነው” በማለት መለሱለት፥20እግዚአብሔር እነዚህን አዋላጆች ጠበቃቸው። ሕዝቡ በቍጥር በዙ፣ እጅግ ብርቱዎችም ሆኑ። 21አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ፣ እግዚአብሔር ቤተ ሰቦችን ሰጣቸው። 22ፈርዖን፣ “የተወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፣ ሴትን ልጅ ግን በሕይወት እንድትኖር ታደርጋላችሁ” በማለት ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
1ከሌዊ ወገን የሆነ አንድ ሰው ሌዋዊት ሴት አገባ፡፡ 2ሴትዮዋ ፀነሰች ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ ሕፃኑ መልከ መልካም መሆኑን ስታይ፣ ሦስት ወር ሸሸገችው፡፡3ከዚያ በላይ ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፣ የደንገል ቅርጫት ወስዳ በዝፍትና በቅጥራን ለቀለቀችው፡፡ ከዚያም ልጁን በውስጡ አስተኝታ ውሃው ውስጥ በቄጠማው መካከል በወንዙ ዳርቻ አስቀመጠችው፡፡ 4የሚያጋጥመውን ለማየት የሕፃኑ እኅት በርቀት ቆማ ነበር፡፡5ጠባቂዎቿ በወንዙ ዳር እየሄዱ ሳለ፣ የፈርዖን ልጅ በወንዙ ለመታጠብ ወረደች፡፡ ልዕቲቱ ቅርጫቱን በቄጠማዎች መካከል አየችው፡፡ ቅርጫቱን እንዲያመጣላት ጠባቂዋን ላከች፡፡ 6ቅርጫቱን ስትከፍተው፣ ሕፃኑን አየች፡፡ እነሆ፣ ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፡፡ ራራችለትና፣ «ይህ በእርግጥ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው» አለች፡፡7 ከዚያም በኋላ የሕፃኑን እኅት የፈርዖንን ልጅ፣ «ልሂድና ሕፃኑን የምታሳድግልሽ ዕብራዊት ሴት ልፈልግልሽ?» አለቻት፡፡ 8የፈርዖንም ልጅ «ሂጂ» አለቻት፡፡ ወጣቷም ልጅ ሄዳ የሕፃኑን እናት አመጣች፡፡9የፈርዖን ልጅ የሕፃኑን እናት፣ «ይህ ሕፃን ውሰጅና አሳድጊልኝ፤ ደሞዝ እከፍልሻለሁ» አለቻት፡፡ ሴትዮዋም ሕፃኑን ወስዳ አሳደገችው፡፡ 10ሕፃኑ ባደገ ጊዜም ወደ ፈርዖን ልጅ አመጣችው፤ የልዕልቲቱም ልጅ ሆነ፡፡ «ከውሃ አውጥቼዋለሁና» ብላም ስሙን ሙሴ አለችው፡፡11ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወገኖቹ ሄዶ የሚሠሩትን ከባድ ሥራ ተመለከተ፡፡ ከገዛ ወገኖቹ መካከል አንዱን ዕብራዊ አንድ ግብፃዊ ሲደበድበው አየ፡፡ 12ግራና ቀኙን ተመልክቶ ማንም አለመኖሩን ሲያረጋግጥ፣ ግብፃዊውን ገድሎ በአሸዋ ውስጥ ደበቀው፡፡13ቀን ሙሴ ወደ ውጭ ወጣ፤ እነሆም ሁለት ዕብራውያን ወንዶች እየተጣሉ ነበር፡፡በደለኛ የነበረውን ሰውየ፣ «ባልንጀራህ ለምን ትደበድበዋለህ?» አለው፡፡ 14ሰውየው ግን፣ «አንተን በእኛ ላይ አለቃና ዳኛ ማን አደረገህ? ያን ግብፃዊ እንድ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ታስባለህ?» አለ፡፡ ሙሴም ፈራና፣ «ያደረግሁት በሌሎች ሰዎች ዘንድ በእርግጥ ታውቋል» አለ፡፡15ስለ ጉዳዩ ሲሰማ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ፡፡ ነገር ግን ከፈርዖን ሸሽቶ በምድያም አገር ኖረ፡፡ እዚያም በአንድ የውሀ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፡፡16ካህን ሰባት ሴት ልጆች ነበሩት፡፡ እነርሱም ወደ ጉድጓዱ መጥተው ውሀ ቀዱ፣ የአባታቸውን መንጋ ለማጠጣትም ገንዳውን ሞሉት፡፡ 17መጥተው ሊያባርሯቸው ሞከሩ፣ ነገር ግን ሙሴ ሄዶ ዐገዛቸው፡፡ መንጋቸውንም አጠጣላቸው፤18ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤል ሲሄዱም፣ አባታቸው፣ «ዛሬ እንዴት ቶሎ ወደ ቤት መጣችሁ?» አለ፡፡ 19«አንድ ግብፃዊ ከእረኞች አዳነን፤ ውሀም ቀድቶ መንጋውን አጠጣልን» አሉ፡፡ 20ልጆቹን፣ «ታዲያ የት አለ?» ሰውየውን ለምን ተዋችሁት? ምግብ ከእኛ ጋር እንዲበላ ጥሩት» አላቸው፡፡21ሲፓራን እንዲያገባትም እንኳ ከሰጠው ሰውየ ጋር ለመኖር ሙሴ ተስማማ፡፡ 22ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም፣ «የባዕድ ምድር ኗሪ ነኝ» ሲልም ስሙን ጌርሳም አለው፡፡23 ከረጅም ጊዜ በኋላ፣ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፡፡ እስራኤላውያን ከባርነት ሥራ የተነሣ አለቀሱ፣ ለርዳትም ጮኹ፤ ከባርነት ቀበራቸው የተነሣም ያሰሙት ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ወጣ፡፡ 24እግዚአብሔር ልቅሶአቸውን ሲሰማ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳኑን ዐሰበ፡፡ 25እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አየ፤ ሁኔታቸውንም ተረዳ፡፡
1ሙሴ የምድያምን ካህን፣ የዐማቱን የየቶርን በጎች ጠብቅ ነበር፡፡ በጎቹን ወደ ምድረ በዳው ዳርቻ ነድቶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ ደረሰ፡፡ 2በዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቊጥቋጦ ውስጥ በእሳት ነበልባል ተገለጠለት፡፡ ሙሴ ተመለከተ፣ እነሆም ቊጥቋጦው እየተቀጣጠለ ነበር፤ ነገር ግን ቊጥቋጦው አልተቃጠለም፡፡ 3ሙሴም፣ «ልቅረብና ቊጥቋጦው ለምን እንዳልተቃጠለ ይህን አስደናቂ ነገር ልይ» አለ፡፡4ሊመለከት እንደ ቀረበ እግዚአብሔር ሲያየው፣ ከቊጥቋጦው ውስጥ ጠራው፤ «ሙሴ፣ ሙሴ» አለውመ፡፡ ሙሴም፣ «እነሆኝ» አለ፡፡ 5እግዚአብሔር፣ «አትቅረብ! የቆምህበት ምድር ለእኔ ተቀድሶአልና ጫማህን አውልቅ» አለው፡፡ 6ደግሞም፣ «እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ» አለው፡፡ ከዚያም በኋላ ሙሴ እግዚአብሔርን ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ፡፡7እንዲህ አለ፤ «በግብፅ የሚኖሩትን የሕዝቤን ሥቃይ በእርግጥ አይቻለሁ፡፡ አሠሪ አለቆቻቸው ከሚያደርሱባቸው ጭቈና የተነሣ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ስለ ሥቃያቸው ዐውቃለሁና፡፡ 8ከግብፃውያን አገዛዝ ነጻ ላወጣቸውና ከዚያም ጋር አውጥቼ ማርና ወተት ወደምታፈሰው መልካምና ለም ወደሆነችው፤ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያንን፣ ፌርዛውያን፣ ኤውያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ላሰገባቸው ወርጃለሁ አለ፡፡9የእስራል ሕዝብ ጩኸት ወደ እኔ ደርሶአል፡፡ ይልቁንም ግብፃውያን ያደረሱባቸውን ጭቈና አይቻለሁ፡፡ 10ስለዚህ ሕዝቤን፣ እስራኤላውያንን ከግብፅ እንድታወጣ ወደ ፈርዖን እልክልሃለሁ፡፡»11ግን፣ እግዚአብሔርን «ወደ ፈርዖን የምሄድና እስራኤላውያንን ከግብፅ የማወጣቸው እኔ ማን ነኝ?» አለው፡፡ 12ሙሴን መልሶ፣ «እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፡፡ ይህ እኔ እንደ ላክሁህ ምልክት ይሆናል፡፡ ሕዝቡን ከግብፅ ስታወጣቸው፣ በዚህ ተራራ ላይ ታመልኩኛላችሁ» አለው፡፡13ሙሴም እግዚአብሔርን፣ «ወደ እስራኤላውያን ስሄድና ‹የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል› ብዬ ስነግራቸው፣ እነርሱም፣ «ስሙ ማን ነው? ሲሉኝ ምን እነግራቸዋሉ? አለው፡፡ 14እግዚአብሔርም ሙሴን፣ «እኔ ያለሁ የምኖርም ነኝ፡፡ ያለና የሚኖር ወደ እናንተ ልኮኛል ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው» አለው፡፡ 15ደግሞም እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል፡፡ ስሜ ለዘለዓለም ይህ ነው፤ ለትውልዶች ሁሉ የታስበውም በዚህ ነው ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው፡፡»16ሂድና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ለእኔ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፣ «ጐብኝቻችኋለሁ፤ በግብፅ ውስጥ የደረሰባችሁንም አይቻለሁ፡፡ 17በግብፅ ከደረሰባችሁ ጭቈና ነጻ ላወጣችሁና ማርና ወተት ወደምታፈሰው ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፌርዛውያን፣ ወደኤዊያውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ላገባችሁ ቃል ገብቻለሁ፡፡» 18ሽማግሌዎቹም ይሰሙሃል፡፡ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ሂዱና፣ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገለጠልን፡፡ ስለዚህም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት እንድንችል በምድረ በዳው ውስጥ የሦስት ቀን ጕዞ እንሂድ በሉት፡፡19ነገር ግን የግብፅ ንጉሥ እጁ ካልተገደደ በቀር ለመሄድ እንደማይፈቅድላችሁ ዐውቃለሁ፡፡ 20በመካከላቸው በማድረጋቸው ተአምራት ሁሉ ግብፃውያንን እመታቸዋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ፣ እንድትሄዱ ይፈቅድላችኋል፡፡ 21ሕዝብ ከግብፃውያን ዘንድ መወደድን እንዲያገኝ አደርጋለሁ፣ ስለዚህ ስትወጡ፣ ባዶ እጃችሁን አትወጡም፡፡ 22ሴት ከግብፃውያት ጎረቤቶቿና በጎረቤቶቿ ቤቶች ውስጥ ከምትኖር ማንኛውም ሴት የብርና የወርቅ ጌጣጌጦች፣ ልብስም እንዲሰጣት ትጠይቃለች፡፡ እነርሱንም በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጓቸዋላችሁ፡፡ ግብፃውያንን በዚህ መንገድ ትበዘብዟቸዋላችሁ፡፡
1ሙሴም መልሶ፣ «ባያምኑኝስ ወይም ባይሰሙኝ ነገር ግን በምትኩ፣ እግዚአብሔር አልተገለጠልህም» ቢሉኝስ? 2እግዚአብሔር ሙሴን፣ «በእጅህ ያለው ምንድን ነው?» አለው፡፡ ሙሴም «በትር» አለ፡፡ 3እግዚአብሔር፣ «መሬት ላይ ጣለው» አለው፡፡ ሙሴም በትሩን መሬት ላይ ጣለው፤ በትሩም እባብ ሆነ፡፡ ሙሴ ከእባቡ ሸሸ፡፡4እግዚአብሔር ሙሴን፣ «እጅህን ዘርግተህ የእባቡን ጅራት ያዝ» አለው፡፡ ሙሴም እጁን ዘረገና እባቡን ያዘው፡፡ እባቡ በእጁ ላይ እንደ ገና በትር ሆነ፡፡ 5«ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር የተገለጠልህ መሆኑን እነዲያምኑ ነው፡፡»6ደግሞም እግዚአብሔር ሙሴን፣ «እጅህን በብትህ ውስጥ አግባ» አለው፡፡ እጁን ሲያወጣው እነሆ፣ እንደ በረዶ ነጽቶ ለምጽ ሆኖአል፡፡ 7እግዚአብሔር፣ «እጅህን እንደ ገና በብብትህ ውስጥ አግባ» አለው፡፡ ሙሴም እጁን በብብቱ ውስጥ አገባ፣ ከብብቱ ሲወጣውም እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆኖ አየው፡፡8እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ «ባያምኑህ፣ የመጀመሪያውን የተአምር ምልክት ባይቀበሉ ወይም ባያምኑበት፣ ሁለተኛውን ያምናሉ፡፡ 9እነዚህን ሁለት የተአምር ምልክቶች ባያምኑም እንኳ፣ ወይም ባይሰሙህ፣ ከወንዙ ጥቂት ውሀ ወስደህ በደረቁ መሬት ላይ አፍስሰው፡፡ ያፈሰስኸውም ውሀ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል፡፡»10እግዚአብሔርን፣ «ጌታ ሆይ፣ በፊትም፣ አንተ ለባሪያህ ከተናገርህ ወዲህም ርቱዕ አንደበት ያለኝ አይደለሁም፡፡ ኮልታፋና ንግግር የማልችል ሰው ነኝ» አለው፡፡ 11እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የሰውን አንደበት የፈጠረ ማን ነው? ሰውን ዲዳ ወይም ደንቈሮ ወይም እንዲያይ ወይም እንዲታወር የሚያደርግስ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለምን? 12አሁን ሂድ፤ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፤ ምን እንደምትናገርም አስተምርሃለሁ፡፡» 13ሙሴ ግን፣ «ጌታ ሆይ፣ እባክህ ልትልከው የምትፈልገውን ሌላ ሰው ላክ» አለ፡፡14በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ተቈጣው፡፡ እንዲህም አለው፤ «ሌዋዊው ወንድምህ አሮንስ? እርሱ በሚገባ መናገር እንደሚችል ዐውቃለሁ፡፡ እንዲያውም ከአንተ ጋር ለመገናኘት እየመጣ ነውና ሲያይህ በልቡ ደስ ይሰኛል፡፡ 15አንተ ለእርሱ ትናገራለህ፤ የሚናገራቸውንም ቃላት በአፉ ውስጥ ታስቀምጣለህ፡፡ እኔ በአፍህና በአፉ እሆናለሁ፣ ምን እነደምታደርጉም አሳያችኋለሁ፡፡ 16ለሕዝቡ ይናገርልሃል፡፡ እርሱ የአንተ አፍ ይሆናል፤ አንተም ለእርሱ እንደ እኔ፣ አምላክ ትሆነዋህ፡፡ 17ይህን በትር በእጅህ ትይዛለህ፣ በእርሱም ተአምራትን ታደርጋለህ፡፡»18ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የቶር ተመልሶ ሄደ፤ «ግብፅ ውስጥ ወዳሉት ዘመዶቼ ተመልሼ እንድሄድና አሁንም ድረስ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ» አለው፡፡ ዮቶርም ሙሴን፣ «በሰላም ሂድ» አለው፡፡ 19ምድያም ውስጥ እያለ እግዚአብሔር «ሂድ፣ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ ሊገድሉህ የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ሞተዋል» አለው፡፡ 20መሴም ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ፣ በአህያ ላይም አስቀምጦ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ የእግዚአብሔርን በትርም በእጁ ይዞ ነበር፡፡21ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ወደ ግብፅ ተመልሰህ ስትሄድ፣ በእጅህ ያስቀመጥኋቸውን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት እንደምታደርግ ዐስብ፡፡ ነገር ግን እኔ ልቡን አደነድነዋለሁ፤ ሕዝቡ እንዲሄዱም አይፈቅድም፡፡ 22እንዲህ ብለህ ንገረው፤ «እግዚአብሔር እየተናገረ ያለው ይህን ነው፤ እስራኤል ልጄ፣ በኵሬ ነው፤ 23«እንዲያመልከኝ ልጄን ልቀቅ ብዬ እነግርሃለሁ፡፡» ነገር ግን ለመልቀቅ እምቢ ስላለህ፣ በኵር ልጅህን እገድላለሁ፡፡»24ላይ ለምሽቱ ዐርፈው ሳለ፣ እግዚአብሔር ሙሴን አግንኝቶ ሊገድለው ነበር፡፡ 25ግን ስለታም ቢላዋ ይዛ የልጇን ሸለፈት ገረዘች፤ እግሩንም አስነካችው፡፡ ከዚያም በኋላ «አንተ ለእኔ በእውነት የደም ሙሽራዬ ነህ» አለች፡፡ 26እግዚአብሔር ሙሴን ተወው፡፡ «አንተ የደም ሙሽራ ነህ» ብላ የተናገረችው በግርዘቱ ምክንያት ነው፡፡27አሮንን፣ «ወደ ምድረ በዳ ሂድና ከሙሴ ጋር ተገናኝ» አለው፡፡ አሮን ሄደ፣ ሙሴንም በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አግኝቶ ሳመው፡፡ 28እንዲናገር የላከለትን የእግዚአብሔር ቃሎች ሁሉና እንዲፈጽማቸው ያዘዘውን ተአምራት በሙሉ ለአሮን ነገረው፡፡29በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ፡፡ 30እግዚአብሔር ተአምራትም በሕዝቡ ፊት አሳየ፡፡ 31አመኑ፡፡ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን የጐበኛቸውና የደረሰባቸውን ጭቈና የተመለከተ መሆኑን ሲሰሙም ሰገዱ፣ አመለኩትም፡፡
1እነዚህ ነገሮች ከሆኑ በኋላ፣ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ እንደዚህ አሉ፤ «የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹በምድረ በዳው ለእኔ በዓል እንዲያደርጉ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡»› 2ፈርዖንም፣ «እግዚአብሔር ማን ነው? ቃሉን የምሰማው፣ እስራኤልንስ የምለቅ ለምንድን ነው? እግዚአብሔርን አላውቀውም፤ እስራኤልንም አልለቅም» አለ፡፡3ሙሴና አሮንም፣ «የዕብራውያን አምላክ ከእኛ ጋር ተገናኝቶአል፡፡ በመቅሠፍትና በሰይፍ እንዳይመታን፣ ወደ ምድረ በዳው የሦስት ቀን ጕዞ እንድናደርግና ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ ፍቀድልን» አሉት፡፡ 4የግብፅ ንጉሥ ግን፣ «አንተ ሙሴ አንተም አሮን! ሕዝቡን ሥራቸውን አስፈትታችሁ የምትወስዷቸው ለምንድን ነው? ወደ ሥራችሁ ሂዱ» አላቸው፡፡ 5እንዲህ አላቸው፤ «በምድራችን አሁን ብዙ ዕብራውያን አሉ፤ እናንተም ሥራ ታስፈቷቸዋላችሁ፡፡»6በዚያው ቀን ፈርዖን ለሕዝቡ አሠሪዎችና ተቈጣጣሪዎች ትእዛዝ ሰጠ፡፡ እንዲህም አለ፤ 7«እንደ ቀድሞው፣ ከእንግዲህ ወዲያ ለሸክላ ሥራ ጭድ አታቅርቡ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ይሂዱና ጭድ ይሰብስቡ፡፡ 8ሆኖም በፊት የሚሠሩትን አንድ ዐይነት የሸክላ ቊጥር አሁንም ሠርተው እንዲያቀርቡ ማድረግ አለባችሁ፡፡ ከዚያ ያነሰ አትቀበሉ፤ ምክንያቱም ሰነፎች ናቸው፡፡ ‹እንሂድ ፍቀድልንና ለአምላካችን እንሠዋ› እያሉ የሚጮኹትም ለዚህ ነው፡፡ 9እንዲተጉና ለማይረባ ንግግር ትኵረት እንዳይሰጡ ሥራውን ጨምራችሁ አክብዱባቸው፡፡»10ስለዚህ የሕዝቡ አሠሪ አለቆችና ተቈጣጣሪዎች ወጥተው ሄዱ፤ ለሕዝቡም ነገሯቸው፡፡ እንዲህም አሉ፤ «ፈርዖን የሚለው ይህ ነው፡- ‹ከእንግዲህ ወዲያ ምንም ጭድ አልሰጣችሁም፡፡ 11ሂዱና ማግኘት ከምትችሉበት ፈልጋችሁ አምጡ፤ የሥራችሁ መጠንም አይቀላለም፡፡»12ሕዝቡ በጭድ ፈንታ ገለባ ለመሰብሰብ በግብፅ ምድር ሁሉ ተሠራጩ፡፡ 13አለቆቹ፣ «ጭድ በሚቀርብላችሁ ጊዜ የምትሠሩትን ሥራችሁን ጨርሱ» ይሏቸውና ያስጠነቅቋቸው ነበር፡፡» 14ፈርዖን የመደባቸው አሠሪ አለቆች የሠራተኞች ተቈጣጣሪ ያደረጓቸውን እስራኤላውያን ኀላፊዎች ገረፏቸው፡፡ አሠሪ አለቆቹ፣ «በፊት ታደርጉት እንደ ነበረው፣ ትናንትናም ዛሬም የሚጠበቅባችሁን ሸክላ በሙሉ ሠርታችሁ ያላቀረባችሁ ለምንድን ነው?» እያሉ ይጠይቋቸው ነበር፡፡15እስራኤላውያን ተቈጣጣሪዎቹም ወደ ፈርዖን መጥተው አቤቱታ አቀረቡ፡፡ እንደዚህም አሉት፤ «ባሪያዎችህን በዚህ መንገድ ለምን እንድንኖር ታደርጋለህ? 16ጭድ አይሰጡንም፤ ነገር ግን አሁንም ‹ሸክላ ሥሩ!› ይሉናል፡፡ እኛ ባሪያዎችህ ተገርፈናልም፤ ስሕተቱ ግን የገዛ ሕዝብህ ነው፡፡» 17ግን እንዲህ አለ፤ «እናንተ ሰነፎች! እናንተ ሰነፎች! ‹ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ ፍቀድልን› ትላላችሁ፡፡ 18ወደ ሥራ ተመለሱ፡፡ አንዳችም ጭድ አይሰጣችሁም፤ ነገር ግን አሁንም ያንኑ የሸክላ ቊጥር መሥራት አለባችሁ፡፡»19«የየቀኑን የሸክላ ቊጥር መቀነስ የለባችሁም» የሚለው ሲነገራቸው፣ እስራኤላውያን ተቈጣጣሪዎች ችግር ውስጥ እንደ ነበሩ አስተዋሉ፡፡ 20ከፈርዖን ዘንድ ሲወጡ፣ ከቤተ መንግሥቱ ውጭ ቆመው ከነበሩት ከሙሴና ከአሮን ጋር ተገናኙ፡፡ 21ለሙሴና ለአሮንም እንዲህ አሏቸው፣ «እግዚአብሔር ይይላችሁ፣ ይፍረድባችሁም፤ ምክንያቱም በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት አስጸያፊዎች እንድንሆን አድርጋችሁናል፡፡»22ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፣ «ጌታ ሆይ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ እንዲደርስበት ያደረግህ ለምንድን ነው? እኔንስ ቀድሞውኑ ለምን ላክኸኝ? 23ስም ልነግረው ወደ ፈርዖን ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ አምጥቶአል፤ አንተም ሕዝብህን ከቶ ነጻ አላወጣኸውም» አለው፡፡
1ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን፣ «በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ይለቃቸዋልና፣ ይህን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ከምድሩ ያስወጣቸዋል» አለው፡፡2ለሙሴ እንዲህ አለው፤ «እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ 3እኔ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን በስሜ፣ በእግዚአብሔር ለእነርሱ አልታወቅሁላቸውም ነበር፡፡ 4የተሰደዱባትን፣ በእንግድነት የኖሩባትን የከነዓንን ምድር ልሰጣቸው፣ ከእነርሱ ጋር ኪዳን አጽንቻለሁ፡፡ 5ደግሞም ግብፃውያን ባሪያ ያደረጓቸውን የአስራኤላውያንን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ፡፡6ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ በግብፃውያን ሥር ከምትኖሩባት ባርነት እታደጋችኋለሁ፤ ከአገዛዛቸውም ነፃ አወጣችኋለሁ፡፡ በታላቅ ፍርድና ኀይሌን በማሳየት እታደጋችኋለሁ፡፡ 7አድርጌ ወደ ራሴ እወስዳችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፡፡ ግብፃውያን ከጫኑባችሁ ባርነት ነፃ ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡8ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ልሰጥ ቃል ወደገባሁባት ምድር አስገባችኋለሁ፡፡ ምድሪቱን ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡» 9ይህን ለእስራኤላውያን በነገራቸው ጊዜ፣ በአስከፊው ባርነታቸው ተስፋ ከመቊረጣቸው የተነሣ አላደመጡትም፡፡10ሙሴን እንዲህ አለው፤ 11ሂድና ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን የእስራኤልን ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቅ ንገረው፡፡ 12ሙሴም እግዚአብሔርን፣ «ተብታባ በመሆኔ እስራኤላውያን ካልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል? 13እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አናገራቸው፡፡ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር እንዲያስወጡ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖንና ስለ እስራኤላውያንም ትእዛዝ ሰጣቸው፡፡14የአባቶቻቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል በኵር ልጅ የሮቤል ልጆች ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮንና ከርሚ ነበሩ፡፡ እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው፡፡ 15የስምዖን ልጆች ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ዱሐርና የከነዓናዊቷ ሴት ልጅ ሳኡል ነበሩ፡፡ እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው፡፡16የሌዊ ልጆች ስሞች ከትውልዶቻቸው ጋር እነዚህ ናቸው፤ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ነበሩ፡፡ ሌዊ መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፡፡ 17የጌድሶን ልጆች ሉቤኒና ሰሜኢ ነበሩ፡፡ 18የቀዓት ልጆች እንበረም፣ ይሰዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፡፡ ቀዓት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ኖረ፡፡ 19የሜራሪ ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ፡፡ እነዚህ በትውልዶቻቸው መሠረት፣ የሌዋውያን የነገድ አባቶች ሆኑ፡፡20የአባቱን እኅት ዮካብድን አገባ፤ እርሷምአሮንንና ሙሴን ወለደችለት፡፡ እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖሮ ሞተ፡፡ 21የይስዓር ልጆች ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ፡፡ 22ልጆች ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ፡፡23የአሚካዳብን ልጅ፣ የነኦሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፡፡ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢተምርን ወለደችለት፡፡ 24የቆሬ ልጆች አሴር፣ ሕልቃናና አብያሳፍ ነበሩ፡፡ እነዚህ የቆሬ ነገድ አባቶች ናቸው፡፡ 25ልጅ አልዓር ከፏትኤል ልጆች አንዲቱን አገባ፡፡ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት፡፡ እነዚህ በየትውልዶቻቸው የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናቸው፡፡26ሁለት ሰዎች፣ «እስራኤላውያንን በየተዋጊ ሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አውጡ» ብሎ እግዚአብሔር ያዘዛቸው አሮንና ሙሴ ነበሩ፡፡ 27ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ለማውጣት እንዲፈቅድላቸው ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ተናገሩ፡፡ እነዚህ ሙሴና አሮን እነዚያው ራሳቸው ነበሩ፡፡28እግዚአብሔር በግብፅ ውስጥ ሙሴን ባናገረው ጊዜ፣ 29«እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው» አለው፡፡ 30ግን እግዚአብሔርን፣ «እኔ ተብታባ ነኝ፤ ፈርዖን ታዲያ እንዴት ይሰማኛል? አለው፡፡
1ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ልብ በል፤ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አድርጌሃለሁ፡፡ ወንድምህ አሮን ነቢይህ ይሆናል፡፡ 2እንድትናገር ያዘዝሁህን ሁሉ ትናራለህ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቀ፣ ወንድምህ አሮን ለፈርዖን ይናገራል፡፡3ነገር ግን እኔ የፈርዖንን ለብ አደነድነዋሁ፤ የተአምራቴን ብዙ ምልክቶች፣ ብዙ ድንቆችም በግብፅ ምድር አሳያለሁ፡፡ 4ነገር ግን ፈርዖን አይሰማችሁም፤ ስለዚህ እጄን በግብፅ ላይ አደርጋሁ፤ ሰራዊቱን፣ ሕዝቤን፣ የእስራኤልን ልጆች በታላቅ ፍርድ ከግብፅ ምድር አወጣለሁ፡፡ 5በግብፅ ላይ ስዘረጋና እስራኤላውያንን ከመካከላቸው ሳወጣ፣ ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፡፡»6አሮን እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ፈጸሙ፡፡ 7ባጋገሩት ጊዜ፣ የሙሴ ዕድሜ ሰማንያ፣ የአሮን ደግሞ ሰማንያ ሦስት ነበር፡፡8ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ 9‹ተአምር አሳዩ› ሲላችሁ፣ አሮንን እንዲህ በለው፤ ‹በትርህን ውሰድና በፈርዖን ፊት ጣለው፤ እባብም ይሀናል፡፡»› 10ሙሴ አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ እግዚአብሔር አዝዞአቸው የነበረውን አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት ጣለው፤ እባብም ሆነ፡፡11ደግሞ ለጥበበኛ ሰዎቹና ለጠንቋዮቹ ጥሪ አደረገ፡፡ እነርሱም በምትሀታቸው ያንኑ አደረጉ፡፡ 12እያንዳንዱ ሰው በትሩን ጣለ፤ በትሮቹም እባብ ሆኑ፣ ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን እባቦች ዋጣቸው፡፡ 13አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ አልሰማምም፡፡14እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የፈርዖን ልብ ደንድኖአል፤ ሕዘቡም እንዲሄዱ አይፈቅድም፡፡ 15ወደ ውሃው በሚሄድበት ጊዜ፣ በጠዋት ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እንዳገኘውም በወንዙ ዳር ቁም፤ ወደ እባብነት ተለውጦ የነበረውን በትርህን ውሰድ፡፡16እንዲህ በለው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን እንድናገር ወደ አንተ ላከኝ፤ «በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፤ እስካሁን ድረስ አልሰማህም፡፡» 17የሚናገረው ይህ ነው፤ «እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፡፡ የአባይን ወንዝ ውሀ በእጄ በያዝሁት በትር እመታዋለሁ፣ ወንዙም ወደ ደምነት ይለወጣል፡፡ 18ውስጥ የሚገኙት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙ ይከረፋል፡፡ግብፃውያኑም ከወንዙ ውሀ መጠጣት አይችሉም፡፡»19ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ አሮንን፣ ‹በትርህን ውሰድና ውሀቸው ደም እንዲሆን፣ በግብፅ ውሀዎች ላይ፣ በወንዞቻቸውም፣ በምንጮቻቸውም፣ በውሀ ማጠራቀሚያዎቻቸውና በኩሬዎቻቸው ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ ብለህ ንገረው፡፡ በመላው የግብፅ ምድር፣ ከዕንጨትና ከድንጋይ በተሠሩ ውሀ መያዣዎች ያለው ውሀም እንኳ ደም እንዲሆን ይህን አድርግ፡፡»›20ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን አንሥቶ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት የወንዙን ውሀ መታው፡፡ የወንዙ ውሀ በሙሉ ወደ ደምነት ተለወጠ፡፡ 21ውስጥ ያለው ዓሣ ሞተ ወንዙም መከርፋት ጀመረ፡፡ ግብፃውያኑ ከወንዙ ውሀ መጠጣት አልቻም፤ ደሙም በግብፅ ምድር በየትኛውም ስፍራ ነበረ፡፡ 22የግብፅ ጠንቋዮችም በምትሀታቸው ያንኑ ዐይነት ነገር አደረጉ፡፡ ስለዚህ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እግዚአብሔር ይሆናለ ብሎ ተናግሮት እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን ለመስማት እምቢ አለ፡፡23ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ለዚህ ጉዳይ ትኵረትም እንኳ አልሰጠም፡፡ 24ግብፃውያኑ ሁሉ በወንዙ ዙሪያ የሚጠጣ ውሀ ለማግኘት ቈፈሩ፤ ነገ ርግን የወንዙን ውሀ መጠጣት አልቻሉም፡፡ 25እግዚአብሔር ወንዙን ከመታው በኋላ ሰባት ቀን ዐለፈ፡፡
1ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ በለው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡ 2ካልህ፣ አገርህን በሙሉ በጓጕንቸው መቅሠፍት እመታዋለሁ፡፡ 3ጓጕንቸር ይርመሰመሳል፡፡ ጓጕንቸሮቹ ከወንዙ ይወጡና ወደ ቤትህ፣ ወደ መኝታ ክፍልህና ወደ ዐልጋህ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ አገልጋዮችህም ቤቶች ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ ሕዝብህ፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሃቆችም ይዛመታሉ፡፡ 4ጓጕንቸሮቹ አንተን፣ ሕዝብህንና አገልጋዮችህን ሁሉ ይመታሉ፡፡»5ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «አሮንን፣ እጅህንና በትርህን በወንዞች፣ በምንጮችና በቦዮች ላይ ዘርጋና በግብፅ ምድር ላይ ጓጕንቸሮች እንዲወጡ አድርግ» በለው፡፡ 6በግብፅ ውሆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕንቸዎቹም ወጥተው የግብፅን ምድር ሸፈኑት፡፡ 7ጠንቋዮቹም በምትሃቸው ያንኑ አደረጉ፤ ጓጕንቸሮቹ በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አደረጉ፡፡8ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ «ጓጕንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ላይ አንዲያስወግድ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፡፡ ከዚያም ለእግዚአብሔር እንዲሠዉ ሕዝቡን እለቃቸዋለሁ» አላቸው፡፡ 9ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ «ጓጕንቸሮቹ ከአንተና ከቤቶችህ እንዲወገዱ፣ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን እንዲቈዩ፣ ለአንተ፣ ለአገልጋዮችህና ለሕዝብህ የምጸልይበትን ጊዜ ለእኔ መንገሩ የአንተ ድርሻ ነው፡፡»10«ነገ» አለው፡፡ ሙሴም ፈርዖንን መልሶ፣ «እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ እንድታውቅ አንተ እንደምትለው ይሁን፡፡ 11ጓጕንቸሮቹ ከአንተ፣ ከቤቶችህ ከአገልጋዮችህና ከሕዝብህ ይወገዳሉ፡፡ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን ይቈያሉ» አለው፡፡ 12አሮን ከፈርዖን ወጥተው ሄዱ፡፡ ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖን ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፡፡13ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- ጓጕንቸሮቹ በየቤቱ፣ በየግቢውና በየሜዳው ሞቱ፡፡ 14ሕዝቡ የሞቱትን ሰብስበው ከመሯቸው፤ ምድሩም ከረፋ፡፡ 15ነገር ግን ፈርዖን ፋታ መገኘቱን ሲያይ፣ ልቡን አደነደነ፤ እንደዚህ ያደርጋል ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ እንድ ነበረ፣ ሙሴንና አሮንንም አልሰማቸውም፡፡16ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «አሮንን እንዲህ በለው ‹በመላው የግብፅ ምድር ተባይ እንዲሆን የምድሩን ትቢያ በበትርህ ምታ፡፡» 17እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፡- አሮን እጁን ዘርግቶ በበትሩ የምድሩን ትቢያ መታው፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባይ መጣ፡፡ የምድሩ ትቢያ ሁሉ በመላው የግብፅ ምድር ተባይ ሆነ፡፡18በምትሃቸው ተባይ እንዲመጣ ሙከራ አደረጉ፤ ነገር ግን አልቻም፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባዮች ነበሩ፡፡ 19ጠንቋዮቹ ታዲያ ፈርዖንን፣ «ይህ የእግዚአብሔር ጣት ነው» አሉት፡፡ ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እነርሱንም ለማድመጥ እምቢ አለ፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንዲህ እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ተናግሮት በነበረው መሠረት ነው፡፡20እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በማለዳ ተነሣና ፈርዖን ወደ ወንዙ ሲወጣ በፊት ለፊቱ ቁም፡፡ እንደዚህም ብለህ ንገረው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡ 21የማትለቅ ከሆነ ግን፣ በአንተ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ፣ ወደ ቤቶችህም ውስጥ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፡፡ የግብፃውያን ቤቶች በዝንብ መንጋ ይሞላሉ፤ የሚቆሙበት ምድርም እንኳ ዝንብ ብቻ ይሆናል፡፡22ግን በዚያ ቀን የዝንብ መንጋ እንዳይገኝባ፣ ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሤምን ምድር በተለየ ሁኔታ እይዛታለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር በዚህ ምድር እንዳለሁ እንድታውቅ ይህ ይሆናል፡፡ 23በሕዝቤና በሕዝብህ መካከል ልዩነት እንዲኖር አደርጋለሁ፡፡ ይህ ተአምራዊ ምልክት ነገ ነው የሚሆነው፡፡» 24እግዚአብሔር እንዲሁ አደረገ፤ ጥቅጥቅ ያለ የዝንብ መንጋም ወደ ፈርዖን ቤትና ወደ አገልጋዮቹ ቤቶች መጣ፡፡ በመላው የግብፅ ውስጥ ምድሩ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ተበላሽቶ ነበር፡፡25ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ «ሂዱና በምድራችሁ ለአምላካችሁ ሠዉ» አላቸው፡፡ 26እንዲህ ለማድረግ ለእኛ ትክክል አይደለም፤ ለአምላካችን በእግዚአብሔር የምንሠዋቸው መሥዋዕቶች ለግብፃውያን አስጸያፊዎች ናቸውና፡፡ ለግብፃውያን አስጸያፊ የሆኑትን መሥዋዕቶች እያን በፊታቸው ብንሠዋ፣ በድንጋይ አይወግሩንም? 27ባዘዘን መሠረት፣ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት ያለብን ወደ ምድረ በዳወ የሦስት ቀን ጕዞ ሄደን ነው» አለ፡፡28«እንድትሄዱና በምድረ በዳው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንድትሠዉ እፈቅድላችኋለሁ፡፡ ርቃችሁ መሄድ ግን የለባችሁም፡፡ ለእኔም ጸልዩልኝ» አለ፡፡ 29«ከአንተ ወጥቼ እንደ ሄድሁ፣ የዝንቦቹ መንጋ አንተን ፈርዖንን፣ አገልጋዮችህንና ሕዝብህን ነገ ለቀው እንዲሄዱ ወደ እግዚአብሔር እጸልይልሃለሁ፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ሕዝባችን እንዲሄድ ባለመፍቀድ ከእንግዲህ ወዲያ ልታታልለን አይገባም» አለ፡፡30ከፈርዖን ወጥቶ ሄደና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ 31እግዚአብሔር ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- የዝንቡን መንጋ ከፈርዖን፣ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ላይ አስወገደ፡፡ አንድም አልቀረም፡፡ 32ነገር ግን ፈርዖን በዚህም ጊዜ ልቡ አደነደነ፤ ሕዝቡም እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡
1ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ይናገራል፡፡ «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡» 2ብትልና አሁንም ከልክለህ ብታስቀራቸው፣ 3የእግዚአብሔር እጅ መስክ ላይ ባለው ከብትህ፣ በፈረሶችህ፣ በአህዮችህ፣ በግመሎችህ፣ በፍየሎችህና በበጎችህ ላይ ይሆናል፤ አስከፊ በሽታም ያመጣል፡፡ 4እግዚአብሔር በእስራኤል ከብትና በግብፅ ከብት መካከል ልዩነት አድርጓል፡- የእስራኤል ከብት አይሞትም፡፡5ጊዜ ወስኖአል፤ «በምድሪቱ ላይ ይህን የማደርገው ነገ ነው» ብሎአል፡፡ 6ይህን በሚቀጥለው ቀን አደረገው፡- የግብፅ ከብት ሁሉ ሞተ፡፡ ከእስራኤል ከብት ግን አንድም አልሞተም፡፡ 7ተከታትሎ አጣራ፣ ከእስራኤል ከብት አንድም እንኳ አለመሞቱን ተረዳ፡፡ ነገር ግን ልቡ ደንድኖ ነበር፤ ስለዚህ ሕዝቡ እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡8እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አላቸው፤ «ከምድጃ ላይ እፍኝ ዐመድ ውሰዱና አንተ ሙሴ ወደ ሰማይ ፈርዖን እያየ ዐመዱን በትነው፡፡ 9በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ትቢያ ይሆናል፡፡ ይህም በመላው የግብፅ ምድር በሰውና በእንስሳት ላይ ዕባጭና ቊስል ያመጣል፡፡» 10ስለዚህ ሙሴና አሮን ከምድጃ ዐመድ ወስደው ከፈርዖን ፊት ለፊት ቆሙ፡፡ ከዚያም ሙሴ ዐመዱን ወደ ሰማይ በተነው፡፡ ዐመዱ በሰውና በእንስሳ ላይ የሚወጣ ዕባጭና ቊስልን አመጣ፡፡11በእነርሱና በሌች ግብፃውያን ሁሉ ላይ ወጥቶ በነበረው ዕባጭ ምክንያት ጠንቋዮቹ በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፡፡ 12እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስለ አደነደነው፣ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንደዚህ እንደሚደርግ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት እንድ ነበረው ነው፡፡13እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በጠዋት ተነሣና ከፈርዖን ፊት ለፊት ቁም፤ እንደዚህ ብለህም ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናገሯል፡- «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡ 14ጊዜ በአንተ በራስህ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ እልካለሁ፡፡ ይህን የማየደርገውም በድምር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ እንድታውቅ ነው፡፡15ጊዜ እጄን ዘርግቼ አንተንና ሕዝብህን በበሽታ በመምታት ከምድር ባጠፋኋችሁ ነበር፡፡ 16ግን በሕይወት እንድትቈይ ያደረግሁህ፣ ኀይሌን እንድገልጥብህና ስሜም በምድር ሁሉ እንዲታወቅ ነው፡፡ 17ሕዝቤን እንዳይሄድ በማድረግ በሕዝቤ ላይ ራስህን እያሳበይህ ነው፡፡18ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሠረተችበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግብፅ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የበረዶ ማዕበል አመጣለሁ፡፡ 19አሁን ሰው ላክና ከብትህን፣ በመስክ ላይ ያለህን ማንኛውንም ነገር ወደ ጠለያ ስፍራ ሰብስብ፡፡ መስክ ላይ የቀረና ወደ ቤት ያልመጣ ማንኛውም ከብትና ሰው ሁሉ በረዶው ይወርድባቸውና ይሞታሉ፡፡»20አገልጋዮች የእግዚአብሔር ቃል የተቀበሉት ባሮቻቸውንና ከብቶቻቸውን ወደ ቤት ለማምጣት ተጣደፉ፡፡ 21የእግዚአብሔርን ቃል ከምር ያልተቀበሉት ግን ባሮቻቸውንና ከብታቸውን መስክ ላይ ተዉ፡፡22ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በሁሉም የግብፅ ምድር፣ በሕዝብ፣ በእንስሳትና በመላው የግብፅ ምድር መስክ ላይ ባሉ ተክሎች ሁሉ ላይ በረዶ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፡፡» 23በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድ፣ በረዶና መብረቅ ወደ ምድር ላከ፡፡በግብፅም ምድር ላይ በረዶ አዘነበ፡፡ 24ግብፅ አገር ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ በምድሪቱ ሁሉ ያልታየ እጅግ ከባድ የበረዶና የመብረቅ ቅልቅል ነበር የዘነበው፡፡25የግብፅ ምድር፣ በረዶው መስክ ላይ ያለውን ማንኛውንም ነገር፣ ሰውንም እንስሳቱንም መታ፡፡ በመስክ ያለውን ተክል ሁሉ መታው፣ ዛፉንም ሁሉ ሰባበረው፡፡ 26እስራኤላውያን በሚኖሩበት በጌሤም ምድር ብቻ በረዶ አልነበረም፡፡27በኋላ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን እንዲጠሩ ሰዎችን ላከ፡፡ እንዲህም አላቸው፤ «በዚህ ጊዜ ኀጢአት ፈጽሜአለሁ፡፡ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢአተኞች ነን፡፡ 28እግዚአብሔር ጸልዩ፤ ምክንያቱም ከባዱ ነጐድጓድና በረዶ እጅግ በዝቶብናል፡፡ እለቅቃችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ እዚህ አትቆዩም፡፡29ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ «ከከተማዪቱ እንደ ወጣሁ፣ እጆቼን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፡፡ ነጐድጓዱ ያቆማል፣ በረዶም አይኖርም፡፡ በዚህ መንገድ አንተ ምድር የእግዚአብሔር መሆኗን ታውቃለህ፡፡ 30ግን አንተንና አገልጋዮችህን በሚመለከት እግዚአብሔር አምላክን ገና በእውነት እንደማታከብሩ ዐውቃለሁ፡፡»31ጊዜ ተልባው አብቦ፣ ገብሱም ፍሬ በመያዝ ላይ ነበረ፣ ተልባውና ገብሱ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፡፡ 32አጃው ግን ቈይተው የሚደርሱ ሰብሎች በመሆናቸው አልተጐዱም፡፡ 33ሙሴ ከፈርዖንና ከከተማዪቱ ሲወጣ፣ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱና በረዶው ቆሙ፤ ዝናብም አልዘነበም፡፡34ፈርዖን ዝናቡ፣ በረዶውና ነጐድጓዱ መቆሙን ሲያይ፣ እንደ ገና ኀጢአት አደረገ፤ ከአገልጋዮቹ ጋርም በአንድነት ልቡን አደነደነ፡፡ 35የፈርዖን ልብ ስለ ደነደነ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንዲሄዱ አልፈቀደም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን ልቡን እንድሚያደነድን እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት የነበረው መንገድ ነው፡፡
1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የፈርዖንና የአገልጋዮቹን ልብ አደነድናለሁና ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እነዚህን የተአምራቴን ምልክቶች ለማሳየት ይህን አድርጌአለሁ፡፡ 2ይህን ያደረግሁት ግብፃውያንን እንዴት በከባድ አያያዝ እንደያዝኋቸውና በመካከላቸውም የተአምራትን ልዩ ልዩ ምልክቶች እንዳሳየሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትነግሯቸው ነው፡፡ በዚህ መንገድ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡3አሮንም ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ አሉት፤ «የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹ራስህን በፊቴ ለማዋረድ እምቢ የምትለው እስከ መቼ ነው? እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡ 4ግን ሕዝቤን አልለቅም ብትል፣ እነሆ፣ በነገው ቀን በአገርህ ላይ አንበጣዎችን አመጣለሁ፡፡5ማንም ሰው መድሩን ማየት እስከማይችል ድረስ የምድሩን ገጽ ይሸፍኑታል፡፡ ከበረዶው አምልጦ የቀረውን ሁሉ ይበሉታል፡፡ መስክ ላይ የሚያድግላችሁንም ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፡፡ 6አንበጣዎቹ የአንተን፣ የአገልጋዮችህን ቤቶች ሁሉ ይሞሏቸዋል፤ ይህም፣ አባትህም አያትህም በዚህ ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ቀን አነሥቶ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡» ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ሄደ፡፡7ፈርዖንን፣ «ይህ ሰው ወጥመድ የሚሆንብን እስከ መቼ ነው? አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩት እስራኤላውያን ይሂዱ፡፡ ግብፅ መጥፋቷን ገና አልተገነዘብህምን?» አሉት፡፡ 8ሙሴና አሮን፣ «ሂዱ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፡፡ ነገር ግን የሚሄዱት የትኞቹ ናቸው?» ወዳላቸው ወደ ፈርዖን እንደገና እንዲመጡ ተደረገ፡፡9የምንሄደው ከወጣቶቻችንና ከሽማግሌዎቻችን፣ ከወንድና ከሴት ልጆችን ጋር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር በዓል ማክበር ስለሚገባን፣ የበግና የፍየል መንጎቻችንን፣ የቀንድ ከብቶቻችንንም ይዘን እንሄዳለን» አለ፡፡ 10ፈርዖንም እንዲህ አላቸው፤ «እናንተንና ታናናሽ ልጆቻችሁን ስለችሁ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡ ነገር ግን ተመልከቱ፣ ክፉ ነገር ዐስባችኋል፡፡ 11ከመካከላችሁ ወንዶች ብቻ ይሂዱና እግዚአብሔርን ያምልኩ፤ የምትፈልጉት ያንን ነውና፡፡» ከዚያም በኋላ ሙሴና አሮን ከፈርዖን ዘንድ እንዲወጡ ተደረገ፡፡12እግዚአብሔርም ሙሴን፣ «አንበጣዎች የግብፅን ምድር እንዲወርሩትና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን፣ በምድሩ ያለውን ተክል ሁሉ እንዲበሉት እጅህን በግብፅ ምድር ላይ ዘርጋ» አለው፡፡ 13ሙሴም በትሩን በግብፅ ምድር ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያ ቀንና ሌሊት ሁሉ የምሥራቅ ነፋስ በምድሩ ላይ እንዲነፍስ አደረገ። ማለዳ ላይ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አምጥቶ ነበር።14በግብፅ ምድር ሁሉ ተሠራጩ፤ አገሩንም ሁሉ ወረሩት። እንደዚህ እጅግ የበዙ አንበጣዎች በምድሩ ውስጥ ከዚህ በፊት አልነበሩም፤ ወደፊትም አይኖሩም። 15ጨለማ እስኪሆን ድረስ የምድሩን ሁሉ ገጽ ሸፈኑት። በምድሩ ላይ ያለውን ማንኛውንም ተክልና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን የዛፍ ፍሬ ሁሉ በሉት። በግብፅ ምድር ሁሉ ለምለም ቅጠል ያለው ተክል አልቀረም፤ በመስክም ላይ ምንም ዛፍ አልነበረም።16ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔርና በእናንተ ላይ ኀጢአት ሠርቻለሁ። 17እንግዲህ አሁን ኀጢአቴን ይቅር በሉኝና ይህን ሞት ከእኔ እንዲያስወግድልኝ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ።” 18ስለዚህ ሙሴ ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።19አንበጣዎቹን ለቃቅሞ ወደ ቀይ ባሕር የሚከትታቸውን ብርቱ የምዕራብ ነፋስ አመጣ፤ በግብፅ ግዛት ሁሉ የቀረ አንድም አንበጣ አልነበረም። 20ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ፈርዖን እስራኤላውያንን አልለቀቃቸውም።21ሙሴን፣ “በግብፅ ምድር ላይ የሚዳስስ ከባድ ጨለማ እንዲሆን እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው። 22እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግብፅም ምድር ሁሉ ለሦስት ቀን ድቅድቅ ጨለማ ሆነ። 23ቀኖች አንዱ ሌላውን ማየት አልቻለም፤ ከቤቱም የወጣ ማንም የለም። ለእስራኤላውያን ግን በሚኖሩበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው።24ፈርዖን ሙሴን አስጠርቶ፣ “ሂዱ እግዚአብሔርን አምልኩ። ቤተ ሰቦቻችሁም እንኳ ዐብረዋችሁ መሄድ ይችላሉ፤ በጎቻችሁና ከብቶቻችሁ ግን እዚህ መቅረት አለባቸው” አለው። 25እንዲህ አለው፤ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንድንሠዋቸው ለመሥዋዕትና ለሚቃጠል መሥዋዕት እንስሳቱንም ልትሰጠን ይገባል። 26ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር መሄድ አለባቸው፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማምለክ ልንወስዳቸው ይገባልና ከእነርሱ ሰኮናም እንኳ እዚህ አይቀርም። ምክንያቱም እግዚአብሔርን በምን እንደምናመልከው እዚያ እስክንደርስ ድረስ አናውቅም።”27ግን የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው ፈርዖን ሕዝቡን አልለቀቃቸውም። 28ሙሴን፣ “ሂድ ከእኔ ዘንድ! ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና” አለው። 29ሙሴም፣ “አንተ ራስህ ተናግረሃል። ፊትህን እንደ ገና አላየውም” አለው።
1ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ የማመጣው ገና አንድ መቅሠፍት አለ። ከዚያ በኋላ ከዚህ እንድትሄዱ ይፈቅድላችኋል። በመጨረሻ እንድሄድ ሲያደርግም፣ ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል። 2ወንድና እያንዳንዱ ሴት ከጎረቤቱ ወይም ከጎረቤቱ የብርና የወርቅ ዕቃዎችን ስጡን ብለው እንዲጠይቁ ለሕዝቡ ተናገር።” 3እስራኤላውያንን ደስ ለማሰኘት ግብፃውያን እንዲነሣሡ አደረገ። ሙሴም በፈርዖን አገልጋዮችና በግብፅ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የሚደነቅ ሰው ሆነ።4እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ይህን ተናግሯል፦ ‘እኩለ ሌሊት ላይ በመላው ግብፅ ዐልፋለሁ። 5ላይ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ልጅ ጀምሮ፣ ወፍጮ ላይ እስከምትፈጨዋ እስከ ባሪያዪቱ በኵር ልጅና እስከ እንስሳቱ በኵር ሁሉ ድረስ በግብፅ ምድር ያሉ በኵር በሙሉ ይሞታል።6በቀድሞው ጊዜ ያልነበረ እንደገናም የማይደገም ታላቅ ዋይታ በግብፅ ምድር ሁሉ ይሆናል። 7ሕዝብ ላይ ግን፣ በሰውም ሆነ በእንስሳ ላይ ውሻ እንኳ አይጮኽም። በዚህም ግብፃውያንንና እስራኤላውያንን የማስተናግድበት መንገድ የተለያየ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።’ 8እነዚህ አገልጋዮችህ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ። ‘አንተና ተከታዮችህ ሁሉ ሂዱ!’ ብለውም ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ እወጣለሁ።” ከዚያም ሙሉ ከፈርዖን ዘንድ በትልቅ ቊጣ ወጥቶ ሄደ።9ሙሴን፣ “ፈርዖን እናንተን አይሰማችሁም። ይህም የሆነው ብዙ አስደናቂ ነገሮችን በግብፅ ምድር ላይ እንዳደርግ ነው” አለው። 10አሮን እነዚህን ድንቆች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ። ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ፈርዖን የእስራኤል ሕዝብ ከምድሩ እንዲወጡ አልፈቀደም።
1በግብፅ ምድር ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ነገራቸው፤ 2ወር ለእናንተ የወሮች መጀመሪያ፣ የዓመቱም የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ።3ጉባኤ ይህን ንገሩ፤ ‘በዚህ ወር ዐሥረኛ ቀን ላይ እያንዳንዳቸው ለራሳቸው አንድ ጠቦት የሚያንስ ከሆነ፣ 4የቅርብ ጎረቤቱ ከቊጥራቸው ጋር የሚመጣጠን ጠቦት ያዘጋጁ። የሚመገቡትን በቂ ሥጋ መውሰድ እንዲችሉ፣ ጠቦቱ ለሁሉም የሚበቃ መሆን አለበት።5ወይም የፍየል ጠቦታችሁ እንከን የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ሊሆን ይገባል። ከበጎቹ ወይም ከፍየሎቹ አንዱን ልትወስዱ ትችላላችሁ። 6እስከ ወሩ ዐሥራ አራተኛ ወር ድረስ አቆዩአቸው። ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ እነዚህን እንስሳት ፀሐይ ስትጠልቅ ይረዷቸው። 7ከዚያም ከደሙ ጥቂት ውሰዱና ሥጋውን በምትበሉበት ቤት በር መቃንና ጉበን ላይ አድርጉት። 8በእሳት ከጠበሳችሁት በኋላ፣ በዚያው ሌሊት ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ብሉት።9ወይም ቅቅሉን አትብሉት። ይልቁን ከጭንቅላቱ፣ ከእግሮቹና ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት ጠብሳችሁ ብሉት። 10ድረስ ከሥጋው አንዳችም አታስቀሩ። የተራረፈ ነገር ቢኖር፣ በእሳት ይቃጠል። 11ወገባችሁን ታጥቃችሁ፣ ጫማችሁን አጥልቃችሁና በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ ነው። ተጣድፋችሁ ልትበሉት ይገባል። የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።12በዚያ ሌሊት በግብፅ ምድር ሁሉ ዐልፋለሁ፤ በግብፅ ምድርም የሰውንና የእንስሳትን በኵር በሙሉ እመታለሁ። በግብፅ አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ። 13ደሙ እኔ ወደ እናንተ በቤቶቻችሁ ላይ ምልክት ይሆናል። ደሙንም በማይበት ጊዜ የግብፅን ምድር ስመታ እናንተን ዐልፌአችሁ እሄዳለሁ። ይህ መቅሠፍት በእናንተ ላይ አይመጣም፤ አያጠፋችሁምም። 14ቀን የእግዚአብሔር በዓል ቀን አድርጋችሁ የምታከብሩት የመታሰቢያ ቀን ይሆንላችኋል። ቀኑን እንድታከብሩት ለእናንተ፣ ለትውልዶቻችሁም ሁሉ ቋሚ ሥርዐት ይሆናችኋል።15ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ከቤታችሁ ታስወግዳላችሁ። ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የበላ ሰው ሁሉ ከእስራኤል ይወገድ። 16በመጀመሪያው ቀን ለእኔ የተቀደሰ ጉባኤ ይደረጋል፤ በሰባተኛውም ቀን እንደዚሁ ያለ ሌላ ጉባኤ ይሆናል። ሁሉም የሚበላውን ከመቀቀል በቀር፣ በእነዚህ ቀኖች ሥራ አይሠራም። የምትሠሩት የምግብ ዝግጅቱን ሥራ ብቻ ነው።17በዓልን አክብሩት ምክንያቱም ሕዝባችሁን ሰራዊት በሰራዊት አድርጌ ከግብፅ ምድር ያወጣሁት በዚህ ቀን ነው። ስለዚህ ይህን ቀን በትውልዶቻችሁ ሁሉ አክብሩት፤ ለእናንተ ቋሚ ሥርዓት ይሆናችኋል። 18የመጀመሪያ ወር ዐሥራ አራተኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ አንሥቶ፣ እስከ ወሩ ሃያ አንደኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ።19በሰባቱ ቀኖች በቤታችሁ ውስጥ እርሾ መገኘት የለበትም። እርሾ ያለበት እንጀራ የሚበላ እንግዳም ሆነ በምድራችሁ የተወለደ ሰው ከእስራኤል ማኅበረ ሰ ይወገዳል። 20የተጋገረ አንዳችም መብላት የለባችሁም። የትም ብትኖሩ፣ መብላት የሚገባችሁ እርሾ የሌለበትን ነው።”21በኋላ ሙሴ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሂዱና ቤተ ሰቦቻችሁን ለመመገብ የሚበቁ ጠቦቶችን ወይም ግልገሎችን መርጣችሁ የፋሲካን በግ ዕረዱ። 22ጭብጥ የሂሶጵ ቅጠል ያዙና በሳሕን ውስጥ በሚቀመጠው ደም ውስጥ በመንከር፣ የቤታችሁን ጉበን ዐናትና ሁለቱን መቃኖች እርጩ። እስኪነጋ ድረስ ከእናንተ አንድም ከቤቱ አይወጣ።23ለመቅሠፍት እግዚአብሔር ስለሚያልፍ፣ ደሙን በጉበኑ ዐናትና በሁለቱ መቃኖች ላይ ሲያይ፣ በበራፋችሁ ላይ ያልፋል፣ ቀሣፊውም ወደ ቤታችሁ እንዲገባና እናንተን እንዲቀሥፋችሁ አይፈቅድም።24ይህ ሥርዐት ለእናንተም ለልጆቻችሁም የሁልጊዜ ሥርዐት ስለ ሆነ ልታከብሩት ይገባል። 25ቃል በገባላችሁ መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ ይህን የአምልኮ ሥርዐት ጠብቁት።26‘ይህ የአምልኮ ሥርዐት ምን ትርጕም አለው?’ ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ፣ 27እንደዚህ ብላችሁ ልትነግሯቸው ይገባል፤ ‘ይህ የእግዚአብሔር ፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ግብፃውያንን ሲቀሥፍ፣ በግብፅ ውስጥ በእስራኤላውያን ቤቶች ዐልፎ ሄዶአል። ቤተ ሰቦቻችንን ነጻ አውጥቷቸዋል።” ከዚያም ሕዝቡ ሰገዱ፣ እግዚአብሔርንም አመለኩት። 28ሄደው እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዝዛቸው አደረጉ።29 እኩለ ሌሊት ላይ በዙፋኑ ላይ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ልጅ ጀምሮ፣ በእስር ቤት ውስጥ እስካለው ሰው በኵር ልጅና እስከ እንስሳት በኵር ሁሉ ድረስ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር የሚገኝን በኵር በሙሉ ቀሠፈ። 30አገልጋዮቹ ሁሉና ግብፃውያን በሙሉ ሌሊት ላይ ተነሡ። በግብፅ ውስጥ ጕልሕ የልቅሶ ጩኸት ነበረ፤ ሰው ያልሞተበት እንደም ቤት አልነበረምና።31ሙሴንና አሮንን በሌሊት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ተነሡ፤ እናንተና እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ። ማድረግ የምትፈልጉትን እንደ ተናገራችሁ ሂዱ፣ እግዚአብሔርን አምልኩ። 32እንደ ተናገራችሁት፣ የበግና የፍየል መንጎቻችሁን፣ የቀንድና የጋማ ከብቶቻችሁንም ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።” 33እስራኤላውያንን ከአገራቸው ለማባረር በትልቅ ጥድፊያ ላይ ነበሩ፤ “ሁላችንም ማለቃችን ነው” ብለው ነበርና።34ሕዝቡ እርሾ ያልተጨመረበትን ሊጣቸውን ያዙ። የቡሆ እቃዎቻቸውን ቀድሞውኑ በጨርቃቸው አስረው በትከሾቻቸው ተሸክመዋቸዋል። 35ሕዝብ ሙሴ እንደ ነገራቸው አደረጉ። የወርቅና የብር ዕቃዎችን፣ ልብስም እንዲሰጧቸው ግብፃውያንን ጠየቁ። 36ደስ ለማሰኘት እግዚአብሔር ግብፃውያንን አነሣሣ። ስለዚህ እስራኤላውያን የጠየቋቸውን ሁሉ ግብፃውያን ሰጧቸው። በዚህ መንገድ፣ እስራኤላውያን ግብፃውያንን በዘበዟቸው።37ከራምሴ በመነሣት ወደ ሱኮት ተጓዙ። ቊጥራቸው ከሕፃናቱና ከሴቶቹ ሌላ ስድስት መቶ ሺሕ ያህል እግረኛ ነበር። 38እስራኤላዊ ያልሆነ ድብልቅ ሕዝቤም፣ ከበግና ከፍየል፣ እጅግ ብዙ ከሆነ የከብት መንጋ ጋር ዐብሯቸው ሄደ። 39ከግብፅ ያመጡትን እርሾ ተባርረው ስለ ወጡና ምግብ ማዘጋጀት ስላልቻሉ ነው። 40እስራኤላውያን በግብፅ ውስጥ የኖሩት አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር።41መቶ ሠላሳው ዓመት ፍጻሜ፣ በዚያው ቀን፣ ሁሉም የእግዚአብሔር ሰራዊት ከግብፅ ምድር ወጣ። 42ሌሊት እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር እንዲያወጣቸው ለእስራኤላውያን ነቅቶ የመቆያ ሌሊት ነበር። ይህ ሌሊት እስራኤላውያን ሁሉ፣ መላ ትውልዶቻቸው ሊያከብሩት የሚገባ ሌሊት ነው።43እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ ሕግ እነሆ፦ ባዕድ ሰው ፋሲካን አይበላውም። 44የተገዛ እያንዳንዱ የእስራኤል ባሪያ ግን ከገረዛችሁት በኋላ መብላት ይችላል።45ቅጥር አገልጋዮች መብላት አይገባቸውም። 46ምግቡ በአንድ ቤት ውስጥ መበላት አለበት። ሥጋ ከቤት ማውጣት፣ ዐጥንትም መስበር የለባችሁም።47የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በዓሉን ሊያከብር ይገባል። 48ባዕድ ሰው ከእናንተ ጋር ቢኖርና ፋሲካን ለእግዚአብሔር ለማክበር ቢፈልግ፣ ወንድ ዘመዶቹ ሁሉ መገረዝ አለባቸው። ከዚያም በኋላ፣ ሰውየው መምጣትና በዓሉን ማክበር ይችላል። በምድሩ እንደ ተወለዱት ሰዎች ይሆናል። ይሁን እንጂ፣ ያልተገረዘ ሰው የፋሲካን ምግብ አይበላም።49አንድ ዐይነት ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው በሁለቱም ማለት በአገሬው ተወላጅና በመካከላችሁ በሚኖረው ባዕድ ሰውም ላይ ነው።” 50እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ። 51በዚያው ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አወጣቸው።
1ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2‘በእስራኤላውያን ዘንድ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት በመጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ። በኵር የእኔ ነው።”3ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስታውሱት፤ በዚህ ቀን እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከዚህ ስፍራ አውጥቶአችኋልና። እርሾ ያለበት ምግብ አይበላም። 4በዚህ ቀን፣ በአቢብ ወር ከግብፅ ወጥቷችኋል። 5ለእናንተ ለመስጠት ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ኤውያውያን፣ ኢያቡሳውያን ምድር እግዚአብሔር ሲያስገባችሁ፣ ይህን አምልኮ በዚህ ወር ትፈጽማላችሁ።6ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት በዓል ይሆናል። 7ቀን ሁሉ መበላት ያለበት ቂጣ ነው፤ እርሾ ያለበት እንጀራ በእናንተ ዘንድ መታየት የለበትም። በአዋሳኞቻችሁም ዘንድ እርሾ አይኑር።8ቀን፣ ‘ይህ እንዲህ የሚሆነው ከግብፅ ስወጣ እግዚአብሔር ለእኔ ካደረገው የተነሣ ነው’ ብላችሁ ለልጆቻችሁ ትነግሯቸዋላችሁ።’ 9ይህም በእጃችሁና በግንባራችሁ ላይ መታሰቢያ ይሆናል። ይኸውም እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከግብፅ ስላወጣችሁ፣ የእግዚአብሔር ሕግ በአፋችሁ እንዲሆን ነው። 10ይህን ሕግ በየዓመቱ በተወሰነለት ጊዜ ልትጠብቁት ይገባል።11ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በማለው መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደ ከነዓናውያን ምድር ሲያስገባችሁ፣ 12በመጀመሪያ የተወሰደውን፣ የእንስሶቻችሁንም በኵር ሁሉ ለእግዚአብሔር ቀድሱ። ወንዶች የእግዚአብሔር ናቸው። 13ከአህያ በመጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ በጠቦት ትዋጁታላችሁ። ካልዋጃችሁት፣ ዐንገቱን ስበሩት። ከወንድ ልጆቻችሁ መካከል በኵር የሆኑትን ሁሉ ዋጇቸው።14ልጅህ፣ ‘ይህ ምን ማለት ነው? ብሎ ወደፊት ቢጠይቅህ፣ እንደዚህ ትነግረዋለህ ‘ከባርነት ቤት፣ ከግብፅ እግዚአብሔር ያወጣን በብርቱ እጅ ነበር። 15እኛን ለመልቀቅ በግትርነት እንቢ ባለ ጊዜ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ፣ የሰውንም ሆነ የእንስሳትን በኵር በሙሉ ገደለ። ከእንስሳት ሁሉ በመጀመሪያ የተወለደውን ለእግዚአብሔር የምሠዋውና ከወንድ ልጆችም በኵር የሆነውን የምዋጀውን በዚህ ምክንያት ነው።’ 16ከግብፅ ያወጣን በብርቱ እጅ ነውና፣ ይህ በእጅህና በግንባር ላይ ማስታወሻ ይሆናል።”17ሕዝቡን ሲለቅቃቸው፣ እግዚአብሔር ምንም እንኳ ቅርብ ቢሆንም፣ በፍልስጥኤማውያን ምድር ባለው መንገድ አልመራቸውም። እግዚአብሔር፣ “ሕዝብ ጦርነት ቢያጋጥማቸው፥ ምናልባት ሐሳባቸውን ይለውጣሉ፣ ወደ ግብፅም ይመለሳሉ” ብሎ ነበርና። 18እግዚአብሔር ሕዝቡን በምድረ በዳው ዙሪያ ውደ ቀይ ባሕር መራቸው። እስራኤላውያን ለውጊያ ተዘጋጅተው ከግብፅ ምድር ወጥተው ሄዱ፣19ሙሴ የዮሴፍን ዐፅም ይዞ ሄደ፤ ምክንያቱም ዮሴፍ፣ “እግዚአብሔር በእርግጥ ይታደጋችኋልና ዐፅሜን ይዛችሁ እንድትሄዱ” በማለት እስራኤላውያንን አስምሎአቸው ነበር። 20ከሱኮት በመጓዝ ምድረ በዳው ዳር ላይ በሚገኘው በአታም ሰፈሩ። 21እግዚአብሔር ሕዝቡን በመንገድ ላይ ሊመራቸው ቀን ቀን በደመና ዐምድ በፊታቸው ሄደ። ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን ሊሰጣቸው በእሳት ዐምድ ሄደ። በዚህ ዐይነት ሕዝቡ በቀንም በሌሊትም መጓዝ ቻሉ። 22እግዚአብሔር የቀኑን የደመና ዐምድ ወይም የሌሊቱን የብርሃን ዐምድ ከሕዝቡ ፊት አላነሣም።
1ለሙሴ እንዲህ ብሎ ተናገር፤ 2በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በፊሀሒሮት ፊት፣ በበኣልዛፎንም አንጻር እንዲሰፍሩ ለእስራኤላውያን ንገር። በፊሀሒሮት ትይዩ በባሕሩ አጠገብ ትሰፍራላችሁ። 3ፈርዖን ስለ እስራኤላውያን፣ ‘በምድሪቱ እየተንከራተቱ ነው፤ ምድረ በዳውም ዘግቶባቸዋል’ ይላል።4የፈርዖንን ልብ እኔ አደነድነዋለሁ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ይከታተላቸዋል። በፈርዖንና በመላው ሰራዊቱ ምክንያት እኔ እከብራለሁ። ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” ስለዚህ እስራኤላውያን በተነገራቸው መሠረት ሰፈሩ። 5ንጉሥ እስራኤላውያን እንደ ሄዱ ሲነገረው፣ ፈርዖንና አገልጋዮቹ ሐሳባቸውን በመለወጥ፣ እስራኤላውያን ለእኛ ከመሥራት ነጻ ሆነው እንዲሄዱ መፍቀዳችን ምን ማድረጋችን ነው? አሉ።6ሠረገላዎቹ እንዲዘጋጁለት አደረገ፤ ሰራዊቱንም ከእርሱ ጋር ይዞ ሄደ። 7መቶ ምርጥ ሠረገሎችንና የግብፅን ሌሎች ሠረገሎች በሙሉ፣ በያንዳንዳቸው ላይ መኮንኖች ያሉባቸውን ይዞ ተንቀሳቀሰ። 8እግዚአብሔር የግብፅን ንጉሥ፣ የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ንጉሡ እስራኤላውያንን ተከታተላቸው። አሁን እስራኤላውያን በድል ወጥተው ሄደዋል። 9ነገር ግን ግብፃውያን፣ ሁሉም የፈርዖን ፈረሶችና ሠረገሎች፣ የፈርዖን ፈረሰኞችና ሰራዊቱ እስራኤላውያንን አሳደዷቸው። በበኣልዛፎን አንጻር በባሕሩ አጠገብ ፊሀሒሮት ጥግ ሰፍረው እንዳሉ ደረሱባቸው።10ፈርዖን በቀረ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ወደ ላይ ተመለከቱ፣ ተደነቁም። ግብፃውያን ከኋላ እየተከተሏቸው ነበርና ፈሩ። እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። 11እንዲህ አሉት፤ “እዚህ ያመጣኸንና በምድረ በዳ እንድንሞት ያደረግኸው በግብፅ መቃብር ታጥቶ ይህን ነግረንህ አልነበረምን? 12ሠራተኞች እንድንሆን ተወን’ ብለንህ ነበር። በምድረ በዳ ከምንሞት፣ ለእነርሱ ሠራተኞች ሆነን ብንቀር ይሻል ነበር።’”13እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ። ጸንታችሁ ቁሙና ዛሬ እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርግላችሁን ትድግና ታያላችሁ። ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ዳግም አታዩአቸውም። 14እግዚአብሔር ለእናንተ ይዋጋል፤ እናንተ መታገሥ ብቻ ነው ያለባችሁ።”15እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሙሴ ለምን ትጮኽብኛለህ? እስራኤላውያን ወደ ፊት እንዲሄዱ ንገራቸው። 16የእስራኤል ስዎች በባሕሩ ውስጥ በደረቅ መሬት እንዲሻገሩ በትርህን አንሣና እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርግተህ ለሁለት ክፈለው። 17ተከትለዋቸው እንዲገቡ እኔ የግብፃውያንን ልብ የማደነድን መሆኔን ዕወቅ። ከፈርዖንና ከሰራዊቱ ሁሉ፣ ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ የተነሣ እኔ እከብራለሁ። 18በፈርዖን፣ ሠረገሎቹና በፈረሰኞቹ ምክንያት ክብርን ሳገኝ፣ ግብፃውያኑ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”19ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ በስተ ኋላቸው ሄደ። የደመናውም ዐምድ ከፊታቸው ተንቀሳቅሶ በስተኋላቸው ሄዶ ቆመ። 20በግብፅ ሰራዊትና በእስራኤል መካከል መጣ። ለግብፃውያን የጨለማ ደመና ሲሆን፣ ለእስራኤላውያን ግን ሌሊቱን ብሩህ ያደረገ ደመና ነበር፤ ይህም ሌሊቱን ሙሉ አንደኛው ወገን ወደ ሌላው እንዳይጠጋ አደረገ።21እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ። እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት ባሕሩን በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ወደ ኋላ እንዲሄድ በማድረግ ባሕሩን ደረቅ መሬት አደረገው። በዚህ መንገድ ውሃው ተከፈለ። 22እስራኤላውያን በባሕሩ መካከል ገብተው በደረቅ መሬት ዐለፉ። ውሃው በቀኛቸውና በግራቸውና በኩል ግድግዳ ሆነላቸው።23ተከታትለዋቸው መጡ። እነርሱ፣ የፈርዖን ፈረሶች ሠረገሎችና ፈረሰኞች ሁሉ እስራኤላውያኑ ተከትለው በባሕሩ መካከል ገቡ። 24ላይ እግዚአብሔር በእሳቱና በደመናው ዐምድ ውስጥ የግብፃውያንን ሰራዊት ወደ ታች ተመለከተ። በግብፃውያን መካከልም ሽብር እንዲፈጠር አደረገ። 25የሠረገሎቻቸው መንኯራኵሮች ተቆላለፉ፤ ፈረሰኞችም ለመንቀሳቀስ እጅግ ተቸገሩ። ስለዚህ ግብፃውያኑ፣ እግዚአብሔር እኛን እየወጋላቸው ነውና፣ ከእስራኤል እንሽሽ” አሉ።26ሙሴን፣ “ውሃው በግብፃውያኑ፣ በሠረገሎቻቸውና በፈረሰኞቻቸው ላይ ተመልሶ እንዲመጣባቸው እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ” አለው። 27እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ንጋት ላይም ባሕሩ ወደ ተለመደ ስፍራው ተመለሰ። ግብፃውያኑ ከባሕሩ ሸሹ፤ እግዚአብሔር ግን ወደ ባሕሩ መካከል አስገባቸው። 28ውሃው ተመስሎ በመምጣት የፈረዖንን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞችን ሠረገሎቹን ተከትለው ወደ ባሕሩ የገቡትን ጠቅላላ ሰራዊቱን ሸፈናቸው። አንድም ሳይሰምጥ የቀረ አልነበረም።29ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ላይ ተራምደው ሄዱ። ውሃው በቀኛቸውም በግራቸውም በኩል ለእነርሱ ግድግዳ ሆናላቸዋል። 30እግዚአብሔር በዚያ ቀን እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ ታደጋቸው፤ እስራኤላውያኑም የግብፃውያኑን ሬሳ በባሕሩ ዳር አዩ። 31እግዚአብሔር በግብፃውያኑ ላይ የገለጠውን ታላቅ ኀይል ሲያዩ፣ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አከበሩ፣ በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሙሴም ታመኑ።
1ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል።2ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆኖልኛል። እርሱ አምላኬ ነው፣ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፣ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።3ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።4ሠረገሎችና ሠራዊት በባሕር ውስጥ ጥሎአል። የፈርዖን ምርጥ መኮንኖች በቀይ ባሕር ውስጥ ሰመጡ።5ማዕበሎቹ ሽፈናቸው፤ እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቆቹ ወረዱ።6እግዚአብሔር ሆይ፣ ቀኝ እጅህ ጠላትን ሰባበረ።7ላይ የተነሡትን በታላቅ ግርማ ገለበጥሃቸው። ቊጣህን ላክህ፤ እንደ ገለባም አርጎ በላቸው።8በአፍንጫህ እስትንፋስ ውሆች ተከመሩ፤ ፈሳሾች እንደ ክምር ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ በባሕሩ ውስጥ ረጋ።9ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፣ እይዛቸዋለሁ፣ ምርኮም እካፈላለሁ፤ ፍላጎቴ በእነርሱ ርዳታ ያገኛል፤ ሰይፌን እመዝዛለሁ፤ እጄም ታጠፋቸዋለች’ አለ።10ግን በነፋስህ እፍ አልህ፣ ባሕሩም ሸፈናቸው፤ በኀይለኛ ውሆች ውስጥ እንደ ብረት ሰመጡ።11ሆይ፣ ክአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና የከበረ፣ ተአምራትን በማድረግ በምስጋና ከፍ ያለ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?12እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው።13ፍቅርህ የታደግሃቸውን ሕዝብህን መራህ። በብርታትህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ መራሃቸው።14ይሰማሉ፣ ይንቀጠቀጣሉም፤ የፍልስጥኤምን ኗሪዎች ሽብር ይይዛቸዋል።15ጊዜ የኤዶም እለቆች ይደነግጣሉ፤ የሞዓብ መሪዎች ይርበደበዳሉ፤ የከነዓን ኗሪዎች ሁሉ ይቀልጣሉ።16ሆይ፣ ሕዝብህ እስከሚያልፉ፣ የታደግሃቸው ሕዝብህ ዐልፈው እስከሚሄዱ ድረስ፣ ሽብርና ድንጋቴ ይወድቅባቸዋል፤ ከክንድህ ብርታት የተነሣ፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።17ሆይ፣ ማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፣ ጌታችን ሆይ፣ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣ በርስትህ ተራራ ላይ ሕዝብህን ታመጣቸዋለህ፣ ትተክላቸዋለህም።18ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል።”19ፈረሶች ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ ጋር ወደ ባሕሩ ውስጥ ሲገቡ፣ እግዚአብሔር የባሕሩን ውሀ መልሶ በላያቸው አመጣባቸው። እስራኤላውያን ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ሄዱ። 20ይአሮን እኅት፣ ነቢይቱ ማርያም ከበሮ አነሣች፤ ሌሎቹ ሴቶችም በሙሉ ከበሮ ይዘው ከእርሷ ጋር እያሸበሸቡ ወጡ። 21“ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል፤ በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና፣ ለእግዚአብሔር ዘመሩ” እያለች ዘመረችላቸው።22ሙሴ እስራኤላውያንን ከቀይ ባሕር እየመራቸው ወደ ሱር ምድረ በዳ ሄዱ። በምድረ በዳው ውስጥ ሦስት ቀን ሲጓዙ ውሀ አላገኙም። 23ማራም ደረሱ፤ ነገር ግን እዚያ የሚገኘው ውሀ መራራ ስለ ነበረ ሊጠጡት አልቻሉም። ቦታውን ማራ ያሉት ከዚህ የተነሣ ነው።24ሕዝቡ፣ “ምን እንጠጣ?” ብለው በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። 25ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፣ እግዚአብሔርም አንድ ዛፍ አሳየው። ሙሴም የዛፉን ዕንጨት ወደ ውሀው ውስጥ ጣለው፣ ውሀውም ጣፋጭ ሆነ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሕግና ሥርዐት የሰጣቸውና የፈተናቸው በዚያ ስፍራ ነበር። 26እንዲህ አለ፤ “የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፥ ትክክለኛ የሆነውንም በፊቱ ብታደርጉ፣ ትእዛዛቱንም ብታስተውሉና ሕግጋቱን ሁሉ ብትጠብቁ፣ ግብፃውያን ላይ ካመጣኋቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤ እኔ ፈዋሻችሁ እግዚአብሔር ነኝና።”27በኋላ ሕዝቡ ዐሥራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ወደ ነበሩበት ወደ ኤሊም መጡ። በዚያም በውሀው አጠገብ ሰፈሩ።
1የእስራኤል ማኅበር አባላት ከኤሊም ተንሥተው፣ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ዐሥራ አምስተኛ ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ። 2በዳው ውስጥም ጠቅላላ የማኅበሩ አባላት በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ። 3ሙሴንና አሮንንም፣ “በሥጋ ምንቸቶች ዙሪያ ተቀምጠን እስክንጠግብ ምግብ በምንበላበት በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን ኖሮ፤ ከዚያ አውጥታችሁ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁን መላውን ማኅበራችንን በረኃብ ልትጨርሱ ነውና” አሏቸው።4ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንጀራ ከሰማይ አዘንብላችኋለሁ። በሕጌ የሚመሩ ወይም የማይመሩ መሆናቸውን እንድፈትናቸው፣ ሕዝቡ ይውጡና በየቀኑ ለአንድ ቀን የሚሆነውን ይሰብስቡ። 5ቀን በየቀኑ ከሚሰበስቡት ዕጥፍ ይሰብስቡ፤ ያመጡትንም ያዘጋጁ።”6ከዚያም ሙሴና አሮን ለእስራኤል ሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “ከግብፅም ምድር ያወጣችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ማታ ታውቃላችሁ። 7በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶአልና፣ የእግዚአብሔርንም ክብር ጠዋት ታያላችሁ። በእኛ ላይ ልታጕረመርሙ እኛ ለእናንተ ምንድን ነን?” 8ደግሞ እንዲህ አለ፤ በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶታልና፣ እግዚአብሔር ማታ ሥጋ፣ ጠዋትም ምግብ እስክትጠግቡ ሲሰጣችሁ፣ ይህን ታውቁታላችሁ። አሮንና እኔ ምንድን ነን? የምታጕረመርሙት በእኛ ላይ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ ነው።”9ሙሴ አሮንን፣ “‘ጕርምርምታችሁን ሰምቶታልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በልህ ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ ተናገር’” አለው። 10አሮን ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ እንደ ተናገረ፣ ወደ ምድረ በዳው ተመለከቱ፤ እነሆም፣ የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ውስጥ ታየ። 11እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዲህ ብሎ ነገረው፤ 12“የእስራኤልን ሕዝብ ጕርምርምታ ሰምቻለሁ። እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ማታ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ጠዋት ደግሞ እንጀራ ትበሉና ትጠግባላችሁ። ከዚያም በኋላ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።13ላይ ድርጭቶች መጡና ሰፈሩን ሸፈኑት። በጠዋቱም የሰፈሩን ዙሪያ ጤዛ ተኝቶበታል። 14ሲጠፋ፣ እንደ ዐመዳይ ያለ ስስ ቅርፊት በምድረ በዳው ላይ ታየ። 15ሰዎች ሲያዩት፣ አንዳቸው ለአንዳቸው፣ “ምንድን ነው?” ተባባሉ። ምን እንደ ነበረ አላወቁም። ሙሴም እንዲህ አላቸው፤ “ይህ እንድትበሉት እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው።16እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶአል፦ ‘ለመብላት የምትፈልጉትን መጠን በሕዝባችሁ ቊጥር ለያንዳንዱ ሰው አንድ ጎሞር ሰብስቡ። የምትሰበስቡት እንደዚህ ነው፦ በድንኳናችሁ ውስጥ ለሚኖር ለእያንዳንዱ ሰው ለመብላት የሚበቃውን ሰብስቡ።” 17የተነገራቸውን አደረጉ። አንዳንዶች የበለጠ፣ አንዳንዶችም ያነሰ ሰበሰቡ። 18በጎሞር መጠን ሲለኩት፣ ብዙ የሰበሰቡት የተረፈ አላገኙም፤ ትንሽ የሰበሰቡትም ያጡትናየጎደለባቸው አልነበረም። እያንዳንዱ ሰው የሰበሰበው ለፍላጎቱ የሚበቃውን ያህል ነበር።19“ማንም ሰው ለነገ ከእርሱ ምንም ማስተረፍ የለበትም” አላቸው። 20ግን ሕዝቡ ሙሴን አልሰሙትም። አንዳንዶቻቸው ከሰበሰቡት እስከሚቀጥለው ጠዋት የተወሰነ አስቀሩ፤ ያስቀሩት ምግብ ግን ተላ፣ ሸተተም። ሙሴ ተቆጣቸው። 21የሰበሰቡት ጠዋት ጠዋት ነበር። እያንዳንዱ ሰው ለቀኑ የሚበቃውን ሰበሰበ። ፀሐይ ስትሞቅ ቀለጠ።22ቀን ለያንዳንዱ ሰው ሁለት ሁለት ጎሞር እንጀራ አድርገው ዕጥፍ ሰበሰቡ። የማኅበረ ሰቡ አለቆችም በሙሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት። 23“እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘ነገ ፍጹም ዕረፍት፣ ለእግዚአብሔር ክብር የተቀደሰ ሰንበት ነው። መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤ መቀቀል የምትፈልጉትንም ቀቅሉ። ተርፎ የሚቀረውን ሁሉ እስከ ጠዋት ለራሳችሁ አስቀምጡት’” አላቸው።24የተረፈውን ሙሴ በነገራቸው መሠረት እስከ ጠዋት አቆዩት። አልሸተተም፤ ትልም አልነበረበትም። 25እንዲህ አለ፤ “ዛሬ እግዚአብሔርን ለማክበር የተቀደሰ ሰንበት ነውና፣ ያስተረፋችሁትን ያን ምግብ ዛሬ ብሉት። ዛሬ ሜላ ላይ አታገኙትም።26ቀኖች ትሰበስቡታላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የሰንበት ቀን ነው። በሰንበት ቀን መና የለም።” 27ቀን አንዳንዶች መና ሊሰበስቡ ወጡ፣ ነገር ግን ምንም አላገኙም።28ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ትእዛዛቴንና ሕገጋቴን ለመጠበቅ እንቢ የምትሉት እስከ መቼ ነው? 29በሉ፤ እግዚአብሔር ሰንበትን ሰጥቶአችኋል። ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሰጣችሁ ለሁለት ቀን የሚሆን እንጀራ ነው። ከእናንተ እያንዳንዱ በገዛ ስፍራው ይቆይ፤ በሰባተኛው ቀን ማንም ሰው ከስፍራው መውጣት የለበትም።” 30በሰባተኛው ቀን ዐረፉ።31ምግቡን “መና” ብለው ጠሩት። ምግቡም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ፣ ጣዕሙም በማር በስሱ እንደ ተጋገረ ቂጣ ነበረ። 32ሙሴም፣ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፦ ‘ከግብፅ ምድር ካወጣኋችሁ በኋላ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ልጆቻችሁ ማየት እንዲችሉ፣ አንድ ጎመር መና ለትውልዶቻችሁ ሁሉ ይቀመጥ” አለ።33አሮንን፣ “አንድ ማሰሮ ውሰድና አንድ ጎሞር መና አስቀምጥበት፤ ለትውልዶች ሁሉ ተጠብቆ እንዲቆይም በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው” አለው። 34ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ አሮን መናውን በምስክሩ ፊት አስቀመጠው። 35ወደሚኖሩበት ምድር እስከሚመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ። ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስከሚመጡ ድረስ የተመገቡት እርሱን ነው። 36አንድ ጎመር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ነው።
1የእስራኤል ማኅበር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመከተል ከሲን ምድረ በዳ ተነሡ፤ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሀ አልነበረም። 2ሕዝቡ ሙሴን ወቀሡት፤ “የምንጠጣው ውሀ ስጠን” ብለውም ተናገሩት። ሙሴም፣ “ለምን እኔን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አላቸው። 3ያ ሕዝቡ ውሀ በጣም ጠምቷቸው ስለ ነበር በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እንዲህም አሉት፤ “እኛንና ልጆቻችንን፣ ከብቶቻችንንም በውሀ ጥም ለመፍጀት ከግብፅ ለምን አወጣኸን?”4እነዚህን ሰዎች ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። 5እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች አንዳንዶችን፣ ወንዙን የመታህበትንም በትር ያዝና ከሕዝቡ ፊት ቀድመህ ሂድ። 6ኮሬብ ባለው ዐለት ላይ እኔ ከፊትህ እቆማለሁ፤ ዐለቱንም ትመታዋለህ። ከእርሱም ሕዝቡ የሚጠቱት ውሀ ይወጣል።” ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት የታዘዘውን አደረገ። 7ስላጕረመረሙና “እግዚአብሔር በመካከላችን አለ ወይስ የለም?” በማለት እግዚአብሔርን ስለ ተፈታተኑት ያን ስፍራ ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው።8መጥተው እስራኤልን ራፊዲም ላይ ወጉ። 9ስለዚህም ሙሴ ኢያሱን፣ “ጥቂት ሰዎችን ምረጥና ውጣ፤ ከአማሌቃውያን ጋርም ተዋጋ። ነገ እኔ የእግዚአብሔን በትር ይዤ በኮረብታው ዐናት ላይ እቆማለሁ” አለው። 10ሙሴ ባዘዘው መሠረት አማሌቃውያን ተዋጋቸው፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኮረብታው ዐናት ወጡ።11እጁን ወደ ላይ ሲያነሣ፣ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር፤ እጁን ሲያወርድ ግን አማሌቃውያን ለማሸነፍ ይጀምሩ ነበር። 12የሙሴ እጆች እየደከሙ ሲሄዱ፣ አሮንና ሖር ድንጋይ ወስደው እንዲቀመጥበት ከእርሱ ሥር አስቀመጡለት። በዚያውም ጊዜ አሮንና ሖር አንዳቸው በአንድ ጎኑ፣ የቀረውም በሌላው ጎኑ በኩል በመሆን የሙሴን እጆች ወደ ላይ ደግፈው ያዙ። የሙሴ እጆችም ፀሐይ እስክትገባ ድረስ ጠንክረው ቆዩ። 13ስለዚህም ኢያሱ አማሌቃውያንን በሰይፍ ድል አደረጋቸው።14እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአማሌቃውያንን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ሙሉ በሙሉ ስለምደመስስ፣ ይህን በመጽሐፍ ጽፈህ ኢያሱ እየሰማ አንብበው” አለው። 15ሙሴም መሠዊያ ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር አርማዬ ነው” ብሎ ሰየመው። 16“እጅ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተነሥቶአልና፣ እግዚአብሔር በአማሌቃውያን ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጦርነት ያደርጋል” አለ።
1ካህን፣ የሙሴ ዐማት ዮቶር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ሰማ። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ያወጣቸው መሆኑን ዮቶር ሰምቶ ነበር። 2ሙሴ ወደ ቤት ከመለሳት በኋላ፣ የሙሴ ዐማት ዮቶር የሙሴን ሚስት ሲፓራን፣ 3ምድር ባዕድ ነበርሁ” ሲል ጌርሳም ብሎ የጠራውንና ሌላውንም ልጅ ተቀብሏቸው ነበር። 4“የአባቶቼ አምላክ ረድቶኛል፤ ከፈርዖንም ሰይፍ አድኖኛል” ብሎ ነበርና፣ የሌላው ልጁ ስም አልዓዛር ነው።5ዐማት ዮቶር ከሙሴ ልጆችና ከሚስቱ ጋር በምድረ በዳው ውስጥ በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ ሰፍሮ ወደ ነበረው ወደ ሙሴ መጣ። 6ሙሴን፣ “እኔ ዐማትህ፣ ዮቶር ከሚስትህና ከልጆችህ ጋር ወደ አንተ እየመጣሁ ነው” አለው።7ዐማቱን ሊቀበለው ወጣ፤ ሰገደ፤ ሳመውም። ስለ እያንዳንዳቸው ደኅንነት ተጠያይቀው ወደ ድንኳኑ ውስጥ ገቡ። 8ሙሴም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሲል በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ያደረገውን በሙሉ፣ በመንገድም በእነርሱ ላይ የደረሰባቸውን ችግር ሁሉና እግዚአብሔር እንዴት እንደታደጋቸው ለዐማቱ ነገረው።9ዮቶር እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ በመታደግ እግዚአብሔር ባደረገው መልካም ነገር ሁሉ ተደሰተ። 10እንዲህ አለ፤ “ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ አድኖአችኋል፤ ሕዝቡንም ከግብፃውያን እጅ ታድጎአቸዋልና እግዚአብሔር ይመስገን። 11እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ ታላቅ እንደ ሆነ አሁን ዐውቃለሁ፤ ምክንያቱም ግብፃውያን እስራኤላውያንን በትዕቢት ይዘዋቸው በነበረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ታድጎአል።”12ዐማት ዮቶር የሚቃጠል መሥዋዕቶችን ለእግዚአብሔር አቀረበ። አሮንና የእስራኤል አለቆች ሁሉ ከሙሴ ዐማት ጋር በእግዚአብሔር ለመብላት መጡ።13በሚቀጥለው ቀን ሙሉ ሕዝቡን ሊዳኝ ተቀመጠ። ሕዝቡ ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ በእርሱ ዙሪያ ቆሙ። 14የሙሴ ዐማት ሙሴ ለሕዝቡ ያደረገውን ሁሉ ተመልክቶ፣ “ምን እያደረግህ ነው? ብቻህን ለምን ትቀመጣለህ? ሰዎችስ ሁሉ ከጧት እስከ ማታ ድረስ ለምን በአንተ ዙሪያ ይቆማሉ?” አለው።15ዐማቱን እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ። 16ሲኖራቸው፣ ወደ እኔ ይመጡና በመካከላቸው ላለው ችግር ውሳኔ እሰጣለሁ፤ የእግዚአብሔርን ሕገጋትና ሥርዐትም አስተምራቸዋለሁ።”17ዐማቱም ሙሴን መልሶ እንዲህ አለው፤ “የምታደርገው ተገቢ አይደለም። 18ዐብረውህ ያሉ ሰዎች በእውነት ራሳችሁን ታደክማላችሁ። ይህ ለአንተ ከባድ ሸክም ነው። ይህን ተግባር ብቻህን ማከናወን አትችልም። 19ስማኝ። ምክር እሰጥሃለሁ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ ምክንያቱም አንተ በእግዚአብሔር ፊት የሕዝቡ ወኪል ነህ፤ አቤቱታቸውንም ወደ እግዚአብሔር ታቀርባለህ። 20ሥርዐታትና ሕገጋት ልታስተምራቸው፣ የሚሄዱበትን መንገድና የሚሠሩትን ሥራም ልታሳያቸው ይገባል።21እግዚአብሔርን የሚፈሩ ችሎታቸውን፣ ኢፍትሓዊ ጥቅምን የሚጠሉ የእውነት ሰዎችንከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ። ዕነርሱን መሪዎች እንዲሆኑ በሕዝቡ ላይ ሸለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች አድርገህ ሹማቸው። 22ጉዳዮችን ሁሉ በሚመለከት ሕዝቡን የሚዳኙት እነርሱ ይሆናሉ፤ ከባድ ከባድ ጉዳዮችን ግን ወደ አንተ ያቀርባሉ። አነስተኛ ጉዳዮችን ሁሉ በሚመለከት፣ እነርሱ ራሳቸው ውሳኔ ሊሰጡባቸው ይችላሉ። በዚህ መንገድ ሥራው ለአንተ ይቀልልሃል፤ እነርሱም ሸክሙን ከአንተ ጋር ይሸከማሉ። 23ይህን ብታደርግና እግዚአብሔርም እንደዚሁ እንድታደርግ ቢያዝዝህ፣ በርትተህ መሥራት ትችላለህ፤ መላው ሕዝብም ረክቶ ወደ ቤት መሄድ ይችላል።”24የዐማቱን ምክር በመስማት የነገረውን ሁሉ አደረገ። 25ሙሴ ከእስራኤል ሁሉ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ ሸለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች አድርጎም የሕዝቡ መሪዎች እንዲሆኑ ሾማቸው። 26በቀላላል ጉዳዮች ሕዝቡን ይዳኙ ነበር። ከበባድ ጉዳዮችን ለሙሴ አቀረቡ፤ ትንንሽ ጉዳዮችን ሁሉ ግን እነርሱ ለራሳቸው ብያኔ ሰጡባቸው። 27በኋላ ሙሴ ዐማቱን አሰናበተው፤ ዮቶርም ወደ ገዛ ምድሩ ተመልሶ ሄደ።
1ወር፣ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡበት በዚያው ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። 2ከራፊዲም ከተነሡ በኋላ፣ ወደ ሲና ምድረ በዳ መጥተው በምድረ በዳው ውስጥ ከተራራው ፊት ለፊት ሰፈሩ።3ወደ እግዚአብሔር ወጣ። እግዚአብሔርም ከተራራው ጠርቶት እንዲህ አለው፤ 4“ለያዕቆብ ቤት፣ ለእስራኤል ሕዝብ እንደዚህ ብለህ ተናገር፦ በግብፃውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ ፣ እናንተንም በርግም ክንፎች እንዴት እንደ ተከከምኋችሁና ወደ ራሴ እንዴት እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል። 5ቃሌን በታዛዥነት ብትሰሙና ኪዳኔንም ብትጠብቁ፣ ከሕዝብ ሁሉ መካከል የእኔ ርስት ትሆናላችሁ፤ ምድር ሁሉ የእኔ ነውና። 6እናንተ ለእኔ የካህናት መንግሕትና ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃሎች እነዚህ ናቸው።7መጣ፤ የሕዝቡንም ሽማግሌዎች ጠርቶ እግዚአብሔር ያዘዘውን እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፊታቸው ተናገረ። 8ሁሉ በአንድነት፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ እናደርጋለን” በማለት መልስ ሰጡ። ሙሴ ሕዝቡ የተናገሩትን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ መጣ። 9ሙሴን፤ “እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር፣ መስማት እንዲችሉና አንተንም ሁልጊዜ እንዲያምኑህ፣ ወደ አንተ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም ሕዝቡ የተናገሯቸውን ቃሎች ለእግዚአብሔር ነገረው።10ሙሴን፣ “ወደ ሕዝቡ ሂድ። ዛሬና ነገ ለእኔ ቀድሳቸው፤ ልብሳቸውንም እንዲያጥቡ አድርግ። 11ቀንም ይዘጋጁ፤ በሦስተኛው ቀን እኔ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ እወርዳለሁና።12ዙሪያ ሁሉ ለሕዝቡ ወሰን አብጅና ለሕዝቡ እንዲህ በላቸው፤ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ወይም የተራራውን ግርጌ ጫፍ እንዳትነኩ ተጠንቀቁ። ተራራውን የነካ ይሞታል።’ 13ዐይነቱን ሰው ማንም አይንካው። እንዲያውም የነካው በድንጋይ ይወገራል ወይም በቀስታ ይወጋል። ሰውም ሆነ እንስሳ ይሞታል። መለከቱ የማያቋርጥ ድምፅ ሲያሰማ፣ ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት ይችላሉ” አለው።14ሙሴም ከተራራው ወደ ሕዝቡ ወረደ። ሕዝቡን ለእግዚአብሔር ቀደሳቸው፤ ልብሳቸውንም አጠቡ። 15“በሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ፤ ወደ ሚስቶቻችሁም አትጠጉ” አላቸው።16ቀን ጠዋት ላይ ነጏድጓድና የመብረቅ ብልጭታ፣ ከባድ ደመና እና ጉሉሕ የመለከት ድምፅ በተራራው ላይ ነበሩ። በሰፈሩ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንቀጠቀጡ። 17ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኙ ሕዝቡን ከሰፈር አወጣቸው፤ በተራራው ግርጌም ቆሙ። 18እግዚአብሔር በእሳትና በጢስ ወርዶበት ስለ ነበረ፣ የሲና ተራራ ሙሉ በሙሉ በጢስ ተሸፈነ። ጢሱ እንደ ምድጃ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ጠቅላላ ተራራውም በኀይል ተናወጠ።19ድምፅ እየጨመረና እየጎላ ሲሄድ፣ ሙሴ ተናገረ፤ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት። 20እግዚአብሔር በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ወርዶ፣ ሙሴን ወደ ተራራው ጫፍ እንዲወጣ ጠራው። ሙሴም ወጣ። 21ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለማየት ዐልፈው ወደ እኔ እንድይመጡ፣ ሂድና ሕዝቡን አስጠንቅቃቸው፤ አለዚያ ብዙዎች ይሞታሉ። 22ወደ እኔ የሚቀርቡ ካህናትም ራሳቸውን ይቀድሱ፤ እንዳላጠፋቸውም ለእኔ መምጣት ራሳቸውን ያዘጋጁ።”23እግዚአብሔርን፣ “ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት አይችሉም፤ ምክንያቱም ‘በተራራው ዙሪያ ወሰን አብጅና ለእግዚአብሔር ቀድሰው’ ብለህ አዝዘኸናል” አለው። 24ሙሴን፣ “ከተራራው ወርደህ ሂድና አሮንን ክአንተ ጋር ይዘኸው ና፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን ወሰን ዐልፈው ወደ እኔ እንዲመጡ አትፍቀድላቸው፤ አለዚያ አጠፋቸዋለሁ” አለው። 25ስለዚህ ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው።
1እነዚህን ቃሎች እንዲህ በማለት ተናገረ፦ 2ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። 3ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።4በላይ በሰማይ ያለውን፣ ወይም በታች በምድር ያለውን፣ ከምድርም በታች በውሀ ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስልና ሥዕል ለራስህ ጣዖት አታብጅ። 5አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። የሚጠሉኝን ሦስትና አራት ትውልድ በልጆች ላይ ቅጣት በማምጣት የአባቶችን ኀጢአት እቀጣለሁ። 6በሚወዱኝና ትእዛዛቴን በሚጠብቁት በሺዎች ላይ ግን የኪዳን ታማኝነት አሳያለሁ።7የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ ስሜን በከንቱ የሚያነሣውን በደል ዐልባ አላደርገውምና።8እንድትቀድሰው፣ የሰንበትን ቀን ዐስብ። 9ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን። 10ቀን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በሰንበት ቀን አንተም ወንድ ልጅህም፣ ሴት ልጅህም፣ ወንድ አገልጋይህም፣ ሴት አገልጋይህም፣ እንስሳትህም፣ በግቢህ ያለ እንግዳም ሥራ አትሠሩም። 11እግዚአብሔር ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በእነርሱ ውስጥ ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀን ፈጥሬ በሰባተኛው ቀን ዐርፌአለሁና። ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባረክሁት፤ ለራሴም ቀደስሁት።12እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር ብዙ ጊዜ እንድትቆይ፣ አባትህንና እናትህን አክብር።13አትግደል።14አታመንዝር።15አትስረቅ።16በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።17የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፣ ወንድ አገልጋዩን፣ ሴት አገልጋዩን፣ በሬውን፣ አህያውን፣ ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።”18ሰዎች ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን አዩ፤ የመለከቱን ድምፅም ሰሙ፤ የሚጨሰውንም ተራራ ተመለከቱ። ሕዝቡ ይህን ሲያዩ፣ ተንቀጠቀጡ፤ ርቀውም ቆሙ። 19ሙሴን፣ “አንተ ተናገረን፤ እኛም እንሰማሃለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲናገረን አታድርግ፤ አለዚያ እንሞታለን” አሉት። 20ሙሴም ሕዝቡን፣ “አትፍሩ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር በእናንተ ዘንድ እንዲገኝና ኀጢአት እንዳትሠሩ ሊፈትናችሁ እግዚአብሔር መጥቶአልና” አላቸው። 21ስለዚህ ሕዝቡ ርቀው ቆሙ፤ ሙሴም እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጨለማው ተጠጋ።22ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ‘እኔ ከሰማይ ከእናንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል። 23በቀር ሌሎች አማልክትን፣ የብር ወይም የወርቅ አማልክትን ለራሳችሁ አታብጁ።24የጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፣ በእርሱም ላይ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶችህን፣ የኅብረት መሥዋዕቶችህን፣ በጎችህንና በሬዎችህን ሠዋበት። ስሜ እንዲከበር በማደርግበት ስፍራ ሁሉ፣ ወዳንተ እመጣለሁ፤ እባርክሃለሁም። 25መሠዊያ የምትሠራልኝ ከሆነ፣ በተጠረበ በድንጋይ አትሥራው፤ ለመጥረብ ስትል መሣሪያህን በላዩ ካሳረፍህበት ታረክሰዋለህና። 26ሆነህ እንዳትጋለጥ፣ በመሠዊያዬ ላይ በደረጃ አትውጣ።”
1የምትመሠርታቸው ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፦2አገልጋይ ብትገዛ፣ ስድስት ዓመት ያገልግልህና በሰባተኛው ዓመት ያለ ክፍያ ነጻ ይውጣ። 3ከመጣ፣ ብቻውን ነጻ ይውጣ፤ ሚስት ያገባ ከሆነ፣ ሚስቱም ዐብራው ነጻ ትውጣ። 4ጌታው ሚስት አጋብቶት ከሆነና እርሷም ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆችን ከወለደችለት፣ ሚስቲቱና ልጆቿ የጌታዋ ይሆናሉ፤ ባልዮው ግን ብቻውን በነጻ ይሂድ።5ግን አገልጋይ፣ “ጌታዬን፣ ሚስቴንና ልጆቼን እወድዳለሁ፤ ነጻ ወጥቼ አልሄድም” ቢል፣ 6ውደ ዳኞች ይውስደው፥ ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ ወስዶም ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም አገልጋይ ጌታውን ለዘለዓለም ያገለግለዋል።7ሰው ሴቶ ልጁን በአገልጋይነት ቢሸጣት፣ እንደ ወንዶቹ አገልጋዮች በነጻ መሄድ የለባትም። 8ለራሱ የመረጣትን ጌታዋን ደስ ባታሰኝ፣ በዎጆ ይልቀቃት። ለባዕዳን እንዲሸጣት መብት የለውም፤ ምክንያቱም አታልሎአታል።9ለልጁ አያያዝ ያድርግለት። 10ሌላ ሚስት ቢያጋባውም፣ የመጀመሪያዋን ሚስቱን ምግብ፥ ልብስ፣ ወይም ቊሳዊ መብት ማጕደል የለበትም። 11ነገር ግን እነዚህን ሦስት ነገሮች የማይሰጣት ቢሆን፣ ያለ ምንም የገንዘብ ክፍያ በነጻ መሄድ ትችላለች።12ሰው ሰውን ቢደበድብና ቢገድል፣ ሊሞት ይገባዋል። 13ሰውየው ዐስቦ ሳይሆን ድንገት አድርጎት ከሆነ፣ የሚሸሽበት ስፍራ አዘጋጃለሁ። 14አንድ ሰው ባልንጀራውን ሆነ ብሎ በተንኮል ቢያጠቃውና ቢገድለው፣ ከእግዚአብሔር መሠዊያም እንኳ ተወስዶ ይገደል።15ወይም እናቱን የሚመጣ ይገደል።16የሚጠልፍና የሚሸጥ፣ ወይም የተጠለፈው ሰው በእጁየሚገኝበት ይገደል።17ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል።18ቢጣሉና እንደኛው ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታው፣ የተመታው ሰውም ባይሞትና ዐልጋው ላይ ቢቀር፤ 19በኋላም ቢያገግምና በትሩን ተደግፎ በአካባቢው መንቀሳቀስ ቢችል፣ ለባከነበት ጊዜ የመታው ሰውን ይክፈል፤ ያገገመበትንም በሙሉ ይክፈል። ነገር ግን ያ ሰው የነፍስ ተጠያቂ አይደለም።20አንድ ሰው ወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን በበትር ሲመታና አገልጋዩም ከድብደባው የተነሣ ቢሞት፥ ያ ሰው መቀጣት አለበት። 21ነገር ግን አገልጋዩ አንድ ወይም ሁለት ቀን በሕይወት ቢቆይ፣ ጌታው መቀጣት የለበትም፤ አገልጋዩ የግል ንብረቱ ነውና።22ሰዎች ቢጣሉና ነፍሰ ጡር ሴት ቢጎዱ፣ እርሷም ብትጨነግፍ፣ ሆኖም ሌላ ጉዳት ባይደርስባት፣ በደለኛው ሰውዬ የሴትዮዋ ባል የሚጠብቅበትንና ዳኞቹ የሚወስኑትን መክፈል አለበት። 23ጉዳት ካደረሰ ግን፣ ሕይወትን ለሕይወት፣ 24ዐይንን ለዐይን፣ ጥርስን ለጥርስ፣ እጅን ለእጅ፣ እግርን ለእግር፣ 25ቃጠሎን ለቃተሎ፣ ቊስልን ለቊስል፣ ወይም ግርፋትን ለግርፋት በቅጣት ታስከፍላለህ።26አንድ ሰው የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ዐይን ቢመታና ቢያጠፋው፣ አገልጋዩን ስለ ዐይኑ ካሣ ነጻ ሊያደርገው ይገባል። 27የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ጥርስ ቢያወልቅ፣ አገልጋዩን ለጥርሱ ካሣ ነጻ ሆኖ እንዲሄድ ማድረግ አለበት።28በሬ አንድን ሰው ወይም ሴት ቢወጋና የሞት አደጋ ቢያደርስ፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፣ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ከተጠያቂነት ነጻ ይሁን። 29ግን በሬው የመዋጋት ልማድ ከቀድሞ ጀምሮ ካለበትና ባለቤቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በሬውን ሳይጠብቀው ቀርቶ፣ በሬው አንድ ወንድ ወይም ሴት ወግቶ ቢገድል፣ ያ በሬ በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም በሞት ይቀጣ። 30ለሕይወቱ ካሣ እንዲከፍል ካስፈለገ፣ የተጠየቀውን ይክፈል።31በሬው የአንድን ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ይህ ሕግ የሚጠብቅበትን ያድርግ። 32ወንድ ወይም ሴት አገልጋይን ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለአገልጋዩ ጌታ መክፈልና በሬውም በድንጋይ መወገር አለበት።33ሰው ጕድጓድ ቢከፍት ወይም ቢቆፍርና ሳይደፍነው ቀርቶ በሬ ወይም አህያ ቢገባበት፣ 34ባለቤት ለጠፋው መክፈል ይኖርበታል። ለሞተው እንስሳ ባለቤት ገንዘብ መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል።35የአንድ ሰው በሬ የሌላ ሰውን በሬ ቢወጋና ቢሞት፣ የበሬዎቹ ባለቤቶች በሕይወት ያለውን በሬ ሽጠው የተሸጠበትንና የሞተውንም በሬ ይካፈሉ። 36ነገር ግን በሬው ከቀድሞ ጀምሮ የመውጋት ልማድ ያለበት መሆኑ ከታወቀና ባለቤቱም ያልጠበቀው ከሆነ፣ በበሬው ፈንታ በሬውን መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል።
1ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅና ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፣ ለአንድ በሬ ዐምስት በሬ፣ ለአንድ በግም ዐምስት በግ መክፈል አለበት፥ 2ሌባ በር ሰብሮ ሲገባ ቢገኝና ተደብድቦ ቢሞት፣ በማንም ሰው ላይ የደም ዕዳ አይኖርም። 3ነገር ግን ሰብሮ ከመግባቱ በፊት ፀሐይ ከወጣ፣ በገደለው ሰው ላይ የደም ተጠያቂነት ይኖራል። ሌባ የሰረቀውን መመለስ አለበት። ምንም ነገር ከሌለው፣ የሰረቀውን እንዲከፍል እርሱ ራሱ መሸጥ ይኖርበታል። 4ሆነ አህያ ወይም በግ ቢሆን የተሰረቀው እንስሳ በሕይወት እርሱ ዘንድ ከተገኘ፣ ዕጥፉን መልሶ መክፈል አለበት።5ሰው ከብቱን መስክ ላይ ወይም የወይን ዕርሻ ውስጥ አሰማርቶ ቢለቅቀውና በሌላ ሰው ዕርሻ ውስጥ ገብቶ ቢግጥ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክና የወይን ዕርሻ መካስ ይኖርበታል።6እሳት ቢነሣና በእሾኾችም ውስጥ ቢዛመት፣ ክምሩም፣ ያልታጨደውም እህል ወይም ዕርሻው ቢቃጠል፣ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይካሥ።7ሰው እንዲጠበቅለት ገንዘቡን ወይም ዕቃውን ለጎረቤቱ ቢሰጥ፣ በዐደራ ያስቀመጠውንም ከሰውዬው ቤት ሌባ ቢሰርቀውና ሌባውም ቢገኝ፣ ያ ሌባ ዕጥፍ መክፈል አለበት፤ 8ባይገኝ ግን፣ የቤቱ ባለቤት እጁን በጎረቤቱ ንብረት ላይ መዘርጋቱንና አለመዘርጋቱን ለማየት፣ በዳኞች ፊት ሊቀርብ ይገባል። 9ስለ በሬ፣ ስለ አህያ፣ ስለ በግ፣ ስለ ልብስ ወይም አንድ ሰው፣ “ይህ የእኔ ነው” ስለሚለው ስለ ማንኛውም የጠፋ ነገር የሚነሣ ክርክር ሁሉ፣ የሁለቱም ወገን አቤቱታ በዳኞች ፊት መቅረብ አለበት። ዳኞች በደለኛ ሆኖ ያገኙት ሰው ለጎረቤቱ ዕጥፍ መክፈል ይኖርበታል።10አንድ ሰው አህያ፣ በሬ፣ በግ፣ ወይም ማንኛውም እንስሳ እንዲጠበቅለት ለጎረቤቱ በዐደራ ቢሰጥና እንስሳው ቢሞት፣ ወይም ጕዳይ ቢደርስበት፣ ወይም ማንም ሳያይ ቢወሰድ፣ 11ሰው በጎረቤቱ ንብረት ላይ እጁን መዘርጋቱን ወይም አለመዘርጋቱን ለመለየት፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት መማል አለባቸው። ባለቤቱ ይህን ሊቀበል ይገባል፤ ሌላውም ሰው ካሣ አይክሥም። 12ነገር ግን እንስሳው ከእርፍሱ ተሰርቆ ከሆነ፣ ሌላው ሰው ለባለቤቱ ካሣ መካሥ አለበት። 13አንድን እንስሳ አውሬ ቢዘነጥለው፣ ሌላው ሰውዬ እንስሳውን ማስረጃ አድርጎ ያቅርብ። ለተዘነጣጠለው እንስሳ ካሣ መክፈል የለበትም።14አንድ ሰው ከጎረቤቱ እንስሳ ቢዋስና እንስሳው ባለቤቱ በሌለበት ቢጎዳ ወይም ቢሞት፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መካሥ አለበት። 15ባለቤቱ ካለበት ከሆነ ግን፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መክፈል የለበትም፤ እንስሳ ተከራይቶ የነበረ ከሆነ፣ በተከራየበት ዋጋ ይከፈላል።16አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድን ቢያታልልና ዐብሯት ቢተኛ፣ ለዚህ ተገቢ የሆነውን ማጫ ከፍሎ ሚስቱ ሊያደርጋት ይገባል። 17አባቷ በሚስትነት አልሰጥህም ካለው፣ ልጃገረዶች ማጫ ከሚከፈለው ጋር እኩል የሆነ ገንዘብ መክፈል አለበት።18መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ። 19ከእንስሳት ጋር የወሲብ ግንኙነት የሚያደርግ መምት አለበት።20ከእግዚአብሔር በቀር ለማንኛውም ባዕድ አምላክ መሥዋዕት የሚሠዋ ፈጽሞ መጥፋት ይኖርበታል። 21መጻተኛውን አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና።22ማንኛዋንም መበለት ወይም አባትና እናት የሌለውን ልጁ ማስጨነቅ የለባችሁም። 23የምታስጨንቋቸው ከሆነና እነርሱም ወደ እኔ ከጮኹ፤ እኔ እግዚአብሔር ጩኸታቸውን እሰማለሁ። 24ቊጣዬ ይቀጣጠላል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለታት፣ ልጆቻችሁም አባት ዐልባዎች ይሆናሉ።25ከሕዝቤ መካከል ድኻ ከሆኑት ለአንዱ ገንዘብ ብታበድሩ፣ እንደ አራጣ አበዳሪ አትሁኑበት ወይም ወለድ አታስከፍሉት። 26የጎረቤትህን ልብስ በመያዣነት ብትወስድ፣ ፀሐይ ከመግባቷ በፊት ልትመልስለት ይገባል። 27ሰውነቱን የሚሸፍንበት ልብሱ እርሱ ብቻ ነውና። ምን ሌላ ልብስ ለብሶ መተኛት ይችላል? ወደ እኔ ሲጮኽ፣ ርኅሩኅ ነኝና እሰማዋለሁ።28ፈራጆችንም አትስደብ፤ የሕዝብህን አለቃም አትርገም።29ወይም ከወይን ጭማቂዎችህ የምታቀርባቸውን ስጦታዎች ማዘግየት የለብህም። የወንድ ልጆችህንም በኵር ለእኔ መስጠት አለብህ። 30በበጎችህ ላይም ይህንኑ ማድረግ ይኖርብሃል። ልጆቹ ሰባት ቀን ክአእናቶቻቸው ጋር መቆየት ይችላሉ፤ በስምንተኛው ቀን ግን ለእኔ መስጠት አለብህ። 31ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ስለዚህ መስክ ላይ አውሬ የዘነጣጠለውን ሥጋ ለውሾች ጣሉት፣ ልትበሉት አይገባም።
1ማንም ሰው የሐሰት ወሬ እትናገር። ሐሰተኛ ምስክር ለመሆን ከክፉ ሰው ጋር አትተባበር። 2ክፋት ለመፈጸም ሕዝብን አትከተል፤ ወይም ፍትሕን ለማጣመም ከሰዎች ጋር ተባብረህ ምስክርነት አትስጥ። 3ድኻውን በሙግቱ አታድላለት።4በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኘው መልስለት። 5የሚጠላህን ሰው አህያ እንደ ተጫነ ከጭነቱ ሥር ወድቆ ብታየው፣ ያን ሰው ትተኸው አትሂድ። አህያውን ለማንሣት ልታግዘው ይገባል።6ጊዜ ለድኻው ወገንህ የሚሰጠውን ፍትሕ አታጣምም። 7በሐሰት ክስ ከሌሎች ጋር አትተ ባበር፤ ንጹሑንም ወይም ጻድቁንም አትግደል፤ እኔ ኀጢአተኛውን ንጹሕ አላደርግምና። 8አትቀበል፤ ጕቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራል፤ የታማኝ ሰዎችን ቃልም ያጣምማልና። 9የመጻተኛነትን ስለምታውቁት፣ መጻተኛን አታስጨንቁ፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና።10ስድስት ዓመት በመሬትህ ላይ ዘር ዝራ፤ መከሩንም ሰብስብ። 11በሰባተኛው ዓመት ግን በሕዝብህ መካከል ያሉ ድኾች መብላት እንዲችሉ ሳታርሰው ዕዳሪውን ተወው። ከድኾች የሚተርፈውንም የዱር እንስሳት ይበሉታል። በወይን ቦታዎችህና በወይራ ዛፎችህም ይህንኑ ታደርጋለህ።12ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ። ይህን የምታደርገውም፦ በሬህ፣ አህያህ፣ የሴት አገልጋይህ ወንድ ልጅና መጻተኛው ሁሉ ዕረፍት እንዲያገኙና እንዲዝናኑ ነው። 13የነገርኋችሁን ሁሉ ጠብቁ። የሌሎች አማልክትን ስም አትጥሩ፤ ወይም ስማቸው ከአፋችሁ አይሰማ።14በየዓመቱ ሦስት ጊዜ ልአእኔ በዓል ታከብራላችሁ። 15በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት ሰባት ቀን ቂጣ ትበላለህ። በዚያ ጊዜ፣ ለዚህ በተወሰነው በአቢብ ወር በፊቴ ትቀርባለህ። ከግብፅ የወጣኸው በዚህ ወር ነበር። ነገር ግን በፊቴ ባዶ እጅህን መቅረብ የለብህም።16ላይ የዘራኸውን የእህልህን በኵራት፣ የመከርን በዓል አክብር። በዓመቱ መጨረሻ ምርትህን ከማሳ ስትሰበስብ፣ የመክተቻውን በዓል አክብር። 17ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይቅረብ።18የመሥዋዕቱን ደም እርሾ ካለበት ዳቦ ጋር ለእኔ አታቅርብ። በበዓሎቼ የሚቀርበው የመሥዋዕቴ ሥብ እስከ ንጋት ድረስ መቆየት የለበትም። 19የመሬትህን ምርጥ ፍሬ በኵራት ወደ እኔ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።20በመንገድ የሚጠብቅህንና ወዳዘጋጀሁልህ ስፍራ መርቶ የሚያስገባህን መልአክ በፊትህ እልካለሁ። 21ተከተለው፤ ታዘዝለትም። ኀጢአትህን ይቅር አይልህምና አታስቆጣው። ስሜ በእርሱ ላይ ነው። 22ድምፁን በእውነት ብትሰማና የምነግርህን ሁሉ ብታደርግ፣ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ።23መልአክ በፊትህ ይሄዳል፤ አንተንም ወደ አሞራውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ያስገባሃል። እኔ እነርሱን አጠፋቸዋለሁ። 24ለአማልክታቸው አትስገድ፤ አታምልካቸውም፤ ወይም ሕዝቡ እንደሚያደርጉት አታድርግ፤ ይልቁን ፈጽመህ ልታፈራርሳቸው፣ የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም ልትሰባብራቸው ይገባል። 25እኔን አምላክህን እግዚአብሔርን አምልክ። ይህን ካደረግህ፣ የምትባውንና የምትጠጣውን እባርካለሁ። በሽታንም ከመካከልህ አጠፋለሁ።26የምትጨነግፍ ወይም የምትመክን ሴት አትምርም። ለአንተ ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ። 27ምድር ሕዝብ ላይ ማስፈራቴን እልካለሁ። የሚያጋጥሙህን ሰዎች ሁሉ እገድላለሁ። ጠላቶችህን ሁሉ ከፍርሀት የተነሣ ጀርባቸውን ወደ አንተ እንዲያዞሩ አደርጋለሁ። 28ከነዓናውያንና ኬጤያውያንን ከፊትህ እንዲያበሯቸው ተርቦችን በፊትህ እሰድዳለሁ። 29ወና እንዳትሆንና የዱር አራዊትም እጅግ እንዳበዙብህ፣ የምድሪቱን ኗሪዎች በአንድ ዓመት ውስጥ ከፊትህ አላባርራቸውም።30ነገር ግን አንተ እስክትበዛና ምድሪቱን እስክትወርሳት ድረስ በትንሽ በትንሹ አስወጣቸዋለሁ። 31ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድር በዳውም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አደርገዋለሁ። በምድሪቱ ኗሪዎች ላይ ድል እንድትጎናጸፍ አደርጋለሁ፤ ከፊትህም ታባርራቸዋለህ። 32ወይም ከአማልክታቸው ጋር ኪዳን አታድርግ። 33እነርሱ በምድርህ ውስጥ መኖር አይገባቸውም፤ አልዚያ በእኔ ላይ ኀጢአት እንድትሠራ ያደርጉሃል። አማልክታቸውን ብታመልክ፣ ይህ በእውነት ወጥመድ ይሆንብሃል።”
1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ እኔ ኑ፤ በርቀት ሆናችሁም ስገዱልኝ። 2ሙሴ ብቻ ወደ እኔ መቅረብ ይችላል። ሌሎች መቅረብ የለባቸውም፤ ወይም ሕዝቡ ከሙሴ ጋር መምጣት አይችሉም።”3ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎችና ሕጎቹን ሁሉ ነገራቸው። ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፣ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ። 4ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ ጻፈ። ማለዳ ላይም በተራራው ግርጌ መሠዊያ ሠራ፤ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ነገዶች እንዲወክሉም፣ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ።5የሚቃጠልና የኅብረት መሥዋዕቶችን ከበሬዎች ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡም፣ ጥቂት የእስራኤል ወጣት ወንዶችን ላከ። 6ሙሴ የደሙን እኩሌታ በሣህን አደረገው፣ የቀረውንም እኩሌታ በመሠዊያው ላይ ረጨው።7መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ ጮኽ ብሎ አነበበላቸው። ሕዝቡም፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉእናደርጋለን፤ እንታዘዛለንም” ብለው ተናገር። 8ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው። “ይህ፣ ይህን የተስፋ ቃል ከእነዚህ ቃሎች ጋር ለእናንተ በመስጠት፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባው የኪዳኑ ደም ነው” በማለትም ተናገረ።9ከዚያም በኋላ ሙሴ፣ አሮን፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ተራራው ወጡ። 10የእስራኤልን አምላክ አዩት። ከእግሮቹ ሥርም እንደ ንጹሕ ሰማይ ከጠራ የሰንፒር ድንጋይ የተሠራ ወለል ነበረ። 11በእስራኤላውያን ሽማግሌዎች ላይ ተቆጥሮ እጅ አላሳረፈባቸውም። እነርሱ እግዚአብሔርን አዩ፤ በሉ፣ ጠጡም።12እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ተራራው ላይ ወደ እኔ ና፤ በዚያም ቆይ። የድንጋይ ጽላቱን ሕዝቡን እንድታስተምራቸውም የፋጽሏቸውን ሕጉንና ትእዛዛቱን እሰጥሃለሁ” አለው። 13ስለዚህ ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋር ወደ እግዚአብሔር ተራራ ሄደ።14ሙሴ ሽማግሌዎቹን፣ “ተመልሰን ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ እዚህ ቆዩን። አሮንና ሖር ከእናንተ ጋር ናቸው። ክርክር የሚኖርበት ሰው ካለ፣ ወደ እነርሱ ይቅረብ” አላቸው። 15ወደ ተራራው ወጣ፤ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው።16የእግዚአብሔር ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመናውም ተራራውን ስድስት ቀን ሸፈነው። በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው። 17የእግዚአብሔርን ክብር እስራኤላውያን ሲያዩት እንደሚያጋይ እሳት ነበር። 18ሙሴ ደመናው ውስጥ ገብቶ ወደ ተራራው ወጣ። በተራራውም ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየ።
1ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“እያንዳንዱ ሰው ልቡ በፈቀደለት መሠረት ስጦታ ለእኔ እንዲያመጣ ለእስራኤላውያን ንገር። እነዚህን ስጦታዎች ተቀበልልኝ።3ከእነርሱ የምትቀበላቸውም ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ወርቅ፣ ብርና ነሐስ፤ 4ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጕር፣ 5ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቁርበት፣ የግራር ዕንጨት፤ 6ለመቅደሱ መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያው ዘይት ቅመሞችና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፤ 7ለኤፉድና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቆች።8እንዳድር ሕዝቡ መቅደስ ይሥሩልኝ። 9ለመገናኛው ድንኳንና ለዕቃዎቹ ሁሉ እኔ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ሥሩት።10ሁለት ክንድ ተኩል፣ ስፋቱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት ይሠሩ። 11ውስጡንም ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።12የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህለት በታቦቱ አራት እግሮች ላይ፣ ሁለቱን በአንድ ጎኑ፣ ሁለቱን ደግሞ በሌላው ጎኑ አስቀምጣቸው። 13መሎጎያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና አወርቅ ለብጣቸው። 14ታቦቱን ለመሸከም መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎን ባሉ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ።15መሎጊያዎቹ ምንጊዜም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ይቀመጣሉ እንጂ ከዚያ አይወጡም። 16የኪዳኑን ምስክሮች በታቦቱ ውስጥ ታስቀምጣለህ። 17ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሥራ። 18ለሁለቱ የስርየት መክደኛ ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ ትሠራለህ።19ኪሩብ ለስርየት መክደኛው አንድ ጫፍ፣ ሌላውን ኪሩብ ደግሞ ለሌላው ጫፍ በማድረግ ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው መሠራት አለባቸው። 20ክንፎቻቸውን ወደ ላይ መዘርጋትና የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው መጋረድ ይኖርባቸዋል። እርስ በርሳቸው መተያየትና ወደ ስርየት መክደኛውም መመልከት አለባቸው። 21መክደኛውን በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ በታቦቱ ውስጥም የምሰጥህን የኪዳኑን ምስክሮች ታስቀምጣለህ።22እኔ ከአንተ ጋር የምገናኘው በታቦቱ ነው። በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ ከአንተ በተናገርሁበት በምስክሩ ታቦት ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ነው።23እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሥራ። 24ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።25አንድ ስንዝር ስፋት ያለው ጠርዝ ለጠርዙ በዙሪያው ከሚኖረው የወርቅ ክፈፍ ጋር አብጅለት። 26አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራለትና ቀለበቶችን አራቱ እግሮቹ ባሉበት ከሚገኙት አራት ማዕዘኖች ጋር አያይዛቸው። 27ለማስቀመጥና ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል፣ ቀለበቶቹ ከክፈፉ ጋር መያያዝ አለባቸው።28የጠረጴዛው መሸከሚያ እንዲሆኑም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና በወርቅ ለብጣቸው። 29ቊርባኑን ለማፍሰስ ጥቅም እንዲሰጡ ወጭቶችን፣ ጭልፋዎችን፣ ማንቆርቆሪያዎችንና ጎድጓዳ ሣህኖችን ከንጹህ ወርቅ ሥራ። 30በጠረጴዛውም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።31መቆሚያና ዘንግ አበጅተህበት ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ መቅረዝ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ ሁሉ ወጥ ሆነው ከመቅረዙ ጋር ይሠራሉ። 32ሦስት ቅርንጫፎች በአንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፍ ደግሞ በሌላው ጎን፣ ስድስት ቅርንጫፎች ለመቅረዙ ይውጡለት።33የመጀመሪያው ቅርንጫፍ የለውዝ አበቦችን መስለው የተሠሩ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ክአበባ ጋር፣ በሌላው ቅርንጫፍም እንደዚሁ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች የተቀረጹበት ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ሊኖሩት ይገባል። ከመቅረዙ በሚወጡት በስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ ላይ የሚሆነውም እንደዚሁ አንድ ዐይነት ነው። 34ላይ የለውዝ አበባ መስለው የተቀረጹ አራት ጽዋዎች ከቀንበጦቹና ከአበባዎቹ ጋር ሊኖሩበት ይገባል።35በመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ፣ በሁለተኛው የቅርንጫፎች ጥንድ ሥርም እንደዚሁ ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይኖረዋል። በሦስተኛው የቅርንጫፎቹ ጥንድ ሥርም ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይበጅለታል። ከመቅረዙ በሚወጡ በስድስቱ ቅርንጫፎች ሁሉ የሚሆነውም ይኸው አንድ ዐይነት ነው። 36ቀንበጦቻቸውና ቅርንጫፎቻቸው ሁሉ አንድ ወጥና ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መሆን አለባቸው።37መቅረዙንና ሰባት መብራቶችን ሠርተህ ፊት ለፊት ላለው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጥ አድርግ። 38የኵስታሪ መሰብሰቢያ ሣህኖቻቸው ከንጹሕ ወርቅ መሠራት አለባቸው። 39መቅረዙንና የመቅረዙን ዕቃ ሁሉ ለመሥራት አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ተጠቀም። 40ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት የሠራሃቸው ስለ መሆንህ እርግጠኛ ሁን።
1ከተፈተለ በፍታ ድር፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከተሠሩና ኪሩቤል ከተጠለፉባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ጋር ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ። ይህም ብልኅ ሠራተኛ የሚሠራው ሥራ ነው። 2የያንዳንዱ መጋረሣ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። መጋረጃዎቹ ሁሉ እኩል መጠን ይኑራቸው። 3ዐምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርስ መያያዝ አለባቸው፤ ሌሎቹ ዐምስት መጋረጃዎችም እንደዚሁ እርስ በርሳቸው መገጣጠም ይኖርባቸዋል።4በአንደኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ ግምጃ ቀለበቶችን አድርግ። ለሁለተኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝም ይህንኑ አበጅለት። 5ዐምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው የመጋረጃ ወገን፣ ዐምሳ ቀለበቶችን በሌላው የመጨረሻ መጋረጃ ላይ አድርግ። ይህን የምትሠራውም ቀለበቶቹ እርስ በርስ እንዲተያዩ በማድረግ ነው። 6ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዊችብ ሠርተህ ማደሪያ ድንኳኑ አንድ እንዲሆን፣ መጋረጃዎቹን በእነርሱ አያይዛቸው።7ከማደሪያው በላይ ለድንኳን የሚሆኑ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሥራ። 8መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። ዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች እኩል መጠን ይኑራቸው። 9ዐምስት መጋረጃዎችን በአንድነት፣ ስድስት መጋረጃውችንም እንዲሁ እርስ በርስ አያይዛቸው። ስድስተኛውን መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ዕጠፈው።10በመጀመሪያ ተገጣጣሚ የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ ሁለተኛውን የመጋረጃ አካል በሚያገጣጥመው የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አድርግ። 11ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሥራና በቀለበቶቹ ውስጥ አስገ ባቸው። ከዚያም አንድ ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን አገጣጥመው።12መጋረጃዎች ተንጠልጥሎ ያለው ቀሪ ግማሽ መጋረጃ ከማደሪያ ድንኳኑ ጀርባ ይንጠልጠል። 13ከመጋረጃዎቹ እርዝመት የተረፈው በአንድ በኩል አንድ ክንድ ምጋረጃ፣ 14በሌላው ጎንም አንድ ክንድ መጋረጃ ማደሪያው ድንኳን መሸፈኛ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና ከዚያም በላይ የሚሆን የአስቆጣ ቁርበት አዘጋጅ።15ለማደሪያው ድንኳን የሚሆኑ ወጋግራዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅ። 16ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን። 17በርስ የሚያገናኗቸው ሁለት ጕጣጕጦች በያንዳንዱ ወጋግራ ላይ ይኑር። የመገናኛ ድንኳኑን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሥራ። 18ድንኳን ወጋግራዎችን ስታበጅ፣ በደቡብ መኩል ላለው ሃያ ወጋግራዎችን አብጅ።19ወጋግራዎች የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ። ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መጋጠሚያዎች እንዲሆኑ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ። በሌሎች ወጋግራዎች በያንዳንዳቸው ሥርም ለሁለት መጋጠሚያዎቻቸው ሁለት መቆሚያዎች ይዘጋጁ።20በሰሜን በኩል ላለው ለሁለተኛው የመገናኛው ድንኳን ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና አርባ የብር መቆሚያዎቻቸውን ሥራ። 21በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች. በእያንዳንዱ ሥር ይሁኑ።22በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳኑ የኋላ ጎን ስድስት ወጋግራዎችን አብጅ። 23ለኋላ ማእዘኖቹም ሁለት ወጋግራዎችን አብጅ። 24እነዚህ ወጋግራዎች ከታች ጥንድ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የተያያዙ መሆን አለባቸው። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የሚሆነው በዚህ መንገድ ነው። 25ወጋግራዎች ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ሊኖሩ ይገባል። በሁሉም ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ናቸው ያሉት፤ በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋራ ሥርም ሁለት መቆሚያዎችና በእያንዳንዱም ሥር እንዲሁ።26ድንኳኑ አንደኛ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን ከግራር ዕንጨት አዘጋጅ፤ 27ለማደሪያ ድንኳኑ ሌላ ጎንም ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛ ድንኳኑ የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን እንዲሁ አብጅ። 28በወጋግራዎቹ መካከል ላይ ያለው አግዳሚ ከዳር እስከ ዳር መድረስ አለበት።29ወጋግራዎቹን በወርቅ ለብጣቸው። አግዳምዎችን ደግፍ በመያዝ እንዲያገለግሉም የወርቅ ቀለበቶቻቸውን ሥራላቸው፤ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለብጣቸው። 30ድንኳኑን መትከል ያለብህ በተራራው ላይ ያየኸውን ምሳሌ በመተከትል ነው።31ብልኅ ሠራተኛ ኪሩቤልን የጠለፈበት፣ የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ግምጃና አምሮ የተፈተለ በፍታ መጋረጃ አብጅ። 32በወርቅ በተለበጡ የግራር ዕንጨት አራት ዐምዶች ላይ ልትሰቅለው ይገባል። እነዚህ ዐምዶች በአራት የብር መቆሚያዎች ላይ የተቀመጡ የወርቅ ኵላቦች ይኖሯቸዋል። 33መጋረጃውን በማያያዣዎቹ አንጠልጥለው፤ የምስክሩንም ታቦት አግባው። መጋረጃው ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳን ይለየዋል።34በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ባለ ውበምስክሩ ታቦት ላይ የስርየት መክደኛውን አስቀምጥ። 35ከመጋረጃው ውጭ፣ መቅረዙንም ከመገናኛው ድንኳን ደቡባዊ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ አስቀምጥ። ጠረጴዛው በሰሜናዊ ጎኑ በኩል መቀመጥ ይኖርበታል።36መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ በጥልፍ ብሚያስጌጥ ሠራተኛ የተሠራ መጋረጃ አብጅለት። 37ዐምስት ምሰሶዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅና በወርቅ ለብጣቸው። ኵላቦቻቸውም የውርቅ መሆን እላቸው፤ ዐምስት የነሐስ መቆሚያዎችንም ሥራላቸው።
1ዐምስት ክንድ ወርዱም ዐምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ። መሠዊያው አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ከፍታ ይኑረው። 2ማእዘኖች የበሬ ቀንድ ቅርጽ እንዲኖራቸው ታደርጋለህ። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር አንድ ወጥና በነሐስ የተለበጡ ይሆናሉ።3የመሠዊያውን ዕቃዎች፦ የዐምድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ የሥጋ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ሁሉ ከነሐስ አብጃቸው። 4ለመሠዊያው ከነሐስ እንደ መረብ የተሠራ ፍርግርግ አብጅለት። በፍርግርጉ አራት ማእዘኖች በያንዳንዳቸው ላይም የነሐስ ቀለበት አድርግ።5አጋማሽ ወገብ እስከ ታች እንዲደርስ ፍርግርጉን ከመሠዊያው እርከን ሥር አድርገው። 6ለመሠዊያው መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት አበጅተህ በነሐስ ለብጣቸው።7በቀለበቶቹ ውስጥ መግባትና መሠዊያውን ለመሸከም በሁለቱ ጎኖቹ ላይ መቀመጥ አለባቸው። 8ባዶ እንዲሆን ከሳንቃዎች አብጀው። በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ልትሠራው ይገባል።9ድንኳን አደባባይ ሥራለት። በአደባባዩ ደቡብ ጎንም አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው የአማረ በፍታ መጋረጃዎች ይደረጉ። 10መጋረጃዎቹ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች ጋር ሃያ ምሰሶዎች ይኑሯቸው። ከምስሶዎቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎችም መኖር አለባቸው።11በሰሜን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎች፣ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎችም ጋር ከምሰሶውቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎች ሊኖሩ ይገባል። 12በአደባባዩ ምዕራብ ጎንም ዐምሳ ክንድ ርዝመት ያለው መጋረጃ ይደረግ። ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎችም ይኑሩት። 13በምሥራቅም በኩል አደባባዩ ዐምሳ ክንድ እርዝመት ይኑረው።14የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ሊኖራቸው ይገባል። ሦስት ምሰዎችም ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ይኖሯቸዋል። 15ሌላው ጎንም ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖሩታል። የራሳቸው ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ይኖሯቸዋል።16መግቢያ መጋረጃ ሃያ ክንድ እርዝመት ያለው፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ጠላፊ ጠልፎበት የተሠራ ይሁን። አራት ምሰሶዎች ከአራት መቆሚያዎች ጋር ሊኖሩት ይገባል።17የአደባዩ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎችና ኵላቦች፣ የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሯቸው። 18የአደባባዩ እርዝመት አንድ መቶ ክንድ፣ ወርዱ ዐምሳ ክንድ፣ ቁመቱ ዐምስት ክንድ ይሁን፤ የበፍታ መጋረጃዎችና የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሩት። 19በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ ዕቃ ሁሉ፣ የድንኳኑ ካስማዎችም በሙሉ፣ አደባባዩም ከነሐስ መሠራት አለባቸው።20ሁልጊዜ እንዲበሩ ለመብራቶቹ የወይራ ጭማቂ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡ እስራኤላውያንን እዘዛቸው። 21በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣ ከመጋረጃው ውጭ በምስክሩ ታቦት ፊት፣ አሮንና ልጆቹ መብራቶቹን ከማታ እስከ ንጋት ድረስ በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ። ይህም ለእስራኤል ትውልድ ሁሉ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
1ሆነው እንዲያገለግሉኝ ወንድምህን ዘሮንንና ልጆቹን ናዳብን፣ አብድዩን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ከእስራኤል መካከል ወደ አንተ ጥራ። 2ለወንድምህ ለአሮን ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን አዘጋጅ። እነዚህ ልብሶች ለአሮን ክብርና ማዕርግ የሚሆኑ ናቸው። 3ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግለኝ የአሮንን ልብሶች የሚሠሩለትን፣ በልባቸው ጥበበኛ የሆኑትን፣ የጥበብን መንፈስም የሞላሁባቸውን ሰዎች ሁሉ አነጋግር።4የሚሠሯቸው ልብሶችም የደረት ኪስ፣ ኤፉድ፣ ቀሚስ፣ ጥልፍ የተጠለፈበት ሸሚዝ፣ መጠምጠሚያና መታጠቂያ ናቸው። ለእኔ የተቀደሱትን እነዚህን ልብሶች መሥራት አለባቸው። ልብሶቹ ካህናት ሆነው እንዲያግለግሉኝ ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናሉ። 5ወርቅ፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የአማረ በፍታ ይጠቀሙ።6ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግን ኣአምሮ ከተፈተለ በፍታ ይሥሩት። ሥራው የብልኀተኛ ሙያተኝ ሥራ ሊሆን ይገባል። 7ኤፉዱ ከሁለቱ ጠርዞቹ ጋር የሚያያዙ ሁለት የትከሻ ንጣዮች ይኑሩት። 8በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉድ መሆን አለበት፦ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን። 9ሁለት የመረግድ ድንጋዮችን ወስደህ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅረጽባቸው።10ስድስቱ ስሞቻቸው በአንድ ድንጋይ፣ ስድስቱ ሌሎች ደግሞ በሌላው ድንጋይ ላይ እንደየልጁ ልደት ቀደም ተከተል ይቀረጹ። 11ሠራተኛ ማኅተም እንደሚቀርጽ የእስራኤልን ዐሥራ ሁለት ልጆች ስሞች በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ቅረጽ። ድንጋዮቹንም በወርቅ ክፈፋቸው። 12ሁለቱን ድንጋዮች የእስራኤልን ልጆች አምላክ የሚያስታውሱ ድንጋዮች እንዲሆኑ በኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ አስቀምጥ። መታሰቢያ እንዲሆኑ አሮን ስሞቻቸውን በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ይሸከማል።13ፈርጦችንና 14እንደ ገመድ የተጎነጎኑ የንጹሕ ወርቅ ድሪዎችን አበጅተህ ከፈርጦቹ ጋር አያይዛቸው።15ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ ኤፉዱ በተሠራበት መንገድ ፍርድ የሚሰጥበትን የደረት ኪስ አብጅ። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሥራው። 16አራት ማእዘን ያለ ውይሁን። የደረት ኪሱን ዐጥፈህ ድርብ አድርገው። አንድ ስንዝር እርዝመት፣ አንድ ስንዝር ስፋትም ይኑረው።17ዕንቆችን በአራት ረድፍ አስቀምጥ። የመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶነዝዮንና አብረቅራቂ ዕንቊ ሊኖሩት ይገባል። 18ሁለተኛው ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና አልማዝ ይኑሩት። 19ሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶንና አማቴስጢኖስ ይገኙበታል። 20አራተኛው ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ይኑሩት። በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ ሊደረግላቸው ይገባል።21ድንጋዮቹ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት መቀመጥ፣ ከእስራኤል ነገዶች አንዱን በመወከልም በቀለበት ማተሚያ እንደሚቀረጽ እያንዳንዱ ስም የተቀረጸባቸው መሆን አለባቸው። 22ኪሱ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አብጅለት። 23ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከደረት ኪሱ ሁለት ጎኖች ጋር አያይዛቸው። 24የወርቅ ድሪዎች ከደረት ኪሱ ሁለት ማእዘኖች ጋር አያይዛቸው።25ጕንጕን ድሪዎች ሌሎች ጎኖች ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋር አገናኛቸው። ከኤፉፉ የትከሻ ንጣዮች ጋርም በፊቱ በኩል አያይዛቸው። 26የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከውስጠኛው የኤፉዱ ጎን ቀጥሎ ባለው ጠርዝ ላይ፣ በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጎኖች ላይ አድርጋቸው።27ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን አብጅና በብልኀት ከተጠለፈው ከሴፉዱ መታጠቂያ በላይ፣ መጋጠሚያው አጠገብ ከኤፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያይዛቸው። 28ከኤፉዱ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችሉ፣ የደረት ኪሱን ቀለበቶቹ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ ማሰር አለባቸው። ይህም የሚሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋር ሳይያያዝ እንዳይቀር ነው።29አሮን ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ፣ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች በደረት ኪሱ ላይ ለፍርድ በልቡ ላይ ይሸከም። ይህም በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም መታሰቢያ ሆኖ ያገለግላል።30በፍርድ መስጫው የደረት ኪስ ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አስቀምጥ። አሮን ወደ እግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ፣ ኡሪምና ቱሚም በደረቱ ላይ መኖር አለባቸው፤ አሮንም ለእስራኤል ፍርድ መስጫውን በእግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ ሁልጊዜ መሸከም ይኖርበታል።31ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ሰማያዊ ይሁን። 32ለራስ ማስገቢያ ክፍተት ይኑረው፤ ክፍተቱም እንዳይቀደድ ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ይኑረው። ይህ ሥራ የሸማኔ ሥራ መሆን አለበት።33የግርጌ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ፣ የሐምራዊና የቀይ ማግ ሮማኖችን በዙሪያው አድርግ። በመካከላቸውም ዙሪያውን የወርቅ ሻኵራዎችን አብጅ። 34የወርቅ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ እየተፈራረቁ መቀመጥ አለባቸው። 35ወደ መቅደሱ ሲገባና በእግዚአብሔር ፊት ሲሆን፣ ከመቅደስ ሲወጣም፣ ድምፁ እንዲሰማ ቀሚሱን አሮን ሲያገለግል ይልበሰው። ይህም የሚደረገው አሮን እንዳይሞት ነው።36ከንጹሕ ወርቅ ሳሕን አብጅና በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ፣ “ቅዱስ ለእግዚአብሔር” ብለህ በላዩ ቅርጽበት። 37ሳሕን ከመጠምጠሚያው ፊት ጋር በሰማያዊ ገመድ አያይዘው። 38ሁልጊዜም በአሮን ግንባር ላይ ይሁን፤ አሮን እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ለይተው ከሚያቀርቧቸው የተቀደሱ ስጦታዎች ጋር የሚያያዝ ማንኛውንም በደል ይሸከማል። እግዚአብሔር ስጦታዎቻቸውን እንዲቀበል፣ መጠምጠሚያ ሁልጊዜ በአሮን ግንባር ላይ መሆን አለበት።39ሸሚዙንም፣ መጠምጠሚያውንም ከአማረ በፍታ ትሠራለህ። መታጠቂያውም በጥልፍ ጠላፊ እንዲሠራ ታደርጋለህ።40ለአሮን ልጆችም ሸሚዞቹን፣ መታጠቂያዎችንና የራስ ማሰሪያዎችን ለክብራቸውና ለማዕረጋቸው ታደርጋለህ። 41ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው። ቅባቸው፣ ሹማቸውም፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም ለእኔ ቀድሳቸው።42እስከ ጭን የውስጥ ሰውነታቸውን የሚሸፍን የውስጥ ልብሶችን ከበፍታ ሥራ። 43ልጆቹ ውደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ፣ ወይም መቅደሱ ውስጥ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ እነዚህን የውስጥ ልብሶች መልበስ አልባቸው። በደል እንዳይገኝባቸውና እንዳይሞቱ ይህን ማድረግ ይገባቸዋል። ይህ ለአሮንና ከእርሱም በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
1ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነርሱን ለእኔ ለመቀደስ አሁን የምታደርገው ይህ ነው። ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች፣ 2የሌለበትን እንጀራና ዘይት የተቀላቀለበትን እንጎቻ ውሰድ፤ ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣም አድርግ።3በአንድ ሌማት አድርጋቸውና ከወይፈኑና ከአውራ በጎቹ ጋር አቅርባቸው። 4አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ አቅርባቸው። በውሀም እጠባቸው።5ውሰድና፦ ሸሚዙን፣ የኤፉዱን ቀሚስ፣ ኤፉዱን፣ የደረት ኪሱን፣ በብልኀት የተጠለፈውን የኤፉዱን መታጠቂያ በወገቡ ዙሪያ በማስታጠቅ አሮን አልብሰው። 6ቅዱሱን አክሊል በላዩ አስቀምጠህ መጠምጠሚያውን በአሮን ራስ አድርግ። 7ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ቅባው።8አምጥተህ ሸሚዞችን አልብሳቸው። 9መታጠቂያዎችን ለአሮንና ለልጆቹ ታስታጥቃቸዋለህ፤ የራስ ማሰሪያዎችንም ታደርግላቸዋለህ። የክህነቱ ሥራ በዘለዓለማዊ ሕግ የእነርሱ ይሆናል። እኔን እንዲያገለግሉኝ አሮንና ልጆቹን ትክናቸዋለህ።10በመገናኛው ድንኳን ፊት አቅርብ፤ አሮንና ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ። 11በእኔ በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ዕረደው።12ከወይፈኑ ደም ጥቂት በጣትህ ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ታደርጋለህ፤ 13የሆድ እቃዎችን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ ጉበቱን የሚሸፍነውንና ሁለቱን ኩላሊቶች በላያቸው ካለው ስብ ጋር ወስደህ ሁሉንም በመሰዊያው ላይ ታቃጥላቸዋለህ። 14ነገር ግን የወይፈኑን ሥጋ ግን ቁርበቱንና ፈርሱን ጭምር ከሰፈር ውጭ አውጥተህ ታቃጥላለህ። ያ የኀጢአት መሥዋዕት ይሆናል።15የአውራ በግም ውሰድና አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን ይጫኑበት። 16በጉን ዕረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው። 17በጉን ለሁለት ክፈልና የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን እጠብ፤ የሆድ ዕቃውንም ከተቆራተጡ ብልቶችና ከራሱ ጋር 18ላይ አስቀምጥ። ከዚያም እውራ በጉን ሙሉ በሙሉ አቃጥለው። ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል። ይህም ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል።19ሌላውንም አውራ በግ ወስደህ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት። 20በኋላ አውራ በጉን ዕረደው፤ ከደሙም ጥቂት ውሰድና በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍና በልጆቹ ቀኝ ጆሮዎች ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጆቻቸውና በቀኝ እግሮቻቸው አውራ ጣቶች ላይ አድርግ። ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው።21ካለው ደም፣ ከመቅቢያው ዘይትም ጥቂት ውሰድና በአሮንና በልብሶቹ፣ በልጆቹና በልብሶቻቸውም ላይ እርጨው። አሮንና ልብሶቹ፣ ልጆቹና ልብሶቻቸው ከእርሱ ጋር ይቀደሱልኛል።22በጉን ሥብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በላያቸው የሚገኘውን ሥብ፣ የቀኙን ወርችም ውሰድ፤ ይህ አውራ በግ ካህኑ ለእኔ የሚቀደስበት ነውና። 23እንጀራ፣ አንድ በዘይት የተጋገረ እንጎቻና አንድ ስስ ቂጣ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ከሚሆነው ያለ እርሾ ከተጋገረው ኅብስት ሌማት ትወስዳለህ።24እነዚህን በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታስቀምጣለህ። እነርሱ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዟቸው፤ መሥዋዕት አድርገውም ለእኔ ያቅርቧቸው። 25ከእጆቻቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ አቃጥለው። ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል።26የአሮንን የክህነት አውራ በግ ፍርምባ ወስደህ ወዝውዘውና መሥዋዕት አድርገህ ለእኔ ለእግዚአብሔር አቅርበው። ይህም አንተ የምትበላው የአንተ ድርሻ ይሆናል። 27የመሥዋዕቱን ፍርምባና የቀረበውን የመሥዋዕቱን ወርች ለእኔ ቀድስልኝ፤ ሁለቱም አሮንና ልጆቹ ለእኔ ካህናት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከአውራ በጉ የሚገኙ ናቸው። 28የሚሰጧቸው እነዚህ የሥጋ ክፍሎች ምንጊዜም የአሮንና የልጆቹ ናቸው። በኅብረቱ መሥዋዕቶች ሥርዐት፣ ከእስራኤላውያን ለካህናቱ፣ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ይሆናሉ።29የአሮን የተቀደሱ ልብሶች ከእርሱ በኋላ ለልጆቹም ይሆናሉ። በልብሶቹ የአሮን ልጆች ለእኔ መቀባትና መካን አለባቸው። 30በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እኔን ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባ፣ አሮንን ከልጆቹ መካከል የሚተካ እነዚያን ልብሶች ሰባት ቀን ይልበስ።31የክህነቱን አውራ በግ ውሰድና ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ቀቅለው። 32ልጆቹ የአውራ በጉን ሥጋና በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር ባለው ሌማት የተቀመጠውን ኅብስት ይብሉት። 33ለማስተስረይና ለእኔ እንዲቀደሱ የቀረቡትን ሥጋውንና ኅብስቱን መብላት አለባቸው። ሌላ ሰው መብላት አይችልም፤ ምክንያቱም ምግቡን ለእኔ የተቀደሰ አድርገው ሊይዙት ይገባል። 34መሥዋዕቱ ሥጋ፣ ወይም ከኅብስቱ እስከሚቀጥለው ጠዋት ድረስ አንዳች የሚተርፍ ከሆነ፣ አቃጥለው። ለእኔ የተቀደሰ ስለ ሆነ መበላት የለበትም።35በዚህ መንገድ እንድታደርገው ያዘዝሁህን ሁሉ በመከተል ለአሮንና ለልጆቹ ትፈጽምላቸዋለህ። እነርሱን ሰባት ፍቀን ቀድስልኝ። 36ለስርየት የሚሆን የኀጢአት መሥዋዕት በየቀኑ አንድ ወይፈን አቅርብ። ማስተሰረያውን በማድረግም መሠዊያውን አንጻ፤ ለእኔ ለመቀደስም ቅባው። 37ሰባት ቀን ማስተሰረያ አድርግለትና ለእግዚአብሔር ቀድሰው። ከዚያ በኋላ መሠዊያው ሙሉ በሙሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ መሠዊያውን የሚነካውም ሁሉ ይቀደሳል።38የአንድ ዓመት ጠቦቶችን ዘወትር በየቀኑ በመሠዊያው ላይ አቅርብ። 39ጠቦት ማለዳ፣ ሌላውን ደግሞ ምሽት ላይ ታቀርበዋህ።40ከመጀመሪያው ጠቦታ ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛን ያማረ ዱቄት ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋር በመለወስ፣ ሩብ ወይንንም የመጠጥ ቍርባን በማድረግ አቅርብ።41ሁለተኛውን ጠቦት በምሽት ሠዋው። በማለዳ እንደ ተሠዋው ጠቦት ተመሳሳይ የእህልና የመጠት ቍርባን ማቅረብ አለብህ። እነዚህ መሥዋዕቶች ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያላቸው በእሳት የቀረቡልኝ መሥዋዕቶች ናቸው። 42ትውልዶች ሁሉ ዘወትር የሚቀርቡ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ናቸው። ላናግራችሁ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በእኔ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕቶቹን አቅርቧቸው።43ከእስራኤላውያን ጋር የምገናኝበት ቦታ ያ ነው፤ ድንኳኑ በክብሬ ይቀደስልኛል። 44የመገናኛውን ድንኳንና መሠዊያውን የእኔ ብቻ እንዲሆኑ እቀድሳቸዋለሁ። ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን እለያቸዋለሁ።45በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤ አምላካችውም እሆናለሁ። 46በመካከላቸው እንድኖር፣ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካችው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1ዕጣን የሚጤስበት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ። 2እርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ይሁን። አራት ማእዘንና ሁለት ክንድ ከፍታ ይኑረው። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር ወጥ ይሁኑ።3የዕጣን መሠዊያውን ላይኛ ክፍል፣ ጎኖቹንና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለብጣቸው። የመሠዊያውን ዙሪያ በወርቅ ክፈፈው። 4ከክፈፉ በታች በሁለቱ ትይዩ ጎኖቹ ላይ እንዲያያዙ ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አብጅ። ቀለበቶቹ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎችን ደግፈው የሚይዙ ናቸው።5ከግራር ዕንጨት ሥራና በወርቅ ለብጣቸው። 6የዕጣን መሠዊያውን ከመጋረጃው ፊት በምስክሩ ታቦታ አጠገብ አስቀምጠው። ይህም እኔ ከአንተ ጋር በምገናኝበት፣ በምስክሩ ታቦታ ላይ ካለው ከስርየት መክደኛው ፊት ይሆናል።7ደስ የሚያሰኝ መዐዛ ያለውን ዕጣን ሁልጊዜ ጧት ቷት ያጢስ። ማጤስ ያለበትም መብራቶቹን በሚያዘጋጅበት ጊዜ ነው። 8መብራቶቹን በምሽት ሲያበራም፣ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ማጤስ አለበት። ይህ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር በትውልዶች ሁሉ የሚጤስ ዕጣን ይሆናል። 9ነገር ግን ሌላ ዕጣን፣ አንዳችም የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የእህል ቍርባን በዕጣን መሠዊያው ላይ አታቅርብ፤ ምንም ዐይነት የመጠጥ ቍርባንም አታፍስስበት።10መሠዊያው ቀንዶች ላይ አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ማስተስረያ ያድርግ ይህንም የሚያደርገው የኀጢአት ስርየት ደሙን በመጠቀም ነው። ሊቀ ካህናቱ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህን ያድርገው። ይህ መሥዋዕት ሙሉ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።”11ሙሴን እንዲህ አለው፤ 12ስትቆጥራቸው፣ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ሕይወት ቤዛ ለእግዚአብሔር መክፈል አለበት። ስትቆጥራቸውና ከቆጠርሃቸውም በኋላ በመካከላቸው መቅሠፍት እንዳይኖር ይህን አድርግ። 13የተመዘገበ እያንዳንዱ ሰው በመቅደሱ ሰቅል ክብደት መሠረት የብር ግማሽ ሰቅል ይክፈል። ይህ ግማሽ ሰቅልም ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ይሆናል። 14ከሃያ እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው የተቆጠረ ሁሉ ይህን መሥዋዕት ለእኔ ማቅረብ አለበት።15ለሕይወታቸው ማስተስረያ ለማድረግ ይህን መሥዋዕት ለእኔ ሲያቀርቡ፣ ባለጠጋው ከግማሽ ሰቅል የበለጠ፣ ድኻውም ከዚያ ያነሰ መስጠት የለባቸውም። 16የማስተስረያ ገንዘብ ከእስራኤላውያን ተቀበልና ለመገናኛ ድንኳኑ ሥራ አውለው። ለሕይወታችሁ ማስተስረያ ማድረግ በፊቴ ለእስራኤላውያን መታሰቢያ ይሁን።”17ሙሴን እንዲህ አለው፤ 18ትልቅ የናስ ሳሕን ከናስ መቆሚያ ጋር አብጅ። በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠውና ውሀ አድርግበት።19ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ውስጡ ባለው ውሀ ይታጠቡ። 20መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ እኔን ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ እንዳይሞቱ በውሀ መታጠብ አለባቸው። 21እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ሊታጠቡ ይገባል። ይህ ለአሮንና ለዘሮቹ በትውልዶቻቸው ሁሉ የሁልጊዜ ሕግ ይሁን።”22ሙሴን እንዲህ አለው፤ 23ምርጥ ቅመሞች፦ ዐምስት መቶ ሰቅል ፈሳሽ ከርቤ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጣፋጭ ሽታ ያለው ቀረፋ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጠጅ ሣር፣ 24ዐምስት መቶ ሰቅል ብርጕድ በመቅደሱ ሰቅል ክብደት ተለክቶ፣ አንድ የኢን መስፈሪያ ወይራ ዘይትም ውሰድ። 25ቅመሞች በሽቶ ቀማሚ ሥራ የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት አዘጋጅ። ይህ ለእኔ የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት ይሆናል።26ዘይት የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦትም፣ 27ጠረጴዛውንና ዕቃውንም ሁሉ፣ መቅረዙንና ዕቃውን፣ የዕጣን መሠዊያውንም፣ 28የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረቢያ መሠዊያውን ከዕቃው ሁሉ ጋር፣ መታጠቢያ ሳሕኑንም ከመቆፕሚያው ጋር ቅባ።29ለእኔ የተቀደሱ እንዲሆኑ እነርሱን ለይልኝ። እነርሱን የሚነካ ማንኛውም ነገርም የተቀደሰ ይሆናል። 30ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፣ ለእኔም ለያቸው። 31እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት መሆን አለበት።32የሰው ቆዳ ሊቀባበት አይገባም፤ እንደዚህ ያለ አንዳችም ዘይት በአንድ ዐይነት ቀመር መሥራት የለባችሁም ምክንያቱም ይህ ዘይት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዘይት ነው። እናንተም ቅዱስ መሆኑን ዐስቡ። 33እንደዚህ የሚሠራ ሁሉ፣ ወይም ከዚህ ዘይት ጥቂት በሰው ላይ የሚያፈስስ ሁሉ፣ ከወገኑ ይወገድ።’”34ሙሴን እንዲህ አለው፤ “የጣፋጭ ሽቶ ቅመሞችን፦ የሚንጠባጠብ ሙጫ፣ በዛጎል ውስጥ ያለ ሽቶ፣ የሚሸት ሙጫ ከንጹሕ ዕጣን ጋር፣ እያንዳንዱን በእኩል መጠን ውሰድ፥ 35በሽቶ ቀማሚ እንደ ተሠራ፣ በጨው የተቀመመ፣ ንጹሕና ለእኔ የተቀደሰ ዕጣን አድርገው። 36አድቅቀህ ትወቅጠዋለህ። ከፊሉን ከአንተ ጋር በምገናኝበት፣ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ባለው በምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት አስቀምጥ። ለእኔ የተቄደሰ መሆኑንም ዐስብ።37እንደምትዘጋጀው ዕጣን በአንድ ዐይነት ቀመር ለራስህ ምንም አታድርግ። ለአንተ እጅግ ቅዱስ ይሁን። 38እንደ ሽቶ ለመጠቀም እንደዚህ አድርጎ የሚሠራ ሁሉ ከገዛ ወገኑ ይወገድ።”
1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስሙ ጠርቼዋለሁ።3ለሁሉም ዐይነት የእጅ ሞያ ጥበብን፣ ማስተዋልንንና ዕውቀትን እንዲሰጠው፣ ባስልኤልን በመንፈስ ሞልቼዋለሁ፤ 4ይኸውም ጥበባዊ ሥራዎችን በወርቅ፣ በብርና በነሐስ እንዲሠራ፣ 5ዐይነት የእጅ ሞያ ለማከናወንም ድንጋይ እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው።6ከእርሱም በተጨማሪ የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ከዳን ነገድ መርጬዋለሁ። ያዘዝሁህንም ሁሉ እንዲሠሩ የእጅ ሞያ ዐዋቂዎች በሆኑት ልብ ውስጥ ብልኀትን አስቀምጫለሁ። 7የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦት፣ በታቦቱ ላይ ያለውን የስርየት መክደኛና የድንኳኑን ዕቃ ሁሉ፦ 8ጠረጴዛውንና ዕቃውን፣ ንጹሑን መቅረዝ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር፣ የዕጣኑን መሠዊያ: 9የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋርና ትልቁን ሰን ከነመቆሚያው የሚያካትት ይሆናል።10የተሠሩትን ልብሶች፦ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ ለእኔ የተለዩትን የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም ይጨምራል። 11ዘይቱንና የመቅደሱን ጣፋጭ ዕጣንም ያካትታል። እነዚህ የእሥ ሞያ ዐዋቂዎች እነዚህን ሁሉ እኔ ባዘዝሁህ መሠረት ይሥሯችው።”12ሙሴን እንዲህ አለው፤ 13“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የእግዚአብሔርን የሰንበት ቀኖች ጠብቁ፤ እናንተን ለራሱ የለያችሁ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ፣ ይህ በእርሱና በእናንተ መካከል በትውልዶቻችሁ ሁሉ ምልክት ነውና። 14ስለዚህ ለእናንተ የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰንበት ነውና አክብሩት። ሰንበትን የሚያረክስ ሁሉ ይሞታል። በሰንበት የሚሠራም ከወገኑ ተነጥሎ ይጥፋ። 15ስድስት ቀን ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ክብር የተጠበቀና የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት ሰንበትን ያክብሩ።16በትውልዶቻቸው ሁሉ ቋሚ ሕግ አድረገው ሰንበትን ሊያከብሩት ይገባል። 17እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፣ ሰንበት በእግዚአብሔርና በእስራኤላውያን መካከል ሁልጊዜ ምልክት ይሆናል።”18እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ከሙሴ ጋር የሚያደርገውን ንግግር ከጨረሰ በኋላ፣ በገዛ እጁ የጻፈባቸውን የምስክሩን ሁለት የድጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።
1ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ሕዝቡ ሲመለከቱ፣ በአሮን ዙሪያ ተሰብስበው እንዲህ አሉት፤ “በፊታችን የሚሄድ ጣዖት ሥራልን። ከግብፅ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳጋጠምው አናውቅም።” 2እንዲህ አላቸው፤ “በሚስቶቻችሁ ጆሮዎች፣ በወንድና በሴት ልጆቻችሁ ጆሮዎችም ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቁና ወደ እኔ እምጧቸው።”3ሁሉም በጆሮዎቻቸው ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቀው ወደ አሮን አመጧቸው። 4ወርቁን ከእነርሱ ተቀብሎ በማቅለጥ ቅርጽ ሰጠው፤ የጥጃ ምስልም አደረገው። ሕዝቡም፣ “እስራኤል፣ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ነው” አሉ።5ይህን ባየው ጊዜ፣ በጥጃው ምስል ፊት መሠዊያ ሠራ፤ “ነገ ለእግዚአብሔር ክብር በዐል ይሆናል” ብሎም ዐወጀ። 6ሕዝቡ በማግስቱ ማልደው በመነሣት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረቡ። ሊበሉና ሊጠጡም ተቀመጡ፤ ለመዝፈንም ተነሡ።7ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ራሳቸውን በክለዋልና ቶሎ ሂድ። 8መንገድ ፈጥነው ወጥተዋል። ለራሳቸው የጥጃ ምስል ሠርተው ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለታል። ‘እስራኤል፣ ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው ብለውም ተናግረዋል።’”9እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ። ተመልከት፣ ዐንገተ ደንዳናዎች ናቸው። 10በእነርሱ ላይ እንዲቀጣጠልና እንዳጠፋቸው ተወኝ። ከአንተም ታላቅ ሕዝብ አደርጋለሁ (አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ) ።” 11ግን አምላኩ እግዚአብሔር ዝም እንዲልለት ፈለገ፤ እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፣ በታላቁ ኀይልና በኀያል እጅ ከግብፅ ባወጣሃው ሕዝብህ ላይ ቊጣህ ለምን ይቀጣጠላል?12‘እግዚአብሔር በተራሮች ላይ ሊገድላቸውና ከገጸ ምድር ሊያጠፋቸው ዐስቦ ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከሚነድደው ቊጣህ ተመለስ፤ በሕዝብህ ላይ ይህን ቊጣ ከማምጣትም ታገሥ። 13‘ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፣ የተናገርሁትን ይህንም ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጠዋለሁ፤ የዘለዓለም ርስታቸው ይሆናል’ ያልሃቸውንና በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህ አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን ዐስብ።” 14ከዚያም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ አመጣባቸዋለሁ ካለው ቊጣ ታገሠ።15ተመለሰ፤ የምስክሩን ሁለት ጽላት በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ። ጽላቱ በሁለቱም ጎኖቻቸው፣ በፊትም በኋላም ተጽፎባቸው ነበር። 16የእግዚአብሔር ሥራ ነበር፤ በጽላቱ ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር።17ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር። 17 ኢያሱ የሕዝቡን ጫጫታ ሲሰማ፣ ሙሴን፣ “በሰፈር ውስጥ የጦርነት ድምፅ አለ” አለው። 18ሙሴም “የድል አድራጊ ድምፅ አይደለም፤ ድል የተደረገ ሕዝብ ድምፅም አይደለም፤ የምሰማው የዘፈን ድምፅ ነው” ብሎ መለሰለት።19ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ፣ ጥጃውንና የሚጨፍረውን ሕዝብ አይቶ በጣም ተናደደ። ጽላቱን ከእጁ ወርውሮ በተራራው ግርጌ ሰበራቸው። 20ሠርተውት የነበረውን ጥጃም ወስዶ አቃጠለው፤ ዱቄት እስከሚሆን ድረስ በመፍጨትም በውሀ ውስጥ በተነው። ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ እንዲጠጣው አደረገ።21“እንደዚህ ያለ ታላቅ ኀጢአት ያመጣህበት ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው?” አለው። 22እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ “ጌታዬ ሆይ ቊጣህ አይንደድ። እነዚህ ሰዎች ለክፋት የተዘጋጁ እንደ ሆኑ ታውቃለህ። 23እንደዚህ ብለውኛል፤ ‘በፊታችን የሚሄድ አምላክ አብጅልን። ከግብፅ ያወጣን ሰውየ ይህ ሙሴ ምን እንዳጋጠመው አናውቅም።’ 24እኔም፣ ‘ወርቅ ያለው ሰው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው። እነርሱም ወርቁን ሰጡኝ። በእሳት ውስጥም ጣልሁትና ይህ ጥጃ ወጣ።”25መዘባበቻ እንዲሆኑ አሮን መረን ስለ ለቀቃቸው፣ ሕዝቡ ከቊጥጥር ውጭ መሆናቸውን ሙሴ አስተዋለ። 26በሰፈሩ መግቢያ ቆሞ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ” አለ። ሌዋውያን ሁሉ በሙሴ ዙሪያ ተሰበሰቡ። 27ሌዋውያኑን እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ይታጠቅና በሰፈሩ ሁሉ ከበር እስከ በር ወደ ኋላና ወደ ፊት እየተመላለሰ ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል።’”28ሌዋውያኑ ሙሴ ያዘዘውን ፈጸሙ። በዚያ ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺሕ ያህል ሰዎች ሞቱ። 29ሌዋውያኑን፣ “ዛሬ ከእናንተ እያንዳንዱ በልጁና በወንድሙ ላይ እርምጃ ስለ ወሰደ፣ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀድሳችኋል። ስለዚህም እግዚአብሔር ዛሬ ባርኳችኋል” አላቸው።30በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን፣ “ታላቅ ኀጢአት ሠርታችኋል። አሁን ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ። ምናልባት ለኀጢአታችሁ ማስተሰረያ ማድረግ እችል ይህናል” አላቸው። 31ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ ሄደ፤ እንዲህም አለ፤ “ወዮ! እነዚህ ስዎች ታላቅ ኀጢአት ሠርተዋል፤ ለራሳቸውም ከወርቅ ጣዖት አበጅተዋል። 32ግን እባክህ ኀጢአታቸውን ይቅር በል፤ ይቅር የማትላቸው ከሆነ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍ እኔን ደምስስልኝ።”33ሙሴን እንዲህ አለው፤ እኔን የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ። 34ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ነገርኋችሁ ስፍራ ምራው። እነሆ፣ የእኔ መልአክ በፊትህ ይሄዳል። ሕዝቡን በምቀጣበት ቀን ግን ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።” 35አሮን በሠራው ጥጃ ስላደረጉት፣ እግዚአብሔር በሕቡ ላይ መቅሠፍት ላከባቸው።
1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተና ከግብፅ ያወጣሃው ሕዝብ ከዚህ ሂድ። ‘ለዘርህ እሰጠዋለሁ’ ባልሁ ጊዜ፣ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማልሁበት ምድር ሂድ። 2በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ፤ ከነዓናውያንን፣ አሞራውያንን፣ ኬጤያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያንንም አስወጣቸዋለሁ። 3ማርና ወተት ወደምታፈስሰዋ ምድር ሂዱ፤ ነግር ግን እናንተ ግትሮች ስለ ሆናችሁ፣ እኔ ከእናንተ ጋር አልወጣም። በመንገድ ላይ ላጠፋችሁ እችላለሁ።”4እነዚህን አስጨናቂ ቃሎች ሲሰሙ፣ አለቀሱ፤ ምንም ዐይነት ጌጥ ያደረገ ሰውም አልነበረም። 5ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበር፤ “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እናንተ ግትር ሰዎች ናችሁ። ለአፍታ እንኳ ዐብሬአችሁ ብሄድ፣ አጠፋችኋለሁ። ስለዚህ ምን እንደማደርግባችሁ ለመወሰን ጌጣጌጦቻችሁን አውልቁ።” 6እስራኤላውያንም ከኮሬብ ተራራ ጀምረው ጌጦቻቸውን አወለቁ።7አንድ ድንኳን ወሰደና በተወሰነ ርቀት ላይ ከሰፈር ውጭ ተከለው። የመገናኛ ድንኳን ብሎ ጠራው። ስለ ማንኛውም ጕዳይ እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ሰው ሁሉ ከሰፈሩ ውጭ ወደሚገኘው የመገናኛ ድንኳን ይሄድ ነበር። 8ወደ ድንኳኑ ሲሄድ፣ ሕዝቡ ሁሉ በየድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሞ ወደ ድንኳኑ ሲገባ ሙሴን ይመለከት ነበር። 9ወደ ድንኳኑ በሚገባበት ጊዜ ሁሉ፣ የደመና ዐምድ ይወርድና በድንኳኑ መግቢያ ላይ ይቆማል። እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር ይነጋገራል።10ሕዝቡ በድንኳኑ መግቢያ ላይ የደመናውን ዐምድ ቆሞ ሲያዩት፣ እያንዳንዱ ሰው በራሱ ድንኳን መግቢያ ላይ ይነሣና ይሰግዳል። 11እግዚአብሔር አንድ ሰው ጓደኛውን እንደሚያነጋግር፣ ሙሴን ፊት ለፊት ያነጋግረዋል። ከዚያም በኋላ ሙሴ ወደ ሰፈሩ ይመለሳል፤ አገልጋዩና ወጣት የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ ግን ከድንኳኑ አይለይም ነበር።12ሙሴ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሕዝብ ምራው ብለኸኝ ነበር፤ ከእኔ ጋር ማንን እንደምትልክ ግን አላሳወቅኸኝም። ‘በስም ዐውቅሃለሁ፤ በፊቴም ሞገስ አግኝተሃል’ ብለሃል። 13በፊትህ ሞገስ ካገኘሁ፣ እንዳውቅህና በፊትህ ሞገስን በማግኘት እንድቀጥል መንገዶችህን አሳየኝ። ይህ ሕዝብ የአንተ ሕዝብ እንደ ሆነም አስታውስ።”14እግዚአብሔርም መልሶ፣ “የእኔ ሀልዎት ከአንተ ጋር ዐብቶ ይሄዳል፤ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው። 15እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “የአንተ ሀልዎት ዐብሮን የማይሄድ ከሆነ፣ ከዚህ አታውጣን። 16ከእኛ ጋር ካልሄድህ፣ እኔና ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ ያገኘን መሆናችን እንዴት ሊታወቅ ይችላል? እኔና ሕዝብህ በምድር ገጽ ካለው ሕዝብ ሁሉ የተለየን የምንሆነው አንተ ከእኛ ጋር ብትሄድ ብቻ አይደለምን?”17ሙሴን፣ “በፊቴ ሞገስን ስላገኘህና በስምም ስለማውቅህ፣ የጠየቅኸውን አድረጋለሁ” አለው። 18“እባክህ ክብርህን አሳየኝ” አለ።19እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ ስሜን እግዚአብሔርንም በፊትህ ዐውጃለሁ። የምምረውን እምረዋለሁ፤ የምራራለትንም እራራለታለሁ።” 20ነገር ግን እግዚአብሔር፣ ፊቴን ማየትና በሕይወት መኖር የሚችል ሰው ስለሌለ፣ አንተ የእኔን ፊት ማየት አትችልም” ብሎ መለሰለት።21እንዲህ አለ፤ “እነሆ፣ በእኔ ዘንድ ስፍራ አለ፤ አንተ በዚህ ዐለት ላይ ትቆማለህ። 22ክብሬ በዚያ ሲያልፍ፣ እኔ እስከማልፍ ድረስ አንተን በዐለቱ ስንጥቅ ውስጥ በእጄ እሸፍንያለሁ። 23ከዚያም እጁን አነሣውና ጀርባዬን ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም።”
1እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንደ መጀመሪያዎቹ ጽላት አድርገህ ጥረብ። በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላት ላይ ተጽፈው የነበሩ ቃሎችን በእነዚህ ጽላት ላይ እጽፍባቸዋለሁ። 2ማለዳ ላይ ተዘጋጅተህ ወደ ሲና ተራራ ውጣና በዚያ በተራራው ዐናት ላይ በፊቴ ቁም።3ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይምጣ። በተራራው ላይ በየትኛውም ስፍራ ማንም እንዲታይ አታድርግ። የበግና የፍየል መንጋዎች፣ የቀንድ ከብቶችም እንኳ በተራራው ፊት ለፊት ሣር መጋጥ የለባቸውም።” 4ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንድ መጀመሪያዎቹ አድርጎ ጠረበ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ሲና ተራራ ወጣ። ሙሴ ሁለቱን የድንጋይ ጽላት በእጁ ይዞ ነበር።5እግዚአብሔር በደመና ወርዶ ከሙሴ ጋር በእዚያ ቆመ፤ ስሙን እግዚአብሔርንም ዐወጀ። 6በሙሴ ፊትም እንዲህ እያለ በማወጅ ዐለፈ፤ “እግዚአብሔር፣ ርኅሩኅም ቸርም አምላክ እግዚአብሔር፣ ለቊጣ የዘገየ፣ በጽኑዕ ፍቅርና በታማኝነት ባለ ጸጋ፣ 7ጽኑዕ ፍቅሩን ለሺሕ ትውልድ የሚጠብቅ፣ ክፋትን፣ ዐመፅንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፤ በደለኛውን ግን ከቶ ንጹሕ አያደርገውም። ለአባቶች ኀጢአት ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ይቀጣል።”8ሙሴ ወዲያውኑ ወደ መሬት ዝቅ ብሎ ሰገደ። 9አለ፤ “ጌታዬ ሆይ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ እባክህ ዐብረኸን ሂድ፤ ይህ ሕዝብ ግትር ሕዝብ ቢሆንም፣ ክፋታችንና ኀጢአታችንን ይቅር በለን፤ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።”10እንዲህ አለ፤ “እነሆ፣ ኪዳን እገባለሁ። በምድር ሁሉ አየትኛውም ሕዝብ ዘንድ ተደርገው የማያውቁ ድንቆችን በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ። በአንተ ዘንድ የማደርገው የሚያስፈራ ነውና፣ ዐብሮህ ያለው ሕዝብ ሁሉ ሥራዬን ያያል። 11የማዝዝህን ፈጽም። አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጤያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኢዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን በፊትህ አስወጣቸዋለሁ።12አገር ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ አለዚያ በመካከልህ ወጥመድ ይሆኑብሃል። 13ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን አድቅቋቸው፤ የአሼራ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ። 14ስሜ ‘ቀናተኛ’ የሆነ እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና ሌላ አምላክ አታምልክ።15ስለዚህም ከምድሪቱ ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን በመከተልያመነዝራሉና፣ መሥዋዕትም ያቀርቡላቸዋልና አንተንም አንዱ ስለሚጋብዝህና ከመሥዋዕቱም ጥቂት ስለምትበላ፣ 16ከዚያም ከሴቶች ልጆቹ የተወሰኑትን ለወንዶች ልጆችህ ትወስዳለህ፤ ሴት ልጆቹም አማልክታቸውን በመከተል ያመነዝራሉ፤ ወንዶች ልጆችህንም ለአማልክታቸው እንዲያመነዝሩ ያደርጓቸዋል። 17የተሠሩ አማልክትን ለራስህ አታብጅ።18የቂጣ በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት እርሾ ያልገባበትን ዳቦ በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር ሰባት ቀን ብላ፤ ከግብፅ የወጣሃው በአቢብ ወር ነበርና።19በኵር ሁሉ፣ የከብትህም እንኳ ተባዕት በኵር በሙሉ፣ የበሬዎችህም የበጎችም በኵር የእኔ ነው። 20የአህያውን በኵር በጠቦት ዋጀው፤ ካልዋጀኸው ግን ዐንገቱን ስበረው። በኵር ወንድ ልጆችህን ሁሉ ዋጃቸው። ባዶ እጁን በፊቴ የሚቀርብ ማንም እይኑር።21ቀን ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍ። በዕርሻና በመከር ጊዜም እንኳ ዕረፍ። 22ሱባዔ በዓል ከስንዴው በኵራት ጋር፣ የመክተቻውንም በዓል በዓመቱ መጨረሻ አክብር።23በአንተ ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእስራኤል አምላክ ፊት ይቅረብ። 24በፊትህ አስወጣቸዋለሁ፤ ወሰንህንም አሰፋዋለሁ። በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ለመውረርና ለመቆጣጠር ማንም አይመኝም።25ደም ከእርሾ ጋር አታቅርብ፤ ወይም በፋሲካ በዓል የቀረበው መሥዋዕት ሥጋ እስከ ማለዳ ተርፎ አይቆይ። 26የዕርሻህ ምርጥ በኵራት ወደ ቤቴ አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።”27እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እነዚህን ቃሎች ጻፋቸው፤ በተናገርሏቸው በእነዚህ ቃሎች ክአንተና ከእስራኤል ጋር ኪዳን አድርጌአለሁና አለው። 28አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር እዚያው ነበረ። ምግብም አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም።29ሁለቱን የምስክሩን ጽላት በእጁ ይዞ ከሲና ተራራ ወረደ። ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገረ ሳለ፣ ፊቱ የሚያበራ ምሆኑን አላወቀም። 30እስራኤላውያን ሙሴን ሲያዩት፣ ፊቱ ይበራ ነበር፤ ስለዚህም ወደ እርሱ ለመጠጋት ፈሩ። 31ግን ጠራቸው፤ አሮንና የሕዝቡ መሪዎችም ወደ እርሱ መቱ፣ ሙሴም ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ።32ከዚያ በኋላም፣ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ሙሴ መጡ፤ እርሱም በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሔር ሰጥቶት የነበረውን ትእዛዝ ሁሉ ነገራቸው። 33ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ፣ በፊቱ ላይ መሸፈኛ አደረገ።34ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር በፊቱ በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያወልቀው ነበር። ሲወጣ ምን እንዲል እንደታዘዘ ለእስራኤላይዋን ይነግራቸዋል። 35እስራኤላውያን የሚያበራውን ፊቱን ሲያዩ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ መሸፈኛውን እንደ ገና በፊቱ ላይ ያደርገዋል።
1የእስራኤልን ማኅበረ ሰብ ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፤ “እንድትፈጽሟቸው እግዚአብሔር የሰጣችሁ ትእዛዝት እነዚህ ናቸው። 2ስድስት ቀን ሥራ ትሠራላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት የሰንበት ቀን ይሁንላችሁ። በዚያ ቀን ሥራ የሚሥዐራ ሁሉ ይሞታል። 3በሰንበት ቀን በማንኛችሁም ቤት ውስጥ እሳት አይንደድ።”4ሁሉን የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው። 5ከልብ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቅርቡ። ሁሉም ለእግዚአብሔር የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ መባያምጣ፤ 6ሐምራዊና ቀይ ማግ፣ ቀጭን በፍታ፣ የፍየል ጠጒር፣ 7በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር ዕንጨት፣ 8መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያ ዘይቱ ቅመምና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፣ 9መረግዶችና ለኤፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ ሌሎች ዕንጨቶችንም መባ አድርጎ ያቅርብ።10በመካከላችሁ ያሉ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ይምጡና እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ይሥሩ፦ 11ከድንኳኑ ጋር፣ መደሪያውን፣ ማያያዣዎቹን፣ ክፈፎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ቋሚዎቹንና መሠረቶቹን፤ 12ታቦቱንም ከነመሎጊያዎቹ፣ የስርየት መክደኛውንና የሚሸፍነውን መጋረጃ፤13ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ ዕቃዎቹንም ሁሉን ኣየገጽ ኅብስቱን፤ 14የመብራቶቹን መቅረዝ ከዐባሪ ዕቃዎቹ ጋር፣ መብራቶቹንና የመብራቶቹን ዘይት፤ 15የዕጣኑን መሠዊያ ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣ የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መጋረጃ፣ 16የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ ከነሐስ መጫሪያው፣ ከመሎጊያዎቹና ከዕቃዎቹ ጋር፤ ትልቁን የመታጠቢያ ሰን እስከ ማስቀመጫው፤17የአድደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመሠረቶቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢይ ኣመጋረጃ፤ 18የማደሪያውን ድንኳን ካስማዎች ከነገመዶቻቸው፤ 19ውስጥ ለማገልገል በብልኀት የተሠሩ ልብሶችን፣ ካህናት ሆነው ለማገልገል ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ የሚሆኑ የተቀደሱ ልብሶችን ያምጡ።”20ከዚያም ሁሉም የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጥተው ሄዱ። 21ልቡ የተነሣሣና ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለውስጡም ለሚደረገው አገልግሎትና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ስጦታን ሰጡ። 22ፈቃደኛ የነበሩ ወንዶችም ሴቶችም መጥተው የአፍንጫ ጌጦችን፣ የጆሮ ጌጦችን፣ ቀለበቶችን፣ ድሪዎችንና ሁሉንም ዓይነት የወርቅ ጌጣጌጦች አመጡ።23ሐምራዊ፣ ቀይም ቀይ ማግ፣ ያማረ በፍታ፣ የፍየል ጠጕር፣ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ወይም የአስቆጣ ቆዳ የነበራቸውም አመጡ። 24ለማንኛውም ተግባር የሚጠቅም የግራር ዕንጨት የነራቸው፣ የብርና የነሐስ ስጦታ ማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ በስጦታነት ለእግዚአብሔር አቀረቡ።25ብልኀተኛ ሴቶችም ሁሉ ማግ ፈትለው፣ የፈተሉትን ሰማያዊ፣ ሕዐምራዊ፣ ወይም ቀይ ማግ አመጡ። 26ያነሣሣቸውና ብልኀተኛ የሆኑ ሴቶች ሁሉ የፍየል ጠጕር ፈተሉ።27ለአፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችንና ሌሎች ዕንቆችን አመጡ፤ 28ለመቅቢያው ዘይትና ጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን ዘይትና ቅመምም አመጡ። 29የነጻ ፈቃድ ስጦታ ለእግዚአብሔር በሙሴ በኩል እንዲፈጸም አዝዞት ለነበረው ሥራ ሁሉ ቍሳቍሶችን አመጡ።30እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እግዚአብሔር የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስም ጠርቶታል። 31ለሁሉም ዐይነት የጥበብ ሥራ ጥበብን፣ ማስተዋልንና ዕውቀትን ሊሰጠው ባስልኤልን በመንፈሱ ሞልቶታል፤ 32የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ጥበባዊ ሥራዎችን ለመሥራት፣ 33የጥበባዊ ሥራ ዐይነቶችን ሁሉ ለመሥራት ድንጋዮችን እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው።34እግዚአብሔር በባስልኤልና ከዳን ነገድ በሆነው በአሂሳሚክ ልጅ በኤልያብ ልብ ይህን ችሎታ አስቀመጠ። 35ጥበበኛ ሰዎች፣ እንደ ቀራጺዎች፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ፣ ባማረ በፍታም እንደ ጥልፍ ጠላፊዎችና እንደ ሸመና ሠራተኞች እንዲሠሩም ብልኀትን ሞላባቸው። እነርሱ በሥራ ዐይነቶች ሁሉ ጥበበኞች የሆኑ የጥበብ ባለሙያዎች ናቸው።
1ስለዚህ ባስልኤልና ኤልያብ፣ የልብ ጥበበኞች የነበሩና እንዲፈጽሙት እግዚአብሔር ያዘዘውን በመከተል መቅደሱ እንዴት እንደሚሠራ ለማወቅ ብልኀትንና ማስተዋልን ያስቀመጠባቸውም ሁሉ ይሠራሉ።2ባስልኤልንና ኤልያብን፣ እግዚአብሔር በልቡ ብልኀትን አስቀምጦበት የነበረ ጥበበኛ ስውን ሁሉ፣ መጥቶ ሥራውን ለመሥራት ልቡ ያነሣሣውንም ጠራ። 3የጠራቸውም ለመቅደሱ ሥራ እስራኤላውያን አምጥተውት የነበረውን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ተቀበሉ። ሕዝቡ የነጻ ፈቃድ ስጦታዎችን ጠዋት ጠዋት ወደ ሙሴ ማምጣት አላቋረጡም ነበር። 4ስለዚህ በመቅደሱ ሥራ ላይ የተሰማሩ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ከሚሠሩት ሥራ ተነሥተው መጡ።5ሙሴን፣ “እግዚአብሔር እንድንሠራው ላዘዘን ሥራ ከሚበቃው በጣም የሚበልጥ ሕዝቡ እያመጡ ነው” አሉት። 6ሙሴም በሰፈሩ ውስጥ ያለ ማንም ሰው ለመቅደሱ ሥራ ሌላ ስጦታ እንዳያመጣ ትእዛዝ ሰጠ። ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ስጦታ ማምጣቱን አቆሙ። 7ለሥራው ሁሉ ከሚበቃው በላይ ቍሳቍሶች ነበሯቸው።8ያሉ ጥበበኞችም ሁሉ ከአማረ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግም ከተሠሩትና ኪሩቤልም ከተጠለፉባቸው ዕሥር መጋረጃዎች ጋር የመገናኛውን ድንኳን ሠሩት። ይህም እጅግ ጥበበኛ የነበረው የባስልኤል ሥራ ነው። 9መጋረጃ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ሁሉም መጋረጃዎች እኩል መጠን ነበራቸው። 10ባስልኤል ዐምስት ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርጎ እርስ በርስ አገጣጠማቸው።11መጋረጃዎች የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይና በሁለተኛውም ተገጣጣሚ መጋረጃ የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይ ሰማያዊ ቀለበቶችን አደረገ። 12በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዞች ዐምሳ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ። ስለሆነም ቀለበቶቹ እርስ በርስ ትይዩ ሆነው የተደረጉ ነበር። 13ባስልኤል ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርቶ የመገናኛው ድንኳን ወጥ እንዲሆን መጋረጃዎቹን አያያዛቸው።14ባስልኤል በማደሪያው ላይ ላለው ድንኳን ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሠራ። 15የእያንዳንዱ መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ዐሥራ አንድ መጋረጃዎች እያንዳንዳቸው እኩል መጠን ነበራቸው። 16መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው፣ ስድስቱንም መጋረጃዎች እንደዚሁ እርስ በርሳቸው አያያዛቸው። 17ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን በሁለተኛዎቹ ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ።18ባስልኤል ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን ለማገጣጠም ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሠራ። 19ለድንኳኑ መሸፈኛ በቀይ ቅለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ከበላዩም የሚህን የአቆስጣ ቆዳ ሠራ።20ባስልኤል ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ። 21ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 22እርስ በርስ ለማያያዝ በያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ማያያዣዎች ነበር። የመገናኛውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሠራ። 23ባስልኤል በዚህ መንገድ ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ። ለደቡቡ ጎንም ሃያ ወጋግራዎችን አበጀ።24ባስልኤል ከሃያዎቹ ወጋግራዎች ሥር የሚሆኑ አራ የብር መቆሚያዎችን አበጀ። ማያያዣዎች ለመሆን ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ከያንዳንዱ ሌላ ወጋግራ በታችም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች ነበሩ። 25ጎን ላለው ለመገናኛው ድንኳን ሁለተኛ ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና 26የብር መቆሚያዎቻቸውን አበጀ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንዲሁ ሁለት ሁለት መቆሚያ አበጅቶአል።27በስተ ምዕራብ ላለው ለመገናኛው ድንኳን ጀርባ ባስልኤል ስድስት ወጋግራዎችን ሠራ። 28ድንኳን የኋላ ማእዘኖች ሁለት ወጋግራዎችን አበጀ።29እነዚህ ወጋግራዎች ከታች የተነጣጠሉ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የየያያዙ ነበር። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የተደረገው በዚህ መንገድ ነበር። 30ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ስምንት ወጋግራዎች ነበሩ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለውም ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ለያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ሁለት በመሆን ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ነበሩ።31ባስልኤል የግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን አበጀ፦ ለመገናኛው ድንኳን አንድ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት፣ አግዳሚዎችን፣ 32የመገናኛው ድንኳን ጎን ወጋግራዎች አምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳን የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን ሠራ። 33አግዳሚዎቹን የሥራቸውም በወጋግራዎች መካከል ላይ ከዳር እስከ ዳር እንዲደርሱ አድርጎ ነው። 34ወጋግራዎቹን በወርቅ ለበጣቸው። አግዳሚዎችን ለማያያዝ የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ፣ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለበጣቸው።35በብልኀተኛ ሠራተኛ ሥራ ኪሩቤል የተጠለፉበትን መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም ሠራው። 36አራት የግራር ዕንጨት ምሰሶዎችን አበጅቶ በውርቅ ለበጣቸው። ለምሰሶዎችም የወርቅ ኵላቦችን ሠርቶ አራት የብር መቆሚያዎችን አደረገላቸው።37ለድንኳኑ መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም በጥልፍ ጠላፊ ሥራ የተዘጋጀ መጋረጃ አበጀለት። 38የመጋረጃውን ዐምስት ምሰሶዎች ከኵላቦች ጋር ሠራ። የምሰሶዎችን ዐናትና ዘንግ በወርቅ ለበጣቸው። ዐምስት መቆሚያዎቻቸውም ከነሐስ የተሰሩ ነበሩ።
1ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱ አንድ ተኩል ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦታ ከግራር ዕንጨት ሠራ። 2ውስጡንና ውጩንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት። 3ለአራት እግሮቹም አራት የወርቅ ቀለበቶችን፣ በአንዱ ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን፣ በሌላውም ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን ጨምሮ ሠራ።4ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 5ታቦቱን ለመሸከም በታቦቱ ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አስገባቸው። 6ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።7ባስልኤል ለስርየት መክደኛው ሁለት ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ አበጀ። 8አንዱ ኪሩብ ለአንዱ የስርየት መክደኛ፣ ሌላውም ለሌላው የስርየት መክደኛ ጫፍ ነበረ። ኪሩቤል ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው ተበጅተው ነበር። 9ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት የስርየት መክደኛውን በድንፎቻቸው ጋረዱት። እርስ በርስ ትይዩ ሆነውም ወደ ስርየት መክደኛው መካከል ይመለከቱ ነበር።10ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሠራ። 11ወርቅ ለበጠው፤ ዙሪያውንም በንጹሕ ወርቅ ከፈፈው። 12አንድ ስንዝር ጠርዝ ከወርቅ ክፈፍ ጋር አበጀለት። 13የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርቶ የጠረጴዛው እግሮች ካሉበት ማእዘኖች ጋር አያያዛቸው።14ለመሸከም መሎጊያዎችን ማስገባት እንዲቻል ቀለበቶቹ ከጠርዙ ጋር ተያይዘው ነበር። 15ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 16በጠረጴዛው ላይ የሚቀመጡ ዕቃዎችን፦ ድስቶችን፣ ዝርግና ጎድጓዳ ሳሕኖችን ጭልፋዎችን፣ ወጭቶችንና የመጠጥ መሥዋዕቱን ማፍሰሻ ማንቆርቆሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።17ከነማቆሚያውና ከነዘንጉ ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ ሠራ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ በሙሉ ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ነበር የተሠሩት። 18ቅርንጫፎች በመቅረዙ አንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፎች ደግሞ በሌላው የመቅረዙ ጎን ተሠርተው ስድስት ቅርንጫፎች ነበር። 19ቅርንጫፍ ከቀንበጥና ክአበባ ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ነበሩት፤ በሌላውም ቅርንጫፍ እንደዚሁ የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ነበር። ከመቅረዙ ለሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር።20በመቅረዙ መካከል ላይ ባለው ዘንግ ላይ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ እራት ጽዋዎች ከቀንበጦቻቸውና ከአበቦቻቸው ጋር ተሠርተዋል። 21በመጀመሪያ የቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮት የተሠሩ ቀንበጦች ነበር። ከመቅረዙ በሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር። 22ቅርንጫፎቻቸው ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበር።23መቅረዙንና ሰባቱን መብራቶች፣ መኮስተሪያዎቹንና የኵስታሪ ማስቀመጫዎቻቸውን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። 24መቅረዙንና ዐባሪ ዕቃዎቹን ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠራቸው።25እርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ የሆነውን የዕጣኑን መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። አራት ማእዘንና ቁመቱም ሁለት ክንድ ነበር። ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበር። 26የዕጣኑን መሠዊያ፦ ዐናቱን፣ ጎኖቹንና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጣቸው። ለዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።27በሁለቱ ተነጻጻሪ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ ሥር እንዲያያይዙት ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ። ቀለበቶቹ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎችን ለመያዝ የሚያገለግሉ ናቸው። 28ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 29የተቀሰውን የመቅቢያ ዘይትና የሽቶ ቀማሚ ሥራ የሆነውን፣ ንጹሕና ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን ሠራ።
1የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። ዐምስት ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ስፋት፣ አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ቁመት ነበረው። 2ማእዘኖችም የበሬ ቀንዶችን የሚመስሉ ቅርጾችን በመሥራት አስረዘማቸው። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ መሠዊያውንም በነሐስ ለበጠው። 3ለመሠዊያው የሚያስፈልገውን ዕቃ ሁሉ፦ ለዐመድ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን በሙሉ ከነሐስ ሠራ።4ከደረጃው ሥር ከመሠዊያው እኩሌታ እስከ ታች የሚደርስ እንደ መረብ የተሠራ የነሐስ ፍርግርግ ለመሠዊያው አበጀ። 5ፍርግርግ አራት ማእዘኖች ለመሎጊያዎቹ መያዣ አራት ቀለበቶችን ሠራላቸው።6ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በነሐስ ለበጣቸው። 7መሎጊያዎቹን መሠዊያውን ለመሸከም በመሠዊያው ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። መሠዊያውን ክፍት አድርጎ በሳንቃዎች ሠራው።8ባስልኤል ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን ከነሐስ መቆሚያ ጋር ሠራ። ሳሕኑን የሠራውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ የሚያገለግሉት ሴቶች ይጠቀሙባቸው ከነበሩ መስተዋቶች ነው።9ሠራው። በአደባባዩ ደቡብ ጎን ላይ የነበሩት መጋረጃዎች ከአማረ በፍታ የተሠሩና አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው ነበሩ። 10መጋረጃዎቹ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ መቆሚያዎች ነበሯቸው። ከምሰሶዎቹና ከብር ዘንጎቹ ጋር የተያያዙ ኵላቦችም ነበሩ።11ጎን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎችና ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች፣ ከምሰሶዎቹ ጋር ከተያያዙ ኲላቦችና ከብር ዘንጎች ጋር ነበር። 12የምዕራቡ ጎን መጋረጃዎች ዐምሳ ክንድ የሚረዝሙ፣ ዐሥር ምሰስዎችና መቆሚያዎች ያሏቸው ነበሩ። የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎች ብር ነበሩ።13አደባባዩም በምሥራቁ ጎን ላይ ዐምሳ ክንድ ይረዝም ነበር። 14የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች እርዝመት ዐሥራ ዐምስት ክንድ ነበረ። ሦስት ምሰሶዎች ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ነበሯቸው። 15በአደባባዩ መግቢያ ሌላ ጎን ላይም ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሚረዝሙና ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው መጋረጃዎች ነበሩ። 16በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች ሁሉ አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ ነበሩ።17የምሰሶዎቹ መቆሚያዎች ከነሐስ፣ የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎቻቸው፣ የዐናታቸውም መሸፈኛ ከብር የተሠሩ ነበሩ። የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ በብር የተለበጡ ነበር። 18የአደባባዩ በር መጋረጃቅ እርዝመት ሃያ ክንድ ነበረ። ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠራ ነበረ። እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች ሃያ ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ቁመት ነበረው። 19የነሐስ መቆሚያዎችና የብር ኵላቦች ነበሩት። የዐናታቸው መሸፈኛና ዘንጎቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ። 20የመገናኛው ድንኳን ካስማዎች ሁሉ የተሠሩት ከነሐስ ነበር።21የሙሴን ትእዛዝ በመከተል በተመዘገበው መሠረት የመገናኛው ድንኳን፣ ይኸውም የምስክሩ ድንኳኝ ቆጠራ ይህ ነው። በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር መሪነት ይህ የሌዋውያኑ ሥራ ነበረ። 22ከይሁዳ ነገድ የሆነው፣ የሖር የልጅ ልጅ፣ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ ፈጸመ። 23ከባስልኤልም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ቅርጽ አውጪ ሠራተኛ፣ የእጅ ጥበብ ሙያተኛ፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ግምጃና በአማረ በፍታ ጥልፍ ጠላፊም ሆኖ ዐብሮት ሠራ።24ከመቅደሱ ሥራ ጋር ለተያያዘው ተግባር ሁሉ ጥቅም ላይ የዋለው ወርቅ ማለትም፣ ከስጦታው የተገኘው ወርቅ ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል መጠን መሠረት ሃያ ዘጠኝ መክሊትና ሰባት መቶ ሠላሳ ሰቅል ነበረ። 25ማኅበረ ሰቡ የሰጠው ብር በመቅደሱ ሰቅል መጠን ተመዝኖ አንድ መቶ መክሊትና አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰባ ዐምስት ሰቅል፣ 26በአንድ ሰው አንድ ቤካ ይኸውም በመቅደሱ ሰቅል መጠን ግማሽ ሰቅል ነበረ። ይህ ቍጥር የተደረሰበት በሕዝብ ቆጠራው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆናቸው ተቆጥረው በተገኘው ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ወንዶች ቍጥር በያንዳንዱ ሰው ተሰልቶ ነው።27የመቅደሱንና የመጋረጃዎችን መቆሚያዎች ለመሥራት አንድ መቶ የብር መክሊት ወጪ ሆኖአል፦ መቆሚያዎቹ በጠቅላላ አንድ መቶ ሆነው፣ ለያንዳንዱ መቆሚያ አንድ መክሊት ተከፍሎአል ማለት ነው። 28በቀሩት አንድ ሺሕ ሰባቶ መቶ ሰባ ዐምስት የብር ሰቅሎች ባስልኤል የምሰሶዎቹን ኵላቦች ሠርቶ ዐናታቸውን ሸፈነባቸው፤ ዘንጎችንም ለምሰሶዎቹ ሠራባቸው። 29ከስጦታ የተገኘው ነሐስ ተመዝኖ ሰባ ታለንትና ሁለት ሺሕ አራት መቶ ሰቅል ሆነ።30በዚህም የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የነሐስ መሠዊያውን፣ የእርሱንም የነሐስ ፍርግርግ፣ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ፣ 31የአደባባዩን መቆሚያዎች፣ የአደባባዩን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የመገናኛውን ድንኳንና የአደባባዩን ድንኳን ካስሞች ሁሉ ሠራበት።
1በመቅደሱ ውስጥ ለሚከናወነው አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተሠሩ ልብሶችን አበጁ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለቤተ መቅደሱ የሚሆኑ የአሮንን ልብሶች ሠሩ።2ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሠራ። 3ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በአማረ በፍታ ለመ|ሥራት ወርቁን ቀጥቅጠው ወደ ሽቦነት ቆራረጡት።4የትከሻ ንጣዮችን ሠርተው ከላይኛዎቹ ጠርዞቹ ጋር አያያዙት። 5በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉዱ ሲሆን፣ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፣ አምሮ ከተፈተለ በፍታ ይኸውም ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከኤፉድ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ።6የመረግድ ድንጋዮችን በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ አበጁላቸው፤ እንደ ማኅተምም የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቀረጹባቸው። 7እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ ባስልኤል በሴፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች አድርጎ አስቀመጣቸው።8ኪሱንም ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ እንደ ኤፉዱ አበጀው። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከአማረ በፍታ ሠራው። 9ኪሱ አራት ማእዘን ነበረ። ርዝመቱም ወርዱም አንድ ስንዝር ሆኖ የተደረበ ዕጥፍ ነበረ።10በውስጡም አራት የዕንቍ ድንጋዮች ፈድፎች አበጅተዋል። በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮንና አብራቅራቂ ዕንቍ ነበሩት። 11ረድፍ በሉር፣ ሰንፔር፣ አልማዝ፤ 12በሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶን፣ አሜቴስጢኖስ፤ 13በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ነበሩ። ድንጋዮቹ በወርቅ ፈርጥ ዙሪያቸውን የተከፈፉ ነበር።14እያንዳንዳቸው በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት የተቀመጡ ነበር። እያንዳንዱ ስም ከዐሥራ ሁለቱ ነገዶች አንዱን በመወከል በማተሚያ ቀለበት ላይ እንደሚቀረጽ የተቀረጸባቸው ነበሩ። 15ኪሱ ላይ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አበጁ። 16ሁለት የወርቅ ፈርጦችንና ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ሁለቱን ቀለበቶች ከደረት ኪሱ ሁለት ጠርዞች ጋር አያያዟቸው።17ሁለቱን የተጎነጎኑ የወርቅ ድሪዎች በደረት ኪሱ ጠርዞች ሁለት ቀለበቶች ውስጥ አስቀመጧቸው። 18ሌሎች ሁለት ጫፎች ከሁለት ፈርጦች ጋር አያያዟቸው። ከኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ጋር በኤፉዱ ፊት አገናኗቸው።19የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከውስጠኛው ጠርዝ ቀጥሎ በሚገኘው ጎን በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጠርዞች ላይ አስቀመጧቸው። 20ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው፣ በመያዣው አጠገብ በብልኀት ከተሠራው የወገብ መታጠቂያ በላይ፣ ከአፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያያዟቸው።21በብልኀት ከተሠራው ከኤፉዱ የወገብ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችል፣ የደረት ኪሱን በራሱ ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ፈትል አሰሩት። ይህ የሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ የተነጠለ እንዳይሆን ነው። የተደረገውም እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።22የኤፉዱን ቀሚስ ሙሉ በሙሉ የሸማኔ ሥራ ከሆነው ከሐምራዊ ጨርቅ ሠራው። 23መካከሉ ላይ ዐንገት ማስገቢያ ነበረው። እንዳይቀደድም ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ነበረው። 24በታችኛው የቀሚሱ ዘርፍ ላይም የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ማግና የአማረ በፍታ ሮማኖችን አበጁ።25ሻኵራዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በታችኛው የቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ላይ በሮማኖቹም መካከል፣ 26አገልግሎት በቀሚሱ ጠርዝ ላይ ሻኵራን ሮማን፣ ሻኵራና ሮማን እያደረጉ አስቀመጧቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።27ለአሮንና ለልጆቹ ሸሚዞችን ከአማረ በፍታ ሠሩ። 28የራስ መጠምጠሚያዎችን፣ ቆቦችንና ሱሪዎችን ከአማረ በፍታ፣ 29መታጠቂያዎችንም ከአማረ በፍታ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ጥልፍ ጠላፊ እንደሚሠራው አድርገው አበጇቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።30አክሊል ሠሌዳ ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ በላዩ ቅዱስ ለእግዚአብሔርን ቀረጹበት። 31እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ በመጠምጠሚያው ዐናት ላይ ለማንጠልጠል ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት።32ድንኳን፣ የማደሪያው ሥራ ተጠናቀቀ። የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጣቸውን መመሪያዎች በመከተል ሁሉንም አደረጉ። 33ድንኳኑንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ ካስማዎቹን፣ ወጋግራዎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ምሰሶዎቹንና መቆሚያዎቹን፣ 34በቀይ ቀለም የተነከረውን የአውራ በግ ቆዳ መሸፈኛ፣ የአስቆጣ ቆዳዊን መሸፈኛና የሚሸፍነውን መጋረጃ፣ 35የምስክሩን ታቦት፣ መሎጊያዎቹንና የስርየት መክደኛውን ወደ ሙሴ አመጡ።36ጠረጴዛውን፣ የጠረጴዛውን ዕቃዎች ሁሉና የገጽ ኅብስቱን፤ 37የንጹሑን ወርቅ መቅረዝና የረድፍ መብራቶችን ከዐባሪ ዕቃዎቹና ከመብራቶቹ ዘይት ጋር፤ 38መሥዐዊያውን፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዐዛ ያለን ዕጣን፣ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃ፤ 39የነሐስ መሠዊያውን ከነሐስ ፍርግርጉና ከመሎጊያዎቹ፣ ከዕቃዎቹ፣ ከትልቁ የመታጠቢያ ሳሕንና ከመቆሚያው ጋር አመጡ።40የአደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመቆሚያዎቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃም፣ ገመዶቹንና የድንኳን ካስማዎችን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውለውን ዕቃ ሁሉ አመጡ። 41አገልግሎት በጥበብ የተሠሩትን ልብሶች፣ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም አመጡ።42ስለዚህም የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሥራውን በሙሉ አከናወኑ። 43ሙሴ ሥራውን ሁሉ ሲፈትሽ፣ እነሆ ሁሉን አከናውነውታል። ያከናወኑትም እግዚአብሔር አዝዞት በነበረው በዚያው መንገድ ነው። ሙሴም ሕዝቡን ባረካቸው።
1ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“በዐዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ወር የመጀመሪያ ቀን ማደረያውን፣ የመገናኛውን ድንኳን ትከለው።3ታቦት በውስጡ አስቀምጠው፤ ታቦቱንም በመጋረጃ ከልለው። 4ጠረጴዛውንም ወደ ውስጥ አምጣና በላዩ የሚቀመጡትን ዕቃዎች በሥርዐት አስቀምጥ። ከዚያም መቅረዙን አስገብተህ መብራቶቹን አስተካክል።5የወርቅ የዕጣን መሠዊያውን በምስክሩ ታቦት ፊት አስቀምጥ፤ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃም አድርግ። 6የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት አስቀምጥ። 7ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠው፤ ውሀም አድርግበት።8በዙሪያውም አደባባይ ሥራለትን በአደባባዩ መግቢያ ላይ መጋረጃውን ስቀል። 9መቅቢያ ዘይቱን ውሰድና መገናኛውን ድንኳንና አውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ቅባ። እርሱንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም የተቀደሰ ይሆናል። 10የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያና የመሠዊያውን ዕቃዎች ሁሉ ቅባቸው። 11መሠዊያውን ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም ለእኔ እጅግ የተቀደሰ ይሆንልኛል።12ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ አምጣና በውሀ እጠባቸው። 13ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን ለአሮን አልብሰው፤ ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግልም ቅባው፤ ቀድሰውም።14ልጆቹንም አምጣና ሸሚዞችን አልብሳቸው። 15ካህናቴ ሆነው እንዲያገለግሉኝ፣ አባታቸውን እንደ ቀባኸው እነርሱንም ቅጣቸው። የእነርሱ መቀባት በትውልዶች ሁሉ የዘለቄታ ካህንነትን ለእነርሱ ያስገኛል።” 16ሙሴ ያደረገው ይህ ነው፦ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ተከተለ። እነዚህንም ሁሉ አደረገ።17በሁለተኛው ዓመት የመጀመሪያ ወር አንደኛ ቀን ላይ የመገናኛው ድንኳን ተተከለ። 18ሙሴ መገናኛውን ድንኳን ተከለ፤ መቆሚያዎቹንም በስፍራቸው አስቀመጠ፤ ወጋግራዎቹን አቁሞ አግዳሚዎቹን አያያዘ፤ ምሰሶዎቹንም አቆመ። 19በማደሪያው ላይ መሸፈኛውን ዘረጋ፤ ድንኳኑንም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ከበላዩ አስቀመጠው። 20ምስክሩን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጠው።21ወደ መገናኛው ድንኳን አመጣው። እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ የምስክሩን ታቦት ለመከለል መጋረጃውን አደረገ። 22ሰሜን ጎን ከመጋረጃው ውጭ ጠረጴዛውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ። 23እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው፣ ኅብስቱን በጠረጴዛው ላይ በሥርዐት በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጠው።24መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ደቡብ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ በማደሪያው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠው። 25መብራቶቹን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእግዚአብሔር ፊት አበራቸው።26የተሠራውን የዕጣን መሠዊያም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ፊት ለፊት አደረገው። 27ላይም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን አቀጣጠለ።28መጋረጃውን በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሰቀለ። 29የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ አስቀመጠ። በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን እግዚአብሔር እንዳዘዘው አቀረበ። 30የመታጠቢያ ሳሕኑን በመገናኛው ድንኳንና በመሠውያው መካከል አኖረው፤ የመታጠቢያ ውሀም በውስጡ አደረገ።31ሙሴ፣ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በመታጠቢያው ውሀ ይታጠቡ ነበር፤ 32መገናኛው ድንኳን ውስጥ በሚገቡትና መሠዊያው ወዳለበት ወደ ላይ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ታጥበውታል። 33ሙሴ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን አቆመ። መጋረጃውንም በአደባባዩ መግቢያ ዘረጋ። ሙሴ በዚህ መንገድ ሥራውን ፈጸመ።34ደመናውም የመገናኛውን ድንኳን ሸፈነ፤ የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ሞላው። 35ደመናው በላዩ ስላረፈና የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ስለ ሞላው፣ ሙሴ መገናኛው ድንኳን ውስጥ መግባት አልቻለም ነበር።36ከማደሪያው ድንኳን በተነሣ ጊዜ ሁሉ፣ የእስራኤል ሰዎች ይጓዛሉ። 37ግን ደመናው ከማደሪያው ላይ ካልተነሣ፣ ሕዝቡ አይጓዙም። ደመናው እስከሚነሣበት ቀን ድረስ ይቆያሉ። 38በሁሉም የእስራኤል ሕዝብ ፊት በጕዟቸው ሁሉ ቀን የእግዚአብሔር ደመና፣ ማታ ደግሞ እሳቱ በማደሪያው ላይ ነበረ።
1ያህዌ ከመገናኛው ድንኳን ሆኖ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ አለው፣ 2“ለእስራኤላዊያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ከእናንተ መሃል ማንም ሰው ለያህዌ መባ በሚያቀርብበት ጊዜ ከከብቶቻችሁ ወይም ከመንጋው እንስሳት መሃል አንዱን ያቅርብ፡፡3መባው ከመንጋው መሃል የሚቃጠል መስዋዕት ከሆነ፣ ነውር የሌለበት ወንድ መስዋዕት ያቅርብ፡፡ መስዋዕቱ በያህዌ ፊት ተቀባይነት ያለው ይሆን ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያቅርበው፡፡ 4በሚቃጠለው መስዋዕት ራስ ላይ እጁን ይጭናል፣ ይህም በእርሱ ምነትክ ያስተሰርይለት ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል፡፡5ከዚያ በያህዌ ፊት ወይፈኑን ይረድ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ካህናቱ የአሮን ልጆች ደሙን ያቀርቡና በመሰዊያው ላይ ይረጩታል፡፡ 6ከዚያም ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ቆዳ መግፈፍና ብልቶችንም ማውጣት ይኖርበታል፡፡7ከዚያም ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ላይ ዕሳት ይለኩሱና እንጨት ይጨምሩበታል፡፡ 8ካህናቱ የአሮን ልጆች የስጋውን ብልቶች፣ የከብቱን ጭንቅላትና ስቡን በመስዋዕቱ ምድጃ ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ በስርዓት ይደረድሩታል፡፡ 9ነገር ግን ካህኑ የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ማጠብ ይኖርበታል፡፡ በመስዋዕቱ ላይ የሚገኘውን ሁሉ የሚቃጠል መስዋዕት አብርጎ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለእኔ ጣፋጭ ሽታ ይሆናል፤ ይህም ለእኔ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡10ለመስዋዕት የሚያቀርበው የሚቃጠል መስዋዕት ከመንጋው ከሆነ፣ ከበጎች ወይም ከፍየሎች መሃል ነውር የሌለበት ተባዕት መስዋዕት ማቅረብ አለበት፡፡ 11በያህዌ ፊት መስዋዕቱን ከመሰዊያው በስተቀኝ በኩል ይረደው፡፡ ካህናቱ የአሮን ልጆች የመስዋዕቱን ከብት ደም በመሰዊያው ዙሪያ ሁሉ ይርጩት፡፡12ከዚያ ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ጭንቅላቱንና ስቡን እንዲሁም ብልቶቹን ይቆራርጥ፡፡ ከዚያም በመሰዊያው በሚገኘው የሚነድ እንጨት ላይ በስርዓት ይደርድረው፡፡ 13ነገር ግን የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፡፡ ከዚያ ካህኑ መባውን በሙሉ ያቅርብና በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህም የሚቃጠል መስዋዕት ነው፣ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፤ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡14“ካህኑ ለያህዌ የሚያቀርበው የሚቃጠል የወፎች መስዋዕት ከሆነ፣አንድ ወፍ ወይም ዕርግብ ማቅረብ አለበት፡፡ 15ካህኑ መስዋዕቱን ወደ መሰዊያው ያመጣና አንገቱን ይቆለምመዋል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ደሙም በመሰዊያው ጎን ተንጠፍጥፎ ይፈሳል፡፡16የወፉን ማንቁርትና በውስጡ ያሉትን ያስወግድ፣ ከዚያም አመድ በሚደፉበት ከመሰዊያው በስተ ምስራቅ ይወርውረው፡፡ 17ክንፎቹን ይዞ ይሰንጥቀው፣ ነገር ግን ለሁለት አይክፈለው፡፡ ከዚያ ካህኑ በዕሳቱ ላይ ባለው እንጨት መሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡”
1ማንኛውም ሰው ለያህዌ የእህል ቁርባን ሲያቀርብ፣ መባው መልካም ዱቄት ይሁን፣ ዘይት ያፈስበታል ደግሞም ዕጣን ያድርግበት፡፡ 2ቁርባኑን ወደ ካህናቱ ወደ አሮን ልጆች ይወስደዋል፣ ካህኑ ከዘይቱና በላዩ ካለው ዕጣን ጋር ከመልካሙ ዱቄት እፍኝ ይወስዳል፡፡ ከዚየም ካህኑ የያህዌን በጎነት ለማሰብ መስዋዕቱን በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ነው፣ ለእርሱ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡ 3ከእህል መስዋዕቱ የተረፈው ሁሉ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ በዕሳት ከተዘጋጀው መስዋዕት ለእርሱ የተለየ ነው፡፡4በምድጃ የተጋገረ እርሾ የሌለበት የእህል ቁርባን ስታቀርብ፣ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ለስላሳ ዳቦ መሆን አለበት፣ ወይም እርሾ የሌለበት በዘይት የተቀባ ቂጣ መሆን አለበት፡፡ 5የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ ላይ የተጋገረ ከሆነ፣ እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን፡፡6ቆራርሰህ በላዩ ዘይት ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡ 7የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ የሚዘጋጅ ከሆነ ከመለካም ዱቄትና ዘይት ይዘጋጅ፡፡8ከእነዚህ ነገሮች የተዘጋጀውን የእህል ቁርባን ወደ ያህዌ ማቅረብ አለብህ፣ እናም ይህ ወደ መሰዊያው ወደሚያመጣው ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡ 9ከዚያም የያህዌን በጎነት ለማሰብ ካህኑ ከእህል ቁርባኑ ጥቂት ይወስዳል፣ ቀጥሎም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፡፡ 10ከእህል ቁርባኑ የሚተርፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ለያህዌ በዕሳት ከሚዘጋጀው ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየ ነው፡፡11ለያህዌ በምታቀርቡት የእህል ቁርባን ውስጥ እርሾ አይግባበት፣ ለያህዌ በዕሳት በምታዘጋጁት ቁርባን ውስጥ ምንም እርሾ፣ ወይም ማር አታቃጥሉ፡፡ 12እነዚህን እንደ በኩራት ፍሬዎች ለያህዌ ታቀርባላችሁ፣ ነገር ግን በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ ለመስጠት አታቀርቧቸውም፡፡ 13የእህል ቁርባንህን ሁሉ በጨው አጣፍጠው፡፡ ከእህል ቁርባንህ በፍጽም የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨው አይታጣ፡፡ በመስዋዕቶችህ ሁሉ ጨው ማቅረብ አለብህ፡፡14ለያህዌ ከፍሬህ በኩራት የእህል ቁርባን ስታቀርብ ከእሸቱ በእሳት የተጠበሰውንና የተፈተገውን አቅርብ፡፡ 15ከዚያ በላዩ ላይ ዘይትና እጣን ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡ 16ከዚያ ካህኑ የተፈተገውን እህል እና ዘይት እንዲሁም ዕጣን የያህዌን በጎነት በአንክሮ ለማሰብ ከፊሉን ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ የሚቀርብ የዕሳት መስዋዕት ነው፡፡
1ማንኛውም ሰው ከመንጋው መሃል ወንድም ሆነ ሴት እንስሳ የህብረት መስዋዕት እንስሳ ቢያቀርብ፣በያህዌ ፊት ነውር የሌለበት እንስሳ ያቅርብ፡፡ 2እጁን በመስዋዕቱ እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፣ ከዚያም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያርደዋል፡፡ ከዚያ ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ይረጩታል፡፡3የህብረት መስዋዕቱን ለያህዌ በዕሳት ያቀርባል፡፡ ሆድቃውን የሸፈነውን ወይም ከዚያ ጋር የተያያዘውን ስብ፣ 4እና ሁለቱን ኩላሊቶች እንዲሁም በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን ስብ፣ እና የጉበቱን መረብ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡ 5የአሮን ልጆች ከሚቃጠለው መስዋዕት ጋር እነዚህን በዕሳቱ ላይ በሚገኘው እንጨት በመሰዊያው ላይ ያቃጥሉታል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ይሆናል፡፡6ለያህዌ የሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት ወንድም ይሁን ሴት እንስሳ ነውር የሌለበት ይሁን፡፡ 7መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነ፣ በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡ 8እጁን በመስዋዕቱ ራስ ላይ ይጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡9የህብረት መስዋዕቱን በእሳት እንደሚቀርብ መስዋዕት አድርጎ ለያህዌ ያቀርባል፡፡ ስቡን፣ላቱን እስከ ጀርባ አጥንቱ ድረስ፣እንዲሁም የሆድ እቃውን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ፣ 10እና ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር ያለውን ስብ፣ በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን እና የጉበቱን መሸፈኛ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡ 11ከዚያም ካህኑ ሁሉንም ለያህዌ በመሰዊያው ላይ በእሳት የመበል ቁርባን አድርጎ ያቃጥላል፡፡12የሚያቀርበው መስዋዕት ፍየል ከሆነ፣በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡ 13እጁን በፍየሉ ራስ ላይ መጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ማረድ ይኖርበታል፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡ 14በእሳት የተዘጋጀውን መስዋእቱን ለያህዌ ያቀርባል፡፡ የሆድ እቃውን የሸፈነውንና በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡15እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር የሚገኘውን ስብ፣ በጎድኖች እና ከኩላሊቶቹ ጋር በጉበቱን መሸፈኛው ላይ የሚገኘውን ስብ እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡ 16ካህኑ እነዚህን ሁሉ በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ እንዲሆን እንደ መብል መስዋዕት አድርጎ ሁሉንም ያቃጥለዋል፡፡ ስቡ ሁሉ የያህዌ ነው፡፡ 17“‘ይህ ለእናንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቀዋሚ መታሰቢያ ነው፣ እናንተ ስብ ወይም ደም አትብሉ፡፡’”
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2“ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ማንም ሰው ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር በማድረግ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ደግሞም የተከለከለ አንዳች ነገር ቢያደርግ፣ እንዲህ ይደረግ፡፡ 3ኃጢአት የሰራው ሊቀ ካህኑ ቢሆንና በህዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኃጢአት ቢሰራ ስለ ሰራው ኃጢአት ለያህዌ ነውር የሌለበት ወይፈን የኃጢአት መስዋእት አድርጎ ያቅርብ፡፡4ወይፈኑን በያህዌ ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣ፤ ካህኑ እጆቹን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫንና በያህዌ ፊት ይረደው፡፡ 5የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውድና ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣው፡፡6ካህኑ ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ ሰባት ጊዜ በቅድስተ ቅዱሳኑ መጋረጃ ላይ ከደሙ ጥቂት በያህዌ ፊት ይረጫል፡፡ 7ደግሞም ካህኑ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በያህዌ ፊት ከደሙ ጥቂት ወስዶ መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን በመሰዊያው ቀንዶች ይጨምራል፤ የቀረውን ወይፈኑን ደም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡8የሆድ ዕቃውን የሸፈነውንና ከሆድ ዕቃው ጋር የተያያዘውን የበደል መስዋዕቱን የሆነውን ወይፈን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡ 9(ቁጥር 9?) 10ለህብረት መስዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን አውጥቶ እንዳቀረበ ሁሉ ይንንም አውጥቶ ያቀርባል፡፡ ከዚያም ካህኑ እነዚህን ክፍሎች ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡11የወይፈኑን ቆዳና ማንኛውንም ስጋ ከጭንቅላቱና ከእግሮቹ እንዲሁም ከሆድዕቃው ክፍሎችና ከፈርሱ ጋር፣ 12የቀረውን የወይፈኑን ክፍሎች ሁሉ ከእነዚህ ክፍሎች ሁሉ ከመንደር ተሸክሞ አመዱን ወደ ደፉበት ለእኔ ወደሚነጹበት ስፍራ ወስዶ እነዚያን ክፍሎች በእንጨት ላይ ያቃጥላቸው፡፡ እነዚያን የከብቱን ክፍሎች አመዱን በደፉበት ስፍራ ያቃጥለው፡፡13መላው የእስራኤል ጉባኤ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ጉባኤውም ኃጢአት መስራቱን ባያውቅና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ፈጽሞ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣ 14ከዚያም፣ የፈጸሙት በደል በታወቀ ጊዜ፣ ጉባኤው ለኃጢአት መስዋዕት ወይፈን ይሰዋና ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ያምጣው፡፡ 15የጉባኤው ሽማግሌዎች በያህዌ ፊት በወይፈኑ ላይ እጃቸውን ይጫኑና በያህዌ ፊት ይረዱት፡፡16የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣል፣ 17ከዚያ ካህኑ ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በመጋረጃው ላይ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡18በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣በያህዌ ፊት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ከደሙ ጥቂት ይጨምርበታል፤ ደግሞም ለሚቃጠል መስዋዕት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በመሰዊያው ታች ደሙን በሙሉ ያፈሳል፡፡ 19ስቡን ሁሉ ከእንስሳው ቆርጦ ያወጣና በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡20ወይፈኑን በዚህ መልክ ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለኃጢአት መስዋዕት እንዳቀረበው ወይፈን ሁሉ፣ በዚህኛውም ወይፈን ይህንኑ ያደርጋል፣ እናም ካህኑ ለህዝቡ ማስተስረያ ያደርጋል፣ እናም ጉባኤው ይቅር ይባላል፡፡ 21ካህኑ ወይፈኑን ከመንደር ያወጣና የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለ ይህኛውንም ያቃጥለዋል፡፡ ይህ ለጉባኤው የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡22የህዝቡ መሪ ኃጢአት ለመስራት ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ አምላኩ ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ማናቸውም ነገሮች አንዱን አድርጎ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣ 23ከዚያም የሰራው ኃጢአት ቢታወቀው፣ ነውር የሌለበት ተባዕት ፍየል ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡24እጁን በፍየሉ ራስ ላይ ይጭንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ በያህዌ ፊት ይረደው፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡ 25ካህኑ ያኃጢአት መስዋዕቱን ደም በጣቱ ይውሰድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረው፣ ደግሞም ደሙን ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፍስሰው፡፡26ልክ እንደ ሰላም መስዋዕት ሁሉ ስቡን በሙሉ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ካህኑ የህዝቡ መሪ ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያድርግለታል፣ መሪውም ይቅር ይባላል፡፡27ከተራው ህዝብ መሃል አንድ ሰው ኃጢአት ለማድረግ ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ከእነዚህ ነገሮች መሃል አንዱን ቢፈጽም፣ እናም በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ 28ከዚያም የፈጸመው በደል ቢታወቀው፣ ለበደሉ መስዋዕት ነውር የሌለበት ሴት ፍየል ያቅርብ፡፡29በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጭናል ከዚያም በሚቃጠል መስዋዕቱ ስፍራ የኃጢአት መስዋዕቱን ያርዳል፡፡ 30ካህኑ በጣቱ ጥቂት ደም ወስዶ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ የተቀረውን ደም ሁሉ በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡31መስዋዕቱ በተወሰደበት ሁኔታ ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፡፡ ካህኑ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፣የሰውየውንም ኃጢአት ያስተሰርያል፡፡32ለኃጢአት መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ቢያቀርብ ነውር የሌለባት ሴት ጠቦት ያምጣ፡፡ 33በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርድበት ስፍራ ለኃጢአት መስዋዕት ያርዳል፡፡34ካህኑ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን ሁሉ ያፈሰዋል፡፡ 35ከሰላም መስዋዕቱ የጠቦቱ ስብ በወጣበት ሁኔታ፣ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፣ከዚያ ካህኑ በያህዌ መስዋዕቶች ላይ በእሳት በሚቀርበው መሰዊያ ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ካህኑ መስዋእት አቅራቢው የሰራውን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፣ እናም ሰውየው ይቅር ይባላል፡፡
1ማንም ሰው ያየውንም ሆነ የሰማውን አንዳች ነገር መምስከር ሲገባው ባለመመስከር ኃጢአት ቢሰራ፣ ይጠየቅበታል፡፡ 2ወይም ማንም ሰው እግዚአብሔር ንጹህ አይደለም ያለውን ማናቸውንም ነገር ቢነካ፣ ይህ ንጹህ ያልሆነ ነገር የዱር እንስሳ ስጋ ወይም የሞተ የቤት እንስሳ ቢሆን፣ ወይም ማናቸውንም ያልነጻ ሰው ቢነካ፣ ደግሞም ይህን ማድረጉን ባያውቅ፣ ስለ ነገሩ ባወቀ ጊዜ ኃጢአጠኛ ይሆናል፡፡3ቁጥር 3 (?) 4ወይም ማንም ሰው በችኮላ ክፉ ወይም በጎ ለማድረግ በከንፈሮቹ ቢምል፣በችኮላ የማለው መሀላ ምንም አይነት ይሁን፣ ስለ ነገሩ ባያውቅ እንኳን፣ ነገሩን ባወቀ ጊዜ ከእነዚህ በማናቸውም ነገር ኃጢአተኛ ይሆናል፡፡5አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በማንኛውም በደለኛ ሆኖ ሲገኝ፣የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት መናዘዝ አለበት፡፡ 6ከዚያም ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕቱን ወደ ያህዌ ማምጣት አለበት፣ ለኃጢአት መስዋዕት ሴት ጠቦት በግ ወይም ሴት ፍየል ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፡፡7ጠቦት መግዛት ካልቻለ፣ ለኃጢአቱ የበደል መስዋዕት ለያህዌ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች ማምጣት ይችላል፤ አንዱ ለኃጢአት መስዋዕት እና ሌላኛው ለሚቃጠል መስዋዕት ያመጣል፡፡ 8እነዚህን ወደ ካህኑ ያመጣል፣ እርሱም በመጀመሪያ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ያቀርባል - እርሱም የመስዋዕቱን ራስ ከአንገቱ ይቆለምማል ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ አይለያየውም፡፡ 9ከዚያ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በመሰዊያው ጎን ይረጫል፣ ከዚያ የቀረውን ደም በመሰዊያው ስር ደሙን ያንጠፈጥፈዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡10ከዚያ ሁለተኛውን ወፍ በህጉ መሰረት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል፣ እናም ካህኑ ሰውየው ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያደርገዋል፤ ይቅር ይባላል፡፡11“ነገር ግን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች መግዛት ሳይችል ቢቀር፣ ለሰራው ኃጢአት የኢፍ መስፈሪያ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ያኃጢአት መስዋዕት ስለሆነ ዘይት ወይም ዕጣን አይጨምርበት፡፡12መስዋዕቱን ወደ ካህኑ ያቅርበው፣ካህኑም ለያህዌ በጎነት ምስጋና ለማቅረብ ከዱቄቱ እፍኝ ይወስዳል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ለያህዌ በመስዋዕቱ ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡ 13ካህኑ ሰውየው የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ይቅር ይባላል፡፡ ከመስዋዕት የተረፈው እንደ እህል ቁርባኑ ሁሉ የካህኑ ይሆናል፡፡’”14ከዚያም ያህዌ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣ 15“ማንም ሰው የያህዌን ትዕዛዝ በመጣስ እርሱ ካለው ውጭ ሆኖ ኃጢአት ቢሰራ፣ ነገር ግን ይህንን ሁን ብሎ ባያደርግ ለያህዌ የበደል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ይህ መስዋዕት ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ዋጋውም ለኃጢአት መስዋዕት በቤተ መቅድስ ገንዘብ በጥሬ ብር መገመት አለበት፡፡ 16ቅዱስ ከሆነው በማጉደል ለሰራው በደል ዕዳውን በመክፈል ያህዌን ደስ ማሰኘት አለበት፣ እናም አንድ አምስተኛውን በዚህ ላይ ጨምሮ ለካህኑ ይስጥ፡፡ ከዚያ ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጠቦት ጋር ያስተሰርይለታል፤ እናም ይቅር ይባላል፡፡17ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ቢያደርግ፣ ምንም እንኳን ነገሩን ሳያውቅ ቢያደርገውም በደለኛ ነው፤ ስለዚህም በበደሉ ጥፋተኛ ነው፡፡ 18ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ጠቦት ያቅርብ ለካህኑ ለበደል መስዋዕት ተመጣጣኝ ዋጋ ያምጣ፡፡ ከዚያም ካህኑ ሳያውቅ ከሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ይቅር ይባላል፡፡ 19ይህ የበደል መስዋዕት ነው፣ በያህዌ ፊት በእርግጥ ኃጢአተኛ ነው፡፡”
1ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2“ ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና የያህዌን ትዕዛዝ ቢተላለፍ፣ ታማኝነቱን አፍርሶ ሃሰተኛ ቢሆን፣ ወይም ጎረቤቱ በአደራ የሰጠውን ቢክድ፣ ወይም ቢያታልል ወይም ቢሰርቀው፣ወይም ጎረቤቱን ቢበድል 3ወይም ከጎረቤቱ የጠፋ ነገር አግኝቶ ቢዋሽ፣ እናም በሃሰት ቢምል፣ ወይም እነዚህን በመሰሉ ሰዎች በሚበድሉባቸው ጉዳዮች ኃጢአት ቢሰራና፣ 4በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ በስርቆት የወሰደውን ይመልስ ወይም የበደለውን ይካስ፣ ወይም ታማኝነቱን አጉድሎ የወሰደውን ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፡፡5ወይም በማንኛውም ጉዳይ ላይ ቢዋሽ፣ ሙሉ ለሙሉ ይመልስ፤ እንዲሁም ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ለባለንብረቱ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይክፈል፡፡ 6ከዚያም የበደል መስዋዕቱን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ነውር የሌለበት ጠቦት ከመንጋው የኃጢአት መስዋእት ለያህዌ ወደ ካህኑ ያምጣ፡፡ 7ካህኑ የኃጢአት ማስተስረያ በያህዌ ፊት ያቀርባል፣ እናም በዳዩ ለሰራው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል፡፡”8ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 9“አሮንን እና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘የሚቃጠል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የሚቃጠለው መስዋዕት በመሰዊያው ምድጃ ላይ ሌሊቱን ሁሉ እስከ ማለዳ ይገኝ፣ ደግሞም የመሰዊያው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡10ካህኑ የበፍታ ልብሱን ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ ቀሚን ይልበስ፡፡ እሳቱ በመሰዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠለውን መስዋዕት ከበላ በኋላ አመዱን ይፈስ፣ ከዚያም አመዱን ከመሰዊያው ጎን ይድፋው፡፡ 11አመዱን ከሰፈር ውጭ ንጹህ ወደ ሆነ ስፍራ ለመውሰድ የለበሰውን አውልቆ ሌላ ልብስ ይልበስ፡፡12በመሰዊው ላይ ያለው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡ መጥፋት የለበትም፣ እናም ካህኑ በየማለዳው እንጨት ይጨምርበት፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ በላዩ የሚቃጠል መስዋዕት ያድርግበታል፣ ደግሞም የሰላም መስዋዕት ስብ በላዩ ያቃጥልበታል፡፡ 13እሳቱ ሳያቋርጥ በመሰዊያው ላይ ይንደድ፤መጥፋት የለበትም፡፡14የእህል ቁርባን ህግ ይህ ነው፡፡ የአሮን ልጆች ከያህዌ ፊት በመሰዊያው ላይ ያቀርቡታል፡፡ 15ካህኑ የእህል ቁርባን አድርጎ እፍኝ መልካም የእህል ዱቄትና ዘይት እንዲሁም ዕጣን ለመስዋዕት ይውሰድና የያህዌን በጎነት ምስጋና ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡16አሮንና ልጆቹ ከመስዋዕቱ የቀረውን ይመገቡት፡፡ ይህም እርሾ ሳይገባበት በተቀደሰው ስፍራ ይብላ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረ ግቢ ይመገቡት፡፡ 17በእርሾ መጋገር የለበትም፡፡ እኔ በእሳት የተዘጋጀ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ የኃጢአት መስዋዕትና የበደል መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው፡፡ 18ለሚመጣው ተውልድ ሁሉ ለዘመናት ሁሉ ወንድ የሆነ የአሮን ትውልድ ድርሻው አድርጎ ከያህዌ ከሚቀርበው የእሳት ቁርባን ሊበላው ይችላል፡፡ ማናቸውም እርሱን የሚነካ ቅዱስ ይሆናል፡፡”19ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 20“ይህ አሮንና ልጆቹ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፣ እያንዳንዳቸው የአሮን ልጆች በሚቀቡበት ቀን ለያህዌ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፡፡ እንደ ተለመደው የእህል ቁርባን የኢፍ አንድ አስረኛ ክፍል መልካም ዱቄት፤ በጠዋት ግማሹን የተቀረውን ግማሽ ደግሞ ምሽት ያቀርቡታል፡፡21በመጥበሻ ላይ በዘይት ይጋገራል፡፡ በእርጥቡ ሳለ፣ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ታቀርበዋለህ፡፡ የእህል ቁርባኑን ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ቆራርሰህ ታቀርበዋለህ፡፡ 22ከሊቀ ካህኑ ልጆች መሃል ተተኪ ካህን የሚሆነው ወንድ ልጅ መስዋዕቱን ያቀርባል፡፡ ለዘለዓለም እንደታዘዘው፣ መስዋዕቱ በሙሉ ለያህዌ ይቃጠላል፡፡ 23ካህኑ የሚያቀርበው እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ይቃጠላል፤አይበላም፡፡”24ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 25“አሮንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፣ ‘የኃጢአት መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የኃጢአት መስዋዕት የሚታረደው የሚቃጠል መስዋዕት በሚታረድበት ስፍራ ያህዌ ፊት ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡ 26የኃጢአት መስዋዕት የሚያቀርበው ካህን ይመገበዋል፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረግቢ በተቀደሰው ስፍራ ይበላ፡፡27የመስዋዕቱን ስጋ የሚነካ ሁሉ ይቀደሳል፣ደሙ በየትኛውም ልብስ ላይ ቢረጭ ደሙ የነካውን የጨርቁን ስፍራ በተቀደሰ ቦታ እጠበው፡፡ 28የተቀቀለበት የሸክላ ማሰሮ ግን ይሰበር፡፡29ከካህናቱ መሀል ማናቸውም ወንድ ከዚህ መብላት ይችላል ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡ 30በተቀደሰው ስፍራ ወደ መገናኛው ድንኳን ለማስተስረይ ደሙ ከቀረበው የኃጢአት መስዋዕት ምንም አይበላ፡፡
1የበደል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡ 2የበደል መስዋዕቱን በሚታረድበት ስፍራ የበደሉንም መስዋዕ ይረዱት፣ ደሙን በመሰዊያው እያንዳንዱ ጎን ይርጩት፡፡ 3በመስዋዕቱ ከብት ውስጥ ያለው ስብ ሁሉ ይቃጠል፤ ላቱ፣የሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነው ስብ በመሁሉ፣ 4በጎድኑ አጠገብ ያለው ስብ፣ ሁለቱ ኩላሊቶችና በላያቸው ያለው ስብ፣ ጉበቱን የሸፈነው ስብ፣ ከኩላሊቶቹ ጋር - እነዚህ ሁሉ ይቅረቡ፡፡5ካህኑ እነዚህን ክፍሎች በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት አድርጎ በመሰዊያው ላይ ለያህዌ ያቃጥል፡፡ ይህ የበደል መስዋዕት ነው፡፡ 6እያንዳንዱ ካህን ከዚህ መስዋዕት መብላት ይችላል፡፡ በተቀደሰ ስፍራ ይበላ ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡7የኃጢአት መስዋዕት ልክ እንደ በደል መስዋዕት ነው፡፡ የሁለቱም ህግ ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህ ህጎች የማስተስረይ አገልግሎት ለሚሰጡ ካህናት ያገለግላሉ፡፡ 8የየትኛውንም ሰው የሚቃጠል መስዋዕት የሚያቀርብ ካህን የመስዋዕቱን ቆዳ መውሰድ ይችላል፡፡9በምድጃ የሚዘጋጅ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን፣ እና በመጥበሻ የሚዘጋጅ እንዲህ ያለው እያንዳንዱ መስዋዕት ወይም በመጋገሪያ መጥበሻ ላይ የሚዘጋጅን መስዋዕት፣ መስዋዕቱን የሚያሳርገው ካህን ይወስደዋል፡፡ 10ደረቅም ሆነ በዘይት የተለወሰ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ለአሮን ትውልዶች እኩል የእነርሱ ነው፡፡11ይህ ሰዎች ለያህዌ የሚያቀርቡት የሰላም መስዋዕት ህግ ነው፡፡ 12ማንም ሰው ምስጋና ለማቅረብ ይህን ቢያደርግ፣ እርሾ የሌለበት መስዋዕት አድርጎ ያቅርበው፣ ነገር ግን ቂጣውን በዘይት ይለውሰው፣ ቂጣው በመልካም ዱቄት የተዘጋጀ በዘይት የተለወሰ ይሁን፡፡13ደግሞም ምስጋና ለማቅረብ፣ ከሰላም መስዋዕቱ ጋር በእርሾ የተዘጋጀ ህብስት ያቅርብ፡፡ 14ከእነዚህ መስዋዕቶች ከእያንዳንዳቸው አንድ አይነት መስዋዕት ለያህዌ ያቅርብ፡፡ ይህ የሰላም መስዋዕቱን ደም በመሰዊያው ላይ ለሚረጩት ካህናት ይሰጥ፡፤15ምስጋና ለማቅረብ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርበው ሰው መስዋዕቱ በሚቀርብበት ዕለት የመስዋዕቱን ስጋ ይብላ፡፡ ከስጋው እስከ ማግስቱ አይደር፡፡ 16ነገር ግን መስዋዕቱ የሚያቀርበው ለስዕለት ከሆነ፣ ወይም በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ መስዋዕት ከሆነ ስጋው መስዋዕቱን ባቀረበበት ዕለት ባያልቅ በማግስቱ ሊበላ ይችላል፡፡17ሆኖም፣ ከመስዋዕቱ የተረው ስጋ በሶስተኛው ቀን ይቃጠል፡፡ 18አንድ ሰው ካቀረበው የበጎ ፈቃድ መስዋዕት አንዳች ስጋ በሶስተኛው ቀን ቢበላ ይህ ተቀባይነት የለውም፤ መስዋዕቱን ላቀረበውም ዋጋ የለውም፡፡ ደስ የማያሰኝ ነገር ይሆናል፣ ስጋውን ለሚበላውም ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል፡፡19ንጹህ ያልሆነ ነገር የነካ ከዚህ ስጋ አይበላም፡፡ ስጋው መቃጠል ይኖርበታል፡፡ የተረውን ስጋ፣ ማንኛውም ንጹህ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል፡፡ 20ሆኖም፣ ለያህዌ የሚቀርበውን የሰላም መስዋዕት ስጋ የበላ ንጹህ ያልሆነ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡21ማንኛውም ሰው ንጹህ ያልሆነ ነገር ቢነካ - ንጹህ ያልሆነን ሰው፣ ወይም ንጹህ ያልሆነን አውሬ፣ ወይም ንጹህ ያልሆነ እና ደስ የማያሰኝ ነገር ቢነካ፣ እና ከዚያም ለያህዌ ከቀረበው የሰላም መስዋዕት ስጋ ቢበላ ያሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡22ቀጥሎም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 23“የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ አትብሉ፡፡ 24ሳይታረድ ሞቶ የተገኘ እንስሳ ስብ፣ ወይም በዱር አውሬ የተገደለ እንስሳ ስብ ለሌላ ተግባር ሊውል ይችላል፣ ነገር ግን የዚያን እንስሳ ስብ በፍጹም አትብሉ፡፡25ሰዎች በእሳት ለያህዌ መስዋዕት አድርገው ሊያቀርቡ የሚችሉትን እንስሳ ስብ የሚላ ማንኛውም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡ 26በቤቶቻችሁ የወፍም ሆነ የእንስሳ ማናቸውም ዐይነት ደም አትብሉ፡፡ 27ማናቸውንም ደም የበላ ማንም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡’”28ደግሞም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 29“የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ለያህዌ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርብ ከመስዋዕቱ ላይ ወስዶ ለያህዌ ያቅርብ፡፡ 30ለያህዌ በእሳት የሚዘጋጀውን መስዋዕት፣ በእርሱ በራሱ እጅ ያቅረበው፡፡ ስቡን ከፍርምባው ጋር ያቅርበው፣ ስለዚህ ፍርምባውን በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ያቅርበው፡፡31ካህኑ ስቡን በመሰዊያ ላይ ያቃጥለው፣ ነገር ግን ፍርምባው የአሮንና የትውልዱ ነው፡፡ 32የቀኙን ወርች ከሳለም መስዋዕታችሁ የቀረበ ስጦታ አድርጋችሁ ለካህኑ ስጡት፡፡33የሰላም መስዋዕቱንና ስቡን ደም የሚያቀርበው ከአሮን ትውልድ ውስጥ የሆነው ካህን ከመስዋዕቱ ውስጥ የቀኝ ወርቹ የእርሱ ድርሻ ነው፡፡ 34ለእኔ የተወዘወዘውንና የቀረበውን የፍርምባውንና የወርቹን መስዋዕት እኔ ስለ ወሰድኩ፣ እነዚህን ሊቀካህን ለሆነው ለአሮንና ለዘሩ ሰጥቻለሁ፣ ይህ ሁልጊዜም በእስራኤል ህዝብ ከሚዘጋጀው የሰላም መስዋዕት ድርሻቸው ይሆናል፡፡35ሙሴ በካህናት አገልግሎት ያህዌን እንዲያገለግሉ እነርሱን ባቀረበ ቀን ይህ ለአሮንና ለዘሮቹ በእሳት ለያህዌ ከሚቀርበው መስዋዕት ድርሻቸው ነው፡፡ 36እርሱ ካህናትን በቀባ ቀን ያህዌ ከእስራኤል ህዝብ ድርሻቸው ሆኖ ለእነርሱ እንዲሰጥ ያዘዘው ይህ ነው፡፡ ይህ ሁልጊዜም በትውልዶች ሁሉ ድርሻቸው ይሆናል፡፡37ይህ የሚቃጠል መስዋዕት፣ የእህል ቁርባን፣ የኃጢአት መስዋዕት፣ በደል መስዋዕት፣ የክህነት ሹመት መስዋዕት እና የሰላም መስዋዕት ስርዓት ነው፤ 38ይህ ያህዌ ለሙሴ በሲና ተራራ ላይ የእስራኤል ህዝብ መስዋዕታቸውን በሲና ምድረበዳ የሚያቀርቡበትን ህግጋት ለሙሴ በሰጠበት ቀን የተሰጠ ስርዓት ነው፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“አሮንንና ልጆቹን፣ የክህነት ልብሶቹን፣ የቅባት ዘይቱን፣የኃጢአት መስዋዕቱን ወይፈኖች፣ ሁለቱን ጠቦቶች፣ እርሾ የሌለበትን ህብስት መሶብ ከእርሱ ጋር ውሰድ፡፡ 3በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሁሉንም ጉባኤ ሰብስብ፡፡”4ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፣ ጉባኤውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ተሰበሰበ፡፡ 5ከዚያም ሙሴ ለጉባኤው እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ይህ ነው፡፡”6ሙሴ አሮንንና ልጆቹን አቀረበና በውሃ አጠባቸው፡፡ 7አሮንን እጀ ጠባብ አለበሰውና በወገቡ ዙሪያ መቀነት አስታጠቀው፣ ቀሚ አጠለቀለትና ኤፉድ ደረበለት፣ ከዚያም ኤፉዱን በጥበብ በተጠለፈ መቀነት አስታጠቀው፡፡8በቀሚሱ ላይ ደረት ኪስ አደረገለት፣ በደረት ኪሱ ውስጥ ኡሪምና ቱሚም አደረገበት፡፡ 9ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው በራሱ ላይ ጥምጥሙን ጠመጠመለት፣ በጥምጥሙ ላይ ከፊት በኩል ወርቃማ ቅብና ቅዱስ አክሊል አደረገለት፡፡10ሙሴ የቅባቱን ዘይት ወሰደ፣ ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀባው፤ እናም ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡ 11በመሰዊያው ላይ ዘይቱን ሰባት ጊዜ ረጨው፣ እናም መሰዊያውንና መገልገያዎቹን ሁሉ ቀባቸው፣ እንዲሁም የመታጠቢያ ሳህኑንና ማስቀመጫውን፣ ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡12አሮንን ያህዌ ለመለየት ከቅባቱ ዘይት ጥቂቱን በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰው፡፡ 13ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው የአሮንን ወንድ ልጆች አቅርቦ እጀጠባብ አለበሳቸው፣ በወገባቸው ዙሪያ መታጠቂያ አሰረላቸው፣ በራሳቸው ላይ በፍታ ጨርቅ ጠቀለለላቸው፡፡14ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት በሬ አመጣ፣ አሮንና ልጆቹ ለኃጢአት መስዋዕት ባመጡት በሬ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ፡፡ 15በሬውን አርዶ ደሙን በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ በጣቱ ጨመረ፣ በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፣ ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር ለየው፡፡16በመስዋዕቱ ሆድ ዕቃ ውስጥ ያለውን ስብ ሁሉ አወጣ፣ በጉበቱ መሸፈኛና በሁለቱ ኩላሊቶች ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሰዊያው ላይ ሁሉንም አቃጠለው፤ 17ነገር ግን በሬውን፣ ቆዳውን፣ ስጋውን እና ፈርሱን ያህዌ እንዳዘዘው ከሰፈር አውጥቶ አቃጠለው፡፡18ሙሴ ለሚቃጠል መስዋዕት ጠቦቱን አቀረበ፣ አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፡፡ 19ሙሴም ጠቦቱን አርዶ በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ረጨ፡፡20ጠቦቱን ቆራርጦ ራሱንና ቁርጥራጩን እንዲሁም ስቡን አቃጠለ፡፡ 21የሆድ ዕቃውን ክፍሎችና እግሮቹን በውሃ አጠበ፣ ከዚያም ጠቦቱን በሙሉ በመሰዊያው ላይ አቃጠለ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፤ ደግሞም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ ጣፋጭ መዓዛ ነው፡፡22ከዚያም ሙሴ ሌላውን ጠቦት ያቀርባል፣ ይህም የክህነት ሹመት መስዋዕት ነው፣ እናም አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ይጭናሉ፡፡ 23አሮን ጠቦቱን ያርዳል፣ ሙሴም ከደሙ ጥቂት ወስዶ በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ያደርጋል፡፡ 24የአሮንን ልጆች አቅርቦ፣ በቀኝ ጆሯቸው ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጃቸው አውራ ጣት ላይ እና በቀኛ እግራቸው አውራ ጣት ላይ ከደሙ ጥቂት ወስዶ ያደርጋል፡፡ ከዚያ ሙሴ የበጉን ደም በመሰዊያው ጎኖች ሁሉ ይረጫል፡፡25ስቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃ ክፍሎች ውስጥ ሁሉ የሚገኘውን ስብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኩላሊቶች እና በላያቸው የሚገነውን ስብ እንዲሁም ቀኝ ወርቹን ወሰደ፡፡ 26በያህዌ ፊት ከነበረው መሶብ እርሾ የሌለበት አንድ ህብስት ይወስዳል፣ደግሞም በዘይት ተለውሶ ከተሰራው ዳቦ አንዱን እና አንድ ስስ ቂጣ ይውሰድና በስቡና በቀኝ ወርች ላይ ያኖረዋል፡፡ 27ሁሉንም በአሮን እጆችና በአሮን ወንድ ልጆች እጆች ላይ ያስቀምጠዋል፣ ይህንንም ለሚወዘወዝ መስዋዕት በያህዌ ት ያቀርባሉ፡፡28ከዚያም ሙሴ ከእጃቸው ይወስድና የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበው፡፡ እነዚህ የክህነት ሹመት መስዋዕት ናቸው፤ ጣፋጭ መዓዛ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ነው፡፡ 29ሙሴ ፍርምባውን ወስዶ ለያህዌ መስዋዕት አድርጎ ይወዝውዘው፡፡ ያህዌ እንዳዘዘው ይህ ከጠቦቱ የክህነት ሹመት የሙሴ ድርሻ ነው፡፡30ሙሴ በመሰዊያው ላይ ካለው ከቅባት ዘይቱና ከደሙ ጥቂት ወስዶ እነዚህን በአሮን ላይ፣ በልብሶ ላይ፣ በወንድ ልጆቹ ላይ እና ከእርሱ ጋር በልጆቹ ልብሶች ላይ ይረጫል፡፡ በዚህ መንገድ አሮንና የክህነት ልብሱን እንዲሁም ልጆቹንና ልብሳቸውን ለያህዌ ይቀድሳል፡፡31ደግሞም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ አለ፣ “በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ስጋውን ቀቅሉት፣ በዚያም ስፍራ በሹመት መስጫው መሶብ ውስጥ ያለውን ህብስትም ‘አሮንና ልጆቹ ይብሉት’ ብዬ እንዳዘዝኩት ብሉት፡፡ 32ከስጋውና ከህብስቱ የተረፈውን በሙሉ አቃጥሉት፡፡ 33የሹመት ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሰባት ቀናት ከመገናኛው ከመገናኛው ድንኳን መግቢያ አትለፉ፡፡ ያህዌ በሰባት ቀናት ውስጥ ይሾማችኋል፡፡34በዚህ ቀን የሚሆነው እናንተን ለማስተረይ ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ነው፡፡ 35ለሰባት ቀናት ቀንም ሆነ ሌሊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ትቆያላችሁ፣ ደግሞም የያህዌን ትዕዛዝ ትጠብቃላችሁ፣ ይህን ካደረጋችሁ አትሞቱም፣ ምክንያቱም የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡” 36ስለዚህም አሮንና ልጆቹ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን ሁሉንም ነገር አደረጉ፡፡
1በስምንተኛው ቀን ሙሴ አሮንንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራ፡፡ 2አሮንን እንዲህ አለው፣ “ለኃጢአት መስዋዕት ከመንጋው እምቦሳ እና ነውር የሌለበትን አውራ በግ ወስደህ በያህዌ ፊት ሰዋቸው፡፡3እስራኤል ሰዎች እንዲህ ባላቸው፣ ‘ለኃጢአት መስዋዕት ወንድ ፍየል ውሰድ እንደዚሁም ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት እምቦሳና ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዓት ውሰድ፤ 4እንዲሁም በያህዌ ፊት የሰላም መስዋት ለመስዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ውሰድ፣ በዘይት የተለወሰ የእህል ቁርባንም አቅርብ፣ ምክንያቱም ዛሬ ያህዌ ይገለጥላችኋል፡፡” 5ስለዚህም ሙሴ ያዘዘውን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን አመጡ፣ የእስራኤል ጉባኤም ሁሉ ቀርበው በያህዌ ፊት ቆሙ፡፡6ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንድታደርጉት ያዘዘው ይህንን ነው፣ስለዚህም ክብሩ ይገለጥላችኋል፡፡” 7ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ወደ መዊያው ቀርበህ የኃጢአት መስዋዕትህንና የሚቃጠል መስዋዕትህን አቅርብ፣ ደግሞም ያህዌ እንዳዘዘው ለራስህና ለህዝቡ አስተስርይ፣ ለህዝቡ ማስተስረያ ለማቅረብ መስዋዕቱን ሰዋ፡፡” 8ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡8ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡ 9የአሮን ልጆቸ ደሙን አቀረቡለት፣ እርሱም ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ጨመረ፤ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፡፡10ሆኖም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ስቡን፣ ኩላሊቶቹን እና በመሰዊያው ላይ የጉበቱን ሽፋን የኃጢአት መስዋዕት አድርጎ አቃጠላቸው፡፡ 11ስጋውንና ቆዳውን ከሰፈር ውጭ አቃጠለው፡፡12አሮን የሚቃጠለውን መስዋዕት አረደ፣ ልጆቹ በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደም ሰጡት፡፡ 13ከዚያ የሚቃጠለውን መስዋዕት ከከብቱ ራስ ጋር እየቆራረጡ ሰጡት፣ እርሱም በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡ 14የሆድ ዕቃዎቹንና እግሮቹን አጥቦ በመሰዊያው ላይ በሚቃጠል መስዋዕቱ ላይ አቃጠላቸው፡፡15አሮን አንድ ፍየል የህዝቡን መስዋዕት አቀረበ፣ ከዚያ ለኃጢአታቸው መስዋዕት አድርጎ አረደው፤ በመጀመሪያው ፍየል ላይ እንዳደረገው ሁሉ ለኃጢአት መስዋዕትነት ሰዋው፡፡ 16ያህዌ እንዳዘዘው የሚቃጠል መስዋዕቱን አቅርቦ ሰዋው፡፡ 17የእህል ቁርባኑን፣ ከእህል ቁርባኑ እፍኝ ሙሉ ወስዶ ከማለዳው የሚቃጠል መስዋዕት ጋር በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡18እንዲሁም ለህዝቡ የሰላም መስዋዕት የሆነውን መስዋዕት በሬውንና አውራ በጉን አረደ፡፡ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደሙን ሰጡት፡፡ 19ሆኖም፣ የበሬውንና የአውራ በጉን ስብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነውን ስብ፣ ኩላሊቶቹን፣ የጉበቱን ሽፋን20እነዚህን በፍርምባው ላይ አደረጉ፣ ከዚያም አሮን ሙሴ ባዘዘው መሰረት ስቡን በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡ 21አሮን ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ይወዝስዘውና እነዚህን ለያህዌ ያቅርብ፡፡22ከዚያ አሮን አጆቹን ወደ ህዝቡ አንስቶ ይባርካቸው፤ ቀጥሎ የኃጢአት መስዋዕቱን፣ የሚቃጠል መስዋዕቱንና የሰላም መስዋዕቱን አቅርቦ ይወርዳል፡፡ 23ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ይሂዱ፣ ከዚያ ተመልሰው ይውጡና ህዝቡን ይባርኩ፣ እናም የያህዌ ክብር ለህዝቡ ሁሉ ይገለጣል፡፡ 24ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥቶ የሚቃጠል መስዋዕቱንና በመሰዊያው ላይ ያለውን ስብ ሁሉ በላ፡፡ ህዝቡ ሁሉ ይህንን ባዩ ጊዜ ጮኸው በፊታቸው ተደፉ፡፡
1የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናዎቻቸውን ወስደው እሳት አደረጉበት ከዚያም ዕጣን ጨመሩበት፡፡ ከዚያ በያህዌ ፊት እርሱ እንዲያቀርቡ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ ዕሳት አቀረቡ፡፡ 2ስለዚህም ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥታ በላቻቸው፣ እነርሱም በያህዌ ፊት ሞቱ፡፡3ከዚያም ሙሴ አሮንን፣ “ያህዌ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ ላይ ቅድስናዬን እገልጻለሁ፡፡ በሰዎች ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ሲል ይህን ማለቱ ነው” አለው፡፡ አሮንም ምንም አልመለሰም፡፡ 4ሙሴ የአሮን አጎት የሆነውን የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ “ወደዚህ ኑና ከመቅደሱ ደጃፍ ወንድሞቻችሁን ተሸክማችሁ ከሰፈር አውጣቸው፡፡”5ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው ቀርበው የክህነት ቀሚሳቸውን እንደለበሱ ተሸክመው ከሰፈር አወጧቸው፡፡ 6ከዚያም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምር እንዲህ አላቸው፣ “እንዳትቀሰፉ ፀጉራችሁን አትንጩ፣ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፣ ያህዌ በህዝቡ ላይ ሁሉ እንዳይቆጣ ተጠንቀቁ፡፡ ነገር ግን ቤተዘመዶቻችሁና መላው የእስራኤል ቤት የያህዌ እሳት ለበላቻቸው ያልቅሱ፡፡ 7እናንተ ግን ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትለፉ፣ የያህዌ የቅባት ዘይት በእናንተ ላይ ነውና ትሞታላችሁ፡፡ ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው አደረጉ፡፡8ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ 9“አንተ፣ ወይም ከአንተ ጋር የሚሆኑ ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ እንዳትሞቱ ወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፣ 10ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው መሃል ለመለየት፣ ንጹህ በሆነውና ንጹህ ባልሆነው መሃል ለመለየት፣ 11ለእስራኤል ህዝብ ሁሉ በሙሴ በኩል ያህዌ ያዘዘውን ስርዓት ሁሉ አስተምሩ፡፡”12ሙሴ ለአሮንና ለተረፉት ልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምርን እንዲህ አላቸው፣ “በእሳት ለያህዌ ከቀረበው የእህል ቁርባን የተረፈውን መስዋዕት ውሰድ፣ እጅግ ቅዱስ ነውና እርሾ ሳይገባበት ከመሰዊያው አጠገብ ብሉት፡፡ 13በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፣ ምክንያቱም በእሳት ለያህዌ ከቀረበው መስዋዕት ይህ የአንተና የልጆችህ ድርሻ ነው፣ እንድነግርህ የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡14ለመስዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና ለያህዌ የቀረበውን ወርች እግዚአብሔር ደስ በሚሰኝበት በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፡፡ እነዚህን ድርዎቻችሁን አንተ፣ እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ብሉት፣ እነዚህ የእስራኤል ህዝብ ከሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት የአንተና የልጆችህ ድርሻ ሆነው ተሰጥተዋል፡፡ 15ለያህዌ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን ወርች እና መስዋዕት ሆኖ የተወዘወዘውን ፍርምባ በእሳት ከተዘጋጀው የስብ መስዋዕቶች ጋር ከፍ አድርገው ለመወዘወዝና ለያህዌ መስዋዕት ለማድረግ በአንድነት ያቅርቧቸው፡፡ ይህም ያህዌ እንዳዘዘው ለዘለዓለም የአንተና የልጆችህ ድርሻ ይሆናል፡፡”16ከዚያ ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት ስለሚሆነው ፍየል ጠየቀ፣እናም በእሳት እንደተቃጠለ አወቀ፡፡ ስለዚህም በአልአዛርና በኢታምር በተቀሩትም የአሮን ልጆች ላይ ተቆጣ፤ እንዲህም አላቸው፣ 17“ይህ የኃጢአት መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ሆኖ ሳለና የጉባኤውን በደል በእረሱ ፊት እንድታስወግዱበትና ኃጢአታቸውንም እንድታስተረዩላቸው ሰጥቷችሁ ሳለ ስለምን በቤተ አምልኮው ስፍራ አልበላችሁትም? 18ተመልከቱ፣ ደሙ ወደ ቤተመቅደስ ውስጥ አልመጣም፤ እንዳዘዝኳችሁ በቤተ መቅደሱ አካባቢ ለትበሉት ይገባ ነበር፡፡”19ከዚያም አሮን ለሙሴ እንደህ ሲል መለሰለት፣ “እነሆ፣ ዛሬ የኃጢአት መስዋዕታቸውን እና የሚቃጠል መስዋዕታቸውን በያህዌ ፊት አቀርቡ፣ እናም ይህ ነገር በእኔ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ እኔ የኃጢአት መስዋዕቱን ብበላ ኖሮ ይህ በያህዌ ፊት ደስ ያሰኝ ነበርን?” 20ሙሴ ያንን ሲሰማ መልሱ አረካው፡፡
1ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ 2“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በሏቸው፣ ‘በምድር ላይ ከሚገኙ እንስሳት ሁሉ የምትመገቧቸው ህያዋን ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡3የተሰነጠቀ ሰኮና ያላቸውንና የሚያመሰኩትን ትመገባላችሁ፡፡ 4ሆኖም፣ የሚያመሰኩ ቢሆኑም ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የሌላቸውን እንደ ግመል ያሉትን አትብሉ፤ምክንያቱም ያመሰኳሉ ነገር ግን ሰኮናው አልተሰነጠቀም፡፡ ስለዚህ ግመል ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡5እንዲሁም ሽኮኮ ያመሰኳል ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የለውም፣ ይህም ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡ 6ጥንቸል ቢያመሰኳም የተሰነጠቀ ሰኮና ስለሌለው ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡ 7አሳማ የተሰነጠቀ ሰኮና ቢኖረውም፣ አያመሰኳም ስለዚህ ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡ 8የእነዚህን ስጋ ፈጽሞ አትብሉ፣ ጥንባቸውንም አትንኩ፡፡ እነርሱ ለእናንተ ንጹህ አይደሉም፡፡9በውቂያኖስም ሆነ በባህር በውሃ ውስጥ ከሚኖሩ እንስሳት የምትበሏቸው ክንፍና ቅርፊት ያላቸው ናቸው፡፡ 10ነገር ግን በውቂያኖስ ወይም በባህር የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ህያዋን ፍጥረታት ሁሉ፣በውሃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን ጨምሮ እንዲሁም በውሃ ውስጥ ያሉት እንዲህ ያሉ ህያዋን ፍጥረታት በሙሉ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡11ጸያፍ ሊሆኑ ስለሚገባቸውም፣ ስጋቸውን ልትበሉ አይገባም፣ እንደዚሁም በድናቸውም ጸያፍ ነው፡፡ 12በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ቅርፊት የሌላቸው እንስሳት ሁሉ፣በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡13ልትጸየፏቸው የሚገቡና የማትበሏቸው ወፎች እነዚህ ናቸው፤ ንስር፣ ጥንብ አንሳ፣ 14ጭላት፣ ማንኛውም አይነት የሎስ 15ማንኛውም አይነት ቁራ፣ 16የተለያ አይነት ጉጉት፣ የባህር ወፍ እና ማንኛውም ዐይነት ጭልፊት፡፡17ትናንሽና ትላልቅ ጉጉቶችን ትጸየፋላችሁ፣ርኩምና ጋጋኖ፣ 18የተለያዩ ጉጉቶች፣ ይብራ፣ 19ሽመላ፣ ማናቸውም ዐይነት የውሃ ወፍ፣ ሳቢሳ፣ ጅንጁላቲ ወፍና የለሊት ወፍ፡፡20በእግራቸው የሚራዱ ክንፍ ያላቸው በራሪ ነፍሳት በሙሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው፡፡ 21ሆኖም ግን ከእግራቸው በላይ በምድር ላይ የሚፈናጠሩበት አንጓ ያላቸውን ማናቸውንም የሚበሩ ነፍሳት መብላት ትችላላችሁ፡፡ 22እንደዚሁም ደግሞ ማናቸውንም ዐይነት አንበጣ፣ ትልቅ የአንበጣ ዝርያ፣ ፌንጣና ዝንቢት መብላት ትችላላችሁ፡፡ 23ነገር ግን አራት እግር ያላቸው የሚበሩ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጠሉ ናቸው፡፡24ከእነዚህ እንስሳት ውስጥ የአንዱን በድን ብትነኩ እስከ ማታ ድረስ የረደሳችሁ ናችሁ፡፡ 25ከእነዚህ የአንዱን በድን ያነሳ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ነው፡፡26ማንኛውም ሙሉ ለሙሉ ያልተሰነጠቀ ሰኮና ያለው እንስሳ ወይም የማያመሰኳ እንስሳ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ነው፡፡ እነዚህን የነካ ሁሉ ይረክሳል፡፡ 27በአራት እግሩ ከሚራመድ እንስሳ መሃል በመዳፋቸው የሚሄዱ ሁሉ በእናንተ ዘንድ እርሱስ ናቸው፡፡ እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን የነካ እስከ ማታ እርኩስ ነው፡፡ 28እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን ያነሳ ልብሱን ይጠብ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡ እነዚህ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ ናቸው፡፡29በምድር ላይ ከሚሳቡ እንስሳት መሃል፣ በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡ አቁስጣ፣ አይጥ፣ ማናቸውም አይነት እንሽላሊት 30ትንሽ የቤት ላይ እንሽላሊት እና እስስት31ከሚሳቡ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡፡ ከእነዚህ የሞቱትን አንዳቸውን የነካ ሰው እስከ ምሽት እርሱስ ይሆናል፡፡ 32ከእነዚህ መሃል አንዱ ሞቶ በማናቸውም ከእንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቆዳ ወይም ከበርኖስ በተሰራ ነገር ላይ ቢወድቀቅ ያዕቃ እርኩስ ይሆናል፡፡ ዕቃው ምንም ይሁን ለምንም አይነት ተግባር ይዋል ውሃ ውስጥ ይነከር እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡ 33ንጹህ ያልሆነ እንስሳ የገባበት ወይም የነካው የሸክላ ማሰሮ እንዲሁም በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ እርኩስ ይሆናል፤ ያንን ማሰሮ ሰባብረው፡፡34ማናቸውም ለመበላት የተፈቀደ ምግብ፣ ንጹህ ካልሆነ ማሰሮ ውሃ ቢገባበት እርኩስ ይሆኖል፡፡ እንዲህ ካለው ማሰሮ ማንኛውም ነገር ቢጠጣ ያረክሳል፡፡ 35እርኩስ ከሆነ እንስሳ በድን ማናቸውም አካሉ የወደቀበት ምድጃም ሆነ የማብሰያ ሸክላ እንዲሁም ማንኛውም ነገር ይረክሳል፡፡ ይሰባበር፡፡ እርኩስ ነው፣ በእናንተም ዘንድ የተጠላ ይሁን፡፡36የመጠጥ ውሃ የሚገኝበት ምንጭ ወይም የውሃ ጉድጓድ እንዲህ ያሉ እንስሳት ቢገኙበትም ንጹህ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው በውሃው ውስጥ የሚገኘውን እርኩስ የሆነውን በድን ቢነካ እርኩስ ይሆናል፡፡ 37ንጹህ ያልሆነ እንስሳ በድን በዘር ላይ ቢወድቅ፣ እነዚያ ዘሮች የረከሱ ይሆናሉ፡፡ 38ነገር ግን በዘሮቹ ላይ ውሃ ቢፈስ ንጹህ ያልሆነው እንስሳ በድን ማንኛውም አካል የተክል ዘሩ ላይ ቢወድቅ ዘሩ በእናንተ ዘንድ እርኩስ ይሆናል፡፡39ለመበላት ከተፈቀደው እንስሳ አንዱ ቢሞት፣ በድኑን የነካው ሰው እስከ ምሽት እርኩስ ይሆናል፡፡ 40ደግሞም እንዲህ ያለውን በድን ያነሳ ሰው ልብሱን ያጥባል፣ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡41ማንኛውም በምድር ላይ የሚሳብ እንስሳ ጸያፍ ነው፤ አይበላም፡፡ 42በሆዱ የሚሳብ እንስሳ ሁሉ፣ እና በአራቱም እግሮቹ የሚራመድ፣ወይም ማንኛውም ብዙ እግሮች ያሉት - በምድር የሚሳብ እንስሳን ሁሉ፣ አትብሉ፤ እነዚህ ጸያፍ ናቸው፡፡43በደረቱ በሚሳብ ማናቸውም ህያው ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፤ እነዚህ እናንተን ያረክሳሉ፡፡ 44እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ በምድር በሚንቀሳቀስ በማናቸውም አይነት እንስሳ ራሳችሁን አታርክሱ፡፡ 45እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ ስለዚህ እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱስ መሆን አለባችሁ፡፡46ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በውሃ ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ማናቸውም ህያዋን ፍጥረታት፣ እንዲሁም በምድር ላይ ስለሚሳቡ ፍጥረታት ህጉ ይህ ነው፤ 47ንጹህ ባልሆኑና ንጹህ በሆኑት መካከል ልዩነት ለመፍጠር፣ እና በሚበሉ ህያዋን ነገሮችና በማይበሉ ህያዋን ነገሮች መሃል ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡’”
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“ለእስራኤል ሰዎች እንደህ በላቸው፣ ‘አንዲት ሴት ብታረግዝና ወንድ ልጅ ብትወልድ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ወቅት ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለችም፡፡ 3በስምንተኛው ቀን ህጻኑ ልጅ መገረዝ አለበት፡፡4ከዚያ የእናቲቱ ከደሟ መንጻት ለሰላሳ ሶስት ቀናት ይቆያል፡፡ ምንም አይነት የተቀደሰ ነገር መንካት የለባትም ወይም የመንጻቷ ቀናት እስኪፈጸም ድረስ ወደ ቤተመቅደስ አትምጣ፡፡ 5ሴት ልጅ ከወለደች፣ በወር አበባዋ ወቅት እንደነበረችው ለሁለት ሳምንታት ንጹህ አትሆንም፡፡ ከዚያ የእናትየው የመንጻት ስርዓት ለስድስት ቀናት ይቀጥላል፡፡6ወንድ ልጅም ሆነ ሴት ልጅ ከወለደች በኋላ የመንጻቷ ቀናት ሲያበቃ ለካህኑ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ የአንድ አመት ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዕት እንዲሁም ለኃጢአት መስዋዕት ዋኖስ ወይም ዕርግብ ታቅርብ፡፡7ከዚያ ካህኑ መስዋዕቱን በያህዌ ፊት ይሰዋና ያስተሰርይላታል፣ እናም ከደሟ መፍሰስ ንጹህ ትሆናለች፡፡ ወንድም ይሁን ሴት ልጅ ለወለደች ሴት ህጉ ይህ ነው፡፡ 8ጠቦት ማቅረብ ባትችል፣ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት ርግቦች ትውሰድ፣ አንዱን ለሚቀጠል መስዋዕት ሌላውን ለኃጢአት መስዋዕት ታቅርብ እናም ካህኑ ያስተሰርይላታል፣ ከዚያም ንጹህ ትሆናለች፡፡’”
1ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ 2“ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ችፍታ ወይም ቋቁቻ ቢወጣና ቢቆስል በሰውነቱ ላይ የቆዳ በሽታ ይሆናል፣ በዚህ ጊዜ ወደ ሊቀካህኑ አሮን ይምጣ፣ አሊያም ካህናት ከሆኑት ልጆቹ ወደ አንዱ ይምጣ፡፡3ከዚያ በሰውነቱ ቆዳ ላይ ያለውን በሽታ ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ በበሽታው ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠ፣ እና በሽታው በቆዳው ላይ ከሚታየው ይልቅ የከፋ ሆኖ ከተገኘ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ካህኑ ከመረመረው በኋላ፣ ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ 4በቆዳው ላይ የታየው ቋቁቻ ነጭ ከሆነ፣ እና ወደ ቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ እንዲሁም በህመሙ አካባቢ የሚገኘው ጸጉር ወደ ነጭነት ካልተለወጠ፣ ካህኑ በሽታው ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያገልግለው፡፡5በሰባተኛው ቀን፣ ካህኑ በእርሱ እይታ በሽታው አየከፋ በቆዳው ላይ እየሰፋ አለመሄዱን ለማየት ይመርምረው፡፡ በሽታው ለውጥ ካላሳየ፣ ካህኑ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት ሰውየውን አግልሎ ያቆየው፡፡ 6በሰባተኛው ቀን በሽታው እየተሻለው እንደሆነና በቆዳው ላይ እየሰፋ እንደላሆነ ለማየት ካህኑ ሰውየውን ደግሞ ይመረምረዋል፡፡ በሽታው ለውጥ ካለው፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆነኑን ይገልጻል፡፡ ይህ ሽፍታ ነው፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚህ በኋላ ንጹህ ነው፡፡7ነገር ግን ሰውየው ራሱን ለካህን ካሳየ በኋላ ሽፍታው በቆዳው ላይ ከተስፋፋ፣ እንደገና ራሱን ለካህን ያሳይ፡፡ 8ሽፍታው ይበልጥ በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ መሆኑን ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ከተስፋፋ፣ ከዚያ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አይደለም ይላል፡፡ ይህ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ነው፡፡9ተላላፊ የቆዳ በሽታ በአንድ ሰው ላይ ሲገኝ፣ ይህ ሰው ወደ ካህን ይምጣ፡፡ 10ካህኑ በሰውየው ቆዳ ላይ ነጭ ዕብጠት መኖሩን ለማየት ይመረምረዋል፣ ጸጉሩ ወደ ነጭነት መቀየሩን፣ ወይም በዕብጠቱ ላይ የስጋ መላጥ መኖሩን ይመልከት፡፡ 11እንዲህ ያለ ነገር ካለ፣ ይህ ጽኑ የቆዳ ህመም ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፡፡ ሰውየውን አያገለውም፣ ምክንያቱም ቀድሞውኑም ንጹህ አይደለም፡፡12በሽታው በቆዳው ላይ በሰፊው ጎልቶ ከታየና የሰውየውን ቆዳ ከአናቱ እስከ እግሩ ከሸፈና፣ ካህኑ ይህ እስከ ታየው ድረስ፣ በሽታው የሰውየውን አካል ሸፍኖት እንደሆነ ለማየት ይመርምረው፡፡ 13እንዲህ ሆኖ ከተገኘ፣ በሽታው ያለበት ሰው ንጹህ አለመሆኑን ካህኑ ይግለጽ፡፡ ሁሉም ወደ ንጣት ተለውጦ ከሆነ ንጹህ ነው፡፡ 14ነገር ግን የስጋ መላጥ ከታየበት፣ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡15ካህኑ የስጋውን መላጥ ማየትና ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፣ ምክንያቱም የተላጠ ስጋ ንጹህ አይደለም፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ 16ነገር ግን የተላጠው ስጋ መለልሶ ነጭ ቢሆን፣ ሰውየው ወደ ካህኑ ይሂድ፡፡ 17ካህኑ ስጋው ወደ ነጭነት ተመልሶ እንደሆነ ይመረምረዋል፡፡ እንዲህ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ይገልጻል፡፡18አንድ ሰው በቆዳው ላይ እባጭ ወጥቶ ሲድን፣ 19እና በዕባጩ ስፍራ እብጠት ወይም ቋቁቻ፣ ቀላ ያለ ንጣት፣ ሲኖር ይህን ካህኑ ሊያየው ይገባል፡፡ 20ካህኑ ይህ ወደ ታማሚው ቆዳ ዘልቆ የገባ መሆኑን እና በዚያ ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት መለወጡን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቃል፡፡ እብጠቱ በነበረበት ስፍራ እየሰፋ ከሄደ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡21ነገር ግን ካህኑ ይህንን መርምሮ በውስጡ ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ከተመለከተ፣ እና ይህም ከቆዳው ስር ካልሆነ ሆኖም ከደበዘዘ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡ 22በቆዳው ላይ በሰፊው ከተስፋፋ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አይደለም ይበል፡፡ ይህ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡ 23ነገር ግን ቋቁቻው በቦታው ከሆነና ካልተስፋፋ፣ ይህ የእባጩ ጠባሳ ነው፣ እናም ካህኑ ንጹህ ነው ብሎ ያስታውቅ፡፡24አንድ ሰው ቆዳው ቃጠሎ ሲኖርበትና የስጋው መላጥ ቀላ ያለ ንጣት ወይም ነጭ ጠባሳ ሲሆን፣ 25ካህኑ ያጠባሳ ስፍራ ወደ ንጣት መለወጡን እና ወደ ቆዳው ዘልቆ መግባቱን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንደዚህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ከቃጠሎው አልፎ ከውስጥ የመጣ ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡26ነገር ግን ካህኑ በሚመረምርበት ጊዜ በስፍራው ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ቢደርስበትና ቁስሉ ከቆዳው ስር ሳይሆን ቢቀር እየከሰመ ቢመጣ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡ 27ከዚያም ካህኑ በሰባተኛው ቀን ይመርምረው፡፡ ምልክቱ በሰፊው በቆዳው ላይ ቢስፋፋ፣ ካህኑ ንጹህ አይደለም ብሎ ያሳውቅ፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ 28ምልክቱ በስፍራው ከቆየና በቆዳው ላይ እየሰፋ ካልሄደ ነገር ግን ከከሰመ ይህ በቃጠሎው የመጣ እብጠት ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፣ ይህ ከቃጠሎው የመጣ ጠባሳ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፡፡29በአንድ ወንድ ወይም ሴት ራስ ወይም አገጭ ላይ ተላላፊ በሽታ ቢኖር፣ 30ችግሩ ከቆዳው ስር የዘለቀ መሆኑና በላዩ ቢጫ ስስ ጸጉር እንዳለ ለማየት ካህኑ ካህኑ የተላላፊ በሽታ ምርመራ ያድርግለት፡፡ ይህ ከተገኘ፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ይህ የሚያሳክክ በሽታ ነው፣ በራስ ወይም አገጭ ላይ የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡31የሚያሳክከውን በሽታ መርምሮ ከቆዳ ስር ያልዘለቀ መሆኑን ቢያይ፣ ደግሞም በውስጡ ጥቁር ጸጉር ባይኖር፣ ካህኑ ሰውየውን በሚያሳክክ በሽታው ምክንያት ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡32በሰባተኛው ቀን በሽታው ተስፋፍቶ እንደሆነ ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ቢጫ ጸጉር ከሌለና፣ በሽታው ላይ ላዩን ብቻ ከታየ፣ 33ሰውየው ይላጭ፣ ነገር ግን በሽታው የሚገኝበት ዙሪያ መላጨት የለበትም፣ እናም ካህኑ የሚያሳክክ በሽታ ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡34በሰባተኛው ቀን በሽታው በቆዳው ላይ መስፋፋቱን ማቆሙን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያደርጋል፡፡ በሽታው ቆዳውን ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ ካህኑ የሰውየውን ንጹህ መሆን ያሳውቅ፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡35ነገር ግን ካህኑ ንጹህ መሆኑን ካሳወቀ በኋላ የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ ከሄደ ፣ 36ካህኑ ዳግም ይመርምረው፡፡ በሽታው በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ ከሄደ፣ካህኑ ቢጫ ጸጉር መኖሩን መፈለግ አይኖርበትም፡፡ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡ 37ነገር ግን ካህኑ ሰውየውን የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ መሄዱን እንዳቆመ ከተመለከተ ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፡፡38አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በቆዳቸው ላይ ነጭ ምልክቶች ቢወጣ 39ምልክቱ ዳለቻ መልክ ያለው በቆዳ ላይ የወጣ ሽፍታ ብቻ መሆኑን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግ፡፡ ሰውየው ንጹህ ነው፡፡40የሰውየው ጸጉር ከራሱ ላይ ካለቀ፣መላጣ ነው፣ ነገር ግን ንጹህ ነው፡፡ 41ደግሞም ከፊት ለፊት ጸጉሩ ተመልጦ ራሰ በራ ቢሆንም ንጹህ ነው፡፡42ነገር ግን በህመም ምክንያት ፈዘዝ ያለ ቅላት በተመለጠው ራሱ ላይ ወይም በግምባሩ ላይ ቢኖር፣ ይህ በተላላፊ በሽታ ምክንያት የመጣ ነው፡፡ 43በቆዳ ላይ ተላላፊ በሽታ ሲኖር እንደሚታየው በመላጣው ወይም በበራው ላይ በህመሙ ዙሪያ ፈዘዝ ያለ ቅላት መኖሩን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግለት፡፡ 44ይህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ አለበት እናም ንጹህ አይደለም፡፡ በእርግጥ ካህኑ ሰውየው በራሱ ላይ ካለበት በሽታ የተነሳ ንጹህ እንደልሆነ ያስታውቅ፡፡45ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው የተቀደደ ልብስ ይልበስ፣ ጸጉሩን በከፊል ይሸፍን፣ እስከ አፍንጫው ይከናነብና ‘እርኩስ ነኝ፣ እርኩስ ነኝ’ እያለ ይጩህ፡፡ 46ተላላፊው በሽታ ባለበት ቀናት ሁሉ እርኩስ ነው፡፡ እየሰፋ ሊሄድ በሚችል በሽታ ምክንያት ንጹህ ስላልሆነ፣ ለብቻው ይኑር፡፡ ከሰፈር ውጭ ይኑር፡፡47በማናቸውም ነገር የተበከለ የሱፍም ሆነ የተልባ ዕግር ጨርቅ፣ 48ወይም ከሱፍም ሆነ ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ፣ ወይም ቆዳም ሆነ ከቆዳ በተሰራ ልብስ - 49በልብሱ ላይ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ ብክለት ቢገኝበት፤ በቆዳው፣ በተጠለፈው ወይም በተሰፋው ነገር፣ ወይም ማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ለይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ካህኑ ይህን ይመልከት፡፡50ካህኑ የሚበከለውን ዕቃ ይመርምር፣ የተበከለውን ማናቸውንም ነገር ለሰባት ቀናት ይለየው፡፡ 51በሰባተኛው ቀን እንደገና ብክለቱን ይመርምር፡፡ በልብሱ ወይም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ በተሸመነው ወይም በተጠለፈው ማናቸውም ልብስ ላይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ወይም በቆዳ ወይም ከቆዳ በተሰራ ማናቸውም ነገር ላይ ብክለቱ ቢሰፋ ጎጁ ነው፣ እናም ዕቃው ንጹህ አይደለም፡፡ 52ካህኑ ያንን ልብስ ያቃጥል፣ ወይም ማናቸውም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ነገር፣ ማናቸውም ጎጂ ብክለት የተገኘበት ነገር በሽታ ያመጣልና ያቃጥለው፡፡ ዕቃው ሙሉ ለሙሉ ይቃጠል፡፡53ካህኑ ዕቃውን መርምሮ ብክለቱ በልብ ወይም በተሸመነው ወይም በተለጠፈው ልብስ ወይም በቆዳ ዕቃዎቹ ላይ እየሰፋ የሚሄድ አለመሆኑን ካወቀ፣ 54ብክለቱ የተገኘባቸውን ዕቃዎች እንዲያጥቡ ያዛቸዋል፤ ደግሞም ዕቃውን ለሰባት ቀናት ያግልል፡፡ 55ከዚያ ካህኑ የተበከለውን ዕቃ ከታጠበ ከሰባት ቀናት በኋላ ይመረምረዋል፡፡ ብክለቱ ቀለሙን ካልቀየረውና እየሰፋ ባይሄድ እንኳን ንጹህ አይደለም፡፡ ብክለቱ የትም ላይ ይሁን ዕቃዎቹን አቃጥሏቸው፡፡56ካህኑ ዕቃውን ከመረመረና ልብሱ ከታጠበ በኋላ ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ከተበከለው የልብሱ ወይም የቆዳው ክፍል ወይም ከተሸመነው ወይም ከተጠለፈው ዕቃ ቀድዶ ያውጣው፡፡ 57እንዲህም ሆኖ ብክለቱ አሁንም በተሸመነው ወይም በተጠለፈው፣ ወይም በማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ላይ ከተገኘ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው፡፡ ብክለት ያለበትን ማናቸውንም ነገር አቃጥለው፡፡ 58ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተሰራ ወይም የተለጠፈ ልብስ ወይም ማናቸውም ነገር፣ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ማናቸውም ነገር - ስታጥበው ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ዕቃው ዳግመኛ ይታጠብ እናም ንጹህ ይሆናል፡፡59ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ለተሸመነ ወይም ለተጠለፈ፣ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ ለተሰራ ማናቸውም ነገር ብክለት ህጉ ይህ ነው፣ ስለዚህ ንጹህ ነው ወይም እርኩስ ነው ብለህ ማሳወቅ ትችላለህ፡፡”
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“የታመመ ሰው በሚነጻበት ቀን ህጉ ይህ ነው፡፡ ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡3ካህኑ የሰውየው ተላላፊ የቆዳ በሽታ መዳኑን ለመመርመር ከሰፈር ይወጣል፡፡ 4ከዚያም ካህኑ የሚነጻው ሰው ህይወት ያላቸው ሁለት ንጹህ ወፎችን፣ የጥድ ዕንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድርና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል፡፡ 5ካህኑ የታመመው ሰው ከወፎቹ አንዱን አርዶ በሸክላ ማሰሮ ውስጥ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡6ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ፣የጥዱን እንጨትና፣ ደማቁን ቀይ ድርና ሂሶጵ ይቀበለውና ህይወት ያለውን ወፍ ጨምሮ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ቀደም ሲል በታረደው ወፍ ደምና ንጹህ ውሃ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ 7ከዚያ ካህኑ ይህንን ውሃ ከበሽታው በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጫል፣ ከዚያ በኋላ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡8የነጻው ሰው ልብሱን ያጥባል፣ ፀጉሩን በሙሉ ይላጫል፣ገላውንም ይታጠባል፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር ይመለስ፣ ነገር ግን ከድንኳኑ ውጭ ለሰባት ቀናት ይቆያል፡፡ 9በሰባተኛው ቀን የራሱን ፀጉር በሙሉ ይላጭ፣ ልብሶቹን ይጠብ፣ ገላውን በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡10በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸው ሁለት ወንድ የበግ ጠቦቶች፣አንድ ነውር የሌለበት የአንድ አመት የበግ ጠቦት ያምጣ፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ የላመ ዱቄት እና አንድ ሊትር ዘይት ለእህል ቁርባን ያቅርብ፡፡ 11የመንጻት ስርዓቱን የሚያስፈጽመው ካህን የሚነጻውን ሰው ከእነዚህ ነገሮች ጋር ይዞ፣ በያህዌ ፊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይቆማል፡፡12ካህኑ ወንዱን ጠቦት ወስዶ ለኃጢአት መስዋዕት ከአንዱ ሊትር ዘይት ጋር ያቀርባል፤ እነዚህንም በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ይወዘውዘዋል፤ ለእርሱም ያቀርበዋል፡፡ 13ወንዱን ጠቦት የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ባቀረቡበት ስፍራ በቤተ መቅደስ ያርደዋል፤ እንደ በደል መስዋዕቱ ሁሉ የኃጢአት መስዋዕቱም ለካህኑ ይሰጥ፣ ምክንያቱም ይህ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡14ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባ፡፡ 15ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ወስዶ በእርሱ በራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣ 16ከዚያም በግራ እጁ መዳፍ ላይ በፈሰሰው ዘይት ውስጥ የቀኝ እጁን ጣት ያጠልቃል፣ በጣቱ ላይ ካለው ዘይት በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡17ካህኑ በእጁ ላይ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት፣ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡ ይህንን ዘይት በበደል መስዋዕቱ ደም ላይ ያድርገው፡፡ 18ካህኑ በእጁ የቀረውን ዘይት፣ በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፍስስ፣ እናም ካህኑ በያህዌ ፊት የሚነጻውን ሰው ያሰርይለታል፡፡19ከዚያ ካህኑ የኃጢአት መስዋዕቱን ይሰዋል፤ ደግሞም ንጹህ ባለመሆኑ ምክንያት መንጻት ላለበት ሰው ያሰርይለታል፣ እናም ከዚህ በኋላ የሚቃጠል መስዋዕቱን ይሰዋል፡፡ 20ካህኑ የሚቃጠለውን መስዋዕትና የእህል ቁርባኑን በመሰዊያ ላይ ያቀርባል፡፡ ካሁኑ ለሰውየው ማስተስረያ ያቀርብለታል፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡21ሆኖም ሰውየው ደሃ ከሆነና እነዚህን መስዋዕቶች ማቅረብ ካልቻለ ለኃጢአቱ ማስተስረያ የበደል መስዋዕት አንድ ወንድ ጠቦት፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄትና አንድ ሊትር ዘይት ያቅርብ፣ 22ሰውየው በአቅሙ ከሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ጋር፣ አንደኛውን ወፍ የኃጢአት መስዋዕት ሌላኛው ደግሞ የሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል፡፡ 23በስምንተኛው ቀን ስለ መንጻቱ ወደ መገናኛው ድንኳን በያህዌ ፊት ያምጣቸው፡፡24ከዚያ ካህኑ ጠቦቱን ለበደል መስዋዕት ደግሞም አንዱን ሊትር ዘይት፣ይወስድና ለያህዌ የበደል መስዋዕት ይወዘውዛል፣ እናም ለእርሱ እነዚህን ያቀርባቸዋል፡፡ 25ለበደል መስዋዕት ጠቦቱን ያርዳል፣ እናም ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡26ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ጥቂቱን በገዛ ራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣ 27በቀኝ ጣቱ ከዘይቱ በግራ እጁ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡28ከዚያ ካህኑ በእጁ ካለው ዘይት ጥቂቱን በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ የበደል መስዋዕቱን ደም ባደረገበት ተመሳሳይ ስፍራዎች ይቀባል፡፡ 29የተረፈውን በእጁ ያለውን ዘይት ያስተሰርይለት ዘንድ በያህዌ ፊት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሳል፡፡30ሰውየው በአቅሙ ካቀረበው ከእርግቦቹ ወይም ከዋኖሶቹ አንዱን ይሰዋ - 31ከእህል ቁርባኑ ጋር፣ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ከዚያም ካህኑ ለሚነጻው ሰው በያህዌ ፊት ያስተሰርይለታል፡፡ 32ለመንጻት ዋናውን መስዋዕት ማቅረብ ለማይችል ተላላፊ የቆዳ በሽታ ላለበት ሰው የመንጻት ህጉ ይህ ነው፡፡”33ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣ 34“ርስት አድርጌ ወደሰጠኋችሁ ወደ ከነዓን ምድር ስትመጡ፣ ርስት በሆናችሁ ምድር በቤታችሁ እየሰፋ የሚሄድ ብክለት ባደርግባችሁ፣ 35የቤቱ ባለቤት ወደ ካህኑ መጥቶ ይናገር፡፡ እንዲህም ይበል፣ “በቤቴ ብክለት ያለ ይመስለኛል፡፡’36ከዚያ ካህኑ በቤቱ ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም ነገር እርኩስ እንዳይሆን ብክለት መኖሩን ለማየት ወደዚያ ቤት ከመግባቱ አስቀድሞ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉ ያዛል፣ ከዚህ አስቀድሞ ካህኑ ያንን ቤት ለማየት ይገባል፡፡ 37ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መኖሩን፣ ደግሞም አረንጓዴ ሆኖ ወይም ቀላ ብሎ በግርግዳዎቹ ላይ መታየቱን ይመርምር፡፡ 38ቤቱ ሻጋታ ካለው፣ ካህኑ ከዚያ ቤት ይወጣና ለሰባት ቀናት በሩን ይዘጋዋል፡፡39በሰባተኛው ቀን ካህኑ ተመልሶ ይመጣና ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መስፋፋቱን ለማየት ይመረምራል፡፡ 40እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ሻጋታ የተገኘባቸውን ድንጋዮች ከግድግዳው ላይ እየፈነቀሉ እንዲያወጡና ከከተማ ውጭ ቆሻሻ ስፍራ መጣያ እንዲጥሏቸው ያዛል፡፡41የቤቱ የውስጥ ግድግዳዎች ሁሉ እንደዲፋቁ ይጠይቃል፣ እነርሱም እየተፋቁ የተነሱትን የተበከሉትን ቁሶች ከከተማ አውጥተው በቆሻሻ መጣያ ስፍራ ይጥላሉ፡፡ 42ባስወገዷቸው ድንጋዮች ስፍራ ሌሎች ድንጋዮች ወስደው ያስቀምጡ፣ ቤቱን ለመምረግ አዲስ ጭቃ ይጠቀሙ፡፡43ድንጋዮቹ ተነስተውና ግርግዳው ተፍቆ እንዲሁም ተለስኖ ዳግም ብክለቱ ከወጣና ከታየ፣ 44ካህኑ ብክለቱ መስፋፋቱን ለመመልከት ቤቱን ይመርምር፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ይህ ጎጂ ብክለት ነው፤ ቤቱ ንጹህ አይደለም፡፡45ቤቱ ይፍረስ፡፡ የቤቱ ድንጋዮች፣ በሮች፣ እና ፍርስራሾች ከከተማ ውስጥ በቆሻሻ መጣያ ይጣል፡፡ 46በተጨማሪም፣ ቤቱ በተዘጋባቸው ጊዜያት ወደዚያ ቤት የሄደ ሁሉ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡ 47ማንም በዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እንዲሁም በዚህ ቤት ውስጥ የተመገበ ሰው ልብሱን ይጠብ፡፡48ቤቱ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ ወዴት እንደተስፋፋ ለመመርመር ካህኑ ወደዚያ ቤት ቢገባ፣ እናም ብክለቱ ተወግዶ ቢሆን ቤቱ ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡49ከዚያ ካህኑ ቤቱን ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የጥድ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድር እና ሂሶጵ ይውሰድ፡፡ 50ከወፎቹ አንዱ ንጹህ ውሃ በያዘ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ያርደዋል፡፡ 51የጥድ እንጨት፣ሂሶጵደማቅ ቀይ ድር እና በህይወት ያለ ወፍ ይውድና በታረደው ወፍ ደም ውስጥ እና በንጹህ ውሃ ውስት ይነክራቸዋል፣ከዚያም ቤቱን ሰባት ጊዜ ይርጨው፡፡52ቤቱን በወፉ ደምና በንጹህ ውሃ፣ በህይወት በሚገኘው ወፍ፣ በጥድ እንጨት፣በሂሶጵና በደማቅ ቀይ ድር ያነጻዋል፡፡ 53በህይወት የሚገኘውን ወፍ ግን ከከተማ ውጭ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡ በዚህ መንገድ ቤቱን ያስተሰርያል፣ ቤቱም ንጹህ ይሆናል፡፡54ለሁሉም አይነት ተላላፊ የቆዳ በሽታና እንዲህ ያለውን በሽታ ለሚያመጡ ነገሮች፣ እንዲሁም ለሚያሳክክ ህመም፣ 55እንዲሁም ለልብስና ለቤት ብክለት፣ 56ለእብጠት፣ ለሚያሳክክ ህመም፣ እና ለቋቁቻ፣ 57በእነዚህ ሁኔታዎች እርኩስና ንጹህ የሚሆነውን ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡”
1ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣ 2‹ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብላችሁ ንገረቸው፣ ‹ማንም ሰው ከሰውነቱ የሚወጣ የሚመረቅዝ ፈሳሽ ሲኖርበት፣ ንጹኅ አይደለም፡፡ 3ንጹኅ የማይሆነ ከሚመረቅዝ ፈሳሽ የተነሳ ነው፡፡ ከሰውነቱ የሚወጣ ፈሳሽ ቢቀጥል ወይም ቢቆም ንጹህ አይደለም፡፡4የሚተኛበት አልጋ ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፣ የሚቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፡፡ 5አልጋን የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ ሰውየውም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹኅ አይደለም፡፡6የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበት ሰው በተቀመጠበት ማናቸውም ነገር ላይ የተቀመጠ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 7የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበትን ሰው አካል የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፡፡ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡8እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ሰው ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ፣ ያ ሰው ልብሱን ማጠብና እርሱም በውሃ መታጠብ አለበት፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡ 9ፈሳሽ ያለበት ሰው የተቀመጠበት ማንኛውም ኮርቻ ንጹኅ አይደለም፡፡10ከዚያ ሰው በታች ያለን ማንኛውንም ነገር የነካ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፣ እነዚያን ነገሮች የተሸከመ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡ 11እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ማንም ቢሆን አስቀድሞ እጆቹን በውሃ ሳያጠራ ቢነካ፣ የተነካው ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡ 12እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበትን ሰው የነካ ማናቸውም አይነት የሸክላ ዕቃ ይሰበር፣ የእንጨት የተሰራ ማጠራቀሚያ ሁሉ በውሃ ይንጻ፡፡13ፈሳሽ ያለበት ሰው ከፈሳሹ ሲነጻ ለመንጻቱ ለእራሱ ሰባት ቀናትን ይቁጠር፤ ከዚያ ልብሶቹን ይጠብ ሰውነቱን በምንጭ ውሃ ይታጠብ፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡ 14በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ኖሶች ይውሰድና ወደ መገናኛ ድንኳን ያህዌ ፊት ይቅረብ፣ በዚያ ወፎቹን ለካህኑ ይስጥ፡፡ 15ካህኑ አንዱን ለሀጢአት መስዋዕት እና ሌላውን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርባቸው፣ እናም ካህኑ ለሰውዬው ስለ ፈሳሹ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡16የማንንም ሰው የዘር ፈሳሽ ሳይታሰብ በድንገት ከእርሱ ቢወጣ፣ መላ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡ 17ማናቸውም የዘር ፈሳሽ የነካ ልብስ ወይም ሌጦ በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡ 18አንዲት ሴትና አንድ ወንድ አብረ ቢተኙና ወደ እርሷ የዘር ፈሳሽ ቢተላለፍ ሁለቱም በውሃ ይታጠቡ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደሉም፡፡19አንዲት ሴት የወር አበባ ሲፈሳት፣ ያለመንጻቷ ለሰባት ቀናት ይቀጥላል፣ እርሷን የነካ ሁሉ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 20በወር አበባ ወቅት የምትተኛበት ማንኛውም ነገር ንጹህ አይደለም፤ እንደዚሁም የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይደለም፡፡21አልጋውን የነካ ማንኛም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ ያሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 22የተቀመጠችበትን ማናቸውንም ነገር የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ ያ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 23በአልጋም ይሁን በማንኛም ነገር ላይ ብትቀመጥ የተቀመጠችበትን ነገር የነካ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡24ከእርሷ ጋር የተኛ ንጹህ ያልሆነ ፈሳሽ ቢነካ፣ ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለም፡፡ የሚተኛበትም አልጋ ንጹህ አይደለም፡፡25አንዲት ሴት ከወር አበባ ቀናት በኋላ ለብዙ ቀናት ደም መፍሰሱን ቢቀጥል፣ ይህም ከወር አበባ ጊዜያት በኋላ ፈሳሽ ቢኖርባት፣ ንጹኅ ባልሆነችባቸው ፈሳሽ ባለባት ጊዜያት ሁሉ፣ በወር አበባ ወቅት ላይ እንዳለች ሁሉ እርኩስ ይሆናል ንጹህ አይደለችም፡፡26ደሟ በሚፈስባቸው ጊዜያት የምትተኛበት አልጋ ሁሉ በወር አበባ ወቅት እንደምትተኛበት እርኩስ ይሆናል፣ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ልክ በወር አበባ ወቅት እንደሚሆነ ንጹህ አይደለም፡፡ 27ደግሞም ከእነዚህ ነገሮች ማናቸንም የነካ ሁሉ ንጹህ አይደለም፤ ልብሶቹን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡28ነገር ግን ከደም መፍሰሳ ብትነጻ፣ ለራስዋ ሰባት ቀናትን ትቆጥራለች፣ እናም ከዚያ በኋላ ንጹኅ ናት፡፡ 29በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ትወሰድና ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለካህኑ ትስጥ፡፡ 30ካህኑ አንዱን ወፍ ለሀጢአት መስዋእት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፣ ስለ ፈሳሽም እርኩሰት በያህዌ ፊት ያስተሰርይላታል፡፡31የእስራኤል ሰዎች ከእርኩሰታቸው የምትይች እንደዚህ ነ፣ ይህ ከሆነ በመካከላቸ የምኖርበትን ቤተ መቅደሴን በማርከስ በእርኩሰታቸ አይሞቱም፡፡32ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚጣ፣ የዘረ ፈሳሹ ከእርሱ ለሚጣና ለሚያረክሰ ማንኛም ሰ ህግጋቱ እነዚህ ናቸ፡፡ 33ለማንኛም በር አበባ ላይ ላለች ሴት፣ ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚፈሰ ሰ ሁሉ፣ ንድም ይሁን ሴት፣ እንዲሁም ንጹህ ካልሆነች ሴት ጋር ለሚተኛ ንድ ህጉ ይህ ነ፡፡”
1ያህ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረ፡ - ይህ የሆነ የአሮን ሁለቱ ልጆች ¨ደ ያህ«ከቀረቡና ከሞቱ በሀላ ነበር፡፡ 2ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለ፣ “ለ¨ንድምህ ለአሮን እንዲህ ብለህ ተናገረ፣ በፈለገ¬ ጊዜ ሁሉ በመጋረጃ ¬ስጠኛ ¨ዳለ ¨ደ ቅድስተ ቅዱሳኑ፣ በታቦቱ ላይ ወዳለ ወደ ማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ላይ እገለጣለሁ፡፡3ስለዚህም አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መቅረብ ያለበት እንደዚህ ነው፡፡ ለሀጢአት መስዋዕት ወይፈን፣ ለሚቃጠል መስዋዕት አ¬ራ በግ ይዞ መግባት አለበት፡፡ 4ቅዱሱን በፍታ ቀሚስ ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ የስጥ ሱሪ ይልበስ፣ ደግሞም የበፍታ መጠምጠሚያ የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፡፡ ቅዱሳኑ አልባሳት እነዚህ ናቸው፡፡ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብና እነዚህን ልብሶች ይልበስ፡፡ 5ከእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁለት ወንድ ፍየሎችን ለሀጢአት መስዋዕት እንዲሁም አንድ አ¬ራ በግ ለሚቃጠል መስዋዕት ይውሰድ፡፡6ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማ¬ን ለኃጢአት መስዋዕት ያቅርብ፣ ይህም ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ነው፡፡ 7ቀጥሎም ሁለቱም ፍየሎች ወስዶ በመገናኛ¬ ድንኳን መግቢያ ላይ በያህዌ ፊት ያቁማቸው፡፡8ከዚያ አሮን በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጣል፣ አንዱን ዕጣ ለያህዌ ሌላ¬ን ዕጣ ለሚለቀቀው ፍየል ይጣል፡፡ 9ከዚያም አሮን ዕጣ ለያህ«የ¨ጣለትን ፍየል ያቀርባል፣ ያንን ፍየልም ለኃጢአት መስªዕት ያቀርበªል፡፡ 10ለመለቀቅ ዕጣ የጣትን ፍየል ግን ወደ ምድረበዳ በመልቀቅ ለስርየት ከነህይ¨ት ለያህዌ መቅረብ አለበት፡፡11ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማን ለሀጢአት መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ማድረግ አለበት፣ ስለዚህ ኮርማን ለራሱ የሀጢአት መስዋዕት አድርጎ ይረዳ፡፡12አሮን በያህዌ ፊት ከመሰዊያ የከሰል እሳት የሞላውን ማጠንት ይውሰድ፣ በእጆቹ ሙሉ የላመ ጣፋጭ ዕጣን ይያዝና እዚህንም ነገሮች ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡ 13በዚያም በያህ«ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ይጨምር፣ ከእጣኑ የሚ¨ጣ ጢስ በምስክሩ ላይ ያለ የማስተሰርያን ክዳን ይሸፍናል፡፡ እንዳይሞት ይህንን ያድርግ፡፡14ከዚያም ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውሰድና በጣቱ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ ከደሙ ጥቂት ¨ስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡15ከዚያም ለህዝቡ ኃጢአት የኃጢአት መስªዕት ፍየሉን ይረድና ደሙን ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡ በዚያም በኮርማ ደም እንዳደረገ ሁሉ ያድርግ በማስተሰርያ¬ ክዳን ላይ ደሙን ይርጭ ከዚያም በማስተሰርያ¬ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡ 16በእስራኤል ህዝብ ያልተቀደሱ ተግባራት፣ በአመጻቸ¬ና በኃጢአቶቻቸ¬ ሁሉ ምክንያት ለተቀደሰ ስፍራ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡ ንጹህ ያልሆኑ ተግባሮቻቸ¬ በታዩ ጊዜያት፣ ያህ በመካከላቸ¬ ለሚያድርበት ለመገናኛ¬ ድንኳንም ይህን ያድርግ፡፡17አሮን ለማስተሰርይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚገባበት ሰዓትና እንዲሁም ለእርሱ፣ ለቤተሰቡና ለእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ማስተሰርዩን እስከሚጨርስ ድረስ ማንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አይገኝም፡፡ 18በያህ«ፊት ወዳለ መሰዊያ ይሂድና መሰዊያን ያስተሰርይ፣ ከኮርማ ደም ጥቂት እንዲሁም ከፍየሉ ደም ጥቂት ይ¬ስድና በመሰዊያ ዙሪያ ባሉ ቀንዶች ሁሉ ¬ስጥ ያስነካ፡፡ 19መሰዊያዉን ንጹህ ካልሆነ የእስራኤል ሰዎች ድርጊቶች ለማንጻትና ለያህዌ ለመለየት በላዩ ካለ ጥቂት ደም ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭ፡፡20ቅድስተ ቅዱሳኑን፣ የመገናኛን ድንኳንና መሰዊያን ማስተሰርያ¬ን ሲጨርስ በህይወት የሚገኘ¬ን ፍየል ያቅርብ፡፡ 21አሮን ህይወት ባለው ፍየል ላይ ሁለቱንም እጆቹን ይጫንና የእስራኤልን ህዝብ በደልን ሁሉ፣ አመጻቸውን ሁሉ፣ እና ሀጢአታቸውን ሁሉ በላዩ ላይ ይናዘዝበት፡፡ ከዚያም ያንን ሃጢአተኛነት በፍየሉ ራስ ላይ አድርጎ ፍየሉን ወደ በረሃ ለመስደድ ኃላፊነት ባለበት ሰው አማካይነት ወደ በረሃ ያባው፡፡ 22ፍየሉ የሰቹን በደል ሁሉ ይሸከምና ገለልተኛ ¨ደ ሆነ ስፍራ ይሄዳል፡፡ በበረሃ ስፍራም፣ ሰ¬ዬ¬ ፍየሉን ይለቀªል፡፡23ከዚያም አሮን ወደ መገናኛ ድንኳን ይመለስና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ከመሄዱ አስቀድሞ የለበሰን የበፍታ ልብሶች ያወልቃል፣ እነዚያን ልብሶችም በዚያ ስፍራ ያስቀምጣቸዋል፡፡ 24በተቀደሰ ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያም የዘወትር ልብሱን ይልበስ፣ ከዚያም ወጥቶ የራሱን የሚቃጠል መስዋዕቱን የህዝቡን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መንገድ ለራሱና ለህዝቡ ማስተሰርያ ያቀርባል፡፡25በመሰዊያ ላይ የኃጢአት መስዋዕቱን ስብ ያቃጥል፡፡ 26የሚሰደደውን ፍየል የለቀቀው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡27በተቀደሰው ስፍራ ለማስተሰርያው ደማቸው የቀረበው የኃጢአት መስªዕቱ ኮርማ እና የኃጢአት መስªዕቱ ፍየል ከሰፈር ውጭ ይውስዳቸው። በዚያም ቆዳቸውን፣ ስጋቸውንና ፈርሳቸውን ያቃጥላFቸው፡፡ 28እነዚህን የእንስሳውን ክፍሎች የሚያቃጥለው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ፣ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡29በሰባተኛው ወር፣ በወሩ በአስረኛው ቀን ራሳችሁን ትሁት ታደርጋላችሁ ስራም አትሰሩበትም ለእናንተም ሆነ ለመጻተኛው ይህ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፡፡ 30ይህ የሚሆነው በዚህ ዕለት በያህዌ ፊት ቅዱስ ትሆኑ ዘንድ ከኃጢአቶቻችሁ ሁሉ እንድትነጹ ማስተሰርያ ስለሚደረግላችሁ ነው፡፡ 31ይህ ለእናንተ ክቡር ሰንበት ዕረፍት ነው፣ ራሳችሁን ትሁት ማድረግ አለባችሁ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡ይህ በእናንተ መሀል ሁልጊዜም መታሰቢያ ነው32ሊቀ ካህኑ፣ በአባቱ ስፍራ ሊቀካህን ሊሆን የሚቀባውና የሚሾመው፣ ይህን ማስተሰርያ ማስፈጸምና ቅዱስ የሆነውን የበፍታ ልብሶች መልበስ አለበት፡፡ 33ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመስዋዕቱ፣ ማስተሰርያ ያደርጋል፤ እንደዚሁም ለካህናቱና ለጉባኤው ሰዎች በሙሉ ማስተሰርያ ያደርጋል፡፡34"ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፣ ለእስራኤል ሰዎች ለኃጢአቶቻቸው ሁሉ ማስተሰርያ ለማቅረብ ይህ በየአመት አንድ ጊዜ ይደረግ፡፡” ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ተደረገ፡፡
1እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣2አሮንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤል ህዝብ ሁሉ እንዲህ በላቸው፡፡ ያህዌ ያዘዘውን ንገራቸው፡፡ 3“ከእስራኤል ሰዎች መሀል ማንም ለመስዋዕት በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈር ውጭ በሬ፣ በግ፣ ወይም ፍየል ያረደ ሰው፣ 4ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ በመቅደሱ ፊት ለያህዌ መስዋዕት ለማድረግ ባመጣው ውሃ ያ ሰው ስላፈሰሰው ደም በደለኛ ነው” ደም አፍስሷልና ያ ሰው ከህዝቡ መሃል ተለይቶ ይጥፋ፡፡5የዚህ ትእዛዝ ዓላማ የእስራኤል ሰዎች ለያህዌ በሜዳ ላይ የሚያቀርቧቸውን መስዋዕቶች ወደ ካህናት ለያህዌ የህብረት መስዋዕት አድርገው በመገናኛው ድንኳን መግቢያ እንዲያቀርቡ ነው፡፡ 6ካህኑ የመስዋዕቱን ደም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በያህዌ መሰዊያ ላይ ይረጫል፤ ስቡን ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ አድርጎ ያቃጥለዋል፡፡7ሕዝቡ ከእንግዲህ መስዋዕቱን ለጣኦት አይሰዋ፣ እንዲህ ያለው ተግባር ምንዝርና ነው፡፡ ይህ በትወልዶቻቸው ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡8እንዲህ በላቸው፣ “ማንኛውም እስራኤላዊ፣ ወይም ማንኛውም በእነርሱ መሀል የሚኖር መጻተኛ፣ የሚቃጠል መስዋዕት የሚሰዋ ወይም መስዋዕት የሚያቀርብ 9እና ለያህዌ ለመሰዋት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ የማያመጣው ያ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡10ደግሞም ከእስራኤል አንዱ፣ ወይም በእነርሱ መሀል ከሚኖር መጻተኛ አንዱ፣ ደም ቢበላ፣ ፊቴን ከዚያ ሰው አስቆጣለሁ፣ ማንንም ደም የሚበላን ሰው ከህዝቡ መሃል አጠፋዋለሁ፡፡ 11የእንስሳ ህይወቱ በደሙ ውስጥ ነው፡፡ በመሰዊያ ላይ ማስተሰርያ ይሁናችሁ ዘንድ ደሙን ለሕይወታችሁ ሰትቻችኋለሁ፣ ምክንያቱም ማስተሰርያ የሚሆነው ደም ነው፣ ለሕይወት ስርየት የሚያስገኘው ደም ነው፡፡12ስለዚህም ለእስራኤላውያን ከመሀላችሁ ማንም ደም አይብላ እላለሁ፣ በመሀላችሁ የሚኖር ማንም ሙያተኛም ቢሆን ደም አይብላ፡፡ 13ከእስራኤል ሰዎች መሀል ማንም ቢሆን፣ ወይም በእነርሱ መሃል የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣ የሚበላ እንስሳ ቢያርድ ወይም ወፍ ቢያጠምድ ደሙን ያፍስና በአፈር ይሸፍነው፡፡14የእያንዳንዱ ፍጥረት ነፍስ ደሙ ነውና፡፡ ስለዚህም ነው ለእስራኤላውያን፣ የማንኛውም ፍጥረት ደም አትብሉ፣ የእያንዳንዱ ሕያው ፍጥረት ሕይወት ደሙ ነው፡፡ ማንም ይህን የሚበላ ተቆርጦ ይጥፋ” ብዬ የተናገርኩት፡፡15እያንዳንዱ የሞተ፣ ወይም በዱር አውሬ የተዘነጠለ እንስሳ የበላ ሰው የአገር ተወላጅ ይሁን በመሀላችሁ የሚኖ መጻተኛ ልብሶቹን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስ ምሽት ድረስ ንጹህ አይሆንም፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡ 16ነገር ግን ልብሱን ባያጥብ ወይም ሰውነቱን ባይታጠብ፣ በበደሉ ተጠያቂ ነው፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 3እኔ በማስገባችሁ ምድር፤ ቀድሞ ትኖሩበት በነበረው በግብጽ የነበሩ ሰዎች ያደርጓቸው የነበሩ ነገሮችን አታድርጉ፣ ደግሞም በከነአን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ያደርጓቸው የነበሩ ነገሮችን አታድርጉ፡፡ የእነርሱን ልምዶች አትከተሉ፡፡4እናንተ መፈጸም ያለባችሁ የእኔን ህጎች ነው መጠበቅ ያለባችሁ የእኔን ትዕዛዛት ነው፣ ስለዚህም በእነርሱ ትኖራላችሁ፣ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ 5ስለዚህም እኔን ትዕዛዛትና ህጎች ትጠብቀላችሁ፡፡ አንድ ሰው እነዚህን ቢጠብቅ፣ በእነርሱ ምክንያት በህይወት ይኖራል፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡6ማንም ሰው ከቅርብ ዘመዱ ጋር አይተኛ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 7ከእናትህ ጋር በመተኛት አባትህን አታዋርድ፡፡ እርሷ እናትህ ናት! እርሷን ማዋረድ የለብህም፡፡ 8ከአባትህ ሚስት ከየትኛዋም ጋር አትተኛ፤ አባትህን በዚያን አይነት ማዋረድ የለብህም፡፡9የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ ብትሆን በቤት ውስጥ አብራህ ብታድግ ወይም ርቃ ብታድግም ከየትኛዋም እህትህ ጋር አትተኛ፡፡ 10ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ጋር ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ ይህ እፍረት ይሆንብሃል፡፡ 11ከአባትህ ከተወለደች ከእንጀራ እናትህ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ እህትህ ናት፣ እናም ከእርሷ ጋር መተኛት የለብህም፡፡12ከአባትህ እህት ጋር አትተኛ፡፡ ለአባትህ የቅርብ ዘመድ ናት፡፡ 13ከእናትህ እህት ጋር አትተኛ፡፡ ለእናትህ የቅርብ ዘመድ ናት፡፡ 14ወንድም ከሚስቱ ጋር በመተኛት አታዋርደው” ለዚያ ተግባር ወደ እርሷ አትቅረብ፣ አክስትህ ናት፡፡15ከምራትህ ጋር አትተኛ፡፡ የወንድ ልጅህ ሚስት ናት፣ ከእርሷ ጋር አትተኛ፡፡ 16ከወንድምህ ሚስት ጋር አትተኛ፣ በዚህ መንገድ አታዋርደው፡፡17ከአንዲት ሴትና ከልጇ ጋር ወይም ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ጋር ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ እነርሱ ለእርሷ የቅርብ ዘመዶች ናቸው፣ እናም ከእነርሱ ጋር መተኛት ጸያፍ ነው፡፡ 18የሚስትህን እህት ሁለተኛ ሚስት አድርገህ አታግባ፤ ሚስትህ በህይወት ሳለች ከእህቷ ጋር አትተኛ፡፡19አንዲት ሴት በወር አበባዋ ወቅት ላይ ሳለች አብረሃት አትተኛ፡፡ በዚያን ጊዜ ንጹኅ አይደለም፡፡ 20ከጎረቤትህ ሚስት ጋር አትተኛ፣ በዚህ መንገድ ራስህን አታርክስ፡፡21ከልጆችህ አንዳቸውንም በእሳት ውስጥ እንዲያልፉ አትስጥ፣ በዚህ ድርጊት ለሞሎክ መስዋዕት አድርህ ትሰጣቸዋለህ፣ የአምላክህን ስም ማቃለል የለብህም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡22ከወንዶች ጋር ከሴት ጋር እንደምትተኛው አትተኛ፡፡ ይህ ጻያፍ ነው፡፡ 23ከማናቸውም እንስሳ ጋር አትተኛ ራስህን አታርክስ፡፡ ማንም ሴት ከማናቸውም እንስሳ ጋር መተኛት የለባትም፡፡ ይህ አስጸያፊ ወሲብ ነው፡፡24ከእነዚህ መንገዶች በየትኛውም ራስህን አታርክስ፣ ከአንተ አስቀድሞ ያባረርኳቸው ህዝቦች በእነዚህ ሁሉ መንገዶች ረክሰዋል፡፡ 25ምድሪቱ ረከሰች፣ ስለዚህም በኃጢአታቸው ቀጣኋቸው፣ ምድሪቱም በላይዋ የሚኖሩትን ተፋቻቸው፡፡26ስለዚህ እናንተ የእኔን ትዕዛዛትና ህግጋቴን መጠበቅ አለባችሁ፣ እናንተ ተወላጅ እስራኤላዊያንም ሆናችሁ በእንተ መሀል የሚኖሩ እንግዶች ከእነዚህ ያልተገቡ ነገሮች የትኞቹንም ማድረግ የለባችሁም፡፡ 27ከእናንተ አስቀድሞ በዚህ ምድር የኖሩ ሰዎች የሰሩት ጸያፍነት ይህ ነው፣ እናም አሁን ምድሪቱ ረከሰች፡፡ 28ስለዚህም ምድሪቱ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ሰዎች እንደተፋች እናንተንም ካረከሳችኋት በኋላ እንዳትተፋችሁ ተጠንቀቁ፡፡29ከእነዚህ አስነዋሪ ነገሮች መሀል የትኛውንም ነገር ያደረገ፣ እንዲህ ያለ ነገሮችን ያደረገው ሰው ከህዝቡ መሀል ተለይቶ ይጠፋል፡፡30ስለዚህ በእነዚህ ነገሮች እንዳታረክሱ ከእናንተ አስቀድሞ በዚህ ስፍራ ይፈፀሙ የነበሩትን ጸያፍ ልምዶች ባለማድረግ ትዕዛዛቴን መጠበቅ አለባችሁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ።
1ሙሴን እንዲህ አለው 2“ለእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ቅዱስ እንደሆንኩ እናተም ቅዱሳን ሁኑ፡፡ 3እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፣ እናንተም ሰንበቴን ጠብቁ፡፡ እኔ አምላካች ያህዌ ነኝ፡፡ 4ጥቅም ወደሌላቸው ጣኦታት ዘወር አትበሉ፣ ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልዕክትን አታብጁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡5ለያህዌ የህብረት መስዋእቶችን ስታቀርቡ፣ ተቀባይነት ልታገኙ በምትችሉበት መንገድ አቅርቡ፡፡ 6መስዋዕቱ ባቀረባችሁበት ቀን አሊያም በማግስቱ ይበላ፡፡ አንዳች ነገር እስ ሶተኛው ቀን ቢተርፍመ ይቃጠል፡፡ 7በሶስተኛው ቀን ቢበላ የረከሰ ነው፡፡ ተቀባይነት አያገኝም፣ 8ነገር ግን የበላው ሁሉ በበደለኛነቱ ይጠየቅበታል ምክንያቱም ለያህዌ የተለየውን አርክሷል፡፡ ያ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡9የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ፤ የእርሻችሁን ቀርጢያ ሁሉ አትልቀሙ፣ አሊያም የአዝመራችን ምርት ሁሉ አትሰብስቡ፡፡ 10ከወይን ተክልህ እያንዳንዱን ወይን ፍሬ አትሰብስብ፣ አሊያም በወይን ስፍራ የወዳደቁትን የወይን ፍሬዎች አትልቀም፡፡ ለድሆችና ለመጻተኞች እነዚህን ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡11አትስረቁ፡፡ አትዋሹ፡፡ አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ፡፡ 12በሃሰት በስሜ አትማሉ የአምላካችን ስም አታርክሱ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡13ጎረቤትህን አትበድል ወይም አትዝረፈው፡፡ የቀን ሰራተኛውን ክፍያ በአንተ ዘንድ አታሳድር፡፡ 14መስማት የተሳነውን ሰው አትርገመው ወይም ከእውሩ ፊት ማሰናከያ ድንጋይ አታስቀምጥ ይልቁንም አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡15ፍትህን አታጣም፡፡ አንድ ሰው ድሃ ስለሆነ ልታደላለት አይገባም፣ እንደዚሁም አንድ ሰው ባለጸጋ ስለሆነ አታዳላለት፡፡ ይልቁንም ለጎረቤትህ በጽድቅ ፍረድ 16በሰዎች መሃል በሀሳት ሃሜትን አታሰራጭ 16በሰዎች መሃል ሀሜትን እያሰራጨህ አትዙር፣ ይልቁንም የጎረቤትህን ሕይወት አቅና፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡17በልብህ ወንድምህን አትጥላ፡፡ በእርሱ ምክንያት የኃጢአቱ ተካፋይ እንዳትሆን ጎረቤትህን በቅንነት ገስጸው፡፡ 18ከህዝብህ ማንንም አትቀበል ወይም በማንም ላይ ቂም አይኑርህ፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ ጎረቤትህን እንደራስህ ውደድ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡19ትዕዛዛቴን መጠበቅ አለብህ፡፡ እንስሳትህን ከሌሎች ልዩ ዝርያ ካላቸው እንስሳት ጋር አታዳቅል፡፡ በእርሻህ ላይ ስትዘራ የተለያየ የዘር ዐይነቶችን አትደባልቅ፡፡ ከሁለት የተለያዩ አይነት ነገሮች ተደባልቆ የተሰራ ልብስ አትልበስ፡፡20ቤዛ ካልተከፈለላት ወይም ነጻ ካልወጣች ለባል ከታጨት ባሪያ ከሆነች ልጃገረድ የተኛ ሁሉ ይቀጡ፡፡ ሊገደሉ ግን አይገባም ምክንያቱም ነጻ አልወጣችም፡፡ 21ሰውዬው ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለበደል መስዋዕት ለያህዌ አውራ በግ ያምጣ፡፡ 22ከዚያ ካህኑ በያህዌ ፊት ሰውዬው ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕት አውራ በግ በማቅረብ ያስተሰርይለታል፡፡ ከዚያ የሠራው ኃጢአት ይቅር ይባልለታል፡፡23ወደምድሪቱ ስትገቡና ለምግብ የሚሆን ሁሉንም ዐይነት ዛፎች ስትተክሉ፣ ዛፎቹ ያፈሩትን ፍሬ ለመብላት እንደተከለከለ ቁጠሩት፡፡ ፍሬው ለእናንተ ለሶስት ዓመታት የተከለከለ ነው፡፡ አይበላም፡፡ 24ነገር ግን በአራተኛው አመት ፍሬው ሁሉ ለያህዌ ለምስጋና የሚሰዋ ቅዱስ ይሆናል፡፡ 25አመት ፍሬውን መብላት ትችላላችሁ፡፡ በመጠበቃችሁ ዛፎቹ ብዙ ያፈራሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡26ደሙ በውስጡ ያለበትን ስጋ አትብሉ፡፡ ስለ ወደፊቱ መናፍስትን አታማክሩ፣ ደግም ከተፈጥሮ በላይ በሆኑ ኃይላት ሌሎችን ለመቆጣጠር አትፈልጉ፤፡፡ 27እንደ ጣኦት አምላኪዎች የጸጉራችሁን ዙሪያ አትላጩ ወይም የጺማችሁን ዙሪያ አትቆረጡ፡፡ 28ለሙታን ሰውነታችሁን በስለት አትቁረጡ ወይም በሰውነታችሁ ላይ ንቅሳት አታድርጉ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡29ሴት ልጅህን ሴተኛ አዳሪ በማድረግ አታወርዳት፣ በዚህ ነገር አገረ ወደ ግልሙትና ትገባለች ምድሪቱም በእርኩሰት ትሞላለች፡፡ 30ጠብቁ የቤተመቅደሴን ቅድስና አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡31ወደ ሙታን ጠሪዎችና መናፍስትን ወደሚያነጋግሩ ዘወር አትበሉ፡፡ እነዚህን አትፈልጉ፣ ካልሆነ ያረክሷችኋል፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡32ፀጉሩ ለሸበተ ሰው ተነስለት ደግሞም በዕድሜ የገፋውን ሰው አክብር፡፡ አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡33በምድርህ በመካከልህ መጻተኛ ቢኖር፣ አትግፋው፡፡ 34በመካከላችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደ ተወላጅ እስራኤላዊ ወገናችሁ ቁጠሩት ደግሞም እንደ ራሳችሁ ውደዱት፣ ምክንያቱም እናንተም በግብጽ ምድር መጻተኞች ነበራችሁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡35ርዝመትን፣ ክብደትን፣ ወይም ብዛትን ስትለኩ፡፡ ሀሰተኛ መለኪያ አትጠቀሙ፡፡ 36ትክክለኛ መስፈሪያን፣ ትክክለኛ ሚዛኖችን፣ ትክክለኛ የኢፍ እና የኢን መለኪያዎችን ተጠቀሙ፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 37ትዕዛዛቴንና ህግጋቴን ሁሉ ጠብቁ፣ አድርጓቸውም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእስራኤል ሰዎች መሃል ማንም ሰው፣ ወይም ማንኛውም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ከልጆቹ መሃል አንዱን ለሞሎክ ቢሰጥ በዕርግጥ ይገደል፡፡ በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች በድንጋይ ይውገሩት፡፡3እኔም በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አዞርበታለሁ፣ ከህዝቡም መሃል እቆርጠዋለሁ ምክንያቱም የተቀደሰውን ስፍራዬን ለማርከስና ቅዱሱን ስሜን ለማቃለል ልጁን ለሞሎክ ሰጥቷል፡፡ 4ያ ሰው ከልጆቹ አንዱን ለሞሎክ ሲሰጥ ዚያች ምድር ሰዎች እንዳላዩ ቢሆን፣ ባይገድሉት፣ 5እኔ ራሴ በዚያ ሰውና በቤቱ ላይ ፊቴን አዞራለሁ፣ እኔ ቆርጬ እጥለዋለሁ እንደዚሁም ከሞሎክ ጋር በሚያመነዝረው በማንኛውም ላይ ይህን አደርጋለሁ፡፡6ወደ ሙታን ጠሪዎች ዘወር የሚል፣ ወይም ከመናፍስት ጋር ከሚነጋገሩ ጋር የሚመነዝርን ሰው ፊቴን አዞርበታለሁ፤ ከህዝቡም መሃል አጠፋዋለሁ፡፡ 7ስለዚህ ራሳችሁን ለያህዌ ስጡ ተቀደሱም፣ ምክንያቱም እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡8ትዕዛዛቴን ጠብቁ አድርጓቸውም፡፡ ለራሴ የመረጥኳችሁ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 9ወይም እናቱን የሚረግም ሁሉ ይገደል፡፡ አባቱን ወይም እናቱን ረግሟልና በደለኛ ነው ሞት ይገባዋል፡፡10ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ዝሙት የፈጸመ ሰው፣ ከጎረቤቱ ሚስት፣ ጋር ያመነዘረ ይገደል አመንዝራውና አመንዝራይቱም ሁለቱም ይገደሉ፡፡ 11ከአባቱ ሚስት ጋር ሊተኛት የወደቀ የገባ አባቱን ያዋርዳል፡፡ ልጅየውም የአባቱ ሚስትም ሁለቱም ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡ 12አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ሊገደሉ ይገባል ያልገባ ፍትወት ፈጽመዋል በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡13አንድ ወንድ ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከሌላ ወንድ ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ጸያፍ ነገር አድርገዋል፡፡ በእርግጥ ሞት ይገባቸዋል፡፡ ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡ 14አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቲቱንም ቢያገባ፣ ይህ አሳፋሪ ነው፡፡ እርሱና ሴቲቱ ሁለቱም በእሳት ይቃጠሉ፣ ይህ ሲደረግ በመሀላችሁ ክፋት አይኖርም፡፡15አንድ ሰው ከእንስሳ ጋር ቢተኛ፣ በእርግጥ ይገደል፣ እንስሳይቱንም ግደሏት፡፡ 16አንዲት ሴት ለመገናኘት ወደ ማንኛውም አይነት እንስሳ ብተቀርብ ሴትየዋንም እንስሳውንም ግደሏቸው፡፡ በእርግጥ ሊገደሉ ይገባል፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡17አንድ ሰው የአባቱ ልጅ ከሆነችውም ሆነ የእናቱ ልጅ ከሆነች እህቱ ጋር ቢተገኛ እህትም ከእርሱ ጋር ብትተኛ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፤ ምክንያቱም ከእህቱ ጋር ተኝቷል፡፡ በደሉን ይሸከማል፡፡ 18አንድ ሰው አንዲትን ሴት በወር አበባዋ ወቅት አብሯት ቢተኛና ቢገናኛት፣ የደሟ ምንጭ የሆነውን የደም መፍሰሷን ገልጧል፡፡ ወንዱም ሴቷም ሁለቱም ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፡፡19ከእናትህ ወይም ከአባትህ እህት ጋር አትተኛ፣ ምከንያቱም የቅርብ ቤተ ዘመድህን ታዋርዳለህ፡፡ በደልህን ልትሸከም ይገባሃል፡፡ 20አንድ ሰው ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ አጎቱን አዋርዷል፡፡ በደላቸውን ሊሸከሙ ይገባል ያለ ልጅ ይቀራሉ፡፡ 21አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ቢያገባ ይህ እርኩስ ነው ምክንያቱም ዘመዱ ሆኖ ሳለ የወንድሙን ትዳር አፍርሷል፣ ልጅ አልባ ይሆናሉ፡፡22ስለዚህም ስርአቶቼንና ህግጋቶቼን ሁሉ መጠበቅ አለባችሁ፤ እንድትኖርባት ያመጣኋቸው ምድር እንዳትተፋችሁ ህግጋቴንና ሥርዓቶቼን ጠብቁ፡፡ 23ከፊታችሁ በማባርራቸው ህዝቦች ልምዶች አትመላለሱ፣ እነርሱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርገዋል፣ እኔም እነርሱን ጠላሁ፡፡24እኔ እንዲህ እላችኋለሁ፣ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፣ ምድሪቱን እንድትወርሷት ለእናንተ እሰጣችኋለሁ፣ ወተትና ማር የምታፈስ ምድር ናት፡፡ ከሌላው ህዝብ የለየኋችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ” 25ስለዚህ እናንተ ንጹህ በሆኑና ንጹኅ በሆኑ እንስሳት መሃል፣ ንጹኅ በሆኑና ንጹህ ባልሆኑ ወፎች መሃል ልዩነት አድርጉ፡፡ ለእናንተ ርኩስ ናቸው ብዬ በለየኋቸው ንጹኅ ባልሆኑ እንስሳት ወይም ወፎች ወይም በማንኛውም በምድር ላይ በሚሳብ ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፡፡26እኔ ያህዌ ቅዱስ እንደሆንኩ፣ ደግሞም ለእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ህዝቦች እንደለየኋችሁ ቅዱሳን ሁኑ፡፡27ከሙታን ጋር የሚነጋገር አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ወይም ከመናፍስት ጋር የሚነጋገር በእርግጥ ይገደል፡፡ ህዝቡ በድንጋይ ወግፎ ይግደላቸው በደለኞች ናቸውና ሞት ይገባቸዋል፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው “ለካህናቱ፣ ለአሮን ልጆች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእናንተ መሃል ማንም በመካከላችሁ በሞተ ሰው አይርከስ፣ 2ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በስተቀር ማንም አይርከስ ለእናቱ እና አባቱ፣ ለወንድ ልጁና ለሴት ልጁ፣ ወይም ለወንድሙ 3ወይም በቤቱ ከምትኖር ባል ካላገባች ልጃገረድ እህቱ በስተቀር አይርከስ፡፡ ለእርሷ ግን ራሱን ንጹህ ላያርግ ይችላል፡፡4ለሌሎች ዘመዶቹ ግን እስኪረክስ ድረስ ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡ 5ካህናት ራሳቸውን አይላጩ ወይም የጺማቸውን ዳርቻ አይላጩ፣ አሊያም ሰውነታቸውን በስለት አይቁረጡ፡፡ 6እነርሱ ለአምላካቸው የተለዩ ይሆኑ፣ የአምላካቸውን ስም አያቃሉ፣ ምክንያቱም ካህናቱ የአምላካቸውን “ምግብ” መስዋዕቱን ለያህዌ በእሳት ያቀርባሉ፡፡ ስለዚህም እነርሱ የተለዩ ይሁኑ፡፡7ለአምላካቸው የተለዩ ስለሆኑ ማናቸውንም ጋለሞታ እና የረከሰች ሴት እንደዚሁም ከባሏ የተፋታችን ሴት ማግባት የለባቸውም፡፡ 8የአምላክህን “ምግብ” የሚያቀርብ ነውና እርሱን መለየት አለብህ፡፡ በፊትህ ቅዱስ መሆን አለበት፣ ምክንያቱም ለራሴ የለየሁህ እኔ፣ ያህዌ ቅዱስ ነኝ፡፡ 9ማንኛዋም የማንኛውም ካህን ሴት ልጅ ጋለሞታ ብትሆን አባቷን ታሳፍራለች፡፡ በእሳት ትቃጠል፡፡10ከወንድሞቹ መሃል ሊቀ ካህን የሆነው፣ የሹመቱ ዘይት በራሱ ላይ የፈሰሰበት፣ ደግሞም የሊቀ ካህኑን ልዩ ልብሶች ለመልበስ የተጾመ ጸጉሩን ይሸፍን ልብሱን አይቅደድ፡፡ 11ለአባቱ ወይም ለእናቱም ቢሆን እንኳን የሞተ ሰው በሚገኝበትና ራሱን በሚያረክስበት ማናቸውም ስፍራ አይሂድ፡፡ 12ሊቀካህኑ የቤተ መቅደሱን የተቀደሰ ስፍራ ትቶ አይሂድ ወይም የአምላኩን ቅድስና አያቃል፣ ምክንያቱም በአምላኩ የቅባት ዘይት ሊቀ ካህን ሆኖ ተሾሞ ነበርና፡፡እኔ ያህዌ ነኝ፡፡13ካህኑ ድንግሊቱን ሚስቱ አድርጎ ያግባት፡፡ 14ባሏ የሞተባትን ሴት፣ የተፋታችን ሴት፣ ወይም ጋለሞታን ሴት አያግባ፡፤ እንዲያ ካሉት ሴቶች መሃል አያግባ፡፡ ከራሱ ህዝብ መሃል ድንግሊቱን ብቻ ማግባት ይችላል፡፡ 15እነዚህን ህጎች ይጠብቅ፣ በህዝቡ መሃል ልጆቹን እንዳያረክስ ህግጋቱን ይጠብቅ፣ እርሱን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ፡፡16ያህዌ እንደህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣ 17“አሮንን እንዲህ ብለህ ንገረው፣ ማናቸውም ከወገንህ መሀል በትወልዳቸው ውስጥ አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ የአምላኩን ‹ምግብ› ለመሰዋት መቅረብ የለበትም፡፡18ማናቸውም አካላዊ እንከን ያለበት ሰው ወደ ያህዌ መቅረብ የለበትም፣ እንደ ዐይነ ስውር፣ ሽባ የሆነ ሰው፣ አካሉ የጎደለ ወይም አካሉ የተወላገደ፣ 19እጆቹ ወይም እግሮቹ ሽባ የሆነ፣ 20መጻጉ ወይም ድንክ ሰው፣ ወይም በዐይኖቹ ላይ እንከን ያለበት ሰው፣ ወይም በሽታ የያዘው፣ ሞጭሟጫ፣ እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ ወደ ያህዌ አይቅረብ፡፡ 21ከካህኑ ከአሮን መሃል ምንም አካላዊ ጉድለት ያለበት ሰው ለያህዌ የእሳት መስዋዕቶች ለመሰዋት አይቅረብ፡፡ አካላዊ ጉድለት ያለበት እንዲህ ያለው ሰው የአምላኩን ‹ምግብ ለማቅረብ መቅረብ የለበትም፡፡22ከቅድስተ ቅዱሳኑም ሆነ ከቅዱሱ የአምላኩ ምግብ ሊበላ ግን ይችል፣ 23ሆኖም፣ ወደ መጋረጃው መግባት የለበትም ወይም ወደ መሰዊያው አይቅረብ፣ ምክንያቱም አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ ስለዚህም ቅዱሱን ስፍራዬን አያርክስ፣ ለራሴ የለየኋቸው እኔ ያህዌ ነኝ፡፡” 24ሙሴ እነዚህን ቃላት ለአሮን፣ ለልጆቹ፣ እና ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ ተናገረ፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2“ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፣ የእስራኤል ሕዝብ ለእኔ ከለይዋቸው የተቀደሱ ነገሮች እንዲጠበቁ ንገራቸው፡፡ የተቀደሰው ስሜን አያርክሱ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 3እንዲህ በላቸው፣ በዘመን ሁሉ ከትውልዳችሁ መሀል ማንም ንጹህ ያልሆነ ሰው የእስራኤል ህዝብ ለያህዌ ወደ ለየው ቅዱስ ነገሮች ቢቀርብ፣ ያ ሰው እኔ ፊት ከመቅረብ የተከለከለ ነወ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡4ከአሮን ትውልድ ውስጥ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ያለበት፣ ወይም ከሰውቱ ፈሳሽ የሚወጣ ንጹኅ እስኪሆን ድረስ ለያህዌ ከሚቀርብ መስዋዕት አይብላ፡፡ማንም ከሞተ ጋር በመነካካት ንጹህ ያልሆነውን ማንኛውንም ነገር የነካ፣ ወይም የዘር ፈሳሽ ካለበት ሰው ጋር በመነካካት፣ 5ወይም የሚያረክሰውን ማናቸውንም በሆዱ የሚሳብ እንስሳ የነካ፣ ወይም ማናቸውንም የሚያረክሰውን ሰው የነካ፣ ማንኛውም አይነት እርኩሰት የሚያስከትል ነገር የነካ 6ማናቸውንም እርኩስ ነገር የነካ ካህን እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ ሰውነቱን በውሃ ካልታጠበ በቀር ከተቀደሱት ነገሮች አንዳች አይብላ፡፡7ፀሐይ ስትጠልቅ፣ በዚያን ሰዓት ንጹህ ይሆናል፡፡ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ከተቀደሱት ነገሮች መብላት ይችላል፣ ምክንያቱም ለእርሱ የተፈቀዱ ምግብ ናቸው፡፡ 8ሞቶ የተገኘን ማናቸውም ነገር አይብላ ወይም እርሱን የሚያረክሰውን በዱር እንስሳ የተገደለውን አይብላ፡፡ 9ካህናት ትእዛዛቴን ይጠብቁ፣ ይህን ካላደረጉ በኃጢአት በደለኛ ይሆናሉ ደግም ስሜን በማቃለል ይሞታሉ፡፡ ለራሴ የለየኋቸው እኔ ያህዌ ነኝ፣10ማንም የካህኑ ቤተሰብ ያልሆነ ሰው፣ የካህኑን እንግዶች ጨምሮ፣ ወይም ቅጥር አገልጋዮቹ ጭምር ቅዱስ ከሆነው አንዳች አይብሉ፡፡ 11ነገር ግን ካህኑ በገንዘቡ ባሪያ ቢገዛ ያ ባሪያ ለያህዌ ከተለዩ ነገሮች መብላት ይችላል፡፡ የካህኑ ቤተሰብ አባላት እና በቤቱ የተወለዱ ባሪያዎች ከእርሱ ጋር ከእነዚህ የተቀደሱ ነገሮች መብላት ይችላሉ፡፡12የካህኑ ሴት ልጅ ካህን ያልሆነ ሰው ብታገባ ለመስዋዕት ከመጣው ውስጥ አንዳች አትበላም፡፡ 13ነገር ግን የካህኑ ሴት ልጅ ባሏ የሞተባት ከሆነች፣ ወይም ከባሏ ከተፋታች፣ እና ልጅ ያልወለደች ከሆነች እንደ ልጅነቷ ዘመን ለመኖር ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ ከአባቷ ምግብ መብላት ትችላለች፡፡ ነገር ግን ማንም የካህን ቤተሰብ ያልሆነ ከካህናት ምግብ መብላት አይችልም፡፡14አንድ ሰው ሳያውቅ ቅዱሱን ምግብ ቢበላ፣ ከወሰደው አንድ አምስተኛ ጨምሮ ለካህኑ ይመልስ፡፡ 15የእስራኤል ህዝብ ለያህዌ የወዘወዙትንና ያቀረቡትን ቅዱስ ነገሮች ማቃለል የለባቸውም፣ 16ያልተፈቀደላቸውን ቅዱሱን ምግብ በመብላት ራሳቸውን በደለኛ የሚያደርጋቸውን ኃጢአት እንዲሸከሙ ማድረግ የለባቸውም እነርሱን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ”17ያህዌ እንዲህ አለው፣ 18“ለአሮንና ልጆቹ እንዲሁም ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንዲህ በላቸው፣ ‹ማንኛውም እስራኤላዊ፣ ወይም በእስራኤል የሚኖር ባይተዋር፣ ለስዕለትም ይሁን፣ ወይም ለበጎ ፈቃድ መስዋዕት ሲያቀርቡ፣ ወይም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ሲያቀርቡ፣ 19ተቀባይነትን እንዲያገኝ ከቀንድ ከብታቸው፣ ከበግ ወይም ፍየሎች ውስጥ ነውር የሌለበትን ተባዕት እንስሳ ያቅርቡ፡፡20ነውር ያለበትን ግን አታቅርቡ፡፡ ይህን እኔ አልቀበልም፡፡ 21ከከብቱ ወይም ከመንጋው ለስዕለት የህብረት መስዋዕት ለያህዌ የሚሰዋ ሁሉ፣ ወይም የበጎ ፍቃድ መስዋዕት የሚያቀርብ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ነውር የሌለበትን መስዋዕት ያቅርብ፡፡ በእንስሳው ላይ እንከን አይኑርበት፡፡22ዕውር፣ አንካሳ ወይም ሰንካላ፣ ወይም ኪንታሮት፣ ህመም፣ ወይም ቁስል ያለበትን እንስሳ አትሰዉ፡፡ እዚህን በእሳት መስዋዕት አድርጋችሁ በመሰዊያ ላይ ለያህዌ አታቅርቡ፡፡ 23የበጎ ፈቃድ መስዋዕት አድርጋችሁ ጎደሎ ወይም ትንሽ በሬ ወይም በግ ማቅረብ ትችላላችሁ፣ እንዲህ ያለው መስዋዕት ግን ለስዕለት ተቀባይነት የለውም፣24ለያህዌ ሰንበር ያለበት፣ የተሰበረ፣ የተዘነጠለ፣ ወይም የዘር ፍሬው የተቀጠቀጠ እንስሳ አታቅርቡ፡፡ እነዚህን በምድራችሁ አታቅርቡ፣ 25ለእግዚአብሔር ለምግብ የሚቀርብ አድርጋችሁ ከመጻተኛው እጅ አትቀበሉ፣ ምክንያቱም በእነዚህ ላይ ጉድለቶች ወይም ነውሮች አሉባቸው እነዚህን ከእናንተ አልቀበለም፡፡›”26ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 27“አንድ ጥጃ ወይም አንድ የበግ ወይም የፍየል ግልገል ሲወለድ፣ ከእናቱ ጋር ሰባት ቀናት ይቆይ፡፡ ከዚያም ከስምንተኛው ቀን አንስቶ፣ ለያህዌ በእሳት መስዋዕት ሆኖ መቅረብ ይችላል፡፡28አንዲትን ላም ወይም ሴት በግ ከጥጃዋ ወይም ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ፡፡ 29ለያህዌ የምስጋና መስዋዕት ስታቀርቡ፣ ተቀባይነት ባለው መንገድ አቅርቡ፡፡ 30መስዋዕቱ በቀረበበት ቀን ይበላ፡፡ እስከ ማለዳው አንዳች አታስቀሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡31ትዕዛዛቴን ጠብቁ አድርጓቸውም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 32ቅዱስ ስሜን አታቃሉ፡፡ በቅድስናዬ በእስራኤል ህዝብ መታወቅ አለብኝ፡፡ እናንተን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ፣ 33አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ በላቸው፣ ‹ለያህዌ የተለዩ የተቀደሱ ባዕሎቻችሁ፣ እንደ ቅዱስ ጉባኤዎቻችሁ የምታውጇቸው፣ የእኔ መደበኛ በዓላት ናቸው፡፡3ስድስት ቀናት ትሰራላችሁ፣ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ እረፍት የሚደረግበት ሰንበት ነው፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለያህዌ ሰንበት ስለሆነ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡4እነዚህ ለያህዌ የተመረጡ በዓላት ብላችሁ በተወሰነላቸው ጊዜ የምታውጇቸው የተቀደሱ ስብሰባዎች ናቸው፡፡ 5በመጀመሪያው ወር በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን ጸሀይ ስትጠልቅ የያህዌ ፋሲካ ነው፡፡ 6በዚያው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን የያህዌ የቂጣ በዓል ነው፡፡ ለሰባት ቀናት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ትበላላችሁ፡፡7በመጀመሪያው ቀን ለያህዌ የተለየ ጉባኤ ይኖራችኋል፣ የተለመደ ተግባራችሁን አትሰሩበትም፡፡ 8ለሰባት ቀናት በእሳት የሚቀርብ መስዋዕት ለያህዌ ታቀርባላችሁ ሰባተኛው ቀን የተለመደ ተግባራችሁን የማታከናውኑበት ለያህዌ የተለየ ጉባኤ የሚደረግበት ነው›”9ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 10”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው ‹ወደምሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ እና የመጀመሪያውን አዝመራ ስትሰበስቡ፣ ከበኩራቱ ፍሬዎች ለካህኑ አንድ ነዶ ታመጣላችሁ፡፡ 11ነዶው ተቀባይነትን እንዲያገኝ ካህኑ በያህዌ ፊት ይወዘውዘውና ለእርሱ ያቀርበዋል፡፡ ካህኑ ነዶውን የሚወዘውዘውና ለእኔ የሚያቀርበው በሰንበት ቀን ማግስት ነው፡፡12ነዶውን በምትወዘውዙበትና ለእኔ በምታቀርቡበት ቀን ለያህዌ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡13የእህል ቁርባን ለያህዌ መልካም መዓዛ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት፣ እና ከነዚህም ጋር የኢን አንድ አራተኛ ወይን የመጠጥ ቁርባን መቅረብ አለበት፡፡ 14ለአምላካችሁ ይህን መስዋዕት እስከምታቀርቡበት ቀን ድረስ ምንም ዓይነት ዳቦ፣ አሊያም የተጠበሰ እሸት ወይም ለምለሙን እሸት አትብሉ፡፡ ይህ ለትወልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡15ከዚያ ሰንበት ቀን ማግስት አንስቶ ነዶውን ለመወዝወዝና ለያህዌ ለማቅረብ ካመጣችሁት ቀን ጀምራችሁ ሰባት ሙሉ ሳምንታት፣ ሰባት ሰንበት ትቆጥራላችሁ፣ 16እስከ ሰባተኛው ሰንበት ማግስት ድረስ ትቆጥራላሁ፡፡ ያም ማለት ሀምሳ ቀናት ትቆጥራላችሁ፡፡ ከዚያ ለያህዌ የአዲስ አዝመራ መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡17ከየቤቶቻችሁ ከኢፍ ሁለት አስረኛ የተጋገሩ ሁለት ዳቦዎች ታመጣላችሁ፡፡ ከመልካም ዱቄት የሚዘጋጅና በእርሾ የተጋገሩ ይሁኑ፤ ከበኩራት ፍሬዎች የሚቀርቡ የሚወዘወዙና ለያህዌ የሚቀርቡ መስዋዕቶች ይሆናሉ፡፡ 18ከዳቦው ጋር ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እድሜ ያላቸው ሰባት ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈን በሬ፣ እና ሁለት አውራ በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ እነርሱም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናሉ፣ ከእህል ቁርባን ከመጠጥ ቁርባን ጋር፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት እና ለያህዌ መልካም መዓዛ ያለው መስዋዕት ይሆናሉ፡፡19ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ታቀርባላሁ፣ እንዲሁም ለህብረት መስዋዕት የአንድ አመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ወንድ ጠቦቶች ለመስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ 20ካህኑ ከበኩራት ፍሬዎች ዳቦ ጋር በያህዌ ፊት ይወዘወዛቸው፣ እነርሱንም መስዋዕት አድርጎ ለእርሱ ከሁለት ጠቦቶች ጋር ያቅርብ፡፡ ለያህዌ ቅዱስ መስዋዕቶች ሲሆኑ የካህኑ ድርሻ ናቸው፡፡ 21በዚያው ቀን ማወጅ አለባችሁ፡፡ የተቀደሰ ጉባኤ ይኖራል፣ እናም የተለመደ ስራችሁን አትሰሩም፡፤ ይህ የህዝባችሁ በትውልዶች ሁሉ በምትኖሩበት ሥፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡22የምድራችሁን ፍሬ ስትሰበስቡ፣ የእርሻችሁን ጥግጋት ሁሉ ሙሉ ለሙሉ አትሰብስቡ፣ የሰብላችን ቃርሚያ ሁሉ አትሰብስቡ፡፡ እነዚህን ለድሆችና ለመጻተኛው ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”23ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 24”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር፣ የወሩ የመጀመሪያው ቀን ለእናንተ ታላቅ እረፍት ይሆናል፣ በመለኮት ድምጽ መታሰቢያ የሚደረግበት፣ እና የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል፡፡ 25የተለመደ ሥራ አትሰሩበትም፣ ለያህዌ የእሳት መስዋዕት አቅርቡበት፡፡›”26ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 27“አሁን የዚህ የሰባተኛው ወር አስረኛ ቀን የስርየት ቀን ይሆናል፡፡ ለያህዌ የተለየ ጉባኤ መሆን አለበት፣ ራሳችሁን ማዋረድና ለያህዌ በእሳት መስዋዕት መሰዋት አለባችሁ፡፡28በዚያን ቀን ምንም ሥራ አትስሩ ምክንያቱም በአምላካችሁ በያዌ ፊት ለራሳች ማስታሰርያ የምታቀርቡበት የስርየት ቀን ነው፡፡ 29በዚያን ቀን ራሱን የማያዋርድ ማንም ቢሆን ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡30በዚያን ቀን ማናቸውንም ሥራ የሚሰራውን ማንንም ቢሆን፣ እኔ ያህዌ ከህዝቡ መሀል አጠፋዋለሁ፡፡ 31በዚያ ቀን ማናቸውንም ዐይነት ሥራ አትሰሩም፡፡ ይህ በህዝባችሁና ትውልዶቻችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ 32ይህ ቀን ለእናንተ የከበረ የሰንበት ዕረፍት ይሁንላችሁ፣ እናንተም በወሩ በዘጠነኛው ቀን ራሳችን አዋርዱ፡፡ ከምሽት እስከ ምሽት ሰንበትን ጠብቁ፡፡”33ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 34“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር አስራ አምስተኛው ቀን ለያህዌ የዳስ በዓል ይሆናል፡፡ ይህም ሰባት ቀናት ይወስዳል፡፡35በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይኖራል፡፡ የተለመደውን ሥራ አትስሩበት፡፡ 36ለሰባት ቀናት ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡበት፡፡ በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሁን፣ እናንተም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ይህ ክቡር ጉባኤ ነው፣ እናም አንዳች የተለመደ ሥራ አትስሩበት፡፡37እነዚህ ለያህዌ የተለዩ በአላት ናቸው፣ ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ለማቅረብ ቅዱስ ጉባኤ የምታውጁበት፣ የሚቃጠል መስዋዕትና የእህል ቁርባን፣ የመስዋዕቶችና የመጠጥ ቁርባች እያንዳንዱን በየራሱ ቀን ለይታችሁ ለእግዚአብሔር የምታውጁባቸው በዓላት ናቸው፡፡ 38እነዚህ በአላት ከያህዌ ሰንበታትና ከእናንተ ስጦታዎች ተጨማሪ ናቸው፣ ስጦቻችሁ ሁሉ፣ እና ለያህዌ የምትሰጧቸው የበጎ ፈቃድ መስዋዕቶቻችሁ ሁሉ ናቸው፡፡39የዳስ በዓልን በሚመለከት፣ በሰባተኛው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን፣ እናንተ የምድሪቱን ፍሬዎች ስትሰበስቡ ይህን የያህዌ በዓል ለሰባት ቀናት ማክበር አለባችሁ፡፡ የመጀመሪያው ቀን የፍፁም ዕረፍት ቀን ይሆናል፣ ስምንተኛው ቀንም እንደዚሁ የፍጹም ዕረፍት ቀን ይሆናል፡፡40በመጀመሪያው ቀን ከዛፎቹ መልካሞቹን ፍሬዎች ውሰዱ፣ የዘንባባ ዛፎች ዝንጣፊዎች፣ እና የለምለሙ ዛፎች ቅርንጫፎች፣ ከወንዝ ዳርቻ ለምለም ዛፎች ቅርንጫፎች ወስዳችሁ በአምላካችሁ በያህዌ ፊት ለሰባት ቀናት ሃሴት ታደርጋላችሁ፡፡ 41በየአመቱ ለሰባት ቀናት፣ ይህን በዓል ለያህዌ ታከብራላችሁ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ ይህን በዓል በሰባተኛው ወር አክብሩ፡፡42ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ትኖራላችሁ፡፡ እስራኤላዊ የሆነ ሁሉ ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ይቀመጥ፣ 43ከእናንተ በኋላ የሚመጣው ትውልድ፣ የልጅ ልጆቻችሁ፣ እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ሳወጣ በእንደዚህ ዐይነት ዳሶች ውስጥ እንዴት እንዲኖሩ እንዳደረግኩ ያውቃሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡›” 44በዚህ መንገድ፣ ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ ለያህዌ የተለዩትን በዓላት አስታወቁ፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“የእስራኤል ሰዎች መቅረዞች ሁልጊዜም እንዲነዱና ብርሃን እንዲሰጡ ከወይራ ፍሬ የተጠመቀ ንጹኅ ዘይት ለመቅረዞችህ ወደ አንተ እንዲያመጡ እዘዛቸው፡፡3አሮን ያለማቋረጥ ከምሽት እስከ ማለዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ውጭ በቃልኪዳኔ ድንጋጌ ፊት መቅረዙን በያህዌ ፊት ያለማቋረጥ ያብራ፡፡ ይህ በትወልዳች ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፡፡ 4ሊቀ ካህኑ በንጹኅ ወርቅ በተሰራው የመቅረዝ መያዣ ላይ መቅረዞቹ ሁልጊዜም በያህዌ ፊት እንዲበሩ ያደርጋል፡፡5መልካም ዱቄት ወስደህ አስራ ሁለት ዳቦዎች ጋግር፡፡ ለእያንዳንዱ ዳቦ የኢፍ ሁለት እስረኛ መጠን ተጠቀም፡፡ 6ከዚያ በሁለት ረድፍ ደርድራቸው፣ በአንዱ መስመር ስድስቱን በንጹኅ ወርቅ በተሰራ ጠረጴዛ ላይ በያህዌ ፊት ደርድር፡፡7በእያንዳንዱ የዳቦዎቹ ረድፍ እንደ ዳቦዎቹ ምልክት ንጹኅ ዕጣን አድርግበት፡፡ ይህ ዕጣን ለያህዌ በእሳት የሚቀርብ መስዋእት ይሆናል፡፡ 8በእያንዳንዱ የሰንበት ዕለት ሊቀ ካህኑ የእስራኤልን ህዝብ ወክሎ የዘላለም ቃልኪዳን ምልክት አድርጎ ህብስቱን በመደበኛነት ለያህዌ ያቀርባል፡፡ 9ይህ መስዋዕት የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሆናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየና ለያህዌ በእሳት ከሚቀርበው መስዋዕት የተወሰደ ስለሆነ ቅዱስ በሆነው ስፍራ ይብሉት፡፡”10እናቱ እስራኤላዊ የሆነች እና አባቱ ግብፃዊ የሆነ ልጅ በእስራኤል ህዝብ መሀል ወጣ፡፡ ይህ እስራኤላዊት ሴት ልጅ በሰፈር ውስጥ ከእስራኤላዊ ሰው ጋር ተጣላ፡፡ 11የእስራኤላዊቷ ሴት ልጅ የያህዌን ስም ሰደበ እግዚአበሔርንም ረገመ፣ ስለዚህም ህዝቡ ወደ ሙሴ አመጡት፡፡ የእናቱ ስም ሰሎሚት ነበር፣ የደብራይ ልጅ ስትሆን ከዳን ወገን ነበረች፡፡ 12ያህዌ ራሱ ፈቃዱን እስኪገልጽላቸው ድረስ በጥበቃ ስር አቆዩት፡፡13ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 14“እግዚአብሔርን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር አውጡት የሰሙት ሁሉ እጆቻቸውን በላዩ ይጫኑ፣ ከዚያም መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገረው፡፡15ለእስራኤል ሰዎች ብለህ ግለጽላቸው፣ ‹አምላኩን የተሳደበ ማንኛውም ሰው በደሉን ይሸከም፡፡ 16ተወላጅ የሆነ እስራኤላዊም ቢሆን ወይም መጻተኛ የያህዌን ስም በስድብ ያቃለለ መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገሩትና ይገደል፡፡ ማንም ሰው የያህዌን ስም ቢሳደብ፣ ይገደል፡፡17ሌላ ሰው የገደለ ይገደል፡፡ 18የሌላውን ሰው እንስሳ የገደለ በገደለው ፈንታ ይክፈል፣ ህይወት ስለ ህይወት ነው፡፡19አንድ ሰው ጎረቤቱን ቢጎዳ፣ እርሱ በጎረቤቱ ላይ ያደረገው ነገር ይደረግበት፡፡ 20ስብራት ስለ ስብራት፣ አይን ስለ አይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፡፡ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት እንዳደረሰ፣ በእርሱም ላይ እንደዚያው ይደረግበት፡፡ 21ማንም እንስሳ የገደለ ሰው መልሶ ይክፈል ማንም ሰው የገደለ ይገደል፡፡22ለመጻተኛውም ይሁን ለተወላጅ እስራኤላዊው አንድ አይነት ህግ ይኑራችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝና፡፡” 23ሙሴ ለእስራኤል ሰዎች ይህን ነገራቸው፣ ሰዎቹም ያህዌን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር ውጭ አመጡት፡፡ በድንጋይ ወገሩት፡፡ የእስራኤል ሰዎች የያህዌን ትዕዛዝ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ፈጸሙ፡፡
1ያህዌ በሲና ተራራ ላይ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‹እኔ ወደሰጠኋችሁ ምድር ስትገቡ፣ ምድሪቱ ለያህዌ የሰንበት ዕረፍት ታክብር፡፡3እርሻህን ለስድስት አመታት ታርሳለህ፣ ለስድስት አመታት የወይን ተክልህን እየገረዝህ ምርቱን ትሰበስባህ፡፡ 4በሰባተኛው አመት ግን፣ ለምድሪቱ የከበረ የሰንበት ረፍት ይሁንላት፣ ለያህዌ ሰንበት ነው፡፡ እርሻህን አታርስም፡፡ ወይም የወይን ተክልህን አትገርዝም፡፡5ሳትዘራው የበቀለውን አትጨደው፣ ያልገረዝከውን የወይን ተክል ፍሬ አትለቅመውም፡፡ ይህ ለምድሪቱ የከበረ የእረፍት አመት ነው፡፡ 6ያልሰራህበት ምድር በሰባተኛው ዓመት ያፈራችው ሁሉ ለአንተ ምግብ ይሆናል፡፡ አንተ፣ ወንድና ሴት ባሮችህ፣ ለቅጥረኛ አገልጋዮችህ እና ከአንተ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞች ምግብ ይሁን፡፡ 7ምድሪቱ ያፈራችውን ሁሉ የቤት እንስሳትህና የዱር እንስሳት ይመገቡት፡፡8ሰባት የሰንበት አመታትን ቁጠር፣ ይህም ማለት፣ ሰባት ጊዜ ሰባት አመታት ነው፣ ስለዚሀ ሰባት የሰንበት አመታት ይሆናሉ፣ ድምሩ አርባ ዘጠኝ አመታት ነው፡፡ 9በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን ከፍ ያለ የመለከት ድምጽ በሁሉም ስፍራ ንፉ፡፡ በማስተሰርያ ቀን በምድራችሁ ላይ ሁሉ መለከት ንፉ፡፡10አምሳኛውን አመት ለያህዌ ለዩና በምድሪቱ ላይ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ሁሉ ነጻነትን አውጁ፡፡ ይህ ለእናንተ ንብረትና ባሮች ወደየቤተሰቦቻቸው የሚመለሱበት ኢዩቤልዩ ይሆንላችኋል፡፡11አምሳኛው አመት ለእናንተ ኢዮቤልዮ ይሆናል፡፡ አትተክሉም ወይም አዝመራ አትሰበስቡም፡፡ ሳትዘሩ የበቀለውን ብሉ፣ ሳትገርዙት ወይናችሁ ያፈራውን ፍሬ ሰብስቡ፡፡ 12ኢዮቤልዩ ነውና፣ ለእናንተ ቅዱስ ይሆናል፡፡ በሜዳ ሳትዘሩት የበቀለውን ምርት ብሉ፡፡13በዚህ የኢዮቤልዩ አመት የእያንዳንዱን ሰው ንብረት መልሱለት፡፡ 14ለጎረቤትህ ማናቸውንም መሬት ሸጠህለት ቢሆን ወይም ከጎረቤትህ ማንኛውንም መሬት ገዝተህ ቢሆን አንዱ ሌላውን አያታል ወይም እርስ በእርሱ ያልተገባ ነገር አታድርጉ።15ከጎረቤትህ መሬት ብትገዛ፣ እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ድረስ ያሉትን አመታት እና ሊሰበሰብ የሚችለውን ሰብል ከግምት አስገባ፡፡ መሬቱን የሚሸጠው ጎረቤትህም እነዚህን ነገሮች ከግምት ያስገባል፡፡ 16እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ብዙ አመታት የሚቀር ከሆነ ይህ የመሬቱን ዋጋ ከፍ ያደርገዋል፣ እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ጥቂት አመታት የሚቀር ከሆነ ይህ የመሬቱን ዋጋ ዝቅ ያደርገዋል፣ ምክንያቱም ለአዲሱ የመሬቱ ባለቤት መሬቱ የሚሰጠው አዝመራ መጠን ለሚቀጥለው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ከቀረው አመታት ቁጥር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ 17አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ ወይም አንዳች ሌላችሁን አታሳስቱ፤ ይልቁንም አምላካችን አክብሩ፣ እኔ አምላካች ያህዌ ነኝ፡፡18ስለዚህ ትዕዛዛቴን ጠብቁ፣ ህግጋቴን ፈጽሙ እናም አድርጓቸው፡፡ ይህን ካደረጋችሁ በምድሪቱ ላይ በሰላም ትቀመጣላችሁ፡፡ 19ምድሪቱ ምርቷን ትሰጣለች፣ እናንተም ትጠግባላችሁ በዚያም በሰላም ትኖራላችሁ፡፡20እንዲህ ልትሉ ትችላላችሁ “በሰባተኛው አመት ምን እንበላለን አንዘራም፣ ምርታችንንም አንሰበስብምና፡፡” 21በስድስተኛው አመት በረከቴ እንዲሆንላችሁ በእናንተ ላይ አዛለሁ፣ ምድሪቱ ለሶስት አመታት የሚሆን ምርት ትሰጣለች፡፡ 22በስምንተኛው አመት ትተክላላችሁ፣ በቀደሙት አመታት ካመረታችሁትና ከሰበሰባችሁት ምግብ መብላት ትቀጥላላችሁ፡፡23መሬት ለአዲስ ጊዜያዊ ባለቤቶች አይሸጥ፣ ምክንያቱም መሬቷ የእኔ ናት፡፡ እናንተ ሁላችሁም በምድሬ ላይ እንግዶችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች ናችሁ፡፡ 24የያዛችሁትን ምድር ሁሉ የመቤዠት መብት እንዳላችሁ ማስተዋል አለባችሁ፤ በገዛችሁት ቤተሰብ መሬቱ ተመልሶ እንዲገዛ መፍቀድ አለባችሁ፡፡ 25እስራኤላዊ ወገናችሁ ደሃ ቢሆንና በዚህም ምክንያት ከንብረቱ ቢሸጥ፣ የቅርብ ዘመዱ ለአንተ የሸጠልህን ንብረት መልሶ ይግዛ፡፡26ሰውዬው ንብረቱን የሚቤዥለት ምንም ዘመድ ባይኖረው፣ ነገር ግን ሀብት ቢያፈራና ንብረቱን መልሶ መቤዠት ቢችል፣ 27መሬቱ ከተሸጠበት ጊዜ አንስቶ ያሉትን አመታት ያሰላና ለሸጠለት ሰው ቀሪ ሂሳቡን ይክፈል፡፡ ከዚያ ወደ ራሱ ንብረት ይመለስ፡፡ 28ነገር ግን መሬቱን ለራሱ ማስመለስ ባይችል፣ የሸጠው መሬት እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ በገዛው ሰው ባለቤትነት ስር ይቆያል፡፡ በኢዮቤልዩ አመት፣ መሬቱ ለሸጠው ሰው ይመለስለታል፣ ከመሰረቱ ባለቤት የነበረው ወደ ንብረቱ ይመለሳል፡፡29አንድ ሰው በተቀጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ቤቱን ቢሸጥ፣ በተሸጠበት በአመት ጊዜ ውስጥ መልሶ ሊገዛው ይችላል፡፡ 30ለአንድ ሙሉ አመት ውስጥ ካልተቤዠ፣ በተቀጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቤት፣ የገዛው ሰው ትውልድ የልጅ ልጅ ቋሚ ንብረት ይሆናል፡፡ ያ ቤት በኢዮቤልዩ ተመላሽ አይሆንም፡፡31ነገር ግን በዙሪያቸው ቅጥር የሌላቸው መንደሮች ቤቶች ከአገሩ የእርሻ መሬት ጋር የሚታዩ ንብረቶች ይሆናሉ፡፡ ተመልሰው ሊዋጁ ይችላሉ፣ በኢዮቤልዩ ተመላሽ ይሆናሉ፡፡ 32ሆኖም፣ የሌዋውያን ንብረት የሆኑ ቤቶች በማንኛውም ጊዜ ሊዋጁ ይችላሉ፡፡33ከሌዋዊያን አንዱ የሸጠውን ቤት መልሶ ባይቤዥ፣ በከተማ ውስጥ የሚኘው የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ተመላሽ ይሆናል፣ በከተማ የሚገኝ የሌዋዊ ቤቶች በእስራኤል ሰዎች መሀል የእነርሱ ንብረት ነው፡፡ 34በከተማዎቻቸው ዙሪያ የሚገኙ እርሻዎች ግን አይሸጡም ምክንያቱም እነዚህ የሌዋዊያን ቋሚ ንብረት ናቸው፡፡35የአገራቸው ሰው ወገናችሁ ደሃ ቢሆን፣ ስለዚህም ራሱን መቻል ቢያቅተው፣ መጻተኛውን እንደምትረዱ እርዱት ወይም በመሀከላችሁ የሚኖርን ባዕድ እንደምትረዱ ዕርዱት፡፡ 36ወለድ አታስከፍሉት ወይም በማናቸውም መንገድ ከእርሱ ትርፍ ለማግኘት አትሞክሩ፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን አክብሩ በመሆኑም ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር አብሮ መኖር ይችላል፡፡ 37በወለድ ገንዘብ አታበድሩት፣ ወለድም አታስከፍሉት፣ ትርፍ ለማግኘት ምግባችሁን አትሽጡለት፡፡ 38የከነዓንን ምድር እሰጣችሁና አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡39የአገርህ ሰው ወገንህ ደሃ ቢሆንና ራሱን ለአንተ ቢሸጥ፣ እንደ ባሪያ አታሰራው፡፡ 40እንደ ተቀጣሪ አገልጋይ አስተናግደው፡፡ ከአንተ ጋር በጊዜያዊነት እንደሚኖር ሰው ይሁን፡፡ እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ በአንተ ዘንድ ያገለግል፡፡ 41ከዚያ ከአንተ ዘንድ ይሄዳል፣ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉ ልጆቹ፣ ወደ ራሱ ቤተሰቦችና ወደ አባቱ ይዞታ ይመለሳሉ፡፡42እነርሱ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ናቸውና፡፤ እንደ ባሪያዎች አይሸጡም፡፡ 43በጭካኔ ልትገዛቸው አይገባም፣ ነገር ግን አምላክህን አክብር፡፡ 44በዙሪያህ ከሚኖሩ ህዝቦች ወንድና ሴት ባሪያዎችን ከእነርሱ መሀል መግዛት ትችላለህ፡፡45በመሀልህ ከሚኖሩ መጻተኞችም ባሪያዎችን መግዛት ትችላለህ፣ ይህም ማለት፣ ከአንተ ጋር ካሉ ቤተሰቦቻቸው፣ በምድርህ ከተወለዱ ልጆች ባሪያዎችን መግዛት ትችላለህ፡፡ እነርሱ የአንተ ሀብት ይሆናሉ፡፡ 46እንዲህ ያሉትን ባሪያዎች ንብረት አድርገው እንዳይዟቸው ከአንተ በኋላ ለልጆችህ ውርስ አድርገህ መስጠት ትችላለህ፡፡ ከእነርሱ ሁልጊዜም ባሪያዎችህን መግዛት ትችላለህ ነገር ግን ከእስራኤላዊያን መሀል በወንድሞችህ ላይ በጭካኔ መግዛት የለብህም፡፡47መጻተኛው ወይም ከአንተ ጋር በጊዜያዊነት ከሚኖረው እንግዳ መሃል አንዱ ባለጸጋ ቢሆንና ከእስራኤላዊ ወገንህ መሃል አንዱ ደሃ ቢሆን፣ ለራሱም ለዚያ ባዕድ ቢሸጥ፣ ወይም ከባዕዳን ቤተሰብ መሃል ለአንዱ ቢሸት፣ 48እስራኤላዊ ወገንህ ከተገዛ በኋላ ተመልሶ ይገዛ፡፡ ከቤተሰቡ መሃል አንዱ ይቤዠው፡፡49የሚቤዠው አጎቱ፣ የአጎቱ ልጅ፣ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ከቤተሰቡ ውስጥ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ ሊቤዠው ይችላል፡፡ ወይም፣ እርሱ ራሱ ባለፀጋ ቢሆን፣ ራሱን መቤዠት ይችላል፡፡ 50ከገዛው ሰው ጋር ይደራደር፣ ለገዛው ሰው ራሱን ከሸጠበት አመት ጀምረው እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ ይቁጠሩ፡፡ የመቤዣው ዋጋ ለገዛው ሰው መስራቱን መቀጠል በሚኖርበት አመታት ቁጥር ለተቀጣሪ አገልጋይ በሚከፍለው ክፍያ ይሰላል፡፡51እስከ ኢዮቤልዩ ለመድረስ ብዙ አመታት የሚኖር ከሆነ፣ ለቤዣው መልሶ የሚከፍለው የገንዘብ መጠን ከእነዚያ ቀሪ አመታት ጋር የተመጣጠነ ይሁን፡፡ 52ለኢዮቤልዩ አመት የቀሩት አመታት ጥቂት ከሆኑ፣ ከገዛው ሰው ጋር ለኢዮቤልዩ በቀሩት አመታት ልክ ይደራደር፣ ለመቤዣው በቀሩት አመታት ውስጥ ይክፈለው፡፡53በየዓመቱ እንደ ቅጥር ሰው ይኑር፡፡ በግፍ አለመስተናገዱን ማረጋገጥ ይገባሃል፡፡ 54በእነዚህ መንገዶች ካልተዋጀ፣ እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ እርሱና ከእርሱ ጋር ልጆቹም አብረው ያገልግሉ፡፡ 55እስራኤላውያን የእኔ አገልጋዮቼ ናቸው፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
1“እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፤ ጣኦታትን አታብጁ፣ የተቀረጸ ምስልንም አታቁሙ፣ ወይም ለአምልኮ የድንጋይ አምዶችን አታቁሙ፣ እንደዚሁም ልትሰግዱላቸው ማናቸውንም የቀረፀ የድንጋይ ምስል በምድራችሁ አታድርጉ፡፡ 2ሰንበቴን ጠብቁ የተቀደሰውን ስፍራዬን አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡3በህጌ ብትኖሩና ትዕዛዛቴን ብትጠብቁ ብትታዘዟቸውም፣ 4ዝናብን በወቅቱ እሰጣችኋለሁ፤ ምድር ምርቷን ትሰጣችኋለች፣ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጧችኋል፡፡5የወቃችሁት እስከ ወይን አዝመራችሁ ድረስ ይቆያል፣ የወይን ፍሬ አዝመራችሁም እስከምትዘሩበት ወቅት ድረስ ይቆያል፡፡ እንጀራችሁን በምድሪቱ ቤታችን በሰራችሁበት ጠግባችሁ ትበላላችሁ በእረፍት ትኖራላችሁ፡፡ 6በምድሪቱ ሰላምን እሰጣለሁ፣ ምንም ነገር ሳያስፈራችሁ ተዘልላችሁ ትቀመጣላችሁ፡፡ ከምድሪቱ አደገኛ እንስሳትን አስወጣለሁ፣ በምድራች ሰይፍ አያልፍም፡፡7ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፣ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡ 8ከእናንተ አምስታችሁ መቶውን ታሳድዳላችሁ፣ ከእናንተ መቶው አስር ሺኅ ያሳድዳል፤ ጠላቶቻች በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡9ወደ እናንተ በሞገስ እመለከታለሁ፣ ፍሬያማም አደርጋችኋለሁ፣ አበዛችሁማለሁ፤ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ፡፡ 10ለረጅም ጊዜ የተከማቸ እህል ትበላላችሁ፡፡ ለአዲሱ ምርታችሁ ስፍራ ስለሚያስፈልጋችሁ የተከማቸውን እህል ታወጣላችሁ፡፡11ማደሪያዬን በመካከላችሁ አደርጋለሁ፣ እኔም እናንተን አልጣላችሁም፡፡ 12በመካከላችሁ እሆናለሁ አምላካችሁም እሆናለሁ፣ እናንተም የእኔ ህዝብ ትሆናላችሁ፡፡ 13ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፣ ስለዚህም የእነርሱ ባሮች አትሆኑም፡፡ የቀንበራችሁን ብረት ሰብሬያሁ፣ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌያለሁ፡፡14ነገር ግን እኔን ባትሰሙኝ፣ እነዚህን ትዕዛዛቴን ሁሉ ባትጠብቁ፣ 15ትዕዛዛቴን ብትተዉና ህግጋቴን ብትጠሉ፣ እናም ትዕዛዞቼን ሁሉ ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ነገር ግን ቃልኪዳኔን ብታፈርሱ16እነዚህን ነገሮች ብታደርጉ፣ እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፡ ፍርሃትን እሰድባችኋለሁ፣ ዐይኖችንና ሕይወታችሁን የሚያጠፋ በሽታና ትሳት አደርስባችኋለሁ፡፡ በከንቱ ትዘራላችሁ፣ ምክንያቱም ፍሬያቸውን ጠላቶቻችሁ ይበሉታል፡፡ 17ፊቴን በጠላትነት ወደ እናንተ እመልሳለሁ፣ ከጠላቶቻችሁ ሀይል በታች ትወድቃላችሁ፡፡ የሚጠሏችሁ ሰዎች ይገዙዋችኋል፣ ማንም ሳያሳድዳችሁ እንኳን ትሸሻላችሁ፡፡18ትዕዛዛቴን ባትሰሙ፣ ከዚህ በኋላ ስለ ሀጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡ 19የትእቢታችሁን ኃይል እሰብራለሁ፡፡ ሰማይን በላያችሁ እንደ ብረት ምድራችሁንም እንደ ናስ አደርጋለሁ፡፡ 20ብርታታችሁ ለአንዳች ነገር አይጠቅምም፣ ምክንያቱም ምድራችሁ አዝመራዋን አትሰጥም፣ በምድራችሁ ዛፎቻችሁ ፍሬያቸውን አይሰጡም፡፡21በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ ብትመላለሱና ከኃጢአታችሁ በላይ እኔን ባትሰሙኝ፣ በእናንተ ላይ ሰባት ዕጥፍ ድንጋጤ አመጣለሁ፡፡ 22ልጆቻችን የሚነጥቁ፣ ከብቶቻችሁን የሚያጠፉ፣ እናንተን በቁጥር ጥቂት የሚያደርጉ አደገኛ አውሬዎችን እሰድባችኋሉሁ፡፡ ስለዚህም ጎዳናዎቻችሁ በረሃ ይሆናሉ፡፡23በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ትምህርቶቼን ባትሰሙ ነገር ግን በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ መመላለሳችሁን ብትቀጥሉ፣ 24እኔም በእናንተ ላይ ጠላት እሆናለሁ፡፡ እኔ ራሴ በሀጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡25ቃልኪዳን በማፍረሳችሁ በእናንተ ላይ የበቀል ሰይፍ አመጣለሁ፡፡ በከተሞቻችሁ ውስጥ በአንድነት ትሰበሰባላችሁ፣ በዚያም በማህላችሁ በሽታን እልካለሁ፣ እናንተም በጠላቶቻችሁ ሀይል ትሸነፋላችሁ፡፡ 26የምግብ አቅርቦታችሁን ስቆርጥ፣ አስር ሴቶች በአንድ ምድጃ እንጀራችሁን ይጋግራሉ፣ እንጀራችሁንም በሚዛን ያካፍሏችኋል፡፡ ትበላላችሁ ነገር ግን አትጠግቡም፡፡27እነዚህ ነገሮች ሁሉ ሆነው ባትሰሙት፣ ነገር ግን በእኔ ላይ በጠላትነት መመላሳችሁን ብትቀጥሉ፣ 28እኔ በቁጣ እመጣባችኋለሁ፣ በኃጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡29ወንድ ልጆቻችሁን ስጋና የሴት ልጆቻችሁን ስጋ ትበላላችሁ፡፡ 30የአምልኮ ሥፍራችሁን አጠፋለሁ፣ የእጣን መሰዊያዎቻችሁን እቆርጣለሁ፣ በድኖቻችሁን በድን በሆኑ በጣኦቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፣ ደግሞም እኔ ራሴ እጸየፋችኋለሁ፡፡31ከተሞቻችሁን ፍርስራሽ አደርጋለሁ የተቀደሱ ቦታዎቻችሁን አጠፋለሁ፡፡ በመስዋዕቶቻችሁ መዓዛ ደስ አልሰንም፡፡32ምድሪቱን አጠፋለሁ፡፡ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁ በጥፋቱ ይደነግጣሉ፡፡ 33በአገራት መሃል እበትናችኋለሁ፣ ሰይፌን መዝዤ አሳድዳችኋለሁ፡፡ ምድራችሁ ባድማ ትሆናለች፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ፡፡34ከዚያም ምድሪቱ ባድማ ሆኖ እስከቆየች ድረስና እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር እስከቆያችሁ ድረስ የሰንበት ዕረፍቷን ታገኛለች፡፡ በነዚያ ጊዜያት፣ ምድሪቱ ታርፋለች ሰንበቶቿንም ታገኛለች፡፡ 35ፍርስራሽ ሆና እስከቆየች ድረስስ እረፍት ይሆንላታል፣ እናንተ በውስጧ ስትኖሩ በሰንበቶቻችሁ ያላገኘችውን ዕረፍት ታገኛች፡፡ 36እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር በቀራችሁት ላይ በልቦቻችሁ ውስጥ ፍርሃት እሰዳለሁ፣ ስለዚህም የቅጠል ኮሰሽታ እንኳን ያስደነግጣችኋል፣ ከሰይፍ እንደሚሸሽ ትሆናላች፡፡ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትወድቃላች፡፡37ማንም ባያሳድዳችሁም እንኳን ከሰይፍ እንደሚሸሽ ሰው አንዳችሁ በሌላችሁ ላይ ትደነቃቀፋላችሁ፡፡ በጠላቶቻችሁ ፊት ለመቆም ምንም ሀይል አይኖራችሁም፡፡ 38ከአገራት መሀል ተለይታችሁ ትጠፋላችሁ፣ የጠላቶቻችሁ ምድር ራሱ በፍርሃት ይሞላችኋል፡፡ 39ከእናንተ መሃል የቀሩት በዚያ በጠላቶቻችሁ ምድር በሀጢአቶቻቸው ይጠፋሉ፣ እንዲሁም በአባቶቻቸው ሀጢአቶች ምክንያት ይጠፋሉ፡፡40ሆኖም የእነርሱንና የአባቶቻቸውን ሀጢአቶች ቢናዘዙ፣ ለእኔ ታማኝ ካልሆኑበት ክህደታቸው ቢመለሱ፣ ከእኔ ጋር ተላት ከሆኑበት አካሄዳቸው ቢመለሱ 41እኔ በእነርሱ ላይ እንድነሳ ካደረገንና ለጠላቶቸው ምድር አሳልፌ እንድሰጣቸው ካደረገ አካሄዳቸው ቢመለሱ ያልተገረዙ ልቦቻቸው ዝቅ ቢሉ፣ እናም በሀጢአቶቻቸው የደረሰባቸውን ቅጣታቸውን ቢቀበሉ፣ 42ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባለሁ፤ እንዲሁም፣ ምድሪቱን አስባለሁ፡፡43ምድሪቱ ለቀዋት ስለሄዱ ባዶ ትቀራለች፣ ስለዚህ ካለእነርሱ በተተወችበት ጊዜ በሰንበቶቿ ታርፋለች፡፡ እነርሱ በሀጢአታቸው ቅጣታቸውን ይቀበላሉ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው ስርአቴን ትተዋል ህግጋቴንም ጠልተዋል፡፡44ሆኖም ከዚህ ሁሉ ባሻገር፣ በጠላቶቸው ምድር ውስጥ ሲሆኑ፣ እኔ አልተዋቸውም ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ አልጠላቸውም፣ ደግሞም ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አልረሳም፣ እኔ አምላካቸው ነኝ፡፡45ነገር ግን ስለ እነርሱ ስል አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባሁ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”46በሙሴ በኩል ያህዌ በሲና ተራራ ላይ በራሱና በእስራኤል ህዝብ መሃል ያደረጋቸው ትዕዛዛት፣ ደንቦችና ህጎች እነዚህ ናቸው፡፡
1ያህዌ ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለ፣ 2“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‹አንድ ሰው ለያህዌ ሰውን ለመስጠት የተለየ ስዕለት ቢሳል ተመጣጣን ዋጋ ለመክፈል ተከታዮን ዋጋዎች ተጠቀም፡፡3ከዚያ እስከ ስልሳ አመት ዕድሜ ላለው ወንድ መደበኛው ዋጋ በቤ መቅደሱ ሰቅል መለኪያ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ይሁን፡፡ 4ለተመሳሳይ ዕድሜ ክልል ለሴቷ መደበኛው ዋጋ ሰላሳ ሰቅሎች ይሁን፡፡5ከአምስት አመት እስከ ሀያ አመት ዕድሜ ለወንድ መደበኛው ዋጋ ሀያ ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴቷ አስር ሰቅሎች ነው፡፡ 6ከአንድ ወር ዕድሜ እስከ አምስት አመት ለወንድ መደበኛው ዋጋ አምስት የብር ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴት ሶስት የብር ሰቅሎች ነው፡፡7ከስልሳ አመት በላይ ለወንድ መደበኛው ዋጋ አስራ አምስት ሰቅሎች፣ ለሴት አስር ሰቅሎች ይሁን፡፡ 8ነገር ግን ስዕለቱን የገባው ሰው መደበኛውን ዋጋ መክፈል ባይችል፣ በስለት የተሰጠው ሰው ወደ ካህኑ ይቅረብ፣ ካህኑም ያንን ሰው የተሳለው ሰው ሊከፍል በሚችል ዋጋ ይተምነዋል።9አንድ ሰው ለያህዌ እንስሳ መሰዋት ቢፈልግ፣ ያህዌ ያንን ቢቀበል፣ ከዚያ ያ እንስሳ ለእርሱ ይለያል፡፡ 10ሰውዬው እንዲህ ያለውን እንስሳ መለወጥ ወይም መቀየር የለበትም፣ መልካሙን በመጥፎው ወይም መጥፎውን በመልካሙ አይቀይርም፡፡ አንዱን እንስሳ በሌላው ቢለውጥ፣ ያ እንስሳና የተለወጠው ሁለቱም ንጹህ ይሆናሉ፡፡11ሆኖም፣ ሰውዬው ለያህዌ ሊሰጥ የተሳለው ንጹህ ካልሆነ ስለዚህ ምክንያት ያህዌ ያንን አይቀበልም፣ ከዚያ ሰውዬው እንስሳውን ወደ ካህኑ ማምጣት አለበት፡፡ 12ካህኑ በገበያው የእንስሳ ዋጋ ይተምነዋል፡፡ ማናቸውም ካህኑ ለእንስሳው የሰጠው ዋጋ፣ ያ የእንስሳው ዋጋ ይሆናል፡፡ 13እናም ባለቤቱ እንስሳውን ሊዋጅ ቢፈልግ፣ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይዋጀው፡፡14አንድ ሰው ቤቱን ለያህዌ መቀደስ ሲፈልግ፣ ካህኑ የቤቱን ዋጋ ይተምናል፡፡ ማናቸውም ካህኑ የተመነው ዋጋ ያ የዚያ ቤት ዋጋ ነው፡፡ 15ነገር ግን ባለቤቱ ቤቱን ቢለይና በኋላ ሊዋጀው ቢፈልግግ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አመስተና ይጨመር፣ እናም ከዚያ እንደገና የእርሱ ይሆናል፡፡16አንድ ሰው ከመሬቱ ለያህዌ ለመለየት ቢፈልግ፣ የመሬቱ ዋጋ ግምት ለመዝራት በሚያስፈልገው ፍሬ መጠን ይተመናል፡፡ አንድ ሆሜር መስፈሪያ ገብስ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ያወጣል፡፡17እርሻውን በኢዮቤልዩ አመት ቢለይ፣ የተገመተው ዋጋ ይፀናል፡፡ 18እርሻውን ከኢዮቤልዩ በኋላ ቢለይ ግን፣ ካህኑ የእርሻ መሬቱን ዋጋ እስከ ቀጣዩ የኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባሉ አመታት ቁጥር ያሰላና የተገመተው ዋጋ ይቀነሳል፡፡19እርሻውን የለየው ሰው ሊዋጀው ቢፈልግ፣ በተገመተው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛ ይጨምራ፣ እናም መሬቱ ተመልሶ የእርሱ ይሆናል፡፡ 20እርሻውን ካልዋጀ ወይም ለሌላ ሰው ሸጦት ከሆነ፣ ከዚያ በኋላ ተመልሶ ሊዋጅ አይችልም፡፡ 21ይልቁንም፣ እርሾው፣ በኢዮቤልዩ ተመልሶ ሲለቀቅ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ እንደተሰተ እርሻ ሁሉ ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ ይሆናል፡፡ የካህናቱ ንብረት ይሆናል፡፡22አንድ ሰው የገዛውን መሬት ለያዌ ቢለይ፣ ነገር ግን መሬቱ ከሰውዬው ቤተሰቦች መሬት ውስጥ ባይሆን፣ 23ካህኑ የእርሻውን ዋጋ እስ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባለው ጊዜ መተን ይተምናል፣ ሰውዬውም ዋጋውን በዚያ ቀን ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ አድርጎ ይከፍላል፡፡24በኢዮቤልዮ አመት፣ እርሻው ከገዛው ሰው ተወስዶ ወደ መሬቱ የቀድሞ ባለቤት ይመለሳል፡፡ 25የሚተመኑ ዋጋዎች ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል ዋጋ ሊተመኑ ይገባል፡፤ ሃያ ጌራ ከአንድ ሰቅል ጋር እኩል ነው፡፡26ከእንስሳት በመጀመሪያ የሚወለደው ግን አስቀድሞም ቢሆነ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው 27ንጹህ ያልሆነ እንስሳ ከሆነ፣ ባለቤቱ በተመገተው ዋጋ መልሶ ይግዛውው ደግሞም ከዋጋው በላይ አንድ አምስተኛ ይጨምርበት፡፡ እንስሳው ካልተዋጀ፣ በተተመነው ዋጋ ይሸጥ፡፡28ሆኖም፣ አንድ ሰው ለያህዌ ከለየው ሰውም ሆነ ወይም እንስሳ፣ ወይም የቤተሰቡ ርዕስት ምንም ነገር አይሽጥ ወይም አይዋጅ ማናቸውም የተለየ ነገር ለያህዌ ቅዱስ ነው፡፡ 29እንዲጠፋ ለተለየ ሰው ምንም መዋጃ አይከፈልለትም፡፡ ያ ሰው መገደል አለበት፡፡30አስራት ሁሉ፣ በምድሪቱ ላይ የበቀለ ሰብልም ሆነ ወይም የዛፍ ፍሬ የያህዌ ነው፡፡ ለያህዌ የተቀደሰ ነው፡፡ 31አንድ ሰው ከአስራቱ አንዳች ቢዋጅ፣ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛ ይቸምር፡፡32ከመንጋ ወይም ከከብት አስራት ሁሉ፣ ከእረኛው በትር ስር የሚያልፍ ሁሉ፣ ከአስር አንዱ ለያህዌ ይለይ፡፡ 33እረኛው የተሸለውን ወይም የከፋውን እንስሳ አይፈልግም፣ ደግሞም አንዱን በሌላው አይተካ፡፡ ቢለውጠው እኗን፣ የተለወጠውና የሚለወጠው ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ፡፡ ሊዋጅ አይችልም፡፡”34ያህዌ በሲና ተራራ ለሙሴ የሰጣቸው ለእስራኤላውያን የተሰጡ ትእዛዛት እነዚህ ናቸው፡፡
1ያህዌ በሲና ምድረ በዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ተናገረው፡፡ ይህ የሆነው የእስራኤል ህዝብ ከግብጽ ምድር በወጣበት በሁለተኛው አመት በሁለኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ነበር፡፡ ያህዌ እንዲህ አለ፣ 2“በየነገዱ፣ በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የእስራኤል ወንዶች ቆጠራ ይደረግ፡፡ በስም ቁጠራቸው፡ እያንዳንዱ ወንድ፣ በሰው ቁጠር፣ 3ሀያ አመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ወንድ ሁሉ ይቆጠር፡፡ ለእስራኤል ወታደር ሆኖ ሊዋጋ የሚችለውን ሁሉ ቁጠር፡፡ አንተና አሮን በታጣቂ ቡድኖቻቸው የወንዶችን ቁጥር መዝግቡ፡፡4ከእያንዳንዱ ጎሳ አንድ ሰው፣ የነገድ አለቃ ከአንተ ጋር የጎሳው መሪ ሆኖ ያገልግል፡፡ እያንዳንዱ መሪ ለጎሳው የሚዋጉትን ወንዶች ይምራ፡፡ 5ከአንተ ጋር ሆነው መዋጋት ያለባቸው መሪዎች ስሞቻቸው እነዚህ ናቸው፡ ከሮቤል ጎሳ፣ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር፣ 6ከስምዖን ጎሳ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፤7ከይሁዳ ጎሳ፣ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፤ 8ከይሳኮር ጎሳ የሶገር ልጅ ናትናኤል፤ 9ከዛብን ጎሳ፣ የኬሎን ልጅ ኤልያብ፤10ከኤፍሬም ጎሳ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ፤ ከምናሴ ጎሳ፣ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል፤ 11ከብንያም ጎሳ የዮሴፍ ልጅ፣ የጌዲዮን ልጅ አቢዳን፤12ከዳን ጎሳ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር፣ 13ከአሴር ጎሳ፣ የኤክራን ልጅ ፉግኤል፣ 14ከጋድ ጎሳ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ፤ 15እና ከንፍታሌም ጎሳ፣ የዔናን ልጅ አኪሬ” ናቸው፡፡16ከሕዝቡ የተመረጡት ወንዶች እነዚህ ነበሩ እነርሱ የአባቶቻቸውን ጎሳዎች ይመራሉ፡፡ በእስራኤል የነገዶች መሪዎች ነበሩ፡፡17ሙሴና አሮን በስም የተመዘገቡትን እነዚህን ወንዶች ወሰዱ፣ 18ከእዚህ ወንዶች ጋር በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የእስራኤል ወንዱን ሁሉ ሰበሰቡ፡፡ ከዚያም ሃያ አመት የሞላውና ከዚያ በላይ የሆነ እያንዳንዱ ወንድ የትውልድ ሐረጉን ተናገረ፡፡ እያንዳንዱ የነገዱን ስም እና የትውልድ ሐረጉን መጥራት ነበረበት፡፡ 19ከዚያም ሙሴ በሲና ምድረ በዳ ያህዌ እንዲያደርገው ባዘዘው መሠረት ቁጥራቸውን መዘገበ፡፡20የእስራኤል በኩር ከሆነው ከሮቤል ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉት ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 21ከሮቤል ጎሳ 46500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡22ከስምኦን ትውልዶች ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉት ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 23ከስምዖን ጎሳ 59300 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡24ከጋድ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 25ከጋድ ጎሳ 45650 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡26ከይሁዳ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስም ተቆጠሩ፡፡ 27ከይሁዳ ጎሳ 7460 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡28ከይሳኮር ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 29ከይሳኮር ጎሳ 54400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡30ከዛብሎን ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 31ከዛብን ጎሳ 57400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡32ከዮሴፍ ልጅ ከኤፍሬም ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 33ከኤፍሬም ጎሳ 40500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡34ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፤ 35ከምናሴ ጎሳ 32200 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡36ከብንያም ትውልዶች ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፤ 37ከብንያም ጎሳ 35400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡38ከዳን ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 39ከዳን ጎሳ 62700 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡40ከአሴር ትውልዶች፣ ወደ ጦርት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 41ከአሴር ጎሳ 41500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡42ከንፍታሌም ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 43ከንፍታሌም ጎሳ 53400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡44ሙሴና አሮን እነዚህን ወንዶች ሁሉ አስራ ሁለቱን የእስራኤል ጎሳዎች ከሚመሩ አስራ ሁለት ሰዎች ጋር ሆነው ቆጠሩ፡፡ 45ስለዚህም ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው ለጦርነት መውጣት የሚችሉ የእስራኤል ወንዶች ሁሉ በየቤተሰባቸው ተቆጠሩ፡፡ 46የቆጠሯቸው ወንዶች 603550 ናቸው፡፡47ከሌዊ ትውልድ የሆኑት ግን አልተቆጠሩም፣ 48ምክንያቱም ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበር፣ 49“የሌዊን ጎሳ አትቆጥርም ወይም እነርሱን በእስራኤል ህዝብ ቆጠራ ውስጥ አታስገባቸው፡፡50ይልቁንም፣ ሌዋውያንን የቃልኪዳኑን ስርዓቶች በቤተመቅደስ እንዲፈጽሙ መድባቸው፣ እንደዚሁም በቤተመቅደስ ውስጥ የሚገኙ መገልገያዎችንና ማናቸውንም ነገሮች እንዲንከባከቡ ሹማቸው፡፡ ሌዋውያን ጽላቱን ይሸከሙ፣ እንዲሁም የቤተመቅደሱን ዕቃዎች ይሸከሙ፡፡51ቤተመቅደሱ ወደ ሌላ ስፍራ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ፣ ሌዋውያኑ ይንቀሉት፡፡ ቤተመቅደሱ ሲተከል፣ ሌዋውያን ይትከሉት፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚጠጋ ማናቸውም እንግዳ ይገደል፡፡ 52እስራኤላውያን ድንኳኖቸውን ሲተክሉ፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ራሱ የጦር ቡድን ዐርማ አጅግ ቀርቦ ይስራ፡፡53ሆኖም፣ ሌዋውያኑ ቁጣዬ በእስራኤላውያን ላይ እንዳይሆን ድንኳናቸውን በቃል ኪዳኑ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፡፡ ሌዋውያኑ የቃልኪዳኑን ማደሪያ ሀላፊዎች ናቸው፡፡” 54እስራኤላውያን እነዚህን ሁሉ ነገሮች አደረጉ፡፡ ያህዌ በሙሴ በኩል ያዘዛቸውን ነገሮች ሁሉ አደረጉ፡፡
1ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንደገና እንዲህ አለ፣ 2“እያንዳንዱ እስራኤላዊ በየአባቶቻቸው ቤቶች በአርማው ስር በቦታው ይሰፈር፡፡ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ በሁሉም አቅጣጫ ይሰፍራሉ፡፡3ፀሐይ በምትወጣበት፣ በመገናኛው ድንኳን በስተምስራቅ ይሁዳ በቦታው ይሰፍራል፡፡ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን የይሁዳ ህዝብ መሪ ነው፡፡ 4የይሁዳ ህዝብ ቁጥር 74600 ነው፡፡5የይሳኮር ጎሳ ከይሁዳ ቀጥሎ ይስፈር፡፡ የሶገር ልጅ ናትናኤል የይሳኮርን ሰራዊት ይምራ፡፡ 6በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 54400 ነው፡፡7የዛብሎን ጎሳ ከይሳኮር ቀጥሎ ይስፈር፡፡ የኬሎን ልጅ ኤልያብ የኤሎንን ሰራዊት ይምራ፡፡ 8በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 57400 ነው፡፡9ጠቅላላው የይሁዳ ሠራዊት ቁጥር 186400 ነው፡፡ እነርሱ በቅድሚያ ይወጣሉ፡፡10በስተደቡብ አቅጣጫ የሮቤል ምድብ በስፍራው ይሆናል፡፡ የሮቤል ምድብ መሪ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነው፡፡ 11በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 46500 ነው፡፡12ስምዖን ከሮቤል ቀጥሎ ይሰፍራል፡፡ የስምዖን ህዝብ መሪ የሱሪሰዳይ ልጅ ስለሚኤል ነው፡፡ 13በእርሱ ምድብ የሚገኘው የሰራዊት ቁጥር 59, 300 ነው፡፡14የጋድ ጎሳ ይቀጥላል፡፡ የጋድ ህዝብ መሪ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነው፡፡ 15በእርሱ ምድብ የሚገኘው የሰራዊት ቁጥር 45650 ነው፡፡16በሮቤል ምድብ የሚገኙት በክፍላቸው መሠረት 151450 ናቸው፡፡ እነርሱ ቀጥለው ይወጣሉ፡፡17ቀጥሎ፣ የመገናኛው ድንኳን ሌዋውያንን ከሁሉም ምድብተኞች መሃል አድርጎ ከሰፈር ይወጣል፡፡ ወደ ሰፈር በገቡበት ስርዓት ከሰፈር ይውጡ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በዐርማው ስር በስፍራው ይሁን፡፡18የኤፍሬም ሰፈር ክፍሎች በስፍራቸው ይሁኑ፡፡ የኤፍሬም ህዝብ መሪ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነው፡፡ 19በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 40500 ነው፡፡20ከእነርሱ የሚቀጥለው የምናሴ ጎሳ ነው፡፡ የምናሴ መሪ የፍርዱሱር ልጅ ገማልኤል ነው፡፡ 21በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 32200 ነው፡፡22ቀጣይ የሚሆነው የብንያም ጎሳ ነው፡፡ የብንያም መሪ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነው፡፡ 23በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 35400 ነው፡፡24በኤፍሬም ምድብ የሚኙት በክፍላቸው መሰረት 108100 ናቸው፡፡ እነርሱ ሶስተኛ ሆነው ይወጣሉ፡፡25በሰሜን የዳን ሰፈር ምድብተኞች ይሰፍራሉ፡፡ የዳን ህዝብ መሪ የአሚሳዓይ ልጅ አብዔዘር ነው፡፡ 26በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 62700 ነው፡፡27የአሴር ጎሳ ህዝብ ሰፈር ከዳን ቀጥሎ ነው፡፡ የአሴር መሪ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነው፡፡ 28በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 41500 ነው፡፡29ቀጣዩ የንፍታሌም ጎሳ ነው፡፡ የንፍታሌም መሪ የዔናን ልጅ አኪሬ ነው፡፡ 30በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 53400 ነው፡፡31ከዳን ጋር በሰፈር የሚገኙት ቁጥራቸው 157600 ነው፡፡ እነርሱ በዐርማቸው ስር ከሰፈር በመጨረሻ ይወጣሉ፡፡”32በየቤተሰባቸው የተቆጠሩት እስራኤላውያን እነዚህ ናቸው፡፡ በየክፍሎቻቸው በሰፈሮቻቸው የተቆጠሩት በጠቅላላ 603550 ናቸው፡፡ 33ነገር ግን ሙሴና አሮን በእስራኤል ሕዝብ መሀል ሌዋውያንን አልቆጠሩም፡፡ ይህም ያህዌ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነበር፡፡34የእስራኤል ሕዝብ ያህዌ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ በየአርማቸው ስር ሰፈሩ፡፡ በአባቶቻቸው ቤቶች መሠረት በየነገዳቸው ከሰፈር ወጡ፡፡
1ያህዌ በሲና ተራራ ከሙሴ ጋር በተነጋገረበት ጊዜ የአሮንና የሙሴ ትውልዶች ታሪክ ይህ ነበር፡፡ 2የአሮን ልጆች ስሞቻቸው የበኩር ልጁ ናዳብ፣ እንዲሁም አብዩድ፣ አልዓዛር እና ኢታምር ነበሩ፡፡3የአሮን ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፣ እነዚህ የተቀቡ ካህናትና እንደ ካህናት ሊያገለግሉ የተሾሙ ነበሩ፡፡ 4ነገር ግን ናዳብ እና አብዩድ በሲና ምድረበዳ ተቀባይነት የሌለው እሳት ለእርሱ ሲሰዉ በያህዌ ፊት ወድቀው ሞቱ፡፡ ናዳብና አብዩድ ልጅ አልነበራቸውም፣ ስለዚህም አልዓዛርና ኢታምር ብቻ ከአባታቸው ከአሮን ጋር ካህናት ሆነው አገለገሉ፡፡5ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 6“የሌዊን ጎሳ ይረዱት ዘንድ ወደ ካህኑ ወደ አሮን አምጣቸው፡፡7በአሮንና በመላው ማህበሩ ስም በመገናኛው ድንኳን ፊት አገልግሎት ይስጡ፡፡ በቤተመቅደሱ ውስጥ ያገልግሉ፡፡ 8በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ላሉ ነገሮች ሁሉ ጥንቃቄ ያድርጉ፣ እንዲሁም የእስራኤል ጎሳዎች የቤተ መቅደሱን አገልግሎት እንድፈጽም ይርዱ፡፡9ሌዋውያኑን ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፡፡ እነርሱ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲያገለግል ሙሉ ለሙሉ የተሰጡ ናቸው፡፡ 10አሮንንና ልጆቹን ካህን አድርገህ ሹማቸው፣ ነገር ግን ማናቸውም ባዕድ ወደ ቤተ መቅደሱ ቢቀርብ ይገደል፡፡”11ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 12“እነሆ፣ እኔ ከእስራኤል ህዝብ መሃል ሌዋውያንን መረጥኩ፡፡ ከእስራኤል ሕዝብ መሃል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ከመውሰድ ፈንታ ይህን አድርጌያለሁ፡፡ ሌዋዊያን የእኔ ናቸው፡፡ 13ማናቸውም በኩር የእኔ ነው፡፡ በግብጽ ምድር በኩሩን ሁሉ በመታሁ ዕለት፣ በእስራኤል በኩር ሆኖ የተወለደውን የሰውንም ሆነ የእንስሳትን በኩር ሁሉ ለራሴ ለየሁ፡፡ እነርሱ የእኔ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”14በሲና ምድረበዳ ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 15“በእያንዳንዱ ቤተሰብ፣ በአባቶቻቸው ቤቶች የሌዊን ትውልዶች ቁጠር፡፡ አንድ ወር እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለውን ወንድ ሁሉ ቁጠር፡፡” 16ሙሴ እንዲያደርግ በታዘዘው መሠረት የያህዌን ቃል ሰምቶ ቆጠራቸው፡፡17የሌዊ ልጆች ስም፣ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው፡፡ 18ከጌድሶን ልጆች የመጡ ነገዶች ሎቢኒ እና ሰሜኢ ናቸው፡፡ 19ከቀዓት ልጆች የመጡ ነገዶች፣ አንበረም፣ ይስዓር፣ኬብሮን እና ዑዝኤል ናቸው፡፡ 20ከሜራሪ ልጆች የመጡ ነገዶች፣ ሞሖሊና ሙሴ ናቸው፡፡ በነገድ የተዘረዘሩ የሌዋውያን ነገዶች እነዚህ ናቸው፡፡21የሊቤናና የሰሜአ ነገዶች የመጡት ከጌርሶን ነው፡፡ እነዚህ የጌርሶን ነገዶች ናቸው፡፡ 22አንድ ወር ከሞላው አንስቶ ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው ወንድ ሁሉ ተቆጥሮ ነበር፣ በጠቅላላው 7500 ነበሩ፡፡ 23የጌርሶን ነገዶች ከቤተመቅደሱ ምዕራብ አቅጣጫ ይስፈሩ፡፡24የጌርሶንን ትውልዶች የላኤለ ልጅ ኤሊሳፍ ይምራ፡፡ 25የጌርሶን ቤተሰብ የመገናኛው ድንኳን ጨምሮ የማደሪያውን ድንኳን ኃላፊነት ይውሰድ፡፡ እነርሱ ለድንኳኑ፣ ለመደረቢያዎቹና ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ ሆኖ ለሚያገለግለው መጋረጃ ጥንቃቄ ያደርጉ፡፡ 26ለአደባባዩ ጌጦች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፣ በአደባባይ መግቢያ ላይ ለሚገኘው መጋረጃ፣ ቅዱሱን ስፍራና መሰዊያውን የሚከበውን አደባባይ ይጠብቁ፡፡ የመገናኛው ድንኳን ገመዶች እና በውስጡ የሚገኘውን ነገር ሁሉ ይጠብቁ፡፡27ከቀዓት የመጡት ነገዶች እነዚህ ናቸው የአንበረማውያን ነገድ የይሰዓራውያን ነገድ፣ የኬብሮናውያን ነገድ፣ እና የዑዝኤላውያን ነገድ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገዶች የቀዓት ወገኖች ናቸው፡፡ 28አንድ ወር እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው 8600 ወንዶች የያህዌ የሆኑ ነገሮችን ለመጠበቅ ተቆጠሩ፡፡ 29የቀዓት ቤተሰብ ትውልዶች ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ አቅጣጫ ይስፈሩ፡፡30የዑዝኤል ልጅ ኤሊሳፈን የቀዓታዊያንን ነገድ ይምራ፡፡ 31እነርሱ ታቦቱን፣ ጠረጴዛውን፣ የመቅረዝ ማስቀመጫውን፣ መሰዊያዎቹን፣ ለአገልግሎታቸው የሚጠቀሙባቸውን ቅዱሳን ዕቃዎች፣ መጋረጃውን፣ እና በዚያ ዙሪያ ያለውን ስራ ሁሉ ይንከባከቡ፡፡ 32የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ሌዋውያንን የሚመሩትን ሰዎች ይምሩ፡፡ እርሱ ቅዱሱን ስፍራ የሚንከባከቡትን ሰዎች ይቆጣጠር፡፡33ሁለቱ ነገዶች ኮሜራሪ ነገድ የመጡ ናቸው፡ እነዚህም የሞሖላውያን ነገድ እና የሙሳያውያን ነገድ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገዶች የመጡት ከሜራሪ ነው፡፡ 34አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው 6200 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 35የሜራሪን ነገድ የአቢካኤል ልጅ ሲሪኤል ይምራ፡፡36እነርሱ የቤተመቅደሱን ጣውላዎች፣ መቀርቀሪያዎች፣ ምሰሶዎች፣ መሰረቶች፣ ሁሉንም መገልገያዎች፣ እና ከእነርሱ ጋር የተያያዙ ነገሮች ሁሉ፣ 37መቅደሱ ዙሪያ የሚገኙ ምሰሶዎችና ቋሚዎችን ጨምሮ፣ ከማስገቢያዎቻቸው፣ ችካሎችና ገመዶች ጋር ይጠብቁ፡፡38ሙሴ፣ አሮን እና ልጆቹ ከመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት፣ በፀሀይ ማውጫ ከቤተ መቅደሱ በስተ ምስራቅ ይስፈሩ፡፡ እነርሱ በቅድስተ ቅዱሳን ለሚከናወኑ ተግባራት እና ለእስራኤል ህዝብ ግዴታዎች ሀላፊነት አለባቸው፡፡ ማንኛውም ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚቀርብ ባዕድ ይገደል፡፡ 39ሙሴና አሮን ያህዌ እንዳዘዘው በሌዊ ነገዶች ውስጥ የሚገኙትን አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን ወንዶች ሁሉ ቆጠሩ፡፡ ሃያ ሁለት ሺህ ወንዶችን ቆጠሩ፡፡40ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አንድ ወር ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን በኩር የሆኑ የእስራኤል ወንዶች ቁጠር፡፡ ስሞቻቸውን ጻፍ፡፡ 41በእስራኤል ህዝብ በኩር ምትክ ሌዋውያንን ለእኔ ውሰድ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ እንደዚሁም የሌዋውያንን ቀንድ ከብቶች፣ በመጀመሪያ በሚወለዱ የእስራኤላውያን የቀንድ ከብቶች ምትክ ውሰድ፡፡”42ያህዌ እንዳዘዘው ሙሴ የእስራኤልን ሰዎች በኩር በሙሉ ቆጠረ፡፡ 43ዕድሜያቸው አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆኑትን በኩር ወንዶች ሁሉ በስም ቆጠረ፡፡ 22273 ወንዶችን ቆጠረ፡፡44እንደገና፣ ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 45“በእስራኤል ህዝብ በኩር ሁሉ ምትክ ሌዋውያንን ውሰድ፡፡ በህዝቡ የቀንድ ከብት ምትክ የሌዋውያንን ቀንድ ከብት ውሰድ፡፡ ሌዋውያን የእኔ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡46ከሌዋውያን ቁጥር በላይ የሆኑትን 273 የእስራኤል በኩሮች ለመዋጀት ለእያንዳንዳቸው አምስት ሰቅሎች ተቀበል፡፡ 47የቅድስተ ቅዱሳኑን ሰቅል እንደ መደበኛ ክብደት ተጠቀም፡፡ (አንድ ሰቅል አምሳ አምስት ግራም ነው) 48ያገኘኸውን የመዋጆ ዋጋ ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፡፡” 49ስለዚህም ሙሴ በሌዋውያን ከተዋጁት በላይ ቁጥራቸው ያለፈውን መዋጃ ክፍያ ሰበሰበ፡፡ 50ሙሴ ከእስራኤል ሕዝብ በኩሮች ገንዘብ ሰበሰበ፡፡ በቤተ መቅደሱ ሚዛን መዝኖ 1365 ሰቅሎች ሰበሰበ፡፡ 51ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ የመዋጃውን ገንዘብ ሰጣቸው፡፡ ሙሴ ያህዌ እንዲያደርግ የተናገረውን ሁሉ አደረገ፣ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡
1ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንዲህ አላቸው፡፡ 2“ከሌዋውያን መሃል የቀዓት ትውልዶችን ወንዶችን፣ በነገድ እና በየአባቶቸው ቤተሰቦች ቁጠሩ፡፡ 3ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ወንዶች ሁሉ ቁጠሩ፡፡ እነዚህ ወንዶች በመገናኛው ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይምጡ፡፡ 4የቀዓት ትውልድ በመገናኛው ድንኳን ለእኔ የተለዩትን እጅግ ቅዱስ የሆኑ ነገሮች ይጠብቁ፡፡5ህዝቡ ጉዞውን ለመቀጠል ሲነሳ፣ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳን ውስጥ ይግቡ፣ ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳን የሚለየውን መጋረጃ ያውርዱት፣ ከዚያም የቃልኪዳኑን ታቦት ምስክር በእርሱ ይሸፍኑት፡፡ 6ታቦቱን በአስቆጣ ቁርበት ይሸፍኑት፡፡ በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑት፡፡ ለመሸከም ምሰሶ ያስገቡበት፡፡7በህብስት ማቅረቢያው ጠረጴዛ ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ያንጥፉበት፡፡ በላዩ ድስቶቹን፣ ማንኪያዎችን እና ለመቅጃ ገንቦ ያስቀምጡበት፡፡ 8በጠረጴዛው ላይ ህብስት አይታጣ፡፤ በደማቅ ቀይ ጨርቅ እና እንደገና በአቆስጣ ቁርበት ይሸፍኗቸው፡፡ ጠረጴዛውን ለመሸከም ምሰሰዎች ያስገቡ፡፤9ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው የመቅረዝ መያዣውን ይሸፍኑ፣ ከመብራቶቹ ጋር፣ መቆንጠጫ፣ ዝርግ ሰሃኖች፣ እና ለመብራቶቹ የዘይት ገንቦዎችን ይውሰዱ፡፡ 10መቅረዞቹንና መገልገያዎቹን በአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ ውስጥ ያድርጉ፣ ከዚያም በመሸከሚያ መያዣ ላይ ያስቀምጡቱ፡፡ 11በወርቅ መሰዊያው ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ያንጥፉ፡፤ እርሱንም በአቆስጣ ቁርበት ይሸፍኑት፣ ከዚያ መሸከሚያ ምሰሶ ያስገቡበት፡፡12ዕቃዎቹን ሁሉ ለሥራ ወደተቀደሰው ስፍራ ይውሰዱና በሰማያዊ ጨርቅ ይጠቅልሉ፡፡ በአስቆጣ ቁርበት ሸፍነው ዕቃዎቹን በመሸከሚያ መያዣ ላይ ያስቀምጡ፡፡ 13ከመሰዊያው አመዱን ያራግፉና ሐምራዊ ጨርቅ በመሰዊያው ላይ ያንጥፉ፡፡ 14በመሰዊያው ላይ የሚጠቀሙባቸውን መሳሪያዎች ሁሉ በመሸከሚያው መሎጊያ ላይ ያስቀምጡ፡፡ እነዚህ ዕቃዎች፣ የእሳት ማንደጃዎች፣ ሜንጦዎች የእሳት መጫሪያዎች፣ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ እና ለመሰዊያው የሚያገለግሉ ሌሎች መሳሪያዎች ናቸው፡፡ መሰዊያውን የአስቆጣ ቁርበት ይሸፍኑትና ከዚያ መሸከሚያ ምሰሶ ያስገቡበት፡፡15አሮንና ልጆቹ ቅዱሱን ስፍራና መገልገያዎቹን ሙሉ ለሙሉ ሸፍው ሲጨርሱ፣ እና ህዝቡ ወደፊት ሲንቀሳቀስ በዚያን ጊዜ የቀዓት ትውልዶች ቅዱሱን ስፍራ ለመሸከም ይቅረቡ፡፡ የተቀደሱ ዕቃዎችን ከነኩ ይገደሉ፡፡ የቀዓት ትውልዶች የሥራ ድርሻ በመገናኛው ድንኳን የሚገኙ መገልገያዎችን መሸከም ነው፡፡ 16የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ለመብራት የሚሆነውን ዘይት ያዘጋጃል፡፡ የጣፋጩን እጣን ዝግጅት ይቆጣጠራል፣ መደበኛውን የእህል ቁርባን፣ የቅባት ዘይቱን፣ ጠቅላላውን ቤተ መቅደስ እና በውስቱ ያሉትን ሁሉ፣ እንዲሁም በቅዱስ መገልገያዎችና ቁሳቁሶች ላይ ሀላፊነት ይኖረዋል፡፡”17ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ 18“የቀዓት የጎሳ ነገዶች ከሌዋዊያን መሃል እንዲወገዱ አትፍቀዱ፡፡ 19በህይወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እንዳይሞቱ ይህን በማድረግ ጠብቋቸው፡፡ እጅግ ወደ ተቀደሱ ነገሮች ሲቀርቡ 20ለአፍታ እንኳን የተቀደሰውን ስፍራ ለማየት ወደ ውስጥ አይግቡ፣ አሊያ ይሞታሉ፡፡ 20አሮንና ልጆቹ ወደ ውስጥ ይግቡ፣ ከዚያ አሮንና ልጆቹ ለእያንዳንዱ ቀዓታዊ የሚሰራውን ሥራ ይስጡት፣ ለእያንዳንዳቸው የየራሳቸውን ተግባራት ይስጧቸው፡፡21ያህዌ እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፣ 22“ጌድሶናውያንንም በአባቶቻቸው ቤተሰቦች፣ በየነገዳቸው ቁጠራቸው፡፡ 23ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠራቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ማገልገል የሚችሉትን ሁሉ ቁጠራቸው፡፡24የጌድሶናውያን ነገዶች ሲያገለግሉና ሲሸከሙ ተግባራቸው ይህ ነው፡፡ 25የመቅደሱን መጋረጃዎች ይሸከሙ፣ የመገናኛውን ድንኳን፣ መሸፈኛውን፣ በላዩ ላይ የሚገኘውን የአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ እና ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ የሚሆኑትን መገረጃዎች ይሸከሙ፡፡ 26የአደባባዩን መጋረጃ ይሸከሙ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃ፣ በቤተ መቅደሱና በመሰዊያው አጠገብ ያሉትን፣ ገመዶቻቸውን፣ ለአገልግሎታቸው የሚጠቀሙባቸውን መሳሪያዎች ሁሉ ይሸከሙ፡፡ በእነዚህ ነገሮች መደረግ ያለበትን ሁሉ፣ እነርሱ ያድርግ፡፡27አሮንና ልጆቹ የጌድሶናውያን ትውልዶች ማገልገል ያለባቸውን አገልግሎት ይምሯቸው፡፡ በሚያጓጉዟቸው ነገሮች ሁሉ፣ በሁሉም አገልግሎቶቻቸው ይምሯቸው፡፡ ያለባቸውን ሀላፊነቶች ሁሉ ትሰጧቸዋላችሁ፡፡ 28ለመገናኛው ድንኳን የጌድሶናዊያን ነገድ ትውልዶች አገልግሎት ይህ ነው፡፡ የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታምር በአገልግሎታቸው ይምራቸው፡፡29የሜራሪ ትውልዶችን በነገዳቸው ቁጠራቸው፣ በአባቶቻቸው ቤተሰቦችም እዘዛቸው፣ 30ከሰላሳ አመት እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠራቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የሚመጡትን ሁሉ ቁጠር፡፡31በመገናኛው ድንኳን የሚሰጧቸው አገልግሎቶችና የሥራ ድርሻቸው ይህ ነው፡፡ ቤተ መቅደሱን ለማስጌጥ እንክብካቤ ያድርጉ፣ የድንኳኑን ወርዶችና ቋሚዎች እና ካስማዎች ይሸከማሉ፣ 32በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ከሚገኙ ቋሚዎች ጋር፣ ችካሎቻቸውን፣ ካስማዎችን እና ገመዶቻቸውን ከተለያዩ መገልገያዎች ጋር ይሸከማሉ፡፡ መሸከም ያለባቸውን ቁሶች በስም ዘርዝር፡፡33የሜራሪ ነገድ ትውልዶች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር መሪነት በመገናኛው ድንኳን የሚሰጡት አገልግሎት ይህ ነው፡፡”34የማህበሩ መሪ የሆኑት ሙሴና አሮን የቀዓታውያንን ትውልዶች በአባቶቻቸው ቤተሰቦች ነገዶች ቁጠሯቸው፡፡ 35ሰላሳ አመት ዕድሜ የሞላቸውንና ከዚያ በላይ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠሯቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የሚመጡትን ሁሉ ቁጠሯቸው፡፡ 36በየነገዳቸው 2750 ወንዶች ቁጠሩ፡፡37ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ቀዓታዊያንን ወንዶች ሁሉ በየነገዳቸውና በየቤተሰባቸው ቁጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡38የጌድሶናውያን ትውልዶች በየነገዳቸው፣ በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ተቆጠሩ፣ 39ዕድሜያቸው ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት የሆኑ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የመጡ እያንዳንዳቸው ተቆጠሩ፡፡ 40በየነገዳቸው እና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የተቆጠሩት ወንዶች ቁጥር 2630 ነበሩ፡፡41ሙሴና አሮን በመገናኛው ድኗን የሚያገለግሉትን የጌድሶናውያንን ነገዶች ትውልዶች ቆጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ፣ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡42የሜራሪያውያን ትውልዶች፣ በየነገዳቸውና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ተቆጠሩ፣ 43ዕድሜያቸው ከሰላሳ እስከ አምሳ የሆኑ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የመጡ እያንዳንዳቸው ተቆጠሩ፡፡ 44በየነገዳቸው እና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የተቆጠሩት ወንዶች ቁጥር 3200 ነበሩ፡፡45ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉትን የሜራሪ ትወልዶች የሆኑትን እነዚህን ወንዶች ሁሉ ቆጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ፣ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡46ስለዚህም ሙሴ፣ አሮን፣ እና የእስራኤል መሪዎች ሁሉንም ሌዋውያን በየነገዳቸው በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ቆጠሯቸው 47ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቆጠሯቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ ማገልገል የሚችሉትን፣ እና በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙ ዕቃዎችን መንከባከብና መሸከም የሚችሉትን እያንዳንዳቸውን ቆጠሯቸው፡፡ 48በጠቅላላው 8580 ወንዶች ቆጠሩ፡፡49በያህዌ ትዕዛዝ፣ ሙሴ እያንዳንዱን ወንድ ቆጠረ፣ እያንዳንዱን በተሰጠው የሥራ አይነት መሰረት ቆጠረ፡፡ እያንዳዱን ሰው በሚሸከመው ሀላፊነት አይነት ቆጠረ፡፡ ይህን በማድረግ ያህዌ በሙሴ በኩል ያዘዛቸውን በመስራት ያህዌ ያዘዘውን አደረጉ፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2“የእስራኤል ሰዎች ተላላፊ የቆዳ በሽታ ያለበትን ሁሉ፣ በስቃይ የሚመግለውን ሁሉ፣ እና ማንኛውንም በድን በመንካት ረከሰውን ሁሉ ከሰፈር እንዲያስወጡ እዘዛቸው፡፡ 3ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች እነዚህን ከሰፈር አስወጣቸው፡፡ እኔ በውስጡ እኖራለሁና ሰፈሩን አያርክሱ፡፡” 4የእስራኤለ ሰዎችም ይህንኑ አደረጉ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከሰፈር አስወጧቸው፡፡ የእስራኤል ሰዎች ያህዌን ታዘዙ፡፡5ያህዌ ሙሴን እንደገና እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 6“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፡፡ አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት አንዱ በሌላው ላይ በደል ሲፈጽም፣ እና ለእኔ ታማኝ ሳይሆን ሲቀር ያ ሰው በደለኛ ነው፡፡ 7በዚህን ጊዜ በዳዩ ኃጢአቱን ይናዘዝ፡፡ በዳዩ የበደሉን ዋጋ ሙሉ ለሙሉ ይክፈል፣ ደግሞም አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይክፈል፡፡ ይህንን ለበደለው ይስጥ፡፡8ነገር ግን ተበዳዩ ክፍያውን ለመቀበል የቅርብ ዘመድ ባይኖረው፣ በዳዩ የበደሉን ዋጋ ከአውራ በግ ጋር ለራሱ ማስተስረያ በካህኑ በኩል ለእኔ ይክፈል፡፡ 9ከተቀደሱ ነገሮች ሁሉ የሚቀርቡ መስዋዕቶች ሁሉ፣ በእስራኤል ሰዎች ለእኔ የሚለዩ ነገሮች፣ የዚያ ካህን ይሆናሉ፡፡ 10የእያንዳንዱ ሰው የተቀደሱ ነገሮች የካህኑ ይሆናሉ፡፡ አንድ ሰው ለካህኑ የሚሰጣቸው ማናቸውም ነገሮች የዚያ ካህን ይሆናሉ፡፡”11ያህዌ እንደገና ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 12“ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ እንዲህ በላቸው፣ “ምናልባት የአንድ ሰው ሚስት ወደ ሌላ ሰው ሄዳ በባሏ ላይ ኃጢአት ሰርታ ይሆናል፡፡13ከባሏ ሌላ ሰው ከእርሷ ጋር ተኝቶ ይሆናል፡፡ በዚያ ሁኔታ፣ እርሷ ረክሳለች፡፡ ምንም እንኳን ባሏ ነገሩን ባያይም ወይም ስለነገሩ ባያውቅም፣ ደግሞም ድርጊቱን ስትፈጽም ማንም ባይዛትም፣ በእርሷ ላይ የሚያረጋግጥ ማንም ባይኖርም፣ 14የሆነ ሆኖ፣ የቅናት መንፈስ ሚስቱ እንደ ረከሰች ለባልየው ይነግረው ይሆናል፡፡ ሆኖም፣ ሚስቱ ሳትረክስ የቅናት መንፈስ በሀሰት በሰውየው ላይ መጥቶ ይሆናል፡፡15በዚህ ሁኔታ፣ ሰውየው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፡፡ ባልየው የመጠጥ ቁርባን ለእርሷ ያምጣ፡፡ የኢፍ አንድ አስረኛ የገብስ ዱቄት ያምጣ፡፡ ስለ ቅናት የሚቀርብ የእህል ቁርባን ነውና፣ምንም ዘይት ወይም እጣን አይጨምርበት፤ ምናልባት ተፈጽሞ ሊሆን ለሚችል ኃጢአት ጠቋሚ የእህል ቁርባን ነው፡፡16ካህኑ ያምጣትና በያህዌ ፊት ያቁማት፡፡ 17ካህኑ አንድ ገንቦ ቅዱስ ውሃና ከማደሪያ ድንኳኑ ወለል አፈር ይውሰድ፡፡ አፈሩን ውሃው ውስጥ ይጨምረው፡፡18ካህኑ ሴትየዋን በያህዌ ፊት ያቁማት የሴትየዋን ጸጉርም ይግለጥ፡፡ ካህኑ የቅናት መስዋእት የሆነውን የእህል ቁርባን በእጇ ያስይዛታል፡፡ ካህኑ በሴትየዋ ላይ እርግማን ሊያስከትል የሚችለውን በውስጡ አቧራ ያለበትን መራራ ውሃ በእጆቹ ይያዝ፡፡ 19ካህኑ ሴትየዋን ያስሞላት፤ እንደህም ይበላት፣ “ማንም ሰው ከአንቺ ጋር ተኝቶ ካልሆነ፣ እና ተሳስተሸ ካልሆነ እናም እርኩሰት ካልፈጸምሽ፣ እርግማን ከሚያጣው ከዚህ መራራ ውሃ በእርግጥ ነፃ ትሆኛለሽ፡፡20ነገር ግን፣ አንቺ በባልሽ ስር ያለሽ ሴት፣ ተሳስተሸ ቢሆን፣ ረክሰሽ ቢሆን፣ እና ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር ተኝቶ ቢሆን፣ 21ከዚያ፣ (ካህኑ በእርሷ ላይ ዕርግማን የሚያስከትል መሃላ ያስምላታል፣ ከዚያ በኋላ ሴትየዋን እንዲህ ማለቱን ይቀጥል) ‘ያህዌ ህን ማድረግሽን ለህዝብሽ በመርገምሽ ያሳያል፡፡ ያህዌ ጭንሽን ካሰለለና ሆድሽን ካሳበጠ ይህ ይታወቅ፡፡ 22ዕርግማኑን የሚያጣው ይህ ውሃ ወደ ሆድሽ ይገባል፣ ሆድሽን ያሳብጣል፣ እንዲሁም ጭኖችሽን ያሰልላል፡፡” ሴትየዋ እንዲህ ብላ ትመልስ፣ “አሜን፣ በደለኛ ከሆንኩ ይህ በእኔ ላይ ይሁን፡፡”23ካህኑ እነዚህን ዕርግማኖች በጥቅል ብራና ላይ ይጻፍ፣ ከዚያ የተጻፉትን እርግማኖች በመራራው ውሃ አጥቦ ያስለቅቅ፡፡24ካህኑ ዕርግማን የሚያመጣውን መራራ ውሃ እንድትጠጣ ያድርግ፡፡ ዕርግማኑን የሚያመጣው ውሃ ወደ ውስጧ ገብቶ መራራ ይሆናል፡፡ 25የቅናት መስዋዕቱን የእህል ቁርባን ከሴትየዋ እጅ ይቀበል፡፡ የእህል ቁርባኑን በያህዌ ፊት ወደ መሰዊያው ያምጣው፡፡ 26ካህኑ ከእህል ቁርባኑ እፍኝ ሙሉ ዘግኖ ይውሰድና በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ከዚያ ለሴትየዋ መራራውን ውሃ እንድትጠጣው ይስጣት፡፡27ውሃውን እንድትጠጣው ሲሰጣት በባሏ ላይ በደል በመፈፀም ረክሳ ከሆነ፣ ዕርግማን የሚያስከትለው ውሃ ወደ ውስጧ ይገባና መራራ ይሆናል፡፡ ሆዷ ያብጣል ጭኗ ይመነምናል፡፡ ሴትየዋ ከህዝቧ መሃል የተረገመች ትሆናለች፡፡ 28ሴትየዋ የረከሰች ካልሆነችና ንጹህ ከሆነች፣ ነጻ ትሆናለች፡፡ ልጆችን መጸነስ ትችላለች፡፡29የቅናት ህግ ይህ ነው፡፡ ከባሏ ውጭ ለሄደች እና ለረከሰች ሴት ህጉ ይህ ነው፡፡ 30የቅናት መንፈስ ለያዘውና በሚስቱ ለቀና ሰው ህጉ ይህ ነው፡፡ ሴትየዋን በያህዌ ፊት ያምጣ፣ ካህኑም ይህ የቅናት ህግ የሚገልጸውን ሁሉ በእርሷ ላይ ያድርግ፡፡31ሰውየው ሚስቱን ወደ ካህን በማቅረቡ ከበደል ነጻ ይሆናለ፡፡ ሴትየዋ በድላ ከሆነ ማናቸውንም በደል ትሸከማለች፡፡”
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ እንዲህ በላቸው፣ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ናዝራዊ ሆኖ ራሱን ለያህዌ በተለየ ስዕለት ሲለይ፣ 3ከወይንና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፡፡ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የተሰራ ኮምጣጤ አይጠጣ፡፡ ማናቸውንም የወይን ጭማቂ አይጠጣ ወይም የወይን ፍሬ ወይም ዘቢብ አይብላ፡፡ 4ለእኔ በተለየባቸው ቀናት ሁሉ፣ ከፍሬያቸው ግልፋፊ የተሰራ ማናቸውንም ነገር ጨምሮ ከወይን የተሰራ ምንም ነገር አይብላ፡፡5ለያህዌ ራሱን የለየባቸው ቀናት እስኪያበቁ ድረስ በስለቱ ጊዜያት ሁሉ ራሱን ምላጭ አይንካው፡፡ ለያህዌ የተለየ ይሁን፡፡ ፀጉሩ በራሱ ላይ እንዲያድግ ይተወው፡፡6ራሱን ለያህዌ በለየባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ ወደ ሞተ ሰው አይቅረብ፡፡ 7አባቱ፣ እናቱ፣ ወንድሙ ወይም እህቱ ቢሞቱ እንኳን ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡ ይህም የሚሆነው ማንም ሰው በረጅም ጠጉሩ እንደሚመለከተው፣ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው፡፡ 8በተለየበት ጊዜ ሁሉ ለያህዌ የተለየ ቅዱስ ነው፡፡9አንድ ሰው ድንገት አጠገቡ ቢሞት እና ማንነቱን የለየበትን ፀጉሩን ቢያረክስበት፣ መንጻት ባለበት ከሰባተኛው ቀን በኋላ ራሱን ይላጭ፡፡ ራሱን መላጨት ያለበት በዚያን ጊዜ ነው፡፡10በስምተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ያቅርብ፡፡ 11ካህኑ አንዱን ወፍ ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን የሚቃተል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ሬሳ አጠገብ በመሆን ኃጢአት ሰርቷልና እነዚህ ለእርሱ ስርየት ይቀርባሉ፡፡ በዚያው ዕለት ራሱን መልሶ ለያህዌ ይስጥ፡፡12ለተለየበት ጊዜ ራሱን ለያህዌ መልሶ ይስጥ፡፡ ለበደል መስዋዕት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት ያምጣ፡፡ ራሱን ከማርከሱ በፊት የነበሩ ቀናት አይቆጠሩም፣ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ተለይቶ ባለበት ጊዜ ረክሷል፡፡13ናዝራዊ መለየቱ ስለሚያበቃበት ጊዜ የተሰጠው ህግ ይህ ነው፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያምጡት፡፡ 14መስዋዕቱን ለያህዌ ያቅርቡ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ለህብረት መስዋዕት ነውር የሌለበት አውራ በግ ያምጣ፡፡ 15እንደዚሁም እርሾ ያልገባበት አንድ መሶብ ዳቦ፣ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ዳቦዎች፣ በዘይት የተቀባ እርሾ የሌለበት የገብስ ቂጣ፣ ከእህል ቁርባንና ከመጠጥ መስዋዕቶች ጋር ያምጣ፡፡16ካህኑ እነዚህን በያህዌ ፊት ያቅርባቸው፡፡ እርሱ የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ያቅርብ፡፡ 17ለያህዌ የህብረት መስዋዕቱን፣ እርሾ ካልገባበት ከመሶቡ ዳቦ ጋር፣ አውራ በጉን መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ እንዲሁም ካህኑ የእህል ቁርባኑን እና የመጠጥ መስዋዕቱን ጭምር ያቅርብ፡፡18ናዝራዊው ለእግዚአብሔር መለየቱን የሚያሳየውን ፀጉሩን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጭ፡፡ ፀጉሩን ከራሱ ወስዶ የህብረት መስዋዕቶቹ በሚቀርቡበት በሚነደው እሳት ውስጥ ይጨምረው፡፡19ካህኑ የተቀቀለውን አውራ በግ ወርች፣ ከመሶቡ ውስጥ እርሾ ያልገባበትን አንድ ዳቦ፣ እና አንድ እርሾ ያልገባበት የገብስ ቂጣ ይውሰድ፡፡ ናዝራዊው መለየቱን የሚያሳየውን ጸጉሩን ከተላጨ በኋላ ካህኑ እነዚህን በእጆቹ ያስይዘው፡፡ 20ካህኑ እነዚህን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ከፍ አድርጎ ያንሳቸውና ለእርሱ ያቅርባቸው፡፡ ይህ ከፍ ተደርጎ ከተነሳው ፍርምባና ከቀረበው ወርች ጋር ለካህኑ ተለየ ቅዱስ ምግብ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል፡፡21ለያህዌ ለመለየት ስዕለቱን ያቀረበ ናዝራዊ ህጉ ይህ ነው፡፡ ማናቸውንም ሌሎች ነገሮች ቢሰጥ በናዝራዊነት ህግ መሠረት እንዲጠብቃቸው የተሰጡትን ቃል ኪዳኖች ለመጠበቅ የገባውን የስዕለት ግዴታዎች መጠበቅ አለበት፡፡”22ያህዌ እንደገና ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 23“ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፣ ‘የእስራኤልን ሰዎች በዚህ መንገድ ባርኳቸው፡፡ እንደዚህ በሏቸው፣ 24“ያህዌ ይባርችሁ ይጠብቃችሁ፡፡25ያህዌ ብርሃኑን በእናንተ ላይ ያብራራ ፊቱን ይመልስላችሁ፣ ይራራላች፡፡ 26ያህዌ በሞገስ ያጥግባችሁ፣ ሰላምንም ይስጣችሁ፡፡’” 27ለእስራኤል ሕዝብ ስሜን የሚያስተዋውቁት በዚህ መንገድ ነው፡፡ እኔም እባርካቸዋለሁ፡፡”
1ማደሪያ ድንኳኑን በጨረሰ ቀን፣ ከመገልገያ ዕቃዎቹ ጋር ቀብቶ ለያህዌ ለየው፡፡ በመሰዊያውና በዕቃዎቹ ላይ እንዲሁ አደረገ፡፡ ቀብቶ ለያህዌ ለያቸው፡፡ 2በዚያ ቀን፣ የእስራኤል መሪዎች፣ የአባቶቻቸው ቤተሰቦች አባቶች መስዋዕቶችን አቀረቡ፡፡ ጎሳዎቹን የሚመሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የህዝብ ቀጠራውን ተቆጣጠሩ፡፡ 3መስዋዕቶቻቸውን ያህዌ ፊት አመጡ፡፡ ስድስት የተሸፈኑ ሰረገሎችና አስራ ሁለት በሬዎች አመጡ፡፡ ለየሁለቱ መሪዎች አንድ ሰረገላ አመጡ፣ እያንዳንዱ መሪ አንድ በሬ አመጣ፡፡ እነርሱ እነዚህን ነገሮች በማደሪያው ድንኳን ፊት አቀረቡ፡፡4ከዚያም ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 5“መስዋዕታቸውን ከእነርሱ ተቀበልና ለመገናኛው ድንኳን ሥራ አውላቸው፡፡ ለሥራው እንደሚያስፈልጋቸው ለእያንዳንዱ፣ መስዋዕቶቹን ለሌዋውያን ስጥ፡፡”6ሙሴ ሰረገሎቹንና በሬዎቹን ወስዶ ለሌዋውያኑ ሰጣቸው፡፡ 7ለጌድሶናውያን ተውልዶች ለስራቸው እንደሚያስፈልግ ሁለት ሰረገላዎችና አራት በሬዎች ሰጠ፡፡ 8ለሜራሪ ትውልዶች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር በኩል አራት ሰረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጠ፡፡ ይህን ያደረገው ሥራቸው ይህን ስለሚጠይቅ ነው፡፡9ለቀዓት ትውዶች ከእነዚህ ነገሮች ምንም አልሰጠም፣ ምክንያቱም የእነርሱ የሥራ ድርሻ የያህዌ የሆኑትን ነገሮች በገዛ ትከሻቸው ከመሸከም ጋር የተያያዘ ነው፡፡10መሪዎቹ ሙሴ መሰዊያውን በቀባ ዕለት ስጦታዎቻቸውን ለመሰዊያው መቀደስ ሰጡ፡፡ መሪዎቹ መስዋዕቶቻቸውን በመሰዊያው ፊት አቀረቡ፡፡ 11ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እያንዳንዱ መሪ ለመሰዊያው መቀደስ በራሱ ቀን መስዋዕቱን ማቅረብ አለበት፡፡”12በመጀመሪያው ቀን፣ ከይሁዳ ጎሳ የሆነው፣ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፣ መስዋዕቱነ አቀረበ፡፡ 13መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የብር ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሳህን ነበሩ፡፡ እነዚህ ሁለትም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 14በተጨማሪም በእጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሃን ሰጠ፡፡15ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ፣ እና የአንድ አመት ወንድ ጠቦት በግ ሰጠ፡፡ 16ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 17ሁለት በሬዎች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ የበግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የአሚናዳብ ልጅ የነአሶን መስዋዕት ነበር፡፡18በሁለተኛው ቀን፣ የይሳኮር መሪ፣ የሶገር ልጅ ናትናኤል፣ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 19አንድ መቶ ሰላሳ ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡20በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 21ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 22ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 23ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሶገር ልጅ የናትናኤል መስዋዕት ነበር፡፡24በሶስተኛው ቀን የዛብሎን መሪ፣ የኬሎን ልጅ ኤልያብ፣ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 25አንድ መቶ ሰላሳ ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 26በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡27ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 28ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 29ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኬሎን ልጅ የኤልያብ መስዋዕት ነበር፡፡30በአራተኛው ቀን፣ የሮቤል ትውልድ መሪ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 31መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 32በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡33ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 34ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 35ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሰዲዮር ልጅ የአሌሊሱር መስዋዕት ነበር፡፡36በአምስተኛው ቀን፣ የስምዖን ትውልድ መሪ፣ የሱሪሰዳይ ልጅ ስልሚኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 37መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 38በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ።39ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 40ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 41ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሱሪሰዳይ ልጅ የስልሚኤል መስዋዕት ነበር፡፡42በስድስተኛው ቀን፣ የጋድ ትውልድ መሪ፣ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 43መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 44በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡45ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 46ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 47ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የራጉኤል ልጅ የኤሊሳፍ መስዋዕት ነበር፡፡48በሰባተኛው ቀን፣ የኤፍሬም ትውልድ መሪ፣ የዓመሁድ ልጅ ኤሊሳማ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 49መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 50በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡51ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 52ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 53ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የራጉኤል ልጅ የኤሊሳፍ መስዋዕት ነበር፡፡54በስምንተኛው ቀን፣ የምናሴ ትውልድ መሪ፣ የፍደሱር ልጅ ገሚልኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 55መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 56በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡57ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 58ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 59ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የፍደሱር ልጅ የገማልኤል መስዋዕት ነበር፡፡60በዘጠነኛው ቀን፣ የብንያም ትውልድ መሪ፣ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 61መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 62በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡63ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 64ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 65ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የጋዲዮን ልጅ የአቢዳን. መስዋዕት ነበር፡፡66በአስረኛው ቀን፣ የዳን ትውልድ መሪ፣ የአሚሳይ ልጅ አኪዔዘር መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 67መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 68በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡69ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 70ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 71ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የፍደሱር ልጅ የገማልኤል መስዋዕት ነበር፡፡72በአስራ አንደኛው ቀን፣ የአሴር ትውልድ መሪ፣ የኤክራን ልጅ ፋግኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 73መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 74በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡75ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 76ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 77ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኤክራን ልጅ የፋግኤል መስዋእት ነበር፡፡78በአስራ ሁለተኛው ቀን፣ የንፍታሌም ትውልድ መሪ፣ የዔናን ልጅ ኢኬሬ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 79መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 80በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡81ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 82ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 83ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኤናን ልጅ የኤኪሬ መስዋዕት ነበር፡፡84የእስራኤል መሪዎች ሙሴ መሰዊያውን በቀባበት ቀን እነዚህን ሁሉ ነገሮች አቀረቡ፡፡ አስራ ሁለት የብር ሳህኖች፣ አስራ ሁለት የብር ጎድጓዳ ሳህኖች እና አስራ ሁለት የወርቅ ሰሃኖች አቀረቡ፡፡ 85እያንዳንዱ የብር ሳህን 130 ስቅሎች ሲመዝን እያንዳንዱ ጎድጓዳ ሰሀን ሰባ ሰቅሎች ይመዝናል፡፡ ሁሉም የውሃ መያዣዎች በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 2400 ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡ 86አስራ ሁለቱ ዕጣን የተሞሉ የወርቅ ሰሃኖች እያንዳንዳቸው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አስር ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡ ሁሉም የወርቅ ሳህኖች 120 ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡87ለሚቃጠል መስዋዕት አስራ ሁለት በሬዎች፣ አስራ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ ሁለት የአንድ አመት ጠቦቶች አቀረቡ፡፡ የእህል ቁርባናቸውን ሰጡ፡፡ ለኃጢአት መስዋዕት አስራ ሁለት ወንድ ፍየሎች ሰጡ፡፡ 88ከብቶቻቸው ሁሉ፣ ሀያ አራት በሬዎች፣ ስልሳ አውራ በጎች፣ ስልሳ ወንድ ፍየሎች እና አንድ አመት የሆናቸው ስልሳ ወንድ ጠቦት በጎች የህብረት መስዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡ እነዚህ ሁሉ መሰዊያውን ለመቀደስ በሚቀባበት ጊዜ የቀረቡ ስጦታዎች ናቸው፡፡89ሙሴ ከያህዌ ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ሲነጋገር ድምጹን ሰማ፡፡ ያህዌ ከማስተሰርያ መክደኛ በላይ ሆኖ በቃል ኪዳን ታቦቱ ላይ፣ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ለእርሱ ተናገረ፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“አሮንን እንዲህ በለው፣ ‘ሰባቱ መብራቶች በምትለኩሳቸው ጊዜ በመቅረዙ ፊት ለፊት ብርሃን ይስጡ፡፡’”3አሮን ይህን አደረገ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ብርሃን እንዲሰጡ መብራቶቹን በመቅረዙ ላይ ለኮሳቸው፡፡ 4መቅረዙ የተሰራው በዚህ መንገድ ነበር፡፡ ያህዌ አሰራሩን ለሙሴ አሳይቶት ነበር፡፡ ከመሰረቱ እስከ ጫፍ በአበባ መልክ የዋንጫ መልክ ቅርጽ አስይዘህ ወርቁን ቀጥቅጠህ አብጀው፡፡5እንደገና፣ ያህዌ ሙሴን እንዲሀ ሲል ተናገረው፣ 6“ከእስራኤል ሰዎች መሃል ሌዋውያንን ወስደህ አንጻቸው፡፡7እነርሱን ለማንጻት ይህን አድርግ፣ የማንጻት ውሃ እርጫቸው፡፡ ፀጉራቸው በሙሉ እንዲላጩ፣ ልብሶቻቸውን እንዲያጥቡ፣ እና በዚህ መንገድ ራሳቸውን እንዲያነጹ አድርግ፡፡ 8ከዚያ ጥጃና በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት የእህል ቁርባን ይውሰዱ፡፡ ሌላ ጥጃ ለኃጢአት መስዋዕት ያዘጋጁ፡፡9ሌዋውያኑን ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት አቅርባቸውና መላውን የእስራኤል ማህበረሰብ ሰብስብ፡፡ 10በእኔ በያህዌ ፊት ሌዋውያንን አቅርብ፡፡ የእስራኤል ሰዎች እጃቸውን በሌዋውያን ላይ ይጫኑ፡፡ 11አሮን ሌዋውያኑን በእኔ ፊት ያቅርባቸው፣ የእስራኤልን ህዝብ ወክለው በእርሱ ፊት ከፍ አድርገው እንደሚያቀርቡ አቅርባቸው፡፡ ሌዋውያን እኔን እንደሚያገለግሉ እርሱ ይህን ያድርግ፡፡12ሌዋውያኑ በበሬዎቹ ላይ እጃቸውን ይጫኑ፡፡ ሌዋውያኑን ለማስተሰርይ፣ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ኮርማ አቅርቡ፣ ደግሞም ሌላውን ኮርማ የሚቃጠል መስዋዕት አድርገህ ለእኔ አቅርብ፡፡ 13ሌዋውያኑን በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፣ እናም እንደ ሚወዘወዝ መሥዋዕት ለእኔ ከፍ አድርገህ አቅርባቸው፡፡14በዚህ መንገድ ሌዋውያኑን ከእስራኤል ሰዎች መሃል ለያቸው፡፡ ሌዋውያን ለእኔ ይለዩ፡፡ 15ከዚያ በኋላ ሌዋውያኑ ወደ መገናኛው ድንኳን ለአገልግሎት ይግቡ፡፡ እነርሱን አንጻቸው፡፡ እንደ ስጦታ ለእኔ ከፍ አድርገህ አንሳቸው፡፡16ከእስራኤል ህዝብ መሀል እነርሱ ሙሉ ለሙሉ የእኔ ናቸውና ይህን አድርግ፡፡ ከእስራኤል ወገን በኩር ሁሉ፣ ማህጸን ከከፈተው ከእያንዳንዱ ወንድ ልጅ ቦታውን ይወስዳሉ፡፡ እኔ ሌዋውያንን ለራሴ ለይቻለሁ፡፡ 17ከሰውም ሆነ ከእንስሳው የእስራኤል ህዝብ በኩሩ ሁሉ የእኔ ነው፡፡ በግብፅ ምድር የበኩሩን ህይወት ሁሉ በወሰድኩ ቀን፣ እኔ እናንተን ለራሴ ለየኋችሁ፡፡18በበኩሩ ሁሉ ምትክ፣ ከእስራኤል ሰዎች መሀል ሌዋውያንን ወሰድኩ፡፡ 19ሌዋውያንን ለአሮንና ለልጆቹ እንደ ስጦታ ሰጠኋቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን የእስራኤልን ሰዎች ሥራ ይስሩ ዘንድ ከእስራኤል ሰዎች መሃል ወሰድኳቸው፡፡ ወደተቀደሰው ስፍራ ሲቀርብ ምንም ጥፋት እንዳይደርስባቸው ለእስራኤል ሰዎች እንዲያስተሰርዩ እነርሱን ሰጠኋቸው፡፡”20ሙሴ፣ አሮንና መላው የእስራኤል ህዝብ ይህንን ከሌዋውያን ጋር አደረጉ፡፡ ሌዋውያንን በሚመለከት ያህዌ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ የእስራኤል ሰዎች ከእነርሱ ጋር ይህን አደረጉ፡፡ 21ሌዋውያን ልብሶቻቸውን በማጠብ ራሳቸውን ከኃጢአት አነጹ፡፡ አሮን ለያህዌ ስጦታ አድርጎ አቀረባቸው፤ ደግም ይነጹ ዘንድ የንስሃ ማስተስረያ አደረገላቸው፡፡22ከዚያ በኋላ፣ ሌዋውያኑ በአሮንና በአሮን ልጆች ፊት አገልግሎታቸውን ይሰጡ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፡፡ ይህም ያህዌ ስለ ሌዋውያን ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነበር፡፡ ሌዋውያንን በሙሉ በዚህ መንገድ ተቀበሉ፡፡23ያህዌ እንደገና ለሙሴ ተናገረ፡፡ እንዲህም አለ፣ 24“ይህ ሁሉ፤ ሃያ አምስት አመት እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ላላቸው ሌዋውያን ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል መምጣት አለባቸው፡፡25አምሳ አመት ሲሞላቸው በዚህ መንገድ ማገልገላቸውን ያቁሙ፡፡ በዚያ ዕድሜ መደበኛ አገልግሎታቸውን ያቁሙ፡፡ 26በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ወንድሞቻቸውን ሊያግዙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዕድሜያቸው አምሳ ከሆነ በኋላ በዚህ መንገድ አያገለግሉ፡፡ ለሌዋውያን በእነዚህ ጉዳዮች ሁሉ መመሪያ ልትሰጣቸው ይገባል፡፡
1ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው አመት በመጀመሪያው ወር፣ በሲና ምድረ በዳ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2“የእስራኤል ሰዎች በተወሰነው የአመቱ ወቅት ፋሲካን ያድርጉ፡፡ 3በዚህ ወር በእስራ አራተኛው ቀን፣ ምሽት ላይ፣ በተወሰነው በአመቱ ወቅት ፋሲካን አድርጉ፡፡ ፋሲካን አድርጉ፣ ደንቦቹን ጠብቁ፣ ከዚህ ጋር የተያያዙ ደንቦችን ሁሉ ታዘዙ፡፡”4ስለዚህ፣ ሙሴ የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ ነገራቸው፡፡ 5ስለዚህ በመጀመሪያው ወር በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን፣ ምሽት ላይ፣ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አከበሩ፡፡ የእስራኤል ሰዎች ያህዌ ለሙሴ እንዲያደርግ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፡፡6በሞተ ሰው በድን የረከሱ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነርሱ በዕለቱ ፋሲካን አላከበሩም፡፡ በዚያ ቀን እነዚህ ሰዎች ሙሴና አሮን ፊት ቀረቡ፡፡ 7እነዚያ ሰዎች ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “እኛ በሰው በድን አካል ምክንያት ንጹህ አይደለንም፡፡ ሆኖም በእስራኤል ሰዎች መሃል በተወሰነው የአመቱ ወቅት ለያህዌ መስዋዕት ከማቅረብ ለምን ትከለክለናለህ” 8ሙሴ እንዲህ አላቸው፣ “ያህዌ ስለ እናንተ ምን ትዕዛዝ እንደሚሰጥ እስከምሰማ ጠብቁኝ፡፡”9ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 10”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ከእናንተ ማናችሁም ወይም ከትውልዳችሁ ማንም በበድን አካል ምክንያት እርኩስ ቢሆን፣ ወይም ሩቅ መንገድ ሄዶ ቢሆን፣ ለያህዌ ፋሲካን ማክበር ይችላል፡፡’11እነርሱ በሁለተኛው ወር በአስራ አራተኛው ቀን ፋሲካን ያክብሩ፡፡ እነርሱ ፋሲካን እርሾ ባስገባበት እንጀራ ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉ፡፡ 12እስከ ማለዳ አንዳች አያስተርፉለት፣ አሊያም ከእንስሳቱ አጥንት አይስበሩ፡፡ የፋሲካን ህግጋት ሁሉ ይጠብቁ፡፡13ነገር ግን ማናቸውም ንጹህ የሆነና ሩቅ መንገድ ያልሄደ ሰው፣ ነገር ግን ፋሲካን ሳያከብር የቀረ ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፤ ምክንያቱም እርሱ በተወሰነው የአመቱ ወቅት የሚቀርበውን ያህዌ የሚጠይቀውን መስዋዕት አላቀረበም፡፡ ያሰው ኃጢአቱን ይሸከም፡፡ 14እንግዳ በመሀላችሁ ቢኖርና ፋሲካን ለያህዌ ክብር ቢያብር፣ ፋሲካን መጠበቅና እርሱ ያዘዘውን ሁሉ ማድረግ አለበት፣ የፋሲካን ህግጋት ሁሉ መጠበቅ እንዲሁም የፋሲካን ህግነት መጠበቅ አለበት፡፡ ለመጻተኞች እና በምድሪቱ ለተወለዱ ሁሉ ተመሳሳይ ህግ ይኑርህ፡፡”15የማደሪያው ድንኳን በተተከለበት ቀን፣ ደመና የማደሪያውን ድንኳን ፣ የቃል ኪዳኑን ምስክር ድንኳን ሸፈነው፡፡ በምሽት ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ነበር፡፡ እስከ ንጋት እሳት ይመስል ነበር፡፡ 16በዚያ መልክ ቀጠለ፡፡ ደመናው የማደሪያ ድንኳኑን ሸፍኖ በምሽት እሳት ይመስል ነበር፡፡ 17ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተወሰደ ጊዜ ሁሉ፣ የእስራኤል ሰዎች ከመጓዝ ያቋርጡ ነበር፡፡ ደመናው በቆመ ጊዜ ሁሉ፣ ህዝቡ አንድ ቦታ ይሰፍራል፡፡18የእስራኤል ሰዎች በያህዌ ትዕዛዝ ይጓዛሉ፣ በእርሱም ትእዛዝ በሰፈራቸው ይቆያሉ፡፡ ደመናው በማደሪያው ድንኳን ላይ ሲቆም፣ በሰፈራቸው ይቆያሉ፡፡ 19ደመናው በማደሪያው ድንኳን ለብዙ ቀናት ሲቆይ፣ የእስራኤል ሰዎች የያህዌን ትዕዛዝ ተከትለው መጓዝ ያቆማሉ፡፡20አንዳንድ ጊዜ ደመናው በማደሪያው ድንኳን ላይ ለጥቂት ቀናት ይቆያል፡፡ በዚህ ሁኔታ የያዌን ትእዛዝ ተከትለው በአንድ ቦታ ይሰፍራሉ፣ ከዚያ በእርሱ ትእዛዝ እንደገና ይጓዛሉ፡፡ 21አንዳንድ ጊዜ ደመናው ከምሽት እስከ ማለዳ በሰፈር ይገኛል፡፡ ማለዳ ደመናው ሲነሳ፣ እነርሱ ይጓዛሉ፡፡ ቀንም ይሁን ሌሊት ጉዟቸውን የሚቀጥሉት ደመናው ከተነሳ ብቻ ነው፡፡22ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ለሁለት ቀናት፣ ለወር ወይም ለአመት ቢቆይ በዚያ ስፍራ እስከ ቆየ ድረስ የእስራኤል ሰዎች በሰፈሮቻቸው ይቆያሉ አይጓዙም፡፡ ነገር ግን ደመናው ሲንቀሳቀስ እነርሱም ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡ 23በያህዌ ትዕዛዝ ይሰፍራሉ፣ በእርሱ ትዕዛዝ ይጓዛሉ በሙሴ በኩል የተሰጣቸውን የያህዌን ትዕዛዝ ይፈጽማሉ፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2”ሁለት የብር መለከቶች አብጁ፡፡ በብር ቀጥቅጠህ አብጃቸው፡፡ መለከቶቹን ማህበረሰቡን በጋራ ለመጥራትና ከመንደሮቸው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ለማሰማት ተጠቀምባቸው፡፡3ካህናቱ ማህበረሰቡን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በፊትህ ለመሰብሰብ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡ 4ካህናቱ አንድ መለከት ብቻ ከነፉ፣ የእስራኤል ነገድ መሪዎች ይሰበስቡ፡፡ 5ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፉ፣ በስተምስራቅ የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡6ለሁለተኛ ጊዜ ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፋ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡ ለጉዟቸው ከፍ ያለ የመለከት ድምጽ ያሰሙ፡፡ 7ማህበረሰቡ በአንድነት ሲበሰበሰብ፣ መለከቶች ይነፉ ነገር ግን ድምጹ ከፍ አይበል፡፡ 8የካህኑ የአዘሮን ልጆች፣ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘንድ ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም ስርዓት ይሆናል፡፡9በሚወሯችሁ ተቃዋሚዎቻች ላይ በምድራች ለጦርነት ስትወጡ፣ ለማንቂያ የመለከት ድምጽ ታሰማላችሁ፡፡ እኔ፣ አምላካችሁ ያህዌ፣ አስባችኋለሁ ደግሞም ከጠላቶቻችሁ አድናችኋለሁ፡፡10እንደዚሁም፣ በመደበኛ ባዕላቶቻችሁም ሆነ በወራቶች መጀመሪያ ላይ በክብረ በዓል ወቅት ለሚቃጠል መስዋዕቶቻችሁ ክብርና በህብረት መስዋዕቶቻችሁ መስዋዕቶች ላይ መለኮቶችን መንፋት አለባች፡፡ እነዚህ እናንተ የእኔ የአምላካችሁ ለመሆናችሁ መታሰቢያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡”11በሁለተኛው አመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በወሩ ሀያኛ ቀን ደመናው ከቃል ኪዳኑ ምስክር ማደሪያ ላይ ተነሳ፡፡ 12የእስራኤል ሰዎች ከሲና ምድረበዳ ተነስተው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ደመናው በፋራን ምድረ በዳ ውስጥ ቆመ፡፡ 13የመጀመሪያ ጉዟቸው፣ በሙሴ በኩል የተሰጣቸውን የያህዌን ትዕዛዝ ተከትለው አደረጉ፡፡14በይሁዳ ትውልዶች ዓርማ ስር ያለው ሰፋሪዎች በመጀመሪያ ተንቀሳቀሱ፡፡ የይሁዳን ሠራዊት የሚመራው የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር፡፡ 15የይሳኮርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበር፡፡ 16የዛብሎንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበር፡፡17የማደሪያ ድንኳኑን የተሸከሙት የጌድሶን እና የሜራሪ ትውልዶች፣ ማደሪያ ድንኳኑን ነቅለው ጉዟቸውን ጀመሩ፡፡ 18ቀጥሎ፣ በሮቤል ሰፈር ሰራዊት ዓርማ ስር የነበሩት ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ የሮቤልን ሰራዊት የሚመራው የሶዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበር፡፡ 19የስምዖንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራዊ የሱሪስዓይ ልጅ ስለሚኤል ነበር፡፡ 20የጋድን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነበር፡፡21ቀዓታውያን ተነሱ፡፡ እነርሱ የቅድስተ ቅዱሳኑን ቅዱስ ዕቃዎች ተሸከሙ፡፡ ቀዓታውያን ቀጣዩ ሰፈር ከመድረሳቸው አስቀድሞ ሌሎች ማደሪያ ድንኳን ይተክላሉ፡፡ 22የኤፍሬምን ሰራዊት የሚመራው የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበር፡፡ 23የምናሴን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበር፡፡ 24የብንያምን ትውልዶች ሠራዊት የሚመራው የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበር፡፡25በዳን ትውልዶች ዓርማ ስር የሰፈሩት ሠራዊቶች በመጨረሻ ይወጣሉ፡፡ የዳንን ሰራዊት የሚመራው የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር፡፡ 26የአቤርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነበር፡፡ 27የንፍታሌምን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የዔናን ልጅ አኪሬ ነበር፡፡ 28የእስራኤል ሰዎች ሰራዊቶች ጉዟቸውን ያደረጉት በዚህ መልክ ነው፡፡29ሙሴ ከምድያማዊው የራጉኤል ልጅ ከአባብ ጋር ተነጋገረ፡፡ ራጉኤል የሙሴ ሚስት አባት ነበር፡፡ ሙሴ ከአባብ ጋር ተነጋገረ እንዲህም አለ፣ “ያህዌ እሰጣችኋለሁ ወዳለን ስፍራ እየተጓዝን ነው፡፡ ያህዌ እንዲህ ብሎን ነበር፣ ‘እኔ ለእናንተ የተናገርኩትን እርሷኑ ስፍራ እሰጣችኋለሁ፡፡’ አንተ ከእኛ ጋር አብረኸን ና እኛም መልካም እናደርግልሃለን፡፡ ያህዌ ለእስራኤል መልካም ለማድረግ ቃል ገብቷል፡፡” 30አባብ ግን ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እኔ ከአንተ ጋር አልሄድም፡፡ እኔ ወደ ገዛ ምድሬና ወደ ራሴ ህዝብ እሄዳለሁ፡፡”31ከዚያም ሙሴ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “እባክህን ከእኛ አትለይ፡፡ በበረሃ እንዴት መስፈር እንደሚቻል ታውቃለህ፡፡ ስንሰፍር ልትመለከተን ይገባል፡፡ 32ከእኛ ጋር ብትሄድ፣ ያህዌ ለእኛ የሚያደርግልንን በጎነት ያንኑ እኛም ለአንተ እናደርግልሃለን፡፡”33ከያህዌ ተራራ ተነስተው ለሶስት ቀናት ተጓዙ፡፡ የያህዌ የቃልዳኑ ታቦት የሚያርፍበትን ስፍራ እንዲያገኙ ለመፈለግ ለሶስት ቀናት በፊታቸው ተጓዘ፡፡ 34ሲጓዙ የያህዌ ደመና በቀን ብርሃን በላያቸው ነበር፡፡35ታቦቱ በተነሳበት ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ እንዲህ ይላል፣ “ያህዌ ሆይ፣ ተነስ፡፡ ጠላቶችህን በትን፡፡ የሚጠሉህ ከአንተ እንዲሸሹ አድርግ፡፡” 36ታቦቱ በቆመ ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ “ያህዌ ሆይ፣ ብዙ አስር ሺህ ወደሚሆኑት እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር፡፡
1ህዝቡ ያህዌ እየሰማ ስለ ችግሮቻቸው አጉረመረሙ፡፡ ያህዌ ህዝቡን ሰምቶ ተቆጣ፡፡ ከያህዌ ዘንድ እሳት መጥታ በሰፈሩ ዙሪየ ከነበሩ ሰዎች አንዳንዶችን በላች፡፡ 2ከዚያም ህዝቡ ወደ ሙሴ ጮኸ፣ ስለዚህም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እሳቱም ቆመ፡፡ 3ስፍራው ተቤራ ተብሎ ተጠራ፣ ምክንያቱም የያህዌ እሳት ከመሀላቸው ሰዎችን አቃጥላለች፡፡4አንዳንድ ባዕዳን ከእስራኤላውያን ትውልዶች ጋር መስፈር ጀመሩ፡፡ እነርሱ የተሻለ ምግብ መብላት ፈለጉ፡፡ ከዚያ የእስራኤል ሰዎች ማልቀስና “እንድንበላ ማን ስጋ ሊሰጠን ይችላል” ማለት ጀመሩ፡፡ 5በግብጽ በነጻ እንበላ የነበረውን አሳውን፣ ዱባውን፣ በጢኹን፣ ባሮ ሽንኩርቱን፣ ቀይ ሽንኩርቱንና ነጭ ሽንኩርቱን እናስታውሳለን፡፡ 6አሁን ደካሞች ነን፡፡ ከመና በስተቀር ምንም የምንበላው የለም፡፡”7መና እንደ ድንብላል ፍሬ ያለ መልክ ነበረው፡፡ ሙጫ ይመስላል፡፡ 8ሰዎቹ እየተዘዋወሩ ይሰበስቡታል፡፡ በወፍጮ ይፈጩታል፣ በሙጫ ያደቁታል፣ በገንቦዎቹ ይቀቅሉታል፣ ቂጣ አድርገውም ይጋግሩታል፡፡ እንደ ንጹህ የወይራ ዘይት ይጣፍጣል፡፡9ምሽት በሰፈር ውስጥ ጤዛ ሲወርድ፣ መናውም ይወርዳል፡፡ 10ሙሴ ህዝቡ በየቤቱ ሲያለቅስ አዳመጠ፣ ደግሞም እያንዳንዱ ሰው በእርሱ ድንኳን ደጃፍ ነበር፡፡ ያህዌ በጣም ተቆጥቶ ነበር፣ ደግም የእነርሱ ማጉረምረም በሙሴ እይታ ስህተት ነበር፡፡11ሙሴ ወደ ያህዌ እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “ለምን ባሪያህን እንዲህ አስጨነከው? ስለምን በእኔ ደስ አልተሰኘህም? የዚህን ህዝብ ሁሉ ሸክም እንድሸከም አደረግከኝ፡፡ 12እኔ ይህን ህዝብ ሁሉ ፀንሼዋለሁን? ‘አባት ልጁን እነደሚያቅፍ ይህን ህዝብ ወደ ደረትህ አስጠግተህ ተሸከመው’ ትለኝ ዘንድ እኔ ወልጃቸዋለሁን?’ ትሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው ወደ ማልክላቸው ምድር እንዲገቡ እኔ ልሸከማቸውን?13ለእነዚህ ሁሉ ሰዎች የምሰጣቸውን ስጋ ከየት አገኛለሁ? በእኔ ፊት እያለቀሱ እንዲህ ይላሉ ‘የምንበላው ስጋ ስጠን፡፡’ 14እኔ ብቻዬን ይህን ሁሉ ህዝብ ልሸከም አልችልም፡፡ እጅግ በዝተውብኛል፡፡ 15እንዲህ እስካደረግኸኝ ድረስ፣ አሁኑኑ ግደለኝ፣ ለእኔ መልካም ከሆንክ፣ መከራዬን ከእኔ አርቅ፡፡”16ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ከእስራኤል መሪዎች ሰባዎቹን ወደ እኔ አምጣ፡፡ የህዝቡ መሪዎችና አለቃዎች መሆናቸውን እርግጠኛ ሁን፡፡ ከአንተ ጋር እንዲቆሙ ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣው፡፡ 17እኔ ወርጄ በዚያ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፡፡ ከአንተ ላይ ካለው መንፈስ ጥቂት ወስጄ በእነርሱ ላይ አደርገዋለሁ፡፡ እነርሱ ከአንተ ጋር የህዝቡን ሸክም ይሸከማሉ፡፡ አንተ ብቻህን ሸክሙን አትሸከምም፡፡18ለህዝቡ እንዲህ በል፣ ‘ነገ ራሳችሁን ለያህዌ ለዩ፡፡ ያህዌ እየሰማ አልቅሳችኋልና፣ በእርግጥ ስጋ ትበላላች፡፡ እንዲህ ብላችኋል፣ “እንበላ ዘንድ ማን ስጋ ይሰጠናል? ለእኛስ በግብጽ መሆን መልካም ነበር፡፡” ስለዚህ ያህዌ ስጋ ይሰጣችኋል፣ እናም ስጋ ትበላላችሁ፡፡ 19ስጋ የመትበሉት ለአንድ ቀን፣ ለሁለት ቀናት፣ ለአምስት ቀናት፣ ለአስር ቀናት ወይም ለሃያ ቀናት አይደለም፣ 20ነገር ግን በአፍንጫችሁ እስኪወጣ ድረስ ወር ሙሉ ስጋ ትበላላችሁ፡፡ ነገሩ ያስጸይፋችኋል፣ ምንያቱም በመሀላችሁ ያለውን ያህዌ እምቢ ብላችኋል፡፡ በፊቱ አልቅሳችኋል፡፡ እንዲህ ብላችኋል፣ “ለምን ከግብጽ ወጣን?”21ከዚያ ሙሴ እንዲህ አለ፣ “እኔ ከ600000 ሰዎች ጋር ነኝ፣ አንተ ግን እንዲህ አልክ፣ ‘ወር ሙሉ እንዲበሉ ስጋ አበላቸዋለሁ፡፡’ 22እነርሱን ለማጥገብ እኛ እንስሳትንና የከብት መንጋ ሁሉ እናርዳለን? እነርሱን ለማርካት የባህር አሶችን ሁሉ እናጠምዳን?” 23ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እጄ አጭር ናትን? አሁን ቃሌ እውነት መሆን አለመሆኑን ታያለህ፡፡”24ሙሴ ወጥቶ ለህዝቡ የያህዌን ቃላት ነገራቸው፡፡ ሰባዎቹን የህዝብ መሪዎች ሰበሰበና በድንኳኑ ዙሪያ አቆማቸው፡፡ 25ያህዌ በደመና ውስጥ ወረዳና ሙሴን ተናገረው፡፡ ያህዌ በሙሴ ላይ ከነበረው መንፈስ ጥቂት ወሰደና በሰባዎቹ ሽማግሌዎች ላይ አደረገው፡፡ መንፈሱ ሲያርፍባቸው፣ ትንቢት ተናገሩ፣ ነገር ግን በዚያ ወቅት እንጂ በሌላ ጊዜ ደግመው አልተነበዩም፡፡26አልዳድና ሞድ የተባሉ ሁለት ሰዎች በሰፈር ቀርተው ነበር፡፡ መንፈሱ በእነርሱ ላይም አረፈ፡፡ ስሞቻቸው በመዝገብ ተጽፎ ነበር፣ ነገር ግን ወደ ድንኳኑ አልሄዱም ነበር፡፡ ሆኖም ግን፣ እነርሱም በሰፈር እያሉ ተነበዩ፡፡ 27በሰፈር የነበረ አንድ ወጣት ሰው ወደ ሙሴ ሮጦ መጥቶ እንዲህ አለው፣ “ኤልዳድና ሞዳድ በሰፈር ውስጥ እየተነበዩ ነው፡፡”28ከእርሱ የተመረጡ ሰዎች አንዱ የሆነው የሙሴ ረዳት የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አለቃዬ ሙሴ ሆይ፣ ከልክላቸው፡፡” 29ሙሴ እያሱን እንዲህ አለው፣ “አንተ ለእኔ ተቆርቁረህ ነውን? እኔ መላው የያህዌ ህዝቦች ነቢያት ቢሆኑ እርሱ በሁሉም ላይ መንፈሱን ቢያደርግ እመኛለሁ!” 30ከዚያ ሙሴና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ሰፈር ተመለሱ፡፡31ከዚያ ከያህዌ ዘንድ ነፋስ ወጥቶ ከባህር ድርጭቶችን አመጣ፡፡ ከሰፈሩ በአንድ በኩል የአንድ ቀን የእግር መንገድ ርቀት ላይ፣ ደግሞም በሌላኛው በኩል በአንድ ቀን የእግር መንገድ ርቀት ድረስ ድርጭቶቹ ወደቁ፡፡ ድርጭቶቹ ሰፈሩን ከመሬት ሁለት ኪዩብ ከፍታ በሚሆን መጠን ሞሉት፡፡ 32ሰዎቹ ያን ዕለት ምሽቱን ጨምሮ እንዲሁም በማግስቱም ድርጭቶችን በመሰብሰብ ሥራ ተጠምደው ነበር፡፡ ማንም ከአስር የቆሮስ መስፈሪያ ያነሰ ድርጭት አልሰበሰበም፡፡ በሰፈሩ ሁሉ ድርጭቶቹን ተከፋፈሉ፡፡33ስጋው ገና በጥርሳቸው ውስጥ እያላመጡት ሳለ፣ ያህዌ በእነርሱ ላይ ተቆጣ፡፡ ህዝቡን በታላቅ በሽታ መታው፡፡ 34በዚያ ሥፍራ ስጋ ለማግኘት የጎመጁትን ሰዎች ስለቀበሯቸው የስፍራው ስም ቂብሮት ሃታአባ ተባለ፡፡ 35ሰዎቹ ከቂብሮት ሃታአባ ወደ ሰፈሩበት ወደ ሐጽሮት ተጓዙ፡፡
1“ከዚያ ማርያም እና አሮን ሙሴ ባገባት ኩሻዊ ሴት ምክንያት በሙሴ ላይ በተቃውሞ ተናገሩ፡፡ 2እንዲህም አሉ፣ “ያህዌ የተናገረው ከሙሴ ጋር ብቻ ነውን? ከእኛስ ጋር አልተናገረምን?” ያህዌ እነርሱ የተናገሩትን ሰማ፡፡ 3ሙሴ ፣ በምድር ላይ ከሚገኝ ከማንኛውም ሰው ይልቅ በጣም ትሁት ሰው ነበር፡፡4ወዲያውኑ ያህዌ ከሙሴ፣ ከአሮንና ማርያም ጋር ተናገረ “እናንተ ሶስታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን ውጡና ኑ፡፡” ስለዚህም ሶስቱም ወጥተው መጡ፡፡ 5ከዚያም ያህዌ በደመና አምድ ወረደ፡፡ በድንኳኑ መግቢያ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራቸው፡፡ ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ፡፡6ያህዌ እንዲህ አለ፣ “አሁን ቃሎቼን ስሙ፡፡ አንድ የእኔ ነብይ በመካከላችሁ ሲሆን፣ ራሴን፣ በራዕይ እገልጥለታለሁ፣ በህልምም እናገረዋለሁ፡፡ 7አገልጋዬ ሙሴ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ እርሱ በቤቴ ላይ ሁሉ የታመነ ነው፡፡ 8እኔ ከመሴ ጋር በቀጥታ እናገራሁ፣ በራዕይ ወይም በዘይቤ አይደለም፡፡ እርሱ የእኔን መልክ ያያል፡፡ ስለዚህ በአገልጋዬ በሙሴ ላይ ስትናገሩ ለምን አልፈራችሁም?”9የያህዌ ቁጣ በእነርሱ ላይ ነደደ፣ ከዚያም ትቷቸው ሄደ፡፡ 10ደመናው ከድንኳኑ ላይ ተነሳ፣ እናም ማርያም በድንገት በለምጽ ተመታች እንደ በረዶ ነጭ ሆነች፡፡ አሮን ወደ ማርያም ዞር ብሎ ሲመለከታት በልምጽ መመታቷን አየ፡፡11አሮን ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እባክህን በአንተ ላይ የፈጸምነውን ይህን በደል አትቁጠርብን፡፡ በስንፍና ተናግረናል፣ ደግሞም በድለናል፡፡ 12እባክህን ከእናቱ ማህጸን ሲወጣ ጭንጋፍ ሆኖ እንደ ተወለደ ከፊል አካሉ እንደተበላ ሆና አትተዋት፡፡”13ስለዚህም ሙሴ ወደ ያህዌ ጮኸ፡፡ እንዲህም አለ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህ፣ እባክህ ፈውሳት፡፡” 14ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አባቷ በፊቷ ላይ ቢተፋባት፣ ለሰባት ቀናት በሀፍረት ትቆያለች፡፡ ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት ዝጋባት፡፡ ከዚያ በኋላ መልሰህ አምጣት፡፡” 15ስለዚህም ማርያም ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት ተዘጋባት፡፡ እርሷ ወደ ሰፈር እስክትመለስ ድረስ ህዝቡ ጉዞ አላደረገም፡፡16ከዚያ በኋላ፣ ህዝቡ ከሐዴሮት ተነስቶ ተጓዘና በፋራን ምድረበዳ ሰፈረ፡፡
1ዚያም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2”ለእስራኤላውያን የሰጠኋቸውን የከነዐንን ምድር እንዲያዩ ጥቂት ሰዎችን ላክ፡፡ ከአባቶቻቸው ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሰው ላክ፡፡ ከመሀላቸው የሚላከው እያንዳንዱ ሰው መሪ መሆን አለበት፡፡”3ሙሴ የያህዌን ትእዛዝ እንዲያደርጉ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፡፡ ሁሉም ከእስራኤል ሰዎች መሃል የተመረጡ መሪዎች ነበሩ፡፡ 4ስሞቻቸው እነዚህ ነበሩ፡ ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፡፡5ከስምዖን ነገድ፣ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፡፡ 6ከይሁዳ ነገድ፣ የዩፎኒ ልጅ ካልብ፡፡ 7ከይሳኮር ነገድድ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፡፡ 8ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፡፡9ከብንያም ነገድ፣ የራፋ ልጅ ፈልጢ፡፡ 10ከዛብን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፡፡ 11ከዮፍ ትውልዶች፣ ይህም፣ ከምናሴ ነገድ ነው፣ የሱሲን ልጅ ጋዲ፡፡ 12ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፡፡13ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፡፡ 14ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፡፡ 15ከጋድ ነገድ፣ የማኪ ልጅ ጉዲኤል ነበሩ፡፡ 16ምድሪቱን እንዲያዩ ሙሴ የላቸው ሰዎች ስሞች እነዚህ ነበሩ፡፡ ሙሴ የነዌ ልጅ አውሴን፣ ኢያሱ ብሎ ጠራው፡፡17ሙሴ እነርሱ የከነዓንን ምድር እንዲያዩ ላካቸው፡፡ እንዲህ አላቸው፣ “ከነጌብ ጀምራችሁ እስከ ተራራማው አገር ድረስ ሂዱ፡፡ 18ምድሪቱ ምን እንደምትመስል ተመልከቱ፡፡ በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን እዩ፣ ጠንካሮች ወይም ደካሞች መሆናቸውን፣ እና ጥቂት ወይም ብዙ መሆናቸውን ተመልከቱ፡፡ 19የሚኖሩባት ምድር ምን እንደምትመስል እዩ፡፡ መልካም ናት ወይስ መጥፎ? በዚያ ምን አይነት ከተሞች አሉ? ሰፈር አይነት ናቸው? የተቀጠሩ ከተሞችስ ናቸውን? 20ምድሪቱ ምን እንደምትመስል እዩ፣ ለእርሻ የተመቸች ናት ወይስ አይደለችም፣ በዚያ ዛፎች አሉ ወይስ የሉም፡፡ ብርቱ ሁኑና ከምድሪቱ ምርት ከየአይነቱ ይዛችሁ ኑ፡፡” ወቅቱ የወይን ፍሬ ማፍራት የጀመረበት ነበር፡፡21ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው በሌለቦ ሐማት አጠገብ፣ ከጺን ምድረበዳ እስከ ሌቦ ድረስ ምድሪቱን ተመለከቱ፡፡ 22ከኔጌብ ወጥተው እስከ ኬብሮን ደረሱ፡፡ ከዔናቅ ነገድ ዝርያ የሆኑ የአኪመን፣ የሴሲና፣ እና የተላሚ ነገዶች በዚያ ነበሩ፡፡ ኬብሮን ግብጽ ውስጥ የተመሰተረችው ከከጣኔዎስ ሰባት አመት ቀደም ብላ ነበር፡፡23ኤሽኮል ሸለቆ ሲደርሱ፣ የወይን ዘለላ የያዘ ቅርንጫፍ ቆረጡ፡፡ ከቡድናቸው በሁለቱ መሃል በበትር አድርገው የወይኑን ዘለላ ተሸከሙት፡፡ እንደዚሁም ሮማንና በለስም አመጡ፡፡ 24የእስራኤል ሰዎች በዚየ ከቆረጡት የወይን ዘለላ የተነሳ፣ ያቺ ስፍራ የኤሽኮል ሸለቆ ተብላ ተጠራች፡፡25ምድሪቱን መርምረው ከአርባ ቀናት በኋላ ተመለሱ፡፡ 26የተላኩት ሰዎች፣ ሙሴና አሮን እንዲሁም መላው የእስራኤል ማህበረሰብ ወዳሉበት በፋራን ምድረበዳ ወደምትገኘው ወደ ቃዴስ መጡ፡፡ ወደ እነርሱና ወደ መላው ማህበረሰብ ተመልሰው መጥተው፣ የምድሪቱን ፍሬ አሳይዋቸው፡፡27ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “ወደ ላከን ምድር ደረስን፡፡ በእርግጥም ወተትና ማር ታፈሳለች፡፡ ከምድሪቱ ምርት እነሆ፡፡ 28ሆኖም፣ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ናቸው፤¨ከተሞቹም የተመሸጉና ትላልቅ ናቸው፡፡ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዝርያዎችም አይተናል፡፡ 29አማሌቃውያን በነጌብ ይኖራሉ፡፡ ኬጢያውያን፣ ኢያቡሳዊያን፣ እና አሞራዊያን በተራራማው አገር ይኖራሉ፡፡ ከነዓናዊያን በባህሩ አቅራቢያ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ይኖራሉ፡፡”30ከዚያ ካሌብ በሙሴ ዙሪያ የተሰበሰቡበትን ሰዎች ሊያበረታታቸው ተነሳ፣ እንዲህም አለ፣ “በአንድ ጊዜ ተነስተን እንውጣና ምድራቸውን እንውረስ፣ ምክንያቱም በሚገባ ልናሸንፍ እንችላለን፡፡” 31ግን ከእርሱ ጋር የሄዱት ሌሎች ሰዎች እንዲህ አሉ፣ “እኛ ሰዎቹን ማጥቃት አንችልም ምክንያቱም እነርሱ ከእኛ ይልቅ ጠንካሮች ናቸው፡፡”32ስለዚህም ስለተመለከቷት ምድር በእስራኤለ ሰዎች መሀል ተስፋ አስቆራጭ ወሬ አሰራጩ፡፡ እንዲህም አሉ፣ “የተመለከትናት ምድር በላይዋ የሚኖሩትን የምትበላ ናት፡፡ በዚያ ያየናቸው ሰዎ ሁሉ ቁመተ ረጃጅም ሰዎች ናቸው፡፡ 33በዚያ የኤናቅ ዝርያዎችን አይተናል፣ ከግዙፋኑ ሰዎች የመጡትን ግዙፎቹን ሰዎች አይተናል፡፡ ከእነርሱ ጋር ስንተያይ፣ በእኛ በራሳችን ዐይን እንደ አንበጣ ነበርን፣ ደግሞም በእነርሱም ዐይን እንደዚሁ ነበርን፡፡”
1“በዚያን ምሽት ማህበረሰቡ በሙሉ ድምጹን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፡፡ 2እስራኤል ሰዎች ሁሉ ሙሴንና አሮንን ነቀፉ፡፡ መላው ማህበረሰብ እንዲህ አሏቸው፣ “በግብጽ ምድር ብንሞት ይሻለን ነበር፡፡ ውይም ምነው በዚህ በረሃ በሞትን ኖሮ! 3ያህዌ ለምን በዚህ ምድረበዳ በሰይፍ እንድንሞት ወደዚህ ምድር አመጣን? ሚስቶቻችንና ትናንሽ ልጆቻችን የተጠቁ ይሆናሉ፡፡ ወደ ግብጽ መመለስ አይሻለንምን?”4እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “ሌላ መሪ እንምረጥ፣ እናም ወደ ግብጽ እንመለስ፡፡” 5ከዚያ ሙሴና አሮን በእስራኤል ህዝብ በማህበረሰቡ ጉባኤ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፡፡6ምድሪቱን ለማየት ከወጡት ውስጥ ከነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዩፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፡፡ 7እስራኤል ሰዎች መላው ማህበረሰብ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፣ “በውስጧ ያለፍነውና የተመለከትናት ምድር በጣም መልካም መድር ናት፡፡ 8ያህዌ በእኛ ደስ ከተሰኘ፣ ወደዚህች ምድር ያስገባናል ደግሞም እርሷን ለእኛ ይሰጠናል፡፡ ምድሪቱ ወተትና ማር የምታፈስ ናት፡፡9ነገር ግን በያህዌ ላይ አታምጹ፣ ደግሞም በምድሪቱ የሚኖሩትን ህዝቦች አትፍሩ፡፡ በቀላሉ እንደ ምግብ እንበላቸዋለን፡፡ ጥላቸው ከእነርሱ ተገፏል፣ ምንያቱም ያህዌ ከእኛ ጋር ነው፡፡ እነርሱን አትፍሯቸው”፡፡ 10ነገር ግን መላው ማህበረሰብ እስከ ሞት ሊወግሯቸው ተነሰቡቸው፡፡ ከዚያ የያህዌ ክብር በመገናኛው ድንኳን ለመላው የእስራኤል ሰዎች ታየ፡፡11ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ይህ ህዝብ እስከ መቼ እኔን ይንቀኛል በመካከላቸው በሃይሌ ያደረኳቸውን ምልክቶች እያዩ እንኳን እስከ መቼ በእኔ አያምኑም 12በበሽታ እመታቸዋለሁ፣ ወደ ርስታቸው አላስገባቸውም፣ ሆኖም ከአንተ ከራስህ ነገድ ከእነርሱ ይልቅ ታላቅና ሃያል ህዝብ አበጃለሁ፡፡”13ሙሴ ያህዌን እንዲህ አለው፣ “ይህን ብታደርግ፣ ግብጻዊያን ስለዚህ ነገር ይሰማሉ፣ ምክንያቱም አንተ ይህን ህዝብ በኃይልህ ከእነርሱ አድነሃቸዋል፡፡ 14ለዚህች ምድር ነዋሪዎች ይህንን ይናገራሉ፡፡ አንተ ያህዌ፣ ከዚህ ህዝብ ጋር እንደሆንክ እነርሱ ሰምተዋል፣ ምክንያቱም አንተ ፊት ለፊት ታይተሃል፡፡ የአንተ ደመና በእኛ ህዝብ ላይ ሆኗል፡፡ አንተ በእነርሱ ፊት በቀን በደመና አምድ በምሽት በእሳት አምድ ሄደሃል፡፡15አሁን ይህንን ህዝብ እንደ አንድ ሰው ብትገድል፣ ዝናህን የሰሙ ህዝቦች እንዲህ ይላሉ፣ 16‘ያህዌ ይህንን ህዝብ ሊሰጣቸው ወደ ማለላቸው ምድር ሊያስገባቸው ባለመቻሉ ምክንያት፣ በምድረበዳ ገደላቸው፡፡17አሁን፣ እኔ እለምንሃለሁ፣ ታላቁን ሀይልህን ተጠቀም፡፡ አንተ እንዲህ ብለሃልና፣ 18‘ያህዌ ለቁጣ የዘገየ ነው፣ በቃል ኪዳን ታማኝነቱ የተትረፈረፈ ነው፡፡ እርሱ በደልና መተላለፍን ይቅር ይላል፡፡ የአባቶችን ኃጢአት ቅጣት እስከ ሁለትና ሶስት ትውልድ በልጆቻቸው ላይ ሲያመጣ በደላቸውን በምንም አይነት ሳይቀጣ አይቀርም፡፡’ 19የቃል ኪዳን ታማኝነነትህን ታላቅነት ስላልተረዳ ይህ ህዝብ ይበድላል፣ በግብጽ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ሁልጊዜም ይቅር እንዳልካቸው ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፡፡”20ያህዌ እንዲህ አለው፣ “ልመናህን ሰምቼ ይቅር ብያቸዋለሁ፣ 21ነገር ግን፣ እኔ ሕያው ስለሆንኩና መላው ምድርም በእኔ ክብር የተሞላች ስለሆነች፣ 22ክብሬን፣ በግብጽና በምድረበዳው ጉዟቸው ያደረኳቸውን የሀይሌን ምልክቶች አይተው እነዚያ ህዝቦች ሁሉ - እስከ አሁን ድረስ በእነዚህ አስር ጊዜ ተፈታተኑኝ እንጂ ድምጼን አልሰሙም፡፡23ስለዚህ ለአባቶቻቸው የማልኩላቸውን ምድር በፍጹም አያዩም፡፡ እኔን ከናቁት ውስጥ አንዳቸውም ምድሪቱን አያዩም፣ 24ከባሪያዬ ከካሌብ በስተቀር፣ ምክንያቱም እርሱ የተለየ መንፈስ አለው፡፡ እርሱ እኔን በሙሉ ልቡ ተከትሎኛል፣ ሊያያት ወደሄደበት ምድር እኔ እመጣዋለሁ፡፡ የእርሱ ትውልዶች ይወርሷታል፡፡ 25(አሁን አማሌቃዊያንና ከነዓናውያን በሸለለቆው ይኖራሉ፡፡) ነገ ተመልሳችሁ በሸምበቆው ባህር በኩል ወደ ምድረ በዳው ሂዱ፡፡”26ህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ 27”እኔን የሚነቅፈውን ይህን ክፉ ማህበረሰብ እስከ መቼ እታገሳለሁ የእስራኤል ሰዎች በእኔ ላይ ሲያጉረመርሙ ሰምቻለሁ፡፡28እንዲህ በላቸው ‘እኔ ሕያው ነኝ’ ይላል ያህዌ፣ ‘እኔ እየሰማሁ፣ የተናገራችሁትን፣ ያንኑ አደርግባችኋለሁ፡፡ 29በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፣ እናንተ በእኔ ላይ ያጉረመርማችሁ ሁላችሁም፣ በህዝብ ቆጠራው የተቆጠራችሁ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ ትሞታላችሁ፡፡ 30መኖሪያችሁ ትሆን ዘንድ እንደምሰጣችሁ ቃል ወደገባሁላችሁ ምድር ከዮፍኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከእናንተ አንዳችሁም አትገቡም፡፡31ነገር ግን ተጠቂ ይሆናሉ ያላችኋቸው ትንንሽ ልጆቻችሁን፣ እኔ ወደ ምድሪቱ አስገባቸዋለሁ፡፡ እናንተ የናቃችኋትን ምድር እነርሱ ይገቡባታል! 32እናንተ ግን፣ በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፡፡ 33ልጆቻችሁ ለአርባ አመታት በምድረዳ ይንከራተታሉ፡፡ በረሃው ሁላችሁንም እስኪገድላችሁ ድረስ፣ እነርሱ እናንተን የአመጽ ድርጊቶች ዋጋ ይከፍላሉ፡፡34ምድሪቱን በተመለከታችሁባቸው አርባ ቀናት ልክ፣ ለአርባ አመታት ስኃጢአታችሁ መከራ ትቀበላላችሁ - ለእያንዳንዱ ቀን አንድ አመት፣ እናም የእኔ ጠላት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ 35እኔ ያህዌ፣ ይህንን ተናግሬያለሁ፡፡ በእኔ ላይ በተነሱ በዚህ ክፉ ማህበረሰብ ላይ በእርግጥ ይህን አደርጋሁ፡፡ በዚህ ምድረ በዳ ይጠፋሉ፡፡ በዚህ ስፍራ ይሞታሉ፡፡”36-37ስለዚህ ሙሴ ምድሪቱን እንዲያዩ የላካቸው ሰዎች ሁሉ በያህዌ ፊት በወረርሽኝ አለቁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው የተመለሱ ነበሩ፡፡ ይህም መላው ማህበረሰብ በሙሴ ላይ እንዲያጉረመርም አደረገ፡፡ 38ምድሪቱን ለማየት ከሄዱት ሰዎች መሀል፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የዩፎኒ ልጅ ካሌብ ብቻ በህይወት ቀሩ፡፡39ሙሴ እነዚህን ቃላት ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች ሲናገር፣ በጥልቅ አዘኑ፡፡ 40ማልደው ተነስተው ወደ ተራራው ጫፍ ወጥተው እንዲህ አሉ፣ “እነሆ፣ አሁን በዚህ አለን፣ ደግሞም ያህዌ ቃል ወደገባልን ስፍራ እንሄለን፣ እኛ በድለናል፡፡”41ነገር ግን ሙሴ እንዲህ አለ፣ “ለምን አሁን የያህዌን ትእዛዝ ትሽራላችሁ ድል አይቀናችሁም፡፡ 42አትውጡ፣ ምክንያቱም በጠላቶቻችሁ እንዳትሸነፉ ሊጠብቃችሁ ያህዌ ከእናንተ ጋር አይደለም፡፡ 43በዚያ አማሌቃዊያንና ከነዓናዊያን አሉ፣ እናንተም በሰይፍ ታልቃላችሁ ምክንቱም ያህዌን ከመከተል ፊታችሁን መልሳችኋል፡፡ ስለዚህ እርሱ ከእናንተ ጋር አይሆንም፡፡”44እነርሱ ግን ወደ ተራራማው አገር ለመሄድ በድፍረት ተነሱ፣ ሆኖም፣ ሙሴም ሆነ የያህዌ የቃል ኪዳኑ ታቦት ከሰፈር አብሯቸው አልወጣም፡፡ 45ከዚያ አማሌቃዊያን ወርደው መጡ፣ እንደዚሁም በተራሮቹ የሚኖሩ ከነዓናዊያን መጡባቸው፡፡ እነርሱም እስራኤላውያንን አጠቋቸው እስከ ሔርማ መንገድ ድረስ አሳደዷቸው፡፡
1ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ያህዌ ለእናንተ ወደሚሰጣችሁ ወደ ምትኖሩባት ምድር ስትገቡ 3ለእርሱ በእሳት መስዋዕት ስታቀርቡ፣ የሚቃጠል መስዋዕት ወይም ስዕለት ስታመጡ ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ፣ ወይም በባዕላቶቻችሁ ለያህዌ ስጦታዎችን ከከብቶች ወይም ከመንጋችሁ ስታቀርቡ4ለያህዌ መስዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው፣ በአንድ አራተኛ ኢን ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ 5እንዲሁም የኢን አንድ አራተኛ ወይን ለመጠጥ መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ይህን ከሚቃጠል መስዋዕት ጋር ወይም እያንዳንዱ ጠቦት ሲቀርብ አድርጉት6አውራ በግ የምታቀርቡ ከሆነ፣ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት በአንድ ሶስተኛ ኢን ዘይት የተለወሰ የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ 7ለመጠጥ መስዕት፣ የኢን አንድ ሶስተኛ ወይን አቅርቡ፡፡ ይህ ለያዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፡፡8ለሚቃተል መስዋዕት በሬ፣ ወይም ስዕለት ለማድረስ መስዋዕት ወይም ለያህዌ የህብረት መስዋዕት ስታዘጋጁ 9ከበሬው ጋር በግማሽ ኢን ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ 10ለያዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ለመጠጥ ቁርባን የኢን ግማሽ ወይን፣ በእሳት የሚረብ መስዋዕት አቅርቡ፡፡11እያንዳንዱ በሬ፣ እያንዳንዱ አውራ በግ፣ እና እያንዳንዱ ወንድ ጠቦት በግ ወይም ጠቦት ፍየል ሲቀርበ በዚህ አይት ይሁን፡፡ 12እያንዳንዱ የምታዘጋጁት መስዋዕት እና ስጦታ እዚህ እንደተገለፀው ይቅረብ፡፡ 13ማንም ሰው ለያህዌ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ለማቅረብ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ሲያመጣ፣ የአገር ተወላጅ የሆነ እስራኤላዊ ሁሉ እነዚህን ነገሮች በዚህ መንገድ ያድርግ፡፡14መጻተኛው ከእናንተ ጋር ቢኖር፣ ወይም በእናንተ ትውልድ መሀል የሚኖር ማናቸውም ሰው፣ ለያህዌ መልካም መዓዛ ለማቅረብ በእሳት የተዘጋጀ መስወዕት ያድርግ፡፡ እርሱ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ፡፡ 15ለማህበረሰቡ እና ከእናንተ ጋር ለሚኖር መጻተኛ ተመሳሳይ ህግ ይሁን፣ ይህ በትውልዳች ሁሉ የፀና ህግ ይሁን፡፡ እናንተ እንደ ታያችሁት፣ ከእናንተ ጋር የሚኖሩ እንግዶች በአንድ አይነት ይታያሉ፡፡ 16ለእናንተም ሆነ ከእናንተ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞች ተመሳሳይ ህግና ደንቦች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡”17ያህዌ ዳግም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 18”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ወደ ማስገባችሁ ምድር በመጣች ጊዜ፣ 19በምድሪቱ የተመረተውን ምግብ በበላችሁ ጊዜ፣ መስዋዕት መሰዋትና ለእኔ ማቅረብ አለባችሁ፡፡20ከመጀመሪያው ቡኬታችሁ ከአውድማው የማንሳት መስዋዕት ህብስት አቅርቡ፡፡ በዚህ መንገድ መስዋዕታችሁን አቅርቡ፡፡ 21በትውልዶች ሁሉ ከመጀመሪያው ቡኬታችሁ የማንሳት መስዋዕት ለእኔ ትሰጣላችሁ፡፡22አንዳንድ ጊዜ ለማድረግ ሳታስቡ ለሙሴ የነገርኩትን እነዚህን ህጎች ሁሉ በተመላለፍና 23ትዕዛዛትን ለእናንተ መስጠት ከጀመርኩበት ቀን አንስቶ በትውልዳችሁ ቀጣይ ዘመናት በሙሴ በኩል ያዘዝኳችሁን ነገሮች በሙሉ ባታደርጉ ኃጢአት ትሰራላችሁ፡፡ 24ማህበረሰቡ ሳያውቅ በደል ፈጽሞ ሲገኝ፣ መላው ህብረተሰብ ለያህዌ መልካም መዓዛ እንዲሆን አንድ ወይፈን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ከዚሁ ጋር የእህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን እንዲሁም ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል በደንቡ መሠረት ያቅርብ፡፡25ካህኑ ለመላው የእስራኤል ማህበረሰብ ማስተስረያ ያቀርባል፡፡ ኃጢአቱ የተፈፀመው፣ ባለማወቅ ስለሆነ ይቅር ይባላሉ፡፡ ለእኔ በእሳት የተዘጋጀውን መስዋዕታቸውን አቅርበዋልና ይቅር ይባለሉ፡፡ በእኔ ፊት ሳያውቁ ለፈጸሙት ስህተት የኃጢአት መስዋዕታቸውን አቅርበዋልና፡፡ 26ከዚያ መላው የእስራኤል ማህበረሰብና ከእነርሱ ጋር የሚኖሩ መጻተኞች ይቅር ይባላሉ፣ ምክንያቱም ሁሉም ኃጢአቱን የፈፀሙት ሆን ብለው አይደለም፡፡27አንድ ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሰራ ለኃጢአት መስዋዕት የአንድ አመት ሴት ፍየል ያቅርብ፡፡ 28ካህኑ ሳያውቅ ኃጢአት ለሰራው ሰው በያህዌ ፊት ያስተሰርይለታል፡፡ ያ ሰው ማስተሰርያ ሲደረግ ይቅር ይባላል፡፡ 29ማናቸውንም ነገር ሁን ብሎ ላላደረገ ተመሳሳይ ህግ ይኑራችሁ፣ በእስራኤል ሰዎች መሀል ለሚኖረው ተወላጅም ሆነ መጻተኛ ተመሳሳይ ህግ ይኑራቸው፡፡30ነገር ግን ራሱን ለመከላከል አንዳች ነገር ያደረገ ሰው፣ የአገር ተወላጅም ይሁን መጻተኛ እኔን ያቃልላል፡፡ ስለዚህ ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ፡፡ 31ምክንቱም እርሱ ቃሌን ንቋል ደግሞም ትዕዛዛቴን ተላልፏል፣ ያ ሰው ሙሉ ለሙሉ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡ ኃጢአቱ በራሱ ላይ ይሆናል፡፡”32የእስራኤል ህዝቦች በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ፣ አንድ ሰው በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም አገኙት፡፡ 33ያገኙት ሰዎች ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው ማህበረሰብ አቀረቡት፡፡ 34በእርሱ ላይ ምን መደረግ እንዳለበት የታወቀ ህግ ስላልበረ በጥበቃ ሥር አቆዩት፡፡35ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “በእርግጥ ሰውየው መገደል አለበት፡፡ መላው ማህበረሰብ ከሰፈር ውጭ በድንጋይ ይውገረው፡፡” 36ስለዚህም መላው ማህበረሰብ ሰውየውን ከሰፈር ውጭ አውጥተው ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው እስኪሞት ድረስ ወገሩት፡፡37ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 38“ለእስራኤል ትውልዶች በየለብሳቸው ጠርዝ ዘርፍ እንዲያስሩ ንገራቸው፣ ዘርፎቹን በእያንዳንዱ ጠርዝ በሰማያዊ ገመድ እንዲያንጠለጥሉ እዘዛቸው፡፡ በሚቀጥሉት ትውልዶቻቸው ሁሉ ይህን ያድርጉ፡፡ 39ይህንን ስትመለከቱ፣ በትዕዛዛት ሁሉ፣ እንድትሄዱ፣ የራሳችሁን ልቦናና እይታ ሳትከተሉ ቀድሞ ታደርጉት ከነበረው መንፈሳዊ አመንዝራነት ለመመለስ ይህ ለእናንተ ልዩ ማስታወሻ ይሆናችኋል፡፡40ትዕዛዛቶቼን ሁሉ እንድትጠብቁና አስተዋዮች እንድትሆኑ ይህን አድርጉ፣ ደግሞም ቅዱሳንና ለእኔ ለአምላካችሁ የተለያችሁ ትሆናላች፡፡ 41አምላካችሁ እሆን ዘንድ፣ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
1የይስዓር ልጅ ቆሬ የቀዓት ልጅ የሌዊ ልጅ፣ ከኤሊያብ ልጆች ከዳታንና አቤሮን ጋር፣ እንዲሁም የፍሬት ልጅ ኦን፣ የሮቤል ትውልዶች ሆነው ተሰበሰቡ፡፡ 2እነርሱም ከእስራኤል ሌሎች ሰዎች ጋር ሆነው በሙሴ ላይ ተቃውመው ተነሱ፣ የማህበረሰቡ መሪዎች የሆኑ የታወቁ ሁለት መቶ ሀምሳ ሰዎች ተነሱበት፡፡ 3ሙሴንና አሮንን ለመቃወም በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ሙሴንና አሮንን እንደዚህ አሏቸው፣ “እናንተ ያለ ልክ አብዝታችሁታል፡፡ መላው ማህበረሰብ ቅዱስ ነው፣ ለያህዌ የተለየ ነው፣ እያንዳንዳቸው ንጹሃን ናቸው፣ ያህዌም በመሀከላቸው ነው፡፡ ለምን ራሳችሁን ከተቀረው የያህዌ ማህበረሰብ ከፍ ታደረጋላችሁ?”4ሙሴ ይህንን ሲሰማ፣ በግምባሩ ተደፋ፡፡ 5ለቆሬና ለእርሱ ወገኖች እንዲህ አላቸው፤ “ማለዳ ያህዌ የእርሱ የሆኑት እነማን እንደሆኑ ይለያል፣ ማን ለእርሱ እንደ ተለየ ይታወቃል፡፡ የመረጠውን ሰው ወደ ራሱ ይለያል፡፡ የመረጠውን ወደ ራሱ ያመጣዋል፡፡6ቆሬና የአንተ ቡድን ሁላች ይህን አድርጉ፡፡ ማጠንት ያዙ 7ነገ በያህዌ ፊት እሳትና እጣን በላያቸው ጨምሩ፡፡ ያህዌ የሚመርጠው ሰው እርሱ፣ ለያህዌ የተለየ ይሆናል፡፡ እናንተ የሌዊ ትውልዶች ከልክ አልፋችኋል፡፡”8እንደገና፣ ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፣ “አሁን ስማ፣ እናንተ የሌዊ ትውልዶች 9የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማህበረሰብ እናተን ለይቶ ወደራሱ ማቅረቡ፣ በያህዌ የማደሪያ ድንኳን እንድታገለግሉ ማድረጉ፣ እነርሱን እንድታገለግሉ በማህበረሰቡ ፊት እናንተን ማቆሙ ለእናንተ ትንሽ ነገር ነውን? 10እርሱ አንተን፣ የቅርብ ዘመዶችህንና የሌዊ ትውልዶችን ከአንተ ጋር አቅርቧችኋል፣ እናንተ ግን ክህነቱንም እየፈለጋችሁ ነው! 11አንተና የአንተ ተከታዮች ሁሉ በያህዌ ላይ በአንድ ላይ ተነሳችሁ፡፡ ስለዚህ ለምን እግዚአብሔርን በሚታዘዘው በአሮን ላይ ታጉረመርማላችሁ?”12ከዚያ ሙሴ የኤልያብን ልጆች ዳታንንና አብሮንን ጠራቸው፣ እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፣ “እኛ ወደዚያ አንመጣም፡፡ 13እኛን በምድረበዳ ልትገድለን ወተትና ማር ከሚፈስባት ምድር ያወጣኸን ትንሽ ነገር ሆኖ ነውን? አሁን ራስህን በእኛ ላይ ገዢ ማድረግ ትፈልጋለህ! 14በተጨማሪም፣ እኛን ወተትና ማር ወደምታፈስ ምድር አላመጣኸንም፣ ወይም እርሻዎችንና የወይን ተክሎችን ውርስ አድርገህ አልሰጠኸንም፡፡ አሁን በባዶ ተስፋ ልታታልለን ትፈልጋህ? ወደ አንተ አንመጣም፡፡”15ሙሴ እጅግ ተቆጥቶ ነበር፣ ወደ ያህዌ እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “መስዋዕታቸውን አትቀበል፡፡ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳን አልወሰድኩም፣ ከእነርሱ አንዳቸውንም አልበደልኩም፡፡” 16ከዚያ ሙሴ ቆሬን እዲህ አለው፣ “ነገ አንተና የአንተ የሆኑ በያህዌ ፊት ይቅረቡ፤ አንተ፣ እነርሱና አሮን በያህዌ ፊት ቁሙ፡፡ 17እያንዳንዱ የራሱን ማጠኛ ይያዝና በውስጡ እጣን ይጨምርበት፡፡ ከዚያ እያንዳንዱ ሰው ማጠኛውን በያዌ ፊት ያምጣ፣ ሁለት መቶ አምሳዎቹ ሰዎችህ ማጠኛዎቻቸውን ይዘው ይቅረቡ፡፡ አንተና አሮንም ደግሞ የየራሳቸችሁን ማጠኛ አምጡ፡፡”18ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ማጠኛውን ወሰደ፣ በውስጡ እሳት አደረገ፣ እጣንም ጨመረበት ከሙሴና ከአሮን ጋር በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ቆሙ፡፡ 19ቆሬ መላውን ማህበረሰብ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በሙሴና በአሮን ላይ በተቃውሞ ሰበሰበ፣ የያህዌ ክብር ደግሞ ለማህበረሰቡ ሁሉ ታየ፡፡20ከዚያ ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፣ 21”በቶሎ ከማጠፋው ከዚህ ማህበረሰብ መሀል ራሳችሁን ለዩ፡፡” 22ሙሴና አሮን በግንባራቸው ተደፍተው እንዲህ አሉ፣ “ የሰው ልጆች ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሰራ ማህበረሰቡን በሙሉ ልትቆጣ ይገባልን?”23ያህዌ ለሙሴ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ 24”ለማህበረሰቡ እንዲህ በል፣ ‘ከቆሬ፣ ከዳታንና ከኤብሮን ድንኳኖች ውጡ፡፡’”25ከዚያ ሙሴ ተነስቶ ወደ ወደ ዳታንና አብሮን ሄደ፤ የእስራኤል መሪዎች እርሱን ተከተሉት፡፡ 26ለማህበረሰቡ እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ “አሁን የእነዚህን ክፉ ሰዎች ድንኳኖች ልቀቁ፣ የእነርሱ የሆነውን አንዳች ነገር አትንኩ፣ አለበለዚያ በእነርሱ ኃጢአቶች ሁሉ እናንተም ትጠፋላችሁ፡፡” 27ስለዚህ በቆሬ፣ በዳታንና በኤብሮን ድንኳኖች በእያንዳንዱ አቅጣጫ የሚገኝ ማህበረሰብ ከእነርሱ ራቁ፡፡ ዳታንና አብሮን ወደ ውጭ ወጥተው ከሚስቶቻቸው፣ ከወንዶች ልጆቻቸውና ከህፃናቶቻቸው ጋር በድንኳኖቸው ደጃፍ ላይ ቆሙ፡፡28ከዚያ ሙሴ እንዲህ አለ፣ “በዚህም ያህዌ እነዚህን ስራዎች ሁሉ እንድሰራ እንደላከኝ ታውቃላችሁ፣ እኔ በራሴ ፈቃድ እነዚህን ነገሮች አልሰራኋቸውም፡፡ 29እነዚህ ሰዎች በተለመደው ሁኔታ ተፈጥሯዊ ሞት ቢሞቱ፣ ያህዌ እኔን አላኝም ማለት ነው፡፡ 30ነገር ግን ያህዌ ምድሪቷን ቢከፍትና እርሷ እንደ ተከፈተ አፍ ሆና፣ ከነቤተሰቦቻቸው ብትውጣቸው፣ ደግሞም በህይወታቸው ሳሉ ወደ ሲኦል ቢወርዱ፣ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች ያህዌን እንደናቁ ታውቃላችሁ፡፡”31ሙሴ እነዚህን ቃላቶች ተናግሮ እንደጨረሰ፣ ምድሪቱ ከነዚህ ሰዎች በታች ተከፈተች፡፡ 32መሬት አፏን ከፈተችና ዋጠቻቸው፣ ቤተሰቦቻቸው፣ እና የቆሬ ሰዎች ሁሉ እንዲሁም ያላቸው ሀብት ሁሉ ተዋጠ፡፡33እነርሱና በየቤተሰባቸው እያንዳንዱ በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ወረዱ፡፡ መሬት በላያቸው ተከደነች፣ እናም በዚህ መንገድ ከማህበረሰቡ መሀል ጠፉ፡፡ 34በዙሪያቸው የነበሩ እስራኤላዊያን ሁሉ ከጩኸታቸው የተነሳ ሸሹ፡፡ እንዲህ እያሉም ጮኹ፣ “መሬት እኛንም ደግሞ ልትውጠን ነው!” 35እሳት ከያህዌ ዘንድ ወጥታ የሚያጥኑትን 250 ሰዎች በላቻቸው፡፡36ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 37”ጥናዎቹ ለእኔ የተለዩ ናቸውና ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአላዓዛር ከሚጤሱት የተረፉትን ጥናዎች እንዲወስድ ንገረው፡፡ ከዚያ ረመጡን ይበትኑት፡፡ 38በኃጠአታቸው ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡትን ሰዎች ጥናዎች ውሰድ፡፡ ጥናዎቹ የተቀጠቀጡ ሰሀኖች ተደርገው ለመሰዊያው መሸፈኛነት ይዋሉ፡፡ ለእኔ የተለዩ ናቸውና፣ እነዚያ ሰዎች በእኔ ፊት ያቅርቧቸው፡፡ እነዚህም ለእስራኤል ሰዎች ለእኔ መገኘት ምልክት ይሆናሉ፡፡”39ካህኑ አልዓዛር የተቃጠሉት ሰዎች ይጠቀሙባቸው የነበሩትን የናስ ጥናዎች ይውሰድና ለመሰዊያው መሸፈኛነት ይቀጥቅጣቸው፣ 40ይህም፤ ለእስራኤል ሰዎች ማስታወሻ እንዲሆን፣ ማንም የአሮን ትውልድ ያልሆነ መጻተኛ በያህዌ ፊት ለማጠን እንዳያቀርብና እንደ ቆሬና እንደ እርሱ ተከታዮች እንዳይሆኑ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዳዘዘው ልክ እንደዚያ እንዳይሆንባቸው ነው፡፡41ነገር ግን በማግስቱ የእስራኤል ማህበረሰብ በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ በማጉረምረም ተነሱባቸው፡፡ እነዲህም አሉ፣ “እናንተ የያህዌን ሰዎች ገድላችኋል፡፡” 42ከዚያም እንዲህ ሆነ፣ ማህበረሰቡ በሙሴና በአሮን ላይ በተቃውሞ ሲሰበሰብ፣ ወደ መገናኛው ድንኳን አሻግሮ ሲመለከቱ፣ እነሆ ደመናው ድንኳኑን ሸፍኖት ነበር፡፡ የያህዌ ክብር ታየ፣ 43እናም ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ወደፊት መጡ፡፡44ከዚያ ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንደህም አለው፣ 45“ከዚህ ማህበረሰብ ፊት ራቅ፣ እኔ በቶሎ አጠፋቸዋለሁ፡፡” ከዚያ ሙሴና አሮን በግምባራቸው ተደፉ፡፡ 46ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ማጥንቱን ውሰድ፣ ከመሰዊያው እሳት ወስደህ አድርግበት፣ በውስጡ እጣን ጨምርበት፣ በቶሎ ወደ ማህበረሰቡ ውሰደው፣ እናም ለእነርሱ አስተሰርይ፣ ምክንያቱም ከያህዌ ዘንድ ቁጣ እየመጣ ነው፡፡ መቅሰፍቱ ጀምሯል፡፡”47ስለዚህም አሮን ሙሴ እንደመራው አደረገ፡፡ ወደ ማህበረሰቡ መሃል ሮጠ፡፡ መቅሰፍቱ በህዝቡ መካከል በፍጥነት መስፋፋት ጀመሮ ነበር፣ ስለዚህም እርሱ እጣኑን ጨምሮ ለህዝቡ ማስተሰርያ አደረገ፡፡ 48አሮን በሙታኑና በህያዋኑ መሀል ቆመ፣ በዚህ መንገድ መቅሰፍቱ ቆመ፡፡49በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 14700 ነበር፣ ይህም በቆሬ ምክንያት የሞቱትን ሳይጨምር ነው፡፡ 50አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ወደ ሙሴ ተመለሰ፣ መቅሰፍቱም አበቃ፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2”ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ ከእነርሱ በትሮችን ውሰድ፣ ከየነገዱ አባቶች አንድ በትር ውሰድ፡፡ ከእያንዱ መሪ አንድ በአጠቃላይ ከየነገድ የተመረጡ አስራ ሁለት በትሮችን ውሰድ፡፡ የእያንዳንዱን ሰው ስም በበትሩ ላይ ጻፍ፡፡3የአሮንን ስም በሌዊ በትር ላይ ጻፍ፡፡ ለእያንዳንዱ መሪ ከየአባቶቹ ነገድ አንድ በትር ሊኖር ያስፈልጋል፡፡ 4በትሮቹን ከአንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ከምስክሩ ኪዳን ፊት አስቀምጣቸው፡፡ 5እንዲህ ይሆናል፣ እኔ የምመርጠው ሰው በትር ታቆጠቁጣለች፡፡ የእስራኤለ ሰዎች በአንተ ላይ የሚያደርጉትን ማጉረምረማቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ፡፡”6ሙሴ ለእስራኤል ሰዎች ተናገረ፡፡ ሁሉም የነገዱ መሪዎች በትሮቻቸውን ሰጡት፣ ከእያንዳንዱ መሪ አንድ በትር፣ ከየነገዱ አባቶች ተመረጠ፣ በአጠቃላይ አስራ ሁለት በትሮች ተመረጡ፡፡ የአሮን በትር ከእነዚህ መሀል ነበር፡፡ 7ከዚያ ሙሴ እነዚህን በትሮች ወስዶ በያህዌ ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡8በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሄደ፣ እናም የሌዊ ነገድ የሆነችው የአሮን በትር አቆጥቁጣ አየ፡፡ እምቡጥ አብቅላ፣ አበባና ለውዝም አፍርታ ነበር! 9ሙሴ በትሮቹን ሁሉ ከያህዌ ፊት ወደ እስራኤል ሰዎች ሁሉ አመጣቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱን በትር አግኝቶ ወሰደ፡፡10ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አስቀምጣት፡፡ ባመፁት ሰዎች ላይ ለበደላቸው ምልክት ይሆን ዘንድ አስቀምጣት፣ ስለዚህም በእኔ ላይ የሚያሰሙትን ማጉረምረም ፍጻሜ ታደርግለታለህ፤ ይህ ካልሆነ ይሞታሉ፡፡” 11ሙሴ ልክ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡12የእስራኤል ሰዎች ሙሴን፣ “እኛ ሁላችንም እዚህ መሞታችን ነው፣ ሁላችንም መጥፋታችን ነው! 13ወደ ያህዌ ማደሪያ ድንኳን የቀረቡ፣ እያንዳንዳቸው ወደዚህ የመጡ ይሞታሉ፡፡ ሁላችንም መጥፋት ይኖርብናልን?” አሉት፡፡
1“ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “አንተ፣ ወንዶች ልጆችህና የአባትህ ቤቶች በቤተ መቅደሱ ላይ ለሚሰራው በደል ተጠያቂ ትሆናላች፡፡ በክህነቱ ላይ ለሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ግን አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ወንዶች ልጆች ብቻ ተጠያቂ ትሆናላችሁ፡፡ 2ከአባትህ ነገድ የሆኑት ሌዋዊያንን በሚመለከት ከአንተ ጋር ይሆኑና አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ስታገለግሉ እንዲረዷችሁ አምጣቸው፡፡3እነርሱ አንተንና መላውን ድንኳን ያገልግሉ፡፡ ሆኖም፣ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ማናቸውም ነገሮች አይቅረቡ ወይም ከመሰዊያው ጋር አይነካኩ፣ አለበለዚያ እነርሱና አንተም ጭምር ትሞታላችሁ፡፡ 4እነርሱ ከአንተ ጋር ሆነው ለመገናኛው ድንኳንና ከድንኳኑ ጋር ለተያያዙ ስራዎች ሁሉ እንክብካቤ ማድረግ አለባቸው፡፡ መጻተኛው ወደ አንተ አይጠጋ፡፡ 5አንተ ለተቀደሰው ስፍራና ለመሰዊያው ሀላፊነት መውሰድ አለብህ፣ እንደገና ቁጣዬ በእስራኤል ሰዎች ላይ እንዳይመጣ ይህን አድርግ፡፡6ከእስራኤል ትውልዶች መሀል ሌዋውያንን የመረጥኩት እኔ ራሴ ነኝ፡፡ እነርሱ ከመገናኛው ድንኳን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመስራት ለእኔ የተሰጡ ለእናንተ ስጦታዎች ናቸው፡፡ 7ከመሰዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ያሉትን አገልግሎቶች ሁሉ በሚመለከት ግን የክህነቱን ስራ የምትሰሩት አንተና ወንዶች ልጆችህ ብቻ ናችሁ፡፡ አንተ ራስህ እነዚያን ሀላፊነቶች መወጣት አለብህ፡፡ እኔ ክህነቱን ስጦታ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፡፡ ማናቸውም መጻተኛ ወደዚህ ቢጠጋ ይገደል፡፡”8ከዚያ ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ለእኔ የሚወዘወዙትን መስዋዕቶችና የእስራኤል ሰዎች ለእኔ የሰጧቸውን ቅዱስ መስዋዕቶች አያያዝ ሀላፊነቶች ሰጥቼሃለሁ፡፡ እነዚህን ስጦታዎች ቀጣይ ድርሻህ አድርጌ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ሰጥቻለሁ፡፡ 9ለያህዌ ሙሉ ለሙሉ ከተለዩ ከእነዚህ ስጦታዎች ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የማይቃጠሉት የአንተ ናቸው፡፡ ህዝቡ የሚያመጣው ማናቸውም መስዋዕት፣ የእህል ቁርባኑን፣ የኃጢአት መስዋዕቱን፣ እና የበደል መስዋዕቱን ሁሉ ጨምሮ፣ እነዚህ እጅግ ቅዱስ የሆኑ ለእኔ የሚለይዋቸውና የሚያመጧቸው ስጦታዎች የአንተና የወንዶች ልጆችህ ይሆናሉ፡፡10አንተ የምትመገባቸው እነዚህ ስጦታዎች፣ ሙሉ ለሙሉ ለእኔ የተለዩ ናቸው፡፡ በመሀል የሚገኝ ማናቸውም ወንድ እነዚህን ስጦዎች ይብላ፡፡ እነርሱ በእናንተ ዘንድ ለእኔ የተለዩ ተደርገው ይቆጠሩ፡፡ 11እነዚህ የእናንተ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ከእስራኤል ሰዎች ከሚሰበሰቡ መስዋዕቶች ውስጥ የተለዩት ስጦታዎቻቸው ሁሉ፣ በእኔ ፊት የተወዘወዙና ለእኔ የቀረቡ ስጦዎች ሁሉ የእናንተ ናቸው፡፡ እነዚህን ለእናንተ፣ ለወንዶች ልጆቻችሁ፣ እና ለሴቶች ልጆቻችሁ፣ ቀጣይ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻለሁ፡፡ እያንዳንዱ በቤተሰብህ ውስጥ የመንጻት ሥርዓት የፈፀመ ሁሉ ከእነዚህ ስጦታዎች መመገብ ይቻላል፡፡12ከዘይቱ ምርጥ የሆነውን፣ ከአዲሱ ወይንና ሰብል ምርጡን፣ ህዝቡ ለእኔ ካቀረበው በኩራቱን፣ እነዚህን ሁሉ ለእናንተ ሰጥቻለሁ፡፡ 13ለእኔ የሚያመጡት፣ በምድራቸው ካለው በመጀመሪያ የደረሰው ፍሬ ሁሉ የአንተ ነው፡፡ በቤተሰብህ ውስጥ ያለ ንጹህ የሆነ ሁሉ እነዚህን ነገሮች መብላት ይችላል፡፡14በእስራኤል ማናቸው ፈጽሞ የተሰጠ ነገር የአንተ ይሆናል፡፡ 15እያንዳንዱ ማህጸን የሚከፍት ሁሉ፣ ሰዎች ለያህዌ የሰጡት በኩር ሁሉ፣ የሰውም ይሁን የእንስሳ በኩር የአንተ ይሆናል፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ሰዎቹ መጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ መልሰው ይግዙ፣ ንጹህ ያልሆኑ እንስሳትን በኩራት መልሰው ይግዙ፡፡ 16በሰዎች ተመልሰው የሚገዙ አንድ ወር ከሞላቸው በኋላ መልሰው ይገዙ፡፡ ከዚያ ሰዎቹ በመቅደሱ ሰቅል ዋጋ መልሰው ከሀያ ጌራ ጋር እኩል ዋጋ ባለው በአምስት ሰቅሎች ዋጋ ሊገዟቸው ይችላሉ፡፡17ነገር ግን የላም በኩር፣ ወይም የበግ በኩር፣ ወይም የፍየል በኩር ከሆነ እነዚህን እንስሳት መልሰህ አትግዛ፤ እነዚህ ለእኔ የተሰዉ ናቸው፡፡ ለእኔ ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ፣ ደማቸውን በመሰዊያ ላይ እርጨው፣ ስባቸውን በእሳት የቀረበ መስዋዕት አድርገህ ኣቃጥለው፡፡ 18ስጋቸው ለአንተ ይሁን፡፡ ልክ እንደ ሚወዘወዘው ፍርምባና እንደ ቀኙ ወርች ስጋቸው የአንተ ይሆናል፡፡19የእስራኤል ሰዎች ለእኔ ያቀረቧቸውን ቅዱስ የሆኑ መስዋዕቶች ሁሉ እኔ፤ ለአንተ፣ ለወንድ ልጆችህ እና ለሴት ልጆችህ ቀጣይ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፡፡ ለጨው ኪዳንና ለዘለዓም የአንድነት መስዋዕት ሆነው በፊቴ ከአንተና ከትውልድህ ጋር ይኖራሉ፡፡” 20ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “አንተ በህዝቡ ምድር ርስት አይኖርህም፣ ወይንም ደግሞ በህዝቡ መሀል የሀብት ድርሻ አይኖርህም፡፡ በእስራኤል ህዝብ መሀል እኔ ድርሻህና ርስትህ ነኝ፡፡21እስራኤላዊያን የሚያመጡትን አስራት ሁሉ፣ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚሰጡት አገልግሎት ድርሻቸው አድርጌ ለሌዊ ትውልድ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ 22ከአሁን አንስቶ ከእስራኤል ህዝቡ ወደ መገናኛው ድንኳን አይቅረብ፣ ከቀረቡ በኃጢአታቸው ሀላፊነትን ይወስዳሉ፤ እናም ይሞታሉ፡፡23ከመገናኛው ድንኳን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ሌዋውያን ይስሩ፡፡ ይህን በሚመለከት ለማናቸውም ኃጢአት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ይህ በእናተ ህዝብ ትውልዶች ሁሉ ቀዋሚ ህግ ይሆናል፡፡ በእስራኤል ህዝብ መሀል ሌዋውያን ርስት ሊኖቸው አይገባም፡፡ 24እስራኤላዊያን መባ አድርገው ለእኔ ያቀረቡትን አስራት እኔ ለሌዋውያን ርስታቸው አድርጌ የሰጠሁት እነዚህን ነው፡፡ ለዚህም ነው እንዲህ የምላቸው፣ ‘እነርሱ በእስራኤል ህዝብ መሀል ርስት አይኖራቸውም፡፡’”25ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 26”ለሌዋውያን እንዲህ በላቸው፣ ‘ከእነርሱ የአንተ ርስት አድርጎ ያህዌ ለእናንተ የሰጣችሁን አስራት ከእስራኤል ሰዎች ስትቀበሉ፣ ከዚያ አስራት ለእርሱ አንድ አስረኛውን መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፡፡ 27እናንተ የምታቀርቡት መስዋዕት በእናንተ ዘንድ ከአውድማ እንደ ቀረበ የእህል አስራት ወይም ከወይን መጥመቂያ እንደ ቀረበ አስራት ሊቆጠር ይገባዋል፡፡28እንደዚሁም ከእስራኤል ሰዎች ከተቀበላችሁት አስራት ሁሉ ለያህዌ መባ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ከእነዚህም ለካህኑ ለአሮን ለእግዚአብሔር ከቀረበው ስጦታ መስጠት አለባች፡፡ 29ከተቀበላችሁት ስጦታ ሁሉ፣ ከእያንዳንዱ ለያህዌ መባ መስጠት አለባችሁ፡፡ ይህንን ምርጥ ከሆነው ሁሉና ለእናንተ ከሰጠኋችሁ እጅግ ከተቀደሱት ነገሮች ማድረግ አለባችሁ፡፡’30ስለዚህም እንደዚህ በላቸው፣ ‘ከተቀበላችሁት ምርጡን ስታቀርቡ፣ ይህ በሌዋውያን ዘንድ ከአውድማ እንደቀረበ ምርትና ከወይን መጥመቂያ እንደቀረበ ሊቆጠር ይገባል፡፡ 31የተቀረውን ስጦታዎቻችሁን በማንኛውም ስፍራ ልትበሉ ትችላላችሁ፣ እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ብሉት፣ ምክንያቱም በመገናኛው ድንኳን ለምትሰጡት አገልግሎት ክፍያችሁ ነው፡፡ 32ከተቀበላችሁት ምርጥ የሆነውን ለያህዌ ካቀረባችሁ፣ ያን በመብላታችሁና በመጠጣታችሁ ምንም አይት በደል በራሳችሁ ላይ አታመጡም፡፡ ነገር ግን የተቀደሱ የእስራኤል ህዝቦች ስጦታዎች አታቃሉ፣ አሊያ ትሞታላች፡፡
1ያህዌ ለሙሴና ለአሮን ተናገረ፤ እንዲህም አለ፣ 2”ይህ እናንተን የማዛችሁ ትዕዛዝ መታሰቢየ ነው፡፡ የእስራኤል ሰዎች ወደ አንተ ቀንበር ተጭኟት የማታውቅ፣ እንከን ወይም ነውር የሌለባት ቀይ ጊደር እንዲያመጡ ንገራቸው፡፡3ጊደሯን ለካህኑ ለአልዓዛረ ስጠው፡፡ ከሰፈር ውጭ ያውጣት አንድ ሰው በፊቱ ይረዳት፡፡ 4ካህኑ አልአዛር ከጊደሯ ደም በጣቱ ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ፊት ባለው አቅጣጫ ሰባት ጊዜ ይርጨው፡፡ 5ሌላ ካህን እርሱ እያየ ጊደሯን ያቃጥላት፡፡ ቆዳዋን፣ ስጋ እና ደሟን ከፈርሷ ጋር ያቃጥል፡፡ 6ካህኑ የዝግባ እንጨት፣ ሂሶጵ፣ እና ደማቅ ሱፍ ይውሰድና ጊደሯ በምትቃጠልበት እሳት ውስጥ ይጨምር፡፡7ከዚየ ልብሱን ይጠብ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፡፡ ከዚያ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ከቆየበት ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡ 8ጊደሯን ያቃጠለው ሰው ልብሱን በውሃ ይጠብ ገላውንም ይታጠብ፡፡ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡9ንጹህ የሆነ አንድ ሰው የጊደሯን አመድ አፍሶ ከሰፈር ውጭ ንጹህ በሆነ ስፍራ ይድፋው፡፡ ይህ አመድ ለእስራኤል ሰዎች ለማህበረሰቡ ይጠበቅ፡፡ አመዱ ከኃጢአት መስዋዕት የተገኘ እንደመሆኑ፣ ከኃጢአት ለመንጻት በውሃ ይበጠብጡታል፡፡ 10የጊደሯን አመድ ያፈሰው ሰው ልብሱን ይጠብ፡፡ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡ ይህ ለእስራኤላዊያንና ከእነርሱ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞችም ቋሚ ህግ ይሆናል፡፡11ማንም የሞተን ሰው አካል የነካ ሁሉ ለሰባት ቀናት እርኩስ ነው፡፡ 12እንዲህ ያለው ሰው በሶስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፡፡ ከዚያ ንጹህ ይናል፡፡ ነገር ግን በሶስተኛው ቀን ራሱን ካላነጻ፣ በሰባተኛው ቀን ንጹህ አይሆንም፡፡ 13የሞተን ሰው የነካ ማንም ቢሆን፣ የሞተን ሰው የነካ ሁሉ፣ እናም ራሱን ያላነጻ ይህ ሰው የያህዌን ማደሪያ ያረክሳል፡፡ ያ ሰው ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ፤ ምክንያቱም ከእርኩሰት የሚያነጻው ውሃ አልተረጨበትም፡፡ እርኩስ ሆኖ ይቆያል፣ ያለመንጻቱ በእርሱ ላይ ይቆያል፡፡14አንድ ሰው በድንኳን ውስጥ በሚሞትበት ጊዜ ህጉ ይህ ነው፡፡ ወደ ድንኳኑ የገባ እያንዳንዱ ሰውና ቀድሞውኑም በድንኳኑ ውስጥ የነበረ ሰው ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለም፡፡ 15ያልተከደነና ያልተሸፈነ ማናቸውም ዕቃ ይረክሳል፡፡ 16በተመሳሳይ፣ በሰይፍ የተገደለንም ሰው ሆነ ማናቸውንም በሌላ ሁኔታ የሞተን ሰው፣ ወይም የሞተን ሰው አጽም፣ ወይም መቃብር የነካ ማናቸውም ከድንኳን ውጭ ያለ ሰው ለሰባት ቀናት ንጹህ አደለም፡፡17ለረከሰ ሰው ይህን አድርግ፡ ከተቃጠለው የኃጢአት መስዋዕት ጥቂት አመድ ውሰድና በንጹህ ውሃ በዕቃ ውስጥ በጥብጠው፡፡ 18ንጹህ የሆነ ሰው ሂሶጵ ይውሰድና ውሃው ውስጥ ይንከረው፤ ከዚያም በድንኳኑ ላይ፣ በድንኳኑ ውስጥ ባሉ ዕቃዎች ሁሉ ላይ፣ በዚያ በሚገኙ ሰዎች ላይ፣ እንዲሁም የሞተ ሰውን አጽም፣ የተገደለን ሰው፣ የሞተን ሰው ወይም መቃብር በነካ ሰው ላይ ይርጨው፡፡ 19በሶስተኛው ቀንና በሰባተኛው ቀን፣ ንጹህ የሆነው ሰው ንጹህ ያልሆነውን ሰው ይርጨው፡፡ ያልነጻው ሰው በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፡፡ ልብሱን ይጠብ ገላውንም በውሃ ይታጠብ፡፡ ምሽት ላይ ንጹህ ይሆናል፡፡20ነገር ግን ሳይነጻ የሚቆይ ማናቸው ሰው፣ ራሱን ለማንጻት ያልፈቀደ ሰው ያ ሰው ከማህበረሰቡ ተለይቶ ይጥፋ፣ ምክንቱም የያህዌን መቅደስ አርክሷል፡፡ ከእርኩሰት የሚያነጻው ውሃ በእርሱ ላይ አልተረጨምና እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡ 21ለእነዚህ ሁኔታዎች ይህ ቀጣይ ህግ ይሆናል፡፡ ለመንጻት የሚሆንን ውሃ የሚረጨው ሰው ልብሶቹን ይጠብ፡፡ የሚያነጻውን ውሃ የሚነካ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 22ማናቸውም ንጹህ ያልሆነ ሰው የነካው ነገር እርኩስ ይሆናል፡፡ ያንን የነካ ሰው እስከ ምሽት እርኩስ ይሆናል፡፡”
1የእስራኤል ሰዎች፣ መላው ማህበረሰብ በመጀመሪያው ወር ወደ ሲና ምድረ በዳ ሄደው በቃዴስ ሰፈሩ፡፡ማርያም በዚያ ሞታ ተቀበረች፡፡2ማህበረሰቡ ውሃ ተጠማ፣ ስለዚህ በሙሴና በአሮን ላይ አምጸው ተሰበሰቡ፡፡ 3ህዝቡ በሙሴ ላይ አጉረመረሙ፡፡ እንዲህም አሉ፣ “ወገኖቻችን እስራኤላውያን በያህዌ ፊት በሞቱበት ጊዜ እኛም ብንሞት ኖሮ ይሻል ነበር!4እዚህ እንሞት ዘንድ የያህዌን ማህበረሰብ፣ እኛንና ከብቶቻችንን ለምን ወደዚህ ምድረበዳ አመጣችሁን? 5ወደዚህ አስፈሪ ስፍራ ልታመጡን ለምን ከግብጽ እንድንወጣ አደረጋችሁን? እዚህ፤ እህል፣ በለስ፣ ወይም ወይም ሮማን የለም፡፡ የሚጠጣም ውሃ የለም፡፡”6ስለዚህ ሙሴና አሮን ከጉባኤው ፊት ወጥተው ሄዱ፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ሄደው በግምባራቸው ተደፉ፡፡ ከዚያ የያህዌ አንጸባራቂ ክብር ታያቸው፡፡7ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 8“በትርህን ውሰድና አንተና ወንድምህ አሮን ማህበረሰቡን ሰብስቡ፡፡ በፊታቸው ለዓለቱ ተናገር፣ ውሃ እንዲያፈስም አለቱን እዘዘው፡፡ ከዚያ ዓለት ውሃ አውጥተህ ትሰጣቸዋለህ፣ ማህበረሰቡና ከብቶቻቸው ይጠጡ ዘንድ ውሃ ስጣቸው፡፡” 9ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው ከያህዌ ፊት በትሩን ወሰደ፡፡10ከዚያ ሙሴና አሮን ጉባኤውን በአለቱ ፊት ሰበሰቡ፡፡ ሙሴ ጉባኤውን እንዲህ አለ፣ “እናንተ አመጸኞች፣ አሁን ስሙ፡፡ ከዚህ ዓለት ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን?” 11ከዚያ ሙሴ እጁን አንስቶ በበትሩ አለቱን ሁለት ጊዜ መታው፣ እናም ብዙ ውሃ ወጣ፡፡ ማህበረሰቡ ጠጣ፣ እንዲሁም ከብቶቻቸው ጠጡ፡፡12ከዚያ ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ “እኔን ስላላመናችሁ ወይም በእስራኤል ሰዎች ዐይኖች ፊት ቅዱስ አድርጋች ስላለያችሁኝ፣ ይህን ጉባኤ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር አታስገቧቸውም፡፡” 13ይህ ቦታ የመሪባ ውሃ ተብሎ ተጠራ፣ ምክንያቱም በዚያ የእስራኤል ሰዎች ከያህዌ ጋር ተጣልተው ነበር፣ እርሱም ራሱን በቅድስናው ገለፀላቸው፡፡14ሙሴ ከቃዴስ መልዕክተኞችን ወደ ኤዶም ንጉስ ላከ፡ ወንድምህ እስራኤል ይህን ይላል፡ “በእኛ ላይ የደረሱትን አስቸጋሪ ነገሮች ታውቃለህ፡፡ 15አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወርደው ለዘመናት በግብጽ መኖራቸውን ታውቃለህ፡፡ ግብጻውያን በእኛና በአባቶቻችን ላይ እጅግ ከፉብን፡፡ 16እኛ ወደ ያህዌ ስንጮህ፣ እርሱ ድምጻችንን ሰምቶ መልዓክ ልኮ ከግብጽ አወጣን፡፡ እነሆ፣ በምድርህ ዳርቻ በምትገኘው በቃዴስ እንገኛለን፡፡17በምድርህ እንድናልፍ እንድትፈቅድልን እጠይቅሃለሁ፡፡ በእርሻዎች ወይም በወይን ሥፍራዎች ውስጥ አናልፍም፣ አሊያም ከጉድጓዶቻችሁ ውሃ አንጠጣም፡፡ የንዱን አውራ ጎዳና ይዘን እንሄዳለን፡፡ ድንበርህን እስክናልፍ ድረስ ወደ ግራም ወደ ቀኝም አንልም፡፡”18የኤዶም ንጉስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “በዚህ በኩል ማለፍ አትችሉም፡፡ ይህን ብታደርጉ፣ ሰይፍ ይዤ እወጣባችኋለሁ፡፡” 19ከዚያ የእስራኤል ሰዎች እንዲህ አሉት፣ “እኛ በአውራ ጎዳናው እንሄዳለን፡፡ እኛም ሆን ከብቶቻችን ውሃህን ብንጠጣ፣ ለዚያም እንከፍላለን፡፡ ሌላ ምንም ነገር ሳናደርግ በእግራችን እንለፍ፡፡”20የኤዶም ንጉስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፣ “በዚህ በኩል አታልፉም፡፡” ስለዚህም የኤዶም ንጉስ በብርቱ ክንድ አያሌ ወታደሮች ይዞ በእስራኤላዊያን ላይ መጣባቸው፡፡ 21የኤዶም ንጉስ እስራኤላውያን በድንበሩ አቋርጠው እንዳያልፉ ተቃወመ፡፡ በዚህ ምክንያትና እስራኤል ከኤዶም ምድር ተመለሱ፡፡22ስለዚህ ህዝቡ ከቃዴስ ተነስቶ ተጓዘ፡፡ የእስራኤል ህዝብ፣ መላው ማህበረሰብ ወደ ሖር ተራራ መጣ፡፡ 23ያህዌ በሖር ተራራ ለሙሴና አሮን ተናገራቸው፡፡ እንዲህም አለ፣ 24”አሮን ለእስራኤል ህዝብ ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባምና ወደ አባቶቹ ይሰበሰባል፡፡ ይህም የሚሆነው እናንተ ሁለታችሁም በመሪባ ውሃ በእኔ ቃሎች ላይ ስላመፃችሁ ነው፡፡25አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ አምጣቸው፡፡ 26የአሮንን የክህነት ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቀህ ልጁን አልዓዛርን አልብሰው፡፡ አሮን በዚያ ይሞትና ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል፡፡”27ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡ መላው ማህበረሰብ እያየ ወደ ሖር ተራራ ወጡ፡፡ 28ሙሴ የአሮንን የክህነት ልብሶች ከእርሱ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው፡፡ አልዓዛር በተራራው አናት ላይ በዚያ ሞተ፡፡ ከዚያ ሙሴና አልዓዛር ከተራራው ወደ ታች ወረዱ፡፡ 29መላው ማህበረሰብ አሮን እንደ ሞተ ባየ ጊዜ፣ ጠቅላላው አገሩ ለሰላሳ ቀናት ለአሮን አለቀሰ፡፡
1በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓረድ ንጉስ እስራኤል ወደ አታሪም እየመጣ በመንገድ ላይ መሆኑን ሲሰማ፣ ከእስራኤል ጋር ተዋግቶ አንዳንዶቹን በምርኮ ወሰደ፡፡ 2እስራኤል ለያህዌ እንዲህ ብሎ ማለ፣ “በእነዚህ ህዝቦች ላይ ድል ብትሰጠን፣ ከዚያም ከተማቸውን ሙሉ ለሙሉ እናጠፋለን፡፡” 3ያህዌ የእስራኤልን ድምጽ ሰምቶ በከነዓናዊያን ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ ሙሉ ለሙሉ እነርሱንና ከተማቸውን አጠፉ፡፡ ያ ስፍራ ሖርማ ተብሎ ተጠራ፡፡4ከሖር ተራራ ተነስተው ኤዶም ምድር ዙሪያ ለመድረስ በቀይ ባህር መንገድ ተጓዙ፤ ህዝቡ በመንገድ ሳለ እጅግ ተስፋ ቆረጡ፡፡ 5በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ እንዲህ ሲሉ አጉረመረሙ፡፡ “በበረሃ እንሞት ዘንድ ለምን ከግብጽ አወጣችሁን በዚህ ዳቦ የለም፣ አንዳች ውሃ የለም፣ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል፡፡”6ከዚያ ያህዌ በሰዎቹ መካከል መርዛም እባቦችን ሰደደ፡፡ እባቦቹ ሰዎችን ነደፉ፤ ብዙ ሰዎችም ሞቱ፡፡ 7ሰዎች ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉ፣ “እኛ በድለናል ምክንያቱም በያህዌና በአንተ ላይ በተቃውሞ ተናግረናል፡፡ እባቦቹን ከእኛ እንዲያርቅ ወደ ያህዌ ጸልይልን፡፡” ስለዚህም ሙሴ ለህዝቡ ጸለየ፡፡8ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እባብ አብጅና በምሰሶ ላይ አንጠለጠለው፡፡ እንዲህ ይሆናል፣ የተነደፈ ሁሉ ያንን ከተመለከተ ይድናል፡፡” 9ስለዚህም ሙሴ የናስ እባብ አበጅቶ በምሰሶ ላይ አንጠለጠለው፡፡ እባብ ማናቸውንም ሰው በነከሰ ጊዜ፣ ሰውየው ወደ ናሱ እባብ ከተመለከተ ይድናል፡፡10ከዚያ የእስራኤል ሰዎች ተጉዘው በአቦት ሰፈሩ፡፡ 11ከአቦት ተጉዘው በስተምስራቅ በሞአብ አንጻር በዒዮዓባሪም በምድረ በዳ ሰፈሩ፡፡12ከዚያ ተጉዘው በዘሬድ ሸለቆ ሰፈሩ፡፡ 13ከዚያ ተጉዘው እስከ አሞራዊያን ድንበር በሚዘልቀው በምድረበዳ ባለው በአሮን ወንዝ ሌላኛው ዳርቻ ሰፈሩ፡፡ የአርኖን ወንዝ በሞዐብና አሞራዊያን መሀል የሞአብን ወሰን ያበጃል፡፡14በያህዌ የጦርነት መጽሐፍ ጥቅልል፣ በሱፋ ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ እና የአርኖን ሸለቆዎች፣ 15ወደ ዔር ከተማና ወደ ሞአብ ዳርቻ የሚወስዱ የሸለቆዎች ቁልቁለት” ተብሎ የተፃፈው ስለዚህ ነው፡፡16ከዚያ ተነስተው ወደ ብኤር ተጓዙ፣ ይህም ስፍራ የውሃ ጉድጓድ የሚገኝበትና ያህዌ ሙሴን፡ - “ውሃ እሰጣቸው ዘንድ ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸው” ብሎ የተናገረበት ነው፡፡17ከዚያ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፡፡ “አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ፡፡ ስለዚህ እናንተም ዘምሩ፡፡ 18መሪዎቻችን የቆፈሩት ጉድጓድ፣ የተከበሩ የህዝብ አለቆች በበትረ መንግስታቸውና በበትሮቻቸው የማሱት ጉድጓድ፡፡” ከዚያ ከምድረበዳው ተነስተው ወደ መቴና ተጓዙ፡፡19ከመቴና ተነስተው ወደ ነሃሊኤል፣ ከነሃሊኤል ወደ ባሞት እና ከባሞት በሞአብ ምድር ወደሚገኘው ሸለቆ ተጓዙ፡፡ 20በፈስጋ ተራራ ጫፍ ሆኖ ምድረበዳው ቁልቁል የሚታይበት ይህ ስፍራ ነው፡፡21ከዚያ እስራኤል ወደ አሞራዊያን ንጉስ ወደ ሴዎን እንዲህ ብለው መልእክተኞችን ላኩ፣ 22”በምድርህ እንለፍ፡፡ ወደ እርሻዎች ወይም ወደ ወይን አትክልቶች አንገባም፡፡ ከጉድጓዶችህ ውሃ አንጠጣም፡፡ ድንበርህን እስክናልፍ ድረስ በንጉሱ አውራ መንገድ እንጓዛለን፡፡” 23ንጉስ ሴዎን ግን እስራኤልን በድንበሩ እንዲያልፉ አልፈቀደም፡፡ ይልቁንም፣ ሴዎን ወታደሮቹን አሰባስቦ በምድረ በዳ እስራኤልን ለመውጋት ወጣ፡፡24እስራኤል የሴዎንን ጦር በሰይፍ ወግቶ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ወንዝና እስከ አሞን ሰዎች ወሰን ድረስ ምድሩን ወሰደ፡፡ የአሞን ሰዎች ድንበር ግን የተመሸገ ነበር፡፡ 25እስራኤል የአሞራዊያንን ከተሞች ሁሉ፣ ሐስቦንንና መንደሮቹን ጭምር ይዞ በእነዚያ ውስጥ ተቀመጠ፡፡ 26ሐስቦን ከሞአብ የቀድሞ ንጉስ ጋር የተዋጋው የአሞራዊያን ንጉስ የሴዎን ከተማ ነበረች፡፡ ሴዎን እስከ አርኖን ወንዝ ድረስ ያለውን ምድሩን ሁሉ ወሰደበት፡27በምሳሌያዊ ንግግር የተናገሩ፣ “ወደ ሐሴቦን ኑ፡፡ የሴዎን ከተማ እንደ ገና ትገንባና ዳግም ትታነጽ፡፡ 28እሳት ከሐሴቦን ተንቦገቦገ፣ ነበልባል ከሴዎን ከተማ የሞአብን ዔር አጠፉ፣ ደግሞም የአርን ተራሮች ባለቤቶችን በላ፡፡29ሞአብ ዋይታ ሆነብህ! የከሞስ ህዝብ እናንተ ጠፋችሁ፡፡ ለአሞራውያን ንጉስ ለሴዎን ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት ሴቶች ልጆቹን ለምርኮ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ 30እኛ ግን ሴዎንን አሸንፈናል፡፡ ሐስቦን እስከ ዴናን ድረስ ወድማለች፡፡ ወደ ሜድባ እስከምታደርሰው ኖፋ ድረስ ሁሉንም አሸንፈናቸዋል፡፡”31ስለዚህ እስራኤል በአሞራዊያን ምድር መኖር ጀመረ፡፡ 32ከዚያ ሙሴ ሰዎችን ምድሪቱን እንደያዙ ወደ ኢያዜር ላከ፡፡ እነርሱ መንደሮቿን ማረኩ በዚያ የነበሩትንም አሞራዊያን አባረሩ፡፡33ከዚያ ወደ ባሳን በሚስደው መንገድ ዞረው ሄዱ፡፡ የባሳን ንጉስ ዐግ በእነርሱ ላይ ዘመተ፣ እርሱና ሰራዊቱ ሁሉ በኤድራይ ሊዋጓቸው ወጡ፡፡ 34በዚያን ጊዜ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እርሱን አትፈራው፣ ምክንያቱም እኔ በእርሱ፣ በሰራዊቱና በምድሩ ላይ ሁሉ ላይ ድል ሰጥቼሃለሁ፡፡ በሔስቦን እንደነበረው በአሞራዊያን ንጉስ በሴዎን ላይ እንዳደረከው በእርሱ ላይ አድርግበት፡፡” 35ስለዚህም እርሱን፣ ወንዶች ልጆቹን እና መላውን ሰራዊቱን አንድም ሰው በህይወት እስከ ማይተርፍለት ድረስ ፈጇቸው፡፡ ከዚያም ምድሩን ወረሱ፡፡
1የእስራአል ህዝብ ከከተማዋ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሌላ ዳርቻ ኢያሪኮ አጠገብ ወደሚገኘው የሞአብ ሜዳ ደርሰው እስኪሰፍሩ ደረስ ተጓዙ፡፡2የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞራዊያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ፡፡ 3ሞአብ የእስራኤልን ህዝብ በጣም ፈርቶ ነበር ምክንያቱም ብዙ ነበሩ፣ እናም ሞአብ በእስራኤል ህዝብ ተሸብሮ ነበር፡፡ 4የሞብ ንጉስ ለምድያም ሽማግሌዎች፣ “ይህ ብዙ ህዝብ፣ በሬ በሜዳ ላይ ያለን ሳር በልቶ እንደሚጨርስ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ በልቶ ይጨርሳል፡፡” አለ፡፡ በዚያን ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉስ ነበር፡፡5እርሱም በአገሩና በወገኖቹ መሀል በኤፍራጦስ ወንዝ አጠገብ በፋቱራ ወደተቀመጠው የቢያር ልጅ በልዓም መልዕክተኞችን ላከ፡፡ አስጠርቶትም እንዲህ አለው፣ “እነሆ፣ ከግብጽ አንድ ህዝብ ወደዚህ መጥቷል፡፡ የምድርን ፊት ሸፍነዋል፣ ደግሞም እዚሁ አጠገቤ ናቸው፡፡ 6ስለዚህ አሁን መጥተህ ይህን ህዝብ ርገምልኝ፣ ምክንያቱም ከእኔ አቅም በላይ ናቸው፡፡ ምናልባት ከረገምክልኝ በኋላ እነርሱን ለማጥቃትና ከምድሪቱ ለማባረር እችል ይሆናል፡፡ የባረከው ሁሉ እንደሚባረክ አውቃለሁ፣ የረገምከው ሁሉ እንደሚረገም አውቃለሁ፡፡”7ስለዚህ የሞአብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎች የምዋርቱን ዋጋ ይዘው ሄዱ፡፡ ወደ በለዓም መጥተው የባላቅን ቃል ነገሩት፡፡ 8በለዓምም እንዲህ አላቸው፣ “ዛሬ ምሽት እዚህ እደሩ፡፡ ያህዌ የሚለኝን አሳውቃችኋለሁ፡፡” ስለዚህም የሞብ መሪዎች ያን ምሽት ከበለዓም ዘንድ ተቀመጡ፡፡9እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፣ “ወደ አንተ የመጡት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው” 10በለዓም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “የሞአብ ንጉስ የሴፎር ልጅ ባላቅ፣ እነርሱን ወደ እኔ ልኳቸዋል፡፡ እንዲህም አለ፣ 11‘እነሆ፣ ከግብጽ የመጡ ሰዎች የምድሬን ገጽ ሸፍነዋል፡፡ አሁን መጥተህ እነርሱን ርገምልኝ፡፡ ይህ ከሆነ ምናልባት እነርሱን መዋጋትና ማባረር እችል ይሆናል፡፡”12እግዚአብሔር ለበለዓም እንዲህ መለሰለት፣ “ከእነዚህ ሰዎች ጋር መሄድ የለብህም፡፡ የእስራአልን ህዝብ መርገም የለብህም ምክንያቱም እነርሱ የተባረኩ ናቸው፡፡” 13በለዓም በጠዋት ተነስቶ ለባላቅ መሪዎች እንዲህ አላቸው፣ “ወደ ምድራችሁ ተመልሳችሁ ሂዱ ምክንያቱም ያህዌ ከእናንተ ጋር እሄድ ዘንድ አልፈቀደልኝም፡፡ 14ስለዚህም የሞብ መሪዎች ተመልሰው ወደ ባላቅ ሂዱ፡፡ እንደህም አሉት፣ “በለዓም ከእኛ ጋር ለመምጣት አልፈቀደም፡፡”15ባላቅ እንደገና ከመጀመሪያዎቹ መልዕክተኞች የከበሩ ብዙ መሪዎችን ላከ፡፡ 16እነርሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፣ “የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ብሏል፣ ‘እባክህ ወደ እኔ ለመምጣት አንዳች ነገር አያግድህ፣ 17ምክንያቱም እጅግ ከፍ ያለ ክፍያ እከፍልሃለሁ፣ ታላቅ ክብርም እሰጥሃለሁ፣ ደግሞም እንዳደርገው የምትነግረኝን ሁሉ አደርጋሁ፡፡ ስለዚህ እባክህ መጥተህ ይህን ህዝብ ርገምልኝ”18በለዓለም ለባላቅ ሰዎች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “ባላቅ ብርና ወርቅ የሞላበትን ቤተ መንግስቱን ቢሰጠኝ እንኳን ከአምላኬ፣ ከያህዌ ቃል አልፌ መሄድ አልችልም፣ ደግሞም እርሱ ከነገረኝ አሳንሼ ወይም ጨምሬ አላደርግም፡፡ 19ስለዚህ አሁን፣ እባካችሁ ያህዌ የሚለኝን ተጨማሪ ነገር አውቅ ዘንድ ዛሬ ምሽትም ደግሞ በዚህ እደሩ፡፡” 20እግዚአብሔር በምሽት ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፣ “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ እስከ መጡ ድረስ ተነስተህ ከእነርሱ ጋር ሂድ፡፡ ነገር ግን እንድታደርገው የምነግርህን ብቻ አድርግ፡፡”21በለዓም በጠዋት ተነስቶ አህያውን ጫንና ከሞአብ መሪዎች ጋር ሄደ፡፡ 22ነገር ግን በመሄዱ፣ የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደ፡፡ የያህዌ መልአክ፣ በአህያው ላይ ተቀምጦ የሚሄደውን በለዓምን ሊቃወመው በመንገድ ላይ ቆመ፡፡ የበለዓም ሁለቱ አገልጋዮቹም አብረውት ነበሩ፡፡ 23አህያዋ የያህዌን መልአክ የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በመንገድ ላይ ቆሞ አየችው፡፡ አህያዋ ከመንገድ ዘወር ብላ ወደ ሜዳው ሄደች፡፡ በለዓለም አህያይቱን ወደ መንገድ እንድትለስ መታት፡፡24የያህዌ መልአክ በመንገዱ ጠባብ መተላፊያ ላይ በወይን እርሻው መሀል፣ በስተቀኙና በስተግራው ግድግዳ ባለበት ስፍራ ቆመ፡፡ 25አህያይቶ የያህዌን መልአክ አየች፡፡ ወደ ግድግዳው ተጠግታ የበለዓምን እግር አጣበቀችው፡፡ በለዓም እንደገና አህያይቱን መታት፡፡26የያህዌ መልአክ እንደ ገና ራቅ ብሎ ሄዶ ወደ የትኛውም አቅጣጫ መዞሪያ በሌለበት ሌላ ጠባብ መተላፊያ ስፍራ ቆመ፡፡ 27አህያይቱ የያህዌን መልአክ አይታ ከበለዓም በታች ተኛች፡፡ የበለዓም ቁጣ ነደደ፣ በበትሩም አህያይቱን መታት፡፡28ያህዌ የአህያይቱን አፍ ስለከፈተ መናገር ቻለች፡፡ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “እነዚህን ሶስት ጊዜያት እንድትመታኝ የሚያደርግ ምን ነገር አደረግሁብህ” 29በለዓም አህያይቱን፣ “በእኔ ላይ የማይረባ ድርጊት ስለፈጸምሽ ነው፡፡ በእጄ ላይ ሰይፍ ቢኖር እወድ ነበር፡፡ በእጄ ላይ ሰይፍ ቢኖር ኖሮ፣ ይህን ጊዜ ገድዬሽ ነበር” አላት፡፡ 30አህያይቱ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ስትቀመጥብኝ የኖርክብኝ አህያህ አይደለሁምን? ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ነገር በአንተ ላይ የማድረግ ልማድ ነበረኝን?” በለዓም “እይ” አለ፡፡31ከዚያ ያህዌ የበለዓምን ዐይኖች ከፈተ፣ እናም የያህዌ መልአክ በእጁ ሰይፉን ይዞ በመንገዱ ላይ ቆሞ አየ፡፡ በለዓም ዝቅ ብሎ በግምባሩ ተደፋ፡፡ 32የእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “አህያህን ለምን በእዚህ ሶስት ጊዜያት መታሀት የምቃወምህ ሆኜ መጥቻለሁ ምክንያቱም ድርጊቶችህ በፊቴ መጥፎዎች ነበሩ፡፡ 33አህያይቱ አይታኝ በእነዚህ ሶስት ጊዜያት ከእኔ ዞር አለች፡፡ እርሷ ዞር ባትልልኝ ኖሮ፣ በእርግጥ አንተን እገድልህና የእርሷን ነፍስ እተው ነበር፡፡”34በለዓም ለያህዌ መልአክ እንዲህ አለ፣ “እኔ በድያለሁ፡፡ እኔን ተቃውመህ በፊቴ ቆመህ እንደነበር አላወቅሁም፡፡ አሁን እንግዲህ፣ ይህ ጉዞ አንተን ደስ ካላሰኘ፣ ወደመጣሁበት እመለሳለሁ፡፡” 35የያህዌ መልአክ ግን በለዓምን እንዲህ አለው፣ “ከሰዎቹ ጋር ጉዞህን ቀጥል፡፡ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ መናገር አለብህ፡፡” ስለዚህም በለዓም ከባላቅ መሪዎች ጋር ሄደ፡፡36ባላቅ የበለዓምን መምጣት ሲሰማ፣ ሞአብ ውስጥ ወዳለችው በድንበር ላይ ወደምትገኘው አርኖን ከተማ ሊቀበለው ወጣ፡፡ 37ባላቅ በለዓምን እዲህ አለው፣ “እንዲጠሩህ ሰዎችን ወደ አንተ አልላኩም ነበርን? ለምን ወደ እኔ አልመጣህም? እኔ ላከብርህ አልችልምን?”38ከዚያም በለዓም ለባላቅ መለሰለት፣ “በእርግጥ ወደ አንተ መጥቻለሁ፡፤ አሁን አንዳች ነገር ለመናገር እኔ አንዳች ሀይል አለኝን? መናገር የምችለው እግዚአብሔር በአፌ ላይ ያስቀመጠውን ቃል ብቻ ነው፡፡” 39በለዓም ከባላቅ ጋር ሄደ፣ እነርሱም ወደ ቂርያት ሐጾት ደረሱ፡፡ 40ከዚያ ባላቅ በሬዎችንና በጎችን ሰዋ፣ ለበለዓምና ከእርሱ ጋር ለነበሩ መሪዎችም ሰጣቸው፡፡41ማለዳ፣ ባላቅ በለዓምን ወደ ካሞት በኣል ይዞት ሄደ፡፡ በለዓም ከዚያ ሆኖ ማየት የሚችለው በሰፈሮቻቸው ካሉት እስኤላዊያን ጥቂቶቹን ብቻ ነበር፡፡
1በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “በዚህ ሰባት መሰዊያዎችንና ሰባት በሬዎችን እንዲሁም ሰባት አውራ በጎችን አዘጋጅልኝ፡፡” 2ስለዚህም ባላቅ በለዓም እንደጠየቀው አደረገ፡፡ ከዚያም ባላቅና በለዓም በእያንዳንዱ መሰዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረቡ፡፡ 3ከዚያ በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “አንተ በሚቃጠል መስዋዕትህ አጠገብ ቁም እኔ እሄዳለሁ፡፡ ምናልባት ያህዌ ሊገናኘኝ ይመጣ ይሆናል፡፡ እርሱ የሚያሳየኝን ሁሉ እነግርሀለሁ፡፡” ስለዚህም በለዓም ዛፎች ወደ ሌሉበት የተራራ ጫፍ ሄደ፡፡4እግዚአብሔር እርሱን ተገናኘው፣ በለዓምም ለእግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ “እኔ ሰባት መሰዊያዎችን አበጅቻለሁ፣ ደግሞም በእያንዳንዱ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቅርቤያለሁ፡፡” 5ያህዌ በበለዓም አፍ ላይ መልዕክት አኑሮ እንዲህ አለ፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና እንዲህ በለው፡፡” 6ስለዚህ በለዓም በሚቃጠል መስዋዕቱ አጠገብ ወደቆመው ወደ ባላቅ ከእነርሱ ጋር ወደ ነበሩት የሞአብ መሪዎች ሁሉ ተመለሰ፡፡7ከዚያ በለዓም ትንቢቱን መናገር ጀመረ እንዲህም አለ፣ “ባላቅ እኔን ከአራም አመጣኝ፣ የሞአብ ንጉስ ከምስራቅ ተራሮች አመጣኝ፡፡ ‘ና፣ ያዕቆብን ዕርገምልኝ’ አለኝ፡፡ ‘ና፣ እስራኤልን ተፈታተንልኝ’ አለኝ፡፡ 8እግዚአብሔር ያልረገመውን እኔ እንዴት መርገም እችላለሁ? ያህዌ ያልተቃወማቸውን እኔ እንዴት መቃወም እችላለሁ?9ከአለቶች በላይ ሆኜ አየዋለሁ፣ ከተራሮች ላይ ሆኜ ወደ እርሱ አያለሁ፡፡ ተመልከት፣ ብቻውን የሚኖር ራሱን እንደ ተራ ህዝብ አድርጎ የማይቆጥር ህዝብ አለ፡፡10የያዕቆብን ትቢያ ማን መቁጠር ይችላል ወይም ከእስራኤል ሩቡን እንኳን ማን ይቆጥራል? የጻድቁነ ሞት እኔ ልሙት፣ ደግሞም የህይወቴ መጨረሻ እንደ እርሱ ይሁን!”11ባላቅ በለዓምን እንዲህ አለው፣ “ምን እያደረግክብኝ ነው ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፣ ነገር ግን እነሆ አንተ እነርሱን ባረካቸው፡፡” 12በለዓም መለሰለት እንዲህም አለ፣ “ያህዌ በአፌ ላይ ያደረገውን ብቻ ለመናገር መጠንቀቅ የለብኝምን?”13ስለዚህም ባላቅ እንዲህ አለው፣ “እባክህ ከእኔ ጋር ልታያቸው ወደ ምትችልበት ሌላ ቦታ ና፡፡ ከእነርሱ ሁሉንም ሳይሆን፣ በቅርብ ያሉትን ብቻ ታያለህ፡፡ በዚያ እነርሱን ትረግምልኛለህ፡፡” 14ስለዚህ በለዓምን ወደ ጾፊም ሜዳ፣ ወደ ፊስጋ ተራራ ጫፍ ይዞት ሄደና ተጨማሪ ሰባት መሰዊያዎችን አበጀ፡፡ በእያንዳንዱ መሰዊያ አንድ በሬና አንድ አውራ ጠቦት ሰዋ፡፡ 15ከዚያ በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “እኔ በዚያ ያህዌን ለመገናኘት ስሄድ፣ አንተ እዚህ በሚቃጠል መስዋዕትህ አጠገብ ቁም፡፡”16ያህዌ በለዓምን ተገናኝቶ በአፉ ምልክት አኖረ፡፡ እንዲህም አለው፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና መልዕክቴን ንገረው፡፡” 17በለዓም ወደ ባላቅ ተመልሶ በሚቃጠል መስዋዕቱ አጠገብ አገኘው፣ የሞአብ መሪዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ ባላቅ እንዲህ ሲል ጠየቅ፣ “ያህዌ ምን ነገረህ?” 18በለዓም ትንቢቱን መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “ባላቅ፣ ተነስና አድምጥ፡፡ አንተ የሴፎር ልጅ እኔን አድምጠኝ፡፡19እግዚአብሔር ይዋሽ ዘንድ ሰው አይደለም፣ ወይም ሀሳቡን ይቀየር ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፡፡ ላያደርግ አንዳች ነገር ቃል ይገባልን? ላይፈጽመውስ አንዳች ነገር አደርጋለሁ ይላልን? 20እነሆ፣ ለመባረክ ታዝዣለሁ፡፡ እግዚአብሔር በረከትን ለቋል፣ እኔ ልከለክል አልችልም፡፡21እርሱ በያዕቆብ ላይ አንዳች ችግር ወይም በእስራኤል ላይ ድካም አላየም፡፡ ያህዌ አምላካቸው ከእነርሱ ጋር ነው፣ የንጉሳቸውም እልልታ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ 22እግዚአብሔር እንደ ጎሽ በሆነ ሀይል ከግብጽ አወጣቸው፡፡23በያዕቆብ ላይ የሚሰራ ምንም አስማት የለም፣ የትኛውም ሟርት እስራኤልን አይጎዳም፡፡ ይልቁንም ስለያዕቆብና ስለ እስራኤል እንዲህ ይባልላቸዋል፣ ‘እግዚአብሔር ያደረገውን እዩ!’24እዩ፣ ህዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሳል፣ እንደ አንበሳ ተነስቶ ያጠቃል፡፡ ያደነውን እስኪበላ የገደለውን ደም እስኪጠጣ አያርፍም፡፡”25ከዚያ ባላቅ በለዓምን እንዲህ አለው፣ “እነርሱን ባትረግማቸው እንኳን ጨርሰህ አትባርካቸው፡፡” 26በልዓም ግን ባላቅን መልሶ እንዲህ አለው፣ “እንድናገር ያህዌ የነገረኝን ሁሉ መናገር እንዳለብኝ አልነገርኩህምን?” 27ስለዚህም ባላቅ ለበለዓም እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “አሁን ና፣ እኔ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፡፡ ምናልባት በዚያ እነርሱን እንድትረግምልኝ እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል፡፡”28ስለዚህም ባላቅ በለዓምን ምድረበዳውን ቁልቁል ወደሚያይበት ወደ ፌጎር ተራራ ጫፍ ወሰደው፡፡ 29በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “በዚህ ስፍራ ሰባት መሰዊያዎችን አብጅና ሰባት በሬዎች እንዲሁም ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅ፡፡” 30ስለዚህ ባላቅ ባለዓም እንደነገረው አደረገ፤ በእያንዳንዱ መሰዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ሰዋ፡፡
1በለዓምም ያህዌ እስራኤልን መባረክ እንደፈቀደ ባየ ጊዜ፣ በሌላ ጊዜ እንደሚያደርገው አስማት ለማድረግ አልወጣም፡፡ ይልቁንም፣ ወደ ምድረበዳው ቁልቁል ተመለከተ፡፡2ዐይኖቹን አቅንቶ እስራኤልን በየነገዱ ሰፍሮ አየ፣ የእግዚአብሔር መንፈስም በእርሱ ላይ መጣ፡፡ 3ይህን ትንቢት ተቀብሎ እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “ዐይኖቹ እጅግ የተከፈቱለት የቢዖር ልጅ በለዓም እዲህ ይላል፡፡4እርሱ የእግዚአብሔርን ቃላት ይናገራል ይሰማልም፡፡ እርሱ ሁሉን ቻይ ከሆነው ዘንድ ዐይኖቹ ተከፍተውለት በፊቱ ከሚሰግድለት ዘንድ የሆነውን ራእይን ይመለከታል፡፡ 5ያዕቆብ ሆይ ድንኳኖችህ ምንኛ ያማሩ ናቸው፣ እስራኤል ሆይ መኖሪያዎችህ እንዴት ያምራሉ!6እንደ ሸለቆዎች ተዘርግተዋል፣ በወንዝ ዳር እንዳሉ መናፈሻ ስፍራዎች፣ በያህዌ እንደተተከሉ ሬቶች፣ በውሃ ዳርቻ እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው፡፡7ማድጋዎቻቸው በውሃ የተትረፈረፉ ናቸው፣ ሰብላቸው ውሃ አይታጣውም፡፡ ንጉሳቸው ከአጋግ ይበልጣል፣ መንግስታቸው የከበረ ነው፡፡8እግዚአብሔር እርሱን ከግብጽ አውጥቶታል፡፡ እንደ ጎሽ ብርታት አለው፡፡ የሚዋጉትን መንግስታት ይፈጃቸዋል፡፡ አጥንቶቻቸውን ይሰባብራል፡፡ በቀስቶቹ ይወጋቸዋል፡፡9እንደ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፣ እንደ ሴት አንበሳ ያደቃቸዋል፡፡ ማን ሊቋቋመው ይችላል? የሚባርኩት ሁሉ ይባረኩ፤ የሚረግሙት ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፡፡”10የባላቅ ቁጣ በበለዓም ላይ ነደደ፣ እጆቹን አጣፍቶ በለዓምን እንዲህ አለው፣ “እኔ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፣ ነገር ግን አንተ ሶስት ጊዜም ባረካቸው፡፡ 11ስለዚህ አሁኑኑ ከእኔ ተለይተህ ወደ ቤትህ ሂድልኝ፡፡ እጅግ አድርጌ አከብርሃለሁ ብዬ ነበር፣ ነገር ግን አንዳች ሽልማት እንዳታገኝ ያህዌ ከለከለህ፡፡”12ከዚያ በለዓም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “ወደ እኔ ለላካቸው መልዕክተኞች እንዲህ ብያቸው ነበር፣ 13‘ባላቅ በብርና ወርቅ የተሞላውን ቤተ መንግስቱን ቢሰጠኝ እንኳን፣ ያህዌ ከተናገረው ውጭ አንዳች መጥፎ ወይም መልካም፣ ወይም አንዳች እኔ ላደርግ የምፈልገውን አልናገርም፡፡ መናገር የምችለው ያህዌ ተናገር ያለንን ብቻ ነው፡፡’ ይህን ለእነርሱ አልተናገርኩምን? 14ስለዚህ እነሆ አሁን ወደ ህዝቤ እመለሳለሁ፡፡ ነገር ግን አሁን በቅድሚያ ይህ ህዝብ በሚመጡት ቀናት በአንተ ህዝብ ላይ ሊያደርግ ያለውን ላስጠንቅህ፡፡”15በለዓም ይህን ትንቢት መናገር ጀመረ፣ “ዐይኖቹ እጅግ የተከፈቱለት የቢዖር ልጅ በልዓም ይህን ናገራል፡፡ 16ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቃል የሚሰማ ሰው ትንቢት ነው፣ ከልዑል ዘንድ ዕውቀት ከተሰጠው፣ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ራዕይ ከተቀበለው፣ በተከፈተ ዐይን በፊቱ ከሚሰግደው፣ ሰው የተነገረ ትንቢት ነው፡፡17እኔ እርሱን አያለሁ፣ ነገር ግን እርሱ አሁን እዚህ አይደለም፡፡ እኔ እርሱን እመለከታለሁ፣ ነገር ግን እርሱ በቅርብ አይደለም፡፡ ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፣ በትረ መንግስት ከእስራኤል ይነሳል፡፡ እርሱ የሞአብን መሪዎችን ይበታትናል፣ የሴትንም ትውልዶች ያጠፋል፡፡18ከዚያ እስራኤል በሃይል ድል የሚነሳው ኤዶም፤ የእስራኤል ርስት ይሆናል፣ ደግሞም የእስራኤል ጠላት የሆነው ሴይር፣ የእነርሱ ርስት ይሆናል፣ 19ከያዕቆብ ግዛት ያለው ንጉስ ይወጣል፣ እርሱም ከከተማቸው የተረፉትን ቅሬታዎች ያጠፋል፡፡”20ከዚያ በለዓም አማሌቅን ተመልክቶ ትንቢት መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “አማሌቅ ታላቅ ህዝብ ነበር፣ነገር ግን መጨረሻው ጥፋት ይሆናል፡፡”21ከዚያ በለዓም ወደ ቄናውያን ተመልክቶ ትንቢቱን ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “የምትኖርበት ስፍራ አስተማማኝ ነው፣ ጎጆችህም በአለቶች መሀል ነው፡፡ 22ሆኖም ግን እናንተ ቄናውያን አሶር ምርኮ አድርጎ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ፡፡”23ከዚያ በለዓም የመጨረሻውን ትንቢቱን መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “አወይ! እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ ማን ይተርፋል? 24መርከቦች ከኪቲም ዳርቻዎች ይመጣሉ፤ አሶርን ያጠቃሉ ዔቦርን ይይዛሉ፣ ነገር ግን እነርሱም ደግሞ መጨረሻቸው መደምሰስ ነው፡፡ 25ከዚያ በለዓም ተነስቶ ሄደ፡፡ ወደ ቤቱ ተመለሰ፣ ባላቅም ተነስቶ ሄደ፡፡
1እስራኤል በሰጢም ተቀመጠ፣ ወንዶቹም ከሞዓብ ሴቶች ጋር ተኙ፣ 2ይህም ሞአባዊያኑ ህዝቡን ለእነርሱ አማልዕክት የተሰዋውን ስለጋበዟቸው ነው፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ለጣኦት የተሰዋውን በሉ ደግሞም ለሞአባውያን አማልዕክት ሰገዱ፡፡ 3የእስራኤል ወንዶች የፌጎርን በኣል በማምለክ ተባበሩ፣ እናም የያህዌ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፡፡4ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ብርቱ ቁጣዬ ከእስራኤል ይርቅ ዘንድ የህዝቡን መሪዎች ሁሉ ግደልና እነርሱን በቀን ብርሃን ለማጋለጥ ስቀላቸው፡፡” 5ስለዚህም ሙሴ ለእስራኤል መሪዎች እንዲህ አለ፣ “እያንዳንዳችሁ የፌጎርን በኣል በማመልክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ፡፡”6ከዚያ ከእስራኤል ወንዶች አንዱ ቀርቦ ከቤተሰቡ አባላት ጋር አንዲት ምድያማዊት ሴት አመጣ፡፡ ሙሴና መላው የእስራኤል ህዝብ እያዩ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ሆነው እያለቀሱ ሳለ ይህ ሆነ፡፡ 7የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ካህኑ ፊንሀስ ይህን ሲመለከት፣ ከማህበሩ መሀል ጦሩን በእጁ ይዞ ተነሳ፡፡8እርሱም ወደ ድንኳኑ እስራኤላዊውን ሰው ተከትሎ ገብቶ የእስራኤላዊውን ወንድና የምድያማዊቷን ሴት የሁለቱንም አካላት በአንድነት በጦሩ ወጋ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ህዝብ ላይ የላከው መቅሰፍት አቆመ፡፡ 9በመቅሰፍቱ የሞቱት በቁጥር ሃያ አራት ሺ ነበሩ፡፡10ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 11“ካህኑ፣ የአሮን ልጅ የአልአዛር ልጅ ፊንሀስ፣ ቁጣዬን ከእስራኤል ህዝብ አርቋል ምክንያቱም በእነርሱ መሃል የእኔን ቅንአት ቀንቷል፡፡ ስለዚህ የእስራኤልን ህዝብ በቁጣዬ ፈጽሞ አላጠፋኋቸውም፡፡12ስለዚህ እንዲህ በል፣ ‘ያህዌ እንዲህ ይላል፣ “እነሆ፣ ለፊንሐስ የሰላሜን ኪዳን እሰጠዋለሁ፡፡ 13ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለትውልዱ፣ ዘለዓለማዊ የክህነት ኪዳን ይሆናል፤ ምክንያቱም እርሱ ለእኔ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ቀንቷል፡፡ ለእስራኤል ህዝብ አስተሰርይዋል፡፡”14ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው የእስራኤላዊ ሰው የሰሉ ልጅ ስም ዘንበሪ ሲባል፣ የስምኦናውያን አባቶች ቤተሰብ መሪ ነበር፡፡ 15የተገደለችው የምድያም ሴት ስም ከስቢ ነበር፣ እርሷም ከምድያም ቤተሰብ የጎሳው መሪ የሱር ሴት ልጅ ነበረች፡፡16ስለዚህም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 17”ምድያማዊያንን እንደ ጠላት ቆጥራችሁ አጥፏቸው፣ 18እነርሱ በአታላይነታቸው እንደ ጠላት አስተናግደዋችኋልና፡፡ በፌጎር በሆነውና በእናታቸው በከስቢ ጉዳይ በፌጎር ምክንያት በመቅሰፍቱ ቀን በተገደለችው በምድያም አለቃ ልጅ ወደ ክፉ መርተዋችኋል፡፡”
1ከመቅሰፍቱ በኋላ እንዲህ ሆነ፣ ያህዌ ለሙሴና ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር እንዲህ አላቸው፡፡ 2“የእስራኤልን ማህበረሰብ ሁሉ ቁጠሩ፣ ሀያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን፣ ለእስራኤል ለመዋጋት ወደ ጦርነት መውጣት የሚችሉትን ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤቶች ቁጠሯቸው፡፡”3ስለዚህም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በሞአብ ሜዳ በዮርዳኖስ አጠገብ ኢያሪኮ ሳለ ለህዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፣ 4“ከሃያ አመት ጀምሮ ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን ከግብጽ ምድር የወጡትን ያህዌ ሙሴንና የእስራኤል ሰዎችን እንዳዘዘው ሁሉ ቁጠሯቸው፡፡”5ሮቤል የእስራኤል በኩር ነበር፡፡ ከወንድ ልጁ ከሄኖክ የሄኖካውያን ጎሳዎች መጡ፡፡ ከፈለስ የፈለሳውያን ጎሳ መጡ፡፡ 6ከአስሮን የአስሮናውያን ጎሳ መጡ፡፡ ከከርሚ የከርማውያን ጎሳ መጡ፡፡ 7እነዚህ የሮቤል ጎሳ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 43730 ወንዶች ነበሩ፡፡8ኤልያብ የፈሉስ ልጅ ነበር፡፡ 9የኤልያብ ወንዶች ልጆች ነሙኤል፣ ዳታን፣ እና አቤሮን ነበሩ፡፡ እነዚህ ቆሬን ተከትለው ሙሴንና አሮንን በመቃወም በያህዌ ላይ ያመጹት እነዚያው ዳታንና ኤብሮን ነበሩ፡፡10ሁሉም የእርሱ ተከታዮች ሲሞቱ፣ ምድር አፏን ከፍታ ከቆሬ ጋር ሁሉንም በአንድነት ዋጠቻቸው፡፡ በዚያ ጊዜ፣ በእሳት መቀጣጫ የሆኑትን 250 ወንዶችን በላች፡፡ 11ነገር ግን የቆሬ የዘር ሀረግ አልጠፋም፡፡12የስምዖን ትውልዶች እዚህ ነበሩ፡ በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጎሳ፣ በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጎሳ፣ በያኪን በኩል የያኪናውያን ጎሳ፣ 13በዛራ በኩል የዛራውያን ጎሳ፣ በሳኡል በኩል የሳኡላውያን ጎሳ ነበሩ፡፡ 14እነዚህ የስምዖን ጎሳ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 22200 ወንዶች ነበሩ፡፡15የጋድ ጎሳ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በጽፎን በኩል የጽፎናውያን ጎሳ፣ በሐጊ በኩል የሐጋውያን ጎሳ፣ በሺኒ በኩል፣ የሺናውያን ጎሳ፣ 16በኤስና በኩል፣ የኤሶናውያን ጎሳ፣ በዔሪ በኩል የዔራውያን ጎሣ፣ 17በአሮዲ በኩል የሮዳውያን ጎሳ፣ በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጎሳ፡፡ 18እነዚህ የጋድ ጎሳ ትውልድ ነበሩ፣ ቁጥራቸው 40500 ወንዶች ነበሩ፡፡19የይሁዳ ልጆች ዔር እና አውናን ነበሩ፣ እነዚህ ወንዶች ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል፡፡ 20የይሁዳ ጎሳ ሌሎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፣ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጎሳ፣ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጎሳ፣ እና በዛራ በኩል የዛራውያን ጎሳ ነበሩ፡፡ 21የፋሬስ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ በኤስሮም በኩል የኤስሮማውያን ጎሳ፣ በሐሙል በኩል፣ የሐሙላውያን ጎሳ፡፡ 22እነዚህ የይሁዳ ጎሳ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 76500 ነበሩ፡፡23የይሳኮር ጎሳዎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡፡ በቶላ በኩል የቶላውያን ጎሳ፣ በፋዋ በኩል ቦፋውያን ጎሳ፣ 24በያሱብ በኩል፣ የያሱባውዩን ጎሳ፣ በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጎሳ፡፡ 25እነዚህ የይሳኮር ጎሳዎች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 64300 ወንዶች ነበሩ፡፡26የዛብሎን ጎሳዎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡፡ በሴሬድ በኩል የሴሬዳውያን ጎሳ፣ በኤሎን በኩል የኤሎናውያን ጎሳ፣ በያህልኤል በኩል የያህልኤላውያን ጎሳ፡፡ 27እነዚህ የዛብሎን ጎሳዎች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 60500 ወንዶች ነበሩ፡፡28የዮሴፍ ጎሳ ትውልዶች ምናሴና ኤፍሬም ነበሩ፡፡ 29የምናሴ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጎሳ (ማኪር የገለዓድ አባት ነበር) ፣ በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጎሳ ነበሩ፡፡30ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በኢዔዝር በኩል የኢዔዝራውያን ጎሳ፣ በኬሌግ በኩል የኬሌጋውያን ጎሳ፣ 31በእስራኤል በኩል የእስራኤላውያን ጎሳ፣ በሴኬም በኩል፣ የሴካማውያን ጎሳ፣ 32በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጎሣ፣ በኦፌር በኩል የኦፌራውያን ጎሣ፣33ልጅ ሰለጳዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፣ ነገር ግን ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት፡፡ የሴት ልጆቹ ስሞች እነዚህ ነበሩ፡ ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግሳ፣ ሚልካና ቲርዳ፡፡ 34እነዚህ የምናሴ ጎሳዎች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 52700 ወንዶች ነበሩ፡፡35የኤፍሬም ጎሳዎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በሲቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጎሣ፣ በቤኬር በኩል የቤኬራውያን ጎሣ፣ በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 36የሱቱላ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 37እነዚህ የኤፍሬም ጎሣ ትውልዶች ነበሩ፡ ቁጥራቸው 32500 ወንዶች ነበሩ፡፡ እነዚህ የዮሴፍ ትውልዶች፣ በየጎሣቸው ተቆጠሩ፡፡38የብንያም ጎሣ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጎሣ፣ በአስቤል በኩል የአስቤላውያን ጎሣ፣ በኢኪራን በኩል፣ የኢኪራናውያን ጎሣ፣ 39በሶፋን በኩል፣ የሶፋናውያን ጎሣ፣ በሑፋም በኩል፣ የሑፋፋማውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 40የቤላ ወንዶች ልጆች አርድ እና ናዕመን ነበሩ፡፡ ከአርድ የአርዳውያን ጎሣ መጣ፣ ከናዕማን የናዕመናውያን ጎሣ መጣ፡፡ 41የብንያም ጎሣ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡፡ ቁጥቸው 45600 ወንዶች ነበሩ፡፡42የዳን ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በስምዔ በኩል፣ የስምዔያናውያን ጎሣዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የዳን ትውልድ ጎሣዎች ነበሩ፡፡ 43የስምዔያውያን ጎሣዎች በጠቅላላ 64400 ወንዶች ነበሩ፡፡44የአሴር ትውልድ ጎሣዎች እነዚህ ነበሩ፡ በዩምና በኩል የዩምናውያን ጎሣ፣ በዩሱዋ በኩል፣ የየሱዋውያን ጎሣ፣ በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 45የብንያም ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጎሣ፣ በመልኪኤል በኩል የመልኪኤላውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 46የአሴር ሴት ልጅ ስም ሤራህ ነበር፡፡ 47እነዚህ የአሴር ጎሣ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 53400 ወንዶች ነበር፡፡48የንፍታም ጎሣ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በያሕድኤል በኩል፣ የያህጽኤላውያን ጎሣ፣ በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጎሣ፣ 49በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 50እነዚህ የንፍታሌም ጎሣ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 45400 ወንዶች ነበር፡፡51ይህ በእስራኤል ህዝብ መሃል ጠቅላላው የወንዶች ቁጥር ነበር፡፡በጠቅላላው 601730 ነበሩ፡፡52ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣ 53“ምድሪቱ በእነዚህ ሰዎች መሃል ርስት ሆኖ እንደ ስሞቻቸው ቁጥር መሰረት ትከፋፈል፡፡54ብዙ ቁጥር ላለው ጎሳ ሰፋ ያለውን ርስት ስጥ፣ አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ጎሣዎች አነስ ያለውን ርስት ስጣቸው ለእያንዳንዱ ቤተሰብ እንደ ተቆጠረው ወንድ ብዛት ርስት ስጣቸው፡፡ 55ሆኖም ምድሪቱ በዕጣ ትከፋፈል፡፡ ምድሪቱን በየአባቶቸው ጎሳዎች መሀል እንደምትከፋፈል ይወርሷት፡፡ 56ርስታቸው በየጎሳው ብዛትና አነስተኛት መጠን ይከፋፈል፣ ክፍፍሉ በዕጣ ይሁን፡፡”57በየነገዳቸው የተቆጠሩት የሌዋውያን ነገዶች እነዚህ ነበሩ፡ በጌድሶን በኩል፣ የጌድሶናውያን ጎሣ፣ በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጎሣ፣ በሜራሪ በኩል፣ የሜራርያውን ጎሣ ነበሩ፡፡ 58የሌዊ ጎሳዎች እነዚህ ነበሩ፡ የሊብናውያን ጎሣ፣ የኬብሮናውያን ጎሣ፣ የሞሐላውያን ጎሣ፣ የሙሳውያን ጎሣ፣ እና የቆሬያውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ ቀዓት የእንበረም የዘር ሀረግ ነበር፡፡ 59የእንበረም ሚስት ስሟ ዮካብድ ነበር፣ ከሌዋውያን ወገን ግብጽ ውስጥ የተወለደች ነበረች፡፡ ከእንበረም ልጆቻቸውን አሮንን፣ ሙሴን እና እህታቸውን ማርያምን ወለደች፡፡60ለአሮን የተወለዱለት ናዳብ እና አብዩድ፣ ኤልዓዛር እና ኢታምር ነበሩ፡፡ 61ናዳብና አብዩድ ያህዌ በፊቱ ተቀባይነት የሌለውን የእሳት መስዋዕት ሲያቀርቡ ሞቱ፡፡ 62አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያቸው ሌዋውያን ወንዶች ቁጥር ሃያ ሶስት ሺ ነበር፡፡ ነገር ግን ከእስራኤል ትውልዶች ጋር አብረው አልተቆጠሩም፡፡ ምክንያቱም ለእነርሱ በእስራኤል ሕዝብ መሃል ምንም ርስት አልተሰጣቸውም ነበር፡፡63በሙሴና በካህኑ አልዓዛር የተቆጠሩት እነዚህ ናቸው፡፡ በሞአብ ሜዳ በዮርዳኖስ ኢያሪኮ ውስጥ የእስራኤልን ህዝበ ቆጠሩ፡፡ 64የእስራአል ትውልዶች በሲና ምድረ በዳ በተቆጠሩ ጊዜ በእነዚህ መሀል በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር የተቆጠረ ሌላ ሰው ግን አልነበረም፡፡65ያህዌ እነዚያ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ በምድረበዳ እንደሚሞቱ ተናግሮ ነበር፡፡ ከዩፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከመሀላቸው በህይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
1ከዚያ ከዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ የአፌር ወንድ ልጅ የገለአድ ወንድ ልጅ የማኪር ወንድ ልጅ የምናሴ ወንድ ልጅ የሰለጵዓድ ሴት ልጆች ወደ ሙሴ መጡ የሰለዓድ ሴት ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፡፡ ማህላህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጳ፡፡2እነርሱም በሙሴ፣ በካህኑ አልዓዛር፣ በመሪዋች፣ እና በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በመላው ማህበረሰቡ ፊት ቆሙ፡፡ እንዲህም አሉ፣ 3“አባታችን በምድረበዳው ሞተ፡፡ እርሱ በቆሬ አመጽ በያህዌ ፊት አምጸው በአንድነት ከተነሱት መሀል አልነበረም፡፡ የሞተው በራሱ ኃጢአት ነበር፣ አባታችን የሞተው በራሱ ኃጢአት ምክንያት ነበር፡፡4ስለምን ወንድ ልጅ ስለሌለው የአባታችን ስም ከጎሳው አባላት ተለይቶ ይጠፋል? በአባታችን ቤተዘመዶች መሀል መሬት ስጠን፡፡” 5ሙሴ ጉዳያቸውን ያህዌ ፊት አቀረበ፡፡6ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 7”የሰለጰዓድ ሴት ልጆች የተናገሩት ትክክል ነው፡፡ በአባታቸው ዘመዶች መሃል በእርግጥ ርስት አድርገህ መሬት ስጣቸው፣ ደግሞም የአባታቸው ርስት ወደ እነርሱ መተላፉን አረጋግጥ፡፡ 8ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይኖው ቢሞት፣ ርስቱ ወደ ሴት ልጁ እንዲተላፍ አድርጉ፡፡9ሴት ልጅ ባይኖረው፣ ርስቱን ለወንድሞቹ ስጡ፡፡ 10ወንድሞች ባይኖት፣ ርስቱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ፡፡ 11አባቱ ወንድሞች ባይኖሩት ርስቱን በጎሳው ውስጥ ለቅርብ ዘመዱ ስጡ፣ ያም ሰው ይውሰደው፡፡ ይህም ያህዌ እንዳዘዘኝ፣ ለእስራኤል ህዝብ በአዋጅ የፀና ህግ ይሆናል፡፡’”12“ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ወደ ዓባሪም ተራሮች ወጥተህ ለእስራኤል ህዝብ የሰጠሁትን ምድር ተመልከት፡፡ 13ከተመለከትካት በኋላ፣ አንተም ደግሞ ወደ ሰዎችህ እንደ ወንድምህ አሮን ሁሉ ትሰበስባለህ፡፡ 14ይህ ይሆናል፤ ምክንያቱም በጺን ምድረበዳ እናንተ ሁለታችሁ በትእዛዛቶቼ ላይ አምጻችኋል፡፡ በዚያ፣ ውሃው ከአለቱ ሲፈስስ በቁጣህ ምክንያት በመላው ማህበረሰብ ዐይኖች ፊት እኔን በቅድስና ማክበር አልቻልክም፡፡” ይህ በጺን ምድረበዳ በቃዴስ የሚገኝ የመሪባ ውሃ ነው፡፡15ከዚያ ሙሴ ለያህዌ እንዲህ አለ፣ 16“የሰዎች ሁሉ መንፈስ አምላክ ያህዌ ሆይ፣ በዚህ ማህበረሰብ ላይ መሪ የሚሆን ሰው ሹም፣ 17በፊታቸው የሚወጣና የሚገባ ሰው፣ እየመራ የሚያስወጣቸውና የሚያስገባቸው፣ ህዝብህ እረኛ እንደሌላቸው በጎች እንዳይሆን ሰው ሹምለት፡፡”18ያህዌ ሙሴን፣ “የእኔ መንፈስ የሚኖርበትን፣ የነዌን ልጅ ኢያሱን ውሰድና እጆችህን በእርሱ ላይ ጫን፡፡ 19በካህኑ አልዓዛር ፊትና በመላው ማህበረሰብ ፊት አቁመህ እንዲመራቸው በፊታቸው ሹመው፡፡20ከአንተ ስልጣን በእርሱ ላይ አድርግ፣ ስለዚህም መላው የእስራኤል ማህበረሰብ እርሱን ይታዘዙታል፡፡ 21እርሱም በኡሪም በመጠየቅ ፍቃዴን ለማወቅ በካህኑ አልዓዛር ፊት ይሄዳል፡፡ ህዝቡ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር መላው የእስራኤል ሰዎች፣ መላውም ማህበረሰብ የሚወጣውና የሚገባው በእርሱ ትዕዛዝ ይሆናል፡፡22ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እርሱን እንዳዘዘው አደረገ፡፡ ኢያሱን ወስዶ በካህኑ አልዓዛርና በመላው ማህበር ፊት አቆመው፡፡ 23ያህዌ እንዲያደርግ እንዳዘዘው ሁሉ እጆቹን በላዩ ጫነና እንዲመራ ሾመው፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2”የእስራኤል ሰዎችን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘በወቅቱ ለእኔ መስዋዕቶችን አቅርቡ፣ ለእኔ ጣፋጭ መዓዛ ያለው በእሳት የተበጀ መስዋዕት ለእኔ አቅርቡልኝ፡፡’3ደግሞም እንዲህ በላቸው፣ ‘ይህ ለያህዌ የምታቀርቡት የእሳት መስዋዕት ነው፡፡ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ጠቦት፣ እንደ መደበኛ መስዋዕት በእያንዳንዱ ቀን ሁለት ጠቦቶች አቅርቡ፡፡ 4አንዱን ጠቦት በማለዳ ታቀርባላችሁ፣ ሌላውን ጠቦት በምሽት ታቀርባላችሁ፡፡ 5በተጠለለ የኢን አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የአፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አድርጋችሁ አቅርቡ፡፡6ይህ በሲና ተራራ የተደነገገ ለያህዌ የሚቀርብ በእሳት የተዘጋጀ መልካም መዓዛ ያለው መደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፡፡ 7ከዚህ ጋር የሚቀርበው የመጠጥ መስዋዕት ለአንዱ ጠቦት የኢን አንድ አራተኛ ይሁን፡፡ በተቀደሰው ስፍራ ለያህዌ የመጠጥ ስጦታ አፍስሱ፡፡ 8ሌላውን ጠቦት ከሌላ የእህል ቁርባን ጋር በማለዳ ባቀረባችሁት መስዋዕት አይነት በምሽት አቅርቡ፡፡ ከዚህ ጋር ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን በእሳት የተዘጋጀ ሌላ የመጠጥ መስዋዕትም አቅርቡ፡፡9በሰንበት ቀን ነውር የሌላቸው ሁለት የአንድ አመት ጠቦቶች፣ እና በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አድርጋችሁ ከመጠጥ መስዋዕት ጋር አቅርቡ፡፡ 10ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ በየሰንበቱ የሚቃጠል መስዋዕት እንዲሆን ነው፡፡11በየወሩ መጀመሪያ፣ ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እና ነውር የሌለባቸው ሰባት ወንድ የበግ ጠቦት መስዋዕት አድርጋችሁ አቅረቡ፡፡ 12ለእያንዳዱ ወይፈን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፣ ደግሞም ከአውራ በጉ ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ 13እንደዚሁም ለእያንዳንዱ ጠቦት የኢፍ አንድ አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ ይህ ለያህዌ የሚቀርብ በእሳት የተዘጋጀ መልካም መዓዛ የሚሰጥ የሚቃጠል መስዋዕት የሚሆን ነው፡፡14የሰዎች የመጠጥ ቁርባን ላንድ ኮርማ በሬ የኢን ግማሽ ወይን ጠጅ ይሁን፣ ከአውራ በጉ ጋር የኢን አንድ ሶስተኛ፣ ለአንድ ጠቦት በግ የኢን አንድ አራተኛ ወይን ጠጅ ይሁን፡፡ ይህ አመቱን በሙሉ በእያንዳንዱ ወር የሚቃጠል መስዋዕት ነው፡፡ 15ለያህዌ አንድ ወንድ ፍየል የኃጢአት መስዋዕት መቅረብ አለበት፡፡ ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርብ የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ነው፡፡16በመጀመሪያው ወር፣ በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን የያህዌ ፋሲካ ይውላል፡፡ 17በዚህ ወር የአስራ አምስተኛው ቀን ክብረ በዓል ይሆናል፡፡ ለሰባት ቀናት እርሾ የሌለበት ቂጣ ይበላል፡፡ 18በመጀመሪያው ቀን ያህዌን ለማክበር ቅዱስ ጉባኤ ይደረጋል፡፡ በዚያ ቀን የዘወትር ሥራችሁን አትሰሩም፡፡19ሆኖም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ የሚቃጠል መስዋዕት ስጦታ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ሰባት ወንድ የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፡፡ 20ከወይፈኑ ጋር በዘይት የተለወሰ የኢን ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን፣ ከአውራ በግ ጋር የኢን ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ 21ከእያንዳንዳቸው ከሰባቱ ጠቦቶች ጋር፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት አቅርቡ፣ 22እንዲሁም አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአት መስዋዕት ለማስተሰርያ አቅርቡ፡፡23እነዚህን በየጠዋቱ ከሚያስፈልገው መደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት በተጨማሪ አቅርቡ፡፡ 24እዚህ እንደ ተገለፀው፣ እነዚህን መስዋዕቶች በየቀኑ ማቅረብ አለባችሁ፣ በፈሲካ ሳምንት፣ በእሳት የተዘጋጀው የምግብ መስዋዕት ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይቅረብ፡፡ ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ መቅረብ አለበት፡፡ 25በሰባተኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፣ ደግሞም በዚያ ቀን የየዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑ፡፡26እንደዚሁም በበኩራት ፍሬ ቀን፣ በክብረ በዓላችሁ ሳምንታት የአዲስ እህል ስጦታ ለያህዌ ስታቀርቡ፣ ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ ደግሞም በዚያ ቀን የተለመደ የየዕለት ተግባራችሁን አትስሩ፡፡ 27ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ሰባት የአንድ አመት ጠቦት በጎች አቅርቡ፡፡ 28ከእነዚህ ጋር እነዚህን የእህል ቁርባን አቅርቡ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ ለእያንዳንዱ ወይፈን የኢፍ ሶስት አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ እና ለአውራ በጉ ሁለት አስረኛ የእህለ ቁርባን አቅርቡ29የኢፍ አንድ አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለእያንዳንዳቸው ሰባት ጠቦቶች አቅርቡ፣ 30ደግሞም አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአታችሁ ማስተሰርያ አቅርቡ፡፡ 31ነውር የሌለባቸውን እነዚያን እንስሳት ከመጠጥ ቁርባናቸው ጋር ስታቀርቡ ይህ ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የእህል ቁርባን በተጨማሪ መሆን አለበት፡፡’”
1”በሰባተኛው ወር፣ በወሩ በመጀመሪያው ቀን፣ ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፡፡ በዚያ ቀን የተለመደውን የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑ፡፡ ይህ ቀን መለከቶችን የምትነፉበት ቀን ይሆናል፡፡2ለያህዌ መልካም መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና እያንዳንዳቸው ነውር የሌለባቸው ሰባት የአንድ አመት ጠቦቶች አቅርቡ፡፡3ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባናቸውን፣ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት አቅርቡ፤ ለወይፈኑ የኢፍ ሶስት አራተኛ፣ ለአውራ በጉ የኢፍ ሁለት አስረኛ 4እና ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት አቅርቡ፡፡ 5ለኃጢአት ማስተስረያ አንድ ወንድ ፍየል አቅርቡ፡፡6በየወሩ መጀመሪያ ከምታደርጉት የተለየ የሚቃጠል መስዋዕትና አብሮ ከሚቀርበው የእህል ቁርባን በተጨማሪ፣ እነዚህን መስዋዕቶች በሰባተኛው ወር አድርጉ፡፡ እነዚህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት ከእህል ቁርባኑና የመጠጥ ቁርባኖች በተጨማሪ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ እነዚህን መስዋዕቶች ስታደርጉ፣ ለያህዌ በእሳት የሚዘጋጀውን መስዋዕት ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ የተደነገገውን ትፈጽማላችሁ፡፡7በሰባተኛ ወር በአስረኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት ታዋርዳላችሁ በዕለቱ ሥራ አትሰሩም፡፡ 8ለያህዌ ጣፋጭ ማዐዛ ያለው የሚቃጠል መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና የአንድ አመት ሰባት ወንድ ጠቦት በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ እያንዳንዳቸው ነውር የሌለባቸው ይሁኑ፡፡9ከዚህ ጋር የእህል ቁርባን፤ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ ለወይፈኑ የኢፍ ሶስት አስረኛ፣ ለአውራ በጉ የኢፍ ሁለት አስረኛ፣ 10እና ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ አንድ አስረኛ ታቀርባላችሁ፡፡ 11አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአት መስዋዕት ማቅረበ አለባችሁ፡፡ ይህ ለኃጢአት ማስተስረያ፣ ለመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና ከእነዚህ ጋር በሚቀርበው የመጠጥ መስዋእቶች በተጨማሪ የሚቀርብ ነው፡፡12በሰባተኛው ወር አስራ አምስተኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ በዚያ ቀን የተለመደውን የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑም፣ ደግሞም ለሰባት ቀናት ክብረ በዓሉን ለእርሱ ታደርጋላችሁ፡፡ 13በእሳት የተዘጋጀ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መስዋዕት ማቅረብ አለባችሁ፡፡ አስራ ሶስት ወይፈኖች፣ እና የአንድ አመት ዕድሜ ያላቸው አስራ አራት ወንድ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ እያንዳንችው ነውር የሌለባቸው መሆን አለባቸው፡፡14ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባን፣ ለአስራ ሶስቱም ወይፈኖች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ ሶስት አስረኛ፣ ለሁለቱ አውራ በጎች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ ሁለት አስረኛ 15እና ለአስራ አራቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ አንድ አስረኛ፤ በዘይትየተለወሰ መልካም ዱቄት አቅርቡ፡፡ 16ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት፤ ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የእህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡17በስብሰባው ሁለተኛ ቀን፣ አስራ ሁለት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 18ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባን የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 19ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡20በስብሰባው ሶስተኛ ቀን፣ አስራ አንድ ወይፈኖች ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 21ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሰረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 22ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮ ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡23በስብሰባው አራተኛ ቀን፣ አስር ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 24ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች፣ ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 25ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡26በስብሰባው አምስተኛ ቀን፣ ዘጠኝ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 27ከእነዚህም ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ፣ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 28ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡29በስበሰባው ስድስተኛ ቀን ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 30ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 31ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው እህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረበ አለባችሁ፡፡32በስብሰባው ሰባተኛ ቀን፣ነውር የሌለባቸው፣ ሰባት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 33ከወይፈኖች፣ከአውራ በጎች እና ጠቦቶች ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ታቀርባላችሁ፡፡ 34ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እንዲሁም ከመጠጥ ቁርባኑ በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡35በስብሰባው ስምንተኛ ቀን፣ ሌላ የከበረ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ በዚያን ቀን የተለመደ የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑም፡፡ 36የሚቃጠል መስዋዕት ታደርጋላችሁ፣ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ያለው መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ነውር ሌለባቸው ሰባት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት በጎች ታቀርባላችሁ፡፡37ለወይፈኑ፣ ለአውራ በጉ፣ እና ለጠቦቶቹ የእህል ቁርባናቸውንና የመጠጥ ቀርባናቸውን በተወሰነው ቁጥር መሰረት እንደ ትእዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 38ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡39በተወሰነ ክብረ በዓላቶቻችሁ ለያህዌ የምታቀርቧቸው እነዚህ ናቸው፡፡ እነዚህም ከስለቶቻችሁና የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ናቸው፡፡ እነዚህን የሚቃጠሉ መስዋዕቶቻችሁ፣ የእህል ቁርባኖች፣ የመጠጥ ቁርባኖች፣ እና የህብረት መስዋዕቶች አድርጋችሁ አቅርቧቸው፡፡” 40ሙሴ ያህዌ ለእስራኤል ሰዎች እንዲናገር ያዘዘውን ሁሉ ተናገረ፡፡
1ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ የጎሳ መሪዎች እንዲህ አላቸው፣ “ያህዌ ያዘዘው ይህን ነው፡፡ 2ማንም ሰው ለያህዌ ስዕለት ሲሳል፣ ወይም በቃል ኪዳን ራሱን በመሀላ ሲያስር፣ ቃሉን ማፍረስ የለበትም፡፡ ከአፉ የወጣውን ማናቸውንም ነገር ለማድረግ ቃልኪዳኑን መጠበቅ አለበት፡፡3አንዲት ወጣት ሴት በአባቷ ቤት እያለች ለያህዌ ብትሳልና በመሀላ ራሷን ብታስር፣ 4አባቷም ስዕለቷንና ራሷን ያሰረችበትን መሀላ ቢሰማ፣ እርሱም እርሷን ለመመለስ አንዳች ነገር ባይናገር መሀላዎቿ ሁሉ መፈፀም አለባቸው፡፡ ራሷን ያሰረችባቸው ቃልኪዳኖች ሁሉ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡5ነገር ግን አባቷ ስለ ስዕለቷና ስለገባችው ቃል ኪዳን ሰምቶ ምንም ነገር ባይነግራት በራሷ ላይ የወሰደቻቸው የገባቻቸው መሀላዎችና ቃል ኪዳኖች መፈጸም አለባቸው፡፡6ሆኖም ግን፣ አባቷ የገባቻቸውን መሀላዎች ሁሉና የከበሩ ቃል ኪዳኖቿን ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ነገር ቢሰማ፣ ደግሞም በዚያው ቀን ማድረግ ያለበትን ቢነግራት መሀላዋን ለመፈጸም አትገደድም፡፡ ያህዌ ይቅር ይላታል ምክንያቱም አባቷ ማድረግ ያለባትን ነግሯታል፡፡ 7እነዚያ መሀላዎች እያሉባት ባል ብታገባ ወይም በችኮላ መሀላ ብታደርግና ራሷን ግዴታ ውስጥ ብታስገባ እነዚያ ግዴታዎች መፈጸም አለባቸው፡፡8ነገር ግን ባሏ በዚያው ቀን ሰምቶ ቢከለክላት የገባቸውን መሀላና በችኮላ ራሷን ያሰረችበትን መሀላዋን ያስቀራል፡፡ ያህዌ ከዚህ ነጻ ያደርጋታል፡፡9ባሏ የሞተባት ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት ግን ራሷን የሰራችባቸው ነገሮች ሁሉ ተፈፃሚ ይሆኑባታል፡፡ 10ከባሏ ቤተሰቦች ጋር ያለች ሴት ብትሳል ራሷን በቃል ኪዳን መሀላ ብታስር፣ 11እና ባልዋ ሰምቶ ምንም ነገር ባይነግራት ስእለቷን ባያስቀር፣ ስዕለቶቿ ሁሉ መፈጸም አለባቸው፡፡ ራሷን ያሰረችባቸው ቃልኪዳኖች ሁሉ መፈጸም አለባቸው፡፡12ነገር ግን ባሏ ስለ ስዕለቶቿ በሰማ ቀን እንዲቀሩ ካደረገ፣ ስለ ስዕለቶቿ ወይም ቃልኪዳኖቿ ከከንፈሯ የወጡ ነገሮች ሁሉ የግዴታ መፈጸም አይኖርባቸውም፡፡ ባልዋ አስቀርቷቸዋል፡፡ ያህዌ ነጻ ያደርጋታል፡፤13አንዲት ሴት የገባችውን እያንዳንዱን መሀላ ወይም ስእለት እንድታጥፍ የሚያደርጋትን አንዳች ነገር በባሏ ሊጸና ወይም ሊሻር ይችላል፡፡ 14ነገር ግን ቀናት ሲያልፉ ባሏ አንዳች ካልነገራት፣ ስዕቶቿን ሁሉ እና ቃል የገባቻቸውን ነገሮች ያፀናባታል፡፡ ስዕቶቿንና መሀላዎቿን የሚያፀናባት ስለእነዚህ በሰማበት ጊዜ ምንም ስላልነገራት ነው፡፡15ባሏ የሚስቱን ስዕለት ከሰማ ከረጅም ጊዜ በኋላ ሊሽር ቢሞክር፣ ስለእርሷ ኃጢአት ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡” 16ያህዌ ሙሴ እንዲያውጃቸው የሰጠው ቋሚ መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፡፡ በአንድ ወንድና በሚስቱ መሀል፣ እንዲሁም በአባትና በወጣትነቷ በአባቷ ቤት ስለምትኖር ሴት ልጁ ያህዌ የሰጠው ቋሚ መመሪያ ይህ ነው፡፡
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“የእስራኤል ህዝብ ምድያማውያንን ይበቀሉ፡፡ ያን ካደረግህ በኋላ፣ ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ፡፡”3ስለዚህም ሙሴ ለህዝቡ እንዲህ አለ፣ “በምድያማውያን ላይ የያህዌን በቀል ይፈጽሙ ዘንድ ከወንዶቻችሁ አንዳንዶቹን ወደ ጦርነት እንዲወጡ አስታጥቋቸው፡፡ 4እያንዳንዱ በእስራኤል ውስጥ ያለ ጎሳ ለጦርነት አንድ ሺህ ወታደሮችን መላክ አለበት፡፡” 5ስለዚህ ከእስራኤል ብዙ ሺህ ወንዶች መሀል ከእያንዳንዱ ጎሳ አንድ ሺህ ሰው ለጦርነት ቀረበ፣ በጠቅላላው አስራ ሁለት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡6ከዚያ ሙሴ ከየጎሳው አንድ ሺህ ሰዎችን ከካህኑ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሃስ ጋር እና ከተቀደሰው ስፍራ ከጥቂት ቁሳቁሶችና እንዲሁም ምልክቶችን ለማሰማት በእጁ ያሉትን መለከቶች አስይዞ ወደ ጦርነት ላካቸው፡፡ 7እነርሱም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ከምድያማውያን ጋር ተዋጉ፡፡ ሰዎቹን ሁሉ ፈጇቸው፡፡ 8የምድያምን ነገስታት ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር ሑርን እና እና ሪባን ከተቀሩት ጋር በሰይፍ ገደሏቸው፡፡9የእስራኤል ጦር፤ የምድያምን ሴቶች፣ ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውን ሁሉ፣ መንጋዎቻቸውን እና ንብረቶቻቸውን ሁሉ ምርኮ አደረጉ፡፡ እዚህን ሁሉ ዘርፈው ወሰዱ፡፡ 10የሚኖሩባቸውን ከተሞችና ሰፈሮች ሁሉ አቃጠሉ፡፡11የሰውና እንስሳት ምርኮዎቻቸውንና እስረኞችን ወሰዱ፡፡ 12እስረኞችን፣ የዘረፉትን፣ እና የያዙትን ነገሮች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛር፣ እና ወደ እስራኤል ማህበረሰብ አመጡ፡፡ እነርሱም እነዚህን ኢያሪኮ አጠገብ ዮርዳስ፣ በሞአብ ሜዳ ላይ ወደ ሚገኘው ሰፈር አመጡ፡፡13ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛር፣ እና የማህበረሰቡ መሪዎች በሙሉ ሊቀበሏቸው ከሰፈር ወጡ፡፡ 14ሙሴ ግን ከጦርነት በተመለሱት በጦሩ መኮንኖች፣ በሻለቃዎችና በመቶ አለቆች ላይ ተቆጥቶ ነበር፡፡ 15ሙሴ መኮንኖቹን እንዲህ አላቸው፣ “ሴቶቹ ሁሉ በህይወት እንዲኖሩ ተዋችኋቸውን?”16እነዚህ ሴቶች በበለዓም ምክር፣ የእስራኤል ህዝብ በያህዌ ላይ በፌጎር ኃጢአት እንዲሰራና መቅሰፍት እንዲወርድበት ያደረጉ ናቸው፡፡ 17ስለዚህ አሁን፣ ትናንሾቹን ወንዶች ሁሉ ግደሉ፣ ከወንድ ጋር የተኙ ሴቶችን ሁሉ ግደሉ፡፡18ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁትን ወጣት ልጃገረዶች ግን ለራሳችሁ ውሰዱ፡፡ 19ከእስራኤል ሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት መቆየት አለባችሁ፡፡ ማንንም ሰው የገደላችሁ ሁሉና ወይም የሞተ ሰው የነካችሁ ሁሉ በሶስተኛው ቀንና በሰባተናው ቀን ራሳችሁን ማንጻት አለባችሁ፡፡ እናንተና ምርኮኞቻችሁ መንጻት አለባችሁ፡፡ 20ልብሶቻችሁን አንጹ፣ ከእንስሳት ቆዳ እና ከፍየል ፀጉር የተሰሩ ማናቸውንም ነገሮች፣ እንዲሁም ከእንጨት የተሰሩ ነገሮችን ሁሉ አንጹ፡፡”21ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነት የሄዱትን ወታደሮች እንዲህ አላቸው፣ “ይህ ያህዌ ለሙሴ የሰጠው የተደገነገገ ህግ ነው፡ 22ወርቁ፣ ብሩ፣ ነሀሱ፣ ብረቱ፣ ቆርቆሮውና እርሳሱ 23እና ማናቸውም እሳት የሚቋቋምን ነገር በእሳት ውስጥ አሳልፉት እናም የተቀደሰ ይሆናል፡፡ እነዚያን ነገሮች በማንጻት ውሃ አንጹዋቸው፡፡ በእሳት ውስጥ ማለፍ የማይችለውን ማናቸውንም ነገር በውሃ አንጹ፡፡ 24እናም ልብሶችሁን በሰባተኛው ቀን እጠቡ፣ ከዚያም የተቀደሳችሁ ትሆናላች፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ እስራኤል ሰፈር መግባት ትችላላችሁ፡፡”25ከዚያም ያህዌ ሙሴን እንደዚህ አለው፣ 26”ሰዎችም ይሁኑ እንስሳት፣ የተማረኩትንና የተወሰዱትን ነገሮች ሁሉ ቁጠሩ፡፡ አንተ፣ ካህኑ አልዓዛር፣ እና የማህበረሰቡ መሪዎች እንዲሁም የጎሳ አባቶች 27ምርኮዎቹን ለሁለት ክፍል ክፈሏቸው፡፡ ለጦርነት በወጡ ወታደሮችና በተቀረው ማህበረሰብ መሃል ምርኮውን አከፋፍሉ፡፡28ከዚያ ወደ ጦርነት ከወጡ ወታደሮች ለእኔ የሚሰጥ ግብር ጣል፡፡ ይህ ግብር ከሰዎችም ይሁን፣ ከቀንድ ከብት፣ ከአህዮች፣ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ከየአምስት መቶው አንዱ ይሁን፡፡ 29ይህን ግብር የእነርሱ ከሆነው ከከፊሉ ድርሻቸው ወስደህ ለእኔ የሚቀርብ ስጦታ እንዲሆን ለካህኑ አልዓዛር ስጠው፡፡30ደግሞም ከከፊሉ የእስራኤል ህዝብ ድርሻ ከሆነው ሰዎች፣ ከቀንድ ከብቶች፣ ከአህዮች፣ ከበጎች ከፍየሎች፣ ከየሀምሳው መሀል አንዱን ወሰድ፡፡ እነዚህን ማደሪያዬን ለሚያገለግሉት ለሌዋውያን ስጣቸው፡፡” 31ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ፡፡32ወታደሮቹ በዝብዘው የወሰዱት ምርኮ 675000 በጎች፣ 33ሰባሁለት ሺህ በሬዎች፣ 34ስልሳ አንድ ሺህ አህዮች፣ 35እና ሰላሳ ሁለት ሺህ ከወንድ ጋር ያልተኙ ሴቶች ነበሩ፡፡36ለወታደሮች የተጠበቀላቸው ግማሹ 337000 በጎች ነበሩ፡፡ 37ከዚህ ውስጥ የያህዌ ድርሻ 675 በጎች ነበር፡፡ 38በሬዎቹ ሰላሳ ስድስት ሺህ ሲሆኑ የያህዌ ግብር 72 ነበር፡፡39አህዮች 30500 ነበሩ፣ ከዚህ ውስጥ የያህዌ ድርሻ 61 ነበር፡፡ 40ሰዎቹ አስራ ስድስት ሺ ሴቶች ነበሩ፣ ከዚህ ውስጥ ለያህዌ የተሰጠው ግብር 32 ነበር፡፡ 41ሙሴ ለያህዌ የሚቀርቡትን ስጦታዎች ግብር ወሰደ፡፡ እርሱም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ለካህኑ አልዓዛር ይህንን ሰጠ፡፡42ሙሴ ወደ ጦርት ከሄዱ ወታደሮች የወሰደውን የእስራኤል የሆነውን ግማሽ ምርኮ በተመለከተ፤ 43የማህበረሰቡ ከምርኮ ግማሹ 337500 በጎች፣ 44ሰላሳ ስድስት ሺህ በሬዎች፣ 45ሰላሳ ሺ አምስት መቶ አህዮች፣ 46እና አስራ ስድስት ሺ ሴቶች ነበሩ፡፡47ከእስራኤል ህዝብ ግማሽ ከሆነ ድርሻው፣ ሙሴ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት ከየአምሳው መሀል አንድ ወሰደ፡፡ እርሱም ያህዌ እንዲያደርገው ባዘዘው መሠረት የያህዌን ማደሪያ ለሚያገለግሉ ለሌዋውያን እነዚህን ሰጠ፡፡48ከዚያ የሰራዊቱ መኮንኖች፣ የሻለቃ አዛዦች እና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ መጡ፡፡ 49እንዲህም አሉ፣ “ባሮችህ በእኛ ስር ያሉትን ወታደሮች ቆጠርን፣ አንድ ሰው እንኳን አልጎደለም፡፡50እኛ የያህዌን ስጦታ አምጥተናል፣ እያንዳንዱ ሰው ያገኘውን፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ አልቦዎችና አንባሮች፣ የጣት ቀለበቶች፣ የጆሮ ጉትቻዎች፣ እና የአንገት ሀብሎች ማስተስረያ እንደሆነን በያህዌ ፊት አምጥተናል፡፡” 51ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁንና የእጁ ጥበብ ውጤት የሆኑትን የጌጥ ዕቃዎች ሁሉ ከእነርሱ ተቀበሉ፡፡52ለያህዌ ያቀረቧቸው የወርቅ ስጦታዎች ሁሉ ከሻለቃዎችና ከመቶ አለቃዎች የተቀበሏቸው ስጦታዎች ክብደታቸው 16750 ሰቅሎቸ ነበር፡፡ 53እያንዳንዱ ወታደርና እያንዳንዱ ሰው ከምርኮው ለራሱ ወስዷል፡፡ 54ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ወርቁን ወሰዱ፡፡ ለያህዌ የእስራኤል ህዝብ ማስታወሻ አድርገው ወርቁን ወደ መገናኛው ድንኳን አስገቡት፡፡
1በዚህ ጊዜ የሮቤልና የጋድ ትውልዶች ብዙ የቀንድ ከብቶች ነበራቸው፡፡ የኢያዜርንና የገለዓድን ምድር ሲመለከቱ፣ ምድሪቱ ለከብቶቻቸው መልካም መሆኗን አዩ፡፡ 2ስለዚህ የጋድና ሮቤል ትውልዶች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛርና ወደማህበሩ መሪዎች መጥተው እንዲህ አሉ፣ 3“ያህዌ በእስራኤል ህዝብ ፊት የመታው አጣሮት፣ ዲቦን ኢያዜር፣ ኒምራ፣ ሐሴናን፣ ኤልያሊ፣ ሴባማ፣ ናባውና ባያን4ምድሩ ለከብቶች መልካም ነው፡፡ እኛ፣ የአንተ አገልጋዮች ብዙ ከበቶች አሉን፡፡” 5ደግሞም እንዲህ አሉ፣ “በፊትህ ሞገስ አግኝተን ከሆነ፣ ይህች ምድር ለእኛ ለአገልጋዮችህ ርስት ሆና ትሰጠን፡፡ ዮርዳኖስን አቋርጠን እንድንሄድ አታድርግ፡፡”6ሙሴ ለጋድና ሮቤል ትውልዶች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እናንተ በዚህ ተቀምጣችሁ ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሊሄዱ ይገባልን? 7የእስራኤል ህዝብ ያህዌ ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ ለምን ልባቸውን ታደክማላችሁ?8አባቶቻችሁ ከቀዴስ በርኔ ምድሪቱን እንዲያዩ በላክኋቸው ጊዜ ያደረጉት ተመሳሳይ ነገር ነበር፡፡ 9እነርሱ ወደ ኤሽኮል ሸለቆ ሄዱ፡፡ ምድሪቱን ካዩ በኋላ የእስራኤልን ልብ አደከሙ፤ ስለዚህም ያህዌ ወደ ሰጣቸው ምድር ለመግባት ተቃወሙ፡፡10በዚያ ቀን የያህዌ ቁጣ ነደደ፡፡ በመሀላ እንዲህ አለ፣ 11‘ከግብጽ ምድር ከወጡ ሰዎች ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ከሆናቸው፣ መሃል አንዳቸውም ለአብርሃም፣ ለይስሃቅ፣ እና ለያዕቆብ ልሰጣቸው በመሀላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩም፣ ምክንያቱም እነርሱ በሙሉ ልባቸው አልተከተሉኝም፤ 12ከቂኔዛዊው ከዩፎኒ ልጅ ከካሌብ፣ እና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር፡፡ ካሌብና ኢያሱ ብቻ በሙሉ ልባቸው ተከትለውኛል፡፡’13ስለዚህም የያህዌ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፡፡ በፊቱ ክፉ ያደረገው ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ ለአርባ አመታት በምድረበዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው፡፡ 14እናንተ እንደ ሌሎች ኃጢአተኛ ሰዎች የያህዌን ቁጣ በእስራኤል ላይ ለመጨመር በአባቶቻችሁ እግር ተተካችሁ፡፡ 15እርሱን ከመከተል ፊታችሁን ብታዞሩ፣ እርሱ እስራኤልን ዳግም በበረሃ ይተዋል እናንተም ይህን ሁሉ ህዝብ ታጠፋላችሁ፡፡”16ስለዚህም ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉ፣ “በዚህ ለከብቶቻችን አጥር እና ለቤተሰቦቻችን ከተማ እንድንገነባ ፍቀድል፡፡ 17ሆኖም፣ እኛ እራሳችን ወደ ስፍራቸው እስክናባርራቸው ድረስ ከእስራኤል ጦር ጋር ለመውጣት እንነሳለን እንታጠቃንም፡፡ ቤተሰቦችን ግን እስከ አሁን በዚህ ምድር ከሚኖሩ ሌሎች ሰዎች የተነሳ በተቀጠሩ ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ፡፡18የእስራኤል ህዝብ እያንዱ ሰው ርስቱን እስኪያገኝ ድረስ ወደ ቤቶቻችን አንመለስም፡፡ 19እኛ ከእነርሱ ጋር ከዮርዳኖስ ማዶ ያለውን ምድር አንወርስም፣ ምክንያቱም የእኛ ርስት እዚህ በዮርዳኖስ ምስራቅ በኩል ያለው ነው፡፡”20ስለዚህም ሙሴ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “የተናገራችሁትን ካደረጋችሁ፣ ወደ ጦርነት በያህዌ ፊት ለመውጣት ራሳችሁን ካስታጠቃችሁ፣ 21ከዚያ በኋላ እያንዳንዳቸው የእናንተ የታጠቁ ወንዶች ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያባርራቸው ድረስ በያህዌ ፊት ዮርዳኖስን ማቋረጥ አለባቸው፡፡ 22ደግሞም ምድሪቱ በእርሱ ፊት ጸጥ ብላ ትገዛለች፡፡ ከዚያ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፡፡ እናንተም በያህዌና በእስራኤል ፊት ጥፋተኛ አትሆኑም፡፡ ይህ ምድር በያህዌ ፊት ርስታችሁ ይሆናል፡፡23እንዲህ ካላደረጋችሁ ግን፣ በያህዌ ፊት በደለኞች ትሆናላችሁ ኃጢአታችሁ እንደሚከተላችሁ እርግጠኞች ሁኑ፡፡ 24ለቤተሰቦቻችሁ ከተሞችን ገንቡ ለበጎቻችሁም ጉረነዎች ስሩላቸው፤ ከዚያ ያላችሁትን አድርጉ፡፡” 25የጋድና ሮቤል ትውልዶች ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “እኛ አገልጋዮችህ አንተ ጌታችን ያዘዝከንን እናደርጋለን፡፡26ልጆቻችን፣ ሚስቶቻችን፣ መንጎችንና የቀን ከብቶቻችን በገለዓድ ከተሞች ይቆያሉ፡፡ 27ሆኖም፣ እኛ፣ የአንተ አገልጋዮች ለጦርነት በያህዌ ፊት እንወጣን፤ ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ሰው አንተ ጌታችን እንዳልከው ያደርጋል፡፡”28ስለዚህም ሙሴ ለካህኑ አልዓዛር፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና በእስራኤል ህዝብ መሃል የጎሳዎች አባቶች ለሆኑ መሪዎች እነርሱን በሚመለከት መመሪያዎቻችን ሰጠ፡፡ 29ሙሴ እንዲህ አላቸው፣ “የጋድና የሮቤል ትውልዶች ከእናንተ ጋር ዮርዳስን ቢሻገሩና በያህዌ ፊት ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ወንድ እና ምድሪቱ በፊታችሁ ቢገዙ፣ የገለዓድን ምድር ለእነርሱ ርስት አድርገህ ትሰጣቸዋለህ፡፡ 30ነገር ግን ታጥቀው ከአንተ ጋር ዮርዳኖስን ባይሻገሩ፣ ርስታቸውን በከነአን ምድር ከአንተ ጋር ያገኛሉ፡፡”31ስለዚህም የጋድና ሮቤል ትውልዶች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ያህዌ ለእኛ ለባሮችህ እንደተናገረው፣ የምናደርገው ነገር ይህ ነው፡፡ እንሻገራለን፡፡ 32እኛ ታጥቀን በያህዌ ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፣ ነገር ግን የተወረሰው ርስታችን በዚህኛው የዮርዳስ ክፍል ከእኛ ጋር ይቀራል፡፡”33ስለዚህ ሙሴ ለጋድና ለሮቤል ትውልዶች፣ እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ከፊል ነገድ፤ የአሞውያንን ንጉስ የሴዎንን ግዛት እና የባሳንን ንጉስ የዓግን ግዛቶች ሰጣቸው፡፡ ለእነርሱ ምድሪቱን ሰጣቸው፣ እንዲሁም ከተማዎቿን ከዳርቻዎቻቸው ጋር እና በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችን አደላቸው፡፡34የጋድ ትውልዶች ዲቦንን፣ አጣሮትን፣ አሮዔርን፣ 35ዓጥሮት ሾፋንን፣ አያዜርን፣ ዮግብሃን፣ 36ቤት ነምራንን እና ቤት ሃራንን የተቀጠሩ ከተሞችና ለበጎች ጉረኖዎች ያላቸው አድርገው እንደገና ገነቧቸው፡፡37የሮቤል ትውልዶች ሐሴቦንንና፣ ኤልያሊንና ቂርያትይምን፣ 38ናባውን፣ በአልሜዎንን (ስማቸው በኋላ ተቀይሯል) እና ሴባማንን እንደገና ገነቧቸው፡፡ እነርሱም ዳግም ለገነቧቸው ከተሞች ሌላ ስሞችን ሰጡ፡፡ 39የምናሴ ልጅ የማኪር ትውልዶች ወደ ገለዓድ ሄደው በውስጧ ይኖሩ ከነበሩት ከአሞራውያን ከለአድን ወሰዱ፡፡40ከዚያ ሙሴ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ገለዓድን ሰጠው፣ የእርሱም ሰዎች መኖሪያችን በዚያ አደረጉ፡፡ 41የምናሴ ልጅ ኢያዕር ሄዶ ከተማቸውን ይዞ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ሰየማቸው፡፡ 42ኖባህ ሄዶ ቄናትንና መንደሮቿን ይዞ፣ በራሱ ስም ኖባህ ብሎ ሰየማት፡፡
1የእስራኤል ህዝብ በሙሴና አሮን መሪነት በየታጣቂ በድኖቻቸው ሆነው ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ ያደረጓቸው ጉዞዎች እነዚህ ነበሩ፡፡ 2ሙሴ በያህዌ እንደታዘዘው፣ ከተነሰቡት አንስቶ እስሚሄዱበት ድረስ ያሉትን ስፍራዎች ጻፈ፡፡ ከስፍራ ስፍራ ያደረጓቸው እንቅስቃሴዎች እነዚህ ነበሩ፡፡3በመጀመሪያው ወር፣ በወሩ በአስራ አምስተኛ ቀን ከራምሴ ተነስተው ተጓዙ፡፡ ከፋሲካው በኋላ በማለዳ፣ የእስራኤል ሕዝብ በግልጽ ግፃዊያን ሁሉ እያይዋቸው ወጡ፡፡ 4ግብፃዊያን ያህዌ በመካከላቸው የገደላቸውን በኩሮቻቸውን እየቀበሩ ሳለና በአማልክቶቻቸው ላይ ጥፋት እያደረሰ ሳለ ይህ ሆነ፡፡5የእስራኤል ሕዝብ ከራምሴ ወጥቶ በሱኮት ሰፈረ፡፡ 6ከሱኮት ወጥተው በኤታሞ፣ በምድረ በዳው 7ከኤታም ወጥተው ከበአልዛፎን በተቃራኒ ወደ ፊሀሔርት ተመልሰው በሚግዶል በተቃራኒ ሰፈሩ፡፡8ከዚያም ከፈሀሔርት በተቃራኒ ተነስተው በባህሩ መሃል ወደ ምድረበዳው ሄዱ፡፡ ለሶስት ቀናት በኤታም ምድረ በዳ ተጉዞው በማራ ሰፈሩ፡፡ 9ከማራ ተነስተው ኤሊም ደረሱ፡፡ በኤሊም አስራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የቴምር ዛፎች ነበሩ፡፡ የሰፈሩት በዚያ ስፍራ ነው፡፡ 10ከኤሊም ተነስተው ቀይ ባህር አጠገብ ሰፈሩ፡፡11ከቀይ ባህር ተነስተው በሲን ምድረበዳ ሰፈሩ፡፡ 12ከሲን ምድረበዳ ተነስተው በራፍቃ ሰፈሩ፡፡ 13ከራፍቃ ተነስተው በኤሉስ ሰፈሩ፡፡ 14ከኤሉስ ተነስተው የሚጠጣ ውሃ በሌለበት ሰራፊዲም ሰፈሩ፡፡15ከራፊዲም ተነስተው በሲና ምድረበዳ ሰፈሩ፡፡ 16ከሲና ምድረበዳ ተነስተው በቂብሮት ሃታቫ ሰፈሩ፡፡ 17ከቂብሮት ሃታቫ ተነስተው በሐዴሮት ሰፈሩ፡፡ 18ከሐዴሮት ተነስተው በሪትማ ሰፈሩ፡፡19ከሪትማ ተነስተው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ፡፡ 20ከሬምን ዘፋሬስ ተነስተው በልብና ሰፈሩ፡፡ 21ከልብና ተነስተው በሪሳ ሰፈሩ፡፡ 22ከሪሳ ተነስተው በቀሄላታ ሰፈሩ፡፡23ከቀሄላታ ተነስተው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ፡፡ 24ከሻፍር ተራራ ተነስተው በሐራዳ ሰፈሩ፡፡ 25ከሐራዳ ተነስተው በመቅሄሎት ሰፈሩ፡፡ 26ከመቅሄሎት ተነስተው በታሐት ሰፈሩ፡፡27ከታሐት ተነስተው በታራ ሰፈሩ፡፡ 28ከታራ ተነስተው በሚትቃ ሰፈሩ፡፡ 29ከሚትቃ ተነስተው በሐሹምና ሰፈሩ፡፡ 30ከሐሽምና ተነስተው በምሴሮት ሰፈሩ፡፡31ከሞሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ፡፡ 32ከብኔያዕቃን ተነስተው በሖር ሃጊድጋድ ሰፈሩ፡፡ 33ከሖር ሃጊድጋ ተነስተው በዮጥባታ ሰፈሩ፡፡ 34ከዮጥባታ ተነስተው በዔብሮና ሰፈሩ፡፡35ከዔብሮና ተነስተው በዔድዮን ጋብር ሰፈሩ፡፡ 36ከዔድዮን ጋብር ተነስተው በቃዴስ በምትገኘው ጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፡፡ 37ከቃዴስ ተነስተው በሖር ተራራ፣ በኤዶም ምድር ዳርቻ ሰፈሩ፡፡38ካህኑ አሮን፤ በያህዌ ትዕዛዝ ወደ ሖር ተራራ ወጣ፣ የእስራኤል ህዝብ ከግብጽ ምድር በወጣበት በአርባኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ በወሩ በመጀመሪያው ቀን ካህኑ አሮን በዚያ ሞተ፡፡ 39አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት ዕድሜው 123 ነበር፡፡40በከነዓን ምድር በደቡባዊ በረሃ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉስ የእስራኤልን ህዝብ መምጣት ሰማ፡፡41እነርሱ ከሖር ተራራ ተነስተው በሴልምና ሰፈሩ፡፡ 42ከሴልምና ተነስተው በፋኖን ሰፈሩ፡፡ 43ከፋኖን ተነስተው በአቦት ሰፈሩ፡፡44ከአቦት ተነስተው በሞአብ ዳርቻ በኢየ አባሪም ሰፈሩ፡፡ 45ከኢየ አባሪም ተነስተው በዲቦን ጋድ ሰፈሩ፡፡ 46ከዲቦን ጋድ ተነስተው በዓልምን ዲብላታይም ሰፈሩ፡፡ 46ከዲቦን ጋድ ተነስተው በዓልምን ዲብላታይም ሰፈሩ፡፡47ከዓልምን ዲብላታይም ተነስተው ከናባው ተራራ በተቃራኒ በዓብሪም ተራራ ሰፈሩ፡፡ 48ከዓብሪም ተራራ ተነስተው በሞብ ሜዳዎች በዮርዳኖስ ኢያሪኮ ላይ ሰፈሩ፡፡ 49በሞብ ሞአብ ዮርዳስ ላይ ከቤት የሺሞት እስከ አቤልስጢም ድረስ ሰፈሩ፡፡50ያህዌ ሙሴን በሞአብ ሜዳዎች ዮርዳስ ውስጥ በኢያሪኮ ሳለ እንዲህ አለው፣ 51“ለእስራኤላዊያን እንዲህ በላቸው፣ ‘ዮርዳኖስን አቋርጣችሁ ወደ ከነዓን ስትገቡ፣ 52የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አስወጡ፡፡ የተቀረጹ ምስሎቻቸውን በሙሉ አጥፉ፡፡ የማምለኪያ ስፍራዎቻቸውንና የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ሁሉ ደምስሱ፡፡53የምድሪቱን ሀብት ውሰዱ በዚያም መኖር ጀምሩ፣ ምክንያቱም እኔ ምድሪቱን ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቻቸኋለሁ፡፡ 54ምድሪቱን በእጣ እንደየ ጎሳው ብዛት ውረሱ፡፡ ብዙ ህዝብ ላለው ጎሳ ሰፊ መሬት ስጥ፣ አነስተኛ ቁጥር ላለው ጎሳ አነስ ያለ መሬት ስጥ፡፡ እያንዳንዱ ጎሳ እጣው በወደቀለት ስፍራ ያ መሬት ርስቱ ይናል፡፡ ምድሪቱን በአባቶችሁ ጎሳ መሰረት ትወርሳላችሁ፡፡55የምድሪቱን ነዋሪዎች ከፊታችሁ ጨርሳችሁ ባታስወጡ ግን፣ እንዲቀሩ ያደረጋችኋቸው ሰዎች በዐይናችሁ ውስጥ እንደገባ ባዕድ አካል እና በጎናችሁ እንደገባ እሾህ ይሆኑባችኋል፡፡ በመትኖሩበት ምድር ሕይወታችሁን ከባድ ያደርጉባችኋል፡፡ 56እኔ በእነዚህ ህዝቦች ላይ ላደርስባቸው ያቀድኩትን በእናንተም ላይ ደግሞ አደርገዋለሁ፡፡’”
1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2“የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘የእናንተ ወደምትሆን የከነዓን ምድርና ወደ ድንበሮቿ ስትገቡ፣ 3ደቡባዊ ድንበራችሁ ከሲና ምድረ በዳ እስከ ኤዶም ይደርሳል፡፡ የደቡባዊ ድንበር ምስራቃዊ ጫፍ በጨው ባህር ደቡባዊ ጫፍ ድረስ ይሆናል፡፡4ከአቅራቢም ኮረብታ ድንበራችሁ ወደ ደቡብ ይዞርና በሲና ምድረበዳ በኩል ያልፋል፡፡ ከዚያ ተነስቶ፣ በቃዴስ በርኔ ደቡብ ያልፍና ወደ ሐጸር አዳር እና ርቆ ዓጽምን ይደርሳል፡፡ 5ከዚያ ተነስቶ፣ ድንበሩ ከጽሞን ወደ ግብጽ ጅረት ዞሮ እስከ ባህሩ ይከተለዋል፡፡6ምዕራባዊው ድንበር የታላቁ ባህር ዳርቻ ይሆናል፡፡ ይህ ምዕራባዊ ድንበራችሁ ይሆናል፡፡7ሰሜናዊ ድንበራችሁ ከታላቁ ባህር እስከ ሆር ተራራ እስከ ምትይዙት ስፍራ ድረስ ይሰፋል፣ 8ከዚያ ከሖር ተራራ እስከ ሌና ሐማት፣ ከዚያ እስከ ጽዳድ ይደርሳል፡፡ 9ከዚያ ድንበሩ እስከ ዚፍሮን ይቀጥልና ሐጻር ዔርን ሲደርስ ይጨርሳል፡፡ ይህ ሰሜናዊ ድንበራችሁ ይሆናል፡፡10ምስራቃዊ ድንበራችሁን ከሐጸር ዔናን በደቡብ እስከ ሴፋም ታደርጋላችሁ፡፡ 11ምስራቃዊ ድንበራችሁ ታች እስከ ሴፋም ወርዶ በዓይን ምስራቅ በኩል ራብላ ይደርሳል፡፡ ድንበሩ እስከ ከኔሬት ባህር ምስራቅ ይዘልቃል፡፡ 12ከዚያ ድንበሩ በደቡብ በዮርዳኖስ ወንዝ በኩል እስከ ጨው ባህር እና ታች የጨው ባህር ምስራቅ ዳርቻ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ይህች ድንበሩን ተከትሎ ዙሪያውን በሙሉ የእናንተ ምድራችሁ ናት፡፡13ሙሴ የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ ሲል አዘዘ፣ “ያህዌ ለዘጠኙ ጎሳዎችና ለአንዱ ጎሳ እኩሌታ እንዲሰጣችሁ ያዘዘው፣ በዕጣ የምትካፈሏት ምድር ይህች ናት፡፡ 14የሮቤል ጎሣ ትውልዶች እና የጋድ ጎሣ ትውልዶች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ በየአባቶቻቸው ጎሣዎች የንብረት አከፋፈልን ስርዓት ተከትለው ርስታቸውን ተቀብለዋል፡፡ 15ሁለቱ ጎሣዎችና የአንዱ ጎሣ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ወዲያ በኢያሪኮ በስተ ምስራቅ በጸሀይ መውጫ የርስታቸውን ድርሻ ተቀብለዋል፡፡”16ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣ 17“ምድሪቱን ርስታችሁ አድርገው የሚያፋፍሏችሁ ሰዎች ስማቸው እነዚህ ናቸው፡ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፡፡ 18ለየጎሣቸው ምድሪቱን እንዲያካፍሉ ከየነገዱ አንድ መሪ ምረጡ፡፡19የሰዎቹም ስሞች እነዚህ ናቸው፡ ከይሁዳ ነገድ የዩፎኒ ልጅ ካሌብ፡፡ 20ከስምኦን ጎሣ ትውልዶች የዓሁድ ልጅ ሰላሚኤል፡፡21ከቢኒያም ጎሣ፣ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፡፡ 22መሪ ከሆነው ከዳን ጎሣ ትውልዶች፣ የዩግሊ ልጅ ቡቂ፡፡ 23ከዮሴፍ ትውልዶች፣ መሪ ከሆነው ከምናሴ ትውልዶች የሱፊድ ልጅ አኒኤል፡፡24መሪ ከሆነው ከኤፍሬም ጎሣ ትውልዶች፣ የሺፍጣን ልጅ ቱሙኤል፡፡ 25መሪ ከሆነው ከዛብሎን ጎሣ ትውልዶች የፈርናክ ልጅ ኤሊሳፈን፡፡ 26መሪ ከሆነው ከይሳኮር ጎሣ ትውልዶች፣ የሖዛ ልጅ ፈልጢኤል፡፡27መሪ ከሆነው ከኤሴር ጎሣ፣ የሴሌሚ ልጅ አሒሁድ፡፡ 28መሪ ከሆነው ከንፍታሌም ጎሳ ትውልዶች፣ የዓሚሁድ ልጅ ፈዳሄል” ናቸው፡፡ 29ያህዌ እነዚህን ሰዎች የከነዓንን ምድር እንዲያካፍሉና ለእያንዳንዱ የእስራኤል ጎሣዎች ድርሻቸውን እንዲሰጡ አዘዘ፡፡
1ያህዌ ሙሴን በሞአብ ሜዳ ዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ እንዲህ አለው፣ 2”የእስረኤል ሰዎችን ለሌዋውያን ርስታቸው ከሆነው ከድርሻቸው እንዲሰጧቸው እዘዝ፡፡ የሚኖሩባቸውን ከተሞችና በዙሪያቸውም የግጦሽ መሬት ይስጧቸው፡፡3ሌዋውያን እነዚህን ከተሞች መኖሪያቸው ያድርጓቸው፡፡ የግጦሽ መሬቱ ለከብቶቻቸው ለመንጎቻቸው እና ለእንስሳቻቸው ይሁኑ፡፡ 4ለሌዋውያኑ የምትሰጣቸው በከተሞቹ ዙሪያ የሚገኘው የግጦሽ መሬት ከከተማ ቅጥር በየአቅጣጫው ስፋቱ አንድ ሺህ ክንድ ይሆናል፡፡5ከከተማዋ በምስራቅ አቅጣጫ ሁለት ሺህ ክንድ ለካ፣ በስተደቡብ በኩልም ሁለት ሺህ ክንድ ለካ፣ በምዕራብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፣ እና በሰሜን በኩል ሁለት ሺህ ክንድ ለካ፡፡ ይህ በከተማቸው ዙሪያ የግጦሽ መሬት ይሆናል፡፡ ከተማይቱ በመሃል ትሆናለች፡፡6ለሌዋውያን የምትሰጧቸው ስድስቱ ከተሞች የስደተኞች ከተሞች ሆነው ያገለግሉ፡፡ እነዚህን ከተሞች በነፍስ መግደል ለተከሰሱ መሸሻ ስፍራ እንዲሆኑ ስጣቸው፡፡ እንዲሁም ሌሎች አርባ ሁለት ከተሞችን ስጣቸው፡፡ 7ለሌዋውያን የምትሰጣቸው ከተሞች በጠቅላላው አርባ ስምንት ይሆናሉ፡፡ ከከተሞቹ ጋር የግጦሽ መሬትም ትሰጣቸዋለህ፡፡8ብዙ የሆኑ የእስራኤል ህዝብ ጎሳዎችና ብዙ መሬት ያላቸው ጎሣዎች ብዙ ከተሞች ይሰጣቸዋል፡፡ አነስተኛዎቹ ጎሣዎች ጥቂት ከተሞች ይሰጣቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ነገድ እንደ ተቀበለው እንደ ድርሻው መጠን ለሌዋውያኑ መስጠት አለበት፡፡”9ከዚያም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 10“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ዮርዳኖስን አቋርጣችሁ ወደ ከነዓን ስትገቡ፣ 11ይሁነኝ ብሎ ሰው ያልገደለ ሰው ወደ እነዚያ ከተሞች መግባት እንዲችል የመሸሸጊየ ከተማ ሆነው የሚያገለግሉ ከተሞችን ምረጡ፡፡12እነዚህ ከተሞች ከደመኞቻችሁ የምትሸሸጉባቸው ይሁኑ፣ ስለዚህም የተከሰሰው ሰው በቅድሚያ በማህበሩ ፊት ለፍርድ ሳይቀርብ አይገደልም፡፡ 13የመሸሸጊያ ከተማ አድርጋችሁ ስድስት ከተሞችን ምረጡ፡፡14ከዮርዳኖስ ወዲያ ሶስት ከተሞችን፣ በከነዓን ምድር ደግሞ ሶስት ከተሞችን ስጡ፡፡ እነዚህ የመሸሸጊያ ከተሞች ይሆናሉ፡፡ 15እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ሰዎች፣ ለመጻተኞች፣ እና ለማናቸውም በመሀላቸው ለሚኖር ሳያውቅ ሰውን ለገደለ መሸሸጊያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡16ነገር ግን የተከሰሰው ሰው ተበዳዩን በብረት መሳሪያ ቢመታውና ተጠቂው ቢሞት፣ ተከሰሹ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ እርሱ በእርግጥ ይገደል፡፡ 17የተከሰሰው ሰው በእጁ በያዘው ድንጋይ ተበዳዩን ቢመታና ተበዳዩ ቢሞት ተከሳሹ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ በእርግጥ ይገደል፡፡ 18የተከሰሰው ሰው ተበዳዩን ሊገድል በሚችል የእንጨት መሳሪያ ቢመታውና ተበዳዩ ቢሞት ተከሳሹ በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ ሊገደል ይገባዋል፡፡19ደም ተበቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው፡፡ ሲያገኘው፣ ሊገድለው ይችላል፡፡ 20ተከሳሹ አንድን እየተደበቀ ወይም እየተሸሸገ ያለ ሰው በጥላቻ ቢገፈትረው ወይም አንዳች ነገር ቢወረውርበትና ከዚህም የተነሳ ተበዳዩ ቢሞት፣ 21ወይም በጥላቻ መትቶ ቢጥለውና ከዚህም የተነሳ ተበዳዩ ቢሞት መትቶ የገደለው በእርግጥ ይገደል፡፡ ነብስ ገዳይ ነው፡፡ ደም ተበቃዩ ነብሰ ገዳዩን ሲያገኘው ይግደለው፡፡22ነገር ግን ተከሳሹ ሰው ቀድሞ ባልታሰበበት ጥላቻ ተበዳዩን ቢመታው ወይም ሳያስበው አንዳች ነገር ወርውሮ ቢመታው፣ 23ተበዳዩን ሳይመለከት ሊገድለው የሚችል ድንጋይ ቢወረውርበት፣ ተከሳሹ የተበዳዩ ጠላት አይደለም፤ ተበዳዩን ለመጉዳት እየሞከረ አልነበረም፡፡ የሆነ ሆኖ ተበዳዩ ቢሞት፣24በዚህ ሁኔታ፣ ማህበረሰቡ በተከሳሹና በደም ተበቃዩ መሀል በእነዚህ ህጎች መሠረት ይዳኝ 25ማህበረሰቡ ተከሳሹን ከደም ተበቃዩ እጅ ያድነው፡፡ ማህበረሰቡ ተከሳሹን በመጀመሪያ ወዳሸሸበት መሸሸጊያ ከተማ ይመልሰው፡፡ ተከሳሹ፣ በቅዱሱ ዘይት የተቀባው በወቅቱ ያለው ሊቀካህን እስኪሞት ድረስ በዚያ ይኑር፡፡26ነገር ግን የተከሰሰው ሰው በማንኛውም ጊዜ ከሸሸበት ከተማ ድንበር አልፎ ቢሄድ፣ 27እና ደም ተበቃዩ ከመሸሸጊያ ከተማው ድንበር ውጭ ቢያገኘውና ቢገድለው፣ ደም ተበቃዩ በነብሰ ገዳይነት ጥፋተኛ አይሆንም፡፡ 28ለዚህም ምክንያቱ ተከሳሹ ሰው እስከ ሊቀ ካህኑ ሞት ድረስ በመሸሸጊያ ከተማው መቆየት ስለነበረበት ነው፡፡29እነዚህ ህጎች፤ በምትኖባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ በትውልዳቸው ሁሉ ለእናንተ የጸኑ ናቸው፡፡ 30ሰውን የገደለ ማንኛውም ሰው፣ በምስክሮች ቃል እየረጋገጠ መገደል አለበት፡፡ ነገር ግን የአንድ ምስክር ቃል ብቻውን ማንንም ሰው ለመግደል በቂ አይደለም፡፡31ደግሞም፣ በነብስ ገዳይነት ጥፋተኛ ለሆነ ሰው ሕይወት የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፡፡ ያ ሰው በእርግጥ ይገደል፡፡ 32ወደ መሸሸጊያ ከተማ ለሄደ የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፡፡ ሊቀ ካህኑ እስኪሞት ድረስ የነፍስ ዋጋ በመቀበል ወደ ራሱ ርስት ተመልሶ እንዲገባ አትፍቀዱለት፡፡33በዚህ መንገድ የምትኖሩባትን ምድር አታርክሱ፣ ምክንቱም በነፍስ ግድያ የሚፈስ ደም ምድሪቱን ያረክሳል፡፡ ምድር በላይዋ ደም ሲፈስ፣ ደም ካፈሰሰው ሰው ደም በስተቀር ሌላ ምንም ማስተስረያ ማድረግ አይቻልም፡፡ 34ስለዚህ የምትኖሩባትን ምድር አታርክሱ ምክንያቱም እኔ በውስጧ እኖራለሁ፡፡ እኔ፣ ያህዌ፣ በእስራኤል ሰዎች መሃል እኖራለሁ፡፡”
1ከዚያ ከዮሴፍ ትውልዶች ጎሣ የሆኑት፣ የአባቶቻቸው ቤተሰቦች መሪዎች፣ የምናሴ ልጅ በሆነው በሚኪር ልጅ ገለዓድ የተመሠረተው ጎሳ በሙሴና በእስራኤላዊያን አባቶች ቤተሰቦች አለቆች ፊት መጥተው ተናገሩ፡፡ 2እንዲህም አሉ፣ “ጌታችን ሆይ፣ ያህዌ ለእስራኤል ህዝብ ርስታቸውን በዕጣ እንድታካፍላቸው አዞሃል፡፡ የወንድማችንን የሰለጰዓድን ድርሻ ለሴት ልጆቹ እንድትሰጥ ያህዌ አዝዞህ ነበር፡፡3ነገር ግን ሴት ልጆቹ ከእስራኤል ሰዎች ከሌላ ጎሣ ወንዶችን ቢያገቡ፣ ድርሻቸው የሆነው መሬት ከአባቶቻችን ድርሻ ተነቅሎ ወደ ሌላ ጎሣ ይተላለፋል፡፡ መሬቱ የገቡበት የሌላ ጎሳ ድርሻ ይሆናል፡፡ በዚያ ሁኔታ፣ ከእኛ ርስትነት ይነቀላል፡፡ 4ይህ ሲሆን፣ የእስራኤል ኢዮቤልዩ ሲመጣ፣ የእነርሱ ድርሻ የተጋቧቸው ጎሣዎች ርስት ይሆናል፡፡ በዚህ መንገድ የእነርሱ ድርሻ ከእኛ አባቶች ጎሣ ይወሰዳል፡፡5ስለዚህም ሙሴ በያህዌ ቃል ለእስራኤል ሰዎች ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ እንዲህም አለ፣ “የዮሴፍ ትውልዶች ጎሣ የተናገሩት ትክክል ነው፡፡ 6ያህዌ ስለ ሰለጰዓድ፣ ሴት ልጆች ያዘዘው ይህ ነው፡፡ እንዲህም አለ፣ ‘የመረጡትን ያግቡ፣ ነገር ግን ማግባት ያለባቸው ከአባታቸው ጎሣ ብቻ ነው፡፡’7የእስራኤል ሰዎች ድርሻ ከአንድ ጎሣ ወደ ሌላው መሄድ የለበትም፡፡ እያንዳንዱ እስራኤላዊ የራሱን ጎሣ ድርሻ ይዞ መቀጠል አለበት፡፡8ከጎሣዋ ርስት የወረሰች እያንዳንዷ የእስራኤል ሴት፣ ማግባት ያለባት ከአባቷ ጎሣ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው እያንዳንዱ እስራኤላዊ የአባቶቹን ርስት ይዞ እንዲኖር ነው፡፡ 9ከአንዱ ጎሣ ወደ ሌላው ምንም ርስት መተላለፍ የለበትም፡፡ የእስራኤል ህዝብ እያንዳንዱ ጎሣ የራሱን ርስት ይዞ መቀጠል አለበት፡፡”10ስለዚሀ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ፡፡ 11የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ማህለህ፣ ቲርጳ፣ ጌግላ፣ ሚልካ፣ ኑዔ 12ልጅ የምናሴትን ትውልዶች አገቡ፡፡ በዚህ መንገድ፣ ርስታቸው የአባታቸው ጎሣ ርስት ሆኖ ቀረ፡፡13ያህዌ በሙሴ በኩል በሞአብ ሜዳዎች በዮርዳኖስ ኢያሪካ ላይ ለእስራኤል ሰዎች የሰጣቸው ትዕዛዛትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፡፡
1ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በምድር በዳ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ሜዳ በዓረባ፥ በፋራን፥ በጦፌል፥ በላባን፥ በሐጼሮት፥ በዲዛሃብ መካከል ሳሉ፥ ለአስራኤል ሁሉ የተናገራቸው እነዚህ ቃላት ናቸው። 2በሴይር ተራራ መንገድ ከኮሬብ እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ የአሥራ አንድ ቀን ጉዞ ነው።3በአርባኛው ዓመት በአሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሙሴ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ያዘዘውውን ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ነገራቸው። 4ይህም እግዚአብሔር በሐሴቦን ይኖር የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስታዎትና በኤድራይ ይኖር የነበረውንም የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመታ በኋላ ነበር።5በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ምድር ሙሴ እንዲህ ብሎ እነዚህን መመሪያዎች ይናገር ጀመር፦ 6እግዚአብሔር አምላካችን በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን፦ በዚህ ተራራ የኖራችሁበት ይብቃችሁ።7ጉዞኣችሁን ወደ ኮረብታማው ወደ አሞራውያን አገር ወደ ድንበሮቹም፥ ሁሉ በዓረባም በደጋውና በቆላው፥ በደቡብና በባሕር ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስ ወንዝ ሸለቆ እስከ ታላቁ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ሄዱ። 8እነሆ ምድሪቱን በፊታችሁ አድርጌአለሁ፤ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሂዱና ውረሱ።9በዚያን ጊዜ እንዲህ ብዬ ተናግሬአችሁ ነበር፦ እኔ በራሴ ብቻዬን ልሸከማችሁ አልችልም። 10እግዚአብሔር አምላካችሁ አብዝቶአችኋል፥ እነሆም እናንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዙ ናችሁ። 11የአባቶቻችሁ እግዚአብሔር አምላክ ሺህ ጊዜ ሺህ ያድርጋችሁ፤ ተስፋ እንደሰጣችሁም ይባርካችሁ።12ነገር ግን እኔ በራሴ ድካማችሁን፥ ሸክማችሁንና ክርክራችሁን እሸከም ዘንድ ብቻዬን እንዴት እችላለሁ? 13ከእናንተ መካከል ከየነገዶቻችሁ ጥበበኞች፥ አስተዋዮችና አዋቂዎች የሆኑትን ሰዎች ምረጡ፤ እኔም እነርሱን የእናንተ አለቆች አደርጋቸዋለሁ ብዬኣችሁ ነበረ። 14እናንተም እንዲህ ብላችሁ መለሳችሁ፦ የተናገርከንን ነገር ለማድረግ ለእኛ መልካም ነው።15ስለዚህም ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን ወሰድሁ፥ በእናንተም ላይ አለቆች እንዲሆኑ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳ አለቆች፥ የአሥር አለቆችና ሹማምንት በየገዶቻችሁ አደረግኋቸው። 16በዚያን ጊዜም ፈራጆቻችሁን እንዲህ ብዬ አዘዝኳቸው፦ በወንድሞቻችሁ መካከል፤ በሰውና በወንድሙ መካከልና በመጻተኛ ላይ በጽድቅ ፍረዱ።17በክርክርም ጊዜ ለማንም ፊት አድልዎ አታድርጉ፥ ታላቁን እንደምትሰሙ፥ ታናሹንም ስሙ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለሆነ የሰው ፊት መፍራት አይገባችሁም። ከክርክርም አንድ ስንኳ ቢከብዳችሁ ወደ እኔ አምጡት እኔም እሰማዋለሁ። 18በዚያን ጊዜም ልታደርጉት የሚገባችሁን ነገር ሁሉ አዘዝኋችሁ።19ከኮሬብም ተነስተን፥እግዚአብሔር አምላካችን እንዳዘዘን እንዳያችሁትም በታላቁና እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ምድረ በዳ ሁሉ ተጉዘን በተራራማው በአሞራውን አገር ሄድን፥ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን።20እኔም እንዲህ አልኋችሁ፦ እግዚአብሔር አምላካችን ወደ ሚሰጠን ወደ ተራራማው አሞራውያን አገር መጣችኋል። 21እነሆ እግዚአብሔር አምላካችሁ ምድሪቱን በፊታችሁ አድርጎአል፤ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንዳላችሁ ውጡ፥ ውረሱአት፥ አትፍሩ አትደንግጡም።22ከእናንተም ሁላችሁ ወደ እኔ መጥታችሁ እንዲህ አላችሁ፦ ምድሪቱን እንዲሰልሉልንና እናጠቃቸው ዘንድ የሚገባንን የመንገዱንና የምንገባባቸውን ከተሞች ሁኔታ ተመልሰው እንዲነግሩን ከፊታችን ሰዎችን እንድስደድ። 23ነገሩም ደስ አሰኘኝ፤ ከእናንተም ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎችን መረጥሁ። 24እነርሱም ወደ ተራራማው አገር ሄዱ፥ ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጥተው ሰለሉአት።25እነርሱም ከምድሪቱ ፍሬ በእጃቸው ወሰዱ፥ ወደ እኛም ይዘውት መጡ። እነርሱም ደግሞ፦ እግዚአብሔር አምላካችን የሚሰጠን ምድር መልካም ናት ብለውም አወሩልን።26ምድሪቷንም ማጥቃት እንቢ ብላችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፥ ። 27በድንኳናችሁም ውስጥ እንዲህ እያላችሁ አጉረመረማችሁ፦ እግዚአብሔር ስለ ጠላን እንዲያጠፋን በአሞራውያን እጅ አሳልፎ ይሰጠን ዘንድ ከግብፅ ምድር አወጣን። 28አሁን ወዴት መሄድ እንችላለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሽጉና እስከ ሰማይም የደረሱ ናችው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፤ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን እንዲቀልጥ አደረጉ።29እኔም አልኋችሁ፦ አትደንግጡ፥ እነርሱንም አትፍሩአቸው። 30በፊታችሁ የሚሄደው እግዚአብሔር አምላካችሁ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ በፊታችሁም በግብፅና በምድረ በዳ እንዳደረገላችሁ ሁሉ፤ 31ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄድዳችሁበት መንገድ ሁሉ ሰው ልጁን እንደሚሸከም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተሸከማችሁ እናንተ አይታችኋል።32ዳሩ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁን በዚህ ነገር አላመናችሁትም፤ 33በፊታችሁም ሆኖ በምትሄዱበት መንገድ ድንኳናችሁን እንድታቆሙ ቦታ እንድታገኙና በሌሊት በእሳት፥ በቀንም በደመና እንድትሄዱ መንገዱን ያሳታችሁ እርሱ ነው።34እግዚአብሔርም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቆጣ፥ ምሎም፥ እንዲህ አለ፦ 35በርግጥ ለአባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ የማልሁላቸውን መልካሚቱን ምድር ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር ከእነዚህ ሰዎች ከዚህ ክፉ ትውልድ ማንም አያይም። 36እርሱም እግዚአብህሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱና ለልጆቹ እሰጣለሁ ብሎ ማለ።37እግዚአብሔርም ደግሞ በእናንተ ምክንያት እኔን ተቆጣኝ እንዲህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደዚያ አትገባም 38በፊትህ የሚሄድ አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደዚያ ይገባል፥ እርሱም እስራኤላውያን ምድሪቱን እንዲወርሱ ይመራቸዋልና፤ አደፋፍረው።39ከዚህም በተጨማሪ፦ ለጉዳት ይዳረጋሉ፥ ዛሬም መልካሙንና ክፉውን መለየት የማይችሉ ናቸው ያላችኋችሁ ታናናሽ ሕፃናታችሁ ልጆቻችሁ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ። ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ ይወርሱታልም። 40እናንተ ግን ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።41እናንተም፦ እግዚአብሔርን በድለናል፥ እግዚአብሔር አምላክችሁ እንዳዘዘን ሁሉ እንወጣለን፥ እንዋጋማለን ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር ለመውጣትና ለማጥቃት ተዘጋጀ። 42እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ እኔ በእናንተ መካከል ስለማልገኝ፥ በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትሸነፉ አትውጡ፥ አትዋጉም በላቸው አለኝ።43እኔም ተናገርኋችሁ እናንተም አልሰማችሁም። በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፥ አልሰማችሁም በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ለማጥቃት ወጣችሁ። 44ነገር ግን በተራራማው አገር ይኖሩ የነበሩ አሞራውያን በእናንተ ላይ ወጥተው እንደ ንብ አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር መቱአችሁ።45ተመልሳችሁም በእግዚአብሔር ፊት አለቀሳችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ድምፃችሁን አልሰማም፥ ወደ እናንተም አላዳመጠም። 46ሁሉም ቀናት በቆያችሁባችሁ ለብዙ ቀን በቃዴስ ተቀመጣችሁ።
1ከዚያም እግዚአብሔርም እንደተናገረኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ጉዞአችንን በምድረ በዳ ውስጥ ተመለስን፤ 2በሴይርም ተራራ ዙሪያ ለብዙ ቀናት ተጓዝን። 3እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ይህን ተራራ የዞራችሁበት ይበቃችኋል፤ ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሄዱ።4ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር በሚኖሩ በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ድንበር ታልፋላችሁ፤ እነርሱም ይፈሩአችኋል። 5ስለዚህ የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ያህል እንኳ አልሰጣችሁም፥ ከእነርሱም ጋር እንዳትዋጉ እጅግ ተጠንቀቁ።።6የምትበሉትንም ምግብ ከእነርሱም በገንዘብ ትገዛላችሁ፤ የምትጠጡትንም ውኃ ደግሞ በገንዘብ ትገዛላችሁ። 7አምላካችሁ እግዚአብሔር ፤ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መጓዛችሁን ስላወቀ የእጃችሁን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና። በእነዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አልጎደለባችሁም።8በሴይርም ከሚኖሩት ከወንድሞቻችሁ ከዔሳው ልጆች በዓረባ መንገድ ከኤላትና ከዔጽዮን ጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን።9እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ሞዓብን አታስጨንቁአቸው፤ አትውጋቸውም። ምክንያቱም የእነርሱን ምድር ርስት እንዲሆንላችሁ አልሰጣችሁም፤ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ሰጠኋችሁ።10አስቀድሞ ታላቅና ብዙ ሕዝብ ሆነው እንደ ዔናቅምልጆች በቁመት የረዘሙ ኤሚማውያን በዚያ ይኖሩ ነበር፤ 11እነርሱም ደግሞ እንደ ዔናቅ ልጆች ራፋይም ይባሉ ነበር፤ ሞዓባውያን ግን ኤሚም ይሉአቸዋል።12ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ይኖሩ ነበር፥ የዔሳው ልጆች ግን አሳደዱአቸው። እግዚአብሔርም በሰጠው በርስቱ ምድር እስራኤል እንዳደረገ፥ ከፊታቸው አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም መኖር ጀመሩ።13እግዚአብሔርም፦ ተነሡ የዘሬድንም ወንዝ ተሻገሩ አለ። የዘሬድንም ወንዝ ተሻገርን። 14ከቃዴስ በርኔ ከመጠንበት ዘሬድን ወንዝን እስከ ተሻገርንበት ቀኖች ድረስ ሠላሳ ስምንት ዓመታት ነበሩ። እግዚአብሔር እንደ ማለላቸው ለመዋጋት ብቁ የሆኑ ሰዎች ትውልድ ሁሉ ከሕዝብ መካከል የጌድይት በዚያን ጊዜ ነበር። 15ከዚህ በተጨማሪ፥ ከመሄዳቸው በፊት ከሕዝቡ መካከል ለማጥፋት የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ከብዶ ነበረ።16ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ሁሉ ከሕዝቡ መካከል በሞቱና በጠፉ ጊዜ 17እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ 18አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ። 19ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ በአሞን ልጆች አቅረቢያ ስትደርስ አታስጨንቁአቸው አትውጋቸውም፤ ምክንያቱም ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና ።20ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቆጠረ። ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ይኖሩ ነበር፤ 21አሞናውያን ግን ዛምዙማውያን ብለው የሚጠሩአቸው እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው ረጅም ነበር። 22እግዚአብሔር ከአሞራውያን ፊት አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ይኖሩ ነበር። ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍተው በሴይር ለሚኖሩት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፤እነርሱም አሳድደው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።23እስከ ጋዛ ድረስ ባሉ መንደሮች ይኖሩ የነበሩትን ኤዋውያንን ከከፍቶር የወጡ ከፍቶራውያን አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ኖሩ።24ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንንና ምድሪቱን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻለሁ። እርስዋን ለመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ። 25ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ወሬህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፥ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።26ከቅዴሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦ 27ወደ ቀኝና ግራ ሳልል በአገርህ ላይ በአውራ ጎዳና ልለፍ።28የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፥ የምጠጣውንም ውኃ በገንዘብ እንድገዛ ስጠኝ፤ 29በሴይር የሚኖሩ የዔሳው ልጆች፥ በዔርም የሚኖሩ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ ብቻ በእግሬ ልለፍ።30እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችሁ ዘንድ ልቡን ስላደነደነና ስላጸና የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም ። 31እግዚአብሔርም፦ እነሆ ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት ጀመርሁ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር አለኝ።32ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊጋጠሙን ወደ ያሀጽ ወጡ። 33እግዚአብሔር አምላካችንም አሳልፎ ስለሰጠን አሸነፈነው፥እርሱንና ልጆቹን፥ ሕዝቡንም ሁሉ እስኪሞቱ ድረስ አሸነፍን፤መታንም።34በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን የተቀመጡባቸውንም ሰዎች ሁሉ ሴቶችንና ሕፃናትን አንዳችም ሳናስቀር አጠፋን። 35ከብቶቻቸውንና በከተሞቻቸው ያሉትን ብቻ ብዝበዛ ለራሳችን ወሰድን።36በአርኖን ቆላ ጫፍ ካለው ከአሮዔር ከሸለቆውም ውስጥ ካለው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ ማናቸውም ከተማ ከእኛ በላይ አልሆነም። እግዚአብሔር አምላካችን በፊታችን ባሉት ጠላቶቻችን ላይ ድልን ሰጠን። 37ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ወደ ከለከለን ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማው አገር ወዳሉት ከተሞች አልደረስንም።
1ተመልሰን በባሳን መንገድ ሄድን፥ የባሳን ንጉሥ ዐግና ሕዝቡ ሁሉ በኤድራይ ሊዋጉን መጡ። 2እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴሶን ላይ እንዳደረግህ በእርሱም ታደርግበታለህ አለኝ።3እግዚአብሔር አምላካችንም በባሳን ንጉሥ በዐግ ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን ድልን ሰጠን። እኛም አንድ እንዳይቀር እስኪሞቱ ድረስ መታነው። 4በዚያን ጊዜም አንድም ያልወሰድነው ሳይቀር ሁሉንም ስድሳ ከተሞችን፦ በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት፥ የአርጎብን አገር ሁሉ ከተሞችን ወሰድን።5እነዚህም ከተሞች ሁሉ ዙሪያቸው በረጅም ቅጥር፥ በበሮቻቸውና በመወርወሪያዎች የተመሸጉ ነበር፤ በአጠገባቸውም ብዙ ያልተመሸጉት ከተሞች ነበሩ። 6በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ከወንዶችና ሴቶች ከሕፃናትም ጋር ፈጽሞ አጠፋናቸው። 7ነገር ግን ከአጠፋናቸው ከተሞች ሁሉ ከብቶቹን ሁሉ ምርኮም ለራሳችን ወሰድን።8በዚያም ጊዜ ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ ምድሪቱን ከዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩ ከሁለቱ ከአሞራውያን ነገሥታት እጅ ወሰድን፤ 9(ሲዶናውያን አርሞንዔምን ሢርዮን ብለው ይጠሩታል፥ አሞራውያንም ሳኔር ብለው ይጠሩታል) ፤ 10በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ በባሳንም ያሉትን የዐግን መንግሥት ከተሞች እስከ ስልካና፤እስከ ኤድራይ ድረስ ባሳንን ሁሉ ወሰድን።11ከራፋይም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ተርፎ ነበር፤ እነሆም አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች አገር በረባት አልኖረምን? ይህም በሰው ክንድ ልክ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ።12በዚያን ጊዜ በአርሞን ሸለቆ ከአሮዔር ርስት አድርገን የወሰደነውን ይህን የገለዓድን ተራራማ ምድር እኩልታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገድ ሰጠኋቸው። 13ከገለዓድም የቀረውን የዐግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ የአጎብንም ምድር ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ። (ይህም ተመሳሳይ አገር የራፋይም ምድር ተብሎ ይቆጠራል።)14የምናሴ ነገድ አንዱ ኢያዕር እስከ ሄሸራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አካባቢ ሁሉ ወሰደ። ይህንም የባሳንን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ የሚጠራውን በስሙ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ጠራ።15ለማኪርም ገለዓድን ሰጠሁት። 16ለሮቤል ነገድና ለጋድም ነገድ ከገለዓድ ጀምሮ እስከ አርግኖን ሸለቆ ድረስ የሸለቆውን እኩሌታ ዳርቻውንም እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ሰጠኋቸው።17ከኪኔሬት እስከ ዓርባ ባሕር (እርሱም የጨው ባሕር) ድረስ ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ ያለውን የዮርዳኖስን ሸለቆ ዳቻውንም ሰጠኋቸው።18በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ እናንተ የጦር ሰዎች መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ ከእስራኤል ልጆች ፊት ታልፋላችሁ።19ነገር ግን ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ (ብዙ ከብቶች እንዳሉአችሁ አውቃለሁ) በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀመጣሉ፤ 20ይኸውም እግዚአብሔር እናንተን እንዳሳረፈም ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁላችሁ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።21በዚያም ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ብዬ አዘዝሁት፦አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ያደረገውን ሁሉ ዓይኖችህ አይተዋል፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታትም ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል። 22አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ ስለ እናንት ስለሚዋጋ አትፈራቸውም ብዬ አዘዝሁት።23በዚያም ጊዜ እኔ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ለመንሁ፦ 24ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህንና ብርቱ እጅህን ለእኔ ለባሪያህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይ ወይም በምድር እንደ አንተ፥ እንደ ኃይልህ፥ ያደርግ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው? 25እኔም ወደዚያ ልሂድና በዮርዳኖስም ማዶ ያለውን መልካሙን ምድርና መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ለመየት እለምንሃለሁ።26እግዚአብሔር ግን እናንተ ባለመስማታችሁ ምክንያት ተቆጣኝ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ስለዚህም ነገር ደግመህ እንዳትናገረኝ ይበቃሃል። 27ይህን ዮርዳኖስን ስለማትሻገር ወደ ፈስጋ ራስ ውጣና ዓይንህንም ወደ ምዕራብ፥ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብምና ወደ ምሥራቅ ዓይንህን አንሥተህ ተመልከት።28በዚህ ፈንታ ኢያሱን አስተምራው፥ አደፋፍረው እንዲሁም አጽናው፤ ምክንያቱም እርሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሄዳል፥ አንተም የምታየውን ምድር ያወርሳቸዋል። 29ስለዚህም በቤተ ፌጎርም በሸለቆው ውስጥ ቆየን።
1አሁንም እስራኤል ሆይ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወት እንድትኖሩና የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ሄዳችሁ እንድትወርሱ የማስተምራችሁን ሥርዓትንና ድንጋጌን ስሙ። 2እኔ የማዛችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዛትን ሁሉ ሳትጨምሩና ሳታጎሉ ትጠብቃላችሁ።3ከብዔልፌጎርም የተነሣ፥ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከመካከላችሁ እንዳጠፋ ዓይኖቻችሁ አይተወል። 4እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁን የተከተላችሁ እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወት አላችሁ።5እነሆ እናንተ ለመውረስ በምትሄዱባቸው ምድር ሰዎች መካከል ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር አምላኬ እንዳዘዘኝ ሥርዓትንና ድጋጌን አስተማርኋችሁ። 6ስለዚህ ጠብቁአቸው፥ አድርጉአቸውም፤ ምክንያቱም ስለእነዚህ ሥርዓት ሰምተው፦ 'በእውነት ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው' በሚሉ ሰዎች ሁሉ ፊት ይህ ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ነው።7በምንጠራው ጊዜ ሁሉ እንደምቀርበን እንደ እግዚአሔር አምላካችን፥ ወደ እነርሱ የቀረበ አምላክ ያለው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነው? 8ዛሬ በፊታችሁ እንደማኖራው ሥርዓት ሁሉ ጽድቅ የሆነው ሥርዓትና ድንጋጌ ያለው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?9ዓይኖቻችሁ ያዩትን ነገር እንዳትረሱ በሕይወታችሁም ዘመን ሁሉ ከልባችሁ እንዳይጠፋ ብቻ አስታውሉ፤በጥንቃቄም ራሳችሁን ጠብቁ። እግዚአብሔር፦ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ እንደተናገረኝ፥ 10በእግዚአብሔር አምላካችሁ ፊት በኮሬብ በቆማችሁ ቀን እንደሰማችሁ፥ይህን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ዘንድ እንዲታውቅ አድርጉ።11እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር። እስከ ሰማይም መካከል ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፤ ጨለማና ደመና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ። 12እግዚአብሔርም በእሳት ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ ድምፅን በቃል ሰማችሁ መልክን ግን አላያችሁም፤ ድምፅን ብቻ ሰማችሁ።13ታደርጉትም ዘንድ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን አሥሪቱን ቃላት አስታወቃችሁ። በሁለቱም በድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው። 14በዚያን ጊዜ ትወርሱአት ዘንድ በምትሄዱባት ምድር የምታዳርጉትን ሥርዓትና ድንጋጌ አስተምራችሁ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዝኝ።15እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት መካከል ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክን ከቶ እንዳላያችሁ፤ለራሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ። 16የማናቸውንም ፍጥረት ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል በወንድ ወይም በሴት፥ 17ወይም በማናቸውም በምድር ባለው በዱር እንስሳ መልክ፥ ወይም ከሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ምሳሌ፥ 18ወይም በምድር ላይ የሚሳበውን ሁሉ ምሳሌ፥ ወይም ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ በማድረግ እንዳትረክሱ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።19ዓይኖቻችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት ሕዝብ ሁሉ የመደባቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊት ሁሉ ባያችሁ ጊዜ አምልኮና ስግደት በማቅረብ እንዳትስቱ ተጠንቀቁ። 20እናንተን ግን እግዚአብሔር እንደ ዛሬው ሁሉ የርስቱ ሕዝብ ትሆኑለት ዘንድ ወስዶ ከብረት እሳት ከግብፅ አወጣችሁ።21ከዚህም በተጨማሪ እግአብሔር በእናንተ ምክንያት ተቆጣኝ፣ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር ፥እግዚአብሔር አምላካችሁም ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደመልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ። 22እኔ ግን በዚህች ምድር እሞታለሁ፥ ዮርዳኖስንም አልሻገርም፥ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፥ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ።23እግዚአብሔር አምላካችሁም ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እግዚአብሔር አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ። 24እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።25ልጆችን የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ብዙ ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ በማናቸውም ምስል የተቀረጸውን ምስል አድርጋችሁ በረከሳችሁም ጊዜ፥ ታስቆጡትም ዘንድ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በሠራችሁ ጊዜ ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ፤ 26ከምትገቡባት ምድር እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆኑ እጠራለሁ፤ ዘመናችሁም አይረዝምም፥ ፈጽሞም ትጠፋላችሁም።27እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ በአሕዛብም መካከል ጥቂት ትሆናላችሁ፥እግዚአብሔርም ያስወጣችሁኋል። 28በዚያም የማያዩትን፥ የማይሰሙትን፥ የማይበሉትን፥ የማያሸቱትንም በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት ታመልካላችሁ።29ነገር ግን ከዚያ እግዚአብሔር አምላካችሁን ትሻላችሁ፤ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም የፈለጋችሁት እንደ ሆነ ታገኛላችሁ።30በተጨነቃችሁና ይህም ሁሉ በደርሰባችሁ ጊዜ በዘመኑ ፍጻሜ ወደ እግዚአብሔር አምላካችሁ ትመለሳላችሁ፥ ድምፁንም ትሰማላችሁ። 31እግዚአብሔር አምላካችሁ መሓሪ አምላክ ነውና፥ አይተዋችሁም፥ አያጠፋችሁምም፤ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን ቃል ኪዳኑን አይረሳም።32እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ከሰማይ እስከ ዳርቻዋ ድረስ ከቶ እንዲህ ያለ ታላቅ ነገር ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰምቶ እንደ ሆነ ከእናንተ በፊት የነበረውምን የቀደመውን ዘመን ጠይቁ። 33እናንተ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደሰማችሁት ሌላ ሕዝብ ሰምቶአልን?34ወይም እግዚአብሔር አምላካችሁ በዓይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንዳደረገው ሁሉ በፈተናና በተአምራት በድንቅና በጦርነት በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ በታላቅም ማስፈራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ለራሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ በዐይናችሁ ፊት አድርጎ ያውቃልን?35እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ የተገለጡ ናቸው፤ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም። 36ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳት አሳያችሁ፤ ድምፁንም ከእሳት መካከል ሰማችሁ።37አባቶቻችሁን ስለወደደ ከእነሱም በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ከግብፅም በታላቁ ኃይል በመገኘቱ አወጣችሁ፤ 38ዛሬ እንደ ሆነ ከእናንተ የጸኑትን ታላላቆችን አሕዛብ ከፊታችሁ ሊስያወጣቸውና ለእናንተም ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ሊሰጣችሁ ነው።39እንግዲህ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቁ፤ በልባችሁም ያዙት። 40ለእናንተ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችሁም ለዘላለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።41በዚያን ጊዜ ሙሴ አስቀድሞ ጠላት ያልነበረውን ሰው ሳያውቅ የገደለው ሰው 42ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖር ዘንድ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞች መረጠ። 43ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቦሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።44ሙሴ በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት። 45ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ እግዚአብሔር የተናገራቸው የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች፥ ሥርዓቶች፥ ሌሎችም ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤ 46በቤተ ፌጎር አንጻር ባለው ሸለቆ፥ በሴዎን ምድር፣ ከዮርዳኖስ በስትምሥራቅ፥ በነበሩበት ጊዜ፥ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ በወጡበት ጊዜ ድል ያደረጉአቸው በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአራውያን ንጉሥ ነበር።47የእርሱንና የባሳንን ንጉሥ የዐግን ምድር ወሰዱ፤ 48በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩትን የሁለቱ የአሞራያን ነገሥታት እነዚህ ናቸው። ይህም ምድር ከአርኖን በአሮዔር ዳርቻ እስከ ሴዎን ተራራ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ፥ 49በምሥራቅ በኩል የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ሜዳ በሙሉ ጨምሮ በዮርዳኖስ ማዶ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለውን ዓረባ ሁሉ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ያለው ነው።
1ሙሴም የእስራኤል ልጆችን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአቸውና እንድትጠብቁአቸው ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራውን ሥርዓቶችንና ድንጋጌዎችን ስሙ። 2እግዚአብሔር አምላካችን ከእኛ ጋር በኮሬብ ቃል ኪዳን አድርጎአል። 3እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ቃል ኪዳን አላደረገም ዛሬ በሕይወት ካለነው ከእኛ ጋር ነው።4እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ፊት ለፊት በተራራው ላይ በእሳት መካከል ተናገረ፥ 5(በዚያን ጊዜ ከእሳቱም የተነሣ ፈርታችሁ ወደ ተራራው ባልቀረባችሁ ጊዜ ቃሉን ልገልጥላችሁ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር) ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ 6ከባርነት ቤት፥ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።7ከእኔ በቀር በፊቴ ሌሎች አማልክት አይኑራችሁ። 8በላይ በሰማይ፥ወይም በታች በምድር፣ወይም ከምድርም በታች በውኃ፥ ማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል ለራሳችሁ አታድርጉ።9እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ ስለሆንኩ ለአማልክት አትስገዱላቸው፥ ወይም እነርሱን አታገልግሉአችሁ። በሚጠሉኝ ላይ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የእባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ ቅጣትን ያመጣል፥ 10ለቃል ኪዳኔም ታማኝነት ለሚያሳዩኝና ለሚወዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ አምላክ ነኝ።11የአምላካችሁን ስም በከንቱ አትጠቀሙ፥ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠቀመውን ከበደል አያነጻውምና።12እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ የሰንበትን ቀን ትቀድሱት ዘንድ ጠብቁ። 13ስድስት ቀን ሥሩ ተግባራችሁንም ሁሉ አድርጉ፤ 14ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ሰንበት ነው። እናንተ እንደምታርፉ ሁሉ አገልጋያችሁና የቤት ሠራተኛችሁ ያርፉ ዘንድ እናንተ ወንድ ልጆቻችሁ፥ ሴት ልጆቻችሁም ፥ አገልጋዮቻችሁ፥ የቤት ሠራተኞቻችሁም በፊታችሁ፥ አህዮቻችሁም፥ ከብቶቻችሁም፥ ሁሉ በደጆቻችሁ ውስጥ ያለው እንግዳም ጭምር በሰንበት ምንም ሥራ አትሥሩ።15እናንተም በግብፅ በሪያ እንደ ነበራችሁ አስቡ፥ እብዚአብሔር አምላካችሁ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ከዚያ አውጣችሁ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሰንበትን ቀን ትጠብቁ ዘንድ አዘዛችሁ።16እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ ምድር ላይ ዕድሜአችሁ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንላችሁ አባታቸውንና እናታቸውን አክብሩ።17አትግደሉ። 18አታመንዝሩ። 19አትስረቁ። 20በባልንጀራችሁ ላይ በሐሰት አትመስክሩ።21የባልንጀራችሁን ሚስት አትመኙ፤ የባልጀራችሁን ቤት፥ እርሻውንም፥ አገልጋዩንም፥ የባልጀራችሁንም በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከባልጀራችሁ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኙ።22እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳትና በደመና በጨለማም ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምፅ፥ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤአችሁ ሁሉ ከተናገረው ምንም አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላችቶች ላይ ጻፋቸው ለእኔም ሰጠኝ።23ተራራው በእሳት ሲነድድ ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ እናንተ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም ወደ እኔ ቀረባችሁ። 24አላችሁም፦ እነሆ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳትም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰዎችም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።25አሁን እንግዲህ ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን እንሞታለን? እኛ የእግዚአብሔርን የአምላካችንን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን። 26ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወቱ የኖረ ማን ንው? 27አንተ ቅረብ፤ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ ስማ፤ እግዚአብሔር አምላካችንም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እናደርገዋለን አላችሁ።28በተናገራችሁኝም ጊዜ እግዚአብሔር የእናንተን ቃል ሰማ። እግዚአብሔርም አለኝ፦ይህ ሕዝብ የተናገሩህን ቃል ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩትም ሁሉ መልካም ነው። 29ለእነርሱ ለዘላለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዘዜን ሁሉ እንዲጠብቁ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው በነበራቸው! 30ሄደህ እንዲህ በላቸው፦ ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ።31አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁሙ፥ ርስት አድርጌ በምሰጣቸውም ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዓቴን፥ ድንጋጌንም ሁሉ እነግርሃለሁ።32ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ። 33በሕይወት እንድትኖሩ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሄዱ።
1ከዮርዳኖስ ማዶ በምትውርሱአት ምድር የምትጠብቃችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳስተምራችሁ ያዘዘኝ እነዚህ ትእዛዘት፥ ሥርዓትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤ 2እኔ የማዛችሁን ሥርዓትንና ትእዛዘትን በመጠበቅ እናንተ፥ ልጆቻችሁ፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዘመናችሁ ዕድሜአችሁ እንዲረዝም እግዚአብሔር አምላካችሁን አክብሩ።3እንግዲህ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ መልካምም እንዲሆንላችሁ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ተስፋ እንደሰጣችሁ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር እጅግ እንድትበዙ ነው።4እስራኤል ሆይ፥ ስማ፥ እግዚአብሔር አምላካችን አንድ እግዚአብሔር ነው። 5እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ፥ በፍጹም ኃይላችሁ ውደዱ።6እኔም ዛሬ እናንተን የማዝዘው ቃል በልባችሁ ይሁን፤ 7በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድም ስትሄዱ፥ ስትተኙም፥ ስትነሡም፥ ልጆቻችሁን አስተምሩአቸው።8በእጃችሁም ምልክት አድርጋችሁ እሰሩት፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁንላችሁ። 9በቤታችሁም መቃኖች በደጃፋችሁም በሮች ላይ ጻፉት።10እግዚአብሔር አምላካችሁ ለእናንተ ሊሰጣችሁ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባገባችሁ ጊዜ፥ ያልሠራሃችኋቸውን ታላላቅና መልካም ከተሞች፥ 11በመልካም ነገሮች ሁሉ የተሞሉ ቤቶች ያልማስሃችኋቸውን የተማሱ ጉድጓዶች፥ ያልተከልሃችኋቸውን ወይንና ወይራ በሰጣችሁ ጊዜ፥ 12በበላችሁና በጠገባችሁ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።13አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ፤ እርሱንም አምልኩት በስሙም ማሉ። 14በዙሪያችሁ ያሉትን አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት ፍለጋ እንዳትሄዱ፥ እንዳከተከተሉ፤ 15ምክንያቱም በመካከላችሁ ያለው እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ አምላክ ስለሆነ፥ ቁጣው እንዳይነድባችሁና ከምድር ገጽ እንዳያጠፋችሁ ተጠንቀቁ።16በማሳህ እንደተፈታተናችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁን አትፈታተኑት። 17ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዘትንና ሥርዓቱን አጥብቃችሁ ጠይቁ።18መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን ነገር አድርጉ፤ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ 19እግዚአብሔርም እንደተናገረ ጠላቶቻችሁን ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣላችሁ ዘንድ።20በኋለኛው ዘመንም ልጆቻችሁ እንዲህ ብለው በጠየቃችሁ ጊዜ፦ እግዚአብሔር አምላካችን ያዘዛችሁ የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች፥ ሥርዓትና ሌሎችስ ድንጋጌዎች እነዚህ ምንድን ናቸው? 21እናንተም ለልጆቻችሁ እንዲህ በሉአችው፦ በግብፅ አገር የንጉሥ ፈርዖን አገልጋዮች ነበርን፥ እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ ከግብፅ አወጣን፥ 22እግዚብብሔርም በግብፅና በፈርዖን፥ በቤቱም ሁሉ ላይ በዓይናችን ፊት ታላቅና ክፉ፥ ምልክትና ተአምራትን አደረገ። 23ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር አምጥቶን እርስዋን ይሰጠን ዘንድ ከዚያ አወጣን።24እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን እግዚአብሔር አምላካችንን እንፈራ ዘንድ ይህችንም ሥርዓት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን። 25እርሱም እንዳዘዘን በእግዚአብሔር በአምላካችን ፊት እንፈጽመው ዘንድ ይህን ትእዛዝ ሁሉ ብንጠብቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።
1እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወሱአት ወደምትገቡባት ምድር ባመጣችሁ ጊዜ፤ ከፊታችሁም ብዙ አሕዛብ ከእናንተ የበለጡትንና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ ኬጢያዊውን፥ ጌርጌሳውያንን፥ አሞራውያንብ፥ ከነዓናውያንን፥ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አወጣቸው።2እንዲሁም ጦርነት በገጠማችሁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁ ድል በሰጣችሁ ጊዜ፥ እነርሱን ማጥቃት አለባችሁ፥ ከዚያም ፈጽሞ ማጥፋት ይኖርባችኋል። 3ከእርሱም ጋር ቃል ኪዳን ማድረግ ወይም ምሕረት አለማድረግ፥ ከእነርሱም ጋር አትጋቡም፤ ሴት ልጆቻችሁን ለወንድ ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴት ልጃቸውንም ለወንድ ልጃችሁ አትውሰዱ።4ሌሎች አማልክትን እንዳያመልኩ፥ ልጆቻችሁን እኔን እንዳይከተሉ ይመልሳሉ፥ የእግዚአብሔርም ቁጣ ይነድድባችኋል ፈጥኖም ያጠፋችኋል። 5በእነርሱ ላይ የምታደርጉባቸው እንደዚህ ነው፥ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቁረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ።6እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የተለያችሁ ሕዝብ ናችሁ። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምድርም ገጽ ከሚኖሩ ሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ መረጣችሁ።7እግዚአብሔርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቁጥር ስለ ባዛችሁ አይደለም፤ እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቁጥር ጥቂቶች ነበራችሁና፤ 8ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን ቃል ኪዳን ስለ ጠበቀ ነው። እግዚአብሕር በጽኑ እጅ ያወጣችሁ፥ ከባሪነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ ለዚህ ነው።9ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ እርሱ አምላክ እንደ ሆነ ለሚወድዱትና ትእዛዘትንም ለሚጠብቁት፥ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆን እወቁ፥ 10ነገር ግን የሚጠሉትን በፊታቸው ሊያጠፋቸው ብድራትን ይመልሳል፤እንዲሁም ብድራትን ለመመለስ አይዘገይም። 11እንግዲህ ታደርጉት ዘንድ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘት፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎችን ጠብቁ።12እነዚህን ድንጋጌዎችን ሰምታችሁ ብትጠብቁና ብታደርጉ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ለአባቶቻችሁ የማለላችውን ቃል ኪዳን በታማኝነት ለእናንተ ይጠብቅላችኋል። 13እርሱም ይወድዳችኋል፥ ይባርካችኋል፥ ያበዛላችኋል፤ እንዲሁም የሆዳችሁንና የምድራችሁን ፍሬ፥ እህላችሁን፥ ወይናችሁን፥ ዘይታችሁን፥ የከብቶቻችሁንና የበጎቻችሁን መንጋ ይባርካል።14ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረካችሁ ትሆናላችሁ፥ በሰዎቻችሁና በከብቶቻችሁ ዘንድ ወንድ ወይም ሴት ቢሆኑ መካን አይሆንባችሁም። 15እግዚአብሔርም ሕመምን ሁሉ ከእናንተ ያርቃል፥ የምታውቁአችሁን ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በእናንተ ላይ አያደርስባችሁም በሚጠሉባችሁም ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል።16እግዚአብሔር አምላካችሁም በእጃችሁ አሳልፎ የሚሰጣችሁን አሕዛብ ሁሉ ታጠፋቸዋላችሁ፥ ዓይናችሁም አያዝኑላቸውም። ወጥመድ እንዳይሆኑባችሁአማልክታቸውንም አታምልኩአችሁም።17በልብህም እንዲህ ብትሉ፦ እነዚህ አሕዛብ ከእኔ ይልቅ ይበዛሉና አወጣቸው ዘንድ እንዴት እችላለሁ? 18እግዚአብሔር አምላካችሁ በፈዖንና በግብፅ ሁሉ ያደረገውን ትዝ ስለሚላችሁ እነሱን አትፍራቸው፤ 19አምላካችሁ እግዚአብሔር ዓይናችሁ ፊት ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንና ተአምራትን በማድረግ በጸናችው እጅ፥ በተዘረጋውም ክንድ አወጣችሁ። እንዲሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተ በምትፈሩአችሁ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።20በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላካችሁ ራሳቸውን የተሸሸጉትን ከፊታችሁ እስኪጠፉ ድረስ በመካከላችው ተርብ ይሰድድባቸዋል። 21እግዚአብሔር አምላካችሁ ታላቅና የተፈራ አምላክ በመካከላችሁ ስላለ፤ ከእነርሱ የተነሣ አትደንግጡ። 22እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን አሕዛብ ጥቂት በጥቂት ከፊታችሁ ያወጣቸዋል። ሁሉንም አንድ ጊዜ አታጠፋቸውም፤ ወይም የዱር አራዊት በዙሪያችሁ በጣም ብዙ ይሆናሉ።23እግዚአብሔር አምላካችሁ እነርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ እስኪጠፉም ድረስ በታላቅ ድንጋጤ ያስደነግጣቸዋል። 24ነገሥታታቸውንም በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋቸዋላችሁ። እስክታጠፏቸውም ድረስ ማንም በፊታችሁ ይቆም ዘንድ አይችልም።25የተቀረጸውንም የአማልክታቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላላችሁ፤ ከብር ወይም ከወርቅ የተሠሩትንም ለራሳችሁ ለመውሰድ አትመኙ፥ በእግዚአብሔር በአምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመዱበት ከእርሱ ምንም አትውሰዱ። 26እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆኑ ርኩስን ነገር ወደ ቤታችሁ አታግቡ ለማምለክም አትቃጡ፥ ለጥፋት የተለየ ስለ ሆነ ፈጽሞ ተጸየፉት፥ ጥሉትም።
1በሕይወት እንድትኖሩና እንድትበዙ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱአት ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘትን ሁሉ ጠብቁ። 2እግዚአብሔር አምላካችሁ በልባችሁ ያለውን፥ ትእዛዘቱን መጠበቃችሁን ወይም አለመጠበቃችሁን ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁና ትሁት እንድትሆኑ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራችሁን መንገድ ሁሉ አስቡ።3አስጨነቃችሁ፥ እንድትራቡም አደረጋችሁ፥ እንዲሁም እናንተና ልጆቻችሁ፥ አባቶቻችምሁ የማያውቁአቸውን መና መገባችሁ። ይህም ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል እንጂ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ያስታውቃችሁ ዘንድ ነው።4በእነዚህ አርባ ዓመታት ውስጥ የለበሳችሁት ልብስ አላረጀም፥ እግራችሁም አላበጠም። 5ሰውም ልጁን እንደሚገሥጽ እንዲሁም እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን እንደሚገሥጽ በልባችሁ አስቡ። 6በመንገዱም እንድትሄዱ እርሱንም እንድትፈሩ የእግዚአብሔ የአምላካችሁን ትእዛዝ ጠብቁ።7እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደ መልካምና፥ ከሸለቆና ከኮረብታ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾች የሚመነጩ ምንጮች ወዳሉባት ምድር፤ ስንዴና ገብስ፤ 8በለስና ሮማን፥ ወይራና ማር ወደ ሞሉባት፥9ሳይጎድላችሁ እንጀራ ወደምትበሉባት ምድር፥ አንዳችም ወደማታጡባት፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር አመጣችሁ። 10እናንተም ትበላላችሁ፥ ትጠግባላችሁ፥ ስለ ሰጣችሁም ስለ መልካሚቱ ምድር እግዚአብሔር አምላካችሁን ትባርካላችሁ።11ዛሬ እኔ እናንተን የማዝዛውን ትእዛዘትን፥ ድንጋጌዎችንና ሥርዓቶችን ባለመጠበቅ እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ። 12ከበላችሁና ከጠገባችሁ ሙሉም ከሆናችሁ በኋላ መልካምም ቤት ሠርታችሁ በዚያ መኖር ከጀመራችሁ በኋላ እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።13የላምና የበግ መንጋ ከበዛላችሁ በኋላ፥ ብራችሁና ወርቃችሁም፥ ያላችሁም ሁሉ ከበዛላችሁ በኋላ፥ 14ልባችሁ እንዳይኮራ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።15መርዛማ እባብና ጊንጥ፥ውኃ በሌለባትና ጥማትም ባለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራችሁን፥ ከዐለት ድንጋይም ውኃን ያወጣላችሁን፥ 16በመጨረሻም ዘመን መልካም ያደርግላችሁ ዘንድ ሊፈትናችሁ ሊያዋርዳችሁም አባቶቻችሁ ያላውቁትን መና በምድረ በዳ ያበላችሁን እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዳትረሱ፥ 17በልባችሁም፦ ጉልባታችን የእጃችን ብርታት ይህን ሀብት አመጣልን እንዳትሉ።18ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶቻችሁ የማለላችሁን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ሀብት ለማከማቸት ጉልበት ሰጥቶአችኋል፥ እግዚአብሔር አምላካችሁን አስቡ። 19አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ብትረሳ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል፥ ብታመልካቸውም፥ ብትሰግድላቸውም ፈጽሞ እንደምትጥፉ እኔ ዛሬውኑ እመሰክርባችኋልለሁ። 20የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ቃል ስላልሰማችሁ እግዚአብሔር ከፍታችሁ እንደሚያጠፋቸው እንደ አሕዛብ እንዲሁ እናንተ ትጠፋላችሁ።
1እስራኤል ሆይ፥ ስሙ፥ ከእናንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ እስከ ሰማይም ድረስ የተመሸጉትን ታላላቅ ከተሞች ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው፤ 2የኤናቅ ልጆች ፥ ታላቅና ረጅም ሕዝብ፥ እናንተም የምታውቃቸው ስለ እነርሱም እንዲህ ያላችኋቸው፦ በዔናቅ ልጆች ፊት ማን መቆም ይችላል?3ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁም እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊታችሁ ስለሚያልፍ፥ ዛሬ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊታችሁም ያዋርዳቸዋል፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገራችሁ እናንተ ታሳድዳቸዋላችሁ ፈጥናችሁም ታጠፋቸዋላችሁ።4እግዚአብሔር አምላካችሁ ከፊታችሁ ካወጣቸው በኋላ ፦ እንወርሳት ዘንድ ወደዚህች ምድር እግዚአሔር ያመጠን፥ ስለ ጽድቄ ነው፥ እነዚህንም አሕዛብ እግዚአብሔር ከፊታችን ያወጣቸው ኃጢአተኞች ስለ ሆኑ ነው፥ ብላችሁ በልባችሁ እንዳትናገሩ።5ምድራቸውን ትወርሱአት ዘንድ የምትገቡት ስለ ጽድቃችሁ ወይም ስለ ልባችሁ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ከፊታችሁ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኃጢአት ምክንያትና ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ይፈጽም ዘንድ ነው።6እንግዲህ እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆናችሁና እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጣችሁ ስለጽድቃችሁ እንዳይደለ እወቁ።7እግዚአብሔር አምላካችሁን በምድረ በዳ እንዳስቁጣችሁት ከግብፅ አገር ከወጣችሁበት ቀን ጀምሮ ወደዚህ ስፍራ እስከ መጣችሁ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ አስቡ። 8በኮሬብ ደግሞ እግዚአብሔርን አስቆጣችሁ፤ እግዚእብሔርም ሊያጠፋችሁ ተቆጣባችሁ።9እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባውን የቃል ኪዳን፥ የድንጋዩን ጽላቶችን ከእግዚአብሔር ለመቀበል ወደ ተራራ ወጥቼ በተራራው ላይ ለአርባ ቀናትና አርባ ሌሊት በቆየሁበት ጊዜ እንጀራም አልበለሁም፥ ውኃም አልጠጠሁም። 10እግዚአብሔርም በእርሱ ጣት የተጻፉትን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶችን ሰጠኝ፤ በጽላቶቹም ላይ በተራራው ሥር በነበረው ጉበዔ እግዚአብሔር በእሳት መካከል ሆኖ የተናገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር።11ከአርባ ቀንና ከእርባ ሌሊትም በኋላ እግዚአብሔር ሁለቱን የድግንጋይ ጽላቶች፥ ያቃል ኪዳኑን ጽላቶች ሰጠኝ። 12እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥተህ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ረክሰዋል። ፈጥነው ካዘዝኋቸውም መንገድ ፈቀቅ ብለዋል። ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሰቸው አድርገዋል።13ከዚህም በተጨማሪ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና መሆኑን አይቼአለሁ። 14ስለዚህ አጠፋቸው፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስሳለሁ፥ አንተንም ከእነርሱ ለሚበረታና ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ።15እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድሁ፥ ተራራውም በእሳት ይነድድ ነበር። ሁለቱም የቃል ኪንን ጽላቶች በእጆቼ ነበሩ። 16እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁን እንደበደላችሁ አየሁ። ለእናንተም ለራሳችሁ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር። እግዚአብሔርም ካዘዛችሁ መንገድ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር።17ሁሉቱንም ጽላቶች ወስጄ፥ ከእጆቼ ጣልኋቸው። በዓይናችሁም ፊት ሰበርኋቸው። 18ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ከማድረጋችሁ የተነሣ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ወደቅሁ፥ እንጀራም አልበላሁም፥ ውኃም አጠጣሁም ነበር።19ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ ከተቆጣባችሁ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ስለ ፈራሁ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያን ጊዜም ሰማኝ። 20እግዚአብሔርም አሮንን ሊያጠፋው እጅግ ተቆጣው፤ ስለ አሮንም ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ጸለይሁ።21ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወስድሁ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቅዝቅሁትም፤ ዱቄትም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት። ዱቄቱንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት።22እግዚአብሔርንም በቀቤራ፥ በማሳህ፥ በምኞት መቃብርም አስቆጥታችሁት ነበር። 23እግዚአብሔርም ውጡ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ትእዛዝ ላይ አመፃችሁ፥ በእርሱም አላመናችሁም፤ወይም ድምፁንም አልሰማችሁም። 24እናንተን ካወቅሁበት ቀን ጀምሮ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀኞች ነበራችሁ።25እግዚአብሔር ያጠፋችሁ ዘንድ ስለ ተናገረ በእነዚያ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ወደቅሁ። 26ጌታ በእግዚአብሔርም ፊት እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ በታላቅነትህና በኃያልነትህ ከግብፅ ያወጣቸውን፥ የተበዠሃቸውን ሕዝብህንና ርስትህን አታጥፋ ።27አገልጋዮችህን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ደንዳናነት፥ ክፋቱንና ኃጢአቱን አትመልከት፤ 28እኛንም ያወጣህባት ምድር ሰዎች እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ ስላልቻለ፤ ስለጠላቸውም በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው ይላሉ። 29እነርሱም በታላቅ ኃይልህ በጸነችውም ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዛብህና ርስትህ ናቸው።
1በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ እንደ መጀመሪያ ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራ ውጣ፤ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ። 2በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት በእነዚህ ጽላቶች ላይ እጽፋለሁ፤ አንተም በታቦቱ ውስጥ ታደርጋቸዋለህ።3ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደፊተኞቹም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ፥ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። 4በተራራው ሥር የጉባዔው ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት መካከል ሆኖ የተናገራችሁን አሥርቱን ቃላት በመጀመሪያ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፤ ከዚያም እግዚአብሔር እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።5ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፤ ጽላችቶችንም በሠረሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው፤እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ሆኑ።6የእስራኤልም ልጆች ከብኤሮት ብኔ ያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ። በዚያ አሮን ሞተ፥ በዚያም ተቀበረ፥ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆኖ አገለገለ። 7ከዚያም ወደ ጉድጎዳ ተጓዙ፤ከጉድጎዳም ወደ ውኃ ምንጮች ምድር ወደ ዮጥባታ ተጓዙ።8በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር የሌዊን ነገድ እግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከሙና እርሱንም እንዲያገለግሉ፥ በፊቱም ይቆሙ ዘንድ በስሙም እንዲባርኩ መረጠ። 9ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው እግዚአብሔር ርስቱ ነው።10በተራራውም ላይ እንደ መጀመሪያውም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየሁ። እግዚአብሔርም እንደገናም ሰማኝ፤ እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ አልፈለገም። 11እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥተህ በሕዝቡ ፊት ሆነህ ሕዝቡን በጉዞው ምራው፤ ለአባቶቻቸው የማለሁላቸውን ምድር ሄደው ይገባሉ።12እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትውድድ ዘንድ፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ መልካምም እንዲሆንልህ 13ዛሬ ለአንተ የማዘዘውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ከሆነ በቀር እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?14እነሆ፥ ሰማይና ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ነው። 15ብቻ እግዚአብሔር ስለ አባቶቻችሁ ደስ ተሰኝቶአል፥ እነርሱንም ወድዶቸዋል፤ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራችሁን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዝብ ሁሉ መካከል መረጣችሁ።16ስለዚህ እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ አንገተ ደንዳኖች አትሁኑ። 17እግዚአብሔር አምላካችሁ የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል።18እግዚአብሔር ለድሃ አደጉና ባል ለሞተባት ይፈርዳል፥ ምግብና ልብስም የሚሰጥ ነው። 19ስለዚህ እናንተም በግብፅ አገር ስደተኞች ስለ ነበራችሁ ስደተኛውን ውደዱ።20እግዚአብሔር አምላካችሁን ፍሩ፥ እርሱንም አምልኩት። በእርሱም ተጣበቁ፤ በስሙም ማሉ። 21እርሱ ዓይኖቻችሁ ያዩትን እነዚህን ታላላቆችንና የሚያስፈሩትን ነገሮች ያደረገላችሁ ክብራችሁ ነው፤ አምላካችሁም ነው፤ ።22አባቶቻችሁ ሰባ ሰዎች ሆነው ወደ ግብፅ ሄዱ፤ አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁ ብዛታችሁን እንደ ሰማይ ክዋክብት አደረገ።
1ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውዳዱት፥ ሁልጊዜም መመሪያዎቹን፥ ሥርዓቶቹን፥ ድንጋጌዎችንና ትእዛዛትን ጠብቁ።2የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ቅጣት፥ታላቅነቱን፥ ኃያልነቱን፥ የተዘረጋውንም ክንዱን፥ ላላወቁት ወይም ላላዩት ልጆቻችሁ እየተናገርሁ እንዳልሆነ አስታውሉ፤ 3በግብፅም መካከል በንጉሡ በፈርዖንና በአገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋውን ተአምራቱንና ሥራውን፥4በተከተሉአችሁም ጊዜ በግብፅ ጭፍራ፥ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ያደረገውን፥በኤርትራ ባሕር ውኃ እንዳሰጠማቸው፥ እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው፥ 5ወደዚህ ስፍራ እስከትመጡ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን፥አይተዋል።6በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተ ሰቦቻቸውን ድንኳኖቻቸውንም ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ፥ በኤልያብ ልጆች፥ በዳታንና በአቤሮን እግዚአብሔር ያደረገውን አላዩም። 7ነገር ግን እግዚአብሔር ያደረገውን ታላቁ ሥራ ሁሉ ዓይኖቻቸው አይተዋል።8እንግዲህ እንድትጠነክሩ ትወርሱአትም ዘንድ ወደምትሄዱባት ምድር እንድትሄዱ ዛሬ ለእናንተ የማዘዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤ 9እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁና ለዘራቸው ይሰጣቸው ዘንድ በማለላቸው ወተትና ማርም በምታፈስሰው ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዘም ትእዛዘትን ጠብቁ።10ትወሱአት ዘንድ የምትሄዱባት ምድር በመጣችሁበት በግብፅ አገር ዘር እንደዘራችሁና ውኃ በእግራችሁ ታጠጡ እንደነበረ፥ እንደ አትክልት ቦታ አይደለችም፤ 11ነገር ግን ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ የምትገቡባት ምድር ኮረብታና ሸለቆ ያለባት በሰማይ ዝናብ ውኃ የምትጠጣ አገር ናት፤ 12አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ የሆነ አገር ናት።13እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ እግዚአብሔር አምላካችሁን ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ፥ ትወድዱና ታገለግሉት ዘንድ ዛሬ የማዝዛችሁን ትእዛዘትን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥ 14እህላችሁን፥ ወይናችሁን፥ ዘይታችሁን ትሰበስቡ ዘንድ በየዚዜው ለምድራችሁ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን የወቅቱን ዝናብ ይሰጣችኋል። 15በሜዳ ለእንስሶቻችሁም ሣርን እሰጣለሁ፤ትበላላችሁ፣ ትጠግባላችሁም።16ልባችሁ እንዳይስት ፈቀቅ እንዳትሉ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም፥ 17የእግዚአብሔርም ቁጣ እንዳይነድድባችሁ ዝናብ እንዳይዘንብ ምድሪቱም ፍሬዋን እንዳትሰጥ ሰማይን እንዳይዘጋባችሁ፤ እግዚአብሔርም ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ እንዳትጠፉ ተጠንቀቁ።18ስለዚህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደ ክታብ ይሁኑላችሁ። ፥ 19በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድ ላይም ስትሄዱ፥ ስትተኙ፥ ስትነሡም ልጆቻችሁንም አስተምሩአቸው።20በቤታችሁ መቃኖችና በከተሞቻችሁ በሮች ላይ ጻፈው፥ 21እግዚአብሔርም እንዲሰጣቸው ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር፥ እንደ ሰማይ ቀኖች በላይ በምድር ከፍ ያሉና የልጆቻችሁም ዘመን የረዘመ ይሁን ።22እግዚአብሔር አምላካችሁን ትወድዱ ዘንድ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘት ሁሉ ብትጠብቁ፥ ብታደርጉአቸውም፥ 23እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣል፤ ከእናንተም የሚበልጡትን፥ የሚበረቱትንም አሕዛብ ትወርሳላችሁ።24የእግራችሁ ጫማ የሚረግጥበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም ከሊባኖስ ወንዝ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል። 25በእናንተም ፊት ማንም መቆም አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ እንደ ተናገራችሁ ማስፈራታችሁና ማስደንገጣችሁ በምትረግጡበት ምድር ሁሉ ላይ ያኖራል።26እነሆ፥ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤ 27በረከትም የሚሆነው፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ትእዛዝ ብትሰሙ 28እንዲሁም መርገም የሚሆነው የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ትአዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አምልክት ብትከተሉ ነው።29እግዚአብሔር አምላካችሁ ትወሱአት ዘንድ እናንተም ወደምትሄዱባት ምድር ባገባሃችሁ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙንም በጌባል ተራራ ይሆናል። 30እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ከምዕራብ ካለው መንገድ በኋላ በዓረባ በሚኖሩት በከነዓናውያን ምድር በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ አይደለምን?31እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፥ ትወርሱአታላችሁ፥ ትቀመጡባታላችሁም። 32እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራውን ሥርዓትና ድንጋጌዎች ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።
1የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንድትወርሱ በሚሰጣችሁ ምድር፥ ሁልጊዜ በምድር እያላችሁ የምትጠብቁአችሁ ሥርዓትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው። 2እናንተ የምትወርሱአቸው አሕዛብ አማልክታቸውን ያመለኩባቸውን በረጅም ተራሮች በኮረብቶችም ከለምለምም ዛፍ በታች ያለውን ስፍራ ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉአቸው።3መሠዊያቸውንም አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥የማልመኪያ ዐፀዶቻችቸውንም በእሳት አቃጥሉ፥የአማልክታቸውንም የተቀረጹ ምስሎች ቆራርጡአቸው፥ ከዚያም ስፍራ ስማቸውን አጥፉ። 4እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዲህ ባለ ሁኔታ አታምልኩ።5ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ከነገዶቻችሁ ሁሉ ስሙን በዚያ ያኖር ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ ትመጣላችሁ፥ ማደሪያውንም ትሻላችሁ። 6ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላም መሥዋዕታችሁንም፥ አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቁርባን፥ ስእለታችሁንም በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት ውሰዱ።7በዚያም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ብሉ፥ እጃችሁንም በምትዘረጉበት እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ ነገር ሁሉ እናንተና ቤተ ሰባችሁ ደስ ይበላችሁ።8ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን፥ እኛ በዚህ ዛሬ የምናደርገውን ሁሉ አታደርጉም፥ 9እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ዕረፍትና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና።10ነገር ግን ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁም በሚያወርሳችሁ ምድር በተቀመጣችሁ ጊዜ ያለ ፍርሃትም እንድትኖሩ፥ ከከበቡአችሁ ጠላቶች ሁሉ ዕረፍት በሰጣችሁ ጊዜ በዚያ ጊዜ 11እግዚአብሔር አምላካችሁ ፥ ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላም መሥዋዕታችሁን አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁ ያነሣችሁትንም ቁርባን፥ ለእግዚአብሔርም ተስላችሁ የመረጣችሁትን ስእልታችሁን ሁሉ ውሰዱ።12እናንተም፥ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ አገልጋዮቻችሁና የቤት አገልጋዮቻችሁ፥ ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ የተቀመጠው ሌዋዊም፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።13የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን በሚታያችሁ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርቡ ተጠንቀቁ። 14ነገር ግን እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አቅርቡ፥ በዚያም የማዝዛችሁን ሁሉ አድርጉ።15ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሰጣችሁ በረከት ሰውነታችሁ እንደ ፈቀደ በደጆቻችሁ ሁሉ ውስጥ አርዳችሁ ብሉ፤ንጹሕም ያልሆነ ሰው እንደ ሚቋና እንደ ዋላ ያለውን ይብላው። 16ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ ያፍስሰው፤ ደሙን አትብሉ።17የእህላችሁን፥ የወይናችሁን፥ የጠጃችሁን የዘይታችሁንም፥ አሥራት፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት የተሳላችሁትንም ስእለት ሁሉ በፈቃዳችሁም ያቀረባችሁትን፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቁርባን በደጆቻችሁ መብላት አትችሉም።18በዚህ ፈንታ እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም አገልጋዮቻችሁና የቤት አገልጋዮቻችሁ፥በአገራችሁ ደጅ ያለው ሌዋዊ እግዚአብሔር አምላካችሁ በመረጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ብሉት፥ እጃችሁንም በምትዘረጉባችሁ ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ። 19በምድራችሁ ላይ በምትኖሩባት ዘመን ሁሉ ሌዋዊውን ቸል እንዳትሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።20እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ነገራችሁ አገራችሁን ባሰፋ ጊዜ፥ ሰውነታችሁም ሥጋ መብላት ስለ ወደደ፦ ሥጋ እንብላ፥ ስትሉ እንደ ሰውነታችሁ ፈቃድ ሥጋን ብሉ።21እግዚአብሔር አምላካችሁ በዚያ ስሙን ያኖር ዘንድ የመረጠው ስፍራ ከእናንተ ሩቅ ቢሆንም እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከላምና ከበግ መንጋችሁ እንዳዛዝኋችሁ እረዱ፥ እንደ ሰውነታችሁም ፈቃድ ሁሉ በአገራችሁ ደጅ ብሉ። 22ሚዳቋና ዋላ እንደሚበሉ እንዲሁ ብሉ፥ ንጹሕ ሰው ንጹሕ ያልሆነም ይብለው።23ደሙ ሕይወት ነውና፥ ነፍሱንም ከሥጋው ጋር መብላት አይገባችሁምና፥ ደሙን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ። 24በምድር ላይ እንደ ውኃ አፍስሱት እንጂ አትብሉ። 25በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ስታደርጉ ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላችሁ አትብሉ።26ነገር ግን የተቀደሰውን ነገራችሁን ስእለታችሁንም ይዛችሁ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ሂዱ። 27የሚቃጠለውንም መሥዋዕታችሁን ሥጋውንና ደሙን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርቡ፤ የመሥዋዕታችሁም ደም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፥ ሥጋውንም ብሉ።28በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርጉ ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዛችሁን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምታችሁ ጠብቁ።29እግዚአብሔር አምላካችሁ ትወርሱአቸው ዘንድ የምትሄዱባቸውን አሕዛብን ፊታችሁ ባጠፋ ጊዜ፥ እናንተም በወረሳችሁ ጊዜ፥ በምድራቸውም በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ 30ከፊታችሁ ከጠፉ በኋላ እነርሱን ለመከተል እንዳትጠመዱ፦ እነዚህ አሕዛብ አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እንዲሁ ደግሞ እኔም አደርጋለሁ ብላችሁ ስለ አማልክታቸው እንዳትጠይቁ ተጠንቀቁ።31እግዚአብሔር የሚጠላውን ርኩሰት ሁሉ እነዚህን ለአማልክታቸው አድርገዋል፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ለአማልክታቸው በእሳት አቃጥሎአቸዋል፥ እናንተም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ እንዲሁ አታድርጉ። 32እኔ የማዝዛችሁን ነገር ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምሩ ከእርሱም ምንም አታጉድሉ።
1በመካከላችሁም፦ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክት ወይም ተአምራት ቢሰጣችሁ፥ እንደ ነገራችሁም 2ምልክቱ ወይም ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም፦ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት ሄደን እንከተል እናምልካቸውም ቢላችሁ፥ 3እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ እግዚአብሔር አማላካችሁ ሊፈትናችሁ ነውና፥ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስሙ።4እግዚአብሔር አምላካችሁን ተከተሉ፥ እርሱንም አክብሩ፥ ትእዛዘትንም ጠብቁ፥ ድምፁንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩት፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ። 5ከግብፅ ምድር ካወጣችሁና ከባርነት ቤት ካዳናችሁ ከእግዚአብሔር ከአምላካችሁ ሊያስታችሁ ስለተናገረ ያ ነቢይ ወይም ያ ሕልም አላሚ ይገደል። ያም ነቢይ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ ሊያወጣችሁ ነው። ስለዚህ ክፉውን ነገር ከመካከላችሁ አርቁ።6የእናታችሁ ልጅ፥ ወንድማችሁ ወይም ወንድ ልጃችሁ ወይም ሴት ልጃችሁ ወይም በብብታችሁ ያለች ሚስታሁ ወይም እንደ ነፍሳችሁ የምትቆጥሩት ወዳጃችሁ በስውርም ሊፈትናችሁ፦ ኑ፥ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ የማታውቁአችሁን አማልክት ሄደን እናምልክ ብሉአችሁ፥ 7ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ሌላኛው ምድር ዳር ድረስ ወደ እናንተ የቀረቡት ከእናንተም የራቁት በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት ቢያስታችሁ እሺ አትበሉ።8አትስማሙአቸው፤አትስማቸውም። ዓይናችሁም አይራራላቸው፥ አትምራቸውም፥ አትሸሽጋቸውም። 9በዚህ ፈንታ ፈጽማችሁ ግደሉአቸው፤ እርሱን ለመግደል የእናንተ እጅ በእርሱ ላይ ይሁን፤ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ይሁን።10ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣችሁ ከእግዚአብሔር ከአምላካችሁ ሊያርቃችሁ ወድዶአልና፥ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገሩት። 11እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ፥ በመካከላችሁም እንዲህም ያለ ክፉ ሥራ ለማድረግ አይቀጥሉም።12እግዚአብሔር አምልካችሁ ልትኖሩባችሁ በሚሰጣችሁ በአንዲቱ ከተማችሁ እንዲህ ሲባል ብትሰሙ፡- 13አንዳንድ ክፉ ሰዎች ከእናንተ መካከል ወጥተው፦ የማታውቋቸውን ሌሎችን አማልክት ሄደን እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ፥ ሲሉ ብትሰሙ፤ 14ታጣራላችሁ፥ ትመረምራላችሁ፥ በሚገባም ትጠይቃላችሁ። እነሆም፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከላችሁ እንደ ተደረገ እውነት ሆኖ ቢገኝ።15የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋላችሁ፤ ከተማይቱን በእርስዋም ያለውን ሁሉ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፉአቸዋላችሁ። 16ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባላችሁ፥ ከተማይቱንም ዕቃዋንም ሁሉ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በእሳት ፈጽማችሁ ታቃጥላላችሁ፤ እንደ ገና የማትሠራ ሆና ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቀራለች።17ለጥፋት ከተለዩ ነገሮች ምንም እርም ነገር በእጃችሁ አይገኙ። እግዚአብሔር ከቁጣ ትኩሳት ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶቻችሁም እንደማለላቸው ይምራችሁና ይራራላችሁ ዘንድ፥ ያበዛላችሁም ዘንድ ነው። 18ዛሬ እኔ የማዝዛችሁን ትእዛዘት ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኘውን ታደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ቃል ስሙ።
1እናንተ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ሕዝብ ናችሁ። ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አታቆስሉ፥ የትኛውንም የፊታችሁን ክፍል አትላጩ። 2ምክንያቱም እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ፤ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለራሱ ሕዝብ ትሆኑ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን መርጦአልና።3ርኩስን ነገር ሁሉ አትብሉ። 4የምትበሉአቸው እንስሶች እነዚህ ናቸው፦ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፥ 5ዋላ፥ ሚዳቋ፥ የበረሃ አጋዘን፥ አጭ፥ በራይሌ፥ የተራራ በግ (ድኩላ)።6ከእንስሶች ሰኮናው የተሰነጠቀውን ጥፍሩም ከሁለት የተከፈለውን የሚያመነዥከውንም እንስሳ ሁሉ ትበላላችሁ። 7ነገር ግን ከማያመሰኩ ወይም ሰኮናቸው ካልተሰነጠቀ፥ እነዚህን አትበሉም፤ ግመል፥ ጥንቸል፥ ሽኮኮን፥ አትበሉም። የሚያመነዥኩና ነገር ግን ሰኮናቸው ያልተሰነጠቀም እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው።8እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስለማያመነዥክ፥ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋውን አትብሉ በድኑንም አትንኩ።9በውኃ ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው፤ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ። 10ነገር ግን ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸውን አትበሉም፥ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።11ንጹሕ የሆኑትን ወፎችን ሁሉ ትበላላችሁ። 12ነገር ግን ከወፎች ሊበሉ የማይገባቸው እነዚህ ናቸው። ንስር፥ ገዴ፥ ዓሣ አውጭ፥ 13ጭልፊት፥ ጭላት፥ በየወገኑ፥14ቁራም ሁሉ በየወገኑ፥ 15ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቃል፥ በየወገኑ፥ 16ጉጉት፥ ጋጋኖ፥ 17የውኃ ዶሮ ይብራ፥18ጥምብ አንሣ፥ አሞራ፥ እርኩም ሽመላ ሳቢሳ፥ በየወገኑ፥ ጅንጅላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ፥። 19የሚበርርም ተንቀሳቃሽ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ አይበሉም። 20ንጹሕ የሆኑትን ወፎች ሁሉ ብሉ።21የበከተውን ሁሉ አትብሉ፥ ይበላው ዘንድ በአገራችሁ ደጅ ለተቀመጠ፥ መጻተኛ ትሰጠዋላችሁ፥ ወይም ለእንግዳ ትሸጣላችሁ። ምክንያቱም እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የተቀደሰ ሕዝብ ናችሁ። የፍየሉን፥ ጠቦት፥ በእናቱ ወተት አትቀቅሉ።22ከእርሻችሁ በየዓመቱ ከምታገኙት ከዘራችሁ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣላችሁ። 23ሁልጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁን መፍራት ትማሩ ዘንድ ስሙ፤ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት የእህላችሁን የወይን ጠጃችሁንም የዘይታችሁንም አሥራት የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት ብሉ።24እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ ጊዜ መንገዱ ሩቅ ቢሆን፥ እግዚአብሔር አምላካችሁም ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ ቢርቅባችሁ ግን ወደዚያ ለመሸከም ባትችሉ ትሸጣላችሁ፥ 25የዋጋውንም ገንዘቡ በእጃችሁ ይዛችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደ መረጠው ስፍራ ትሄዳላችሁ።26በዚያም በገንዘቡ የፈለጋችሁትን በሬ ወይም፥ በግ ወይም፥ የወይን ጠጅ፥ ወይም ብርቱ መጠጥ፥ ወይም የፈለጋችሁትን ሁሉ ትገዛላችሁ፤ በዚያም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፥ እናንተና ቤተ ሰባችሁም ደስ ይላችኋል። 27ድርሻና ርስት ከእናንተ ጋር ስለሌለው በአገራችሁ ደጅ ውስጥ ያለውን ሌዋዊውን ቸል አትበሉ።28በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት ሌዋዊው ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለ የፍሬአችሁን አሥራት ሁሉ አምጥታችሁ በአገራችሁ ደጅ ታኖራላችሁ፤ 29በአገራችሁም ደጅ ያለ መጻተኛ፥ ድሀ አደግ፥ ባል የሞተባት መጥተው ይበላሉ፤ ይጠግባሉም። ይኸውም እግዚአብሔር አምላካችሁ በምታደርጉት በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ይባርካችሁ ዘንድ ነው።
1በየሰባት ዓመት የዕዳ ምሕረት ታደጋላችሁ። 2ይህ ዕዳ ምሕረት አፈጻጸም እንከሚከተለው ነው፤ አበዳሪ ሁሉ ለባልንጀራው ላበደረው እንዲተውዋውና ከባልጀራው ወይም ወንድሙ መልሶ እንዳይጠይቅ እግዚአብሔር ያወጀው ይህ ነው። 3ለእንግዳ ያበደራችሁትን መጠየቅ የምትችሉ ሲሆን፥ ለእስራኤላዊ ወንድማችሁ ያበደራችሁትን ግን ምሕረት አድርጉለት።4ይሁን እንጂ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ትወርሱአት ዘንድ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ውስጥ አብዝቶ ስለሚባርካችሁ በመካከላችሁድኻ አይኖርም። 5ይህ የሚሆነው የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ድምፅ ፈጽማችሁ ስትሰሙና ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዘትን ሁሉ ስትታዘዙ ብቻ ነው። 6እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ተሰፋ መሠረት ስለሚባርካችሁ እናንተ ለብዙ አሕዛብ ታበድራላችሁ እንጂ እናንተ አትበደሩም፤ብዙ አሕዛብን ትገዛላችሁ እንጂ ማንም እናንተን አይገዛችሁም።7እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ደኻ ቢኖር፥ በደኻ ወንድማችሁ ላይ ልባችሁ አይጨክን፥ለደኻ ወንድማችሁ ላይም እጃችሁን ከመዘርጋት አትቆጥቡ፤ 8ነገር ግን እጃችሁን በትክክል ፍቱለት ለማያስፈልገውም ቅር ሳትሉ አበድሩት።9ዕዳ የሚሠርዝበት ሰባተኛ ዓመት ቀርቦአል፥ በማለት ክፉ አሳብ አድሮባችሁ በችግረኛ ወንድማችሁ ላይ እንዳትጨክኑና ምንም ሳትሰጡት እንዳይቀር እርሱ በእናንተ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኾ በደለኞች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። 10በቅን ልቦና ስጡት፥ ስትሰጡትም ልባችሁ አይጸጸት፥ከዚያም የተነሣ ግዚአብሔር አምላካችሁ ሥራችሁንና እጃችሁን ያረፈበትን ሁሉ ይባርክላችኋል።11በምድሪቱ ላይ ሁልጊዜ ድኾች አይጠፉም፥ስለዚህ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞቻችሁ ለድኾችና ለችግራኞች እጃችሁን እንድትዘረጉ አዛችኋለሁ።12እናንተም ወንድማችሁን ዕብራዊውን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዙ ስድስት ዓመት ያገልግላችሁ በሰባተኛውም ዓመት ከእናንተ ዘንድ አርነት አውጡት። 13ከእናንተም ዘንድ አርነት በሚታወጣበት ጊዜ ባዶውን አትስደዱት። 14ነገር ግን ከመንጋህ፥ ከአውድማችሁም፥ ከወይራችሁም መጥመቂያም ትለግሱታላችሁ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን ትሰጡት ዘንድ ይገባል።15እናንተም በግብፅ አገር ባሮች እንደ ነበራችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁም እንደ ነበራችሁ አስቡ፤ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን እንድታደርጉ አዛችሁኋለሁ። 16ነገር ግን አገልጋያችሁ እናንተንና ቤተ ሰቦቻችሁን በመውደዱና ከእናንተ ጋር ደስተኛ ሆኖ ከመኖሩ የተነሣ፦ ከእናንተ መለየት አልፈልግም ቢላችሁ፦ 17ጆሮውን ከቤታችሁ መዝጊያ ላይ በማስደግፍ በወስፌ ትበሳላችሁ፤ከዚያም ዕድሜ ልኩን አገልጋያችሁ ይሆናል። በቤት አገልጋዮችሁም ላይ እንዲሁ አድርግ።18አገልጋያችሁን አርነት ማውጣት ከባድ መስሎ አይታያችሁ፤ ምክንያቱም የስድስት ዓመት አገልግሎቱ አንድ የቅጥር ሠራተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምታደጉት ነገር ሁሉ ይባርካችኋልና።19የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን ተባዕት በኩር ሁሉ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቀድሱ። የበሬአችሁን በኩር አትሥሩባቸው፥ የበጋችሁንም በኩር አትሸልቱ፥ 20እርሱ በሚመርጠው ስፍራ እናንተና ቤተ ሰባችሁ በየዓመቱ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ትበሉታላችሁ። 21አንድ እንስሳ እንከን ካለበት፤ አንካሳ ወይም ዕውር ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ፤ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር አትሠዉ።22የከተሞቻችሁ ትበላላችሁ፤ በሥርዓቱ መሠረት ንጹሕ የሆነውም ሆነ ያልሆነው ሰው፥ እንደ ድኩላ እንደ ዋላ ያሉትን ይበላዋል። 23ደሙን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሱት እንጂ አትብሉት።
1እግዚአብሔር አምላካችሁ በአቢብ ወር ከግብፅ በሌሊት ስላወጣችሁ የአቢብ ወር ጠብቁ፥ የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ፋሲካ አክብሩበት። 2እግዚአብሔር ለሰሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋችሁ አንዱን እንስሳ እግዚአብሔር በአምላካችሁ ፋሲካ አድርጋችሁ ሠዉ።3ከቦካ ቂጣ ጋር አትብሉ፤ ከግብፅ የወጣችሁ በችኮላ ነውና፥ ከግብፅ የወጣችሁበትን ጊዜ በሕይወታችሁ ዘመን ሁሉ ታስቡ ዘንድ ያልቦካ ቂጣ ሰባት ቀን ብሉ። 4ከምድራችሁ ሁሉ ላይ በእናንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዉም ላይ ማናቸውም ሥጋ እስከ ጧት ድረስ እንዲቆዩ አታድርጉ።5እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ በማናቸውም ከተማ በሮች ላይ ፋሲካን መሠዋት አይገባችሁም። 6በዚህ ፈንታ፥ ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችን በመረጠው ስፍራ ፀሐይ ስትጠልቅ በምሽት ላይ ከግብፅ ከወጣችሁበት ሰዓት ላይ በዚያ ፋሲካ ሰዉ።7ሥጋውንም ጠብሳችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚመርጠው ስፍራ ብሉ፥ ሲነጋም ወደ ድንኳናችሁ ተመልሳችሁ ሂዱ። 8ለስድስት ቀንም ያልቦካ ቂጣ ብሉ፤ በሰባተኛው ቀን በእግዚአብሔር በአምላካችሁ የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ ሥራም አትሥሩበት።9እህላችሁን ማጨድ ከምትጀምሩበት ዕለት አንሥቶ ለራሰችሁም ሰባት ሳምንታትን ቁጠሩ። 10ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን በፈቃዳችሁ የምታመጡትን ስጦታ በማቅረብ በመከሩ በዓል እግዚአብሔር አምላካችሁን አክብሩ።11እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ወንዶችና ሴቶች አጋልጋዮቻችሁ በከተሞቻችሁ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ በመካከላችሁ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና ባል የሞተባቸው እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ። 12እናንተም በግብፅ ባሪያዎች እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፥ እነዚህንም ሥርዓቶች በጥንቃቄ ጠብቁ አድርጉም።13የእህላችሁን ምርት ከዐውድማችሁ ፤ ወይናችሁንም ከመጭመቂያችሁ ከሰበሰባችሁ በኋላ የዳስን በዓል ሰባት ቀን አክብሩ። 14በበዓላችሁ እናንተና ወንድና ሴት ልጆቻችሁ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮቻችሁ፥ በከተማው ያለ ሌዋዊ መጻተኛ፥ አባት አልባውና ባል የሞተባት ደስ ይበላችሁ።15እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በዓሉን ሰባት ቀን አክብሩ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በእህል ምርታችሁና በእጆቻችሁ ሥራ ሁሉ ይበርካችኋል፤ ደስታችሁም ፍጹም ይሆናል።16ወንዶቻችሁ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በመከር በዓልና በዳስ በዓል ላይ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ይቅረቡ፥ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ባዶ እጁን አይቅረብ፥ 17በዚህ ፈንታ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን እያንዳንዱ እንደ ችሎታው ይስጥ።18እግዝዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ከተማ ሁሉ ለየነገዶቻችሁ ዳኞችንና አለቆችን ሹሙ፥ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ፥ 19ፍርድ አታዛቡ፥ አድልዎ አታደርጉ፥ ጉቦም አትቀበሉ፥ ጉቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። 20በሕይወት እንድትኖሩና እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣችሁን ምድር እንድትወርሱ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተሉ።21ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በምታደርጉት መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የእንጨት ዐምድ አታቁሙ። 22እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለእናንተ አታቁሙ።
1እንከን ወይም ጉድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ እግዚአብሔር ለአምላክችሁ አትሠዉ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነውና።2እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ከተሞች በሮች አብሮአችሁ የሚኖር ወንድ ወይም ሴት ኪዳኑን በማፍረስ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ሲፈጽም ቢገኝ፥ 3ትእዛዜንም በመተላለፍ ባዕዳን አማልክትን ያመለከ፥ ለእርሱም ማለትም ለፀሐይ ወይምለጨረቃ ወይም ለሰማይ ከዋክብት የሰገደ፥ 4እናንተ ይህ መደረጉን ብትሰሙ ነገሩን በጥንቃቄ መርምሩ፥ የተባለውም እውነት ከሆንና እንዲህ ያለ አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ዘንድ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፥5ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስዳችሁ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገሩት። 6ሞት የሚገባው ሰው በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፥ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል። 7ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት ክፉን ከመካከላችሁ አስወግዱ።8በአንድ የነፍስ ግድያ ዓይነትና በሌላ በአንድ ዓይነት ሕጋዊ ክርክርን በሌላ ወይም በአንድ የክስ ዓይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጉዳይ ቢነሣ፥ ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ጉዳይ በከተሞቻችሁ ውስጥ ቢያጋጥማችሁ፥ ተነሥታችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚመርጠው ስፍራ ውጡ። 9ካህናት ወደ ሆኑት ሌዋውያንና በዚያን ጊዜ ዳኛ ወደ ሆነው ሰው ሄዳችሁ ስለ ጉዳዩ ጠይቁአቸው፥ እነርሱም ውሳኔውን ይነግሩአችኋል።10እናንተም እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ እነርሱ በሚሰጡአችሁ ውሳኔ መሠረት ፈጽሙ። እንድፈጽሙ የሚሰጡአችሁን መመሪያ ሁሉ በጥንቃቄ አድርጉ፥ 11በሚያስተምሩአችሁ ሕግና በሚሰጡአችሁ መመሪያዎች መሠረት ፈጽሙ፥ እነርሱ ከሚነግሩአችሁ ቀኝም ግራም አትበሉ።12እግዚአብሔር አምላካችሁን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህን ወይም ዳኛ የሚንቅ ይገደል፥ ከእስራኤልም መካከል ክፉውን አስወግዱ። 13ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲሰማ ይፈራል፤ ከዚያ ወዲያም እንዲህ ያለውን የንቀት ድርጊት አይደግመውም።14እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፥ በምትወርሱአትና በምትቀመጡባት ምድር በዙርያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፥ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ ብትሉ፥ 15ከዚያ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚመርጠውን ንጉሥ በላይህ ታነግሣለህ፥ ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንጂ እስራኤላዊ ወንድምህ ያልሆነውን ባዕድ በላይህ አታንግሥ።16ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ ወይም ደግሞ የፈረሰኞችን ቁጥር ለመጨመር ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስ፤ 17እግዚአብሔር በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ፥ ብሎአችኋልና፤ ልቡ እንዳይስትም ብዙ ሚስቶችን አያግባ፥ ብዙ ብር ወይም ወርቅ ለራሱ አያብዛ።18በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ የዚህን ሕግ ቅጅ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ በጥቅልል መጽሐፍ ለራሱ ይጻፍ። 19እግዚአሔር አምላኩን ማክበር ይማር ዘንድ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዓት በጥንቅቄ ይጠብቅ ዘንድ ከእርሱ ጋር ይሁን፤በሁሉም ቀኖች ያንብበው።20ይህን የሚያደርገው ከወንድሞቹ ላይ ልቡ እንዳይኮራ፥ ከትእዛዘትም ወደ ኋላ እንዳይመለስ፥ እርሱና ልጆቹም ረጅም ዘመን ይገዙ ዘንድ፥ ከሕጉ ቀኝ ወይም ግራም አበል።
1ሌዋውን ካህናት፥ የሌዊ ነገድ ሁሉ ከእስራኤል ጋር የመሬት ድርሻ ወይም ርስት ስለማይኖራቸው ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርበው ድርሻቸው ነውና ይብሉ። 2እግዚአብሔር በሰጣቸው ተስፋ መሠረት እርሱ ራሱ ርስታቸው ስለሆነ በወንድሞቻቸው መካከል ርስት አይኖራቸውም።3ኮርማ ወይም በግ የሚሠዋው ሕዝብ ለካህኑ የሚሰጠው ድርሻ ወርቹን፥ ሁለት ጉንጮችንና የሆድ ዕቃውን ነው። 4የእህላችሁን፥ የአዲሱን ወይናችሁንና የዘይታችሁን በኩራት እንዲሁም ከበጎቻችሁ በመጀመሪያ የተሸለተውን ጠጉር ትሰጣላችሁ። 5በእግዚአብሔር ስም ቆሞ ለዘላለም ያገለግል ዘንድ እግዚአብሔር አምላክህ ከነገዶቻችሁ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጦአል።6አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በእስራኤል ካሉት ከተሞቻችሁ መካከል በፍጹም ፈቃድ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ቢመጣ፥ 7በእግዚአብሔር ፊት ቆመው እንደሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ፥ እርሱም በእዚግአብሔር በአምላኩ ስም ያገልግል። 8ከቤተ ሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳ ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል።9እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ምድር በምትገቡበትጊዜ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተሉ። 10በመካከላችሁ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሥዋ ሟርተኛ፥ ወይም መተተኛ፥ ሞራ ገለጭ፥ ጠንቋይ፥ ወይም በድግምት የሚጠነቁል፥ 11መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከላችሁ ከቶ አይገኝ።12እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ከእነዚህ አጸያፊ ልምዶች የተነሣ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚያን አሕዛብ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል። 13በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ነውር የሌላው ይሁን። 14ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፥ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያዳምጣሉ፤ እናንተ ግን ይህን እንድታደርጉ እግዚአብሔር አምላካችሁ አልፈቀደላችሁም።15እግዚአብሔር አምላካችሁ ከገዛ ወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል። እርሱን አድምጡ። 16በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት እንዳልሞት የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ድምፅ አንስማ፤እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግመን አንይ ብላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን የጠየቃችሁት ይህ ነውና።17እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ የተናገሩት መልካም ነው። 18ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ። ቃሌን በአፉ አደርጋለሁ፤ የማዘውንም ሁሉ ይነግራቸዋል። 19ማንም ሰው ነቢዩ በስሜ የሚናገረውን ቃሌን ባይሰማ፤ እኔ ራሴ ተጠያቂነት አደርገዋለሁ።20ነገር ግን እንዲናገር እኔ ያላዘዝሁትን ቃል በድፍረት በስሜና በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ይገደል። 21እናንተም በልባችሁ እግዚአብሔር ያልተነገረውን መልእክት እንዴት ማወቅ እንችላለን? ብትሉ፥22ነቢዩም በእግዚአብሔር ስም የተናገርው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገኘ፤ መልእክቱ እግዚአብሔር የተናገርው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።
1እግዚአብሔር አምላካችሁ ምድራቸውን ለእናንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ በሚደመስሳቸው ጊዜና እናንተም እነርሱን አስለቅቃችሁ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጡበት ጊዜ፥ 2እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር አማካይ ስፍራ ሦስት ከተሞችን ለራሳችሁ ምረጡ፥ 3ሰው የገደለ ሁሉ እንዲሸሽባቸው እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር መንገዶችን ሠርታችሁ በሦስት ክፈሉአቸው።4በተንኮል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ገድሎ ሕይወቱን ለማትረፍ ለሚሸሽ ሰው መመሪያው የሚከተለው ነው። 5እነሆ፥ አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ለመቁረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፥ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፥ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።6አለበለዚያ በተንኮል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፥ መንገዱ ረጅም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል። ይህ ከመሆኑ በፊት ባልንጀራውን ያልጠላ ከሆነ መሞት አይገባውም። 7ሦስት ከተሞችን ለራሳችሁ እንድትመርጡ ያዘዙአችሁ በዚሁ ምክንያት ነው።8ለአባቶቻችሁ በመሐላ በገባላቸው ቃል መሠረት አምላካችሁ እግዚአብሔር ወሰናችሁን ሲያሰፋውና ለእነርሱ በሰጣቸው መሠረት ምድሪቷን ሁሉ ሲሰጣችሁ፤ 9እግዝክአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱና ምን ጊዜም በመንገዱ እንድትሄዱ ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ሕግጋት ሁሉ በጥንቃቄ የምትጠብቁ ከሆነ በእነዚህ ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራላችሁ። 10እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር የንጹሕ ሰው ደም እንዳይፈስና በሚፈሰውም ደም በደለኛ እንዳትሆኑ ይህን አድርጉ።11ነገር ግን አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው አድፍጦ ጥቃት ቢያደርስበት፥ ቢገድለውና ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥ 12የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፥ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት። 13አትራራለት፥ ነገር ግን መልካም እንዲሆንላችሁ የንጹሑን ደም በደል ከእስራኤል አስወግዱ።14እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወርሱአት በሚሰጣችሁ ምድር ውስጥ ለእናንተ በሚተላለፍላችሁ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልጀራችሁን የድንበር ምልክት አታንሡ።15በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍ ሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ አንድ ምስክር አይበቃም፥ጉዳዩ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት መረጋገጥ አለበት። 16ተንኮለኛ የሆነ ምስክር አንድን ሰው በሐሰት ለመመስከር ቢነሣ፤17ክርክሩ የሚመለከታቸው ሁለቱ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ። 18ፈፋጆችም ጉዳዩን በጥልቅ ይመርምሩት፥ 19ያም ምስክሩ በወንድሙ ላይ በሐሰት የመሰከረ መሆኑ ከተረጋገጠ በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያሰበውን በእርሱ ላይ አድርጉበት ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።20የቀሩትም ሰዎች ይህን ሰምተው ይፈራሉ፤ እንዲህ ያለው ክፉ ነገርም ለወደፊቱ በመካከላችሁ ከቶ አይደገምም። 21ርኅራኄ አታድርጉ ሕይወት ለሕይወት፥ ዐይን ለዐይን፥ ጥርስ ለጥርስ፥ እጅ ለእጅ፥ እግር እግር ይመለስ።
1ጠላቶቻችሁን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄዱ ሠርገሎችንና ፈረሶችን ከእናንተ የሚበልጥ ሰራዊትንም በምታዩበት ጊዜ፥ አትፍሩአቸው፥ ከግብፅ ያወጣችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንተ ጋር ነውና።2ወደ ውጊያው ቦታ ስትቃረቡ፥ 3ካህኑ ወደ ፊት ወጣ ብሎ ለሠራዊቱ ይናገር፥ እንዲህም ይበል እስራኤል ሆይ ስማ በዛሬው ቀን ጠላቶቻችሁን ለመግጠም ወደ ጦርነት ልትገቡ ነው። ልባችሁ አይባባ፤ አትፍሩ፤ አትደግጡ፤ በጠላቶቻችሁ ፊት አትሸበሩ። 4ድልን ያቀዳጃችሁ ዘንድ ስለ እናንተ ጠላቶቻችሁን ሊወጋ አብሮአችሁ የሚወጣው አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና።5አለቆቹም ለሠራዊት እንዲህ ይበሉ፥ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፥ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ሲሞት፥ ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል።6ወይን ተክሎ ገና ያልበላለት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፣ ያለበለዚያ በጦርነቱ ሲሞት፥ ሌላ ሰው ይበለዋል። 7ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፥ ያለበለዚይ በጦርነቱ ሲሞት ሌላ ሰው ያገባታል።8በዚያም አለቆቹ፦ የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞችም ልብ እንዳይባባ፥ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ በማለት ጨምረው ይናገሩ። 9አለቆቹ ለሰራዊቱ ተናግረው ሲያበቁ አዛዦችን በሰራዊቱ ላይ ይሹሙ።10አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምቱበት ጊዜ አስቀድማችሁ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፉ፥ 11ከተቀበሉአችሁና ደጃቸውን ከከፊቱላችሁ በከተማዋ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ የጉልበት ሥራ ይሥሩ፥ ያገልግላችሁም።12ዕርቀ ሰላምን ባለመቀበል ውጊያ ከመረጡ፥ ከተማዪቱን ክበቡአት። 13እግዚአብሔር አምላካችሁ አሳልፎ በእጃችሁ በሰጣችሁ ጊዜ በውስጧ ያሉትን ወዶች በሙሉ በሰይፍ ግደሉአቸው።14ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን እንስሳትንና በከተምዩቱ ውስጥ የሚገኘውን ማናቸውንም ነገር በምርኮ ለራሳችሁ አድርጉ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከጠላቶቻችሁ የሚሰጣችሁን ምርኮ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ። 15እንግዲህ የአካባቢያችሁ አሕዛብ ከተሞች ባልሆኑትና ከእናንተ እጅግ ርቀው በሚገኙት ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርጉት ይኸው ነው።16እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ በአሕዛብ ከተሞች ውስጥ እስትንፋስ ያለውን ነገር አታስተርፉ። 17በዚህ ፈንታ፥ ኬጢያዊውን፥ አሞራዊውን፥ ከነዓናዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውን፥ ኢያቡሳዊውን እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መሠረት ፈጽማችሁ ደምስሱአቸው። 18አለበለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጻያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩአችኋል፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ላይ ኃጢአት ትሠራላችሁ።19አንድን ከተማ ተዋገታችሁ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ በምታድርጉበት ጊዜ፥ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፋችሁ ማጥፋት የለባችሁም። የዛፎችን ፍሬ መብላት ስለምትችሉ አትቁረጡአቸው። ከባችሁ የምታጠፉአችሁ የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን? 20የሚበላ ፍሬ እንደማያፈራ የምታውቁትን ዛፍ ግን ልትቆርጡና ጦርነት የምታካሄዱባትን ከተማ በድል እስክትቆጣጠሩአት ድረስ ለከበባው ምሽግ መሥሪያ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
1እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወርሱአት በሚሰጣችሁ ምድር ላይ አንድ ሰው ተገድሎ ሜዳ ላይ ቢገኝና ገዳዩም ማን እንደ ሆነ ባይታወቁ፥ 2ሽማግሌዎቻችሁና ዳኞቻችሁ ወጥተው የተገደለ ሰው ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት አንሥቶ በአቅራቢያው እስካሉት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ።3ከዚያም የተገደለ ሰው ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ በጣም ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችና ቀንበር ያልተጫነባትን ጊደር ይዘው፥ 4ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን አንገት ይስበሩ፥5እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ፥ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጉዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።6ከዚያም ሬሳው በተገኘበት አቅራቢያ ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎች ሁሉ፥ በሸለቆው ውስጥ፥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤ 7እንዲህም ብለው ይናገሩ፥ እጆቻችን ደም አላፈሰሱም፤ ድርጊቱ ሲፈጸምም ዐይኖቻችን አላዩም።8እግዚአብሔር ሆይ፥ ስለ ተቤዥኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፥ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ። ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል። 9በዚህም መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ቀና የሆነውን ስታደርጉ የንጹሑን ደም የማፍሰስ በደልን ከመካከላችሁ ታስወግዳላችሁ።10ከጠላቶቻችሁ ጋር ጦርነት ልትገጥሙ ወጥታችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር እነርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአችሁ በማረካችሁ ጊዜ፥ 11ከምርኮኞቹ መካከል ቆንጆ ሴት አይታችሁ ብትማርኩ፥ ሚስታችሁ ልታደርጉአት ትችላላችሁ፤ 12ወደ ቤታችሁ ውሰዱአት፥ ጠጉሯን ትላጭ፥ ጥፍሯንም ትቁረጥ።13ስትማርኩአት የለበሰችውንም ልብስ ታውልቅ፥ እቤታችሁ ተቀምጣ ለአባትና ለናቷ ወር ሙሉ ካለቀሰችላቸው በኋላ፥ ከእርሷ ጋር ለመተኛና ባል ልትሆለት፥ እርሷም ሚስት ልትሆናችሁ ትችላለች። 14ነገር ግን በእርሷ ደስተኛ ባትሆን፥ ወደምትፈልገው እንድትሄድ ነጻነት ስጡአት፥ ውርደት ላይ ስለ ጠላችኋት በገንዘብ ልትሸጡአት ወይም እንደ ባሪያ ልትቆጥሩአት አይገባችሁም።15አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት አንደኛዋን የሚወዳት፥ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፥ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት፥ በኩር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥ 16ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፥ የብኩርናን መብት ከማይወዳት ሚስቱ ከወለደው በኩር ልጅ ገፎ ከሚወዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤ 17በዚህ ፈንታ፥ ከተጠላችው ሚስቱ ለተወለደው ልጅ ካለው ሁብት ሁሉ ሁለት እጥፍ ድርሻውን በመስጠት ብኩርናውን ያስታውቅ ያ ልጅ የአባቱ ኃይል መጀመሪያ ነውና የብኩርና መብት የራሱ ነው።18አንድ ሰው የአባቱን ወይም የእናቱን ትእዛዝ የማይሰማ፥ ቢቀጡትም የማይታረም እልከኛና ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥ 19አባትና እናቱ ይዘው በሚኖሩበት ከተማ በር ወዳሉት አለቆች ያምጡት፥20ይህ ልጃችን እልከኛና ዐመፀኛ ነው፥ አይታዘዘንም አባካኝና ሰካራም ነው ብለው ለአለቆች ይንገሯቸው። 21ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይወገሩት፥ ክፉውንም ከመካከላችሁ ታስወግዳላችሁ፥ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።22አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ፈጽሞ ቢገደልና ሬሳው በእንጨት ላይ ቢሰቀል፥ 23ሬሳውን በእንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድሩት ምክንያቱም በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሚሰጣችሁን ምድር እንዳታረክሱ በዚያኑ ዕለት ቅበሩት።
1የእስራኤላዊ ወንድማችሁ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታዩ ወደ እርሱ መልሳችሁ አምጡለት እንጂ ዝም ብላችሁ አትለፉት፥ 2ወንድማችሁ በአቅራቢያ ባይኖር፥ ወይም የማን መሆኑን የማታውቁ ከሆነ ባለቤቱ ፈልጎ እስኪ መጣ ድረስ ወደ ቤታችሁና ወስዳችሁ ከእናንተ ዘንድ አቆዩት፤ ከዚያም መልሳችሁ ስጡት።3የእስራኤላዊ ወንድማችሁን አህያ ወይም ልብስ ወይም የጠፋበትን ማናቸውንም ነገር ስታገኙ እንደዚህ አድርጉ፥ በቸልታ አትለፉት። 4የወንድማሁ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታዩት በእግሩ እንዲቆም ርዳው እንጂ አልፋችሁ አትሂዱ።5ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ እንዲህ የሚያደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ይጸየፈዋልና።6በመንገድ ስታልፉ አንዲት ወፍ ጫጩቶቿን ወይም ዕንቁላሎቿን የታቀፈችበትን ጎጆ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ብታገኙም እናቲቱን ከነጫጩቶቿ አትውሰፉ፤ 7ጫጩቶቿን መውሰድ ትችላላችሁ እናቲቱን ግን መልካም እንዲህንላችሁና ዕድሜአችሁም እንዲርዝም ልቀቁት፤8አዲስ ቤት በምትሠሩበት ጊዜ፥ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ ቤታችሁ ላይ የደም በደል እንዳታመጡ፥ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጁለት።9በወይን ተክል ቦታችሁ ውስጥ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝሩ ይህን ካደረጋችሁም የዘራችሁት ሰብል ብቻ ሳይሆን የወይን ፍሬአችሁ ይጠፋል። 10በሬና አህያ በአንድ ላይ ጠምዳችሁ አትረሱ። 11ሱፍና ሐር አንድ ላይ ተፈትሎ የተሠራ ልብስ አትልበሱ።12በምትለብሱት ልብስ ላይ በአራቱ ማእዘኖች ዘርፍ አድርጉ።13አንድ ወንድ ሚስት አግብቶ አብሮአት ከተኛ በኋላ ቢጠላት፥ 14ስሟንም በማጥፋት፥ ይህችን ሴት አገባኋት፥ዳሩ ግን በደረስሁባት ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁም ቢል፥15የልጂቱ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዪቱ በር ወዳሉት አለቆች ይምጡ።16የልጂቱም አባት ለአለቆቹ እንዲህ ይበል፥ ልጄን ለዚህ ሰው ዳርሁለት፥ እርሱ ግን ጠላት፤ 17ስሟንም በማጥፋት ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም ብሎኛል፤ ነገር ግን የልጄ ድንግልና ማረጋገጫ ይኸውላችሁ። ከዚያም ወላጆቿ የደሙን ሸማ በከተማዪቱ አለቆች ፊት ይዘርጉት።18ከዚያም በኋላ አለቆቹ ሰውየውን ይዘው ይቅጡት፥ 19ይህ ሰው የአንዲት እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቶአልና አንድ መቶ ሰቅል ብር ያስከፍሉት፥ ገንዘቡንም ለልጂቱ አባት ይስጡት፥ ሴቲቱም ሚስቱ ሆና ትኖራለች፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።20ሆኖም ክሱ እውነት ሆኖ ሴቲቱ ድንግል ለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ ማቅረብ ካልተቻለ፥ 21በአባቷ ቤት ሳለች በማመንዘር በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪ ተግባር ፈጽማለችና ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያምጣት፥ እዚያም የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት።22አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አብሮአት የተኛው ሰውና ሴቲቱ ሁለቱም ይገደሉ። ክፉውን ከእስራኤል ማስወገድ አለባችሁ።23አንድ ሰው የታጨች ድንግል በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርሷ ጋር ቢተኛ፥ ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፥ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስግድዶ ስለ ደፈረ፥ 24ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከላችሁ ማስወገድ አለባችሁ።25ነገር ግን አንድ ሰው የታጨችውን ልጃገረድ ከከተማ ውጭ አግኝቶ በማስገደድ ቢደፍራት፥ ይህን ድርጊት የፈጸመው ሰው ብቻ ይገደል። 26በልጃገረዲቱ ላይ ግን ምንም አታድርጉባት፥ ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ምንም አልሠራችም፥ ይህ ዓይነቱ ጉዳይ አደጋ ጥሎ ባልንጀራውን ከሚገድል ሰው አድራጎት ጋር የሚመሳሰል ነው። 27ምክንያቱም ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ከተማ ውጭ ስላገኛትና ብትጮኽም እንኳ ለርዳታ የደረሰላት ምንም ሰው ስላልነበር ነው።28አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድ አግኝቶ በማስገደድ ቢደርስባትና ቢጋለጡ 29ሰውየው ለልጅቷ አባት አምሳ ስቅል ብር ይክፈል፥ ልጃገረዲቱን አስገድዶ ደፍሮአታልና እርሷን ማግባት አለበት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።30አንድ ሰው አባቱን ሚስት ማግባት የለበትም፥ የአባቱንም መኝታ አያርክስ።
1ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቆረጠ ማናቸውም ሰው ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። 2ዲቃላም ይሁን፥ የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።3አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ አሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። 4ምክንያቱም ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህልና ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም። በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም እናንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት።5ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ በብዓምን አልሰማውም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለሚወዳችሁ ርግማኑን ወደ በረከት አደረገላችሁ። 6በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ሰላምን ለእነርሱ አትመኙ።7ወንድማችሁ ስለ ሆነ ኤዶማዊውን አትጸየፈው፤ መጻተኛ ሆናችሁ በአገሩ ኖራችኋልና ግብፃዊውን አትጥሉት። 8ለእነርሱ የተወለዳቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ መግባት ይችላሉ።9ጠላታችሁን ለመውጋት ወጥታችሁ በሰፈራችሁ ጊዜ ከማናቸውም ርኩሰት ራሳችሁን ጠብቁ። 10ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከስሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቆይ። 11እየመሸ ሲመጣ ግን ገላውን ይታጠብ ፀሐይ ስትጠልቅም ወደ ሰፈሩ ይመለስ።12ለመጸዳጃ የሚሆንህን ቦታ ከሰፈር ውጭ አዘጋጅ። ከትጥቅህም ጋር መቆፍሪያ ያዝ፥ 13በምትጸዳዳበት ጊዜ አፈር ቆፍረህ በዐይነ ምድርህ ላይ መልስበት። 14እግዚአብሔር አምላክህ ሊጠብቅህ ጠላቶህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈር ውስጥ ስለሚዘዋወር በመካከልህ አንዳች ነውር አይቶ ከአንተ እንዳይመለስ፥ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን።15አንድ ባሪያ ከአሳዳሪው ኮብልሎ ወደ እናንተ ቢመጣ፥ 16ለአሳዳሪው አሳልፋችሁ አትስጡት፥ ደስ በሚያሰኘው ቦታን ራሱ በመረጠው ከተማ በመካከላችሁ ይኑር፤ እናንተም አታስጨንቁት።17ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይኑራችሁ። 18ለዝሙት አዳሪ ሴት ወይም ለወንድ ዝሙተኛ የተከፈለውን ዋጋ ለማናቸውም ስእለት አድርጋችሁ ለመስጠት ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካችሁ ቤት አታምጡ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና።19የገንዘብ፥ የእህል ወይም የማንኛውንም ነገር ወለድ ለማግኘት ለወንድማችሁ በወለድ አታበድሩ። ባዕድ ለሆነ ሰው በወለድ ማበደር ትችላላችሁ። 20ነገር ግን ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር እጃችሁ በሚነካው በማናቸውም ነገር እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲባርካችሁ ለእስራኤልዊ ወንድማችሁ በወለድ አታበድሩት።21ለእግዚአብሔር ለአምልካችሁ ስእለት ከተሳላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ አጥብቆ ከእናንተ ይሻዋልና፤ ኃጢአት እንዳይሆንባችሁ ለመክፈል አትዘግዩ። 22ሳትሳሉ ብትቀሩ ግን በደለኛ አትሆኑም። በአንደበታችሁ የተናገራችሁትን ሁሉ ለመፈጸም ጠንቃቃ ሁኑ፥ 23ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር በገዛ አንደበታችሁ ፈቅዳችሁ ስእለት ተስላችኋልና።24ወደ ባልንጀራችሁ የወይን ተክል ቦታ በምትገቡበት ጊዜ ያሰኛችሁን ያህል መብላት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን አንዳችም በዕቃችሁ አትያዙ። 25ወደ ባልንጀራችሁ እርሻ በምትገቡበት ጊዜ እሸት መቅጠፍ ትችላላችሁ፤ በሰብሉ ላይ ግን ማጭድ አታሳርፉበት።
1አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት የፍቺ ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት። 2ከቤቱ ከወጣች በኋላ ሌላ ባል ሊታገባ ትችላለች።3ሁለተኛ ባሏም እንደዚሁ ጠልቷት የፍቺ ወረቀት በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ቢሰዳት፥ ወይም ቢሞት፥ 4ከዚያ በኋላ ፈቶአት የነበረው የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደ ገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጡ።5አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፥ ለጦርነት አይሂድ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሥራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ እቤቱ ይቆይ፥ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።6ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም እንኳ ቢሆን፥ የብድር መያዣ አድርጋችሁ አትውሰዱ፤ የሰውን ነፍስ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆናልና።7አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባሪያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግድ።8የለምጽ ደዌን በተመለከተ ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡአችሁን መመሪያ በትክክል ለመፈጸም ጥንቃቄ አድርጉ። እኔ ለእነርሱ የሰጠሁትን ትእዛዝ በጥንቃቄ ተከተሉ። 9ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በመንገድ ላይ ሳላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሙሴ እህት በምርያም ላይ ያደረገባትን አስታውሱ።10ማናቸውንም ነገር ለባልንጀራችሁ ስታበድሩ መያዣ አድርጎ የሚሰጣችሁን ለመቀበል ወደ ቤቱ አትግቡ። 11እንንተ ከውጭ ሆናችሁ ጠብቅ፥ ያበደራችሁም ሰው መያዣውን ከቤት ያምጣላችሁ።12ሰውየው ድኻ ከሆነ መያዣውን ከእናንተ ዘንድ አታሳድሩበት። 13መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሐይ ሳትጠልቅ መልሱለት። ከዚያም ያመሰግናችኋል፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቆጠርላችኋል።14ድኻና ችግረኛ የሆነውን የምንዳ ሠራተኛ እስራኤላዊ ወንድማችሁም ሆነ፥ከከተሞቻችሁ ባንዲቱ የሚኖረውን መጻተኛ አትበዝብዙት፤ 15የሠራበትን ሒሳብ በዕለቱ ፀሐይ ሳትጠልቅ ክፈሉት፤ ድኻ በመሆኑ በጉጉት ይጠባበቀዋልና። ያለበለዚያ ወደ እግዚአብሔር ይጮኸና ኃጢአት ይሆንባችኋል።16አባቶች ስለ ልጆቻቸው፥ ልጆችም ስለ አባቶቻቸው አይገደሉ፤ እያንዳንዱ በራሱ ኃጢአት ይገደል።17መጻተኛው ወይም አባት ለሌለው ልጅ ፍትሕ አትንፈጉት፤ ባል የሞትባትንም መደረቢያ መያዣ አታድርጉ። 18እናንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበራችሁና እግዚአብሔር አምላካችሁ ከዚያ እንደ ተቤዣችሁ አስታውሱ፤ ይህን እንድታደርጉ ያዘዙአችሁ ለዚህ ነው።19የእርሻችሁን ሰብል በምታጭዱበት ጊዜ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሳችሁ አትሂዱ፤እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ ሥራ ሁሉ እንዲባርካችሁ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ። 20የወይራ ዛፋችሁን ፍሬ በምታራግፉበት ጊዜ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሳችሁ አትሂዱ ለመጻተኛ፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ።21የወይን ተክላችሁን ፍሬ ስትሰበስቡ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለሱበት የቀረውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ። 22በግብፅ ባሮች እንደነበራችሁ አስታውሱ፤ ይህን እንድታደርጉ ያዘዙአሁን ለዚህ ነው።
1በሰዎች መካከል ጠብ ቢነሣ ወደ ፍርድ አደባባይ ቢሄዱ፥ ዳኞች ተበዳይን ነጻ፥ በዳይን ግን ጥፋተኛ፥ በማድረግ የፍርድ ውሳኔ ይስጡ። 2በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፥ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፥ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ።3ሆኖም ግርፋቱ ከአርባ የሚበልጥ አይሁን፥ ከዚህ ካለፈ ግን እስራኤላዊ ወንድማችሁ በፊታችሁ የተዋረደ ይሆናል።4እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰሩ።5ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና፥ ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥የሟቹ ሚስት ከቤተ ሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት። 6በመጀመሪያ የምትወልደውም ልጅ ስሙ ከእስራኤል ፈጽሞ እንዳይጠፋ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራ።7ሆኖም ግን አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ለማግባት ባይፈልግ ሴትዮዋ በከተማዋ በር ወዳሉት ሽማግሌዎች ሄዳ የባለቤቴ ወንድም የወንድሙን ስም በእስራኤል ለማስጠራት አልፈለገም፥ የዋርሳነት ግዴታውንም አልፈጸመልኝም ትበላቸው። 8ከዚያም የከተማው ሽማግሌዎች ያን ሰው ጠርተው ያነጋግሩት እርሱም እርሷን ላገባት አልፈልግም ብሎ በሐሳቡ ቢጸና፥9የወንድሙንም ሚስት በሽማግሌዎች ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፥ የአንድ እግሩን ጫማ በማውለቅ በፊቱ ላይ ትትፋበትና የወንድሙን ቤት ማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ያለው ድርጊት ይፈጸምበታል ትበል። 10የዚያም ሰው የዘር ሐረግ በእስራኤል ዘንድ ጫማው የወለቀበት ቤት ተብሎ ይታወቃል።11ሁለት ሰዎች ቢደባደቡ፥ የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል መጥታ እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዘው 12፥እጇን ቁረጡ አትራሩላት።13በከረጢታችሁ ውስጥ ከባድና ቀላል የሆኑ ሁለት የተለያዩ ሚዛኖች አይኑሩአችሁ። 14በቤታችሁም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት የተለያዩ መስፈሪያዎች አይኑሩአችሁ።15እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም ትክክለኛና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑራችሁ። 16እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲህ ያሉትን ጽድቅ ያልሆን ነገሮች የሚፈጽመውንና የሚያምታታውን ሁሉ ይጸየፈዋልና።17ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ በእናንተ ላይ ያደረጉባችሁን አስታውሱ፤ 18ደክማችሁና ዝላችሁ በነበራችሁበት ጊዜ በጉዞ ላይ አግኝቶአሁ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአቤርንም አልፈሩም። 19እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ ባሳረፋችሁ ጊዜ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስሱ፤ ከቶ እንዳትረሱ!
1እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ ወደ ሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፥ ስትወርሱአትና ስትኖሩባት፤ 2እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሚሰጣችሁ ምድር ከሁሉም የመጀመሪያ ፍሬ ውሰዱት። ከዚያም በቅርጫት ውስጥ አድርጉትና እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ሂዱ።3በዚያን ወቅት ወደ ሚያገለግለው ካህን ሄዳችሁ ፦ እግዚአብሔር ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ እግዚአብሔር አምላካችሁን ለማምስገን እቀባለለሁ በለው። 4ካህኑም ቅርጫቱን ከእጃችሁ ተቀብሎ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ መሠዊያ ፊት ለፊት ያኖረዋል።5እናንተም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት እንዲህ ብላችሁ ትናገራላችሁ፦ አባቴ ዘላን ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ፥ ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።6ግብፃውያንም በመጥፎ ሁኔታ እንገላቱን፥ አሠቃዩንም። እንደ ባሪያ ከባድ ሥራ እንድንሠራ አደረጉን። 7ከዚያ በኋላ ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኸን፥ እርሱም ጩኸታችንን ሰማ፤ መከራችንን፣ ድካማችንንና የተፈጸመብንን ግፍ ተመለከተ።8ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር በብርቱ እጅና በተዘረጋው ክንዱ፥ በታላቅ ድንጋጤና ታምራት በምልክትና በድንቅ ከግብፅ አወጣን፤ 9ወደዚህም ስፍራ አመጣን፥ ማርና ወተት የምታፈሰውን ይህችን ምድር ሰጠን።10እግዚአብሔር ሆይ እነሆ፥ አንተ ከሰጠኸኝ ከምድሪቱ የመጀመሪያ ፍሬ አምጥቻለሁ፤ ቅርጫቱንም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አኑራሃው አምልከው፤ 11ለአንተና ለቤትህ ባደረገው መልካም ነገር አንተ፥ ሌዋውያንና መጻተኞች በእግአብሔር በአምላክህ ፊት ደስ ይበላችሁ።12የአሥራት ዓመት የሆነውን የሦስተኛውን ዓመት ፍሬ አንድ አሥረኛ ለይታችሁ ካወጣችሁ በኃላ በየከተሞቻችሁ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፥ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥አባት ለሌለውና ባል ለሞተባቸው ስጡአቸው። 13ከዚያ በኋላ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንዲህ በል፦ በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ከቤቴ አምጥቼ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም።14በሐዘን ላይ ሳለሁ፥ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም ባልነጻሁበትም ጊዜ ከዚህ ላይ ያነሣሁትምና ለሙታን ያቀረብሁት ምንም ነገር የለም። አምላኬን እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፥ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። 15ከቅዱስ ማደሪያ ሆነህ ከሰማይ ተመልከት፥ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በማለህላቸው መሠረት፥ ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ባርክ።16እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን ሥርዓትንና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ዛሬ ያዝዛችኋል፤ እናንተም በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትፈጽሙት ዘንድ ተጠንቀቁ። 17እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆነ በመንገዱም እንደምትሄዱ፥ ሥርዓቱን፥ ትእዛዙንና ሕጉን እንደምትጠብቁ እንደምትታዘዙለት በዛሬው ዕለት ተናግራችኋል።18እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት እንንተ ሕዝቡና ርስቱ መሆናችሁን ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቁ በዛሬው ዕለት ተናግሮአል፤ 19ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ ለማመስገን፥ ለማክበረና ከፍ ለማድረግና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቅዱስ ሕዝብ እንደምትሆኑ ማረጋገጫ ሰጥቶአል።
1ሙሴና የእስራኤል አለቆች ሕዝቡን እንዲህ ብለው አዘዙ፦ ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ። 2አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁሙና በኖራ ለስኑአቸው። 3የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማርና ወተት ወደምታፈሰው፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገሩ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፉባቸው።4ዮርዳኖስን እንደ ተሻገራችሁም ዛሬ ባዘዙአችሁ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከሉአቸው በኖራም ለስኑአቸው። 5እዚያም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የድንጋይ መሠዊያ ሥራ፥ በድንጋዮቹም ላይ ማናቸውንም የብረት መሣሪያ አታሳርፉባቸው።6የእግዚአብሔር የአምላካችሁን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥሩ፥ በላዩም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡበት። 7በላዩም የኅብረት መሥዋዕት ሠዉ፤ ብሉም፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ። 8በድንጋዮቹም ላይ የዚህ ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርጋችሁ ጻፉባቸው።9ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም፥ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ እስራኤል ሆይ፥ ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! እናንተ ዛሬ የእግዚአብሔር የአላካችሁ ሕዝብ ሆናችኋል። 10ስለዚይም እግዚአብሔር አምላካችሁን ታዘዙ፥ ዛሬ የሚሰጣችሁን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ጠብቁ።11ሙሴ በዚያኑ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ 12ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ስምዖን ፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዮሴፍና ብንያም ወገኖች ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ።13ሮቤል፥ ጋድ፥ አሴር፥ ዛብሎን፥ ዳንና ንፍታሌምወገኖች በጌባል ተራራ ላይ ለመርገም ይቁሙ። 14ሌዋውያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦15ጥበበኛ የሠራውን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ የሆነውን ምስል የሚቀርጽ ወይም ጣዖትን የሚያበጅ በስውርም የሚያቆም ሰው የተረገመ ይሁን። ሕዝብም ሁሉ፥ አሜን ይበል።16አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገም ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። 17የባልንጀራውን የድንበር ድንጋይ ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።18ዐይነ ስዉርን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። 19በመጻተኛው፥ አባት በሌለውና ባል በሞተባት ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።20ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን፤ የአባቱን መኝታ ያረክሳልና። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። 21ከማናቸውም እንስሳ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።22የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው ከእኅቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን። 23ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። ከሚስቱ እናት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።24በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። 25ንጹሕውን ሰው ለመግደል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።26የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
1ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በፍጹም ብትታዘዙና እኔ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዘትን ሁሉ በጥንቃቄ ብትከተሉ አምላካችሁ እግዝአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ አሕዝብ ሁሉ በላይ ከፍ ያደርጋችኋል። 2እግዚአብሔር አምላካችሁን ብትታዘዙ እነዚህ በረከቶች ሁሉ የእናንተ ይሆናሉ፤ አይለዩአችሁምም።3በከተማና በእርሻ ትባረካላችሁ። 4የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ የምድራችሁ አዝመራ፥ የእንስሳታችሁ ግልገሎች፥ የክብታችሁ ጥጃ፥ የበግና የፍየል ግልገሎቻችሁም ይባረካሉ።5እንቅባችሁና ቡሓቃያችሁም ይባረካሉ። 6ስትጓዙ ትበረካላችሁ፤ ስትወጡም ትባረካላችሁ።7እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶቻችሁን በፊታችሁ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤በአንድ አቅጣጫ ቢመጡባችሁ በሰባት አቅጣጫም ከእናንተ ይሸሻሉ። 8እግዚአብሔር በጎተራችሁና እጃችሁ በነካው ሁሉ በረከቱን ይልካል። አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ይባርካችኋል።9የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ትእዛዞች የምትጠብቁና በመንገዱ የምትሄዱ ከሆነ በማለላቸው ተስፋ መሠረት የተቀደሰ ሕዝቡ አድርጎ ያቆማችኋል። 10ከዚያ የምድር አሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም መጠራታችሁን ያያሉ፤ ይፈርሁማል።11እግዚአብሔርም ሊሰጣችሁ ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ በእንስሳታችሁ፥ ግልገል፥ በምድራችሁም ሰብል፥ የተትረፈረፈ ብልጽግና ይሰጣችኋል። 12እግአብሔር ለምድራችሁ በወቅቱ ዝናብን ለመስጠትና የእጃችሁን ሥራ ሁሉ ለመባረክ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትላችኋል፤ እናንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራላችሁ እንጂ ከአንዳቸውም አትበደሩም።13እግዚአብሔም ራስ እንጂ ድራት አያደርጋችሁም፤ ዛሬ የምሰጣችሁን የአምላካችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ብትጠብቁ መቼውንም ቢሆን በላይ እንጂ ፈጽሞ በታች አትሆኑም። 14ሌሎች አማልክት በመከተል እነርሱን በማገልገል ዛሬ ከምሰጣችሁ ትእዛዞች ቀኝም ግራም አትበሉ።15ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ባትታዘዙ በዛሬዋ ዕለት የምሰጣችሁን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ሁል በጥንቃቄ ባትከተሉአቸው እነዚህ ርግማኖች ሁሉ ይደርሱባችኋል፤ ያጥለቀልቁአችኋልም።16በከተማ ትረገማላችሁ፤ በእርሻም ትረገማላችሁ። 17እንቅባችሁና ቡሓቃያችሁ የተረገሙ ይሆናሉ።18የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ የእርሻህ ሰብል፥ የመንጋችሁ ጥጆች፥ የበግና የፍየል ግልገሎቻችሁ ይረገማሉ። 19ስትገቡ ትረገማላችሁ፤ ስትወጡም ትረገማላችሁ።20እርሱን በመተው ክፉ ድርጊት ከመፈለጋችሁ የተነሣ እስክትደመስሱ ፈጥናችሁም እስክትጠፉ ድረስ እጃችሁ በነካው ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ርግማንን መደናገርንና ተግሣጽን ይሰድባችኋል። 21እግዚአብሔር ልትወርሱአት ከምትገቡባት ምድር ላይ እስኪያጠፋችሁ ድረስም በደዌ ይቀሥፋችኋል።22እግዚአብሔር እስክትጠፉ ድረስ በሚቀሥፍ ደዌ ትኩሳትና ዕባጭ ኃይለኛ ሙቀትና ድርቅ ዋግና አረማሞ ይመታችኋል።23ከራሳችሁ በላይ ያለው ሰማይ ናስ ከእግራችሁ በታች ያለው ምድርም ብረት ይሆናል። 24እግዚአብሔር የምድራችሁን ዝናብ ወደ አቧራነትና ወደ ትቢያነት ይለወጠዋል፤ ይህም እስክትጠፉ ድረስ ከሰማይ ይወርድባችኋል።25እግዚአብሔር በጠላቶቻችሁ ፊት እንድትሸነፉ ያደርጋችኋል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣበቸዋላችሁ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሽሻላችሁ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀያ ትሆናላችሁ። 26ሬሳችሁ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ በማስፈራራትም የሚያባርሩአቸው አይኖርም።27እግዚአብሔር በማትድኑበት በግብፅ ብጉጅ፥ በእባጭ በሚመግል ቁስልና በእከክ ያሠቃያችኋል። 28እግዚአብሔር በእብደት፥ በዕውርነትና ግራ በማጋባት ያስጨንኣቃችል። 29በእኩለ ቀን በጨለማ እንዳለ ዕውር በዳበሳ ትሄዳላችሁ። የምታደርጉት ሁሉ አይሳካላችሁም። በየዕለቱ ትጨቆናላችሁ፤ ትመዘበራላችሁም፤ የሚታደጋችሁም አይኖርም።30ሚስት ለማግባት ልጃገረድ ታጫላችሁ ሌላው ግን ወስዶ በኃይል ይደፍራታል። ቤት ትሠራላችሁ፤ ግን እናንተ አትኖሩበትም። ወይን ትተክላላችሁ ፍሬውን ግን አትበሉም። 31በሬህ ዐይናችሁ እያየ ይታረዳል፤ ከሥጋውም አንዳች አትቀምሱም። አህያችሁም በግድ ይወሰድባችኋል፤ አትበሉም። በጎቻችሁ ለጠላቶቻችሁ ይሰጣሉ፤ የሚያሰጥላቸውም አይኖርም።32ወዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ለባዕድ ሕብብ ይሰጣሉ፤ እጃችሁንም ለማንሣት እቅም ታጣላችሁ፤ ይመጣሉ፤ በማለትም ዐይኖቻችሁ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።33የምድራችሁንና የድካማሁን ፍሬ ሁሉ የማታውቁት ሕዝብ ይበላዋል፤ 34ሁልጊዜ በጭቆናና በጫን ትኖራላችሁ፤ በምታዩት ሁሉ ትጃጀላላችሁ። 35እግዚአብሔር ከእግራችሁ ጥፍር እስከ ራስህ ጠጉር በሚወርር ሊድን በማይችልና በሚያሠቃይ ቁስል ጉልበታችሁንና እግራችሁን ይመታችኋል።36እግዚአብሔር እናንተንና በላያችሁ ያነገሣችሁትን ንጉሥ፥ እናንተና አባቶቻችሁ ወደ ማታውቁት ሕዝብ ይወሰዳችኋል፤ ከዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማክልትን ታመልካላችሁ። 37እግእብብሔር እንድትገቡ በሚመራችሁ ምድር ለአሕዛብ ሁሉ መሸማቀቂያ ማላገጫና መዘባበቻ ትሆናላችሁ።38በእርሻ ላይ ብዙ ዘር ትዘራላችሁ አንበጣ ስለሚበላው የምትሰበስቡ ጥቂት ይሆናል። ወይን ትተክላላችሁ ትንከባከበዋላችሁ፤ 39ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጡም ዘለላውንም አትሰበስቡም።40በአገራችሁ ምድር ሁሉ የወይራ ዛፍ ይኖራችኋል፤ ፍሬው ስለሚረግፍባችሁ ግን ዘይቱን አትቀቡም። 41ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻችሁን ትወልዳላችሁ ነገር ግን በምርኮ ስለሚወሰዱ፤ አብረዋችሁ አይኖሩም።42ዛፋችሁንና የምድራችሁን ሰብል ሁሉ አንበጣ መንጋ ይወረዋል። 43በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ከእናንተ በላይ ከፍ ከፍ ሲል እናንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላላችሁ። 44እርሱ ያበድራችኋል እንጂ እናንተ አታበድሩም። እርሱ ራስ ይሆናል፤ እናንተ ግን ጅራት ትሆናላችሁ።45እነዚህ ርግማኖች እስክትጠፉ ድረስ ይከተሉአችኋል፤ ሁሉ በእናንተ ላይ ይመጣሉ፤ ይህም የሚሆነው አምላካችሁን እግዚአብሔርን ስላልታዘዛችሁና የሰጣኋችሁን ትእዛዝና ሥርዓት ስላልጠበቃችሁ ይወርዱባችኋልም። 46እነዚህ ርግማኖች እንደ ምልክትና ድንቅ ነገሮች ሆነው በእንንተና በዘራችሁ ለዘላለም ይሆናል።47በብልጽግና ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁን በደስታና በሐሤት ስላላገለገችሁ በራብና በጥም በእርዛትና በከፋ ድኽነት 48እግዚአብሔር የሚያስነሣባችሁን ጠላቶቻችሁን ታገለግላላችሁ፤ እስኪያጠፉአችም ድረስ በአንገታችሁ ላይ የብረት ቀንበር ይጭንባችኃል።49እግዚአብሔር እንደ ንስር በፈጣን የሚበሩና ቋንቋውን የማታውቁአችሁን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፥ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣነሰባችኋል፤ 50ሽማግሌ የማያከብር፥ ለወጣትም መልካም ያልሆኑና የሚያስፈራና ጨካኝ ሕዝብ ነው። 51እስክትጠፉም ድረስ የእንስሳታችሁን ግልገልና የምድራችሁን ሰብል ይበላል፤ እስኪያጠፋችሁም ድረስ እህል፤አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት የመንጋችሁን ጥጃና የበግና ፍየል መንጋችሁን ግልገል አያስቀሩላችሁም።52የምትታመኑባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገራችሁ ያሉትን ከተሞቻችሁን ሁሉ ይከባል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጥጣችሁምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል። 53ጠላቶቻችሁ ከበው በሚያስጨንቁአችሁ ጊዜ ከሥቃይ የተነሣ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችህን የአብራካችሁ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆቻችሁን ሥጋ ትበላላችሁ።54ሌላው ይቅርና በመካከላችሁ በጣም ደግና ርኅሩኅ የሆነው ሰው እንኳ ለገዛ ወንድሙ ወይም ለሚወዳት ሚስቱ ወይም ለተረፉት ልጆቹ አይራራላቸውም። 55ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ያህል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ከተሞቻችሁ ሁሉ በመከበባቸው ጠላቶቻችሁ ከሚያደርሱባችሁ ሥቃይ የተነሣ ለእርሱ የቀረለት ይህ ብቻ ነውና።56በመካከላችሁ ተመቻችታና ተቀማጥላ የምትኖር ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ እግሯን አፈር ነክቶት የማያውቅ ሴት የምትወደውን ባሏን፥ የገዛ ወንድና ሴት ልጆቿን ትንቃለች። 57ከማሕፀኗ የወጣውን የምትወልዳቸውን ሕፃናት ትጠየፋለች፤ በመከራው ወቅት ጠላቶቻችሁ ከተሞቻችሁን ከበው በሚያስጨንቁአችሁ ጊዜ ሌላ የሚበላ ስለማይኖር እነርሱን ደብቃ ትበላለች።58በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን የዚህን ሕግ ቃሎች ባትከተሉና የተከበረውና አስፈሪ የሆነውን የአምላካችሁን 59የእግዚአብሔርን ስም ባታከብሩ እግዚአብሔር አስፈሪ መቅሠፍት፥ አስጨናቂና ለብዙ ጊዜ የሚቋይ መዓት አሠቃቂና በቀላሉ የማይወገድ ደዌ በእናንተና በዘሮቻችሁ ላይ ይልክባችኋል።60የምትፈሩአችሁንም የግብፅ በሽታዎች ሁሉ ያመጣባችኋል፤ በእናንተም ላይ ይጣበቃሉ። 61ደግሞም እግዚአብሔር በዚህ የሕግ መጽሐፍ ያልተጸፈውን ማንኛውንም ዓይነት ደዌና መከራ እስክትጠፉ ድረስ ያመጣባችኋል። 62ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስላልታዛዝችሁ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝታችሁ ቢሆን እንኳ እናንተ ጥቂት ብቻ ትቀራላችሁ።63እግዚአብሔር ለእናንተ መልካም በማድረግና ቁጥራችሁን በማብዛት ደስ እንዳተሰኘ ሁሉ ፤ እናንተን በመደምሰስና በማጥፋት ደስ ይለዋል። ከምትወርሱዋት ምድር ትነቀላላችሁ። 64ከዚያም እግዚአብሔር ከአንዱ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ዳርቻ በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይበትናችኋል። በዚያም አባቶአኣችሁ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ።65በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኙም፤ ለእግራችሁም ጫማ ማረገጫ አይኖርም፤ እዚያም እግዚአብሔር የሚጨነቅ አእምሮ፥ የሚደክም ዐይንና ተስፋ የሚቋርጥ ልብ ይሰጣችኋል። 66ዘመናችሁን በሙሉ ቀንና ሌሊት በፍርሃት እንደ ተዋጣችሁ ሕይወትታችሁ ዘወትር በሥጋት ትኖራላችሁ።67ልባችሁ በፍርሃት ከመሞላቱና ዐይናችሁ ከሚያየው ነገር የተነሣ ሲነጋ ምነው አሁን ሲመሽ ፥ደግሞ ምነው አሁን በነጋ ትላላችሁ። 68ዳግመኛ አትመለሱባትም ባልሁ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብፅ ይመልሳችኋል። እዚያም እንደ ወንድና ሴት ባሪያ ለጠላቶቻችሁ ለመሸጥ ራሳችሁን ታቀርባላችሁ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።
1እግዚአብሔር በኮሬብ ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞዓብ ምድር ከእስራኤላውያን ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው የኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው።2ሙሴ እስራኤላውያንን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እግዚአብሔር በግብፅ በፈርዖን፥ በሹማምንቱ ሁሉና በመላ አገሩ ያደረተውን ሁሉ ዐይኖቻችሁ አይተዋል። 3እነዚያን ከባድ ፈተናዎች ታምራዊ ምልክቶችና ታላቅ ድንቆች በገዛ ዐኖቻችሁ አይታችኋል። 4ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር የሚያስተውል አእምሮ ወይም የሚያይ ዐይን ወይም የሚሰማ ጆሮ አልሰጣችሁም።5በምድረ በዳ በመራኋችሁ በእነዚያ አርባ ዓመታት ውስጥ ልብሳችሁ አላረጀም፥ የእግራችሁም ጫማ አላለቀም፥ 6ቂጣ አልበላችሁም፥ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንህ ታውቁ ዘንድ ነው።7ወደዚህ ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ የሐሴንቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው። 8ምድራቸውንም ወስደን ለሮቤላውያን ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠን። 9እንግዲህ የምታደርጉት ሁሉ እንዲከናወንላችሁ፤ የዚህ ኪዳን ቃሎች በጥንቃቄ ተከተሉ።10እናንተ ሁላችሁ መሪዎቻችሁና አለቆቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁና ሹሞቻችሁ እንዲሁም ሌሎች የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል፤ 11ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ እንጨታችሁን እየፈለጡ ውሃዎቻችሁንም እየቀዱ በሰፈራችሁ የሚኖሩ መጻተኞችም አብረአችሁ ቆመዋል።12እዚህ የቆማችሁ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ከእናንተ ጋር ወደ ሚያደርገውና በመሐላ ወደሚያጸናው ኪዳን፥ከእግዚአብሔር ከአምላካችሁ ጋር ትገቡ ዘንድ ለእናንተ በሰጣችሁ ተስፋና፥ 13ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት እርሱ አምላካችሁ ይሆን ዘንድ እናንተም ሕዝቡ መሆናችሁን በዛሬው ዕለት ለማረጋገጥ ነው።14እኔም ይህ የቃል ኪዳን የማደርገው ከእናንተ ጋር ብቻ አይደለም፤ 15አብራችሁን በእግዚአብሔር በአምላካችን ፊት እዚህ ከቆማችሁት ጋር ብቻ ሳይሆን ዛሬ እዚህ ከሌሉትም ጋር ነው። 16በግብፅ ምድር እንዴት እንደኖርንና ወደዚህ ስንመጣም በየአገሮቹ ውስጥ እንዴት እንዳለፍን ራሳችሁ ታውቃላችሁ።17በመካከላቸውም አስጸያፊ ነገሮቻቸውን፦ የእንጨትና የድንጋይ፥ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል፤ 18የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከእግዚአብሔር ከአምላካችን የሚመልስ ወንድ፥ ሴት፥ቤተ ሰብ፥ ወይም ጎሣና ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ አይገኙ፤ ከመካከላችሁ እንዲህ ያለውን መራራ መርዝ የሚያወጣ ሥር እንዳይኖር ተጠንቀቁ። 19እንዲህ ያለው ሰው የዚህን ቃል ኪዳን በሚሰማበት ጊዜ በልቡ ራሱን በመባረክ፦ እንደ ልቤ ግትርነት ብመላለስም እንኳ ሰላም አለኝ ብሎ ያስባል። ይህም እርጥቡን ከደረቁ ጋር ያጠፋል።20እግዚአብሔር ለዚህ ሰው ፈጽሞ ምሕረት አያደርግለትም፥ ቁጣውና ቅናቱ በእርሱ ላይ ይነድበታል፤ በዚህ መጽሐፍ የተጸፉት ርግማን ሁሉ ይወርድበታል፤ እግዚአብሔርም ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል። 21በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የኪዳኑ ርግማን መሠረት እግዚአብሔር እርሱን ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ለጥፋት ይለየዋል።22የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሩቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና እግዚአብሔር ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ፤ 23ምድሩቱ በሙሉ የተቃጠለ ጨውና ዲን ዐመድ ትሆናለች፤ አንዳች ነገር አይተከልባት፤ ምንም ነገር አያቆጠቁጥባትም። የሚያድግ ተክል አይገኝባትም። የምደርስባት ውድመት እግዝክአብሔር በታላቅ ቁጣ እንደ ገለባበጣቸው እንደሰዶምና ገሞራ እንደ አዳማና ሊባዮ ጥፋት ይሆናል። 24አሕዛብም ሁሉ፤ እግዚአብሔር በዚች ምድር ላይ ይህን ለምን አደረገባት? ይህ አስፈሪና የሚነድ ቁጣስ ለምን መጣባት? ብለው ይጠይቃሉ።25ሕዝቡም እንዲህ ይላሉ፦ የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር ያወጣቸውንና ከእነርሱም ጋር ያደረጉትን ቃል ኪዳን ሕዝቡ ስለ ተዉ ነው፤ 26ወጥተውም የማያውቋቸውን እርሱም ያላዘዛቸውን ሌሎችን አማልክት ስለአመለኩአቸውና ስለሰገዱላቸውም ነው።27ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ የተጸፈውን ርግማን ሁሉ እስኪያመጣባት ድረስ የእግዚአብሔር ቁጣው በዚህች ምድር ላይ ነደደ። 28እግዚአብሔር በታላቅ አስፈሪነት፥በቁጣና በንዴት ከምድራቸው ነቀላቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው የሚል ይሆናል።29ምስጢር የሆነው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ ለዘላለም እንድንተገብረው ዘንድ የኛና የልጆቻችን ነው።
1በፊታችሁ ያስቀመጥሁት ይህ በረከትና መርገም ሁሉ በእናንተ ላይ ሲመጣና አምላካችሁ እግዚአብሔር በትኖአችሁ ከምትኖሩበት አሕዛብ መካከል ሆናችሁ፤ 2ወደ ልባችሁ ተመልሳችሁ ነገሮቹን በምታስተውሉበት ጊዜ፥ እንዲሁም ዛሬ እኔ በማዝዛችሁ ሁሉ መሠረት እናንተና ልጆቻችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመልሳችሁ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እርሱን ስትታዘዙ፤ 3እግዚአብሔር አምላካችሁ ምርኮአችሁን ይመልስላችኋል፤ ይራራላችሁማል፤ እናንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከል እንደ ገና ይሰበስባችኋል።4ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ብትጋዙ እንኳ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከዚያ ይሰበስባችኋል፤ መልሶም ያመጣችኋል። 5የአባቶቻችሁ ወደ ሆነችው ምድር ያመጣችኋል፤ እናንተም ትወርሱታላችሁ፤ ከአባቶቻችሁ ይበልጥ ያበለጽጋችኋል፤ያበዛችሁማል።6እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እንድትወዱት፤በሕይወትም እንድትኖሩ እግዚአብሔር አምላካችሁ የእናንተንና የዘራችሁን ልብ ይገርዛል። 7አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህን ርግማን ሁሉ በሚጠሉአችሁና በሚያሳድዱአችሁ ጠላቶቻችሁ ላይ ያደርገዋል። 8እናንተም ተመልሳችሁ ለእግዚአብሔር ትታዘዛላችሁ፥ ዛሬ እኔ የማዛችሁን ትእዛዛ ሁሉ ትጠብቃላችሁ።9በዚያም እግዚአብሔር በእጃችሁ ሥራ ሁሉን በወገባችሁ ፍሬ በእንስሳታችሁ፥ ግልገሎችና በምድራችሁ ሰብል እጅግ ያበለጽጋችኋል። በአባቶቻችሁ ደስ እንደ ተሰኘ ሁሉ እግዚአብሔር እናንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋልና። 10ይህም የሚሆነው አምላካችሁን እግዚአብሔርን ከታዘዛችሁና በዚህ የሕግ መሕሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን በመጠበቅ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ስትመለሱ ነው።11ዛሬ የምሰጣችሁ ትእዛዝ ይህን ያህል አስቸጋሪ ወይም ከእናንተ የራቀ አይደለም። 12እንድንፈጽሙት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? እንዳትሉ በሰማይ አይደለም።13ደግሞም እንድናደርገው አምጥቶ ይነግረን ዘንድ ማን ባሕሩን ይሻገራል? እንዳትሉም ከባሕር ማዶ አይደለም። 14ነገር ግን ቃሉ ለእናንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ታደርጉትም ዘንድ በአፋችሁና በልባችሁ ውስጥ ነው።15እነሆ ዛሬ ሕይወትንና በረከትን፥ ሞትንና ጥፋትን በፊታችሁ አኑሬአለሁ። 16እግዚአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱ በመንገዱም እንድትሄና ትእዛዙን፥ ሥርዓቱንና ሕጉን እንድትጠብቁ አዝዛችኋል፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ ትበዛላችሁም፤ አምላካችሁም ትወርሱአት ዘንድ በምትገቡበት ምድር ይባርካችህኋል።17ዳሩ ግን ልባችሁን ወደ ኋላ በመለሰና ባትታዘዙ ለሌሎች አማልክት ለመስገድ ብትታለሉና ብታመልኩአችሁ፤ 18በርግጥ እንደምትጠፉ እኔ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ትወርሱአት ዘንድ በምትገቡባት ምድር ብዙ አትኖሩባትም።19ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና ርግማንን በፊታችሁ እንዳስቀመጣችሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራችኋለሁ። እንግዲህ እናንተና ልጆቻችሁ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጡ፤ 20ይኸውም እግዚአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱ ቃሉን እንድታደምጥና ከእርሱ ጋር እንድትጣበቁ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወታችሁ ነው፤ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለሕስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ ይሰጣችኋል።
1ሙሴም ወጥቶ እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል በሙሉ ነገራቸው። 2እንዲህም አላቸው፦ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል ከእንግዲህ መወጣትና መግባት አልችልም፤ እግዚአብሔርም ዮርዳኖስን አትሻገርም ብሎኛል፥ 3እግዚአብሔር አምላካችሁ ራሱ በፊታችሁ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊታችሁ ያጠፋቸዋል፤ እናንተም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው፤ ኢያሱም እናንተን ቀድሞ ይሻገራል።4እግዚአብሔር የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው እነዚህንም ያጠፋቸዋል። 5እግዚአብሔር እነርሱን በፊታችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ያዘዝኋችሁን ሁሉ በእነርሱ ላይ ታደርጋላችሁ። 6ብርቱና ደፋር ሁኑ፥ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡል አላቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንት ጋር ይሄዳልና አይተዋችሁም አይጥላችሁምም።7ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ሊሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ከዚህ ሕዝብ ጋር አብረህ ስለምትገባ፤ ምድሪቱን ርስታችው አድርገህ ስለምታከፋፍል በርታ፤ ደፋርም ሁን። 8እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ይሄዳል፤ ከአንተም ጋር ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አተውህምም አትፍራ ተስፋም አትቁረጥ።9ሙሴም ይህን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት ለሚሸከሙ፥ ለሌዊ ልጆች፤ ለካህቱና ለእስራኤል አለቆች ሁሉ ሰጠ። 10ከዚያም በኋላ ሙሴ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ዕዳ በሚተውበት የዳስ በዓልም በሚከበርበት በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ 11እስራኤል ሁሉ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ሲታይ ይህ ሕግ በእነርሱ ፊት በጆሮአቸው ታነባቸዋላችሁ።12እነርሱም ይስሙና አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት ይማሩ ዘንድ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ በጥንቃቄ እንዲከተሉ ሕዝቡን ይኸውም ወንዶችን፥ ሴቶችንና ልጆቻቸሁንና በከተሞቻችሁን የሚኖረውንም መጻተኛ ሰብስቡ። 13ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸሁም መስማትና አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት ሊማሩ ይገባቸዋል።14እግዚአብሔር ሙሴን እነሆ የምትሞትበት ቀን ቀርቦአል፥ ትእዛዝ እንድሰጠው ኢያሱን ጥራውና ወደ መገናኛው ድንኳንም ቅረቡ። 15እግዚአብሔር በድንኳኑ ላይ በደመና ዐምድ ተገለጠ፤ የደመናውም ዐምድ ከድንኳኑ ደጃፍ ላይ ቆመ።16እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ እነሆ ከአባቶቻችሁ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል፤ እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።17በዚያም ቀን ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ይነዳል፤ እተዋቸዋለሁም። ፊቴንም ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያም ቀን ይህ ጥፋት የደረሰሰብን አምላካችን ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን? ይላሉ። 18ወደ ባዕዳን አማልክት በመዞር በፈጸሙት ክፋታቸው የተነሣ በዚያን ቀን ፊቴን ከእነርሱ ፈጽሞ እሰውራለሁ።19እንግዲህ ይህን መዝሙር ለራሳችሁ ጻፉና ለእስራኤል ልጆች አስተምሩ። ስለ እኔ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ እንዲዘምሩ አድርጉ። 20ወተትና ማር ወደምታፈሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር ባመጣሃቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፥ ከበለጸጉም በኋላ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።21ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዛሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸውም አፍ የሚረሳ አይሆንም፤ ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ አውቃለሁ።22ስለዚህም ሙሴ ይህን መዝሙር በዚያን ቀን ጻፈና እስራኤላውያንን አስተማራቸው። 23እግዚአብሔርም ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በር ደፋር ሁን፤ የእስራኤልን ልጆች በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ታስገባቸዋለህና እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ በማለት ትእዛዝ ሰጠው።24ሙሴ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የዚህን ሕግ ቃል በመጽሐፍ ጽፎ እንዳበቃ፤ 25የእስራኤልን የኪዳን ታቦት የሚሸከሙ ሌዋውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ 26ይህን የሕግ መጽሐፍ ውሰዱ፤ በዚያም በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት።27ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆናችሁ አውቃለሁ፥ተመልከቱ እኔ ዛሬ በሕይወት ከእናንተ ጋር እያለሁ እንኳን በእግዚአሔር ላይ እንደህ ካመፃችሁ ከሞትሁ በኋላማ እንዴት አታደርጉም? 28ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ ጠርቼባቸው ይህን ቃል ይሰሙ ዘንድ ብጆሮኣቸው እንድናገር ፤ የነገድ አለቆቻችሁን በሙሉና ሹሞቻችሁን ሁሉ በፊቴ ሰብስቡ። 29እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ አውቃለሁና። በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፤ ይህ የሚሆነው እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ለቁጣ ስለምታነሣሡት በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል።30ሙሴ የዚህን መዝሙር ቃል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ለተሰበሰበው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በጆሮአቸው አሰማ።
1ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ እኔም እናገራለሁ፤ ምድር ሆይ፥ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ። 2ትምህርቴም እንደ ዝናብ ይውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፥ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ።3እኔ የእግዚአብሔርን ስም አውጃለሁ፤ የአምላካችንን ታላቅነት አወድሱ። 4እርሱ ዐለትና ሥራውም ፍጹም፥ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው። የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፤ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው።5በእርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል። ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም። ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው። 6እናንተ ተላላና ጥበብ የጎደላችሁ ሕዝብ፤ለእግዚአብሔር የምትመልሱለት በዚህ መንገድ ነውን? አባታችሁና ፈጣሪያችሁ የሠራችሁና ያበጃችሁእርሱ አይደለምን?7የጥንቱን ዘመን፥ የብዙ ዓመቶችን አስታውሱ፤ አባቶቻችሁን ጠይቁ ይነግሩማልም፥ ሽማግሌዎቻችንም ጠይቁ ያስረዱአችኋል። 8ታላቁ አምላክ ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፤ በእስራኤል ልጆች ቁጥር ልክ፤ የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ።9የእግዚአብሔር ድርሻ የገዛ ሕዝቡ ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና። 10እርሱን በምድረ በዳ፤ ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አግኘው፤እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው።11ንስር ጎጆዋን እንደትጠብቅ፤ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፥ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፥ እግዚአብሔር ክንፎቹን ዘርግቶ፥ ተሸከሞ ወሰዳቸው። 12እግዚአብሔር ብቻ መራው ምንም ባዕድ አምላክ ከእርሱ ጋር አልነበረም።13በምድር ከፍታ ላይ አስኬደው፤ የእርሻንም ፍሬ መገበው፤ ከዐለት ድንጋይ ማር አበላው፤ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው። በወንድና በሴት ልጆቹ ተቆጥቶአልና።14የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወትት የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፤ የባሳንን ሙኩት በግ፤ መልካም የሆነውንም ስንዴ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ ጠጠህ።15ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ስብ ጠገበ፥ ሰውነቱ ደነደነ፥ ለሰለሰም። የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ የመጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀው። 16በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፤ በአስፈያፊ ጣዖቶቻቸውም አስቆጡት።17አምላክ ላልሆኑ አጋንንት፥ ላላወቋቸው አማልክት፥ ከጊዜ በኋላ ለተነሡ አማልክት፥ አባቶቻችውም ላልፈሯቸው አማልክት ሠዉ። 18አባት የሆናችሁን ዐለት ከዳችሁት፤ የወለዳችሁን አምላክ ረሳችሁ።19እግዚአብሔር ይህን አይቶ ተዋቸው፤ በወንድና በሴት ልጆቹ አስጥተውታልና። 20እርሱም እንዲህ ብሎአል፦ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆንም አያለሁ፤ ጠማማ ትውልድ፤ የማይታሙንም ልጆች ናቸውና።21አምላክ ላልሆነው አስቀኑኝ፤ በከንቱ ጣዖቶቻቸውም አስቆጡኝ። እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋል፤ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣቸዋለሁ።22በቁጣዬ እሳት ተቀጣጥሎአልና፤እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነዳል፤ ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል።23በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ። ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እተኩሳለሁ። የሚያጠፋ ራብ፤በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድባቸዋለሁ፤ 24የአራዊትን ሹል ጥርስ፥ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድባቸዋለሁ።25ሰይፍ መንገድ ላይ ያስቀራቸዋል፤ በመኝታቸውም ድንጋጤ ይነግሣል፤ጎልማሳውና ልጃገረዷ፤ ሕፃኑና ሽማግሌው ይጠፋሉ። 26ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ፥ እበትናቸዋለሁም፤አልሁ፤27ድል ያደረገው እጃችን ነው ብለው፥ ጠላቶቻቸው በስሕተት እንዳይታበዩ፥ የጠላት ማስቆጣት እንዳይሆን እሠጋለሁ።28እስራኤላውንም አእምሮ የጎደላቸው፤ ማስተዋልም የሌላቸው ናቸው። 29አስተዋዮች ቢሆኑ ኖሮ ይህን በተገነዘቡና መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን ባስተዋሉ ነብር።30መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው እግዚአብሔር ካልተዋቸው በቀር፥ አንድ ሰው እንዴት ሺሁን ያሳድዳል፥ ሁለቱስ እንዴት አሥር ሺሁን እንዲሸሹ ያደጋሉ? 31የእነርሱ መጠጊያ ዐለታቸው እንደ እኛ መጠጊያ ዐለት አለመሆኑን፤ ጠላቶቻችንም እንኳ አይክዱም።32ወይናቸው ከሰዶም ወይን ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤ የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፥ ዘለላቸውም መራራ ነው።33ወይናቸው የእባብ መርዝ፤ መርዙም የጨካኝ እባብ ነው። 34ይህስ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፤ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን?35በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፥ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቦአል፤ የሚመጣባቸውም ነገሮች ይፈጥንባቸዋል።36ኃይላቸው መድከሙን ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል።37እንዲህም ይላል፦ መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፤ አማልክታቸው ወዴት አሉ? 38የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፤ የመጠጥ ቁርባናችውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው? እስቲ ይነሡና ይርዷችሁ! እስቲ መጠለያ ይስጧችሁ!39እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤እገድላለሁ፤ አድናለሁ፤አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም። 40እጄን ወደ ሰማይ አነሣለሁ፤ ለዘላለምም ሕያው እንደ ሆንሁ እናገራለሁ።።41የሚያብራቀርቅ ሰይፌን ስዬ እጄ ለፍርድ ስይዘው፤ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ ለሚጠሉኝም እንደሥራቸው እከፍላቸዋለሁ።42ሰይፌ ሥጋ በሚበላበት ጊዜ፥ ፍላጾቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ደሙ የታረዱትና የምርኮኞች የጠላት አለቆችም ራስ ደም ነው።43አሕዛብ ሆይ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ይቤዣቸዋል።44ሙሴም ከነዌ ልጅ ከኢያሱ ጋር መጥቶ የመዝሙር ቃሎችን በሕዝቡ ጆሮ ተናገረ። 45ሙሴም እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለመላው እስራኤል ተናገሮ ጨረሰ።46እርሱም እንዲህ አላቸው፦ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዟቸው እኔ ዛሬ በግልጥ የምነግራችሁን ቃሎች ሁሉ በልባችሁ አኑሩ። 47ቃሎቹ ለእናንተ ሕይወታችሁ ናቸው፥ ባዶ ቃሎች አይደሉም፥ በእነርሱ ዮርዳንስን ተሻገራችሁ በምትወርሷትም ምድር ረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።48በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ 49ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር ከዓብሪም ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ናባው ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓን ምድር አሻግረህ ተመልከት።50ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተስበስበ ሁሉ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ። 51ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሁለታችሁም በሲን ምድረ በዳ በቃዴስ በምሪባ ውሃ አጠገብ በእስራኤላውያን መካከል በእኔ ላይ ባለመታመናችሁ፤ እንዲሁም በእስራኤላውያን መካከል የሚገባውን አክብሮት ባለመስጠታችሁ ነው። 52ስለዚህ ምድሪቱን ከሩቅ ሆነህ ታያታለህ እንጂ ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።
1የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት ለእስራኤላውያን የሰው ቃለ ቡራኬ ይህ ነው። 2እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሐይ ወጣ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጣ፤ በስተቀኙ የሚነድ እሳት ነበር።3በእርግጥ ሕዝቡን የምትወድ አንተ ነህ፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው። ከእግርህ ሥር ሁሉ ይስገዳሉ፤ ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤ 4ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው።5የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፤ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፤ እግዚአብሔር በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር። ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት። 6የወገኖቹ ቁጥርም ጥቂት ይሁን።7ስለይሁዳ የተነገረው ባትኮት ይህ ነው። ሙሴም እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ የይዳን ጩኸት ስማ፤ ወደ ወገኖቹም እንደገና አምጣው። ስለእርሱ ተዋጋለት፤ አቤቱ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!8ስለ ሌዊም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ቱሚምህና ኡሪምህ ለምትወደው ሰው ይሁን፤ ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤ በመሪባም ውሃ ከእርሱ ጋር ተከራከርህ።9ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፤ ስለ እነርሱ ግድ የለኝም አለ። ወንድሞቹን አልለያቸውም፤ ልጆቹንም አላወቃቸውም። ስለቃልህ ከለላ አደረገ፤ ኪዳንህንም ጠበቀ።10ሥርዓትህን ለያዕቆብ፤ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራል። ዕጣን በፊትህ፤ ያሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በምሠዊያህ ላይ ያቀርባል።11እግዚአብሔር ሆይ፥ ኃይሉን ሁሉ ባርክለት፤ በእጁ ሥራ ደስ ይበልህ፤ በእርሱ ላይ የሚነሡበትን ሽንጣቸውን ቁረጠው፤ ጠላቶቹንም እንደገና እንዳይነሡ አድርገህ ምታቸው።12ሙሴ ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ በእርሱ ተጠብቆ በሰላም ይረፍ፤ ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር የሚወደውን ሰው በትክሻዎቹ መካከል ያርፋል።13መሴ ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦ እግአብሔር ምድሩን ይባርክ፤ ውድ በሆኑ ሰማያዊ ነገሮች፥ ጠል ከላይ በማውረድ፤ ከታች በጥልቅ በተንጣለለው ነገሮች ይባርክ።14ከፀሐይ በተሠሩ ምርጥ ፍሬ፤ ጨረቃም በምትሰጠው እጅግ መልካም ነገር፤ 15ከጥንት ተራሮች በተገኘ ምርጥ ስጦታ፤ በዘላለማዊ ኮረብቶች ፍሬያማነት ይባርክ።16ምድር በምታስገኘው ውድ ስጦታና በብዛት በቁጥቋጦም ውስጥ በነበረው በእርሱ መልካም ሞገስ። እነዚህ ሁሉ በረከቶች በወንድሞቹ መካከል ገዥ በሆነው፤ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ።17በግርማው እንደ በኩር ኮርማ ነው፤ ዘንዶቹም የጎሽ ቀንዶች ናቸው። በእነርሱም ሕዝቦችን በምድር ዳርቻ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ይወጋል፤ እነርሱም የኤፍሬም አሥር ሺዎቹ ናቸው።18ስለ ዛብሎንም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ዛብሎን ሆይ፥ ወደ ውጭ በመውጣትህ፤ አንተም ይሳኮር በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ። 19እነርሱም አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ። እነርሱም ከባሕሮች በአሸዋ ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ያወጡበታል።20ስለ ጋድም ሙሴ እንዲህ አለ፦ የጋድን ግዛት የሚያሰፋ የተባረከ ይሁን! ክንድንና ራስን በመገነጣጠል፤ ጋድ እንደ አንበሳ በዚያ ይኖራል።21ለአለቃን ድርሻ ሆኖ የተጠበቀለትን ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ። ከሕዝብ አለቆች ጋር መጣ። በእስራኤል ላይ የወሰነውን የእግዚአብሔርን ሥርዓትንና ፍርዱን ፈጸመ።22ስለ ዳንም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ዳን ከባሳን ዘሎ የሚወጣ፤ የአንበሳ ደቦል ነው።23ስለ ንፍታሌምም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም በእግዚአብሔር ሞገስ ረክቶአል፤ በበረከቱም ተሞልቶአል፤ ባሕሩንና የደቡብን ምድር ይወርሳል።24ስለ አሴርም ሙሴ እንዲህ አለ፦ አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ይሁን፤ በወንሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ። 25በዘመንህና ደህንነትህ ሁሉ የደጃፍህ መቀርቀሪያ ብረትና ናስ ይሁን፤ ኃይልህም በዘመንህ ሁሉ ይኖራል።26አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ በግርማው በደመናትም የሚገሠግሥ፤ እንደ ይሽሩን አምላክ ያለ ማንም የለም።27ዘላለማዊ አምላክ መኖርያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከበታችህ ናቸው፤ እርሱን አጥፋው! በማለት፤ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።28ስለዚህ እስራኤል በሰላም ይሆራል።። የሰማያት ጠል በሚወርድበት፤ እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር የያዕቆብን ምንጭ የሚነካው የለም።29እስራኤል ሆይ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፤ እንዳንተ ያለ ማን ነው? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፤ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ ተሸብራው በፍርሃት፤ ወደ አንተ ይመጣሉ። አንተም ከፍታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።
1ሙሴ ከሞዓብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ ወደ ናባው ተራራ ሄደ። በዚያም እግዚአብሔር ከገለዓድ እስከ ዳን ያለውን ምድሪቱን ሁሉ፤ 2ንፍታሌምን ሁሉ፥የኤፍሬምንና የምናሴን ግዛት እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ አሳየው፤ 3ኔጌብንና የዘንባባ ከተማ ከሆነችው ከኢያሪኮ ሸለቆ እስከ ዞዓር ያለውን ምድር ሁሉ አሳየው።4ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለአብርሃም፥ ለይስሐንና ለያዕቆብ ለአባቶቻችሁ እሰጣለሁ ብዬ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው ምድር፥ በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም አለው። 5እግዚአብሔር እንደተናገረው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞዓብ ምድር ሞተ። 6በሞዓብ ምድር በቤተ ፌጎር ፊት ለፊት ባለው ሸለቆ እግዚአብሔር ቀበረው፤ ይሁን እንጂ መቃብሩ የት እንደ ሆን እስከ ዛሬ ማንም አያውቅም።7ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሃያ ዓመት ነበር፤ ሆኖም ዐይኑ አልፈዘዘም፤ ጉልበቱም አልደከመም። 8የልቅሶውና የሐዘኑ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ እስራኤላውያን በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን አለቀሱለት።9ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ አደመጡት፤ እግዚአብሔር ሙሴን አዞት የነበረውንም ሁሉ አደረገ።10እግዚብብሔር ፊት ለፊት ያወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል አልተነሣም። 11እግዚአብሔር ልኮት እነዚያን ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆች ሁሉ በግብፅ በፈርዖን በሹማምንቱና በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንዲያደርግ የላከውን ያደረገ ማንም ሰው አልነበረም። 12ሙሴ በእስራኤል ሁሉ ፊት ያሳየውን ታላቅ ኃይል ያሳየ ወይም ያደረገውን አስደናቂ ተግባር የፈጸመ ማንም ነቢይ የለም።
1እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴ ዋና ረዳት የሆነውን የነዌ ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2አገልጋዬ ሙሴ ሞቶአል። ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ። 3የእግራችሁ ጫማ የሚረግጥውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።ለሙሴም ተስፋ እንደ ሰጠሁት ሰጥቻችኋለሁ።4ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ፤ የኪጢያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻእሁ ይሆናል። 5በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም ሊቋቋምህ አይችልም። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ። አልጥልህም አልትውህም።6ለአባቶቻቸው፦እሰጣችኋለሁ ብዬ ተስፋ የሰጠ'ኋችሁውን ምድር ይህ ሕዝብ እንዲወርስ ታደርጋለህና ጽና አይዞህ። 7ስለዚህም ጽና እጅግ በርታ። አገልጋዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግን ሁሉ ትጠብቀው ዘንድ ተጠንቀቅ። በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አትበል።8ስለዚህ ሕግ መጽሐፍ ሁልጊዜ ተናገር። የተጻፈበትንም ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ በቀንና በሌሊትም አሰላስለው። የዚያን ጊዜም የተከናወነልህና የተሳከልህ ትሆናለህ። 9በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና፦ "ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ ተስፋ አትቁረጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?"10ኢያሱም የሕዝቡን አለቆች እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ 11"በሰፈሩ መካከል እለፉ፤ ሕዝቡንም፦ ለራሳችሁ ስንቃችሁን አዘጋጁ ብላችሁ እዘዙአቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲትወርሱ ወደሚሰጣችሁ ምድር በሦስት ቀናት ውስጥ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ትወርሳላችሁ።12ኢያሱም የሮቤልን ልጆች የጋድንም ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ 13የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛቸውን ቃል አስቡ፦አምላካችሁ እግዚአብሔር እረፍት ይሰጣችኋል፤ይህንንም ምድር ይሰጣችኋል።14ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጣሉ። ነገር ግን ተዋጊ የሆኑ ሰዎቻችሁ እግዚአብሔር ለእናንተ እንደሰጣችሁ 15ወንድሞቻችሁን እረፍት እስኪሰጥ ድረስ ከወንድሞቻችሁ ፊት በመሆን እነርሱንም ለመርዳት ይሄዳሉ ። እነርሱም ደግሞ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር ይወርሳሉ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ብዮርዳኖሴ ማዶ በፀሐይ መውጫ ወደሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ትመለሳላችሁ፤ ትወርሳላችሁም።16እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሰለት፦ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን። 17ለሙሴ እንደ ታዘዝን ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን። ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ እግዚአብሔር አምላክህ ብቻ ከአንተጋር ይሁን። 18በትእዛዝህ ላይ የሚያምፅና ቃልህን የማይታዘዝ ማንም ቢሆን ይገደል። ብቻ ጽና፥ በርታ።
1የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ "ሄዳችሁ ምድሪቱን፥ በተለይም ኢያሪኮን ሰልሉ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰዎች በስውር ላከ። እነርሱም ሄደው ረዓብ ወደምትባል ሴተኛ አዳሪ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። 2ለኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ የእስራኤል ሰዎች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ ገብተዋል ብለው ነገሩት። 3የኢያሪኮም ንጉሥ፡-አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ ወደ አንቺ የመጡትንና ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ መልእክት ላከ።4ነገር ግን ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሽሸገቻቸው። እርስዋም፦አዎን ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ ሆኑ አላወቅሁም፤ 5የከተማውም በር የሚዘጋበት ጊዜ ላይ ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፤ፈጥናችሁ ከተከተላችሁ ምናልባት ልትይዙአቸው ትችላላችሁ አለች።6እርስዋ ግን ወደ ሰገንቱ አውጥታቸው፤ በዚያም በጣሪያ ውስጥ ባዘጋጀችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሸጋቸው። 7ሰዎቹ ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው። አሳዳጆችም እንደወጡ በሮቹ ተቆለፉ።8ሰዎቹም ሳይተኙ ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች። 9ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦እግዚአብሔር ምድሪቱን አሳልፎ እንደሰጣችሁ እናንተንም መፍራት በላያችን እንደ ወደቀ፤ በምድሪቱም በሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደ ቀለጡ አውቃለሁ።10ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፤ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል። 11ይህን በሰማን ጊዜ ልባችን ቀለጠ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተንሣ ከዚያ ወዲያ ለማንም ነፍስ አልቀርለትም።12እሁንም እባካችሁ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንዳደረግሁ እናንተ 13ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼንና እኅቶቼንና ቤተ ሰቦቻቸውን ሁሉ እንድታድኑ፤ እንዲሁም ከሞት እንድታድኑን በእግዚአብሔር ማሉልኝ እውነተኛ ምልክትም ስጡኝ።14ሰዎቹ፦ "ይህን ነገራችንን ባትገልጪ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ እስከሞት እንኳ ይሆናል፤ እግዚአብሔርም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ምሕረትን እናደርጋለን እንዲሁም ታማኝ ሆነን እንገኛለን፤" አሉአት።15ቤትዋም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ስለነበረ በመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው። 16እርስዋም፦አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ ኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለቻቸው። 17ሰዎቹም አሉአት፦ይህን የምንልሽን ካላደረግሽ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን።18እነሆ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ክር እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው ፤አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የእባትሽንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ቤት ሰብስቢ። 19ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ሁሉ ደሙ በራሱ ላይ ይሆንበታል፤ እኛም ንጹሐን እንሆናለን። ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን አንድ ሰው ቢነካው ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል።20ነገር ግን ይህንን ጉዳያችንን ብትገልጪ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን። 21እርስዋም፦ እንደቃላችሁ ይሁን አለች። ሰደደቻቸውም እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ክር በመስኮቱ በኩል አንጠለጠልችው።22እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ እዚያ ለሦስት ቀናት ቆዩ። በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም።23ሁለቱም ሰዎች ተመለሱ፤ ከተራራውም ወርደው ተሻገሩ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደረሰባቸውንም ሁሉ ነገሩት። 24ለኢያሱም እንዲህ አሉት፦ በእውነት እግዚአብሔር ይህን አገር ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤ በአገሩም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከእኛ የተነሣ እየቀለጡ አሉት።
1ኢያሱም በጠዋት ተነሣ፥ እነርሱም ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፤ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሳይሻገሩም በዚም ሰፈሩ።2ከሦስት ቀንም በኋላ አለቆች በሰፈሩ መካከል ሄዱ። 3ሕዝቡንም እንዲህ ብለው አዘዙ፦የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ መከትል አለባችሁ። 4በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን። በዚህ መንገድ በከዚሄ በፊት አልሄዳችሁበትምና የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ።5ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ እግዚእአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ነገ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱ። 6ከዚያም ኢያሱ ካህናቱን እንዲህ አለ፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ። ስለዚህ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት አለፉ።7እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በዚህ ቀን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከእንተ ጋር መሆኔን ያውቃሉ።8አንተም የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት፦ በዮርዳኖስ ውኃ ዳር ስትደርሱ በዮርዳኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ ታዛቸዋለህ።9ከዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አለ፦ ወደዚህ ቀርባችሁ የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ቃል ስሙ አለ። 10ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነና እርሱም ኤዊያዊውንም ፈርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ከፊታችሁ ፈጽሞ እንደሚያወጣ በዚህ ታውቃላችሁ። 11እነሆ የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ በዮርዳኖስ ውስጥ ያልፋል።12አሁምን ከእስራኤል ነገዶች አሥራ ሁለት ሰዎችን ምረጡ፤ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን። 13እንዲህም ይሆናል የምድርም ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት የእግራቸው ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ሲቆም የዮርዳኖስም ውኃ ይቆማል፤ ከላይ የሚፈሰው ውኃ ሳይቀር መፍሰሱን ያቆማል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።14ሕዝቡም ዮርዳኖስን ለመሻገር ከድንኳናቸው በወጡ ጊዜ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ቀድመው ሄዱ። 15የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ወደ ዮርዳኖስ እንደመጡ፤ እግራቸውም የውኃውን ጫፍ በጠለቁ ጊዜ (በመከር ወራት ሁሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ እንደሚፈስ) 16ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ እንደ ክምርም ሆነ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ አጠገብ ተሻገሩ።17የእስራኤልም ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው አስኪሻሩ ድረስ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካክል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር።
1ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ 2"ከሕዝቡ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎች ምረጥ። 3እንዲህ ብለህ ትእዛዝ ስጣቸው፦"በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ አሥራ ሁለት ድንጋዮችን አንሡ፤ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው።"4ከዚያም ኢያሱ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ አንድ ሰው የመረጣቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ጠራቸው። 5ኢያሱም አላቸው፦"በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል፤ እያንዳንዱም ሰው በጫንቃው ከአንዳንድ ድንጋይ ጋር በእስራኤል ልጆች ሁሉ ነገድ ቁጥር አሥራ ሁለት ድንጋዮችን ተሸክመው ይለፉ።6፤ልጆቻችሁም በሚመጣው ዘመን፦ እነዚህ ድንጋዮች ለእናንተ ምን ትርጉም አላቸው? ብለው በሚጠይቁበት ጊዜ ይህ በመካከላችሁ ምልክት ይሆናል። 7በዚያን ጊዜ እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትመልሳላችሁ፦ "በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት የዮርዳኖስ ውኃ ስለተቋረጠ ነው። በተሻገሩም ጊዜ የዮርዳኖስ ውኃ ቆመ፤ እነዚህም ድንጋዮች ለእስራኤል ልጆች ለዘላለም መታሰቢያ ይሆናሉ።"8የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቁጥር ከዮርዳኖስ መካከል እንደ እስራኤል ነገድ ቁጥር አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ። በዚያም በሚያድሩበት ስፍራ አኖሩአቸው። 9ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎችን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ተከለ። እስከ ዛሬም ድረስ መታሰቢያ ሆነው በዚያ አሉ።10ሙሴም ኢያሱን እንዳዘዘው ሁሉ እግዚአብሔር ኢያሱን ለሕዝቡ እንዲነገር ያዘዘው ነገር ሁሉ እስክፈጸም ድረስ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበር። ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ። 11ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው መሻገራቸውን በጨረሱ ጊዜ የእግዚአብሔር ታቦትና ካህናቱ በሕዝቡ ፊት ተሻገሩ።12ሙሴም እንዳዘዘቸው የሮቤል ልጆች፥ የጋድም ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእስራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ። 13አርባ ሺህ ያህል ሰዎች ጋሻና ጦራቸውን ይዘው ለጦርነት በእግዚእብሔር ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ። 14በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው። ሕዝቡም ሙሴን እንዳከበሩት በዕድሜው ሁሉ አከበሩት።15እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 16"የምስክርን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት ከዮርዳኖስ እንዲወጡ እዘዝ።"17ኢያሱም ካህናቱን፦ ከዮርዳኖስ ውጡ ብሎ አዘዛቸው። 18የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜና የካህናቱም እግር ጫማ ደረቅ መሬት መርገጥ በጀመረ ጊዜ የዮርዳኖስ ውኃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፤ ቀድሞም ከአራት ቀናት በፊት እንደ ነበረ በዳሩርቻው ሁሉ መፍሰስ ጀመረ።19ሕዝቡም በመጀመሪያው ወር በአሥረኛው ቀን ከዮርዳኖስ ወጡ። ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ በኩል በጌልገላ ሰፈሩ። 20ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን አሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አቆማቸው። 21ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ "በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ አባቶቻቸውን፦ እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው? ብለው ሲጠይቁ፥22ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ። 23እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ። 24የእግዚአብሔርም እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ለዘላለሙ እንድታከብሩ ነው።
1በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በታላቁም ባሕር አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነገሥታት ሁሉ፥ የእስራኤል ሕዝብ እስኪሻገሩ ድረስ የዮርዳኖስን ውኃ እግዚአብሔር እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ ልባቸው ቀለጠ፤ ከእስራኤልም ሕዝብ የተነሣ የአንድም ሕዝብ ነፍስ አልቀረላቸውም።2በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፦"የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርተህ የእስራኤልን ሕዝብ እንደገና ግርዛቸው።" 3ኢያሱም የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርቶ ግብት ሃራሎት (ትርጉሙም የግርዛት ኮረብታ) በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ወንዶች ሁሉ ገረዛቸው።4ኢያሱም የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ከግብፅ የወጡት ወንዶች ሁሉ ጦረኞችን ሁሉ ጭምር ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ። 5የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ነገር ግን ከግብፅ በወጡበት መንገድ በምድረ በዳ የተወለዱት ሕዝብ ሁሉ አልተገረዙም ነበር።6ከግብፅ የወጡ የእስራኤል ሕዝብና ጦረኞች ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው እስኪሞቱ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይጓዙ ነበር ። እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንደማያሳያቸው ማለላቸው። 7እግዚአብሔር በእነርሱ ፋንታ ያስነሳቸው በመንገድ ሳሉ ሳይገረዙ የነበሩ ኢያሱም ገረዛቸው እነዚህን ልጆቻቸው ነበሩ።8ሕዝቡም ሁሉ በተገዙ ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ በየስፍራቸው ነበሩ። 9እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ይጠራል።10የእስራኤልም ሕዝብ በጌልገላ ሰፈሩ። ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ። 11ከፋሲካውም በዓል ቀን በኋላ በዚያው ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ቂጣና ቆሎ በሉ።.12ከምድሪቱም ፍሬ ከበሉበት ቀን በኋላ መና ተቋረጠ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ለእስራኤል ልጆች መና አልነበራቸውም፤ ነገር ግን በዚያ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።13ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ አጠገብ በነበረ ጊዜ ዓይኖቹን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው።14እርሱም፦ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ እዚህ መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ ጌታዬ ለአገልጋዩ የሚነግረው ምንድን ነው? አለው። 15የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፦ አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።
1ከእስራኤልም ሠራዊት የተነሣ የኢያሪኮ በሮች መጽሞ ተዘግተው ነበር። ወደ እርስዋም የሚገባና የሚወጣ ማንም አልነበረም። 2እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን የሠለጠኑ ወታደሮችዋንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁ።3ሠራዊቶኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ መዞር አለባቸው። ይህንንም ለስድስት ቀናት አድርጉት። 4ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።5ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ የመለከቱንም ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኽ፥ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል። እያንዳንዱ ወታደር ወደፊት በመሄድ ማጥቃት አለባቸው።6ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አላቸው። 7ሕዝቡንም፦ ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ሠራዊቱም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አለ።8ኢያሱም ለሕዝቡ እንደተናገረው ሰባቱ ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይዘው ወደፊት እያለፉ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ከኋቸው ይከተላቸው ነበር። 9ሠራዊቱም በካህናቱ ፊት ቀንደ መለከታቸውን እየነፉ ይሄዱ ነበር፤ ከዚያም ከቃል ኪዳን ታቦት ኋላ ደጀን ጦር ይሄድ ነበር፤እንዲሁም ካህናቱ ቀንደ መለከታቸውን ያለማቋረጥ ይነፉ ነበር።10ኢያሱ ግን ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ እኔ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ፥ ከአፋችሁም ድምፅ አይውጣ፤ በዚያን ጊዜ ብቻ ትጮኻላችሁ። 11ስለዚህ እግዚአብሔር የዚያን ቀን የቃል ኪዳን ታቦት አንድ ጊዜ ከተማይቱን እንዲዞር አደረገው፤ ከዚያም ወደ ማደሪያቸው ገቡ፤ ሌሊቱንም እዚያው አደሩ።12ከዚያም ኢያሱ ማለዳ ተነሣ ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸከሙ። 13ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በቀስታ እየሄዱ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። ሠራዊቱም በፊታቸው ይሄዱ ነበር። የደጀን ጦር ከእግዚአብሔር ታቦት ኋላ በሚድበት ጊዜ የቀንደ መለከት ድምፅ ያልማቋረጥ ይሰማ ነበር። 14በሁለተኛውም ቀን ከተማይቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀንም እንዲሁ አደረጉ።15በሰባተኛውም ቀን ሲነጋ ማልደው ተነሡ፥ ከዚህ በፊት በተለመደው ሁኔታ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ፤ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ የዞሩት በዚያ ቀን ነው። 16በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ሲነፉ ኢያሱ ሕዝቡን አዘዘ፦ እግዚአብሔር ከተማይቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።17ከተማይቱና በእርስዋም ያለው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየና ለጥፋት ይሆናሉ። የላክናቸውን መልክተኞች ስለ ሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋ ረዓብ ብቻና ከእርስዋም ጋር በቤትዋ ውስጥ ያሉት ሁሉ በሕይወት ይኖራሉ። 18እናንተ ግን ለጥፋት የተለዩ ነገሮችን ከለያችሁት በኋላ አንዳች እንዳትወስዱ ራሳችሁን ጠብቁ። ለጥፋትም ከሆነው ነገር አንዳች የወሰዳችሁ እንደ ሆነ የእስራኤልን ሰፈር እንዲጠፋ ታደርጉታላችሁ፥ ችግርም ታመጣላችህ። 19ብር፥ ወርቅ፥ ናስና ከብረት የተሠሩ ዕቃዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን። ወደ እግዚአብሔርም ግምጃ ቤት ይግባ።20ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ። ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታልቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ሲወድቅ፤ ሕዝቡም እያንዳንዱ አቅንቶ ወደ ፊቱ ወደ ከተማይቱ ወጣ፤ ከተማይቱንም ያዙ። 21በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም ፥በጉንና አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።22ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉትን ሁለቱን ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ ወደ ሴተኛ አዳሪዋ ቤት ግቡ ከዚያም ሴቲቱንና ከእርስዋ ጋር ያሉትን ሁሉ እንደ ማላችሁላት አውጡ።23ሰላዮቹም ወጣቶች ሄደው ረዓብን አውጧአት፤ አባትዋንና እናትዋን፥ ወንድሞችዋንም፥ አብሯት የነበሩ ቤተ ዘምዶችዋንም ሁሉ አወጡ። ከእስራኤልም ሰፈር ውጭ ወዳለው ስፍራ አመጦአቸው። 24ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። ብሩ፥ ወርቅ፥የናሱና የብረት ዕቃዎች ብቻ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አስቀመጡአቸው።25ነገር ግን ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውን መልክተኞች የሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋን ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተ ሰብ፥አብሯት የነበሩትንም ሁሉ ኢያሱ በሕይወት እንዲሆሩ ፈቀደላቸው። እርስዋም ኢያሱ ኢያሪኮን እንዲሰልሉ የላካቸውን ሰዎች ስለሸሸገች በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ትኖራለች።26በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ ይህችን ኢያሪኮ ከተማን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን። መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይሙት፥ እርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይሙት፥ ብሎ ማለ። 27እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበር፤ ዝናውም በምድር ሁሉ ላይ ወጣ።
1የእስራኤል ሕዝብ ግን እንዲጠፉ ከተለዩ ነገሮች በመውሰድ ታማኝነትን አጎደሉ። ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እንዲጠፉ ከተለዩት ነገሮች ወስደ፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ።2ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤት አዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ከኢያሪኮ ሰዎችን ላከ። እርሱም፦ ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ ብሎ ተናገራቸው። ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ። 3እነርሱም ወደ ኢያሱ ተመልሰው፡- ሕዝብን ሁሉ ወደ ጋይ አትላክ። ጋይን እንዲመቱ ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ይላክ። የጋይ ሰዎች በቁጥር ጥቂቶች ስለሆኑ ሕዝብ ሁሉ በውጊያ እንዲደክም አታድርግ።4ከሠራዊቱ ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ወደዚያ ወጡ፤ እነርሱም ከጋይ ሰዎች ፊት ሸሹ። 5የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያህል ሰዎችን መቱ፥ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው፤ በቁልቁለቱም መቱአቸው። የሕዝቡም ልብ ፈራ፤ ድፍረትንም አጡ።6ኢያሱም ልብሱን ቀደደ። እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድርስ በግምባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ። 7ኢያሱም አለ፦ ወዮ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ ይህን ሕዝብ ቀድሞኑ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? እንዲያጠፉን በአሞራውያን እጅ ለምን አሳልፈህ ሰጠሃን? ከዚህ የተለየ ምርጫ ማድረግ በቻልንና በዮርዳኖስም ማዶ በተመቀመጥን ይሻለን ነበር።8ጌታ ሆይ የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት ከሸሹ በኋላ ምን ማለት እችላለሁ? 9ይህንን ከነዓናውያንና በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ይሰማሉ። እነርሱም ይከብቡናል፥ በምድር ያሉትም ሕዝብ ስማችን እንዲረሳ ያደርጋሉ። ለታላቁ ስምህስ የምታደርገው ምንድን ነው?10እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ተነስተህ ቁም! ለምን በግምባርህ ተደፍተሃል? 11እስራኤል ኃጢአትን አድርጎአል። ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል። ለጥፋት ከተለዩት ነገሮችን ሰርቀዋል፤ ሰርቀው የወሰዱትንም ኃጢአት በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት። 12በዚህም ምክንያት የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት መቆም አይችሉም። ራሳቸው ለጥፋት የተለዩ ሆነው በጠላቶቻቸው ፊት ሸሹ። በመካከላችሁ እስካሁን ያለውን መወገድ ያለበትን እርም ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ ከዚህ በኃላ ከእናንተ ጋር አልሆንም።13ተነሣና ሕዝቡን ቀድስልኝ፤ እንዲህም በላቸው፦ራሳችሁን ለነገ ለእግዚአብሔር ቀድሱ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፤ እስራኤል ሆይ ፥ሊጠፉ የሚገቡ ነገሮች እስካሁን በመካከላችሁ አለ። መጥፋት ያልባቸው ነገሮች ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።14ነገም ራሳችሁን በየነገዳችሁ ታቀርባላችሁ፤ እግዚአብሔርም በዕጣ የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ቤተ ሰብ አንድ በአንድ ይቀርባል። 15ለጥፋትም የተለየ ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን በማፍረሱና በእስራኤልም ላይ ክፉ ነገር እንዲመጣ በማድረጉ እርሱና ለእርሱም ያለው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠላል።16ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው አቀረበ፤ የይሁዳም ነገድ ተለየ። 17የይሁዳንም ወገን አቀረበ፥የዛራም ወገን ለየ። የዛራንም ወገን እያንዳንዱን አቀረበ፤ ዘንበሪም ተለየ። 18የቤተ ሰቡንም እያንዳንዱን አቀረበ፤ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ።19ከዚያ ኢያሱ አካንን አለው፦ ልጄ ሆይ፥ በእስራኤልም አምላክ ፊት እውነቱን ተናገር፥ ለእርሱም ተናዘዝ። ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ ከእኔም አትሸሽግ። 20አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእውነት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ። ያደረግሁትም ይህንን ነው፦21በዘረፋ መካከል አንድ የሚያምር የባቢሎን ኮት፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም። እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው አለው።22ኢያሱም መልእክተኞችን ሰደደ፥ ወደ ድንኳኑም ሮጡ፤ ዕቃዎቹም ነበሩ። በድንኳኑም ውስጥ ተሸሽጎ አገኙት ብሩም ከበታች ነበረ። 23ከድንኳኑም መካከል ዕቃዎቹን ወስደው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ አመጡት። በእግዚአብሔርም ፊት አኖሩት።24ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ኮቱንም፥ ወርቁንም፥ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያውዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው።25ኢያሱም እንዲህ አለው፦ ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔርም ዛሬ ያስጨንቅሃል። እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ሁሉንም በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው። 26በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ሆነ። እግዚአብሔርም ከቁጣው ትኩሳት ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ነው።
1እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራ አትደንግጥ። ጦረኞችንም ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ። ተመልከት፥ የጋይን ንጉሥ፥ ሕዝቡን፥ ከተማውንና ምድሩን በእጅህ ሰጥቼሃለሁ። 2በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ ምርኮውንና ከብቱን ግን ለራሳችሁ ትወስዳላችሁ። ከከተማይቱም በስተ ኋላ ድብቅ ጦር አዘጋዝጅ አለው።3ኢያሱም ተነሣና ጦረኞቹንም ሁሉ ወደ ጋይ ወሰዳቸው። ኢያሱም ጽኑዓን ኃያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መርጦ በሌሊትም ሰደዳቸው። 4እንዲህም ብሎ አዘዘቸው፦ እነሆ፥ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ። ከከተማይቱ በጣም ርቃችሁ አትሂዱ፤ነገር ግን ሁላችሁም ተዘጋጁ።5እኔና ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማይቱ እንቀርባለን። እንደ በፊቱ ሊያጠቁን በሚመጡበት ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን። 6አስቀድመን እንደ ሸሸን፥ የምንሸሸ ይመስላቸዋል፥ ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል። እንዲህም ይላሉ፦ባለፈው እንዳደረጉት ከፊታችን እየሸሹ ነው። እኛም ከእነርሱ እንሸሻለን። 7እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ መጥታችሁ ከተማዋን ትይዛላችሁ። እግዚአብሔር አምላካችሁም እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል።8ከተማይቱንም በያዛችኋት ጊዜ በእሳት አቃጥሉአት። በእግዚአብሔርም ቃል እንደታዘዛሁ ታደርጋላችሁ። እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ። 9ኢያሱም ሰደዳቸው፤ እነርሱም ወደሚደበቁበት ስፍራ ሄደው፥ በጋይና በቤቴል መካከልም ከጋይ በስተምዕራብ ተደበቁ። ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።10ኢያሱም ማልዶ ተነሣና ሕዝቡን አሰለፈ፤እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች የጋይን ሕዝብ አጠቁ ። 11ከእርሱም ጋር የነበሩ ጦረኞች ሁሉ ሄደው፥ ወደ ከተማይቱ ደረሱ። ወደ ከተማይቱ አጠገብ መጡና በሰሜን በኩል በጋይ ሰፈሩ። በእነርሱና በጋይ መካከል ሸለቆ ነበረ። 12አምስት ሺህ ያህል ሰዎችንም ወስዶ በቤቴልና በጋይ መካከል በከተማይቱም በምዕራብ በኩል በድብቅ አስቀመጣቸው።13በከተማይቱ የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ፤ በከተማይቱ ሰሜን በኩል ዋና ጦርና በከተማይቱ ምዕራብ በኩል ደጀን ጦር ጠባቂዎችን አኖሩ። ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው አደረ። 14የጋይም ንጉሥ ባየ ጊዜ ይህ ስለታወቀ፥እርሱና ሠራዊቱ በማለዳ ተነስተው እስራኤልን ለማጥቃት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ወዳለው ሰፍራ ቸኮሉ። ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር ለማጥቃት እንዳለ አያውቅም ነበር።15ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ራሳቸው በፊታቸው ድል የተነሡ መስለው ወደ ምድረ በዳው መንገድ ሸሹ። 16በከተማይቱም የነበሩ ሰዎች ሁሉ በአንድነት ከኋላቸው እንዲሄዱ ተጠሩ፤ ኢያሱንም አሳደዱት፥ ከከተማይቱም ርቀው ወጡ። 17በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም። ከተማይቱንም ክፍት አድርገው፥ እስራኤልን አሳደዱ።18እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእጅህ ያለውን ጦር በጋይ አነጣጥር፤ ጋይንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ። ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ። 19የተደበቁትም ሠራዊት ፈጥነው ከስፍራቸው ወጥተው ኢያሱም እጁን እንደ ዘረጋ ሮጡ። ወደ ከተማይቱም ሮጡ፤ ገብተውም ያዙአት። ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት።20የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ተመለከቱ። ከከተማይቱ ወደ ሰማይ የሚወጣውን ጢስ አዩ፤ ወዲህ ወይም ወዲያም መንገድ ማምለጥ አልቻሉም። ወደ ምድረ በዳ ሸሽተው የነበሩ የእስራኤላውያን ጦር ሠራዊት ያሳድዱአቸው የነበሩትን ለመግጠም ተመለሱ። 21ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ድብቅ ጦር ከተማይቱን እንደ ያዙ ወደ ላይ ከሚወጣ ጢስ ጋር ባዩ ጊዜ፥ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉ።22ሌሎቹም ወደ ከተማይቱ ሄደው የነበሩ የእስራኤል ሠራዊት ለማጥቃት ወጡ። ስለዚህም የጋይ ሰዎች በእስራኤል ሠራዊት መካከል ሌሎቹ በዚህ በኩልና ሌሎቹ በዚያ በኩል ተያዙ። እስራኤልም የጋይን ሰዎች አጠቁአቸው፤ አንዳቸውም አልተረፉም፤ አላመለጡምም። 23በሕይወት የያዙትን የጋይንም ንጉሥ ማርከው ወደ ኢያሱ አመጡት።24እንዲህም ሆነ፤ የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ አጠገብ እስራኤልን ሲያሳድዱ በነበሩበት ቦታ ሁሉም የመጨረሻ በሰይፍ ስለት እስኪ ወድቁ ድረስ ጨርሰው ከገደሉአቸው በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ። በሰይፍም ስለት መቱአቸው። 25በዚያም ቀን በሰይፍ ስለት የወደቁት ወንዶችና ሴቶች የጋይ ሰዎች ሁሉ አሥራ ሁለት ሺህ ነበሩ። 26ኢያሱም የጋይን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ ጦር የዘረጋባትን እጁን አላጠፈም።27እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ለራሳቸው ወሰዱ። 28ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ ለዘላለም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆን አደረጋት። እስከ ዛሬም ድረስ ባዶ ስፍራ ሆነች።29የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው። ኢያሱም ፀሐይ በገባች ጊዜ የንጉሡን አስክሬን ከዛፍ አወርደው፥ በከተማይቱ በር አደባባይ እንዲጥሉት አዘዘ። በላዩም ታላቅ የድንጋይ ክምር አደረጉት። እስከ ዛሬ ድረስም ይህ የድንጋይ ክምር አለ።30ከዚያም ኢያሱ በጌበል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ። 31የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዳዘዘ፦ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደተጻፈው፥ መሠዊያው ካልተወቀረ ድንጋይና ብረት ካልነካው ነበረ። በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዉ። 32የእስራኤልም ሰዎች ፊት በድንጋዮቹ ላይ የሙሴን ሕግ ቅጂ ጻፈባቸው።33እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ በመጻተኞችና በአገሩ ልጆች ፥እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ሆነው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በካህናትና በሌዋውያን ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘ፥የእስራኤልን ሕዝብ አስቀድሞ ባረኩ።34ከዚህም በኋላ ኢያሱ በሕጉ መጽሐፍ እንደ ተጻፉ የሕጉን ቃሎች ሁሉ በረከቱንና እርግማኑን አነበብ። 35ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ፊት በሴቶቹም፥ በሕፃናቱም፥ በመካከላቸውም በሚኖሩት መጻተኞች ፊት ሙሴ ካዘዘው አንዲት ቃል ሳያስቀር ሁሉን አነበበ ።
1ከዚያም በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማውና በቆላማው በታላቁ ባሕር ዳርቻ በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥታት ሁሉ፥ ኬጢያዊ አሞራዊም ከነዓናዊም ፌርዛዊም ኤዊያዊም ኢያቡሳዊም 2ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ።3የገባዖን ሰዎችም ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥ 4እነርሱ ደግሞ የማታለል ዕቅድ አደረጉ። ራሳችውን እንደ መልእክተኛ አድርገው ቀረቡ። ያረጀና የተቀደደ ጆኒያ ወስደው በአህዮቻቸውም ላይ ጫኑ። ደግሞም ያረጀ፥የተቀደደና የተሰፋ አሮጌ ወይን ጠጅ አቁማዳ ጫኑ። 5ያረጀ የተሰፋም ጫማ በእግራቸው አደረጉ፤ አሮጌምና የተቀደድ ልብስም ለበሱ። ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ።6ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሕዝብ፦በጣም ሩቅ አገር ከሆነ ተጉዘን የመጠን ነን፥ ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ አሉ። 7የእስራኤልም ሰዎች ኤዊያውያንን፦ ምናልባት በመካከላችን የምትቀመጡ ትሆናላችሁ። እንዴትስ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን? አሉአቸው። 8እነርሱም እንዲህ አሉት፦ እኛ የእናንተ አገልጋዮች ነን። ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?9እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ አሉት፦ እኛ አገልጋዮችህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር እዚህ መጥተናል። ዝናውንም በግብፅም ያደረገውን ሁሉ፥ 10በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን በንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል።11ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፦ ለጉዞአችሁም ስንቅ በእጃችሁ ያዙ። ልትገናኙአቸውም ሂዱና እንዲህ በሉአቸው፦ እኛ አገልጋዮቻችሁ ነን፤ ከእኛም ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ። 12ወደ እናንተ ለመምጣት በተነሣንበት ቀን ይህን እንጀራ ትኩስን ለስንቅ ከቤታችን የወሰደነው ነው። ነገር ግን ተመልከቱ፥ አሁንም ደረቅና የሻግብተ ነው። 13እነዚህም የጠጅ አቁማዳዎች ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ እነሆም፥ ተቀድደዋል። ጉዞአችንም እጅግ ሩቅ ስለ ነበረ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል።14እስራኤላውያንም ከስንቃቸው ወሰዱ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔርም ምክርን አልጠይቁም ነበር። 15ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ስምምነት አደረገ፥ በሕይወት እንዲተዋቸውም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። የማኅበሩም አለቆች ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ።16የእስራኤላውያንም ከገባዖን ሰዎች ጋር ቃል ኪዳኑን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ፥ ሰዎቹ እዚያው አጠገባቸው የሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ዐወቁ። 17ከዚያም እስራኤላውያን ተዘጋጅተው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ። የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ክፈራ፥ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ናቸው።18የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን አድርገው ስለነበረ እስራኤላውያንም ጥቃት አልደረሱባቸውም። የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጉረመረሙ፥ 19ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ አሉ፦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን ስለገባንላቸው አሁን ጉዳት ልናደርስባቸው አንችልም፥20የምናደርግላቸው ነገር ቢኖር ይህ ነው፦ የገባንላቸውን የቃል ኪዳን ማሐላ ብናፈርስ ቁጣ እንዳይደርስብን በሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ ነው። የሕዝቡም አለቆች ለሕዝባቸው እንዲህ አሉ፦ በሕይወት ይኑሩ። 21ስለዚህም የእስራኤል አለቆች ስለእነርሱ እንደ ተናገሩት ገባዖናውያን ለእስራኤላውያን ሁሉ እንጨት ሰባሪና ውኃ ቀጂ ሆኑ።22ከዚያም ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እዚሁ በመካከላችን እየኖራችሁ፥ ከእናንተ ሩቅ ስፍራ ነው የመጠነው፥ ብላችሁ ያታለላችሁን ለምንድን ነው? 23ስለዚህ በዚህ ምክንያት እናንተ የተረገማችሁ ናችሁ፥ አንዳንዶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ሁል ጊዜ እንጨት ሰባሪና ውኋ ቀጂ አገልጋዮች ትሆናላችሁ።24እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፥ እግዚአብሔር አምላክህ አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው፥ ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንደሚሰጣችሁና ነዋሪዎቿንም ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው በእርግጥ ለእኛ አገልጋዮችህ ተነግሮናል፥ ስለዚህ ከእናንተ የተነሣ ለሕይውታችን በመሥጋት ይህን አድርገናል። 25እነሆ አሁን በእጅህ ነን፥ መልካምና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።26ስለዚህ ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ከእስራኤል ሰዎች እጅ አዳናቸ እስራኤላውያንም አልገደሏቸውም። 27በዚያም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ሰባሪችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው።
1የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶነጼዴቅ ኢያሱ ጋይን ይዞ ፈጽሞ እንደ ደመሰሳት፤ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ ያደረገውን ሁሉ ሰማ። እንዲሁም የገባዖን ሰዎች ከእስራኤል ጋር እንዴት የሰላም ውል አድርገው በመካከላቸው መኖራቸውን ሰማ። 2የኢየሩሳሌም ሕዝብ ፈሩ፥ ምክንያቱም ገባዖን እንደ ነገሥታቱ ከተማ ሁሉ ታላቅ ከተማ ነች። ገባዖንም ከጋይ ይልቅ ትልቅና ሰዎቿም ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ።3ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፥ ወደ የኬብሮን ንገሥ ሆነም፥ ወደ የያርሙት ንጉሥ ጲርአም ፥ ወደ የለኪሶ ንጉሥ ያፈዓና ወደ የዔግሎን ንጉሥ ዳቤር ላከ። 4ወደዚህ መጥታችሁ አግዙኝ። ገባዖን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ስላደረጉ ገባዖንን እንምታ።5ከዚያም አምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለት የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥና የዔግሎን ንጉሥ ያላቸውን ሠራዊታቸውን ሁሉ አስተባብረው፥ ገባዖንን ወጓት።6የገባዖንም ሰዎች ወደ ኢያሱና ወደ ጌልገላ ሠራዊት መልእክት ላኩ። እንዲህም አሉ፦ ከአገልጋዮቻችሁ እጃችሁን አታውጡ ፍጠኑ። በፍጥነት መጥታችሁ አድኑን። በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ኃይላቸውን አስተባብረው እኛን ለማጥቃት ተሰልፈውብናልና እርዱን። እኛን ባሮችህን አትተወን ርዳን ፈጥነህ በመድረስም አድነን ብለው ላኩበት። 7ስለዚህ ኢያሱ እርሱና ተዋጊዎች ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ጨምሮ ከጌልገላ ወጣ።8እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራቸው። በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ ማንም ሊቋቋሙህ አይችልም።9ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሥ አድሮ ድንገት ደረሰባቸው። 10እግዚአብሔም የጠላትን ሠራዊት በእስራኤል ፊት ግራ አጋባቸው። እጅግ መታቸው። በገባዖንም ወደ ቤት ሖሮን በሚያስወጣው መንገድ እስከ ዓዜቅ መንገድ እስከ መቄዳም ድረስ ተከትሎአቸው አሳድዶ መታቸው።11ከቤት ሖሮን ወደ ዓዜቃ ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ላይ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሽሹበት ጊዜ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ ድንጋዮች ወረወረባቸው ሞቱም። በእስራኤል ሰዎች ሰይፍ ከሞቱት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋዮች የሞቱት የበለጡ ነበሩ።12ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል በአሞራውያን ላይ ድል በሰጠበት ዕለት ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ። ኢያሱም በእስራኤል ፊት እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ "ፀሐይ፥ በኤሎን ሸለቆ በገባዖን ላይ ይቁም።"13ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪ በቀል ድረስ፤ ፀሐይ ባለችበት ቆመች፥ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህም በያሻር መጽሐፍ ላይ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይ በሰማዩ መካከል ቆመች፥ ለሙሉ ቀን ያህል አልተንቀሳቀሰችም ነበር። 14እግዚአብሔር የሰውን ቃል እንደዚያ የሰማበት ዕለት ከዚያ በፊት ወይም ከዚያ በኋላ አልነበረም። እግዚእአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበር።15ኢያሱና መላው እስራኤል ወደ ጌልገላ ሰፈር ተመለሱ። 16በዚህ ጊዜ አምስቱ የአሞራውያን ገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ራሳቸውን ደብቀው ነበር። 17ኢያሱም አምስቱ ነገሥታት በመቄዳ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ሰማ፤18ኢያሱም እንዲህ አለ፦ ትልልቅ ድንጋዮች ወደ ዋሻው አፍ አንከባልሉ፤ወታደሮችንም እንዲጠብቁአቸው በዚያ አቁሙ። ቸልም አትበሉ። 19ጠላቶቻችሁን አሳዱአቸው፤ ከበስተ ኋላ ሆናችሁም ጥቃት አድርሱባቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ አድርጉአቸው።20ኢያሱና እስራኤል ልጆች ፈጽሞ እስኪያጠፉ ድረስ ከታላቅ ጭፍጨፋ ጋር ጨረሱ። የተረፉት ጥቂቶቹ ብቻ ወደ ተመሸጉት ከተሞቻቸው ደረሱ። 21ከዚያም ሠራዊቱ በሙሉ በደኅና ተመልሶ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ ተመለሰ። በእስራኤላውያንም ላይ አንድት ቃል ለመናገር ማንም ሰው የደፈረ አልነበረም።22ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ የዋሻውንም አፍ ክፈቱና ከዋሻው እነዚህን አምስቱን ነገሥታት አምጡልኝ። 23እነርሱም እንዳለው አደረጉ። እነዚህንም አምስቱን ነገሥታት፦ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፥ የኬብሮንን ንጉሥ፥ የያርሙትን ንጉሥ የለኪሶን ንጉሥና የዔግሎንን ንጉሥ አውጥተው አመጡለት።24እነዚህን ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባማጡበት ጊዜ፥ እርሱም እያንዳንዱን የእስራኤል ሰዎች ጠራቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት ሄደው የነበሩትን የጦር አዛዦችን እንዲህ አላቸው፦ እግሮቻችሁን በእነዚህ ነገሥታት አንገት ላይ አድርጉ። እነርሱም ወደ ፊት ቀርበው እግሮቻቸውን በነገሥታቱ አንገት ላይ አሳረፉ። 25ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ አትፍሩ፥ አትደንግጡም። በርቱ፥ ጽኑም። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምትዋጉበት ጊዜ በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲህ ያደርጋል።26ከዚያም ኢያሱ ነገሥታቱን መትቶ ገደላቸው። በአምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው። አስክሬናቸውም እስኪመሽ ድረስ ተሰቅለው ነበር። 27የፀሐይ መጥለቂያ በሆነ ጊዜ ኢያሱ ትእዛዝ ሰጠ፦ ከዚያም የነገሥታቱን አስክሬኖች ከዛፎቹ ላይ እንዲያወርዱ ቀድሞ ራሳቸውን ደብቀው ወደነበሩበት ዋሻ ውስጥ እንዲጥሉአቸው አዘዛቸው። በዋሻውም አፍ ላይ ትልልቅ ድንጋዮች አኖሩ። እነዚያ ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።28በዚህ መንገድ በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከንጉሥዋም ጭምር ሁሉንም በሰይፍ ገደለ። በሕይወት ያሉትንም ፍጥረት ሁሉ ምንም ሳያስቀር ፈጽሞ አጠፋቸው። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፥ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።29ኢያሱና እስራኤላውያን ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ። ወጓትም። 30እንደገናም ከልብና ጋር ጦርነት ገጠሙ። እግዚአብሔርም ከተማይቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱም በተከማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ። ሕይወት ያለውን ምንም አላስቀረም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ አደረገ።31ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከእርሱ ጋር ከልብና ወደ ለኪሶ አለፉ። በእርስዋም ሰፈሩ፤ ጦርነትም አደረጉ። 32እግዚአብሔርም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠው። ኢያሱም በሁለተኛው ቀን ያዛት። በልብና እንዳደርገው በሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ።33ከዚያ የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት መጣ። ኢያሱ ግን አንድ እንኳ ሳያስተርፍ እርሱንና ሕዝቡን መታቸው።34ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን በሙሉ ከለኪሶን ወደ ዔግሎን አለፉ። እዚያም ሰፈሩ፤ ወጓትም፤ 35በዚያኑ ዕለት ከተማዋንም ያዟት። ኢያሱም በለኪሶ እንዳደረገ ከተማይቱንና በውስጧ የሚገኙትን ፈጽመው በሰይፍ ስለት አጠፏት።36ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከዔግሎን ወደ ኬብሮን አለፉ። በከተማይቱም ጦርነት አደረጉ። 37ከተማዪቱንም ከንጉሥዋ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጭምር ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። በዔግሎን እንዳደርጉት ሁሉ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ። ማንኛውንም ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ አጠፋ።38ከዚያ ኢያሱና እስራኤል ሠራዊት ከእርሱ ጋር ወደ ኋላ ተመልሰው በደቤርን አለፉ፤ ጦርነቱንም አደረጉ። 39ከተማዪቱን ንጉሥዋንና በአካባቢ ያሉ መንደሮቿን ሁሉ ያዙ። ከተማይቱንና በውስጧ ያለውንም ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ፥ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። ኢያሱ በኬብሮን ያደረጉትን ሁሉ በዳቤርና በንጉሥዋ ላይ አደረጉት።40ኢያሱ ተራራማውን አገር ኔጌቭን ቆላና የተራራውን ሸንተረሮች ጨምሮ ምድሪቱን በሙሉ ከነገሥታቷ ጋር አሸነፈ። ከነገሥታቱንም ያስቀረው ማንም የለም። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረትሕይወት ያላቸውን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው። 41ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ፥ የጎሶምን ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ በሙሉ አጠፋ።42ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን የያዘው በአንድ ጊዜ፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ስለተዋጋ ነው። 43ኢያሱ ከመላው እስራኤላውያን ጋር ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።
1የአሦርም ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ዮባብ ንጉሥ፥ ወደ ማዶን ንጉሥ፥ ወደ ሺምሮን ንጉሥና ወደ አዚፍ ንጉሥ መልእክት ላከ። 2ደግሞም በሰሜናዊ በተራራማው አገር፥ በየርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ከኪኔሬት በስተ ደቡብ ፥ በምዕራቡ ቆላማ አገሮችና ከኮር ኮረብታማ በስተ ምዕራብ ወዳሉት ነገሥታት ላከ። 3በምሥራቅና በምዕራብ ወደሚገኙት ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያንና በኮረብታማው አገር ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሳውያን እንዲሁም በምጽጳ ምድር በአርሞንዔም ተራራ ወዳሉት ወደ ኤዊያውያን ነገሥታት መልእክት ላከ።4እንዚህም ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በቁጥርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ እጅግ ከብዙ ወታደሮች ጋር መጡ። ታላቅም ቁጥር ፈረሶችና ሠረገሎች ነበሩአቸው። 5እነዚህ ሁሉ ነገሥታት እስራኤልን ለመውጋት ኃይላቸውን አስተባብረው በማሮን ውሃ አጠገብ በተቀጠረው ጊዜ ሰፈሩ።6እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቆርጣለህ፥ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ። 7ኢያሱና ሠራዊቱ ሁሉ መጡ። በድንገትም ወደ ማሮን ውሃ መጥተው ጠላቶቻቸውን አጠቁኣቸው።8እግዚአብሔርም ጠላትን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። በሰይፍም ስለት አጠቁአቸው፥ ወደ ሲዶና፥ወደ ማስሮን፥ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ በስተምሥራቅ አሳደዷቸው። ከእነርሱም በሕይወት አንድንም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። 9ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእነርሱ ላይ አደረጉ። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቆረጠ፥ ሠረገሎቻቸውንም አቃጠለ።10በዚያን ጊዜም ኢያሱ ወደ ኋላ ተመልሶ አጾርን ያዘ። ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለው። (አጾርም የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ የበላይነት ነበራች።) 11በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ በሕይወት ካለው ፍጡር አንድ እንኳ ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ። አሦርንም በእሳት አቃጠሏት።12ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውን ሁሉ ማረካቸው፥ በሰይፍም ስለት አጠፋቸው። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው በሰይፍ ስለት አጠፋቸው። 13እስራኤልም በተራራው ላይ ከተሠሩ ከተሞች ከአጾር በስተቀር ሌሎችን አላቃጠሉም። ኢያሱ ይህችን ለብቻዋ አቃጠላት።14እስራኤላውያንም ምርኮውን በሙሉ ከእነዚህም ከተሞች የተገኙትን እንስሳት ለራሳቸው ወሰዱ። ሕዝቡን በሙሉ ሁሉም ሙት እስኪሆኑ ድረስ በሰይፍ ስለት ገደሉአቸው። በሕይወት ካለው ፍጡር አንድም አልቀሩም። 15እግዚአብሔር አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ሙሴም ኢያሱን አዘዘው። ኢያሱም እግዚአብሔር ሙሴን ካዘዘው ሁሉ እርሱ ያልፈጸመው አንዳች ነገር አልነበረም።16ኢያሱም ማለት ተራራማውን አገር፥ ኔጌቭን ሁሉ፥ የጎሶምን ምድር በሙሉ፥ የኮረብታ ግርጌ። የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ፥ የእስራኤልም ኮረብታማ አገርና ቆላማውን የምዕራቡን ቆላዎችን ሁሉ፥ያንን ምድር በሙሉ ወሰደ። 17እንዲሁም እስከ ሴይር በሚደርሰው ከሐላቅ ተራራ አንሥቶ ከአርሞንዔም ተራራ በታች በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ እስካለው እስከ በዓል ጋድ ድረስ ያለውን ምድር በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውንም ሁሉ ያዘ፥ መትቶም ገደላቸው።18ኢያሱ ከእነዚህ ነገሥታት ጋር ረጅም ጊዜ ጦርነት አደረገ። 19በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በስተቀር ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ያደረገ አንድም ከተማ አልነበረም። እስራኤል ሁሉንም ከተሞች የያዙት በጦርነት ነበር። 20እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ያለ አንዳች ርኅራኄ ፈጽሞ ይደመስሳቸው ዘንድ እስራኤልን እንዲወጉ ልባቸውን ያደነደናቸው ራሱ እግዚአብሔር ነበር።21በዚያንም ጊዜ ኢያሱ መጥቶ ዔናቅን አጠፋ። ይህንንም በተራራማው አገር በኬብሮን፥ በዳቤርና በአናብ እንዲሁም በመላው ይሁዳና የእስራኤል ተራራማ አገሮች ያሉትን ላይ አደረገ። እርሱም እነርሱንና ከተሞቻቸውን በሙሉ አጠፋቸው። 22ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ በጋዛ፥ በጌትና በአሽዶድ ከቀሩት በስተቀር በእስራኤል አገር ከዓናቅ የቀሩት አልነበሩም።23ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ምድሪቱን በሙሉ ያዘ። ኢያሱም እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራእላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
1የእስራኤልም ሰዎች ድል ያደረጉአቸው ነገሥታት እነዚህ ነበሩ። እስራኤላውያንም ከአዮርዳኖንም ሸለቆ በስተ ምሥራቅ ጀምሮ እስከ ፀሐይ መውጫ ድረስ፥ ከአርሞን ወንዝ ሸለቆ ወደ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ። የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን በሐሴቦን ተቀመጠ። 2በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ገዛ።3ሴዎንም በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓርባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥በቤት የሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር (እስከ ጨው ባሕር) ወደ ምሥራቅ ድረስ በደቡብም በኩል ከፍስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር ገዛ። 4የባሳን ንጉሥ ዐግ ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀመጠ። 5እርሱም የአርሞንዔምንም ተራራ፥ ስልካንና ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ፥ እስከ ንጉሥ ሀሴቦን ድረስ ገዛው ።6የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፤ ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።7ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ያሸነፉአቸ ነገሥታትና አገሮች እነዚህ ናቸው፡- በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል፥ በሊባኖስ ሸለቆ አጠገብ ወደ ኤዶን አጠገብ ሃላክ ተራራ ድረስ ነው። ኢያሱም ለእስራኤል ነገዶች ሁሉ ምድሪቱን ርስት አድርጎ ሰጣቸው። 8ተራራማውን አገር፥ በቆላውንም፥ በዓረባንም፥ የተራሮችን ቁልቁለት፥ ምድረ በዳውንም፥ የደቡቡም ያሉትን ኬጢያውያን፥ አሞራውያንም፥ ከነዓናውያንም፥ ፌርዛውያንም፥ ኤዊያውያንም፥ ኢያቡሳውያንም ሰጣቸው።9የኢያሪኮ ንጉሥ ጨምሮ፦ በቤቴል አጠገብ ያለው የጋይ ንጉሥ፥ 10የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ 11የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ 12የአግሎን ንጉሥ፥ የጌዝር ንጉሥ፥13የዳቤር ንጉሥ፥ የጌድር ንጉሥ፥ 14የሔርማ ንጉሥ፥ የዓራድ ንጉሥ፥ 15የልብና ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ 16የመቄዳ ንጉሥ፥ የቤቴል ንጉሥ፥17የታጱዋ ንጉሥ፥ ይአፌር ንጉሥ፥ 18የአፌቅ ንጉሥ፥ የሽሮን ንጉሥ፥ 19የማዶ ንንጉሥ፥የአሶር ንጉሥ፥ 20የሺምሮን፥ ሚሮን ንጉሥ፥ የአዚፍ ንጉሥ፥21የታዕናክ ንጉሥ፥የመጊዶ ንጉሥ፥ 22የቃዴስ ንጉሥ፥ በቀርሜሎስ የነበረ የዮቅንዕም ንጉሥ፥ 23በዶር ኮረብታ የነበረ የዶር ንጉሥ፥ የጌልገላ አሕዛብ ንጉሥ፥ 24የቲርሳ ንጉሥ፥ ነገሥታቱ ሁሉ ሠላሳ አንድ ናቸው።
1ኢያሱም ሸመገለ በዕድሜም አረጀ፤ እግዚአብሔርም አለው፦ አንተ ሸመገልህ፥ በዕድሜህም አረጀህ ያልተወረሰ እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርቶአል።2የቀረውም ምድር ይህ ነው፤ የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ፥ 3(በግብፅ ፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል አስካለው የከነዓናውያን ንብረት ሆኖ ተቆጠረው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን የአስቀሎና፥የጌትና የአቃሮን አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት።)4በደቡብም በኩል የከነዓናውያንም ምድር ሁሉ፥ ለሲዶናውያንም የምትሆን መዓራ እስከ አሞራውያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥ 5የጌባላውያንም ምድር፥ በፀሐይ መውጫ በኩል ሊባኖስ ሁሉ፥ ከኣል ጋድ ከአርሞንዔም ተራራ በታች እስከ ሐማት ድረስ ያለው ።6በተራራማውም አገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሮን ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ። እነዚህን ከእስራኤል ፊት አባርራቸዋለሁ። እንዳዘዝሁም፤ምድራቸውን ለእስራኤል ርስት አድርገህ ለመመደብ እርግጠኛ ሁን። 7አሁንም ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገድ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ አከፋፍል።8የእግዚእብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ ሰጣቸው ከሌላ እኩሌታ የምናሴ ነገድ ጋር የሮብልና የጋድ ሰዎች በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ አዞአቸው የነበረውን ርስታቸውን ተቀበሉ። 9በአርኖን ወንዝ ሸለቆ ዳር ካለው ከአሮዔር፥ (በሸለቆውም መካከል ካለው ከተማ ጀምሮ) የሜድባን ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥10በሐሴቦንም የአሞርውያን ንጉሥ የሴዎን ከተሞች ሁሉ እስከ አሞራውያን ዳርቻ ድረስ፥ 11ገለዓድንም፥ የጌሹራውያንና የማዕካታውያንን አካባቢ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥ 12በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፥ እነርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም።13ነገር ግን የእስራኤል ሰዎች ጌሹራውያንን ወይም ማዕካታውያንን አላወጡም ነበር። በዚህ ፈንታ ጌሹርና ማዕካት እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤል መካከል ይኖራሉ።14ሙሴም ለሌዊ ነገድ ለብቻ ርስት አልሰጠም። እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ ተናገረው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የሚቀረበው፥ በእሳት የተደረገ መሥዋዕት ርስታቸው ነው።15ሙሴም ለሮቤል ልጆች ነገድ በየወገናቸው ርስትን ሰጥጣቸው። 16ድንበራቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀሞሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥17ሐሴቦንና በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ዲቦን፥ ባሞት በኣል፥ ቤት በኣልምዖን፥ 18ያሀጽና ቅዴሞት፥ ሜፍዓት፥ 19ቂርያታይም፥ ሴባማ፥ ጼሬትሻሐና በሸለቆውም ተራራ ያለውና ሁሉ ሮቢን ተቀበለ።20ሮቤም ቤተ ፌጎርን፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድርን፥ ቤት የሺሞትን፥ 21የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት፥ በሐሴቦንም የነገሠው፥ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የምድያምን አለቆች፥ ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርንና ሪባን፥ የሴዎን መሳፍንት፥ መታቸው።22የእስራኤል ሰዎች ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉ። የሮቤልም ልጆች ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝና ዳርቻው ነበረ። 23የሮቤል ነገድ ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝ ነው፥ ይህም ድንበራቸው ነው። ይህም ከከተሞቻቸውና መንደሮቻቸው በየወገኖቻቸው ለሮቤል ነገድ የተሰጣቸው ርስት ነበረ።24ይህም መሴ ለጋድ ነገድ በየውገኖቻቸው ርስት አድርጎ የሰጣቸው ነው። 25ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያንም ምድር እኩሌታ፥ 26ከረባት በስተምሥራቅ፥ አስካለው እስከ አሮዔር ድረስ፥ ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ ነበር።27ሙሴም ቤትሀራምን፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን፥ የቀሩትንም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ከዮርዳኖስን እንደ ድንበር በምሥራቅ በኩል ባለው በዩርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ሰጣቸው። 28ይህም የጋድ ነገድ ከከተሞቻቸውና ከመንደሮቻቸው ጋር በየወገኖቻቸው ርስት ነበረ።29ሙሴም ለምናሴ እኩሌታ ነገድ ርስትን ሰጣቸው። ለምናሴም ነገድ እኩሌታ በየወገኖቻቸው መሠረት የተመመደበ ነበረ። 30ድንበራቸውም ባሳን ሁሉ፥ ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ በባሳንም ያሉት የኢያፅር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፤ 31የገለዓድም እኩሌታ፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበር፤ (የ'ዐግ በባሳን ያሉ የመንግሥት ከተሞች) ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለማኪር ሰዎች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።32ይህም ሙሴ በምሥራቅ በኩል በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሳለ፥ የከፈለው ርስት ነው። 33ሙሴም ለሌዊ ነገድ ርስት አልሰጣም ነበር። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው ርስታቸው ነው።
1የእስራኤልም ሕዝብ በካነዓን ምድር የወረሱት ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ በእስራኤልም ነገድ መካከል የአባቶቻቸው አለቆች ያካፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፤2እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገዶችና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አካፈሉአቸው፤ 3ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም። 4የዮሴፍ ነገድ፥ ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ። ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተወሰኑ ከተሞች፥ ለእንስሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን መሰምርያቸው በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም። 5እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የእስራኤል ሕዝብ አደረጉ፥ ምድሩንም ተካፈሉ።6የይሁዳም ነገድ በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ። ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ። 7የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ፤ እኔም በልቤ እንደ ነበረ መረጃ አመጠሁለት።8ነገር ግን ከእኔ ጋር የሄዱ ወንድሞቼ የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ። እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ። 9ሙሴም በዚያ ቀን፦ አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም በእርግጥ ርስት ይሆናል ብሎ ማለ።10አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገር በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲጓዙ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ። እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ። 11ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጉልበታም ነኝ፥ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበር፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት፥ ለመውጣትና ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው።12እንግዲህ በዚያን ቀን እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ተራራማ አገር ስጠኝ። አንተም በዚያ ቀን ታላላቅና በተመሸጉ ከተሞቻቸው ጋር ዔናቃውያን በዚያ እንደ ነበሩ ሰምተህ ነበር። እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ይሆናል፥ አሳድዳቸዋለሁ።13ኢያሱም ባረከው፤ ለዮፎኒም ልጅ ለካሌብ ኬብሮንን ርስት አድርጎ ሰጠው። 14ስለዚህም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆንች። 15የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር። (አርባቅም በዔናቅ ሰዎች መካከል ከፍ ያለ ነበረ።) ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
1ለይሁዳም ልጆች ነገድ በየወገናቸው መሬትን ማከፋፈል እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብም መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ዕጣ ሆነላቸው። 2በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ እስከሚያይ እስከ ባሕረ ልሳን ነበረ።3ከዚያም ቀጥሎ ከኮረብታ በስተደቡብ በኩል ወደ ጺንም አለፈ፤በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይዘልቃል፤ በሐጽሮንም በኩል አልፎ ወደ አዳርም ደረሰ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥ 4ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንባሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበር፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው።5በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዩርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበር። 6ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሖግላ ወጣ፥ በቤት ዓርባ በሰሜን በኩል አለፈ። (ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን) ድንጋይ ወጣ።7ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ኮረብታ ፊት ለፊት፥በወንዙም በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ዞረ። ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ መውጫውም በዓይን ሮጌል አጠገብ ነበረ። 8ከዚያ ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ (ኢየሩሳሌም) ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ።9ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ። ቂርያትይዓሪም ወደምትበል ወደ በኣላ ደረሰ። (ከዚያም ድንበሩ በባኣላ ዙሪያ እንደ ቂርያት በተመሳሳይ ታጠፈ) ። 10ድንበሩም ከባአላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓሪም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረድ፥ በተምና በኩልም አለፈ።11ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ወደ ሽክሮን ደረሰ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። 12በምዕራቡም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ።ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው።13እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት አርበቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም ዘርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። 14ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴስን፥ አኪመንንና ተላሚን ከዚያ አሳደደ። 15ከዚምም በዳቤር ሰዎች ላይ ወጣ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ ቂርያት ሤፍር ትባል ነበር።16ካሌብም እንዲህ አለ፦ ቂርያት ሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ አለ። 17የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት። ስለዚህም ካሌብ ልጁን ዓክሳን አጋባው።18ዓክሳም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ ለመለምን ገፋፈችው፤ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፤ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት።19እርስዋም፦ ስጦታ ስጠኝ፤ የኔጌቭ ምድር ሰጥተኸኛል፥ አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።20በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ የተሰጠ ርስት ይህ ነው።21በድቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉትን የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ ቀብስኤል፥ ዓዴር፥ ያጉር፥ 22ቂና፥ ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥ 23ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ዪትናን 24ዚፍ፥ጠሌም፥በዓሎት።25ሐጾርሐ ዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርታይሐጾር፥ 26አማም ሽማዕ፥ ሞላዳ፥ 27ሐጸርጋዳ፥ሐሽሞን፥ ቤትጳሌጥ፥ 28ሐጸርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ፥29በኣላ፥ ዒዮም፥ ዓጼም፥ 30ኤልቶላድ፥ ኪሲል፥ ሔርማ፥ 31ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥ 32ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን፥ ሪሞም፤ ሀያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።33በቆላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥ 34ዛኖዋ፥ ጫይንገኒም፥ ያጱዋ፥ ዓይናም፥ 35የሩት፥ ዓዶላም፥ ሰኮት፥ ዓዜቃ፥ 36ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግርራ፥ ግርሮታይም፤ አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው።37ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥ 38ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅትኤል፥ 39ለኪሶ፥ በጽቃት፥ አግሎን40አዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ 41ግዴሮት፥ ቤት ዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ፤አሥራ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።42ልብና፥ ዔቴር፥ ዓሻን፥ 43ይፍታሕ፥ አሽና፥ንጺብ፥ 44ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።45አቃሮን፥ ከተመሸጉና ካልተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ ጋር፤ 46ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕር ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር። 47በአዛጦን የተመሸጉና መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ካርቻ ክረስ።48በተራራማውም አገር ሳምር፥ የቲር፥ ሶኮ፥ 49ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና፥ 50ዓባብ፥ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥ 51ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ፤ አሥራ አንድ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።52አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥ 53ያንም፥ ቤትታጱዋ፥ አፌቃ፥ 54ሑምጣ፥ ኬብሮን የምትባል ቂርያትአርባቅ፥ ጺዖር ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።55ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣም 56ኢይዝራሴል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥ 57ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፤ አሥር ከተሞና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።58ሐልሑል፥ ቤት ጹር፥ ጌዶር፥ 59ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን፤ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።60ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያት በኣል፥ ረባት፤ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 61በምድረ በዳ ቤትዓረባ፥ ሚዲን፥ ስካካ፥ 62ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ፤ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው።63በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
1የዮሴፍም ልጆች የመሬት ድልድል በኢያሪኮ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳውና በተራራማው በኩል ከኢያሪኮ ወደ ቤቴል ወጣ። 2ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አለፈ።3ወደ ምዕራብም እስከ የፍርሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤት ሖሮን ዳርቻ እስከ ጌዝር ድረስ ዘልቆ፥ መጨራሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበር። 4የዮሴፍም ነገድ ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን የተቀበሉት በዚህ መንገድ ነበር።5የኤፍሬምም ነገድ ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፦ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮት አዳር እስከ ላይኛው ቤት ሖሮን ድረስ ነበረ፤ 6ከዚያ ወደ ባሕሩ ቀጠለ። ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ ሚክምታት በሰሜን በኩል ወደ ምሥራቅ ወደ ተአናት ሴሎ ዞረ፥ ከዚያም ወደ ኢያኖክ በምሥራቅ በኩል አለፈ። 7ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ።8ድንበሩም ካታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መውጫውም በባሕሩ መጨራሻ ነበረ። የኤፍሬም ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ፤ 9ይኸውም፥ በምናሴ ነገድ ርስት መካከል ለኤፍሬምም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ነው።10በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም ነበር፤እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ሆኖም እነዚህ ሰዎች የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ ተደርገው ነበር።
1ለምናሴ ነገድ የተመደበው ይህ ነበር፤ እርሱም የዮሴፍ በኩር ነበር። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ራሱም የገለዓድ አባት ነበር። የማኪርም ወገኖች የገለዓድና የባሳን ምድር ተሰጣቸው ምክንያቱም ማኪር የጦር ሰው ነበርና። 2ለቀሩት ለምናሴ ልጆች በየወገኖቻቸው ለአቢዔዝር ልጆች፥ለኬሴግ ልጆች ለአሥሪኤል ልጆች፥ ለሴኬም ልጆች፥ ለአፌር ልጆች፥ልሸሚዳ ልጆች ተሰጣቸው። የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ወንዶች ልጆች በየወገኖቻቸው የተሰጣቸው እነዚህ ናቸው።3ለምናሴ ልጅ፥ ለማኪር ልጅ፥ ለገለዓድ ልጅ፤ ለኦፌር ልጅ፥ ለሰለጰዓድግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩአቸውም የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። 4እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ አለቆች ቀርበው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርም ሙሴን ከወንድሞቻችን ጋር ርስት እንዲሰጠን አዝዞ ነበር። ስለዚህ ትእዛዙን በመከተል በአባታቸው ወንድሞች መካከል ለእነዚያ ሴቶች ርስት ሰጣቸው።5በዮርዳኖስ ማዶ ካለው በገለዓድና በባሳን ምድር ለምናሴ አሥር የመሬት መደቦች ተመድቦ ነበር፤ 6ምክንያቱም የምናሴ ሴቶች ልጆች ከወንዶቹ ጋር ርስት ተቀብለዋል። የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ነገድ ተመደበ።7የምናሴም የድንበር ክልል ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ደረሰ። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ታጱዋ ምንጭ አጠገብ ወደሚኖሩ ሰዎች አለፈ። 8(የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፤ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ከተማ ግን ለኤፍሬም ነገድ ሆነ።)9ድንበሩም ወደ ቃና በኩል ወደ ታች ወረደ። እነዚህ ከወንዙ በስተደቡብ ያሉ ከተሞች በምናሴም ከተሞች መካከል ለኤፍሬም ሆኑ። የምናሴም ድንበር በወንዙ በስተሰሜን በኩል ሆኖ በባሕሩ መጨራሻ ነበረ። 10በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፥ በሰሜንም በኩል ያለው ለምናሴ የነበረው ድንበሩ ባሕር ነበረ። በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅ ም በኩል ወደ ይሳኮር ደረሰ።11በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤት ሳንና መንደሮችዋን፥ ይብልዓምንና መንደሮችዋን፥ ዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የዓይንዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን፥ የታዕናክ ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የመጊዶ ሰዎችንና መደሮችዋን ፥ ሦስቱ ኮረብቶች ምናሴ ወረሳቸው። 12ሆኖም የምናሴ ነገድ ግን እነዚህን ከተሞች ርስት አድርጎ ሊወስዳቸው አልቻሉም፤ ምክንያቱም ከነዓናውያን በዚያ ምድር መኖራቸውን ቀጥለው ነበር።13የእስራኤልም ሕዝብ እየጠነከሩ በመጡ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከምካከላቸው እንዲወጡ አላደረጉም ነበር።14ከዚያም የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ እኛ ብዙ ሕዝብ ሆነን ሳለን፥ እግዚአብሔርም ባርኮን እያለ ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን? አሉት። 15ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ በቁጥር ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ወደ ዱር ወጥታችሁ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለራሳችሁ መንጥሩ። ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦአችሁ እንደ ሆነ ይህንን አድርጉ።16የዮሴፍም ልጆች እንዲህ አሉ፦ '"ተራራማውም አገር አይበቃንም። ነገር ግን በሸለቆውም ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤት ሳንና በመንደሮችዋ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የብረት ሰርገሎች አላቸው።" 17ከዚያም ኢያሱ ለዮሴፍ ልጆች መለሰላቸው፦ ለመሆኑ ለኤፍሬምና ለምናሴ እናንተ ብዙ ሕዝብ ናችሁ፥ ጽኑም ኃይልም አላችሁ። አንድ ክፍል መሬት ብቻ ሊኖራችሁ አይገባም። 18ተራራማውም አገር ለእናንተ ይሆናል። ዱር እንኳ ቢሆንም ትመነጥሩአቸዋላችሁ፥ ለእናንተም እንዲሆኑ ታደርጋላችሁ። ከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ያሉአቸውና ኃይለኞች ቢሆኑም ልታስለቅቁአቸው ትችላላችሁ። ታሳድዳቸዋላችሁ አላቸው።
1የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ። በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው። 2ከእስራኤልም ልጆች መካከል ያልተካፈሉ ሰባት ነገዶች ቀርተው ነበር።3ኢያሱም ለእስራኤል ሰዎች አላቸው፦ የአባቶቻቸሁ እግዚአብሔር አምላክ የሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ እስከ መቼ ድረስ ቸል ትላላችሁ? 4ከየነገዱም ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ። ተነሥተውም የምድሪቱን ላይና ታች ይለካሉ። እንደ ርስታቸውም መጠን ይጽፉታል፤ ወደ እኔም ይመለሳሉ።5በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል። ይሁዳም በደቡብ ድንበር ባሉበት ይጸናሉ፤ የዮሴፍ ወገኖች በሰሜን በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀጥላሉ። 6እናንተም ምድሪቱን በሰባት ክፍል ትጽፋላችሁ፥ የጻፋችሁትንም ወደ እኔ ታመጣላችሁ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።7ለሌዋውያንም ርስት የላቸውም፤ የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና። የጋድም፥ የሮቤልም፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀበሉ።ይህም የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸው ርስታቸው ይህ ነው።8ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ ሂዱ፥ በምድሩም ላይና ታች ዞራችሁ ጻፉት፥ ከዚያም ወደ እኔ ተመለሱ። በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ። 9ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ላይና ታች ዞሩ። እንደ ከተሞችም በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ ዝርዝራቸውንም ጻፉት። ከዚያም ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ።10ኢያሱም በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣጠላቸው። በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደ ክፍሎቻቸው ምድሩን አካፈላቸው።11የምድሩም ዕጣ ለብንያምም ነገድ በየወገኖቻቸው ተሰጠ። የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ነበረ። 12በሰሜን በኩል ድንብራቸው ከዮርዳኖስ ይጀራል። ድንበሩም ወደ ኢያሪኮ ወደ ሰሜን በኩል፥በተራራማው አገር ወደ ምዕራብ ደረሰ። መውጫውም በቤት አዌን ምድረ በዳ ነብረ።13ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ። ድንበሩም በታችኛው ቤት ሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮት አዳር ወረደ። 14ድንበሩም ወደ ምዕራብ ዘለቀ፥ በቤⶆሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ይዞራል፤ መውጫውም ቂርታትይዓሪም በትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያት በኣል ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።15የደቡብም ዳርቻ ከቂርያት ይዓሪም ውጪ ይጀምራል። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ሄደ። 16ድንበሩም በበን ሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰንን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይን ሮጌልም ወረደ።17ወደ ሰሜንም ዞረ፤ በኢን ሳሚስ አቅጣጫ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎትወጣ፤ ከዚያሜ ወደ ሮቤ ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፤ 18በሰሜንም ወገን ወደ ዓረባ አጠገብ አለፈ፥ ወደ ዓረባም ወረደ።19ድንበሩም ወደ ቤት ሖግላ ወደ ሰሜን በኩል አለፈ። መውጫውም በዮርዳንስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበር፥ ይህም የደቡቡ ዳርቻ ነበረ። 20በምሥራቅም በኩል ድንበሩ ዮርዳኖስ ነበረ። ይህ በዙሪያቸው ዳርቻ በየወገኖቻቸው የብንያም ልጆች ርስት ነበረ።21የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻችቸው እነዚህ ነበሩ፦ ኢያሪኮ፥ ቤት ሖግላ፥ ዓመቀጺጽ፥ 22ቤት ዓረባ፥ ዘማራይም፥ ቤቴል፥ 23ዓዊም፥ ፋራ፥ ኤፍራታ፥ 24ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ፣ ጋባ፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።25ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት፥ 26ምጽጳ፥ ከፊራ፥አሞቂ፥ 27ፍርቄም፥ይርጵኤል፥ ተርአላ፥ 28ዼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባልየኢያቡስ ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት፤ አሥራ ሦስት ከትሞችና መንደሮቸችው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
1ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መካከል ነበረ።2እነርዚህም ርስታቸው ሆኑላቸው፤ ቤርሳቤህም ሤባ፥ሞላዳ፥ 3ሐጸርሹዕል፥ ባለ፥ዔጼም፥ 4ኤልቶላድ፥ በቱል፥ ሔርማ፥ ጺቅላግ፥5ቤትማርካቦት፥ ሐጸርሱሳ፥ 6ቤተ ለባኦት፥ ሻሩሔን፤ አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 7ዓይን፥ ሪሞን፥ ዔቴር፥ ዓሻን፤ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው፤8እስከ ባዕላት ብኤርና እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞችና ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። 9ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ። የይሁዳም ልጆች ዕድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸ መካከል ወረሱ።10ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። የርስታቸውም ድንበር ወደ ሣሪድ ደረሰ። 11ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼትም ደረሰ፤ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ።12ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎት ታቦር ዳርቻ ዞረ። ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ። 13ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒታቃጺን አለፈ፥ ወደ ሪምንና ወደ ኒዓ ወጣ።14ድንበሩም በሰሜን በኩል ወደ ሐናቶን ዞረ፥ መውጫውም በይፍታሕኤል ሸለቆ ነበረ። 15ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 16የዛብሎን ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።17አራተኛውም ዕጣ ለይሳኮር ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። 18ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥ወደ ከስሎት፥ወደ ሱነም፥ 19ወደ ሐፍራይም፥ ወደ ሺአን፥ ወደ አናሐራት፥20ወደ ረቢት፥ ወደ ቂሶን፥ ወደ አቤጽ፥ 21ሬሜት፥ ወደ ዓይንጋቢም፥ ወደ ዓይንሐዳ፥ ወደ ቤት ጳጼጽ ደረሰ፤ ድንበሩም ወደ ብቦርና ወደ ሻሕጽይማ፥ ወደ ቤት ሳሚስ ደረሰ። 22የድንበራቸውም መውጫ ዮርዳኖስ ነበረ፤ አሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።23የይሳኮር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።24አምስተኛውም ዕጣ ለአሴር ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። 25ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥ ቤጤን፥ አዚፍ፥ አላሜሌክ፥ ዓምዓድ፥ ሚሽአል ነበረ፤ 26በምዕራብ በኩል ወደ ቀርሜሎስና ወደ ሺሖርሊብናት ደረሰ።27ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤት ዳጎን ዞረ፥ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤት ዓሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፤ በስተ ግራ ቡልም ወደ ካቡል ወጣ። 28ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲኖናም ደረሰ።29ድንበርም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፤ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፤ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤ 30ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ። እነዚህም ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።31የአሴር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።32ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። 33ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ ከጸዕነኒም ዛፍ፥ ከአዳሚኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ። 34ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ከዚያም በደቡም በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳስም ወንዝ በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።35የተመሸጉትም ከትሞች እነዚህ፦ ነበሩ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥ 36አዳማ፥ ራማ፥ አሶር፥ 37ቃዴስ፥ኤድራይ፥ ዓይንሐጽር፥ ይርአን፥38ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤት ዓናት፥ ቤት ሳሚስ፤ አሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ያልተቆጠሩ። 39የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።40ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። 41የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ፤ ጾርዓ፥ ኤሽታኦል፥ ዒርሼሜሽ፥ 42ሸዕለቢን፥ ኤሎን፥ ይትላ፥ ኤሎን፥43ተምና፥አቃሮን፥ 44ኢልተቄ። ገባቶን።ባዕላት፥ ይሁድ፥ 45ብኔንርቅ፥ ጋትሪሞ፥ 46ሜያርቆን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆን።47የዳንም ልጆች ዳርቻ አልበቃቸውም፥ የዳንም ልጆች ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለመቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። ስምዋንም በአባቶታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠርአት። 48የዳን ነገድ ርስት በየወገኖቻቸ እነዚህ ከትሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።49ምድሩንም ሁሉ በየድንበሩ ርስት እንዲሆን ከፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት። 50በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት። ከተማውንም እንደ ገና ሠርቶ ተቀመጠበት።51ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ነገዶችና የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። የምርሪቱንም ማከፋፈል ሥራ ጨረሱ።
1ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፡ 3ሳያውቅም ሰውን የገደለ እንዲሸሽባቸው በሙሴ እጅ የነገርኋችሁን የመማፀኛ ከተሞችን ለዩ። እነዚህም ከተሞች ከተገደለበት ከማንኛውም ከደም ተበቃይ የሚሸሹበት ቦታ ይሆኑላችኋል።4ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ ለከተማይቱ ሽማግሌዎች ጉዳዩን ያስረዳል። እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡታል።5ሰው የሞተበትም ደም ተበቃዩ መጥቶ ለመበቀል ቢሞክር፥ የከተማውም ሰዎች ሰውየውን ለከተማው ባለሥልጣናት አሳልፈው መስጠት አይኖርባቸውም። ይህን ማድረግ የማይገባቸው እርሱ የገደለው ከዚህ በፊት ጥላቻ ሳይኖርና ሆነ ብሎ ባለመሆኑ ነው። 6በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያን ጊዜ ያለው በሊቀ ካህንነት የሚያገለግለው እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ። ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ፥ ሸሽቶ ከነበረበት ከተማ ወደ ከተማውና ወደ ቤቱ ይመለሳል።7በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ። 8ከዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፣ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ቶላንን ለዩ።9ማንም ሰው ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽና በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ናቸው። ይህም ሰው በማኅብሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ነው።
1ከዚያም የሌዋውያን ወገኖች አለቆች ወደ ካህኑ አልዓዘር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ እስራኤል ነገዶች አለቆች ቀርቡ። 2እነርሱም በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ እንዲህ አሉአቸው፡- እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውንና ለከብቶቻችንም መሰማሪያ የሚሆኑ ከተሞች እንድትሰጡን አዞአችኋል።3ስለዚህም የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሚከተሉትን ከተሞች ለከብቶቻቸውም መሰማሪያ ጭምር እንዲሆኑ ርስታቸውን ለሌዋውያን ሰጡአቸው።4ለቀዓትም ወገኖች የዕጣው ውጤት እንዲህ ሆነ፦ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች፥ ከይሁዳ ነገድ ከስምዖንም ነገድ ከብንያምም ነገድ አሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጣቸው። 5ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድና ከምናሴ ነገድ እክኩሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ተቀበሉ።6ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴር ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳን ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጣቸው። 7ለሜራሪም ልጅች በየወገኖቻቸው ከሮቤል ነገድ፥ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድአሥራ ሁለት ከተሞ ተቀበሉ።8እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዛቸው የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ። 9ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው እነዚህን ከተሞች ሰጡ። 10እነዚህ ከተሞች ከሌዊ ልጆች ነገድ የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ተሰጥቶአቸው ነበር። የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ወጥቶላቸው ነበር።11እንደ ኬብሮን ተመሳሳይ ቦታ በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት አርባቅ (ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ) የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን የከብቶች መሰማሪያዋን ሰጡአቸው። 12የከተማይቱንም እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።13ለካህኑም ለአሮን ልጆች ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና መሰማሪያዋን፥ ልብናን ከመሰማሪያዋን ጋር ሰጡ፤ 14የቲርንና መሰማሪያዋን፥ ኤሽት ሞዓንና መሰማሪያዋን፥ 15ሖሎንንና መሰማሪያዋን፥ ዳቤርንና መሰማሪያዋን፥ 16ዓይንንና መሰማሪያዋን፥ ዮጣንና መሰማሪያዋን፥ ቤት ሳሚስንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ነበሩ።17ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰማሪያዋን፥ ናሲብንና መሰማሪያዋን፥ 18ዓናቶትንና መሰማሪያዋን፥ አልሞንንና መሰማሪያዋን፤አራት ከተሞችን ሰጡ። 19ለአሮን ልጆች ለካህናት የተሰጡ ከተሞች ከመሰማሪያቸው ባጠቃላይ አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው።20ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ወገኖች ሌዋውያን የተሰጣቸ ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ዕጣ ወጥቶላቸው ነበር። 21ለእነርሱም በኤፍሬም ተራራማ አገር ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥ 22ቂብጻይምንና መስማሪያዋን፥ ቤት ሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።23ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና መሰማሪያዋን፥ ገባቶንንና መሰማሪያዋን፥ 24ኤሎንንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።25ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 26ለቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች የተሰጡ ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸውን ጋር አሥር ከተሞችናቸው።27ለሌሎች ሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነችውን ጎላንንና መሰማሪያዋን፥ በኤሽትራንና መሰማይያዋን ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው።28ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰማሪያዋን፥ ዳብራትንና መሰማሪያዋን፥ 29የያርሙትንና መሰማሪያዋን፥ ዓይንጋኒምንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ለጋሪሶን ነገድ ሰጡአቸው። 30ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰማሪያዋን፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋን፥ 31ሔልቃትንና መሰማሪያዋን፥ ረአብንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው።32ከንፍታሌምም ነገድ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞትዶርንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ለጌድሶን ነገድ ሰጡአቸው። 33የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ከመሰማሪያቸው ጋር አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው።34ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንና መሰማሪያዋን፥ 35ዲሞናንና መሰማሪያዋን፥ ነህላልንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ።36ለሜራሪ ነገድ ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰማሪያዋን፥ ያሀጽንና መሰምሪያዋን፥ 37ቅዴሞትንና መሰማሪያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 38ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ከጋድም ነገድ በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንማ መሰማሪያዋን ሰጡ።39ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን ሜራሪ ነገድ ደግሞ የተሰጡ ባጠቃላይ አራት ከተሞች ናቸው። 40ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ባጠቃላይ አሥራ ሁለት ከተሞች ነበሩ።41በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማሪያቸው ነበሩ። 42እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰማሪያቸው ጋር ነበሩ፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ በዚህ ዓይነት መንገድ ነበሩ።43እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ። ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። 44እግዚአብሔርም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው። ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ይቋቋማቸው ዘንድ ማንም ሰው አልቻለም፤ እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። 45እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።
1በዚያን ጊዜም ኢያሱ የሮቤል ልጆችንና የጋድ ልጆችን የምናሴንም ነገድ እኩሌታ ጠራቸው። 2እንዲህም አላቸው፦ የእግዚእአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ሁሉ ጠብቃችኋል፥ እኔም ላዘዝኋችሁ ነገር ሁሉ ታዝዛችኋል። 3ይህንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወንድሞቻችሁን አልተዋችሁም፥ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቃችኋል።4አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራቸው ወድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል። አሁን እንግዲህ ተመለሱ፥ ወደ ቤታችሁና የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ። 5የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችሁን ትወድዱ ዘንድ መንገዱንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ወደ እርሱም ትጠጉ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩ ዘንድ ብቻ እጅግ ተጠንቀቁ። 6ኢያሱም መረቃቸው፥ ሰደዳቸውም፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።7ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ በባሳን ውስጥ ርስት ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለቀረው እኩሌታው ግን ኢያሱ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕብብ ወንን በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ሰጣቸው። ኢያሱም ወደ ቤታቸው በሰደዳቸው ጊዜ 8እንዲህ ብሎ መረቃቸው፦ በብዙ ብልጥግና በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።9የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ የእስራኤል ሕዝብ በከነዓን በሴሎ ትተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ። በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉአት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ ሄዱ።10በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዩርዳኖስ አጠገብ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ። 11ለእስራኤልም ልጆች፦ እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርውዋል፤ የሚል ወሬ ደረሰላቸው።12የእስራኤል ሕዝብ ይህን በሰሙ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወጥተው እነርሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰበስቡ።13የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መልእክት ላኩ። የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ደግሞ ላኩ፥ 14ከእርሱም ጋር አሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ እያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበሩ።15በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ግድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መጡ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩአቸው፦ 16የእግዚአብሔር ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፦ ይህ በእስራኤል አምላክ ላይ ያደረጋችሁት ኃጢአት ምንድን ነው? ዛሬ እግዚእአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋል ዛሬም በራሳችሁ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል።17በፌጎር ያደረገነው ኃጢአታችን አይበቃምን? እስከ ዛሬም ድረስ ከዚያ ኃጢአት ራሳችንን አላነጸንበትም። ከዚያም ኃጢአት የተነሣ በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ወረደ። 18እናንተ ዛሬ እግዚአብሔርን ከመከተል መመለስ ይገባችኋልን? ዛሬ በእግዚአሔር ላይ ብታምፁ ነገ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ይቆጣል።19የርስታችሁም ምድር የረከሰ ቢመስላችሁ የእግዚአብሔር ማደሪያ ወደ ሚቀመጥበት ወደ እግዚአብሔር ርስት ምድር አልፋችሁ በመካከላችን ውረሱ። ከአምላካችንም ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለእናንተ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔርና በእኛ ላይ አታምፁ። 20የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኃጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቁጣ አልወረደምን? እርሱም በኃጢአት ብቻውን አልሞተም።21ከዚያም የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል አለቆች እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ 22ሁሉን የሚችል አምላክ እግዚአብሔር ታላቁ አምላክ እግዚአብሔር እርሱ ያውቃል፥ እስራኤልም እንዲያውቅ ያደርጋል! በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደ ሆነ ዛሬ አታድነን እግዚአሔርን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን 23መሥዋዕትና የእህልን ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅነትትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይበቀለን።24ይልቁንም ከልባችን ፍርሃት የተነሣ፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችንን፦ እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ?25እግዚአብሔር በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአል። እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታ የላችሁም ይሉአቸዋል ብለን ይህን አደረግን። በዚህም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እግዚአብሔርን ከመፍራት ያስተዋቸዋል።26ስለዚህ፦ መሠዊያ እንሥራ አልን፤ ነገር ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት አይደለም፤ 27ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንት የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።28ስለዚህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ወይም ለትውልዳችን፥ ይህን እንላለን እኛ፦ እነሆም አባቶቻችን ያደረጉትን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ምሳሌ እዪ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ ስለሚቃጠል መሥዋዕታችን ስለሌላ መሥዋዕት አይደለም። በማደሪያው ፊት ካለው ከአምላካችን 29ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእህል ቁርባን ለሌላ መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ እግዚአብሔርንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።30ካህኑ ፊንሐና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር ከነበሩት የእስራኤል አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው። 31የካህኑም በአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች፦ ይህን መተላለፍ በእግዚአብሔር ላይ አላደረጋችሁምና እግዚአብሔር በመካከላችን እንዳለ ዛሬ እናውቃለን፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል አላቸው።32የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም አመጡላቸው። 33ነገሩም የእስራኤል ልጆችን ደስ አሰኘ፤ የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ወጥተው አንዲወጉአቸው አልተናገሩም።34የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፦ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት።
1ከብዙ ቀናት በኋላ፥እግዚአብሔርም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ካሳረፈ፥ ኢያሱ ሸምግሎ ነበር። 2ኢያሱም እስራኤልን ሁሉ ሽማግሌዎቻቸውን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እኔ በጣም ሸምግያለሁ። 3እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው።4ተመልከቱ! እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ መድቤላችኋለሁ። 5እግዚአሔር አምላካችሁም እርሱ ከፊታችሁ በብርቱ ይበትናቸዋል፥ ከፊታችሁም ያሳድዳቸዋል። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ።6ስለዚህም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለመጠበቅና ለማድረግ በጣም በርቱ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ። 7በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም። 8እስከ ዛሬ ድረስ እንዳደረጋችሁት በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ተጣበቁ።9እግዚአብሔርም ታላላቆችንና ኃይለኞችን መንግሥታት ከፊታችሁ አስወጣላችሁ። እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም። 10እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተጋገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና፥ ከእናንተ አንድ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል። 11እግዚእብሔር አምላካችሁን ትወድዱት ዘንድ ትኩረት አድርጉ።12እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ አሕዛብ ጋር ብትጣበቁ፥ወይም ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ ወይም እናንተ ወደ እነርሱም ወደ እናንተ ኅብረት ብታደርጉ፥ 13ከዚያም እግዚአብሔር አምላካችሁ ከመካከላችሁ እነዚህን ሰዎች እንደማያስወጣችሁ በርግጥ እወቁ። በዚህ ፈንታ ከዚህች እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ ለእናንተም መውደቂያና ወጥመድ፥ በጎናችሁም መግረፊያ፥ በዓይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል።14እነሆም ዛሬ የምድርን መንገድ ሁሉ እሄዳለሁ፤ እናንተም እግዚአብሔር ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፥ ሁሉ ደርሶላችኋል፤ ከእርሱም አንድ ነገር አልቀረም። 15እግዚአብሔ አምላካችሁ የተናገረው መልካም ነገር ሁሉ እንደ ደረሰላችሁ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እናንተን እስኪያጠፋችሁ ድረስ እግዚአብሔር እንዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመጣባችኋል።16የእግዚአብሔር አምላካችሁን ቃል ኪዳን ብታፈርሱ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ከሰጣትችሁም ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።
1ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበስበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎችን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠራቸው፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። 2ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ፥ የአብርሃምና የናኮር አባት ታራ፥ አስቀድመው በወንዝ ማዶ ተቀመጡ፤ ሌሎችንም አማልክት አመለኩ።3አባታችሁንም አብርሃምን ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ወስጄ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሩንም በልጁ በይስሐቅ በኩል እንዲበዛ ሰጠሁት። 4ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት። ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፥ ነገር ግን ያዕቆብና ልጂቹ ወደ ግብፅ ወረዱ።5ሙሴንና አሮንንም ላክሁ፥ ግብፃውያንን በመቅሠፍት መታሁ። ከዚያም በኋላ አወጣኋችሁ። 6አባቶቻችሁንም ከግብፅ አወጣኋችው፤ ወደ ባሕሩም መጣችሁ። ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አሳደዱአቸው።7አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ። ባሕሩንም በእነርሱ ላይ መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም። ዓናኖቻችሁም በግብፃውያን ላይ ያደረግሁትን አይታችኋል። ለረጅም ጊዜም በምድረ በዳ ተቀመጣችሁ።8እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ። ከእናንም ጋር ተዋጉ፥ በእጃችሁ አሳልፌ ሰጠኋችሁ። ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው።9-10የሞዓብም ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ ተንሥቶ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ እንዲረግማችሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን ልኮ አስጠራው።እኔ ግን በለዓምን አልሰማሁትም። እርሱም በዚህ ፈንታ ባረካችሁ፥ እኔም ከእጁ አዳንኋችሁ።11ዮርዳኖስንም ተሻግራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ። የኢያሪኮም ሰዎች፥ ከአሞራዊውያን፥ ከፌርዛዊውያን፥ ከከነዓናዊውያን፥ ከኬጢያዊውያን፥ ከጌርጌሳዊውያን፥ ከኤዊያዊውያንና ከኢያቡሳዊውያን፥ ጋር ተዋጉአችሁ። በእነርሱም ላይ ድልን ሰጠኋችሁ፤አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ። 12በፊታችሁ ያሉትን ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታት እንዲያስወጡአቸው በፊታችሁም ተርብን ሰደድሁባቸው። ይህም በእናንተ ሰይፍና ቀሥት አይደለም።13ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ዛሬ የተቀመጣችሁባቸውን ከተሞች ሰጠኋችሁ። ያልተከላችኋቸውን ወይንና ወይራ በላችሁ።14አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በግብፅም ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፤ እግዚአብሔርንም አምልኩ። 15እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ እባቶቻችሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤተ ሰቦቼ ግን እግዚአብሔርን እናመካለን።16ሕዝቡም መልሰው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርን ትተን ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከእኛ ይራቅ፥ 17እኛንና አባቶቻችንን ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በዓይናችንም ፊት እነዚያን ታላላቅ ተአምራት ያደረገ፥ በሄድንባትም መንገድ ሁሉ ባለፍንባችውም አሕዛብ ሁሉ መካከል የጠበቀን፥ እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ነው። 18እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ በምድሪቱም የተቀመጡትን አሞራውያን ከፊታችን አስወጣ። ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና፤ እግዚአብሔርን እናመልካለን።19ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ እርሱ ቅዱስና፥ ቀናተኛ አምላክ ነውና፥ እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም። 20እግዚአብሔርን ትታችሁ እንግዶችን አማልክት ብታመልኩ፥ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፥ መልካም ካደረገላችሁ በኋላ ያጠፋችኋል።21ሕዝቡም ኢያሱን፦ እንዲህ አይሁን እግዚአብሔርን እናመልካለን አሉት። 22ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን፦ እግዚአብሔርን እንድታመኩት እንደመረጣችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ አላቸው። እነርሱም፦ ምስክሮች ነን አሉ። 23እርሱም፦ አሁን እንግዲህ በመካከላችሁ ያሉትን እንግዶችን አማልክት አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አዘንብሉ አላቸው።24ሕዝቡም ኢያሱን፦ አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፥ ድምፁንም እንሰማለን፥ አሉ። 25በዚያን ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። በሴምም አዋጅንና ሕግን አደረገላቸው። 26ኢያሱም እነዚህን ቃላት ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ። ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው።27ኢያሱም ለሕዝቡ፦ ተመልከቱ፥ የተናገረነውን ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል። እግዚአብሔር የተናገርነውን ሁሉ ሰምቶአል። እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል አላቸው። 28ስለዚህም ኢያሱ ሕዝቡን ወደ እያንዳንዱ ርስት እንዲሄዱ አደረገ።29ከዚህ ነገር በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድሜው መቶ አሥር ዓመት ሞልቶት ሞተ። 30በተራራማውም በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በራሱ ርስት በተምና ሴራ ቀበሩት።31ኢያሱ በነረበት ዘመን ሁሉ፤ከኢያሱም በኋላ በነበሩት ለእስራኤልም ያደረገውን የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ባወቁት በሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አመለኩ።32የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ የወጡት የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴም አባት ከኤሞር ልጆች በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት። እርሱም በአንድ መቶ ብር ገዛው፤እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ። 33የአሮንም ልጅ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራውም በኤፍሬም አገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓ መሬት ቀበሩት።
1 ከኢያሱ ሞት በኋላ፣ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው ጠየቁ፡- “ከነዓናውያንን ለመዋጋት ወደላይ ስንሄድ ማን ይመራናል?”2እግዚአብሔርም አላቸው፡- “ይሁዳ ይመራችኋል፡፡ ተመልከቱ፣ ምድሪቱን ለእነርሱ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፡፡”3የይሁዳም ሰዎች ለወንድሞቻቸው ለስምዖን ሰዎች እንዲህ አሏቸው፡- “ከነዓናውያንን አብረን እንወጋቸው ዘንድ ከእኛ ጋር ለእኛ ወደተሰጠው ክልል ኑ፡፡ እኛም እንዲሁ ለእናንተ ወደተሰጠው ክልል እንመጣለን፡፡” ስለዚህም የስምዖን ነገድ ከእነርሱ ጋር ሄዱ፡፡4የይሁዳ ሰዎችም ወደ ላይ ወጡ፣ እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ በቤዜቅም ከእነርሱ አስር ሺህ ሰዎችን ገደሉ፡፡ 5አዶኒ ቤዜቅን በቤዜቅ አገኙት፣ ከእርሱም ጋር ተዋግተው ከነዓናውያንና ፌርዛውያንን አሸነፉ፡፡6አዶኒ ቤዜቅ ግን ሸሸ፣ ተከታትለውም አገኙትና ያዙት፣ የእጁንና የእግሩን አውራጣቶች ቆረጡ፡፡ 7አዶኒ ቤዜቅም እንዲህ አለ፡- “የእግርና የእጅ አውራ ጣቶቻቸው የተቆረጠባቸው ሰባ ነገስታት ከእኔ ማዕድ ስር መብላቸውን ሰበሰቡ፡፡ እኔ እንዳደረግሁት፣ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አደረገብኝ፡፡” እርሱንም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፣ በዚያም ሞተ፡፡8የይሁዳ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ከተማ ጋር ተዋግተው ተቆጣጠሯት፡፡ በሰይፍ ስለት ወጓት፣ ከተማዋንም አቃጠሏት፡፡ 9ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሰዎች በኮረብታማው አገር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ለመዋጋት፣ወደ ኔጌብና ወደ ምዕራቡ ኮረብታ ግርጌ ወረዱ፡፡ 10ይሁዳም በኬብሮን (የኬብሮን ስም ቀድሞ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር) የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ለመውጋት ሄደ፣ ሴሲን፣ አክመንና ቴላሚንም ድል አደረጉ፡፡11 ከዚያም የይሁዳ ሰዎች ወደ ዴብር (የዴብር ስም ቀድሞ ቅርያት ሤፍር ተብላ ትጠራ ነበር) ሄዱ፡፡12ካሌብም አለ፣ “ቅርያት ሤፍርን የሚዋጋና የሚቆጣጠራትን ሰው፣ ሴት ልጄን ዓክሳን ሚስት ትሆነው ዘንድ እሰጠዋለሁ፡፡”13የካሌብ ታናሽ ወንድም የቄናዝ ልጅ ጎቶንያልም ዴብርን ተቆጣጠረ፣ ስለዚህ ካሌብ ሴት ልጁን ዓክሳን ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፡፡14 ዓክሳም ወዲያውኑ ወደ ጎቶንያል መጣች፣ ለእርሱም አባቷ እርሻ እንዲሰጣት እንዲለምነው ጠየቀችው፡፡ ከአሕያዋም በወረደች ጊዜ፣ ካሌብ እንዲህ ብሎ ጠየቃት፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?”15እርሷም እንዲህ አለችው፣ “በረከትን ስጠኝ፡፡ በኔጌብ ምድር ያለውን መሬት ሰጥተኸኛልና፣ የውሃ ምንጭንም ስጠኝ፡፡” ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት፡፡16የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮችም ከባለ ዘንባባዋ ከተማ ለቀው ከይሁዳ ሰዎች ጋር በኔጌብ ወዳለችው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ከይሁዳ ሰዎች ጋር በዓራድ አጠገብ ለመኖር ሄዱ፡፡ 17የይሁዳ ሰዎችም ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ሰዎች ጋር ሄዱና በጽፋት ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ወጓቸው፣ፈጽሞም አጠፏት፡፡ የከተማይቱም ስም ሔርማ ይባል ነበር፡፡18በተጨማሪ የይሁዳ ሰዎች ጋዛንና በዙርያዋ ያለውን አገር፣ አስቀሎናንና በዙርያዋ ያለውን አገር እንደዚሁም አቃሮንንና በዙርያዋ ያለውን አገር ሁሉ ተቆጣጠሩ፡፡ 19እግዚአብሔርም ከይሁዳ ሰዎች ጋር ነበር፣ የኮረብታማውንም አገር ተቆጣጠሩ፣ ነገር ግን በረባዳው ምድር የሚኖሩትን ሰዎች ማስወጣት አልቻሉም ነበር ምክንያቱም ነዋሪዎቹ የብረት ሰረገሎች ነበሯቸው፡፡20 ሙሴም እንደተናገረ ኬብሮንን ለካሌብ ሰጡት፣ እርሱም የዔናቅን ሶስት ልጆች ከዚያ አስወጣቸው፡፡21ነገር ግን የቢንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ኢያቡሳውያንን አላስወጧቸውም፡፡ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከዛሬ ድረስ ከቢንያም ሰዎች ጋር በኢየሩሳሌም ይኖራሉ፡፡22 የዮሴፍ ወገንም ቤቴልን ለመውጋት ተዘጋጁ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነበር፡፡23ቀድሞ ሎዛ ተብላ ትጠራ የነበረችውን ቤቴልን ለመሰለል ሰዎችን ላኩ፡፡24ሰላዮቹም ከከተማው አንድ ሰው ሲወጣ አዩ፣ እንዲህም አሉት፣ “ወደ ከተማው እንዴት መግባት እንደምንችል እባክህ አሳየን፣ ለአንተም ቸርነት እናደርግልሃለን፡፡”25እርሱም ወደ ከተማው መግቢያውን መንገድ አሳያቸው፡፡ እነርሱም በሰይፍ ስለት ከተማውን ወጉ፣ ያንን ሰውና ቤተሰቦቹንም እንዲያመልጡ አደረጓቻው፡፡ 26ሰውየውም ወደ ኬጢያውያን ሐገር ሄደና ከተማ ገነባ ስሙንም ሎዛ አለው፣ የዚያ ቦታ ስምም እስከዛሬ ሎዛ ነው፡፡27 የምናሴ ሰዎች በቤትሳንና በመንደሮቿ፣ በታዕናክና በመንደሮቿ፣ በዶርና በመንደሮቿ፣ በይብለዓምና በመንደሮቿ፣ በመጊዶና በመንደሮቿ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አላስወጡአቸውም፣ ምክንቱም ከነዓናውያን በዚያ ለመቀመጥ ወስነው ስለነበር ነው፡፡ 28እስራኤልም በበረታ ጊዜ፣ ከነዓናውያንን የጉልበት ስራ እየሰሩ እንዲያገለግሉአቸው አስገደዷቸው፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አላስወጧቸውም፡፡29 ኤፍሬም በጌዝር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያን አላስወጣቸውም፣ ስለዚህ ከነዓናውያን በእነርሱ መካከል በጌዝር መኖር ቀጠሉ፡፡30ዛብሎንም በቂድሮን የሚኖሩትን ሰዎች ወይም በነህሎል ይኖሩ የነበሩትንም ሰዎች አላስወጣቸውም፣ ስለዚህ ከነዓናውያን በእነርሱ መካከል መኖር ቀጠሉ፣ ነገር ግን ዛብሎን ከነዓናውያን የጉልበት ስራ እየሰሩ እንዲያገለግሉአቸው ያስገድዳቸው ነበር፡፡31 አሴር በዓኮ፣ በሲዶን፣ በአሕላብ፣ በአክዚብ፣ በሒልባን፣ በአፌቅ፣ በረአብም የሚኖሩትን ሰዎች አላስወጣቸውም፡፡ 32ስለዚህ የአሴር ነገድ በምድሪቱ በሚኖሩት በከነዓናውያን መካከል ኖሩ፣ ምክንያቱም አላስወጧቸውም ነበር፡፡33የንፍታሌም ነገድ በቤት ሳሚስና በቤት ዓናት ይኖሩ የነበሩትን ሰዎችን አላስወጧቸውም፡፡ ስለዚህ የንፍታሌም ነገድ በምድራቸው ይኖሩ በነበሩ በነዓናውያን ሰዎች መካከል አብረው ኖሩ፡፡ ይሁን እንጂ የቤት ሳሚስና የቤት ዓናት ነዋሪዎች ለንፍታሌም ሰዎች የጉልበት ስራ እንዲሰሩ ይገደዱ ነበር፡፡34 አሞራውያንም የዳን ነገድ በኮረብታማው አገር እንዲኖሩ አስገደዷቸው፣ ወደ ሜዳማ ስፍራ ወርደው እንዲኖሩ አልፈቀዱላቸውም ነበር፡፡ 35ስለዚህ አሞራውያን በሔሬስ ተራራ፣ በኤሎን፣ በሸዓልቢምም ኖሩ፣ ነገር ግን የዮሴፍ ቤት ወታደራዊ ኃይል በእነርሱ ላይ በረቱባቸው፣ ከዚህ የተነሳ ከባድ የጉልበት ስራ እየሰሩ 36የአሞራውያንም ድንበር በሴላ ካለው ከአቅረቢም ኮረብታ ጀምሮ እስከ ኮረብታማው አገር ድረስ ነው፡፡
1የእግዚአብሔር መልዓክም ከጌልጌላ ወደ ቦኪም ወጣ፣ እንዲህም አለ፣ “ከግብጽ አወጣኋችሁ፣ ለአባቶቻችሁ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፡፡ እንዲህም አልሁ፣ ‘ከእናንተ ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን አላፈርስም፡፡ 2በዚህ ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ፡፡ መሰዊያቸውን ማፍረስ አለባችሁ፡፡’ እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም፡፡ ይህ ያደረጋችሁት ምንድን ነው?3 አሁንም እላለሁ፣ ‘ከነዓናውያንን ከእናንተ ፊት አላወጣም፣ ነገር ግን እነርሱ የጎን እሾህ ይሆኑባችኋል፣ ጣዖቶቻቸውም ለእናንተ ወጥመድ ይሆናሉ፡፡’”4የእግዚአብሔር መልዓክም እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ጮሁ አለቀሱም፡፡5ያንንም ቦታ ቦኪም ብለው ጠሩት፡፡ በዚያም ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረቡ፡፡6 ኢያሱም ሰዎችን ወደ መንገዳቸው በላካቸው ጊዜ፣ የእስራኤል ሕዝብ ምድሩን ለመውሰድና የራሳቸው ለማድረግ ለእንዳንዳቸው ወደተመደበላቸው ቦታ ሄዱ፡፡7ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራንና ለእስራኤል ምን እንዳደረገም ያዩ ከእርሱ በኋላም በኖሩ ሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አገለገለ፡፡8የእግዚአብሔር አገልጋይ፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ በመቶ አስር ዓመቱ ሞተ፡፡9እነርሱም በኤፍሬም ኮረብታማው አገር በሰሜናዊው ገአስ ተራራ በምድሪቱ ድንበር በተዘጋጀለት ቦታ በተምናሔሬስ ቀበሩት፡፡ 10ያ ሁሉ ትውልድም ወደ አባቶቻቸው ተሰበሰቡ፡፡ ከእነርሱም በኃላ እግዚአብሔርንና እርሱ ለእስራኤል ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሳ፡፡11 የእስራኤል ሕዝብም በእግዚአብሔር ዓይን ክፉ የሆነውን ነገር አደረጉ፣ የበኣል አማልክትንም አመለኩ፡፡12ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፡፡ ሌሎች አማልክትን፣ በዙርያቸው የነበሩ ሕዝቦች አማልክትን ተከተሉ፣ ለእነርሱም ሰገዱ፡፡ እግዚአብሔርንም አስቆጡት ምከንያቱም13እግዚአብሔርን ትተዋልና፣ በኣልንና አስታሮትንም አምልከዋልና፡፡14 የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ ንብረታቸውን ለሰረቋቸው ወራሪዎች አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ራሳቸውን ከጠላታቸው መከላከል እንዳይችሉ፣ በዙርያቸው በጠላቶቻቸው ብርታት ተይዘው እንደ ነበሩት ባርያዎች አሳልፎ ሸጣቸው፡፡15እስራኤል ለውጊያ በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ፣ ለእነርሱ እንደማለላቸው ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ይከፋ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ እነርሱም በጣም ተጨነቁ፡፡16ያን ጊዜ ንብረታቸውን ከሚሰርቋቸው ሰዎች ኃይል ያድናቸው ዘንድ እግዚአብሔር መሳፍንትን አስነሳላቸው፡፡ 17ይሁን እንጂ እነርሱ መሳፍንቶቻቸውን ሊሰሟቸው አልቻሉም፡፡ ለእግዚአብሔር አልታመኑም፣ ራሳቸውንም እንደ አመንዝራዎች ለሌሎች አማልክት ሰጡ፣ አመለኳቸውም፡፡ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይከተሉ ከነበሩት ከአባቶቻቸው መንገድ ወዲያውኑ ዘወር አሉ፣ እነርሱ ራሳቸው እንደ አባቶቻቸው አላደረጉም፡፡18እግዚአብሔር ለእነርሱ መሳፍንትን ባስነሳላቸው ጊዜ፣ መሳፍንቱ በኖሩበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር መሳፍንቱን ረዳቸው፣ ከጠላቶቻቸውም ጉልበት ሁሉ አዳናቸው፡፡ በጨቆኗቸውና መከራ ባሳዩአቸው ሰዎች ምክንያት ወደ እርሱ በጮኹ ጊዜ እግዚአብሔር ለእነርሱ አዘነላቸው፡፡ 19ነገር ግን መስፍኑ በሞተ ጊዜ፣ ተመልሰው አባቶቻው ያደርጉ ከነበረውም እጅግ የከፋ ነገር አደረጉ፡፡ ሌሎች አማልክትን በመከተል እነርሱን ያገለግሉና ያመልኩ ነበር፡፡ ክፉ ድርጊታቸውንና እልኸኛ መንገዳቸውንም ለመተው ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡20የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ እንዲህም አለ፣ “ይህ ሕዝብ ለአባቶቻቸው የገባሁትን ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱ፣ ድምጼንም ስላልሰሙ 21ከአሁን በኋላ ኢያሱ ሲሞት ሳያወጣቸው የተዋቸውን አሕዛብ ከፊታቸው አላወጣቸውም፡፡ 22ይህን የማደርገው እስራኤል አባቶቻቸው እንዳደረጉት የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁና በዚያም ይሄዱ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እፈትናቸው ዘንድ ነው፡፡” 23እግዚአብሔርም እነዚያን አሕዛብ የተዋቸው፣ በፍጥነትም ያላስወጣቸው፣ ኢያሱም እንዲያሸንፋቸው ያልፈቀደለት ለዚህ ነው፡፡
1እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ሳያስወጣ ያስቀራቸው እስራኤልን ይልቁንም ደግሞ በከነዓን በተደረጉት ጦርነቶች ያልተዋጉትን በእስራኤል የሚገኙትን እያንዳንዱ ሰው ይፈትን ዘንድ ነው፡፡ 2(ይህንን ያደረገው ውጊያ የማያውቁትን አዲሱ የእስራኤል ትውልድ ውጊያን ለማስተማር ነው) ፡- 3አምስቱ የፍልስጤማውያን ነገስታት፣ ከነዓናውያንም ሁሉ፣ ሲዶናውያን እና ከበዓልኤርሞንየም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች ይኖሩ የነበሩትም ኤውያውያን ነበሩ፡፡4 እነዚህ ሕዝቦች ሳይወጡ እንዲቀሩ የተደረጉት እግዚአብሔር እስራኤልን መፈተኛ እንዲሆኑ ነው፣ እነርሱ ለአባቶቻቸው በሙሴ በኩል የሰጣቸውን ሕግ ይታዘዙና አይታዘዙ እንደሆነ ለማረጋገጥ ነው፡፡5ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፌርዛውያን ከኤውያውያንና ከኢያቡሳውያን ጋር አብረው ኖሩ፡፡6ሴት ልጆቻቸውንም ሚስት እንዲሆኗቸው ወሰዷቸው፣ የራሳቸውን ሴት ልጆችም ለወንድ ልጆቻቸው ሰጧቸው፣ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ፡፡7 የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ዓይን ጸያፍ የነበረውን ነገር ፈጸሙ፣ አምላካቸው እግዚአብሔርንም ረሱ፡፡ የኣልንና የአስታሮትን አማልክት አመለኩ፡፡8ስለዚህም የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ ለመስጶጣምያ ንጉስ ለኩሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ የእስራኤል ሕዝብም ኩሰርሰቴን ለስምንት አመታት አገለገሉ፡፡9የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር በጮሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ለመርዳት የሚመጣና ካሉበት ሁኔታም የሚያድናቸው ሰው አስነሳ፡- ይህም ሰው የካሌብ ታናሽ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ነበር፡፡ 10የእግዚአብሔር መንፈስም አበረታው፣ እስራኤላውያን ላይም ይፈርድ ነበር፣ ወደ ውጊያም ይወጣ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በመስጶጣምያ ንጉስ በኩሰርሰቴ ላይ ድልን ሰጠው፡፡ ኩሰርሰቴንም ያሸነፈው የጎቶንያል እጅ ነበር፡፡ 11ምድሪም ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች፡፡ የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያልም ሞተ፡፡12የእስራኤልም ሕዝብ ክፉ ነገሮችን በማድረግ ደግመው እግዚአብሔርን ሳይታዘዙ ቀሩ፣ እርሱም ምን እንዳደረጉ ተመለከተ፡፡ ስለዚህ እስራኤል ክፉ ነገሮችን ስላደረጉና፣ እግዚአብሔርም ስላያቸው የሞኣብ ንጉስ ኤግሎም እስራኤልን ለመውጋት በመጣ ጊዜ እግዚአብሔር ብርታትን ሰጠው፡፡ 13ኤግሎምም ከአሞንና ከአማሌቃውያን ጋር ተባበረ፣ እነርሱም ሄዱ እስራኤልንም አሸነፉ፣ ከዚያም የዘንባባ ከተማን ተቆጣጠሩ፡፡ 14የእስራኤልም ሕዝብ የሞኣብን ንጉስ ኤግሎምን ለአስራ ስምንት አመታት አገለገሉ፡፡15ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር በጮሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሚረዳቸውን ሰው አስነሳ፣ ይህም ግራኝ የነበረው ብንያማዊው የጌራን ልጅ ናኦድ ነው፡፡ የእስራኤልም ሕዝብ እርሱን ወደ ሞኣብ ንጉስ ወደ ኤግሎም የሚከፍሉትን ግብር አስይዘው ላኩት፡፡16 ናኦድ በሁለት በኩል የተሳለ ርዝመቱ አንድ ክንድ የሆነ ሰይፍን ሰራ፤ ከልብሱም በታች በቀኝ ጭኑ አሰረው፡፡ 17ግብሩንም ለሞኣብ ንጉስ ለኤግሎም ሰጠው፡፡ (ኤግሎም በዚያን ጊዜ እጅግ ወፍራም ሰው ነበር፡፡) 18ናኦድም የግብሩን ክፍያ ካቀረበ በኋላ፣ ግብሩን ተሸክመው ገብተው ከነበሩ ሰዎች ጋር ወጣ፡፡19 ይሁን እንጂ ናኦድ በጌልጌላ አጠገብ የተቀረጹ ምስሎች ተሰርተውበት ወደነበረው ስፍራ ሲደርስ ተመልሶ ሄደና እንዲህ አለ፡- “ንጉስ ሆይ፣ ለአንተ የሚስጥር መልዕክት አለኝ፡፡” ኤግሎምም እንዲህ አለ፡- “ጸጥታ!” ስለዚህም አገልጋዮቹ ሁሉ ክፍሉን ትተው ወጡ፡፡ 20ናኦድም ወደ እርሱ መጣ፡፡ ንጉሱም ቀዝቃዛ በሆነው ሰገነት ላይ ብቻውን ተቀምጦ ነበር፡፡ናኦድም እንዲህ አለ፣ “ለአንተ ከእግዚአብሔር የመጣ መልዕክት አለኝ፡፡” ንጉሱም ከመቀመጫው ተነሳ፡፡21ናኦድም ግራ እጁን ዘረጋና ሰይፉን ከቀኝ ጭኑ አወጣ፣ ሰይፉንም በንጉሱ ሰውነት ውስጥ ሰካው፡፡ 22የሰይፉም እጀታ ከስለቱ ጋር ወደ ሰውነቱ ገባ፣ ጫፉም በጀርባው ወጣ፣ ሞራም ስለቱን ሸፈነው፣ ናኦድም ሰይፉን ከንጉሱ ሰውነት አላወጣውም፡፡ 23ከዚያም ናዖድ ወደ በረንዳው ወጣና የሰገነቱን በር በንጉሱ ላይ ዘግቶ ቈለፈው፡፡24ናዖድም ከሄደ በኋላ፣ የንጉሱ ባሪያዎች መጡ፤ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ አዩ፣ ስለዚህ እንዲህ ሲሉ አሰቡ፣ “ምናልባት በቀዝቃዛው ሰገነት ውስጥ እየተጸዳዳ ይሆናል፡፡” 25ንጉሱ የሰገነቱን በር ሳይከፍት በቆየም ጊዜ ስራቸውን ችላ እንዳሉ እስኪሰማቸው ድረስ ስጋት እያደረባቸው ጠበቁ፡፡ ስለዚህ ቁልፉን ወሰዱና በሮቹን ከፈቱ፣ እነሆም ጌታቸው ተጋድሞ፣ በወለሉም ላይ ወድቆ፣ ሞቶም አገኙት፡፡26 ባርያዎቹ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እያሰቡ ሲጠባበቁ፣ ናዖድ አመለጠ፣ የጣኦታት ምስል በተቀረጸበት ስፍራ በኩል አለፈ፣ ወደ ቤይሮታም አመለጠ፡፡ 27በደረሰም ጊዜ፣ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ቀንደ መለከት ነፋ፡፡ ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ ከእርሱ ጋር ከኮረብታማው አገር ወረዱ፣ እርሱም ይመራቸው ነበር፡፡28 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ተከተሉኝ፣ እግዚአብሔር ጠላቶቻችሁን፣ ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና፡፡” እነርሱም ተከትለውት ወረዱና የዮርዳኖስን መሻገርያ ከሞዓባውያን ቀምተው ያዙ፣ እነርሱም ማንም ሰው ወንዙን እንዳይሻገር ከለከሉ፡፡29በዚያን ጊዜም ከሞዓብ አሥር ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ገደሉ፣ የተገደሉትም ሁሉ ጠንካራና ኃይለኛ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድም እንኳ አላመለጠም፡፡30በዚያም ቀን ሞዓብ በእስራኤል ብርታት ድል ሆነች፡፡ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ዐረፈች፡፡31ከናኦድ በኋላ የተነሳው መስፍን ስድስት መቶ የፍልስጥኤም ሰዎችን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሰሜጋር ነበር፡፡ እርሱም ደግሞ እስራኤልን ከአደጋ አዳነ፡፡
1 ናዖድም ከሞተ በኋላ፣ የእስራኤል ሕዝብ ክፉ ነገሮችን በመስራት እንደገና እግዚአብሔርን አልታዘዙም፣ እርሱም ምን እንዳደረጉ ተመለከተ፡፡ 2እግዚአብሔርም በሐጾር ሆኖ ይገዛ በነበረው፣ በከነዓን ንጉሥ በኢያቢስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ የሠራዊቱም አለቃ ሲሣራ ተብሎ ይጠራ ነበር፣ እርሱም የአሕዛብ በሆነችው በአሪሶት ኖረ፡፡ 3የእስራኤልም ሕዝብ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፣ ምክንያቱም ሲሳራ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩት፣ እርሱም የእስራኤልን ሕዝብ ለሀያ ዓመት በኃይል አስጨንቆ ገዛቸው፡፡4በዚያ ጊዜ ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ፣ በእስራኤል ላይ ዋነኛ ፈራጅ ነበረች፡፡ 5እርስዋም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዘንባባ ዛፍ ስር ትቀመጥ ነበር፣ የእስራኤልም ሕዝብ ለክርክራቸው መፍትሔ ለማግኘት ወደ እርስዋ ይመጡ ነበር፡፡6 እርስዋም በንፍታሌም ውስጥ ካለው ከቃዴስ የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን ጠራች፡፡ እንዲህም አለችው፣ “የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይልሃል፣ ‘ወደ ታቦር ተራራ ሂድ፣ ከንፍታሌምና ከዛብሎን አሥር ሺህ ሰዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፡፡ 7እኔ የኢያቢስን ሠራዊት አዛዥ ሲሣራን በቂሶን ወንዝ አቅራቢያ ከሰረገሎቹና ከሰራዊቱ ጋር እንዲያገኝህ አስወጣዋለሁ፣ እኔም በእርሱ ላይ ድልን እሰጥሃለሁ፡፡’”8-9ባርቅም እንዲህ አላት፣ “አንቺ ከእኔ ጋር ከሄድሽ እኔም እሄዳለሁ፣ ነገር ግን አንቺ ከእኔ ጋር ካልሄድሽ እኔም አልሄድም፡፡” እርስዋም እንዲህ አለች፣ “በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፡፡ ይሁን እንጂ፣ አንተ የምትሄድበት መንገድ ወደ ክብር አያደርስህም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሲሣራን በጥንካሬዋ ድል ታደርገው ዘንድ ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና፡፡” ከዚያም ዲቦራ ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች፡፡10 ባርቅም የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች በአንድነት ወደ ቃዴስ እንዲመጡ ጠራቸው፡፡ አሥር ሺህም ሰዎች ተከተሉት፣ ዲቦራም ከእርሱ ጋር ሄደች፡፡11 ቄናዊው ሔቤርም ከቄናውያን ራሱን ለየ፣ እነርሱም የሙሴ አማት የኦባብ ልጆች ነበሩ፣ እርሱም በቃዴስ አጠገብ በጻዕናይም በነበረው በበሉጥ ዛፍ ጥግ ድንኳኑን ተከለ፡፡12ለሲሳራም የአቢኔኤም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደወጣ በነገሩት ጊዜ፣ 13ሲሣራም ሰረገሎቹን ሁሉ፣ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ወታደሮቹን ሁሉ፣ የአሕዛብ ከሆነችው ከአሪሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰባቸው፡፡14ዲቦራም ባርቅን እንዲህ አለችው፣ “ሂድ! ዛሬ እግዚአብሔር በሲሣራ ላይ ድል እንድታደርግ በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ነውና፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ከፊትህ አልወጣምን?” ስለዚህ ባርቅ ከታቦር ተራራ አብረውት ከነበሩት አስር ሺህ ሰዎች ጋር ወረደ፡፡15 እግዚአብሔርም የሲሣራን ሰራዊት ግራ አጋባ፣ ሰረገሎቹንም ሁሉ፣ ሠራዊቱንም ሁሉ፣ የባርቅም ሰዎች የሲሳራን ሰዎች አጠቋቸው፣ ሲሳራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ፡፡ 16ባርቅ ግን ሰረገሎችንና ሠራዊቱን እስከ አሪሶት ድረስ አባረራቸው፣ የሲሣራም ሠራዊት ሁሉ በሰይፍ ስለት ተገደሉ፣ አንድ ሰው እንኳ አልቀረም፡፡17 ሲሳራ ግን በእግሩ ወደ ቄናዊው ሔቤር ሚስት፣ ወደ ኢያዔል ድንኳን ሸሸ፣ ምክንያቱም በሐሶር ንጉስ በኢያቢስና፣ በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ስለነበር ነው፡፡ 18ኢያዔልም ሲሣራን ለመገናኘት ወጣች እንዲህም አለችው፣ “ግባ፣ ጌታዬ ሆይ፤ ወደ እኔ ግባ አትፍራም፡፡” እርሱም ወደ እርስዋ ወደ ድንኳንዋ ገባ፣ በብርድ ልብስም ሸፈነችው፡፡19 እርሱም እንዲህ አላት፣ “ጠምቶኛልና፣ እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጭኝ፡፡” እርስዋም ከቆዳ የተሰራ የወተቱን ማስቀመጫ ከፍታ የሚጠጣ ሰጠችው፣ ከዚያም እንደገና ሸፈነችው፡፡ 20እርሱም አላት፣ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፡፡ ሰውም ቢመጣና ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠይቅሽ ‘የለም’ በይ፡፡”21 ከዚያም የሔቤር ሚስት ኢያዔል የድንኳን ካስማ ወሰደች በእጅዋም መዶሻ ያዘች በቀስታ ወደ እርሱ ሄደች፣ እርሱም በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር፣ እርስዋም ካስማውን በጆሮ ግንዱ ላይ ሰካችው፣ ካስማውም ሰውነቱን ወግቶ አለፈና ወደ መሬት ጠለቀ፡፡ እርሱም ሞተ፡፡22ባርቅም ሲሣራን ሲያባርር፣ ኢያዔል ልታገኘው ወጣችና እንዲህ አለችው፣ “ና፣ የምትፈልገውንም ሰው አሳይሃለሁ፡፡” እርሱም ወደ ውስጥ ከእርስዋ ጋር ገባ፣ እነሆም በዚያ ሲሣራ ሞቶ ተጋድሞ ነበር፣ ካስማውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ተሰክቶ አገኘው፡፡”23 ስለዚህ በዚያ ቀን እግዚአብሔር የከነዓንን ንገሥ ኢያቢስን በእስራኤል ሕዝብ ፊት አሸነፈው፡፡ 24የእስራኤል ሕዝብ ጉልበት የከነዓን ንጉሥ ኢያቢስን እስከሚያጠፉ ድረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መጣ፡፡
1 በዚያም ቀን ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህንን መዝሙር ዘመሩ፡- 2“በእስራኤል ውስጥ መሪዎች የመሪነት ስፍራውን ሲይዙ፣ ሕዝቡም በደስታና በፈቃዳቸው ለጦርነት ሲወጡ፣ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን!3 ስሙ፣ እናንተ ነገሥታት! አድምጡ፣ እናንተም መኳንንት! እኔ፣ እኔ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋናን እዘምራለሁ፡፡4እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ ከኤዶምያስም በተነሳህ ጊዜ፣ ምድር ተናወጠች፣ ሰማያት ደግሞ ተንቀጠቀጡ፤ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠባጠቡ፡፡5ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት ተንቀጠቀጡ፤ ሲና ተራራም እንኳ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተንቀጠቀጠ፡፡ 6በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣ በኢያዔል ዘመን፣ መንገዶች ተተዉ፣ መንገደኞችም በጠመዝማዛ መንገድ ብቻ ይጠቀሙ ነበር፡፡7 እኔ ዲቦራ አለቃ እስከሆንሁበት ጊዜ ድረስ፣ ለእስራኤል እናት ሆኜ አለቅነትን እስከወሰድሁበት ጊዜ ድረስ፣ በእስራኤል ውስጥ ገበሬዎች አልነበሩም፡፡ 8አዲስ አማልክትን መረጡ፣ በከተማዋ ደጆች ጦርነት ነበረ፤ በእስራኤል ውስጥ በአርባ ሺህ መካከል ጋሻ ወይም ጦር አልታየም፡፡9 ልቤ ወደ እስራኤል አለቆች ሄደ፣ በሕዝቡ መካከል ራሳቸውን በደስታ ስለ ሰጡትም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ 10እናንተ በነጫጭ አህዮች ላይ ትንሽ የምንጣፍ ኮርቻ ላይ ተቀምጣችሁ የምትጓዙ፣ በመንገድም የምትሄዱ እናንተ ስለዚህ ነገር አስቡ፡፡11በማጠጫው ስፍራ መካከል ሆነው በጎችን የሚከፋፍሉትን ሰዎች ድምጽ ስሙ፡፡ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ድርጊትና ተዋጊዎቹ በእስራኤል ውስጥ የሰሩትን የጽድቅ ተግባር በዚያ እንደገና እየተናገሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ ከተማው በሮች ወረዱ፡፡12 ንቂ፣ ንቂ፣ ዲቦራ ሆይ! ንቂ፣ ንቂ፣ መዝሙርን ዘምሪ! ባርቅ ሆይ፣ ተነሣ፣ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፣ ምርኮኞችህን ማርከህ ውሰድ፡፡13የዚያን ጊዜ የተረፉት ወደ ኃያላኑ መጡ፣ ከተዋጊዎቹም መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ እኔ መጡ፡፡14 መሰረታቸው ከአማሌቅ ወገን የሆኑ ከኤፍሬም መጡ፤ የብንያም ሕዝብም ተከተሉህ፡፡ ከማኪርም አዛዦች ወረዱ፣ የስልጣን በትር የያዙ ከዛብሎን ወረዱ፡፡15 የይሳኮርም መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ ይሳኮርም ከባርቅ ጋር በትዕዛዙ መሰረት ከኋላው እየተከተለ ወደ ሸለቆው ሄደ፡፡ በሮቤል ጎሳ መካከል ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ፡፡16የበጎች እረኞች ለመንጎቻቸው በፉጨት ሲጫወቱ እያዳመጥህ በእሳት ማንደጃ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ጎሳ መካከል ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ፡፡17 ገለዓድ በዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤ ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ቀረ? አሴርም በባሕሩ ዳርቻ ቀረ፣ በወንዞቹም ዳርቻ ኖረ፡፡18ዛብሎን ነፍሱን ወደ ሞት አሳልፎ የሚሰጥ ሕዝብ ነው፣ ንፍታሌምም በውጊያ ሜዳ ላይ ነው፡፡19 ነገሥታት መጡ ተዋጉም፣ የዚያን ጊዜ የከነዓን ነገስታትም በመጊዶ ውኆች አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፡፡ ምንም የብር ምርኮ አልወሰዱም፡፡20ከሰማይ ከዋክብት ተዋጉ፣ በሰማያት ላይ በአካሄዳቸውም ሲሣራን ተዋጉት፡፡21 ከዱሮ ጀምሮ የታወቀው፣ የቂሶን ወንዝም፣ ጠርጎ ወሰዳቸው፡፡ ነፍሴ ሆይ ገስግሺ፣ በርቺ! 22የፈረሶች የግልብያ ኮቴዎች ድምጽ፣ የኃያላኑ ግልቢያ ድምጽም፡፡23የእግዚአብሔር መልአክ “ሜሮዝን እርገሙ!” ይላል፡፡ ‘ነዋሪዎቿን ፈጽማችሁ እርገሙ! ምክንያቱም እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡም፣ ከኃያላን ጦረኞች ጋር በተደረገው ውጊያ እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡምና፡፡'24 የቄናዊው የሔቤር ሚስት፣ ኢያዔል፣ ከሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ናት፣ በድንኳን ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ናት፡፡ 25ሰውየው ውኃ ለመናት፣ እርስዋም ወተት ሰጠችው፤ ለመሳፍንት በሚሆን በተከበረ ሳህን ቅቤ አመጣችለት፡፡26 እጅዋን ወደ ድንኳን ካስማ፣ ቀኝ እጅዋንም ወደ ሠራተኛ መዶሻ አደረገች፤ በመዶሻውም ሲሣራን መታች፣ ራሱንም ቀጠቀጠች፡፡ ጆሮ ግንዱን በወጋችው ጊዜ ጭንቅላቱንም ፈረከሰችው፡፡ 27በእግሮችዋ መካከል ተደፋ፣ ወደቀ ተኛም፡፡ በእግሮችዋ አጠገብ ተሰብሮ ወደቀ፡፡ የተደፋበት ስፍራ በክፉ ሁኔታ የሞተበት ነው፡፡28ከመስኮት ሆና ወደ ውጭ ተመለከተች፣ የሲሣራ እናት በርብራብ በኩል በኃዘን ወደ ውጭ ጮኸች፣ ‘ወደዚህ ለመምጣት ሰረገላው ረዥም ጊዜ ለምን ወሰደበት? ለምንስ ሰረገላዎቹን የሚጎትቱት የፈረሶቹ ኮቴዎች ዘገየ?’29 ብልሃተኞች ልዕልቶቿም መለሱላት፣ ለራስዋም ተመሳሳይ መልስ መለሰች፡- 30ምርኮውን አግኝተው ተካፍለው የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረድ፤ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ቀለም ያለው ልብስ፣ የተጠለፈ ባለቀለም ጨርቅ ምርኮ፣ ለማረኩ ሰዎች ለአንገታቸው የሚሆን በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ባለቀለም ጨርቆች ምርኮን አላገኙምን?’31 ስለዚህ፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ! ነገር ግን እርሱን የሚወዱት በኃይል እንደሚወጣ ጸሐይ ይሁኑ፡፡” ምድሪቱም ለአርባ ዓመት ያህል ዐረፈች፡፡
1 የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ሥራ ሠሩ፤ እርሱም በምድያም ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ለሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ 2የምድያምም ኃይል በእስራኤል ላይ በረታ፡፡ ከምድያምም የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ በኮረብታዎች ላይ ጕድጓድ፣ ዋሻና ምሽግም ለራሳቸው መሸሸጊያ አበጁ።3እንዲህም ሆነ፣ እስራኤል ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና ከምሥራቅም የመጡ ሰዎች እስራኤላውያንን ያጠቁ ነበር፡፡ 4ሰራዊታቸውን በምድሪቱ ላይ ያሰፍሩና እስከ ጋዛ ድረስ ያለውን ሰብል ያጠፉ ነበር፡፡ በእስራኤልም ምንም መብል፣ በጎች፣ ከብቶችና አህያዎች አይተዉም ነበር፡፡5 እነርሱ እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ እንደ አንበጣ መንጋ ሆነው ይመጡ ነበር፤ እነርሱንና ግመሎቻቸውንም መቁጠር አይቻልም ነበር፡፡ ምድሪቱንም ያጠፉ ዘንድ ይወርሩአት ነበር፡፡6ምድያም እስራኤልን ክፉኛ ከማዳከማቸው የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡7 የእስራኤል ሕዝብ በምድያም ምክንያት ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ፣ 8እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ልጆች ነቢይ ላከ፡፡ ነቢዩም እንዲህ አለ፡- “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ‘እኔ ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤ ከባርነትም ቤት አወጣኋችሁ፡፡9 ከግብፃውያንም እጅ እንደዚሁም ይጨቁኑአችሁ ከነበሩ ኃይላት ሁሉ አዳንኋችሁ፡፡ ከፊታችሁም አሳድጄ አወጣኋቸው፣ ምድራቸውንም ሰጠኋችሁ፡፡ 10ለእናንተንም እንዲህ አልኋችሁ፣ “እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን፣ የአሞራያውያንን አማልክት እንዳታመልኩ አዘዝኋችሁ፡፡ ነገር ግን እናንተ ድምጼን አልታዘዛችሁም፡፡11 የእግዚአብሔርም መልአክ መጣና በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው ለኢዮአስ በነበረችው ከበሉጥ ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን ከምድያማውያን ለመሸሸግ በወይን መጥመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር፡፡ 12የእግዚአብሔርም መልአክ ለእርሱ ተገልጠለትና እንዲህ አለው፣ “አንተ ብርቱ ተዋጊ ሰው፣ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለው!”13ጌዴዎንም ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ይህ ነገር ሁሉ ለምን በእኛ ላይ ደረሰብን? አባቶቻችንስ የነገሩን እርሱ የሰራቸው አስደናቂ ነገሮች ወዴት አሉ፣ እንዲህ ብለው የነገሩን፣ ‘እግዚአብሔር ከግብፅ አላወጣንምን?’ አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፣ ለምድያማውያንም ብርታት አሳልፎ ሰጥቶናል፡፡14 እግዚአብሔርም ወደ እርሱ ተመለከተና እንዲህ አለው፣ “በዚህ ባለህ ብርታት ሂድ፡፡ እስራኤልንም ከምድያም ኃይል አድን፤ እነሆ እኔ አልላክሁህምን?”15ጌዴዎንም እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ እባክህ፣ እኔ እስራኤልን እንዴት ማዳን እችላለሁ? ተመልከት፣ የእኔ ቤተሰብ ከምናሴ ነገድ ከሁሉ ይልቅ ደካማ ነው፣ እኔም በአባቴ ቤት ውስጥ የመጨረሻ ነኝ፡፡16 እግዚአብሔርም፣ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፣ አንተም የምድያምን ሰራዊት በሙሉ ታሸንፋለህ” አለው፡፡17ጌዴዎንም እንዲህ አለው፣ “በእኔ ደስተኛ ከሆንህ፣ የምትናገረኝ አንተ እንደሆንህ እርግጠኛ እሆን ዘንድ ምልከትን ስጠኝ፡፡18ወደ አንተ እስክመጣና መስዋእቴን አምጥቼ በፊትህ እስካቀርብ ድረስ እባክህ ከዚህ አትሂድ፡፡” እግዚአብሔርም “እስክትመለስ ድረስ እቆያለሁ” አለ፡፡19 ጌዴዎን ሄደ የፍየሉንም ጠቦት አረደ፣ የኢፍ መስፈሪያም ዱቄት ወስዶ ያልቦካ ቂጣ አዘጋጀ፡፡ ሥጋውን በቅርጫት አኖረ፣ መረቁንም በምንቸት ውስጥ አኖረ፣ ሁሉንም ይዞ በበሉጥ ዛፍ በታች አቀረበለት፡፡20የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ አለው፣ “ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ ውሰድና በዚህ ድንጋይ ላይ አኑረው፣ መረቁንም በላዩ ላይ አፍስሰው፡፡” ጌዴዎንም እንዲሁ አደረገ፡፡21 የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ የያዘውን የበትሩን ጫፍ ወደዚያ ዘረጋ፡፡ በበትሩም ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ ነካው፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥቶ ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ በላ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ ሄደ፣ ጌዴዎንም ሊያየው አልቻለም፡፡22 ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አወቀ፡፡ ጌዴዎንም፣ “አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮልኝ! የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና” አለ፡፡23እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፣ “ሰላም ለአንተ ይሁን! አትፍራ፣ አትሞትም፡፡”24ስለዚህ ጌዴዎን በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፡፡ ስሙንም፣ እግዚአብሔር ሰላም ብሎ ጠራው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በአቢዔዝራውያን ጎሳ በምትሆነው በዖፍራ አለ፡፡25 እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት እንዲህ አለው፣ “የአባትህን በሬ፣ ሰባት ዓመት የሆነውን ሁለተኛውንም በሬ ውሰድ፣ የአባትህ የሆነውን የበኣል መሠዊያ አፍርስና በአጠገቡ ያለውን አሼራን ሰባብረው፡፡ 26በዚህ መሸሸጊያ ስፍራ ጫፍ ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ፣ በትክክለኛው መንገድም ስራው፡፡ ከአሼራ ሰባብረህ በጣልኸው እንጨት ሁለተኛውን በሬ የሚቃጠል መስዋእት አድርገህ አቅርበው፡፡”27 ስለዚህ ጌዴዎን ከባሪያዎቹ አሥር ሰዎችን ወሰደና እግዚአብሔር እንደነገረው አደረገ፡፡ ነገር ግን በቀን ለማድረግ የአባቱን ቤተ ሰቦችና የከተማውንም ሰዎች እጅግ በጣም ስለፈራ፣ በሌሊት አደረገው፡፡28 በማለዳ የከተማው ሰዎች በተነሱ ጊዜ፣ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ ነበር፣ በአጠገቡ የነበረውም አሼራ ተሰባብሮ ነበር፣ ሁለተኛውም በሬ አዲስ በተሰራው መሠዊያ ላይ ተሠውቶ ነበር፡፡ 29የከተማውም ሰዎች እርስ በርሳቸው፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ተባባሉ፡፡ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩና መልስ ሲፈልጉ ሳሉ፣ “ይህን ያደረገው የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ነው” አሉ፡፡30የዚያን ጊዜ የከተማው ሰዎች ኢዮአስን እንዲህ አሉት፣ “የበኣልን መሠዊያ አፍርሶአልና፣ በአጠገቡ የነበረውንም አሼራ ሰባብሮታልና እንዲሞት ልጅህን አውጣ፡፡”31 ኢዮአስም ለተቃወሙት በሙሉ እንዲህ አላቸው፣ “ለበኣል ትምዋገቱለታላችሁን? እርሱን ታድኑታላችሁን? ለእርሱ የሚምዋገትለት ሁሉ እስከ ነገ ጠዋት ይገደል፡፡ በኣል አምላክ ከሆነ፣ መሠዊያውን ሲያፈርሱበት ራሱን ይከላከል፡፡32ስለዚህም በዚያ ቀን ጌዴዎን “ይሩበኣል” የሚል ስም ተሰጠው፣ ምክንያቱም እርሱ “በኣል ራሱን ይከላከል” ብሏልና፣ ጌዴዎን መሠዊያውን አፍርሶአልና፡፡33 ምድያማውያንና አማሌቃውያን ሁሉ፣ የምሥራቅም ሰዎች አንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ ዮርዳኖስን ተሻግረው በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ ሰፈሩ፡፡34 ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ጌዴዎንን ሊረዳው በእርሱ ላይ ወረደ፡፡ ጌዴዎንም ቀንደ መለከት ነፋ፣ የአቢዔዝር ጎሳ ሰዎች ይከተሉት ዘንድ ጠራቸው፡፡35እርሱም ወደ ምናሴ ነገድ ሁሉ መልክተኞችን ሰደደ፣ እነርሱም ደግሞ እንዲከተሉት ተጠርተው ነበር፡፡ መልክተኞችንም ወደ አሴር፣ ዛብሎንና ንፍታሌምም ላከ፣ እነርሱም እርሱን ሊየገኙት ሄዱ፡፡36 ጌዴዎንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፣ “እንደ ተናገርኸው እስራኤልን ለማዳን እኔን የምትጠቀምብኝ ከሆነ37ተመልከት፣ በአውድማው ላይ የበግ ጠጕር ባዘቶ አኖራለሁ፡፡ በጠጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆንና በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፣ የዚያን ጊዜ እንደተናገርኸው አንተ እስራኤልን ለማዳን እንደምትጠቀምብኝ አውቃለሁ፡፡”38 እንዲሁም ሆነ፣ ጌዴዎን በነጋው ማልዶ ተነሣ፣ ጠጕሩንም በአንድ ላይ ጨመቀው፣ ከጠጕሩም የተጨመቀው ጠል አንድ ቆሬ ለመሙላት በቂ ሆነ፡፡39 ጌዴዎንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፣ “አትቈጣኝ፣ አንድ ጊዜ እንደገና እናገራለሁ፡፡ እባክህ፣ የጠጉሩ ባዘቶ በመጠቀም አንድ ተጨማሪ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፡፡ በዚህ ጊዜ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ይሁን፣ በምድሩና በዙርያውም ሁሉ ላይ ደግሞ ጠል ይሁን፡፡” 40እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት የጠየቀውን አደረገ፡፡ ጠጕሩ ደረቅ ነበረ፣ በምድሩም ሁሉ ላይ ጠል ነበረ፡፡
1 ከዚያም ጌዴዎን የተባለው ይሩበኣልና ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ በጠዋት ተነሡ፣ በሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ፡፡ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ፡፡2 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ምድያማውያንን እንድታሸንፍ የሚያደርጉህ እጅግ በጣም ብዙ ወታደሮች አሉኝ፡፡ ‘የራሳችን ኃይል አዳነን’ ብለው እስራኤል እንዳይታበዩብኝ እርግጠኛ ሁን፡፡ 3ስለዚህም አሁን፣ በሕዝቡ ጆሮዎች እንዲህ ብለህ ተናገር፣ “ማንም የፈራ ቢኖር፣ ማንም የደነገጠ ቢኖር፣ የገለዓድን ተራራ ትቶ ይመለስ፡፡” ስለዚህ 22, 000 ሰዎች ተመለሱ፣ 10, 000 ሰዎችም ቀሩ፡፡4 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ሕዝቡ አሁንም ገና ብዙ ነው፡፡ ሕዝቡን ወደ ውኃ ውሰዳቸው፣ በዚያም ቁጥራቸውን ጥቂት አደርግልሃለሁ፡፡ እኔ ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሄዳል’ ካልሁህ እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ነገር ግን እኔ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሄድም’ ካልሁህ እርሱ ከአንተ ጋር አይሄድም፡፡”5 ስለዚህ ጌዴዎን ሕዝቡን ወደ ውኃ ወሰዳቸው፣ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ውሻ እንደሚጠጣ ውኃ የሚጠጣውን ሁሉ፣ ውኃ ለመጠጣት በጕልበታቸው ከሚንበረከኩት ሰዎች መካከል ለይ፡፡”6ሦስት መቶ ሰዎች ውኃ እንደ ውሻ ጠጡ፡፡ የቀሩት ሰዎች ግን ውኃ ለጠጡ በጉልበታቸው ተንበረከኩ፡፡7 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ውኃን እንደ ውሻ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች ከምድያማውያን አድንሃለሁ፣ በእነርሱም ላይ ድል እሰጥሃለሁ፡፡ ሌሎቹ ሰዎች በሙሉ ወደ ስፍራቸው ይመለሱ፡፡”8ስለዚህ የተመረጡት ሰዎች ስንቃቸውንና ቀንደ መለከታቸውን ወሰዱ፡፡ ጌዴዎን የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ፣ እያንዳንዱን ሰው ወደ ድንኳናቸው ሰደዳቸው፣ ነገር ግን ሦስቱን መቶ ሰዎች በእርሱ ዘንድ አቆያቸው፡፡ የምድያምም ሰፈር ከእርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበረ፡፡9 በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ተነስ! ሰፈራቸውን ምታ፣ በእነርሱ ላይ እኔ ድል እሰጥሃለሁና፡፡10ነገር ግን አንተ ወደ ለመውረድ ከፈራህ፣ ከአገልጋይህ ከፉራ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፣11የሚናገሩትንም አድምጥ፣ ከዚያም በኋላ ሰፈሩን ለመውጋት ድፍረት ታገኛለህ፡፡” ስለዚህ ጌዴዎን ከአገልጋዩ ከፉራ ጋር በሰፈሩ ወደ ነበሩት ጠባቂዎች ወረዱ፡፡12ብዛታቸውም እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና የምሥራቅም ሰዎች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፡፡ የግመሎቻቸውም ብዛት መቁጠር አይቻልም ነበር፤ ቁጥራቸው በባህር ዳርቻ ካለው አሸዋ ይልቅ የሚበልጥ ነበር፡፡13 ጌዴዎን በዚያ በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕልምን ለጓደኛው ሲነግረው ነበር፡፡ ሰውየውም እንዲህ አለ፣ “ተመልከት! ሕልም አለምሁ፣ አንዲት ክብ የገብስ ቂጣ ወደ ምድያም ሰፈር ተንከባልላ ስትወርድ አየሁ፡፡ ወደ ድንኳኑም ደረሰች፣ እስኪወድቅ ድረስም በጣም መታችው ከዚህ የተነሳ ወደቀ፣ ደግሞም ተገለበጠ፣ ስለዚህም ድንኳኑ ተጋደመ፡፡”14ሌላኛውም ሰው እንዲህ አለ፣ “ይህ ነገር ከእስራኤል ሰው ከኢዮአስ ልጅ ከጌዴዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በምድያምና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ ድል ሰጥቶታል፡፡”15 ጌዴዎን የሕልሙን ዝርዝርና ትርጓሜውን በሰማ ጊዜ በጸሎት ተደፍቶ ሰገደ፡፡ እርሱም ወደ እስራኤል ሰፈር ሄደና እንዲህ አለ፣ “ተነሱ! እግዚአብሔር በምድያም ሠራዊት ላይ ድል ሰጥተአችኋል፡፡”16እርሱም ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፈላቸው፣ ለሁሉም ሰዎች ቀንደ መለከትና ባዶ ማሰሮ፣ በማሰሮውም ውስጥ ችቦ ሰጣቸው፡፡17 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “እኔን ተመልከቱ፣ የማደርገውንም አድርጉ፡፡ አስተውሉ! ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በመጣሁ ጊዜ፣ እኔ የማደርገውን እናንተም ታደርጋላችሁ፡፡18እኔና ከእኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከት ስንነፋ፣ እናንተ ደግሞ በሰፈሩ በሁሉም አቅጣጫ ቀንደ መለከታችሁን ንፉና “ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን” ብላችሁ ጩኹ፡፡19ስለዚህ ጌዴዎንና ከእርሱ ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች የመካከለኛው የጥበቃ ሰዓት በተጀመረ ጊዜ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፡፡ ምድያማውያን የጥበቃ ሰዎችን በሚቀይሩበት ጊዜ፣ ቀንደ መለከቶቹን ነፉ፣ በእጃቸውም የነበሩትንም ማሰሮች ሰባበሩ፡፡20 ሦስቱም ቡድኖች ቀንደ መለከቶቹን ነፉ፣ ማሰሮችንም ሰበሩ፡፡ በግራ እጃቸው ችቦችን ያዙ፣ በቀኝ እጃቸው ደግሞ ቀንደ መለከቶችን ይዘው ለመንፋት ተዘጋጁ፡፡ እነርሱም “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ፡፡21ሁሉም ሰው በሰፈሩ ዙሪያ በየቦታው ቆመ፣ የምድያማውያን ሠራዊት ሁሉ ሮጡ፡፡ እነርሱም ጮኹና ሸሹ፡፡22 ሦስት መቶውንም ቀንደ መለከቶች በነፉ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የእያንዳንዱን ምድያማዊ ሰው ሰይፍ በጓደኛውና በራሳቸው ሰራዊት ሁሉ ላይ አዘጋጀ፡፡ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሺጣ፣ በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ፡፡23የእስራኤል ሰዎች ከንፍታሌም፣ ከአሴርና ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን ከኋላ እየተከተሉ አሳደዱ፡፡24 ጌዴዎን መልክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ኮረብታማ አገር ሁሉ በመስደድ እንዲህ አለ፣ “ምድያምን ለመዋጋት ውረዱና እነርሱን ለማስቆም የዮርዳኖስን ወንዝ እስከ ቤትባራም ድረስ ተቆጣጠሩ፡፡” ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰብስበው እስከ ቤትባራና ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ውኃውን ተቆጣጠሩ፡፡ 25የምድያምን ሁለቱን መሪዎች ሔሬብንና ዜብን ያዙ፡፡ ሔሬብንም በሔሬብ ዓለት ገደሉት፣ ዜብንም በዜብ ወይን መጥመቂያ ላይ ገደሉት፡፡ ምድያማውያንንም አሳደዱ፣ የሔሬብንና የዜብንም ራስ ይዘው በዮርዳኖስ ማዶ ወደነበረው ወደ ጌዴዎን አመጡ፡፡
1የኤፍሬም ሰዎች ለጌዴዎን እንዲህ አሉት፣ “ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ምንድር ነው? ምድያምን ለመዋጋት በሄድህ ጊዜ እኛን አልጠራኸንም?” ከእርሱም ጋር በኃይል ተጣሉ።2 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ከእናንተ ጋር ሲነጻጸር አሁን እኔ ያደረግት ምንድን ነው? ከኤፍሬም የወይን ቃርሚያ ይልቅ የአቢዔዝር ሙሉ የወይን መከር አይሻልምን? 3እግዚአብሔር በምድያም መሪዎች በሔሬብና በዜብ ላይ ድልን ሰጥቶአችኋል! ከእናንተ ጋር ሲነጻጸር እኑ ምን ፈጸምሁ?” ይህን በተናገረ ጊዜ ቍጣቸው በረደ።4 ጌዴዎን ከእርሱ ጋር ከነበሩት ከሦስቱ መቶ ሰዎች ጋር ወደ ዮርዳኖስ መጣና ተሻገረ፡፡ እጅግ በጣም ደክመው ነበር፣ ይሁን እንጂ ያሳድዱ ነበር።5እርሱም ለሱኮት ሰዎች እንዲህ አላቸው፣ “ደክመዋልና እባካችሁ ለተከተሉኝ ሰዎች እንጀራ ስጡአቸው፣ እኔም የምድያምን ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን እያሳደድሁ ነው፡፡”6 የሱኮትም መሪዎች እንዲህ አሉ፣ “ዛብሄልንና ስልማናን በጉልበትህ አሸነፍኃቸውን?” እኛ ለሠራዊትህ እንጀራ ለምን እንደምንሰጥ አናውቅም?7ጌዴዎንም እንዲህ አለ፣ “እግዚአብሔር በዛብሄልና በስልማና ላይ ድል በሰጠኝ ጊዜ፣ እኔ በምድረ በዳ እሾህና በኵርንችት ሥጋችሁን እቦጫጭቀዋለሁ፡፡”8 ከዚያም ወደ ጵኒኤል ወጣና በተመሳሳይ መንገድ በዚያ ለሚገኙ ሰዎች ተናገራቸው፣ ነገር ግን የጵንኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለሱለት።9እርሱም የጵኒኤልን ሰዎች ደግሞ እንዲህ አላቸው፣ “በሰላም በተመለስሁ ጊዜ፣ ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ፡፡10ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር፣ ከምሥራቅም ሰዎች ሠራዊት ሁሉ የቀሩ 15, 000 ያህል ሰዎች በቀርቀር ነበሩ፡፡ በሰይፍ ለመዋጋት ስልጠና የወሰዱ መቶ ሀያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና፡፡11 ጌዴዎንም ዘላኖች ባሉበት መንገድ በኖባህና በዮግብሃ አልፎ ወደ ጠላት ሰፈር ሄደ፡፡ እርሱም የጠላትን ሰራዊት አሸነፈ፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት አደጋ ይገጥመናል ብለው አላሰቡም ነበርና፡፡ 12ዛብሄልና ስልማናም ሸሹ፣ ጌዴዎንም ባሳደዳቸው ጊዜ ሁለቱንም የምድያም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ያዛቸው፣ ሠራዊታቸውንም ሁሉ ድንጋጤ ላይ ጣላቸው፡፡13 የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎንም በሔሬስ ዳገት በኩል በማለፍ ከጦርነት ተመለሰ፡፡14እርሱም ከሱኮት ሰዎች አንድ ወጣት ይዞ ጠየቀውና ከእርሱ ምክር ፈለገ፡፡ ወጣቱም የሱኮትን መሪዎችና ሽማግሌዎች ሰባ ሰባት ሰዎች እነማን እንደሆኑ ገለጸለት።15 ጌዴዎንም ወደ ሱኮት ሰዎች መጣና እንዲህ አላቸው፣ “‘ዛብሄልንና ስልማናን በጉልበትህ አሸነፍኃቸውን? እኛ ለሠራዊትህ እንጀራ መስጠት እንዳለብን አናውቅም?’ ብላችሁ ያላገጣችሁብኝ ዛብሄልና ስልማና ተመልከቱአቸው፡፡”16ጌዴዎንም የከተማይቱን ሽማግሌዎች ያዛቸው፣ የሱኮትንም ሰዎች በምድረ በዳ እሾህና በኵርንችት ገረፋቸው፡፡17የጵኒኤልንም ግንብ አፈረሰ፣ የዚያችን ከተማ ሰዎችን ገደለ፡፡18 ጌዴዎንም ለዛብሄልና ለስልማና እንዲህ አላቸው፣ “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ነበሩ?” እነርሱም፣ “እንደ አንተ ያሉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዳቸው የንጉሥ ልጅ ይመስላሉ” አሉት፡፡19ጌዴዎንም “እነርሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ነበሩ፡፡ በሕይወት እንዲኖሩ አድናችኋቸው ቢሆን ኖሮ፣ ሕያው እግዚአብሔርን፣ እኔ አልገድላችሁም ነበር” አለ፡፡20 ለበኵር ልጁ ለዬቴር እንዲህ አለው፣ “ተነሳና ግደላቸው!” ነገር ግን ወጣቱ ልጅ ስለፈራ ሰይፉን አልመዘዘም፣ ምክንያቱም ገና ወጣት ልጅ ነበረና፡፡21የዚያን ጊዜ ዛብሄልና ስልማና እንዲህ አሉ፣ “አንተ ተነሳና ግደለን! የሰው ኃይሉ እንደ ሰውነቱ ነውና፡፡” ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደላቸው፡፡ በግመሎቻቸውም አንገት ላይ የነበሩትን ጌጦች ወሰደ፡፡22 የእስራኤልም ሰዎች ጌዴዎንን “አንተ ግዛን፣ አንተ፣ የአንተ ልጅና የልጅ ልጆችህ ግዙን፣ ምክንያቱም አንተ ከምድያም ብርታት አድነኸናልና፡፡”23ጌዴዎንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “እኔ በእናንተ ላይ አልገዛም፣ ልጄም በእናንተ ላይ አይገዛም፣ እግዚአብሔር ይገዛችኋል አላቸው፡፡24 ጌዴዎን ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፡- እያንዳንዳችሁ ከምርኮአችሁ ጕትቻችሁን እንድትሰጡኝ እለምናችኋለሁ፡፡” (ምድያማውያን የወርቅ ጕትቻ ነበራቸው ምክንያቱም እነርሱ እስማኤላውያንም ነበሩና፡፡)25እነርሱም፣ “ለአንተ ልንሰጥህ ደስተኞች ነን” አሉት፡፡ እነርሱም ልብስ አነጠፉና ሁሉም ሰው የምርኮውን ጕትቻ በዚያ ላይ ጣለ፡፡26 እርሱ የጠየቀው የወርቅ ጕትቻ ክብደት 1, 700 ሰቅል ወርቅ ነበር፡፡ ይህም ምርኮ ከጌጣ ጌጦቹ ሌላ የአንገት ጌጥ፣ የምድያምም ነገሥታት ከሚለብሱት ሐምራዊ ልብስ፣ እንደዚሁም በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ጌጦች ሌላ ነበረ፡፡27 ጌዴዎንም ከጉትቻዎቹ ባገኘው ወርቅ ኤፉድ ሠራና በከተማው፣ በዖፍራ አኖረው፣ እስራኤልም ሁሉ እርሱን በማምለክ አመነዘረበት፡፡ ለጌዴዎንና በቤቱም ላሉት ወጥመድ ሆነባቸው፡፡28ስለዚህም ምድያም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ተዋረደ፣ ራሳቸውንም እንደገና አላነሡም፡፡ በጌዴዎንም ዘመን ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም ሆነች።29 የኢዮአስም ልጅ ይሩበኣል ሄደና በራሱ ቤት ተቀመጠ።30ጌዴዎንም ብዙ ሚስቶች ነበሩትና ሰባ ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡31በሴኬም የነበረችው ቁባቱም ወንድ ልጅ ወለደችለት፣ ጌዴዎንም ስሙን አቤሜሌክ ብሎ ጠራው፡፡32 የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በመልካም የሽምግልና ዕድሜ ሞተ፣ በአቢዔዝራውያን ጎሳ በሆነው በዖፍራ በነበረው በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ፡፡33ጌዴዎን ከሞተ በኋላ ብዙ ሳይቆይ እንዲህ ሆነ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ተመለሱ፣ የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፡፡ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፡፡34 የእስራኤልም ሕዝብ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከነበሩት ከጠላቶቻቸው ኃይል ያዳናቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን አላሰቡትም፡፡ 35እነርሱም ለእስራኤል ስላደረገው በጎ ነገር አስበው ለይሩበኣል (የጌዴዎን ሌላኛው ስም ነው) ውለታ ለመመለስ ቃል ኪዳናቸውን አልጠበቁም፡፡
1 የይሩበኣል ልጅ አቤሜሌክ ወደ እናቱ ዘመዶች ወደ ሴኬም ሄደና ለእነርሱና ለእናቱ ቤተሰብ ጎሳ በሙሉ እንዲህ አላቸው፣2“በሴኬም የሚገኙ መሪዎች በሙሉ ይሰሙ ዘንድ ይህን ተናገሩ፣ ‘ለእናንተ የሚሻለው የትኛው ነው? የይሩበኣል ሰባ ልጆች ሁሉ ቢገዙአችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ?’ እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ የሥጋችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ፡፡”3 የእናቱም ዘመዶች ስለ እርሱ ለሴኬም መሪዎች ተናገሩ፣ እነርሱም አቤሜሌክን ለመከተል ተስማሙ፣ “እርሱ ወንድማችን ነው” ብለዋልና፡፡4እነርሱም ከበኣልብሪትም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፣ አቤሜሌክም እርሱን የተከተሉትን ስርዓት አልበኞችንና ወሮበሎችን ለመቅጠር ተጠቀበመት፡፡5 እርሱም ወደ አባቱ ቤት ወደ ዖፍራ ሄደ፣ የይሩበኣልን ልጆች ሰባ ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ አረዳቸው፡፡ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ስለነበር እርሱ ብቻ ተረፈ፡፡6የሴኬምና የቤትሚሎ መሪዎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፣ እነርሱም ሄደው በሴኬም በዓምዱ አጠገብ ባለው በበሉጥ ዛፍ ስር አቤሜሌክን አነገሡት፡፡7 ለኢዮአታም ይህን ነገር በነገሩት ጊዜ፣ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ሄደና ቆመ፡፡ ድምፁንም ከፍ አድርጎ ጮኸና እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ የሴኬም መሪዎች፣ እግዚአብሔርም እናንተን ይሰማ ዘንድ፣ እኔን ስሙኝ፡፡8አንድ ጊዜ ዛፎች በእነርሱ ላይ የሚያነግሱት ለመቀባት ሄዱ፡፡ እነርሱም ለወይራ ዛፍ ‘በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡9 የወይራ ዛፍ ግን ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ ‘እግዚአብሔርና ሰዎችን ለማክበር የሚጠቅመውን ቅባቴን ትቼ ተመልሼ በሌሎች ዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን?’ 10ዛፎቹም ለበለስ ዛፍ እንዲህ አሉት፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ፡፡’ 11ነገር ግን የበለሱ ዛፍ፣ ጣፋጭነቴንና መልካሙን ፍሬዬን ትቼ ተመልሼ በሌሎች ዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን?’ አላቸው፡፡12 ዛፎችም ለወይኑ፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡13ወይኑም፣ እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኘውን አዲስ የወይን ጠጄን ትቼ ተመልሼ በዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን? አላቸው፡፡14ከዚያም ዛፎች ሁሉ የእሾህ ቁጥቋጦን፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡15 የእሾህ ቁጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በእውነት እኔን በእናንተ ላይ እንድነግስ ልትቀቡኝ የምትፈልጉ ከሆነ፣ ኑና በጥላዬ ስር ተጠለሉ፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን እሳት ከእሾህ ቁጥቋጦ ይውጣና የሊባኖስንም ዝግባ ያቃጥል’ አላቸው፡፡ 16አሁን እንግዲህ፣ አቤሜሌክን ባነገሳችሁት ጊዜ በእውነትና በቅንነት አድርጋችሁ ከሆነ፣ ለይሩበኣልና ለቤቱም በጎነት አስባችሁ አድርጋችሁ ከሆነ፣ እንዳደረገውም መጠን ለእርሱ የተገባውን ቀጥታችሁት ከሆነ17 አባቴ ስለ እናንተ ተዋግቶ እንደነበር፣ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠት፣ ከምድያምም እጅ እናንተን እንዳዳናችሁ አሰባችሁ ማለት ነው18ነገር ግን ዛሬ እናንተ በአባቴ ቤት ላይ ተነሥታችኋል፣ በአንድ ድንጋይ ላይ ልጆቹን፣ ሰባ ሰዎችን፣ አረዳችኋቸው፡፡ ከዚያም የሴት አገልጋዩን ልጅ አቤሜሌክን ዘመዳችሁ ስለ ሆነ በሴኬም መሪዎች ላይ እንዲነግስ አደረጋችሁት፡፡19 ያንጊዜ ለይሩበኣልና ለቤቱ በእውነትና በቅንነትን አድርጋችሁ ከሆነ፣ እንግዲያው እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ሊላችሁ ይገባል፣ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው፡፡20ነገር ግን እንዲህ ባይሆን፣ ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣና የሴኬምንም ሰዎችና የቤትሚሎን ቤት ያቃጥል፡፡ ከሴኬምም ሰዎችና ከቤትሚሎ እሳት ይውጣና አቤሜሌክን ያቃጥል፡፡21ኢዮአታምም ሸሽቶ አመለጠ፣ ከዚያም ወደ ብኤር ሄደ፡፡ እርሱም በዚያ ተቀመጠ ምክንያቱም ከአቤሜሌክ ከወንድሙ በጣም ሩቅ ነበረ፡፡22 አቤሜሌክም በእስራኤል ላይ ለሦስት ዓመት ገዛ፡፡23እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም መሪዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ፡፡ የሴኬም መሪዎችም በአቤሜሌክ ላይ የነበራቸውን እምነት ጥለው ከዱት፡፡24እግዚአብሔር ይህንን ያደረገው በሰባዎቹ የይሩበኣል ልጆች ላይ የተደረገውን ዓመፅ ለመበቀል ነው፣ ወንድማቸው አቤሜሌክም እነርሱን በመግደሉ ተጠያቂ እንዲሆን ለማድረግ ነው፤ የሴኬም ሰዎችም እርሱ ወንድሞቹን እንዲገድላቸው ስለተባበሩት ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው፡፡25ስለዚህ የሴኬም መሪዎች በኮረብቶች ራስ ላይ እርሱን አድፍጠው የሚጠብቁ ሰዎች መደቡ፣ እነርሱም በዚያ መንገድ በአጠገባቸው ያለፉትን ሰዎች በሙሉ ዘረፉ፡፡ ይህም ወሬ ለአቤሜሌክ ደረሰው፡፡26 የአቤድም ልጅ ገዓል ከዘመዶቹ ጋር መጣና ወደ ሴኬም ሄዱ፡፡ የሴኬም መሪዎች በእርሱ ተማመኑበት፡፡ 27እነርሱም ወደ እርሻው ወጥተው ሄዱና ከወይን አትክልት ቦታ ወይን ለቅመው ጨመቁት፡፡ በአምላካቸው ቤት የደስታ በዓል አደረጉ፣ በሉም ጠጡም፣ አቤሜሌክንም ሰደቡ፡፡28 የአቤድም ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፣ “እናገለግለው ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ማን ነው? እርሱ የይሩብኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ሹም አይደለምን? ለኤሞር ሰዎች፣ ለሴኬም አባት አገልግሉ! ለምን እርሱን እናገለግላለን?29ይህ ሕዝብ በእኔ አዛዥነት ስር ቢሆን እመኝ ነበር! የዚያን ጊዜ አቤሜሌክን አስወግደው ነበር፡፡ ለአቤሜሌክም ‘ሠራዊትህን ሁሉ ጥራ’ እለው ነበር፡፡”30 የከተማይቱ ሹም፣ ዜቡል የአቤድን ልጅ የገዓልን ቃል በሰማ ጊዜ ቁጣው ነደደ፡፡ 31ወደ አቤሜሌክም ያታልለው ዘንድ እንዲህ ብሎ መልክተኞች ላከ፣ “ተመልከት፣ የአቤድ ልጅ ገዓልና ዘመዶቹ ወደ ሴኬም እየመጡ ነው፣ ከተማይቱን በአንተ ላይ እንድትሸፍት አነሳስተዋል፡፡32 አሁንም አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ወታደሮች በሌሊት ተነሡ፣ ሜዳውም ላይ አድፍጡ፡፡ 33ከዚያም በጠዋት ፀሐይ በወጣች ጊዜ ማልደህ ተነሣና በከተማይቱ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽምባት፡፡ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉት ሕዝብ በአንተ ላይ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ላይ ልታደርግ የምትችለውን ማንኛውንም ነገር አድርግባቸው፡፡”34 ስለዚህ አቤሜሌክ በሌሊት ተነሳ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በሙሉ፣ በአራት ወገን ተከፋፍለው በሴኬም ላይ አደፈጡ፡፡ 35የአቤድ ልጅ ገዓል ወጥቶ በከተማይቱ በር መግቢያ ቆመ፡፡ አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎችም ከተደበቁበት ስፍራ ወጥተው መጡ፡፡36 ገዓልም ሰዎቹን ባየ ጊዜ ዜቡልን፣ “ተመልከት፣ ሰዎች ከኮረብቶች ራስ ወርደው እየመጡ ነው!” አለው፡፡ ዜቡልም እንዲህ አለው፣ “አንተ የምታየው ሰዎች የሚመስለውን የኮረብቶች ጥላ ነው፡፡”37ገዓልም እንደገና እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “ተመልከት፣ በምድር መካከል ሰዎች ወርደው እየመጡ ነው፣ አንድም ወገን በቃላተኞች የበሉጥ ዛፍ መንገድ እየመጣ ነው፡፡38 የዚያን ጊዜ ዜቡል እንዲህ አለው፣ “‘እናገለግለው ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው?’ ብለህ የተናገርሃቸው እነዚያ የትዕቢት ቃላቶችህ አሁን የት አሉ? እነዚህ ሰዎች አንተ የናቅሃቸው አይደሉምን? አሁን ውጣና ከእነርሱ ጋር ተዋጋ፡፡” 39ገዓል ወጣና የሴኬም ሰዎችን ይመራ ነበር፣ ከአቤሜሌክም ጋር ተዋጋ፡፡ 40አቤሜሌክም አሳደደው፣ ገዓልም በፊቱ ሸሸ፡፡ ብዙዎቹም በከተማይቱ በር መግቢያ ፊት ለፊት በከባድ ሁኔታ ቆስለው ወደቁ፡፡41 አቤሜሌክም በአሩማ ተቀመጠ፡፡ ዜቡልም ገዓልንና ዘመዶቹን ከሴኬም እንዲወጡ አስገደዳቸው፡፡ 42በሚቀጥለው ቀን የሴኬም ሕዝብ ወደ እርሻ ሄዱ፣ ይህም ወሬ ለአቤሜሌክ ደረሰው፡፡ 43ሕዝቡንም ወሰደ፣ በሦስት ወገንም ከፈላቸውና በእርሻዎቹ ውስጥ አደፈጡ፡፡ እርሱም ተመለከተ፣ ሕዝቡ ከከተማ ወጥተው ሲመጡ አየ፡፡ እርሱም ተዋጋቸውና ገደላቸው፡፡44 አቤሜሌክና ከእርሱም ጋር የነበሩት ወገኖች ተዋጉና የከተማይቱን በር መግቢያ ዘጉ፡፡ ሌሎቹ ሁለት ወገኖች ደግሞ በእርሻው ውስጥ የነበሩትን ሁሉ ወጓቸውና ገደሉአቸው፡፡ 45አቤሜሌክም ቀኑን ሙሉ ከከተማይቱ ጋር ተዋጋ፡፡ ከተማይቱንም ተቆጣጠረና በውስጧ የነበሩትን ሕዝብ ገደላቸው፡፡ የከተማይቱንም ቅጥር አፈራረሰው፣ በላይዋም ጨው በተነባት፡፡46 የሴኬም ግንብ መሪዎች በሙሉ ይህንን ወሬ በሰሙ ጊዜ፣ ወደ ኤልብሪት ቤት ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡ 47አቤሜሌክም መሪዎቹ በሙሉ በሴኬም ግንብ ውስጥ በአንድ ላይ እንደተሰበሰቡ ተነገረው፡፡48 አቤሜሌክ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጣ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፡፡አቤሜሌክም በእጁ መጥረቢያ ወሰደና የዛፉን ቅርንጫፎች ቆረጠ፡፡ እርሱም አንሥቶ በትከሻው ላይ አደረገውና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፣ “እኔ ሳደርግ ያያችሁትን፣ ፈጥናችሁ እኔ እንዳደረግሁ አድርጉ፡፡” 49ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው የዛፉን ቅርንጫፎች ቈረጠና አቤሜሌክን ተከተሉት፡፡ እነርሱም ቅርንጫፎቹን በምሽጉ ላይ ከመሩአቸው፣ በላዩም ላይ እሳት አቀጣጠሉበት፣ ከዚህ የተነሳ የሴኬም ግንብ ሰዎች ሁሉ፣ አንድ ሺህ የሚያህሉ ወንድና ሴት ሞቱ፡፡50 ከዚያ በኋላ አቤሜሌክ ወደ ቴቤስ ሄደ፣ ቴቤስንም ከበባትና ተቆጣጠራት፡፡ 51ነገር ግን በከተማይቱ ጠንካራ ግንብ ነበረ፣ የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ፣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ፣ የከተማይቱም መሪዎች ሁሉ ወደዚያ ሸሹና በውስጥ ሆነው ደጁን ዘጉት፡፡ ከዚያም እስከ ግንቡ ሰገነት ድረስ ወደ ላይ ወጡ፡፡52 አቤሜሌክም ወደ ግንቡ መጣና ተዋጋ፣ በእሳትም ሊያቃጥለው ወደ ግንቡ በር አጠገብ መጣ፡፡53ነገር ግን አንዲት ሴት በአቤሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ ጣለችበት፣ መጁም ጭንቅላቱን ሰባበረው፡፡54ከዚያም እርሱ በአስቸኳይ ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፣ “አንድም ሰው እኔን ‘ሴት ገደለችው’ እንዳይል ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው፡፡ ስለዚህ ወጣቱ ሰው ወጋውና ሞተ፡፡55 የእስራኤልም ሰዎች አቤሜሌክ እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ 56እግዚአብሔርም ሰባ ወንድሞቹን በመግደል አቤሜሌክ በአባቱ ላይ ያደረገውን ክፋት ተበቀለው፡፡ 57እግዚአብሔርም የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው፣ የይሩበኣልም ልጅ የኢዮአታም እርግማን በእነርሱ ላይ መጣባቸው፡፡
1 ከአቤሜሌክ በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነውና በኮረብታማውም በኤፍሬም አገር ባለችው በሳምር ይኖር የነበረው የዱዲ ልጅ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፡፡2እርሱም በእስራኤል ላይ ሀያ ሦስት ዓመት ፈረደ፡፡ እርሱም ሞተ፣ በሳምርም ተቀበረ፡፡3 ከእርሱም በኋላ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፡፡ በእስራኤልም ላይ ሀያ ሁለት ዓመት ፈረደ፡፡4በሠላሳ አህያዎች የሚጋልቡ ሠላሳ ልጆች ነበሩት፣ እነርሱም በገለዓድ ምድር ያሉ እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው፡፡5ኢያዕርም ሞተ፣ በቃሞንም ተቀበረ፡፡6 የእስራኤል ሕዝብ ከዚህ በፊት ከሰሩት በላይ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ስራ ጨምረው ሠሩ፣ በኣልን፣ አስታሮትን፣ እንደዚሁም የሶርያን አማልክት፣ የሲዶናን አማልክት፣ የሞዓብን አማልክት፣ የአሞንን ሕዝብ አማልክት፣ የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፡፡እግዚአብሔርን ተዉ፣ እርሱንም አላመለኩትም፡፡7የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ እርሱም ፍልስጥኤማውያንና አሞናውያን ያሸንፉአቸው ዘንድ ለእነርሱ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡8 እነርሱም በዚያን ዓመት የእስራኤልን ሕዝብ አደቀቋቸው፣ አስጨነቋቸው፣ ለአሥራ ስምንት ዓመት በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን ምድር በገለዓድ ውስጥ የነበሩትን የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ አስጨነቋቸው፡፡9የአሞንም ሰዎች ከይሁዳ፣ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ለመዋጋት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፣ ከዚህ የተነሳ እስራኤል እጅግ በጣም ተጨነቁ፡፡10 የዚያን ጊዜ የእስራኤልም ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮሁ፣ እንዲህ በማለት፣ “በአንተ ላይ በድለናል፣ ምክንያቱም አምላካችንን ትተን የበኣል አማልክትን አምልከናልና፡፡” 11እግዚአብሔርም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ አላቸው፣ “ከግብፃውያን፣ ከአሞራውያንም፣ ከአሞናውያን፣ ከፍልስጤማውያንና 12ከሲዶናውያን አላዳንኋችሁምን? አማሌቃውያንና ማዖናውያን አስጨነቋችሁ፤ ወደ እኔም ጮኻችሁ፣ እኔም ከእነርሱ ኃይል አዳንኋችሁ፡፡13 ይሁን እንጂ እናንተ እንደገና ተዋችሁኝና ሌሎችን አማልክት አመለካችሁ፡፡ ስለዚህ፣ እኔም ከእንግዲህ ወዲህ አላድናችሁም፡፡ 14ሂዱና ወደምታመልኳቸው አማልክት ጩኹ፡፡ በመከራችሁ ጊዜ እነርሱ ያድኑአችሁ፡፡15 የእስራኤልም ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዲህ አሉት፣ “እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፡፡ ለአንተ ደስ የሚያሰኝህን ማንኛውንም ነገር በእኛ ላይ አድርግብን፡፡ እባክህ፣ የዛሬን ብቻ አድነን፡፡”16እነርሱም በመካከላቸው ካሉት ባዕዳን አማልክት ዘወር አሉ፣ እግዚአብሔርንም አመለኩ፡፡እርሱም የእስራኤልን ጕስቍልና ሊታገሰው የማይቻለው ሆነ፡፡17 ከዚያም አሞናውያን በአንድ ላይ ተሰበሰቡና በገለዓድ ሰፈሩ፡፡ እስራኤላውያንም በአንድ ላይ ተሰበሰቡና ሰፈራቸውን በምጽጳ ላይ አደረጉ፡፡ 18የገለዓድ ሕዝብ መሪዎችም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “አሞናውያንን ለመዋጋት የሚጀምር ሰው ማን ነው? እርሱ በገለዓድ በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ መሪ ይሆናል፡፡”
1 ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ኃያል ተዋጊ ነበር፣ ነገር ግን የጋለሞታ ሴት ልጅ ነበረ፡፡ አባቱም ገለዓድ ነበረ፡፡2የገለዓድም ሚስት ደግሞ ሌሎች ወንዶች ልጆችን ወለደችለት፡፡ የሚስቱ ልጆች ባደጉ ጊዜ፣ ዮፍታሔን ቤቱን ለቅቆ እንዲወጣ አስገደዱት፣ እንዲህም አሉት፡- “አንተ ከቤተሰባችን ምንም ነገር አትወርስም፡፡ አንተ የሌላ ሴት ልጅ ነህ፡፡”3ስለዚህ ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ፊት ሸሸና በጦብ ምድር ተቀመጠ፡፡ ስርዓት አልበኛ ሰዎችም ተከተሉት፣ ተሰብስበውም ከእርሱ ጋር ሄዱ፡፡4 ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ የአሞን ሰዎች ከእስራኤል ጋር ውጊያ አደረጉ፡፡5የአሞንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር ውጊያ ባደረጉ ጊዜ፣ የገለዓድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር ለማምጣት ሄዱ፡፡6ዮፍታሔንም፣ “ና፣ ከአሞን ሰዎች ጋር እንድንዋጋ አለቃችን ሁን” አሉት፡፡7 ዮፍታሔም ለገለዓድ ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ ጠልታችሁኛል፣ የአባቴንም ቤት ትቼ እንድሄድ አስገድዳችሁኛል፡፡ አሁን በተቸገራችሁ ጊዜ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ?” 8የገለዓድም ሽማግሌዎችም ለዮፍታሔ፣ “አሁን ወደ አንተ የተመለስነው ለዚህ ነው፤ ከእኛ ጋር ና፣ ከአሞንም ሰዎች ጋር ተዋጋ፣ ከዚያም በኋላ በገለዓድ በሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ” አሉት፡፡9 ዮፍታሔም ለገለዓድ ሽማግሌዎች፣ “ከአሞን ሰዎች ጋር እንድዋጋ እንደገና ወደ ቤቴ ከመለሳችሁኝ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ከሰጠን መሪያችሁ እሆናለሁ” አላቸው፡፡10የገለዓድ ሽማግሌዎችም ለዮፍታሔ፣ “እንደተናገርነው የማናደርግ ከሆነ እግዚአብሔር በእኛ መካከል ምስክር ይሁን” አሉት፡፡11ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፣ ሕዝቡም በላያቸው ላይ መሪና የጦር አዛዥ አደረጉት፡፡ እርሱ በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት በነበረ ጊዜ፣ ዮፍታሔ የገባውን ቃል ኪዳን ሁሉ ደገመው፡፡12 ዮፍታሔም ወደ አሞን ሰዎች ንጉሥ እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላከ፡- “በእኛ መካከል ያለው ጠብ ምንድን ነው? ምድራችንን ለመውሰድ በጦር ለምን መጣህ?”13የአሞንም ሰዎች ንጉሥም ለዮፍታሔ መልክተኞች “እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ወስደዋል፡፡ አሁን እነዚህን መሬቶች በሰላም መልሱልኝ” ብሎ መለሰላቸው፡፡14 ዮፍታሔም ወደ አሞን ሰዎች ንጉሥ መልክተኞችን እንደ ገና ላከ፣ 15እንዲህም አለው፣ “ዮፍታሔ የሚለው ይህንን ነው፡- እስራኤል የሞዓብን ምድር የአሞንንም ሰዎች ምድር አልወሰደም፣ 16ነገር ግን ከግብፅ በወጡ ጊዜ፣ እስራኤል በምድረ በዳ በኩል ወደ ቀይ ባሕር ከዚያም ወደ ቃዴስ ሄዱ፣17 እስራኤል ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፣ ‘በምድርህ እንድናልፍ እባክህ ፍቀድልን፣’ ነገር ግን የኤዶምያስ ንጉሥ አልሰማም፡፡ እንዲሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ መልእክተኞች ላኩ፣ እርሱም አልፈቀደም፡፡ ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ ተቀመጠ፡፡18እነርሱም በምድረ በዳ በኩል ሄዱና ከኤዶምያስና ከሞዓብ ምድር ተመለሱ፣ በሞዓብም ምድር በምሥራቅ በኩል ሄዱ፣ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፡፡ ነገር ግን ወደ ሞዓብ ክልል ውስጥ አልገቡም፣ አርኖን የሞዓብ ድንበር ነበረና፡፡19 እስራኤልም በሐሴቦን ውስጥ ገዥ ወደነበረው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም ‘እባክህ፣ በምድርህ በኩል ወደ ስፍራችን እንድናልፍ ፍቀድልን’ አለው፡፡20ነገር ግን ሴዎን እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ አላመነውም፡፡ ስለዚህ ሴዎን ሰራዊቱን ሁሉ ሰበሰበና ወደ ያሀጽ ተንቀሳቀሰ፣ በዚያም ከእስራኤል ጋር ተዋጋ፡፡21 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርም ለእስራኤል በሴዎን ላይ ድል ሰጠውና ሕዝቡን ሁሉ በቁጥጥራቸው ስር እንዲሆኑ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ስለዚህም እስራኤል በዚያች አገር ተቀምጠው የነበሩትን የአሞራውያንን አገር ሁሉ ወሰዱ፡፡22በአሞራውያን ክልል ውስጥ የነበረውን ሁሉንም ነገር ወሰዱ፣ ከአርኖንም እስከ ያቦቅ ድረስ፣ ከምድረ በዳውም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ፡፡23 ያንጊዜ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አሞራውያንን ከሕዝቡ ከእስራኤል ፊት አስወጣቸው፣ ታዲያ አንተ አሁን ምድራቸውን ልትወስድ ይገባልን?24አምላክህ ካሞሽ የሚሰጥህን ምድር አትወስድምን? ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችን የሰጠንን ምድር ሁሉ እንወስዳለን፡፡25አሁን አንተ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ በእውነት ትሻላለህን? እርሱ ከእስራኤል ጋር ከቶ ክርክር ነበረውን? ከእነርሱ ጋር ጦርነት አካሂዷልን?26 እስራኤል በሐሴቦንና በቀበሌዎችዋ፣ በአሮዔርና በቀበሌዎችዋ፣ በአርኖንም ዳርቻ ባሉት ከተሞች ሁሉ ለሦስት መቶ ዓመት ሲኖር በነበረበት ጊዜ፣ ለምን ታዲያ በዚያን ጊዜ መልሳችሁ አልወሰዳችኋቸውም ነበር?27እኔ አልበደልሁህም ነገር ግን አንተ እኔን በመውጋት እየበደልከኝ ነው፡፡ ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር በእስራኤል ሰዎችና በአሞን ሰዎች መካከል ዛሬ ይፈርዳል፡፡28ነገር ግን የአሞን ሰዎች ንጉሥ ዮፍታሔ የላከበትን ማስጠንቀቂያ አልተቀበለም፡፡29 ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፣ እርሱም በገለዓድና በምናሴ አለፈ፣ በገለዓድ ባለው ምጽጳም አለፈ፣ ከዚያም በገለዓድ ካለው ምጽጳ ወደ አሞን ሰዎች አለፈ፡፡30ዮፍታሔም ለእግዚብሔር እንዲህ ሲል ስእለት ተሳለ፡- “በአሞንን ሰዎች ላይ ድልን ብትሰጠኝ፣31ከአሞን ሰዎች በሰላም በተመለስሁ ጊዜ እኔን ሊያገኘኝ ከቤቴ በር የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል፣ እርሱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀርበዋለሁ፡፡32 ስለዚህ ዮፍታሔ እነርሱን ለመውጋት ወደ አሞን ሰዎች አለፈ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ሰጠው፡፡33እርሱም ከአሮዔርም እስከ ሚኒት፣ እንደዚሁም እስከ አቤልክራሚም ድረስ ያሉ ሀያ ከተሞችን ወጋቸው፣ ታላቅ እልቂትም አደረሰባቸው፡፡ ስለዚህ የአሞን ሰዎች በእስራኤል ሰዎች ቁጥጥር ስር ሆኑ፡፡34 ዮፍታሄ ምጽጳ ወዳለው ቤቱ መጣ፣ በዚያም የእርሱ ልጅ ከበሮ ይዛ እያሸበሸበች ልታገኘው ወጣች፡፡ እርስዋም ብቸኛ ልጁ ነበረች፣ ከእርስዋ ሌላ ወንድ ልጅም ይሁን ሴት ልጅ አልነበረውም፡፡35እርስዋንም ባየ ጊዜ፣ ልብሱን ቀደደ እንዲህም አለ፡- “ወይኔ! ልጄ ሆይ! በኀዘን አደቀቅሽኝ፣ በእኔ ላይ ጭንቅ ያመጣብኝ ሰው ሆንሽብኝ! ለእግዚአብሔር ስእለት ተስያለሁና፣ ቃሌን ማጠፍ በፍጹም አልችልም፡፡”36 እርስዋም እንዲህ አለችው፡- “አባቴ ሆይ፣ ለእግዚአብሔር ስእለት ተስለሃል፣ ቃል የገባኸውን ሁሉ በእኔ ላይ አድርግብኝ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላቶችህ በአሞናውያን ላይ ተበቅሎልሃልና፡፡”37አርስዋም ለአባትዋ እንዲህ አለች፡- “ይህ ቃል ለእኔ ይደረግልኝ፡፡ ይህንን አካባቢ እንድለቅና ወደ ታች ወደ ኮረብታዎቹ እንድወርድ፣ ከጓደኞቼም ጋር ስለ ድንግልናየ እንዳለቅስ ለሁለት ወራቶች ያህል ብቻየን እንድሆን ፍቀድልኝ፡፡38 እርሱም፣ “ሂጂ” አለ፡፡ ለሁለት ወራትም አሰናበታት፡፡ እርስዋም ትታው ሄደች፣ ከባልንጀሮችዋም ጋር ስለ ድንግልናዋ በኮረብታዎቹ ላይ አለቀሱ፡፡39በሁለት ወር መጨረሻ ላይ ወደ አባትዋ ተመለሰች፣ እርሱም ቃል እንደገባው እንደ ስእለቱ አደረገባት፡፡ እርስዋም ከወንድ ጋር ተኝታ አታውቅም፣ ይህም በእስራኤል ዘንድ ልማድ ሆነ፣40የእስራኤል ሴቶች ልጆች በየዓመቱ፣ ለአራት ቀናት፣ የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ሴት ልጅ ታሪክ እየተናገሩ ያስቡአታል፡፡
1 ወደ ኤፍሬም ሰዎችም ጥሪ ደረሰ፤ በጻፎን በኩል ተሻግረው ዮፍታሔን፣ “ከአሞን ሕዝብ ጋር ለመዋጋት ስታልፍ ከአንተ ጋር እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምድን ነው? ቤትህን በአንተ ላይ እናቃጥለዋለን” አሉት፡፡ 2ዮፍታሔም እንዲህ አላቸው፣ “እኔና ሕዝቤ ከአሞን ሕዝብ ጋር በታላቅ ጦርነት ውስጥ ነበርን፡፡ በጠራኋችሁም ጊዜ ከእነርሱ አላዳናችሁኝም፡፡3 እናንተም እንዳላዳናችሁኝ ባየሁ ጊዜ፣ ሕይወቴን በራሴ ብርታት አስቀምጬ በአሞን ሕዝብ ላይ ለመዋጋት አለፍሁ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ሰጠኝ፡፡ ዛሬ እኔን ለመውጋት ለምን መጣችሁ?4ዮፍታሔም የገለዓድን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበና ከኤፍሬምም ጋር ተዋጋ፡፡ የገለዓድም ሰዎች የኤፍሬምን ሰዎች ወጓቸው ምክንቱም፣ “እናንተ ገለዓዳውያን በኤፍሬም ውስጥ ሸሽታችሁ የተጠጋችሁ፣ በኤፍሬምና በምናሴ ውስጥ ጥገኞች የሆናችሁ ናችሁ” ይሏቸው ነበርና፡፡5 ገለዓዳውያንም ወደ ኤፍሬም የሚወስደውን የዮርዳኖስን መሻገሪያ ያዙባቸው፡፡ አምልጦ የሚሸሽ የኤፍሬም ሰው፣ “ወንዙን ተሻግሬ ልለፍ” ባለ ጊዜ፣ የገለዓድ ሰዎች ደግሞ እንዲህ ይሉታል፣ “አንተ ኤፍሬማዊ ነህን?” እርሱም፣ “አይደለሁም” ቢል፣6እነርሱም “ሺቦሌት በል” ይሉታል፡፡ እርሱም “ሲቦሌት” ብሎ ከተናገረ (ምክንያቱም እርሱ ቃሉን አጥርቶ መናገር አይችልምና) ፣ ገለዓዳውያን እርሱን ይዘው በዮርዳኖስ መሻገሪያ ላይ ይገድሉታል፡፡ በዚያም ጊዜ አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ፡፡7 ዮፍታሔም በእስራኤል ላይ ለስድስት ዓመት እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ ከዚያም ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ሞተ፣ ከገለዓድ ከተሞችም በአንዱ ተቀበረ።8 ከእርሱም በኋላ የቤተ ልሔሙ ኢብጻን በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡9እርሱም ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡ ሠላሳ ሴቶች ልጆችንም ወደ ውጭ በትዳር ለሌሎች ሰጠ፣ ሠላሳ ሴቶች ልጆችን ደግሞ ከሌሎች ሰዎች በትዳር ለወንድ ልጆቹ አመጣ። በእስራኤልም ላይ ለሰባት ዓመት ፈረደ።10 ኢብጻንም ሞተ፣ በቤተ ልሔምም ተቀበረ፡፡11ከእርሱም በኋላ ዛብሎናዊው ኤሎም በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ እርሱም በእስራኤል ላይ ለአሥር ዓመት ፈረደ፡፡12ዛብሎናዊውም ኤሎም ሞተ፣ በዛብሎንም ምድር ባለችው በኤሎም ተቀበረ፡፡13 ከእርሱም በኋላ የጲርዓቶናዊው የሂሌል ልጅ ዓብዶን በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡14እርሱም አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ወንዶች የልጅ ልጆች ነበሩት፡፡ በሰባ አህያዎች ላይ ይጋልቡ ነበር፣ እርሱም በእስራኤል ላይ ለስምንት ዓመት ፈረደ፡፡15የጲርዓቶናዊውም የሂሌል ልጅ ዓብዶን ሞተ፣ በተራራማውም በአማሌቃውያን አገር በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ውስጥ ባለችው በጲርዓቶን ውስጥ ተቀበረ፡፡
1 የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ስራ እንደ ገና ሠሩ፣ እርሱም ፍልስጥኤማውያን በእነርሱ ላይ ለአርባ ዓመት እንዲገዙ ፈቀደላቸው፡፡2ከዳን ቤተሰብ የሆነ ስሙም ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፡፡ ሚስቱም መካን ስለነበረች ልጅ አልወለደችም፡፡3 የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፣ “ተመልከቺ፣ አንቺ መካን ነበርሽ፣ ልጅም አልወለድሽም፣ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ 4አሁንም የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ጠንካራ መጠጥ እንዳትጠጪ ተጠንቀቂ፣ ሕጉ ርኩስ እንደሆነ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብዪ፡፡ 5ተመልከቺ፣ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ልጁ ከአንቺ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፡፡ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን ጉልበት ማዳን ይጀምራል፡፡6 የዚያን ጊዜ ሴቲቱ ወደ ባልዋ መጥታ እንዲህ ብላ ነገረችው፣ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፣ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ የሚመስል ነበረ፣ በጣምም አስደነገጠኝ፡፡ ከወዴት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፣ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፡፡ 7እርሱም እንዲህ አለኝ፣ ‘ተመልከቺ! ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ስለዚህ ልጁ ከአንቺ ማኅፀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ጠንካራ መጠጥ እንዳትጠጪ፣ ሕጉ ርኩስ እንደሆነ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብዪ፡፡’”8 ከዚያም ማኑሄ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፣ “ጌታ ሆይ፣ አሁን በቅርቡ ለሚወለደው ልጅ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲያስተምረን እባክህ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና ወደ እኛ ይምጣ፡፡”9እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት መለሰ፣ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና ወደ ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች መጣ፡፡ ነገር ግን ባልዋ ማኑሄ ከእርስዋ ጋር አልነበረም፡፡10 ስለዚህ ሴቲቱም ፈጥና ሮጠችና ለባልዋ ነገረችው፣ “ተመልከት! በሌላኛው ቀን ወደ እኔ የመጣው ሰው እንደገና ተገለጠልኝ፡፡” 11ማኑሄም ተነሳና ሚስቱን ተከተላት፡፡ ወደ ሰውዮውም በመጣ ጊዜ እንዲህ አለው፣ “ከሚስቴ ጋር የተነጋገርህ ሰው አንተ ነህን?” ሰውየውም፣ “እኔ ነኝ” አለው፡፡12 ስለዚህ ማኑሄ እንዲህ አለ፣ “አሁንም ቃሎችህ እውነት ይሁኑ፡፡ ነገር ግን ልጁ የሚመራው በምንድን ነው፣ እኛስ ለእርሱ የምንሰራው ምንድን ነው?” 13የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄ እንዲህ አለው፣ “እርስዋ የነገርኋትን ነገር ሁሉ በጥንቃቄ ማድረግ አለባት፡፡ 14ከወይን ከሚወጣው ማንኛውንም ነገር አትብላ፣ የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ሌላ ጠንካራ መጠጥ አትጠጣ፤ ሕጉ ርኩስ ነው ብሎ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብላ፡፡ እኔ እንድታደርገው ያዘዝኋትን ማንኛውንም ነገር መታዘዝ አለባት፡፡15 ማኑሄም ለእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “ለአንተ የፍየል ጠቦት ለማዘጋጀት ጊዜ እናገኝ ዘንድ፣ እባክህ ለአጭር ጊዜ ቆይ፡፡” 16የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄ እንዲህ አለው፣ “ብቆይም እንኳ፣ መብልህን አልበላም፡፡ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ፣ ያንን ለእግዚአብሔር አቅርበው፡፡” ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር፡፡17 ማኑሄም ለእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “የተናገርሃቸው ቃሎች እውነት በሆኑ ጊዜ እናከብርህ ዘንድ ስምህ ማን ነው?”18የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ አለው፣ “ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? ስሜ ድንቅ ነው!”19 ስለዚህ ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቍርባን ጋር ወሰደና በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው፡፡ ማኑሄና ሚስቱ እያዩ እርሱ አስደናቂ ነገር አደረገ፡፡20ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ላይ ዐረገ፡፡ ማኑሄና ሚስቱም ይህን ተመለከቱና በግምባራቸው ምድር ላይ ተደፉ፡፡21 የእግዚአብሔርም መልአክ ላማኑሄ ወይም ለሚስቱ እንደገና አልተገለጠም፡፡ ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ፡፡ 22ማኑሄም ለሚስቱ እንዲህ አላት፣ “እግዚአብሔርን ስላየን በእርግጠኝነት እንሞታለን፡፡”23ነገር ግን ሚስቱ እንዲህ አለችው፣ “እግዚአብሔር ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፣ ለእርሱ ያቀረብነውን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባልተቀበለን ነበር፡፡ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን ነበር፣ በዚህ ጊዜ እንዲህ ያሉ ነገሮችንም እንድንሰማ ባላደረገን ነበር፡፡”24 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፣ ስሙንም ሳምሶን ብላ ጠራችው፡፡ ልጁም አደገ እግዚአብሔርም ባረከው፡፡ 25የእግዚአብሔርም መንፈስ እርሱን በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ያነቃቃው ጀመር፡፡
1 ሳምሶንም ወደ ተምና ወረደ፣ በዚያም ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች አንዲት ሴት አየ፡፡2ከዚያ በተመለሰ ጊዜ፣ ለአባቱና ለእናቱ እንዲህ ሲል ነገራቸው፣ “በተምና ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች መካከል አንዲት ሴት አየሁ፡፡ ሚስቴ እንድትሆነኝ አሁን እርስዋን አምጡልኝና አጋቡኝ፡፡3 ነገር ግን እንዲህ አሉት፣ “ከዘመዶችህ ሴቶች ልጆች ወይም ከሕዝባችን ሁሉ መካከል ሴት የለምን? ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለመውሰድ ትሄሄዳለህን?” ሳምሶንም ለአባቱ እንዲህ አለው፣ “እርስዋን አምጣልኝ፣ እርስዋን ባየኋት ጊዜ ደስ አሰኝታኛለችና፡፡”4ነገር ግን አባቱና እናቱ ይህ ነገር የመጣው ከእግዚአብሔር እንደሆነ አላወቁም፣ እርሱ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ግጭት ለመፍጠር ይፈልግ ነበርና፡፡ በዚያን ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ይገዙ ነበርና፡፡5 ከዚያም ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ተምና ወረዱ፣ እነርሱም በተምና ወዳለው ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ መጡ፡፡ ከዚያም ከአንበሳ ደቦሎች መካከል አንዱ ተነስቶ መጣና በእርሱ ላይ አገሳበት፡፡ 6የእግዚአብሔር መንፈስ በድንገት በእርሱ ላይ ወረደ፣ ትንሽ የፍየል ጠቦት እንደሚቆራርጥ እንዲሁ አንበሳውን በቀላሉ ቈራረጠው፣ በእጁም ምንም ነገር አልያዘም ነበር፡፡ ነገር ግን ያደረገውን ነገር ለአባቱ ወይም ለእናቱ አልነገራቸውም፡፡7 እርሱም ሄደና ከሴቲቱ ጋር ተነጋገረ፣ እርስዋንም ባያት ጊዜ ሳምሶንን ደስ አሰኘችው፡፡8ከጥቂትም ቀን በኋላ ሊያገባት ተመለሰ፣ የአንበሳውንም በድን ያይ ዘንድ ከመንገድ ዘወር አለ፡፡ በአንበሳ በድን ትራፊ ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮበት ነበር፣ ማርም ነበረበት፡፡9ማሩንም በእጁ ወስዶ መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፡፡ ወደ አባቱና ወደ እናቱ በመጣ ጊዜ፣ ለእነርሱም ሰጣቸውና እነርሱም በሉ፡፡ ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን ትራፊ ውስጥ እንደ ሆነ አልነገራቸውም፡፡10 የሳምሶን አባትም ሴቲቱ ወደ ነበረችበት ወረደ፣ ሳምሶንም በዚያ ግብዣ አደረገ፣ ይህን ማድረግ የወጣት ወንዶች ወግ ነበርና፡፡ 11የእርስዋ ዘመዶች ባዩት ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ይሆኑ ዘንድ ሌሎች ሠላሳ ጓደኞች አመጡለት፡፡12 ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “አሁን እንቆቅልሽ ልንገራችሁ፡፡ ከእናንተ ውስጥ አንዱ ሰው እንቆቅልሹን ማግኘት ቢችልና በሰባቱ የግብዣ ቀኖች ውስጥ መልሱን ቢነግረኝ፣ ሠላሳ የቀጭን በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ እሰጠዋለሁ፡፡ 13ነገር ግን እናንተ መልሱን ልትነግሩኝ ካልቻላችሁ፣ ሠላሳ የቀጭን በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ ትሰጡኛላችሁ፡፡” እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “እንሰማው ዘንድ እንቆቅልሽህን ንገረን፡፡”14እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ከበላተኛው ውስጥ መብል ወጣ፤ ከብርቱም ውስጥ ጣፋጭ ወጣ፡፡” ነገር ግን የእርሱ እንግዶች በሦስት ቀን ውስጥ መልሱን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡15በአራተኛውም ቀን ለሳምሶን ሚስት እንዲህ አሏት፣ “የእንቈቅልሹን መልስ እንዲነግረን ባልሽን አግባቢልን፣ አለዚያ ግን እንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፡፡ ወደዚህ የጠራችሁን ድሃ ልታደርጉን ነውን፡፡”16 የሳምሶን ሚስት በፊቱ ማልቀስ ጀመረች፤ እንዲህም አለችው፣ “ይህን ሁሉ ያደረግኸው እኔን ስለምትጠላኝ ነው! አንተ አትወደኝም፡፡ ከሕዝቤ ውስጥ ለአንዳንዶቹ እንቈቅልሽ ነግረሃቸዋል፣ ነገር ግን መልሱን ለእኔ አልነገርኸኝም፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “ወደዚህ ተመልከቺ፣ ለአባቴና ለእናቴ ካልነገርኋቸው፣ ለአንቺ ልነግርሽ ይገባልን?”17ግብዣቸው በሚቆይበት በሰባቱም ቀናት ውስጥ በፊቱ አለቀሰች፡፡ መልሱንም በሰባተኛው ቀን ነገራት ምክንቱም እጅግ በጣም አጥብቃ ስለነዘነዘችው ነው፡፡ መልሱንም ለሕዝቧ ዘመዶች ነገረቻቸው፡፡18በሰባተኛው ቀን ፀሐይ ከመግባትዋ በፊት የከተማይቱ ሰዎች እንዲህ አሉት፣ “ከማር የበለጠ የሚጣፍጥ ምንድን ነው? ከአንበሳስ የበለጠ የሚበረታ ምንድን ነው?” ሳምሶንም እንዲህ አላቸው፣ “በጊደሬ ባታርሱ ኖሮ፣ ለእንቈቅልሼ መልስ ባላገኛችሁ ነበር፡፡”19 በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በድንገት በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደ፡፡ ሳምሶንም ወደ አስቀሎና ወረደና ከሕዝቡ መካከል ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፡፡ እርሱም የለበሱትን ሁሉ ከገፈፈ በኋላ ልብሳቸውን በሙሉ ወስዶ እንቈቅልሹን ለመለሱለት ሰዎች ሰጣቸው፡፡ እርሱም በጣም ተናደደና ወደ አባቱ ቤት ወጣ፡፡ 20የሳምሶን ሚስት ግን በጣም ቅርብ ለሆነው ጓደኛው ተሰጠች፡፡
1 ከጥቂት ቀናትም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ፣ ሳምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደ፡፡ ለራሱም እንዲህ አለ፣ “ወደ ሚስቴ ወደ ጫጉላው ቤት ልግባ፡፡” ነገር ግን አባትዋ ወደ ውስጥ እንዳይገባ ከለከለው፡፡ 2አባትዋም እንዲህ አለ፣ “እኔ በእርግጠኝነት የጠላሃት መሰለኝ፣ ስለዚህም ለጓደኛህ ሰጠኋት፡፡የእርስዋ ታናሽ እኅት ከርስዋ የበለጠች ቆንጆ ናት፣ አይደለችም እንዴ? በእርስዋ ፋንታ ታናሽዋን ውሰዳት፡፡”3 ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ጉዳት ባደረስሁባቸው ጊዜ እኔ ንጹሕ ነኝ፡፡”4ሳምሶንም ሄደና ሦስት መቶ ቀበሮዎች ያዘ፣ ሁለት ሁለቱንም ቀበሮዎች በአንድ ላይ በጅራታቸው አሰራቸው፡፡ ከዚያም ችቦዎችን ወስዶ በእያንዳንዱ ጥንድ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አሰራቸው፡፡5 ችቦውንም በእሳት ባቀጣጠለው ጊዜ፣ ቀበሮዎቹን በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል እንዲሄዱ አደረጋቸው፣ የእህሉን ነዶና በእርሻ ውስጥ የቆመውንም እህል፣ ከወይኑ አትክልት ስፍራና ከወይራውም ተክል ጋር አቃጠሉት፡፡6ፍልስጥኤማውያንም እንዲህ በማለት ጠየቁ፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” እነርሱም “ይህን ያደረገው የተምናዊው አማች ሳምሶን ነው፣ ምክንያቱም ተምናዊው የሳምሶንን ሚስት ወስዶ ለጓደኛው ሰጥቶአታልና” አሉ፡፡ ፍልስጥኤማያንም ሄደው እርስዋንና አባትዋን በእሳት አቃጠሉ፡፡7 ሳምሶንም “እናንተ ይህንን ካደረጋችሁ፣ እኔ እበቀላችኋለሁ፣ እኔ የማርፈው ይህን ካደረግሁ በኋላ ነው” አላቸው፡፡ 8እርሱም ዳሌአቸውንና ጭናቸውን ቆራረጣቸውና በታላቅ አገዳደል ገደላቸው፡፡ ከዚያም ወርዶ በኤጣም ዓለት ባለው ዋሻ ውስጥ ተቀመጠ፡፡9 የዚያን ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ወጡና በይሁዳ ጦርነት ለማካሄድ ተዘጋጁ፣ ሰራዊታቸውንም በሌሒ ውስጥ አሰፈሩ፡፡ 10የይሁዳም ሰዎች እንዲህ አሉ፣ “እኛን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?” እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “የምንወጋችሁ ሳምሶንን ለመያዝ ነው፣ እርሱ በእኛ ላይ እንዳደረገው እኛም በእርሱ ላይ ልናደርግበት ነው፡፡”11ሦስት ሺህ የይሁዳ ሰዎችም በኤጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወረዱና፣ ለሳምሶን እንዲህ አሉት፣ “ፍልስጥኤማውያን በእኛ ላይ ገዢዎች እንደሆኑ አታውቅምን? ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “እነርሱ በእኔ ላይ አደረጉብኝ፣ እኔም በእነርሱ ላይ አደረግሁባቸው፡፡”12 እነርሱም ለሳምሶን እንዲህ አሉት፣ “አንተን አስረን ለፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ ራሳችሁ እንደማትገድሉኝ ማሉልኝ፡፡”13እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “አንገድልህም፣ በገመድ አስረን ብቻ ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን፡፡ እንደማንገድልህ ቃል እንገባልሃለን፡፡” ከዚያም በሁለት አዲስ ገመዶች አሰሩትና ከዓለቱ ውስጥ አወጡት፡፡14ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን እየጮሁ መጡ፣ አገኙትም፡፡ የዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል ወረደበት፡፡ ክንዶቹ የታሰሩበት ገመዶችም በእሳት እንደ ተቃጠለ የተልባ እግር ፈትል ከእጆቹ ላይ ወደቁ፡፡15ሳምሶንም አዲስ የአህያ መንጋጋ አገኘ፣ እጁንም ዘርግቶ አነሳውና በእርሱ አንድ ሺህ ሰዎች ገደለ፡፡ 16ሳምሶንም እንዲህ አለ፣ “በአህያ መንጋጋ ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፣ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰዎች ገድያለሁ፡፡”17 ሳምሶንም መናገሩን በፈጸመ ጊዜ፣ የአህያ መንጋጋውን ከእጁ ጣለው፣ ያም ስፍራ ራማትሌሒ ተብሎ ተጠራ፡፡ 18ሳምሶን በጣም ተጠምቶ ነበርና ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጮኸ፣ “አንተ ይህን ታላቅ ድል ለአገልጋይህ ሰጥተሃል፣ ነገር ግን አሁን በጥም እሞታለሁ፣ ባልተገረዙትም ሰዎች እጅ እወድቃለሁ፡፡”19እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን ክፍት ስፍራ ሰንጥቆ ከፈተው፣ ከእርሱም ውኃ ወጣ፡፡እርሱም በጠጣ ጊዜ፣ ብርታቱ ተመለሰና ተጠናከረ፡፡ ስለዚህ የዚያ ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ተብሎ ተጠራ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ ይገኛል፡፡ 20ሳምሶን በፍልስጥኤማውያን ዘመን በእስራኤል ላይ ለሀያ ዓመት ፈረደ፡፡
1 ሳምሶን ወደ ጋዛ ሄደና በዚያ ዝሙት አዳሪ ሴት አየ፣ ከእርስዋም ጋር ወደ አልጋ ሄደ፡፡2የጋዛ ሰዎችም “ሳምሶን ወደዚህ መጥቶአል” የሚል ወሬ ሰሙ፡፡ የጋዛ ሰዎች ስፍራውን ከበቡትና ሌሊቱን ሁሉ ተደብቀው በከተማይቱ በር ጠበቁት፡፡ ሌሊቱን ሁሉ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፡፡ እንዲህ ብለዋልና፣ “እስኪነጋ ድረስ እንጠብቀው፣ ከዚያም እንገድለዋለን፡፡”3ሳምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በአልጋ ላይ ተኛ፡፡ እኩለ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ተነሳና የከተማይቱን በር መዝጊያና ሁለቱን መቃኖች ያዘ፡፡ እነርሱንም ከመወርወሪያው ጋር ከመሬት ነቀላቸው፣ በትከሻውም ላይ አደረጋቸው፣ በኬብሮንም ፊት ለፊት ወዳለው ኮረብታ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ፡፡4 ከዚህ በኋላ ሳምሶን በሶሬቅ ሸለቆ የምትኖር አንዲት ሴት ወደደ፡፡ ስምዋም ደሊላ ይባል ነበር፡፡5የፍልስጥኤማውያንም አለቆች ወደ እርስዋ መጡና እንዲህ አሏት፣ “እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ በእርሱ ያለው ታላቅ ኃይል የት እንደሆነና በምን መንገድ እርሱን ማሸነፍ እንደምንችል እንዲያሳይሽ ሳምሶንን አባብዪው፡፡ ይህንን አድርጊልን፣ እኛም እያንዳንዳችን 1, 100 ብር እንሰጥሻለን፡፡6 ደሊላም ለሳምሶን እንዲህ አለችው፣ “እባክህ፣ እንዲህ በጣም ብርቱ የሆንከው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፣ በቁጥጥር ስር መዋል እንድትችል ሰው ሊያስርህ የሚችለው እንዴት ነው?7ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “ባልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች ቢያስሩኝ፣ እደክማለሁ፣ እንደ ማንኛውም ሰውም እሆናለሁ፡፡”8 የፍልስጥኤማውያን አለቆችም ያልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች አመጡላት፣ እርስዋም ሳምሶንን በእነርሱ አሰረችው፡፡ 9በዚህን ጊዜ በጓዳዋ ውስጥ ሰዎች በምስጢር ተደብቀው ይጠብቁ ነበር፡፡ እርስዋም፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው፡፡ ነገር ግን የተልባ እግር ፈትል እሳት በነካው ጊዜ እንደሚበጣጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፡፡ እነርሱም የብርታቱ ምስጢር ምን እንደሆነ አላወቁም፡፡10 ከዚያም ደሊላ ሳምሶንን እንዲህ አለችው፣ “አንተ እኔን እንዴት እንዳታለልኸኝ ግልጽ ሆኗል፣ ሐሰትንም ነገርኸኝ፡፡ እባክህ፣ እንዴት እንደምትታሰር ንገረኝ፡፡”11እርሱም እንዲህ አላት፣ “ለሥራ ጥቅም ላይ ፈጽሞ ባልዋሉ በአዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ፣ እደክማለሁ፣ እንደ ማንኛውም ሰው እሆናለሁ፡፡”12ስለዚህ ደሊላ አዲስ ገመዶች ወሰደችና በእነርሱ አሰረችው፣ እንዲህም አለችው፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ፡፡” ተደብቀው ሲጠብቁ የነበሩት ሰዎች በጓዳዋ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሳምሶን ገመዶቹን እንደ ፈትል ክር ከክንዶቹ በጣጠሰው፡፡13 ደሊላም ሳምሶንን እንዲህ አለችው፣ “እስከ አሁን ድረስ አታልለኸኛልና የነገርኸኝም ውሸት ነው፡፡ አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “የራሴን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድር ጋር ጎንጉነሽ በችካል ብትቸክዪው፣ እንደ ሌላ ሰው እሆናለሁ፡፡”14እርሱም በተኛ ጊዜ፣ ደሊላ የራሱን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድሩ ጋር ጐነጐነችው፣ በችካልም ቸከለችውና፣ እንዲህ አለችው፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” እርሱም ከእንቅልፉ ነቃና ችካሉን ከነቆንዳላውና ከነድሩ ነቀለው፡፡15 እርስዋም እንዲህ አለችው፣ “ምስጢርህን ለእኔ ሳትነግረኝ ‘እወድሻለሁ’ ልትለኝ እንዴት ትችላለህ? ሦስት ጊዜ ቀለድህብኝ፣ እንዲህ ዓይነቱን ታላቅ ኃይል እንዴት ሊኖርህ እንደቻለ አልነገርኸኝም፡፡”16ሞት እስኪመኝ ድረስ ዕለት ዕለት በቃሎችዋ እጅግ በጣም ጨቀጨቀችው፣ ከመጠን በላይም ጫና አደረገችበት፡፡17 ስለዚህ ሳምሶን ሁሉንም ነገር ነገራትና እንዲህ አላት፣ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ሆኜ ስለተለየሁ በራሴ ላይ ምላጭ ደርሶና ጸጉሬን ተላጭቼ አላውቅም፡፡ የራሴን ጸጕር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል፣ እደክማለሁም እንደ ማንኛውም ሰው እሆናለሁ፡፡”18 ደሊላም ስለ ሁሉ ነገር እውነቱን እንደነገራት ባየች ጊዜ፣ ሰዎች ላከችና የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ጠራች፣ እንዲህም አለቻቸው፣ “ሁሉንም ነገር ነግሮኛልና እንደገና ኑ፡፡” የዚያን ጊዜ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርስዋ ሄዱ፡፡19እርስዋም በጭኗ ላይ እንዲተኛ አደረገችው፡፡ ሰባቱን የራሱን ጕንጕን እንዲላጨው አንድ ሰው ጠራች፣ ኃይሉ ስለተለየው እርስዋ በቁጥጥሯ ስር ልታደርገው ጀመረች፡፡20 እርስዋም፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው፡፡ እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ እንዲህ አለ፣ “እንደ ሌላው ጊዜ እወጣለሁ፣ ራሴንም ነጻ አወጣለሁ፡፡” ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ተወው አላወቀም፡፡21ፍልስጥኤማውያንም ያዙትና ዓይኖቹን አወጡት፡፡ ወደ ጋዛም ወሰዱትና በናስ ሰንሰለት አሰሩት፡፡ በእስር ቤትም ውስጥ ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር፡፡22ነገር ግን ከተላጨ በኋላ የራሱ ጠጕር እንደገና ያድግ ጀመር፡፡23 የፍልስጥኤማውያንም አለቆች ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፣ ደስም ይላቸው ዘንድ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ እነርሱ “አምላካችን ጠላታችንን ሳምሶንን አሸንፏል፣ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል” ብለዋልና፡፡24ሕዝቡም እርሱን ባዩት ጊዜ አምላካቸውን አመሰገኑ፣ እንዲህ ብለዋልና፣ “አገራችንን ያጠፋውን፣ ከእኛም ብዙ ሰው የገደለውን ጠላታችንን አምላካችን አሸነፈው፣ በእጃችንም አሳልፎ ሰጠው፡፡”25 እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፣ እንዲህ አሉ፣ “እንዲያስቀን ሳምሶንን ጥሩት፡፡” ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠሩትና እንዲስቁ አደረጋቸው፡፡ በምሰሶና በምሰሶ መካከል እንዲቆም አደረጉት፡፡26ሳምሶንም እጁን የያዘውን ልጅ፣ “እደገፍባቸው ዘንድ ሕንጻውን የደገፉትን ምሰሶዎች እንድነካቸው አስጠጋኝ” አለው፡፡27 በዚያን ጊዜ ቤቱ በወንዶችና በሴቶች ተሞልቶ ነበር፡፡ የፍልስጥኤም አለቆች ሁሉ በዚያ ነበሩ፡፡ ሳምሶን እነርሱን ሲያዝናናቸው ይመለከቱ የነበሩ ሦስት ሺህ የሚያህሉ ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ፡፡28 ሳምሶንም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደገና አስበኝ! አምላኬ ሆይ፣ ሁለት ዓይኖቼን ስላወጡ ፍልስጥኤማውያንን አሁን በአንድ ምት እንድበቀል፣ እባክህ፣ ይህን አንድ ጊዜ ብቻ አበርታኝ፡፡”29ሳምሶንም ሕንጻው ተደግፎባቸው የነበሩትን ሁለቱን መካከለኞች ምሰሶዎች ጠምጥሞ ያዘ፣ አንዱን ምሰሶ በቀኝ እጁ ሌላውን ደግሞ በግራ እጁ ይዞ በእነርሱ ላይ ተደገፈ፡፡30 ሳምሶንም እንዲህ አለ፣ “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት!” በሙሉ ኃይሉ ገፋው፣ ሕንጻውም በውስጡ በነበሩት አለቆችና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፡፡ ስለዚህ እርሱ በሞተ ጊዜ የገደላቸው ሰዎች በሕይወት ሳለ ከገደላቸው ይልቅ የበለጡ ነበሩ፡፡31የዚያን ጊዜ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰቦች በሙሉ ወረዱ፣ እርሱንም ይዘው ወሰዱት፣ መልሰው አመጡትና በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ውስጥ ቀበሩት፡፡ ሳምሶን በእስራኤል ላይ ለሀያ ዓመት ፈረደ፡፡
1 በኮረብታማውም በኤፍሬም አገር አንድ ሰው ነበር፣ ስሙም ሚካ ይባላል፡፡ 2ለእናቱም እንዲህ አላት፣ “ከአንቺ ዘንድ ተወስዶ የነበረው 1, 100 ብር፣ የእርግማን ንግግር የተናገርሽበትና እኔም የሰማሁት እነሆ እዚህ አለ! ብሩ በእኔ ዘንድ አለ፡፡ እኔ ሰርቄዋለሁ!” እናቱም እንዲህ አለች፣ “ልጄ ሆይ፣ እግዚአብሔር ይባርክህ!”3 እርሱም 1, 100 ብር ለእናቱ መለሰላት፣ እናቱም እንዲህ አለችው፣ “ስለ ልጄ የተቀረጸ የእንጨት ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል ለማድረግ ይህን ብር ለእግዚአብሔር ለይቼዋለሁ፡፡ ስለዚህ አሁን፣ ለአንተ መልሼዋለሁ፡፡” 4ለእናቱም ገንዘቡን በመለሰላት ጊዜ፣ እናቱ ሁለቱን መቶ ብር ወሰደችና የተቀረጸ የእንጨት ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጎ ለሰራው ለብረት ሰራተኛ ሰጠችው፡፡ ያም በሚካ ቤት ተቀመጠ፡፡5 ሚካ የተባለውም ሰው የጣዖታት አምልኮ ቤት ነበረውና አንድ ኤፉድና ተራፊም ሰራ፣ ከልጆቹም አንዱ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ፡፡6በዚያን ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፣ ሰውም ሁሉ በዓይኖቹ ፊት ትክክል መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር፡፡7 አሁን በቤተ ልሔም ይሁዳ ከይሁዳ ወገን የሆነ አንድ ሌዋዊ ወጣት ሰው ነበረ፡፡ እርሱም ተግባሩን ለመፈጸም በዚያም ይቀመጥ ነበር፡፡ 8ይህ ሰው የሚቀመጥበትን ስፍራ ለመፈለግ ቤተ ልሔም ይሁዳን ለቅቆ ሄደ፡፡ ሲጓዝም ወደ ኮረብታማው የኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጣ፡፡ 9ሚካም ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ከወዴት መጣህ?” እርሱም እንዲህ አለው፣ “እኔ ከቤተ ልሔም ይሁዳ የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፣ የምኖርበትን ስፍራ ለማግኘት እየተጓዝሁ ነው፡፡”10 ሚካም እንዲህ አለው፣ “ከእኔ ጋር ተቀመጥ፣ ለእኔም አማካሪና ካህን ሁነኝ፡፡ እኔም በየዓመቱ አሥር ብር፣ እንደዚሁም ልብሶችንና ምግብህን እሰጥሃለሁ፡፡” ስለዚህ ሌዋዊው ወደ ቤቱ ገባ፡፡ 11ሌዋዊውም ከሰውዮው ጋር ለመቀመጥ ፈቃደኛ ሆነ፣ ወጣቱም ሰው ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት፡፡12 ሚካም ሌዋዊውን ለተቀደሰ ሃላፊነት ቀደሰው፣ ወጣቱም ሰው ካህኑ ሆነለት፣ በሚካም ቤት ነበረ፡፡13ከዚያም ሚካ እንዲህ አለ፣ “አሁን እግዚአብሔር ለእኔ መልካም እንደሚሰራልኝ አውቄአለሁ፣ ምክንያቱም ይህ ሌዋዊ ካህን ሆኖልኛል፡፡”
1 በዚያን ዘመን በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ አልነበረም፡፡ የዳን ነገድ ተወላጆች የሚቀመጡበትን ርስት ይፈልጉ ነበር፣ እስከዚያ ቀን ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልተቀበሉም ነበርና፡፡ 2የዳን ሰዎች ከአጠቃላይ ወገናቸው በሙሉ ከጾርዓ ጀምሮ እስከ ኤሽታኦል ድረስ በጦርነት ልምድ ያላቸውን አምስት ሰዎች በእግራቸው ሄደው ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲያዩ ላኩ፡፡ ለእነርሱም እንዲህ አሉአቸው፣ “ሂዱና ምድሪቱን ሰልሉ፡፡” እነርሱም ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጡና ሌሊቱን በዚያ አሳለፉ፡፡3 በሚካ ቤት አጠገብ በነበሩ ጊዜ፣ የአንድ ወጣት ሌዋዊ ንግግር አወቁ፡፡ ስለዚህ አስቆሙትና እንዲህ ብለው ጠየቁት፣ “ወደዚህ ማን አመጣህ? በዚህ ስፍራ ምን ታደርጋለህ? ለምን ወደዚህ መጣህ?” 4እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ሚካ ለእኔ ያደረገው ነገር ይህ ነው፡- የእርሱ ካህን እንድሆን ቀጠረኝ፡፡”5 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “የምንሄድበት መንገድ መቃናቱን ወይም አለመቃናቱን እናውቅ ዘንድ፣ እባክህ፣ የእግዚአብሔርን ምክር ጠይቅልን፡፡” 6ካህኑም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “በሰላም ሂዱ፡፡ ልትሄዱ በሚገባችሁ መንገድ እግዚአብሔር ይመራችኋል፡፡”7 የዚያን ጊዜ አምስቱ ሰዎች ሄዱና ወደ ላይሽ መጡ፣ ሲዶናውያን በጸጥታ ያለስጋት ይኖሩ እንደነበረ ሁሉ፣ በዚያም ተዘልለው ይኖሩ የነበሩትን ሕዝብ አዩ፡፡ በምድሪቱም በየትኛውም መልኩ የገዛቸው፣ ወይም ያስቸገራቸው አልነበረም፡፡ ከሲዶናውያን በጣም ርቀው ይኖሩ ነበር፣ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡8በጾርዓና በኤሽታኦል ውስጥ ወደነበሩት ወንድሞቻቸው ተመለሱ፡፡ ዘመዶቻቸውም እንዲህ ብለው ጠየቁአቸው፣ “ምን ወሬ ይዛችኋል?”9 እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ኑ! እንውጋቸው! ምድሪቱን አይተናታል፣ በጣም ጥሩ ናት፡፡ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ምድሪቱን ከመውጋትና ከመውረስ አትዘግዩ፡፡ 10በሄዳችሁ ጊዜ፣ ያለ ስጋት እንደሚኖሩ ወደሚያስቡ ሕዝብ ትደርሳላችሁ፣ ምድሪቱም ሰፊ ናት! እግዚአብሔርም ለእናንተ ሰጥቶአችኋል፣ በምድር ካለው ነገር ሁሉ አንዳች የማይጎድልባት ስፍራ ናት፡፡11 ከዳን ወገን የሆኑና የጦር መሳርያ የታጠቁ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሥተው ሄዱ፡፡ 12እነርሱም ሄዱና በይሁዳ ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዳን ሰፈር ብለው የሚጠሩት ለዚህ ነው፤ እርሱም ከቂርያትይዓሪም በምዕራብ በኩል ነው፡፡13 እነርሱም ከዚያ ተነስተው ወደ ኮረብታማው የኤፍሬም አገር አልፈው ሄዱ፣ ወደ ሚካም ቤት መጡ፡፡14ከዚያም የላይሽን አገር ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ለዘመዶቻቸው እንዲህ አሉአቸው፣ “በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ኤፉድና ተራፊም፣ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል እንዳሉ ታውቃላችሁን? ምን እንደምታደርጉ አሁን ወስኑ፡፡”15 ስለዚህ ከዚያ ዘወር አሉና ወጣቱ ሌዋዊ ይኖርበት ወደነበረው ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላምታም አቀረቡለት፡፡ 16በዚያን ጊዜ የጦር መሳርያ የታጠቁት ስድስት መቶ ዳናውያን በበሩ መግቢያ ቆሙ፡፡17 ካህኑ የጦር መሳርያ ከታጠቁት ከስድስት መቶ ሰዎች ጋር በበሩ አካባቢ ቆሞ በነበረበት ጊዜ፣ ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ወደዚያ ሄዱና የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ፡፡18እነዚህ ወደ ሚካ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል በወሰዱ ጊዜ፣ ካህኑ ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ምን ታደርጋላችሁ?”19 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “ዝም በል! እጅህን በአፍህ ላይ ጫንና ከእኛ ጋር ና፣ ለእኛም አባትና ካህን ሁንልን፡፡ ለአንተስ ለአንድ ሰው ቤት ካህን መሆን ወይስ በእስራኤል ውስጥ ላለው ነገድና ወገን ሁሉ ካህን መሆን ይሻልሃል?” 20የካህኑም ልብ ደስ አለው፡፡ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና የተቀረጸውንም ምስል ወሰደና ከሕዝቡ ጋር ሄደ፡፡21 ስለዚህ እነርሱ ዞሩና ሄዱ፡፡ ሕፃናቶችን፣ ከብቶችንና ንብረታቸውን በፊታቸው አስቀደሙ፡፡22ከሚካም ቤት ጥቂት በራቁ ጊዜ፣ በሚካ ቤት አጠገብ በነበሩት ቤቶች ውስጥ የነበሩ ሰዎች ተጠራርተው ተሰበሰቡ፣ የዳን ሰዎችንም ተከትለው ደረሱባቸው፡፡23ወደ ዳንም ሰዎች ጮኹ፣ ዘወር ብለው ለሚካም እንዲህ አሉት፣ “ተሰብስባችሁ በአንድ ላይ የመጣችሁት ለምንድን ነው?”24 እርሱም፣ “የሠራኋቸውን አማልክቴን ሰረቃችሁ፣ ካህኔንም ይዛችሁ ሄዳችሁ፡፡ ሌላ ምን የቀረኝ ነገር አለ? ‘ያስጨነቀህ ምንድን ነው?’ ብላችሁ እንዴት ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ፡፡” 25የዳን ሰዎችም እንዲህ አሉት፣ “ምንም ዓይነት ንግግር ስትናገር እንድንሰማ አታድርገን፣ አለዚያ አንዳንድ የተቈጡ ሰዎች ይጎዱሃል፣ አንተና ቤተሰቦችህም ትሞታላችሁ፡፡” 26የዚያን ጊዜ የዳን ሰዎች መንገዳቸውን ሄዱ፡፡ ሚካ ከእርሱ ይልቅ እነርሱ እጅግ በጣም የበረቱ እንደሆኑ ባየ ጊዜ፣ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡27 የዳን ሰዎችም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወሰዱና ወደ ላይሽ መጡ፣ በሰላምና ያለ ስጋት ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ መጥተው በሰይፍ ስለት ገደሉአቸው፣ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሉአት፡፡28እነርሱን የሚያድን አንድም ሰው አልነበረም ምክንያቱም ከተማይቱ ከሲዶና በጣም ራቅ ያለች ነበረች፣ እነርሱም ከሌሎች ሰዎች ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡ እርስዋም በቤትሮዖብ አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ነበረች፡፡ የዳን ሰዎችም ከተማይቱን እንደገና ሠሩና ተቀመጡባት፡፡29ከተማይቱንም ከእስራኤል ወንዶች ልጆች አንዱ በሆነው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ የከተማይቱ ስም ላይሽ ነበረ፡፡30 የዳን ሰዎችም ለራሳቸው የተቀረጸ ምስል አቆሙ፣ የሙሴ ልጅ የጌርሳም ልጅ ዮናታን፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹ ምድሪቱ እስከምትያዝበት ቀን ድረስ ለዳን ሰዎች ካህናት ነበሩ፡፡ 31ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ ሚካ የሰራውን የተቀረጸ ምስል አመለኩ፡፡
1 በዚያም ዘመን፣ በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ ባልነበረበት ጊዜ፣ በኮረብታማው የኤፍሬም አገር እጅግ በጣም ሩቅ በሆነ አካባቢ ለአጭር ጊዜ የኖረ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም አንዲትን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት፡፡2ነገር ግን ቁባቱ ለእርሱ ታማኝ አልነበረችም፤ እርሱን ተወችውና ተመልሳ ወደ አባትዋ ቤት ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄደች፡፡ እርስዋም በዚያ አራት ወር ቆየች፡፡3 የዚያን ጊዜ ባልዋ ተነሣና ተመልሳ ወደ እርሱ እንድትመጣ ለማባበል ተከትሏት ሄደ፡፡ የእርሱ አገልጋይና ሁለት አህዮች ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ እርስዋም ወደ አባትዋ ቤት አስገባችው፡፡የልጅቱ አባት ባየው ጊዜ ደስ አለው፡፡4የልጂቱ አባት፣ አማቱም በቤቱ ለሦስት ቀን እንዲቆይ ለመነው፡፡ እነርሱም በሉ፣ ጠጡ፣ ሌሊቱንም በዚያ አሳለፉ፡፡5 በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፣ እርሱም ለመሄድ ተዘጋጀ፣ ነገር ግን የልጂቱ አባት አማቹን እንዲህ አለው፣ “እንድትበረታ እንጀራ ብላ፣ ከዚያ መሄድ ትችላለህ፡፡”6ስለዚህ ሁለቱም በአንድ ላይ ለመብላትና ለመጠጣት ተቀመጡ፡፡ ከዚያም የልጂቱ አባት እንዲህ አለ፣ “እባክህ ሌሊቱን ደግሞ እዚህ ለማሳለፍ ፈቃደኛ ሁን፣ መልካም ጊዜም ይሁንልህ፡፡”7 ሌዋዊው ለመሄድ በማለዳ በተነሳ ጊዜ፣ የወጣቷ ሴት አባት እንዲቆይ ለመነው፣ ከዚህ የተነሳ እቅዱን ለወጠና ሌሊቱን በዚያ አሳለፈ፡፡8በአምስተኛው ቀን ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፣ ነገር ግን የልጂቱ አባት እንዲህ አለ፣ “ሰውነትህን አበርታ፣ እስከ ማምሻ ድረስ ቆይ አለው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም አብረው በሉ፡፡9 ሌዋዊው፣ ቁባቱና አገልጋዮቹ ለመሄድ በተነሱ ጊዜ፣ የልጂቱ አባት አማቱ እንዲህ አለው፣ “ተመልከት፣ አሁን ቀኑ እየመሸ ነው፡፡ እባክህ ሌላ ሌሊት በዚህ ቆዩ፣ መልካም ጊዜም ይሁንልህ፡፡ ነገ በማለዳ ተነስታችሁ ወደ ቤታችሁ ተመልሳችሁ መሄድ ትችላላችሁ፡፡”10 ነገር ግን ሌዋዊው ሌሊቱን በዚያ ለማሳለፍ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ተነሳና ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለችው ወደ ኢያቡስ ሄደ፡፡ ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩት፣ ቁባቱም ከእርሱ ጋር ነበረች፡፡11ወደ ኢያቡስም በቀረቡ ጊዜ መሸባቸው፣ አገልጋዩም ለጌታው እንዲህ አለው፣ “ና፣ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ እንሂድና ሌሊቱን በዚያ እናሳልፍ፡፡”12 ጌታውም፣ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን ወዳልሆነ ወደ እንግዳ ሕዝብ ከተማ ውስጥ አንገባም፡፡ እኛ ወደ ጊብዓ እንሄዳለን፡፡”13ሌዋዊውም ለወጣቱ ሰው እንዲህ አለው፣ “ና፣ ከእነዚህ ስፍራዎች ወደ አንዱ እንሂድ፣ ሌሊቱንም በጊብዓ ወይም በራማ እናሳልፍ፡፡”14 ስለዚህ መንገዳቸውን ቀጠሉ፣ የብንያም ነገድ ወደምትሆነው ወደ ጊብዓ ግዛት ሲቀርቡ ፀሐይ ገባችባቸው፡፡ 15እነርሱም ሌሊቱን በጊብዓ ለማሳለፍ ወደዚያ አቀኑ፡፡ እርሱም ወደ ውስጥ ገባና በከተማው አደባባይ ተቀመጠ፣ ሌሊቱን በዚያ ያሳልፉ ዘንድ ወደ ቤቱ የወሰዳቸው ማንም ሰው አልነበረምና፡፡16 ነገር ግን በዚያን ጊዜ አንድ ሽማግሌ ሰው ከእርሻ ሥራው በምሽት እየመጣ ነበር፡፡ እርሱም ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር ነበረ፣ እርሱም በጊብዓ በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያ ስፍራ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ብንያማውያን ነበሩ፡፡ 17እርሱም ዓይኑን አነሳና መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየው፡፡ ሽማግሌውም እንዲህ አለ፣ “ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ?”18 ሌዋዊውም እንዲህ አለው፣ “እኛ ከቤተ ልሔም ይሁዳ በጣም ሩቅ ወደሆነው ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር እንሄዳለን፣ እኔም የመጣሁት ከዚያ ነው፡፡ ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄጄ ነበር፣ አሁን ወደ እግዚአብሔር ቤት እየሄድሁ ነው፣ ነገር ግን ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ማንም ሰው የለም፡፡ 19ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፣ ለእኔና እዚህ ላለችው ለሴት አገልጋይህ፣ ከአገልጋዮችህም ጋር ላለው ለዚህ ወጣት ሰው እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፡፡ አንዳችም አላጣንም፡፡”20 ሽማግሌውም ሰላምታ አቀረበላቸው፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን! የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ እኔ እሰጣችኋለሁ፡፡ በአደባባይ ግን ሌሊቱን አትደሩ” አለው፡፡ 21ስለዚህም ሰውየው ሌዋዊውን ወደ ቤቱ ወሰደው፣ ለአህዮቹም ገፈራ ሰጣቸው፡፡ እግራቸውን ታጠቡ፣ በሉም ጠጡም፡፡22 እነርሱም መልካም ጊዜ ነበራቸው፣ ክፉ የሆኑ የከተማይቱ ሰዎች ያደሩበትን ቤት ከበቡ፣ በሩንም ይደበድቡ ነበር፡፡ የቤቱ ባለቤት ለሆነው ለሽማግሌው እንዲህ አሉት፣ “ከእርሱ ጋር መተኛት እንድንችል ወደ ቤትህ የገባውን ሰው አምጣው፡፡”23ሰውየውም፣ የቤቱ ባለቤት፣ ወደ እነርሱ ሄደና እንዲህ አላቸው፣ “አይሆንም፣ ወንድሞቼ ሆይ፣ ይህን ክፉ ነገር እባካችሁ አታድርጉ! ይህ ሰው ወደ ቤቴ የገባ እንግዳ ስለሆነ፣ ይህን ክፉ ነገር አትሥሩ፡፡24 ተመልከቱ፣ ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት እዚህ አሉ፡፡ አሁን ሄጄ ላምጣቸው፡፡ አስነውሩአቸው፣ የፈለጋችሁትንም አድርጉባቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ክፉ ነገር አታድርጉበት!”25ነገር ግን ሰዎቹ እርሱን አልሰሙትም፣ ስለዚህ ሰውዮው ቁባቱን ያዛትና ወደ ውጭ አወጣላቸው፡፡ እነርሱም ያዟትና ከእርሷ ጋር ተኙ፣ ሌሊቱን በሙሉ አመነዘሩባት፣ ጎህም ሲቀድ ለቀቁአት፡፡26ሴቲቱም በማለዳ መጣችና ጌታዋ ባለበት በሰውዮው ቤት በር ወደቀች፣ ጸሐይ እስኪወጣ ድረስ እዚያው ተዘረረች፡፡27 ጌታዋም በማለዳ ተነሣና የቤቱን በር ከፈተ፣ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፡፡ እርሱም ቁባቱ እጅዋን በመድረኩ ላይ ዘርግታ በበሩ ተዘርራ አያት፡፡28ሌዋዊውም እንዲህ አላት፣ “ተነሺ፡፡ እንሂድ፡፡” ነገር ግን ምንም መልስ አልነበረም፡፡ እርሱም በአህያው ላይ ጫናት፣ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ፡፡29 ሌዋዊውም ወደ ቤቱ በመጣ ጊዜ፣ ቢላዋ ወሰደ፣ ቁባቱንም ይዞ ቆራረጣት፣ ብልት በብልት ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ቁራጮቹን ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ላከው፡፡30ይህንን ያየ ሁሉ እንዲህ አለ፣ “የእስራኤል ሕዝብ ከግብፅ ምድር ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልተደረገም ወይም አልታየም፡፡ ስለ ነገሩ አስቡበት! ምክር ስጡን! ምን ማድረግ እንዳለብን ንገሩን!”
1 የዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፣ የገለዓድ አገር ሰዎችንም ጨምሮ፣ በእግዚአብሔር ፊት በምጽጳ ተሰበሰቡ፡፡2የሕዝቡም ሁሉ መሪዎች፣ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ፣ እግረኞች ሆነው በሰይፍ የሚዋጉ 400, 000 ሰዎች በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ውስጥ ስፍራቸውን ያዙ፡፡3 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ እስከ ምጽጳ ድረስ እንደ ሄዱ የብንያም ሕዝብ ሰሙ፡፡ የእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “ይህ ክፉ ነገር እንዴት እንደ ተደረገ ንገሩን?” 4ሌዋዊውም፣ የተገደለችው ሴት ባል፣ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ “እኔና ቁባቴ ሌሊቱን በዚያ ለማሳለፍ የብንያም ግዛት ወደሆነችው ወደ ጊብዓ መጣን፡፡5 በዚያ ሌሊት የጊብዓ ሰዎች በእኔ ላይ ተነሱ፣ ሊገድሉኝም አስበው ቤቱን ከበቡት፡፡ ቁባቴንም ያዙና ከእርስዋ ጋር ተኙ፣ እርስዋም ሞተች፡፡ 6እኔም ቁባቴን ወሰድሁና ሰውነቷን ቆራረኋጥኋት፣ ቁርጥራጩንም በእስራኤል ርስት ወደሚገኝ ወደ እያንዳንዱ ክልል ላክሁት፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነቱን ክፋትና መአት በእስራኤል ላይ ፈጽመዋልና፡፡ 7አሁንም፣ እናንተ እስራኤላውያን ሁላችሁም ተነጋገሩ፣ ምክራችሁንም ስጡ፣ ለዚህ ነገርም ፍርዳችሁን ስጡ!”8 ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በአንድ ላይ ተነሱ፣ እንዲህም አሉ፣ “ከእኛ ዘንድ ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ አይሄድም፣ ማንም ሰው ወደ ቤቱ አይመለስም! 9ነገር ግን አሁንም በጊብዓ ላይ ማድረግ ያለብን ነገር ይህ ነው፡- ዕጣው እንደሚመራን እንወጋታለን፡፡10 ከእስራኤል ነገዶች በሙሉ ለሕዝቡ ስንቅ እንዲይዙ ከመቶው አስር ሰው፣ ከሺህ መቶ ሰው፣ ከአስር ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን፣ ይህም ሕዝቡ ወደ ብንያም ጊብዓ በሚመጣበት ጊዜ እነርሱ በእስራኤል ላይ ለፈጸሙት ክፋት ይቀጧቸው ዘንድ ነው፡፡”11ስለዚህም የእስራኤል ወታደሮች በሙሉ በአንድ ዓላማ በመስማማት በከተማይቱ ላይ ለመዝመት ተሰበሰቡ፡፡12 የእስራኤልም ነገዶች ወደ ብንያም ነገድ ሁሉ እንዲህ ብለው ሰዎችን ላኩ፣ “በእናንተ መካከል የተደረገው ይህ ክፉ ነገር ምንድር ነው?13ስለዚህ እንድንገድላቸውና ይህንን ክፋት ከእስራኤል ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ በጊብዓ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ክፉ ሰዎች አውጥታችሁ ስጡን፡፡” ነገር ግን ብንያማውያን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ሕዝብ ቃል አልሰሙም፡፡14የዚያን ጊዜ የብንያም ሕዝብ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ለመዋጋት ዝግጅት ያደርጉ ዘንድ ከየከተማው ወጥተው ወደ ጊብዓ ተሰበሰቡ፡፡15 የብንያም ሕዝብ ከየከተማው በአንድ ላይ ለመዋጋት መጡ፣ በዚያም ቀን በሰይፍ ስለት ለመዋጋት የሰለጠኑ 26, 000 ወታደሮች ነበሩ፤ ከዚህ በተጨማሪ ከጊብዓ ነዋሪዎች ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ፡፡16ከእነዚህ ወታደሮች መካከል ሰባት መቶ የተመረጡ ግራኝ ሰዎች ነበሩ፤ እያንዳንዳቸውም ድንጋይ ወንጭፈው አንዲት ጠጕርስ እንኳ አይስቱም፡፡17 የእስራኤል ወታደሮች፣ ከብንያም ወገን የሆኑትን ሳይጨምር፣ በሰይፍ ስለት ለመዋጋት የሰለጠኑ አራት መቶ ሺህ ሰዎች ተቆጠሩ፡፡ እነዚህ በሙሉ የጦር ሰዎች ነበሩ፡፡18የእስራኤልም ሕዝብ ተነሱ፣ ወደ ቤቴል ወጡ፣ ከእግዚአብሔርም ምክር ጠየቁ፡፡ እንዲህም ብለው ጠየቁ፣ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት ለእኛ መጀመርያ ማን ይውጣልን?” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ “ይሁዳ በመጀመርያ ይዋጋል፡፡”19 የእስራኤልም ሕዝብ በማለዳ ተነሱና በጊብዓ ፊት ለውጊያ ተዘጋጁ፡፡20የእስራኤልም ወታደሮች ከብንያም ጋር ለመዋጋት ወጡ፡፡ እነርሱም በጊብዓ ከእነርሱ ጋር ለመዋጋት ቦታ ቦታቸውን ይዘው ተሰለፉ፡፡21የብንያም ወታደሮች ከጊብዓ ወጥተው መጡ፣ በዚያም ቀን ከእስራኤላውያን ሰራዊት 22, 000 ሰዎች ገደሉ፡፡22 ነገር ግን የእስራኤል ወታደሮች ራሳቸውን አበረቱ፣ በመጀመርያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደገና ቦታ ቦታቸውን በመያዝ የውጊያውን መስመር አዘጋጁ፡፡23የእስራኤልም ሕዝብ ወደ ላይ ወጡና እስከ ማታ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሱ፡፡ከእግዚአብሔርም ምሪትን ፈለጉ እንዲህም ብለው ጠየቁ፣ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ሕዝብ ጋር ለመዋጋት እንደገና ወደዚያ መቅረብ ይገባናልን?” እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡና ግጠሟቸው” አለ፡፡24 ስለዚህም በሁለተኛው ቀን የእስራኤል ወታደሮች የብንያምን ወታደሮች ለመዋጋት ሄዱ፡፡ 25በሁለተኛው ቀን የብንያም ወታደሮች ከጊብዓ እነርሱን ሊወጉ ወጡና ከእስራኤል ወታደሮች 18, 000 ሰዎች ገደሉ፡፡ እነዚህም ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ለመዋጋት የሰለጠኑ ነበሩ፡፡26 የዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡና አለቀሱ፣ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፣ እነርሱም በዚያ ቀን እስከ ምሽት ድረስ ጾሙ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት አቀረቡ፡፡27 የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን ጠየቁ፣ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በዚያ ነበረ፣28በእነዚህ ጊዜያቶች የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በታቦቱ ፊት ያገለግል ነበር፣ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ሕዝብ ጋር አንድ ጊዜ ለመዋጋት እንደገና እንሂድ ወይስ እንቅር?” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ “ጥቃት ፈጽሙባቸው፣ ነገ እነርሱን እንድታሸንፉ እረዳችኋለሁና፡፡”29 ስለዚህ እስራኤል በጊብዓ ዙሪያ በምስጢራዊ ስፍራዎች የተደበቁ ሰዎች አኖሩ፡፡30የእስራኤል ወታደሮች ከብንያም ወታደሮች ጋር ለሦስተኛ ቀን ተዋጉ፣ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት በጊብዓ ላይ የውጊያ መስመራቸውን ዘርግተው ተሰለፉ፡፡31 የብንያምም ሕዝብ ሄዱና ሕዝቡን ተዋጉ፣ ከከተማይቱም እንዲወጡ ተደረጉ፡፡ ከሕዝቡም አንዳንዶቹን መግደል ጀመሩ፡፡ ከእስራኤልም ወገን የሞቱ ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎች በእርሻዎቹና በመንገዶቹ ነበሩ፣ ከመንገዶቹ አንዱ ወደ ቤቴል የሚወስድ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ ወደ ጊብዓ የሚወስድ ነው፡፡32 የዚን ጊዜ የብንያምም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “እንደ በፊቱ ተሸንፈዋል፣ ከእኛ እየሸሹ ነው፡፡” ነገር ግን የእስራኤል ወታደሮች እንዲህ አሉ፣ “እንሽሽ፣ ከከተማይቱ እንዲወጡና ወደ መንገዶቹ እንዲሄዱ እናድርጋቸው፡፡”33የእስራኤልም ወታደሮች በሙሉ ከስፍራቸው ተነሱና በበኣልታማር ለውጊያ ራሳቸውን አዘጋጅተው ተሰለፉ፡፡ በምስጢራዊ ስፍራ ተደብቀው የነበሩት የእስራኤል ወታደሮችም ከነበሩበት ስፍራ ከጊብዓ ወጥተው ሮጡ፡፡34 ከእስራኤልም ሁሉ 10, 000 የተመረጡ ሰዎች በጊብዓ ላይ መጡ፣ ጦርነቱም በርትቶ ነበር፣ ነገር ግን ብንያማውያን ጥፋት ወደ እነርሱ ቀርቦ እንደነበር አላወቁም፡፡35እግዚአብሔርም ብንያምን በእስራኤል ፊት ድል አደረገ፡፡ በዚያም ቀን የእስራኤል ወታደሮች 25, 100 የብንያም ሰዎችን ገደሉ፡፡ የሞቱት ሰዎች በሙሉ በሰይፍ ለመዋጋት ስልጠና የወሰዱ ነበሩ፡፡36 ስለዚህ የብንያም ወታደሮች እንደ ተሸነፉ አዩ፡፡ የእስራኤልም ሰዎች ለብንያም ስፍራ ለቀቁላቸው፣ ምክንያቱም ከጊብዓ ውጭ በድብቅ ስፍራዎች ባስቀመጡአቸው ሰዎች ላይ ተማምነው ነበርና፡፡37የዚያን ጊዜ ተደብቀው የነበሩት ሰዎች ተነሱና ፈጥነው ወደ ጊብዓ ሮጡ፣ በከተማይቱም ውስጥ የሚኖረውን ሰው በሙሉ በሰይፋቸው ገደሉ፡፡38በእስራኤል ወታደሮችና በምስጢር በተደበቁት ሰዎች መካከል ከከተማው የታላቅ ጢስ ደመና በምልክትነት እንዲያስነሡ ስምምነት ተደርጎ ነበር፡፡39የእስራኤልም ወታደሮች በውጊያው ጊዜ ከጦርነቱ ርቀው እንዲያፈገፍጉ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ ብንያማውያን ማጥቃት ጀመሩ ሠላሳ የእስራኤልንም ሰዎች ገደሉ፣ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “እንደ መጀመርያው የጦርነት ጊዜ በእኛ ፊት መሸነፋቸው እርግጠኛ ነው፡፡”40 ነገር ግን የጢሱ ዓምድ ከከተማው ወደ ላይ መውጣት በጀመረ ጊዜ፣ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ሲመለከቱ ጢሱ ከከተማዋ በሙሉ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፡፡41የዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች ዞረው አጠቋቸው፡፡ የብንያም ሰዎችም ደነገጡ፣ በእነርሱ ላይ ጥፋት እንደመጣባቸው አይተዋልና፡፡42 ስለዚህ ከእስራኤል ወታደሮች ተመልሰው ወደ ምድረ በዳው መንገድ ሸሹ፡፡ ነገር ግን ውጊያው ተከታትሎ ደረሰባቸው፡፡ የእስራኤልም ወታደሮች ከከተማዎቹ ወጡና በቆሙበት ስፍራ ገደሉአቸው፡፡43 እነርሱም ብንያማውያንን ከበቡና ተከትለዋቸው ሄዱ፤ በመኑሔም አሸነፉአቸው፣ ከጊብዓ በስተ ምሥራቅ በኩል እስካለው ስፍራ ድረስ አሳደዱአቸው፡፡44ከብንያም ነገድም 18, 000 ወታደሮች ሞቱ፣ እነዚህ ሰዎች በሙሉ በጦርነት ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ፡፡45 እነርሱም ተመልሰው በምድረ በዳ ወዳለው ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፡፡ እስራኤላውያንም ከእነርሱ ተጨማሪ አምስት ሺህ ሰዎችን በየመንገዱ ገደሉ፡፡ እነርሱም ተከታተሉአቸው፣ ወደ ጊድአምም በቅርብ እየተከታተሉአቸው ተጨማሪ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደሉ፡፡46በዚያ ቀን የሞቱት የቢኒያም ወታደሮች በሙሉ 25, 000 በሰይፍ ለመዋጋት ልዩ ስልጠና የወሰዱ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህ በሙሉ በጦርነት ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ፡፡47 ነገር ግን ስድስት መቶ ሰዎች ተመልሰው በምድረ በዳ ወዳለው ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፡፡ ለአራት ወራት ያህል በሬሞን ዓለት ተቀመጡ፡፡ 48የእስራኤልም ወታደሮች በብንያም ሕዝብ ላይ እንደገና ተመለሱ፣ ሞላውን ከተማ፣ ከብቶችንና ያገኙትንም ሁሉ አጠቁ ደግሞም ገደሉ፡፡ በመንገዳቸው ያገኙትን ማንኛውንም ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፡፡
1 በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በምጽጳ “ከእኛ ማንም ሰው ሴት ልጁን በጋብቻ ለብንያማውያን መዳር የለበትም” በማለት ቃል ገብተው ነበር፡፡ 2ከዚያም ሕዝቡ ወደ ቤቴል ሄዱና በዚያ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ምሽቱ ድረስ ተቀመጡ፣ ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ አምርረው አለቀሱ፡፡ 3እነርሱም እንዲህ ሲሉ ጮኹ፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህ በእስራኤል ለምን ሆነ? ዛሬ ከእኛ አንዱ ነገድ መታጣቱ ለምንድን ነው?”4 በሚቀጥለውም ቀን ሕዝቡ በጠዋት ተነሡና በዚያ መሠዊያ ሠሩ፣ የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትንም አቀረቡ፡፡ 5የእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “ከእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ያልመጣ የትኛው ነው?” በምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ፊት ስላልመጣ ማንም ሰው በጣም ወሳኝ የሆነ ቃል ኪዳን አድርገው ነበርና፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “እርሱ ፈጽሞ ሊገደል ይገባዋል፡፡”6 የእስራኤልም ሕዝብ ስለ ወንድማቸው ስለ ብንያም አዘኑ፡፡ አነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ዛሬ ከእስራኤል ነገድ አንዱ ተቆርጧል፡፡ 7ሴቶች ልጆቻችንን ከእነርሱ ለአንዳቸውም ቢሆን በጋብቻ ላንሰጥ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለገባን ለተረፉት ሚስቶችን የሚሰጣቸው ማን ነው?”8 እነርሱም አሉ፣ “ከእስራኤል ነገድ በምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ያልመጣ የትኛው ነው?” ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ጉባኤው አንድም ሰው አለመምጣቱን አወቁ፡፡ 9ሕዝቡም በቅደም ተከተል ተሰልፈው እንዲቆጠሩ በተደረገ ጊዜ፣ እነሆ፣ ከኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ማንም ሰው በዚያ አልነበረም፡፡ 10ጉባኤውም 12, 000 ኃያላን ሰዎችን ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ልከው በዚያ ያሉትን ሰዎች ሴቶችንና ሕፃናትንም ጭምር ጥቃት እንዲያደርሱባቸውና እንዲገድሏቸው አዘዙአቸው፡፡11 “እንግዲህ የምታደርጉት ይህ ነው፡- ወንዱን በሙሉ እንዲሁም ከወንድ ጋር የተኛችውንም ሴት በሙሉ ግደሉ፡፡” 12ሰዎቹም በኢያቢስ ገለዓድ ከሚኖሩት መካከል ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ አራት መቶ ወጣት ሴቶች አገኙ፣ እነርሱንም በከነዓን ወዳለው በሴሎ ወደሚገኘው ሰፈር ወሰዷቸው፡፡13 ጉባኤውም በሙሉ መልክት ላኩ፣ በሬሞን ዓለት ለነበሩት ለብንያም ሕዝብ የሰላም ጥሪ እንዳቀረቡላቸውም ነገሩአቸው፡፡14ሲለዚህ በዚያን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፣ የኢያቢስ ገለዓድንም ሴቶች ሰጧቸው፡፡ ነገር ግን ለሁሉም የሚበቁ ሴቶች አልነበሩም፡፡15ሕዝቡም በብንያም ላይ በሆነው ገር አዘኑ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በእስራኤል ነገዶች መካከል ስብራት አድርጓልና፡፡16 የዚያን ጊዜ የጉባኤው መሪዎች እንዲህ አሉ፣ “የብንያም ሴቶች ተገድለዋልና፣ ለተረፉት ብንያማውያን ሚስቶችን እንዴት እናግኝላቸው?”17እንዲህም አሉ፣ “ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዳይጠፋ ከብንያም አሁን በሕይወት ላሉት ሰዎች ርስት ሊኖራቸው ይገባል፡፡18 ከሴቶች ልጆቻችን ሚስቶች ልንሰጣቸው አንችልም፡፡ የእስራኤል ሕዝብ፣ ‘ለብንያም ሚስት የሚሰጥ ርጉም ይሁን’ የሚል ቃል ኪዳን ገብተው ነበርና፡፡”19ስለዚህ እንዲህ አሉ፣ “በቤቴል በሰሜን በኩል፣ ከቤቴልም ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ በምሥራቅ በኩል፣ በለቦና በደቡብ በኩል ባለችው በሴሎ በየዓመቱ የእግዚአብሔር በዓል እንዳለ ታውቃላችሁ፡፡”20 እነርሱም ለብንያም ሰዎች እንዲህ ብለው አዘዙአቸው፣ “ሂዱና በምስጢር ተሸሸጉ፣ በወይኑ ስፍራም ተደበቁ፡፡ 21የሴሎ ልጃገረዶች ለመጨፈር የሚወጡበትን ጊዜ ተመለክቱ፣ የዚያን ጊዜ ከወይኑ ስፍራ ፈጥናችሁ ውጡና እያንዳንዳችሁ ከሴሎ ልጃገረዶች ለየራሳችሁ ሚስት ውሰዱ፣ ከዚያም ወደ ብንያም ምድር ተመለሱ፡፡22አባቶቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ሊጣሉን በመጡ ጊዜ፣ እንዲህ እንላቸዋለን፣ ‘ምህረት አድርጉልን! ባልና ሚስት ሆነው ይጽኑ ምክንያቱም በጦርነቱ ጊዜ እኛ ለያንዳንዳቸው ሚስት አላገኘንላቸውም፡፡ እናተ ደግሞ ሴቶች ልጆቻችሁን ለእነርሱ ስላልሰጣችሁ፣ ቃል ኪዳኑን በተመለከተ በደለኞች አይደላችሁም፡፡’”23 የብንያምም ሕዝብ እንዲሁ አደረጉ፣ በቍጥራቸው መጠን የሚያስፈልጋቸውን ያህል ሚስቶች ይጨፍሩ ከነበሩት ልጃገረዶች ወሰዱ፣ ሚስትም ይሆኗቸው ዘንድ ይዘዋቸው ሄዱ፡፡ እነርሱም ወደ ርስታቸው ስፍራ ተመልሰው ሄዱ፤ ከተሞችንም እንደገና ሠሩ፣ በውስጣቸውም ኖሩ፡፡24በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ያን ስፍራ ለቀቁና ወደ ቤታቸው ሄዱ፣ እያንዳንዱም ወደ ነገዱና ወደ ወገኑ ሄደ፣ እያንዳንዱም ወደ ርስቱ ተመለሰ፡፡25በዚያም ዘመን በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ አልነበረም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በዓይኖቹ ፊት መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር፡፡
1መሳፍንት ይገዙ በነበረበት ዘመን በምድሪቱ ላይ ራብ ነበረ። አንድ ከበተልሔም ይሁዳ የሆነ ሰው ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር ወደ ሞአብ አገር ሄደ፡፡2የሰውዮው ስም አቤሜሌክ ይባል ነበር፣ የሚስቱም ስም ኑኃሚን ይባላል፡፡ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን፣ የይሁዳ ቤተልሔም ኤፍራታውያን ነበሩ፡፡ እነርሱም ወደ ሞዓብም አገር ደረሱና በዚያ ተቀመጡ፡፡3የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ ሞተ እርስዋም ከሁለቱ ወንዶች ልጆችዋ ጋር ቀረች፡፡4እነዚህ ወንዶች ልጆች ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስቶችን ወሰዱ፤ የአንዷ ስም ዖርፋ ነበር፣ የሌላኛዋ ስም ደግሞ ሩት ነበረ። በዚያም ለአሥር ዓመታት ያህል ተቀመጡ፡፡5ከዚያም መሐሎንና ኬሌዎን ሁለቱም ሞቱ፣ ኑኃሚንም ያለ ባልዋና ያለ ሁለቱ ልጆችዋ ብቻዋን ተለይታ ቀረች፡፡6በዚያን ጊዜ ኑኃሚን ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ሞአብን ለመልቀቅና ወደ ይሁዳ ለመመለስ ወሰነች፡፡ እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር የተቸገሩትን ሕዝቡን እንደረዳቸውና መብልን እንደ ሰጣቸው ሰማች፡፡7ስለዚህ እርስዋ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከነበረችበት ስፍራ ለቀቀች፣ ከዚያም ወደ ይሁዳ ምድር ለመመለስ መንገዱን ይዘው ወደታች ሄዱ፡፡8ኑኃሚን ለምራቶችዋ “ሂዱ፣ እያንዳንዳችሁ ወደ እናታችሁ ቤት ተመለሱ፡፡ ለሞቱትና ለእኔ ታማኝነት እንዳሳያችሁን ሁሉ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ታማኝነቱን ያሳያችሁ፡፡9ጌታ እያንዳንዳችሁን በሌላ ባል ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ” አለቻቸው፡፡ ከዚያም ሳመቻቸው፣ እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፡፡10እነርሱም “አይሆንም! ከአንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን” አሉአት፡፡11ኑኃሚን ግን “ልጆቼ ሆይ፣ ተመለሱ! ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ባሎቻችሁ ይሆኑ ዘንድ ለእናንተ የሚሆኑ ወንዶች ልጆች በማሕጸኔ አሁን አሉን?12ልጆቼ ሆይ፣ ተመለሱ፣ በራሳችሁ መንገድ ሂዱ፤ ባል ለማግባት በጣም አርጅቻለሁና፡፡ ዛሬ ማታ ባል አገኛለሁ ብየ እንኳ ተስፋ ባደርግና ወንዶች ልጆችን ብወልድ፣13እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትጠብቃላችሁን? እየጠበቃችሁ አሁን ባል ሳታገቡ ትቀራላችሁን? አይሆንም፣ ልጆቼ ሆይ! ከእናንተ ይልቅ ሁኔታው እኔን እጅግ በጣም ያስመርረኛል፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ወጥቶአልና፡፡14በዚያን ጊዜ ምራቶችዋ ድምፃቸውንም ከፍ አደረጉና እንደገና አለቀሱ፡፡ ዖርፋም አማትዋን ሳመቻትና ተሰናበተቻት፣ ሩት ግን ተጠግታ ያዘቻት፡፡15ኑኃሚንም “አድምጪኝ፣ እነሆ የባልሽ ወንድም ሚስት ወደ ሕዝብዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፡፡ ከባልሽ ወንድም ሚስት ጋር አንቺም ተመለሽ” አለቻት፡፡16ነገር ግን ሩት “ከአንቺ ርቄ እንድሄድ አታድርጊኝ፣ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፤ በምትቆይበትም እቆያለሁና፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ ይሆናል፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፡፡17በምትሞችበትም እሞታለሁ፣ በዚያም እቀበራለሁ፡፡ ከሞት በቀር እኛን አንድም ነገር ቢለየን እግዚአብሔር ይቅጣኝ፣ ከዚህም በላይ ያድርግብኝ” አለቻት፡፡18ኑኃሚን ሩት ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ወሰነች ባየች ጊዜ፣ ከእርስዋ ጋር መከራከር አቆመች፡፡19ስለዚህ ሁለቱም ወደ ቤተ ልሔም ከተማ እስኪመጡ ድረስ ተጓዙ፡፡ ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ፣ ከተማው በሙሉ ስለ እነርሱ እጅግ በጣም ተደነቁ፡፡ ሴቶችም “ይህች ኑኃሚን ናትን?” አሉ፡፡20እርስዋ ግን “ኑኃሚን ብላችሁ አትጥሩኝ፡፡ ሁሉን የሚችል አምላክ ሕይወቴን መራራ አድርጎታልና፣ ማራ በሉኝ” አለቻቸው፡፡21በሙላት ሄድሁ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ ቤቴ ባዶዬን እንደገና መለሰኝ፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር አዋርዶኝ፣ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስጨንቆኝ እያያችሁ ለምን ኑኃሚን ትሉኛላችሁ?” አለቻቸው፡፡22ስለዚህ ኑኃሚንና ምራትዋ ሞአባዊት ሩት ከሞዓብ አገር ተመለሱ፡፡ እነርሱ የገብስ መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ፡፡
1የኑኃሚን ባል አቤሜሌክ፣ በጣም ባለጠጋና ኃያል ሰው የሆነ ቦዔዝ የሚባል ዘመድ ነበረው፡፡2ሞዓባዊቱ ሩት ኑኃሚንን “አሁን ልሂድና ወደ እርሻዎች ገብቼ እህል ልቃርም፡፡ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ሰው እከተላለሁ” አለቻት፡፡ ኑኃሚንም “ልጄ ሆይ፣ ሂጂ” አለቻት፡፡3ሩት ሄደችና ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፡፡ እርስዋም የአቤሜሌክ ዘመድ ወደሆነው ወደ ቦዔዝ እርሻ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ደረሰች።4እነሆም፣ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣና ለአጫጆቹ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው፡፡ እነርሱም “እግዚአብሔር ይባርክህ” ብለው መለሱለት፡፡5ከዚያም ቦዔዝ በአጫጆቹ ላይ ተቆጣጣሪ የነበረውን አገልጋዩን “ይህች ወጣት ሴት የማን ናት?” አለው፡፡6አጫጆቹንም የሚቆጣጠረው አገልጋይ “ይህች ወጣት ሞዓባዊት ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ናት” አለው፡፡7እርስዋም ‘ከአጫጆቹ በኋላ እየተከተልሁ የእህል ቃርሚያ እንድቃርምና እንድለቅም እባክህ ፍቀድልኝ አለች’ አለው፡፡ ስለዚህ እርስዋም ወደዚህ መጣች፣ በቤት ጥቂት ከማረፍዋ በስተቀር፣ ከጠዋት ጀምራ እስከ አሁን ድረስ መቃረም ቀጥላለች፡፡”8የዚያን ጊዜ ቦዔዝ ሩትን “ልጄ ሆይ፣ እኔን እያዳመጥሽኝ ነውን? ወደ ሌላ እርሻ ሄደሽ አትቃርሚ፤ ከእርሻየ አትሂጂ፣ ይልቁንም በዚህ ቆዪና ከወጠት ሴቶች ሰራተኞቼ ጋር አብረሽ ስሪ፡፡9ዓይኖችሽ ሰዎቹ ወደሚያጭዱበት ስፍራ ብቻ ይመልከቱ፣ ሌሎቹንም ሴቶች ተከተያቸው፡፡ ሰዎቹን እንዳይነኩሽ አላዘዝኋቸውምን? ሲጠማሽ ወደ ውኃ ማሰሮዎቹ ሄደሽ ወንዶቹ ከቀዱት ውኃ መጠጣት ትችያለሽ” አላት፡፡10ከዚያም በግንባርዋ መሬቱን በመንካት በቦዔዝ ፊት ሰገደች፡፡ እርስዋም “እኔ እንግዳ የሆንሁት ታስበኝ ዘንድ በአንተ ፊት ሞገስ ያገኘሁት ለምንድን ነው?” አለችው፡፡11ቦዔዝም ለእርስዋ “ባልሽ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ የሰራሽው ስራ ሁሉ ለእኔ ተነግሮኛል፡፡ አማትሽን ለመከተልና ወደ ማታውቂው ሕዝብ ለመምጣት አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሻል፡፡12ስለ ስራሽ እግዚአብሔር ይክፈልሽ፡፡ ከክንፉ በታች መጠጊያ ካገኘሽበት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ሙሉ ደመወዝሽን ተቀበይ” አላት፡፡13እርስዋም “ጌታዬ ሆይ፣ ምንም እንኳ እኔ ከሴት አገልጋዮችህ እንደ አንዲቱ ባልሆንም አጽናንተኸኛልና፣ እኔን በደግነት አናግረኸኛልና በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለቸው፡፡14በምሳም ጊዜ ቦዔዝ ለሩት እንዲህ አላት፡- “ወደዚህ ነይ፣ እንጀራም ብዪ፣ ጉርሻሽንም በሆምጣጤው ወይን አጥቅሺው፡፡” በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች፣ እርሱም የተጠበሰ እህል ሰጣት፣ እርስዋም እስክትጠግብ ድረስ በላች፣ የቀረውንም አተረፈች፡፡15ለመቃረም ስትነሳ፣ ቦዔዝ ወጣት አገልጋዮቹን “በነዶው መካከልም እንድትቃርም ፍቀዱላት፣ ምንም መጥፎ ነገር ለእርስዋ አትናገሩአት፡፡16ደግሞም ከነዶው ዘለላዎች አስቀርታችሁ በእርግጠኝነት ልተተዉላት ይገባል፣ እንድትቃርም ለእርስዋ ተዉላት፡፡ እርስዋንም አትውቀሱአት” ብሎ አዘዛቸው፡፡17ስለዚህ በእርሻው ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፡፡ ከዚያም የቃረመችውን እህል ወቃችው፣ የወቃችውም እህል አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህል ገብስ ሆነ፡፡18እርስዋም ተሸክማው ወደ ከተማ ሄደች፡፡ አማትዋም የቃረመችውን አየች፡፡ ሩትም በልታ ከጠገበች በኋላ የተረፋትን የተጠበሰ እህል አውጥታ ለእርስዋ ሰጠቻት፡፡19አማትዋም ለእርስዋ እንዲህ አለቻት፡-“ዛሬ የቃረምሽው ወዴት ነው? ለመስራትስ ወዴት ሄድሽ? የረዳሽ ሰው የተባረከ ይሁን፡፡” ከዚያም ሩት ለአማትዋ የቃረመችበት እርሻ ባለቤት ስለሆነው ሰው ነገረቻት፡፡ እርስዋም “ዛሬ ቃርሚያ የቃረምሁበት እርሻ ባለቤት ስሙ ቦዔዝ ይባላል” አለቻት፡፡20ኑኃሚንም ለምራትዋ “ታማኝነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ ባልተወው በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን” አለቻት፡፡ ኑኃሚንም ደግሞ “ይህ ሰው ለእኛ የቅርብ ዘመዳችን ነው፣ ከሚቤዡን አንዱ ነው” አለቻት፡፡21ሞዓባዊቱ ሩትም “በእርግጥም፣ እንዲህ አለኝ፣ ‘መከሬን ሁሉ እስኪጨርሱ ድረስ ከወጣት ወንዶች ሰራተኞቼ አትራቂ፡፡’”22ኑኃሚንም ለምራትዋ ለሩት “ልጄ ሆይ፣ ከወጣት ሴቶች ሰራተኞቹ ጋር ብትወጪ መልካም ነው፣ በሌላ በየትኛውም እርሻ ጉዳት እንዳያገኝሽ” አለቻት፡፡23ስለዚህም እርስዋ እስከ ገብሱና ስንዴው መከር መጨረሻ ድረስ ልትቃርም ወደ ቦዔዝ ሴቶች ሰራተኞች ተጠግታ ቆየች፡፡ እርስዋም ከአማትዋ ጋር ትኖር ነበር፡፡
1አማትዋም ኑኃሚን ለእርስዋ “ልጄ ሆይ፣ ታርፊ ዘንድ፣ ነገሮችም ለአንቺ መልካም ይሆኑልሽ ዘንድ፣ የምታርፊበትን ስፍራ አልፈግልሽምን?” አለቻት፡፡2አሁንም ቦዔዝ፣ ከወጣት ሴቶች ሰራተኞቹ ጋር የነበርሽበት ሰው፣ ዘመዳችን አይደለምን? ተመልከቺ፣ እርሱ ዛሬ ማታ በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል፡፡3ስለዚህ፣ ታጠቢ፣ ሽቶሽን ተቀቢ፣ ልብስሽን ቀይሪ፣ ወደ አውድማውም ውረጂ፡፡ ነገር ግን መብላትና መጠጣት እስኪጨርስ ድረስ ለሰውዮው አትታወቂ፡፡4በተኛም ጊዜ፣ ወደ እርሱ መሄድ እንድትችይ እርሱ የተኛበትን ስፍራ ማስታወስሽን እርግጠኛ ሁኚ፣ እግሩን ግለጪ፣ በዚያም ተጋደሚ፡፡ ከዚያም የምታደርጊውን እርሱ ይነግርሻል፡፡5ሩትም ለኑኃሚን “የተናገርሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አለቻት፡፡6ስለዚህ ወደ አውድማውም ወረደች፣ እርስዋም አማትዋ የሰጠቻትን ትዕዛዝ ተከተለች፡፡7ቦዔዝም በበላና በጠጣ ጊዜ፣ ልቡም ደስ ባለው ጊዜ፣ በእህሉ ክምር ጫፍ ሊተኛ ሄደ፡፡ ከዚያም ሩት በቀስታ መጣች፣ እግሩንም ገለጠች፣ ተኛችም፡፡8እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፡፡ እርሱም ዘወር አለ፣ አንዲትም ሴት እዚያው እግርጌው ተኝታ ነበረች፡፡9እርሱም “ማን ነሽ? አለ፡፡ እርስዋም “እኔ ሴት አገልጋይህ ሩት ነኝ” አለችው፡፡ አንተ የቅርብ ዘመዴ ነህና ልብስህን በሴት አገልጋይህ ላይ ዘርጋ አለችው፡፡10ቦዔዝም፣ “ልጄ ሆይ፣ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፡፡ ከመጀመርያው ይልቅ በመጨረሻ ብዙ ደግነት አሳይተሻል፣ ምክንያቱም ድሃም ይሁን ባለጠጋ ከወጣት ወንዶች ከአንዳቸውም ጋር አልሄድሽምና” አላት፡፡11አሁንም፣ ልጄ ሆይ፣ አትፍሪ! ያልሽውን ሁሉ አደርግልሻለሁ፣ ምክንያቱም በከተማየ ያሉ ሕዝብ ሁሉ ምግባረ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ ያውቃሉ፡፡12አሁን እኔ የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፤ ይሁን እንጂ ከእኔ የበለጠ የሚቀርብ ዘመድ አለ፡፡13ዛሬ ሌሊት እዚህ ቆዪ፣ ነገም ጠዋት የዋርሳነትን ግዴታ እርሱ የሚፈጽም ከሆነ፣ መልካም ነው፣ የዋርሳነትን ግዴታ ይፈጽም፡፡ ነገር ግን እርሱ ለአንቺ የዋርሳነትን ግዴታ ባይፈጽም፣ ሕያው እግዚአብሔርን እኔ አደርገዋለሁ፡፡ እስከ ማለዳ ድረስ ተኚ፡፡14ስለዚህ እስከ ማለዳ ድረስ በእግርጌው ተኛች፡፡ ነገር ግን አንዱ ሌላውን ማወቅ ከመቻሉ በፊት ተነሳች፡፡ ቦዔዝ “ሴት ወደ አውድማው መምጣትዋን ማንም እንዳያውቅ” ብሎ ነበርና፡፡15ከዚያም ቦኤዝ “የለበስሽውን ልብስ አምጭና ያዢው” አላት፡፡ በያዘችም ጊዜ ስድስት ትልቅ መስፈሪያ ገብስ በልብሷ ላይ ሰፍሮ አሸከማት፡፡ የዚያን ጊዜ እርሱ ወደ ከተማ ሄደ፡፡16ሩት ወደ አማትዋ በመጣች ጊዜ “ልጄ ሆይ፣ እንዴት ነሽ?” አለቻት፡፡ ሩትም ሰውዮው ለእርስዋ ያደረገውን ሁሉ ነገረቻት፡፡17እርስዋም “እነዚህ ስድስት መስፈሪያ ገብስ እርሱ የሰጠኝ ናቸው፣ ‘ወደ አማትሽ ባዶ እጅሽን አትሂጂ’” ብሏልና፡፡18ኑኃሚንም “ልጄ ሆይ፣ ይህ ጉዳይ እንዴት እንደሚሆን እስከምታውቂ ድረስ በዚህ ቆዪ፣ ሰውዮው ይህን ነገር ዛሬ እስኪጨርስ ድረስ አያርፍምና” አለች፡፡
1ቦዔዝም ወደ ከተማይቱ በር ሄደና በዚያ ተቀመጠ፡፡ ወዲያውኑ ቦዔዝ ሲናገርለት የነበረው የቅርብ ዘመድ መጣ፡፡ ቦዔዝም ለእርሱ “ወዳጄ ሆይ፣ ና በዚህም ተቀመጥ” አለው፡፡ ሰውየውም መጣና ተቀመጠ፡፡2ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች አሥር ሰዎች ወሰደ፣ “በዚህ ተቀመጡ” አላቸው፡፡ እነርሱም ተቀመጡ፡፡3ቦዔዝም የቅርብ ዘመድ ለሆነው፣ “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቤሜሌክን ቁራሽ መሬት ትሸጣለች፡፡4እኔም ለአንተ አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ እንዲህም አልሁ፡- ‘ይህንን መሬት በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት ግዛው፡፡’ መቤዠት ብትፈልግ ተቤዠው፡፡ ነገር ግን መቤዠት የማትፈልግ ከሆነ ግን ከአንተ በቀር ሌላ የሚቤዥ የለምና፣ እኔም ከእአንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ” አለው፡፡ የዚያን ጊዜ ሌላኛው ሰው “እቤዠዋለሁ” አለው፡፡5ቦዔዝም “ከኑኃሚን እጅ እርሻውን በምትገዛበት ቀን፣ የሞተውን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንድታስነሣለት የምዋቹን ሰው ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ደግሞ መውሰድ አለብህ” አለ፡፡6የቅርብ ዘመድ የሆነውም “የራሴን ርስት ሳልጎዳ እርሻውን ለራሴ መቤዠት አልችልም፡፡ እኔ ልቤዠው አልችልምና የእኔን የመቤዠት መብት ለራስህ ውሰድ” አለ፡፡7በጥንት ዘመን መቤዠትና የሸቀጦች መለዋወጥ በተመለከተ በእስራኤል ዘንድ አንድ ልማድ ነበረ፡፡ ሁሉንም ነገር ለማጽናት ሰው ጫማውን ያወልቅና ለባልንጀራው ይሰጠዋል፤ በእስራኤል ውስጥ ሕጋዊ ስምምነት የሚኖረው በዚህ ሁኔታ ነበር፡፡8ስለዚህ የቅርብ ዘመዱ ቦዔዝ፣ “አንተ ለራስህ ግዛው” አለው፡፡ እርሱም ጫማውን አወለቀ፡፡9ቦዔዝም ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ፣ “ለአቤሜሌክ የነበረውን ሁሉ እንደዚሁም ለኬሌዎንና ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እኔ መግዛቴን እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ፡፡10ከዚህም በላይ ስለ መሐሎን ሚስት ስለ ሞዓባዊቷ ሩት፡- የምዋቹን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ፣ ስሙ ከወንድሞቹ መካከልና ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፣ እኔ ደግሞ እርስዋ ሚስቴ እንድትሆን ወስጃታለሁ፡፡ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው፡፡11በበሩ የነበሩ ሕዝብ ሁሉና ሽማግሌዎቹም እንዲህ አሉ፡- “እኛ ምስክሮች ነን፡፡ እግዚአብሔር ወደ ቤትህ የመጣችውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ገነቡት እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና ልያ ያድርጋት፡፡ አንተም በኤፍራታ ባለጠጋ ሁን፣ በቤተ ልሔምም እንደገና የታወቅህ ሁን፡፡12ቤትህ እግዚአብሔር ከዚህች ወጣት ሴት በሚሰጥህ ዘር በኩል ትዕማር ለይሁዳ እንደወለደችለት እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን” አሉት፡፡13ስለዚህ ቦዔዝ ሩትን ወሰደ፣ ሚስቱም ሆነች፡፡ እርሱም ከእርስዋ ጋር ተኛ፣ እግዚአብሔርም ልጅ እንድትፀንስ ፈቀደላት፣ እርዋም ወንድ ልጅ ወለደች፡፡14ሴቶችም ለኑኃሚን፣ “ዛሬ የሚቤዥ የቅርብ ዘመድ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ይህ ሕጻን ስሙ በእስራኤል ውስጥ የገነነ ይሁን፡፡15ይህ ልጅ ለአንቺ ሕይወትሽን የሚያድስ እርጅናሽንም የሚመግብ ይሁን፣ የምትወድሽ፣ ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ የምትሻል፣ ምራትሽ ይህን ልጅ ወልዳለችና፡፡16ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደችው፣ በእቅፍዋም አስቀመጠችው፣ እርሱንም ተንከባከበችው፡፡17ጎረቤቶቿ የሆኑት ሴቶችም “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት” እያሉ ስም ሰጡት፡፡እነርሱም ስሙን ኢዮቤድ ብለው ጠሩት፡፡ እርሱም የዳዊት አባት የሆነው፣ የእሴይ አባት ሆነ፡፡18አሁንም እነዚህ የፋሬስ ትውልድ ነበሩ፡- ፋሬስ የኤስሮም አባት ሆነ፣19ኤስሮምም የአራም አባት ሆነ፣ አራምም የአሚናዳብ አባት ሆነ፣20አሚናዳብም የነአሶን አባት ሆነ፣ ነአሶንም የሰልሞን አባት ሆነ፣21ሰልሞንም የቦዔዝ አባት ሆነ፣ ቦዔዝም የኢዮቤድ አባት ሆነ፣22ኢዮቤድ የእሴይ አባት ሆነ፣ እሴይም የዳዊት አባት ሆነ፡፡
1በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማ መሴፋ የሚኖር አንድ ሰው ነበር፤ ስሙ ሕልቃና ይባላል፥ እርሱም የኤፍሬማዊው የናሲብ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የኤሊዮ ልጅ፥ የኢያርምኤል ልጅ ነበር። 2እርሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ስማቸውም የአንደኛዋ ሐና፥ የሁለተኛዋም ፍናና ነበር። ፍናና ልጆች ነበሯት፣ ሐና ግን አንድም ልጅ አልነበራትም።3ይህም ሰው በየዓመቱ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ለመስገድና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ሴሎ ይሄድ ነበር። የእግዚአብሔር ካህናት የሆኑት ሁለቱ የኤሊ ወንዶች ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በዚያ ነበሩ። 4በየዓመቱ ሕልቃና የሚሠዋበት ጊዜ ሲደርስ፥ ለሚስቱ ፍናና፥ ለወንዶችና ሴቶች ልጆችዋ በሙሉ ሁልጊዜ ከመሥዋዕቱ ሥጋ ድርሻቸውን ይሰጣቸው ነበር።5ነገር ግን ሐናን ይወዳት ስለነበር ሁልጊዜም ድርሻዋን ሁለት ዕጥፍ አድርጎ ይሰጣት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶት ነበር። 6እግዚአብሔር ማኅፀንዋን ዘግቶት ስለነበር ጣውንቷ እርስዋን ለማስመረር ክፉኛ ታስቆጣት ነበር።7ስለዚህ በየዓመቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ከቤተሰብዋ ጋር በምትወጣበት ጊዜ ጣውንቷ ሁልጊዜ ታበሳጫት ነበር። በዚህ ምክንያት ታለቅስ ነበር፤ ምግብም አትበላም ነበር። 8ባሏ ሕልቃና ሁልጊዜ "ሐና ሆይ፥ ለምንድነው የምታለቅሽው? ምግብስ የማትበዪው ለምንድነው? ልብሽ የሚያዝነውስ ለምንድነው? ከዐሥር ወንዶች ልጆች ይልቅ ላንቺ እኔ አልሻልም?" ይላት ነበር።9ከእነዚህ ወቅቶች በአንዱ፥ በሴሎ መብላታቸውንና መጠጣታቸውን ከጨረሱ በኋላ ሐና ተነሣች። ካህኑ ዔሊ በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በራፍ በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር። 10እርሷም እጅግ አዝና ነበር፤ ወደ እግዚአብሔር ጸለየች፥ አምርራም አለቀሰች።11እንዲህ ስትልም ስዕለት ተሳለች፣ "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ የአገልጋይህን ጉስቁልና ብትመለከትና ብታስበኝ፥ አገልጋይህን ባትረሳኝ፥ ነገር ግን ወንድ ልጅን ብትሰጠኝ፥ እኔም የሕይወት ዘመኑን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ መቼም ቢሆን ጸጉሩ አይላጭም"።12በእግዚአሔር ፊት ጸሎቷን ቀጥላ እያለች ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር። 13ሐና በልቧ ትናገር ነበር። ከንፈሮችዋ ይንቀሳቀሱ ነበር፥ ድምፅዋ ግን አይሰማም ነበር። ስለዚህ ዔሊ ሰክራለች ብሎ አሰበ። 14ዔሊም "ስካርሽ የሚቆየው እስከ መቼ ነው? ወይንሽን ከአንቺ አርቂው" አላት።15ሐናም፣ "ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፥ እኔ ልቤ በሐዘን የተጎዳብኝ ሴት ነኝ። ወይን ወይም የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም፥ ነገር ግን ነፍሴን በእግዚአብሔር ፊት እያፈሰስኩ ነው። 16አገልጋይህን እንደ ኃፍረተ ቢስ ሴት አትቁጠረኝ፤ ይህን ያህል ጊዜ የተናገርኩት እጅግ ከበዛው ሐዘኔና ጭንቀቴ የተነሣ ነው" በማለት መለሰችለት።17ከዚያም ዔሊ፣ "በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ልመና ይስጥሽ" ብሎ መለሰላት። 18እርሷም፣ "አገልጋይህ በዐይንህ ፊት ሞገስን ላግኝ" አለችው። ከዚያም መንገዷን ሄደች፥ በላችም፤ ከዚያም በኋላ ፊቷ ሐዘንተኛ አልሆነም።19እነርሱም ማልደው ተነሥተው በእግዚአብሔር ፊት ሰገዱ፥ ከዚያም ወደ መኖሪያቸው ወደ አርማቴም ተመለሱ። ሕልቃና ከሚስቱ ከሐና ጋር ተኛ፥ እግዚአብሔርም አሰባት። 20ጊዜው ሲደርስም ሐና አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደች። "ከእግዚአብሔር ስለ እርሱ ለምኜ ነበር" ስትል ስሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው።21ሕልቃናና ቤተ ሰቡ በሙሉ ለእግዚአብሔር ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብና ስዕለታቸውን ለመፈጸም ዳግመኛ ወደ ሴሎ ወጡ። 22ሐና ባሏን "ልጁ ጡት መጥባት እስኪያቆም እኔ አልሄድም፤ ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት እንዲታይና ለዘላለም በዚያ እንዲኖር አመጣዋለሁ" ብላው ስለነበረ አልሄደችም። 23ባሏም ሕልቃና፥ "መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ። ጡት መጥባቱን እስኪያቆም ቆዪ፥ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽና" አላት። ስለዚህ ልጇ ጡት መጥባቱን እስኪያቆም ድረስ በቤት በመቆየት ተንከባከበችው።24ጡት መጥባቱን ባስቆመችው ጊዜ፥ እርሱን ከሦስት አመት ወይፈን፥ አንድ ኢፍ ዱቄትና አንድ ጠርሙስ ወይን ጋር በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው። ልጁ ገና ሕፃን ነበር። 25ወይፈኑን አረዱት፤ ልጁንም ወደ ዔሊ አመጡት።26እርሷም፥ "ጌታዬ ሆይ፥ ሕያው እንደመሆንህ፥ እዚህ አጠገብህ ቆማ ወደ እግዚአብሔር የጸለየችው ሴት እኔ ነኝ። 27ስለዚህ ልጅ ጸለይኩኝ፥ እግዚአብሔርም የለመንኩትን ልመና ሰጥቶኛል። 28ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል"። እነርሱም በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
1ሐናም እንዲህ በማለት ጸለየች፥ “ልቤ በእግዚአሔር በደስታ ተሞላ። ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ አለ። በማዳንህ ደስ ብሎኛልና አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ።2አንተን የሚመስልህ የለምና፥ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለም ዐለት የለም።3ከእንግዲህ አትታበዩ፤ አንዳች የዕብሪት ንግግር ከአፋችሁ አይውጣ። እግዚአብሔር ዐዋቂ አምላክ ነውና፤ ሥራዎች ሁሉ በእርሱ ይመዘናሉ። 4የኃያላን ሰዎች ቀስት ተሰብሯል፥ የተሰናከሉት ግን ኃይልን ታጥቀዋል።5ጠግበው የነበሩት እንጀራ ለማግኘት ሲሉ ለሥራ ተቀጠሩ፤ ተርበው የነበሩት ረሃብተኝነታቸው አብቅቷል። መካኒቱ እንኳን ሰባት ወልዳለች፥ ብዙ ልጆች የነበሯት ሴት ግን ጠውልጋለች።6እግዚአብሔር ይገድላል፥ ያድናልም። ወደ ሲዖል ያወርዳል፥ ያነሣልም። 7እግዚአብሔር ድሃ ያደርጋል፥ ባለጸጋም ያደርጋል። እርሱ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ያደርጋል።8እርሱ ድሃውን ከመሬት ያነሣዋል። ምስኪኖችን ከልዑላን ጋር ሊያስቀምጣቸውና የክብርን ወንበር ሊያወርሳቸው ከአመድ ክምር ላይ ብድግ ያደርጋቸዋል። የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጓል።9የታመኑ ሰዎችን እግር ይጠብቃል፥ ማንም በኃይሉ አያሸንፍም፤ ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ወዳለው ጸጥታ ይጣላሉ።10እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፤ እርሱ ከሰማይ ያንጎደጉድባቸዋል። እግዚአብሔር በምድር ዳርቻዎች ላይ ይፈርዳል፤ የእርሱ ለሆነው ንጉሥ ኃይልን ይሰጠዋል፥ ለቀባውም ቀንዱን ከፍ ያደርግለታል።”11ከዚያም ሕልቃና በራማ ወደሚገኘው ቤቱ ሄደ። ልጁም በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።12የዔሊ ወንዶች ልጆች ምንም የማይረቡ ነበሩ። እግዚአብሔርን አያውቁም ነበር። 13የካህናቱ ልማድ ከሕዝቡ ጋር እንደዚያ ነበርና፥ ማንኛውም ሰው መሥዋዕት ሲያቀርብ፥ ሥጋው እየተቀቀለ እያለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ይዞ ይመጣ ነበር። 14እርሱም ወደ ድስቱ፥ ወይም ወደ አፍላሉ፥ ወይም ወደ ምንቸቱ ውስጥ ያጠልቀው ነበር። ሜንጦው ያወጣውንም ሁሉ ካህኑ ለራሱ ይወስደው ነበር። ይህንን ወደዚያ ወደ ሴሎ በሚመጡት እስራኤላውያን ሁሉ ላይ ያደርጉ ነበር።15ይልቁንም ስቡን ከማቃጠላቸው በፊት የካህኑ አገልጋይ ይመጣና የሚሠዋውን ሰው፥ “ጥሬውን ብቻ እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይቀበልምና ለካህኑ እንድጠብስለት ሥጋ ስጠኝ" ይለው ነበር። 16ሰውየው፥ "መጀመሪያ ስቡን ማቃጠል አለባቸው፥ ከዚያም የፈለከውን ያህል መውሰድ ትችላለህ" ካለው ያ ሰው መልሶ፥ "አይደለም፥ አሁኑኑ ስጠኝ፤ እምቢ ካልክም በግድ እወስደዋለሁ" ይለው ነበር። 17የእግዚአብሔርን መስዋዕት ንቀዋልና የእነዚህ ወጣቶች ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበር።18ትንሹ ልጅ ሳሙኤል ግን ከተልባ እግር ጨርቅ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። 19እናቱም ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብ ከባሏ ጋር በምትመጣበት ጊዜ በየዓመቱ አነስተኛ መደረቢያ ልብስ እየሠራች ታመጣለት ነበር።20ዔሊም ሕልቃናን እና ሚስቱን እንዲህ በማለት ባረካቸው፥”ከእግዚአብሔር በለመነችው ልመና ምክንያት እግዚአብሔር ከዚህች ሴት ተጨማሪ ልጆችን ይስጥህ።“ ከዚያም ወደ ራሳቸው መኖሪያ ተመለሱ። 21እግዚአብሔር እንደገና ሐናን ረዳት፥ እንደገናም አረገዘች። እርሷም ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴት ልጆችን ወለደች። እንዲሁም ትንሹ ልጅ ሳሙኤል በእግዚአብሔር ፊት አደገ።22ዔሊ በጣም አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹ በእስራኤላውያን ሁሉ ላይ እያደረጉ ያሉትን በሙሉ እና በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደ ተኙ ሰማ። 23እርሱም እንዲህ አላቸው፥”ስለ ክፉ ሥራችሁ ከዚህ ሕዝብ ሁሉ ሰምቻለሁና እንደዚህ ያሉትን ነገሮች የምትፈጽሙት ለምንድነው? 24ልጆቼ ሆይ፥ የምሰማው መልካም ወሬ አይደለምና ልክ አይደላችሁም። የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲያምጽ ታደርጉታላችሁ።25አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል፥ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ይፈርዳል፤ አንድ ሰው ግን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ቢሠራ ስለ እርሱ የሚናገር ማን ነው?" እነርሱ ግን እግዚአሔር ሊገድላቸው ፈልጓልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም። 26ትንሹም ልጅ ሳሙኤል አደገ፥ በእግዚአብሔርና በሰዎችም ፊት ደግሞ በሞገስ እያደገ ሄደ።27አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'በግብፅ አገር፥ በፈርዖን ቤት ባሪያዎች በነበሩ ጊዜ ለአባትህ ቤት ራሴን ገለጥኩኝ፤ 28ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ካህን እንዲሆነኝ፥ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፥ ዕጣን እንዲያጥንልኝ፥ በፊቴም ኤፉድ እንዲለብስ መረጥኩት። የእስራኤል ሕዝብ በእሳት የሚያቀርበውን መባ ሁሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።29ታዲያ በማደሪያዬ ያዘዝኩትን መሥዋዕትና መባ የምትንቁት ለምንድነው? በሕዝቤ በእስራኤል ከሚቀርበው መስዋዕት ሁሉ በተመረጠው እየወፈራችሁ ልጆችህን ከእኔ በላይ ያከበርከው ለምንድነው?' 30የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'ቤትህና የአባትህ ቤት ለዘላለም በፊቴ እንዲመላለስ ተስፋ ሰጥቼ ነበር'። አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'ይህንን ማድረግ ከእኔ ይራቅ፥ የሚያከብሩኝን አከብራለሁና የሚንቁኝ ግን ፈጽሞ ይናቃሉ።31ተመልከት፥ ከእንግዲህ በቤትህ ሽማግሌ የሚሆን አንድም ሰው እንዳይኖር ያንተን ኃይልና የአባትህን ቤት ኃይል የምቆርጥበት ቀን ቀርቧል። 32በማድርበት ስፍራም መከራን ታያለህ። ለእስራኤል መልካም ነገር ቢሰጥም ከእንግዲህ በቤትህ ሽማግሌ የሚሆን አንድ ሰው አይኖርም። 33ያንተ የሆኑትና ከመሠዊያዬ የማልቆርጣቸው ማናቸውም ዐይኖችህን እንዲያፈዝዙና ሕይወትህን በሐዘን እንዲሞሉት አደርጋቸዋለሁ። በቤተ ሰብህ ውስጥ የተወለዱ ወንዶች ሁሉ ይሞታሉ።34በሁለቱ ወንዶች ልጆችህ በአፍኒን እና በፊንሐስ የሚደርስባቸው ምልክት ይሆንሃል፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ። 35በልቤና በነፍሴ ውስጥ ያለውን የሚፈጽም ታማኝ ካህን ለራሴ አስነሣለሁ። የማያጠራጥር ቤት እሠራለታለሁ፤ ለዘላለምም በቀባሁት ንጉሥ ፊት ይሄዳል።36ከቤተ ሰብህ የተረፈ ሁሉ ጥቂት ጥሬ ብርና ቁራሽ እንጀራ እንዲሰጠው ለመለመን በዚያ ሰው ፊት መጥቶ ይሰግዳል፥ 'ቁራሽ እንጀራ መብላት እንድችል እባክህ ከካህናቱ ኃላፊነቶች በአንዱ ስፍራ መድበኝ'" ይለዋል።
1ትንሹ ልጅ ሳሙኤል በዔሊ ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። 2በእነዚያ ቀናት የእግዚአብሔር ቃል እምብዛም አይገኝም ነበር፤ ትንቢታዊ ራዕይም አይዘወተርም ነበር። በዚያን ጊዜ፥ ዔሊ ዐይኖቹ ከመፍዘዛቸው የተነሣ አጥርቶ ማየት ባቃተው ጊዜ፥ በአልጋው ላይ ተኝቶ እያለ፥ 3የእግዚአብሔር መብራት ገና አልጠፋም ነበር፥ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተኝቶ ነበር። 4እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው፥ እርሱም፥ “አቤት!” አለው።5ሳሙኤል ወደ ዔሊ ሮጠና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው፤ ዔሊም፥ “እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው። ስለዚህ ሳሙኤል ሄደና ተኛ። 6እግዚአብሔር እንደገና፥ “ሳሙኤል” ብሎ ተጣራ። ሳሙኤልም እንደገና ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም፥ "ልጄ ሆይ፥ እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ" ብሎ መለሰለት።7ሳሙኤል እግዚአብሔርን ገና አላወቀም ነበር፥ ከእግዚአብሔር ምንም ዓይነት መልዕክት ገና አልተገለጠለትም ነበር። 8እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው። ሳሙኤልም እንደገና ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው። ከዚያም ልጁን እግዚአብሔር እንደ ጠራው ዔሊ አስተዋለ።9ዔሊም ሳሙኤልን፥ "ሂድና ተመልሰህ ተኛ፤ ደግሞ ከጠራህም፥ 'እግዚአብሔር ሆይ፥ አገልጋይህ እየሰማህ ነውና ተናገር' ማለት አለብህ" አለው። ስለዚህ ሳሙኤል እንደገና ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ።10እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፤ እንደ ቀድሞው ሁሉ፥ "ሳሙኤል፥ ሳሙኤል" ብሎ ጠራው። ከዚያም ሳሙኤል፥ "አገልጋይህ እየሰማህ ነውና ተናገር" አለው። 11እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፥ "ተመልከት፥ የሚሰማውን ሁሉ ጆሮውን ጭው የሚያደርግ አንድ ነገር በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ።12በዚያም ቀን፥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ስለ ቤቱ የተናገርኩትን ሁሉ በዔሊ ላይ አመጣበታለሁ። 13ልጆቹ በራሳቸው ላይ እርግማንን ስላመጡና እርሱም ስላልከለከላቸው፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እርሱ ስለሚያውቀው ኃጢአት በቤቱ ላይ እንደምፈርድ ነግሬዋለሁ። 14በዚህ ምክንያት የቤቱ ኃጢአት በመሥዋዕት ወይም በመባ ይቅር እንዳይባል ለዔሊ ቤት ምያለሁ።"15ሳሙኤል እስኪነጋ ተኛ፤ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ። ሳሙኤል ግን ስላየው ራዕይ ለዔሊ ለመንገር ፈራ። 16ከዚያም ዔሊ ሳሙኤልን ጠርቶ፥ "ልጄ ሳሙኤል ሆይ" አለው። ሳሙኤልም፥ "አቤት!" ብሎ መለሰለት።17እርሱም፥ "የነገረህ ቃል ምንድነው? እባክህ አትደብቀኝ። ከነገረህ ቃል ሁሉ አንዱን ብትደብቀኝ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብህ፤ ከዚያም የባሰውን ጨምሮ ያድርግብህ" አለው። 18ሳሙኤል ሁሉንም ነገር ነገረው፤ ከእርሱም ምንም አልደበቀም። ዔሊም፥ "እርሱ እግዚአብሔር ነው። መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ" አለ።19ሳሙኤል አደገ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበር፥ ከትንቢታዊ ቃሉ ሳይፈጸም የቀረ አንድም አልነበረም። 20ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉት እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ነቢይ እንዲሆን መመረጡን ዐወቁ። 21እግዚአብሔር እንደገና በሴሎ ተገለጠ፥ እርሱም በቃሉ አማካይነት በሴሎ ራሱን ለሳሙኤል ገለጠለት።
1የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤላውያን ሁሉ መጣ። በዚህ ወቅት እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ጋር ለመዋጋት ሄዱ። የጦር ሰፈራቸውንም በአቤንኤዘር አደረጉ፥ ፍልስጥኤማውያንም የጦር ሰፈራቸውን በአፌቅ አደረጉ። 2ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት ተሰለፉ። ውጊያው በተፋፋመ ጊዜ እስራኤላውያን አራት ሺህ ሰዎቻቸው በውጊያው ሜዳ በመገደላቸው በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ።3ሕዝቡ ወደ ጦር ሰፈሩ በመጣ ጊዜ፥ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ "እግዚአብሔር ዛሬ በፍልስጥኤማውያን ፊት እንድንሸነፍ ያደርገን ለምንድነው? ከእኛ ጋር እንዲሆንና ከጠላቶቻችን ኃይል እንዲያድነን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ እናምጣው" አሉ። 4ስለዚህ ሕዝቡ ወደ ሴሎ ሰዎችን ላኩ። ከዚያ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠውን የሠራዊቱን ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ። ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።5የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ጦር ሰፈሩ በመጣ ጊዜ፥ የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ በታላቅ ዕልልታ ጮኹ፥ ምድሪቱም አስተጋባች። 6ፍልስጥኤማውያን የዕልልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “ይህ በዕብራውያኑ የጦር ሰፈር የሚሰማው የዕልልታ ድምፅ ምን ማለት ይሆን? አሉ። ከዚያም የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ጦር ሰፈሩ እንደ መጣ ተገነዘቡ።7ፍልስጥኤማውያኑ ፈሩ፤ እነርሱም፥”እግዚአብሔር ወደ ጦር ሰፈሩ መጥቷል" አሉ። 8እነርሱም፥ "ወዮልን! እንደዚህ ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልሆነም! ወዮልን! ከዚህ ኃያል አምላክ ክንድ ማን ያድነናል? ይህ በምድረ በዳ ግብፃውያንን በልዩ ልዩ ዓይነት መቅሠፍት የመታቸው አምላክ ነው። 9እናንተ ፍልስጥኤማውያን በርቱ፥ ወንድነታችሁንም አሳዩ፥ ካልሆነ እነርሱ ባሪያዎቻችሁ እንደነበሩ ባሪያዎቻቸው ትሆናላችሁ። ወንድነታችሁ ይታይ፥ ተዋጉም" አሏቸው።10ፍልስጥኤማውያኑ ተዋጉ፥ እስራኤላውያንም ተሸነፉ። እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሸሸ፥ የተገደሉትም እጅግ ብዙ ነበሩ፤ ከእስራኤል ሠላሳ ሺህ እግረኛ ወታደር ወደቀ። 11የእግዚአብሔር ታቦት ተወሰደ፥ ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስም ሞቱ።12በዚያው ቀን አንድ ብንያማዊ ከውጊያው መስመር ወደ ሴሎ በሩጫ መጣ፥ በደረሰ ጊዜ ልብሱን ቀድዶና በራሱ ላይ አፈር ነስንሶ ነበር። 13እርሱ በደረሰ ጊዜ፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት በመስጋት ልቡ ታውኮበት ስለነበረ በመንገዱ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር። ሰውየው ወደ ከተማ ገብቶ ወሬውን በነገራቸው ጊዜ፥ ከተማው በሙሉ አለቀሱ።14ዔሊ የልቅሶውን ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “የዚህ ሁካታ ትርጉሙ ምንድነው?” አለ። ሰውየው ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው። 15በዚህ ጊዜ ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ ዓይኖቹ አጥርተው አያዩም ነበር፥ ማየትም አይችልም ነበር።16ሰውየውም ዔሊን፥ “ከውጊያው መስመር የመጣሁት እኔ ነኝ። ዛሬ ከውጊያው ሸሽቼ መጣሁ” አለው። ዔሊም፥ “ልጄ ሆይ፥ ነገሩ እንዴት እየሆነ ነው?” አለው። 17ወሬውን ያመጣው ያ ሰው መልሶ፥ “እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ። ደግሞም በሕዝቡ መካከል ታላቅ ዕልቂት ሆኗል። ሁለቱ ወንዶች ልጆችህ፥ አፍኒን እና ፊንሐስ ሞተዋል፥ የእግዚአብሔር ታቦትም ተወስዷል” አለው።18እርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ጠቅሶ በተናገረ ጊዜ፥ ዔሊ በመግቢያው በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ወደ ኋላው ወደቀ። ስላረጀና ውፍረት ስለነበረው አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤላውያን ላይ ለአርባ ዓመታት ፈርዶ ነበር።19በዚህ ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት አርግዛ የመውለጃ ሰዓቷ ደርሶ ነበር። የእግዚአብሔር ታቦት መማረኩን፥ ዐማቷና ባሏ መሞታቸውን በሰማች ጊዜ ተንበርክካ ወለደች፥ ነገር ግን ምጡ አስጨነቃት። 20ለመሞት በምታጣጥርበት ጊዜ ያዋልዷት የነበሩ ሴቶች፥ "ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ“ አሏት። እርሷ ግን አልመለሰችላቸውም ወይም የነገሯትን በልቧ አላኖረችውም።21እርሷም የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከና ስለ ዐማቷና ስለ ባልዋ "ክብር ከእስራኤል ተለየ!" ስትል ልጁን ኤካቦድ ብላ ጠራችው። 22እርሷም፥”የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከ ክብር ከእስራኤል ተለየ!" አለች።
1ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት በመማረክ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ አመጡት። 2እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ማርከው ወደ ዳጎን ቤት ወስደው በዳጎን አጠገብ አቆሙት። 3የአሽዶድ ሰዎች በቀጣዩ ቀን ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። ስለዚህ ዳጎንን አንሥተው በስፍራው መልሰው አቆሙት።4ነገር ግን በማግስቱ ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። በደጁ መግቢያ ውስጥ የዳጎን ራሱና እጆቹ ተሰብረው ወድቀው ነበር። የቀረው የዳጎን ሌላው የአካል ክፍሉ ብቻ ነበር። 5ለዚህ ነው እስካሁን እንኳን የዳጎን ካህናትና ሌላ ማንኛውም ሰው በአሽዶድ ወደሚገኘው ወደ ዳጎን ቤት በሚመጣበት ጊዜ የዳጎንን ደጅ መግቢያ ሳይረግጥ የሚያልፈው።6የእግዚአብሔር እጅ በአሽዶድ ሰዎች ላይ ከብዶ ነበር። በአሽዶድና በዙሪያው ባሉት ላይ ጥፋትን በማምጣት በእባጭ መታቸው። 7የአሽዶድ ሰዎች የሆነባቸውን ባስተዋሉ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ከብዳለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ጋር መቆየት የለበትም” አሉ።8ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ልከው በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ "በእስራኤል አምላክ ታቦት ላይ ምን እናድርግ?" አሏቸው። እነርሱም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይምጣ” ብለው መለሱላቸው። የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደዚያ ወሰዱት። 9ነገር ግን ወደዚያ ካመጡት በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፥ ታላቅ መደናገርንም አደረገባቸው። ልጅና ዐዋቂውን፥ የከተማውን ሰዎች አስጨነቀ፤ ሰውነታቸውም በእባጭ ተወረረ።10ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ አቃሮን ላኩት። ነገር ግን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቃሮን እንደ መጣ፥ አቃሮናውያን፥ "እኛንና ሕዝባችንን እንዲገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ እኛ አምጥተዋል" በማለት ጮኹ።11ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች በመላክ ሁሉንም በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ “እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ላኩት፥ ወደ ስፍራውም ይመለስ" አሏቸው። በዚያ የእግዚአብሔር እጅ እጅግ ስለበረታባቸው በከተማው ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበረ። 12ከሞት የተረፉት ሰዎች በእባጮቹ ይሠቃዩ ስለነበር የከተማዪቱ ጩኸት ወደ ሰማያት ወጣ።
1የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን አገር ከተቀመጠ ሰባት ወር ሆነው። 2ከዚያም የፍልስጥኤም ሰዎች ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የእግዚአብሔርን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ አገሩ እንዴት አድርገን መመለስ እንዳለብን ንገሩን” አሉአቸው።3ካህናቱና ጠንቋዮቹም፥ "የእስራኤልን አምላክ ታቦት መልሳችሁ የምትልኩ ከሆነ ያለስጦታ አትላኩት፤ በተቻለ መጠን የበደል መስዋዕትም ላኩለት። ከዚያም ትፈወሳላችሁ፥ እናንተም እስካሁን ድረስ እጁን ከላያችሁ ላይ ያላነሣው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ"። 4ሕዝቡም፥ “የምንመልሰው የበደል መስዋዕት ምን መሆን አለበት?”አሏቸው። እነርሱም እንዲህ በማለት መለሱላቸው፥ "አምስት የወርቅ እባጮችንና አምስት የወርቅ አይጦችን፥ በቁጥር አምስት መሆኑም የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች ቁጥር የሚወክል ነው። እናንተንና ገዢዎቻችሁን የመታው ተመሳሳይ መቅሰፍት ነውና።5ስለዚህ ምድራችንን ባጠፋው በእባጮቻችሁና በአይጦቻችሁ አምሳል ማድረግ አለባችሁ፥ ለእስራኤል አምላክም ክብርን ስጡ። ምናልባት እጁን ከእናንተ፥ ከአማልክቶቻችሁና ከምድሪቱ ላይ ያነሣ ይሆናል። 6ግብፃውያንና ፈርዖን ልባቸውን እንዳደነደኑ ለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? ያን ጊዜ ነበር የእስራኤል አምላክ ክፉን ያደረገባቸው፤ ታዲያ ግብፃውያኑ ሕዝቡን አልለቀቋቸውም?እነርሱስ ከዚያ አልወጡም?7እንግዲህ አዲስ ሠረገላና እስካሁን ቀንበር ያልተጫነባቸውን ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፥ እምቦሳዎቻቸውን ግን ከእነርሱ ለይታችሁ በቤት አስቀሩአቸው። 8ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩት። የበደል መስዋዕት አድርጋችሁ የምትመልሱለትን የወርቁን አምሳያዎች በሳጥን ውስጥ አድርጋችሁ በአንደኛው ጎኑ አስቀምጡ። ከዚያም ልቀቁትና በራሱ መንገድ እንዲሄድ ተዉት። 9ከዚያም ተመልከቱ፥ ወደ ራሱ ምድር፥ ወደ ቤት ሳሚስ በመንገዱ ከሄደ፥ ይህንን ታላቅ ጥፋት ያመጣው እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ካልሆነ ግን፥ ይህ በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን"።10ሰዎቹም እንደተነገራቸው አደረጉ፤ ሁለት የሚያጠቡ ላሞችን ወሰዱና በሠረገላው ጠመዷቸው፥ እምቦሳዎቻቸውንም ከቤት እንዳይወጡ አደረጉ። 11የወርቁን አይጥና የእባጮቻቸው ምሳሌ የሆነውን ከያዘው ሳጥን ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት በሠረገላው ላይ አደረጉት። 12ላሞቹም በቤት ሳሚስ አቅጣጫ ቀጥ ብለው ሄዱ። እነርሱም በዚያው ጎዳና፥ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳይሉ ቁልቁል ሄዱ። የፍልስጥኤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤት ሳሚስ ዳርቻ ድረስ ከበስተኋላቸው ተከተሏቸው።13በዚህ ጊዜ የቤት ሳሚስ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን በማጨድ ላይ ነበሩ። ቀና ብለው ባዩ ጊዜ ታቦቱን ተመለከቱ፥ ደስም አላቸው።14ሠረገላው የቤት ሳሚስ ሰው ወደሆነው ወደ ኢያሱ እርሻ መጥቶ በዚያ ቆመ። በዚያም ትልቅ ቋጥኝ ነበር፥ የሠረገላውን እንጨት በመፍለጥ ላሞቹን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። 15ሌዋውያኑ የእግዚአብሔርን ታቦትና አብሮት የነበረውን፥ የወርቁ ምስሎች የነበሩበትን ሳጥን፥ ከሠረገላው አውርደው በትልቁ ቋጥኝ ላይ አስቀመጡት። በዚያው ቀን የቤት ሳሚስ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቀርቡ፥ መሥዋዕቶችንም ሠዉ።16አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ይህንን ባዩ ጊዜ በዚያው ቀን ወደ አቃሮን ተመለሱ።17የፍልስጥኤም ሰዎች ለእግዚአብሔር የበደል መስዋዕት አድርገው የመለሷቸው የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት እና አንዱ ስለ አቃሮን ነበር። 18የወርቁ አይጥ አምስቱ ገዢዎች ከሚገዟቸው የተመሸጉ የፍልስጥኤማውያን ከተሞችና መንደሮች ቁጥር ሁሉ ጋር ቁጥሩ ተመሳሳይ ነበር። የእግዚአብሔርን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ታላቅ ቋጥኝ በቤት ሳሚስ በኢያሱ እርሻ ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ምስክር ሆኖ ይኖራል።19ወደ ታቦቱ ውስጥ ተመልክተዋልና እግዚአብሔር ከቤት ሳሚስ ሰዎች ጥቂቶቹን መታቸው። እርሱም ሰባ ሰዎችን ገደለ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ክፉኛ ስለመታቸው ሕዝቡ አለቀሱ። 20የቤት ሳሚስ ሰዎችም፥ “በዚህ ቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚችል ማነው? ከእኛስ ወደ ማን ይሄዳል?” አሉ።21በቂርያትይዓሪም ወደሚኖሩት መልዕክተኞች ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰዋል፤ ወደዚህ ውረዱና ውሰዱት” አሏቸው።
1የቂርያትይዓሪም ሰዎች መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ፥ በኮረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አስገቡት። የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ለዚህ አገልግሎት ለዩት። 2ታቦቱ በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠ ብዙ ዓመት አለፈው፥ ሃያ ዓመትም ሆነው። የእስራኤል ቤት ሁሉ አዘኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስም ፈለጉ።3ሳሙኤል የእስራኤልን ሕዝብ በሙሉ እንዲህ አላቸው፥ "በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱ ከሆነ እንግዶቹን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፥ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር መልሱ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩት፥ ያን ጊዜ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል"። 4ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ በኣልንና አስታሮትን አስወገዱ፥ እግዚአብሔርን ብቻም አመለኩ።5ከዚያም ሳሙኤል፥ "እስራኤልን በሙሉ ምጽጳ ላይ ሰብስቡ፥ እኔም ስለ እናንተ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ“ አላቸው። 6እነርሱም በምጽጳ ተሰበሰቡ፥ ውሃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ። በዚያም ቀን ጾሙ፥”በእግዚአብሔር ላይም ኃጢአትን አድርገናል“ አሉ። ሳሙኤል በእስራኤል ሕዝብ ላይ የፈረደውና ሕዝቡን የመራው በዚያ ነበር።7የእስራኤል ሕዝብ በምጽጳ መሰብሰባቸውን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፥ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች እስራኤልን ለማጥቃት መጡ። የእስራኤል ሰዎች ይህንን በሰሙ ጊዜ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ። 8ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ ሳሙኤልን፥”ከፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲያድነን፥ ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር መጣራትህን አታቁም“ አሉት።9ሳሙኤል የሚጠባ ግልገል ወስዶ ለእግዚአብሔር ሙሉውን የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ሠዋው። ከዚያም ሳሙኤል ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም መለሰለት።10ሳሙኤል የሚቃጠለውን መስዋዕት በማቅረብ ላይ እያለ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለማጥቃት ቀረቡ። ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ በታላቅ ድምፅ አንጎደጎደባቸው፥ አሸበራቸውም፥ በእስራኤልም ፊት ተሸንፈው ሸሹ። 11የእስራኤል ሰዎችም ከምጽጳ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን አሳደዱ፥ ከቤትካር በታች እስካለው ቦታ ድረስ ተከትለው ገደሏቸው።12ከዚያም ሳሙኤል አንድ ድንጋይ አንሥቶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው።”እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል“ በማለት አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።13ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፥ የእስራኤልን ድንበርም አልፈው አልገቡም። በሳሙኤል የሕይወት ዘመን ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር። 14ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከአቃሮን እስከ ጌት ያሉ መንደሮች ለእስራኤል ተመለሱላቸው፤ እስራኤላውያን ድንበሮቻቸውን ከፍልስጥኤማውያን አስመለሱ። በዚያን ጊዜ በእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከል ሰላም ነበረ።15ሳሙኤል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በእስራኤል ላይ ፈረደ። 16በየዓመቱ ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌልገላና ወደ ምጽጳ ይዘዋወር ነበር። በእነዚህ ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤላውያን መካከል ባሉ አለመግባባቶች ላይ ይፈርድ ነበር። 17ከዚያም መኖሪያው በዚያ ነበርና ወደ ራማ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ደግሞ በእስራኤላውያን አለመግባባት ላይ ይፈርድ ነበር። በዚያም ደግሞ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ።
1ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ላይ ፈራጆች አድርጎ ሾማቸው። 2የመጀመሪያ ልጁ ስም ኢዮኤል፥ የሁለተኛው ስም አብያ ነበር። እነርሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ። 3ነገር ግን ልጆቹ ነውረኛ ጥቅም ፈላጊዎች ሆኑ እንጂ በእርሱ መንገድ አልሄዱም። ጉቦ እየተቀበሉ ፍትሕን አዛቡ።4ከዚያም የእስራኤል ሽማግሌዎች በአንድነት ተሰብስበው በራማ ወደሚኖረው ወደ ሳሙኤል መጡ። 5እነርሱም፥ "ተመልከት፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም። እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ እንዲፈርድልን ንጉሥ አንግሥልን" አሉት።6ነገር ግን፥ “እንዲፈርድልን ንጉሥ ስጠን” ባሉት ጊዜ ነገሩ ሳሙኤልን ቅር አሰኘው። ስለዚህ ሳሙኤል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። 7እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፥ “በላያቸው ላይ ንጉሥ እንዳልሆን የተቃወሙት እኔን እንጂ አንተን አይደለምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ታዘዝ።8ከግብፅ ካወጣዃቸው ጊዜ ጀምሮ እኔን ትተው ሌሎች አማልክቶችን በማምለክ ሲያደርጉት የነበረውን ያንኑ አሁን እያደረጉ ነው፤ በአንተም ላይ የሚያደርጉት እንደዚሁ ነው። 9አሁንም የሚሉህን ስማቸው፤ ነገር ግን በላያቸው የሚገዛው ንጉሥ የሚያደርግባቸውን እንዲያውቁ አጥብቀህ አስጠንቅቃቸው"።10ስለዚህ ሳሙኤል ንጉሥ ለጠየቀው ሕዝብ የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ነገራቸው። 11እርሱም እንዲህ አላቸው፥ "ንጉሡ በላያችሁ ላይ የሚገዛው እንዲህ ነው። ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ፈረሰኞች እንዲሆኑና በሠረገላዎቹ ፊት እንዲሮጡ በሠረገላዎቹ ላይ ይሾማቸዋል። 12እርሱም ለራሱ ሻለቃዎችንና ሃምሳ አለቃዎችን ይሾማል። አንዳንዶቹ መሬቱን እንዲያርሱ፥ ሌሎቹም እህሉን እንዲያጭዱ፥ አንዳንዶቹ የጦር መሳሪያዎችንና ሌሎቹም የሠረገላ ዕቃዎችን እንዲሠሩለት ያደርጋቸዋል።13ሴቶች ልጆቻችሁን ደግሞ ሽቶ ቀማሚዎች፥ ወጥ ሠሪዎችና እንጀራ ጋጋሪዎች እንዲሆኑ ይወስዳቸዋል። 14በጣም ምርጥ የሆነውን መሬታችሁን፥ የወይን ቦታችሁንና የወይራ ዛፋችሁን ወስዶ ለአገልጋዮቹ ይሰጣቸዋል። 15ከእህላችሁና ከወይናችሁ አንድ ዐሥረኛውን ወስዶ ለሹማምንቱና ለአገልጋዮቹ ይሰጣቸዋል።16ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁን፥ ከወጣት ልጆቻችሁና ከአህዮቻችሁ የተመረጡትን ይወስዳል፤ ሁሉንም ለእርሱ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል። 17ከበግና ከፍየል መንጋዎቻችሁ አንድ ዐሥረኛውን ይወስዳል፥ እናንተም አገልጋዮቹ ትሆናላችሁ። 18በዚያም ቀን ለራሳችሁ ስለመረጣችሁት ንጉሥ ታለቅሳላችሁ፤ ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር አይመልስላችሁም”።19ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን ለመስማት እምቢ አሉ፤ 20ሳሙኤልንም፥ “አይሆንም፥ ንጉሣችን እንዲፈርድልን፥ በፊታችን እንዲሄድና ጦርነቶቻችንን እንዲዋጋልን፥ እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ለእኛም ንጉሥ ሊሆንልን ይገባል” አሉት።21ሳሙኤል የሕዝቡን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ እርሱም በእግዚአብሔር ጆሮ ደግሞ ተናገረው። 22እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “ቃላቸውን ታዘዝና ንጉሥ አድርግላቸው” አለው። ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤልን ሰዎች፥ “እያንዳንዱ ወደገዛ ከተማው ይሂድ” አላቸው።
1ከብንያም ወገን ጽኑ ኃያል የሆነ አንድ ሰው ነበር። ስሙ ቂስ ሲሆን እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጽሮር ልጅ፥ የብኮራት ልጅ፥ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ ነበር። 2እርሱም ሳኦል የሚባል መልከ መልካም ወጣት ልጅ ነበረው። ከእርሱ የሚበልጥ መልከ መልካም ሰው በእስራኤል ሕዝብ መካከል አልነበረም። ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ ቁመቱ ረጅም ነበር።3የሳኦል አባት የቂስ ሴት አህዮች ጠፍተው ነበር። ስለዚህ ቂስ ልጁን ሳኦልን፥ “ከአገልጋዮቻችን አንዱን ውሰድ፤ ተነሥናም አህዮቹን ፈልግ” አለው። 4ስለዚህ ሳኦል በኮረብታማው በኤፍሬም አገር በኩል አልፎ ወደ ሻሊሻ ምድር ሄደ፥ ነገር ግን አላገኟቸውም። ከዚያም በሻዕሊም ምድር በኩል አለፉ፥ ነገር ግን በዚያ አልነበሩም። ከዚያም በብንያማውያን ምድር በኩል አለፉ፥ ነገር ግን አላገኟቸውም።5ወደ ጹፍ ምድር በመጡ ጊዜ፥ ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን አገልጋዩን፥ "ና እንመለስ፥ አለበለዚያ አባቴ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ ይጀምራል" አለው። 6ነገር ግን አገልጋዩ እንዲህ አለው፥ “ስማኝ፥ በዚህ ከተማ ውስጥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ። እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረው ነገር ሁሉ ይፈጸማል። ወደዚያ እንሂድ፤ በየትኛው አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን ሊነግረን ይችል ይሆናል"።7ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን፥ "ታዲያ ወደ እርሱ የምንሄድ ከሆነ ለዚያ ሰው ምን ልንሰጠው እንችላለን? እንጀራው ከከረጢታችን አልቋል፥ ለእግዚአብሔር ሰው የምናቀርበው ምንም ስጦታ የለንም። ምን አለን?"አለው። 8አገልጋዩም ለሳኦል፥ "ይኸውና፥ የሰቅል ጥሬ ብር አንድ አራተኛው አለኝ፥ በየትኛው አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ" ሲል መለሰለት።9(ቀደም ሲል በእስራኤል ውስጥ፥ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ በሚሄድበት ጊዜ፥ "ኑ፥ ወደ ባለ ራዕዩ እንሂድ" ይል ነበር። የዛሬው ነቢይ ቀደም ሲል ባለ ራዕይ ተብሎ ይጠራ 10ነበር።)ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን፥”መልካም ብለሃል። ና፥ እንሂድ“ አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወደነበረበት ከተማ ሄዱ። 11ኮረብታው ላይ ወዳለው ከተማ በመውጣት ላይ እያሉ ወጣት ሴቶች ውሃ ለመቅዳት ሲወጡ አገኟቸው፤ ሳኦልና አገልጋዩም፥”ባለ ራዕዩ በዚህ አለ? “ በማለት ጠየቋቸው።12እነርሱም እንዲህ በማለት መለሱላቸው፥ "አዎን፤ ተመልከቱ፥ እንዲያውም ከፊታችሁ እየቀደመ ነው። ዛሬ ሕዝቡ በኮረብታው ራስ ላይ ስለሚሠዉ ወደ ከተማው ይመጣልና ፍጠኑ። 13ወደ ከተማው እንደገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ራስ ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን የሚባርከው እርሱ ስለሆነ፥ እርሱ ከመምጣቱ በፊት ሕዝቡ አይበሉም፤ ከዚያ በኋላም የተጋበዙት ይበላሉ። ወዲያውኑ ታገኙታላችሁና አሁን ወደ ላይ ውጡ።”14ስለዚህ ወደ ላይ ወደ ከተማው ወጡ። ወደ ከተማይቱ በመግባት ላይ እያሉም ሳሙኤል ወደ ኮረብታው ራስ ለመውጣት በእነርሱ አቅጣጫ ሲመጣ አዩት።15ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል እንዲህ ሲል ገልጦለት ነበር፥ 16“ነገ በዚህ ሰዓት ከብንያም ምድር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፥ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መስፍን እንዲሆን ትቀባዋለህ። እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናቸዋል። እርዳታ በመፈለግ መጮኻቸው ወደ እኔ ደርሷልና ሕዝቤን በርኅራኄ ተመልክቻለሁ።”17ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፥”ስለ እርሱ የነገርኩህ ሰው ይህ ነው! ሕዝቤን የሚገዛው ሰው እርሱ ነው።“ 18ከዚያም ሳኦል በበሩ አጠገብ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፥”የባለ ራዕዩ ቤት የት እንደሆነ ንገረኝ“ አለው። 19ሳሙኤልም ለሳኦል እንዲህ በማለት መለሰለት፥”ባለ ራዕዩ እኔ ነኝ። ከእኔ በፊት ቀድማችሁ ወደ ኮረብታው ራስ ውጡ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር ትበላላችሁና። ነገ ጠዋት በአዕምሮህ ያለውን ነገር ሁሉ እነግርህና አሰናብትሃለሁ።20ከሦስት ቀን በፊት ጠፍተው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋልና ስለ እነርሱ አታስብ። የእስራኤል ሁሉ ምኞት የተቀመጠው በማን ላይ ነው? በአንተና በአባትህ ቤት ሁሉ ላይ አይደለም? “ 21ሳኦልም፥ "ከእስራኤል ነገዶች ትንሹ የሆነው ብንያማዊ አይደለሁም? ጎሳዬስ ከብንያም ነገድ ጎሳዎች ሁሉ የመጨረሻው አይደለም? ታዲያ እንዲህ ባለ ሁኔታ ለምን ትናገረኛለህ?"ሲል መለሰለት።22ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ አዳራሹ አስገብቶ ሠላሳ ከሚያህሉ ከተጋበዙት ሰዎች ከፍ ባለው ስፍራ ላይ አስቀመጣቸው።23ሳሙኤልም ወጥ ሠሪውን፥ "'ለብቻ አስቀምጠው' ብዬ የሰጠሁህን ድርሻ አምጣው" አለው። 24ወጥ ሠሪውም በመሥዋዕቱ ጊዜ ያነሣውን ጭኑንና ከእርሱ ጋር ያለውን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ከዚያም ሳሙኤል፥ "የተቀመጠልህን ተመልከት! ለአንተ እስከተወሰነው ሰዓት ድረስ የቆየልህ ነውና ብላው። አሁን 'ሕዝቡን ጋብዣለሁ' ማለት ትችላለህ" አለው። ስለዚህ በዚያን ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ።25ከኮረብታው ራስ ወደ ከተማው በወረዱ ጊዜ፥ በቤቱ የጣሪያ ወለል ላይ ሳሙኤል ከሳኦል ጋር ተነጋገረ። 26ከዚያም በነጋ ጊዜ ሳሙኤል በጣሪያው ወለል ላይ ሳኦልን ተጣርቶ፥ "መንገድህን እንድትሄድ አሰናብትህ ዘንድ ተነሥ" አለው። ስለዚህ ሳኦል ተነሣ፥ እርሱና ሳሙኤል ሁለቱም ወደ ጎዳናው ሄዱ።27ወደ ከተማው ዳርቻ በመሄድ ላይ እያሉ፥ ሳሙኤል ሳኦልን፥ "አገልጋዩ ከፊታችን ቀድሞ እንዲሄድ ንገረው፥ (እርሱም ቀድሞ ሄደ) አንተ ግን የእግዚአብሔርን መልዕክት እንዳስታውቅህ እዚህ ጥቂት መቆየት አለብህ" አለው።
1ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ጠርሙስ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። እርሱም እንዲህ አለው፥ "በርስቱ ላይ ገዢ እንድትሆን እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ 2ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፥ የብንያም ወሰን በሆነው በጼልጻህ፥ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፥ 'ስትፈልጋቸው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋል። አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፥ "ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?" በማለት ተጨንቋል“ ይሉሃል።3ከዚያ አልፈህ ትሄድና በታቦር ወደሚገኘው ወደ በሉጥ ዛፍ ትመጣለህ። ወደ ቤቴል፥ ወደ እግዚአብሔር የሚሄዱ አንደኛው ሦስት የፍየል ጠቦቶች ይዞ፥ ሌላኛው ሦስት ዳቦ ተሸክሞ፥ ሌላኛው ደግሞ ወይን ጠጅ የተሞላ አንድ አቁማዳ ተሸክሞ ሦስት ሰዎች ይገናኙሃል። 4ሰላምታ ከሰጡህ በኋላ ሁለት ዳቦ ይሰጡሃል፥ ከእጃቸውም ትቀበላቸዋለህ።5ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤም የጦር ሠፈር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ። ወደ ከተማው በምትደርስበት ጊዜ፥ አንድ የነቢያት ቡድን በፊታቸው መሰንቆ፥ ከበሮ፥ እምቢልታና በገና ይዘው ከተራራው ሲወርዱ ትገናኛቸዋለህ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገራሉ። 6የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ይመጣብሃል፥ አንተም ከእነርሱ ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰው ሆነህም ትለወጣለህ።7እነዚህ ምልክቶች በሚፈጸሙልህ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ ያገኘውን ሁሉ አድርግ። 8ቀድመኸኝ ወደ ጌልገላ ውረድ። ከዚያም የሚቃጠለውን መባ ለማቅረብና የሰላሙን መባ ለመሠዋት ወደ አንተ እወርዳለሁ። ወደ አንተ እስክመጣና ልታደርገው የሚገባህን እስከማሳይህ ድረስ ሰባት ቀን ቆይ።”9ሳኦል ከሳሙኤል ተለይቶ ለመሄድ ፊቱን ባዞረ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ሰጠው። እነዚህ ምልክቶች ሁሉ በዚያው ቀን ተፈጸሙ። 10እነርሱም ወደ ኮረብታው በመጡ ጊዜ፥ የነቢያት ቡድን ተገናኙት፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል መጣበት፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ተናገረ።11ቀድሞ ያውቁት የነበሩት ሁሉ እርሱም ከነቢያት ጋር ትንቢት ሲናገር ባዩት ጊዜ፥ እርስ በእርሳቸው፥ “የቂስን ልጅ ምን ነካው? አሁን ሳኦል ከነቢያት አንዱ መሆኑ ነው?” ተባባሉ። 12በዚያው ስፍራ የነበረ አንድ ሰው፥ “አባታቸው ማነው?” ሲል መለሰ። በዚህ ምክንያት፥ “ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ነው?” የሚል ምሳሌአዊ አባባል የተለመደ ሆነ። 13ትንቢት መናገሩን በጨረሰ ጊዜ ወደ ተራራው ራስ መጣ።14ከዚያም የሳኦል አጎት፥ እርሱንና አገልጋዩን፥ “የት ነበር የሄዳችሁት?” አላቸው። እርሱም፥ “አህዮቹን ለመፈለግ ነበር፤ ልናገኛቸው እንዳልቻልን ባየን ጊዜ ወደ ሳሙኤል ሄድን” ብሎ መለሰለት። 15የሳኦልም አጎት፥ “ሳሙኤል የነገረህን እባክህ ንገረኝ" አለው። 16ሳኦልም አጎቱን፥ "አህዮቹ መገኘታቸውን በግልጽ ነገረን" ብሎ መለሰለት። ሳሙኤል ነግሮት የነበረውን የንግሥና ጉዳይ ግን አልነገረውም።17ሳሙኤል ሕዝቡን በአንድነት በእግዚአብሔር ፊት ወደ ምጽጳ ጠራቸው። 18እርሱም የእስራኤልን ሕዝብ እንዲህ አላቸው፥”የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፥ 'እስራኤልን ከግብፅ አወጣሁት፥ ከግብፃውያን እጅና ካስጨነቋችሁ መንግሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ'። 19ነገር ግን ዛሬ እናንተ ከመከራና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ተቃውማችኋል፤ እርሱንም፥ 'በላያችን ላይ ንጉሥ አንግሥልን' ብላችሁታል። አሁን በየነገዳችሁና በየጎሣችሁ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ"።20ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ አቀረበ፥ የብንያም ነገድም ተመረጠ። 21ከዚያም የብንያምን ነገድ በየጎሣቸው አቀረበ፤ የማጥሪ ጎሣም ተመረጠ፤ የቂስ ልጅ ሳኦልም ተመረጠ። ነገር ግን በፈለጉት ጊዜ ሊያገኙት አልቻሉም።22ከዚያም ሕዝቡ”ገና የሚመጣ ሌላ ሰው አለ? “ በማለት እግዚአብሔርን ተጨማሪ ጥያቄዎች ለመጠየቅ ፈለጉ። እግዚአብሔርም፥”ራሱን በዕቃዎቹ መካከል ደብቋል" በማለት መለሰላቸው። 23ከዚያም ሮጠው ሄዱና ሳኦልን ከዚያ አመጡት። በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜ፥ ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ ቁመቱ ረጅም ነበር።24ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ "እግዚአብሔር የመረጠውን ይህንን ሰው ታዩታላችሁ? በሕዝቡ ሁሉ መካከል እንደ እርሱ ያለ የለም! “ አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ፥”ንጉሥ ለዘላለም ይኑር! “ በማለት ጮኹ።25ከዚያም ሳሙኤል የንግሥናን ደንብና ልማዶች ለሕዝቡ ነገራቸው፥ በመጽሐፍ ጽፎም በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጣቸው። ከዚያም ሳሙኤል እያንዳንዱ ወደ ገዛ መኖሪያው እንዲሄድ ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ።26ሳኦልም ደግሞ በጊብዓ ወደሚገኘው መኖሪያው ሄደ፥ እግዚአብሔር ልባቸውን የነካቸው አንዳንድ ኃያላን ሰዎችም ከእርሱ ጋር ሄዱ። 27አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች ግን፥”ይህ ሰው ሊያድነን እንዴት ይችላል? “ አሉ። እነዚህ ሰዎች ሳኦልን ናቁት፥ ምንም ዓይነት ስጦታዎችንም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።
1አሞናዊው ናዖስ ሄዶ ኢያቢስ ገለዓድን ከበባት። የኢያቢስ ሰዎች ሁሉ ናዖስን፥ "ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እኛም እናገለግልሃለን" አሉት። 2አሞናዊው ናዖስም፥ "የሁላችሁንም ቀኝ ዐይኖቻችሁን በማውጣት በመላው እስራኤል ላይ ኃፍረትን አመጣለሁ፥ በዚህ ቅድመ ሁኔታ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ" ብሎ መለሰላቸው።3የኢያቢስ ሽማግሌዎችም፥ "ወደ እስራኤል ወገኖች ሁሉ መልዕክተኞችን እንድንልክ ለሰባት ቀናት ታገሰን። ከዚያም የሚያድነን አንድም ባይኖር ለአንተ እንገዛለን" በማለት መለሱለት።4መልዕክተኞቹም ሳኦል ወደሚኖርበት ወደ ጊብዓ መጥተው የሆነውን ነገር ለሕዝቡ ነገሯቸው። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። 5በዚህ ጊዜ ሳኦል ከእርሻ በሬዎቹን እየነዳ መጣ። ሳኦልም፥ "ሕዝቡ ምን ሆኖ ነው የሚያለቅሰው?" አለ። እነርሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሉትን ለሳኦል ነገሩት።6ሳኦል የነገሩትን በሰማ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል መጣበት፥ እጅግም ተቆጣ። 7የበሬዎቹን ቀንበር ወስዶ ፈለጣቸውና ወደ እስራኤል ወሰኖች ሁሉ በመልዕክተኞች እጅ ላከው። እርሱም፥ "ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ በማይመጣው ሁሉ በበሬዎቹ ላይ እንዲህ ይደረግበታል" አለ። ከዚያም ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍርሃት በሕዝቡ ላይ ወደቀ፥ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰብስበው መጡ። 8ቤዜቅ በተባለ ስፍራ በሰበሰባቸው ጊዜ፥ የእስራኤል ሰዎች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይሁዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።9እነርሱም ለመጡት መልዕክተኞች፥ "ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፥ 'ነገ ፀሐይ ሞቅ በሚልበት ሰዓት እንታደጋችኋለን' ብላችሁ ንገሯቸው" አሏቸው። መልዕክተኞቹ ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሯቸው፥ እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው። 10ከዚያም የኢያቢስ ሰዎች ናዖስን፥”ነገ እንገዛልሃለን፥ አንተም ደስ የሚያሰኝህን ልታደርግብን ትችላለህ“ አሉት።11በቀጣዩ ቀን ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ቡድን ከፈላቸው። ሊነጋጋ ሲል ወደ ጦር ሠፈሩ መካከል መጡ፥ አሞናውያንንም አጠቁ፥ ቀኑ እስኪሞቅ ድረስም አሸነፏቸው። በሕይወት የተረፉትም ከእነርሱ ሁለቱ አንድ ላይ ሆነው እስከማይታዩ ድረስ ተበታተኑ።12በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ሳሙኤልን፥ "'ሳኦል በእኛ ላይ እንዴት ይነግሣል?' ያለው ማን ነበር? እንድንገድላቸው ሰዎቹ ይምጡልን" አሉት። 13ነገር ግን ሳኦል፥ "ዛሬ እግዚአብሔር እስራኤልን ታድጎታልና በዚህ ቀን ማንም መገደል የለበትም" አላቸው።14ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ "ኑ፥ ወደ ጌልገላ እንሂድና በዚያ መንግሥቱን እናድስ" አላቸው። 15ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ሳኦልን አነገሡት። በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የሰላምን መባ ሠዉ፥ ሳኦልና የእስራኤል ሰዎችም ሁሉ እጅግ ደስ አላቸው።
1ሳሙኤል እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አላቸው፥”የነገራችሁኝን በሙሉ ሰምቻችኋለሁ፥ ንጉሥንም በላያችሁ ላይ አንግሼላችኋለሁ። 2አሁንም፥ በፊታችሁ የሚሄድላችሁ ንጉሥ ይኸውላችሁ፤ እኔ አርጅቻለሁ፥ ጸጉሬም ሸብቷል፤ ልጆቼም ከእናንተ ጋር ናቸው። ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በፊታችሁ ኖሬአለሁ።3ይኸው በፊታችሁ ነኝ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ። የማንን በሬ ወስጃለሁ? የማንንስ አህያ ወስጃለሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? ዓይኖቼን ለማሳወር ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? መስክሩብኝና እመልስላችኋለሁ።“4እነርሱም፥”አላታለልከንም፥ ግፍም አልሠራህብንም ወይም ከማንም እጅ ምንም ነገር አልሰረቅህም“ አሉ። 5እርሱም፥”በእጄ ላይ ምንም እንዳላገኛችሁ ዛሬ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ምስክር ነው፥ እርሱ የቀባውም ምስክር ነው“ አላቸው። እነርሱም፥”እግዚአብሔር ምስክር ነው“ ብለው መለሱ።6ሳሙኤልም ሕዝቡን፥”ሙሴንና አሮንን የመረጣቸው፥ አባቶቻችሁንም ከግብፅ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር ነው። 7አሁን እንግዲህ፥ እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ስለ ሠራላችሁ የጽድቅ ሥራ ሁሉ እንድሟገታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን አቅርቡ።8ያዕቆብ ወደ ግብፅ በመጣ ጊዜ አባቶቻችሁ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔር፥ ከግብፅ ምድር እየመሩ አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲቀመጡ ያደረጓቸውን ሙሴንና አሮንን ላከ። 9እነርሱ ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፤ እርሱም የሐጾር ሠራዊት አዛዥ በሆነው በሲሣራ እጅ፥ በፍልስጥኤማውያን እጅና በሞአብ ንጉሥ እጅ ሸጣቸው፤ እነዚህ ሁሉ አባቶቻችሁን ተዋጓቸው።10እነርሱም ወደ እግዚአብሔር በመጮህ፥ "እግዚአብሔርን ትተን በኣልንና አስታሮትን በማገልገላችን ኃጢአት አድርገናል። አሁን ግን ከጠላቶቻችን እጅ አድነን፥ እኛም እናገለግልሃለን' አሉት። 11ስለዚህ እግዚአብሔር ይሩበኣልን፥ ባርቅን፥ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ በሰላም እንድትኖሩ በዙሪያችሁ ባሉ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ ድልን ሰጣችሁ።12እናንተም የአሞን ሕዝብ ንጉሥ ናዖስ እንደመጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሆኖ እያለ፥ 'አይሆንም፥ ይልቁን በላያችን ላይ ንጉሥ መንገሥ አለበት' አላችሁኝ። 13አሁንም እናንተ የመረጣችሁት፥ እንዲሆንላችሁ የጠየቃችሁትና እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ንጉሥ እንዲሆን የመረጠው ንጉሥ ይኸውላችሁ።14እናንተም እግዚአብሔርን ብትፈሩት፥ ብታገለግሉት፥ ድምፁንም ብትታዘዙና በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ባታምጹ ያን ጊዜ እናንተና በላያችሁ የሚገዛው ንጉሣችሁ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ተከታዮች ትሆናላችሁ። 15የእግዚአብሔርን ድምፅ ባትታዘዙ፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ብታምጹ፥ ያን ጊዜ በአባቶቻችሁ ላይ እንደነበረ የእግዚአብሔር እጅ በእናንተ ላይ ይሆናል።16አሁንም፥ ራሳችሁን አቅርቡና እግዚአብሔር በዓይናችሁ ፊት የሚያደርገውን ይህንን ታላቅ ነገር ተመልከቱ። 17ዛሬ የስንዴ መከር ነው አይደል? ነጎድጓድና ዝናብን እንዲልክ እግዚአብሔርን እጠራለሁ። ከዚያም ለራሳችሁ ንጉሥ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደረጋችሁት ክፋት ታላቅ እንደሆነ ታውቃላችሁ፥ ታያላችሁም“። 18ስለዚህ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ጠራ፤ በዚያው ቀን እግዚአብሔር ነጎድጓድንና ዝናብን ላከ። ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን በጣም ፈሩ።19ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሳሙኤልን፥ "እንዳንሞት፥ ስለ አገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። ለራሳችን ንጉሥ በመጠየቃችን በኃጢአታችን ሁሉ ላይ ይህንን ክፋት ጨምረናልና” አሉት። 20ሳሙኤል እንዲህ ሲል መለሰላቸው፥ “አትፍሩ። ይህንን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችሁ አገልግሉት እንጂ ከእግዚአብሔር ፊታችሁን አትመልሱ። 21የማይጠቅሙ ናቸውና ሊረዷችሁ ወይም ሊረቧችሁ የማይችሉትን ከንቱ ነገሮች አትከተሉ።22እግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ስለ ወደደ፥ ስለ ታላቅ ስሙ ሲል ሕዝቡን አይጥላቸውም። 23ስለ እናንተ መጸለይን በመተው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ማድረግ ከእኔ ይራቅ። ይልቁንም፥ መልካሙንና ትክክለኛውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።24ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩት፥ በሙሉ ልባችሁም በእውነት አገልግሉት። ያደረገላችሁን ታላላቅ ነገሮች አስቡ። 25ክፉ በማድረግ ብትጸኑ ግን እናንተና ንጉሣችሁ ትጠፋላችሁ”።
1ሳኦል መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት በነገሠ ጊዜ፥ 2ከእስራኤል ሦስት ሺህ ሰዎች መረጠ። አንዱ ሺህ ከዮናታን ጋር በብንያም ጊብዓ ሲሆኑ ሁለቱ ሺህ በኮረብታማው አገር በቤቴልና በማክማስ ከእርሱ ጋር ነበሩ። የቀሩትን ወታደሮች ወደየቤታቸው፥ እያንዳንዱንም ወደ ድንኳኑ አሰናበታቸው።3ዮናታን በጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ድል አደረገ፥ ፍልስጥኤማውያንም ይህንን ሰሙ። ከዚያም ሳኦል፥ “ዕብራውያን ይስሙ” በማለት በምድሪቱ ሁሉ ላይ መለከት አስነፋ። 4ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር እንዳሸነፈ፥ ደግሞም እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን እንደ ግም መቆጠራቸውን እስራኤላውያን በሙሉ ሰሙ። ከዚያም ወታደሮቹ በጌልገላ ሳኦልን ለመከተል በአንድ ላይ ተሰበሰቡ።5ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፤ ሦስት ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ሠረገላ ነጂዎችና የሠራዊቱም ቁጥር በባህር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ነበሩ። እነርሱም መጥተው ከቤትአዌን በስተምሥራቅ ማክማስ ላይ ሰፈሩ።6የእስራኤል ሰዎች ችግር ውስጥ መግባታቸውንና ሕዝቡም መጨነቁን ባዩ ጊዜ፥ ሕዝቡ በዋሻዎች፥ በየቁጥቋጦ ሥር፥ በዐለቶች፥ በገደሎችና በጉድጓዶች ውስጥ ተደበቁ። 7አንዳንድ ዕብራውያንም የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ጋድና ገለዓድ ምድር ሄዱ። ሳኦል ግን ገና በጌልገላ ነበር፥ የተከተለው ሕዝብ በሙሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጥ ነበር።8እርሱም ሳሙኤል በሰጠው ቀጠሮ መሠረት ሰባት ቀን ቆየ። ነገር ግን ሳሙኤል ወደ ጌልገላ አልመጣም ነበር፥ ሕዝቡም ከሳኦል ተለይቶ መበታተን ጀምሮ ነበር። 9ሳኦልም፥ "የሚቃጠለውን መባና የሰላሙን መባዎች አምጡልኝ" አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መባ አቀረበ። 10የሚቃጠለውን መባ ማቅረቡን እንደ ጨረሰ ሳሙኤል ወደዚያ ደረሰ። ሳኦልም ሊገናኘውና ሰላምታ ሊሰጠው ሄደ።11ከዚያም ሳሙኤል፥ "ያደረግከው ምንድነው?" አለው። ሳኦልም፥ "ሕዝቡ ትተውኝ እየሄዱ እንዳሉ፥ አንተም በቀጠሮው ሰዓት አለመምጣትህን፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን ባየሁ ጊዜ፥ 12'አሁን ፍልስጥኤማውያን ወደ ጌልገላ በእኔ ላይ ሊወርዱብኝ ነው፥ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንኩም' ብዬ አሰብኩኝ። ስለዚህ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ ግድ ሆነብኝ“ ብሎ መለሰለት።13ሳሙኤልም ሳኦልን፥”ያደረግከው ስንፍና ነው። አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትዕዛዝ አልጠበቅክም። በዚህ ቀን እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ሊያጸናልህ ነበር። 14አሁን ግን አገዛዝህ አይቀጥልም። እግዚአብሔር ያዘዘህን አልታዘዝክምና እርሱ እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው ፈልጓል፥ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ መስፍን እንዲሆን መርጦታል" አለው።15ከዚያም ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ ወደ ብንያም ጊብዓ ወጣ። ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ቆጠራቸው፥ ስድስት መቶ የሚያክሉ ነበሩ። 16ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ከእነርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በብንያም ጊብዓ ቆዩ። ፍልስጥኤማውያን ግን በማክማስ ሰፍረው ነበር።17ከፍልስጥኤም ጦር ሰፈር ወራሪዎች በሦስት ቡድን ተከፍለው መጡ። አንደኛው ቡድን ወደ ሦጋል ምድር ወደ ዖፍራ ታጠፈ። 18ሌላኛው ቡድን በቤትሖሮን አቅጣጫ ታጠፈ፥ ሌላኛውም ቡድን በምድረ በዳው አቅጣጫ ወደ ስቦይም ሸለቆ ቁልቁል ወደሚያሳየው ወሰን ዞረ።19ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ለራሳቸው ሰይፍ ወይም ጦር እንዳይሠሩ" ብለው ስለነበረ፥ በመላው እስራኤል ብረት ሠሪ አልተገኘም። 20ነገር ግን የእስራኤል ወንዶች ሁሉ፥ እያንዳንዱ የማረሻውን ጫፍ፥ ዶማውን፥ ጠገራውንና ማጭዱን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርድ ነበር። 21የክፍያው ዋጋ ለማረሻው ጫፍና ለዶማው የሰቅል ሁለት ሦስተኛ፥ ጠገራ ለማሳልና መውጊያውን ለማቃናት የሰቅል አንድ ሦስተኛ ነበር።22ስለዚህ በጦርነቱ ቀን ሰይፍና ጦር በሳኦልና በዮናታን እጅ ብቻ እንጂ ከእነርሱ ጋር ከነበሩት ወታደሮች በአንዱም እጅ ሰይፍ ወይም ጦር አልነበረም። 23የፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጣ።
1አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣቱን ጋሻ ጃግሬውን፥”ና፥ በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ላይ በሌላ አቅጣጫ እንሂድባቸው“ አለው። ለአባቱ ግን አልነገረውም።2ሳኦል መጌዶን በሚባል በጊብዓ ዳርቻ በሮማኑ ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር። 3እርሱም በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ የሆነው፥ ኤፉድ ይለብስ የነበረውን አኪያን ጨምሮ ስድስት መቶ ያህል ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ። ዮናታን መሄዱን ሕዝቡ አላወቀም ነበር።4ዮናታን ወደ ፍልስጥኤማውያኑ ጦር ሰፈር አቋርጦ ለመሄድ ባሰበባቸው በመተላለፊያዎቹ መካከል በግራና በቀኙ በኩል ሾጣጣ ድንጋዮች ነበሩ። የአንደኛው ሾጣጣ ድንጋይ ስም ቦጼጽ ሲሆን የሁለተኛው ስም ሴኔ ነበር። 5አንደኛው ቀጥ ያለው ድንጋይ የቆመው በስተሰሜን በሚክማስ ፊት ለፊት ሲሆን ሌላኛው በጊብዓ ፊት ለፊት በስተደቡብ ነበር።6ዮናታንም ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ "ና፥ ወደእነዚህ ወዳልተገረዙት ጦር ሰፈር እንሻገር። እግዚአብሔር በብዙ ወይም በጥቂት ሰዎች ከማዳን ሊከለክለው የሚችል ነገር የለምና፥ ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል" አለው። 7ጋሻ ጃግሬውም፥ "በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ። ወደፊት ቀጥል፥ ተመልከት፥ የምታዝዘኝን ሁሉ ለመፈጸም ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ መለሰለት።8ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው፥ "ወደ እነርሱ ተሻግረን እንታያቸዋለን። 9እነርሱም፥ 'ወደ እናንተ እስክንመጣ እዚያው ቆዩ' ካሉን በስፍራችን እንቆያለን፥ ወደ እነርሱም አንሻገርም። 10ነገር ግን፥ 'ወደ እኛ ውጡ' ብለው ቢመልሱልን እግዚአብሔር በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናልና ወደ እነርሱ እንሻገራለን።”11ስለዚህ ሁለቱም ራሳቸውን ለፍልስጥኤማውያን ጦር ገለጡ። ፍልስጥኤማውያኑም፥ “ተመልከቱ፥ ዕብራውያኑ ከተደበቁባቸው ጉድጓዶች ወጥተው እየመጡ ነው" ተባባሉ። 12ከዚያም የጦር ሰፈሩ ሰዎች ወደ ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በመጣራት፥”ወደ እኛ ውጡ፥ አንድ ነገርም እናሳያችኋለን" አሏቸው። ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “እግዚአብሔር በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና ተከተለኝ" አለው።13ዮናታን በእጁና በእግሩ ተንጠላጥሎ ወጣ፥ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው ተከተለው። ፍልስጥኤማውያኑ በዮናታን ተገደሉ፥ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው ተከትሎ ጥቂቶቹን ገደለ። 14ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በፈጸሙት በዚያ የመጀመሪያ ጥቃት አንድ ጥማድ በሬ ሊያርሰው በሚችለው የመሬት ስፋት ላይ ሃያ ያህል ሰዎችን ገደሉ።15በጦር ሰፈሩ፥ በእርሻውና በሕዝቡ መካከል ሽብር ሆነ። የጦር ሰፈሩና ወራሪዎቹም እንኳን ተሸበሩ። ምድሪቱ ተንቀጠቀጠች፥ ታላቅ ሽብርም ሆነ።16በብንያም ጊብዓ የነበሩ የሳኦል ጠባቂዎች፥ የፍልስጥኤም ወታደሮች ሲበተኑና ወዲያና ወዲህ ሲራወጡ ተመለከቱ። 17ከዚያም ሳኦል ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሰዎች፥”ቁጠሩና ከእኛ የጎደለ ማን እንደሆነ ዕወቁ“ አላቸው። በቆጠሩ ጊዜም ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው ታጡ።18ሳኦልም አኪያን፥ "የእግዚአብሔርን ኤፉድ ወደዚህ አምጣው" አለው። በዚያ ቀን አኪያ ኤፉድ ለብሶ ከእስራኤል ወታደሮች ጋር ነበር። 19ሳኦል ከካህኑ ጋር በመነጋገር ላይ እያለ በፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር የነበረው ሁከት መጨመሩን ቀጠለ። ሳኦልም ካህኑን፥ "እጅህን መልስ" አለው።20ሳኦልና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በሩጫ ወደ ጦርነቱ ሄዱ። የእያንዳንዱ ፍልስጥኤማዊ ሰይፍ በራሱ ዜጋ ላይ ነበር፥ ታላቅ ግራ መጋባት ውስጥ ነበሩ። 21ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበሩና አብረዋቸው ወደ ጦር ሰፈሩ የገቡት ዕብራውያን እነርሱም እንኳን አሁን ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ከነበሩት እስራኤላውያን ጋር ተባበሩ።22በኤፍሬም አቅራቢያ በኮረብታዎቹ ውስጥ የተደበቁ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን መሸሻቸውን በሰሙ ጊዜ እነርሱም እንኳን ለውጊያ በኋላቸው አሳደዷቸው። 23ስለዚህ እግዚአብሔር በዚያን ቀን እስራኤልን አዳነ፥ ውጊያውም ቤትአዌንን አልፎ ሄደ።24ሳኦል፥”ጠላቶቼን እስከምበቀልበት እስከ ምሽት ድረስ የትኛውንም ዓይነት መብል የሚበላ ቢኖር የተረገመ ይሁን“ ብሎ ሕዝቡን አምሎ ስለነበረ በዚያን ቀን የእስራኤል ሰዎች ተጨነቁ። ስለዚህ ከሠራዊቱ አንዱም ምግብ አልቀመሰም። 25ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጫካ ውስጥ ገባ፥ ማርም በምድሩ ላይ ነበር። 26ሕዝቡ ወደ ጫካ በገባ ጊዜ ማሩ ይፈስስ ነበር፥ ነገር ግን ሕዝቡ መሓላውን ስለፈራ በእጁ ጠቅሶ ወደ አፉ ያደረገ አንድም አልነበረም።27ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን በመሓላ ማሰሩን አልሰማም ነበር። በእጁ ላይ የነበረውን በትር ጫፉን በማሩ እንጀራ ውስጥ አጠቀሰው። እጁን አንሥቶ ወደ አፉ አደረገው፥ ዐይኖቹም በሩለት። 28ከዚያም ከሰዎቹ አንዱ፥”ሕዝቡ በረሃብ ቢደክምም እንኳን አባትህ፥ 'በዚህ ቀን ምግብ የሚበላ የተረገመ ይሁን' ብሎ ሕዝቡን ከመሓላ ጋር አጥብቆ አዝዞአል" ብሎ መለሰለት።29ከዚያም ዮናታን፥ "አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል። ከዚህ ማር ጥቂት በመቅመሴ ዐይኖቼ እንዴት እንደበሩ ተመልከቱ። 30ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው ከበዘበዙት ላይ ዛሬ በነጻነት በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ በተሻለ ነበር? ምክንያቱም አሁን በፍልስጥኤማውያን መካከል የተገደሉት ያን ያህል ብዙ አይደሉም“ አለ።31እነርሱም በዚያን ቀን ፍልስጥኤማውያንን ከሚክማስ ጀምሮ እስከ ኤሎን ድረስ መቱአቸው። ሕዝቡም እጅግ ደከሙ። 32ሕዝቡም ተስገብግበው ወደ ብዝበዛው ተጣደፉ፥ በጎችን፥ በሬዎችንና ጥጆችንም በመሬት ላይ አረዱ። ሕዝቡም ከነደሙ በሉ።33ከዚያም ለሳኦል፥ "ተመልከት፥ ሕዝቡ ከነደሙ በመብላታቸው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት በመሥራት ላይ ናቸው" አሉት። ሳኦልም፥ "ተላልፋችኋል፥ አሁንም ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አምጡልኝ“ አለ። 34በመቀጠልም፥ "ወደ ሕዝቡ ሂዱና፥ 'እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን እዚህ አምጥቶ በማረድ ይብላ። ከነደሙ በመብላት በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን አታድርጉ' ብላችሁ ንገሯቸው" አለ። ስለዚህ በዚያ ምሽት እያንዳንዱ በሬውን እያመጣ በዚያ ዐረደው።35ሳኦል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ ይኸውም ለእግዚአብሔር የሠራው የመጀመሪያው መሠዊያ ነበር።36ከዚያም ሳኦል፥ "ሌሊቱን ፍልስጥኤማውያንን እናሳድ፥ እስኪነጋም ድረስ ሀብታቸውን እንበዝብዝ፤ ከእነርሱም አንድ በሕይወት አናስቀር“ አለ። እነርሱም፥”መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ“ ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፥”እዚሁ እግዚአብሔርን እንጠይቅ“ አለ። 37ሳኦልም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀ፥”ፍልስጥኤማውያንን ላሳድዳቸው? በእስራኤል እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ? “። ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር አልመለሰለትም።38ከዚያም ሳኦል፥”የሕዝቡ አለቆች የሆናችሁ ሁሉ ወደዚህ ቅረቡ፤ ዛሬ ይህ ኃጢአት እንዴት እንደመጣብን መርምሩና ዕወቁ። 39እስራኤልን ያዳነ ሕያው እግዚአብሔርን! ልጄ ዮናታን ቢሆን እንኳን በእርግጥ እርሱ ይሞታል" አለ። ነገር ግን ከሕዝቡ ሁሉ አንዱም እንኳን አልመለሰለትም።40እርሱም እስራኤልን በሙሉ፥ “እናንተ በአንድ በኩል ቁሙ፥ እኔና ልጄ ዮናታን በሌላው በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት። 41ስለዚህ ሳኦል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን፥ “በቱሚም አሳየኝ” አለው። ዮናታንና ሳኦል በዕጣ ተያዙ፥ ሕዝቡ ግን የተመረጠ ሆነና አመለጠ። 42ከዚያም ሳኦል፥ “በእኔና በልጄ በዮናታን መክከል ዕጣ ጣሉ” አለ። ዮናታንም በዕጣ ተያዘ።43ሳኦልም ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በእጄ በነበረው በትር ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ። ይኸው ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለ። 44ሳኦልም፥ “ዮናታን ሆይ፥ ባትሞት እግዚአብሔር በእኔ ላይ እንዲሁ ያድርግ፥ ይጨምርም” አለ።45ሕዝቡም ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህንን ታላቅ ድል ያመጣ ዮናታን መሞት ይገባዋል? ይህ ከእርሱ ይራቅ! እርሱ ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር ሠርቷልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራስ ጸጉሩ አንድ በምድር ላይ አይወድቅም" አሉት። ስለዚህ ሕዝቡ ዮናታንን ከመሞት አዳነው። 46ከዚያም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ማሳደዱን አቆመ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ስፍራቸው ሄዱ።47ሳኦል እስራኤልን መግዛት በጀመረ ጊዜ፥ በየአቅጣጫው ከነበሩ ጠላቶቹ ሁሉ ጋር ተዋጋ። እርሱም ከሞዓብ፥ ከአሞን ሰዎች፥ ከኤዶም፥ ከሱባ ነገሥታትና ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ። በደረሰበት ሁሉ በቅጣት ያሰቃያቸው ነበር። 48ከአማሌቃውያን ጋር በጀግንነት ተዋግቶ ድል አደረጋቸው። እስራኤላውያንንም ከዘራፊዎቻቸው እጅ አዳናቸው።49የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ የሱዊና ሜልኪሳ ነበሩ። የሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ስም፥ የመጀመሪያ ልጁ ሜሮብና ታናሿ ሜልኮል ይባሉ ነበሩ። 50የሳኦል ሚስት ስም አኪናሆም ነበር፥ እርሷም የአኪማአስ ልጅ ነበረች። የሠራዊቱ አዛዥ ስም፥ የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አበኔር ነበር። 51ቂስ የሳኦል አባት ነበር፤ የአበኔር አባት ኔርም የአቢኤል ልጅ ነበር።52በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ከባድ ጦርነት ይካሄድ ነበር። ሳኦል ኃያል ወይም ብርቱ የሆነ ሰው ባየ ጊዜ ሁሉ ያንን ወደ ራሱ ይሰበስብ ነበር።
1ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፥”እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ እንድቀባህ ላከኝ። አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። 2የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው፥ 'እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ አማሌቅ እየተቃወመ በመንገዱ ላይ ያደረገበትን አስታውሻለሁ። 3አሁንም ሂድና አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውን ሁሉ ፈጽመህ ደምስስ። አትራራላቸው፥ ወንድና ሴቱን፥ ልጅና ሕፃኑን፥ በሬና በጉን፥ ግመልና አህያውን ግደል።"4ሳኦል ሕዝቡን በጥላኢም ከተማ ሰብስቦ ቆጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺህ እግረኞችና ዐሥር ሺህ የይሁዳ ሰዎች ነበሩ። 5ከዚያም ሳኦል ወደ አማሌቅ ከተማ መጥቶ በሸለቆው ውስጥ አደፈጠ።6ከዚያም ሳኦል ቄናውያንን፥ "ከግብፅ በመጡ ጊዜ ለእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ደግነትን አሳይታችኋልና ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ፥ ከአማሌቃውያን መካከል ተለይታችሁ ውጡና ሂዱ" አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ። 7ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ ከግብፅ በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው።8የአማሌቃውያኑን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ያዘው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። 9ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ አጋግን፥ እንዲሁም ምርጥ የሆኑትን በጎች፥ በሬዎች፥ የሰቡትን ጥጆችና የበግ ጠቦቶች በሕይወት ተዉአቸው። መልካም የሆነውን ሁሉ አላጠፉም። የተናቀውንና ዋጋ ቢስ የሆነውን ነገር ሁሉ ግን ፈጽመው ደመሰሱ።10ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሳሙኤል መጣ፥ 11"እኔን ከመከተል ስለተመለሰና ያዘዝኩትንም ስላልፈጸመ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ"። ሳሙኤልም ተቆጣ፤ ሌሊቱን በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጮህ አደረ።12ሳሙኤልም ሳኦልን በጠዋት ለመገናኘት ማልዶ ተነሣ። ለሳሙኤልም፥ "ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ መጥቶ ለራሱ ሐውልት አቆመ፥ ከዚያም ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወረደ" ብለው ነገሩት። 13ከዚያም ሳሙኤል ወደ ሳኦል መጣ፥ ሳኦልም፥ "አንተ በእግዚአብሔር የተባረክህ ነህ! የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ፈጽሜአለሁ" አለው።14ሳሙኤልም፥ "ታዲያ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ድምፅና የበሬዎች ግሣት ምንድነው?" አለው። 15ሳኦልም፥ "ከአማሌቃውያኑ ያመጧቸው ናቸው። ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ምርጥ የሆኑትን በጎችና በሬዎች በሕይወት አስቀሯቸው። የቀሩትን ፈጽመን አጥፍተናል" ብሎ መለሰለት። 16ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልን፥ "አድምጠኝ፥ በዛሬው ሌሊት እግዚአብሔር የነገረኝን እነግርሃለሁ" አለው። ሳኦልም፥ "ተናገር!" አለው።17ሳሙኤልም እንዲህ አለው፥ "በራስህ ግምት ታናሽ ብትሆንም በእስራኤል ነገዶች ላይ አለቃ ተደረግህ። እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ ቀባህ፤ 18እግዚአብሔርም፥ 'ሂድና ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ተዋጋቸው' ብሎ በመንገድህ ልኮህ ነበር። 19ታዲያ የእግዚአብሔርን ድምፅ ያልታዘዝከው ለምንድነው? ከዚያ ይልቅ ግን ከምርኮው በመውሰድ በእግዚአብሔር ፊት ክፋትን አደረግህ።"20ሳኦልም ሳሙኤልን፥ "የእግዚአብሔርን ድምፅ በትክክል ታዝዣለሁ፥ እግዚአብሔር በላከኝም መንገድ ሄጃለሁ። የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን ማርኬዋለሁ፥ አማሌቃውያንንም በሙሉ ፈጽሜ ደምስሻለሁ። 21ሕዝቡ ግን ከምርኮው ላይ ጥቂት በጎችንና በሬዎችን፥ ሊጠፉም የነበሩ ምርጥ ነገሮችን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ሊሠዉአቸው ወሰዱ" አለው።22ሳሙኤልም፥ "የእግዚአብሔርን ድምፅ ከመታዘዝ የበለጠ በሚቃጠል መባና መሥዋዕት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛል? ከመሥዋዕት መታዘዝ ይሻላል፥ ከአውራ በግ ስብም መስማት ይሻላል። 23እምቢተኝነት እንደ ምዋርተኝነት ኃጢአት ነው፥ እልኸኝነትም እንደ አመጸኝነትና እንደ ክፋት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እርሱም ደግሞ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል“ አለው።24ከዚያም ሳኦል ሳሙኤልን፥”ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ ሕዝቡን ስለፈራሁና ቃላቸውን ስለታዘዝኩ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝና የአንተን ቃል ተላልፌአለሁ። 25አሁንም እባክህን ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፥ ለእግዚአብሔር እንድሰግድም ከእኔ ጋር ተመለስ“ አለው።26ሳሙኤልም ሳኦልን፥”ከአንተ ጋር አልመለስም፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና አንተም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን እግዚአብሔር ንቆሃል" አለው። 27ሳሙኤል ለመሄድ ዘወር ባለ ጊዜ፥ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፥ እርሱም ተቀደደ።28ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ዛሬ የእስራኤልን መንግሥት ከአንተ ቀደደው፥ ከአንተ ለሚሻለው ለጎረቤትህም አሳልፎ ሰጠው። 29ደግሞም የእስራኤል ኃይል አይዋሽም፥ አሳቡንም አይለውጥም፥ እርሱ አሳቡን መለወጥ ይችል ዘንድ ሰው አይደለምና“ አለው።30ከዚያም ሳኦል፥”ኃጢአትን አድርጌአለሁ። አሁን ግን እባክህ በሕዝቤ ሽማግሌዎችና በእስራኤል ፊት አክብረኝ። ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንድሰግድ ከእኔ ጋር ተመለስ“ አለው። 31ስለዚህ ሳሙኤል ከሳኦል ኋላ ተመለሰ፥ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ።32ከዚያም ሳሙኤል፥”የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ“ አለ። አጋግ በሠንሠለት አንደታሠረ ወደ እርሱ መጣና፥”ለካስ ሞት እንዲህ መራራ ነው“ አለ። 33ሳሙኤልም፥”ሰይፍህ እናቶችን ልጅ ዐልባ እንዳደረጋቸው አሁን እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ ዐልባ ትሆናለች“ ብሎ መለሰለት። ከዚያም ሳሙኤል አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቆራረጠው።34ሳሙኤል ወደ ራማ ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ሳኦል ጊብዓ ሄደ። 35ሳሙኤል እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ሳኦልን አላየውም፥ ለሳኦልም አለቀሰለት። እግዚአብሔርም ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ አዘነ።
1እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ንጉሥ እንዳይሆን ለናቅኩት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? በወንዶች ልጆቹ መካከል ለራሴ ንጉሥ የሚሆነውን መርጫለሁና ወደ ቤተ ልሔማዊው ወደ እሴይ እልክሃለሁ። የዘይት መያዣ ቀንድህን በዘይት ሞልተህ ሂድ” አለው።2ሳሙኤልም፥ “እንዴት መሄድ እችላለሁ? ሳኦል ከሰማ ይገድለኛል” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፥ 'ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ' በል። 3እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ ጥራው፥ እኔም የምታደርገውን አሳይሃለሁ። የምነግርህንም እርሱን ትቀባልኛለህ” አለው።4ሳሙኤልም እግዚአብሔር እንደተናገረው አደረገ፥ ወደ ቤተ ልሔምም ሄደ። የከተማይቱም ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡና፥ “በሰላም ነው የመጣኸው?” አሉት። 5እርሱም፥ “በሰላም ነው። ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ። ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱና ከእኔ ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ”አላቸው። እሴይንና ወንዶች ልጆቹንም ቀደሳቸው፥ ወደ መሥዋዕቱም ጠራቸው።6እነርሱ በመጡ ጊዜም፥ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ እግዚአብሔር የሚቀባው በእርግጥ በፊቱ ቆሟል ብሎ በልቡ አሰበ። 7ነገር ግን እግዚአብሔር ሳሙኤልን፥ "እኔ ንቄዋለሁና ውጫዊ ገጽታውን ወይም የቁመቱን ዘለግታ አትመልከት። እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ አያይምና፤ ሰው ውጫዊ ገጽታን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል" አለው።8ከዚያም እሴይ አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገው። ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ይኸኛውንም አልመረጠውም“ አለ። 9ከዚያም እሴይ ሳማን አሳለፈው። ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ይኸኛውንም አልመረጠውም“ አለ። 10እሴይ ሰባቱን ወንዶች ልጆቹን በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረጋቸው። ሳሙኤልም እሴይን፥”እግዚአብሔር ከእነዚህ አንዳቸውንም አልመረጠም“ አለው።11ሳሙኤልም እሴይን፥”ወንዶቹ ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸው? “ አለው። እርሱም፥”የሁሉ ታናሽ የሆነው ገና ቀርቷል፥ እርሱ ግን በጎች እየጠበቀ ነው" ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም እሴይን፥ "ልከህ አስመጣው፤ እርሱ እዚህ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥምና" አለው። 12እሴይም ልኮ አስመጣው። በመጣ ጊዜም ልጁ ቀይ፥ ዐይኖቹ የተዋቡና መልከ መልካም ገጽታ ነበረው። እግዚአብሔርም፥ "ያ ሰው እርሱ ነውና ተነሣ፤ ቀባውም" አለው።13ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ አንሥቶ በወንድሞቹ መካከል እርሱን ቀባው። ከዚያን ቀን ጀምሮ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል መጣበት። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።14የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ተለየ፥ በምትኩም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ክፉ መንፈስ አሠቃየው። 15የሳኦል አገልጋዮችም፥ "ተመልከት፥ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ እያሠቃየህ ነው። 16ደህና አድርጎ በገና መደርደር የሚችል ሰው እንዲፈልጉ ጌታችን በፊቱ ያሉትን አገልጋዮቹን ይዘዝ። ከዚያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሆነብህ ጊዜ እርሱ ይጫወትልሃል፥ አንተም ደኅና ትሆናለህ" አሉት።17ሳኦልም አገልጋዮቹን፥ "በገና በደንብ መደርደር የሚችል ሰው ፈልጋችሁ አምጡልኝ" አላቸው። 18ከዚያም ከወጣቶቹ አንዱ እንዲህ ሲል መለሰ፥ "ደኅና አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን፥ ጽኑ፥ ኃያል፥ ተዋጊ፥ በንግግሩ ጠንቃቃና መልከ መልካም የሆነውን የቤተ ልሔማዊውን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው።" 19ስለዚህ ሳኦል መልዕክተኞችን ወደ እሴይ ልኮ፥ "ከበጎች ጋር ያለውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ" አለው።20እሴይም እንጀራና ወይን ጠጅ የተሞላ አቁማዳ የተጫነበትን አህያ፥ ከፍየል ጠቦት ጋር አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው። 21ከዚያም ዳዊት ወደ ሳኦል መጣና አገልግሎቱን መስጠት ጀመረ። ሳኦል እጅግ ወደደው፥ ዳዊትም ጋሻ ጃግሬው ሆነ።22ሳኦልም፥ "በዐይኔ ፊት ሞገስን አግኝቷልና ዳዊት በፊቴ እንዲቆም ፈቃድህ ይሁን“ ብሎ ወደ እሴይ ላከ። 23በሳኦል ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ዳዊት በገና አንሥቶ ይደረድርለት ነበር። ስለዚህ ሳኦል ይታደስና ደኅና ይሆን ነበር፥ ክፉውም መንፈስ ከእርሱ ይርቅ ነበር።
1ፍልስጥኤማውያን ሠራዊታቸውን ለውጊያ አዘጋጁ። እነርሱም የይሁዳ በሆነችው በሰኮት ተሰበሰቡ። በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በምትገኘው በኤፌስደሚምም ሰፈሩ።2ሳኦልና የእስራኤል ሰዎችም ተሰብስበው በኤላ ሸለቆ ሰፈሩ፥ ፍልስጥኤማውያንን ለመግጠምም ስፍራቸውን ያዙ። 3ፍልስጥኤማውያን በአንደኛው ወገን ተራራ ላይ ቆሙ፥ በዚህኛው ወገን ባለው ተራራ ላይ እስራኤላውያኑ ቆሙ፥ በመካከላቸውም ሸለቆ ነበር።4የጌት ሰው ጎልያድ የሚባል አንድ ጀግና ከፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር ወጣ፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር ነበር። 5በራሱ ላይ ከነሐስ የተሠራ የራስ ቁር ደፍቶ፥ ጥሩርም ለብሶ ነበር። ጥሩሩም አምስት ሺህ የነሐስ ሰቅል ይመዝን ነበር።6በእግሮቹ ላይ የነሐስ ገምባሌዎች አድርጎ ነበር፥ በትከሻዎቹም መሓል ቀለል ያለ የነሐስ ጦር ነበር። 7የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ወፍራም ነበር። የጦሩ ጫፍ ስድስት መቶ የብረት ሰቅል ይመዝን ነበር። ጋሻ ጃግሬው በፊቱ ሄደ።8እርሱም ተነሥቶ በእስራኤል ሠልፈኞች ላይ እንዲህ በማለት ጮኸ፥ “ለውጊያ የተሰለፋችሁት ለምንድነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ፥ እናንተ የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁም? ለራሳችሁ አንድ ሰው ምረጡና ወደ እኔ ይውረድ። 9እርሱ ሊዋጋኝ ቢችልና ቢገድለኝ እኛ አገልጋዮቻችሁ እንሆናለን። ነገር ግን ባሸንፈውና ብገድለው እናንተ አገልጋዮቻችን በመሆን ታገለግሉናላችሁ።”10ፍልስጥኤማዊው ደገመና፥ “ዛሬ የእስራኤልን ሰልፈኞች እገዳደራቸዋለሁ። እንድንዋጋ አንድ ሰው ስጡኝ" አለ። 11ፍልስጥኤማዊው የተናገረውን ሳኦልና እስራኤላውያን ሁሉ በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፥ ተስፋም ቆረጡ።12ዳዊት በይሁዳ የሚኖረው የቤተ ልሔም ኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር። እሴይ ስምንት ወንዶች ልጆች ነበሩት። በሳኦል ዘመን እሴይ በዕድሜው ያረጀና ከወንዶቹ ሁሉ በዕድሜ የገፋ ሰው ነበር። 13የእሴይ ሦስቱ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነቱ ሄደው ነበር። ወደ ጦርነት የሄዱት የሦስቱ ወንዶች ልጆች ስም፥ የመጀመሪያው ልጅ ኤልያብ፥ ተከታዩ አሚናዳብና ሦስተኛው ሣማ ይባሉ ነበር።14ዳዊት የሁሉም ታናሽ ነበር። ትልልቆቹ ሦስቱ ሳኦልን ተከተሉት። 15ዳዊት በሳኦል ሠራዊትና በቤተ ልሔም የሚገኙትን የአባቱን በጎች በመጠበቅ ተግባር ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ናበር። 16ፍልስጥኤማዊው ኃያል ሰው ለአርባ ቀናት በየጠዋቱና በየምሽቱ ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን ለማሳየት ይቀርብ ነበር።17ከዚያም እሴይ ልጁን ዳዊትን እንዲህ አለው፥”ከዚህ ከተጠበሰው እሸት ዐሥር ኪሎና እነዚህን ዐሥር ዳቦዎች በጦር ሰፈሩ ውስጥ ላሉት ወንድሞችህ ፈጥነህ ውሰድላቸው። 18በተጨማሪም እነዚህን ዐሥር የአይብ ጥፍጥፎች ለሻለቃቸው ስጠው። ወንድሞችህ ያሉበትን ሁኔታ ተመልከትና ደኅና ስለመሆናቸው ማረጋገጫ አምጣልኝ።19ወንድሞችህ ከሳኦልና ከእስራኤል ሰዎች ሁሉ ጋር ፍልስጥኤማውያንን እየተዋጉ በኤላ ሸለቆ ናቸው።“ 20ዳዊት ማልዶ ተነሣና በጎቹን ለእረኛ ዐደራ ሰጠ። እርሱም እሴይ እንዳዘዘው የወንድሞቹን ስንቅ ይዞ ሄደ። ሠራዊቱ ወደ ውጊያው ግምባር እየፎከረ በመውጣት ላይ እያለ ዳዊት ወደ ጦር ሰፈሩ ደረሰ። 21እስራኤላውያንና ፍልስጥኤማውያን፥ ሠራዊት በሠራዊት ላይ ለውጊያ ተሰለፉ።22ዳዊት የያዘውን ዕቃ ለስንቅ ጠባቂው ዐደራ ሰጥቶ ወደ ሠራዊቱ በመሮጥ ለወንድሞቹ ሰላምታ አቀረበ። 23ከእነርሱ ጋር እየተነጋገረ እያለ ጎልያድ ተብሎ የሚጠራው፥ ከጌት የመጣው ፍልስጥኤማዊ ከሰልፈኞች መካከል ወጥቶ የቀድሞውን የሚመስል ቃል ተናገረ። ዳዊትም ሰማቸው። 24የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ሰውዬውን ባዩት ጊዜ፥ ከእርሱ ሸሹ፥ እጅግም ፈርተውት ነበር።25የእስራኤልም ሰዎች፥ "ይህን የሚወጣውን ሰው አያችሁት? እስራኤልን ለመገዳደር ነው የመጣው። እርሱን የሚገድለውን ሰው ንጉሡ እጅግ ያበለጽገዋል፥ ልጁን ይድርለታል፥ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ውስጥ ከግብር ነጻ ያደርጋቸዋል" ይባባሉ ነበር።26ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ "ይህንን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድልና ከእስራኤል ኀፍረትን ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ሊንቅ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ሆነና ነው?" አላቸው። 27ከዚያም ሰዎቹ ቀደም ሲል የተናገሩትን ደግመው፥ "ስለዚህ እርሱን ለሚገድለው የሚደረግለት ይህ ነው" አሉት።28ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር የሁሉ ታላቅ የሆነው ወንድምየው ኤልያብ ሰማው። ኤልያብም በዳዊት ላይ ቁጣው ነድዶ፥ "ወደዚህ የወረድከው ለምንድነው? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ውስጥ ለማን ተውካቸው? እኔ ትዕቢትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁ፤ ወደዚህ የወረድከው ውጊያውን ለማየት ነውና" አለው። 29ዳዊትም፥ "አሁን እኔ ምን አደረኩ? እንዲያው መጠየቄ ብቻ አልነበረም?" አለው። 30ከእርሱ ወደ ሌላው ዞር ብሎ በተመሳሳይ መንገድ ተናገረ። ሰዎቹም የቀድሞውን የሚመስል መልስ ሰጡት።31ዳዊት የተናገረው ቃል በተሰማ ጊዜ፥ ወታደሮች ቃሉን ለሳኦል ነገሩት፥ እርሱም ዳዊትን አስጠራው። 32ከዚያም ዳዊት ሳኦልን፥ "በዚያ ፍልስጥኤማዊ ምክንያት የማንም ልብ አይውደቅ፤ አገልጋይህ ሄዶ ከፍልስጥኤማዊው ጋር ይዋጋል" አለው። 33ሳኦልም ዳዊትን፥ "አንተ ከዚህ ፍልስጥኤማዊ ጋር ለመዋጋት መሄድ አትችልም፤ አንተ ገና ልጅ ነህ፥ እርሱ ደግሞ ከወጣትነቱ ጀምሮ ተዋጊ ነው" አለው።34ዳዊት ግን ሳኦልን፥ "አገልጋይህ የአባቴን በጎች እጠብቅ ነበር። አንበሳ ወይም ድብ መጥቶ ከመንጋው ጠቦት በሚወስድበት ጊዜ 35በኋላው ተከትዬ እመታውና ከአፉ አስጠለው ነበር። ሊያጠቃኝ በተነሣብኝ ጊዜም ጉሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር።36አገልጋይህ አንበሳና ድብ ገድያለሁ። የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ስለተገዳደረ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል" አለው።37ዳዊትም፥ "እግዚአብሔር ከአንበሳና ከድብ መዳፍ አድኖኛል። ከዚህም ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል" አለው። 38ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ "ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን" አለው። ሳኦል የራሱን የጦር መሣሪያ ለዳዊት አስታጠቀው። በራሱ ላይ የነሐስ ቁር ደፋለት፥ ጥሩርም አለበሰው።39ዳዊትም ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጠቀው። ነገር ግን አልተለማመደውምና ለመራመድ አቃተው። ከዚያም ዳዊት ሳኦልን፥ "አልተለማመድኳቸውምና በእነዚህ መዋጋት አልችልም" አለው። ስለዚህ ዳዊት ከላዩ ላይ አወለቃቸው። 40በትሩን በእጁ ያዘ፥ ከጅረቱም አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች መርጦ በእረኛ ኮሮጆው ውስጥ ጨመራቸው። ፍልስጥኤማዊውን በሚቀርብበት ጊዜ ወንጭፉን ይዞ ነበር።41ፍልስጥኤማዊውም በፊት ለፊቱ ከሚሄደው ጋሻ ጃግሬው ጋር መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ። 42ፍልስጥኤማዊው ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊትን ባየው ጊዜ ቀይ፥ መልከ መልካም ገጽታ ያለው ትንሽ ልጅ ብቻ ስለነበረ ናቀው። 43ፍልስጥኤማዊው ዳዊትን፥ "በትር ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝ?" አለው። ፍልስጥኤማዊውም በአማልክቶቹ ስም ዳዊትን ረገመው።44ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፥ "ወደ እኔ ና፥ እኔም ሥጋህን ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ" አለው። 45ዳዊትም ለፍልስጥኤማዊው እንዲህ ሲል መለሰለት፥ "አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ። እኔ ግን አንተ ባቃለልከው፥ የእስራኤል ሠራዊት አምላክ በሆነው፥ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።46ዛሬ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ድልን ይሰጠኛል፥ እገድልሃለሁ፥ ራስህንም ከሰውነትህ ላይ አነሣዋለሁ። ዛሬ የፍልስጥኤምን ሠራዊት ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፥ ይኸውም ምድር ሁሉ በእስራኤል አምላክ እንዳለ እንዲያውቅና 47በዚህ የተሰበሰበው ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍ ወይም በጦር ድልን እንደማይሰጥ እንዲያውቁ ነው። ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነውና እናንተንም በእጃችን ላይ አሳልፎ ይሰጣችኋል።"48ፍልስጥኤማዊው ተነሥቶ ዳዊትን በቀረበው ጊዜ ዳዊት ሊገናኘው ወደ ጠላት ጦር በፍጥነት ሮጠ። 49ዳዊት እጁን ወደ ኮሮጆው አስገብቶ አንድ ድንጋይ ከዚያ ወሰደ፥ ወነጨፈውና የፍልስጥኤማዊውን ግንባር መታው። ድንጋዩም በፍልስጥኤማዊው ግንባር ውስጥ ጠልቆ ገባ፥ እርሱም በግንባሩ በምድር ላይ ተደፋ።50ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው። ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። በዳዊት እጅ ሰይፍ አልነበረም። 51ከዚያም ዳዊት ሮጠና በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፥ ከእርሱም ሰይፉን ወሰደ፥ ከሰገባው አወጣና ገደለው፥ በእርሱም ራሱን ቆርጦ አነሣው። ፍልስጥኤማውያን ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ።52ከዚያም የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች እልል እያሉ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን እስከ ሸለቆውና እስከ ኤቅሮን መግቢያ ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያኑ ሬሳ ከሸዓራይም እስከ ጌትና ዔቅሮን ድረስ በየመንገዱ ወድቆ ነበር። 53የእስራኤል ሰዎች ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመለሱና የጦር ሰፈራቸውን በዘበዙ። 54ዳዊት የፍልስጥኤማዊውን ራስ ወስደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣው፥ የጦር መሣሪያውን ግን በድንኳኑ ውስጥ አኖረው።55ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመጋጠም ሲሄድ ሳኦል ባየው ጊዜ፥ የሰራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ "አንተ አበኔር፥ ይህ ወጣት የማን ልጅ ነው?" አለው። አበኔርም፥ "ንጉሥ ሆይ፥ በሕያውነትህ እምላለሁ፥ አላውቅም" አለው። 56ንጉሡም፥ "የማን ልጅ እንደሆነ ምናልባት ሊያውቁት የሚችሉትን ጠይቅ" አለው።57ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ አበኔር ወሰደው፥ የፍልስጥኤማዊውን ራስ በእጁ እንደያዘ ወደ ሳኦል አመጣው። 58ሳኦልም፥ "አንተ ወጣት፥ የማን ልጅ ነህ?" አለው። ዳዊትም፥ "እኔ የቤተ ልሔማዊው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ" ብሎ መለሰለት።
1ለሳኦል መናገሩን በጨረሰ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፥ ዮናታንም እንደ ራሱ ነፍስ አድርጎ ወደደው። 2በዚያ ቀን ሳኦል ዳዊትን ወደ ራሱ አገልግሎት ወሰደው፤ ወደ አባቱ ቤት እንዲመለስ አላሰናበተውም።3ዮናታን ዳዊትን እንደ ራሱ ነፍስ አድርጎ ስለወደደው በመካከላቸው የወዳጅነት ቃል ኪዳን አደረጉ። 4ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከጦር ልብሱ ጋር፥ እንዲሁም ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ለዳዊት ሰጠው።5ዳዊት ሳኦል ወደሚልከው ቦታ ሁሉ ይሄድ ነበር፥ ይከናወንለትም ነበር። ሳኦልም በተዋጊዎቹ ላይ ሾመው። ይህም በሕዝቡ ዓይን ሁሉ ደግሞም በሳኦል አገልጋዮች ፊት ደስ የሚያሰኝ ሆነ።6ፍልስጥኤማውያንን ድል አድርገው ወደ መኖሪያቸው በመመለስ ላይ እያሉ ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመገናኘት፥ ሴቶች በከበሮና በሙዚቃ መሳሪያዎች በደስታ እየዘመሩና እየጨፈሩ መጡ። 7ሴቶቹም ሲጫወቱ እየተቀባበሉ ይዘምሩ ነበር፤ እነርሱም፥ "ሳኦል ሺዎችን ገደል፥ ዳዊትም ዐሥር ሺዎችን ገደለ" እያሉ ዘመሩ።8ሳኦል እጅግ ተቆጣ፥ ይህም መዝሙር አስከፋው። እርሱም፥ "ለዳዊት ዐሥር ሺዎች አሉ፥ ለእኔ ግን ሺዎችን ብቻ። ታዲያ ከመንግሥት በቀር ምን ቀረው?" አለ። 9ሳኦል ከዚያን ቀን ጀምሮ ዳዊትን በጥርጣሬ ዐይን ተመለከተው።10በቀጣዩ ቀን በሳኦል ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ መጣበት። እርሱም በቤት ውስጥ እንደ ዕብድ ይለፈልፍ ነበር። ስለዚህ ዳዊት በየቀኑ ያደርግ እንደነበረው በገናውን ይደረድር ነበር። ሳኦልም በእጁ ጦር ይዞ ነበር። 11ሳኦል፥ "ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ" ብሎ በማሰብ ጦሩን ወረወረበት። ነገር ግን ዳዊት ከሳኦል ፊት ሁለት ጊዜ እንዲህ ባለ መንገድ አመለጠ። 12እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንጂ ከእርሱ ጋር ስላልነበረ ሳኦል ዳዊትን ፈራው።13ስለዚህ ሳኦል ከፊቱ አራቀው፥ ሻለቃም አድርጎ ሾመው። በዚህ ሁኔታ ዳዊት በሕዝቡ ፊት ይወጣና ይገባ ነበር። 14እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበረ ዳዊት የሚሠራው ሁሉ ይከናወንለት ነበር።15እንደ ተከናወነለት ሳኦል ባየ ጊዜ እጅግ ፈራው። 16ነገር ግን በፊታቸው ይወጣና ይገባ ስለነበረ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊትን ወደዱት።17ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ "ትልቋ ልጄ ሜሮብ ይቹት። እርሷን እድርልሃለሁ። ብቻ ጎብዝልኝ፥ የእግዚአብሔርን ጦርነቶችም ተዋጋ" አለው። ሳኦል፥ "እጄ በእርሱ ላይ አይሁን፥ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ይሁን" ብሎ አስቦአልና። 18ዳዊትም ሳኦልን፥ "የንጉሥ አማች ለመሆን እኔ ማነኝ? ሕይወቴ ወይም የአባቴ ቤተ ሰብ በእስራኤል ውስጥ ምንድነው?" አለው።19ነገር ግን የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለዳዊት የምትዳርበት ጊዜ ሲደርስ ለመሓላታዊው ለኤድሪኤል ተዳረች።20ነገር ግን የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደችው። ለሳኦል ነገሩት፥ ይህም እርሱን ደስ አሰኘው። 21ከዚያም ሳኦል፥ "ወጥመድ እንድትሆነውና የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ እንድትሆን እርሷን እድርለታለሁ" ብሎ አሰበ። ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን ለሁለተኛ ጊዜ፥ "አማቼ ትሆናለህ" አለው።22ሳኦል አገልጋዮቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፥ "ዳዊትን በምስጢር እንዲህ በሉት፥ 'አስተውል፥ ንጉሡ በአንተ ደስ ብሎታል፥ አገልጋዮቹም ሁሉ ይወዱሃል። እንግዲያው የንጉሡ አማች ሁን'"23ስለዚህ የሳኦል አገልጋዮች ይህንን ቃል ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ "እኔ ድሃና ብዙም የማልታወቅ ሰው ሆኜ እያለሁ የንጉሥ አማች እንድሆን ማሰባችሁ ጉዳዩ እንዴት ቀልሎ ታያችሁ?" አላቸው። 24የሳኦል አገልጋዮችም ዳዊት የተናገረውን ቃል ነገሩት።25ሳኦልም፥ "ለዳዊት እንዲህ ትሉታላችሁ፥ 'የንጉሡን ጠላቶች ለመበቀል ከአንድ መቶ የፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ብቻ በቀር ንጉሡ ምንም ጥሎሽ አይፈልግም"። ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲወድቅ ለማድረግ ሳኦል አሰበ። 26አገልጋዮቹ ይህንን ቃል ለዳዊት በነገሩት ጊዜ የንጉሡ አማች መሆን ዳዊትን ደስ አሰኘው።27እነዚያ ቀናት ከማብቃታቸው በፊት፥ ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሄዶ ሁለት መቶ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ። ዳዊት የንጉሡ አማች ይሆን ዘንድ ሸለፈቶቹን አመጣ፥ ለንጉሡም ሙሉውን ቁጥር አስረከቡ። ስለዚህ ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ዳረለት። 28እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደነበረ ሳኦል አየ፥ ዐወቀም። የሳኦል ልጅ ሜልኮልም ወደደችው። 29ሳኦልም ዳዊትን የበለጠ ፈራው። ሳኦል የዳዊት ጠላቱ እንደሆነ ቀጠለ።30ከዚያም የፍልስጥኤም ልዑላን ብዙ ጊዜ ያደርጉት እንደነበረው ለጦርነት መጡ፥ ዳዊት ከሳኦል አገልጋዮች ሁሉ በበለጠ ሁኔታ የተሳካለት ሆነ፥ በመሆኑም ስሙ እጅግ የተከበረ ሆነ።
1ሳኦል ልጁን ዮናታንን እና አገልጋዮቹን በሙሉ ዳዊትን እንዲገድሉት ነገራቸው። የሳኦል ልጅ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር። 2ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን፥ "አባቴ ሳኦል ሊገድልህ ይፈልጋል። በመሆኑም ለራስህ ጥንቃቄ አድርግ፥ በነገውም ቀን በምስጢራዊ ቦታ ተደበቅ። 3አንተ ባለህበት አካባቢ ሄጄ በአባቴ አጠገብ እቆማለሁ፥ ስለ አንተም አነጋግረዋለሁ። አንዳች ነገር ካገኘሁኝም እነግርሃለሁ“ አለው።4ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል ስለ ዳዊት መልካምን ነገር ተናገረ፥ እንዲህም አለው፥”ንጉሡ በአገልጋዩ በዳዊት ላይ ክፉ ነገር አያድርግ። እርሱ ክፉ አላደረገብህም፥ እርሱ የሠራው ሥራ ለአንተ መልካም ሆኖልሃልና። 5ነፍሱን በእጁ ላይ ጥሎ ፍልስጥኤማዊውን ገደለ። እግዚአብሔርም ለእስራኤል በሙሉ ታላቅ ድልን ሰጠ። አንተም አይተህ ደስ ብሎህ ነበር። ያለምንም ምክንያት ዳዊትን በመግደልህ በንጹህ ደም ላይ ለምን ኃጢአት ትሠራለህ?“6ሳኦልም ዮናታንን ሰማው። ሳኦልም፥”ሕያው እግዚአብሔርን! ዳዊት አይገደልም“ ብሎ ማለ። 7ከዚያም ዮናታን ዳዊትን ጠራው፥ ዮናታንም ይህንን ነገር ሁሉ ነገረው። ዮናታንም ዳዊትን ወደ ሳኦል አመጣው፥ እርሱም እንደቀድሞው በፊቱ ነበረ።8እንደገናም ጦርነት ሆነ። ዳዊት ወጥቶ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፥ በታላቅ አገዳደልም ድል አደረጋቸው። እነርሱም ከፊቱ ሸሹ። 9ሳኦል በእጁ ጦሩን እንደያዘ በቤቱ ተቀምጦ እያለ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሳኦል ላይ መጣበት፥ ዳዊትም በገና ይደረድር ነበር።10ሳኦል በጦሩ ዳዊትን ከግድግዳው ጋር ለማጣበቅ ሞከረ፥ ዳዊት ግን ከሳኦል ፊት ዘወር አለ፥ ስለዚህ የሳኦል ጦር በግድግዳው ላይ ተሰካ። በዚያ ምሽት ዳዊት ሸሽቶ አመለጠ። 11ሳኦልም በማግስቱ ይገድለው ዘንድ ከብበው እንዲጠብቁት ወደ ዳዊት ቤት መልዕክተኞች ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮልም፥”በዚህ ሌሊት ሕይወትህን ካላዳንክ ነገ መገደልህ ነው“ አለችው።12ስለዚህ ሜልኮል ዳዊትን በመስኮት እንዲወርድ አደረገችው። እርሱም ሄደ፥ ሸሽቶም አመለጠ። 13ሜልኮልም የቤተሰቡን የጣዖት ምስል ወስዳ በአልጋው ውስጥ አጋደመችው። በራስጌው ከፍየል ጸጉር የተሠራ ትራስ አስቀመጠች፥ በልብስም ሸፈነችው።14ሳኦል ዳዊትን የሚወስዱ መልዕክተኞች በላከ ጊዜ እርሷ፥ "አሞታል" አለቻቸው። 15ከዚያም ሳኦል ዳዊትን እንዲያዩት መልዕክተኞች ላከ፥ እርሱም፥ "እንድገድለው ከነዐልጋው አምጡልኝ" አላቸው።16መልዕክተኞቹ ወደ ቤት በገቡ ጊዜ፥ በዐልጋው ውስጥ የቤተሰቡ የጣዖት ምስል፥ በራስጌውም ከፍየል ጸጉር የተሠራው ትራስ ነበር። 17ሳኦል ሜልኮልን፥ "ጠላቴ እንዲሄድና እንዲያመልጥ በማድረግ ለምን አታለልሽኝ?" አላት። ሜልኮልም ለሳኦል፥ "'ልሂድ፥ አለበለዚያ እገድልሻለሁ' ስላለኝ ነው" ብላ መለሰችለት።18ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፥ ሳሙኤል ወዳለበት ወደ ራማም ሄደ፥ ሳኦል ያደረገበትንም ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ሄዱ፥ በነዋትም ተቀመጡ። 19ለሳኦልም፥ "ዕወቀው፥ ዳዊት በራማ ነዋት ነው" ተብሎ ተነገረው። 20ሳኦልም ዳዊትን እንዲይዙት መልዕክተኞችን ላከ። እነርሱም ትንቢት የሚናገሩ የነቢያትን ጉባዔ፥ ሳሙኤልንም መሪያቸው ሆኖ ባዩ ጊዜ በሳኦል መልዕክተኞች ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ መጣባቸው፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።21ይህ ሁኔታ ለሳኦል በተነገረው ጊዜ፥ ሌሎች መልዕክተኞችን ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። ስለዚህ ሳኦል እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ሌሎች መልዕክተኞችን ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። 22ከዚያም እርሱ ደግሞ ወደ አርማቴም ሄደ፥ በሤኩ ወዳለው ጥልቅ የውሃ ጉድጓድም መጣ። እርሱም፥”ሳሙኤልና ዳዊት የት ነው ያሉት? “ ብሎ ጠየቀ። አንደኛው ሰው፥”በራማ ነዋት ናቸው“ ብሎ መለሰለት።23ሳኦልም በራማ ወዳለው ነዋት ሄደ። የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ መጣ፥ በራማም ወደሚገኘው ወደ ነዋት እስኪደርስ ድረስ በመንገድ ላይ ትንቢት ይናገር ነበር። 24እርሱም ደግሞ ልብሶቹን አወለቀ፥ በሳሙኤል ፊት እርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገረ፥ ያን ቀንና ሌሊቱን ሁሉ ራቁቱን ተጋደመ። እነርሱም፥”ሳኦል ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ? “ ያሉት በዚህ ምክንያት ነው።
1ከዚያም ዳዊት በራማ ካለው ከነዋት ሸሽቶ መጣና ዮናታንን፥”ምን አድርጌአለሁ? ጥፋቴስ ምንድነው? በአባትህ ፊት ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገው? “ አለው። 2ዮናታንም ዳዊትን፥”ይህ ከአንተ ይራቅ፥ አትሞትም። ነገሩ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሳይነግረኝ አባቴ ምንም አያደርግም። አባቴ ይህንን ነገር ለምን ይደብቀኛል? ነገሩ እንዲህ አይደለም።3ዳዊት ግን እንደገና ማለና፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ ያውቃል። እርሱም፥ 'ይህንን ዮናታን አይወቅ፥ ካልሆነ ያዝናል' ይላል። በሕያው እግዚአብሔር ስም፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፥ በእኔና በሞት መካከል የቀረው አንድ እርምጃ ነው" አለው።4ዮናታን ዳዊትን፥ "የምትጠይቀኝን ሁሉ አደርግልሃለሁ" አለው። 5ዳዊትም ዮናታንን፥ "ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት ቀን ነው፥ ከንጉሡ ጋር ለመብላት መቀመጥ ይኖርብኛል። እስከ ሦስተኛው ቀን ምሽት ድረስ በመስኩ ውስጥ ሄጄ እንድደበቅ ፍቀድልኝ" አለው።6አባትህ እኔን በማጣቱ ከጠየቀህ፥ "ዳዊት፥ መላው ቤተ ሰቡ ዓመታዊ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡ ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት አጥብቆ ለመነኝ' በለው። 7እርሱም፥ 'መልካም ነው' ካለህ ነገሩ ለአገልጋይህ ሰላም ሆኗል ማለት ነው። ነገር ግን እርሱ እጅግ ከተቆጣ ክፉ ሊያደርግብኝ እንደወሰነ በዚህ ታውቃለህ።8እንግዲህ አገልጋይህን በርኅራኄ ተመልከተኝ። በእግዚአብሔር ፊት ከአገልጋይህ ጋር ቃል ኪዳን አድርገሃልና። ኃጢአት ቢገኝብኝ ግን አንተው ግደለኝ፤ ለምንስ ወደ አባትህ ትወስደኛለህ?" አለው። 9ዮናታንም፥ "ይህ ከአንተ ይራቅ! አባቴ ክፉ ሊያደርግብህ መወሰኑን ባውቅ አልነግርህም?"10ዳዊትም ዮናታንን፥ "አባትህ አንደ አጋጣሚ በቁጣ ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል?" አለው። 11ዮናታንም ዳዊትን፥ "ና፥ ወደ መስኩ እንሂድ" አለው። ሁለቱም ወደ መስኩ ሄዱ።12ዮናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው፥ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁን። ነገ ወይም በሦስተኛው ቀን እንደዚህ ባለው ሰዓት አባቴን በምጠይቀው ጊዜ፥ ስለ ዳዊት በጎ አሳብ ካለው ልኬብህ አላሳውቅህም? 13አባቴ በአንተ ላይ ክፉ ማድረጉ የሚያስደስተው ከሆነ በሰላም እንድትሄድ ባላሳውቅህና ባላሰናብትህ እግዚአብሔር በዮናታን ላይ ይህንን እና ከዚህም የከፋውን ያድርግበት። ከአባቴ ጋር እንደነበረ እግዚአብሔር ከአንተም ጋር ይሁን።14አንተስ በሕይወት በምኖርበት ዘመን እንዳልሞት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታማኝነት አታሳየኝም? 15እግዚአብሔር የዳዊትን ጠላቶች፥ እያንዳንዳቸውን ከምድር ላይ በሚያጠፋበት ጊዜ የቃል ኪዳን ታማኝነትህን ከቤቴ አታጥፋ"። 16ሰለዚህ ዮናታን ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገና”እግዚአብሔር ከዳዊት ጠላቶች እጅ ይጠይቀው“ አለ።17ዮናታን ነፍሱን እንደሚወዳት ዳዊትን ይወደው ስለነበረ፥ ለእርሱ ከነበረው ፍቅር የተነሣ ዳዊት እንደገና እንዲምልለት አደረገ። 18ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው፥”ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት የወር መጀመሪያ ቀን ነው። ወንበርህ ባዶ ስለሚሆን ላትኖር ነው። 19ለሦስት ቀናት ከቆየህ በኋላ፥ ፈጥነህ ውረድና በዚህ ጉዳይ ካሁን በፊት ወደተደበቅህበት ስፍራ መጥተህ በኤዜል ድንጋይ አጠገብ ቆይ።20በዒላማ ላይ የምወረውር መስዬ ሦስት ፍላጻዎችን ወደዚያ አቅራቢያ እወረውራለሁ። 21ከእኔ ጋር ያለውን ታዳጊ ወጣት እልከውና፥ 'ሂድ ፍላጻዎቹን ፈልግ' እለዋለሁ። ታዳጊውን ልጅ፥ 'ተመልከት፥ ፍላጻዎቹ አጠገብህ ናቸው፤ ውሰዳቸው' ካልኩት ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ደኅንነት እንጂ ጉዳት አይሆንብህምና ትመጣለህ።22ነገር ግን ታዳጊውን ወጣት፥ 'ተመልከት፥ ፍላጻዎቹ ከአንተ በላይ ናቸው' ካልኩት እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። 23እኔና አንተ ያደረግነውን ስምምነት በሚመለከት እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ለዘላለም ምስክር ነው።"24ስለዚህ ዳዊት በመስኩ ውስጥ ተደበቀ። አዲስ ጨረቃ በሆነ ጊዜ ንጉሡ ምግብ ለመብላት ተቀመጠ። 25ንጉሡ እንደተለመደው በግድግዳው አጠገብ በነበረው በመቀመጫው ላይ ተቀመጠ። ዮናታን ተነሣ፥ አበኔርም በሳኦል አጠገብ ተቀምጦ ነበር። የዳዊት ቦታ ግን ባዶ ነበር።26በዚያን ቀን ሳኦል ገና ምንም አልተናገረም፥ ምክንያቱም፥ "አንድ ነገር ደርሶበት ይሆናል፥ ወይም በሕጉ መሰረት አልነጻም ይሆናል፤ በርግጥ ባይነጻ ነው" ብሎ ሳላሰበ ነው። 27ነገር ግን አዲስ ጨረቃ በታየችበት ማግስት፥ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶ ነበር። ሳኦል ልጁን ዮናታንን፥ "የእሴይ ልጅ ዳዊት ትላንትም ይሁን ዛሬ ወደ ማዕድ ያልመጣው ለምንድነው?" አለው።28ዮናታንም ለሳኦል እንዲህ በማለት መለሰለት፥ "ዳዊት ወደ ቤተ ልሔም ለመሄድ እንድፈቅድለት አጥብቆ ለመነኝ። 29እርሱም፥ 'እባክህን እንድሄድ ፍቀድልኝ። በዚያ ከተማ ቤተሰባችን የሚያቀርበው መሥዋዕት አለ፥ እኔም በዚያ እንድገኝ ወንድሜ አዞኛል። አሁንም በፊትህ ሞገስን ካገኘሁ፥ ወንድሞቼን አያቸው ዘንድ እንድሄድ እባክህን ፍቀድልኝ' አለኝ። ወደ ንጉሡ ማዕድ ያልመጣው በዚህ ምክንያት ነው።"30ከዚያም የሳኦል ቁጣ በዮናታን ላይ ነደደ፥ እርሱም እንዲህ አለው፥ "አንተ የጠማማና አመጸኛ ሴት ልጅ! ለራስህ ኃፍረትና ለእናትህ የዕርቃንነት ኃፍረት የእሴይን ልጅ እንደ መረጥክ የማላውቅ መሰለህ? 31የእሴይ ልጅ በምድር ላይ እስካለ ድረስ አንተም ሆንክ መንግሥትህ አትጸኑም። አሁንም በእርግጥ መሞት የሚገባው ነውና ልከህ አስመጣልኝ።“32ዮናታንም አባቱን ሳኦልን፥”የሚገደለው በምን ምክንያት ነው? ያደረገውስ ምንድነው? “ ሲል መለሰለት። 33በዚያን ጊዜ ሳኦል ሊገድለው ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ አባቱ ዳዊትን ለመግደል መወሰኑን ዮናታን ተረዳ። 34ዮናታን እጅግ ተቆጥቶ ከማዕድ ተነሣ፥ አባቱ ስላዋረደው ስለ ዳዊት አዝኖ ነበርና በወሩ በሁለተኛው ቀን ምንም ምግብ አልበላም።35በማግስቱ ዮናታን ከዳዊት ጋር ወደተቀጣጠሩበት መስክ ሄደ፥ አንድ ታዳጊ ወጣትም አብሮት ነበር። 36እርሱም ታዳጊውን ወጣት፥”ሩጥ፥ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ሰብስብ“ አለው። ታዳጊው ወጣት በሚሮጥበት ጊዜ ፍላጻውን ከበላዩ ላይ ወረወረው። 37ታዳጊው ወጣት ዮናታን የወረወረው ፍላጻ ወደ ወደቀበት ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ ዮናታን ታዳጊውን ተጣርቶ፥ "ፍላጻው ከአንተ በላይ ነው" አለው።38ዮናታንም ታዳጊውን፥ "ቶሎ በል፥ ፍጠን፥ አትዘግይ!" አለው። ስለዚህ የዮናታኑ ታዳጊ ወጣት ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ። 39ታዳጊው ወጣት ግን አንዳች የሚያውቀው አልነበረም። ጉዳዩን የሚያውቁት ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነበሩ። 40ዮናታን የጦር መሣሪያዎቹን ለታዳጊው ወጣት ሰጥቶ፥ "ሂድ፥ ወደ ከተማ ውሰዳቸው" አለው።41ታዳጊው ወጣት እንደ ሄደ፥ ዳዊት ከጉብታው ኋላ ተነሣ፥ ወደ ምድርም ተጎንብሶ ሦስት ጊዜ ሰገደ። እርስ በእርሳቸው ተሳሳሙ፥ ተላቀሱም፥ ዳዊትም አብዝቶ አለቀሰ። 42ዮናታንም ዳዊትን፥”'እግዚአብሔር፥ በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም ይሁን' ተባብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናልና በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።
1ከዚያም ዳዊት ካህኑን አቢሜሌክን ለማግኘት ወደ ኖብ መጣ። አቢሜሌክም ዳዊትን ለመገናኘት እየተንቀጠቀጠ መጣና፥ “አንድም ሰው አብሮህ ያልሆነውና ብቻህን የሆንከው ለምንደነው?” አለው። 2ዳዊትም ካህኑን አቢሜሌክን፥ “ንጉሡ ለአንድ ጉዳይ ልኮኛል። እርሱም፥ 'ስለምልክህ ጉዳይና ያዘዝኩህን ነገር ማንም እንዳያውቅ'ብሎኛል። ወጣቶቹንም የሆነ ቦታ ላይ እንዲጠብቁኝ ነግሬአቸዋለሁ።3ታዲያ አሁን እጅህ ላይ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም ያለውን ነገር ስጠኝ” አለው። 4ካህኑም ለዳዊት መልሶ፥ “ማንኛውም ሰው የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን ታዳጊ ወጣቶቹ ራሳቸውን ከሴቶች ጠብቀው ከሆነ የተቀደሰ እንጀራ አለ” አለው።5ዳዊትም ለካህኑ እንዲህ ሲል መለሰለት፥ “በእርግጥ በእነዚህ ሦስት ቀናት ከሴቶች ተጠብቀናል። ለተራ ተልዕኮ በሚወጡበት ጊዜ ራሳቸውን ካነጹ ለዚህ ተልዕኮማ ከእኔ ጋር ያሉት ወጣቶች ሰውነት ለእግዚአብሔር እንዴት የበለጠ የተቀደሰ አይሆንም?” 6ስለዚህ ከተነሣ በኋላ በስፍራው ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ፊት ከተነሣው፥ ከገጸ ሕብስቱ በስተቀር ሌላ እንጀራ በዚያ አልነበረምና፥ ካህኑ ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን እንጀራ ሰጠው።7በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንዱ በእግዚአብሔር ፊት በእዚያ ቆይቶ ነበር፤ ስሙ ዶይቅ የሚባል ኤዶማዊ፥ የሳኦል የእረኞቹ አለቃ ነበር።8ዳዊት አቢሜሌክን፥ "እዚህ ጦር ወይም ሰይፍ ይኖርሃል? የንጉሡ ጉዳይ አስቸኳይ ስለነበረ ሰይፌንም ሆነ መሣሪያዬን ይዤ አልመጣሁም“ አለው። 9ካህኑም፥”በዔላ ሸለቆ የገደልከው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ በጨርቅ ተጠቅልሎ እዚህ ከኤፉዱ ኋላ አለ። ሌላ የጦር መሣሪያ በዚህ የለምና እርሱን ልትወስደው ብትፈልግ ውሰደው።" ዳዊትም፥ "እንደ እርሱ ያለ ሌላ ሰይፍ የለም፤ እርሱን ስጠኝ" አለው።10በዚያን ቀን ዳዊት ተነሥቶ ከሳኦል ፊት ሸሸ፥ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አንኩስም ሄደ። 11የአንኩስ አገልጋዮችም ንጉሡን፥ "ይህ የምድሪቱ ንጉሥ የሆነው ዳዊት አይደለም? 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ' እያሉ ስለ እርሱ በዘፈን እየተቀባበሉ ዘምረውለት አልነበረም? አሉት።12ዳዊት ይህንን ቃል በልቡ አኖረው፥ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው። 13በፊታቸውም አዕምሮውን ለወጠ፥ በያዙት ጊዜም እንደ ዕብድ ሆነ፤ የቅጥሩን በር እየቧጨረም ለሃጩን በጺሙ ላይ አዝረከረከ።14አንኩስም አገልጋዮቹን፥ “ተመልከቱ፥ ሰውዬው ዕብድ እንደሆነ ታያላችሁ። 15ወደ እኔ ለምን አመጣችሁት? ይህንን ሰው በፊቴ እንዲያብድ ወደ እኔ ያመጣችሁት ያበዱ ሰዎችን ስላጣሁኝ ነው? በእርግጥ እንዲህ ያለው ሰው ወደ ቤቴ ይገባል?” አላቸው።
1ስለዚህ ዳዊት ያንን ትቶ ወደ ዓዶላም ዋሻ አመለጠ። ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰብ በሙሉ ይህንን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ወደ እርሱ ወረዱ። 2የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። ዳዊትም አዛዣቸው ሆነ። ከእርሱም ጋር ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ።3ዳዊት ከዚያ በሞዓብ ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ። እርሱም የሞዓብን ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ እባክህን አባቴና እናቴ አንተጋ እንዲኖሩ ፈቃድህ ይሁን” አለው። 4እነርሱንም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ ተዋቸው። ዳዊት በጠንካራው ምሽግ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ሁሉ አባቱና እናቱ ከንጉሡ ጋር ኖሩ። 5ከዚያም ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፥ “በጠንካራው ምሽግ ውስጥ አትቆይ። እርሱን ትተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ያንን ትቶ ወደ ሔሬት ጫካ ሄደ።6ዳዊት ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሰዎች ጋር መገኘቱን ሳኦል ሰማ። ሳኦል በጊብዓ ከአጣጥ ዛፍ ስር በእጁ ጦሩን እንደያዘ ተቀምጦ ነበር፥ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር።7ሳኦል በዙሪያው የቆሙትን አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የብንያም ሰዎች ሆይ፥ አሁን ስሙ! የእሴይ ልጅ ለእያንዳንዳችሁ እርሻና የወይን ቦታ ይሰጣችኋል? ሁላችሁም በእኔ ላይ ስላደማችሁበት ምትክ ሻለቆችና መቶ አለቆችስ አድርጎ ይሾማችኋል? 8ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ከእናንተ አንዱም አልነገረኝም። አንዳችሁም ስለ እኔ አላዘናችሁም። ልጄ አገልጋዬን ዳዊትን በእኔ ላይ ሲያነሣሣው ከእናንተ ማንም አልነገረኝም። ዛሬ ተደብቋል፥ እኔን ለማጥቃትም ይጠባበቃል።"9ከዚያም በሳኦል አገልጋዮች መካከል ቆሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ፥ "የእሴይን ልጅ ወደ ኖብ፥ ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ መጥቶ አይቼዋለሁ። 10አቤሜሌክም እግዚአብሔር ዳዊትን እንዲረዳው ጸለየለት፥ እርሱም ስንቅና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው" አለው።11ንጉሡም የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቢሜሌክንና የአባቱን ቤተሰብ በሙሉ፥ እንዲሁም በኖብ ይኖሩ የነበሩትን ካህናት እንዲጠራ መልዕክተኛ ላከ። ሁሉም ወደ ንጉሡ መጡ። 12ሳኦልም፥ "የአኪጦብ ልጅ ሆይ፥ አሁን ስማ!" አለው። እርሱም፥ "ጌታዬ ሆይ፥ ይኸው አለሁ” ብሎ መለሰለት። 13ሳኦልም እንዲህ አለው፥ “አንተና የእሴይ ልጅ በእኔ ላይ ያሤራችሁት ለምንድነው? ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ በእኔ ላይ እንዲነሣና በምስጢራዊ ቦታ እንዲደበቅ እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፥ ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የጸለይክለት ለምንድነው?”14አቢሜሌክም ለንጉሡ፥ “የንጉሡ አማችና በጠባቂዎቹ ላይ የበላይ የሆነ፥ በቤትህም የተከበረ፥ በአገልጋዮችህ ሁሉ መካከል እንደ ዳዊት የታመነ ማነው? 15እግዚአብሔር እንዲረዳው ስጸልይለት የዛሬው የመጀመሪያዬ ነውን? ይህ ከእኔ ይራቅ! ንጉሡ ምንም ነገር በአገልጋይህ ወይም በአባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያኑር። አገልጋይህ ከዚህ ሁሉ ነገር አንዱንም አላውቅምና" ብሎ መለሰለት።16ንጉሡም፥ "አቢሜሌክ ሆይ፥ አንተና የአባትህ ቤት በሙሉ በእርግጥ ትሞታላችሁ" ብሎ መለሰለት። 17ንጉሡም በዙሪያው የቆሙትን ጠባቂዎች፥ "መሸሹን እያወቁ አላስታወቁኝምና፥ እጃቸውም ከዳዊት ጋር ነውና፥ ዙሩና የእግዚአብሔርን ካህናት ግደሏቸው” አላቸው። የንጉሡ አገልጋዮች ግን የእግዚአብሔርን ካህናት ለመግደል እጆቻቸውን አላነሡም።18ከዚያም ንጉሡ ዶይቅን፥ "ዙርና ካህናቱን ግደላቸው" አለው። ስለዚህ ኤዶማዊው ዶይቅ ዞረና መታቸው፤ በዚያም ቀን ከተልባ እግር የተሠራ ኤፉድ የለበሱ ሰማንያ አምስት ሰዎችን ገደለ። 19እርሱም የካህናቱን ከተማ ኖብን፥ ወንዶችንና ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ በሬዎችን፥ አህዮችንና በጎችን በሰይፍ ስለት መታቸው። ሁሉንም በሰይፍ ስለት ገደላቸው።20ነገር ግን አብያታር የተባለው የአኪጦብ ልጅ፥ የአቢሜሌክ ልጅ አመለጠ፥ ወደ ዳዊትም ሸሸ። 21አብያታርም ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንደ ገደለ ለዳዊት ነገረው።22ዳዊትም አብያታርን፥ “ኤዶማዊው ዶይቅ በዚያ በነበረ ጊዜ በእርግጥ ለሳኦል እንደሚነግረው በዚያን ቀን ዐውቄ ነበር። ለአባትህ ቤተ ሰብ ሁሉ መሞት ተጠያቂው እኔ ነኝ! ። 23ከእኔ ጋር ተቀመጥ፥ አትፍራ። ያንተን ነፍስ የሚፈልግ የእኔንም ነፍስ የሚፈልግ ነው። ከእኔ ጋር በሰላም ትኖራለህ” አለው።
1ለዳዊትም፥ "ፍልስጥኤማውያን ቅዒላን በመውጋት ላይ ናቸው፥ ዐውድማውንም እየዘረፉ ነው“ ብለው ነገሩት። 2ስለዚህ ዳዊት እግዚአብሔር እንዲረዳው ጸለየ፥ እርሱም፥”እነዚህን ፍልስጥኤማውያን ሄጄ ልምታቸው? “ ብሎ ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፥”ሂድና ፍልስጥኤማውያንን ምታ፥ ቅዒላንም አድን“ አለው።3የዳዊት ሰዎችም፥”ተመልከት፥ እዚሁ በይሁዳ ሆነን እየፈራን ነው። በፍልስጥኤማውያን ላይ ወደ ቅዒላ ለመውጣትማ ይልቁን እንዴት አስፈሪ አይሆንብንም? “ አሉት። 4ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔር እንዲረዳው እንደገና ጸለየ። እግዚአብሔርም፥”ተነሥ፥ ወደ ቅዒላ ውረድ። በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን እሰጥሃለሁ“ ብሎ መለሰለት።5ዳዊትና ሰዎቹም ሄደው ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጉ። የቀንድ ከብቶቻቸውን ወሰዱ፥ እነርሱንም በታላቅ አገዳደል መቷቸው። ስለዚህ ዳዊት የቅዒላን ነዋሪዎች አዳናቸው። 6የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ቅዒላ ወደ ዳዊት በሸሸ ጊዜ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር።7ዳዊት ወደ ቅዒላ መሄዱ ለሳኦል ተነገረው። ሳኦልም፥ "በሮችና መቀርቀሪያዎች ወዳሏት ከተማ በመግባቱ በራሱ ላይ ዘግቷልና እግዚአብሔር በእጄ ላይ ጥሎታል" አለ። 8ሳኦልም ወደ ቅዒላ ወርደው ዳዊትንና ሰዎቹን እንዲከቡ ሠራዊቱን ሁሉ ለጦርነት ጠራቸው። 9ዳዊትም ሳኦል ክፉ ሊያደርግበት እንዳቀደ ዐወቀ። እርሱም ካህኑን አብያታርን፥ "ኤፉዱን ወደዚህ አምጣው" አለው።10ዳዊትም፥ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ሳኦል በእኔ ምክንያት ከተማይቱን ለማጥፋት ወደ ቅዒላ ለመምጣት እንደሚፈልግ አገልጋይህ በእርግጥ ሰምቷል። 11አገልጋይህ እንደ ሰማው፥ ሳኦል ወደዚህ ይወርዳል? የቅዒላ ሰዎችስ በእጁ አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እባክህን ለአገልጋይህ እንድትነግረኝ እለምንሃለሁ” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አዎን፥ ወደዚህ ይወርዳል” አለው።12ዳዊትም፥ “የቅዒላ ሰዎች እኔንና ሰዎቼን በሳኦል እጅ አሳልፈው ይሰጡናልን?” ብሎ ጠየቀው። እግዚአብሔርም፥ “አሳልፈው ይሰጧችኋል" አለ።13ከዚያም ዳዊትና ወደ ስድስት መቶ የሚደርሱ ሰዎቹ ተነሡ፥ ከቅዒላም ወጥተው ሄዱ፥ ከቦታ ቦታም እየተዘዋወሩ ሄዱ። ዳዊት ከቅዒላ መሸሹ ለሳኦል ተነገረው፥ እርሱም ማሳደዱን አቆመ። 14ዳዊትም በዚፍ ምድረ በዳ ውስጥ ባለው በኮረብታማው አገር፥ በምድረ በዳው ባለ ምሽግ ውስጥ ኖረ። ሳኦል በየቀኑ ይፈልገው ነበር፥ እግዚአብሔር ግን በእጁ ላይ አልጣለውም።15ዳዊት በዚፍ ምድረ በዳ ሖሬሽ በተባለ ቦታ ነበር፤ ሳኦልም የእርሱን ሕይወት ለማጥፋት እንደ ወጣ አየ። 16ከዚያም የሳኦል ልጅ ዮናታን ተነሥቶ በሖሬሽ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት ሄደ፥ በእግዚአብሔር ስም አበረታታው።17እንዲህም አለው፥ "የአባቴ የሳኦል እጅ አያገኝህምና አትፍራ። አንተ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆናለህ፥ እኔም ምክትልህ እሆናለሁ። አባቴ ሳኦልም ደግሞ ይህንን ያውቃል።" 18እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ዳዊት በሖሬሽ ቆየ፥ ዮናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ።19ዚፋውያንም በጊብዓ ወዳለው ወደ ሳኦል መጥተው፥ "ዳዊት ከየሴሞን በስተደቡብ በሚገኘው በኤኬላ ኮረብታ ላይ፥ በሖሬሽ ምሽጎች ውስጥ በመካከላችን ተደብቋል፤ 20አሁንም ንጉሥ ሆይ! ወደዚህ ውረድ፥ ደስ ባለህ ጊዜ ወደዚህ ውረድ! በንጉሡ እጅ አሳልፎ የመስጠቱ ድርሻ የእኛ ይሆናል” አሉት።21ሳኦልም፥ “ስለ እኔ ተቆርቁራችኋልና እግዚአብሔር ይባርካችሁ። 22ሂዱና በይበልጥ እርግጠኛ ሁኑ። የት እንደ ተደበቀና በዚያ ማን እንዳየው መርምሩና ዕወቁ። እጅግ ተንኮለኛ ስለመሆኑ ተነግሮኛል። 23ስለዚህ ልብ በሉ፥ ራሱን የሚደብቅባቸውን ቦታዎች በሙሉ መርምሩ። የተረጋገጠ መረጃ ይዛችሁልኝ ተመለሱ፥ ከዚያ በኋላ እኔም ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ። በምድሪቱ ላይ ካለ፥ በይሁዳ ሺዎች ሁሉ መካከል እፈልገዋለሁ” አላቸው።24እነርሱም ተነሡ፥ ሳኦልንም ቀድመው ወደ ዚፍ ሄዱ። ዳዊትና ሰዎቹ ከየሴሞን በስተደቡብ በዓረባ በምትገኘው በማዖን ምድረ በዳ ውስጥ ነበሩ። 25ሳኦልና ሰዎቹም እርሱን ሊፈልጉት ሄዱ። ይህም ለዳዊት ተነገረው፥ ስለዚህ ወደ ዐለታማው ኮረብታ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ውስጥ ኖረ። ሳኦል በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ አሳደደው።26ሳኦል በተራራው በአንዱ ወገን ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በወዲያኛው ወገን ይሄዱ ነበር። ዳዊት ከሳኦል ለማምለጥ ተቻኮለ። ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመያዝ እየከበቧቸው በነበሩበት ጊዜ 27አንድ መልዕክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ምድሪቱን ወረዋታልና ፈጥነህ ና" አለው።28ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን ከማሳደድ ተመልሶ ፍልስጥኤማውያንን ለመዋጋት ሄደ። በዚህ ምክንያት ያ ስፍራ የማምለጫ ዐለት ተብሎ ተጠራ። 29ዳዊት ከዚያ ወጥቶ በዓይንጋዲ ባሉ ምሽጎች ውስጥ ኖረ።
1ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ በተመለሰ ጊዜ፥ "ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ ውስጥ ነው" ተብሎ ተነገረው። 2ከዚያም ሳኦል ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ ወደ ዓይንጋዲ ሄደ።3እርሱም በመንገዱ በበጎች ማደሪያ አቅራቢያ ወደነበረ ዋሻ መጣ። ሳኦልም ለመጸዳዳት ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹ በዋሻው ውስጥ ከኋላ ጥጉጋ ተቀምጠው ነበር። 4የዳዊት ሰዎችም፥ "'ደስ ያሰኘህን እንድታደርግበት ጠላትህን በእጅህ ላይ አሳልፌ እሰጥሃለሁ' ባለህ ጊዜ እግዚአብሔር የተናገረው ስለዚህ ቀን ነው” አሉት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ በጸጥታ በደረቱ እየተሳበ ወደ ፊት በመሄድ የሳኦልን የካባውን ጫፍ ቆረጠው።5ከዚህ በኋላ የሳኦልን የካባውን ጫፍ ስለ ቆረጠ ዳዊትን ኅሊናው ወቀሰው። 6እርሱም ሰዎቹን፥ "እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን በማንሣት እንዲህ ያለውን ነገር ማድረግን እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው" አላቸው። 7ስለዚህ ዳዊት የእርሱን ሰዎች በዚህ ቃል ገሰጻቸው፥ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲጥሉበት አልፈቀደላቸውም። ሳኦል ተነሥቶ ከዋሻው ወጣና መንገዱን ቀጠለ።8ከዚህ በኋላ ዳዊት ተነሥቶ ከዋሻው በመውጣት ሳኦልን፥ "ጌታዬ፥ ንጉሥ ሆይ!" በማለት ተጣራ። ሳኦል ወደ ኋላው ዘወር ብሎ በተመለከተ ጊዜ፥ ዳዊት በመስገድ አክብሮትን አሳየው። 9ዳዊትም ሳኦልን፥ “ 'ዳዊት ሊጎዳህ ይፈልጋል' የሚሉህን ሰዎች ለምን ትሰማቸዋለህ?10በዋሻው በነበርን ጊዜ እግዚአብሔር ዛሬ እጄ ላይ ጥሎህ እንደነበረ ዓይኖችህ አይተዋል። አንዳንዶቹ እንድገድልህ ነግረውኝ ነበር፥ እኔ ግን ራራሁልህ። እኔም፥ 'በእግዚአብሔር የተቀባ ስለሆነ፥ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም' አልኩኝ። 11አባቴ ሆይ ተመልከት፥ በእጄ ላይ ያለውን የካባህን ቁራጭ ተመልከት። የካባህን ጫፍ ቆረጥኩኝ እንጂ አልገደልኩህም፥ በመሆኑም በእጄ ላይ ክፋትና ክህደት እንደሌለ ዕወቅ፤ ምንም እንኳን ሕይወቴን ለማጥፋት ብታሳድደኝም፥ እኔ አልበደልኩህም።12እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፥ እግዚአብሔር ይበቀልልኝ፥ እጄ ግን ባንተ ላይ አትሆንም። 13የጥንቱ ምሳሌ፥ 'ከክፉ ሰው ክፋት ይወጣል' ይላል። እጄ ግን ባንተ ላይ አትሆንም።14የእስራኤል ንጉሥ የወጣው በማን ላይ ነው? የምታሳድደው ማንን ነው? የሞተን ውሻ! ቁንጫን! 15እግዚአብሔር ፈራጅ ይሁን፥ በእኔና በአንተ መካከል ይመልከት፥ ይፍረድም፥ ጉዳዬን ተመልክቶም ከእጅህ እንዳመልጥ ይርዳኝ።”16ዳዊት ይህንን ቃል ለሳኦል ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት! ይህ ድምፅህ ነው?” አለው። ሳኦልም ድምፁን አሰምቶ አለቀሰ።17እርሱም ዳዊትን እንዲህ አለው፥ "በክፋት ስመልስልህ በደግነት መልሰህልኛልና ከእኔ ይልቅ አንተ ጻድቅ ነህ። 18እግዚአብሔር በእጅህ ላይ በጣለኝ ጊዜ አልገደልከኝምና በጎነትን እንዳደረግህልኝ ዛሬ አሳይተሃል።19አንድ ሰው ጠላቱን ቢያገኘው በሰላም ያሰናብተዋል? ዛሬ ስላደረግህልኝ ነገር እግዚአብሔር ቸርነትን ያድርግልህ። 20አሁንም፥ በእርግጥ ንጉሥ እንደምትሆንና የእስራኤል መንግሥት በእጅህ እንደሚጸና ዐውቃለሁ።21ከእኔ በኋላ ዘሮቼን እንደማታጠፋና ስሜንም ከአባቴ ቤት እንደማትደመስሰው በእግዚአብሔር ማልልኝ።" 22ስለዚህ ዳዊት ለሳኦል ማለለት። ከዚያም ሳኦል ወደ ቤቱ ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ግን ወደ አምባው ወጡ።
1ሳሙኤል ሞተ። እስራኤላውያን ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፥ በራማም በቤቱ ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።2በማዖን አንድ ሰው ነበር፥ ንብረቱም በቀርሜሎስ ይኖር ነበር። ሰውዬው እጅግ ባለጸጋ ነበር። እርሱም ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት። በቀርሜሎስም በጎቹን ይሸልት ነበር። 3የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበር። ሴቲቱ ብልህና መልኳም የተዋበ ነበረች። ሰውየው ግን አስቸጋሪና በምግባሩ ክፉ ነበር። እርሱም የካሌብ ቤተ ሰብ ተወላጅ ነበር።4ዳዊት በምድረ በዳ ውስጥ ሳለ ናባል በጎቹን እንደሚሸልት ሰማ። 5ስለዚህ ዳዊት ዐሥር ወጣቶችን ላከ። ዳዊትም ወጣቶቹን እንዲህ አላቸው፥ “ወደ ቀርሜሎስ ውጡ፥ ወደ ናባልም ሂዱና በስሜ ሰላምታ አቅርቡለት። 6እርሱንም እንዲህ በሉት፥ 'በብልጽግና ኑር፥ ሰላም ላንተ፥ ለቤትህና ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን።7ሸላቾች እንዳሉህ ሰምቻለሁ። እረኞችህ ከእኛ ጋር ነበሩ፥ ምንም ጉዳት አላደረስንባቸውም፥ በቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ አንድም አላጡም። 8ወጣቶችህን ጠይቃቸው፥ እነርሱም ይነግሩሃል። አሁንም በግብዣህ ቀን መጥተናልና ወጣቶቼ በዓይንህ ፊት ሞገስ ያግኙ። በእጅህ ያለውን ማንኛውንም ነገር ለአገልጋዮችህና ለልጅህ ለዳዊት እባክህን ስጠው።"9የዳዊት ወጣቶች በደረሱ ጊዜ፥ በዳዊት ስም ይህንን ሁሉ ለናባል ነገሩትና ምላሹን ጠበቁ። 10ናባልም ለዳዊት አገልጋዮች፥ "ዳዊት ማነው? የእሴይስ ልጅ ማነው? በእነዚህ ቀናት ከጌቶቻቸው የሚኮበልሉ ብዙ አገልጋዮች አሉ። 11ታዲያ እንጀራዬን፥ ውሃዬንና ለሸላቾቼ ያረድኩትን ሥጋ ወስጄ ከየት እንደ መጡ ለማላውቃቸው ሰዎች መስጠት ይኖርብኛል?" ሲል መለሰላቸው።12ስለዚህ የዳዊት ወጣቶች ዞረው በመመለስ የተባለውን ሁሉ ነገሩት። 13ዳዊትም ሰዎቹን፥ "ሁሉም ሰው ሰይፉን ይታጠቅ" አለ። ስለዚህ ሁሉም ሰይፎቻቸውን ታጠቁ። ዳዊትም ደግሞ ሰይፉን ታጠቀ። አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ዳዊትን ተከተሉት፥ ሁለት መቶዎቹም ከስንቅና ትጥቃቸው ጋር ቆዩ።14ነገር ግን ከወጣቶቹ አንዱ፥ ለናባል ሚስት ለአቢግያ እንዲህ ሲል ነገራት፥”ዳዊት ከምድረ በዳ ለጌታችን ሰላምታ ለማቅረብ መልዕክተኞች ላከ፥ ጌታችን ግን ሰደባቸው። 15ሰዎቹ ግን ለእኛ በጣም ጥሩዎች ነበሩ። በመስኩ ላይ እያለን ከእነርሱ ጋር በሄድንበት ጊዜ ሁሉ አንድም አልጎደለብንም፥ እነርሱም አልጎዱንም።16በጎቹን እየጠበቅን ከእነርሱ ጋር በቆየንበት ጊዜ ሁሉ ቀንና ሌሊት አጥር ሆነውልን ነበር። 17በጌታችንና በቤተሰቡ ሁሉ ላይ ክፉ ታስቦአልና ይህንን ዕወቂ፥ ምን ማድረግ እንዳለብሽም አስቢበት። እርሱ የሚረባ ሰው አይደለምና ማንም ሊያነጋግረው አይችልም“።18አቢግያም ፈጥና ሁለት መቶ እንጀራ፥ ሁለት ጠርሙስ የወይን ጠጅ፥ ቀደም ብሎ የተዘጋጀ አምስት በግ፥ አምስት መስፈሪያ የተጠበሰ እሸት፥ አንድ መቶ የወይን ዘለላና ሁለት መቶ የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ ወስዳ በአህዮች ላይ ጫነች። 19ከእርሷ ጋር የነበሩትንም ወጣቶች፥ "በፊቴ ቅደሙ፥ እኔም እከተላችኋለሁ" አለቻቸው። ለባልዋ ለናባል ግን አልነገረችውም።20እርሷም በአህያዋ ላይ በመቀመጥ ተራራውን ተከልላ በመውረድ ላይ እያለች ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እርሷ ወረዱ፥ እርሷም አገኘቻቸው።21ዳዊትም፥”የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ እንኳን እንዳይጠፋበት፥ ይህ ሰው የነበረውን ሁሉ በምድረ በዳ መጠበቄ በእርግጥም በከንቱ ነበር፥ ስላደረግሁት በጎነት ክፋትን መልሶልኛልና። 22ነገ ጠዋት የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ ወንድ እንኳን ባስቀርለት እግዚአብሔር በእኔ በዳዊት ላይ ይህንኑ ያድርግብኝ፥ ደግሞም ይጨምርብኝ" ብሎ ነበር።23አቢግያ ዳዊትን ባየችው ጊዜ፥ ከአህያዋ ላይ ፈጥና ወረደች፥ በዳዊትም ፊት አጎንብሳ ወደ ምድር ሰገደች። 24በእግሩ ላይ ወድቃም እንዲህ አለችው፥ "ጌታዬ ሆይ፥ በደሉ በእኔ ላይ ብቻ ይሁን። እባክህን አገልጋይህ እንድናገርህ ፍቀድልኝ፥ የአገልጋይህንም ቃል ስማ።25ጌታዬ ለዚህ ለማይረባው ናባል ትኩረት አይስጥ፥ እርሱ እንደ ስሙ ነው። ስሙ ናባል ነውና ጅልነትም ከእርሱ ጋር ነው። እኔ አገልጋይህ ግን የላካቸውን የጌታዬን ወጣቶች አላየሁም። 26አሁንም ጌታዬ ሆይ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በራስህ እጅ ከመበቀል እግዚአብሔር አግዶሃልና፥ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ ለማድረግ የሚፈልጉ እንደ ናባል ይሁኑ።27አሁንም አገልጋይህ ወደ ጌታዬ ያመጣሁት ይህ ስጦታ ጌታዬን ለሚከተሉ ወጣቶች ይሰጥ። 28እባክህን የአገልጋይህን መተላለፍ ይቅር በል፥ አንተ ጌታዬ፥ የእግዚአብሔርን ጦርነት በመዋጋት ላይ ስላለህ፥ እግዚአብሔር በርግጥ ለጌታዬ እውነተኛ የሆነን ቤት ይሠራል፥ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም።29ሰዎች ተነሥተው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድዱህም የጌታዬ ሕይወት በአምላክህ በእግዚአብሔር በሕያዋን አንድነት የታሰረች ትሆናለች፤ እርሱም የጠላቶችህን ሕይወት ከወንጭፍ ኪስ እንደሚወረወር፥ በወንጭፍ ይወረውራል።30ይህ በሆነ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠህን መልካም ነገር ሁሉ ለጌታዬ በፈጸመ ጊዜ፥ በእስራኤልም ላይ መሪ ባደረገህ ጊዜ፥ 31ይህ ጉዳይ ሐዘን አይሆንብህም፥ ለጌታዬም የልብ ጸጸት አይሆንም፥ ያለ ምክንያት ደም ያፈሰስክ፥ በራስህም እጅ የተበቀልክ አትሆንም። እግዚአብሔር ለጌታዬ ስኬትን ባመጣልህ ጊዜ አገልጋይህን አስበኝ።"32ዳዊትም አቢግያን፥ "ዛሬ እንድታገኚኝ የላከሽ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን። 33ደም በማፍሰስ ከሚሆን በደልና በራሴ እጅ ስለ ራሴ ከመበቀል ጠብቀሽኛልና ጥበብሽ የተባረከ ነው፥ አንቺም የተባረክሽ ነሽ።34በእውነት፥ አንቺን ከመጉዳት የጠበቀኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን፥ እኔን ለመገናኘት ፈጥነሽ ባትመጪ ኖሮ፥ ያለምንም ጥርጥር ነገ ጠዋት ለናባል አንድ ወንድ ሕፃን ልጅ አይቀርለትም ነበር“ አላት። 35ስለዚህ ዳዊት ያመጣችለትን ከእጇ ተቀበላት፤ እርሱም፥ "ወደ ቤትሽ በሰላም ሂጂ፤ ይኸው ቃልሽን ሰማሁ፥ ተቀበልኩሽም" አላት።36አቢግያም ተመልሳ ወደ ናባል ሄደች፤ እርሱም የንጉሥ ግብዣን የመሰለ ግብዣ በቤቱ ያደርግ ነበር፤ ናባልም በጣም ሰከሮ፥ ልቡም ደስ ብሎት ነበር። ስለዚህ እስኪነጋ ድረስ ምንም ነገር አልነገረችውም።37ከነጋ በኋላ፥ የናባል ስካር በበረደ ጊዜ፥ ሚስቱ እነዚህን ነገሮች ነገረችው፤ ልቡ ቀጥ አለ፥ እርሱም እንደ ድንጋይ ሆነ። 38ዐሥር ቀን ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ናባልን ስለመታው ሞተ።39ናባል መሞቱን ዳዊት በሰማ ጊዜ፥”የመሰደቤን ምክንያት ከናባል እጅ የተቀበለና አገልጋዩን ከክፉ የጠበቀ ጌታ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን። እርሱም የናባልን ክፉ ሥራ በራሱ ላይ መለሰበት“ አለ። ከዚያም ዳዊት ወደ አቢግያ መልዕክተኛ ልኮ ሚስት አድርጎ ሊወስዳት አናገራት። 40የዳዊት አገልጋዮች ወደ ቀርሜሎስ፥ ወደ አቢግያ በመጡ ጊዜ፥ "ሚስቱ እንድትሆኚው ልንወስድሽ ዳዊት ወዳንቺ ልኮናል" አሏት።41እርሷም ተነሣች፥ በግምባርዋ ወደ ምድር ሰግዳ፥ "ይኸው፥ ሴት አገልጋይህ፥ የጌታዬን አገልጋዮች እግር የማጥብ አገልጋይ ነኝ" አለች። 42አቢግያም ፈጥና ተነሣች፥ ከተከተሏት ከአምስት ሴት አገልጋዮቿ ጋር በአህያ ተቀመጠች፥ የዳዊትን መልዕክተኞች ተከትላ ሄደች፥ ሚስትም ሆነችው።43በተጨማሪም ዳዊት ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ሚስት እንድትሆነው ወሰዳት፥ ሁለቱም ሚስቶቹ ሆኑ። 44ሳኦል የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን፥ በጋሊም ለሚኖረው ለሌሳ ልጅ ለፈልጢ ሰጥቶ ነበር።
1ዚፋውያን ወደ ሳኦል ወደ ጊብዓ መጥተው፥ “ዳዊት በምድረ በዳው ፊት ለፊት በኤኬላ ኮረብታ ላይ ተደብቋል?” አሉት። 2ከዚያም ሳኦል ተነሣ፥ ከእስራኤል የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ዳዊትን ለመፈለግ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ።3ሳኦልም በምድረ በዳው ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ፥ በመንገዱ ዳር ሰፈረ። ዳዊት ግን በምድረ በዳው ቆይቶ ነበር፥ ሳኦል በምድረ በዳው ከበስተኋላው እንደመጣ አየ። 4ስለዚህ ዳዊት ሰላዮችን ላከና በርግጥም ሳኦል በመምጣት ላይ መሆኑን ዐወቀ።5ዳዊት ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ስፍራ ሄደ፤ ሳኦልና የሰራዊቱ አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ፤ ሳኦል በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፥ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር፥ ሁሉም እንቅልፍ ወስዷቸው ነበር።6ከዚያም ዳዊት ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የኢዮአብን ወንድም የጽሩያን ልጅ አቢሳን፥ "ወደ ሳኦል ወደ ጦር ሰፈሩ ውስጥ ከእኔ ጋር የሚወርድ ማነው?" አላቸው። አቢሳም፥ "እኔ ከአንተ ጋር እወርዳለሁ" አለው። 7ስለዚህ ዳዊትና አቢሳ በሌሊት ወደ ሰራዊቱ ሄዱ። ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ፥ ጦሩም ከራስጌው በምድር ላይ ተተክሎ ነበር። አበኔርና ወታደሮቹ በዙሪያው ተኝተው ነበር። 8አቢሳም ዳዊትን፥ "እግዚአብሔር ዛሬ ጠላትህን በእጅህ ላይ ጣለው። አሁንም፥ በአንድ ምት ብቻ በጦር ከምድር ጋር እንዳጣብቀው ፍቀድልኝ፥ ሁለተኛ መምታትም አያስፈልገኝም" አለው።9ዳዊትም አቢሳን እንዲህ አለው፥ "አትግደለው፤ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን ዘርግቶ ከበደል መንጻት የሚችል ማነው? 10ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር ራሱ ይገድለዋል፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል፥ ወይም ወደ ጦርነት ሄዶ ይሞታል።11እርሱ በቀባው ላይ እጄን ማንሣትን እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፤ አሁን ግን፥ በራስጌው ያለውን ጦርና የውሃውን ኮዳ ይዘህ እንድንሄድ እለምንሃለሁ።" 12ስለዚህ ዳዊት በሳኦል ራስጌ የነበረውን ጦርና የውሃ ኮዳ ወሰደና ሄዱ። ከእግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ ስለወደቀባቸው ሁሉም አንቀላፍተው ነበርና አንድም የነቃ፥ ያየ ወይም ያወቀ አልነበረም።13ከዚያም ዳዊት በሌላኛው ወገን ወጣ፥ በተራራው ጫፍ ላይም ርቆ ቆመ፤ በመካከላቸው ሰፊ ርቀት ነበረ። 14ዳዊትም ወደ ኔር ልጅ ወደ አበኔርና ወደ ሕዝቡ ጮኾ፥ "አበኔር ሆይ፥ አትመልስምን?" አለው። አበኔርም፥ "በንጉሡ ላይ የምትጮኸው አንተ ማነህ?" ብሎ መለሰለት።15ዳዊትም አበኔርን፥ "አንተ ጀግና አይደለህም? በእስራኤልስ አንተን የሚመስልህ ማነው? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን ያልጠበቅኸው ለምንድነው? አንድ ሰው ጌታህን ንጉሡን ለመግደል መጥቶ ነበርና። 16ይህ ያደረግኸው ነገር መልካም አይደለም። ሕያው እግዚአብሔርን! ሞት የሚገባህ ነህ፥ ምክንያቱም እግዚአብሔር የቀባውን ጌታህን አልጠበቅኸውም። አሁንም፥ የንጉሡ ጦርና በራስጌው የነበረው የውሃ ኮዳ የት እንዳለ ተመልከት" አለው።17ሳኦልም የዳዊት ድምፅ መሆኑን ለየና፥ "ልጄ ዳዊት፥ ይህ ድምፅህ ነው?" አለው። ዳዊትም፥ "ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ድምፄ ነው" አለው። 18እርሱም እንዲህ አለው፥ "ጌታዬ አገልጋዩን የሚያሳድደው ለምንድነው? ምን አድርጌአለሁ? በእጄስ ያለው ክፋት ምንድነው?19አሁንም ጌታዬ ንጉሡ የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ። በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ከሆነ መስዋዕትን ይቀበል፤ ሰዎች ከሆኑ ግን በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ 'ሄደህ ሌሎች አማልክቶችን አምልክ' ብለው የእግዚአብሔርን ርስት አጥብቄ እንዳልይዝ ዛሬ አባረውኛልና። 20ስለዚህ፥ አንድ ሰው በተራሮች ላይ ቆቅን እንደሚያድን፥ የእስራኤል ንጉሥ ቁንጫን ለመፈለግ መጥቷልና ደሜ ከእግዚአብሔር ፊት ርቆ በምድር ላይ እንዲፈስ አታድርግ።“21ከዚያም ሳኦል፥”ኃጢአትን አድርጌአለሁ። ልጄ ዳዊት፥ ተመለስ፤ ዛሬ ሕይወቴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ አላደርግብህም። ስንፍናን አድርጌአለሁ፥ እጅግም ተሳስቻለሁ“ አለው።22ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰለት፥”ንጉሥ ሆይ ተመልከት! ጦርህ ያለው እዚህ ነው፥ ከወጣቶቹ አንዱ ይምጣና ይውሰድልህ። 23ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ላይ ጥሎህ እያለ በእርሱ የተቀባውን አልመታሁትምና እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደ ጽድቁና ታማኝነቱ ይክፈለው።24ተመልከት፥ ዛሬ ሕይወትህ በዐይኔ ፊት እንደ ከበረች የእኔም ሕይወት በእግዚአብሔር ዐይን አብልጣ የከበረች ትሁን፥ ከመከራዬም ሁሉ ያድነኝ።“ 25ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥”ልጄ ዳዊት፥ በርግጥ ታላላቅ ነገሮችን እንድታደርግና እንዲከናወንልህ የተባረክህ ሁን“ አለው። ስለዚህ ዳዊት መንገዱን ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።
1ዳዊትም፥”አሁንም አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ከመሸሽ የሚሻል አማራጭ የለኝም፤ ያን ጊዜ ሳኦል በእስራኤል ወሰኖች ሁሉ ውስጥ እኔን መፈለጉን ያቆማል፤ በዚህ መንገድ ከእጁ አመልጣለሁ" ብሎ በልቡ አሰበ።2ዳዊትም ተነሣ፥ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ ተሻገሩ። 3ዳዊትና ሰዎቹ እያንዳንዱ ከቤተሰቡ ጋር፥ እርሱም ከሁለቱ ሚስቶቹ፥ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ ጋር በጌት ከአንኩስ ጋር ኖሩ። 4ዳዊት ወደ ጌት መሸሹን ሳኦል ሰማ፥ ስለዚህ ከዚህ በኋላ አልፈለገውም።5ዳዊትም አንኩስን፥ "በዐይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፥ በዚያ እኖር ዘንድ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ስፍራ ይስጡኝ፤ አገልጋይህ በንጉሣዊ ከተማ ከአንተ ጋር ለምን ይኖራል?" አለው። 6ስለዚህ በዚያን ቀን አንኩስ ጺቅላግን ሰጠው፤ እስከዛሬ ድረስ ጺቅላግ የይሁዳ ነገሥታት የሆነችው ለዚህ ነው። 7ዳዊት በፍልስጥኤም ምድር የኖረበት ቀን ሲቆጠር አንድ ዓመት ከአራት ወር ሆነው።8ዳዊትና ሰዎቹ ጌሹራውያንን፥ ጌርዛውያንን እና አማሌቃውያንን በመውረር የተለያዩ ቦታዎችን አጠቁ፤ እነዚህ ሕዝቦች እስከ ሱርና እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። እነርሱም ከጥንት ጀምሮ በዚያ ምድር ይኖሩ ነበር። 9ዳዊትም ምድሪቱን መታ፥ ወንዱንም ሆነ ሴቱን በሕይወት አልተወም፤ በጎችን፥ በሬዎችን፥ አህዮችን፥ ግመሎችን እና ልብሶችን ወሰደ፤ ተመልሶም እንደገና ወደ አንኩስ መጣ።10አንኩስ፥ "ዛሬ በማን ላይ ወረራ ፈጸማችሁ?" ብሎ ይጠይቅ ነበር፥ ዳዊትም፥ "በይሁዳ ደቡብ ላይ" ወይም "በደቡብ ይረሕምኤላውያን ላይ" ወይም "በደቡብ ቄናውያን ላይ" ብሎ ይመልስለት ነበር።11"ስለዚህ ስለ እኛ፥ 'ዳዊት እንዲህና እንዲህ አደረገ' ለማለት እንዳይችሉ" ብሎ ነበርና ዳዊት ወደ ጌት ይዞ ለመምጣት በማሰብ ወንድ ወይም ሴት በሕይወት አያስቀርም ነበር። በፍልስጥኤም አገር በኖረበት ጊዜ ሁሉ ያደረገው እንደዚህ ነበር። 12አንኩስም፥ "የራሱ የሆነው የእስራኤል ሕዝብ አምርሮ እንዲጠላው አድርጓል፤ ስለዚህ ለዘላለም አገልጋዬ ይሆናል“ ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።
1በዚያም ዘመን ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ሠራዊታቸውን ሁሉ በአንድ ላይ ሰበሰቡ። አንኩስም ዳዊትን፥ “አንተና ሰዎችህ ያለ ጥርጥር ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ እንደምትወጡ ዕወቅ” አለው። 2ዳዊትም አንኩስን፥ “ስለዚህ አገልጋይህ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ታያለህ” አለው። አንኩስም ዳዊትን፥ “ስለዚህ እኔም በቋሚነት የግል ጠባቂዬ አደርግሃለሁ" አለው።3ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤል ሁሉ አልቅሰውለት በከተማው በራማም ቀብረውት ነበር። ሳኦል ከሙታንና ከመናፍስት ጋር የሚነጋገሩትን ከምድሪቱ አጥፍቶ ነበር። 4ፍልስጥኤማውያን በአንድነት ተሰባስበው በመምጣት ሱነም ላይ ሰፈሩ፤ ሳኦልም እስራኤልን በሙሉ በአንድነት ሰብስቦ ጊልቦዓ ላይ ሰፈረ።5ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ባየ ጊዜ ፈራ፥ ልቡም እጅግ ተንቀጠቀጠ። 6ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜም እግዚአብሔር በህልም፥ ወይም በኡሪም፥ ወይም በነቢያት አልመለሰለትም። 7ከዚያም ሳኦል አገልጋዮቹን፥ "ወደ እርሷ ሄጄ ምክሯን እንድጠይቅ ከሞተ ጋር መነጋገር እችላለሁ የምትል ሴት ካለች ፈልጉልኝ" አላቸው። አገልጋዮቹም፥ "ከሞተ ጋር መነጋገር እችላለሁ የምትል ሴት በዓይንዶር አለች" አሉት።8ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ ራሱን ቀይሮ ከሁለት ሰዎች ጋር ሄደ፤ እነርሱም በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄዱ። እርሱም፥ "የምነግርሽን ሰው አስነሥተሽ ከሞተው ጋር በመነጋገር እንድትጠነቁይልኝ እለምንሻለሁ" አላት። 9ሴቲቱም፥ "ሳኦል ከሙታንና ከመናፍስት ጋር የሚነጋገሩትን ከምድሪቱ በማጥፋት ያደረገውን ታውቃለህ። ታዲያ እንድሞት ለሕይወቴ ወጥመድ የምታዘጋጀው ለምንድነው?" አለችው። 10ሳኦልም በእግዚአብሔር ስም ምሎላት፥ "ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ጉዳይ ምንም ቅጣት አይደርስብሽም” አላት።11ሴቲቱም፥ “ማንን ላስነሣልህ?” አለችው። ሳኦልም፥ “ ሳሙኤልን አስነሽልኝ” አላት። 12ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኻ ሳኦልን፥ "አንተ ራስህ ሳኦል ሆንህ ሳለ ለምን አታለልከኝ?" አለችው።13ንጉሡም፥ "አትፍሪ፤ ምንድነው ያየሽው?" አላት። ሴቲቱም ሳኦልን፥ "አንድ መንፈስ ከምድር ሲወጣ አያለሁ" አለችው። 14እርሱም፥ “ምን ይመስላል?” አላት። እርሷም፥ "አንድ ካባ የለበሰ ሽማግሌ እየመጣ ነው" አለችው። ሳኦልም ሳሙኤል እንደሆነ ዐወቀ፥ አክብሮቱን ለማሳየትም በምድር ላይ ሰገደለት።15ሳሙኤልም ሳኦልን፥ "እኔን በማስነሣት የምታስቸግረኝ ለምንድነው?" አለው። ሳኦልም፥ "በጣም ተጨንቄአለሁ፥ ፍልስጥኤማውያን ጦርነት ዐውጀውብኛል፥ እግዚአብሔር ትቶኛል፥ በሕልምም ሆነ በነቢያት አይመልስልኝም። ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንድታስታውቀኝ ለዚህ ነው የጠራሁህ" ብሎ መለሰለት።16ሳሙኤልም እንዲህ አለው፥ "ታዲያ እግዚአብሔር ከተወህና ጠላት ከሆነህ የምትጠይቀኝ ምንድነው? 17እግዚአብሔር አደርገዋለሁ ብሎ የነገረህን እርሱን ነው ያደረገብህ። እግዚአብሔር መንግሥትን ከእጅህ ቀዶ ለሌላ ሰው፥ ለዳዊት ሰጥቶታል።18የእግዚአብሔርን ድምፅ ስላልታዘዝክና ጽኑ ቁጣውን በአማሌቅ ላይ ስላልፈጸምክ ዛሬ ይህንን አድርጎብሃል። 19በተጨማሪም እግዚአብሔር አንተንና እስራኤልን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል። አንተና ልጆችህ ነገ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ። በተጨማሪም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል።“20ከዚያም ሳኦል በሳሙኤል ቃል ምክንያት እጅግ ስለፈራ ወዲያውኑ በቁመቱ ሙሉ በምድር ላይ ወደቀ። በዚያ ቀንና ሌሊት ምግብ ስላልበላ ምንም አቅም አልነበረውም። 21ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ እጅግ መጨነቁን አየች፥ እርሷም እንዲህ አለችው፥ "እኔ አገልጋይህ ቃልህን ሰምቻለሁ፤ ሕይወቴን በእጄ ላይ ጥዬ የነገርከኝን ቃል ሰምቻለሁ።22አሁንም እንግዲህ አንተም ደግሞ የእኔን የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማና ጥቂት ምግብ እንዳቀርብልህ እለምንሃለሁ። መንገድህን ለመሄድ ዐቅም እንድታገኝ ብላ። 23ሳኦል ግን፥ "አልበላም" በማለት እንቢ አለ። ነገር ግን አገልጋዮቹ ከሴቲቱ ጋር በመሆን ለመኑት፥ እርሱም ቃላቸውን ሰማ። ስለዚህ ከምድር ላይ ተነሥቶ ዐልጋ ላይ ተቀመጠ።24ሴቲቱም በቤቷ የደለበ ጥጃ ነበራት፤ ፈጥና አረደችው፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰችው፤ ቂጣ አድርጋም ጋገረችው። 25እርሷም በሳኦልና በአገልጋዮቹ ፊት አቀረበችላቸው፥ እነርሱም በሉ። ከዚያም በዚያው ሌሊት ተነሥተው ሄዱ።
1ፍልስጥኤማውያንም ሰራዊታቸውን ሁሉ አፌቅ ላይ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። 2የፍልስጥኤማውያኑ መሳፍንት በመቶዎችና በሺዎች እየሆኑ አለፉ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋር በደጀንነት አለፉ።3ከዚያም የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?" አሉ። አንኩስም ለሌሎቹ የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "ይህ በእነዚህ ቀናት ሁሉ ከእኔ ጋር የነበረው፥ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ ዳዊት አይደለምን? ደግሞም በእነዚህ ዓመታት ሁሉ ወደ እኔ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁበትም” አላቸው።4ነገር ግን የፍልስጥኤም መሳፍንት በእርሱ ላይ ተቆጥተው፥ “ያንን ሰው ወደ ሰጠኸው ወደ ስፍራው እንዲመለስ አሰናብተው፥ በውጊያው ውስጥ ጠላት እንዳይሆንብን ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አትላከው። ይህ ሰው ከጌታው ጋር ሰላምን የሚፈጥረው በምንድነው? የሰዎቻችንን አንገት በመቁረጥ አይደለምን?5ይህ በዘፈን እየተቀባበሉ፥ 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ" ያሉለት ዳዊት አይደለምን?" አሉት።6ከዚያም አንኩስ ዳዊትን ጠርቶ፥ "ሕያው እግዚአብሔርን! አንተ ጥሩ ሰው ነህ፥ በእኔ አመለካከት በሰራዊቱ ውስጥ መውጣትህና መግባትህ መልካም ነው፤ ወደ እኔ ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬው ቀን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁብህም። ይሁን እንጂ መሳፍንቱ አልደገፉህም። 7ስለዚህ አሁን የፍልስጥኤም መሳፍንት ቅር እንዳይሰኙ ተመለስና በሰላም ሂድ" አለው።8ዳዊትም አንኩስን፥ “ግን ምን አድርጌአለሁ፥ እንዳልሄድና ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ በእነዚህ በፊትህ በኖርኩባቸው ቀናት በአገልጋይህ ላይ ምን አግኝተህብኛል?” አለው። 9አንኩስም ለዳዊት፥ “አንተ በእኔ ዕይታ ነቀፌታ እንደማይገኝበት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ ይሁንና የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ 'ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አይሄድም' ብለዋል።10ስለዚህ ከአንተ ጋር ከመጡት ከጌታህ አገልጋዮች ጋር ማልዳችሁ ተነሡ፤ ማልዳችሁ ተነሡና ሲነጋላችሁ ሂዱ" ብሎ መለሰለት። 11ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ በጠዋት ለመሄድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ለመመለስ ማልደው ተነሡ። ፍልስጥኤማውያን ግን ወደ ኢይዝራኤል ወጡ።
1እንዲህም ሆነ፥ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ በመጡ ጊዜ አማሌቃውያን በኔጌቭና በጺቅላግ ላይ ወረራ ፈጽመው ነበር። እነርሱም ጺቅላግን መቱ፥ አቃጠሏትም፥ 2ሴቶችንና በውስጧ የነበረውን ትንሽና ትልቅ ሁሉ ማረኩ። ይዘዋቸው መንገዳቸውን ሄዱ እንጂ አንዱንም አልገደሉም።3ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ ከተማይቱ በእሳት ተቃጥላ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ተማርከው ተወስደው ነበር። 4ከዚያም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ለማልቀስ ኃይል እስከማይኖራቸው ድረስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።5ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች፥ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያ ተማርከው ነበር። 6የሕዝቡም ሁሉ መንፈስ፥ እያንዳንዱም ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ስላዘነ በድንጋይ ሊወግሩት ይነጋገሩ ስለነበር ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አበረታ።7ዳዊትም የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፥ "ኤፉዱን ወደዚህ እንድታመጣልኝ እለምንሃለሁ" አለው። አብያታር ኤፉዱን ለዳዊት አመጣለት። 8ዳዊትም ምሪት ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር፥ "ይህንን ወራሪ ብከተል እደርስበታለሁ?" ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም፥ "ተከተላቸው፥ ያለጥርጥር ትደርስባቸዋለህ፥ ሁሉንም ነገር ታስመልሳለህ" ብሎ መለሰለት።9ስለዚህ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ ከእነርሱ ወደ ኋላ የቀሩት ወደሚቆዩበት ወደ ባሦር ወንዝ መጡ። 10ነገር ግን ዳዊት ከአራት መቶ ሰዎች ጋር መከታተሉን ቀጠለ፤ ሁለት መቶዎቹ በጣም ስለ ደከሙ የባሦርን ወንዝ መሻገር አልቻሉምና ወደ ኋላ ቀሩ።11እነርሱም በሜዳው ላይ አንድ ግብፃዊ አገኙና ወደ ዳዊት አመጡት፤ ምግብ ሰጡትና በላ፥ እንዲጠጣም ውሃ ሰጡት፤ 12ደግሞም ከበለስ ጥፍጥፍ ቁራጭና ሁለት የወይን ዘለላ ሰጡት። ለሦስት ቀንና ሌሊት ምንም ምግብ አልበላም፥ ውሃም አልጠጣም ነበርና በበላ ጊዜ እንደገና ብርታት አገኘ።13ዳዊትም፥ "አንተ የማን ነህ? ከየትስ ነው የመጣኸው?" አለው። እርሱም፥ "እኔ የአማሌቃዊ አገልጋይ፥ ግብፃዊ ወጣት ነኝ፤ ከሦስት ቀናት በፊት ታምሜ ስለነበር ጌታዬ ትቶኝ ሄደ። 14እኛም በከሊታውያን ኔጌቭ፥ የይሁዳ በሆነው ምድርና በካሌብ ኔጌቭ ላይ ወረራ ፈጸምን፥ ጺቅላግንም አቃጠልናት“ አለው።15ዳዊትም፥”ወደዚህ ወራሪ አካል መርተህ ልታወርደኝ ትፈቅዳለህ? “ አለው። ግብፃዊውም፥”እንዳትገድለኝ ወይም በጌታዬ እጅ ላይ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ ወደ ወራሪው አካል መርቼ አወርድሃለሁ“ አለው።16ግብፃዊው ዳዊትን እየመራው ወደ ታች ባወረደው ጊዜ፥ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያን ምድርና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ምርኮ ሁሉ የተነሣ እየበሉና እየጠጡ፥ እየጨፈሩም በምድሩ ሁሉ ተበትነው ነበር። 17ዳዊትም ደንገዝገዝ ሲል ጀምሮ እስከ ማግስቱ ምሽት ድረስ መታቸው። በግመሎች ተቀምጠው ከሸሹት ከአራት መቶ ወጣቶች በስተቀር አንድም ሰው አላመለጠም።18ዳዊት አማሌቃውያን ወስደዋቸው የነበሩትን ሁሉ አስመለሰ፤ ሁለቱን ሚስቶቹንም አዳነ። 19ትንሽ ይሁን ትልቅ፥ ወንዶች ልጆች ይሁኑ ሴቶች ልጆች፥ ምርኮም ይሁን ወራሪዎቹ ለራሳቸው ከወሰዱት ማንኛውም ነገር አንዱም አልጠፋም። ዳዊት ሁሉን ነገር አስመለሰ። 20ዳዊትም ሰዎቹ ከሌሎች ከብቶች ፊት ይነዷቸው የነበሩትን የበጉን፥ የፍየሉንና የላሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ። እነርሱም፥ "ይህ የዳዊት ምርኮ ነው" አሉ።21ዳዊት ሊከተሉት እጅግ ደክሟቸው በባሦር ወንዝ አጠገብ እንዲቆዩ ወደተደረጉት ወደ ሁለት መቶዎቹ ሰዎች መጣ። እነዚህ ሰዎች ዳዊትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመገናኘት ወጡ። ዳዊት ወደ እነዚህ ሰዎች በመጣ ጊዜ ሰላምታ ሰጣቸው። 22ከዚያም ከዳዊት ጋር ሄደው በነበሩት ሰዎች መካከል ክፉዎችና የማይረቡት ሁሉ፥”እያንዳንዱ ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ ከመሄድ በስተቀር እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር ስላልሄዱ፥ ካስመለስነው ምርኮ ምንም አንሰጣቸውም“ አሉ።23ከዚያም ዳዊት፥”ወንድሞቼ ሆይ፥ እግዚአብሔር በሰጠን ነገር እንዲህ ልታደርጉ አይገባም። እርሱ ጠበቀን፥ በእኛ ላይ የመጡትንም ወራሪዎች በእጃችን ላይ አሳልፎ ሰጠን። 24በዚህ ጉዳይ ማን ይሰማችኋል? ወደ ጦርነት የሄደው የየትኛውም ሰው ድርሻ ስንቅና ትጥቅ ከጠበቀ ከየትኛውም ሰው ድርሻ ጋር እኩል ይሆናል፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ" አላቸው። 25ዳዊት ለእስራኤል ደንብና ሥርዓት ስላደረገው፥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ እንደዚሁ ሆነ።26ዳዊት ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ፥ ከምርኮው ጥቂቱን፥ "ይህ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ካገኘነው ምርኮ ለእናንተ የተላከ ስጦታ ነው“ብሎ ለይሁዳ ሽማግሌዎችና ለወዳጆቹ ላከላቸው። 27የላከውም፥ በቤቴል፥ በደቡብ ራሞት፥ በየቲር፥ 28በአሮኤር፥ በሢፍሞት፥ በኤሽትሞዓ ለነበሩ ሽማግሌዎች ነበር።29እንዲሁም በራካል፥ በይረሕምኤላውያንና በቄናውያን ከተሞች፥ 30በሔርማ፥ በቦራሣን፥ በዓታክ፥ 31በኬብሮን፥ እንዲሁም ዳዊት ራሱና ሰዎቹ አዘውትረው ይሄዱባቸው በነበሩ ስፍራዎች ሁሉ ለሚኖሩ ሽማግሌዎች ላከላቸው።
1ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ተዋጉ። የእስራኤል ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ በጊልቦዓ ተራራ ላይም ተገድለው ወደቁ። 2ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በቅርብ ርቀት ተከተሏቸው። ፍልስጥኤማውያንም ልጆቹን ዮናታንን፥ አሚናዳብንና ሜልኪሳን ገደሏቸው። 3ውጊያው በሳኦል ላይ በረታበት፥ ቀስተኞችም አገኙት። በእነርሱም ምክንያት በጽኑ ሕመም ላይ ነበር።4ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥”ሰይፍህን ምዘዝና ውጋኝ። አለበለዚያ፥ እነዚህ ያልተገረዙ መጥተው ይሳለቁብኛል“ አለው። 5ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበረ እምቢ እለ። ስለዚህ ሳኦል የራሱን ሰይፍ ወስዶ በላዩ ላይ ወደቀበት። ጋሻ ጃግሬው ሳኦል መሞቱን ባየ ጊዜ እርሱም ደግሞ ሰይፉ ላይ ወድቆ አብሮት ሞተ። 6ስለዚህ ሳኦል፥ ሦስቱ ወንዶች ልጆቹና ጋሻ ጃግሬው ሞቱ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ በአንድ ቀን ሞቱ።7ከሸለቆው በወዲያኛው ወገን የነበሩትና ከዮርዳኖስ በላይ የነበሩት የእስራኤል ሰዎች፥ የእስራኤል ሰዎች መሸሻቸውን፥ ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ትተው ሸሹ፥ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው። 8በማግስቱ እንዲህ ሆነ፥ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ሰዎች ትጥቅ ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።9እነርሱም ራሱን ቆረጡት፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈፉት፥ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ሁሉ ለጣዖት መቅደሶቻቸውና ለሕዝቡ ወሬውን እንዲያደርሱ መልዕክተኞችን ላኩ። 10የጦር መሣሪያውን በአስታሮት መቅደስ ውስጥ አስቀመጡት፥ ሬሳውንም በቤትሳን ከተማ የግንብ አጥር ላይ አንጠለጠሉት።11የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ 12ተዋጊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ተጉዘው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከአጥሩ ላይ ወሰዱ። ወደ ኢያቢስ ሄዱ፥ በዚያም አቃጠሏቸው። 13ከዚያም አጥንቶቻቸውን በመውሰድ በኢያቢስ ባለው የአጣጥ ዛፍ ሥር ቀበሯቸው፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።
1ሳዖል ከሞተ በኋላ፣ ዳዊት በአማሌቃውያን ላይ ጥቃት ከማድረስ በመመለስ በጺቅላግ ሁለት ቀን ቆየ፡፡ 2በሦስተኛው ቀን የተቀዳደደ ልብስ የለበሰ፣ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ፡፡ ወደ ዳዊት እንደ ደረሰም ወደ መሬት ለጥ ብሎ ሰገደለት፡፡3ዳዊትም “ከወዴት መጣህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “ከእስራኤላውያን ሰፈር አምልጬ የመጣሁ ነኝ” ሲል መለሰ፡፡ 4ዳዊትም፣ “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው፡፡ እርሱም “ሰዎቹ ከጦርነት ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል ደግሞም ሞተዋል፤ ሳዖልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ፡፡ 5ዳዊትም ለወጣቱ፤ “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት አወቅህ?” ሲል ጠየቀው፡፡6ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ፣ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከታትለው ደረሱበት፤ 7ወደ ኋላውም ዞር ሲል እኔን ስላየ ጠራኝ፤ እኔም ‘እነሆኝ አለሁ’ አልኩት፡፡8እርሱም፣ ‘አንተ ማን ነህ?’ ሲል ጠየቀኝ፡፡ አኔም፣ ‘አማሌቃዊ ነኝ’ ብዬ መለስሁለት፡፡ 9እርሱም አለኝ ‘እኔ በታላቅ ስቃይ ውስጥ እገኛለሁ፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ፡፡ 10ስለሆነም፣ ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፤ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፣ ለጌታዬ አምጥቻለሁ፡፡” አለው፡፡11ከዚያም ዳዊት ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ፡፡ 12የወደቁት በሰይፍ ነበርና ለሳኦል ለልጁ ለዮናታንና ለእግዚአብሔር ሕዝብ አዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾ፡፡ 13ዳዊትም ወጣቱን ሰውዬ፣ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “በአገሪቱ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር አማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ፡፡14ዳዊትም፣ “እግዚአብሔር የቀባውን ንጉሥ በገዛ እጅህ ስትገድል ለምን አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው፡፡ 15ዳዊትም ከጎልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፣ “ግደለው” አለው፤ ጎልማሳው ሰው ሄዶ መታው፣ አማሌቃዊውም ሞተ፡፡ 16ከዚያም ዳዊት ለሞተው አማሌቃዊ፣ “‘እግዚአብሔር የቀባውን ገድያለሁ’ ስትል አፍህ መስክሮብሃልና ደምህ በራስህ ላይ ነው” አለው፡፡17ከዚያም ዳዊት ለሳዖልና ለልጁ ለዮናታን የሚከተለውን የሐዘን እንጉርጉሮ አንጎራጎረ፡፡ 18እንዲሁም የቀስት እንጉርጉሮ የተባለውን ለይሁዳ ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ ይህም በያሸር መጽሐፍ ተጽፎአል፡፡ 19“እስራኤል ሆይ፣ ክብርህ ሞቶአል፣ በተራሮችህ ላይ ተገድሎአል! ኃያላኑ እንዴት ወደቁ! 20የፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፣ ያልተገረዙት ሴት ልጆች ፌሽታ እንዳያደርጉ ይህን በጌት አትናገሩ፣ በአስቆሎናም መንገዶች አታውጁት፡፡21እናንት የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ ጠል አያረስርሳችሁ፣ ዝናብም አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች በዚያ አይኑሩ፤ በዚያ የኃያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፣ የሳዖል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም፡፡ 22ከሞቱት ሰዎች ደም፣ ከኃያላኑም ገላ የዮናታን ቀስት ተመልሶ አልመጣም፤ የሳዖልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰም፡፡23ሳዖልና ዮናታን በሕይወት እያሉ የሚዋደዱና ግርማ ያላቸው ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ፡፡ 24እናንተ የእስራኤል ቆነጃጅት ሆይ፤ ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ ፤ ልብሶቻችሁንም በወርቀ-ዘቦ ላስጌጠላችሁ ለሳዖል አልቅሱለት፡፡25ኃያላን እንዴት እንዲህ በጦርነት መካከል ወደቁ! ዮናታን ከፍ ባሉ ስፍራዎቻችሁ ላይ ሞቶአል፡፡ 26ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ አዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበር፤ ከሴት ፍቅርም የላቀ ነበር፡፡ 27ኃያላን እንዴት ወደቁ፤ የጦር መሣሪዎቹስ እንዴት ከንቱ ሆኑ!”
1ከዚህ በኋላ ዳዊት፤ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፣ እግዚአብሔርም፣ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት፡፡ 2ስለዚህ ዳዊት ከሁለቱ ሚስቶቹ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ ጋር ሄደ፡፡ ጠየቀ፡፡ እግዚአብሔርም፣ “ውጣ” ብሎ መለሰለት፡፡ ዳዊትም፣ “ወደ የትኛው ከተማ ልሂድ?” ብሎ ጠየቀ፡፡ 3ዳዊት ቤተ ሰቦቻቸውን ይዘው የመጡትን ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን ይዟቸው መጣ፡፡4ከዚያ በኋላም የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጥተው ዳዊትን በይሁዳ ቤት ላይ ንጉሥ አድርገው ቀቡት፡፡ የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ሳኦልን እንደቀበሩት ለዳዊት ነገሩት፡፡ 5ስለዚህ ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች መልእክተኞች ልኮ እንደዚህ አላቸው፣ “ጌታችሁን ሳኦልን በመቅበር ይህንን በጎነት ስላሳያችሁ በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ናችሁ፡፡6አሁንም እግዚአብሔር ጽኑ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይገለጥላችሁ፤ እናንተ ይህን ስላደረጋችሁ እኔም እንደዚሁ በጎ ነገር አደርግላችኋለሁ፡፡ 7እንግዲህ እጆቻችሁ ይጠንክሩ፣ በርቱ፤ ጌታችሁ ሳኦል ሞቶአልና፣ የይሁዳ ቤትም እኔን ቀብተው በላያቸው አንግሠውኛል፡፡”8የሳኦል ሠራዊት አዛዥ፣ የኔር ልጅ አብኔር ግን የሳዖልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ መሃናይም አሻገረው፤ 9ኢያቡስቴንም በገለዓድ፣ በአሴር፣ በኢይዝራኤል፣ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ ላይ አነገሠው፡፡10የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በእስራኤል ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበረ፣ ሁለት ዓመትም ገዛ፡፡ የይሁዳ ቤት ግን ዳዊትን ተከተለ፡፡ 11ዳዊት በኬብሮን በይሁዳ ቤት ላይ ንጉሥ የሆነበት ዘመን ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበር፡፡12የኔር ልጅ አብኔርና የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ አገልጋዮች ከመሃናይም ተነሥተው ወደ ገባዖን ሄዱ፡፡ 13እነርሱንም የጽሩይ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች በገባዖን ኩሬ አጠገብ ተገናኟቸው፤ በዚያም አንዱ ወገን በኩሬው ወዲህ ማዶ፣ ሌላው ወገን ደግሞ በኩሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ፡፡14አበኔርም ለኢዮአብ፣ “ጎልማሶች ይነሡና እርስ በርሳቸው ይጋጠሙ” አለው፡፡ ኢዮአብም፣ “እሺ፣ ይነሡ” አለ፡፡ 15ከዚያ በኋላም ከብንያምና ከሳኦል ልጅ ከኢየቡስቴ ወገን አሥራ ሁለት፣ የዳዊት አገልጋዮች ከሆኑት ደግሞ አሥራ ሁለት ጎልማሶች ተነሥተው በአንድነት ተሰባሰቡ፡፡16እያንደንዱም ሰው የባላጋራውን ራስ በመያዝ ሰይፉን በጎኑ እየሻጠበት ተያይዘው ወደቁ፡፡ ስለዚህ በገባዖን ያለው ያ ስፍራ በዕብራይስጥ ‘ሐልቃት አዙሪም’ ወይም ‘የሰይፍ ምድር’ ተባለ፡፡ 17በዚያን ዕለት ጦርነቱ እጅግ ከባድ ነበር፣ አበኔርና የእስራኤል ሰዎች በዳዊት አገልጋዮች ድል ሆኑ፡፡18ሦስቱ የጽሩይ ወንዶች ልጆች ኢዮአብ፣ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ፡፡ አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበር፤ 19አሣሄል በየትኛውም አቅጣጫ ዞር ሳይል አበኔርን በቅርበት ተከታተለው፡፡20አበኔርም ወደ ኋላው ዞር ብሎ በመመልከት፣ “አሣሄል አንተ ነህን?” አለው፡፡ እርሱም፣ “እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት፡፡ 21አበኔርም፣ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጎልማሳ ይዘህ መሣሪያውን ንጠቀው” አለው፤ አሣሄል ግን እርሱን መከታተሉን አልተወም ነበር።22እንደገናም አቤኔር “እኔን መከታተል ብትተው ይሻልሃል፤ እኔስ ለምን ከመሬት ጋር ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት ቀና ብዬ እንዴት አያለሁ?” አለው። 23አሣሄል ግን ዘወር ለማለት እምቢ አለ፤ ስለዚህ አብኔር በጦሩ ጫፍ አከላቱን ወጋው፤ ጦሩም በአካሉ በሌላው ወገን ዘልቆ ወጣ፤ አሣሄልም ወደቀ፣ በዚያ ስፍራም ሞተ፡፡ ስለሆነም አሣሄል ወደ ወደቀበት ይመጣ የነበረ እያንዳንዱ ሰው በዚያ ስፍራ ሲደርስ ይቆም ነበር፡፡24ኢዮአብና አቢሳ ግን አበኔርን አሳደዱት፤ ፀሐይም በምትጠልቅበት ጊዜ ወደ ገባዖን ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ከጋይ አጠገብ ወዳለው ወደ አማ ኮረብታ ደረሱ፡፡ 25የብንያም ሰዎችም ከአበኔር በስተኋላ ተሰብስበው በተራራው ጫፍ ላይ ቆሙ፡፡26ከዚያ በኋላም አበኔር ኢዮአብን ጠርቶ፣ “ሰይፍ ለዘላለም ማጥፋት አለበትን? ውጤቱ በመጨረሻ መራራ መሆኑን አንተ አታውቅምን? ሰዎችህ ወንድሞቻቸውን ማሳደድ እንዲያቆሙ የማትነግራቸውስ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አለው፡፡ 27ኢዮአብም ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን፣ ይህን ባትናገር ኖሮ፣ ወታደሮቼ እስኪነጋ ድረስ ወንድሞቻቸውን ባሳደዱ ነበር” ብሎ መለሰ፡፡28ስለዚህ ኢዮአብ ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ ሰዎቹም ሁሉ ቆሙ፤ ከዚያ በኋላም እስራኤልን አላሳደዱም፣ መዋጋታቸውንም አልቀጠሉም፡፡ 29አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ በዓረባ በኩል አለፉ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረው በማግሥቱ ጥዋት ሲጓዙ ቆይተው ከዚያ በኋላ ወደ መሃናይም ደረሱ፡፡30ኢዮአብም አበኔር ከማሳደድ ተመለሰ፡፡ አሣሄልና ከዳዊት ወታደሮች አሥራ ዘጠኙ የጎደሉባቸውን ሰዎቹን ሁሉ ሰበሰበ፡፡ 31የዳዊት ሰዎች ግን ከአበኔር ጋር ከነበሩት ሦስት መቶ ሥልሳ ብንያማውያንን ገድለዋል፡፡ 32ከዚያ በኋላም አሣሄልን ከወደቀበት አንሥተው ቤተ ልሔም በነበረው በአባቱ መቃብር ቀበሩት፡፡ ኢዮአብና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሠው ኬብሮን ሲደርሱ ሌሊቱ ነጋላቸው፡፡
1በሳዖል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየ ጦርነት ነበረ፡፡ ዳዊት እየበረታ ሲሄድ የሳዖል ቤት ግን እየደከመ ሄደ፡፡2በኬብሮን ለዳዊት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፡፡ የበኩር ልጁ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበር፡፡ 3ሁለተኛው፣ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ የተወለደው ኪልአብ ነበር፡፡ ሦስተኛ የነበረው፣ አቤሴሎም የጌሹር ንጉሥ ከነበረው ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው ነበር፡፡4አራተኛው፣ ልጁ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፣ አምስተኛው፣ ከአቢጣል የተወለደው ሰፋጥያ፣ 5ስድስተኛው፣ ከዳዊት ሚስት ከዔግላ የተወለደው ይትርኃም ነበር፤ እነዚህ ወንዶች ልጆች ለዳዊት በኬብሮን የተወለዱለት ነበሩ፡፡6የሳኦል ቤትና የዳዊት ቤት በጦርነት ላይ በነበሩበት ጊዜ አበኔር በሳዖል ቤት ራሱን ጠንካራ አድርጎ ነበር፡፡ 7ሳኦል የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ የተባለች ቁባት ነበረችው፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፣ “ለምንድን ነው ከአባቴ ቁባት ጋር የተኛኸው?” አለው፡፡8አብኔርም በዚያን ጊዜ በኢያቡስቴ ንግግር እጅግ ስለተቆጣ እንዲህ አለ፣ “እኔ ለይሁዳ የተሰጠሁ የውሻ ራስ ነኝን? አንተን ለዳዊት አሳልፌ ባለመስጠቴ እኔ ዛሬ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹና ለወዳጆቹ ታማኝነቴን አሳይቻለሁ፤ ይህም ሆኖ ሳለ አንተ ከዚህች ሴት ጋር በፈጸምሁት ነገር ትከሰኛለህን?9እግዚአብሔር ለዳዊት መንግሥትን ከሳዖል ቤት አውጥቶ 10ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ዙፋኑን እንደሚያጸና በመሐላ የገባለት ተስፋ እንዲፈጸም ባለደርግ እግዚአብሔር በእኔ በአበኔር ላይ ክፉ ያድርግብኝ ከዚያ የባሰም ያምጣብኝ፡፡” 11ኢያቡስቴም አበኔርን ፈርቶት ስለነበረ አንዲት ቃል ስንኳ ሊመልስለት አልቻለም፡፡12ከዚያም አበኔር ለዳዊት፣ “ይህች ምድር የማን ናት? ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፣ እነሆ፣ እስራኤል ሁሉ ወደ አንተ እንዲመለሱ ለማድረግ እጄ ከአንተ ጋር እንደሆነ ትመለከታለህ” ብለው እንዲነግሩለት መልእክተኞችን ላከ፡፡ 13ዳዊትም፣ “መልካም ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ነገር ግን ከአንተ የምሻው አንድ ነገር፤ ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜ የሳዖልን ሴት ልጅ ሜልኮልን ይዘህልኝ ካልመጣህ ፊቴን ማየት እንደማትችል እንድታውቅ ነው፡፡” አለው፡፡14ከዚያም ዳዊት፣ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልእክተኞች ላከበት፡፡ 15ስለዚህም ኢያቡስቴ መልእክተኛ ልኮ፣ ሜልኮልን ከባሏ ከሌሳ ልጅ ከፍልጢኤል ወሰዳት፡፡ 16ባሏም እስከ ብራቂም ከተማ ድረስ እያለቀሰ ተከትሎአት ሄደ፤ ከዚያም አበኔር፣ “አሁን፣ ወደ ቤትህ ተመለስ” አለው፡፡ ስለዚህም ተመለሰ፡፡17አበኔር ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር እንደዚህ በማለት ተመካከረ፤ “ባለፈው ጊዜ ዳዊትን በላያችሁ ለማንገሥ ሞክራችሁ ነበር፤ 18እግዚአብሔር ለዳዊት፣ ‘በባሪያዬ በዳዊት ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅና ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ እታደጋቸዋለሁ’ ብሎ ስለተናገረው፣ ይህን አሁኑኑ አድርጉት፡፡”19አበኔርም ራሱ ሄዶ ለብንያማውያን ይህንን ነገራቸው፤ ከዚያም በኋላ አበኔር እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለገውን ሁሉ በመግለጽ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ፡፡ 20ከሃያ ሰዎች ጋር አበኔር በዳዊት ፊት ለመቅረብ ወደ ኬብሮን በመጡ ጊዜ ዳዊት ግብዣ አደረገላቸው፡፡21አበኔርም ለዳዊት፣ “ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያደርጉና በፈለግኸውም ሁሉ ላይ እንድትገዛ ተነሥቼ እስራኤልን ሁሉ ወደ አንተ እሰበስባለሁ” በማለት ገለጸለት፡፡ ዳዊትም አሰናበተው፤ አበኔርም በሰላም ሄደ፡፡22ከዚያ በኋላ የዳዊትና የኢዮአብ ወታደሮች ከዘመቻ ሲመለሱ ብዙ ምርኮ ይዘው መጡ፡፡ ዳዊት አሰናብቶት ስለነበረና እርሱም በሰላም ስለሄደ አበኔር በኬብሮን ከዳዊት ጋር አልነበረም፡፡ 23ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ሁሉ እዚያ እንደ ደረሱ፣ “የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሡ መጣ ንጉሡም አሰናበተው እርሱም በሰላም ሄደ” ብለው ለኢዮአብ ነገሩት፡፡24ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ገብቶ እንዲህ አለ፣ “ምን ማድረግህ ነው? እነሆ አበኔር መጥቶልህ ለምን ይሄድ ዘንድ አሰናበትኸው? 25የኔር ልጅ አበኔር የመጣው አንተን ሊያታልልህ፣ ዕቅድህን ለማወቅና የምታደርገውን ማንኛውንም ነገር ለማጥናት እንደሆነ አታውቅምን?” 26ኢዮአብ ከዳዊት ዘንድ በወጣ ጊዜ አበኔር ዘንድ መልእክተኞችን ላከ እነርሱም ከሴይር የውሃ ጉድጓድ አጠገብ መለሱት፡፡ ዳዊት ግን ይህን አላወቀም ነበር፡፡27አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በቆይታ ለማነጋገር ወደ ቅጥሩ ዞር አደረገው በዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንገድ የወንድሙን የአሣሄልን ደም ተበቀለ፡፡28ዳዊት ይህንን በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ፣ “እኔም ሆንሁ መንግሥቴ ከኔር ልጅ ከአብኔር ደም በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ንጹሕ ነን፤ 29ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም አሠቃቂ የቆዳ በሽታ ያለበት፣ በምርኩዝ የሚሄድ አንካሳ፣ ወይም በሰይፍ የሚገደል ወይም ምግብ አጥቶ የሚራብ ሰው ከኢዮአብ ቤት አይታጣ፡፡” 30ስለዚህ ወንድማቸውን አሣሄልን በገባዖን በተደረገው ጦርነት ገድሎባቸው ነበርና፣ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ አበኔርን ገደሉት፡፡31ዳዊት ለኢዮአብና አብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፣ “ልብሳችሁን ቀዳችሁ፣ ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር አስከሬን ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ንጉሥ ዳዊትም አስከሬኑን ከሚያጅበው ሕዝብ ጋር አብሮ ይሄድ ነበር፡፡ 32አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም በአበኔር መቃብር ላይ ጮኾ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ፡፡33ንጉሡም በሐዘን እንጉርጉሮ ለአበኔር አለቀሰ፣ “አበኔር እንደ ተራ ሰው ሊሞት ይገባው ነበር? 34እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰዎች በግፈኞች ፊት እንደሚወድቁ አንተም እንደዚሀ ወደቅህ፡፡” ሕዝቡም ሁሉ እንደገና አለቀሱለት፡፡35ገና ቀን ሳለ ምግብ እንዲበላ ለማድረግ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ዳዊት መጡ፤ ዳዊት ግን፣ “ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ማንኛውንም ነገር ብቀምስ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ፡፡ 36ሕዝቡም ሁሉ የዳዊትን ሐዘን ተመለከቱ፤ ንጉሡ የሚያደርገው ሁሉ በእርግጥ ደስ ያሰኛቸው ስለነበረ፣ በዚህም ደስ አላቸው፡፡37ስለዚህ የኔር ልጅ አበኔር ይገደል ዘንድ የንጉሡ ፍላጎት እንዳልነበረ ሕዝቡ ሁሉና እስራኤል በሙሉ በዚያን ዕለት ዐወቁ፡፡ 38ንጉሡ ለአገልጋዮቹ እንደዚህ አላቸው፣ “በዛሬይቱ ዕለት በእስራኤል መስፍንና ታላቅ ሰው መውደቁን አላወቃችሁምን? 39ምንም እንኳን የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም እኔ ደካማ ነኝ፤ እነዚህ የጽሩይ ልጆች እጅግ ጨካኞች ሆነውብኛል፡፡ እንደ ክፋቱ በመቅጣት እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊው እንደ እጁ ሥራ መጠን ይክፈለው፡፡”
1አበኔር በኬብሮን መሞቱን የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በሰማ ጊዜ እጆቹ ዛሉ፣ መላው እስራኤልም ተጨነቀ፡፡ 2በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ የወታደር ጭፍራ መሪዎች የነበሩ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ የአንደኛው ስም በዓና ሲሆን የሌላኛው ስም ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር፡፡ እነርሱም ከብንያም ነገድ የብኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች ነበሩ (ብኤሮት ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ትቆጠር ነበር፤ 3የብኤሮት ሕዝብ ወደ ጌቴም በመሸሽ እስከ ዛሬ በዚያ ይኖራሉ) ፡፡4የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው፡፡ እርሱም የሳዖልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ ሞግዚቱ ይዛው ለመሸሽ አነሣችው፣ ነገር ግን ይዛው በምትሮጥበት ጊዜ የዮናታን ልጅ ወደቀና ሽባ ሆነ፡፡ ስሙም ሜምፊቦስቴ ይባል ነበር፡፡5በዚህ ጊዜ የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ሞቃት በነበረበት በቀትሩ ሰዓት እርሱ ዕረፍት እያደረገ ሳለ ወደ ኢያቡስቴ ቤት ሄዱ፡፡ 6ትጠብቅ የነበረችው ሴት ስንዴ በምታበጥርበት ጊዜ እንቅልፍ ወስዷት ነበርና ሬካብና በዓና በቀስታ አልፈዋት ገቡ፡፡ 7ስለዚህ ወደ ቤት ከገቡ በኋላ በክፍሉ ተኝቶ ሳለ አጠቁት ገደሉትም፡፡ ከዚያ በኋላ ራሱን ቆርጠው በመውሰድ ሌሊቱን ሁሉ በዓረባ መንገድ ተጓዙ፡፡8የኢያቤስቴንም ራስ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት ዘንድ አምጥተው፣ “አንተን ሊገድል ይፈልግ የነበረው የጠላትህ የሳዖል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ እነሆ እግዚአብሔር በዛሬው ቀን ስለ ጌታዬ ስለ ንጉሡ ሳዖልንና ዘሩን ተበቅሎአል፡፡” አሉት፡፡ 9ዳዊትም ለብኤሮታዊው ለሬሞን ልጆች ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና ምላሽ በመስጠት እንዲህ አላቸው፣ “ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን፣ 10የምሥራች ያመጣልኝ መስሎት ‘እነሆ ሳኦል ሞተ’ ብሎ የነገረኝን ሰው ይዤ ጺቅላግ ላይ ገደልሁት፤ እንግዲህ ወሬውን ላመጣው ለዚያ ሰው የሸለምሁት ይህንን ነበር፡፡11ታዲያ በገዛ ዐልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው ክፉ ሰዎች የገደሉት ከሆነ እንዴት ይልቅ ደሙን ከእጃችሁ አልፈልግ፣ ከዚህ ምድርስ አልደመስሳችሁ?” 12ስለዚህም ዳዊት ጎልማሶቹን አዘዘ፤ እነርሱም ገደሏቸው፤ እጅና እግራቸውንም ቆርጠው በኬብሮን ካለው ኩሬ አጠገብ ሰቀሏቸው፡፡ ነገር ግን የኢያቡስቴን ራስ ወስደው ኬብሮን በሚገኘው በአብኔር መቃብር ውስጥ ቀበሩት፡፡
1የእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉ፣ “እነሆ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቁራጭ ነን፤ 2ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረበት ባለፈው ጊዜ የእስራኤልን ሠራዊት የምትመራ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፣ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፣ በእስራኤልም ላይ ገዥ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር፡፡”3ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፡፡ 4ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረr፤ አርባ ዓመትም ገዛ፡፡ 5በኬብሮን በይሁዳ ላይ ለሰባት ዓመት ከስድስት ወር፣ ኢየሩሳሌም ሆኖም በመላው እስራኤልና በይሁዳ ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፡፡6ንጉሡና ሰዎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች በሆኑት በኢያቡሳውያን ላይ ለመዝመት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡ እነርሱም ለዳዊት፣ “በዕውሮችና በአንካሶች ልትመለስ ካልሆነ በስተቀር አንተ ወደዚህ አትገባም፤ ዳዊት እዚህ መምጣት አይችልም” አሉት፡፡ 7ይሁን እንጂ ዳዊት የጽዮንን አምባ ያዘ፤ ይህችም አሁን የዳዊት ከተማ የሆነችው ነች፡፡8በዚያን ጊዜ ዳዊት እንደዚህ አለ፣ “ኢያቡሳውያንን የሚያጠቃ በውሃ መተላለፊያው ሽቅብ መውጣት አለበት፤ በዚያም ዳዊትን የሚጠሉትን ዕውሮችንና አንካሶችን ያገኛል፡፡” እንግዲህ ሰዎች፣ “አንካሶችና ዕውሮች ወደ ቤተ መንግሥት መግባት አይችሉም” ያሉት ከዚህ የተነሣ ነው፡፡ 9በመሆኑም ዳዊት በአምባይቱ ኖረ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራት፡፡ ከሸንተረሩ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ምሽግ ገነባባት፡፡ 10የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበረ፣ ዳዊት እጅግ እየበረታ ሄደ፡፡11በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም መልእክተኞችን፣ የዝግባ እንጨት፣ አናጢዎችንና ድንጋይ ጠራቢዎችን ወደ ዳዊት ላከ፤ እነርሱም ለዳዊት ቤት ሠሩለት፡፡ 12እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገለት ዳዊት አወቀ፡፡13ኬብሮንን ትቶ ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ዳዊት በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ቁባቶችን አስቀመጠ ሚስቶችንም አገባ፤ ተጨማሪ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፡፡ 14በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች ስም፣ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፣ 15ኢያቤሔር፣ ኤሊሱዔ፣ ናፌቅ፣ ናፍያ፣ 16ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባሉ ነበር፡፡17ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱን ለመፈለግ በሙሉ ኃይላቸው ወጡ፤ ዳዊት ግን ይህን ሰምቶ ወደ ምሽጉ ወረደ፡፡ 18በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ፡፡19ዳዊትም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ ሲል ዕርዳታ ጠየቀ፣ “ፍልስጥኤማውያንን ወጥቼ ልውጋቸውን? በእነርሱስ ላይ ድል ትሰጠኛለህ?” እግዚአብሔርም ለዳዊት፣ “በፍልስጥኤማውያን ላይ በእርግጥ ድል እሰጥሃለሁና ውጋቸው” አለው፡፡ 20ስለዚህ ዳዊት በበአልፐራሲም ወጋቸው በዚያም ድል አደረጋቸው፡፡ እርሱም፣ “የጎርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” በማለት ስሜቱን ገለጸ፡፡ ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም በአልፐራሲም ተባለ፡፡ 21ፍልስጥኤማውያን ጣዖቶቻቸውን እዚያ ትተው ስለነበር ዳዊትንና ሰዎቹን ወሰዷቸው፡፡22ፍልስጥኤማውያን እንደ ገና መጥተው በራፋይም ሸለቆ በድጋሚ ተበታትነው ሰፈሩ፡፡ 23ስለዚህ ዳዊት እንደገና ከእግዚአብሔር ዕርዳታ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “በፊት ለፊት በኩል አትውጋቸው፤ ይልቁኑ በስተኋላቸው በኩል በመክበብ በበለሳኑ ዛፎች ፊት ለፊት ግጠማቸው፡፡24በበለሳኑ ዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ጉዞ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ለመምታት እግዚአብሔር ቀድሞ ወጥቶአልና በዚያን ጊዜ በኃይል አጥቃ” አለው፡፡ 25ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ፍልስጥኤማውያንን ከገባዖን እስከ ጌዘር ድረስ ገደላቸው፡፡
1ዳዊት እንደ ገና ከእስራኤል የተመረጡትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች ሰበሰበ፡፡ 2ዳዊትና አብረውት ያሉት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ በዙፋኑ በተቀመጠው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ለማምጣት በይሁዳ ወዳለው ወደ በአል ሄዱ፡፡3የእግዚአብሔርን ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው በኮረብታ ላይ ካለው ከአሚናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፡፡ ልጆቹ ዖዛና አሒዩ አዲሱን ሠረገላ ይመሩ ነበር፡፡ 4የእግዚአብሔርን ታቦት በላዩ ላይ አኑረው ሠረገላውን በኮረብታ ላይ ካለው ከአሚናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ አሒዩ ከታቦቱ ፊት ለፊት ይሄድ ነበር፡፡ 5ዳዊትና የእስራኤል ቤት በሙሉ በጥድ እንጨት በተሠሩ የሙዚቃ መሣሪያዎች ማለትም በበገና፣ በመሰንቆ፣ በከበሮ፣ በጸናጽልና በቃጭል መጫወትና ደስታቸውን መግለጽ ጀመሩ፡፡6ወደ ናኮን ዐውድማ ሲደርሱም በሬዎቹ ስለተደናቀፉ፤ ዖዛ የእግዚአብሔርን ታቦት ለመያዝ እጁን ዘረጋ በእጁም ያዘው፡፡ 7ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ በዚያም ስፈራ እግዚአብሔር ስለ ኃጢአቱ መታው፡፡ ዖዛም በዚያ በእግዚአብሔር ታቦት አጠገብ ሞተ፡፡8እግዚአብሔር ዖዛን ስለመታው ዳዊት ተቆጣ፤ የዚያን ቦታም ስም ፔሬዝ ዖዛ ብሎ ጠራው፡፡ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ፔሬዝ ዖዛ ተብሎ ይጠራል፡፡ 9ዳዊት በዚያን ቀን እግዚአብሔርን ስለ ፈራ፣ “የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ሊመጣ ይችላል?” ብሎ ጠየቀ፡፡10ስለዚህ ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ከእርሱ ጋር ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈቀደም፤ በዚህ ፋንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ወሰደው፡፡ 11የእግዚአብሔርም ታቦት የጌት ሰው በሆነው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እርሱንና ቤተሰቡንም ሁሉ እግዚአብሔር ባረካቸው፡፡12በዚህ ጊዜ፣ “በእግዚአብሔር ታቦት ምክንያት የአቢዳራን ቤተሰብና ያለውን ሁሉ እግዚአብሔር ባረከለት” ብለው ለዳዊት ነገሩት፡፡ ስለዚህ ዳዊት ወደዚያ ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከኦቤድ ኤዶም ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደስታ አመጣው፡፡ 13የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸክመው የነበሩት ሰዎች ስድስት እርምጃ በሄዱ ቁጥር አንድ በሬና አንድ የሰባ ጥጃ ይሠዋ ነበር፡፡14ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ ብቻ በወገቡ ታጥቆ በሙሉ ኃይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይጨፍር ነበር፡፡ 15ስለዚህ ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት እልል እያሉና ቀንደ መለከት እየነፉ የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘውት መጡ፡፡16የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ እየገባ ሳለ የሳዖል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሥ ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልና ሲጨፍር አየችው፤ ከዚያ በኋላም በልቧ ናቀችው፡፡ 17ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን በተዘጋጀለት በማዕከላዊ ስፍራ አኖሩት፡፡ ከዚያ በኋላም ዳዊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ፡፡18ዳዊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ በፈጸመ ጊዜ ሕዝቡን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም ባረከ፡፡ 19ከዚያ በኋላ ለመላው እስራኤል፣ ለሕዝቡ ሁሉ ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እንጀራ፣ አንዳንድ ሙዳ ሥጋና አንዳንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ አከፋፈለ፡፡ ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዱ ወደየቤቱ ሄደ፡፡20ከዚያ በኋላ ቤተሰቡን ለመባረክ ተመለሰ፡፡ የሳዖል ልጅ ሜልኮልም ዳዊትን ልትቀበለው መጣችና እንደዚህ አለች፣ “ራሳቸውን ከሚያራቁቱ ባለጌዎች እንደ አንዱ ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ በአገልጋዮቹ መካከል በነበሩት ገረዶች ፊት ራሱን በማራቆቱ ምን ያህል የተከበረ ነበር!”21ዳዊትም ለሜልኮል እንዲህ ሲል መለሰላት፣ “እኔን ከአባትሽና ከቤተሰቡ ሁሉ በላይ በመረጠኝና በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ መሪ አድርጎ በሾመኝ በእግዚአብሔር ፊት ያንን አድርጌአለሁ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሐሴት አደርጋለሁ! 22እንዲያውም ከዚህም የበለጠ ራሴን ዝቅ አደርጋለሁ፣ ከዚህም የባሰ የተናቅሁ እሆናለሁ፤ ነገር ግን በጠቀስሻቸው ገረዶች ፊት እከብራለሁ፡፡” 23ስለዚህም የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከምትሞተችበት ጊዜ ድረስ ልጅ አልወለደችም ነበር፡፡
1ንጉሡ በቤቱ ተደላድሎ ከተቀመጠና እግዚአብሔርም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ካሳረፈው በኋላ፣ 2ለነቢዩ ለናታን ንጉሡ እንደዚህ አለው፣ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው፡፡3ከዚያ በኋላ ናታን ለንጉሡ፣ “እግዚአብሔር ካንተ ጋር ስለሆነ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ” አለው፡፡ 4ነገር ግን በዚያች ሌሊት እንደዚህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፣ 5“ሂድና ለባሪያዬ ለዳዊት እንደዚህ በለው፣ ‘እግዚአብሔር የሚልህ እንደዚህ ነው፣ የምኖርበትን ቤት አንተ ትሠራልኛለህን?6የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ካወጣሁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳን ማደሪያ ውስጥ ሆኜ እንቀሳቀስ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ ኖሬ አላውቅምና፤ 7በመላው የእስራኤል ሕዝብ መካከል በተመላለስሁባቸው በሁሉም ስፈራዎች ሕዝቤን እስራኤልን እንዲጠብቁ ከሾምኋቸው መሪዎች ለአንዱ ስንኳ፣ ‘ከዝግባ እንጨት ለምን ቤት አልሠራህልኝም?’ ብያለሁን?8እንግዲህ አሁን ለባሪያዬ ለዳዊት እንደዚህ በለው፣ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፣ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ከመስክ በጎችን ትከተል ከነበርህበት ስፍራ ወሰድሁህ፤ 9በሄድህበት ሁሉ እኔ ከአንተ ጋር ነበርሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁልህ’፤ በምድር ላይ ስማቸው ታላቅ እንደሆነው እንደ አንዱ ለአንተ ታላቅ ስም አደርግልሃለሁ፡፡10ከእንግዲህ ወዲያ በራሳቸው መኖሪያ እንዲኖሩ እንጂ እንዳይናወጡ ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፣ በዚያም እተክላቸዋለሁ፡፡ ከዚህ በፊት እንደሆነውም ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ሕዝብ አይጨቁናቸውም፤ 11መሳፍንትን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ባዘዝሁበት ጊዜ እንዳደረጉባቸው ከእንግዲህ ወዲህ አያደርጉባቸውም፤ ከጠላቶችህም ሁሉ አሳርፍሃለሁ፡፡ ከዚህም ባሻገር፣ እኔ እግዚአብሔር ቤት እንደምሠራልህ እነግርሃለሁ፡፡12ዕድሜህ በሚጠናቀቅበት ጊዜና ከአባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣ ዝርያ አስነሳልሃለሁ፣ መንግሥቱንም አጸናለሁ፡፡ 13እርሱ ለእኔ ቤት ይሠራልኛል፤ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ፡፡ 14እኔ አባት እሆነዋለሁ፣ እርሱም ልጄ ይሆናል፡፡ ኃጢአት በሚያደርግበት ጊዜ በሰዎች በትር እቀጣዋለሁ፣ የሰው ልጆች በሚገረፉበትም ግርፋት እገርፈዋለሁ፤15ከፊትህ ካስወገድሁት ከሳኦል ላይ እንደወሰድሁ ኪዳናዊ ታማኝነቴ ከእርሱ አይርቅም፡፡ 16ቤትህና መንግሥትህ በፊትህ ለዘላለም የጸና ይሆናል፤ ዙፋንህም ለዘላለም የጸና ይሆናል፡፡” 17ናታን ለዳዊት እንደዚህ ተናገረ፣ ይህንንም ሁሉ ነገር ነገረው፤ ጠቅላላውንም ራእይ ገለጸለት፡፡18ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባና በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጠና እንደዚህ አለ፣ “እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ እኔ ማን ነኝ? እስከዚህ ደረጃስ ታደርሰኝ ዘንድ ቤተሰቤስ ምንድን ነው? 19ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህ በፊትህ ታናሽ ነገር ነው፡፡ ስለ ባሪያህ ቤተሰብ እንኳን ለረጅም ጊዜ የሚሆነውን ተናገርህ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ከዚህ በኋላ የሚኖረውንም ትውልዴን አሳየኸኝ! 20እኔ ዳዊት ከዚህ በላይ ለአንተ ምን እላለሁ? ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ባሪያህን አክብረኸዋል፡፡21ስለ ቃልህ ብለህ፣ ዓላማህንም ትፈጽም ዘንድ ይህን ታላቅ ነገር አድርገሃል፤ ለባሪያህም ገልጸህለታል፡፡ 22ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ታላቅ ነህና እንደ አንተ ያለም የለም፤ በገዛ ጆሮቻችንም እንደ ሰማን ከአንተም በቀር አምላክ የለም፡፡ 23አንተ እግዚአብሔር መጥተህ ለራስህ እንዳዳንከው በምድር ላይ እንዳለው እንደ ሕዝብህ ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ? ይህንን ያደረግኸው ለራስህ ሕዝብን ታስነሳ ዘንድ፣ ለራስህም ስምህን ታስጠራ ዘንድና ታላቅና አስፈሪ ነገር በምድርህ ታደርግ ዘንድ ነው፡፡ ከግብፅ ከዋጀኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብንና ጣዖቶቻቸውን አባረርህ፡፡24እስራኤልን ሕዝብህ አድርገህ ለዘላለም አጸናህ፣ አንተም፣ እግዚአብሔር ሆይ አምላክ ሆንህላቸው፡፡ 25አሁንም ባሪያህንና ቤተሰቡን በሚመለከት የሰጠኸውን ተስፋ ለዘላለም አጽናለት፤ እንደተናገርኸውም አድርግለት፡፡ 26የእኔ፣ የባሪያህ የዳዊት ቤት በፊትህ በሚጸናበት ጊዜ ሕዝቦች፣ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው’ ይሉ ዘንድ ስምህ ለዘላለም ታላቅ ይሁን፡፡27አንተ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል አምላክ ለባሪያህ ቤት እንደምትሠራለት ገልጸህለታልና፤ ለዚህ ነው እኔ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት ያገኘሁት፡፡ 28አሁን፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ አምላክ ነህ፣ ቃሎችህም የታመኑ ናቸው፤ ይህንን መልካም የተስፋ ቃል ለባሪያህ ገብተህለታል፡፡ 29በፊትህ ለዘላለም የሚቀጥል ይሆን ዘንድ፣ እንግዲህ አሁን የባሪያህን ቤት መባረክ አንተን ደስ ያሰኝህ፡፡ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ተናግረሃልና በበረከትህ የባሪያህ ቤት ለዘላለም የተባረከ ይሆናል፡፡”
1ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው ድልም አደረጋቸው፡፡ ስለዚህ ዳዊት ጋትና መንደሮችዋን ከፍልስጥኤማውያን ቁጥጥር ነጻ አወጣት፡፡2ከዚያ በኋላም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር፡፡ ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፣ ግብርም ገበሩለት፡፡3ከዚህ በኋላ ደዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛቱን ለማስመለስ ይጓዝ በነበረበት ጊዜ የሱባን ንጉሥ የረአብን ልጅ አድርአዛርን ድል አደረገው፡፡ 4ዳዊትም ከእርሱ ላይ 1700 ሠረገሎችና 20, 000 እግረኞች ማረከ፡፡ ለመቶ ሠረገሎች የሚሆኑትን አስቀርቶ ዳዊት የሠረገሎቹን ፈረሶች ሁሉ ቋንጃዎች ቆረጠ፡፡5ከደማስቆ አራማውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ሃያ ሁለት ሺህ አራማውያን ሰዎችን ገደለ፡፡ 6ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው በአራም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ አራማውያንም ለእርሱ አገልጋዮች ሆነው ተገዙለት፣ ግብርም ገበሩለት፡፡ ዳዊት በሄደበት ሁሉ እግዚአብሔር ድልን ሰጠው፡፡7የአድርአዛር አገልጋዮች ይዘዋቸው የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ዳዊት ወሰዳቸው ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው፡፡ 8ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፡፡9የሐማት ንጉሥ ቶዑ ዳዊት መላውን የአድርአዛርን ሠራዊት ድል ማድረጉን በሰማ ጊዜ፣ 10ዳዊት ከአድርአዛር ጋር ስለ ተዋጋና ድል ስላደረገው ደግሞም አድርአዛር ከቶዑ ጋር ተዋግቶ ስለ ነበረ፣ ቶዑ ልጁን ዮራምን ሰላምታ ይሰጠው ዘንድና ይባርከው ዘንድ ወደ ዳዊት ላከው፡፡ ዮራምም ከእርሱ ጋር የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃዎች ይዞ መጣ፡፡11ንጉሥ ዳዊትም ድል ካደረጋቸው መንግሥታት ሁሉ ማለትም 12ከአራም፣ ከሞዓብ፣ የአሞን ሕዝብ፣ ከፍልስጥኤማውያን ከአማሌቅ እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር ከበዘበዛቸው ዕቃዎችና ካገኛቸው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ለእግዚአብሔር ቀደሰ፡፡13ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ከአሥራ ስምንት ሺህ ሰዎቻቸው ጋር የነበሩትን አራማውያንን ድል አድርጎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ፡፡ 14በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያን ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ስፈራ ሁሉ ድልን ሰጠው፡፡15ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ሕዝቡንም ሁሉ በፍትሐዊነትና በጽድቅ አስተዳደረ፡፡ 16የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሠራዊቱ አለቃ ሲሆን፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥም ታሪክ ጸሐፊ ነበረ፡፡ 17የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቢሜሌክ ካህናት ሲሆኑ፣ ሠራያ ጸሐፊ ነበር፡፡ 18የዮዳሔ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፣ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ የንጉሡ ተቀዳሚ አማካሪዎች ነበሩ፡፡
1ዳዊትም፣ “ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳዖል ቤት የቀረ ሰው ይኖር ይሆን?” በማለት ጠየቀ፡፡ 2በሳኦል ቤተሰብ ውስጥ ሲባ የሚባል አንድ አገልጋይ ነበረ፤ እነርሱም ወደ ዳዊት እንዲሄድ ነገሩት፡፡ ንጉሡም፣ “አንተ ሲባ ነህን?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ሲባም፣ “አዎን፣ እኔ አገልጋይህ ነኝ” ብሎ መለሰ፡፡3ንጉሡም፣ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን?” በማለት ጠየቀው፡፡ ሲባም ለንጉሡ፣ “ዮናታን እግሩ ሽባ የሆነ አንድ ልጅ አለው” ብሎ መለሰ፡፡ 4ንጉሡም፣ “ወዴት ነው ያለው?” አለው፡፡ ሲባም ለንጉሡ፣ “ሎዶባር በተባለ ስፍራ በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት ይገኛል” ብሎ መለሰለት፡፡5በዚህን ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ሎደባር ወደሚገኘው ወደ ዓሚኤል ልኮ ከማኪር ቤት ሜምፊቦስቴን አስመጣው፡፡ 6የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት መጥቶ ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት ለዳዊት አክብሮቱን ገለጠ፡፡ ዳዊትም፣ “ሜምፊቦስቴ” ብሎ ጠራው፡፡ እርሱም፣ “እነሆ፣ አገልጋይህ” አለ፡፡7ዳዊትም፣ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል በእርግጥ ቸርነት አደርግልሃለሁና፡፡ የአያትህንም የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከገበታዬ ትበላለህ፡፡” አለው፡፡ 8ሜምፊቦስቴም ለጥ ብሎ እጅ ነሣና፣ “እንደ ሞተ ውሻ የሆንኩትን እኔ አገልጋይህን በሞገስ ትመለከተኝ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?”9ከዚያም ንጉሡ የሳኦልን አገልጋይ ሲባን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “የሳኦልና የቤተሰቡ የሆነውን ሁሉ ለጌታህ ልጅ ሰጥቼዋለሁ፡፡ 10አንተ፤ ልጆችህና አገልጋዮችህ የጌታችሁ የልጅ ልጅ የሚበላውን እንዲያገኝ መሬቱን እረሱለት፣ ምርቱንም አግቡለት፡፡ የጌታህ የልጅ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ምን ጊዜም ከገበታዬ ይበላል፡፡” በዚያን ጊዜ ሲባ ዐሥራ አምስት ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት፡፡11ከዚያም ሲባ ንጉሡን፣ “ጌታዬ ንጉሥ፣ አገልጋዩን ያዘዘውን ሁሉ፣ አገልጋይህ ይፈጽመዋል” አለው፡፡ ንጉሡም በተጨማሪ፣ “ሜምፊቦስቴ በበኩሉ ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከገበታዬ የሚበላ ይሆናል” አለ፡፡ 12ሜምፊቦስቴ ሚካ የተባለ አንድ ትንሽ ልጅ ነበረው፤ የሲባ ቤተሰቦች በሙሉ የሜምፊቦስቴ አገልጋዮች ነበሩ፡፡ 13ስለዚህ ሜምፊቦስቴ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነበር፣ ሁለት እግሮቹም ሽባ ቢሆኑም ሁልጊዜ ከንጉሡ ገበታ ይበላ ነበር፡፡
1ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ሞተ፣ ልጁ ሐኖንም በእርሱ ምትክ ንጉሥ ሆነ፡፡ 2ዳዊትም፣ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ ሁሉ እኔን ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነትን አደርግለታለሁ፡፡” አለ፡፡ ስለዚህ በአባቱ ምክንያት ከደረሰበት ኃዘን ያጽናኑት ዘንድ ዳዊት አገልጋዮቹን ላከ፡፡ አገልጋዮቹም ወደ አሞን ምድር ገቡ፡፡ 3የአሞን ሕዝብ መሪዎች ግን ለጌታቸው ለሐኖን እንደዚህ አሉት፣ “አንተን እንዲያጽናኑ ሰዎቹን በመላኩ ዳዊት በእርግጥ አባትህን በማክበር ነው ብለህ ታስባለህን? ዳዊት ሰዎቹን የላከው ከተማይቱን እንዲመለከቱና ያጠፏትም ዘንድ እንዲሰልሏት አይደለምን?”4ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ፤ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፣ ልብሳቸውንም እስከ ቂጣቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ሰደዳቸው፡፡ 5ይህንን ለዳዊት በገለጹለት ጊዜ፣ ሰዎቹ እጅግ አፍረው ነበርና መልእክተኞችን ወደ እነርሱ ላከ፡፡ ንጉሡም፣ “ጢማችሁ እስኪያድግ በኢያሪኮ ቆዩና ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው፡፡6የአሞን ሰዎች ለዳዊት መጥፎ ጠረን እንዳላቸው ሰዎች እንደሆኑበት ባወቁ ጊዜ የአሞን ሰዎች መልእክተኞችን ልከው ከቤትሮዖብና ከሱባ ሃያ ሺህ አራማውያን እግረኛ ወታደሮችን፣ ከንጉሥ መዓካ አንድ ሺህ ሰዎችን ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፡፡ 7ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን ከመላው ተዋጊ ሠራዊት ጋር ላከው፡፡ 8አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ሲሰለፉ፤ የሱባና የረአብ አራማውያን ሰዎች ለብቻቸው ሜዳው ላይ ቆሙ፡፡9ኢዮአብም ከፊትና ከኋላው ጦር እንደ ከበበው ባየ ጊዜ፣ በእስራኤል በጀግንነታቸው ከታወቁት ጥቂቶቹን መርጦ በአራማውያን ግንባር አሰለፋቸው፡፡ 10የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ ሥር መድቦ በአሞናውያን ሠራዊት ግንባር አሰለፋቸው፡፡11ኢዮአብም እንዲህ አለ፤ “አራማውያን የሚያይሉብኝ ከሆነ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን የሚያይሉብህ ከሆነ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ፡፡ 12እንግዲህ በርታ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ጠንካሮች መሆናችንን እናስመስክር፤ እግዚአብሔርም ለዓላማው መልካም መስሎ የታየውን ያደርጋል፡፡”13ከዚያም ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ከእስራኤል ሠራዊት ፊት እንዲሸሹ ወደ ተገደዱት ወደ አራማውያን በመገሥገሥ ወደ ጦርነቱ ሄዱ፡፡ 14አራማውያን መሸሻቸውን አሞናውያን ባዩ ጊዜ፣ እነርሱም ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ ውስጥ ገቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ከአሞናውያን ሕዝብ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፡፡15አራማውያን በእስራኤላውያን እየተሸነፉ እንደሆኑ ባዩ ጊዜ እንደ ገና ተሰባሰቡ፡፡ 16አድርአዛር ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ወደነበሩት ወደ አራማውያን ሠራዊት መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም በአድርአዛር ሠራዊት አዛዥ በሶባክ መሪነት ወደ ዔላም መጡ፡፡17ይሄ ነገር ለዳዊት በተነገረው ጊዜ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ፡፡ አራማውያን ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን ገጠሙት ተዋጉትም፡፡ 18አራማውያን ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደለ፡፡ የሠራዊቱ አዛዥ ሶባክም ቆስሎ በዚያ ሞተ፡፡ 19የአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩት ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል መሸነፋቸውን ባዩ ጊዜ ከእስራኤላውያን ጋር ሰላም መሠረቱ ተገዙላቸውም፡፡ ስለዚህም ሶርያውያን ከዚያ በኋላ አሞናውያንን መርዳት ፈሩ፡፡
1ነገሥታት ወደ ጦርነት መውጣታቸው የተለመደ በነበረበት በፀደይ ወራት ዳዊት ኢዮአብን፣ አገልጋዮቹንና መላውን የእስራኤል ሠራዊት ወደ ዘመቻ ላካቸው፤ እነርሱም አሞናውያንን አጠፉ፤ ረባትንም ከበቡአት፡፡ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀረ፡፡2ከዚህም የተነሣ በአንድ የምሽት ወቅት ዳዊት ከዐልጋው ተነስቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ በዚያም ስፍራ ሆኖ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ በጣም ውብ ነበረች፡፡ 3ዳዊትም ሰው ልኮ ስለ ሴቲቱ የሚያውቁ ሰዎችን አጠያየቀ፡፡ አንድ ሰውም፣ “ይህች የኤልያብ ልጅ፣ የኬጢያዊው የኦርዮን ሚስት አይደለችምን?”4ከዚያም ዳዊት መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፣ (ከወር አበባ ጊዜዋ የነጻችበት ወቅት ነበርና) አብሮአት ተኛ፡፡ ከዚያም ተመልሳ ወደ ቤቷ ሄደች፡፡ 5ሴቲቱ ፀነሰች፣ “አርግዣለሁ” ብላም ወደ ዳዊት መልእክት ላከችበት፡፡6ከዚያ በኋላም ዳዊት ለኢዮአብ፣ “ኬጢያዊውን ኦርዮንን ወደ እኔ ላክልኝ” ብሎ መልእክት ላከበት፡፡ ስለዚህም ኢዮአብ ኦርዮንን ወደ ዳዊት ላከው፡፡ 7ኦርዮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብና ሠራዊቱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንዲሁም ጦርነቱ እንዴት እየተካሄደ እንዳለ ጠየቀው፡፡ 8ዳዊትም ለኦርዮን፣ “ወደ ቤትህ ሄደህ እግርህን ተታጠብ” አለው፡፡ ኦርዮንም ከቤተ መንግሥቱ ወጣ፣ ንጉሡም ኦርዮን ከወጣ በኋላ ስጦታ አስከትሎ ላከለት፡፡9ኦርዮን ግን ከጌታው አገልጋዮች ጋር በቤተ መንግሥቱ ቅጥር በር ተኛ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም ነበር፡፡ 10ለዳዊት “ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” ብለው በነገሩት ጊዜ፣ ዳዊት ኦርዮንን፣ “ከመንገድ መግባትህ አይደለምን? ለምን ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ 11ኦርዮም ዳዊትን፣ “ታቦቱ፣ እስራኤልና ይሁዳ በድንኳን ሆነው፣ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም አገልጋዮች ገላጣ ሜዳ ላይ ሰፍረው፤ ለመብላትና ለመጠጣት እንዲሁም ከሚስቴ ጋር ለመተኛት እንዴት ወደ ቤቴ እሄዳለሁ? እንዲህ ያለውን ነገር እንደማላደርገው በነፍስህ እምላለሁ፡፡” አለው፡፡12ከዚህም የተነሣ ዳዊት ለኦርዮ፣ “ዛሬ ደግሞ በዚህ እደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው፡፡ ስለዚህ ኦርዮ በዚያ ዕለትና በማግሥቱ እዚያው ኢየሩሳሌም ቆየ፡፡ 13ዳዊትም ባስጠራው ጊዜ በእርሱ ፊት በላ ደግሞም ጠጣ፣ ዳዊትም እንዲሰክር አደረገው፤ ሲመሽም ኦርዮን በአልጋው ላይ ለመተኛት የጌታው አገልጋዮች ወዳሉበት ሄደ፣ ወደ ቤቱ ግን አልሄደም፡፡14ስለዚህ በማግስቱ ሲነጋ ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጽፎ በኦርዮን እጅ ላከለት፡፡ 15በደብዳቤውም ውስጥ ዳዊት፣ “ኦርዮንን ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም እንዲመታና እንዲሞት ከኋላው አፈግፍጉ” ብሎ ጻፈ፡፡16ስለዚህ ኢዮአብ የከተማይቱን መከበብ እየተመለከተ ሳለ ጠንካሮቹ የጠላት ሠራዊት እየተዋጉ እንዳሉ በሚያውቅበት ግንባር ኦርዮንን መደበው፡፡ 17የከተማይቱ ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ጦርነት በገጠሙበት ጊዜ ከዳዊት ወታደሮች ጥቂቶቹ ሞቱ፣ እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮንም በዚያ ሞተ፡፡18ኢዮአብም በጦርነቱ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት በላከበት ጊዜ፣ 19መልእክተኛውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፣ “ጦርነቱን በሚመለከት ሁሉንም ነገር ለንጉሡ ከጨረስክ በኋላ፣ 20ምናልባት ንጉሡ ይቆጣና፣ ‘ለመዋጋት ስትሉ ወደ ከተማይቱ ይህን ያህል የተጠጋችሁት ስለምንድን ነው? በግንቡ ቅጥር ላይ ሆነው ፍላፃ እንደሚወርውሩባችሁ አታውቁም ኖሮአል?21የይሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ እንዲሞት ያደረገችው አንዲት ሴት ከግንቡ ላይ የወፍጮ መጅ ስለለቀቀችበት አይደለምን? ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ይልህ ይሆናል፡፡ በዚያን ጊዜ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቶአል’ ብለህ ንገረው፡፡”22ስለዚህ መልእክተኛው ተነሥቶ ወደ ዳዊት ዘንድ ሄደ፣ ኢዮአብ እንዲናገር የላከውን ማንኛውንም ነገር ነገረው፡፡ 23መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፣ “እኛ በመጀመሪያ ከነበረው ይልቅ ጠላት በርትቶ ነበር ወደ ሜዳው ወደ እኛ ዘንድ መጡ፤ እኛም እስከ ቅጥሩ መግቢያ በር ድረስ አሳድደን መለስናቸው፡፡24የእነርሱም ባለ ፍላጻዎች ከግንቡ ላይ ሆነው በወታደሮችህ ላይ ቀስት ወረወሩ፣ ከንጉሡ አገልጋዮችም ጥቂቶችን ገደሉ፤ አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞተ፡፡” 25ከዚያ በኋላ ዳዊት ለመልእክተኛው፣ “ለኢዮአብ፣ ‘መቼም ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፣ ሌላ ጊዜም ሌላውን ይበላልና ይህ አያሳዝንህ፡፡ በከተማይቱ ላይ ውጊያህን አጠናክረህ አፍርሳት፡፡’ በለው፣ ኢዮአብን አበረታታው፡፡”26ስለዚህ የኦርዮ ሚስት ባሏ መሞቱን በሰማች ጊዜ አምርራ አለቀሰችለት፡፡ 27የሐዘኗም ጊዜ ካበቃ በኋላ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ ወሰዳት፣ ሚስቱም ሆነች፣ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር እግዚአብሔርን አሳዘነው፡፡
1እግዚአብሔር ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፣ “በአንድ ከተማ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ባለጠጋ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ድኻ ነበረ፡፡ 2ባለጠጋው እጅግ ብዙ መንጋዎችና የቀንድ ከብቶች ነበሩት፤ 3ድኻው ግን ከገዛትን ካሳደጋት ከአንዲት መሲና በግ በስተቀር ሌላ አልነበረውም፡፡ ይህች በግ ከእርሱ ጋር ኖረች ከልጆቹም ጋር አደገች፡፡ በጊቱ እንዲያውም ከእርሱ ጋር ትበላ፣ ከጽዋውም ትጠጣ ነበር፤ በእቅፉም ትተኛ ነበር፣ ለእርሱም እንደ ሴት ልጁ ነበረች፡፡4አንድ ቀን አንድ እንግዳ ወደ ባለጠጋው ቤት መጣ፤ ባለጠጋው ግን ለእንግዳው ምግብ ለማቅረብ ከራሱ መንጋ ወይም ከቀንድ ከብቶቹ አንድ እንሰሳ ለመውሰድ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ከዚያ ይልቅ የድኻውን መሲና ጠቦት ወስዶ ለእንግዳው ምግብ አድርጎ አዘጋጀለት፡፡” 5ዳዊትም በባለጠጋው ላይ ቁጣው ነደደ፣ በንዴትም ለናታን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን ይህን ያደረገው ሰው ሞት ይገባዋል! 6እንዲህ ያለውን ነገር በማድረጉና ለደኻውም ባለመራራቱ ስለ በጊቱ አራት ዕጥፍ መክፈል አለበት፡፡”7ከዚያ በኋላም ናታን ለዳዊት፣ “ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፣ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ ከሳኦልም እጅ ታደግሁህ፤ 8የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፣ የጌታህንም ሚስቶች በብትህ አስታቀፍሁህ፤ የእስራኤልና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ብዙ ሌሎች ነገሮችንም ጨምሬ በሰጠሁህ ነበር፡፡9ስለዚህ በእርሱ ፊት ክፉ የሆነውን ታደርግ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሕግ ለምን አቃለልህ? ኬጢያዊውን ኦርዮንን በሰይፍ ገደለህ፣ ሚስቱንም ወስደህ የራስህ ሚስት አደረግኸት፡፡ ኦርዮንን በአሞናውያን ሠራዊት ሰይፍ ገደልኸው፡፡ 10እኔን አቃለኸኛልና የኬጢያዊውንም የኦርዮንን ሚስት ሚስትህ አድርገህ ወስደሃልና ሰይፍ ከቤትህ በፍጹም አይርቅም፡፡’11እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ከራስህ ቤት ጥፋት አስነሳብሃለሁ፤ ዓይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለጎረቤትህ እሰጠዋለሁ፣ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል፡፡ 12አንተ ኃጢአትህን በስውር እኔ ግን ይህንን ነገር በቀን ብርሃን በእስራኤል ሁሉ ፊት እገልጠዋለሁ፡፡’” 13ከዚያም ዳዊት ለናታን፣ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው፡፡ ናታንም ለዳዊት መለሰለት፣ “እግዚአብሔር ኃጢአትህን አስወግዶልሃል፡፡ አንተ አትሞትም፤14ይሁን እንጂ በዚህ ድርጊትህ እግዚአብሔርን ስላቃለልህ የተወለደልህ ልጅ በእርግጥ ይሞታል፡፡” 15ከዚያ በኋላ ናታን ወጥቶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ እግዚአብሔርም የኦርዮን ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ እግዚአብሔር አስጨነቀው እጅግም ታመመ፡፡16ዳዊት ስለ ልጁ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም ከዚያም ወደ ክፍሉ ገብቶ ሌሊቱን ወለሉ ላይ ተኝቶ አደረ፡፡ 17የቤተሰቡ ሽማግሌዎችም ከወለሉ ላይ ያነሱት ዘንድ በአጠገቡ ቆሙ፣ እርሱ ግን አልተነሳም፣ ከእነርሱም ጋር አልበላም፡፡ 18በሰባተኛውም ቀን ልጁ ሞተ፡፡ “እነሆ፣ ልጁ ገና በሕይወት ሳለ ስናነጋግረው ድምፃችንን አልሰማንም፣ ታዲያ፣ ልጁ ሞቶአል ብንለው በራሱ ላይ ምን ያደርግ ይሆን?!” ብለው ስለነበረ፣ የዳዊት አገልጋዮች ልጁ እንደ ሞተ ለመንገር ፈርተው ነበር፡፡19ነገር ግን እርስ በርሳቸው ሲንሾካሾኩ ዳዊት በተመለከተ ጊዜ፣ ልጁ እንደ ሞተ ዳዊት ተገነዘበ፤ ለአገልጋዮቹም፣ “ልጁ ሞተ?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም፣ “ሞቶአል” ብለው መለሱለት፡፡ 20ከዚያም ዳዊት ከወለሉ ላይ ተነስቶ ታጠበ፣ ቅባት ተቀባ ደግሞም ልብሱን ለወጠ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤትም ሄዶ አምልኮ አቀረበ፣ ከዚያ በኋላም ወደ ራሱ ቤተ መንግሥት ተመለሰ፡፡ ምግብ እንዲያቀርቡለት በጠየቀ ጊዜ አቀረቡለት፣ እርሱም በላ፡፡21ከዚያ በኋላ አገልጋዮቹ፣ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ልጁ በሕይወት እያለ ጾምህ አለቀስህም፤ ልጁ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” አሉት፡፡ 22ዳዊትም፣ “ልጁ ገና በሕይወት ሳለ ጾምሁ አለቀስሁም፤ ‘ልጁ በሕይወት ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር ቸርነት ያደርግልኝ እንደሆነ ማን ያውቃል’ ብዬ ነበር፡፡ 23አሁን ግን፣ እርሱ ሞቶአልና ለምን እጾማለሁ? መልሼ ላመጣው እችላለሁን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም፡፡”24ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ አብሮአት ተኛ፡፡ ከዚህም የተነሣ ወንድ ልጅ ወለደች፣ ልጁም ሰሎሞን የሚል ስም ተሰጠው፤ እግዚአብሔርም ወደደው፡፡ 25ስለሆነም እግዚአብሔር ስለወደደው ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ፡፡26በዚያን ጊዜም ኢዮአብ የአሞናውያን የንጉሥ ከተማ የነበረችውን ረባትን ወግቶ ምሽጉን ያዘ፡፡ 27ስለሆነም ኢዮአብ ወደ ዳዊት መልእክተኞችን በመላክ እንዲህ አለው፣ “ረባትን ወግቼ የከተማይቱን የውሃ ማከፋፈያ ይዤአለሁ፡፡ 28እንግዲህ አሁን፣ የቀረውን ሠራዊት አሰባስበህ በከተማይቱ ዙሪያ ሠፍረህ ያዛት፤ ምክንያቱም እኔ ከተማይቱን ከያዝኳት በስሜ መጠራቷ ነው፡፡”29ስለዚህ ዳዊት መላውን ሠራዊት አሰባስቦ ወደ ረባት ሄዶ ከተማይቱን ወግቶ ያዛት፡፡ 30ዳዊት ከሞሎክ ራስ ላይ ዘውዱን ወሰደ፤ የዘውዱም ክብደት አንድ መክሊት ወርቅ ሲሆን የከበረ ዕንቁም በላዩ ላይ ነበረበት፡፡ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ፡፡ ከዚያም እጅግ ብዙ የከተማይቱን ምርኮ አመጣ፡፡31በከተማይቱ የነበሩትንም ሰዎች አውጥቶ በመጋዝ፣ በብረት መቆፈሪያና በመጥረቢያ እንዲሠሩ አስገደዳቸው፤ የሸክላ ጡብም እንዲሠሩ አደረጋቸው፡፡ ዳዊት የአሞን ሕዝብ ከተሞች ሁሉ ይህንኑ ተግባር እንዲፈጽሙ አደረጋቸው፡፡ ከዚያም ዳዊትና ሠራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
1ከዚህ በኋላ የዳዊት ልጅ አምኖን የዳዊት ሌላ ልጅ የአቤሴሎም ሙሉ እኅት በነበረችው በውቧ ግማሽ እህቱ በትዕማር እጅግ ተማረከ፡፡ 2በእኅቱ በትዕማር ምክንያት እስኪታመም ድረስ አምኖን እጅግ ተጨነቀ፡፡ ድንግል ስለነበረች በእርሷ ላይ ምንም ነገር ማድረግ ለአምኖን የማይቻል መሰለው፡፡3አምኖን ግን የዳዊት ወንድም የሳምዕ ልጅ ኢዮናዳብ የተባለ ወዳጅ ነበረው፡፡ ኢዮናዳብ እጅግ ተንኮለኛ ሰው ነበር፡፡ 4ኢዮናዳብም ለአምኖን፣ “የንጉሥ ልጅ ሆይ፣ በየጥዋቱ ጭንቀት የሚሰማህ ለምንድን ነው? አትነግረኝምን?” ብሎ ጠየቀው፡፡ አምኖንም፣ “የወንድሜን የአቤሴሎምን እህት ትዕማርን አፍቅሬ ነው” ብሎ መለሰለት፡፡5በዚህን ጊዜ ኢዮናዳብ፣ “የታመምህ መስለህ አልጋህ ላይ ተኛ፣ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣም፣ ‘እህቴ ትዕማር የምበላውን ምግብ ታቀርብልኝ ዘንድ እባክህ ላክልኝ፤ ምግቡንም ዓይኔ እያየ ከእጇ እንድጎርስ እዚሁ መጥታ ታዘጋጅልኝ’ ብለህ ጠይቀው፡፡” 6ስለዚህ አምኖን የታመመ ሰው መስሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊጠይቀው በመጣ ጊዜ አምኖን ለንጉሡ፣ “ለሕመሜ የሚሆን ጥቂት ምግብ በፊቴ እንድታዘጋጅልኝና ከእጇም እንድበላ እባክህ እህቴን ትዕማርን ላክልኝ” ብሎ ጠየቀው፡፡7ከዚያም ዳዊት፣ “አሁን ሂጂና ለወንድምሽ ለአምኖን ምግብ አዘጋጂለት” በማለት በቤተ መንግሥቱ ወደ ነበረችው ትዕማር መልእክት ላከባት፡፡ 8ስለዚህም ትዕማር ወንድሟ አምኖን ወደተኛበት ቤት ሄደች፤ ጥቂት ሊጥ ወስዳ ካቦካችው በኋላ ቂጣ አደረገችው፣ ጋገረችውም፡፡ 9ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ ቂጣውን አቀረበችለት፣ እርሱ ግን መብላት አልፈለገም፡፡ ስለዚህ አምኖን በዘያ ለነበሩት ለሌሎቹ፣ “ማንኛውንም ሰው ከዚህ ከእኔ ዘንድ አስወጡልኝ” አላቸው፤ ስለዚህ ሰው ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ፡፡10ከዚያም አምኖን ትዕማርን፣ “ምግቡን ከእጅሽ እበላ ዘንድ ወደዚህ ወደ ክፍሌ አምጭልኝ” አላት፡፡ 11ምግቡን ባመጣችለት ጊዜ አምኖን እጇን ያዛትና፣ “እህቴ ሆይ፣ ነይ ከእኔ ጋር ተኚ” አላት፡፡ 12እርሷም፣ “አይሆንም፣ ወንድሜ ሆይ፣ አታስገድደኝ፤ ይህን የመሰለ ነገር በእስራኤል ሊደረግ አይገባውምና፡፡ ይህን አሳፋሪ ነገር አታድርግ፡፡13ይሄ ነገር ከሚያስከትልብኝ ዕፍረት ለማምለጥስ ወዴት መሄድ እችላለሁ? ይህም ድርጊት አንተን በመላው እስራኤል ኀፍረተ-ቢስ ጅል አድርጎ ያስቆጥርሃል፡፡ እባክህ፣ ለንጉሡ እንድትነግረው እጠይቅህሃለሁ፤ እንድታገባኝ ይፈቅድልሃል፡፡” 14ይሁን እንጂ አምኖን አልሰማትም፡፡ ከትዕማር ይልቅ ብርቱ ስለ ነበረ ይዟት ከእርሷ ጋር ተኛ፡፡15ከዚያም አምኖን ትዕማርን ከመጠን በላይ ጠላት፤ አፍቅሯት ከነበረውም ይልቅ ጠላት፡፡ አምኖንም፣ “ተነሺ፣ ውጭልኝ” አላት፡፡ 16እርሷ ግን፣ “አይሆንም፣ ምክንያቱም እኔን በማስወጣት የምታደርገው ይህ ክፉ ነገር ቀድመህ ካደረግኸው ይልቅ የከፋ ነው፡፡” አምኖን ግን እርሷን አልሰማትም፡፡ 17ከዚያ ይልቅ የግል አገልጋዩን ጠርቶ፣ “ይህችን ሴት ከእኔ ዘንድ አስወጥተህ፣ በሩን ቀርቅረው” አለው፡፡18ከዚህ በኋላ አገልጋዩ አስወጣትና በሩን ከበስተኋላዋ ቀረቀረባት፡፡ ድንግል የሆኑት የንጉሡ ሴት ልጆች እንደዚያ ይለብሱ ነበርና፣ ትዕማር በጣም ያጌጠ ቀሚስ ለብሳ ነበር፡፡ 19ትዕማር በራሷ ላይ ማቅ ነሰነሰች፣ ቀሚሷንም ቀደደች፡፡ እጇንም በራሷ ላይ አድርጋ ሄደች፣ በምትሄድበትም ወቅት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ አለቀሰች፡፡20ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋር ነበርን? ሆኖም፣ እህቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በይ፡፡ ወንድምሽ ስለሆነ ነገሩን በልብሽ አትያዢው፡፡” ስለሆነም ትዕማር በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሆና ኖረች፡፡ 21ነገር ግን ንጉሥ ዳዊት ይህንን ሁሉ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፤ 22አቤሴሎም ለአምኖን ምንም አልተናገረውም፤ ስላደረገባት ነገር እህቱንም ትዕማርን ስላስነወራት ጠልቶት ነበርና፡፡23ከሁለት ሙሉ ዓመት በኋላ አቤሴሎም በጎቹን በኤፍሬም አጠገብ በነበረው በቤላሶር ከተማ በጎችን የሚሸልቱ ሰዎች አስመጥቶ ነበር፤ አቤሴሎምም የንጉሡን ልጆች ወደዚያ ስፍራ ጋበዛቸው፡፡ 24አቤሴሎም ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “እነሆ፣ ባሪያህ በጎችን የሚሸልቱ አስመጥቷል፣ንጉሡና አገልጋዮቹ እባክህን ከባሪያህ ጋር ይምጡ” አለው፡፡25ንጉሡም ለአቤሴሎም፣ “ልጄ ሆይ፣ ሁላችንም መሄድ የለብንም፤ ሸክም እንሆንብሃለን” ብሎ መለሰለት፡፡ አቤሴሎም ንጉሡን አደፋፈረው፣ እርሱ ግን መሄድ ባይፈልግም አቤሴሎምን ባረከው፡፡ 26ከዚህ በኋላ አቤሴሎም፣ “ይሄ ካልሆነ፣ እባክህ ወንድሜ አምኖን ከእኛ ጋር ይሂድ” አለው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ አቤሴሎምን፣ “አምኖን አብሮአችሁ የሚሄደው ለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡27አቤሴሎም አጥብቆ ስለለመነው፣ አምኖንና የንጉሡ ልጆች አብረውት እንዲሄዱ ፈቀደ፡፡ 28አቤሴሎም አገልጋዮቹን፣ “ልብ ብላችሁ አድምጡ፣ አምኖን ወይን ጠጅ ጠጥቶ መስከር ሲጀምርና እኔ ‘አምኖንን ምቱት’ ስላችሁ፣ በዚያን ጊዜ ግደሉት፤ አትፍሩ፡፡ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝና በርቱ፣ ጠንክሩ፡፡” ብሎ አዘዛቸው፡፡ 29ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች እንዳዘዛቸው በአምኖን ላይ አደረጉበት፡፡ ከዚያ በኋላም የንጉሡ ልጆች በየበቅሎአቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ፡፡30እነርሱም እየሄዱ በመንገድ ላይ ሳሉ፣ “አቤሴሎም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ገደለ፣ አንድም የተረፈ የለም” የሚል ዜና ለዳዊት ደረሰው፡፡ 31ከዚያ በኋላ ንጉሡ ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፣ በወለሉም ላይ ተጋደመ፣ አገልጋዮቹም ልብሳቸውን ቀደው በአጠገቡ ቆሙ፡፡32የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ ግን፣ “የሞተው አምኖን ብቻ ነውና የንጉሡ ልጆች የሆኑትን ጎልማሶች ሁሉ ገድለዋቸዋል ብሎ ጌታዬ አይመን፡፡ አምኖን እህቱን ትዕማርን ከደፈራት ቀን አንስቶ አቤሴሎም ይህንን ሲያቅድ ነበር፤ 33ስለሆነም የሞተው አምኖን ብቻ ነውና፣ የንጉሡ ልጆች ሁሉ ሞተዋል ብሎ እስከሚያምን ድረስ ጌታዬ ንጉሡ የሚለውን ዜና ወደ ልቡ አያስገባው፡፡”34አቤሴሎም ሸሸ፡፡ ለጥበቃ የቆመውም አገልጋይ ቀና ብሎ ሲመለከት ከእርሱ በስተምዕራብ ካለው ኮረብታ ጥግ ባለው መንገድ ብዙ ሰዎች ሲመጡ አየ፡፡ 35በዚያን ጊዜ ኢዮናዳብ ለንጉሡ፣ “እነሆ፣ የንጉሡ ልጆች እየመጡ ነው፤ ልክ ባሪያህ እንዳለው ነው፡፡” 36ስለሆነም ተናግሮ እንደጨረሰ፣ የንጉሡ ልጆች ደረሱ፣ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፡፡ ንጉሡና አገልጋዮቹም ሁሉ አምርረው አለቀሱ፡፡37አቤሴሎም ኮብልሎ የጌሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ተልማይ ሄደ፡፡ ዳዊትም ስለ ሞተው ልጁ ዘወትር ያለቅስ ነበር፡፡ 38አቤሴሎም ለሶስት ዓመታት ወደ ቆየበት ወደ ጌሹር ሸሽቶ ሄደ፡፡ 39በልጁ በአምኖን ሞት ከደረሰበት ሐዘን ተጽናንቶ ስለነበረ ንጉሥ ዳዊት በሃሳቡ ወደ አቤሴሎም የመሄድ ናፍቆት አደረበት፡፡
1የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የንጉሡ ልብ አቤሴሎምን እንደ ናፈቀ ተረዳ፡፡ 2ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ቴቁሔ ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጥቶ፣ “ሐዘንተኛ በመምሰል የሐዘን ልብስ ልበሺ፣ እባክሽን ዘይት አትቀቢ ነገር ግን ለብዙ ጊዜ እንዳዘነች መስለሽ ታዪ፡፡ 3ከዚያም ወደ ንጉሡ ሄደሽ እኔ የምገልጽልሽን ንገሪው፡፡” ስለዚህ ኢዮአብ ለንጉሡ የምትናገረውን ነገር ነገራት፡፡4ከቴቁሔ የመጣችውም ሴት ለንጉሡ ለመንገር በገባችበት ጊዜ በንጉሡ ፊት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት፣ “ንጉሥ ሆይ፣ እርዳኝ” አለች፡፡ 5ንጉሡም፣ “ችግርሽ ምንድን ነው?” አላት፡፡ ሴቲቱም፣ “እኔ በእውነቱ ባሏ የሞተባት ባልቴት ነኝ፡፡ 6እኔ ባሪያህ ሁለት ልጆች ነበሩኝ፣ እነርሱም ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፣ የሚገላግላቸውም ሰው አልነበረም፡፡ አንደኛውም ሌላኛውን መታውና ገደለው፡፡7መላው ቤተሰብም አሁን በባሪያህ ላይ ተነሥቶ፣’ስለገደለው ስለ ወንድሙ ዋጋ እንዲከፍልና እኛም እንድንገድለው ወንድሙን የገደለውን ሰው አውጥተሸ ስጪን’ አሉኝ፤ ወራሽ የሆነውንም ያጠፉ ዘንድ ይፈልጋሉ፡፡ በዚህም ዓይነት የቀረኝን አንድ የጋለ ፍም አጥፍተው፣ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው፡፡”8ስለዚህ ንጉሡ ለሴቲቱ፣ “አንቺ ወደ ቤትሽ ሂጂ፣ አንድ ነገር እንዲደረግልሽ እኔ ትዕዛዝ እሰጣለሁ” አላት፡፡ 9የቴቁሔዪቱም ሴት ለንጉሡ፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤተሰብ ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ከበደል የነጹ ይሁኑ” አለች፡፡10ንጉሡም፣ “ማንም ሰው ቢናገርሽ ወደ እኔ ዘንድ አምጪው ከዚያ በኋላም አያስቸግርሽም” በማለት መለሰላት፡፡ 11ከዚያ በኋላ ሴቲቱ፣ “ደም ተበቃዩ ሌላ ሰው እንዳያጠፋና ልጄንም እንዳያጠፉት፣ እባክህን ንጉሥ እግዚአብሔር አምላክህን አሳስብልኝ” አለችው፡፡ ንጉሡም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን ከልጅሽ ራስ አንዲት ፀጉር እንኳ አትወድቅም” ብሎ መለሰላት፡፡12ከዚያ በኋላም ሴቲቱ፣ “ባሪያህ ለጌታዬ ለንጉሡ ተጨማሪ ቃል እንድናገር እባክህ ፍቀድልኝ” አለችው፡፡ ንጉሡም፣ “ተናገሪ” አላት፡፡ 13ስለዚህ ሴቲቱ፣ “ታዲያ፣ እንዲሀ ያለውን ነገር በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ያሰብኸው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ይህንን በመናገሩ ንጉሡ ራሱን በደለኛ እንደሚያደርግ ሰው ነው፣ የኮበለለውን ልጁን ንጉሡ ወደ ቤቱ አልመለሰውምና፡፡ 14ሁላችንም እንሞት ዘንድ ይገባናልና፣ እንደገናም ሊሰበሰብ እንደማይችል እንደ ፈሰሰ ውሃ ነንና፡፡ እግዚአብሔር ግን የሰውን ሕይወት አይወስድም ይልቁንም ከፊቱ ራሱን ያስኮበለለውን ሰው ወደ ራሱ የሚመልስበት መንገድ ይፈልጋል እንጂ፡፡15እንግዲህ አሁን ለጌታዬ ለንገሡ ይህንን ልናገር የመጣሁት ሕዝቡ እንድፈራ ስላደረጉኝ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ባሪያህ ለራሷ፣ ‘አሁን ለንጉሡ እናገራለሁ፣ ምናልባትም ንጉሡ የባሪያውን ጥያቄ ይቀበል ያደርግላት ይሆናል፡፡ 16እኔንና ልጄን ከእግዚአብሔር ርስት ሊያጠፋን ካለው ሰው እጅ ያድን ዘንድ ባሪያውን ያወጣ ዘንድ ንጉሡ ይሰማኛልና፣’ አለች፡፡ 17ከዚያ በኋላም ባሪያህ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ የጌታዬ የንጉሡ ቃል እፎይታን የሚሰጠኝ ይሁን፣ ምክንያቱም መልካሙን ከክፉው በመለየት ጌታዬ ንጉሡ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና’ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡”18ከዚያ በኋላም ንጉሡ ለሴቲቱ፣ “እኔ ለምጠይቅሽ ጥያቄ እባክሽ ምንም ነገር አትደብቂኝ” አላት፡፡ 19ንጉሡም፣ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ ከአንቺ ጋር የለም?” ሴቲቱም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከተናገረው አንዳችም ነገር ማንም ሰው ወደ ቀኝም ወደ ግራም ማምለጥ አይችልም፡፡ ያዘዘኝና ባሪያህም የተናገረችውን እነዚህን ነገሮች እንድናገር የነገረኝ ባሪያህ ኢዮአብ ነው፡፡ 20ባሪያህ ኢዮአብ ይህንን ያደረገው ነገሮች እየሄዱበት ያለውን አቅጣጫ ለመለወጥ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ጥበብ ጌታዬ ጠቢብ ነው፤ በምድሪቱም የሚሆነውን ማንኛውንም ነገር ያውቃል፡፡”21ስለዚህ ንጉሡ ለኢዮአብ፣ “እነሆ፣ እኔ አሁን ይህንን አደርጋለሁ፡፡ እንግዲህ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን አምጣው” አለው፡፡ 22ስለዚህ ኢዮአብ ለንጉሡ አክብሮቱንና ምስጋናውን ለመግለጽ ጎንበስ ብሎ እጅ ነሳ፡፡ ኢዮአብም፣ “ዛሬ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ፊት ሞገስ እንዳገኘ አወቅሁ፣ ንጉሡ የባሪያውን ጥያቄ ፈጽሞለታልና”23ስለዚህ ኢዮአብ ተነሥቶ ወደ ጌሹር ሄደ፣ አቤሴሎምንም ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡ 24ንጉሡም፣ “ወደ ራሱ ቤት መመለስ ይችላል፣ ነገር ግን ፊቴን አያይም” ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ቤቱ ተመለሰ፣ የንጉሡን ፊት ግን አላየም፡፡25በመላው እስራኤል ከአቤሴሎም ይልቅ በመልከ መልካምነቱ የተመሰገነ ማንም አልነበረም፡፡ ከእግር ተረከዙ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ ምንም እንከን አልነበረበትም፡፡ 26ይከብደው ስለ ነበረ የራሱን ፀጉር በሚቆረጥበት ጊዜ ፀጉሩን ይመዝነው ነበር፣ በንጉሡም የመመዘኛ ልክ ሁለት መቶ ሰቅል ይመዝን ነበር፡፡ 27አቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና ትዕማር የምትባል አንድ ሴት ልጅ ነበሩት፡፡ ሴት ልጁም ውብ ነበረች፡፡28አቤሴሎምም የንጉሡን ፊት ሳያይ ሁለት ሙሉ ዓመት በኢየሩሳሌም ኖረ፡፡ 29ከዚህ በኋላ ወደ ንጉሡ ይወስደው ዘንድ አቤሴሎም ወደ ኢዮአብ መልእክት ላከ፣ ኢዮአብ ግን ሊመጣ አልፈለገም፡፡ ስለዚህ አቤሴሎም ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢዮአብ መልእክት ላከ፣ ኢዮአብ ግን አሁንም አልመጣም፡፡30ስለዚህ አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ፣ “ኢዮአብ በእኔ እርሻ አጠገብ እርሻ አለው፣ በዚያም ገብስ አለው፤ ሂዱና በገብሱ ላይ እሳት ልቀቁበት” አላቸው፡፡ ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች በእርሻው ላይ እሳት ለቀቁበት፡፡ 31ከዚያም ኢዮአብ ተነስቶ ወደ አቤሴሎም ቤት መጣና፣ “አገልጋዮችህ በእርሻዬ ላይ እሳት የለቀቁበት ለምንድን ነው?” አለው፡፡32አቤሴሎምም ለኢዮአብ፣ “እነሆ፣ ወደ አንተ ዘንድ፣ ‘ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ዘንድ መጥተህ ለንጉሡ፣ ከጌሹር ለምን መጣሁ? እዚያው ብቆይ ይሻለኝ ነበር’ ብለህ እንድትነግርልኝ መልእክት ልኬብህ ነበር፡፡ ስለዚህ አሁን የንጉሡን ፊት ልይ፣ በደለኛ ከሆንኩም ይግደለኝ” አለው፡፡ 33ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ዘንድ ሄዶ ነገረው፡፡ ንጉሡም አቤሴሎምን ባስጠራው ጊዜ አቤሴሎም በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፣ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው፡፡
1ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች እንዲሁም ፊት ፊቱ የሚሮጡ ሃምሳ ሰዎች ለራሱ አዘጋጀ፡፡ 2አቤሴሎም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማይቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆማል፡፡ ሙግት ያለበት ማንኛውም ሰው ዳኝነት ለማግኘት ወደ ንጉሡ ሲመጣ፣ በዚያን ጊዜ አቤሴሎም ወደ እርሱ ይጠራውና፣ “ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” ይለው ነበር፡፡ ሰውዬውም፣ “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች ከአንዱ ነው?” ይለው ነበር፡፡3ከዚህም የተነሣ አቤሴሎም፣ “ተመልከት፣ ጉዳይህማ ትክክልና ተገቢም ነው፤ ነገር ግን ጉዳይህን ለመመልከት ከንጉሡ ሥልጣን የተሰጠው ማንም ሰው የለም፡፡” ይለው ነበር፡፡ 4ከዚህ ጋር በማያያዝ አቤሴሎም፣ “ሙግት ወይም ጉዳይ ያለው ማንኛውም ሰው ወደ እኔ እንዲመጣና እኔም ፍትሕ እንድሰጠው በምድሪቱ ዳኛ ሆኜ መሾም እመኛለሁ” ይል ነበር፡፡5ስለዚህ ክብርን ሊሰጠው ማንኛውም ሰው ወደ አቤሴሎም በሚመጣበት ጊዜ አቤሴሎም እጁን ዘርግቶ ይይዘውና ይስመው ነበር፡፡ 6ከንጉሡ ፍትሕ ለማግኘት በሚመጡ እስራኤላውያን ሁሉ አቤሴሎም እንደዚህ ያደርግ ነበር፡፡ በዚህም ሁኔታ አቤሴሎም የእስራኤላውያንን ልብ ሰረቀ፡፡7በአራተኛው ዓመት ፍጻሜ አቤሴሎም ለንጉሡ፣ “ለእግዚአብሔር የተሳልሁትን ስእለት ለማድረስ ወደ ኬብሮን እንድሄድ እባክህን ፍቀድልኝ፡፡ 8ባሪያህ በአራም በጌሹር በነበርኩበት ጊዜ፣ ‘እግዚአብሔር በእርግጥ ወደ ኢየሩሳሌም ዳግመኛ የመለሰኝ እንደሆነ በኬብሮን እሰግዳለሁ’ ብዬ ተስዬ ነበር፡፡”9ንጉሡም፣ “በሰላም ሂድ” አለው፤ ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ኬብሮን ሄደ፡፡ 10አቤሴሎም ግን ወደ መላው የእስራኤል ነገዶች፣ “የመለከትን ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ‘አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ’ ማለት ይገባችኋል” የሚሉ ሰላዮችን ላከ፡፡11ከአቤሴሎምም ጋር ሁለት መቶ የተጋበዙ ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡ አቤሴሎም ምን እንዳቀደ ምንም ነገር ሳያውቁ በየዋህነት ነበረ የሄዱት፡፡ 12አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ለሆነው ለአኪጦፌል ወደሚኖርበት ወደ ጊሎ መልእክት ላከበት፡፡ አቤሴሎምን ይከተለው የነበረው ሕዝብ እየጨመረ ስለነበረ የአቤሴሎም ሤራ ጠንካራ ነበር፡፡13“የእስራኤል ሰዎች ልብ አቤሴሎምን እየተከተለ ነው፡፡” የሚል መልእክተኛ ወደ ዳዊት መጣ፡፡ 14ስለዚህ ዳዊት በኢየሩሳሌም ለነበሩት አገልጋዮቹ ሁሉ፣ “ተነሡ እንሽሽ፤ ያለበለዚያ አንዳችንም ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ አንችልም፤ አሁኑኑ ለመውጣት ተዘጋጁ አለዚያ እርሱ መጥቶ ይይዘናል በእኛም ላይ ጥፋት ያደርስብናል፣ ከተማይቱንም በሰይፍ ይመታታል፡፡” አላቸው፡፡ 15የንጉሡም አገልጋዮች፣ “እነሆ፣ ጌታችን የወሰነውን ማንኛውንም ለማድረግ አገልጋዮችሀ ዝግጁ ነን” በማለት ለንጉሡ ነገሩት፡፡16ንጉሡ ከእርሱም ጋር መላው ቤተሰቡ ሄዱ፣ ነገር ግን ቤተ መንግሥቱን ይጠብቁ ዘንድ ቁባቶች የነበሩ አሥር ሴቶችን እንዲቀሩ አደረገ፡፡ 17ንጉሡና እርሱን ተከትሎ መላው ሕዝብ ከሄደ በኋላ ከመጨረሻው ቤተ ሲደርሱ ቆሙ፡፡ 18ሠራዊቱ ሁሉ ከእርሱ ጋር ተጓዙ፣ ከሊታውያን፣ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡት ስድስት መቶ ጌታውያን በንጉሡ ፊት አለፉ፡፡19ከዚያም ንጉሡ ጌታዊውን ኢታይን፣ “አንተ ደግሞ ከእኛ ጋር የመጣኸው ለምንድን ነው? እንግዳና ስደተኛ ነህና ተመልሰህ ሄደህ ከአቤሴሎም ጋር ቆይ፤ ወደ ራስህ አገር ሂድ፡፡ 20የወጣኸው ገና ትላንት ስለሆነ፣ ከእኔ ጋር በየቦታው ለምን እንድትንከራተት ላድርግህ? ወዴት እንደምሄድ እንኳን አላውቅም፡፡ ስለዚህ ተመለስ የአገርህንም ሰዎች መልሳቸው፤ በጎነትና ታማኝነት ከአንተ ጋር ይሁን፡፡” አለው፡፡21ኢታይ ግን ለንጉሡ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሁም በጌታዬ በንጉሡ እምላለሁ፤ ሕይወትም ይሁን ሞት ንጉሡ ወደሚሄድበት ወደየትኛውም ቦታ አገልጋይህም ይሄዳል፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡ 22ስለዚህ ዳዊት ለኢታይ፣ “እንግዲያውስ፣ ከእኛ ጋር መሄድህን ቀጥል” አለው፡፡ ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሰዎች ሁሉና አብረውት ከነበሩት ቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ጌታዊው ኢታይ ከንጉሡ ጋር ተጓዘ፡፡ 23ሕዝቡ ሁሉ ንጉሡም ራሱ የቄድሮንን ወንዝ ሲሻገሩ የአገሩ ሕዝብ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፡፡ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ምድረ-በዳ በሚወስደው መንገድ ተጓዘ፡፡24ሳዶቅም እንኳን የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት ከተሸከሙት ሌዋውያን ጋር በዚያ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን ታቦት አስቀመጡትና አብያታር ከእነርሱ ጋር ሆነ፤ እነርሱም ሕዝቡ ሁሉ ከከተማይቱ እስኪወጡ ድረስ ጠበቁ፡፡ 25ንጉሡም ሳዶቅን፣ “ታቦቱን ወደ ከተማይቱ ይዘህ ተመለስ፣ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ካገኘሁ ወደዚህ መልሶ ያመጣኛል፣ ታቦቱንና እርሱም የሚኖርበትን ስፍራ እንደገና ያሳየኛል፡፡ 26ነገር ግን እርሱ፣ ‘በአንተ አልተደሰትሁም’ ካለኝ፣ እነሆ፣ በፊቱ አለሁ፣ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግብኝ፡፡”27ንጉሡ ለካህኑ ለሳዶቅ፣ “አንተ ነቢይ አይደለህምን? አንተ ከሁለቱ ልጆችህ፣ ከልጅህ አኪማአስና ከአብያታር ልጅ ከዮናታን ጋር ሆናችሁ በሰላም ወደ ከተማይቱ ተመለሱ፡፡ 28ከአንተ ዘንድ መልእክት እስካገኝ ድረስ፣ እነሆ፣ እኔ በአረባ በሚገኘው በወንዙ መሻገሪያ እቆያለሁ፡፡” 29ስለዚህ ሳዶቅና አብያታር የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው እዚያው ቆዩ፡፡30ዳዊት ግን እያለቀሰ በባዶ እግሩ የደብረ ዘይትን ተራራ ሽቅብ ወጣ፣ ራሱንም ተከናንቦ ነበር፡፡ ከእርሱ ጋር የነበረውም እያንዳንዱ ሰው ራሱን ተከናንቦ ነበር፤ እየሄዱም ሳሉ ያለቅሱ ነበር፡፡ 31አንድ ሰውም ለዳዊት፣ “በሤራው ውስጥ ከአቤሴሎም ጋር ካሉት አንደኛው አኪጦፌል ነው” ብሎ ነገረው፡፡ ስለዚህ ዳዊት፣ “እባክህ፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ የአኪጦፌልን ምክር ወደ ሞኝነት ለውጠው” ብሎ ጸለየ፡፡32ዳዊት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ወደ መንገዱ ጫፍ በደረሰ ጊዜ፣ አርካዊው ኩሲ መጎናጸፊያውን ቀድዶ ትቢያ በራሱ ላይ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ፡፡ 33ዳዊትም ለእርሱ፣ “አብረኸኝ ብትሄድ ሸክም ትህንብኛለህ፤ 34ነገር ግን ወደ ከተማይቱ ተመልሰህ አቤሴሎምን ‘ንጉሥ ሆይ፣ አገልጋይህ እሆናለሁ፣ ቀድሞ የአባትህ አገልጋይ እንደ ነበርሁ ሁሉ አሁን ደግሞ የአንተ አገልጋይ እሆናለሁ’ ብትለው የአኪጦፌልን ምክር በማደናገር ትረዳኛለህ፡፡35ካህናቱ ሳዶቅና አብያታር እዚያው ከአንተ ጋር አሉልህ አይደለምን? በንጉሡ ቤተ መንግሥት የምትሰማውን ማንኛውንም ነገር ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር መንገር አለብህ፡፡ 36የሳዶቅ ልጅ አኪማአስና የአብያታር ልጅ ዮናታን ሁለቱ ወንዶች ልጆች በዚያ አብረዋቸው መሆናቸውን አረጋግጥ፡፡ የምትሰማውን ማንኛውንም ነገር በእነርሱ በኩል ላክልኝ፡፡” 37ስለዚህ የዳዊት ወዳጅ ኩሲ አቤሴሎም ኢየሩሳሌም በገባበት በዚያው ወቅት ወደ ከተማይቱ መጣ፡፡
1ዳዊት ከተራራው ጫፍ ባሻገር ጥቂት እልፍ ብሎ እንደሄደ ሲባ የተባለው የሜምፊቦስቴ አገልጋይ፣ ሁለት መቶ እንጀራ አንድ ሙሉ ጥፍጥፍ ዘቢብ አንድ መቶ ጥፍጥፍ በለስና አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች ይዞ ተገናኘው፡፡ 2ንጉሡም ሲባን፣ “ይህን ሁሉ ያመጣኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ ሲባም፣ “አህዮቹን የንጉሡ ቤተ ሰቦች እንዲቀመጡባቸው፣ እንጀራውንና በለሱን ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች እንዲበሉት፣ የወይን ጠጁ ደግሞ በምድረ-በዳ የደከመ ማንኛውም ሰው እንዲጠጣው ነው” አለው፡፡3ንጉሡም፣ “የጌታህ የልጅ ልጅ የት ነው?” አለው፡፡ ሲባም ለንጉሡ፣ “’ዛሬ የእስራኤል ቤት የአባቴን መንግሥት ለእኔ ይመልስልኛል’ እያለ ስለነበረ፣ እነሆ፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” ብሎ መለሰለት፡፡ 4ከዚያም ንጉሡ ሲባን፣ “የሜምፊቦስቴ የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ፣ እነሆ፣ የአንተ ሆኖአል” አለው፡፡ ሲባም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ በትሕትና በፊትህ እጅ እነሣለሁ፣ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው፡፡5ንጉሥ ዳዊት ወደ ብራቂም ሲደርስ ከሳዖል ቤተሰብ ነገድ የሆነ የጌራ ልጅ ሳሚ ብቅ አለ፡ እርሱም እየመጣ ሳለ ይራገም ነበር፡፡ 6የንጉሡ ወታደሮችና የክብር ዘቦቹ ሁሉ በዳዊትና ግራና ቀኝ ቢኖሩም እንኳን፣ በዳዊትና በሹማምንቱ ላይ ድንጋይ ይወረውርባቸው ነበር፡፡7ሳሚም እንደዚህ ብሎ ተራገመ፣ “ውጣ፣ ከዚህ ውጣ፣ አንተ ወሮበላ፣ አንተ የደም ሰው፤ 8በእርሱ ምትክ የነገሥህበትን የሳዖልን ቤተሰብ ደም ብድራት ሁሉ እግዚአብሔር እየከፈለህ ነው፡፡ እግዚአብሔር መንግሥቱን በልጅህ በአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ አሁንም አንተ የደም ሰው ስለሆንክ ጥፋት ደርሶብሃል፡፡”9ከዚህ በኋላ የጽሩይ ልጅ አቢሳ፣ “ይህ የሞተ ውሻ ንጉሡ ጌታዬን ለምን ይራገማል? እባክህ፣ ተሻግሬ ልሂድና ራሱን ልቁረጠው” አለ፡፡ 10ንጉሡ ግን፣ “እናንተ የጽሩያ ልጆች፣ እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? እርሱ የሚረግመኝ ምናልባት እግዚአብሔር፣ ‘ዳዊትን ርገመው’ ብሎት ይሆናል፡፡ ታዲያ እርሱን፣ ‘ንጉሡን ለምን ትረግማለህ?’ ሊለው የሚችለው ማን ነው?”11ስለዚህ ዳዊት ለአቢሳና ለአገልጋዮቹ ሁሉ፣ “ከአብራኬ የወጣው ልጄ ነፍሴን ሊያጠፋት ከፈለገ፣ ይህ ብንያማዊ ምን ያህል ጥፋቴን አይፈልግ? እግዚአብሔር እንዲራገም አዞት ይሆናልና፣ ተዉት፣ ይራገም፡፡ 12ምናልባት የተሰነዘረብኝን ውርደት እግዚአብሔር ተመልክቶ ስለ ዛሬው እርግማኑ በጎ ያደርግልኝ ይሆናል፡፡”13ስለዚህም ዳዊትና ሰዎቹ በመንገዱ ጉዟቸውን ቀጠሉ፣ ሳሚም በኮረብታው ጥግ ጥግ እየሄደ ድንጋይ ይወረውር አቧራም ይበትንበት ነበር፡፡ 14ከዚህ በኋላ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ደከሙ፣ እነርሱም ለምሽቱ በሚቆሙበት ጊዜ እርሱ ዕረፍቱ አደረገ፡፡15አቤሴሎምና ከእነርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ በበኩላቸው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፣ አኪጦፌልም ከእርሱ ጋር ነበረ፡፡ 16የዳዊት ወዳጅ፣ አርካዊው ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ፣ “ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ንገሥ! ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ንገሥ!” አለው፡፡17አቤሴሎምም ኩሲን፣ “ለወዳጅህ ያለህ ታማኝነት ይሄ ነው? ለምን ከእርሱ ጋር አልሄድህም?” አለው፡፡ 18ኩሲም አቤሴሎምን፣ “አይሆንም፣ ይልቁኑ እግዚአብሔርና ይህ ሕዝብ እንዲሁም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ከመረጡት ከእርሱ ጋር ነው እኔ የምሆነው፣ ከእርሱም ጋር እቆያለሁ፡፡19ላገለግለው የሚገባኝ ሰው ማን ነው? በልጁስ ፊት ላገለግል አይገባኝምን? በአባትህ ፊት እንዳገለገልሁ በአንተም ፊት አገለግላለሁ፡፡”20ከዚያ በኋላ አቤሴሎም ለአኪጦፌል፣ “ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክርህን ስጠን” አለው፡፡ 21አኪጦፌልም ለአቤሴሎም፣ “ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ አባትህ ከተዋቸው ቁባቶቹ ጋር ግባና ተኛ፣ ከዚያም አንተ ለአባትህ መጥፎ ጠረን እንዳለው ሰው እንደሆንክበት እስራኤል ሁሉ ይሰማል፤ ከዚያም ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች ሁሉ እጅ ይበረታል፡፡”22ስለዚህ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ ለአቤሴሎም ድንኳን ተከሉለት፤ አቤሴሎምም መላው እስራኤል እያየው ከአባቱ ቁባቶች ጋር ተኛ፡፡ 23በዚያን ጊዜ አኪጦፌል ይሰጠው የነበረው ምክር ከእግዚአብሔር ከራሱ አፍ እንደ መስማት ያለ ነበር፡፡ ዳዊትም ሆነ አቤሴሎም ለአኪጦፌል ምክር የነበራቸው ግምት እንደዚህ ነበር፡፡
1ከዚህ በኋላ አኪጦፌል ለአቤሴሎም፣ “አሥራ ሁለት ሺህ ሰው መርጬ በዛሬይቱ ሌሊት አባትህን አሳድደዋለሁ፤ 2በደከመውና ዐቅም ባነሰው ጊዜ ድንገት ደርሼ በማስፈራት አስደንቀዋለሁ፤ አብሮት ያለው ሕዝብም ይሸሻል፣ በንጉሡ ላይ ብቻ ጥቃት አደርስበታለሁ፡፡ 3ሙሽራ ወደ ባሏ እንደምትመጣ ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንተ ሥር በሰላም ይሆናል፡፡” 4አኪጦፌል የተናገረውም አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ደስ አሰኛቸው፡፡5ከዚያ በኋላ አቤሴሎም፣ “አርካዊውን ኩሲን አሁን ጥሩትና እስቲ፣ እርሱ ደግሞ የሚለውን እንስማ” አለ፡፡ 6ኩሲ ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ፣ አኪጦፌል ያለውን ከገለጸለት በኋላ፣ ኩሲን፣ “አኪጦፌል ያለውን እናድርግ? ካልሆነም የምትመክረንን አንተ ንገረን፡፡” 7ስለዚህ ኩሱ ለአቤሴሎም፣ “አኪጠፌል በዚህን ጊዜ የሰጠው ምክር መልካም አይደለም፡፡” ካለ በኋላ፣8ኩሲ በመቀጠል፣ “አባትህና ሰዎቹ ብርቱ ተዋጊዎችና ግልገሎቿ በሜዳ እንደተነጠቁባት ድብ መራሮች እንደሆኑ አንተ ታውቃለህ፡፡ አባትህ የጦር ሰው ነው፣ በዛሬው ሌሊት ከሠራዊቱ ጋር አይተኛም፡፡ 9እነሆ፣ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል፡፡ በውጊያው መጀመሪያ ላይ ከአንተ ሰዎች ጥቂቶቹ ቢሞቱ፣ ያንን የሰማ ማንኛውም ሰው፣ ‘አቤሴሎምን ይከተሉ በነበሩት ላይ እልቂት ተፈጽሟል’ ይላል፡፡ 10ከዚያ በኋላ አባትህ ኃያል ሰው ስለሆነና ከእርሱም ጋር ያሉት በጣም ብርቱዎች መሆናቸውን መላው እስራኤል ስለሚያውቅ ልባቸው እንደ አንበሳ ልብ የሆነው እጅግ ጀግና የሆኑት እንኳን ይፈራሉ፡፡11ስለዚህ እኔ የምመክርህ በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ የሆነው ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለው መላው የእስራኤል ሕዝብ ወደ አንተ ይሰብሰብ፣ አንተም በግልህ ወደ ጦርነቱ ግባ፡፡ 12ከዚያ በኋላ እርሱ በየትኛውም ቦታ ቢሆን እንመጣበታለን፣ ጤዛም ምድርን እንደሚሸፍን በላዩ ላይ እንወድቅበታለን፡፡ ከእርሱ ማንኛውንም ሰው ወይም እርሱን ራሱንም እንኳን ቢሆን በሕይወት አንተውም፡፡13ወደ አንዲት ከተማ የሚያፈገፍግ እንኳ ቢሆን፣ እስራኤል ሁሉ ገመድ አምጥቶ አንድ እንኳ እስከማይቀር ድረስ ከተማይቱን ወደ ወንዝ ውስጥ ስበን እንከታታለን፡፡” 14ከዚያም አቤሴሎምና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ፣ “የአርካዊው ኩሲ ምክር ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የተሻለች ነች” አሉ፡፡ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ይመጣ ዘንድ እግዚአብሔር የአኪጦፌል መልካም ምክር ተቀባይነት እንዳያገኝ አደረገ፡፡15ከዚያም ኩሲ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፣ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው መክሮአቸው ነበር፣ እኔ ግን የተለየ ምክር ሰጠኋቸው፡፡ 16እንግዲህ እናንተ ፈጥናችሁ ወደ ዳዊት ዘንድ ሂዱና ፣ ‘በአረባ ባለው የወንዙ መሻገሪያ እንዳታድር፣ ነገር ግን እንደ ምንም ብለህ ተሻገር፤ አለበለዚያ ንጉሡና አብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ትዋጣላችሁ’ በሉት፡፡”17በዚህ ጊዜ፣ ዮናታንና አኪማአስ በዓይንሮጌል ባለችው ምንጭ ይጠብቁ ነበር፣ ወደ ከተማ ሲገቡ እንዳይታዩ አንዲት ሴት አገልጋይ ወደ እነርሱ እየሄደች መልእከቶችን ታቀብላቸው ነበር፤ እነርሱም በዚያን ጊዜ ለዳዊት ሄደው ይነግሩት ነበር፡፡ 18በዚህን ጊዜ ግን አንድ ወጣት አያቸውና ለአቤሴሎም ሄዶ ነገረ፡፡ ስለዚህ ዮናታንና አኪማአስ ፈጥነው በግቢው ውስጥ የውሃ ጉድጓድ ወደነበረው በብራቂም ወደ ነበረ ሰው ቤት መጡ፡፡19የሰውዬው ሚስት የውሃ ጉድጓዱን መሸፈኛ ወስዳ በጉድጓዱ አፍ ላይ ዘረጋችው ከዚያ በኋላም ዮናታንና አኪማአስ በውሃ ጉድጓድ ዘንድ እንዳሉ ማንም እንዳያውቅ በላዩ ላይ እህል አሰጣችበት፡፡ 20የአቤሴሎም ሰዎች በቤት ወደነበረችው ሴትዮ መጡና፣ “አኪማአስና ዮናታን ወዴት አሉ?” አሏት፤ እርሷም፣ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” አለቻቸው፡፡ ስለዚህ ፈልገው ሊያገኟቸው ስላልቻሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡21እነርሱ ከሄዱ በኋላ አኪማአስና ዮናታን ከጉድጓዱ ወጡ፤ ወደ ዳዊትም ዘንድ ሄደው፣ “ተነሣና ፈጥነህ ወንዙን ተሻገር፣ ምክንያቱም አኪጦፌል አንተን በሚመለከት እንደዚህና እንደዚያ ብሎ ምክር ሰጥቶአል፡፡” 22ከዚያ በኋላ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበረው ሕዝብ ተነሡ፣ የዮርዳኖስንም ወንዝ ተሻግረው ሄዱ፤ ሲነጋም ዮርዳኖስን መሻገር አቅቶት የቀረ አንድም ሰው አልነበረም፡፡23አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተቀበሉት ባየ ጊዜ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወዳለበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፣ ጉዳዩንም መልክ ካስያዘ በኋላ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፡፡ በዚህ አኳኋን ሞተና በአባቱ መቃብር ተቀበረ፡፡24ከዚያ በኋላ ዳዊት ወደ መሃናይም መጣ፤ አቤሴሎምም ከእርሱ ጋር ከነበሩት ከመላው የእስራኤል ሰዎች ጋር ዮርዳኖስን ተሻገረ፡፡ 25ከዚህ በኋላም አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ አሜሳይን በሠራዊቱ ላይ ሾመ፤ አሜሳይ የእስራኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበር፡፡ ዮቴር ከኢዮአብ እናት ከጽሩያ እህት ከናዖስ ልጅ ከአቢግያ ጋር ተኝቶ የነበረ ነው፡፡ 26ከዚህ በኋላ እስራኤላውያንና አቤሴሎም ከበገለዓድ ምድር ሰፈሩ፡፡27ዳዊት ወደ መሃናይም በመጣ ጊዜ ከአሞናውያን ከተማ ከራባ የመጣው፣ የናዖስ ልጅ ሾቢ፣ ከሎዶባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ፣ 28መተኛ ምንጣፎችና ብርድ ልብሶች፣ ጎድጓዳ ሳህኖችና ድስቶች እንዲሁም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ይበሉ ዘንድ ስንዴ፣ የገብስ ዱቄት፣ የተጠበሰ እሸት፣ ባቄላ፣ ምስር፣ 29ማር፣ ቅቤ፣ በግና እርጎ አመጡ፡፡ እነዚህ ሰዎች፣ “ሕዝቡ በምድረ-በዳ ተርቦአል፣ ደክሞአል ደግሞም ተጠምቶአል” ብለው ነበር፡፡
1ዳዊት አብሮት የነበሩትን ወታደሮች ቆጠረ፤ በእነርሱም ላይ የሻለቆችንና የመቶ አለቆችን ሾመላቸው፡፡ 2ከዚህ በኋላ ዳዊት ሠራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፣ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩይ ልጅ በአቢሳ፣ ሲሦውን ደግሞ በጌታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው፡፡ ንጉሡም ለሠራዊቱ፣ “እኔ ራሴም አብሬአችሁ በእርግጥ እወጣለሁ” አላቸው፡፡3ሰዎቹ ግን፣ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፣ ሰዎቹ ስለ እኛ ግድ አይኖራቸውም ወይም ከእኛ ግማሻችን እንኳን ብንሞት ደንታም የላቸውም፡፡ አንተ ግን ከእኛ አሥር ሺሁ ያህል ነህ፤ ስለዚህ በከተማ ሆነህ ልትረዳን ዝግጁ ብትሆን የተሻለ ነው፡፡” አሉት፡፡ 4ስለዚህ ንጉሡ፣ “መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አደርጋለሁ” አላቸው፡፡ ስለዚህ ሠራዊቱ ሁሉ በመቶና በሺህ እየሆነ ተሰልፎ ሲወጣ ንጉሡ በከተማይቱ ቅጥር በር ቆሞ ነበር፡፡5ንጉሡ ኢዮአብን፣ አቢሳንና ኢታይን፣ “ለእኔ ስትሉ ለወጣቱ ለአቤሴሎም ራሩለት” ብሎ አዘዛቸው፡፡ ሕዝቡ ሁሉ አቤሴሎምን በሚመለከት ንጉሡ ይህንን ትዕዛዝ ለአዛዦቹ ሲሰጣቸው ሰሙ፡፡6ስለዚህ እስራኤልን ይወጋ ዘንድ ሠራዊቱ ከከተማ ወጣ፤ ውጊያውም እስከ ኤፍሬም ደን ተስፋፋ፡፡ 7በዚያ የእስራኤል ሠራዊት በዳዊት ወታደሮች ድል ሆነ፤ በዚያ ሃያ ሺህ ሰው የሞተበት ታላቅ እልቂት በዚያ ቀን ነበረ፡፡ 8ውጊያው በገጠሩ ሁሉ ተስፋፋ፣ በሰይፍ ካለቀውም ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረበው ሰው በለጠ፡፡9አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ከጥቂቶቹ ጋር ተገናኘ፡፡ አቤሴሎምም በበቅሎው እየጋለበ ነበር፤ በቅሎውም ጥቅጥቅ ያሉ ቅርንጫፎች በነበሩት የወርካ ዛፍ ሥር ያልፍ ነበርና ራሱ በዛፉ ቅርንጫፎች ተያዘ፡፡ የተቀመጠበት በቅሎ ከሥሩ አልፎ ሲሄድ እርሱ በሰማይና በምድር ተንጠልጥሎ ቀረ፡፡ 10አንድ ሰው ይህንን ተመልክቶ፣ “እነሆ፣ አቤሴሎም በወርካ ዛፍ ላይ ተንጥልጥሎ አየሁት” ብሎ ለኢዮአብ ነገረው፡፡ 11ኢዮአብም ስለ አቤሴሎም ለነገረው ሰው፣ “እነሆ፣ አንተ አየኸው፣ ታዲያ መትተህ ለምን ወደ መሬት አልጣልከውም? እኔ አሥር የብር ሰቅልና ቀበቶ በሸለምኩህ ነበር፡፡”12ሰውዬውም ለኢዮአብ፣ “አሥር ሺህ ሰቅል የምቀበል ብሆንም እንኳን እጄን ዘርግቼ የንጉሡን ልጅ ባልነካሁም ነበር፤ ምክንያቱም አንተን፣ አቢሳንና ኢታይን ንጉሡ፣ ‘አንድም ሰው ወጣቱን አቤሴሎምን እንዳይነካው’ ብሎ ሲያዛችሁ ሁላችንም ሰምተናል፡፡ 13ውሸት በመናገር ሕይወቴን አደጋ ላይ ብጥል እንኳን (ከንጉሡ የሚደበቅ ምንም ነገር አይኖርምና) አንተ ታጋልጠኝ ነበር፡፡” አለው፡፡14ከዚህ በኋላ ኢዮአብ፣ “እኔ አንተን አልጠብቅም” አለ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብ ሦስት ጦር ወስዶ ገና በሕይወት እያለና በወርካው ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሳለ በአቤሴሎም ልብ ላይ ተከላቸው፡፡ 15ከዚያ በኋላም ከኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች አሥሩ አቤሴሎምን በመክበብ ወግተው ገደሉት፡፡16ከዚያም ኢዮአብ ቀንደ-መለከቱን ነፋ፣ ኢዮአብም ከልክሏቸው ስለነበረ ሠራዊቱ እስራኤልን ከማሳደድ ተመለሰ፡፡ 17አቤሴሎምን ወስደው በጫካ ውስጥ ወደነበረ አንድ ትልቅ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ እስራኤልም ሁሉ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ በሚሸሽበት ጊዜ በአስከሬኑ ላይ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት፡፡18አቤሴሎም፣ “የስሜን መታሰቢያ የሚያስጠራ ልጅ የለኝምና” በማለት ገና በሕይወቱ ሳለ ለራሱ አንድ ትልቅ የድንጋይ ሐውልት በንጉሡ ሸለቆ አቁሞ ነበር፡፡ ሐውልቱንም በስሙ ጠርቶት ስለነበረ፣ እስከዚህ ቀን ድረስ ‘የአቤሴሎም ሐውልት’ ተብሎ ይጠራል፡፡19በዚህ ጊዜ የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እንዳዳነው ሄጄ ለንጉሡ የምሥራች ልንገረው አለ፡፡ 20ኢዮአብም፣ “ዛሬ የምሥራቹን የምታደርስለት አንተ አይደለህም፣ ሌላ ጊዜ ታደርስለታለህ፤ የንጉሡ ልጅ ስለሞተ ምንም የምሥራች አታደርስም፡፡”21ከዚያም ኢዮአብ ለአንድ ኩሻዊ፣ “ሂድና ለንጉሡ ያየኸውን ተናገር” አለው፡፡ ኩሻዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ፡፡ 22የሳዶቅ ልጅ አኪማአስም እንደገና ለኢዮአብ፣ “ምንም ዓይነት ነገር ይሁን፣ እባክህ፣ ኩሻዊውን ተከትዬው ልሩጥ” አለው፡፡ ኢዮአብም፣ “ለየምሥራቹ ምንም ብድራት እንደማታገኝ እያወቅህ፣ ልጄ ሆይ፣ ለምን ትሮጣለህ?” ብሎ መለሰለት፡፡ 23“የሆነው ይሁን፣ እሮጣለሁ” አለ፣ አኪማአስ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብ ፣ “እንግዲያውስ፣ ሩጥ” ብሎ መለሰለት፡፡ ከዚያም አኪማአስ በሜዳው መንገድ በኩል ሮጠ፣ ኩሻዊውንም ቀደመው፡፡24ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ነበር፡፡ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ዓይኑን አንስቶ ሲመለከት አንድ ብቻውን የሚሮጥ ሰው እየተቃረበ ነበር፡፡ 25ጠባቂው ተጣራና ለንጉሡ ነገረው፤ ከዚያም ንጉሡ፣ “ብቻውን ከሆነ መልካም ዜና በአንደበቱ አለ” አለ፡፡ ሯጩ እየተጠጋ መጥቶ ወደ ከተማይቱ ቀረበ፡፡26ከዚያም ጠባቂው ሌላ የሚሮጥ ሰው አስተዋለ፤ ጠባቂውም ዘበኛውን ጠራና፣ “እነሆ፣ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አለ” አለው፡፡ ንጉሡም፣ “እርሱም መልካም ዜና አለው” አለ፡፡ 27ስለዚህ ጠባቂው፣ “ከፊት እየሮጠ ያለው ሰው አሯሯጥ የሳዶቅን ልጅ የአኪማአስን ሩጫ ይመስለኛል” አለ፡፡ ንጉሡም፣ “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፣ እርሱም የሚመጣው የምሥራች ይዞ ነው” አለ፡፡28ከዚያ በኋላ አኪማአስ ተጣርቶ ለንጉሡ፣ “ሁሉም ደኅና ነው” አለና በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሥቶ፣ ወደ መሬት እያቀረቀረ፣ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ የተባረከ ይሁን” አለው፡፡ 29ንጉሡም፣ “ወጣቱ አቤሴሎም ደህና ነውን? ሲል ጠየቀ፡፡ አኪማአስም፣ “ኢዮአብ እኔን የንጉሡን አገልጋይ በላከኝ ጊዜ ትልቅ ሁካታ ነበር፣ ምን እንደሆነ ግን እኔ አላወቅሁም” አለው፡፡ 30ከዚያ በኋላ ንጉሡ፣ “እልፍ በልና ቁም” አለው፡፡ ስለዚህ አኪማአስ እልፍ ብሎ ዝም ብሎ ቆመ፡፡31ከዚያ በኋላ ወዲያውኑ ኩሻዊው ደረሰና፣ “ለጌታዬ ለንጉሡ የምሥራች አለኝ፣ እግዚአብሔር በንጉሡ ላይ የተነሡብህን ሁሉ ዛሬ ተበቅሎልሃልና” አለው፡፡ 32ንጉሡም ኩሻዊውን፣ “ወጣቱ አቤሴሎም ደህና ነውን?” አለው፡፡ ኩሻዊውም፣ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶች እንዲሁም በእርሱ ላይ ጉዳት ለማድረስ በአንተ ላይ የሚነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ” ብሎ መለሰለት፡፡ 33በዚያን ጊዜ ንጉሡ ጥልቅ የሆነ ሐዘን አዘነ፤ በቅጥሩ በር ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ገብቶም አለቀሰ፡፡ እየሄደም ሳለ፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ልጄ፣ ልጄ!” እያለ ያለቅስ ነበር፡፡
1“እነሆ፣ ንጉሡ ለልጁ ለአቤሴሎም እያለቀሰ ነው” ተብሎ ለኢዮአብ ተነገረው፡፡ 2“ንጉሡ ለልጁ እያለቀሰ ነው” የሚለውን ሠራዊቱ በዚያን ቀን ሰምቶ ስለነበረ፣ የዚያን ቀኑ ድል ለሠራዊቱ ወደ ኃዘን ቀንነት ተለወጠ፡፡3ከጦርነት ሸሽተው የሚመጡ በኀፍረት ሹልክ ብለው እንደሚገቡ በዚያን ቀን ወታደሮቹ ሹልክ ብለው ወደ ከተማ ይገቡ ነበር፡፡ 4ንጉሡ ፊቱን ሸፍኖና ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፣ አቤሴሎም፣ ልጄ፣ ልጄ!” እያለ አለቀሰ፡፡5ከዚያም ኢዮአብ ወደ ቤት ወደ ንጉሡ ዘንድ ገብቶ፣ “የሚወዱህን ትጠላለህና የሚጠሉህንም ትወዳለህና ዛሬ ሕይወትህን፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሕይወት፣ የሚስቶችህን ሕይወት እንዲሁም የቁባቶችህን ሕይወት ያዳኑትን የወታደሮችህን ሁሉ ፊት አሳፍረሃል፡፡ 6የሚጠሉህን ትወዳለህ የሚወዱህን ትጠላለህ፤ የጦር አዛዦችና ወታደሮች ለአንተ ምንም እንዳይደሉ ዛሬ አሳይተሃልና፡፡ ዛሬ አቤሴሎም በሕይወት በኖረና እኛ ሁላችንም ብንሞት፣ ያ ደስ ያሰኝህ እንደነበረ አምናለሁ፡፡7ስለዚህ አሁንም ተነሥተህ ውጣና ለወታደሮችህ በትሕትና ተናገራቸው፣ ባትሄድ ግን፣ በእግዚአብሔር ስም እምላለሁ፣ በዛሬው ሌሊት አንድም ሰው ከአንተ ጋር አይቀርም፡፡ ይሄ ደግሞ ከልጅነትህ ጀምሮ እስካሁን ከደረሰብህ መከራ ሁሉ የከፋ ይሆንብሃል፡፡” 8ስለዚህ ንጉሡ ተነሥቶ በከተማይቱ በር አጠገብ ተቀመጠ፣ ለሰዎችም ሁሉ፣ “እነሆ፣ ንጉሡ በበሩ ተቀምጦአል” ተብሎ ተነገራቸው፡፡ ከዚያ በኋላም ሰዎች ሁሉ በንጉሡ ፊት መጡ፡፡ በዚህን ጊዜ በእስራኤል ሰው ሁሉ ወደየቤቱ ሸሽቶ ነበር፡፡9በመላው እስራኤል በየነገዱ ያሉ ሰዎች ሁሉ እርስ በርሳቸው፣ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ አስጥሎናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፤ አሁን ደግሞ ከአቤሴሎም ሸሽቶ ከአገር ወጥቷል፡፡ 10በላያችን ላይ የቀባነውም አቤሴሎም በጦርነቱ ተገድሏል፡፡ ስለዚህ ንጉሡን መልሰን ስለማምጣት ለምን አንነጋገርም?” እያሉ ይነጋገሩ ነበር፡፡11ንጉሥ ዳዊት ወደ ካህናቱ ወደ ሳዶቅና ወደ አብያታር ልኮ፣ “ለይሁዳ ሽማግሌዎች፣ ‘ወደ ቤተ መንግሥቱ ይመልሰው ዘንድ የመላው የእስራኤል ልብ ለንጉሡ ድጋፍ የሚሰጥ ነውና፣ ንጉሡን ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ እናንተ የመጨረሻዎቹ የምትሆኑት ለምንድን ነው? 12እናንተ የሥጋዬ ቁራጭ የአጥንቴ ፍላጭ ናችሁ፡፡ ታዲያ፣ ንጉሡን ለመመለስ እናንተ የመጨረሻዎቹ የሆናችሁት ለምንድን ነው?’13ለአሜስያም፣ ‘አንተስ የሥጋዬ ቁራጭ የአጥንቴ ፍላጭ አይደለህምን? ከአሁን ጀምሮ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ ባለደርግህ እግዚአብሔር ይህንን ያድርግብኝ፣ ከዚህም የባሰ ይጨምርብኝ’” በሉ ብሎ መልእክት ላከ፡፡ 14“አንተና ሰዎችህ ሁሉ ተመለሱ” ብለው ወደ ንጉሡ መልእከት እስኪልኩ ድረስ የአንድ ሰው ልብ እንደነበራቸው ያህል የይሁዳን ሁሉ ልብ ማረከ፡፡ 15ስለዚህ ንጉሡ ተመልሶ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ የይሁዳም ሰዎች ዮርዳኖስን ሲሻገር ለማጀብ፣ ንጉሡን ለመገናኘት ወደ ጌልጌላ መጡ፡፡”16ከብራቂም የሆነው የጌራ ልጅ ሳሚ ንጉሥ ዳዊትን ለመቀበል ከይሁዳ ሰዎች ጋር ፈጥኖ ወረደ፡፡ 17ከእርሱ ጋር ከብንያም አንድ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ ደግሞም ከሲባ ከሳዖል አገልጋይ ጋር አሥራ አምስት ልጆቹና ሃያ አገልጋዮቹ ነበሩ፡፡ በንጉሡ ፊት ዮርዳኖስን አቋረጠው ተሻገሩ፡፡ 18የተሻገሩት የንጉሡን ቤተሰብ ለማምጣትና እርሱ መልካም ነው ያለውን ለማድረግ ነበር፡፡19ሳሚ ለንጉሡ፣ “ጌታዬ እኔን በደለኛ አድርጎ አይቁጠረኝ ወይም ጌታዬ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም በወጣበት ቀን ባሪያህ በግትረኛነት ያደረገውን ትኩረት አይስጠው፡፡ ንጉሥ ሆይ፣ እባክህ ይህንን በልብህ አታኑረው፡፡ 20ባሪያህ ኃጢአት ማድረጌን አውቃለሁ፡፡ ከመላው የዮሴፍ ቤት ጌታዬ ንጉሡን ለመቀበል የመጀመሪያ ሆኜ ዛሬ የመጣሁት እነሆ፣ ለዚህ ነው፡፡” አለ፡፡21ነገር ግን የጽሩይ ልጅ አቢሳ፣ “እግዚአብሔር የቀባውን ተራግሟልና ስለዚህ ጉዳይ ሳሚ ሊገደል አይገባውምን?” 22ከዚያ በኋላ ዳዊት፣ “ዛሬ ለእኔ ጠላቶች ትሆኑኝ ዘንድ እናንተ የጽሩያ ልጆች ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ዛሬ በእስራኤል አንድ ሰው ሊገደል ይገባዋል? በእስራኤል ላይ ንጉሥ መሆኔን ያወቅሁት በዛሬው ቀን አይደለምን?” 23ስለዚህ ንጉሡ ለሳሚ፣ “አትሞትም” አለው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ በመሐላ ቃል ገባለት፡፡24ከዚያ በኋላ የሳዖል ልጅ ሜምፊቦስቴ ንጉሡን ለመቀበል መጣ፡፡ ንጉሡ ከሄደበት ቀን ጀምሮ በሰላም ወደ ቤቱ እስከተመለሰበት ቀን ድረስ በእግሩ ሱሪ አላስገባም፣ ጢሙን አልተላጨም ወይም ልብሱን አላጠበም፡፡ 25ስለዚህም ንጉሡን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ፣ ንጉሡ፣ “ሜምፊቦስቴ ከእኔ ጋር ለምን አልሄድክም?” አለው፡፡26እርሱም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ አገልጋዬ አታለለኝ፣ ምክንያቱም፣ ‘እኔ ባሪያህ ሽባ ስለሆንኩኝ እንድቀመጥበትና ከንጉሡ ጋር እንድሄድ አህያዬን እጭናለሁ’ ብዬ ነበርና፡፡ 27አገልጋዬ ሲባ እኔን ባሪያህን ለጌታዬ ለንጉሡ አማ፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነው፡፡ ስለዚህ በዓይንህ ፊት መልካም መስሎ የታየህን አድርግብኝ፡፡ 28የአባቴ ቤት ሰዎች ሁሉ በጌታዬ በንጉሡ ዘንድ የሞት ሰዎች ነበሩና፤ ነገር ግን ባሪያህን በገበታህ ከሚበሉት አንዱ አድርገህ አስቀመጥኸኝ፡፡ ስለዚህ አሁንም በንጉሡ ፊት ልቅሶዬን ለመቀጠል እኔ ምን መብት አለኝ?”29ከዚያ በኋላም ንጉሡ፣ “ከዚህ በላይ መግለጫ መስጠት ምን ያስፈልጋል? እርሻውን አንተና ሲባ እንድትካፈሉት ወስኛለሁ፡፡” 30ስለዚህ ሜምፊቦስቴ ለንጉሡ፣ “ጌታዬ ንጉሡ ወደ ራሱ ቤት በሰላም ስለመጣ፣ ግድ የለም፣ እርሱ ሁሉንም ይውሰደው” አለው፡፡31ከዚያም ገለዓዳዊው ቤርዜሊ ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን ለመሻገር ከሮግሊም መጣ፣ ንጉሡም ዮርዳኖስን ሲሻገር አጀበው፡፡ 32ቤርዜሊ ሰማንያ ዓመት የሆነው ሽማግሌ ሰው ነበር፡፡ እጅግ ባለጠጋ ሰው ስለነበረ፣ ንጉሡ በመሃናይም በቆየበት ጊዜ ስንቅ አምጥቶለት ነበር፡፡ 33ንጉሡም ለቤርዜሊ፣ “ከእኔ ጋር ና፣ እኔ በኢየሩሳሌም የምትመገበውን አቀርብልሃለሁ” አለው፡፡34ቤርዜሊም ለንጉሡ፣ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም እሄድ ዘንድ ከሕይወት ዘመኔ ምን ያህል ቢቀር ነው? 35እኔ ሰማንያ ዓመቴ ነው፤ መልካሙንና ክፉውን መለየት እችላለሁን? ባሪያህ የሚበላውንስ ሆነ የሚጠጣውን ጣዕም መለየት ይችላልን? የሚዘፍኑ ወንዶችንና የሚዘፍኑ ሴቶችን ከእንግዲህ መስማት እችላለሁን? ስለዚህ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ላይ ለምን ሸክም ይሆናል? 36ባሪያህ የሚፈልገው ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን መሻገር ብቻ ነው፡፡ ንጉሡ ለባሪያው ይህንን ያህል ብድራት ለምን ይከፍለኛል?37በአገሬ እሞት ዘንድ፣ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ እቀበር ዘንድ፣ እባክህ ወደ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ፡፡ ነገር ግን አገልጋይህ ከመዓም ከዚህ አለ፣ እርሱ ከአንተ ጋር ይሻገር፣ የመሰለህን መልካም ነገር አድርግለት፡፡”38ንጉሡም፣ “ከመዓም ከእኔ ጋር ይሻገራል፣ ለአንተም መልካም መስሎ የታየህን አደርግለታለሁ፤ ከእኔም የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር እኔ አደርግልሃለሁ፡፡” 39ከዚያም ሰዎቹ ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ ከዚያም ንጉሡ ተሻገረ፣ ንጉሡም ቤርዜሊን ሳመው ባረከውም፡፡ ከዚህ በኋላ ቤርዜሊ ወደ ራሱ አገር ተመለሰ፡፡40ስለዚህ ንጉሡ ወደ ጌልጌላ ተሻገረ፣ ከመዓምም ከእርሱ ጋር ተሻገረ፡፡ የይሁዳ ሠራዊት ንጉሡንና የእስራኤልን ግማሽ ሠራዊት ይዞ ተመለሰ፡፡ 41ወዲያውም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጥተው ለንጉሡ፣ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች አንተን ዳዊትንና ቤተሰቡን እንዲሁም የዳዊትን ሰዎች ሰርቀው ዮርዳኖስን አሻግረው ለምን አመጧቸው?”42ስለዚህ የይሁዳ ሰዎች ለእስራኤል ሰዎች፣ “ይህንን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለሆነ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ በዚህ ለምን ትቆጣላችሁ? እኛ የበላነውና ንጉሡ መክፈል ያለበት አንዳች ነገር አለ? ለእኛስ አንዳች ስጦታ ሰጥቶናል?” 43የእስራኤል ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች፣ “እኛ ከዳዊት ጋር የሚዛመዱ አሥር ነገዶች አሉን፣ ስለዚህ እኛ ከእናንተ ይልቅ በዳዊት ዘንድ መብት አለን፡፡ ታዲያ እናንተ እኛን ለምን ትንቁናላችሁ? ንጉሡን ለማምጣት ያቀረብነው ሃሳብ በመጀመሪያ ሊሰማ የሚገባው አልነበረምን? ነገር ግን የይሁዳ ሰዎች የሰጡት መልስ የእስራኤል ሰዎች ከሰጡት መልስ ይልቅ እጅግ የከረረ ነበር፡፡”
1በዚህ ጊዜ በዚሁ ስፍራ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የተባለ አንድ ችግር ፈጣሪ ብንያማዊ ነበር፡፡ እርሱም መለከት ነፍቶ፣ “እኛ ከዳዊት ጋር ድርሻ የለንም፣ ከእሴይ ልጅም ጋር ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ ይመለስ” አለ፡፡ 2ስለዚህ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዳዊትን ከድተው የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ተከተሉ፡፡ የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንስተው እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ንጉሣቸውን አጥብቀው ተከተሉ፡፡3ዳዊት በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ በመጣ ጊዜ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥሩን ቁባቶች በአንድ ቤት ውስጥ አስገብቷቸው በአንድ ዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፡፡ የሚያስፈልጋቸውን አቀረበላቸው፣ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር አልተኛም፡፡4እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ተዘግቶባቸው እንደ መበለት ይኖሩ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ንጉሡ ለአሜሳይ፣ “በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እንዲሰባሰቡ ጥራቸው፣ አንተም እዚህ መገኘት አለብህ” አለው፡፡ 5ስለዚህ አሜሳይ የይሁዳ ሰዎች እንዲሰባሰቡ ለመጥራት ሄደ፣ ነገር ግን ንጉሡ ካዘዘው ቀነ-ገደብ በላይ ቆየ፡፡6ስለዚህ ዳዊት ለአቢሳ፣ “አሁን የቤክሪ ልጅ ሳቤዔ አቤሴሎም ካደረሰው ይልቅ የባሰ ጉዳት ያደርስብናል፡፡ የጌታህን አገልጋዮች ወታደሮቼን ያዝና አሳደው፣ አለበለዚያ የተመሸጉ ከተሞችን ያገኝና ከዓይናችን ይሰወራል፡፡” አለው፡፡ 7በዚያን ጊዜ የኢዮአብ ሰዎች ከከሊታውያን ከፈሊታውያን እንዲሁም ከሌሎች ኃያላን ጦረኞች ጋር ተከትለውት ወጡ፡፡ የቤክሪን ልጅ ሳቤዔን ያሳድዱ ዘንድ ከኢየሩሳሌም ወጡ፡፡8ገባዖን ከሚገኘው ታላቅ ዐለት በደረሱ ጊዜ አሜሳይ ሊገናኛቸው መጣ፣ ኢዮአብ በሰገባው ውስጥ የገባ ሰይፍ በወገቡ የታጠቀበትን ቀበቶ የሚያካትት የጦር ሜዳ ልብሱን ለብሶ ነበር፡፡ ወደፊት እየተራመደ ሳለም ሰይፉ ወደቀ፡፡9ኢዮአብም አሜሳይን፣ “ወንድሜ ሆይ፣ ደህና ነህን?” አለው፡፡ ኢዮአብም አሜሳይን እንደሚያፈቅረው አድርጎ ለመሳም ጢሙን ይዞ ሳበው፡፡ 10አሜሳይ ኢዮአብ በግራ እጁ ይዞት የነበረውን ጩቤ አላስተዋለም፡፡ ኢዮአብ አሜሳይን ሆዱን ወጋው፣ ሆድ-ዕቃውም በምድር ላይ ተዘረገፈ፡፡ ኢዮአብ እንደገና አልወጋውም፣ አሜሳይም ሞተ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቤክሪን ልጅ ሳቤዔን አሳደዱ፡፡11ከዚያ በኋላ ከኢዮአብ ሰዎች አንዱ በአሜሳይ አጠገብ ቆመና፣ “ኢዮአብን የሚደግፍና የዳዊት የሆነ ኢዮአብን ይከተል” አለ፡፡ 12በዚህን ጊዜ አሜሳይ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፡፡ ሰዎች ሁሉ ቆመው እንደቀሩ ሰውዬው ተመልክቶ የአሜሳይን ሬሳ ከመንገድ ጎትቶ ወደ እርሻ ውስጥ አስገባው፡፡ ወደ አጠገቡ የደረሰ ማንኛውም ሰው ቆሞ ይቀር እንደነበረ ተመልክቶ ልብስ በላዩ ጣል አደረገበት፡፡ 13አሜሳይ ከመንገድ ዞር ከተደረገ በኋላ የቤክሪ ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ሰዎች ሁሉ ኢዮአብን ተከተሉ፡፡14ሳቤዔአም በእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል አልፎ ወደ አቤል ቤትማዓካና ተሰባስበው ሳቤዔን ያሳድዱ ወደነበሩት ወደ መላው የቤክሪያውያን ግዛት መጣ፡፡ 15ደረሱበትና አቤል ቤትመዓካ ላይ ከበቡት፡፡ በከተማይቱም ላይ ግድግዳውን አስጠግተው የአፈር ድልድል ሠሩበት፡፡ ከኢዮአብ ጋር የነበረውም ሠራዊት ግንቡን ለመናድ ደበደበው፡፡ 16ከዚያ በኋላ አንድ ብልህ ሴት ከከተማ ውስጥ ተጣራችና፣ “ስማኝ፣ እባክህን ስማኝ ኢዮአብ፤ እንዳነጋግርህ ወደዚህ ጠጋ በል” አለችው፡፡17ስለዚህ ኢዮአብ ጠጋ አለ፣ ሴቲቱም፣ “አንተ ኢዮአብ ነህን?” አለችው፡፡ እርሱም፣ “አዎን፣ ነኝ” አለ፡፡ እርሷም ከዚያ በኋላ ለእርሱ፣ “የባሪያህን ቃል ስማ” አለችው፡፡ እርሱም፣ “እየሰማሁ ነው” ብሎ መለሰላት፡፡ 18ከዚያ በኋላም እርሷ፣ “በቀደሙት ጊዜያት ‘በእርግጥ ምክርን ከአቤል ጠይቅ ምክሩም ችግሮችን ይፈታል’ ይሉ ነበር፡፡ 19እኛ በእስራኤል ውስጥ እጅግ ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑት ከተሞች አንዱ ነን፡፡ በእስራኤል ውስጥ እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት እየሞከርክ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ርስት ለምን ለመዋጥ ትፈልጋለህ?”20ስለዚህ ኢዮአብ፣ “መዋጥ ወይም ማጥፋት ከእኔ የራቀ ይሁን፣ 21ያ እውነት አይደለም፡፡ ነገር ግን ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር የሆነ ሳቤዔ የተባለ የቤክሪ ልጅ እጁን በንጉሡ ላይ ፣ በዳዊት ላይ አንስቷል፤ እርሱን ብቻ አሳልፋችሁ ስጡኝ፣ ከተማውን ለቅቄ እወጣለሁ” ብሎ መለሰላት፡፡ ሴቲቱም ለኢዮአብ፣ “ራሱ በቅጥሩ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው፡፡ 22ከዚያም ሴቲቱ በጥበብዋ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፡፡ የቤክሪን ልጅ የሳቤዔን ራስ ቆርጠው በቅጥሩ ላይ ለኢዮአብ ወረወሩለት፡፡ እርሱም ቀንደ-መለከቱን ነፋ፣ የኢዮአብም ሰዎች ከተማይቱን ለቀው እያንዳንዱ ሰው ወደየቤቱ ሄደ፡፡23በዚህን ጊዜ ኢዮአብ በሠራዊቱ ሁሉ ላይ የበላይ ነበር፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ደግሞ በከሊታውያንና በፈሊያታውያን ላይ አለቃ ሆነ፡፡ 24አዶኒራም በግዳጅ ሥራ ላይ ለተሰማሩት አለቃ ሆነ፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ ታሪክ ጸሐፊ ሆነ፤ 25ሱሳ ጸሐፊ፣ ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ፤ 26እንዲሁም የኢያዕር ሰው ዒራስ የዳዊት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነ፡፡
1በዳዊት ዘመን ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ራብ ሆነ፣ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ፊት ፈለገ፡፡ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “ሳዖልና ገዳይ ቤተሰቡ ገባዖናውያንን እንዲሞቱ ስላደረገ ይህ ረሃብ በአንተ ላይ ነው” አለ፡፡2እንግዲህ ገባዖናውያን ከአሞራውያን የተረፉ እንጂ የእስራኤል ሕዝብ ወገን አልነበሩም፡፡ የእስራኤል ሕዝብ እንደማይገድሏቸው ምለውላቸው ነበር፣ ሳዖል ግን ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ ከነበረው ቅናት የተነሣ እንዲሁ ሁሉንም የመግደል ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡ 3ስለዚህ ዳዊት ገባዖናውያንን በአንድነት ጠራቸውና፣ “ምን ላደርግላችሁ? የእርሱን በጎነትና ተስፋ ቃሉን የሚወርሱትን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ትባርኩ ዘንድ ስርየትን እንዴት ማድረግ እችላለሁ?” አላቸው፡፡4ገባዖናውያንም፣ “በእኛና በሳዖል ወይም በቤተሰቡ መካከል ያለው የብርና የወርቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ በእስራኤልም ውስጥ ማንም ሰው እንየዲገደል የምናደርግ እኛ አይደለንም፡፡” ብለው መለሱለት፡፡ ዳዊትም፣ “የምትጠይቁትን ማንኛውንም ነገር ቢሆን እኔ ያንን አደርግላችኋለሁ” አላቸው፡፡5እነርሱም ለንጉሡ፣ “እንድንጠፋና በእስራኤል ክልል ውስጥ ምንም ስፍራ እንዳይኖረን ሁላችንንም ለመግደል ሙከራ ካደረገውና በእኛ ላይ ሤራ ካውጠነጠነው 6ከእርሱ ዝርያዎች ሰባት ሰዎች ለእኛ ተላልፈው ይሰጡን እኛም በእግዚአብሔር በተመረጠው በሳዖል አገር በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” አሉት፡፡ ስለዚህ ንጉሡ፣ “እነርሱን እሰጣችኋለሁ” አላቸው፡፡7ንጉሡ ግን በእርሱና በሳዖል ልጅ በዮናታን ስለነበረው የእግዚአብሔር መሐላ የሳዖልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነው፡፡ 8ነገር ግን ንጉሡ የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ለሳዖል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን ወሰዳቸው፣ በተጨማሪም ዳዊት የሳዖል ልጅ ሜልኮል ለመሓላታዊው ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደቻቸውን አምስት ወንዶች ልጆች ወሰዳቸው፣ 9በገባዖናውያንም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም በተራራው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ሰቀሏቸው፣ ሰባቱም አንድ ላይ ሞቱ፡፡ የተገደሉት በመከራ ወቅት፣ የገብስ መከር በሚሰበሰብባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ነበረ፡፡10ከዚያ በኋላ የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ከመከር መሰብሰብ ጊዜ ጀምሮ ዝናብ በእነርሱ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ በአስከሬኖቹ አጠገብ ባለው ተራራ ለራሷ ማቅ ወስዳ ዘረጋች፡፡ የሰማይ ወፎች በቀን፣ የዱር አራዊት በማታ እንዲነኳቸው አልፈቀደችም፡፡ 11የሳዖል ቁባት የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ያደረገችው ለዳዊት ተነገረው፡፡12ስለዚህ የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ሳዖልን በጊልቦዓ ከገደሉት በኋላ ሰቅለውት ከነበረበት ከቤትሻን አደባባይ ከሰረቁት ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ዘንድ ዳዊት ሄዶ አመጣ፡፡ 13ዳዊት ከዚያ ስፍራ የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት እንዲሁም በዚያ የተሰቀሉትን የሰባት ሰዎች አጥንትም ሰብስቦ ወሰደ፡፡14የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት በብንያም አገር በጼላ በአባቱ በቂስ መቃብር ቀበሩአቸው፡፡ ንጉሡም ያዘዘውን ነገር ሁሉ አከናወኑ፡፡ ከዚያ በኋላ ለምድሪቱ የተደረገውን ጸሎት እግዚአብሔር መለሰ፡፡15ከዚያ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር እንደገና ውጊያ ገጠሙ፡፡ ስለዚህ ዳዊት ከሠራዊቱ ጋር ወርዶ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፡፡ ዳዊት በጦርነቱ የሰውነት መዛል አጋጠመው፡፡ 16የኃላኑ ዝርያ የነበረውና የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝነው እንዲሁም አዲስ ሰይፍ የታጠቀው ይሽቢብኖብ ዳዊትን ለመግደል አቀደ፡፡ 17ነገር ግን የጽሩይ ልጅ አቢሳ ፍልስጥኤማዊውን ወግቶ በመግደል ዳዊትንም ታደገው፡፡ ከዚያ በኋላም የዳዊት ሰዎች፣ “የእስራኤል መብራት እንዳታጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት፡፡18ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ የራፋይም ዝርያ የነበረው ኩስታዊው ሴቦካይ ሳፋንን የገደለበት ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር እንደገና ተደረገ፡፡ 19ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ጦርነት የቤተልሔሙ የየዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለ፡፡20ጋዛ ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት በእጆቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች በእግሮቹም ላይ ስድስት ጣቶች ባጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት ታላቅ ቁመት የነበረው ሰው ነበር፡፡ እርሱም የራፋይም ዝርያ ነበር፡፡ 21እርሱም በእስራኤል ላይ ባፌዘ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሣማ ልጅ ዮናታን ገደለው፡፡ 22እነዚህ የጋዛዋ ራፋይም ዝርያዎች ነበሩ፣ እነርሱም በዳዊት እጅና በወታደሮቹ እጅ ተገደሉ፡፡
1እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳዖል እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት በዚህ መዝሙር ያሉትን የቅኔ ቃላት ለእግዚአብሔር ዘመረ፡፡ 2እንዲህም እያለ ጸለየ፣ “እግዚአብሔር ዐለቴ፣ አምባዬና ታዳጊዬ ነው፡፡3እግዚአብሔር የምጠጋበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው፡፡ እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊዬና ከግፍ የሚያድነኝ ነው፡፡ 4ሊመሰገን የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ፡፡5የሞት ማዕበል ከበበኝ፤ የከንቱነት ጎርፍም አጥለቀለቀኝ፡፡ 6የሲዖል ገመድ ተጠመጠመብኝ፣ የሞትም ወጥመድ አጥምዶ ያዘኝ፡፡7በጨነቀኝ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፣ አምላኬን ጠራሁት፣ ከመቅደሱ ድምፄን ሰማኝ፤ ለረድኤት ያደረግሁት ጥሪም ወደ ጆሮው ደረሰ፡፡8በዚያን ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች እግዚአብሔር ተቆጥቶ ነበረና የሰማይ መሠረቶች ተናወጡ ተንቀጠቀጡም፡፡ 9ከአፍንጫው ጢስ፣ ከአፉም ፍሙን የሚያግል የሚንበለበል እሳት፡፡10ሰማይን ከፍቶ ወረደ፣ ድቅድቅ ጨለማም ከእግሩ በታች ነበር፡፡ 11በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፣ በንፋስም ክንፍ ተቀምጦ ሲበር ታየ፡፡ 12በሰማይ ላይ ያሉ ከባድ የዝናብ ደመናዎችን በማሰባሰብ ጨለማን እንደ ድንኳን እንዲከበው አደረገ፡፡13በፊቱ ካለው ነጎድጓድ የእሳት ፍም ወረደ፡፡ 14እግዚአብሔር ከሰማይ አንጎደጎደ፣ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ፡፡ 15ፍላፃውን ወረወረ ጠላቶቹንም በተነ - መብረቁ እንዲበርቅ አደረገ፣ በታተናቸውም፡፡16በዚያን ጊዜ የውሃ መውረጃዎች ታዩ፣ እግዚአብሔር ባስተጋባው የክተት ድምፅ፣ ከአፍንጫው በሚወጣ የእስትንፋስ ግፊት የምድር መሠረቶች ተጋለጡ፡፡17ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፣ እየተንዶለዶለ ካለውም ውሃ አወጣኝ፡፡ 18ብርቱ ከሆነው ጠላቴ፣ ከሚጠሉኝም ታደገኝ፣ በእኔ ላይ እጅግ በርትተውብኝ ነበርና፡፡19በጭንቀቴ ጊዜ መጡብኝ፣ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ፡፡ 20እርሱም ሰፋ ወዳለ ስፍራ አወጣኝ፡፡ በእኔ ደስ ተሰኝቶ ነበርና አዳነኝ፡፡ 21እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መጠን ብድራትን ከፍሎኛል፣ እንደ እጄም ንጽሕና መጠን ወደ ስፍራዬ መልሶኛል፡፡22የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፣ ከአምላኬም ዞር በማለት ክፋትን አላደረግሁም፡፡ 23የጽድቅ ሥርዓቱ በፊቴ ናቸውና፣ ከድንጋጌም ፈቀቅ አላልሁም፡፡24ቅንነቴን በፊቱ ጠብቄ ነበርና፣ ራሴንም ከኃጢአት አርቄ ነበር፡፡ 25ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ ጽድቅ ደረጃዬ፣ በፊቱ ካለኝ የንፅሕና አቋሜ መልሶኛል፡፡26ታማኝ ለሆነው ታማኝነትህን ታሳያለህ፣ ነቀፋ ለሌለበትም ሰው ነቀፋ የሌለብህ መሆንህን ታሳያለህ፡፡ 27ከንጹሖች ጋር ንጹሕ መሆንህን ስታሳይ ለተጣመሙት ግን ጠማማ ነህ፡፡28የተጎሳቆሉትን ታድናለህ፣ ዐይኖችህ ግን በትዕቢተኞች ላይ ነው፣ ታዋርዳቸውማለህ፡፡ 29እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ መብራቴ ነህና፣ እግዚአብሔር ጨለማዬን ያበራል፡፡30በአንተ መሰናክሉን ጥሼ አልፋለሁ፣ በአምላኬ ቅጥሩን እዘላለሁ፡፡ 31የእግዚአብሔር መንገድማ ፍጹም ነው፣ የእግዚአብሔር ቃል ንፁሕ ነው፡፡ ወደ እርሱ ለሚጠጋ ለማንኛውም ሰው ጋሻ ነው፡፡32ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው? 33እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነው፣ ነቀፋ የሌለበትንም ሰው በመንገዱ ይመራዋል፡፡34እንደ ዋላ እግሮች እግሮቼን ፈጣን ያደርጋቸዋል፣ በተራራም ላይ ያቆመኛል፡፡ 35እጆቼን ለውጊያ፣ ክንዴንም የናስ ቀስት ለመለጠጥ ያሠለጥናቸዋል፡፡36የድነትን ጋሻ ሰጥተኸኛል፣ ሞገስህም ታላቅ አድርጎኛል፡፡ 37በእግሮቼ ሥር ያለውን ስፍራ ሰፊ አድርገህልኛል፣ ስለዚህ እግሮቼ አልተንሸራተቱም፡፡38ጠላቶቼን አሳደድኋቸው፣ አጠፋኋቸውም፡፡ እስካጠፋቸውም ድረስ አልተመለስሁም፡፡ 39ፈጽሜ አጠፋኋቸው፣ አደቀቅኋቸውም፣ ተመልሰው መነሣት አይችሉም፡፡ በእግሬ ሥር ወድቀዋል፡፡40እንደ ጦር መታጠቂያ ኃይልን በእኔ ላይ አደረግህ፣ በላዬ ላይ የተነሡትንም ከእኔ በታች አደረግኸቸው፡፡ 41የጠላቶቼን ማጅራት ሰጠኸኝ፣ የሚጠሉኝንም አፈራረስኳቸው፡፡42ዕርዳታ ለማግኘት ተጣሩ ነገር ግን ማንም አላዳነቸውም፣ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም፡፡ 43እንደ አቧራ መሬት ላይ ፈጨኋቸው፣ በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃም ረገጥኋቸው፡፡44ከራሴ ሕዝብ ክርክር አድነኸኛል፣ የሕዝቦችም ራስ አድርገህ አጽንተኸኛል፣ የማላውቀው ሕዝብ ያገለግለኛል፡፡ 45ባዕድ ሕዝቦች ለእኔ ለመስገድ ተገደዱ፣ ስለ እኔ እንደሰሙ ወዲያውኑ ታዘዙኝ፡፡ 46ባዕዳን ከምሽጋቸው እየተንቀጠቀጡ ወጡ፡፡47እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተመሰገነ ይሁን፣ የድነቴ ዐለት እግዚአብሔር ከፍ ይበል፡፡ 48በቀልን የሚበቀልልኝ፣ ሕዝብንም ከእኔ ሥር የሚያደርግልኝ አምላክ ይሄ ነው፡፡ 49ከጠላቶቼ ነፃ ያወጣኛል፡፡ እንዲያውም በእኔ ላይ ከተነሡት በላይ አውጥተኸኛል፡፡ ከግፍኞች ታድገኸኛል፡፡50ስለዚህ እግዚብሔር ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ፣ ለስምህም ምስጋና መዝሙር እዘምራለሁ፡፡ 51እግዚአብሔር ለንጉሡ ታላቅ ድልን ይሰጠዋል፣ ኪዳናዊ ታማኝነቱን እርሱ ለቀባው፣ ለዳዊትና ለዘሮቹ ለዘላለም ያሳየዋል፡፡”
1እነዚህ ተወዳጁ የእስራኤል ዘማሪ፣ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ እጅግ የተከበረው፣ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሎች ናቸው፡፡ 2የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፣ ቃሉም በምላሴ ላይ ነበረ፡፡3የእስራኤል አምላክ ተናገረ፣ የእስራኤልም ዐለት እንደዚህ አለኝ፣ “ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣ በፈሪሀ-እግዚአብሔር የሚያስተዳድር፣ 4እርሱ ከዝናብ በኋላ ብሩሕ በሆነው የፀሐይ ብርሃን ከምድር እንደሚበቅል ለምለም ሣር፣ ደመና የሌለባት ፀሐይ ጥዋት ስትወጣ እንደሚፈነጠቅ የማለዳ ብርሃን ነው፡፡5በእርግጥ የእኔ ቤተሰብ በእግዚአብሔር ፊት እንደዚህ አይደለምን? ከእኔስ ጋር ሥርዓት ያለውና በሁሉም መንገድ እርግጠኛ የሆነ የዘላለም ቃል ኪዳን አልገባምን? ድነቴን ከፍ ከፍ አድርጎ፣ ማንኛውንም ፍላጎቴን አይፈጽምልኝምን?6ነገር ግን በእጅ ሊሰበሰቡ ስለማይችሉ ሁላቸውም እንደሚጣሉ እሾሆች ከንቱዎች ናቸው፡፡ 7እነርሱን የሚነካ የብረት መሣሪያ መጠቀም ወይም የጦር ዘንግ መያዝ ስላለበት ባሉበት መቃጠል ይገባቸዋል፡፡”8የዳዊት ምርጥ ወታደሮች ስም የሚከተለው ነው፡- የታህክሞን ሰው ዮሴብ የሦስቱ አለቆች አለቃና በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰዎችን የገደለ ነው፡፡9ከእርሱ ቀጥሎ የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ ኤልዔዘር ነበረ፣ እርሱም ከሶስቱ ኃያላን ሰዎች አንዱ ነበር፡፡ እርሱም ጦርነት ለመግጠም የተሰባሰቡ ፍልስጥኤማውያን በተገዳደሩ ጊዜና የእስራኤልም ሰዎች በፈገፈጉ ጊዜ በዚያ ነበር፡፡ 10ኤልኤዘር እስኪዝልና እጁ ከሰይፉ ጋር ተጣብቆ እስኪቀር ድረስ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ቆሞ ተዋጋ፡፡ የዚያን ቀን እግዚአብሔር ታላቅ ድል አስገኘ፡፡ ከኤልኤዘር በኋላ ሠራዊቱ የተመለሰው አስከሬኖቹን ለመግፈፍ ብቻ ነበር፡፡11ከእርሱም በኋላ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበር፡፡ ፍልስጥኤማውያኑ የምስር እርሻ በነበረበት ተሰብስበው ሳሉ ሠራዊቱ ከ እነርሱ ሸሸ፡፡ 12ሣማ ግን በእርሻው መካከል ቆሞ ተቋቋማቸው ፍልስጥኤማዊውንም ገደለው እግዚአብሔርም ታላቅ ድል ሰጣቸው፡፡13ከሰላሳዎቹ ወታደሮች ሶስቱ በመከር ጊዜ ወደ አዶላም ዋሻ ወደ ዳዊት ዘንድ ሄዱ፡፡ የፍልስጥኤም ሠራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍረው ነበር፡፡ 14በዚያን ጊዜ ዳዊት በአንድ ዋሻ በምሽጉ ውስጥ ሲሆን ፍልስጥኤማውያን ግን በቤተልሔም ተደራጅተው ነበር፡፡15ዳዊትም ውሃ ተጠምቶ፣ “በበሩ አጠገብ ካለችው ጉድጓድ የምጠጣውን ውሃ ምነው አንድ ሰው በሰጠኝ!” አለ፡፡ 16ስለዚህ እነዚህ ሶስቱ ኃያላን ፍልስጥኤማውያንን ጥሰው አልፈው በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ጉድጓድ ውሃ ቀዱ፡፡ ውሃውንም ይዘው ለዳዊት አመጡለት፣ እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈቀደ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው፡፡ 17ከዚያ በኋላም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን እጠጣው ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የጣሉ ሰዎችን ደም ልጠጣ ይገባኛልን?” ከዚህም የተነሣ ሊጠጣው አልፈቀደም፡፡ ሶስቱ ኃያላን ያደረጓቸው ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡18የኢዮአብ ወንድምና የጽሩያ ልጅ አቢሳ የሶስቱ አለቃ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ከሶስት መቶዎቹ ጋር በጦሩ ተዋግቶ ገደላቸው፡፡ ከሶስቱ ወታደሮች ጋር በተያያዘ ብዙውን ጊዜ ስሙ ይጠቀሳል፡፡ 19እርሱ ከእነርሱም ይልቅ ዝነኛ አልነበረምን? እርሱ የሶስቱ አለቃ ሆኖ ተሾመ፡፡ ይሁን እንጂ የእርሱም ዝና ከሶስቱ እጅግ ዝነኛ ከነበሩት ወታደሮች ጋር የሚስተካከል አልነበረም፡፡20የቀብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ታላቅ ጀብዱ የሠራ ጠንካራ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም ሁለቱን የአርኤል ልጆች ገደለ፡፡ በረዶ በጣለበትም ወቅት በጉድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሎአል፡፡ 21ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብፃዊም ገድሎአል፡፡ ግብፃዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም በናያስ በትር ብቻ ይዞ ገጠመው፡፡ ጦሩን ከግብፃዊው እጅ ቀምቶ በራሱ ጦር ገደለው፡፡22በናያስ እነዚህን ጀብዱዎች ፈጸመ ከሶስቱም ኃያላን ጋርም ስሙ የተጠራ ሆነ፡፡ 23በአጠቃላይ ከነበሩት ሰላሳ ወታደሮች ይልቅ ከፍ ያለ ግምት የተሰጠው ነበረ፣ ሆኖም የሶስቱ እጅግ ምርጥ ወታደሮችን ያህል ታላቅ ግምት የተሰጠው አልነበረም፡፡ ሆኖም ዳዊት የክቡር ዘበኞቹ አለቃ አደረገው፡፡24ሰላሳዎቹ የሚከተሉትን ያካተተ ነበር፣ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣ የቤተልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣ 25አሮዳዊው ሣማ፣ አሮዳዊው ኤሊቃ፣ 26ፈሊጣዊው ሴሌስ፣ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ፣ 27ዓኖቶታዊው አቢዔዜር፣ ኩስታዊው ምቡናይ ፣ 28አሆሃዊው ጸልሞን፣ ነጦፋዊው ማህራይ፣29የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፣ ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣ 30ጲርዓቶናዊው በናያስ፣ የገዓስ ሸለቆ ሰው ሂዳይ፣ 31ዓረባዊው አቢዔልቦን፣ በርሑማዊው ዓዝሞት፣ 32ሸዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣ የአሳን ልጆች፤ ዮናታን የተባለው፣33የአሮዳዊው የሣማ ልጅ፣ የአሮዳዊው የሻራር ልጅ አሒአም፣ 34የማዕካታዊው የአሐሰባይ ልጅ ኤልፋላት፣ የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊኦም፣ 35ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣ አርባዊው ፈዓራይ፣ 36የሱባ ሰው የሆነው የናታን ልጅ ይግዓል፣37አሞናዊው ጻሌቅ፣ የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጦር መሣሪያ ያዥ የነበረው ብኤሮታዊው ነሃራይ፣ 38ይትራዊው ዔራስ ፣ ይትራዊው ጋሬብ፣ 39እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮ፤ በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ፡፡
1እንደገናም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ፤ ዳዊትንም በእነርሱ ላይ በማስነሳት፣ “ሂድ እስራኤልንና ይሁዳን ቁጠር” አለው፡፡ 2ንጉሡ አብሮት ለነበረው ለኢዮአብ፣ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወደ እስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፣ ለጦርነት ብቁ የሆኑትንም ጠቅላላ ብዛት ማወቅ እችል ዘንድ ሕዝቡን ሁሉ ቁጠሩ፡፡” አለው፡፡3ኢዮአብም ለንጉሡ፣ “እግዚአብሔር አምላክህ የሕዝቡ ቁጥር መቶ እጥፍ ያብዛ፣ የጌታዬ የንጉሡ ዓይንም ይህንን ለማየት ያብቃው፡፡ ነገር ግን ጌታዬ ይህንን ለማድረግ ለምን ፈለገ?” 4ይሁን እንጂ የንጉሡ ቃል የኢዮአብንና የሠራዊት አለቆችን ቃል የሚሽር የመጨረሻ ቃል ነበር፡፡ ስለዚህ የእስራኤልን ሕዝብ ይቆጥሩ ዘንድ ኢዮአብና የሠራዊቱ አለቆች ከንጉሡ ፊት ወጡ፡፡5ዮርዳኖስን ተሻገሩና ከከተማው በስተደቡብ በሸለቆው ዘንድ ባለው በአሮዔር አጠገብ ሠፈሩ፡፡ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ኢያዜር ተጓዙ፡፡ 6ወደ ገለዓድና ወደ ተባሶን አደሰይ፣ ቀጥሎም ወደ ዳንየዓን ከዚያም ዞረው ወደ ሲዶና ሄዱ፡፡ 7ወደ ጢሮስ ምሽግና ወደ ኤዊያውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች ደረሱ፡፡ ከዚያም በይሁዳ ቤርሳቤህ ወዳለችው ወደ ኔጌቭ ወጡ፡፡8በመላው ምድሪቱ ከተዘዋወሩ በኋላ ከዘጠኝ ወር ከሃያ ቀናት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡ 9ከዚያም ኢዮአብ ለንጉሡ የተዋጊ ወንዶችን ጠቅላላ ቁጥር ዘገባ አቀረበ፡፡ በእስራኤል ሰይፍን መምዘዝ የሚችሉ ስምንት መቶ ሺህ ጀግኖች ሲኖሩ በይሁዳ ደግሞ አምስት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፡፡10ሰዎቹን ከቆጠረ በኋላ ዳዊት በልቡ ተጨነቀ፡፡ ስለዚህ ለእግዚአብሔር፣ “ይህንን በማድረጌ ታላቅ ኃጢአት ሠርቻለሁ፡፡ የሠራሁት እጅግ የስንፍና ሥራ ነውና፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ የባሪያህ በደል አስወግድ፡፡”11ዳዊት ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዳዊት ባለ ራእይ ወደ ነቢዩ ጋድ እንዲህ ሲል መጣ፣ 12“ሂድና ለዳዊት፣ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፣ ሶስት ምርጫ እሰጥሃለሁ፣ አንዱን ምረጥ’”13ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ሄደና፣ “የሦስት ዓመት ረሃብ ወደ ምድርህ ይምጣን? ወይስ እነርሱ እያሳደዱህ ከጠላቶችህ ለሶስት ወራት ብትሸሽ ይሻልሃል? ወይስ በአገርህ የሶስት ቀን ቸነፈር ይምጣብህ? ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አሁን ወስን” አለው፡፡ 14ዳዊትም ጋድን፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረታዊ አደራረጉ እጅግ ታላቅ ስለሆነ በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ እንጂ በሰው እጅ አንውደቅ” አለው፡፡15ስለዚህ እግዚአብሔር ህከጥዋት እስከ ተወሰነ ጊዜ ቸነፈሩን በእስራኤል ላይ ላከ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህም ሰባ ሺህ ሰዎች ሞቱ፡፡ 16መልአኩ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ስለደረሰው ጉዳት ተፀፀቶ ሕዝቡን እያጠፋ የነበረውን መልአክ፣ “ይበቃል፣ እጅህን ሰብስብ” አለው፡፡ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡17ሕዝቡን እየቀሠፈ የነበረውን መልአክ ባየ ጊዜ ዳዊት ለእግዚአብሔር፣ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፣ የማይገባም ነገር አድርጌአለሁ፡፡ ነገር ግን እነዚህ በጎች ምን ያደረጉት ነገር አለ? እባክህን የአንተ እጅ እኔንና የአባቴን ቤተሰብ ይቅጣ፡፡” ብሎ ለእግዚአብሔር ተናገረ፡፡18ከዚያ በኋላ ጋድ በዚያን ቀን ወደ ዳዊት መጣና፣ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ” አለው፡፡ 19ስለዚህ ዳዊት ጋድ እንደ ነገረውና እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወጣ፡፡ 20ኦርና ሲመለከት ንጉሡና አገልጋዮቹ ሲደርሱ አየ፡፡ ስለዚህ ኦርና ወጣ ብሎ በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፡፡21ከዚያ በኋላም ኦርና፣ “ጌታዬ ንጉሡ ወደ ባሪያው ዘንድ ለምን መጣ?” ዳዊትም መለሰ፣ “ቸነፈሩ ከሕዝቡ ይወገድ ዘንድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ የምሠራበትን የአንተን ዐውድማ እገዛ ዘንድ ነው፡፡” 22ኦርናም ለዳዊት፣ “ጌታዬ ንጉሡ የራስህ አድርገህ ውሰደው፡፡ በፊትህ ደስ ያሰኘህንም አድርግበት፡፡ እነሆ፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፣ ለማገዶም የሚሆን የመውቂያ ዕቃና ቀንበር በዚህ አለ፡፡ 23ይህንን ሁሉ ንጉሤ ሆይ፣ እኔ ኦርና ለአንተ እሰጣለሁ” አለና ከዚያ በኋላ፣ “እግዚአብሔር አምላክህ ይቀበልህ” አለው፡፡24ንጉሡም ለኦርና፣ “አይሆንም፣ ይህንን በዋጋ መግዛት ይኖርብኛል፡፡ ምንም ነገር ያላወጣሁበትን አንድም ነገር ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም” አለው፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በሃምሳ የብር ሰቅል ገዛ፡፡ 25ዳዊት በዚያ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራና የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ምድሪቱ ተለመነው፣ በእስራኤል የነበረውም ቸነፈር ቆመ፡፡
1ንጉስ ዳዊትም ሸምግሎ እና እድሜውም ገፍቶ ነበር። ምንም እንካ ልብስ ቢድርቡለትም፣ ሊያሞቀው አልቻለም። 2ስለዚህ አገልጋዮቹ፣ "ለንጉስ አንዲት ወጣት ልጃገረድ እንፈልግለት እና ታገልግለው ትንከባከበውም። ንጉሱም እንዲሞቀው ክንዱ ውስጥ ትተኛ፣' አሉት።3ስለዚህም አንዲት ቆንጆ ልጃገረድ ለማግኘት በመላው እስራኤል ፈለጉ። ሱነማዊቱን አቢሳን አገኙ፤ ወደ ንጉሡም አመጡአት። 4እርስዋም እጅግ ውብ ነበረች፤ እርስዋም ንጉሡን አገለገለችው፣ ተንከባከበችውም፤ ነገር ግን ንጉሡ ከእርስዋ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አላደረገም።5በዚያን ጊዜ የአጊት ልጅ አዶንያስ “ንጉሥ እሆናለሁ” በማለት ራሱን ከፍ አደረገ። ስለዚህ በፊቱ የሚሮጡ ሃምሳ ፈረሰኞችንና ሠረገሎችን ለራሱ አዘጋጀ። 6አባቱም ይህን ወይም ያንን ለምን ታደርጋለህ ብሎ ገስጾት አያውቅም ነበር። አዶንያስም ከአቤሴሎም በኋላ የተወለደ፣ እጅግ መልከ መልካም ነበር።7እርሱም ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር አሤረ፤ እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ረዱት። 8ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅ፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ነቢዩ ናታን፣ ሳሚ፣ ሬሲምና ዳዊትን የሚደግፉ ኃያላን አዶንያስን አልተከተሉትም።9አዶንያስም ዓይንሮጌል አቅራቢያ ባለው በዞሔሌት ድንጋይ ላይ በጎችን፣ በሬዎችንና የሰቡ ወይፈኖችን ሠዋ። እርሱም፣ የንጉሡን ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፣ የይሁዳን ሰዎች ሁሉና የንጉሡን አገልጋዮች ጋበዛቸው። 10ነገር ግን ነቢዩ ናታንን፣ በናያስን፣ ኃያላን ሰዎችን፣ ወይም ወንድሙን ሰሎሞንን አልጋበዛቸውም።11ከዚያም ናታን፣ ለሰሎሞን እናት ለቤርሳቤህ እንዲህ ሲል ነገራት፦ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ መንገሡን አልሰማሽምን? 12ስለዚህ የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት ለማትረፍ እንድትችዪ ልምከርሽ።13ወደ ንጉሥ ዳዊት ሂጂ፤ እንዲህም በዪው፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣’ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ ምለህልኝ አልነበረምን? ታዲያ አዶንያስ የሚነግሠው ለምንድን ነው?”። 14በዚያም ከንጉሡ ጋር በመነጋገር ላይ እያለሽ እኔም ካንቺ በኋላ እገባና የተናገርሽው ሁሉ እውነት መሆኑን አረጋግጣለሁ” አላት፡፡15ስለዚህ ቤርሳቤህ ወደ ንጉሡ ክፍል ሄደች። ንጉሡ እጅግ ስለ ሸመገለ ሱነማይቱ አቢሳ ታገለግለው ነበር። 16ቤርሳቤህም ራስዋን ዝቅ አድርጋ ለንጉሡ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት፡፡ 17እርሷም እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ ሆይ፣ ለአገልጋይህ፣ ‘በእርግጥ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ በአምላክህ በጌታ እግዚአብሔር ስም ምለህ ነበር፡፡18ይኸው አሁን አዶንያስ ነግሦአል፤ አንተም ጌታዬ ንጉሡ ይህንን አታውቅም። 19ስለዚህ በሬዎችን፣ የሰቡ ኮርማዎችንና ብዙ በጎች ሠውቷል። ደግሞም የንገሡን ልጆች፣ ካህኑን አብያታርንና የሠራዊቱን አዛዥ ኢዮአብን ጋብዟቸዋል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጋበዘውም፡፡20ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ከአንተ ከጌታዬ በኋላ በዙፋንህ የሚቀመጠው ማን መሆኑን አንድታስታውቀው በመጠባበቅ ላይ ነው፡፡ 21አለበለዚያ ግን ጌታዬ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር በሚያንቀላፋበት ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎሞን እንደ ወንጀለኛ እንቆጠራለን።22እርስዋ ለንጉሡ በመናገር ላይ እያለች ነቢዩ ናታን ገባ። 23አገልጋዮቹም ለንጉሡ፣ “ነቢዩ ናታን እዚህ ነው” ብለው ነገሩት። እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በቀረበ ጊዜ በግምባሩ ምድር ላይ በመደፋት ለንጉሡ ሰላምታ አቀረበ።24ናታንም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ‘አዶንያስ ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለሃልን? 25እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችን፣ የሰቡ ጥጆችንና በጎችን ሠውቷል፤ ደግሞም የንጉሡን ልጆች ሁሉ፣ የሠራዊቱን አዛዥ ኢዮአብንና ካህኑን አብያታርን ጋብዟል። ንጉሥ አዶንያስ ለዘላለም ይኑር! በማለት በፊቱ በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው፡፡26ነገር ግን እኔን አገልጋይህን፣ ካህኑን ሳዶቅን፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስንና አገልጋይህን ሰሎሞንን ወደ ግብዣው አልጠራንም። 27ከአንተ በኋላ በዙፋንህ ላይ የሚቀመጠው ማን እንደሆነ ለእኛ ለአገልጋዮችህ ሳትነግረን ይህንን ያደረግኸው ጌታዬ ንጉሡ ነህን?”28ከዚያም ንጉሡ ዳዊት፣ “ቤርሳቤህን ጥሩልኝ” አለ። እርስዋም ንጉሡ ወዳለበት መጥታ በፊቱ ቆመች። 29ንጉሡም ማለና፣ “ከደረሰብኝ መከራ ሁሉ የታደገኝ ጌታ እግዚአብሔር ሕያው የመሆኑን ያህል፤ 30‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፣ በዙፋኔም ላይ በእኔ ቦታ ይቀመጣል’ ብዬ በእስራኤል አምላክ በጌታ እግዚአብሔር ስም የማልኩትን መሓላ ዛሬ እፈጽመዋለሁ” አላት። 31ቤርሳቤህም ወደ መሬት በግንባሯ በመደፋት ለንጉሡ አክብሮቷን ካሳየች በኋላ፣ “ጌታዬ ንጉሡ ዳዊት ለዘለዓለም ይኑር!” አለች።32ንጉሥ ዳዊትም፣ “ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንን እና የዮዳሄን ልጅ በናያስን ጥሩልኝ” አለ። እነርሱም በንጉሡ ፊት ቀረቡ። 33ንጉሡም እንዲህ አላቸው፡- የጌታችሁን አገልጋዮች ከእናንተ ጋር ውሰዱ፤ ልጄን ሰሎምንንም እኔ በምቀመጥባት በቅሎ አስቀምጡትና ወደ ግዮን አውርዱት። 34ካህኑ ሳዶቅና ነቡዩ ናታን ቀብተው በእስራኤል ላይ ያንግሡትና መለከት በመንፋት “ንጉሥ ሰለሞን ለዘላለም ይኑር!” በሉ።35ከዚያም ተከትላችሁት ትመጣላችሁ፣ እርሱም መጥቶ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል፤ በእኔ ምትክ ይነግሣልና። በእስራኤልና በይሁዳ ላይ እንዲገዛ ሾሜዋለሁ”። 36የዮዳሄ ልጅ በናያስም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፡- “ይሁን! ይህንንም የጌታዬ የንጉሡ አምላክ ጌታ እግዚአብሔር ያጽናው። 37ጌታ እግዚአብሔር ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር እንደ ሆነ እንዲሁ ከሰሎሞን ጋር ይሁን፤ ዙፋኑንም ከጌታዬ ከንጉሥ ዳዊት ዙፋን የበለጠ ያድርገው” አለው፡፡38ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ወረዱ፤ ሰሎሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ ላይ በማስቀመጥ ወደ ግዮን አመጡት። 39ካህኑ ሳዶቅ ዘይት ያለበትን ቀንድ ከድንኳን ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው። በዚያን ጊዜ መለከት ነፉ፣ ሕዝቡም፣ “ንጉሥ ሰሎሞን ለዘላለም ይኑር!” አሉ። 40ሕዝቡም ሁሉ ተከትሎት ወጣ፣ ሕዝቡም እምቢልታ እየነፉ በታላቅ ደስታ ደስ አላቸው፣ ከድምፃቸው የተነሣ ምድር ተንቀጠቀጠች።41አዶንያስና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንግዶች ሁሉ ምግባቸውን እንደጨረሱ ይህንን ድምፅ ሰሙ። ኢዮአብ የእምቢልታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ፣ “ይህ በከተማ ውስጥ የሚሰማው ሁካታ ምንድን ነው?” አለ። 42እርሱ ገና በመናገር ላይ እያለ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ። አዶንያስም፣ “ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው።43ዮናታንም ለአዶንያስ እንዲህ ሲል መለሰለት፡- “ጌታችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን እንግሦታል፤ 44ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅን፣ ነቢዩን ናታንን፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን፣ ከሊታውያንን እና ፈሊታውያንን ልኳል። እነርሱም ሰለሞንን በንጉሡ በቅሎ ላይ አስቀመጡት። 45ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታንም በግዮን ቀብተው አነገሡት፤ ደስ እያላቸውም ከዚያ ወጡ፣ በከተማው ሁካታ የሆነው ለዚህ ነው። የሰማችሁት ድምፅም ይኸው ነው።46ደግሞም ሰሎሞን በመንግሦቱ ዙፋን ላይ ተቀምጧል። 47ከዚህም በላይ ከፍተኛ ሥልጣን ያላቸው ባለሟሎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ዳዊት ቀርበው አምላክህ እግዚአብሔር ሰሎሞንን ከአንተ ይበልጥ ዝናውን ያግንነው፣ መንግሥቱንም ይበልጥ ታላቅ ያድርገው ሲሉ አክብሮታቸውን ገልጠዋል፤ ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳዊት በአልጋው ላይ ሳለ ለእግዚአብሔር ሰገደ፡፡ 48ዛሬ ከእኔ ዘሮች መካከል አንዱ በእኔ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ ያደረገና ይህን ለማየት ያበቃኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ሲል እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡49አዶንያስ የጠራቸው ተጋባዦች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ሁሉም ተነሡ፤ እያንዳኑዱም በየፊናው ተበተነ፤ 50አዶንያስም ሰሎሞንን ስለፈራ ወደ ተቀደሰው ድንኳን ሄዶ የመሠዊያውን ቀንዶች በመያዝ ተማጠነ፡፡ 51ሰዎቹም ሰሎሞንን፣ አዶንያስ አንተን ከመፍራቱ የተነሣ የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ከሁሉ በፊት ንጉሥ ሰሎሞን የማይገድለኝ መሆኑን በማረጋገጥ በመሐላ ቃል ይግባልኝ በማለት እየተማጠነ ነው ሲሉ ነገሩት፡፡52ንጉሥ ሰሎሞንም መልካም ሰው ከሆነ ከራስ ጠጉሩ አንዲት እንኳን አትነካበትም፤ ክፉ ሆኖ ከተገኘ ግን ይሞታል ሲል መለሰ። 53ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን አዶንያስን ከመሠዊያው አውርደው ያመጡት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ፤ አዶንያስ ወደ ንጉሡ ፊት በመቅረብ ወደ መሬት ራሱን ዝቅ አድርጎ እጅ ነሣ፤ ንጉሡም ወደ ቤትህ ሂድ አለው።
1ዳዊት የሚሞትበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ 2እነሆ እኔ ሰው ሁሉ እንደሚሞት የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እንግዲህ በርታ ቆራጥ ሰው ሁን፡፡ 3አምላክህ እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፣ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማናቸውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግ ትእዛዝ፣ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፡፡ 4በዚህ ሁሉ ታዛዥ ሆነው ቢኖሩ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም ብሎ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል፡፡5የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በእኔና የእስራኤል ሕዝብ የጦር መሪዎች በነበሩት በሁለቱ፣ በኔር ልጅ በአበኔርና በዬቴር ልጅ በአሜሳይ ላይ ያደረገውን ታውቃለህ፤ ሁለቱ በጦርነት ጊዜ ላፈሰሱት ደም ተበቅሎ በሰላም ጊዜ እነርሱን በመግደል የወገቡን ቀበቶና የእግሩን ጫማ በደም በከለ። 6እንግዲህ ባለህ ጥበብ በኢዮአብ ላይ ልትፈጸምበት የሚገባውን አድርግ፤ ዕድሜ ጠግቦ በሰላም እንዲሞት አትፍቀድለት።7ይሁን እንጂ የገለዓዳዊው የቤርዜሊ ልጆች ከወንድምህ ከአቤሌሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ወደ እኔ መጥተው የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ፣ መልካም አድርግላቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡ መካከል ይሁኑ።8ከዚህም ጋር መረሳት የሌለበት የብንያም ክፍል በሆነችው በባሑሪም ከተማ ውስት የሚኖረው የጌራ ልጅ ሳሚ ወደ መሃናይም በሄድኩበት ቀን በእኔ ላይ የስደብ ውርጅብኝ አውርዶብኛል፤ ይሁን እንጂ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባገኘኝ ጊዜ እንደማላስገድለው በእግዚአብሔር ስም ምየለታለሁ። 9ስለዚህ አንተ እርሱንም ከቅጣት ነጻ አታድርገው። አንተ ጥበበኛ ሰው ስለሆንህ ምን መደረግ እንዳለበት ታውቃለህ። በሸመገለም ጊዜ በሞት ትቀጣዋለህ፡፡10ከዚያም ዳዊት ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ። 11ዳዊት በኬብሮን ሰባት ዓመት፣ በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በድምሩ አርባ ዓመት በእስራኤል ላይ ነገሠ። 12ሰሎሞንም በአባቱ ዙፋን ተተክቶ ነገሠ፤ የመንግሥቱም ሥልጣን እጅግ የጸና ሆነ።13የአጊት ልጅ አዶንያስ ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ መጣ። ቤርሳቤህም ወደ እኔ የመጣኸው በሰላም ነውን? ስትል ጠየቀችው፤ እርሱም አዎን በሰላም ነው ሲል መለሰላት። 14ቀጠል አድርጎም እኔ የምጠይቅሽ ጉዳይ አለኝ አላት። እርስዋም ጉዳይህን ተናገር አለችው። 15አዶንያስም እንዲህ አላት፣ ንጉሥ መሆን የሚገባኝ እኔ እንደ ነበርኩና ይህንንም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በተስፋ ይጠባበቅ እንደ ነበር አንቺ ታውቂያለሽ። ነገር ግን ጉዳዩ ከእግዚአብሔር ስለ ተወሰነ ነገሩ ተለውጦ መንግሥቱ ለወንድሜ ተሰጥቶአል።16አሁንም የምጠይቅሽ አንድ ጉዳይ ስላለኝ እምቢ በማለት አታሳፍሪኝ። ቤርሳቤህም ጉዳይህን ተናገር አለችው። 17እርሱም እንዲህ አላት፡- ንጉሥ ሰሎሞን አንቺን እምቢ እንደማይልሽ አውቃለሁ፤ ስለዚህ አቢሳ ተብላ የምትጠራውን ሱነማይት ልጃገረድ ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እንዲሰጠኝ እባክሽ አማልጅኝ አላት። 18እርስዋም መልካም ነው፤ ይህን ለንጉሡ እነግርልሃለሁ አለችው።19ስለዚህ ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግረው ወደ ንጉሡ ገባች። ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት። እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት። 20እርስዋም እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፣ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ አለችው። ንጉሡም እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ጠይቂኝ አላት። 21እርስዋም ወንድምህ አዶንያስ አቢሳን እንዲያገባት ፍቀድለት አለችው።22ንጉሡም አቢሳን ለሚስትነት እንድሰጠው ብቻ ለምን ትጠይቂኛሽ? መንግሥቴንም ጭምር እንድለቅለት ለምን አልጠየቅሽኝም? እርሱ ታላቅ ወንድሜ ነው፤ ለምንስ ለካህኑ አብያታርና ለኢዮአብም ልዩ አስተያየት እንዳደርግላቸው አትጠይቂላቸውም? አላት። 23ከዚህ በኋላ ሰሎሞን፣ በእግዚአብሔር ስም እንዲህ ሲል ማለ፡- አዶንያስ ይህን በመናገሩ በሕይወቱ እንዲከፍል ባላደርግ እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ በበለጠም ይቅጣኝ አለ።24እግዚአብሔር በአባቴ በዳዊት ዙፋን ላይ አስቀምጦኝ መንግሥቴን የጸና አድጎልኛል፤ ይህን መንግሥት ለእኔና ለዘሮቼ በመስጠት ቃሉን ጠብቆአል፤ እንግዲህ አዶንያስ በዚህ በዛሬው ቀን በሞት እንደሚቀጣ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።25ስለዚህ አዶንያስን እንዲገድለው ንጉሥ ሰሎሞን ለዮዳሄ ልጅ ለበናያስ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያስም ሄዶ አዶንያስን ገደለው።26ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን እንዲህ አለው፡- በአናቶት ወዳለው እርሻህ ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፣ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለተሸከምህ፣ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም። 27ከዚህ በኋላ ሰሎሞን አብያታርን የእግዚአብሔር ካህን ሆኖ ከሚያገለግልበት የክህነት ሥልጣን ሽሮ አባረረው፤ በዚህም ዓይነት እግዚአብሔር በሴሎ ስለ ካህኑ ዓሊ፣ ስለ ትውልዱ የተናገረው ቃል ተፈጸመ።28የአቤሌሎም ደጋፊ ባይሆንም የአዶንያስ ደጋፊ የነበረው ኢዮአብ፣ ይህን የተፈጸመውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ስለዚህም ሸሽቶ ወደ ጌታ እግዚአብሔር ድንኳን ሄደ፤ በዚያም የመሠዊያውን ቀንዶች ይዞ ተማጠነ። 29ኢዮአብ ወደ ጌታ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያስ ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡30እርሱም ወደ ጌታ እግዚአብሔር ድንኳን ሄዶ ኢዮአብን ከዚህ ድንኳን እንድትወጣ ንጉሡ አዞሃል አለው። ኢዮአብ ግን፣ አልወጣም እዚሁ እሞታለሁ አለ። በናያስም ተመልሶ ኢዮአብ ያለውን ለንጉሡ ነገረው። 31ሰሎሞን በናያስን እንዲህ አለው፡- ኢዮአብ እንዳለህ ግደለውና ቅበረው፤ በዚህ ሁኔታ ኢዮአብ ካፈሰሰው ንጹሕ ደም የእኔንና የአባቴን ቤት የነጻን ታደርገናለህ።32አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ ስለ ገደላቸው ስለ እነዚያ ሁለት ሰዎች ደም እግዚአብሔር ኢዮአብን ይቀጣዋል፤ ኢዮአብ ከእርሱ የተሻሉትን ሁለት ንጹሓን ሰዎች ገድሎአል፤ እነርሱም የአስራኤል ጦር አዛዥ አበኔርና የይሁዳ ጦር ኣዛዥ አሜሳይ ነበሩ። 33ኢዮአብ እነዚህን ሰዎች በመግደሉ ደማቸው በእርሱና በዘሮቹ ለዘለዓለም ይመለስባቸው። ነገር ግን ለዳዊትና ለዘሮቹ፣ ለቤቱና በዙፋኑ ለሚቀመጡት የእግዚአብሔር ሰላም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር።34ስዚህ በናያስ በታዘዘው መሠረት ኢዮአብን ገደለው፤ በቤቱም አጠገብ በሚገኘው በረሓ ተቀበረ። 35ንጉሥ ሰሎሞን በኢዮአብ ፈንታ በናያስን የሠራዊት አዛዥ፣ በአብያታርም ፈንታ ሳዶቅን ካህን አድርጎ ሾማቸው።36ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ሳሚን አስጠርቶ እንዲህ ሲል አዘዘው፡- በዚህ በኢየሩሳሌም የራስህን መኖሪያ ቤት ሠርተህ ተቀመጥ፤ ከዚያ የትም እንዳትሄድ፤ 37ከከተማይቱ ወጥተህ የቄድሮንን ወንዝ ተሻግረህ ብትገኝ በእርግጥ ትሞታለህ፤ ለደምህም ተጠያቂው ራስህ ነህ። 38ሳሚም ንጉሥ ሆይ፣ ውሳኔህ መልካም ነው። አገልጋይህ አንተ ጌታዬ እንዳልከው አደርጋለሁ ሲል መለሰ። ስለዚህ በኢየሩሳሌም ብዙ ጊዜ ተቀመጠ።39ከሦስት ዓመት በኋላ ግን ሁለቱ የሳሚ አገልጋዮች የመዓካ ልጅ ወደ ሆነው አንኩስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ጌት ንጉሥ ኮብልለው ሄዱ፤ ሳሚም ባሪያዎቹ በጌት መኖራቸው ተነገረው። 40ሳሚም አህያውን ጭኖ እነርሱን ለመፈለግ በጌት ወደሚኖረው ወደ ንጉሥ አንኩስ ሄደ፤ እነርሱንም በዚያ ስላገኛቸው ወደ ቤት መልሶ አመጣቸው።41ንጉሥ ሰሎሞን ሳሚ ከኢየሩሳም ወደ ጌት ሄዶ መመለሱን ሰማ። 42ንጉሡም ሳሚን አስጠርቶ ከኢየሩሳሌም እንዳትወጣ በእግዚአብሔር ስም አስምዬህ አልነበረምን? ወጥተህ ብትገኝ ግን በእርግጥ እንደምትሞት አስታውቄህ አልነበረምን? በዚህስ ተስማምተህ ትእዛዜን እንደምትፈጽም ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? አለው።43ታዲያ በእግዚአብሔር ስም ከማልህ በኋላ ትእዛዜንስ ስለምን አላከበርክም? 44በአባቴ በንጉሥ ዳዊት ላይ የፈጸምከውን በደል ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ፤ አንተ ስላደረግኸው ክፉ ነገር እግዚአብሔር ራሱ ይቀጣሃል።45እኔን ግን እግዚአብሔር ይባርከኛል፤ የዳዊት መንግሥትም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል። 46ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያስ ሳሚን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያስም ሄዶ ሳሚን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ፡፡
1ሰሎሞን የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ሴት ልጅ በማግባት ከንጉሡ ጋር ወዳጅነት መሠረተ። የፈርዖንንም ልጅ አምጥቶ ቤተ መንግሥቱን፣ ቤተ መቅደሱንና የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጥር ዙሪያውን ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አኖራት። 2በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደሱ ገና አልተሠራም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ በየኮረብታው መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር። 3ሰሎሞን እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኮረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብና ዕጣንም ያጥን ነበር።4ታላቅ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለነበር አንድ ቀን ንጉሥ ሰሎሞን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ። በዚያም መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። 5እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት በገባዖን ለሰሎሞን በሕልም ተገለጠለትና ምን እንድሰጥህ ትፈልጋህ? ጠይቅ አለው።6ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፡- አገልጋይህ የነበረው አባቴ ዳዊት፣ ታማኝና ቅን ሰው በመሆኑ ጽኑ ፍቅርህን አሳይተኸዋል። ዛሬም በእርሱ ፈንታ በዙፋኑ የሚቀመጥ ልጅ በመስጠት ታላቅና ጽኑ የሆነውን የማያቋርጥ ፍቅርህን ገልጠህለታል።7እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ እነሆ እኔ በዕድሜዬ ልጅ ብሆንም በአባቴ ቦታ ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል። እኔም መግባትንና መውጣትን የማልችል ነኝ። 8እነሆ፣ የአንተ እንዲሆን በመረጥከውና ከብዛቱ የተነሣ ሊቆጠር በማይችል ሕዝብ መካከል አለሁ። 9ስለዚህ ክፉውንና በጎውን በመለየት ሕዝብህን በማስተዋል በትክክኛ ፍርድ ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብ ስጠኝ። ይህ ካልሆን ይህን ታላቅ ሕዝብህን ሊመራ ማን ይችላል?10ይህ የሰሎሞን ጥያቄ እንግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ 11ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- ለራስህ ረጅም ዕድሜ ወይም ሀብት ለማግኘት ወይም ጠላቶችህ እንዲጠፉልህ መመኘት ሳይሆን በትክክለኛ ፍርድ ማስተዳደር የምትችልበትን ጥበብ ጠይቀሃል። 12እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊት ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ።13ከዚህም በላይ አንተ ያልጠየቅከውንም ሁሉ ጨምሬ ሰጥቼሃለሁ፤ ይኸውም በዘመንህ ማናቸውም ንገሥታት ያላገኙትን ብጽግናና ክብር አሰጥሃለሁ። 14አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድ ለእኔም ብትታዘዝ ሕጌንና ትእዛዞቼንም ብትፈጽም ረጅም ዕድሜ እሰጥሃሁ።15ሰሎሞን ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ ያነጋገረው መሆኑን ተገነዘበ፤ ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆሞ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ከዚህም በኋላ ለአገልጋዮቹ ሁሉ ግብዣ አደረገ።16አንድ ቀን ሁለት ሴተኛ አዳሪዎች መጥተው በሰሎሞን ፊት ቀረቡ፡፡ 17ከእነርሱም አንደኛይቱ እንዲህ አለች ንጉሥ ሆይ ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት አብረን ስንኖር፣ በዚያውም በምንኖርበት ቤት ወንድ ልጅ ወለድኩ።18እኔ በወለድኩ በሦስተኛው ቀን እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደች። በዚያ ቤት ውስጥ ከሁለታችን በቀር ሌላ ማንም አልነበረም። 19ከዕለታት አንድ ቀን ሌሊት በላዩ ላይ ተኝታበት ስለ ታፈነ ልጇ ሞተ። 20እኔ ተኝቼ ሳለሁ ሌሊት ተነሥታ ታቅፌው የተኛሁትን ልጄን ወስዳ በእርስዋ አልጋ ላይ ካስተኛች በኋላ የሞተውን ልጅዋን አምጥታ በእኔ አልጋ ላይ በጎኔ አስተኛችው።21በማግስቱ ማለዳ ተነሥቼ ልጄን ለማጥባት ስዘጋጅ ሞቶ አገኘሁት፤ ትኩር ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድኩት ልጅ አለመሆኑን ተገነዘብኩ። 22ሁለተኛይቱ ሴት ግን አይደለም፣፣ በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፣ የሞተው ግን የአንቺ ነው አለች። የመጀመሪያይቱ ሴት አይደለም የሞተው የአንቺ ነው፤ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው አለች። በዚህ ዓይነት በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።23ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን አንደኛዋ በሕይወት ያለው ልጅ የእኔ ነው፣ የሞተው ግን የአንቺ ነው ትላለች፤ ሌላይቱም ደግሞ አይደለም የአንቺ ልጅ ሞቶአል፤ የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው ትላታለች አለ። 24ንጉሡም ሰይፍ እንዲያመጡለት አዘዘ፤ ሰይፍም አመጡለት። 25በሉ እንግዲህ በሕይወት ያለውን ልጅ ለሁለት ቁረጡና ለእያንዳንዱ ሴት ግማሽ አካሉን ስጡ ሲል አዘዘ፡፡26እውነተኛይቱ ግን ለልጅዋ በመራራት አዝና ንጉሥ ሆይ፣ እባክህ ልጁን አትግደለው፤ ለእርስዋ ይሰጣት አለች። ሌላይቱ ሴት ግን፣ ለእኔም ለእርስዋም አይሁን፤ ለሁለት ይቆረጥ አለች። 27ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ሕፃኑን አትግደሉት፤ እውነተኛይቱ እናት እርስዋ ስለሆነች ለመጀመሪያይቱ ሴት ስጡአት ሲል አዘዘ። 28እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
1ንጉሡ ሰሎሞን በመላው አስራኤል ላይ ነግሦ ነበር። 2ንጉሡም የሾማቸው ባለሥልጣኖች እነዚህ ናቸው። እነርሱም፡- ዓዛርያስ የተባለው የሳዶቅ ልጅ፡- ካህን ነበር። 3ኤልያፍና አኪያ የተባሉ የሴባ ልጆች የቤተ መንግሥት ጻሐፊዎች ነበሩ። ኢዮሣፍጥ የተባለው የአሒሉድ ልጅ ታሪክ ጻሐፊና የመዛግብት ኃላፊ ነበር። 4በናያስ የተባለው የዮዳሄ ልጅ የጦር ሠራዊት አዘዥ ነበር። ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ።5ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፡- የክፍለተ አገራት ገዢዎች የበላይ ኃላፊ ነበር። የናታን ልጅ ዛቡድ፡- ካህንና የንጉሡ አማካሪ ነበር። 6አሒሳር የተባለው፡- የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኃላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፡- የግዳጅ ሥራ ተቆጣጣሪና ኃላፊ ነበር።7ንጉሡ ሰሎሞንም በመላው እስራኤል ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተ ሰብ ቀለብ የሚያዘጋጁ ዐሥራ ሁለት ባለሥልጣኖች ነበሩት፡፡ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው፡፡ 8የእነዚህም ዐሥራ ሁለት ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸው ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፡- ቤንሑር፡- ኮረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤ 9ቤንዴር፡- የማቃጽ የሻዓልቢም፤ የቤትሻሜሽ፡- የኤሎንና የቤት ሐናን ከተሞች ገዢ፤ 10ቤንሔሴድ፡- የአሩቦትና የሶኮ ከተሞችና የመላው የሐፌር ግዛት አስተዳዳሪ፤11ጣፋት የተባለችውን የሰሎሞንን ሴት ልጅ አግብቶ የነበረው ቤን አሚናዳብ የመላው የዶር ግዛት አስተዳዳሪ፤ 12በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፡-የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፤ እንዲሁም በቤትሳን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ በጸርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተደቡብ ያለው ግዛት፤ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅምዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ፤ 13በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የኢያዕር ጎሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፤ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጥር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስልሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ፤ 14አሒናዳብ የተባለው የዔዶ ልጅ፡- የመሃናይም ክፍለ አገር ገዢ፤15መካከል ባስማት ተብላ የምትጠራውን የሰሎሞንን ሴት ልጅ አግብቶ የነበረው አኪማአስ፡- የንፍታሌም ግዛት አስተዳዳሪ፤ 16በዓና የተባለው የሔሻይ ልጅ፡- የአሴር ግዛትና የበዓሎት ከተማ ገዢ፤ 17ኢዮሣፍጥ የተባለው የፋሩሕ ልጅ፡- የይሳኮር ግዛት አስተዳዳሪ፤18ሳሚ የተባለው የኤላ ልጅ፡- የብንያም ግዛት አስተዳዳሪ፤ 19ጊቤር የተባለው የኡሪ ልጅ፡- በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎንና በባሳን ንጉሥ በዐግ ትገዛ የነበረችው የገለዓድ ግዛት አስተዳዳሪ፤ እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን አስተዳዳሪዎች የሚቆጣጠር በመላ አገራቱ ሌላ አንድ የበላይ ኃላፊ ነበር፡፡20የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ እየበሉና እየጠጡ ዘወትር ደስ እየተሰኙ ነበር፡፡ 21የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፣ ከዚያም አልፎ እስከ ግብፅ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር፡፡ 22ሰሎሞንም በየቀኑ ለቀለብ የሚሆን አምስት ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ምርጥ ዱቄት፤ ዐሥር ሺህ ኪሎ ግራም ያህል ነበር፡፡ 23በበረት ውስጥ እየተመገቡ የደለቡ ዐሥር ሰንጋዎችና በግጦሽ መስክ ተሰማርተው የተመገቡ ሃያ ፍሪዳዎች፣ አንድ መቶ በጎች፤ ከዚህም ሌላ አጋዘኖች፣ የሜዳ ፍየሎች፤ ሚዳቆዎችና ምርጥ ወፎች ያስፈልጉት ነበር፡፡24ሰሎሞን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምዕራብ ያለው ምድር ሁሉ ከቲፍሳ ከተማ ጀምሮ እስከ ጋዛ ከተማ ድረስ ይገዛ ነበር፤ ይህም ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኙትን ነገሥታት ሁሉ ያጠቃልላል፤ ጎረቤቱ ከሆኑት አገሮችም ሁሉ ጋር በሰላም ይኖር ነበር፡፡ 25በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳር እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለ ስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱ ቤተ ሰብ ለራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር፡፡26ሰሎሞን ሠረገላ የሚስቡ አርባ ሺህ ፈረሶች፣ ለጦርነት የሚያገለግሉ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት፡፡ 27ለሰሎሞንና በቤተ መንግሥቱ ለሚቀለቡት ሁሉ የሚያስፈልገውን ምግብ የሚያቀርቡ ዐሥራ ሁለቱ ገዢዎች እያንዳንዳቸው በተመደበላቸው ወር ምንም ነገር ሳያጓድሉ በወቅቱ ያመጡ ነበር፡፡ 28ከዚህም በቀር እያንዳንዱ ገዢ እንደሚችለው ሌላም አገልግሎት ለሚያበረክቱ የጋማ ከብቶች ገብስና ገለባ ያቀርብ ነበር፡፡29እግዚአብሔር ለሰሎሞን አጅግ አስደናቂ የሆነ ጥበብንና አስተተዋይነትን እንዲሁም እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ወሰን የማይገኝለትን ዕውቀት ሰጠው፡፡ 30የሰሎሞንም ጥበብ ከምሥራቅ አገርና ከግብፅም ጥበበኞች እጅግ የላቀ ነበረ፡፡ 31እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኢይዝራኤላዊው ኤታን፣ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሮማን ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጎረቤት ሕዘቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፡፡32ሦስት ሺህ ምሳሌዎችንና አንድ ሺህ አምስት የመዝሙር ድርስቶች ነበሩት፡፡ 33ሰሎሞን ከሊባኖስ ዛፍ ጀምሮ በቤት ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ድረስ ስለ ዛፎችና ስለ ተክሎች ምሳሌዎችን ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ ልዩ ልዩ እንስሶች፣ ወፎች፣ በሆዳቸው እየተሳቡ ስለሚሄዱ ፍጥረቶችና ስለዓሣዎች አስተምሮአል፡፡ 34በመላው ዓለም የሚገኙ ነገሥታት ስለ ሰሎሞን ጥበብ ለመስማት ይመጡ ነበር፡፡ ስለ ጥበቡም የሰሙት ከምድር ነገሥታት ሁሉ ወደ እርሱ መጥተዋል፡፡
1የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቆይቶ ነበር፤ እርሱም ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት ፈንታ መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ፡፡ 2ሰሎሞንም ወደ ኪራም እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፡፡ 3አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት ከብዙ ጦርነቶች የተነሣ ለእግዚአብሕሔር አምላክ በስሙ ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉን ታውቃለህ፤ እግዚአብሔርም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ጠላቶቹን ከእግሩ በታች አንበረከካቸው፡፡4አሁን ግን አምላኬ እግዚአብሔር በሁሉም ድንበር እረፍት ሰጥቶኛል፡፡ ምንም ዓይነት ጠላት ወይም አደጋ የሚጥል የለብኝም፡፡ 5ስለዚህ እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፡- ከአንተ በኋላ የማነግሠው ልጅህ ለእኔ በስሜ ቤተ መቅደስ ይሠራልኛል ሲል ተናግሮት ስለነበር፤ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር በስሙ ቤተ መቅደስ ለመሥራት አሁን አቅጃለሁ፡፡6ስለዚህም የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቆርጡ ሰዎች ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፡፡ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደረጋለሁ፤ ለአንተም ሰዎች የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተም እንደምታውቀው፣ የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቆራረጥ የአንተን ሰዎች ያህል ዕውቀት የላቸውም፡፡7ኪራም የሰሎሞን መልእክት ሲደርሰው እጅግ ተደሰቶ፣ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ በዚህ በታላቅ ሕዝብ ላይ እንዲነግሥ ይህን የመሰለ ጥበበኛ ልጅ ለዳዊት የሰጠው እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለ፡፡ 8ከዚህ በኋላ ኪራም ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ለሰሎሞን ላከ፤ የላክልኝን መልእክት ሰምቻለሁ፤ የምትፈልገውን ሁሉ፣ የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባውን ግንድ አዘጋጅልሃለሁ፡፡9የእኔ ሰዎችም ግንዶችን ከሊባኖስ ወደ ባሕር ያወርዳሉ፤ አስረውም አንተ ወደምትፈልገው ጠረፍ በውኃ ላይ ተንሳፍፈው እንዲደርሱ ያደርጋሉ፤ በዚያም የእኔ ሰዎች ማሰሪያውን ፈተው ለአንተ ሰዎች ያስረክቡአቸዋል፤ አንተም በበኩልህ ለቤተ ሰቤ ምግብ በመስጠት ፍላጎቴን ትመልስልኛለህ፡፡10በዚህ ዓይነት ኪራም ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖሱን ዛፍና የዝግባ ግንድ ሁሉ ሰጠው፡፡ 11ሰሎሞንም በበኩሉ ለኪራም ቤተ ሰቦች ቀለብ የሚሆን ሃያ ሺህ መስፈሪያ ስንዴና ሃያ መስፈሪያ ንጹሕ ዘይት ሰጠ፡፡ ይህንንም በየዓመቱ ይሰጥ ነበር፡፡ 12እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብ ሰጠው፤ በሰሎሞንና በኪራም መካከል ሰላም ነበር፤ ሁለቱም የጋራ ስምምነት አደረጉ፡፡13ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል ሠራተኞችን መለመለ፤ የግዳጅ ሠራተኞችም ሠላሳ ሺህ ነበሩ፡፡ 14ዐሥር ሺህ የሚያህሉትን ለአንድ ወር ወደ ሊባኖስ በፈረቃ ላካቸው፡፡ ለአንድ ወር በሊባኖስ ሁለት ወር በቤታቸው ነበሩ፡፡ አዶኒራም የተባለው ሰው በግዳጅ ሠራተኞች ላይ ኃላፊ ነበር፡፡15ንጉሥ ሰሎሞን በኮረብታማው አገር ድንጋይ የሚፈልጡ ሰማኒያ ሺህ፣ የተፈለጠውን ድንጋይ ተሸክመው የሚያመጡ ሰባ ሺህ ሰዎች ነበሩት፡፡ 16የእነዚህ ሠራተኞች የበላይ ሆነው ሥራውን የሚቆጣጠሩ ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰዎች ነበሩ፡፡17በዚህ ዓይነት ሠራተኞቹ በንጉሥ ሰሎሞን ትእዛዝ ለቤተ መቅደሱ መሠረት የሚሆን ታላላቅ ድንጋዮችን ፈለጡ፡፡ 18የሰሎሞንና የኪራም አናጢዎችና ግንበኞች የጌባላውያንም ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የሚያስችላቸውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ አዘጋጁ፡፡
1ስለዚህ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ፡፡ ይህም የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጡ ከአራት መቶ ሰማኒያ ዓመት በኋላ፣ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር ነበር፡፡ 2ቤተ መቅደሱም በውስጥ በኩል ርዝመቱ ሃያ ሰባት ሜትር፣ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፣ ቁመቱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር፡፡3በመግቢያው በር የሚገኘው በረንዳ ቁመቱ አራት ሜትር ተኩል፣ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ዘጠኝ ሜትር ነበር፡፡ 4የቤተ መቅደሱም ሕንፃ ከውስጥ ሰፋ፣ ከውጪ ጠበብ ያሉ መስኮቶች ነበሩት፡፡5በቤተ መቅደሱን ሕንፃ ፊት ለፊት ግድግዳ ዙሪያ ክፍሎችን ሠራ፤ በዋናው መግቢያ በር በውጪና በውስጥ ክፍሎች ሠራ፤ በዙሪያውም ክፍሎችን አደረገ፡፡ 6የታችኛው ፎቅ ክፍል ወርዱ አምስት ክንድ፣ የመካከለኛ ፎቅ ክፍል ስድስት ክንድ፣ የሦስተኛው ፎቅ ክፍል ወርድ ሰባት ክንድ ነበር፤ የእንያዳንዱ ወለል ግንብ ከታች በኩል ካለው የወለል ግንብ የሳሳ ነበር፤ ሠረገሎቹ ወደ ቤተ መቅደሱ ግድግዳ እንዳይገቡ ለማድረግ ከቤተ መቅደሱ ግድግዳ ውጪ ዐረፍቶችን አደረገ፡፡7ቤተ መቅደሱ የታነጸባቸው ድንጋዮች ተጠርበው የተዘጋጁት በዚያው በተፈለጡበት ቦታ ነበር፤ ቤተ መቅደሱ በሚሠራበት ጊዜ የመዶሻ፣ የመጥረቢያ ወይም የሌላ ብረት ነክ መሣሪያ ድምፅ አይሰማም ነበር፡፡ 8ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ በኩል በምድር ደረጃው ላይ መግቢያ በር ነበር፡፡ ከዚያ በደረጃዎቹ መካከለኛ ደረጃ ወደ ላይ ያስኬዳል፡፡ እንዲሁም ከመካከለኛው ደረጃ ወደ ሦስተኛ ደረጃ ይወስዳል፡፡9በዚህ ሁኔታ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሕንፃ ሥራ ፈጸመ፤ ጣራውንም ከውስጥ በኩል ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ አግዳሚ ሠረገላና ጠርብ ቤቱን ሸፈነው፡፡ 10የእያዳንዱ ፎቅ ቁመት አምስት ክንድ ከፍታ ሆኖ ከውጪ በኩል ወደ ቤተ መቅደሱ ተጠግቶ የተሠራው ባለ ሦስት ፎቅ ተጨማሪ ሕንፃ ከዋናው ሕንፃዎች ከሊባኖስ ዛፍ በተሠሩት አግዳሚ ወራጆች የተያያዘ ነበር፡፡11የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሰሎሞን እንዲህ ሲል መጣ፡- 12እየተሠራ ያለውን ቤተ መቅሰደስ በተመለከተ፣ በትእዛዜ መንገድ ብትሄድና ቅን ፍርድ ብታደርግ ለአባትህ ለዳዊት እንዳደረግሁ የሰጠሁትን ተስፋ አጸናልሃለሁ፡፡ 13በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እኖራለሁ፣ ከቶም አልተዋቸውም፡፡14ስለዚህ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ጨረሰ፡፡ 15ከዚያ የቤተ መቅደሱን የውስጥ ግድግዳዎች በሊባኖስ ዝግባ ሠራ፤ ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርበው በተሠሩ ሳንቃዎች ለበደ፤ የወለሉም ጣውላ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር፡፡16ውስጣዊ ክፍል ከቤተ መቅደሱ በስተ ኋላ ገባ ብሎ ተሠራ፣ የእርሱም ርዝመት ዘጠኝ ሜትር ሲሆን ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተከፈለ ነበር፤ ይህንን ክፍል ቅድሰተ ቅዱሳን ውስጠኛ ክፍል እንዲሆን ነው፡፡ 17ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት የሚገኘውም የተቀደሰ ክፍል ርዝመት አርባ ክንድ ነበር፡፡ 18የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሳንቃዎች በአበባ እንቡጦችና በፈኩ አበባዎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ውስጡም ሁሉ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ ስለ ተለበጠ የግንቡ ድንጋዮች አይታዩም ነበር፡፡19ሰሎሞንም ከቤተ መቅደሱ ውስጥ በስተኋላ በኩል የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የሚቀመጥበት ውስጣዊ ክፍል አዘጋጀ፡፡ 20ይህም ውስጣዊ ክፍል ርዝመቱ ዘጠኝ ሜትር፣ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፣ ቁመቱ ዘጠኝ ሜትር ሲሆን፣ በሙሉ በንጹሕ ወርቅ የተለበጠ ነበር፤ መሠዊያውም ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ የተለበጠ ነበር፡፡21ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ እርሱም ክፈፉን በተሸጋገሩ የወርቅ ሰንሰለቶች አስጌጠው፡፡ 22የቅድስት ቅዱሳኑ ውስጠኛ በወርቅ ለበጠው፡፡23ሰሎሞንም እያንዳንዱ ዐሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት በሁለት ኪሩቤል አምሳል የተቀረጹ ሥዕሎች በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ሠራ፡፡ 24የኪሩቡ አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ፤ የኪሩቡም ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ፡፡ 25ሁለተኛውም ኪሩብ ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የሁለቱም ኪሩቤል ቅርጽና መጠን ተመሳሳይ ነበር፡፡ 26የአንዱ ኪሩብ ቁመት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የሁለተኛውም ኪሩብ እንዲሁ ነበረ፡፡27ኪሩቤልንም በቅድስት ቅዱሳኑ ውስጥ እንዲቆሙ አደረገ፤ ስለዚህም የተዘረጉ ሁለቱ ክንፎቻቸው በክፍሉ መካከለኛ ቦታ ላይ ተገናኝተው ሌሎቹ ሁለቱ ክንፎቻቸው ደግሞ በተዘረጉበት አቅጣጫ ግንቦቹን ይነኩ ነበር፡፡ 28ሰሎሞንም ሁለቱን ኪሩቤል በወርቅ ለበጣቸው፡፡29የዋናውን ክፍልና የውስጠኛውን ክፍል ግንቦች በሙሉ በኪሩቤል፣ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፡፡ 30እርሱም ከውስጥና ከውጪ በኩል ያሉትን ክፍሎች ወለል በወርቅ ለበጣቸው፡፡31ከወይራ እንጨት የተሠራ ሁለት ተካፋች በር በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ እንዲቆም አደረገ፤ በሩም አምስት ማእዘን ያለው ሆኖ አናቱ ላይ ቀጥ ብሎ የተሠራ ቅስት ነበር፡፡ 32ሁለቱን በሮች በኪሩቤል፤ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፤ እርሱም በሮቹን፣ ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎቹንና ቅርጾቹን በወርቅ ለበጣቸው፡፡33በዚህ ዓይነት ሰሎሞን ደግሞ ወደ ዋናው ክፍል ለሚያደርሰው መግቢያ በር ከወይራ እንጨት የተሠራ ባለ አራት ማእዘን ክፈፍ አበጀለት፡፡ 34ሁሉቱንም በሮች ከዝግባ እንጨት ሠራ፤ አንዱ በር በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ፤ ሁለተኛውም በር በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ፡፡ 35እነርሱን ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፣ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው፡፡36በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አንድ የውስጥ አደባባይ ሠራ፤ በዚህም አደባባይ ዙሪያ በየሦስቱ ዙር የድንጋይ ረድፍ አንድ የሊባኖስ ዛፍ ሠረገላ ሳንቃ የተጋደመበት ግንብ አደረገ፡፡37የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረቱ የተጣለው ሰሎሞን በነገሠ በአራተኛው ዓመት ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር ነበር፡፡ 38ሰሎሞን በነገሠ በዐሥራ አንደኛ ዓመቱ ቡል ተብሎ በሚጠራው በስምንተኛው ወር ላይ የቤተ መቅደሱ ሁሉም ክፍሎችና ሁሉም ንድፍ ተጠናቀቀ፡፡ ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ሰባት ዓመት ወሰደበት፡፡
1ሰሎሞንም ለራሱ የሚሆን ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ቤተ መንግሥቱንም ለመሥራት ዐሥራ ሦስት ዓመት ፈጀበት፡፡ 2እርሱም የሊባለኖስ ጫካ ተብሎ የተጠራውን ቤተ መንግሥት ሠራ፡፡ ርዝመቱም ወርዱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱም አምሳ ክንድ፤ ቁመቱም ሠላሳ ክንድ ነበር፡፡ ቤተ መንግሥቱ አራት ረድፍ ሆኖ ከዝግባ እንጨት ምስሶዎች የተሠሩ ሲሆን፣ በምስሶዎቹ ላይ አግዳሚ ሠረገላዎች ተጋድመው ነበር፡፡3የእነዚህ ዕቃ ቤቶች ጣራ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠራ ነበር፡፡ በምስሶዎቹም ላይ በነበሩ አግዳሚዎች ቤቱ በዝግባ ሳንቃ ተሸፍኖ ነበር፡፡ ምስሶዎቹም በአንዱ ረድፍ ዐሥራ አምስት፣ በአንዱ ረድፍም አምስት እየሆኑ አርባ አምስት ነበሩ፡፡ 4ትይዩ የሆኑት የሕንፃው ሁለት ግንቦች እያንዳንዳቸው በመደዳ ሦስት፣ ሦስት መስኮቶች ነበሩአቸው፡፡ 5በሮቹና መስኮቶቹ ሁሉ ባለአራት ማእዘን መቃኖች ነበሩአቸው፤ ለእያንዳንዱ ግንብ በረድፍ የተሠሩ ሦስት ሦስት መስኮቶች ነበሩት፤ የእያንዳንዱ ግንብ መስኮቶች ከሌላው ግንብ መስኮቶች ጋር ትይዩ ነበሩ፡፡6ምሶሶዎች ያሉበትን ቤት ሠራ፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፣ ስፋቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ፤ በእርሱም ፊት ደግሞ ምሶሶና መድረክ ያለበት ወለል ነበረ፡፡7ሰሎሞን ችሎት ተቀምጦ የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበትም የዙፋን አዳራሽ ሠራ፡፡ ከወለሉ እስከ ጣራው ድረስ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ሳንቃ የተሸፈነ ነበር፡8ከችሎቱም አዳራሽ በስተ ኋላ በሚገኘው ሌላ አደባባይ ሰሎሞን የሚኖርበትን ሕንጻ እንደ ሌሎቹ ሕንጻዎች አድርጎ አሠራ፤ የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ ለነበረቸው ሚስቱም ተመሳሳይ መኖሪያ ቤት አሠራላት፡፡9እነዚህ ሁሉ ሕንፃዎችና ታላቁ አደባባይ ጭምር ከመሠረታቸው እስከ ድምድማታቸው በጥሩ ታላላቅ ድንጋዮች አጊጠው የተሠሩ ነበሩ፣ ድንጋዮቹም በዚያ በድንጋይ መፍለጫ ስፍራ በፊትም በኋላም በልክ ተፈልፍለውና ተጠርበው የመጡ ነበር፡፡ 10የቤቱ መሠረት የተሠራው በጣም ታላላቅና ውድ በሆኑ ስምንትና ዐሥር ክንድ ርዝመት ባላቸው ድንጋዮች የተሠሩ ነበር፡፡11እነዚህም ውድና በልክ ከተፈለፈሉ ድንጋዮችና ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት የተሠሩ አግዳሚ ሠረገሎች ነበሩ፡፡ 12የቤተ መንግሥቱ አደባባይ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባው በር በእያንዳንዱ ባለ ሦስት ረድፍ የጥርብ ድንጋይ ሕንፃ ላይ አንዳንድ ረድፍ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሠረገላ የተጋደመባቸው ግንቦች ነበሩ፡፡13ንጉሡ ሰሎሞንም ሔራም የተባለውን ሰው ከጢሮስ ከተማ አመጣ፡፡ 14ሔራም እናቱ ባል የሞተባት የንፍታሌም ነገድ ተወላጅ ነበረች፣ አባቱም የጢሮስ ተወላጅ ሲሆን እርሱም ነሐስ አቅልጦ በመሥራት ጥበብ የሠለጠነ ባለሙያ ነበር፡፡ ሔራም በእጅ ጥበብ ብዙ ልምድ ያለው ብልህ ሰው ነበር፤ እርሱም የነሐስ ጥበብ ሥራ ለንጉሡ ለመሥራት ወደ ንጉሥ ሰሎሞን መጣ፡፡15ሔራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ፣ የዙሪያ ስፋታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ ሁለት የነሐስ ምሶሶዎችን ሠራ፡፡ 16እንዲሁም በምሶሶዎቹ ላይ የሚቆሙ የእያንዳንዳቸው ቁመት አምሰት ክንድ የሆነ ሁለት የነሐስ ጉልላቶችን ሠራ፡፡ 17በምሶሶዎቹም ራስ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ያስጌጡ ዘንድ በሰባት ረድፍ የተሠሩ መረቦችን ሠራ፡፡ አንዱን መረብ ለአንድ ጉልላት ሁለተኛውን መረብ ለሁለተኛው ጉልላት አደረገ፡፡18ስለዚህም ሔራም ምሶሶዎቹ ጫፍ ላይ ያሉትን ጉልላቶች ለማስጌጥ ሮማኖችን በሁለት ረድፍ ሠራ፡፡ ለየእያንዳንዱም ጉልላት እንዲሁ አደረገ፡፡ 19በወለሉ ምሶሶዎች አናት ላይ ያሉት ጉልላቶች ቁመታቸው አራት ክንድ ሲሆን የሱፍ አበባን በሚመስል ሥራ ተጊጠው ነበር፡፡20እነርሱም ከመረቡ በላይ ባለው ክብ ስፍራ እንዲቆሙ ተደረገ፤ በእያንዳንዱም ጉልላት ዙሪያ በሁለት ረድፍ የተደረደሩ ሁለት መቶ የሮማን ቅርጾች ነበሩ፡፡ 21ሔራም ከነሐስ የተሠሩትን ሁለት ምስሶዎች በቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ፊት ለፊት አቆማቸው፡፡ ከቤተ መቅደሱም መግቢያ በር በስተደቡብ በኩል የቆመው ምሶሶ «ያኪን» ተብሎ ተጠራ፤ በስተ ሰሜን በኩል የቆመው ምሶሶ ደግሞ «ቦዔዝ» ተባለ፡፡ 22በምሶሶዎቹ ጫፍ ላይ የሱፍ አበባ የሚመስሉ ከነሐስ የተሠሩ ጉልላቶች ነበሩ፡፡ የምስሶዎቹም ሥራ በዚህ ዓይነት ተፈጸመ፡፡23ሔራም ዐሥር ክንድ ጥልቀት፣ የክብ ማእከል ርዝመት አምስት ክንድ ዙሪያ ያለው አንድ ክብ ገንዳ ከነሐስ ሠራ፡፡ ባሕሩም ዙሪያው ሠላሳ ክንድ ነበር፡፡ 24የገንዳው አፍ ውጪኣዊ ክፈፍ ሁሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በቅል አምሳል ከነሐስ የተሠሩና በሁለት ረድፍ የተደረደሩ ቅርጾች ነበሩት፡፡25ገንዳውም ከነሐስ በተሠሩ ዐሥራ ሁለት የበሬ ምስሎች ጀርባ ላይ ተቀመጠ። ኮርማዎቹም በየአቅጣጫው ፊታቸውን ወደ ውጪ መልሰው ሦስቱ ወደ ሰሜን፤ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ የሚመለከቱ ይመስሉ ነበር፡፡ 26የገንዳውም ጎኖች ውፍረት አንድ መዳፍ ነበር፤ የጽዋ ቅርጽ ያለው አበባ የሚመስል የአፉ ክፈፍ የሱፍ አበባ ቅርጽ ነበረው፤ ይህም ገንዳ አርባ ሺህ ሊትር ያህል ውሃ የሚይዝ ነበር፡፡27ሔራም ዐሥር መቀመጫዎችን ከነሐስ ሠራ፡፡ የእያንዳንዱ ርዝመት አራት ክንድ፣ ቁመቱ አራት ክንድ፣ ሦስት ክንድ ስፋት ነበር፡፡ 28የመቀመጫዎቹ ሥራም እንዲህ ነበር፡፡ የዕቃ መቀመጫዎቹም የተሠሩት በክንፎቹ መካከል ልሙጥ በሆነ ነገር ነበር፡፡ 29ልሙጥ በሆነውም ነገር ላይ በአንበሶች፣ በበሬዎችና በኪሩቤል አምሳል የተቀረፁ ምስሎች ነበሩ፡፡ ከአንበሶቹ፣ ከበሬዎቹና ከኪሩቤሉ ቅርፆች ራስጌና ግርጌ የአበባ ጉንጉን የሚመስሉ ቅርፆች ነበሩ፡፡30እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ከነሐስ የተሠሩ አራት መንኮራኩሮች ነበሩባቸው፡፡ መንኮራኩሮቹም የሚሽከረከሩበት የነሐስ ወስከምቶች ነበራቸው፤ እንዲሁም በአራቱ ማእዘኖች የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበሩ፤ መደገፊያዎቹም የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርፆች አጊጠው ነበር፡፡ 31የመታጠቢያ ገንዳውም አንገት አንድ ክንድ ነበር፤ እርሱም ክብ ነበር፤ ቁመቱም አንድ ክንድ ነበር፤ በአንገቱም ላይ ማስጌጫ ቅርፅ ነበረበት፤ የገንዳው ተሸካሚ ግን አራት ማእዘን ነበር እንጂ ክብ አልነበረም፡፡32የመንኮራኩሮቹም ቁመት አንድ ተኩል ክንድ ነበር፤ መንኮራኩሮችም በዕቃ ማስቀመጫው ጠፍጣፋ ነሐስ ሥር ነበሩ፤ የመንኮራኩሮቹም ወስከምቶች ከዕቃ ማስቀመጫዎቹ ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፡፡ 33መንኮራኩሮቹም የሠረገላ መንኮራኩሮችን ይመስሉ ነበር፡፡ ወስከምቶቻቸው፣ ቅርጾቻቸውና አቃፊዎቻቸው ሁሉም ከብረት ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ፡፡34እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ አራት ማእዘን በየግርጌአቸው ከእነርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው ከነሐስ የተሠሩ አራት ደጋፊዎች ነበሩአቸው፡፡ 35በእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ጫፍ ዙሪያ ክፈፍ ላይ ተኩል ክንድ ርዝመት ያለው አንድ ክብ ቅርፅ ነበር፤ መደገፊያዎቹና ጠፍጣፋ ነሐሶቹ ከዕቃ ማስቀመጫው ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፡፡36በእነዚህ መደገፊያዎችና ጠፍጣፋ ነሐሶች መካከል ባለው ክፍት ቦታ ሁሉ በኪሩቤል፣ በአንበሶችና በዘንባባ ዛፎች አምሳል ሔራም ሠራቸው፡፡ እንዲሁም ዙሪያቸው የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርፆች አጊጠው ነበር፡፡ 37እንግዲህ ዐሥሩን ባለመንኩራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎች የሠራቸው በዚህ ዓይነት ነበር፡፡ መጠናቸውና ቅርፃቸው እኩል ስለተቀረጹ ሁሉም ተመሣሣይ ነበሩ፡፡38ሔራም ለእያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ዐሥር የነሐስ መታጠቢያ ገንዳዎች ሠራ፡፡ የእያንዳንዱ ገንዳ ዙሪያ አጋማሽ ስፋት አራት ክንድ ያህል ሲሆን፣ አርባ ሊትር ያህል ውሃ ይይዝ ነበር፡፡ 39ሔራም አምስቱን የዕቃ ማስቀመጫዎች ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ፣ የቀሩትንም አምስቱን ከቤተ መቅደሱ በስተሰሜን በኩል አቆመ፡፡ ገንዳውን ደግሞ በቤተ መቅደሱ ደቡባዊ ምሥራቅ ማእዘን ላይ አቆመው፡፡40ሔራምም ድስቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጎድጓዳ ሳህኖችን ሠራ፡፡ በዚህ ዓይነትም ለንጉሥ ሰለሞን ሊሠራለት የጀመረውን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ፈጸመ፡፡ 41ሁለቱ ምሰሶዎች፣ በምሶሶዎቹም ላይ የነበሩትን ጉልላቶች የሚመስሉ ሳህኖችን፣ በምሶሶውም ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጉልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መረቦች ሠራ፡፡42በእያንዳንዱ ጉልላት ላይ በመረብ አምሳል የተሠሩት ሰንሰለቶች፣ በእያንዳንዱ ጉልላት ቅርፅ ላይ በሁለት ዘርፍ አንዳንድ መቶ ዙር የሆኑ ከነሐስ የተሠሩ አራት መቶ የሮማን ቅርፆችን ሠራ፡፡43ዐሥሩ ባለመንኮራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎች፣ ዐሥሩ የመታጠቢያ ገንዳዎች ነበሩ፡፡44ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፣ ገንዳውን ደግፈው የሚይዙ የዐሥራ ሁለቱን በሬዎች ቅርፅ ሠራ፡፡ 45ድስቶቹን፣ መጫሪያዎቹንና ጎድጓዳ ሳህኖቹን ሠራ፡፡ ሌሎችንም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሔራም እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ለሰለሞን የሠራለት ከተወለወለ ንፁህ ነሐስ ነበር፡፡46ንጉሥ ሰለሞን እነዚህን ሁሉ ያሠራው በዮርዳኖስ ሸለቆ በሱኮትና ጻርታን መካከል በሚገኘው በሸክላ ስፍራ ነበር፡፡ 47ከነሐስ የተሠራው ይህ ሁሉ ዕቃ እጅግ ብዙ ስለ ነበር፣ ሰለሞን በሚዛን እንዲለካ አላደረገውም፣ ስለዚህ ክብደቱ ምን ያህል እንደሆነ ተወስኖ አልታወቀም፡፡48ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሰለሞን ያሠራቸው ዕቃዎች ሁሉ በንጹሕ ወርቅ ያጌጡ ነበሩ፡፡ እነርሱም የወርቁ መሠዊያ፣ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ የወርቅ ጠረጴዛ ናቸው፡፡ 49በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በስተደቡብ፣ አምስቱ ደግሞ በስተ ሰሜን የሚቀመጡት ዐሥሩ የወርቅ መቅረዞች፣ አበባዎች፣ የመብራት ቀንዲሎች፣ የእሳት መቆስቆሻዎች ሁሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡50ሰሎሞንም ጽዋዎችን፣ የአመድ ማጠራቀሚያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳህኖችን፣ የዕጣን ማቅረቢያ ሳህኖችን፣ ማንደጃዎችን፣ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችንና ለቤተ መቅደሱ ውጪኣዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎችን ከንጹሕ ወርቅ አሠራ፡፡51በዚህ ዓይነት ንጉሥ ሰለሞን የቤተ መቅደሱን ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት እንዲውል የለየውን ብሩን፣ ወርቁንና ሌላውንም ዕቃ በሙሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ውስጥ አኖረው፡፡
1ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን ለማምጣትና ወደ ቤተ መቅደሱ ለማስገባት የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጎሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ፡፡ 2የእስራኤልም ወንዶች ሁሉ በዓሉ በሚከበርበት ኤታኒም ተብሎ በሚጠራው በሰባተኛው ወር ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ተሰበሰቡ፡፡3መሪዎቹ ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜም ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሥተው ተሸከሙ፡፡ 4ካህናቱም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት፣ የመገናኛ ድኳንና በድንኳኑም ውስጥ የነበሩትን ንዋያተ ቅዱሳት ሁሉ አምጥተው ወደ ቤተ መቅደስ አገቡ፡፡ 5ንጉሥ ሰሎሞንና መላው የእስራኤል ሕዝብ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ተሰበሰቡ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቆጠር የማይችል ብዙ በጎቸና የቀንድ ከብት መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡6ከዚህም በኋላ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል፣ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ወደ ቦታው አምጥተው በኪሩቤል ክንፎች ሥር አኖሩት፡፡ 7የተዘረጉ የኪሩቤል ክንፎችም የታቦቱን መሸከሚያ መሎጊያዎች ሸፍነው ነበር፡፡ 8መሎጊያዎቹ ረጃጅሞች ስለ ሆኑ ጫፎቻቸው በቤተ መቅደሱ ውስጥ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ለሚቆም ሰው ሁሉ በግልጽ ይታዩ ነበር፤ በሌላ አቅጣጫ የሚቆም ግን አያያቸውም፡፡ እስከ ዛሬም እዚያው ይገኛል፡፡9የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳ በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳን ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር በቃል ኪዳን ታቦት ውስጥ ሌላ ምንም ነገር አልነበረም፡፡ 10ካህናቱ ከቅድስተ ቅዱሳን እንደ ወጡ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ድንገት በደመና ተሞልቶ ነበር፡፡ 11በደመናውም ውስጥ የነበረው የእግዚአብሔር ክብር ቤቱን ስለ ሞላ ካህናቱ ቆመው አገልግሎታቸውን ለማከናወን አልቻሉም ነበር፡፡12በዚህ ጊዜ ሰሎሞን እንዲህ ሲል ጸለየ፡- እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አንተ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እኖራለሁ ብለሃል፤ 13እነሆ አሁን ግርማ ሞገስ ያለው ቤተ መቅደስ ለአንተ ሠርቻለሁ፤ እርሱም አንተ ለዘለዓለም የምትኖርበት ቦታ ይሆናል፡፡14የእስራል ጉባኤ ሁሉ ቆመው ሳሉ፤ ንጉሥ ሰሎሞን ፊቱን ወደ እነርሱ መልሶ የእግዚአብሔር በረከት በእርሱ ላይ እንዲወርድ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ 15የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን አጽንቶ ጠብቆአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፡- 16ሕዝቤን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዓይነት ከተማ አልመረጥኩም ነበር፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መረጥኩ፡፡17ቀጥሎም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤ አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስን ለመሥራት አቅዶ ነበር፤ 18እግዚአብሔርም አባቴን ዳዊትን ስሜ የሚጠራበትን ቤተ መቅደስ ትሠራ ዘንድ በልብህ ማሰብህ መልካም ነው፡፡ 19ነገር ግን እርሱን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው እንጂ አንተ አይደለህም፤ ከአንተ የሚወለደው ልጅ ቤተ መቅደሴን ይሠራል አለው፡፡20እነሆ እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቆአል፤ ስለዚህ እኔ በአባቴ ፈንታ ተተክቼ የእስራኤል ንጉሥ ሆኜአለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስን ሠርቼአለሁ፡፡ 21እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር ቃል ኪዳን የገባበት የድንጋይ ጽላት ለሚገኝበት ታቦት ማኖሪያ የሚሆን ቦታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አዘጋጅቼአለሁ፡፡22ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በሕዝቡ ፊት ተነሥቶ በእግዚአብሔር መሠዊያው ፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘረጋ፡፡ 23እንዲህም አለ፡- የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአገልጋዮቹ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቅና ከልባቸው ታማኞች እስከ ሆኑ ድረስ ፍቅሩን የሚያጸና በላይ በሰማይ በታችም በምድ እንደ አንተ ያለ አምላክ የለም! 24ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውንም የተስፋ ቃል አጽንተሃል፤ በአፍህ የተናገርከውም ቃል ሁሉ እነሆ ዛሬ በእጅህ ተፈጽሞአል፡፡25አሁን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ለአባቴ ለዳዊት አንተ ታደርገው በነበረው ዓይነት ልጆችህ ታዛዦች ቢሆኑና በፊቴም በቅንነት ቢመላለሱ ሁልጊዜ ከዘርህ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚነግሥ ልጅ አላሳጣህም ስትል የተናገርከውን የተስፋ ቃል ፈጽም፡፡ 26አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ! አገልጋይህ ለነበረው ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ሁሉ እንዲፈጸም አድርግ፡፡27በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፤ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስ ምንኛ ያንስ፡፡ 28ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ወደ አገልጋይህ ጸሎትና ልመና ተመልክት፤ ዛሬም አገልጋይህ በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ጩኸት ስማ፡፡29ስሜ ይጠራበታል ወዳልከው ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቀንና ሌሊት ተመልከት፤ እኔም አገልጋይህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ የምጸልየውን ጸሎት ስማ፡፡ 30ፊታችንን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰን በምንጸልይበት ጊዜ የእኔንና የእስራኤልን ሕዝብ ጸሎት ስማ፤ ከመኖሪያህ ከሰማይ ሆነህ ስማን፤ ይቅርም በለን፡፡31አንድ ሰው ባልንጀራውን መበደሉን የሚገልጥ ክስ ቀርቦበት በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደሚገኘው መሠዊያ አምጥተውት ከበደል ንጹሕ መሆኑን በመሐላ በሚያረጋግጥበት ጊዜ፣ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ 32ለአገልጋዮችህም ፍርድን ስጥ፤ ይኸውም በደል የሠራው ሰው በጥፋቱ መጠን እንዲቀጣ፣ ንጹሕ የሆነውም ነጻ እንዲወጣ አድርግ፡፡33ሕዝብህ እስራኤል በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት በጠላቶቻቸው ድል ሲሆኑ ተጸጽተው ወደ አንተ በመመለስ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢመጡና የአንትን ይቅርታ ለማግኘት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በትሕትና ቢለምኑህ፤ 34አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ በምርኮ የሚገኙትንም ሕዝብህን ኃጢአት ይቅር በማለት ለቀድሞ አባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሰህ አግባቸው፡፡35የእስራኤል ሕዝብ በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት ዝናብ እንዳይዘንብላቸው አድርገህ በምትቀጣቸው ጊዜ በፈጸሙት በደል በመጸጸት ፊታቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰው በትሕትና ቢለምኑህ፤ 36አንተ በሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፣ በልብ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፣ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።37በምድሪቱ ላይ ረሐብ ወይም ቸነፈር በሚመጣበት ጊዜ፣ እንዲሁም እህላቸው በውርጭ በዋግና በአንበጣ ወይም በኩብኩባ መንጋ በሚወድምበት ጊዜ ወይም ጠላቶቻቸው በሕዝብህ ላይ አደጋ በሚጥሉበት ጊዜ ወይም በሕዝብህ ላይ ልዩ በሽታና ደዌ በሚደርስባቸው ጊዜ፣ 38በሕዝብህ በእስራኤል መካከል ልብ የሚያሸብር መራር ሐዘን ደርሶባቸው እጃቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፣ ጸሎታቸውን ስማ፡፡39በምትኖርበት በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን በመስማት ይቅር በላቸው፤ እርዳቸውም፣ በሰው ልብና አእምሮ ያለውን አሳብ ሁሉ መርምረህ የምታውቅ አንተ ብቻ ነህ፤ ስለዚህ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን የሚገባውን ዋጋ ስጠው፡፡ 40በዚህም ዓይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ፡፡41በተጨማሪም የሕዝብህ የእስራኤል ወገን ያልሆነ፣ የውጪ አገር ሰው ከስምህ የተነሣ ከሩቅ ቢመጣ፤ 42ስለስምህ ገናናነት፣ ስለታላቁ እጅህና ከፍ ስላለው ክንድህ ሰምተው፣ በዚህ ቤተ መቅደስ ቢመጡና ቢጸልዩ፣ 43ከምትኖርበት ከሰማይ ሆነህ የዚያን ሰው ጸሎት ስማ፤ እንድታደርግለት የሚለምንህንም ሁሉ ፈጽምለት፤ ሕዝብህ እስራኤላውያን እንደሚያደርጉት በመላው ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች አንተን በማወቅ እንዲታዘዙህና እንዲያከብሩህ አድርግ፣ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ይህ እኔ የሠራሁት ቤተ መቅደስ የአንተ ስም የሚጠራበት መሆኑን ያውቃሉ፡፡44ጠላቶቻቸውን ለመዋጋት እንዲዘምቱ ሕዝብህን በምታዝበት ጊዜ በየትኛውም ስፍራ ሆነው ወደዚህች ወደ መረጥኻት ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው በሚጸልዩበት ጊዜ፣ 45በሰማያት ሆነህ ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማ፤ በችግራቸውም እርዳቸው፡፡46ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ አንተም ተቆጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምታደርግበት ጊዜ፣ ሩቅ ወይም ቅርብ ቢሆን፣ 47ምርኮኞች ሆነው በሚኖሩባት በዚያች አገር ሳሉ ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለና፤ ዐምፀናል ብለው በመናዘዝ ተጸጽተው ንስሓ ቢገቡ፣48ማርከው በወሰዱአቸው በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ በፍጹም ልባቸው በእውነትና በቅን መንፈስ ተጸጽተው ንስሓ በመግባት አንተ ለቀድሞ አባቶቻችን ወደ ሰጠሃቸው ወደዚህች ምድር፣ አንተም ወደ መረጥኻት ወደዚህች ከተማ፣ እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፣49ከዚያ በመኖሪያህ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውንና እርዳታ ፈልገው ሲለምኑህ በመስማት ፍረድላቸው፤ 50ኃጢአታቸውንና አንተን ያሳዘኑበትን በደል ሁሉ ይቅር በል፤ ጠላቶቻቸውም እንዲራሩላቸው አድርግ፤51እነርሱ እንደ እቶን እሳት ከሚያቃጥል ከግብጽ ምድር ያወጣሃቸውና የመረጥካቸው ሕዝብህ ናቸው፡፡ 52በጠሩህ ጊዜ ሁሉ ትሰማቸው ዘንድ ለአገልጋይህና ለሕዝብህ ልመና ዓኖችህ የተገለጡ ይሁኑ፡፡ 53እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! የቀድሞ አባቶቻችንን ከግብጽ ምድር ባወጣህ ጊዜ ከዓለም ሕዝብ ሁሉ መካከል እስራኤልን የራስህ ሕዝብ እንዲሆን የመረጥከው መሆኑን በአገልጋይህ በሙሴ አማካይነት ተናግረሃል፡፡54ሰሎሞንም እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ በመሠዊያው ፊት ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ቆይቶ ጸሎቱን ከፈጸመ በኋለ ተነሥቶ ቆመ፡፡ 55ድምፁንም ከፍ አድርጎ በዚያ ተሰብስቦ የነበረውን ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ሲል ባረከ፡- 56በገባው የተስፋ ቃል. መሠረት ለሕዝቡ ለእስራኤል ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠው መልካም ተስፋ አንድም የቀረ ቃል የለም፡፡57አምላካችን እግዚአብሔር ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር እንደነበረ ሁሉ ከእኛ ጋርም ይኑር፡፡ ምን ጊዜም አይተወን፤ አይጣለንም፡፡ 58ለቀድሞ አባቶቻችን የሰጠውን ትዕዛዞች፣ ደንቦችና ሥርዓቶች በመጠበቅ ወደ እርሱ ልባችንን በማዘንበል ለእርሱ ታዛዦች እንድንሆን ያድርገን፡፡59የእኔ የአገልጋዩና የሕዝቡ የእስራኤል የየዕለት ፍላጎት ይሟላ ዘንድ ለእግዚአብሔር ያቀረብኳቸው ልመናዎች ቀንና ሌሊት ወደ እግዚአብሔር አምላክ ይቅረቡ፡፡ 60የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ መሆኑንና ከእርሱም ሌላ አምላክ አለመኖሩን ያውቃሉ፡፡ 61ስለዚህም በዛሬው ቀን በድንጋጌው ለመመላለስና ትእዛዞቹንም ታከብሩ ዘንድ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ለአምላካችን በልባችሁ ታማኞች ሁኑ፡፡62ስለዚህ ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፡፡ 63ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶችንና አንድ መቶ ሃያ በጎችን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፡፡ በዚህም ዓይነት ንጉሥ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሔር የተለየ አድርገው ቀደሱት፡፡64አሁንም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ አድርጎ ቀደሰው፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ የእህል ቁርባንና የኅብረት መሥዋዕት፣ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው፡፡65በዚያ ቤተ መቅደስ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ ባጠቃላይ ዐሥራ አራት ቀኖች የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝበ እጅግ ብዙ ነበር፡፡ 66በሚቀጥለው ቀን ሰሎሞን ሕዘቡን ሁሉ አሰናበተ፤ ሁሉም ሰሎሞንን መረቁ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ፣ ለእስራኤል ስለ አደረገው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ብሎአቸው ወደየቤታቸው ሄዱ፡፡
1ንጉሥ ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን እንዲሁም ሊሠራው የፈለገውን ሌላውንም ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣ 2እግዚአብሔር ከዚህ በፊት በገባዖን እንደ ተገጠለት አሁንም እንደገና ተገለጠለት፡፡3ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቻለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም ዓይኔና ልቤ በዚያ ይሆናል፡፡4አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት በፊቴ ብትመላለስ፣ ሕጌንና ሥርዓቴን ብትጠብቅ፣ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፣ 5ለአባትህ ለዳዊት ከዘሮችህ በእስራኤል ዙፋን ላይ የሚነግሥ ልጅ አታጣም በማለት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ዙፋንህ በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ፡፡6ነገር ግን አንተ ወይም ዘሮችህ እኔን መከተል ትታችሁ የሰጠኋችሁን ሕጎችና ትእዛዞች ባትፈጽሙና ባዕዳን አማልክትን ብታመልኩና ብትሰግዱላቸው፤ 7እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህንን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል፡፡8ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ ይህንን አይተው በመደንገጥ እግዚአብሔር ይህንን አገርና ይህንን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ በማለት ይሳለቁበታል፡፡ 9ራሳቸው በሚሰጡት መልስ፣ የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎች አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው የሚል ይሆናል፡፡10ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ሃያ ዓመት ነበር፡፡ 11የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ሃያ ታናናሽ ከተሞችን ለኪራም ሰጠው፡፡12ኪራምም ሄዶ ከተሞቹን አየ፤ ነገር ግን ደስ አላሰኙትም፤ 13ኪራምም ወንድሜ ሆይ! የሰጠኸኝ ከተሞች እነዚህ ምንድን ናቸውን? አለው፡፡ በዚህ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ አካባቢው በሙሉ «ካቡል» እየተባለ ይጠራል፡፡ 14ኪራም ለንጉሥ ሰሎሞን የላከለት ወርቅ አንድ መቶ ሺህ መክሊት ነበር፡፡15ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና ቤተ መንግሥቱን፣ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር የሠሩለትና ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ያለውን ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጎድጓዳ ስፍራ መጥተው ያስተካከሉለት የጉልበት ሥራ ዋጋ ነበር፤ እንዲሁም ሐጸር፤ መጊዶናጊዜር ተብለው የሚጠሩ ከተሞችም እንዲሠሩለት አደረገ፡፡ 16ቀደም ሲል የግብጽ ንጉሥ ፈረዖን በጌዜር ላይ አደጋ ጥሎ፣ ነዋሪዎችዋን ከነዓናውያንን ገድሎ ከተማይቱንም አቃጥሎ በቁጥጥሩ ሥር አድርጓት ነበር፤ ከዚያም በኋላ ለሴት ልጁ ለሰሎሞን ሚስት እንደ ስጦታ ሰጣት፡፡17ሰሎሞንም ጊዜርንና የታችኛው ቤት ሖሮን እንደገና አሠራ፡፡ 18ባዕላት በይሁዳ በረሓማ አገር የምትገኝ ታማር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች እንደገና ሠራ፡፡ 19እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፣ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው ከተሞችን ሠራ፡፡ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፤ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ፡፡20እነዚህም ትውልዶች የእስራኤል ወገን ያልሆኑና የሚያገለግሉ አሞራውያን፣ ሒታውያን፣ ፈሪዛውያን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ 21ለሰሎሞን የጉልበት ሥራ ይሠሩለት የነበሩት የግዳጅ ሥራ ሠራተኞች እስራኤላውያን ምድራቸውን ርስት አድርገው በወረሱ ጊዜ የገደሏቸው የከነዓን ሕዝብ ተውልዶች ነበሩ፡፡22ሰሎሞን ከእስራኤላውያን ወገን ማንንም ባሪያ አድርጎ አላሠራም፤ በዚህ ፈንታ እነርሱ ባለሥልጣኖች፣ ወታደሮች፣ የጦር መኮንኖች፣ የጦር አዛዦች፣ ሠረገላ ለሚነዱ ሁሉ ኃላፊዎችና ፈረሰኞች ሆነው ያገለግሉ ነበር፡፡23ሰሎሞን ለሚያከናውነው የሕንጻ ሥራ የጉልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለተመደቡት ሰዎች አምስት መቶ ኃምሳ ኃላፊዎች ነበሩአቸው፡፡24የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ የነበረችው ሚስቱ ከዳዊት ከተማ ራሱ ወዳሠራላት ቤተ መንግሥት ከተዘዋወረች በኋላ ሰሎሞን የሚሎን ከተማ ገነባ፡፡25ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ባሠራው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በዓመት ሦስት ጊዜ ያቀርብ ነበር፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን ዕጣን ያሳርግ ነበር፤ በዚህም ዓይነት የቤተ መቅደሱ ሥራ ተፈጸመ፡፡26እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ በሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮን ጋብር መርከቦችን ሠራ፡፡ 27ንጉሥ ኪራምም ከሰሎሞን ሰዎች ጋር የሚያገለግሉ የሠለጠኑ መርከበኞችን ላከለት፡፡ 28እነርሱም በመርከብ ተጉዘው ወደ ኦፊር ምድር ከሄዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን ሲመለሱ አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘውለት መጡ፡፡
1ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውንም ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፡፡ 2ብዙ የክብር አጃቢዎችን በማስከተል በግመሎች የተጫነ ሽቶ፣ የከበረ ዕንቁና ብዙ ወርቅ ይዛ መጣች፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኙ ጊዜ በአሳብዋ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤3እርሱም ላቀረበችለት ጥያቄ ሁሉ መልስ ሰጣት፤ ከጠየቀችው ሳይመልስላት የቀረ ምንም ዓይነት እንቆቅልሽ አልነበረም፡፡ 4ንግሥተ ሳባ ጥበብ የተሞላበትን የሰሎሞንን አነጋገር አዳመጠች፤ የሠራውንም ቤተ መንግሥት አየች፡፡ 5በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዓይነት፣ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፣ የቤተ መንግሥቱን አሠራርና አደረጃጃት፣ የደንብ ልብሳቸውን ዓይነት፣ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም ያቀረባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀቸው በላይ ሆነባት፤6ስለሥራህ ውጤትና የጥበብህ ታላቅነት በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ሁሉ እውነት ነው አለች፡፡ 7ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካይ ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል፡፡8ሁልጊዜ በፊትህ በመገኘት ጥበብ የሞላበት ንግግርህን የሚሰሙ ሚስቶችህና አገልጋዮችህ እንዴት የታደሉ ናቸው! 9አምላክህ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ለዓላማው ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል፡፡10ንግሥተ ሳባ ያመጣችለትን ስጦታ ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን አበረከተችለት፤ ይኸውም ከአራት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፣ እጅግ ብዙ ሽቶና የከበረ ዕንቁ ነበር፤ እርስዋ ለሰሎሞን ያበረከተችው የሽቶ ብዛት ከዚያ በኋላ ከቀረበለት የሽቶ ገጸ በረከት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ ነበር፡፡11ከኦፊር ወርቅ ብዙ ያመጡለት የኪራም መርከቦች ከዚያው ከኦፊር ብዙ የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቁ አምጥተውለት ነበር፡፡ 12ሰሎሞን ከዚሁ ከሰንደል እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን መከታዎች፤ መዘምራን የሚያገለግሉባቸውን በገናዎችና መሰንቆዎች አሠራ፤ ይህም የሰንደል እንጨት ወደ እስራኤል አገር ከመጣው የሰንደል እንጨት ሁሉ የሚበልጥ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ይህን የመሰለ የሰንደል እንጨት ከቶ ታይቶ አይታወቅም፡፡13ንጉሥ ሰሎሞን ከተለመደው የልግሥና ስጦታ ጋር የሳባ ንግሥት የጠየቀቸውን ሁሉ ሰጣት። ከዚህ በኋላ ንጉሥተ ሳባ ከክብር አጃቢዎችዋ ጋር ወደ አገርዋ ተመልሳ ሄደች፡፡14ንጉሥ ሰሎሞን በየዓመቱ ሃያ ሦስት ሺህ ኪሎ ያህል የሚመዝን ወርቅ ያገኝ ነበር፤ 15ይህም ሁሉ ነጋዶዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፤ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ አገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር፡፡16ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ታላላቅ ጋሻዎች አሠርቶ እያንዳንዱን ጋሻ በሰባት ኪሎ ያህል ወርቅ አስለበጠው፡፡ 17እንዲሁም ሦስት መቶ ታናናሽ ጋሻዎችን አሠርቶ እያንዳንዱን በሁለት ኪሎ ያህል ወርቅ አስለበጠው፤ እነዚህንም ሁሉ ሊባኖስ ጫካ ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ አኖራቸው፡፡18እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን ከዝሆን ጥርስ አንድ ትልቅ ዙፋን አሠርቶ በንጹሕ ወርቅ አስለበጠው፡፡ 19ወደ ዙፋኑ መወጣጫ ስድስት ደረጃዎች ነበሩ፤ የዙፋኑ ጀርባ ራስጌው ክብ ነበር፤ በዙፋኑ ግራና ቀኝ የክንድ ማሳረፊያዎች ነበሩት፤ በክንድ ማሳረፊያዎቹ ጎን አንዳንድ የአንበሳ ምስሎች ቆመው ነበር፡፡ 20በእያንዳንዱ ደረጃ በሁለት በኩል አንዳንድ የአንበሳ ምስል በድምሩ ዐሥራ ሁለት የአንበሳ ምስሎች ቆመዋል፡፡ ይህን የመሰለ ዙፋን በሌላ በየትኛውም አገር ተሠርቶ አያውቅም ነበር፡፡21በሰሎሞን ዘመን ብር ምንም ዋጋ ስላልነበረው ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዋንጫዎች ሁሉና የሊባኖስ ጫካ ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ እንጂ ከብር አልተሠሩም፤ 22ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱ በየሦስት ዓመት ወርቅ፣ ብር፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር፡፡23ንጉሥ ሰሎሞን ከምድር ነገሥታት ሁሉ የሚበልጥ ሀበታምና ጥበበኛ ነበር፤ 24በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎችም ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠውን ጥበብ የሞላበትን ንግግር ይሰሙ ዘንድ ወደ እርሱ መምጣት ይፈልጉ ነበር፡፡ 25ወደ እርሱም የሚመጡት ሁሉ የብርና የወርቅ፣ የልብስ፣ የጦር መሣሪያዎች፣ የሽቶ፣ የፈረሶች የበቅሎዎች ስጦታዎች ያመጡለት ነበር፤ ይህም በየዓመቱ የሚደረግ ነበር፡፡26ሰሎሞንም ሠረገሎችና ፈረሶች ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሎቹን ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም፣ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ፡፡ 27በግዛቱም ዘመን ሁሉ በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፣ ብዛቱም እንደ ሊባኖስ ዛፍ፣ በይሁዳ ኮረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅለው ሾላም ይቆጠር ነበር፡፡28ሰሎሞን ፈረሶችን ከግብጽና ከቀዌ ያስመጣ ነበር፤ የንጉሡም ነጋዴዎች ፈረሶችን በገንዘብ ገዝተው ከቀዌ ያመጡለት ነበር፡፡ 29እያንዳንዱ ፈረስ በስድስት መቶ ጥሬ ብር፣ እያንዳንዱም ሠረገላ በአንድ መቶ ሃምሳ ጥሬ ብር ከግብጽ አገር ተገዛ፡፡ ከዚያም ለሒታውያንና ለሶርያውያን ነገሥታት ተሸጡ፡፡
1ሰሎሞን ብዙ የባዕዳን አገሮችን ሴቶች አፈቀረ፤ እነዚህም፡- የግብጽ ንጉሥ የፈረዖን ልጅ፣ የሒታውያን፣ የሞአባውያን፣ የአሞራውያን፣ የኤዶማውያንና የሲዶናውያን ሴቶች ልጆችን አፈቀረ፡፡ 2እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን፣ አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደ ሆነ በእርግጥ ወደ አማልክቶቻቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፡፡ እነዚህ ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች እግዚአብሔር እንዳያጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፡፡ ይህ ትእዛዝ ቢኖርም ሰሎሞን ግን በእነርሱ ፍቅር ተነደፈ፡፡3ሰሎሞን የነገሥታት ልጆች የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶችና ሦስት መቶ ቁባቶች ነበሩት፡፡ ሚስቶቹም ሰሎሞንን ከእግዚአብሔር እንዲርቅ አደረጉት፡፡ 4በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልእክት እንዲሰግድ አደረጉት፡፡ ሰሎሞንም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሙሉ ልቡን ለእግዘአብሔር አላስገዛም፡፡5የሲዶናውያን ሴት አምላክ የነበረችውን ለአስታሮትንና ሞሎክ ተብሎ የሚጠራውን ተለይቶ የሚታወቀውን የአሞናውያንን አምላክ ተከተለ፡፡ 6ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በማድረጉ አባቱ ዳዊት እንዳደረገው እግዚአብሔርን በቅንነት አልተከተለም፡፡7ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለአሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን ሠራ፡፡ 8እንዲሁም የባዕዳን አገር ሚስቶቹ ሁሉ ለየአማልክቶቻቸው ዕጣን የሚያጥኑባቸውንና መሥዋዕት የሚያቀርቡባቸውን ስፍራዎች ሠራ፡፡9የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሁለት ጊዜ የተገለጠለት ቢሆንም፣ ከእርሱ እየራቀ በመምጣቱ እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቆጣው፡፡ 10ባዕዳን አማልክትን እንዳያመልክ አዘዘው፡፡ ነገር ግን ሰሎሞን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም፡፡11ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፡- ከእኔ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ስላፈረሰክና ሕጌንም ስላልፈጸምክ መንግሥትህን ከአንተ ወስጄ ከአገልጋዮችህ ለአንዱ እሰጣለሁ፡፡ 12ይሁን እንጂ ለአባትህ ለዳዊት ስል ይህን የማደርገው አንተ ባለህበት ዘመን ሳይሆን በልጅህ መንግሥት ጊዜ ይሆናል፡፡ 13ሆኖም ሁሉንም መንግሥት አልወስድም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለመረጥኩት ከተማ ለኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንዱን ነገድ እሰጠዋለሁ፡፡14ስለዚህም እግዚአብሔር የኤዶማውያኑን ነገሥታት ዘር ሀዳድን በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፡፡ እርሱም ከኤዶም ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ነበር፡፡ 15ዳዊት ከኤዶማውያን ጋር ይዋጋ በነበረ ጊዜ፣ የጦር አዛዡ ኢዮአብ ለመቅበር ወጥቶ በነበረበት ጊዜ፣ በኤዶም ወንዶች ሁሉ ተገድለው ነበር፡፡ 16ኢዮአብና የእስራኤል ሠራዊት የኤዶምን ወንዶች ልጆች ገድለው እስኪጨርሱ ድረስ ስድስት ወራት በዚያ ቆይተዋል፡፡ 17ነገር ግን ከሞት የተረፉትና ሀዳድ በአባቱ አገልጋዮች ወደ ግብጽ ተወሰዱ፡፡ በዚያን ጊዜ ሀዳድ ገና ሕፃን ነበር፡፡18እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ሰዎችን ወደ ግብፅ ወደወሰዱበት ወደ ፋራን ሄዱ፤ በዚያም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ለሀዳድ ቤት፣ መሬትና ምግብ ሰጠው፡፡ 19ሀዳድም በንጉሡ ፈርዖን ፊት ታላቅ ሞገስ አገኘ፡፡ ስለዚህ ንጉሡም የሚስቱን የጣፍኔስን እኅት ለሀዳድ ሚስት እንድትሆነው ሰጠው፡፡20የጣፍኔስንም እኅት ጌንባት ተብሎ የሚጠራውን ወንድ ልጅ ለሀዳድ ወለደችለት፤ እርሱንም ንግሥቲቱ ወስዳ በቤተ መንግሥት አሳደገችው፤ ከፈረዖንም ወንዶች ልጆች ጋር ኖረ፡፡ 21ሀዳድ በግብጽ ሳለ የንጉሥ ዳዊትንና የሠራዊቱን አዛዥ የኢዮአብን መሞት በሰማ ጊዜ፣ ወደ አገሬ ተመልሼ እንድሄድ አሰናብተኝ ሲል ፈረዖንን ጠየቀ፡፡ 22ከዚያም ፈረዖን ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ የፈለግከው ከቶ ምን ተጓድሎብህ ነው? አለው፡፡ ሀዳድም ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ ሲል ለንጉሡ መለሰ፡፡23እንደገናም እግዚአብሔር ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳ ልጅ በሰሎሞን ላይ ሌላ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፡፡ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከዞአብ ንጉሥ ከሀዲድዔዚር ኮብልሎ ነበር፡፡ 24ዳዊት ሀዲድዔዚርን ድል ባደረገበት ጊዜ፣ ረዞን ለራሱ ጦር ሰብስቦ የጥቂት ኃይል አለቃ ሆኖ ነበር፡፡ የረዞን ጦር ወደ ደማስቆ ሄደው እዚያ መኖር ጀመሩ፤ በኋላም ደማስቆን ተቆጣጠረ፡፡ 25በሰሎለሞን ዘመነ መንግሥት ሁሉ ሀዳድ ካደረሰበት ችግር በተጨማሪ ረዞን የእስራኤል ጠላት ነበር፡፡ ስለዚህ ረዞን በሶርያ ላይ ገዢ ሆኖ በእስራኤል ላይ ጠላትነቱን ቀጠለ፡፡26የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም፣ ኤፍሬማዊው የሰሎሞን ባለሥልጣናት አንዱ የሆነው፣ ጸሬዳ ተብሎ የምትጠራው ክፍል ተወላጅ የሆነ፣ የእናቱም ስም ጽሩዓ፣ ባልዋ የሞተባት ሴት ነበረች፤ እርሱም በሰሎሞን ላይ እጁን አነሣ፡፡ 27ኢዮርብዓም በሰሎሞን ላይ እጁን ያነሣበት ምክንያት፤ በዚያን ጊዜ ሰሎሞን ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሚሎ ተብሎ የሚጠራውን ጎድጓዳ ስፍራ በመሙላት እየደለደለና የአባቱን የዳዊትን ከተማ ቅጥሮች እየጠገነ ነበር፡፡28ኢዮርብዓም ጽኑዕ ኃያል ሰው ነበር፡፡ ሰሎሞንም ይህን ተመልክቶ ወጣቱ ትጉህና ብርቱ ሠራተኛ በመሆኑ በዮሴፍ ነገድ ግዛት ላይ ሁሉ ኃላፊ አድርጎ ሾመው፡፡ 29በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ከኢየሩሳሌም ወጥቶ በጉዞ ላይ ሳለ፣ ሴሎናዊው ነቢዩ አኪያ በመንገድ ላይ አገኘው፡፡ አኪያም አዲስ መጎናጸፊያ ለብሶ ሁለት ሰዎች ለብቻ በሜዳ ላይ ነበሩ፡፡ 30አኪያም የለበሰውን አዲስ መጎናጸፊያ አውልቆ ከዐሥራ ሁለት ቆራረጠው፡፡31ኢዮርብዓምንም እንዲህ አለው፤ የእስራኤል አምላክ እግዚያብሔር እንዲህ ይላል፡- «ዐሥሩን ቁራጭ ለራስህ ውሰድ፤ ‹መንግሥትን ከሰለሞን ወስጄ ዐሥሩን ነገድ ለአንተ እሰጥሃለሁ፣ 32ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰለሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ፡፡ 33ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን አማልክትን፡- አስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፣ ካሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞአብ አምላክና ሞሎክ ተብሎ የሚጠራውን የአሞናውያን አምላክ ስላመለከ ነው፡፡ አባቱ ዳዊት እንዳደረገ በፊቴ ትክክል የሆነውን፣ ሕጎቼንና ትእዛዞቼንም አልጠበቀም፡፡34ይሁን እንጂ ከሰለሞን እጅ መንግሥትን በሙሉ አልወስድበትም፤ በዚህ ፈንታ በሕይወት እስካለም ድረስ በሥልጣን ላይ እንዲቆይ አደርገዋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ለመረጥኩትና ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ለፈፀመው ለአገልጋዬ ለዳዊት ስል ነው፡፡ 35ነገር ግን መንግሥትን ከሰለሞን ልጅ ወስጄ ለአንተ ዐሥሩን ነገዶች እሰጥሃለው፡፡ 36ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለው፡፡37ኢዮርብዓም ሆይ! እኔ አንተን የእስራኤል ንጉሥ አድርጌሃለሁ፤ አንተ በወደድከው ግዛት ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ፡፡ 38አገልጋዬ ዳዊት እንዳደረገው በፍፁም ልብህ ብትታዘዘኝ፣ በሕጎቼና በትእዛዞቼ ጸንተህ ብትኖር፣ በእኔ ፊት ሞገስ ብታገኝ፣ እኔ ዘወትር ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥም አደርግሃለሁ፤ ለዳዊት ባደረግሁት ዓይነት ዘሮችህ ከአንተ በኋላ እንደሚነግሡ አረጋግጥልሃለሁ፡፡ 39በሰለሞን ኃጢአት ምክንያት የዳዊትን ትውልዶች እቀጣለሁ፤ ነገር ግን የምቀጣቸው ለዘላለም አይደለም፡፡40ከዚህም የተነሣ ሰለሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ሞከረ፡፡ ነገር ግን ኢዮርብዓም ወደ ግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ በመኮበለል አመለጠ፤ ሰለሞን እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቆየ፡፡41ሰለሞን ያደረገው ሌላው ነገር፣ ያከናወነው ተግባርና ጥበቡ ሁሉ በሰለሞን የታሪክ መጽሐፍ የተመዘገበ አይደለምን? 42ሰለሞንም በኢየሩሳሌም በመላው እስራኤል ላይ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር፡፡ 43ከዚህ በኋላ ሰለሞን ሞተ፣ በአባቱ በዳዊት ከተማም ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በአባቱ በሰለሞን ተተክቶ ነገሠ፡፡
1ሮብዓምም ወደ ሴኬም ሄደ፤ ምክንያቱም እስራኤል ሁሉ እርሱን ለማንገሥ ወደ ሴኬም መጥተው ነበር፡፡ 2ከንጉሡ ሰሎሞን በመሸሽ ወደ ግብጽ ኮብልሎ በዚያው በግብጽ ይኖር የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን ወሬ በሰማ ጊዜ ተመልሶ መጣ፡፡3ስለዚህ የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ወደ እርሱ ልከው ጠሩት፤ ወደ ሮብዓም ቀርበው እንዲህ አሉት፡- 4አባትህ ሰሎሞን በእኛ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር አክብዶብን ነበር፡፡ አሁን አባትህ የጫነብንን ከባድ የሥራ ሸክም አቃልልን፣ ለአንተም እንገዛልሃለን አሉት፡፡ 5ሮብዓምም ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ አላቸው፤ ስለዚህ ሕዝቡ ሄዱ፡፡6ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የአባቱን የሰሎሞን ዘመን አማካሪዎች የነበሩትን ሽማግሌዎች በአንድነት ሰብስቦ እንግዲህ ለዚህ ሕዝብ መልስ መስጠት እንድችል ምን ትመክሩኛላችሁ? ሲል ጠየቃቸው፡፡ 7ሽማግሌዎቹም ዛሬ ለእነዚህ ሰዎች ታዛዥ ሆነህ ብታገለግላቸው ለጥያቄአቸውም ተስማሚ የሆነ መልስ ብተሰጣቸው እነርሱም ዘወትር በታማኝነት ያገለግሉሃል ሲሉ መለሱለት፡፡8ነገር ግን ሮብዓም የሽማግሌዎቹን ምክር ቸል በማለት አብሮ አደጎቹ ወደነበሩት አሁን ደግሞ አማካሪዎቹ ወደሆኑት ወጣቶች ሄደ፡፡ 9የአገዛዝ ቀንበር እንዳቀልላቸው ለጠየቁኝ ምን መልስ እንደምሰጣቸው ምን ትመክሩኛላችሁ? ሲል ጠየቃቸው፡፡10እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ አንተ የምተሰጣቸው መልስ ይህ ነው፤ የእኔ ታናሽ ጣት ከአባቴ ወገብ ይበልጥ ትወፍራለች! 11አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፣ እኔ ደግሞ የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፣ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን በሚናደፍ ጊንጥ እገርፋችኋለሁ!12ከሦስት ቀን በኋላ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ ንጉሡ በሰጣቸው ቀጠሮ መሠረት ተመልሰው ወደ ሮብዓም መጡ፡፡ 13ንጉሥ ሮብዓምም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ትቶ ሕዝቡን በማመናጨቅ መልስ ሰጣቸው፡፡ 14ወጣቶቹ በሰጡት ምክር መሠረት አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ! ሲል መለሰላቸው፡፡15ይህም ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። ነጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን አሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት እግዚአብሔር ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው፡፡16ሕዝቡ ንጉሥ ሮብዓም ጥያቄውን እንዳልተቀበለው በተገነዘበ ጊዜ ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን? የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደየቤትህ ሂድ! ዳዊት ሆይ፣ የራስህን ቤት ጠብቅ ብለው መለሱለት፡፡ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ወደየቤቱ ሄደ፡፡ 17ሮብዓምም በይሁዳ ግዛት በሚኖሩት ሕዝብ ላይ ብቻ ነገሠ፡፡18ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሮብዓም የግዳጅ ሥራ ኃላፊ የነበረውን አዶኒራምን ወደ እስራኤላውያን እንዲሄድ ላከው፤ እነርሱ ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህ ጊዜ ሮብዓም በፍጥነት ወደ ሠረገላው ገብቶ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ አመለጠ፡፡ 19ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ሰሜናዊው ክፍል እስራኤል በሚል በዳዊት ሥርወ መንግሥት ላይ ዐመፀ፡፡20እስራኤልም ሁሉ ኢዮርብዓም ከግብጽ ተመልሶ መምጣቱን በመገንዘብ ወደ ጉባዔያቸው ጠርተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፤ ለዳዊት ትውልዶች ታማኝ ሆኖ የቀረው የይሁዳ ነገድ ብቻ ነበር፡፡21ሮብዓም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከይሁዳና ከብንያም ነገዶች ተውጣጥተው የተመለሱ አንድ መቶ ሰማኒያ ምርጥ ወታደሮች ጠርቶ በአንድነት ሰበሰበ፤ ይህም የእስራኤልን ነገዶች ለመዋጋትና እንደገና መንግሥትን ወደ ሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ለመመለስ ነበር፡፡22ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሳማያ እንዲህ ሲል መጣ፡፡ 23ለሮብዓምና ለመላው የይሁዳና የብንያም ነገዶች ለቀሩትም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ በል፡- 24ከወንድሞቻችሁ ከእስራኤላውያን ጋር በመዋጋት አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነው በእኔ ፈቃድ ነው ብሎ አዘዘው፡፡ እነርሱም ለእግዚብሔር ቃል በመታዘዝ ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡25ኢዮርብዓምም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኘውን ሴኬምን ከተማ አድርጎ ሠርቶ ኖረባት፡፡ ከዚያም ተነሥቶ የጵንኤልን ከተማ ሠራ፡፡ 26ኢዮርብዓምም አሁን መንግሥቱ ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል ብሎ በልቡ አሰበ፡፡ 27ይህ የእስራኤል ሕዝብ ወደ ኢየሩሳሌም እየሄደ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መስዋዕት የሚያቀርብ ከሆነ፣ የሕዝቡ ልብ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ጌታቸው ወደ ሮብዓም ይመለሳል፡፡ ከዚያ እኔን ይገሉኛል፤ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓምም ይመለሳሉ፡፡28ስለዚህ ሮብዓም በጉዳዩ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆች ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ ከዚህ በፊት እንደምታደርጉት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ አድካሚ ነው፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፡- ከግብጽ ምድር ያወጣችሁ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው! አለ፡፡ 29ከዚህ በኋላ ከወርቅ የተሠሩት ሁለት የኮርማ ምስሎች አንዱን በቤቴል ሁለተኛውንም በዳን አቆመ፡፡ 30ስለዚህ ይህ ድርጊት ኃጢአት ሆነ፡፡ ሰዎቹም እስከ ዳን ድረስ በጣዖቱ ፊት ተሰልፈው ሄዱ፡፡31ኢዮርብዓምም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተ ሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ፡፡ 32ኢዮርብዓም በይሁዳ በሚደረገው በዓል ዓይነት ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን የባዕድ አምልኮ በዓል እንዲደረግ ወሰነ፤ ከወርቅ ላሠራውም ምስሎች በቤቴል በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለጥጃ ምሰሉ መሥዋዕት አቀረበ፤ በዚህም በቤተል ለማምለኪያ ባሠራቸው ስፍራዎች የሚያገለግሉ ካህናትን መደበ፡፡33ኢዮርብዓምም በዓል እንዲሆን እርሱ ራሱ በወሰነው ስምንተኛ ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ወደ ቤቴል ሄደ፡፡ በዚያ የእስራኤል ሕዝብ በዓል እንዲያከብር መስዋዕት አዘጋጅቶ ዕጣን ለማጠን ወደ መሠዊያው ሄደ፡፡
1የእግዚአብሔርን ቃል ይዞ አንድ ነብይ ከይሁዳ ወደ ቤቴል ደረሰ፤ ኢዮርብዓም ዕጣን ለማጠን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡ 2ነቢዩም እንዲህ ሲል በጩኸት የትንቢት ቃል ተናገረበት፡- «መሠዊያ! መሠዊያ ሆይ! እግዚአብሔር ስለ አንተ የሚለው ቃል ይህ ነው፡- ‹እነሆ ከዳዊት ቤተ ሰብ ኢዮአስ ተብሎ የሚጠራ ልጅ ይወለዳል፤ እርሱም በኮረብታ ላይ ለተሠራው ለአህዛብ መሠዊያ አገልጋዮች ሆነው መሥዋዕት የሚያቀርቡትን ካህናት በአንተው ላይ ያርዳቸዋል፤ የሰዎችንም አጥንት በአንተ ላይ ያቃጥላል፡፡ 3በዚያው ቀን ነቢዩ ምልክት ሰጠ፤ ይህ መሠዊያ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ በእርሱም ላይ ያለው አመድ ይበተናል፤ ይህንንም የትንቢት ቃል በእኔ አማካኝነት የተናገረው ራሱ እግዚአብሔር ለመሆኑ ምልክት ይሆናል›» አለው፡፡4ንጉሥ ኢዮርብዓምም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት ያዙት የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲውኑ ድርቅ ብሎ ቀረ፤ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም፡፡ 5የእግዚአብሔርም ነቢይ በእግዚአብሔር ስም በተናገረው የትንቢት ቃል መሠረት የተሰጠው ምልክት ተፈጸመ፤ መሠዊያው ወዲያውኑ ተሰባብሮ ወደቀ፤ አመዱም መሬት ላይ ፈሰሰ፡፡6ንጉሡ ኢዮርብዓምም፣ እባክህ እጄ እንዲመለስልኝ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልኝ ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው፡፡ የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች፡፡ እንደ ቀድሞም ሆነች፡፡ 7ከዚህ በኋላ ንጉሡ ነቢዩን ና ከእኔ ጋር አብረህ ወደ ቤቴ ግባ፤ እህልም ቅመስ፤ ስጦታ እሰጥሃለሁ አለው፡፡8የእግዚአብሔር ነቢይ ግን የሀብትህን እኩሌታ ብትሰጠኝ እንኳ ወደ ቤትህ ከአንተ ጋር አልሄድም፤ እህል ውሃም እዚህ ቦታ አልቀምስም አለ፡፡ 9ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳልቀምስና ወደ ቤቴ ስመለስም በመጣሁበት መንገድ እንኳ እንልሄድ እግዚአብሔር አዞኛል ሲል መለሰለት፡፡ 10ስለዚህ ወደ ቤቴል የመጣበትን መንገድ በመተው በሌላ መንገድ ተመልሶ ሄደ፡፡11በዚያን ጊዜ በቤቴል የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነቢይ ነበር፡፡ ወንዶች ልጆቹ ወደ እርሱ ቀርበው፣ ከይሁዳ የመጣው ነቢይ በቤቴል ስላደረገውና በንጉሥ ኢዮርብዓምም ላይ ስለ ተናገረው ቃል ሁሉ አወሩለት፡፡ 12አባታቸውም ታዲያ ያ የእግዚአብሔር ነቢይ ከዚያ ተነሥቶ በየትኛው መንገድ ሄደ? ሲል ጠየቃቸው፤ እነርሱም የሄደበትን መንገድ በማመልከት አሳዩት፤ 13ከዚህም በኋላ እርሱ አህያዬን ጫኑልኝ አላቸው፤ ልጆቹም አህያውን ጭነውለት፣ ሽማግሌው ነቢይ በአህያው ላይ ተቀምጦ፣14ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው፡፡ ሽማግሌውም ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ነቢይ አንተ ነሀን? ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም አዎን እኔ ነኝ ሲል መለሰለት፡፡ 15ሽማግሌውም ወደ ቤቴ ገብተህ ከእኔ ጋር እህል ብላ አለው፡፡ 16ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ ግን ከአንተ ጋር አብሬ ወደ ቤትህ መሄድም ሆነ በዚህ ቦታ ከአንተ ጋር ምንም ዓይነት እህል ውሃ መቅመስ አልችልም ሲል መለሰለት፡፡ 17በዚህ ቦታ ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳልቀምስ፣ በመጣሁበት መንገድ እንኳ ተመልሼ እንዳልሄድ እግዚአብሔር አዞኛል አለው፡፡18ከዚህ በኋላ ከቤቴል የመጣው ሽማግሌው ነቢይ፣ እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል አለው፡፡ ነገር ግን ሽማግሌው ነቢይ የተናገረው በውሸት ነበር፡፡ 19ስለዚህ ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ ከሽማግሌው ነቢይ ጋር አብሮት ወደ ቤቱ ሄደ፤ ከእርሱም ጋር ተመገበ፡፡20በገበታም ቀርበው ሳሉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሽማግሌው ነቢይ መጣ፡፡ 21ከይሁዳ ለመጣው የእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃል አልታዘዝክም፡፡ 22ይህን በማድረግ ፈንታ እኔ በዚያ ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳትቀምስ ወዳዘዝኩህ ወዳዚያ ቦታ ተመልሰህ በላህ፤ ይህንንም በማድረግህ ምክንያት ትገደላለህ፤ ሬሳህም በቤተ ሰብህ መቃብር አይቀበርም፡፡23ከተመገቡም በኋላ ሽማግሌው ነቢይ ከይሁዳ መልሶ ላመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ አህያውን ጫነለት፤ 24እርሱም በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ በመንገድም አንበሳ አገኘውና ገደለው፤ ሬሳውም በመንገድ ላይ ተጋደመ፤ አህያውና አንበሳውም በሬሳው አጠገብ ቆመው ነበር፡፡ 25ሰዎች በዚያ በኩል ሲያልፉ አጠገቡ ከቆመው አንበሳ ጋር ሬሳው በመንገድ ላይ ተጋድሞ አዩ፣ ሽማግሌው ነቢይ ወደሚኖርበት ወደ ቤቴል ከተማ መጥተውም አወሩለት፡፡26ሽማግሌው ነቢይ ይህን በሰማ ጊዜ፣ ያ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ያልጠበቀው ነቢይ ነው፤ ስለዚህም እግዚአብሔር እንደ ተናገረው አንበሳ ቦጫጭቆ እንዲገለው አሳልፎ ሰጥቶታል ማለት ነው አለ፡፡ 27ከዚህም በኋላ ልጆቹን አህያዬን ጫኑልኝ አላቸው፤ እነርሱም ጫኑለት፡፡ 28በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ በነቢዩ ሬሳ አጠገብ አህያውና አንበሳው እስካሁን እንደ ቆሙ በመንገድ ላይ ተጋድሞ አገኘው፡፡ አንበሳውም የነቢዩን ሬሳ አልበላም፤ በአህያውም ላይ አደጋ አላደረሰበትም ነበር፡፡29ሽማግሌው ነቢይ ሬሳውን አንሥቶ በአህያው ላይ ጫነው፤ እንዲለቀስለትና እንዲቀበር ወደ ቤቴል መልሶ ወሰደው፡፡ 30ሽማግሌውም ነቢይ በገዛ ራሱ ቤተ ሰብ መቃብር ቀበረው፤ እነርሱም ወንድሜ ሆይ ወንድሜ ሆይ እያሉ አለቀሱለት፡፡31ከቀብሩም ሥነ ሥርዓት በኋላ ሽማግሌው ነቢይ ለልጆቹ እንዲህ አላቸው፤ እኔ ስሞት በዚህ መቃብር ቅበሩኝ፤ ሬሳዬንም ከእርሱ ሬሳ አጠገብ አጋድሙት፡፡ 32በቤቴል በሚገኘው መሠዊያ ላይና በሰማርያ ታናናሽ ከተሞች በየኮረብታው ባሉት የማምለኪያ ስፍራዎች ላይ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይህ የእግዚአብሔር ነቢይ የተናገረው የትንቢት ቃል በእርግጥ ይፈጸማል፡፡33ይህም ሁሉ ሆኖ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ከሚያደርገው ክፉ ነገር ሁሉ አልተመለሰም፤ ይልቁንም እርሱ በሠራቸው መሠዊያዎች የሚያገለግለውን ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ይሾመው ነበር፡፡ 34ይህም ኃጢአቱ ለቤተ ሰቡ መጥፋትና ከምድር ገጽ ለመደምሰሱ ምክንያት ሆነ፡፡
1በዚያን ጊዜ የንጉሥ ኢዮርብዓም ወንድ ልጅ አቢያ በጠና ታሞ ነበር፡፡ 2ስለዚህ ኢዮርብዓም ሚስቱን እንዲህ አላት፡- የእኔ ሚስት መሆንሽን ማንም እንዳያውቅ ልብስሽን ለውጠሽ ሌላ ሴት በመምሰል እኔ የእስራኤል ንጉሥ እንደምሆን የትንቢት ቃል የተናገረው ነቢይ አኪያ ወደሚኖርባት ወደ ሴሎ ሂጂ፡፡ 3ዐሥር እንጀራ፣ ጥቂት ሙልሙል ዳቦና አንድ ገንቦ ማር ውሰጂለት፤ ስለ ልጁ ሁኔታ እርሱ ይነግርሻል፡፡4ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ይህን ሁሉ አዘጋጅታ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አኪያ ቤት ሄደች፡፡ ነቢዩ አኪያም በዕድሜው ከመሸምገሉ የተነሣ ዓይኖቹ ፈዘው ስለነበር ለማየት አልቻለም፡፡ 5እግዘዚአብሔር ለአኪያ እንዲህ አለው፡- የኢዮርብዓም ሚስት ስለታመመው ልጅዋ ልትጠይቅህ እየመጣች ነው፡፡ የኢዮርብዓም ሚስት እዚያ በደረሰች ጊዜ ሌላ ሴት ለመምሰል ስለምትሞክር ይህንኑ ተናገራት፡፡6ነገር ግን ነቢዩ አኪያ ወደ በሩ ስትቀርብ የኮቴን ድምፅ ሰምቶ እንዲህ አላት፤ ግቢ፣ የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን አውቃለሁ፤ ሌላ ሴት ለመምሰል ስለምን ሞከርሽ? ለአንቺ እነግርሽ ዘንድ የታዘዝኩት አሳዛኝ ዜና አለ፡፡ 7ወደ ኢዮርብዓም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለውን ንገሪው፤ ቃሉም ይህ ነው፤ ‹ከሕዝብ መካከል መርጬ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግሁህ፡፡ 8መንግሥትንም ከዳዊት ትውልድ ወስጄ ለአንተ ሰጠሁህ፤ ነገር ግን አንተ ታማኝ ሆኖ ትእዛዜን እንደጠበቀውና እኔ ደስ የምሰኝበትን እንዳደረገ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ሆነህ አልተገኘህም፡፡9ይልቁንም ከአንተ በፊት መሪዎች ከነበሩ ሰዎች የከፋ ኃጢአት ሠራህ፤ እኔንም ትተህ ጣዖቶችንና ከብረት የተሠሩ ምስሎችን ለማምለክ በመነሣትህ ቁጣዬን አነሣሥተሃል፡፡ 10በዚህ ምክንያት እነሆ፣ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ ከቤቱም ነፃም ሆነ ባርያ ወንድ ልጅን ሁሉ ከእስራኤል አጠፋለሁ፤ ፋንድያን አቃጥለው እንደሚጨርሱት የኢዮርብዓምን ቤት አወድማለሁ፡፡11በከተማ የሚሞተውን ማንኛውንም የቤተ ሰብህን አባል ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞቱንም የሰማይ አሞራ ይበላቸዋል፤ ይህን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡” 12አኪያም የሚናገረውን የትንቢት ቃል በመቀጠል ለኢዮርብዓም ሚስት እንዲህ አላት፣ እንግዲህ አሁን ወደ ቤትሽ ተመልሰሽ ሂጂ፤ ወደ ከተማም እግሮችሽ እንደረገጡ ወዲያውኑ ልጁ ይሞታል፡፡ 13እስራኤላውያንም ሁሉ አዝነውና አልቅሰው ይቀብሩታል፡፡ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተደሰተበት ልጅ እርሱ ብቻ ስለሆነ ከኢዮርብዓም ቤተ ሰብ ሥርዓተ ቀብር በሚገባ የሚፈፀምለት እርሱ ብቻ ይሆናል፡፡14እግዚአብሔርም በዚያን ቀን የኢዮርብዓምን ቤት የሚያጠፋ ንጉሥ ያስነሣል፡፡ ይኸውም አሁን ነው፡፡ 15እግዚአብሔር እስራኤልን ይቀጣል፤ እርሱም በውሃ ውስጥ እንደሚወዛወዝ ሸንበቆ ይወዛወዛል፡፡ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ጣዖት በመሥራት እግዚአብሔርን ስላስቆጡት፣ የእስራኤልን ሕዝብ ቀድሞ ለአባቶቻቸው ከሰጣቸው መልካም ምድር ይነቅላል፤ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ እንዲበታተኑም ያደርጋል፡፡ 16ኢዮርብዓም ኃጢአት ከመሥራቱ የተነሣና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት ስለመራ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ይተዋል፡፡»17ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ተነሥታ ወደ ቲርሳ ተመልሳ ሄደች፡፡ ወደ ቤትዋ ደጃፍ አንደ ደረሰች ወዲያውኑ ልጁ ሞተ፡፡ 18እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ አኪያ በኩል በነገረው መሠረት እስራኤላውያን በሐዘን አልቅሰው ቀበሩት፡፡19ንጉሥ ኢዮርብዓም ያደረጋቸው ሌሎች ነገሮች ሁሉ፣ የተዋጋቸው ጦርነቶችና አገዛዙም እንዴት እንደ ነበር ሁሉም ነገር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 20ኢዮርብዓም ለሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ ከአባቶቹም ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ናዳብ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡21የሰለሞን ልጅ ሮብዓም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ አንድ ዓመቱ ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔር ከመላው የእስራኤል ነገዶች ለስሙ መጠሪያ እንድትሆን በመረጣት ከተማ በኢየሩሳሌም መኖሪያውን አድርጎ ዐሥራ ሰባት ዓመት ገዛ፡፡ የሮብዓምም እናት አሞናዊት ስትሆን፣ ስምዋም ናዕማ ነበር፡፡ 22የይሁዳ ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው ሲያደርጉት ከነበረው ይበልጥ ክፉ ነገር በማድረጋቸው የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡት፡፡23ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፍ ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርፆችና የኤሼራን ምስሎች አቆሙ፡፡ 24ከእነዚህም ሁሉ የከፋ በእነዚያ ሕዝቦች የማምለኪያ ስፍራዎች የቤተ ጣዖት አመንዝራዎች ነበሩ፡፡ አሕዛብ ይፈፅሙት የነበረውን እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ነቃቅሎ ያባረራቸውን አሳፋሪ ነገር ሁሉ ይፈፅሙ ነበር፡፡25ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፅ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለ፡፡ 26በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ተከማችቶ የነበረውንም ሀብት ሁሉ፣ ሰለሞን ከወርቅ ያሠራቸውን ጋሻዎች ጭምር ዘርፎ ወሰደ፡፡27እነርሱንም ለመተካት ንጉሥ ሮብዓም ጋሻዎችን ከነሐስ አሠርቶ የቤተ መንግሥቱን ቅጥር በር በሚጠብቁ አለቆች እንዲጠበቁ አደረገ፡፡ 28ንጉሡ ወደ ቤተ መቅደሱ በመጣ ቁጥር፣ የቤተ መቅደሱ ዘበኞች ጋሻዎችን አንግበው ይቀበሉታል፤ ከሄደም በኋላ ጋሻዎቹን መልሰው ዘበኞች በሚጠበቁበት ማከማቻ ያኖሩ ነበር፡፡29ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 30በዚህም ዘመን ሁሉ ሮብዓምና ኢዮርብዓም እርስ በርሳቸው በማያቋርጥ ጦርነት ላይ ነበሩ፡፡ 31ሮብዓም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታቱ መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡ ልጁም አቢያ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ነገሠ፡፡
1ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት አቢያ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ 2እርሱም በኢየሩሳሌም ሦስት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱ ስም ማዕካ ሲሆን፣ እርስዋም የአቤሴሎም ልጅ ነበረች፡፡ 3አቢያም እንደ ቀደሙት አባቶቹና እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ ፍፁም ታማኝ ሆኖ አልተገኘም፡፡ አባቱ ሮብዓም ይፈፅመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራት ቀጠለ፡፡4የሆነ ሆኖ ከእርሱ በኋላ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥና ኢየሩሳሌምንም እንዲያጠናክር አምላኩ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ለአቢያ አንድ ወንድ ልጅ ሰጠው፡፡ 5እግዚአብሔር ይህንን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሂታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር በእግዚአብሔር ፊት በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ትክክለኛ ነገር አድርጎአል፤ ከትእዛዙም ፈቀቅ አላለም፡፡ 6በሮብዓምና ኢዮርብዓም ዘመን ተጀምሮ የነበረው ጦርነት፣ በአቢያ ዘመነ መንግሥትም ነበር፡፡7አቢያ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 8አቢያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ልጁ አሳ ተተክቶ ነገሠ፡፡9ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ በነገሠ በሃያኛው ዓመት አሳ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ 10እርሱም በኢየሩሳሌም አርባ አንድ ዓመት ገዛ፡፡ አያቱም ማዕካ ተብላ የምትጠራ የአቤሌሎም ልጅ ነበረች፡፡ 11አሳም አያቱ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኝ ነገር ሠራ፡፡12ንጉሥ አሳ የቤተ ጣዖት አመንዝራዎችን ሁሉ ከአገሩ አስወገደ፤ ከእርሱም በፊት የነበሩ ነገሥታት የሠሩአቸውን ጣዖታት ሁሉ ነቃቅሎ ጣለ፡፡ 13አያቱ ማዕካ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ አስጸያፊ ጣዖት ስለ ሠራች ከእቴጌነት ሽሮ ከቤተ መንግሥት አስወጣት፤ የሠራችውንም ጣዖት ሰባብሮ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ በእሳት አቃጠለው፡፡14አሳ በኮረብቶች ላይ የሚገኙ የአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎችን በሙሉ አላስወገደም፤ ይሁን እንጂ በዘመኑ ሁሉ የአሳ ልብ ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ፍጹም ነበር፡፡ 15አባቱ ለእግዚአብሔር ቤት የተለዩ እንዲሆኑ ያደረጋቸውንና እርሱም ራሱ የለያቸውን ወርቅና ብር አሠርቶ ንዋያተ ቅዱሳትን ሁሉ በቤተ መቅደስ አኖረ፡፡16የይሁዳ ንጉሥ አሳና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በሥልጣን በነበሩበት ዘመን ሁሉ የእርስ በርስ ጦርነት ነበር፡፡ 17የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ ማንም ሰው አሳ በሚገዛበት በይሁዳ ምድር እንዳይወጣና እንዳይገባ ለመከላከል ራማን ምሽግ አድርጎ መሥራት ጀመረ፡፡18ከዚያም ንጉሥ አሳ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ የተረፈውን ወርቅና ብር ሁሉ ወሰደ፡፡ እርሱም በአገልጋዮቹ እጅ በደማስቆ ከተማ ለነበረው የአዚን ልጅ የጣብሪሞን ልጅ ለሆነው ለሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ ስጦታ አድርጎ ላከለት፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፡- 19የእኔ አባትና የአንተ አባት ያደርጉት በነበረው ዓይነት በመካከላችን ቃል ኪዳን ይኑር፡፡ እነሆ ብርና ወርቅ ስጦታ እንዲሆንህ ልኬልሃለሁ፡፡ የእሰራኤል ንጉሥ ባኦስ እኔን እንዲለቀኝ ቀደም ሲል ከእርሱ ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳን አሁን እንድታቋርጥ ይሁን፡፡20ንጉሥ ቤን ሀዳድም አሳ ባቀረበው አሳብ ተስማምቶ የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን በመላከ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፡፡ እነርሱም ዒዮን፣ ዳን፣ አቤልቤተማሪካና የገሊላ ባሕር ተብለው የሚጠሩ ከተሞች በገሊላ ባሕር አጠገብ የሚገኘው አገርና የንፍታሌም ግዛት ሁሉ ናቸው፡፡ 21ንጉሥ ባኦስ የሆነውን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ የራማን ምሽግ መሠራት እንዲቆም አድርጎ ወደ ቲርጻ ሄደ፡፡ 22ከዚህም በኋላ ንጉሥ አሳ ባኦስ ራማን ለመመሸግ አከማችቶት የነበረውን ድንጋይና እንጨት ከዚያ ለማንሣት እንዲረዳው ሕዝቡ አንድም ሳይቀር እንዲመጣ ወደ ይሁዳ ግዛቶች ሁሉ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ንጉሥ አሳ ከዚያ የተገኘውን ድንጋይና እንጨት ሁሉ ወስዶ በምጽጳና በብንያም ግዛት ውስጥ የምትገኘውን የጌባዕን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራበት፡፡23ንጉሥ አሳ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራውና የሠራቸውም ከተሞች በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? ንጉሥ አሳ በዕድሜ በሸመገለ ጊዜ ከእግሩ ሕመም የተነሣ ሽባ ሆኖ ነበር፡፡ 24ንጉሥ አሳም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ በሚገኘው በነገሥታት መቃብር ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኢዮሣፍጥ ነገሠ፡፡25አሳ በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የአዮርብዓም ልጅ ናዳብ የእስረኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም ሁለት ዓመት ገዛ፡፡ 26ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት በመሥራት የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፡፡27የይሳኮር ነገድ የሆነው የአኪያ ልጅ ባኦስ ናዳብን ድል አድርጎ ገደለው፤ በዚያም ጊዜ ናዳብና ሠራዊቱ በፍልስጥኤም ግዛት የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ በመክበብ ላይ ነበሩ፡፡ 28ይህም የሆነው የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ነው፤ በዚህ ዓይነት ባኦስ በናዳብ ፈንታ ተተክቶ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡29ንጉሥ ባኦስ እንደነገሠ ወዲያውኑ የኢዮርብዓምን ቤተ ሰብ በሙሉ ገደለ፡፡ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በሴሎኣዊው በነቢዩ አኪያ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት የኢዮርብዓም ወገን በሙሉ ተገደሉ፡፡ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም፤ 30ይህም የሆነበት ምክንያት ኢዮርብዓም ራሱ በሠራው ኃጢአትና የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ ስላነሣሣ ነው፡፡31ናዳብ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 32የይሁዳ ንጉሥ አሳ እና የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በሥልጣን ዘመናቸው ሁሉ የእርስ በርስ ጦርነት ላይ ነበሩ፡፡33አሳ በይሁዳ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፡፡ እርሱም በቲርጻ ሃያ አራት ዓመት ገዛ፡፡ 34ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ባኦስ ኃጢአት በመሥራትና የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
1በሐናኒ ልጅ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት እግዚአብሔር ስለ ባኦስ የተናገረው ቃል እንዲህ ሲል መጣ፡- 2እኔ ግን ከትቢያ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ እንድትሆን ከፍ ከፍ አደረግሁህ፤ ታዲያ አንተ እንደ ኢዮርብዓም ኃጢአት ሠራህ፤ ሕዝቤንም ወደ ኃጢአት መራህ፤ የኃጢአታቸውም ብዛት የእኔን ቁጣ አነሣሥቶአል፡፡3ስለዚህ ኢዮርብዓምን እንዳሰወገድኩ አንተንና ቤተ ሰብህንም አስወግዳለሁ፡፡ 4በከተማይቱ ውስጥ የሚሞተውን ማንኛውንም የባኦስ ቤተ ሰብ ውሾች ይበሉታል፤ በሜዳ ላይ የሚሞተውንም የሰማይ አሞራዎች ይበሉታል፡፡5ባኦስ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራዎቹም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 6ባኦስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቲርጻም ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኤላ ነገሠ፡፡7እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባኦስና በቤተ ሰቡ ላይ የትንቢት ቃል የተናገረው፣ ባኦስ በፈጸመው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ በማድረጉ ነበር፡፡ ባኦስ እግዚአብሔርን ያስቆጣውም ከእርሱ ፊት የነበረው ንጉሥ ባደረገው ዓይነት ስለ ሠራው ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን የኢዮርብዓምንም ቤተ ሰብ ሁሉ በመግደሉ ጭምር ነበር፡፡8አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ስድስተኛው ዓመት የባኦስ ልጅ ኤላ በእስራኤል መንገሥ ጀመረ፡፡ በቲርጻም ሁለት ዓመት ገዛ፡፡ 9የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኃላፊ የሆነ ዚምሪ ከጦር መኮንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፡፡ ኤላም በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር፡፡ 10በዚህ ጊዜ ዚምሪ ወደዚያ ቤት ገብቶ ኤላን ገደለው፤ እርሱም በኤላ ፈንታ የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ተተክቶ ነገሠ፡፡11ዘምሪም በዙፋን ላይ እንደተቀመጠ ወዲያውኑ የባኦስ ቤተ ሰብ አባላት የሆኑትን በሙሉ ገደለ፤ የባኦስ ዘመድና ወዳጅ የሆነውን ወንድ አንድ እንኳ ሳይቀር ሁሉንም በሞት ቀጣ፡፡ 12እግዚአብሔር ነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ በተናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባኦስን ቤተ ሰብ በሙሉ ፈጀ፡፡ 13ይህም የሆነበት ምክንያት ባኦስና ልጁ ኤላ ጣዖት በማምለካቸውና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራታቸው፣ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ በማነሣሣታቸው ነው፡፡14ኤላ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?15አሳ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት ዚምሪ በቲርጻ ለሰባት ቀኖች ብቻ በእስራኤል ላይ ነገሠ፡፡ በዚያን ጊዜ የአስራኤል ወታደሮች በፍልስጥኤም የምትገኘውን የገባቶንን ከተማ ከበው ነበር፡፡ 16ዘምሪ ዐምፆ ንጉሡን መግደሉን በሰሙ ጊዜ በዚያው እንዳሉ ወዲያውኑ የጦር አዛዥ የነበረውን ዖምሪን አነገሡ፡፡ 17ዖምሪና ወታደሮቹ የገባቶንን ከበባ አቆሙ፤ ከዚያም ገሥግሠው ሄደው ቲርጻን ከበቡ፡፡18ዘምሪ ከተማይቱ እንደተያዘች ባየ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ውስጠኛ ክፍል ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገብቶ በቤተ መንግሥቱ ላይ እሳት ለቀቀበት፤ እርሱም በእሳት ነበልባል ተቃጥሎ ሞተ፡፡ 19ይህ የሆነው እርሱ በሠራው ኃጢአትና እስራኤልንም ወደ ኃጢአት በመምራቱ ምክንያት ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ኢዮርብዓም እግዚአብሔርን ስላስቆጣው ነው፡፡ 20ዘምሪ የሠራው ሌላው ነገር ሁሉና ያደረገውም ሤራ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ የሚገኝ አይደለምን?21በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ከሁለት ተከፍለው ነበር፡፡ ከዚህም የተነሣ አንደኛው ክፍል ታምኒን ተብሎ የሚጠራውን የጎናትን ልጅ ለማንገሥ ሲፈልግ ሌላው ክፍል ደግም ዖምሪን ለመደገፍ ይፈልግ ነበር፡፡ 22ነገር ግን የዖምሪ ተከታዮች ከጎናት ልጅ ታምኒን ይልቅ ጠንካራ ነበሩ፡፡ ስለዚህም ታምኒን ተገደለ፤ ዖምሪም ንጉሥ ሆነ፡፡23በዚህ ዓይነት አሳ በይህዳ በነገሠ በሠላሳ አንደኛው ዓመት ዖምሪ በእስራኤል ላይ ነግሦ ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፡፡ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ዓመቶች የገዛውም መቀመጫውን በቲርጻ አድርጎ ነበር፡፡ 24ከዚያም በኋላ ሳምር ተብሎ ከሚጠራው ሰው የሰማርያ ኮረብታን በስድስት ሺህ ጥሬ ብር ገዛው፡፡ ዖምሪ በኮረብታው ላይ ከተማ ቆረቆረ፤ ከተማይቱንም ቀድሞ የኮረብታው ባለንብረት በሆነው በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ሰየማት፡፡25ዖምሪ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ነገሥታት ይበልጥ የከፋ ኅጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡ 26እርሱ በሠራው ኃጢአትና አስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራት ዋጋ ወደሌላው ጣዖት አምልኮ መምራቱ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ኢዮርብዓም የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ፡፡27ዖምሪ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉና ያከናወነውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 28ዖምሪም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አክዓብ ነገሠ፡፡29የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ነገሠ። የዖምሪ ልጅ አክዓብ በሰማርያ ሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ 30የዖምሪ ልጅ አክዓብ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ሁሉ የባሰ ክፉ ነገር በያህዌ ፊት አደረገ።31አክዓብ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኅጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቁጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም፡፡ 32በሰማርያ ለባዓል ቤተ መቅደስ አሠርቶ መሠዊያ ሠራለት፡፡ 33አሼራ ተብላ የምትጠራውንም የሴት አምላክ ምስል አቆመ፤ ከእርሱ በፊት ከነበሩትም የእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚያነሣሣ ኃጢአት ሠራ፡፡34በአክዓብ ዘመነ መንግሥት አኪኤል ተብሎ የሚጠራ የቤቴል ተወላጅ ኢያሪኮን መልሶ ሠራ፤ እግዚአብሔር በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት አኪኤል የኢያሪኮን የመሠረት ድንጋይ በሚያኖርበት ጊዜ በነዌም ልጅ በኢያሱ እንደ ተነገረው እንደ እግዚብሔር ቃል፣ የበኩር ልጁ አቢሮን ሞተበት፤ የቅጥርዋንም በሮች በሚሠራበት ጊዜ ታናሹ ልጁ ሠጉብ ሞተ፡፡
1በገለዓድ የምትገኘው ቴስቢያዊው ነቢዩ ኤልያስ ነጉሥ አክዓብን በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ አለው፡፡2የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ 3ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ፤ እዚያም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ኮራት ተብሎ በሚጠራው ሸለቆ ተሸሽግ፡፡ 4የምትጠጣውንም ውሃ ከዚያው ወንዝ ታገኛለህ፤ ቁራዎችም ምግብ እንዲያመጡልህ አዝዣለሁ፡፡5ኤልያስም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሄዶ በኮራት ሸለቆ ተቀመጠ፡፡ 6ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቁራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፡፡ 7ነገር ግን ዝናብ ጠፍቶ ድርቅ ከመሆኑ የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያ ወንዝ ደረቀ፡፡8የእግዚአብሔርም ኤልያስን እንዲህ አለው፡- 9እንግዲህ አሁን ከዚህ ተነሥተህ ሂድ፤ በሲዶና በምትገኘው በስራፕታ ከተማ ተቀመጥ፤ እነሆ በዚያ የምትኖር አንዲት መበለት እንድተመግብህ እዝዣለሁ አለው፡፡ 10ስለዚህ ኤልያስ ወደ ሰራፕታ ሄደ፤ ወደ ከተማይቱም ቅጥር በር በደረሰ ጊዜ አንዲት ባልዋ የሞተባት ሴት እንጨት ስተለቅም አይቶ እባክሽ የምጠጣው ውሃ አምጪልኝ አላት፡፡11ውሃም ልታመጣለት በመሄድ ላይ ሳለች ወዲያውኑ ጠርቶ እባክሽ በተጨማሪ ትንሽ እንጀራ አምጪልኝ አላት፡፡ 12እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፡- ምንም እንጀራ እንደሌለኝ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ በዱቄት ዕቃዬ ውስጥ ካለችው ከአንድ እፍኝ ዱቄትና በማሰሮዬ ውስጥ ካለችው ከጥቂት የወይራ ዘይት በቀር ምንም የለኝም፤ ወደዚህ የመጣሁት ትንሽ እንጨት ለቃቅሜ ቤቴ በመመለስ ይህችኑ ትንሽ ዱቄት ለእኔና ለልጄ ለመጋገር ነው፤ ይህችም የመጨረሻ ምግባችን ናት፤ ከዚያ በኋላ ይህችኑ በልተን እንሞታለን፡፡ 13ኤልያስም እንዲህ አላት፣ አይዞሽ አትጨነቂ፤ ሄደሽ ምግብሽን አዘጋጂ፤ አስቀድመሽ ግን ከዚች ካለችሽ ዱቄት ለእኔ ትንሽ እንጎቻ ጋግረሽ አምጪልኝ፤ የቀረውንም ለራስሽና ለልጅሽ ጋግሪው፡፡14የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- እኔ እግዚአብሔር ዝናብን እስከማወርድ ድረስ ዱቄቱ ከማስቀመጫው ዕቃ፣ ዘይቱም ከማሰሮው ከቶ አያልቅም ሲል ተናግሮአል፡፡ 15አርስዋም ሄዳ ኤልያስ እንደ ነገራት አደረገች፤ እርስዋ፣ ቤተ ሰብዋና ኤልያስ ለብዙ ቀን የሚሆን በቂ ምግብ አገኙ፡፡ 16እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፣ ዘይቱም ከማሰሮው አላለቀም፡፡17ከጥቂት ጊዜም በኋላ የዚያች ባልዋ የሞተባት ሴት ልጅ ታመመ፤ ሕመሙም እየባሰበት ስለ ሄደ በመጨረሻ ሞተ፡፡ 18እርስዋም ኤልያስን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፣ ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን? ስትል ጠየቀችው፡፡19ኤልያስም ልጅሽን ወደ እኔ አምጪው አላት፡፡ ልጁንም ከዕቅፍዋ ወስዶ እርሱ ወደሚኖርበት ሰገነት አውጥቶ በአልጋው ላይ አጋደመው፡፡ 20ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ስለምን በዚህች ባልዋ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርስዋ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጅዋ እንዲሞት አደረግህ ሲል ጸለየ፡፡ 21ከዚህ በኋላ ኤልያስ በልጁ ላይ ሦስት ጊዜ ተዘርሮ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ይህን ልጅ ከሞት አስነሣው ሲል ጸለየ፡፡22እግዚአብሔርም የኤልያስን ጸሎት ሰማ፤ የልጁም እስትንፋስ እንደገና ተመልሶለት ዳነ፡፡ 23ኤልያስም ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ ሰጣትና እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል! አላት፡፡ 24እርስዋም እነሆ አንተ የእግዚአብሔር ሰው መሆንህንና እግዚአብሔርም በአንተ አማካይነት የተናገረው እውነት መሆኑን አሁን ዐወቅሁ! ስትል መለሰችለት፡፡
1ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡- ሄደህ ራስህን ለንገሥ አከዓብ ግለጥለት እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ አለው፡፡ 2ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አከዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሃብ እጅግ ጸንቶ ነበር፡፡3ስለዚህ ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራው፤ አብድዩ እግዚአብሔርን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነበር፡፡ 4ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረበት ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ መግቦአቸው ነበር፡፡5አከዓብ አብድዩን ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፡፡ ምናልባት እንስሳትን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል አለው፡፡ 6እያንዳንዳቸው በአገሪቱ ወደየትኛው ክፍል ሄደው መፈለግ እንዳባቸው ከተስማሙ በኋላ አክዓብና አብድዩ ለየብቻቸው በሁለት አቅጣጫ ተሰማሩ፡፡7አብድዩ በሚሄድበት መንገድ ላይ ሳለ በድንገት ኤልያስን አገኘው፤ ኤልያስ መሆኑንም ስላወቀ በግንባሩ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ከነሣው በኋላ ጌታዬ ኤልያስ በእውነት አንተ ነህን? ሲል ጠየቀው፡፡ 8ኤልያስም አዎን እኔ ነኝ፤ እዚህ መሆኔን ሄደህ ለጌታህ ንገረው ሲል መለሰለት፡፡9አብድዩም እንዲህ አለው፤ ንጉሥ አክዓብ እኔን ባሪያህን ይገድለኝ ዘንድ በእጁ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ምን በደል ሠርቼ ነው? 10ንጉሡ አንተን ለማግኘት ፈልጎ በዓለም ላይ መልእክተኛ ያልላከበት አገር እንደሌለ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ የአንድ አገር መሪ አንተ በአገሩ ውስጥ አለመኖርህን ለንጉሥ አክዓብ በመሐላ እያረጋገጠለት ቆይቶአል፡፡ 11አሁን አንተ ግን ኤልያስ ተገኝቶአል ብለህ ለጌታህ ንገር ትለኛለህ፡፡12እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርህን ለአከዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ፡፡ 13ደግሞስ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ስታስገድል በነበረችበት ጊዜ አንድ መቶ የሚሆኑትን ነቢያት ከሁለት በመክፈል ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ እህልና ውሃ በማቅረብ ስመግባቸው መኖሬን አልሰማህምን?14ታዲያ፣ አሁን አንተ እዚህ መሆንህን ሄደህ ለንጉሥ አክአብ ንገር ትለኛለህን? ይህን ባደርግ ንጉሡ ይገድለኛል!» 15ኤልያስም «ዛሬ ለንጉሡ እንደምገለጥለት በማገለግለውና ሁሉን ቻይ በሆነው በእግዞአብሔር ስም ቃል እገባልሃለሁ!» ሲል መለሰለት፡፡16ከዚህ በኋላ አብድዩ ሄዶ ለንጉሥ አክዓብ ነገረው፤ አክዓብም ተነሥቶ ኤልያስን ለመገናኘት ሄደ፤ 17አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜም «በእስራኤል ላይ ይህን ችግር ያመጣህ አንተ እዚህ ነህን?» አለው፡፡18ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፡- «የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተ ሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም! 19ይልቅስ እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው አራት መቶ ሃምሳ የበዓል ነቢያትንና በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ የኤሼራ ነቢያትን በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፡፡»20ስለዚህም አክዓብ ለእስራኤላውያን ሁሉና ለነቢያት በሙሉ ጥሪ አድርጎ በቀርሜሎስ ተራራ እንዲሰበሰቡ አስደረገ፡፡ 21ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፡- «እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!» አላቸው፡፡ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም፡፡22ከዚህ በኋላ ኤልያስ እንዲህ አለ፡- «ከእግዚአብሔር ነቢያት የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፡፡ አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያት ግን እነሆ በዚህ አሉ፡፡ 23እንግዲህ ሁለት ኮርማዎችን አምጡና የባዓል ነቢያት አንዱን ወስደው ይረዱት፤ ሥጋውንም ቆራርጠው እንጨት በመረብረብ በዚያ ላይ ያኑሩት፤ ነገር ግን እሳት አያድርጉበት፡፡ እኔም ሁለተኛውን ኮርማ ወስጄ እንደዚሁ አደርጋለሁ፡፡ 24ከዚህ በኋላ የባዓል ነቢያት ወደ አምላካቸው ይጸልዩ፤ እኔም ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ እሳትን ወደ መሥዋዕቱ በመላክ መልስ የሚሰጥ እርሱ እውነተኛ አምላክ ይሁን፡፡ ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድረጎ ይህ መልካም ነው በማለት መልስ ሰጡ፡፡25ከዚህ በኋላ ኤልያስ የባዓልን ነቢያት እናንተ ብዙ ስለ ሆናችሁ በመጀመሪያ አንዱን ኮርማ መርጣቸሁ በማረድ ወደ አምላካችሁ ጸልዩ፤ ነገር ግን እንጨቱ ላይ እሳት አታደርጉበት አላቸው፡፡ 26እነርሱም የመጣላቸውን ኮርማ ወስደው በመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ፡፡ ባዓል ሆይ እባክህ ስማን! እያሉ ጮኹ፡፡ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እየዘፈኑ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም፡፡27እኩለ ቀን ሲሆን ኤልያስ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጸልዩ! እርሱ አምላክ አይደለም እንዴ? እርሱ በአሳብ ተውጦ ይሆናል! ወይም ራሱን ያዝናና ይሆናል! ወይም ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ይሆናል! ወይም ተኝቶ ያንቀላፋ ይሆናልና እንዲነቃ ቀስቅሱት! እያለ ያፌዝባቸው ጀመር፡፡ 28ስለዚህም ነቢያቱ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየጸለዩ በሥርዓታቸው መሠረት ደማቸው እስኪፈስ ድረስ በቢላዋና በጩቤ ሰውነታቸውን ያቆስሉ ነበር፡፡ 29እኩለ ቀን ካለፈም በኋላ የሠርክ መሥዋዕት እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ እየተራወጡ ይቀባጥሩ ነበር፤ ይሁን እንጂ ምንም መልስ አላገኙም፤ ድምፅም አልተሰማም፡፡30ከዚህ በኋላ ኤልያስ ሰዎቹን ወደ እኔ ቅረቡ አላቸው፤ ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ በማደስ ሠራው፡፡ 31እግዚአብሔር ከዚያ በፊት እስራኤል ብሎ ከሰየመው ከያዕቆብ ልጆች በዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን ወሰደ፡፡ 32እነዚህንም ድንጋዮች ረብርቦ በእግዚአብሔር ስም መሠዊያ ሠራ፡፡ በዙሪያውም ዐሥራ አራት ሊትር ውሃ የሚይዝ ጉድጓድ ማሰ፡፡33እንጨቱንም በመሠዊያው ላይ በመረብረብ ኮርማውን በብልት በብልቱ ቆራርጦ በእንጨቱ ላይ አኖረ፡፡ 34በአራት ጋን ውሃ ሞልታችሁ በመሥዋዕቱና በእንጨቱ ላይ አፍስሱት! አላቸው፡፡ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ አሁንም ጨምሩበት አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፡፡ 35ውሃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ፤ ጉድጓዱንም ሞላው፡፡36ከቀትር በኋላ የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ነቢዩ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀርቦ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንህን፣ እኔም እግዚአብሔር ሆይ፣ የአንተ አገልጋይ መሆኔን፣ እኔም ይህንን ሁሉ ያደረግኹት በቃልህ መሠረት መሆኑን አንተ ራስህ ግለጥ፡፡ 37አምላኬ ሆይ፣ ይህ ሕዝብ አንተ እውነተኛ አምላክ መሆንህንና ወደ አንተም ያቀረብከው አንተ ራስህ መሆንህን እንዲያውቅ እባክህ መልስ ስጠኝ፤ አምላክ ሆይ ስማኝ!38ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እሳትን ላከ፤ ያ እሳት መሥዋዕቱን፣ እንጨቱንና ድንጋዩን በላ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጉድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፡፡ 39ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ እግዚአብሔር አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው! አሉ፡፡ 40ኤልያስም የባዓል ነቢያትን ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ ሲል አዘዘ፡፡ ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው፡፡41ከዚህ በኋላ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን እንግዲህ ሄደህ እህልና ውሃ ቅመስ፤ እኔ አሁን የከባድ ዝናም ነጎድጓድ ድምፅ መቃረቡን እየሰማሁ ነው አለው፡፡ 42አክዓብ እህልና ውሃ ለመቅመስ ሲሄድም ኤልያስ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ እዚያም በሁለቱ ጉልበቶቹ መካከል ራሱን ወደ መሬት ደፋ፡፡43አገልጋዩን፣ ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት አለው፡፡ አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ ምንም ነገር አይታየኝም አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው፤ 44በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ አለው፡፡ ኤልያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ዝናቡ ሳያቆምህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ ብለህ ንገረው ሲል አዘዘው፡፡45ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ፤ ነፋሱም ነፈሰ፤ ብርቱ ዝናብም ይዘንብ ጀመረ፡፡ ነጉሥ አክዓብም በሠረገላው ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ 46የእግዚአብሔርም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድረጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር፡፡
1ኤልያስ ያደረገውን ሁሉና የባዓልንም ነቢያት በሙሉ እንዴት እንደ ገደላቸው ንጉሥ አክዓብ ለሚስቱ ለኤልዛቤል ነገራት፡፡ 2ስለዚህ እርስዋ በእነዚያ ነቢያት ላይ ያደረግኸውን እኔም ነገ ልክ በአሁኑ ሰዓት በአንተ ላይ ሳላደርግብህ ብቀር አማልክት በሞት ይቀሥፉኝ ስትል ወደ ኤልያስ የዛቻ መልእክት ላከች፡፡ 3ኤልያስም ስለ ፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአገልጋዩ ጋር በይሁዳ ወደምተገኘው ወደ ቤርሳቤህ ከተማ ሄደ፡፡ አገልጋዩንም በዚያ ተወው፤4ኤልያስ ራሱ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፡፡ ከዚህ በኋላ፣ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፣ ሞቱንም በመመኘት እግዚአብሔር ሆይ፣ አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ! ሲል ጸለየ፡፡ 5ከዚህ በኋላ በዛፉ ሥር ጋደም እንዳለ እንቅልፍ ወሰደው፤ በድንገትም አንድ መልአክ መጥቶ በመዳሰሰ ቀሰቀሰውና ተነሥተህ ብላ! አለው፡፡ 6ኤልያስ ተነሥቶ ዞሮ በተመለከተ ጊዜ በድንጋይ ሙቀት የበሰለ የዳቦ ሙልሙልና አንድ ገንቦ ውሃ በራስጌው ተቀምጦ አየ፤ ከበላና ከጠጣም በኋላ ተመልሶ እንደገና ተኛ፡፡7የእግዚአብሔርም መልአክ ተመልሶ መጥቶ የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ስለ ሆነ ተነሥተህ ብላ! ሲል ዳግመኛ ኤልያስን ቀሰቀሰው፡፡ 8ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፤ ውሃውንም ጠጣ፡፡ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኃይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ፡፡9እዚያም እንደ ደረሰ ወደ አንድ ዋሻ ገብቶ እዚያ ዐደረ፡፡ በድንገትም እግዚአብሔር፣ ኤልያስ ሆይ! እዚህ ምን ታደርጋለህ? ሲል ጠየቀው፡፡ 10ኤልያስም ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ! ሲል መለሰ፡፡11እግዚአብሔርም ኤልያስን ካለህበት ወጥተህ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም አለው፤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በአጠገቡ አለፈ፤ ብርቱ ነፋስም በፊቱ በመላክ ኮረብቶችን ሰነጣጠቀ፤ ዐለቶችንም ሰባበረ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፡፡ ነፋሱም ከቆመ በኋላ ምድሪቱ ተናወጠች፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም፡፡ 12ከምድሪቱም ነውጥ በኋላ እሳት መጣ፤ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፤ ከእሳቱም በኋላ የሹክሹክታ ድምፅ ተሰማ፡፡13ኤልያስ የሹክሹክታውን ድምፅ በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጎናጸፊያ ሸፈነ፤ ወጥቶም በዋሻው መግቢያ በር አጠገብ ቆመ፤ አንድ ድምፅም ኤልያስ ሆይ፣ እዚህ ምን ታደርጋለህ? ሲል ጠየቀው፡፡ 14ኤልያስም ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ፣ እኔ ለአምላኬ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔን እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ ሲል መለሰ፡፡15እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ በደማስቆ ከተማ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓ ተመልሰህ ሂድ፤ እዚያም በደረስህ ጊዜ አዛሄልን ቀብተህ በሶርያ ላይ አንግሠው፤ 16የናሜሲን ልጅ ኢዩንም ቀብተህ በእስራኤል ላይ አንግሠው፤ የአቤል ምሖላ ተወላጅ የሆነውን የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕንም ቀብተህ በአንተ ፈንታ ነቢይ እንዲሆን አድርገው፡፡17ከአዛሄል እጅ ከመገደል ተርፎ የሚያመልጠውን ማንኛውንም ሰው ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ እጅ የሚያመልጠውንም ኤልሳዕ ይገድለዋል፡፡ 18ይሁን እንጂ ለእኔ ታማኞች የሆኑ ለባዓል ያልሰገዱና ለምስሉም ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን በእስራኤል ምድር በሕይወት እንዲተርፉ አደርጋለሁ፡፡19ኤልያስም ከዚያ ከሄደ በኋላ የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ሁለት በሬዎች ጠምዶ ሲያርስ አገኘው፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ በአሥራ አንድ ጥማድ በሬዎች የሚያርሱ ደቦኞች ነበሩ፤ ኤልሳዕም በመጨረሻ አሥራ ሁለተኛውን ጥማድ ያርስ ነበር፤ ኤልያስም መጎናጸፊያውን አውልቆ በኤልሳዕ ላይ ደረበለት፡፡ 20በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ተቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ አባቴና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ አለው፡፡ ኤልያስም፣ እሺ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም! ሲል መለሰለት፡፡21ከዚህ በኋላ ኤልሳዕ ወደ ጥማድ በሬዎቹ ተመልሶ አረዳቸው፡፡ የተጠመዱበትንም ቀንበር በማንደድ ሥጋቸውን ቀቅሎ ለሰዎቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ፤ ከዚህ በኋላ ኤልያስን ተከትሎ በመሄድ ረዳቱ ሆነ፡፡
1የሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ መላ ሠራዊቱን በአንድነት ሰበሰበ፡፡ ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ያሉአቸው ሠላሳ ሁለት ነገሥታት ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ የእስራኤል ዋና ከተማ የሆነችውን ሰማርያ ጦርነት ገጠመ፡፡ 2እርሱም ሀዳድ በከተማይቱ ወደሚገኘው ወደ እስራኤል ነጉሥ ወደ አክዓብ፣ ቤን ሀዳድ እንዲህ ይላል ብሎ መልእክተኞችን ላከ፡- 3ብርህና ወርቅህ ውብ የሆኑት ሚስቶችህና ልጆችህ ምርጥ የሆኑ ሁሉ የእኔ ናቸው፡፡4የእስራል ንጉሥም ጌታዬ ንጉሥ አንተ እንዳልከው ይሁን ብሎ መለሰ፡፡ እኔ የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ናቸው አለ፡፡ 5ከጥቂት ጊዜም በኋላ እነዚያው መልእክተኞች ከንጉሥ ቤን ሀዳድ ሌላ ትእዘዝ ይዘው እንደገና ወደ አክዓብ መጡ፤ ትዕዛዙ እንዲህ የሚል ነበር፤ ብርህን፣ ሚስቶችህንና ልጆችህን ማስረክብ እንዳለብህ መልእክት ልኬብህ ነበር፡፡ 6አሁን ደግሞ ቤትህንና የአገልጋዮችህን ቤት ሁሉ ይበረብራሉ፡፡ በርብረውም በዓይናቸው ደስ ያላቸውን ንብረት ሁሉ ይዘው እንዲመጡ የጦር መኮንኖቼን ነገ በዚህ ጊዜ እልካለሁ፡፡ እነርሱም ነገ ጧት በዚሁ ሰዓት እዚያ ይደርሳሉ፡፡7የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ የአገሪቱን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ ይህ ሰው ምን ዓይነት ጠብ እንደሚፈልግ ተመልከቱ አለ፡፡ ከዚህ በፊት ሚስቶቼንና ልጆቼን፣ ብሬንና ወረቄን እንዳስረክበው ጠይቆኝ ተስማምቼ ነበር አላቸው፡፡ 8ሽማግሌዎቹና ሕዝቡም ሁሉ እርሱ ለሚልህ ነገር ሁሉ ግምት አትስጠው፤ ከፍላጎቱ ጋር አትስማማው አሉት፡፡9ስለዚህም አክዓብ ለቤን ሀዳድ መልእክተኞች ለጌታዬ ለንጉሡ ከዚህ በፊት ባቀረብክልኝ ጥያቄ ተስማምቼ ነበር፤ አሁን ባቀረብክልኝ በሁለተኛው ጥያቄ ግን ልስማማበት አልችልም ብሎአል ብላችሁ ንገሩት አላቸው፡፡ መልእክተኞቹም ተመልሰው በመሄድ መልሱን ነገሩት፤ 10ቤን ሀዳድም በሰማርያ ለእያንዳንዱ ወታደር አንዳንድ ጭብጥ ዐፈር ሊዳረስ እስከማይችል ድረስ ብዙ ወታደሮችን ባላሰልፍ አማልክት ይቅሠፉኝ ብሎ የዛቻ መልእክቱን መልሶ ላከበት፡፡11የእስራኤል ንጉሥ መልእክተኞቹን፣ በወታደር መኩራራት የሚገባው ከጦርነት ድል በኋላ እንጂ ከጦርነት በፊት አይደለም፣ ብላችሁ ለንጉሥ ቤን ሀዳድ ንገሩት ሲል መለሰላቸው፡፡ 12ቤን ሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎችም ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ሲጠጡ ሳሉ የአክዓበ መልእክት ደረሳቸው፤ በዚህን ጊዜ ቤን ሀዳድ ለጦርነት እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ ስለዚህም ፈጥነው በመንቀሳቀስ ከተማውን ለማጥቃት ቦታ ቦታቸውን ያዙ፡፡13በዚያን ጊዜ አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ይህንን ታላቅ ጦር አየህን? እነሆ እግዚአብሔር ዛሬ የቤን ሀዳድን ሠራዊት በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፡፡ አንተም ደግሞ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃለህ ይልሃል አለው፡፡ 14አክዓብም ግንባር ቀደም ሆኖ የሚዘምተው ማን ይሁን? ሲል ጠየቀ፡፡ ነቢዩም እግዚአብሔር በአውራጃ አስተዳዳሪዎች የሚታዘዙ ወጣት ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ይዝመቱ ይላል አለው፡፡ ንጉሡም ጦርነቱን ማን ይጀምር? ሲል ጠየቀ፡፡ ነቢዩም አንተ ራስህ ጀምር አለው፡፡ 15ስለዚህ ንጉሡ ብዛታቸው ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት ብቻ የሆነ በአውራጃ አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ ሥር የሆኑትን ወጣት ወታደሮችን ጠራ፡፡ ቀጥሎም ጠቅላላ ብዛቱ ሰባት ሺህ የሆነ የእስራኤልን ሠራዊት ጠራ፡፡16እነርሱም እኩለ ቀን ላይ ሄዱ፡፡ ቤን ሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞች የሆኑ ሠላሳ ሁለቱ ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ በመጠጥ ሰክረው ነበሩ፡፡ 17ወጣቶቹም ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ወደ ፊት አመሩ፡፡ ቤን ሀዳድ ልኮአቸው የነበሩትም ቃፊሮች አንድ የወታደር ቡድን ከሰማርያ ወጥቶ ወደዚህ እየመጣ መሆኑን ነገሩት፡፡18ቤን ሀዳድም ቃፊሮቹን፣ አመጣጣቸው ለጦርነትም ይሁን ለሰላም ይዛቸሁ አምጡልኝ ሲል አዘዘ፡፡ 19ስለዚህ በእስራኤል ሠራዊት ደጀንነት በአውራጃ አስተዳደሪዎች የሚታዘዙ ወጣቶቹ ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ወጡ፡፡20እያንዳንዱም ውጊያ የገጠመውን ጠላቱን ገደለ፡፡ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤላውያንም ያሳድዱአቸው ጀመር፡፡ ቤን ሀዳድ ግን በፈረሱ ላይ ተቀምጦ ከጥቂት ፈረሰኞች ጋር ሸሽቶ አመለጠ፡፡ 21ንጉሥ አክዓብም ወደ ጦሩ ሜዳ ገብቶ የጠላትን ፈረሶችና ሠረገሎችን ማረከ፡፡ በሶርያውያን ላይ ታላቅ ጥፋት በማድረስ ድል አደረጋቸው፡፡22ስለዚህ ነቢዩ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ፡- የሶርያ ንጉሥ በሚመጣው የጸደይ ወራት እንደገና አደጋ ስለሚጥልብህ ተመልሰህ ሂድና ሠራዊትህን በማጠናከር አደራጅ፤ ጥንቃቄ የሞላበትንም የጦርነት ስልት አዘጋጅ አለው፡፡ 23አገልጋዮቹም ንጉሥ ቤን ሀዳድን እንዲህ አሉት፡- የእስራኤል አማልክት የተራራ አማልክት ናቸው፡፡ እስራኤላውያን እኛን ማሸነፍ የቻሉት ስለዚህ ነው፡፡ በሜዳማ ስፍራዎች ጦርነት ብንገጥማቸው ግን እናሸንፋለን፡፡24ስለዚህ አሁን ሠላሳ ሁለቱን ነገሥታት ከጦር አዛዥነታቸው ሽረህ በእነርሱ ቦታ ሌሎችን የጦር አዛዦች ሹም፡፡ 25ከዚህ በፊት የተደመሰሰውን የሚያህል ብዙ ሠራዊትና በቀድሞዎቹ ልክ ፈረሶችንና ሠረገሎችን አደራጅ፤ ከዚያ በኋላ እስራኤላውያንን በሜዳ ተዋግተን ድል እንነሣቸዋለን፡፡ ስለዚህ ቤን ሀዳድም በእነርሱ ምክር ተስማምቶ ለመፈጸም ወሰነ፡፡26ከዚያም በተከታዩ የጸደይ ወቅት ሠራዊቱን በአንድነት ጠርቶ እስራኤልን ለመዋጋት ወደ አፌቅ ከተማ ገሠገሠ፡፡ 27እስራኤላውያን ተጠርተው ከሚያስፈልጋቸው ስንቅና ትጥቅ ጋር ለጦርነት ተዘጋጁ፤ እነርሱም ወደ ጦርነቱ በመዝመት በሁለት ቡድን ተከፍለው ከሶርያውያን ፊት ለፊት ባለው ቦታ ሰፈሩ፡፡ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር አገሩን ካጥለቀለቀው ከሶርያውያን ሠራዊት ብዛት ጋር ሲነጻጻር ከሁለት የተከፈለሉ የጥቂት ፍየሎች መንጋዎች ይመስሉ ነበር፡፡28አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ሶርያውያን፡- እግዚአብሔር የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ የሆነውን ሠaርዊታቸውን በእጅህ አሳልፌ እሰጣለሁ፡፡ አንተና ሕዝብህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ አለው፡፡29ስለዚህ ሶርያውያንና እስራኤላውያን ፊት ለፊት ተፋጠው በየጦር ሰፈራቸው እስከ ሰባት ቀን ቆዩ፤ በሰባተኛውም ቀን ጦርነት ጀምረው በዚያኑ ቀን እስራኤላውያን አንድ መቶ ሺህ የሶርያውያንን እግረኛ ጦር ወታደሮችን ገደሉ፡፡ 30ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቁጥራቸው ሃያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጥር ተንዶባቸው አለቁ፡፡ ቤን ሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ ገብቶ ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ፡፡31የቤን ሀዳድ አገልጋዮች ወደ እርሱ ቀርበው፣ የእስራኤል ነገሥታት ምሕረት አድራጊዎች መሆናቸውን ሰምተናል፤ ስለዚህ በወገባችን ማቅ ታጥቀን፣ በራሳችንም ገመድ ጠምጥመን ወደ እስራኤል ንጉሥ ሄደን ምሕረት እንድንጠይቀው ፍቀድልን፤ ምናልባትም ሕይወትህን ያተርፍ ይሆናል አሉት፡፡ 32ከዚህም በኋላ እነርሱ በወገባቸው ማቅ ታጥቀው በራሳቸውም ገመድ ጠምጥመው ወደ ንጉሥ አክዓብ በመሄድ አገልጋይህ ቤን ሀዳድ ምሕረት አድርገህ ሕይወቱን እንድታተርፍለት ይማጠንሃል አሉት፡፡ አክዓብም እርሱ እስከ አሁን በሕይወት አለ ማለት ነውን? ከሆነስ መልካም ነው፤ እንግዲህ እርሱ ለእኔ እንደ ወንድም ነው ሲል መለሰላቸው፡፡33የቤን ሀዳድ አገልጋዮችም የምሕረት መልእክት ይጠባበቄ ስለ ነበር አክዓብ ወንድሜ ሲል በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ቀበል አድገርው አንተ እንዳልከው ቤን ሀዳድ በእርግጥ ወንድምህ ነው አሉት፡፡ አክዓብም ወደ እኔ አምጡት! አላቸው፡፡ ቤን ሀዳድም በመጣ ጊዜ አክዓብ ወደ ሠረገላው ገብቶ እንዲቀመጥ ቤን ሀዳድን ጋበዘው፡፡ 34ቤን ሀዳድም አክዓብን አባቴ ከአባትህ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልስልሃለሁ፤ አባቴ በሰማርያ እንዳደረገው ሁሉ አንተም በደማስቆ ለራስህ የንግድ ማእከል ልታቋቁም ትችላለህ አለው፡፡ አክዓብም እንግዲያውስ በዚህ ስምምነት መሠረት እኔም በነጻ እለቅሃለሁ ሲል መለሰለት፡፡ አክዓብም በዚህ ዓይነት ከእርሱ ጋር የውል ስምምነት አድርጎ በነጻ እንዲሄድ ፈቀደለት፡፡35የነቢያት ወገን የሆነ አንድ ነቢይ በእግዚአብሔር ታዞ የእርሱ ጓደኛ የሆነውን ሌላ ነቢይ ምታኝ አለው፡፡ ነቢዩ ግን እርሱን ለመምታት እምቢ አለ፡፡ 36ስለዚህም ያ ነቢይ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም እምቢ ስላልክ ከእኔ ተለይተህ እንደ ሄድክ ወዲያውኑ አንበሳ ይገድልሃል አለው፤ ከእርሱ ተለይቶ እንደ ሄደ አንበሳ በድንገት ወደ እርሱ መጥቶ ገደለው፡፡37ከዚህም በኋላ ነቢዩ ወደ ሌላ ሰው ሄዶ ምታኝ አለው፣ ያም ሰው መትቶ አቆሰለው፤ 38ነቢዩ ማንነቱ እንዳይታወቅ ፊቱን በጨርቅ ሸፈነ፤ ሄዶም በዚያ በኩል የሚያልፈውን የእስራኤል ንጉሥ ለመጠበቅ በመንገድ ዳር ቆመ፡፡39ንጉሡም በአጠገቡ ሲያልፍ ነቢዩ ተጣርቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፡- ንጉሥ ሆይ እኔ በጦርነት ውስጥ በውጊያ ላይ ነበርኩ፤ በዚያን ጊዜም ከወታደሮቹ አንዱ ከጠላት ወገን አንድን ሰው ማርኮ በማምጣት ይህን ሰው ጠብቅ፣ ቢያመልጥ ግን በእርሱ ፈንታ አንተ ትገደላለህ ወይም ሠላሳ አንድ መክሊት የሚመዝን ብር መቀጫ ትከፍላለህ አለኝ፡፡ 40ነገር ግን እኔ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያ ወዲህ ስል ሰውየው አምልጦ ሄደ፡፡ ንጉሡም በራስህ ላይ ስለ ፈረድህ መቀጣት ይገባሃል አለው፡፡41ነቢዩ ፊቱ የተሸፈነበትን ጨርቅ ፈጥኖ አወለቀ፤ ንጉሡም ይህ ሰው ከነቢያት ወገን አንዱ መሆኑን ወዲያውኑ አወቀ፡፡ 42ነቢዩም ንጉሡን እንዲህ አለው፡- እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ እኔ ይገደል ብዬ የፈረድኩበት ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል፡፡ 43ስለዚህ ንጉሡ እያዘነና እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ወደ ሰማርያ ተመልሶ ሄደ፡፡
1ከጥቂት ጊዜ በኋላ ናቡቴ ተብሎ የሚጠራ ሰው በኢይዝራኤል በሚገኘው በንጉሥ አክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ የራሱ ርስት የሆነ አንድ የወይን ተክል ቦታ ነበረው፡፡ 2አንድ ቀን አክዓብ ናቡቴን የወይን ተክል ቦታህን ስጠኝ፤ በቤተ መንግሥቴ አጠገብ ስለ ሆነ የአትክልት ቦታ ላደርገው እፈልጋለሁ፤ በምትኩ ከእርሱ የተሻለ የወይን ተክል ቦታ እሰጥሃለሁ፤ ልትሸጠው ብትፈልግም የተሻለ ዋጋ እከፍልሃለሁ አለው፡፡3ናቡቴም ይህንን የወይን ተክል ቦታ የወረስኩት ከቅድም አያቶቼ ነው፤ ለአንተ ከመስጠትስ እግዚአብሔር ይጠብቀኝ! ሲል መለሰለት፡፡ 4አክዓብ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ ከአባቶቼ የወረስኩትን ለአንተ አልሰጥህም ስላለው በንዴት እየተበሳጨ ወደ ቤቱ ገባ፤ ፊቱንም ወደ ግድግዳ አዙሮ በአልጋው ላይ ተጋደመ፤ ምግብ መብላትም አልፈቀደም፡፡5ሚስቱም ኤልዛቤል ወደ እርሱ ቀርባ እንደዚህ ያበሳጨህ ነገር ምንድን ነው? ስለምንስ ምግብ አትበላም? ስትል ጠየቀችው፡፡ 6እርሱም እኔን ያበሳጨኝ ከናቡቴ ያገኘሁት መልስ ነው፤ ይኸውም የእርሱን የወይን ተክል ቦታ እንድገዛ ወይም ከፈለገ ልዋጩን እንድሰጠው ብጠይቀው የወይን ተክል ቦታውን አልሰጥህ ብሎ አናደደኝ ሲል መለሰላት፡፡ 7ኤልዛቤልም እንግዲህ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ሆነህ ሳለህ እንደዚህ መሆን ይገባሃልን? ይልቅስ ተነሥ ተደሰት፤ እህል ውሃም ቅመስ፡፡ እኔ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ እንድታገኝ አደርጋለሁ አለችው፡፡8ስለዚህ እርስዋ ደብዳቤ ጽፋና በአክዓብ ስም ፈርማ የእርሱን ማኅተም አተመችበት፤ ደብዳቤውንም ናቡቴ ወደሚኖርባት ወደ ኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎች ላከች፡፡ 9ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፡- የአንድ ቀን ጾም አውጁ፤ ሕዝቡንም በአንድነት ሰብስቡ፤ ለናቡቴም የክብር ቦታ ስጡት፤ 10እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው የሚናገሩ ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም አቅርቡ፤ ከዚያ በኋለ ናቡቴን ከከተማው ውጪ አወጥታችሁ በድንጋይ ተወግሮ ይሙት፡፡11ስለዚህ የኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎችም በደብዳቤው እንደተገለጸው ኤልዛቤል ያዘዘቻቸውን አደረጉ፡፡ 12የአንድ ቀን ጾም አወጁ፤ ሕዝቡንም በአንድነት ሰበሰቡ፤ ለናቡቴም የክብር ቦታ ሰጡት፡፡ 13ሁለቱም የሐሰት ምስክሮች ተነሥተው ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው በሕዝቡ ፊት በሐሰት መሰከሩበት፤ ስለዚህም ከከተማይቱ ውጪ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ 14ናቡቴ ተወግሮ ተገድሎአል የሚል መልእክትም ወደ ኤልዛቤል ላኩ፡፡15ኤልዛቤልም መልእክቱን እንደ ተቀበለች ወዲያውኑ አክዓብን ናቡቴ ሞቶአል፤ አሁን ተነሥተህ ሂድና ለአንተ ለመሸጥ እምቢ ያለውን የወይን ቦታ ርስት አድርገህ ውሰድ አለችው፡፡ 16አክዓብም የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ ለመውረስ ወዲያውኑ ተነሥቶ ሄደ፡፡17ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቴስቢያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡፡ 18ተነሥተህ ሂድና የእስራኤልን ንጉሥ አከዓብን በሰማርያ አግኘው፤ እርሱ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ ለመውረስ ሄዶአል፣ በዚያው ታገኘዋለህ፤19እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ መናገር አለብህ፣ ናቡቴን ገድለህ ሀብቱንም ወሰድክበትን? ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የናቡቴን ደም ውሾች በላሱበት ስፍራ የአንተንም ደም እንደዚሁ ይልሱታል። 20አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ ጠላቴ ሆይ አገኘኸኝን? አለው፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፣ አዎን አግኝቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ ለማድረግ ራስህን ሸጠከውን? አለው፡፡21ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፣ እነሆ በአንተ ላይ መቅሠፍትን አመጣብሃለሁ፤ አንተን ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ ከቤተ ሰብህም ውስጥ ወንድ የሆነውን ሁሉ ባሪያ ሆነ ነጻ ሰው አጠፋለሁ፡፡ 22እስራኤልን ወደ ኃጢአት በመምራታችሁ ቁጣዬን ስለ አነሣሣህ ቤተ ሰብህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ንጉሥ ኢዮርብዓም ቤተ ሰብና እንደ አኪያ ልጅ እንደ ንጉሥ ባኦስ ቤተ ሰብ ለጥፋት የተጋለጠ ይሆናል፡፡23ስለ ኤልዛቤልም እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- በኢይዝራኤል ከተማ ውስጥ ሬሳዋን ውሾች ይበሉታል፡፡ 24ከአክዓብም የሆነውን ሁሉ በከተማው ውስጥ የሚሞተውን ማንኛውንም ሰው ውሾች ይበሉታል፤ በገጠርም በየሜዳው የሚሞተውን ሁሉ የሰማይ አሞራዎች ይበሉታል፡፡25በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ ለኤልዛቤል ኃጢአት ራሱን አሳልፎ የሸጠ አክዓብን የሚመሰል ማንም አልነበረም፡፡ ይህን ሁሉ ያደረገው ሚስቱ ኤልዛቤል ወደ ክፋት ስለ መራችው ነው፡፡ 26አክዓብ ከፈጸመው አሳፋሪ በደል ሁሉ ዋናው እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት ነቃቅሎ ያጠፋቸውን የአሞራውያንን ጣዖት ማምለኩ ነበር፡፡27አከዓብም ይህንን በሰማ ጊዜ፡- ልብሱን ቀዶ ማቅ ለበሰ፤ ማቁን እንደ ለበሰ ይተኛ ነበር፤ ሲሄድም ከጭንቀቱ ብዛት የተነሣ አዝኖ ነበር፡፡ 28የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ቴስቢያዊው ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡- 29አክዓብ በእኔ ፊት ራሱን እንዴት እንዳዋረደ ተመልክተሃልን? እግዚአብሔርም በፊቴ ራሱን ስላዋረደ በሕይወቱ ዘመን መቅሠፍትን በአክዓብ ቤተ ሰብ ላይ አላመጣበትም፤ የማመጣውም በልጁ ዘመን ይሆናል፡፡
1በእስራኤልና በሶሪያ መካከል ያለ ጦርነት ሦስት ዓመት አለፈ፡፡ 2ይሁን እንጂ በሦስተኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ለመጎብኘት ሄደ፡፡3የእስራኤል ንጉሥ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፡- በገለዓድ የምትገኘውን ራሞት ከሶርያ ንጉሥ ለማስመለስ ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰድነው ስለምንድን ነው? ራሞት እኮ የእኛ ይዞታ ናት አላቸው፡፡ 4ስለዚህ እርሱም ኢዮሣፍጥን ለጦርነት ወደ ራሞት ከእኔ ጋር ትሄዳለህን? ሲል ጠየቀው፡፡ ኢዮሣፍጥም እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ አንተ ሕዝብ ነው፤ ፈረሶቼም እንደ አንተ ፈረሶች ናቸው አለው፡፡5ኢዮሳፍጥም፣ ነገር ግን መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቅ ሲል መለሰለት፡፡ 6ከዚያም አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ ወደ ራሞት ለጦርነት ልውጣ ወይስ ልቅር? ሲል ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ሄደህ ተዋጋ፤ እግዚአብሔርም በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣል ሲሉ መለሱለት፡፡7ኢዮሣፍጥ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንጠይቅበት ሌላ የእግዚአብሔር ነቢይ የለምን? ሲል ጠየቀ፡፡ 8አክዓብም የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይ አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምን ጊዜም ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም ሲል መለሰለት፡፡ ኢዮሣፍጥም ይህን ማለት አይገባህም፤ አለው፡፡ 9ከዚያም አክዓብ ከቤተ መንግሥቱ አገልጋዮች አንዱን ጠርቶ የይምላ ልጅ ሚክያስን ፈልገህ በማግኘት በፍጥነት እንዲመጣ አድርግ ሲል አዘዘው፡፡10የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ሁለቱ ነገሥታት ልብሰ መንግሥታቸውን ለብሰው በሰማርያ የቅጥር በር አጠገብ በሚገኘው ሜዳ በየዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ነበር፡፡ ነቢያቱም ሁሉ በነገሥታቱ ፊት ቀርበው ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡ 11ከእነርሱም አንዱ ሴዴቅያስ ተብሎ የሚ. ጠራው የክንዓና ልጅ ከብረት የተሠሩ ቀንዶች ይዞ አክዓብን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከብረት በተሠሩ በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ አለው፡፡ 12ሌሎቹም ነቢያት ይህንኑ ቃል በመደገፍ በራሞት ላይ ዝመት፣ ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም ድልን ይሰጥሃል አሉት፡፡13ሚክያስን ለመጥራት ሄዶ የነበረው መልእክተኛ በዚሁ ጊዜ ሚክያስን ሌሎቹ ነቢያት በሙሉ ንጉሥ አክዓብ ድል የሚያደርግ መሆኑን የሚያረጋግጥ የትንቢት ቃል ተናግረዋል፤ ስለዚህ አንተም እንደእነርሱ ብታደርግ ይሻልሃል አለው፡፡ 14ሚክያስ ግን እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ እንደምናገር በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! ሲል መለሰለት፡፡ 15ሚክያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ፣ ሚክያስ ሆይ፣ ንጉሥ ኢዮሣፍጥና እኔ ወደ ራሞት ሄደን ጦርነት እንክፈት ወይስ እንተው? ሲል ጠየቀው፡፡ ሚክያስም ዘምተህ አደጋ ጣልባት ታሸንፋለህ፤ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ ሲል መለሰለት፡፡16ከዚያም አክዓብ፣ አንተ ግን በእግዚአብሔር ስም የትንቢትን ቃል ስትነግረኝ እውነቱን መግለጥ እንደሚገባህ ስንት ጊዜ እነግርሃለሁ አለው፡፡ 17ሚክያስም መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ እግዚአብሔርም፣ እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሎአል ሲል መለሰለት፡፡18አክዓብም ኢዮሣፍጥን እርሱ ሁልጊዜ ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም ብዬህ አልነበረምን? አለው፡፡ 19ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ እንግዲህ እግዚአብሔር የሚለውን ስማ፤ እግዚአብሔር በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፡፡ 20እግዚአብሔርም አክዓብን ወደ ራሞት ሄዶ በዚያ እንዲገደል ሊያሳስተው የሚችል ማን ነው? አለ፤ ከመላእክቱም መካከል አንዱ ሌላ ነገር ሌላውም ሌላ ነገር አለ፡፡21በመጨረሻ ግን አንድ መንፈስ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ እኔ ላሳስተው እችላለሁ አለ፡፡ 22እግዚአብሔርም እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ? አለው፡፡ መንፈሱም፣ ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ ሲል መለሰለት፤ እግዚአብሔርም እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል አለው፡፡ 23ሚክያስም እነሆ እግዚአብሔር እነዚህን የአንተን ነቢያት የሐሰት ቃለ እንዲነግሩህ ያደረገው እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለዚህ በአንተ ላይ ጥፋት ሊያመጣብህ እግዚአብሔር ራሱ ወስኖአል! ሲል ንግግሩን ደመደመ፡፡24ከዚያም የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስ ወደ ሚክያስ ቀርቦ በጥፊ መታውና ከመቼ ወዲህ ነው የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኔ አልፎ አንተን ያነጋገረህ? አለው፡፡ 25ሚክያስም በውስጥ ወዳለው ክፍል ሄደህ በምትሸሽግበት ጊዜ ታውቀዋለህ ሲል መለሰለት፡፡26በዚህን ጊዜ ንጉሥ አክዓብ ከጦር መኮንኖቹ አንዱን ሚክያስን ያዘው፤ ወደ ከተማይቱ ገዢ ወደ አሞንና ወደ ልዑል ኢዮአስ ውሰደው፤ 27እኔም በደህና እስክመለስ ድረስ እስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቆይ ያድርጉ ሲል አዘዘው፡፡ 28ሚክያስም አንተ በደህና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነው! አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ አለ፡፡29ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ወደ ገለዓድ ምድር ወደምትገኘው ራሞት ከተማ ለመዋጋት ሄዱ፡፡ 30አክዓብም ኢዮሣፍጥን ወደ ጦርነት ለመሄድ ስንነሣ እኔ ሌላ ሰው መስዬ ለመታየት ተራ ልብስ እለብሳለሁ፣ አንተ ግን ልብሰ መንግሥትህን ልበስ አለው፡፡ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ሌላ ልብስ ለብሶ ማንነቱን በመሰወር ዘመተ፡፡31የሶርያ ንጉሥም በንጉሡ ላይ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ ብሎ ለሠላሳ ሁለቱ የሠረገላ ጦር አዛዦች ትአዛዝ አስተላለፈ፡፡ 32ስለዚህ ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባዩ ጊዜ በርግጥ እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ነው ብለው በእርሱ ላይ አደጋ ሊጥሉበት ከበቡት፤ ኢዮሣፍጥም በጮኸ ጊዜ፣ 33እርሱ የእስራኤል ንጉሥ አለመሆኑን በማረጋገጥ በእርሱ ላይ አደጋ ከመጣል ተመለሱ፡፡34ነገር ግን በአጋጣሚ አንድ የሶርያ ወታደር ፍላጻ በማስፈንጠር ንጉሥ አክዓብን በጦር ልብሱ መገናኛ ላይ ወጋው፤ ንጉሥ አክዓብም የሠረገላ ነጂውን ክፉኛ ቆስያለሁ፤ ስለዚህ ሠረገላውን መልሰህ ከጦር ሜዳው ውጣ! ሲል አዘዘው፡፡35ጦርነቱም በተፋፋመ ጊዜ ንጉሥ አክዓብ በሶርያውያን ፊት ለፊት በሠረገላው ላይ ተደግፎ ነበር፤ በዚያውም ቀን ምሽት ሞተ፡፡ 36ፀሐይ በመጥለቅ ላይ እያለች፣ እያንዳንዱ ሰው ወደየአገሩና ወደየከተማው ይመለስ የሚል ትእዛዝ ከእስራኤል ጦር አዛዦች ተነገረ፡፡37ስለዚህ ንጉሥ አክዓብ ሞተ፤ ሬሳውም ወደ ሰማርያ ተወስዶ ተቀበረ፡፡ 38ሠረገላውም በሰማርያ ኩሬ ታጠበ፤ እግዚአብሔርም አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ደሙን ውሾች ላሱት፤ በዚያም ኩሬ ሴተኛ አዳሪዎች ታጠቡበት፡፡39ንጉሥ አክዓብ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ ምን እንደ ሠራና የሠራቸውም ከተሞች ሁኔታ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 40ንጉሥ አክዓብም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእርሱም ፈንታ ልጁ አካዝያስ ተተክቶ ነገሠ፡፡41የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ በነገሠ በአራተኛው ዓመት የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ 42ኢዮሣፍጥም በሠላሳ አምስት ዓመት ዕድሜው ነግሦ ሃያ አምስት ዓመት በኢየሩሳሌም ገዛ፡፡ እናቱም ዐዙባ ተብላ የምትጠራ የሺልሒ ልጅ ነበረች፡፡43ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ አሳ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ አደረገ፡፡ ሆኖም ግን የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን አልደመሰሰም ነበር፤ ስለዚህም ሕዝቡ በእነዚያ ቦታዎች መሥዋዕት ማቅረብና ዕጣን የማጠን ተግባሩን አልተወም ነበር፡፡ 44ኢዮሣፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ሰላም መሠረተ፡፡45ኢዮሣፍጥ ያደረጋቸው ነገሮች፣ በጦርነት ላይ ያሳየው ጀግንነትም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 46ከአባቱ ከአሳ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የተረፉትንና በአሕዛብ የማምለኪያ ቦታዎች የጣዖት አመንዝራዎችን ሁሉ አስወገደ፡፡ 47በዚያን ዘመን የኤዶም ምድር የራስዋ ንጉሥ አልነበራትም፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ንጉሥ በሚሾመው እንደራሴ ትገዛ ነበር፡፡48ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስ ዓይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም፡፡ 49ከዚያ በኋላ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ መርከበኞቹ ከኢዮሣፍጥ መርከበኛች ጋር በኅብረት እንዲሠሩ የውል ድርድር አቅርቦ ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን አሳቡን አልተቀበለም፡፡ 50ንጉሥ ኡዮሣፍጥ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አዮራም ነገሠ፡፡51የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ አካዝያስ በሰማርያ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ 52እርሱም የአባቱን የአክዓብን፣ የእናቱን የኤልዛቤልንና የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት በደል ሠራ፡፡ 53ከእርሱም በፊት እንደ ነበረው እንደ አባቱ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ በመስገድና በማገልገል የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ፡፡
1አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞአብ በአስራኤል ላይ ዐመፀ፡፡ 2በዚያን ጊዜ የአስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ ክፉኛ ቆስሎ ነበር፤ እርሱም እኔ ከዚህ ሕመም እድን እንደሆነ በፍልስጥኤም የአቃሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡል ጠይቁልኝ ብሎ መልእክተኞቹን ላከ፡፡3ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ቴስቢያዊውን ኤልያስን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ ተነሥተህ የሰማርያ ንጉሥ አካዝያስ የላካቸውን መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ የአቃሮንን አምላክ ብዔሌዜቡልን ለመጠየቅ የምትሄዱት በእስራኤል ዘንድ አምላክ የለም ብላችሁ ነውን? 4ስለዚህ እግዚአብሔር እነሆ አንተ ትሞታለህ እንጂ አትፈወስም፤ ከተኛህበት አልጋም አትነሣም፤ ብሎሃል በሉት፡፡ ከዚያም ኤልያስ ትቶ ሄደ፡፡5መልእተኞቹም ወደ ንጉሡ ተመልሰው ሄዱ፤ ንጉሡም ስለምን ተመልሳችሁ መጣችሁ? ሲል ጠየቃቸው፡፡ 6እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ አንድ ሰው በመንገድ አግኝቶን ወደ አንተ ተመልሰን እንድንመጣና እግዚአብሔር ስለ አንተ የተናገረውን እንድናስረዳህ አዘዘን፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፤ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ መልእክተኞች የላክህበት ምክንያት ምንድን ነው? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከዚህ ሕመም አትፈወስም፤ ከተኛህበትም አልጋ አትነሣም!7ንጉሡም በመንገድ ያገኛችሁት ይህንን ቃል የነገራችሁ ያ ሰው እንዴት ያለ ነው? ሲል ጠየቃቸው፡፡ 8እነርሱም ጠጉራም ልብስ ለብሶ በወገቡ ዙሪያ የጠፍር ቀበቶ የታጠቀ ነው ሲሉ መለሱለት፡፡ ንጉሡም እርሱማ ኤልያስ ነው! አለ፡፡9ከዚህም በኋላ ንጉሡ አንዱን የጦር መኮንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሄዶ ኤልያስን ይዞ ያመጣለት ዘንድ አዘዘው፡፡ መኮንኑም ኤልያስን በአንድ ኮረብታ ላይ ተቀምጦ አገኘውና የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል አለው፡፡ 10ኤልያስም እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ አለው፤ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ መኮንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ፡፡11ንጉሡም እንደገና ሌላውን መኮንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ላከ፤ እርሱም ወደ ኤልያስ ወጥቶ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፣ አሁኑኑ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል አለው፡፡ 12ኤልያስም እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ አለው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር እሳት መኮንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ፡፡13ንጉሡም ለሦስተኛ ጊዜ ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሌላ መኮንን ላከ፤ ይህኛው መኮንን ግን ወደ ኮረብታው በመውጣት በኤልያስ ፊት በጉልበቱ ተንበርክኮ እንዲህ ሲል ለመነ፤ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፣ ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት ሰዎች ምሕረት አድርግልን፤ ሕይወትችንንም ከሞት አድን፣ 14ሌሎቹን ሁለት መኮንኖችና ተከታዮቻቸውን ሁሉ ከሰማይ የወረደ እሳት በልቶአቸዋል፤ ለእኔ ግን እባክህ ምሕረት አድርግልኝ፡፡15የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን ከእርሱ ጋር አብረህ ውረድ፤ ከቶም አትፍራ አለው፡፡ ስለዚህም ኤልያስ ከመኮንኑ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ፡፡ 16እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁ መልእክተኞችን የላክህ በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቁጠርህ ነውን? ስለዚህ ከተኛህበት አልጋ ሳትወርድ ትሞታለህ እንጂ አትድንም አለው፡፡17ስለዚህ እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፡፡ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ ፈንታ ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ። ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር፡፡ 18ንጉሥ አካዝያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
1እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ የሚወስድበት ጊዜ ደረሰ፤ ኤልያስና ኤልሳዕ ከጌልጌላ ተነሥተው ጉዞ ጀመሩ፡፡ 2በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን እነሆ አንተ በዚህ ቆይ እኔ ወደ ቤቴል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል አለው፡፡ ኤልሳዕ ግን እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፣ ከቶ ከአንተ አልለይም ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤቴል ሄዱ፡፡3በዚያ የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው፣ እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን? ሲሉ ጠየቁት፡፡ ኤልሳዕም አዎን ዐውቃለሁ፣ ነገር ግን ዝም በሉ ሲል መለሰላቸው፡፡ 4ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን እነሆ አንተ በዚህ ቆይ እኔ ወደ ኢያሪኮ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል አለው፡፡ ኤልሳዕ ግን እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ ከቶ ከአንተ አልለይም፣ ሲል መለሰለት፡፡ ስለዚህም አብረው ወደ ኢያሪኮ ሄዱ፡፡5በዚህም የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን? ሲሉ ጠየቁት፡፡ ኤልሳዕም አዎን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ዝም በሉ ሲል መለሰላቸው፡፡ 6ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን እነሆ አንተ በዚህ ቆይ፤ እኔ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል አለው፡፡ ኤልሳዕ ግን እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ ከቶ ከአንተ አልለይም፤ ሲል መለሰለት፡፡ እነዚህም አብረው ጉዞአቸውን ቀጠሉ፡፡7ከነቢያቱም ኀምሳው ተከትለዋቸው ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ፤ ኤልያስና ኤልሳዕም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ቆሙ፤ ኀምሳውም ነቢያት ደግሞ ጥቂት ራቅ ብለው ቆመው ነበር፤ 8ከዚህ በኋላ ኤልያስ ካባውን አውልቆ በመጠቅለል ውሃውን መታው፤ ውሃው ወደ ቀኝና ወደ ግራ ተከፍሎላቸው ኤልያስና ኤልሳዕ በደረቅ ምድር ተሸገሩ፡፡9በዚህም ኤልያስ ኤልሳዕን እኔ ከአንተ ከመወሰዴ በፊት ምን እንዳደርግልህ እንደምትፈልግ ንገረኝ አለው፡፡ ኤልሳዕም ያንተ ተተኪ እንድሆን የሚያስችለኝ መንፈስ በእጥፍ ይሰጠኝ ሲል መለሰለት፡፡ 10ኤልያስም «ያቀረብከው ጥያቄ ከባድ ነው፤ ነገር ግን እኔ ከአንተ ተለይቼ ስወሰድ ብታየኝ ይህን የጠየከውን ስጦታ መቀበል ትችላልህ፤ ባታየኝ ግን ልታገኘው አትችልም» ብሎ መለሰለት፡፡11እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ ፈረሰኞች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ፡፡ 12ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ «የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንከው አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!» እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም፡፡ ኤልሳዕም ከሐዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤13ከኤልያስም የወደቀውን ካባ ከመሬት አነሣ፤ ከዚያም ሄዶ በዮርዳኖስ ወንዝ ደርቻ ቆመ፡፡ 14ውሃውንም በኤልያስ ካባ መትቶ፣ «የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው?» አለ፤ ከዚያም በኋላ እንደገና በመታው ጊዜ ውሃው ወደ ቀኝና ግራ ተከፍሎለት ወደ ማዶ ተሻገረ፡፡15ከኢያሪኮ የመጡት ነቢያት እርሱን ባዩት ጊዜ፣ «በኤልያስ ላይ ዐድሮ የነበረው የመንፈስ ኀይል በኤልሳዕ ላይ አርፏል!» አሉ፤ ወደ እርሱም በመቅረብ ጎንበስ ብለው እጅ ነሡት 16«እነሆ! በዚህ ጠንካራ የሆንን ኀምሳ ሰዎች አለን፤ እንሂድና ጌታህን እንፈልገው፤ ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወስዶ በአንድ ተራራ ወይም ሸለቆ ውስጥ አሳርፎት ይሆናል፡፡» ኤልሳዕም “አትሂዱ” ሲል መለሰ፡፡17እነርሱ ግን እምቢ በማለት እስኪያፍር ድረስ አጥብቀው ስለ ለመኑት በጉዳዩ ተስማማና ኀምሳ ሰዎች ሄደው ሦስት ቀን ሙሉ ኤልያስን ፈለጉት፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ 18ከዚያም በኋላ በኢያሪኮ ሆኖ ወደሚጠብቃቸው ወደ ኤልሳዕ ተመለሱ፤ ኤልሳዕም «እኔ ቀድሞውንስ አትሂዱ ብያችሁ አልነበረምን?» አላቸው፡፡19ጥቂት ሰዎች ከኢያሪኮ ወደ ኤልሳዕ መጥተው «ጌታችን አንተ እንደምታውቀው ይህች ምድር መልካም ናት፤ ውሃው ግን መጥፎ በመሆኑ ምድሪቱ ምርት አትሰጥም፤ ስለሁኔታው እንለምንሃለን» አሉት፡፡ 20ኤልሳዕም «በአዲስ ሳህን ውስጥ ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ» ብሎ አዘዘ፡፡ እነርሱም እንዳዘዛቸው አድርገው አመጡለት፡፡21እርሱም ወደ ምንጩ ሄዶ በውሃ ውስጥ ጨው በመጨመር «እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ‹እኔ ይህን ውሃ በመፈወስ ንፁህ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ የሞትና የምርት መጨንገፍ ምክንያት አይሆንም›» ሲል ተናገረ፡፡ 22ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ኤልሳዕ በተናገረው መሠረት ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ ንጹሕ ሆነ፡፡23ኤልሳዕም ወደ ቤቴል ለመሄድ ከኢያሪኮ ተነሣ፡፡ በመንገድ ሳለ ከከተማይቱ በርከት ያሉ ልጆች ወጥተው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ አንተ ራሰ መላጣ! ራሰ መላጣ! ከዚህ ውጣ እያሉ ጮኹበት፡፡ 24ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት አትኩሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው፡፡ 25ኤልሳዕም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ ዘግየት ብሎ ግን ወደ ሰማርያ ተመለሰ፡፡
1የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በእስራኤል ላይ በሰማርያ ነገሠ፤ እርሱም ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፡፡ 2እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠራ፡፡ ነገር ግን እንደ አባቱና እናቱ አልነበረም፤ ምክንያቱም በዓል ተብሎ የሚጠራውን አባቱ አሠርቶት የነበረውን በዕድ አምላክ ምስል አስወገደ፡፡ 3ይህም ሆኖ ከእርሱ በፊት እስራኤል ወደ ኃጢአት የመራው የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን አምልኮ ተከተለ እንጂ አላስወገደውም፡፡4የሞአብ ንጉሥ ሞሳ በግ አርቢ ነበር፤ በየዓመቱም አንድ መቶ ሺህ ጠቦት የአንድ መቶ ሺህ በጎች ጠጉር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር፤ 5ነገር ግን የእስራኤል ንጉሥ አካዓብ በሞተ ጊዜ የሞአብ ንጉሥ ሞሳ በእስራኤል ላይ ዐመፀ፡፡ 6በዚያን ጊዜ ንጉሥ ኢዮራም ወዲያውኑ ከሰማርያ ወጥቶ ወታደርቹን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ፤7ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥም የሞአብ ንጉሥ በእኔ ላይ አምፆብኛል፤ በእርሱ ላይ በማደርገው ጦርነት ከእኔ ጋር ትተባበራለህን? የሚል መልእክት ላከ፡፡ ንጉሥ ኢሣፍጥም አዎን እተባበርሃለሁ፤ እኔን እንደ ራስህ፣ ሠራዊቴን እንደ ሠራዊትህ፣፣ ፈረሶቼንም እንደ ፈረሶችህ መቁጠር ትችላለህ ሲል መለሰለት፡፡ 8እርሱም ልናጠቃ የምንችለው በየትኛው መንገድ ነው? ሲል ጠየቀው፡፡ ንጉሥ ኢዮራምም በኤዶም በረሓ የሚገኘውን ዙሪያ መንገድ ይዘን እንጓዛለን ሲል መለሰለት፡፡9ስለዚህም ንጉሥ ኢዮራም፣ እንዲሁም የይሁዳና የኤዶም ነገሥታት ለዘመቻ ወጡ፤ ከሰባት ቀን ጉዞም በኋላ ውሃ አለቀባቸው፤ ለሠራዊቱም ሆነ ለጭነት እንስሶቻቸው ምንም ውሃ አልነበረም፡፡ 10የእስራኤል ንጉሥ ይህ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞአብ ንጉሥ አሳልፎ ሊሰጠን ነውን? ወዮልን ሲል ጮኸ፡፡11ንጉሥ ኢዮሣፍጥም በእርሱ አማካይነት እግዚአብሔርን መጠየቅ እንድንችል በዚህ አንድ ነቢይ የለም? ሲል ጠየቀ፡፡ ከንጉሥ ኢዮራም ሠራዊት አዛዦች አንዱ፣ ቀድሞ የኤልያስ ረዳት የነበረው የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ እዚህ አለ ሲል መልስ ሰጠ፡፡ 12ንጉሥ ኢዮሣፍጥም የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ዘንድ ይገኛል አለ፤ ከዚያም በኋላ ሦስቱም ነገሥታት ወደ ኤልሳዕ ሄዱ፡፡13ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮራምን እኔ ለአንተ ማድረግ የሚገባኝ ምንድን ነው? ወደ አባትህና እናትህ ነቢያት ሂድ። ንጉሥ ኢዮራምም መልሶ አይደለም፣ ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞአብ ንጉሥ አሳልፎ ለመስጠት የጠራን እግዚአብሔር ነው አለ፡፡ 14ኤልሳዕም እኔ በማገልግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፣ አንተን ለመርዳት ለመጣው ለይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ክብር ስል ነው እንጂ ለአንተስ ምንም ነገር ላደርግልህ ባልተገባ ነበር፡፡15ነገር ግን በገና የሚደረድር ሰው አምጡልኝ አለ፡፡ ባለ በገናውም በሚደረድርበት ጊዜ የእግዚአብሔር ኃይል በኤልሳዕ ላይ ወርዶ እንዲህ አለ፡፡ 16እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- በዚህ የደረቀ ሸለቆ ሁሉ የውሃ ጉድጓድ ቆፍሩ፡፡ 17ምንም ዝናብና ነፋስ ባታዩም ይህ ሸለቆ በውሃ የተሞላ ይሆናል፡፡ እናንተ፣ የቀንድ ከብቶቻችሁና የጭነት እንስሶቻችሁ ሁሉ የምትጠጡት በቂ ውሃ ታገኛላችሁ፡፡18ነገር ግን ይህን ማድረግ በእግዚአብሔር ዘንድ ቀላል ነገር ነው፡፡ ከዚህ በላይ እርሱ በሞአባውያን ላይ ድልን ያጎናጽፋችኋል፡፡ 19የተመሸጉና ምርጥ የሆኑ ከተሞቻቸውን ሁሉ ድል አድርጋችሁ ትይዛላችሁ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውን ሁሉ ትቆርጣላችሁ፤ ምንጮቻቸውን ትደፍናላችሁ፤ ለም የሆኑ የእርሻ ቦታዎቻቸውን በማበላሸት ድንጋይ ትከምሩባቸዋላችሁ፡፡20በማግስቱም ጠዋት መሥዋዕት የሚቀርብበት ሰዓት ሲደርስ ከኤዶም በኩል የውሃ ምንጭ ፈልቆ ምድሩን ሸፈነው፡፡21ሞአባውያንም ሦስቱ ነገሥታት አደጋ ሊጥሉባቸው መምጣታቸውን በሰሙ ጊዜ፣ ከሽማግሌ እስከ ወጣት መሣሪያ መያዝ የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ተጠርተው ወጥተው ለጦርነት መጡ፡፡ 22በማግስቱም ጠዋት ከእንቅልፋቸው ነቅተው ሲመለከቱ በውሃው ላይ የሚያበራው የፀሐይ ነጸብራቅ እንደ ደም ቀይ መስሎ ታያቸው፡፡ 23ስለዚህም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ፣ ይህ ነገር ደም ነው፤ የሦስቱ ጠላቶቻችን ሠራዊቶች እርስ በርሳቸው በመተራረድ ተላልቀዋል፤ እንግዲህ ሄደን ሰፈራቸውን እንዝረፍ ተባባሉ፡፡24እነርሱ ወደ ሰፈር በደረሱ ጊዜ እስራኤላውያን ተነሥተው አደጋ በመጣል ወደ ኋላ መለሱአቸው፤ እስራኤላውያን አገሪቱን ወርረው ሞአባውያንን ጨፈጨፉአቸው፡፡ 25ከተሞቻቸውን ደመሰሱ፤ ለም በሆነው እርሻ ውስጥ በሚያልፉበትም ጊዜ እያንዳንዱ እስራኤላዊ አንዳንድ ድንጋይ ይወረውርበት ስለ ነበር በመጨረሻ እርሻዎቹ ሁሉ በድንጋይ ተሸፈኑ፤ ምንጮቻቸውን ደፈኑ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውንም ሁሉ ቆረጡ፤ በመጨረሻም የአገሪቱ ዋና ከተማ የነበረችው ቂርሔሬስ ብቻ ቀረች፤ እርስዋንም ድንጋይ የሚወነጭፉ ጦረኞች ከበው አደጋ ጣሉባት፡፡26የሞአብ ንጉሥ ድል እንደ ተመታ ባረጋገጠ ጊዜ ሰይፍ የታጠቁ ሰባት መቶ ሰዎችን እስከትሎ የጠላት ጦር የተሰለፈበትን መስመር ጥሶ ለማምለጥና ወደ ሶሪያ ንጉሥ ለመሄድ ቢሞክርም ከቶ አልተሳካለትም፡፡ 27ስለዚህ በእርሱ ምትክ መንገሥ የሚገባውን የመጀመሪያ ልጁን በከተማይቱ ግንብ ላይ ለሞአብ አምላክ መሥዋዕት አደርጎ አቀረበ፡፡ ስለዚህ በእስራኤል ዘንድ ከፍ ያለ ቁጣ ነበር፡፡ እስራኤላውያንም ለሞአብ ንጉሥ ከተማይቱን ለቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡
1የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ፣ ባልዋ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ፣ ጌታዬ ሆይ፣ ባሌ ሞቶብኛል፤ እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፡፡ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባሪያ አደርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል አለችው፡፡ 2ኤልሳዕም ታዲያ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽ ምን እንዳለሽ ንገሪኝ? ሲል ጠየቃት፡፡ እርስዋም በትንሽ ማሰሮ ከሚገኝ የወይራ ዘይት በቀር ሌላ ምንም የለኝም ስትል መለሰችለት፡፡3ኤልሳዕም እንዲህ አላት፡- ወደ ጎረቤቶችሽ ሄደሽ ማግኘት የምትችዪውን ያህል ባዶ ማድጋ ለምኚ፤ 4ከዚህም በኋላ አንቺና ልጆችሽ ቤት ገብታችሁ በሩን ዝጉ፡፡ የማሰሮውንም ዘይት ወደ ማድጋዎቹ ማንቆርቆር ጀምሪ፤ እያንዳንዱ ማድጋ በሚሞላበት ጊዜ ለብቻው በማግለል አኑሩት፡፡5ስለዚህም ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ሄዳ ከልጆችዋ ጋር በሩን ዘጋች፤ ዘይት የነበረበትን ትንሽ ማሰሮ አንሥታም ልጆችዋ እያቀረቡላት በማንቆርቆር በየማድጋዎቹ ሞላች፡፡ 6ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ ሌላ ትርፍ የለም ወይ ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ ሌላ ማድጋ የለም ሲል መለሰላት፡፡ ከዚያ በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፡፡7እርስዋም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል አላት፡፡8አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፡፡ 9እርስዋም ባልዋን እንዲህ አለችው፤ ብዙ ጊዜ ወደ ቤታችን የሚመጣው ይህ ሰው የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰው ስለ መሆኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡10ስለዚህም በሰገነቱ ላይ አንድ ትንሽ ክፍል ሠርተን በዚያች ውስጥ አል፣ ጠረጳዛ፣ ወንበርና የፋኖስ መብራት እናኑርለት፤ እርሱም ወደ እኛ በሚመጣበት ጊዜ እዚያ ያርፋል፡፡ 11አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደዚያ እንደገና ሄደ፤ ወደ ተሠራለት ክፍል ገብቶ እረፍት አደረገ፡፡12ኤልሳዕም ለአገልጋዩ ግያዝ እንዲህ አለ፡- «ይህችን ሱናማዊት ጥራት» በጠራትም ጊዜ መጥታ በፊቱ ቆመች፡፡ 13ኤልሳዕም ግያዝን እንዲነግራት እንዲህ አለው፡- «እኛን ለመንከባከብ ይህን ሁሉ ተቸገረሽ፤ እኛ ደግሞ ለአንቺ ምን እናድርግልሽ? ለንጉሥ ወይም ለጦር አዛዥ ስለ አንቺ ልንነግርልሽ እንችላለን? በላት አለው፡፡ እርስዋም «በዘመዶቼ መካከል ስለምኖር በዚህ ስፍራ ምንም የሚቸግረኝ ነገር የለም» ስትል መለሰችለት፡፡14ኤልሳዕም ግያዝን «ታዲያ ምን ልናደርግላት እችላለን?» ሲል ጠየቀው፡፡ ግያዝም “እነሆ ልጅ የላትም፣ ባሏም ሸምግሎአል” አለ፡፡ 15ኤልሳዕም ጥራት አለው፡፡ ሲጠራትም መጥታ በበሩ አጠገብ ቆመች፡፡ 16ኤልሳዕም አላት፡- በመጪው ዓመት በዚህ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ አላት፡፡ እርስዋም ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እባክህ አገልጋይህን አትዋሻት አለችው፡፡17ሴቲቱም ፀነሰች፤ ልክ ኤልሳዕ የተናገረው ጊዜ ሲደርስ በዓመቱ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ 18ሕፃኑም በአደገ ጊዜ አንድ ቀን አባቱ ከአጫጆች ጋር ወዳለበት ሄደ፡፡ 19እርሱም በድንገት “ራሴን! ራሴን!” ብሎ ወደ አባቱ ጮኸ፡፡ አባትየውም አንዱን አገልጋይ ጠርቶ፡- “ልጁን ወደ እናቱ ውሰድ” ሲል አዘዘው፡፡ 20አገልጋዩም ልጁን ተሸክሞ ወደ እናቱ ባመጣው ጊዜ እርስዋም ተቀብላው በጉልበትዋ እንደታቀፈችው ቆይቶ እኩለ ቀን ላይ ሞተ፡፡21ሴቲቱም ተነሥታ ልጁን በእግዚአብሔር ሰው አልጋ ላይ አስተኝታ በሩን ዘግታበት ተመልሳ ሄደች፡፡ 22ባልዋንም ጠርታ “አንድ አገልጋይና አንድ አህያ ላክልኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ዘንድ ሄጄ እመለሳለሁ አለችው፡፡23ባልዋ “ለምን መሄድ ትፈልጊያለሽ? ዛሬ ሰንበት ወይም የጨረቃ በዓል የሚከበርበት ቀን አይደለም” አላት፡፡ እርስዋም “ግድ የለም፤ እንዳልኩህ አድርግ” አለችው፡፡ 24እርስዋም አህያው እንዲጫንላት ካደረገች በኋላ አገልጋዩን “በተቻለ መጠን አህያው እንዲፈጥን አድርግ፤ እኔም ካልነገርኩህ በቀር ቀስ ብሎ እንዲሄድ ዕድል አትስጠው” ስትል አዘዘችው፡፡25እርስዋም ከዚያ ተነሥታ ኤልሳዕ ወደነበረበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣች፡፡ የእግዚአብሔርም ሰው ገና በሩቅ ሳለች ወደ እርሱ ስትመጣ አይቶ አገልጋዩን ግያዝን «ተመልከት! ያቺ ሱነማዊት ወደዚህ እየመጣች ነው! አለው፡፡ 26ፈጠን ብለህ ሂድና የእርስዋን፤ የባልዋንና የልጅዋን ደኅንነት ጠይቃት» አለው፡፡ እርስዋም ግያዝን «ሁላችንም ደኅና ነን» ስትል ነገረችው፡፡27ወደ ኤልሳዕ ወደ ተራራው በመጣች ጊዜ እግሮቹን ያዘች፤ በዚህ ጊዜ ግያዝ ሊያርቃት ፈለገ፤ ኤልሳዕ ግን «ተዋት፤ እርስዋ ተጨንቃለች፣ እግዚአብሔርም ከእኔ ሰውሮታልና ምንም የነገረኝ ነገር የለም» አለው፡፡28ሴቲቱም «ጌታዬ፣ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‹አታሳስተኝ› ብዬ ነግሬህ አልነበረምን?» አለችው፡፡ 29ኤልሳዕም ግያዝን አለው፡- «ለጉዞ በፍጥነት ተነሣና ምርኩዜን በእጅህ ያዝ፡፡ ወደ ቤትዋ ሂድ፡፡ በመንገድ ማንንም ብታገኝ ሰላምታ አትስጥ፤ ማንም ሰላምታ ቢሰጥህ መልስ አትስጥ፡፡ ምርኩዜን በልጁ ፊት ላይ አኑር!» አለው፡፡30የልጁ እናት ግን ኤልሳዕን «በምትተማመንበት በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከቶ አንተን ትቼ አልሄድም!» አለችው፤ ስለዚህ እርስዋን ተከትሎ ለመሄድ ተነሣ፤ 31ግያዝም ወደ ፊት ቀድሞአቸው የኤልሳዕን ምርኩዝ በልጁ ፊት ላይ አኖረ፤ ነገር ግን ልጁ ግን አልተናገረም፣ አልሰማም፡፡ ስለዚህም ተመልሶ ሄዶ ኤልሳዕን «ልጁ አልተነሣም» አለው፡፡32ኤልሳዕም ወደ ቤቱ በደረሰ ጊዜ ልጁ ሞቶ አልጋ ላይ ነበር፡፡ 33ስለዚህ ኤልሳዕ ገባና በሩን በልጁና በራሱ ላይ ዘግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ 34ሄዶም በልጁ ላይ ተጋደመ፤ አፉን በአፉ ላይ፣ ዐይኖቹን በአይኖቹ ላይ፣ እጆቹን በእጆቹ ላይ አደረገ፤ ራሱን በልጁ ላይ ዘርግቶ ተጋደመ፤ የልጁም ሰውነት መሞቅ ጀመረ፡፡35ከዚያም፣ ኤልሳዕ ተነሥቶ በክፍሉ ውስጥ ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ጀመር፤ እንደገናም ተመለሰና በመዘርጋት በልጁ ላይ ተጋደመ፡፡ ልጁም ሰባት ጊዜ ካስነጠሰው በኋላ ዐይኖቹን ከፈተ፡፡ 36ስለዚህ ኤልሳዕ ግያዝን ጠርቶ እንዲህ አለ፣ ሱነማይቱን ጥራት አለው፡፡ እርሱም ጠራት፣ እርስዋም በመጣች ጊዜ ኤልሳዕ ልጅሽ ይኸውልሽ አንሽው አላት፡፡ 37እርስዋ ወደ መሬት ለጥ ብላ በኤልሳዕ ጫማ ላይ በመውደቅ እጅ ነሣች፤ ከዚያም በኋላ ልጅዋን ይዛ ሄደች፡፡38ከዚያም ኤልሳዕ ወደ ጌልጌላ መጣ፡፡ በአገሪቱ ራብ በነበረበት ጊዜ የነቢያት ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፡፡ እርሱም አገልጋዩን እንዲህ አለው፡- ትልቅ ድስት ጥደህ ለነቢያቱ ልጆች ወጥ ሥራላቸው አለው፡፡ 39ከነቢያቱም አንዱ ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሄደ፡፡ እርሱም በጫካ ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያህል በርከት ያለ ቅል ቆርጦ አመጣ፡፡ እርሱም ከተፈውና ወጡ ውስጥ ጨመረው፤ ነገር ግን ምን እንደሆነ ዐላወቁም፡፡40እነርሱም ወጡን ለሰዎቹ እንዲመገቡት አወጡ፡፡ በኋላም እየበሉ ሳለ ጮኸው፣ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፣ በድስቱ ውስጥ ሞት አለ! አሉት፤ ስለዚህም ሊበሉት አልቻሉም፡፡ 41ነገር ግን ኤልሳዕ እንዲህ አለ፡- ጥቂት ዱቄት አምጡልኝ፡፡ ያመጡትን ዱቄት በድስቱ ውስጥ ጨምሮ እንዲህ አለ፡- ለሰዎች እንዲበሉ ወጡን አውጡ፡፡ ከዚያ በወጡ ውስጥ የሚጎዳ ነገር አልተገኘም፡፡42በዓል ሻሊሻ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው ወደ እግዚአብሔር ሰው መጥቶ በመከር ጊዜ በመጀመሪያ ከተወቃው ሃያ የገብስ የዳቦ ሙልሙሎችና አዲስ የተቆረጠ እሸት በከረጢቱ አመጣለት፡፡ እርሱም ይህን እንዲበሉ ለነቢያት ልጆች ስጡአቸው አለ፡፡ 43አገልጋዩም እንዲህ አለ፡- በመቶ ሰዎች ፊት ይህን ምን ብዬ ማቅረብ አለብኝ? ነገር ግን ኤልሳዕ አለ፡- እንዲበሉ ለሰዎቹ ስጣቸው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ይበላሉ ያተርፉማል፡፡ 44ስለዚህም አገልጋዩ ምግቡን አቀረበላቸው፣ እግዚአብሔርም በተናገረው መሠረት ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ የተረፈ ምግብ ነበር፡፡
1የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ ታላቅና የተከበረ ነበር፤ ምክንያቱም በእርሱ አማካይነት እግዚአብሔር ለሶርያ ሠራዊት ድልን አጎናጽፎ ነበር፡፡ እርሱም ደግሞ ጠንከራና ብርቱ ሰው ነበር፤ ነገር ግን ለምጻም ነበር፡፡ 2ሶርያውያን በእስራኤላውያን ላይ ወረራ በፈጸሙበት ጊዜ አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጃገረድ ማርከው ወስደው ነበር፤ እርስዋም ለንዕማን ሚስት ሠራተኛ ሆና ታገለግል ነበር፡፡3ልጃገረዲቱም እመቤትዋን እንዲህ አለቻት፡- «ጌታዬ በሰማርያ ወደሚገኘው ነቢይ ቢሄድ እወዳለሁ! እርሱም ጌታዬን ከዚህ ለምጽ ሊያነፃው ይችላል!» አለቻት፡፡ 4ንዕማንም ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ልጃገረዲቱ ያለችውን ሁሉ ነገረው፡፡5ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ እንዲህ አለ፣ «ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እልካለሁ፤ አሁን አንተ ሂድ» ብሎ ፈቀደለት፡፡ ንዕማንም ዐሥር መክሊት ብር፣ ስድስት ሺህ መሐለቅ ወርቅና ዐሥር መለወጫ ልብስ አስጭኖ፣ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ 6እርሱም ለእስራኤል ንጉሥ የተጻፈለትን ደብዳቤ ወሰደ፣ ደብዳቤውም እንዲህ ይላል፡- «ይህ ደብዳቤ የኔ አገልጋይ ስለሆነው ስለ ንዕማን ጉዳይ የሚገልጥ ነው፤ ከለምጹም እንድትፈውሰው ወደ አንተ ልኬዋለሁ» የሚል ነበር፡፡7የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቁጣ ልብሱን ቀደደ፤ እንዲህም አለ፡- «የሶሪያ ንጉሥ ይህን ሰው እንድፈውስለት እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከለምጽ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ ለመጀመር የፈለገ ይመስላል!» አለ፡፡8ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ነቢዩ ኤልሳዕ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን መቅደዱን በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፡- «ስለምን ልብስህን ቀደድክ? ሰውየውን ወደ እኔ ላከው፤ እርሱም በእስራኤል ነቢይ መኖሩን ያውቃል!» አለው፡፡ 9ስለዚህም ንዕማን ከፈረሶችና ከሠረገላዎቹ ጋር ወደ ኤልሳዕ ቤት መጥቶ በር ላይ ቆመ፡፡ 10ኤልሳዕም አንዱን አገልጋይ ልኮ «ሄደህ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ራስህን በማጥለቅ ታጠብ፤ ሰውነትህም ይመለሳል፤ ንጹሕም ትሆናለህ› ብለህ ለዚህ ሰው ንገረው» ሲል ተናገረው፡፡11ንዕማን ግን ተቆጥቶ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም አለ፡- “እኔ ነቢዩ መጥቶ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ በሽታዬ ያለበትን ቦታ በእጆቹ በመዳሰስ ከለምጽ በሽታዬ ይፈውሰኛል ብዬ ነበር፡፡ 12በእስራኤል ከሚገኙት ወንዞች ይልቅ በአገሬ በደማስቆ የሚገኙት አባናና ፋርፋ አይሻሉምን? በእነርሱ ታጥቤ ንጹሕ መሆን አልችልምን?” ስለዚህ ተነሥቶ ሄደ፡፡›13የንዕማንም አገልጋዮች ወደ እርሱ ቀርበው፡- «ጌታችን ሆይ፣ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈፅመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል?» አሉት፡፡ 14ከዚያም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፡፡ ሰውነቱም እንደ ሕፃን ልጅ ገላ በመታደስ ፍፁም ጤናማ ሆነ፡፡15ንዕማንና አጃቢዎቹ ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሰው መጥተው በፊቱ ቆሙ፡፡ ንዕማንም እንዲህ አለ፡- «ከእስራኤል አምላክ በቀር በምድር ላይ ሌላ አምላክ እንደሌለ እነሆ አሁን ዐወቅሁ፡፡ ስለዚህም ከአገልጋይ ይህን ስጦታ እባክህ ተቀበለኝ» አለው፡፡ 16ኤልሳዕ ግን «በፊቱ ቆሜ በማገለግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ምንም ስጦታ አልቀበልህም» ሲል መለሰለት፡፡ ንዕማንም ስጦታውን እንዲቀበል አጥብቆ ቢለምነውም ኤልሳዕ ሊቀበለው አልፈቀደም፡፡17ስለዚህም ንዕማን እንዲህ አለ፡- «ስጦታዬን የማትቀበለኝ ከሆነ ለሌሎች ባዕዳን አማልክት የሚቃጠልም ሆነ ሌላ አይነት መሥዋዕት የማቀርበውን ከአሁን ጀምሮ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ብቻ ለማቅረብ ስለወሰንሁ የሁለት በቅሎ ጭነት አፈር ይዤ እንድሄድ ፍቀድልኝ፡፡» 18ስለዚህም የአገሬን ንጉሥ በማጀብ ሬሞን የተባለ ባዕድ አምላክ ወደሚመለክበት መቅደስ ብገባና ብሰግድም እንኳ እግዚአብሔር በዚህ ጉዳይ ይቅር እንደሚለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በእርግጥም በዚህ ጉዳይ ይቅር ይለኛል፡፡» 19ኤልሳዕም «በሰላም ሂድ!» አለው፤ ንዕማንም ተሰናብቶ ሄደ፡፡20እርሱም ጥቂት ራቅ ብሎ እንደ ሄደ፣ የኤልሳዕ አገልጋይ ግያዝ ለራሱ እንዲህ አለ፡- «ጌታዬ ሶሪያዊው ንዕማን ካመጣው ስጦታ ሳይቀበል አሰናብቶታል፡፡ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፣ ተከትዬው ሄጄ ከእርሱ አንድ ነገር ማግኘት አለብኝ» ሲል በልቡ አሰበ፡፡ 21ስለዚህም ግያዝ ንዕማንን ከኋላው ተከተለው፡፡ ንዕማንም መለስ ብሎ አንድ ሰው እየሮጠ ሲከተለው ባየ ጊዜ እርሱን ለመገናኘት ከሠረገላው ወርዶ እንዲህ አለ፡- «ሁሉ ነገር ሰላም ነው?» 22ግያዝም፡- «ሁሉ ነገር መልካም ነው፡፡ ጌታዬ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖሩ ሁለት ወጣት የነቢያት ልጆች ድንገት መጡብኝ፤ አንድ መክሊት ብርና ሁለት መቀየሪያ ልብሶች ላክልኝ ብሎ ልኮኛል» ሲል መለሰለት፡፡23ንዕማንም፡- «እባክህ ሁለት መክሊት ብር ለመስጠት በጣም ደስተኛ ነኝ» ሲል መለሰለት፡፡ ብሩን በሁለት ከረጢት ሞልቶ ከሁለት መለወጫ ልብሶች ጋር በሁለት አገልጋዮች አስይዞ ከግያዝ ፊት እንዲሄዱ አደረገ፡፡ 24ግያዝም ወደ ኮረብታው በደረሰ ጊዜ፣ ግያዝ ሁለቱን ከረጢት ብር ከእጃቸው ወስዶ ወደ ቤት አስገባ፡፡ እነርሱንም አሰናብቶአቸው ሄዱ፡፡ 25ወደ ቤት ተመልሶ ገብቶ በጌታው በኤልሳዕ ፊት በቆመ ጊዜ ኤልሳዕ እንዲህ አለው፡- «ግያዝ ከወዴት መጣህ?» እርሱም፡- «ጌታዬ፣ አገልጋይህ የትም አልሄድኩም» ሲል መለሰ፡፡26ኤልሳዕም ለግያዝ፡- «ሰውየው አንተን ለመገናኘት ከሠረገላው ሲወርድ እኔ በመንፈስ ከአንተ ጋር አልነበርኩምን? እነሆ አሁን ገንዘብና ልብስ፣ የወይራና የወይን ተክል ቦታ፣ በግና የቀንድ ከብት ወይም አገልጋዮችን ለመቀበል ጊዜው ነውን? 27ስለዚህ እነሆ የንዕማን ለምጽ ወደ አንተና ዘሮችህ ለዘላለም ይተላለፋል» አለው፡፡ ግያዝም ከፊቱ ወጥቶ ሄደ፣ ለምጹም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡
1የነቢያት ልጆችም ኤልሳዕን፡- «ከአንተ ጋር የምንኖርበት ስፍራ ከሁላችንም ጠባብ ነው አሉት፡፡ 2ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄደን ዛፍ ቆርጠን የምንኖርበትን ቤት በዚያ እንድንሠራ ፍቀድልን!» አሉት፡፡ ኤልሳዕም «መልካም ነው ቀጥሉ!» በማለት መለሰላቸው፡፡ 3ከእነርሱም አንዱ ኤልሳዕን አብሮአቸው እንዲሄድ ጠየቀው፤ ኤልሳዕም እሄዳለሁ አላቸው፡፡4እርሱም አብሮአቸው ሄደ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ ዛፍ የመቁረጥ ተግባራቸውን ጀመሩ፡፡ 5ነገር ግን አንዱ ዛፍ በመቁረጥ ላይ ሳለ መጥረቢያው ወድቆ ውሃው ውስጥ ጠለቀ፤ እርሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ: - «ጌታዬ ሆይ! መጥረቢያው የተዋስኩት ነው፣ ምን አደርጋለሁ?» ሲል ጮኸ፡፡6የእግዚአብሔርም ሰው፡- «በየት በኩል ነው የወደቀው?» ሲል ጠየቀው፡፡ ሰውየውም መጥረቢያው የወደቀበትን ስፍራ አሳየው፡፡ እርሱም አንድ እንጨት ቆርጦ ወደ ውሃው በጣለ ጊዜ መጥረቢያው ተንሳፈፈ፡፡ 7ኤልሳዕም፡- «ውሰደው» አለው፡፡ ሰውየውም ጎንበስ ብሎ አነሣው፡፡8እነሆ፣ የሶርያ ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ጦርነት ከፍቶ ነበር፡፡ እርሱም ከጦር አዛዦቹ ጋር ተማክሮ የሚሰፍሩበትን ቦታ መረጠ፡፡ 9የእግዚአብሔርም ሰው: - «ሶርያውያን ደፈጣ አድርገው ስለሚጠብቁህ ከዚህ ወደዚያ ስፍራ አትቅረብ» ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ፡፡10የእስራኤልም ንጉሥ ወታደሮቹ ወደሚኖሩበት፣ የእግዚአብሔር ሰው ወደተናገረበትና ወዳስጠነቀቀበት ስፍራ ላከ፡፡ ይህም ድርጊት ከአንድ ጊዜ ወይም ከሁለት ጊዜ በላይ ንጉሡ እዚያ ሲሄድ ከጥበቃ ጋር ነበር፡፡ 11የሶርያ ንጉሥም፡- «ከእኛ መካከል ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ግንኙነት ያለው ማን እንደሆነ አትነግሩኝምን?» ሲል ጠየቃቸው፡፡12ከእነርሱም አንዱ «ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው» ሲል መለሰለት፡፡ 13የሶርያው ንጉሥ፡- «እርሱ የሚገኝበትን ስፍራ ፈልጉ፤ እኔም ልኬ እማርከዋለሁ» አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ በዶታይን እንደሚኖር ተነገረው፡፡14ስለዚህ ንጉሡ በፈረሶችና በሠረገሎች የተጠናከረ ብዙ ሠራዊት ወደ ዶታይን ላከ፡፡ እነርሱም በሌሊት ደርሰው ከተማዪቱን ከበቡ፡፡ 15በማግስቱም ማለዳ የኤልሳዕ አገልጋይ ከመኝታው ተነሥቶ ከቤት ሲወጣ፣ በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀቡ የሶርያ ወታደሮች ከተማዪቱን መክበባቸውን አየ፡፡ ወደ ኤልሳዕም ተመልሶ: - «ጌታዬ ወዮ! ምን ማድረግ ይሻለናል?» ሲል ጠየቀው፡፡ 16ኤልሳዕም «አይዞህ አትፍራ፤ ከእነርሱ ጋር ከተሰለፈው ይልቅ ከእኛ ጋር የተሰለፈው ሠራዊት ይበልጣል» አለው፡፡17ኤልሳዕም «እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችል ዐይኖቹን ክፈትለት!» ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን አገልጋይ ዐይኖች ከፈተለት፤ በኮረብታው ብዙ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ እንዳሉ ተመለከተ፡፡ 18ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ እንዲህ ሲል ጸለየ፡- «እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ!» እግዚአብሔርም ኤልሳዕ እንደ ጸለየው፣ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ፡፡ 19ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ሶርያውያንን፡- «መንገድ ተሳስታችኋል፤ የምትፈልጓት ከተማ ይህች አይደለችም፤ ይልቅስ ወደምትፈልጉት ሰው እኔ ልምራችሁ፣ ተከተሉኝ» ብሎ ወደ ሰማርያ መራቸው፡፡20ወደ ሰማርያም በደረሱ ጊዜ ኤልሳዕ፡- «እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች ማየት እንዲችሉ ዐይኖቻቸውን ክፈት!» ሲል ጸለየ፡፡ እግዚአብሔርም ዐይኖቻቸውን በከፈተላቸው ጊዜ በሰማርያ መካከል መሆናቸውን ተረዱ፡፡ 21የእስራኤልም ንጉሥ ሶርያውያንን ባያቸው ጊዜ «ጌታዬ! ልግደላቸውን? ልግደላቸውን?» ሲል ኤልሳዕን ጠየቀው፡፡22ኤልሳዕም «አይሆንም! እንኳን እነዚህን በሰይፍህና በቀስትህ የማረካቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትንና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ» አለው፡፡ 23ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ለእነርሱ ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ ከበሉና ከጠጡም በኋላ ወደ ሶርያ ንጉሥ መልሶ ላካቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሶርያውያን በእስራኤል ምድር ላይ ወረራ ማድረጋቸውን አቆሙ፡፡24ከዚህ በኋላ የሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ መላ ሠራዊቱን ሰብስቦ በእስራኤል ላይ በማዝመት ጉዳት አደረሰ፤ የሰማርያን ከተማም ከበበ፡፡ 25ስለዚህ በሰማርያ ጽኑ ራብ ነበር፡፡ ከዚህም የተነሣ የአንድ አህያ ራስ ሰማኒያ መክሊት ብር፣ ሁለት መቶ ግራም የሚያህል የርግብ ኩስ ዋጋ እስከ አምስት መክሊት ብር ይሸጥ ነበር፡፡ 26አንድ ቀን የእስራኤል ንጉሥ በከታማዪቱ የቅጥር ግንብ ላይ በሚመላለስበት ጊዜ አንዲት ሴት: - «ንጉሥ ሆይ እባክህ እርዳኝ!» ስትል ጮኸች፡፡27ንጉሡም «እግዚአብሔር ካልረዳሽ እኔ እንዴት ልረዳሽ እችላለሁ? ከአውድማው ወይንስ ከወይን መጭመቂያው ይመጣልን? 28ለመሆኑ ችግርሽ ምንድን ነው?» ሲል ጠየቃት፡፡ እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፡- «ባለፈው ቀን ይህች ሴት ‹ዛሬ ያንቺን ልጅ እንብላ፤ በማግስቱ ደግሞ የእኔን ልጅ እንበላለን› ስትል አሳብ አቀረበች፡፡ 29ስለዚህም የእኔን ልጅ ቀቅለን በላን፤ በማግስቱም ‹ልጅሽን አምጪና እንብላ› ብዬ ጠየቅኋት፤ እርስዋ ግን ደበቀችው፡፡»30ንጉሡም ይህንን የሴትዮዋን ቃል በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ በግንቡ ላይ በመሆኑ በአቅራቢያው የነበረው ሕዝብ ንጉሡ በውስጡ ማቅ ለብሶ እንደ ነበር አዩ፡፡ 31ንጉሡም ድምፁን ከፍ በማድረግ «የዛሬይቱ ጀምበር ከመጥለቅዋ በፊት የሳፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ሳይቆረጥ ቢያድር እግዚአብሔር እኔን በሞት ይቅጣኝ!» ሲል ተናገረ፡፡32በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ ከሽማግሌዎች ጋር በቤቱ ተቀምጦ ነበር፡፡ ንጉሡም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ፡፡ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን፡- «ይህ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል» አላቸው፡፡ 33ገና ይህን ተናግሮ ሳይጨርስ ንጉሡ ድንገት ከተፍ ብሎ «ይህን መከራ ያመጣው እግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ ከዚህ በላይ እግዚአብሔርን የምጠብቀው ለምንድን ነው?» አለ፡፡
1ኤልሳዕም፡- «እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ስማ! ነገ በዚህ ጊዜ ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር በሰማርያ በር ይሸመታል» አለ፡፡ 2በዚህ ጊዜ የንጉሡ ባለሥልጣን ለእግዚአብሔር ሰው እንዲህ ሲል መለሰለት፡- እግዚአብሔር የሰማይ መስኮቶችን እንኳ ቢከፍት ይህ ሊሆን ይችላልን? ኤልሳዕም እንዲህ ሲል መለሰለት፡- ይህ ሲፈጸም በዐኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፤፤ አንተ ግን ከዚህ ምንም አትበላም፡፡3አራት ለምጻሞች ከሰማርያ ከተማ በር ቆመው ነበር፡፡ እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፡- እስክንሞት ለምን እዚህ እንቀመጣለን? 4ወደ ከተማ እንግባ ካልን በከተማው ራብ ስላለ እንሞታለን፡፡ ነገር ግን እዚህ ከተቀመጠንም መሞታችን ነው፤ ወደ ሶርያውያን ጦር ሰፈር እንሂድ፤ በሕይወት ካቆዩንም በሕይወት እንኖራለን፤ ከገደሉንም መሞት ብቻ ነው፡፡5ስለዚህም ቀኑ ሊመሽ ሲል ወደ ሶርያውያን ጦር ሰፈር ሊሄዱ ተነሡ፤ ወደ ሰፈሩም በደረሱ ጊዜ እዚያ ማንም አልነበረም፡፡ 6ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር የሶርያ ጦር የፈረሶች፣ የሠረገሎችና ሌሎችንም ከፍተኛ የሠራዊት ድምፅ እንዲሰሙ አድርጎ ስለነበረ ነው፤ እርስ በርሳቸውም እንዲህ አሉ፡- የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብፃውያንን ሠራዊት ቀጥሮ እኛን እያጠቃ ነው፡፡7ስለዚህ ሠራዊቱ በሌሊት ተነሥቶ ሸሸ፤ ድንኳኖቻቸውን፣ ፈረሶቻቸውንና በሰፈሩ ያለውን ሁሉ ትተው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሸሹ፡፡ 8ለምጻሞቹም ወደ ሶርያውያን ሰፈር ዳርቻ በደረሱ ጊዜ ወደ አንዱ ድንኳን በገቡ ጊዜ በሉ፣ ጠጡ፤ ብር፣ ወርቅና ልብስም ወስደው ደበቁ፡፡ እንደገና ተመልሰው ወደ ሌላ ድንኳን ገብተው ያለውን ወስደው እንደበፊቱ አደረጉ፡፡9ከዚያም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፡- መልካም አላደረግንም፡፡ ዛሬ የምሥራች የሚሆን ታላቅ ነገር አግኝተናል፤ ነገር ግን ዝም ብለናል፡፡ እስኪነጋም ዝም ብንል ቅጣት ይደርስብናል፡፡ አሁን ተነሥተን እንሂድና ለንጉሡ ቤተ ሰብ እንንገር፡፡ 10ስለዚህ ሄደው የከተማውን በር ጠባቂዎች ተጣሩ፤ እንዲህ ብለውም ነገሩአቸው፡- ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ማንም አልነበረም፤ አንዲት ድምፅ እንኳን የለም፤ ነገር ግን ፈረሶችና አህዮች እንደታሰሩ አሉ፣ እንዲሁም ድንኳኖቹም እንዳሉ ናቸው፡፡ 11ከዚያም የበር ጠባቂዎቹ ወሬውን ተናገሩ፤ ከዚያም እስከ ንጉሡ ቤተ ሰብ ድረስ ተሰማ፡፡12ንጉሡም በሌሊት ተነሥቶ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፡- ሶርያውያን የደረጉብንን እነግራችኋለሁ፤ እንደተራብን ስለሚያውቁ ራሳቸውን ለመሰወር ሰፈሩን ለቀው ወደ ገጠር ሄደዋል፤ እንዲህም ይላሉ፡- ምግብ ፍለጋ ከከተማ ሲወጡ በሕይወት እንይዛቸዋለን፤ ወደ ከተማም እንወስዳቸዋለን፡፡ 13ከንጉሡም ባለሥልጣናት አንዱ መልሶ እንዲህ አለ፡- ጥቂት ሰዎች ከሞት ከተረፉት አምስት ፈረሶች እንድንወስድ እለምንሃለሁ፡፡ በዚህ ከተማ የተረፈው ሕዝብ ከዚህ በፊት እንደሞቱ ሰዎች ሁሉ ከሞት የሚያመልጥ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሆነውን ነገር ለማወቅ እንድንችል እነርሱን እንላክ፡፡14ንጉሡም ሁለት ሠረገላዎችን ከፈረሶች ጋር ከሶርያውያን ሠራዊት በኋላ እንዲህ ሲል ላካቸው፡- ሂዱና ተመልከቱ፡፡ 15እነርሱም ከሶርያውያን ኋላ ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ፤ በየመንገዱም ሁሉ ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለው የሄዱትን ብዙ ልብስና መሣሪያ ሁሉ አገኙ፡፡ መልእክተኞቹም ተመልሰው ለንጉሡ ነገሩት፡፡16ሕዝቡ ሄደው የሶርያውያንን ሰፈር ዘረፉ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ከዚህ በፊት እንደተናገረው ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም አምስት ኪሎ የገብስ ዱቄት በአንድ ብር ተሸመተ፡፡ 17ንጉሡም የከተማዪቱ ቅጥር በር በባለሥልጣኑ ኃላፊነት እንዲጠበቅ አድርጎ ነበር፤ ነገር ግን ያንን አገልጋይ ሕዝቡ ረጋጦት በዚያው ሞተ፡፡ ይህም የሆነው ንጉሡ የእግዚአብሔርን ሰው ለማነጋገር በሄደ ጊዜ የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ነበር፡፡18ስለዚህም የእግዚአብሔር ሰው ለንጉሡ፣ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ከተማ በር ሦስት ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ብር ይሸመታል ብሎት ነበር፡፡ 19በዚያም ባለሥልጣኑ ለእግዚአብሔር ሰው እንዲህ ሲል መልሶ ነበር፡- እግዚአብሔር የሰማይ መስኮቶችን እንኳ ቢከፍት ይህ እንዴት ይሆናል? ኤልሳዕም፡- ይህ ሲሆን በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤ ነገር ግን ከዚህ ምንም አትበላም ብሎት ነበር፡፡ 20እንግዲህ ያ የንጉሡ ባለሥልጣን በሰማርያ ከተማ ቅጥር በር ላይ ሕዝብ ረጋግጦት ለመሞት የበቃው ይህ ትንቢት ስለ ተፈጸመበት ነው፡፡
1ኤልሳዕም ልጅዋን ከሞት ያስነሣላትን፣ በሱነም የነበረችውን ሴት አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፡- እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቆይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተ ሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ፡፡ 2ስለዚህም የኤልሳዕን ምክር ሰምታ ከነቤተ ሰብዋ ወደ ፍልስጥኤም አገር በመሰደድ እስከ ሰባት ዓመት ቆየች፡፡3ሴቲቱም ከሰባቱ የራብ ዓመቶች ፍፃሜ በኋላ ከፍልስጥኤም አገር ተመልሳ መጣች፤ ስለ መኖሪያ ቤትዋና ስለ እርሻ መሬትዋ ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ሄደች፡፡ 4ንጉሡም ከእግዚአብሔር ሰው አገልጋይ ከግያዝ ጋር፡- «ኤልሳዕ ስላደረጋቸው ታላላቅ ነገሮች ንገረኝ» እያለ ይነጋገር ነበር፡፡5ግያዝም ኤልሳዕ እንዴት የሞተውን ሕፃን እንዳስነሣው ለንጉሡ እየነገረ እያለ ኤልሳዕ ሕፃኑን ከሞተ ያስነሣላት ሴት ንጉሡን ስለ መኖሪያ ቤትዋና ስለ እርሻ መሬቷ ለመጠየቅ መጣች፡፡ ግያዝም እንዲህ አለ፡- «ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሴቲዮዋ እነሆ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣው ልጅዋም ይሄ ነው!» 6ንጉሡም ሴቲቱን ስለ ሕፃኑ በጠየቃት ጊዜ በሚገባ አስረዳችው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ አንዱን ባለሥልጣን ስለ እርስዋ እንዲህ ሲል አዘዘ፡- የእርስዋ የሆነውን ማናቸውንም ነገርና የእርሻ መሬትዋን ከሰባት ዓመት ጀምሮ አገሩን ከለቀቀችበት እስካሁን ያለውን ሰብል ጭምር እንዲመልስላት አዘዘው፡፡7የሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ በታመመ ጊዜ ኤልሳዕ ወደ ደማስቆ ሄደ፡፡ ንጉሡም የእግዚአብሔር ሰው መምጣቱን ሰማ፡፡ 8ንጉሡም አዛሄልን፡- «በእጅህ አንድ ስጦታ ይዘህ ወደ እግዚአብሔር ሰው ሂድና ከዚህ ሕመም እድናለሁን? ብለህ ጠይቅ አለው፡፡ 9ስለዚህ አዛሄል በደማስቆ ከሚገኘው ምርጥ የምድር በረከት ሁሉ በአርባ ግመሎች ጭኖ ወደ ኤልሳዕ ሄደ፡፡ አዛሄልም መጥቶ በኤልሳዕ ፊት ቆመና፡- «ልጅህ ንጉሥ ቤን ሀዳድ ከሕመሙ ይድን እንደሆነ እንድትነግረው እጠይቅህ ዘንድ ልኮኛል» አለው፡፡10ኤልሳዕም፡- «ቤን ሀዳድን አንተ በርግጥ ትድናለህ ብለህ ንገረው፣ ነገር ግን እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤» አለው፡፡ 11ከዚያም ኤልሳዕ ፊቱን በማጥቆር ትኩር ብሎ እስኪያፍር ድረስ አዛሄልን ተመለከተው፤ የእግዚአብሔርም ሰው እንባውን ማፍሰስ ጀመረ፡፡ 12አዛሄልም፡- «ጌታዬ ስለምን ታለቅሳለህ?» ሲል ጠየቀው፡፡ ኤልሳዕም፡- «በእስራኤል ሕዝብ ላይ የምትፈፅመውን አሰቃቂ ነገር ስለማውቅ ነው፡፡ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ወጣቶቻቸውን በሰይፍ ትገድላለህ፤ ሕፃናቶቻቸውን በድንጋይ ትከሰክሳለህ፤ የእርጉዞች ሴቶችንም ሆድ ትሰነጥቃለህ» ሲል መለሰለት፡፡13አዛሄልም፡- «ይህን ታላቅ ነገር የሚያደርግ አገልጋይህ ማን ሆኖ ነው? ይህ ሰው ውሻ ብቻ ነው ሲል ጠየቀው፡፡ ኤልሳዕም፡- «አንተ የሶርያ ንጉሥ እንደምትሆን እግዚአብሔር ገልጦልኛል» ሲል መለሰለት፡፡ 14ከዚያም አዛሄል ተመልሶ ወደ ጌታው ወደ ንጉሡ መጣ፡፡ «ኤልሳዕ ምን አለህ?» ሲል ቤን ሀዳድ ጠየቀው፡፡ አዛሄልም፡- «አንተ በእርግጥ እንደምትድን ነግሮኛል» ሲል መለሰለት፡፡ 15ነገር ግን በማግስቱ አዛሄል ብርድ ልብስ ወስዶ ውሃ ውስጥ ነከረ፤ ከዚያም በቤን ሀዳድ ፊት ወረወረውና ታፍኖ ሞተ፡፡ አዛሄልም በቤን ሀዳድ ፈንታ ተተክቶ የሶርያ ንጉሥ ሆነ፡፡16የእስራኤል ንጉሥ የአክአብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት ኢዮራም በይሁዳ መንገሥ ጀመረ፡፡ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ልጅ ነበር፡፡ 17እርሱም በነገሠ ጊዜ ሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነበር፡፡ መቀመጫውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ስምንት ዓመት ነገሠ፡፡18ሚስቱም የአክዓብ ልጅ ስለነበረች የእስራኤል ነገሥታት ይፈፅሙት የነበረውን እንደ አክዓብ ቤተ ሰብ የክፋት መንገድ ተከተለ፡፡ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ሥራ ሠራ፡፡ 19ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከዘሩ መንግሥታትን እንደማያጠፋ ለአገልጋዩ ለዳዊት ተስፋ ሰጥቶት ስለ ነበር ይሁዳን ማጥፋት አልፈለገም፡፡20በኢዮራም ዘመነ መንግሥት ኤዶም በይሁዳ ላይ ዐመፀ፤ ለራሳቸውም ንጉሥ አነገሡ፡፡ 21ስለዚህም ኢዮራም ሠረገሎቹን በመላ አሰልፎ ወደ ጸዒር ዘመተ፡፡ የኤዶም ሠራዊትም ኢዮራምን በከበቡ ጊዜ፤ በሌሊት ተነሥተው የሠረገሎቹን አዛዦች አጠቁአቸው፤ ነገር ግን የኢዮራም ሠራዊት ሮጠው ወደየቤታቸው ተበታተኑ፡፡22ስለዚህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኤዶም በይሁዳ አገዛዝ ላይ አመፁ፡፡ በተመሳሳይ ጊዜም የልብና ከተማ አመፀች፡፡ 23ኢዮራም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ የነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 24ኢዮራም ሞተ፤ በዳዊት ከተማም በሚገኘው በአባቶቹ መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡ ከዚያም አካዝያስ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ ነገሠ፡፡25የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ 26አካዝያስ በነገሠ ጊዜ የሃያ ሁለት ዓመት ወጣት ነበረ፡፡ እርሱም በኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱ ጎቶልያ ተብላ የምትጥራው የእስራኤል ንጉሥ የዘንበሪ ልጅ ነበረች፡፡ 27አካዝያስ የንጉሥ አክዓብን መንገድ ተከተለ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፡፡ ምክንያቱም አካዝያስ የንጉሥ አከዓብን ልጅ ስለሚያገባ ነበር፡፡28አካዝያስም ከንጉሥ አከዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሆኖ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር ለመዋጋት ወደ ራሞት ገለዓድ ዘመተ፡፡ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቆሰሉት፡፡ 29ኢዮራምም ከሶሪያ ንጉሥ አዛሄል ጋር በሬማት በተደረገው ጦርነት የደረሰበትን ቁስሉን ለመታከም ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ተመለሰ፡፡ ስለዚህ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ የአከዓብ ልጅ ኢዮራም ስለደረሰበት ጉዳት ለመጠየቅ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ፡፡
1ነቢዩ ኤልሳዕም ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለ፡- «በገለዓድ ወደምትገኘው ወደ ሬማት ለመሄድ ተዘጋጅ፤ ይህንንም የዘይት ማሰሮ ያዝ፡፡ 2እዚያም በደረስህ ጊዜ የኢዮሳፍጥ ልጅ የናሜሲ ልጅ የሆነውን ኢዩን ፈልግ፤ እርሱንም ከጓደኞቹ በመለየት ወደ ውስጥ አስገባው፡፡ 3ይህን የወይራ ዘይት በራሱ ላይ አፍስስበትና እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ‹አንተ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን ቀብቼሃለሁ» ብለህ ንገረው አለው፡፡ ከዚያም በሩን ከፍተህ ከዚያ ስፍራ ተነሥተህ ሽሽ፤ አትዘገይም፡፡»4ስለዚህም ወጣቱ ነቢይ ወደ ሬማት ሄደ፡፡ 5እዚያም በደረሰ ጊዜ የጦር አዛዦች ተቀምጠው ነበር፡፡ ወጣቱም ነቢይ እንዲህ አለ፡- «ጌታዬ የምነግርህ መልእክት አለኝ» አለው፡፡ ኢዩም፡ «ለማናችን ነው የምትነግረው?» ሲል ጠየቀው፡፡ ወጣቱም ነቢይ፡- «የምናገረው ለአንተ ነው ጌታዬ» ሲል መለሰለት፡፡ 6ስለዚህ ኢዩ ተነሥቶ ወደ ቤት ገባ፤ ወጣቱ ነቢይም ዘይቱን በኢዩ ራስ ላይ አፈሰሰበትና እንዲህ አለው፡- «የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚናገረው ይህ ነው፡- ‹በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን ቀብቼሃለሁ፡፡7አንተም የአክዓብን የጌታህን ቤተ ሰብ መግደል አለብህ፤ በዚህም በኤልዛቤል የተገደሉትን፣ የአገልጋዮቼን የነቢያቴንና የእግዚአብሔር አገልጋዮችን ደም በሙሉ እበቀላለሁ፡፡ 8መላው የአክዓብ ቤተ ሰብና ትውልዱ ሁሉ ይጠፋሉ፤ ከእርሱ ቤተ ሰብ ወንድ የሆነውን ማንኛውንም ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አጠፋለሁ፡፡9የእስራኤል ነገሥታት በነበሩት በናባጥ ልጅ በኢዮርብአምና በአኪያ ልጅ በባኦስ ቤተሰቦች ላይ ያደርግኹትን ሁሉ በአክዓብ ቤተ ሰብ ላይ እፈፅማለሁ፡፡ 10ኤልዛቤል የመቀበር ዕድል እንኳ አታገኝም፤ የኤልዛቤልን ሬሳ በኢይዝራኤል ከተማ ውሾች ይበሉታል፤ ማንም አይቀብራትም፡፡» ከዚያም ወጣቱ ነቢይ በሩን ከፍቶ ከዚያ ክፍል ወጥቶ ሸሸ፡፡11ከዚያም ኢዩ ወደ ንጉሡ አገልጋዮች በመጣ ጊዜ አንዱ፡- «ሁሉ ነገር ሰላም ነውን? ለመሆኑ ይህ እብድ ወደ አንተ ለምን መጣ?» ሲሉ ጠየቁት፡፡ ኢዩም «ሰውየውንም ሆነ እርሱ የሚናገረውን እናንተ ታውቁታላችሁ» አላቸው፡፡ 12እነርሱም «ይህ ሐሰት ነው፡፡ አንተ ንገረን» ሲሉ መለሱለት፡፡ ኢዩም፡- «በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እግዚአብሔር ቀብቼሃለሁ»› አለኝ ሲል አስረዳቸው፡፡ 13ከዚያም እነርሱ ወዲያውኑ ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፡፡ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው «ኢዩ ንጉሥ ነው!» ሲሉ ጮኹ፡፡14በዚህ ሁኔታ የኢዮሳፍጥ ልጅ የናሜሲ ልጅ ኢዩ በንጉሥ ኢዮራም ላይ ሤራ ማካሄድ ጀመረ፡፡ ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ አዛሄል ጋር በሬማት ገለዓድና እስራኤል በሙሉ ሲከላከሉ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ በኢይዝራኤል ውስጥ በማገገም ላይ ነበር፡፡ 15ስለዚህም ኢዩ የጦር መኮንኖች «እናንተ በእርግጥ ከእኔ ጋር ከሆናችሁ በኢይዝራኤል የሚኖረውን ሕዝብ ለማስጠንቀቅ አንድ ወሬ ከሬማት ወጥቶ እንዳያመልጥ አድርጉ» አላቸው፡፡ 16ከዚህም በኋላ ኢዩ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ገሠገሠ፤ በዚህ ጊዜ ኢዮራም ገና ከቁስሉ አልዳነም ነበር፤ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም ሊጠይቀው መጥቶ በዚያ ነበር፡፡17በኢይዝራኤል ከተማ መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ጠባቂ ኢዩና ተከታዩ ጭፍራ ሲመጡ ከሩቅ አይቶ «ሰዎች እየጋለቡ በቡድን ሲመጡ አያለሁ!» አለ፡፡ ኢዮራምም «አንድ ፈረሰኛ ልከህ የሚመጡትን ሰዎች ሰላም ነውን? ብሎ እንዲጠይቅ አድርግ» አለው፡፡ 18መልእክተኛውም ጋልቦ ሄዶ ኢዩን፡- «ንጉሡ አመጣጥህ በሰላም ነውን?» ይልሃል ሲል ጠየቀው፡፡ ኢዩም፣ «አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ!» ሲል መለሰለት፡፡ ከዚያም ጠባቂው፡- «መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም» ሲል ለንጉሡ ነገረው፡፡19ሌላም መልእክተኛ ተልኮ ያንኑ ተመሳሳይ ጥያቄ ለኢዩ አቀረበለት፡፡ ኢዩም፡- «አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ!» ሲል መለሰለት፡፡ 20ጠባቂውም እንደገና፡- «እርሱ ተገናኝቶአል ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም» አለ፡፡ ‹ምክንያቱም የሠረገላ አነዳዱ እንደ እብድ ሰው እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ ነው! ልክ ኢዩን ይመስላል!» ሲል ተናገረ፡፡21ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም፡- «ሠረገላ አዘጋጁልኝ» አለ፡፡ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት ኢዮራም የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላችው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፡፡ እነርሱም ኢዩን የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት፡፡ 22ኢዮራምም፡- «ኢዩ ሆይ አመጣጥህ በሰላም ነውን?» ሲል ጠየቀ፡፡ ኢዩም፡- «የእናትህ የኤልዛቤል የአመንዝራይቱ ጣዖትና ጥንቆላ ሥራ በዝቶ እያለ ምን ሰላም አለ?» ሲል መለሰለት፡፡23በመሆኑም ኢዮራም፡- «አካዝያስ ሆይ! ይህ ክሕደት ነው!» እያለ ሠረገላውን መልሶ ሸሸ፡፡ 24ኢዩ ቀስቱን ስቦ ባለው ኀይል ሁሉ ፍላጻውን ባስፈነጠረ ጊዜ ኢዮራምን ወግቶ በትከሻዎቹ መካከል ወደ ልቡ ዘለቀ፤ ኢዮራምም ሞቶ በሠረገላው ውስጥ ወደቀ፡፡25ኢዩም ቢድቃር ተብሎ የሚጠራውን የጦር አዛዥ «ሬሳውን አንሥተህ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ ወርውረህ ጣለው አለው፡፡ እኔና አንተ የንጉሥ ኢዮራም አባት ከነበረው ከአክዓብ በስተኋላ እየጋለብን ስንሄድ እግዚአብሔር በአክዓብ ላይ የተናገረውን ቃል አስታውስ፡፡ 26‹ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ› የሚል ነበር፡፡» ስለዚህ ኢዩ «እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈፀም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው» ሲል የጦር አዛዡን አዘዘው፡፡27የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ይህን ባየ ጊዜ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ቤት ሀጋን ከተማ ሸሸ፡፡ ኢዩ ተከታትሎ እያሳደደው «እርሱንም ደግሞ በሠረገላው ውስጥ ግደሉት» አለ፡፡ እነርሱም ተከታትለው በኢዮርብዓም ከተማ አጠገብ በጉር በሠረገላው ሳለ ወጉት፤ አካዝያስም ወደ መጊዶ ከተማ ሸሸ፤ በዚያም ሞተ፡፡ 28አገልጋዮቹም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው በዳዊት ከተማ በሚገኘው በአባቶቹ መካነ መቃብር ቀበሩት፡፡29አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ የሆነው የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በዐሥራ አንደኛው ዓመት ነበር፡፡30ኢዩም ወደ ኢይዝራኤል በደረሰ ጊዜ፣ ኤልዛቤል ይህን ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በመስኮት ትመለከት ነበር፡፡ 31ኢዩም የቅጥሩን በር አልፎ ሲገባ «አንተ ዘምሪ! አንተ የጌታህ ገዳይ፣ እዚህ ደግሞ የመጣሃው በሰላም ነውን?» አለችው፡፡ 32ኢዩ ቀና ብሎ ወደ ላይ በመመልከት፡- «ከእኔ ጋር የሚተባበር ማን ነው?» አለ፡፡ ቁጥራቸው ሁለት ወይም ሦስት የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በመስኮት ወደ እርሱ ተመለከቱ፡፡33ኢዩም «ኤልዛቤልን ወደ ታች ወርውሯት!» አላቸው፡፡ እነርሱም አንሥተው በወረወሯት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ ኢዩም ሬሳዋን በፈረስና ሠረገላው ረጋገጠ፡፡ 34ኢዩም ወደ ቤተ መንግሥቱ ገብቶ ተመገበ፤ ጠጣም፡፡ ከዚያም «የንጉሥ ልጅ ነችና ያችን የተረገመች ሴት ቅበሩአት» አለ፡፡35ሊቀብሩዋት የሄዱ ሰዎች ግን ከራስ ቅልዋ፣ ከእግሮችዋና ከእጆችዋ መዳፍ በቀር ምንም አላገኙም፡፡ 36ይህንንም ለኢዩ በነገሩት ጊዜ ኢዩ እንዲህ አለ፤ «ይህ ሁሉ የተፈፀመው እግዚአብሔር በአገልጋዩ በቴስቢያዊው በኤልያስ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው፤ ይኸውም ‹የኤልዛቤልን ሬሳ በኢይዝራኤል ውሾች ይበሉታል፡፡ 37ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርሷነቷን ለየቶ በማወቅ፡- ይህች ኤልዛቤል ናት ሊል አይችልም፡፡»
1በዚህ ጊዜ የአክዓብ ሰባ ትውልድ በሰማርያ ይገኝ ነበር፡፡ ኢዩ ደብዳቤ ጽፎ አንዳንድ ቅጂ ለከተማዪቱ ገዢዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የአክዓብ ትውልድ ጠባቂዎች ሁሉ ላከ፡፡ ደብዳቤውም እንዲህ ይላል፡- 2«እናንተ ለንጉሡ ትውልድ፣ ፈረሶችና ሠረገሎች የጦር መሣሪያዎችና የተመሸጉ ከተሞች በእናንተ በእጃችሁ ለሚገኙ ሁሉ ኃላፊዎች ናችሁ፡፡ እንግዲህ ይህ ደብዳቤ እንደ ደረሳችሁ ወዲያውኑ፡- 3ከንጉሡ ትውልድ የተሻለውን አንዱን መርጣችሁ በአባቱ ዙፋን አንግሡት፤ ለእርሱም ለሥርወ መንግሥቱ ተዋጉለት!» የሚል ነበር፡፡4ነገር ግን እነርሱም በፍርሃት ተሸብረው «ንጉሥ ኢዮራምና ንጉሥ አካዝያስ ሊቋቋሙት ያልቻሉትን እኛ እንዴት ኢዩን ልንቋቋመው እንችላለን?» አሉ፡፡ 5ስለዚህም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊና የከተማዪቱ ገዢ ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና ከአሳዳጊ ሞግዚቶች ጋር በመተባበር ለኢዩ «እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ አንተ የምታዘንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ አንተ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ» ሲሉ መልእክት ላኩ፡፡6ኢዩም፡- «እናንተ ከእኔ ጋር ከተባበራችሁና ትእዛዜንም ለመፈፀም ዝግጁዎች ከሆናችሁ ነገ በዚህ ጊዜ የንጉሥ አክዓብን ዘሮች ሁሉ ራሶቻቸውን ቆርጣችሁ ወደ ኢይዝራኤል ይዛችሁልኝ እንድትመ›ጡ› ሲል ሌላ ደብዳቤ ጻፈላቸው፡፡ ሰባውም የንጉሥ አክዓብ ትውልድ በታወቁ የአገር ሽማግሌዎች ጥበቃ ሥር ነበሩ፡፡ 7የኢዩ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው የሰማርያ መሪዎች ሰባውንም የአክዓብ ተወላጆች በሙሉ ገደሉ፤ ራሶቻቸውንም በመቁረጥ በቅርጫት ሞልተው በኢይዝራኤል ወደ ነበረው ወደ ኢዩ ላኩለት፡፡8ኢዩም የአክዓብ ትውልድ ራሶች ተቆርጠው መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በከተማይቱ ቅጥር በር በሁለት ረድፍ ተከምረው እስከ ተከታዩ ቀን ጠዋት ድረስ እንዲቆዩ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ 9በማግስቱ ማለዳ ላይ ኢዩ ወደ ከተማይቱ ቅጥር በር ሄዶ በዚያ ለተሰበሰቡት ሕዝብ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ «በንጉሥ ኢዮራም ላይ በማሤር የገደልኩት እኔ ነበርኩ፤ ስለዚህም እናንተ በዚያ ጉዳይ አትጠየቁበትም፤ ነገር ግን እነዚህን ሁሉ የገደለ ማነው?10ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ስለ አክዓብ ትውልድ የተናገረው ቃል እውነት መሆኑን ያስረዳል፤ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት የተናገረውን ቃል ፈፅሞታል፡፡» 11ከዚህም በኋላ ኢዩ በኢይዝራኤል የሚኖሩትን ሌሎቹን የአክዓብን ዘመዶችና ባለሥልጣናት የነበሩትን እንዲሁም የቅርብ ወዳጆቹንና ካህናቱን አንድም ሳይቀር ሁሉንም ገደለ፡፡12ኢዩ ከኢይዝራኤል ተነሥቶ ወደ ሰማርያ ሄደ፤ በመንገድ ሳለም «የእረኞች ሰፈር» ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲደርስ፡- 13ከሟቹ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ዘመዶች መካከል ጥቂቶቹን አግኝቶ «እናንተ እነማን ናችሁ?» ሲል ጠየቀ፡፡ እነርሱም ‹እኛ የአካዝያስ ዘመዶች ነን፤ አሁንም የንግሥት ኤልዛቤልን ልጆችና የቀሩትንም ንጉሣውያን ቤተ ሰብ እጅ ለመንሣት ወደ ኢይዝራኤል መሄዳችን ነው» ሲሉ መለሱለት፡፡ 14ኢዩም «እነዚህን ሰዎች ከነሕይወታቸው ያዙአቸው!» ሲል ለጭፍሮቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ ጭፍሮቹም ያዙአቸው፤ ኢዩም በዚያው በቤት ኤክድ አጠገብ ገደላቸው፡፡ ብዛታቸውም በሙሉ አርባ ሁለት ሲሆን ከእነርሱ አንድ እንኳ በሕይወት አልተረፈም፡፡15ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ «የእኔ ልብ ከአንተ ጋር እንደ ሆነ የአንተ ልብ ከእኔ ጋር ነውን?» ሲል ጠየቀው፡፡ ኢዮናዳብም «አዎን ከአንተ ጋር ነው» ሲል መለሰለት፡፡ ኢዩም «እንግዲያውስ ጨብጠኝ» ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠው፡፡ 16«ከእኔ ጋር ሆነህ እኔ ለእግዚአብሔር ምን ያህል ታማኝ እንደ ሆንኩ ራስህ ተመልከት» አለው፤ አብረውም እየጋለቡ ወደ ሰማርያ ሄዱ፡፡ 17ወደ ሰማርያ በደረሱ ጊዜ ኢዩ አንድም ሳያስቀር በሰማርያ ያሉትን የአክዓብን ዘመዶች በሙሉ ፈጀ፤ ይህም ሁሉ የሆነው እግዚአብሔር በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት ነበር፡፡18ከዚያም ኢዩ የሰማርያን ሕዝብ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ «ንጉሥ አክዓብ ባዓልን ያገለገለው በመጠኑ ነበር፤ እኔ ግን ከእርሱ ይበልጥ ላገለግለው እፈልጋለሁ፤ 19ስለዚህም የባዓልን ነቢያት በሙሉ ባዓልን የሚያመልኩትንና ካህናቱን ጭምር በአንድነት ጠርታችሁ ሰብስቡልኝ፤ በምንም ምክንያት የሚቀር አይኑር፤ እኔ ለባዓል ታላቅ መሥዋዕት ስለማቀርብ በዚያ የማይገኝ ማንም ሰው ቢኖር በሕይወት አይኖርም፡፡» ይህም ሁሉ ባዓልን የሚያመልኩትን ሁሉ ለመግደል ኢዩ ያቀደው የተንኮል ዘዴ ነበር፡፡ 20ከዚህም በኋላ ኢዩ «ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት ክብረ በዓል ይደረግ!» ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ይህም በዐዋጅ ተነገረ፡፡21ኢዩም በእስራኤል ምድርና ባዓልን ለሚያመልኩ ሁሉ መልእክት ላከ፡፡ ማንም ከጫፍ እስከ ጫፍ ሳይመጣ የቀረ አልነበረም፤ ሁሉም ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፡፡ 22ከዚያ ኢዩ የተቀደሱ አልባሳት ኀላፊ የሆነው ካህን አልባሳትን ሁሉ አውጥቶ ለባዓል አምላኪዎች እንዲያመጣላቸው አዘዘ፡፡ እንደታዘዘውም አልባሳቱን አመጣላቸው፡፡23ስለዚህም ኢዩ ራሱ ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ጋር አብሮ ወደ ባዓል ቤተ መቅደሱ ገባ፤ በዚያም ለሕዝቡ በዚህ የሚገኙት የባዓል አምላኪዎች ብቻ መሆናቸውንና እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንድም አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ ሲል ተናገረ፡፡ 24ከዚያም እርሱና ኢዮናዳብ ለባዓል ልዩ ልዩ መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ለማቅረብ ሄዱ፡፡ ኢዩም በባዓል ቤተ መቅደሱ ዙሪያ ሰማኒያ ወታደሮች በማሰለፍ እነዚህን ሁሉ ሰዎች እንድትገድሉ፣ ከእነርሱ አንድ እንኳ የሚያመልጥ ሰው ቢኖር በዚያ ሰው ምትክ እርሱ ራሱ ይገደላል ሲል መመሪያ ሰጥቶአቸው ነበር፡፡25ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለጠባቂዎችና ለአዛዡ፡- ሂዱና ማንም ሰው እንዳያመልጥ ግደሉአቸው አለ፡፡ እነርሱም በሰይፍ ስለት ሁሉንም ገደሉአቸው፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጎተቱ ወደ ውጪ ጣሉ፤ ጠባቂና የጦር አዛዦቹ ወደ ባዓል ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገቡ፡፡ 26ከዚያም በባዓል ቤተ መቅደስ የነበረውን የድንጋይ ዐምዶች ወደ ውጪ አውጥተው በእሳት አቃጠሉት። 27ከዚያም የባዓል አምላኪዎቹን አጸድ አፍርሰው የባዓልን ቤተ መቅደስ አጠፉ፤ እስከዛሬ ድረስ ቤተ መቅደሱንም መጸዳጃ እንዲሆን አደረጉት፡፡ 28ኢዩ በእስራኤል የነበረውን የባዓልን አምልኮ ያስወገደው በዚህ ዓይነት ነበር፡፡29ነገር ግን ኢዩ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን፣ በቤተልና በዳን፣ የወርቅ ጥጃ የጣዖት ማምለኪያ ምስል ያቆመበትን የኃጢአት መንገድ አልተከተልም፡፡ 30ስለዚህም እግዚአብሔር ኢዩን፡- በአክዓብ ትውልድ ሁሉ ላይ ልታደርግ የሚገባህን በዐይኖቼ ፊት ትክክል የሆነውን ፈጽመሃል፤ ከዚህም የተነሣ የአንተ ትውልድ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ላይ እንደሚነግሡ የተስፋ ቃል እስጥሃለሁ አለው፡፡ 31ኢዩ ግን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ እርሱም እስራኤልን ወደ ኃጢአት ከመራበት ከኢዮርብዓም ኃጢአት አልተመለሰም፡፡32በዚያም ዘመን እግዚብሔር የእስራኤልን ግዛት እንዲቀነስ አደረገ፤ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል እስራኤልን ድል ነሥቶ የእስራኤልን ግዛት ድንበሮች ያዘ፡፡ 33እርሱም የያዘው ግዛት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ በስተ ደቡብ በኩል ከአርኖን ወንዝ በላይ እስከምትገኘው እስከ አሮዔር ከተማ የሚደርስ ሲሆን ይህም የጋድ የቶቤልና በምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኖሩባቸው የነበሩትን ሸለቆ የገለዓድንና የባሳንን ግዛቶች ያጠቃልላል፡፡34ኢዩ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 35ከዚህም በኋላ ኢዩ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኢዮአካዝ ነገሠ፡፡ 36ኢዩም በሰማርያ እስራኤልን ለሃያ ስምንት ዓመት ገዛ፡፡
1የንጉሥ አካዝያስ እናት ጎቶልያ የልጅዋን መገደል እንደ ሰማች ተነሥታ የንጉሣውኑን ቤተ ሰብ አባላት በሙሉ ገደለች፡፡ 2ከእርስዋም እጅ ማምለጥ የቻለ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ ብቻ ነበር፤ ነገር ግን አክስቱ የነበረችው በአባትዋ በኩል የንጉሥ አካዝያስ እኅት የንጉሥ ኢዮራም ልጅ ዮሳቤት ከሞቱት ከንጉሥ ልጆች መካከል ወስዳ በመደበቅ ከሞት አዳነችው፤ እርሰዋም ሞግዚቱን ወስዳ በቤትዋ መኝታ ክፍል ውስጥ ስለደበቀችው በጎቶልያ እጅ ሳይገደል ቀረ፡፡ 3ጎቶልያ በነገሠችበት ስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ዮሳቤት ሕፃኑን ኢዮአስን በመደበቅ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመንከባከብ አሳደገችው፡፡4ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ለንጉሡ ክብር ዘቦችና ለቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ሁሉ ኃላፊ ወደሆኑት የጦር አዛዦች ሁሉ ልኮ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አስጠራቸው፤ በዚያም ሊያደርገው ያቀደውን ይስማሙበት ዘንድ በመሐላ እንዲያረጋግጡለት አደረገ፤ ከዚያም በኋላ የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን አሳያቸው፡፡ 5የሚከተለውንም ትእዛዝ ሰጣቸው፤ በሰንበት ቀን ለጥበቃ በምትሰማሩበት ጊዜ ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤ 6ሌላው አንድ ሦስተኛ እጅ የሱርን የቅጥር በር ይጠብቅ፤ የቀረው አንድ ሦስተኛ እጅ ደግሞ ከሌሎቹ ጥበቃዎች በስተኋላ ያለውን ቅጥር በር ይጠብቅ፡፡7በሰንበት ቀን ከጥበቃ ነጻ የሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ንጉሡን ለመከላከል ቤተ መቅደሱን ይጠብቁ፤ 8ንጉሥ ኢዮአስን በዙሪያው በምትጠብቁበትም ጊዜ ሰይፋችሁን መዛችሁ ወደሚሄድበት ስፍራ ሁሉ አብራችሁ ሂዱ፤ ወደ እናንተ ለመቅረብ የሚደፍር ማንም ቢኖር ይገደል፡፡ ንጉሡ ሲወጣና ሲገባ ከእርሱ አትለዩ፡፡9የጦር አዛዦቹም ካህኑ ዮዳሄ የሰጠውን መመሪያ በመቀበል በሰንበት ቀን ለጥበቃ የሚሰማሩትንና ከጥበቃም የሚወጡትን ጭፍሮቻቸውን ጭምር አሰልፈው ወደ ካህኑ ዮዳሄ አመጡ፡፡ 10ዮዳሄም በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የንጉሥ ዳዊት ጦሮችና ጋሻዎች አውጥቶ ለጦር አለቆቹ ሰጣቸው፡፡11ጭፍሮቹም ሰይፋቸውን እንደ መዘዙ ንጉሡን ከበው በቤተ መቅደሱ በቀኝና በግራ በመሠዊያው አጠገብ እንዲቆሙ አደረጋቸው፡፡ 12ከዚያም ዮዳሄ ኢዮአስን አቅርቦ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነለት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጂ አስረከበው፤ በዚህ ዓይነት ኢዮአስ ተቀብቶ ነገሠ፡፡ ሕዝቡም በእጃቸው እያጨበጨቡ፣ ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ አሉ፡፡13ንግሥት ጎቶልያ የክብር ዘቦቹንና የሕዝቡን ጩኸት ድምፅ በሰማች ጊዜ ሕዝቡ ወደተሰበሰበበት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መጣች፡፡ 14እዚያ እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባሕል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየቸው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ጎቶልያ በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው ስትል ጮኸች፡፡15ዮዳሄም የጦር አለቆችን ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል ጎቶልያን አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርስዋን ለመከተል የሚሞክር ቢኖር ይገደል ሲል አዘዛቸው፡፡ 16እነርሱም እርስዋን አፈፍ አድርገው በመያዝ ወደ ቤተ መንግሥት ወሰዱአት፤ እዚያ የፈረስ መግቢያ ቅጥር በር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ገደሉአት፡፡17ዮዳሄ፣ ንጉሡና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ከእግዘአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፤ እንዲሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ፡፡ 18ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ሄዶ አፈራረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበረ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የባዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት፡፡ ዮዳሄም ቤተ መቅደሱን በየተራ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ፤19ከዚህም በኋላ እርሱ፣ የጦር አለቆች፣ የንጉሡ የክብር ዘብና የቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ንጉሡን ከቤተ መቅደስ እስከ ቤተ መንግሥት አጅበው እንዲሄዱና ሕዝቡም ሁሉ ከኋላ እንዲከተል አደረገ፤ ኢዮአስም በዘብ ጠባቂዎች ቅጥር በር በኩል ገብቶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፡፡ 20ጎቶልያ በቤተ መንግሥት በሰይፍ ስለ ተገደለች ሰው ሁሉ ተደሰተ፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች፡፡21ኢዮአስም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር፡፡
1ኢዩ በእስራኤል በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም በኢየሩሳሌም አርባ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ሳብያ ተብላ የምትጠራ የቤርሳቤህ ከተማ ተወላጅ ነበረች፡፡ 2ካህኑም ዮዳሄ ይመክረውና ያስተምረው ስለ ነበር፣ ኢዮአስ በዕድሜው ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡ 3ነገር ግን በየኮረብታዎቹ ላይ የሚገኙት የአሕዛብ ማምለኪያዎች ስላልተደመሰሱ ሕዝቡ በዚያ ዕጣን እያጠኑ መሥዋዕት ማቅረባቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፡፡4ኢዮአስም ካህናትን ጠርቶ በቤተ መቅደስ ከሚቀርበው መሥዋዕት ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ መባ ሆኖ የሚገባውን ገንዘብ ሁሉ በጥንቃቄ እንዲጠብቁ አዘዘ፤ ይኸውም ቋሚ ከሆነው ከዘወትር መሥዋዕት ጋር መባ ሆኖ የሚቀርበውንና በበጎ ፈቃድ ሕዝቡ የሚያመጣውን ስጦታ ሁሉ የሚያጠቃልል ነበር፡፡ 5እያንዳንዱ ካህን ከሚያገለግላቸው ሰዎች የሚገኘውን የገንዘብ መባ ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጠው፡፡ ገንዘቡንም እንዳስፈላጊነቱ ለቤተ መቅደሱ ጥገና አገልግሎት እንዲያውሉት ነገራቸው፡፡6ነገር ግን ኢዮአስ እስከ ነገሠበት እስከ ሃያ ሦስተኛው ዓመት ድረስ ካህናቱ በቤተ መቅደሱ ላይ ምንም ዓይነት እድሳት አላደረጉም፡፡ 7ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ አላቸው፡፡ 8ካናቱም በዚህ ተስማምተው ቤተ መቅደሱን በራሳቸው ለማደስ የነበራቸውን ተግባር አቆሙ፡፡9በዚህ ፈንታ ዮዳሄ አንድ ሣጥን ወስዶ በመክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀ፤ ሣጥኑንም ወስዶ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ በስተ ቀኝ በሚገኘው መሠዊያ አጠገብ አኖረው፤ የየዕለቱ ተረኞች የነበሩትም ካህናት ለአምልኮ የሚመጡት ሰዎች የሚሰጡትን የገንዘብ መባ እየተቀበሉ በሣጥኑ ውስጥ ያስገቡት ነበር፡፡ 10ሣጥኑም በሚሞላበት ጊዜ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ እየመጡ ገንዘቡን በመቁጠር በከረጢት እያሰሩ ያኖሩት ነበር፡፡11ትክክለኛውን ሒሳብ አጣርተው ከመዘገቡ በኋላ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ሥራ ኃላፊዎች ያስረክቡ ነበር፤ እነርሱም ገንዘቡን ተረክበው ለአናጢዎችና ለግንበኞች ይሰጡ ነበር፡፡ 12ለድንጋይ ጠራቢዎች፣ ለማደሻ አገልግሎት የሚውል እንጨትና ድንጋይ ለሚገዙና እንዲሁም ለልዩ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች ለሚውል ተግባር ሁሉ ይከፍሉ ነበር፡፡13ነገር ግን ከብር ለሚሠሩ ጎድጓዳ ሳሕኖች የዐመድ ማጠራቀሚያ ጎድጓዳ ወጭት፣፣ እምቢልታ ወይም ደግሞ ከብርና ከወርቅ ለሚሠሩ ንዋያተ ቅዱሳት ከዚያ ገንዘብ ላይ ተነሥቶ የሚከፈል ሒሳብ አልነበረም፡፡ 14ያ ገንዘብ በሙሉ በቤተ መቅደሱ እድሳት ተግባር ላይ ለተሰማሩት ሠራተኞች ብቻ የሚውል ነበር፡፡15ለሥራው ኃላፊነት የተመረጡትም ሰዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ነበሩ ገንዘቡን የሰጡአቸው ሰዎች አይቆጣጠሩአቸውም ነበር፡፡ 16ስለ በደልና ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚከፈለው ገንዘብ ግን ለካህናቱ ጥቅም የሚውል እንጂ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጥ አይገባም ነበር፡፡17በዚያ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል በጌት ከተማ ላይ አደጋ ጥሎ ያዛት፤ ቀጥሎም በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ተመለሰ፡፡ 18የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስም ከእርሱ በፊት የነበሩትን ነገሥታት ማለትም ኢዮሳፍ፣ ኢዮራምና አካዝያስ ለእግዚአብሔር ለይተው ያኖሩትን መባና የራሱን መባ ጨምሮ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ግምጃ ቤቶች የነበረውን ወርቅ ሁሉ በመሰብሰብ ገጸ በረከት አድርጎ ለንጉሥ አዛሄል ላከለት፡፡ ሐዛሄልም ይህን ተቀብሎ ሠራዊቱን ከኢየሩሳሌም መለሰ፡፡19ንጉሥ ኢዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን? 20ከዚህ በኋላ የንጉሥ ኢዮአስ ባለሥልጣኖች አንድ ላይ ተነሥተው አድመውበት ወደ ሲላ ሲሄድ በሚሎ ጥቃት አደረሱበት፡፡ 21የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ኢዮአስን ገደሉት፡፡ በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ፡፡
1የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት የኢዩ ልጅ ኢዮአካዝ በሰማርያ ለዐሥራ ሰባት ዓመት ለመግዛት የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ 2እርሱም ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ናባጥ ልጅ ንጉሥ ኢዮርብዓም ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠራ፡፡ ከክፉ ሥራውም ከቶ አልራቀም፡፡3ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ ተቆጥቶ ለሶርያ ንጉሥ አዛሄል፣ እንዲሁም ለልጁ ለቤን ሀዳድ በተደጋጋሚ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል፡፡ 4ከዚህ በኋላ ኢዮአካዝ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ የፈጸመባቸው ግፍ እጅግ ከባድ መሆኑን ተመልክቶ የኢዮአካዝን ጸሎት ሰማ፡፡ 5ስለዚህም እግዚአብሔር እስራኤልን ከሶርያውያን እጅ ነጻ የሚያወጣቸውን መሪ ላከላቸው፤ እነርሱም ከዚያ በፊት በነበረው ዓይነት በሰላም ኖሩ፡፡6ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ኢዮርብዓም እስራኤልን ወደ ኃጢአት ከመራበት ከክፉ ሥራቸው አልተመለሱም፤ እስካሁንም አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስል በሰማርያ ማምለክ ቀጠሉ፡፡ 7ንጉሥ ኢዮአካዝ ከኀምሳ ፈረሰኞች፣ ከዐሥር ሰረገሎችና ከዐሥር ሺህ ወታደሮች በቀር ሌላ የተደራጀ የጦር ኃይል አልነበረውም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሠራዊቱን የሶርያ ንጉሥ በአውድማ እንዳለ እብቅ አድርጎ ስለ ደመሰሰበት ነው፡፡8ንጉሥ ኢዮአካዝ የፈጸመው ሌላው ተግባርና የጀግንነት ሥራው ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 9ኢዮአካዝም ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ዮአስ ነገሠ፡፡10የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስ በነገሠ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በሰማርያ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ በዚያም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፡፡ 11እርሱም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ ምሳሌነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡12ዮአስ የፈጸመው ሌላው ነገር ሁሉ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ ላይ ባደረገው ጦርነት የፈጸመው ጀግንነት ጭምር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 13ከዚህ በኋላ ዮአስ ሞተ፤ በሰማርያም በሚገኘው መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ነገሠ፡፡14ነቢዩ ኤልሳዕ በብርቱ ደዌ ታሞ ነበር፤ ተኝቶም ሊሞት በሚያጣጥርበት ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ሄዶ፣ ድምፁን ከፍ በማድረግ «አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! አንተ እኮ የእስራኤል ሕዝብ ኀይላቸውና ጋሻ መከታቸው ነህ!» እያለ አለቀሰለት፡፡ 15ኤልሳዕም ንጉሡን «አንድ ቀስትና ፍላጻዎች ውሰድ» ሲል አዘዘው፤ ዮአስም እንደታዘዘው አደረገ ኤልሳዕም 16ለማስፈንጠር ተዘጋጅ» አለው፤ ንጉሡም እንደታዘዘው አደረገ፤ ኤልሳዕም እጆቹን በንጉሡ እጆች ላይ አኖረ፡፡17ኤልሳዕ «የምሥራቁን መስኮት ክፈት» አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም «ፍላጻውን አስፈንጥር!» አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፣ «ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ፡፡» 18ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ንጉሡን «ሌሎቹንም ፍላጻዎች አንሥተህ በእነርሱ ምድርን ምታ!» አለው፡፡ ንጉሡም ምድርን ሦስት ጊዜ መትቶ አቆመ፡፡ 19ይህም ኤልሳዕን አስቆጣው፤ ስለዚህም ንጉሡን «አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መተህ ቢሆን ኖሮ በሶርያውያን ላይ ፍጹም ድልን ትቀዳጅ ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ድል ትነሣቸዋለህ» አለው፡፡20ኤልሳዕም ሞተ፤ ተቀበረም፡፡ ከሞአብ የመጡ አደጋ ጣዮች በየዓመቱ የእስራኤልን ምድር ይወጉ ነበር፡፡ 21አንድ ጊዜ የአንድ ሰው ሥርዓተ ቀብር በሚፈጸምበት ሰዓት በእነዚያ አደጋ ጣዮች መካከል አንድ ቡድን ሲመጣ ስለታየ የሚቀበረውን ሬሳ ወደ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ በችኮላ በመወርወር ጥለውት ሸሹ፤ ያም ሬሳ ከኤልሳዕ አስክሬን ጋር በተገናኘበት ቅጽበት ወዲያውኑ ከሞት ተነሥቶ ቆመ፡፡22ኢዮአካዝ በነገሠበት ዘመን ሁሉ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል እስራኤላውያንን በመውረር ያስጨንቃቸው ነበር፤ 23እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ምሕረትን በማድረግ ረዳቸው እንጂ እንዲደመሰሱ አልፈቀደም፤ ይህንን ያደረገበት ምክንያት ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን ቃል ኪዳን በማሰብ ሕዝቡን ስላልረሳው ነው፡፡ 24የሶርያ ንጉሥ አዛሄል በሞተ ጊዜ፣ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ ልጁ ቤን ሀዳድ ነገሠ፡፡ 25ከዚህም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ቤን ሀዳድን ሦስት ጊዜ ድል ነሥቶ በኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ቤን ሀዳድ ይዞአቸው የነበሩትን ከተሞች አስመለሰ፡፡
1የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በእስራኤል ላይ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ 2እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ከኢየሩሳሌም ዮዓዳን ተብላ የምትጠራ ነበረች፡፡ 3አሜስያስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቶአል፤ ይሁን እንጂ እንደ ቀድሞ አያቱ እንደ ንጉሥ ዳዊት አልነበረም፤ እንደ ዳዊት በመሆን ፈንታ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ፡፡4ይኸውም በየኮረብታዎቹ ላይ የተሠሩትን የአሕዛብ ማምለኪያዎችን አላፈረሰም፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ በየኮረብታዎቹ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጠኑን እንደቀጠለ ነበር፡፡ 5አሜስያሰ መንግሥቱን አደላድሎ እንደ ያዘ ወዲያውኑ፣ ቀደም ሲል ነግሦ የነበረውን አባቱን የገደሉትን ባለሥልጣኖች በሞት ቀጣ፤6ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ይልቁንም በኦሪት ሕግ እግዚአብሔር «ልጆቻቸው በፈጸሙት ኃጢአት ወላጆች በሞት አይቀጡበትም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ኃጢአት ልጆች በሞት አይቀጡበትም፤ እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ በሞት ይቀጣል» ሲል የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞአል፡፡ 7አሜስያስ «የጨው ሸለቆ» እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ «ዮቅትኤል» ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች፡፡8ከዚህ በኋላ አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞችን በመላክ «እንግዲህ ና ፊት ለፊት ጦርነት እንግጠም!» ሲል ለጦርነት አነሣሣው፡፡ 9ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት «አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኩርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‹ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ› ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኩርንችት ሞተች፡፡ 10አሜስያስ ሆይ! እነሆ አንተ ኤዶማውያንን ድል ስላደረግህ ልብህ በትዕቢት ተሞልቶአል፤ ባገኘኸውም ድል በመደሰት ዐርፈህ በቤትህ ብትቀመጥ ይሻልሃል፤ በአንተና በሕዝብህ ላይ መከራና ውድቀት ስለ ምን ታስከትላለህ?»11አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቆጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤት ሳሚስ ጦርነት ገጠመው፡፡ 12ይሁዳም ድል ተመታ፤ ወታደሮቹም ሁሉ ተበታትነው ወደየቤታቸው ተመለሱ፡፡13ዮአስም የአካዝያስን ልጅ፣ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ለመድረስ ገሠገሠ፤ እዚያም እንደ ደረሰ ከኤፍሬም ቅጥር በር «የማዕዘን ቅጥር በር» ተብሎ እስከሚጠራው በር ድረስ ጠቅላላ ርዝመቱ ሁለት መቶ ሜትር የሆነውን የቅጥር ግንብ አፈረሰ፡፡ 14በዚያም ያገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ፣ የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅዱሳትና የቤተ መንግሥቱን ሀብት ሁሉ ጭኖ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፤ በመያዣ ስም የተማረኩ ሰዎችንም ይዞ ሄደ፡፡15ንጉሥ ዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ በአሜስያስ ላይ ባደረገው ጦርነት የፈጸመው የጀግንነት ሥራ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 16ዮአስ ሞተ፤ በሰማርያ በሚገኘውም የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ነገሠ፡፡17የእስራኤል ንጉሥ የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ ከሞተ በኋላ፣ የይሁዳ ንጉሥ የዮአስ ልጅ አሜስያስ ዐሥራ አምስት ዓመት ቆየ፡፡ 18አሜስያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 19አሜስያስን ለመግደል በኢየሩሳሌም ሤራ ተጠንስሶ ነበር፤ ስለዚህ አሜስያስ ሸሽቶ ወደ ለኪሶ ከተማ ሄደ፤ ነገር ግን ጠላቶቹ ወደ ለኪሶ ሰዎችን ልከው እዚያ አስገደሉት፡፡20ሬሳውም በፈረስ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡ 21የይሁዳም ሕዝብ የዐሥራ ስድስት ዓመት ልጁ የነበረውን ዓዛርያስን አነገሡት፤ 22ዓዛርያስም ቀድሞ ተይዛ የነበረችውን ኤላትን ከአባቱ ሞት በኋላ በጦር ኃይል ድል ነሥቶ አስመልሶ እንደገና ሠራት፡፡23የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእስራኤል ነገሠ፤ እርሱም በሰማርያ አርባ አንድ ዓመት ገዛ፡፡ 24ዳግማዊ ኢዮርብዓምም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ ከእርሱ በፊት የነበረውን የናባጥ ልጅ የኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡ 25ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነበር፡፡26እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን አሠቃቂ መከራ ተመለከተ፤ በእስራኤል ውስጥ ባርያዎችም ሆኑ ነጻ ሰዎች ረዳት አልነበራቸውም፡፡ 27ይሁን እንጂ እነርሱ ለዘለዓለም ፈጽሞ እንዲደመሰሱ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፤ ስዚህ በዳግማዊ ኢዮርብዓም አማካይት አዳናቸው።28ዳግማዊ ኢዮርብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ፣ በጦርነት ላይ ያሳየው ጀግንነት፣ እንዲሁም የይሁዳ ግዛት የነበሩት ደማስቆና ሐማት ለእስራኤል እንዲመለሱ ያደረገበት ታሪካዊ ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 29ከዚህ በኋላ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ሞተ፤ በነገሥታት መካነ መቃብርም ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ዘካርያስ ነገሠ፡፡
1ዳግማዊ ኢዮርብዓም በእስራኤል በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ በይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ 2እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስድስት ዓመት ነበረ፤ እርሱም በኢየሩሳሌም ሃምሳ ሁለት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ይኮልያ ተብላ የምትጠራ የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች፡፡ 3እርሱም የአባቱን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡4ነገር ግን በየኮረብቶቹ ላይ የነበሩትን የአሕዛብን የማምለኪያ ቦታዎች አላጠፋቸውም ነበር፤ ስለዚህም ሕዝቡ በየኮረብቶቹ ላይ መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ 5በኋላም እግዚአብሔር ዓዛርያስን በቆዳ በሽታ መታው፤ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ይህ በሽታ ስላልለቀቀው ከሥራው ሁሉ ተገልሎ በተለየ ቤት ውስጥ ለብቻው ይኖር ነበር፤ በዚህም ጊዜ መንግሥቱን ሲመራ የቆየው ልጁ ኢዮአታም ነበር፡፡6ንጉሥ ዓዛርያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 7ዓዛርያስም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በቀድሞ አባቶቹ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ፡፡8ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዳግማዊ ኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ በእስራኤል ነገሠ፤ እርሱም በሰማርያ ስድስት ወር ገዛ፡፡ 9እርሱም ከእርሱ በፊት እንደ ነበሩት ነገሥታት ሁሉ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ እዲሁም እስራኤልን ወደ ኃጢአት መራ፤ የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት ተከተለ፡፡10ሰሎም ተብሎ የሚጠራው የኢያቤስ ልጅ ሤራ በማድረግ ይብልዓም ተብላ በምትጠራው ስፍራ ንጉሥ ዘካርያስን ገድሎ በእርሱ ፈንታ ነገሠ፡፡ 11ንጉሥ ዘካርያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 12በዚህም ዓይነት እግዚአብሔር ለንጉሥ ኢዩ ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ በእስራኤል ይነግሣሉ ሲል የተናገው የተስፋ ቃል ተፈጸመ፡፡13ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት የኢያቤስ ልጅ ሰሎም የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም በሰማርያ አንድ ወር ብቻ ገዛ፡፡ 14ምናሔ ተብሎ የሚጠራው የጋዲ ልጅ ከቲርጻ ተነሥቶ ወደ ሰማርያ ሄደ፤ የኢያቤስን ልጅ ሰሎምን ገድሎም በእርሱ ፈንታ ነገሠ፡፡15ሰሎም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ እንዲሁም እርሱ የጠነሰሰው ሤራ ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 16ምናሔም ከቲርጻ ተነሥቶ በሚያልፍበት ጊዜ የቲፍሳን ከተማ ነዋሪዎችና በዙሪያዋ የነበረውን ግዛት ሁሉ ደመሰሰ፡፡ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የከተማይቱ ነዋሪዎች ለእርሱ እጃቸውን ለመስጠት ባለመፍቀዳቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ነፍሰ ጡሮችን እንኳ ሳይምር ሆዳቸውን ቀደደ፡፡17ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት የጋዲ ልጅ ምናሔም በእስራኤል ነገሠ፡፡ እርሱም በሰማርያ ዐሥር ዓመት ገዛ፡፡ 18እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ የኢርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱም እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡19የአሦር ንጉሠ ነገሥት ፎሐ እስራኤልን ወረረ፤ ምናሔም በአገሩ መንግሥት ላይ ሥልጣኑን እንዲያጸናለትና እንዲደግፈው ለመማጠን ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር እጅ መንሻ አድርጎ ለፎሐሰጠው፡፡ 20ምናሔም ገንዘቡን የሰበሰበው የእስራኤል ከበርቴዎች እየንዳንዳቸው ኀምሳ ጥሬ ብር አዋጥተው እንዲሰጡ በማስገደድ ነበር፡፡ በዚህም ዓይነት ፎሐ በሰላም ወደ አገሩ ተመልሶ ሄደ፡፡21ምናሔም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 22ምናሔም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ፋቂስያስ ነገሠ፡፡23ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በኀምሳኛው ዓመት የምናሔም ልጅ ፋቂስያስ በእስራኤል ነገሠ፤ እርሱም በሰማርያ ሁለት ዓመት ገዛ፡፡ 24እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት ስለ ሠራ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡25በፋቂስያስ ሠራዊት መካከል ፋቁሔ ተብሎ የሚጠራው የሮሜልዩ ልጅ የሆነ አንድ የጦር አዛዥ ከኀምሳ የገለዓድ ሰዎች ጋር ሆኖ ሤራ ጠነሰሰ፤ በሰማርያ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ዘልቆ በመግባትም ፋቂስያስን ከአርጎብና ከአርዬ ጋር ገድሎ በፋቂስያስ ፈንታ ተተክቶ ነገሠ፡፡ 26ፋቂስያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡27ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በኀምሳ ሁለተኛው ዓመት የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል ነገሠ፤ እርሱም በሰማርያ ሃያ ዓመት ገዛ፡፡ 28እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት ስለ ሠራ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡29የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቴልጌልቴልፌልሶር ዒዮን፣ አቤልቤትመዓካ፣ ያኖዋ፣ ቃዴስና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች እንዲሁም የገለዓድን፣ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደው ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር፡፡ 30የዖዝያንም ልጅ ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠ በሃያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በንጉሥ ፋቁሔ ላይ ሤራ ጠነሰሰ፤ እርሱንም ገድሎ በእስራኤል ላይ ነገሠ፡፡ 31ፋቁሔ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡32የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ 33በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ዐሥራ ስድሰት ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ኢየሩሳ ተብላ የምትጠራ የሳዶቅ ልጅ ነበረች፡፡34የአባቱንም የዖዝያንን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡ 35ነገር ግን በየኮረብቶቹ ላይ የነበሩትን የአሕዛብን መሠዊያዎች አላስወገደም፤ ሕዝቡም መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ ቅጥር በር ያሠራው ይኸው ኢዮአታም ነበር፡፡ 36ኢዮአታም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 37እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በይሁዳ ላይ አደጋ እንዲጥሉባት የላካቸው ይኸው ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠበት ዘመን ነበር፡፡ 38ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብርም ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አካዝ ነገሠ፡፡
1የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ 2አካዝም በሚነግሠበት ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፡፡ እርሱም በኢየሩሳሌም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፡፡ እርሱም የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት አልተከተለም፡፡ በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ደስ የማያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡3ይልቁንም የእስራኤልን ነገሥታት መጥፎ አርአያነት ተከተለ፡፡ የራሱን ልጅ እንኳ ሳይቀር ለጣዖታት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ ይህንንም ድርጊት የእስራኤል ሕዝብ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባቱ በፊት እግዚአብሔር ከእስራኤል ምድር ያስወገዳቸውን አሕዛብ ይሠሩት የነበረውን አስጸያፊ ድርጊት በመከተል ነበር፡፡ 4አካዝ በየኮረብቶቹ ላይ በተሠሩት የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና በእያንዳንዱም ዛፍ ሥር መሥዋዕት በማቅረብ ዕጣን አጠነ፡፡5የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል መጡ፤ ከበቧትም፡፡ ነገር ግን አካዝን ድል ሊያደርጉት አልቻሉም፡፡ 6በዚያን ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የኤላትን ከተማ አስመልሶ በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ በዚያ የነበሩትን አይሁድ አስወጣ፡፡ ከዚያም በኤላት የሰፈሩት ኤዶማውያን እስከ አሁንም በዚያ ይኖራሉ፡፡7ስለዚህም ንጉሥ አካዝ ወደ አሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር «እኔ ለአንተ ታማኝ አገልጋይህ ነኝ፤ አደጋ ከጣሉብኝ ከሶርያና ከእስራኤል ነገሥታት እጅ መጥተህ እኔን አድነኝ» በማለት መልእክተኞችን ላከ፡፡ 8አካዝም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤት የተገኘውን ብርና ወርቅ ሰብስቦ ለዚሁ ለአሦር ንጉሥ ገጸ በረከት በማድረግ ላከለት፡፡ 9ከዚያም የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ዘምቶ ደማስቆን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፡፡ ንጉሥ ረአሶንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው፡፡10ንጉሥ አካዝም ከንጉሠ ነገሥት ቴልጌልቴልፌልሶር ጋር ለመገናኘት ወደ ደማስቆ ሄደ፡፡ በደማስቆም አንድ መሠዊያ አየ፡፡ ያንንም መሠዊያ በተመሳሳይ ሁኔታ መሥራት የሚያስችለውን ቅርጽ አዘጋጅቶ ለካህኑ ለኦሪያ ላከለት፡፡ 11ስለዚህ ኦሪያ ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ በላከለት ንድፍ መሠረት መሠዊያ ሠራ፡፡ 12ንጉሡም ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ መሠዊያውን ተመለከተ፤ ወደ መሠዊያው ቀርቦም መሥዋዕት አቀረበ፡፡13በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠል የእንስሶች መሥዋዕትና የእህል መባ አቀረበ፡፡ የመባውን ወይን ጠጅና የኅብረት መሥዋዕት ደም አፈሰሰበት፡፡ 14ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያ፣ በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ ያንንም መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተሰሜን በኩል አኖረው፡፡15ከዚያም ካህኑን ኦሪያን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ ይህንን የእኔን ታላቅ መሠዊያ ማለዳ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት በምሽት ለሚቀርበውም የእህል መባ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡ የሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል መባ የሚቀርብበትና የሕዝቡ የወይን ጠጅ መባ የሚፈስበት እንዲሆን አድርግ፤ የሚሠዉትንም የእንስሳት ደም ሁሉ በእርሱ ላይ አፍስስ፤ ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ግን እኔ ራሴ የምፈልገውን ነገር የምጠይቅበት እንዲሆን አድርግ፡፡ 16ካህኑም ኦሪያን ንጉሡ አካዝ እንዳዘዘው አደረገ፡፡17ንጉሥ አካዝም በቤተ መቅደስ ውስጥ መገልገያ የነበሩትን ከነሐስ የተሠሩ መንኩራኩሮች ቆርጦ ልሙጥ የሆነውን ነገር ከጎናቸው ወስደ፡፡ በእነርሱ ላይ የነበሩትንም የመታጠቢያ ሳሕኖች ወሰደ፤ ከነሐስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ከታች በኩል ተሸክመውት ከነበሩት ከነሐስ ከተሠሩት ከዐሥራ ሁለት የበሬ ቅርጾች ጀርባ ላይ አንሥቶ ከድንጋይ በተሠራ መሠረት ላይ አኖረው፡፡ 18አካዝ ከአሦር ንጉሠ ነገሥት የተነሣ በቤተ መቅደሱ የሠሩትን የሰንበት መግቢያ መንገድ ንጉሡ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በውጪው በኩል ከሚገባበት መግቢያ ጋር አስወገደው፡፡19ንጉሥ አካዝ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 20አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በአባቶቹ መካነ መቃበር ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ፡፡
1አካዝ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም በሰማርያ ዘጠኝ ዓመት እስራኤልን ገዛ፡፡ 2እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፡፡ ሆኖም እርሱ ያደረገው ኃጢአት ከእርሱ በፊት የነበሩ የእስራኤል ነገሥታት የፈጸሙት አልነበረም፡፡ 3የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር ጦርነት በገጠመው ጊዜ ተሸንፎ ሆሴዕ እጁን በመስጠት በየዓመቱ ይገብርለት ጀመር፡፡4ነገር ግን ከጥቂት ዓመቶች በኋላ ንጉሥ ሆሴዕ ሴጎር ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ግብጽ ንጉሥ መልእክተኞች በመላክ ይረዳው ዘንድ ጠየቀው፤ በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ይሰጠው የነበረውንም ግብር አቆመ፡፡ ስልምናሶር ይህን በሰማ ጊዜ ሆሴዕን አስይዞ ወህኒ ቤት አስገባው፡፡5ከዚህ በኋላ ስልምናሶር አገሪቱን ወርሮ ሰማርያን ለሦስት ዓመት ከበባት፡፡ 6ከዚያም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ስልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹን በአላሔ ከተማ፣ ጥቂቶቹን በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በአቦር ወንዝ አጠገብ፣ እንዲሁም ሌሎቹን በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፡፡7ይህም ምርኮ የሆነው እስራኤላውያን በሠሩት ኃጢአት ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ በመታደግ አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር የመራቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ኃጢአት በመሥራት በማሳዘናቸው ነበር፡፡ ሕዝቡም ባዕዳን አማልክትን አመለኩ፡፡ 8ሕዝቡም ከፊታቸው ያጠፋላቸውን የአሕዛብን መጥፎ ልማድ ተከተሉ፤ እንዲሁም የእስራኤል ነገሥታት ያሠራጩትን መጥፎ ልማድ ተቀባዮች ሆኑ፡፡9እስራኤላውያንም አምላካቸው እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ ከዘብ ጠባቂዎች ማማ አንሥቶ እስከ ትልቅ ከተማ ድረስ በገጠር ከተሞቻቸው ሁሉ በየኮረብታዎቹ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፡፡ 10በኮረብቶች ሁሉ ላይና በየዛፉ ጥላ ሥር የድንጋይ አምዶችንና አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎች አቆሙ፡፡11እግዚአብሔርም ከፊታቸው ያስወጣቸውን የአረማውያን ሕዝብ ልማድ በመከተል በአሕዛብ መሠዊያዎች ሁሉ ላይ ዕጣን አጠኑ፤ በዚህም ክፉ ሥራቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፤ 12እግዚአብሔርም እንዳያደርጉ የተናገራቸውን ጣዖታትን አመለኩ፡፡13እግዚአብሔርም እስራኤልንና ይሁዳን የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችንና ነቢያትን በመላክ፣ ከክፉ መንገዳችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ አገልጋዮቼ በሆኑት ነቢያትና ባለ ራዕዮች አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተም በሰጠሁት ሕጎችና ትእዛዞች የተጻፈውን ሥርዓቱን ጠብቁ ብሎ ነግሮአቸው ነበር፡፡14እነርሱ ግን መታዘዝ አልፈለጉም፤ በአምላካቸው በእግዚአብሔር እንዳልታመኑ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው እልከኞች ሆኑ፡፡ 15የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሰሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ ባለመስማት በዙሪያቸው የሚኖሩትን የአሕዛብ ልማድ ሁሉ ተከተሉ፡፡16የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ቸል አሉ፡፡ የሚሰግዱላቸውን ከብረት የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፡፡ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፣ ለከዋክብትም ሰገዱ፣ ባዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ፡፡ 17ለእነዚያም አሕዛብ አማልክት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፤ ከሙታን ጠሪዎችና ከጠንቋዮችም ምክር ጠየቁ፤ እግዚአብሔር ለሚጠላው ክፉ ነገር ሁሉ ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፡፡ 18ስለዚሀም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ተቆጥቶ የይሁዳን መንግሥት ብቻ በማስቀረት እስራኤላውያንን ከፊቱ አስወገደ፡፡19የይሁዳ ሰዎችም ቢሆኑ አምላካቸው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዞች አልጠበቁም ነበር፡፡ እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ የተቀበሉትን ልማድ ተከታዮች ነበሩ፡፡ 20ስለዚህም እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ሁሉ ተዋቸው፤ ከፊቱም እስኪወገዱ ድረስ ለጠላቶቻቸው አሳልፎ በመስጠት ቀጣቸው፡፡21እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከይሁዳ ከለየ በኋላ እስራኤላውያን የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምን መርጠው አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን እንዲተዉ በማድረግ አሠቃቂ ወደ ሆነ ኃጢአት መራቸው፡፡ 22በአገልጋዮቹ ነቢያት ሁሉ አማካይነት እግዚአብሔር እስራኤልን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ እስራኤላውያን የኢዮርብዓምን ኃጢአት ሲሠሩ ኖሩ እንጂ ከዚያ አልራቁም፡፡ 23ስለዚህ እስራኤላውያን ከአገራቸው ተማርከው በመወሰድ እስከ ዛሬ ድስ በአሦር ይኖራሉ፡፡24የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን ኩታ፣ ዓዋና፣ ሐማትና ሴፈርዋይ ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ፡፡ 25እነርሱም በዚያ ሰፍረው መኖር እንደ ጀመሩ እግዚአብሔርን አላመለኩትም ነበር፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አንበሶችን በመላክ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ሰባብረው እንዲገድሉ አደረገ፡፡ 26ለአሦርም ንጉሠ ነገሥት በሰማርያ ከተሞች ሰፍረው እንዲኖሩ ያደረግሃቸው ሕዝቦች የዚያችን አገር አምላክ ሕግ የሚያውቁ ሆነው አልተገኙም፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሰባብረው የሚገድሉ አንበሶችን ላከባቸው የሚል ወሬ ደረሰው፡፡27ስለዚህ ንጉሠ ነገሥቱ ማርኮ ካመጣቸው ካህናት አንዱን ወደዚያ ላኩ፤ ወደዚያ ተመልሶ በመሄድ የዚያች አገር አምላክ ያዘዘውን ሕግ ለሕዝቡ እንዲያስተምራቸው አድርጉ ሲል አዘዘ፡፡ 28ስለዚህም ከሰማርያ ተማርኮ የተወሰደ አንድ እስራኤላዊ ካህን ተመልሶ በመሄድ በቤተል ተቀመጠ፤ በዚያ ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዴት ማምለክ እንደሚገባቸው አስተማራቸው፡፡29በሰማርያ የሰፈሩት ሕዝቦች ግን የየራሳቸውን ጣዖት መሥራት ቀጥለው እስራኤላውያን ባሠሩአቸው በከፍተኛ ማምለኪያ ቦታዎች አኖሩአቸው፤ እያንዳንዱ ቡድን በሚኖርበት ከተማ ሁሉ የየራሱን ጣዖት አቆመ፡፡ 30በዚህም ዓይነት የባቢሎን ሰዎች ሱኮትበኖት በተባለው አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤ እንዲሁም የኩታ ሰዎች ኤርጌል ተብሎ በሚጠራው ባዕድ አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤ የሐማት ሕዝብ አሲማት ተብሎ በሚጠራው ባዕድ አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤ 31የዓዋ ሕዝብ ኤልባዝርና ተርታቅ ተብለው በሚጠሩ አማልክቶቻቸው ስም ጣዖቶቻቸውን ሠሩ፤ የሴፈርዋይምም ሕዝብ አድራሜሌክና ዓናሜሌክ ተብለው ለሚጠሩ አማልክቶቻቸው ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡32እነዚሁ ሰዎች በተጨማሪ ለእውነተኛው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ነበር፡፡ ከእያንዳዳቸውም ቡድን በአረማውያን የማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉና መሥዋዕት የሚያቀርቡላቸውን ካህናት መረጡ፡፡ 33በዚህ ዓይነት እግዚአብሔርን ማክበርና ማምለክ ጀመሩ፡፡ በሌላ በኩል ግን ቀድሞ ይኖሩባቸው በነበሩት ሕዝቦች ይፈጽሙት በነበረው ልማድ መሠረት ለባዕዳን አማልክት ይሰግዱ ነበር፡፡34ይህንኑ አሮጌ ልማዳቸውን እስከ አሁን ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን አያመልኩም ወይም ስሙ እስራኤል ተብሎ ለተጠራው ለያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር በሰጣቸው ደንቦች፣ ሥርዓቶች፣ ሕጎችና ትእዛዞች ጸንተው አልኖሩም፡፡ 35እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዞአቸው ነበር፡- ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ፣ ለእነርሱም አገልጋዮች በመሆን አትስገዱላቸው፣ መሥዋዕትንም አታቅርቡላቸው፡፡36በታላቅ ኃይልና በሥልጣን ከግብጽ ምድር ላወጣኋችሁ ለእኔ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤ መስገድና መሥዋዕት ማቅረብ የሚገባችሁ ለእኔ ብቻ ነው፡፡ 37ጽፌ የሰጠኋችሁንም ድንጋጌና ሥርዓቱን ሕጎችና ትእዛዞቹን ሁልጊዜ ጠብቁ፣ ባዕዳን አማልክትንም አትከተሉ፡፡ 38እኔ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ባዕዳን አማልክትንም አታምልኩ፡፡39እኔን አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፍሩ፤ እኔም ከኃይለኛው ጠላቶቻችሁ እጅ አድናችኋለሁ፡፡ 40ነገር ግን እነዚያ ሕዝቦች ይህን መስማት ትተው አሮጌ ልማዳቸውን ተከተሉ፡፡ 41እነዚያ ሕዝቦች በዚሁ ዓይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ለጣዖቶቻቸው ይሰግዱ ነበር፤ ዘሮቻቸውም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ዓይነት አምልኮ እንደ ቀጠሉ ናቸው፡፡
1የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ 2ሕዝቅያስም ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፡፡ እርሱም በኢያሩሳሌም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም አቢያ የምትባል የዘካርያስ ልጅ ነበረች፡፡ 3ሕዝቅያስም የአባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡4የአሕዛብን የማምለክያ ስፍራዎች አስወገደ፤ የድንጋይ ዐምዶችንም ሰባብሮ አጠፋ፤ ኣሼራ ተብላ በምትጠራው ሴት አምላክ ስም የተቀረጹትን ምስሎች ሁሉ አፈረሰ፡፡ ሙሴ ከነሐስ ሠርቶት የነበረውን ኔሑሽታን ተብሎ የሚጠራውን የእባብ ምስል ሰባብሮ አደቀቀ፤ ምክንያቱም እስከዚያን ጊዜ ድረስ እስራኤላውያን ለእርሱ ዕጣን ያጥኑለት ነበር፡፡ 5ሕዝቅያስ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ተማመነ፤ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ ወዲህ እርሱን የመሰለ ሌላ ንጉሥ በይሁዳ አልተነሣም፡፡6ሕዝቅያስም ለእግዚአብሔር ታማኝ ስለ ሆነ ከእግዚአብሔር መንገድ የራቀበት ጊዜ የለም፤ ለሙሴ የሰጣቸውን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ይፈጽም ነበር፡፡ 7ስለዚህም እግዚአብሔር ከሕዝቅያስ ጋር ስለነበረ የሚሠራው ሁሉ ይከናወንለት ነበር፡፡ ሕዝቅያስም በአሦር ንጉሠ ነገሥት ላይ ዐምፆ ለእርሱ መገዛትን አሻፈረኝ አለ፡፡ 8ፍልስጥኤማውያንንም ድል ነሥቶ ከትንሽ እስከ ታላቅ የተመሸጉ ከተማ ጋዛንና በዙሪያው የሚገኘውን ግዛት፣ የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ አጠቃ፡፡9ሕዝቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ማለትም የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል በነገሠ በሰባተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር በእስራኤል ላይ አደጋ በመጣል ሰማርያን ከበበ፡፡ 10በሦስተኛውም ዓመት መጨረሻ ሰማርያ በሙሉ ተያዘች፤ ይህም የሆነው ሕዝቅያስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት ሆሴዕም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ነበር፡፡11የአሦር ንጉሠ ነገሥት እስራኤላውያንን ማርኮ ወደ አሦር በመውሰድ ከእነርሱ ጥቂቶቹን በአላሔ ከተማ፣ ጥቂቶቹን በጋዛ አውረጃ በሚገኘው በአቦር ወንዝ አጠገብ፣ ሌሎቹን ደግሞ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፡፡ 12ይህም የሆነበት ምክንያት እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው ነበር፤ ይኸውም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን አፈረሱ፣ በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ አማካይነት ለተሰጠ ሕግ ሁሉ ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ለመስማትም ሆነ ሕጉን ለመጠበቅ አሻፈረን አሉ፡፡13ከዚያም ሕዝቅያስ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም አደጋ በመጣል የተመሸጉትን የይሁዳ ከተሞች ያዘ፡፡ 14ስለዚህም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ በለኪሶ ሰፍሮ ለነበረው ለሰናክሬም፣ እኔ በድያለሁ፤ እባክህን እኔን ተወኝ፤ የምትጠይቀኝን ሁሉ እልክልሃለሁ ሲል መልእክት ላከ፡፡ ንጉሠ ነገሥቱም ለይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ እኔ የምፈልገው ሦስት መቶ መክሊት ብርና ሠላሳ መክሊት ወርቅ እንድትልክልኝ ነው ሲል መለሰለት፡፡ 15ስለዚህም ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥተ ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረውን ብር ሁሉ ሰብስቦ ላከለት፡፡16እንዲሁም በእግዚዚብሔር ቤተ መቅደስ መግቢያ በሮች ላይ ተለብጦ የነበረውን ወርቅና እርሱም ራሱ በቤተ መቅደሱ የበር ዐምዶች ላይ ለብጦት የነበረውን ወርቅ ጭምር ወደ ሰናክሬም ላከ፡፡ 17ነገር ግን የአሦር ንጉሠ ነገሥት እንደገና የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት ከለኪሶ ተንቀሳቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመዝመት በሕዝቅያስ ላይ አደጋ እንዲጥልበት አዘዘ፤ ሠራዊቱም ከፍተኛ ሥልጣን ባላቸው ሦስት የጦር አዛዦቹ የሚመራ ነበር፡፡ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ከላይኛው ኩሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አጠገብ ወደ ልብስ አጣቢዎች መስክ የሚወስደውን መንገድ ያዙ፡፡ 18ከዚያ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም አገልጋዮቹ የሆኑ ሦስት ባለሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፡፡ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነው የኬልቂያስ ልጅ ኤልያቄም፣ የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሳምናስና የቤተ መዛግብት ኃላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአስ ነበሩ።19ስለዚህም የአሦር ዋና የጦር አዛዥ እንዲህ አላቸው፡- ለሕዝቅያስ እንዲህ በሉት፣ ‘ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፡- እንደዚህ የተማመንክበት ነገር ምንድን ነው? 20በጦርነት የሚረዳ ኃይል እንዳለህ የተናገርከው ከንቱ ቃላት ናቸው፤ በእኔ ላይ ለማመጽ የቻልከው በምን ተማምነህ ነው? 21የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኮዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቆስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲህ ነው’ ሲል ተናገረ፡፡22የአሦር የጦር አዛዥ ንግግሩን በመቀጠል እንደገና እንዲህ አለ፡- አምላክህ እግዚአብሔር እንደሚረዳህ ታስብ እንደሆነ፣ ይህ እንዳይሆን አንተ የእግዚአብሔርን የተቀደሱ ስፍራዎችንና መሠዊያዎችን ደምስሰህ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ማምለክ የሚገባቸው ኢየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው በአንድ መሠዊያ ብቻ ነው ብለህ ወስነሃል፡፡ 23አሁንም በንጉሠ ነገሥቱ ስም ለፍልሚያ እጠይቅሃለሁ፤ መጋለብ የሚችሉ በቂ ሰዎች ታገኝ አንደ ሆነ እስቲ ሁለት ሺህ ፈረሶች ልስጥህ፡፡24አንተ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከሆነው ከአሦር ተራ የጦር መኮንን ጋር እንኳ መወዳደር አትችልም፤ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይልኩልኛል ብለህ የምትጠባበቀውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ 25እኔ በአንተ አገር ላይ አደጋ የጣልኩባትና የደመሰስኳት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እግዚአብሔር ራሱ በዚህች አገር ላይ አደጋ እንድጥልባትና እንድደመስሳት አዞኛል፡፡26ኤልያቄም፣ ሳምናስና ዮአስ ይህን የጦር አዛዥ ትርጉሙን ስለምናውቅ በሶርያ ቋንቋ እንድትነግረን እንለምንሃለን፤ በቅጥር ላይ ያሉት ሕዝብ ሁሉ በሚሰሙት በዕብራይስጥ ቋንቋ አትናገረን አሉት፡፡ 27የጦር አዛዡም፣ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይህን ሁሉ ለእናንተና ለንጉሣቸሁ ብቻ እንድናገር የላከኝ መሰላችሁን? እንደ እናንተ ኩሳቸውን ለመብላትና ሽንታቸውን ለመጠጣት ለሚገደዱ ሰዎችም ጭምር ስለ ሆነ እኔ የምናገረውን በቅጥር ላይ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲሰሙት እንድናገር አልላከኝምን? ሲል መለሰላቸው፡፡28ከዚያም የአሦር የጦር አዛዥ ከተቀመጠበት ተነሥቶ ቆመ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ እያለ ጮኸ፡- የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሚነግራችሁን ስሙ፤ 29በሕዝቅያስ አትታለሉ፤ እርሱ ሊያድናችሁ ከቶ አይችልም፡፡ 30ሕዝቅያስ፣ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ ያድናችኋል፤ ከተማችንም በአሦርያውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል እያለ የሚሰብካችሁን አትስሙት፡፡31ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ከከተማችሁ ወጥታችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ አዞአችኋል፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁም እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላና የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጉድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፡፡ 32ይህም ሁሉ የሚሆነው ንጉሠ ነገሥቱ የእናንተን አገር ወደምትመስል ምድር ወስዶ እስከሚያሰፍራችሁ ድረስ ነው፤ በዚያችም ምድር ወይን ጠጅ የሚገኝባቸው የወይን ተክል ቦታዎችና በቂ የእንጀራ እህል የሚመረትባቸው እርሻዎች አሉ፤ ምድሪቱም የወይራ ፍሬና የወይራ ዘይት እንዲሁም ማር የሞላባት ናት። ንጉሠ ነገሥቱ የሚያዛችሁን ብትፈጽሙ በሕይወት ትኖራላችሁ እንጂ አትሞቱም፡፡ ስለዚህ ሕዝቅያስ፣ “እግዚአብሔር ይታደጋችኋል” እያለ በመስበክ አያሙኛችሁ፡፡33ለመሆኑ ከሌሎች ሕዝቦች አማልክት አንዱ እንኳ ከአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ አገሩን ያዳነ ይገኛልን? 34ታዲያ ይህ ከሆነ የሐማትና የአርፋድ አማልክት የት አሉ? የሴፈርዋይ፣ የሄናና የዒዋ አማልክትስ የት ደረሱ? ከእነርሱ አንዱ እንኳ ሰማርያን ከእጄ ማዳን ችሎአልን? 35የእነዚህ ሁሉ አገሮች አማልክት ንጉሠ ነገሥቶቻቸውን ለማዳን የቻሉበት ጊዜ አለን? ታዲያ እንግዲህ እናንተ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድናታል ብላችሁ የምታስቡት እንዴት ነው?36ሕዝቡም ቀደም ሲል ንጉሥ ሕዝቅያስ ባዘዛቸው መሠረት አንዲት ቃል ሳይናገሩ ዝም አሉ፡፡ 37ከዚያም ኤልያቄም፣ ሳምናስና ዮአስ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ቀርበው የአሦራውያን የጦር አዛዥ የተናገረውን አስረዱት፡፡
1ንጉሥ ሕዝቅያስ ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደ፡፡ 2ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፣ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሳምናስንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፡፡3ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፡- ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፡፡ 4የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢው ይቀጣ ይሆናል። ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ለተረፉት ሰዎች እባክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡5የንጉሥ ሕዝቅያስ መልእክተኞች ወደ ኢሳይያስ በመጡ ጊዜ፣ 6ኢሳይያስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብላችሁ ለንጉሣችሁ ንገሩት አላቸው፣ የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች ሲሰድቡኝ ስለ ሰማችሁት ቃል አትፍሩአቸው፡፡ 7እነሆ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህ ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድ፣ እዚያ በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ፡፡8ከዚያ የአሦር የጦር አዛዥ፣ የአሦር ንጉሥ ከሰፈሩ ከለኪሶ ተነሥቶ ልብናን ሊያጠቃ እንደ ሄደ በመስማቱ እርሱም ወደ ለኪሶ ሄደ፡፡ 9በኢትየጵያ ንጉሥ በቲርሃቅ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን ሰናክሬም ሰማ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፡-10«የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሆይ፣ የምትታመንበት አምላክ ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ አትወድቅም ብሎ አያታልልህ፤ 11የአሦር ነገሥታት አገሮችን ሁሉ እንዴት ፈጽመው እንደ ደመሰሱ ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?12የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፣ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዓዴንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን፣ ከአማልክቶቻቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን? 13ለመሆኑ የሐማት፣ የአርፋድ፣ የሴፈርዋይም፣ የሄናዕና የዒዋ ከተሞች ነገሥታት የት አሉ?»14ንጉሥ ሕዝቅያስ ደብዳቤውን ከመልእክተኞች ተቀብሎ አነበበው፤ ወደ ቤተ መቅደስም ወስዶ ደብዳቤውን በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው፡፡ 15እንዲህ ሲልም ጸለየ፡- «የሠራዊት አምላክ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በኪሩቤል ላይ የተቀመጥህ፣ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፡፡16አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፣ አንተን ሕያው የሆነከውን አምላክ በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤ 17እግዚአብሔር ሆይ፣ የአሦር ነገሥታት ብዙ ሕዝቦችንና ምድራቸውን መደምሰሳቸው እርግጥ ነው፡፡ 18ከእንጨትና ከድንጋይ ተጠርበው የተሠሩ የሰው እጅ ሥራ እንጂ አማልክት ስላልነበሩ በእሳት ላይ ጥለው አጠፉአቸው፡፡19እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፣ አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም መንግሥታት ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦር ንጉሥ አድነን፡፡»20ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፡- «የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‹ስለ አሦር ንጉሠ ነገሥት ስለ ሰናክሬም ዛቻ ወደ እኔ የጸለይከውን ጸሎት ሰምቻለሁ፡፡ 21ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፡- የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፣ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል፡፡ 22የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሳኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡23በመልእክተኞችህ አማካይነት፣ በእግዚአብሔር ላይ ስድብን አብዝተሃል፤ ‹በሠረገሎቼ ከፍተኛ ወደ ሆኑት ተራራዎች፣ ወደ ሊባኖስ ጫፍ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን የሊባኖስ ዛፎችዋንና ምርጦቹን ዝግባ ቆርጬአለሁ፤ ወደ ዳርቻዋና ውብ ወደሆነው ጫካዋ ደርሼአለሁ፤› ብለሃል፡፡ 24‹በባዕድ አገር ጉድጓድ ቆፍሬ ውሃ ጠጣሁ፤ በእግሬ ኮቴዎች የግብጽን ወንዞች አድርቄአለሁ› ብለህ ታብየሃል፡፡25ሰናክሬም ሆይ! አስተውል፤ ጥንቱኑ እኔ እንደ ወሰንኩት፣ በቀድሞው ዘመን እንዳቀድኩትና አሁን በሥራ ላይ ባዋልኩት መሠረት የተጠናከሩ ከተሞችን ወደ ፍርስራሽ ክምርነት እንድትለውጥ ያደረግኹህ እኔ መሆኔን አልሰማህምን? 26የእነዚያ አገር ነዋሪዎች ኃይላቸው ተዳክሞ፣ ተስፋ በመቁረጥ እንዲያፍሩ ተደርገው በምሥራቅ ነፋስ እንደተመቱ የመስክ አትክልቶች፣ እንደ ቀጨጩ አረንጓዴ ቡቃያዎች፣ በጣራ ላይ እንደበቀሉ ሣር ናቸው፡፡27እኔ ግን መነሣትህንና መቀመጥህን፣ መውጣትህንና መግባትህን፣ እንዲሁም እኔን መቃወምህን ዐውቃለሁ፡፡ 28በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ትናጋ፣ በአፍህም ልጓም አድርጌ፣ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ፡፡»29ከዚያም ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን አንዲህ አለው፤ «ይህ ሁሉ እንደሚፈጸም ምልክቱ ይህ ነው፣ በአሁኑና በሚቀጥለው ዓመት ሳይዘሩት የሚበቅለውንና የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን የራሳችሁን እህል ዘርታችሁ ታመርታላችሁ፤ ወይንም ተክላችሁ ፍሬውን ትበላላችሁ፤ 30በይሁዳ ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ወደ መሬት ሥር ሰድዶ እንደሚያድግና እንደሚያፈራ ተክል ይሆናሉ፤ 31ከኢየሩሳሌምና ከጽዮን ተራራ የተረፉት ወገኖች ይወጣሉ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ይፈጽማል፡፡»32ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦራውያን ንጉሠ ነገሥት የተናገረውም ቃል ይህ ነው፡- «ሰናክሬም ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባባትም፤ አንድ ፍላጻ እንኳ አይወረውርባትም፤ ጋሻ ያነገበ ወታደርም ወደ እርስዋ አይቀርብም፤ በአፈር ቁልልም አትከበብም፡፡ 33እርሱ ወደዚህች ከተማ ሳይገባ በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይሄዳል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ 34ስለ ራሴ ክብርና ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ይህችን ከተማ እኔ ራሴ ተከላክዬ አድናታለሁ፡፡»35በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ፡፡ 36ስለዚህ የአሦራውያን ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም ወደ ኋላው በማፈግፈግ ወደ ነነዌ ተመለሰ፡፡ 37ከዕለታት በአንዱ ቀን ናሳራክ በሚል ስም በሚጠራው ባዕድ አምላኩ ቤተ መቅደስ ውስጥ በስግደት ላይ እንዳለ፣ ከልጆቹ ሁለቱ በተለይ አደራሜሌክና ሳራሳር ተብለው የሚጠሩት በሰይፍ ገደሉት፤ እነርሱም ወደ አራራት አምልጠው ሄዱ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ከልጆቹ አንዱ አስራዶን የተባለው ነገሠ፡፡
1በዚያን ዘመን ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፡፡ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጎበኘው ሄዶ፡- «እግዚአብሔር ‹ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህም ስለማይቀር ሁሉን ነገር አስተካክል› ብሎሃል» ሲል ነገረው፡፡ 2ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፡- 3«እግዚአብሔር ሆይ! በታማኝነትና በቅንነት እንዳገለገልኩህ፣ አንተ የምትደሰትበትንም ነገር ለማድረግ ዘወትር እጥር እንደነበር ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ!» እያለ በመጸለይ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡4ኢሳይያስ ከንጉሡ ፊት ወጥቶ የቤተ መንግሥቱን መካከለኛ አደባባይ አልፎ ከመሄዱ በፊት፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፡- 5«ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፡- ‹እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፡፡6በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችን የኢየሩሳሌምን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ በመታደግ አድናለሁ፡፡ ስለ ክብሬና ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ከተማይቱን በመከላከል እጠብቃታለሁ፡፡” 7ስለዚህ ኢሳይያስ የንጉሡን አገልጋዮች «የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ አምጡልኝ» ብሎ አመጡለት፤ በቁስሉ ላይ ባደረጉለት ጊዜ የሕዝቅያስ ቁስል ተፈወሰ፡፡8ንጉሥ ሕዝቅያስም ኢሳይያስን «እግዚአብሔር እንደሚፈውሰኝና ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ መሄድ እንደምችል በምን ምልክት ዐውቃለሁ?» ሲል ጠየቀው፡፡ 9ኢሳይያስም «እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል የሚፈጽም ስለ መሆኑ ራሱ ምልክት ይሰጥሃል፤ እንግዲህ አሁን የምትመርጠው ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ነው? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ?» ሲል ጠየቀው፡፡10ሕዝቅያስም «ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ማድረግ ይቀላል፤ ስለዚህ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አድርግልኝ» አለው፡፡ 11ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ንጉሥ አካዝ ባሠራው ደረጃ ላይ ያረፈው ጥላ ዐሥር ደረጃ ላይ ያረፈው ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፡፡12በዚያኑ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባላዳን ልጅ መሮዳክ ባላዳን፣ ንጉሥ ሕዝቅያስ መታመሙን ሰምቶ ከገጸ በረከት ጋር ደብዳቤ ላከለት፡፡ 13ሕዝቅያስ መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበላቸው፤ በቤተ መንግሥቱም የዕቃ ግምጃ ቤት ያለውን ሀብት በሙሉ፣ ብሩንና ወርቁን፣ ቅመማ ቅመሙንና ሽቶውን፣ የጦር መሣሪያውንም ሁሉ አሳያቸው፤ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤትም ሆነ በመንግሥቱ በማንኛውም ስፍራ ካለው ሀብት ሁሉ ያላሳያቸው አንድም አልነበረም፡፡14በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ፣ «እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ?» ብሎ ጠየቀው፡፡ ሕዝቅያስም «እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው» ሲል መለሰለት፡፡ 15ኢሳይያስም «በቤተ መንግሥቱ ምን አዩ» ሲል ጠየቀው፡፡ ሕዝቅያስም «ሁሉን ነገር አይተዋል፤ በግምጃ ቤቱ ካለው ሀብት ሁሉ ለእነርሱ ያላሳየኋቸው አንድም ነገር የለም» አለ፡፡16ኢሳይያስም ንጉሡን እንዲህ አለው፡- «ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 17‹የቀድሞ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ድረስ ያከማቹት፣ በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርም። 18ከዘሮችህም አንዳንዶቹ ወደ ባቢሎን ተማርከው በመሄድ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ጃንደረቦች ሆነው እንዲያገለግሉ ይደረጋል፡፡»19ንጉሥ ሕዝቅያስም በተለይ በእርሱ ዘመን በሰላም የመኖር ዋስትና እንዳለው ስለ ተረዳ «ከእግዚአብሔር ተልከህ የተናገርከኝ ቃል መልካም ነው» ሲል መለሰ፡፡ 20ንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራው ጭምር፣ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ እንዴት እንደ ሠራና ወደ ከተማይቱ ውሃ ለማምጣት ያስቆፈረው የመሬት ውስጥ ቦይ አሠራር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 21ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ምናሴ ነገሠ፡፡
1ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ እርሱም በኢየሩሳሌም ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ሐፍሴባ ተብላ ትጠራ ነበረ፡፡ 2እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋቸውን የአሕዛብን አሳፋሪ ልማድ በመከተል ምናሴ የሠራው ኃጢአት እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡ 3ምናሴ አባቱ ሕዝቅያስ አጥፍቶአቸው የነበሩትን የአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች እንደገና እንዲሠሩ አደረገ፡፡ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ባደረገውም ዐይነት ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሠዊያዎችን፣ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስልን ሠራ፤ የሰማይ ከዋክብትንም አመለከ፡፡4እግዚአብሔር እንዲመለክበት ባዘዘው ስፍራ ማለትም በቤተ መቅደስ ውስጥ አረማዊ መሠዊያዎችን አቆመ፡፡ 5በሁለቱም የቤተ መቅደሱ አደባባዮች የሰማይ ከዋክብት የሚመለኩባቸውን መሠዊያዎች ሠራ፡፡ 6የገዛ ልጁንም መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት በመሥራቱ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ፡፡7በቤተ መቅደሱም ውስጥ የአሼራን ምስል አኖረ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን «ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እኔ ለዘለዓለም እንድመለክበት ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት ስፍራ ነው፡፡ 8የእስራኤል ሕዝብ ትእዛዞቼን ቢጠብቁና ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትንም ሕግ ቢፈጽሙ፣ ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ከዚህች ምድር ተነቃቅለው እንዲጠፉ አላደርግም» ሲል ነግሮአቸው የነበረው ነው፡፡ 9የይሁዳ ሰዎች ግን ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ይልቁንም ምናሴ እስራኤላውያን ወደፊት እየገፉ ሲመጡ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸው ሕዝቦች ይፈጽሙት ከነበረው ይበልጥ ወደ ክፉ ኃጢአት መራቸው፡፡10ስለዚህ እግዚአብሔር በአገልገጋዮቹ በነቢያት አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፡- 11«የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፡፡ 12ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ የመጣው በጣም ከባድ መቅሰፍት ይህ ነው፤ ስለ እርሱም የሚሰማ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ጆሮው ጭው ይላል፡፡13ሰማርያንና የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ከነዘሮቹ እንደ ቀጣሁ ኢየሩሳሌምንም እቀጣለሁ፤ ሳሕን ከተወለወለ በኋላ ተደፍቶ እንደሚቀመጥ፣ እኔም ኢየሩሳሌምን ከኃጢአት አጸዳታለሁ፡፡ 14ከጥፋት የተረፈውን ሕዝቤን ለጠላቶቹ ተላልፎ እንዲሰጥ እተወዋለሁ፤ እርሱም ይማረካል፤ ንብረቱም ይዘረፋል፡፡ 15በእነርሱም ላይ ይህን ሁሉ የማደርግበት ምክንያት የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ ኃጢአት ሠርተው እኔን በማሳዘናቸውና ቁጣዬን በማነሣሣታቸው ነው፡፡»16ከዚህም በተጨማሪ ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፣ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል፡፡ 17ምናሴ ያደረገው ሌላው ነገርና የፈጸመው ኃጢአት ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሓፍ ተመዝቦ ይገኛል፡፡ 18ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቤተ መንግሥቱ ግቢ «የዖዛ አትክልት ስፍራ» ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አሞን ነገሠ፡፡19አሞን በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሁለት ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ሜሶላም ተብላ የምትጠራ የዮጥባ ከተማ ተወላጅ የሐሩስ ልጅ ነበረች፡፡ 20አሞን እንደ አባቱ እንደ ምናሴ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሠራ፡፡21የአባቱንም መጥፎ አርአያነት ሁሉ ተከተለ፤ አባቱ ይሰግድላቸውና ያመልካቸው የነበሩትንም ጣዖቶች ሁሉ አመለከ፡፡ 22የቀድሞ አባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርንም ተወ፤ እግዚአብሔርንም አልተከተለም፡፡ 23አገልጋዮቹ ባለሥልጣኖችም በአሞን ላይ አድመው በራሱ ቤት ውስጥ ገደሉት፡፡24የይሁዳም ሕዝብ የአሞንን ገዳዮች ደምስሰው ልጁን ኢዮስያስን አነገሡ፡፡ 25አሞን ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 26አሞን «የዖዛ አትክልት ስፍራ» ተብሎ በሚጠራው መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኢዮስያስ ነገሠ፡፡
1ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ገና ስምንት ዓመት ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ይዲዳ ተብላ የምትጠራ የባሱሮት ከተማ ተወላጅ የሆነው የአዳያ ልጅ ነበረች፡፡ 2ኢዮስያስ የቀድሞ አባቱን የዳዊትን መልካም ምሳሌነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ፡፡ ወደ ግራም ቀኝም አላለም፡፡3ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የሜሶላም የልጅ ልጅ፣ የኤዜልያስ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱን ጸሓፊ ሳፋንን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በማለት መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፡፡ 4«ኬልቂያስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደህ፣ ወደ ቤተ መቅደስ በሚያስገባው በር አጠገብ በየተራ ከሕዝቡ ገንዘብ የመሰብሰብ ኃላፊነት የተሰጣቸው ካህናት እስከ አሁን ምን ያህል ገንዘብ ከሕዝቡ እንደሰበሰቡ የሚገልጥ የሒሳብ ማስረጃ ይዘህ እንድትመጣ አለው፡፡ 5የመቅደሱን እድሳት ለመቆጣጠር ለተሾሙት ሰዎች ያስረክቡ፤ እነርሱም የተረከቡትን ገንዘብ ቤተ መቅደሱን ለሚጠግኑ፣ ለአናጢዎች፣ ለግንበኞችና ለድንጋይ ጠራቢዎች ይክፈሉ፡፡6እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ እድሳት ሳንቃዎችንና የተጠረቡ ድንጋዮችን ይግዙ፡፡ 7ነገር ግን የሥራው ኃላፊዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ሆኑ እነርሱን ስለ ገንዘቡ አወጣጥ መቆጣጠር አያስፈልግም፡፡»8ጸሐፊው ሳፋን ከንጉሡ የተላከውን ትእዛዝ ለኬልቂያስ ሰጠው፤ ኬልቂያስም «የሕጉን መጽሐፍ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኘሁ» ብሎ ለሳፋን ሰጠው፤ ሳፋንም ተቀብሎ አነበበው፡፡ 9ጸሐፊውም ሄደና «አገልጋዮችህ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበረውን ገንዘብ ተቀብለው ለእድሳቱ ሥራ ኃላፊዎች ለሆኑት ሰዎች አስረክበዋል» ሲል አስረዳ፡፡ 10ከዚያም ጸሐፊው ሳፋን ለንጉሡ «ካህኑ ኬልቂያስ አግኝቶ የሰጠኝ መጽሐፍ» ነው አለው፡፡11ንጉሡም፣ የሕጉ መጽሐፍ ሲነበብ በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፡፡ 12እርሱም ለካህኑ ለኬልቂያስ፣ የሳፋን ልጅ ለሆነው ለአኪቃም፣ የሚክያስ ልጅ ለሆነው ለዓክቦር፣ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ለሆነው ለሳፋንና የንጉሡ የቅርብ አገልጋይ ለሆነው ለዓሳያ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጠ፡፡ 13«እንግዲህ ሂዱና እኔና የይሁዳ ነዋሪ ሕዝብ በዚህ በተገኘው መጽሐፍ ስላለው ትምህርት ማወቅ እንችል ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን መመሪያ ስላልተከተሉ እግዚአብሔር በእኛ ላይ በጣም ተቆጥቶአል፡፡»14ካህኑ ኬልቂያስ፣ አኪቃም፣ ዓክቦር፣ ሳፋንና ዓሳያ በኢየሩሳሌም አዲስ በተሠራው ሰፈር የምትኖረውን ሕልዳና ተብላ የምትጠራውን ነቢይቱን የሴሌም ሚስት ለመጠየቅ ሄዱ። የሐርሐስ የልጅ ልጅ የቲቅዋ ልጅ የሆነው የቤተ መቅደስ አልባሳት ኃላፊ ነበር፤ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ለነቢይቱ አስረዱአት፡፡ 15እርስዋም እንዲህ አለቻቸው፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፡- 16«እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው መሠረት በዚህች ቦታና በሕዝብዋ ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፡፡17እነርሱ እኔን ትተው ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቅርበዋል፤ በእጃቸው በሠሩአቸው ጣዖታት ሁሉ እኔን አስቆጥተውኛል፤ ቁጣዬም አይበርድም፡፡ 18እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ እንዲህ በሉት፤ እኔ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ‹አንተ በዚያ መጽሐፍ የተነገረውን ቃል ሰምተህ፡- 19ይህችን ቦታና ሕዝብዋን የተረገሙና ባድማ እንደማደርግ የተናገርኩትን ቃል በሰማህ ጊዜ ልብህ ተነክቶ ራስህን በማዋረድህ፣ ልብስህን በመቅደድና በፊቴም በማልቀስህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ፡፡20ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም ላይ የማመጣውን ቅጣት በዐይንህ ሳታየው እስከምትሞትበት ጊዜ ድረስ ተፈጻሚ አይሆንም፤ ስለዚህም አንተ በሰላም እንድትሞት አደርጋለሁ፡፡» ሰዎቹም ይህን መልእክት ይዘው ወደ ንጉሥ ኢዮስያስ ተመለሱ፡፡
1ስለዚህ ንጉሥ ኢዮስያስ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን የታወቁ ሽማግሌዎችን ሁሉ ጠርቶ ሰበሰባቸው፡፡ 2እነርሱም ካህናት፣ ነቢያት፣ ሌሎችም ሰዎች ከታናሾች ጀምሮ እስከ ታላቆች ድረስ ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ ንጉሡም በዚያ ጠፍቶ በነበረውና በቤተ መቅደስ በተገኘው መጽሐፍ የሰፈረውን ቃል በሙሉ ለሕዝቡ አነበበ፡፡3ንጉሡም በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና አሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፣ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ስለዚህም በዚህ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳኑ ለመቆም ተስማሙ፡፡4ንጉሡም ኢዮስያስ ሊቀ ካህናቱን ኬልቅያስን፣ ረዳቶቹ የሆኑትን ካህናትና የቤተ መቅደስ በር ዘብ የሚጠብቁ ተረኞችን ጠርቶ ለባዓልና አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ፣ እንዲሁም ለከዋክብት ማምለኪያ ያገለግሉ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ ንጉሡም እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ከኢየሩሳሌም ውጪ ባለው በቄድሮን ሸለቆ በእሳት አቃጥሎ ዐመዱን ወደ ቤቴል ወሰደው፡፡ 5በይሁዳ ከተማዎችና በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ባሉት ስፍራዎች ሁሉ በየኮረብታው ላይ በነበሩት መሠዊያዎች መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ የይሁዳ ነገሥታት ሾመዋቸው የነበሩትን ካህናት ሁሉ ከሥራ አሰናበተ፤ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ፣ ለፕላኔቶች፤ ለፀሐይ፣ ለጨረቃ፣ ለፀሐይና ለሰማይ ከዋክብት ሁሉ መሥዋዕት በማቅረብ የሚያገለግሉ ካህናትን ሁሉ አስወገደ፡፡6አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ከቤተ መቅደስ ነቅሎ ከከተማይቱ በማውጣት ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ትቢያ እስኪሆንም አድቅቆ፣ በሕዝብ መቃብር ላይ በተነው፡፡ 7ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉ ሴቶች አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ መጋረጃ የሚፈትሉበትን ክፍል ሁሉ አጸዳ፡፡8በይሁዳ ከተሞችና በመላ አገሪቱ ከጌባ እስከ ቤርሳቤህ የነበሩትን ካህናት ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣ፡፡ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን መሠዊያዎች ሁሉ ርኩስ መሆናቸውን አወጀ፤ እንዲሁም የከተማይቱ ገዢ ኢያሱ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ከዋናው ቅጥር በር በስተግራ በኩል ባሠራው ቅጥር በር አጠገብ የሚገኙትን መስገጃዎች አፈራረሰ፡፡ 9የከፍታ ቦታ ካህናት በቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ለማገልገል ያልተፈቀደላቸው ቢሆንም በወንድሞቻቸው ዘንድ የነበረውን እርሾ ያልነካውን ሕብስት በሉ፡፡10ንጉሥ ኢዮስያስ በሔኖም ሸለቆ የነበረውን «ቶፌት» ተብሎ የሚጠራውን የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ «ሞሌክ» ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፡፡ 11የይሁዳ ነገሥታት ለፀሐይ አምልኮ መድበዋቸው የነበሩትን ፈረሶች ሁሉ አስወገደ፡፡ ለዚሁ አምልኮ ያገለግሉ የነበሩትን ሠረገሎች አቃጠለ፡፡ እነዚህ ሁሉ ቀደም ሲል ታላቁ ባለሥልጣን ናታን ሜሌክ በሚኖርባቸው ክፍሎች አጠገብና በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቅጥር በር አጠገብ ይገኙ ነበር፡፡12ንጉሥ አካዝ ባሠራቸው መኖሪያ ክፍሎች ጣራ ላይ በሚገኘው ቤተ መንግሥት የይሁዳ ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትን መሠዊያዎችና በቤተ መቅደሱ ሁለት አደባባዮች ንጉሥ ምናሴ አሠርቶአቸው የነበሩትን መስገጃዎቸ ሁሉ ኢዮስያስ ደመሰሳቸው፤ መሠዊያዎቹን ሰባብሮ ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ ጣላቸው፡፡ 13ንጉሡም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኩሰት ተራራ በስተ ደቡብ አስታሮት ተብሎ ለሚጠራው ለአሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩትን አስጸያፊ ምስሎች፣ የሲዶናውያንና የሞዓባውያን አስጸያፊ የሆኑ ጣዖታትን ሁሉ ደመሰሰ፡፡ 14ንጉሥ ኢዮስያስ የድንጋይ አምዶችን ሁሉ ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውንም የሴት አምላክ ምስሎች ሰባብሮ ጣለ፡፡ እነርሱም ቆመውበት የነበረውን የድንጋይ ዐምዶች ሰባብሮ ስፍራውንም የሙታን አጥንት ሞላበት፡፡15እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤቴል አሠርቶት የነበረውን የማምለኪያ ቦታ ኢዮስያስ አፈራርሶ ጣለው፤ መሠዊያውን ነቅሎ የተመሠረተበትን ድንጋይ ሁሉ ሰባብሮ በማድቀቅ እንደ ትቢያ አደረገው፤ የአሼራንም ምስል በእሳት አቃጠለ፡፡ 16ከዚያም ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት፣ በኮረብቶች ላይ የተሠሩ መቃብሮች አየ፤ በእነዚያም መቃብሮች ውስጥ የነበረውን አፅም ሁሉ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በእሳት አቃጠለው፡፡ በዚህም ዓይነት መሠዊያው የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ኢዮስያስ ይህንን ሁሉ በማድረጉ ከብዙ ጊዜ በፊት በተደረገ የአምልኮ በዓል ላይ ንጉሥ ኢዮርብዓም በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ ነቢዩ የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈጸመ፡፡ ንጉሥ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት ይህንን የእግዚአብሔር ቃል ተናግሮ የነበረው ነቢይ የተቀበረበትን መካነ መቃብር የማን ነው ሲል ጠየቀ፡፡17የቤቴል ሕዝብ ከይሁዳ መጥቶ በዚህ መሠዊያ ላይ ይህንን አንተ ያደረግኸውን ነገር ሁሉ እንደሚፈጸምበት ተናግሮ የነበረው የነቢዩ መቃብር ነው ሲሉ መለሱለት፡፡ 18ኢዮስያስም እንዳለ ይኑር፣ የእርሱ አፅም ከዚህ መንቀሳቀስ የለበትም ሲል መለሰ፡፡ ስለዚህም የእርሱም ሆነ የሰማርያው ነቢይ አፅሞች ከዚያ እንዲነሡ አልተደረገም፡፡19ከዚያም ንጉሥ ኢዮስያስ በማንኛይቱም የእስራኤል ከተማ የእስራኤል ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትን የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማነሣሣት ምክንያት የሆኑ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሁሉ አፈራረሰ፡፡ በቤቴል ያደረገውን ሁሉ በእነዚያ መሠዊያዎች ላይ ፈጸመ፡፡ 20በእነዚያ መሠዊያዎች ላይ ያገለግሉ የነበሩትንም የአሕዛብ ካህናት ሁሉ አረዳቸው፡፡ በመሠዊያዎቹም ላይ አጥንቶቻቸውን አቃጠለ፡፡ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡21ከዚያም ንጉሥ ኢዮስያስ በቃል ኪዳን መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር የፋሲካ በዓል ያከብሩ ዘንድ ሕዝቡን አዘዘ፡፡ 22መሳፍንት የሕዝቡ ገዢዎች ከነበሩበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን በማናቸውም የእስራኤል ወይም የይሁዳ ነገሥታት አማካይነት ይህንን የመሰለ የፋሲካ በዓል ተከብሮ አያውቅም፡፡ 23ነገር ግን ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የእግዘአብሔር ፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ተከበረ፡፡24ሊቀ ካህናቱ ኬልቂያስ በቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው ሕግ ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው በማሰብ፣ ንጉሥ ኡዮስያስ ከኢየሩሳሌምና ከሌላውም የይሁዳ ከተማ ሁሉ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ሁሉ የቤተ ሰብ አማልክት ጣዖቶችንና ሌሎችም አረማዊ የአምልኮ መፈጸሚያ ዕቃዎችን ሁሉ አስወገደ፡፡ 25ለኦሪት ሕግ በመታዘዝ በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱና በፍጹም ኃይሉ እግዚአብሔርን ያገለገለ እንደ ንጉሥ ኢዮስያስ ያለ ከእርሱም በፊት ሆነ ከእርሱ በኋላ ከቶ አልነበረም፡፡26ይሁን እንጂ ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው የእግዚአብሔር ቁጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር፡፡ 27ስለዚህ እግዚብሔር እንዲህ አለ፡- በእስራኤል ላይ ያደረግኹትን ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ አደርጋለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ሕዝብ ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኳትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራል ብዬ የነበረውንም ቤተ መቅደስ እተዋለሁ፡፡28ንጉሥ ኢዮስያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 29በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ኒካዑ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፡፡ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፡፡ 30አገልጋዮቹም ባለሥልጣኖች ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እዚያ በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡ የይሁዳም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን መረጡ፣ በአባቱም ፈንታ አነገሡት፡፡31ኢዮአክስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ ሦስት ዓመት ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም አሚጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፡፡ 32ኢዮአክስ የቀድሞ አባቶቹ እንዳደረጉት በእግዚብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡ 33እርሱንም ኒካዑ ተብሎ የሚጠራው የግብጽ ንጉሥ ኢዮአክስ በኢየሩሳሌም እንዳይነግሥ በሐማት ምድር በምትገኘው በሪብላ አስሮ ይሁዳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ብር ሠላሳ አራት ኪሎ ወርቅ ግብር እንዲከፍል ባደረገው ጊዜ የኢዮአክስ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ፡፡34ንጉሥ ኒካዑ የኢዮአክስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ ፈንታ ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፡፡ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፡፡ ኢዮአክስ በንጉሥ ኒካዑ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ፡፡ 35ኢዮአቄም ለግብጽ ንጉሥ ለኒዑዑ የጠየቀውን ብርና ወርቅ ከፈለ፡፡ ይህንንም ለማድረግ እንደየችሎታቸው በሕዝቡ ላይ ግብር ጣለ፡፡36ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ዘቢዳ ተብላ የምትጠራ የሩማ ከተማ ተወላጅ የሆነው የፈዳያ ልጅ ነበረች፡፡ 37ኢዮአቄም የቀድሞ አባቶቹ እንዳደረጉት በእግዚብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
1በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይሁዳን ወረረ፤ ኢዮአቄምም ሦስት ዓመት ከገበረለት በኋላ እንደገና አመፀ፡፡ 2እግዚብሔር በአገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት ይሁዳን ስለ ማጥፋት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ወራሪ ቡድኖች ባቢሎናውያንን፣ ሶርያውያንን፣ ሞአባውያንንና አሞናውያንን በኢዮአቄም ላይ አስነሣበት፡፡3ይህም ሁሉ የሆነው ንጉሥ ምናሴ በፈጸመው ኃጢአት ምክንያት የይሁዳን ሕዝብ ከፊቱ ለማስወገድ እግዚብሔር ባዘዘው መሠረት ነው፡፡ 4በተለይ ምናሴ የንጹሓንን ሰዎች ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓ ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፡፡ ከዚህም የተነሣ እግዚብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም፡፡5ኢዮአቄም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ 6ኢዮአቄምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእርሱም ፈንታ ልጁ ዮአኪን ነገሠ፡፡7የባቢሎን ንጉሥ ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ግብጽ ሰሜናዊ ጠረፍ ድረስ የግብጽ ይዞታ የነበረውን ሁሉ በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ ስለ ነበረ፣ የግብጽ ንጉሥና ሠራዊቱ ከዚያ በኋላ ከግብጽ ውጪ ዘመቻ አላደረጉም፡፡8ዮአኪን በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌም ሦስት ወር ገዛ፡፡ እናቱም ኔስታ ተብላ የምትጠራው የኢየሩሳሌም ተወላጅ የሆነው የኤልናታን ልጅ ነበረች፡፡ 9አባቱ እንዳደረገው ሁሉ በእግዚብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡10በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን አጠቃ፤ ከተማይቱንም ከበባት፡፡ 11ሠራዊቱ ከብቦ በነበረበት ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ 12የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከልዑላን መሳፍንቱ፣ ከጦር አዛዦቹና ከባለሥልጣናቱ ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ተወሰዱ፡፡ የባቢሎን ንጉሥም በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማረከው፡፡13ናቡከደነፆርም በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ ጠራርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደ፡፡ ቀደም ሲል እግዚብሔር በተናገውም ቃል መሠረት ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚብሔር ቤተ መቅደስ አሠርቶት የነበረውን የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰባበረ፡፡ 14ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ልዑላን፣ መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎች ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፡፡ ከእርሱም ጋር የዕደ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎቹን ድኾች ብቻ ነበር፡፡15ናቡከደነፆር ዮአኪንን አስሮ ከእናቱ፣ ከሚስቶቹ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከባለሥልጣኖቹና ከይሁዳ ታላላቅ ሰዎች ጋር በአንድነት ሰብስቦ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፡፡ 16የባቢሎን ንጉሥ ሰባት ሺህ ለውጊያ ብቃት ያላቸው ወንዶችን እንዲሁም አንድ ሺህ ብረት ቀጥቃጮችንና ዕደ ጥበበኞችን ወደ ባቢሎን ወሰደ፡፡ 17ናቡከደነፆርም በዮአኪን ምትክ ማታንያ ተብሎ የሚጠራውን የዮአኪንን አጎት በይሁዳ አነገሠው፤ ስሙንም በመለወጥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው፡፡18ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም አሚጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የነበረው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፡፡ 19እርሱም አባቱ ኢዮአቄም ባደረገው ዓይነት በእግዚአብሔር ክፉ አደረገ፡፡ 20እግዚብሔር ከፊቱ እስኪያስወግዳቸው ድረስ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ተቆጥቶ ነበር፡፡ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ፡፡
1ናቡከደነፆር መላው ሠራዊቱን አስከትቶ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ ዐሥረኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ከባቢሎን መጥቶ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ ወታደሮቹ ከከተማይቱ ውጪ ሰፍረው ዙሪያውን የሚከብብ አጥር ሠሩ፡፡ 2ከበባው እስከ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛ ዓመት ዘመነ መንግሥት ድረስ ቆየ፡፡ 3ስለዚህም አራተኛው ወር በገባ በዘጠነኛው ቀን ራቡ በጣም ስለ ጸና ሕዝቡ የሚመገበው እንዳችም ምግብ አልነበረም፡፡4ከዚያም የከተማይቱ ቅጥር ተጣሰ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጥሮች በሚያያይዘው የቅጥር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ፡፡ 5ነገር ግን የከላደውያን ሠራዊት ንጉሥ ሴዴቅያስን በኢያሪኮ አጠገብ በሚገኝ ሜዳ ላይ አሳደደው፡፡ ወታደሮቹም ጥለውት ሸሹ፡፡6ሴዴቅያስ ተይዞ በሪብላ ከተማ ወደሚገኘው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ተወሰደ፡፡ በዚያም ፍርድ አስተላለፉበት፡፡ 7ሴዴቅያስም ዐይኑ እያየ ልጆቹ በፊቱ ታረዱ፡፡ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ አሳወረው፤ እጆቹንም በነሐስ ሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፡፡8ናቡከደነፃር በባቢሎን በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት፣ አምስተኛው ወር በገባ በሰባተኛው ቀን ናቡዘረዳን ተብሎ የሚጠራው የናቡከደነፆር የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ 9እርሱም ቤተ መቅደሱን፣ ቤተ መንግሥቱን፣ በከተማው የሚኖሩትን የታላላቅ ሰዎች ቤት፣ በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፡፡ 10በክብር ዘቡ አዛዥ ሥር የነበሩት የባቢሎናውያን ወታደሮች በሙሉ የኢየሩሳሌምን ዙሪያ አጥር ደመሰሱ፡፡11ከዚህ በኋላ ናቡዘረዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ምርኮ አድርጎ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፡፡ 12ነገር ግን ምንም ሀብት የሌላቸውን የመጨረሻ ድኾች አትክልት ኮትኳቾችና መሬት አራሾች እንዲሆኑ በይሁዳ ምድር ትቶአቸው ሄደ፡፡13ባቢሎናውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን የነሐስ አምዶች፣ ባለ መንኮራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎችንና ከነሐስ የተሠራውን ታላቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ሰባበሩ፤ ነሐሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱት፡፡ 14እነርሱም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ መኮስተሪያዎችን፣ የዕጣን ማስቀመጫዎችንና ከነሐስ የተሠሩ የቤተ መቅደስ መገልገያ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰዱ፡፡ 15ጽናዎችንና ዱካዎችን ከብርና ከወርቅ የተሠሩ በመሆናቸው ወሰዱአቸው፡፡16ንጉሥ ሰሎሞን ለቤተ መቅደስ ያሠራቸውን ሁለቱን አምዶች፣ ባለመንኮራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎችንና ታላቁን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎቸ፣ በክብደታቸው ምክንያት ሊመዝኑአቸው አልቻሉም፡፡ 17አንዱ አምድ ስምንት ሜትር ነበረው፤ ጉልላቱ ከነሐስ የተሠራ ነበር፤ የጉልላቱም ቁመት አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ነበር፤ በዙሪያውም ከነሐስ በተሠራ መረብ ላይ የሮማን ፍሬ ቅርጽ የመሰለ ባለፈርጥ ጌጥ ተሠርቶበት ነበር፡፡18የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዘረዳን ሊቀ ካህናቱን ሠራያን በማዕርግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሦስቱን የቤተ መቅደስ ዘበኞች እስረኛ አደርጎ ወሰዳቸው፡፡ 19ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነው አንድ ባለሥልጣን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ የነበሩትን አምስቱን የንጉሥ አማካሪዎች፣ የአገሩን ሕዝብ ለወታደርነት ይመለምል የነበረው መኮንንና ሌሎችንም ስልሳ ሰዎችን ወሰደ፡፡20ከዚያም ናቡዘረዳን እነዚህን ሁሉ ይዞ በሐማት ግዛት በምትገኘው በሪብላ ከተማ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወሰዳቸው፡፡ 21የባቢሎንም ንጉሥ በዚያ እነርሱን አስደብድቦ በማሠቃየት በሞት ቀጣቸው፡፡ በዚህም ዐይነት የይሁዳ ሕዝብ ከአገራቸው ተማርከው ተወሰዱ፡፡22የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የሳፋን የልጅ ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ወደ ባቢሎን ተማርከው ሳይወሰዱ ለቀሩት ሰዎች ሁሉ ኃላፊ ይሆን ዘንድ የይሁዳ ገዢ አድርጎ ሾመው፡፡ 23እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኮንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ጎዶልያስን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኮንኖች የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የተንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው ያእዛንያ ነበሩ፡፡ 24ጎዶልያስ እነርሱንና ወታደሮቻቸውን እንዲህ አላቸው፤ ከባቢሎናውያን ባለሥልጣኖች የተነሣ ምንም ዐይነት ፍርሃት ሊያድርባችሁ እንደማይገባ ቃል እገባላችኋለሁ፤ በዚህች ምድር ኑሮአችሁን መሥርቱ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ገብሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁሉ ነገር ይቃናላችኋል፡፡25ነገር ግን በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የነበረውና የኤሊሳማ የልጅ ልጅ የሆነው የናታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ምጽጳ ሄደ፤ በዚያም አደጋ ጥሎበት ጎዶልያስን ገደለው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተገኙትን አይሁዳውያንንና ባቢሎናውያንን ሁሉ ገደለ፡፡ 26ከዚህም የተነሣ ባቢሎናውያንን ስለፈሩ እስራኤላውያን ሀብታሞችና ድኾች ከጦር ሠራዊት መኮንኖች ጋር በአንድነት ተነሥተው ወደ ግብጽ ሸሹ፡፡27ዮርማሮዴቅ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን ከእስራት በመፍታት ምሕረት አደረገለት፤ ይህም የሆነው ዮአኪን ተማርኮ በሄደ በሠላሳ ሰባት ዓመቱ፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር በሃያ ሰባተኛው ቀን ነበር፡፡28ዮርማሮዴቅ ለዮአኪን መልካም ነገር አደረገለት፤ እንደ እርሱ ተማርከው በባቢሎን በስደት ከሚኖሩ ነገሥታት ሁሉ የላቀ የክብር ማዕረግ ሰጠው፡፡ 29ስለዚህም ዮአኪን በእስር ቤት የነበረውን ልብስ ለውጦ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ ከንጉሡ ማዕድ እንዲመገብ ተፈቀደለት፡፡ 30እርሱም በኖረበት ዘመን ሁሉ በየቀኑ ለማናቸውም ለሚያስፈልገው ነገር ያውለው ዘንድ የዘወትር ቀለብ ይሰጠው ነበር፡፡
1አዳም፣ ሴት፣ ሄኖስ፣ 2ቃይናን፣ መላልኤል፣ ያሬድ፣ 3ሄኖክ፣ ማቱሳላ፣ ላሜሕ፣ኖኅ። 4የኖኅ ወንዶች ልጆች፤ ሴም፣ካምናያፌት።5የያፌት ወንዶች ልጆች፤ ጋሜር፣ማጎግ፣ማዴ፣ያዋን፣ቶቤል፣ሞሳሕ፣ቴራስ። 6የጋሜር ወንዶች ልጆች፤ አስከናዝ፣ሪፋት፣ቴርጋማ። 7የያዋን ወንዶች ልጆች፤ ኤሊሳ፣ተርሴስ፣ኪቲም፣ሪድኢ።8የካም ወንዶች ልጆች፤ ኪሽ፣ ምፅራይም፣ ፋጥናከነዓን። 9የኩሽ ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማናሰብቃታ። ያራዕማ ወንዶች ልጆች፤ ሳባናድዳን ነበሩ። 10ኩሽ ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ የመጀመሪያው ኅያል ጦረኛ ሆነ።11ምፅራይም የሉዲማውያን፣ የዐናማውያን፣ የላህባማውያን፣ የነፍተሂማውያን፣ 12የፈትሩሲማውያን፣ የፍልስጥኤማውያን ቅድመ አባቶች የሆኑት የከስሉሂማውያንና የከፍቶሪማውያን ነገዶች አባት ነው።13ከነዓን የበኩር ልጁ የሆነው የሶዶን እንዲሁም የከጢያውያን፣ 14የኢያቡሳውያን፣ 15የኤዊውያን፣ የዐርካውያን፣ 16የሲኒውያን፣ የአራዴዎውያን፣ የሰማርያውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነው።17የሴም ወንዶች ልጆች፤ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም። የአራም ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሳሕ። 18አርፋክስድ ሳላን ወለደ። 19ዔርቦ ወንዶች ልጆች ወለደ፤ በዘመኑ ምድር ስለተከፈለች፣ የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተብሎ ተጠራ፣20ዮቅጣንም፡ አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣ 21ሀዶራምን፣አውዛልን፣ደቅላን፣ 22ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣ 23ኦፋርን፣ ኤውላጥን፣ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ወንዶች ልጆች ናቸው።24ሴም፣ አርፋክስድ፣ ሳለ፣ 25ዔቦር፣ ፋሌቅ፣ ራግው፣ 26ሴሮህ፣ ናኮር፣ ታራ፣ 27እንዲሁም በኋላ አብርሃም የተባለ አብራም።28የአብርሃም ወንዶች ልጆች፤ይስሐቅና እስማኤልሲሆኑ። 29የእነዚህ ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ የእስማኤል በኩር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብ፣ ዳኤል፣ መብሳም፣ 30ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ ኩዳን፣ ቴማን፣ 31ኢጡር፣ ናፌስ፣ ቄድማ፣ እነዚህ የእስማኤል ወንዶች ልጆች ናቸው።32የአብርሃም ቁባት ኬጡራ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ዘምራን፣ ዮቅሳን፣ ሜዳን፣ ምድያም፣ የስቦቅና፣ ስዌሕ ናቸው። የዮቅሳን ወንዶች ልጆች፤ ሳባ፣ ድዳን፣ 33የምድያም ወንዶች ልጆች፤ ጌፈር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕ፣ ኤልዳዓ፣ እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ዘሮች ናቸው።34አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅ ወንዶች ልጆች፤ ዔሳው፣ እስራኤል። 35የዔሳው ወንዶች ልጆች፤ ኤልፋዝ፣ ራጉኤል፣ የዑስ፣ የዕላም፣ ቆሬ። 36የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች ቴማር፣ ኦማር፣ ሰፎ፣ ጎቶም፣ ቄኔዝ፣ ቲምናዕ፣ አማሌቅ። 37የራጉኤል ወንዶች ልጆች፤ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማ፣ ሚዛህ።38የሴይር ወንዶች ልጆች፤ ሎጣን፣ ሦባል፣ ጽብዖን፣ ዓና፣ ዲሶን፣ ኤጽር፣ ዲሳን። 39የሎጣን ወንዶች ልጆች፤ ሖሪ፣ ሄማም፣ ቲሞናዕ፣ የሎጣን፣ እኅት ነበረች። 40የሦባል ወንዶች ልጆች፤ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔናል፣ ስፎ፣ አውናም። የጽብዖን ወንዶች ልጆች፤ አያ፣ ዓና።41የዓና ወንድ ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶን ወንዶች ልጆች፤ ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን፣ ክራን። 42የኤጽር ወንዶች ልጆች፤ ቢልሐን፣ ዛዕዋን፣ ዓቃን። የዲሳን ወንዶች ልጆች፤ ዑፅ፣ አራን።43በእስራኤል አንድም ንጉሥ ገና ሳይነግሥ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ ከተማይቱም ዲንሃባ ትባል ነበር። 44ባላቅ ሲሞትም የባሳራ ሰው የሆነው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። 45ኢዮባብ ሲሞት የቴማን አገር ሰው የሆነው ሑሳም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።46ሑሳም ሲሞት በሞዓብ ምድር ምድያ ምን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። የከተማይቱም ስም ዓዊት ተባለ። 47ሃዳድም ሲሞት የመሥሬቃ ሰው የሆነው ሠምላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። 48ሠምላም ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለችው የረኆቦት ሰው የሆነው ሳኡል በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።49ሳኡልም ሲሞት የዓክቦል ልጅ የሆነው በኣልሕናንም ሲሞት በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። 50በኣልሐናን ሲሞት ሀዳድ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። ከተማው ፋዑ ትባል ነበር፤ ሚስቱ መሄጣብኤል ትባልላለች፤ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።51ሀዳድም ሞተ። ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣ 52አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣ ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣ 53ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣ 54መግዲኤል፣ ዒራም። እነዚህ የኤዶም አለቆች ነበሩ።
1የእስራኤል ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ 2ዳን፣ ዮሴፍ፣ ብንያም፣ ንፍታሌም፣ ጋድ፣ እሴር።3የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ እነዚህን ጆስቱን ከከነዓን ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኩር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔር ቀፈፈው። 4የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም ባጠቃላይ አምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።5የፋሬስ ወንዶች ልጆች፤ ኤስሮም፣ ሐሙል። 6የዛራ ወንዶች ልጆች፤ ዘምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ከልኮል፣ ዳራ፣ ባጠቃላይ አምስት ናቸው። 7የከሚር ወንድ ልጅ አካን፤ እርሱም ፈፅሞ መደምሰስ የነበረበት ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው። 8የኤታን ወንድ ልጅ፤ አዛርያ።9የኤስሮን ወንዶች ልጆች፤ ይረሕምል፣አራም፣ካሌብ። 10አራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብም የይሁዳ ሕዝብ መሪ የሆነውን ነአሶንን ወለደ፤ 11ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ሰልሞን ቦዔንን ወለደ። 12ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ኢዮብይድ እሴይን ወለደ።13የእሴይ ወንዶች ልጆች፤ የብኩር ልጁ ኤልያብ፣ ሁለተኛ ልጁ አሚናዳብ፣ ሦስተኛ ልጁ ሣማ፣ 14አራተኛው ልጁ ናትናኤል፣ አምስተኛ ልጁ ራዳይ፣ 15ስድስተኛ ልጁ አሳም፣ ሰባተኛ ልጁ ዳዊት።16እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጹሩያ ሦስት ወንዶች ልጆች አቢሳ፣ ኢዮአብና አሣኤል ነበሩ። 17አቢግያ አሜሳይን ወለደች፣ አባቱም ዬቴር የተባለ እስማኤላዊ ነበረ።18የኤስሮም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባና እንዲሁም ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፥ ከዓዜባ የተወለዱት ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። ያሳብ፣ ሶባብ፣ አርዶን፣ 19ዓዙባ ስትሞት፣ ካሌብ ኤፍራታን አገባ፤ እርሷም ሆርን ወለደችለት። 20ሆርኡሪን ወለደ፤ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።21ከዚህም በኋላ ኤስሮም ሥልሳ ዓመት ሲሆነው የገለዓድን አባት የማኪርን ልጅ አገባ፤ እርሷም ሠጉብን ወለደችለት። 22ሠጉብም ኢያዕርን ወለድደ፤ እርሱም በገለዓድ ምድር ሃያ ሦስት አተሞች ያስተዳድር ነበር።23ይሁን እንጂ ጌሹና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኑትን ሥልሳ መነደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባትየማኪር ዘሮች ነበሩ። 24ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።25የኤስሮም የበኩር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤ የበኩር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼን፣ አኪያ። 26ይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናምን እናት ነበረች። 27የይረሕምኤል የበኩር ልጁ የራም ወንዶች፤ መዓስ፣ ያሚን፣ ዔቄር። 28የኦናም ወንዶች ልጆች፤ ሸማይና ያዳ። የሸማይ ወንዶች ልጆች፤ ናዳብና አቢሱር።29የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት። 30የናባድ ወንዶች ልጆች፤ ሴሌድ፣አፋይም፣ሴሌድ፣ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ። 31የአፋይም ወንድ ልጅ፤ይሸዒ።ይሽዒም ሶሳን ወለደ።ሶሳን አሕልይን ወለደ። 32የሸማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች፤ዬቴር፣ዮናታን፣ዬቴርም ልጅ ሳይወልድ ሞተ። 33የዮናታን ወንዶች ልጆች፤ፌሌት፣ዛዛ። እነዚህ የይረሕምኤል ዘሮች ነበሩ።34ሶሳን ሴቶች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። እርሱም ኢዮሄል የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበርረው። 35ሶሳን ልጁን ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፤ እርሷም ዓይታ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት።36ዓታይ ናታንን ወለደ፣ናታንም ዛባድን ወለደ፣ 37ዛባድ ኤፍላን ወለደ፤ ኤፍላል ዖቤድን ወለደ፤ 38ዖቤድ ኢዩን ወለደ፤ ኢዩ ዓዛርያስን ወለደ፤39ዓዛርያስ ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስ ኤልዓሣ ወለደ፤ 40ኤልዓሣ ሲስማይን ወለደ፤ ሲስማይ ሰሎምን ወለደ፤ 41ሰሎም የቃምያን ወለደ፤ የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።42የይረሕምኤል ወንድም የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ የበኩር ልጁ ሞሳ ሲሆን፤ እርሱም ዚፍን ወለደ፤ ዚፍም መሪሳን ወለደ፤ መሪ ሳም ኬብሮንን ወለደ። 43የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ ቆሬ፣ ተፋዋ፣ ሬቄም፣ ሽማዕ። 44ሽማዕ ርችሐምን ወለደ፤ ረሐምም ዮርቅዓምን ወለደ። ሬቄም ሽማይን ወለደ፤45ሽማይም ማዖንን ወለደ፤ ማዖንም ቤት ጹርን ወለደ። 46የካሌብ ቁባት ዔፋ ሐራንን፣ ሞዳን፣ ጋዜዝን ወለደች። ሐራንም ጋዜዝን ወለደ። 47የያህዳይ ወንዶች ልጆች፤ ሬጌም፣ ኢዮታም፣ ጌሻን፣ ፋሌጥ፣ ዔፋ፣ ሸዓፍ።48የካሌብ ቁባት ማዕካ ሼቤርን፣ ቲርሐናን ወለደለችለት። 49እንዲሁም የመድማናን አባት ሸዓፍን፣ የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች። ካሌብ ዓክሳ የተባለች ልጅ ነበረችው። 50የኤፍራታ የበኩር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች ሦባል የቂርያት ይዓሪም አባት፤51ሰልሞን የቤተልሔም አባት፤ ሐሬፍ የቤት ጋዴር አባት።52የቂርያትይዓሪም አባት የሦባል ዘሮች፤ የመናሕታውያን ነዋሪዎች እኩሌታ፣ ሀሮኤ፤ 53እንዲሁም የቂርያትይዓሪም ጎሣዎች፤ ይትራውያን፤ ፋታውያን፣ ሹማታውያን፣ ሚሽራውያን፤ ጾርዓውያንና ኤሽታኦውያን ከእነዚህ የመጡ ጎሣዎች ነበሩ።54የሰልሞን ዘሮች፤ ቤተልሔም፣ ነጦፋውያን፣ ዓጣሮት ቤት ዮአብ፣ የመናሕታውያን እኩሌታ፣ ጾርዓውያን። 55በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጎሣዎች ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።
1ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው የብኩር ልጁ አምኖን፣ሁለተኛው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ የተወለደው ዳንኤል፣ 2ሦስተኛው ከጌሹር ንጉሥ ከተማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው አቤሴሎም፣አራተኛው የአጊት ልጅ አዶንያስ፣ 3አምስተኛው ከሚስቱ ከዔግላ የተወለደው ይትረኃም።4እነዚህ ስድስቱ የተወለዱት ዳዊት በኬብሮን ሆኖ ሰባት ዓመት ተኩል በገዛበት ጊዜ ነበር። ዳዊት በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፤ 5በዚያም የወለዳቸው ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰለሞን፣ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።6እንዲሁም ሌሎች ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ኢያቤሐር፣ ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣ 7ኖጋ፣ ናፌቅ፣ ያፍያ፣ 8ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባላል፤ ባጠቃላይ ዘጠነኛ ነበሩ። 9ከቁባቶቹ ከወለዳቸው ወንዶች ልጆች ሌላ እነዚህ ሁሉ ልጆቹ ነበሩ፤ እነዚህም ትዕማር የምትባል እኅት ነበረቻቸው።10የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ የሮብዓም ልጅ አቢያ፣ የአቢያ ልጅ አሳ፣ የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣ 11የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም፣ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ፣ 12የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፣ የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ፣ የዓዛርያስ ልጅ ኢዮአታም፣13የኢዮአታም ልጅ አካዝ፣ የአካዝዝ ልጅ ሕዝቅያስ፣ የሕዝቅያስ ልጅ ማናሴ፣ 14የምናሴ ልጅ አሞጽ፣ የአሞጽ፣ የአሞጽ ልጅ ኢዮስያስ፣15የኢዮስያስ ወንዶች ልጆች፣ በኩሩ ዮሐናን በኩሩ ዮሐናን፣ ሁለተኛ ልጁ ኢዮአቄም፣ ሦስተኛ ልጁ ሴዴቅያስ፣ አራተኛ ልጁ ሰሎም። 16የኢዮአቄም ዘሮች፤ ልጁ ኢኮንያ፣ ልጁ ሴዴቅያስ።17የምርኮኛው የኢኮንያን ዘሮች፣ ልጁ ሰላትያል፣ 18መልኪራም፣ ፈዳያ፣ ሼናጻር፣ ይቃምያ፣ ሆሻማ፣ ነዳብያ።19የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤ ዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፥ ሜሱላም፣ ሐናንያ፣ እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች። 20ሌሎችም አምስት ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም ሐሹባ፣ ኦሄል፣ በራክያ፣ ሐሳድያ፣ ዮሻብሒሴድ። 21የሐናንያ ዘሮች፤ ፈላጥን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች።22የሴኬንያ ዘሮች፤ ሸማያና ወንዶች ልጆቹ፤ ሐሙስ፣ ይግአል፣ ባሪያሕ፣ ነዓርያ፣ ሻፋጥ፣ ባጠቃላይ ስድስት ነበሩ። 23የነዓርያ ወንዶች ልጆች፤ ኤልዩዔናይም 24ወንዶች ልጆች፤ ሆዳይዋ፣ ኤልያሴብ፣ ፌልያ፣ ዓቁብ፣ ዮሐናን፣ ደላያ፣ ዓናኒ፤ ባጠቃላይ ሰባት ናቸው።
1የይሁዳ ዘሮች፤ ፋሬስ፣ ኤስሮም፣ ከርሚ፣ ሆር፣ ሦባል። 2የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዝዝዚህ የጾርዓውያን ጎሣዎች ናቸው።3የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች። 4ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻ ምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኩር ልጅና የቤተልሔም አባት የሆነው የሆር ዘሮች ናቸው።5የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለቱ ሚስቶች ነበሩት። 6ነዕራም አሑዛምን፣ ኦፌርን፣ ቴምኒን፣ አሐሽታሪን ወለደችለት፤ የነዕራ ዘሮች እነዚህ ነበሩ። 7የሔላ ወንዶች ልጆች፤ ዴሬት፣ ይጽሐር፣ ኤትናን ናቸው። 8የቆጽ ወንዶች ልጆች ደግሞም ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ናቸው።9ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም "በጣር የወለድድኩት" ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው። 10ያቤጽም፣ "አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፣ እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን፣ ከሥቃይና ከጉዳትም ጠብቀኝ" በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ።እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።11የሹሐ ወንድም ክሉብ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርን ወለደ፤ ምሒርም ኤሽቶን ወለደ፤ 12ኤሽቶን ቤትራፋንና ፋሴሐን ወለደ፤ የዒርናሐሽን ከተሞች የቁረቁረ እርሱ ነው። እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።13የቄኔዝ ወንዶች ልጆች፤ ሐታት፣ መዖኖታይ። 14መዖታይ ደግሞ ዖፍራን ወለደ። ሠራያ የኢዮአብ አባት ሲሆን፣ ኢዮአብ ጌሐራሺምን ወለደ፤ የእደ ጥበብ ባለ ሙያዎች ስለ ነበሩ ይህ ስም ተሰጣቸው። 15የዮፎኔ ልጅ የካሌብ ወንዶች ልጆች፤ ዒሩ፣ ኤላ፣ ነዓም። የኤላ ልጅ ቄኔዝ። 16የይሃልኤል ወንዶች ልጆች፤ ዚፍ፣ ዚፋ፣ ቲርያ፣አሣርኤል።17የዕዝራ ሜሬድ፣ዔፌር፣ያሎን። ከሜሬድ ሚስቶች እንዲቱ ማርያምን፣ ሽማይንና የኤሽትምዓን አባት ፅሽባን ወለደች። 18አይሁዳዊት ሚስቱም የጌዶርን አባት ዮሬድን፣ የጆኮን አባት ሔቤርን፣ የዛኖዋን አባት ይቁቲኤልን ወለደች፤ እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።19የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤ የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ። 20የሺሞን ወንዶች ልጆች፤ አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት።21የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤ የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጎሣዎች አባት ለዓዳ፣ 22ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ኢዮአስ፣ ሞዓብን የገዛ ሣራፍና ያሹቢሌሔም። ታሪካቸውም ጥንታዊነት ያለው ነው። 23ሰዎቹ ነበጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር።24የስምዖን ዘሮች፤ ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪን፣ ዛራ፣ ሳኡል፣ 25ሰሎም የሳኡል ልጅ ነው፤ መብሳም የሰሎም ልጅ ነው፤ ማስማዕ ደግሞ የመብሳም ልጅ ነው። 26የማስማዕ ዘሮች ልጁ ሃሙኤል፣ ልጁ ዘኩር፣ ልጁ ሰሜኢ።27ሰሚኤ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሯቸው፤ ስለዚህ ጎሣቸው በሙሉ እንደ ይሁዳ ሕዝብ ብዙ አልነበረም። 28የኖረባችውም ቦታዎች እነዚህ ናቸው። ቤርሳቤህ፣ ሞላደ፣ ሐጻርሹዓል፣29ቢልሃ፣ ዔጼም፣ ቶላድ፣ 30ቤቱኤል፣ ሔርማ፣ ፊቅላግ፣ 31ቤትማርካቦት፣ ሐጸርሲሲም፣ ቤትቢሪ፣ ሽዓራይም፣ እስከ ዳዊት ዘመነ መንግስት ድረስ የኖሩት በእነዚህ ከተሞች ነው።32በአካባቢያቸው የሚገኙት ወንደሮች ደግሞ ኤጣም፣ ዓይን፣ ሬሞን፣ ቶኬን፣ ዓሻን የተባሉ አምስት ከተሞች ናቸው፤ 33በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ በአል የሚዝችልቁ መንደሮች ነበሩ፤ መኖሪያቸው በዚሁ ሲሆን፤ የትውልድ መዝገብም አላቸው።34ሞሾብብ፣ የምሌክ፣ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያስ፣ 35ኢዮኤል፣ የዮሺብያ ልጅ፣ የሠራያ የዓጂኤል ልጅ ኢዩ 36እንዲሁም ኤልዩዔናይ፣ ያዕቆብ፣ ፅሾሐያ፣ ዓሣያ፣ ዓሲዔል፣ ዩሲምኤል፣ በናያስ፣ 37የሺፊ ልጅ ዚዛ፣ የአሎን ልጅ፣ የይዳያ ልጅ፣ የሺምሪ ልጅ፤ የሸማያ ልጅ፤ 38እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘረው ሰዎች የየጎሣቸው መሪዎች ነበሩ፤ የቤተሰባቸው ብዛት እጅግ በጣም እየጨመረ ሄደ፤39እነርሱም ለከብቶቻቸው ግጦሽ ፍለጋ ከሸለቆው በስተምስራቅ እስካለው እስከ ጌደር መግቢያ ድረስ ዘልቀው ሄዱ። 40በዚያም ለምለምና ያማረ የግጦሽ ቦታ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊ፤ ሰላምና ጸጥታ የሰፈነበት ነበረች። በቀድሞ ቀመን በዚህ ምድር ይኖሩ የነበሩት አንዳንድ የካም ዘሮቼ ናቸው። 41እነዚህ ስማቸው ከላይ የተዘረዘሩው ወደዚሁ ቦታ የመቱት በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ነበረ፤ እነርሱም በድንኳኖቻቸው ውስጥ በነበሩበት በካም ወገኖችና በምዑናውያን ላይ አደጋ በመጣል ፈፅመው አላጠፋአቸው፤ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል። ለመንጎቻቸው በቂ ግጦሽ ቦታ ስላላገኙ፣ በዚያ መኖር ጀመሩ።42ከእነዚሁ አምስት መቶ የሚሆኑ የስምዖን ወገኖች በይሽዒ ልጆች በፈላጥያ፣ በነዓርያ፣ በረፋያና በዑዝኤል ተመርተው የሴይርን ኩረብታማ አገር ወረሩ። 43አምልጠው የቀሩትን አማሌቅውያን ፈጅተው እስከ ዛሬ በዚያው ይኖራሉ።
1የእስራኤሌ በኩር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኩር ልጅ ቢሆንም፤ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፤ የበኩርናው መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቶአል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኩርነቱን ተራ ይዞ ሊቁጥል አልቻለም። 2ይሁዳ ከወንድሞቹ ይልቅ ብርቱ ነበረ፤ ገዥ የወጣው ከእርሱ ቢሆንም፣ የበኩርነት መብቱ የተላለፈው ለዮሴፍ ነበረ። 3የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች፤ ሄኖኅ፣ ፋሉሶ፣ አስሮን፣ ከርሚ ነበሩ።4የኢዮኤል ዘሮች ልጁ ሽማያ፣ ልጁ ጎግ፣ ልጁ ስሜኢ፣ 5ልጁ ሚካ፣ ልጁ ራያ፣ ልጁ ቢኤል፣ 6የአጆር ንጉስ ቴልጌል ቴልፌልሶር ማኮር የወሰደው ልጅ ብኤራ ነበሩ።7የቤተሰቡ የዘር ትውልድ በየጎሣ በየጎሣው ሲቁጠር እንደሚከተለው ነው፤ የጎሣ አለቃ የሆነው ኢዮኤል፣ ዘካርያስ፣ 8የኢዮኤል ልጅ፣ እነዚህ ከአሮዔር እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በሚገኘው ምድር ላይ ሰፈሩ። 9ከብቶቻቸው በገለዓድ ምድር በዝተው ስለነበር በምስራቅ በኩል ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድረ በዳው ዳርቻ ድረስ የሚገኘውን ምድር ያዙ።10በሳኦልም ዘመነ መንግሥት በእጃቸው ተመትተው ድል ከተደረጉት አጋራውያን ጋር ተዋጉ፤ በመላው የገለዓድ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኙትን መኖሪያዎቻቸውን ያዙ።11የጋድ ነገድ ደግሞ ከእነርሱ ቀጥሎ እስከ ሰልካ ድረስ በሚገኘው በባሳን ምድር ኖሩ፤ 12አለቃው ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ሳፋም ከዚህም ያናይና ሰፋጥ ሆነው በባሳን ተቀመጡ። 13ቤተ ዘመዶቻቸውም በየቤተሰቡ እነዚህ ነበሩ፤ ሚካኤል፣ ሜሱላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዙኤ፣ ኦቤድ፣ ባጠቃላይ ስባት ነበሩ።14እነዚህ ደግሞ የቢዝ ልጅ፣ የዬዳይ ልጆች፣ ኦቤድ፣ የኢዬሳይ ልጅ፣ የሚካኤል ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የኢዳይ ልጅ፣ የዑሪ ልጅ፣ የሑሪ ልጅ፣ የአቢካኢል ልጆች ናቸው። 15የቤተሰባቸው አለቃ የኑጊ ልጅ፣ የአብዲኤል ልጅ አሒ ነበረ።16እነዚህም በገለኣድ፣ በባሳንና እስከ ዳርቻዋ በሚገኙት መንደሮች እንዲሁም በሳሮን በሚገኙ የግጦሽ ስፍራዎች ሁሉና ከዚያም ወዲያ አልፈው ተቀመጡ። 17እነዚህ ሁሉ ትውልድ በመዝገብ የሰፈሩት በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአታምና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት ነው።18የሮቤል፣ የጋድና፣ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አርባ አራት ሺህ ብቁ የጦር ሰዎች ነበሩአቸው። እነርሱም ጋሻ መያዝ፣ ሰልፍ መምዘዝና ቀስት መሳብ የሚችሉ ጠንካራና በውጊያ የሠለጠኑ ናቸው። 19እነዚህም በአጋራውያን፣ በኢጡር፣ በናፌስ፣ በናዳብ ላይ ዘመቱ።20በጦርነቱም ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው ስለ ነበር፣ በውጊያው ረዳቸው፣ አጋራው ያንንና የጦር አጋሮቻቸውን ሁሉ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ስለ ታመኑበትም ፀሎታቸውን ሰማ። 21የአጋራውያንንም እንስሶች ማረኩ፤ እነዚህም አምሳ ሺህ ግመሎች፣ 250 000 በጎችና ሁለት ሺህ አህዮች ነበሩ። እንዲሁም 100 000 ሰው ማረኩ። 22ውጊያው የእግዚአብሔር ስለነበር ሌሎችም ብዙ ሰዎች ተገደሉ። እስከ ምርኮ ጊዜ ምድሪቱ በእጃቸው ነበረች።23የምናሴ ነገድ እኩሌታ ህዝብ ቁጥር ብዙ ነበረ፣ እነርሱም ከባሳን ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንዔም ድረስ ባለው ምድር ሰፈሩ፤ ይህም እስከ ሳኔር አርሞንዔም ተራራ ድረስ ማለት ነው። 24የየቤተሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፤ ይሽዒ፣ ኤሊኤል፣ ዓዝርኤል፣ ኤርምያ፣ ሆዳይዋ፣ ኢየድኤ፤ እነዚህ ጀግና ተዋጊዎች የታወቁ ሰዎችና የየቤተሰባቸው አለቆች ነበሩ።25ይሁን እንጂ ለአባቶቻቸው አምላክ ታማኞች አልሆኑም፤ እግዚአብሔር ከፊታቸው ያጠፋቸው የምድሪቱን ከሕዝብ አማልክት በማምለክ አመነዘሩ 26ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐት መንፈስ ይኸውም የቴልጌል ቴፌልሶርን መንፈስ አነሣሥቶ የሮቤልን፣ የጋድንና፣ የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ እንዲወሰድ አደረገ። እነዚህንም ወደ ጎዛን ወንዝ ዳርቻ አፈለሳቸው፤ እነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።
1የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌድሶን፣ቀዓት፣ሜራሪ፣ 2የቀዓት ወንዶች ልጆች፤እንበረም፣ ይሰዓር፣ኬብሮን፣ዑዝኤል። 3የእምበረም ልጆች፤ አሮን፣ሙሴ፣ማርያም። የአሮን ወንዶች ልጆች፤ናዳብ፣አብዮድ፣አልዓዛር፣ኢታምር።4አልዓዘር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቡሲን ወለደ፤ 5አቢሲ ኦዚን ወለደ፤6ኦዚ ዘራእያን ወለደ፤ዘራእያ መራዮትን ወለደ፤7መራዮት አማርያን ወለደ፤አማርያ አኪጦብን ወለደ፤ 8አኪጦብ ሳዶቅን ወለደ፤ 9ሳዶቅ አኪማአስን ወለደ፤አኪማአስ ዓዛርያስን ወለደ፤ዓዛርያስ ዮሐናን ወለደ፤10ዮሐናን ዓዛርያስ ወለደ፤እርሱም ሰለሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለግል ነበር፤ 11ዓዛርያስ አማርን ወለደ፤አማርያም አኪጦብን ወለደ፤12አኪጦብ ስሳዶቅን ወለደ፤ሳዶቅ ሰሎምን ወለደ፤13ሰሎም ኬሌቅያስን ወለደ፤ኬሌቅያስ ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤ 14ዓዛርያስ ሠራያን ወለደ፤ሠራያ ኢዮሴዴቅን ወለደ፤ 15እግዚአብሔር የይሁዳና የእየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም አብሮ ተማርኮ ሄደ።16የሌዊ ወንዶች ልጆች፤ ጌድሶን፣ቀዓት፣ሜራሪ። 17የጌድሶን ወንዶች ልጆች፤ሎቢኒ፣ሰሜኢ።18የቀሃት ወንዶች ልጆች፤እምበረም፣ይስዓር፣ኬቤሮን፣ዑዝኤል።19የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊ፣ሙሲ። በየአባቶቻቸው ቤተሰብ የተቁጠሩ የሌዊ ጎሣዎች የሚከተሉት ናቸው፤ 20ከጌርሶን፤ ልጁ ሎቢኒ፣ልጅ ኢኤት፣ልጁ ዛማት፣21ልጁ ዮአክ፣ልጁ አዶ፣ልጁ ዛራ፣ልጁ ያትራይ።22የቀዓት ዘሮች፤ ልጁ አሚናዳብ፣ልጁ ቆሬ፣ልጁ አሴር፣23ልጁ ህልቃና፣ልጁ አቢሳፍ፣ልጁ አሴር፣24ልጁ ኢኢት፣ልጁ ኡርኤል፣ልጁ ዖዝያ፣ልጁ ሳውል።25የሕልቃና ዘሮች፤ አማሢ፣አኪሞት። 26ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሱፊ፣ልጁ ናሐት፣27ልጁ ኤልያብ፣ልጁ ይሮሐም፣ልጁ ሕልቃና፣ልጁ ሳሙኤል።28የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤የበኩር ልጁ ኢዮኤል፣ሁለተኛው ልጁ አብያ። 29የሜራሪ ዘሮች፤ ሞሖሊ፣ልጁ ሎቤኒ፣ልጁ ሰሜኢ፣ልጁ ዖዛ፣ 30ልጁ ሳምን፣ልጁ ሐግያ፣ልጁ ዓሣያ።31ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሄር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤32እርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣በማደሪያው ይኸውም በመገናኛ ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፣አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።33ከወንዶች ልጆቻቸው ጋር ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ከቀዓታዊያን ልጆች፤ሙዚቃ ተጫዋቹ ኤማን፣የኢዮኤል ልጅ፣የሳሙኤል ልጅ፤ 34ሳሙኤል የሕልቃና ልጅ ነበረ፤ ሕልቃና ፣የይሮሐም ልጅ፣ይብኤሊኤል ልጅ፣የቶዋ ልጅ፣ 35የሱፍ ልጅ፣የሥልቃና ልጅ፣የመሐት ልጅ፣የአማሢ ልጅ፣36የሕልቃና ልጅ፣የኢዮኤል ልጅ፣የዓዛርይስስ ልጅ፣የሶፎንያስ ልጅ፣37የታሐት ልጅ፣የአሴር ልጅ፣የአብያሳፍ ልጅ፣የቆሬ ልጅ፣38የይስዓር ልጅ፣የቃዓት ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣የእስራኤል ልጅ።39እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የበራክያ ልጅ፤የሳምዓ ልጅ፤40የሚካኤል ልጅ፣41የኤትኒ ልጅ፣የዛራ ልጅ፣የዓዳያ ልጅ፣42የኤታን ልጅ፣የዛማት ልጅ፣የሰሜኢ ልጅ፣43የኢኤት ልጅ፣የጌድሶን ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣44በስተግራቸው በኩል አብረዋቸው ያሉት የሜራሪ ልጂች፣የቂሳ ልጅ ኤታን፣የአብዲ ልጅ፣የማሎክ ልጅ፣45የሐሸብያ ልጅ፣የአሰያሰ ልጅ፣የኬልቅያስ ልጅ፣46የአማሲ ልጅ፣የባኒ ልጅ፣የሰሜር ልጅ፣ 47የሞሖሊ ልጅ፣የሙሲ ልጅ፣የሜራሪ ልጅ፣የሌዊ ልጅ፣48ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔር ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር።49አሮንና ልጆቹ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ባዘዝው ምሠረት ስለእስራኤል ማስተሰሪያ በቅድስት ቅዱሳኑ ውስጥ የሚያከናውነውን ተግባር ሁሉ፣በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥቃዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውም መሥዋዕት የሚቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ።50የአሮን ዝርያዎች እነዚህ ነበሩ፤ ልጁ አልዓዛር፣ልጅ ፊንሐስ፣ልጁ አቢሹ፣51ልጁ ቡቂ፣ልጁኦዚ፣ልጁ ዘራአያ፣52ልጁ መራዮት፣ልጁ አማርያ፣ልጁ አኪጦብ፣53ልጁ ሳዶቅ፣ልጁ አኪማአስ።54መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታቸው እነዚህ ናቸው፤የመጀመሪያ ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ከቀዓት ጎሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያቸው እነዚህ ነበሩ። 55ለእነርሱም በይሁዳ ምድር የሚገኘው ኬብሮንና በዙሪያዋ ያለው የግጦሽ ቦታ ተሰጠ፣56በኬብሮን ዙሪያ የሚገኙት የዕርሻ ቦታዎችና መንደሮች ግን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ተሰጡ።57ለአሮን ዘሮች የመማፀኛ ከተሞች የሆኑትን ኬብሮንን፣ልብናን፣የቲርን፣ኤሽትሞዓን፣ 58ሖሎንን፣ዳቤርን፣ከነመሰማሪዎቻቸው።59ዓሳንን፣ዮታን፣ቤትሳኒስን ከነመሰማሪዎቻቸው ሰጡ።60ከብንያም ነገድ ድርሻ ላይ ገባዖንን፣ጌባን፣ጋሌማን፣ዓናቶትን ከነመሰማሪያዋቻቸው ሰጡ። ለቀዓት ዘሮች የተከፋፈሉ እነዚህ ከተሞች ባጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ናቸው።61ለቀሩት የቀዓት ዘሮች ደግሞ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ በዕጣ ዐሥር ከተሞች ተሰጧቸው።62ለጌድሶን ነገድ በየጎሣቸው ከይሳኮር፣ከአሴር፣ከንፍታሌምና በባሳን ከሚገኘው ከምናሴ ነገድ ድርሻ ላይ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተመደቡላቸው።63ለሜራሪ ዘሮች በየጎሣቸው ከሮቤል፣ከጋድና ከዛብሎን ድርሻ ላይ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።64እስራኤላዊያን ከተሞቹን በዚሁ ሁኔታ መድበው ከነመሰማሪያዎቻቸው ለሌዋውያኑ ሰጧቸው።65ቀደም ብለው የተጠቀሱትንም ከተሞች ከይሁዳ ከስምዖንና ከብንያም ነገድ ላይ ወስደው በዕጣ መደቡላቸው።66ለአንዳንድ የቀዓት ጎሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ ከተሞች ተሰጣቸው። 67በኮረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን ሴኬምን(የማማፀኛ ከተማ) ፣ኔዝርን፣68ዮቅምዓምን፣ቤትሖሮን፣69ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪዎቻቸው ሰጧቸው።70እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለሩት የቀዓት ጎሣዎች ሰጧቸው።71ለጌድሶናውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ተሰጠ፤72ከይሳኮር ነገድ፤ ቃዴስን፣ዳብራትን 73ራሞትንና ዓኔምናን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤74ከአሴር ነገድ መዓሳልን፣ዓብዶን፣75ሑቆቅንና፣ረአብን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤76ከንፍታሌም ነገድ በገሊላ የሚገኘውን ቃዴስን፣ሐሞንንና፣ቂርያታይምን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።77ከሌዋውያን የቀሩት የሜራሪ ጎሣዎች ደግሞ ከዚህ የሚከተለው ወሰዱ፤ከዛቢሎን ነገድ ዮቅኒዓምን፣ቀርታህን፣ሬሞንና፣ታቦርን፣ከነመሰማሪዮቻቸው ወሰዱ።78ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ኪኢያሪኮ በስተምስራቅ ከሚገኘውን ቦሶርን፣ያሳን፣79ቅዴሞትንና ሜፍዓትን ከነመሰማሮያዎቻችው ወሰዱ፤80ከጋድ ነገድ በገለዓድ የምትገኘውን ሬማትን፣መሃናይምን፣81ሐሴቦንና ኢያዜርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
1የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤ ቶላ፣ፋዋ፣ያሱብ፣ሺምሮን፣ባጠቃላይ አራት ናቸው። 2የቶላ ወንዶች ልጆች፤ኦዚ፣ርረፋያ፣ይሪኤል፣የሕማይ፣ይብሣም፣ሽሚኤል፣እነዚህ የየቤተሰባቸው አለቆች ናቸው።በዳዊት ዘመነመንግሥት ከቶላ ዘሮች በየትውልድ ሀረጋቸው የተቁጠሩ የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ቁጥራቸው ሃያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ። 3የኦዚ ወንድ ልጅ፤ይዝረሕያ። የይዝረሐያ ወንዶች ልጆች፤ሚካኤል፣አብድዩ፣ይሺያ፣አምስቱም አለቆች ነበሩ።4ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሩአቸው፣ከነቤተሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ 36000 ሰዎች ነበሩአቸው።5ከይስኮር ጎሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተሰቦቹ ትውልድ ቁጥር ባጠቃላይ 87000 ነበሩ።6ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ ቤላ፣ቤኬብ፣ይዲኤል። 7የቤላ ወንዶች ልጆች፤ ኤሴቦንም፣ኦዚ፣ዑዝኤል፣ኢያሪሙት፣ዒሪ፣ባጠቃላይ አምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው 22034 ተዋጊ ሰዎች ተመዝገበዋል።8የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ዝሚራ፣ኢዮአስ፣አልዓዛር፣ኤልዮዔናይ፣ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣አብያ፣ዓናቶት፣ዔሌሜት፣እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።9በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል። 10የይዲኤል ልጅ፤ ቢልሐን።የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤ የዑስ፣አሲሳኦር፣11እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተሰቡ አለቆች ነበሩ፤እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ 17200 ተዋጊዎች ነበሯቸው።12(ሳፈንና ሁፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ ሑሺም ደግሞ የአሐር ዘር ነው።)13የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤ ያህጽሔል፣ጉኒ፣ዬጽር፣ሺሌም፤እነዚህ የባላ የልጅ ልጆች ናቸው።14የምናሴ ዘሮች፤ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥርኤል ነው።እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርያ የወለደች ናት፤15ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ።እኅቱም መዓካ ትባል ነበር።ሌላው ዘሩ ሰለጸዓድ ሲሆን፣እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት። 16የሚከር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፣ስሙንም ፋሬስ አለችው።የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።17የኡላም ወንድ ልጅ፤ባዳን፣እነዚህ የምናሴ ልጅ፣የማኪር ልጅ፣የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው፤፤18እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣አቢዔዝርንና መሐላን ወለድች።19የሽሚዳ ወንዶች ልጆች ደግሞ እነዚህ ነበሩ፤ አሒያንምምሴኬም፣ሊቅሒ፣አኒዓም።20የኤፍሬም ዘሮች፤ ሹቱላ፣ልጁ ባሬድምምልጁ ታሐት፣ልጁ ኤልዓዳ፣ልጁ ታሐት፣21ልጁ ዛባድ፣ልጁ ሹቱላ።ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣የአገሩ ተወለጆች በሆኑት በጌት ሰዎች ተገደሉ።22አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ዘመዶቹም መጥተው አፅናኑት።23ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤እርሷም ፀነሰች፤ወንድ ልጅም ወለደች፤በቤተሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪያ አለው።24ሴት ልጁ ስሟ ሲኢራ ይባላል፤እርሷም የታችኛውና የላይኛውን ቤት ሖሮንንና ኡዜን ሼራን የተባሉትን ከተሞች የቁረቁረች ናት።25ልጁ ፋፌ፣ልጁ ሬሴፍ፣ልጁ ቴላ፣ልጁ ታሐን፣26ልጁ ለአዳን፣ልጁ ዓሚሁድ ልጁ ኤሊሳማ፣27ልጁ ነዌ፣ልጁ ኢያሱ።28በምድራቸውና መኖሪያቸው ቤቴልንና በዙሪያዋ የሚገኙት ከተሞች በስተምሥራቅ ነዓራን፣በስተ ምዕራብ ጌዝርንና መንደሮቿን በሙሉ ታጠቃልል ነበር።29በምናሴ ወሰን ላይ ቤትሳን፣ታዕናክ፣መጊዶና ዶና ከነመንደሮቻቸው ነበሩ።በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ነበር።30የአሴር ወንዶች ልጆች፤ዩምና፣የሱዋ፣የሱዊ፣በሪዓ፣እኅታቸውም ሤራሕ ትባል ነበር።31የበሪዓ ወንዶች ልጆች፤ሐቤርም የቢርዛዊት አባት መልኪኤል።32ሔቤርም ያፍሌጥን፣ሳሜርን፣ኮታምንና እኅታቸውን ሶላን ወለደ።33የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች፤ ፋሴክ፣ቢምሃል፣ዓሲት፣የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ ።34የስሜር ወንዶች ልጆች፤ አ፣፥ሮኦጋ፣ይሑባ፣አራም።35የወንድሙ የኤላም ወንዶች ልጆች፤ጾፋ ይምና፣ሰሌስ፣ዓማል።36የጻፋ ወንዶች ልጆች፤ ሱዋ፣ሐርኔፍር፣ሦጋል፣ቤሪ፣ይምራ፣37ቤጼር፣ሆድ፣ሳማ፣ ሰሊሳ፣ይትራን፣ብኤራ።38የዬቴር ወንዶች ልጆች፤ዮሮኒ፣ፊስጻ፣አራ።39የዑላ ወንዶች ልጆች፤ኤራ፣ሐኒኤል፣ሪጽያ። 40እነዚህ ሁሉ የአሴር ዜሮች ናቸው።እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ምርጥ ሰዎች፣ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ።ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቁጥር 26000 ነበር።39የዑላ ወንዶች ልጆች፤ኤራ፣ሐኒኤል፣ሪጽያ። 40እነዚህ ሁሉ የአሴር ዜሮች ናቸው።እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ምርጥ ሰዎች፣ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ።ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቁጥር 26000 ነበር።
1የብንያም አምስት ወንድ ልጆች የነበሩት የብኩር ልጅን ቤላን ፤ አስቤልን፣ አሐራን፣2ኖሐን፣ ራፋን ወለደ።3የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤አዳር ጌራ፣አቢሁድ፣አቡሁድ፣4አቢሱ፣ናዕማን፣ኦሖዋ፣5ጌራ፣ሰፋፋ፣ሒራም።6በጌባ ይኑሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው።7ናዕማን፣አኪያ፣ጌራ፣በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የኢሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።8ሽሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፍታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።9ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ዲብያን፣ማሴን፣ማልካምን፣10ይዑጽን፣ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው።11ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች።12የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች፤ ዔቤር፣ሚሻም፣እንዲሁም ኦኖንና ሎድ የተባሉ ከተሞች ከነመንደሮቻቸው የቁረቁረ ሻሜድ፣13በኤሌን ይኖሩ ለነበሩ ቤተሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ።14አሒዮ፣ሻሻቅ፣ይሬምት፣15ዝባድያ፣ዓራያ፣ዔድር፣ 16ሚካኤል፣ይሽጻናዮሐ የበሪያ ወንዶች ልጆች ነበሩ።17ዝባድያ፣ሜሱላም፣ህዝቂ፣ሔቤር፣18ይሽምራይ፣ ይዝሊያና፣ዮባብ፣የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ።19-21ሺሜኢ እነዚህ ወንዶች ልጆች ያቃም፣ዝክሪ፣ዘብዲ፣ኤሊዔናይ፣ጺልታይ፣ኤሊኤል ፣ዓዳያ፣ብራያና፣ሺምራት ነበሩት።22ይሽጻን፣ዔቤር፣ኤሊኤል፣23ዓብዶን፣ዝክሪ፣ሐናን፣ 24ሐናንያ፣ኤላም፣ዓንቶትንያ 25ይፍዴያና ፋኑኤል የሶሴቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ።26ሽምሽራይ፣ሽሃሪያ፣ጎቶልያ፣27ያሬሽያ፣ኤልያስና፣ዝክሪ የይሮሐም ወንዶች ልጆች ነበሩ።28እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐርረጋቸው የተቁጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።29የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ኖረ፣ሚስቱ መዓካ ትባል ነበር።30የበኩር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፣የእርሱም ተከታታዮች ዱር፣ቂስ፣በኣል፣ኔር፣ናዳብ፣31ጌዶር፣አሂዮ፣ዛኩርና፣32የሺምዓ አባት ሚቅሎት ነበሩ።እነዚህም ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም ከተማ አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።33ኔር ቂስን ወለደ፣ቂስ ሳኦልንወለደ፣ሳኦልም ዮናታንን፣ሜልኪሳን፣አሚናዳብን፣አስበኣልን ወለደ።34የዮናትን ወንድ ልጅ መሪበኣልን፣እርሱም ሚካን ወለደ።35የሚካ ወንዶች ልጆች ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ ነበሩ። 36አካዝ ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዔሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞዳን ወለደ። 37ሞጻ ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ረፋያን ወለደ፤ ረፋያ ኤልዓሣን ወለደ። ኤልዓሣም ኤሴልን ወለደ።38ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሽዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ። 39የእርሱ ወንድም የኤሴቅ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛው ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛው ልጁ ኤላፋላት ናቸው። 40የኡላም ልጆች ጦረኞችና ቀስተኞች ነበሩ። ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩዋቸው፤ ጠቅላላ ቁጥራቸው አንድ መቶ ሃምሳ ነበር። እነዚህ ሁሉ የብንያም ዘሮች ናቸው።
1እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቁጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ።የይሁዳ ሕዝብ ከፈፀሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ።2በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ካህናት፣ሌዋውያንና ቤተመቅደሱ ውስጥ የጉልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።3በእየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የይሁዳ፣የብንያም፣የኤፍሬምና ምናሴ ነገዶች የሚከተሉት ናቸው፤4ከሰፋሪዎችም መካከል ይሁዳ ልጅ፣ከፋሬስ ዘሮች፣የባኒ ልጅ፣የአምሪ ልጅ፣የዖምሪ ልጅ፣የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ። 5ከሴሎናውያን፦የበኩር ልጁ ዓሣያና ወንዶች ልጆቹ። 6ከዛራውያን ዝርያዎች መካከል ይዑኤል፤ የሕዝቡ ቁጥር 690 ነበረ።7ከብንያማዊን፦የሐስኑኤ ልጅ፣የሆዳይዋ ልጅ፣የሜሱላ ልጅ ስሉ።8የይሮሐም ልጅ ብኔያ፣የሚክሪ ልጅ፣የኦዚ ልጅ ኤላ፣የይብንያ ልጅ፣የራጉኤል ልጅ፣የሰፋ ጥያ ልጅ ሜሱላም። 9በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቁጥር ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበረ፤እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተሰብ አለቆች ነበሩ።10ከካህናቱ፦ ዮዳኤ፣ዮአሪብ፣ያኪን፣11የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የሆነው የአኪጦብ ልጅ፣የጳስኮር ልጅ፣የይሮሐም ልጅ፣የሜሱላም ልጅ፣የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ።12የመልክያ ልጅ፣የጳስኮር ልጅ፣የሳዶቅ ልጅ፣ዓዳያ፣የኢሜር ልጅ፣የምሺላሚት ልጅ፣የሜሴላም ልጅ፣የየሕዜራ ልጅ፣የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።13የቤተሰብ አለቃ የነበሩ ካህናት ቁጥር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሥልሳ ነበረ፤እነዚህም በእግዚአብሔር ብት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።14ከሌዋውያን ወገን፦ ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣የዓዝሪቃም ልጅ፣የአሱብ ልጅ፣ሽማያ፣15በቅበቃር፣ኤሬስ፣ጋላልና የአሳፍ ልጅ የዝክሪ፣የሚካ ልጅ፣መታንያ።16የኤዶም ልጅ፣የጋላል ልጅ፣ይችሰሙስ ልጅ፣አብድያ።እንዲሁም በነጦፋውያን ከተሞች የኖረው የሕልቅና ልጅ፣የአሳ ልጅ በራክያ።17የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎች፦ሰሎም፣ዓቁብ፣ጡልሞን፣አሂማንና ወንድሞቻቸው፣አለቃቸው ሰሎም ነበረ፤18እነርሱም በስተ ምስራቅ በሚገኝው በንጉስ በር እካሁን ድረስ ተመድቦአል።እነዚህ የሌዋያኑ ሰፈር በር ጠባቂዎች ነበሩ።19የቆሬ የአብያሳፍ ልጅ፣የቆሬ ልጅ ሰሎምና ክእነሱም ቤተሰብ የሆኑት ቆሬያውያን ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ እንደ ነበር ሁሉ፣እነዚህም ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያስገባውን በር ይጠብቁ ነበር።20በቀድሞ ጊዜ የበር ጠባቂዎቹ አለቃ የአላዓዛር ልጅ ፊንሐስ ነበረ፥እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ።21ወደ መገኛው ድንኳን የምያስገባው በር የሚጠብቀው ደግሞ የሜሱላም ልጅ ዘካሪያስ ነበረ።22መግቢያ በሮቹን እንዲጠብቁ የተመረጡ ባጠቃላይ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።እነርሱም በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት በሚኖሩባቸው መንደሮች ተቁጥረው ተመዘገቡ፤በር ጠባቂዎቹን በዚያ ቦታ ላይ የመደቡላቸው ዳዊትና ባለ ራእዩ ሳሙኤል ነበሩ።23የማደሪያውን ድንኳን ምማለትም የእግዚአብሔርን ቤት የሚጠብቁትንም እነርሱና ዘሮቻቸው ነበሩ።24በር ጠባቂዎቹም በምሥራቅ፣በምዕራብ፣በሰሜንና፣በደቡብ በሚገኙት በአራቱም ማዕዘኖች ላይ ነበሩ።25ወንድሞቻቸውም በየመንደሮቻቸው ሆነው በየጊዜው እየወጡ የጥበቃውን ሥራ ሰባት ሰባት ቀን ያግዙአቸው ነበር።26ሌዋውያን የነበሩት አራቱ የበር ጠባቂ አለቆች ግን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች በኃላፊነት ይጠብቁ ነበር።27የጥበቃውን ሥራ የሚያከናውኑት እነርሱ በመሆናቸው የሚያድሩትም በዚያው በእግዚአብሔር ቤት አካባቢ ነበረ፤ጠዋት ጠዋትም ደጆቹን የሚከፋፍቱት እነርሱ ነበሩ።28ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለብቤተመቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኃላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወቱበት ጊዜ ሁሉ ይቁትሩ ነበር፤29ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ዕቃዎቹንና የቤተ መውደሱን ንዋያት ቅድሳት፣ዱቄቱን፣የወይን ጠጁን፣የወይራ ዘይቱን፣ዕጣኑን የሽቱውን ቅመማ ቅመም እንዲጠብቁ ተምመድበው ነበር።30ከካህናቱም አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅመማ ቅመም ይለውሱ ያዘጋጁ ነበር።31የቆሬያዊው የሰሎም በኩር ልጅ ሌዋዊው ማቲትያ የቁርባኑን እንጀራ የመጋገር ኅላፊነት ተሰጥቶት ነበር።32በየሰንበቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።33የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በብይተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነፃ ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።34እነዚሁ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣በትውልድ ሐረጋቸ መሠረት ተመዘገቡ፤የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።35የገባዖን አባት ይዒኤል የሚኖረው በገባዖን ነበረ፤የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።36የበኩር ልጁ ዓብዶን ሲሆን፣የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ቂስ፣በኣል፣ኔር፣ናዳብ፣37ጌዶር፣አሒዮ፣ዛኩር፣ሚቅሎት ነበሩ።38ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፣እርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።39ኔር ቂስን ወለደ፤ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ሳኦል ዮናታን፣ሜልኪሳን፣አሚናዳብን፣አስበኣልን ወለደ።40የዮናታ ወንድ ልጅ፤ መሪበኣል ነው፤መሪበኣል ሚካን ወለደ41የሚካ ወንዶች ልጆች፤ፒቶን፣ሜሌክ፣ታሬዓ፣አካዝ።42አካዝ የዕራን ወለደ፤ዘምንሪን ሞፃን ወለደ። 43ሞፃም ቢንዓን ወለደ፤ልጁ ረፋያ ነበረ፤ልጁ ኤልዓሣ፣ልጁ ኤሴል።44ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ስማቸውም፦ ዓዝሪቃም፣ቦክሩ፣እስማኤል፣ሸዓርያ፣አብድዩ ሐናን እነዚህ የኤሴል ወንዶች ልጆች ናቸው።
1ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ራኤላውያንም ከፊታቸ ሸሹ፤ብዙዎች በጊቦልቦን ተራራ ላይ ሞቱ።2ፍልስጥኤማውያን ሳኦልንና ልጆቹን ይበልጥ አሳደዱአቸው የሳኦልም ልጆች ዮናታን፣አሚናዳብንና ሜልካሳን ገደሉ፤3ሳኦል በተሰለፈበት ግንባር ውጊያው በረታ፤ቀስተኞችም አግኝተው አቁሰሉት።4ሳኦል ጋሻ ጃግሬውን፣"እነዚህ ሸለፈታምፕች መሳለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰልፍህን መዝዘህ ውጋኝ"አለው።ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ሰለ ነበር አልደፍርም፤ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።5ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል መሞቱን ሲያይ፤እርሱም በሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።6ስለዚህ ሳዖልና ሦስት ልጆቹ ሞቱ፤ቤተ ሰዎቹም ሁሉ አብረው ሞቱ።7በሸለቆው ውስጥ የነበሩት እስራኤላዊያን ሁሉ ሰራዊቱ እንደ ሸሽ፣ሳኢልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ፍልስጥኤማውያንመጥተው ከተሞቹን ያዙ።8በማግሥቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ ሲመጡ፣ሳኦልና ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።9ሳኦልን ከገፈፉ፣ረሱን ከቁረጡና መሣሪያውንም ከወሰዱ በኋላ፣ለአማልክቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራቹን እንዲነግሩ ወደ መላው የፍልስጥኤም ምድር መልክዕተኞች ላኩ።10ከዚህም መሣሪያውን በአማልክቶቻቸው ቤተ ጣዖት አኖሩ፤ራሱንም በዳጎን ቤተ ጣዖት ውስጥ አንጠለጠሉት።11የኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ፤12ብርቱ የሆኑ ሰዎች ሄደው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ አንሥተው ወደ ኢያቢስ አመጡ፤ዐጽማቸውንም ኢያቢስ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ከዚህያም ሰባት ቀን ጾሙ።13ሳኦል እግዚአብሔር ስላታዘዘ ሞተ፤የእግዚአብሔር ቃል አልጠበቀም፤ይልቁንም ከሙታን ጠሪ ምክርን ጠየቀ፤14ይህን ከእግዚአብሔር አልጠየቀም፤ስስለዚህ እግዚአብሔር ገደለው፤መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት እንዲተላለፍ አደረገ።
1እስራኤል ሁሉ በኬብሮን ወደ እነሆ፤እኛ የገዛ ሥጋህና ደምህ ነን፤2-3በቀደመው ዘመን ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን ወደ ጦርነት የምትመራ አንተ ነበርህ፤እግዚአብሔር አምላክም፣ሕዝቤን እስራኤልን የምትጠብቅ አንተ ነህ፤ንጉሥ ዳዊት ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ከእነሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባ።እግዚአብሔር በሳሙኤል አማካይነት በሰጠው ተስፋ መሠረት ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።4ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ ኢያቡስ ወደምትባለው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ።በዚያም የሚኖሩ ኢያቡሳዊያን፤5ዳዊትን "ወደዚያ ፈፅሞ አትገባም"አሉት፤ዳዊትግን የጽዮንን ምሽግ ያዘ፤እርሷም የዳዊት ከተማ ናት። 6ዳዊትና "ኢያቡሳዊያንን ቀድሞ የሚወጋ ሰው የሰራዊቱ አዛዥ ይሆናል"አለ፤ስለዚህ የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ወጣ፤እርሱም አዛዥ ለመሆን በቃ።7ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐባምዩቱ ውስጥ አደረገ፤ከዚያም የተነሣ የዳዊት ከተማ ተባለች።8ዳዊትም ከሚሎ ጀምሮ የከተማይቱን ዙሪያ ቅጥር ሠራ፤ኢዮአብ ደግሞ የቀረውን የከተማይቱን ክፍል መልሶ ሠራ።9እግዚአብሔር ጸባኦት ከእርሱ ጋር ሰለ ነበር ዳዊት በየጊዜው እየበረታ ሄደ።10የዳዊት ኅያላን ሰዎች አለቆች እነዚህ ናቸው፤እነርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንግሥቱን በምድሪቱ ሁሉ ትስፋ ዘንድ ከሌሎች እስራኤላዊያን ጋር ሆነው ለመንግሥቱ ብርቱ ድጋፍ ሰጡ።11ዳዊት ኅያላን ሰዎች ስም ዜርዜር ይህ ነው፤ ሐክሞናዊው ያሶብዓም የጦር መኮንኖች አለቃ ነበረ፤እነርሱም ጦሩን አንጅቶ በአንድ ጊዜ ሦስት መቶ ሰው ገደለ።12ከእርሱም ቀጥሎ ከሦስቱ ኅያላን አንዱ የሆነው የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ አልዓዘር ነው፤13እርሱም ፍልስጥኤማዊያን ለጦርነት በተሰበሰቡ ጊዜ በፈስደሚም ከዳዊት ጋር አብሮ ነበረ፤ገብስ በሞላበት የእርሻ ቦታ ወታደሮቹ ከፍልስትኤማውያን ፊት ሸሹ፤14ይሁን እንጂ በእርሻው መካከል ቦታ ይዘው ስለ ነበረ ፍልስጥኤማውያንን ገደሉ፤እግዚአብሔር ታላቅ ድል ሰጣቸው።15ከፍልስጥኤማውያን ሰራዊት ጥቂቱ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፣ከሠላሳዎቹ አለቆች ጆስቱ ዳዊትን ለመገናኘት በዓዶላም ዋሻ አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ዐለቱ ወረዱ።16በዚያን ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፤የፍልስጥኤማዊያን ሰራዊት ደግሞ በቤተልሕም ነበረ።17ዳዊትም ውሃ ፈልጎ ነበርና፣"ከቤተ ልሔም በር አቅራቢያ ከሚገኘው ጉድጓድ የምጠጣው ውሃ ማን ባመጣልኝ!" አለ።18በዚህ ጊዜ ጆስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ጥሰው በማለፍ በቤተ ልሔም በር አጠገብ ከሚገኘው ጉድጓድ ውሃ ቀድተው ለዳዊት አመጡለት፤እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈለገ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው፤19ከዚያም "ይህን ከማድረግ እግዚአብሔር የጠብቀኝ፤ይህ በሕይወታችን ቁርጠው የሄዱትን የእነዚህን ሰዎች ደም እንደ መጠጣት አይደለምን?"አለ።ይህን ለማምጣት በሕይወታቸው ቁርጠው ስለ ነበር፣ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም።20የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የጆስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ፤21ከጆስቱ አንዱ ሆኖ ባይቁጠርም እንኳን፣እጥፍ ክብር አገኘ፤አዛዣቸውም ሆነ።22ከቀብስኤል የወጣውና ታላቅ ጀብዱ የሠውው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ብርቱ ተዋጊ ነበረ።እርሱም እጅግ ያታወቁ ሁለት የሞአብ ሰዎች ገደለ።እንዲያውም አንድ ጊዜ በረዶ ምድርን በሰፈነበት ቀን ወደ አንድ ጉድጓድ ወርዶ አንበሳ ወደለ።23ደግሞም ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ አንድ ግብፃዊው የሸማኔ መጥቅለያ የመሰለ ቶር በእጁ ይዞ ገጠመው፤ክችግብፃዊው ጋር እጅ ጦሩ ነጥቆ በገዛ ጦሩ ገደለው።24የዮሄዳ ልጅ በናያስ የፈፀመው ጀብዱ ይህ ነበር፤እርሱም እንደ ሦስቱ ኅያላን ዝነኛ ሆነ።25ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ አንዱ አልነበረመ፤ዳዊትም የክብር ዘቡ አዛዥ አደረገው።26ኅያላኑ ወንድም አሣሄል፤የቤተ ልሔም የዱዲ ልጅ ኤልያናን፤27ሃሮራዊው ሳሞት፣ፊሎናዊው ሴሌዴ፣28የቴቁሔ ሰው የሆነው የዓስካ ልጅ፣ዒራስ፣የዓናቶቱ ሰው፣አቢዔዜር፣29ኩሳዊው ሴቤካይ፣ኦሆሃዊው ዔላይ፣30ነቶፋዊው ማህራይ፣የነቶፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፣31ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኤታል፣ጲርዓቶናዊው በናያስ፣32የገዓስ ሸለቆዎች ሰው የሆነው ኡሪ፣ዓረባዊው አቢኤል፣33ባሕሩማዊው ዓዝሞት፣ሰዓልቦዊው ኤልያሕባ፣34የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፣የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፣35የሃራራዊው የሳኮር ልጅ አሒአም፣የኡር ልጅ ኤሊፋል፣36ምኬራታዊው ኦፌር፣ፍሎናዊው አኪያ፣37ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣የኤዝባይ ልጅ ነዕራይ፤38የናታን ወንድም ኢዮኤል፣የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፣39አሞናዊ ጼሌቅ፣የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮ ታዊው ነሃራይ፣40ይትራዊው ዒራስ፣ይትራዊው ጋሬብ፣41ኬጤያዊው ኦርዮ፣የአህላይ ልጅ ዛባድ፣42የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ ዓዲና፣እርሱም የሮቤላዊያንና አብረውት ለነበሩት የሠላሳ ሰዎች አለቃ ነበረ።43የማዕካ ልጅ ሐናን፣ሚትናዊው ኢዮሣፍጥ፣44አስታሮዊው ዖዝያ፣የአሮዔራዊው የኮታም ልጆች ሻማና ይዒኤል፣45የሺምሪ ልጅ ይዲኤል፣ወንድሙም ቴዳዊው ዮሐ፣46መሐዋዊው ኤሊኤል፣የኤልነዓም ልጆች ይባሪይና ዮሻውያ፣ሞዓባዊው ይትማ፣47ኤሊኤል፣ዖቤድና ምጾባዊው የዕሢኤል።
1ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በጺቅላግ ሳለ ወደ እርሱ የመጡት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤እነርሱም በጦርነቱ ላይ ከረዱት ተዋጊዎች መካከል ነበሩ።2ሰዎቹ ቀስተኞች ሲሆኑ፣በቀኝም ሆነ በግራ እጃቸው ፍላጻ መወርወርና ድንጋይ መወንጨፍ የሚችሉ ነበሩ፤እነርሱም ከብንያም ነገድ የሆነው የሳኦል ሥጋ ዘመዶች ነበሩ፤3አለቃቸው አሐዔዝር ነበረ፥ከእርሱም በኋላ ኢዮአስ ነበረ፤ሁለቱም የጊብዓዊው የሸማዓ ልጆች ነበሩ፤የዓዝሞት ልጆች ይዝኤልና ፋሌጥ፣በራኪያ፣ዓናቶታዊው ኢዩ፣4ገባናዊው ሰማያስ ከሠላሳዎቹም መሪ ነበረ፤ርርሚያስ፣የሕዚኤል ዮሐንስ፣ገድሮታዊው ዮዛባት፣5ኤሊዛይ፣ኢያሪሙት፣በዓልያ፣ሰማራያ፤ሐሩፋዊው ሰፋትያስ፣6ቆሬያውያኑ ሕልቃና፣ይሺያ፣ዓዘኤል፣ዮዛር፣ያሻብዓም፣7የጌዶር ሰው ከሆነው ደግሞ የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዝባድያ።8ዳዊት በምድረ በዳ በሚገኘው ምሽጉ ውስጥ ሳለ፣ከጋድ ነገድ የሆኑ ሰዎች መጥተውው የእርሱን ሰራዊት ተቀላቀሉ፤ከእነሱም ለውጊያ የተዘጋጁ ጋሻና ጦር ለመያዝ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ፊታቸው እንደ አንበሳ እንደሚይዝ ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ ።9የእነዚህም አለቃ ዔፌር ነበረ፤ሁለተኛ አዛዥ አብድዩ፣ሦስተኛው ኤልያብ፣10አራተኛ መስመና፣አምስተኛው ኤርሚያስ፤11ስድስተኛው ዓታይ፣ሰባተኛው ኢሊኤል፣12ስምንተኛው ዮሐናን፣ዘጠነኛው ኤልዛባድ፣13ዐሥረኛው ኤርሚያስ፣ዐሥራ አንድኛው መክበናይ።14እነዚህ ጋዳውያን የጦር አዛዦች ነበሩ፣ከእነሱም ታናሽ የሆነው እንደ መቶ፣ታላቅ የሆነው ደግሞ እንደ ሺህ አለቃ ይቁጠር ነበር።15በመጀመሪያው ወር የዮርዳኖስ ወንዝ ከአፍ እስከ ሞልቶ ሳለ፣ወንዙን ተሻግረው በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ሸለቆዎች ይኖሩ የነበሩትን ሁሉ ከዚያ ያባረሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ።16ሌሎች ከብንያምና ከይሁዳም ወገን የሆኑ ሰዎች ዳዊት ወደሚገኝበት ምሽግ መጡ።17ዳዊትም እነዚህን ሰዎች ሊቀበል ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤የመጣችሁት ልትረዱኝና በሰላም ከሆነ፤ከእኔ ጋር እንድትሰለፉ ልቀበላችሁ ዝግጁ ነኝ፤ነገር ግን እጄ ከበደል ንጹሕ ሆኖ ሳለ፤ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ፤የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፤ይፍረድውም።18ከዚያም እግዚአብሔር መንፈስ በሠላሳዎቹ አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፤እርሱም እንዲህ አለ፤"ዳዊት፤እኛ ክችአንተ ጋር ነን፤ሰላም ፍፁም ሰላም ለአንተ ይሁን፤አንተን ለሚረዱም ሁሉ ሰላም ይሁን፤አምላክህ ይረዳሃል"።ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤የሰራዊቱም አለቃ አደረረጋቸው።19ዳዊት ከፍልስጥኤማዊያን ጋር ተባብሮ ሳኦልን ለመውጋት በሄደ ጊዜ፤ከምናሴ ነገድ የሆኑ ጥቂት ሰዎች ከድተው ከዳዊት ሰራዊት ጋር ተቀላቀሉ።እርሱ ግን ርዳታ አላደረገላቸውም፤ምክንዩም የፍልስትኤማዊያን ገዦች ምክር ካደረጉ በኋላ እንዲህ ሲሉ ልከውት ነበር፤"ከድቶ ወደ ጌታው ውደ ሳኦል ቢሄድ እኛን ያስጨርሰናል።20ዳዊት ወደ ጺውላግ በሄደ ጊዝዜ ከድተው ወደ እርሱ የተቀላቀሉ የምናሴ ነገድ ሰዎች እነዚህ ነበሩ፤ዓድና፣ዮዛባት፣ይዲኤል፣ሚካኤል፣ዮዛባት፣ኤሊሁ፣ ጺልታይ፤እነዚህ በምናሴ ግዛት ሳሉ የሸለቆች ነበሩ።21ሁሉ ብርቱ ተዋጊዎችና በዳዊትም ሰራዊት ውስጥ አዛዦች ሰለ ነበሩ፣አደጋ ጣዮችን በመውጋት ረዱት።22ሰራዊቱም እንደ እግዚአብሔር ሰራዊት እስኪሆን ድረስ፤፣ዳዊትን ለመርዳት በየዕለቱ ብዙ ሰዎች ይጎርፉ ነበር።23እግዚአብሔር ለዳዊት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት የሳኦል መንግሥት አንሥተው ለእርሱ ለመስጠት ዳዊት ወደ ሚገኝበት ወደ ኬቤሮን የመጡት ሰዎች ቁጥር ይህ ነው፤24ጋሻና ጦር አንግበው ለጦርነት የተዘጋጁት የይሁዳ ሰዎች ስድስት ሺህ ስምንት መቶ።25ከስምዖን ነገድ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ሰባት ሺህ አንድ መቶ።26ከሌዊ ነገድ አራት ሺህ ስድስት መቶ፤27የአሮን ቤተ ሰብ መሪ የሆነውን ዮዳሄን ጨምሮ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፤28ወጣቱ ብርቱ ተዋጊ ጻዶቅና ከቤተ ሰቡ ሃያ ሁለት የጦር አለቆች፤29የሳኦል ሥጋ ዘመድ የሆኑ የብንያም ሰዎች ሦስት ሺህ፤ከነዚህም አብዛኞቹ እስከዛያች ጊዜ ድረስ ለሳኦል ቤት ታማኝ ነበሩ፤30ከኤፍሬም ሰዎች በጎሣዎቻቸው ዘንድ ታዋቂ የሆኑ ብርቱ ተዋጊዎች ሃያ ሺህ ስምንት መቶ፤31ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች፤እነርሱም ዳዊትን ለማንገሥ በየስማቸው ተጽፈው የመጡ ነበሩ።32ዘመኑን የተረዱና እስራኤላዊያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ የይሳኮር ሰዎች ሁለት መቶ አለቆች፤በእነሱም ሥር ሆነው የሚታዘዙ ዘመዶቻቸው።33ልምድ ያላቸው፤በሁለቱም ዐይነት መሣሪያ ለመዋጋት የተዘጋጁትና ዳዊትን ለመርዳት የመጡት መንታ ልብ የሌላቸው የዛቢሎን ሰዎች ሃምሳ ሺህ፤34ከንፍታሌም ሰዎች አንድ ሺህ የጦር አለቆች፤ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የያዙ ሠላሳ ሰባት ሺህ ሰዎች፤35ከዳን ሰዎች ለጦርነት የተዘጋጁ ሀያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ፤36ከአሴር ሰዎች ልምድ ያላቸውና ከጦርነት የተዘጋጁ ወታደሮች አርባ ሺህ፤37ከምስራቅ ዮርዳኖስ ከሮቤል፣ከጋድና ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ልዩ ልዩ ዐይነት መሣሪያ የታጠቁ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች።38እነዚህ ሁሉ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ፈቃደኞች የሆኑ ተዋጊዎች ናቸው፤ወደ ኬብሮን የመጡትንም ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ለማንገሥ ወስነው ስለ ነበር ነው።የቀሩትም እስራኤላዊያን ሁሉ ዳዊትን ለማንገሥ በአንድ ሐሳብ ጸኑ።39የሚያስፈልጋቸውን ቤተ ሰቦቻቸው አዘጋጅተውላቸው ሰለ ነበር፣ሰዎቹ እየበሉና እየጠቱ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ቁዩ።40እንዲሁም ሩቅ ከሆነው ከይሳኮር፣ከዛቢሎንና ከንፍታሌም አገር ሳይቀር ጎረቤቶቻቸው በአህያ፣በግመል፣በበቅሎና በበሬ ጭነው ምግብ አመጡላቸው፤በእስራኤል ታላቅ ደስታ ሰለ ሆነ ዱቄት፣የበለስና የዘቢብ ጥፍጥፍ፣የወይን ጠጅ፣የወይራ ዘይት፣የቀንድ ከብትና በጎች በገፍ ቀርበው ነበር።
1ዳዊትም ሻለቆችና መቶ አለቆች ከሆኑት የጦር ሹማምቱ ሁሉ ጋር ተማከረ።2ከዚያም ለመላምው የእስራኤል ማኅበር እንዲህ አለ፤"እንግዲህ ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁ የአምላካችን የእግዚአብሔር ፍቃድ ከሆነ፤በእስራኤል ግዛት ሁሉ ለሚኖሩ በሩቅም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩትም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም በየራሳቸው ከተሞና መሰማሪያዎች የሚኖሩ ካህናትና ሌዋውያን መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰባሰቡ እንላክላቸው።3በሳኦል ዘምን መንግሥት ሳንፈልገው የነበረውን የአምላካችንን ታቦት መልሰን ወደ እኛ እናምጣ።4በገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ መላው ማኅበር ይህንኑ ለማድረግ ተስማማ።5ስለዚህ ዳዊ የእግዚአብሔር ታቦት ከቂርያትይዓሪም ለማምጣት ከግብፅ ወንዝ ከሺሖር ጀምሮ እስከ ሐማት መተላለፊያ ድረስ የሰፈሩትን እስራኤላውያን ሁሉ ሰበሰበ።6ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ በኩሩብና በኪሩብ መካከል የተቀመጠውን፣የእግዚአብሔር በይሁዳ ወዳለችው ቂርያትይዓሪም ወደ ተባለችው ወደ በኣላ ሄዱ።7የእግዚአብሔርም ታቦት ከአሚናዳብ ቤት በእዲስ ሠረገላ ላይ እድርገው አመጡ፤ሠረገላውን ይነዱየነበሩትም ዖዛና አሒዮ ነበሩ።8ዳዊትና እስራኤላዊያን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሆነው በቅኔና በበገና፣በመሰንቆ በከበሮ፣በጽናጽልና በመለከት በሙሉ ኅይላቸው በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር።9ወደ ኪዶን ዐውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ አደናቅፏቸው ሰለ ነበር፣ዖዛ ታቦቱን ለመደገፍ እጁን ዘረጋ።10ታቦቱን በእጁ ሰለ ነካ፣የእግዚአብሔር ቁጣ ዖዛን ላይ ነደደ፤ስለዚህም በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።11የእግዚአብሔር ቁጣ ዖዛን በድንገት ስለ ቀሠፈው ዳዊት አዘነ፤ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ የዖዛ ስብራት ተብሎ ይጠራል።12ዳዊት በዚያን ዕለት የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ማምጣት እንችላለሁ?"አለ።13-14ስለዚህ ታቦቱን ወደ ዳዊት ከተማ በመውሰድ ፈንታ የጋት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ከቤተ ሰቡ ጋር ሦስት ወር ተቀመጠ፤እግዚአብሔርም ቤተ ሰቡንና ያለውንም ሁሉ ባረከ።
1በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ድንጋይ ጠራቦዎችንና አናጢዎችም ከዝግባ ዕንጨት ጋር ላከ።2ዳዊትም እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ አንግሦ እንዳጽናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግጅቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት አስተዋለ።3ዳዊትም በኢየሩሳሌም ብዙ ሚስቶች አገባ፤ከእነሱም ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።4በዚያ ሳለ የወለዳቸው የልጆች ስም ይህ ነው፤ሳሙስ፣ሶባብ፣ናታን፣ሰለሞን፣5ኢያቤሐር፣ኤሊሱዔ፣ ኤሊፋላት፣6ኖጋ፣ናፌቅ፣ያፍያ፣7ኤሊሳማ፣ኤሊዳሄ፣ኤሊፋላት።8ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ተቀብቶ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣እርሱን ፍለጋ በሙሉ ኅይላቸው ወቱ፤ዳዊት ይህን ሰምቶ ሰለ ነበር ሊገጥማቸውው ወጣ።9በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ውጥተው የራፋይምን ሸለቆ ወረሩ።10ስለዚህ ዳዊት፣"ወጥቼ በፍልስጥኤማዊያን ላይ አደጋ ልጣልን? አንተስ በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ሲል እግዚአብሔር ጠየቀ።እግዚአብሔር "አዎን ውጣ! በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ"ብሎ መለሰለት።11ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ በኣልፐራሲም ወጡ፤በዚያም ድል አደረጋቸው።ዳዊትም "ውሃ ነድሎ እንደሚውጣ ሁሉ እግዚአብሄርም ጠላቶችይን በእጄ አፈርሳቸው"አለ፤ከዚህ የተነሳ ያን ቦታ "በኣልፐራሲም"ብለው ሰየሙት።12ፍልስጥኤማውያን አማልዕክቶቻቸውን በዚያው ጥለዋቸው ስለ ነበር፣ዳዊትት በእሳት እንዲያቃጥሏቸው አዘዘ።13ፍልስጥኤማውያን ሸለቆውን እንደ ገና ወረሩ፣14ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔር ጠየቀ።እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት "ዙሪያውን ከበህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት አደጋ ጣልባቸው እንጂ በቀጥታ ወደ ላይ አትውጣ፤15በሾላው ዐናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ወዲያኑ ለጦርነት ውጣ፤ይህም የፍልስጥኤማውያንን ስራዊት ለመምታት እግዚአብሔር በፊትህ ወጥቶአል ማለት ነውና።16ዝዝዚህ ዳዊት እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ፤ከገባዖን ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ ፍልስጥኤማውያንን መቷቸው።17ከዚህም የተነሳ የዳዊት ዝና በየአገሩ ሁሉ ተሰማ፤እግዚአብሔርም መንግሥታት ሁሉ እንዲፈሩት አደረገ።
1ዳዊት በስሙ በተጠራችው ከተማ ለራሱ ብይቶችን ሠራ፤በእግዚአብሔር ታቦት ቦታ አዝጋጅቶ ድንኳን ተከለ።2ከዚያም ዳዊት፣"የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙና ለዘላለም በፊቱ እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር፣የእግዚአብሔርን ታቦት ማንም አይሸከምም ሲል አዘዘ።3ዳዊት የእግዚያብሔር ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያወጡ እስራኤላዊያን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበስበ።4የአሮንን ዘሮችና ሌዋዊያውያንኑም በአንድነት ሰበሰበ፤ 5ከቀዓት ዘሮች፣አለቃውን ኡርኤልንና አንድ መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤6ከሜራሪ ዘሮች፤አለቃው ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤7ከጌድሶን ዘሮች፤ አልቃው ኤሊኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤8ከኤሊጻፍን ዘሮች፤አለቃውን ሽማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤9ከኬብሮን ዘሮች፤ አለቃው ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹ፤10ከዑዝኤል ዘሮች፤አለቃውን አሚናሳብንና አንድ መቶ ዐሥራ ሁለት የሥጋ ዘመዶቹን።11ከዚያም ዳዊት ከህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፣ሌዋውያኑን ኡርኤልን፣ዓሣያን፣ኢዩኤልን፣ሽማያን፣ኤሊኤልንና አሚናዳብን ጠርቶ፣12እንዲህ አልቸው፤"እንግዲህ እናንተ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሰለ ሆናችሁ፣እናንተና ወንድሞቻችሁ ሌዋውያን ራሳችሁን ቀድሱ፤ከዚያም የእስራኤል አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደአዘጋጀሁለት ቦታ አምጡ።13የአምላካችን የእግዚአብሔር ቁጣ በላያችን ላይ እንዲህ የነደደው እናንተ ሌዋውያኑ ቀድሞም ስላላመጣችሁት ነው፤እኛም ብንሆን ምን ማድረግ እንዳለብን በታዘዘው መሠረት አልጠየቅነውም።14ስለዚህ ካህናቱና ሌዋውያኑ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔር ታቦት ለማምጣት ራሳቸውን ቀደሱ።15ሙሴ በእግዚአብሔር ቃል እንዳዘዘው፣ሌዋውያኑ የእግዚአብሔር ታቦት በትከሻቸው ላይ በሙሎጊያዎች አድርግገው ተሸከሙ።16ዳዊትም በዜማ መሣሪያ ማለትም በመሰንቆ፣በበገና፣በፅናፅል እየታጀቡ የደስታ ዜማዎችን እያዜሙ መዘመራንን ከወንድሞቻቸው መካከል እንዲሾሙ ሌዋውያኑ መሪዎች ነገራቸው። 17ስለዚህ ሌዋውያኑ የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን ሾሙ፤ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፣ከወንድሞቻቸው ከሜራራ ዘሮች የቂሳን ልጅ ኤታንን ሾሙ፤18ከእነሱም ጋር ወንድሞቻቸውን በደረጃ ተሾሙ፤እነሱም ዘካሪያስ፣ያዝኤል፣ሰሚራ ሞት፣ይሒኤል፣ዑኒን፣ኤልያብ፣በናያስ፣መዕሤያን፣መቲትያ፣ ኤሊፍሌሁ፣ሚቅኔያ፣ደግሞም በር ጠባቂዎቹ ዖቤድ ኤዶምና ይዒኤል ነበሩ።19መዘመራኑ ኤማን፣አሳፍ ኤታን በናስ ጸናጽል ድምፁን ከፍ እድርገው እንዲያሰሙ ተሾሙ፤20ዘካሪያስ፣ዓዝኤል፣መዕሤያና በናያስ ደግሞ በአላሞት ቅኝት መሰንቆ ይገርፉ ነበር።21እንዲሁም መቲትያ፣ኤሊፍሌሁ፣ሚቅኔያ፣ዖብድኤዶም፣ይዒረድኤ፣ ዓዛዝያ፣በሺሚኒት ቅኝት በገና ይደረድሩ ነበር።22የዝማሬው ኅላፊ ሌዋዊው አለቃ ክንያን ነበረ፤ይህን ኅላፊነት የወሰደው በዝማሬ የተካነ ስለ ነበር ነው።23በራክያና ሕልቃና ያታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤24ካህናቱ ሰበኒያ፤ኢዮሣፍጥ፣ናትናኤል፣ዓማሣይ፣ዘካሪያስ፣በናያስና አልዓዛር በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፋ ነበር።ዖቤድኤዶምና ይሒያ ደግሞ ያታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ።25ስለዚህ ዳዊት የእስራኤል ሽማግሌዎችና የሻለቃው አዛዦች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ።26የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያን እግዚአብሔር ረድቶአቸው ስለ ነበር፣ሰባት ኮርማዎችና ሰባት አውራ በጎች ሠው።27ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣መዘመራኑና የመዘመራኑ አለቃ ክናንያ የለበሱትና ዐይነት ከቀጭን በፍታ የተሠራ ልብስ ዳዊትም ለብሶ ነበር፤እንዲሁም በከፍታ የተሠራ ኤፋድ ለብሶ ነበር።28በዚህ ሁኔታ መላው የእስራኤል ህዝብ በሆታ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፣ጽናጽል እየጸነጸሉ፣መሰንቆና በገና እየደረደሩ የእግዚአብሔር የኪዳኑን ታቦት አመጡ።29የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ የሳኦል ልጅ ሚልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች ፤ንጉሥ ዳዊት ደስ ብሎት ሲያሸበሽብ አይታ በልቧ ናቀችው።
1ከዚያም የእግዚአብሔር ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤የሚዋጠል መሥዕዋትና የኅብረት መሥዕዋትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።2ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዕዋትና የኅብረቱ መሥዕዋት ከሠዋ በኋላ፣ህዝቡን በእግዚአብሔር ስም ባረከ።3ከዚያም ለእስራኤል ሁሉ ለወንዱም ልችሴቱም አንዳንድ ሙልሙል ዳቦ፣አንዳንድ ጥፍጥፍ ዘቢብ ሰጠ።4በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እንዲያገለግሉና ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ልመና፣ምስጋናና ውዳሴ እንዲቀርቡ ከሌዋውያን ሰዎች ሾሙ፤5አለቃው አሳፍ ነበረ፤ከእርሱ ቀጥሎ ዘካሪያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ከዚያም ይዒኤል፣ሰሚራሞት፣ይሒኤል፣መቲትያ፣ኤልያብ፣በናያስ፣ ዖቤድኤዶም፣ይዒኤል ተሾሙ፤እነሱም በመሰንቆና በበገና ይዘምሩ ነበር፤አሳፍ ደግሞ ጽናጽል የሚጸነጽል ሆኖ ተመደበ።6እንዲሁም ካህናቱ በናያስና የሕዚኤል ዘውትር በእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦቱ ፊት መለከት እንዲነፉ ተመደቡ።7በዚያም ቀን ዳዊት በመጀመሪያ ለአሳፍና ለሥራ ጓደኞቹ ይህን የእግዚአብሔር ምስጋና መዝሙር ሰጠ፤8ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤ስሙንም ጥሩ፤ለአሕዛብ ያደረገውን ሁሉ ንገሩ፤9ዘምሩለት፤ውዳሴም አቅርቡለት፤ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤10በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤እግዚአብሔር የሚፈልግ ሁሉ፤ልባቸው ሐሤት ያድርግ፤11ወደ እግዚአብሔር ወደ ኅይሉ ተምልከቱ፤ዘውትር ፊቱን ፈልጉ፤12ይደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤13እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች።14እርሱ እግዚአብሔር አምልካችን ነው፤ፍርዱም በምድር ሁሉ ላዬ ነው፤15ኪዳኑን እስከ ዘላለም፣ይያዘዘውንም ቃል እስከ ሺህ ትውልድ ያስባል፤16ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣ለይስሐቅ የማለውን መሐላ።17ይህንንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ አጸና፤ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አደረገ፤18እንዲህ ሱል "የምትወርሰው ርስት እንዲሆን፣የከነዓንን ምድር ለአንተ እሰታለሁ።"19ቁጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፤በርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፤ 20ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ተንከራተቱ።21ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቅድም፤ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤22እንዲህ ሲል፤"የቀባኋቸውን አትንኩ፤በነብያቴ ላይ ክፉ አታድርጉ።"23ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ማዳኑንም ዕለት ዕለት ዐውጁ።24ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፤ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።25እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤ምስጋናውም ብዙ ነው፤ከአማልዕክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ የሚገባው ነው።26የአሕዛብ ሁሉ አማልክት ጣዖታት ናቸው፤እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።27በፊቱ ክብርና ሞገስ አለ፤ ብርታትና ደስታም በማድሪያው ስፍራ።28የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርና ኅይልን ለእግዚአብሔር አምጡ።29ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ሰጡ፤መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ሰገዱ።30ምድር ሁሉ በፊቱ ትንቀጥቀጥ፤ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤አትናወጥምም።31ሰማያት ደስ ይባላቸው፤ምድር ሐሤት ታድርግ፤በአሕዛብ መካከል፣"እግዚአብሔር ነገሠ!"ይበሉ።32ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ይናውጥ፤ሜዳዎችና በእርሷ ላይ ያሉ ሁሉ ሐሤት ያድርጉ።33ያን ጊዜ የዱር ዛፎች በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላቸው፤በደስታ ይዘምራሉ፤በምድር ላይ ሊፈርዱ ይመጣልና።34ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ፍቅሩንም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።35«አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ፤ታደገን፤ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣በምስጋናም እንድንከብር ስብሰበን"ብላችሁ ጩኹ።36ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ፣"አሜን፤እግዚአብሔር ይመስገን"አለ።37ዳዊትም ለእያንዳንዱ ቀን በተመደበው መሠረት ዘውትር እንዲያገለግሉ አሳፍና የሥራ ባልደረቦቹን በዚያው በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።38እንዲሁም ዖቡድኤዶምና ሥልሳ ስምንቱ የሥራ ባልደረቦቹ አብረዋቸው እንዲያገለግሉ በዚያው ተዋቸው።የኤዶታም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖላ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ሆኑ።39ዳዊት ካህኑን ሳዶቅንና የሥራ ባልደረቦቹን ካህናት በገባዖን ከፍተኛ ቦታ ላይ በሚገኘው በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ተዋቸው፤40የተዋቸውም ለእስራኤል በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈው ሁሉ በመሠዊያው ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዕዋት ላይ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ጧትና ማታ በየጊዜው እንዲያቀርቡ ነው።41ደግሞም፤"ፍቅሩ ለዘላለም ነውና"እያሉ ምስጋና እንዲያቀርቡ ኤማንና ኤዶታም እንዲሁም ተመርጠውና ስማቸው ተመዝግቦ የተመደቡ ሌሎችም አብረዋቸው ነበሩ።42ድምፅ መለከቱንና ጽናጽሉን ለማሰማት፤ደግሞም መንፈሳዊ መዝሙር ሲዘመር ሊጠቀሙባቸው ሌሎች መሣሪያዎች ኅላፊዎች ኤማንና ኤዶታም ነበሩ፤የኤዶታምም ልጆች በሩን እንዲጠብቁ ተመድበው ነበር።43ከዚያም ህዝቡ ተነሣ፤እያንዳንዱም ወደየቤቱ ሄደ።ዳዊትም ቤተ ሰቡን ለመባረክ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
1ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፤ነቢዩ ናታንን"እነሆ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤የእግዚአብሔር የኮዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል"አለው።2ናታንም ለዳዊት፣"እግግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለሆነ፣ያሰብከውን ሁሉ እድርግ"ሲል መለሰለት።3በዚያም ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጥቶ እንዲህ አለው፤4"ሂድና ለባርያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤እግዚአብሔር የሚለውን ይህን ነው፤እኔ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንንተ አይደለህም።5እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ፤ከአንዱ ድንኳን ወደ ሌላው ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ፣በቤት ውስጥ አልኖርሁም።6ከእስራኤላዊያን ጋር በሄድኩባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ሕዝቤን እንዲጠብቁ ላዘዝኋቸው መሮዎቻቸው ከቶ፣"ለምን ከዝግባ ዕንጨት ቤት አልሰራችሁልኝምያልሁበት ጊዜ አለን?፤7"ከእንግዲህ አሁንም ለባሪያዬ ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤የሕዝቤ ይእስራኤል ገዥ እንድትሆን በጎችን ከመጠበቅና ከመከትተል አንሥቶ ወሰድሁህ።8በሄድህበት ሁሉ ከአንተ አልተለየሁህም፤ጠላቶችህም ስምህን እንደ ምድር ታላላቅ ሰዎች ስም ገናና አደርገዋለሁ።9ለሕዝቤ ለእስራኤል መኖሪያ ስፍራ እሰጥተዋለሁ፤የራሳቸውም መኖሪያ ስፍራ እንዲኖራቸው ከእንግዲህም በኋላ እንዳይናወጡ አደርጋቸዋለሁ።ክፉ ሰዎች በመጀመሪያ እንዳደረጉት ሁሉ፤ከእንግዲህ አይጨቁናቸውም፤10ከዚህ ቀደም በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪዎች በሾምሁ ጊዜ ጨቋኞቹ ያደረጉትን ዛሬ አያደርጉትም፤ጠላቶቻችሁም ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ።"እግዚአብሄር ቤት እንደሚሠራልህ በግልፅ እነግርሃለሁ፤11ዘመንህን ጨርሰህ ወደ አባቶችህ በምትሄድበት ጊዜ፤ከአብራክህ ከተከፈሉት ልጆችህ አንዱ በእግርህ እንዲተካ አደረጋለሁ፤መንግሥቱንም አፅናለሁ፤12ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው፤እኔም ዙፋኑን ለዘላለም አፀናለሁ።13አባት እሆነዋለሁ፤እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ፅኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድሁ፣ከእርሱ ላይ ከቶ አልወስድም።14በቤቴና በመንግሥቴ ላይ ለዘላለም እኖረዋለሁ፤ዙፋኑም ለዘላለም ይፀናል።"15ናታንም የዚህን ሁሉ ራእይ ቃል ለዳዊት ነገረው።16ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባ፤በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ለመሆኑ እስከዚህ ያደረሰኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤተ ሰብይስ ምንድን ነው? 17አምላክ ሆይ፤ይህ በፊትህ በቂ እንዳልሆነ ቁጥረህ ስለ ወደፊቱ የባሪያህ ቤት ተናገረ።እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤እኔንም ከሰዎች ሁሉ እጅግ የከበርረ ሰው አድርገህ ተመለከትኸኝ።18ባሪያህን ስላከበትኸው፣ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ማለት ይችላል? ባሪያህ እኮ ታውቀቃለህ፤19እግዚአብሔር ሆይ፤ስለ ባሪያህ ብለህና እንደ ፈቃድህም መሠረት ይህን ታላቅ ነገር አድርግሃል፤እነዚህም ታላላቅ ተስፋዎች ሁሉ እንዲታወቁ አደረግህ።20አቤቱ፤እንደ አንተ ያለ የለም፤በጆሮአቸን አንደ ሰማነው ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም21ከግብፅ ተቤዠተህ እንዳወጣኸው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ማን አለ? እነርሱ እግዚአብሔር ለራሱ ሊቤዣቸው ናቸው፤በሕዝብህም ፊት ታላቅና አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ መንግሥታትን በፊታቸው አሳደድህ።22ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘላለም የራስህ ሕዝብ አደረግኸው፤እግዚአብሔር ሆይ፤አንተም አምላክ ሆንህለት።23እግዚአብሔር ሆይ፤አሁንም ስለባሪያህ ስለ ቤቱ የሰጠኸው ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤የሰጠኸውንም ትተስፋ ፈፅም፤24ይህም ስምህ ጸንቶ እንዲኖርና ለዘላለም ታላቅ እንዲሆን ነው።ከዚያም ሰዎች "የእስራኤል አምላክ ጌታ እግዚአብሔር በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው!"ይላሉ፤የባሪያህ የዳዊትም ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።25አምላክ ሆይ፤ቤት እንደምትሠራለት ለባሪያህ ገልጸህለታል፤ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት አገኘ።26እግዚአብሄር ሆይ፤በእውነት አንተ አምላክ ነህ፤ይህንንም መልካም ተስፋ ለባሪያህ ስጥተሃል።27በፊትህ ለዘላለም እንዲኖር አሁንም የባሪያህን ቤት ልትባርክ ወደሃል፤እግዚአብሔር ሆዩ፤የባረክኸውን አንተ ስለ ሆንህ፣ለዘላለም የተባረከ ይሆናል።
1ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማዊያንን ድል መትቶ ተገዢ አደረጋቸው፤ጌትንና በዙሪያዋም የሚገኙትን መንደሮች ከፍልስጥኤማዊያን እጅ ወስደ።2እንዲሁም ዳዊት ሞዓባዊያንድል አደረጋቸው፤እነሱም ገባሮቹ ሆኑ፤ግብርም አመጡለት።3ከዚያም በላይ ዳዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረው ግዛት ለመቁጣጠር በሄደ ጊዜ፣የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን እስከ ሐማት ድረስ ዘልቆ ወጋው።4ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገላ. ሰባት ሺህ ፈረሰኛና ሃያ ሺህ እግረኛ ወታደር ማረከ፤አንድ መቶ የሠረገላ ፈረሳች ብቻ አስቀርቶ የቀሩትን ቋንጃቸውን ቁረጠ።5ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ እድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ፣ከእነሱ ሃያ ሁለት ሺህ ሰው ገደለ።6ከዚያም በሶርያ ግዛት ውስጥ ባለችው ወደማስቆ የጦር ሰፈር ፤አቋቋመ፤ሶርያውያን ገባሮቹ ሆኑ፤ግብርም አመጡለት።እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አጎናፀፈው።7ዳዊትም የአድርአዘር ጦር አለቆች ያነገቡትን የወርቅ ጋሻ ወሰደ፤ወደ ኢየሩሳሌም አመጣው።8ዳዊት ከአድርአዛር ከተሞች ከጢብሐትና ከኩን እጅግ ብዙ ናስ ወስደ፤ሰለሞን የናሱን ባሕር፤ዐምዶቹንና ልዩ ልዩ የናስ ዕቃዎቹን የሠራው በዚሁ ነበር።9የሐማት ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ሰራዊት ሁሉ ድል እንደመታ ሲሰማ፣10እጅ እንዲነሳውና ደስታውንም እንዲገልጥለት ልጁን አዳራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ቶዑ ከአድርአዛር ጋር ብዙ ጊዜ ጦርነት ገጥሞ ነበር።አዶራምም ከወርቅ፣ከብርና ከነስ የተጀሩ ልዩ ልዩ ዕቃዎች አመጣለት። 11ንጉሥ ዳዊት ከሞዓብ፣ከአሞናዊያን፣ከፍልስጥኤማውያንና ከአማሌቃውያን ከእነዚህ ሁሉ መንግሥትታት የማረከውን ወርቅና ብር ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ሁሉ፤እነዚህንም ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ቀደሰ።12የጹሩያ ልጅ አቢሳ በጨው ሸለቆ ዐሥራ ስምንት ሺህ ኤዶማውያን ገደለ።13እርሱም በኤዶም የጦር ሰፈሮች አቋቋም፤ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ።እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድል አጎናጸፈው።14ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕና ጽድቅን አሰፈናላቸው።15የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሰራዊት አዛዥ ነበረ፤የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ የቤተ መዛግብቱ ኃላፊ ነበረ።16የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአቤምሜሌክ ልጅ አብያታር ካህናት ነበሩ፤ሱሳ ደግሞ ጸሓፊ ነበረ።17የዮሄድ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፊልታውያን አዛዥ ነበረ።የዳዊት ወንዶች ልጆች ከንጉሥ ቀጥሎ የበላይ ሹማምት ነበሩ።
1ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ. ልጁም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።2ዳዊትም "አባቱ ለእኔ በጎ ነገር እንዳደረገልኝ እስቲ እኔም ለናዖስ ልጅ ለሐኖን በጎ ነገር ላድርግለት"ብሎ አስብ።ስለዚህ ዳዊት ስለ አባቱ ሞት ሐዘኑን ለመግለጽ ወደ ሐኖን መልክተኞችን ላከ።የዳዊት ሰዎች ሐናቸውን ለመግለጽ ሐኖን ወደሞኖርበት ወደ አሞናውያን ምድር በመጡ ጊዜ፣3የአሞናውያን መኳንንት ለሐኖን "ዳዊት ሀዘኑን ለመግለጽ ሰዎችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃን? ሰዎች ወደ አንተ የመቱት አገሩቱን ለመመርመር፣ለመሰለልና ለመያዝ አይደለምን? አሉት።4ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ ላጫቸውል ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ መኻል ለመኻል ቀዶ ሰደዳቸው።5በሰዎቹ ላይ የደረሰባቸውን ዳዊት በሰማ ጊዜ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር፣ወደ እነርሱ መልክተኞችን ላከ፤ንጉሥም፣"ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያኮር ቁዩና ከዚያ በኋላ ትመጣላችሁ"አለ።6አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉባወቁ ጊዜ፣ሐኖንና አሞናውያን ከመሰጴጦምያ፣ከአራምመዓካና ከሱባ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ለመከራየት አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ፤7ከዚያም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሠረገሎችንና ፈረሶኞችን እንዲሁም የመካዓን ንጉሥና ወታደሮች በገንዘብ ቀጠሩ፤እነርሱም መጥተው በሜድባ አጠገብ ሲሰፍሩ፣አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት ወጡ።8ዳዊት ይህን ሲሰማ ኢዮአብንና መላውን ተዋጊ ሰራዊት ላከ።9አሞናውያንም መጥተው ወደ ከተማቸው በሚያስገባው በር ላይ ለጦርነት ተሰለፉ፤የመጡት ነገሥታት ደግሞ ብቻቸውን በሜዳው ላይ ነበሩ።10ኢዮአብም ከፊቱና ከኋላው ጦር መኖሩንና አየ፤ስለዚህ በእስራኤል የታወቁትን ጀግኖች መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው።11የቀሩትም ሰዎች በወንድሙ በአቢሳ ሥጋ ሆነው አሞናውያንን እንዲገጥሙ አስለፋቸው።12ኢዮአብም እንዲህ አለ፤"ሶርያውያን ከበረቱብኝ አንተ ትረዳኛለህ"አሞናውያን ከበረቱብህ ደግሞ እኔ እረዳሃለሁ።13እንግዲህ በርቱ፤ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችን ከተሞች ብለን በጀግንነት እንዋጋ፤እግዚአብሔር ደስ ያሰኘውን ያድርግ።"14ከዚያም ኢዮአብና አብረውት ያሉት ወታደሮች ሶርያውያን ለመዋጋት ወደ ፊት ገሠገሠ፤ሶርያውያንም ከፊታቸው ሸሹ።15አሞናውያንም ሶርያውያን መሸሻቸውን ሲያዩ፣እርሱም ከውንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ ገቡ፤ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።16ሶርያውያን በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣መልክተኞችን ልከው ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ያሉትን ሶርያዊያን አስመጡ፤እነዚህንም የሚመራቸው የአድርአዛር ስራዊት አዛዥ ሾፋክ ነበረ።17ዳዊት ይህን ሲሰማ፣እስራኤልን ሁሉ ሰብስቦ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ወደፊት በመገሥገሥም ከፊት ለፊታቸው የውጊያ መሥመሩን ያዘ።ዳዊትም ሶርያውያንን ጦርነት ለመግጠም ወታደሮቹን አሰለፈ፤እነርሱም ተዋጉት።18ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ።ዳዊትም ሰባት ሺህ ሠረገለኞችና አርባ ሺህ እግረኛ ወታደሮች ገደለ።የሠራዊታቸው አዛዥ ሾፋክም በጦርነት ላይ ሞተ።19የአድርአዛርም ሹማምት በእስራኤል መሸነፋቸውን ሲያዩ፣ከዳዊት ጋር ታረቁ፤ገባሮቹም ሆኑ።ስለዚህ ሶርያውያን ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አሞናውያንን ለመርዳት ፍቃደኞች አልሆኑም።
1ነገሥታት ለጦርነት በሚሄዱበት በፈደይ ወራት፣ኢዮአብ የጦር ሰራዊቱን እየመራ ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ወደ ራባትም ሄዶ የአሞናውያንን አገር አጠፋ፤ወደ ራባትም ሄዶ ከበባት፤ዳዊት ግን ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።ኢዮአብም ራባትን ወግቶ አፈራረሳት፤2ዳዊት የንጉሣቸውን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ነበረ፤ይህንንም በዳዊት ራስ ላይ ጫኑለት፤እንዲሁም ከከተማይቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ።3በዚያ የነበረውን ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ዶማና መጥረቢያ ይዘው እንዲሠሩ አደረጋቸው።ዳዊት በሌሎቹም የአሞን ከተሞች ሁሉ ይህንኑ አደረጉ።ከዚያም ዳዊትና መላው ሰራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።4ከዚያም በኋላ ከፍልስጥኤማዊያን ጋር በጌዝር ጦርነት ተደረገ፤በዚያ ጊዜ ኩሳታዊው ሴቦካይ የራፋይም ዘር የሆነውን ሲፋይን ገደለ፤ፍልስጥኤማውያንም ድል ተመቱ።5ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሌላ ጦርነት ተደረገ፤የያዒር ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦውፍረቱ እንደ ሽማኔ መጠቅለያ የሚያህለውን የጌት ተወላጅ የሆነውን የጎልያድን ወንድም ላሕሚን ገደለ።6ደግሞም ጌት ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት፣በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣት በድምሩ ሃያ አራት ጣት የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ይህም እንደዚሁከራፋይም ዘር ነበረ።7እርሱም እስራኤልን በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።8በጌት የነበሩ የራፋይም ዘሮች እነዚህ ናቸው፤እነሱም በዳዊትና ሰዎቹ እጅ ወደቁ።
1ሰይጣን በእስራኤል ላይ ተነሥቶ ዳዊት የእስራኤልን ሕዝብ እንዲቁጥር አነሣሣው።2ዳዊትም ኢዮአብንና የሰራዊቱን አዛዦች፤"ሄዳችሁ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ያሉትን እስራኤላዊያን ቁጠሩ፤ከዚያም ምን ያህል እንደ ሆኑ ዐውቅ ዘንድ ንገሩኝ አላቸው።3ኢዮአብ ግን፣እግዚአብሔር የእስራኤል ሰራዊት አሁን ካለው በላይ በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ሁልስ ቢሆኑ የጌታዬ ተገዢዎች አይደሉምን? ታዲያ ጌታዬ ይህን ማድረግ ለምን አስፈለገው? ለምንስ በእስራኤል ላይ በደል ያመጣል?"አለ።4ይሁን እንጂ የንጉሥ ቃል ኢዮአብን አሸነፈው፤ስለዚህ ኢዮአብ ወጣ፤በመላው እስራኤል ከተዘዋወረ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።5ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ሰዎች ቁጥር ለዳዊት አቀረበ፤እነዚህም በመላው እስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ፣በይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ሲሆኑ፣ሁሉም ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ነበሩ።6ነገር ግን የንጉሡ ትእዛዝ በእርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነበረና፣ኢዮአብ የሌዊንና የብንያም ነገድ ጨምሮ አልቁጠረም።7ይህ ትእዛዝ በእግዚአብሄር ዘንድ የተጠላ ነበር፤ስለዚህ እግዙአብሔርን ቀጣ።8ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔርን፣"ይህን በማድረጌ እጅግ በድያለሁ፤የፈጸምኩትም የስንፍና ሥራ ስለሆነ፣የባሪያህን በደል እንድታስወግድ እለምንሃለሁ"አለ።9እግዚአብሔር የዳዊት ባለ ራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤10ሂድና ለዳዊት እንዲህ ብለህ ንገረው፤እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤እነሆ፣ሦስት ምርጫ ሰጥሃለሁ፤በአንተ ላይ እንዳደርስብህ እንዱን ምረጥ።"11ስለዚህ ጋድ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤"እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤አንዱን ምረጥ፤12የሦስት ዓመት ራብ ወይስ የጠላቶችህን ሰይፍ ለሦስት ወር አይሎብህ ተሰዶ መጥፋት ወይስ ሦስት ቀን የእግዚአብሔር ስይፍ መቅሠፍት በምድሪቱ ላይ ወርዶ የእግዚአብሔር መልአክ እስራኤልን ሁሉ ያጥፋ? እንዲህ ላልከኝ ምን እንደምመልስ ቁርጡን ነገረኝ።13ዳዊትም ጋድን፣"ችጅግ ተጨንቅይአለሁ፤ምሕረቱ ታላቅ ስለሆነ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል፤በሰው እጅስ አልወድቅ"አለ።14እለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ሰባ ሺህ ሰው ዐለቀ።15እንዲሁም እግዚአብሔር እየሩሳሌምን እንዲያጠፋ መልአክ ላከ፤መልአኩም ሊያጠፋት ሲል እግዚአብሔር አይቶ ስለሚያደርሰው ጥፋት ዐዘን፤ህዝቡን የሚያጠፋውንም መልአክ፣"እጅህን መልስ"አለው።የእግዚአብሔር መልአክ በኢያቡሳዊያ በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።16ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት፣የእግዚአብሔር መልአክ በሰማይና በምድር መካከል ቆሞ አየ፤መልአኩም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ከዚያም ዳዊትና ሽማግሌዎች ማቅ እንደሚለብሱ በግንባራቸው ተደፉ።17ዳዊት እግዚአብሔር "ተዋጊዎቹ እንዲቁጠሩ ያዘዝሁ እኔ እይደለሁም? ኅጢአት የሠራሁበትም ሆነ የበደልሁት እኔ ነኝ፤እነዚህ እኮ በጎች ናቸው፤ታዲያ እነርሱ ምን አደረጉ? እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን እንጂ፣መቅሠፍት በሕዝብህ ላይ አይውረድ"አለ።18ከዚያም እግዚአብሔር መልአክ ዳዊት ወጥቶ በአቡሳዊያን በኦርና ዐውድማ ላይ ልችእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።19ዳዊትም ጋድ በእግዚአብሔር ስም በነገረው ቃል መሠረት ለመፈፀም ውጣ።20ኦርና ስንዴ በመውቃት ላይ ሳለዘወር ሲል መለአኩን አየ፤አብረውት የነበሩት አራት ወንዶች ልጆችም ተሸሸጉ።21ዳዊት ወደ እርሱ እየቀረበ መጣ፤ኦርናቀና ብሎ ሲመለከት፣ዳዊትን አየው፤ከዐውድማውም ወጥቶ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ዳዊትን እጅ ነሣ።22ዳዊትም፣"በሕዝቡ ላይ የወረደው መቅሠፍት እንዲወገድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ዐውድማህን ልውሰደው፤ሙሉውን ዋጋ እከፍልሃለሁ"አለው።23ኦርናም ዳዊትም፣"እንዲሁ ወስደው፤ጌታዬ ንጉጅ ደስ ያለውን ያድርግ፤እነሆ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎቹን፣መውቂያ በትሮቹን ለማቀጣጠያ ዕንጨት፣ስንዴው ደግሞ ለእህል ቁርባን እንዲሆን እሰጣለሁ፤ሁሉንም እኔ እሰጣለሁ።አለ።24ንጉሥ ዳዊት ግን ለኦርና "አይደረግም፤ሙሉውን ዋጋ እኔ እከፍላለሁ፤የአንተ የሆነውን ለእግዚአብሔር ለማውረብ አልፈልግም፤ዋጋ ያልከፈልኩበትም የሚቃጠል መሥዋዕት እድርጌ አላቀርብም" ሲል መለሰለት።25ስለዚህ ዳዊት ለኦርና የቦታውን ዋጋ ስድስት መቶ ስቅል ወርቅ ከፈለ።26ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠል መሥዕዋትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ።እግዚአብሔርም ጠራ፤እግዚአብሔርም የሚቃጠል መሥዕዋት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ከሰማይ በእሳት መለሰለት።27ከዚያም እግዚአብሔር ለመልአኩ ተናገረ፤መልአኩም ሰይፉን ወደ አፎቱ መለሰ።28በዚያን ጊዜ ዳዊት፤እግዚያብሔር በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ እንደ መለሰለት ሲያይ፤በዚያው ቦታ መሥዕዋት ማቅረብ ጀመረ።29ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳንና የሚቃጠል መሥዕዋት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚያ ጊዜ በገባዖን ኮረብታ ላይ ነበረ።30ዳዊት የእግዚአብሔር መልአክ ሰይፍ ሰለፈራ ወዲያ ሄዶ እግዚአብሔር ለመጠየቅ አልቻለም።
1ከዚያም ዳዊት፣"ከእንግዲህ የእግዚአብሔር አምላክ ቤት በዚህ ይሆናል፤እንዲሁም ስለ እስራኤል የሚቃጠል መሥዕዋት የሚቀርብበት መሠዊያ በዚሁ ይቆማል"አለ። 2ስለዚህ ዳዊት በእስራኤል የሞኖሩ መጻተኞች እንዲሰበሰቡ አዘዘ፤ከመካከላቸም እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚሠራበትን ጥጋብ ድንጋይ እንዲያዘጋጁ ጠራቢዎች መደበ።3ለቅጥር በሮች ምስማርና ማጠፊያ የሚሆን ብዙ ብረትና ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይችል ናስ አዘጋጀ። 4እንዲሁም ሲዶናውያንና ጢሮሳውያን በብዛት አውጥተውለት ስለ ነበር፣ስፍር ቁጥር የሌለው የዝግባ ዕንጨት አሰናዳ። 5ዳዊትም፣"ልጅ ሰሎሞን ወጣት ነው፤ልምዱም የለውም፤ለእግዚአብሔር የሚሠራው ቤተ መቅደስ ደግሞ እጅግ የሚያምር፣በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ አለበት፤ስለዚህ ሁሉንም እኔ አዘጋጃለሁ"እንዳለው ዳዊት ከመሞቱ በፊት በብዛት አዘጋጀ።6ከዚያም ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚያብሔር ቤት እንዲሥራ አዘዘው። 7ዳዊትም ሰሎሞን እንዲህ አለ፤"ልጄ ሆይ ለአምላክህ እግዚአብሔር ስም ቤት ለመሥራት በልቤ አሰብ ነበር፤ 8ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንዲህ የሚል ቃል መጣልኝ፤"አንተ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ያፈሰስህ ስለሆነ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም፤9ነገር ግን የሰላምና የዕረፍት ሰው የሆነ ልጅ ትወልዳለህ፤ በየአቅጣጫው ካሉ ጠላቶቹ ዐሳርፈዋለሁ፤ ስሙም ሰሎሞን ይባላል። በዘመኑም ለእስራኤል ሰላምና ጸጥታን እሰጣለሁ። 10ለስሜ ቤት የሚሰራልኝ እርሱ ነው። እርሱ ልጅ ይሆነኛል 'እኔም አባት እሆነዋለሁ። ዙፋንም በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።11አሁንም ልጅ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ እንድትፈጽሙ በተናገረውም መሠረት፣ ተሳክቶልህ የአምላክን የእግዚአብሔር ቤት ለመሥራት ያብቃህ። 12በእስራኤል ላይ አለቃ ባደረገህ ጊዜ የአምላክህ እግዚአብሔርን ትእዛዝ ትፈጽም ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋል ይስጥህ። 13ችግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤል የሰጠውን ሕጉንና ሥርዐቱን ተጠንቅቀን ብትጠብቅ ይሳካልሃል፤ አይዞህ ጠንክር፤ በርትስ፤ ተስፋም አትቁረጥ።14"ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺህ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት፣ ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጅ በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ። ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት።15ድንጋይ ጠራቢዎች፣ግን በኞች አናጢዎች የሆኑ ልዩ ሙያ የተጠበቡ ሰዎች አሉህ፤ 16አነዚህ ቁጥራቸው እጅግ የበዛ የውርቅ፣የብር፣የናስና የብረት ሠራተኞች ናቸው።በል ሥራህን ጀምር፤እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።"17ከዚያም ዳዊት የእስራኤል መሪዎች ሁሉ ልጁን ሰሎሞንን እንዲረዱት አዘዘ፤ 18እንዲህም አለ፤"እግዚአብሔር አምላካችን እስካሁን ከእናንተ ጋር አይደለምን? በየአቅጣጫውስ ዕረፍትን ስጥቷችሁ የለምን? የምድሪቱንም ነዋሪዎች በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኛል፤ምድሪቱም ለእግዚአብሔር ለሕዝቡ ተገዝታለች። 19አሁንም እግዚአብሔር የኪዳኑን ታቦትና ንዋያት ቅዱሳቱን ለእግዚአብሔር ስም ወደሚሠራው ቤተ መቅደስ አምጥታችሁ የአምላክ የእግዚአብሔር መቅድደስ ሥሩ።
1ዳዊት በሽመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፤ልጁን ሰሎሞንን በእራኤል ላይ አነገጀው። 2እንዲሁም መላውን የእስራኤል መሪዎች፣ካህናቱ ሌዋውያኑን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ። 3ዕድሜውቸው ሥላሳና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቁጠሩ፤ቁጥራቸውም በጠቅላላው ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ4ዳዊትም እንዲህ አለ፤ "ከእነዚህ መካከል ሃያ አራቱ ሺህ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ይቁጣጠሩ፤ ስድስቱ ሺህ ደግሞ ሹሞችና ዳኞች ይሁኑ፤ 5አራቱ ሺህ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራት ሺህ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ እግዚአብሔር ያመስግኑ"። 6ዳዊትም ሌዋውያኑን በሌዊ ልጆች በጌድሶን፣ በቀነዓና በሜራሪ በየጎሣቸው መደባቸው።7ከጌድሳናውያን ወገን፤ ለአዳን፣ሰሜኢ። 8የለእአዳን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሒኤል፣ ዜቶም፣ ኢዮኤል፣ባጠቃላይ ሦስት ናቸው። 9የስማኢ ወንዶች ልጆች፤ ሰሎሚት፣ ሀዝዝኤል፣ ሐራን፣ ባጠቃላይ ሦስት ናቸው። እነዚህ የለአዳን ቤተሰብ አለቆች ናቸው።10የስማኢ ወንዶች ልጆች፤ ኢኢት፣ ዚዛ፣ የዑስ፣ በሪዓ፣ እነዚህ አራቱ የስሚኤ ልጆች ናቸው። 11የመጀመሪያው ኢኢት፣ ሁለተኛው ደግሞ ዚዛ፣ ነበረ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ የተቁጥዐሩት በሥራ መደብ እንደ ቤተሰብ ሆነው ነው።12የቀነዓት ወንዶች ልጆች፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል፣ ባጠቃላይ አራት ናቸው። 13የእንበረት ወንዶች ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ። አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀደሱ፣ እግዚአብሔር ፊት መሥዕዋት እንዲያቀርቡ፤ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባረኩ ተለዩ። 14እግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቁጠሩ።15የሙሴ ወንዶች ልጆች፤ ጌርሳም፣ አልዓዛር። 16የጌሳም ዘሮች፤ ሱባኤል። 17የአልዓዛር ዘሮች፤ የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ። 18የይስዓር ዶዶችች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሰሎሚት።19የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ዬሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛ ይቅምዓም ነበሩ። 20የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።21የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሚሖሊ፣ ሙሲ፣ የሞሐሊ ወንዶች ልጆች አልዓዛር ቂስ ነበሩ። 22አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቡአቸው። 23የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ኢያሪሙት ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።24እንግዲህ እነዚህ የቤተሰብ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቁጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜአቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስት የሚያገለግሉ ነበሩ። 25ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፣ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቷል፤ በእየሩሳሌምም ለዘላለም ለመኖር መጥቷል፤ 26ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።"27ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቁጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ። 28የሌዋውያኑ ተግባር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደሱን ቅጥር ግቢና ክፍሎች መንከባከብ፣ የተቀደሱ ዕቃዎች ሁሉ ማጻትና በእግዚአብሔር ቤት ያሉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናውን ነበር። 29እንዲሁም መባ ሆኖ የሚቀረውን ኅብስት ገፅ፣ የእህል ቁርባኑን ዱቄት፣ ያለ እርሾ የሚጋገረውን ቂጣ የሚጋግሩ፣ የሚያቦኩና የሚሰፍረውንም ሆነ የሚለካውን ሁሉ በኅላፊነት የሚቁጣጠሩ እኔሩ ነበር።30በየለዕቱ እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለመወደስ ጠዋት ጠዋት ይቆኑ ነበር፤ይህንንም ማታ ማታ፣ 31እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ፣ የሚቃጠል መሥዕዋት ለእግዚአብሔር በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ ይፈፅሙ ነበር። በተወሰነላቸው ቁጥርና በተሰጠው መመሪያ መሠረት ዘውትር በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ነበር።32ስለዚህ ሌዋውያኑ ለመገናኘት ድንኳንና ለመቅደሱ እንዲሁም በወንድሞቻቸው በአሮን ዘሮች ሥር ሆነው ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያለባቸውን ኅላፊነት ያከናውኑ ነበር።
1የአሮን ልጆች አመዳደብ እንደ ሚከተለው ነበረ፤ የኦ ልጆች ናዳብ፣ አብድዩ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር፣ ነበሩ። 2ናዳብና አብድዩ ግን ዘር ሳይተኩ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ ስለዚህ አልዓዛርና ኢታምር ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር። 3ዳዊትም የአላዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር ሆነው አቢሜሌክ እየረዱ እንደየአገልግሎታቸው ሥርዓት እየለየ መደባቸው።4ከኢታምር ይልቅ በአልዓዛር ዘሮች መካከል ብዙ መሪዎች ተገኙ፤ አከፋፈላቸውም እንደሚከተለው ነበር፤ ከአልዓዛር ዘሮች ዐሥራ ስድስት የቤተሰብ አለቆች። 5ከአልዓዛርና ከኢታምር ዘሮች መካከል የመቅደሱ ሹማምትና የእግዚአብሔር ሹማምት ስለ ነበሩ፣ ያለ አድልዎ በዕጣ ለዩአቸው።6የሌዋውያ የናትናኤል ልጅ ጻሓፊው ሸማያ በንጉሥና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፊ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመወሰድ ነው፤7የመጀመሪያው ዕጣ ለዮአሩብ፣ ሁለተኛውም ዕጣ ለዮዳሄ ወጣ። 8ሦስተኛው ለካሪም፣ አራተኛው ለሥዖሪም፣ 9አምስተኛው ለመልክያ፣ ስድስተኛው፤ 10ሰባተኛው ለአቆስ፣ ስምንተኛው ለአብያ፣11ዘጠናኝው ለኢያሱ፣ ዐሥረኛ ለሴኬንያ፣ 12ዐሥራ አንደኛው ልች ኤሊያሴብምም ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣ 13ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፣ዐሣር አራተኛው ለየሼብአብ፣ 14ዐሥራ ሰባተኛው ለቢልጋ፣ ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፤15ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፣ ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፣ 16ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታያ፣ ሃያኛው ለኤዜቄል፣ 17ሃያ አንደኛው ለያኪያ፣ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣ 18ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፣ ሃያ አራተኛ ለመዓዝያ ውጣ።19የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መጠረት ወደ እግዞአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር።20የቀሩት የሌዊ ዘሮች አግሚ፦ከእንበረም ወንዶች ልጆች፤ ሱባኤል፤ ከሱባኤል ወንዶች ልጆች፤ ዬሕድያ። 21ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤ አለቃው ይሺው። 22ከይስዓራውያን ወገን፤ ሰሎሚት ከሰሎሚት ወንዶች ልጆች፤ ያሐት።23የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቀምዓም። 24የዑዝኤል ልጅ፤ ሚካ። የሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር። 25የሚካ ወንድም ይሺያ፤ ከይሺያ ወንዶች ልጆች ዘካርያስ።26የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊምም ሙሲ።የያዝያ ወንድ ልጅ በኖ፤ 27የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ከያዝያ በኖ፣ ሾሃም፣ ዘኩር፣ ዔብሪ። 28ከሞሒሊ፤ አልዓዛር፤ ይህ ሰው ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።29ከቂስ፣ የቂስ ወንድ ልጅ፤ ይረሕምኤል። 30የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔዳር፣ ኢያሪሙት። እነዚህ እንግዲህ እንደቤተሰባቸው የተቁጠሩ ሌዋውያን ነበሩ። 31ወንድሞቻቸው የአሮን እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱ የሌዋውያኑ ቤተሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኩሩም ቤተሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።
1ዳዊት ከሰራዊቱ አለቆች ጋር ሆኖ በመሰንቆ፣ በበገና በጽናጽል ድምፅ እየታጀቡ ትንቢት የሚናገሩትን ከአሳፍ፣ ከኤማንና ከኤዶም ቤተሰብ መካከል መርጦ መደብ፤ ይህን አገልግሎት የሚያከናውኑትም ሰዎች ዝርዝር እንደ ሚከተለው ነው፤ 2ከአሳፍ ወንዶ ልጆች፤ ዘኩር፣ ዮሴፍ፣ ነታንያ፣ አሼርኤላ። እአሳፍ ልጆች በአሳፍ አመራር ሥር ነበሩ፤ አሳፍም በንጉሥ አመራር ሥር ነበረ። 3ከኤዶምወንዶች ልጆች፤ ዶልያስ፣ ጽሪ፣ የሻያ፣ ሰሜኢ፣ ሐሸብያ፣ መቲትያ። እነዚህ ስድስቱ በመሰንቆ እግዚአብሔርን እያመሰገነና እየወደሰ ትንቢት በተናገረው አባታቸው በኤዶታም አመራር ሥር ነበሩ።4ከኤማን ወንዶች ልጆች፤ ቡቅያ፣ መንታያ፣ ዓዛርዔል፣ ሱባኤል፣ ኢያሪሙት፣ ሐናንያ፣ ናኒ፣ ኤልያታ፣ ጊዶልቲ፣ ሮማንቲዔዘር፣ ዮሽብቃሻ፣ መሎቲ፣ ሆቲር፣ መሐዝዮት። 5እነዚህም ሁሉ የንጉሡ ባለራእይ የኤማን ልጆች ነበሩ። እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉትም እግዚአብሔር በገባለት ቃል መሠረት ተሰጡት፤ እግዚአብሔር ለኤማን ዐሥራ አራት ወንድሞችና ሦስት ሴቶች ልጆች ሰጠው።6እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በጽናጽል፣ በመሰንቆ በበገና አገልግሎት በአባቶቻቸው አመራር ሥር ነበሩ። አሳፍ፣ ኤዶታምና ኤማን ደግሞ በንጉሥ የበላይ አመራር ሥር ነበሩ። 7እነዚህም ከቤተዘመዶቻቸው ጋር በመሆን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር በሚቀርበው ዜማ የሠለጠኑ የተካኑ ነበሩ፤ ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ። 8የሥራ ድርሻቸውንም ለመወሰን ወጣት፣ ሽማግሌ፣ መምህርም ሆነ ደቀ መዝሙር ሳይባል እኩል ዕጣ ተጣጣሉ።9የመጀመሪያው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለሆነው ዮሴፍ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸው12 ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እነሱን ጨምሮ ለቤተ ዘመዶቹና ለወንዶች ልጆቹ፤ ቁጥራቸውም12 10ሦስተኛው ለዛኩር፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም12 11አራተኛው ላይጽሪ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 12አምስተኛው ለነታንያ ለወንዶቹ ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 1213ስድስተኛው ለቡቃያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 14ሰባተኛው ለይሽርኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 15ስምንተኛው ለየሻያ፤ ለወንዶች ልጆቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 16ዘጠነኛው ለመታንያ፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ቁጥራቸውም 1217ዐሥረኛው ለሰሜኢ፣ ወጣ ወንዶች ልጆችና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 12 18ዐሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 19ዐሥራ ሁለተኛው ለሐሻብያ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 20ዐሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ ቁጥራቸውም 1221ዐሥራ አራተኛው ለመቲትያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 22ዐሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 23ዐሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 24ዐሥራ ሰባተኛ ለዮሽብቃሻ፣ ለወንዶች ልጆቹና ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 1225ዐሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 26ዐሥራ ዘጠነኛ ለመሎቲ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጧ፤ ቁትራቸውም 12 27ሃያኛው ለኤልያታ፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 28ሃያ አንድኛው ለሆቲር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸው 1229ሃያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ፣ ወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 30ሃያ ሦስተኛው ለመሐዝዮት፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12 31ሃያ አራተኛውም ለሮማንቲዔዘር፣ ለወንዶች ልጆቹና ለቤተ ዘመዶቹ ወጣ፤ ቁጥራቸውም 12
16 የቤተ መውደሱ በር ተባቂዎች አመዳደብ፤ ከቆሬያውያን ወገን፤ ከአሳፍ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የቆሬ ወንድ ልጅ ሜሱላም። 2ሜሱላም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ዘካሪያስ ሁለተኛው ይዲኤል፣ ሦስተኛው ዮዛባት፣ አራተኛው የትኒኤል፣ 3አምስተኛው ኤላም፣ ስድስተኛው ይሆሐናን፣ ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።4ዖቤድኤዶምም እንደዚሁም ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሽማያ፣ ሁለተኛው ዮዛባት፣ ሦስተኛው ኢዮአስ፣ አራተኛው ሣካር፣ አምስተኛው ናትናኤል፣ 5ስድስተኛው ዓሚኤል፣ ሰባተኛው ይሳኮር፣ ስምንተኛው ፒላቲ፤ እግዚአብሔር ዖቤድኤዶምን ባርኮታልና። 6እንዲሁም ልጁ ሽማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነሱም በቂ ችሎታ ስለነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎችች ሆኔ ነበር።7የሽማያ ወንዶች ልጆች፤ ዖትኒ፣ ራፋቼል፣ ዖቤድ፣ ኤልዛባድ፣ ዘመዶቹ ኤሊሁና ስማክያም እንደዚሁ በቂ ችሎታ ነበራቸው። 8እነዚሁ ሁሉ የዖቤድኤዶም ዘሮች ሲሆኑ፣ እነሱም ሆኑ ወንዶች ልጆቻቸውና ቤተ ዘመዶቻቸው ሥራውን ለመጅርት በቂ ችሎታ ነበራቸው። የዖቤድኤዶም ዘሮች ባጠቃላይ ሥልሳ ሁለት ነበሩ። 9ሜሱላም በቂ ችሎታ ያላቸው ወንዶች ልጆችና ቤተ ዘመዶች ነበሩ፤ ቁጥራቸውም ባጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ነበሩ።10ከሜራሪ ወገን የሆነው ሖሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ የመጀመሪያው ሽምሪ ነበረ፤ የበኩር ልጅ ባይሆንም እንኳን አባቱ ቀዳሚ አድርጎ ነበር። 11ሁለተኛው ኬልቅያስ፣ ሦስተኛው ጥበልያ፣ አራተኛው ዘካሪያስ፤ የሖሳ ወንዶች ልጆች ቤተ ዘመዶቹ ባጠቃላይ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።12የቤተ መቅደሱም ጠባቂዎች በአለቆቻቸው ሥር ተመድበው ልክ እንደ በተ ዘመዶቻቸው ሁሉ እግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ለማከናውን ምድብ ተራ ነበራቸው። 13ለእያንዳንዱም በር ወጣት ሽማግሌ ሳይባል ለሁሉም እኩል ዕጣ ተጣለ። 14የምስራቁ በር ዕጣ ለሴሌምያ ወጣ።ከዚያም ምክር ዕዋቂ ለሆነው ለልጁ ለዘካሪያስ ዕጣ ጣሉ፤እርሱም የሰሜኑ በር ደረሰው።15የደቡብ በር ዕጣ ለዖቤኤዶም ሲወጣ፤ የግምጃ ቤቱ ዕጣ ደግሞ ለልጆቹ ወጣ። 16የምዕራቡ በርና በላይኛው መንገድ ላይ የሚገኘው የሸሌኬት በር ዕጣዎችች ለሰፊንና ለሖሳ ወጣ።17በአንዱ ዘብ ጥበቃ ትይዩ ሌላ ዘብ ትበቃ ነበረ፣ በየቀኑም በምሥራቅ በኩል ስድስት፤ በሰሜን በኩል አራት፣ በደቡብ በኩል አራት፣፣ በዕቃ ቤቱ በኩል በአንድ ሂዜ ሁለት ሌዋውያን ይጠብቁ ነበር። 18በምዕራቡ በኩል የሚገኘው አደባባዩ ደግሞ ሁለት ሆነው ይጠብቁ ነበር። 19እንዲህ የቆየና የሜራሪ ዘሮች የሆኑት በር ጠባቂዎች ድልድይ ይህ ነበር።20ከሌዋውያን መካከል አኪያ የእግዚአብሔር ቤት ግምጃ ቤትና የተቀደሱት ዕቃዎች የሚቀመጡበት ግምጃ ቤት ኅላፊ ነበረ። 21የለአዳን ዘሮች፣ በለኣዳን በኩል ጌድሶናውያን የሆኑትና ለጌድሶዊው ለለአዳን ቤተሰቦች አለቆች የሆኑት ለለአዳን ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ ይሒኤሊ፣ 22የይሒኤሊ ወንዶች ልጆች፣ ዜቶምና ወንድሙ ኢዩኤል። እነዚህም እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት ኅላፊዎች ነበሩ።23ከእንበረማውያን፣ ከይስዓራውያን፣ ከኬብሮናውያን፣ ለዑዝኤላውያን፤ 24የሙሴ ልጅ የግርሳም ዘር የሆነው ሱባኤል የግምጃ ቤቱ የበላይ ኅላፊ ነበረ። 25በአልዓዛር በኩል የሚዛመዱት፤ ልጁ ረዓብያ፣ ልጁ የሻያ፣ ልጁ ኢዮራም ልጁ ዝክሪ፣ ልጁ ሰሎሚት።26ሰሎሚትና የሥጋ ዘመዶቹ ንጉሥ ዳዊት፣ የቤተሰቡ ኅላፊዎች፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም ሌሎች የሰራዊቱ አዦች ቀድሰው ላቀረቧቸው ንዋያት ቅድሳት ኅላፊዎች ነበሩ። 27በጦርነቱ ከተገኘውም ምርኮ ከፊሉን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ማደሻ እንዲሆን ቀደሱት። 28ባለ ራእይ ሳሙኤል፣ የቂስ ልጅ ሳኦል፣ የኔር ልጅ አቤኔር፣ ቅድሳት ሰሎሚናትና ቤተ ዘመዶቹ ይጠብቁ ነበር።29ከይስዓራውያን፤ ከናንያና ወንዶች ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ባለው ሥራ በእስራኤል ላይ ሹማምትና ዳኞች ሆነው ተመደቡ። 30ከኬብሮናውያን፤ ሐሽብያ፣ ጠንካራና ጎበዝ የሆኑ ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች ከዮርዳኖስ በሰተ ምዕራብ በሚገኘው የእስራኤል ምድር ላለው የእግዚአብሔር ሥራና ለንጉሥም አገልግሎት ኅላዎች ሆነው ተመደቡ።31በኬብሮናውያን በኩል በቤተሰቦቻቸው የትውልድ መዝገብ መሠረት ይሪያ አለቃቸው ነበረ። በዳዊት ዘመነ መንግሥት በአርባኛው ዓመት መዛግብቱ ተመርምረው ስለ ነበር፣ በገለዓድ ውስጥ ኢያዜ በተባለ ቦታ ከኬብሮናውያን መካከል ጠንካራ ሰዎች ሊገኙ ችለዋል። 32ይሪያም ጠንካሮችና የቤተሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለ ሺህ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሥም በሆነው ጎዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ ኅላፊ አድርጎ ሾማቸው።
1የእስራኤል የቤተሰብ አለቆች፣ የሻልለቆች፣ መቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትና ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዜርዜር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረው። 2በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ዋና ክፍል የበላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ሲሆን፣ በሥሩ የሚታዘዙ ሃያ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ። 3እርሱም የፋሬስ ዘር ሲሆን፣ በመጀመሪያው ወር የሰራዊቱ ሹማምት ሁሉ የበላይ ነበር።4በሁለተኛው ወር የክፍለ ጦሩ የበላይ አዛዥ ኢሆሃዊው ዱዲ ሲሆን፣ የዚሁ ክፍል መሪ ደግሞ ሚቅሎት ነው፤ በጅሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ። 5በሦስተኛውም ወር የሦስተኛው ክፍለ ጦር የበላይ አዛዥ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ ዋናው እርሱ ሲሆን፤ በሥሩ ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ። 6ይህም ከሠላሳዎቹ ይልቅ ኅያል ሲሆን፤ የሠላሳዎቹ የበላይ ነበረ፤ ልጁ ዒሚዛባድም የክፍሉ ሰራዊ አዛዥ ነበረ።7በአራተኛው ወር አራተኛው የበላይ አዛዥ የኢዮአብ ወንድም አሣሣል ሲሆን፤ በእግሩ የተተካውም ልጁ ዝባድያ ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ። 8በእብምስተኛው ወር አምስተኛው የበላይ አዛዥ ይዝራዊው ሸምሁት ሲሆን፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ። 9በስድስተኛው ወር ስድስተኛው የበላይ አዛዥ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።10በሰባተኛው ወር ሰባተኛው የበላይ አዛ የኤፍሬም ወገን የሆነው ፍሎናዊው ሴሌስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ። 11በስምንተኛው ወር ስምንተኛው የበላይ አዛዥ ከካዛራውያን ወገን የሆነው ኩሳታዊ ሲቦካይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ። 12በዘጠነኛው ወር ዘጠነኛው የበላይ አዛዥ ከብንያም ወገን የሆነው ዓናቶታዊው አቢዔዘር ሲሆን፣በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ።13በዐሥረኛው ወር ዐሥረኛው የበላይ አዛዥ ከከዛራውያን ወገን የሆነው ነጦፋዊው ኖኤሬ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ። 14በዐሥራ አንደኛው ወር እስራ አንደኛው የበላይ አዛዥ ከኤፌሬም ነገድ የሆነው ጲርዓቶናዊው በናያስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺህ ሰው ነበረ። 15በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሁለተኛ የበላይ አዛዥ ከጎቶንያል ቤተሰብ የሆነው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ፤ በጅሩም ሃያ አራት ሰው ነበረ።16የየነገዱ የእስራኤል የጦር ሹማምት፤ በሮቤል ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፤ በስምዖን ነገድ ላይ የተሶመው፣ የመዓካ ልጅ ሰፍጢያስ። 17በሌዊ የተሾመው የቀሙኤል ልክ ሐሸቡያ፤ በእሮን ነገድ ላይ የተሾመው፣ ሳዶቅ። 18በይሁዳ ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዳዊት ወንድም ኤሊሁ፤ በይሳኮር ነገድ ላይ የተሾመው፣ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ።19በዛቢሎን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአብዱዩ ልጅ ይሽማያ፤ በንፍታሌም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝሪኤል ልጅ ኢያሪሙት። 20በኤፍሬም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዓዝያ ልጅ ሆሴዕ፤ በምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾው፣ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል። 21በገለዓድ ባለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾመው፣ የዛካርያስ ልጅ አዶ፣ በብንያም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአቤኔር ልጅ የዕሢኤል። 22በዳን ነገር ላይ የተሶመው፣ የይህሮም ልጅ ዓዛርኤል፤ እንግዲህ የእዝራኤል ነገድ እነዚሁ ነበሩ።23እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ሰማይ ክዋክብት እንደሚያዛቸው ሃያና ከዚያ በታች ይየሆነው አልቁጠረም ነበር። 24የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቁጠር ጀመረ፤ ሆኖም አልፈፀመውም፤ መቁጠራቸው በእስራኤል ላይ ቁጣ ስላመጣ፣ የተቁጠረውም በንጉሥ ዳዊት መዝገብ አልገባም።25የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት የቤተ መንግሥቱ ዕቃ ኅላፊ ነበረ፤ 26የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ምድሪቱም ለሚያርሱት ገበሬዎች ኅላፊ ነበረ። 27ራማታዊው ስሜኢ የውይን ተክል ቦታዎች ኅላፊ ነበረ፤ ሽፋማዊው ዘብዲ የወይን ጠጅ ዕቃ ኅላፊ ነበረ።28ጌድራዊው በአሐናን በምራባዊው ኩረብታዎች ግርጌ ለሚገኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኅላፊ ነበረ፤ ኢዮአስ የዘይት ቤቱ ኅላፊ ነበረ። 29ሳሮናዊው ሰጥራይ በሳሮን ለሚሰሩት የከብት መንጋዎች ኅላፊ ነበረ። የዓድላይ ልጅ ሻፋጥ በሸለቆው ውስጥ ላሉት የከብት መንጋዎች ኅላፊ ነበረ።30እስማኤላዊው ኡቢያስ የግመሎች ኅላፊ ነበረ። ሜሮታዊው ዬሕድያ የአህዮች ኅላፊ ነበረ። 31አረጋዊው ያዚዝ የበግና የፍየል መንጋዎች ኅላፊ ነበረ።32አስተዋይ የሆነው አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሐፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሥ ልጆች ሞግዚት ነበረ። 33አኪጦፌል የንጉሥ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሥ ልጆች ሞግዚት ነበረ። አኪጦፌል የንጉሥ አማካሪ ሲሆን፣ አርካዊው ኩሲ ደግሞ የንጉሥ ወዳጅ ነበረ። 34የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር በአኪጦፌል እእግር ተተኩ። ኢዮአብም የንጉሥ የክብር ዘብ አዛዥ ሆነ።
1ዳዊት በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ የነገዱን የጦር አለቆች፣ ንጉሡን የሚያገለግሉትን የክፍለ ጦር አዛዦች፣ የሻለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን፣ የንጉሥና የልጆቹ ንብረትና ከብት ሁሉ ኅላፊ የሆኑትን፣ እንዲሁም የቤተ መንግሥቱን ሹማምት፣ ኅያላንና ጀግና ተዋጊዎቹን፣ በአጠቃላይ የእስራኤልን ሹማምት ሁሉ ጠራ።2ከዚያም ንጉሥ ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ አላቸው፤ "ወንድሞቼንና ወገኖቼ ሆይ፤ እስቲ አድምጡኝ፤ እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦት ማደሪያና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን ኔት ለመሥራት ዐስቤ ዕቅድ አውጥቼ ነበር። 3እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ ጦረኛ ለስሜ ቤት አትሠራም።4ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንድነግሥ ከቤተሰቤ ሁሉ እኔን አረጠ፤ መሪ እንድሆንም ይሁዳን መረጠ፤ ከአባቴ ልጆች መካከል ደግሞ በመላው እስራኤል ላይ እንድነግሥ ፈዋዱ ሆነ። 5እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ሰጥቶኛል፤ ከወንዶቹ ልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ሁሉ ላይ እንዲነግሥ ደግሞ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።6እንዲህም አለኝ፤ ቤቴንና አደባባዮቼን የሚሠራልኝ ልጅህ ሰሎሞን ነው፤ ምክንያቱም ልጄ እንዲሆን መርጩዋለሁ፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ። 7አሁን እንደሚያድርገው ሁሉ፤ ትህዛዛቶቼንና ሕጎቼን ምንጊዜም ሳያውላውል የሚፈጽም ከሆነ መንግሥቱም ለዘላለም አጸናታለሁ።8እንግዲህ አሁንም ይህቺን መልካሚቱን ምድር እንድትወርሱና ለልጆቻችሁም የዘላለም ርስት አድርጋችሁ እንድታወርስይአቸው፣ የእግዚአብሔርም ትእዛዝ ሁሉ ፊት፣ በእግዚአብሔር ጉባኤና እግዚአብሔር እየሰማ አዛችኋለሁ።9"አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፍቃድ አገግለው። 10ለመቅደስ የሚሆን ቤት እንድትሠራ እግዚአብሔር የመረጠህ መሆኑን አሁንም ዕስብ፤ በትርተህም ሥራ።11ከዚያም ዳዊት የቤተ መቅደሱን መመላለሻ፣ የሕንጻውን፣ የዕቃ ቤቶቹን፣ 12የፎቁንና የውስጥ ክፍሎቹን እንዲሁም የማስተሰሪያውን ቦታ ንድፍ ለልጁ መንፈስ ቅዱስ በልቡ ያሳደረውን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ፤ በዙሪያው ውያሉትን ክፍሎች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ዕቃ ቤቶችና የንዋይ ቅድሳቱን ግምጃ ቤቶች ንድፍ ሁሉ ሰጠው፤13እንዲሁም የካህናቱንና የሌዋውያኑን አመዳደብ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራና ለአገልግሎቱ ስለሚጠቀምባቸው ዕቃዎች ሁሉ መመሪያ ሰጠው። 14ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የወርቅ ዕቃዎች ሁሉ መጠን፤ ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉትን የብር ዕቃዎች ሁሉ መጠን አሳወቀው፤ 15እንደሚቀዞችና ለቀንዲሎቻቸው የሞሆነው የእያንዳንዳቸውን የውርቅ መጠን፤ ለብሩ መቅረዞችና ለቀንዲሎቻቸው የሚያድፈልገውን የእያንዳንዳቸውን የብር መጠን፤16ለያንዳንዱ ኅብስት ገጽ ጠረጼዛ የሚያስፈልገውን የወርቅ መጠን፣ ለእያንዳንዱ የብር መጠን፣ 17ለሹካዎቹ፣ ለጎዳጓዳ ሳሕኖቹ፣ ለማንቆርቆሪያዎች የሚያስፈልገውን ንጹሕ የውርቅ መጠን፤ ለእያንዳንዱ የብር መጠን፣18ለዕጣኑ መሠዊያ የሞሆነውን የጠራ ውርቅ መጠን እንዲሁም ክንፎቻቸውን ዘርግተው የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸፍኑት ከወርቅ የተሠሩትን የኪሩቤል ጀረገላዎች ንድፍ ሰጠው። 19ዳዊትም "ይህ ሁሉ፣በእኔ ላይ ባለው በእግዚአብሔር እጅ በጽሑፍ ተገለተልኝ፤ የንድፋንም ዝርዝር እንድረዳ ማስተዋልን ስጠን"አለ።20ደግሞም ዳዊት ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ "እንግዲህ በል በርታ፤ ጠንክር፤ ሥራውንም ጀመር። አትርፍ፤ ተስፋም አትቁረጥ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ከአንተ ጋር ነውና፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራ እስኪፈጸም ድረስ አይተውህም፤ አይጥልህም። 21ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ሁሉ የሚያስፈልጉትን ካህናትና ሌዋዋን ምድብም ዝግጁ ነው።በሁሉም የእጅ በሥራው ሁሉ ይረዱሃል። ሹማምቱና ሕዝቡ ሁሉ ትእዛዝህን ይፍፈጽማሉ።
1ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነውው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራውን ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔ አምላክ በምሆን፣ ጅራው ከባድ ነው። 2እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናስ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ጅራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሞሆነው መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ።3ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለን ፍቅር የተነሣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ ምቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤ 4ይህም ሦስት ሺህ መክሊት ንጹሕ ብር ለቤተ መቅደሱ የግድግዳ ግንብ ማስጌጫ 5እንዲሁም ለወርቁ ሥራ፣ ለብሩ ሥራ፣ በባለሞያዎች ለሚሠራው ሥራ ሁሉ የሚሆን ነው። ታዲያ ዛሬ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ፍቃደኛ የሚሆን ማን ነው?።6ከዚያም የቤተሰቡ አሪዎች፣ የነገዱ የእስራኤል ሹማምት፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም በንጉሥ ሥራ ላይ የተመደቡ ሹማምት፣ በፍቃዳቸው ሰጡ፤ 7ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሰጡትም አምስት ሺህ መክሊት ወርቅ፣ ዐሥር ሺህ ዳሪክ ወርቅ፣ ዐሥር ሺህ መክሊት ናስ አንድ መቶ ሺህ መክሊት ብረት ነው።8የከበሩ ድንጋዮች ያለውም ሁሉ፣ በጌድሶናዊው በይሒኤል አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግምጃ ቤት አስገባ። 9ስጦታው በገዛ ፈቃደና በፍጹም ልብ የቀረበ በመሆኑ፣ አለቆች ስላደረጉት የብበጎ ፈቃድ ስጦታ ሕዝቡ ደስ አለው፤ ንጉሥ ዳዊትም እንደዚሁ እጅግ ደስ አለው።10ዳዊትም በመላው ጉባኤ ፊት እግዚአብሔር እንዲህ ሲል አመሰገነ፤ "የአባታችን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአንተ ምስጋና ትሁን። 11እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ ለአንተ ነውና፤ ታላቅነት፣ ኅይል ክብርና ግርማ የአንተ ነው። እግዚአብሄር ሆይ፤ መንግሥትህም የአንተ ነው፤ አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።12ባለጠግነት ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተም የሁሉ ገዢ ነህ፤ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም በርታትን ለመስጠት፣ ብርታትና ኅይል በእጅህ ነው። 13አምላካችሁ ሆይ፤ አሁንም እናመሰግንሃለን፤ ለከበረው ስምህም ውዳሴ እናቀርባለን።14"ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነው ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናድርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማንኝ? 15እኛም እንደ ቀድሞ አባቶቻችን በፊትህ መጻተኞችና እንግዶች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፤ ተስፋ ሲስም ነው።16እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ለተቀደሰው ስምህ ቤተ መቅደስ እንሠራለን ዘንድ ይህ በብዛት ያዘጋጀውን ሁሉ፤ ከእጅህ የተገኘውና ሁሉም ለአንተ ነው። 17አምልኬ ሆይ፤ ልብን እንደምትመረምርና ቅንነትን እንደምትወድ ዐውቃለሁ፤ እኔም ይህን ሁሉ የሰጠሁት በበጎ ፈቃደና በቀና መንፈስ ነው። አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በበጎ ፈቃዱ እንዴት እንደ ሰጠ አይቻለሁ።18የአባታቸው የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ዐሳብ ለዘላለም በሕዝብህ ልብ ጠብቀው፤ ልባቸውንም ለአንተ ታማኝ አድርገው። 19ትእዛዞችህን፣ እኔ ባዘጋጀሁለት ነገሮች ታላቅ ህንጻ ለመጅራት እንዲችል፣ ለልጄ ለሰሎሞ ፍጹም ፈቃደኛነት ሰጠው።20ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ፣ "አምላካችሁን እግዚአብሔር ወሰዱት" አላቸው። ስለዚህ የአባታቻችን አምላክ እግዚአብሔር ወደሱ፤ በእግዚአብሔር በንጉሡም ፊት ተደፍተው ሰገዱ። 21በማግስቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠው፤ የሚቃጠል መስሥዕዋትም አቀረቡ፤ ይህም አንንድ ሺህ ወይፈን፣ አንድ ሺህ አውራ በግ፣ አንድ ሺህ የበግ ጠቦት ሲሆን፤ ከመጠጥ ቁርባኖቻቸውና ከሌሎች መሥዕዋቶች ጋር ስለ እስራኤል ሁሉ በብዛት አቀረቡ።22በዚህችም ዕለት በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ ደስታ በሉ፤ ጠጡም። ከዚያም የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን ሁለተኛ ጊዜ በይፋ ዐወቁ፤ ገዥ እንዲሆንም በእግዚአብሔር ፊት ቀቡት፤ 23ሰለሞንም ነግሦ በአባቱ በዳዊት ምትክ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ተከናወነለት፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።24የጦር አለቆችና ኅያላኑ ሁሉ እንዲሁም የንጉሥ የዳዊት ወንዶች ልጆች በሙሉ ታማኝነታቸውን ለንጉሥ ሰሎሞን አረጋ ገጡለት። 25እግዚአብሔር ሰሎሞንን በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ሁሉ እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከእነሱ በፊት ለነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ያላጎናጸፋቸውን ንጉሣዊ ክብር ሁሉ ሰጠው።26የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር። 27እርሱም በኬብሮን ሰባት ዓመት፤ በእየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በአጠቃላይ አርባ ዓመት ነገሠ። 28ብዙ ዘመን ባለጠግነትና ክብር ሳይጎድልበት ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ጅጁ ልምሞን በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።29በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻ የተከናወነው ድርጊት በባለ ራእዩ በሳሙኤል የታሪክ መጽሐፍ፣ በነብዩ በናታን የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል። 30የተጻፈውም በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ዝርዝር ጉዳዮችና በዙሪያው ከከበቡት፤ ከእስራኤልና ከሌሎች አገር መንግሥታት ታሪክ ጋር ነው።
1የዳዊት ልጅ ሰለሞንም በመንግሥቱ በረታ፤ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር፤ እጅግም ብርቱ ንጉሥ አደረገው።2ሰለሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለዳኞችም፥ በመላው እስራኤልም ሁሉ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ፤ 3የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን በገባኦን ስለነበር ሰለሞንና ጉባኤው ሁሉ እዚያ ወደነበረው የአምልኮ ሥፍራ ሄዱ። 4ዳዊት ግን ለእግዚአብሔር ታቦት በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎለት ስለነበር ከቂርያት ይዓሪም ወዳዘጋጀለት ሥፍራ አምጥቶት ነበር። 5በተጨማሪም በሆር ልጅ በኡሪ ልጅ በባስልኤል የተሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ፊት ነበረ፤ ሰለሞንና ጉባኤውም ወደ እርሱ ሄዱ።6ሰለሞንም በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ወደነበረው ወደ ናሱ መሰዊያ ወጣ። በዚያም አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ። 7በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ለሰለሞን ተገልጦ ፦ እንድሰጥህ የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለምነኝ አለው።8ሰለሞንም እግዚአብሔርን፦ ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ የቃል ኪዳን ታማኝነት አሳይተሃል፤ እኔንም በእርሱ ምትክ ንጉሥ አድርገኸኛል፤ 9አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፦ ቁጥራቸው እንደ ምድር ትቢያ በሆነው ሕዝብ ላይ አንግሠኸኛልና ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም። 10አሁንም እንደዚህ ቁጥራቸው በበዛ ሕዝብህ ላይ ሊፈርድ የሚችል ማንም ስለሌለ ይህንን ሕዝብ እመራ ዘንድ ጥበብና እውቀት ስጠኝ አለው፡፡ 11እግዚአብሔርም ሰለሞንን፡- በልብህ የነበረው ይህ ስለነበር ባለጠግነትን፥ ሀብትን፥ ወይም ክብርን ወይም የሚጠሉህን ሰዎች ነፍስ ወይም ለራስህ ረጅም እድሜ ስላልጠየቅህ ነገር ግን ባነገሥሁህ በህዝቤ ላይ ለመፍረድ ትችል ዘንድ ለራስህ ጥበብንና እውቀትን ስለጠየቅህ12አሁን ጥበብና እውቀት ተሰጥተውሃል፤ ከአንተ በፊት የነበሩት ከነበራቸው እና ከአንተም በኋላ የሚመጡት ከሚኖራቸው ከየትኛውም ነገሥታት ይበልጥ ባለጠግነት፥ ሀብት፥ ክብርም እሰጥሃለሁ አለው፡፡ 13ስለሆነም በገባኦን ከመገናኛው ድንኳን ፊት ከነበረው ከኮረብታው መስገጃ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ እዚያም በእስራኤል ላይ ነገሠ፡፡14ሰለሞን ሰረገሎችን እና ፈረሰኞችን ሰበሰበ፡፡ በሰረገሎች ከተማዎችና ከራሱ ከንጉሡ ጋር በኢየሩሳሌም ያኖራቸው አንድ ሺህ አራት መቶ ሰረገሎች እና አሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፡፡ 15ንጉሡም ብርና ወርቅ በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት በቆላ እንዳሉት የሾላ ዛፎች እንዲበዛ አደረገው፡፡16ከግብጽና ከቀዌ ለሰለሞን ፈረሶችን ስለ ማስመጣት የእርሱ ነጋዴዎች በገንዘብ እየገዙ ያመጡአቸው ነበር፡፡ 17ከግብጽ አንዱን ሰረገላ በስድስት መቶ ሰቅል ብር፥ አንዱን ፈረስ በመቶ ሃምሳ ሰቅል ብር ዋጋ ያስመጡ ነበር፡፡ ለኬጢያውያንና ለሶርያ ነገሥታትም ልከው ይሸጡአቸው ነበር፡፡
1በዚህ ጊዜ ሰለሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤት እንዲገነባ እና ለመንግሥቱ ቤተ መንግሥት እንዲገነባ አዘዘ፡፡ 2ጭነት የሚሸከሙ ሰባ ሺህ ሰዎች እና ከተራሮች እንጨት የሚቆርጡትን ሰማንያ ሺህ ሰዎች እነርሱንም የሚቆጣጠሩ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች መደበ፡፡ 3ሰለሞንም ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ፦የሚኖርበትን ቤት እንዲሠራ የዝግባ እንጨት በመላክ ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ ለእኔም እንደዚሁ አድርግልኝ፡፡4እነሆ በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ቅመም ሽታ ለማጠን፥ የመገኘቱን ኅብስት ዘወትር ለማኖር፥ በጠዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም ፥ በመባቻዎቹና ለአምላካችን ለእግዚአብሔር በተመደቡት ልዩ በዓላት የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ልገነባና ልቀድሰው ነው፡፡ ይህ ለእስራኤል ለሁልጊዜ ሕግ ነው፡፡ 5አምላካችን ከአማልክት ሁሉ በላይ ታላቅ ስለሆነ የምሠራው ቤት እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡6ነገር ግን መላው አጽናፈ ዓለምና ሰማይ ራሱ ሳይቀር ሊይዘው ለማይችለው ለእርሱ ለእግዚአብሔር ቤት ይሠራ ዘንድ የሚችል ማን ነው? በፊቱ መሥዋዕት ከማቅረብ በስተቀር ለእርሱ ቤት እሰራ ዘንድ እኔ ማን ነኝ? 7በመሆኑም በወርቅ፥ በብር፥ በናስ፥ በብረት፥ እንዲሁም ሐምራዊውን፥ ቀዩን፥ ሰማያዊውን ግምጃ በመሥራት የተካነ ሰው፥ የእንጨት ቅርጻ ቅርጽ ዓይነቶችን ሁሉ መሥራት የሚያውቅ ሰው ላክልኝ፡፡ እርሱም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት የተካኑ ሰዎች ጋር ይሆናል፡፡8አገልጋዮችህ እንጨት ከሊባኖስ መቁረጥ እንደሚያውቁ ስለማውቅ ከሊባኖስ የዝግባ እንጨቶች፥ የጥድ እንጨቶች፥ የሰንደልም እንጨቶች ላክልኝ፡፡ እነሆ ባሪያዎችህ ከባሪያዎቼ ጋር ይሆናሉ፡፡ 9ልሠራ ያሰብኩት ቤት ታላቅና ድንቅ ይሆናልና የተትረፈረፈ ሳንቃ እንጨት እንዲያዘጋጁልኝ ነው፡፡ 10እነሆ እንጨቱን ለሚቆርጡ ሰዎች ሀያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ የተፈጨ ስንዴ፥ ሀያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ፥ ሀያ ሺህ የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ ሀያ ሺህ የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ለባሪያዎችህ እሰጣለሁ፡፡11ንጉሥ ኪራም፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚወዳቸው በላያቸው አንግሦሃል ብሎ መልሶ ወደ ሰለሞን መልእክት ላከ፡፡ 12በተጨማሪም ኪራም፦ ሰማይንን ምድርን የፈጠረ፥ ለእግዚአብሔር ቤት እና ለመንግሥቱ ቤት የሚሠራ ጥበበኛና ብልሃተኛ አስተዋይም ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት የሰጠ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለ፡፡13አሁንም ማስተዋል የተሰጠውን የተካነውን ባለሙያዬን ሁራምን ልኬልሃለሁ፡፡ 14ከዳን ሴት ልጆች የአንዲቱ ልጅ ነው፡፡ አባቱ የጢሮስ ሰው ነበር፡፡ ወርቁን፥ ብሩን፥ ናሱን፥ ብረቱን፥ ድንጋዩን እንዲሁም እንጨቱን፥ ሐምራዊውን፥ ሰማያዊንና ቀዩን ግምጃ ጥሩ በፍታውንም በመሥራት የተካነ ነው፡፡ የትኛውንም ዓይነት ቅርጽ በመሥራት እና የትኛውንም ዓይነት ንድፍ በማውጣትም የተካነ ነው፡፡ በተካኑት ሠራተኞችህ መካከል እና ከጌታዬ ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር ይሆን ዘንድ ስፍራ ይዘጋጅለት፡፡15አሁንም ጌታዬ የተናገረውን ስንዴውንና ገብሱን ዘይቱንና የወይን ጠጁን እነዚህን ነገሮች ወደ አገልጋዮቹ ይላክ፡፡ 16እኛም የሚያስፈልግህን ያህል እንጨት ከሊባኖስ እንጨት እንቆርጣለን፡፡ እንደ ታንኳ በባሕር ላይ ወደ ኢዮጴ እንወስድልሃለን፤ አንተም እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ታጓጉዘዋለህ፡፡17ሰለሞንም ኣባቱ ዳዊት በእስራኤል ምድር የነበሩትን የውጪ አገር ዜጎች ሁሉ እንደቆጠረ እርሱ ያደረገበትን ዘዴ ተከትሎ ቆጠራቸው፡፡ እነርሱም አንድ መቶ ሃምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሆነው ተገኙ፡፡ 18ሰባ ሺህው ጭነት እንዲሸከሙ ሰማንያ ሺህው በተራሮችም ላይ እንጨት እንዲቆርጡ እና ሦስት ሺህ ስድስት መቶው ደግሞ ሕዝቡን ለሥራ የሚያሰማሩ ተቆጣጣሪዎች እንዲሆኑ መደባቸው፡፡
1ከዚህ በኋላ ሰለሞን እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠለት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤት መሥራት ጀመረ፡፡ ዳዊት እንዳቀደለት በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ሥፍራውን አዘጋጀ፡፡ 2በነገሠ በአራተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር በሁለተኛው ቀን መሥራት ጀመረ፡፡ 3ሰለሞንም ለእግዚአብሔር ቤት የጣለው መሠረት ስፍሮች እነዚህ ናቸው፡፡ ርዝመቱ በድሮው መለኪያ ስልሳ ክንድ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፡፡4በቤቱም ፊት የነበረው በረንዳ ርዝመቱ ከቤቱ ወርድ ተመሳሳይ ሆኖ ሃያ ክንድ ነበር፡፡ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበረ፡፡ ሰለሞንም ውስጡን በንጹህ ወርቅ ለበጠው፡፡ 5የዋናውን ቤት ጣሪያ በጥድ እንጨት ሠራው፡፡ በንጹህ ወርቅም ለበጠው፡፡ የዘንባባ ዛፎችንና የሰንሰለቶችን አምሳል ቀረጸበት፡፡6ቤቱንም በከበሩ ድንጋዮች አስጌጠው፤ ወርቁም የምሥራቅ ፈርዋይም ወርቅ ነበር፡፡ 7አውታሮቹን፥ ሰረገሎቹን፥ ግድግዳዎቹንና በሮቹንም በወርቅ ለበጣቸው፡፡ በግድግዳዎቹም ላይ ኪሩቤልን ቀረፀ፡፡8ቅድስተ ቅዱሳኑንም ሠራ፤ ርዝመቱም ከቤቱ ወርድ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፡፡ ስድስት መቶ መክሊት በሚያህል በጥሩ ወርቅም ለበጠው፡፡ 9የሚስማሮቹም ክብደት ሃምሳ ሰቅል ወርቅ ነበር፡፡ ከፍ ያሉ ገጽታዎቹን/ሰሌዳዎቹን በወርቅ ለበጣቸው፡፡10ለቅድስተ ቅዱሳን ሁለት የኪሩቤል አምሳያዎችን ሠራ፤ ባለሙያዎችም በወርቅ ለበጡዋቸው፡፡ 11ክንፎቹ በአጠቃላይ ከዳር እስከ ዳር ሃያ ክንድ ይረዝሙ ነበር፡፡ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ ክፍሉ ግድግዳ ድረስ የሚደርስ አምስት ክንድ ይረዝም ነበር፤ ሌላኛው ክንፍ እንደዚሁ እስከ ሌላኛው ኪሩብ ክንፍ ድረስ የሚደርስ አምስት ክንድ ነበር፡፡ 12የሌላኛው ኪሩብ ክንፍም ክፍሉ ግድግዳ ድረስ የሚደርስ አምስት ክንድ ይረዝም ነበር፤ ሌላኛው ክንፉም እንደዚሁ የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ የሚነካ አምስት ክንድ ነበር፡፡13የእነዚህም ኪሩቤሎች ክንፎች በአጠቃላይ ሃያ ክንድ ያህል ተዘርግተው ነበር፡፡ ኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ዋናው ቤት እየተመለከቱ በእግሮቻቸው ቆመው ነበር፡፡ 14ከሰማያዊም፥ ከሐምራዊም፥ ከቀዩም፥ ሐር እና ከጥሩ በፍታ መጋረጃውን ሠራ፤ የኪሩቤሎችንም ቅርፅ ሠራባቸው፡፡15ሰለሞንም ለቤቱ ፊት ለፊት እያንዳንዳቸው ሠላሳ አምስት ክንድ ከፍታ ያላቸውን ሁለት ምሰሶዎች ሠራ፡፡ በእያንዳንዳቸውም ጫፍ ላይ የነበሩት ርዕሰ አእማድ አምስት ክንድ ከፍታ ያላቸው ነበሩ፡፡ 16ለምሰሶዎቹም ሰንሰለቶችን አድርጎ በጫፋቸው ላይ አኖራቸው፡፡ መቶም ሮማኖች ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋር አገናኛቸው፡፡ 17ምሰሶዎቹንም በቤት መቅደሱ ፊት ለፊት አንደኛውን በቀኝ ሌላኛውንም በግራ አቆማቸው፤ በስተቀኝ የነበረውን ምሰሶ የሚያቆም/ያኪን፥ የበስተግራውንም ምሰሶ የሚያበረታ/ቦኤዝ ብሎ ሰየመው፡፡
1በተጨማሪም የናሱን መሠዊያ ሠራ፤ ርዝመቱ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ቁመቱም አሥር ክንድ ነበር፡፡ 2ክፈፉ ከጫፍ እስከ ጫፉ አሥር ክንድ የሆነ ከቀለጠ ብረት ትልቅ ክብ ውሃ መያዣ ኩሬም ሠራ፡፡ ቁመቱም አምስት ክንድ ነበር፤ ዙሪያውም ሰላሳ ክንድ ነበር፡፡ 3ውሃ መያዣው ቀልጦ ሲሰራ ከአርሱ ጋር አብረው የተሠሩ ከውሃ መያዣው ዙሪያ ከክፈፉ በታች በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት አሥር ኮርማዎች ነበሩበት፡፡4ውሃ መያዣው ሦስቱ ወደ ሰሜን በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ምዕራብ በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ በሚመለከቱ በአሥራ ሁለት በሬዎች ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ውሃ መያዣው በላያቸው ላይ ሆኖ የጀርባ የሠውነት ክፍላቸው በስተ ውስጥ ነበር፡፡ 5ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበር፡፡ የአፉ ክፈፍም እንደ ጽዋ ከንፈር እንደ ፈነዳ የሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፡፡ ሦስት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ውሃ ይይዝ ነበር፡፡ 6ደግሞም የተለያዩ ነገሮችን ማጠቢያ አሥር ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፤ አምስቱን በስተግራ አምስቱንም በስተቀኝ አኖራቸው፤ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ለማቅረብ ጥቅም የሚሰጡ ነገሮች በውስጣቸው ይታጠቡባቸው ነበር፡፡ የውሃ መያዣው ኩሬ ግን ለካህናቱ መታጠቢያ ነበር፡፡7ለንድፋቸው በተሰጠው መመሪያ መሠረት አሥሩን የወርቅ መቅረዞች ሠራ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተግራ አምስቱን በስተቀኝ አኖራቸው፡፡ 8አሥሩንም ገበታዎች ሠርቶ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተግራ አምስቱን በስተቀኝ አኖራቸው፡፡ አንድ መቶ የወርቅ ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፡፡9በተጨማሪም የካህናቱን አደባባይ እና ታላቁንም አደባባይ የአደባባዮቹንም በሮች ሠራ፤ በሮቻቸውንም በናስ ለበጠ፡፡ 10የውሃ መያዣውንም ኩሬ በቤቱ በስተቀኝ በስተምስራቅ ፊቱን ወደ ደቡብ አዙሮ አኖረው፡፡11ኪራምም ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹንና መሠዊያውን መርጪያ ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፡፡ ኪራምም እንደዚህ ለንጉሥ ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ - 12ሁለቱን አዕማድ፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ጨረሰ፡፡ 13በአዕማዱ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ለሚሸፍኑት ሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ተርታ ሮማኖች አድርጎ ለሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች አራት መቶ ሮማኖች ሠራ፡፡14ማቆሚያዎቹንና በማቆሚያዎቹ ላይ የሚቀመጡትን የመታጠቢያ ሰሃኖችንም ሠራ፤ 15አንድ የውሃ መያዣ ኩሬ እና ከስሩ የሚሆኑትን አስራ ሁለት ኮርማዎች፥ 16እንዲሁም ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹን፥ ሜንጦዎቹን እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ቁሳቁሶችን ሁሉ ሠራ፤ ኪራም ለንጉሥ ሰለሞን ለእግዚአብሔር ቤት ከአንፀባራቂ ናስ ሠራቸው፡፡17ንጉሡም በዮርዳኖስ ሜዳ በሱኮትና ዛሬታን መካከል በሸክላው መሬት ውስጥ ብረታ ብረቱ እንዲቀልጥ አስደረገ፡፡ 18ሰለሞንም እነዚህን እቃዎች ሁሉ በብዛት እንዲሰሩ አስደረገ፤ በእርግጥም የናሱ ክብደት ሊታወቅ አይችልም ነበር፡፡19ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የቤት ዕቃዎች፥ የወርቁን መሠዊያ፥ የመገኘቱ ሕብስት የሚቀመጥባቸውን ገበታዎች፥ 20በቅድስተ ቅዱሳን ፊት ያበሩ ዘንድ የታቀዱትን መቅረዞችን ከቀንዲሎቹ ጋር ሠራ፡፡እነዚህ ከንጹሕ ወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡ 21አበባዎቹም፥ ቀንዲሎቹና መኮስተሪያዎቹም የጥሩ ወርቅ ነበሩ፡፡22ጉጠቶቹም፥ ጎድጓዳ ሳህኖቹም፥ ማንኪያዎቹም ፥ እጣን ማጨሻዎቹም ሁሉ ከንጹህ ወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡ ወደ ቤቱ ውስጥ መግቢያዎቹን በተመለከተ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያስገቡት የውስጥ በሮች እና የቤቱ ማለትም የቤተ መቅደሱ በሮች ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡
1ሰለሞንም እንደዚህ ለእግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተጠናቀቀ፡፡ ሰለሞንም አባቱ ዳዊት የቀደሳቸውን እቃዎች ብሩን፥ ወርቁንና የቤት እቃዎችን ሁሉ ጨምሮ አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩት ግምጃ ቤቶች ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡2ከዚያም ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ማለትም ከጽዮን እንዲያመጡ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ፥ የነገድ አለቆችን ሁሉ እና የእስራኤልን ሕዝብ ቤተሰብ መሪዎች ሰበሰበ፡፡ 3የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ በሰባተኛው ወር በበዓሉ ወቅት በንጉሡ ፊት ተሰበሰቡ፡፡4የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ፤ ሌዋውያንም ታቦቱን አነሱ፡፡ 5ታቦቱንም፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ በድንኳኑም ውስጥ የነበሩትን ቅዱሳት ዕቃዎች በሙሉ አመጡ፡፡ ከሌዊ ነገድ የነበሩት ካህናት እነዚህን ነገሮች ሁሉ አመጡ፡፡ 6ንጉሥ ሰለሞንና የእስራኤል ማህበር ሁሉ ሊቆጠሩ የማይችሉትን በጎችና በሬዎች እየሰዉ በታቦቱ ፊት ተሰበሰቡ፡፡7ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከኪሩቤል ክንፍ በታች ወደ ቦታው አመጡት፡፡ 8ኪሩቤልም በታቦቱ ስፍራ ላይ ክንፎቻቸውን ዘርግተው ነበር፤ ኪሩቤልም ታቦቱንና መሸከሚያዎቹን ምሶሶዎችም ይሸፍኑ ነበር፡፡9መሸከሚያዎቹ ምሶሶዎችም እጅግ ረጅም ከመሆናቸው የተነሳ ጫፎቻቸው ከውስጠኛው ክፍል ፊት ለፊት ከቅዱሱ ሥፍራ ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ክውጪ መታየት አይችሉም ነበር፡፡ እስከዚህች ቀንም ድረስ በዚያ ይገኛሉ፡፡ 10በታቦቱም ውስጥ የእስራኤል ሰዎች ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በስተቀር ምንም ነገር አልነበረባቸውም፡፡11ካህናቱም ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ወጡ፡፡ በዚያ የነበሩትም ካህናት በተመደቡበት ክፍል ላይ ሳያተኩሩ ሁሉም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀድሰው ነበር፡፡ 12መዘምራን የነበሩትም ሌዋውያንም አሳፍን፥ ኤማንን፥ ኤዶታምን ልጆቻቸውንና ወንድሞቻቸውን ጨምሮ ሁሉም ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽል፥ በገና እና መሰንቆ/ክራር እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በስተምሥራቅ ቆመው ነበር፡፡ ከእነርሱም ጋር መቶ ሃያ መለከት የሚነፉ ካህናት ነበሩ፡፡13መለከቱን የሚነፉትና መዘምራኑም ከመቅደሱ ሲወጡ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያወደሱ በአንድ ቃል ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር፡፡ ከመለከቶቹና ከጸናጽሎቹ ከሌሎቹም መሳሪያዎች ጋር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፡፡" ቸር ነውና የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም የሚጸና ነውና" ብለው ዘመሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ቤቱ የእግዚአብሔር ቤት በደመና ተሞላ፡፡ 14የእግዚአብሔር ክብር ቤቱን ሞልቶት ስለነበር ከደመናው የተነሳ ካህናቱ ለማገልገል መቆም አልቻሉም ነበር፡፡
1ሰለሞንም፦"እግዚአብሔር በድቅድቅ ጨለማ እንደሚኖር ተናግሯል፤2 እኔ ግን ለዘላለም እንድትኖርበት የላቀ መኖሪያ ቤት ሠራሁልህ" አለ፡፡3ከዚያም የእስራኤል ጉባኤ ቆመው በነበሩበት ንጉሡ ፊቱን ዘወር አድርጎ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ ባረከ፡፡4እርሱም ፦ "ለአባቴ ለዳዊት የተናገረ እና በገዛ እጆቹ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤ 5"ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ የሚሆንበት ቤት በዚያ ይሠራልኝ ብዬ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ማንኛውንም ከተማ አልመረጥኩም፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ አንድም ሰው አልመረጥኩም፤ 6ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲሆንባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ" ብሎአል፡፡7አሁንም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት መስራት በአባቴ በዳዊት ልብ ነበር፡፡ 8ነገር ግን እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፦ "ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በልብህ ነበረ፤ ያ በልብህ የነበረ መሆኑ መልካም አደረግህ፡፡ 9ነገር ግን ቤቱን አንተ ልትገነባው አይገባም፤ ይልቁንም ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራልኛል" አለው፡፡10እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠ በአባቴ በዳዊት ፈንታ ስለተነሳሁ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ስለተቀመጥሁ እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ፈጽሞአል፡፡ ለእስራኤል አምላክም ለእግዚአብሔር ስም ቤት ሠራሁ፡፡ 11ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ያደረገው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦቱን በዚያ ውስጥ አኖርሁ፡፡12ሰለሞን የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ባሉበት በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት እጆቹን ዘርግቶ ቆመ፡፡ 13ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መድረክ ሰርቶ ነበር፡፡ በአደባባዩም መሃል ላይ አድርጎት ነበር፡፡ በእርሱም ላይ በመቆም በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ተንበርክኮ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ፡፡14እንዲህም አለ፦ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ በፍጹም ልባቸው በፊትህ ከሚሄዱ ባሪያዎችህ ጋር ኪዳንንና የቃል ኪዳን ታማኝነትን የምትጠብቅ በሰማይም ሆነ በምድር እንዳንተ ያለ አምላክ የለም፤ ለባሪያህ 15ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ የጠበቅህ አንተ፥ አዎ በአፍህ የተናገርኸውን ዛሬም እንደሆነው በእጅህ ፈጽመኸዋል፡፡16አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት፦ "'አንተ በፊቴ እንደተመላለስህ ልጆችህ በሕጌ ይሄዱ ዘንድ ቢጠነቀቁ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው በፊቴ አታጣም' በማለት የሰጠኸውን ተስፋ ፈጽምለት፡፡ 17እንግዲህ የእስራኤል አምላክ ሆይ ለባሪያህ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም፡፡18በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ መላው አጽናፈ ዓለም እና ሰማየ ሰማያት ራሱ ሊይዝህ አይችልም - ይልቁንም እኔ የሠራሁት ቤት ምንኛ ያነሰ ይችላል! 19ነገር ግን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ የባሪያህን ይህንን ጸሎትና ልመናውን እባክህን ተቀበል፤ ባሪያህ በፊትህ የሚጸልየውን ጩኸትና ጸሎት ስማ፡፡ 20ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ስምህን እንደምታደርበት ወደተናገርከው ወደዚህ ስፍራ ዓይኖችህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ በቀንና በሌሊት የተገለጡ ይሁኑ፡፡21ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ በሚጸልዩበት ጊዜ ልመናዎቻቸውን ስማ፤ ከማደሪያህ ስፍራ ከሰማያት ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል፡፡22አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢበድልና እንዲምል ቢጠየቅ እርሱም መጥቶ በዚህ ቤት ውስጥ በመሠዊያህ ፊት ቢምል 23ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ አድርግም፤ በደሉን በራሱ ላይ በማድረግ በደለኛውን መልሰህ በመክፈል በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ፡፡ ለጽድቁ ብድራትን ለመስጠት ጻድቁ ንጹህ መሆኑንም አስታውቅለት፡፡24ሕዝብህ እስራኤል አንተን ከመበደላቸው የተነሳ በጠላት ድል ሲነሱ ወደ አንተ ቢመለሱ፥ በዚህም ቤተ መቅደስ ውስጥ በፊትህ ስምህን ቢጠሩ፥ ቢጸልዩና ምህረትን ቢለምኑ 25እባክህን ከሰማያት ስማና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሳቸው፡፡26አንተን ከመበደላቸው የተነሳ ሰማያት ቢዘጉና ምንም ዝናብ በማይኖርበት ጊዜ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩ፥ ስምህን ቢጠሩና ስታስጨንቃቸው ከኃጢአታቸው ቢመለሱ 27ከሰማይ ስማ፤ ሊመላለሱበት ወደሚገባቸው መልካሙ መንገድ ስትመራቸው የባሪያዎችህንና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፡፡ ለሕዝብህ ርስት አድርገህ በሰጠሃት በምድርህ ላይ ዝናብን ላክ፡፡28በምድሪቱ ላይ ርሃብ ቢኖር ወይም ቸነፈር ወይም ዋግ ወይም አረማሞ ወይም አንበጣ ወይም ኩብኩባ ቢኖር ወይም ጠላቶች በምድራቸው ውስጥ የከተማ በሮችን ቢያጠቁ ወይም ማናቸውም መቅሰፍት ወይም ደዌ ቢኖር 29አንድም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል ሁሉ እያንዳንዱ መቅሰፍቱንና ሐዘኑን በልቡ አውቆ ወደዚህ ቤተ መቅደስ እጆቹን ዘርግቶ ጸሎትና ልመና ቢያቀርብ 30በሰማይ በምትኖርበት ሆነህ ስማ፤ ይቅርም በል፤ የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቅ አንተ ብቻ ስለሆንክ ልቡን ታውቃለህ፤ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱ ሁሉ ብድራትን ስጠው፡፡ 31ለአባቶቻችን በሰጠሃቸው ምድር ላይ በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ አንተን እንዲፈሩህ በመንገድህም ይሄዱ ዘንድ ይህንን አድርግ፡፡32ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ ባእድ ሰው ደግሞ ከታላቁ ስምህ ፥ ከኃያሉ እጅህና ከተዘረጋችው ክንድህ የተነሳ ከሩቅ አገር ሲመጣ፥ ወደዚህ ቤተ መቅደስ መጥተው በሚጸልዩበት ጊዜ 33በሰማይ በምትኖርበት ስፍራ ሆነህ ስማ፤ በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ሁሉ ስምህን እንዲያውቁ፥ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል እንዲፈሩህ እና ይህ የሠራሁት ቤት በስምህ የሚጠራ መሆኑን እንዲያውቁ ባእዱ ሰው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ፡፡34ሕዝብህ አንተ በምትልካቸው በምንም መንገድ ከጠላቶቻቸው ጋር ለመዋጋት ቢወጡ ፥ አንተ ወደመረጥካት ወደዚች ከተማና ለስምህ ወደሠራሁት ወደዚህ ቤት ቢጸልዩ 35ከሰማያት ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማና በጉዳያቸው አግዛቸው፡፡36ኃጢአት የማይሰራ ማንም የለምና አንተን በበደሉህ ጊዜ ተቆጥተሃቸውም ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው ጠላት ወደ ቅርብም ሆነ ሩቅ አገር ቢያግዛቸውና እንደ ምርኮኛ ወደ ምድራቸው ቢወስዳቸው 37በግዞት አገር ውስጥ መሆናቸውን ቢገነዘቡ፥ ንስሃ ቢገቡና በተማረኩበት ምድር ሞገስን ካንተ ቢፈልጉ፥ 'ጠማማን ነገር አድርገናል፤ በድለናል፤ እኩይ ምግባር ፈጽመናል፤' ቢሉ 38ምርኮኛ ተደርገው በተወሰዱባት በተማረኩባት ምድር በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ወዳንተ ቢመለሱና ለአባቶቻቸው ወደሰጠሃቸው ምድር፥ ወደ መረጥካት ከተማና ለስምህ ወደሠራሁት ቤት ቢጸልዩ 39በሰማያት በምትኖርበት ስፍራ ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማና በጉዳያቸው አግዛቸው፡፡ የበደሉህን የሕዝብህን ኃጢአት ይቅር በል፡፡40አሁንም አምላኬ ሆይ በዚህ ስፍራ ወደሚደረገው ጸሎት ዓይኖችህ የተገለጡና ጆሮዎችህ የሚያተኩሩ እንዲሆኑ እለምንሃለሁ፡፡ 41አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ አንተና የኃይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ተነስ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ካህናትህ ደህንነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በመልካምነትህ ደስ ይበላቸው፡፡ 42እግዚአብሔር አምላክ ሆይ የቀባኸውን ሰው ፊት ካንተ አትመልሰው፡፡ ለባሪያህም ለዳዊት ያደረግህለትን የቃል ኪዳን ታማኝነት አስብ፡፡
1ሰለሞን ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕቶችን በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ፡፡ 2የእርሱ ክብር ቤቱን ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት አልቻሉም፡፡ 3የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ እሳቱ ሲወርድና የእግዚአብሔር ክብር በቤቱ ላይ እንደነበር ያዩ ነበር፡፡ በድንጋዩ ወለል ንጣፍ ላይ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና አቀረቡ፡፡ "መልካም ነውና የቃል ኪዳን ታማኝነቱም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና" አሉ፡፡4ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፡፡ 5ንጉሥ ሰለሞንም ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሃያ ሺህ በጎች በጎችና ፍየሎች ሰዋ፡፡ እንደዚህ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ፡፡ 6ካህናቱም እያንዳንዳቸው በሚያገለግሉበት ቦታ ቆመው ሌዋውያኑም "የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና" በሚለው መዝሙር እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ንጉሥ ዳዊት ያዘጋጀውን የእግዚአብሔር የዜማ መሳሪያዎች ይዘው ቆመው ነበር፡፡ ካህናቱ ሁሉ በፊታቸው መለከቶቻቸውን ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆሙ፡፡7ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት ፊት ለፊት የነበረውን የአደባባዩን መካከል ቀደሰ፡፡ በዚያም የሠራው የናስ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉን ቁርባንና ስቡን መያዝ ስላልቻለ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሕብረት መሥዋዕቱን ስብ በዚያ አቀረበ፡፡8በዚያን ጊዜ ሰለሞን ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከሐማት መግቢያ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ የመጡ እጅግ ታላቅ ጉባኤ ለሰባት ቀናት ለሰባት ቀናት በዓል አደረጉ፡፡ 9መሠዊያውን ለሰባት ቀናት ቀድሰው እና በዓሉን ለሰባት ቀናት ጠብቀው ስለነበር በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አደረጉ፡፡ 10ሰለሞንም በሰባተኛው ወር በሃያ ሦስተኛው ቀን እግዚአብሔር ለዳዊት፥ ለሰለሞንና ለሕዝቡ ለእስራኤል ካሳየው በጎነት የተነሳ በደስታና በሐሴት ልብ ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ ሕዝቡን አሰናበተ፡፡11በመሆኑም ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የገዛ ራሱን ቤት ጨረሰ፡፡ ለእግዚአብሔር ቤትና ለገዛ ራሱ ቤት ሰለሞን በልቡ ያሰበውን ማናቸውንም ነገር በስኬት አከናወነ፡፡ 12እግዚአብሔርም በሌሊት ለሰለሞን ተገልጦ፦" ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህንንም ስፍራ ለራሴ የመስዋዕት ቤት እንዲሆን መርጫለሁ" አለው፡፡13ዝናብ እንዳይኖር ሰማያትን ብዘጋ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣን ባዝዘው ወይም በሕዝቡ መካከል ቸነፈርን ብሰድድ 14በስሜ የተጠሩት ህዝቤ ራሳቸውን ቢያዋርዱ፥ ቢጸልዩ፥ ፊቴን ቢፈልጉና ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ ከሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ፡፡ 15አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚደረግ ጸሎት ዓይኖቼ ክፍት ይሆናሉ፤ ጆሮዎቼም ያደምጣሉ፡፡16አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህንን ቤት መርጫለሁ፤ ቀድሻለሁም፤ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ፡፡ 17አንተ ደግሞ ያዘዝሁህን ሁሉ በመፈጸም እና ሥርዓቶቼንና ሕግጋቴን በመጠበቅ አባትህ ዳዊት እንደሄደ በፊቴ ብትሄድ፥ 18ከአባትህ ከዳዊት ጋር በገባሁት በቃል ኪዳን "ከዘርህ በእስራኤል ላይ አለቃ የሚሆን አይታጣም" እንዳልኩት የመንግሥትህን ዙፋን አጸናለሁ፡፡19ነገር ግን እኔን ከመከተል ብትመለሱና በፊታችሁ ያኖርኳቸውን ሥርዓቶቼንና ትዕዛዛቶቼን ብትተዉ፥ ሄዳችሁ ሌሎችንም አማልክት ብታመልኩ ብትሰግዱላቸውም፥ 20ያን ጊዜ ከሰጠኋችሁ ምድሬ እነቅላቸዋለሁ፤ ለስሜ የቀደስኩትን ይህንን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፡፡ በሕዝቦችም ሁሉ መካከል ምሳሌና መቀለጃ አደርገዋለሁ፡፡21ምንም እንኳን ይህ ቤተ መቅደስ እጅግ የላቀ ቢሆንም በአጠገቡ የሚያልፉ ሰዎች ይደነግጣሉ፤ በጥላቻ ይነጋገራሉ፡፡ "እግዚአብሔር በዚህ ምድርና በዚህ ቤት ላይ ይህንን እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ፡፡ 22ሌሎችም፦ "ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክትን የሙጥኝ ከማለታቸው የተነሳ ፥ ስለሰገዱላቸው ስላመለኳቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሔር ይህንን ሁሉ አደጋ ያመጣባቸው" ብለው ይመልሳሉ፡፡
1ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት የሠራበትን ሃያው ዓመት መጠናቀቂያ ላይ 2ሰለሞን ኪራም የሰጠውን ከተሞች እንደገና ሠርቶ የእስራኤል ሰዎች እንዲኖሩባቸው አደረገ፡፡3ሰለሞን ሐማትሱባን አጥቅቶ አሸነፋት፡፡ 4በምድረ በዳም የነበረችውን ታድሞርን እና በሐማትም የሠራቸውን የዕቃ ቤቱን ከተሞች ሁሉ ሠራ፡፡5በቅጥሮች፥ በበሮችና በመዝጊያዎች የተመሸጉትን የላይኛውን ቤትሆሮንን እና የታችኛዋን ቤትሆሮንን ከተሞች ሠራ፡፡ 6የባዕላትንም ከተማ፥ ሰለሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፥ የሰረገላዎቹንም ከተሞች፥ የፈረሰኞቹንም ከተሞች እንዲሁም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስ እና በግዛቱ ሥር በነበሩት ስፍራዎች ሊሠራ የተደሰተባቸውን ነገሮች ሁሉ ሠራ፡፡7ከኬጢያውያን፥ ከአሞራውያን፥ ከፌርዜያውያን፥ ከኤዊያውያን እና ከኢያቡሳውያን የቀሩትን የእስራኤል ወገን ያልሆኑትን ሕዝብ ሁሉ፥ 8የእስራኤል ሕዝብ ያላጠፉአቸውን በምድሪቱ ላይ ከእነርሱ በኋላ የቀሩትን ዝርያዎቻቸውን ሰለሞን እስከ ዛሬ ድረስ የግዳጅ የጉልበት ሠራተኞች አደረጋቸው፡፡9ነገር ግን ሰለሞን የእስራኤል ሰዎችን አንድም የግዳጅ የጉልበት ሠራተኞች አላደረጋቸውም፤ ይልቁንም ወታደሮቹ፥ አዛዦቹ፥ ሹማምንቶቹ እና የሠረገሎቹና የፈረሰኞቹ አዛዦች አደረጋቸው፡፡ 10እነዚህ ሁለት መቶ ሃምሳው፥ ሥራውን የሚሰሩትን ሰዎች የሚቆጣጠሩ የንጉሥ ሰለሞን ዋና ተቆጣጣሪዎችን የሚያስተዳድሩ ዋና ሹማምንቶችም ነበሩ፡፡11ሰለሞንም፦ "የእግዚአብሔር ታቦት የደረሰበት ቦታ ሁሉ ቅዱስ ስለሚሆን ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት መኖር አይገባትም" በማለቱ ምክንያት የፈርኦንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ውጪ ለእርሷ ወደ ሰራላት ቤት አመጣት፡፡12ከዚያም ሰለሞን በመተላለፊያው ፊት ለፊት በሠራው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፡፡ 13ዕለታዊው መርሀ ግብር በሚጠይቀው መሰረት መሥዋዕቶች አቀረበ፤ በሙሴ ትዕዛዝ የሚገኙትን መመሪያዎች በመከተል በሰንበታቱ ቀናት፥ በየመባቻዎቹ እና በተደነገጉት በዓላት በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓል፥ በየሰባቱ ሱባኤ በዓል እና በየዳሱም በዓል አቀረባቸው፡፡14ሰለሞን የአባቱን የዳዊትን ትዕዛዝ በመከተል ካህናቱን በየክፍላቸው፥ ሌዋውያንንም ዕለታዊው መርሀ ግብር እንደሚጠብቅባቸው እግዚአብሔርን ለማወደስና በካህናቱ ፊት ለማገልገል በየሥራቸው መደባቸው፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ይህንንም አዝዞ ስለነበር ደጅ ጠባቂዎችን ደግሞ በእያንዳንዱ በር በየክፍላቸው መደባቸው፡፡ 15እነዚህ ሰዎች ንጉሡ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ማናቸውንም ጉዳይ ወይም መጋዘኖቹን በተመለከተ ከሰጠው ትዕዛዛቱ አላፈነገጡም፡፡16እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ቤት መሠረት ከተጣለበት ቀን አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ የሰለሞን ሥራ ተከናወነ፡፡ በዚህ ሁኔታ የእግዚአብሔር ቤት ተጠናቅቆ ጥቅም ላይ ዋለ ፡፡17ከዚህ በኋላ ሰለሞን በኤዶምያስ ምድር የባሕር ዳርቻ ወዳሉት ወደ ዔጽዮንጋብር እና ኤላት ሄደ፡፡ 18ኪራምም የባህርን ነገር በሚገነዘቡ መርከበኞች የሚታዘዙ መርከቦችን ላከለት፡፡እነርሱም ከሰለሞን አገልጋዮች ጋር ወደ ኦፊር ሄዱ፡፡ ከዚያም አራት መቶ ሃምሳ መክሊት ወርቅ ለንጉሥ ሰለሞን አመጡ፡፡
1የሳባም ንግሥት የሰለሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በከባባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፡፡ ቅመማ ቅመሞች፥ ብዙ ወርቆች እና በርካታ የከበሩ ማዕድናት ከተጫኑ ግመሎች ጋር ከብዙ ጓዝ ጋር መጣች፡፡ ወደ ሰለሞን በመጣች ጊዜ በልብዋ የነበረውን ሁሉ አጫወተችው፡፡ 2ሰለሞንም ጥያቄዎችዋን ሁሉ መለሰላት፤ ለሰለሞንም የከበደው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ያልመለሰውም ምንም ጥያቄ አልነበረም፡፡3የሳባም ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ፥ ሠርቶትም የነበረውን ቤተ መንግሥት፥ 4በጠረጴዛው ላይ የነበረውን ምግብ፥ የአገልጋዮቹን አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥራ እና አለባበሳቸውን፥ አስተናጋጆቹንና አለባበሳቸውንም፥ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥም መስዋዕት የሚያቀርብበትን ሁኔታ ባየች ጊዜ አንዳች መንፈስ አልቀረላትም፡፡5ንጉሡንም ፦ "ስለምትናገረው ነገርና ስለ ጥበብህ በገዛ አገሬ የሰማሁት ዘገባ እውነት ነው፤ 6እዚህ እስክመጣ ድረስ ግን የሰማሁትን አላመንኩም ነበር፤ አሁን ዓይኖቼ አይተውታል፡፡ ስለ ጥበብህና ሃብትህ ግማሹ እንኳን አልተነገረኝም ነበር! ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ፡፡" አለችው፡፡7"ጥበብህን ስለሚሰሙ ህዝብህ ምንኛ የተባረኩ፥ ዘወትር በፊትህ የሚቆሙ አገልጋዮችህም ምንኛ የተባረኩ ናቸው፡፡ 8ለአምላክህ እግዚአብሔር ንጉሥ ትሆን ዘንድ ባንተ ደስ የተሰኘ እና በዙፋን ላይ ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር ብሩክ ይሁን፡፡ አምላክህ እስራኤልን ለዘላለም ያፀናቸው ዘንድ ስለወደደ ፍትህንና ጽድቅን እንድታደርግላቸው በላያቸው ላይ አነገሠህ" አለችው፡፡9ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እና ከፍተኛ መጠን ያላቸው ቅመሞችንና የከበሩ ድንጋዮችን ሰጠችው፡፡ የሳባም ንግሥት ለንጉሡ ለሰለሞን ከሰጠችው ከእደነዚህ የሚበልጥ መጠን ያላቸው ቅመሞች እንደገና ተሰጥቶት አያውቅም፡፡10ከኦፊር ወርቅ ያመጡት የኪራም አገልጋዮችና የሰለሞን አገልጋዮች የሰንደል እንጨትና የከበሩ ድንጋዮችን አመጡ፡፡ 11ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለራሱ ቤት ደረጃዎችን እንዲሁም ለሙዚቀኞቹ በገናዎችንና መሰንቆዎችን/ክራሮችን አስደረገ፡፡ እንደዚህ ያለ እንጨት ከዚያ በፊት በይሁዳ ምድር ታይቶ አይታወቅም ነበር፡፡ 12የሳባም ንግሥት ወደ ንጉሡ ካመጣችው የበለጠ ንጉሥ ሰለሞን የተመኘችውን ሁሉ፥ የለመነችውንም ሁሉ ሰጣት፡፡ እርስዋም ተመልሳ ከአገልጋዮችዋ ጋር ወደ ራሷ ምድር ሄደች፡፡13በአንድ ዓመት ለሰለሞን የመጣለት ወርቅ ክብደት ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት መክሊት ወርቅ ነበር፡፡ 14ይህም ነጋድራሶችና ነጋዴዎች ካመጡት ወርቅ በተጨማሪ ነው፡፡ የዓረብም ነገሥታት ሁሉ እና የአገሪቱ ሹማምንት ለሰለሞን ወርቅና ብር ያመጡ ነበር፡፡15ንጉሡም ሰለሞን በጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ ትልልቅ ጋሻዎችን ሠራ፡፡ በእያንዳንዳቸውም ውስጥ ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ገብቶባቸው ነበር፡፡ 16ከጥፍጥፍ ወርቅም ሦስት መቶ ጋሻዎችን ሠራ፡፡ በእያንዳንዱም ጋሻ ውስጥ ሦስት ምናን ወርቅ ገብቶበት ነበር፡፡ ንጉሡም በሊባኖስ ዱር ቤተ መንግሥት ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡17ከዚያም ንጉሡ ከዝሆን ጥርስ ታላቅ ዙፋን አሠርቶ ከሁሉ በበለጠ ወርቅ አስለበጠው፡፡ 18ወደ ዙፋኑ የሚያደርሱ ስድስት ደረጃዎች ነበሩት፤ የዙፋኑም የላይኛው ክፍል ከጀርባው ክብ ነበር፡፡ በመቀመጫው በእያንዳንዱ ጎን በኩል የክንድ መደገፊያዎች እና ከመደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር፡፡19በስድስቱም ደረጃዎች በእያንዳንዱ ላይ በእያንዳንዱ ጎን በኩል አንድ አንበሳ አስራ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር፡፡ በሌላ በየትኛውም መንግሥት እንደ እርሱ ያለ ዙፋን አልነበረም፡፡ 20ንጉሥ ሰለሞን የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ የወርቅ ነበሩ፤ በሊባኖስ ዱር ቤተ መንግሥት ውስጥ የነበሩትም የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ ከንፁህ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡ በሰለሞን ዘመን ብር ዋጋ እንዳለው የማይቆጠር ስለነበር አንዳቸውም ብር አልነበሩም፡፡ 21ከኪራም መርከቦች ጋር በመሆን በባሕር ላይ የሚሄዱ ብዙ መርከቦች ነበሩት፡፡ በየሦስት ዓመቱም አንድ ጊዜ መርከቦቹ ወርቅ፥ ብር እና የዝሆን ጥርስ እንዲሁም ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ይዘው ይመጡ ነበር፡፡22በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን ከዓለም ነገሥታት ሁሉ በባለጠግነትና በጥበብ በለጠ፡፡ 23ምድር ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበቡን ይሰሙ ዘንድ የሰለሞንን መገኘት ይፈልጉ ነበር፡፡ 24ከዓመት ዓመት የሚጎበኙትም ግብር፥ የብርና የወርቅ ዕቃዎች፥ አልባሳት፥ የጦር መሣሪያዎች እና ቅመማ ቅመሞች እንዲሁም ፈረሶችና በቅሎዎችን ያመጡ ነበር፡፡25ሰለሞንም በሰረገሎች ከተሞችና ከራሱ ጋር በኢየሩሳሌም በተመደበላቸው ሥፍራ ለሚያኖራቸው ለፈረሶችና ለሰረገላዎች አራት ሺህ ጋጣዎች አስራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፡፡ 26ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጤም ምድርና እስከ ግብፅ ዳርቻ ድረስ ባሉ ነገሥታት ሁሉ ላይ ይገዛ ነበር፡፡27ንጉሡም በምድር ላይ እንዳለ ድንጋይ ያህል የበዛ ብር በኢየሩሳሌም ነበረው፡፡ የዝግባውንም እንጨት በቆላ እንዳሉት የሾላ ዛፎች የተትረፈረፈ እንዲሆን አደረገው፡፡ 28ለሰለሞንም ከግብፅና ከየአገሩ ሁሉ ፈረሶችን ያመጡለት ነበር፡፡29ሰለሞንን የሚመለከቱ ሌሎች ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራዕዩ በአዶ የተፃፉ አይደለምን? 30ሰለሞንም በኢየሩሳሌም በእስራኤል ሁሉ ላይ አርባ ዓመት ነገሠ፡፡ 31ከአባቶቹም ጋር አንቀላፋ፤ ሕዝቡም በአባቱ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ልጁም ሮብዓም በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
1እስራኤልም ሁሉ ሊያነግሡት ወደ ሴኬም እየመጡ ስለነበር ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ፡፡ 2የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህንን ሰማ (ከንጉሡ ከሰለሞን ፊት ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ነበር፤ ነገር ግን ኢዮርብዓም ከግብፅ ተመለሰ)3ልከውም አስጠሩት፤ ኢዮርብዓም እና እስራኤልም ሁሉ መጡ፤ ሮብዓምንም ተናገሩት፤ 4"አባትህ ቀንበራችንን ከባድ አድርጎት ነበር፤ ስለዚህ አሁን አንተ ጽኑውን የአባትህን ሥራ ቀሊል፥ በእኛ ላይ ያደረገውንም ከባድ ቀንበር የማያስቸግር አድርግልን፤ እኛም እንገዛልሃለን" አሉት፡፡ 5ሮብዓምም ፦ "ከሦስት ቀናት በኋላ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ኑ" አላቸው፤ ሕዝቡም ሄዱ፡፡6ንጉሥ ሮብዓም፦ "ለእነዚህ ሰዎች መልስ እንድሰጣቸው እንዴት ትመክሩኛላችሁ?" ብሎ አባቱ ሰለሞን በሕይወት እያለ በፊቱ ይቆሙ የነበሩትን ሽማግሌዎች አማከራቸው፡፡ 7እነርሱም ፦ "ለዚህ ሕዝብ መልካም ብታደርግላቸውና ብታስደስታቸው፥ በመልካም ቃል ብታናግራቸው ሁልጊዜ አገልጋዮችህ ይሆኑልሃል፤" ብለው ተናገሩት፡፡8ሮብዓም ግን ሽማግሌዎቹ የመከሩትን ምክር ችላ ብሎ ከእርሱ ጋር ያደጉትን በፊቱም የሚቆሙትን ወጣቶች አማከራቸው፡፡ 9"'አባትህ በእኛ ላይ ያደረገውን ቀንበር አቅልልልን' ላሉኝ ሰዎች መልስ እንድሰጣቸው ምን ምክር ትሰጡኛላችሁ?" አላቸው፡፡10ከሮብዓም ጋር ያደጉት ወጣቶች ተናገሩት፦ "'አባትህ ሰለሞን ቀንበራችንን አከበደብን፤ አንተ ግን ልታቀልልን ይገባል' ብለው ለነገሩህ ሰዎች፦ 'ትንሿ ጣቴ ክአባቴ ወገብ ትወፍራለች' ልትላቸው ይገባል፡፡ 11"በመሆኑም አሁን ምንም እንኳን አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ የነበረ ቢሆንም እኔ ቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ ነገር ግን እኔ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ" አላቸው፡፡12በመሆኑም ንጉሡ፦ "በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመልሳችሁ ኑ" ባላቸው መሠረት ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ፡፡ 13ንጉሡም በጽኑ ምላሽ መለሰላቸው፤ ንጉሡም ሮብዓም የሽማግሌዎችን ምክር ቸል አለ፡፡ 14የወጣቶቹን ምክር ተከትሎ ተናገራቸው፤ "ቀንበራችሁን ይበልጥ አከብድባችኋለሁ፤ እጨምርባችኋለሁ፡፡ አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ ነገር ግን እኔ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ" አላቸው፡፡15በመሆኑም ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም፤ እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአሒያ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብአም የተናገረውን ቃሉን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔር የተደረገ ክስተት ነበር፡፡16እስራኤል ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ሲያዩ ሕዝቡ ፦ "ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይም ልጅ ምንም ርስት የለንም! እስራኤል ሆይ እያንዳንዳችሁ ወደየድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፡፡ ዳዊት ሆይ የገዛ ራስህን ቤት ተመልከት" ብለው መለሱለት፡፡ በመሆኑም እስራኤል ሁሉ ወደየድንኳኖቻቸው ተመለሱ፡፡17በይሁዳ ከተሞች በሚኖሩት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ግን ሮብዓም ነገሠባቸው፡፡ 18ከዚያም ንጉሡ ሮብዓም አስገባሪውን አዶኒራምን ላከው፤ ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ንጉሥ ሮብዓም ፈጥኖ በሰረገላው ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ፡፡ 19በመሆኑም እስራኤል እስከ ዛሬ ድረስ በዳዊት ቤት ላይ አመጸ፡፡
1ሮብዓም ኢየሩሳሌም ሲደርስ ከእስራኤል ጋር ተዋግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም ለመመለስ ወታደሮች የሆኑ መቶ ሰማንያ ሺህ የተመረጡ ሰዎች ከይሁዳና ከቢንያም ቤት ሰበሰበ፡፡2ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሸማያ እንዲህ ሲል መጣ፤ 3"ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም በይሁዳና በቢንያምም ላሉት ለእስራኤል ሁሉ ተናገር፦ 4እግዚአብሔር ይህንን ይላል፦ "ወንድሞቻችሁን ማጥቃት ወይም መዋጋት አይገባችሁም፡፡ ይህ ነገር በእኔ እንዲሆን የተፈቀደ ስለሆነ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ መመለስ ይገባዋል፡፡" በመሆኑም የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ፤ በኢዮርብዓምም ላይ ለማጥቃት ከመውጣት ተመለሱ፡፡5ሮብዓም በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ በይሁዳም ለምሽግነት ከተሞችን ገነባ፡፡ 6ቤቴልሔምን፥ ኤጣምን፥ ቴቁሔን፥ 7ቤትጹርን፥ ሦኮን፥ ዓዶላምን፥ 8ጌትን፥ መሪሳን፥ ዚፍን፥ 9አዶራይምን፥ ለኪሶን፥ ዓዜቃን፥ 10ጾርዓን፥ ኤሎንን፥ ኬብሮንን ሠራ፡፡ እነዚህ በይሁዳና በብንያም ያሉት የተመሸጉት ከተሞች ናቸው፡፡11ምሽጎቹንም አጠናክሮ ምግቡንም፥ ዘይቱንም፥ እና ከወይን ጠጁም መጋዘኖች ጋር አለቆቹንም አኖረባቸው፡፡ 12በከተሞቹ ሁሉ ጋሻዎችና ጦሮችም አኖረባቸው፤ ከተሞቹንም እጅግ ጠንካራ አደረጋቸው፡፡ ይሁዳና ብንያምም የእርሱ ወገን ነበሩ፡፡13በመላው እስራኤል የነበሩት ካህናትና ሌዋውያን ከነበሩባቸው ድንበሮች ወደ እርሱ መጡ፡፡ 14ለእግዚአብሔር የክህነት ግዴታቸውን ከዚያ በኋላ መወጣት እንዳይችሉ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያንም ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣት መሠማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ነበር፡፡ 15ኢዮርብዓም ለመስገጃዎቹና ለሠራቸው የጥጆችና የፍየሎች ጣኦታት ለራሱ ካህናትን ሾመ፡፡16የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልባቸው የቆረጠ ሰዎች ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ተከትለዋቸው መጡ፤ ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ለመሰዋት ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ 17በመሆኑም ለሦስት ዓመታት በዳዊትና በሰለሞን መንገድ ስለሄዱ በሦስቱ ዓመታት ውስጥ የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፤ የሰለሞንንም ልጅ ሮብዓምን ጠንካራ አደረጉ፡፡18ሮብዓም የዳዊትን ልጅ የኢያሪሙትን እና የእሴይን ልጅ የኤልያብን ሴት ልጅ የአቢካኢልን ሴት ልጅ መሐላትን ለራሱ ሚስት አድርጎ ወሰደ፤ 19እርስዋም ወንዶች ልጆችን የዑስን፥ ሰማራያን፥ እና ዘሃምን ወለደችለት፡፡20ከመሐላት በኋላ ሮብዓም የአቤሴሎምን ሴት ልጅ መዓካን ወሰደ፤ እርስዋም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛን እና ሰሎሚትን ወለደችለት፡፡ 21ሮብዓምም ከሌሎቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ሴት ልጅ መዓካን ወደደ፤ (አስራ ስምንት ሚስቶችና ስልሳ ቁባቶች ወስዶ የሃያ ስምንት ወንዶች ልጆችና የስልሳ ሴቶች የልጅ ልጆች አባት ሆኖ ነበር፡፡)22ሮብዓምም ንጉሥ ሊያደርገው ስላሰበ የመዓካን ልጅ አብያን በወንድሞቹ መካከል መሪ እንዲሆን አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ 23ሮብዓም በጥበብ ያስተዳድር ነበር፤ ልጆቹንም ሁሉ ወደ ይሁዳና ቢንያም ምድር ሁሉ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ በተናቸው፡፡ የተትረፈረፈም ምግብ ሰጣቸው፤ ብዙ ሚስቶችንም ፈለገላቸው፡፡
1እንዲህም ሆነ፤ የሮብዓም መንግሥት በጸናች ጊዜና እርሱም በበረታበት በዚያን ጊዜ እርሱና እስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ፡፡2ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ታማኞች ባለመሆናቸው ንጉሥ ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ሊያጠቃ መጣባት፡፡ 3ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰረገሎችና ከስልሳ ሺህ ፈረሰኞች ጋር መጠባት፡፡ ከእርሱም ጋር ሊቆጠሩ የማይችሉ ወታደሮች ሊቢያውያን፥ ሱካውያን እና ኢትዮጵያውያን መጡ፡፡ 4የይሁዳ ይዞታ የነበሩትን የተመሸጉ ከተሞች ወሰደና ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡5ይሄኔ ነቢዩ ሸማያ ወደ ሮብዓምና ከሺሻቅ የተነሳ ወደ ኢየሩሳሌም በአንድነት ወደተሰበሰቡት መሪዎች መጣ፡፡ ሸማያ እንዲህ አላቸው፦ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ትታችሁኛል፤ ስለዚህ እኔ ደግሞ ለሺሻቅ እጅ አሳልፌ ሰጠኋችሁ፡፡" 6በዚያን ጊዜ የእስራኤል መሳፍንትና ንጉሡ ራሳቸውን አዋረዱ፤ "እግዚአብሔር ጻድቅ ነው" አሉ፡፡7እግዚአብሔርም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሽማያ መጣ፦ "ሰውነታቸውን አዋርደዋል፡፡ አላጠፋቸውም፤ በተወሰነ ደረጃ አድናቸዋለሁ፡፡ ቁጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም፡፡ 8ነገር ግን እኔን ማገልገል እና የሌሎች አገራትን ገዢዎች ማገልገል ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲገባቸው አገልጋዮቹ ይሆናሉ" አለ፡፡9ስለሆነም የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ሊያጠቃ መጥቶ የእግዚአብሔርን ቤት የከበሩ መዝገቦችና የንጉሡን ቤት የከበሩ መዝገቦች ወሰደ፡፡ ሁሉንም ነገር ወሰደ፤ ሰለሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻዎችም ጭምር ወሰደ፡፡ 10ንጉሥ ሮብዓም በእነርሱ ምትክ የናስ ጋሻዎች ሠርቶ የንጉሡን ቤት በሮች በሚጠብቁት ዘበኞች አለቃዎች እጅ አስቀመጣቸው፡፡11ከዚያ በኋላ ንጉሡ ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባ ቁጥር ዘበኞቹ ይሸከሙአቸው ነበር፤ ከዚያም ወደ ዘበኞቹ ቤት ይመልሷቸው ነበር፡፡ 12ሮብዓም ሰውነቱን ባዋረደ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዳያጠፋው የእግዚአብሔር ቁጣ ከእርሱ ተመለሰ፤ ደግሞም በይሁዳ የተወሰነ መልካምነት ገና ይገኝ ነበር፡፡13ንጉሡም ሮብዓም ንግሥናውን በኢየሩሳሌም አጠናከረ፤ በዚህ ሁኔታም ገዛ፡፡ ሮብዓም መንገሥ ሲጀምር አርባ አንድ ዓመቱ ነበር፤ እግዚአብሔር ስሙን ያኖርባት ዘንድ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በመረጣት በኢየሩሳሌም ከተማ አስራ ሰባት ዓመታት ነገሠ፡፡ የአሞናዊቷ እናቱም ስም ናዕማ ነበር፡፡ 14እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልቡን አላዘጋጀም ነበርና ክፉውን ነገር አደረገ፡፡15ሮብዓምን የሚመለከቱ ሌሎች ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው የትውልዶች ስም ዝርዝርና በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የነበሩት ያልተቋረጡ ጦርነቶች በተመዘገቡበት በነቢዩ ሸማያና በባለ ራዕዩ በአዶ ጽሑፎች ውስጥ የተጻፉ አይደለምን? 16ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አብያ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
1ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያ በይሁዳ ላይ መንገሥ ጀመረ፡፡ 2በኢየሩሳሌም ለሦስት ዓመታት ገዛ፤ የገብዓው ሰው የኡርኤል ልጅ የነበረችው የእናቱ ስም ሚካያ ነበር፡፡ በአብያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበረ፡፡ 3አብያም ከአራት መቶ ሺህ የተመረጡ ጠንካራ፥ ደፋር ሰዎች ሠራዊት ጋር ወደ ጦርነት ሄደ፡፡ ኢዮርብዓምም ከተመረጡት ስምንት መቶ ሺህ የተመረጡ ጠንካራ፥ ደፋር ወታደሮች ጋር ሊጋጠመው ተሰለፈ፡፡4አብያም በተራራማው በኤፍሬም አገር ባለው በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ፦ "ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ስሙኝ! 5የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መንግሥት ለዳዊት ለዘላለም ለልጆቹ በደንብ በተጠበቀ ቃል ኪዳን እንዲገዙ እንደሰጠ አታውቁምን?" አለ፡፡6የዳዊት ልጅ የሰለሞን ባሪያ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ግን ተነሳና በጌታው ላይ ዐመፀ፡፡ 7የማይረቡ ሰዎችም ጸያፍ ሰዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፡፡ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም ወጣትና ልምድ የለሽ በነበረበትና ሊቋቋማቸው በማይችልበት ጊዜ በሮብዓም ላይ ተነሱበት፡፡8አሁንም በዳዊት ዝርያዎች እጅ ውስጥ የሆነውን የእግዚአብሔር አገዛዝ ኃይል ልትቋቋሙ እንደምትችሉ ትናገራላችሁ፡፡ እናንተም ታላቅ ሠራዊት ናችሁ፤ ኢዮርብዓም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ ጥጃዎች ከእናንተ ጋር አሉ፡፡ 9የአሮንን ትውልዶች የእግዚአብሔርን ካህናትና ሌዋውያን አላባረራችሁምን? እንደ ሌሎች ምድር ሕዝቦች ልማድ ለራሳችሁ ካህናት አላደረጋችሁምን? ከአንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ጋር ራሱን ሊቀድስ የሚመጣው ሁሉ አማልክት ላልሆኑ ነገሮች ካህን ይሆናል፡፡10ለእኛ ግን እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ እኛም አልተውነውም፡፡ የአሮን ዝርያዎች የሆኑት እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናትና በሥራቸው ላይ የተሰማሩ ሌዋውያን አሉን፡፡ 11በየማለዳውና በየምሽቱ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያቃጥላሉ፤ የመገኘቱንም ሕብስት በንጹህ ገበታ ላይ ያዘጋጃሉ፤ በየምሽቱ እንዲያበሩ የወርቁን መቅረዝ ከቀንዲሎቹ ጋር ይንከባከባሉ/ይጠብቃሉ፡፡ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል፡፡12እነሆ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ አለቃችን ነው፤ በእናንተ ላይ መለከቶቹን ለመንፋት የእርሱ ካህናትም እዚህ ይገኛሉ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ ስለማይሳካላችሁ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አትዋጉ፡፡13ኢዮርብዓም ግን ክጀርባቸው ድብቅ ጦር አዘጋጅቶ ነበር፤ የእርሱ ሠራዊት ከይሁዳ ፊት ለፊት ሆኖ ድብቁ ጦር ግን ክጀርባቸው ነበር፡፡ 14ይሁዳ ከወደ ኋላ ሲመለከቱ እነሆ ውጊያው ከፊታቸውና ከኋላቸውም ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከቶቹን ነፉ፡፡ 15የይሁዳም ሰዎች ጮኹ፤ በጮኹም ጊዜ እግዚአብሔር ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በአብያና በይሁዳ ፊት መታቸው፡፡16የእስራኤል ሕዝብ ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በይሁዳ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ 17አብያና ሠራዊቱ በታላቅ አገዳደል ገደሏቸው፤ አምስት መቶ ሺህ የተመረጡ የእስራኤል ሰዎች ተገድለው ወደቁ፡፡ 18በዚህ መንገድ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ተሸነፉ፤ የይሁዳ ሕዝብ በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ስለነበር አሸነፉ፡፡19አብያ ኢዮርብዓምን አሳደደ፤ ከእርሱም ከተሞችን ወሰደ፤ ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ እንዲሁም ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ፤ 20ኢዮርብዓምም በአብያ ዘመን እንደገና ኃይሉ ከቶም አላገገመም፡፡ እግዚአብሔርም ቀሰፈው፤ እርሱም ሞተ፡፡ 21አብያ ግን በረታ፤ ለራሱ አስራ አራት ሚስቶችን ወሰደ፤ ሃያ ሁለት ወንዶች ልጆችንና አስራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡ 22የተቀሩት የአቢያ ድርጊቶችና ባሕርዩ የተናገራቸው ነገሮችም በነቢዩ አዶ ትርጓሜ/አንድምታ ተጽፈዋል፡፡
1አብያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡ ልጁም አሳ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡ በእርሱም ዘመን በምድሪቱ ላይ ለአሥር ዓመታት ፀጥታ ነበር፡፡ 2አሳ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤ 3የእንግዶቹን አማልክት መሠዊያ እና መስገጃዎቹን አስወገደ፤ የተቀደሱትን የድንጋይ ሐውልቶች ሰባበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቆራረጠ፡፡ 4የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ይሹ ዘንድ እና ሕጉንና ትዕዛዛቱን ይፈጽሙ ዘንድ ይሁዳን አዘዘ፡፡5ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ መስገጃዎቹንና ዕጣን የሚጨስባቸውን መሠዊያዎች አስወገደ፡፡ መንግሥቱም በእርሱ ሥር በሰላም ተቀመጠች፡፡ 6በምድሪቱ ላይ ጸጥታ ስለነበርና እግዚአብሔርም ሰላም ስለሰጠው በእነዚያ ዓመታት ምንም ጦርነት ስላልነበረበት በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ፡፡7አሳም ይሁዳን፡-"እነዚህን ከተሞች እንገንባ፤ በዙሪያቸው ቅጥር ፥ ማማዎች፥ መዝጊያዎች፥ እና መወርወሪያዎች እንሥራ፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ስለፈለግነው ምድሪቱ እስከ አሁንም የእኛ ናት፡፡ እኛም ፈልገነዋል እርሱም በሁሉም በኩል እረፍት ሰጥቶናል፡፡" አላቸው፡፡ እነርሱም ገነቡ፤ ተሰካላቸውም፡፡ 8ለአሳም ጋሻና ጦር የሚይዙ ከይሁዳ ሦስት መቶ ሺህ ሰዎች፥ ጋሻ የሚይዙና ቀስት የሚስቡ ደግሞ ከቢኒያም ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች የያዘ ሠራዊት ነበረው፡፡9ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚሊዮን ወታደሮችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ያሉት ሠራዊት ይዞ ሊያጠቃቸው መጣባቸው፤ ወደ መሪሳም መጣ፡፡ 10አሳም ሊጋጠመው ወጣ፤ በመሪሳም በጽፋታ ሸለቆ ውስጥ በጦርነቱ ግንባር ተሰለፉ፡፡ 11አሳም ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ፦ "እግዚአብሔር ሆይ ምንም ጉልበት የሌለው ሰው ብዙዎችን በሚጋፈጥበት ጊዜ ካንተ በቀር ማንም የሚረዳው የለም፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በአንተ ላይ ተማምነናልና እርዳን፤ ይህንን የመጣብንን ብዙ ቁጥር ያለው ሠራዊት በስምህ እንመጣባቸዋለን፡፡ እግዚአብሔር ሆይ አንተ አምላካችን ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ" ብሎ ጮኸ፡፡12እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ፡፡ 13አሳና ወታደሮቹም እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ሙሉ በሙሉ ስለተደመሰሱ ማገገም እስከማይችሉ ድረስ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደቁ፡፡ሠራዊቱም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ፡፡14የእግዚአብሔር ድንጋጤ በነዋሪዎቹ ላይ ስለመጣባቸው ሠራዊቱ በጌራራ ዙሪያ ያሉ መንደሮችን ሁሉ ደመሰሱ፡፡ በውስጣቸውም እጅግ ብዙ ምርኮ ስለነበር ሠራዊቱ መንደሮቹን ሁሉ በዘበዙ፡፡ 15የከብት አርቢ ዘላኖቹን የድንኳን ሰፈራዎችም ደመሰሱ፤ ከመጠን በላይ በጎችን እንዲሁም ግመሎችን ወስደው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
1የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በዓዛርያስ ላይ መጣ፡፡ 2አሳንም ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፦ "አሳ፥ ይሁዳ ሁሉና ቢኒያም ሆይ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፡፡ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፡፡3እስራኤል ለረጅም ጊዜ ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪ ካህን እና ያለ ሕግ ይኖሩ ነበር፡፡ 4በጭንቃቸው ጊዜ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ሲፈልጉት ይገኝላቸው ነበር፡፡ 5በዚያን ዘመን ርቆ ለሚሄደውና ወደዚህ ቅርብ ለሚመጣው ሰላም አልነበረም፤ ይልቁንም በምድሪቱ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ታላቅ ጭንቅ ነበር፡፡6እግዚአብሔር በሁሉም ዓይነት መከራዎች ያስጨንቃቸው ስለነበር ፍርስርሳቸው ወጥቶ ነበር፤ ህዝብ ከህዝብ ጋር፥ ከተማም ከከተማ ጋር ይዋጋ ነበር፡፡ 7እናንተ ግን ሥራችሁ ብድራት ስለአለው በርቱ እጃችሁም እንዲደክም አትፍቀዱ፡፡"8ይህንን ቃል፥ የነቢዩን የዖዴድን ትንቢት በሰማ ጊዜ ብርታት አግኝቶ ከይሁዳና ከቢኒያም ምድር ሁሉ፥ ከተራራማው የኤፍሬም አገር ከያዛቸው ከተሞች ጸያፉን ነገር አስወገደ፤ በእግዚአብሔርም ቤት መተላለፊያ ፊት ለፊት የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ እንደገና ሠራ፡፡ 9ይሁዳንና ቢኒያምን ሁሉ ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴም ከስምዖንም ወገን የሆኑትን ከእርሱም ጋር የዘለቁትን ሰበሰበ፡፡ እግዚአብሔር አምላኩ ከእርሱ ጋር እንደነበር ሲያዩ ከእስራኤል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ እርሱ መጡ፡፡10በመሆኑም አሳ በነገሠ በአስራ አምስተኛው ዓመት በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ 11በዚያም ቀን ካመጡት ምርኮ የተወሰነውን ሰባት መቶ በሬዎችና ሰባት ሺህ በጎችና ፍየሎች ለእግዚአብሔር ሠዉ፡፡12የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ሊፈልጉት ቃል ኪዳን አደረጉ፡፡ 13የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ማንም ቢኖር ሰውየው ታናሽ ይሁን ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ሊገደል እንደሚገባው ተስማሙ፡፡14በታላቅ ድምጽና በጩኸት፥ በእምቢልታና በቀንደ መለከት ለእግዚአብሔር ማሉ፡፡ 15በሙሉ ልባቸው መሐላውን ስለፈጸሙ፥ እግዚአብሔርንም በሙሉ ፍላጎታቸው ስለፈለጉት እርሱም ተገኝቶላቸው ስለነበር ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፡፡ እግዚአብሔር በዙሪያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፡፡16ንጉሡም አሳ ሴት አያቱ መዓካ ከማምለኪያ አጸድ አስጸያፊ ምስል/ጣኦት ስላበጀች ከንግሥትነትዋ አስወገዳት፡፡ አሳም አስጸያፊ ምስሏን/ጣኦቷን ቆርጦ አቧራ አድርጎ ፈጨው፤ በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው፡፡ 17መስገጃዎቹ ግን ከእስራኤል አልራቁም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፍጹም ታማኝና ታዛዥ ነበር፡፡18የእግዚአብሔር የሆኑትን የአባቱን ነገሮችና የገዛ ራሱን ነገሮች፥ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ወደ እግዚአብሔር ቤት ውስጥ አስገባቸው፡፡ 19አሳም እስከነገሠበት እስከ ሠላሳ አምስተኛው ዓመት ድረስ ከዚያ ወዲያ ጦርነት አልነበረም፡፡
1አሳ በነገሠ በሠላሳ ስድስተኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ የጠብ ጫሪነት ድርጊት ፈጸመ፡፡ ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ አሳ ምድር ማንም መውጣትና መግባት እንዳይፈቀድለት ራማን ዙሪያዋን ሠራ፡፡2አሳም ከእግዚአብሔር ቤት እና ከንጉሡ ቤት መጋዘኖች ብርና ወርቅ አውጥቶ በደማስቆ ይኖር ወደ ነበረው ወደ አራም ንጉሥ ወደ ቤንሃዳድ ላከው፡፡ 3"በአባትህና በአባቴ መካከል እንደነበረው በእኔና በአንተ መካከል የሰላም ስምምነት ይኑር፡፡ እነሆ ብርና ወርቅ ሰድጄልሃለሁ፤ ከእኔ ርቆ እንዲተወኝ ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያደረግኸውን የሰላም ስምምነት አፍርስ" አለው፡፡4ቤንሃዳድም ንጉሡን አሳን ሰማው፤ የእስራኤልን ከተሞች እንዲያጠቁም የሠራዊቱን አለቆች ላከ፡፡ እነርሱም ኦዮንን፥ ዳንን፥ አቤልማይምንና የንፍታሌምን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ መቱ፡፡ 5ባኦስም ይህንን ሲሰማ የራማን ዙሪያዋን መሥራቱን አቆመ፤ ሥራውንም አቋረጠ፡፡ 6በዚያን ጊዜ ንጉሡ አሳ ይሁዳን ሁሉ ሰበሰበ፤ ባኦስ ከተማይቱን ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋዮችና ጣውላዎች ወሰዱ፡፡ ከዚያም ንጉሡ አሳ ያንን የግንባታ ዕቃ ጌባንና ምጽጳን ለመሥራት ተጠቀመበት፡፡7በዚያን ጊዜ ባለ ራዕዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ ሄዶ፦ "በአራም ንጉሥ ስለታመንህና በአምላክህ በእግዚአብሔር ስላልታመንህ የአራም ንጉሥ ሠራዊት ከእጅህ አምልጦአል፡፡ 8እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሯቸው ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ታላቅ ሠራዊት አልነበሩምን? ነገር ግን በእግዚአብሔር ስለታመንህ በእነርሱ ላይ ድልን ሰጠህ፡፡9ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የተሰጠ የሆነውን ሰው በኃይሉ ያበረታ ዘንድ የእግዚአብሔር ዓይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይዘዋወራሉ፡፡ ነገር ግን አንተ በዚህ ጉዳይ ስንፍና አድርገሃል፡፡ ከአሁን ጊዜ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል" አለው፡፡ 10በዚያን ጊዜ ንጉሡ አሳ በባለ ራዕዩ ላይ ተቆጣ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ተቆጥቶ ስለነበር እስር ቤት ውስጥ አኖረው፡፡ በዚያው ጊዜ አሳ ከሕዝቡ የተወሰኑትን አስጨነቀ፡፡11እነሆ የአሳ ድርጊቶች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል፡፡ 12አሳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠኝ ዓመቱ እግሩን ታመመ፤ ሕመሙም እጅግ ጽኑ ነበር፡፡ እንዲህም ሆኖ ከባለ መድኃኒቶች ብቻ እንጂ ከእግዚአብሔር እርዳታ አልፈለገም፡፡13አሳ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በነገሠም በአርባ አንደኛው ዓመት ሞተ፡፡ 14በዳዊት ከተማ ለእርሱ ለራሱ በቆፈረው በራሱ መቃብር ቀበሩት፡፡ በተካኑ ቀማሚዎች በተሰናዳ ልዩ ልዩ የቅመም ዓይነቶች በጣፋጭ መዓዛ በተሞላ ቃሬዛ ላይ አኖሩት፡፡ ለክብሩም እጅግም ታላቅ የሆነ እሳት ለኮሱለት፡፡
1ልጁ ኢዮሳፍጥ በእርሱ ቦታ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ራሱን አጠነከረ፡፡ 2በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አስቀመጠ፤ በይሁዳም ምድር እና አባቱ አሳ በያዛቸው የኤፍሬም ከተሞች ውስጥ የጦር ሠፈር አደራጀ፡፡3በአባቱ በዳዊት በፊተኛይቱ መንገድ ስለሄደና በአሊምንም ስላልፈለገ እግዚአብሔር ከኢዮሣፍጥ ጋር ነበረ፡፡ 4በዚያ ፈንታ በአባቱ አምላክ ላይ ተደገፈ፤ እንደ እስራኤል ባህርይ ሳይሆን በአምላኩ ትዕዛዛት መሠረት ሄደ፡፡5በመሆኑም እግዚአብሔር መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ ይሁዳ ሁሉ ለኢዮሣፍጥ ግብር ያመጡለት ነበር፡፡ የተትረፈረፈ ባለጠግነትና ክብርም ነበረው፡፡ 6ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ የጸና ነበረ፡፡ መስገጃዎቹንና የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ከይሁዳ አስወገደ፡፡7በነገሠም በሦስተኛው ዓመት ያስተምሩ ዘንድ ባለሥልጣናቱን ቤንኃይልን፥ አብድያስን፥ ዘካርያስን፥ ናትናኤልንና ሚኪያስን ወደ ይሁዳ ከተሞች ላካቸው፡፡ 8ከእነርሱም ጋር ሌዋውያኑ ሸማያ፥ነታንያ፥ ዝባድያ፥ አሣኤል፥ ሰሚራሞት፥ዮናትን፥ አዶንያስ፥ ጦብያ እና ጠባዶንያ ነበሩ፡፡ ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ኤሊሳማና ኢዮራም ነበሩ፡፡ 9እነርሱም የእግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ ከእነርሱ ጋር ስለነበር በይሁዳ አስተማሩ፡፡በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ተዘዋውረው በሕዝቡ መካከል አስተማሩ፡፡10በይሁዳ ዙሪያ በነበሩት አገራት ነገሥታት ላይ የእግዚአብሔር ድንጋጤ ስለወደቀባቸው ከኢዮሣፍጥ ጋር ምንም ጦርነት አላደረጉም፡፡ 11የተወሰኑት ፍልስጤማውያን ለኢዮሳፍጥ ስጦታዎችና ብር እንደ ግብር ያመጡለት ነበር፡፡ አረቦችም ሰባት ሺህ ሰባት መቶ የአውራ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ የፍየሎች መንጋዎችን አመጡለት፡፡12ኢዮሣፍጥም እጅግ ብርቱ ሆነ፤ በይሁዳም ትልልቅ ምሽጎችንና የመጋዘን ከተሞችን ሠራ፡፡ 13በይሁዳም ከተሞች በርካታ አቅርቦት እና በኢየሩሳሌምም ጠንካራና ደፋር ሰዎች - ወታደሮች ነበሩት፡፡14በአባቶቻቸው ቤቶች ስም ቅደም ተከተል ዝርዝራቸው ይህ ነው፤ ከይሁዳ የሺዎች አዣዦች፥ አዣዡ ዓድና ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ተዋጊ ሰዎች፤ 15ከእርሱም ቀጥሎ አለቃው ይሆሐናን፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ 16ከእርሱም ቀጥሎ ራሱን በፈቃዱ እግዚአብሔርን ለማገልገል ያቀረበ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ተዋጊ ሰዎች ነበሩ፤17ከቢኒያም ኃይለኛ ደፋር ሰው የነበረው ኤሊዳሄ ከእርሱም ጋር ቀስትና ጋሻ የሚይዙ ሁለት መቶ ሺህ ተዋጊ ሰዎች ነበሩ፤ 18ከእርሱም ቀጥሎ ዮዛባት ከእርሱም ጋር ለጦርነት የተዘጋጁ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ 19ንጉሡ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካስቀመጣቸው በተጨማሪ እነዚህ ንጉሡን የሚያገለግሉ ነበሩ፡፡
1ኢዮሣፍጥ ታላቅ ባለጠግነትና ክብር ነበረው፡፡ ከቤተሰቦቹ አንዱ ሴት ልጁን እንዲያገባ በማድረግ ከአክዓብ ጋር ራሱን አዛመደ፡፡ 2ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ፡፡ አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ በርካታ በጎችንና በሬዎችን አረደላቸው፡፡ ከእርሱም ጋር ሬማት ዘገለአድን ለማጥቃት ይሄድ ዘንድም አክዓብ አሳመነው፡፡ 3የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ፦ "ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገለአድ ትሄዳለህን?" አለው፡፡ ኢዮሣፍጥም ፦"እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ናቸው፤ በጦርነቱ ውስጥ ካንተ ጋር አብረን እንሆናለን" ብሎ መለሰለት፡፡4ኢዮሣፍጥም የእስራኤልን ንጉሥ ፦ "እባክህን ለመልስህ በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ቃል ጠይቅ" አለው፡፡ 5ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ ነቢያቱን አራት መቶ ሰዎች በአንድነት ሰብስቦ፦ "ወደ ሬማት ዘገለአድ ለጦርነት መሄድ ይገባናል ወይስ መሄድ አይገባኝም?" አላቸው፡፡ እነርሱም ፦" እግዚአብሔር ለንጉሡ ድል ይሰጠዋልና አጥቃት!" አሉት፡፡6ኢዮሣፍጥ ግን፦ "ምክር የምንጠይቀው አሁንም ሌላ የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ ሰው በእዚህ የለምን?" አለ፡፡ 7የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ፦" የእግዚአብሔርን ምክር የምንጠይቅበት አሁንም አንድ ሰው የይምላ ልጅ ሚክያስ አለ፤ ነገር ግን ችግር ብቻ እንጂ ስለእኔ ምንም ነገር መልካም ትንቢት ከቶም ተናግሮልኝ ስለማያውቅ እጠላዋለሁ" አለው፡፡ኢዮሣፍጥ ግን ፦ "ንጉሥ እንደዚያ አይበል" አለ፡፡ 8ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ አንድ ሹም ጠርቶ ፦"የይምላን ልጅ ሚክያስን በፍጥነት አምጣው" ሲል አዘዘው፡፡9የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የአስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥ መጎናጸፊያቸውን እንደለበሱ እያንዳንዳቸው በዙፋን ላይ በሰማርያ በር መግቢያ በግልጽ ሥፍራ ላይ ተቀምጠው ነቢያቱም ሁሉ በፊታቸው ትንቢት እየተናገሩ ነበር፡፡ 10የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስም ለራሱ የብረት ቀንዶች ሠርቶ፦ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'በእነዚህ ቀንዶች አርመናውያን እስኪያልቁ ድረስ ትወጋቸዋለህ'" አለ፡፡ 11ነቢያቱም ሁሉ፦" እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ስለሚሰጣት ሬማት ዘገለዓድን አጥቃና አሸንፍ" እያሉ ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡12ሚክያስን ሊጠራ የሄደው መልዕክተኛ ፦" እነሆ የነቢያቱ ቃላት በአንድ አፍ ለንጉሡ መልካም ነገሮች ያውጃሉ፡፡ እባክህን ያንተም ቃል ከእነርሱ የአንዱን ቃል ዓይነት ይሁንና መልካም ነገሮች ተናገር" ሲል ተናገረው፡፡ 13ሚክያስም፦"ሕያው እግዚአብሔርን የምናገረው አምላኬ እርሱ የሚለውን ነው" ብሎ መለሰ፡፡ 14ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦" ሚክያስ ሆይ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለጦርነት መሄድ ይገባናል ወይስ መቅረት?"አለው፡፡ ሚክያስም፦" አጥቃና አሸንፍ! ታላቅ ድል ይሆንልሃልና!" ብሎ መለሰለት፡፡15ከዚያም ንጉሡ ፦" በእግዚአብሔር ስም ከእውነቱ በቀር ሌላ ምንም ነገር እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ እንድትምል ላደርግህ ይገባኛል?" አለው፡፡ 16ሚክያስም፦" እስራኤል ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበትነው አየኋቸው፤ እግዚአብሔርም፦ 'እነዚህ እረኛ የላቸውም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በሰላም ወደ ቤቱ ይመለስ' አለ" ብሎ ተናገረ፡፡17በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ለኢዮሳፍጥ ፦" እኔን በተመለከተ ጥፋት ብቻ እንጂ መልካም ትንቢት እንደማይናገርልኝ አልነገርኩምን?" አለው፡፡ 18ከዚያም ሚክያስ፦" እንግዲህ ሁላችሁም የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ይገባችኋል፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ የሰማይም ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው እንደነበር አየሁ፡፡19እግዚአብሔርም ፦" የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ወደ ሬማት ዘገለዓድ እንዲወጣና እንዲወድቅ የሚያታልለው ማነው?" አለ፡፡ አንዱ በእዚህ መንገድ ብሎ ሲመልስ ሌላውም በዚያ መንገድ ብሎ መለሰ፡፡20ከዚያም አንድ መንፈስ መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ፦" እኔ አታልለዋለሁ" አለ፡፡ እግዚአብሔርም ፦"እንዴት?" አለው፡፡ 21መንፈሱም፡-" ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ" አለ፡፡ እግዚአብሔርም፦" ታታልለዋለህ፤ ይሳካልሃልም፤ አሁንም ሂድና እንደዚሁ አድርግ" ብሎ መለሰ፡፡22አሁንም እነሆ እግዚአብሔር በእነዚህ ነቢያትህ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አስቀምጧል፤ እግዚአብሔርም ጥፋት እንዲመጣብህ ተናግሯል፡፡23የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስም ቀረብ ብሎ ሚክያስን በጥፊ መታውና ፦"የእግዚአብሔር መንፈስ ለአንተ ሊናገር በየትኛው መንገድ ከእኔ ሄደ?" አለው፡፡ 24ሚክያስም፦" እነሆ በዚያ ቀን ልትሸሸግ ወደ አንድ የውስጥ ክፍል ስትሸሽ ታውቀዋለህ" አለው፡፡25የእስራኤል ንጉሥም ለአገልጋዮቹ ፦" እናንተ ሰዎች ሚክያስን ያዙና ወደ ከተማይቱ አስተዳዳሪ ወደ አሞንና ወደ ልጄ ወደ ኢዮአስ ውሰዱት፤" 26ንጉሡ፦' በደህና እስከምመለስ ድረስ ይህንን ሰው እስር ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ጥቂት ምግብ ብቻ እና ጥቂት ውሃ ብቻ መግቡት' ይላል በሉት" አላቸው፡፡ 27ሚክያስም፦" አንተ በደህና ከተመለስህ በእኔ የተናገረው እግዚአብሔር አይደለም" አለ፡፡ ጨምሮም፦"እናንተ ሕዝብ ሁሉ ይህንን ስሙ" አለ፡፡28በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ሬማት ዘገለዓድን ሊዋጉ ወጡ፡፡ 29የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን፡-"እኔ እንዳልታወቅ አለባበሴን ለውጬ ወደ ጦርነቱ እገባለሁ፤ አንተ ግን ንጉሣዊ መጎናፊያህን ልበስ" አለው፡፡ በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ በአለባበሱ እንዳይታወቅ ራሱን ለውጦ ወደ ጦርነቱ ሄዱ፡፡ 30የአራምም ንጉሥ የሰረገሎቹን አዛዦች፦ "ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ ወታደሮችን እንዳታጠቁ፤ ይልቁንም የእስራኤል ንጉሥን ብቻ አጥቁ" በማለት አዝዟቸው ነበር፡፡31የሰረገሎቹ አለቆች ኢዮሳፍጥን ባዩ ጊዜ፦"የእስራኤል ንጉሥ ያ ነው ፤" አሉ፡፡ ሊያጠቁትም ወደ እርሱ ዞሩበት፤ ነገር ግን ኢዮሳፍጥ ሲጮህ እግዚአብሔር ረዳው፡፡ እግዚአብሔርም ከእርሱ ዞር አደረጋቸው፡፡ 32የሰረገሎቹም አለቆች የእስራኤል ንጉሥ እንዳልነበረ ባዩ ጊዜ እርሱን ከመከታተል ተመለሱ፡፡33አንድ ሰው ግን በዘፈቀደ ቀስቱን ሲስበው የእስራኤል ንጉሥን በጥሩር መገጣጠሚያዎቹ መካከል ወጋው፡፡ ያን ጊዜ አክዓብ የሰረገላውን ነጂ፦" ክፉኛ ተወግቻለሁና አቅጣጫህን ቀይርና ከጦርነቱ ውስጥ አውጣኝ፡፡ 34በዚያን ጊዜ ጦርነቱ እጅግ የከፋ ሆነ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አርመናውያንን እየተመለከተ እስኪመሽ ድረስ ሰረገላውን እንደተደገፈ ነበር፡፡ ፀሐይ በምታዘቀዝቅበት ጊዜ አካባቢ ሞተ፡፡
1የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥም ወደ ቤቱ ወደ ኢየሩሳሌም በደህና ተመለሰ፡፡ 2ያኔ የባለ ራዕዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሳፍጥን፦"ክፉውን ልትረዳ ይገባሃልን? እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ልትወድ ይገባሃልን? ለዚህ ድርጊትህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል፡፡ 3ነገር ግን የማምለኪያ አፀዶቹን ከምድሪቱ ላይ አስወግደሃልና እግዚአብሔርን ለመፈለግ ቆርጠህ ልብህን አዘጋጅተሃልና በአንተ ዘንድ መልካምነት ተገኝቶብሃል" አለው፡፡4ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ ከቤርሳቤህ እስከ ተራራማው የኤፍሬም አገር ድረስ እንደገና በሕዝቡ መካከል ወጥቶ ወደ አባቶቻቸው አምላክ መለሳቸው፡፡ 5በምድሪቱ ላይ በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ፈራጆችን አስቀመጠ፡፡6ፈራጆቹንም፦"የምትፈርዱት ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው ስላልሆነ ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ አጢኑ፤ በፍርድ ነገር እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ 7አሁንም የእግዚአብሔር ፍርሃት በእናንተ ላይ ይሁን፡፡ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ምንም በደል የለምና፤ ለሰው ፊት ማድላት ወይም መማለጃ መውሰድ የለምና በምትፈርዱበት ጊዜ ተጠንቀቁ" አላቸው፡፡8በተጨማሪም ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም ከሌዋውያኑንና ከካህናቱ የተወሰኑትንና ከእስራኤል የአባቶች ቤቶች መሪዎች የተወሰኑትን የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዲያስፈጽሙና ጠቦችን እንዲፈቱ ሾማቸው፡፡ እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ 9"እግዚአብሔርን በመፍራት፥ በታማኝነትና በፍጹም ልብ የምታደርጉት ይህ ነው፤10በደም መፍሰስ ጉዳይ ቢሆን፥ በሕግና በትእዛዝ፥ በሥርዓት ወይም በድንጋጌ ጉዳዮች ቢሆን በከተሞቻቸው ከተቀመጡት ከወንድሞቻችሁ ምንም ኣይነት ጠብ ወደ እናንተ ቢመጣ እግዚአብሔርን እንዳይበድሉ፥ ቁጣ በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይወርድ ልታስጠነቅቋቸው ይገባል፡፡ እንደዚህ ብታደርጉ በኃጢአት በደለኛ አትሆኑም፡፡11እነሆ ለእግዚአብሔር በሚሆኑት ነገሮች ሁሉ ላይ ሊቀ ካህናቱ አማርያ፥ በንጉሡ ጉዳዮች ሁሉ ላይ የተሾመው የይሁዳ ቤት መሪ የእስማኤል ልጅ ዝባድያ አለቆች ናቸው፡፡ ሌዋውያኑም ደግሞ የሚያገለግሏችሁ ባለሥልጣናት ይሆናሉ፡፡ በድፍረት አድርጉ፤ እግዚአብሔርም መልካም ከሆኑት ጋር ይሁን፡፡
1ከዚህ ጊዜ በኋላ የሞዓብና የአሞን ሕዝቦች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሳፍጥን ሊዋጉት መጡ፡፡ 2አንዳንድ ሰዎች መጥተው፦"ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም ዓይንጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ናቸው" ብለው ነገሩት፡፡3ኢዮሳፍጥም ፈራ፤ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ራሱን አቀና፤ በመላው ይሁዳ ፆምን አወጀ፡፡ 4ይሁዳም እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ በአንድነት ተሰበሰበ፤ ከመላው የይሁዳ ከተሞች ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ መጡ፡፡5ኢዮሳፍጥም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ጉባዔ በአዲሱ አደባባይ ፊት ቆመ፡፡ 6"የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ሆይ አንተ በሰማይ ያለህ አምላክ አይደለህምን? በሕዝቦች ነገሥታት ሁሉ ላይ ገዢ አይደለህምን? ኃይልና ብርታት በእጅህ ናቸው፤ በመሆኑም ማንም ሊቋቋምህ የሚችል የለም፡፡ 7አምላካችን ሆይ በዚህ ምድር ላይ የነበሩትን ነዋሪዎች ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት አሳድደህ ለዘላለም ለአብርሃም ዝርያዎች አልሰጠሃትምን?" አለ፡፡8እነርሱም በውስጧ ኖሩባት፤ 9"አደጋ/መቅሰፍት ቢመጣብን - ሰይፍ፥ ፍርድ፥ ወይም በሽታ፥ ወይም ረሃብ - (ስምህ በዚህ ቤት ስላለ) በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆምና በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ" በማለት ለስምህም ቅዱስ ሥፍራ በውስጥዋ ሠሩ፡፡10አሁንም እነሆ እስራኤል ከግብጽ ምድር በሚወጡበት ጊዜ እንዲወሩዋቸው ያልፈቀድክላቸው ይልቁንም ዞር ብለው ያላጠፏቸው የአሞን፥ የሞዓብና የሴይር ተራራ ሕዝቦች እዚህ ናቸው፤ 11እነሆ ለወረታችን እንዴት እንደሚመልሱልን ተመልከት፤ እንድንወርሰው ከሰጠኸን ከምድርህ ሊያስወጡን መጥተዋል፡፡12አምላካችን ሆይ አትፈርድባቸውምን? ይህንን ሊያጠቃን የመጣብንን ታላቅ ሠራዊት እንቋቋም ዘንድ ምንም ኃይል የለንም፡፡ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን በአንተ ላይ ናቸው" አለ፡፡ 13ይሁዳ ሁሉ ከሕጻናቶቻቸው፥ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በእግዚአብሔር ፊት ቆመው ነበር፡፡14በጉባዔው መካከል የእግዚአብሔር መንፈስ ከአሳፍ ልጆች አንዱ በነበረው በሌዋዊው በማታንያ ልጅ በይዒኤል ልጅ በበናያስ ልጅ በዘካርያስ ልጅ በየሕዚኤል ላይ መጣ፡፡ 15የሕዚኤልም፦" ይሁዳ ሁሉ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እና ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ስሙ፤ እግዚአብሔር የሚላችሁ ይህ ነው፦"ከዚህ ታላቅ ሠራዊት የተነሳ አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ምክንያቱም ጦርነቱ የእግዚአብሔር እንጂ የእናንተ አይደለም፡፡16ነገ በእነርሱ ላይ ለጦርነት ልትወጡ ይገባል፤ እነሆ በጺጽ መተላለፊያ መንገድ ይመጣሉ፡፡ በይሩኤል ምድረ በዳ ፊት ለፊት በሸለቆው መጨረሻ ታገኙዋቸዋላችሁ፡፡ 17በዚህ ጦርነት እናንተ መዋጋት የሚያስፈልጋችሁ አይደላችሁም፡፡ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ በቦታችሁ ቁሙ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርገውን ማዳን ተመልከቱ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለሆነ አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገ ለጦርነት ውጡባቸው" አለ፡፡18ኢዮሳፍጥም በምድር ላይ በፊቱ ተደፋ፤ ይሁዳ ሁሉና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እግዚአብሔርን በማምለክ በፊቱ ወደቁ፡፡ 19የቀዓትና የቆሬ ዝርያዎች ሌዋውያን የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በታላቅ ድምጽ ለማወደስ ቆመው ነበር፡፡20ጥዋት በማለዳ ተነስተው ወደ ቴቁሔ ምድረ በዳ ሄዱ፡፡ እየሄዱም እያለ ኢዮሳፍጥ ቆሞ፦" ይሁዳና እናንተ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ስሙኝ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፤ ድጋፍ ታገኛላችሁ፡፡ በነቢያቱም እመኑ፤ ይቃናላችኋልም" አለ፡፡ 21ከሕዝቡ ጋር ከተማከረ በኋላም ከሠራዊቱ ፊት ቀድመው እየሄዱ "የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ ለእግዚአብሔር ምሥጋናን ስጡ" በማለት ለእግዚአብሔር የሚዘምሩትንና ለቅዱስ ክብሩ ውዳሴ የሚሰጡትን ሾመ፡፡22መዘመርና ማወደስ ሲጀምሩ ይሁዳን ሊዋጉ በመጡት በአሞን፥ በሞዓብና በሴይር ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ድብቅ ጦር አስነስቶ በድንገት እንዲያጠቋቸው አደረገ፡፡ እነርሱም ተሸነፉ፡፡ 23የአሞንና የሞዓብ ሰዎች የሴይርን ተራራ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ እስኪገድሉዋቸውና እስኪያጠፏቸው ድረስ ሊዋጉዋቸው ተነስተው ነበር፡፡ የሴይርን ተራራ ነዋሪዎች በጨረሷቸው ጊዜ ሁሉም እርስ በእርስ ለመጠፋፋት ተረዳዱ፡፡24ይሁዳ ምድረ በዳውን ወደሚመለከቱበት ቦታ ሲመጡ ሠራዊቱን ተመለከቱ፡፡ እነሆ ሞተው በምድሩም ላይ ወድቀው ነበር፤ አንድም ያመለጠ ሰው አልነበረም፡፡25ኢዮሳፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ በመጡ ጊዜ ሊሸከሙት ከሚችሉት በላይ የተትረፈረፈ ባለጸግነትና የከበሩ ጌጦች አገኙ፤ ለራሳቸውም በዘበዙ፡፡ እጅግ ብዙ ስለነበርም ምርኮውን ለመውሰድ ሦስት ቀናት ፈጀባቸው፡፡ 26በአራተኛው ቀን በበረከት ሸለቆ ውስጥ ተሰበሰቡ፡፡ በዚያም እግዚአብሔርን አወደሱ፤ ስለዚህም የዚያ ሥፍራ ስም እስከዛሬ ድረስ "የበረከት ሸለቆ" ነው፡፡27የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው ላይ ደስ አሰኝቷቸዋልና በደስታ እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ኢዮሳፍጥ እየመራቸው ተመለሱ፡፡ 28በበገናና በመሰንቆ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ እግዚአብሔር ቤት መጡ፡፡29እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንደተዋጋ በሰሙ ጊዜ በሕዝቦች ነገሥታት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ፍርሃት ሆነ፡፡ 30በመሆኑም አምላኩ በዙሪያው ሁሉ ሰላም ስለሰጠው የኢዮሳፍጥ መንግሥት ጸጥታ ሰፈነባት፡፡31ኢዮሳፍጥ በይሁዳ ላይ ነገሠ፡፡ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሠላሳ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ለሃያ አምስት ዓመታት ነገሠ፡፡ የእናቱ የሺልሒ ሴት ልጅ ስም ዓዙባ ነበር፡፡ 32በአባቱም በዓሳ መንገዶች ሄደ፤ ከእነርሱም ፈቀቅ አላለም፤ በእግዚአብሔር ፊት ቅን የነበረውን ነገር አደረገ፡፡ 33ነገር ግን የኮረብታው መስገጃዎች ገና አልተወገዱም ነበር፡፡ ሕዝቡም ልባቸውን ወደ አባቶቻቸው አምላክ ገና አላቀኑም ነበር፡፡34ኢዮሳፍጥን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ እንደተመዘገበው በአናኒ ልጅ በኢዩ ታሪክ ውስጥ ተጽፈዋል፡፡35ከዚህ በኋላ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ እጅግ ክፋት ከፈጸመው ከእስራኤል ንጉሥ ከአካዝያስ ጋር ራሱን አዛመደ፡፡ 36በባህር ላይ የሚሄዱ መርከቦችን ለመገንባት ከእርሱ ጋር ተባበረ፡፡ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር ገነቡ፡፡ 37የመሪሳም ሰው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር ፦" ከአካዝያስ ጋር ተባብረሃልና እግዚአብሔር ሥራዎችህን አፍርሷል፤" ብሎ በኢዮሳፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረበት፡፡ መርከቦቹም ተሰባበሩ፤ ጉዞ ለማድረግም አልቻሉም፡፡
1ኢዮሳፍጥም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ከእነርሱ ጋር ተቀበረ፤ ልጁም ኢዮራም በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡ 2ኢዮራም የኢዮሳፍጥ ልጆች የሆኑ ወንድሞች ዓዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤልና ሰፋጥያስ ነበሩት፡፡ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ልጆች ነበሩ፡፡ 3አባታቸው ብዙ የብር፥ የወርቅ እና የሌሎች የከበሩ ነገሮች እንዲሁም በይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን ሰጣቸው፤ ዙፋኑን ግን የመጀመሪያ ልጁ ስለነበር ለኢዮራም ሰጠው፡፡4ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ በወጣና ራሱን እንደ ንጉሥ አጽንቶ በመሠረተ ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉና የተለያዩ የእስራኤል ሌሎች መሪዎችን ጭምር በሰይፍ ገደላቸው፡፡ 5ኢዮራምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፡፡6የአክዓብን ሴት ልጅ አግብቶ ስለነበር የአክዓብ ቤት ያደርግ እንደነበር በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ የነበረውን ነገር አደረገ፡፡ 7ነገር ግን እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር ካደረገው ቃል ኪዳን የተነሳ የዳዊትን ቤት ለማጥፋት አልፈለገም፤ ለአርሱና ለዝርያዎቹ ሁልጊዜ ሕይወት እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸው ነበር፡፡8በኢዮራም ዘመን ኤዶምያስ በይሁዳ ኃይል ላይ ዐመፀ፤ በራሳቸውም ላይ ንጉሥ ሾሙ፡፡ 9በዚያን ጊዜ ኢዮራም ከአዛዦቹና ከሠረገላዎቹ ሁሉ ጋር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እርሱንና የሠረገላዎቹን አዛዦች ከብበው የነበሩትን ኤዶማውያንን መታ፡፡ 10በመሆኑም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ኤዶምያስ በይሁዳ ኃይል ላይ እንዳመፀ ነው፡፡ ኢዮራም የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለተወ የልብና ከተማ ጭምር በዚያው ጊዜ በኃይሉ ላይ ዐመጸ፡፡11በተጨማሪም ኢዮራም በይሁዳ ተራራዎች ላይ መስገጃዎችን ሠርቶ ነበር፤ የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎችም እንደ አመንዝራ ሌሎች አማልክትን እንዲከተሉ አደረጋቸው፡፡ በዚህ መንገድ ይሁዳን ከትክክለኛው መስመር አስወጣቸው፡፡12ከነቢዩም ከኤልያስ አንድ ደብዳቤ ወደ ኢዮራም መጣለት፤ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦" በአባትህ በኢዮሳፍጥ መንገድ ወይም በይሁዳ ንጉሥ በአሳ መንገድ ስላልሄድህ 13ነገር ግን በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ስለሄድህ ይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች የአክዓብ ቤት እንዳደረገ እንደ አመንዝራ ሌሎች አማልክትን እንዲከተሉ ስላደረግሃቸው፤ በአባትህ ቤተሰብም ውስጥ ከአንተ የሚሻሉ የነበሩትን ወንድሞችህን በሰይፍ ስለገደልካቸው 14እነሆ እግዚአብሔር ሕዝብህን፥ ልጆችህን፥ ሚስቶችህን እና ሀብትህንም ሁሉ በታላቅ መቅሰፍት ይመታል፡፡ 15አንተም ራስህ ከበሽታው የተነሳ ከቀን ወደ ቀን አንጀትህ እስኪወጣ ድረስ በአንጀትህ ሕመም እጅግ ትታመማለህ፡፡"16እግዚአብሔርም የፍልስጤማውያንን እና በኢትዮጵያውያን አጠገብ ይኖሩ የነበሩትን የዓረባውያንን መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሳበት፡፡ 17እነርሱም ይሁዳን አጠቁ፤ ወረሩአትም፤ በንጉሡ ቤት ውስጥ የተገኘውን ሀብት ሁሉ ወሰዱ፤ ወንዶች ልጆቹንና ሚስቶቹንም ወሰዱ፡፡ ከታናሹ ልጁ ከአካዝያስ በስተቀር ምንም ልጅ አልቀረለትም፡፡18ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር ሊድን በማይችል በሽታ አንጀቱን መታው፤ 19በተገቢው ጊዜ በሁለቱ ዓመት መጨረሻ ከሕመሙ የተነሳ አንጀቱ ወጣ፤ በብርቱ በሽታም ሞተ፡፡ ሕዝቡም ለእርሱ አባቶች እንዳደረገው ለክብሩ ምንም ችቦ አላበራም፡፡ 20በሠላሳ ሁለት ዓመቱ ላይ መንገሥ ጀምሮ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያዝንለት ሞተ፡፡ በነገሥታቱ መቃብር ሳይሆን በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡
1የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም የኢዮራምን ታናሽ ልጅ አካዝያስን በእርሱ ቦታ አነገሡት፤ ምክንያቱም ከአረቢያኖቹ ጋር ወደ ካምፑ የመጡባቸው የሽፍቶች ቡድን የእርሱን ታላላቆች ሁሉ ገድለዋቸው ስለነበር ነው፡፡ በመሆኑም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ፡፡ 2አካዝያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ አርባ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሁለት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱ ስም ጎቶልያ ነበረ፤ እሷም የዖምሪ ልጅ ነበረች፡፡ 3እናቱ ክፉ ነገሮችን ለማድረግ መካሪው ስለነበረች እርሱም በአክዓብ ቤት መንገድ ሄደ፡፡4ከአባቱ ሞት በኋላ ለገዛ ራሱ ጉዳት እስኪሆን የአክዓብ ቤት መካሪዎቹ ስለነበሩ የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡ 5ምክራቸውንም ተከተለ፤ የአራምን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገለዓድ ሊዋጋ ከእስራኤል ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሄደ፡፡ አርመናውያንም ኢዮራምን አቆሰሉት፡፡6ኢዮራምም የአራምን ንጉሥ አዛሄልን በራማ በተዋጋ ጊዜ ካቆሰሉት ቁስል ይፈወስ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፡፡ ኢዮራም ቆስሎ ስለነበር የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ፡፡7አካዝያስ ኢዮራምን በመጎብኘቱ አማካይነት እንዲጠፋ እግዚአብሔር ፈቅዶ ነበር፡፡ በመጣ ጊዜ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ እግዚአብሔር የመረጠውን የናሚሴን ልጅ ኢዩን ለማጥቃት ከኢዮራም ጋር ሄደ፡፡ 8ኢዩም የእግዚአብሔርን ፍርድ በአክዓብ ቤት ላይ እየፈጸመ በነበረበት ጊዜ የይሁዳን መሪዎችና አካዝያስን የሚያገለግሉትን የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አገኛቸው፡፡ ኢዩም ገደላቸው፡፡9ኢዩ አካዝያስን ፈለገው፤ በሰማርያም ተሸሽጎ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አመጡት፤ እርሱም ገደለው፡፡ ከዚያም "እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሳፍጥ ልጅ ነው" ብለው ቀበሩት፡፡ በመሆኑም የአካዝያስ ቤት መንግሥቱን ለመምራት ምንም የቀረ ኃይል አልነበረውም፡፡10የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ ተነስታ በይሁዳ ቤት ውስጥ የነገሥታቱን ዝርያ ልጆች ሁሉ ገደለች፡፡ 11ነገር ግን የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል ሰርቃ ወሰደችው፤ እርሱንና ሞግዚቱን በመኝታ ክፍል ውስጥ አስቀመጠቻቸው፡፡ ስለዚህ የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት (የአካዝያስ እኅት ስለነበረች) ጎቶልያ እንዳትገድለው ከጎቶልያ ሸሸገችው፡፡ 12ጎቶልያ በምድሪቱ ላይ ስትገዛ ሳለ እርሱ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ለስድስት ዓመታት ተሸሽጎ ከእነርሱ ጋር ነበረ፡፡
1በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ ውጤት ያለው ነገር አደረገ፡፡ የመቶ አለቆቹን የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንን ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድን ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሴያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፡፡ 2በይሁዳ ሁሉ ዞረውም ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ ሌዋውያንንና የእስራኤልን ቤቶች አባቶች መሪዎች ሰብስበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ 3ጉባኤውም ሁሉ ከንጉሡ ጋር በእግዚአብሔር ቤት ቃል ኪዳን አደረጉ፡፡ ዮዳሄም፦ "እነሆ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ዝርያዎች እንደተናገረው የንጉሡ ልጅ ይነግሣል" አላቸው፡፡4"ማድረግ የሚገባችሁ ይህ ነው፤ በሰንበት ቀን ለማገልገል ከምትመጡት ከእናንተ ከካህናትና ከሌዋውያን አንድ ሦስተኛው በበሮቹ ላይ ጠባቂዎች ትሆናላችሁ፡፡ 5አንድ ሦስተኛችሁ ደግሞ በንጉሡ ቤት ትሆናላችሁ፤ ሌላው አንድ ሦስተኛ በመሠረቱ በር ላይ ይሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ላይ ይሁኑ፡፡6ከካህናቱና ከሚያገለግሉት ሌዋውያን በስተቀር ማንም ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲገባ አትፍቀዱ፤ እነርሱ ለዛሬው ሥራቸው ተለይተው ተመድበዋልና መግባት ይገባቸዋል፡፡ ሁሉም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጠበቅ ይገባቸዋል፡፡ 7ሁሉም ሰው የጦር መሣሪያውን በእጁ ይዞ ሌዋውያኑ ንጉሡን በሁሉም በኩል ሊከቡት ይገባቸዋል፡፡ ማንም ወደ ቤቱ ውስጥ ቢገባ ይገደል፡፡ ንጉሡም በሚገባበትና በሚወጣበት ጊዜ ሁሉ ከእርሱ ጋር ሁኑ፡፡8በመሆኑም ሌዋውያኑና ይሁዳ ሁሉ በሁሉም መንገድ ካህኑ ዮዳሄ ባዘዘው መሠረት አገለገሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን በሰንበት ለማገልገል የሚገቡትንና በሰንበትም ከአገልግሎት ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ወሰደ፤ ምክንያቱም ካህኑ ዮዳሄ የትኞቹንም የሥራ ክፍሎች አላሰናበተም ነበር፡፡ 9ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የንጉሡን የዳዊትን ጦሮች፥ ትንንሽና ትልልቅ ጋሻዎች ለአለቆቹ አመጣላቸው፡፡10ዮዳሄ እያንዳንዱ ሰው የጦር መሣሪያውን እንደያዘ ከቤተ መቅደሱ ቀኝ በኩል እስከ ቤተ መቅደሱ ግራ በኩል በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አጠገብ ንጉሡን እንዲከቡ ሁሉንም ወታደሮች በቦታቸው አቆማቸው፡፡ 11ከዚያም የንጉሡን ልጅ አውጥተው፥ ዘውዱን በላዩ ላይ ደፍተው የቃል ኪዳኑ ሕግጋት የተጸፈበትን ጥቅልል ሰጡት፡፡ ከዚያም አነገሡት፤ ዮዳሄና ልጆቹም ቀቡት፡፡ ከዚያም ፦" ንጉሡ ረጅም ዘመን ይኑር!" ብለው ጮኹ፡፡12ጎቶልያ የህዝቡን መሯሯጥና ንጉሡን ማወደስ ጫጫታ ስትሰማ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ሕዝቡ መጣች፡፡ 13እነሆም ንጉሡ መግቢያው ላይ በራሱ ምሰሶ አጠገብ ቆሞ እንደነበርና አዛዦቹና መለከት ነፊዎቹ ከንጉሡ አጠገብ ቆመው እንደነበር አየች፡፡ የአገሩ ህዝብ ሁሉ ደስ እያላቸውና መለከት እየነፉ ነበር፡፡ ዘማሪዎቹም የሙዚቃ መሣሪያዎች እየተጫወቱ የውዳሴ መዝሙሮችን ይዘምሩ ነበር፡፡ ጎቶልያ ልብሷን ቀድዳ፦" አገር ከመክዳት የሚቆጠር ዓመፅ ነው! ዓመፅ ነው!" ብላ ጮኸች፡፡14ካህኑ ዮዳሄ በሠራዊቱ ውስጥ መሪዎች የነበሩትን የመቶ አለቆች አውጥቶ፦ "ወደ ወታደሮቹ መካከል አውጡአት፤ የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል" አላቸው፡፡ ካህኑ ፦"በእግዚአብሔር ቤት አትግደሉአት" ብሎ ነበር፡፡ 15በመሆኑም ገለል ብለው ሲያሳልፏት ወደ ንጉሡ ቤት ፈረሱ በር በሚወስደው መንገድ ሄደች፤ እዚያም ገደሏት፡፡16ከዚያም ዮዳሄ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእርሱ፥ በሕዝቡና በንጉሡ መካከል ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ 17ሕዝቡም ሁሉ ወደ በኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፡፡ የበኣል መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን አደቀቁ፤ የበኣል ካህንን ማታንን በእነዚያ መሠዊያዎች ፊት ገደሉት፡፡18ዮዳሄም በሙሴ ሕግ ተጽፎ እንደነበረው በእግዚአብሔር ቤት ከደስታና ከመዝሙር ጋር የሚቃጠለውን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት ላይ የሾማቸው ሌዋውያን ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት ከካህናቱ እጅ በታች እንዲያገለግሉ ለእግዚአብሔር ቤት ኃላፊዎችን ሾመ፡፡ 19ርኩስ የሆነ ማንም በማናቸውም መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዳይገባ በበሮቹ ላይ ጠባቂዎችን አኖረ፡፡20ዮዳሄ ከእርሱ ጋር የመቶ አለቆቹን፥ ባላባቶቹን ፥ የሕዝቡን አስተዳዳሪዎችና የአገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፡፡ ንጉሡንም በኮረብታ ላይ ከነበረው ከእግዚአብሔር ቤት አወረደው፡፡ ሕዝቡም በላይኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጥተው ንጉሡን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡ 21የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አላቸው፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች፡፡ ጎቶልያንም በሰይፍ ገድለዋት ነበር፡፡
1ኢዮስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሰባት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፡፡ የቤርሳቤዋ እናቱ ስም ሳብያ ነበር፡፡ 2ኢዮስያስ ካህኑ ዮዳሄ በነበረበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፡፡ 3ዮዳሄ ለኢዮስያስ ሁለት ሚስቶችን አጋባው፤ የወንዶችና የሴቶች ልጆች አባት ሆነ፡፡4ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ የእግዚአብሔርን ቤት ለመጠገን ወሰነ፡፡ 5ካህናቱንና ሌዋውያኑን በአንድነት ሰብስቦ ፦"በየዓመቱ ወደ ይሁዳ ከተሞች ውጡና የአምላካችሁን ለማደስ ከእስራኤል ሁሉ ገንዘብን ሰብስቡ፡፡ በፍጥነት መጀመራችሁን እርግጠኛ ሁኑ" አላቸው፡፡ ሌዋውያኑ በመጀመሪያ ምንም አላደረጉም፡፡6በመሆኑም ንጉሡ ሊቀ ካህናቱን ጠርቶ፦"ሌዋውያኑ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ለቃል ኪዳኑ ድንኳን ድንጋጌ የእስራኤል ጉባኤ የተጣለባቸውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲያስመጡ ለምን አላደረግሃቸውም?" አለው፡፡ 7የዚያች ክፉ ሴት የጎቶልያ ልጆች የእግዚአብሔርን ቤት አፍርሰው እና የእግዚአብሔርንም ቤት የተቀደሱ ነገሮች ሁሉ ለበኣል ሰጥተው ነበር፡፡8በመሆኑም ንጉሡ ስለአዘዘ የገንዘብ ሳጥን ሰርተው በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በስተውጪ አስቀመጡት፡፡ 9የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ በእስራኤል ላይ የጣለባቸውን ግብር ለእግዚአብሔር እንዲያመጡ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሁሉ አዋጅ ነገሩ፡፡ 10መሪዎቹ ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ደስ ብሎአቸው ገንዘብ አመጡ፤ እስኪሞሉትም ድረስ በገንዘብ ሳጥኑ ውስጥ አስቀመጡት፡፡11የገንዘብ ሳጥኑ በሌዋውያኑ እጅ ወደ ንጉሡ ሹማምንት በሚመጣበት ጊዜ ሁሉና ብዙ ገንዘብ እንዳለበት ባዩ ጊዜ ሁሉ የንጉሡ ጸሐፊና የሊቀ ካህናቱ ሹም መጥተው ከገንዘብ ሳጥኑ ገንዘቡን አውጥተው በመውሰድ ሳጥኑን ወደ ሥፍራው ይመልሱት ነበር፡፡ ከፍ ያለ መጠን ያለው ገንዘብ በመሰብሰብ ይህንንም ዕለት ዕለት ያደርጉት ነበር፡፡ 12ንጉሡና ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የማገልገል ሥራ ለሚሠሩት ሰዎች ገንዘቡን ይሰጡ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቤት ለሚያድሱት ድንጋይ ጠራቢዎችና አናጢዎች እንዲሁም የብረትና የነሃስ ሥራ የሚሠሩትን ቀጥረው ያሠሩበት ነበር፡፡13በመሆኑም ሠራተኞቹ አብዝተው ሠሩ፤ የጥገናውም ሥራ በእጃቸው ተከናወነ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት በመጀመሪያ ንድፉ አቁመው አጠናከሩት፡፡ 14በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ዮዳሄ አመጡት፡፡ ይህ ገንዘብ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ፥ ለአገልግሎትና መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሆኑ ማንኪያዎችንና የወርቅና የብር ዕቃዎች ለማሟላት ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ በዮዳሄ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚቃጠል መሥዋዕት ባለማቋረጥ ያቀርቡ ነበር፡፡15ዮዳሄም ሸመገለ፤ ዕድሜም ጠግቦ ሞተ፡፡ በሚሞትበት ጊዜ ዕድሜው መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር፡፡ 16በእስራኤልም ለእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ቤት መልካም ስላደረገ በነገሥታቱ መካከል በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡17ዮዳሄ ከሞተ በኋላ የይሁዳ መሪዎች መጥተው ለንጉሡ ክብርን ሰጡት፡፡ ንጉሡም አዳመጣቸው፡፡ 18የአባቶቻቸውን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ትተው የማምለኪያ ዐፀዶችንና ጣዖታቱን አመለኩ፡፡በዚህም ኃጢአታቸው ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ መጣ፡፡ 19ሆኖም ግን ወደ እግዚአብሔር ወደ ራሱ እንደገና እንዲያመጧቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ ነቢያቱም በሕዝቡ ላይ ይመሰክሩባቸው ነበር፤ እነርሱ ግን ለመስማት እምቢ አሉ፡፡20የእግዚአብሔር መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም ከሕዝቡ በላይ ቆሞ፦"እግዚአብሔር ይህንን ይላል፤ 'የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? መልካም ነገር ሊሆንላችሁ አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን ስለተዋችሁ እርሱም ትቶአችኋል'" አላቸው፡፡ 21እነርሱ ግን አሴሩበት፤ በንጉሡ ትዕዛዝም በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት፡፡ 22በዚህ ሁኔታ ንጉሡ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት ችላ አለ፡፡ ይልቁንም የዮዳሄን ልጅ ገደለ፡፡ ዘካርያስም በሚሞትበት ጊዜ፦" እግዚአብሔር ይህንን ይየው፤ ይጠይቃችሁም" አለ፡፡23በዓመቱ መጨረሻም የአራም ሠራዊት ሊያጠቁት በኢዮአስ ላይ መጡበት፡፡ ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ የሕዝቡን መሪዎች ሁሉ ገደሉ፤ ከእነርሱ የወሰዱትንም ምርኮ ሁሉ ወደ ደማስቆ ንጉሥ ላኩ፡፡ 24የሶርያውያንም ሠራዊት የመጡት ከትንሽ ሠራዊት ጋር ነበር፤ ነገር ግን ይሁዳ የአባቶቻቸውን አምላክ ከመተዋቸው የተነሳ እግዚአብሔር እጅግ ታላቅ በነበረው ሠራዊት ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ በዚህ መንገድ የሶርያውያን ሠራዊት በኢዮአስ ላይ ፍርድን አመጡበት፡፡25ሶርያውያን ከሄዱ በኋላ ኢዮአስ ክፉኛ ቆስሎ ነበር፡፡ ከካህኑ ከዮዳሄ ልጆች ግድያ የተነሳ የገዛ አገልጋዮቹ አሲረውበት ነበር፡፡ በአልጋው ላይ ገደሉት፤ እርሱም ሞተ፤ በነገሥታቱ መቃብር ሳይሆን በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡ 26ያሴሩበትም ሰዎች የአሞናዊቷ የሰምዓት ልጅ ዛባድ፥ የሞዓባዊቷ የሰማሪት ልጅ ዮዛባት ነበሩ፡፡27የልጆቹ ነገርና ስለ እርሱ የተነገሩት ዋና ዋና ትንቢቶች እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤት እንደገና መገንባቱ እነሆ በነገሥታቱ መጽሐፍ ማብራሪያ ተጽፈዋል፡፡ ልጁም አሜስያስ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
1አሜስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፡፡ የኢየሩሳሌሟ እናቱ ስም ዮዓዳን ነበር፡፡ 2በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን በፍጹምና በተሰጠ ልብ አይደለም፡፡3መንግሥቱ በሚገባ በጸናለት ጊዜ አባቱን ንጉሡን የገደሉትን አገልጋዮቹን ገደላቸው፡፡ 4በሙሴ ሕግ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት፦"አባቶች ስለ ልጆች መሞት አይገባቸውም፤ ልጆችም ስለ አባቶች መሞት አይገባቸውም፡፡ ይልቁንም ማንኛውን ሰው ለራሱ ኃጢአት መሞት ይገባዋል" በማለት እግዚአብሔር እንዳዘዘው በማድረግ የገዳዮቹን ልጆች አልገደለም፡፡5በተጨማሪም አሜስያስ ይሁዳን በአንድነት ሰበሰበ፤ ይሁዳንና ቢንያምን ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤቶች ከሺህ አለቆችና ከመቶ አለቆች በታች መዘገባቸው፡፡ ከሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉትን ቆጠረ፤ ወደ ጦርነት ሊሄዱ የሚችሉ፥ ጋሻና ጦርም ሊይዙ የሚችሉ ሦስት መቶ ሺህ የተመረጡ ሰዎች አገኘ፡፡ 6ከእስራኤልም መቶ ሺህ ጦረኛ ሰዎች በመቶ መክሊት ብር ቀጠረ፡፡7ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እርሱ መጥቶ፦"ንጉሥ ሆይ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር፥ ከኤፍሬምም ሰዎች ከአንዳቸውም ጋር አይደለምና የእስራኤል ሠራዊት ከአንተ ጋር አይሂዱ፡፡ 8ነገር ግን ብትሄድ በጦርነትም ደፋርና ብርቱ ብትሆን እግዚአብሔር በጠላት ፊት ይጥልሃል፤ ምክንያቱም የመርዳት ኃይል እና የመጣል ኃይል ያለው እግዚአብሔር ነው" አለው፡፡9አሜስያስም ለእግዚአብሔር ሰው፦" ለእስራኤል ሠራዊት ስለሰጠሁት መቶ መክሊትስ ምን እናደርጋለን?" አለው፡፡ የእግዚአብሔር ሰውም፦ "እግዚአብሔር ከዚያ እጅግ የበለጠ ሊሰጥህ ይችላል" ብሎ መለሰለት፡፡ 10በመሆኑም አሜስያስ ከኤፍሬም ወደርሱ የመጡትን ሠራዊት ለይቶአቸው እንደገና ወደ ቤት ላካቸው፡፡ ስለዚህም በይሁዳ ላይ ቁጣቸው እጅግ ነደደ፤ ወደ ቤትም በጋለ ቁጣ ተመለሱ፡፡11አሜስያስም በርትቶ ሕዝቡን አውጥቶ ወደ ጨው ሸለቆ መራቸው፤ በዚያም አሥር ሺህ የሴይርን ሰዎች ድል ነሳቸው፡፡ 12የይሁዳም ሠራዊት አሥር ሺህ ሰዎች ከነሕይወታቸው ማርከው ወሰዱ፡፡ ወደ ኮረብታው ጫፍ ላይ ወሰዱአቸውና ሁሉም እስኪንኮታኮቱ ድረስ ከዚያ ወደ ታች ወረወሩአቸው፡፡13ነገር ግን አሜስያስ ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄዱ ያስመለሳቸው የሠራዊት ሰዎች ከሰማርያ እስከ ቤትሖሮን በይሁዳ ከተሞች ላይ ጥቃት አደረሱ፤ ከሕዝቡም ሦስት ሺህ ሰዎች መትተው እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ፡፡14አሜስያስ የኤዶምያስን ሰዎች ገድሎ ከተመለሰ በኋላ የሴይርን ሰዎች ጣኦታት አምጥቶ የገዛ ራሱ አማልክት እንዲሆኑ አቆማቸው፡፡ በፊታቸውም ሰገደ፤ እጣንም አጠነላቸው፡፡ 15ስለዚህም የእግዚአብሔር ቁጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ፡፡ አንድ ነቢይ ልኮ፦"የገዛ ሕዝባቸውን እንኳን ከአንተ እጅ ያላዳኑትን የአሕዛብን አማልክት ለምን ፈለግሃቸው?" አለው፡፡16ነቢዩም ከእርሱ ጋር እየተነጋገረ እያለ ንጉሡ፦"የንጉሡ አማካሪ እንድትሆን አድርገንሃል? አቁም! ለምን መገደል ይገባሃል?" አለው፡፡ ነቢዩም ንግግሩን አቁሞ፦"ይህንን ድርጊት በመፈጸምህና ምክሬን ባለመስማትህ እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንደወሰነ አውቃለሁ" አለ፡፡17ከዚያም የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ፦" ና በጦርነት ፊት ለፊት እንጋጠም" ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ኢዮአስ ላከ፡፡18የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ መልዕክተኞችን ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ መልሶ ላከና፦"በሊባኖስ የነበረ አንድ ኩርንችት፦ 'ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው' ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ መልዕክት ላከ፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ መንገድ ሲያልፍ ኩርንችቱን ረገጠው፡፡ 19አንተም ፦'እነሆ ኤዶምያስን መትቻለሁ' ብለህ ልብህ ከፍ ከፍ ብሏል፡፡ በድልህ ኩራ፤ ነገር ግን በቤትህ ተቀመጥ፤ አንተና ካንተ ጋር ይሁዳ ሁሉ ለምን በራስህ ላይ ችግር ፈጥረህ ትወድቃለህ?" አለው፡፡20የይሁዳ ሰዎች ከኤዶምያስ አማልክት ምክር ከመፈለጋቸው የተነሳ የይሁዳን ሰዎች ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ዘንድ ይህ ከእግዚአብሔር ታስቦ ነበርና አሜስያስ ሊሰማ አልፈለገም፡፡ 21ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮአስ ጥቃት አደረሰ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ የይሁዳ በነበረችው በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ተጋጠሙ፡፡ 22ይሁዳም በእስራኤል ፊት ተመታ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደ ቤቱ ሸሸ፡፡23የእስራኤል ንጉሥ ኢዮአስ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ልጅ አሜስያስን በቤትሳሚስ ማረከው፡፡ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞት መጣና ከኤፍሬም በር እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አራት መቶ ክንድ ርቀት ያህል አፈረሰው፡፡ 24ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ከዖቤድኤዶም ጋር የነበሩትን ዕቃዎች በሙሉ እንዲሁም በንጉሡ ቤት የነበሩትን ዋጋ ያላቸውን ነገሮች ከታገቱት ጋር ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፡፡25የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፥ ከእስራኤል ንጉሥ ከኢዮአካዝ ልጅ ከኢዮአስ ሞት በኋላ አሥራ አምስት ዓመት ኖረ፡፡ 26አሜስያስን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፉ አይደለምን?27አሜስያስም እግዚአብሔርን ከመከተል ከራቀበት ጊዜ አንስቶ በኢየሩሳሌም ሴራ ያሴሩበት ጀመር፡፡ ወደ ለኪሶም ሸሸ፤ ነገር ግን ከበስተኋላው ሰዎች ላኩበት፤ እነርሱም በዚያ ገደሉት፡፡ 28በፈረስም ጭነው መልሰው አመጡት፤ በይሁዳም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፡፡
1የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ አሥራ ስድስት ዓመት የነበረውን ዖዝያንን ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ቦታ አነገሡት፡፡ 2ኤላትን እንደገና የገነባትና ወደ ይሁዳ ወደቀድሞ ይዞታዋ የመለሳት እርሱ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፡፡ 3ዖዝያን መንገሥ በጀመረ ጊዜ አሥራ ስድስት ዓመቱ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌምም ሃምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱም ስም ይኮልያ ነበር፤ የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች፡፡4በሁሉም ነገር የአባቱን የአሜስያስ ምሳሌነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፡፡ 5እግዚአብሔርን መታዘዝ ባስተማረው በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ለመፈለግ በልቡ ቆርጦ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር የተሳካለት አደረገው፡፡6ዖዝያን ወጥቶ ከፍልስጤማውያን ጋር ተዋጋ፡፡ የጌትንና የየብናንና የአዛጦንን የከተማ ቅጥሮች አፈረሰ፤ በአዛጦን አገርና በፍልስጤማውያን መካከል ከተሞችን ገነባ፡፡ 7እግዚአብሔርም በፍልስጤማውያን ላይ፥ በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን ላይና በምዑናውያን ላይ ረዳው። 8አሞናውያንም ለዖዝያን ግብር ይከፍሉ ነበር፤ እጅግ ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ዝናውም እስከ ግብጽ መግቢያ ድረስ ወደ ሌሎች አገሮች ተሰራጨ።9በተጨማሪም ዖዝያን በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በር፥ በሸለቆው በርና በቅጥሩ መዞሪያ ላይ ረጃጅም ማማዎችን ገንብቶ መሸጋቸው። 10በቆላው እንዲሁም በደጋው እጅግ ብዙ ከብቶች ስለነበሩት በምድረ በዳው የመጠባበቂያ ማማዎችን ሠራ፤ በርካታ ጉድጓዶችንም ቆፈረ። እርሻ ይወድ ስለነበርም በኮረብታማው አገርና በፍሬያማው መስክ ውስጥ ገበሬዎችና የወይን አትክልተኞች ነበሩት።11በተጨማሪም ዖዝያን በጸሐፊው በይዒኤልና ከንጉሡ አለቆች በአንዱ በሐናንያ ሥልጣን ስር በነበረው በመዕሤያ በሚቆጠሩበት ቁጥር መሰረት የተደራጁ በቡድን ወደ ጦርነት ይሄዱ የነበሩ የተዋጊ ሰዎች ሠራዊት ነበሩት። 12የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች የተዋጊ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። 13ከበታቻቸውም ንጉሡን ከጠላቱ ለመጠበቅ የሚረዳ በብርቱ ኃይል የሚዋጋ የሦስት መቶ ሰባት ሺህ እምስት መቶ ሰዎች ሠራዊት ነበር።14ዖዝያንም ለሠራዊቱ ሁሉ ጋሻዎች፥ ጦሮች፥ የራስ ቁሮች፥ ጥሩሮች፥ ቀስቶችና የሚወነጭፉአቸውን ድንጋዮች አዘጋጅቶላቸው ነበር። 15በኢየሩሳሌምም ፍላጻዎችንና ትልልቅ ድንጋዮችን ለመወርወር በግንብና በመታኮሻ ቅጥር ላይ እንዲሆኑ የተካኑ ባለሙያዎች የፈለሰፏቸውን ማንቀሳቀሻ ሞተሮች ገነባ። እጅግ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በብዙ ረድቶታልና ዝናው እስከ ሩቅ ቦታዎች ተሰራጨ።16ነገር ግን ዖዝያን በበረታ ጊዜ እስኪበላሽ ድረስ ልቡ ታበየ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን በማጠኑ አምላኩን እግዚአብሔርን በደለ። 17ካህኑም ዓዛርያስ ከእርሱም ጋር ደፋር ሰዎች የነበሩ ሰማንያ የእግዚአብሔር ካህናት ተከትለውት ገቡ። 18ንጉሡንም ዖዝያንን ተቃውመው፦"ዖዝያን ሆይ፦ ለእግዚአብሔር ዕጣን ማጠን ለእግዚአብሔር ለተቀደሱት ለካህናቱ ለአሮን ልጆች የተሰጠ እንጂ ዕጣን ማጠን ለአንተ አይደለም። ተላልፈሃልና ከቅዱሱ ቦታ ውጣ። በዚህ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ላንተ ምንም ክብር አይሆንልህም" አሉት።19ዖዝያንም ተቆጣ። ዕጣን የሚያጥንበትን ጥና በእጁ ይዞ ነበር። በካህናቱ ላይ በተቆጣ ጊዜ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ በካህናቱ ፊት ግንባሩ ላይ ለምጽ ወጣበት። 20ዋናው ካህንና ካህናቱ ሁሉ ተመለከቱት፤ እነሆ ግንባሩ ላይ ለምጻም ሆኖ ነበር። በፍጥነትም ከዚያ ቦታ አስወጡት። በእርግጥም እግዚአብሔር በለምጽ መትቶት ስለነበር እርሱም ለመውጣት ቸኮለ።21ንጉሡም ዖዝያን እስከሚሞትበት ቀን ድረስ ለምጻም ነበረ፤ ለምጻም በመሆኑም ከእግዚአብሔር ቤት ተገልሎ ስለነበር ከሰዎች ርቆ በተለየ ቤት ይኖር ነበር። ልጁም ኢዮአታም በንጉሡ ቤት ላይ የበላይ ሆኖ የምድሩን ሕዝብ ይገዛ ነበር።22ዖዝያንን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ በጻፈው ውስጥ ይገኛሉ። 23ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ "ለምጻም ነው" ብለውም ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር ሥፍራ ቀበሩት።
1ኢዮአታምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ። የእናቱም ስም ኢየሩሳ ነበር፤ እርሷም የሳዶቅ ልጅ ነበረች። 2በሁሉም ነገር የአባቱን የዖዝያንን ምሳሌ ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ። ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከመግባትም ተቆጠበ። ሕዝቡ ግን ገና በክፉ መንገድ ይሄዱ ነበር።3የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም ኮረብታ ላይ እጅግ ብዙ የግንባታ ሥራዎችን ሠራ። 4በተጨማሪም በኮረብታማው የይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን፥ በደኖቹ ውስጥ ደግሞ አምባዎችንና ማማዎችን ገነባ።5ከአሞንም ሕዝብ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ አሸነፋቸው። በዚያው ዓመት የአሞን ልጆች አንድ መቶ መክሊት ብር፥ አሥር ሺህ መስፈሪያ ስንዴ፥ አሥር ሺህ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። የአሞን ሕዝብ በሁለተኛውና በሦስተኛውም ዓመት ተመሳሳዩን ያህል ሰጡት።6በመሆኑም ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በጽናት ስለተራመደ ብርቱ ሆነ። 7ኢዮአታምን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች ጦርነቶቹ ሁሉና መንገዱ እነሆ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።8ኢዮአታም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ለአሥራ ስድስት ዓመታት ነገሠ። 9ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት። ልጁም አካዝ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
1አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ ዓመቱ ነበረ፤ በኢየሩሳሌም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ። ዝርያው ዳዊት እንዳደረገው በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አላደረገም። 2ይልቁንም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ ለበኣሊምም ከብረት ቀልጠው የተሠሩ ምስሎችን ሠራ።3በተጨማሪም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ዕጣን ዐጠነ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ያሳደዳቸውን ሕዝቦች ክፉ ልማድ ተከትሎ ልጆቹን እንደሚቃጠል መሥዋዕት በእሳት ውስጥ አሳለፋቸው። 4በኮረብታው መስገጃዎች፥ በኮረብቶች ላይ እና በለመለመው ዛፍ ሁሉ በታች መስዋዕት ይሰዋና ዕጣን ያጥን ነበር።5ስለዚህ የአካዝ አምላክ እግዚአብሔር ለሶርያ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው። ሶርያውያንም ድል አደረጉት፤ የብዙ እስረኞችን ስብስብ ከእርሱ ወስደው ወደ ደማስቆ አመጡአቸው። አካዝ ለእስራኤልም ንጉሥ እጅ ተላልፎ ተሰጥቶ ነበር፤ እርሱም በታላቅ ግድያ አሸነፈው። 6የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመተዋቸው የተነሳ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ ሁሉም ደፋር የሆኑ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ወታደሮችን ገደለ።7ኤፍሬማዊው ኃይለኛ ሰው ዝክሪ የንጉሡን ልጅ መዕሤያንና የቤተ መንግሥቱን ባለሥልጣን ዓዝሪቃምን ለንጉሡ በማዕረግ ሁለተኛ የነበረውን ሕልቃናን ገደለ። 8የእስራኤል ሠራዊት ከዘመዶቻቸው ሁለት መቶ ሺህ ሚስቶች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ምርኮ አድርገው ወሰዱ። ወደ ሰማሪያም ተሸክመው ያመጡትን እጅግ ብዙ ምርኮም ወሰዱ።9ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ በዚያ ነበረ፤ ስሙም ዖዴድ ነበር። ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ሠራዊት ለመገናኘት ወጣ።" የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ስለተቆጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው። እናንተ ግን ወደ ሰማይ በሚደርስ ቁጣ ገደላችኋቸው። 10አሁንም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ወንዶችና ሴቶች እንደ ባሪያዎቻችሁ አድርጋችሁ ልትይዟቸው ታስባላችሁ። በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ በገዛ ራሳችሁ ኃጢአት በደለኞች አይደላችሁምን? 11እንግዲያውስ አሁን ስሙኝ፤ የእግዚአብሔር የጋለ ቁጣ በእናንተ ላይ ስለሆነ ከገዛ ወንድሞቻችሁ የወሰዳችኋቸውን እስረኞች መልሳችሁ ስደዱ" አላቸው።12ከዚያም የተወሰኑ የኤፍሬም ሰዎች መሪዎች የዮሐናን ልጅ ዓዛርያስ፥ የምሺሌሞትም ልጅ በራክያ፥ የስሎምም ልጅ ይሒዝቅያ፥ የሐድላይም ልጅ ዓሜሳይ ከጦርነቱ ተመልሰው የመጡትን ተቃወሙአቸው። 13"መተላለፋችን ታላቅ ስለሆነና በእስራኤል ላይ የጋለ ቁጣ ስላለባት በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት የሚሆንብንን ነገር ልታመጡብን፥ ኃጢአታችንንና መተላለፋችንን ልትጨምሩብን ስላሰባቸሁ እስረኞቹን እዚህ ልታመጧቸው አይገባችሁም" አሏቸው።14የታጠቁት ሰዎችም እስረኞቹንንና ምርኮውን በመሪዎቹና በጉባኤው ሁሉ ፊት ተዉአቸው። 15በስማቸው የተመደቡትም ሰዎች ተነስተው እስረኞቹን ወስደው ከመካከላቸው እርቃናቸውን የነበሩትን ሁሉ ከተማረከው ልብስ አለበሷቸው። አጎናጸፉአቸው፤ ጫማም አደረጉላቸው። የሚበሉትን ምግብና የሚጠጡትን ሰጡአቸው። ቁስላቸውን አከሙላቸው፤ የደከሙትንም በአህዮች ላይ አስቀመጧቸው። የዘንባባ ከተማ ተብላ በምትጠራዋ ኢያሪኮ ወዳሉት ቤተሰቦቻቸው መልሰው ወሰዷቸው። ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሱ።16በዚያን ጊዜ ንጉሥ አካዝ እንዲረዱት እንዲጠይቋቸው ወደ አሦርያ ነገሥታት መልዕክተኞችን ላከ። 17የኤዶምያስ ሰዎች አንድ ጊዜ ደግመው መጥተው ይሁዳን በማጥቃት እስረኞችን ይዘው ወስደው ነበር። 18ፍልስጤማውያንም የቆላውን ከተሞች እና የይሁዳን ደቡባዊ ክልሎች ወርረው ነበር። ቤት ሳሚስንና ኤሎንን ፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮን ከነመንደርዎቿ፥ ተምናን ከነመንደርዎቿ እና ጊምዞን ከነመንደርዎቿ ወስደው ነበር። በእነዚያ ቦታዎችም ውስጥ ለመኖር ሄደው ነበር።19በይሁዳ ክፉ ስላደረገና እግዚአብሔርንም እጅግ በጣም ስለበደለ ከእስራኤል ንጉሥ ከአካዝ የተነሳ እግዚአብሔር ይሁዳን ዝቅ ዝቅ አድርጎ ነበር። 20የአሦርም ንጉሥ ቴልጌልፌልሶር አካዝን በማበርታት ፈንታ መጥቶ አስጨንቆት ነበር። 21ለሦርያ ነገሥታት የከበሩትን ነገሮች ለመስጠት አካዝ የእግዚአብሔርን ቤት እና የንጉሡንና የመሪዎቹን ቤቶች ዘርፎ ነበር፤ ነገር ግን ይህ አልጠቀመውም።22ይኸው ንጉሥ አካዝ በመከራው ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ይበልጥ ኃጢአት ሠራ። 23ድል ላደረጉት አማልክት ለደማስቆ አማልክት መስዋዕት አቀረበ። "የሦርያ ነገሥታት አማልክት እነርሱን ስለረዷቸው መስዋዕት ባቀርብላቸው እኔንም ይረዱኝ ይሆናል" አለ። ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ ውድመት ሆኑ።24አካዝም የእግዚአብሔርን ቤት እቃዎች ሁሉ በአንድ ላይ ሰብስቦ ሰባበራቸው። የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ዘጋ፤ ለራሱም በኢየሩሳሌም በየማዕዘኑ ሁሉ መሰዊያዎችን ሠራ። 25በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚቃጠልባቸው መስገጃዎችን ሠራ፤ በዚህ መንገድ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለቁጣ ቀሰቀሰ።26የአካዝ የተቀሩት ድርጊቶቹና መንገዶቹ ሁሉ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል። 27አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በከተማይቱ በኢየሩሳሌምም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላስገቡትም። ልጁ ሕዝቅያስ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
1ሕዝቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። የእናቱ ስም አቡ ነበር፤ የዘካርያስ ልጅ ነበረች። 2በማንኛውም ነገር የዝርያውን የዳዊትን ምሳሌ ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ።3በነገሠም በመጀመሪያው ዓመት በመጀመሪያው ወር የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ አደሳቸውም። 4ካህናቱንና ሌዋውያኑን አምጥቶ በምሥራቅ በኩል ባለው አደባባይ ላይ በአንድነት ሰበሰባቸው። 5"እናንተ ሌዋውያን ሆይ ስሙኝ! ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱ፤ የአባቶቻችሁን አምላክ የእግዚአብሔርንም ቤት ቀድሱ፤ ከተቀደሰው ሥፍራም ርኩሱን ነገር ሁሉ አስወግዱ" አላቸው።6አባቶቻችን ሕጉን ስለተላለፉና በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር ስላደረጉ፥ እርሱንም ትተውታል፤ ፊታቸውንም እግዚአብሔር ከሚኖርበት ሥፍራ መልሰዋል፤ ጀርባቸውንም ሰጥተውታል። 7የበሮቹንም በረንዳዎች ዘግተዋል፤ መብራቶቹንም አጥፍተዋል። ለእስራኤል አምላክ በተቀደሰው ሥፍራ እጣን አላጠኑም ወይም የሚቃጠለውንም መስዋዕት አላቀረቡም።8ስለዚህ የእግዚአብሔር ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ፤ በገዛ ራሳችሁ ዓይኖች ማየት እንደምትችሉት ለሽብር፥ ለድንጋጤና ለመዘበቻም ማረፊያ አደረጋቸው። 9ለዚህ ነው አባቶቻችን በሰይፍ የወደቁት፤ ለዚህም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ሚስቶቻችንም በምርኮ ውስጥ አሉ።10አሁንም የጋለ ቁጣው ከእኛ እንዲመለስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለማድረግ በልቤ አስቤአለሁ። 11ልጆቼ እግዚአብሔር በፊቱ ትቆሙ፥ ታመልኩትና፥ አገልጋዮቹ ልትሆኑና ዕጣንን ልታጥኑለት ስለመረጣችሁ አሁን ታካች አትሁኑ።12ከዚያም ሌዋውያኑ የቀዓት ሰዎች የአሚሳ ልጅ መሐትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮኤል፥ የሜራሪ ሰዎች የአብዲ ልጅ ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፥ የጌድሶን ሰዎች የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ዔድን፥ 13የኤሊጸፋንም ልጆች ሺምሪና ይዒኤል፥ የአሳፍም ልጆች ዘካርያስና መታንያ፥ 14የኤማንም ልጆች ይሒኤልና ሰሜኢ፥ የኤዶታምም ልጆች ሸማያና ዑዝኤል ተነሡ።15ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀደሱ፤ የእግዚአብሔርን ቃል በመከተል ንጉሡ እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቤት ለማንጻት ወደ ውስጥ ገቡ። 16ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቤት ለማንጻት ወደ ውስጠኛው ክፍል ገቡ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ያገኙትን ቆሻሻ ነገር ሁሉ ወደ ቤቱ አደባባይ አወጡት። ሌዋውያንም ወደ ቄድሮን ዥረት ተሸክመው ሊወስዱት አወጡት። 17ቤቱን ለእግዚአብሔር መቀደስን በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ጀምረው በወሩ በስምንተኛው ቀን ወደ እግዚአብሔር በረንዳ ደረሱ። የእግዚአብሔርን ቤት በስምንት ቀናት ቀደሱ። በመጀመሪያው ወር በአሥራ ስድስተኛው ቀን ጨረሱ።18ከዚያም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ገብተው፦" የእግዚአብሔርን ቤት፥ የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበትን መሠውያ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር እና የመገኘቱን ሕብስት ገበታ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር አንጽተናል። 19በተጨማሪም ንጉሥ አካዝ ነግሦ በነበረበት ጊዜ በመተላለፍ የወረወራቸውን ዕቃዎች ሁሉ አዘጋጅተን ለእግዚአብሔር ቀድሰናል። እነሆ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ለፊት ይገኛሉ" አሉት።20ከዚያም ንጉሡ ሕዝቅያስ በማለዳ ተነስቶ የከተማዋን መሪዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ወጣ። 21ለመንግሥቱ፥ ለቤተ መቅደሱና ለይሁዳ የኃጢአት መስዋዕት አድርገው ሰባት ወይፈኖች፥ ሰባት አውራ በጎችና ሰባት የበግ ጠቦቶችና ሰባት ወንድ ፍየሎች አመጡ። ካህናቱን የአሮንን ልጆች በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ እንዲያቀርቧቸው አዘዛቸው።22በመሆኑም ወይፈኖቹን አረዷቸውና ካህናቱ ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ላይ ረጩት። አውራ በጎቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ የበግ ጠቦቶቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት። 23ለኃጢአት መስዋዕት ወንድ ፍየሎቹን በንጉሡና በጉባዔው ፊት አመጧቸው፤ እጃቸውንም ጫኑባቸው። 24ካህናቱም አረዷቸው፤ ንጉሡም ለእስራኤል ሁሉ የሚቃጠል መስዋዕትና የኃጢአት መስዋዕት ሊደረግ እንደሚገባው አዝዞ ስለነበር ለእስራኤል ሁሉ ለማስተሰረይ በመሠዊያው ላይ ደማቸውን የኃጢአት መስዋዕት አደረጉት።25ሕዝቅያስ ትዕዛዙ በነቢያቱ አማካይነት ከእግዚአብሔር ስለ ነበር በዳዊትና በንጉሡ ባለ ራዕይ በጋድ፥ በነቢዩ ናታንም ትዕዛዝ ሌዋውያኑን ከጽናጽል፥ ከበገናና ከመሰንቆ ጋር በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አደራጅቶ አስቀመጣቸው። 26ሌዋውያኑም ከዳዊት የሙዚቃ መሣሪያዎች ጋርና ካህናቱ ከመለከቶች ጋር ቆሙ።27ሕዝቅያስም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እንዲያቀርቡ አዘዛቸው። የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ሲጀመር የእግዚአብሔር መዝሙርም በመለከቶችና በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት የሙዚቃ መሣሪያዎች ተጀመረ። 28ጉባዔውም ሁሉ አመለኩ፤ መዘምራኑም ዘመሩ፤ መለከቶቹም ተነፉ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ሁሉ ቀጠለ።29መስዋዕት ማቅረቡን በፈጸሙ ጊዜ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ አጎነበሱ፤ ሰገዱም። 30በተጨማሪም ንጉሡ ሕዝቅያስና መሪዎቹ ሌዋውያኑ በዳዊትና በባለራዕዩ በአሳፍ ቃል ለእግዚአብሔር ውዳሴ እንዲዘምሩ አዘዙ። በደስታም ውዳሴዎችን ዘመሩ፤ አጎነበሱ፤ ሰገዱም።31ከዚያም ሕዝቅያስ፦"አሁን ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሳችኋል። ወደዚህ መጥታችሁ ለእግዚአብሔር ቤት መሥዋዕቱንና የምስጋና መሥዋዕቱን አቅርቡ" አላቸው። ጉባዔውም መሥዋዕቱንና የምስጋና መሥዋዕቱን አቀረቡ፤ ፈቃደኛ ልብ የነበራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ።32ጉባዔው ያቀረቡት የሚቃጠል መሥዋዕት ቁጥር ሰባ ወይፈን፥ አንድ መቶ አውራ በጎችና ሁለት መቶ ወንድ ጠቦቶች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ። 33ለእግዚአብሔር የተቀደሱት እንስሳት ስድስት መቶ በሬዎችና ሦስት ሺህ በጎች ነበሩ።34ነገር ግን ካህናቱ የሚቃጠሉትን መሥዋዕት ሁሉ ለመግፈፍ እጅግ ጥቂት ነበሩ፤ በመሆኑም ወንድሞቻቸው ሌዋውያኑ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ፥ ሌዋውያኑም ከካህናቱ ይልቅ ራሳቸውን ለመቀደስ ይበልጥ ጥንቁቅ ስለ ነበሩ ካህናቱ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር እስኪቀድሱ ድረስ ረዷቸው።35በተጨማሪም እጅግ ብዙ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ነበሩ፤ ከሕብረት መሥዋዕት ስብ ጋር ይከናወኑም ነበር፤ ለእያንዳንዱም የሚቃጠል መሥዋዕት የመጠጥ መሥዋዕትም ነበር። በመሆኑም የእግዚአብሔር አገልግሎት በደንብ ተደራጅቶ ነበር። 36እግዚአብሔር ለሕዝቡ ካዘጋጀው ነገር የተነሳ ሥራው በፍጥነት በመከናወኑ ሕዝቅያስ ሕዝቡም ሁሉ ደስ አላቸው።
1ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የፋሲካን በዓል ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ መልዕክተኞችን ላከ፤ ወደ ኤፍሬምና ምናሴም ደብዳቤዎችን ጻፈ። 2ንጉሡ፥ መሪዎቹና የኢየሩሳሌሙ ጉባዔ ሁሉ በአንድነት ከተመካከሩ በኋላ ፋሲካውን በሁለተኛው ወር ለማክበር እየወሰኑ ነበር። 3ካህናቱ በበቂ ቁጥር ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ስላልቀደሱና ሕዝቡም ገና ወደ ኢየሩሳሌም በአንድነት ስላልተሰበሰበ ወዲያውኑ በዓሉን ሊያከብሩ አልቻሉም ነበር።4ይህ እቅድ በንጉሡና በጉባዔው ሁሉ ፊት መልካም ሆኖ ታይቶ ነበር። 5በመሆኑም በመላው እስራኤል ከቤርሳቤህ እስከ ዳን የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ለማክበር ሕዝቡ እንዲመጡ አዋጅ እንዲነገር ድንጋጌ አወጡ። በእርግጥም በጽሑፍ እንደታዘዘው በብዙ ቁጥር አላከበሩትም ነበር።6በንጉሡ ትእዛዝ መልዕክተኞች ወደ መላው ይሁዳና እስራኤል ሁሉ የንጉሡንና የመሪዎቹን ደብዳቤ ይዘው ሄዱ። "እናንተ የእስራኤል ሰዎች ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠው ቅሬታችሁ እንዲመለስ ወደ አብርሃም፥ ይስሐቅና እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።7እንደምታዩት ለጥፋት አሳልፎ እስኪሰጣቸው ድረስ በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ላይ እንደተላለፉት እንደ አባቶቻችሁ ወይም ወንድሞቻችሁ አትምሰሉ። 8አሁንም አባቶቻችሁ እንደነበሩት እናንተም አንገተ ደንዳና አትሁኑ። ይልቁንም ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡና የጋለ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለማምለክ ለዘላለም ለእግዚአብሔር ወደ ተሰጠው ቅዱስ ሥፍራው ኑ! 9አምላካችሁ እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ስለሆነ ወደ እርሱ ብትመለሱ ፊቱን ከእናንተ ስለማይመልስ ወደ እግዚአብሔር ብትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ እንደ እስረኛ በወሰዷቸው ሰዎች ፊት ሃዘኔታ ያገኛሉ። ወደዚህችም ምድር ይመለሳሉ።10በመሆኑም መልዕክተኞቹ እስከ ዛብሎን ድረስ በመላው የኤፍሬምና የምናሴ ክልሎች ሁሉ ከከተማ ወደ ከተማ አለፉ፤ ሕዝቡ ግን ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም። 11ነገር ግን የተወሰኑ የአሴርና የምናሴ የዛብሎንም ሰዎች ራሳቸውን አዋርደው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። 12በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡንና የመሪዎቹን ትዕዛዝ ለመፈጸም አንድ ልብ ሊሰጣቸው የእግዚአብሔር እጅ በይሁዳ ላይም መጣ።13በሁለተኛው ወር የቂጣውን በዓል ለማክበር ብዙ ሰዎች፥ እጅግ ታላቅ ጉባዔ ለማክበር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። 14ተነስተው በኢየሩሳሌም የነበሩትን መሠዊያዎችና ለጣዖታት የሚያጥኑበትን ማጠኛዎች ሁሉ አስወገዱ፤ ወደ ቄድሮን ወንዝም ጣሉአቸው። 15ከዚያም በሁለተኛው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን ጠቦቶቹን አረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ አፍረው ነበርና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጡ። ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።16በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ የተሰጠውን መመሪያ በመከተል በየሥራ ክፍላቸው በቦታቸው ቆሙ፤ ካህናቱም ከሌዋውያኑ እጅ የተቀበሉትን ደም ይረጩ ነበር። 17በጉባዔው ውስጥ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያልሰጡ እጅግ ብዙ ነበሩ፤ ስለዚህ ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ጠቦቶቹን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ነጽተው ላልነበሩት ሰዎች ሁሉ የፋሲካውን ጠቦቶች የማረዱ ኃላፊነት የእነርሱ ነበር።18እጅግ ብዙ ሰዎች ብዙዎቹም ከኤፍሬምና ከምናሴ፥ ከይሳኮርና ከዛብሎን በሕጉ መሠረት ራሳቸውን አላነጹም ነበር፤ ነገር ግን እንደ ተጻፈው ትዕዛዝ ባይሆንም የፋሲካውን ምግብ በሉ፤ ሕዝቅያስም ፦" ምንም እንኳን እንደ ቅዱሱ ሥፍራ የመንጻት መለኪያ መሠረት የነጻ ባይሆንም 19የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔር አምላክን ለመፈለግ በልቡ የቆረጠውን ሰው ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው" በማለት ፀልዮላቸው ነበር። 20እግዚአብሔርም ሕዝቅያስን ሰማው፤ ሕዝቡንም ፈወሰ።21በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ሰዎች በታላቅ ደስታ የቂጣውን በዓል ለሰባት ቀናት አከበሩ። ሌዋውያኑና ካህናቱም ድምጹ በጎላ የሙዚቃ መሣሪያ ለእግዚአብሔር በመዘመር ከእለት ወደ እለት እግዚአብሔርን ያወድሱ ነበር። 22ሕዝቅያስም ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን አገልግሎት ያስተዋሉትን ሌዋውያን ሁሉ በማበረታታት ተናገራቸው። በመሆኑም የሕብረት ሥጦታ መሥዋዕት እያቀረቡና ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር እየተናዘዙ በሰባቱ ቀናት በዓል ሁሉ ይመገቡ ነበር።23ከዚያም መላው ጉባዔ ለሌላ ሰባት ቀናት በዓሉን ለማክበር ወሰኑ፤ እንደዚህም በደስታ አደረጉ። 24የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ለጉባዔው እንደ ሥጦታ ሰጥቶ ነበር፤ መሪዎቹም ለጉባዔው አንድ ሺህ ወይፈኖችና አሥር ሺህ በጎችና ፍየሎች ሰጡ። ብዙ ቁጥር ያላቸው ካህናትም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጥተው ነበር።25የይሁዳ ጉባዔ ሁሉ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ጋር፥ ከእስራኤል በአንድነት የመጡት ሕዝብ ሁሉ፥ እንዲሁም ከእስራኤል ምድር እና በይሁዳ ይኖሩ ከነበሩት የመጡት እንግዶች ሁሉም ደስ አላቸው። 26በመሆኑም በኢየሩሳሌም ታላቅ ደስታ ነበር፤ ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰለሞን ጊዜ አንስቶ እንደዚህ ያለ ነገር በኢየሩሳሌም ምንም አልነበረም። 27ከዚያም ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ ተነስተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምጻቸውም ተሰማ፤ ፀሎታቸውም ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ ቅዱስ ሥፍራ ወደ ሰማይ አረገ።
1ሁሉም ነገር ከተጠናቀቀ በኋላ እዚያ የተገኙት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው የአምልኮ ድንጋይ ምሶሶዎችን ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹን ቆረጡ፤ በይሁዳና በብንያም ሁሉ መስገጃዎችንና መሠዊያዎችን ሰባበሩ፤ ሁሉንም እስኪያጠፉ ድረስ ይህንኑ በኤፍሬምና በምናሴም ጭምር አደረጉት። ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ምድሩና ወደ ገዛ ከተማው ተመለሰ።2ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን በየሥራ ክፍል በማደራጀት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ለእያንዳንዱ ሥራ በመስጠት በየአገልግሎታቸው መደባቸው። የሚቃጠል መሥዋዕትና የሕብረት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ እንዲያገለግሉ፥ እንዲያመሰግኑና በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሮች እንዲያወድሱ መደባቸው። 3በእግዚአብሔር ሕግ ተጽፎ እንደነበረውም ለሚቃጠል መሥዋዕት ማለትም ለጠዋትና ለማታ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለሰንበት ቀናት፥ ለመባቻዎቹና ለመደበኛ በዓላትም የሚቃጠል መሥዋዕት ከንጉሡ ከገዛ ራሱ ሃብት ድርሻውን መደበ።4በተጨማሪም ካህናቱና ሌዋውያኑ የእግዚአብሔርን ሕግ በመታዘዝ ላይ እንዲያተኩሩ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች ለካህናቱና ሌዋውያኑ ድርሻቸውን እንዲሰጡ አዘዘ። 5ትእዛዙ እንደወጣም የእስራኤል ሕዝብ የእህሉን፥ የአዲሱን ወይን፥ የዘይቱን፥ የማሩን እንዲሁም ከእርሻው መከር ሁሉ በኩራት አትረፍርፈው ሰጡ፤ የሁሉንም ነገር አሥራትም አትረፍርፈው አመጡ።6በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ የበሬዎቹንና በጎቹን አሥራት፥ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር የተሰጡ ነገሮችን ጭምር አሥራት አምጥተው ከምረው አስቀመጡት። 7በሦስተኛው ወር መከመር ጀምረው በሰባተኛው ወር ጨረሱ። 8ሕዝቅያስና መሪዎቹ መጥተው ክምሮቹን ሲያዩ እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ባረኩ።9ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ጠየቀ። 10የሳዶቅም ቤት የሆነው ሊቀ ካህን ዓዛርያስ፦" ሕዝቡ ሥጦታዎቻቸውን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማምጣት ከጀመሩ አንስቶ በልተናል፤ ጠግበናልም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን ስለባረከ ብዙ ተርፎአል። የተረፈውም ነገር ይህ እዚህ ያለው ታላቅ መጠን ነው" ብሎ መልስ ሰጠ።11ከዚያም ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ መጋዘኖች እንዲዘጋጁ አዘዘ፤ እነርሱም አዘጋጇቸው። 12ሥጦታዎቹን፥ አሥራቱንና የእግዚአብሔር የሆኑትን ነገሮች በታማኝነት አመጡ። ሌዋዊው ኮናንያ የበላያቸው አስተዳዳሪ ነበር፤ ወንድሙም ሰሜኢ በደረጃ ከእርሱ ቀጥሎ ሁለተኛ ነበረ። በንጉሡም በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት ላይ ባለ ሥልጣን በነበረው በዓዛርያስ የተሾሙ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች 13ይሒዒል፥ ዓዛዝያ፥ ናሖት፥ አሣኤል፥ ይሬሞት፥ ዮዛባት፥ ኤሊኤል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስ አስተዳዳሪዎች ነበሩ።14ሌዋዊው የይምና ልጅ የምሥራቁ በር ጠባቂ ቆሬ ለእግዚአብሔር የተቀደሱትን ሥጦታዎችና በእግዚአብሔር የበጎ ፈቃድ ሥጦታዎች ላይ የበላይ ሆኖ ለእግዚአብሔር የቀረቡ ሥጦታዎችን ለማከፋፈል አዛዥ ነበር። 15ከበታቹም በካህናቱ ከተሞች ውስጥ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሽማያ፥ አማርያና ሴኬንያ ነበሩ። እነዚህን ሥጦታዎች ለታላላቆቹና ለታናናሾቹ ወንድሞቻቸው እንደየሥራ ክፍላቸው ለመስጠት በመታመን ሥልጣን ተሰጣቸው።16በዕለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚጠበቅባቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡ ሁሉ በቦታቸው ሆነው በየሥራ ክፍላቸው ሥራቸውን ለመሥራት በዘር ሐረጋቸው ተቆጥረው የነበሩ ሦስት ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ወንዶችም ሰጡ።17በቦታቸው ሆነው በየሥራ ክፍላቸው ሥራቸውን ለመሥራት በአባቶቻቸው ቤቶች በዘር ሐረጋቸው ተቆጥረው የነበሩ ሌዋውያን ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑትም ሰጡ። 18በዘር ሐረጋቸው ተቆጥረው ለነበሩ ለሕፃናቱ፥ ለሚስቶቻቸው፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻቸው ሁሉ በመላው ሕዝብ መካከል በተቀደሰ ሁኔታ በአመኔታ ለተሰጣቸው ሥልጣን ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ስለቀደሱ ለእነርሱም ሰጡ። 19በየከተማቸው ወይም በከተሞቹ ሁሉ ባሉ መንደሮች መስኮች ላይ ለነበሩ ለአሮን ዝርያዎች በካህናቱ መካከል ለሁሉም ወንዶች በስማቸው ድርሻቸውን ለመስጠትና በሌዋውያን መካከል እንደሆኑ በትውልድ ሐረጋቸው ለተቆጠሩ ሁሉ የተመደቡላቸው ሰዎች ነበሩ።20ሕዝቅያስም ይህንን በይሁዳ ሁሉ አደረገ። በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት መልካም፥ ትክክለኛና ታማኝ ነገርን አከናወነ። 21በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በጀመረው በየትኛውም ሥራ በሕጉና በትዕዛዛቱ አምላኩን ለመፈለግ በሙሉ ልቡ አከናወነው፤ እርሱም ተሳካለት።
1ከእነዚህ ነገሮችና ከእነዚህ የታማኝነት ድርጊቶች በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፤ ለራሱ ሊይዛቸው ያሰባቸውን የተከበቡ ከተሞች ሊያጠቃ ሰፈረ።2ሕዝቅያስም ሰናክሬም እንደ መጣ ኢየሩሳሌምንም ሊዋጋ እንዳሰበ ባየ ጊዜ 3ከከተማው በስተውጪ የነበሩትን የምንጭ ውሃዎች ለመድፈን ከመሪዎቹና ከኃያላን ሰዎቹ ጋር ተመካከረ፤ እነርሱም እንደዚህ ለማድረግ ረዱት። 4በመሆኑም በርካታ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው ምንጮቹን ሁሉና በምድሪቱ መካከል አልፎ ይፈስ የነበረውን ጅረት አስቆሙ። እነርሱም "የአሦር ነገሥታት መጥተው ለምን ብዙ ውሃ ያገኛሉ?" አሉ።5ሕዝቅያስም ተደፋፈረና የፈረሰውን ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ እስከ ማማዎቹ ድረስ ሠራው፤ በስተውጪ ሌላ ግንብም ሠራ። በዳዊትም ከተማ ውስጥ የነበረችውን ሚሎንም አጠነከረ፤ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የጦር መሣርያዎችንና ጋሻዎችንም ሠራ።6በሕዝቡ ላይም የጦር አዛዦችን አስቀመጠ። በአንድነትም በከተማይቱም በር በሰፊ ቦታ ወደራሱ ሰብስቦአቸው በማበረታታት ተናገራቸው። 7"በርቱ አይዞአችሁ። ከእርሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያለው እርሱ እግዚአብሔር የሚበልጥ ስለሆነ ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ሠራዊት የተነሳ እንዳትፈሩ ወይም እንዳትደነግጡ። 8ከእርሱ ጋር ያለው የሥጋ ክንድ ብቻ ነው፤ ከእኛ ጋር ግን ሊረዳንና ጦርነታችንን ሊዋጋልን ያለው አምላካችን እግዚአብሔር ነው" አላቸው። ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ራሳቸውን አጽናኑ።9ከዚህ በኋላ የሦርያ ንጉሥ ሰናክሬም (በዚህ ጊዜ በለኪሶ ፊት ለፊት ነበረ፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ጋር ነበሩ) አገልጋዮቹን ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስና በኢየሩሳሌም ወደነበሩት ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ 10"የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም የሚለው ይህንን ነው፦'በኢየሩሳሌም የተከበባችሁበትን ለመቋቋም የምትደገፉት በምን ላይ ነው?11ሕዝቅያስ፦ 'አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ይታደገናል' ብሎ ሲነግራችሁ በረሃብና በጥማት እንድትሞቱ አሳልፎ ሊሰጣችሁ እያሳሳታችሁ አይደለምን? 12የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ያስወገደና 'በአንድ መሠዊያ ላይ ታመልካላችሁ፤ በእርሱም ላይ መሥዋዕታችሁን ታቃጥላላችሁ' ብሎ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ያዘዘው ይኸው ሕዝቅያስ አይደለምን?13እኔና አባቶቼ በሌሎች ምድሮች ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደረግነው ምን እንደሆነ አላወቃችሁምን? የእነዚህ ምድሮች ሕዝቦች አማልክት በየትኛውም መንገድ ምድራቸውን ከኃይሌ ሊታደጉ ችለው ነበርን? 14አባቶቼ ሙሉ በሙሉ ካጠፏቸው ከእነዚያ ሕዝቦች አማልክት ሁሉ መካከል ሕዝቡን ከእጄ መታደግ የቻለ አምላክ ነበርን? አምላካችሁስ እናንተን ከኃይሌ ሊታደጋችሁ እንዴት ይችላል? 15አሁንም ሕዝቅያስ በዚህ መንገድ አያታልልላችሁ ወይም አያሳምናችሁ። የየትኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት አማልክት ሕዝቡን ከእጄ ወይም ከአባቶቼ እጅ ሊታደግ ስላልቻለ አትመኑት። ይልቁንም አምላካችሁ ከእጄ እንዴት ሊያድናችሁ ይችላል?" አለ።16የሰናክሬም አገልጋዮችም እግዚአብሔር አምላክና አገልጋዩ ሕዝቅያስ ላይ ይበልጥ የተቃውሞ ነገር ተናገሩ። 17ሰናክሬም በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ላይ ለማፌዝና እርሱንም በመቃወም ለመናገር ደብዳቤዎችንም ጻፈ። "የምድሪቱ ሕዝቦች አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ እንዳልታደጉ እንደዚሁ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ አይታደግም" አለ።18ከተማይቱን ለመያዝም በቅጥሩ ላይ የነበሩትን የኢየሩሳሌም ሰዎች ለማስፈራራትና ለማስጨነቅ በአይሁድ ቋንቋ በጎላ ድምጽ ይጮሁ ነበር። 19የሰዎች የእጅ ሥራ ብቻ በነበሩት በምድር ሌሎች ሕዝቦች አማልክት ላይ እንደተናገሩት በኢየሩሳሌም አምላክም ላይ ተናገሩ።20ንጉሡ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ከዚህ ጉዳይ የተነሳ ፀለዩ፤ ወደ ሰማይም ጮኹ። 21እግዚአብሔርም መልአክን ላከ፤ እርሱም ተዋጊዎቹን ሰዎች፥ አዛዦቹንና የንጉሡን ባለሥልጣናት በሰፈሩበት ቦታ ገደላቸው። በመሆኑም ሰናክሬም አፍሮ ወደ ገዛ ምድሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩ ቤት በገባ ጊዜ እዚያ ከገዛ ራሱ ልጆች አንዳንዱ በሰይፍ ገደሉት።22በዚህ መንገድ እግዚአብሔር ሕዝቅያስንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅና ከሌሎች ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በሁሉም መንገድም መራቸው። 23በርካቶችም ለእግዚአብሔር ሥጦታዎችን፥ የከበሩ ነገሮችንም ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡ ነበር። እርሱም ከዚያን ጊዜ አንስቶ በሕዝቦች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።24በዚያን ወቅት ሕዝቅያስ ለመሞት እስኪቀርብ ድረስ ታምሞ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም ፀለየ፤ እርሱም ተናገረው፤ እንደሚፈወስም ምልክትን ሰጠው። 25ሕዝቅያስ ግን ልቡ ታብዮ ስለ ነበር እግዚአብሔር ለሰጠው እርዳታ ውለታ ቢስ ሆነ። በመሆኑም በእርሱ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣ መጣባቸው። 26ቢሆንም ግን በኋላ ላይ ሕዝቅያስ ስለ ልቡ ትዕቢት እርሱና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁለቱም ራሳቸውን አዋረዱ። የእግዚአብሔርም ቁጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።27ሕዝቅያስ እጅግ ብዙ ባለጠግነትና ብዙ ክብር ነበረው። ለራሱም ለብር፥ ለወርቅ፥ ለከበሩ ድንጋዮችና ለቅመማ ቅመሞች እንዲሁም ለጋሻዎችና ዋጋ ላላቸው ነገሮች ሁሉ መጋዘኖችን ሠራ። 28ለእህል፥ ለአዲስ ወይንና ዘይት መጋዘኖች፥ ለሁሉም ዓይነት እንስሳት ጋጣዎችም ነበሩት። በጋጣቸውም መንጋዎችም ነበሩት። 29በተጨማሪም እግዚአብሔር እጅግ ብዙ ሃብት ስለሰጠው ለራሱ ከተሞችን፥ የተትረፈረፉ የበጎችና የከብቶች መንጋዎች ንብረት አዘጋጀ።30የግዮንን የላይኛውን ውሃ ምንጮች የደፈነና በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል በቀጥታ ቁልቁል እንዲመጡ ያደረጋቸው ይኸው ሕዝቅያስ ነው። ሕዝቅያስም በሠራው ሥራ ሁሉ ተሳካለት። 31ነገር ግን በምድሪቱ ስለተደረገው ተዓምራዊ ምልክት የሚያውቁ ሰዎችን ጥያቄ ለመጠየቅ የተላኩትን የባቢሎን መሳፍንት መልዕክተኞችን በተመለከተ ጉዳይ እግዚአብሔር ሊፈትነውና በልቡ ያለውን ለማወቅ ለራሱ ተወው።32ሕዝቅያስን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮች የቃል ኪዳን ታማኝነት ድርጊቶቹን ጨምሮ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራዕይና በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ መጻፋቸውን መመልከት ትችላላችሁ። 33ሕዝቅያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ዝርያዎች መቃብር በኮረብታው ላይ ቀበሩት። የይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ በሞቱ ጊዜ አከበሩት። ልጁ ምናሴ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
1ምናሴ መንገሥ በጀመረ ጊዜ አሥራ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሃምሳ አምስት ዓመት ነገሠ። 2እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ፊት እንዳስወጣቸው ሕዝቦች ዓይነት አስጸያፊ ነገር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ። 3አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች እንደገና ገነባ፤ ለበኣልም መሠዊያዎችን ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም አቆመ፤ ለሰማይም ከዋክብት ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።4ምንም እንኳን እግዚአብሔር፦ "ስሜ ለዘላለም የሚኖረው በኢየሩሳሌም ነው" ብሎ ያዘዘ ቢሆንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ለጣዖታት መሠዊያዎችን ገነባ። 5በእግዚአብሔር ቤት ሁለቱ አደባባዮች ውስጥ ለሰማይ ከዋክብት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ። 6በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት ውስጥ እንደሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤ ሞራ ገላጭ ሆነ፤ አስማት አደረገ፤ መተተኛም ነበረ፤ ከሙታን ጋር ከሚነጋገሩና ከመናፍስት ጋር ከሚነጋገሩ ጋር ይማከር ነበር። በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፋት በመለማመድ እግዚአብሔርን ለቁጣ አነሳሳ።7የአሼራን የተቀረጸ ምስል ሠርቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አኖረው፤ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን ሲናገር፦" ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ስሜ ለዘላለም እንዲኖርበት የመረጥኩት በዚህ ቤትና በኢየሩሳሌም ነው" ብሎ የነበረው ስለዚህ ቤት ነበር። 8በሙሴ አማካይነት የሰጠኋቸው ሕግ፥ ደንቦችና ድንጋጌዎች በመከተል ያዘዝኳቸውን ሁሉ ለመጠበቅ ቢጠነቀቁ ለአባቶቻቸው ከመደብኩላቸው ምድር የእስራኤልን ሕዝብ ከዚህ በኋላ አላወጣም" ብሎ ነበር። 9ምናሴም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ካጠፋቸው ሕዝቦች የበለጠ ክፋትን እንዲያደርጉ መራቸው።10እግዚአብሔርም ምናሴንና ሕዝቡን ተናገራቸው፤ ነገር ግን አልሰሙትም። 11በመሆኑም የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አዛዦች አመጣባቸው፤ ምናሴንም በእግር ብረት ያዙት፤ በሰንሰለት አሰሩት፤ ወደ ባቢሎንም ወሰዱት።12ምናሴ በተጨነቀ ጊዜ አምላኩን እግዚአብሔርን ተማፀነ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ራሱን እጅግ አዋረደ። 13ወደ እርሱም ፀለየ፤ እግዚአብሔርም ተለመነው። እግዚአብሔር ልመናውን ሰምቶ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ንግሥናው መለሰው። ምናሴም እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደሆነ አወቀ።14ከዚህ በኋላ ምናሴ በዳዊት ከተማ በግዮን ምዕራብ በኩል በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሣው በር መግቢያ ድረስ የውጫዊውን ግንብ ገነባ። የኦፊልንም ኮረብታ በእርሱ ከበበው። ግንቡንም እጅግ ታላቅ ከፍታ ድረስ አነሳው። በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ደፋር አዛዦችን አኖረ። 15የባዕድ አማልክትን ጣዖቱንም ከእግዚአብሔር ቤት አስወገደ፤ በእግዚአብሔር ቤት ተራራ ላይና በኢየሩሳሌም ውስጥ የገነባቸውን መሠዊያዎች ከከተማው ውጪ ወረወራቸው።16የእግዚአብሔርም መሠዊያ አደሰ፤ የሕብረት መሥዋዕትና የምሥጋናን መሥዋዕት ሥጦታዎች አቀረበበት፤ የይሁዳ ሕዝብ የእስራኤልን አምላክ እንዲያገለግሉ አዘዘ። 17ነገር ግን ሕዝቡ እስከ አሁንም በኮረብታው መስገጃዎች ላይ ይሰዋ ነበር፤ ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ብቻ ነበር።18ምናሴን የሚመለከቱት ሌሎች ነገሮች ወደ አምላኩ የፀለየው ፀሎትና በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም የተናገሩት የነቢያት ቃል እነሆ በእስራኤል ነገሥታት ድርጊቶች መካከል ተጽፈዋል። 19ፀሎቱም እግዚአብሔርም እንዴት እንደተለመነው፥ ኃጢአቱና መተላለፉ ሁሉ ራሱንም ከማዋረዱ በፊት የኮረብታ መስገጃዎች የገነባባቸው፥ የማምለኪያ አጸዶችንና የተቀረጹትን ምስሎች ያቆመባቸው ቦታዎች በባለ ራዕዮቹ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል። 20ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በገዛ ራሱ ቤት ውስጥ ቀበሩት። ልጁም አሞጽ በእርሱ ቦታ ነገሠ።21አሞጽ መንገሥ በጀመረ ጊዜ እድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሁለት ዓመት ነገሠ። 22አባቱ ምናሴ እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ። አሞጽ አባቱ ምናሴ ለሠራቸው ለተቀረጹ ምስሎች ሁሉ ሠዋ፤ አመለካቸውም። 23አባቱ ምናሴ እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ራሱን አላዋረደም። ይልቁንም ይኸው አሞጽ መተላለፉን ይበልጥ ጨመረው።24አገልጋዮቹ በእርሱ ላይ አሲረው በገዛ ቤቱ ውስጥ ገደሉት። 25የምድሪቱ ሕዝብ ግን በንጉሡ በአሞጽ ላይ ያሴሩበትን ሰዎች ሁሉ ገደሉ፤ ልጁንም ኢዮስያስን በእርሱ ቦታ አነገሡት።
1ኢዮስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ እድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ። 2በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም። 3በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ወጣት እያለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ መፈለግ ጀመረ። በአሥራ ሁለተኛው ዓመትም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎች፥ ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረጹት ምስሎችና ቀልጠው ከተሠሩት ምስሎች ማጽዳት ጀመረ።4ሕዝቡ የበኣሊምን መሠዊያዎች በእርሱ ፊት አፈረሱ፤ እርሱ ከበላያቸው የነበሩትን የዕጣን መሠዊያዎች ሰባበረ። የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ሰባበረ፤ የተቀረጹትን ምስሎች፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች አፈር እስኪሆኑ ድረስ አደቀቃቸው። ትቢያውንም መሥዋዕት ይሰዉላቸው በነበሩ ሰዎች መቃብር ላይ በተነው። 5የካህናቶቻቸውንም አጥንቶች በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ። በዚህ መንገድ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አጸዳ።6በምናሴ፥ በኤፍሬም፥ በስምዖን ከተሞችም እስከ ንፍታሌም ድረስና በዙሪያቸው ባሉት ፍርስራሾች ሁሉ ተመሳሳይ ነገር አደረገ። 7መሠዊያዎቹን አፈረሰ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረጹትን ምስሎች አደቀቃቸው፤ በእስራኤል ምድር ሁሉ የዕጣን መሠዊያዎችን ሁሉ ቆራረጠ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።8ኢዮስያስ ምድሪቱንና ቤተ መቅደሱን ካጸዳ በኋላ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት የኤዜልያስን ልጅ ሳፋን፥የከተማይቱንም ገዢ መፅሤያ፥ የታሪክ ጸሐፊውንም የኢዮአካዝን ልጅ ኢዮአክን የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲያድሱ ላካቸው። 9እነርሱም ወደ ሊቀ ካህኑ ወደ ኬልቅያስ ሄደው ሌዋውያኑ፥ የበሮቹ ጠባቂዎች ከምናሴና ከኤፍሬም፥ ከእስራኤል ቅሬታዎች ሁሉ፥ ከይሁዳና ከብንያም ሁሉ፥ ከኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የመጣውን ገንዘብ አደራ ሰጡት።10ገንዘቡን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ በበላይነት ለሚቆጣጠሩት ሰዎች ሰጧቸው። እነዚህ ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለሚጠግኑና ለሚያድሱ ሠራተኞች ከፈሏቸው። 11የተጠረበውን ድንጋይ፥ ለማጋጠሚያ ጣውላ እንጨትና አንዳንድ የይሁዳ ነገሥታት እንዲፈርስ ለተዉት መዋቅር ወራጆች እንዲገዙ ለአናጢዎቹና ግንበኞቹ ከፈሏቸው።12ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት ሠሩ። ሥራውን በበላይነት የሚቆጣጠሯቸው ሌዋውያኑ ከሜራሪ ልጆች ኢኤትና አብድዩ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ሁሉም መልካም የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾች የነበሩ ሌሎች ሌዋውያንም ሠራተኞቹን በቅርበት አቅጣጫ ይመሯቸው ነበር። 13እነዚህ ሌዋውያን የግንባታ ዕቃ የሚሸከሙትንና በሌላም መንገድ የሚሠሩትን ሌሎች ሰዎች ሁሉ ይቆጣጠሩ ነበር። ጸሐፊዎች፥ አስተዳዳሪዎችና የበር ጠባቂዎች የነበሩ ሌሎች ሌዋውያንም ነበሩ።14ወደ እግዚአብሔር ቤት የመጣውን ገንዘብ ወደ ውጪ ሲያመጡት ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ በኩል የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ። 15ኬልቂያስም ጸሐፊውን ሳፋንን፦" በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሕጉን መጽሐፍ አግኝቼአለሁ" አለው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ወደ ሳፋን አመጣው። 16ሳፋንም መጽሐፉን ወደ ንጉሡ ወስዶ፦"አገልጋዮችህ በኃላፊነት የተሰጣቸው ማናቸውንም ነገር እያደረጉ ናቸው።17በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የተገኘውን ገንዘብ ወደ ውጪ አውጥተው ለተቆጣጣሪዎቹና ለሠራተኞቹ አደራ ሰጥተዋል" በማለት ነገረው። 18ጸሐፊውም ሳፋን ለንጉሡ ፦"ካህኑ ኬልቅያስ አንድ መጽሐፍ ሰጥቶኛል" ብሎ ነገረው። ከዚያም ለንጉሡ አነበበለት። 19ንጉሡ የሕጉን ቃላት በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ።20ንጉሡም ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ ዓብዶንን፥ ጸሐፊውንም ሳፋንን የራሱንም አገልጋይ ዓሳያን፦ 21"ሄዳችሁ ከተገኘው መጽሐፍ ቃል የተነሳ ለእኔና በእስራኤልና በይሁዳ ለተረፉት ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቁ። በእኛ ላይ የፈሰሰው የእግዚአብሔር ቁጣ ታላቅ ስለሆነ፥ በውስጡ የተጻፈውን ሁሉ ለመታዘዝ አባቶቻችን የዚህን መጽሐፍ ቃላት ስላልሰሙ ቁጣው ታላቅ ነው።22በመሆኑም ኬልቅያስና ንጉሡ ያዘዛቸው ሰዎች (በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ትኖር ወደ ነበረችው) ወደ ልብሰ ተክህኖ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ፥ ወደ ቲቁዋ ልጅ፥ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢይቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እንዲህም ብለው አናገሯት።23እርሷም፦"የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፦ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው ንገሩት፥ 24"እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፦ 'እነሆ በይሁዳ ንጉሥ ፊት ባነበቡት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን እርግማን ሁሉ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ ጥፋትን ላመጣ ነው። 25ባደረጓቸው ተግባራት ሁሉ ለቁጣ ሊያነሳሱኝ እኔን ትተው ለሌሎች አማልክት ዕጣንን ከማጠናቸው የተነሳ ስለዚህ ቁጣዬ በዚህ ሥፍራ ላይ ይነድዳል፤ ምንም ነገርም አያቆመውም'" አለቻቸው።26ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ የምትሉት ይህ ነው፦" የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ሰማኸው ቃል፦ 27' ልብህ ለስላሳ ስለ ነበርና በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ እንደሚመጣ የተነገረውን ቃሉን ስትሰማ በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ስላዋረድህ፥ ራስህንም በፊቴ አዋርደህ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ ስላለቀስህ እኔም ሰምቼሃለሁ' እግዚአብሔር የሚናገረው ይህ ነው፤ 28'እነሆ ወደ ዝርያዎችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ የማመጣውን የትኛውንም ጥፋት ዓይኖችህ አያዩም'" በመሆኑም ሰዎቹ ይህንን መልዕክት ለንጉሡ መልሰው ወሰዱለት።29ከዚያም ንጉሡ መልዕክተኞችን ልኮ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ። 30ንጉሡም የይሁዳ ወንዶችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑና ከትልቅ እስከ ትንሽ ሕዝቡ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ። በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ እየሰሙት አነበበላቸው።31ንጉሡም በቦታው ቆሞ እግዚአብሔርን ተከትሎ ለመሄድ፥ ትዕዛዛቱን፥ የቃል ኪዳን ድንጋጌዎቹንና ደንቦቹን ለመጠበቅ፥ በሙሉ ልቡና በሙሉ ነፍሱ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን የቃል ኪዳኑን ቃላት ለመታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ። 32በኢየሩሳሌምና በብንያም የሚገኙትን ሁሉ በቃል ኪዳኑ እንዲቆሙ አደረጋቸው። የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በመታዘዝ አደረጉ።33ኢዮስያስም የእስራኤል ሕዝብ ከነበረው ምድር ላይ አስጸያፊውን ነገር ሁሉ አስወገደ። በእስራኤልም የነበሩት ሰዎች ሁሉ አምላካቸው እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አደረጋቸው። በእርሱ ዘመን ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመከተል ዘወር አላሉም።
1ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር የፋሲካን በዓል አከበረ፤ በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካ ጠቦቶቹን አረዱ። 2ካህናቱን በየሥራ ቦታቸው አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት አበረታታቸው።3እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት ለእግዚአብሔር ለተሰጡት ሌዋውያን ፦ "ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰለሞን በገነባው ቤት ውስጥ አስቀምጡት። ከዚህ በኋላ በትከሻችሁ እየተሸከማችሁ አታዟዙሩት፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ሕዝቡንም እስራኤልን አገልግሉ። 4በእስራኤል ንጉሥ ዳዊት የተጻፈና በልጁም በሰለሞን ጭምር የተሰጠውን መመሪያ በመከተል በየአባቶቻችሁ ቤቶችና በየሥራ ክፍላችሁ ስም ራሳችሁን አደራጁ።5በሕዝቡ ዝርያዎች በወንድሞቻችሁ የአባቶች ቤቶች ውስጥ በየሥራ ክፍላችሁ የኃላፊነት ቦታችሁን በመያዝና በሌዋውያን አባቶች ቤቶች ውስጥ በየሥራ ክፍላችሁ ቦታችሁን በመያዝ በተቀደሰው ሥፍራ ቁሙ። 6የፋሲካውን ጠቦቶች እረዱ፤ እናንተም ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ። ለወንድሞቻችሁ ለእስራኤል ጠቦቶቹን ዝግጁ አድርጉላቸው፤ በሙሴ አማካይነት ለተሰጠው ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ አድርጉት።7ኢዮስያስ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን እዚያ ለነበሩት ሕዝብ ሁሉ ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች ሰጠ። ሦስት ሺህ ወይፈኖችንም ሰጠ፤ እነዚህም የንጉሡ ኃብት ከነበሩት ነበሩ። 8መሪዎቹም ለህዝቡ፥ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የበጎ ፈቃድ ሥጦታዎችን ሰጡ። በእግዚአብሔር ቤት ባለሥልጣናት የነበሩት ኬልቅያስ፥ ዘካርያስና ይሒኤል ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ትንንሽ ከብቶችና ሦስት መቶ በሬዎች ለካህናቱ ሰጡ። 9የሌዋውያኑ አለቆች ኮናንያ፥ ወንድሞቹም ሸማያና ናትናኤል፥ ሐሸቢያ፥ ይዒኤልና ዮዛባት ለፋሲካው መሥዋዕት አምስት ሺህ ትንንሽ ከብቶችና አምስት መቶ በሬዎች ለሌዋውያኑ ሰጡ።10በመሆኑም አገልግሎቱ ዝግጁ ነበረ፤ ካህናቱም ለንጉሡ ትዕዛዝ ምላሽ በመስጠት በየሥራ ክፍላቸው ከሆኑት ከሌዋውያኑ ጋር በየቦታቸው ቆመው ነበር። 11የፋሲካ ጠቦቶቹንም አረዱ፤ ካህናቱም ከሌዋውያኑ እጅ የተቀበሉትን ደም ረጩ፤ ሌዋውያኑም የጠቦቶቹን ቆዳቸውን ገፈፉ። 12በሙሴ መጽሐፍ እንደተጻፈ ለእግዚአብሔር ለማቅረብና በሕዝቡ የአባቶች ቤቶች መሠረት በየሥራ ክፍላቸው ሊያድሏቸው የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለይተው አስቀመጡ። በወይፈኖቹም ላይ እንደዚሁ አደረጉ።13መመሪያዎቹን በመከተል የፋሲካውን ጠቦቶች በእሳት ጠበሷቸው። የተቀደሱትን ሥጦታዎች በምንቸቶች፥ በሰታቴዎችና በመጥበሻዎች ቀቀሏቸው፤ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አዳረሷቸው። 14ከዚያም በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱም መሥዋዕቱን አዘጋጁ፤ የአሮን ልጆች ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን በማቅረብ እስከ ምሽት ድረስ በሥራ ተጠምደው ስለነበር ሌዋውያኑ ለራሳቸውና ለአሮን ልጆች ለካህናቱ መሥዋዕቱን አዘጋጁ።15ዳዊት፥ አሳፍ፥ ኤማንና የንጉሡ ባለ ራዕይ ኤዶታም በሰጡት መመሪያ መሠረት የአሳፍም ዝርያዎች መዘምራኑ በሥፍራቸው ቆመው ነበር። ጠባቂዎቹም በየበሮቹ ላይ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን መሥዋዕቱን ያዘጋጁላቸው ስለነበር የሥራ ቦታቸውን መልቀቅ አያስፈልጋቸውም ነበር።16ስለዚህ ንጉሡ ኢዮስያስ ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ፥ በዚያን ጊዜ መላው የእግዚአብሔር አገልግሎት የፋሲካን በዓል ለማክበር ተፈፀመ። 17በዚያን ቦታ ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ሕዝብ በዚያን ጊዜ ፋሲካውንና ከዚያም ለሰባት ቀናት የቂጣ በዓልን አከበሩ።18ከነቢዩ ከሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ የፋሲካ በዓል በእስራኤል ተከብሮ አያውቅም፤ ከእስራኤልም ሌሎች ነገሥታት ሁሉ የትኛውም ኢዮስያስ ከካህናቱ፥ ከሌዋውያኑና ከይሁዳና እዚያ ከነበሩ ከእስራኤል ሕዝብና ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ጋር እንዳደረገው ያለ ፋሲካ አክብሮ አያውቅም። 19ይህ ፋሲካ የተከበረው ኢዮስያስ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት ነበር።20ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢዮስያስ ቤተ መቅደሱን ካስተካከለ በኋላ የግብጽ ንጉሥ ኒካዑ በኤፍራጥስ ወንዝ ከርከሚሽን ሊዋጋ ወጣ፤ ኢዮስያስም ሊዋጋው ሄደ። 21ኒካዑ ግን ወደ እርሱ ፦" የይሁዳ ንጉሥ ሆይ ካንተ ጋር ምን አለኝ? ጦርነት የምዋጋው በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ ለጦርነት አልመጣሁብህም። እግዚአብሔር እንድፈጥን አዝዞኛል፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር በሆነው በእግዚአብሔር ላይ ጣልቃ አትግባ፤ አለበለዚያ ያጠፋሃል" በማለት መልዕክተኞችን ላከበት።22ነገር ግን ኢዮስያስ ከእርሱ መመለስን እምቢ አለ። ከእርሱ ጋር ለመዋጋት ራሱን በሌላ መልክ ሸፈነ። ከእግዚአብሔር አፍ የመጣውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፤ ስለሆነም በመጊዶ ሸለቆ ውስጥ ሊዋጋ ሄደ።23ቀስተኞችም ንጉሥ ኢዮስያስን ወጉት፤ ንጉሡም ለአገልጋዮቹ፦" ክፉኛ ቆስያለሁና ወደዚያ ውሰዱኝ" አላቸው። 24ስለዚህ አገልጋዮቹ ከሰረገላው አውርደው በሌላኛው ተጨማሪ ሰረገላ ውስጥ አስቀመጡት። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፤ በዚያም ሞተ። በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ። ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱለት።25ኤርምያስም ለኢዮስያስ የሐዘን እንጉርጉሮ አወጣለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ውንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ ስለ ኢዮስያስ የሐዘን እንጉርጉሮ ያወጣሉ። እነዚህ መዝሙሮች በእስራኤል ልማድ ሆኑ፤ እነሆ በሐዘን እንጉርጉሮ መዝሙር ውስጥ ተጽፈዋል።26ኢዮስያስን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮችና በእግዚአብሔር ሕግ ለተጻፈው ነገር በመታዘዝ ያደረጋቸው መልካም ድርጊቶች፥ 27የእርሱ ድርጊቶች ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
1የምድሪቱም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወስደው በአባቱ ቦታ በኢየሩሳሌም አነገሡት። 2ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ።3የግብጽ ንጉሥ ከኢየሩሳሌም ከመንግሥቱ አስወገደው፤ ምድሩንም አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መቶ መክሊት ወርቅ ቅጣት ጣለባት። 4የግብጽ ንጉሥ ወንድሙን ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ንጉሥ አደረገው፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። የኤልያቄምን ወንድሙን ኢዮአክስን ወሰደና ወደ ግብጽ አመጣው።5ኢዮአቄም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ክፉውን ነገር አደረገ። 6ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ጦርነት ከፍቶበት በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው። 7ናቡከደነፆር ከእግዚአብሔር ቤት ዕቃዎችም አንዳንዶቹን ወደ ባቢሎን ወሰደ፤ በባቢሎንም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ አስቀመጣቸው።8ኢዮአቄምን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮችና ያደረጋቸው አስጸያፊ ድርጊቶች፥ በእርሱ ላይ በክፉነት የተያዙበት ድርጊቶች እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል። ልጁም ዮአኪን በእርሱ ቦታ ነገሠ።9ዮአኪን መንገሥ በጀመረ ጊዜ ስምንት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወርና አሥር ቀን ነገሠ። በእግዚአብሔር ፊት ክፉውን ነገር አደረገ። 10በፀደይ ወራት ንጉሥ ናቡከደነፆር ሰዎችን ልኮ ከእግዚአብሔር ቤት ከተወሰዱ የከበሩ ነገሮች ጋር ወደ ባቢሎን አመጣው፤ ዘመዱንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።11ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። 12በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ክፉውን ነገር አደረገ። ከእግዚአብሔርም አፍ በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊት ራሱን አላዋረደም።13ሴዴቅያስም ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር እንዲምል ባደረገው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ አመፀ። ሴዴቅያስ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ላለመመለስ አንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ። 14በተጨማሪም የካህናቱ መሪዎችና ሕዝቡ የሌሎችን ሕዝቦች አስፀያፊ ነገሮች ምሳሌነት በመከተል እጅግ በጣም መተላለፍ አበዙ። እግዚአብሔር ለራሱ በኢየሩሳሌም የቀደሰውን የእግዚአብሔርን ቤት በከሉት።15የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ሥፍራ ከመራራቱ የተነሳ ደግሞ ደጋግሞ በመልዕክተኞቹ በኩል ቃል ይልክላቸው ነበር። 16እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሳ ድረስ፥ መሸሻ መንገድ እስከማይኖር ድረስ የእግዚአብሔርን መልዕክተኞች ይሳለቁባቸው፥ ቃሉንም ያቃልሉና በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።17ስለዚህም እግዚአብሔር የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ወጣቶቻቸውን በሰይፍ ገደላቸው፤ ለወጣቶቻቸው ወይም ለደናግልቱ፥ ለሽማግሌዎች ወይም ለሸበቶዎች አልራራም። እግዚአብሔር ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።18የእግዚአብሔርንም ቤት እቃዎች ሁሉ ትልልቁንም ትንንሹንም የእግዚአብሔርንም ቤት ሃብትና የንጉሡንና የመሪዎቹን ሃብት እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ። 19የእግዚአብሔርን ቤት አቃጠሉ፤ የኢየሩሳሌምን አጥር አፈረሱ፤ ቤተ መንግሥቶቹን ሁሉ አቃጠሉ፤ በውስጧ ያሉትን ውብ ነገሮች ሁሉ አጠፉ።20ከሰይፍም ያመለጡትን ንጉሡ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው። የፋርስ መንግሥት አገዛዝ እስኪደርስ ድረስ ለእርሱና ለልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ። 21ይህ የሆነው ምድሪቱ የሰንበት እረፍትዋን እስክታገኝ ድረስ በነቢዩ በኤርምያስ አፍ የተነገረውን የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈፀም ነው። በዚህ መንገድ ሰባ ዓመት በማሳለፍ ተትታ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ሰንበቷን አከበረች።22በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈፀም በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሳሳ። እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ አስነገረ፤ በጽሑፍም አደረገው። 23"የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ የሚለው ይህ ነው፦ 'የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ለእርሱ ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል። በመካከላችሁ ከእርሱ ሕዝብ መካከል ማንም ቢሆን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም ወደ ምድሪቱ ይውጣ" አለ።
1የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠበት የመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር በኤርምያስ አፍ የተነገረውን ቃሉን ፈጸመና የቂሮስን መንፈስ አነሣሣ። የቂሮስ ድምጽ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ተሰማ። የተነገረውና የተጻፈው እንዲህ የሚል ነው፤ 2"የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፤ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድር መንግሥታትን ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳ ባለች በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዞኛል።3ማንም ከሕዝቡ ጋር የሚመጣ ቢኖር አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣና የኢየሩሳሌም አምላክ ለሆነው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት ይሥራ። 4የሚቀሩት በሚኖሩባቸው በመንግሥቱ በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ ሰዎች ብርና ወርቅ፥ ንብረትና እንስሳ በተጨማሪም በኢየሩሳሌም ላለው የእግዚአብሔር ቤት የበጎ ፈቃድ ቁርባን ይስጡ"።5ከዚያም የይሁዳና የብንያም ነገድ የቤተሰብ አለቆች፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና እንዲሄዱና ቤቱን እንዲሠሩለት እግዚአብሔር መንፈሳቸውን ያነሣሣ ሁሉ ተነሡ። 6በዙሪያቸው ያሉትም ሥራቸውን በብርና ወርቅ ዕቃ፥ በቁሳቁስ፥ በእንስሳ፥ በጠቃሚ ዕቃዎችና በበጎ ፈቃዳቸው በሰጡት መባ አገዟቸው።7ደግሞም ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም አምጥቶ በአማልክቶቹ ቤቶች ያኖራቸውን የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃዎች ንጉሡ ቂሮስ አወጣቸው። 8ቂሮስ በግምጃ ቤቱ ኃላፊ በሚትሪዳጡ እጅ ሰጠ፥ እርሱም ለይሁዳው አለቃ ለሰሳብሳር ቆጥሮ አስረከበው።9ብዛታቸው እንደሚከተለው ነበር፤ ሠላሳ የወርቅ ሳሕን፥ አንድ ሺህ የብር ሳሕን፥ ሃያ ዘጠኝ ሌሎች ሳሕኖች። 10ሠላሳ ጎድጓዳ የወርቅ ሳሕን፥ 410 ትናንሽ ጎድጓዳ የብር ሳሕኖችና ሌሎች አንድ ሺህ ዕቃዎች ነበርሩ። በአጠቃላይ 5400 የብርና የወርቅ ዕቃዎች ነበሩ። 11ምርኮኞቹ ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም በሄዱ ጊዜ እነዚህን ሁሉ ሰሳብሳር አመጣቸው።
1ንጉሡ ናቡከደነፆር ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወዳሉ ወደየከተሞቻቸው የተመለሱት እነዚህ ናችው፤ 2እነርሱም ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ከሬሁምና ከበዓና ጋር መጡ። የሚከተለው የእስራኤል ሰዎች የወንዶቹ ዝርዝር ነው፤3የፋሮስ ተወላጆች 2172። 4የሰፋጥያስ ተወላጆች 372። 5የኤራ ተወላጆች 775። 6በኢያሱና በኢዮአብ በኩል የፊሐት ሞዓብ ተወላጆች 2812።7የኤላም ተወላጆች 1254። 8የዛቱዕ ተወላጆች 945። 9የዘካይ ተወላጆች 760። 10የባኒ ተወላጆች 642።11የቤባይ ተወላጆች 623። 12የዓዝጋድ ተወላጆች 1222። 13የአዶኒቃም ተወላጆች 666። 14የበጉዋይ ተወላጆች 2056።15የዓዲን ተወላጆች 454። 16በሕዝቅያስ በኩል የአጤር ሰዎች 98። 17የቤሳይ ተወላጆች 323። 18የዮራ ተወላጆች 112።19የሐሱም ሰዎች 223። 20የጋቤር ሰዎች 95። 21የቤተልሔም ሰዎች 123። 22የነቶፋ ሰዎች 56።23የዓናቶት ሰዎች 128። 24የዓዝሞት ሰዎች 42። 25የቂርያት ይዓሪም፥ የከፊራና የብኤሮት ሰዎች 743። 26የራማና የጌባ ሰዎች 621።27የማክማስ ሰዎች 122። 28የቤቴልና የጋይ ሰዎች 223። 29የናባው ሰዎች 52። 30የመጌብስ ሰዎች 156።31የሌላው ኤላም ሰዎች 1254። 32የካሪም ሰዎች 320። 33የሎድ፥ የሐዲድና የኦኖም ሰዎች 725።34የኢያሪኮ ሰዎች 345። 35የሴናዓ ሰዎች 3630።36ካህናቱ፤ ከኢያሱ ቤተሰብ የዮዳኤ ተወላጆች 973። 37የኢሜር ተወላጆች 1052። 38የፋስኮር ተወላጆች 1247። 39የካሪም ተወላጆች 1017።40ሌዋውያኑ፤ በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ተወላጆች 74። 41የቤተ መቅደሱ መዘምራን፤ የአሳፍ ተወላጆች 128። 42የበረኞቹ ተወላጆች፤ የሴሎም፥ የአጤር፥ የጤልሞን፥ የዓቁብ፥ የሐጢጣና የሶባይ ተወላጆች በአጠቃላይ 139።43በቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግሉ ተመድበው የነበሩት፤ የሲሐ፥ ሐሡፋ፥ ጠብዖት፥ 44ኬራስ፥ ሲዓ፥ ፋዶን፥ 45ልባና፥ አጋባ፥ ዓቁብ፥ 46አጋብ፥ ሰምላይና ሐናን ተወላጆች፤47የጌዴል፥ ጋሐር፥ ራያ፥ 48ረአሶን፥ ኔቆዳ፥ ጋሴም፥ 49ዖዛ፥ ፋሴሐ፥ ቤሳይ፥ 50አስና፥ ምዑናውያንና ንፉሰሲም ተወላጆች፤51የበቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ 52በስሎት፥ ምሒዳ፥ ሐርሳ፥ 53በርቆስ፥ ሲሣራ፥ ቴማ፥ 54ንስያና ሐጢፋ ተወላጆች።55የሰለሞን አገልጋዮች ተወላጆች፤ የሶጣይ፥ ሶፌሬት፥ ፍሩዳ፥ 56የዕላ፥ ደርቆን፥ ጌዴል፥ 57ሰፋጥያስ፥ ሐጢል፥ ፈክራት፥ ሐፂቦይምና አሚ ተወላጆች። 58በቤተ መቅደስ እንዲያገለግሉ የተመደቡት ተወላጆችና የሰለሞን አገልጋዮች ተወላጆች በድምሩ 392 ነበሩ።59ቴልሜላን፥ ቴላሬሳን፥ ክሩብን፥ አዳንና ኢሜርን ትተው የመጡ፥ ነገር ግን አባቶቻቸው እስራኤላውያን ስለመሆናቸው ማስረዳት ያልቻሉ 60652 የዳላያ፥ የጦብያና የኔቆዳ ተወላጆች ተካተቱ።61የካህናቱ ተወላጆችም፤ የኤብያ፥ የአቆስና የቤርዜሊ (እርሱም ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ሴቶች ሚስት በማግባቱ በስማቸው የተጠራው ነው) ተወላጆች። 62እነዚህ በመዝገቡ ውስጥ የትውልዳቸውን ሐረግ ቢፈልጉም ለማግኘት ስላልቻሉ ከክህነት አገልግሎት ታገዱ። 63በኡሪምና በቱሚም የሚዳኝ ካህን እስኪገኝ ድረስ ከማንኛውም የተቀደሰ መሥዋዕት እንዳይበሉ አስተዳዳሪው አዘዛቸው።64ጠቅላላ ሕዝቡ7337 65ወንድና ሴት አገልጋዮቻቸውን እኔዲሁም 200 ወንድና ሴት የቤተ መቅደስ መዘምራኖቻቸውን ሳይጨምር 42360 ነበር።66736 ፈረሶች፥ 245 በቅሎዎች፥ 67435 ግመሎችና 6720 አህዮች ነበሯቸው።68በኢየሩሳሌም ወዳለው የእግዚአብሔር ቤት በሄዱ ጊዜ የአባቶች አለቆች ለቤቱ መሥሪያ የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻቸውን ሰጡ። 69ለሥራው የሚያስፈልገውን እንደ ችሎታቸው መጠን ሰጡ፤ የሰጡትም ስልሳ አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህ ምናን ብርና አንድ መቶ የክህነት ልብስ ነበር።70ካንናቱና ሌዋውያኑ፥ ሕዝቡ፥ የቤተ መቅደስ መዘምራን፥ በረኞቹና በቤተ መቅደስ እንዲያገለግሉ የተመደቡት በየከተሞቻቸው ተቀመጡ። የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በከተምቻቸው ነበሩ።
1የእስራኤል ሕዝብ በኢየሩሳሌም እንደ አንድ ሰው ሆነው በሚሰበሰቡበት ጊዜ ወደ ከተሞቻቸው ከመጡ ሰባት ወር ሆኗቸው ነበር። 2የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱና ካህናት ወንድሞቹ፥ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ወንድሞቹ ተነሥተው በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደታዘዘው የሚቃጠለው መሥዋዕት የሚቀርብበትን የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።3ከዚያም በምድሪቱ ከሚኖሩ ሰዎች የተነሣ ሥጋት ስለነበረባቸው መሠዊያውን በሥፍራው አቆሙት። የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጠዋትና በማታ ለእግዚአብሔር አቀረቡ። 4ደግሞም የዳሱን በዓል እንደተጻፈው አከበሩ፥ ለየዕለቱ እንደታዘዘው የሚቃጠለውን መሥዋዕት ዕለት በዕለት አቀረቡ። 5እንዲሁም በበጎ ፈቃድ ከሚቀርበው መባ ሁሉ ጋር ለዕለት፥ ለወርና ለተደነገጉት የእግዚአብሔር በዓላት ሁሉ መሥዋዕት ይቀርብ ነበር።6የቤተ መቅደሱ መሠረት ባይጣልም በሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ማቅረብ ጀመሩ። 7እንዲሁም ለድንጋይ ጠራቢዎችና ለአናጺዎች ብር ሰጧቸው፤ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዳዘዘላቸው የዝግባ ዛፎችን ከሊባኖስ በባህር ወደ ኢዮጴ እንዲልኩላቸው ለጢሮስና ለሲዶና ሰዎች ምግብ፥ መጠጥና ዘይት ሰጧቸው።8ከዚያም ዘሩባቤል፥ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩት ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና ከምርኮ ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር ሥራውን ጀመሩ። ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑትን ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ እንዲቆጣጠሩ መደቧቸው። 9ኢያሱም ወንዶች ልጆቹንና ወንድሞቹን፥ ቀድምኤልና ወንዶች ልጆቹን፥ እንዲሁም የይሁዳን ተወላጆች የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ሰዎች ላእንዲቆጣጠሩ ደለደላቸው። ከእነርሱም ጋር የኤንሐዳድ ተወላጆች፥ ደግሞም ተወላጆቻቸውና ባልደረቦቻቸው ሌዋውያን ነበሩ።10ግንበኞቹ የእግዚአብሔርን ቤት መሠረት ጣሉ። ይህ ካህናቱ ልብሰ ተክህኗቸውን ለብሰውና መለከቶችን ይዘው እንዲቆሙና ሌዋውያኑ የአሳፍ ወንዶች ልጆች በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት እጅ እንደታዘዘው በጸናጽል እግዚአብሔርን ለማመስገን አስቻላቸው። 11እነርሱም፥ "ቸር ነው! ለእስራኤልም የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም ነው" እያሉ በምስጋናና በውዳሴ ለእግዚአብሔር ዘመሩ። የቤተ መቅደሱ መሠረት ስለተጣለ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በታላቅ የደስታ ድምጽ እልል አሉ።12ነገር ግን በርካታ ካህናት፥ ሌዋውያን፥ የአባቶች አለቆችና የመጀመሪያውን ቤት ያዩ አዛውንቶች የዚህኛው ቤት መሠረት ሲጣል ባዩ ጊዜ በታላቅ ድምጽ አለቀሱ። ብዙዎቹ ግን የመደነቅና የደስታ ጩኸት ይጮሁ ነበር። 13ሰዎች የደስታውንና የሐሴቱን ድምጽ ክሕዝቡ የልቅሶ ድምጽ ለመለየት አልቻሉም፥ ሕዝቡ በታላቅ ደስታ ይጮኹ ስለነበር ድምጻቸው ከሩቅ ተሰማ።
1አንዳንድ የይሁዳና የብንያም ጠላቶች ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመሥራት ላይ መሆናቸውን ሰሙ። 2እነርሱም ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶቻቸው የነገድ አለቆች መጡ። እነርሱም፥ "እንደናንተው አምላካችሁን እንፈልገዋለንና የአሶር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ስፍራ ካመጣን ጊዜ ጀምሮም ስንሠዋለት ነበርና አብረናችሁ እንሥራ"አሏቸው።3ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የአባቶቻቸው የነገድ አለቆች ግን፥ "የአምላካችንን ቤት መሥራት የሚገባን እኛ እንጂ እናንተ አይደላችሁም፥ የፋርስ ንጉሥ እንዳዘዘው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የምንሠራው እኛ ነን" አሏቸው።4ስለዚህ የምድሩ ሕዝብ የይሁዳን ሰዎች እጅ አደከሙ፤ እንዳይሠሩም የይሁዳን ሰዎች አስፈራሩ። 5ደግሞም ዕቅዳቸውን ለማጨናገፍ ለአማካሪዎች ጉቦ ሰጡ። ይህንንም በቂሮስ ዘመን ሁሉና እስከ ፋርስ ንጉሥ ዳርዮስ እስከ ነገሠበት ጊዜ ድረስ አደረጉ። 6ከዚያም አርጤክስስ መንገሥ በጀመረበት ዘመን በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ነዋሪዎች ላይ ክስ ጻፉባቸው።7በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፥ ሚትሪዳጡ፥ ጣብኤልና ተባባሪዎቻቸው ነበር ለአርጤክስስ የጻፉት። ደብዳቤውም በአረማይስጥ ቋንቋ ተጽፎ የተተረጎመ ነበር። 8አዛዡ ሬሁምና ጸሐፊው ሲምሳይ ስለ ኢየሩሳሌም ለአርጤክስስ እንዲህ ብለው ጻፉ፤9ከዚያም ዳኞች የነበሩት ሬሁም፥ ሲምሳይና ተባባሪዎቻቸው እንዲሁም በአርክ፥ በባቢሎንና በኤላሙ ሱሳ የነበሩ ሌሎች የመንግሥት ኃላፊዎች ደብዳቤውን ጻፉ - 10እነርሱንም ታላቁና ኃያሉ አሹርባኒጳል በወንዙ ማዶ ባለው አውራጃ ከቀሩት ከሌሎቹ ጋር በሰማርያ እንዲሰፍሩ ያስገደዷቸው ሰዎች ደገፏቸው።11ለአርጤክስስ የላኩት የደብዳቤው ግልባጭ ይህ ነው፤ "ይህንን የሚጽፉት ከወንዙ ማዶ ያሉት ሰዎች፥ አገልጋዮችህ ናቸው፤ 12ካንተ ዘንድ የወጡት አይሁድ እኛን በመቃወም አመጸኛይቱን ከተማ በኢየሩሳሌም ውስጥ ለመሥራት መጀመራቸውን ንጉሡ ይወቅ። እነርሱም ቅጥሮቹን ጨርሰው መሠረቶቹን አድሰዋል።13ይህቺ ከተማ ከተሠራችና ቅጥሯም ከተጠናቀቀ ምንም ዓይነት እጅ መንሻና ቀረጥ እንደማይሰጡና ንጉሡን እንደሚጎዱት ንጉሡ ይወቅ።14በርግጥ የቤተመንግሥቱን ጨው ስለ በላን በንጉሡ ላይ ማናቸውም ዓይነት ውርደት ሲደርስበት ማየት አይገባንም። 15ለዚህም ነው የአባትህን መዛግብት እንድትመረምርና ነገሥታትንና አውራጃዎችን የምትጎዳ አመጸኛ ከተማ መሆኗን እንድታረጋግጥ ለንጉሡ ያስታወቅነው። በነገሥታትና በአውራጃዎች ላይ ብዙ ችግር የፈጠረች ነች። ከብዙ ዘመን ጀምሮም የአመጽ ማዕከል ነች። ከተማይቱ ተደምስሳ የነበረችውም በዚሁ ምክንያት ነበር። 16ይህቺ ከተማ ከቅጥሯ ጋር ከተሠራች ከዚህ በኋላ ከታላቁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ምንም የሚቀርልህ ነገር እንደማይኖር ለንጉሡ እናስታውቃለን"።17ስለዚህ ንጉሡ ለሬሁም፥ ሲምሳይ፥ በሰማሪያ ላሉ ተባባሪዎቻቸውና ከወንዙ ማዶ ላሉት ለቀሩት ምላሽ ላከ፤ "ሰላም ይሁንላችሁ። 18የላካችሁልኝ ደብዳቤ ተተርጉሞ ተነቦልኛል። 19በመሆኑም ምርመራ እንዲደረግ አዘዝኩኝና ባለፉት ዘመናት በነገሥታት ላይ ስታምጽ የኖረች አመጸኛ መሆኗ ታውቋል።20በኢየሩሳሌም ላይ ኃያላን ነገሥታት ገዝተዋል፥ ከወንዙ ማዶ ባለው ሁሉ ላይም ሥልጣን ነበራቸው። እጅ መንሻና ቀረጥም ይሰጣቸው ነበር። 21አሁንም እነዚህ ሰዎች ሥራውን እንዲያቆሙና እኔ እስከማዝዝ ድረስ ይህቺን ከተማ እንዳይሠሩ ትዕዛዝ ስጡ። 22ይህንን ማድረጉን ቸል እንዳትሉ ተጠንቀቁ። ነገሥታቱን የሚጎዳው ጥፋት ለምን ይጨምራል?"23የንጉሡ የአርጤክስስ ትዕዛዝ በሬሁም፥ በሲምሳይና በተባባሪዎቻቸው ፊት በተነበበ ጊዜ በፍጥነት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱና አይሁድ ሥራውን እንዲያቆሙ አስገደዷቸው። 24ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ የፋርስ ንጉሥ ዳርዮስ እስከ ነገሠበት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተቋረጠ።
1ከዚያም ነቢዩ ሐጌና የአዶ ልጅ ንቢዩ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ አይሁድ በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩ። 2የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ካደፋፈሯቸው ነቢያት ጋር በመሆን በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔር ቤት መሥራት ጀመሩ።3ከወንዙ ማዶ ያለው አውራጃ አስተዳዳሪ ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው መጥተው፥ "በማን ትዕዛዝ ነው ይህንን ቤት የምትሠሩትና የቅጥሮቹን ጥገና እየጨረሳችሁ ያላችሁት?" አሏቸው። 4ደግሞም፥ "ይህን ሕንፃ የሚሠሩት ሰዎች ስም ማን ማን ነው?" አሏቸው። 5ነገር ግን የእግዚአብሔር ዓይን በአይሁድ አለቆች ላይ ነበር፥ ጠላቶቻቸውም አላስቆሟቸውም። እነርሱም በዚህ ጉዳይ ለንጉሡ ደብዳቤ ለመጻፍና ትዕዛዝ እስኪመጣላቸው ይጠብቁ ነበር።6ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው የሆኑት አለቆች ለንጉሡ ለዳርዮስ የጻፉት ደብዳቤ ይህ ነበር፤ 7እንዲህ ሲሉ ለንጉሡ ዳርዮስ ጻፉለት፤ "ሙሉ ሰላም ለአንተ ይሁን።8ወደ ይሁዳ ወደ ታላቁ አምላክ ቤት ሄደን እንደነበረ ንጉሡ ይወቅ። እርሱም በታላላቅ ድንጋዮች እየተሠራና በቅጥሮቹም መሐል እንጨቶችን እያስገቡበት ነው። ሥራው በትጋት እየተሠራና በእጆቻቸው ላይ በመከናወን ላይ ይገኛል። 9አለቆቹንም፥ "ይህንን ቤትና ቅጥሮቹን እንድትሠሩ የፈቀደላችሁ ማነው?" ብለን ጠየቅናቸው። 10ደግሞም የሚመሯቸውን ሰዎች የእያንዳንዳቸውን ስም ታውቅ ዘንድ ስሞቻቸውን እንዲነግሩን ጠየቅናቸው።11እነርሱም መልሰው፤ "እኛ የሰማይና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙ ዓመታት በፊት ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ የሠራውንና የጨረሰውን ይህንን ቤት በማደስ ላይ ነን።12ይሁንና አባቶቻችን የሰማይን አምላክ ባስቆጡት ጊዜ ይህንን ቤት ባፈረሰውና ሕዝቡን ማርኮ ወደ ባቢሎን በወሰዳቸው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። 13ሆኖም ቂሮስ በባቢሎን ላይ በነገሠ ጊዜ በመጀመሪያው ዓመት የእግዚአብሔር ቤት እንዲሠራ ትዕዛዝ ሰጠ።14ደግሞም ንጉሥ ቂሮስ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በባቢሎን ወደሚገኘው መቅደስ ያመጣቸውን የእግዚአብሔር ቤት መገልገያ የሆኑትን የወርቁንና የብሩን ዕቃዎች መለሰ። አስተዳዳሪ እንዲሆን ለሾመው ለሰሳብሳር አስረከበው። 15እርሱንም፥ "እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ። ሂድና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑራቸው። በዚያም የእግዚአብሔር ቤት ይሠራ" አለው።16ከዚያም ይህ ሰሳብሳር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ የእግዚአብሔርን ቤት መሠረት ጣለ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በመሠራት ላይ ነው፥ ይሁን እንጂ እስካሁን አላለቀም።17አሁንም ንጉሡ መልካም መስሎ ከታየው በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤት እንዲሠራ ንጉሥ ቂሮስ ያዘዘው ትዕዛዝ በባቢሎን መዝገብ ቤት ይገኝ እንደሆን ይመርመር፤ ከዚያም ንጉሡ ውሳኔውን ይላክልን።
1ስለዚህ ንጉሥ ዳርዮስ በባቢሎን ባሉት ቤተ መዛግብት ምርመራ እንዲደረግ አዘዘ። 2በሜዶን አገር ቅጥር ባላት ኤክባታና ከተማ አንድ የመጽሐፍ ጥቅልል ተገኝ፥ ጽሑፉም የሚለው እንዲህ ነበር፤3"ንጉሡ ቂሮስ በነገሠ በመጀመሪያው ዓምት በኢየሩሳሌም ስላለው የእግዚአብሔር ቤት ቂሮስ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ ሰጥቷል፤ የመሥዋዕቱ ቤት ይሠራ። ቅጥሩም ስልሳ ክንድ ከፍታ፥ ስልሳ ክንድ ወርድ ተደርጎ 4በሦስት ዙር ትላልቅ ድንጋዮችና በአንድ ዙር አዲስ እንጨት ይሠራ። ወጪውም በንጉሡ ቤት ይሸፈን። 5ደግሞም ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ወደ ባቢሎን ቤተ መቅደስ ያመጣቸውን የእግዚአብሔር ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች መልሱላቸው። በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ላኩና በዚያ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ይቀመጥ።6አሁንም በወንዙ ማዶ ያላችሁት ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻችሁ ከእነርሱ ራቁ። 7ይህንን የእግዚአብሔር ቤት ሥራ ለእነርሱ ብቻ ተዉሏቸው። ይህንን የእግዚአብሔር ቤት አስተዳዳሪውና የአይሁድ አለቆች በዚያው ሥፍራ ላይ ይሠሩታል።8ለእነዚህ የእግዚአብሔርን ቤት ለሚሠሩት ይህንን እንድታደርጉላቸው አዝዣለሁ፤ ሥራቸውን እንዳያስተጓጉሉ በወንዙ ማዶ ካሉት ለንጉሡ ከሚሰበሰበው ገቢ ላይ ወጪ እየተደረገ ይከፈላቸው። 9ለሰማይ አምላክ ለሚቃጠለው መሥዋዕት የሚፈለገው ሁሉ ወይፈኖችን፥ አውራ በጎችን ወይም ጠቦቶችን እንዲሁም በኢየሩሳሌም ባሉት ካህናት ትዕዛዝ መሠረት ስንዴ፥ ጨው፥ ወይን ወይም ዘይት እነዚህን ነገሮች ሳታቋርጡ በየዕለቱ ስጧቸው። 10ለሰማይ አምላክ መሥዋዕት እንዲያቀርቡና ለእኔ ለንጉሡና ለልጆቼም እንዲጸልዩ ይህንን አድርጉላቸው።11ይህንን ትዕዛዜን የሚተላለፍ ማንም ቢሆን የቤቱ ምሶሶ ተነቅሎ እርሱ እንዲሰቀልበት አዝዣለሁ። በዚህ ምክንያት መኖሪያ ቤቱ የቆሻሻ መጣያ ይሁን። 12በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእግዚአብሔር ቤት ለማፍረስ የሚነሳውን ንጉሥና ሕዝብ በዚያ የሚኖረው አምላክ ያጥፋው። እኔ ዳርዮስ ይህንን አዝዣለሁ። ሙሉ በሙሉ ይፈጸም።13ከዚያም ተንትናይ፥ ሰተር ቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው ንጉሡ ዳርዮስ ያዘዘውን ሁሉ ፈጸሙ። 14ስለዚህ የአይሁድ አለቆች ሐጌና ዘካርያስ በትንቢት በነገሯቸው መሠረት ሥራውን ሠሩ። እነርሱም በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር እና በፋርስ ነገሥታት በቂሮስ፥ በዳርዮስና በአርጤክስስ ትዕዛዝ መሠረት ሠሩ። 15ቤቱም ንጉሡ ዳርዮስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት አዳር በሚባለው ወር በሦስተኛው ቀን ተጠናቀቀ።16የእስራኤል ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና የቀሩት ምርኮኞች የዚህን የእግዚአብሔር ቤት ምረቃ በደስታ አከበሩ። 17እነርሱም ለእግዚአብሔር ቤት ምረቃ አንድ መቶ ወይፈኖችን፥ ሁለት መቶ አውራ በጎችንና አራት መቶ ጠቦቶችን አቀረቡ። ለእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ፥ ለእስራኤል ሁሉ የኃጢአት መሥዋዕት አሥራ ሁለት ወንድ ፍየሎች ቀረቡ። 18ደግምም ካህናቱና ሌዋውያኑ በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በየተራቸው እንዲፈጽሙ ተመደቡ።19እንዲሁም በምርኮ የነበሩት በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል አከበሩ። 20ካህናቱና ሌዋውያኑ ሁሉ ራሳቸውን አነጹና እራሳቸውን ጨምሮ በምርኮ ለነበሩት ሁሉ የፋሲካውን መሥዋዕቶች አረዱ።21የፋሲካውን ሥጋ ከበሉት እስራኤላውያን ውስጥ አንዳንዶቹ ከምርኮ የተመለሱና ራሳቸውን ከሚኖሩበት ምድር ሰዎች እርኩሰት በመለየት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ነበሩ። 22እግዚአብሔር ደስታን ስለ ሰጣቸውና በቤቱ፥ በእስራኤል አምላክ ቤት ሥራ ላይ እጆቻቸውን እንዲያበረቱ የአሶር ነገሥታትን ልብ መልሶላቸው ስለነበረ የቂጣውን በዓል ለሰባት ቀናት በደስታ አከበሩ።
1ከእነዚህ ነገሮች በኋላ በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በትውልዱ የሠራያ፥ ዓዛርያስ፥ ኬልቅያስ፥ 2ሰሎም፥ ሳዶቅ፥ አኪጦብ፥ 3አማርያ፥ ዓዛርያስ፥ መራዮት፥ 4ዘራአያ፥ ኦዚ፥ ቡቂ፥ 5አቢሱ፥ ፊንሐስ፥ አልዓዛር ከዚያም የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ የሆነው ዕዝራ -6ዕዝራ ባቢሎንን ለቆ ወጣ። እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ሕግ በሚገባ የተካነ ጸሐፊ ነበር። የእግዚአብሔር እጅ ከእርሱ ጋር ስለነበረ የጠየቀውን ሁሉ ንጉሡ ሰጠው። 7ደግሞም በንጉሥ አርጤክስስ በሰባተኛው ዓመት አንዳንድ የእስራኤል ተወላጆችና ካህናቱ፥ ሌዋውያን፥ የቤተ መቅደስ መዘምራን፥ በር ጠባቂዎችና በቤተ መቅደስ እንዲያገለግሉ የተመደቡት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።8እርሱም በዚያው ዓመት በአምስተኛው ወር ኢየሩሳሌም ደረሰ። 9በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ባቢሎንን ለቀቀ። መልካሚቱ የእግዚአብሔር እጅ ከእርሱ ጋር ስለነበረ ኢየሩሳሌም የደረሰው በአምስተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ነበር። 10ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ለማጥናት፥ ለመተግበርና ሥርዓትና ትዕዛዙን ለማስተማር ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።11ንጉሡ አርጤክስስ ለካህኑና እግዚአብሔር ለእስራኤል በሰጠው ትዕዛዝና ሥርዓት ጸሐፊና ለሆነው ለዕዝራ የሰጠው ትዕዛዝ ይህ ነበር፤ 12ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ፥ የሰማይ አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለሆነው ለካህኑ ዕዝራ፤ 13በመንግሥቴ ውስጥ እስራኤላዊ የሆነ ማንም ቢሆን ከካህናቶቻቸውና ከሌዋውያኖቻቸው ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚወዱ ካንተ ጋር እንዲሄዱ አዝዣለሁ።14ይሁዳና ኢየሩሳሌምን በሚመለከት በምታውቀው በእግዚአብሔር ሕግ እንድትመረምር፥ 15ለእስራኤል አምላክ በፈቃዳቸው ያቀረቡትን ብርና ወርቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤቱ እንድትወስድ እኔ ንጉሡና ሰባቱ አማካሪዎቼ ልከንሃል። 16ሕዝቡና ካህናቱ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ካቀረቡት በተጨማሪ ባቢሎናዊያን በሙሉ የሰጡትን ወርቅና ብር ሁሉ በነጻ ስጥ።17ስለዚህ በሬዎችን፥ አውራ በጎችንና ጠቦቶችን፥ ስንዴና የመጠጥ ቁርባኑን በርከት አድርገህ ግዛ። በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላክህ ቤት መሠዊያ ላይ ሠዋቸው። 18በቀረው ብርና ወርቅ አምላክህን ለማስደሰት አንተና ወንድሞችህ መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አድርጉበት።19በፈቃደኝነት የተሰጡህን ዕቃዎች በኢየሩሳሌም በሚገኘው በአምላክህ ቤት ለአገልግሎት እንዲሆን በፊቱ አስቀምጥ። 20ለአምላክህ ቤት ያስፈልጋል ብለህ ለምትጠይቀው ለየትኛውም ተጨማሪ ወጪ ገንዘቡን ከግምጃ ቤቴ ውሰድ።21እኔ ንጉሥ አርጤክስስ በወንዙ ማዶ ላላችሁት የግምጃ ቤት ኃላፊዎች በሙሉ፥ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ማናቸውንም ነገር በዛ አድርጋችሁ እንድትሰጡት አዝዣለሁ፥ 22እስከ አንድ መቶ መክሊት ብር፥ አንድ መቶ ቆሮስ ስንዴ፥ አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ ወይንና አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ ዘይት፥ ደግሞም ያለ መጠን የሆነ ጨው ስጡአቸው። 23ከሰማይ አምላክ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ለቤቱ በትጋት አድርጉት። በእኔና በልጆቼ መንግሥት ላይ ቁጣው ለምን ይምጣብን?24በካህናቱ፥ በሌዋውያኑ፥ በሙዚቀኞቹ፥ በበር ጠባቂዎቹ ወይም ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት በተመደቡት ሰዎችና የዚህ አምላክ ቤት አገልጋዮች በሆኑት ላይ ምንም ዓይነት እጅ መንሻም ሆነ ቀረጥ እንዳይጥሉ ስለ እናንተ እናስታውቃቸዋለን።25አንተም ዕዝራ፥ እግዚአብሔር በሰጠህ ጥበብ መሠረት በወንዙ ማዶ ያሉትን ሰዎች ሁሉ እና የአምላክህን ሕግ የሚያውቀውን ማንኛውንም ሰው እንዲያገለግሏቸው ፈራጆችንና አስተዋዮችን ሰዎች መሾም አለብህ። አንተ ደግሞ እነዚያን ሕጉን የማያውቁትን ሰዎች አስተምራቸው። 26የእግዚአብሔርን ሕግ ወይም የንጉሡን ሕግ ሙሉ በሙሉ የማይፈጽመውን ማንኛውንም ሰው በሞት፥ በስደት፥ ንብረቱን በመውረስ ወይም በእስራት ቅጣው።"27ዕዝራም አለ፥ "በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ለማስዋብ ይህንን ሁሉ በንጉሡ ልብ ያኖረና ደግሞም በንጉሡ፥ 28በአማካሪዎቹና በኃያላን አለቆቹ ሁሉ ፊት የቃል ኪዳን ታማኝነቱን በእኔ ላይ ያበዛ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን። በአምላኬ በእግዚአብሔር እጅ በረታሁኝ፥ ከእኔ ጋር እንዲሄዱም የእስራኤልን አለቆች ሰበሰብሁ።
1በንጉሡ አርጤክስስ የንግሥና ዘመን ከእኔ ጋር ከባቢሎን የወጡት የአባቶች ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው፤ 2ከፊንሐስ ተወላጆች ጌርሶን። ከኢታምር ተወላጆች ዳንኤል። ከዳዊት ተወላጆች ሐጡስ። 3ከሴኬንያ ተወላጆች፥ ከፋሮስ ተወላጆች ዘካርያስ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ወንዶች 150 ነበሩ።4ከፋሐት ሞዓብ ተወላጆች የዘራእያ ልጅ ኤሊሆዔናይ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሁለት መቶ ወንዶች ነበሩ። 5ከሴኬንያ ተወላጆች የየሕዚኤል ልጅ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሦስት መቶ ወንዶች ነበሩ። 6ከዓዲን ተወላጆች የዮናታን ልጅ ዔቤድ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሃምሳ ወንዶች ነበሩ። 7ከኤላም ተወላጆች የጎቶልያ ልጅ የሻያ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሰባ ወንዶች ነበሩ።8ከሰፋጥያስ ተወላጆች የሚካኤል ልጅ ዝባድያ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሰማንያ ወንዶች ነበሩ። 9ከኢዮአብ ተወላጆች የይሒኤል ልጅ አብድዩ። ክእርሱ ጋር የተመዘገቡት218 ወንዶች ነበሩ። 10ከሰሎሚት ተወላጆች የዮሲፍያ ልጅ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት 160 ወንዶች ነበሩ። 11ከቤባይ ተወላጆች የቤባይ ልጅ ዘካርያስ። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት ሃያ ስምንት ወንዶች ነበሩ።12ከዓዝጋድ ተወላጆች የሃቃጣን ልጅ ዮሐናን። ከእርሱ ጋር የተመዘገቡት 110 ወንዶች ነበሩ። 13የአዶኒቃም ተወላጆች ዘግይተው መጡ። ስማቸው እንደሚከተለው ነው፤ ኤሊፋላት፥ ይዑኤል፥ ሸማያ። ከእነርሱ ጋር ስልሳ ወንዶች መጡ። 14ከበጉዋይ ተወላጆች ዑታይና ዘቡድ። ከእነርሱ ጋር የተመዘገቡት ሰባ ወንዶች ነበሩ።15ዕዝራም አለ፥ "መንገደኞቹን ወደ አኅዋ በሚወርደው ወንዝ አጠገብ ሰበሰብኋቸው፥ በዚያም ሦስት ቀን ቆየን። ሕዝቡንና ካህናቱን ተመለከትኩ፥ ከሌዊ ተወላጆች ግን በዚያ አንድም አላገኘሁኝም። 16እኔም አለቆች ወደነበሩት ወደ አልዓዛር፥ አርኤል፥ ሸማያ፥ ኤልናታን፥ ያሪብ፥ ኤልናታን፥ ናታን፥ ዘካርያስ፥ ሜሱላምና አስተማሪዎች ወደነበሩት ዮያሪብና ኤልናታን መልዕክት ላክሁ።17በመቀጠልም በካሲፍያ አለቃ ወደ ሆነው ወደ አዶ ላክኋቸው። ለአዶ፥ ለወንድሞቹና በካሲፍያ ለሚኖሩ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ምን ማለት እንዳለባቸው አስታወቅኋቸው፤ ይኸውም ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋዮችን እንዲልኩልን ነበር።18ስለዚህ በመልካሚቱ በእግዚአብሔር እጅ ምክንያት ሰራብያ ተብሎ የሚጠራውን አስተዋይ ሰው ላኩልን። እርሱም ከእስራኤል ልጅ፥ ከሌዊ ልጅ፥ ከሞሖሊ ተወላጆች አንዱ ነበር። እርሱም ከአሥራ ስምንት ወንዶች ልጆቹና ወንድሞቹ ጋር መጣ። 19ሐሸብያም ከእርሱ ጋር መጣ። ደግሞም ከሜራሪ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነው የሻያን ከወንድሞቹና ከወንዶች ልጆቹ ጋር በድምሩ ሃያ ወንዶች ነበሩ። 20በቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግሉ ከተመደቡት ውስጥ ዳዊትና ሹማምንቱ ሌዋውያኑን ለማገልገል የሰጡት 220 ነበሩ፥ እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመደቡ።21ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት ለማዋረድ፥ ለእኛ፥ ለታናናሽ ልጆቻችንና ለንብረታችን ሁሉ መንገዳችንን እንዲያቃናልን በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅኩ። 22ንጉሡን፥ 'የአምላካችን እጅ ለመልካም በሚፈልጉት ሁሉ ላይ ናት፥ ቁጣውና ኃይሉ ግን እርሱን በሚተዉት ሁሉ ላይ ነው' ብለን ስለነበር በመንገድ ላይ ከጠላቶቻችን የሚጠብቁንን ሠራዊት ወይም ፈረሰኞችን እንዲሰጠን ንጉሡን ለመጠየቅ አፈርኩኝ። 23ስለዚህ በእግዚአብሔ ፊት ጾምንና ጸለይን፥ ስለዚህም ጉዳይ ለመንነው።24ከዚያም ከካህናቱ ዋና ዋናዎቹን ሰራብያን፥ ሐሸቢያንና አሥር ወንድሞቻቸውን፥ አሥራ ሁለት ሰዎች መረጥኩ። 25ንጉሡ፥ አማካሪዎቹ፥ አለቆቹና በዚያ የነበሩ እስራኤል ሁሉ ለእግዚአብሔር ቤት በፈቃዳቸው ያቀረቡትን ብር፥ ወርቅ፥ ቁሳቁስና መባ መዝኜ ሰጠዃቸው።26ስለዚህ 650 መክሊት ብር፥ አንድ መቶ መክሊት የብር ዕቃዎች፥ አንድ መቶ መክሊት ወርቅ፥ አንድ ሺህ ዳሪክ የሚያወጡ 27ሃያ ጎድጓዳ የወርቅ ሳሕኖች፥ የወርቅ ያህል የከበሩ ሁለት አብረቅራቂ የነሐስ ዕቃዎች መዝኜ በእጃቸው ሰጠኋቸው።28ከዚያም እንዲህ አልኳቸው፥ 'እናንተና እነዚህ ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ተቀድሳችኋል። ይህ ብርና ወርቅ ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር በፈቃደኝነት የቀረበ መባ ነው። 29በካህናቱ ኃላፊዎች፥ በሌዋውያኑና በእስራኤል የነገድ አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት ክፍሎች ውስጥ እስክትመዝኑት ድረስ በጥንቃቄ ጠብቁት። 30ካህናቱና ሌዋውያኑ የተመዘነውን ብር፥ ወርቅና ቁሳቁስ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ አምላካችን ቤት ለመውሰድ ተረከቡት።31በመጀመሪያው ወር በአሥራ ሁለተኛው ቀን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ከአኅዋ ወንዝ አጠገብ ተነሣን። የአምላካችን እጅ በእኛ ላይ ነበረች፤ እርሱም ከጠላቶቻችን እጅና በመንገድ ላይ አድፍጠው ሊያጠቁን ከፈለጉት አዳነን። 32ወደ ኢየሩሳሌም ደርስንና ሦስት ቀን በዚያ ቆየን።33ከዚያም በአራተኛው ቀን ብሩ፥ ወርቁና ቁሳቁሱ በአምላካችን ቤት ውስጥ በካህኑ በኦርዮ ልጅ በሜሪሞት እጅ ተመዝነው ተሰጡ። የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፥ ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ከእርሱ ጋር ነበሩ። 34የሁሉም ነገር ቁጥሩና ክብደቱ ታወቀ፤ በዚያኑ ጊዜም ጠቅላላ የክብደቱ መጠን ተጻፈ።35ተማርከው የነበሩት፥ ከምርኮም የተመለሱት ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ ለእስራኤል ሁሉ አሥራ ሁለት ወይፈኖችን፥ ዘጠና ስድስት አውራ በጎችን፥ ሰባ ሰባት ጠቦቶችንና ለኃጢአት መሥዋዕት አሥራ ሁለት አውራ ፍየሎችን አቀረቡ። ሁሉም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበር። 36ከዚያም የንጉሡን ትዕዛዝ በወንዙ ማዶ ላሉት የንጉሡ ሹማምንትና አስተዳዳሪዎች ሰጧቸው፥ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት አገዙ።
1"እነዚህ ነገሮች በተደረጉ ጊዜ አለቆቹ ወደ እኔ መጥተው፥ 'የእስራአል ሕዝብ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ራሳቸውን ከሌላው ምድር ሕዝብ፤ ከከነዓናውያን፥ ኬጢያውያን፥ ፌርዛውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞናውያን፥ ሞዓባውያን፥ ግብፃውያንና አሞራውያን እና ከርኩሰቶቻቸው አልለዩም። 2ከወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ጋር በመጋባት ቅዱሱን ሕዝብ ከሌላው ምድር ሕዝብ ጋር ደባልቀዋል። በዚህ እምነት የለሽነት ቀዳሚዎቹ ሹማምንቱና አለቆቹ ናቸው።'3ይህንን በሰማሁ ጊዜ፥ ልብሴንና ካባዬን ቀደድሁ፥ ከራሴና ከፂሜም ላይ ፀጉሬን ነጨሁ። አፍሬም ተቀመጥኩ። 4ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ቃል የተነሣ ስለዚህ እምነት የለሽነት በፍርሃት የተንቀጠቀጡ ሁሉ እስከ ምሽቱ መሥዋዕት ማቅረቢያ ጊዜ ድረስ በእፍረት ተቀምጬ ሳለሁ ወደ እኔ መጡ።5የምሽት መሥዋዕት በማቅረቢያ ጊዜ ግን የተቀደደ ልብሴንና ካባዬን ለብሼ በእፍረት ከተቀመጥኩበት ተነሣሁ፥ ተንበርክኬም እጆቼን ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ዘረጋሁ። 6እንዲህም አልኩ፥ 'አምላኬ ሆይ፥ ኃጢአታችን በራሳችን ላይ በዝቷል፥ በደላችንም እስከ ሰማያት ደርሷልና ፊቴን ወደ አንተ ለማቅናት እፈራለሁ፥ እጅግም አፍራለሁ።7ከአባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በታላቅ በደል ውስጥ አለን። ዛሬ እንደሆነብን ሁሉ በበደላችን ምክንያት ነገሥታቶቻችንና ካህናቶቻችን በዚህ ዓለም መንግሥታት እጅ ለሰይፍ፥ ለምርኮ፥ ለመበዝበዝና ለእፍረት ፊት ተሰጡ።8አሁንም ገና ለጥቂት ጊዜ የተረፍነው እኛ ጥቂቶቹ በሕይወት እንድንኖርና በዚህም ቅዱስ ሥፍራ የእግር መቆናጠጫ ሊሰጠን ከእግዚአብሔር ከአምላካችን ቸርነት መጥቶልናል። ዓይኖቻችንን ለማብራትና በባርነት እያለን ጥቂት እረፍት ሊሰጠን ይህ የአምላካችን ሥራ ነበር። 9ባሪያዎች ነንና፥ አምላካችን ግን የቃል ኪዳን ታማኝነቱን ለእኛም አስረዘመልን እንጂ አልረሳንም። ፍርስራሹን እንድናነሣና የአምላካችንን ቤት እንደገና መሥራት እንድንችል አዲስ ጉልበት ሊሰጠን በፋርስ ንጉሥ ፊት ይህንን አድርጓል። በኢየሩሳሌምና በይሁዳ የመከላከያ ቅጥር ሊሰጠን ይህንን አደረገ።10አሁን ግን አምላካችን ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ምን ማለት እንችላለን? ትዕዛዝህን እረስተናል፥ 11የረሳነውም፤ "ልትወርሷት የምትገቡባት ይህቺ ምድር የረከሰች ምድር ናት። በምድሪቱ በሚኖሩት ሰዎች እርኩሰት ረክሳለች። ከአንደኛው ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ በእርኩሰታቸው ሞልተዋታል። 12አሁንም፥ እንድትበረቱና የምድሪቱን ፍሬ እንድትበሉ፥ ለልጆቻችሁም ለዘላለም እንድታወርሷቸው ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ለወንዶች ልጆቻችሁም ሴቶች ልጆቻቸውን አትውሰዱ፥ ሰላምና ደኅንነታቸው እንዲቀጥልም አትፈልጉ ብለህ ለአገልጋዮችህ ለነቢያት የሰጠኸውን ትዕዛዝ ነው።"13ይሁን እንጂ በክፉ ሥራችንና በብዙ በደላችን ምክንያት ከደረሱብን ነገሮች በኋላ አንተ አምላካችን ለኃጢአታችን የሚገባውን ተውክልንና የተረፍነውን በሕይወት እንድንኖር ፈቀድክ። 14ታዲያ እንደገና ትዕዛዝህን መጣስና ከእነዚህ ከረከሱ ሕዝቦች ጋር በጋብቻ መደባለቅ ነበረብን? አንተስ አንድም የሚቀር ወይም የሚያመልጥ እስከማይኖር ድረስ ታጠፋን ዘንድ ልትቆጣን አይገባህምን?15የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ እኛም ጥቂቶች ተርፈን በሕይወት አለን። እነሆ፥ ከበደላችን ጋር በፊትህ ነን፥ ከዚህ የተነሣ በፊትህ ለመቆም የሚችል ማንም የለም።"
1ዕዝራ እየጸለየና እየተናዘዘ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ተደፍቶ አለቀሰ። ወንዶች፥ ሴቶችና ልጆች ያሉበት እጅግ ታላቅ የእስራኤል ጉባዔ በዙሪያው ተሰበሰቡ፥ ሕዝቡም ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ። 2የኤላም ተወላጅ የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፥ "እኛ ራሳችን በአምላካችን ላይ ክህደት ፈጽመናል፥ ከሌላ ምድር ሰዎችም ሚስቶችን አግብተናል። ይሁን እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ።3አሁንም ጌታዬና የአምላካችንን ትዕዛዝ የሚፈሩት በምትሰጡን መመሪያ መሠረት ሴቶቹን ሁሉ ከልጆቻቸው ጋር ለማሰናበት ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እናድርግ፥ ይህም በሕጉ መሠረት ይፈጸም። 4ይህ አንተ ልታደርገው የሚገባህ ጉዳይ ነውና ተነሥ፥ እኛም አብረንህ ነን። በርታና አድርገው።5ዕዝራ ተነሣና የካህናቱን ዋነኞች፥ ሌዋውያኑንና እስራኤላውያኑን በሙሉ በዚሁ መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቃል አስገባቸው። እነርሱም ቃል ገቡ። 6ከዚያም ዕዝራ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ክፍል ገባ። በምርኮ የነበሩት እምነት የለሽ ስለመሆናቸው ያለቅስ ነበርና ምንም ዓይነት ምግብ አልተመገበም አንዳች ውሃም አልጠጣም ነበር።7በይሁዳና በኢየሩሳሌም የሚገኙ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ መልዕክት ላኩ። 8በሦስት ቀን ውስጥ የማይመጣ ማንም ቢኖር በሹማምንቱና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሠረት ንብረቱ ይወረሳል፥ እርሱም ከምርኮ ከተመለስው ታላቅ የሕዝብ ጉባዔ ይለያል።9ስለዚህ የይሁዳና የብንያም ሰዎች በሙሉ በሦስት ቀናት ውስጥ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ይህም የሆነው በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሃያኛው ቀን ነበር። ሕዝቡ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆመው ነበር፥ ከሚሰሙት ቃልና ከዝናቡ የተነሣም ይንቀጠቀጡ ነበር። 10ካህኑ ዕዝራም ተነሥቶ እንዲህ አለ፥"እናንተ ራሳችሁ ክህደት ፈጽማችኋል። የእስራኤልን በደል ለማብዛት ባዕዳን ሴቶችን አግብታችኋል።11አሁን ግን ለአባቶቻችሁ አምላክ ክብርን ስጡ፥ ፈቃዱንም አድርጉ። ከምድሩ ሰዎችና ከባዕዳን ሴቶች ተለዩ።"12ጉባዔውም ሁሉ በታላቅ ድምጽ፥ "እንደ ተናገርከው እናደርጋለን። 13ይሁንና ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ወቅቱም የዝናብ ጊዜ ነው። እንዲህ ሜዳው ላይ ለመቆም አቅም የለንም፥ በዚህ ጉዳይ እጅግ ተላልፈናልና ሥራው የአንድ ወይም የሁለት ቀን ብቻ አይደለም።14ስለዚህ ሹማምንቶቻችን ጉባዔውን በሙሉ ይወክሉ። የአምላካችን ብርቱ ቁጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ ባዕዳን ሴቶች በከተሞቻችን እንዲኖሩ የፈቀዱ ሁሉ የከተማው ሽማግሌዎችና የከተማው ዳኞች በሚወስኑት ቀን ይምጡ።" 15የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ይህንን ሃሳብ ተቃወሙ፥ ሌዋውያኑ ሜሱላምና ሳባታይም ደገፉአቸው።16ስለዚህ ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች እንዲህ አደረጉ። ካህኑ ዕዝራም ከነገድ አባቶችና ከቤተሰቡ መሪዎች የሚሆኑ ሰዎችን ሁሉንም በየስማቸው መረጠ፥ እነርሱም በዘጠነኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጉዳዩን መመልከት ጀመሩ። 17በመጀመሪያው ወር የመጀመሪያው ቀን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡት እነማን እንደሆኑ ምርመራቸውን ጨረሱ።18ከካህናቱ ወገን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ነበሩ። ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱና ከወንድሞቹ ተወላጆች መካከል መዕሤያ፥ አልዓዛር፥ ያሪብና ጎዶልያስ። እነዚህ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ወሰኑ። 19በደለኞች ነበሩና ከመንጋዎቻቸው ስለ በደል መሥዋዕት አንዳንድ አውራ በግ አቀረቡ።20ከኢሜር ተወላጆች አናኒና ዝባድያ። 21ከካሪም ተወላጆች መዕሤያ፥ ኤልያስ፥ ሸማያ፥ ይሒኤልና ዖዝያ። 22ከፋስኩር ተወላጆች ኤልዮዔናይ፥ መዕሤያ፥ ይስማኤል፥ ናትናኤል፥ ዮዛባትና ኤልዓሣ።23ከሌዋውያኑ መካከል፤ ዮዛባት፥ ሰሜኢ፥ ቆሊጣስ የሚባለው ቆልያ፥ ፈታያ፥ ይሁዳና አልዓዛር። 24ከመዘምራኑ መካከል፤ ኤልያሴብ። በር ከሚጠብቁት መካከል፤ ሰሎም፥ ጤሌምና ኡሪ። 25ከተቀሩት እስራኤላውያን መካከል፤ ከፋሮስ ተወላጆች መካከል፥ ራምያ፥ ይዝያ፥ መልክያ፥ ሚያሚን፥ አልዓዛር፥ መልክያና በናያስ።26ከኤላም ተወላጆች መካከል፤ ሙታንያ፥ ዘካርያስ፥ ይሒኤል፥ አብዲ፥ ይሬሞትና ኤልያ። 27ከዛቱዕ ተወላጆች መካከል ዔሊዮዔናይ፥ ኢልያሴብ፥ ሙታንያ፥ ይሬሞት፥ ዛባድና ዓዚዛ። 28ከቤባይ ተወላጆች መካከል፤ ይሆሐናን፥ ሐናንያ፥ ዘባይና አጥላይ። 29ከባኒ ተወላጆች መካከል፤ ሜሱላም፥ መሉክ፥ ዓዳያ፥ ያሱብና ሸዓል ራሞት።30ከፈሐት ሞዓብ ተወላጆች መካከል፤ ዓድና፥ ክላል፥ በናያስ፥ መዕሤያ፥ ሙታንያ፥ ባስልኤል፥ ቢንዊና ምናሴ። 31ከካሪም ተወላጆች መካከል፤ አልዓዛር፥ ይሺያ፥ መልክያ፥ ሸማያ፥ ስምዖን፥ 32ብንያም፥ መሉክና ሰማራያ።33ከሐሱም ተወላጆች መካከል መትናይ፥ መተታ፥ ዛባድ፥ ኤሊፋላት፥ ይሬማይ፥ ምናሴና ሰሜኢ። 34ከባኒ ተወላጆች መካከል፤ መዕዳይ፥ ዓምራም፥ ኡኤል፥ 35በናያስ፥ ቤድያ፥ ኬልቅያ፥ 36ወንያ፥ ሜሪሞት፥ ኤሌያሴብ፥37መታንያ፥ መትናይ፥ የዕሡ፥ 38ባኒ፥ ቢንዊ፥ ሰሜኢ፥ 39ሰሌምያ፥ ናታን፥ ዓዳያ፥ 40መክነድባይ፥ ሴሴይ፥ ሸራይ፥41ኤዝርኤል፥ ሰምምያ፥ ሰማራያ፥ 42ሰሎም፥ አማርያና ዮሴፍ። 43ከናባው ተወላጆች መካከል፤ ይዔኤል፥ መቲትያ፥ ዛባድ፥ ዘቢና፥ ያዳይ፥ ኢዮኤልና በናያስ። 44እነዚህ ሁሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡና አንዳንዶቹም ከእነርሱ የወለዱ ነበሩ።
1እኔ የሐካልያ ልጅ ነህምያ ነኝ፡፡ ንጉስ አርጤክስስ የፋርስን መንግስት መግዛት በጀመረበት በሃያኛው አመት፣ ካሴሉ በተባለው ወር፤ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሼ ያደረግሁትን ይህን ነገር ጻፍሁ፡፡ እኔም በፋርስ ዋና ከተማ በሱሳ ነበርሁ፡፡2ወንድሜ አናኒ እኔን ለማየት መጣ፡፡ እርሱና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ከይሁዳ መጥተው ነበር፡፡ ከባቢሎን ምርኮ ስላመለጡ ጥቂት አይሁዶች፣ እና ስለ ኢየሩሳሌም ከተማ ጥያቄዎችን ጠየቅኳቸው፡፡3እነርሱም እንዲህ አሉኝ፣ “ከምርኮ ያመለጡት አይሁዶች በዚያ በታላቅ መከራ እና ውርደት እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ የከተማዋ ቅጥሮች በብዙ ስፍራዎች ተገፍተው ስለወደቁ ጠላት በቀላሉ ይገባባታል፣ ይህም ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን የከተማዋ በሮች ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥለዋል፡፡”4ይህንን በሰማሁ ጊዜ፣ ተቀምጬ አለቀስኩ፡፡ ለብዙ ቀናት በሰማይ ወዳለው አምላክ በለቅሶ ጾምኩ ጸለይኩ፡፡ 5እንዲህ ስል ጸለይኩ፣ “ያህዌ፣ አንተ በሰማይ ያለህ አምላክ ነህ፡፡ አንተ ታላቅና አስደናቂ አምላክ ነህ፣ ለሚወዱህና ህግጋትህንና ትዕዛዛትህን ለሚጠብቁ ሁሉ የተቀደሰውን አብሮነትህንና ቃልኪዳንህን ትጠብቃለህ፡፡6እባክህ አሁን ወደ እኔ ተመልከት ወደ ጸሎቴም አድምጥ፡፡ በቀንና በለሊት ለህዝብህ ለእስራኤል እጸልያለሁ፡፡ ኃጢአት መስራታችንን እናዘዛለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቤ ጭምር አንተን በድለናል፡፡ 7በጣም ክፉ አድርገናል፡፡ ከብዙ አመታት አስቀድሞ ባሪያህ ሙሴ አንተ እናደርገው ዘንድ ያዘዝከውን ህግጋትና ስርዓቶች ሰጥቶናል፣ እኛ ግን ህግጋትህን አልጠበቅንም፡፡8እባክህ ለአገልጋይህ ለሙሴ የተናገርከውን አስብ፡፡ እንዲህ ብለሃል፣ ‘በፊቴ በታማኝነት እና በመታዘዝ ባትመላለሱ በአገራት መሃል እበትናችኋለሁ፡፡ 9ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ እና ትዕዛዞቼን ብትጠብቁ፣ ወደ ሩቅ ሥፍራዎች ብትጋዙም እንኳን፣ ሁላችሁንም ሰብስቤ የእኔን ታላቅነትና ክብር ወደማሳያችሁ ወደዚህ ስፍራ እመልሳችኋለሁ፡፡10እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን፡፡ በታላቁ ሀይልህ ከባርነት ነጻ ያወጣኸን ህዝብ ነን፡፡ አንተ ያንን ያደረግከው ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ ማድረግ ስለምትችል ነው፡፡ 11ያህዌ፣እባክህ የእኔን የአገልጋይህን ፀሎት ስማ፡፡ እባክህ በማንነትህና በስራህ አንተን ሲያከብሩ፣ ታላቅ ሀሴት የሚያደርጉትን የህዝብህን ሁሉ ጸሎት ስማ፡፡ ወደ ንጉሱ ፊት ስቀርብ መከናወንን እንድትሰጠኝ እጸልያለሁ፤ ለንጉሱ ጥያቄዬን ሳቀርብ ህይወቴ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ ጠብቃት፡፡ ምህረትህ ይከተለኝ፡፡” እኔ ለንጉሱ እጅግ ከታመኑት አገልጋዮች አንዱ ሆኜ አገለግል ነበር፡፡
1በንጉስ አርጤክስ፣ አገዛዝ ሃያኛ ዓመት፣ ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር፣ በክብረ በዓሉ ለንጉሱ ወይን ጠጅ የሚቀርብበት ሰዓት ነበር፡፡ ወይን ወስጄ ለንጉሱ አቀረብኩ፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በንጉሱ ፊት እንዲህ አዝኜ ቀርቤ አላውቅም ነበር፡፡2በዚያን ቀን ግን፣ ንጉሱ እኔን ተመልክቶ እንዲህ አለኝ፣ “ለምን እንዲህ እጅግ አዘንህ? የታመምክ አትመስልም፡፡ ምናልባት መንፈስህ ታውኮ ይሆንን?” እኔም በጣም ፈርቼ ነበር፡፡3እንዲህ ስል መለስኩ፣ “ንጉስ ሆይ፣ ለዘለዓለም ንገስ! ያዘንኩት ያለ ምክንያት አይደለም፣ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፍርስራሽ ሆናለች፣ በከተማዋ ዙሪያ ያሉ በሮቿ በሙሉ ተቃጥለው አመድ ሆነዋል፡፡”4ንጉሱ እንዲህ ሲል መለሰልኝ፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” እናም ለእርሱ መልስ ከመስጠቴ አስቀድሞ፣ በሰማይ ወዳለው አምላክ ጸለይኩ፡፡5ከዚያ እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠሁ፣ “ታደርገው ዘንድ ፈቃድህ ከሆነ፣ እኔም አንተን ደስ አሰኝቼ ከሆነ፣ አባቶቼ የተቀበሩባትን ከተማ ኢየሩሳሌምን መልሼ እንድገነባ ወደዚያ እንድሄድ ፈቀድልኝ፡፡” 6ንጉሱ (ንገስቲቱ አጠገቡ ተቀምጣ ሳለ) እንደህ ሲል ጠየቀኝ፣ “እንድትሄድ ብፈቅድልህ፣ ለስንት ጊዜ በዚያ ትቆያለህ? ደግሞስ መቼ ትመለሳለህ?” እርሱም፣ ወደዚያ የምሄድበትንና ተመልሼ የምመጣበትን ቀን እንዳሳወቅሁት፣ ወዲያውኑ እንድሄድ ፈቃድ ሰጠኝ፡፡7 ደግሞም ለንጉሱ እንዲህ አልኩት፣ “ለአንተ ለሰጠሁት ታማኝ አገልግሎቴ እንደ ሽልማት አድርገህ፣ ከአፍራጦስ ወንዝ ባሻገር ለሚያስተዳድሩ ገዥዎች ደብዳቤ ስጠኝ፡፡ ወደ ይሁዳ ስገባና ስወጣ በግዛቶቻቸው በደህንነት መጓዝ እችል ዘንድ እንዲፈቅዱልኝ እባክህን ትዕዛዝ ስጣቸው፡፡ 8 እንዲሁም፣ እባክህን ደኖችህን ለሚያስተዳድረው ለአሳፍ ደብዳቤ ፃፍልኝ፣ ደግሞም በቤተ መቅደሱ አጠገብ የሚገኘውን ግንብ በሮች አምዶቹን ለማበጀት፣ የከተማዋን ቅሮች ለመጠገን፣ እና የምኖርበትን ቤት እንዲሰጠኝ ፃፍለት፡፡” እግዚአብሔር ለዚህ ስራ የሚያስፈልገኝን እንዳገኝ እየረዳኝ ስለነበር፣ ንጉሱ እንዲያደርግ የጠየቅኩትን አደረገልኝ ፡፡9ወደ ይሁዳ ለመሄድ ተነሳሁ፡፡ ንጉሱ፣ እኔን እንዲያጅቡኝና እንዲጠብቁኝ አንዳንድ ፈረሰኛ የጦር መኮንኖችንና ወታደሮችን ላከ ፡፡ ገዥዎቹ ወደሚያስተዳድሩት ግዛት ስንደርስ፣ ከንጉሱ ዘንድ የተላከውን ደብዳቤ ሰጠኋቸው፡፡10ነገር ግን ሁለቱ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ሖሮናዊው ሰንበላጥና አሞራዊው አገልጋይ ጦቢያ፣ እኔ መድረሴን ሲሰሙ የእስራኤልን ህዝብ የሚረዳ በመምጣቱ በጣም ተቆጡ፡፡11ስለዚህም እኔ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቼ በዚያ ለሶስት ቀናት ቆየሁ፡፡ 12በምሽት ከከተማ ወጣሁ፣ ከእኔ ጋርም ጥቂት ሰዎች ነበሩ፡፡ እኛ የነበረን እኔ የተቀመጥኩበት አንድ እንስሳ ብቻ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ እግዚአብሔር በልቤ ስላስቀመጠው ነገር ለማንም ሰው ምንም አልተናገርኩም፡፡13በሸለቆው መግቢያ አለፍኩና ከከተማው ቅጥር ውጭ ሄድኩ፡፡ ከዚያ በከተማዋ ዙሪያ ተዟዙሬ የቀበሮዎች ጉድጓድ በሚባለው ጉድጓድ በኩል አለፍኩ፡፡ ከዚያ ወደ ፋንድያ መድፊያ በር አለፍኩ፡፡ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የሚገኙ ቅጥሮችን ሁሉ ዞሬ ተመለከትኩ፣ እናም ሁሉም በሮች ተሰባብረው ቅጥሮቹ ክፍት መሆናቸውን አየሁ፣ ደግሞም በቅጥሩ ዙሪያ የነበሩ የእንጨት በሮች ሁሉ አመድ እስኪሆኑ ተቃጥለው ነበር፡፡ 14ከዚያ ወደ ፏፏቴ በር እና የንጉስ ገንዳ ወደሚባለው ገንዳ ሄድኩ፣ ነገር ግን የተቀመጥኩበት አህያ በጠባቡ መተላለፊያ ማለፍ አልቻለችም፡፡15ስለዚህ ወደ ኋላ ዞሬ ወደ በቄድሮን ሸለቆ አጠገብ እያለፍኩ ወደ ኋላ ከመመለሴና ወደ ሸለቆው በር ወደ ከተማዋ ከመግባቴ አስቀድሞ በዚያ የነበሩ ቅጥሮችን ተመለከትኩ፡፡16የከተማዋ ባለስልጣናት እኔ ወዴት እንደሄድኩ ወይም ምን እንዳደረግኩ አላወቁም ነበር፡፡ ለአይሁድ መሪዎች ወይም ለባለስልጣናቱ ወይም ለካህናቱ ወይም በእድሳቱ ስራ ለሚሳተፉ ለማናቸው ሌሎች ሰዎች ስለዚህ ምንም ነገር አልተናገርኩም፡፡17እንዲህ አልኩ፣ “በከተማችን ላይ የደረሰውን መጥፎ ነገሮች ሁሉ ሁላችሁም በሚገባ ታውቃላችሁ፡፡ ከተማዋ ፍርስራሽ ሆናለች፣ ሌላው ቀርቶ በሮቿ ተቃጥለው ወድቀዋል፡፡ ኑ፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደገና ለመገንባት ስራውን እንጀምር፡፡ እኛ ያንን ብናደርግ፣ ከዚህ በኋላ በከተማችን አናፍርም፡፡” 18ከዚያ ከንጉሱ ጋር በተነጋገርኩ ጊዜ እግዚአብሔር እንዴት በመልካምነቱ እንዲረዳንና ንጉሱ ምን እንዳለኝ ነገርኳቸው፡፡ እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ተነስተን የእድሳቱን ስራ እንጀምር!” ስለዚህም ይህን መልካም ሥራ ለመስራት ተነሱ፡፡19ነገር ግን ሰንበላጥ፣ አሞናዊው አገልጋይ ጦቢያ፣ እና አረባዊው ጌሻም፣ እኛ ለመስራት ያቀድነውን ሰሙ፡፡ በእኛ ላይ ቀለዱ አፌዙብንም፡፤ እንዲህም አሉ፣ “ይህ እናንተ የምትሰሩት ስራ ምንድን ነው? በንጉሱ ላይ እያመጻችሁ ነውን?”20እኔ ግን እንዲህ አልኳቸው፣ “በሰማይ ያለው አምላክ ስኬት ይሰጠናል፡፡ እናንተ ግን በዚህ ከተማ ላይ መብት የላችሁም፣ ተሳትፎ የላችም፣ በዚህ ላይ ህጋዊ መብት የላችሁም፣ በኢየሩሳሌም ከተማ ላይ ምንም ታሪካዊ መታሰቢያ የላችሁም፡፡”
1ከዚያ የእስራኤል ሊቀ ካህን የሆነው ኤልያብ፣ ከሌሎች ካህናት ጋር የበጎች በር የተባለውን እንደገና ሰሩ፡፡ ይህንንም ለያህዌ ክብር ለዩት፣ እናም የመግቢያውን በሮች በስፍራው አቆሙ ቀጥሎ ቅጥሩን የመቶ ማማ እስከሚባለው ድረስ መልሰው ገነቡ፣ እናም ያህዌን ለማክበር ለዩት፡፡ እንዲሁም የሐንኤልን ማማ መልሰው ገነቡ፡፡ 2ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የኢያሪኮ ሰዎች መልሰው ይገነቡ ነበር፡፡ ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የአምሪ ልጅ ዘኩር መልሶ ይገነባ ነበር፡፡3የአሳ በር የሚባለውን የሃስና ልጆች ገነቡት፡፡ እነርሱ የእንጨት አምዶቹን ከመግቢያዎቹ በላይ አጋደሙ፣ ደግሞም በሮቹን በስፍራቸው አኖሩ፡፡ ከዚያ ጠንካራ ቁልፍ እንዲኖር መቀርቀሪያ እና መወርወሪያዎችን አበጁ፡፡ 4ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የአቆስ የልጅ ልጅ፣ የአርዮ ልጅ የሆነው ሜርሞት ቅጥሮቹን ለማጠናከር ጠገናቸው፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሜሴዜቤል የልጅ ልጅ፣ የበራክየ ልጅ የሆነው ሜሱላም የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ የበዓና ልጅ ሳዶቅ የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፡፡ 5ከእርሱ ቀጥሎ፣ የተቁሖ ሰዎች ቅጥሩን በከፊል ጠገኑ፣ ነገር ግን የቴቁ መሪዎች አሰሪዎቻቸው እንዲሰሩ የሰጣቸውን ለመስራት አልፈለጉም፡፡6የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄ እና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም አሮጌውን መግቢያ ጠገኑ፡፡ ከመግቢያው በላይ ያሉትን አምዶችም በስፍራቸው አደረጉ፣ እንዲሁም መቀርቀሪያዎችንና መወርወሪያዎችን መግቢያውን ለመቆለፍ አስገቡ፡፡ 7ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የገባኦንና ከምጽጳ ሰዎች የሆኑት ገባኦናዊው መልጥያ እና ሜሮኖታዊው ያዶን፣ ከባህሩ ማዶ የሚገኘው አውራጃ ገዢ የሚኖርበትን ክፍል ጠገኑ፡፡8ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሖርሃያ ልጅ ዑዝኤል፣ እና ሐናንያ ነበሩ፣ ነገር ግን እነርሱ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ያለውን ክፍል ሰሩ፡፡ ሐርሃያ ወርቅ አንጥረኛ፣ ሐናንያ ደግሞ ሽቶ ቀማሚ ነበሩ፡፡ 9ከእርሱ ቀጥሎ፣ የኢየሩሳሌምን ከፊል አውራጃ የሚገዛው የሆር ልጅ ረፋ የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡ 10ከእርሱ ቀጥሎ፣ የኤርማፍ ልጅ ይዳያ ከቤቱ አጠገብ የሚገኘውን ቅጥር ከፊሉን መልሶ ሰራ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ የአሰቦንያ ልጅ ሐጡስ የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡11የሃሪም ልጅ መልክያ፣ እና የፈሐት ሞዓብ ልጅ አሱብ የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፣ እንዲሁም የእቶን ማማ የተባለውን መልሶ ሰራ፡፡ 12ከእርሱ ቀጥሎ፣ ሌላውን የኢየሩሳሌም ከፊል አውራጃ የሚገዛው የአጦሎኤስ ልጅ ሰሎም የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡ ሴት ልጆቹ በስራው ረዱት፡፡13ሐኖንና የዛኖ ከተማ ሰዎች የሸለቆ መግቢያ ተብሎ የሚጠራውን መልሰው ሰሩ፡፡ እነርሱም መግቢያዎቹን መልሰው በስፍራቸው አቆሙ፣ ደግሞም መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን በሮቹን ለመቆለፊያ አበጁ፡፡ ቅጥሩን የቆሻሻ መጣያ በር እስከሚባለው ድረስ 460 ሜትር መልሰው ሰሩ፡፡14የበት ሐካሪም አውራጃ ገዢ የሆነው የረካብ ልጅ መልክያ የቆሻሻ መጣያ በር ተብሎ የሚጠራውን መልሶ ሰራ፡፡ መግቢያውን ለመቆለፊያ መወርወሪያዎቹንና ፍርግርጎቹን መልሶ ሰራ፡፡ 15የምጽጳ አውራጃን የሚገዛው የኮልሐዜ ልጅ ሰሎም የፏፏቴ በር ተብሎ የሚጠራውን መግቢያ መልሶ ሰራ፡፡ ከመግቢያው በላይ ጣራ አበጀ፣ በሩን ለመቆለፍ መግቢያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን እንዲሁም ፍርግርጎቹን አበጀ፡፡ ከዳዊት ከተማ ተነስቶ ቁልቁል እስከ ሼላን ገንዳ አጠገብ ከንጉሱ መናፈሻ ቀጥሎ ቅጥሩን ገነባ፡፡16ከእርሱ ቀጥሎ፣ የቤት ዱር አውራጃን በከፊል የሚገዛው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ፣ በዳዊት ከተማ ውስጥ እስከ መቃብር ስፍራ ያለውን ቅጽር፣ ሰው ሰራሽ እስከ ሆነው መዋኛ እና እስከ ፈረስ ቤቶች ድረስ መልሶ ሰራ፡፡17 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ካህናቱን የረዱት ብዙ የሌዊ ትውልዶች የቅጥሩን ክፍሎች መልሰው ሰሩ፡፡ የባኒ ልጅ ሬሁ አንዱን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ የቅኢላን ግማሽ አውራጃ የሚገዛው ሐሽብያ የአውራጃውን ህዝብ ወክሎ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡18የቅዒሊን ቀሪውን ግማሽ አውራጃ የሚገዛው የኤንሐዳድ ልጅ በዋይና ከሌሎች የሌዊ ትውልዶች ጋር ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ 19ከእርሱ ቀጥሎ፣ የምጽጳ ከተማን የሚገዛው የኢያሱ ልጅ ኤጽር እስከ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ደጃፍ፣ መአዘን ላይ እስከ ሚገኘው የቅጥሩ ቅስት ድረስ ያለውን ሌላውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡20ከእርሱ ቀጥሎ፣ የዘባይ ልጅ ባሮክ የቀረውን የቅጥሩን ክፍል በታላቅ ትጋት መልሶ ሰራው፡፡ ከሊቀ ካህኑ ከኤልያሴብ ቤት በር እስከ ራሱ እስከ ባሮክ ቤት መጨረሻ ድረስ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ 21ከእርሱ ቀጥሎ፣ የአቆስ የልጅ ልጅ፣ የኦርዮ ልጅ የሆነው ሜሪሞት ከኤልያሴብ ቤት በር እስከ ራሱ እስከ ሜሪምት ቤት መጨረሻ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡22 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ብዙ ካህናት የቅጽሩን ክፍሎች መልሰው ሰሩ፡፡ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ያሉ ካህናት አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡ 23ከእነርሱ ቀጥሎ፣ ብንያምና አሱብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡ የሖናንያ የልጅ ልጅ፣ የመፅሤያ ልጅ የሆነው ዓዛርያስ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ 24 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ከዓዛርያስ ቤት ቅጽሩ በጥቂቱ ዞር እስከሚልበት ድረስ ያለውን አንዱን ክፍል የኤንሐዳድ ልጅ ቢንዊ መልሶ ሰራ፡፡25ከእርሱ ቀጥሎ፣ ቅጥሩ ከሚዞርበትና የመጠበቂያ ማማው ከላይኛው ቤተ መንግስት ከፍ ብሎ እስከሚታይበት ድረስ ያለውን አንድ ክፍል የኡዛይ ልጅ ፉላል መልሶ ሰራ፡፡ መጠበቂያ ማማው ጠባቂዎቹ ከሚኖሩበት አደባባይ አጠገብ ይገኛል፡፡ ከፉላል ቀጥሎ፣ የፋሮስ ልጅ ፈዳ ቅጥሩን መልሶ ሰራ፡፡ 26ከእርሱ ቀጥሎ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች በትልቁ ማማ ምስራቅ አቅጣጫ ፊቱን ወደ ውሃ በር ያደረገውን አንድ ክፍል መልሰው ጠገኑ፡፡ 27ከእርሱ ቀጥሎ፣ የተቁሐ ሰዎች ከትልቁ ማማ ፊት ለፊት እስከ ኦፌል ቅጥር ድረስ ያለውን ሁለተኛውን ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡28ከፈረስ መግቢያ ሰሜን አንስቶ ያለውን ቅጽር አንድ የካህናት ቡድን መልሶ ሰራው፡፡ እያንዳንዱ ካህን ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ 29ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የኢሜር ልጅ ሳዶቅ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ በስተምስራቅ የሚገኘው በር ጠባቂ የነበረው የሴኬንያ ልጅ ሸማያ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ 30ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያ፣ እና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡ ያም እነርሱ መልሰው የጠገኑት ሁለተኛው ክፍል ነበር፡፡ ከእርሱ በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም እርሱ ይኖርበት በነበረው ቤት ፊት ለፊት የሚገኙትን ቅጥሮች ክፍል መልሶ ሰራ፡፡31ከእነርሱ ቀጥሎ፣ ወርቅ አንጣሪው መልክያ ከቀጠሮ በር ማዕዘን ላይ እስከሚገኘው የላይኛው መኖሪያዎች የሚገኙትን የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና ነጋዴዎች እስከ ሚገለገሉባቸው ህንጻዎች ድረስ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ 32ሌሎች ወርቅ አንጥረኞች፣ ከነጋዴዎች ጋር ሆነው የቅጥሩን የመጨረሻ ክፍያ እስከ በጎች በር ድረስ መልሰው ሰሩ፡፡
1ሰንበላጥ የከተማዋን ቅጥር እንደገና እየሰራን መሆኑን በሰማ ጊዜ፣ እኛ ኢየሩሳሌምን እንደ ገና መገንባታችን በውስጡ እንደ እሳት አቃጠለው፣ እናም በጣም ተቆጥቶ በአይሁዶች ላይ በጥላቻ ተሞልቶ ተናገረ፡፡ 2ከሰማርያ በመጡት አማካሪዎቹና የጦር አለቆቹ ፊት እንዲህ አለ፣ “እነዚህ አይሁዶች ራሳቸውን ችለው መቆም አይችሉም፣ ምን እያደረጉ ያሉ መስሏቸዋል? ከተማዋን እንደገና ገንብተው ራሳቸው ሊኖሩባት ነውን? ቤተ መቅደሱን እንደገና ገንብተው ካህናቱ ለያህዌ የሚያቀርቡትን መስዋእት ሁሉ ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት ቀን እንዲህ ያለውን ታላቅ ሥራ ይጨርሳሉን? እነዚህን የተቃጠሉና ከጥቅም ውጭ የሆኑ ድንጋዮች ቅጥሩን እንደገና ለመገንባት ሊጠቀሙበትና ለከተማዋ ዳግም ሕይወት ሊሰጧት ይችላሉን?3ጦቢያ ከሰንበላጥ አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፣ “ያ እነርሱ የሚገነቡት ቅጥር እጅግ ደካማ ነው፤ ትንሽ ቀበሮዎች ቢወጡበት እንኳን ይፈርሳል፤ የእነርሱ የድንጋይ ቅጥር ቀበሮ ቢወጣበት ይፈርሳል!”4ከዚያ እኔ እንዲህ ስል ጸለይኩ፣ “አምላካችን ሆይ፣ ስማን፣ እነርሱ እየቀለዱብን ነው! የስድባቸውን ቃል ወደ ራሳቸው እንዲመለስ አድርግ! ጠላቶቻቸው እንዲመጡባቸውና እንዲይዟቸው ወደ ባዕድ ምድርም እንዲያሳድዷቸው አድርግ! 5እነርሱ በደለኞች ናቸው፡፡ በደላቸውን ከእነርሱ አታርቅ በፊትህ ለሰሩት ኃጢአት ዋጋ ይክፈሉ፡፡ በስድቦቻቸው፣ ቅጥሩን መልሰው የሚገነቡትን በጣም አስቆጥተዋል!”6ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን፣ ሰራተኞቹ ከጠቅላላው በከተማይቱ ዙሪያ ከሚገኘው የቅጥሩ ከፍታ ግማሽ ያህሉን ሰሩ፡፡ ይህን ማከናወን የቻሉት ሊሰሩ የሚችሉትን በሙሉ ልባቸው ለመስራት ስለፈለጉ ነበር፡፡7ነገር ግን ሰንበላጥ፣ ጦብያ፣ ዐረቦች፣ አሞናዊያን፣ እና አሽዶዳዊያን የቅጥሩ ስራ መሰራቱ እንደ ቀጠለና የፈረሰውን ቅጥር እየጠገንን መሆኑን ሲሰሙ በጣም ተቆጡ፡፡ 8እነርሱም መጥተው የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለመውጋት እና በከተማይቱ ውስጥ ሀብት ለመፍጠር በአንድነት ዕቅድ አወጡ፡፡ 9እኛ ግን ቅጥሩን መልሰን በመገንባታችን እጅግ በተቆጡት በእነዚህ ሰዎች ምክንያት ወደ አምላካችን ጸለይን፣ ደግሞም ከተማዋን ቀንና ሌሊት ይጠብቁ ዘንድ ወንዶችን በቅጥሮቹ ዙሪያ አቆምን፡፡10ከዚያ የይሁዳ ሰዎች እንዲህ ማለት ጀመሩ፣ “ቅጥሩን የሚሰሩት ወንዶች መላ አቅማቸውን እየተጠቀሙ ነው፡፡ ልናነሳው የሚገባ እጅግ ብዙ ፍርስራሽ አለ፤ እኛ ይህን ስራ መጨረስ አልቻልንም ስራው እጅግ በዝቶብናል፡፡11ከዚህም ባሻገር፣ ጠላቶቻችን እንዲህ እያሉ ነው! ‘አይሁዶች እኛን ከማየታቸው አስቀድሞ፣ በእነርሱ ላይ እንውጣባቸውና እንግደላቸው፣ የቅጥሩን ስራቸውንም እናስቁማቸው!”12በጠላቶች አቅራቢያ ይኖሩ የነበሩ አይሁዶች ብዙ ጊዜ ወደ እኛ እየመጡ ጠላቶቻችን በእኛ ላይ ሊፈጽሙ የሚያስቡትን ክፉ እቅድ ይነግሩን ነበር፡፡ 13ስለዚህ ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ቅጥሩን እንዲጠብቁ ሰዎችን አቆምኩ፡፡ እነዚህ ሰዎች ቅጥሩን በቀላሉ መሻገር በሚቻልባቸው በቅጥሩ ዝቅተኛ ስፍራዎች እንዲቆሙ ተደረገ፡፡ እነርሱም ሰይፎቻቸውን ጦሮቻቸውን፣ እና ደጋኖቻቸውንና ቀስቶቻቸውን ይዘው ይጠብቁ ነበር፡፡ 14ከዚያ እያንዳንዳቸውን ከተመለከትኩ በኋላ፣ መሪዎችንና ሌሎች ሹማምንቶችን እንዲሁም ሌሎች ብዙ ሰዎችን ሰብስቤ እንዲህ አልኳቸው፣ “ጠላቶቻችንን አትፍሯቸው! እግዚአብሔር ታላቅና በክብር የተሞላ እንደሆነ አስቡ! እናም ቤተሰባችሁን፣ ወንድና ሴቶች ልጆቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን እና ቤቶቻችሁን ለመጠበቅ ተዋጉ!”15ጠላቶቻችን፣ ዕቅዶቻቸውን እንደሰማን አወቁ፣ እግዚአብሔርም ስራችንን ለማስቆም ያወጡትን ዕቅድ ከንቱ አደረገባቸው፡፡ ስለዚህ እኛ ሁላችንም ወደ ፊት እንሰራበት ወደነበረው ወደዚያው ስፍራ ቅጥሩን ለመገንባት ተመለስን፡፡16ነገር ግን ከዚያ በኋላ፣ በዚያ ከነበሩት ወንዶች ግማሾቹ ብቻ የቅጥሩን ሥራ ይሰሩ ነበር፡፡ ሌሎቹ ጦሮቻቸውን፣ ጋሻዎቻቸውን፣ ደጋኖቻቸውንና ቀስቶቻቸውን ይዘውና የጦር ልብሶቻቸውን ለብሰው ይጠብቁ ነበር፡፡ መሪዎቹ የይሁዳን ሕዝብ ይጠብቁ ነበር፡፡17መሪዎች ቅጥሩን የሚሰሩትንና የጉልበት ሥራ የሚሰሩትን ይጠብቁ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ሰው በአንድ እጁ ቅጥሩን ሲገነባ በሌላው እጁ መሳሪያ ይይዛል፡፡ 18ቅጥሩን የሚገነባ ሁሉ በወገቡ ሰይፍ ይታጠቃል፡፡ ጠላቶቻችን ቢመጡ መለከት የሚነፋው ሰው ከእኔ አጠገብ ይሆናል፡፡19 ከዚያ ለባለስልጣናቱ፣ ለሌሎች ታላላቅ ሰዎች፣ እና ለሌሎች ሰዎች እንዲህ አልኳቸው፣ “ይህ ሥራ ታላቅ ነው፣ እኛ በቅጥሩ ዙሪያ የምንገኝ አንዳችን ከሌላችን ተራርቀን እንገኛለን፡፡ 20የመለከት ድምጽ ስትሰሙ፣ መለከቱ በሚነፋበት ስፍራ ተሰብስቡ፡፡ አምላካችን ለእኛ ይዋጋልናል!”21ስለዚህም ስራችንን መስራት ቀጠልን፡፡ ከህዝቡ እኩሌታው ቀኑን ሙሉ ጦሩን ይዞ፣ ጠዋት ጸሀይ ስትወጣ አንስቶ ምሽት ከዋክብት እስኪታዩ ድረስ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ 22በዚያን ጊዜ፣ እኔ ለህዝቡ፣ “ለእያንዳንዱ ሰራተኛ እና ለረዳቱ በምሽት ኢየሩሳሌም ውስጥ እንዲቆዩ ይነገራቸው፡፡ ያንን በማድረግ፣ በምሽት እኛን መጠበቅና በቀን ቅጥሩን መገንባት ይችላሉ” በማለት እናገራሁ፡፡ 23በእነዚያ ጊዜያት፣ ልብሴን አላወልቅም፣ የጦር መሳሪያዬንም ሁልጊዜ እይዛለሁ፡፡ ወንድሞቼ፣ አገልጋዮቼ እና እኔን የሚከተሉ ወንዶች እና ዘብ ሆነው የሚያገለግሉ ሁሉ ይህንኑ ያደርጋሉ፡፡ ሁላችንም ውሃ ለመጠጣት ስንሄድ እንኳን የጦር መሳሪያዎችንን እንደያዝን ነበር፡፡
1ቆይቶ፣ ሌሎቹ አንዳንድ አይሁዶች በሚያደርጉት ብዙዎቹ ወንዶችና ሚስቶቻቸው ፍትህ ለማግኘት ጮኹ፡፡ 2አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፣ “እኛ ብዙ ልጆች አሉን፡፡ በልተን ለማደርና በህይወት ለመቆየት እንኳን ብዙ እህል ያስፈልገናል፡፡”3ሌሎቹ ደግሞ እንዲህ አሉ፣ “በዚህ የረሃብ ወቅት የምንበላው እህል ለማግኘት የእርሻ መሬታችንን፣ የወይን ተክላችንንና ቤቶቻችንን ማስያዝ ግድ ሆኖብናል፡፡4ሌሎቹም እንዲህ አሉ፣ “ለእርሻ መሬቶቻችንና ለወይን ተክላችን ለንጉሱ ግብር ለመክፈል ገንዘብ መበደር የግድ ሆኖብናል፡፡ 5እኛም እንደ ሌሎቹ አይሁዶች አይሁዳውያን ነን፡፡ የእነርሱ ልጆች ለእነርሱ ጠቃሚ እንደሆኑ ሁሉ፤ የእኛም ልጆች ለእኛ እንደዚያው ናቸው፡፡ ነገር ግን መክፈል የሚገባንን ለመክፈል ስንል ልጆቻችንን ለባርነት ለመሸጥ ተገደናል፡፡ አንዳንድ ሴት ልጆቻችንን አሁን ለባርነት ሸጠናል፡፡ የእርሻ መሬቶቻችንና የወይን ተክሎቻችን ከእኛ ተወስደዋል፣ ስለዚህም መክፈል ያለብንን ገንዘብ ለመክፈል ገንዘቡ የለንም፡፡”6እነዚህን እነርሱ የተጨነቁባቸውን ነገሮች በሰማሁ ጊዜ በጣም ተቆጣሁ፡፡ 7ስለዚህም ማድረግ ያለብኝን ነገር አሰብ፡፡ ለመሪዎችና ለሹማምንቱ እንዲህ አልኳቸው፣ “ገንዘብ ሲበደሯችሁ የገዛ ዘመዶቻችሁን ወለድ ታስከፍላላችሁ፡፡ ይህ ልክ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ!” ከዚያም ክስ እንዲያቀርቡባችሁ ብዙ ሰዎችን በእነርሱ ላይ ሰብስቤ ጠራሁ፡፡ 8እንዲህም አልኳቸው፣ “አንዳንድ አይሁዳዊ ወገኖቻችን የአህዛብ ባሪያዎች ለመሆን ራሳቸውን ለመሸጥ ተገደው ነበር፡፡ የቻልነውን ያህል፣ መልሰን ገዝተናቸው ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን እናንተ የገዛ ወገኖችሁን እንኳን እየሸጣችሁ ነው፤ ይኸውም የገዛ ወገኖቻቸው ወደ ሆኑ አይሁዶች ተመልሰው ይሸጡ ዘንድ ነው!” ይህን ስናገራቸው፣ ምላሽ አልሰጡም፡፡ አንዲት ቃል እንኳን አልመለሱም፡፡9ከዚያ እንዲህ አልኳቸው፣ “የምታደርጉት ነገር ክፉ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ልትታዘዙና ትክክል የሆነውን ልታደርጉ አይገባችሁምን? ይህን ብታደርጉ፣ ጠላቶቻችን በንቀት እንዳያዩን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ 10እኔና አይሁዳዊ ወገኖቼ እንዲሁም አገልጋዮቼ ለህዝቡ ገንዘብና እህል አበደርን፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ከእነዚህ ብድሮች በአንዱም ወለድ መቀበል እናቁም፡፡ 11እንደዚሁም፣ የወሰዳችሁባቸውን የእርሻ መሬቶቻቸውን፣ የወይን ስፍራቸውን፣ የወይራ ዛፍ ቦታቸውን እንዲሁም ቤቶቻቸውን ልትመልሱላቸው ይገባል፡፡ እንደዚሁም ገንዘብ፣ እህል፣ ወይን፣ እና የወይራ ዘይት ሲበደሯችሁ ያስከፈላችኋቸውን ወለዶች ልትመልሱላቸው ይገባል፡፡ ይህን ዛሬውን ልታደርጉ ይገባል!”12መሪዎች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ያልከንን እናደርጋለን፡፡ እንዲሰጡን ያስገደድናቸውን ነገር ሁሉ እንመልስላቸዋለን፣ ደግም ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዲሰጡን አንጠይቅም፡፡” ከዚያ ካህናቱን ሰበሰብኩ፣ እናም ቃል የገቡትን እንዲያደርጉት አስማልኳቸው፡፡ 13የክህነት ልብሴን እጥፋት አራግፌ እንዲህ አልኳቸው፣ “ልታደርጉት አሁን ቃል የገባችሁትን ባታደርጉ፣ እኔ ልብሴን እንዳራገፍኩ እግዚአብሔር ያራግፋችኋል፡፡” እነርሱም “አሜን እንዳልከው ይሁን!” ሲሉ መለሱ፤ ደግሞም ያህዌን አወደሱ፡፡ ከዚያ ለማድረግ ቃል የገቡትን አደረጉ፡፡14አርጤክስስ የፋርስ ንጉስ በነበረበት በሀያኛው ዓመት የይሁዳ ገዥ ሆኜ ተሹሜ ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስከ ሰላሳ ሁለተኛው የንግስናው አመት ድረስ እኔም ሆንኩ የእኔ ሹማምንት ገዥ በመሆኔ ለቀለብ የተፈቀደልኝን ገንዘብ አልተቀበልንም፡፡ 15ከእኔ አስቀድሞ ገዥ የነበሩ ሰዎች በየቀኑ አርባ የብር ሳንቲሞች ለምግብና ለወይን በመጠየቅ በህዝቡ ላይ ሸክም አክብደውበት ነበር፡፡ አገልጋዮቻቸው ጭምር ህዝቡን ይጨቁኑ ነበር፡፡ እኔ ግን ያን አላደረግኩም፣ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ክብር መስጠት እፈልግ ነበር፡፡16በዚህ ቅጥር ላይ መስራቴንም ቀጠልኩ፣ እኛም ከህዝቡ ምንም መሬት አልገዛንም፡፡ ለእኔ የሚሰሩት ሁሉ በቅጥሩ ስራ ተባበሩን፡፡ 17እንዲሁም፣ በየዕለቱ ከገበታችን አይሁዶችንና ሹማምንቱን፣ አንድ መቶ ሀምሳ ሰዎችን፣ እና በዙሪያችን ካሉ አገሮች የመጡ ጎብኚዎችን እንመግብ ነበር፡፡18በየቀኑ አገልጋዮቼ አንድ በሬ፣ ስድስት ሙክቶች እና የዶሮዎች ስጋ እንዲያቀርቡ አደርግ ነበር፡፡ በየአስሩ ቀን ብዙ የሆነ አዲስ ወይን ጠጅ አቀርብላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡ እጅግ ብዙ ግብር በመክፈል ጫና እንደሚበዛበት አውቅ ነበር፣ ስለዚህም እንደ አገረ ገዥ የተፈቀደልኝን ገንዘብ እንኳን አልቀበልም ነበር፡፡ 19አምላኬ፣ አስበኝ፣ እናም ለዚህ ህዝብ ላደረግኩት ሽልማት ስጠኝ፡፡
1ምንም እንኳን እስከ አሁን በሮቹን በመግቢያዎቹ ላይ ገና ባንገጥምም፣ የቅጥሩን ሥራ መጨረሳችንንና ያልተጠገነ የፈረሰ ስፍራ አለመኖሩን ሰንበላጥ፣ ጦቢያ፣ ጌሳምና ሌሎች ጠላቶቻችን ሰሙ፡፡ 2ስለዚህ ሰንበላጥና ጌሳም እንዲህ የሚል መልዕክት ወደ እኔ ላኩ፣ “ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን በሚገኘው ኦኖ በሚባለው ሜዳ መጥተህ እንነጋገር፡፡” ነገር ግን ይህን ያሉት እኔን ለመጉዳት አስበው እንደነበር ግልጽ ነው፡፡3ስለዚህም እንዲህ ብለው እንዲነግሯቸው መልዕክተኞችን ላክሁ፣ “ከፍ ያለ ስራ እየሰራሁ ነው፣ እናም ወደዚያ ልሄድ አልችልም፡፡ እኔ ከእናንተ ጋር ለመነጋገር ወደዚያ በመሄድ ይህ ስራ መስተጓጎል አይኖርበትም፡፡ 4እነርሱ ይህንኑ መልዕክት አራት ጊዜ ወደ እኔ ላኩ፣ እኔም በእያንዳንዱ ወቅት ተመሳሳይ መልስ ሰጠኋቸው፡፡5ከዚያም ሰንበላጥ አምስተኛውን መልዕክት አስይዞ አንዱን አገልጋዩን ወደ እኔ ላከ፡፡ ይህኛው መልዕክት በጽሁፍ ነበር፣ በእርግጥ ማህተም ያልተደረገበትና ያልታሸገ ደብዳቤ ነበር፡፡6በመልዕክቱ የተጻፈው ይህ ነበር፡ “በባቢሎን ንጉስ ላይ አመጽ ለማስነሳትና አንተም የእስራኤል ንጉስ ለመሆን አቅደህ አንተና ሌሎች አይሁዶች ቅጥሩን እንደገና እየገነባችሁ እንደሆነ በአቅራቢያ ባሉ አገሮች ያሉ አንዳንድ ሰዎች ወሬ ሰምተዋል፡፡ እውነቱ ይህ መሆኑን ጌሳም ነግሮናል፡፡7ደግሞም ሰዎች፣ አንተ ነህምያ፣ አሁን የአይሁድ ንጉስ መሆንህን እንዲያውጁ ነቢያትን መሾምህን እየተናሩ ነው፡፡ ንጉስ አርጤክስስ በእርግጥ ይህን ወሬ መስማቱ አይቀርም፣ ያን ጊዜ ትልቅ ችግር ላይ ትወድቃለህ፡፡ ስለዚህ ተገናኝተን በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር እንደሚኖርብን አሳስባለሁ፡፡”8ያን መልዕክት ካነበብኩ በኋላ መልዕክተኛው ወደ ሰንበላጥ ይህን መልዕክት መልሶ እንዲያደርስ ላክሁ፣ “ከምትናገረው ውስጥ አንዱም እውነት አይደለም፡፡ ይህን የምትለው ከገዛ ልብህ ፈጥረህ ነው፡፡” 9ይህንን የምለው እነርሱ እኛን ለማስፈራራት እየሞከሩ እንደነበር ስለማወቅ ነው፣ ስለዚህም እንዲህ ብለው ያስባሉ፣ “ከዚህ በኋላ ቅጥሩን ለመስራት ፍጹም ተስፋ ይቆርጣሉ፣ ስራውም በፍጹም ከፍጻሜ አይደርስም፡፡” ስለዚህም እኔ፣ “አምላኬ ሆይ፣ ብርታትን ስጠኝ፡፡” ስል ጸለይኩ፡፡10አንድ ዕለት የመሔጣብኤል የልጅ ልጅ፣ የድልያ ልጅ፣ ከሆነው ከሸማያ ጋር ለመነጋገር ሄድኩ፡፡ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ቤቱ ሄድኩ፡፡ ከቤቱ እንዳይወጣ ትዕዛዝ ተሰጥቶት ነበር፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ፣ “አንተና እኔ ከቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍሎች ወደ አንዱ መግባትና በሮቹን መቆለፍ አለብን፡፡ ዛሬ ምሽት ሊገድሉህ ይመጣሉ፡፡”11እኔም እንዲህ ስል መለስኩለት፣ “እኔ እንዲያ ያለ ሰው አይደለሁም! ህይወቴን ለማትረፍ ራሴን ቤተመቅደስ ውስጥ ሸሽቼ ገብቼ አልደብቅም! አይ፣ ያንን አላደርግም!”12የተናገረውን አሰላሰልኩ፣ ሸማያ እግዚአብሔር ያላለውን እንደነገረኝ አወቅሁ፡፡ ጦቢያ እና ሰንበላጥ ቀጥረውት ነበር፡፡ 13እንዲያስፈራራኝ እነርሱ ቀጥረውት ነበር፡፡ እነርሱ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንዳልጠብቅ በመቅደስ ውስጥ በመደበቅ እንድበድል ይፈልጉ ነበር፡፡ ያንን ባደርግ፣ ስሜን ያጠፉና ከዚያም ያዋርዱኛል፡፡14ስለዚህም እንዲህ ስል ጸለይኩ “አምላኬ ሆይ፣ ጦቢያና ሰንበላጥ ያደረጉትን አትርሳ፡፡ ነቢይቱ ኖዓድያ እና ሌሎች ነቢያት ሊያስፈራሩን የሞከሩትን አትርሳ፡፡”15በኤሉል ወር በወሩ ሃያ አምስተኛው ቀን የቅጥሩን ጥገና አጠናቀቅን፡፡ ጠቅላላውን ስራ በሀምሳ ሁለት ቀናት አጠናቀቅን፡፡ 16በአቅራቢያችን በሚገኙ አገሮች የሚኖሩ ጠላቶቻችን ይህንን ሲሰሙ፣ በጣም ፈሩ፣ ዕፍረትም ተሰማቸው ምክንያቱም ይህን ሥራ እንድናጠናቅቅ የረዳን እግዚአብሔር እንደሆነ አውቀው ነበር፡፡17በዚህ ጊዜ ውስጥ፣ የአይሁድ መሪዎች ብዙ መልዕክቶችን ወደ ጦቢያ ይልኩ ነበር፣ ጦቢያም መልሶ መልዕክቶችን ወደ እነርሱ ይልክ ነበር፡፡ 18በይሁዳ ያሉ ብዙ ሰዎች ታማኝታቸውን በመሀላ ለጦቢያ አረጋግጠውለት ነበር፡፡ እርሱም የኤራ ልጅ የሴኬንያ አማት ሲሆን፣ የጦቢያ ወንድ ልጅ የቤሪክያን ልጅ የሆሐና የሚሹ ሀላምን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር፡፡ 19ሰዎች ብዙ ጊዜ እኔ ባለሁበት ጦቢያ ስለ ሰራቸው መልካም ስራዎች ይናገሩና፣ ከዚያ እኔ የተናገርኩትን እያንዳንዱን ነገር ይነግሩታል፡፡ ስለዚህም ጦቢያ እኔን ለማስፈረራት በርካታ ደብዳቤዎችን ወደ እኔ ይልክልኝ ነበር፡፡
1ቅጥሩ ተሰርቶ ከተጠናቀቀና በሮቹም በስፍራቸው ከቆሙ በኋላ፣ የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎችና የዝማሬ አባላቱ እንዲሁም የተቀሩት የሌዊ ትውልዶች በየስራ መደባቸው ተመደቡ፡፡ 2ወንድሜን አናኒን የኢየሩሳሌም ገዥ አድርጌ ሾምኩት፡፡ እርሱ ከብዙ ሌሎች ሰዎች ይልቅ ታማኝና እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያከብር ሰው ነበር፡፡ በተጨማሪም ሐናንያ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የከተማይ ግንብ አዛዥ ሆኖ ተሾሙ፡፡3እነርሱን እንዲህ አልኳቸው፣ “ፀሀይ ሞቅ እስክትል የኢየሩሳሌምን መግቢያ በሮች አትክፈቱ፡፡ በሮችን የምትቆልፉትና የበሮችን መቀርቀሪያዎች የምትዘጉት በር ጠባቂዎች መግቢያዎችን እየጠበቁ ሳለ ነው፡፡” አንዳንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችን ዘቦችና በከተማዋ ዙሪያ ያሉ ማረፊያዎችን ጠባቂዎች እንዲያደረጓቸው፤ እንዲሁም አንዳንዶችን ከራሳቸው ቤቶች አቅራቢያ ጠባቂ እንዲያደረጓቸው ነገርኳቸው፡፡4የኢየሩሳሌም ከተማ ሰፊ ናት፣ ነገር ግን በዚያን ጊዜ በከተማዋ ብዙ ህዝብ አይኖርም ነበር፣ እንዲሁም ከቤቶቹ አንዱንም እንደገና አልገነቡም ነበር፡፡5እግዚአብሔር መሪዎችንና ሹማምንቱን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን እንድሰበስብ እና በየቤተሰባቸው መዛግብት እንድጽፍ አሳብ በልቤ አኖረ፡፡ እንደዚሁም ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱትን የመጀመሪያዎቹን ተመላሾች ዝርዝር አገኘሁ፡፡ በእዚያ መዛግብት ተጽፎ ያገኘሁት ይህንን ነው፡፡6”ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ሌሎች ስፍራዎች የተመለሱ ሰዎች ዝርዝር ይህ ነው፡፡ እነርሱ ባቢሎን ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ናቡከደነጾር ወደዚያ ወስዷቸው ነበር፡፡ እነርሱ ወደ ኢየሩሳሌምና ይሁዳ ተመለሱ፡፡ እያንዳንዱ ተመላሽ አባት ከልደት በፊት ይኖርበት ወደነበረበት ወደ ራሱ ከተማ ተመልሶ ሄደ፡፡ 7እነርሱ ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከላሶን፣ ከሚስጴሬት፣ ከጉዋይ፣ ከነሑም፣ እና ከዓና ጋር ተመልሰው መጡ፡፡ ከህዝቡ የተመለሱት የወንዶች ቁጥር ዝርዝር እንደሚከተለው ነበር፡8ከፋሮስ ትውልዶች 21729ከሰፋጥያስ ትውልዶች 37210ከኤራ ትውልዶች፣ 65211ሞዓብ ትውልዶች፣ የኢያሱና ኢዮብአብ ትውልዶች 281812ከኤላም ትውልዶች 1254፣13ከዛቱዕ ትውልዶች፣ 845፣14ከዘካይ ትውልዶች፣ 845፣15ትውልዶች፣ 648፣16ከቤባይ ትውልዶች፣ 628፣17ከዓዝጋድ ትውልዶች፣ 2322፣18ከአዶኒቃም ትውልዶች፣ 667፣19ከበጉዋይ ትውልዶች፣ 2067፣20ከዓዲን ትውልዶች፣ 655፣21ከአጤር ትውልዶች ሌላ ስማቸው ሕዝቅያስ ከሚባለው፣ 98፣22ከሐሱም ትውልዶች፣ 32823ከቤሳይ ትውልዶች፣ 324፣24ከሐሪፍ ትውልዶች፣ ሌላ ስማቸው ጆራህ ከሚባለው፣ 11225ከገባዖን ትውልዶች 9526አባቶቻቸው በእነዚህ ከተሞች የኖሩ ወንዶችም ደግሞ ተመለሱ ከቤተልሔምና ከነጦፉ የመጡ ወንዶች፣ 188፡፡27ከዓናቶት የመጡ ወንዶች፣ 128 ነበሩ28ከቤት አዛምት የመጡ ወንዶች 42፣29ከቂርያት ይዓሪም ከከፈሪና ከብኤሮት 743 ወንዶች30ኮራማና ከጌባ 621 ወንዶች31122 ወንዶች ነበሩ32ከቤቴልና ከጋይ፣ 123 ወንዶች33ከናባው፣ 52 ወንዶች34ከኤላም፣ 1254 ወንዶች35ከካሪም 320 ወንዶች ነበሩ36ከኢያሪኮ፣ 345 ወንዶች37ከሎድ፣ ሐዲድና አኖ 721 ወንዶች ነበሩ እነዚህ ካህናትም ደግሞ ተመልሰዋል38ከሴናዓ ትውልድ 3930 ነበሩ39የኢያሱ ቤተሰብ የሆኑ፣ የዮዳኤ ትውልዶች፣ 97340ከኢሜር ትውልዶች 1052፣41ከፋስኮር ትውልዶች፣ 1247፣42ከካሪም ትውልዶች፣ 101743ከሌዋውያን ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ፣ የኢያሱ፣ ቀደምኤል፣ ቤትኢ እና የሆዳይዋ ትውልዶች 74 ናቸው44ከመዘምራኑ ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ ከኤሳፍ ትውልድ 14845እንዲሁም ከሰሎም፣ አጤር፣ ጤልሞን፣ ዓቁብ፣ ሐጢጣ፣ እና ሶባይ ትውልዶች የተመለሱ 138 የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች ናቸው፡፡46የተመለሱት የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች የእነዚህ ሰዎች ትውልዶች ነበሩ የሲሐ፣ ሐሡፋ፣ ጠብዖት47የኬረስ፣ ሲዓዓ ሩዶን48የልባና አገባ፣ ሰሞላይ49የሐናን ጌዱል፣ ጋሐር፣50ራያ፣ ራአሰን፣ ኔቆዳ51ጋሴም፣ አዛ፣ ፋሴሐ52ቤሳይ፣ ምዑኒም፣ ንፉሰሊም፣ እነዚህ ንፉሰሲም ተብለውም ይጠራሉ53በቅቡቅ፣ ሐቀፋ፣ ሐርሑር፣54በሰሎት፣ እነዚህ በሰሉት ተብለውም ይጠራሉ ምሒዳ፣ ሐርሻ55ቦርቆስ፣ ሲሣራ፣ ቴማ56ንስያ፣ ሐጢፋ57ከንጉስ ዳዊት አገልጋዮች ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ፣ ሶጣይ፣ ሶፌሬት፣ ፍሩዳ58የዕላ፣ ደርቆን፣ ጊዴል59ሰፋጥያስ፣ ሐጢል፣ ፈከራት፣ ሐፂቦይምና አሞን60በአጠቃላይ፣ 392 የቤተ መቅደስ ሰራተኞችና የሰለሞን ትውልዶች አገልጋዮች ተመላሾች ነበሩ፡፡61ከዳላያ፣ ጦብያ እና ኔቆዳ ጎሣዎች 62ሰዎች ያሉት ሌላ ቡድን ከቴልሜላ ቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ አዳን፣ በባቢሎን አዳን እና ኢሜር ተብሎም ይታወቃል፤ ከእነዚህ ከተሞች ይመለሳሉ፡፡ ነገር ግን እነርሱ እስራኤላዊያን መሆናቸውን ማረጋገጥ አልቻሉም፡፡63የኤብያ፣ አቆስ፣ እና ቤርዜሊ ትውልድ የሆኑ ካህናትም ደግሞ ተመለሱ፡፡ ቤርዜሊ ከገለዓድ አካባቢ የቤርዜሊ ትውልድ የሆነችን አንዲት ሴት አገባ፤ እርሱም የሚስቱን ቤተሰቦች ስም መጠሪያው አድርጎ ወሰደ፡፡64እነዚህ የአባቶችን ስሞች በያዙ መዛግብቶች ውስጥ የትውልድ ሀረጋቸውን ፍለጋ አደረጉ፣ ነገር ግን የቤተሰቦቻቸውን ስሞች ማግኘት አልቻሉም፤ ስለዚህ ካህናት ያሏቸውን መብቶችና ግዴታዎች ማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡ በመሆኑም ንጹህ እንዳልሆኑ ስተቆጠረ ካህናት ለመሆን አልበቁም ምክንያቱም የትውልድ ሀረጋቸውን ማመላከት አልቻሉም፡፡65ስለዚህ አገረ ገዥው በኡሪምና ቱሚም የሚያገለግል ከህን እስኪነሳ ድረስ ከመስዋዕቱ ከተወሰደው እጅግ ከተቀደሰው ከካህናቱ ድርሻ ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው፡፡66በአጠቃላይ፣ ከይሁዳ የተመለሱት ሰዎች 42360 ነበሩ፡፡ 67እንደዚሁም 7337 አገልጋዮቻቸውና 245ዘማሪዎች ከወንዶችም ከሴቶችም በአንድነት ተቆጠሩ፡፡68እስራኤላዊያኑ ከባቢሎን 736 ፈረሶችና 245 በቅሎዎች፣ 69አራት መቶ ሰላሳ አምስት ግመሎችና 6720 አህዮችንም ጭምር ይዘው ተመለሱ፡፡70አንዳንዶቹ የጎሣው መሪዎች ለመቅደሱ ግንባታ ሠራተኞች ስጦታዎችን ሰጡ፡፡ አገረ ገዥው 8. 5 ኪሎግራም ወርቅ ለመቅደስ አገልግሎት ሀምሳ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ እና 530 የክህነት ልብሶችን ለካህናቱ ሰጠ፡፡ 71ሌሎቹ መሪዎች ለግምጃ ቤት ሀላፊው 170 ኪሎግራም ወርቅ ሰጡ፣ የጎሣው መሪዎች በአጠቃላይ 1. 2 ሜትሪክ ቶን ብር ሰጡ፡፡ 72ሌላው ህዝብ 170 ኪሎግራም ወርቅ፣ እና 1. 1 ሜትሪክ ቶን ብር እንዲሁም 67 የክህነት ልብስ ለካህናቱ ሰጡ፡፡73ስለዚህም ካህናቱ፣ ካህናቱን የሚረዱ ሌዋውያን፣ የቤተመቅደሱ ጠባቂዎች፣ ዘማሪዎቹ፣ የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች፣ እና በርካታው ተራ ህዝብ እንዲሁም እስራኤላዊ የሆኑ ሁሉ አባቶቻቸው ይኖሩባቸው በነበሩ በይሁዳ ከተሞች መኖር ጀመሩ፡፡
1ህዝቡ ሁሉ በውሃ በር አጠገብ በሚገኘው አደባባይ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ የሚነገረውን መረዳት የሚችሉ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ልጆች በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ እነርሱም ህግጋቱንና ትዕዛዛቱን ይጠብቁ ዘንድ፣ ያህዌ ለእስራኤል ህዝብ መመሪያ አድርጎ የሰጠውን ሙሴ የፃፈውን የህግ ጥቅልል መጽሐፍ እንዲመያጣ ዕዝራን ጠየቁት፡፡ 2በቤተ መቅደስ መስዋዕቶችን በማቅረብ እግዚአብሔርን የሚያገለግለው ዕዝራ፣ ለወንዶችና ለሴቶች እንዲሁም ለማናቸውም የሚነበበውን መረዳት ለሚችሉ ህጉን አውጥቶ በህዝቡ ሁሉ ፊት አነበበ፡፡ ይህንን በዚያ አመት በሰባተኛው ወር በወሩ በመጀመሪያው ቀን አደረገ፡፡ 3ስለዚህም መጽሐፉን አውጥቶ ለህዝቡ አነበበ፡፡ ጠዋት ከማለዳ አንስቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስ የህጉን መጽሐፍ አነበበ፡፡ ወንዶና ሴቶች እንዲሁም የሚያነበውን መረዳት የሚችሉ ሁሉ ሰሙት፡፡ ዕዝራ ከህጉ መጽሐፍ የሚያነበውን፣ ህዝቡ በታላቅ ፍላጎት አደመጠ፡፡4ዕዝራ ለዚህ ተግባር በህዝቡ በተዘጋጀ ከፍ ያ የእንጨት መድረክ ላይ ቆመ፡፡ ከእርሱ በስተቀኝ መቲትያ፣ ሽማዕ፣ ዓናያ፣ ኦርዮ፣ ኬልቅያስ እና መዕሤያ ቆመው ነበር፡፡ በስተግራው በኩል ደግሞ ፈዳያ፣ ሚሳኤል፣ መልክያ፣ ሐሱም፣ ሐሽበዳ፣ ዘካርያስና ሜሱላም ቆመው ነበር፡፡5ዕዝራ በመድረኩ ላይ ሁሉም ሰዎች ሊያዩት በሚችሉት ቦታ ቆሞ ጥቅልሉን ተረተረው፣ እርሱ መጽሐፉን ሲከፍት ህዝቡ ሁሉ ተነስቶ ቆመ፡፡6ከዚያም ዕዝራ ታላቁን አምላክ ያህዌን አመሰገነ፣ ህዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን አንስተው፣ “አሜን! አሜን!” አሉ፡፡ ከዚያም ሁሉም በግምባራቸው ወደ ምድር እየሰገዱ ያህዌን አመለኩ፡፡7ኢያሱ፣ ባኒ፣ ሰራብያ፣ ያሚን፣ ዓቁብ፣ ሳባታይ፣ ሆዲያ፣ መዕሤያ፣ ቆሊጣስ፣ ዓዛርያስ፣ ዮዛባት፣ ሐናን እና ፌልያ ሁሉም ሌዋውያን ነበሩ፡፡ እነርሱም የሙሴን ህግጋት ትርጉም በዚያ ቆመው ለነበሩ ህዝቦች አብራሩ፡፡ 8እንደዚሁም እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ህግ ከመጽሐፉ ጥቅልሎች አነበቡ፣ ደግም ወደ አረማይክ ቋንቋ እየተረጎሙ ህዝቡ ሊረዱት እንዲችሉ ትርጉሙን ግልጽ አደረጉ፡፡9ከዚያ አገረ ገዥው ነህምያ እና ጸሓፊውና ካህኑ ዕዝራ፣ እንዲሁም የተነበበውን ለህዝቡ ይተረጉሙ የነበሩ ሌዋውያን፣ እንዲህ አሏቸው፣ “ያህዌ አምላካችሁ ይህን ቀን ከሌሎች ቀናት ለይቶታል፡፡ ስለዚህ በዚህ ቀን አትዘኑ ወይም አታልቅሱ!” ይህን የተናገሩት፣ ዕዝራ ህጉን ሲያነብ፤ የሚሰሙት ሁሉ ያለቅሱ ስለነበር ነው፡፡10ከዚያም ነህምያ እንደዚህ አላቸው፣ “አሁን ወደየቤታችሁ ሄዳችሁ መልካም ምግብ ተመገቡ ደስ የሚያሰኝ ጣፋጭ መጠጥም ጠጡ፡፡ ከምትበሉትና ከምትጠጡት የሚበሉትና የሚጠጡት ለሌላቸው አካፍሉ፡፡ ይህ ቀን፣ ጌታችንን ለማምለክ የተለየ ቀን ነው፡፡ ሀዘን አይሙላባችሁ! ያህዌ የሚሰጣችሁ ደስታ ብርቱ ያደርጋችኋል፡፡”11ሌዋውያኑም ህዝቡን “ዝም በሉ አታልቅሱ፣ ይህ ቀን ለያህዌ የተለየ ቀን ነው፡፡ አትዘኑ!” በማለት ፀጥ አሰኙ፡፡12ስለዚህም ህዝቡ ተነስቶ ሄደ፤ በሉም ጠጡም፣ እንዲሁም ምንም ለሌላቸው ከምግባቸው አካፈሉ፡፡ የተነበባላቸውን ቃላት ትርጉሙን ስለተረዱ በጣም ደስተኞች ነበሩ፡፡13በማግስቱ፣ የየቤተሰቡ አባወራዎች እና ካህናቱ እንዲሁም ሌዋውያኑ የህጉን ቃላት ይበልጥ ለመረዳት በአንድነት ወደ ዕዝራ መጡ፡፡ 14አያቶቻቸው በበረሃ ሲጓዙ በዳሶች ውስጥ እንደኖሩ ያስታውሱ ዘንድ፣ በእነዚያ ወራት ሁሉ የእስራኤል ህዝብ እንዴት በጊዜያዊ ዳሶች ውስጥ መኖር እንደሚገባቸው ያህዌ ለሙሴ የሰጠውን ተዕዛዝ በህጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ፡፡ 15እንደዚሁም ህዝቡ ወደ ኮረብቶች ሄዶ፤ ከወይራ ዛፎች ቅርንጫፎችን፣ ከበረሃ ወይራ ዛፎችና ከባርሰነት ዛፎች፣ ከዘንባባ ዛፎችና ሰፊ ጥላ ከሚሰጡ ዛፎች ዝንጣፊዎችን እየቆረጡ እንዲያመጡና በኢየሩሳሌምና በሌሎች ከተሞች ማወጅ እንዳለባቸው ተረድተዋል፡፡ ሙሴ እንደፃፈው፣ በበዓላቱ ወቅቶች ለመኖሪያነት የሚገለገሉባቸውን እነዚህን ዳሶች ከእነዚህ ዛፎች ቅርንጫፎች ማበጀት አለባቸው፡፡16ስለዚህም ህዝቡ ከከተማ ወጥቶ ቅርንጫፎችን ቆርጦ ዳሶችን ለመስራት ተጠቀመባቸው፡፡ ዳሶችንም በየቤቶቻቸው ሰገነቶችች በየአደባባዮቻቸው፣ በቤተ መቅደስ አደባባዮች፣ እና በውሃ በር አጠገብ በሚገኘው አደባባይና በኤፍሬም መግቢያ ሰሩ፡፡ 17ከባቢሎን የተመለሱ እስራኤላዊያን ሁሉ ዳሶችን ገንብተው ለአንድ ሳምንት ኖሩባቸው፡፡ እስራኤላዊያን ያንን በዓል ከኢያሱ ዘመን አንስቶ እስከዚያ ጊዜ ድረስ እንዲህ አላከበሩም፡፡ ህዝቡ በጣም ተደስቶ ነበር፡፡18ዕዝራ በዚያን ሳምንት በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ህግ ለህዝቡ ያነብ ነበር፡፡ ከዚያ በስምንተኛው ቀን፣ ድንጋጌውን ተከትለው ህዝቡ እንዲሰበሰብ አደረጉ፣ ይህም የበዓሉ ፍጻሜ ነበር፡፡
1በዚያው ወር በሃያ አራተኛው ቀን፣ ህዝቡ በአንድነት ተሰበሰበ፡፡ ለጥቂት ጊዜ አልበሉም፣ ሰንዴና ሌላ እህል ለመያዣ የተዘጋጁ ጆንያዎችን ልብስ አደርገው ለበሱ፣ በራሳቸው ላይ የምድር ትቢያ ነሰነሱ፡፡ 2የእስራኤል ትውልዶች ራሳቸውን ከሌሎች መጻተኞች ሁሉ ለዩ፡፡ በዚያ ቆመው የራሳቸውን ኃጢአትና አባቶቸው የሰሯቸውን ክፉ ነገሮች ተናዘዙ፡፡3ቆመው ለሶስት ሰዓቶች ከያህዌ ህግ አነበቡ፣ ደግሞም ለሌላ ሶስት ሰዓቶች በያህዌ ፊት ኃጢአቶቻቸውን ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፣ ከዚያ በመሬት ላይ ተደፍተው እርሱን አመለኩ፡፡ 4ሌዋውያኑ በደረጃው ላይ ቆመው ነበር፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ባኒ፣ ቀድምኤል፣ ሰበንያ፣ ቡኒ፣ ሰራብያ፣ ባኒ፣ እና ከናኒ ነበሩ፡፡5ከዚያ የሌዋውያኑ መሪዎች በህዝቡ ፊት ተሰየሙ፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ባኒ፣ አሰበንያ፣ ሰራብያ፣ ሆዲያ፣ ሰበንያና ፈታያ ነበሩ፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ቁሙና ከዘለዓም እስከ ዘለዓለም ለነበረውና ለሚኖረው ለአምላካችሁ ለያህዌ ምስጋና አቅርቡ! ያህዌ፣ የከበረውን ስምህን እናወድሳለን! መልካምና ድንቅ ከሆነው ነገር ሁሉ ስምህ የበለጠ ጠቃሚ ነው! 6አንተ ያህዌ ነህ፣ ሌላ ማንም ዘለዓለማዊና በራሱ ህልውና ያለው የለም፡፡ አንተ ሰማይንና ሰማያትን ከሁሉም በላይ ሰራህ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽሙትን መላዕክት ሁሉ ፈጠርህ፡፡ ምድርንና በላይዋ ያሉትን አንተ አበጀህ፣ ባህሮችንና በውስጣቸው የሚገኙትን ሰራህ፡፡ አንተ ለሁሉም ነገር ህይወት ሰጠህ፡፡ በሰማይ ያሉ የመላዕክት ሰራዊት ሁሉ አንተን ያመልኩሃል፡፡7ያህዌ፣ አንተ እግዚአብሔር ነህ፡፡ አንተ አብራምን መርጠህ ከኡር ከከለዓድ አወጣኸው፡፡ አብርሃም የሚል ስም ሰጠኸው፡፡ 8አንተ የእርሱን ልብ አየህ፣ የታመነ ሰው እንደነበረ ታውቅ ነበር፡፡ ከዚያ ከእርሱ ጋር በደም ቃል ኪዳን አደረግህ፣ የከነዓናዊያንን፣ የኬጢያውያንን፣ የአሞራውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የኢያቡሳውያንንና የጌርሳውያንን ምድር ለትውልዶች እንደምትሰጠው ቃል ገባህለት፡፡ እና አንተ ያህዌ፣ ቃል የገባኸውን ፈጸምክ፣ ምክንያቱም አንተ ሁልጊዜም ትክክል የሆነውን ታደርጋለህ፡፡9አባቶቻችን በግብጽ ምን ያህል ይሰቃዩ እንደ ነበር አንተ አይተሃል፡፡ ቀይ ባህር አጠገብ በነበሩ ጊዜ ወደ አንተ ለእርዳታ ሲጮኹ ሰማሃቸው፡፡ 10ንጉሱ፣ አገልጋዮቹና የእርሱ ህዝቦች ሁሉ እንዲጨነቁ የሚያደርግ ብዙ አይነት ተአምራቶችን አደረግህ፡፡ በዚህም፣ አንተ፣ ያህዌ፣ ለራስህ ስም አደረግህ፣ እናም ዛሬም ድረስ ስምህ ታላቅ መሆኑ ይታወቃል!11ለሁለት ክፍል ከፈልህ፣ እናም ህዝብህ በደረቅ ምድር በመሀሉ ተራመደ፡፡ አንተ የግብጽን ወታደሮች በውሃዎች ስር አሰመጥክ፣ ድንጋይ በጥልቅ ውሃ እንደሚሰምጥ ሰመጡ!12በቀን ደመና እንደ አምድ እየተከተላቸው መራሃቸው፣ በምሽት ወዴት እንደሚሄዱ ልታሳያቸው የእሳት አምድ ብርሃን ሰጠሃቸው፡፡13አንተ ከሰማይ ወርደህ በሲና ተራራ ላይ አናገርካቸው፡፡ የታመኑና እውነተኛ የሆኑ ብዙ ድንጋጌዎችንና ደንቦችን ሰጠሃቸው፣ መልካም የሆኑ ትዕዛዛትንና ህግጋትንም ሰጠሃቸው፡፡14ስለ ቅዱሱ ሰንበትህ አስተማርካቸው፣ ትዕዛዛትንና ህግጋትን እንዲሁም ይፈጽሟቸው ዘንድ የህግጋት አይቶችን በአገልጋይህ በሙሴ በኩል ሰጠሃቸው፡፡ እርሱ ለህዝቡ ይነግራቸዋል፡፡ 15በተራቡ ጊዜ፣ ከሰማይ እንጀራ ሰጠሃቸው፡፡ በተጠሙ ጊዜ፣ ከአለት ውሃ አጠጣሃቸው፡፡ ትሰጣቸው ዘንድ በመሀላ ቃል የገባህላቸውን ምድር ሄደው እንዲወርሱ ነገርካቸው፡፡16ነገር ግን አባቶቻችን በጣም ኩራተኞችና ግትሮች ነበሩ፡፡ እንዲያደርጉት ያዘዝካቸውን ለማስማት እንኳን ተቃወሙ፡፡ 17አንተን ለመስማት አልወደዱም፡፡ ለእነርሱ ያደረግከውን ተአምራቶች ሁሉ ረሱ፡፡ ደንዳኖች ሆኑ፣ በአንተ ላይ ስላመጹ፣ ዳግም ባሪያዎች ወደሚሆኑበት! ወደ ግብጽ የሚመልሳቸውን መሪ መረጡ፡፡ ነገር ግን አንተ ደግመህ ደጋግመህ ይቅር የምትል አምላክ ነህ፡፡ ለመቆጣት አትቸኩልም፣ ለእነርሱ ያለህ ፍቅርም በፍጹም የማያልቅና ታላቅ ነው፡፡ እነርሱን አልተውካቸውም፡፡18ስለዚህ፣ ምንም እንኳን የከበሩ ማዕድናትን አቅልጠው ጥጃ የሚመስል ጣኦት ቢቀርጹም ሙሉ ለሙሉ አልተወካቸውም፡፡ እግዚአብሔርን በመራገምና እርሱ የከለከለውን በማድረግ፣ ይህን ጥጃ ወደ ህዝቡ አቅርበው፣ ‘ይህ እናንተን ከግብጽ ያወጣችሁ አምላካችሁ ነው’ አሉ፡፡19አንተ ሁልጊዜም መሃሪ ነህ፣ በበረሃ በነበሩ ጊዜም አልተውካቸውም፡፡ እንደ ታላቅ አምድ የሆነው ብሩህ ደመና በቀን ይመራቸው ነበር፣ የእሳት ደመናው በምሽት የሚሄዱበትን ይመራቸው ነበር፡፡20መልካሙን መንፈስህን እንዲመራቸው ላክህላቸው፡፡ በተራቡ ጊዜ መናውን አልከለከልካቸውም፣ በተጠሙ ጊዜ ውሃ ሰጠሃቸው፡፡ 21ለአርባ አመታት በበረሃ ተጠነቀቅክላቸው፡፡ በነዚያ ጊዜያት ሁሉ፣ የአንዳች ነገር ጉድለት አልነበረባቸውም፡፡ ልብሳቸው አላረጀም፣ እግሮቻቸው አላበጡም፡፡22የአህዛብን ነገስታትና መንግስታት ሰጠሃቸው፡፡ በዚህ ምድር እጅግ ሩቅ የሆነውን ስፍራ እንኳን ርስት አድርገው ወሰዱ፡፡ ንጉስ ሴዎን የሚገዛውን ምድር ከሐሴቦን ወሰዱ እንዲሁም የንጉስ ዐግን ግዛት ባሳንን ወረሱ፡፡23አባቶቻችንን በሰማይ እንዳሉ ከዋክብት እንዲበዙ ረዳሃቸው፣ አባቶቻቸው ይገቡባትና ይኖሩባት ዘንድ ወደ ነገርካቸው ወደዚህ ምድር አመጣሃቸው፡፡ 24የእስራኤል ህዝቦች ገብተው በዚያ ከሚኖሩ ህዝቦች ምድሪቱን ወሰዱ፡፡ አንተ ከነአናዊያንንና ነገስታቶቻውን እንዲያሸንፉ ረዳሃቸው፣ አንተም በዚይ ምድር ህዝቦች ላይ ገዛህ፡፡ በእነዚያ ህዝቦች ላይ ማድረግ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲያደርጉ አንተ ረዳሃቸው፡፡25አባቶቻችን ዙሪያቸው የተቀጠሩትን ከተሞች ያዙ፡፡ የለምለሚቱን ምድር ሀብት ወረሱ፡፡ በመልካም ነገሮች የተሞሉትን ቤቶችና የተቆፈሩ የውሃ ጉድጓዶችን ወረሱ፡፡ የወይን እርሻዎችን፣ የወይራ ዛፎችን እና የፍራፍሬ ዛፎችን ወረሱ፡፡ የፈለጉትን ሁሉ በልተው ረኩ፡፡ አንተ በሰጠሃቸው ብዙ ስጦታዎች ራሳቸውን ደስ አሰኙ፡፡26ነገር ግን አልታዘዙህም በአንተ ላይም አመጹ፡፡ በህግጋትህ ላይ ጀርባቸውን ሰጡ፡፡ ወደ አንተ መመለስ እንዳለባቸው ያስጠነቀቋቸውን ነቢያት ገደሉ፡፡ ስምህን ተራገሙ፡፡ 27ስለዚህም ያሸንፏቸው ዘንድ ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው፡፡ ነገር ግን ጠላቶቻቸው ባሰቃይዋቸው ጊዜ፣ ወደ አንተ ጮኹ፡፡ አንተ ከሰማይ ጩኸታቸውን ሰማህ፣ አንተ እጅግ መሃሪ ስለሆንክ ከጠላቶቻቸው ነጻ የሚያወጧቸውን ሁሉ ላክህላቸው፡፡ እነርሱም ነፃ አወጧቸው፡፡28ነገር ግን እንደገና የሰላም ጊዜ ከሆነ በኋላ፣ አባቶቻችን ዳግም አንተ የምትጠላውን ክፉ ነገሮች አደረጉ፡፡ ስለዚሀ ጠላቶቻቸው እንዲያሸንፏቸውና እንዲገዟቸው ፈቀድህ፡፡ ነገር ግን እንደገና እንድትረዳቸው በጮኹ ጊዜ ሁሉ አንተ ከሰማይ ሆነህ ትሰማቸዋለህ፣ አንተ በምህረት የተሞላህ ስለሆንክ ትታደጋቸዋለህ፡፡29አንተ እንደገና ህግጋትህን እንዲታዘዙ ታስጠነቅቃቸዋለህ፣ ነገር ግን እነርሱ ኩራተኞችና ግትሮች ይሆናሉ፣ ድንጋጌዎችህንም ይጥሳሉ፡፡ እንዲያደርጉ ያዘዝካቸውን ሳይታዘዙ ይቀራሉ፡፡ ለትዕዛዛትህ አንዳች ትኩረት አይሰጡም፡፡ አንተን መስማትን በግትርነት ይቃወማሉ፡፡30አንተ ለብዙ አመታት ታግሰሃቸው ነበር፡፡ መንፈስህ ለነቢያት በሚሰጣቸው መልዕክት አማካይነት ታስጠነቅቃቸዋለህ፡፡ ነገር ግን እነርሱን እነዚያን መልዕክቶች አይሰሙም፡፡ ስለዚህ እንደገና በአጠገባቸው ያሉ የአህዛብ ነገስታት እንዲያሸንፏቸው ትፈቅዳለህ፡፡ 31ነገር ግን አንተ በይቅርታ ስለተሞላህ ሙሉ ለሙሉ አታጠፋቸውም ወይም ለዘለዓለም አትተዋቸውም አንተ መሀሪና ይቅር ባይ አምላክ ነህ!32አምላካችን ሆይ፣ አንተ ታላቅ ነህ! አንተ ሃያል ነህ! አንተ አስደናቂ ነህ! አንተ እንደምታደርግልን በኪዳንህ ቃል እንደ ገባህልን በታማኝነት ትወደናለህ! ነገር ግን እኛ በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ታላቅ ችግሮች አሉብን፡፡ መከራችን በፊትህ እንደ ቀላል አይታይ! ይህ በእኛ ነገስታት ልዑላን፣ ካህናት፣ ነቢያት፣ አባቶች እና በመላው ህዝብህ ላይ ከአሶር ነገስታት ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ደርሷል፡፡ 33በቀጣኸን ጊዜ ሁሉ በጥፋታችን እንደተቀጣን እናውቃለን፡፡ እጅግ በድለናል፣ አንተ ግን በምህረትህ አይተኸናል እኛ ክፉ አድርገናል፡፡ 34ንጉሶቻችን እና ሌሎች መሪዎች፣ ካህኖቻችን እና የእኛ አባቶች ህግህን አልጠበቁም፡፡ እነርሱ ትዕዛዛትን ወይም የሰጠኃቸውን ማስጠንቀቂያዎች አልሰሙም፡፡35የራሳቸው ነገስታት በኖራቸው ጊዜ እንኳን፣ በዚህ በሰጠሃቸው ሰፊና ለም ምድር ለእነርሱ ባደረግካለቸው መልካም ነገሮች በተደሰቱ ጊዜ እንኳን፣ አንተን አላገለገሉህም ደግሞም ክፉ ማድረጋቸውን አላቆሙም፡፡36ስለዚህ አሁን ምድሪቱ በምታበቅለው መልካም ነገሮች ሁሉ ደስ እንዲሰኙ ለአባቶቻችን በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ባሮች ነን፡፡ እነሆ ዛሬም በዚህ ባሮች ነን! 37ስለበደልን ምድሪቱ የምታበቅለውን ነገሮች መብላት አልቻልንም፡፡ አሁን እኛን የሚገዙ ነገስታት በዚህ በሚበቅሉ ነገሮች ደስ እየተሰኙ ነው፡፡ እነርሱ ይገዙናል ከብቶቻችንንም ይወስዳሉ፡፡ እኛ እነርሱን የማገልገልና ደስ የሚያሰኛቸውን ነገሮች የማድረግ ግዴታ አለብን፡፡ በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እንገኛለን፡፡38ከዚህ ሁሉ የተነሳ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች በጥቅልል ጽሁፍ ታላቅ ስምምነት እናደርጋለን፡፡ በጥቅልሉ ላይ የመሪዎቻችንን፣ የሌዋውያንን፣ የካህናትን ስሞች እንጽፍና ማህተም እናደርግበታለን፡፡”
1በስምምቱ ላይ የፈረሙት የስማቸው ዝርዝር ይህ ነው፡2በጽሁፉ ላይ የፈረሙ ካህናት እነዚህ ናቸው፡ ሠራያ፣ ዓዛርያስ፣ ኤርምያስ3ፉስኮር፣ አማርያ፣ መልክያ፣4ሐጡስ፣ ሰበንያ፣ መሉክ5ካሪም፣ ሜሪምት፣ አብድዩ6ዳንኤል፣ ጌንቶን፣ ባሮክ7ሜሱላም፣ አብያ፣ ሚያሚን፣8መዓዝያ፣ ቤልጋይ፣ ሸማያ እነዚህ ካህናት ነበሩ፡፡9የፈረሙት ሌዋውያን ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፣ ቤንዊ፣ ከኤንሐዳድ፣ ቀድምኤል፣10ሰባንያ፣ ሆዲያ፣ ቆሊጣስ፣ ፌልያ፣ ሐናን11ሚካ፣ ሪአብ፣ ሐሽብያ፣12ዘኩርር ሰራብያ፣ ሰበንያ፣13ሆዲያ፣ ባኒ፣ ብኒኑ፡፡14በመጽሐፍ ጥቅሉ ላይ የፈረሙት የእስራኤል መሪዎች እነዚህ ነበሩ፡ ፋሮስ፣ ፈሐት፣ ሞዓብ፣ ኤላም፣ ዛቱዕ፣ ባኒ፡፡15ቡኒ፣ ዓዝጋድ፣ ቤባይ፣16አዶንያስ፣ በጉዋይ፣ ዓዲን17አጤር፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዙር፣18ሆዲያ፣ ሐሱም፣ ቤሳይ19ሐሪፍ፣ ዓናቶት፣ ኖባይ፣20መግጲዓስ፣ ሜሱላም፣ ኤዘር21ሜሴዜቤል፣ ሳዶቅ፣ ያጹአ፣22ፈላጥያ፣ ሐናን፣ ዓናያ፣23ሆሴዕ፣ ሐናንያ፣ አሱብ፣24አሎኤስ፣ ፈልሃ፣ ሶቤቅ25ሬሁም፣ ሐሰብና፣ መዕሤያ፣26አኪያ፣ ሐናን፣ ዓናን፣27ሙሉክ፣ ካሪምና በዓና፡፡28ካህናቱን በር ጠባቂዎቹን፣ ዘማሪዎቹን እና የመቅደስ ሰራተኞቹን ጨምሮ የቀረው ሕዝብ የከበረ ስምምነት አደረጉ፡፡ እንደዚሁም አገራቸውን ለቀው የወጡትንና በእስራኤል ይኖሩ የነበሩትን ጎረቤቶቻቸው ከሆኑ ከሌሎች ህዝቦች ወንዶችን ሁሉ ጨመሩ፡፡ እነዚህ ወንዶች ከሚስቶቻቸውና የሚያደርጉትን ለይተው ከሚያውቁ ከፍ ካሉ ወንድና ሴት ልጆቻቸው ጋር ሆነው የእግዚአብሔርን ህግ እንደሚጠበቁ ቃል ገቡ፡፡ 29ይህን የከበረ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም ከመሪዎቻቸው ጋር ተባበሩ፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ህግጋት ሁሉ ለመታዘዝ ተስማሙ፡፡ ያህዌ አምላካችን ያዘዘውን፣ ድንጋጌዎቹንና ትዕዛዛቱን ሁሉ ለመከተልና ለመፈፀም ተስማሙ፡፡ ተከታዩን ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡30“ሴቶች ልጆቻችን ያህዌን የማያመልኩትን የዚህ ምድር ሰዎች እንዲያገቡ አንሰጥም፣ ወንድ ልጆቻችን ሴት ልጆቻቸውን እንዲያገቡም አንፈቅድም፡፡31ምድር የሚኖሩ የሌላ አገር ሰዎች በሰንበት ወይም በሌላ በተቀደሰ ቀን እህል ወይም ሌሎች ነገሮችን ሊሸጡልን ቢያመጡ፣ አንዳች ነገር አንገዛቸውም፡፡ እናም በየሰባት አመቱ አንዴ ለምድሪቱ እረፍት እንሰጣለን፤ በዚያን አንድ አመት ምንም አይነት እህል አንዘራም፤ እንዲሁም ለሌሎች አይሁዶች እዳቸውን ሁሉ እንሰርዛለን፡፡32እንዲሁም እያንዳንዳችን ቤተ መቅደሱን ለሚያገለግሉና ለሚንከባከቡ በየአመቱ 5 ግራም ብር ለመክፈል ቃል ገባን፡፡ 33በዚያ ገንዘብ እነዚህን ነገሮች መግዛት ይችላሉ፡ በእግዚአብሔር ፊት በገበታው ላይ የሚቀርብ ዳቦ፣ በእያንዳንዱ ቀን በመሰዊያው ላይ የሚቀርብ የእህል ቁርባን፣ በመሰዊያ ላይ ታርደው ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠሉ እንስሳት፣ ለእግዚአብሔር በሰንበት የሚርቡ የተቀደሱ መስዋዕቶች እና የአዲስ ጨረቃ በዓልን ለማክበርና ለሌሎች በዓላት መስዋዕቶች፣ ለእስራኤል ህዝቦች ኃጢአት መስዋዕት የሚሆኑ እንስሳት፣ እና ማናቸውም የቤተመቅደሱን ሥራ ለመንከባከብ የሚያስፈልጉ ሌሎች ነገሮች መግዛት ይችላሉ፡፡34በየአመቱ ካህናቱ፣ ካህናቱን የሚረዱ የሌዊ ትውልዶች እና የተቀረነው በእግዚአብሔር ሕግ እንደተፃፈው በዚያ አመት ከሌዋውያን መሃል የትኛው ቤተሰብ በአምካላችን በእግዚአብሔር ቤት መስዋዕቶቹን ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ የሚነደውን እንጨት እንደሚያቀርቡ ለመወሰን እጣዎችን እንጥላለን፡፡35በእያንዳንዱ አመት እያንዳንዱ ቤተሰብ በእርሻችን ካበቀልነውና ለምግብ ካጨድነው እንዲሁም በዚያ አመት ከፍራፍሬ ዛፎች የተገኘውን በኩራት መስዋዕት አድረገን ወደ ቤተ መቅደስ ለማምጣት ቃል እንገባለን፡፡36የበኩር ወንድ ልጆችንና የላም፣ የበግና የፍየል በኩሮችን ለእግዚአብሔር መታሰበያ አድርገን ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣለን፡፡ ማድረግ የሚገባን፣ በእግዚአብሔር ሕግጋት የተፃፈው ይህ ነው፡፡37በየአመቱ ካመረትነው እህል ከበኩራቱ የተዘጋጀ ዱቄት ለካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ እናመጣለን፣ እንዲሁም ሌሎች የወይን፣ የወይራ ዘይትና የፍራፍሬ መስዋዕቶችንም ከበኩራቱ እናመጣለን፡፡ ካህናቱን ለሚረዱ የሌዊ ትውልዶች አስራቶችንም እናመጣለን፡፡38የአሮን ትውልድ የሆነ አንድ ካህን፣ ከሌዋውያን ጋር ሆኖ አስራቶችን ሲሰበስቡ አብሮ ይገኛል፡፡ ከዚያ የሌዊ ትውልዶች ድርሻቸውን ይወስዳሉ፤ ህዝቡ ካመጣው ነገሮች አንድ አስረኛውን ይወስዱና በቤተ መቅደስ በግምጃ ቤት ያስቀምጣሉ፡፡39የሌዊ ትወልዶችና አንዳንድ የእስራኤል ሰዎች በቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉ የእህል፣ የወይን፣ እና የወይራ ዘይት ስጦታዎችን የተለያዩ መገልገያዎች ወደ ሚከማቹበት ግምጃ ቤቶች መውሰድ አለባቸው፡፡ በዚያን ጊዜ የሚያገለግሉ ካህናት፣ በር ጠባቂዎች፣ እና በቤተ መቅደስ የሚዘምሩ የዝማሬ ቡድን የሚኖሩበት ስፍራ ይህ ነው፡፡ “የአምላካችንን ቤተ መቅደስ ከመጠበቅ ቸል እንደማንል ቃል እንገባለን፡፡”
1የእስራኤል መሪዎችና ቤተሰቦቻቸው በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ ለእግዚአብሔር በተለየችው ከተማ የሚኖሩትን ከአስሩ ቤተሰብ አንዱን ለመለየት የተቀሩት ሰዎች እጣ ተጣጣሉ፡፡ 2በኢየሩሳሌም ለመኖር ፈቃደኛ የሆኑትን ሰዎች እግዚአብሔር እንዲባርካቸው ጸለዩላቸው፡፡3እነዚህ ቢየሩሳሌም ለመኖር የመጡት የአውራጃው ባለስልጣናት ናቸው፡፡ ነገር ግን በይሁዳ ከተሞች እያንዳንዱ በየራሱ ቤተሰብ ንብረት በየራሱ ከተማ ኖረ፡፡ አንዳንዶች ካህናት፣ ሌዋውያን፣ የቤተመቅደስ አገልጋዮች እና የሰለሞን አገልጋዮች ትውልዶች የሆኑ እስራኤላውያን በኢየሩሳሌም ውስጥ ለመኖር መጡ፡፡ 4ነገር ግን አንዳንድ የይሁዳ ሰዎች እና የብንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም ቆዩ በዚያም ኖሩ፡፡ እነዚህ ከይሁዳ ወገን ናቸው፡፡ የፋሬስ ትውልድ፣ የመላልኤል ልጅ፣ የሶፋጥያስ ልጅ፣ የአማርያ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የኦዝያ ልጅ አታያ ናቸው፡፡5እና የይሁዳ ልጅ ሴሎ ትውልድ የሆነው የዘካርያስ ልጅ፣ የዮያሪብ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣ የኦዛያ ልጅ፣ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ ነበር፡፡ 6በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ትውልዶች 468 ወንዶች ነበሩ፡፡7ከብንያም ትውልድ በኢየሩሳሌም ለመኖር ከወሰነው ጎሳ ሰዎች መሀል አንዱ የየሻያ ልጅ፣ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ፣ የቆላያ ልጅ፣ የፈዳያ ልጅ፣ የዮእድ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ ነው፡፡ 8የሳሉ ሁለቱ ቤተ ዘመዶች ጌቤ እና ሳላይም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ በአጠቃላይ ከብንያም ጎሣ 928 ሰዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ 9መሪያቸው ዝክሪ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሹም ሐስኑአ ነበር፡፡10በኢየሩሳሌም የተቀመጡት ካህናት የዮያሪብ ልጅ ዮዳኤ፣11አስቀድሞ የካህናቱ ሁሉ መሪ የነበረው የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ የሜሱላም ልጅ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ ነበር፡፡ 12በአጠቃላይ ከዚያ ነገድ የቤተ መቅደሱ ሠራተኞች 822 ሰዎች ናቸው፡፡ በኢየሩሳሌም የተቀመጠ ሌላው ካህን የመልክያ ልጅ፣ የፋስኮር ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ የአማሲ ልጅ፣ የፈላልያ ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ ነበር፡፡13በኢየሩሳሌም የተቀመጡ የዚያ ነገድ መሪዎች በጠቅላላው 242 አባላት ነበሩ፡፡ በኢየሩሳሌም የተቀመጠው ሌላው ካህን የኢሜር ልጅ፣ የምሺሌሞት ልጅ፣ የአሕዛይ ልጅ፣ የኤዝርኤል ልጅ፣ አማስያ ነበር፡፡ 14ከዚያ ነገድ ደፋር የሆኑ 128 ወታደሮች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ የእነርሱ መሪ የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበር፡፡15በኢየሩሳሌም የተቀመጠው ሌላው የሌዊ ትውልድ የቡኒ ልጅ የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሻማያ ነበር፡፡16ከቤ ተመቅደሱ ውጭ ያለውን ሥራ የሚከታተሉ ሁለቱ ሌዋውያን ታላላቅ ሰዎች ሳባታይ እና ዮዛባት ነበሩ፡፡17ሌላው የአሳፍ ልጅ፣ የዘብዲ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ ነበር፡፡ መታንያ የቤተ መቅደሱ የመዘምራን ቡድን እግዚአብሔርን ለማመስገን ዝማሬ ሲያቀርብ ቡድኑን ይመራ ነበር፡፡ ረዳቱ በቅበቃር ነበር፡፡ ሌላው በኢየሩሳሌም የተቀመጠው የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ አብድያ ነበር፡፡ 18በጠቅላላው፣ ለእግዚአብሔር በተለየችው ከተማ 284 ሌዋውያን ነበሩ፡፡19በኢየሩሳሌም የተቀመጡት በር ጠባቂዎች ዓቁብ እና ጤልሞን ነበሩ፡፡ እነርሱና በአጠቃላይ በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ቤተሰቦቸው 172 ነበሩ፡፡20ሌሎቹ የእስራኤል ትውልዶች የሌዊና ካህናትን ትውልዶች ጨምሮ በገዛ ይዞታቸውና በሌሎች ከተሞችና በይሁዳ ከተማዎች ተቀመጡ፡፡ 21የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች ግን በኦፌል ኮረብታ ኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀመጡ፡፡ እነርሱን የሚያዙት ሲሐ እና ጊሽጳ ነበሩ፡፡22በኢየሩሳሌም የሚኖሩት የሌዊ ትውልዶች አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሻብ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበር፡፡ ኦዚ የአሳፍ ነገድ፣ በቤተ መቅደስ የዝማሬ ክፍሉ ሀላፊ ወገን ነበር፡፡23የፋርስ ንጉስ እያንዳንዱ ነገድ በእያንዳንዱ ቀን በቤተ መቅደስ በሚቀርበው ዝማሬ እያንዳንዱ ነገድ የሚሰራውን ነገዶቹ እንዲወስኑ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡24የይሁዳ ትውልድ የዛራ ነገድ የሆነው የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ በፋርስ መንግስት የእስራኤል አምባሳደር ነበር፡፡25በኢየሩሳሌም ያልተቀመጡት አንዳንድ ሰዎች በእርሻቸው አቅራቢያ በሚገኙ መንደሮች ይኖሩ ነበር፡፡ ከይሁዳ ነገድ የሆኑ አንዳንዶች በቂርያት አርባቅ፣ በዲቦን፣ እና በይቀብጽኤል አጠገብ በሚገኙ መንደሮች ኖሩ፡፡ 26አንዳንዶቹ በኢያሱ፣ በምላዳ፣ በቤትጳሌጥ፣ 27በሐጸርሹዓል እና በቤርሳቤህ እንዲሁም በአቀራቢያው ባሉ መንደሮች ኖሩ፡፡28ሌሎቹ በጺቅላግ፣ በምኮና እና በአካባቢው ባሉ መንደሮች፣ 29በዓይንሪሞን፣ በጸርዓ፣ በየርሙት፣ 30በዛኖዋ፣ በዓዶላም፣ እና በእነዚያ ከተሞች አቅራቢያ ተቀመጡ፡፡ አንዳንዶቹ በለኪሶ እና በአካባቢ ባሉ መንደሮች፣ እንዲሁም አንዳንዶች በዓዜቃና በአካባቢዋ ባሉ መንደሮች ተቀመጡ፡፡ እነዚህ ሁሉ ህዝቦች በደቡብ በቤርሳቤህ መሀል ባሉ ስፍራዎች እና በሰሜን ቦኖም ሸለቆ በኢየሩሳሌም ዳርቻ በይሁዳ ተቀመጡ፡፡31የብንያም ጎሣ ሰዎች በጌባ፣ ማክማስ፣ በጋያ ይህ አይ ቤቴል ተብሎም ይታወቃል፣ እና በአካባቢው ባሉ መንደሮች፣ 32በዓናቶች፣ በኖብ፣ በሐናንያ፣ 33በሐጾር፣ በራማ፣ በጊቴም፣ 34በሐዲድ፣ በስቦይም፣ በንቦላት፣ 35በሎድ፣ በአኖ፣ እና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ሸለቆ በሚባሉ ቦታዎች ተቀመጡ፡፡36በይሁዳ የኖሩ አንዳንድ ሌዋውያን ከብንያም ሰዎች ጋር ለመኖር ሄዱ፡፡
1ብዙ ካህናትና የሌዊ ትውልዶች ከዘሩባቤል እና ከኢያሱ ጋር ከባቢሎን ተመለሱ፡፡ እነዚህም፡ ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣2አማርያ፣ ሙሉክ፣ ሐጡስ፣3ሴኬንያ፣ ሬሁም፣ ሜሪሞት፣4አዶ፣ ጌንቶን፣ አብያ፣5ሚያሚን፣ መዓድያ፣ ቢልጋ፣6ሸማያ፣ ዮያሪብ፣ ዮዳኤ፣7ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ ነበሩ፡፡ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቸው አለቆች ነበሩ፡፡8የተመለሱት የሌዊ ትውልዶች ዝርዝር ይህ ነው፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እና መታንየ ነበሩ፡፡ የእነዚሀ ሀላፊነት ለእግዚአብሔር የምስጋና ዝማሬ ማቅረብ ነበር፡፡ 9በቅቡቅያ፣ ዑኒም እና ሌሎች የሌዊ ትውልዶች በዝማሬ ወቅት በትይዩ የሚቆሙ የዝማሬ ቡድን አበጁ፡፡10ከብዙ አመታት አስቀድሞ አያሱ ሊቀ ካህን ነበር፡፡ ኢያሱ የዩአቂም አባት ነበረ፣ ዮአቄም የኤልያሴብ አባት ነበረ፣ ኤልያሴብ የዩአዳን አባት ነበረ፣ 11ዩአዳ የዮናታን አባት ነበረ፣ ዮናታን የያዱአን አባት ነበረ፡፡12ዮአቂም የካህናቱ ሁሉ መሪ ነበረ፡፡ የካህናቱ ቤተሰቦች መሪዎች እነዚህ ነበሩ፡ የሠራያ ቤተሰብ መሪ ምራያ፣ የኤርምያስ ቤተሰብ መሪ ሐናንያ፣13የዕዝራ ቤተሰብ መሪ ሜሱላም፣ የአማርያ ቤተሰብ መሪ ይሆሐናን 14የሙሊኪ ቤተሰብ መሪ ዮናታን፣ የሰብንያ ቤተሰብ መሪ ዮሴፍ15ከካሪም ቤተሰብ ብዙዎቹ መሪዎች ዓድና ነበሩ፣ ከመራዮት ቤተሰብ ሔልቃይ16ከአዶ ቤተሰብ ዘካርያስ ከጌንቶን ቤተሰብ ሜሱላም17ከአብያ ቤተሰብ ዝክሪ መሪዎች ነበሩ፡፡ ከሚያሚን ቤተሰብም አንድ መሪ ነበር፡፡ ከሞዓድያ ቤተሰብ ፈልጣይ ነበር፡፡18ከቢልጋ ቤተሰብ ሳሙስ፣ ከሸማያ ቤተሰብ ዮናታን19ከዮያሪብ ቤተሰብ መትናይ፣ ከዮዳኤ ቤተሰብ ኦዚ፣20ከሳላይ ቤተሰብ ቃላይ፣ ከዓምቅ ቤተሰብ ዔቤር፣21ከኬልቅያስ ቤተሰብ ሐሽብያ፣22ኤሊያሴብ ሌዋውያንን በሚመራበት ወቅት፣ የእነርሱ ሁሉ ዝርዝር ይህ ነው፡ ኤሊያሴብ፣ ዮአዳ፣ ዮሐና እና ያዱአ የካህናቱ ሁሉ መሪዎች ነበሩ፡፡ እነርሱ የሌዊ ትውልድ የሆኑትን ቤተሰቦች ስሞች መዘገቡ፡፡ዳርዮስ የፋርስ ንጉስ በነበረበት ዘመን የየቤተሰቡን መሪዎች የመመዝገቡ ሀላፊነት የካህናቱ ነበር፡፡ 23የሌዊ ትውልድ የሆኑ የቤተሰብ መሪዎችን ስሞች ዝርዝር በታሪክ መጽሐፍ ጽፈው ነበር፡፡ የኤልያሴብ የልጅ ልጅ የሆነው ዮሐና የካህናት ሁሉ መሪ እስከ ሆነበት ጊዜ ድረስ ያሉትን ክንዋኔዎች መዝግበው ነበር፡፡24እነዚህ የሌዋውያን መሪዎች ነበሩ፡ ሐሽብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድመኤል ልጅ ኢያሱ፣ እና ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና ለማቅረብ ከእነርሱ ፊት ለፊት የቆሙ ወንድሞቸው፡፡ ይህንንም የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነው ንጉስ ዳዊት እንዳዘዛቸው እንደዚያው አደረጉ፡፡25በር ጠባቀዎቹ፣ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ፡፡ 26አገረ ገዢው ነህምያ እና ካህኑ ዕዝራ በነበሩበት ወቅት፣ በኢዮሴዴቅ የልጅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮቂም ዘመን ይህንን ሥራ ሰሩ፡፡ ዕዝራ የአይሁድን ህግጋትም በሚገባ ያውቅ ነበር፡፡27የኢየሩሳሌምን ቅጥር ስንመርቅ፣ የሌዊን ትወልዶች ከሚኖሩባቸው የእስራኤል አካባቢዎች የቅጥሩን ምርቃት ያከብሩ ዘንድ ጠራናቸው፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ብዙዎቹም በጽናጽልና፣ በበገና፣ በክራርና በሌሎች የክር ሙዚቃ መሳሪያዎች በመጫወት ይዘምሩ ነበር፡፡ 28በህብረት ያለማቋረጥ የሚዘምሩትን የሌዊ ወገኖች ሰበሰብን፡፡ ከሰፈሩበት ከኢየሩሳሌም ዙሪያ ከነጦፋውያን መንደሮችና ከደቡብ ምስራቅ ኢየሩሳሌም ወደ መሃል ኢየሩሳሌም መጡ፡፡29ከሰሜን ምስራቅ የኢየሩሳሌም ሶስት ቦታዎችም ከቤት ጌልገላ፣ ከጌባ አካባቢና ከዓዝሞት አካባቢ መጡ፡፡ መዘምራኑ ኢየሩሳሌም አቅራቢያ መንደሮችን መሰረቱ፡፡30ካህናቱና የሌዊ ወገኖች ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት የመንጻት ሥርዓት አደረጉ፣ ለህዝቡም ይህንኑ ስርዓት አደረጉ፣ ለከተማዋ መግቢያዎችና በመጨረሻም ለቅጥሩ ጭምር ስርዓቱን ፈጸሙ፡፡31ከዚያ በቅጥሩ ጫፍ የይሁዳ መሪዎችን በአንድነት ሰበሰብኩ፣ እግዚአብሔርን እያገገኑ በቅጥሩ ላይ በከተማዋ ዙሪያ በሰልፍ እንዲዞሩ ሁለት ትላልቅ ቡድኖችን እዲመሩ ሾምኳቸው፡፡ በከተማይቱ ትይዩ ሲሆኑ፣ አንዱ ቡድን ወደ ቀኝ የቆሻሻ መጣያው በር ወደሚባለው ሄደ፡፡32ከመሪዎቻቸው በኋላ ሆሻያና የይሁዳ እኩሌቶቹ መሪዎች ተሰለፉ፡፡ 33ከእነርሱ በኋላ የተከተሏቸው ዓዛርያስ፣ ዕዝራ፣ ሜሱላም፣ 34ይዳ፣ ብንያም፣ ሸማያ፣ ኤርምያስ፣ 35እና መለከት የሚጫወቱ አንዳንድ የክህናቱ ወንዶች ልጆች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የአሳፍ ትውልድ የሆኑት የዘኩር ልጅ፣ የሚካያ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሸማያ ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ ይገኙበታል፡፡36ከእነዚህ በኋላ የሚገዙት የዘካርያስ ቤተሰቦች ሌሎች አባላት ነበሩ፡፡ ከእነዚህም ሸማያ፣ ኤዝርኤል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ መዓይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳ፣ እና አናኒምን ያካትታል፡፡ ሁሉም ንጉስ ዳዊት ከብዙ አመታት አስቀድሞ ይጫወትበት የነበሩ እነዚያኑ አይነት የሙዚቃ መሳሪያዎችን ይጫወቱ ነበር፡፡ የአይሁድን ህግጋት በሚገባ የሚያውቀው ሰው ዕዝራ፣ ከዚህ ቡድን ፊት ሰልፉን ይመራ ነበር፡፡ 37የፋፏቴ በር ሲደርሱ፣ ወደ ዳዊት ከተማ ደረጃዎችን ወጡ፣ የዳዊትን ቤተ መንግስት አልፈው፣ ከዚያ ውሃ በር አጠገብ ወደሚገኘው ቅጥር በከተማዋ ምስራቅ አቅጣጫ ሄዱ፡፡38ለያህዌ ይዘምርና ያመሰግን የነበረው ሌላው የዝማሬ ቡድን በቅጥሩ ላይ በግራ በኩል በሰልፍ አለፈ፡፡ እኔ ከህዝቡ ከፊሉን ይዤ ተከተልኳቸው፡፡ እኛ የእቶን ግንቡን አልፈን ወደ ሰፊው ቅጥር አለፍን፡፡39ከዚያ ተነስተን የኤፍሬምን በር፣ የጄቫናን በር፣ የአሣን በር፣ የሐናንኤልን ግንብ፣ የመቶ ወታደሮችን በር አልፈን ወደ በጎች በር ተጓዝን፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ስንቃረብ ሰልፋችንን ጨረስን፡፡40ሁለቱም ቡድኖች እየዘመሩና እርሱን እያመሰገኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት ደረሱ፡፡ በዚያም በየስፍራቸው ቆሙ፡፡ እኔና ከእኔ ጋር የነበሩ መሪዎችም በስፍራችን ቆምን፡፡41የእኔ ቡድን መለከት የሚነፉትን እነዚህን ካህናት ያጠቃልላል፡ ኤልያቄም፣ መዕሤያ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያ፣ ኤልዮዔናይ፣ ዘካርያስ እና ሐናንያ፣ 42ሌሎቹም መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ይሆሐናን፣ መልክያ፣ ኤላም እና ኤድር ናቸው፡፡ መሪያቸው ይዝራሕያ የሆነው መዘምራኑ ድምቸውን ከፍ አድርገው ዘመሩ፡፡43ከቤተ መቅደሱ ውጭ ከሄድን በኋላ ብዙ መስዋዕቶችን አቀረብን፡፡ እኛ ወንዶች ሁላችን እግዚብሔር በጣም ደስተኞች ስላደረገን ደስ አለን፡፡ ሴቶቹና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ በሩቅ ያሉ ሰዎች እኛ በኢሩሳሌም ውስጥ ሆነን የምናሰማውን ድምጽ መስማት ይችሉ ነበር፡፡44በዚያን ቀን ህዝቡ ለቤተ መቅደስ የሰጠውን ገንዘብ ለሚያስቀምጡበት ግምጃ ቤት ሀላፊ የሚሆኑ ወንዶች ተሾሙ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለአስራትና በየአመቱ ለሚሰበሰበው እህልና ፍራፍሬ በኩራቶችም ሀላፊዎች ነበሩ፡፡ እነዚሁ ሰዎች ወደ ግምጃ ቤቶቹ ከእርሻዎች ምርት ለካህናቱና ለሌዊ ትውልዶች ያመጡ ነበር፡፡ ይህ የተደረገው የይሁዳ ሰዎች በያህዌ ቤት የሚያገለግሉ አገልጋዮች እንዲኖር ይፈልጉ ስለነበር ነው፡፡ 45ካህናቱና ሌዋውያኑ ነገሮችን ለማንጻት፣ በማንጻት ስርዓቱ ያህዌን ያገለግሉ ነበር፤ መዘምራኑ በቤተ መቅደስ፣ እንዲሁም በር ጠባቂዎቹ ንጉስ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን እንዲደረግ እንደ ደነገጉት ስራቸውን ያከናውኑ ነበር፡፡46ከዳዊትና ከአሳፍ ዘመን አንስቶ፣ የዘማሪዎች መሪዎች ነበሩ፤ መዘምራኑም እግዚአብሔርን ለማወደስና ለማመስገን ይዘምሩ ነበር፡፡ 47ዘሩባቤል በነበረበት አመታትና በአገረ ገዥው ነህምያ ዘመን፣ ዘማርያኑና የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎች በየዕለቱ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ መላው እስራኤል ያወጣ ነበር፡፡ ህዝቡ ለሌዋውያን ኑሮ የሚያስፈልገውን ያስቀምጡላቸውና ሌዋውያኑ ደግሞ ከካህናቱ ቀዳሚ መሪ ለሆኑት ለአሮን ትውልዶች የሚያስፈልገውን ያስቀምጡላቸው ነበር፡፡
1በዚያን ቀን እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን አሞናዊያን ወይም ሞአባዊያን የእግዚአብሔር ህዝቦች ወደሚያመልኩበት ስፍራ አይግቡ የሚለውን የህጉን ክፍል ካህናቱ ለህዝቡ አነበቡ፤ ህዝቡም አደመጠ፡፡ 2ይህ የሆነው የአሞንና የሞአብ ሰዎች እስራኤላዊያን ከግብጽ ወጥተው ወደሚገቡበት አገር ሲጓዙ ምንም ምግብ ወይም ውሃ ስላልሰጧቸው ነበር፡፡ ይልቁንም፣ የአሞንና የሞብ ሰዎች በለዓም እስራኤላዊያንን እንዲረግም ገንዘብ ከፈሉት፡፡ እግዚአብሔር ግን እስራኤልን ለመርገም የተደረገውን ያን ጥረት ወደ በረከት ለወጠው፡፡ 3ስለዚህም ህዝቡ እነዚያ ህጎች ሲነበቡላቸው በሰሙ ጊዜ፣ አባቶቻቸው ከሌሎች አገሮች የሆኑትን ሰዎች ሁሉ አስወጡ፡፡4አስቀድሞ፣ ካህኑ ኤልያሴብ በቤተ መቅደሱ የግምጃ ቤቱ ኃላፊ ሆኖ ተሹሞ ነበር፡፡ እርሱም የጦቢያ ቤተዘመድ ነበር፡፡ እነርሱም የእህል ቁርባኖቹንና እጣኑን በዚያ ስፍራ አከማቹ፡፡ 5ለቤተ መቅደስ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን በዚያ አስቀመጡ፡፡ ህዝቡ ለሌዋውያን የሰጠውን ስጦታዎች በግምጃ ቤት አስቀመጡ፡፡ እግዚአብሔር ለሌዋውያኑ፣ ለዘማሪዎቹና ለበር ጠባቂዎች እንዲሰጡ ያዘዘውን የእህል፣ የወይንና የወይራ ዘይት አስራት አመጡ፡፡ ሌሎች ካህናትን ለመደገፍም ስጦታዎቹን አመጡ፡፡6በዚያን ጊዜ እኔ ኢየሩሳሌም ውስጥ አልነበርኩም፡፡ አርጤክስስ የባቢሎን ንጉስ በነበረበት በሰላሳ ሁለተኛው አመት ያከናወንኩትን ለንጉሱ ለመናገር ተመለስኩ፡፡ ለጥቂት ጊዜ በዚያ ከቆየሁ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም እንድመለስ እንዲፈቅደልኝ ንጉሱን ጠየቅሁት፡፡ 7ስመለስ፣ ኤልያሴብ ያደረገውን ክፉ ነገር አወቅሁ፡፡ ጦቢያ ለእግዚአብሔር የተለየውን አንድ ክፍል ቤት ለገዛ ጥቅሙ እንዲያውለው ትቶለት ነበር፡፡8እኔም በጣም ተቆጣሁ፡፡ ወደዚያ ክፍል ገብቼ የጦቢያ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አውጥቼ ጣልኩ፡፡ 9ከዚያ ያንን ክፍል እንደገና ለማንጻት የማንጻት ሥርኣት እንዲደረግ አዘዝኩ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ማናቸውም ዕቃዎችና የእህል ቁርባኖችን እንዲሁም እጣኑ ወደነበሩበት ወደዚያ ክፍል እንዲመለሱ አዘዝኩ፡፡10የእስራኤል ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ቀለብ ወደ ግምጃ ቤት ስላላመጡአቸው፣ የቤተ መቅደሱ ዘማሪዎችና ሌሎች ሌዋውያን ኢየሩሳሌምን ለቀው ወደ እርሻዎቻቸው መመለሳቸውን ተረዳሁ፡፡ 11ስለዚህ ሹማምንቱን እንዲህ ስል ገሰጽኳቸው፣ “በቤተ መቅደስ ለሚካሄደው አገልግሎት ጥንቃቄ ያላደረጋችሁት ለምንድን ነው?” ስለዚህም እነርሱን በአንድነት ሰብስቤ ወደ መጀመሪያ ስፍራቸው መለስኳቸው፡፡12ከዚያ የይሁዳ ሰዎች በሙሉ የእህል፣ የወይንና የወይራ ዘይት አስራታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት ዳግም ማምጣት ጀመሩ፡፡ 13እኔም እነዚህን ሰዎች የግምጃ ቤቶቹ ሀላፊዎች አድርጌ ሾምኳቸው፡፡ እነርሱም ካህኑ ሰሌምያ፣ የአይሁድ ህግ አዋቂው ሳዶቅ፣ እና ከሌዊ ወገን የሆነው ፈዳያ ናቸው፡፡ እነርሱን እንዲረዳ የመታንያን የልጅ ልጅ የዘኩርን ልጅ ሐናን ሾምኩት፡፡ እነዚያ ሰዎች ለሠራተኞቹ ወገኖቸው ስጦታዎችን በትክክል እንደሚያከፋፍሉ ልተማመንባቸው እንደምችል አውቅ ነበር፡፡14አምላኬ ሆይ፣ ለአንተ ቤተ መቅደስ የሰራኋቸውን እነዚህን መልካም ሥራዎችና እዚህ ለተሰራው ሰራ ሁሉ ያደረኩትን አትርሳ!15በእነዚያ ጊዜያት፣ ይሁዳ ውስጥ አንዳንዶች በሰንበት ቀን ሲሰሩ አየሁ፡፡ አንዳንዶች ወይን ለመጥመቅ የወይን ፍሬ ይረግጡ ነበር፡፡ ሌሎች እህል፣ የወይን አቁማዳዎች፣ የወይን ፍሬ የሞሉ ቅርንጫቶች፣ በለስ፣ እና ሌሎች ብዙ ነገሮች በአህዮቻቸው ጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ይወስዱ ነበር፡፡ በሰንበት ለይሁዳ ሰዎች ምንም ነገር እንዳይሸጡ አስጠነቀቅኳቸው፡፡16ደግሞም በኢየሩሳሌም የሚኖሩ አንዳንድ የጢሮስ ሰዎች በሰንበት ቀን አሳና ሌሎች ነገሮችን ለአይሁድ ሰዎች ለመሸጥ ወደ ኢየረሳሌም ሲያመጡ አይሁ፡፡ 17ስለዚህ የአይሁድን መሪዎች በመገሰጽ እንዲህ አልኳቸው፣ “ይህ የምታደርጉት በጣም ክፉ ነገር ነው! በሰንበት ቀን እግዚአብሔር በፍጹም እንዲሆን የማይወደውን ነገር እያደረጋችሁት ነው፡፡ 18አባቶችሁ እንደዚህ ያለ ነገሮችን አደረጉ፣ ስለዚህም እግዚአብሔር ቀጣቸው፡፡ በእነርሱ ኃጢአት ምክንያት ይህች ከተማ እንድትጠፋ ፈቅዶ ነበር! እና አሁን የሰንበት ቀን ህግጋትን በመተላፍ እግዚአብሔር በእኛ ላይ እንዲቆጣ ምክንያት እየሆናችሁ ነው፣ እናም የከፋ ቅጣት ይቀጣናል!”19ቀኑ ሲመሽ በኢየሩሳሌም መግቢያ ላይ አንዳንድ የራሴን ሰዎች አቆምኩ፣ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች በዚያን ቀን ምንም አይነት የሚሸጥ ዕቃ ማንም ሰው ወደ ከተማይቱ እንዳያስገባ ያደርጋሉ፡፡ 20ነጋዴዎችና ሻጮች የተለያዩ አይነት ዕቃዎችና ሸቀጦች እንዲሁም አንዳንድ ነገሮችን በማግስቱ ለመሸጥ ተስፋ አድርገው ሰንበት ከሚጀምርበት ከአርብ ምሽት አንስቶ ከኢየሩሳሌም ውጭ ለጥቂት ጊዜ ይሰፍራሉ፡፡21እኔም እንዲህ ስል አስጠነቀቅኳቸው፣ “ዓርብ ምሽት ከቅጥሩ ውጭ በዚህ ማደራችሁ አይጠቅማችሁም! ይህን ደግማችሁ ብታደርጉ፣ እኔ ራሴ አስወጣችሁና አባርራችኋለሁ!” ስለዚህ ከዚያ በኋላ፣ ዳግመኛ በሰንበት ቀናት ተመልሰው አልመጡም፡፡ 22እንደዚሁም ደግሞ የሌዊ ትውልዶች፤ ራሳቸውን ለማንጻት የማንጻት ሥርዓቱን እንዲፈጽሙና የከተማዋን በሮች ለመጠበቅ ስፍራቸውን እንዲይዙ፣ በዚያ የተቀደሰ ቀን ነጋዴዎች እንዳይገቡ በመከልከል ሰንበት ቅዱስ ሆኖ መጠበቁን እንዲያረጋግጡ አዘዝኳቸው፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ስለዚህም ደግሞ አሰበኝ! እንደ ታላቅ ፍቅርህ መጠን ምህረትህን አድርግልኝ፡፡23በዚያን ጊዜ ብዙዎቹ የአይሁድ ወንዶች ከአሽዶድ፣ አሞንና ሞዓብ ሴቶች ጋር መጋባታቸውን አወቅሁ፡፡ 24ከልጆቻቸው እኩሌቶቹ የኖሩበትን ህዝብ የአሽዶድ ሰዎችን ቋንቋ ወይም ሌላ ቋንቋ ይናገሩ እንጂ የአይድን ቋንቋ መናገር አይችሉም ነበር፡፡25ስለዚህም እነዚያን ሰዎች ገስጽኳቸው፣ እግዚአብሔር የተረገሙ እንዲያደርጋቸው ጠየቅኩት፤ አንዳንዶቹን በቡጢ መታኋቸው፤ የአንዳንዶቹንም ጸጉር ነጨሁ! ከዚያ እግዚአብሔር እንደሚሰማ በማወቅ ዳግመኛ ባዕዳንን እንዳያገቡና ልጆቻቸውም ከባዕዳን ጋር እንዲጋቡ እንዳይፈቅዱ ጥብቅ ቃል ኪዳን እንዲገቡ አስገደድኳቸው፡፡ 26እንዲህ አልኳቸው፣ “የእስራኤል ንጉስ፣ ሰለሞን፣ ከባዕድ ሴቶች ጋር በመጋባቱ ምክንያት ኃጢአት ሰራ፡፡ እርሱ ከሌሎች መንግስታት ነገስታት ሁሉ ታላቅ ነበር፡፡ እግዘአብሔር ወዶት በመላው የእስራኤል ህዝብ ላይ ንጉስ አደረገው፡፡ ነገር ግን ባዕዳን የሆኑት ሚስቶቹ ኃጢአት እንዲሰራ ምክንያት ሆኑ፡፡ 27እናንተ ስህተት መሆኑን እያወቃችሁ ባዕድ ሚስቶችን እንዳገባችሁና ጣኦት አምላኪ የሆኑ ባዕድ ሴቶችን በማግባት በአምላካችሁ ላይ ታላቅ ኃጢአት እንደፈፀማችሁ እኛም ያንን ማድረግ ያለብን ይመስላችኋልን?”28ከዮአዳ ልጆች አንዱ፣ የሊቀ ካህኑ የአልያሴብ ልጅ የሰንበላጥን ልጅ አገባ፡፡ ስለዚህ የዮአዳን ልጅ ከኢየሩሳሌም አባረርኩት፡፡29አምላኬ ሆይ በክህነት ማዕረግ ላይ ዕፍረት ያስተሉትን አስብ፣ እናም በስራቸው የክህነትንና የሌዋዊነትን ቃል ኪዳን ተላልፈዋል!30ከሌሎች አገሮችና ሀይማኖቶች ካመጧቸው ማናቸውም ነገር አነፃኋቸው፣ እንደዚሁም ለካህናቱና ለሌዊ ወገኖች ደንቦችን ሰጠሁ፣ ስለዚህም እያንዳንዳቸው ማድረግ የለባቸውን ያውቃሉ፡፡ 31በተወሰነው ጊዜና ቀናት በመሰዊያው ላይ የሚነድ ማገዶ ስለመኖሩ አረጋገጥሁ፡፡ ህዝቡ ከምርቱ በኩራቱን ወደ ግምጃ ቤት እንዲያመጣ መመሪያ ሰጠሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ እዚህን ሁሉ ነገሮች ማድረጌን አትርሳ፣ እነዚህን በማድረጌም ባርከኝ፡፡
1በአርጤክስስ ዘመን (እርሱም ከህንድ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በአንድ መቶ ሃያ ሰባት አገሮች የነገሠው ነው) 2በእነዚያ ጊዜያት ንጉሡ አርጤክስስ በሱሳ ግንብ ውስጥ ባለው የመንግሥቱ ዙፋን ላይ ተቀመጠ።3በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ለሹማምንቱና ለአገልጋዮቹ በሙሉ ግብዣ አደረገላቸው። የፋርስና የሜዶን የጦር አዛዦች፥ ባላባቶችና የአውራጃ አስተዳዳሪዎችም በፊቱ ነበሩ። 4የመንግሥቱን ውበት ባለጸግነትና የግርማውን ክብር ታላቅነት ለብዙ ቀናት ማለትም ለ180 ቀናት አስጎበኛቸው።5እነዚህ ቀናት ካበቁ በኋላ ንጉሡ ለሰባት ቀናት የሚቆይ ግብዣ አዘጋጀ። ግብዣው የተዘጋጀው ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በሱሳ ቤተመንግሥት ውስጥ ለነበሩት ሰዎች ሁሉ ነበር። ይህም የተደረገው በንጉሡ ቤተመንግሥት መናፈሻ በሚገኘው አደባባይ ውስጥ ነበር። 6ከጥጥ የተሠሩ ነጭና ሰማያዊ መጋረጃዎች ነጭና ሐምራዊ ገመድ በብር ቀለበቶቹ ውስጥ አልፈው በእምነበረዱ ቋሚዎች ላይ በመሰቀላቸው የመናፈሻው አደባባይ ተውቦ ነበር። በቀይ ዓለት፥ በእምነበረድ፥ በእንቁ እናትና የተለያየ ቀለም ባላቸው የንጣፍ ድንጋዮች ባሉት ሥዕላዊ ወለል ላይ የወርቅና የብር ድንክ አልጋዎች ነበሩ።7መጠጡ በወርቃማ መጠጫዎች ይቀርብ ነበር። እያንዳንዱ መጠጫ የተለያየ ነበር፥ ከንጉሡ ለጋስነት የተነሣም የቤተመንግሥቱ ወይን የተትረፈረፈ ነበር። 8መጠጡ ይቀርብ የነበረውም፥ "ግዴታ መኖር የለበትም" የሚለውን መመሪያ በመከተል ነበር። እንግዶቹ እያንዳንዳቸው በሚፈልጉት መጠን እንዲቀርብላቸው ንጉሡ የቤተመንግሥቱን ሠራተኞች አዝዞ ነበር።9ንግሥት አስጢን በበኩሏ በንጉሡ አርጤክስስ ንጉሣዊ ቤተመንግሥት ለሴቶች ግብዣ አደረገች። 10በሰባተኛው ቀን ንጉሡ ከወይን ጠጅ የተነሣ ልቡን ደስታ በተሰማው ጊዜ ምሁማንን፥ ባዛንን፥ ሐርቦናን፥ ገበታን፥ ዘቶልታን፥ ዜታርንና ከርከስን (በፊቱ የሚያገለግሉትን ሰባቱን ሹማምንት) ንግሥት አስጢን ዘውዷን ደፍታ በፊቱ እንድትቀርብ አዘዛቸው። 11ተክለ ሰውነቷ ያማረ ነበርና ውበቷን ለሕዝቡና ለሹማምንቱ ለማሳየት ፈለገ።12ንግሥት አስጢን ግን ንጉሡ በሹማምንቱ በላከባት ቃል መሠረት ለመምጣት እምቢ አለች። ከዚያም ንጉሡ በጣም ተቆጣ፥ ቁጣውም በውስጡ ነደደ።13ስለዚህ ንጉሡ ዘመኑን ከሚመረምሩ ጥበበኞች ሰዎች ጋር ተመካከረ (ሕግንና ዳኝነትን ስለሚያውቁት ሰዎች ሁሉ የንጉሡ ልምድ እንዲህ ነበርና) ። 14የቅርቦቹ የነበሩትም ሰባቱ የፋርስና የሜዶን መሳፍንት የሆኑት አርቄስዮስ፥ ሼታር፥ አድማታ፥ ተርሺሽ፥ ሜሬስ፥ ማሌሴዓርና ምሙካን ነበሩ። እነዚህ ለንጉሡ የሚቀርቡና በመንግሥቱ ውስጥ ከፍተኛውን ሥልጣን የያዙ ናቸው። 15"በሹማምንቱ የተላከባትን የንጉሡን የአርጤክስስን ትዕዛዝ አልታዘዘችምና በሕጉ መሠረት በንግሥት አስጢን ላይ መደረግ ያለበት ምንድነው?"16ምሙካንም በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት እንዲህ አለ፥ "ንግሥቲቱ አስጢን የበደለችው መኳንንቱን ሁሉና በንጉሡ በአርጤክስስ ግዛቶች ሁሉ የሚገኘውን ሕዝብ በሙሉ ደግሞ እንጂ ንጉሡን ብቻ አይደለም። 17የንግሥቲቱ ጉዳይ በሁሉም ሴቶች የሚታወቅ ይሆናል። ይህም ባሎቻቸውን እንዲንቁ ያደርጋል። እነርሱም፥ 'ንግሥት አስጢንን በፊቱ እንዲያቀርቧት ንጉሡ አርጤክስስ አዘዘ፥ እርስዋ ግን እምቢ አለች' ይላሉና። 18የንግሥቲቱን ጉዳይ የሰሙ የመኳንንቱ ሚስቶችም ይህ ቀን ከማለፉ በፊት ለንጉሡ መካንንቶች በሙሉ ተመሳሳዩን ቃል ይናገራሉ። ብዙ ንቀትና ቁጣም ይሆናል።19ንጉሡን ደስ የሚለው ከሆነ፥ አስጢን ዳግመኛ በፊቱ እንዳትቀርብ ንጉሣዊ ትዕዛዝ ያውጣ፥ ሊለወጥ የማይቻል ሆኖም በፋርስና በሜዶን ሕግ ውስጥ ይጻፍ። የንግሥትነቷን ክብርም ንጉሡ ክእርስዋ ለምትሻል ለሌላይቱ ይስጥ። 20የንጉሡ ትዕዛዝ በሰፊው መንግሥቱ ሁሉ በሚታወጅበት ጊዜ፥ ከታላቁ እስከ ታናሹ ድረስ ሚስቶች ሁሉ ባሎቻቸውን ያከብራሉ።"21ንጉሡና መካንንቶቹ በዚህ ምክር ተደሰቱ፥ ንጉሡም የምሙካንን ምክር ተግባራዊ አደረገው። 22እርሱም ደብዳቤዎችን ለእያንዳንዱ አውራጃ በየራሱ ጽሕፈትና ለእያንዳንዱ ሕዝብ በየራሱ ቋንቋ አድርጎ ወደ መንግሥቱ አውራጃዎች በሙሉ ላከው። እርሱም እያንዳንዱ በቤተሰቡ ላይ ገዥ እንዲሆን አዘዘ። ይህም ትዕዛዝ በመንግሥቱ ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ሕዝብ በየቋንቋው ተሰጠው።
1ከእነዚህ ነገሮች በኋላ የንጉሡ አርጤክስስ ቁጣ በበረደለት ጊዜ ንግሥት አስጢንን፥ እርሷም ያደረገችውን አሰበ። እንዲሁም በእርሷ ላይ ያስተላለፈውን የፍርድ ውሳኔ አሰበ። 2ከዚያም ያገለግሉት የነበሩት የንጉሡ ወጣቶች፥ "የተዋቡ ልጃገረዶች ለንጉሡ ይፈለጉለት።3የተዋቡ ልጃገረዶችን በሙሉ በሱሳ ቤተመንግሥት ወደሚገኘው የሴቶች መኖሪያ እንዲሰበስቧቸው በመንግሥቱ አውራጃዎች ሁሉ ንጉሡ ኃላፊዎችን ይሹም። እነርሱም የሴቶች ኃላፊ በሆነው የንጉሡ ሹም በሄጌ ጥበቃ ሥር ይደረጉ፥ እርሱም መዋቢያዎቻቸውን ይስጣቸው። 4ንጉሡን ደስ የምታሰኘው ልጃገረድ በአስጢን ፈንታ ንግሥት ትሁን።" ይህም ምክር ንጉሡን አስደሰተው፥ እርሱም እንደዚሁ አደረገ።5በሱሳ ከተማ መርዶክዮስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ነበር፥ እርሱም ብንያማዊ ሲሆን የቂስ ልጅ፥ የሰሜኢ ልጅ፥ የኢያዕር ልጅ ነበር። 6እርሱም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረከው ከይሁዳ ንጉሥ ከኢኮንያን ጋር ተማርከው ከተወሰዱት ምርኮኞች ጋር ከኢየሩሳሌም ተወስዶ ነበር።7እርሱም አባትም ሆነ እናት አልነበራትምና የአጎቱን ልጅ ሀደሳ የተባለችውን አስቴርን ያሳድግ ነበር። ልጃገረዲቱም የተዋበ ተክለሰውነትና ማራኪ ገጽታ ነበራት። መርዶክዮስ እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ ወስዷት ነበር።8የንጉሡ መመሪያና ትዕዛዝ በታወጀ ጊዜ ብዙ ልጃገረዶችን ወደ ሱሳ ቤተመንግሥት ሰበሰቧቸው። እነርሱም ከሄጌ ጥበቃ ሥር ተደረጉ። አስቴርም ደግሞ ወደ ቤተመንግሥቱ ተወስዳ ከሴቶቹ ተቆጣጣሪ ከሄጌ ሥር ተደረገች። 9ልጃገረዲቱ ደስ አሰኘችው፥ በፊቱም ሞገስን አገኘች። ወዲያውም የምግብ ድርሻዋንና መዋቢያዎቿን ሰጣት። ለእርሷም ከንጉሡ ቤተመንግሥት የሚያገለግሏትን ሰባት ልጃገረዶች መደበላት፥ እርሷንና የሚያገለግሏትን ልጃገረዶች በሴቶቹ መኖሪያ ውስጥ ወደ ተሻለው ክፍል አዛወራቸው።10መርዶክዮስ እንዳትናገር አዝዟት ስለ ነበር፥ አስቴር ሕዝቧንም ሆነ ወገንዋን ለማንም አልተናገረችም ነበር። 11መርዶክዮስ የአስቴርን ደኅንነትና ያለችበትን ሁኔታ ለማወቅ በየዕለቱ በሴቶቹ መኖሪያ በስተውጭ ባለው አደባባይ ይመላለስ ነበር።12እያንዳንዷ ልጃገረድ ወደ ንጉሡ አርጤክስስ የምትሄድበት ተራ በደረሰ ጊዜ - ለሴቶቹ በወጣው ደንብ መሠረት እያንዳንዷ ልጃገረድ ስድስት ወር በከርቤ ዘይት፥ ስድስት ወር ደግሞ በሽቶዎችና በመዋቢያዎች ለአሥራ ሁለት ወራት የውበት አያያዝ ጊዜአቸውን ማጠናቀቅ ነበረባቸው - 13አንዲት ልጃገረድ ወደ ንጉሡ በምትሄድበት ጊዜ ወደ ቤተመንግሥት እንድትወስደው የፈለገችው ሁሉ ከሴቶቹ መኖሪያ ይሰጣት ነበር።14ሲመሽ ትገባና ሲነጋ ወደ ሁለተኛው የሴቶች መኖሪያ፥ በቁባቶቹ ላይ ኃላፊ ወደሆነው የንጉሥ ሹም ወደ ሻአሽጋዝ ጥበቃ ሥር ትመለስ ነበር። ንጉሡ ተደስቶባት ዳግም ካልጠራት በስተቀር ሁለተኛ ወደ እርሱ መመለስ አትችልም ነበር።15ወደ ንጉሡ ለመግባት የአስቴር (መርዶክዮስ እንደ ራሱ ልጅ አድርጎ የወሰዳት የአቢካኤል ልጅ) ተራ በደረሰ ጊዜ በሴቶች ላይ ኃላፊ የሆነው የንጉሡ ሹም ሄጌ ከነገራት በቀር ምንም ነገር አልጠየቀችም። አስቴርም በሚያዩዋት ሁሉ ፊት ሞገስን ታገኝ ነበር። 16አስቴርም ንጉሡ አርጤክስስ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት፥ ቴቤት ተብሎ በሚጠራው በአሥረኛው ወር፥ ወደ ንጉሣዊ መኖሪያው ተወሰደች።17ንጉሡም ከሌሎቹ ሴቶች ሁሉ ይልቅ አስቴርን ወደዳት፥ ከደናግሉም ሁሉ ይልቅ በፊቱ ሞገስንና መወደድን አገኘች፥ ስለዚህ የእቴጌነትን ዘውድ በራሷ ላይ አደረገላት፥ በአስጢንም ምትክ ንግሥት አደረጋት። 18ንጉሡም "የአስቴር ግብዣ" ብሎ የጠራውን ታላቅ ግብዣ ለሹማምንቱና ለአገልጋዮቹ ሁሉ አደረገ፥ አውራጃዎቹንም ከቀረጥ አሳረፋቸው። ደግሞም በንጉሣዊ ልግስናው ስጦታዎችን ሰጠ።19ደናግሎቹ ለሁለተኛ ጊዜ በተሰበሰቡ ጊዜ መርዶክዮስ በንጉሡ በር ይቀመጥ ነበር። 20አስቴር ሕዝቧን ወይም ወገኗን መርዶክዮስ ባዘዛት መሠረት ገና ለማንም አልተናገረችም ነበር። እርሷም በልጅነትዋ ጊዜ ታደርግ አንደነበረው የመርዶክዮስን ምክር መከተልዋን ቀጠለች። 21በእነዚያም ቀናት መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ እያለ በሩን ይጠብቁ የነበሩት ሁለቱ የንጉሡ ሹማምንት ገበታና ታራ ተቆጡ፥ ንጉሡን አርጤክስስንም ለመግደል ፈለጉ።22መርዶክዮስ ጉዳዩን ባወቀ ጊዜ ለንግሥት አስቴር ነገራት፥ እርሷም በመርዶክዮስ ስም ለንጉሡ ነገረችው። 23መረጃው ሲመረመር እውነት ሆኖ ተገኝ፥ ሁለቱም ሰዎች በስቅላት ተቀጡ። ታሪኩም በንጉሡ ፊት በታሪክ መዝገብ ላይ ተጻፈ።
1ከእነዚህ ነገሮች በኋላ ንጉሡ አርጤክስስ አጋጋዊውን የሐመዳቱን ልጅ ሐማን በሹመት አላቀው፥ የሥልጣኑንም ወንበር ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሹማምንት ሁሉ በላይ አደረገለት። 2በንጉሡ በር የሚጠብቁ የንጉሡ አገልጋዮች ሁሉ ንጉሡ በሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ሁልጊዜ ለሐማ በመንበርከክ አክብሮታቸውን ያሳዩት ነበር። መንዶክዮስ ግን አልተንበረከከለትም፥ አክብሮትም አላሳየውም።3ከዚያም በንጉሡ በር የሚጠብቁት የንጉሡ አገልጋዮች መርዶክዮስን፥ "የንጉሡን ትዕዛዝ የማታከብረው ለምንድነው?" አሉት። 4ይህንን በየቀኑ ቢናገሩትም እርሱ ግን ቃላቸውን ለመቀበል እምቢ አለ። አይሁዳዊ መሆኑን ነግሯቸው ስለነበረ መርዶክዮስ በዚህ ሁኔታ እንዴት እንደሚቀጥል ለማየት ጉዳዩን ለሐማ ነገሩት።5ሐማም መርዶክዮስ ተንበርክኮ እንዳልሰገደለት ባየ ጊዜ ሐማ በንዴት ተሞላ። 6የመርዶክዮስን የዘር ማንነት የንጉሡ አገልጋዮች ነግረውት ስለ ነበረ መርዶክዮስን ብቻ የመግደልን ሃሳብ ናቀው። በመላው አርጤክስስ መንግሥት ውስጥ የነበሩትን የመርዶክዮስ ወገን የሆኑትን አይሁድ በሙሉ ለመደምሰስ ፈለገ።7ንጉሡ አርጤክስስ በነገሠ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት፥ በመጀመሪያው ወር (እርሱም የኒሳን ወር ነው) ፥ ፉር የሚባለውን፥ ቀኑንና ወሩን ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የእያንዳንዱን ቀንና ወር ዕጣ በሐማ ፊት ጣሉ። በዕጣው መሠረት የአዳርን (አሥራ ሁለተኛውን ወር) መረጡ።8ከዚያም ሐማ ንጉሡን አርጤክስስን፥ "በመንግሥትህ አውራጃዎች ሁሉ ተበታትኖና ተሠራጭቶ የሚኖር አንድ ሕዝብ አለ። ሕጋቸው ከሌላው ሕዝብ የተለየ ነው፥ የንጉሡንም ሕጎች አያከብሩም፥ ስለዚህ ንጉሡ በሕይወት እንዲኖሩ ሊተዋቸው አይገባውም። 9ንጉሡ ደስ የሚለው ከሆነ እንዲገደሉ ትዕዛዝ ይስጥ፥ እኔም ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ገቢ እንዲያደርጉት በንጉሡ ንብረት ኃላፊዎች በሆኑት እጅ አሥር ሺህ መክሊት ብር መዝኜ እሰጣለሁ"አለው።10ከዚያም ንጉሡ ማኅተም ያለበትን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ ለአይሁዶቹ ጠላት፥ ለአጋጋዊው ለሐመዳቱ ልጅ ለሐማ ሰጠው። 11ንጉሡም ሐማን፥ "ገንዘቡ ለአንተና ለሕዝብህ ተመልሶ ማየት እፈልጋለሁ። አንተም በእርሱ የፈለግኸውን ሁሉ ታደርግበታለህ" አለው።12ከዚያም በመጀመሪያው ወር በአሥራ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠሩ፥ ለንጉሡ የአውራጃ አስተዳዳሪዎች፥ በአውራጃዎቹ ሁሉ ላይ ለነበሩት፥ ልዩ ልዩ ሕዝቦችን ለሚያስተዳድሩትና ለሕዝቡ ሁሉ ሹማምንት፥ ለየአውራጃዎቹ በየራሳቸው ጽሑፍና ለእያንዳንዱም ሕዝብ በየራሱ ቋንቋ ሐማ ያዘዘው ሁሉ በዐዋጁ ውስጥ ተጻፈ። ዐዋጁም በንጉሡ አርጤክስስ ስም ተጽፎ በቀለበቱ ታተም። 13በአሥራ ሁለተኛው ወር (እርሱም የአዳር ወር ነው) ፥ በአሥራ ሦስተኛው ቀን፥ በአንድ ቀን ውስጥ አይሁዶችን በሙሉ፥ ከወጣት እስከ ሽማግሌ፥ ልጆችንና ሴቶችን በአንድ ቀን እንዲያጠፉ፥ እንዲገድሉና እንዲደመስሱና ንብረታቸውንም እንዲዘርፉ ደብዳቤዎቹም በመልዕክተኞቹ እጅ ለንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ ተላከ።14የደብዳቤው ቅጅም በየአውራጃው ሕግ ተደረገ። ለዚያ ቀን ይዘጋጁ ዘንድ በየአውራጃው ያሉ ሕዝቦች ሁሉ እንዲያውቁት ተደረገ። 15መልዕክተኞቹም የንጉሡን ዐዋጅ ለማሰራጨት በጥድፊያ ሄዱ። አዋጁ በሱሳ ቤተመንግሥት ውስጥም ደግሞ ተሰራጨ። ንጉሡና ሐማ ለመጠጣት ተቀመጡ፥ የሱሳ ከተማ ግን ተበጥብጣ ነበር።
1መርዶክዮስ የተደረገውን ሁሉ ባወቀ ጊዜ ልብሶቹን ቀደደ፥ ማቅ ለብሶም በራሱ ላይ አመድ ነሰነሰ። ወደ ከተማይቱ መካከል በመሄድም በታላቅ ጩኸት መራራ ልቅሶ አለቀሰ። 2ማቅ ለብሶ በንጉሡ በር በኩል ማለፍ አይፈቀድም ነበርና እስከ አቅራቢያው ድረስ ብቻ ሄደ። 3የንጉሡ ዐዋጅና ትዕዛዝ በደረሰበት አውራጃ ሁሉ በአይሁድ መካከል ከጾም፥ ከልቅሶና ከዋይታ ጋር ታላቅ ሀዘን ሆነ። ብዙዎቹም በማቅና በአመድ ላይ ተኙ።4የአስቴር ወጣት ሴቶችና አገልጋዮቿ መጥተው ስለ ሁኔታው በነገሯት ጊዜ ንግሥቲቱ እጅግ አዘነች። እርሷም መርዶክዮስን እንዲያለብሱት (ማቁን አውጥቶ እንዲጥል ነበር) ልብሶችን ላከችለት፥ እርሱ ግን አልተቀበለም። 5ከዚያም አስቴር እርሷን ለማገልገል የተመደበውንና ከንጉሡ ሹማምንት አንዱ የሆነውን ሀታክን ጠራችው። ምን እንደ ተፈጠረና ምን ማለትም እንደሆነ ያጣራ ዘንድ ወደ መርዶክዮስ እንዲሄድ አዘዘችው።6ስለዚህ ሀታክ በንጉሡ በር ፊት ለፊት ወደሚገኘው የከተማው አደባባይ ወደ መርዶክዮስ ሄደ። 7መርዶክዮስም የገጠመውን ነገር ሁሉ፥ አይሁድን ለመግደል ሐማ ወደ ንጉሡ ግምጃ ቤት ለማስገባት ቃል የገባውን የገንዘብ መጠን አስታወቀው። 8በተጨማሪም አይሁድን ለማጥፋት በሱሳ የታወጀውን የዐዋጁን ቅጅም ሰጠው። ይህንንም ያደረገው ሀታክ ለአስቴር እንዲያሳያትና ወደ ንጉሡ ሄዳ ስለ ሕዝቧ ምህረት እንዲያደርግ እንድትለምነውና እንድትማልደው ኃላፊነት እንዲሰጣት ነበር።9ሀታክ ሄደና መርዶክዮስ ነግሮት የነበረውን ለአስቴር ነገራት። 10ከዚያም አስቴር ሀታክ ተመልሶ ወደ መርዶክዮስ እንዲሄድ ነገረችው። 11እንዲህም አለችው፥ "ወንድ ሆነ ሴት ማንኛውም ሰው ሳይጠራ ወደ ውስጠኛው አደባባይ ቢገባ አንድ ሕግ ብቻ እንዳለ የንጉሡ አገልጋዮች ሁሉና በንጉሡ አውራጃዎች የሚኖሩ ሕዝቦች ያውቃሉ፥ ሕጉም በሕይወት እንዲኖር ንጉሡ የወርቅ በትሩን ከሚዘረጋለት በስተቀር መገደል አለበት የሚል ነው። እነዚህን ሠላሳ ቀናት ወደ ንጉሡ ለመቅረብ አልተጠራሁም።" 12ስለዚህ ሀታክ የአስቴርን ቃል ለመርዶክዮስ አስታወቀው።13መርዶክዮስም እንዲህ የሚል መልዕክት መለሶ ለከባት፥ "በንጉሡ ቤተመንግሥት ውስጥ ስለሆንሽ ከሌሎቹ አይሁዶች ሁሉ ይልቅ እንደምትድኚ ማሰብ የለብሽም። 14አንቺ በዚህ ጊዜ ዝምታን ብትመርጪ ለአይሁድ እርዳታና መዳን ከሌላ ሥፍራ ይነሣላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ። ወደ ንግሥትነት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ቀን እንደሆነስ ማን ያውቃል?"15ከዚያም አስቴር ይህን መልዕክት ወደ መርዶክዮስ ላከች፥ 16"ሂድ፥ በሱሳ የሚኖሩትን አይሁድ ሁሉ በአንድ ላይ ሰብስባቸውና ስለ እኔ ጹሙ። ለሦስት ቀንና ሌሊት አትብሉ፥ አትጠጡም። እኔና ወጣት ልጃገረዶቼም እንደዚሁ እናደርጋለን። ከዚያም ከሕጉ ውጪ ቢሆንም ወደ ንጉሡ እገባለሁ፥ ከጠፋሁም እጠፋለሁ።" 17መርዶክዮስም ሄዶ አስቴር ያለችውን ሁሉ አደረገ።
1ከሥስት ቀን በኋላ አስቴር የንግሥትነትዋን ልብስ ለብሳ በንጉሡ መኖሪያ ፊት ለፊት፥ በንጉሡ ቤተመንግሥት ውስጠኛው አደባባይ ልትቆም ሄደች። ንጉሡም በቤቱ መግቢያ በር ትይዩ በንጉሣዊ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ነበር። 2ንጉሡ ንግሥት አስቴርን አደባባዩ ላይ ቆማ ባያት ጊዜ፥ በፊቱ ሞገስን አገኘች። እርሱም የወርቁን በትር አንስቶ ዘረጋላት። ስለዚህ አስቴር ቀረበችና የበትሩን ጫፍ ነካች።3ከዚያም ንጉሡ፥ "ንግሥት አስቴር! ምንድነው የምትፈልጊው? ጥያቄሽስ ምንድነው? የመንግሥቴን ግማሽ ከሆነም ይሰጥሻል።" 4አስቴርም፥ "ንጉሡን ደስ የሚለው ከሆነ ንጉሡ ከሐማ ጋር ወዳዘጋጀሁለት ግብዣ ዛሬ ይምጣ" አለችው።5ከዚያም ንጉሡ፥ "አስቴር ያለችው እንዲደረግ፥ በአስቸኳይ ሐማን ጥሩት" አለ። ስለዚህ ንጉሡና ሐማ አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ ሄዱ። 6በግብዣው ላይ ወይኑ እየቀረበ እያለ ንጉሡ አስቴርን፥ "ልመናሽ ምንድነው? ይሰጥሻል። ጥያቄሽ ምንድነው? እስከ መንግሥቴ ግማሽ ይሰጥሻል" አላት።7አስቴርም፥ "በንጉሡ ዓይን ሞገስን ካገኘሁ፥ 8የለመንኩትን ሊሰጠኝና ጥያቄዬን ሊያከብርልኝ ንጉሡን ደስ የሚለው ከሆን ልምናዬና ጥያቄዬ ይህ ነው። ነገ በማዘጋጅልህ ግብዣ ላይ ንጉሡ ከሐማ ጋር ይምጣ፥ እኔም የንጉሡን ጥያቄ እመልሳለሁ" አለችው።9ሐማ በዚያን ቀን ደስ ብሎት፥ ልቡም ሐሴት አድርጎ ሄደ። ነገር ግን ሐማ መርዶስዮስን በፊቱ ሳይፈራና ሳይንቀጠቀጥ፥ ከተቀመጠበትም ሳይነሳ በንጉሡ በር ባየው ጊዜ በመርዶክዮስ ላይ እጅግ ተናደደ። 10ሆኖም ሐማ ራሱን ተቆጣጠረና ወደ ራሱ ቤት ሄደ። 11ጓደኞቹን አስጠራና ከሚስቱ ዞሳራ ጋር በአንድ ላይ ሰበሰባቸው። ሐማም የብልጽግናውን ክብርና የልጆቹን ብዛት፥ ከንጉሡ አገልጋዮችና ከሹማምንቱ ሁሉ በላይ እንዴት በማዕረግ አንደበለጣቸው አወራላቸው።12ሐማም፥ "ንግሥት አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ እንኳን ከእኔ በቀር ከንጉሡ ጋር እንዲመጣ የጋበዘችው የለም። ነገም ደግሞ ከንጉሡ ጋር ግብዣዋ ላይ እንድገኝ ጋብዛኛለች። 13ነገር ግን አይሁዳዊው መርዶክዮስ በንጉሡ በር ተቀምጦ ካየሁት ይህ ሁሉ ልምምዴ ምንም አይጠቅመኝም።"14ከዚያም ሚስቱ ዞሳራ ሐማንና ጓደኞቹን ሁሉ፥ "ቁመቱ ሃምሳ ክንድ የሆነ መስቀያ ያዘጋጁ። መርዶክዮስን በዚያ ላይ እንዲሰቅሉት ነገ ጠዋት ለንጉሡ ንገረው። ከዚያም ደስ ብሎህ ከንጉሡ ጋር ወደ ግብዣው ሂድ" አለቻቸው። ይህም ሐማን አስደሰተው፥ መስቀያው እንዲዘጋጅም አስደረገ።
1በዚያ ሌሊት ንጉሡ እንቅልፉን መተኛት አልቻለም። እርሱም በዘመነ መንግሥቱ የተከናወኑ ሁነቶች በታሪክነት የተመዘገቡበትን መዝገብ እንዲያመጡለት አገልጋዮቹን አዘዛቸው፥ እነርሱም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ለንጉሡ ያነቡለት ነበር። 2ገበታና ታራ፥ ሁለቱ በር ጠባቂ የንጉሥ ሹሞች ንጉሥ አርጤክስስን ለመግደል ማቀዳቸውን መርዶክዮስ መናገሩ ተመዝግቦ ተገኘ። 3ንጉሡም፥ "ይህንን ስላደረገ ለመርዶክዮስ ክብርና እውቅና ለመስጠት ምን ተደረገለት?" ብሎ ጠየቀ። ከዚያም ንጉሡን የሚያገለግሉ ወጣቶች፥ "ምንም አልተደረገለትም" አሉት።4ንጉሡም፥ "በአደባባዩ ውስጥ ያለው ማነው?" አለ። በዚያን ጊዜ ሐማ መርዶክዮስን ባዘጋጀለት መስቀል ላይ ለማሰቀል ለንጉሡ ለመንገር ወደ ውጪኛው አደባባይ ገብቶ ነበር። 5የንጉሡም አገልጋዮች፥ "ሐማ አደባባዩ ውስጥ ቆሟል" አሉት። ንጉሡም፥ "ይግባ" አለ። 6ሐማ በገባ ጊዜም ንጉሡ፥ "ንጉሥ ሊያከብረው ለሚወደው ሰው ምን ይደረግለት?"አለው። ሐማም በልቡ፥"ከእኔ የበለጠ ንጉሡ ሊያከብረው የሚወደው ማን ይኖራል?" ብሎ አሰበ።7ሐማም ንጉሡን፥ "ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወደው ሰው፥ 8ንጉሡ ይለብሰው የነበረ ንጉሣዊ ልብስ ይምጣለት፥ ንጉሡ ይቀመጥበት የነበረና በራሱ ላይ የክብር ጌጥ የተደረገለት ፈረስ ይምጣለት። 9ከዚያም ልብሶቹና ፈረሱ ከንጉሡ ሹማምንት እጅግ በተመረጡት በአንደኛው እጅ ይሰጡ፥ እነርሱም ንጉሡ ሊያከብረው የወደደውን ሰው ያልብሱት፥ በፈረሱ ላይ በማስቀመጥም በከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች ይምሩት፥ በፊቱም "ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወደው ሰው የሚደረግለት እንዲህ ነው!" እያሉ ያውጁ" አለ።10ከዚያም ንጉሡ ሐማን፥ "ፍጠን፥ እንደተናገርከው ልብሶቹንና ፈረሱን ውሰድ፥ በንጉሡ በር ለሚቀመጠው ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስ ይህንኑ አድርግለት። ከተናገርከውም አንድ አንዳይጎድል" አለው። 11ከዚያም ሐማ ልብሱንና ፈረሱን ወሰደ። መርዶክዮስን አልብሶና ፈረስ ላይ አስቀምጦ በከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች አዟዟረው። በፊቱም፥ "ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወደው ሰው የሚደረግለት እንዲህ ነው!" እያለ ዐወጀ።12መርዶክዮስ ወደ ንጉሡ በር ተመለሰ። ሐማ ግን ፊቱን ሸፍኖና አዝኖ በጥድፊያ ወደ ቤቱ ሄደ። 13ሐማም ለሚስቱ ለዞሳራና ለጓደኞቹ ሁሉ የገጠመውን ነገር በሙሉ ነገራቸው። በጥበባቸው የታወቁት ሰዎቹና ምስቱ ዞሳራም፥ "በፊቱ መውደቅ የጀመርከለት መርዶክዮስ አይሁዳዊ ከሆነ በርግጥ በፊቱ ትወድቃለህ እንጂ አታሸንፈውም" አሉት። 14ከእርሱ ጋር እየተነጋገሩ እያሉ የንጉሡ ሹማምንት መጡ። እነርሱም አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ ሐማን አቻኮሉት።
1ስለዚህ ንጉሡና ሐማ በንግሥት አስቴር ለመጋበዝ ሄዱ። 2በዚህ በሁለተኛው ቀን፥ ወይን እየጠጡ እያሉ፥ ንጉሡ አስቴርን፥ "ልመናሽ ምንድነው ንግሥት አስቴር? እርሱ ይሰጥሻል። ጥያቄሽስ ምንድነው? እስከ መንግሥት አጋማሽ ድረስ ይሰጥሻል?" አላት።3ንግሥት አስቴርም መልሳ፥ "ንጉሥ ሆይ፥ በዓይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ ከሆነና ደስ የምትሰኝበትም ከሆነ ሕይወቴ እንድትሰጠኝ ልመናዬ ይህ ነው፥ ስለ ሕዝቤም የምጠይቀው ይህንኑ ነው። 4እኔና ሕዝቤ ለመጥፋት፥ ለመሞትና ለመደምሰስ ተሽጠናልና። ወንድና ሴት ባሪያዎች እንድንሆን ለባርነት ብቻ ተሽጠን ቢሆን ኖሮ ዝም ባልኩኝ ነበር፥ ይህንን በመሰለው ጭንቀት ንጉሡን ማወክ አይገባምና። 5ከዚያም ንጉሥ አርጤክስስ ንግሥት አስቴርን፥ "ማነው እርሱ? እንዲህ ያለውን ነገር ለማድረግ ልቡ የሞላ ያ ሰው የት ነው የሚገኘው?" አላት።6አስቴርም፥ "ያ ጠላትና ባላጋራው ሰው ይህ ክፉው ሐማ ነው!" ሐማም በንጉሡና በንግሥቲቱ ፊት ደነገጠ። 7ንጉሡም በቁጣ ወይን ከሚጠጣበት ግብዣ ተነሥቶ ወደ ቤተመንግሥቱ መናፈሻ ሄደ፥ ሐማ ግን ንግሥት አስቴር ሕይወቱን እንድትታደገው ሊለምናት በዚያው ቆይቶ ነበር። ከንጉሡ ጥፋት እንደተወሰነበት አይቷልና።8ከዚያም ንጉሡ ከቤተመንግሥቱ መናፈሻ ወደ ወይን መጠጫው ክፍል ተመለሰ። ሐማ አስቴር በነበረችበት ድንክ አልጋ ላይ ልክ መደፋቱ ነበር። ንጉሡም፥ "በገዛ ቤቴ፥ በእኔው ፊት ንግሥቲቱን ሊደፍራት ነው እንዴ?" አለ። ልክ ይህ ቃል ከንጉሡ አፍ እንደወጣ፥ አገልጋዮቹ የሐማን ፊት ሸፈኑት።9ከዚያም ንጉሡን ከሚያገለግሉት ሹማምንቶች አንዱ የሆነው ሐርቦና፥ "ሃምሳ ክንድ ቁመት ያለው መስቀያ በሐማ ቤት ቆሟል። ያቆመውም ንጉሡን ለመታደግ የተናገረውን መርዶክዮስን ለመስቀል ነው" አለ። ንጉሡም "በእርሱ ላይ ስቀሉት" አላቸው። 10ስለዚህ ሐማን ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው መስቀያ ላይ ሰቀሉት። ከዚያም የንጉሡ ቁጣ በረደ።
1በዚያም ቀን ንጉሡ አርጤክስስ የአይሁዶችን ጠላት፥ የሐማን ንብረት፥ ለንግሥት አስቴር ሰጣት። መርዶክዮስ እንዴት እንደሚዛመዳት ለንጉሡ ነግራው ስለ ነበረ፥ መርዶክዮስ በንጉሡ ፊት ማገልገል ጀመረ። 2ንጉሡ ከሐማ መልሶ የወሰደውን ማኅተም ያለበትን ቀለበት አውልቆ ለመርዶክዮስ ሰጠው። አስቴርም መርዶክዮስን በሐማ ይዞታ ላይ ኃላፊ አድርጋ ሾመችው።3ከዚያም አስቴር ንጉሡን ደግማ ተናገረችው። እርሷም በምድር ላይ ተደፍታ አጋጋዊው ሐማ በአይሁድ ላይ ያሴረውን የጥፋት ዕቅድ ማብቂያ እንዲያደርግለት እያለቀሰች ለመነችው። 4ከዚያም ንጉሡ የወርቁን በትረ መንግሥት ለአስቴር ዘረጋላት። እርሷም ተነሥታ በንጉሡ ፊት ቆመች።5እርሷም፥ "ንጉሡን ደስ የሚለው ከሆነና በፊትህ ሞገስን ካገኘሁ፥ ነገሩም በንጉሡ ፊት ትክክል መስሎ ከታየውና እኔም በዓይንህ ፊት ተወድጄ ከሆነ፥ በአጋጋዊው በሐመዳቱ ልጅ በሐማ የተጻፈውን፥ በንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ የሚኖሩትን አይሁድ ለማጥፋት የጻፈውን ድብዳቤ የሚሽር አዋጅ ይጻፍ። 6በሕዝቤ ላይ የሚደርሰውን እልቂት ለማየት እንዴት መታገሥ እችላለሁ? የዘመዶቼን ጥፋት መመልከቱንስ እንዴት መቋቋም እችላለሁ?" አለችው።7ንጉሥ አርጤክስስ ንግሥት አስቴርንና አይሁዳዊውን መርዶክዮስን፥ "ተመልከቱ፥ የሐማን ቤት ለአስቴር ሰጠኋት፥ አይሁድን ሊያጠቃ ስለነበርም እርሱን በመስቀያው ላይ ሰቀሉት። 8ለአይሁዶች በንጉሡ ስም ሌላ ዐዋጅ ጻፉ፥ በንጉሡም የቀለበት ማኅተም አትሙበት። ቀደም ሲል በንጉሡ ስም የተጻፈውና በንጉሡ ቀለበት የታተመው ዐዋጅ ሊሻር አይቻልምና።"9በሦስተኛው ወር፥ እርሱም የኒሳን ወር ነው፥ ከወሩም በሃያ ሦስተኛው ቀን በዚያን ጊዜ የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠርተው ነበር። ዐዋጁም አይሁድን በሚመለከት መርዶክዮስ ያዘዘው ሁሉ ተካትቶ ተጽፎበት ነበር። ለየአውራጃው አስተዳዳሪዎች ተጽፎ ነበር፥ ከህንድ እስከ ኢትዮጵያ ለሚዋሰኑት 127 የአውራጃ አስተዳዳሪዎችና አለቆች፥ ለእያንዳንዱ አውራጃ በየራሱ ጽሑፍና ለእያንዳንዱ ሕዝብ በየራሱ ቋንቋ፥ ደግሞም ለአይሁድ በራሳቸው ጽሑፍና ቋንቋ ተጻፈ።10መርዶክዮስ በንጉሥ አርጤክስስ ስም ጽፎ በንጉሡ የቀለበት ማኅተም አተመው። ደብዳቤዎቹንም ለንጉሡ አገልግሎት በሚውሉና ለዚሁ በተገሩ ፈጣን ፈረሶች በሚጋልቡ መልዕክተኞች ላከው። 11በየከተማው ያሉ አይሁዶች በአንድ ላይ እንዲሰባሰቡና ሕይወታቸውን እንዲከላከሉ፤ ልጆችንም ሆነ ሴቶችን ጨምሮ ከየትኛውም ሕዝብም ሆነ አውራጃ እነርሱን ለማጥቃት መሣሪያ የሚያነሣውን ኃይል ሁሉ እንዲያጠፉ፥ እንዲገድሉና እንዲደመስሱ ንብረታቸውንም እንዲበዘብዙ ንጉሡ ፈቃድ ሰጣቸው። 12ይህ በንጉሥ አርጤክስስ አውራጃዎች ሁሉ በአሥራ ሁለተኛው ወር፥ እርሱም አዳር የሚባለው ወር ነው፥ በአሥራ ሦስተኛው ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ነበር።13የዐዋጁ ቅጅ ሕግ ሆኖ በመውጣት ሕዝብ ሁሉ እንዲያውቀው ተደረገ። አይሁድ በዚያን ቀን ጠላቶቻቸውን ለመበቀል ዝግጁዎች መሆን ነበረባቸው። 14ስለዚህ መልዕክተኞቹ ለንጉሡ አገልግሎት በሚውሉ የቤተመንግሥት ፈረሶች ላይ ተቀመጡባቸው። እነርሱም ፈጥነው ሄዱ። ደግሞም የንጉሡ ዐዋጅ ከሱሳ ቤተመንግሥት ተነገረ።15ከዚያም መርዶክዮስ ንጭና ሰማያዊ የክብር ልብስ ለብሶ፥ ታላቅ የወርቅ አክሊልም ደፍቶ፥ ከሐምራዊና ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ መጎናጸፊያ ደርቦ ከንጉሡ ፊት ወጣ። የሱሳ ከተማም ደስ አላት፥ እልልም አለች። 16ለአይሁድም ብርሃንና ፈንጠዚያ፥ ደስታና ክብር ሆነላቸው። 17የንጉሡ ዐዋጅ በደረሰበት ሁሉ፥ በየአውራጃውና በየከተማው በአይሁድ መካከል ደስታና ፈንጠዚያ፥ ግብዣና በዓል ሆነ። አይሁድን መፍራት በላያቸው ላይ ወድቆ ስለነበረ በምድሩ ከሚኖሩ ልዩ ልዩ ሕዝቦች ብዙዎቹ አይሁድ ሆኑ።
1አዳር ተብሎ በሚጠራው በአሥራ ሁለተኛው ወር፥ በአሥራ ሦስተኛውም ቀን የንጉሡ ሕግና ዐዋጅ ተግባራዊ በሚደረግበት፥ የአይሁድ ጠላቶች ሊያጠፏቸው ተስፋ ባደረጉበት ቀን ነገሩ ተቀየረ። አይሁዶች በሚጠሏቸው ላይ የበላይነትን አገኙ። 2አይሁድ ሊያጠፏቸው በሞከሩት ላይ እጆቻቸውን ለማንሣት ከንጉሥ አርጤክስስ አውራጃዎች ሁሉ ወደ ከተሞቻቸው ተሰበሰቡ። እነርሱን መፍራት በሕዝብ ሁሉ ላይ ወድቆ ስለነበረ ማንም ሊቃወማቸው አልቻለም።3የአውራጃዎቹ አለቆች፥ የአውራጃ ገዢዎች፥ መኳንንቶችና የንጉሡ አስተዳዳሪዎች መርዶክዮስን በመፍራት ተይዘው ስለነበር አይሁድን አገዟቸው። 4መርዶክዮስ በንጉሡ ቤት ታላቅ ነበር፥ ዝናውም በአውራጃዎቹ ሁሉ ተሰራጨ፥ መርዶክዮስ የተባለውም ሰው ታላቅ ሆነ። 5አይሁድም ጠላቶቻቸውን በሰይፍ አጠቋቸው፥ ገደሏቸው፥ አጠፏቸውም፥ በእነዚያ ይጠሏቸው በነበሩት ላይ ደስ ያሰኛቸውን አደረጉባቸው።6አይሁድ በራሱ በሱሳ ግንብ አምስት መቶ ሰዎችን ገደሉ፥ አጠፉም። 7የአይሁድ ጠላት የሐመዳቱን ልጅ 8የሐማን አሥሩን ወንዶች ልጆቱን፥ ፓርሻንዳታን፥ ደልፎንን፥ አስፓታን፥ 9ፖራታን፥ አዳልያን፥ አሪዳታን፥ 10ፓርማሽታን፥ አሪሳይን፥ አሪዳይንና ዋይዛታን ገደሉ። ነገር ግን ምንም ዝርፊያ አልፈጸሙም።11በተመሸገችው ከተማ፥ በሱሳ፥ በዚያን ቀን የተገደሉት ሰዎች ብዛት ለንጉሡ ተነገረው። 12ንጉሡም ንግሥት አስቴርን፥ "አይሁድ አሥሩን የሐማ ወንዶች ልጆች ጨምሮ በሱሳ ከተማ ውስጥ አምስት መቶ ሰዎችን ገደሉ። በቀሩት የንጉሡ አውራጃዎች ምን አድርገው ይሆን? አሁን የምትለምኚው ምንድነው? እርሱም ይሰጥሻል። የምትጠይቂውስ ምንድነው? እርሱም ይደረግልሻል" አላት።13አስቴርም፥ "ንጉሡን ደስ የሚለው ከሆነ፥ በሱሳ የሚገኙ አይሁዶች ዛሬ ያደረጉትን ነገም ደግሞ እንዲያደርጉ ይፈቀድላቸው፥ አሥሩ የሐማ ልጆች ሬሳም በመስቀያ ይሰቀል" አለችው። 14ስለዚህ ንጉሡ ይህ እንዲፈጸም አዘዘ። ዐዋጁም በሱሳ ተሰራጨ፥ አሥሩን የሐማ ወንዶች ልጆች ሰቀሏቸው።15በአዳር ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በሱሳ ይኖሩ የነበሩ አይሁድ አንድ ላይ ተሰብስበው ሦስት መቶ ተጨማሪ ሰዎችን ገደሉ፥ እጆቻቸውን ግን ለመበዝበዝ አልዘረጉም። 16በንጉሡ አውራጃዎች ይኖሩ የነበሩት፥ የቀሩት አይሁድ ሕይወታቸውን ለመከላከል በአንድ ላይ ተሰባሰቡ፥ ይጠሏቸው የነበሩትን ሰባ አምስት ሺህ ሰው ገደሉ፥ ከጠላቶቻቸውም ዐረፉ። ነገር ግን ወደ ገደሏቸው ሰዎች ጠቃሚ ቁሳቁስ እጆቻቸውን አልዘረጉም።17በአዳር ወር በአሥራ ሦስተኛው ቀን ይህ ሆነ፥ በአሥራ አራተኛው ቀን ዐረፉ፥ ቀኑንም የግብዣና የደስታ አደረጉት። 18በሱሳ ይኖሩ የነበሩ አይሁድ ግን በአሥራ ሦስተኛውና በአሥራ አራተኛው ቀን በአንድ ላይ ተሰባሰቡ። በአሥራ አምስተኛው ቀን ዐረፉ፥ የግብዣና የደስታም ቀን አደረጉት። 19በገጠር ከተሞች የሚኖሩ የመንደሩ አይሁድ የአዳርን ወር አሥራ አራተኛውን ቀን የግብዣና የደስታ ቀን አድርገው የሚያከብሩትና እርስ በርሳቸው የምግብ ስጦታ መለዋወጫ ቀን ያደረጉት ለዚህ ነው።20መርዶክዮስ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በመጻፍ በንጉሥ አርጤክስስ አውራጃዎች ሁሉ በቅርብና በሩቅ ለሚኖሩ አይሁዶች በሙሉ በየዓመቱ በአዳር ወር 21አሥራ አራተኛውንና አሥራ አምስተኛውን ቀን እንዲጠብቁት በማዘዝ ደብዳቤዎችን ጻፈላቸው። 22እነዚህ ቀናት አይሁድ ከጠላቶቻቸው ያረፉባቸው፥ ሀዘናቸው ወደ ደስታ፥ ልቅሶአቸውም ወደ ደስታ በዓል የተለወጠባቸው ቀናት ነበሩ። እነርሱም ቀኖቹን የግብዥና የደስታ፥ ለእርስ በርሳቸውም የምግብ ስጦታ የሚለዋወጡበት፥ ለድሆችም ስጦታ የሚያበረክቱባቸው መሆን ነበረባቸው።23ስለዚህ አይሁድ መርዶክዮስ በጻፈላቸው ደብዳቤ መሠረት የጀመሩትን በዓል ማክበራቸውን ቀጠሉ። 24በዚያን ጊዜ የአይሁዶች ሁሉ ጠላት፥ የሐመዳቱ ልጅ ሐማ፥ አይሁድን ለማጥፋት አሢሮ ነበር፥ ሊሰባብርና ሊያፈርሳቸውም ፉር የተባለውን ዕጣ ጥሎ ነበር። 25ጉዳዩ ወደ ንጉሡ ፊት በቀረበ ጊዜ ግን ሐማ በአይሁድ ላይ ያዘጋጀው ክፉ ዕቅድ በእርሱ በራሱ ላይ እንዲመለስበትና ወንዶች ልጆቹ በስቅላት እንዲቀጡ በደብዳቤ አዘዘ።26ስለዚህ ፉር ከሚለው ስም በመነሣት አነዚህን ቀናት ፉሪም ብለው ጠሯቸው። በዚህ ደብዳቤ በተጻፉት፥ እነርሱም ባዩትና በደረሰባቸው ነገር ምክንያት አይሁድ አዲስ ልማድና አደራረግን ተቀበሉ። 27ይህም ልማድ ለእነርሱ፥ ለትውልዳቸውና እነርሱን ለተጠጋ ሁሉ የሚቀጥል ነበር። በየዓመቱ እነዚህ ሁለት ቀናት መከበር ነበረባቸው። ቀኖቹንም በየዓመቱ በተመሳሳይ ጊዜ፥ በአንድ ዓይነት መንገድ ማክበር ነበረባቸው። አነዚህ ቀኖች በየትውልዱ፥ በየቤተሰቡ፥ በየአውራጃውና በየከተማው መታሰብና መከበር ይኖርባቸዋል። 28እነዚህ አይሁዶችና ትውልዶቻቸው እነዚህን የፉሪም ቀናት ፈጽመው እንዳይረሷቸው፥ በታማኝነት መጠበቃቸውንም በፍጹም ማቋረጥ አይኖርባቸውም።29የአቢካኢል ልጅ ንግሥት አስቴርና አይሁዳዊው መርዶክዮስ ስለ ፉሪም ይህንን ሁለተኛ ደብዳቤ በሙሉ ሥልጣን ጽፈው አጸኑት።30በአርጤክስስ መንግሥት በ127 አውራጃዎች ውስጥ ለሚኖሩ አይሁድ በሙሉ ደኅንነትንና እውነትን የሚመኙላቸው ደብዳቤዎች ተጻፉላቸው። 31አይሁዳዊው መርዶክዮስና ንግሥት አስቴር አይሁድን እንዳዘዙት የፉሪም ቀናት በተወሰነላቸው ጊዜያት እንዲደረጉ እነዚህ ደብዳቤዎች አጸኑት። አይሁድ ልክ የጾሙንና የለቅሶውን ጊዜ አንደተቀበሉት ይህንን ትዕዛዝ ደግሞ ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ተቀበሉት። 32ፉሪምን በሚመለከት የአስቴር ትዕዛዝ እነዚህን መመሪያዎች አጸና፥ እርሱም በመጽሐፍ ተጻፈ።
1ከዚያም ንጉሥ አርጤክስስ እስከ ባህር ጠረፍ ባለው ሀገር ላይ ግብር ጣለ። 2የኃይሉና የብርታቱ ሥራ ሁሉ፥ ንጉሡ ከፍ ከፍ ካደረገው ከመርዶክዮስ የታላቅነቱ ሙሉ ታሪክ ጋር በፋርስና በሜዶን ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ላይ ተጽፏል።3አይሁዳዊው መርዶክዮስ ከንጉሥ አርጤክስስ ቀጥሎ በማዕረግ ሁለተኛ ነበር። የሕዝቡን ደኅንነት የፈለገና ስለ ሕዝቡም ሁሉ ሰላም የተናገረ፥ በብዙ አይሁድ ወንድሞቹም የታወቀና በአይሁድ መካከል ታላቅ የሆነ ሰው ነበር።
1ዖጽ በሚባል ምድር ኢዮብ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ኢዮብም በደል የማይገኝበት፤ ትክክለኛ፤ እግዚአብሄርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው ነበረ። 2ለእርሱም ሰባት ወንዶችና ሶስት ሴቶች ልጆች ተወልደውለት ነበር። 3ሰባት ሺህ በጎች፤ ሶስት ሺህ ግመሎች፤ አምስት ሺህ ጥንድ በሬዎችና አምስት ሺህ አህዮች እንዲሁም እጅግ ብዙ ሰራተኞች ነበሩት። ይህም ሰው በምስራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ሰው ነበር።4ወንዶች ልጆቹም በየተመደበላቸው ተራ በያንዳንዳቸው ቤት ግብዣ ያደርጉ ነበር፤ ሦስቱ እኅቶቻቸውም ከእነርሱ ጋር እንዲበሉና እንዲጠጡ ልከው ይጠሩአቸው ነበር። 5የግብዣቸውም ቀናቶች ሲያበቁ ኢዮብ፦ ያስጠራቸውና ለእግዚአብሔር መልሶ ይቀድሳቸው ነበር።ማልዶ በጠዋት ተነስቶ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ረግመው ይሆናል” ብሎ ፤ ለልጆቹ ለእያንዳንዳቸው የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል። ይህንንም ኢዮብ ሁልጊዜ ያደርግ ነበር።6በኋላም የእግዚአብሔር ልጆች በያህዌ ፊት ራሳቸውን የሚያቀርቡበት ቀን ነበረ ፥ ሰይጣንም ደግሞ ከእነርሱ ጋር መጣ። 7እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦“ ከወዴት እየመጣህ ነው?” አለው። ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ፦ “ምድርን ሁሉ ዞርሁ፥ በእርስዋም ላይ ወዲህና ወዲያ ተመላልሼ መጣሁ” አለ። 8እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦”በውኑ ባሪያዬን ኢዮብንስ ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ በደል የማይገኝበት ትክክለኛ ሰው ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም“ አለው።9ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ እንዲህ አለ፦ “ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው እንዲሁ ነውን? 10በእርሱና በቤቱ ባለውም ነገር ሁሉ ዙሪያ በየአቅጣጫው አጥር አላደረግህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ሐብቱም በምድር ላይ በዝቶአል።11ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሀብት ሁሉ አውድም ፤ ፊትለፊት ይክድሃል።” 12እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ “እነሆ እርሱ ያለው ነገር ሁሉ በስልጣንህ ስር ነው፥ በእርሱ ላይ ግን ጉዳት እንዳታደርስ” አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ።13ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ በታላቅ ወንድማቸው ቤት በሚበሉበትና የወይን ጠጅ በሚጠጡበት ቀን እንዲህ ሆነ፤ 14መልክተኛ ወደ ኢዮብ መጥቶ፦”በሬዎች እርሻ እያረሱ፥ በአጠገባቸውም አህዮች ተሰማርተው ነበር፤ 15የሳባም ሰዎች አደጋ አድርሰው ወሰዱአቸው፥ ሰራተኞቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።16እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦“ የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀ፥ በጎቹንና ጠባቂዎችን አቃጥሎ በላቸው፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው። 17እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦”ከለዳውያን በሦስት ቡድን ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጥለው ወሰዱአቸው ፥ ሰራተኞቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።18እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት እየበሉና የወይን ጠጅ እየጠጡ ነበር፤ 19ታላቅ ነፋስ ከምድረ በዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታውና በልጆቹ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም ሞቱ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።20ኢዮብም ተነሣ ልብሱንም ቀደደ፥ ራሱንም ተላጨ፥ በምድርም ላይ በፊቱ ተደፍቶ እግዚአብሔርን አመለከ፤ 21እንዲህም አለ፦”ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።“ 22በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ኢዮብ ሐጢያት አላደረገም፥ በስንፍናም እግዚአብሔርን አልከሰሰም።
1በድጋሚ የእግዚአብሔር ልጆች በያህዌ ፊት ራሳቸውን በሚያቀርቡበት ቀን ፥ ሰይጣንም ደግሞ አብሮ መጣ። 2እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦“ ከወዴት እየመጣህ ነው?” አለው። ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ፦ “ምድርን ሁሉ ዞርሁ፥ በእርስዋም ላይ ወዲህና ወዲያ ተመላልሼ መጣሁ” ብሎ አለ።3እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦”በውኑ ባሪያዬን ኢዮብንስ ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ በደል የማይገኝበት ትክክለኛ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም። ምንም እንኳ ያለምክንያት በእርሱ ላይ በከንቱም ጥፋት እንዲመጣበት ግፊት ብታደርግብኝም ፥ እርሱ ግን እስከ አሁን በታማኝነቱ ጸንቷል“ አለው።4ሰይጣንም መልሶ እግዚአብሔርን፦ “ቆዳ በርግጥ ስለ ቆዳ ነው፤ ሰው ያለውን ነገር ሁሉ ሕይወቱን ለማዳን ሲል ይሰጣል” አለው።5ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሰውነቱ ላይ ጉዳት ብታደርስ ፊተ ለፊት ይክድሃል” አለው። 6እግዚአብሔም ሰይጣንን፦” ሕይወቱን ብቻ ተው፤ እነሆ፥ እርሱ በእጅህ ነው“ አለው።7እናም ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ። ኢዮብንም ከውስጥ እግሩ እስከ ራስ ጸጉሩ ድረስ በሚያሰቃይ ቍስል መታው። 8ኢዮብም ሰውነቱን ለመፋቅ የሸክላ ስባሪ ወሰዶ በአመድ ላይ ተቀመጠ።9በኋላም ሚስቱ ፦”እስከ አሁን በታማኝነት ጸንተሃል እንዴ? እግዚአብሔርን እርገምና ሙት“ አለችው። 10እርሱ ግን መልሶ”አንቺ እንደ ሰነፍ ሴቶች ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ብቻ እንጂ ክፉን አንቀበልም ብለሽ ነው የምታስቢው? “ አላት። በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ኢዮብ በአፉ ቃል ሐጢያት አላደረገም።11ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ከየስፍራቸው መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ከኢዮብ ጋረ ሊያለቅሱና ሊያጽናኑት በአንድነት ጊዜ አመቻችተው መጡ።12ከሩቅ ዓይናቸውን አማትረው ሲመለከቱ በትክክል ሊለዩት አልቻሉም፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ እያንዳንዳቸውም ልብሳቸውን ቀደዱ፥ አቧራ ወደ ላይ እየበተኑ ራሳቸው ላይ ነሰነሱ።13ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት ከእርሱ ጋር መሬት ላይ ተቀመጡ፤ ሕመሙም እጅግ ከባድ እንደነበረ ስላዩ ከእርሱ ጋር አንድ ቃል ለመናገር የደፈረ አልነበረም።
1ከዚህም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ።2እንዲህም አለ፦ 3“ያ የተወለድሁበት ቀን ፤ 'ወንድ ልጅም ተፀነሰ' የተባለበት ሌሊት ይጥፋ”4ያ ቀን ጨለማ ይሁን እግዚአብሔርም ከላይ አያስበው ፤ የጸሀይ ብርሀንም አያግኝው።5ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው እንደሆነ ይቁጠሩ፤ ዳመናም ይኑርበት፤ ቀኑን የሚያጨልሙ ነገሮች ሁሉ በርግጥ ያስደንግጡት።6ያንን ሌሊት ድቅድቅ ጨለማ ይያዘው፤ በዓመቱ ካሉት ቀኖች ጋር ደስ አይበለው፤ በወራት ውስጥ ገብቶ አይቈጠር።7ያቺ ምሽት መካን ትሁን፤ ወደ እርሷም የደስታ ድምጽ አይግባበት።8ሌዋታንን እንዴት ማንቃት እንዳለባቸው የሚያውቁ ያንን ቀን ይርገሙት።9አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፤ ያ ቀን ብርሃንን ሲጠባበቅ አያግኝ፥ የንጋትንም ወገግታ አይመልከት፤10ምክንያቱም የእናቴን ማኅፀን ደጅ አልዘጋምና፥ መከራንም ከዓይኔ አልሰወረምና።11ከማኅፀን ስወጣ ስለ ምን አልሞትሁም? እናቴ ስትወልደኝስ ስለምን አልጠፋሁም?12ጕልበቶቿ ስለ ምን ተቀበሉኝ? ጡቶቿስ እንድጠባ ስለ ምን ተቀበሉኝ?13ይሄኔ በጸጥታ በተጋደምሁ፤14አሁን ፈርሶ ያለውን መቃብር ለራሳቸው ከገነቡት የምድር ነገሥታትና አማካሪዎች ጋር፥ አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤15ወይም ባንድ ወቅት ቤታቸውን በብር ከሞሉ ወርቅም ከነበራቸው መኳንንት ጋር በተጋደምሁ ነበር፥16ወይም ያለጊዜያቸው እንደተወለዱ፥ ብርሃንንም አይተው እንደማያውቁ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።17በዚያ ክፉዎች ረብሻቸውን ያቆማሉ፤ የደከሙትም በዚያ ያርፋሉ።18በዚያ እስረኞች አርፈው በአንድነት ይቀመጣሉ፤ የአስጨናቂውን ጠባቂ ድምፅ አይሰሙም።19ታናናሽና ታላላቅ ሰዎች በዚያ አሉ፤ በዚያም ባሪያ ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።20በመከራ ላለ ሰው ብርሃን ፤ ነፍሳቸው መራራ ለሆነችባቸውስ ህይወት፤21የተሰወረን ሀብት ከሚፈልጉ ይልቅ ሞትን እየተመኙ ላልመጣላቸው ህይወት ለምን ተሰጠ?22መቀበሪያቸውን ባገኙ ጊዜ እጅግ ደስ ለሚላቸው፥ ሐሤትንም ለሚያደርጉ ሕይወት ለምን ተሰጠ?23መንገዱ ለጠፋበት ሰው፥ እግዚአብሔርም አጥር ላጠረበት ሰው ብርሃን ለምን ተሰጠ?24በመመገብ ምትክ ሲቃዬ ፈጥኖ ይመጣልና፥ መቃተቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል።25የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።26በእርጋታና በጸጥታ አልተቀመጥሁም፥ አላረፍሁም ይልቅ መከራና ችግር መጣብኝ።
1ቴማናዊውም ኤልፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ ፦2አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመነጋገር ቢሞክር ታዝናለህን? ነገር ግን ከመናገር ራሱን ሊገታ የሚችል ማን ነው?3እነሆ፥ አንተ ብዙዎችን ታስተምር ነበር፥ የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፥4ቃልህ ሊወድቅ የተሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጕልበት ታጸና ነበር።5አሁን ግን ጥፋት በአንተ ላይ መጥቶአል፥ አንተም ደከመህ፤ በርግጥ ደረሰብህ፥ አንተም ታወክህ።6እግዚአብሔርን መፍራትህ ድፍረትን፥ ያካሄድህስ ቀናነት ተስፋን አይሰጥህምን?7እባክህ ይህን እንድታስብ እለምንሃለሁ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን አለ? ልበ ቅንስ ሆኖ የተደመሰሰ ማን ነው?8እኔ እንዳየሁ፥ ኃጢአትን የሚያርሱ፥ ሁከትንም የሚዘሩ መልሰው ያንኑ ያጭዳሉ።9በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥ በቍጣውም ንዳድ ያልቃሉ።10የአንበሳ ግሳት፥ የቁጡ አንበሳ ድምፅ፥ የደቦል አንበሳ ጥርስ ተሰባብረዋል።11ያረጀ አንበሳ አደን አጥቶ ይሞታል፥ የአንበሳይቱም ግልገሎች የትም ይበተናሉ።12ለእኔም ነገሩ በምሥጢር መጣልኝ፥ ጆሮዬም ስለነገሩ ሹክሹክታን ሰማች።13ከባድ እንቅልፍ በሰው ላይ በሚሆንበት ጊዜ፥ በሃሳብ ብዛት በሌሊት ሕልም ሲመጣ፥14ድንጋጤና መንቀጥቀጥ መጡብኝ አጥንቶቼም ሁሉ ተንቀጠቀጡ15በፊቴም መንፈስ አለፈ የሰውነቴም ጠጕር ቆመ።16መንፈሱም ቆመ፥ መልኩን ግን ለመለየት አልቻልሁም፥ ቅርጹ በዓይኔ ፊት ነበረ፤ ጸጥታም ሆነ እንዲህም የሚል ድምፅ ሰማሁ፤17“በውኑ ሥጋ የለበሰ ሰው ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን?ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹህ ሊሆን ይችላልን?”18እነሆ፥ እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ ካልተማመነ፤ መላእክቱንም በስህተት ከወቀሳቸዋል፤19ይልቁንስ በሸክላ ቤቶች ውስጥ በሚኖሩ፥ መሠረታቸውም በትቢያ ውስጥ ለሆነ፥ ከብል ቀድመው በሚጠፉት ዘንድ ይህ እንዴት እውነት ይሆን?20በጥዋትና በማታ መካከል ይጠፋሉ፤ ማንም ሳያውቀው እስከ ወዲያኛው ይጠፋሉ።21የድንኳናቸው ገመድ ከመካከላቸው የተነቀለ አይደለምን? ይሞታሉ፦ ያለጥበብም ይሞታሉ።
1አሁን እስቲ ተጣራ፤ የሚመልስ አንድ እንኳ አለ? ከቅዱሳንስ ወደየትኛው ትዞራለህ?2ሰነፍን ሰው ቍጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።3ቂል ሰው ሥር ሲሰድድ አየሁ፥ ነገር ግን በድንገት ቤቱን ረገምሁት።4ልጆቹም ከደኅንነት ከለላ ውጪ ናቸው፥ በከተማም አደባባይ የተረገጡ ናቸው፥ አንድም የሚያድናቸው የለም።5የተሰበሰበውን ሰብል በተራቡ በሌሎች ተበላ፥ ከእሾህ ውስጥ እንኳ የወጡ ሰዎች ወሰዱት፤ ያለውም ሁሉ ሀብትን በተጠሙ ሰዎች ተዋጠ።6ችግር እንዲሁ ከአፈር አይመጣም፥ መከራም ከመሬት አይመነጭም፤7ነገር ግን የእሳት ፍንጣሪዎች ወደ ላይ እንደሚበርሩ፥ እንዲሁ ሰው መከራን በራሱ ላይ ያመጣል።8እኔ ግን እግዚአብሔርን ወደራሱ፥ ጉዳዬን ወደ ማቀርብለት ወደ እግዚአብሔር እመለስ ነበር።9እርሱ ታላቅና የማይመረመሩ ዋና ነገሮችንና የማይቈጠሩ አስደናቂ ነገሮችን ያደርጋል።10በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል።11የተዋረዱትን በከፍታ ሊያኖር ፥ ኀዘንተኞችንም ለደኅንነት ከፍ ለማድረግ ይህንን ያደርጋል።12እጃቸው እቅዳቸውን እንዳይፈጽም የተንኰለኞችን ወጥመድ ከንቱ ያደርጋል።13ጠቢባንን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል የተንኮለኞችንም ዕቅድ ያጠፋል።14በቀን ከጨለማ ጋር ይጋጠማሉ፥ በዕኩለቀንም በሌሊት እንዳሉ ያክል በዳበሳ ይሄዳሉ።15ነገር ግን ድሀውን ከአፋቸው ሰይፍ፤ ችግረኛውንም ከኃያላን እጅ ያድነዋል።16ስለዚህ ድሀው ተስፋ አለው፤ ፍትህ አልባነት ግን አፍዋን ትዘጋለች።17እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚያርመው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን አምላክንተግሣጽ አትናቅ።18ምክንያቱም እርሱ ይሰብራል፥ ይጠግናል ያቈስላል በኋላም በእጆቹ ይፈውሳል።19እርሱ ከስድስት ክፉ ነገሮች ውስጥ ያወጣሃል፥ በርግጥ በሰባተኛው ክፋት አይነካህም።20በራብ ጊዜ ከሞት፥ በጦርነትም ከሰይፍ ስለት ያድንሃል።21ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፤ ጥፋትም ሲመጣ አትፈራም።22በጥፋትና በራብ ላይ ትስቃለህ፤ የምድር አውሬዎችንም አትፈራም፤23ከምድርህ ድንጋይ ጋር ኪዳን ይኖርሃል ከምድር አራዊትም ጋር በሰላም ትሆናለህ።24ድንኳንህም በደህንነት እንዳለ ታውቃለህ፤ በረትህን ትጐበኛለህ አንድም አይጠፋብህም።25ዘሮችህም ታላቅ እንደሚሆኑ፥ ትውልድህም እንደ ምድር ሣር እንደሚበዙ ታውቃለህ።26የእህሉ ነዶ ደርሶ በወቅቱ ወደ አውድማ እንደሚገባ፥ ዕድሜን ጠግበህ ወደ መቃብር ትሄዳለህ።27እነሆ፥ ይህንን ነገር መረመርን፥ ነገሩ እውነት ነው፤ ልብ በለው፤ የራስህም እውቀት አድርገው።
1ኢዮብም ሲመልስ እንዲህም አለ፦2ኦ ስቃዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ!3ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና ለዚህ ነው ቃሎቼ የድፍረት ቃላት የሆኑት።4ሁሉን የሚችል አምላክ ቀስት በውስጤ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፤ የእግዚአብሔር ማስደንገጥ በእኔ ላይ ተሰልፎአል።5በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው በዝለት ያናፋልን? በሬስ ገለባ እያለው በረሀብ ይጮኻልን?6ጣዕም የሌለው ነገርስ ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ በእንቁላል ውኃ ውስጥ ጣዕም አለን?7ለመንካት ሰውነቴ እምቢ አላቸው፤ እንደሚያስጸይፍ ምግብ ሆኑብኝ።8ምነው ልመናዬ በደረሰልኝ! እግዚአብሔርም መሻቴን ምነው በሰጠኝ!9እግዚአብሔርም አንድ ጊዜ እኔን ማጥፋት ደስ ቢያሰኘው እጁንም ዘርግቶ ከዚህ ሀይወት ቢያስወግደኝ!10ይህም መጽናናት ይሆንልኛል፤ በማይበርድ ሕመም ውስጥ ብሆንም፥ የቅዱሱን ቃል አልክድምና።11እድጠብቅ አቅሜ ምንድን ነው? የምታገሰውስ የህይወቴ ፍጻሜ ምን ስለሆነ ነው?12ጕልበቴ የድንጋይ ጕልበት ነውን? ወይስ ሥጋዬ የተሰራው ከናስ ነውን?13በእኔ ውስጥ ሊረዳኝ የሚችልነገር እንደሌለ ጥበብም ከእኔ እንደ ተባረረ እውነት አይደለምን?14ሁሉን የሚችል አምላክን መፍራት የተወ ሰው፥ በዝለት ሊወድቅ ለቀረበ ስንኳ ታማኝነት ከወዳጁ ሊሆንለት ይገባል።15ነገር ግን ወንድሞቼ ጥቂት ቆይቶ ውሃ እንደማይኖረው r እንደ በረሃ ወንዝ የማይታመኑ ሆኑብኝ።16ከበረዶ የተነሣ ፥በውስጡም ከተሰወረው አመዳይ፤ ወንዙ ደፍርሶ ይጠቁራል፥17ሙቀትበመጣ ጊዜ ይደርቃሉ፤ በበጋም ወቅት ከስፍራቸው ይጠፋሉ።18ተጔዥ ነጋዴዎች ውሃ ፍለጋ መንገዳቸውን ሲቀይሩ፤ ወደ በረሃ ገብተው ተቅበዝብዘው ይጠፋሉ።19የቴማን ነጋዴዎች በዚያ ተመለከቱ፥ የሳባ መንገደኞችም ተስፋ አደረጉ።20ውሃ እንደሚያገኙ ተማምነው ነበርና አፈሩ፤ ወደዚያ ደረሱ፥ ነገር ግን ተታልለው ነበር።21አሁንም እናንተ እንዲሁ ደረቅ ሆናችሁብኝ መከራዬን አይታችሁ ለራሳችሁ ፈራችሁ።22በውኑ እኔ፦”አንዳች ነገር ስጡልኝ? ፤ ከሃብታችሁ ስጦታ አቅርቡልኝ?23ወይስ፦ ከጠላቴ እጅ አድኑኝ? ከአስጨናቂዎቼ እጅ ተቤዡኝ“ ብያችኋለሁን?24አስተምሩኝ፥ እኔም ዝም እላለሁ፤ ምን ጋር እንደተሳሳትሁ አስረዱኝ።25የእውነት ቃል እንዴት ያማል! ነገር ግን የእናንተ ሙግት እንዴት እኔን ይገሥጻል?26ተስፋ እንደ ሌለው ሰው ንግግር ቃሌን እንደ ነፋስ ችላ ለማለት ታስባላችሁን?27በርግጥ አባት አልባ በሆኑ ልጆች ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፤ ለወዳጆቻችሁም ጕድጓድ ትቈፍራላችሁ።28አሁንም፥ እባካችሁ፥ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ በእርግጥ በፊታችሁ አልዋሽም።29እባካችሁ፥ ተመለሱ፤ ፍትህ አልባነት በእናንተ መካከል አይሁን፤ በርግጥ ምክንያቴ ጽድቅ ነውና መለስ በሉ።30በውኑ በምላሴ ክፋት አለን? አፌስ ተንኰልን መለየት አይችልምን?
1ለእያንዳንዱ ሰው ህይወት በምድር ብርቱ ልፋት አይደለምን?ቀኖቹስ እንደ ተቀጣሪ ሰራተኛ ቀኖች አይደሉምን?2የምሽት ጥላን እንደሚመኝ አገልጋይ፤ደመወዙንም በጽኑ እንደሚፈልግ ቅጥረኛ፤3እንዲሁ የጉስቁልና ወራትና፤ መከራ የተሞሉ ለሊቶችን በጽናት እንዳልፍ ተሰጡኝ።4በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? ሌሊቱስ መቼ ያልፋል እላለሁ። እስኪነጋ ድረስም ወዲያና ወዲህ እገላበጣለሁ።5ሥጋዬ ትልና የአመድ ቅርፊት ለብሶአል፤ ደርቆ የነበረው የቆዳዬም ቁስል እንደ ገና ያመረቅዛል።6ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ፈጣን ናቸው፥ ያለ ተስፋም ያልፋሉ።7ሕይወቴ አንድ ትንፋሽ እንደ ሆነ፤ ዓይኔም መልካም ነገርን ከእንግዲህ አንደማያይ አሳሰበኝ።8የሚያየኝ የእግዚአብሔር ዓይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፤ ዓይኖችህ በእኔ ላይ ይሆናል፥ እኔ ግን አልገኝም።9ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንደዚሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ተመልሶ አይወጣም።10ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፥ የነበረበት ስፍራውም ዳግመኛ አያውቀውም።11ስለዚህም አፌን አልገድበውም፤ በመንፈሴ ስቃይ ሆኜ እናገራለሁ፤ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አቤቱታዬን አቀርባለሁ።12ጠባቂ በላዬ ትቀጥርብኝ ዘንድ፥ እኔ ባሕር ወይስ የባህር አውሬ ነኝን?13እኔም፦ "አልጋዬ ያጽናናኛል፥ መቀመጫዬም የኀዘን እንጕርጕሮዬን ያቀልልኛል" ባልሁ ጊዜ፥14አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፥ በራእይም ታስደነግጠኛለህ፤15ስለዚህም እኔ አጥንቴን ከምታገስ ይልቅ መታነቅንና ሞትን እመርጣለሁ።16ለዘላለም መኖርን እንዳልመኝ፤ ሕይወቴን ናቅኋት። ቀኖቼ ዋጋ ቢስ ናቸውና እባካችሁ ተዉኝ።17ትኩረት ትሰጠው ዘንድ ፥ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ ሰው ምንድር ነው፥18ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥ በየጊዜውስ ትፈትነው ዘንድ?19የማትተወኝ እስከ መቼ ነው? ምራቄንስ እስክውጥ ድረስ የማትለቅቀኝ እስከ መቼ ነው?20ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ ኅጢያትንስ አድርጌ እንደ ሆነ ይህ ላንተ ምንድን ነው? ሸክም እ ሆንብህ ዘንድ? ስለ ምን የኢላማሀ ግብ አደረግኸኝ?21መተላለፌን ይቅር ብለህ ስለ ምን ጉስቁልናዬን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በጥንቃቄም ትፈልገኛለህ፥ አታገኘኝም።
1ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦2እስከ መቼ እነዚህን ነገሮች ትናገራለህ? የአፍህስ ቃል እስከ መቼ እንደ ብርቱ ነፋስ ይሆናል?3በውኑ እግዚአብሔር ፍትህን ያቃውሳልን? ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?4ልጆችህ በድለውት እንደ ሆነ፥ እርሱም በበደላቸው እጅ አሳልፎ እንደሰጣቸው እናውቃለን።5ነገር ግን እግዚአብሔርን በትጋት ብትፈልገውና፥ ሁሉንም ለሚችለው አምላክ ልመናህን ብታቀርብ፥6ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ ስለ አንተ ይቆማል፥ በርግጥ የታመነ መኖሪያ ያደርግልሃል።7ጅማሬህ ትንሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።8ስለ ቀደመው ዘመን ትውልድ ትጠይቅ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ አባቶቻቸውም ከመረመሩና ካገኙት ነገር ለመማር ትጋ፤9(ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ስለሆነ እኛ ትናንት ተወለድን፤ ምንም አናውቅም) ፤10እነዚህ የሚነግሩህና የሚያስተምሩህ አይደሉምን? ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?11በውኑ ረግረግ በሌለበት ደንገል ሳር ይበቅላልን? ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?12ገና ለምለም አረንጓዴ ሆኖ ሳይቈረጥ፥ ከአትክልት ሁሉ በፊት ይጠወልጋል።13እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ የመንገዳቸው ፍጻሜ እንዲሁ ነው፤ አምላክ የሌለው ሰው ተስፋም ይጠፋል።14መታመኛቸው እንደሚናድባቸው፥ እምነቱም የሸረሪት ድር አይነት የሆነበት።15እዲህ አይነት ሰው ቤቱን ይደገፋል፥ነገር ግን አይቆምለትም፤ደግፎም ይይዘዋል፥ አይጸናለትም።16ፀሐይም እንደወጣች ይለመልማል፥ ጫፉም በአትክልቱ ቦታ ጎልቶ ይወጣል።17ሥሮቹ በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጠማሉ፤ በድንጋዮቹም መካከል መልካም ቦታን ይፈልጋሉ።18ነገር ግን ይህ ሰው ከቦታው ቢጠፋ፦ ስፍውም "ፈጽሞ አቼህ አላውቅም" ብሎ ይክደዋል።19እነሆ፥ የደስእንደዚህ አይነትሰው ደስታ ይህ ነው፤ ሌሎች ተክሎች ከዚያው አፈር በፋንታው ይበቅላሉ።20እነሆ፥ እግዚአብሔር ንጹሁን ሰው አይጥለውም፥ የክፉ አድራጊውንም እጅ አያበረታም።21አፍህን እንደ ገና ሳቅ፥ ከንፈሮችህንም በደስታ ጩኊት ይሞላል።22የሚጠሉህ እፍረትን ይለብሳሉ፤ የአመጸኞችም ድንኳን አይገኝም።
1ኢዮብም ሲመልስ እንዲህም አለ፦2“ እንዲህ እንደ ሆነ በእውነት አውቃለሁ፤ ነገር ግን ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል?3ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ቢፈልግ፥ ከሺህ ነገር አንዱን እንኳ መመለስ አይችልም።4እግዚአብሔር በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ እርሱን ተዳፍሮ በደኅና የተሳካለት ማን ነው?5በቍጣው ተራሮችን ሲገለብጣቸው፤ ተራሮችን ሲነቅላልቸው ለማን አስቀድሞ ተናገረ።6ምድርን ከስፍራዋ ያሚያናውጣት እርሱ፥ ምሰሶዎችዋንም ያንቀጠቅጣቸዋል።7ይኸው እግዚአብሔር ፀሐይን እንዳትወጣ ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤ ከዋክብትንም ይከልላቸዋል።8ሰማያትን በራሱ ይዘረጋል፥ የባሕሩን ማዕበል የሚገዛ በላዩም ይራመዳል።9ድብና ኦሪዮን የሚባሉትን ኮከቦች፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ስብስቦች ሠርቶአል።10ይኸው እግዚአብሔር የማይመረመሩ ታላላቅ ነገሮችን፥ በርግጥ የማይቈጠሩ ተአምራቶችን ያደርጋል።11እነሆ፥ ወደ እኔ ቢመጣ አላየውም፤፤ በአጠገቤም ቢያልፍ አላውቀውም።12እነሆ አንድን ሰው ነጥቆ ቢወስድ የሚከለክለው ማን ነው? ምን እያደረግህ ነው? የሚለውስ ማን ነው?13እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ የረዓብ ረዳቶች ከእርሱ በታች ይሰግዳሉ።14ይልቁንስ መልስ ልመልስለት፥ ከእርሱ ጋርስ ለክርክር ቃልን እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?15ጻድቅ ብሆን ኖሮ እንኳ ልመልስለት አልችልም፤ የምችለው ዳኛዬን ምህረት መለመን ብቻ ነው ።16ብጠራውና እርሱ ቢመልስልኝ ም ኖሮ፥ ድምጼን ይሰማ እንደ ነበር አላምንም ።17በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛዋል።18ትንፋሽ እድወስድ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም፥ ይልቅ በመራራነት አጠገበኝ።19ስለ ኃይል ከተናገርን እንደ እርሱ ኃያል ማን ነው፤ የፍርትህ ነገር ከተነሳ፦”የሚጠይቀኝ ማን ነው? “ ይላል።20ጻድቅ ብሆን እንኳ አንደበቴ ይወቅሰኛል፤ ሰበብ ባይገኝብኝ እንኳ ጥፋተኛ ያደርገኛል።21ያለነቀፋ ብሆንም ከእንግዲህ ለራሴ ግድ የለኝም፤ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።22ልዩነት የለውም፤ እርሱ “ጻድቁንና ሃጥኡን ባንድነት ያጠፋል" የምለው ለዚህ ነው።23መቅሠፍ በድንገት ቢገድል፥ በንጹሐን ሰዎች ችግር ይስቃል።24ምድር ለኃጥአን እጅ ታልፋ ተሰጥታለች፤ እግዚአብሔርም የዳኞችዋን ፊት ሸፍኖአል፤ ይህን ያረገው እርሱ ካልሆነ ታድያ ማን ነው?25ዘመኔ ከመልክተኛ ሰው ሩጫ ይልቅ ይፈጥናል፤ ቀኖቼ፥ መልካምን ሳያዩ ይከንፋሉ።26የደንገል ጀልባ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደሚነጥቀው ግዳይ እንደሚበርር ፈጣን ናቸው።27“አቤቱታዬን እረሳለሁ፤ ሐዘንተኛ ፊቴን ትቼ ደስተኛ እሆናለሁ” ብዬ ብል፥28ንጹሕ አድርገህ እንደማትቆጥረኝ ስላወቅሁ መከራዬን ሁሉ እፈራዋለሁ።29ጥፋተኛ ሆኜ መቀጣቴ ላይቀር፤ ለምን በከንቱ እደክማለሁ?30ራሴን በአመዳይ ውሃ ባጥብና እጆቼንም እጅግ ባነጻቸው፥31የገዛ ልብሴ እስኪጸየፈኝ ድረስ እግዚአብሔር በአዘቅት ውስጥ ይመልሰኛል።32መልስ እድሰጠው ፥ አብረን ወደ ፍርድ ችሎት እንዳንገባ፥ እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።33እጁን በሁለታችንም ላይ የሚያኖር ፈራጅ፤ በመካከላችንም የሚዳኝ የለም!34የእርሱን በትሩ ከእኔ ላይ የሚያነሳ፥ ማስደንገጡንም ከኔ የሚያርቅ ሌላ ፈራጅ የለምን?35በሚገባ በተናገርሁ፥ ባልፈራሁም ነበር፤ ነገር ግን አሁን ነገሮች እንዲህ ባሉበት አልችልም።
1በራሴ ሕይወት ዝያለሁ፤ አቤቱታዬን ያለመቆጠብ እገልጻለሁ፤ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።2እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ ለምን እንደ ከሰስከኝ ንገረኝ እንጂ እንዲያው አትፍረድብኝ።3የእጅህን ሥራ መናቅ፤እኔንስ ማስጨነቅ የኃጥአንን እቅድ ግን በፈገግታ ስትተወው ይህ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን?4በውኑ አይኖችህ የሥጋ ለባሽ ዓይኖች ናቸውን? ሰውስ እንደሚያይ ታያለህን?5በደሌን ትከታተል ዘንድ፥ ኃጢአቴንም ትመረምር ዘንድ፥6ቀኖችህ እንደ ሰው ቀኖች ናቸውን? ዓመታትህስ እንደ ሰው ዓመታት ናቸውን?7በደለኛ እንዳልሆንሁ ብታውቅም እንኳ፥ ከእጅህ ሊያድነኝ የሚችል የለም።8እጆቸህ አበጃጁኝ አሳምረህም ሠራኸኝ፤ መልሰህ ግን እያታጠፋኸኝ እኮ ነው።9እለምንሃለሁ፤ እንደ ሸክላ አበጃጅተህ እንደ ሰራኸኝ አስብ፤ እንደገናስ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?10እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን? እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?11ስጋን አደረክልኝ ቁርበትንም አለበስኸኝ፥ በአጥንትና በጅማትም አቀናብረህ አጠነከርኸኝ።12ሕይወትና የታመነ ኪዳን ሰጠኸኝ፤ እርዳታህም መንፈሴን ጠበቀ።13ነገር ግን እነዚህንም ነገሮች በልብህ ሰወርህ፤ ይህንንም ታስብ እንደነበር አውቃለሁ።14ኃጢአትም ባደርግ አንተ ታውቀዋለህ፤ ከአመጻዬም ነጻ አትለቀኝም።15በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፤ ጻድቅ ብሆንም ራሴን ቀና አላደርግም፤ በሃፍረት ተሞልቼአለሁና፥ መከራዬንም እያየሁ ነውና።16ራሴንም ቀና ባደርግ እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፤ እንደገና ሃያል መሆንህን ታሳየኛለህ፤17አዲስ ምስክሮችህን ታቆምብኛለህ ቍጣህንም በላዬ ታበዛብኛለህ፤ በአዲስ ሰራዊትም ታጠቃኛለህ።18ታዲያ ለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ምነው ያኔ ነፍሴ በጠፋችና የሰው ዓይን ባላየኝ።19ኖሮ እንደማያውቅ በሆንሁና፤ ከማኅፀን ቀጥታ ወደ መቃብር በወሰዱኝ።20የቀሩኝ ቀናቶች ጥቂት አይደሉምን? ታዲያ ጥቂት እንዳርፍ ተወት አድርገኝ፤21ወደማልመለስበት ከመሄዴ በፊት፥ ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ ምድር፥22እንደ እኩለ ለሊት ወደ ጨለመች ምድር፥ ሥርዓትም ወደሌለበት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ።
1ነዕማታዊውም ሶፋር እንዲህ በሎ መለሰ፦2ለዚህ ሁሉ ቃል መልስ መስጠት አይገባምን? በንግግር የተማላው ይህ ሰው እንዲያው ይታመናልን?3ትምክህትህስ ሌሎችን ሁሉ ዝም ያሰኛቸዋልን? ትምህርታችንን ስትሳለቅበት፤ የሚያሳፍርህ ማንም የለምን?4ለእግዚአብሔር ስትናገር “ትምህርቴ የተጣራ ነው፥በዓይንህም ፊት ነቀፋ የለብኝም” ትላለህ።5ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት!6በማስተዋሉ ታላቅ ነውና፤ የጥበቡን ምሥጢር ምነው ገልጦ ቢያሳይህ! እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ ታውቅ ነበር።7እግዚአብሔርን መርምረህ ልትረዳው ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን በሙላት ልታውቀው ትችላለህን?8ነገሩ እንደ ሰማይ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?9ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፥ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።10እርሱ በመካከልህ ቢያልፍ፥ የፈለገውን በግዞት ቢዘጋ፥ ለፍርድ የወደደውን ቢጠራ፥ የሚከለክለው ማን ነው?11እርሱ ሃሰተኛ ሰዎችን ያውቃልና፥ አመጻንም ሲመለከት እንዳላየ ያልፋልን?12የሜዳ አህያ ሰው በወለደ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ ሞኞች ሊረዱት አይችሉም።13ነገር ግን ልብህን በትክክል ብታቀና፤ እጅህንም ወደ እግዚአብሔር ብትዘረጋ፥14በደልንም ከእጅህ እጅግ ብታርቀው፤ በድንኳንህም ኃጢአት ባይኖር፤15ያን ጊዜ በእርግጥ ያለ እፍረት ቀና ትላለህ፤ ጠንክረህም ትቆማለህ፥ አትፈራምም።16መከራህንም ትረሳዋለህ፤ እንዳለፎ እንደሔደም ውኃ ታስበዋለህ።17ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ይበራል፤ ጨለማም ቢኖር እንኳ እንደ ጥዋት ይሆናል።18ተስፋ ስላለህ ተማምነህ ትቀመጣለህ፤ በዙሪያህ ሁሉ ደኅንነትን ታያለህ፥ በእረፍትም ትቀመጣለህ።19ለማረፍ ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፤ ብዙዎችም ያንተን እርዳታ ይሻሉ።20ነገር ግን የክፉዎች ዓይን ግን ትጨልማለች፤ የሚያመልጡበትም መንገድ የላቸውም፥ ያላቸው ተስፋም የመጨረሻ ትንፋሻቸውን መስጠት ብቻ ነው።
1በመቀጠልም ኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦2በእርግጥ እናንተ አዋቂ ሰዎች ናቸሁ፤ ጥበብ ከእናንተ ጋር ትሞታለች።3ነገር ግን እኔ እንደ እናንተው ማስተዋል አለኝ፤ ከእናንተም የማንስ አይደለሁም፤ በእርግጥ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች የማያውቅ ማን ነው?4እግዚአብሔርን ሲጠራ የሚመልስለት ሰው የነበርሁ እኔ አሁን ለጎረቤቶቼ መሳለቅያ ሆኛለሁ፤ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት የነበርሁ እኔ አሁን ማሾፊያ ሆኛለሁ።5በደላው ሰው ሃሳብ ውስጥ መከራ የተናቀ ነው፤ እግሩ ለሚሸራተት ሰው ችግሩን ሊጨምርበት ያስባል።6የዘራፊዎች ድንኳን ይበለጥጋል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ በደህና ተቀምጠዋል፤ የገዛ እጃቸውን አምላካቸው አድርገዋል።7አሁን ግን እንስሶችን ጠይቁ፥ ያስተምሯችኋል፤ የሰማይንም ወፎች ጠይቁ፥ ይነግሯችኋል።8ወይም ለምድር ተናገሩ፥ እርስዋም ታስተምራችኋለች፤ የባሕርም ዓሣዎች በግልጥ ይነግሯችኋል።9ከእነዚህ ሁሉ እንስሳት የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፤ የሕያዋን ሁሉ ህይወት፤10የሰው ልጆችንም ሁሉ እስትንፋስ በእጁ እንደያዘ የማያውቅ ማን ነው?።11ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚቀምስ፥ ጆሮ ቃላትን አይለይምን?12እድሜ በገፉት ዘንድ ጥበብ፥ በዘመን ርዝማኔም ማስተዋል ይገኛል።13በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ ምክርና ማስተዋልም በእርሱ ዘንድ ይገኛሉ።14እነሆ፥ እርሱ ያፈርሳል፥ ተመልሶም አይሠራም፤ አንድን ሰው ቢያስር ሊፈታው የሚችል የለም።15እነሆ፥ ውኆቹን ቢከለክል፥ እነርሱ ይደርቃሉ፤ እንደ ገናም ቢለቃቸው፥ ምድርን ያጥለቀልቃሉ።16ብርታትና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ የሚስተውና የሚያስተው በእርሱ ስልጣን ስር ናቸው።17መካሪዎችንም ባዶአቸውን በሃዘን ይሰዳቸዋል፥ ፈራጆችንም አላዋቂ ያደርጋቸዋል።18የነገሥታትንም የስልጣን ሰንሰለት ይፈታል፥ ወገባቸውንም በመታጠቂያ ልብስ ያስርላቸዋል።19ይሽራል ባዶአቸውንምይሰዳቸዋል፥ ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል።20የታመኑ ሰዎችንም ንግግረ ያስወግዳል፥ የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል።21በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈሳል፥ የብርቱ ሰዎችንም ቀበቶ ይፈታል።22ከጨለማ ውስጥ ጥልቅ ነገሮችን ይገልጣል፥ ከሙታንም ሰፈር የመታየትን ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።23ህዝቦችን ብርቱ ያደርጋል፥ ደግሞም ያጠፋቸዋል፤ ህዝቦችንም ያበዛል፥ ደግሞም ወደ ግዞት ይልካቸዋል።24ከምድር ሕዝብ አለቆች ማስተዋልን ይወስዳል፥ መንገድም በሌለበት ምድረበዳ ያቅበዘብዛቸዋል።25ብርሃን በሌለበት በጨለማ ይዳክራሉ፤ እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ።
1እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዓይኔ አይቷል፤ ጆሮዬም ሰምቶ አስተውያለሁ።2እናንተ የምታውቁትን እኔም ደግሞ አውቀዋለሁ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።3ቢሆንም ግን ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር መነጋገር እመርጣለሁ፥ ከእግዚአብሔርም ጋር መዋቀስ እፈልጋለሁ።4እናንተ ግን እውነትን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፤ ሁላችሁ ዋጋ የሌላችሁ ሃኪሞች ናችሁ።5ምነው ሁላችሁ ዝም ብትሉ! ይህም ጥበብ ይሆንላችሁ ነበር።6እንግዲህ ክርክሬን ስሙ፥ የከንፈሬንም ሙግት አዳምጡ።7ለእግዚአብሔር ጽድቅ የሌለበትን ነገር ትናገሩለታላችሁን? ለእርሱስ በማታለል ታወሩለታላችሁን?8ቸርነትንስ ታደርጉለታላችሁን? ለእግዚአብሔርስ በሸንጎ ጠበቃ ትሆኑለታላችሁን?9እንደ ዳኛ ወደ እናንተ ቢዞርና ቢመረምራችሁ ይህ መልካም ይመስላችኋልን? ወይስ አንዱ ሌላውን ሰው እንደሚያታልል፣ በሸንጎ ትሳለቁበታላችሁን?10በስውር ወደ እርሱ ብታደሉ እንኳ፤ እርሱ በእርግጥ ይገስጻችኋል።11ግርማዊነቱ አያስፈራችሁምን? ማስደንገጡስ በላያችሁ አይወድቅምን?12አስገራሚ ንግግራችሁ ከአመድ የተሰሩ ምሳሌዎች ናቸው፤ ምላሻችሁም ከሸክላ የተሰሩ መመከቻዎች ናቸው።13ዝም በሉ፥ እኔም እንድናገር ተዉኝ፤ የሚመጣው ነገር ይምጣብኝ።14ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጆቼ አኖራታለሁ።15እነሆ ቢገድለኝ የሚቀርልኝ ተስፋ የለኝም፤ ቢሆንም ስለ መንገዴ በፊቱ እሟገታለሁ።16አምላክ እንደሌለው ሰው ወደ ፊቱ አልቀረብኩምና፤ለደህንነቴ ይሆንልኛል።17አምላኬ፡ንግግሬን በሚገባ አድምጥ፥ አስረግጬ የምለውም ለጆሮህ ይድረስ።18እነሆ አሁን፥ ሙግቴን አሰናድቻለሁ፤ ነጻ እንደምወጣም አውቃለሁ።19በሸንጎስ ቆሞ የሚከራከረኝ ማን ነው? ጥፋተኛ ሆኜ ከተገኘሁ፤ በዝምታ ህይወቴን ለሞት እሰጣለሁ።20አማላኬ ሁለት ነገር ብቻ አድርግልኝ፤ እኔም ራሴን ከፊትህ አልሸሽግም፤21ጠንካራ እጅህን ከእኔ አርቅ፤ በማስደንገጥህም አታስፈራኝ።22ከዚያም ጥራኝ፥ እኔም እመልስልሃለሁ። ወይም እኔ ልናገር፥ አንተም መልስልኝ።23በደሌና ኃጢአቴ ምን ያህል ሆነ? መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ።24ፊትህን ከእኔ ለምን ትሰውራለህ፥ እንደ ጠላትህስ ለምን ታደርገኛለህ?25የረገፈን ቅጠል ታሳድደዋለህን? ወይስ የደረቀን ገለባ ትከታተለዋለህ?26የመረረ ነገር ስለጻፍህብኝ፤ የወጣትነቴን ኃጢአት ታወርሰኛለህ።27እግሬንም በእግር ግንድ አስገባኸው፥ መንገዶቼን ሁሉ በቅርበት አየኻቸው፤ የእግሬ መርገጫ የተራመደበትን መሬት ሁሉ መረመርህ።28ምንምእንኳ እኔ እንደሚጣል ብስባሽ፥ ብልም እንደበላው ልብስ ብሆንም።
1ከሴት የተወለደ ሰው ጥቂት ቀናት ቢኖርም፥ በመከራ የተሞሉ ሆኑ።2እንደ አበባ ከመሬት ይወጣል፥ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላም ይፈጥናል፥ ነገር ግን አይቆይም።3እንደዚህ ያለውን ሰው ትመለከታለህን? ከአንተስ ጋር እኔን ወደ ፍርድ ታመጣኛለህን?4ከርኩስ ነገር ንጹሕን ማውጣት ማን ይችላል? ማንም የለም።5የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥ የወራቶቹም ቍጥር በአንተ እጅ ነው፥ እርሱም ሊያልፈው የማይችለውን ገደብ ቀጠርህለት።6እንደ ተቀጣሪ ሰው የቀሩትን ቀኖች እዲደሰትባቸው፤ እዲያርፍም ከእርሱ ዘወር በል።7ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ሊያቈጠቍጥ፥ ቅርንጫፉም ማደግ እንዳያቆም ተስፋ ሊኖረው ይችላል።8ምንምእንኳ ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥9የውኃ ሽታ ሲያገኝ ዳግም ያቈጠቍጣል እንደ አትክልትም ቅርንጫፍ ያወጣል።10ሰው ግን ይሞታል፤ ይደክማል፤ በርግጥ ሰው እስትንፋሱን ይሰጣል፥ እርሱስ ወዴት አለ?11ውኃ ከሐይቅ እንደሚያልቅ፤ ወንዙም እንደሚቀንስና እንደሚደርቅ፤12እንዲሁ ሰዎች ይተኛሉ ዳግም አይነሱም፤ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቁም፥ ከእንቅልፉቸውም አይነሱም።13በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!14በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን? መለወጤ እስኪመጣ ድረስ፥ የሰልፌን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።15በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር፤ የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር።16ለእርምጃዬ ጥንቃቄንና ገደብን ታደርግለታለህ፤ ኃጢአቴንም አትቆጣጠርብኝም።17መተላልፌን በከረጢት ውስጥ ታትመዋለህ፥ ኃጢአቴንም ትሸፍንልኛለህ።18ነገር ግን ተራራ እንኳ ይወድቃል ይጠፋልም፥ ዓለቶችም እንዲሁ ከስፍራቸው ይለቃሉ፤19ውኆች በድንጋዮቹ ላይ ይወርዳሉ፤ ጎርፎቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፤ እንዲሁ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።20ሁልጊዜ ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፤ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ወደ ሞት ትሰድደዋለህ።21ልጆቹ ወደ ክብር ቢመጡም አያውቅም፤ ቢዋረዱም ይህ ሲሆን አያይም።22ነገር ግን የራሱ ሰውነት ሕመም ብቻ ይሰማዋል፥ ለራሱም በሃዘን ያለቅሳል።
1ቀጥሎም ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ እንዲህም አለ፦2በውኑ ጠቢብ ሰው ከንቱ በሆነ እውቀት ይመልሳልን? ራሱንስ በምሥራቅ ነፋስ ይሞላልን?3ትርፍ በሌለው ወሬ ወይም በማይጠቅም ንግግር ይሟገታልን?4በእርግጥ አንተ የእግዚአብሔርን አክብሮት ታሳንሳለህ፤ ለእግዚአብሔር ያለህን መሰጠት ታስቀራለህ።5ሃጢያትህ አፍህን ያስተምረዋል፥ የተንኰለኛ አንደበት ቢኖርህ ትመርጣለህ።6የሚፈርድብህ የራስህ አፍ እንጂ እኔ አይደለሁም፤ በርግጥም የራስህ ከንፈሮች ይመሰክሩብሃል።7ከተወለዱት ሁሉ አንተ የመጀመሪያ ሰው ነህን? ወይስ ከኮረብቶች በፊት አንተ ነበርህ?8የእግዚአብሔርን ምሥጢራዊ እውቀት ሰምተሃልን? ጥበብንስ ለራስህ ብቻ ገደብሃትን?9እኛ የማናውቀው አንተ የምታውቀው ምንድር ነው? በእኛ ዘንድ የሌለ አንተ ብቻ የተረዳኸው ምን አለ?10ከአባትህ በዕድሜ የሚበልጡ ሽበትም ያላቸው ሽማግሌዎችም ከእኛ ጋር አሉ።11በውኑ የእግዚአብሔር ማጽናናት፥ በየውሃነት የቀረበልህ ቃልስ ጥቂት ሆነብህን?12የነፍስህ ስሜት ለምን ይወስድሃል? ዓይኖችህስ ለምን በቁጣ ያፈጣሉ?13መንፈስህ በእግዚአብሔር ላይ ተነስቷል፤ እንዲህ ያለ ቃል ከአፍህ እስከ ማውጣት ደረስህ።14ንጹሕ ሆኖ ሊገኝ ሰው ማን ነው? ጻድቅ ሊሆን ከሴት የተወለደ እርሱ ማን ነው?15እነሆ እግዚአብሄር በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ በእርግጥ ሰማያትም በእርሱ አይን ንጹሕ አይደሉም።16ይልቁንስ ኃጢአትን እንደ ውኃ የሚጠጣ ፥ አመጸኛና የተበላሸው የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ?17ስማኝ፥አሳይሃለሁ፤ያየሁትንም አሳውቅሃለሁ፤ በመካከላቸውም እንግዳ ያልገባባቸው ጠቢባን18ጠቢባን ከአባቶቻቸው ተቀብለው ያስተላለፉትን ፤ የእነርሱ ቀደምት ትውልድ ያልሸሸጉትን ነገር እገልጥልሃለሁ።19ለአባቶቻቸውም ፥ ምድሪቱ ለእነርሱ ብቻ ተሰጥታ ነበረ፥ በመካከላቸው እንግዶች አልፈው አያውቁም20ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ በሕመም ይሰቃያል፥ ግፈኛም በፊቱ ያሉት ዓመታት ለስቃይ ይሆኑበታል።21የሽብር ድምፅ በጆሮው ውስጥ ነው፤ በብልጽግናው እያለ አጥፊው ይመጣበታል።22ከጨለማ ተመልሶ እንደሚወጣ አያስብም፥ ሰይፍም አሸምቆ ይጠብቀዋል።23ወዴት አለ? እያለ እንጀራ ፍለጋ ብዙ ስፍራ ይዞራል፤ የጨለማ ቀን እንደ ደረሰበትም ያውቃል።24ጭንቀትና ስቃይ ያስፈራሩታል፤ ለጦርነት ዝግጁ እንደ ሆነ ንጉሥ ይበረቱበታል።25ምክንያቱም እጁን በእግዚአብሔር ላይ አንስቶአል፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ ፊት በትዕቢት ሔዷልና፥26በደንዳና አንገቱና በወፍራም ጋሻው ሆኖ፥ ይህ አመጸኛ ሰው በእግዚአብሔር ላይ ይመጣልና፥27ይህ እውነት ነው፥ምንም እንኳ በስብ ፊቱን ቢከድንም፥ ስቡንም በወገቡ ላይ ቢያጠራቅም፥28በፈረሱ ከተሞች ውስጥ፥ ሰውም በማይኖርበትና፥ ክምር ለመሆን በተመደቡ ቤቶች ውስጥ ይኖራልና፤29ባለጠጋ አይሆንም፥ ሀብቱም አይጸናም፤ ጥላው እንኳ በምድር ላይ አይቆይም፤30ከጨለማ ተለይቶ አይወጣም፤ ነበልባልም ቅርንጫፎቹን ያደርቃቸዋል፥ በእግዚአብሔር አፍ እስትንፋስም ይጠፋል።31ዋጋው ከንቱነት እንዳይሆን፥ ራሱን እያሳተ በከንቱ ነገር አይታመን።32ቀኑ ሳይደርስ የፍጻሜው ሰዓት ይመጣል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም።33እንደ ወይን ያልደረሰውን ዘለላ ይጥላል፤ እንደ ወይራ ዛፍም አበባውን ያረግፋል።34አምላክ የሌለው ህዝብ ጉባኤ ሁሉ ይመክናል፥ የሙሰኞችንም ድንኳን እሳት ትበላለች።35ተንኰልን ይፀንሳሉ፥ በደልንም ይወልዳሉ፥ ማህጸናቸውም ማታለልን ያዘጋጃል።
1ኢዮብም ሲመል እንዲህ አለ፦2እንደዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤ ሁላችሁም የማትጠቅሙ አጽናኞች ናችሁ።3ከንቱ ቃሎች መጨረሻ የላቸውምን? እንደዚህ ለመመለስ የቻላችሁት ምን ነክቷችሁ ነው?4እናንተ በእኔ ቦታ ብትሆኑ፤ እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ እኔም ቃላቶችን ሰብስቤ እያቀናበረሁ፥ በማሾፍም በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ እችል ነበር።5ኦ! በአፌም እንዴት አድርጌ ባበረታታኋችሁ! የከንፈሬም ማጽናናት እንዴት ሃዘናችሁን ባቀለለ ነበር!6ብናገር ሰቆቃዬ አይቀንስም፤ ከመናገር ዝም ብል እንዴት እገዛ ላገኝ እችላለሁ።7አሁን ግን እግዚአብሔር አድክመኸኛል፤ ቤተሰቤን ሁሉ አፈራርሰሃል።8አድርቀኸኛል ይኸውም በላዬ ይመሰክርብኛል፤ የሰውነቴም መጨማተር ምስክር ነው፤ ክሳቴም ተነሥቶ፤በፊቴ ላይ ይመሰክራል።9እግዚአብሔር በቍጣው ቀደደኝ፥ አሳደደኝም፤ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፤ ይህም ሲሆን ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፤10ሰዎችም በግርምት አፋቸውን ከፈቱ፤ እያላገጡም ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በእኔ ላይ ተሰበሰቡ።11እግዚአብሔር አመጸኛ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፥ በክፉዎችም እጅ ጣለኝ።12በሰላም ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰባበረኝ፤ በርግጥም አንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ ኢላማው አድርጎም አቆመኝ።13ቀስተኞቹ ከበቡኝ፤ ኵላሊቶቼንም ወጋቸው፥ አላስተረፈኝምም፤ ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሰ።14ከግድግዳዬም ጋር ደጋግሞ አጋጨኝ፤ እንደ ጦረኛ በላዬ ሮጠብኝ።15በሰውነቴ ላይ ማቅ ሰፋሁ፥ ቀንዴንም በመሬት ላይ ጣልሁት።16ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፤ በዓይኖቼ ቆብ ላይም የሞት ጥላ አለ፤17ቢሆንም ግን በእጄ ዓመፅ የለም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።18ምድር ሆይ፥ ደሜን አትሸፍኚ፥ ለቅሶዬም ማረፊያ ቦታ አይኑረው።19አሁንም ቢሆን፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ ለእኔም የሚሟገትልኝ በአርያም ነው።20ጓደኞቼ ተሳለቁብኝ ነገር ግን አይኖቼ በእግዚአብሔር ፊት እንባን ያፈሳሉ።21የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ያ በሰማይ ያለው ምስክሬ በእግዚአብሔር ፊት እንዲምዋገትልኝ እጠይቃለሁ!22ምክንያቱም ጥቂት ዓመታት ካለፉ በኋላ እኔም ወደማልመለስበት ስፍራ እሄዳለሁ።
1መንፈሴ ተጨረሰ፥ ቀኖቼም አለቁ፥ መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።2በርግጥ አላጋጮች ከእኔ ጋር አሉ፥ ዓይኔም ይህን ማላገጣቸውን ሁልጊዜ ያያል።3አሁንም መያዣን ለራስህ ሰጥተህ ዋስ ሁነኝ፤ ከአንተ ሌላ የሚረዳኝ ማን አለ?4እግዚአብሔር አንተ ልባቸው እንዳያስተውል አድርገሃል፤ በላዬም ከፍ እንዲሉ አታደርጋቸውም።5ለጥቅም ብሎ ጓደኞቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ የልጆቹ ዓይን ይታወራል።6ነገር ግን እርሱ ለሰዎች መተረቻ አደረገኝ፤ በፊቴም ላይ ተፉብኝ።7ዓይኔ ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘ፥ የሰውነቴ ክፍሎች በሙሉ እንደ ጥላ ቀጠኑ።8ጻድቅ ሰዎችም በዚህ ነገር ይደነቃሉ፥ ንጹሑም ሰው በዐመጸኞች ላይ ይበሳጫል።9ጻድቅ ግን መንገዱን ያጸናል፥ ንጹሕ እጆች ያሉትም ሰው ብርታትን እየጨመረ ይሄዳል።10እናንተ ሁላችሁ ግን እስቲ ወደ እኔ ኑ፤ ከመካከላችሁ አንድም ጠቢብ አላገኝም።11ቀኖቼ አለቁ፤ እቅዶቼ አበቃላቸው፥የልቤም ምኞት ሳይቀር ከንቱ ሆነ።12እነዚህ አሿፊ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ ብርሃንም የሚሉተ ወደ ጨለማ የቀረበውን ነው።13ሲኦልን እንደ ቤቴ ካየሁ፤ መቀመጫዬንም በጨለማ ከዘረጋሁ፤14ለጉድጓድም፦ “አንተ አባቴ ነህ” ፤ ለትልም፦ “አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ” ብዬ ካልሁ።15ታዲያ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይልኝ ማን ነው?16ተስፋስ ወደ አፈር ስንወርድ፥ አብሮኝ ወደ ሲኦል ይወርዳልን?
1ሹሐዊው በልዳዶስ ሲመልስ እንዲህ አለ፦2ወሬህን የምታቆመው መቼ ነው? እስቲ አስብ፥ ከዚያም እኛ እንናገራለን።3ለምን እንደ እንስሶች ቆጠርኸን? ለምን በአንተ ፊት እንደ ቆሻሻ ሆንን?4አንተ በራስህ ቍጣ ተወርሰሃል፤ ምድር ለአንተ ሲባል ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለቶች ከስፍራው መወገድ አለባቸው?5በእርግጥ የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል አያበራም።6ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ጨለማ ይሆናል፥ በላዩ ያለው መብራትም ይጠፋል።7የብርታቱም እርምጃ ያጥራሉ፥ የራሱ እቅዶች ወደታች ይጥሉታል።8በገዛ እግሩ ወደ ወጥመድ ይገባል፥ ወደ ጉድጓድም ውስጥ ይገባል።9ወጥመድ ተረከዙን ይይዘዋል፥ ወስፈንጠርም በላዩላይ ይሆናል።10በመሬትም ላይ የሸምቀቆ ገመድ፥ በመንገዱም ላይ ወጥመድ ለእርሱ ተሰውሯል።11ድንጋጤ በሁሉ አቅጣጫ ያስፈራዋል፥ ከኋላውም ሆነው ያሳድዱታል።12ብልጥግናው ወደ ራብ ይለወጣል፥ መቅሠፍትም ካጠገቡ ተዘጋጅቶለታል።13የሰውነቱም ክፍሎች ፈጽመው ይጠፋሉ፤ የሞትም በኵር ልጅም አካል ክፍሎቹን ይበላል።14ከሚታመንበት ቤት፤ ከተቀመጠበትም ድንኳን ይነቀላል፤ የድንጋጤ ንጉሥ ወደሆነው ወደ ሞት ያመጡታል።15ዲን በመኖሪያው እንደተበተነ ይመለከታሉ፤ የራሱያልሆኑ ሰዎችም በድንኳኑ ውስጥ ይኖራሉ።16ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥ ቅርንጫፉም ከላዩ ይወድቃል።17መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በመንገድም ላይ ስሙ አይነሳም።18ከብርሃን ወደ ጨለማ ይወስዱታል፥ ከዚህም ዓለም ያሳድዱታል።19በሕዝቡ መካከል ልጅ የልጅ ልጅም አይኖረውም፤ ጥቂት የሚቆይበትም ዘመድ እንኳ አያገኝም።20በአንድ ቀን የሆነበትን ሲያዩ የምዕራብ ሰዎች 、ይደነግጣሉ፥ በምስራቅ የሚኖሩ ሰዎችም ይፈራሉ ።21በርግጥ የኃጥዕ ቤቶች እንዲህ ናቸው፥ እግዚአብሔርንም የማያውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።
1ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦2በቃላቶቻችሁ የምታሰቃዩኝና፥ የምትሰባብሩኝ እስከ መቼ ነው?3አሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ በጭካኔ ስትበድሉኝም አላፈራችሁም።4በርግጥ ተሳስቼ ቢሆን እንኳ፥ ስሕተቱ የእኔ ጉዳይ ይሆናል።5በእርግጥ ራሳችሁን በላዬ ከፍ ብታደርጉ፥ እኔንም እንደተላላፊ ለሁሉ ብታስቆጥሩኝም፥6ግን ደግሞ እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፥ በመረቡም እንደ ያዘኝ ማወቅ ነበረባችሁ።7ስለ መበደሌ ልናገር ብጮኽም አልሰማም፤ እርዳታ ለማግኝት ብጠራም ፍትህ የለም።8እንዳላልፍ መንገዴን አጥሮታል፥ በመንገዴም ላይ ጨለማ አኑሮበታል።9ክብሬን ከላዬ ገፈፈ፥ ዘውዴንም ከራሴ ላይ አነሳ።10እስክጠፋ ድረስ፥ በየአቅጣጫው ሰበረኝ፤ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቀለው፤11ቍጣውንም በላዬ አነደደው፥ ከጠላቶቹም እንደ አንዱ አድርጎ ቈጠረኝ።12ሠራዊቱ በአንድነት መጡብኝ፥ መወጣጫም በእኔ ላይ አዘጋጁ፥ በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።13ወንድሞቼን ከእኔ አራቃቸው፥ የሚያውቁኝም ፈጽመው ተለዩኝ።14ዘመዶቼ ተዉኝ፥ የቅርብ ጓደኞቼም ረሱኝ።15አንድ ወቅት በቤቴ በእንግድነት የተቀመጡ፥ ሴቶች ሰራተኞቼም እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤ በፊታቸውም እንደ ባዕድ ሆንሁ።16አገልጋዬን ተጣራሁ፥ በአፌም ለመንሁት ነገር ግን መልስ አልሰጠኝም።17ትንፋሼም ለሚስቴ የሚያስጠላት ሆነ፥ ልመናዬም በገዛ ወንድሞቼና እህቶቼ ተጠላ።18ሕፃናቶች እንኳ አንቋሸሹኝ፤ ለመናገር ብነሣም መልሰው ይናገሩኛል።19የሚያማክሩኝ ጓደኞቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤ የምወድዳቸው በእኔ ላይ ተነሱ።20አጥንቴ ከሥጋዬና ከቆዳዬ ጋር ተጣበቀ በድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።21ጓደኞቼ ሆይ፥ እዘኑልኝ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና እዘኑልኝ።22እግዚአብሔር እንደሆናችሁ ያክል ለምን ታሳድዱኛላችሁ? ሥጋዬን ማጥፋታችሁ ስለ ምን አይበቃችሁም?23ኦ ምነው ቃሎቼ ቢጻፍ! ምነው በመጽሐፍ ቢታተሙ!24ምነው በብረት ብዕርና በእርሳስ ተጽፎ፥ በዓለት ላይ ለዘላለም ቢቀረጽ!25እኔ ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም በምድር ላይ እንዲቆም አውቃለሁ፥26ይህ ቆዳዬ ማለትም ሰውነቴ ከጠፋ በኋላ፥ በአካሌ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።27አየዋለሁ፥ እኔ ራሴ በአጠገቤ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼ ይመለከቱታል፥ እንግዳም አይሆንብኝም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።28“ 'እንዴት እናሳድደዋለን! የችግሩ ሥር በእርሱ ውስጥ ነው' ብትሉ፥29ቍጣ የሰይፍን ቅጣት ያስከትላልና፣ ሰይፍን ፍሩ፤ ፍርድ እንዳለም ታውቃላችሁ።”
1ናዕማታዊውም ሶፋር ሲመልስ እንዲህ አለ፦2ከውስጤ ጭንቀት የተነሳ አሳቤ መልስ እንድሰጥ አስቸኮለኝ።3የሚያሳፍረኝን ተግሣጽ ከአንተ ሰምቻለሁ፥ ነገር ግን ከመረዳቴ የሚያልፍ መንፈስ ይመልስልኛል።4እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ካኖረበት፥ ከጥንት ጀምሮ እንዴት እንደ ነበር አታውቅም?5የኃጢአተኛ መፈንጨት አጭር ፣ የአመጸኛም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?6ቁመቱ እስከ ሰማይ ቢደርስ፥ ራሱም እስከ ደመና ቢሆን፥7እንዲህ ያለ ሰው እንደ ምናምን ፈጽሞይጠፋል፤ አይተውት የነበሩም፦ ወዴት ነው? ይላሉ።8እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፤ በርግጥ እንደ ሌሊት ራእይ በርሮ ይጠፋል።9ያየውም ዓይን ዳግመኛ አያየውም፤ የነበረበት ስፍራም እንደገና አይመለከተውም።10ልጆቹ ድሆችን ይቅርታ ይላሉ፤ እጆቹም ሀብቱን መመለስ ይገባቸዋል።11አጥንቶቹ በወጣትነት ጉልበት ተሞልተዋል፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በአፈር ውስጥ ይተኛል።12ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥ ከምላሱም በታች ቢደብቀው፥13ምንም እንኳ እዚያው ቢያቆየው ባይለቅቀውም፥ በአፉ ውስጥ ቢይዘው፥14ምግቡ በአንጀቱ ውስጥ ወደ መራራነት ይለወጣል፤ በውስጡ እንደ እባብ መርዝ ይሆንበታል።15የዋጠውን ሀብት መልሶ ይተፋል፤ እግዚአብሔርም ከሆዱ ያስወጣዋል።16የእባብን መርዝ ይመጣል፤ የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።17በማርና በቅቤ ፈሳሾች፥ በወንዞችም ተደስቶ አይኖርም።18የደከመበትንም ሳይበላው መልሶ ይሰጣል፤ ባገኝውም ሃብት ደስ አይለውም።19ድሆችን አስጨንቆአልና፥ ትቷቸዋልም፤ ያልሠራውንም ቤት በጉልበት ነጥቋል።20በራሱ እርካታን ስለማያውቅ፤ የሚደሰትበትን አንድ ነገር ሊያስቀምጥ አይችልም።21ሳያጠፋ የሚያስቀረው ነገር ስለማይኖር የሚዘልቅ ብልጽግና አይኖረውም።22በሃብት ጠግቦ እያለ ይቸገራል፤ በድህነት ያሉ እጆች ሁሉ ይነሱበታል።23ሆዱን ሊሞላ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር ብርቱ ቍጣውን ይሰድበታል፥ እየበላም ሳለ ያዘንብበታል።24ከብረት መሣርያ ይሸሻል፥ የናስ ቀስት ግን ይወጋዋል።25በርግጥ ቀስቱም ከኋላ ይወጋዋል፤ የጫፉም ብልጭታ በጉበቱ በኩል ይወጣል፤ ፍርሃትም ይመጣበታል።26ለከበረ ዕቃው ፍጹም ጥፋት ተዘጋጅቶለታል፤ ያልተራገበ እሳት ይበላዋል፤ በድንኳኑም የተረፈውን ይጨርሰዋል።27ሰማያት ኃጢአቱን ይገልጡበታል፥ ምድርም ምስክር ሆና ትነሣበታለች።28የቤቱም ባለጠግነት ይጠፋል፤ በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን የቤቱን ዕቃ ጎርፍ ይወስድበታል።29ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ ከእግዚአብሔርም የተመደበለት ርስቱ ይህ ነው።
1ቀጥሎም ኢዮብ ሲመልስ እንዲህ አለ፦2ንግግሬን በጥንቃቄ ስሙ፤ የምታጽናኑኝም እንደዚህ ይሁን።3እንድናገር ፍቀዱልኝ፤ ከተናገርሁም በኋላ ተሳለቁ።4ቅሬታዬን የማሰማው ሰው ላይ ነውን? ትዕግስት ባጣስ፤ አይገባኝምን?5እስቲ ተመልከቱኝና ተደነቁ፤ አፋችሁንም በእጃችሁ ያዙ።6እኔ ስቃዬን ባሰብሁ ቍጥር እጨነቃለሁ፥ በፍርሃትምሥጋዬ ይንቀጠቀጣል።7ለምን ኃጢአተኞች በሕይወት እስከ እርጅና ይኖራሉ? ለምን በሃይልስ ይበረታሉ?8ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ተደላድለዋል፥ ልጆቻቸውም በአይናቸው ፊት ጸንተው ይኖራሉ።9ቤቶቻቸው ያለስጋት ናቸው፥ የእግዚአብሔርም በትር በላያቸው የለም።10ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩም በከንቱ አይወድቅም፤ ላማቸውም አትጨነግፍም በጊዜዋ ትወልዳለች፥ ።11ሕፃናቶቻቸውን እንደ መንጋ ያሰማራሉ፥ ልጆቻቸውም ይቦርቃሉ።12በከበሮና በክራር ይዘምራሉ፥ በእምቢልታም ሙዚቃ ይደሰታሉ።13ዕድሜያቸውንም በብልጥግና ይፈጽማሉ፤ በጸጥታም ወደ ሲኦል ይወርዳሉ።14እግዚአብሔርንም፦" ከእኛ ራቅ፤ የመንገድህን እውቀት አንፈልግም' ይሉታል።15እናመልከው ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወደ እርሱ በመጸለይስ ምን ጥቅም ይገኛል? ይላሉ።16እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? ከኃጥአን ምክር ጋር ምንም አይነት ህብረት የለኝም። የኃጥአን መብራት የጠፋው፥17መቅሠፍትም በላያቸው የመጣባቸው ስንት ጊዜ ነው ፥ እግዚአብሔርም በቍጣው መከራ የከፈላቸው መቼ ነው፥18በነፋስ ፊት እንደ ገለባ፥ በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ትቢያ የሆኑ ስንት ጊዜ ነው?19እናንተ፦ 'እግዚአብሔር የበደለኛውን ቅጣት ለልጆቹ ይጠብቃል' ብላችኋል። ጥፋቱን እንዲያው ቅጣቱን ራሱ ይክፈል።20የገዛ ዓይኖቹ ጥፋቱን ይዩ፥ ሁሉን የሚችል አምላክን ቍጣ ራሱ ይጠጣ።21ወራቶቹስ ካለቁ በኋላ፥ ከራሱ ሌላ ስለቤተሰቦቹ ምን ገዶት?22በከፍታ ያሉትን ለሚፈርድ ለእግዚአብሔር ማን እውቀትን ሊያስተምረው ይችላል?23አንድ ሰው በፍጹም ሰላምና ጤና ሲቀመጥ በሙሉ ብርታቱ ሳለ ይሞታል።24በሰውነቱ ወተት ሞልቶአል፥ የአጥንቶቹም መቅን እርጥብና በጤንነት ናቸው።25ሌላው ሰው ደግሞ መልካምን ነገር ፈጽሞ ሳይቀምስ፤ በተመረረች ነፍስ ይሞታል።26በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይጋደማሉ፥ ሁለቱንም ትል ይጨርሳቸዋል።27አሳባችሁን፥ያሴራችሁብኝንም ክፉ ምክር አውቄዋለሁ።28እናንተ፦ 'የልኡሉ ቤት የት አለ? ኃጢአተኛውም ሰው ይኖርበት የነበረ ድንኳን የት ነው?" ብላችኋል።29መንገድ ተጓዦችን አልጠየቃችሁምን? ሊናገሩ የሚችሉትን ማስረጃ አታውቁምን?30ኃጢአተኛው ከመቅሠፍት ቀን እንደ ተጠበቀ፥ ከቍጣው ቀን ዘወር እንደተደረገ።31የሃጥያተኛውን መንገድ ፊት ለፊትl የሚቃወም ማን ነው? በሠራው ስራ የሚቀጣው ማን ነው?32እርሱን ግን ወደ መቃብር ይሸከሙታል፥ ሰዎቹም መቃብሩን ይጠብቃሉ።33የተቀበረበት አፈር እንኳ ይጣፍጥለታል፤ ሰዎች ሁሉ ይከተሉታል፥ እጅግ ብዙ ሕዝብም ከፊቱ ይሄዳል።34መልሳችሁ ከውሸት በቀር ምንም ስለሌለበት፤ በከንቱ ነገር እንዴት ልታጽናኑኝ ትችላላችሁ?
1ቴማናዊውም ኤልፋዝ ሲመልስ እንዲህ አለ፦2ሰው እግዚአብሔርን መጥቀም ይችላልን? ጥበበኛ ቢሆን እንኳ ይጠቅመዋልን?3ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን ለሚችለው አምላክ የሚጨምረው ደስታ አለን? መንገድህ ፍጹም ቀና ቢሆን የሚጠቅመው ነገር አለን?4የሚገስጽህና ወደ ፍርድስ ስፍራ የሚያመጣ፥ እርሱን ስለፈራህ ነውን?5በደልህ እጅግ የበዛ፣ ኃጢአትህም ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?6ያለምክንያት ከወንድሞችህን መያዣን ወስደሃል፥ ሰዎችን ልብሳቸውን ገፈህ እርቃናቸውን አስቀረሃቸው።7ለዛሉም ሰዎች ውኃ አልሰጠሃቸውም፥ ከራብተኛ ሰዎችም እንጀራን ከልክለሃል።8ምድርን የገዛህ ሃያል፤ ክቡር ሰው ብትሆንም።9መበለቶን ባዶአቸውን ሰድደሃቸዋል አባት የሌላቸው ልጆችም ክንድ ተሰብሮአል።10ስለዚህ ወጥመድ በዙሪያህ አለ፥ ድንገተኛ ፍርሃት ያናውጥሃል።11እንዳታይም ጨለማ ሆነብህ፥ የጎርፍ ውሃም አሰጠመህ።12እግዚአብሔር በሰማያት ከፍታ ላይ አይልምን? የዋክብትን ከፍታ ተመልከት ምን ያህል ከፍ ይላሉ!13አንተም፦ 'እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን?14እንዳያየን ጥቅጥቅ ደመና ጋርዶታል፤ በሰማይም ክበብ ላይ ይራመዳል' አልህ።15እነዚያ ኃጢአተኞች የሄዱበትን፥ የቀድሞውን መንገድ አንተ ደግሞ ትደግመዋለህን?16ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም እንደ ወንዝ ፈሳሽ ተወሰደ።17እግዚአብሔርንም፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ ሁሉንም የሚችል አምላክ ምን ሊያደርግልን ይችላል?” አሉት።18ነገር ግን እርሱ ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞላ፤ የኃጥአን ምክር ከእኔ ይራቅ።19ጻድቃን የነዚህን ፍጻሜ ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፤ ንጹሐንም በንቀት እዲህ በማለት ይስቁባቸዋል።20'በእርግጥ በእኛ ላይ የተነሱ ጠፍተዋል፥ ሃብታቸውንም እሳት በልቶታል።'21አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም መንገድ መልካም ነገር ያገኝሃል።22እለምንሃለሁ፥ ከእርሱ አፉ መመሪያ ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤23ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ እንደገና ትሰራለህ፥ ኃጢአትንም ከድንኳንህ አርቀህ ብትጥል፥24የከበረ ሃብትህን በአፈር ውስጥ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥25ሁሉን የሚችል አምላክ የከበረ ሃብትና የተመረጠ ብር ይሆንልሃል።26በዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።27ወደ እርሱ ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፤ ስእለትህንም ለእርሱ ትሰጣለህ።28በማናቸውም ነገር አዋጅ ትናገራለህ፥ እርሱም ይጸናልሃል፤ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።29እግዚአብሔር ትዕቢተኛን ሰው ያዋርዳል፤ ትሑቱንም ሰው ያድነዋል።30ንጹሕ ያልሆነውን ሰው እንኳ፤ በእጅህ ንጽሕና በኩል ይታደገዋል።
1ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦2ዛሬም ቢሆን የኅዘን አቤቱታዬ መራራ ነው፤ መከራዬም ማቃሰት ከምችለው በላይ ይከብዳል።3ኦ! እርሱን ወዴት እንደማገኘው ምነው ባውቅ! እርሱ ወዳለበት ስፍራ በሔድሁ!4ጉዳዬን በፊቱ በተገቢ ሁኔታ ባቀረብሁ፥ አፌንም ለሙግት ሞልቼ አዘጋጅ ነበር።5የሚመልስልኝን ቃሎች አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም በተረዳሁ ነበር።6በኃይሉ ብዛት ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? እንኳን! ያደምጠኝ ነበር።7ጻድቅ ሰው ከእርሱ ጋር በዚያ ይዋቀሳል፤ እንደዚህም በዳኛዬ በእርሱ ለዘላለም ነጻ እወጣ ነበር።8ነገር ግን፥ ወደ ምስራቅ ብሄድ፥ በዚያ የለም፤ ወደ ምዕራብም ብሔድ ላየው አልቻልኩም፤9ወደሚሠራበት ወደ ሰሜን ብሄድ አላየሁትም፤ ራሱን ወደሚሰውርበት በደቡብም፥ላየው አልቻልኩም፤10ነገር ግን የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።11እግሮቼ እርምጃውን በጽናት ተከተሉ፤ ውልፍት ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ።12ከከንፈሩም ትእዛዝ አላፈገፈግሁም፤ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ።13እርሱ ግን በአይነቱ ብቸኛ ነው፤ እርሱንስ ማን ሊመልሰው ይችላል? እርሱ የወደደውን ነገር ያደርጋል።14በእኔ ላይ የተወሰነብኝን ይፈጽማል፤ እንደነዚህም አይነት ብዙ አለ።15ስለዚህ በእርሱ ፊት ደነገጥሁ፤ ስለእርሱም ባሰብሁ ጊዜ እፈራዋለሁ።16እግዚአብሔር ልቤን አድክሞታል፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደንግጦኛል።17እንጂ ጨለማ ወይም ድቅድቁ ጨለማ ፊቴን ከመክደኑ የተነሣ አልጠፋሁም።
1ሁሉን ከሚችል አምላክ ሃጢያተኛ የሚፈረድበት ጊዜ ለምን አልተወሰነም? ለእርሱስ ታማኝ የሆኑት የፍርዱ ቀን እንደመጣ ለምን አያዩም?2የድንበር ምልክትን የሚያፈርሱ ኅጢያተኛ ሰዎች አሉ፤ የሌሎችን መንጋ በግፍ ወስደው የሚያሰማሩ አመጸኞች አሉ።3የድሀ አደጎችን አህያ ቀምተው ይነዳሉ ፤ የመበለቲቱንም በሬ በመያዣ ይወስዳሉ።4ድሆችን ከመንገዳቸው ያስወጣሉ፤ የምድርም ችግረኞች ሁሉ ከእነርሱ ይሸሸጋሉ።5እነዚህ ችግረኞች፥ በምድረ በዳ እንዳሉ የሜዳ አህዮች ወደ ስራቸው ይወጣሉ፥ ምግብን ፍለጋ በጥንቃቄ ይሄዳሉ፤ ምንአልባት ምድረ በዳው ለልጆቻቸው መብልን ይሰጣቸዋል።6ድሆቹም በሌሎች ሰዎች በእርሻ ውስጥ በምሽት ያጭዳሉ፤ ከበደለኞችም መከር ወይንን ይቃርማሉ።7ራቁታቸውን ያለ ልብስ ምሽቱን ሁሉ ይተኛሉ፥ በብርድም ጊዜ መጐናጸፊያ የላቸውም።8ከተራሮች በሚወርድ ዝናብ ይረጥባሉ፤ መጠለያም ስለሌላቸው ከቋጥኝ ስር ይጋደማሉ።9ድሀ አደጉን ህጻን ከእናቱ ጡት የሚነጥሉ ኅጢያተኞች አሉ፤ በደለኞችም ልጆችን በመያዣነት ይወስዳሉ።10ነገር ግን ድሃዎቹ ያለ ልብስ ራቁታቸውን ይሄዳሉ፤ ተርበውም ቢሆን የሌሎችን እህል ነዶ ይሸከማሉ፤11ድሃ ሰዎች በኁጢኣን አጥር ውስጥ ዘይት ይሰራሉ፤ ወይንም ይጠምቃሉ፥ ነገር ግን እነርሱ በጥም ይሰቃያሉ።12በከተማ ውስጥ ሰዎች ያቃስታሉ ፤ የቆሰሉም ለእርዳታ ይጮኻሉ፤ እግዚአብሔር ግን ልመናቸውን አይመለከትም።13እነዚህ ኅጢያተኞች በብርሃን ላይ ያምጻሉ፤ መንገዱን አያውቁም፥ በጎዳናውም አይጸኑም።14ነፍሰ ገዳዩም ማልዶ ይነሣል፤ ችግረኞችንና ድሆችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ነው።15የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል። "የማንም ዓይን አያየኝም" ይላል፥ ፊቱንም እንደሌላ ይለውጣል።16አመጸኞች ቤቶችን በጨለማ ይሰረስራሉ፤ በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ ለብርሃንም ግድ የላቸውም።17ለእነርሱ ጥዋት እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነውና፤ ከድቅድቅ ጨለማ ሽብር ጋርም ተወዳጅተዋል።18ይሁን እንጂ በውኃ ላይ እንዳለ አረፋ በርረው ይጠፋሉ፤ የርስት እድል ፈንታቸውም የተረገመ ነው፤ በወይን ቦታቸውም ላይ ለመስራት ማንም አይሄድም።19ድርቅና ሙቀት በረዶውን እንደሚያቀልጥ፤ እንዲሁ ሲኦል ሃጢያተኞችን ታጠፋለች።20የተሸከመችው ማኅፀን ትረሳዋለች፤ ትልም በደስታ ይበላዋል፤ ዳግመኛም አይታሰብም፤ በዚህ ሁኔታ ዓመጸኝነት እንደ ዛፍ ይሰበራል።21የማትወልደውን መካኒቱን ሃጥያተኛው ይጎዳታል፤ ለመበለቲቱም ምንም አይነት በጎነት አያደርግም።22ነገር ግን እግዚአብሔር በኃይሉ ኃያላንን ጎትቶ ይጥላል፤ እርሱም ይቆማል በሕይወቱ ግን አይጠነክርም።23እግዚአብሔር በደኅንነት እንዳሉ እንዲያስቡ ይፈቅዳል፥ በዚያም ደስ ይላቸዋል፤ ነገር ግን ዓይኖቹ በመንገዳቸው ላይ ናቸው።24እነዚህ ሰዎች ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ በርግጥ ግን፥ ይዋረዳሉ፤ እንደ ሌሎች ሁሉ ተሰብስበው፤ እንደ እሸት ራስ ጫፍ ይቈረጣሉ። 25እንደዚህስ ባይሆን ሐሰተኛ የሚያደርገኝ፥ ንግግሬንም ከንቱ የሚያደርግ ማን ነው?
1ሹሐዊው በልዳዶስ ሲመልስ እንዲህ አለ፦2ገዢነትና መፈራት የእርሱ ናቸው፤ በሰማይ ከፍታውም ስርአትን ያደርጋል።3በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር ፍጻሜ አላቸውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?4እንግዲህ ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ ይሆናል፥ ከሴትስ የተወለደ እንዴት ንጹሕና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋል?5ጨረቃ እንኳ ለእርሱ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።6ይልቁንስ ትል የሆነ ሰው፥ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!
1ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦2ኃይል የሌለውን እንዴት ረዳኸው! ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው!3ጥበብስ የሌለውን እንዴት መከርኸው! መልካም እውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!4እነዚህን ቃሎች በማን እርዳታ ተናገርህ? ስትናገርስ ከአንተ የወጣው መንፈስ የማን ይሆን?5በልዳዶ ስ መለሰ “ሙታን ሰዎች ከውሃዎች በታች የሚኖሩ፥ጥላዎ ቻቸውም ይንቀጠቀጣሉ።6ሲኦል በእግዚአብሔር ፊቱ ራቁትዋን ናት፥ ጥፋትም ቢሆን ራሱን መሸፈኛ የለውም።7ሰሜንን በባዶ ሕዋ ውስጥ ዘረጋው፥ ምድርንም እንዲያው ባዶ ላይ አንጠለጠላት።8ውሃዎችን በደመናዎች ውስጥ ያስራል፥ ደመናውም ከታች አልተቀደደችም።9የጨረቃን ፊት ይጋርዳል፥ ደመናውንም በላይዋ ይዘረጋበታል።10በብርሃንና በጨለማ መካከል እንዳለ መስመር፥ በውሃዎች ላይ ድንበርን አደረገ።11የሰማይ አዕማድ ተንቀጠቀጡ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ደነገጡ።12በኃይሉ ባሕርን ጸጥ አደረገ፥ በማስተዋሉም ረዓብን መታ።13በእስትንፋሱ የሰማያትን ማዕበል ያነጻል፤ ሰማያትም ውበትን አገኙ፥ እጁም በራሪይቱን እባብ ወጋች።14እነዚህም ገና የመንገዱ መጀመሪያ ብቻ ናቸው፤ ከእርሱ የሰማነው ይህ ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉን ነጐድጓድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?
1ኢዮብም መናገሩን ቀጠለ እንዲህም አለ፦2ፍርዴን ያስወገደ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል አምላክን!3ነፍሴ በእኔ ውስጥ፥ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ በአፍንጫዬ እስካለ ድረስ፥4በርግጥ ከንፈሬ ኃጢአትን አይናገርም፥ ምላሴም ሽንገላን አያወራም።5እናንተን ትክክል አድርጎ መቀበል ከእኔ ይራቅ፤ እስክሞት ድረስ ትክክለኛነቴን በፍጹም አልጥልም።6ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ እርሱንም አለቅም፤ ከኖርኩባቸው ቀኖቼ ስለ አንዱም ህሊናዬ አይወቅሰኝም።7ጠላቴ እንደ በደለኛ ሰው ይሁን፥ በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን።8እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በለየ ጊዜ፥ አምላክ የሌለው ሰው ተስፋው ምንድር ነው?9መከራ በመጣበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?10ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?11ስለ እግዚአብሔር እጅ አስተምራችኋለሁ፤ የሁሉን ቻይ አምላክን ሃሳብ አልሸሽግም።12እናንተ ሁላችሁ ይህንን አይታችሁ፤ ለምን ይህን ሁሉ ከንቱ ነገር ተናገራችሁ?13ይህ እግዚአብሔር ለክፉ ሰው ያቆየው እድል ፈንታ፥ ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ የሚቀበለው ርስት ነው፤14ልጆቹ ቢበዙ ለሰይፍ ይዳረጋሉ፤ ዘሩም በቂ እንጀራን አያገኝም።15የተረፉለትም በመቅሰፍት ምክንያት ይቀበራሉ፤ መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።16አመጸኛ ሰው ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ ልብስንም እንደ ሸክላ ቢያከማች፥17እርሱ ያከማቸውን ልብስ፥ ጻድቃን ይለብሱታል፤ ብሩንም ንጹሐን ሰዎች ይከፋፈሉታል።18ቤቱን እንደ ሸረሪት ይሠራል፥ ጠባቂም እንደሚቀልሰው ጎጆ ይመስላል።19ባለጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ነገር ግን አይዘልቅበትም፤ ዓይኑን በከፈተ ጊዜ፥ ሃብቱ ሁሉ የለም።20ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ያገኘዋል፤ ማዕበልም በሌሊት ይወስደዋል።21የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፥ እርሱም ይለቃል፤ ከስፍራውም ይጠርገዋል።22ከነፋሱ ሊያመልጥ ይሞክራል፥ ነገርግን ሳያቋርጥ እየተወረወረ ይደርስበታል።23በመሳለቅም እጁን ያጨበጭብበታል፤ በፉጨትም ከስፍራው ያስወጣዋል።
1በእርግጥ ብር የሚወጣበት፥ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።2ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥ መዳብም ከድንጋይ ቀልጦ ይወጣል።3ሰው የጨለማ መጨረሻ ድረስ ይወርዳል፤ በጨለማና ባስፈሪ ስፍራ ውድ ድንጋይ ይፈላልጋል።4ሰው ከሚኖርበት ርቆ መውረጃ ይቈፍራሉ፤ ከሁሉ እግር በተረሳ ስፍራ፥ ከሰዎችም ሩቅ ሆኖ እየተንጠላጠለ ይወዛወዛል።5ከምድር እንጀራ ቢገኝም፤ ከታችኛው ክፍል ግን እሳት ይገላበጣል።6ድንጋይዋ ሰንፔር የሚገኝበት ስፍራ ነው፥ አፈሯም ወርቅን ይዟል።7ያን መንገድ ጭልፊት አያውቀውም፥ የአሞራም ዓይን አላየውም።8ኲሩ እንስሶች ይህን መንገድ አልሄዱበትም፥ አስፈሪው አንበሳም በዚያ አላለፈም።9ሰው ቡላድ ድንጋይ ላይ እጁን ይጭናል፥ ተራራዎችንም ከሥራቸው ይገለብጣል።10በድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያን ፈልፍሎ ይሰራል፤ በዚያም ዓይኑ የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያል።11ፈሳሹም እንዳያልፉ ይገድባል፤ በዚያም የተሰወሩትን ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል።12ጥበብ ግን የት ትገኛለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?13ሰው ዋጋዋን አላወቀም በሕያዋንም ምድር አትገኝም።14ከምድር ጥልቅ ያለ ውሃ፦ "በእኔ ውስጥ የለችም' አለ፤ ባሕርም፦ "እኔ ጋር የለችም" አለ።15ወርቅ ሊገዛት አይችልም፥ ዋጋዋም በብር አይመዘንም።16በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።17ወርቅና ብርሌ አይተካከሉአትም፥ በነጠረ ወርቅ ጌጥም አትለወጥም።18ዛጐልና አልማዝ ከቁጥር አይገቡም። በርግጥ የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይበልጣል።19የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይስተካከላትም፥ በንጹህ ወርቅም አትገመትም።20ታዲያ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ የት ነው?21ጥበብ ሕይወት ካላቸው ነገሮች ሁሉ ዓይን ተሰውራለች፥ ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች።22ጥፋትና ሞት፦ “ወሬዋን ብቻ በጆሮቻችን ሰምተናል” አሉ።23እግዚአብሔር ወደ እርሷ የሚወስደውን መንገድ ያስተውላል፥ስፍራዋንም ያውቃል።24ምክንያቱም እርሱ የምድርን ዳርቻ፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።25እርሱ አስቀድሞ ለነፋስ ሃይል መጠንን አደረገ፥ ውኆችንም በስፍር ሰፈረ፥26እርሱ ለዝናብ ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን አደረገ፥27በዚያን ጊዜ ጥበብን አያት፥ ገለጣትም አጸናት፥ በርግጥም መረመራት።28ለሰዎችም፦ እነሆ፥ “እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው” አለ።
1ኢዮብም መናገሩን ቀጠለ፥ እንዲህም አለ፦2እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንደ ነበረው ጊዜ፥ እንዳለፉት ወራት ምነው በሆንሁ!3መብራቱ በራሴ ላይ እንደበራበት ወቅት፥ በጨለማ ውስጥ በብርሃኑ አልፌ እንደሄድሁበት ጊዜ፥4ቀኖቼ ወደ ሙላታቸው በደረሱ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር ወዳጅነት በድንኳኔ በነበረ ጊዜ፥5ሁሉን የሚችል አምላክ ገና ከእኔ ጋር በነበረ ጊዜ፥ ልጆቼም በዙሪያዬ እያሉ፥6መንገዴ በቅቤ ይታጠብ በነበረ ጊዜ፥ ድንጋዩ የዘይት ፈሳሽ ያፈስስልኝ በነበረ ጊዜ።7ወደ ከተማው በር በወጣሁ ጊዜ፥ በአደባባዩ መሃል ወንበሬ ላይ በተቀመጥሁ ጊዜ፥8ወጣቶች አይተው በአክብሮት ገለል አሉ፥ ሽማግሌዎችም ተነሥተው ቆሙ።9በመጣሁ ጊዜ ልኡላን ከመናገር ይቆጠባሉ፥ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር።10የብልሆች ድምፅ ጸጥ ይል፤ ምላሳቸውም በላንቃቸው ተጣበቀች።11በጆሮአቸው ከሰሙኝ በኋላ ይባርኩኝ ነበር፥` በአይናቸው ዓይተው ያሞግሱኝና ይመሰክሩልኝ ነበር፤12ምክንያቱም የሚጮኸውን ችግረኛ፥ ድሀ አደጉንና ረዳት የሌላቸውን አድን ነበረና።13ሊጠፋ የቀረበ በረከት ወደ እኔ ይመጣል፤ ባል የሞተባትንም ሴት ልብ በደስታ እንድትዘምር አደርግ ነበርና።14ጽድቅን ለበስሁ እርስዋም ለበሰችኝ፤ ፍትሃዊነቴም እንደ መጐናጸፊያዬና ጥምጣሜ ነበረ።15ለአይነ ስውራን ዓይናቸው፥ መራመድ ለማይችሉም ሰዎች እግር ነበርሁ።16ለችግረኞች አባት ነበርሁ፤ የማላውቀውንም ሰው ሙግት እመረምር ነበር።17የኃጢአተኛውን መንጋጋ ሰበርሁ፥ የያዘውንም ከጥርሱ ውስጥ አስጣልሁ።18እንዲህም አልሁ፦ “በጎጆዬ ሆኜ እሞታለሁ፥ ቀኖቼን እንደ አሸዋ አበዛለሁ፤19ሥሮቼ ወደ ውኃ ይሰራጫሉ፥ ጠልም ምሽቱን ሁሉ በቅርንጫፎቼ ላይ ያድራል፤20በእኔ ዘንድ ያለው ክብር ሁልጊዜ ትኩስ ነው፥ በእጄ ያለው የብርታቴ ቀስት አዲስ ነው።21ሰዎች እኔን ለመስማት በትዕግሥት ተጠባበቁ፥ ምክሬንም ለማዳመጥ በጸጥታ ተቀመጡ።22ንግግሬንም ከጨረስኩ በኋላ መልሰው አልተናገሩም፤ ቃሎቼም በላያቸው እንደ ውሃ ተንጠባጠበ።23ዝናብን እንደሚጠብቁ ሁልጊዜ ይጠብቁኛል፤ የበልግ ዝናብን እንደሚሹት፥ ከቃሎቼ ለመጠጣት አፋቸውን ከፈቱ ።24እነርሱ ባልጠበቁተ ጊዜ ሳቅሁላቸው፤ የፊቴንም ብርሃን ቸል አላሉትም።25መንገድን እመርጥላቸውና አለቃቸው ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ኅዘነተኞችን በቀብር ጊዜ እንደሚያጽናና ሰው፥ በሠራዊቱም መካከል እንዳለ ንጉሥ በመካከላቸው ኖርሁ።
1አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ጠባቂ ውሾች ጎን እንዳይሰሩ ልከለክላቸው የምችል የነበሩ እነዚህ ወጣቶች፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ።2በርግጥ የአባቶቻቸው ክንድ ጥንካሬ ምን ሊፈይድልኝ ይችል ነበር? የጉልምስናቸው ጥንካሬ ጠፍቶባቸው ነበርና።3በድህነትና በራብ የመነመኑ ናቸው፤ በደረቅ መሬት በምድረ በዳ ጨለማና ጥፋት ይሰቃያሉ።4ከቍጥቋጦ አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚሉትን ቅጠሎች ይለቅማሉ፤ የክትክታ ሥራሥር ምግባቸው ነበር።5ሌባን እየተከታተሉ እንደሚጮኹበት፤ ከሚጮኹባቸው ሰዎች ተለይተው ተሰደዱ።6በወንዝ ሸለቆ በምድር ጕድጓድና በድንጋይም ዋሻ ውስጥ ይኖራሩ ነበር።7በቍጥቋጦ መካከል እንደ አህያ ይጮኻሉ፤ ከቁጥቋጦ በታች በጋራ ተሰብስበዋል።8በርግጥ የሰነፎችና ዋጋ የሌላቸው ሰዎች ልጆች ናቸው፤ እየተገረፉ ከምድሪቱ ተባረዋል።9አሁን ግን ለልጆቻቸው የስላቅ ዘፈን ሆንኩላቸው፤ በርግጥም የነሱ መቀለጃ ሆኛለሁ።10ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ርቀው ይቆማሉ፤ ፊቴም ላይ መትፋትን አያቆሙም።11እግዚአብሔር የቀስቴን መወጠሪያ አላልቶብኛል፥ መከራም አሳይቶኛል፤ እነርሱም በፊቴ ይሉኝታ የላቸውም።12በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥ ያሳድዱኛል፤ ለእግሬም የጥፋትን ወጥመድ ያደርጋሉ።13መንገዴን ያበላሻሉ፤ ከልካይ እንደሌላቸው ሰዎች ጥፋትን ገፍተው ያመጡብኛል።14በሰፊ ፍራሽ ቀዳዳ እንደሚመጣ ሰራዊት ይመጡብኛል፤ በጥፋት ላይ ተንከባልለው መጡብኝ።15ድንጋጤ በላዬ መጥቶብኛል፥ ክብሬም በነፋስ ያሳደዱት ያክል በነነ፤ ብልጥግናዬም እንደ ደመና ተበተፈ።16አሁንም ነፍሴ በውስጤ ፈሰሰች፤ የብዙ ቀናት መከራም ያዘኝ።17በሌሊት አጥንቶቼ በውስጤ ተወጉ፥ የሚያሰቃየኝ ህመም ፋታ አይሰጠኝም።18ከእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል የተነሣ ልብሴ ተያዘ፥ እንደ ቀሚስ መቀነት ተጠቀለለብኝ።19እርሱ ጭቃ ውስጥ ወረወረኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ።20ወደ አንተ ጮኽሁ እግዚአብሔር፥ አንተም አልመለስህልኝም ቆምሁኝ፥ አልተመለከትኸኝም።21ተለወጥህብኝ ፤ ጨካኝም ሆንህብኝ፤ በእጅህም ሃይል አሳደድኸኝ።22በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስቀምጠኸ ወሰድኸኝም፤ በማእበልም ውስጥ አቀለጥኸኝ።23ለሕያዋን ሁሉ ወደተወሰነው ቤት፤ ወደ ሞት እንደምትወስደኝ አውቄአለሁ።24ነገር ግን ሰው ሲወድቅ እጁን እርዳታ ፍለጋ አይዘረጋምን? በችግር ውስጥ ያለ ማንም ለእርዳታ አይጮኽምን?25በችግር ላለ ሰው አላለቀስሁምን? ለድሆችስ ነፍሴ አላዘነችምን?26መልካምን በተጠባበቅሁ ጊዜ ክፉ መጣብኝ፤ ብርሃንን ስጠባበቅ፥ ጨለማ መጣ።27ልቤ ታወከ፥ እረፍትም አላገኘም የስቃይም ቀናቶች መጡብኝ።28ያለ ፀሐይ በጨለመ ሰማይ በትካዜ ሄድሁ፤ በጉባኤም መካከል ቆሜ ለእርዳታ እጮኻለሁ።29ለቀበሮ ወንድም፥ ለሰጐንም ጓደኛ ሆንሁ።30ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከላዬም ተቀርፎ ወደቀ፤ አጥንቶቼም በትኵሳት ተቃጠሉ።31ስለዚህ በገናዬ ለኀዘን እንጉርጉሮ ፥ እምቢልታዬም ለለቅሶ ጩኸት ተቃኙ።
1ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ስለገባሁ፤ እንዴት ድንግሊቱን በምኞት እመለከታለሁ?2ከላይ ከእግዚአብሔር የሆነው እድል ፈንታ ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክስ ርስት ከአርያም ምንድን ነው?3መዓት ለኃጢአተኛ፥ ጥፋትም ክፋትን ለሚያደርጉ ነው ብዬ አስብ ነበር።4እግዚአብሔር መንገዴን አያይምን? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?5በሐሰት ሄጄ እንደ ሆነ እግሬም ለሽንገላ ቸኵሎ እንደ ሆነ፥6በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ትክክለኛቴን ይወቅ።7እርምጃዬ ከትክክለኛው መንገድ ፈቀቅ ብሎ፥ ልቤም የዓይኔን ምኞት ተከትሎ፥ ነውርም በእጄ ላይ ተጣብቆ እንደ ሆነ፥8እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብላው፤ መከሩም ከእርሻዬ ላይ ይነቀል።9ልቤ ወደ ሌላይቱ ሴት ጐምጅቶ እንደ ሆነ፥ የጎረቤቴን ሚስት ለማየት ደጃፉ አድብቼ እንደ ሆነ፥10ሚስቴ ለሌላ ሰው እህል ታዘጋጅ፥ ሌሎችም ከእርስዋ ጋር ይተኙ።11ይህ ክፉ ወንጀል ነውና፥ በፈራጆችም ሊቀጣ የሚገባው በደል ነውና፤12ይህ እስከ ሲኦል ድረስ የሚበላ እሳት፥ ያመረትኩትን ሁሉ የሚያቃጥል ነውና።13ወንድ ወይም ሴት ባሪያዎቼ ከእኔ ጋር በተምዋገቱ ጊዜ፥ ሙግታቸውን በትክክል ሳላይ ቀርቼ እንደ ሆነ፥14እግዚአብሔር ሊከሰኝ በተነሣ ጊዜ ምን አደርጋለሁ? ሊፈርደኝም በመጣ ጊዜ እንዴት እመልስለታለሁ?15እኔን በማኅፀን የሰራኝ እነርሱንስ የፈጠረ አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ ሁላችንን የሠራን አንድ አይደለምን?16ድሀዎችን ከፍላጎታቸው ከልክዬ፥ የመበለቲቱንም ዓይን በለቅሶ አጨልሜ እንደ ሆነ፥17እንጀራዬን ለብቻዬ በልቼ እንደ ሆነ፥ አባት የሌላቸውንም ከእርሱ እንዳይበሉ ከልክዬ እንደ ሆነ፤18ይልቁን እርሱ ከታናሽነቴ ጀምሬ እንደ አባቱ ሆኜ ከእኔ ጋር አሳድጌው ነበር፥ እናቱንም ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ መራኋት፤19አንድ ሰው የሚለብሰው አጥቶ ሲጠፋ፥ ወይም ድሀ ያለ ልብስ ሲሆን እንዲያው አይቼ እንደ ሆነ፥20በበጎቼም ጠጕር ያልሞቀና፥ በልቡ ያልባረከኝ እንደ ሆነ፤21በከተማው በር ረዳት ስላለኝ፥ አባት በሌላቸው ላይ እጄን አንሥቼ እንደ ሆነ፥22ትከሻዬ ከመጋጠሚያው ይውደቅ፥ ክንዴም ከመገናኛው ይሰበር።23ከእግዚአብሔር የሆነ ቁጣ ለእኔ አስደንጋጭ ነውና ከግርማውም የተነሳ እነዚህን ነገሮች ማድረግ አልችልም።24ወርቅን ተስፋዬ አድርጌ፥ ጥሩውንም ወርቅ”በአንተ እታመናለሁ“ ብዬ እንደ ሆነ፤25ሀብቴ ስለ በዛ፥ እጄም ብዙ ስላከማቸ ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፤26ፀሐይ ሲበራ ተመልክቼ፥ ጨረቃ በድምቀት ስትሄድ አይቼ፥27ልቤ እነርሱን ለማምለክ በስውር ተስቦ፥ አፌም እጄን ስሞ እንደ ሆነ፤28በላይ ያለውን እግዚአብሔርን መካድ ነውና ይህም ዳኞች ሊቀጡት የሚገባ ወንጀል በሆነ ነበር።29በሚጠላኝ በማንም መጥፋት ደስ ብሎኝ ወይም ክፉ ነገር በሆነበት ጊዜ ራሴን አስደስቼው እንደ ሆነ፤30ለነፍሱ እርግማንን በመናገር፥ አንደበቴ ኃጢአት እንዲሰራ በርግጥ አልፈቀድኩለትም፤31በድንኳኔ የሚኖሩ ሰዎች፦ “ከኢዪብ ማዕድ ያልጠገበ ማን ይገኛል?” ብለው ካልተናገሩ፤32መጻተኛው በከተማ ጎዳና እንዳያድርም፥ ሁልጊዜ ደጄን ለመንገደኛ እከፍት ነበር፤33በደሌንም በብብቴ በመሸሸግ ኃጢአቴን እንደ ሰዉ ሁሉ ደብቄ እንደ ሆነ፤34የሕዝብን ብዛት ከመፍራቴ የተነሳ፥ የዘመዶቼም ንቀት አስደንግጦኝ፥ ዝም ብዬ ከቤቴ ሳልወጣ ቀርቼ እንደ ሆነ፤35ኦ የሚያዳምጠኝ አንድ ሰው ምነው በኖረኝ! ይኸው የእጄ ፊርማ ምልክት፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ! ባላጋራዬ የጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!36በግልጽ ትከሻዬ ላይ አድርጌ እሸከመው ነበር፥ እንደ አክሊልም ራሴ ላይ አስቀምጠው ነበር።37የእርምጃዎቼን ቍጥር በግልጽ አስታውቀው፥ እንደ ተማመነ አለቃም ፊትለፊቱ እወጣ ነበር።38የእርሻዬ መሬት በእኔ ላይ ጮሆ እንደ ሆነ፥ ትልሞቹም አብረው አልቅሰው እንደ ሆነ፤39የምርቱን ዋጋ ሳልከፍል በልቼ፥ የባለቤቶቹንም ነፍስ አሳዝኜ እንደ ሆነ፥40በስንዴ ፋንታ እሾኸ፥ በገብስም ፋንታ አረም ይብቀልበት።“ የኢዮብም ንግግር ተፈጸመ።
1ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ስላስቀመጠ እነዚያ ሦስቱ ሰዎች ምላሽ መስጠት አለብህ።2ከራም ቤተሰብ የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እጅግ ተቆጣ፤ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ስላጸደቀ ኢዮብን ተቈጣው።3ደግሞም በኢዮብ ፈረዱበት እንጂ የሚገባ መልስ ስላልሰጡት በሦስቱ ጓደኞቹ ላይ ተቈጣ።4ከእርሱ ይልቅ ሰዎቹ ሽማግሌዎች ስለነበሩ ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር ለመነጋገር ተራውን ይጠብቅ ነበር።5ቢሆንም ግን ኤሊሁም በእነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ሲያይ በጣም ተቆጣ።6ቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ መናገር ሲጀምር እንዲህም አለ፦ እኔ በዕድሜ ወጣት ነኝ፥ እናንተም ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ሰጋሁ፤ እውቀቴን እንዳልናገር ራሴን ገታሁ።7እንደዚህም አልሁ፦ የቀናት ርዝመት ንግግርን፥ የዓመታትም ብዛት ጥበብን ሊያስተማሩ ይገባ ነበር።8ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፤ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጠዋል። 9ታላላቅ ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ጥበበኞች አይደሉም፣ በእድሜ የገፉ ስለሆኑ ብቻም ፍትሕን አያስተውሉም። 10ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፥ 'አድምጡኝ፤ እኔም ደግሞ የማውቀውን እነግራችኋለሁ'።11ተመልከቱ፥ እስክትናገሩ ጠበቅኋችሁ፥ ምን መናገር እንዳለባችሁ በማሰብ ላይ እያላችሁም ክርክራችሁን አዳመጥኩኝ። 12በርግጥ ትኩረቴን ሰጠዃችሁ፥ ነገር ግን፥ ተመልከቱ፥ አንዳችሁም ኢዮብን ማስረዳት ወይም ለቃሎቹ ምላሽ መስጠት አልቻላችሁም።13'ጥበብን አግኝተናል!' እንዳትሉ ተጠንቀቁ ኢዮብን ማሸነፍ ያለበት እግዚአብሔር ነው፤ ተራ ሰው ይህንን ለማድረግ አይችልም። 14ኢዮብ እኔን በመቃወም አልተናገረምና እኔም የእናንተን በሚመስል ቃል አልመልስለትም።15እነዚህ ሦስት ሰዎች ዲዳ ሆነዋል፤ ከዚህ በኋላ ለኢዮብ ሊመልሱለት አይችሉም፤ ቀጥለው የሚናገሩት አንድም ቃል የላቸውም። 16እዚያ በዝምታ ስለቆሙና ከእንግዲህ ስለማይመልሱ፥ ስለማይናገሩም፥ መጠበቅ አለብኝ?17አይሆንም፥ እኔም ደግሞ የበኩሌን እመልሳለሁ፤ እኔም ደግሞ ዕውቀቴን እነግራቸዋለሁ። ቃል 18ተሞልቻለሁና፤ በውስጤ ያለው መንፈስም ይገፋፋኛል። 19ተመልከቱ፥ ውስጤ ተከድኖ እንደሚብላላ ወይን ነው፤ ሊፈነዳ እንደተቃረበ አዲስ የወይን ጠጅ አቁማዳም ነው።20አርፍ ዘንድ እናገራለሁ፤ አፌንም ከፍቼ መልስ እሰጣለሁ። 21አድልዎ አላደርግም፤ የትኛውንም ሰው አላቆላምጥም። 22እንዴት እንደማቆላምጥ አላውቅምና፤ እንዲህ ባደርግ ኖሮ ፈጣሪዬ ፈጥኖ ያስወግደኝ ነበር።
1አሁንም ኢዮብ ሆይ፥ ቃሎቼን እንድትሰማ፥ ንግግሬንም እንድታደምጥ እለምንሃለሁ። 2ይኸው አሁን አፌን ከፍቻለሁ፤ ምላሴም በአፌ ውስጥ ተናግሯል። 3ቃሎቼ የልቤን ቅንነት ይናገራሉ፤ ከንፈሮቼ የሚያውቁትን በታማኝነት ይናገራሉ።4የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፤ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ። 5ከቻልክ መልስልኝ፤ በፊቴም ቃሎችህን በቅደም ተከተል አዘጋጅና ቁም።6ተመልከት፥ በእግዚአብሔር ፊት አንተ እንደሆንከው እንዲሁም እኔም ነኝ፤ እኔም ደግሞ ከጭቃ ተሠርቻለሁ። 7ተመልከት፥ ማስፈራራቴ አያስፈራህም፤ ተጽዕኖዬም ቢሆን አይከብድብህም።8በእርግጥ በጆሮዬ ተናግረሃል፤ እንዲህ የሚለውንም የቃልህን ድምፅ ሰምቻለሁ፥ 9ንጹሕ ነኝ መተላለፍም የለብኝም፤ አልበደልኩም፥ ኃጢአትም የለብኝም።10ይኸው፥ እግዚአብሔር ሊያጠቃኝ አጋጣሚ ይፈልጋል፤ እንደ ጠላቱ አድርጎ ይቆጥረኛል። 11እግሮቼን በግንድ ውስጥ ያስገባቸዋል፤ መንገዶቼንም ሁሉ ይመለከታል። 12እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣልና እንደዚህ መናገርህ ትክክል አይደለም ብዬ እመልስልሃለሁ።13ለየትኛውም ሥራው ትኩረት አይሰጠውም በማለት ከእርሱ ጋር ለምን ትታገላለህ? 14ሰው ባያስተውለውም እግዚአብሔር አንድ ጊዜ፥ አዎን፥ ሁለት ጊዜ ይናገራል። 15ሰዎች አልጋቸው ላይ ተኝተው ከባድ እንቅልፍ በሚወድቅባቸው ጊዜ በህልም፥ በሌሊት ራዕይ ይናገራቸዋል።16በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የሰዎችን ጆሮ ይከፍትና በማስጠንቀቂያው ያስፈራራቸዋል፤ 17ይህንን የሚያደርገውም ሰውን ከኃጢአታዊ ዓላማው ሊመልሰውና ከትዕቢት ሊጠብቀው ነው። 18እግዚአብሔር የሰውን ሕይወት ከጉድጓድ ይጠብቃል፥ ሕይወቱንም ወደ ሞት ከመውረድ።19ደግሞም ሰው በአልጋው ላይ በሕመም ይቀጣል፥ በአጥንቶቹም ውስጥ በማያቋርጥ ስቃይ፤ 20ሕይወቱ ምግብን፥ ነፍሱም ጣፋጩን መብል እስክትጠላ ድረስ።21ሥጋው ሊታይ እስከማይችል ድረስ ጠፍቷል፥ የማይታዩ የነበሩት አጥንቶቹም አሁን ገጠው ወጥተዋል። 22በርግጥ ነፍሱ ወደ ጉድጓድ ቀርባለች፥ ሕይወቱም ሊያጠፏት ወደሚፈልጉት።23ነገር ግን መካከለኛ ሊሆንለት የሚችል አንድ መልአክ ቢኖር፥ የትኛውን መልካም ነገር ማድረግ እንዳለበት የሚያሳየው፥ መካከለኛ የሚሆንለት ከሺህ መላእክት አንድ ቢገኝለት፥ 24መልአኩም ለእርሱ ደግ ቢሆንና እግዚአብሔርን፥ 'ቤዛ የሚሆንለት አግኝቻለሁና ይህንን ሰው ወደ ጉድጓድ ከመውረድ አድነው' ቢለው25በዚያን ጊዜ ሥጋው ከሕፃን ገላ ይልቅ ይታደሳል፤ ወደ ወጣትነት የብርታቱ ዘመንም ይመለሳል። 26እርሱ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እግዚአብሔርም ይራራለታል፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ፊት በደስታ ያያል። እግዚአብሔርም ለሰውየው ድልን ይሰጠዋል።27ከዚያም ያ ሰው በሌሎች ሰዎች ፊት እንዲህ ሲል ይዘምራል፥ 'ኃጢአትን ሠርቻለሁ፥ ትክክለኛ የሆነውንም አጣምሜአለሁ፥ ይሁን እንጂ ስለኃጢአቴ አልተቀጣሁም። 28እግዚአብሔር ነፍሴን ወደ ጉድጓድ ከመውረድ አዳናት፤ ሕይወቴም ብርሃን ማየቷን ትቀጥላለች"።29ተመልከቱ፥ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ሁሉ በሰው ሕይወት ሁለት ጊዜ፥ አዎን፥ እንዲያውም ሦስት ጊዜ ያደርጋቸዋል፤ 30ይኸውም የሕይወት ብርሃን ይበራለት ዘንድ ነፍሱን ከጉድጓድ ለመመለስ ነው።31ኢዮብ ሆይ አስተውለህ ስማኝ፤ ዝም በል፥ እኔም እናገራለሁ። 32የምትናገረው ነገር ካለህ መልስልኝ፤ ትክክለኛ መሆንህን ለማረጋገጥ እፈልጋለሁና ተናገር። 33ካልሆነ ግን ጸጥ ብለህ ስማኝ፤ እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ“።
1ኤሊሁም በመቀጠል እንዲህ አለ፥ 2”እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሎቼን አድምጡ፤ እውቀት ያላችሁ እናንተ ስሙኝ። 3ምላስ ምግብን እንደሚያጣጥም ጆሮም ቃላትን ያመዛዝናል።4ትክክለኛ የሆነውን ለራሳችን እንምረጥ፤ መልካም የሆነውንም በመካከላችን እንፈልገው። 5ኢዮብ 'እኔ ጻድቅ ነኝ እግዚአብሔር ግን መብቴን ነፍጎኛል። መብት ቢኖረኝም እንደ ሐሰተኛ ተቆጥሬአለሁ። 6ምንም እንኳን ኃጢአት ባይኖርብኝም ቁስሌ የማይፈወስ ነው' ብሏልና።7ስድብን እንደ ውሃ የሚጠጣ፥ 8ክፋትን ከሚያደርጉት ጋር እንደሚወዳጅ፥ ከአመጸኞችም ጋር እንደሚመላለስ እንደ ኢዮብ ያለ ማነው? 9እርሱ፥ 'ሰው እግዚአብሔር የሚፈልገውን በማድረግ መደሰቱ ምንም አይጠቅምም' ብሏልና።10ስለዚህ እናንተ አዋቂዎች ስሙኝ፤ አመጻን ማድረግ ከእግዚአብሔር ይራቅ፤ ኃጢአትን ማድረግም ሁሉን ቻይ ከሆነው ይራቅ። 11ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋልና፤ እያንዳንዱም በየራሱ መንገድ ወደ ብድራቱ እንዲመጣ ያደርገዋል። 12በእርግጥ እግዚአብሔር አንዳችም አመጻን አያደርግም፥ ደግሞም ሁሉን ቻዩ ከቶም ፍትሕን አያዛባም።13በምድር ላይ እርሱን ፈራጅ ያደረገው ማነው? ዓለሙንስ በሙሉ ከእርሱ በታች ያደረገው ማነው? 14እርሱ ፍላጎቱን በራሱ ላይ ብቻ ቢያደርግና መንፈሱንና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢመልስ ኖሮ 15ያን ጊዜ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በጠፋ፥ ሰውም እንደገና ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር።16አሁን እንግዲህ ማስተዋል ካለህ ይህንን ስማ፤ የቃሌንም ድምፅ አድምጥ። 17ፍትሕን የሚጠላ ማስተዳደር ይችላል? ጻድቅና ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ትኮንነዋለህ?18እግዚአብሔር ንጉሡን፥ 'በደለኛ ነህ' ወይም ባለስልጣኖችን፥ 'አመጸኞች ናችሁ' አይልምን? 19እግዚአብሔር ለመሪዎች አያዳላም፤ ባለጸጋዎችንም ከድኾች አስበልጦ አይመለከታቸውም፤ ሁሉም የእጁ ሥራዎች ናቸውና። 20በቅጽበት ይሞታሉ፤ እኩለ ሌሊት ላይ ሰዎች ይንቀጠቀጣሉ፥ ይሞታሉም፤ ኃያላን ሰዎች ይወሰዳሉ፥ በሰው እጅ ግን አይደለም።21የእግዚአብሔር ዐይኖች በሰው አካሄድ ላይ ናቸው፤ እርምጃዎቹንም ሁሉ ያያቸዋል። 22ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት ጨለማ ወይም ድቅድቅ ጭጋግ የለም። 23እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ሰውን መመርመር አይፈልግም፥ የትኛውም ሰው በእርሱ ፊት ቆሞ መሟገት አያስፈልገውም።24ስለ አካሄዳቸው ተጨማሪ ምርመራ እንዳያስፈልጋቸው ኃያላኑን ሰዎች ይሰባብራቸዋል፤ በስፍራቸውም ሌሎችን ይሾማል። 25እንዲህ ባለ መንገድ ሥራቸውን ያውቃል፤ እነዚህን ሰዎች በጨለማ ይጥላቸዋል፤ እነርሱም ይጠፋሉ።26በሌሎች ፊት፥ በአደባባይ ስለ ክፉ ሥራቸው እንደ ወንጀለኛ ይገድላቸዋል፥ 27እርሱን ከመከተል ተመልሰዋልና፥ ከመንገዶቹም የትኛውንም ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑምና። 28እንዲህ ባለ መንገድ የድኾች ጩኸት በፊቱ እንዲወጣ አደረጉ፤ እርሱም የተጨነቁትን ሰዎች ጩኸት ሰማ።29በዝምታ በሚቆይበት ጊዜ ማን ሊወቅሰው ይችላል? ፊቱንስ ቢሰውር ማን ሊገነዘበው ይችላል? 30አመጸኛው ሰው ገዢ እንዳይሆን፥ በሕዝቡም ላይ ወጥመድን የሚያደርግ እንዳይገኝ እርሱ በሀገሮችና በግለሰቦች ላይ ይገዛል።31አንድ ሰው እግዚአብሔርን እንዲህ እንደሚለው ገምቱ፥ 'በርግጥ በድያለሁ፥ 32ከዚህ በኋላ ግን ከቶ ኃጢአትን አላደርግም፤ ላየው የማልችለውን አስተምረኝ፤ ኃጢአትን ሠርቻለሁ፥ ከእንግዲህ ግን አላደርግም'። 33እግዚአብሔር የሚያደርገውን የምትጠላ ሰው ብትሆንም፥ እግዚአብሔር የዚያን ሰው ኃጢአት የሚቀጣ ይመስልሃል? እኔ ሳልሆን አንተው መምረጥ አለብህ። ስለዚህ ትክክል ነው ብለህ የምታውቀውን ተናገር።34ዐዋቂዎች ሰዎችም እንዲህ ይሉኛል፥ በእርግጥ የሚሰማኝ ጥበበኛ ሰው ሁሉ የሚለው እንዲህ ነው፥ 35'ኢዮብ የሚናገረው የማያውቀውን ነው፤ ቃሎቹም ጥበብ የለባቸውም'።36እንደ አመጸኞች ሰዎች ተናግሯልና ምነው ኢዮብ ብቻውን ከጉዳዮቹ ስለ ጥቂቶቹ በዝርዝር በተመረመረ። 37በኃጢአቱ ላይ አመጽን ጨምሯልና፤ በመካከላችን እጆቹን እያጨበጨበ ተሳድቧልና፤ እግዚአብሔርን በመቃወምም ብዙ ቃል ተናግሯል።"
1ኤሊሁ እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፥ 2“ንጹሕ ነኝ ብለህ ታስባለህ? 'ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ነኝ' ብለህስ ታስባለህ? 3ጻድቅ መሆኔ ምን ይጠቅማል? ኃጢአት አድርጌ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የሚበልጥ ምን ያገኘኝ ነበር?' ብለሃልና።4ለአንተና ለወዳጆችህ ምላሽ እሰጣለሁ። 5ወደ ሰማይ ቀና በሉና ተመልከቱት፤ ከእናንተ ከፍ የሚለውን ሰማይ ተመልከቱ።6ኃጢአትን ብታደርግ እግዚአብሔርን ምን ትጎዳዋለህ? መተላለፍህ እጅግ የበዛ ቢሆን ለእርሱ ምኑ ነው? 7ጻድቅ ብትሆንስ ምን ልትሰጠው ትችላለህ? ከእጅህስ ምን ይቀበላል? 8አንተም ሰው ነህና ክፋትህ ሌላውን ይጎዳ ይሆናል፤ ጽድቅህም ሌላውን የሰው ልጅ ይጠቅመው ይሆናል።9በብዙ በደል ምክንያት ሰዎች ይጮኻሉ፤ ከኃያላኑ እጅ የሚያድናቸውን ፍለጋ ይጣራሉ። 10ነገር ግን 'በሌሊት ዝማሬን የሚሰጥ፥ 11የምድር አራዊትን ከሚያስተምርበት በበለጠ የሚያስተምረን፥ ከሰማይ አዕዋፍም ይልቅ ጥበበኞች የሚያደርገን ፈጣሪያችን እግዚአብሔር የት አለ?' ማንም አላለም።12በዚያን ጊዜ ይጮኻሉ፥ ነገር ግን በክፉ ሰዎች ትዕቢት ምክንያት እግዚአብሔር ምንም ምላሽ አይሰጣቸውም። 13ያለጥርጥር እግዚአብሔር የሞኞችን ጩኸት አይሰማም፤ ሁሉን ቻዩም ትኩረት አይሰጠውም። 14ጉዳይህን በፊቱ አቅርበህ እየተጠባበቅኸው እያለህ እንዳላየኸው ከተናገርክ እንዴት አድርጎ መልስ ይሰጥሃል!15ማንንም ተቆጥቶ አይቀጣም፥ በሰዎች ትዕቢት እምብዛም ግድ አይለውም ካልክ እንዴት አድርጎ መልስ ይሰጥሃል? 16ስለዚህ ኢዮብ አፉን የሚከፍተው ስንፍናን ለመናገር ብቻ ነው፤ ዕውቀት የሌለበትን ቃል መናገርንም ያበዛል"።
1ኤሊሁ እንዲህ በማለት ንግግሩን ቀጠለ፥ 2"ትንሽ ጨምሬ እንድናገር ፍቀድልኝ፥ እግዚአብሔርን በመወገን ትንሽ አክዬ የምናገረው አለኝና ጥቂት ነገሮችን አሳይሃለሁ። 3ዕውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፤ ጽድቅ የፈጣሪዬ ነው እላለሁ።4በርግጥ ቃሎቼ ሐሰት አይደሉም፤ አንድ በዕውቀት የበሰለም ከአንተ ጋር ነው። 5ተመልከት፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፤ እርሱ በማስተዋል ብርታቱም ኃያል ነው።6እርሱ የአመጸኞች ሰዎችን ሕይወት አይጠብቅም ነገር ግን ከዚያ ይልቅ መከራ ለሚቀበሉት ትክክል የሆነውን ነገር ያደርግላቸዋል። 7ፊቱን ከጻድቃን አይመልስም ነገር ግን ከዚያ ይልቅ እንደ ነገሥታት በዙፋኖች ላይ ያስቀምጣቸዋል፥ እነርሱም ይከብራሉ።8ይሁንና፥ በሰንሰለት ቢገቡ፥ በመከራም ገመድ ቢታሰሩ 9ያን ጊዜ ያደረጉትን መተላለፋቸውንና በግፍ እንደተመላለሱ ይገልጥላቸዋል።10ደግሞም እርሱ ጆሮዎቻቸውን ለትምህርቱ ይከፍታቸዋል፥ ከክፋታቸው እንዲመለሱም ያዛቸዋል። 11ቢሰሙትና ቢያመልኩት ቀኖቻቸውን በብልጽግና ዓመቶቻቸውንም በእርካታ ያሳልፋሉ። 12ይሁን እንጂ፥ ባይሰሙት በሰይፍ ይጠፋሉ፤ ዕውቀት ስለሌላቸው ይሞታሉ።13ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ እነዚያ ቁጣቸውን ያከማቻሉ፤ እግዚአብሔር በሚያስራቸው ጊዜ እንኳን ለዕርዳታ አይጮኹም። 14በወጣትነታቸው ይሞታሉ፤ ሕይወታቸውም በቤተ ጣዖት ዝሙት አዳሪዎች መካከል ይጠፋል።15የሚሰቃዩትን ሰዎች በስቃያቸው አማካይነት ያድናቸዋል፤ በመከራቸው አማካይነትም ጆሮዎቻቸውን ይከፍታል። 16በእርግጥ እርሱ ከጭንቀት አውጥቶ የሰባ ምግብ የሞላበት ጠረጴዛ በፊትህ ወደሚቀመጥበትና ስቃይ ወደሌለበት ሰፊ ስፍራ ሊያወጣህ ይፈልጋል።17ነገር ግን አንተ በክፉ ሰዎች ፍርድ ተሞልተሃል፤ ፍርድና ፍትሕም ይዘውሃል። 18ብልጽግና ወደ መታለል እንዲስብህ እትፍቀድለት፤ መጠኑ የበዛ ጉቦም ፍትሕን እንድታዛባ እንዲያደርግህ አትፍቀድለት።19ብልጽግናህ ከሐዘን ሊያርቅህ ይችላል? ወይም የኃይልህ ብርታት ሁሉ ሊረዳህ ይችላል? 20ሰዎች በየስፍራቸው በሚወገዱበት ጊዜ በሌሎች ላይ ኃጢአትን ለመሥራት ጨለማን አትመኝ። 21ኃጢአትን ከማድረግ ትርቅ ዘንድ በመከራ ተፈትነሃልና ወደ ኃጢአት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።22ተመልከት፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለ ነው፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማነው? 23ስለ መንገዱ ከቶ ማን አስተምሮታል? 'በደለኛ ነህ' ሊለውስ ከቶ ማን ይችላል? 24ሰዎች የዘመሩለትን ሥራዎቹን ለማወደስ አስታውስ።25እነዚያን ሥራዎች ሰዎች ሁሉ አይተዋል፥ ነገር ግን እነዚያን ሥራዎች የሚያዩት ከርቀት ብቻ ነው። 26ተመልከት፥ እግዚአብሔር ትልቅ ነው፤ እኛም በሚገባ አናውቀውም፤ ዘመኖቹም አይቆጠሩም።27እርሱ እንፋሎቱ ዝናብ ሆኖ ይወርድ ዘንድ የውሃ ነጠብጣቦችን ወደ ላይ ስቦ ያከማቻል፥ 28ደመናዎች ወደ ታች ያፈስሱታል፥ በሰዎች ላይም በብዙ ያንጠባጥቡታል። 29በርግጥ የደመናዎቹን መዘርጋትና ከድንኳኑ የሚወጣውን መብረቅ ሊያስተውል የሚችል አለ?30ተመልከት፥ መብረቁን በዙሪያው ይበትናል፤ ባህሩን በጨለማ ይከድነዋል። 31በዚህ መንገድ ሰዎችን ይመግባቸዋል፥ ብዙ ምግብንም ይሰጣቸዋል።32ዒላማቸውን እንዲመቱ እስኪያዛቸው ድረስ እጆቹን በመብረቅ ነጓድጓድ ይሸፍናቸዋል። 33ዐውሎ ነፋስ እንደሚመጣ ድምፁ ለሰዎች ይነግራቸዋል፤ መቃረቡንም እንስሶች ደግሞ ያውቃሉ።
1በርግጥ በዚህ ጉዳይ ልቤ ተናውጧል፤ ስፍራውንም ለቋል። 2ኦ እስቲ አድምጡ፤ የድምፁን ሁካታ፥ ከአፉም የሚወጣውን ድምፅ አድምጡ። 3እርሱ ድምፁን ከሰማይ በታች ወዳለ ስፍራ ሁሉ ይልካል፥ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም መብረቁን ይልካል።4ከእርሱ በኋላ ድምፅ ይጮኻል፤ በግርማዊ ድምፁም ያንጎደጉዳል፤ ድምፁ በሚሰማበት ጊዜ የመብረቁን ብልጭታ አይከለክልም። 5እግዚአብሔር በድምፁ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጎደጉዳል፤ ልናስተውላቸው የማንችላቸውን ታላላቅ ነገሮችንም ያደርጋል። 6በረዶውን፥ 'በምድር ላይ ውደቅ'፤ እንዲሁም ዝናቡን፥ 'ብርቱ ዝናብ ሆነህ ውረድ' ይለዋል።7ሰዎች ሁሉ ያደረገውን ሥራውን እንዲያዩ የእያንዳንዱን ሰው እጅ ከመሥራት ይከለክላል። 8ከዚያም አራዊት ወደ መደበቂያቸው ይሄዳሉ፥ በዋሻዎቻቸውም ውስጥ ይቆያሉ። 9ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ መኖሪያው ይመጣል፤ ቅዝቃዜም በሰሜን ከተበተነው ነፋስ።10በእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ይገኛል፤ የውኆቹም ስፋት እንደ ብረት ይቀዘቅዛል። 11በርግጥ ጥቅጥቁን ደመና በሙቀት ይበትነዋል፤ መብረቆቹን በደመናዎች መካከል ይበትናቸዋል።12በመላው ዓለም ላይ ፈቃዱን ያደርጉ ዘንድ በአመራሩ ደመናትን ያሽከረክራቸዋል። 13እነዚህ ሁሉ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፤ ይህንን የሚያደርገው አንዳንድ ጊዜ ለማቅናት፥ አንዳንዴም ምድሩን ለማጠጣት፥ አንዳንዴም የቃል ኪዳን ታማኝነቱን ለማሳየት ነው።14ኢዮብ ሆይ፥ ይህንን ስማ፤ ቆም በልና የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራዎች አስብ። 15እግዚአብሔር እንዴት ፈቃዱን በደመናት ላይ እንደሚፈጽም፥ የመብረቁንም ብልጭታ በእነርሱ ውስጥ እንዲበራ እንደሚያደርግ ታውቃለህ?16በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራዎች፥ የደመናትንም መንሳፈፍ ታስተውላለህ? 17ከደቡብ በሚመጣው ነፋስ ምክንያት ምድር ጸጥ በምትልበት ጊዜ ልብስህ እንዴት እንደሚሞቅ ታስተውላለህ?18ከብረት የተሠራ ጠንካራ መስታወት የሚመስለውን ሰማይ እንደ እርሱ መዘርጋት ትችላለህ? 19አዕምሮአችን ከመጨለሙ የተነሣ ክርክራችንን በሥርዓት ማቅረብ አልቻልንምና ምን እንደምንመልስለት አስተምረን። 20ላነጋግረው እንደምፈልግ ይነገረው ዘንድ ይገባል? አንድ ሰው እንዲዋጥ ይፈልጋል?21እነሆ፥ ነፋስ በውስጡ ካለፈና ደመናውን ካጠራው በኋላ በሰማይ ላይ የሚያበራውን ፀሐይ ሰዎች ለማየት አይችሉም። 22እንደ ወርቅ የሚያብረቀርቅ ብርሃን ከሰሜን ይመጣል- በእግዚአብሔር ዘንድ አስፈሪ ግርማ አለ።23ሁሉን ቻዩን በሚመለከት እኛ ልናገኘው አንችልም፤ እርሱ በጽድቁና በኃይሉ ታላቅ ነው። ሰዎችን አያስጨንቅም። 24ስለዚህ፥ ሰዎች ይፈሩታል። ጥበበኞች ነን ብለው የሚያስቡትን አይመለከታቸውም"።
1ያን ጊዜ እግዚአብሔር ከብርቱ ዐውሎ ነፋስ ውስጥ ኢዮብን ጠራውና እንዲህ አለው፥ 2"ዕውቀት በጎደለው ቃል ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማነው? 3ጥያቄዎችን እጠይቅሃለሁና አሁን እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፥ አንተም ልትመልስልኝ ይገባሃል።4የምድርን መሠረቶች ባቆምኩ ጊዜ አንተ የት ነበርክ? ከፍ ያለ ማስተዋል ካለህ ነገረኝ። 5መጠኑን የወሰነው ማነው? የምታውቅ ከሆነ ንገረኝ። በላዩ ላይስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማነው?6መሠረቶቹስ የቆሙት በምን ላይ ነው? 7የንጋት ከዋክብት በአንድነት በዘመሩና የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በደስታ በዘመሩ ጊዜ የማዕዘኑን ድንጋይ ያስቀመጠ ማን ነበር?8ደመናትን ልብሱ፥ ድቅድቁንም ጨለማ መጠቅለያው ባደረግሁ ጊዜ 9ከማኅፀን የሚወጣ ይመስል ፈንድቶ በወጣ ጊዜ የባህሩን መዝጊያ የዘጋ ማነው?10ያን ጊዜ ነበር ለባህሩ ገደብን ያደረግሁለት፥ በሮችንና መወርወሪያዎችን ባደረግሁለት ጊዜ፥ 11እንዲህም ባልኩት ጊዜ፥ 'እስከዚህ ድረስ መምጣት ትችል ይሆናል፥ ከዚህ ግን አትለፍ፤ ለሞገድህ ትዕቢት ገደብ የማደርግለት እዚህጋ ነው'።12ከተወለድክበት ጊዜ ጀምሮ ንጋት እንዲጀምር ከቶ ትዕዛዝ ሰጥተኸዋል? ወጋገኑስ በነገሮች መካከል ስፍራውን እንዲያውቅ አድርገኸዋል? 13የምድርን ማዕዘናት በመያዝ ክፉዎች ሰዎች ከእርሱ ላይ እንዲራገፉ አድርገሃል?14ጭቃው ከማኅተም በታች እንደሚለወጥ የምድርም መልክ ተለውጧል፤ በእርሱ ላይ ያለው ነገር ሁሉ በግልጽ እንደ ቁራጭ ጨርቅ ተጠቅልሎ ቆሟል። 15ከክፉ ሰዎች 'ብርሃናቸው' ተወስዷል፤ ወደ ላይ የተነሣው ክንዳቸውም ተሰብሯል።16ወደ ባህሩ መገኛ ሄደህ ታውቃለህ? ዝቅ ወዳለው ጥልቅ ስፍራስ ወርደህ ታውቃለህ? 17የሞት በሮች ተገልጠውልሃል? የሞት ጥላ በሮችንስ አይተኻቸዋል? 18ምድርን በስፋቱ ታውቀዋለህ? ይህንን ሁሉ የምታውቅ ከሆነ ንገረኝ።19ብርሃን የሚያርፍበት ስፍራ መንገዱ የት ነው? የጨለማውስ ስፍራው የት ነው? 20ብርሃንና ጨለማን ወደ ሥራቸው ስፍራ ልትመራቸው ትችላለህ? ወደ መኖሪያቸው የሚመለሱበትን መንገድስ ልትፈልግላቸው ትችላለህ? 21ያን ጊዜ ተወልደህ ስለነበርና የዕድሜህም ቁጥር ታላቅ ስለሆነ ያለጥርጥር ታውቃለህ!22ወደ በረዶው መጋዘን ገብተሃል? ወይም የአመዳዩን ማከማቻ አይተሃል? 23እነዚህን ነገሮች ለመከራ ጊዜ፥ ለጦርነትና ለውጊያ ቀናት ያስቀመጥኳቸው ናቸው። 24የመብረቅ ብልጭታ የሚሰራጭበት መንገድ የትኛው ነው? ወይም ነፋሳት ከምስራቅ በምድር ላይ የሚበተኑበት መንገድ የቱ ነው?25ለዶፍ ዝናብ መውረጃን ያበጀለት ወይም ለመብረቅ ብልጭታ መንገድ ያዘጋጀለት ማነው? 26ሰው በሌለበት ምድር፥ ማንም በሌለበት ምድረ በዳ ላይ እንዲዘንብ ያደረገ ማነው? 27ሰው የሌለበትንና የባድማውን አካባቢ ፍላጎት የሚያረካ፥ ሣር እንዲበቅልበትስ የሚያደርግ ማነው?28ዝናብ አባት አለው? የጤዛን ጠብታ የወለደው ማነው? 29በረዶስ የመጣው ከማን ማኅፀን ነው? የሰማዩን አመዳይ ማን ወለደው? 30ውኆች ራሳቸውን ይደብቁና እንደ ድንጋይ ይጠነክራሉ፤ የጥልቁም ገጽታ ግግር ይሆናል።31ፕልያዲስ የተባለውን ኮከብ በሠንሰለት ልታስረው ወይም የኦሪዮንን እስራት ልትፈታ ትችላለህ? 32የከዋክብት ክምችት በተገቢው ጊዜአቸው እንዲታዩ ልትመራቸው ትችላለህ? ድብ የተባለውን ከነልጆቹ ልትመራቸው ትችላለህ? 33የሰማይን ሥርዓት ታውቃለህ? የሰማይን ሥርዓት በምድር ላይ መተግበር ትችላለህ?34ብዙ የዝናብ ውሃ እንዲያጥለቀልቅህ ድምፅህን ወደ ደመናት ማሰማት ትችላለህ? 35'ይኸው እዚህ አለን' ብለው ይላኩህ ዘንድ የመብረቅ ብልጭታዎችን ልትልካቸው ትችላለህ?36በደመናት ውስጥ ጥበብን ያኖረ ወይም ለእርጥበት ዕውቀትን የሰጠ ማነው? 37በጥበቡ ደመናትን ለመቁጠር የሚችል ማነው? 38ብናኙ ዐፈር ተበጥብጦ ጠንካራ ጓል በሚሆንበትና ጭቃው አፈር በአንድ ላይ በሚጣበቅበት ጊዜ የሰማይን የውሃ መያዣ አዘንብሎ ማፍሰስ የሚችል ማነው?39በዋሻዎቻቸው በሚያደቡበትና በመኖሪያቸው ተጋድመው በሚጠባበቁበት ጊዜ 40ለአንበሳዪቱ አደን ልታድንላት ወይም ግልገሎቿን ልታጠግብላት ትችላለህ?41ጫጩቶቻቸው ወደ እግዚአብሔር በሚጮኹበትና ምግብ በማጣት በሚንከራተቱበት ጊዜ ለቁራዎች ምግብ የሚሰጣቸው ማነው?
1የበረሃ ፍየሎች በዐለቶች መካከል የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህ? አጋዘኖችስ ግልገሎቻቸውን በሚወልዱበት ጊዜ ልታያቸው ትችላለህ? 2የእርግዝናቸውንስ ወራት ለመቁጠር ትችላለህ? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህ?3ይንበረከኩና ግልገሎቻቸውን ይወልዳሉ፤ የምጣቸውንም ሕመም ያበቃሉ። 4ግልገሎቻቸው ይጠነክራሉ፥ በገላጣው መስክ ላይም ያድጋሉ፤ ርቀው ይሄዳሉ፥ ወደ ወለዷቸውም አይመለሱም።5የሜዳ አህያው በነጻነት እንዲሄድ የፈቀደለት ማነው? 6አራባህን ቤቱ፥ የጨውንም ምድር መኖሪያው ያደረግሁለትን የፈጣኑንስ አህያ እስራት የፈታ ማነው?7በከተማ ባለው ሁካታ በንቀት ይስቃል፤ የነጂውንም ጩኸት አይሰማም። 8በመሰማሪያዎቹ በተራሮች ላይ ይንከራተታል፤ በዚያም የሚመገበውን የለመለመ ሣር ሁሉ ይፈልጋል።9ጎሽ ሊያገለግልህ ይፈቅዳል? በበረትህስ አጠገብ ለማደር ይስማማል? 10ጎሽ ትልሞችህን እንዲያርስልህ በገመድ ልትቆጣጠረው ትችላለህ? ጓሉንስ ይከሰክስልሃል?11ጉልበቱ ብርቱ ስለሆነ ትታመነዋለህ? እርሱ እንዲያከናውንልህ ተግባርህን ትተውለታለህ? 12ምርትህን ዐውድማ ላይ እንዲያከማችልህ፥ እህልህንም ወደ ቤት እንዲያገባልህ ትተማመነዋለህ?13የሰጎን ክንፎች በደስታ ይራገባሉ፤ ነገር ግን እነርሱ የፍቅር ክንፎችና ላባዎች ናቸው? 14እንቁላሎቿን በአፈር ውስጥ ትጥላለች፥ እንዲሞቃቸውም በትቢያ ውስጥ ትተዋቸዋለች። 15እግር እንዲረግጣቸው ወይም የዱር አውሬ እንዲጨፈልቃቸው ትረሳቸዋለች።16የእርስዋ ያልሆኑ ይመስል በጫጩቶቿ ትጨክናለች፤ ድካሟ ሁሉ ከንቱ እንደሚሆን በማሰብ አትፈራም፤ 17እግዚአብሔር ጥበብን ነፍጓታልና አንዳች ማስተዋልንም አልሰጣትም። 18በፍጥነት በምትሮጥበት ጊዜ በፈረሱና በጋላቢው ላይ በንቀት ትሥቃለች።19ለፈረስ ኃይሉን ሰጥተኸዋል? አንገቱንስ በጋማው አልብሰኸዋል? 20እንደ አንበጣ እንዲዘል አድርገኸዋል? የማንኮራፋቱ ገናናነት አስፈሪ ነው።21በኃይል ይጎደፍራል፥ በብርታቱም ደስ ይለዋል፤ የጦር መሳሪያዎችን ለመገናኘት ይፈጥናል። 22በፍርሃት ላይ ይሳለቃል፥ አይደነግጥምም፤ ከሰይፍም ወደ ኋላ አይመለስም። 23ከሚብለጨለጨው ፍላጻና ጦር ጋር የፍላጻዎች መያዣ ጎኑ ላይ ይንኳኳል።24በቁጣና በጭካኔ መሬትን ይውጣል፤ የመለከት ድምፅ ሲሰማ ይቁነጠነጣል። 25የመለከት ድምፅ በሚሰማበት ጊዜ ሁሉ 'አሃ!' ይላል፤ ጦርነትን፥ የአዛዦችን የሚንጎደጎድ ጩኸትና ሁካታ ከሩቅ ያሸታል።26ጭልፊት ርቆ የሚመጥቀው፥ ክንፎቹንም ወደ ደቡብ የሚዘረጋው ባንተ ጥበብ ነው?27ንስር ወደ ላይ የሚበረውና ጎጆውን ከፍ ባሉ ስፍራዎች የሚሠራው ባንተ ትዕዛዝ ነው? 28በገደል ላይ ይኖራል፥ መኖሪያ ምሽጉንም በገደሉ ጫፍ ላይ ያደርጋል።29እዚያ ላይ ሆኖ የሚነጥቀውን ይቃኛል፤ ዐይኖቹም ከርቀት ይመለከቱለታል። 30ጫጩቶቹ ደግሞ ደም ይጠጣሉ፤ በድን ባለበት እርሱም በዚያ አለ"።
1እግዚአብሔር ኢዮብን እንዲህ ሲል መናገሩን ቀጠለ፥ 2"ማንም መተቸት የሚፈልግ ሁሉን ቻዩን አምላክ ማረም አለበት? ከእግዚአብሔር ጋር የሚከራከር እርሱ ምላሹን ይስጥ"።3ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፥ 4"ተመልከት፥ እኔ ከምንም የማልቆጠር ነኝ፤ እንዴትስ መልስ ልሰጥህ እችላለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ። 5አንድ ጊዜ ተናገርኩ፥ መልስ መስጠትም አልችልም፤ በእርግጥ ሁለተኛ ተናግሬ ይሆናል፥ ከዚህ በኋላ ግን አልቀጥልም"።6ከዚያም እግዚአብሔር ከኃይለኛ ዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን እንዲህ ሲል ተናገረው፥ 7"እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁና አንተም ልትመልስልኝ ይገባል።8ፍትሐዊ ስላለመሆኔ ትናገራለህ? ራስህን ትክክለኛ አድርገህ ለመቁጠር እኔን ትኮንናለህ? 9የእግዚአብሔርን የሚያክል ክንድ አለህ? እንደ እርሱስ ድምፅህን ልታንጎደጉድ ትችላለህ?10አሁንም ክብርንና ልዕልናን ልበስ፤ ክብርንና ግርማንም ታጠቅ። 11የቁጣህን ብዛት በዙሪያህ አፍስስ፤ ትዕቢተኛ የሆነውን ሁሉ ተመልከተውና አዋርደው።12ትዕቢተኛ የሆነውን ሁሉ ተመልከተውና ዝቅ አድርገው፤ ክፉዎችንም ሰዎች በቆሙበት ስፍራ አድቅቃቸው። 13አንድ ላይ ዐፈር ውስጥ ቅበራቸው፤ በተሰወረ ስፍራም ፊታቸውን ደብቀው። 14ያን ጊዜ እኔ ደግሞ የገዛ ክንድህ ሊያድንህ እንደቻለ ዐውቃለሁ።15አሁንም አንተን እንደፈጠርኩህ የፈጠርኩትን ጉማሬ ተመልከት፤ እርሱ እንደ በሬ ሣር ይበላል። 16ተመልከት፥ ኃይሉ በወገቡ፥ ብርታቱም በሆዱ ጡንቻ ውስጥ ነው።17ጭራውን እንደ ጥድ ያወዛውዛል፤ የወርቹ ጅማቶችም እርስ በእርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው። 18አጥንቶቹ እንደ ነሐስ ቱቦ ናቸው፤ እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው።19እርሱ እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ዋነኛው ነው። እርሱን የፈጠረው እግዚአብሔር ብቻ ሊያሸንፈው ይችላል። 20ኮረብታዎች ምግቡን ያዘጋጁለታልና፤ በመስክ ላይ ያሉት አራዊትም በአቅራቢያው ይጫወታሉ። 21በረግረጉ ስፍራ ከደንገል ተክሎች ስር ይተኛል።22በውሃ ዳር የሚበቅሉ ዛፎች በጥላዎቻቸው ይሸፍኑታል፤ የአኻያውም ዛፍ ሁሉ በዙሪያው ነው። 23ተመልከት፥ ወንዙ ቢጎርፍም እርሱ አይፈራም፤ የዮርዳኖስ ወንዝ እስከ አፉ ቢሞላም እርሱ ተማምኖ ይኖራል። 24በወጥመድ ሊይዘው ወይስ አፍንጫውን በወጥመድ ሊበሳው የሚችል አለ?
1ሌዋታንን በዓሳ መንጠቆ ልትይዘው ትችላለህ? ወይስ መንጋጋዎቹን በገመድ ታስራለህ? 2በአፍንጫው ገመድ ልታስገባ ወይም አገጩን በችካል ልትበሳው ትችላለህ? 3አብዝቶስ ይለምንሃል? በለሰለሱ ቃላትስ ያናግርሃል?4የሁልጊዜ አገልጋይህ ለመሆን እንድትወስደው ከአንተ ጋር ስምምነት ያደርጋል? 5ከወፍ ጋር እንደምትጫወት ከእርሱ ጋር ትጫወታለህ? ሴት አገልጋዮችህ እንዲጫወቱበት ታስርላቸዋለህ? 6ዓሳ አጥማጆችስ በእርሱ ላይ ይደራደራሉ? ለነጋዴዎችስ ያከፋፍሉታል?7ቆዳውን በአንካሴ ወይም ራሱን በዓሳ መውጊያ ጦር ልትበሳው ትችላለህ? አንድ ጊዜ ብቻ 8እጅህን በላዩ ላይ አድርግ፥ ያን ጊዜ ግብግቡን አትረሳውም፥ እንዲህ ያለውን ተግባርም አትደግመውም። 9ተመልከት፥ ማንም ይህንን ለማድረግ ተስፋ ቢያደርግ ሐሰተኛ ነው፤ እርሱን በማየቱ ብቻ በድንጋጤ የማይወድቅ ማነው?10ሌዋታንን ለመቀስቀስ የሚደፍር የለም፤ ማንስ በፊቱ ሊቆም ይችላል? 11እንድመልስለት ማንኛውንም ነገር አስቀድሞ ለእኔ የሰጠኝ ማነው? ከሰማይ በታች ያለው ሁሉ የእኔ ነው። 12ስለ ሌዋታን እግሮች፥ ስለ ብርታቱና ስለተዋበው ቅርጹ ከመናገር ዝም አልልም።13ቆዳውን ማን ሊገፈው ይችላል? ድርብ መከላከያውንስ ማን ሊበሳው ይችላል? 14አስፈሪ ጥርሶቹ የተገጠገጡበትን የፊቱን ደጆች ማን ሊከፍት ይችላል? 15ጀርባው ተቀራርበው ከተጣበቁ ንብርብር ጋሻዎች የተሠራ ነው።16አንደኛው ከሌላኛው ጋር እጅግ ከመቀራረቡ የተነሣ በመካከላቸው ነፋስ አያስገባም። 17እርስ በእርስ ተገናኝተዋል፥ ሊነቅሏቸው እስከማይቻልም ድረስ በአንድነት ተጣብቀዋል። 18ከእንጥሽታው የብርሃን ብልጭታ ይወጣል፤ ዓይኖቹ እንደ ንጋት ጮራ ያበራሉ።19የሚነድ ፍም፥ የእሳትም ትንታግ ከአፉ ይወጣል። 20በእሳት ላይ ተጥዶ በኃይል እንደሚንተከተክ ድስት ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል። 21እስትንፋሱ ከሰሉን እንዲቀጣጠል ያደርገዋል፤ ከአፉም እሳት ይወጣል።22ብርታት በአንገቱ ውስጥ አለ፥ ሽብርም በፊት ለፊቱ ይጨፍራል። 23የሥጋው እጥፋቶች እርስ በእርሳቸው የተገጠገጡ ናቸው፤ በእርሱ ላይ ጸንተዋል፤ ሊያነቃንቋቸውም አይቻልም። 24ልቡ እንደ ድንጋይ የጠነከረ ነው፤ በእርግጥም እንደ ወፍጮ መጅ ጠንካራ ነው።25ቀና በሚልበት ጊዜ አማልክት እንኳ ይፈራሉ፤ ከፍርሃታቸውም የተነሣ ወደኋላቸው ይመለሳሉ። 26ሰይፍ ቢቆርጠው አንዳች አይሰማውም፤ ጦር፥ ቀስት፥ ወይም የትኛውም የጦር መሣሪያ ቢነጣጠርበት አይሰጋም። 27ብረትን እንደ አገዳ፥ ናስንም እንደ ነቀዘ እንጨት ይቆጥረዋል።28ቀስት እንዲሸሽ አያደርገውም፥ የወንጭፍ ድንጋይም ለእርሱ እንደ ገለባ ነው። 29ዱላ እንደ አገዳ ተቆጥሯል፤ በሚወረወርበት ጦር ላይም ይስቃል። 30የሆዱ ስር እንደ ገል ስብርባሪ የሾለ ነው፤ የእህል መውቂያ መሣሪያ ይመስል በጭቃው ላይ ምልክት ትቶ ያልፋል።31በድስጥ ውስጥ ያለ ውሃ እንደሚፈላ የጥልቁን ውሃ ያናውጠዋል፤ ባህሩንም እንደ ሽቶ ቢልቃጥ ያደርገዋል። 32የሄደበት መንገድ ከበስተኋላው እንዲያበራ ያደርጋል፤ ይህንን ያየም ጥልቁን ነጭ ነው ብሎ ያስባል።33ያለ ፍርሃት እንዲኖር የተፈጠረ በምድር ላይ እርሱን የሚያክል የለም። 34ኩሩ የሆነውን ሁሉ ያያል፤ እርሱ በትዕቢት ልጆች ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።"
1ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፥ 2"ሁሉን ለማድረግ እንደምትችል፥ ዓላማህ ሊደናቀፍ እንደማይችል አውቃለሁ። 3'ያለዕውቀት ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማነው?' ብለህ ጠይቀኸኛል። ስለዚህ የማላውቀውን፥ ያልተረዳሁትን፥ ለማወቅም እጅግ አስቸጋሪ የሆነውን ነገር ተናግሬአለሁ።4አንተም፥ 'አሁንም፥ አድምጥ፥ እኔ እናገራለሁ፤ አንዳንድ ነገሮችን እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ትነግረኛለህ' አልከኝ። 5ስለአንተ መስማትን በጆሮዬ ሰምቼ ነበር፥ አሁን ግን ዓይኖቼ አዩህ። 6ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በአመድና በትቢያ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ"።7እግዚአብሔር ኢዮብን ይህን ቃል ከተናገረው በኋላ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፥ "አንተና ሁለቱ ጓደኞችህ አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ ትክክለኛውን ነገር አለተናገራችሁምና ቁጣዬ በእናንተ ላይ ነዶባችኋል። 8አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ለራሳችሁ ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ኢዮብ ሂዱ፤ ለራሳችሁም የሚቃጠል ምስዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ። እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን እቀበላለሁ። አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ ትክክለኛውን ነገር አልተናገራችሁምና።" 9ስለዚህ ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስና ናዕማታዊው ሶፋር እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ሄደው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም ኢዮብን ተቀበለው።10ኢዮብ ስለ ጓደኞቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር እንደገና አበለጸገው። ቀድሞ ከነበረው በላይ እግዚአብሔር ዕጥፍ አድርጎ ሰጠው። 11ከዚያም የኢዮብ ወንድሞቹና እህቶቹ ሁሉ፥ ቀድሞ ያውቁት የነበሩትም ሁሉ እርሱ ወደነበረበት መጡ፤ ከእርሱም ጋር ምግብ በሉ። እነርሱም ሐዘኑን ተጋሩት፤ እግዚአብሔር አምጥቶበት ስለነበረው መከራ ሁሉ አጽናኑት። እያንዳንዳቸውም ለኢዮብ ጥሬ ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት።12እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ይልቅ የኢዮብን የኋለኛውን ዘመን ባረከለት፤ እርሱም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድስት ሺህ ግመሎች፥ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም ሴት አህዮች ነበሩት። 13ደግሞም ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት። 14የመጀመሪያ ሴት ልጁን ይሚማ፥ ሁለተኛዋን ቃሥያ፥ ሦስተኛዋን አማልቶያስ ቂራስ ብሎ ሰየማቸው።15በሀገሩ ሁሉ እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች የተዋቡ ሴቶች አልተገኙም። አባታቸውም ከወንድሞቻቸው እኩል ርስትን ሰጣቸው። 16ከዚህ በኋላ ኢዮብ 140 አመት ኖረ፤ እርሱም ወንዶች ልጆችን፥ የወንዶች ልጆቹን ወንዶች ልጆች እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ። 17ከዚያም ኢዮብ አርጅቶ፥ ዕድሜንም ጠግቦ ሞተ።
1በክፉዎች ምክር የማይሄድ በኃጢአተኞች መንገድ የማይቆም በፌዘኞች ወንበር የማይቀመጥ ምስጉን ነው፡፡2ነገር ግን ደስ የሚሰኘው በያህዌ ሕግ ነው ሕጉንም ቀንና ሌሊት ያሰላስላል፡፡3እርሱም ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣ ቅጠሏም እንደማይጠወልግ፣ በወራጅ ውሆች እንድ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል፡፡4ኃጢአተኞች ግን እንዲህ አይደሉም ነገር ግን ነፋስ ጠራርጐ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው፡፡5ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ አይቆሙም፡፡6ያህዌ የጻድቃንን አካሄድ ይጠብቃልና የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች፡፡
1አሕዛብ ለምን ያሤራሉ? ሕዝቦችስ ለምን በከንቱ ያድማሉ?2የምድር ነገሥታት በአንድነት ተነሡ ገዦችም በአንድነት አሤሩ እንዲህ በማለትም በያህዌና በመሲሑ ላይ አሤሩ3«እግር ብረታቸውን ከእግራችን እንቁረጥ፣ ሰንሰሰታቸውንም በጥሰን እንጣል፡፡»4በሰማያት የሚቀመጥ እርሱ ያፌዝባቸዋል ጌታም ይሳለቅባቸዋል፡፡5ከዚያም በቁጣው ያናግራቸዋል እንዲህ በማለትም በመዐቱ ያስፈራቸዋል6«እኔ ራሴ በጽዮን፣ በተቀደሰውም ተራራዬ ንጉሤን ሾምሁ፡፡»7የያህዌን ዐዋጅ ዐውጃለሁ፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ፣ «አንተ ልጄ ነህ! በዚህ ቀን አባትህ ሆኛለሁ፡፡8ለምነኝ፤ አሕዛብን ለርስትህ የምድር ነገሥታትንም ለግዛትህ እሰጥሃለሁ፡፡9በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ ሸክላ ሠሪው እንዳበጀው ዕቃ ታደቃቸዋለህ፡፡»10ስለዚህ አሁን እናንት ነገሥታት ተጠንቀቁ እናንት የምድር ገዦች አስተውሉ፡፡11ያህዌን በፍርሃት አምልኩት በመንቀጥቀጥ ተገዙለት፡፡12እንዳይቆጣ በመንገድም እንዳትጠፉ ልጁን ሳሙት፡፡ ቁጣው ፈጥኖ ይነዳልና፡፡ እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የተነሡ ብዙዎች ናቸው፡፡2ብዙ ሰዎች፣ «እግዚአብሔር አያድነውም» እያሉ ስለ እኔ ይናገራሉ፡፡3አንተ ግን ያህዌ ሆይ፣ ዙሪያዬን እንደ ጋሻ ትከልለኛለህ፣ ክብሬንና ራሴንም ከፍ የምታደርግ አንተ ነህ፡፡4ድምፄን ወደ ያህዌ አነሣለሁ እርሱም ከተቀደሰው ተራራው ይመልስልኛል፡፡ ሴላ5በሰላም እተኛለሁ፤ እንቀላፋለሁ ያህዌ ስለ ጠበቀኝ ከእንቅልፌ ተነሣሁ፡፡6በየአቅጣጫው ከተነሡብኝ ሰዎች ብዛት አልፈራም፡፡7ያህዌ ሆይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ አድነኝ! አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መታህ የክፉዎችን ጥርስ ሰበርህ፡፡8መዳን ከያህዌ ነው በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን፡፡
1የጽድቄ አምላክ ሆይ፣ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ ከጭንቀቴም አሳርፈኝ ማረኝ ጸሎቴንም ስማ፡፡2እናንተ ሰዎች እስከ መቼ ክብሬን ታወርዳላችሁ? እስከ መቼ ከንቱ ነገር ትወዳላችሁ፤ ሐሰትንስ ትፈልጋላችሁ? ሴላ3ያህዌ ጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ ዕወቁ፡፡ በጠራሁት ጊዜ ያህዌ ይሰማኛል፡፡4የቱንም ያህል ብትፈሩ ኃጢአት አትሥሩ! በመኝታችሁ እያላችሁ በልባችሁ አሰላስሉ፤ ጸጥም በሉ፡፡ ሴላ5ለያህዌ የጽድቅ መሥዋዕት አቅርቡ እምነታችሁንም እርሱ ላይ አድርጉ፡፡6ብዙዎች፣ «መልካሙን ማን ያሳየናል?» ይላሉ፡፡ ያህዌ ሆይ፣ የፊትህን ብርሃን እኛ ላይ አብራ፡፡7ብዙ እህልና ወይን ካገኙ ሰዎች ይበልጥ አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል፡፡8በሰላም የምታኖረኝ አንተ ብቻ ስለሆንህ በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፡፡
1ያህዌ ሆይ ወደ አንተ ስጣራ ስማኝ መቃተቴንም አስብ፡፡2ንጉሤና አምላኬ ወደ አንተ እጸልያለሁና የልመናዬን ጽምፅ አድምጥ3ያህዌ ሆይ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ በማለዳ ልመናዬን ወደ አንተ አቀርባለሁ፤ እጠባበቃለሁም፡፡4በእርግጥ አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም ክፉ ሰዎች ከአንተ አያድሩም፡፡5እብሪተኛ በፊትህ አይቆምም ዐመፃን የሚያደርጉትህን ሁሉ ጠላህ፡፡6ሐሰተኞችን ታጠፋለህ ደም የተጠሙትን አታላዮችን ያህዌ ይጸየፋል፡፡7እኔ ግን በኪዳናዊ ታማኝነትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ በአክብሮት ፍርሃትም የተቀደሰ ማደሪያህ ውስጥ እሰግዳለሁ፡፡8ጌታ ሆይ፣ በጠላቶች ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ መንገድህንም በፊቴ አቅና፡፡9በአፋቸው እውነት የለም ልባቸው ተንኰለኛ ነው፡፡ ጉሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፡፡ በአንደበታቸው ይሸነግላሉ፡፡10እግዚአብሔር ሆይ፣ የእጃቸውን ስጣቸው ተንኰላቸው መጥፊያቸው ይሁን! አንተ ላይ ዐምፀዋልና ከኃጢአታቸው ብዛት የተነሣ አስወግዳቸው፡፡11በአንተ የተማመኑ ሁሉ ደስ ይበላቸው አንተ ከለላ ሁነሃቸዋልና ለዘላለም ሐሤት ያድርጉ፡፡ ስምህን የሚወዱ በአንተ ደስ ይበላቸው12ያህዌ ሆይ፣ አንተ ጻድቁን ትባርካለህ እንደ ጋሻ በሞገስ ትከልላቸዋለህ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ በቁጣህ አትገሥጸኝ በመዐትህም አትቅጣኝ፡2ያህዌ ሆይ፣ ደካማ ስለሆንሁ ምሕረት አድርግልኝ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተናውጠዋልና፣ ፈውሰኝ፡፡3ነፍሴም ታወካለች፤ ያህዌ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ይቀጥላል?4ወደ እኔ ተመለስ፤ አድነኝም፡፡ ከታማኝ ኪዳንህ የተነሣ አድነኝ5በሞት የሚያስታውስህ የለም መቃብር ውስጥ ሆኖ፣ የሚያመሰግንህ ማን ነው?6ከመቃተቴ የተነሣ ዝዬአለሁ ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ አልጋዬን በእንባ አርሳለሁ መኝታዬንም በእንባ አረጥባለሁ፡፡7ከሐዘን የተነሣ ዐይኖቼ ፈዘዙ፤ ከባላጋራዎቼ የተነሣ ደከሙ፡፡8እናንት ዐመፃን የምታደርጉ ሁሉ ከእኔ ራቁ ያህዌ የለቅሶዬን ድምፅ ሰምቷልና9እንዲምረኝ ወደ እርሱ ያቀረብኩትን ልመና አድምጧል፤ ያህዌ ጸሎቴን ተቀብሏል፡፡10ጠላቶቼ ሁሉ ይፈሩ፤ እጅግም ይታወኩ ወደ ኋላ ይመለሳሉ፤ በድንገትም ይዋረዳሉ፡፡
1ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ አንተ መጠጊያዬ ነህ! ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ ታደገኝም2አለበለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል የሚያድነኝ በሌለበት ሁኔታ ያደቁኛል፡፡3አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶቼ አድርጓል የሚሉትን አላደረግሁም በእኔ ላይ ምንም በደል የለም፡፡4በጐ ለዋለልኝ ክፉ አልመለስሁም፡፡ጠላቶቼን በከንቱ አልጐዳሁም፡፡5የምናገረው እውነት ካልሆነ ጠላቴ አሳድዶ ይያዘኝ ሕይወቴን ከምድር ይቀላቅል ክብሬንም ከትቢያ ጋር ይደበልቅ፡፡ ሴላ6ያህዌ ሆይ፣ በቁጣህ ተነሥ በጠላቶቼ ዛቻ ፍረድ አምላኬ ሆይ ንቃ ትእዛዝም አስተላልፍ፡፡7ሕዝቦችን ሁሉ በዙሪያህ ሰብስብ ከላይም ሆነህ ግዛቸው፡፡8ያህዌ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል ያህዌ ሆይ፣ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ ልዑል ሆይ፣ እንደ ንጽሕናዬ መልስልኝ፡፡9ልብንና አእምሮን የምትመረምር ጻድቅ አምላክ ሆይ፣ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፉ፤ ጻድቃንን ግን አጽና፡፡10ጋሻዬ ልዑል እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ልበ ቅኖችን ያድናቸዋል፡፡11እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፤ ቁጣውንም በየዕለቱ የሚገልጥ አምላክ ነው፡፡12ሰው በንስሐ የማይመለስ ከሆነ እግዚአብሔር ሰይፉን ይስላል፤ ለውጊያም ቀስቱን ይገትራል13የሚገደሉ ጦር ዕቃዎቹን አዘጋጅቷል የሚንበለበሉትን ፍላጻዎቹንም አሰናድቶአል፡፡14ክፋትን ያረገዘ፣ ክፉ ዕቅዶችን የፀነሰና አጥፊ ሐሰቶችን የወለደ ሰውን አስቡ፡፡15ጥልቅ ጉድጓድ ይቆፍራል በቆፈረው ጉድጓድ እርሱ ይገባበታል፡፡16ለሌሎች ያዘጋጀው ክፉ ዕቅድ ወደ ራሱ ይመለሳል፤ ዐመፃውም በገዛ ዐናቱ ላይ ይወርዳል፡፡17ስለ ጽድቁ ያህዌን አመሰግናለሁ ለልዑል አምላክም እዘምራለሁ፡፡
1ክብርህን በላይ በሰማያት የምትገልጥ አንተ ጌታችን ያህዌ፣ ስምህ በምድር ሁሉ ምንኛ ገናና ነው፡፡2ከጠላትህ የተነሣ፤ ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ለማሰኘት ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡3ጣቶችህ የሠሯቸው ሰማያትን፣ በየቦታቸው ያደርግሃቸው ጨረቃና ከዋክብትን ስመለከት4በአሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጠነቀቅለትስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?5ከመላእከት በጥቂት አሳነሰኸው የክብርና የሞገስ ዘውድ አቀዳጀኸው፡፡6በእጆችህ ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አደረግህለት7በጐችና በሬዎችን፣ የዱር አራዊትን፣8የሰማይ ወፎችን፣ የባሕር ዓሦችን ባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትን ሁሉ አስገዛህለት፡፡9ጌታችን ያህዌ፣ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ገነነ!
1በፍጹም ልቤ ያህዌን አመሰግናለሁ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም እናገራለሁ፡፡2በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ ልዑል ሆይ፣ ለስምህ እዘምራለሁ!3ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ ተሰነካክለው በፊትህ ይጠፋሉ፡፡4በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ ጻድቅ ፈራጅ ነህ! የእኔን ጉዳይም ትፈርድልኛለህ፡፡5ሕዝቦችን ገሠጽህ ክፉዎችን አጠፋህ ስማቸውን ከዘላለም እስከ ዘላለም ደመሰስህ፡፡6ጠላቶች ለዘላለም ጠፍተዋል ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው መታሰቢያቸውንም አጠፋህ፡፡7እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ዙፋኑ ላይ ነው ዙፋኑንም ለፍርድ አጽንቶአል፡፡8ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል ለሕዝቦችም በፍትሕ ይፈርዳል፡፡9ያህዌ ለተጨቆኑት ዐምባ ነው፡፡ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል፡፡10ስምህን የሚያውቁ በአንተ ይታመናሉ አንተ ያህዌ፣ የሚፈልጉህን አትተዋቸውም፡፡11በጽዮን ለሚገዛ ለያህዌ ምስጋና ዘምሩ ድንቅ ሥራውን ለሕዝቦች ተናገሩ፡፡12ደም ተበቃዩ አስቦአቸዋልና የጭቁኖችን ጩኸት አልዘነጋም፡፡13ያህዌ ሆይ፣ ማረኝ በሚጠሉኝ የደረሰብኝን ጭቆና ተመልከት አንተ ከሞት አፋፍ ነጥቀህ አድነኝ፡፡14ይህን ብታደርግልኝ፣ በጽዮን አደባባይ ምስጋናህን ሁሉ ለሕዝብ እናገራለሁ በማዳንህም ደስ እሰኛለሁ!15ሕዝቦች ባዘጋጁት አዘቅት ሰጠሙ እግሮቻቸውም በሰወሩት ወጥመድ ተያዙ፡፡16እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ታወቀ ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ፡፡17ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፡፡ እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሰዎች ሁሉ ፍጻሜ ይኸው ነው፡፡18ችግረኞች መቼም ቢሆን አይዘነጉም የድኾችም ተስፋ ከንቱ ሆኖ አይቀርም፡፡19ያህዌ ሆይ ተነሥ፣ ሰውም አያይል ሕዝቦችም በፊት ይፈረድባቸው፡፡20ያህዌ ሆይ፣ አስደንግጣቸው ሕዝቦች ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ይወቁ፡፡ ሴላ
1ያህዌ ሆይ፣ ለምን ርቀህ ቆምህ? በመከራ ጊዜ ለምን ራስህን ሰወርህ?2በእብሪት ተነሳሥተው ክፉዎች ጭቁኖችን ያሳድዳሉ እባክህ ክፉዎች ባጠመዱት ወጥመድ ይጠመዱ፡፡3ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኩራራል ስግብግቡን ይባርካል፤ ያህዌን ይሰድባል፡፡4ክፉ ሰው በራሱ ይመካል፤ እግዚአብሔርንም አይፈልግም፡፡ ስለ እርሱ ምንም ደንታ ስለሌለው ስለ እግዚአብሔር አያስብም፡፡5ነገሩ ዘወትር ለእርሱ የተሳካ ነው የእግዚአብሔርን ፍርድ ግን ሊረዳ አይችልም፡፡ በጠላቶቹ ላይ ይሳለቃል፡፡6በልቡም፣ «በፍጹም አልወድቅም ከትውልድ እስከ ትውልድ መከራ አያገኘኝም» ይላል፡፡7አፉ መርገምን፣ ሸፍጥንና ግፍን የተሞላ ነው፤ በምላሱ ይጐዳል፤ ይገድላልም፡፡8መንደሮች አጠገብ አድፍጦ ይጠብቃል በሰዋራ ቦታ ንጹሐንን ይገድላል ዐይኖቹም ምስኪኖች ላይ ያነጣጥራሉ፡፡9ደን ውስጥ እንዳለ አንበሳ በስውር ያደባል ረዳት የሌለውን ለመያዝ ያሸምቃል፡፡ መረቡን ዘርግቶ ጭቁኖችን ያጠምዳል፡፡10እርሱ መትቶ ይጥላቸዋል፤ ረዳት የሌላቸው ደካሞች ምስኪኖችም የእርሱ ሰለባ ሆነው ይወድቃሉ፡፡11በልቡም፣ «እግዚአብሔር ረስቶአል እንዳያይም ፊቱን ሸፍኖአል» ይላል፡፡12ያህዌ ሆይ፣ ተነሥ! አምላክ ሆይ ኃያል ክንድህ ይነሣ! የተጨቆኑትን ችላ አትበላቸው፡፡13ክፉ ሰው ለምን እግዚአብሔርን ይንቃል? በልቡም ለምን፣ «እግዚአብሔር አይቀጣኝም» ይላል?14አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደጉም አንተ ረዳቱ ነህ፡፡15የክፉና የበደለኛውን ክንድ ስበር አንተ እንደማታገኘው አስቦ ነበር የእጁንም ሰጠው፡፡16ያህዌ ከዘላለም እስከ ዘላለም ንጉሥ ነው ሕዝቦችም ከምድሩ ይወገዳሉ፡፡17ያህዌ የጭቁኖቹን ጩኸት ሰምቷል ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጸሎታቸውንም ትሰማለህ18ከእንግዲህ ማንም በምድር ላይ ሽብር እንዳያደርግ አንተ አባት ለሌላቸውና ለጭቁኖች መከታ ሆንህላቸው፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አደረግሁ ታዲያ፣ ነፍሴ፣ «እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ብረሪ» እንዴት ትሏታላችሁ? 2ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ? ልበ ቅኖችን በጨለማ ለመግደል ክፉዎች ቀስታቸውን ገትረዋል፤ ፍላጻቸውንም በአውታሩ ላይ ደግነዋል፡፡3ያህዌ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አደረግሁ ታዲያ፣ ነፍሴ፣ «እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ብረሪ» እንዴት ትሏታላችሁ? ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ?4ልበ ቅኖችን በጨለማ ለመግደል ክፉዎች ቀስታቸውን ገትረዋል፤ ፍላጻቸውንም በአውታሩ ላይ ደግነዋል፡፡5ያህዌ ጻድቁንና ኃጢአተኛውን ይመለከታል ዐመፅን ማድረግ የሚወዱትን ግን ይጠላቸዋል፡፡6እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስም የእነርሱ ዕጣ ፈንታ ነው፡፡7ያህዌ ጻድቅ ስለ ሆነ የጽድቅን ሥራ ይወዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ደግ ሰው የለምና አንተው እርዳኝ ከሰው ዘር መካከል አንድ ታማኝ አይገኝም፡፡2እያንዳንዱ ሰው ለባልንጀራው ባዶ ቃላት ይናገራል በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራል፡፡3ሸንጋይ ከናፍርቶችንና በትምክህት የሚናገሩ አንደበቶችን ያህዌ ያጥፋ፡፡4እነዚህም፣ «በአንደበታችን እንበረታለን የምንናገረውንስ ማን ማስተባበል ይችላል?» የሚሉ ናቸው፡፡5«ስለ ድኾች መከራ፣ ስለ ችግረኞች ጩኸት ያህዌ አሁን እነሣለሁ፤ የናፈቁትንም ሰላም እሰጣቸዋለሁ» ይላል፡፡6የያህዌ ቃሎች የነጹ ቃሎች ናቸው በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው፡፡7ያህዌ ሆይ፣ አንተ ትጠብቀናለህ ከዚህ ዐመፀኛ ትውልድ ለዘላለም ጻድቃንን ትጠብቃለህ፡፡8በሰው ልጆች መካከል ክፋት በገነነበት ጊዜ ዐመፀኞች እንዳሻቸው በየቦታው ይዘራሉ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ? ፊትህን ከእኔ የምትሰውረውስ እስከመቼ ድረስ ነው?2በስጋት የምኖረው ልቤስ ቀኑን ሙሉ የሚያዝነው እስከ መቼ ነው? ጠላቴ እኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ነው?3ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ ወደ እኔ ተመልከት መልስልኝም!4የሞት እንቅልፍ እንዳይወስደኝ ዐይኖቼን አብራ፡፡ ጠላቴ፣ «አሸነፍሁት» እንዳይል ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ፡፡5እኔ ግን ወሰን በሌለው ፍቅርህ እተማመናለሁ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል፡፡6ቸርነቱ በዝቶልኛልና ለያህዌ እዘምራለሁ፡፡
1ሞኝ በልቡ፣ «እግዚአብሔር የለም» ይላል፡፡ ብልሹዎች ናቸው፤ አስጸያፊ ተግባርም ይፈጽማሉ፡፡ መልካም የሚያደርግ አንድም የለም፡፡2የሚያስተውል፣ እርሱንም የሚፈልግ መኖሩን ለማየት ያህዌ ከሰማይ ወደ ምድር ተመለከተ፡፡3ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ ሁሉም ብልሹዎች ሆነዋል ከእነርሱ አንድ እንኳ መልካም የሚያደርግ የለም፡፡4እነዚያ ዐመፃ የሚያደርጉ ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ፣ የያህዌን ስም የማይጠሩ ሰዎች ዕውቀት የላቸውምን?5እግዚአብሔር በጻድቃን መካከል ይገኛልና እነርሱ በፍርሃት ተርበደበዱ!6ምንም እንኳ ያህዌ መጠጊያው ቢሆንም እናንተ ግን ድኻውን ማዋረድ ትፈልጋላችሁ፡፡7ያህዌ ሕዝቡን ከምርኮ ሲመለስ ለእስራኤል መዳን ከጽዮን ይመጣል ያኔ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ የሚያድር ማን ነው? በተቀደሰው ኮረብታህስ የሚኖር ማን ነው?2አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤3በአንደበቱ የማይሸነግል ሌሎች ሰዎችን የማይጐዳ፤ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታ የማያሰራጭ4ነውረኛውን የሚንቅ፣ ያህዌን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፡፡ ዋጋ ቢያስከፍለው እንኳ የገባውን ቃል የሚፈጽም5ገንዘቡን በወለድ የማያበድር ንጹሕ ሰው ላይ ለመመስከር ጉቦ የማይበላ፤ እነዚህን የሚያደርግ ከቶውንም አይናወጥም፡፡
1በአንተ ተማምኛለሁና ያህዌ ሆይ ጠብቀኝ፡፡2ያህዌን፣ «አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ ውጪ መልካም ነገር የለኝም» አልሁት፡፡3በምድር የሚኖሩ ቅዱሳን የተከበሩ ናቸው፤ በእነርሱም ደስ ይለኛል፡፡4ሌሎች አማልክትን የሚከተሉ መከራቸው ይበዛል እኔ ግን ለአማልክቶቻቸው የደም ቁርባን አላፈስም፤ ስማቸውንም በአፌ አልጠራም፡፡5ያህዌ የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ ፍጻሜዬም በአንተ እጅ ነው፡፡6መለኪያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል በእርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ፡፡7የሚመክረኝን ያህዌን እባርካለሁ፤ ሌሊት እንኳ ልቦናዬ ያስተምረኛል፡፡8ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስለሆነ አልናወጥም!9ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፤ ክብሬም ሐሤት አደረገ፡፡ በእርግጥ ያለ ስጋት እኖራለሁ፡፡10ምክንያቱም አንተ ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም ታማኝህ መበስበስ እንዲደርስበት አታደርግም፡፡11የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍስሐ አለ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርበውን ጸሎት ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፡፡ ከሐሰተኛ ከንፈር ያልወጣውን ጸሎቴን አድምጥ፡፡2ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤ ዐይኖችህም ፍትሕን ይመልከቱ፡፡3ልቤን ብትመረምር፣ በሌሊትም ብትጐበኘኝ፣ ብትፈትነኝም ከእኔ ዘንድ ክፋት አታገኝም፤ አንደበቴም አይስትም፡፡4የሰው ልጆችን ተግባር በተመለከተ አንተ በተናገርኸው ቃል መሠረት ከዐመፀኞች መንገድ ራሴን ጠብቄአለሁ፡፡5አረማመዱ በመንገድህ ጸንቶአል እግሮቼም አልተንሸራተቱም፡፡6ያህዌ ሆይ፣ ስለምትመልስልኝ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ጸሎቴንም ስማ፡፡7የሚተማመኑብህን በቀኝህ ከጠላቶቻቸው የምታድናቸው አንተ ታማኝትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው፡፡8እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሥር ሰውረኝ፡፡9ከሚያስጨንቁኝ፣ ከከበቡኝም አደገኛ ጠላቶቼ ጋርደኝ፡፡10እነርሱ ማንንም አይምሩም፤ አንደበታቸው ትዕቢትን ይናገራል፡፡11ጠላቶቼ አስጨነቁኝ፤ ከበባም አደረጉብኝ መሬት ላይ ሊዘርሩኝም አፈጠጡብኝ፡፡12እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚጓጓ፣ አድፍጦም እንደሚጠብቅ ደቦል አንበሳ ናቸው፡፡13ያህዌ ሆይ፣ ተነሣና አጥቃቸው፤ በአፍጢማቸው ድፋቸው! በሰይፍህ ከክፉዎች አድነኝ፡፡14ያህዌ ሆይ፣ እንዲህ ካሉ ሰዎች፣ ብልጽግናቸው በዚህ ሕይወት ብቻ ከሆነ ከዚህ ዓለም ሰዎች በቀኝህ አድነኝ፡፡ የአንተ የሆነ ሰዎችን ሆድ በመልካም ነገር ትሞላለህ እነርሱም ብዙ ልጆች ይኖሩዋቸዋል፤ ሀብታቸውንም ለልጆቻቸው ያወርሳሉ፡፡15እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ ስነቃም ክብርህን ዐይቼ እረካለሁ፡፡
1ጉልበት የሆንኸኝ ያህዌ እወድሃለሁ፡፡2ያህዌ ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፡፡ እርሱ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፣ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው፡፡3ምስጋና የሚገባውን ያህዌን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ፡፡4የሞት ገመድ አነቀኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፡፡5የሲኦል ማሰሪያ ተጠመጠመብኝ የሞት ወጥመድም ተጠመደብኝ፡፡6በጨነቀኝ ጊዜ ያህዌን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤ ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከፊቱ ደረሰ፤ ወደ ጆሮውም ገባ፡፡7ምድር ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፤ የተራሮችም መሠረት ተናጋ፤ ጌታ እግዚአብሔር ተቆጥቶአልና ተንቀጠቀጡ፡፡8ከአፍንጫው ጢስ፣ ከአፉም የሚባላ እሳት ወጣ፤ የፍም ነበልባል ከእርሱ ፈለቀ፡፡9ሰማያትን ከፍቶ ወረደ፤ ከእግሮቹም በታች ድቅድቅ ጨለማ ነበረ፡፡10በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ መጠቀ፡፡11ጨለማን እንደ ድንኳን፣ ዝናብ አዘል ጥቁር ደመናን በዙሪያው አደረገ፡፡12በፊቱ ካለው መብረቅ የተነሣ የበረዶ ድንጋይና የእሳት ፍም ወጣ፡፡13ያህዌ ከሰማያት አንጐደጐደ! የልዑልም ድምፅ አስተጋባ፡፡14ቀስቱን አስፈንጥሮ ጠላቶቹን በተናቸው፤ መብረቅ አዥጐድጉዶ አሳደዳቸው፡፡15ያህዌ ሆይ፣ ከቁጣህ የተነሣ፣ ከአፍንጫህም እስትንፋስ የተነሣ፣ የባሕር ወለል ታዬ የዓለምም መሠረት ተገለጠ፡፡16ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ስቦ አወጣኝ፡፡17ከኃያላን ጠላቶቼ፣ ከሚጠሉኝ ከዐቅሜ በላይ ከሆኑ ባላንጣዎቼ ታደገኝ፡፡18በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ ያህዌ ግን ድጋፍ ሆነኝ፡፡19በጣም ሰፊ ወደ ሆነ ቦታ አወጣኝ፤ ወዶኛልና አዳነኝ፡፡20ያህዌ እንደ ጽድቄ ከፍሎኛል፤ እጆቼ ንጹሕ ስለ ነበሩ ታድጐኛል፡፡21የያህዌን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ በዐመፅ ተነሣሥቼ ከእርሱ ዘወር አላልሁም፡፡22ሕጐቹ ሁሉ በፊቴ ናቸው፤ ሥርዐቱንም ከፊቴ አላራቅሁም፡፡23በእርሱ ፊት ንጹሕ ነበርሁ፤ ከኃጢአትም ራሴን ጠብቄአለሁ፡፡24ያህዌ እንደ ጽድቄ መጠን፤ በዐይኖቹ ፊት ንጹሕ እንደ ነበሩት እጆቼ መጠን ከፍሎኛል፡፡25አንተ ታማኝ ለሆኑት ታማኝ ነህ እውነተኞች ለሆኑት እውነተኛ ነህ26ለንጹሖች ንጹሕ ነህ፡፡ ለጠማሞች ግን ጠማማ ትሆንባቸዋለህ፡፡27አንተ ትሑታንን ታድናለህ ትዕቢተኛውን ዐይን ግን ታዋርዳለህ፡፡28አንተ መብራቴን ታበራለህ፤ አምላኬ ያህዌ ጨለማዬን ብርሃን ታደርገዋለህ፡፡29በአንተ ጉልበት በሰራዊት እረማመዳለሁ፤ በአምላኬም ኃይል ቅጥሩን እዘላለሁ፡፡30የእግዚአብሔር መንገድ ፍጹም ነው፤ የያህዌ ቃል የነጠረ ነው። መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ እርሱ ጋሻ ነው።31ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ? ከአምላካችንስ በቀር ዐምባ ማን ነው?32ኅይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቃና እግዚአብሔር ነው።33እርሱ እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያጠነክራል፣ በከፍታዎችም ላይ ያቆመኛል፡፡34እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል የናስ ቀስቶች መሳብ እንዲችሉ ክንዶቼን ያበረታል፡፡35የማዳን ጋሻህን ሰጠኸኝ፤ ቀኝ እጅህ ደግፎኛል፤ ሞገስህም ታላቅ አድርጐኛል፡፡36እግሮቼ እንዳይንሸራተቱ ከበታቼ ያለውን ቦታ አሰፋህልኝ፡፡37ጠላቶቼን አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፤ እስኪጠፉ ድረስ ወደ ኃላ አልልም፡፡38እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቀቅኋቸው ከእግሬም ሥር ወደቁ፡፡39አንተ ለጦርነት ኃይልን አስታጠቅኸኝ፤ በእኔ ላይ የተነሡትንም ከበታቼ አደረግህልኝ፡፡40ጠላቴቼ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ የሚጠሉኝንም አጠፋኋቸው፡፡41ለእርዳታ ጮኹ፤ ግን ማንም አላዳናቸውም ወደ ያህዌ ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም፡፡42ነፋስ ጠርጐ እንደሚወስደው ትቢያ አደቀቅኋቸው መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ረጋገጥኋቸው፡፡43ከሕዝብ ክርክር ታደገኸኝ፤ መንግሥታት ላይ መሪ አደረግኸኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ያገለግለኛል፡፡44ዝናዬን እንደ ሰሙ ታዘዙልኝ፤ ባዕዳንም በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አደረጉ፡፡45ባዕዳን በፍርሃት ተዋጡ እየተንቀጠቀጡም ከምሽጋቸው ወጥተው መጡ፡፡46ያህዌ ሕያው ነው፤ ዐለት የሆነልኝ ይባረክ የድነቴ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል፡፡47እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ ሕዝቦችን ከእግሬ ሥር የሚያስገዛልኝም እርሱ ነው፡፡48ከጠላቶቼም የሚታደገኝ እርሱ ነው! በእርግጥም አንተ ከተነሡብኝ በላይ ከፍ አደረግኸኝ! ከጨካኞችም አዳንኸኝ፡፡49ያህዌ ሆይ፣ ስለዚህ ለአንተ ውዳሴ እሰጣለሁ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ፡፡50እግዚአብሔር ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል ለቀባው ለዳዊትና ለዘሮቹም ለዘላለም ታማኝነቱን ይገልጣል፡፡
1ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይ ጠፈርም የእጁን ሥራ ያውጃል።2አንዱ ቀን ለሌላው ቀን ቃል ይናገራል፤ አንዱም ሌሊት ለሌላው ሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፡፡3ንግግር የለም፤ ቃልም የለም፤ ድምፃቸውም አልተሰማም፡፡4ያም ሆኖ ቃላቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ፣ ንግግራቸውም ወደ ዓለም ዳርቻ ወጣ፡፡ በመካከላቸውም ለፀሐይ ድንኳኑን ተከለ5ፀሐይ ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ ይወጣል ወደ ግቡም እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል፡፡6ፀሐይ ከአንዱ አድማስ ሰማይን አቋርጦ ወደ ሌላው አድማስ ይወጣል፤ ከሙቀቱም የሚሰወር የለም፡፡7የያህዌ ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን መልሶ ያለመልማል፤ የያህዌ ምስክር የታመነ ነው፤ ዐላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል።8የያህዌ ሕግ ትክክል ነው፤ ልብን ደስ ያሰኛል፡፡ የያህዌ ትእዛዝ ንጹሕ ነው፤ ዐይንንም ያበራል፡፡9ያህዌን መፍራት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡ የያህዌ ፍርድ የታመነ ነው፤ ሁለንተናውም ጽድቅ ነው፡፡10ከወርቅ ይልቅ የከበረ፤ እጅግ ከጠራ ወርቅም የበለጠ ነው፡፡ ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤ ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል፡፡11እንዲሁም አገልጋይህ በእርሱ ይመከራል፤ ሕግህን በመጠበቁም ወሮታ አለው፡፡12ስሕተቱን ሁሉ ማን ማስተዋል ይችላል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ፡፡13ባርያህን ከድፍረት ኃጢአት ጠብቅ ያኔ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቅ በደልም እነጻለሁ፡፡14ዐለቴና አዳኜ ያህዌ ሆይ፣ የአፌ ቃልና የልቤም ሐሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን፡፡
1በመከራ ቀን ያህዌ ይስማህ የያዕቆብም አምላክ ይጠብቅህ፡፡2ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ3መባህን ሁሉ ያስብልህ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ፡፡4የልብህን መሻት ይስጥህ ዕቅድህንም ሁሉ ያሳካልህ፡፡5በአንተ ደስ ይለናል በአምላካችንም ስም ዐርማችን ከፍ ከፍ እናደርጋለን፡፡ ያህዌ የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ፡፡6ያህዌ የቀባውን እንደሚያድን አሁን ዐወቅሁ፤ ማዳን በሚችለው ቀኝ እጁ ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል፡፡7አንዳንዶች በሰረገላ ሌሎች በፈረስ ይታመናሉ እኛ ግን የያህዌን ስም እንጠራለን፡፡8እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ እኛ ግን ተነሣን፤ ቀጥ ብለንም ቆምን!9ያህዌ ሆይ፣ ንጉሡን አድን ስንጠራህ እኛንም ሰማን፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ንጉሥ በኃይልህ ደስ ይለዋል! በምትሰጠውም ድል እጅግ ሐሤት ያደርጋል፡፡2የልቡን መሻት ሰጠኸው፤ የለመንህንም አልከለከልኸውም፡፡ ሴላ3ብዙ በረከት ሰጠኸው፤ በራሱ ላይ የንጹሕ ወርቅ ዘውድ አደረግህለት፡፡4ሕይወትን ለመነህ አንተም ረጅም ዘመንን ለዘላለም ሰጠኸው5ከሰጠኸው ድል የተነሣ ክብሩ እጅግ በዛ ክብርንና ሞገስንም አጐናጸፍኸው፡፡6ዘላለማዊ በረከት ሰጠኸው በፊትህ ባለው ፍስሐም ደስ አሰኘኸው፡፡7ንጉሡ በያህዌ ተማምኖአልና ከልዑል ታማኝነት የተነሣ ከቶውንም አይናወጥም፡፡8እጅህ ጠላቶችህን ትይዛቸዋለች ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፡፡9በቁጣህ ቀን እሳት በሚንቀለቀልበት ምድጃ ታቃጥላቸዋለህ፤ ያህዌ በመዓቱ ይፈጃቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል፡፡10ትውልዳቸውን ከምድር ላይ ታጠፋለህ ዘራቸውንም ከሰዎች መካከል ለይተህ ትደመስሳለህ፡፡11በአንተ ላይ ክፋት ቢያስቡም፣ ሤራ ቢያውጠነጥኑም፣ አይሳካላቸውም፡፡12በመጡበት ትመልሳቸዋለህና ቀስትህንም በእነርሱ ላይ ታነጣጥራለህ፡፡13ያህዌ ሆይ፣ በብርታትህ ከፍ ከፍ በል እኛም ኃይልህን እንዘምራለን፤ እንወድሳለንም፡፡
1አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ለማዳን፣ ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?2አምላኬ ሆይ፣ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፣ አንተ ግን አልመለሰህልኝም በሌሊት እንኳ አላረፍሁም፡፡3አንተ ቅዱስ ነህ በእስራኤል ምስጋና ውስጥ እንደ ንጉሥ ትቀመጣለህ፡፡4አባቶቻችን በአንተ ተማመኑ፣ በአንተ ተማመኑ አንተም ታደግሃቸው፡፡5ወደ አንተ ጮኹ፤ እነርሱም ዳኑ በአንተ ተማመኑ፤ እነርሱም አላፈሩም፡፡6እኔ ግን ትል እንጂ፣ ሰው አይደለሁም ለሰዎች ማላገጫ፣ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ፡፡7የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል ራሳቸውንም እየነቀነቁ ያፌዙብኛል፡፡8«በያህዌ ተማምኖአል፤ ያህዌ ያድነው፤ በእርሱ ደስ ተሰኝቶበታልና እስቲ ይታደገው» ይላሉ፡፡9አንተ ከእናቴ ማሕፀን አወጣኸኝ በእናቴም ጡት ሳለሁ በአንተ እንድታመን አደረግኸኝ፡፡10ከማሕፀን ጀምሮ በአንተ ተጣልሁ በእናቴ ማሕፀን ከነበርኩበት ጊዜ ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ!11መከራ እየተቃረበ ነው የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ፡፡12ብዙ ኮርማዎች ከበቡኝ ኃይለኛ የባሳን ኮርማዎች ዙሪያዬን ቆመዋል፡፡13እንደሚያገሣና እንደሚቦጫጭቅ አንበሳ አፋቸውን ከፈቱብኝ፡፡14እንደ ውሃ ፈሰሰሁ አጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ ልቤ እንደ ሰም ሆነ በውስጤም ቀጠለ፡፡15ጉልበቴ እንደ ሸክላ ደረቀ ምላሴም ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፡፡ እንደ ሞተ ሰው ትቢያ ላይ አደረግኸኝ፡፡16ውሾች ከበቡኝ የክፉዎች ስብስብ በዙሪያዬ ሰፈሩ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩ17ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ አንድ መቁጠር እችላለሁ እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል፡፡18ልብሶቼን ተከፋፈሉ በእጄ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉ፡፡19ያህዌ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ ብርታቴ ሆይ፣ እባክህ እኔን ለመርዳት ፍጠን!20ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት ውድ ሕይወቴንም ከክፉ ውሾች አድናት፡፡21ከአንበሳ አፍ አድነኝ፣ ከተዋጊ ጐሽ ቀንዶችም ታደገኝ፡፡22ስምህን ለወንድሞቼ እናገራለሁ፤ በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ፡፡23እናንት ያህዌን የምትፈሩ አመስግኑት፡፡ እናንት የያዕቆብ ዘሮች ሁሉ አክብሩት! እናንት የእስራኤል ልጆች ሁሉ እርሱን ፍሩት!24ጭንቀት የደረሰበትን ሰው አልናቀም፤ መከራ ላይ ያለውን አልተጸየፈም፤ ነገር ግን የድረሱልኝ ጩኸቱን ሰማው፡፡25ስለ ሠራኸው መልካም ሥራ፣ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ፤ በሚፈሩህ ሰዎችም ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ፡፡26ችግረኞች ይበላሉ፤ ይጠግባሉም ያህዌን የሚፈልጉም ያመሰግኑታል፡፡ ልባችሁ ለዘላለም ሕያው ይሁን፡፡27የምድር ሕዝቦች ሁሉ ያስታውሳሉ ወደ ያህዌም ይመለሳሉ፤ የምድር ወገኖች ሁሉ በፊትህ ወድቀው ይሰግዳሉ፡፡28መንግሥት የያህዌ ነውና ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው፡፡29የምድር ከበርቴዎች ሁሉ ይበላሉ፤ እርሱንም ያመልካሉ በሕይወት ማቆየት የማይችሉ ወደ አፈር ተመላሽ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በፊቱ ይንበረከካሉ፡፡30የሚመጣው ትውልድ ያገለግለዋል ለቀጣዩ ትውልድም ስለ ጌታ ይነግረዋል31የጽድቅ ሥራውን በማወጅ ገና ላልተወለደ ሕዝብ ጽድቁን፣ እርሱ ያደረገውንም ይነግራሉ፡፡
1ያህዌ እረኛዬ ነው፤ ምንም አላጣም፡፡2በለመለመ መስክ ያሳድረኛል ፀጥ ባለ ውሃ ዘንድ ይመራኛል፡፡3ነፍሴን ይመልሳታል፤ ያድሳታል፡፡ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ ይመራኛል፡፡4በጨለማው የሞት ሸለቆ ውስጥ እንኳ ባልፍ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፡፡5በጠላቶቼ ፊት ለፊት በፊቴ ገበታ አዘጋጀህልኝ ራሴን በዘይት ቀባህ ጽዋዬ ሞልቶ ተርፏል፡፡6በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ደግነትና ፍቅር ዘወትር ከእኔ ጋር ይሆናሉ፤ በያህዌም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ፡፡
1ምድርና በእርሷ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የያህዌ ነው፡፡2እርሱ ባሕር ላይ መሥርቶአታልና በውሆችም ላይ አጽንቶአታል፡፡3ወደ ያህዌ ተራራ ማን ይወጣል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?4ንጹሕ እጅና ንጹሕ ልብ ያለው፣ ነፍሱን ለሐሰት ያላስገዛ በሐሰት የማይምል፣5እርሱ ከያህዌ ዘንድ በረከትን፣ ከመድኃኒቱም አምላክ ጽድቅን ይቀበላል፡፡6እርሱን የሚፈልግ ትውልድ የያዕቆብ አምላክን ፊት የሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው፡፡ ሴላ7እናንተ ደጆች ራሳችሁን ቀና አድርጉ እናንተ የዘላለም በሮች የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!8ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ብርቱና ኃያል የሆነው ያህዌ፣ በጦርነት አሸናፊ የሆነው ያህዌ ነው፡፡9እናንተ ደጆች ራሳችሁን ቀና አድርጉ እናንተ የዘላለም በሮች የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የሰራዊት ጌታ ያህዌ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው፡፡ ሴላ
1ያህዌ ሆይ፣ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁ!2አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፡፡ እባክህ አታሳፍረኝ፤ አታዋርደኝ ጠላቶቼም በእኔ ላይ ደስ እንዲላቸው አታድርግ፡፡3አንተን ተስፋ የሚያደርጉ ከቶ አያፍሩም፤ እንዲያው ያለ ምክንያት የሚያታልሉ ግን ያፍራሉ፡፡4ያህዌ ሆይ፣ አካሄድህን አሳውቀኝ መንገድህንም አስተምረኝ፡፡5በእውነትህ ምራኝ አስተምረኝም፤ አንተ የድነቴ አምላክ ነህና ቀኑን ሙሉ በአንተ ታመንሁ፡፡6ያህዌ ሆይ፣ ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ምሕረትህንና ፍቅርህን አስብ፡፡7የልጅነቴን ኃጢአት፣ መተላለፌንም አታስብብኝ፤ ያህዌ ሆይ፣ እንደ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህም መጠን አስበኝ፡፡8ያህዌ መልካም ቅን ነው፤ ስለዚህ ኃጢአተኞችን መንገድን ያስተምራቸዋል፡፡9ትሑታንን በትክክለኛው መንገድ ይመራቸዋል መንገዱንም ያስተምራቸዋል10ኪዳኑንና ሥርዐቱን ለሚጠብቁ የያህዌ መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው፡፡11ያህዌ ሆይ፣ ኃጢአቴ እጅግ ብዙ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ12ያህዌን የሚፈራ ሰው ማን ነው ጌታ በመረጠው መንገድ ያስተምረዋል፡፡13ዘመኑን በተድላ ደስታ ያሳልፋል ዘሮቹም ምድርን ይወርሳሉ፡፡14ያህዌ ለሚታዘዙት ሁሉ ወዳጃቸው ነው ለእነርሱ የገባውንም ኪዳን ያጸናል፡፡15ዐይኖቼ ዘወትር ወደ ያህዌ ናቸው እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነው፡፡16እኔ ብቸኛና ምስኪን ነኝና ወደ እኔ ተመለስ ማረኝም፡፡17የልቤ ሐዘን በዝቶአል ከጭንቀቴ አወጣኝ፡፡18መከራዬንና ጭንቀቴን ተመልከት ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በል፡፡19ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ እይ፤ እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ ተመልከት፡፡20ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም በአንተ ተማምኛለሁና አልዋረድ፤ አልፈር፡፡21አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ22ያህዌ ሆይ፣ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ያለ ነቀፋ ተመላልሻለሁና አንተው ፍረደኝ፤ ያለ ማወላውል በያህዌ ተማምኛለሁ፡፡2ያህዌ ሆይ፣ ፈትነኝ መርምረኝም የልቤንና የውስጤን ንጽሕና ፈትን!3የኪዳን ታማኝነትህ ዘወትር በፊቴ ነው በታማኝነትህም ተመላለስሁ፡፡4ከአታላይ ሰዎች ጋር አልተባበርሁም ከማይታመኑ ሰዎችም ጋር አልተቀላቀልሁም፡፡5የክፉዎችን ኅብረት ጠላሁ ከዐመፀኞችም ጋር አልተቀመጥሁም፡፡6እጆቼን በየዋህነት እታጠባለሁ ያህዌ ሆይ፣ መሠዊያህንም እዞራለሁ7የምስጋናህን መዝሙር እየዘመርሁ ድንቅ ሥራዎችህን ሁሉ አወራለሁ፡፡8ያህዌ ሆይ፣ የምትኖርበትን ቤት፣ የክብርን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ፡፡9ነፍሴን ከኃጢአተኞች ጋር፣ ሕይወቴንም ደም ከተጠሙ ጋር አታጥፉ10በእነርሱ እጅ የተንኰል ዕቅድ አለ ቀኝ እጃቸውም ጉቦ ያጋብሳል፡፡11እኔ ግን በታማኝነት እጓዛለሁ አድነኝ፤ ምሕረትም አድርግልኝ፡፡12እግሮቼ በተስተካከለ ምድር ላይ ቆመዋል በጉባኤ ፊት ያህዌን እባርካለሁ፡፡
1ያህዌ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው? ያህዌ የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?2ክፉ አድራጊዎች ሥጋዬን ለመብላት በቀረቡኝ ጊዜ፣ ባላጋራዎቼና ጠላቶቼ ተሰነካክለው ወደቁ፡፡3ሰራዊት ቢከብበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ ልበ ሙሉ ነኝ፡፡4ያህዌን አንዲት ነገር ለመንሁት፣ እርሷንም እሻለሁ፤ ያም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በያህዌ ቤት እንድኖር፣ የመቅደሱን ውበት እንዳይና መቅደሱ ውስጥ አሰላስል ዘንድ ነው፡፡5በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ይሰውረኛናል በዐለትም ላይ ያቆመኛል፡፡6ያኔ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ ራሴ ከፍ ከፍ ይላል በድንኳኑም የደስታ መሥዋዕት እሠዋለሁ ለያህዌ እቀኛለሁ፤ እዘምርለታለሁም፡፡7ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ ስጮኽ ድምፄን ስማ ማረኝ መልስልኝም፡፡8«ፊቴን ፈልጉ» ባልህ ጊዜ ልቤ፣ «የያህዌን ፊት እፈልጋለሁ» አለች፡፡9ፊትህን ከእኔ አትሰውር ተቆጥተህም ባርያህን ገሸሽ አታድርገው! መቼም አንተ ረዳቴ ነህና የመድኃኒቴ አምላክ ሆይ፣ አትተወኝ፣ አትጣለኝም10አባትና እናቴ ቢተውኝ እንኳ ያህዌ ይቀበለኛል፡፡11ያህዌ ሆይ መንገድህን አስተምረኝ ስለ ጠላቶቼም በቀናች መንገድ ምራኝ፡፡12ሐሰተኛ ምስክሮች ተነሥተውብኛልና ጠላቶቼ እንደ ፈለጉ እንዲያደርጉብኝ አትተወኝ፡፡ እነርሱ ዐመፃን ይረጫሉ!13በሕያዋን ምድር የያህዌን መልካምነት እንደማይ ባላምን ኖሮ ምን እሆን ነበር?14እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ አይዞህ በርታ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ
1ያህዌ ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ዐለቴ ሆይ፣ ችላ አትበለኝ፡፡ አንተ ዝም ካልኸኝ ወደ መቃብር ከሚወርዱ ጋር እሆናለሁ፡፡2እንድትረዳኝ ወደ አንተ በጮኽኩ ጊዜ እጆቼን ወደ ቅዱስ ማደሪያህ በዘረጋሁ ጊዜ የልመኛዬን ቃል ስማ፡፡3ከዐመፀኞች ጋር፣ ክፋትን ከሚያደርጉ ጋር፣ በልባቸው ክፉ ሐሳብ እያለ ከባልንጀራቸው ጋር በሰላም ከሚናገሩ ጋር ጐትተህ አትውሰደኝ፡፡4የእጃቸውን ስጣቸው፣ እንደ ዐመፃቸውም ክፈላቸው እንደ ክፉ ተግባራቸው መልስቸው፡፡5ለያህዌ ሥራ ግድ ስለሌላቸው፣ ለእጆቹም ተግባር ስፍራ ስላልሰጡ እርሱ ያፈርሳቸዋል፤ መልሶም አይሠራቸውም፡፡6የልመናዬን ቃል ሰምቶአልና ያህዌ ይባረክ፡፡7ያህዌ ብርታቴና ጋሻዬ ነው ልቤ በእርሱ ይተማመናል፤ እርሱም ረዳኝ፡፡ ስለዚህ ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ፡፡8ያህዌ የሕዝቡ ብርታታቸው ነው ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው፡፡9ሕዝብህን አድንን ርስትህንም ባርክ እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ተንከባከባቸው፡፡
1እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ለያህዌ ምስጋና ስጡ ስለ ክብሩና ስለ ብርታቱ ለያህዌ ምስጋና ስጡ፡፡2ለስሙ የሚገባውን ክብር ለያህዌ ስጡ በቅድስናው ውበት ለያህዌ ስገዱ3የያህዌ ድምፅ በውሆች ላይ ያስተጋባል የክብር አምላክ ያንጐዳጉዳል ያህዌ በብዙ ውሆች ላይ ድምፁን ያሰማል፡፡4የያህዌ ድምፅ ኃያል ነው የያህዌ ድምፅ ባለ ግርማ ነው፡፡5የያህዌ ድምፅ የሊባኖስን ዝግባ ይሰብራል6ሊባኖን እንደ ጥጃ፣ ስርዮንን እንደ ኮርማ ያዘልላል፡፡7የያህዌ ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል8የያህዌ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል የያህዌ ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል፡፡9የያህዌ ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል ጫካዎችን ይመነጥራል፡፡ ሁሉም በእርሱ ቤተ መቅደስ፣ «ክብር!» ይላል፡፡10ያህዌ በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል ያህዌ ለዘላለም ይነግሣል፡፡11ያህዌ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል ያህዌ ሕዝቡን በሰላም ይባርካል፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ አንተ አንሥተኸኛልና ጠላቶቼም በእኔ ላይ ደስ እንዲላቸው አላደረግህምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፡፡2ያህዌ ሆይ፣ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ጮኽሁ አንተም ፈውሰኸኝ፡፡3ያህዌ ሆይ፣ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ወደ መቃብር ከመውረድም አዳንኸኝ፡፡4እናንት የእርሱ ታማኝ ሕዝቦች ለያህዌ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፤ ቅድስናውን ስታስታውሱ፣ ውዳሴ ስጡ፡፡5ቁጣው ለአጭር ጊዜ ነው ሞገሱ ግን ለዕድሜ ልክ ነው፡፡ ሌሊት ሲለቀስ አድሮ ማለዳ ደስታ ይሆናል፡፡6በልበ ሙሉነት «አልናወጥም!» አልሁ፡፡7ያህዌ ሆይ በሞገስህ እንደ ተራራ ብርቱ አደረግኸኝ ፊትህን ስትሰውር ግን ውስጤ ታወከ፡፡8ያህዌ፣ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ከጌታም ዘንድ ሞገስ ፈለግሁ፡፡9እኔ ብሞት፣ ወደ መቃብርም ብወርድ ምን ጥቅም አለው? አፈር ያመሰግንሃልን? ታማኝነትህንስ ይናገራልን?10ያህዌ ሆይ፣ ስማኝ ማረኝም፣ ያህዌ ረዳት ሁነኝ፡፡11ዋይታዬን ወደ ሽብሸባ ለወጥህልኝ ማቄን አስወግደህ ደስታን አለበስከኝ፡፡12እንግዲህ፣ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፡፡ አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ አንተን ተማጽኛለሁና እፍረት ከቶ አይድረስብኝ፤ በጽድቅህም ታደገኝ፡፡2ጌታ ሆይ፣ አድምጠኝ ፈጥነህም ታደገኝ የመማጸኛ ዐለት፣ የመዳኛም ምሽግ ሁነኝ፡፡3አንተ ዐለቴና ዐምባዬ ነህ ስለ ስምህ ስትል ምራኝ መንገዱንም አሳየኝ፡፡4አንተ መታመኛዬ ነህና በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ፡፡5መንፈሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ የእውነት አምላክ ያህዌ ሆይ፣ ተቤዠኝ፡፡6ከንቱ ጣዖታትን የሚያገለግሉትን ጠላሁ እኔ ግን በያህዌ እታመናለሁ፡፡7መከራዬን አይተሃልና የነፍሴን ጭንቀት ዐውቀሃልና እኔ በኪዳን ታማኝነትህ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አድርጋለሁ፡፡8በጠላቴ እጅ አሳልፈህ አልሰጠኸኝም እግሮቼን ሰፊ ቦታ ላይ አቆምሃቸው፡፡9ያህዌ ሆይ፣ ጭንቀት ውስጥ ነኝና ማረኝ ዐይኖቼ በሐዘን ደክመዋል፤ ነፍስና ሥጋዬም ዝለዋል፡፡10ሕይወቴ በጭንቀት ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፡፡ ከኃጢአቴ የተነሣ ጉልበቴ ከዳኝ ዐጥንቴም ደቀቀ፡፡11ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ ለጐረቤቶቼ መዘባበቻ ለሚያውቁኝ ሰዎች መሳለቂያ ሆኛለሁ መንገድ ላይ የሚያገኙኝም ይሸሹኛል፡፡12ማንም እንደማያስበው እንደ ሞተ ሰው ተረሳሁ እንደ ተሰበረ የሸክላ ዕቃም ተቆጠርሁ፡፡13የብዙዎችን ሹክሹክታ ሰምቻለሁ በዙሪያዬም የሽብር ወሬ አለ በእኔ ላይ ባሤሩ ጊዜ ሕይወቴን ለማጥፋት ዶለቱ፡፡14እኔ ግን ያህዌ ሆይ፣ በአንተ እተማመናለሁ «አንተ አምላኬ ነህ» አልሁ፡፡15ዘመኔ ሁሉ በእጅህ ነው፡፡ ከጠላቶቼና ከሚያሳድዱኝ ሰዎች እጅ አድነኝ፡፡16ፊትህን ባርያህ ላይ አብራ፡ በኪዳን ታማኝነትህ አድነኝ፡፡17ያህዌ ሆይ፣ አንተን ጠርቻለሁና ለእፍረትና ለውርደት አትዳርገኝ፡፡ ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ ይዋረዱ ሲኦል ገብተው ጸጥ ይበሉ፡፡18ጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩ ትዕቢትና ንቀትን የተሞሉ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ፡፡19ለሚፈሩህ የሰወርኸው፣ በአንተም ለሚታመኑ በሰው ልጆች ሁሉ ፊት የምታደርገው እንዴት ታላቅ ነው!20ከሰዎች ሤራ በማደሪያህ ውስጥ ትሸሽጋቸዋለህ፡፡21በተከበበች ከተማ ለእኔ ድንቅ ታማኝነቱን የገለጠ ያህዌ ይባረክ፡፡22እኔ ግን ባለ ማስተዋል፣ «ከእንግዲህ ከዐይንህ ፊት ተወግጃለሁ» ብዬ ነበር፤ ሆኖም፣ አንተ እንድትረዳኝ ስጮኽ ሰማኸኝ፡፡23እናንተ ታማኝ ተከታዮቹ ሁሉ ያህዌን ወደዱት ያህዌ ታማኞችን ይጠብቃል ለእብሪተኞች ግን የእጃቸውን ይሰጣቸዋል፡፡24እግዚአብሔርን ተስፋ የምታደርጉ ሁሉ በርቱ ልባችሁም ይጽና፡፡
1መተላለፉ ይቅር የተባለለት ኃጢአቱም የተሸፈነለት ሰው ቡሩክ ነው፡፡2ያህዌ በደሉን የማይቆጥርበት በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው ቡሩክ ነው፡፡3ቀኑን ሙሉ በመቃተቴ ዝም ባልሁ ጊዜ፣ አጥንቶቼ ተበላሹ፡፡4ቀኑን ሙሉ እጅህ ከብዳኛለች ብርታቴም የበጋ ትኩሳት እንደ መታው ነገር ከውስጤ ተሟጠጠ፡፡ ሴላ5በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝሁ በደሌንም ከአንተ አልሰወርሁም ደግሞም፣ «መተላለፌን ለያህዌ እናዘዛለሁ» አልሁ አንተም የኃጢአቴን በደል ይቅር አልህ፡፡ ሴላ6ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ ብርቱ ጐርፍ ሞልቶ ቢያጥለቀቅ እንኳ፣ ወደ እነዚህ ሰዎች አይቀርብም፡፡7አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራም ታወጣኛለህ፡፡ በድል ዝማሬ ትከበኛለህ፡፡ ሴላ8አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበት መንገድ እመራሃለሁ እመክርሃለሁ ዐይኔንም አንተ ላይ አደርጋለሁ፡፡9ወደምትፈልጉት ቦታ እንዲሄዱላችሁ በልጓምና በልባብ እንደሚገሩት ማስተዋል እንደሌለው ፈረስና በቅሎ አትሁኑ፡፡10የክፉዎች ሐዘን ይበዛል በያህዌ የሚታመነውን ግን የእርሱ ኪዳን ታማኝነት ይከብበዋል፡፡11ጻድቃን ሆይ፣ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ልበ ቅኖች ሆይ፣ እልል በሉ፡፡
1ጻድቃን ሆይ፣ በያህዌ ደስ ይበላችሁ ቅኖች ሊያመሰግኑት ይገባል፡፡2ያህዌን በመሰንቆ አመስግት ዐሥር አውታር ባለው በገና ዘምሩለት፡፡3አዲስ ዝማሬ አቅርቡለት ባማረ ቅኝት በገና ደርድሩ፤ እልልም በሉ፡፡4የያህዌ ቃል እውነት ነው ሥራውም ሁሉ የታመነ ነው፡፡5እርሱ ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል ምድር በያህዌ ኪዳን ታማኝት ተሞልታለች፡፡6ያህዌ ሰማያትን በቃሉ የሰማይ ሰራዊትን በአፉ እስትንፋስ ፈጠረ፡፡7የባሕርን ውሆች እንደ ክምር ቀላዩንም በመከማቻ ስፍራ አኖረ፡፡8ምድር ሁሉ ያህዌን ትፍራው በዓለም ያሉ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ፡፡9እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤ እርሱ አዞአልና በስፍራቸው ጸኑ፡፡10ያህዌ የሕዝቦችን ምክክር ያጨናግፋል ዕቅዳቸውንም ከንቱ ያደርጋል፡፡11የያህዌ ዕቅድ ግን ለዘላለም ይኖራል የልቡም ሐሳቡም ለትውልድ ሁሉ ነው፡፡12ያህዌ አምላኩ የሆነለት፣ ርስቱ እንዲሆን የመረጠውም ሕዝብ ቡሩክ ነው፡፡13ያህዌ ከሰማይ ይመለከታል የሰው ልጆችንም ሁሉ ያያል፡፡14ከማደሪያው ሆኖ፣ በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ይመለከታል፡፡15የሁሉንም ልብ የሠራ እርሱ ነው የሚያደርጉትንም ሁሉ ይመለከታል፡፡16ንጉሥ በሰራዊቱ ብዛት አይድንም፤ ጀግናም በኃይሉ ብርታት አያመልጥም፡፡17በፈረስ ድል አደርጋለሁ ማለት ከንቱ ተስፋ ነው፤ በብርቱ ጉልበቱም ማንም አይድንም18እነሆ፣ የያህዌ ዐይኖች በሚፈሩት ላይ ናቸው፤ በኪዳን ታማኝነቱ በሚታመኑት ላይ አትኩረዋል፡፡19ይህም የሚሆነው ከሞት ሊያድናቸውና ከራብ ዘመንም ሊጠብቃቸው ነው፡፡20ያህዌን በተስፋ እንጠብቃለን እርሱ ረድኤታችንና ጋሻችን ነው፡፡21በቅዱስ ስሙ ተማምነናልና ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋል፡፡22ያህዌ ሆይ፣ ተስፋችንን አንተ ላይ አድርገናልና ምሕረትህ በእኛ ላይ ይሁን፡፡
1ያህዌን ሁልጊዜ አመሰግናለሁ ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው፡፡2ያህዌን አመሰግናለሁ! ትሑታን ይህን ሰምተው ደስ ይበላቸው፡፡3ያህዌን ከእኔ ጋር አመስግኑት በአንድነት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ፡፡4ያህዌን ፈለግሁ እርሱም መለሰልኝ ከፍርሃቴም ሁሉ አዳነኝ፡፡5ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ ፊታቸውም በፍጹም አያፍርም፡፡6ይህ ችግረኛ ጮኸ እግዚአብሔርም ሰማው ከመከራውም ሁሉ አዳነው፡፡7የያህዌ መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸዋልም፡፡8ያህዌ መልካም መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፡፡ በእርሱ የተማመነ ሰው ቡሩክ ነው፡፡9እናንተ ቅዱሳን ያህዌን ፍሩ እርሱን የሚፈሩ አንዳች አያጡምና፡፡10አንበሶች ሊያጡ ሊራቡም ይችላሉ ያህዌን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም፡፡11ልጆቼ ሆይ፣ ኑ ስሙኝ ያህዌን መፍራት አስተምራችኋለሁ፡፡12ሕይወትን የሚወድ፣ መልካም ነገርን ለማየት ረጅም ዕድሜ የሚፈልግ ማነው?13እንግዲያስ አንደበትህን ከክፉ ከልክል ከንፈርህንም ከውሸት ጠብቅ፡፡14ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ ሰላምን ፈልጋት ደግሞም ተከተላት፡፡15የያህዌ ዐይኖች ጻድቃን ላይ ናቸው፡፡ ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ተከፍተዋል፡፡16መታሰቢያቸውን ከምድር ላይ ለማጥፋት የያህዌ ፊት ክፉ በሚያደርጉ ላይ ነው። 17ጻድቃን ወደ ያህዌ ይጮኻሉ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል፡፡18ያህዌ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል፡፡19የጻድቅ መከራው ብዙ ነው ያህዌ ግን ከሁሉም ያድነዋል፡፡20ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም፡፡21ኃጢአተኛን ክፋት ይገድለዋል ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈርድባቸዋል፡፡22ያህዌ የባርያዎቹን ነፍስ ይታደጋል እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ የሚቃወሙኝን ተቃወማቸው፤ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው፡፡2ትልቁንና ትንሹን ጋሻ ያዝ እኔንም ለመርዳት ተነሥ፡፡3በሚያሳድዱኝ ላይ ጦርና ሰይፍህን ምዘዝና ነፍሴን «እኔ አዳኝሽ ነኝ» በላት፡፡4ሕይወቴን የሚፈልጓት ይፈሩ ይዋረዱም እኔን ለመጉዳት የሚያደቡ አፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ፤ ግራ ይጋቡ፡፡5በነፋስ ፊት እንዳለ እብቅ ይሁኑ የያህዌም መልአክ ያሳድዳቸው፡፡6መንገዳቸው ጨለማና ድጥ ይሁን የያህዌ መልአክ ያባርራቸው፡፡7ያለ ምክንያት ወጥመድ ዘርግተውብኛል ያለ ምክንያት ሕይወቴን ለማጥፋት ጉድጓድ ቆፍረዋል፡፡8ጥፋት በድንገት ይምጣባቸው የዘረጉት ወጥመድ ይያዛቸው ጉድጓድ ውስጥ ወድቀው ይጥፉ፡፡9እኔ ግን በያህዌ ደስ ይለኛል በማዳኑም ሐሤት አደርጋለሁ፡፡10ዐጥንቶቼ ሁሉ፣ «ያህዌ ሆይ፣ ድኻውን ከእርሱ ከሚበረቱ፣ ችግረናውንና ምስኪኑን ከቀማኞች እጅ የሚያድን እንደ አንተ ያለ ማን ነው?» እለዋለሁ፡፡11ሐሰተኛ ምስክሮች ተነሥተውብኛል በሐሰትም ይከስሱኛል፡፡12እኔን ብቸኛ አድርገው በመልካም ፈንታ ክፉ መለሱልኝ፡፡13እኔ ግን እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፤ ለእነርሱ ጾምሁ፤ አንገቴን ደፋሁ፡፡14ለወንድሙ እንደሚያለቅስ ሰው አዘንሁ ለእናቱ ልጅ እንደሚያዝን ሰው ሆንሁ፡፡15እኔ በተሰናከልሁ ጊዜ ደስ ብሎአቸው ተሰበሰቡ ግፈኞች በድንገት ተሰበሰቡብኝ ያለ ዕረፍትም ቦጫጨቁኝ፡፡16እንደ ምናምንቴዎች አፌዙብኝ ጥርሳቸውንም አፋጩብኝ፡፡17ጌታ ሆይ፣ እስከ መቼ ዝም ብለህ ታያለህ? ነፍሴን በእነርሱ ከመጠቃት ሕይወቴንም ከአንበሶች አድናት፡፡18በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበትም እወድስሃለሁ፡፡19ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዲላቸው፣ ተንኰላቸውንም እንዲፈጽሙብኝ አታድርግ፡፡20የሰላም ቃል ከአፋቸው አይወጣም ነገር ግን በምድሪቱ በጸጥታ በሚኖሩት ላይ ተንኮል ይሸርባሉ፡፡21አፋቸውን አስፍተው በመክፈት፣ «እሰይ! እሰይ! በዐይናችን አየነው» አሉ፡፡22ያህዌ ሆይ፣ ይህን አይተሃልና ዝም አትበል ጌታ ሆይ፣ ለእኔም አትራቅ፡፡23አምላኬ ጌታዬ፣ ለእኔ ለመሟገት ተነሥ ልትከራከርልኝም ተንቀሳቀስ፤24ያህዌ ሆይ፣ በጽድቅህ ፍረድልኝ በእኔም ላይ ደስ አይበላቸው፡፡25በልባቸው፣ «እሰይ፣ ያሰብነው ተሳካ» አይበሉ፤ «ዋጥ አደረግነውም» አይበሉ፡፡26በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፡፡ በእኔ ላይ የሚያፌዙ፤ እፍረትና ውርደት ይልበሱ፡፡27ፍትሕ ማግኘቴን የሚፈልጉ እልል ይበሉ ሐሤትም ያድርጉ፣ ዘወትርም፣ «የባርያው ሰላም ደስ የሚለው ያህዌ ይመስገን» ይበሉ፡፡28ያኔ የአንተን ጽድቅ እናገራለሁ ቀኑን ሙሉ አመሰግንሃለሁ፡፡
1ክፉ ሰው በልቡ፣ ክፋትን ያስባል በዐይኖቹም ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም፡፡2በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ እያሰበ ራሱን ይሸነግላል፡፡3ንግግሩ ተንኰልንና ሐሰትን የተሞላ ነው፤ አስተዋይ መሆንንና መልካም ማድረግን አይፈልግም፡፡4በመኝታው ላይ ክፋት ያውጠነጥናል ራሱን ወደ ክፉ መንገድ ይመራል ክፉውንም ነገር አያርቅም፡፡5ያህዌ ሆይ፣ ታማኝነትህ እስከ ሰማይ እውነተኛነትህም እስከ ደመናት ይደርሳል፡፡6ጽድቅህ እንደ እግዚአብሔር ተራራ ነው ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ ያህዌ ሆይ፣ አንተ ሰውንም እንስሳንም ትጠብቃለህ፡፡7እግዚአብሔር ሆይ፣ ታማኝነትህ እንዴት ክቡር ነው! የሰው ልጆች ሁሉ በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ፡፡8ከቤትህ ሲሳይ ተመግበው ይጠግባሉ፤ ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ፡፡9በአንተ ዘንድ የሕይወት ምንጭ አለ በአንተ ብርሃን ብርሃን እናያለን፡፡10ለሚያውቁህ ምሕረትህ፣ ልባቸውም ለቀና ጽድቅህ አይቋረጥባቸው፡፡11የእብሪተኛ እግር አይቅረበኝ የክፉ ሰው እጅም አያሳድደኝ፡፡12ክፉ አድራጊዎች እንዴት እንደ ወደቁ መነሣትም እንደማይችሉ ተመልከት፡፡
1በክፉዎች ምክንያት አትበሳጭ ኃጢአት በሚሠሩም አትቅና፤2እንደ ሣር ቶሎ ይደርቃሉና እንደ ለመለመ ቅጠልም ይጠወልጋሉ፡፡3በያህዌ ተማመን፤ መልካምንም አድርግ በምድሪቱ ተቀመጥ፤ ታምነህም ተሰማራ፡፡4በያህዌ ደስ ይበልህ የልብህንም ፍላጐት ይሰጥሃል፡፡5መንገድህን ለያህዌ አደራ ስጥ በእርሱ ታመን እርሱም ያከናውንልሃል፡፡6ጽድቅህን እንደ ብርሃን ያንተንም ንጽሕና እንደ ቀትር ፀሐይ ያበራዋል፡፡7በያህዌ ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፡፡ ነገር በተሳካለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው አትቅና8አትቆጣ፤ ተስፋም አትቁረጥ መከራን ከማብዛቱ ውጪ ምንም ስለማይጠቅምህ አትከፋ፡፡9ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉ ያህዌን የሚጠባበቁ ግን ምድሪቱን ይወርሳሉ፡፡10ብዙም ሳይቆይ ክፉ ሰው ይጠፋል ብትፈልግም ቦታውን አታገኘውም፡፡11ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ በታላቅ ሰላምም ደስ ይላቸዋል፡፡12ክፉዎች ጻድቃን ላይ ያሤራሉ ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል፡፡13መጥፊያ ቀናቸው እንደ ደረሰ ስለሚያውቅ ጌታ ይስቅባቸዋል፡፡14ድኾችንና ችግረኞችን ለመጣል ልበ ቅኖችንም ለመግደል ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፤ ቀስታቸውንም ገተሩ፡፡15ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል ቀስታቸውም ይሰበራል፡፡16ከክፉ ሰው ብዙ ሀብት ይልቅ፣ የጻድቅ ጥቂት ሀብት ይበልጣል፡፡17የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና ያህዌ ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል፡፡18ያህዌ ያለ ነቀፋ የሚመላለሱትን ዕለት ዕለት ይጠብቃቸዋል፡፡ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል፡፡19በክፉ ቀን አያፍሩም በራብ ዘመንም የሚበሉትን አያጡም፡፡20ክፉዎች ግን ይጠፋሉ የያህዌ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይሆናሉ፡፡ እንደ ጢስም በንነው ይጠፋሉ፡፡21ኃጢአተኛ ይበደራል፣ ግን መልሶ አይከፍልም ጻድቅ ግን በልግስና ይሰጣል፡፡22እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ እርሱ የረገማቸው ግን ይጠፋሉ፡፡23የሰውን አካሄድ የሚያጸና ያህዌ ነው በመንገዱም ደስ ይለዋል፡፡24ያህዌ በእጁ ደግፎ ስለሚይዘው ቢሰናከል እንኳ አይወድቅም፡፡25ጐልማሳ ነበርሁ፤ አሁን አርጅቻለሁ ጻድቅ ሲጣል፣ ዘሩም እንጀራ ስለምን አላየሁም፡፡26ጻድቅ ሁልጊዜ በልግሥና ይሰጣል፣ ደግሞም ያበድራል ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ፡፡27ከክፉ ራቅ መልሙንም አድርግ ለዘላለምም በሰላም ትኖራለህ፡፡28ያህዌ ፍትሕ ይወዳልና ታማኞቹንም በፍጹም አይጥልም፤ ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፡፡ የኃጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል፡፡29ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ በእርሷም ለዘላለም ይኖራሉ፡፡30የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል አንደበቱም ፍትሕን ያወራል፡፡31የአምላኩ ሕግ ልቡ ውስጥ ነው አካሄዱም አይሰናከልም፡፡32ኃጢአተኛው ጻድቅን ይመለከተዋል ሊገድለውም ይፈልጋል፡፡33እግዚአብሔር ግን በእጁ አይጥለውም ፍርድ ፊት ሲቀርቡም አይረታም፡፡34ያህዌን ደጅ ጥና፤ መንገዱንም ጠብቅ እርሱም ምድርን እንድትወርስ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፡፡ ክፉዎች ሲጠፋ ታያለህ፡፡35ክፉና ጨካኙን ሰው ምቹ መሬት ላይ እንዳለ ዛፍ ለምልሞ አየሁት36ተመልሼ ስመጣ ግን በቦታው አልበረም፤ ፈለግሁ ላገኘው ግን አልቻልሁም፡፡37ጻድቅን ሰው ተመልከት ቅን የሆነውንም ሰው እይ የሰላም ሰው ተስፋ አለውና፡፡38ኃጠአተኞች ግን ፈጽሞ ይደመስሳሉ ዘራቸውም ይወገዳል፡፡39የጻድቃን ድነት ከያህዌ ዘንድ ነው በመከራም ጊዜ ይጠብቃቸዋል፡፡40ያህዌ ይረዳቸዋል፤ ደግሞም ይታደጋቸዋል፡፡ ከክፉዎች እጅ ነጥቆ ያወጣቸዋል እርሱን መጠጊያ አድርገዋልና ያድናቸዋል፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ በቁጣህ አትገሥጸኝ በመዓትህም አትቅጣኝ፡፡2ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና እጅህ ተጭናኛለች፡፡3ከቁጣህ የተነሣ መላው አካሌ ታመመ ከኃጢአቴ የተነሣም ዐጥንቶቼ ጤና የላቸውም፡፡4በደሌ ውጦኛል እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል፡፡5በሞኝነት ካደረግሁት የተነሣ ቁስሌ መገለ፤ ሸተተም፡፡6ጐበጥሁ፤ በየቀኑም እያጐነበስኩ ሄድሁ ቀኑን ሙሉ በትካዜ ዋልሁ፡፡7ውስጤ እንደ እሳት ይቃጠላል ሥጋዬም ጤና የለውም፡፡8እንደ ዲዳ ሆንሁ፤ ፈጽሞም ደቀቅሁ ከልቤ ምሬት የተነሣ እቃትታለሁ፡፡9ጌታ ሆይ፣ የጥልቅ ልቤን ናፍቆት አንተ ታውቃለህ መቃተቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም፡፡10ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበት ከድቶኛል የዐይኔም ብርሃን ፈዝዞአል፡፡11ካለሁበት ሁኔታ የተነሣ፣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ ጐረቤቶቼም ርቀው ቆሙ፡፡12ሕይወቴን ማጥፋት የሚወዱ ወጥመድ ዘረጉብኝ ሊጐዱኝ የሚፈልጉም በዛቻ ተናገሩኝ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ፡፡13እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቆሮ ምንም መናገር እንደማይችል ዲዳ ሰው ሆንሁ፡፡14ጆሮው እንደማይሰማ አንደበቱም መልስ መስጠት እንደማይችል ሰው ሆንሁ፡፡15ያህዌ ሆይ፣ በፍጹም ልቤ አንተን እጠብቃለሁ ጌታ ሆይ፣ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ፡፡16ይህን የምለው ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዳይላቸው ነው፤ እግሬ ቢንሸራተት ክፉ ነገር ያደርጉብኛል፡፡17ልወድቅ ተቃርቤአለሁ ሕመሜም ፋታ አልሰጠኝም፡፡18በደሌን እናዘዛለሁ ኃጢአቴም አስጨንቆኛል፡፡19ጠላቶቼ እጅግ ብዙ ናቸው ያለ ምክንያት የሚጠሉንም በዝተዋል፡፡20በመልካም ፈንታ ክፉ መለሱልኝ መልሙን እየተከተልሁ ቢሆንም፣ እነርሱ ግን እኔ ላይ የሐሰት ክስ ደረደሩ፡፡21ያህዌ ሆይ፣ አትተወኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ22ጌታ መድኃኒቴ እኔን ለመርዳት ፍጠን፡፡
1እኔ፣ «በአንደበቴ እንዳልበድል ለምናገረው እጠነቀቃለሁ፣ በክፉዎችም ፊት እስካለሁ ድረስ፣ በአፌ ልጓም አደርጋለሁ» አልሁ፡፡2አንድ ቃል እንኳ ሳልናገር ዝም አልሁ ለመልካም ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤ ያም ሆኖ ጭንቀቴ ባሰ፡፡3ልቤ በውስጤ ጋለ ስለ እነዚህ ነገሮች ሳስብ እንደ እሳት ነደደ፡፡ ከዚያም መናገር ጀመርሁ፡፡4«ያህዌ ሆይ፣ የሕይወቴ መጨረሻ መቼ እንደ ሆነና የዕድሜዬን ልክ አሳውቀኝ አላፊ ጠፊ መሆኔን አሳየኝ፡፡5እነሆ፣ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አኖርህ ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፡፡ በእርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ጥላ ነው፡፡ ሴላ6በእርግጥ ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመላለሳል፡፡ ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል፡፡7ጌታ ሆይ፣ አሁንስ ማንን ልጠብቅ? ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ፡፡8ከኃጢአቴ አድነኝ የሞኞች መዘባበቻ አታድርገኝ፡፡9ይህን ያደረግህ አንተ ነህና ዝም እላለሁ አፌንም አልከፍትም፡፡10ክንድህን አንሣልኝ ከእጅህ ምት የተነሣ ዝዬአለሁ፡፡11ሰውን በኃጢአቱ ትገሥጸዋለህ፤ ትቀጣዋለህም የሚወደውንም ነገር እንደ ብል ታጠፋበታለህ፡፡ በእርግጥ ሰው ሁሉ ተን ነው፡፡ ሴላ12ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ ለቅሶየንም ቸል አትበል፡፡ በአንተ ፊት እንደ መጻተኛ ነኝና እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ፡፡13ከመሞቴ በፊት ዳግመኛ ደስ እንዲለኝ ዐይንህን ከላዬ አንሣ፡፡
1በትዕግሥት ያህዌን ደጅ ጠናሁት እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማኝ፡፡2ከአደገኛ ጉድጓድ፣ ከሚያዘቅጥም ጭቃ አወጣኝ፤ እግሮቼን፣ በዐለት ላይ አቆመ አካሄዴንም አጸና፡፡3ለአምላካችን ምስጋና አዲስ መዝሙር በአፌ አኖረ፡፡ ብዙዎች ዐይተው ያከብሩታል፤ በያህዌም ይታመናሉ፡፡4ያህዌን መታመኛው ያደረገ ወደ ትዕቢተኛው የማይመለከት የሐሰት አማልክት ወደሚከተሉት የሚያይ ቡሩክ ነው፡፡5ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው ለእኛ ያለህም ሐሳብ ከቁጥር በላይ ነው፤ ላወራው ልናገረው ብል ስፍር ቁጥር አይኖረውም፡፡6መሥዋዕትንና መባን አልፈለግህም ጆሮዎቼን ግን ከፈትህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንና የኃጢአት መሥዋዕትን አልጠየቅህም፡፡7እኔም እንዲህ አልሁ፣ «እነሆ፣ መጥቻለሁ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ ተጽፎአል፤8አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ ሕግህም ልቤ ውስጥ ነው፡፡9በታላቅ ጉባኤ ውስጥ ጽድቅህን ዐወጅሁ ያህዌ ሆይ፣ ይህን ከማድረግ ወደ ኋላ አለማለቴንም አንተ ታውቃለህ፡፡10ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሸሸግሁም፤ ታማኝነትህንና ማዳንህን ተናገርሁ ምሕረትህንና እውነትህን ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም፡፡11ያህዌ ሆይ ምሕረትህን አትንፈገኝ ቸርነትህና ታማኝነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ፡፡12ስፍር ቁጥር የሌለው ችግር ከብቦኛል የኃጢአቴ ብዛት ስለ ያዘኝ ማየት ተስኖኛል፤ ከራሴ ጠጉር ይልቅ በዝቶአል፤ ልቤም ከድቶኛል፡፡13ያህዌ ሆይ፣ እኔን ለማዳን ፈቃድህ ይሁን እኔን ለመርዳትም ፍጠን፡፡14ነፍሴን ለመንጠቅ የሚፈልጉ ይፈሩ፤ ይዋረዱም፡፡ ጉዳቴን የሚሹ ተዋርደው በመጡበት ይመለሱ፡፡15በእኔ ላይ፣ «እሰይ! እሰይ!» የሚሉ በራሳቸው እፍረት ይደንግጡ16አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፤ ማዳንህን የሚወዱ ዘወትር፣ «ያህዌ ከፍ ከፍ ይበል» ይበሉ፡፡17እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ ጌታ ግን ያስብልኛል፡፡ አንተ ረዳቴ ነህ እኔን ለማዳን ፍጠን አምላኬ ሆይ አትዘግይ፡፡
1ለድኾች የሚያስብ ቡሩክ ነው እርሱንም በመከራ ቀን ያህዌ ያድነዋል፡፡2ያህዌ ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል በምድርም ላይ ይባርከዋል ለጠላቶቹ ምኞትም አሳልፎ አይሰጠውም፡፡3ታሞ በተኛበት አልጋ ያህዌ ይንከባከበዋል በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል፡፡4እኔም፣ «ያህዌ ሆይ፣ ማረኝ! በአንተ ላይ ኃጢአት አድርጌአለሁና ፈውሰኝ» አልሁ፡፡5«የሚሞተው መቼ ነው፤ ስሙ የሚደመሰሰውስ መቼ ነው?» እያሉ ጠላቶቼ እኔ ላይ ክፉ ይናገራሉ፡፡6ሊጠይቀኝ ቢመጣ እንኳ በልቡ ስድብ እያመቀ ከአንገት በላይ ይናገራል ወጥቶም ወሬ ይነዛል፡፡7ጠላቶቼ ሁሉ ተባብረው እኔ ላይ ያሾኮሽካሉ የክፋ ነገርም በላዬ ያውጠነጥናሉ8«ክፉ ደዌ ይዞታል፤ አልጋ ላይ ወድቋል ከእንግዲህ ከተኛበት አይነሣም» ይላሉ። 9እንጀራዬን ተካፍሎ የበላ የተማመንሁበት የቅርብ ወዳጄ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ፡፡10አንተ ግን ያህዌ ሆይ ማረኝ፤ የእጃቸውን እንድሰጣቸውም አስነሣኝ፡፡11ጠላቴ በእኔ ላይ ድል አላገኘምና እንደ ወደድከኝ በዚህ ዐወቅሁ፡፡12ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ፡፡13የእስራኤል አምላክ ያህዌ ከዘላለም እስከ ዘለላለም ይመስገን፡፡ አሜን አሜን፡፡
1ዋላ የምንጭ ውሃ እንደሚናፍቅ አምላኬ ሆይ፣ እኔም እግዚአብሔርን ተጠማሁ፡፡2መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው?3ጠላቶቼ ዘወትር፣ «አምላክህ የት አለ?» ስለሚሉኝ እንባዬ ቀንና ሌሊት ምግቤ ሆነ፡፡4ነፍሴ በውስጤ እየፈሰሰች እነዚህን ነገሮች አስታውሳለሁ፣ ታላቅ ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ቤት እየመራሁ በአእላፍ ሕዝብ መካከል በእልልታና በምስጋና መዝሙር እንዴት ከሕዝቡ ጋር እሄድ እንደ ነበር ትዝ አለኝ፡፡5ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? በውስጤስ ለምን ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡6አምላኬ ሆይ፣ ነፍሴ በውስጤ አዝናለች ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር፣ ከአርሞንኤም ተራራ ጫፍ በሚዛር ተራራ አስብሃለሁ፡፡7በፏፏቴህ ድምፅ ጥልቁ ጥልቁን ይጠራል ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በእኔ ላይ አለፈ፡፡8ያም ሆኖ፣ ያህዌ ምሕረቱን በቀን ያዛል በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ አለ ይህም ለሕይወቴ አምላክ የማቀርበው ጸሎት ነው፡፡9እግዚአብሔር ዐለቴን፣ «ለምን ረሳኸኝ? ጠላቴ ከደረሰብኝ ጭንቀት የተነሣ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?» እለዋለሁ፡፡10ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ፣ «አምክህ የት አለ?» እያሉ የሚያደርሱብን ፌዝ ዐጥንቶቼ ውስጥ እንደ ሰይፍ ሆነ፡፡11ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡
1አምላክ ሆይ፣ ፍረድልኝ ከጽድቅ ከራቀ ሕዝብ ጋር ተሟገትልኝ፡፡2አምላክ ሆይ፣ አንተ ብርታቴ ነህ ለምን ተውኸኝ? ጠላት እያስጨነቀኝ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?3ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እኔንም ይምሩኝ፡፡ ወደ ቅዱስ ኮረብታህና ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ፡፡4እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ እሄዳለሁ ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላኬ አቀናለሁ፡፡ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ በበገና አመሰግንሃለሁ፡፡5ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡
1አምላክ ሆይ፣ በጆሮአችን ሰምተናል በቀድሞ ዘመን እነርሱ በነበሩበት ዘመን ያደረግኸውን አባቶቻችን ነግረውናል፡፡2ሕዝቦችን በእጅህ አሳድዶህ አስወጣህ የእኛን ሕዝብ ግን ተከልህ ሕዝቦችን አደቀቅህ የእኛ ሕዝብ ግን በምድሩ እንዲኖር አደረግህ፡፡3ምድሪቱን የወረሳት በሰይፋቸው አልነበረም፣ ያዳናቸውም የገዛ ክንዳቸው አልነበረም አንተ ወደድሃቸውና ቀኝ እጅህ፣ ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ፡፡4እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ንጉሤ ነህ ያዕቆብ ድል እንዲያገኝ የወሰንህ አንተ ነህ፡፡5በአንተ ርዳታ ጠላቶቻችንን ድል እንነሣለን በስምህም ተቃዋሚዎቻችንን እንረግጣለን፡፡6በቀስቴ አልተማመንምና ሰይፌም አያድነኝም፡፡7አንተ ግን ከጠላቶቻችን አዳንኸን የሚጠሉንንም አሳፈርሃቸው፡፡8ዘወትር በእግዚአብሔር እንመካለን ለዘላለምም ስምህን እንወድሳለን፡፡ ሴላ9አሁን ግን ትተኸናል ለውርደትም ዳርገኸናል ከሰራዊታችንም ጋር አትወጣም፡፡10ከጠላት ፊት እንድንሸሽ አደረግህ ባላንጣዎቻችንም ዘረፉን፡፡11እንደሚታረዱ በጐች አደረግኸን በሕዝቦችም መካከል በተንኸን፡፡12ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው ከሽያጩም ያተረፍኸው የለም፡፡13ለጐረቤቶቻችን ማፈሪያ በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያና መዘባበቻ አደረግኸን፡፡14በሕዝቦች ዘንድ ስድብ፣ በሰዎችም መካከል ራስ የሚነቀነቅብን አደረግኸን፡፡15ውርደቴ ዘወትር በፊቴ ነው ፊቴም እፍረትን ተከናንቦአል፡፡16ይህም ከዘላፊውና ከተሳዳቢው ድምፅ የተነሣ ከጠላትና ከተበቃይ የተነሣ ነው፡፡17ይህ ሁሉ ቢደርስብንም፣ አንተን ግን አልረሳንም ለኪዳንህ ታማኝ መሆንንም አልተውንም፡፡18ልባችን ከአንተ አልተመለሰም ርምጃችንም ከመንገድህ ወደ ኋላ አላለም፡፡19አንተ ግን ተኩላዎች በሚውሉበት ቦታ ሰባብረህ ጣልኸን፤ በሞት ጥላም ሸፈንኸን፡፡20የአምካችንን ስም ረስተን፣ እጆቻችንን ለባዕድ አማልክት ዘርግተን ቢሆን ኖሮ፣21እግዚአብሔር ይህን ማወቅ ይሣነዋልን? እርሱ የሰውን ልብ ምስጢር የሚረዳ ነውና፡፡22ያም ሆኖ፣ ቀኑን ሙሉ ስለ አንተ እንገደላለን እንደሚታረዱ በጐችም ተቆጠርን፡፡23ጌታ ሆይ ንቃ፣ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፣ ለዘላለምም አትተወን፡፡24ፊትህን ለምን ከእኛ ትሰውራለህ? መከራና ጭንቀታችን ለምን ችላ ትላለህ?25እስከ ምድር ትቢያ ድረስ ወርደናል አካላችን ከምድር ጋር ተጣብቆአል፡፡26እኛን ለመርዳት ተነሥ ስለ ኪዳን ታማኝነትህ ስትል ተቤዠን፡፡
1ልቤ መልካም ሐሳብ አፈለቀ ለንጉሡ የተቀኘሁትን ቅኔ አሰማለሁ አንደበቴ እንደ መልካም ጸሐፊ ብዕር ነው፡፡2አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ ከከንፈሮችህ ጸጋ ይፈስሳል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል፡፡3ኃያል ሆይ፣ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ ግርማ ሞገስንም ተላበስ4ስለ እውነት ስለ ፍትሕ ግርማን ተጐናጽፈህ ድል ለማድረግ ገሥግሥ ቀን እጅህ ድንቅ ነገር ታሳይ፡፡5ፍላጻዎችን የሾሉ ናቸው ሕዝቦች ከእግርህ በታች ይወድቃሉ፡፡ ፍላጻዎችህ የንጉሡ ጠላቶችን ልብ ይወጋል፡፡6አምላክ ሆይ፣ ዙፋንህ የዘላለም ዙፋን ነው በትረ መንግሥትህም የፍትሕ በትረ መንግሥት ነው፡፡7ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃንም ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ፡፡8ልብስህ ሁሉ ከከርቤ፣ ከእሬትና ከብርጉድ በተቀመመ ሽቱ ያውዳል፤ በዝሆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶች የሚወጣ የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኝሃል፡፡9በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙ ወይዛዝርት መካከል፤ የነገሥታት ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጤኛ ልብስ ተጐናጽፋ በቀኝህ በኩል ትቆማለች፡፡10ልጄ ሆይ፣ አድምጪ አስተውይ፣ ጆሮሽንም አዘንብይ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ፡፡11ንጉሥ በውበትሽ ተማርኮአል እርሱ ጌታሽ ነውና አክብሪው፡፡12የጢሮስ ሴት ልጅ ስጦታ ይዛ ትመጣለች፤ ሀብታሞች ደጅ ይጠኑሻል፡፡13በቤተ መንግሥት ያለችው ልዕልት አጊጣለች ልብሷም በወርቅ አሸብርቋል፡፡14ጌጠኛ ልብሷን ለብሳ ወደ ንጉሡ ትገባለች፤ ደናግል ጓደኞቿም አጅበዋት ወደ አንተ ይመጣሉ፡፡15በደስታና በሐሤትም አብረው ወደ ንጉሡ ቤት ይገባሉ፡፡16ወንዶች ልጆችህ በአባቶችህ እግር ይተካሉ በምድር ሁሉ ላይ ገዦች አድርገህ ትሾማቸዋለህ፡፡17ስምህን በትውልድ ሁሉ ዘንድ ለመታሰቢያ አደርጋለሁ ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወድሱሃል፡፡
1እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን፣ በመከራም ቀን ረዳታችን ነው፡፡2ስለዚህ ምድር ብትናወጥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ፣ አንፈራም፡፡3ውሆች ቢያስገመግሙ፣ ዐረፋ ቢደፍቁም፣ ከውሃው ሙላት የተነሣ ተራሮች ቢንቀጠቀጡም አንደነግጥም፡፡ ሴላ4የእግዚአብሔርን ከተማ የልዑልንም የተቀደሰ ማደሪያ ደስ የሚያሰኙ ወራጅ ወንዞች አሉ፡፡5እግዚአብሔር በመካከሏ ነውና አትናወጥም ጠዋት በማለዳ እግዚአብሔር ይረዳታል፡፡6ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታት ወደቁ ድምፁን ከፍ አድርጐ አሰማ ምድርም ቀለጠች፡፡7የሰራዊት ጌታ ያህዌ ከእኛ ጋር ነው የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው፡፡ ሴላ8ኑ የእግዚአብሔርን ሥራ በምድር ላይ የደረሰውን ጥፋት ተመልከቱ፡፡9ከምድር ዳር እስከ ዳርቻ ጦርነትን ያስወግዳል ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርንም ያነክታል ጋሻዎችንም በእሳት ያቃጥላል፡፡10ጸጥ በሉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ፡፡11የሰራዊት አምላክ ያህዌ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው፡፡ ሴላ
1ሕዝቦች ሁሉ እጆቻችሁን አጨብጭቡ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፡፡2በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ የሆነው ልዑል ያህዌ እጅግ አስፈሪ ነው፡፡3ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፣ መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን፡፡4ለሚወደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን ርስታችንን እርሱ መረጠልን፡፡5እግዚአብሔር በእልልታ፣ ያህዌም በመለከት ድምፅ ዐረገ6ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ7እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ስለዚህ በማስተዋል ዘምሩለት፡፡8እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ነግሦአል እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል፡፡9ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ የምድር ነገሥታት የእግዚአብሔር ናቸውና እርሱ እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡
1ያህዌ ታላቅ ነው፣ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰ ተራራው ላይ ከፍ ያለ ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል፡፡2የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው፡፡3እግዚአብሔር በቤተ መንግሥት ውስጥ ሆኖ ብርቱ ምሽጓ መሆኑን አስመስክሮአል፡፡4እነሆ፣ ነገሥታት ተባብረው መጡ በአንድነትም ገሠገሡ፡፡5ዐይተው ተደነቁ ደንግጠውም ፈረጠጡ፡፡6በዚያ ፍርሃትና ድንጋጤ ያዛቸው ምጥ እንደያዛት ሴት ብርክ ያዛቸው፡፡7የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር አንተ አንበረከክሃቸው8በጆሮአችን እንደ ሰማን በሰራዊት አምላክ ከተማ በአምላካችን ያህዌ ከተማ በዐይናችን አየን፡፡9አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሆነን ታማኝነትህን እናስባለን፡፡10እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ስምህ ምስጋናህም እስከ ምድር ዳርቻ ነው፤ ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት፡፡11ስለ ጽድቅህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበላት የይሁዳም ልጅ ሐሤት ታድርግ፡፡12በጽዮን ተራራ፣ በዙሪያዋም ተመላለሱ፣ ማማዎቿን ቁጠሩ፤13ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ ጠንካራ ቅጥሮቿን አስተውሉ ምሽጐችዋንም ተመልከቱ፡፡14ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነው፤ እስከ መጨረሻው መሪያዎችንም እርሱ ነው፡፡
1ሕዝቦች ሁሉ ይህን ስሙ በዓለም የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ፡፡2ዝቅተኞችና ከፍተኞች ሀብታሞችና ድኾች ይህን በአንድነት አድምጡ፡፡3አፌ ጥበብን ይናገራል የልቤ ሐሳብም ማስተዋልን ይሰጣል፡፡4ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ በበገናም የምሳሌዎቹን ትርጒም እገልጣለሁ፡፡5ክፉ ቀን ሲመጣና አታላዮች ሲከብቡኝ ለምን እፈራለሁ?6በሀብታቸው የሚመኩትንና በብልጽግናቸው የሚተማመኑትን ለምን እፈራለሁ?7ማንም ወንድሙን መቤዠት ለእርሱም ቤዛ የሚሆነውን ዋጋ ለእግዚአብሔር መክፈል አይችልም፡፡8የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና በቂ ዋጋ ሊገኝለት አይችልም፡፡9እንዳይሞትና ወደ መቃብር እንዳይወርድ ማንም ለዘላለም መኖር አይችልም፡፡10ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ፤ ጠቢባን እንኳ ከሞኞችና ከሞኞች እኩል በአንድት ይጠፋሉ ሀብታቸውንም ለሌላው ጥለው ይሄዳሉ፡፡11እነርሱ የሚያስቡት ቤተ ሰባቸው ለዘላለም እንደሚኖር፣ መኖሪያ ስፍራቸውም ለትውልድ ዘመን እንደማይጠፋ በመሆኑ መሬቶቻቸውን በስማቸው ይሰይማሉ፡፡12ግን ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም አሁን ታይተው በኃላ እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል፡፡13ይህ የምኞት ዕድል ፈንታ የእነርሱንም አባባል የሚከተሉ ሰዎች መጨረሻ ግብ ነው፡፡14እንደ በጐች ለሞት የተመደቡ ናቸው እረኛቸውም ሞት ነው በማለዳ ቅኖች ይገዟቸዋል፤ መኖሪያ ቦታ አጥቶ አካላቸው ሲኦል ውስጥ ይፈራርሳል፡፡15እግዚአብሔር ግን ሕይወቴን ከሲኦል ኃይል ይቤዣል፤ እርሱም ይቀበለኛል፡፡ ሴላ16ሰው ባለጠጋ ቢሆን፣ የቤቱም ክብር ቢበዛለት አትፍራ፡፡17በሚሞትበት ጊዜ ምንም ይዞ አይሄድም ክብሩም አብሮት አይወርድም፡፡18ሰው በሕይወቱ ዘመን ቢደሰትም፣ ሁሉም ነገር ስለ ተሳካለት ቢመሰገንም፣19በሞት ተለይቶ ከእንግዲህ ብርሃን ወደሚያይበት ወደ አባቶች ትውልድ ይሄዳል፡፡20ሁሉም ነገር እያለው ማስተዋል የጐደለው ሰው ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል፡፡
1ኃያሉ አምላክ ያህዌ ተናገረ ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ ምድርን ተናገረ፡፡2ፍጹም ውብ ከሆነችው ከጽዮን እግዚአብሔር አበራ፡፡3አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም የሚባላ እሳት በፊቱ ነው ኃይለኛ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው ነው፡፡4ሕዝቡ ላይ ይፈርድ ዘንድ በላይ ያሉ ሰማያትንና ምድርን፣ «በመሥዋዕት ከእኔ ጋር ኪዳን የገቡትን 5ቅዱሳኔን ሁሉ ወደ እኔ ሰብስቡ» ብሎ ይጣራል፡፡6ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፡፡ እግዚአብሔርን ራሱ ፈራጅ ነው፡፡ ሴላ7«ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ ልንገርህ እስራኤል ሆይ፣ በአንተ ላይ ልመስክር፤ አምላክህ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡8ስለ መሥዋዕትህ አልነቅፍህም የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው፡፡9ከበረትህ ኮርማዎችን፣ ከጉሮኖህም አውራ ፍየሎችን አልወስድም10የዱር አራዊት ሁሉ፣ በሺ ተራሮች ያለው እንስሳ ሁሉ የእኔ ነውና፡፡11በየተራሮች ያሉ ወፎችን ሁሉ ዐውቃለሁ፡፡ በመስክ የሚገኙ እንስሶች ሁሉ የእኔ ናቸው፡፡12ብራብ እንኳ ለአንተ አልናገርም ዓለምና በውስጧ ያለው ሁሉ የእኔ ነውና፡፡13የኮርማዎችን ሥጋ እበላለሁን? ወይስ የፍየሎችን ደም እጠጣለሁን?14የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ስእለትህንም ለልዑል አምላክ ክፈል፡፡15በመከራ ቀን ጥራኝ እኔ እታደግሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ፡፡16ዐመፀኛውን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል ሕጌን ለማነብነብ፣ ኪዳኔንም በአፍህ ለመናገር ምን መብት አለህ?17ትምህርቴን ጠልተሃል፤ ቃሌንም ወደ ኃላህ ጥለሃል፡፡18ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ሮጥህ፣ ዕድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ፡፡19አፍህን ለክፋት፣ አንደበትህንም ሽንገላ ለመናገር አዋልህ፡፡20ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው የእናትህንም ልጅ ስም አጠፋህ፡፡21ይህን ሁሉ ስታደርግ ዝም አልሁህ ስለዚህ እኔም እንዳንተው የሆንሁ መሰለህ፡፡ አሁን ግን ፊት ለፊት ነገርህን ገልጩ እገሥጽሃለሁ፡፡22እናንት እግዚአብሔርን የምትረሱ ይህን አስተውሉ፤ አለበለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ! የሚያስጥላችሁም የለም!23የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤ መንገዱን ቀና ለሚያደርግ የእግዚአብሔር ማዳን አሳየዋለሁ፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ርኅራኄም ብዛት መተላለፌን ደምስስ፡፡2በደሌን ፈጽሞ እጠብልኝ ከኃጢአቴም አንጻኝ፡፡3መተላለፌን ዐውቃለሁና ኃጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው፡፡4አንተን፣ በእርግጥ አንተን ብቻ በደልሁ ስትናገር ትክክል ነህ፤ ስትፈርድም ትክክል ነህ፡፡5ስወለድ ጀምሮ በደለኛ ነህ ገና እናቴም ስትወልደኝ ኃጢአተኛ ነኝ፡፡6እነሆ፣ አንተ ልቤ ውስጥ እውነትን ትሻለህ ስለዚህ ጥልቅ ጥበብን በውስጤ አስተምረኝ፡፡7በሂሶጵ እርጨኝ እኔም እነጻለሁ፡፡ እጠበኝ፤ ከበረዶም ይልቅ እነጻለሁ፡፡8ያደቀቅሃቸው አጥንቶቼ ደስ እንዲላቸው ደስታንና ሐሤትን አሰማኝ፡፡9ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፣ በደሌን ሁሉ ደምስስልኝ፡፡10አምላኬ ሆይ፣ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ11ከፊትህ አትጣለኝ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድብኝ፡፡12የማዳንህን ደስታ መልስልኝ በእሺታ መንፈስም ደግፈኝ ያዘኝ፡፡13በዚያ ጊዜ፣ ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ፡፡ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ፡፡14የድነቴ አምላክ ሆይ፣ ደም አፍሳሽነቴን ይቅር በል አንደበቴም በደስታ ስለ ጽድቅህ በእልልታ ይዘምራል፡፡15ጌታ ሆይ፣ ከንፈሮቼን ክፈት አፌም ምስጋናህን ያውጃል፡፡16መሥዋዕትን ብትወድ ኖሮ፣ እሰጥህ ነበር፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ደስ አያሰኝህም፡፡17የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው አንተ፣ የተሰበረውን የተዋረደውን መንፈስ አትንቅም፡፡18በበጐነትህ ለጽዮን መልካም አድርግ የኢየሩሳሌምንም ቅጥሮች ሥራ፡፡19በዚያ ጊዜ የጽድቅ መሥዋዕት፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና ፈጽሞ የሚቃጠል መሥዋዕት ደስ ያሰኝሃል፡፡ እኛም በመሠዊያህ ላይ እንደ ገና ኮርማዎችን እናቀርባለን፡፡
1ኃያል ሆይ፣ ሁከት በመፍጠር ለምን ትኩራለህ? የእግዚአብሔር ኪዳን ታማኝነት ዕለት ዕለት ነው፡፡2አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ ጥፋትን ያውጠነጥናል፡፡3ከመልካም ይልቅ ክፋትን፣ እውነትን ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ወደድህ፡፡4አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፣ ሌሎችን የሚያጠፋ ቃል ወደድህ፡፡5ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ያጠፋሃል ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤ ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል፡፡6ጻድቃን ይህን ዐይተው ይፈራሉ እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤7«ተመልከቱ፣ እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣ ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ በክፋቱም የበረታ ያ ሰው እነሆ!»8እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ የወይራ ዛፍ ነኝ፤ ከዘላለም እስከ ዘላለም፣ በእግዚአብሔር ምሕረት እታመናለሁ።9ስላደረግኸው ነገር ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤ ስምህ መልካም ነውና ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ በቅዱሳንም መካከል አመሰግንሃለሁ።
1ሞኝ በልቡ፣ «እግዚአብሔር የለም» ይላል ብልሹዎች ናቸው፤ ጸያፍ ነገርም አድርገዋል መልካም የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም፡፡2አስተዋዮችና እርሱን የሚፈልጉ ሰዎች ለማግኘት፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ፡፡3ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር ብለዋል፤ በአንድነትም ብልሹዎች ሆነዋል፡፡ መልካም የሚያደርግ አንድ እንኳ የለም፡፡4ክፉ አድራጊዎች ከቶ አያስተውሉምን እንጀራ እንደሚበላ ሰው ሕዝቤን የሚበሉ፣ እግዚአብሔርንም ጠርተው የማያውቁት ሰዎች አይማሩምን?5ምንም የሚያስፈራ ነገር ሳይኖር እጅግ ፈሩ፤ የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት እግዚአብሔር በተነ፤ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው እንዲህ ያሉ ሰዎች ያፍራሉ፡፡6ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በመጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከምርኮ በመለሰ ጊዜ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፤ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል!
1እግዚአብሔር ሆይ፣ በስምህ አድነኝ በኃይልህም ፍረድልኝ፡፡2እግዚአብሔር ሆይ፣ ጸሎቴን ስማልኝ የአፌንም ቃል አድምጥ፡፡3ባዕዳን ተነሥተውብኛልና ጨካኞችም ነፍሴን ይፈልጓታል እግዚአብሔርንም ከምንም አልቆጠሩትም፡፡ ሴላ4እነሆ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው ጌታም ደግፎ ይይዘኛል፡፡5ክፋታቸውን በጠላቶቼ ላይ መልስባቸው በቃልህ ታማኝ ነህና አጥፋቸው፡፡6በበጐ ፈቃድ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ መልም ነውና ያህዌ ሆይ፣ ስምህን አመሰግናለሁ፡፡7ከመከራ ሁሉ ታድጐኛልና ዐይኔም የጠላቶቼን ውድቀት ለማየት በቅቶአል፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ ልመናዬንም ቸል አትበል፡፡2ችግሬ ዕረፍት ነስቶኛልና ወደ እኔ ተመልከት መልስልኝም፡፡3ከጠላቶቼ ዛቻ የተነሣ፣ ፈርቼአለሁ፤ በክፉዎችም ጭቈና ደቅቄአለሁ፡፡ መከራ አምጥተውብኛል፤ በቁጣም ያሳድዱኛል፡፡4ልቤ በውስጤ ተሸበረብኝ የሞት ድንጋጤም መጣብኝ፡፡5ፍርሃትና እንቅጥቅጥ መጡብኝ ሽብርም በረታብኝ፡፡6እኔም እንዲህ አልሁ፣ «ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ! በርሬ ሄጄ ዐርፍ ነበር፡፡7እነሆ፣ ኮብልዬ በራቅሁ ነበር በምድረ በዳ በሰነበትሁ ነበር፡፡ ሴላ8ከዐውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼ ወደ መሸሽጊያ ፈጥኜ በደረስሁ ነበር፡፡»9ግፍና ሁከት በከተማዪቱ ዐይቻለሁና ጌታ ሆይ ግራ አጋባቸው፤ ቋንቋቸውንም ደበላልቅ!10ቀንና ሌሊት ቅጥሮቿን ይዞራሉ ተንኰልና መከራ በውስጧ አሉ፡፡11ዐመፃ በመካከልዋ ነው፤ ግፍና አታላይነት ከጐዳናዋ አይጠፋም፡፡12የሰደበኝ ጠላት አይደለም ያማ ቢሆን በታገሥኩ ነበር፤ የሚታበይብኝ፣ ራሱንም ቀና ቀና ያደረገብኝ ባላንጣ አይደለም፤ ያማ ቢሆን፣ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር፡፡13ነገር ግን ያን ያደረግህ አንተ እኩያየ፣ ባልንጀራዬና የቅርብ ወዳጄ ነህ፡፡14ደስ የሚል ኅብረት በአንድነት ነበረን በሕዝቡ መካከል በእግዚአብሔር ቤት አብረን ተመላልሰን ነበር፡፡15በድንገት ሞት ይምጣባቸው ክፋት በመካከላቸው ናትና በሕይወታቸው እያሉ ወደ ሲኦል ይወረዱ፡፡16እኔ ግን እግዚአብሔርን እጣራለሁ ያህዌም ያድነኛል፡፡17በማታ፣ በጧትና በቀትር አቃሥታለሁ እቃትታለሁም እርሱም ድምፄን ይሰማል፡፡18ከእኔ ጋር የሚዋጉት ብዙ ናቸውና እርሱ፣ ከተከፈተብኝ ጦርነት በሰላም ይታደገኛል፡፡19ስለማይለወጡና አምኬንም ስለማይፈሩ ከዘላለም እስከ ዘላለም ዙፋኑ ላይ ያለው እግዚአብሔር ሰምቶ ያዋርዳቸዋል፡፡ ሴላ20ጓደኛዬ የምለው ሰው እጁን በወዳጆቹ ላይ ሰነዘረ፤ ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ፡፡21አፉ ከቅቤ ይልቅ የለዘበ ነው በልቡ ግን ጦርነት አለ፤ ቃሉ ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነው ሆኖም የተመዘዘ ሰይፍ ነው፡፡22የከበድህን ነገር በያህዌ ላይ ጣል እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁን መናወጥ ከቶ አይፈቅድም፡፡23አንተ ግን እግዚአብሔር ሆይ፣ ዐመፀኞችን ወደ ጥፋት ጉድጓድ ታወርዳቸዋለህ ደም የተጠሙና አታላዮች የዕድሜያቸውን ግማሽ እንኳ አይኖሩም፡፡ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ ሰዎች ስለሚያጠቁኝና ጠላቶቼም ቀኑን ሙሉ ስለሚያሳድዱኝ ማረኝ፡፡2ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ በእብሪት የሚዋጉኝ ብዙ ናቸውና፡፡3እኔ ግን ፍርሃት ሲይዘኝ እምነቴን አንተ ላይ አደርጋለሁ4ቃሉን በማመሰግው አምላክ በእግዚአብሔር ታምኛሁና አልፈራም ከቶ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?5ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምማሉ ሐሳባቸው ሁሉ እኔን መጉዳት ነው፡፡6ይዶልታሉ፤ ያደባሉ ሕይወቴ ላይ እንደሚያደቡት ሁሉ ርምጃዬንም ይከታተላሉ፡፡7አምላክ ሆይ፣ በምንም መንገድ እንዲያመልጡ አታድርጋቸው፤ በቁጣህ ሕዝቦችን አዋርዳቸው፡፡8የመንከራተት ቀኖቼን ቆጥረሃል እንባዎቼን በመያዣህ አኑረሃል፡፡ ሁሉስ በመጽሐፍህ ያለ አይደለምን?9ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑን በእርግጥ ዐወቅሁ፡፡10ቃሉን በማመሰግነው አምላክ ቃሉን በማመመሰግነው ያህዌ11በአምላክ ታምኛለሁና አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?12አምላኬ ሆይ፣ የተሳልሁትን እፈጽማለሁ ለአንተም የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፡፡13ነፍሴን ከሞት፣ እግሬን ከመሰናከል አድነሃልና በሕያዋን ብርሃን፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለሳለሁ፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ ማረኝ አቤቱ ማረኝ የመከራው ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና፡፡ ጥፋት እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ እጠለላለሁ፡፡2ወደ ልዑል እግዚአብሔር የሚያስፈልገኝን ሁሉ ወደሚሰጠኝ አምላክ እጮኻለሁ፡፡3ከሰማይ ልኮ ያድነኛል የሚያስጨንቁኝንም ያዋርዳቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይልካል፡፡4ነፍሴ በአንበሶች ተከባለች፣ ሊውጡኝ በተዘጋጁ መካከል ወድቄአለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ ምሳቸውም የተሳለ ሰይፍ ነው፡፡5እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ይስፋፋ6ለእግሬ ወጥመድ ዘረጉ፣ ነፍሴንም አጐበጡአት፤ መንገዴ ላይ ጉድጓድ ቆፈሩ፤ ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት፡፡ ሴላ7ልቤ ጽኑ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ ልቤ ጽኑ ነው እቀኛለሁ፤ እዘምራለሁ፡፡8ነፍሴ ሆይ፣ ንቂ በገናና መሰንቆም ተነሡ እኔም በማለዳ እነሣለሁ፡፡9ጌታ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ በመንግሥታት መካከል ምስጋና እዘምራለሁ፡፡10ዘላለማዊ ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው ታማኝነትህም እስከ ደመናት ይደርሳል፡፡11እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ በል ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ይስፋፋ፡፡
1እናንተ ገዢዎች እውነትን ትናገራላችሁ? እናንተ ሰዎች ቅን ፍርድ ትፈርዳላችሁ?2የለም፤ በልባችሁ ክፋት ታውጠነጥናላችሁ በእጃችሁም በምድር ሁሉ ላይ በደል ትፈጽማላችሁ፡፡3ክፉዎች በእናታቸው ማሕፀን እያሉ እንኳ ከመንገድ የወጡ ናቸው ሲወለዱ ጀምሮ የተሳሳቱና ውሸታሞች ናቸው፡፡4መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው5የአስማተኛውን ቃል አልሰማ እንዳለች እፉኝት ጆሮአቸውን ደፍነዋል፡፡6እግዚአብሔር ሆይ፣ ጥርሳቸውን አፋቸው ውስጥ ስበር የአንበሶችንም መንጋጋ አውላልቅ፡፡7ፈስሶ እንደሚያልቅ ውሃ ይጥፉ የቀስታቸው ፍላጻ ዱልዱም ይሁን፡፡8እየሄደ ሟምቶ እንደሚጠፋ ቀንድ አውጣ፣ ፀሐይ እንደማያይም ጭንጋፍ ይሁኑ፡፡9የሚነደው እሾኽ እሳት ገና ድስታችሁን ሳያሞቀው እርጥቡንም ደረቁንም እኩል በዐውሎ ነፋስ ጠራርጐ ይወስዳቸዋል፡፡10ጻድቃን የእግዚአብሔርን በቀል ሲያዩ ደስ ይላቸዋል እግሩንም በግፈኞች ደም ይታጠባል፡፡11በዚህ ጊዜ ሰዎች፣ «በእርግጥ ለጻድቃን ዋጋ አላቸው፤ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ» ይላሉ፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ ከጠላቶቼ አድነኝ በእኔ ላይ ከሚነሡ ሰዎችም ጠብቀኝ፡፡2ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፣ ደም ከተጠሙ ሰዎችም አድነኝ፡፡3ሕይወቴን ለማጥፋት አድብተዋልና ያህዌ ሆይ፣ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኃጢአቴ በላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ፡፡4ምንም በደል ባይኖርብኝም ተዘጋጅተው መጡብኝ፤ አንተ ግን ሁኔታዬን ተመልከት እኔን ለመርዳትም ተነሥ፡፡5የሰራዊት አምላክ የሆንህ ያህዌ አንተ የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝቦችን ለመቅጣት ተነሥ፣ ዐመፀኞችንም ያለ ምሕረት ቅጣቸው፡፡ ሴላ6እንደ ውሻ እያላዘኑ በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ በከተማዪቱም ይራወጣሉ፡፡7ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት ሰይፍ ከንፈራቸው ላይ አለ ደግሞም፣ «ማን ሊሰማን ይችላል?» ይላሉ፡፡8አንተ ያህዌ ግን ትሥቅባቸዋለህ ሕዝቦችን ሁሉ በንቀት ታያቸዋለህ፡፡9እግዚአብሔር ብርታቴ ሆይ አንተን እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ሆይ አንተ መጠጊያዬ ነህና፡፡10እግዚአብሔር በምሕረቱ ይገናኘኛል አምላኬ የጠላቶቼን ውድቀት ያሳየኛል፡፡11እግዚአብሔር ጋሻችን ሆይ፣ ሕዝቤ እንዳይረሱ አትግደላቸው፤ በኃይልህ በትናቸው ዝቅ ዝቅም አድርጋቸው፡፡12ከአፋቸው ስለሚወጣው ኃጢአት ከከንፈራቸውም ስለሚሰነዘረው ቃል በትዕቢታቸው ይያዙ፡፡ ከአፋቸው ስለ ወጣው መርገምና ውሸት13በቁጣ አጥፋቸው፤ ፈጽመህም አስወግዳቸው፡፡ እግዚአብሔር በያዕቆብና በምድር ዳርቻ ሁሉ ገዢ መሆኑን ይወቁ፡፡14እንደ ውሻ እያላዘኑ፣ በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤ በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ፡፡15ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤ ካልጠገቡም ያላዝናሉ፡፡16እኔ ግን ስለ ኃይልህ እዘምራለሁ በማለዳም ስለ ዘላለማዊ ፍቅርህ እዘምራለሁ፡፡ አንተ መጠጊያዬ፣ በመከራዬም ቀን ዐምባዬ ነህና፡፡17ብርታቴ ሆይ፣ በዝማሬ አመሰግንሃለሁ፤ እግዚአብሔር መጠጊያዬ የምትወደኝም አምላኬ ነህና፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ ጣልኸኝ፣ ሰባበርኸን፤ ተቆጣኸንም፤ አሁን ግን መልስህ አብጀኝ፡፡2ምድሪቱን አናወጥኃት፣ ፍርክስክስ አደረግኃት፤ ተንገዳግዳለችና ስብራቷን ጠግን፡፡3ሕዝብህን መከራውን አሳየኸው የሚያንገዳግድ ወይን ጠጅ እንድንጠጣም ሰጠኸን፡፡4ከጠላት ቀስት እንዲያመልጡ ለሚፈሩህ ምልክት አደረግህላቸው፡፡ ሴላ5የምትወደው ሕዝብህ ከጉዳት እንዲድን በቀኝህ ታደገን፤ መልስም ስጠን፡፡6እግዚአብሔር በመቅደሱ ሆኖ እንዲህ አለ፣ «ሲኬምን እሸነሽናለሁ፤ የሱኮትንም ሸለቆ አከፋፍላለሁ፡፡7ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቁሬ፣ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው፡፡8ሞዓብ መታጠቢ ገንዳዬ ነው፤ በኤዶም ላይ ጫማየን እወረውራለሁ ፍልስጥኤማውያን ላይ በድል እልል እላለሁ፡፡9ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ያመጣኛል? ማንስ ወደ ኤዶም ይመራኛል?10 ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ፥ የጣልከን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አልወጣህም11በጠላቶቻችን ላይ ድልን ስጠን የሰው ድጋፍ ከንቱ ነውና።12በእግዚአብሔር እርዳታ ድል እንቀዳጃለን እርሱ ጠላቶቻችንን ከእግሩ በታች ይረግጣቸዋል።
1እግዚአብሔር ሆይ፣ ጩኸቴን ስማ ጸሎቴንም አድምጥ፡፡2ልቤ በዛለ ጊዜ ከምድር ዳርቻዎች ወደ አንተ እጣራለሁ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ፡፡3አንተ መጠጊያዬ ከጠላትም የምከለልብህ ፅኑ ግንብ ሆነኸኛልና፡፡4በማደሪያህ ለዘላለም ልኑር በክንፎችህም ጥላ ልከለል፡፡ ሴላ5እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ስእለቴን ሰምተሃል ስምህን የሚያከብሩ ሰዎችን ርስት ለእኔ ሰጠህ፡፡6የንጉሡን ዕድሜ አርዝመው ዘመኑንም እስከ ብዙ ትውልዶች ድረስ ጨምርለት፡፡7ለዘላለም በእግዚአብሔር ፊት ይንገሥ፡፡8ስእለቴን በየቀኑ እንድፈጽም ለስምህ ለዘላለም የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፡፡
1ድነቴ የሚመጣው ከእርሱ ስለሆነ እግዚአብሔርን ብቻ በጸጥታ እጠብቃለሁ፡፡2ዐለቴና መድኃኒቴ እርሱ ብቻ ነው መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም፡፡3ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው? ይህን የዘመመ ግድግዳ የተንጋደደ ዐጥር ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትፈልጋላችሁ?4እነርሱ የሚፈልጉት እርሱን ከክብሩ ለማዋረድ ስለሆነ በእርሱ ላይ ሐሰት መናገር ይወዳሉ፤ በአፋቸው ይመርቁታል፤ በልባቸው ግን ይረግሙታል፡፡ ሴላ5እግዚአብሔርን ብቻ በጸጥታ እጠብቃለሁ6ዐለቴና መድኃኒቴ እርሱ ብቻ ነው፡፡ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም፡፡7ድነቴና ክብሬ ከእግዚአብሔር ነው እርሱ መጠጊያ ዐምባዬና መሸሸጊያ ነው፡፡8ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ በፊቱም ልባችሁን አፍስሱ እግዚአብሔር ለእኛ መጠጊያችን ነውና፡፡ ሴላ9ከዝቅተኛ ወገን መወለድ ከንቱ ነው፣ ከከፍተኛ ወገን መወለድም ሐሰት ነው ሚዛን ላይ ከፍ ብለው ቢታዩም ሁሉም በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው፡፡10በዝርፊያ አትተማመኑ በቅሚያ በተገኘ ሀብትም ተስፋ አታድርጉ በዚህ አትበለጽጉምና ልባችሁ እነርሱ ላይ አታድርጉ፡፡11እግዚአብሔር አንዴ ተናገረ እኔም ይህን ሁለቴ ሰማሁ፡፡ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፡፡12ጌታ ሆይ፣ የኪዳን ታማኝነት የአንተ ነው አንተ ለእያንዳንዱ፣ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ! ከልቤ አንተን እሻለሁ ውሃ በሌለበት ደረቅና ጭው ያለ ምድረ በዳ ነፍሴ አንተን ተጠማች ሥጋዬም አንተን ናፈቀች፡፡2ስለዚህ መቅደስህ ውስጥ አየሁህ ኃይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ፡፡3ታማኝነትህ ከሕይወት ይበልጣልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል፡፡4እንግዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ በስምህም እጆቼን አነሣሁ፡፡5ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ ደስ እያለኝ የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ6በመኝታዬ ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ፡፡7አንተ ረዳቴ ነህና በክንፎችህ ጥላ ውስጥ ሐሤት አደርጋለሁ፡፡8ነፍሴ አንተን የሙጥኝ ብላለች ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፡፡9ነፍሴን ማጥፋት የሚፈልጉ ግን ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤10በሰይፍ ይገደላሉ ለቀበሮችም ምግብ ይሆናሉ፡፡11ንጉሥ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል በእግዚአብሔ ስም የሚምሉ ሁሉ ይከብራ የሐሰተኞች አንደበትም ትዘጋለች፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ ድምፄን ስማ የብሶቴን ቃል አድምጥ፤ ከሚያስፈራ የጠላት ዛቻ ሕይወቴን አድናት2ከክፉ አድራጊዎች ዐድማ ሰውረኝ ከዐመፀኞችም ሤራ አድነኝ፡፡3እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ስለዋል መርዘኛ ቃላቸውንም እንደ ፍላጻ ያነጣጥራሉ4ካሸመቁበት ቦታ ሆነው ንጹሑን ሰው ይነደፋታል ድንገት ይነድፉታል፤ አይፈሩምም፡፡5ክፉ ዕቅድ ለማውጣት እርስ በርስ ይመካከራሉ፤ ወጥመድ ለመዘርጋትም በምስጢር ይነጋገራሉ፤ «ማንስ ሊያድን ይችላል?» ይባባላሉ፡፡6እነርሱ ክፉ ዕቅድ አወጡ፤ በሐሳባቸውም፣ «በጥንቃቄ ዕቅድ አውጥተናል» ይላሉ፡፡ የሰው ሐሳብና ልብ በጣም ጥልቅ ነው፡፡7እግዚአብሔር ግን በፍላጻው ይነድፋቸዋል እነርሱም በድንገት ይቆስላሉ፡፡8በገዛ ምላሳቸው ያሰናክላቸዋል ጥፋትንም ያመጣባቸዋል የሚያዩአቸው ሁሉ በመገረም ራሳቸውን ይነቀንቃሉ፡፡9የሰው ልጆች ሁሉ ይፈራሉ የእግዚብሔር ያደረገውንም በይፋ ይናገራሉ፡፡10ጻድቅ በያህዌ ደስ ይለዋል፤ እርሱንም መጠጊያው ያደርጋል ልበ ቅኖችም ሁሉ በእርሱ ይመካሉ፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፤ ለአንተ የተሳልነውንም እንፈጽማለን፡፡2ሥጋ ለባሽ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል፡፡3ኃጢአት በርትቶብን በነበረ ጊዜ አንተ መተላለፋችንን ይቅር አልህ፡፡4አንተ የመረጥኸው፣ በአደባባይህም እንዲኖር ወደ አንተ ያቀረብኸው ሰው ቡሩክ ነው፡፡ ከተቀደሰው መቅደስህ፣ ከቤትህም በረከት እንጠግባለን፡፡5የምድር ዳርቻዎችና ከባሕሩ ማዶ ርቀው ያሉ ሁሉ ተስፋ አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ፣ በጽድቅህ ድንቅ አሠራር መልስልን፡፡6በኃይልህ ተራሮችን አጽንተሃል ብርታትንም ታጥቀሃል፡፡7አንተ የባሕሮችን ማስገምገም የማዕበላቸውንም ጩኸት የሕዝቦችንም ውካታ ጸጥ ታሰኛለህ፡፡8ርቀው በምድር ዳርቻዎች ያሉ ካደረግኸው ድንቅ ሥራህ የተነሣ ይደነግጣሉ፡፡ ምሥራቅና ምዕራብ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋቸዋለህ፡፡9ዝናብ በማዝነብ ምድርን ትጐበኛለህ፤ ፍሬያማ በማድረግም ታበለጽጋታለህ፡፡ ለሰው ልጆች እህልን ይሰጡ ዘንድ የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፡፡ አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃል፡፡10ትልሟን ታረሰርሳለህ ወጣ ገባውን ታስተካክላለህ ዐፈሩን በካፊያ ታለሰልሳለህ ቡቃያዋንም ትባርካለህ፡፡11ለዓመቱ በጐነትህን ታቀዳጀዋለህ፤ ሰረገላህም በረከትን ሞልቶ ይፈስሳል፡፡12የምድረ በዳው ግጦሽ ቦታ እጅግ ለመለመ ኮረብቶችም ደስታን ለበሱ፡፡13መሰማሪያዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ ሸለቆዎች በሰብል ተሞሉ እልል እያሉም ዘመሩ፡፡
1ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ2ለስሙ ክብር ዘምሩ ምስጋናውን አድምቁ፡፡3እግዚአብሔርን፣ «ሥራህ እንዴት ድንቅ ነው! ከኃይልህ ታላቅነት የተነሣ ጠላቶችህ ይገዙልሃል፡፡4ምድር ሁሉ ያመልክሃል በዝማሬም ያመሰግኑሃል ለስምህም ይዘምራሉ» ባሉት፡፡ ሴላ5ኑ የእግዚአብሔርን ሥራ እዩ ለሰው ልጆ ያደረገውስ አስፈሪ ነው፡፡6ባሕሩን ደረቅ ምድር አደረገው ወንዙን በእግር ተሻገሩ እኛም እርሱ ባደረገው ነገር ደስ ብሎናል፡፡7በኃይሉ ለዘላለም ይነግሣል ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፡፡ እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ፡፡ ሴላ8ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔርን ባርኩ የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ፡፡9በሕያዋን መካከል አኑሮናል እግራችን እንዲንሸራተት አልፈቀደም፡፡10እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ፈተንኸን ብር እንደሚፈተን እኛን ፈተንኸን11ወደ ወጥመድ አገባኸን በጀርባችንም ከባድ ሸክም ጫንህብን፡፡12ሰዎች ራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ በእሳትና በውሃ መካከል አለፍን የኃላ ኃላ ግን ወደ ሰፊ ስፍራ አመጣኸን፡፡13የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ ቤትህ እመጣለሁ ስእለቴንም ለአንተ እከፍላለሁ፡፡14ይህም መከራ በደረሰብኝ ጊዜ ከአፌ የወጣ፣ በከንፈሮቼም የተናገርሁት ስእለት ነው፡፡15የሰቡ እንስሶችን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ፣ እንዲሁም መዓዛው ደስ የሚያሰኝ የአውራ በግ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፡፡16እናንት እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ኑና ስሙ፣ ለነፍሴ ያደረገላትን እነግራችኃለሁ፡፡17በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፤ በአንደበቴ አመሰገንሁት፡፡18በውስጤ ኃጢአት ይዤ ቢሆን ኖሮ ጌታ አይሰማኝም ነበር፡፡19አሁን ግን እግዚአብሔር በእርግጥ ሰምቶኛል ጸሎቴንም አድምጦአል፡፡20ጸሎቴን ያልናቀ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
1እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም ፊቱንም በላያችን ያብራ፡፡ ሴላ2መንገድህ በምድር ላይ ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ፡፡3እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝቦች ያመስግኑህ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ፡፡4አንተ ለሕዝቦች ቅን ስለምትፈርድላቸው የምድር ሕዝቦችን ስለምትመራ ሕዝቦች ሁሉ ደስ ይበላቸው በእልልታም ይዘምሩ፡፡ ሴላ5እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝቦች ያመስግኑህ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ፡፡6ምድር ፍሬዋን ሰጠች አምላካችን እግዚአብሔር ባርኮናል፡፡7እግዚአብሔር ባርኮናል የምድር ዳርቻዎች ሁሉ እርሱን ያከብሩታል፡፡
1እግዚአብሔር ይነሣ የሚጠሉትም ከፊቱ ይበተኑ፡፡2ጢስ እንደሚበንን፣ እንዲሁ አብንናቸው፤ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ እንዲሁ ክፉች ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ፡፡3ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ ደስታንና ሐሤትን ይሞሉ፡፡4ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም የምስጋና መዝሙር አቅርቡ በደመናት ላይ የሚሄደውን ከፍ አድርጉት፡፡ ስሙ ያህዌ ነው! በፊቱም ሐሤት አድርጉ፡፡5በተቀደሰ ማደሪያው ያለው አምላክ አባት ለሌላቸው አባት ነው፡፡ ለመበለቶችም ዳኛ ነው፡፡6እግዚአብሔር ብቸኞች በቤተ ሰብ መካከል ያኖራቸዋል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃቸዋል፤ ክፉዎች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ፡፡7እግዚአብሔር ሆይ፣ በሕዝብህ ፊት ባለፍህ ጊዜ በምድረ በዳ በተጓዝህ ጊዜ፣8በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ምድር ተንቀጠቀጠች ሰማያትም ዶፍ አወረዱ፡፡9እግዚአብሔር ሆይ፣ በቂ ዝናብ አዘነብህ ደርቆ የነበረውን ርስትህን አረሰረስህ፡፡10ሕዝብህ መኖሪያው አደረጋት፤ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ከመልካምነትህ ለድኾች ሰጠህ፡፡11እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ቃሉን ሰጠ ቃሉን የሚያውጁትም ብዙ ሰራዊት ናቸው፡፡12-13የሰራዊት ነገሥታት ፈጥነው ወደ ኋላ ሸሹ፤ በሰፈር የቀሩ ሴቶችም ምርኮ ተከፋፈሉ በበጐች በረት መካከል ብትገኙ እንኳ በቅጠልያ ወርቅ እንደ ተለበጡ ላባዎች ናችሁ፡፡14ሁሉን ቻዩ በዚያ የነበሩትን ነገሥታት በበተነ ጊዜ፣ ከሰልሞን ተራራ እንደሚወርድ በረዶ አደረጋቸው፡፡15አንተ ብርቱ የባሰን ተራራ ሆይ፤ እናንት ባለ ብዙ ጫፍ ተራሮች ሆይ፣ እግዚአብሔር ሊኖርበት የመረጠውን ተራራ፣ በእርግጥ እግዚአብሔር ለዘላለም16የሚኖርበትን ተራራ ለምን በምቀኝነት ትመለከቱታላችሁ?17የእግዚአብሔር ሰረገላዎች እልፍ አእላፍ ነቸው ሺህ ጊዜም ሺህ ናቸው ጌታ በተቀደሰው ቦታ በሲና በመካከላቸው ነው፡፡ 18ወደ ላይ ዐረግህ፣ ምርኮን አጋበስህ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ በዚያ ትኖር ዘንድ ከአንተ ጋር ከተዋጉት እንኳ ሳይቀር፣ ከሰዎች ስጦታን ተቀበልህ፡፡19በየዕለቱ ሸክማችንን የሚሸከምልን መድኃኒታችን የሆነው እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ሴላ20አምላካችን የሚያድን አምላክ ነው ከሞት ሊታደገን የሚቻለው ጌታ ያህዌ ነው፡፡21እግዚአብሔር የጠላቶችን ራስ በኃጢአታቸውም የሚጸኑትን ሰዎች ጠጉራም ዐናት ይፈነክታል፡፡22ጌታ እንዲህ አለ፤ «ጠላቶቼን ከባሳን መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ ከባሕርም ጥልቅ አውጥቼ አመጣቸዋለሁ፤23እግርህ በጠላትህ ደም እንዲጠልቅ የውሻህም ምላሽ ከጠላትህ ድርሻውን እንዲያገኝ ነው፡፡»24አምላክ ሆይ፣ የክብር አካሄድህን፣ አምላኬና ንጉሤ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚያደርገውን የክብር አካሄድ አዩ፡፡25የሚጫወቱ ከኋላ ሆነው ሲሄዱ መዘምራን ከፊት፤ መሣሪያ መካከላቸው ከበሮ የሚመቱ ደናግል ነበሩ፡፡26እግዚአብሔርን በጉባኤ አመስግኑት በእውነት የእስራኤል ዘር የሆናችሁ ያህዌን አመስግኑት፡፡27በመጀመሪያ በቁጥር ታናሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ ቀጥሎም የይሁዳ መሪዎችና ሰራዊቶቻቸው ታዩ፤ በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ፡፡28እግዚአብሔር ሆይ፣ በቀድሞ ዘመን እንደዳረግኸው ኃይልህን ግለጥ29ነገሥታት ስጦታቸውን ከሚያመጡልህ በኢየሩሳሌም ካለው ቤተ መቅደስህ ኃይልህን ግለጥ፡፡30በሸምበቆ መካከል ያሉትን አራዊት ገሥጽ ኮርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጸቸው፡፡ አዋርዳቸው ስጦታዎች እንዲመጡልህም አድርጋቸው ጦርነትን የሚወዱ ሕዝቦችንም በትናችው፡፡31መሳፍንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች፡፡32እናንት የምድር መንግሥታት ለያህዌ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፡፡ ሴላ33ከጥንት ጀምሮ ከነበሩት ሰማያት በላይ ለሚራመደው በኃያል ድምፁ ለሚያስገመግመው ዘምሩ፡፡34ግርማው በእስራኤል ላይ ኃይሉም በሰማያት ላይ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ኃይል ዐውጁ፡፡35እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ በመቅደስህ ድንቅ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ ለሕዝቡ ኃይልና ብርታት ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ይባረክ!
1የውሃ ሙላት እስከ አንገቴ ደርሶአልና አምላክ ሆይ አድነኝ፡፡2መቆሚያ ስላጣሁ በጥልቁ ረግረግ ውሃ ለመስጠም ተቃርቤአለሁ፡፡3ብዙ ከመጮኼ የተነሣ ዛልሁ ጉሮሮየም ደረቀ፤ አምላኬን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ፡፡4ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ከራስ ጠጉሬ ይልቅ በዝተዋል፤ ብዙ ጠላቶቼ እኔን ማጥፋት ይፈልጋሉ ያልሰረቅሁን ነገር መልሰህ አምጣ ተባልሁ፡፡5እግዚአብሔር ሆይ አንተ ሞኝነቴን ታውቃለህ ኃጢአቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም፡፡6የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ አንተን ተስፋ የሚያደርጉ በእኔ ምክንያት አይፈሩ፡፡ የእስራኤል አምላክ ሆይ፣ አንተን አጥብቀው የሚሹህ በእኔ ምክንያት አይዋረዱ፡፡7ስለ አንተ ስድብን ታግሼአለሁ እፍረትም ፊቴን ሸፍኖአል፡፡8ለወንድሞቼ እንደ እንግዳ ለእናቴም ልጆች እንደ ባዕድ ሆንሁባቸው፡፡9የቤትህ ቅናት በላችኝ ለአንተ የተሰነዘረው ስድብ እኔ ላይ ዐረፈ፡፡10በምጾምበት ጊዜ በጣም አለቀስሁ እነርሱም ሰደቡኝ፡፡11ማቅ በለበስሁ ጊዜ መተረቻ አደረጉኝ፡፡12በከተማው ቅጥር ለሚቀመጡ የመነጋገሪያ ርእስ ለሰካራሞችም መዝፈኛ ሆንሁ፡፡13ያህዌ ሆይ፣ እኔ ግን በወደድኸው ሰዓት ወደ አንተ እጸልያለሁ፡፡ በታላቅ ምሕረትህ፣ በማዳንህም ርግጠኝነት መልስልኝ፡፡14ከረግረግ አውጣኝ እንድሰጥምም አትተወኝ፡፡ ከጥልቁ ውሃ ከእነዚያ ከሚጠሉኝም ታደገኝ፡፡15ጐርፍ አያጥለቅልቀኝ ጥልቁ ውሃም አይዋጠኝ ጉድጓዱም ተደርምሶ አይዘጋብኝ፡፡16ያህዌ ሆይ፣ የኪዳንህ ታማኝነት በጐ ናትና ስማኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መልስልኝ17ከባርያህ ፊትህን አትሰውር ተጨንቄአለሁና ፈጥነህ መልስልኝ፡፡18ወደ እኔ ቀርበህ አድነኝ ስለ ጠላቶቼም ተቤዠኝ፡፡19የደረሰብኝን ስድብ፣ እፍረትና ውርደት ታውቃለህ ጠላቶቼንም አንድ በአንድ ታውቃቸዋለህ፡፡20ስድብ ልቤን ሰብሮታልና ተስፋ ቆረጥሁ፡፡ የሚያዝንልኝ ፈለግሁ ማንም አልነበረም የሚያጽናናኝም ፈለግሁ ማንንም አላገኘሁም፡፡21ምግቤን ከሐሞት ጋር ቀላቀሉ ለጥማቴም ሆምጣጤ ሰጡኝ፡፡22በፊታቸው የቀረበው ማእድ ወጥመድ ይሁንባቸው ደኅና ነን ሲሉ አሽክላ ይሁንባቸው፡፡23ማየት እንዳይችሉ ዐይናቸው ይጨልም ጀርባቸውም ዘወትር ይጉበጥ፡፡24መዓትህን በላያቸው አፍስስ፤ የቁጣህም መቅሠፍት ድንገት ይድረስባቸው፡፡25መኖሪያቸው ወና ይሁን! በድንኳኖቻቸውም የሚኖር አይገኝ፡፡26አንተ የመታኸውን አሳደዋልና ያቆሰልሃቸውንም ሥቃይ አባብሰዋል፡፡27በበደላቸው ላይ በደልን ጨምርባቸው ወደ ጽድቅህ ድል አይግቡ፡፡28ከሕይወት መጽሐፍ ይደምሰሱ ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ፡፡29እኔ ግን ምስኪንና ሐዘነተኛ ነኝና አምላክ ሆይ፣ ማዳንህ ደግፎ ይያዘኝ፡፡30የእግዚአብሔርን ስም በዝማሬ አመሰግናለሁ በውዳሴም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፡፡31ከበሬ ይልቅ፣ ቀንድና ጥፍር ካበቀለ እንቦሳ ይበልጥ ይህ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል፡፡32ገሮች ይህን ባዩ ጊዜ ደስ ይላቸዋል እናንተ እግዚአብሔርን የምትሹ በርቱ፡፡33ያህዌ ችግረኞችን ይሰማልና በእስራት ያለውንም ሕዝቡን አይንቅም፡፡34ሰማይና ምድር፣ ባሕሮችና በውስጡ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያመስግኑት፡፡35እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይሠራቸዋልና ሕዝቡም በዚያ ይሰፍራል ይወርሷታልም፡፡36የባርያዎቹም ዘሮች ይወርሷታል ስሙንም የሚወዱ በዚያ ይኖራሉ፡፡
1አምላክ ሆይ አድነኝ፤ ያህዌ ሆይ፣ ፈጥነህም እርዳኝ፡፡2ሕይወቴን ማጥፋት የሚፈልጉ ይፈሩ ይዋረዱም፤3በእኔ ስቃይ ደስ የሚላቸው ተሸማቅቀው ወደ ኋላ ይመለሱ፡፡4ነገር ግን አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፤ ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ሁልጊዜ፣ «እግዚአብሔር ታላቅ ነው» ይበሉ፡፡5እኔ ምስኪንና ችግረኛ ነኝ፤ አምላክ ሆይ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ አንተ ረዳቴ ታዳጊዬም ነህና ያህዌ ሆይ አትዘግይ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አደረግሁ ፈጽሞ አልፈር፡፡2በጽድቅህ ታደገኝ አስጥለኝም ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድነኝም፡፡3በምሄድበት ቦታ ሁሉ አንተ መጠጊያ ዐምባ ሁነኝ፡፡ አንተ ዐለቴ፣ ምሽጌ ነህና እኔን ለማዳን ትእዛዝ ከአንተ ይውጣ፡፡4አምላኬ ሆይ፣ ከዐመፀኛ ርኅራኄ ከሌለው ከጨካኝ እጅ ታደገኝ፡፡5ጌታ ያህዌ ሆይ፣ አንተ ተስፋዬ ነህና ከልጅነቴ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁና፡፡6ከተወለድሁ ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ ከእናቴ ማሕፀን ያወጣኸኝም አንተ ነህ ምስጋናዬ ዘወትር ለአንተ ነው፡፡7አንተ ብርቱ መጠጊያየ ስለሆንህልኝ ሕይወቴ ለብዙዎች ምሳሌ ሆነ፡፡8አፌ በምስጋናህ ተሞልቶአል ስለ ክብርህም ቀኑን ሙሉ እናገራለሁ፡፡9በእርጅና ዘመኔ አትጣለኝ ጉልበቴም በደከመ ጊዜ አትተወኝ፡፡10ጠላቶቼ ተነጋግረውብኛልና ሕይወቴን ማጥፋት የሚፈልጉም በእኔ በአንድነት አሢረዋል፡፡11እነርሱም፣ «እግዚአብሔር ትቶታል፣ የሚያስጥለው የለምና ተከታትላችሁ ያዙት» አሉ፡፡12አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ፣ አምላኬ ሆይ፣ እኔን ለማዳን ፍጠን፡፡13ተቃዋሚዎቼ ይፈሩ፤ ይጥፉም ሊጐዱኝ የሚፈልጉ ይፈሩ ይዋረዱም፡፡14እኔ ግን ዘወትር አንተን ተስፋ አደርጋለሁ በምስጋና ላይ ምስጋና አቀርብልሃለሁ፡፡15ምንም እንኳ ማስተዋል ቢያዳግተኝ አንደበቴ ዘወትር ስለ ጽድቅህና ስለ ማዳንህ ይናገራል፡፡16መጥቼ የጌታ ያህዌን ብርቱ ሥራ ዐውጃለሁ የአንተን ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ፡፡17እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ከልጅነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ እኔም እስከ ዛሬ ድረስ ድንቅ ሥራህን እናገራለሁ፡፡18አምላክ ሆይ፣ ሳረጅና ስሸብትም አትተወኝ እኔም ኃያልነትህን ለመጪው ትውልድ ብርታህንም ኃላ ለሚነሣ ሕዝብ እናገራለሁ፡፡19አምላክ ሆይ፣ ጽድቅህ እስከ ሰማያት ከፍ ያለ ነው አንተ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?20ብዙ ችግርና መከራ ብታሳየኝም ሕይወቴን እንደ ገና ታድሳለህ፡፡ ከምድር ጥልቅም እንደ ገና ታወጣኛለህ21ክብሬን ትጨምራለህ ተመልሰህም ታጽናናኛለህ፡፡22አምላኬ ሆይ፣ ስለ ታማኝነትህ በበገና አመሰግንሃለሁ፤ የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፣ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ፡፡23ለአንተ የምስጋና መዝሙር ሳቀርብ፣ ከንፈሮቼ በደስታ ይሞላሉ አንተ ያዳንሃት ነፍሴም እልል ትላለች፡፡24አንደበቴ ቀኑን ሙሉ ስለ ጽድቅህ ያወራል፤ የእኔን መጐዳት የሚፈልጉ አፍረዋልና ተዋርደዋልምና፡፡
1እግዚአብአብሔር ሆይ፣ ለንጉሡ ትክክለኛ ፍርድን ለንጉሡም ልጅ ጽድቅህን ስጠው፡፡2እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ፣ ይዳኛል ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል፡፡3ተራሮች ሰላምን፣ ኮረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ያመጣሉ፡፡4ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል የችግረኞችን ልጆች ያድናል ጨቋኙንም ያደቀዋል፡፡5ፀሐይ እስካለች ድረስ፣ ጨረቃም እስከምትኖርበት ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ፣ አንተን ያከብራሉ፡፡6በታጨደ መስክ ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ ይውረድ እንደ ካፊያም ምድርን ያረስርስ፡፡7በዘመኑ ጽድቅ ይስፈን ጨረቃም ብርሃንዋ በምትሰጥበት ዘመን ሁሉ ብርልጽግና ይብዛለት፡፡8ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር ከታላቁም ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይሁን፡፡9በምድረ በዳ የሚኖሩ በፊቱ ይስገዱ ጠላቶቹም ወደ መሬት ወድቀው ትቢያ ይላሱ፡፡10የተርሴስ ነገሥታትና ደሴቶች ስጦታ ያምጡለት የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡11ነገሥታት ሁሉ ይስገዱለት ሕዝቦችም ሁሉ ያገልግሉት፡፡12ወደ እርሱ የሚጮኸውን ችግረኛ ሌላ ረዳት የሌለውን ድኻ ይረዳልና፡፡13ለድኻና ለችግረኛ ይራራል ምስኪኖችንም ከሞት ያድናል፡፡14ሕይወታቸውን ከጭቆናና ከግፍ ያድናል ደማቸውም በፊቱ የከበረ ነው፡፡15ዕድሜው ይርዘም፤ ከዐረብ ወርቅ ይምጣለት፤ ዘወትር ይጸልዩለት የእግዚአብሔር በረከት አይለየው፡፡16በምድሪቱ እህል ይትረፍረፍ በተራሮች አናት ያለው ሰብል ይወዛወዝ፡፡ ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤ በከተማ ያለውም ሕዝብ እንደ ሜዳ ሣር ይብዛ፡፡17ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች በእርሱ ይባረኩ ሰዎች ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበሉት፡፡18ብቻውን ድንቅ የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ ያህዌ ይባረክ፡፡19ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ ምድር ሁሉ በክብሩ ትሞላ፡፡ አሜን፤ አሜን20የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎት እዚህ ላይ ተፈጸመ።
1ልባቸው ንጹሕ ለሆነ ለእስራኤል እግዚአብሔር ቸር ነው፡፡2እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ፡፡3ክፉዎች ሲሳካላቸው ዐይቼ ቅናት አድሮብኝ ነበር፡፡4እስኪሞቱ ድረስ ሕመም አያውቃቸውም ሰውነታቸውም ጤነኛና ጠንካራ ነው፡፡5እንደ ሌሎች ሰዎች አይጨነቁም በሌሎች ላይ የሚደርሰው ስቃይ እነርሱ ላይ አይደርስም፡፡6ትዕቢት የአንገት ጌጣቸው ነው ግፍን እንደ ልብስ ለብሰውታል፡፡7የሰባ ዐይናቸውም ይጉረጠርጣል፣ ልባቸው ክፉ ሐሳብ ያፈልቃል፡፡8በፌዝና በክፋት ይናገራሉ በእብሪት ተነሣሥተው ሌሎች ላይ ይዝታሉ፡፡9አፋቸውን በሰማይ ያላቅቃሉ አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል፡፡10ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይመለሳል ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ፡፡11«እግዚአብሔር እንዴት ሊያውቅ ይችላል በልዑልስ ዘንድ ዕውቀት አለ?» ይላሉ፡፡12እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው ሁልጊዜ እንደ ተዝናኑ ናቸው በሀብት ላይ ሀብት ይጨምራሉ፡፡13ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት እኔን በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሮአል!14ቀኑን ሙሉ ተሰቃየሁ በየማለዳውም ተቀጣሁ፡፡15እኔ እንደዚህ እናገራለሁ ብል ኖሮ የልጆችህን ትውልድ በከዳሁ ነበር፡፡16እነዚህን ነገሮች ለመረዳት ብሞክርም በጣም ከባድ ሆነብኝ፡፡17ወደ መቅደስህ እስክገባ ድረስ ምንም ማወቅ አልቻልሁም በኋላ ግን በክፉዎች ላይ ምን እንደሚደርስባቸው ተረዳሁ፡፡18በእርግጥ በሚያዳልጥ ስፍራ አኑረሃቸዋል ወድቀው እንዲጠፉም አድርገሃል፡፡19እንዴት ፈጥነው በቅጽበት ጠፉ! በከባድ ድንጋጤ ፈጽመው ወደሙ፡፡20ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ ጌታ ሆይ፣ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣ እነርሱ በማለዳ እንደሚረሳ ሕልም ይሆናሉ፡፡21ልቤ በጣም ተማረረች፣ እኔም እጅግ ቆሰልሁ፡፡22ስሜት የሌለው አላዋቂ ሆንሁ በፊትህም እንደ እንስሳ ሆንሁ፡፡23ይህም ሆኖ ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ አንተም ቀኝ እጄን ይዘኸኛል፡፡24በምክርህ ትመራኛለህ በመጨረሻም በክብር ትቀበለኛለህ፡፡25በሰማይ ከአንተ በቀር ማን አለኝ? በምድርም ከአንተ ሌላ የምፈልገው የለኝም፡፡26ሥጋዬና ልቤ ደከሙ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም የልቤ ብርታትና አለኝታ ነው፡፡27እነሆ፣ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ ለአንተ ያልታመኑትንም ታጠፋቸዋለህ፡፡28ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፣ ጌታ ያህዌን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ ሥራህንም ሁሉ እናገራለሁ፡፡
1አምላክ ሆይ፣ ለዘላለም የጣልኸን ለምንድነው? በመሰማሪያህ በጐችህስ ላይ ቁጣህ የነደደው ለምንድነው?2ከጥንት ጀምሮ የመረጥኸውን ሕዝብ ርስትህ እንዲሆን የዋጀኸውን ነገድ፣ መኖርያህ ያደረግሃትን የጽዮን ተራራን አስብ፡፡3ጠላት ለዘለቄታው ባድማ ያደረገውን መቅደስህ ውስጥ ያወደመውን ሁሉ ተመልከት፡፡4ጠላቶችህ አንተ በመረጥኸው ቦታ መካከል ደነፉ፤ የጦርነት ዓርማቸውንም ምልክት አድርገው በዚያ አቆሙ፡፡5እነርሱ ጥቅጥቅ ባለው ደን ውስጥ እንጨቶችን በመጥረቢያ የሚቆርጥ ሰው ይመስላሉ፡፡6በእደ ጥበብ ያጌጠውን ሥራ ሁሉ፣ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰባብረው አደቀቁት፡፡7መቅደስህን አፍርሰው በእሳት አቃጠሉት የስምህን ማደሪ አረከሱ፡፡8በልባቸውም፣ «ገና ሁሉንም እናጠፋቸዋለን!» አሉ፡፡ በምድሪቱ ያሉ የተቀደሱ ቦታዎችን ሁሉ አቃጠሉ፡፡9የምናየው ምልክት የለም ከእንግዲህ ወዲህ ነቢያትም አይኖሩም፤ ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል ከእኛ መካከል የሚያውቅ የለም10አምላክ ሆይ፤ ጠላት የሚሳደበው እስከ መቼ ነው? ባላንጣስ ለዘላለም በስምህ ያላግጣልን?11እጅህን፣ ቀኝ እጅህን የምትመልሰው ለምንድነው? ቀኝ እጅህን ከብብትህ አውጥተህ አጥፋቸው፡፡12እግዚአብሔር ሆይ፣ ከጥንት ጀምሮ አንተ ንጉሤ ነህ ማዳንህንም በምድር ላይ አደረግህ፡፡13በኃይልህ ባሕሩን ከፈልህ የባሕሩንም አውሬ ራስ ውሃ ውስጥ ቀጠቀጥህ፡፡14የሌዋታንን ራሶች አደቀቅህ ሥጋውንም በምድረ በዳ ለሚኖሩ ምግብ አድርገህ ሰጠሃቸው፡፡15ምንጮችንና ፈሳሾችን አፈለቅህ ወራጅ ወንዞችን አደረቅህ16ቀኑ የአንተ ነው፣ ሌሊቱም የአንተ ነው፤ ፀሐይንና ጨረቃንም በቦታቸው አደረግህ፡፡17የምድር ዳርቻዎችን ሁሉ የወሰንህ አንተ ነህ ክረምትና በጋ እንዲፈራረቁ አደረግህ፡፡18ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶችህ በአንተ ላይ መሳለቃቸውን ጅል ሰዎችም ስምህን መዳፈራቸውን ተመልከት፡፡19የርግብህን ነፍስ ለዱር አራዊት አሳልፈህ አትስጥ፤ የተጨቆኑ ሕዝብህንም ለዘላለም አትርሳ፡፡20የምድር ጨለማ ቦታዎች በዐመፅ ተሞልተዋልና ኪዳንህን አስብ፡፡21የተጨቆኑት አፍረው አይመለሱ ችግረኞችና ጭቁኖች ስምህን ያመስግኑ፡፡22አምላክ ሆይ፣ ተነሥ ለክብርህ ተሟገት ከንቱ ሰው ቀኑን ሙሉ አንተ ላይ ማላገጡን ተመልከት፡፡23የባላጋራዎችህን ድንፋታ ዘወትር የሚሰነዝሩትን ስድብ አትርሳ፡፡
1አምላክ ሆይ፣ እናመሰግንሃለን ሐልዎትህን ስለ ገለጥህ ምስጋና ለአንተ እንሰጣለን፤ ሰዎች ድንቅ ሥራህን ይናገራሉ፡፡2አንተም እንዲህ አልህ፣ «ለይቼ በወሰንሁት ሰዓት በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ፡፡3ምድር ብትናወጥ በውስጧ የሚኖሩትም ቢንቀጠቀጡ እኔ የምድርን መሠረት አጸናለሁ፡፡ ሴላ፡፡4ትዕቢተኞችን፣ አትታበዩ ክፉዎችን ‹አታምፁ› እላቸዋለሁ፤5ቀንድህን ወደ ሰማይ አታንሣ፤ ዐንገትህንም መዝዘህ አትናገር፡፡»6ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣም፡፡7ነገር ግን አንዱን ዝቅ፣ ሌላውን ከፍ በማድረግ በትክክል የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፡፡8ያህዌ በእጁ የቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ ይዞአል ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ጨልጠው ይጠጡታል፡፡9እኔ ግን ዘወትር ሥራህን እናገራለሁ፤ ለያዕቆብ አምላክም ዝማሬ አቀርባለሁ፡፡10እርሱ «የክፉዎችን ሁሉ ቀንድ እሰብራለሁ፤ የጻድቃን ቀንድ ግን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ» ይላል፡፡
1እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው፡፡2ድንኳኑ በሳሌም መኖሪያውም በጽዮን ነው፡፡3በዚያም የቀስቱን ፍላጻዎች ጋሻውን፣ ጦሩንና ሌሎች የጦር መሣሪያዎችን ሰበረ፡፡ ሴላ4ጠላቶችህን ካጠፋህበት ተራሮች ስትወርድ ደምቀህ አበራህ፤ ክብርህንም ገለጥህ፡፡5ጀግኖች ተኝተው እያሉ የማረኩትን ተቀሙ ጦረኞችም ሁሉ ዐቅመ ቢስ ሆኑ፡፡6የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሱና ፈረሰኛው ጭልጥ ብለው ተኝተዋል፡፡7መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤ በተቆጣህ ጊዜ ፊትህ መቆም የሚችል ማነው?8አንተ ከሰማይ ፍርድህን አሰማህ ምድርም ፈርታ ጸጥ አለች9አንተ በምድር የተጨቆኑትን ለማዳን ለፍርድ ስትነሣ ዓለም ጸጥ አለ፡፡10በእርግጥ የሰው ልጅ ላይ የሚወርደው ቁጣ ፍርድህ አንተን ያመሰግንሃል ከቁጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ፡፡11ለአምላካችሁ ለያህዌ ተሳሉ፣ ስእለቱንም አግቡ በእርሱ ዙሪያ ያሉ ሁሉ መፈራት ለሚገባው እጅ መንሻ ያምጡ፡፡12እርሱ የገዦችን መንፈስ ይሰብራል በምድር ነገሥታትም ዘንድ የተፈራ ይሆናል፡፡
1ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ ይሰማኝ ዘንድ ድምፄን ከፍ አድርጌ እግዚአብሔርን እጠራለሁ፡፡2በመከራዬ ቀን ጌታን ፈለግሁት በሌሊትም ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘረጋሁ፤ ነፍሴ አልጽናና አለች፡፡3አምላኬ ሆይ፣ አንተን ባሰብሁ ቁጥር ቃተትሁ ባወጣሁ ባወረድሁ መጠን መንፈሴ ዛለች፡፡4ዐይኖቼ እንዳይከደኑ አደረግህ መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ፡፡5የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ የድሮውን ዘመን አወጠነጠንሁ፡፡6በሌሊት ዝማሬዬን አስታወስሁ በጥልቅ በማሰብ እየሆነ ያለውን መረዳት ሞከርሁ፡፡7እግዚአብሔር ለዘላለም ጥሎኛልን? ከእንግዲህስ ቸርነት አያደርግልኝምን?8የኪዳን ታማኝነቱስ እስከ ወዲያኛው ተሻረን? የተስፋ ቃሉንስ ዘነጋ?9እግዚአብሔር ቸርነቱን ረሳ? ወይስ ከቁጣው የተነሣ መራራቱን ትቶአልን? ሴላ10እኔም፣ «የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ ይህ የእኔ ደካማነት ነው» አልሁ፡፡11ያህዌ ሆይ፣ ሥራዎችህን ሁሉ አስታውሳለሁ ድሮ ያደረግኸውን ድንቅ ሥራ አስባለሁ፡፡12ሥራዎችህን ሁሉ አሰላሰላለሁ ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ፡፡13አምላክ ሆይ፣ መንገድህ ቅዱስ ነው እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?14እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ድንቆችን የምታደርግ አምላክ ነህ በሕዝቦች መካከል ኃይልህን ገለጥህ፡፡15በታላቅ ኃይልህ ለሕዝብህ ለያዕቆብና ለዮሴፍ ልጆች ድል ሰጠሃቸው፡፡ ሴላ16አምላክ ሆይ፣ ውሆች አዩህ ውሆች አንተን አይተው ፈሩ፤ ጥልቆችም ተነዋወጡ፡፡17ደመኖች ውሃ አንጠባጠቡ፡፡ ሰማያት አንጐዳጐዱ ፍላጾችህም ዙሪያውን አንጸባረቁ፡፡18የድምፅህ ነጐድጓድ ዐውሎ ነፋስ ውስጥ አስተጋባ የመብረቅ ብልጭታ ዓለምን አበራ ምድር ራደች ተንቀጠቀጠች፡፡19መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው ዱካህንም ማንም አላየም፡፡20በሙሴና በአሮን እጅ ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው፡፡
1ሕዝቤ ሆይ፣ ትምህርቴን ሰሙ የአፌንም ቃል አድምጡ፡፡2አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ ከጥንት ጀምሮ የተሰወረውን ምስጢር እገልጣለሁ፡፡3ይህም የሰማነውና ያወቅነው አባቶቻችንም የነገሩን ነው፡፡4እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም ስለ እግዚአብሔር ኃይል ስላከናወናቸውም ታላላቅ ሥራዎችና ስላደረጋቸው ድንቅ ነገሮች ለተከታዩ ትውልድ እንገራለን፡፡5ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ ለእስራኤልም ሕግን ደነገገ፡፡ ይህንንም ለሚቀጥለው ትውልድ እንዲያስተምሩ አባቶቻችንን አዘዘ፡፡6ይህም የሚመጣው ትውልድ ሥርዐቱን እንዲያውቅ እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው ገና ለሚወለዱትም እንዲነግሩ ነው፡፡7እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመኑ የእግዚአብሔርን ሥራ አይረሱም ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ፡፡8እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው እልኸኛና ዐመፀኛ አይሆኑም፤ እነርሱ እግዚአብሔርን በማመን አልጸኑም ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው አልኖሩም፡፡9የኤፍሬም ሰዎች የታጠቁ ቀስተኖች ቢሆኑም በጦርነት ቀን ወደ ኃላ ተመለሱ፡፡10የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፣ በሕጉ መሠረት መኖርም አልፈለጉም፡፡11ሥራዎቹን ረሱ ያሳያቸውንም ድንቆች ዘነጉ፡፡12በግብፅ ምድር፣ በዞዓር ምድር በአባቶቻቸው ፊት ያደረጋቸውን ድንቆች ዘነጋ፡፡13ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው ውሃውንም እንደ ግድግዳ አቆመው፡፡14ቀን በደመና፣ ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን መራቸው፡፡15በምድረ በዳ ዐለቱን ሰነጠቀ እንደ ባሕር የበዛ ውሃ ሰጣቸው፡፡16ከዐለቱ ምንጭ አፈለቀ ውሃውም እንደ ወንዝ እንዲፈስ አደረገ17እነርሱ ግን ኃጢአት ማድረጋቸውን ቀጠሉ፤ በምድረ በዳ በልዑል ላይ ዐመፁ፡፡18የተመኙትን ምግብ በመጠየቅ፣ ሆን ብለው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፡፡19እንዲህ በማለትም በእግዚአብሔር ላይ ተናገሩ፣ «ለመሆኑ፣ እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድ ማዘጋጀት ይችላልን?»20ዐለቱን ሲመታው ውሃ ተንዶለዶለ ጅረቶችም ጐረፉ፡፡ ታዲያ፣ እርሱ እንጀራንም መስጠት ይችላል? ለሕዝቡስ ሥጋ ማቅረብ ይችላል?21ያህዌ ይህን ሲሰማ እጅግ ተቆጣ በያዕቆብ ላይ እሳት ነደደ በእስራኤልም ላይ ቁጣው ተቀጣጠሉ፡፡22በእግዚአብሔር አላመኑም በእርሱም ማዳን አልተማመኑም፡፡23ሆኖም እርሱ ከላይ ያሉትን ሰማያትን አዘዘ የሰማይንም በሮች ከፈተ24ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ መና አዘነበላቸው የሰማይንም ምግብ ሰጣቸው፡፡25ሰዎች የመላእክትን እንጀራ በሉ፡፡ ጠግበው እስከሚተርፍ ድረስ ምግብ ላከላቸው፡፡26የምሥራቅን ነፋስ ከሰማይ አስነሣ የደቡብንም ነፍስ በኃይሉ አመጣ፡፡27ሥጋን እንደ ዐፈር ብዙ ውፎችንም እንደ ባሕር አሸዋ አዘነበላቸው፡፡28ሰፈራቸው መሓል በድንኳኖቻቸውም ዙሪያ አወረደ፡፡29ስለዚህ እስኪጠግቡ ድረስ በሉ አጥብቀው የተመኙትን ሰጣቸው፡፡30ነገር ግን ገና ምኞታቸውን ሳያረኩ፣ ምግቡ ገና አፋቸው ውስጥ እያለ፣31የእግዚአብሔር ቁጣ እነርሱ ላይ ተነሣ የእስራኤልን ኃያላን ሰዎች ገደለ ምርጥ ወጣቶችንም በአጭር ቀጨ፡፡32ይህም ሆኖ፣ ኃጢአት ማድረጋቸውን ቀጠሉ፤ ድንቅ ሥራዎቹንም አላመኑም፡፡33ስለዚህ ዘመናቸውን አሳጠረ ዕድሜያቸውም በሽብር እንዲያልቅ አደረገ፡፡34እርሱ በገደላቸው ጊዜ ፈለጉት ከልባቸው በመሻትም ወደ እርሱ ተመለሱ፡፡35እግዚአብሔር ዐለታቸው፣ ልዑል አምላክ ታዳጊያቸው እንደ ሆነ አስቡ፡፡36ነገር ግን በአፋቸው ሸነገሉት በአንደበታቸውም ዋሹት፡፡37ልባቸው በእርሱ የጸና አልነበረም ለኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም፡፡38እርሱ ግን መሐሪ ስለሆነ ኃጢአታቸውን ይቅር አለ፤ እነርሱንም አላጠፋም ቁጣውን ብዙ ጊዜ ገታ መዐቱንም አላወረደም፡፡39ካለፈ በኋላ እንደማይመለስ ነፋስ ሥጋ ለባሾች መሆናቸውን አሰበ፡፡40በምድረ በዳ ስንት ጊዜ ዐመፁበት በበረሐስ ምን ያህል አሳዘኑት!41ደግመው ደጋግመው እግዚአብሔርን ተፈታተኑት የእስራኤልንም ቅዱስ አስቆጡት፡፡42ኃይሉን አላሰቡም፣ እነርሱን ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳነበትን፣ ቀንና ታላቁን ኃይሉን አላስታወሱም፡፡43በግብፅ አገር፣ በዞዓር ሜዳ ያደረጋቸውን ታላላቅ ድንቆችና ምልክቶች ዘነጉ፡፡44ከወንዞቻቸው ወሃ መጠጣት እንዳይችሉ የግብፃውያንን ወንዞች ወደ ደም ለወጠ፡፡45ተናዳፊ የዝንብ ሰራዊት ሰደደባቸው፣ ጓጉንቸርም ላከባቸው፤ ምድራቸውንም አጠፋ፡፡46ሰብላቸውን ለኩብኩባ፣ ምርታቸውንም ለአንበጣ ሰጠ፡፡47የወይን ተክላቸውን በበረዶ የበለስ ዛፎቻቸውንም በውርጭ አጠፋ፡፡48ከብቶቻቸውን በበረዶ በጐቻቸውንም በመብረቅ ገደለ፡፡49ጽኑ ቁጣውን በላያቸው ሰደደ መዓቱን፣ የቅናቱንም ቁጣና መቅሠፍት ላከባቸው አጥፊ የመላእክት ሰራዊትም ሰደደባቸው፡፡50ለቁጣው መንገድ አዘጋጀ፤ ከሞትም አላዳናቸውም፡፡ ነገር ግን ሕይወታቸውን ለመቅሠፍት አሳልፎ ሰጠ፡፡51የዐፍላ ጉልበታቸው መጀመሪያ የሆኑትን በካም ድንኳኖች፣ በኩሮቻቸውንም ሁሉ በግብፅ ምድር ፈጀ፡፡52ሕዝቡን ግን እንደ በግ አሰማራቸው በምድረ በዳ እንደ መንጋ መራቸው53በሰላም ስለ መራቸው አልፈሩም ጠላቶቻቸውን ግን ባሕር ዋጣቸው፡፡54ከዚያም ወደ ተቀደሰች ምድሩ፣ ቀኝ እጁም ወዳስገኘው ወደዚህ ተራራ አመጣቸው፡፡55ሕዝቦችን ከፊታቸው አባረረ ምድራቸውንም ርስት አድርጐ አከፋፈላቸው፡፡ የእስራኤል ነገዶችን በጠላቶቻቸው ድንኳን አኖረ፡፡56እነርሱ ግን አምላክን ተፈታተኑት በልዑልም ላይ ዐመፁ፤ ትእዛዞቹንም አልጠበቁም፡፡57እንደ አባቶቻቸው ዐመፀኞችና ከዳተኞች ሆኑ፡፡ እንደማያስተማምን ጠማማ ቀስት ተወላገዱ፡፡58በኮረብታ ማምለኪያዎቻቸው አስቆጡት በጣዖቶቻቸውም አስቀኑት፡፡59እግዚአብሔር በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ እስራኤልንም ፈጽሞ ተወ፡፡60በሰዎች መካከል የኖረባትን ድንኳን፣ በሴሎ የነበረች ማደሪያውን ተዋት፡፡61የኃይሉን ምልክት አስማረካት፣ ክብሩንም ለጠላቶች እጅ አሳልፎ ሰጠ፡፡62ሕዝቡን ለሰይፍ ዳረገ በርስቱም ላይ እጅግ ተቆጣ፡፡63ጐልማሶቻቸውን እሳት በላቸው ለልጃገረዶቻቸውም የሰርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም፡፡64ካህናቶቻቸው በሰይፍ ተገደሉ መበለቶቻቸው ማልቀስ ተሳናቸው፡፡65ጌታም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ድፍረት እንደሚሰማው ጀግና ሆነ፡፡66ጠላቶቹን መትቶ ወደ ኋላ መለሳቸው የዘላለም ውርደትንም አከናነባቸው፡፡67የዮሴፍን ድንኳን ተዋት፣ የኤፍሬምንም ነገድ አልመረጠም፡፡68ነገር ግን የይሁዳን ነገድና የወደዳትን የጽዮን ተራራ መረጠ፡፡69መቅደሱን እንደ ሰማያት፣ እርሱ ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት፡፡70ባርያውን ዳዊትን መረጠ ከበጐች ጉረኖ ወሰደው፤71ለሕዝቡ ለያዕቆብ፣ ለርስቱም ለእስራኤል እረኛ ሊደርገው የሚያጠቡ በጐችን ከመከተል አመጣው፡፡72ዳዊትም በፍጹም ቅንነት ጠበቃቸው፤ በእጁ ብልኃትም መራቸው፡፡
1አምላክ ሆይ፣ ባዕድ ሕዝቦች ርስትህን ወረሩ! የተቀደሰ መቅደስህን አረከሱ ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አደረጓት፡፡2የባሪያዎችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣ የታማኞችህን ሥጋ ለምድር አራዊት ምግብ እንዲሆን ሰጡ፡፡3ደማቸውን በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ የሚቀብራቸውም አልተገኘም፡፡4እኛም ለጐረቤቶቻችን መዘባበቻ በዙሪያችን ላሉትም መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን፡፡5ያህዌ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ነው? የምትቆጣው ለዘላለም ነውን? ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?6አንተን በማያውቁ ሕዝቦች ላይ፣ ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ መዓትህን አፍስስ፤7ያዕቆብን ውጠውታልና መኖሪያ ቦታውንም ባድማ አድርገዋል፡፡8የአባቶቻችንን ኃጢአት እኛ ላይ አትቁጠርብን እጅግ ተዋርደናልና ምሕረትህ ፈጥና ወደ እኛ ትምጣ፡፡9መድኃኒታችን እግዚአብሔር ሆይ፣ ስለ ስምህ ክብር ርዳን፤ ይቅርም በለን፡፡10ሕዝቦች፣ «አምካቸው የት አለ?» ለምን ይበሉ? ስለ ፈሰሰው የባሪያዎችህ ደም፣ ዐይናችን እያየ ሕዝቦችን ተበቀል፡፡11የእስረኞች ሰቆቃ ወደ አንተ ይድረስ በኃይልህ ብርታት ሞት የተፈረደባቸውን አድን፡፡12ጌታ ሆይ፣ ጐረቤቶቻችን አንተ ላይ ስለ ሰነዘሩት ስድብ ሰባት ዕጥፍ ተበቀላቸው፡፡13እኛ ሕዝብህ፣ የመሰማሪያ በጐችህ ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፡፡ ለትውልድ ሁሉ ምስጋናህን እንናገራለን፡፡
1ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፣ ስማን፡፡ በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፣ ብርሃንህ ይብራልን!2በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ኃይልህን ግለጥ፤ መጥተህም አድነን፡፡3አምላክ ሆይ፣ መልሰን ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡4የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በሕዝብህ ጸሎት ላይ የምትቆጣው እስከ መቼ ነው?5የእንባ እንጀራ አበላሃቸው ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው፡፡6የጐረቤቶቻችን መከራከሪያ አደረግኸን ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን፡፡7የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡8የወይን ግንድ ከግብፅ አመጣህ አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልህ፡፡9መሬቱን መነጠርህላት፣ እርሷም ሥር ሰድዳ መሬቱን ሞላች፡፡10ተራሮችም በጥላዋ ተሸፈኑ የቅርንጫፎቿም ጥላ የሊባኖስን ዛፎች ሸፈነ፡፡11ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ ቁጥቋጦዋንም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ዘረጋች፡፡12ታዲያ፣ አላፊ፣ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲቀጥፍ በዙሪያዋ የነበሩ አጥሮችን ለምን አፈረስህ፡፡13የዱር አሳማ ያበላሻታል በሜዳ የሚንጋጋም አራዊት ይበላታል፡፡14የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ ወደ እኛ ተመለስ፣ ከሰማይ ተመልከት እይም ይህችን የወይን ተክልም ተንከባከባት፡፡15ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ተክል አንተም ያጸደቅሃት ተክል ናት፡፡16ነገር ግን ቆራርጠው በእሳት አቃጠሏት ከቁጣህ የተነሣ ይጠፋሉ፡፡17እጅህ የቀኝ እጅህ የሆነው ሰው ላይ፣ አንተ ራስህ ብርቱ ያደረግኸው የሰው ልጅ ላይ ትሁን18እኛም ከአንተ ወደ ኋላ አንልም፤ በሕይወት ጠብቀን፤ እኛም ስምህን እንጠራለን፡፡19ሰራዊት አምላክ ያህዌ ሆይ፣ መልሰን ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡
1ብርታታችን ለሆነው አምላክ በደስታ ዘምሩ ለያዕቆብ አምላክ በደስታ እልል በሉ፡፡2ለመዘመር ተነሡ፤ ከበሮም ምቱ በበገናና በመሰንቆ ደስ የሚል ዜማ አሰሙ፡፡3በሙሉ ጨረቃ በክብረ በዓላችን ቀን በወሩ መግቢያ ጨረቃ ስትወለድ ቀንደ መለከት ንፉ፡፡4ይህም ለእስራኤል የተደነገገ፣ የያዕቆብ አምላክ የሰጠው ሥርዐት ነው፡፡5ግብፅን ለቅቆ በወጣ ጊዜ ይህን ለዮሴፍ ደነገገ፤ በማላውቀውም ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤6«ከትከሻው ሸክምን አስወገድሁ እጆቹንም ቅርጫት ከመያዝ አሳረፍሁ፡፡7በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ረዳሁህ በነጐድጓድ መሰወሪያ ውስጥ መለስሁልህ በመሪባ ውሃ ዘንድ ፈተንሁህ፡፡ ሴላ8ሕዝቤ ሆይ፣ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ እስራኤል ሆይ፣ ምነው ባደመጥኸኝ!9ባዕድ አምላክ በመካከልህ አይሁን ሌሎች አማልክት አታምልክ፡፡10እኔ ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ ያህዌ ነኝ፡፡ አፍህን በሰፊው ክፈት፤ እኔም እሞላዋለሁ፡፡11ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰማም እስራኤልም ለእኔ አልታዘዝም፡፡12ስለዚህ በእልከኝነት መንገዳቸው እንዲሄዱ፣ የፈለጉትንም እንዲያደርጉ ተውኳቸው፡፡13ምነው ሕዝቤ ባደመጠኝ ኖሮ፣ እስራኤል በመንገዴ ሄዶ ቢሆን ኖሮ፡፡14ፈጥኜ ጠላቶቻቸውን አስገዛላቸው ነበር እጄንም በጨቋኞቻቸው ላይ ባነሣሁ ነበር፡፡15ያህዌን የሚጠሉ በፊቱ በፍርሃት ይሸማቀቃሉ! ለዘላለምም ያፍራሉ፡፡16እስራኤልን ግን ምርጡን ስንዴ አበላዋለሁ ከዐለት ከሚገኘውም ማር አጠግባችኋለሁ፡፡»
1እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ ቆመ፤ በአማልክትም ላይ፣ ይፈርዳል እንዲህም ይላል፤2ፍትሕ የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው? ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው? ሴላ3ለድኾችና ለሙት ልጆች ተሟገቱ፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ፡፡4ድኾችንና ምስኪኖችን ታደጉ፤ ከዐመፀኞችም እጅ አስጥሏቸው፡፡5ዕውቀትም ሆነ ማስተዋል የላቸውም በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ የምድር መሠረቶችም ተናወጡ፡፡6እኔም፣ «እናንተ አማልክት ናችሁ፤ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ አልሁ፡፡7ሆኖም፣ እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ፡፡»8እግዚአብሔር ሆይ፣ ተነሥ፤ ሕዝቦች ሁሉ ርስትህ ናቸውና፤ በምድር ላይ ፍረድ፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ ዝም አትበል አትተወን ችላ አትበል፡፡2ጠላቶችህ እንዴት እንደ ተነሣሡ ባላንጣዎችህም እንዴት ራሳቸውን ቀና ቀና እንዳደረጉ ተመልከት፡፡3በሕዝብህ ላይ ያደባሉ፣ አንተ በምትጠብቃቸውም ላይ ያሣራሉ፡፡4‹የእስራኤል ስም ከእንግዲህ እንዳይታሰብ፣ ኑና ሕዝብ እንዳይሆኑ እንደምስሳቸው» አሉ፡፡5በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ተማከሩ አንተም ላይ ተማማሉ፡፡6የኤዶምና የእስማኤላውያን፣ የሞዓብና የአጋራውያን ድንኳኖች፣7ጌባል አሞንና አማሌቅ፣ ፍልስጥኤምም ከጢሮስ ሕዝብ ጋር አብረው ዶለቱ፡፡8አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ የሎጥም ልጆች ረዳት ሆነ፡፡ ሴላ9ምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው በቂሶን ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው፡፡10እነርሱ በዐይንዶር ጠፉ እንደ ምድር ትቢያ ሆኑ፡፡11እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፣ መሳፍንቶቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፤12እነርሱም፣ «የእግዚአብሔርን ግጦሽ ቦታ እንውሰድ» አሉ፡፡13አምላኬ ሆይ፣ በዐውሎ ነፋስ እንደሚወሰድ ትቢያ፣ ነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው፡፡14እሳት ደንን እንደሚያቃጥል ተራራውን እንደሚያዳርስ እሳት ነበልባል15እንዲሁ በማዕበልህ አሳዳቸው በሞገድህም አስደንግጣቸው፡፡16አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ ፊታቸውን በእፍረት ሙላ፤17ለዘላለም ይፈሩ ይታወኩም፤ በውርደትም ይጥፉ፡፡18ስምህ ያህዌ የሆነው አንተ ብቻ በምድር ላይ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ፡፡
1የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ ማደሪያህ ምንኛ ያማረ ነው፡፡2ነፍሴ የያህዌን አደባባዮች ትናፍቃለች እጅግም ትጓጓለች፡፡ ልቤና ሁለንተናዬ ሕያው እግዚአብሔርን ይጣራሉ፡፡3ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ መሠዊያህ ባለበት ስፍራ ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቦታ አገኘች፡፡4በቤትህ የሚኖሩ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱ ለዘላለም ያመሰግኑሃል፡፡ ሴላ5አንተን ብርታታቸው ያደረጉ በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ ቡሩካን ናቸው፡፡6በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ የሚጠጡት የምንጭ ውሃ ያገኛሉ የበልግም ዝናብ ይሞላዋል፡፡7ከኃይል ወደ ኃይል ይሸጋገራሉ እያንዳንዱም በጽዮን ባለው አምላክ ፊት ይቀርባል፡፡8የሰራዊት አምላክ ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፣ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ቃሌን አድምጥ፡፡ ሴላ9አምላክ ሆይ፣ ጋሻችንን ጠብቅ፣ ለቀባኸውም ራራለት፡፡10በሌላ ቦታ ሺህ ቀን ከመኖር፣ አንዲት ቀን በአደባባይህ መዋል ይሻላል፡፡11አምላካችን ያህዌ ፀሐይና ጋሻችን ነውና፤ ያህዌ ጸጋንና ክብርን ይሰጣል፤ በቅንነት የሚሄዱትን መልካም ነገር አይነፍጋቸውም፡፡12የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በአንተ የተማመነ ሰው ቡሩክ ነው፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ለምድርህ ሞገስ አሳየህ የያዕቆብን ምርኮ መለስህ፡፡2የሕዝብህን ኃጢአት ይቅር አልህ በደላቸውንም ሸፈንህ፡፡ ሴላ3መዓትህን ሁሉ አራቅህ ከጽኑ ቁጣህም ተመለስህ፡፡4አዳኛችን እግዚአብሔር ሆይ፣ መልሰን፤ በእኛ ያዘንህብንን ሁሉ አርቅልን፡፡5የምትቆጣን ለዘላለም ነውን? ቁጣህንስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ታስተላልፋለህን?6እኛ ሕዝብህ በአንተ ደስ እንዲለን እንደ ገና በሕይወት አታኖረንምን?7ያህዌ ሆይ፣ የኪዳን ታማኝነትህን አሳየን ማዳንህንም ስጠን፡፡8ያህዌ አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ እንደ ገና በስሕተት መንገድ ካልሄዱ በቀር ለሕዝቡና ለታማኞቹ ሰላምን ያደርጋል፡፡9ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ ማዳኑ ለሚፈሩት በእርግጥ ቅርብ ነው፡፡10ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፡ ጽድቅና ሰላም ተሳሳሙ፡፡11ታማኝነት ከምድር በቀለች ጽድቅ ከሰማይ ተመለከተች፡፡12ያህዌ መልካም ነገር ይሰጣል ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች፡፡13ጽድቅ በፊቱ ትሄዳለች ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ እኔ ድኻና ምስኪን ነኝና እባክህ ስማኝ መልስልኝም፡፡2እኔ ለአንተ ታማኝ ስለሆንሁ ጠብቀኝ አምላኬ ሆይ፤ በአንተ የታመነውን ባርያህን አድነው፡፡3ጌታ ሆይ፣ ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና እባክህ ማረኝ፡፡4ጌታ ሆይ፣ ወደ አንተ እጸልያለሁና ባርያህን ደስ አሰኘው፡፡5ጌታ ሆይ፣ አንተ መልካምና ይቅር ባይ ነህ ለሚጠሩህ ሁሉ ምሕረትህ ወሰን የለውም፡፡6ያህዌ ሆይ ጸሎቴን አድምጥ የልመናዬንም ጩኸት ስማ፡፡7አንተ ስለምትመልስልኝ በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ፡፡8ጌታ ሆይ፣ ከአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ የለም፡፡ ከአንተ ሥራ ጋር የሚወዳደር ሥራ የለም፡፡9ጌታ ሆይ፣ የሠራሃቸው ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊት ይሰግዳሉ፡፡ ስምህን ያከብራሉ፡፡10አንተ ታላቅ ነህና ተአምራትን ታደርጋለህ አንተ ብቻህን አምላክ ነህ፡፡11ያህዌ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረን፤ እኔም በእውነትህ እሄዳለሁ፡፡ ባልተከፋፈለ ልብም እንዳከብርህ አድርገኝ፡፡12ጌታ አምላኬ ሆይ፣ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ13ለእኔ የምታሳየው ዘላለማዊው ፍቅርህ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ነፍሴንም ከጥልቁ ሲኦል አወጣሃት፡፡14አምላክ ሆይ፣ እብሪተኞች ተነሥተውብኛል የክፉዎች ጉባኤ ነፍሴን ይፈልጓታል፡፡ አንተንም ከምንም አልቆጠሩም፡፡15አንተ ግን ጌታ ሆይ፣ መሐሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ ለቁጣ የዘገየህ፣ ምህረትህና ታማኝነትህ የበዛ ነው፡፡16ወደ እኔ ተመለስ ማረኝም ለባሪያህ ብርታትህን ስጥ የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን፡፡17የሞገስህን ምልክት አሳየኝ አንተ ያህዌ ረድተኸኛልና አጽናንተኸኛልምና የሚጠሉኝ ይህን አይተው ያፍራሉ፡፡
1እግዚአብሔር ከተማውን፣ በተቀደሰው ተራራ ላይ መሠረተ2ያህዌ የጽዮንን ደጆች ከያዕቆብ መኖሪያዎች ይበልጥ ይወዳል፡፡3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፣ ስለ አንቺ አስደናቂ ነገሮች ተነግረዋል፡፡ ሴላ4ከሚያውቁኝ መካከል ረዓብንና ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤ እነሆ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋር ሆነው፣ «ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው› ይላሉ፡፡5ስለ ጽዮን ግን፣ ልዑል እግዚአብሔር ራሱ ስለሚመሠርታት፣ «እነዚህ ሁሉ የተወለዱ እዚያ ነው» ይላሉ፡፡6ያህዌ ሕዝቦችን ሲመሠርት «ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው» ብሎ ይጽፋል፡፡7ዘማሪዎችና መሣሪያ ተጫዋቾችም፣ «ምንጩ ሁሉ አንቺ ውስጥ ይገኛል» ይላሉ፡፡
1አዳኜ ያህዌ አምላክ ሆይ፤ ቀንና ሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ፡፡2እባክህ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፡፡3በመከራ ተሞልቻለሁና ነፍሴም ወደ ሲኦል ተቃርባለች፡፡4ወደ መቃብር ከሚወርዱ ጋር ተቆጥሬአለሁ፤ ዐቅም አጣሁ፡፡5በሙታን መካከል ፈጽሞ እንደ ተተዉ ሞተው መቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውና ከእጅህ ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ፡፡6ጥልቁ አዘቅት ውስጥ ጣልኸኝ ጨለማ ጉድጓድ ውስጥ ከተትኸኝ፡፡7ቁጣህ እጅግ ከብዶኛል ማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቆኛል፡፡8ወዳጆቼን ሁሉ ከእኔ አራቅህ እንዲጸየፉኝም አደረግህ ዙሪያውን ተከብቤአለሁና ማምለጥ አልችልም፡፡9ዐይኖቼ በሐዘን ፈዘዙ ያህዌ ሆይ፣ ቀኑን ሙሉ ወደ አንተ እጮኻለሁ እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፡፡10ለሙታን ተአምራት ታደርጋለህን? የሞቱትስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ11ምሕረትህ መቃብር ውስጥ ታማኝነትህስ በሙታን ዓለም ይነገራልን?12ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትቃወቃለችን?13ያህዌ ሆይ፣ እኔ ግን ወደ አንተ እጮኻለሁ በጧትም ጸሎቴን ወደ ፊት አቀርባለሁ፡፡14ያህዌ ሆይ፣ ለምን ትተወኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?15ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ሞት አፋፍ ላይ ያለሁ ሰው ነበርሁ፤ ከማስደንገጥህ የተነሣ ተስፋ ቆርጫለሁ፡፡16ቁጣህ እኔ ላይ ተከነበለ መዓትህም አጠፋኝ፡፡17ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ ዙሪያውን አጥረው ያዙኝ፡፡፡18ወዳጆቼንና የሚቀርቡኝን ሰዎች ሁሉ ከእኔ አራቅህ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡
1ስለ ያህዌ ምሕረት ለዘላለሙ እዘምራለሁ፡፡ ታማኝነትህንም ለሚመጣው ትውልድ እናገራለሁ፡፡2ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት ታማኝነትህንም በሰማያት እንደምታጸና እናገራለሁና3አንተም እንዲህ ብለሃል፣ «ከመረጥሁት ጋር ኪዳን አድርጌአለሁ፤ ለባርያዬ ለዳዊት ምዬአለሁ፡፡4ዘርህን ለዘላለም አተክላለሁ ዙፋንህንም በትውልድ ዘመን ሁሉ አጸናለሁ፡፡» ሴላ5ያህዌ ሆይ፣ ሰማያት ድንቅ ሥራህን ያመሰግናሉ ጽድቅህም በቅዱሳን ጉባኤ ይወደሳል፡፡6በላይ በሰማያት ከያህዌ ጋር ማን ሊስተካከል ይችላል? ከአማልክት ልጆችስ መካከል እንደ ያህዌ ያለ ማን ነው?7እርሱ በቅዱሳኑ ጉባኤ መካከል እጅግ የተፈራ ነው፤ በዙሪያው ካሉትም ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው፡፡8የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ኃያል ማነው? ታማኝነትህም ከቦሃል፡፡9የባሕሩን ቁጣ በሥልጣንህ ታዝዛለህ ማዕበሉንም ጸጥ ታደርጋለህ፡፡10አንተ ረዓብን ቀጥቅጠህ ገደልኸው በታላቁ ኃይልህ ጠላቶችህን በተንሃቸው፡፡11ሰማያት የአንተ ናቸው ምድርም የአንተ ናት፡፡ አንተ ዓለምንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ ፈጠርህ፡፡12ሰሜኑን ደቡቡንም አንተ ፈጠርህ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል፡፡13አንተ ክንደ ብርቱ ነህ እጅህ ኃያል ናት፤ ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለች ናት፡፡14ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረት ናቸው ምሕረትና ታማኝነት በፊት ይሄዳሉ፡፡15ያህዌ ሆይ፣ በፊት ብርሃን የሚሄድ አንተንም የሚያመልክ ሕዝብ ቡሩክ ነው፡፡16ቀኑን ሙሉ በስምህ ደስ ይላቸዋል በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ፡፡17ገናናው ኃይልህ ብርታት ይሰጣቸዋል በሞገስህም ድል ተቀዳጀን፡፡18ጋሻችን የያህዌ ነው ንጉሣችንም የራሱ የእስራኤል ቅዱስ ነውና፡፡19ከረጅም ጊዜ በፊት በራእይ ለሕዝብህ ተናገርህ እንዲህም አልህ፤ «ኃያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁ፤ ከሕዝብ መካከል እኔ የመረጥሁትን አስነሣሁ፡፡20ባርያዬ ዳዊትን መረጥሁት በተቀደሰው ዘይቴም ቀባሁት21እጄ ይደግፈዋል ክንዴም ያበረታዋል፡፡22ጠላት አይረታውም ክፉ ሰውም አያሸንፈውም፡፡23ጠላቶቹን በፊቱ አደቃለሁ፤ ባላንጣዎቹንም እገድላለሁ፡፡24እውነቴና ታማኝነቴ ከእርሱ ጋር ይሆናል በስሜ ድል ይቀዳጃል፡፡25እጁን በባሕሮች ቀኝ እጁንም በወንዞች ላይ አደርጋለሁ፡፡26እርሱም፣ «አንተ አባቴ፣ አምላኬ የድነቴም ዐለት» ብሎ ይጠራኛል፡፡27እኔም ደግሞ በኩሬ አደርገዋለሁ ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ ከፍ ይላል፡፡28ምሕረቴንም ለዘላለም ለእርሱ እዘረጋለሁ ለእርሱ ጋር ያደረግሁትም ኪዳን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡29የዘር ሐረጉን ለዘላለም ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ30ልጆቹ ሕጌን ቢተው፣ ሥርዐቴን ባይጠብቁ፣31ደንቤን ቢተላለፉ፣ ትእዛዞቼ ባያከብሩ፣32ኃጢአታቸውን በበትር፣ በደላቸውንም በአለንጋ እቀጣለሁ፡፡33ለእርሱ ያለኝ ፍቅር ግን አይቋረጥም ታማኝነቴንም አላጓድልበትም፡፡34ኪዳኔን አላፈርስም ከአፌ የወጣውን አላጥፍም፡፡35አንዴ በቅድስናዬ ምያለሁና ለዳዊት አልዋሽም፡፡36ልጆቹ ለዘላለም ዙፋኑም በፀሐይ ዕድሜ ልክ ጸንቶ ይኖራል፡፡37በሰማይ ታማኝ ምስክር ሆና እንደምትኖረው እንደ ጨረቃ እርሱም ለዘላለም ይመሠረታል፡፡ ሴላ38አሁን ግን ናቅኸው፤ ጣልኸውም በቀባኸውም ንጉሥ ላይ ተቆጣህ፡፡39ለባርያህ የገባኸውን ኪዳን አፈረስህ የክብር ዘውዱን መሬት ላይ ጣልህ፡፡40ቅጥሮቹን ሁሉ አፈረስህ ምሽጉንም ደመሰስህ፡፡41ዐላፊ አግዳሚ ሁሉ ዘረፈው ለጐረቤቶቹም መዘባበቻ ሆነ፡፡42የጠላቶቹን ቀኝ እጅ ከፍ አደረግህ ባላንጣዎቹም ሁሉ ደስ አላቸው፡፡43የሰይፉን ስለት አጠፍህ በጦርነትም ጊዜ አልረዳኸውም፡፡44የክብሩን ውበት አጠፋህበት ዙፋኑንም መሬት ላይ ጣልህበት፡፡45የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው ዕፍረትንም አከናነብኸው፡፡46ያህዌ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ነው? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን? ቁጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?47ዕድሜዬ ምን ያህል አጭር እንደ ሆነ አስብ፤ የሰውን ልጆች እንዲሁ ለከንቱ ፈጠርሃቸው!48ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ የሚኖር ማን ነው? ሕይወቱን ከሲኦል እጅ ማዳን የሚችል ማነው? ሴላ49ጌታ ሆይ፣ በታማኝነትህ ለዳዊት የማልህለት የቀድሞ ምሕረትህ የታለ?50ጌታ ሆይ፣ ባርያህ ላይ የደረሰውን ፌዝ የብዙ ሰዎችንም ስድብ እንደ ታቀፍሁ አስብ፡፡51ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶችህ የሚሳደቡትን፣ አንተ የቀባኸውን ሰው ርምጃ የነቀፉበትን ሁኔታ አስብ፡፡52ያህዌ ለዘላለም ይባረክ፡፡ አሜን፣ አሜን
1ጌታ ሆይ፣ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ነህ፡፡2ተራሮችን ከመሥራትህና ዓለምንም ከመፍጠርህ በፊት አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ3ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤ «የሰው ልጆች ሆይ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ» ትላለህ፡፡4ሺህ ዓመት በፊትህ፣ እንዳለፈው ትናንት ቀን እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓቶች ነው፡፡5እንደ ጐርፍ ጠርገህ ስትወስዳቸው እንደ ሕልም ይበናሉ በየማለዳው እንደሚታደስ የሣር ቡቃያ ይሆናሉ፡፡6ሣር ወዲያው አድጐ ያብባል ሲመሽ ግን ጠውልጐ ይጠፋል፡፡7እኛ በቁጣህ ጠፍተናል በመዓትህም ደንግጠናል፡፡8ኃጢአታችንን በፊትህ፣ የተሰወረ ኃጢአታችንንም በግልጽ በሚታይ ቦታ ታኖራለህ፡፡9ዘመናችን ሁሉ በቁጣህ ያልፋል ዕድሜያችንም በቅጽበት እንደሚያልፍ እስትንፋስ ነው፡፡10ዕድሜያችን ሰባ፣ ጤነኞች ከሆንንም ሰማንያ ዓመት ነው፡፡ እነዚያም ቢሆኑ፣ በመከራና ሐዘን የተሞሉ ናቸው፡፡ ዕድሜያችን ቶሎ ያልቃል፤ እኛም ወዲያው እንነጉዳለን፡፡11የቁጣህን ኃይል ማን ያውቃል? መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው፡፡12ጥበበኞች መሆን እንድንችል ዕድሜያችን ምን ያህል መሆኑን አስተምረን፡፡13ያህዌ ሆይ፣ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል፤ ለባሪያዎችህም ራራላቸው፡፡14በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ በማለዳ ምሕረትህን አጥግበን፡፡15መከራ ባየንበት ዘመን መጠን ችግር ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሰኘን፡፡16እኛ ባርያዎችህ ታላቁን ሥራህን፣ ልጆቻችንም ግርማህን እንዲያዩ ፍቀድልን፡፡17የጌታ አምላካችን ሞገስ እኛ ላይ ይሁን የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ ያድርግልን አዎን ፍሬያማ ያድርግልን፡፡
1በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል፡፡2ያህዌን፣ «መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ» እለዋለሁ፡፡3ከአዳኝ ወጥመድ ከአደገኛም መቅሠፍት ያድንሃል4በላባዎቹ ይጋርድሃል በክንፎቹም ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፡፡ ታማኝነቱም ጋሻና መከታ ይሆንልሃል፡፡5የሌሊትን ሽብር፣ በቀን ከሚወረወር ፍላጻም አትፈራም6በጨለማ ከሚያደባ ቸነፈር በቀትርም ከሚወርድ መቅሠፍት አትሰጋም፡፡7በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም ዐሥር ሺህ ይወድቃሉ ወደ አንተ ግን አይቀርብም፡፡8በዐይንህ ብቻ ታያለህ የክፉዎችንም መቀጣት ትመለከታለህ፡፡9አንተ ያህዌን መሸሸጊያ ልዑል አምላክንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና፡፡10ክፉ ነገር አያገኝህም መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይጠጋም፡፡11በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋል፡፡12እግሮችህ በድንጋይ እንዳይሰናከሉ በእጆቻቸው ያነሡሃል፡፡13አንበሳና እፉኝት ላይ ትጫማለህ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ፡፡14ወዶኛልና አታደገዋለሁ በእኔ ተማምኖአልና እጠብቀዋለሁ፡፡15ይጠራኛል እኔም እመልስለታለሁ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ ድል አቀዳጀዋለሁ፤ አከብረውማለሁ፡፡16ረጅም ዕድሜ አጠግበዋለሁ ማዳኔንም አሳየዋለሁ፡፡
1ያህዌን ማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፣ ለስምህ መዘመር መልካም ነው፡፡2ምህረትህን በማለዳ ታማኝነትህን በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፡፡3ዐሥር አውታር ባለው በገና ከመሰንቆም ጣዕመ ዜማ ጋር ማወጅ መልካም ነው፡፡4ያህዌ ሆይ፣ በሥራህ ደስ ስላሰኘኸኝ ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ፡፡5ያህዌ ሆይ፣ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው? ሐሳብህ እጅግ ጥልቅ ነው፡፡6ደነዝ ሰው ይህን አያስተውልም ሞኝም ይህን አይረዳም፣7ክፉ ሰዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ ተንኰለኞችም ቢለመልሙ ለዘላለሙ ይጠፋሉ፡፡8አንተ ግን ያህዌ ሆይ፣ ለዘላለም ትነግሣለህ፡፡9ጠላቶችህ ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶችህ ይጠፋሉ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ፡፡10እንደ ጐሽ ቀንድ ቀንዴን ከፍ ከፍ አደረግህ በትኩስ ዘይትም ቀባኸኝ፡፡11ዐይኖቼ የባላንጣዎቹን ውድቀት አዩ ጆሮቼም የክፉ ጠላቶቼን ጥፋት ሰሙ፡፡12ጻድቃን እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማሉ እንደ ሊባኖስ ዛፍም ያድጋሉ፡፡13በያህዌ ቤት ተተክለዋል በአምላካችን አደባባይ ይንሰራፋሉ፡፡14ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ፡፡15እግዚአብሔር ትክክለኛ ነው፤ እርሱ ዐለቴ ነው፤ በእርሱ ዘንድ እንከን የለም፡፡
1ያህዌ ነገሠ ግርማንም ለበሰ፣ ያህዌ ግርማን ተጐናጸፈ ብርታትንም ታጠቀ ዓለምን በአንድ ስፍራ አጸናት፤ ከቶም አትናወጥም፡፡2ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም ነህ፡፡3ያህዌ ሆይ፣ ባሕሮች ይነሣሉ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ይጮኻሉ ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ፡፡4ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ ከባሕርም ሞገድ ይልቅ ከፍ ብሎ ያለው ያህዌ ብርቱ ነው፡፡5ትእዛዛትህ ያጸኑ ናቸው ያህዌ ሆይ፣ ቤትህ ለዘላለም በቅድስና ይዋባል፡፡
1የበቀል አምላክ አንተ ያህዌ ሆይ፣ የበቀል አምላክ ሆይ፣ ብርሃንህ ይብራልን፡፡2የምድር ዳኛ ሆይ፣ ተነሥ ለትዕቢተኞች የእጃቸውን ስጣቸው፡፡3ያህዌ ሆይ፣ ክፉዎች እስከ መቼ፣ ክፉዎች እስከ መቼ ነው የሚፈነጩት?4የእብሪት ቃሎች ያዥጐደጉዳሉ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ጉራ ይነዛሉ፡፡5ያህዌ ሆይ፣ ሕዝብህን ያደቅቃሉ የአንተን ወገኖች ይጨቁናሉ፡፡6በአገራቸው የሚኖሩ መበለቶችንና መጻተኞችን ይገድላሉ፤7«ያህዌ አያይም፤ የያዕቆብ አምላክም አያስተውልም» ይላሉ፡፡8እናንት አላዋቂዎች ይህን አስተውሉ፤ እናንት ሞኞች ለመሆኑ፣ ጥበበኞች የምትሆኑት መቼ ነው?9ጆሮን የተከለ እርሱ አይሰማምን? ዐይንን የሠራ እርሱ አያይምን?10ሕዝቦችን የሚገሥጸው አይቀጣምን? ለሰው ዕውቀት የሚሰጥ እርሱ ነው፡፡11ያህዌ የሰው ሐሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል፡፡12ያህዌ ሆይ፣ አንተ የምትገሥጸው ሕግህንም የምታስተምረው ሰው ቡሩክ ነው፡፡13ለክፉዎች ጉድጓድ እስኪቆፈር ድረስ አንተ እርሱን ከመከራ ታሳርፈዋለህ፡፡14ያህዌ ሕዝቡን አይጥልምና ርስቱንም አይተውም፡፡15ፍርድ ተመልሶ በጽድቅ አሠራር ላይ ይመሠረታል ልበ ቀናዎችም ሁሉ ይከተሉታል፡፡16ክፉዎችን የሚቋቋምልኝ ማን ነው? ከክፉ አድራጊዎች የሚሟገትልንስ ማን ነው?17ያህዌ ረዳቴ ባይሆን ኖሮ ፈጥኜ ወደ ዝምታው ዓለም በወረድሁ ነበር፡፡18እኔ፣ «እግሬን አዳለጠኝ» ባልሁ ጊዜ ያህዌ ሆይ፣ ምሕረትህ ደግፎ ያዘኝ፡፡19ሐዘኔ በበዛ ጊዜ፣ ማጽናናትህ ደስ አሰኘኝ፡፡20ዓመፅን ሕጋዊ የሚያደርግ የጥፋት ዙፋን ከአንተ ጋር ሊያብር ይችላልን?21ጻድቃንን ለማጥፋት ያሤራሉ በንጹሐን ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ይበይናሉ፡፡22ለእኔ ግን ያህዌ ጠንካራ ምሽግ አምላኬም መጠጊያ ዐለት ሆኖኛል፡፡23ኃጢአታቸውን ወደ ራሳቸው ይመልሳል በገዛ ክፋታቸውም ያጠፋቸዋል፡፡ ያህዌ አምላካችን ይደመስሳቸዋል፡፡
1ኑ፣ ያህዌን እናመስግን የመዳን ዐለታችን ለሆነው ለእርሱ በደስታ እንዘምር፡፡2ወደ ፊቱ በምስጋና እንግባ በዝማሬም እናወድሰው፡፡3ያህዌ ታላቅ አምላክ ነውና ከአማልክትም ሁሉ የበለጠ ታላቅ ንጉሥ ነው፡፡4የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው፡፡5ባሕር የእርሱ ነው፤ እርሱ ሠራው እጆቹም የብሱን አበጁ፡፡6ኑ እናምልከው እንስገድለትም በፈጠረን በያህዌ ፊት እንንበርከክ7እርሱ አምላካችን ነውና እኛ የመሰማሪያው ሕዝብ የእጁም በጐች ነን፡፡ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ8«በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣ በመረባም እንዳደረጋችሁት ልባችሁን አታደንድኑት፡፡9ሥራዬን ቢያዩም አባቶቻችሁ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም፤10ያንን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቆጣሁት፣ እኔም፣ «ልቡ የሸፈተ ሕዝብ ነው፤ መንገዴንም አላወቁም» አልሁ፡፡11ስለዚህ፣ «በፍጹም ወደ እኔ ዕረፍቴ ቦታ አይገቡም» ብዬ በቁጣየ ማልሁ፡፡
1ለያህዌ አዲስ መዝሙር ዘምሩ ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ2ለያህዌ ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ ማዳኑንንም ዕለት በዕለት ተናገሩ፡፡3ክብሩን በሕዝቦች መካከል ድንቅ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፡፡4እግዚአብሔር ታላቅ ነው፣ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋል ከአማልክት ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል፡፡5የሕዝቦች አማልክት ሁሉ ጣዖቶች ናቸው ያህዌ ግን ሰማያትን ሠራ፡፡6ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው ብርታትና ውበትም መቅደሱ ውስጥ አሉ፡፡7የሕዝብ ወገኖች ሁሉ ለያህዌ ምስጋና ስጡ ክብርንና ብርታትን ለያህዌ ስጡ፡፡8ለስሙ የሚገባውን ክብር ለያህዌ ስጡ ስጦታ ይዛችሁ ወደ አደባባዩ ግቡ፡፡9ክብርን በተሞላ ቅድስና ለያህዌ ስገዱ ምድር ሁሉ በፊቱ፤ ተንቀጥቀጡ፡፡10በሕዝቦች መካከል፣ «እግዚአብሔር ነገሠ» በሉ፤ ምድር በጽኑ ስለ ተመሠረተች አትናወጥም፡፡ እርሱ ሕዝቦች ላይ በጽድቅ ይፈርዳል፡፡11ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሴት ታድርግ፡፡ ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ እልል ይበል፡፡12መስክና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፡፡13እርሱ ይመጣልና በያህዌ ፊት ይዘምራሉ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል፡፡
1እግዚአብሔር ነገሠ ምድር ደስ ይበላት፤ በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ፡፡2ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ ጻድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው፡፡3እሳት በፊቱ ይሄዳል በዙሪያው ያሉ ባላንጣዎቹን ይፈጃል፡፡4መብረቁ ዓለምን አበራ ምድር ዐይታ ተንቀጠቀጠች፡፡5ተራሮች ያህዌ ፊት የምድር ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ6ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ፡፡7የተቀረጹ ምስሎች የሚያመልኩ፣ በጣዖቶች የሚመኩ ሁሉ ይፈሩ እናንት አማልክት ሁላችሁ ለእርሱ ስገዱ8ያህዌ ሆይ፣ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት የይሁዳም ከተሞች ሐሤት አደረጉ፡፡9ያህዌ ሆይ፣ አንተ በምድር ሁሉ ልዑል ነህና ከአማልክት ሁሉ ይልቅ እጅግ ከፍ ያልህ ነህ፡፡10ያህዌን የምትወዱ ክፋትን ጥሉ! እርሱ የቅዱሳኑን ሕይወት ይጠብቃል ከክፉዎችም እጅ ይታደጋቸዋል፡፡11ብርሃን ለጻድቃን ሐሤትም ለልበ ቅኖች ወጣ፡፡12እናንተ ጻድቃን በያህዌ ደስ ይበላችሁ ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ፡፡
1እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጐአልና ለያህዌ አዲስ መዝሙር አቅርቡ ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም ድል ሰጥተውታል፡፡2ያህዌ ማዳኑን አሳወቀ ጽድቁንም ለሕዝቦች ሁሉ በግልጽ አሳየ፡፡3ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን ታማኝነቱንም አሰበ፡፡ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ድል አድራጊነት አዩ፡፡4ምድር ሁሉ ለያህዌ እልል በሉ ውዳሴ አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፡፡5በገና በመደርደርና በመዝሙር ለያህዌ ምስጋና አቅርቡ፡፡6በመለከትና በእምቢልታ ድምፅ በንጉሡ በያህዌ ፊት እልል በሉ፡፡7ባሕርና በውስጡ ያለው ሁሉ ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ8ወንዞች ያጨብጭቡ ተራሮችም በደስታ እልል ይበሉ፡፡9ያህዌ በምድር ላይ ለመፍረድ ይመጣል በዓለም ላይ በጽድቅ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል፡፡
1ያህዌ ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ በኪሩቤል ላይ በዙፋኑ ተቀምጧል፤ ምድር ትናወጥ፡፡2ያህዌ በጽዮን ታላቅ ነው ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡3ታላቁንና አስፈሪውን ስምህን ይወድሱ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡4ፍትሕ የምትወድ ኃያል ንጉሥ ሆይ ጽድቅንና ፍትሕን ለያዕቆብ አደረግህ፡፡5አምላካችን ያህዌን አመስግኑት በእግሩ መርገጫ ስገዱ፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡6ሙሴና አሮን ካህናቱ መካከል ነበሩ ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል ነበረ እነርሱ ወደ ያህዌ ጸለዩ እርሱም መለሰላቸው፡፡7በደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው እነርሱም ሥርዐቱንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ፡፡8አምላካችን ያህዌ ሆይ፣ አንተ መለስህላቸው ይቅር ባይ አምላክ ሆንህላቸው ኃጢአታቸውን ግን ቀጣህ፡፡9አምላካችን ያህዌን አመስግኑ አምላካችን ያህዌ ቅዱስ ነውና በቅዱስ ተራራው ሰገዱ፡፡
1ምድር ሁሉ ለያህዌ እልል በሉ2ያህዌን በደስታ አገልግሉት፡፡ በደስታ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ3ያህዌ አምላክ መሆኑን ዕወቁ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፡፡ እኛ ሕዝቡ የመሰማሪያውም በጐች ነን፡፡4በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፡፡ አመስግኑት ስሙንም ባርኩ፤5ያህዌ ቸር ነው፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነው፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ስለ ታማኝነትህና ስለ ትክክለኛ ፍርድህ ምስጋና እዘምራለሁ፡፡2ነቀፋ በሌለበት መንገድ እሄዳለሁ አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? በቤቴ ውስጥ ያለ ነቀፋ እመላለሳለሁ፡፡3በዐይኖቼ ፊት በደል አላኖርም የክፉዎችን ሥራ እጠላለሁ ከቶም አልተባበራቸውም፡፡4ጠማማ ሰዎች ከእኔ ይርቃሉ ከክፋት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፡፡5ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን አጠፋለሁ፡፡ ትዕቢተኛ ዐይንና እብሪተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም፡፡6ከእኔ ጋር እንዲኖሩ፣ ዐይኖቼ በምድሪቱ ያሉ ታማኞች ላይ ናቸው በንጹሕና የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል፡፡7አታላይ ሰው ቤቴ ውስጥ አይኖርም ሐሰተኛም በዐይኖቼ ፊት አይከብርም፡፡8በምድሪቱ ያሉትን ክፉ አድራጊዎች በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ከያህዌ ከተማ አስወግዳቸዋለሁ፡፡
1ያህዌ ሆይ ጸሎቴን ሰማ ጩኸቴንም አድምጥ፡፡2በመከራዬ ጊዜ ፊትህን ከእኔ አትሰውር ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል ወደ አንተ ስጣራ ፈጥነህ አድምጠኝ፡፡3ዘመኔ እንደ ጢስ እየበነነ ነው ዐጥንቶቼም እንደ እሳት እየነደዱ ነው፡፡4ልቤ ተሰብሮአል፤ እኔም እንደ ደረቀ ሣር ሆኛለሁ፡፡ እህል መብላትንም ዘንግቻለሁ፡፡5ዘወትር ከመቃተቴ የተነሣ ዐጥንቴ ከቆዳዬ ጋር ተጣበቀ፡፡6በምድረ በዳ እንዳለ እርኩም መሰልሁ፤ በፍርስራሽ መካከል እንዳ ጉጉት ሆንሁ፡፡7ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤ በቤት ጣራ ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆኛለሁ8ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይሳለቁብኛል የሚያፌዙብኝም ስሜን እንደ ርግማን ቆጥረውታል፡፡9ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁ! እንባዬም ከምጠጣው ነገር ጋር ተደባልቆአል፡፡10ወደ ላይ አነሣኸኝ፤ ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ መልሰህ ጣልኸኝ፡፡11ዘመኖቼ ቶሎ እንደሚያልፍ ጥላ ናቸው እኔም እንደ ሣር ደረቅሁ12አንተ ግን ያህዌ ሆይ፣ ለዘላለም ትኖራለህ ስምህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ገናና ነው፡፡13ትነሣህ፤ ጽዮንንም ትምራታለህ ለእርሷ ርኅራኄህን የምታሳይበት ጊዜ ነው፤14አገልጋዮችህ ድንጋዮዋን ወደዋልና ለፍርስራሾቿ ራርተዋል፡፡15ሕዝቦች የያህዌን ስም የምድር ነገሥታትም ክብርህን ይፈራሉ፡፡16ያህዌ ጽዮንን እንደ ገና ይሠራታልና በክብሩም ይገለጣል፡፡17በዚያ ጊዜ እርሱ ለችግረኞች ጸሎት መልስ ይሰጣል፤ ልመናቸውንም አይንቅም፡፡18ገና ያልተወለዱ ሰዎች እንዲያመሰግኑት ይህ ያህዌ ያደረገው ድንቅ ነገር ለሚመጣው ትውልድ ይጻፍ፡፡19በከፍታ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቶአልና ያህዌ ከሰማይ ምድርን ዐይቶአል፡፡20ይኸውም የእስረኞችን መቃተት ይሰማ ዘንድ ሞት የተፈረደባቸውን ያድን ዘንድ ነው፡፡21ስለዚህ የያህዌ ስም በጽዮን፣ ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይነገራል፡፡22ይህም የሚሆነው ሕዝቦችና መንግሥታት ያህዌን ለማምለክ በአንድት ሲሰበሰቡ ነው፡፡23በሕይወቴ እኩሌታ ብርታቴን ቀጨው ዕድሜዬንም ባጭሩ አስቀረው፡፡24እኔም፣ «አምላኬ ሆይ፣ የአንተ ዘመን ከትውልድ እስከ ትውልድ ስለሆነ በዕድሜዬ እኩሌታ አትውሰደኝ» አልሁ፡፡25አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው፡፡26እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ እነርሱ እንደ ልብስ ያረጃሉ እንደ መጐናጸፊያ ትለውጣቸዋለህ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ፡፡27አንተ ግን ያው አንተ ነህ ዘመኖችህም ፍጻሜ የላቸውም፡፡28የአገልጋዮችህ ልጆች በሰላም ይኖራሉ ትውልዳቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል፡፡
1ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌ አመስግኚ የያህዌን ቅዱስ ስም በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ፡፡2ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመሰግኚ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፡፡3ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር ይላል ደዌሽንም ሁሉ ይፈውሳል፡፡4ሕይወትሽንም ከጥፋት ጉድጓድ ያድናል ምሕረትና ርኅራኄውን ያቀዳጅሻል፡፡5ወጣትነትሽ እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ ሕይወትሽን በመልካም ነገር ያጠግባል፡፡6ያህዌ ለተጨቆኑ ሁሉ፣ ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣል፡፡7መንገዱን ለሙሴ፣ ሥራውንም ለእስራኤል ልጆች አሳወቀ፡፡8ያህዌ መሐሪና ይቅር ባይ ለቁጣ የዘገየ፣ ታማኝነቱም የበዛ ነው፡፡9እርሱ ሁልጊዜ አይገሥጽም ለዘላለምም አይቆጣም፡፡10እንደ ኃጢአታችን አላደረግብንም እንደ በደላችንም አልከፈለንም፡፡11ሰማይ ከምድር ከፍ የማለቱን ያህል እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ነው፡፡12ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ በደልና ኃጢአታችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ፡፡13አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ያህዌም ለሚፈሩት ይራራል፡፡14እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና ትቢያ መሆናችንንም ይገነዘባል፡፡15ሰው እኮ እንደ ሣር እንደሚያድግ የዱር አበባ ነው፡፡16ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ድራሹ ይጠፋል፤ የነበረበት ስፍራ እንኳ አይታወቅም፡፡17የያህዌ ምሕረት ግን ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፡፡ ጽድቁም እስከ ልጅ ልጃቻቸው ዘመን በላያቸው ይሆናል፤18ይህም ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ ትእዛዙንም በሚያከብሩት ላይ ይሆናል፡፡19ያህዌ ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች፡፡20እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክት ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኃያላን፣ ያህዌን አመስግኑ፡፡21አገልጋዩ የሆናችሁ፣ ፈቃዱንም የምትፈጽሙ እናንተ የሰማይ ሰራዊት ያህዌን አመስግኑ፡፡22በግዛቱ ሁሉ የምትገኙ ፍጥረቶቹ ያህዌን አመስግኑ፤ ነፍሴ ሆይ ያህዌን አመስግኚ፡፡
1ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመስግኚ አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ ውበትና ግርማን ለብሰሃል፡፡2ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል ሰማያትን እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፡፡3በጠፈር ላይ ካለው ውሃ በላይ ቤትህን ሠርተሃል ደመናትን ሰረገላህ አደረግህ በነፋስ ክንፎች ትሄዳለህ፡፡4ነፋሶችን መልእክተኞቹ፣ ነበልባልንም አገልጋዮቹ አደረግ፡፡5ምድርን መሠረት ላይ አጸና ከቶም አትናወጥም፡፡6በጥልቁ እንደ ልብስ ሸፈንሃት ውሆችም ከተራሮች በላይ ቆሙ፡፡7በገሠጸካቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ፡፡8በተራሮች ላይ ፈሰሱ አንተ ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ ወደ ሸለቆዎች ወረዱ፡፡9ዳግመኛ ምድርን እንዳይሸፍኑም አልፈውም እንዳይመጡ ድንበር አበጀህላቸው፡፡10ምንጮች በሸለቆው ውስጥ እንዲ ወንዞችም በተራሮች መካከል እንዲወርዱ አደረግህ፡፡11የዱር እንስሳት ከዚያ ይጠጣሉ የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ያረካሉ፡፡12ወንዙ ዳር ወፎች ጐጆአቸውን ይሠራሉ በቅርንጫፎቹም መካከል ይዘምራሉ፡፡13ከላይ ከእልፍኙ ተራሮችን ያጠጣል፤ ምድርም በሥራው ፍሬ ትረካለች፡፡14ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ ለእንስሶች ሣርን ታበቅላለህ ለሰው ልጆች ሥራ አትክልቶችን ታበቅላለህ፡፡15ስለዚህ ልቡን ደስ የሚሰኘውን ወይን ጠጅ፣ ፊቱን የሚያበራ ዘይትና በሕይወት የሚያኖረውን እህል ያዘጋጃል፡፡16ደግሞም የያህዌ ዛፎች፣ እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች በቂ ዝናብ ያገኛሉ፡፡17በዚያ ወፎች ጐጆአቸውን ይሠራሉ ሽመላዎችም በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ያገኛሉ፡፡18ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ ተራራ የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው፡፡19ጨረቃ የወቅቶች ምልክት እንድትሆን አደረገ ፀሐይም የምትጠልቀበትን ጊዜ ታውቃለች፡፡20ጨለማን ፈጠርህ፤ ሌሊትም ሆነ፤ በጨለማም የዱር አውሬዎች ሁሉ ይወጣሉ፡፡21የአንበሳ ግልግሎች ምግብ ለማግኘት ይጫኸሉ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምግባቸውን ይፈልጋሉ፡፡22ፀሐይ በወጣች ጊዜ ሸሽተው ይሄዳሉ፤ በየመኖሪያቸው ውስጥ ይተኛሉ፡፡23ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል እስኪመሽም ድረስ ሲሠራ ይውላል፡፡24ያህዌ ሆይ፣ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ አደረግህ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች፡፡25እዚያ ደግሞ ሰፊና የተንጣለለ ባሕር አለ ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸውም ነፍሳት በውስጡ አሉ፡፡26መርከቦች በላዩ ይመላለሳሉ አንተ የፈጠርኸው ሌዋታን በውስጡ ይፈነጫል፡፡27እነዚህ ሁሉ በጊዜው ምግባቸውን እንድትሰጣቸው አንተን ተስፋ ያደርጋሉ፡፡28በሰጠሃቸው ጊዜ አንድ ላይ ይከማቻሉ፣ እጅህንም ስትዘረጋ በመልካም ነገር ይጠግባሉ፡፡29ፊትህን ስትሰውር፣ በጣም ይደነግጣሉ እስትንፋሳቸውን ስትወስድ ይሞታሉ፤ ወደ አፈርም ይመለሳሉ፡፡30መንፈስህ ስትልክ እነርሱ ይፈጠራሉ የምድርንም ገጽ ታድሳለህ፡፡31ለዘላለም ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ያህዌ በፍጥረቱ ደስ ይበለው፡፡32ከላይ ምድርን ሲመለከት ትንቀጠቀጣለች ተራሮችን ሲዳስሳቸው ይጨሳሉ33በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ለያህዌ እዘምራለሁ በሕይወትም እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፡፡34ደስታዬ በእርሱ ስለሆነ የልቤ ሐሳብ እርሱን ደስ ያሰኘው፡፡35ኅጥአን ከምድር ይጥፉ ዐመፀኞች ከእንግዲህ አይኑሩ፡፡ ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመስግኚ፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
1ያህዌን አመስግኑ፣ ስሙንም ጥሩ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል ግለጡ፡፡2ለእርሱ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ ድንቅ ሥራዎቹን ሁሉ ተናገሩ፡፡3በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ ያህዌን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው፡፡4ያህዌንና ብርታቱን ፈልጉ ፊቱንም ዘወትር ፈልጉ፡፡5ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች ተአምራቱንና ከአፉ የወጣውን ፍርድ ፈልጉ፡፡6እናንት የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች እርሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ አስታውሱ፡፡7እርሱ አምላካችን ያህዌ ነው ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው፡፡8ኪዳኑን ለዘላለም፣ ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺህ ትውልድ ዘመን ያስታውሳል፡፡9ከአብርሃም ጋር ያደረገውን ኪዳን ለይስሐቅም በመሐላ የሰጠውን ተስፋ አይረሳም፡፡10ይህን ለያዕቆብ ሥርዐት ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አድርጐ አጸናው፡፡11እንዲህም አለ፣ «የርስትህ ድርሻ እንዲሆን የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ፡፡12ይህን ያለው እነርሱ በቁጥር አነስተኞች፣ እጅግ ጥቂትና ባይተዋሮች ሳሉ፣13ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ሲንከራተቱ፣ ከአንዱ መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ሲቅበዘበዙ ነበር፡፡14ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፡፡15«የቀባኋቸውን አትንኩ፤ ነቢያቶቼንም አትጉዱ» አለ፡፡16በምድር ላይ ችጋርን ጠራ የምግብንም አቅርቦት ሁሉ አቋረጠ፡፡17ከእነርሱ አስቀድሞ በባርነት የተሸጠው ዮሴፍን ላከ፡፡18እግሮቹ በእግር ብረት ተላላጡ አንገቱም ላይ የብረት ማነቆ ገባ፡፡19የተናገረው እስኪፈጸም ድረስ የያህዌ ቃል ፈተነው፡፡20እርሱን እንዲፈቱ ንጉሡ አገልጋዮቹን ላከ፤ የሕዝቦችም ገዢ ነጻ አወጣው፡፡21የቤቱ ጌታ የንብረቱም ሁሉ አስተዳዳሪ አደረገው፡፡22በንጉሡ ባለ ሥልጣኖች ላይ አዛዥ ሆነ ለንጉሡም አማካሪዎች ጥበብን እንዲያስተምር ሥልጣን ተሰጠው፡፡23ከዚያም እስራኤል ወደ ግብፅ ሄደ እስከ ጊዜው ድረስ ያዕቆብ በካም ምድር ተቀመጠ፡፡24ያህዌ ሕዝቡን እጅግ አበዛ ከጠላቶቻቸውም ይልቅ ብርቱ አደረጋቸው፡፡25ሕዝቡን እንዲጠሉ ባርያዎቹንም እንዲበድሉ ልባቸውን አስጨከነ፡፡26ባርያውን ሙሴን እርሱ የመረጠውንም አሮንን ላከ፡፡27በግብፃውያን መካከል ምልክቶችን በካም ምድርም ድንቆችን አደረጉ፡፡28ጨለማን ልኮ ምድርን ጽልመት አለበሳት ይሁን እንጂ ትእዛዞቹን አልፈጸሙም፡፡29ውሃቸውን ወደ ደም ለወጠ ዓሣዎቻቸውንም ፈጀ፡፡30የነገሥታት እልፍኝ እንኳ ሳይቀር ምድራቸው በእንቁራሪት ተሸፈነች፡፡31እርሱ ሲናገር ተናካሽ ዝንቦችና ተናዳፊ ትንኞች በአገራቸው ተርመሰመሱ፡፡32በአገራቸው ላይ የበረዶ ድንጋይና መብረቅ አወረደ፡፡33ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ ሌሎች ዛፎቻቸውንም ሰባበረ፡፡34እርሱ ሲናገር አንበጣ መጣ ስፍር ቁጠር የሌለውም ኩብኩባ ከተፍ አለ፡፡35አንበጣ የምድሪቱን ዕፅዋት ሁሉ በላ እህላቸውንም ሁሉ ፈጀ፡፡36ደግሞም የእያንዳንዱን ግብፃዊ በኩር ሁሉ የኃይላቸውንም ሁሉ በኩራት መታ፡፡37እስራኤላውያንን ከወርቅና ከብር ጋር ከዚያ መርቶ አወጣ፤ ከነገዶቻቸው አንዱ እንኳ አልተደናቀፈም፡፡38እጅግ ፈርተዋቸው ነበርና እስራኤላውያን አገር ለቀው ሲወጡ ግብፅ ደስ አላት፡፡39በሚሄዱበት ጊዜ በደመና ጋረዳቸው እሳትም በሌሊት አበራላቸው፡፡40ምግብ እንዲሰጣቸው በለመኑት ጊዜ ድርጭት አመጣላቸው የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው፡፡41ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃም ተንዶለዶለ42ለባርያው ለአብርሃም የሰጠውን ቅዱስ የተስፋ ቃል አስታውሶአልና43ሕዝቡን በደስታ፣ ምርጦቹንም በእልልታ መራቸው፡፡44የሕዝቦችን ምድር ሰጣቸው የእነርሱንም ሀብት ወረሱ፡፡45ይህም ሥርዐቱን ይጠብቁ ዘንድ ሕጉንም ይፈጽሙ ዘንድ ነው፡፡ ያህዌ ይመስገን
1ያህዌን አመስግኑ ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፡፡2የያህዌን ብርቱ ሥራ ማን ሊናገር ይችላል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ተናግሮ ይጨርሳል?3ዘወትር መልካሙንና ትክክል የሆነውን የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው፡፡4ያህዌ ሆይ፣ ለሕዝብህ ሞገስ ስታደርግ አስበኝ፤ በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፡፡5ይኸውም፣ አንተ የመረጥሃቸውን መበልጸግ እንዳይ፣ በሕዝብህ ደስ መሰኘት እኔንም ደስ እንዲለኝ በርስትህም ክብር መመካት እንድችል ነው፡፡6እኛም እንደ አባቶቻችን ኃጢአት ሠራን፣ በደልን፣ ክፉም አደረግን፡፡7አባቶቻችን በግብፅ ምድር ያደረግኸውን አላስተዋሉም፡፡ ብዙዎቹን የቸርነት ሥራዎቹን አላስተዋሉም፡፡ በባሕሩ አጠገብ፣ ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ፡፡8እርሱ ግን የኃይሉን ታላቅነት ለማሳየት ስለ ስሙ አዳናቸው፡፡9ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው፡፡10ከባላጋራቸው እጅ አዳናቸው ከጠላትም እጅ ታደጋቸው፡፡11ባላጋራዎቻቸውን ውሃ ዋጣቸው ከእነርሱ አንድ አልተረፈም፡፡12ከዚያ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ በዝማሬም አመሰገኑት፡፡13ሆኖም፣ ወዲያውኑ እርሱ ያደረገውን ረሱ በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም፡፡14በምድረ በዳ ብዙ ነገር ተመኙ፤ በበረሐም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት፡፡15እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው ነገር ግን የሚያኮሰምን ደዌ ሰደደባቸው፡፡16ሰፈር ውስጥ በሙሴ ላይ የተቀደሰው የያህዌ ካህን ላይ ቀኑ፡፡17ምድር ተከፍታ ዳታንን ዋጠች የአቤሮንንም ሰዎች ሰለቀጠች፡፡18በመካከላቸው እሳት ነድዶ ነበልባልም ክፉዎችን ፈጅቶ አስወገደ፡፡19በኮሬብ ጥጃ ሠሩ ቀልጦ ለተሠራ ምስል ሰገዱ፡፡20ክብራቸውን ሣር በሚበላ የበሬ ምስል ለወጡ፡፡21በግብፅ ታላላቅ ነገሮች ያደረገውን ያዳናቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፡፡22እርሱ በካም ምድር ድንቅ ሥራ በቀይ ባሕርም አስደናቂ ነገር አደረገ፡፡23ቁጣውን እንዲመልስ እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ባይገባ ኖሮ እነርሱን ለማጥፋት ወስኖ ነበር፡፡24መልካሚቱን ምድር ናቁ በተስፋ ቃሉም አላመኑም፡፡25ድንኳናቸው ውስጥ አጉረመረሙ ለያህዌም አልታዘዙም፡፡26ስለዚህ በምድረ በዳ እንደሚያጠፋቸው እጁን አንሥቶ ማለ፡፡27ዘሮቻቸውን በአሕዛብ መካከል ለመጣል እነርሱንም ወደ ተለያየ አገሮች እንደሚበትናቸው ማለ፡፡28ብዔል ፌጐርን አመለኩ ለሙታን የተሠዋውን በሉ፡፡29በተግባራቸውም እግዚአብሔርን አስቆጡት፤ በዚህም ምክንያት በመካከላቸው መቅሠፍት ተነሣ፡፡30ፊንሐስ ተነሥቶ ጣልቃ ገባ፤ መቅሠፍቱም ተገታ፡፡31ይህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ለዘላለም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት፡፡32ደግሞም በመሪባ ውሃ አጠገብ ያህዌን አስቆጡት ሙሴም በእነርሱም ምክንያት ችግር ላይ ወደቀ፡፡33ሙሴን ስላስመረሩት ራሱን ባለ መቆጣጠር ተናገረ፡፡34እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት ሕዝቦችን ከማጥፋት ወደ ኃላ አሉ፡፡35እንዲያውም ከእነርሱ ጋር በመደባለቅ የእነርሱን መንገድ ተማሩ፡፡36ጣዖቶቻቸውን አመለኩ፤ ይህም ወጥመድ ሆነባቸው፡፡37ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠዉ፡፡38የወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ደም ለከነዓን ጣዖቶች መሥዋዕት በማቅረባቸው ንጹሕ ደም አፈሰሱ ምድሪቱንም አረከሱ፡፡39እነርሱ በሥራቸው ረከሱ በድርጊታቸውም አመንዝሮች ሆኑ፡፡40ስለዚህ ያህዌ በሕዝቡ ላይ እጅግ ተቆጣ ርስቱንም ተጸየፈ፡፡41ለአሕዛብ አሳልፎ ሰጣቸው ጠላቶቻቸውም በላያቸው ገዢዎች ሆኑባቸው፡፡42ጠላቶቻቸው ጨቆኑአቸው በሥልጣናቸውም ሥር አደረጓቸው፡፡43እርሱ ብዙ ጊዜ ታደጋቸው እነርሱ ግን ዐመፅ ማድረጋቸውን ገፉበት፡፡ በገዛ ኃጢአታቸው ተዋረዱ፡፡44ይህም ሆኖ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ሲጮኹ ጩኸታቸውን ሰማ ጭንቀታቸውንም ተመለከተ፡፡45ለእነርሱ ሲል ቃል ኪዳኑን አሰበ እንደ ምሕረቱም ብዛት ከቁጣው ተመለሰ፡፡46የሚጨቁኑአቸው ሁሉ እንዲራሩላቸው አደረገ፡፡47አምላካችን ያህዌ ሆይ፣ አድነን፤ ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣ አንተን በመወደስ እንድንከብር ከሕዝቦች መካከል ሰብስበህ አምጣን፡፡48የእስራኤል አምላክ ያህዌ ከዘላለም እስከ ዘለላም ይባረክ፡፡ ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል፡፡ ያህዌ ይባረክ፡፡
1ቸር ነውና ምሕረቱም ለዘላለም ነውና ያህዌን አመስግኑ፡፡2ያህዌ የተቤዣቸው ከጠላትም እጅ የታደጋቸው ይናገሩ፡፡3ለባዕድ ምድር፣ ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ ሰበሰባቸው፡፡4በበረሐ መንገድ ጠፍቶአቸው በምድረ በዳ ተንከራተቱ የሚኖሩበትም ከተማ አላገኙም፡፡5ተራቡ፤ ተጠሙ ከድካም የተነሣ ዛሉ፡፡6በተጨነቁ ጊዜ ወደ ያህዌ ጮኹ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው፡፡7ወደሚኖሩበት ከተማ በቀና መንገድ መራቸው፡፡8ለሰው ልጆች ስላደረገው ድንቅ ነገርና ስለዘላለማዊ ፍቅሩ ሕዝቡ ያህዌን ያመስግኑ፡፡9እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቶአልና የተራበችውን ነፍስ በመልካም ነገር አጥግቦአል፡፡10አንዳንዶች በሰንሰለት ታስረው ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡11ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ቃል በማመፃቸው የልዑልንም ምክር በማቃለላቸው ነበር፡፡12በከባድ ሥራ ልባቸውን አዛለ ተዘለፈለፉ፤ የሚረዳቸውም አላገኙም፡፡13በተጨነቁ ጊዜ ወደ ያህዌ ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው፡፡14ከነበሩበት ድቅድቅ ጨለማ አወጣቸው የታሰሩበትንም ሰንሰለት ሰባበረ፡፡15ለሰው ልጆች ስላደረገው ድንቅ ነገርና ስለ ዘላለማዊ ፍቅሩ ሕዝቡ ያህዌን ያመስግኑ፡፡16እርሱ የናሱን በሮች ሰብሮአልና የብረቱንም መወርወሪያ ቆርጦአል፡፡17አንዳንዶች የዐመፃን መንገድ በመከተላቸው ቂሎች ሆኑ ከበደላቸው የተነሣ ችግር ውስጥ ወደቁ፡፡18ምግብ የመብላት ፍላጐት አጡ፤ ወደ ሞት በሮችም ተቃረቡ፡፡19በተጨነቁ ጊዜ ወደ ያህዌ ጮኹ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው፡፡20ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፡፡ ከመቃብር አፋፍ መለሳቸው፡፡21ለሰው ልጆች ስላደረገው ድንቅ ነገርና ስለ ዘላለማዊ ፍቅሩ ሕዝቡ ያህዌን ያመስግኑ፡፡22የምስጋና መሥዋዕት ያቅርቡለት በዝማሬም ሥራውን ያውጁ፡፡23አንዳንዶች በመርከብ እየተጓዙ ንግዳቸውን ያካሄዱ ነበር፡፡24እነርሱ የያህዌን ሥራ አዩ ድንቅ አድራጐቱንም በጥልቅ ውስጥ ተመለከቱ፡፡25ትእዛዝ በሰጠ ጊዜ ባሕሩን የሚያናውጥ ዐውሎ ነፋስ ነፈሰ፡፡26ወደ ሰማይ ወጡ፤ ወደ ጥልቅም ወረዱ ከመከራቸው የተነሣ ልባቸው ቀለጠ፡፡27እንደ ሰካራም ዞሮባቸው ወዲያ ወዲህ ተንገዳገዱ፤ መላው ጠፍቶባቸው የሚያደርጉትን አጡ፡፡28በመከራቸው ጊዜ ወደ ያህዌ ጮኹ፤ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው፡፡29ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ ሞገዱም ረጭ አለ፡፡30ባሕሩ ጸጥ በማለቱ ደስ አላቸው ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው፡፡31ለሰው ልጆች ስላደረገው ድንቅ ነገር ስለ ዘላለማዊ ፍቅሩ ሕዝቡ ያህዌን ያመስግኑ፡፡32በሕዝቦች ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያደርጉት በሽማግሌዎችም ሸንጐ ያመስግኑት፡፡33ወንዞችን ወደ ምድረ በዳ የውሃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ ምድር ለወጠ፡፡34ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን መሬት ደረቅ ምድር አደረገ፡፡35ምድረ በዳውን ወደ ኩሬ ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ፡፡36የተራቡትን በዚያ አኖረ የሚኖሩበትንም ከተማ ሠሩ፡፡37በእርሻዎች እህል ዘሩ ወይንን ተከሉ፤ ብዙ መከርም ሰበሰቡ፡፡38ይባርካቸዋል፤ እነርሱም እጅግ ይበዛሉ የከብቶቻቸውም ብዛት እንዲያንስ አያደርግም፡፡39በጭንቅ፣ በመከራና በሐዘን፣ ቁጥራቸው አንሶ ተዋርደው ነበር፤ በመኳንንቱም ላይ መናቅን አወረደባቸው40መውጪያ መግቢያው በማይታወቅ በረሐ ውስጥም አንከራተታቸው፡፡41ሆኖም፣ ችግረኞችን ከስቃይ አወጣቸው ለቤተ ሰቡም እንደ በግ መንጋ ተጠነቀቀ፡፡42ቅኖች ይህን ዐይተው ደስ ይላቸዋል ክፋትም አፏን ትዘጋለች፡፡43አስተዋይ የሆነ ሰው ይህን ልብ ይበል፤ እርሱም የያህዌን ምሕረት ያስተውል፡፡
1እግዚአብሔር ሆይ፣ ልቤ ጽኑ ነው፡፡ እዘምራለሁ፤ በፍጹም ልቤም እዘምራለሁ፡፡2በገናና መሰንቆም ተነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ፡፡3ያህዌ ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ በመንግሥታት መካከል የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ4ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይደርሳል፡፡5አምላክ ሆይ፣ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ሁሉ ይንሰራፋ፡፡6የምትወደው ሕዝብህ ይድን ዘንድ በቀኝ እጅህ ታደግ መልሰልኝም፡፡7እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ አለ፤ ደስ እያለኝ ሴኬምን እከፍላለሁ የሱከትንም ሸለቆ እለካለሁ፡፡8ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤ ኤፍሬም የራስ ቁሬ፣ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው፡፡9ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው በኤዶም ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤ በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እፎክራለሁ፡፡10ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል? ወደ ኤዶምስ ማን ያደርሰኛል?11እግዚአብሔር ሆይ፣ ያጣልኸን አንተ አይደለህምን? ከሰራዊታችንም ጋር ወደ ጦርነት አልወጣህም፡፡12አሁንም የሰው ማዳን ከንቱ ነውና በጠላታችን ላይ ድል አቀዳጀን፡፡13በእግዚአብሔር ረድኤት ድል እናደርጋለን ጠላቶቻችንንም ከእግሩ በታች የሚረግጥ እርሱ ነው፡፡
1የማመሰግንህ አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበለኝ2ክፉዎችና አታላዮች አጥቅተውኛልና በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ፡፡3በጥላቻ ዙሪያዬን ከበቡኝ ያለ ምክንያትም በድለውኛል፡፡4ስወዳቸው ይወነጅሉኛል፤ እኔ ግን ለእነርሱ እጸልያለሁ፡፡5በመልካም ፈንታ ክፋትን በወደድኃቸው ፈንታ ጥላቻን ይመልሱልኛል፡፡6በእንዲህ ያለው ሰው፣ ክፉ ሰው በላዩ ሹም ከሳሽም በቀኙ ይቁም፡፡7በተሟገተ ጊዜ ተረትቶ ይግባ ጸሎቱ እንኳ እንደ ኃጢአት ይቆጠርበት፡፡8ዕድሜው ይጠር ሹመቱን ሌላው ይውሰደው፡፡9ልጆቹ ድኻ አደጐች ይሁኑ ሚስቱም መበለት ትሁን፡፡10ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ ከፈረሰው ቤታቸው ይሰደዱ፡፡11ንብረቱ ሁሉ በዕዳ ይያዝበት ለፍቶ ያገኘውን ጥሪት ባዕዳን ሰዎች ይውሰዱበት፡፡12ማንም ሰው ደግ አይሁንለት ለድኻ አደግ ልጆቹ የሚራራላቸው አይገኝ፡፡13ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ፡፡14የአባቶቹ ኃጢአት በያህዌ ፊት ይታሰብ የእናቱም ኃጢአት አይደምሰስ፡፡15በደላቸው ሁልጊዜ በያህዌ ፊት ይሁን የእነርሱ መታሰቢያ ግን ጨርሶ ይጥፋ፡፡16ይህ ሰው ምሕረት ከማድረግ ይልቅ፣ ችግረኛውንና ምስኪኑን ልቡም የቆሰለውን እስከ ሞት አሳድዶአልና ያህዌ ይህን ያደርግበት17መርገምን ወደደ፤ ወደ እርሱም መጣች መባረክ አልወደደም በረከት ከእርሱ ይራቅ፡፡18መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፤ ስለዚህ መርገም እንደ ውሃ ወደ ውስጥ ሰውነቱ፣ እንደ ዘይትም ወደ አጥንቱ ዘለቀች፡፡19ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው፡፡20ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣ እኔ ላይ ክፉ ለሚናገሩ ያህዌ የሚከፍለው ይኸው ይሁን፡፡21አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ስለ ስምህ ስትል እኔን በበጐ ተመልከተኝ፡፡22እኔ ድኽና ችግረኛ ነኝ ልቤም በውስጤ ቆስሎአል፡፡23እንደ ምሽት ጥላ ላልፍ ተቃርቤአለሁ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ፡፡24በጾም ምንያት ጉልበቴ ደከመ ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ መሰለ፡፡25ለጠላቶቼ መሣለቂያ ሆንሁላቸው ሲያዩኝም ራሳቸውን ይነቀንቁብኛል፡፡26አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ ርዳኝ ስለ ታማኝነትህም አድነኝ፡፡27ያህዌ ሆይ፣ እጅህ ይህን እንዳደረገች አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ፡፡28እነርሱ ቢራገሙ እንኳ አንተ ግን ባርከኝ እኔን ሲያጠቁኝ ይዋረዱ ባርያህ ግን ሐሤት ያደርጋል፡፡29ባላንጣዎቼ ውርደትን እንደ ልብስ ይልበሱ እፍረትንም እንደ ሸማ ይጐናጸፉ፡፡30በአንደበቴ ያህዌን እጅግ አመሰግለሁ በጉባኤም መካከል እባርከዋለሁ፡፡31በእርሱ ላይ ከሚፈርዱ ለማዳን እርሱ በችግረኛው ቀኝ ይቆማልና፡፡
1ያህዌ ጌታዬን፣ «ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ» አለው፡፡2ያህዌ ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰዳል አንተም በጠላቶችህ መካከል ትገዛለህ፡፡3በኃይልህ ቀን ተከታዮችህ የተቀደሰ ልብስ ተጐናጽፈው በፈቃዳቸው ይከተሉሃል፡፡ ከንጋት ማሕፀን ጐልማሳነትህ እንደ ጠል ይወጣል፡፡4«እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ» ብሎ ያህዌ ምሎአል፤ እርሱም ሐሳቡን አይለውጥም፡፡5ጌታ በቀኝህ ነው በቁጣው ቀን ነገሥታትን ይገድላል፡፡6በሕዝብ ላይ ይፈርዳል የጦር ሜዳዎችን ሬሳ በሬሳ ያደርጋል፡፡ የብዙ አገሮችን ነገሥታት ይደመሰሳል፡፡7መንገድ ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል ከድል በኃላ ራሱን ቀና ያደርጋል፡፡
1ያህዌ ይመስገን፡፡ በቅኖች ሸንጐ በጉባኤም መካከል በፍጹም ልቤ ያህዌን አመሰግናለሁ፡፡2የያህዌ ሥራ ታላቅ ናት፤ የሚፈልጓትም ሁሉ አጥብቀው ይናፍቋታል፡፡3ሥራው ባለ ግርማና ባለ ክብር ነው ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡4ያህዌ ቸርና መሐሪ ነው ሲታወስ የሚኖር ድንቅ ሥራ አደረገ፡፡5ለሚፈሩት ምግባቸውን ይሰጣል ኪዳኑንም ዘወትር ያስባል፡፡6ለእነርሱ የአሕዛብን ርስት በመስጠት የአሠራሩን ብርታት አሳይቶአል፡፡7የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው ትእዛዞቹም የታመኑ ናቸው፡፡8እነርሱም ለዘላለም የጸኑ ናቸው በታማኝነትና በቅንነት ይጠበቃሉ፡፡9ለሕዝቡ ድልን ሰጠ ኪዳኑን ለዘላለም አዘዘ ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው፡፡10ያህዌን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው ትእዛዙንም የሚጠብቁ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፡፡ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል፡፡
1ያህዌ ይመስገን ያህዌን የሚፈራ በትእዛዞቹም እጅግ ደስ የሚሰኝ የተባረከ ነው፡፡2ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል የቅኖች ትውልድ ይባረካል፡፡3ሀብትና ብልጽግና ቤቱን ይሞላል ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል፡፡4ምሕረትና ቸርነት፣ ቅንነትንም ለሚያደርግ ደግ ሰው በጨለማ ውስጥ ብርሃን ይወጣለታል፡፡5ሥራውን በትክክል የሚያከናውን፣ ለጋስና ሳይሰስት የሚያበድር ሰው መልካም ይሆንለታል፡፡6እርሱ ከቶውንም አይናወጥምና ጻድቅ ሰው ሲታወስ ይኖራል፡፡7እምነቱን ያህዌ ላይ ያደረገ ልበ ሙሉ ስለሆነ ክፉ ወሬ አያሸብረውም፡፡8ልቡ እግዚአብሔርን በመተማመን የጸና ነው፡፡ በመጨረሻ የጠላቶቹን ውድቀት ያያል፡፡9በልግስና ለድኾች ይሰጣል ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል፡፡ በክብር ከፍ ከፍ ይላል፡፡10ክፉ ሰው ይህን፤ በማየት ይበሳጫል ጥርሱን ያፋጫል፤ እየመነመነም ይጠፋል፡፡ የክፉዎች ምኞት ትጠፋለች፡፡
1ያህዌ ይመስገን፡፡ የያህዌ አገልጋዮች ሆይ፣ የያህዌን ስም አመስግኑ፡፡2ከአሁን እስከ ዘላለም የያህዌ ስም ይመስገን፡፡3ከፀሐይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ የያህዌ ስም ይመስገን፡፡4ያህዌ ከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው፡፡5እንደ አምላካችን እንደ ያህዌ በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?6ራሱን ዝቅ አድርጐ በሰማይና በምድር ያሉትንስ የሚያይ ማን ነው?7ድኻውን ከትቢያ ያነሣል ችግረኛውንም ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡8ከመኳንንት ጋር፣ ከሕዝቡም ሹማምንት ጋር ያስቀምጠዋል፡፡9መካኒቱን በቤት ያኖራታል ደስ የተሰኘች የልጆች እናት ያደርጋታል፡፡ ያህዌ ይመስገን!
1እስራኤል ከግብፅ ወጥቶ ሲሄድ የያዕቆብም ቤት ከባዕድ ሕዝብ ተለይቶ ሲወጣ2ይሁዳ ቅዱስ ማደሪያው እስራኤልም ግዛቱ ሆነ፡፡3ባሕር ዐይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ላኋው ተመለሰ፡፡4ተራሮች እንደ አውራ በግ ፈነጩ ኮረብቶችም እንደ ጠቦት ዘለሉ፡፡5አንተ ባሕር ምን ሆነህ ሸሸህ? አንተስ ዮርዳኖስ ለምን ወደ ኃላህ ተመለስህ?6እናንተ ተራሮች ስለምን እንደ አውራ በግ ፈነጫችሁ? ኮረብቶችስ ለምን እንደ ጠቦት ዘለላችሁ?7ምድር ሆይ፣ በጌታ ፊት በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፡፡8እርሱ ዐለቱን ወደ ውሃ ኩሬ ቋጥኙንም ወደ ውሃ ምንጭ ለወጠ፡፡
1ለእኛ ሳይሆን፣ ያህዌ ሆይ ለእኛ ሳይሆን ስለ ፍቅርህ፣ ስለ ታማኝነትህ ስምህን አክብረው፡፡2ስለ ምን ሕዝቦች፣ «አምላካቸው የት አለ?» ይበሉ3አምላካችን በሰማይ ነው እርሱ ደስ የሚለውን አደረገ፡፡4የአሕዛብ ጣዖቶች ብርና ወርቅ የሰው እጅ ሥራዎችም ናቸው፡፡5አፍ አላቸው ግን አይናገሩም ዐይን አላቸው ግን አያዩም6ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም አፍንጫ አላቸው ግን አያሸቱም፡፡7እጅ አላቸው ግን አይዳሰስም እግር አላቸው ግን አይራመዱም ድምፅም ማሰማት አይችሉም፡፡8የሠሩአቸውና የሚታመኑባቸው ሁሉ እንደ እነዚህ ጣዖቶች ናቸው፡፡9የእስራኤል ቤት ሆይ፣ በያህዌ ታመኑ ረዳታችሁና ጋሻችሁ እርሱ ነው፡፡10የአሮን ቤት ሆይ፣ በያህዌ ታመኑ ረዳታችሁና ጋሻችሁ እርሱ ነው፡፡11እናንት ያህዌን የምትፈሩ፣ በእርሱ ታመኑ ረዳታችሁና ጋሻችሁ እርሱ ነው፡፡12ያህዌ ያስበናል፤ ይባርከናልም፤ እርሱ የእስራኤልን ቤት ይባርካል የአሮንንም ቤት ይባርካል፡፡13ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች እርሱ የሚፈሩትን ሁሉ ይባርካል፡፡14ያህዌ እናንተንና ልጆቻችሁን በባርኮቱ ይባርካችሁ፡፡15ሰማይና ምድርን የፈጠረ ያህዌ ይባርካችሁ፡፡16ሰማያት የእግዚአብሔር ናቸው ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት፡፡17ወደ ዝምታ ዓለም፣ ወደ መቃብር የወረዱ ሙታን ያህዌን ሊያመሰግኑ አይችሉም፡፡18እኛ ግን፣ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም ያህዌን እንባርካለን፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
1የልመናዬን ድምፅ ስለ ሰማ ያህዌን ወደድሁት፡፡2እርሱ ሰምቶኛልና በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ፡፡3የሞት ወጥመድ ያዘኝ የሲኦልም ጣር አገኘኝ ጭንቅና ሐዘን በረታብኝ፡፡4እኔም የያህዌን ስም ጠራሁ «ያህዌ ሆይ፣ እባክህ ነፍሴን አድናት፡፡»5ያህዌ ቸርና መሐሪ ነው፡፡ አምላካችን ርኅሩኅ ነው፡፡6አምላካችን ገሮችን ይጠብቃል እኔም በተቸገርኩ ጊዜ አድኖኛል፡፡7ያህዌ መልካም ነገር አድርጐልኛልና ከእንግዲህ ነፍሴ ወደ እረፍት ቦታ ትመለሳለች፡፡8አንተ ነፍሴን ከሞት፣ ዐይኔን ከእንባ እግሮቼን ከመሰናክል አድነሃልና፡፡9እኔም በሕያዋን ምድር ያህዌን አገለግላለሁ፡፡10«እጅግ ተጨንቄአለሁ» ባልሁ ጊዜ እንኳ በእርሱ ማመኔን አልተውሁም፡፡11ግራ በተጋባሁ ጊዜ፣ «ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው» አልሁ፡፡12ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ለያህዌ ምን ልክፈለው?13የመዳንን ጽዋ አነሣለሁ የያህዌንም ስም እጠራለሁ፡፡14በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለያህዌ እፈጽማለሁ፡፡15የቅዱሳኑ ሞት በያህዌ ፊት የከበረ ነው፡፡16ያህዌ ሆይ፣ እኔ በእውነት ባርያህ ነኝ፣ የሴት ባርያህም ልጅ ነኝ፡፡ ከእስራቴም ፈታኸኝ፡፡17ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ የያህዌንም ስም እጠራለሁ፡፡18በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለያህዌ እፈጽማለሁ19ኢየሩሳሌም ሆይ፣ በመካከልሽ በያህዌ ቤት አደባባይ ይህን አደርጋለሁ፡፡
1አሕዛብ ሁላችሁ ያህዌን አመስግኑት ሕዝቦችም ሁሉ በምስጋና ከፍ ከፍ አድርጉት፡፡2እርሱ ለእኛ ያሳየው ምሕረት ታላቅ ነውና የያህዌ ታማኝነት ጸንቶ ይኖራል፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
1ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑት ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች፡፡2የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ «ምሕረቱ ለዘላለም ነው» ይበል፡፡3የአሮን ቤት፣ «ምሕረቱ ለዘላለም ነው» ይበል፡፡4ያህዌን የሚፈሩ ሁሉ፣ «ምሕረቱ ለዘላለም ነው» ይበሉ፡፡5በተጨነቅሁ ጊዜ ያህዌን ጠራሁት እርሱም ሰማኝ፤ ነጻም አወጣኝ፡፡6ያህዌ ከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?7ይረዳኝ ዘንድ ያህዌ ከእኔ ጋር ነው የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ፡፡8በሰው ከመታመን ይልቅ ያህዌን መከታ ማድረግ ይሻላል፡፡9በመሪዎች ከመመካት ይልቅ ያህዌን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል፡፡10ሕዝቦች ሁሉ ከበቡኝ ነገር ግን በያህዌ ስም አሸነፍኃቸው11መክበቡንስ፣ ዙሪያዬን ከበቡኝ ነገር ግን በያህዌ ስም አሸነፍኃቸው፡፡12እንደ ንብ መንጋ ከበቡኝ ሆኖም፣ እንደሚነድ እሾኽ ከሰሙ በእርግጥም በያህዌ ስም አሸነፍኃቸው፡፡13ሊጥሉኝ ገፈተሩኝ ያህዌ ግን ረዳኝ፡፡14ያህዌ ብርታቴና ደስታዬ ነው፤ የሚታደገኝም እርሱ ነው፡፡15በጻድቃን ድንኳን፣ የእልልታና የሆታ ድምፅ፣ እንዲህ እያለ ያስተጋባል የያህዌ ቀኝ እጅ አሸነፈ፡፡16የያህዌ ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለ፤ የያህዌ ቀኝ እጅ አሸነፈ፡፡17በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፣ አልሞትም የያህዌንም ሥራ ገና እናገራለሁ፡፡18ያህዌ ክፉኛ ቀጥቶኝ ነበር ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም፡፡19የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ ወደዚያ ገብቼ ያህዌን አመሰግናለሁ፡፡20ይህች የያህዌ ደጅ ናት፤ ጻድቃንም በእርሷ በኩል ይገባሉ፡፡21ሰምተህ መልሰህልኛና፣ አዳኝም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ፡፡22ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማእዘን ራስ ሆነ፡፡23ይህም የያህዌ ሥራ ነው ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፡፡24ያህዌ የሠራት ቀን ይህች ናት፣ በእርሷ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፡፡25ያህዌ ሆይ፣ እባክህ ድል አቀዳጀን! ያህዌ ሆይ፣ እባክህ አከናውንልን፡፡26በያህዌ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እኛም ከያህዌ ቤት ባረክናችሁ፡፡27ያህዌ አምላካችን ነው፤ ብርሃኑንም በላያችን አበራ መሥዋዕቱን መሠዊያው ቀንዶች ላይ በገመድ እሰሩ፡፡28አንተ አምላኬ ነህ፤ አመሰግንሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፡፡29ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑ ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች፡፡
1መንገዳቸው ነቀፋ የሌለበት በያህዌም ሕግ የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው፡፡2ትእዛኦቹን የሚጠብቁ በሙሉ ልባቸውም የሚፈልጉት የተባረኩ ናቸው፡፡3በመንገዱ ይሄዳሉ እንጂ ዐመፅ አያደርጉም፡፡4ጠንቅቀን እንጠብቃት ዘንድ አንተ ሥርዐትን አዝዘሃል፡፡5ሥርዐትህን እጠብቅ ዘንድ ምነው መንገዴ ጽኑ በሆነልኝ ኖሮ!6ትእዛዞችህን ሁሉ በጥንቃቄ ካስተዋልሁ እፍረት ከቶ አይደርስብኝም፡፡7የጽድቅ ፍርድህን ስማር በቅን ልብ ምስጋና አቀርብልሃለሁ፡፡8ሥርዐትህን እጠብቃለሁ አንተ ፈጽሞ አትተወኝ፡፡ ቤት9ጐልማሳ መንገዱን እንዴት ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው፡፡10በሙሉ ልቤ እፈልግሃለሁ ከትእዛዞችህ እንድርቅ አትተወኝ፡፡11አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ አኖራለሁ፡፡12ያህዌ ሆይ፣ አንተ ቡሩክ ነህ ሥርዐትህን አስተምረኝ፡፡13አንተ የገለጥኸውን የጽድቅ ሥርዐት ሁሉ በአንደበቴ እናገራለሁ፡፡14ከብዙ ሀብት ይልቅ በኪዳንህ ሥርዐት ደስ ይለኛል፡፡15ድንጋጌህን አሰላስላለሁ መንገድህም ላይ አተኩራለሁ፡፡16በሥርዐትህ ደስ ይለኛል ቃልህንም አልዘነጋም፡፡ ጋሜል17በሕይወት እንድኖርና ቃልህን እንድጠብቅ ለባርያህ መልካም አድርግ፡፡18ከሕግህ ድንቅ ነገር እንዳይ ዐይኖቼን ክፈት፡፡19በምድር ላይ መጻተኛ ነኝ ትእዛዞችህን ከእኔ አትሰውር፡፡20ጻድቅ ሥርዐትህን ለማወቅ ዘወትር ከመናፈቄ የተነሣ ነፍሴ እጅግ ዛለች፡፡21ከትእዛዞችህ የሳቱትን የተረጉሙ ዕቡያንን ገሠጽህ፡፡22ሥርዐቶችህን ጠብቄአለሁና ስድብና ውርደትን ከእኔ አርቅ፡፡23ገዦች ተሰብስበው በእኔ ላይ ቢዶልቱም እንኳ ባርያህ ሥርዐትህን ያሰላስላል፡፡24ትእዛዝህ ለእኔ ደስታዬ ነው መካሪየም ነው፡፡ ዳሌጥ25ነፍሴ ከዐፈር ጋር ተጣበቀች በቃልህ ሕይወት ስጠኝ፡፡26ስለ መንገዴ ገልጬ ነገርሁህ አንተም መልሰህልኝ ሥርዐትህን አስተምረኝ፡፡27ድንቅ ሥራህን አሰላስል ዘንድ የድንጋጌህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፡፡28ሐዘን በርትቶብኛል በቃልህ አበርታኝ፡፡29የሽንገላን መንገድ ከእኔ አርቅ በቸርነትህ ሕግህን አስተምረኝ፡፡30የእውነትን መንገድ መርጫለሁ ሕግህንም ፊት ለፊቴ አድርጌአለሁ፡፡31ከሥርዐትህ ጋር ተጣብቄአለሁ ያህዌ ሆይ፣ ለውርደት አሳልፈህ አትስጠኝ፡፡32ያን እንዳደርግ አንተ ልቤን አስፍተኸዋል በትእዛዞችህ መንገድ እሮጣለሁ፡፡ ሄ33ያህዌ ሆይ፣ የሥርዐትህን መንገድ አስተምረኝ እኔም እስከ መጨረሻው እጠብቀዋለሁ፡፡34ሕግህን እንድጠብቅ፣ በፍጹም ልቤም እንድታዘዘው ማስተዋልን ስጠኝ፡፡35በዚያ መሄድ ደስ ይለኛልና በትእዛዞችህ መንገድ ምራኝ፡፡36ጽድቅ ከሌለበት ጥቅም ይልቅ ልቤን ወደ ሥርዐትህ አዘንብል፡፡37ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ በጽድቅህ ሕይወቴን አድስልኝ፡፡38ለእኔ ለአገልጋይህና ለሚፈሩህ ሁሉ የሰጠኸውን ተስፋ ቃል ፈጽም፡፡39ጻድቅ ፍርድህ መልካም ነውና የምፈራውን ስድብ አርቅልኝ፡፡40እነሆ፣ ድንጋጌህን ናፈቅሁ በጽድቅህም ሕያው አድርገኝ፡፡ ዋው41ያህዌ ሆይ፣ ዘላለማዊ ፍቅርህን ስጠኝ በተስፋ ቃልህ መሠረት አድነኝ፡፡42በቃልህ ታምኛለሁና ለሚሰድቡኝ መልስ እሰጣለሁ፡፡43ሕግህን ተስፋ አድርጌአለሁና የእውነትን ቃል ከአፌ አታርቅ፡፡44ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕግህን ዘወትር እጠብቃለሁ፡፡45ሥርዐትህን እሻለሁና በፍጹም ነጻነት እኖራለሁ፡፡46ትእዛዞችህን በነገሥታት ፊት እናገራለሁ ይህን በማድረጌም እፍረት አይሰማኝም፡፡47አጥብቄ እወደዋለሁና በትእዛዞችህ ደስ ይለኛል፡፡48እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዞችህ አነሣለሁ፤ ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ፡፡ ዛይ49በዚያ ተስፋ ሰጥተኸኛልና ለባርያህ የገባኸውን ቃል አስብ፡፡50የተስፋ ቃልህ ሕያው አድርጐኛልና ይህ በመከራዬ መጽናኛዬ ሆነ፡፡51ትዕቢተኞች እጅግ ተሳለቁብኝ እኔ ግን ከሕግህ ንቅንቅ አላልሁም፡፡52ያህዌ ሆይ፣ ከጥንት የነበረውን ድንጋጌህን አሰብሁ በዚህም ተጽናናሁ፡፡53ሕግህን ከናቁ ክፉዎች የተነሣ እጅግ ተቆጣሁ፡፡54በእንግድነቴ አገር ሥርዐትህ መዝሙሬ ሆነ፡፡55ያህዌ ሆይ፣ ስምህን በሌሊት አስባለሁ ሕግህንም እጠብቃለሁ፡፡56ሥርዐትህን ጠብቄአለሁና ይህ የሁልጊዜ ልምዴ ሆነ፡፡ ሔት57ያህዌ ዕድል ፈንታዬ ነው ቃልህን ለመታዘዝ ቆርጫለሁ፡፡58በፍጹም ልቤ የአንተን ሞገስ እፈልጋለሁ እንደ ቃልህ ቸርነት አሳየኝ፡፡59መንገዴን መረመርሁ አካሄዴንም ወደ ሥርዐትህ አቀናሁ፡፡60ትእዛዝህን ለመጠበቅ ቸኮልሁ፤ አልዘገየሁም፡፡61የክፉዎች ገመድ ተተበተበብኝ እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም፡፡62ስለ ጻድቅ ሥርዐትህ አንተን ለማመስገን በእኩለ ሌሊት እነሣለሁ፡፡63እኔ አንተን የሚፈሩና ሥርዐትህንም የሚጠብቁ ሁሉ ባልንጀራ ነኝ፡፡64ያህዌ ሆይ፣ ምድር በምሕረትህ ተሞላች ሥርዐትህን አስተምረኝ፡፡ጤት65ያህዌ ሆይ፣ እንደ ቃልህ ለአገልጋይህ መልካም አድርገሃል፡፡66በትእዛዞችህ አምናለሁና ተገቢውን ማስተዋልና ዕውቀትን አስተምረኝ፡፡67አንዳች ጉዳት ሳይደርስብኝ መንገድ ስቼ ሄድሁ አሁን ግን ቃልህን እጠብቃለሁ፡፡68አንተ መልካም ነህ፤ የምታደርገውም መልካም ነው እንግዲህ ሥርዐትህን አስተምረኝ፡፡69እብሪተኞች በሐሰት ስሜን አጠፉ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዝህን እጠብቃለሁ፡፡70ልባቸው የሰባና የደነደነ ነው እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል፡፡71ሥርዐትህን እማር ዘንድ በመከራ ውስጥ ማለፌ መልካም ሆነልኝ፡፡72ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል፡፡ ዮድ73እጆችህ ሠሩኝ፣ አበጃጁኝም ትእዛዞችህን እንድማር ማስተዋልን ስጠኝ፡፡74ቃልህን ተስፋ አድርጌአለሁና የሚፈሩህ እኔን ዐይተው ደስ ይላቸዋል፡፡75ያህዌ ሆይ፣ ፍርድህ እውነተኛ እንደ ሆነ ያስጨነቅኸኝም በታማኝነት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፡፡76ለአገልጋይህ በገባኸው ቃል መሠረት ምሕረትህ መጽናኛዬ ይሁንልኝ፡፡77ሕግህ ደስታዬ ነውና በሕይወት እንድኖር ራራልኝ፡፡78በሐሰት የሚከሱኝ ትዕቢተኞች ይዋረዱ እኔ ግን ሥርዐትህን አሰላስላለሁ፡፡79አንተን የሚፈሩህ ሥርዐቶችህንም የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ፡፡80እፍረት እንዳይደርስብኝ ልቤ በሥርዐትህ ያለ ነቀፋ ይሁን፡፡ ካፍ81ነፍሴ ማዳንህን እጅግ ናፈቀች ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ፡፡82«መቼ ታጽናናኛለህ?» እያልሁ በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ፡፡83ጢስ እንደ ጠገበ የወይን ጠጅ አቁማዳ ሆኛለሁ ሥርዐትህን አልረሳሁም፡፡84እኔ አገልጋይህ እስከ መቼ ልቆይ? በሚያሳድዱኝ ላይ የምትፈርደው መቼ ነው?85ሕግህን የማያከብሩ፤ ትዕቢተኞች ጉድጓድ ቆፈሩልኝ፡፡86ትእዛዞችህ ሁሉ አስተማማኝ ናቸው ሰዎች ያለ ምክንያት እያሳደዱኝ ስለሆነ ርዳኝ፡፡87ከምድር ሊያጠፉኝ ጥቂት ቀራቸው እኔ ግን ትእዛዞችህን ችላ አላልሁም፡፡88ሕግህን እጠብቅ ዘንድ በዘላለማዊ ፍቅርህ ሕያው አድርገኝ፡፡ ላሜድ89ያህዌ ሆይ፣ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡90ታማኝነትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ሁሉ ነው ምድርን መሠረትሃት እርሷም ጸንታ ትኖራለች፡፡91ነገሮች ሁሉ አገልጋዮችህ ስለሆኑ በሕግህ መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ ጸንተው ይኖራሉ፡፡92ሕግህ ደስታዬ ባይሆን ኖሮ፣ በደረሰብኝ መከራ በጠፋሁ ነበር፡፡93በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና ትእዛዞችህን ከቶ አልረሳሁም፡፡94እኔ የአንተ ነኝ፤ እባክህ አድነኝ ሕግህንም ፈልጌአለሁ፡፡95ክፉዎች ሊያጠፉኝ አድብተዋል እኔ ግን ሕግህን መረዳት እፈልጋለሁ፡፡96ማንኛውም ነገር የራሱ ወሰን እንዳለው አየሁ፤ ትእዛእህ ግን እጅግ ሰፊ ነው፡፡ ሜም97አቤቱ ሕግህን ምንኛ ወደዱሁ ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ፡፡98ዘወትር ከእኔ ጋር በመሆኑ፣ ሕግህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ፡፡99ሥርዐቶችህን አሰላስላለሁና ከአስተማሪዎቼ ሁሉ የበለጠ ማስተዋል አለኝ፡፡100መመሪያህን ተከትዬ ስለምሄድ ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋይ ሆንሁ፡፡101ቃልህን እጠብቅ ዘንድ እግሬን ከክፉ መንገድ ከለከልሁ፡፡102አንተው ራስህ አስተምረኸኛልና ከድንጋጌህ ዘወር አላልሁም፡፡103ቃልህ ለምላሴ ምንኛ ጣፋጭ ነው ለአፌም ከማር ወለላ ይልቅ ጣዕም አለው፡፡104ከመመሪያህ ማስተዋል አገኘሁ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ፡፡ ኖን105ቃልህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው፡፡106ጻድቅ ትእዛዞችህን ለመጠበቅ በመሐላ የገባሁትን ቃል አጸናለሁ፡፡107እጅግ ተጐድቻለሁና ያህዌ ሆይ፣ እንደ ቃል ሕያው አድርገኝ፡፡108ያህዌ ሆይ፣ ፈቅጄ የማቀርበውን የአፌን ምስጋና መሥዋዕት ተቀበል፡፡109ነፍሴ ዘወትር አደጋ ላይ ናት፤ እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም፡፡110ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ እኔ ግን ከመመሪያህ ፈቀቅ አላልሁም፡፡111ሕግህ የዘላለም ውርሴ ነው የልቤም ደስታ ይኸው ነው፡፡112ትእዛዝህን እስከ መጨረሻው ለዘላለም ለመፈጸም ልቤን ወደዚያው አዘነበልሁ፡፡ ሳምኬት113መንታ ልብ ያላቸው ወላዋዮችን ጠላሁ፤ ሕግህን ግን ወደድሁ፡፡114አንተ ጋሻዬና መሸሸጊያ ነህ ቃልህን በተስፋ እጠብቃለሁ፡፡115የአምላኬን ትእዛዞች እጠብቅ ዘንድ እናንት ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ራቁ116በሕይወት እኖር ዘንድ በቃልህ ደግፈኝ ተስፋዬም መና ቀርቶ አልፈር፡፡117ያለ ስጋት እንድኖር ደግፈህ ያዘኝ ሥርዐትህንም ዘወትር አሰላስላለሁ፡፡118አታላዮችና የማያስተማምኑ ስለሆኑ ከሥርዐትህ የሚያፈነግጡትን ሁሉ ወዲያ አስወገድሃቸው፡፡119የምድርን ክፉዎች ሁሉ እንደ ጥራጊ አስወገድሃቸው፡፡ ስለዚህ እኔ ትእዛዞችህን ወደድሁ፡፡120አንተን በመፍራት ሥጋዬ ተንቀጠቀጠ ፍርድህን እፈራለሁ፡፡ ዔ121ትክክልና መልም የሆነውን አድርጌአለሁና ለሚጨቁኑኝ አሳልፈህ አትስጠኝ፡፡122ለባርያህ ደኅንነት ዋስትና ሁን ትዕቢተኛ እንዲረግጠኝ አትፍቀድለት፡፡123ማዳንህንና የጽድቅ ቃልህን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ደከሙ፡፡124ለእኔ ለአገልጋይህ ታማኝትህን አሳይ፣ ሥርዐቶችህንም አስተምረኝ፡፡125እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ ሥርዐትህንም እንዳውቅ ማስተዋልን ስጠኝ፡፡126ያህዌ ሆይ፣ ሕግህ እየተጣሰ ነውና ጊዜው አንተ የምትሠራበት ነው፡፡127ከወርቅ፣ ከንጹሕም ወርቅ ይልቅ በእውነት ትእዛዞችህን ወደድሁ፡፡128ስለዚህ መመሪያዎችን በጥንቃቄ ጠበቅሁ የሐሰትንም መንገድ ጠላሁ፡፡ ፌ129ሥርዐቶችህ አስደናቂ ናቸው እኔም በሙሉ ልቤ እታዘዛቸዋለሁ፡፡130የቃልህ ፍቺ ያበራል አላዋቂዎችን አስተዋይ ያደርጋል፡፡131ትእዛዝህን በመናፈቄ አፌን ከፊትሁ አለከለክሁም፡፡132ስምህን ለሚፈሩ ዘወትር እንደምታደርገው ወደ እኔ ተመልሰህ ምሕረት አድርግልኝ፡፡133እንደ ቃልህ አካሄዴን ቀና አድርግልኝ ኃጢአት እንዲሠለጥንብኝም አትፍቀድ፡፡134ትእዛዝህን መጠበቅ እንድችል ከሰዎች ጥቃት አድነኝ፡፡135ፊትህ በባርያህ ላይ ያብራ ሥርዐትህንም አስተምረኝ፡፡136ሰዎች ሕግህን ስለ ጣሱ እንባዬ እንደ ወራጅ ውሃ ፈሰሰ፡፡137ያህዌ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ ነህ ፍርድህም ትክክል ነው፡፡138ሕግህ በፍጹም እውነትና ትክክል ነው፡፡139ጠላቶቼ ቃልህን መዘንጋታቸው በጣም አበሳጨኝ፡፡140ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው ባርያህም ወደደው፡፡141እኔ የማልጠቅምና የተናቅሁ ብሆን እንኳ፣ መመሪያህን አልዘነጋሁም፡፡142ጽድቅህ ለዘላለም ትክክል ነው ሕግህም የታመነ ነው፡፡143መከራና ስቃይ ቢደርስብኝ እንኳ አሁንም ትእዛዝህ ደስታዬ ነው፡፡144ሥርዐትህ ለዘላለም ጻድቅ ነው በሕይወት መኖር እንድችል ማስተዋል ስጠኝ፡፡ ቆፍ145ያህዌ ሆይ፣ በፍጹም ልቤ እጮኻለሁና መልስልኝ፤ ሥርዐትህንም እጠብቃለሁ፡፡146ወደ አንተ እጣራለሁና አድነኝ ሥርዐትህንም እጠብቃለሁ፡፡147ጐሕ ከመቅደዱ በፊት ርዳታህን በመፈለግ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቃልህንም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡148ቃልህን አሰላስል ዘንድ ሌሊቱን ሙሉ ዐይኔ ሳይከደን ያድራል፡፡149እንደ ቸርነትህ መጠን ድምፄን ስማ ያህዌ ሆይ፣ በትእዛዝህ መሠረት ሕይወቴን ጠብቅ፡፡150የሚያሳድዱኝ ወደ እኔ ቀርበዋል ከሕግህ ግን ርቀዋል፡፡151ያህዌ ሆይ፣ አንተ ቅርብ ነህ መመሪያዎችህም የታመኑ ናቸው፡፡152ለዘላለም እንደ መሠረትሃቸው ጥንት ከሥርዐትህ ተምሬአለሁ፡፡ ሬስ153ሕግህን አልረሳሁምና መከራዬን ተመልከት አድነኝም፡፡154ተሟገትልኝ አድነኝም እንደ ተስፋ ቃልህም ጠብቀኝ፡፡155ሥርዐትህን ስለማይፈልጉ ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው፡፡156ያህዌ ሆይ፣ ርኅራኄህ ታላቅ ነው፤ እንደ ሁልጊዜው በሕይወት ጠብቀኝ፡፡157አሳዳጆቼና ጠላቶቼ በዝተዋል፤ እኔ ግን ከሥርዐትህ ፈቀቅ አላልሁም፡፡158ቃህን አልጠበቁም ከዳተኞችን ዐይቼ ተጸየፍኃቸው፡፡159መመሪያህን እንዴት እንደምወድ እይ፤ ያህዌ ሆይ፣ እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፡፡160የቃልህ ሥረ መሠረት እውነት ነው ጻድቅ የሆነው ሕግህም ዘላለማዊ ነው፡፡ ሳን161መመሪያህን እንዴት እንደምወድ እይ፤ ያህዌ ሆይ፣ እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፡፡162የቃልህ ሥረ መሠረት እውነት ነው ጻድቅ የሆነው ሕግህም ዘላለማዊ ነው፡፡ ሳን163ሐሰትን እጠላለሁ፤ እጸየፋለሁ ሕግህን ግን ወደድሁ፡፡164ጻድቅ ስለሆነው ሕግህ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለሁ፡፡165ሕግህን ለሚወዱ ብዙ ሰላም አላቸው ዕንቅፋትም የለባቸውም፡፡166ያህዌ ሆይ፣ ማዳንህን እጠብቃለሁ ትእዛዞችህንም እፈጽማለሁ፡፡167ትእዛዝህን እጠብቃለሁ በሙሉ ልቤም እወዳቸዋለሁ፡፡168ትእዛዝህንና ሕግህን አከብራለሁ አንተ የምሠራውን ሁሉ ታውቃለህ፡፡ ታው169ያህዌ ሆይ፣ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጮኽ ስማኝ እንደ ቃልህም ማስተዋልን ስጠኝ፡፡170ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ በተስፋ ቃልህም መሠረት አድነኝ፡፡171ሥርዐትህን አስተምረኸኛልና ከንፈሮቼ ምስጋናን አፈለቁ፡፡172ትእዛዞችህ ሁሉ ትክክል ስለሆኑ ስለ ቃልህ እዘምራለሁ፡፡173መመሪያህን መርጫለሁና እጅህ እኔን ለመርዳት ዝግጁ ይሁን፡፡174ያህዌ ሆይ፣ ማዳንህን ናፈቅሁ ሕግህም ደስታዬ ነው፡፡175አመሰግንህ ዘንድ በሕይወት ልኑር ሕግህም ይርዳኝ፡፡176እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ ትእዛዞችህን አልረሳሁምና ባርያህን ፈልገው፡፡
1በጨነቀኝ ጊዜ ወደ ያህዌ ተጣራሁ እርሱም መለሰልኝ፡፡2ከሐሰተኛ ከንፈር፣ ከአታላይ ምላስም አድነኝ፡፡3እናንት አታላዮች እግዚአብሔር እንዴት ይቅጣችሁ፣ ምንስ ቢከፍላችሁ ይሻላል?4በተሳለ የጦረኛ ቀስት በግራር ከሰል ፍም ይቀጣችኃል፡፡5የምኖረው በሜሼክ ስለ ሆነ የነበርኩትም በቄዳር ድንኳኖች መካከል ስለ ነበር ወዮልኝ፡፡6ሰላምን ከሚጠሉ ጋር በጣም ረጅም ጊዜ ኖርሁ፡፡7እኔ ሰላም ፈላጊ ነኝ፡፡ በተናገርሁ ጊዜ ግን እነርሱ ጠብ ይፈልጋሉ፡፡
1ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ ረዳቴ ከወዴት ይመጣል?2ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከያህዌ ዘንድ ይመጣል፡፡3እግርህ እንዲንሸራተት አይፈቅድም አንተን የሚጠብቅህም አይተኛም፡፡4እነሆ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፉምም፡፡5ያህዌ ይጠብቅሃል፤ ያህዌ በቀኝህ በኩል ይከልልሃል፡፡6ፀሐይ በቀን አያቃጥልህም ጨረቃም በሌሊት አይጐዳህም፡፡7ያህዌ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል እርሱ ሕይወትህንም ይጠብቃል፡፡8ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም ያህዌ በምታደርገው ሁሉ ይጠብቅሃል፡፡
1«ወደ ያህዌ ቤት እንሂድ» ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ፡፡2ኢየሩሳሌም ሆይ፣ እግሮቻችን በደጆችሽ ውስጥ ቆመዋል፡፡3ኢየሩሳሌም በጥንቃቄ የተገነባች ከተማ ናት!4ለእስራኤል ምስክር ይሆን ዘንድ ነገዶች፣ የያህዌ ነገዶች ወደዚያ ይወጣሉ፡፡5በዚያም የፍርድ ዙፋኖች የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተዘርግተዋል፡፡6ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ፡፡ «የሚወዱሽ ሰላም ይሁንላቸው፡፡7በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም ይሁን በምሽጐችሽም ውስጥ መረጋጋት ይስፈን፡፡»8ስለ ወንድሞቼና ስለ ወዳጆቼ ኢየሩሳሌምን፣ «ሰላም ከአንቺ ጋር ይሁን» እላታለሁ፡፡9ስለ አምላካችን ያህዌ ቤት መልካም እንዲሆንልሽ እሻለሁ፡፡
1በሰማያት የምትኖር ሆይ፣ ዐይኖቼን ወደ አንተ እነሣለሁ፡፡2የባርያዎች ዐይን ወደ ጌታቸው እጅ እንደሚመለከት የባርያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት ምሕረት እስኪያደርግልን ድረስ የእኛም ዐይን ወደ አምላካችን ወደ ያህዌ ይመለከታሉ፡፡3ያህዌ ሆይ፣ እጅግ ተዋርደናልና ማረን፣ አቤቱ ማረን፡፡4በትዕቢተኞች ብዙ ተዋርደናል፣ በትምክሕተኞችም እጅግ ተንቀናል፡፡
1«ያህዌ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ» ይበል እስራኤል፡፡2ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ ያህዌ ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ3ቁጣቸው በእኛ ላይ በነደደ ጊዜ በሕይወት እያለን በዋጡን ነበር፡፡4ጐርፍ በወሰደን፣ ውሃም በሸፈነን ነበር፡፡5ብርቱ ማዕበልም ባሰጠመን ነበር6በጥርሳቸው እንዲቦጫጭቁን ያልፈቀደ ያህዌ ይባረክ7ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኝ ወጥመድ አመለጠች ወጥመዱ ተሰበረ እኛም አመለጥን፡፡8ሰማይና ምድርን የሠራ ያህዌ ረዳታችን ነው፡፡
1በያህዌ የሚተማመኑ ሳትናወጥ ለዘላለም እንደምትኖር የጽዮን ተራራ ናቸው፡፡2ተራሮች ኢየሩሳሌምን እንደ ከበቧት ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ያህዌም በሕዝቡ ዙሪያ ነው፡፡3ጻድቁ ክፉ እንዳያደርግ የዐመፃ በትረ መንግሥት የጻድቃንን ምድር አይግዛ፡፡4ያህዌ ሆይ፣ መልካም ለሆኑ፣ ልባቸውም ቀና ለሆኑት መልካም አድርግ፡፡5ወደ ጠማማ መንገዳቸው የሚመለሱትን ግን ያህዌ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ያጠፋቸዋል፡፡ ሰላም በእስራኤል ላይ ይሁን፡፡
1ያህዌ የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ ሕልም እንጂ፣ እውን አልመሰለንም፡፡2በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ አንደበታችንም በዝማሬ ተሞላ፡፡ በዚያ ጊዜ በሕዝቦች መካከል፣ «ያህዌ ታላቅ ነገር አደረገላቸው» ተባለ፡፡3ያህዌ ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም እጅግ ደስ አለን፡፡4ያህዌ ሆይ፣ በኔጌቭ እንዳሉ ምንጮች ምርኮአችን መልስ፡፡5በእንባ የሚዘሩ በእልልታ ይዘራሉ6ዘሩን ተሸክመው እያለቀሱ የተሰማሩ ነዶአቸውን ተሸክመው እልል እያሉ ይመለሳሉ፡፡
1ያህዌ ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ ያህዌ ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል፡፡2የዕለት ጉርስ ለማግኘት በመጣር ማለዳ መነሣት፣ አምሽቶም መግባት ከንቱ ነው፡፡ ያህዌ ለወዳጆቹ ተኝተው እያለ የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣቸዋል፡፡3እነሆ ልጆች የያህዌ ስጦታ ናቸው የማሕፀንም ፍሬ የእርሱ ችሮታ ነው፡፡4በወጣትነት የተገኙ ልጆች በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው5ኮረጆዎቹን በእነዚህ የሞላ ሰው የተባረከ ነው፡፡ ከጠላቶቹ ጋር በሚሟገትበት ጊዜ አፍሮ አይገባም፡፡
1ያህዌን የሚፈሩ ሁሉ በመንገዶቹም የሚሄዱ የተባረኩ ናቸው፡፡2በእጆችህ ሥራ ደስ ይልሃል ትባረካለህ፤ ይሳካልሃልም፡፡3በቤትህ ውስጥ ሚስትህ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ተክል ይሆናሉ፡4አዎን፣ ያህዌን የሚፈራ እንዲህ ይባረካል፡፡5ያህዌ ከጽዮን ይባርክህ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፡፡6የልጅ ልጆችን ለማየት ያብቃህ እስራኤል ላይ ሰላም ይሁን፡፡
1«ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ» ይበል እስራኤል፡፡2በእርግጥ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ ይሁን እንጂ አላሸነፉኝም፡፡3አራሾች ጀርባዬን አረሱት ትልማቸውንም አስረዘሙት፡፡4እግዚአብሔር ጻድቅ ነው የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለ፡፡5ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደ ኃላቸውም ይመለሱ፡፡6ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ ቤት ጣር ላይ እንዳለ ሣር ይሁኑ፡፡7ደግሞ ለዐጫጁ እጁን ለነዶ ሰብሳቢ እቅፉን እንደማይሞላ ነዶ ይሁኑ፡፡8መንገድ ዐላፊዎችም፣ «የያህዌ በረከት እናንተ ላይ ይሁን፤ በያህዌ ስም ባረክናችሁ አይበሉ፡፡»
1ያህዌ ሆይ፣ ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ፡፡2ጌታ ሆይ፣ ምሕረትን ፈልጌ ስጮኽ ድምፄን ስማ ጆሮህንም ወደ እኔ አዘንብል፡፡3ያህዌ ሆይ፣ አንተ ኃጢአትን ብትከታተል ኖሮ ማን መቆም ይችል ነበር፡፡4ነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ ስለዚህ ልትፈራ ይገባሃል፡፡5ያህዌን በትዕግሥት እጠብቃለሁ በቃሉም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡6ዘብ አዳሪ ንጋትን እንደሚጠብቅ እኔም ጌታን በትዕግሥት እጠብቃለሁ፡፡7ያህዌ መሓሪ ነው፤ ይቅር ለማለትም ፈቃደኛ ነው እስራኤል ሆይ፣ ያህዌን ተስፋ አድርግ፡፡8እርሱ እስራኤልን ከኃጢአቱ ሁሉ ያድነዋል፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ልቤ አልታበየም ዐይኔም ከፍ ከፍ አላለም፡፡ ለራሴም ታላላቅ ነገሮችን ተስፋ አላደረግሁም ከእኔ በላይ በሆነ ነገርም አልተጨነቅሁም፡፡2ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሰኘኃት ነፍሴ ጡት እንዳስተውት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች፡፡3እስራኤል ሆይ አሁንና ለዘላለም ያህዌ ተስፋ አድርግ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ዳዊትን፣ የተቀበለውንም መከራ ሁሉ አስብ፡፡2እርሱ ለያህዌ ማለ፣ ለያዕቆብም ኃያል አምላክ ቃል ገባ፤3እንዲህም አለ፣ «ወደ ቤቴ አልገባም፤ አልጋዬ ላይ አልወጣም4ለዐይኖቼ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶቼም ዕረፍትን አልሰጥም፤5ለያህዌ ስፍራን፣ ለያዕቆብ ኃያል ማደሪያን እስካገኝ ድረስ፡፡6እነሆ፣ በኤፍራታ ሰማነው፣ በይዓሪም አገኘነው፡፡7ወደ ማደሪያው እንግባ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንስገድ፡፡8ያህዌ ሆይ ተነሥ አንተና የኃይልህ ታቦታ ወደ ማደሪያህ ስፍራ ሂዱ፡፡9ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ ታማኞችህ እልል ይበሉ፡፡10ስለ ባርያህ ስለ ዳዊት ስትል የተቀባኸውን ንጉሥ አትተወው፡፡11ያህዌ ለዳዊት በእውነት ማለ በማይታጠፍ መሐላ እንዲህ አለ «ከልጆችህ አንዱን ዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ12ልጆችህ ኪዳኔን፣ የማስተምራቸውንም ሕጌን ቢጠብቁ፣ ልጆቻቸው ለዘላለም በዙፋንህ ላይ ይቀመጣሉ፡፡»13ያህዌ ጽዮንን መርጧልና ማደሪያው እንድትሆን ወዶአልና፡፡14«ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፈልጌአታለሁና በእርሷ እኖራለሁ፡፡15እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ፡፡16ካህናቶቿን ማዳንን አለብሳቸዋለሁ ታማኞቿም እልል ይላሉ፡፡17በዚያ ለዳዊት ቀንድ አበቅላለሁ ለቀባሁትም ሰው መብራት አዘጋጃለሁ፡፡18ጠላቶቹን እፍረት አከናንባቸዋለሁ እርሱ ላይ ግን አክሊሉ ያበራል፡፡
1ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ቢኖሩ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ አስደሳች ነው፡፡2በአሮን ራስና ጢም ላይ እንደሚፈስስ እስከ ልብሱን ዐንገት ጌጥ ድረስ እንደሚወርድ ውድ ሽቱ ነው፡፡3ደግሞም በጽዮን ተራራ ላይ እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፡፡ ያህዌ በዚያ በረከቱን አዞአልና ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዞአል፡፡
1እናንት በሌሊት ቆማችሁ በያህዌ ቤት የምታገለግሉ የያህዌ ባርያዎች ሁላችሁ፣ ያህዌን አመስግኑ፡፡2ወደ መቅደሱ እጃችሁን አንሡና ያህዌን ባርኩ፡፡3ሰማይና ምድርን የሠራ ያህዌ ከጽዮን ይባርካችሁ፡፡
1ያህዌን አመስግኑ የያህዌን ስም ወድሱ፤ እናንት የያህዌ አገልጋዮች አመስግኑት፡፡2በያህዌ ቤት በአምላካችንም ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት፡፡3መልካም ነውና ያህዌን አመስግኑ ደስ የሚያሰኝ ነውና ለስሙ ዘምሩ፡፡4ያህዌ ያዕቆብን ለራሱ፣ እስራኤልም ርስቱ እንዲሆን መርጦአልና፡፡5ያህዌ ታላቅ መሆኑን፣ ጌታችንም ከአማልክት በላይ መሆን ዐውቃለሁ፡፡6በሰማይም ሆነ በምድር በባሕርና በጥልቅ ውቅያኖስ ያህዌ የወደደውን ያደርጋል፡፡7እርሱ ደመናትን ከሩቅ ቦታ ያመጣል ከዝናብ ጋር መብረቅ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል፡፡8ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ የግብፃውያንን በኩር ገደለ፡፡9ግብፅ ሆይ፣ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ሁሉ ላይ፣ በመካከልሽም ምልክቶችንና ድንቆችን አደረገ፡፡10ብዙ ሕዝቦች መታ ኃያላን ነገሥታት ገደለ፡፡11የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎንን የባሰን ንጉሥ ዐግን የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፡፡12ምድራቸውንም ለሕዝቡ ለእስራኤል ርስት አድርጐ ሰጠ፡፡13ያህዌ ሆይ፣ ስምህ ዘላለማዊ ነው መታሰቢያህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል፡፡14ያህዌ ለሕዝቡ ይፈርዳልና ለአገልጋዮቹም ይራራልና፡፡15የአሕዛብ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ በሰው እጅ የተሠሩ ናቸው16አፍ አላቸው አይናገሩም ዐይን አላቸው አያዩም፡፡17ጆሮ አላቸው አይሰሙም፤ በአፋቸውም እስትንፋስ የለም፡፡18የሚሠሩዋቸውና የሚታመኑባቸው ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ፡፡19የእስራኤል ልጆች ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ የአሮን ልጆች ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ፡፡20የሌዊ ልጆች ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ ያህዌን የምትፈሩ ሆይ፣ ያህዌን ባርኩ፡፡21በኢየሩሳሌም የሚኖር ያህዌ ከጽዮን ይባረክ ያህዌን አመስግኑ፡፡
1ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡2የአማልክትን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡3የጌቶችን ጌታ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡4ብቻውን ታላላቅ ተአምራት ያደረገውን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡5በጥበብ ሰማያትን የሠራ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡6ምድርን ውሃ ላይ የዘረጋ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡7ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡8ፀሐይ በቀን እንዲገዛ ያደረገ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡9ጨረቃና ከዋክብት ሌሊት እንዲገዙ ያደረገ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡10የግብፅን በኩር የገደለ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡11እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡12በብርቱ እጅ፣ በተዘረጋችም ክንድ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡13ቀይ ባሕርን የከፈለውን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡14እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡15ፈርዖንና ሰራዊቱን ቀይ ባሕር ውስጥ ያሰጠመ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡16ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራውን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡17ታላላቅ ነገሥታትን የገደለውን ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡18ኃያላን ነገሥታትን የገደለ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡19የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎንን ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡20የባሳንን ንጉሥ ዐግን የገደለ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡21ምድራቸውን ርስት አድርጐ የሰጠ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡22ለባርያው ለእስራኤል ርስት አድርጐ የሰጠ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡23በውርደታች ያሰበን፣ የረዳንም ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡24በጠላቶቻችን ላይ ድል የሰጠን ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡25ለፍጡር ሁሉ ምግብ የሚሰጥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡26የሰማይን አምላክ አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
1በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን፡፡2እዚያ በገናዎቻችንን በአኻያ ዛፎች ላይ ሰቀልን፡፡3የማረኩን ሰዎች እንድንዘምርላቸው ጠየቁን ሲያፌዙብን የነበሩት የደስታ ዜማ ፈለጉብን፣ «እስቲ ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን» አሉን፡፡4የያህዌን መዝሙር እንዴት ብለን በባዕድ ምድር እንዘምራለን?5ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ብረሳሽ ቀኝ እኔ ይክዳኝ፡፡6አንቺን ሳላስታውስ፣ ደስ ከሚያሰኘኝ ነገር ሁሉ በላይ ሳላደርግሽ ብቀር ምላሴ ከትናጋዬ ትጣበቅ፡፡7ያህዌ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፡፡ እነርሱ፣ «አፍርሷት፣ ጨርሳችሁ አፍርሷት!» አሉ፡፡8የባቢሎን ልጅ ሆይ፣ እኛ ላይ ስላደረግሺው ድርጊት ብዙም ሳይቆይ፣ የእጅሽን የሚሰጥሽ የተባረከ ነው9ሕፃናቶችሽን ዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ እርሱ የተመሰገነ ነው፡፡
1በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ በአማልክትም ፊት በመዝሙር እወድስሃለሁ፡፡2ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡ ቃልህንና ስምህን ከሁሉ በላይ ከፍ አደረግህ፡፡3በጠራሁህ ቀን መለስህልኝ ነፍሴን በማጽናናት አደፋፈርሃት፡፡4ያህዌ ሆይ፣ የአፍህን ቃል ሲሰሙ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፡፡5የያህዌ ክብር ታላቅ ነውና ስለ ያህዌ ሥራ ይዘምራሉ፡፡6ያህዌ እጅግ ከፍ ያለ ቢሆንም፣ ዝቅ ያሉትንም ይመለከታል ትዕቢተኞችን ግን ገና ከሩቅ ያውቃቸዋል፡፡7በአደጋ መካከል ብሄድ እንኳ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃለህ፡፡ እጅህን ዘርግተህ ከጠላቶቼ ቁጣ ታወጣኛለህ በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ፡፡8ያህዌ እስከ መጨረሻ ከእኔ ጋር ነህ ያህዌ ሆይ፣ ምሕረትህ ለዘላለም ነው፡፡ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ መረመርኸኝ፤ ደግሞም ዐወቅኸኝ፡፡2አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ የልቤንም ሐሳብ ገና ከሩቅ ትረዳለህ፡፡3መሄድ መተኛቴን በሚገባ ታውቃለህ መንገዶቼንም ሁሉ ዐውቀሃቸዋል4ገና ቃል ከአንደበቴ ሳይወጣ ያህዌ ሆይ፣ ፈጽመህ ታውቃለህ፡፡5አንተ ከኋላም ከፊትም ዙሪያዬን ከለልኸኝ እጅህንም በላዬ አደረግህ፡፡6እንዲህ ያለው ዕውቀት እጅግ ጥልቅ ነው ከእኔም ማስተዋል በላይ ነው፡፡7ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ፡፡8ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ መኝታዬን በሲኦል ባደርግ በዚያ ትገኛለህ፡፡9በንጋት ክንፍ ተነሥቼ ብበር እስከ ባሕሩ መጨረሻ ብሄድ10በዚያም ቢሆን እጅህ ትመራኛለች ቀኝ እጅህም ትይዘኛለች፡፡11ደግሞም፣ «ጨለማው በእርግጥ ይሸፍነኛል በዙሪያዬ ያለውም ብርሃን ሌሊት ይሆናል» ብል12ጨለማ እንኳ ለአንተ አይጨልምም ሌሊቱም እንደ ቀን ያበራል በአንተ ጨለማም ሆነ ብርሃን አንድ ናቸው፡፡13አንተ የውስጥ ሰውነቴን ፈጥረሃል በእናቴ ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ፡፡14ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ሥራህ እጅግ ድንቅ ነው ነፍሴም ይህን በሚገባ ታውቃለች፡፡15እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተደበቁም፡፡ በምድር ጥልቅ ውስጥ በጥበብ በተሠራሁ ጊዜ16በእናቴ ማሕፀን እያለሁ አየኸኝ፡፡ ገና አንዳቸውም ወደ መኖር ሳይመጡ ለእኔ የተወሰኑልኝ ዘመኖች በመጽሐፍህ ተጻፉ፡፡17አምላኬ ሆይ፣ ለእኔ ያለህ ሐሳብ እንዴት ግሩም ነው! ቁጥሩስ ምንኛ የበዛ ነው!18ልቁጠራቸው ብል ከአሸዋ ቁጥር ይበልጣሉ ተኛሁ ነቃሁም፤ ያም ሆኖ ግን አሁንም ከአንተው ጋር ነኝ፡፡19አምላክ ሆይ፣ ክፉዎችን ብትገድላቸው ምናለበት! ደም የጠማችሁ ዐመፀኞች ከእኔ ራቁ፡፡20እነርሱ በአንተም ላይ ክፉ ይናገራሉ በጠላትነትም ስምህን በክፉ ያጠፋሉ፡፡21ያህዌ ሆይ፣ የሚጠሉህን አልጠላሁምን? በአንተ ላይ የሚነሡትንስ አልተጸየፍሁምን?22በፍጹም ጥላቻ ጠልቻቸዋለሁ እነርሱም ባላጋራዎቼ ሆነዋል፡፡23እግዚአብሔር ሆይ፣ መርምረኝ ልቤንም ዕወቅ ፈትነኝ ሐሳቤንም ዕወቅ፡፡24በእኔ ውስጥ የዐመፅ መንገድ ቢኖር እይ በዘላለምም መንገድ ምራኝ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ከክፉ ሰዎች አድነኝ ከዐመፀኞችም ጠብቀኝ፡፡2እነርሱ በልባቸው ክፉ ነገር ያውጠነጥናሉ በየዕለቱም ጦርነት ይጭራሉ፡፡3ምላሳቸው እንደ እባብ ይነድፋል የእፉኝትም መርዝ በከንፈራቸው አለ፡፡ ሴላ4ያህዌ ሆይ፣ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ መትተው ሊጥሉኝ ከሚፈልጉ ዐመፀኛ ሰዎች አድነኝ፡፡5ትዕቢተኞች በስውር ወጥመድ ዘርግተውብኛል የመረባቸውን ገመድ ዘረጉብኝ በመንገዴም አሽክላ አኖሩ፡፡ ሴላ6እኔም ያህዌን፣ «አንተ አምላኬ ነህ እንድትምረኝ የማቀርበውን ጩኸት ስማ» እለዋለሁ፡፡7ያህዌ ሆይ፣ እኔን ለማዳን ብርቱ ነህ በጦርነት ቀን ራሴን ከለልህ፡፡8ያህዌ ሆይ፣ የክፉዎች ምኞት አይሳካ ሤራቸውም አይከናወን፡፡9ዙሪያዬን የከበቡኝ ራሳቸውን ቀና ቀና አደረጉ የገዛ ከንፈራቸው ሸፍጥ ይዋጣቸው፡፡10የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ እሳት ውስጥ ጣላቸው ዳግመኛም እንዳይነሡ ማጥ ወዳለበት ጉድጓድ ይውደቁ፡፡11ምላሰኛ በምድሪቱ ጸንቶ አይኑር ዐመፀኛውን ክፋት አሳድዶ ያጥፋውቨ12ያህዌ ለተበደሉ እንደሚፈርድ ለችግረኛውም ፍትሕ እንደሚሰጥ ዐውቃለሁ፡፡13ጻድቃን በእውነት ስምህን ያመሰግናሉ ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ ፈጥነህ ድረስልኝ ወደ አንተ ስጣራ ድምፄን ስማ2ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ይሁንልኝ ወደ አንተ ያነሣሁት እጄም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ይቆጠርልኝ፡፡3ያህዌ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አኑር የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ4ክፉ ለማድረግ ከመመኘትና ከክፉ አድራጊዎች ጋር ከመተባበር፣ የድግሳቸውም ተካፋይ ከመሆን ጠብቀኝ፡፡5ጻድቅ ሰው ቢቀጣኝ ለእኔ በጐነት ነው፤ እርሱ ቢገሥጸኝ ራሴን እንደሚቀባ ዘይት ነው እኔ ራሴም ይህን እንቢ አልልም፡፡ ጸሎቴ ግን ሁሌም በክፉዎች ተግባር ላይ ነው፡፡6መሪዎቻቸው ከገደል ጫፍ ቁልቁል ይወርወሩ ቃሌ እውነት መሆኗንም ይሰማሉ፡፡7ደግሞም፣ «ሰው ምድርን እንደሚያርስና ዐፈሩን እንደሚፈረካክስ፣ እንዲሁ ዐጥንታችን በሲኦል አፋፍ ላይ ተበታተነ» ይላሉ፡፡8ጌታ፣ ያህዌ ሆይ፣ ዐይኖቼ ወደ አንተ ይመለከታሉ መጠጊያዬ አንተ ነህ፤ ከእንግዲህ ነፍሴን አትተዋት፡፡9ከዘረጉብኝ ወጥመድ ከክፉ አድራጊዎችም አሽክላ ጠብቀኝ፡፡10እኔ በደኅና ሳመልጥ ክፉዎች በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ፡፡
1ድምፄን ከፍ አድርጌ እንዲረዳኝ ወደ ያህዌ እጮኻለሁ ድምፄን ከፍ አድርጌ እንዲምረኝ ልመናየን ወደ ያህዌ አቀርባለሁ፡፡2ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ ችግሬንም እነግረዋለሁ፡፡3መንፈሴ በውስጤ ሲዝል አንተ መንገዴን ታውቃለህ፤ መተላለፊያ መንገዴ ላይ በስውር ወጥመድ ዘረጉብኝ፡፡4ወደ ቀኜ ብመለከት የሚያስብልኝ ሰው አጣሁ ማምለጫም የለኝም ለሕይወቴም ደንታ ያለው የለም፡፡5ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ እጮኻለሁ «አንተ መጠጊያዬ ነህ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ» እላለሁ፡፡6እጅግ ተስፋ ቆርጫለሁና ጩኸቴን ስማ ከእኔ ይበልጥ ብርቱ ስለሆኑ ከአሳዶጆቼ አድነኝ፡፡7ስምህን እንዳመሰግን ነፍሴን ከእስር ቤት አውጣት፡፡ ለእኔ ያደረግኸውን መልካም ነገር ሲመለከቱ ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ፡፡
1ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ ልመናዬንም አድምጥ፡፡ በታማኝነትህና በጽድቅህ ሰምተህ መልስልኝ፡፡2በአንተ ፊት ማንም ጻድቅ አይደለምና ከባርያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ፡፡3ጠላት ነፍሴን አሳደዳት ገፍትሮም ወደ መሬት ጣለኝ፡፡ ቀደም ብለው እንደ ሞቱ ሰዎች በጨለማ ውስጥ አኑሮኛል፡፡4ስለዚህ መንፈሴ በውስጤ ልቤም ተስፋ ቆረጠ፡፡5የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ አንተ ያደረግኸውንም አውጠነጠንሁ፡፡6በጸሎት እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ እንደ ደረቀች ምድር ነፍሴ አንተን ተጠማች፡፡ ሴላ7ያህዌ ሆይ፣ መንፈሴ ዝሎአልና ፈጥነህ ስማኝ፡፡ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ እንዳልሆን ፊትህንም ከእኔ አትሰውር፡፡8በአንተ ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፡፡ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አሳየኝ፡፡9ያህዌ ሆይ፣ አንተን መሸሸጊያ አድርጌአለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ፡፡10አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ማድረግ አስተምረኝ፡፡ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ፡፡11ያህዌ ሆይ፣ ስለ ስምህ በሕይወት ጠብቀኝ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት፡፡12ከታማኝነትሀ የተነሣ ጠላቶቼን አጥፋቸው እኔ ባርያህ ነንና የሕይወቴን ጠላቶች ደምስሳቸው፡፡
1እጆቼን ለጦርነት ጣቶቼንም ለውጊያ የሚያሠለጥን ዐለቴ ያህዌ ይባረክ፡፡2አንተ መታመኛዬና መጠጊያዬ ነህ ጽኑ ዐምባዬና ታዳጊዬ የምከለልበት ጋሻዬም ነህ ሕዝቦችን ከእግሬ በታች የምታስገዛልኝም አንተ ነህ፡፡3ያህዌ ሆይ፣ ይህን ያህል የምትንከባከበው ሰው ምን ስለሆነ ነው? ይህን ያህል የምታስብለት የሰው ልጅስ ምንድነው?4ሰው እንደ እስትንፋስ ነው ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል፡፡5ያህዌ ሆይ፣ ሰማያትን ሰንጥቀህ ውረድ ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስሳቸው፡፡6የመብረቅ ብልጭታ ልከህ ጠላቶቼን በትናቸው ፍላጻህን ሰድደህ ግራ አጋባቸው፡፡7ከላይ እጅህን ሰደህ ከብዙ ውሆች፣ ከባዕድ ሰዎችም እጅ ታደገኝ፡፡8አንደበታቸው ሐሰት ይናገራል ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት፡፡9አምላክ ሆይ፣ አዲስ መዝሙር እዘምርልሃለሁ ዐሥር አውታር ባለው በገና ምስጋና አቀርብልሃለሁ፡፡10አንተ ነገሥታትን ድልን ታጐናጽፋቸዋለህ አገልጋይህ ዳዊትንም ከስለታም ሰይፍ ትታደገዋለህ፡፡11አንደበታቸው ሐሰት ከሚናገር ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው ከባዕዳን እጅ ታደገኝ፡፡12ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ፡፡13ጐተራዎቻችን በተለያዩ የእህል ዐይነቶች የተሞሉ ይሁኑ፡፡ በመስኮቻችን የተሰማሩ በጐች እስከ ሺህ ይወለዱ፣ እስከ ዐሥር ሺህ ይባዙ፡፡14ከብቶቻችን ወላድ ይሁኑ፡፡ አይጨንግፉ አይጥፉ ቅሮቻችን በማንም አይደፈሩ እኛም በምርኮ አንወሰድ፡፡ በአደባባዮቻችን ጩኸት አይሰማ፡፡15እንዲህ የሚሆንለት ሕዝብ የተባረከ ነው ያህዌ አምላኩ የሆነለት ሕዝብ የተባረከ ነው፡፡
1አምላኬና ንጉሤ ሆይ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ፡፡2በየቀኑ እባርክሃለሁ ስምህንም ከዘላለም እስከ ዘላለም እባርካለሁ፡፡3ያህዌ ምስጋናው ታላቅ ነው ታላቅነቱም አይመረመርም፡፡4አንዱ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ ሥራህን ያስተላልፋል ድቅ ሥራህንም ያውጃል፡፡5የክብርህን ግርማ፣ የሥራህንም አስደናቂነት አሰላስላለሁ፡፡6ስለ ድንቅ ሥራህ ኃይል ይናገራሉ እኔም ታላቅነትህን ዐውጃለሁ፡፡7የበጐነትህን ብዛት ያወሳሉ ስለ ጽድቅህም ይዘምራሉ፡፡8ያህዌ ቸር ነው፤ ርኅሩኅም ነው ለቁጣ የዘገየ ምሕረቱም የበዛ ነው፡፡9ያህዌ ለሁሉም ቸር ነው ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው፡፡10ያህዌ ሆይ፣ ፍጥረቶችህ ሁሉ ያመሰግኑሃል ቅዱሳንህም ይባርኩሃል፡፡11ቅዱሳንህ የመንግሥትህን ክብር ይናገራሉ ስለ ኃይልህምይነጋገራሉ፡፡12የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ለሰው ልጆች ያሳውቃሉ የመንግሥቱንም ክብር ይናገራሉ፡፡13መንግሥትህ የዘላለም መግሥት ነው ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል፡፡14ያህዌ የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል፡፡15የሁሉም ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል በተገቢ ጊዜ ምግባቸውን ትሰጣቸዋለህ፡፡16እጅህን ትዘረጋለህ የሕያዋንን ሁሉ ፍላጐት ታረካለህ፡፡17ያህዌ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው፡፡18ያህዌ ለሚጠሩት ሁሉ በእምነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡19የሚፈሩትን ፍላጐት ይፈጽማል ጩኸታቸውንም ሰምቶ ያድናቸዋል፡፡20ያህዌ የሚወዱትን ይጠብቃል ዐመፀኞችን ሁሉ ግን ያጠፋል፡፡21አፌ የያህዌን ምስጋና ይናገራል የሰው ልጅ ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ቅዱስ ስሙን ይባርክ፡፡
1ያህዌን አመስግኑ ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን ባርኪ፡፡2በሕይወት በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለያህዌ እዘምራለሁ፡፡3በገዦች አትተማመኑ ማዳን በማይችል የሰው ልጅም አትመኩ፡፡4የሰው እስትንፋስ ሲያቆም ወደ መሬት ይመለሳል፡፡ ያን ጊዜ ዕቅዱ እንዳልነበረ ይሆናል፡፡5ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ ተስፋውም ያህዌ የሆነለት ሰው የተባረከ ነው፡፡6ሰማይና ምድርን፣ ባሕርንና በውስጡ ያሉትንም የፈጠረ ያህዌ7ለተጨቆኑት የሚፈርድ፣ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፡፡ ያህዌ እስረኞችን ነጻ ያወጣል፡፡8ያህዌ የዕውራን ዐይን ይከፍታል፡፡ ያህዌ የተዋረዱን ከፍ ያደርጋል፡፡ ያህዌ ጻድቃንን ይወዳል፡፡9ያህዌ መጻተኞን በምድር ይጠብቃል ደኸ አደጐችንና መበለቶችን ይደግፋል፡፡ የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል፡፡10ያህዌ ለዘላለም ይነግሣል ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽ ለትውልድ ሁሉ ንጉሥ ነው፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
1ያህዌ ይመስገን አምላካችንን በመዝሙር ማመስገን እንዴት መልካም ነው እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ተገቢም ነው፡፡2ያህዌ ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል የተበተነውን የእስራኤል ሕዝብ ይሰበስባል፡፡3ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል ቁስላቸውንም ይጠግናል፡፡4ከዋክብቱን ይቆጥራል ለእያንዳንዳቸውም ስም ይሰጣቸዋል፡፡5ጌታችን ታላቅ፣ ኃይሉን የሚያስፈራ ነው ማስተዋሉም አይመረመርም፡፡6ያህዌ የተጨቆኑትን ያነሣል ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል፡፡7ለያህዌ በምስጋና ዘምሩ ለአምላካችን በበገና ዘምሩ፡፡8ሰማያትን በደመና ይሸፍናል በተራሮች ሣር እንዲበቅል ለምድር ዝናብ ያዘጋጃል፡፡9ለእንስሳት ምግባቸውን፣ የቁራ ጫጩቶች ሲንጫጩ ምግባቸውን ይሰጣቸዋል፡፡10በፈረስ ኃይል አይደሰትም ደስታውን በሰው ጉልበት ጥንካሬ አያደርግም፡፡11ያህዌ በሚፈሩት፣ በምሕረቱም በሚታመኑ ይደሰታል፡፡12ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ያህዌን አመስግኚ ጽዮንም አምላክሽን አወድሺ13እርሱ የበሮችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና በመካከልሽ ያሉ ልጆችሽንም ባርኮአል፡፡14በድንበርሽ ውስጥ ብልጽግና አድርጐአል ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል፡፡15ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል ቃሉም በፍጥነት ይሮጣል፡፡16በረዶውን እንደ ባዘቶ ያነጥፈዋል ጭጋጉንም እንደ ደመና ይበትነዋል፡፡17የበረዶውን ድንጋይ ቁልቁል ይለቃል በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን መቆም ይችላል?18ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል ነፋሱን ያነፍሳል ውሃንም ያፈስሳል፡፡19ቃሉን ለያዕቆብ፣ ሥርዐት ጽድቁንም ለእስራኤል ያውጃል፡፡20ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ ይህን አላደረገም እነርሱም ፍርዱን አላወቁም፡፡ ያህዌ ይመስገን፡፡
1ያህዌን አመስግኑ በሰማያት ያላችሁ ያህዌን አመስግኑ በከፍታዎች ያላችሁ ያህዌን አመስግኑ፡፡2መላእክቱ ሁሉ አመስግኑ የመላእክቱ ሰራዊት ሁሉ አመስግት፡፡3ፀሐይና ጨረቃ አመስግት የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት፡፡4ሰማየ ሰማያት አመስግኑት ከሰማይ በላይ ያላችሁ ውሆች አመስግኑት፡፡5እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና የያህዌን ስም ያመስግኑ፡፡6ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው የማይሻር ሕግም ደነገገላቸው፡፡7የባሕር ውስጥ ፍጥረትና ጥልቁ ውሃ ሁሉ ያህዌን ከምድር አመስግኑት፡፡8እሳትና በረዶ ዐመዳይና ጭጋግ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ9ተራሮችና ኮረብቶች፣ የፍሬ ዛፎችና ዝግቦች ሁሉ አመስግኑ፡፡10የዱር አራዊት፣ የቤት እንስሳት በምድር የሚርመሰመሱ ፍጥረቶችና ወፎችም ሁሉ11የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ መሳፍንቶችና የምድር ገዦች ሁሉ ያህዌን አመስግኑ፡፡12ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች አረጋውያንና ሕፃናት ያመስግኑት፡፡13የእርሱ ስም ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና ክብሩም ከምድርና ከሰማያት በላይ ነውና የያህዌን ስም ያመስግኑ፡፡14እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቶአል ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ ለእስራኤል ልጆች፡፡ ያህዌን አመስግኑ፡፡
1ያህዌን አመስግኑ ለያህዌ አዲስ መዝሙር ዘምሩ2በቅዱሳን ጉባኤ ምስጋናውን አቅርቡ፡፡ እስራኤል በፈጣሪው ደስ ይበለው የጽዮንም ልጆች በንጉሣቸው ሐሤት ያድርጉ፡፡3ስሙን በሽብሸባ ያመስግኑ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት፡፡4ያህዌ በሕዝቡ ደስ ይለዋል በማዳኑ ትሑታንን ያከብራቸዋል፡፡5ቅዱሳን በድል ደስ ይበላቸው በመኝታቸውም ላይ እልል ይበሉ፡፡6የእግዚአብሔር ምስጋና በአንደበታቸው በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፡፡7ይህም በአሕዛብ ላይ በቀልን፣ በሕዝቦችም ላይ ፍርድን ያደርጉ ዘንድ8ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት መሳፍንቶቻቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፡፡9ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው፡፡ ይህ ለቅዱሳኑ ሁሉ ክብር ይሆናል፡፡ ያህዌን አመስግኑ፡፡
1ያህዌን አመስግኑ እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት2ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት ከአእምሮ በላይ ስለሆነው ታላቅነቱ አመስግኑት፡፡3በመለከት ድምፅ አመስግኑት በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት፡፡4በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑ በባለ አውታርና የእስትንፋስ መሣሪያ አመስግኑት፡፡5ከፍ ያለ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል ወድሱት፡፡6እስትንፋስ ለው ሁሉ ያህዌን ያመስግን፡፡ ያህዌን አመስግኑ፡፡
1የእስራኤል ንጉስ፣ የዳዊት ልጅ የሰለሞን ምሳሌዎች፡፡2እነዚህ ምሳሌዎች የተጻፉት ጥበብንና ተግሳጽን፣ አርቆ ለማስተዋል የሚያስችሉ ቃላትን፣3እርማትን በመቀበል ጽድቅ፣ ፍትሕና ሚዛናዊ የሆነ ብያኔን በማድረግ እንድትኖር ለማስተማር ነው፡፡4ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ ምሳሌዎች የተጻፉት ላልተማሩ ጥበብን፣ ለወጣቶች ደግሞ እውቀትንና ልባምነትን ለመስጠት ነው፡፡5ጥበበኞች ያድምጡና ትምህርታቸውን ያዳብሩ፣ አስተዋዮች ደግሞ ምሪትን ያግኙበት፣6ይህ ደግሞ የጠቢባንን ምሳሌዎች፣ አባባሎችና ቃላቶች እንደዚሁም እንቆቅልሾቻቸውን እንዲረዱ ነው፡፡7እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመርያ ነው፣ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ፡፡8ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ምክር ስማ፣ የእናትህንም ሕግ አትተው፤9ለራስህ የሞገስ አክሊል፣ ለአንገትህ ደግሞ ውበት የሚሰጥ ጌጥ ይሆኑልሃል፡፡10ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች በኃጢአታቸው እንድትሳተፍ ሊያባብሉህ ቢሞክሩ፣ እሺ አትበላቸው፡፡11“ከእኛ ጋር ና፣ ነፍስ ለመግደል ተደብቀን እንጠብቅ፣ ንጹሐን ሰዎችን ያለ ምንም ምክንያት ለማትፋት እንሸምቅበት፡፡12ሲኦል ጤናማ ሰዎችን እንደሚውጣቸው፣ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ፣ እንዲሁ በሕይወት እያሉ እንዋጣቸው፡፡13ሁሉም አይነት ውድ የሆኑ ነገሮች እናገኛለን፤ ከሌሎች ሰዎች በሰረቅናቸው ነገሮች ቤቶቻችንን እንሞላለን፡፡14ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል፤ ሁላችንም አንድ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል፡፡” ቢሉህ፣15ልጄ ሆይ፣ ከእነርሱ ጋር በዚያ መንገድ አትሂድ፤ እነርሱ በሚሄዱበት መንገድ እግርህ አይርገጥ፤16እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፣ ደም ለማፍሰስም ይቸኩላሉ፡፡17ወፍ ፊት ለፊት እያየች ወፍን ለመያዝ ወጥመድ መዘርጋት ጥቅም የለውም፡፡18እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ለመግደል ተደብቀው ይጠብቃሉ፣ በራሳቸው ላይ ወጥመድን ይዘረጋሉ፡፡19ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ሀብትን ያከማቹ ሰዎች መንገዳቸው እንደዚህ ነው፣ ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ የተከማቸ ሃብት የባለቤቱን ሕይወት ያጠፋል፡፡20ጥበብ በጎዳና ላይ ጮኻ ትጣራለች፣ በአደባባይም ድምጿን ከፍ ታደርጋለች፤21ጩኸት በበዛባቸው ጎዳናዎች ላይ ትጣራለች፣ በከተማ መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ በማለት ትናገራለች፣22እናንተ ጥበብ የሌላችሁ አላዋቂነትን የምትወዱት እስከ መቼ ነው? እናንተ ፌዘኞች በፌዝ የምትደሰቱት እስከ መቼ ነው? እናንተ ሞኞች እውቀትን የምትጠሉት እስከ መቼ ነው?23ለዘለፋየ ትኩረት ስጡ፤ ሃሳቤን ሁሉ ለእናንተ አፈስሳለሁ፤ ቃሎቼን አሳውቃችኋለሁ፡፡24ጠራኋችሁ፣ እናንተ ግን ለመስማት እምቢ አላችሁ፤ እጄን ለእናንተ ዘረጋሁ፣ ነገር ግን አንድም ሰው ትኩረት አልሰጠውም፡፡25ነገር ግን እናንተ ተግሳጼን በሙሉ ችላ አላችሁ፣ ለዘለፋየ ደግሞ ትኩረት አልሰጣችሁም፡፡26እኔ ደግሞ በመከራችሁ እስቃለሁ፣ ሽብር በመጣባችሁ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ፣27አስፈሪ ድንጋጤ እንደ ማዕበል በእናንተ ላይ ሲመጣባችሁ፣ ጥፋት እንደ አውሎ ነፋስ እናንተን ሲጠራርጋችሁ፣ ጭንቅና ችግር በእናንተ ላይ በመጣ ጊዜ፡፡28በዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፣ እኔም አልመልስላቸውም፤ አጥብቀው ይፈልጉኛል፣ ነገር ግን አያገኙኝም፡፡29እውቀትን ስለ ጠሉ፣ እግዚአብሔርን መፍራት ስላልመረጡ፣30ምክሬን አልተከተሉምና፣ ዘለፋየንም ሁሉ ናቁ፡፡31የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፣ በእቅዳቸው ፍሬ ይጠግባሉ፡፡32እነዚህ ያልተማሩ ሰዎች ከእውቀት መራቃቸው ይገድላቸዋል፣ ሞኞችንም ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል፡፡33ነገር ግን የሚያደምጠኝ ሁሉ በሰላም ይኖራል፣ ከመከራም ስጋት ያርፋል፡፡
1ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ብትቀበልና ትእዛዛቴን በአንተ ዘንድ ብታኖር፣2ጥበብን ብታደምጥና ልብህን ወደ እውቀት ብትመልስ፡፡3እውቀትን ለማግኘት ብትጣራና ድምጽህን ከፍ አድርገህ ለማስተዋል ብትጮህ፣4ብርን አጥብቀህ እንደምትፈልግ እርስዋንም ብትፈልጋት፣ የተሰወረ ሃብትን እንደምትፈልግ እንደዚሁ ማስተዋልን ብትሻት፣5በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፣ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ፡፡6እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፣ እውቀትና ማስተዋል ከአንደበቱ ይወጣሉ፡፡7እርሱ ደስ ለሚያሰኙት ጥልቅ ጥበብን ያከማቻል፣ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱ ጋሻ ነው፣8የፍትህን መንገድ ይጠብቃል፣ ለእርሱ ታማኞች ለሆኑት ደግሞ መንገዳቸውን ያጸናል፡፡9በዚያን ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትህንና ሚዛናዊነትን እንደዚሁም ማንኛውንም መልካም መንገድ ትገነዘባለህ፡፡10ጥበብ ወደ ልብህ ትመጣለችና፣ እውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፡፡11የመለየት ችሎታ ይጠብቅሃል፣ ማስተዋል ይጋርድሃል፡፡12እነዚህ ከክፋት መንገድ፣ ጠማማ ንግግር ከሚናገሩ ሰዎች፣13ትክክለኛውን መንገድ ከተዉና በጨለማ መንገድ ከሚሄዱ ይጠብቁሃል፡፡14እነዚህ ክፋትን ሲያደርጉ ደስ ይላቸዋል፣ በጠማማነት ሃሴት ያደርጋሉ፡፡15ጠማማ መንገድን ይከተላሉ፣ አካሄዳቸውን ደግሞ በአታላይነታቸው ይደብቃሉ፡፡16ጥበብና ልባምነት ከአመንዝራ፣ ከጀብደኛና በንግግሯ ከምታታልል ሴት ያድኑሃል፡፡17ይህች ሴት የወጣትነት በልዋን የተወችና የአምላክዋን ቃል ኪዳን የረሳች ናት፡፡18ቤቷ ወደ ሞት ያዘነበለ ስለሆነ አካሄዷ በመቃብር ወዳሉት ሙታን ይመራሃል፡፡19ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ እንደገና አይመለሱም፣ የሕይወትንም መንገድ አያገኙም፡፡20ስለዚህ አንተም በመልካም ሰዎች መንገድ ትሄዳለህ፣ የጻድቃንን መንገድ ትከተላለህ፡፡21ጻድቃን ቤታቸውን በምድሪቱ ይሰራሉና፣ እነዚህ ነቀፋ የሌለባቸው ደግሞ በእርሷ ጸንተው ይኖራሉና፡፡22ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይቆረጣሉ፣ ታማኝነት የሌላቸውም ከእርሷ ይወገዳሉ፡፡
1ልጄ ሆይ፣ ትእዛዛቴን አትርሳ፣ ትምህርቴንም በልብህ ጠብቅ፣2በሕይወትህ ብዙ ቀኖችንና ዓመቶችን እንደዚሁም ሰላምን ይጨምሩልሃል፡፡3በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት አይለዩህ፣ በአንገትህ ዙርያ በአንድ ላይ እሰራቸው፣ በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው፡፡4በዚያን ጊዜ ሞገስና መልካም ስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ታገኛለህ፡፡5በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል ላይ አትደገፍ፤6በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም መንገድህን ቀና ያደርገዋል፡፡7በራስህ አስተያየት ጥበበኛ አትሁን፤ እግዚብሔርን ፍራ፣ ከክፉም ራቅ፡፡8ይህም ለስጋህ ፈውስ፣ ለሰውነትህም መታደስ ይሆንልሃል፡፡9እግዚአብሔርን በሀብትህና በምርትህ ሁሉ በኩራት አክብረው፣10ጎተራህ ሙሉ ይሆናል፣ ገንዳህ ደግሞ በአዲስ ወይን ጠጅ ተትረፍርፎ ይሞላል፡፡11ልጄ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቅጣት አትናቅ፣ ተግሳጹንም አትጥላ፣12አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ እንደዚሁ እግዚአብሔርም የሚወዳቸውን ይቀጣልና፡፡13ጥበብን የሚያገኛት ሰው ደስተኛ ነው፣ እውቀትንም ያገኛል፡፡14ከጥበብ የምታገኘው ጥቅም ብር ከሚሰጥህ ትርፍ ይልቅ እጅግ ይበልጣል፣ የጥበብ ትርፍ ከወርቅም ይበልጣል፡፡15ጥበብ ከከበረ ዕንቁ ይልቅ እጅግ ውድ ናት፣ አንተ ከምትመኘው ነገር ሁሉ እርሷን የሚተካከላት ምንም ነገር የለም፡፡16በቀኝ እጇ ረጅም ዕድሜ አለ፤ በግራ እጇ ደግሞ ባለጠግነትንና ክብርን ይዛለች፡፡17መንገዷ የደግነት መንገድ ነው፣ ጎዳናዋም ሰላም ነው፡፡18እርሷ አጥብቀው ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት፣ የሚደገፉባትም ደስተኞች ናቸው፡፡19እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሰረተ፣ ሰማያትን ደግሞ በማስተዋል አጸና፡፡20በእወቀቱ ጥልቆች ተሰንጥቀው ተከፈቱ፣ ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ፡፡21ልጄ ሆይ፣ ትክክለኛ ፍርድንና ነገሮችን በሚገባ መለየትን ጠብቅ፣ እነዚህ ከእይታህ አይራቁ፡፡22እነዚህ ለነፍስህ ሕይወት፣ በአንገትህ ዙርያ የምታስራቸው የሞገስ ጌጥ ይሆናሉ፡፡23በዚያን ጊዜ በመንገድህ ተማምነህ በሰላም ትራመዳለህ፣ እግርህም አይሰናከልም፤24በምትተኛበት ጊዜ አትፈራም፤ ስትተኛ እንቅልፍህ ጣፋጭ ይሆናል፡፡25በድንገተኛ ሽብርና በክፉዎች አማካይነት በሚደርስ ጥፋት አትፍራ፣26እግዚአብሔር በአጠገብህ ይሆናልና፣ እግርህም በወጥመድ እንዳያያዝ ይጠብቅሃልና፡፡27ልታደርግ የሚቻልህ ሲሆን፣ ለሚገባቸው ሰዎች መልካምን ነገር ከማድረግ አትከልክል፡፡28አሁን በእጅህ ገንዘብ እያለ ለጎረቤትህ “አሁን ሂድ፣ እንደገና ተመልሰህ ና፣ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው፡፡29በአጠገብህ የሚኖረውንና በአንተ የሚተማመነውን ጎረቤትህን ለመጉዳት አትምከርበት፡፡30አንድ ሰው አንተን ለመጉዳት ክፉ ካልሰራብህ ያለ በቂ ምክንያት ከዚህ ሰው ጋር አትከራከር፡፡31በክፉ ሰው አትቅና፣ የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ፡፡32ጠማማ ሰው በእግዚብሔር ፊት የተጠላ ነውና፣ ቅን ሰውን ግን ወዳጁ ያደርገዋል፡፡33የእግዚአብሔር እርግማን በክፉ ሰዎች ቤት ላይ ነው፣ የጻድቃንን ቤት ግን ይባርካል፡፡34እርሱ በፌዘኞች ላይ ያፌዛል፣ ለትሁታን ግን ሞገሱን ይሰጣቸዋል፡፡35ጥበበኞች ክብርን ይወርሳሉ፣ የሞኞች ከፍታ ግን ውርደታቸው ነው፡፡
1ልጆች ሆይ፣ የአባትን ተግሳጽ አድምጡ፣ ማስተዋል ምን እንደሆነ እንድታውቁ ልብ በሉ፡፡2እኔ መልካም ትምህርት እሰጣችኋለሁ፣ ትምህርቴን አትተዉ፡፡3የአባቴ ልጅ ሳለሁ፣ ለእናቴም ተወዳጅና ብቸኛ ልጅ ሳለሁ፣4አባቴ አስተማረኝ፣ እንዲህም አለኝ፡- “ቃሎቼን ሁሉ በልብህ ያዝ፤ ሕግጋቴን ጠብቅ በሕይወትም ኑር፡፡”5ጥበብንና ማስተዋልን አግኝ፤ የአፌን ቃላቶች አትርሳ፣ እነርሱንም አትተው፤6ጥበብን አትተዋት፣ እርሷ ከለላ ትሆንሃለች፤ ውደዳት፣ ትጠብቅሃለች፡፡7ጥበብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ናት፣ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፣ ያለህን ሀብት ሁሉ ከፍለህ ማስተዋልን የራስህ አድርጋት፡፡8ለጥበብ ከፍተኛ ስፍራ ስጣት፣ እርሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ እርሷን አጥብቀህ ስትይዛት ታከብርሃለች፡፡9በራስህ ላይ የክብር አክሊል ታስቀምጥልሃለች፤ ውብ የሆነ ዘውድም ትሰጥሃለች፡፡10ልጄ ሆይ፣ አድምጠኝ፣ ለቃሎቼም ትኩረት ስጥ፣ በሕይወት ዘመንህም ብዙ አመታት ይጨመሩልሃል፡፡11በጥበብ ጎዳና አስተምርሃለሁ፤ በቀጥተኛ መንገዶችም እመራሃለሁ፡፡12በምትራመድበት ጊዜ ማንም በመንገድህ ላይ አይቆምም፣ በሮጥህ ጊዜ አትሰናከልም፡፡13ምክርን ያዝ፣ አትልቀቀው፤ ጠብቀው፣ እርሱ ሕይወትህ ነውና፡፡14የክፉዎችን መንገድ አትከተል፣ ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፡፡15ከእርሷ ራቅ፣ በዚያ አትሂድ፤ ከዚያ ተመለስ፣ በሌላ መንገድ ሂድ፡፡16ክፋትን እስኪፈጽሙ ድረስ መተኛት አይችሉምና፣ አንድ ሰው እስኪያሰናክሉ ድረስ እንቅልፋቸው አይመጣምና፡፡17የክፋትን እንጀራ ይበላሉና፣ የአመጽንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና፡፡18ጽድቅን የሚያደርግ ሰው መንገድ ግን እየፈካ እንደሚሔድ የንጋት ብርሃን ነው፤ ሙሉ ቀን እስከሚሆን ድረስ ብርሃኑ የበለጠ እየጨመረ ይሄዳል፡፡19የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ጨለማ ነው፣ምን እንደሚያሰናክላቸው በፍጹም አያውቁም፡፡20ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ልብ በል፣ ንግግሮቼን አድምጥ፡፡21ከአይኖችህ አይራቁ፣ በልብህ ውስጥ ጠብቃቸው፡፡22ቃሎቼ ለሚያገኘኟቸው ሰዎች ሕይወት፣ ለመላው ሰውነታቸውም ፈውስ ናቸውና፡፡23ልብህን በጥንቃቄ ጠብቅ፣ በትጋትም ከልለው፣ የሕይወት ምንጭ የሚፈልቀው ከእርሱ ነውና፡፡24ጠማማ ንግግርን ከአንተ አስወግድ፣ ብልሹ ወሬ ከአንተ አርቅ፡፡25ዓይኖችህ ወደ ፊት በቀጥታ ይመልከቱ፣ በቀጥታ ፊት ለፊት አተኩረህ እይ፡፡26ለእግርህ ደልዳላ ጎዳና አበጅለት፤ ከዚያ በኋላ መንገድህ በሙሉ አስተማማኝ ይሆናል፡፡27ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አትበል፤ እግርህን ከክፉ መልስ፡፡
1ልጄ ሆይ፣ ለጥበቤ ትኩረት ስጥ፤ የማስተዋል ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ፡፡2ይህም ልባምነትን ትማር ዘንድ፣ ከንፈሮችህም እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ነው፡፡3የአመንዝራ ሴት ከንፈር ማርን ያንጠባጥባልና፣ አንደበቷም ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነውና፣4ነገር ግን ፍጻሜዋ እንደ እሬት መራራ ናት፣ እንደ ስለታም ሰይፍ የምትቆርጥ ናት፡፡5እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ፣ እርምጃዎቿም ወደ ሲኦል መንገድ ይሄዳሉ፡፡6ስለ ሕይወት መንገድ ምንም አታስብም፡፡ አረማመዷ የተቅበዘበዘ ነው፣ ወዴት እንደምትሄድም አታውቅም፡፡7አሁንም ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፣ የአፌን ቃል ከማድመጥ ፈቀቅ አትበሉ፡፡8መንገድህን ከእርሷ አርቅ፣ ወደ ቤቷም በር አትቅረብ፡፡9እንዲህ ካደረግህ ክብርህን ለሌሎች ሰዎች፣ የሕይወት ዘመንህንም ለጨካኝ ሰው አሳልፈህ አትሰጥም፤10ባዕዳን በሀብትህ አይፈነጥዙም፣ የደከምክበት ነገር ወደ ባዕዳን ቤት አይገባም፡፡11በሕይወትህ መጨረሻ ስጋህና ሰውነትህ ሲጠፋ ታቃስታለህ፡፡12እንዲህም ትላለህ፡- “ተግሳጽን እንዴት ጠላሁ፣ መታረምን ልቤ ናቀ!13አስተማሪዎቼን አልታዘዝሁም፣ አሰልጣኞቼንም አላደመጥሁም፡፡14በጉባኤና ሰዎች በተሰበሰቡበት መካከል ሙሉ በሙሉ ወደ ጥፋት ተቃርቤ ነበር፡፡”15ከማጠራቀሚያህ ውሃ ጠጣ፣ ከጉድጓድህም የሚፈልቀውን ውሃ ጠጣ፡፡16ምንጮችህ በሁሉም ቦታ ያለገደብ ሊፈስሱ፣ ወንዞችህስ በአደባባዩ ሁሉ ሊጎርፉ ይገባልን?17እነርሱ ለአንተ ብቻ ይሁኑ፣ ከአንተ ጋር ላሉ ባዕዳን አይሁኑ፡፡18ምንጭህ የተባረከ ይሁን፣ በወጣትነት ሚስትህም ደስ ይበልህ፡፡19ምክንያቱም እርሷ በፍቅር እንደተሞላች ዋላ፣ ግርማ ሞገስ እንዳላትም ሚዳቋ ናት፡፡ ጡቷም ሁልጊዜ ያስደስትህ፣ ሁልጊዜም በፍቅሯ ተማረክ፡፡20ልጄ ሆይ፣ ስለምን በጋለሞታ ሴት ትማረካለህ፤ የሌላይቱንስ ሴት ሰውነት ለምን ታቅፋለህ?21እግዚአብሔር ሰው የሚሰራውን በሙሉ ያያል፣ የሚሄድበትንም መንገድ ሁሉ ይመለከታል፡፡22ክፉ ሰው በራሱ ኃጢአት ይጠመዳል፤ የኃጢአቱም ገመድ አጥብቆ ይይዘዋል፡፡23አልተቀጣምና ይሞታል፤ ከሞኝነቱም ብዛት የተነሳ መንገድ ይስታል፡፡
1ልጄ ሆይ፣ ጎረቤትህ ለወሰደው ብድር ዋስ ብትሆንና ገንዘብህን ለዋስትና ብታስይዝ፣ የማታውቀው ሰው ለወሰደው ብድር መተማመኛ ሰጥተህ ከሆነ፣2የዚያን ጊዜ በቃልህ ምክንያት በራስህ ላይ ወጥመድ ዘርግተሃል፣ በአፍህም ቃል ተጠምደህ ተይዘሃል፡፡3ልጄ ሆይ፣ ይህን አድርግ፣ ራስህንም አድን፣ አንተ በጎረቤትህ ምህረት ስር ነህና፡፡ ሂድ፣ ጎረቤትህም እንዲተውህ ሄደህ በትህትና ለምነው፡፡4ለአይንህ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶችህም እንጉልቻን አትስጥ፡፡5የሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ፣ ወፍም ከአጥማጅ እጅ እንደምታመልጥ እንዲሁ ራስህን አድን፡፡6አንተ ሰነፍ ሰው፣ ወደ ጉንዳን ተመልከት፣ መንገዷን አስተውል፣ ጥበበኛም ሁን፡፡7አዛዥ፣ አለቃ ወይም ገዥ የላትም፣8ይሁን እንጂ ምግቧን በበጋ ታዘጋጃለች፣ በመኸር ደግሞ የምትበላውን ታከማቻለች፡፡9አንተ ሰነፍ፣ የምትተኛው እስከ መቼ ነው? ከእንቅልፍህስ የምትነሣው መቼ ነው?10“ጥቂት ማንቀላፋት፣ ጥቂት ማንጎላቸት፣ ጥቂት እጅን አጣጥፎ ማረፍ”11ድህነትህ እንደ ወንበዴ፣ ችግርህም መሳርያ እንደ ታጠቀ ወታደር ይመጣብሃል፡፡12የማይረባ፣ ክፉ ሰው፣ በጠማማ ንግግሩ ይኖራል፣13በዓይኑ ይጠቅሳል፣ በእግሩም ምልክት ያስቀምጣል፣ በጣቶቹም ይጠቁማል፡፡14በልቡ ውስጥ ባለው አጭበርባሪነት ክፋትን ይዶልታል፣ ግጭትንም ሁልጊዜ ይጭራል፡፡15ስለዚህ ጥፋቱ ሳይታሰብ በቅጽበት ይደርስበታል፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደማይድን ሆኖ ይሰበራል፡፡16እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፣ የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፡-17የትዕቢተኛ ሰው አይን፣ ሐሰትን የሚናገር ምላስ፣ የንጹሃን ሰዎችን ደም የሚያፈስስ እጅ፣18ክፋትን የሚፈጥር ልብ፣ ክፋት ለማድረግ በፍጥነት የሚሮጥ እግር፣19ውሸትን የሚለፈልፍ ምስክር፣ በወንድማማቾች መካከል ብጥብጥ የሚዘራ ሰው፡፡20ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ትዕዛዝ ፈጽም፣ የእናትህንም ትምህርት አትተው፡፡21ሁልጊዜ በልብህ አኑራቸው፣ በአንገትህም ዙርያ እሰራቸው፡፡22ስትሄድ፣ ይመሩሃል፤ በተኛህ ጊዜ ይጠብቁሃል፤ በነቃህም ጊዜ ያስተምሩሃል፡፡23ትዕዛዛቱ መብራት ናቸው፣ ትምህርቱም ብርሃን ነው፤ የተግሳጽም ዘለፋዎች የሕይወት መንገድ ናቸውና፡፡24ከምግባረ ብልሹ ሴት፣ ከአመንዝራ ሴትም ጣፋጭ ቃላት ይጠብቅሃል፡፡25በልብህ ውበቷን አትመኝ፣ በሽፋሽፍትዋም አትጠመድ፡፡26ከጋለሞታ ሴት ጋር መተኛት የአንድ ቁራሽ ዳቦ ዋጋ ያሳጣሃል፤ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር መተኛት ግን ሕይወትህን ያሳጣሃል፡፡27አንድ ሰው ልብሱ ሳይቃጠል በደረቱ እሳት መያዝ ይችላልን?28አንድ ሰው እግሩ ሳይቃጠል በፍም ላይ መራመድ ይችላልን?29ከጎረቤቱ ሚስት ጋር የሚተኛም ሰው እንዲሁ ነው፤ ከእርሷ ጋር የሚተኛም ሳይቀጣ አይቀርም፡፡30ሌባ በተራበ ጊዜ ፍላጎቱን ለማሟላት ቢሰርቅ ሰዎች አይንቁትም፡፡31ሆኖም ሌባው ሲሰርቅ ከተያዘ፣ የሰረቀውን ሰባት እጥፍ ይመልሳል፤ በቤቱም ያለውን ንብረት ሁሉ መስጠት አለበት፡፡32የሚያመነዝር ሰው አእምሮው አያመዛዝንም፤ እንዲህ የሚያደርግ ራሱን ያጠፋል፡፡33ቁስልና ውርደት ይገባዋል፣ ውርደቱም አይደመሰስለትም፡፡34ቅናት ሰውን ቁጡ ያደርገዋልና፤ በሚበቀልበት ጊዜ ምህረትን አያደርግም፡፡35እርሱ ምንም ዓይነት ካሳ አይቀበልም፣ ብዙ ስጦታዎችን ብታቀርብለትም እሺ አይልም፡፡
1ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ጠብቅ፣ ትእዛዜንም በአንተ ውስጥ አኑር፡፡2ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ኑር፣ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፡፡3በጣቶችህም ላይ እሰራቸው፤ በልብህም ጽላት ጻፋቸው፡፡4ጥበብ “አንቺ እህቴ ነሽ” በላት፣ ማስተዋልን ደግሞ ዘመዴ ብለህ ጥራው፣5ከአመንዝራ ሴት፣ ቃሏንም ከምታለዝብ ከዘማዊም ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፡፡6በቤቴ መስኮት ላይ ሆኜ ወደ ውጭ ተመለከትሁ፣7ብዙ እውቀት አልባ ወጣቶች ተመለከትሁ፡፡ ከመካከላቸው አንድ የማያስተውል ወጣት ተመለከትሁ፡፡8ያ ወጣት በቤቷ ማዕዘን አጠገብ ባለው መንገድ አለፈ፣ ከዚያም ወደ ቤቷ አቅጣጫ ሄደ9ብርሃን ደንገዝገዝ፣ ቀኑ መሸትሸት ብሎ ነበር፣ በምሽትና በሌሌት ጨለማ፡፡10በዚያ አንዲት ሴት አገኘችው፣ እንደ ሴተኛ አዳሪ የለበሰች፣ እዚያ ለምን እንደ መጣች በሚገባ ታውቃለች፡፡11ጯኺና እምቢተኛ ናት፣ እግሮቿ በቤት አይቀመጡም12አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በገበያ፣ በየማዕዘኑም ተጋድማ ታደባለች፡፡13ስለዚህም ትይዘዋለች፣ ትስመውማለች፣ ፊቷም እፍረት ሳይታይበት እንዲህ አለችው፣14ዛሬ የሰላም መስዋዕቴን አቅርቤአለሁ፣ ስእለቴንም ፈጽሜአለሁ፣15ስለዚህ አንተን ለማግኘት፣ ፊትህን ለመፈለግ ወጣሁ፣ አግኝቼሃለሁም፡፡16በአልጋየ ላይ መሸፈኛ ዘርግቼበታለሁ፣ ከግብጽ የመጣ ባለቀለም የአልጋ ልብስ አንጥፌበታለሁ፡፡17አልጋየን ከርቤ፣ አልሙንና ቀረፋ ረጭቼበታለሁ፡፡18ና፣ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፤ ፍቅራችንን በምንገልጥባቸው የተለያዩ መንገዶች በታላቅ ደስታ እንፈንድቅ፡፡19ባሌ በቤት የለም፤ ወደ ሩቅ መንገድ ሄዷል፡፡20በገንዘብ የተሞላ ቦርሳ ወስዷል፤ ሙሉ ጨረቃ በወጣበት ቀን ይመለሳል፡፡”21በሚያባብል ንግግሯ ታሳስተዋለች፣ በለሰለሰ ንግሯም ታታልለዋለች፡፡22ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፣ ፍላጻ ጉበቱን እስኪወጋው ድረስ በወጥመድ እንደተያዘ አጋዘን፣23ወደ ወጥመድ በርራ እንደምትገባ ወፍ፣ ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ እርሷን ይከተላታል፡፡24አሁን፣ ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፤ የምናገረውንም ልብ ብላችሁ ስሙኝ፡፡25ልባችሁ ወደ መንገዷ እንዲያዘነብል አትፍቀዱ፤ በጎዳናዋም አትሳቱ፡፡26ብዙ ተጎጂዎችን አጥምዳ ጥላለች፤ ቁጥራቸውም እጅግ ብዙ ነው፡፡27ቤቷ ወደ ሲኦል በሚወስደው መንገድ ነው፤ ወደ ሞት ማደርያም የሚያወርድ ነው፡፡
1ጥበብ እየጮኸች አይደለምን? ማስተዋልስ ድምጿን ከፍ አላደረገችምን?2ከመንገድ አጠገብ ባሉት ኮረብታዎች ጫፍ ላይ፣ መንገዶች በሚገናኙበት ቦታ፣ ጥበብ ትቆማለች፡፡3ወደ ከተማይቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣ በከተማይቱ መግቢያ አጠገብ፣ ትጣራለች፡፡4እናተ ሰዎች፣ ወደ እናንተ እጣራለሁ፣ ድምጼንም ከፍ አድርጌ ወደ ሰው ልጆች እጮኸለሁ፡፡5እናንተ ትምህርት ያላገኛችሁ፣ ጠንቃቃነትን ተማሩ፣ እናንተ እውቀትን የምትጠሉ፣ የሚያስተውል ልብ ይኑራችሁ፡፡6የከበሩ ነገሮችን እናገራለሁና አድምጡኝ፣ ከንፈሮቼ ሲከፈቱ ቀና የሆነውን ነገር እናገራለሁ7አንደበቴ እውነትን ይናራልና፣ ከንፈሮቼም ክፋትን ይጠላሉና፡፡8ከአንደበቴ የሚወጡ ቃሎች ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤ በእነርሱ ውስጥ ጠማማ ወይም አሳሳች ነገር የለውም፡፡9ለሚያስተውል ሰው ቃሎቼ በሙሉ ቀና ናቸው፤ እውቀትን ለሚያገኙ ቃሎቼ ትክክለኛ ናቸው፡፡10ከብር ይልቅ ተግሳጼን ምረጡ፣ ከንጹህ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ምረጡ፡፡11እኔ ጥበብ፣ ከከበረ ዕንቁ እበልጣለሁና፤ ከምትመኙት ነገር በሙሉ ከእኔ ጋር የሚስተካከል የለም፡፡12እኔ ጥበብ፣ ከጥንቃቄ ጋር እኖራለሁ፣ እውቀትና ነገሮችን ለይቶ ውሳኔ የመስጠት ኃይልም አለኝ፡፡13እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ ትዕቢት፣ እብሪት፣ ክፉ መንገድና ጠማማ ንግግር እጠላለሁ፣ ፈጽሞም እጠላቸዋለሁ፡፡14እኔ መልካም ምክርና እውነተኛ ጥበብ አለኝ፤ ማስተዋል አለኝ፣ ብርታትም የእኔ ነው፡፡15ነገስታት፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትሃዊነት ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡16መሳፍንቶች፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትህ ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡17የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፣ ተግተው የሚፈልጉኝም ያገኙኛል፡፡18ባለጠግነትና ክብር፣ ዘላቂነት ያለው ሃብትና ጽድቅም በእኔ ዘንድ አሉ፡፡19ፍሬየ ከወርቅ ይበልጣል፣ ከነጠረ ወርቅም ይበልጣል፤ ስጦታየም ከንጹህ ብር ይበልጣል፡፡20እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፣ ወደ ፍትህ በሚወስድ ጎዳና እጓዛለሁ፣21ስለዚህ ለሚወዱኝ ሀብትን እሰጣቸዋለሁ፣ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ፡፡22እግዚአብሄር ከመጀመርያ ፈጠረኝ፣ በቀድሞ ዘመን የስራው መጀመርያ ነኝ፡፡23ከመጀመርያ፣ ምድር ከመፈጠሯ በፊት፣ ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ተሾምሁ፡፡24ውቅያኖሶች ሳይኖሩ፣ የውኃ ምንጮች ሳይፈልቁ በፊት፣ እኔ ተወልጄ ነበር፣25ተራሮች ገና ሳይመሰረቱ፣ ከኮረብቶችም በፊት፣ እኔ ተወለድሁ፡፡26እግዚአብሔር ምድርንና ሜዳዎቿን፣ የመጀመርያውን የዓለም አፈር እንኳ ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ፡፡27እርሱ ሰማያትን ሲመሰርት፣ በውቅያኖስ ገጽ የአድማስን ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡28እርሱ በላይ ያሉትን ደመናት ባጸና ጊዜ፣ የውቅያኖስን ምንጮች በመሰረተ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡29ውሆች የእርሱን ትዕዛዝ አልፈው እንዳያጥለቀልቁ እርሱ ለባህር ድንበርን ባበጀለት ጊዜ፣ የምድርም መሰረት የት መሆን እንዳለበት በወሰነበት ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡30እኔ ዋና ሰራተኛ ሆኜ በአጠገቡ ነበርሁ፣ እኔ ዕለት በዕለት እርሱን ደስ አሰኘው ነበርሁ፣ ሁልጊዜ በፊቱ ደስ ይለኝ ነበር፡፡31የእርሱ በሆነው በመላው ዓለም ደስ ይለኝ ነበር፣ ደስታየም በሰው ልጅ ነበር፡፡32አሁንም፣ ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፣ መንገዴን የሚጠብቁ ሁሉ ደስተኞች ይሆናሉና፡፡33ምክሬን አድምጡ፣ ጥበበኞችም ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት፡፡34እኔን የሚያደምጠኝ ደስተኛ ይሆናል፣ ዕለት በዕለት በመግቢያየ የሚተጋ፣ በቤቴም በሮች አጠገብ የሚጠብቀኝ፡፡35እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና፣ የእግዚአብሔርንም ሞገስ ያገኛል፡፡36እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጎዳል፤ እኔን የሚጠሉኝ በሙሉ ሞትን ይወድዳሉ፡፡
1ጥበብ ቤቷን ሰራች፤ ሰባት ምሰሶዎችን ከድንጋይ ጠርባ አቆመች፡፡2ለእራት እንስሳዎቿን አረደች፤ የወይን ጠጇንም ደባለቀች፤ ማዕዷንም አዘጋጀች፡፡3በሴት ሰራተኞቿ በኩል የጥሪ ወረቀት ላከች፣ ከከተማይቱ ከፍተኛ ቦታ ተጣራች፡፡4እርሷም አእምሮ ለጎደላቸው “እውቀትን ያላገኙ ሁሉ ወደዚህ ይምጡ!” አለች፡፡5“ኑ፣ ምግቤን ተመገቡ፣ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጄን ጠጡ፡፡6የአላዋቂነት መንገዳችሁን ወደኋላ በመተው በሕይወት ኑሩ፤ በማስተዋል መንገድ ተመላለሱ፡፡7ፌዘኛን የሚገስጽ ሰው በራሱ ላይ ስድብን ያመጣል፣ ክፉን ሰው የሚገስጽ ደግሞ ይጎዳል፡፡8ፌዘኛን ሰው አትገስጽ፣ ይጠላሃል፤ ጥበበኛን ሰው ገስጽ፣ ይወድድሃል፡፡9ለጥበበኛ ሰው ትምህርትን ስጠው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ጻድቅን ሰው አስተምረው፣ እርሱም ይበልጥ እውቀትን ይጨምራል፡፡10የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፣ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፡፡11በእኔ ዘመንህ ይበዛልና፣ በሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል፡፡12ጥበበኛ ከሆንህ፣ ጥበበኛ የምትሆነው ለራስህ ነው፣ ነገር ግን የምታፌዝ ከሆንህ፣ ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከመዋለህ፡፡”13ሞኝ ሴት ለፍላፊ ናት፣ ትምህርት የሌላትና ምንም የማታውቅ ናት፡፡14በከተማዋ ከፍተኛ ስፍራ በቤቷ በር በመቀመጫ ላይ ትቀመጣለች፡፡15እርሷ በመንገድ የሚያልፉትን፣ በመንገዳቸውም ቀጥ ብለው የሚሄዱትን ሰዎች ትጣራለች፡፡16እርሷም አእምሮ ለጎደላቸው “እነዚህ ትምህርት የሌላቸው ሰዎች ወደዚህ ይምጡ!” አለች፡፡17“የተሰረቀ ውኃ ጣፋጭ ነው፣ በምስጢር የበሉት እንጀራም አስደሳች ነው፡፡”18ነገር ግን እርሱ ሙታን በዚያ እንዳሉ አያወቅም፣ ተጋባዦቿ በሲዖል ጥልቀት ውስጥ እንዳሉ አያውቅም፡፡
1የሰሎሞን ምሳሌዎች፡፡ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፣ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሃዘንን ያመጣል፡፡2በክፋት የተከማቸ ሃብት ምንም ጥቅም የለውም፣ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል፡፡3እግዚአብሔር በጽድቅ የሚሄዱትን እንዲራቡ አያደርግም፣ የክፉዎችን ምኞት ግን ያከሽፋል፡፡4የሰነፍ እጅ ድሃ ታደርጋለች፣ የትጉ እጅ ግን ብልጽግናን ታመጣለች፡፡5ጥበበኛ ልጅ በበጋ ምርትን ይሰበስባል፣ በመከር መተኛት ግን ለእርሱ ውርደት ነው፡፡6የእግዚአብሔር ስጦታ በጻድቃን ራስ ላይ ነው፣ የክፉ ሰው አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል፡፡7ጻድቅ ሰው ስለ እርሱ ስናስብ ደስ እንድንሰኝ ያደርገናል፣ የክፉ ሰው ስም ግን ይጠፋል፡፡8አዋቂዎች ትእዛዛትን ይቀበላሉ፣ ለፍላፊ ሞኝ ግን ወደ ጥፋት ይሄዳል፡፡9በሀቀኝነት የሚሄድ ሰው ተማምኖ ይሄዳል፣ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይጋለጣል፡፡10በዓይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል፣ ለፍላፊ ሞኝ ግን ወደ ይጠፋል፡፡11ጽድቅን የሚያደርግ ሰው አፍ የሕይወት ምንጭ ነው፣ የክፉ ሰው አፍ ግን ጥፋትን ይደብቃል፡፡12ጥላቻ ጠብን ያነሳሳል፣ ፍቅር ግን ስህተትን ሁሉ ይሸፍናል፡፡13በአስተዋይ ሰው ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፣ በትር ግን አእምሮ ለጎደለው ሰው ጀርባ ነው፡፡14ጥበበኛ ሰዎች እውቀትን ይሰበስባሉ፣ የሞኝ አፍ ግን ጥፋትን ያመጣል፡፡15የባለጠጋ ሰው ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው፤ የድሆች ድህነት ግን መጥፊያቸው ነው፡፡16የጻድቅ ሰው ደመወዝ ወደ ሕይወት ይመራል፤ የክፉዎች ትርፍ ግን ወደ ኃጢአት ይመራቸዋል፡፡17እርምትን ለሚከተል ሰው ወደ ሕይወት የምትመራ ጎዳና አለች፣ ተግሳጽን የማይቀበል ሰው ግን ይስታል፡፡18ጥላቻን የሚደብቅ ሰው ሐሰተኛ ከንፈሮች አሉት፣ ሐሜትን የሚያስፋፋ ሞኝ ነው፡፡19በብዙ ቃላቶች ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፣ ለሚናገረው ነገር ጥንቃቄ የሚደርግ ሰው ግን ጥበበኛ ነው፡፡20የጻድቅ ሰው ምላስ የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ዋጋ የለውም፡፡21የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ያንጻሉ፣ ሞኞች ግን ባለማማዛዘናቸው ምክንያት ይሞታሉ፡፡22የእግዚአብሔር መልካም ስጦታዎች ሃብትን ያመጣሉ፣ መከራንም አያክልበትም፡፡23ክፋት የሞኞች ጨዋታ ነው፣ ጥበብ ግን ለአስተዋይ ሰው ደስታ ነው፡፡24የክፉ ሰው ፍርሃት ድንገት ይደርስበታል፣ የጻድቅ ሰው ምኞት ግን ይፈጸማል፡፡25ክፉ ሰዎች እንደሚያልፍ አውሎ ነፋስ ናቸው፣ ከዚያም በኋላ አይገኙም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን ለዘላለም የሚኖሩ መሰረት ናቸው፡፡26በጥርስ ላይ ያለ ሆምጣጤ፣ በዓይንም ውስጥ ያለ ጢስ እንደሚጎዳ፣ ሰነፍ ሰው ለሚልኩት እንዲሁ ነው፡፡27እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፣ የክፉዎች ዕድሜ ግን አጭር ይሆናል፡፡28ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ተስፋ ደስታቸው ነው፣ የክፉዎች ዕድሜ ግን አጭር ይሆናል፡፡29የእግዚአብሔር መንገድ ሃቀኞችን ይጠብቃቸዋል፣ ለክፉዎች ግን መጥፊያቸው ነው፡፡30ጽድቅን የሚያደርጉ ፈጽሞ አይወድቁም፣ ክፉዎች ግን በምድሪቱ አይቀሩም፡፡31ከጻድቃን አፍ የጥበብ ፍሬ ይወጣል፣ ጠማማ ምላስ ግን ይቆረጣል፡፡32የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢ የሆነውን ነገር ያውቃሉ፣ የክፉዎች አፍ ግን የሚያውቀው ጠማማ የሆነውን ነገር ብቻ ነው፡፡
1እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነ ሚዛን ይጠላል፣ በትክክለኛ ሚዝን ግን ሚዛን ደስ ይለዋል፡፡2ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች፣ ከትህትና ጋር ግን ጥበብ ትመጣለች፡፡3የቅኖች ሀቀኝነታቸው ይመራቸዋል፣ የከዳተኞች ጠማማ መንገድ ግን ራሳቸውን ያጠፋቸዋል፡፡4በቁጣ ቀን ሀብት ዋጋ ቢስ ነው፣ ጽድቅ ግን ከሞት ታድንሃለች፡፡5ነቀፋ የሌለበት ሰው ጽድቅ መንገዱን ያቀናለተል፣ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይወድቃሉ፡፡6እግዚብሔርን ደስ የሚያሰኙ ሰዎች ጽድቃቸው ትታደጋቸዋለች፣ ከዳተኞች ግን በክፉ ምኞታቸው ይጠመዳሉ፡፡7ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ይጠፋል፣ በብርታቱ የተመካበት ተስፋም ከንቱ ይሆናል፡፡8ጽድቅን የሚያደርግ ከመከራ ይድናል፣ ይልቁንም መከራው በክፉው ይመጣበታል፡፡9አምላክ የለሽ ሰው በአንደበቱ ጎረቤቱን ያጠፋል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን በእወቀት ይድናሉ፡፡10ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ሲበለጽጉ ከተማ ትደሰታለች፤ ክፉዎች ሲጠፉ የደስታ ጩኸት ይሆናል፡፡11እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኙ ሰዎች መልካም ስጦታ ከተማ ታላቅ ትሆናለች፤ በክፉዎች አንደበት ግን ከተማ ትፈርሳለች፡፡12ጓደኛውን የሚንቅ ሰው አእምሮ የጎደለው ነው፣ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል፡፡13ለሐሜት የሚሄድ ሰው ምስጢርን ይገልጣል፣ ታማኝ ሰው ግን ምስጢርን ይሰውራል፡፡14በጥበብ አልባ አመራር ሕዝብ ይወድቃል፣ የመካሮች ብዛት ባለበት ግን ድል ይመጣል፡፡15ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሚሆን መከራን ይቀበላል፣ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ዋስ ለመሆን የሚጠላ ሰው ግን ይድናል፡፡16ሞገስ ያላት ሴት ክብር ታገኛለች፣ ጨካኝ ሰዎች ግን ሀብትን ብቻ ያገኛሉ፡፡17ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፣ ጨካኝ ሰው ግን ራሱን ይጎዳል፡፡18ክፉ ሰው ደመወዙን ለማግኘት ይዋሻል፣ ጽድቅን የሚዘራ ግን የእውነትን ደመወዝ ይሰበስባል፡፡19ጽድቅን የሚያደርግ ታማኝ ሰው በሕይወት ይኖራል፣ ክፋትን የሚያደርግ ግን ይሞታል፡፡20እግዚአብሔር ጠማማ ልብ ያላቸውን ይጠላል፣ በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል፡፡21ክፉ ሰዎች ሳይቀጡ እንደማይቀሩ ይህን እርግጠኛ ሁን፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ዘሮች ግን ይድናሉ፡፡22በአሳማ አፍንጫ እንደተሰካ የወርቅ ቀለበት፣ ማስተዋል የሌላትም ቆንጆ ሴት እንዲሁ ናት፡፡23ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ምኞት መልካም ውጤት ያመጣል፣ ክፉ ሰዎች ግን ተስፋ ሊያደርጉት የሚችሉት መቅሰፍት ብቻ ነው፡፡24ዘርን የሚዘራ አንድ ሰው አለ፣ እርሱ ይበልጥ ይሰበስባል፤ ሌላ ደግሞ የማይዘራ አለ፣ እርሱ ይደኸያል፡፡25ለጋስ ሰው ይበለጽጋል፣ ለሌሎች ውኃ የሚሰጥ ደግሞ ለራሱም ውኃ ያገኛል፡፡26እህል ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው ሕዝብ ይረግመዋል፣ በሚሸጠው ግን መልካም ስጦታዎችን በራሱ ላይ እንደ አክሊል ይጎናጸፋል፡፡27መልካምን ነገር ተግቶ የሚፈልግ ሞገስን ይፈልጋል፣ ክፉን የሚፈልግ ግን ክፉ በራሱ ላይ ይመጣበታል፡፡28በባለጠግነታቸው ላይ የሚታመኑ ሰዎች ይወድቃሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ፡፡29በቤተሰቡ ላይ ሁከትን የሚያመጣ ሰው ነፋስን ይወርሳል፣ ሞኝም ሰው በልቡ ጥበበኛ ለሆነው ሰው አገልጋይ ይሆናል፡፡30ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች እንደ ሕይወት ዛፍ ይሆናሉ፣ ሁከት ግን ሕይወትን ያጠፋል፡፡31ጽድቅን የሚደርጉ ሰዎች ለሰሩት ስራ የሚገባቸውን የሚቀበሉ ከሆነ፣ ይልቁንስ ክፉዎችና ኃጢአተኞች እንዴት አይቀበሉ!
1ተግሳጽን የሚወድ እውቀትን ይወዳል፣ እርምትን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው፡፡2እግዚአብሔር ለመልካም ሰው ሞገስን ይሰጠዋል፣ ክፉ እቅድ ለሚያወጣ ሰው ግን ይፈርድበታል፡፡3ሰው በክፋት ላይ ተመስርቶ ጸንቶ ሊቆም አይችልም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን ከመሰረታቸው አይነቀሉም፡፡4መልካም ሴት ለበሏ ዘውድ ናት፣ አሳፋሪ ሴት ግን አጥንቱን እንደሚያበሰብስ በሽታ ናት፡፡5ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች እቅድ ጽድቅ ነው፣ የክፉዎች ምክር ግን ተንኮል ነው፡፡6የክፉ ሰዎች ቃል ድንገት ለመግደል አድፍጦ ያደባል፣ የቅኖች ቃል ግን ይታደጋቸዋል፡፡7ክፉ ሰዎች ይገለበጣሉ፣ አይገኙምም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ቤት ግን ጸንቶ ይቆማል፡፡8ሰው በጥበቡ ብዛት ይመሰገናል፣ ጠማማ ምርጫዎች የሚያደርግ ግን ይናቃል፡፡9የሚበላው ምግብ ሳይኖረው ከሚኩራራ ሰው ይልቅ ራሱን ዝቅ አድርጎ አገልጋይ መሆን ይሻላል፡፡10ጽድቅን የሚያደርግ ሰው እንስሳቱ ስለሚያስፈልጋቸው ነገር ግድ ይለዋል፣ ክፉ ሰው ግን ርህራሄ አደረገ ቢባል እንኳ ስራው ጭካኔ የተሞላ ነው፡፡11መሬቱን በሚገባ የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፣ ዋጋ ቢስ ስራዎችን የሚያሳድድ ሰው ግን አእምሮ አልባ ነው፡፡12ኃጢአተኞች ክፉ ሰዎች ከሌሎች የሰረቁትን ይመኛሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ፍሬ ግን ከገዛ ራሳቸው ይመጣል፡፡13ክፉ ሰው በክፉ ንግግሩ ይጠመዳል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ግን ከመከራ ያመልጣሉ፡፡14ሰው ከቃሎቹ ፍሬ የተነሳ መልካም ነገርን ይጠግባል፣ እንደ እጁ ስራም ዋጋውን ይቀበላል፡፡15የሞኝ መንገድ ለራሱ ትክክል መስሎ ይታየዋል፣ ጥበበኛ ሰው ግን ምክርን ይሰማል፡፡16ሞኝ ቁጣውን በቶሎ ይገልጣል፣ ስድብን ንቆ የሚተው ግን አስተዋይ ነው፡፡17እወነትን የሚናገር ትክክለኛውን ነገር ይናራል፣ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይናገራል፡፡18የለፍላፊ ሰው ቃሎች እንደሚዋጋ ሰይፍ ነው፣ የጥበበኛ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል፡፡19እውነተኛ ከንፈሮች ለዘላለም ይኖራሉ፣ ሀሰተኛ ከንፈር ግን ለቅጽበት ብቻ ነው፡፡20ክፋትን ለማድረግ በሚያቅዱ ሰዎች ልብ ውስጥ ተንኮል አለ፣ ሰላምን ለሚመክሩ ሰዎች ግን ደስታ ይመጣል፡፡21ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች በሽታ አያገኛቸውም፣ ክፉ ሰዎች ግን በመከራ የተሞሉ ናቸው፡፡22እግዚአብሔር ሀሰተኛ ከንፈሮችን ይጠላል፣ በእውነተኛነት በሚኖሩ ሰዎች ግን ደስ ይለዋል፡፡23አስተዋይ ሰው እወቀቱን ይሰውራል፣ የሞኞች ልብ ግን ከንቱነትን ያወራል፡፡24የትጉ ሰዎች እጅ ይገዛል፣ ሰነፍ ሰዎች ግን ለጉልበት ስራተኝነት ታልፈው ይሰጣሉ፡፡25በሰው ልብ ውስጥ የሚገኝ ጭንቀት ያዋርደዋል፣ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል፡፡26ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ለጓደኛው መንገድን ያሳያል፣ የክፉ መንገድ ግን ታስታቸዋለች፡፡27ሰነፍ ሰዎች አድነው ያመጡትን እንስሳ እንኳ አይጠብሱም፣ ትጉ ሰው ግን የከበረ ሀብት ያገኛል፡፡28በጽድቅ መንገድ የሚሄዱ ሰዎች ሕይወትን ያገኛሉ፣ በጎዳናዋም ሞት የለም፡፡
1ጥበበኛ ልጅ የአባቱን ምክር ይሰማል፣ ፌዘኛ ግን ተግሳጽን አያዳምጥም፡፡2ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ነገር ይጠግባል፣ ጠማማ ሰው ግን ዓመጽን ይመኛል፡፡3አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፣ ከንፈሮቹን ያለ ልክ የሚከፍት ግን ይጠፋል፡፡4ሰነፍ ሰው ይመኛል ነገር ግን አንዳችም አያገኝም፣ የትጉ ሰው ምኞት ግን በሙላት ይረካል፡፡5ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ውሸትን ይጠላል፣ ክፉ ሰው ግን ራሱ ጥላቻን ይፈጥራል፣ አሳፋሪ ተግባርንም ይፈጽማል፡፡6በመንገዳቸው ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፣ ክፋት ግን ኃጢአተኞችን ትጥላቸዋለች፡፡7ራሱን ባለጠጋ የሚያስመስል ሰው አለ፣ ነገር ግን አንዳች የለውም፣ ምንም እንደሌለው መስሎ የሚታይ ሰው ደግሞ አለ፣ ይሁን እንጂ እጅግ ባለጠጋ ነው፡፡8ባለጠጋ ሰው ሀብቱን ለሕይወቱ ቤዛ አድርጎ ያቀርብ ይሆናል፣ ድሀ ግን እንዲህ ዓይነት ሥጋት በፍጹም የለበትም፡፡9ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ብርሃን ደምቆ ይበራል፣ የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል፡፡10ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፣ መልካም ምክርን ለሚያደምጡ ግን ጥበብ አለ፡፡11ብዙ ከንቱነት ሲኖር ሀብት እየመነመነ ያልቃል፣ በእጁ እየሰራ ገንዘብ የሚያከማች ሰው ግን ገንዘቡ እየጨመረ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡12ተስፋ ሲዘገይ ልብን ይሰብራል፣ የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው፡፡13ትእዛዝን የሚንቅ በትእዛዝ ይቀጣል፣ ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ያገኛል፡፡14የጥበበኛ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው፣ ከሞት ወጥመድ እንድታመልጥ ያደርግሃል፡፡15መልካም እውቀት ሞገስ ያስገኛል፣ የከዳተኛ ሰው መንገድ ግን አያልቅም፡፡16ጥንቃቄ የተሞሉ ሰዎች ማንኛውንም ውሳኔ የሚያደርጉት በጥበብ ነው፣ ሞኝ ግን ከንቱነቱን ይገልጣል፡፡17ክፉ መልእክተኛ መከራ ውስጥ ይገባል፣ ታማኝ መልእክተኛ ግን እርቅን ያመጣል፡፡18ተግሳጽን የሚንቅ ድህነትና ኃፍረት ይመጣበታል፣ ከእርምት የሚማር ግን ክብር ወደ እርሱ ይመጣል፡፡19ምኞት ሲፈጸም የውስጥ ፍላጎትን ደስ ያሰኛል፣ ሞኞች ግን ከክፋት መመለስን ይጠላሉ፡፡20ከጥበበኞች ጋር ሂድ አንተም ጥበበኛ ትሆናለህ፣ የሞኞች ባልንጀራ ግን እጅግ ይጎዳል፡፡21መቅሰፍት ኃጢአተኞችን ይከታተላቸዋል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን መልካምን ነገር ይቀበላሉ፡፡22መልካም ሰው ለልጅ ልጆቹ የሚያወርሰውን ይተዋል፣ የኃጢአተኛ ሀብት ግን ጽድቅን ለሚያደርጉ ይከማቻል፡፡23የድሆች እርሻ ያልታረሰም ቢሆን ብዙ ምግብ ሊያመርት ይችላል፣ ነገር ግን በፍትህ መጓደል ምክንያት ተጠራርጎ ይወሰዳል፡፡24ልጁን የማይቀጣ ይጠላዋል፣ ልጁን የሚወድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል፡፡25ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ፍላጎቱን እስከሚያረካ ድረስ ጠግቦ ይበላል፣ የክፉዎች ሆድ ግን ሁልጊዜ እንደተራበ ነው፡፡
1ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትሰራለች፣ ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች፡፡2በጽድቅ የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፣ በመንገዱ ታማኝ ያልሆነ ግን ይንቀዋል፡፡3ከሞኝ አፍ የትዕቢት በትር ይወጣል፣ የጥበበኛ ከንፈሮች ግን ይጠብቋቸዋል፡፡4ከብቶች በሌሉበት የመመገቢያ ገንዳ ባዶ ይሆናል፣ በበሬ ጉልበት ግን ብዙ ምርት ይገኛል፡፡5እውነተኛ ምስክር አይዋሽም፣ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይለፈልፋል፡፡6ፌዘኛ ጥበብን ይፈልጋል ሆኖም አያገኛትም፣ እውቀት ግን ወደ አስተዋይ ሰው በቀላሉ ትመጣለች፡፡7ከሞኝ ሰው ራቅ፣ ከከንፈሮቹ እውቀትን አታገኝምና፡፡8የጠንቃቃ ሰው ጥበብ መንገዱን ማስተዋል ነው፣ የሞኞች ከንቱነት ግን ማታለል ነው፡፡9ሞኞች የኃጢአት መስዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ያፌዛሉ፣ በጻድቃን መካከል ግን ቸርነት ይገኛል፡፡10ልብ የራሱን ምሬት ያውቃል፣ ደስታውንም ሌላ ሰው አይጋራውም፡፡11የክፉ ሰዎች ቤት ይጠፋል፣ የጻድቃን ድንኳን ግን ይስፋፋል፡፡12ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፣ ፍጻሜዋ ግን ወደ ሞት ይመራል፡፡13ልብ በሐዘን ውስጥ ሆኖ ሊስቅ ይችላል፣ የደስታም ፍጻሜ ሐዘን ሊሆን ይችላል፡፡14ታማኝ ያልሆነ ሰው ለመንገዱ የሚገባውን ዋጋ ያገኛል፣ መልካም ሰው ግን የራሱ የሆነውን ያገኛል፡፡15እውቀት አልባ ሰው ሁሉንም ነገር ያምናል፣ አስተዋይ ሰው ግን አካሄዱን ያስተውላል፡፡16ጥበበኛ ሰው ይፈራል ከክፉም ይርቃል፣ ሞኝ ግን ራሱን ታምኖ ማስጠንቀቂያን ችላ ይላል፡፡17ለቁጣ የሚቸኩል ሰው ከንቱ ነገሮችን ይፈጽማል፣ ክፋትን የሚያሴር ሰው ደግሞ ይጠላል፡፡18እውቀት አልባ ሰዎች ሞኝነትን ይወርሳሉ፣ አስተዋይ ሰዎች ግን በእውቀት ይከበባሉ፡፡19ክፉዎች በመልካም ሰዎች ፊት ይሰግዳሉ፣ ኃጢአተኞች ደግሞ በጻድቃን ደጅ ይሰግዳሉ፡፡20ድሃ ሰው በራሱ ባልንጀሮችም ጭምር ይጠላል፣ ባለጠጋ ሰዎች ግን ብዙ ወዳጆች አሏቸው፡፡21ለጎረቤቱ ንቀትን የሚያሳይ ኃጢአትን ያደርጋል፣ ለድሃ በጎነትን የሚያሳይ ግን ደስተኛ ነው፡፡22ክፋትን የሚያሴሩ አይስቱምን? መልካምን ለማድረግ የሚያቅዱ ግን በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት ይቀበላሉ፡፡23በብዙ ድካም ትርፍ ይገኛል፣ ወሬ ግን ወደ ድህነት ይመራል፡፡24የጥበበኞች ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው፣ የሞኞች ሞኝነት ግን ተጨማሪ ከንቱነትን ያመጣባቸዋል፡፡25እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፣ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይለፈልፋል፡፡26ሰው እግዚአብሔርን ሲፈራ፣ በእርሱ ይታመናል፤ እነዚህ ነገሮች ደግሞ ለልጆቹ እንደ ብርቱ መጠጊያ ስፍራ ይሆኗቸዋል፡፡27እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፣ ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ያደርገዋል፡፡28የንጉስ ክብር የሚገኘው ከሕዝቡ ብዛት ነው፣ ሕዝብ በሌለበት ግን ልዑል ይጠፋል፡፡29ትዕግስተኛ ሰው ታላቅ ማስተዋል አለው፣ ለቁጣ የሚቸኩል ሰው ግን ሞኝነትን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡30በሰላም የተሞላ ልብ ለሰውነት ሕይወት ነው፣ ቅናት ግን አጥንትን ያበሰብሳል፡፡31ድሀን የሚያስጨንቅ ሰው ፈጣሪውን ይሰድባል፣ ለድሀ ቸርነትን የሚያሳይ ግን ፈጣሪውን ያከብራል፡፡32ክፉ ሰው በክፉ ስራው ይወድቃል፣ ጻድቅ ግን በሞት ጊዜ እንኳ መጠጊያ አለው፡፡33ጥበብ በአስተዋይ ሰው ዘንድ ትኖራለች፣ በሞኞች መካከል እንኳ ራሷን ታሳውቃለች፡፡34ጽድቅን ማድረግ ህዝብን ከፍ ከፍ ያደርጋል፣ ኃጢአት ግን ለማንኛውም ሕዝብ ውርደት ነው፡፡35የንጉስ ሞገስ ተግተው በሚሰሩ አገልጋዮቹ ላይ ነው፣ ቁጣው ግን በአሳፋሪ አገልጋይ ላይ ነው፡፡
1የለዘበ መልስ ቁጣን ይመልሳል፣ መጥፎ ቃል ግን ቁጣን ያስነሳል፡፡2የጥበበኛ ሰዎች ምላስ እውቀትን የተላበሰ ነው፣ የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ያንቆረቁራል፡፡3የእግዚአብሔር ዓይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፣ ክፉውንና መልካሙን ሁሉ ነቅተው ይመለከታሉ፡፡4ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፣ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ይሰብራል፡፡5ሞኝ የአባቱን ተግሳጽ ይንቃል፣ ከእርምት የሚማር ግን አስተዋይ ነው፡፡6ጽድቅን በሚያደርጉ ሰዎች ቤት ብዙ ሀብት አለ፣ ክፉ ሰዎች የሚያገኙት ገቢ ግን መከራ ያመጣባቸዋል፡፡7የጥበበኛ ሰዎች ከንፈሮች እውቀትን ያስፋፋሉ፣ የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም፡፡8እግዚአብሔር የክፉዎችን መስዋዕት ይጠላል፣ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል፡፡9እግዚአብሔር የክፉዎችን መንገድ ይጠላል፣ ጽድቅን የሚከታተለውን ግን ይወደዋል፡፡10ከመንገድ የሚወጣ ሰው ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል፣ እርምትን የሚጠላም ይሞታል፡፡11ሲኦልና ጥፋት በእግዚአብሔር ፊት የተገለጡ ናቸው፤ የሰው ልጆች ልብማ ምንኛ የተገለጠ ይሆን?12ፌዘኛ እርምትን ይንቃል፤ ወደ ጥበበኛም አይሄድም፡፡13ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፣ የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይሰብራል፡፡14የአስተዋይ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፣ የሞኞች አፍ ግን ከንቱነትን ይመገባል፡፡15የተጨቆኑ ሰዎች ቀናት በሙሉ አሰቃቂ ናቸው፣ ደስተኛ ልብ ግን የማይቋረጥ ግብዣ አለው፡፡16እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ከሁከት ጋር ካለ ትልቅ ሃብት ይሻላል፡፡17ፍቅር ባለበት የአትክልት ምግብ መብላት ጥላቻ ባለበት የሰባ ጥጃ ከመብላት ይሻላል፡18ቁጡ ሰው ጭቅጭቅን ያነሳሳል፣ ለቁጣ የዘገየ ሰው ግን ጠብን ጸጥ ያሰኛል፡፡19የታካች ሰው መንገድ በእሾህ እንደ ታጠረ ስፍራ ነው፣ የቅን መንገድ ግን በሚገባ የተገነባ አውራ ጎዳና ነው፡፡20ጥበበኛ ልጅ ለአባቱ ደስታን ያመጣለታል፣ ሞኝ ሰው ግን እናቱን ይንቃል፡፡21ከንቱ ነገር አእምሮ ለጎደለው ሰው ደስ ያሰኛል፣ አስተዋይ ሰው ግን በቅን መንገድ ይሄዳል፡፡22ምክር በሌለበት እቅድ ይበላሻል፣ በአማካሪዎች ብዛት ግን ይከናወናል፡፡23ሰው ተገቢ የሆነ መልስ ሲሰጥ ደስታን ያገኛል፤ የጊዜው ቃል ምንኛ መልካም ነው!24የሕይወት መንገድ አስተዋይ ሰዎችን ወደ ላይ ይመራቸዋል፣ በታች ካለው ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ፡፡25እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ውርስ ያፈራርሳል፣ የመበለቲቱን ንብረት ግን ይጠብቃል፡፡26እግዚአብሔር የክፉ ሰዎችን ሐሳብ ይጠላል፣ የርኅራኄ ቃሎች ግን ንጹሐን ናቸው፡፡27ዘራፊ ለቤተሰቡ መከራን ያመጣል፣ ጉቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል፡፡28ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ልብ መልስ ከመስጠቱ በፊት አጥብቆ ያስባል፣ የክፉ ሰዎች አፍ ግን ክፋትን ሁሉ ያጎርፋል፡፡29እግዚአብሔር ከክፉ ሰዎች እጅግ ሩቅ ነው፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎችን ጸሎት ግን ይሰማል፡፡30የዓይን ብርሃን ለልብ ደስታን ያመጣል፣ መልካም ወሬ ደግሞ ለሰውነት ጤና ነው፡፡31አንድ ሰው እንዴት መኖር እንዳለብህ እርምትን ሲሰጥህ ትኩረት ሰጥተህ የምትሰማ ከሆንህ፣ በጥበበኛ ሰዎች መካከል ትቆያለህ፡፡32ተግሳጽን የማይቀበል ራሱን ይንቃል፣ እርምትን የሚያደምጥ ግን ማስተዋልን ያገኛል፡፡33የእግዚአብሔር ፍርሃት ጥበብን ያስተምራል፣ ትህትናም ከክብር በፊት ትመጣለች፡፡
1የልብ እቅድ የሰው ነው፣ መልስ ግን ከእግዚአብሔር አንደበት ይመጣል፡፡2የአንድ ሰው መንገዶች ሁሉ ለእርሱ ንጹህ ሆኖ ይታየዋል፣ እግዚአብሔር ግን መንፈስን ይመዝናል፡፡3ስራህን ለእግዚአብሔር አስረክብ፣ እቅድህም ይሳካልሃል፡፡4እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለራሱ ዓላማ ፈጠረ፣ ሃጢአተኛውንም እንኳ ለክፉ ቀን፡፡5እግዚአብሔር እምቢተኛ ልብ ያለውን ሁሉ ይጠላል፣ ተባብረው ቢቆሙም ከቅጣት አያመልጡም፡፡6በኪዳን በተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት ኃጢአት ስርየት ያገኛል፣ እግዚአብሔርን በመፍራትም ሰዎች ከክፋት ይርቃሉ፡፡7የሰው መንገዶቹ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ ሲሆኑ፣ እግዚአብሔር የዚያን ሰው ጠላቶች እንኳ ከእርሱ ጋር በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡8ፍትህ በጎደለው መንገድ ከተገኘ በርካታ ገቢ ይልቅ፣ በጽድቅ የተገኘ ጥቂት ገቢ ይሻላል፡፡9ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፣ እግዚአብሔር ግን እርምጃውን ያቀናለታል፡፡10ውሳኔ በንጉስ ከንፈሮች ላይ አለ፣ በፍርድም ጊዜ አፉ በማታለል አይናገርም፡፡11እውነተኛ ሚዛን ከእግዚአብሔር ይመጣል፤ በከረጢትም ውስጥ ያሉት መመዘኛዎች ሁሉ የእርሱ ስራዎች ናቸው፡፡12ነገስታት ክፋትን ሲሰሩ፣ እርሱ አጸያፊ ነገር ነው፣ ዙፋን የሚጸናው ጽድቅን በማድረግ ነውና፡፡13ንጉስ እውነትን በሚናገሩ ከንፈሮች ደስ ይለዋል፣ በግልጽነት የሚናገረውንም ሰው ይወደዋል፡፡14የንጉስ ቁጣ የሞት መልእክተኛ ነው፣ ጥበበኛ ሰው ግን የንጉሱን ቁጣ ያበርዳል፡፡15የንጉስ ፊት ሲያበራ ሕይወት አለ፣ መልካም ፈቃዱም የጸደይን ዝናብ እንደሚያመጣ ደመና ነው፡፡16ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት ምንኛ ይበልጣል፡፡ ከብርም ይልቅ ማስተዋል ይመረጣል፡፡17የጻድቃን መንገድ ከክፋት ትርቃለች፤ ሕይወቱን የሚጠብቅም መንገዱን ይጠብቃል፡፡18ትዕቢት ከጥፋት በፊት ትመጣለች፣ ኩሩ መንፈስም ከውድቀት በፊት፡፡19ከትዕቢተኞች ጋር ዝርፊያን ከመካፈል ይልቅ ከድሆች ጋር ራስን ዝቅ ማድረግ ይሻላል፡፡20የተማሩትን የሚያሰላስሉ ሰዎች መልካምን ነገር ያገኛሉ፣ በእግዚአብሔር የሚታመኑም ደስተኛ ይሆናሉ፡፡21በልቡ ጥበበኛ የሆነ ሰው አስተዋይ ይባላል፣ ጣፋጭ ንግግርም የማስተማር ችሎታን ያዳብራል፡፡22ገንዘብ ላደረገው ማስተዋል የሕይወት ምንጭ ነው፣ የሞኞች ቅጣት ግን ሞኝነታቸው ነው፡፡23የጥበበኛ ሰው ልብ ለአፉ ትምህርትን ይሰጠዋል፣ ለከንፈሮቹም ትምህርትን ይጨምራል፡፡24ደስ የሚያሰኙ ቃላት የማር ወለላ ናቸው፣ ለነፍስ የሚጣፍጡ አጥንትንም የሚፈውሱ ናቸው፡፡25ለሰው ትክክል የሚመስል መንገድ አለ፣ ፍጻሜው ግን ወደ ሞት የሚወስድ ነው፡፡26የሰራተኛ ረሃብ ለእርሱ ይሰራል፤ ረሃቡም ያነሳሳዋል፡፡27የማይረባ ሰው ክፋትን ይቆፍራል፣ ንግግሩም እንደሚያቃጥል እሳት ነው፡፡28ጠማማ ሰው ጥልን ያነሳሳል፣ ሐሜትም የቅርብ ወዳጆችን ያለያያል፡፡29በጥባጭ ሰው ጎረቤቱን ይዋሻል፣ መልካም ወዳልሆነ መንገድም ይመራዋል፡፡30በዓይኑ የሚጠቅስ ሰው ጠማማ ነገሮችን ያስባል፤ ከንፈሮቻቸውን የሚነክሱም ክፋትን ይጎትታሉ፡፡31ሽበት የክብር ዘውድ ነው፤ በጽድቅ መንገድ በመኖር ይገኛል፡፡32ጦረኛ ከመሆን ይልቅ ትዕግስተኛ መሆን ይሻላል፣ መንፈሱን የሚገዛም ከተማን ከሚቆጣጠር ይልቅ ይበረታል፡፡33እጣ በጉያ ይጣላል፣ ውሳኔው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡
1ጥል ባለበት ግብዛ ከሞላበት ቤት ይልቅ ሰላም ባለበት ደረቅ ቁራሽ ዳቦ ይሻላል፡፡2ጥበበኛ ባርያ አስነዋሪ ስራ የሚሰራውን ልጅ ይገዛል፣ ከወንድማማቾችም መካከል እንደ አንዱ ውርስን ይካፈላል፡፡3ማቅለጫ ለብር ነው እቶንም ለወርቅ ነው፣ እግዚአብሔር ግን ልብን ያነጥራል፡፡4ክፋትን የሚያደርግ ሰው ክፋትን የሚናገሩ ሰዎች ምክር ይሰማል፤ ውሸታምም ክፉ ነገሮች የሚያወሩ ሰዎችን ያዳምጣል፡፡5በድሃ የሚቀልድ ሰው ፈጣሪውን ይሰድባል፣ በጥፋትም የሚደሰት ከቅጣት አያመልጥም፡፡6የልጅ ልጆች ለሽማግሌዎች ዘውድ ናቸው፣ ወላጆችም ለልጆቻቸው ክብር ናቸው፡፡7መልካም ንግግር ለሞኝ ሰው አይስማማውም፤ ውሸታም ከንፈሮችም ለንጉሳውያን አይመቹም፡፡8ጉቦ ለሰጪው እንደ አስማት ድንጋይ ነው፤ በሄደበት ስፍራ ሁሉ ስኬትን ያገኛል፡፡9በደልን የሚሸፍን ፍቅርን ይፈልጋል፣ ነገርን የሚደጋግም ግን የቅርብ ወዳጆችን ይለያያል፡፡10መቶ ግርፋት ወደ ሞኝ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሳጽ ወደ አስተዋይ ሰው ጠልቆ ይገባል፡፡11ክፉ ሰው አመጽን ይፈልጋል፣ ጨካኝ መልዕክተኛም ወደ እርሱ ይላክበታል፡፡12ሞኝን በሞኝነቱ ከመገናኘት ይልቅ ግልገሎቿ የተነጠቀችን ድብ መገናኘት ይሻላል፡፡13አንድ ሰው በበጎ ፈንታ ክፋትን ሲመልስ፣ ክፋት ከቤቱ ፈጽሞ አይርቅም፡፡14የጠብ መጀመርያ በሁሉም ስፍራ ውኃ እንደሚለቅ ሰው ነው፣ ስለዚህ ከመበርታቱ በፊት ከግጭት ራቅ፡፡15ክፉ ሰዎችን ነጻ የሚለቅም ሆነ ጽድቅን የሚያደርጉትን ደግሞ የሚኮንን ማንኛውም ሰው፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ናቸው፡፡16ሞኝ ጥበብን ለመማር የማይችል ሆኖ ሳለ፣ ጥበብን ለመማር ለምን ገንዘብ ይከፍላል?17ጓደኛ በዘመኑ ሁሉ ወዳጅ ነው፣ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል፡፡18አእምሮ የጎደለው ሰው ቃል በመግባት ግዴታ ውስጥ ይገባል፣ ለጎረቤቱም ብድር ዋስ ይሆናል፡፡19ጠብ የሚወድ ኃጢአትን ይወዳል፤ መግቢያ በሩን እጅግ ከፍ አድርጎ የሚሰራ አጥንቶች እንዲሰበሩ ያደርጋል፡፡20ጠማማ ልብ ያለው ሰው አንዳችም መልካም ነገር አያገኝም፤ ጠማማ ምላስ ያለውም ወደ መከራ ይወድቃል፡፡21ሞኝን የወለደ ሐዘንን ወደራሱ ያመጣል፣ የሞኝም አባት ደስታን አያገኝም፡፡22ደስተኛ ልብ ጥሩ መድሃኒት ነው፣ የተሰበረ መንፈስ ግን አጥንትን ያደርቃል፡፡23ክፉ ሰው የፍትህን መንገድ ለማጣመም በሚስጥር ጉቦን ይቀበላል፡፡24አስተዋይ ሰው ፊቱን ወደ ጥበብ ያዘነብላል፣ የሞኝ አይኖች ግን ወደ ምድር ዳርቻ ያዘነብላሉ፡፡25ሞኝ ልጅ ለአባቱ ሐዘን ነው፣ ለወለደችውም እናቱ ምሬትን ያመጣል፡፡26ጽድቅ የሚያደርግን ሰው መቅጣት በፍጹም መልካም አይደለም፤ በሐቀኝነት የሚሄዱትን የተከበሩ ሰዎችን መግረፍም መልካም አይደለም፡፡27እውቀት ያለው ሰው ጥቂት ቃላትን ይናገራል፣ አስተዋይ ሰውም ለቁጣ የዘገየ ነው፡፡28ሞኝ እንኳ ዝም ሲል ጥበበኛ እንደሆነ ይታሰባል፤ አፉንም ዘግቶ ዝም ሲል፣ እንደ ምሁር ይቆጠራል፡፡
1ራሱን ከሰው የሚለይ የራሱን ምኞት ይፈልጋል፣ ትክክለኛውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል፡፡2ሞኝ ሰው በማስተዋል ደስታን አያገኝም፣ በራሱ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር በመግለጥ እንጂ፡፡3ክፉ ሰው ሲመጣ፣ ንቀት ከእፍረትና ከስድብ ጋር አብረውት ይመጣሉ፡፡4ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሃ ናቸው፤ የጥበብ ምንጭም የሚፈስ ወንዝ ነው፡፡5ለክፉው ማድላት፣ ጽድቅን ለሚያደርጉም ፍትህን ማጉደል መልካም አይደለም፡፡6የሞኝ ከንፈሮች ጥልን ያመጡበታል፣ አፉም በትርን ትጠራለች፡፡7የሞኝ አፍ መጥፊያው ነው፣ በከንፈሮቹም ራሱን ወጥመድ ውስጥ ይጥላል፡፡8የሐሜት ቃላት እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፣ ወደ ሰውነት ውስጣዊ ክፍሎች ጠልቀው ይገባሉ፡፡9በስራው ችላ የሚልም ብዙውን የአጥፊ ሰው ወንድም ነው፡፡10የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ይድናል፡፡11የባለጸጋ ሐብት የእርሱ የተመሸገ ከተማ ነው፣ ሃሳቡም እንደ ረዥም ግንብ ነው፡፡12ከውድቀቱ በፊት የሰው ልብ ትዕቢተኛ ይሆናል፣ ትህትና ግን ክብርን ቀድሞ ይመጣል፡፡13ከማድመጡ በፊት የሚመልስ ሰው ሞኝነትና ዕፍረት ይሆንበታል፡፡14የሰው መንፈስ ሕመምን ትታገሳለች፣ የተሰበረን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል?15የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፣ የጠቢብም ጆሮ ይፈልገዋል፡፡16የሰው ስጦታ መንገዱን ትከፍትለታለች በተከበሩም ሰዎች ፊት ታቆመዋለች፡፡17ወደ ፍርድ ቀድሞ በመምጣት ጉዳዩን የሚያሰማ ጻድቅ ይመስላል፣ ይህ ግን የሚሆነው ተቀናቃኙ መጥቶ እስከሚጠይቀው ድረስ ነው፡፡18እጣ ማውጣት ክርክርን ያቆማል፣ ሃይለኛ ጠላቶችንም ትለያለች፡፡19የተበደለ ወንድምን መርታት ጠንካራ ከተማን ከማሸነፍ ይልቅ በጣም የከበደ ነው፣ ጠብም እንደ ግንብ ብረት ነው፡፡20የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል፤ በንፈሮቹም ምርት ይረካል፡፡21ሞትና ሕይወት በምላስ ላይ ናቸው፣ የሚወዱትም ፍሬዋን ይበላሉ፡፡22ሚስትን ያገኘ መልካምን ነገር አግኝቷል፣ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን አግኝቷል፡፡23ድሃ ሰው ምህረትን ይለምናል፣ ሃብታም ግን በማመናጨቅ ይመልሳል፡፡24ብዙ ጓደኞች ያለው ሰው በእነርሱ አማካኝነት ወደ ጥፋት ይመጣል፣ ከወንድም የቀረበ ጓደኛ ግን አለ፡፡
1በንግግሩ ጠማማ ከሆነና ከሞኝ ሰው ይልቅ በሃቀኝነት የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡2ደግሞም ያለ እውቀት አንድን ነገር መመኘት መልካም አይደለም፣ በችኮላ የሚሮጥም መንገዱን ይስታል፡፡3የሰው ጅልነት ሕይወቱን ያበላሸዋል፣ ልቡም በእግዚአብሔር ላይ ይቆጣል፡፡4ሐብት ብዙ ጓደኞችን ይጨምራል፣ ድሃ ሰው ግን ከወዳጆቹ የተለየ ነው፡፡5ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይታለፍም፣ ውሸትንም የሚያሰራጭ አያመልጥም፡፡6ብዙዎች ከቸር ሰው ውለታን ይጠይቃሉ፣ ስጦታን ለሚሰጥም ሁሉ ጓደኛ ይሆነዋል፡፡7ድሃ ሰው ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፤ ከእርሱ ብዙ ርቀው የሚገኙ ጓደኞቹማ ምንኛ ይጠሉት! ወደ እነርሱ ይጣራል፣ እነርሱ ግን አይገኙም፡፡8ጥበብን የሚያገኝ ሕይወቱን ይወዳል፤ ማስተዋልንም ገንዘቡ ያደረገ መልካም ነገር ያገኛል፡፡9ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፣ ውሸትን የሚያሰራጭ ግን ይጠፋል፡፡10ለሞኝ በቅንጦት መኖር አይገባውም፣ ባርያ መሳፍንትን ሲገዛ ደግሞ ምንኛ የከፋ ይሆን፡፡11ጠቢብ አእምሮ ሰውን ታጋሽ ያደርገዋል፣ በደልንም መተው ክብር ይሆንለታል፡፡12የንጉስ ቁጣ እንደ ጎረምሳ አንበሳ ግሳት ነው፣ በፊቱ ሞገስ ማግኘት ግን ሳር ላይ እንዳለ ጤዛ ነው፡፡13ሞኝ ልጅ ለአባቱ መጥፊያ ነው፣ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ የውኃ ነጠብጣብ ናት፡፡14ቤትና ሐብት ከወላጆች ይወረሳል፣ ጠንቃቃ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ናት፡፡15ስንፍና ሰውን ወደ እንቅልፍ ይጥለዋል፣ ለመስራት የማይፈቅድ ግን ይራባል፡፡16ትእዛዛትን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፣ ስለ መንገዶቹ የማያስብ ሰው ግን ይሞታል፡፡17ለድሃ ቸር የሆነ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል፣ ለሰራውም ቸርነት መልሶ ይከፍለዋል፡፡18ተስፋ ሳለ ልጅህን ስርዓት አስይዘው፣ ሞቱንም እየተመኘህ ዝም ብለህ አትየው፡፡19ንዴቱን መቆጣጠር የማይችል ሰው ቅጣቱን ማግኘት አለበት፤ ብታድነውም ለሁለተኛ ጊዜ ማድረግህ አይቀርም፡፡20ምክርን ስማ ተግሳጽንም ተቀበል፣ በሕይወትህ መጨረሻ ጥበበኛ እንድትሆን፡፡21በሰው ልብ ብዙ እቅዶች አሉ፣ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው፡፡22ሰው የሚመኘው ታማኝ ሆኖ መገኘት ነው፣ ድሃም ሰው ከውሸታም ይሻላል፡፡23እግዚአብሔርን ማክበር ሰዎችን ወደ ሕይወት ይመራል፤ እንዲህ ያለውም ሰው ይረካል በመከራም አይጎዳም፡፡24ሰነፍ ሰው እጁን በሳህን ውስጥ ያጠልቃል፤ ወደ አፉም እንኳ እንደገና መልሶ አያመጣውም፡፡25ፌዘኛን ብትመታው፣ ያልተማረው ጠንቃቃ ይሆናል፤ አስተዋዩን ብታርመው እውቀትን ያገኛል፡፡26ከአባቱ የሚሰርቅ እናቱንም የሚያሳድድ ዕፍረትና ውርደት የሚያመጣ ልጅ ነው፡፡27ልጄ ሆይ፣ ተግሳጽን አልሰማ ብትል፣ ከእውቀት ቃሎች ትስታለህ፡፡28ምግባረ ብልሹ ምስክር በፍትህ ላይ ያፌዛል፣ የክፉ ሰው አፍም በደልን ይውጣል፡፡29ለፌዘኞች ፍርድ፣ ለሞኞች ጀርባም ጅራፍ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡
1ወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በመጠጥ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም፡፡2የንጉስ ቁጣ እንደሚያገሳ ደቦል አንበሳ ቁጣ ነው፤ የሚያስቆጣውም ሰው ሕይወቱን ይከፍላል፡፡3ጥልን መራቅ ለማንም ሰው ቢሆን ክብር ነው፣ ሞኝ ሰው ግን ወደ ጭቅጭቅ ይገባል፡፡4ሰነፍ ሰው በመከር ወቅት አያርስም፤ በምርት ጊዜ እህል ይለምናል ነገር ግን ምንም አያገኝም፡፡5በሰው ልብ ውስጥ ያለ አሳብ እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፣ አስተዋይ ሰው ግን ከዚያ ቀድቶ ያወጣዋል፡፡6ብዙ ሰው ታማኝ እንደሆነ ይናገራል፣ ታማኝ የሆነውን ግን ማን ሊያገኘው ይችላል?7ጽድቅን የሚያደርግ ሰው በሐቀኝነቱ ይራመዳል፣ ፍለጋውን የሚከተሉ ልጆቹም ደስተኞች ናቸው፡፡8የዳኛን ተግባር በማከናወን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠ ንጉስ በፊቱ ያለውን ክፋት ሁሉ በዓይኖቹ አበጥሮ ይለያል፡፡9“ልቤን በንጽህና ጠብቄያለሁ፤ ከኃጢአቴ ንጹህ ነኝ” ብሎ መናገር የሚችል ማን ነው?101የተለያዩ ሚዛኖችና እኩል ያልሆኑ መስፈሪያዎች፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ይጠላቸዋል፡፡11ወጣት እንኳ ባህርዩ ንጹህና ቅን መሆኑ በስራው ይታወቃል፡፡12የሚሰሙ ጆሮዎችና የሚያዩ ዓይኖች፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ሰራቸው፡፡13እንቅልፍን አትውደድ ወደ ድህነት ትመጣለህና፤ ዓይኖችህን ክፈት፣ የተትረፈረፈ መብል ይኖርሃል፡፡14ዕቃ የሚገዛ ሰው “መጥፎ ነው! መጥፎ ነው!” ይላል፣ በሄደ ጊዜ ግን ይኩራራል፡፡15ወርቅና ብዙ ውድ ድንጋዮች አሉ፣ የእውቀት ከንፈሮች ግን የከበረ ጌጥ ናቸው፡፡16ለማይታወቅ ሰው ብድር በዋስትና ገንዘብ ያስያዘውን ሰው ልብስ ውሰድበት፣ ዝሙት ለምትፈጽም ሴት ዋስትና አስይዞ ከሆነ ውሰድበት፡፡17በማጭበርበር የተገኘ ዳቦ ይጣፍጣል፣ ከዚያ በኋላ ግን አፉ ጠጠር ይሞላል፡፡18እቅዶች በምክር ይጸናሉ፣ በጠቢብ ምክርም ብቻ ጦርነት አድርግ፡፡19ሐሜት ሚስጥርን ያባክናል፣ ስለዚህ ወሬን ከሚያበዙ ሰዎች ጋር አንድነት አትፍጠር፡፡20አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን ከሰደበ፣ መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ መካከል ይጠፋል፡፡21በመጀመርያ በጥድፊያ የተገኘ ሀብት በመጨረሻ ላይ በረከት አይኖረውም፡፡22“ለፈጸምክብኝ በደል ብድራትህን እመልስልሃለሁ” አትበል! እግዚአብሔርን ጠብቅ እርሱም ያድንሃል፡፡23እኩል ያልሆኑ ሚዛኖችን እግዚአብሔር ይጠላል፣ ሐሰተኛ መስፈሪያም መልካም አይደለም፡፡24የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይመራል፤ ታዲያ ሰው የራሱን መንገድ እንዴት ሊያስተውል ይችላል?25ሰው በችኮላ “ይህ ነገር የተቀደሰ ነው” ቢሎ ስእለት ቢሳል፣ ከተሳለም በኋላ ስለ ነገሩ ምንነት ማሰላሰል ቢጀምርና ቢጸጸት ወጥመድ ይሆንበታል፡፡26ጥበበኛ ንጉስ ክፉውን አበጥሮ ያወጣል፣ ከዚያም የመውቂያ ጋሪውን በላያቸው ላይ ይነዳል፡፡27የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው፣ ውስጣዊ ማንነቱንም ይመረምራል፡፡28በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት ንጉስን ይጠብቁታል፤ ዙፋኑም በፍቅር ይጸናል፡፡29የወጣት ወንዶች ክብር ጥንካሬያቸው ነው፣ የሽማግሌዎችም ውበት ሽበታቸው ነው፡፡30የሚያቆስል ምት ክፋትን ያስወግዳል፣ ግርፋትም ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎችን ያነጻል፡፡
1የንጉስ ልብ በእግዚአብሔር እጅ እንዳለ የውኃ ፈሳሽ ነው፤ እርሱ ደስ ወዳሰኘው ይመራዋል፡፡2ለሰው መንገዱ በራሱ ዓይን ፊት ቀና ሊመስለው ይችላል፣ ልብን የሚመዝን ግን እግዚአብሔር ነው፡፡3ከመስዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለው፡፡4ትቢተኛ ዓይንና ኩሩ ልብ፣ የክፉ ሰውም መብራት፣ ኃጢአት ናቸው፡፡5የትጉ ሰው እቅዶች ወደ ብልጽግና ይመራሉ፣ በችኮላ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ግን ወደ ድህነት ይመጣል፡፡6በሐሰተኛ ምላስ ሀብትን ማግኘት በኖ የሚጠፋ ተን፣ የሚገድልም ወጥመድ ነው፡፡7የክፉዎች አመጽ ራሳቸውን ይጠራርጋቸዋል፣ ፍትሕን ማድረግ አይፈቅዱምና፡፡8የበደለኛ ሰው መንገድ ጠማማ ነው፣ ንጹሕ ሰው ግን ጽድቅን ያደርጋል፡፡9ከጠበኛ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር በጣራ ማእዘን ላይ ተጠግቶ መኖር ይሻላል፡፡10የክፉ ሰው ምኞት ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤ ጎረቤቱም በዓይኖቹ ውስጥ ምንም ደግነት አያይም፡፡11ፌዘኛ ሲቀጣ ፣ እውቀት አልባ ሰው ጥበበኛ ይሆናል፣ ጥበበኛ ሰው ሲገሰጽ፣ እውቀትን ይጨምራል፡፡12ጽድቅን የሚያደርግ ሰው የክፉውን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ እርሱ ክፉውን ወደ ጥፋት ያወርደዋል፡፡13የድሆችን ጩኸት የማይሰማ ሰው፣ እርሱም ሲጮህ ማንም አይሰማውም፡፡14በምስጢር የተደረገ ስጦታ ቁጣን ያበርዳል፣ የተሸሸገ ስጦታም ታላቅ ቁጣን ያጠፋል፡፡15ፍትሕ በተደረገ ጊዜ ጽድቅን ላደረገው ሰው ደስታን ያመጣለታል፣ ለክፉ አድራጊዎች ግን ሽብር ያመጣባቸዋል፡፡16ከማስተዋል መንገድ የሳተ ሰው፣ በሙታን ጉባኤ ውስጥ ያርፋል፡፡17ቅንጦት የሚወድ ሰው ድሃ ይሆናል፤ የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድ ደግሞ ባለጠጋ አይሆንም፡፡18ክፉ ሰው ጽድቅን ለሚያደርግ ሰው ቤዛ ይሆናል፣ ከዳተኛ ሰው ደግሞ ለጻድቅ ቤዛ ነው፡፡19ጠብ ከምታነሳሳና ያለማቋረጥ ከምታማርር ሴት ጋር ከመኖር በምድረ በዳ መኖር ይሻላል፡፡20የከበረ ሀብትና ዘይት በጥበበኛ ቤት ይገኛሉ፣ ሞኝ ሰው ግን ያባክናቸዋል፡፡21ጽድቅን የሚያደርግና ደግ ሰው፣ ይህ ሰው ሕይወትን፣ ጽድቅንና ክብርን ያገኛል፡፡22ጥበበኛ ሰው ወደ ኃያላን ከተማ ይገባል፣ የምትታመንበት ምሽጓንም ያፈርሳል፡፡23አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ሰው ራሱን ከመከራ ይጠብቃል፡፡24ኩሩና ትዕቢተኛ ሰው ስሙ “ሞኝ” ይባላል፣ እርሱም በእብሪትና በትዕቢት ያደርጋል፡፡25የሰነፍ ምኞት ራሱን ይገድለዋል፣ እጆቹ ለመስራት አይፈቅዱምና፡፡26እርሱ ቀኑን በሙሉ ይመኛል፣ ተጨማሪ ይመኛል፣ ጽድቅን የሚያደርግ ግን ይሰጣል፣ አይሰስትምም፡፡27የክፉዎች መስዋዕት አስጸያፊ ነው፤ በክፉ ሃሳብ ሲያቀርበው ደግሞ የበለጠ አስጸያፊ ነው፡፡28ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፣ የሚያዳምጥ ሰው ግን ለሁልጊዜ የሚሆን ይናገራል፡፡29ክፉ ሰው ራሱን ጠንካራ አስመስሎ ያቀርባል፣ ጻድቅ ሰው ግን ስለ ድርጊቶቹ ይጠነቀቃል፡፡30እግዚአብሔርን ሊቋቋም የሚችል ጥበብ፣ ማስተዋል ወይም ምክር የለም፡፡31ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፣ ድል ግን የእግዚአብሔር ነው፡፡
1ከብዙ ሐብት ይልቅ ጥሩ ስም ይመረጣል፣ ሞገስም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል፡፡2ሃብታምና ድሃ ሰዎች የሚጋሩት አንድ ነገር አለ፤ ይህም እግዚአብሔር የሁሉም ፈጣሪ መሆኑ ነው፡3ጠንቃቃ ሰው ችግር ሲያይ ራሱን ይሸሽጋል፣ አላዋቂዎች ግን በዚያው ገፍተው ይሄዳሉ በሱም ምክንያት ይጎዳሉ፡፡4የትህትናና እግዚአብሔርን የመፍራት ሽልማት ባለጠግነት፣ ክብርና ሕይወት ነው፡፡5እሾህና አሜኬላ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፤ ሕይወቱን የሚጠብቅም ከእነርሱ ይርቃል፡፡6ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፣ በሸመገለም ጊዜ ከነገርከው መንገድ ፈቀቅ አይልም፡፡7ባለጠጎች ድሆችን ይገዛሉ፣ ተበዳሪም ለአበዳሪው ባርያ ነው፡፡8ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፣ የቁጣውም በትር አይጠቅመውም፡፡9ቸር አይኖች ያሉት ሰው ይባረካል፣ እንጀራውን ከድሆች ጋር ይካፈላልና፡፡10ፌዘኛን ከአንተ አርቀው፣ ጠብም ከአንተ ይርቃል፤ ግጭትና ስድብም ይቆማሉ፡፡11ንጹህ ልብ የሚወድድና ንግግሩም ሞገስ ያለው ሰው፣ ንጉስ ጓደኛው ይሆናል፡፡12የእግዚአብሔር ዓይኖች እውቀትን ይከታተላሉ፣ የከዳተኞችን ቃሎች ግን ይገለብጣል፡፡13ሰነፍ ሰው “አንበሳ በመንገድ ላይ አለ! በውጪ ላይ እገደላለሁ” ይላል፡፡14የአመንዝራ ሴት አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው፤ ወደ እርሱም በሚወድቅ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይሆናል፡፡15ሞኝነት በሕጻን ልብ ላይ ታስሯል፣ የስርዓት በትር ግን ከእርሱ ያርቀዋል፡፡16ሀብቱን ለማካበት ወይም ለሀብታሞች ለመስጠት ሲል ድሆችን የሚያስጨንቅ፣ ወደ ድህነት ይመጣል፡፡17የጠቢብን ቃላት ልብ በል አስተውለህም ስማ፣ ልብህንም ወደ ከእውቀቴ አዘንብል፣18በውስጥህ ብትጠብቃቸውና ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ ዝግጁ ቢሆኑ ለአንተ ደስ ያሰኙሃልና፡፡19እምነትህ በእግዚአብሔር ላይ ይሆን ዘንድ፣ እነዚህን ለአንተ ዛሬ አስተምርሃለሁ፣ ለአንተም ቢሆን አስተምርሃለሁ፡፡20ሰላሳ የተግሳጽና የእውቀት ቃሎችን ለአንተ አልጻፍኩልህምን፣21በእነዚህ ታማኝ ቃሎች እውነትን አስተምርህ ዘንድ፣ አንተም ለላኩህ ታማኝ መልስ ትሰጥ ዘንድ?22ድሃ በመሆኑ ምክንያት ድሃ ሰው አትዝረፍ፣ ችግረኛውንም በበር ላይ አትግፋው፣23እግዚአብሔር ለእነርሱ ይፈርድላቸዋልና፣ የዘረፏቸውንም ሰዎች ሕይወት እርሱ ይነጥቃል፡፡24ግልፍተኛ ሰውን ጓደኛ አታድርግ፣ ቁጣም ካለበት ሰው ጋር አብረህ አትሂድ፣25አለበለዚያ መንገዱን ትማራለህ፣ ራስህንም በወጥመድ ታጠላልፋለህ፡፡26ገንዘብን በተመለከተ ግዴታ የሚያስገባ ውል የምትሰጥ አትሁን፣ ለሌሎችም ብድር ዋስ አትሁን፡፡27መክፈል ካልቻልህ፣ ያንን ሰው አልጋህን ከስርህ ከመውሰድ ሊያቆመው የሚችል ምን ነገር አለ?28አባቶችህ ያስቀመጡትን የጥንቱን የድንበር የምልክት ድንጋይ አታንሳ፡፡29በስራው ስልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን? በነገስታት ፊት ይቆማል፤ በተራ ሰዎች ፊትም አይቆምም፡፡
1ከገዢ ጋር ለመብላት ስትቀመጥ፣ በፊት ያለውን በጥንቃቄ አስተውል፣2ከመጠን ያለፈ ምግብ መብላት የምትወድ ዓይነት ሰው ከሆንህ በጉሮሮህ ላይ ካራ አድርግ፡፡3የእርሱ ጣፋጭ ምግቦች አያስጎምጁህ፣ በውሸት የመጣ ምግብ ነውና፡፡4ባለጠጋ ትሆን ዘንድ ከመጠን በላይ አትልፋ፤ መቼ ማቆም እንዳለብህም ታውቅ ዘንድ ብልህ ሁን፡፡5አይንህን በገንዘብ ላይ በጣልክ ጊዜ፣ እርሱ ይጠፋል፣ በድንገት ክንፍ ያወጣል እንደ ንስርም ወደ ሰማይ እየበረረ ይሄዳል፡፡፤6የክፉ ሰውን፣ እጅግ በጣም ከርቀት በምግብህ ላይ በቅናት የሚመለከተውን ሰው ምግብ አትብላ፣ ጣፋጭ መብሎቹንም አትጎምጅ፣7እርሱ የምግቡን ዋጋ የሚቆጥር ሰው ነውና፡፡ “ብላ፣ ጠጣ!” ይልሃል፣ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም፡፡8ትንሽ የበላኸው ያስታውክሃል፣ የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ፡፡9ሞኝ ሰው ባለበት ንግግር አታድርግ፣ እርሱ የቃሎችህን ጥበብ ያንኳስሳልና፡፡10የጥንቱን የድንበር የምልክት ድንጋይ አታንሳ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች እርሻ አትግፋ፣11ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፣ እርሱ ጉዳያቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳል፡፡12ልብህን ለተግሳጽ ጆሮህንም ለእውቀት ቃሎች ስጥ፡፡13ልጅን ከመቅጣት ወደ ኋላ አትበል፣ በበትር ብትመታው አይሞትምና፡፡14በበትር ብትመታው ነፍሱን ከሲኦል ታድናታለህ፡፡15ልጄ ሆይ፣ ልብህ ጥበበኛ ቢሆን፣ ያኔ ልቤ ደግሞ ደስተኛ ይሆናል፤16ከንፈሮችህ ትክክለኛ የሆነውን በሚናገሩበት ጊዜ ውስጣዊ ሰውነቴ ሁሉ ደስ ይለዋል፡፡17ልብህ በኃጢአተኞች እንዲቀና አትፍቀድ፣ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ተመላለስ፡፡18ለወደፊት እርግጠኛ አለኝታ አለህ፣ ተስፋህም አይጠፋም፡፡19ልጄ ሆይ፣ ስማኝ፣ ጥበበኛ ሁን ልብህንም በትክክለኛው መንገድ ላይ አዘንብል፡፡20ከሰካራሞች ወይም በሆዳምነት ስጋ ከሚበሉ ጋር አትተባበር፣21ሰካራሞችና ሆዳሞች ድሃ ይሆናሉ፣ እንቅልፋምነትም ቁራጭ ጨርቅ ያስለብሳቸዋል፡፡22የወለደህን አባትህን ስማ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት፡፡23እውነትን የራስህ አድርጋት፣ አትሽጣትም፤ ጥበብን፣ ስርዓትንና ማስተዋልንም ገንዘብህ አድርግ፡፡24የጻድቅ አባት በደስታ ይሞላል፣ ጥበበኛ ልጅንም የወለደ በልጁ ይደሰታል፡፡25አባትህና እናትህን ደስ አሰኛቸው፣ የወለደችህ እናትህም ሐሴት ታድርግ፡፡26ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ፣ አይኖችህም የእኔን መንገድ ያስተውሉ፡፡27ዝሙት አዳሪ ሴት ጥልቅ ጉድጓድ፣ የሌላ ሰውም ሚስት ጠባብ ጉድጓድ ናትና፡፡28እንደ ሌባ አድፍጣ ጥጠብቃለች፣ በሰዎችም መካከል የከዳተኞችን ቁጥር ታበዛለች፡፡29ዋይታ የማን ነው? ሃዘን የማን ነው? ጠብስ የማን ነው? ማጉረምረም የማን ነው? ያለ ምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን መቅላት የማን ነው?30ወይን ጠጅ በመጠጣት የሚቆዩ፣ ድብልቅ ወይን ጠጅ የሚቀምሱ ሰዎች ነው፡፡31በቀላ ጊዜ ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት፣ በብርጭቆ ውስጥ መልኩ ባንጸባረቀ ጊዜ የሚያንጸባርቅ በሆነ ጊዜ፣ ስትጠጣውም ያለ ምንም ችግር በገባ ጊዜ፡፡32በመጨረሻ እንደ እባብ ይናከሳል፣ እንደ እፉኝትም ይናደፋል፡፡33አይኖችህ አዲስ ነገሮችን ያያሉ፣ ልብህም ጠማማ ነገሮችን ይናገራል፡፡34በባህር ከፍታ ላይ እንደተኛ፣ በመርከብ ምሰሶ ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ፡፡35“መቱኝ!” “ነገር ግን አልተጎዳሁም፡፡ ደበደቡኝ፣ ነገር ግን አልተሰማኝም፡፡ መቼ ይሆን የምነቃው? ሌላ መጠጥ እፈልጋለሁ፡፡” ትላለህ፡፡
1ክፉ በሆኑ ሰዎች አትቅና፣ ከእነርሱም ጋር ለመተባበር አትፈልግ፣2ምክንያቱም ልባቸው ግጭትን ያሴራል፣ ከንፈራቸውም ችግርን ያወራል፡፡3ቤት በጥበብ ይሰራል፣ በማስተዋልም ይጸናል፡፡4በእውቀትም ውድና ባማሩ እቃዎች ክፍሎቹ ይሞላሉ፡፡5ጥበበኛ ሰው ብርቱ መሆኑን ያረጋግጣል፣ እውቀት ያለውም ሰው ከጠንካራ ሰው ይልቅ ይሻላል፣6በጥበበኛ ምክር ጦርነትህን መዋጋት ትችላለህ፣ በብዙ አማካሪዎችም ድል ይገኛልና፡፡7ለሞኝ ሰው ጥበብ እጅግ ትርቃለች፤ በበርም አፉን አይከፍትም፡፡8ክፋትን ለማድረግ የሚያስብ አንድ ሰው አለ፣ ሰዎችም የተንኮል አለቃ ብለው ይጠሩታል፡፡9የስንፍና እቅድ ኃጢአት ነው፣ ሰዎችም ፌዘኛን ይንቁታል፡፡10በችግር ጊዜ ፍርሃትህን ካሳየህ፣ እንግዲያው አቅምህ ትንሽ ነው፡፡11ወደ ሞት የሚወሰዱትን አድናቸው፣ እየተጎተቱ ለመታረድ የሚነዱትንም ይዘህ መልሳቸው፡፡12አንተም “እዚያ! ስለዚህ ነገር ምንም አናውቅም” ብትል ልብን የሚመረምረው እርሱ ንግግርህን አያስተውለውምን? ሕይወትህን የሚጠብቀው እርሱ አያውቅምን? ለእያንዳንዱ እንደ ስራው መጠን እግዚአብሔር አይሰጠውምን?13ልጄ ሆይ፣ መልካም ነውና ማር ብላ፣ የማር ወለላ ጠብታዎች ለጣዕምህ ጣፋጭ ናቸው፡፡14ጥበብም ለነፍስህ እንዲህ ነው፣ ካገኘኸውም፣ ወደፊት ዋስትና ይኖርሃል፣ ተስፋህም አይጠፋም፡፡15ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎችን ቤት እንደሚዘርፉ ክፉ ሰዎች አድፍጠህ አትጠብቅ፡፡ የጻድቁንም ቤት አታፍርስ፡፡16ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ሰባት ጊዜ ቢወድቅ፣ እንደገና ከወደቀበት ይነሳልና፣ ክፉዎች ግን ይቀሰፋሉ፡፡17ጠላትህ በወደቀ ጊዜ ደስ አይበልህ፣ በተሰናከለም ጊዜ ልብህ ደስ አይበለው፣18እግዚአብሔር ያያል፣ ተመልሶም ቁጣውን ከእርሱ ይመልሳልና፡፡19ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች አትጨነቅ፣ በክፉዎችም አትቅና፣20ክፉ ሰው ተስፋ የለውምና፣ የክፉ ሰውም መብራት ይጠፋልና፡፡21እግዚአብሔርን ፍራ፣ ንጉስንም ፍራ፣ ልጄ ሆይ፤ በእነርሱ ላይ ከሚያምጹ ሰዎችም ጋር አትተባበር፣22ጥፋታቸው በድንገት ይመጣልና፣ ከሁለቱም የሚመጣባቸውን ጥፋት ምን ያህል እንደሆነ ማን ያውቃል?23እነዚህ ደግሞ የጥበበኛ ሰው ንግግር ናቸው፡፡ በዳኝነት አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፡፡24ወንጀለኛውን “ጻድቅ ነህ” የሚለው በሕዝብ ዘንድ ይረገማል፣ በመንግስታትም ዘንድ ይጠላል፡፡25ነገር ግን በደለኛውን የሚገስጹ ደስታ ይሆንላቸዋል፣ የደግነት ስጦታዎችም ወደ እነርሱ ይመጣሉ፡፡26እውነተኛ መልስ የሚሰጥ ሰው ከንፈሮችን ይስማል፡፡27የውጪ ስራህን አዘጋጅ፣ በመስክም ሁሉንም ነገር ለራስህ ዝግጁ አድርግ፣ ከዚያም በኋላ ቤትህን ስራ፡፡28ያለ ምክንያት በጎረቤትህ ላይ አትመስክር፣ በከንፈሮችህም አታታልል፡፡29“እርሱ በእኔ ላይ ያደረገውን እኔም በእርሱ ላይ አደርግበታለሁ፤ በእኔ ላይ ላደረገው ነገር ዋጋውን እከፍለዋለሁ” አትበል፡፡30በሰነፍ ሰው እርሻ በኩል ሄድሁ፣ አእምሮ በሌለውም ሰው የወይን እርሻ አለፍሁ፡፡31እሾህም በየቦታው በቅሎ ነበር፣ መሬቱም በሳማ ተሸፍኖ ነበር፣ የድንጋይ ካቡም ፈርሶ ነበር፡፡32ከዚያም አየሁና አሰብኩኝ፤ ተመለከትሁና ተግሳጽን ተቀበልሁ፡፡33ጥቂት መተኛት፣ ጥቂት እንቅልፍ፣ ጥቂት ለማረፍ እጅን ማጣጠፍ፣34ድህነት እንደ ሌባ በአንተ ላይ ይመጣል፣ ችግርህም መሳርያ እንደታጠቀ ወታደር ይመጣብሃል፡፡
1እነዚህ የይሁዳ ንጉስ፣ የሕዝቅያስ ሰዎች የቀዷቸው ተጨማሪ የሰለሞን ምሳሌዎች ናቸው፡፡2ነገርን መሰወር የእግዚአብሔር ክብር ነው፣ የነገስታት ክብር ግን ነገርን መርምሮ ማውጣት ነው፡፡3ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉ፣ የነገስታት ልብም አይመረመርም፡፡4ቆሻሻውን ከብር አስወግድ፣ የብረት ሰራተኛውም ብሩን ለእጅ ሙያው ሊጠቀምበት ይችላል፡፡5እንደዚሁ ክፉ ሰዎችን ከንጉስ ፊት አርቃቸው፣ ዙፋኑ ጽድቅን በማድረግ ይጸናል፡፡6በንጉስ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፣ ለታላቅ ሰዎች መቆሚያ በተዘጋጀም ስፍራ ላይ አትቁም፡፡7በተከበሩ ሰዎች ፊት ከምትዋረድ ይልቅ፣ እርሱ “ወደዚህ ና” ቢልህ ይሻላል፡፡ ያየኸውን ነገርም፣8ወደ ፍርድ ፈጥነህ አታምጣው፡፡ ጎረቤትህ ባሳፈረህ ጊዜ በመጨረሻ ምን ታርጋለህ?9ጉዳይህን በአንተና በጎረቤትህ መካከል ተከራከር፣ የሌላ ሰው ምስጢር ግን አታውጣ፣10አለበለዚያ ግን አንተን የሰማ ሰው በአንተ ላይ ሃፍረትን ያመጣብሃል፣ ስለ አንተም ልትመልሰው የማትችለው መጥፎ ወሬ ይወራብሃል፡፡11በጥንቃቄ የተመረጠ ቃል መናገር፣ በብር ላይ እንደተቀረጻ የወርቅ ንድፍ ነው፡፡12ለሚሰማ ጆሮ የጥበበኛ ተግሳጽ እንደ ወርቅ ቀለበት፣ ከንጹህ ወርቅም እንደተሰራ ጌጥ ነው፡፡13በምርት መሰብሰቢያ ወቅት እንዳለ የበረዶ ቅዝቃዜ ታማኝ መልዕክተኛ ለላኩት ሰዎች እንዲሁ ነው፤ የጌቶቹን ሕይወት ይመልሳል፡፡14የማይሰጠውን ስጦታ እሰጣለሁ ብሎ የሚመካ ሰው ዝናብ እንደሌለው ደመናና ንፋስ ነው፡፡15በትዕግስት ገዢን እንዲለዝብ ማድረግ ይቻላል፣ መልካም ምላስም አጥንትን ትሰብራለች፡፡16ማር ካገኘህ፣ ለአንተ በቂ የሆነውን ብላ፣ አለበለዚያ ግን ከመጠን በላይ ከበላህ ትተፋዋለህ፡፡17ወደ ጎረቤትህ ቤት እግር አታብዛ፣ ሊሰለችህና ሊጠላህ ይችላልና፡፡18በጎረቤቱ ላይ በሐሰት የሚመሰክር ሰው በጦርነት ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውል ዱላ፣ ሰይፍ ወይም የተሳለ ቀስት ነው፡፡19በችግር ጊዜ የታመንከው ወስላታ ሰው እንደ ተበላሸ ጥርስ ወይም እንደሚያነክስ እግር ነው፡፡20ላዘነ ልብ መዝሙር የሚዘምር፣ በብርድ ጊዜ ልብሱን እንደሚያወልቅ ወይም በሶዳ ላይ ኮምጣጤ እንደሚጨምር ነው፡፡21ጠላትህ ቢራብ እንዲበላ ምግብ ስጠው፣ ቢጠማም እንዲጠጣ ውኃ ስጠው፣22በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህና፣ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይከፍልሃልና፡፡23የሰሜን ንፋስ በእርግጠኝነት ዝናብን ይዞ እንደሚመጣ፣ ሚስጥርን የሚያባክን ሰው ሰዎችን ያስቆጣል፡፡24ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር በጣራ ማእዘን ላይ ተጠግቶ መኖር ይሻላል፡፡25ለተጠማ ሰው ቀዝቃዛ ውሃ እንደሚያረካው ሁሉ፣ ከሩቅ አገር የመጣ የምስራችም እንዲሁ ነው፡፡26በክፉ ሰዎች ፊት የሚንበረከክ መልካም ሰው፣ እንደ ተበከለ ፈሳሽና እንደተበላሸ ምንጭ ነው፡፡27እጅግ በጣም ብዙ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤ በክብር ላይ ክብር እንደመፈለግ ነው፡፡28ራሱን መግዛት የማይችል ሰው እንደፈረሰችና ቅጥር እንደሌላት ከተማ ነው፡፡
1በበጋ ጊዜ እንደሚወርድ በረዶና በመከር ጊዜ እንደሚዘንብ ዝናብ፣ ክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም፡፡2ድንቢጥ ከቦታ ቦታ እንደምትበርር፣ ጨረባም እንደምትሸመጥጥ፣ ያልተገባ እርግማን ማንም ላይ አይደርስም፡፡3ጅራፍ ለፈረስ፣ ልጓምም ለአህያ እንደሆነ፣ በትርም ለሞኞች ጀርባ ነው፡፡4ለሞኝ መልስ አትስጠው፣ በሞኝነቱም አትተባበር፣ አለዚያ እንደ እርሱ ትሆናለህ፡፡5ሞኝን እንደ ሞኝነቱ መልስለት፣ በሞኝነቱም ተባበረው፣ አለዚያ በዓይኖቹ ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል፡፡6በሞኝ ሰው እጅ መልዕክትን የሚልክ ሁሉ የራሱን እግር ይቆርጣል ሁከትንም ይጠጣል፡፡7የሰለሉ የሽባ እግሮች በሞኝ አፍ እንዳለ ምሳሌ ናቸው፡፡8ለሞኝ ክብር መስጠት ድንጋይን በወንጭፍ እንደ ማሰር ነው፡፡9በሰካራም እጅ ላይ ያለ እሾህ በሞኞች አፍ እንዳለ ምሳሌ ነው፡፡10ሁሉንም ሰው የሚያቆስል ቀስተኛ፣ ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን እንደሚቀጥር ሰው ነው፡፡11ውሻ ወደ ትውከቱ እንደሚመለስ፣ ሞኝነቱን የሚደጋግም ሞኝም እንዲሁ ነው፡፡12በራሱ ዓይን ጥበበኛ እንደሆነ የሚያስብን ሰው አይተሃልን? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው፡፡13ሰነፍ ሰው እንዲህ ይላል፣ “አንበሳ በመንገድ አለ! በውጭ በአውራ ጎዳና አንበሳ አለ፡፡”14በር በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በአልጋው ላይ ይዟዟራል፡፡15ሰነፍ ሰው እጁን ወደ ሳህኑ ያስገባል፣ ነገር ግን እጁን ወደ አፉ ለመመለስ ጉልበት የለውም፡፡16ሰነፍ ሰው ማስተዋል ካላቸው ከሰባት ሰዎች የበለጠ ጥበበኛ እንደሆነ በራሱ ዓይን ያስባል፡፡17የውሻን ጆሮ እንደሚይዝ ሰው፣ የራሱ ባልሆነ ጥል ላይ የሚገባ መንገድ አላፊ ሰውም እንዲሁ ነው፡፡18ተቀጣጣይ ቀስት እንደሚወራወር እብድ ሰው፣19“የተናገርሁት እኮ ቀልዴን ነበር?” በማለት ጎረቤቱን የሚያታልል ሰው እንዲሁ ነው፡፡20በእንጨት እጦት እሳት ይጠፋል፣ ሐሜት በሌለበትም ጥል ያቆማል፡፡21ከሰል ፍምን እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣ ጠበኛ ሰውም ሁከትን ያቀጣጥላል፡፡22የሐሜት ቃላቶች እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፤ ወደ ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎችም ይወርዳሉ፡፡23እንሚያቃጥሉ ከንፈሮችና እንደ ክፉ ልብ በብር ፈሳሽ የተለበጠ የሸክላ ድስት እንዲሁ ነው፡፡24ሌሎችን የሚጠላ ሰው ስሜቱን በከንፈሮቹ ይሸነግላል፣ ተንኮሉን ግን በውስጡ ያኖራል፡፡25ማራኪ የሆነ ንግግር ይናገራል፣ ነገር ግን አትመነው፣ በልቡ ውስጥ ሰባት ርኩሰቶች አሉና፡፡26ምንም እንኳ ጥላቻው በሽንገላ የተሸፈነ ቢሆንም፣ ክፋቱ ግን በጉባኤ ይገለጣል፡፡27ጉድጓድን የሚቆፍር ሰው እርሱ ይገባበታል፣ ድንጋይንም የሚያንከባልል ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል፡፡28ውሸታም ምላስ የጎዳቸውን ሰዎች ይጠላል፣ ሸንጋይ አፍም ጥፋትን ያመጣል፡፡
1ነገ በሚሆነው አትመካ፣ ቀኑ የሚያመጣው ምን እንደሆነ አታውቅምና፡፡2ሌላ ያመስግንህ እንጂ በራስህ አፍ ራስህን አታመስግን፤ የማያውቅህ ሰው እንጂ የራስህ ከንፈሮች አያመስግኑህ፡፡3የድንጋይን ክብደትና የአሸዋንም ክብደት አስብ፣ የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም እጅግ የከበደ ነው፡፡4የንዴት ጨካኝነትና የቁጣ ጎርፍ አለ፣ በቅናት ፊት መቆም የሚችል ግን ማን ነው?5ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ተግሳጽ ይሻላል፡፡6የጓደኛ ማቁሰል የታመኑ ናቸው፣ ጠላት ግን ከመጠን በላይ ይስማል፡፡7በጣም ጠግቦ የበላ ሰው የማር ወለላንም አይቀበልም፣ ለራበው ሰው ግን ማንኛውም መራራ ነገር እንኳ ጣፋጭ ነው፡፡8ከጎጆዋ ወጥታ የምትንከራተት ወፍ ከመኖሪያው አካባቢ ወጥቶ እንደሚባዝን ሰው ናት፡፡9ሽቶና እጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፣ የጓደኛ ጣፋጭነት ግን ከምክሩ ይበልጣል፡፡10በችግርህ ጊዜ ጓደኛህንና የጓደኛህን አባት ትተህ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፡፡ በቅርብ ያለ ወዳጅ በሩቅ ካለ ወንድም ይሻላልና፡፡11ልጄ ሆይ፣ ጥበበኛ ሁን፣ ልቤንም ደስ አሰኛት፤ በዚያን ጊዜ ለሚያፌዝብኝ ሰው እኔ መልስ እሰጣለሁ፡፡12ጥንቁቅ ሰው ችግር ሲያይ ራሱን ይሸሽጋል፣ አላዋቂዎች ግን ቀድመው ሄደው በችግሩ ምክንያት ይጎዳሉ፡፡13ለማይታወቅ ሰው ብድር በዋስትና ገንዘብ ያስያዘውን ሰው ልብስ ውሰድበት፤ ዝሙት ለምትፈጽም ሴት ዋስትና አስይዞ ከሆነ ውሰድበት፡፡14ጎረቤቱን በማለዳ ድምጹን በጣም ከፍ አድርጎ የሚባርክ ሰው፣ ባርኮቱ እንደ እርግማን ይቆጠራል!15ጠበኛ ሚስት በዝናብ ቀን እንደማያቋርጥ ነጠብጣብ ናት፤16እሷን ማቆም ንፋስን እንደማቆም ወይም ዘይትን በቀኝ እጅህ ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው፡፡17ብረት ብረትን ይስለዋል፤ በተመሳሳይ መንገድ ሰው ጓደኛውን ይስለዋል፡፡18የበለስ ዛፍ የሚጠብቅ ፍሬውን ይበላል፣ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል፡፡19ውኃ የሰውን ፊት እንደሚያሳይ፣ የሰው ልብ ሰውየውን ያሳያል፡፡20ሲዖልና የሙታን ዓለም መቼም እንደማይጠግቡ፣ የሰውም ዓይኖች መቼም አይጠግቡም፡፡21ማቅለጫ ለብር ከውርም ለወርቅ ነው፣ ሰውም በሚመሰገንበት ጊዜ ይፈተናል፡፡22ሰነፍን ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠውም፣ ሞኝነቱ ግን እርሱን አይለቀውም፡፡23የመንጋህን ሁኔታ በእርግጠኝነት እወቅ፣ ስለ ከብቶችህም ግድ ይበልህ፣24ሐብት ለዘላለም አይኖርምና፡፡ ዘውድ ለትውልድ ሁሉ ይጸናልን?25የነበረው ሳር ጠፍቶ፣ አዲሱ ቡቃያ አድጎ ሲታይ፣ በተራሮች ደግሞ ለከብቶች የሚሆን መብል ተሰብስቦ ይገባል፡፡26ለልብስህ የሚሆን ከበጎች ታገኛለህ፣ ለእርሻህ ዋጋ የሚሆን ደግሞ ከፍየሎችህ ታገኛለህ፡፡27ለአንተና ለቤተሰብህ መብል፣ ሴት አገልጋዮችህንም ለመመገብ የሚበቃ የፍየሎች ወተት ይኖራል፡፡
1ኃጢአተኛ ማንም ሳያባርረው ይሸሻል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ አንበሳ ደፋር ናቸው፡፡2በአገር አመጽ ምክንያት ብዙ ገዢዎች አሏት፣ ማስተዋልና እውቀት ባለው ሰው ግን፣ አገር ለረዥም ዘመን ትቆያለች፡፡3ድሃ ሆኖ ሌሎች ድሆችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ ሰብልን እንሚያጠፋ ዶፍ ዝናብ ነው፡፡4ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያመሰግናሉ፣ ሕግን የሚጠብቁ ግን ከእነርሱ ጋር ይዋጋሉ፡፡5ክፉ ሰዎች ፍትህን አያውቁም፣ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ግን ሁሉን ነገር ያውቃሉ፡፡6በመንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይልቅ፣ በሐቀኝነቱ የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡7ሕግን የሚጠብቅ ማስተዋል ያለው ልጅ ነው፣ የሆዳሞች ጓደኛ ግን አባቱን ያሳፍራል፡፡8ከፍተኛ ወለድ በመሰብሰብ ሀብቱን የሚያከማች ለድሀዎች ለሚራራ ለሌላ ሰው ሀብቱን ይሰበሰብለታል፡፡9አንድ ሰው ሕግን ከማድመጥ ጆሮውን የሚያዞር ከሆነ፣ ጸሎቱ እንኳ የተጠላ ነው፡፡10ቅኑን ሰው ወደ ክፋት መንገድ የሚመራ ሁሉ ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ይገባል፣ ንጹሐን ግን መልካምን ነገር ይወርሳሉ፡፡11ባለጠጋ ሰው በራሱ ዓይኖች ጥበበኛ ሊሆን ይችላል፣ አስተዋይ የሆነ ድሃ ሰው ግን እርሱን ይመረምረዋል፡፡12ጽድቅን የሚያደርጉ ድል በሚያገኙበት ጊዜ፣ ታላቅ ክብር አለ፣ ክፉዎች በሚነሱበት ጊዜ ግን ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ፡፡13ኃጢአቱን የሚሸሽግ አይሳካለትም፣ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምህረትን ያገኛል፡፡14ዘወትር እግዚአብሔርን እየፈራ የሚኖር ሰው ደስተኛ ነው፣ ልቡን የሚያደነድን ግን ወደ መከራ ይወድቃል፡፡15እንደሚያገሳ አንበሳ ወይም እንደ ተቆጣ ድብ በድሆች ላይ የሚገዛ ክፉ ገዥም እንዲሁ ነው፡፡16ማስተዋል የሌለው ገዥ በጭካኔ የሚያስጨንቅ ነው፣ ማታለልን የሚጠላ ግን እድሜውን ያረዝማል፡፡17አንድ ሰው የሌላውን ደም በማፍሰሱ ምክንያት በደለኛ ከሆነ፣ እስከ ሞቱ ቀን ድረስ ኮብላይ ይሆናል፣ ማንም ሰው አይረዳውም፡፡18በሐቀኝነት የሚራመድ ሰው በደህና ይጠበቃል፣ መንገዱ በጠማማነት የተሞላ ግን በድንገት ይወድቃል፡፡19መሬቱን የሚያርስ ሰው ብዙ መብል ይኖረዋል፣ የማይጠቅም ሞያ የሚከተል ግን እጅግ በጣም ይደኸያል፡፡20ታማኝ ሰው ታላቅ በረከት ያገኛል፣ በጥድፊያ ሃብታም የሆነ ግን ሳይቀጣ አይቀርም፡፡21አድልዎን ማሳየት መልካም አይደለም፣ ነገር ግን ለቁራጭ ዳቦ ሲል ሰው ስህተትን ይሰራል፡፡22ስስታም ሰው ሐብትን ያሳድዳል፣ ድህነት በላዩ ላይ እንደሚመጣ ግን አያውቅም፡፡23ሰውን በምላሱ ከሚያሞግስ ይልቅ የሚገስጽ ሰው በኋላ ውሎ አድሮ ከገሰጸው ሰው ብዙ ሞገስ ያገኛል፡፡24አባቱንና እናቱን ሰርቆ “ኃጢአት አይደለም” የሚል ሰው የአጥፊ ተባባሪ ነው፡፡25ስግብግብ ሰው ግጭትን ያነሳሳል፣ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል፡፡26በራሱ ልብ የሚታመን ሰው ሞኝ ነው፣ በጥበብ የሚራመድ ግን ከአደጋ ይርቃል፡፡27ለድሃ የሚሰጥ ምንም ነገር አይጎድልበትም፣ በድሆች ላይ ዓይኖቹን የሚከድን ሰው ግን ብዙ እርግማን ይቀበላል፡፡28ክፉ ሰዎች ሲነሱ፣ ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ፣ ክፉ ሰዎች ሲጠፉ ግን፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ይበዛሉ፡፡
1ብዙ ተግሳጽን ተቀብሎ አንገቱን ያደነደነ ሰው እንደማይድን ሆኖ በቅጽበት ይሰበራል፡፡2ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ሲበዙ፣ ሕዝብ ደስ ይለዋል፣ ክፉ ሰው ገዢ ሲሆን ግን ሕዝብ ያቃስታል፡፡3ጥበብን የሚወድ ሁሉ አባቱን ደስ ያሰኛል፣ አመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያጠፋል፡፡4ንጉስ አገሩን በፍትህ ያጸናል፣ ጉቦን የሚፈልግ ግን ያፈራርሳታል፡፡5ጎረቤቱን የሚሸነግል ሰው ለገዛ እግሩ መረብ እየዘረጋ ነው፡፡6ክፉ ሰው በራሱ ኃጢአት በወጥመድ ይያዛል፣ ጽድቅን የሚያደርግ ግን ይዘምራል፣ ይደሰታልም፡፡7ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ለድሆች ፍትሕ ይጨነቃል፤ ክፉ ሰው ግን እንዲህ ዓይነት እውቀት የለውም፡፡8ፌዘኞች ከተማን ያቃጥላሉ፣ ጥበበኞች ግን ቁጣን ይመልሳሉ፡፡9ጥበበኛ ሰው ከሞኝ ጋር በሚከራከርበት ጊዜ፣ ሞኝ ይቆጣል ይስቃልም፣ እረፍትም አይኖርም፡፡10ደም የተጠማ ሰው ንጹሐንን ይጠላሉ፣ ቅን የሆነውንም ሕይወት ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡11ሞኝ ቁጣውን ሁሉ ይገልጣል፣ ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ይቆጣጠራል፣ ራሱንም ያረጋጋል፡፡12ገዢ ለሐሰተኛ ወሬ ትኩረት የሚሰጥ ከሆነ፣ ሹማምንቶቹ ሁሉ ክፉ ይሆናሉ፡፡13ድሃና ጨቋኝን አንድ የሚያደርጋቸው አለ፣ እግዚአብሔር ለሁለቱም የዓይን ብርሃንን ሰጥቷቸዋልና፡፡14ንጉስ ለድሃ በእውነት ከፈረደ፣ ዙፋኑ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡15በትርና ተግሳጽ ጥበብን ይሰጣሉ፣ ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል፡፡16ክፉ ሰዎች ስልጣን ሲይዙ፣ አመጸኝነት ይጨምራል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን የክፉዎችን ውድቀት ያያሉ፡፡17ልጅህን ቅጣው እረፍትም ይሰጥሃል፤ ለሕይወትህም ደስታን ያመጣል፡፡18ትንቢታዊ ራዕይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፣ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው፡፡19አገልጋይ በቃል አይታረምም፣ ቢገባውም ምላሽ አይሰጥም፡፡20በቃሎቹ የሚቸኩለውን ሰው ተመልክተሃል? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የበለጠ ተስፋ አለው፡፡21አገልጋዩን ከወጣትነቱ ጀምሮ የሚያሞላቅቅ፣ በመጨረሻ ችግር ይገጥመዋል፡፡22ቁጡ ሰው ሁከትን ያነሳሳል፣ ቁጣ የሞላበትም ሰው ብዙ ኃጢአቶችን ይሰራል፡፡23የሰው ትዕቢት ያዋርደዋል፣ ትሁት መንፈስ ያለው ግን ይከበራል፡፡24ከሌባ ጋር የሚካፈል ሰው ሕይወቱን ይጠላል፤ እርግማንን ይሰማል መልስ ግን አይሰጥም፡፡25ሰውን መፍራት ወጥመድ ውስጥ ይከትታል፣ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይጠበቃል፡፡26ብዙዎች የገዢን ፊት ይሻሉ፣ ፍትህ ለሰው የሚመጣው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡27ፍትህን የሚያጓድል ሰው ጽድቅን በሚያደርጉ ሰዎች ፊት የተጠላ ነው፣ መንገዱ ቅን የሆነ ሰው ግን በክፉዎች የተጠላ ነው፡፡
1የያቄ ልጅ የአጉር ቃል፡- ይህ ሰው ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለኡካል ተናገረ፡-2በእርግጠኝነት እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ እንደ እንስሳ ሞኝ ነኝ፣ የሰው ልጅ ማስተዋልም የለኝም፡፡3ጥበብን አልተማርሁም፣ ስለ ቅዱሱም እውቀት የለኝም፡፡4ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ የሄደና ወደታች የተመለሰ ማን ነው? ነፋሳትን በእጁ መዳፍ ሰብስቦ የያዘ ማን ነው? ውሆችንስ በካባው ላይ የሰበሰበ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ስሙ ማን ነው፣ የልጁስ ስም ማን ነው? አንተ በእርግጠኝነት ታውቃለህ!5የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትኗል፣ በእርሱ ለሚታመኑ ጋሻ ነው፡፡6በቃሉ ላይ ምንም አትጨምር፣ አለዚያ ይገስጽሃልና፣ ሐሰተኛም ትሆናለህ፡፡7ሁለት ነገር እጠይቅሃለሁ፣ ከመሞቴም በፊት እነዚህን ነገሮች አትከልክለኝ፡8ከንቱነትንና ውሸትን ከእኔ አርቅ፡፡ ድህነትንም ብልጽግናንም አትስጠኝ፣ የሚያስፈልገኝን መብል ብቻ ስጠኝ፡፡9ብዙ ሃብት ካለኝ፣ አንተን ከድቼ “እግዚአብሔርን ማን ነው?” እላለሁና፣ ድሃ ከሆንኩኝ ደግሞ እሰርቃለሁ፣ የአምላኬንም ስም አሰድባለሁና፡፡10አገልጋዩን በጌታው ፊት ስሙን አታጥፋ፣ ይረግምሃል አንተም በደለኛ ሆነህ ትገኛለህና፡፡11አባቱን የሚረግም፣ እናቱንም የማይባርክ ትውልድ፣12ይህ ትውልድ ራሱን ንጹህ አድርጎ የሚያይ፣ ነገር ግን ከእድፉ ያልጸዳ ትውልድ ነው፡፡13ይህ ትውልድ ዓይናቸው ምንኛ ትዕቢተኛ ነው፣ ሽፋሽፍቶቻቸውም ምንኛ ወደ ላይ ከፍ ያሉ ናቸው!14ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣ መንጋጋቸውም ካራ የሆነ ትውልድ ናቸው፣ ድሆችን ከምድር፣ ችግረኞችንም ከሰው ልጆች መካከል ያጠፉ ዘንድ፡፡15አልቅት “ስጡን፣ ስጡን” እያሉ የሚጮሁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉት፡፡ ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፣ ፈጽሞ “በቃኝ” የማይሉ አራት፤16እነርሱም ሲኦል፣ የማትወልድ ማህጸን፣ ውሃ የተጠማች መሬትና፣ “በቃኝ” የማትል እሳት ናቸው፡፡17በአባት ላይ የሚያፌዝ ለእናት መታዘዝን የሚንቅ ዓይን፣ ዓይኑ በሸለቆ አሞራዎች ይጎጠጉጡአታል፣ በአሞራዎችም ይበላል፡፡18እጅግ የሚያስደንቁኝ ሦስት ነገሮች አሉ፣ አራት ደግሞ ፈጽሞ የማላስተውለው፡-19የንስር መንገድ በሰማይ ውስጥ፤ የእባብ መንገድ በቋጥኝ ላይ፤ የመርከብ መንገድ በባህር ልብ ውስጥ፤ የሰውም መንገድ ከወጣት ሴት ጋር ናቸው፡፡20ይህም የአመንዝራ ሴት መንገድ ነው፣ ትበላለች አፏንም ትጠርጋለች፣ “ምንም ስህተት አልሰራሁም” ትላለች፡፡21በሶስት ነገሮች ምድር ትናወጣለች፣ አራተኛውንም መቋቋም አትችልም፡-22ባርያ ንጉስ ሲሆን፤ ሞኝ በመብል በጠገበ ጊዜ፤23የተጠላች ሴት ትዳር ስትይዝና፤ የቤት ሰራተኛ የእመቤቷን ቦታ ስትወስድ፡፡24በምድር ላይ አራት ነገሮች ትንሽ ናቸው፣ ሆኖም እጅግ ጥበበኞች ናቸው፡-25ጉንዳኖች ጠንካራ ያልሆኑ ፍጡራን ናቸው፣ ነገር ግን ምግባቸውን በበጋ ያዘጋጃሉ፤26ሽኮኮዎች ብርቱ ያልሆኑ ፍጡሮች ናቸው፣ ነገር ግን ቤታቸውን በአለት ውስጥ ይሰራሉ፡፡27አንበጣዎች ንጉስ የላቸውም፣ ነገር ግን ሁሉም በሰልፍ ይሄዳሉ፡፡28እንሽላሊቶችም በሁለት እጅህ ልትይዛቸው ትችላለህ፣ ይሁን እንጂ በነገስታት ቤተ መንግስታት ውስጥ ይገኛሉ፡፡29ግርማ ሞገስ ያለው አረማመድ ያላቸው ሶስት ነገሮች አሉ፣ በአካሄዳቸው ግርማ ሞገስ ያላቸው አራት አሉ፡-30አንበሳ፣ ከዱር እንስሳት ሁሉ ብርቱ የሆነና ከምንም ነገር ወደኋላ የማይመለስ ነው፤31እየተንጎራደደ የሚሄድ አውራ ዶሮ፤ ፍየል፤ እና በወታደሮቹ የታጀበ ንጉስ ናቸው፡፡32ሞኝ ከሆንህ፣ ራስህንም ከፍ ከፍ የምታደርግ ከሆነ ወይም ክፉ ሃሳብን እያሰብክ ከሆነ፣ እጅህን በአፍህ ላይ አድርግ፡፡33የተናጠ ወተት ቅቤ እንደሚወጣው፣ በጣም የታሸ አፍንጫም ደም እንደሚወጣው፣ በቁጣ የሚፈጸሙ ድርጊቶችም ጠብን ያመጣሉ፡፡
1እናቱ ያስተማረችው የንጉስ ልሙኤል ቃሎች፣2ልጄ ሆይ፣ ምንድን ነው? የማሕጸኔ ልጅ ሆይ ምንድን ነው? የስእለቴ ልጅ ሆይ ምንድን ነው?3ብርታትህን ለሴቶች አትስጥ፣ ነገስታትን ለሚያጠፉም መንገድህን፡፡4ለነገስታት አይደለም፣ ልሙኤል ሆይ፣ የወይን ጠጅ መጠጣት ለነገስታት አይደለም፣ “ብርቱ መጠጥ የት ነው” ብለው ይጠይቁ ዘንድ ለገዢዎችም አይደለም፡፡5ምክንያቱም እነርሱ መጠጥ ከጠጡ የተደነገገውን ሕጉን ይረሳሉ፣ የተጨቆኑ ሰዎችንም መብት ያጣምማሉ፡፡6እየጠፉ ላሉ ሰዎች ብርቱ መጠጥ ስጧቸው፣ መራራ ችግር ውስጥ ላሉትም ወይን ስጧቸው፡፡7ይጠጣል ድህነቱንም ይረሳል፣ ችግሩንም አያስታውስም፡፡8መናገር ለማይችሉ ተናገርላቸው፣ እየጠፉም ላሉት ሁሉ ስለ ጉዳያቸው ተናገር፡፡9ትክክል ስለሆነው ነገር ጮህ ብለህ ተናገር፣ ፍርድም ስጥ፣ ስለ ድሆችና ስለ ተቸገሩም ሰዎች ጉዳይ መልስ ስጥ፡፡10ችሎታ ያላትን ሴት ማን ሊያገኛት ይችላል? የእርሷ ዋጋ ከእንቁ የበለጠ ነው፡፡11የባሏ ልብ በእርሷ ይተማመናል፣ ድሃም አይሆንም፡፡12በሕይወት ዘመኗ ሁሉ ለእርሱ መልካም ነገር ታደርግለታለች፣ ክፋትንም አታደርግበትም፡፡13የበግ ጠጉርና የተልባ ትመርጣለች፣ በእጆቿም ደስ ብሏት ትሰራለች፡፡14እርሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤ መብሏን ከሩቅ ታመጣለች፡፡15በሌሊት ተነስታ ለቤተሰቧ መብልን ታቀርባለች፣ ስራዋንም ለሴት አገልጋዮቿ ታከፋፍላለች፡፡16እርሻን ተመልክታ ትገዛለች፣ በእጆቿም ፍሬ የወይን ተክል ትተክላለች፡፡17ራሷን በብርታት ታለብሳለች፣ ክንዶቿንም ታጠነክራለች፡፡18ለእርሷ ጥሩ ትርፍ የሚያመጣላትን ታውቃለች፤ ሌሊቱንም ሙሉ መብራቷ አይጠፋም፡፡19እጆቿን በእንዝርቱ ላይ ታስቀምጣለች፣ የሚሽከረከረውንም ክር ትይዛለች፡፡20እጇን ለድሆች ትዘረጋለች፤ ለተቸገሩትም እጆቿን ትዘረጋለች፡፡21በረዶም ቢዘንብ ስለ ቤተሰቧ አትፈራም፣ ቤተሰቧ ሁሉ ቀይ ልብስ ለብሰዋልና፡፡22ለመኝታዋ የአልጋ ልብስ ትሰራለች፣ ቀጭን ሐምራዊ ልብስም ትለብሳለች፡፡23ባለቤቷም ከአገሩ ሽማግሌዎች ጋር ሲቀመጥ በበሮቹ የታወቀ ይሆናል፣ ፡፡24የሊኖ ልብሶችን ትሰራለች፣ ትሸጣለችም፣ ለነጋዴዎችም መቀነቶችን ታስረክባለች፡፡25ጥንካሬንና ክብርን ተላብሳለች፣ ወደፊት የሚመጣውን ጊዜ እያሰበች ትስቃለች፡፡26አፏን በጥበብ ትከፍታለች፣ የደግነት ሕግም በምላሷ ላይ አለ፡፡27የቤተሰቦቿን መንገዶች ትመለከታለች፣ የስንፍናንም እንጀራ አትበላም፡፡28ልጆቿም አድገው የተባረክሽ ነሽ ይሏታል፤ ባለቤቷም እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፣29“ብዙ ሴቶች መልካምን አድርገዋል፣ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡”30ቁንጅና አሳሳች ነው፣ ውበትም ጠፊ ነው፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች፡፡31የእጆቿን ፍሬ ስጧት፣ ስራዋቿም በአደባባዮች ያስመሰግኗት፡፡
1ይህ በኢየሩሳሌም የነገሠውና የዳዊት ልጅ የሆነው የአስተማሪው ቃል ነው። 2አስተማሪው እንዲህ ይላል፥ "እንደ እንፋሎት ትነት፥ በደመናም ውስጥ እንዳለ እስትንፋስ፥ ሁሉም ነገር ይጠፋል፥ በርካታ ጥያቄዎችን ትቶ። 3ከፀሐይ በታች በሚደክሙበት ሥራ ሁሉ የሰው ልጆች ምን ትርፍ ያገኙበት ይሆን?4አንደኛው ትውልድ ይሄዳል፥ ሌላኛው ትውልድ ይመጣል፥ ምድር ግን ለዘላለም ትኖራለች። 5ፀሐይ ትወጣለች፥ ትጠልቃለችም፥ ዳግም ወደምትወጣበት ሥፍራ ለመመለስም ትቸኩላለች። 6ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፥ ወደ ሰሜንም ያከብባል፥ ሁሌም በመንገዱ ይሄዳል፥ እንደገናም ይመለሳል።7ወንዞች ሁሉ ወደ ባህር ይፈስሳሉ፥ ባህሩ ግን መቼም ቢሆን አይሞላም። ወንዞቹ ወደሚሄዱበት ሥፍራ፥ ወደዚያው ሥፍራ እንደገና ይሄዳሉ። 8ሁሉም ነገር አድካሚ ነው፥ ሊያስረዳ የሚችልም የለም። ዓይን በሚያየው አይረካም፥ ጆሮም በሚሰማው አይሞላም።9የሆነው ሁሉ ወደፊትም የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ሁሉ ወደፊት የሚደረግ ነው። ከፀሐይ በታች አንድም አዲስ ነገር የለም። 10'ተመልከት፥ ይህ አዲስ ነው' ሊባልለት የሚችል አንዳች ነገር አለ? አሁን ያለው ሁሉ ለብዙ ዘመናት አስቀድሞ የነበረ ነው፥ ወደ እኛ ከመምጣቱ በፊት በዘመናት መካከል። 11በቀድሞ ዘመን የሆኑትን ነገሮች የሚያስታውስ ያለ አይመስልም። እጅግ ዘግይተው የሆኑትን ነገሮችና ወደፊት ሊሆኑ ያሉት ሁለቱም የሚታወሱ አይመስሉም።12እኔ አስተማሪ ነኝ፥ በእስራኤልም ላይ በኢየሩሳሌም ንጉሥ ነበርኩ። 13ከሰማይ በታች የተደረገውን ነገር ሁሉ በጥበብ ለማጥናትና ለመመርመር አዕምሮዬን አሠራሁት። ይህ ምርምር እግዚአብሔር የሰው ልጆች በሥራ እንዲጠመዱ የሰጣቸው አድካሚ ተግባር ነው። 14ከሰማይ በታች የተሠሩትን ሥራዎች ሁሉ አየሁ፥ ተመልከቱ፥ ሁሉም የሚተንና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነው። 15የተጣመመ መቃናት አይችልም! የጠፋው መቆጠር አይችልም!16ለልቤ እንዲህ ስል ተናገርኩ፥ "ተመልከት፥ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ጥበብን አከማችቻለሁ። አዕምሮዬ ትልቅ ጥበብንና እውቀትን አይቷል።" 17ስለዚህ ጥበብን ለማወቅ ልቤን አሠራሁት፥ ደግሞም ዕብደትንና ሞኝነትን። ይህም ደግሞ ነፋስን ለማገድ እንደ መሞከር መሆኑን አስተዋልኩኝ። 18ጥበብን በማብዛት ውስጥ ብዙ ተስፋ መቁረጥ አለ፥ እውቀትንም የሚያበዛ ሐዘንን ያበዛል።
1እኔም በልቤ፥ "ና እንግዲህ፥ በደስታ እፈትንሃለሁ። ስለዚህ እንዳሻህ ተደሰት" አልኩ። ግን ተመልከት፥ ይህም ደግሞ ልክ የአፍታ እስትንፋስ ነበር። 2ስለ ሣቅ "እርሱ ዕብደት ነው"፥ ስለ ደስታም "ምን ይጠቅማል?" አልኩ።3በወይን ጠጅ ራሴን እንዴት እንደማስደስተው በልቤ መረመርሁ። እስካሁን ሞኝነትን ብይዛትም አዕምሮዬ በጥበብ እንዲመራ ተውኩት። ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ሊያደርጉት የሚገባቸውን መልካም ነገር ለማግኘት ፈለግሁ።4ታላላቅ ነገሮችን አከናወንኩ። ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፥ ወይንንም ተከልሁ። 5የአትክልትና የመዝናኛ ቦታዎችን ለራሴ ሠራሁ፤ በእነርሱም ላይ ሁሉንም ዓይነት የፍሬ ዛፎች ተከልሁባቸው። 6ዛፎች የሚያድጉበትን ዱር የሚያጠጡ የውሃ ገንዳዎችን አበጀሁ።7ወንድና ሴት ባሪያዎችን ገዛሁ፤ በቤተ መንግሥቴ የተወለዱ ባሪያዎችም ነበሩኝ። ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነገሡት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ የከብት መንጋና የቤት እንስሶች ነበሩኝ። 8ብርና ወርቅን፥ የነገሥታቱንና የአውራጃዎቹንም ሃብት ለራሴ አከማቸሁ። ለእኔ ለራሴ ወንድና ሴት አዝማሪዎች ነበሩኝ፤ እጅግ በበዙት ሚስቶቼና ቁባቶቼም በምድር ማንኛውንም ሰው ሊያስደስተው የሚችለውን ነገር አደረግሁ።9ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ታላቅና ባለጸጋ ሆንኩ፥ ጥበቤም ከእኔው ጋር ቆየች። 10ዓይኖቼ የፈለጉትን ማናቸውንም ነገር አልከለከልኳቸውም። በምሠራው ሁሉ ልቤ ስለ ተደሰተና ደስታ የሠራሁት ሥራ ሁሉ ብድራት ስለ ነበረ ከየትኛውም ደስታ ልቤን አልከለከልኩትም።11ከዚያም እጆቼ ያከናወኗቸውን ተግባራት ሁሉ፥ እኔም የሠራኋቸውን ሥራዎች ተመለከትኩ፥ ነገር ግን ሁሉም እንፋሎትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነበር። በእርሱ ውስጥ ከፀሐይ በታች አንድም ትርፍ አልነበረበትም። 12ከዚያም ጥበብን፥ ደግሞም ዕብደትንና ሞኝነትን ለመመርመር ራሴን መለስኩ። አስቀድሞ ከተደረገው በቀር ከዚህኛው ንጉሥ በኋላ የሚመጣው ንጉሥ ምን ለማድረግ ይችላል?13ከዚያም ልክ ብርሃን ከጨለማ እንደሚሻል ጥበብም ከሞኝነት የሚሻል መሆኑን መረዳት ጀመርሁ። 14ጥበበኛ ሰው የሚሄድበትን እንዲያውቅ ዓይኖቹን በራሱ ላይ አድርጎ ይጠቀምባቸዋል፥ ሞኙ ግን በጨለማ ይሄዳል፥ ቢሆንም ለእያንዳንዱ የተዘጋጀለት ፍጻሜ ተመሳሳይ መሆኑን አውቃለሁ።15እኔም በልቤ፥ "በሞኙ ላይ የሚደርሰው በእኔም ላይ ይደርሳል። ስለዚህ በጣም ጥበበኛ ብሆን ምን ልዩነት ያመጣል?" አልኩ። "ይህም ደግሞ እንፋሎት ብቻ ነው" ብዬ በልቤ ደመደምኩኝ። 16ምክንያቱም ጠቢቡም እንደ ሞኙ ለዘላለም አይታሰብም። በሚመጣው ዘመን ሁሉም ነገር የተረሳ ይሆናል። ልክ ሞኙ እንደሚሞት ጠቢቡም ሰው ይሞታል።17ከፀሐይ በታች የሚሠራው ሥራ ሁሉ ክፉ ስለሆነብኝ ሕይወትን ጠላሁ። ይህም የሆነው ሁሉም ነገር እንፋሎትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ስለሆነ ነው። 18ከፀሐይ በታች በሥራ የደከምኩበትን ሁሉ ጠላሁ፥ ከእኔ በኋላ ለሚመጣው ሰው ልተውለት የግድ ነውና።19እርሱ ጥበበኛ ወይም ሞኝ ይሆን እንደሆነ ማን ያውቃል? ሆኖም ከሰማይ በታች በጥበቤ በሠራሁት ሁሉ ላይ አዛዥ ይሆናል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው። 20ከዚህ የተነሣ ከፀሐይ በታች በሠራሁት ሥራ ሁሉ ላይ ልቤ ተስፋ መቁረጥ ጀመረ።21ምክንያቱም አንዱ በጥበብ፥ በእውቀትና በብልሃት ይሠራ ይሆናል፥ ነገር ግን የነበረውን ነገር ሁሉ አንድም ላልለፋበት ሰው ይተውለታል። 22ይህም ደግሞ እንፋሎትና እጅግ የሚያሳዝን ነው። ከፀሐይ በታች ሰው ተግቶ በመሥራቱና ሥራውን ሁሉ ለማጠናቀቅ በልቡ በመሞከሩ ምን ያተርፋል? 23የየዕለት ሥራው በስቃይና በውጥረት የተሞላ ነው፥ ስለዚህ ነፍሱ በሌሊት እረፍት አታገኝም። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።24ለማንኛውም ሰው ከመብላት፥ መጠጣትና ከሥራው መልካም በሆነው ከመርካት የሚበልጥበት ምንም ነገር የለም። ይህ እውነት የሚመጣው ከእግዚአብሔር እጅ እንደሆነም አየሁ። 25ከእግዚአብሔር ካልሆነ በስተቀር ማን ሊበላ ይችላል? ወይም የትኛውንም ዓይነት ደስታ ማን ሊደሰት ይችላል?26እርሱን ደስ ለሚያሰኝ እግዚአብሔር ጥበብን፥ እውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። እንዲሁም ለኃጢአተኛው የመሰብሰብንና የማከማቸትን ሥራ ይሰጠዋል፥ እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጠው ዘንድ። ይህም ደግሞ እንፋሎትን ማብዛትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነው።
1ለሁሉም ነገር የተቀጠረለት ጊዜ አለው፥ ከምድር በታች ለሚሆነውም ወቅት አለው። 2ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞት ጊዜ አለው፥ ለመትከል ጊዜ አለው፥ ለመንቀል ጊዜ አለው፥ 3ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስ ጊዜ አለው፥ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመገንባት ጊዜ አለው፥4ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሣቅ ጊዜ አለው፥ ለማዘን ጊዜ አለው፥ ለመጨፈር ጊዜ አለው፥ 5ድንጋይ ለመወርወር ጊዜ አለው፥ ድንጋይ ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፥ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍ ለመራቅ ጊዜ አለው፥6ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ፍለጋን ለማቆም ጊዜ አለው፥ ነገሮችን ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ነገሮችን ወርውሮ ለመጣል ጊዜ አለው፥ 7ልብስ ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋት ጊዜ አለው፥ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገር ጊዜ አለው፥8ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላት ጊዜ አለው፥ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላም ጊዜ አለው። 9ሠራተኛው ከጥረቱ የሚያተርፈው ምንድነው? 10እግዚአብሔር እንዲፈጽሙት ለሰው ልጆች የሰጣቸውን ሥራ አይቻለሁ።11እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በጊዜው ተስማሚ አድርጎ ሠራው። ደግሞም በልባቸው ውስጥ ዘላለማዊነትን አስቀመጠ። ነገር ግን የሰው ልጆች ከጅማሬአቸው እስከ ፍጻሜአቸው ድረስ እግዚአብሔር የሠራውን ሥራ ሊያስተውሉት አይችሉም።12ለሰው በሕይወት ዘመኑ ከመደሰትና መልካም ከማድረግ በቀር የሚሻል ምንም ነገር እንደሌለ አውቃለሁ። 13ደግሞም ሰው ሁሉ ሊበላና ሊጠጣ፥ ከሥራውም ሁሉ በሚመጣ መልካም እንዴት መደሰት እንዳለበት ሊያውቅ። ይህ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው።14እግዚአብሔር የሠራው ሁሉ ለዘላለም እንደሚኖር አውቃለሁ። በዚህ ላይ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይቻልም። ምክንያቱም ሰዎች በአክብሮት እንዲቀርቡት ይህንን ያደረገው እግዚአብሔር ነው። 15አሁን ያለው ሁሉ ቀደም ሲል የነበረ ነው፤ ወደ ፊት የሚኖረውም ሁሉ ቀደም ሲል የነበረ ነው። እግዚአብሔር ሰዎችን የተደበቁ ነገሮችን እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል።16ከፀሐይ በታች ፍትሕ ሊኖር በሚገባበት ግፍ መኖሩን አየሁ፥ ጽድቅ ሊኖር በሚገባበትም ሥፍራ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ግፍ ነው። 17እኔም በልቤ፥ "ስለ እያንዳንዱ ጉዳይና ስለ እያንዳንዱ ሥራ በጻድቁና በአመጸኛው ላይ በትክክለኛው ጊዜ እግዚአብሔር ይፈርዳል" አልሁ።18እኔም በልቤ፥ "የሰው ልጆች እንደ እንስሳ መሆናቸውን ለማሳየት እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል" አልሁ።19በእንስሳት ላይ የሚደርሰው ያው ዕድል ፈንታ በሰው ልጆች ላይ ይደርሳልና። እንደ እንስሳቱ፥ ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ። ያንኑ አየር ሁሉም ይተነፍሱታል፥ ስለዚህ በዚህ መንገድ ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም። ሁሉም ነገር ፈጥኖ የሚጠፋ እስትንፋስ አይደለም? 20ሁሉም ወደ አንድ ሥፍራ ይሄዳሉ። ሁሉም ነገር ከአፈር ይመጣል፥ ሁሉም ነገር ደግሞ ወደ አፈር ይመለሳል።21የሰው መንፈስ ወደ ላይ፥ የእንስሳ መንፈስም ወደ ታች ወደ ምድር ውስጥ ይሄድ እንደሆነ የሚያውቅ ማን ነው? 22ስለዚህ ማንም ሰው በሥራው ከመደሰት የሚበልጥ የተሻለ ነገር እንደሌለ እንደገና አስተዋልሁ፥ ያ ዕድል ፈንታው ነውና። ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን እንዲያይ ማን መልሶ ሊያመጣው ይችላል?
1እንደገና ከፀሐይ በታች ስለሚደረገው ግፍ ሁሉ አሰብሁ። የሚጨቆኑትን ሰዎች ዕንባ ተመልከቱ። የሚያጽናናቸውም የለም። በጨቋኞቻቸው እጅ ኃይል አለ፥ ነገር ግን የተጨቆኑት ሰዎች አጽናኝ የላቸውም።2ስለዚህ ካሉት የሞቱት፥ እስካሁን በሕይወት ካሉት ቀደም ሲል የሞቱት ይሻላሉ አልሁ። 3ሆኖም ከሁለቱ የሚሻለው ያልኖረው፥ ከፀሐይ በታች የሚደረገውን ክፉ ድርጊት ያላየው ነው።4ከዚያም የትኛውም ጥረትና የጥበብ ሥራ ባልንጀራውን ለቅንዓት እንደሚያነሣሣው አየሁ። ይህም ደግሞ እንፋሎትና ንፋስን ለማገድ መሞከር ነው።5ሞኝ ሰው እጁን አጣምሮ ይቀመጣል፥ አይሠራምም፥ ስለዚህ የራሱ ሥጋ ምግቡ ነው። 6ንፋስን ለማገድ በመሞከር ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ በጥሞና የተሠራ አንድ እፍኝ ይሻላል።7ከዚያም እንደገና ስለሚበልጠው ከንቱነት፥ ከፀሐይ በታች በይበልጥ ተንኖ ስለሚጠፋው እንፋሎት አሰብሁ። 8ብቻውን የሆነ አንድ ሰው አለ። ወንድ ልጅም ሆነ አባት አንድም የለውም። ለሚሠራው ሁሉ ማለቂያ የለውም፥ ዓይኖቹም ባገኘው ብልጽግና አይረኩም። እርሱም፥ "የምለፋው ለማን ነው? ራሴንስ ከደስታ የማርቀው ለምንድነው?" ብሎ ይደነቃል። ይህ የከፋ ሁኔታ ደግሞም እንፋሎት ነው።9ከአንድ ሰው ይልቅ ሁለቱ የተሻለ ሥራ ይሠራሉ፤ በጋራ ለሥራቸው የተሻለ ገቢ ማግኘት ይችላሉ። 10አንደኛው ቢወድቅ ሌላኛው ጓደኛውን ሊያነሣው ይችላልና። በመሆኑም በወደቀ ጊዜ የሚያነሣው ካልኖረ ብቸኛውን ሰው ሀዘን ይከተለዋል። 11ሁለቱ አብረው ቢተኙ ሊሞቃቸው ይችላል፥ ብቻውን ቢሆን ግን እንዴት ሊሞቀው ይችላል?12አንድ ሰው ብቻውን ሊሸነፍ ይችላል፥ ሁለቱ ግን ጥቃቱን መመከት ይችላሉ። በሦስት የተገመደ ገመድ ቶሎ አይበጠስም።13ማስጠንቀቂያዎችን እንዴት መስማት እንዳለበት ከማያውቅ ሞኝ ሽማግሌ ንጉሥ ይልቅ ድሃ፥ ነገር ግን ጥበበኛ የሆነ ወጣት ይሻላል። 14ወጣቱ ከወህኒ ወጥቶ ቢነግሥ ወይም በሀገሩ በድህነት ተወልዶ ቢያድግም ይህ አውነት ነው።15ይሁንና ከፀሐይ በታች ሕያው የሆነና የሚንቀሳቀሰው ሁሉ ራሳቸውን ንጉሥ ሆኖ ለተነሣው ለሌላው ወጣት ሲያስገዙ አየሁ። 16አዲሱን ንጉሥ መታዘዝ ለሚፈልገው ሕዝብ ሁሉ መጨረሻ የለውም፥ በኋላ ላይ ግን ብዙዎቹ አያመሰግኑትም። በርግጥ ይህ ሁኔታ እንፋሎት፥ ንፋስንም ለማገድ መሞከር ነው።
1ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትሄድበት ጊዜ ጠባይህን ተቆጣጠር። ለመስማት ወደዚያ ሂድ። ሞኞች ክፉ መሥራታቸውን ሳያውቁ ከሚያቀርቡት መሥዋዕት ይልቅ መስማት ይበልጣል።2ለመናገር እጅግ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔር ፊት የትኛውንም ጉዳይ ለማቅረብ ልብህ እጅግ አይፍጠን። እግዚአብሔር በሰማይ ነው፥ አንተ ግን በምድር፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን። 3የምትሠራው ከበዛና ሃሳብ ከሆነብህ፥ ክፉ ህልም ሊገጥምህ ይችላል። ቃልህ ብዙ ሲሆን ብዙ የሞኝነት ነገርም ትናገራለህ።4ለእግዚአብሔር በምትሳልበት ጊዜ ከመፈጸም አትዘግይ፥ እግዚአብሔር በሞኞች ደስ አይለውምና። 5የተሳልከውን ፈጽመው። የተሳሉትን ካለመፈጸም ያለመሳል ይሻላል።6አንደበትህ ሰውነትህን ለኃጢአት እንዲያነሣሣው አትፍቀድለት። ለካህኑ መልዕክተኛ፥ "ያ ስዕለት ስሕተት ነበረ" አትበል። በሐሰት በመሳል እግዚአብሔርን ለምን ታስቆጣዋለህ፥ የእጅህንስ ሥራ እንዲያጠፋ እግዚአብሔርን ለምን ታነሣሣዋለህ? 7በብዙ ሕልም ውስጥ፥ በብዙም ቃል ውስጥ እንፋሎት የሆነ ከንቱነት አለ። ስለዚህ እግዚአብሔርን ፍራ።8በግዛትህ ውስጥ ድሃው ሲበደል፥ ፍትህንና መብቱን ሲነጠቅ በምታይበት ጊዜ፥ ማንም አላወቀም ብለህ አትደነቅ፥ ምክንያቱም ከሥራቸው ያሉትን የሚቆጣጠሩ አለቆች አሉ፥ በእነርሱም ላይ እንኳን የበላይ አለቆች አሉ። 9በአጠቃላይ የምድሪቱ ምርት ለሁሉም ነው፥ ንጉሡ ራሱም ምርቱን ከእርሻ ይወስዳል።10ማንም ብርን የሚወድ በብር አይረካም፥ ማንም ብልጽግናን የሚወድ ሁልጊዜ ተጨማሪውን ይፈልጋል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው። 11ሀብት ሲበዛ በእርሱ የሚጠቀሙ ደግሞ ይበዛሉ። ባለቤቱ በዓይኖቹ ከማየቱ በስተቀር ሀብቱ ምን ይጠቅመዋል?12ብዙም ሆነ ጥቂት ቢበላ፥ የሚሠራ ሰው እንቅልፉ ጣፋጭ ናት፥ የባለጸጋው ሀብት ግን እንቅልፉን ይነሳዋል።13ከፀሐይ በታች ያየሁት እጅግ የከፋ ነገር አለ፡ ይኸውም በባለሌቱ የተከማቸው ሀብት መጥፊያው ሲሆን ነው። 14ባለጸጋው በክፉ አጋጣሚ ሀብቱን በሚያጣበት ጊዜ ለልጁ፥ እርሱ ላሳደገው፥ በእጁ የሚተውለት አይኖረውም።15ሰው ከእናቱ ማኅፀን ራቁቱን እንደ ተወለደ፥ ራቁቱን ደግሞ የምድሩን ሕይወት ይሰናበታል። ከሥራው አንዱን በእጁ መውሰድ አይችልም። 16ሌላው እጅግ ክፉ ነገር፥ ሰው እንደ መጣ እንዲሁ ደግሞ መሄዱ ነው። ስለዚህ ለንፋስ በመሥራት ሰው የሚያገኘው ትርፍ ምንድነው? 17በዘመኑ ሁሉ በጨለማ ይበላል፥ በህመምና በቁጣ በብዙ ይበሳጫል።18ተመልከቱ! እኔ እግዚአብሔር በሰጠን በምድር ሕይወታችን ከፀሐይ በታች በምንደክምበት፥ መልካምና ተስማሚ ሆኖ ያገኘሁት፥ መብላት፥ መጠጣትና ባገኘነው በሥራችን ውጤት ሁሉ መደሰትን ነው። ይህ የሰው ዕድል ፈንታው ነው።19እግዚአብሔር ለማንኛውም ሰው ሀብትንና ባለጸግነትን፥ ድርሻውን የሚያገኝበትን ችሎታና በሥራው መደሰትን መስጠቱ ይህ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው። 20ለመሥራት በሚያስደስተው ነገር እግዚአብሔር ባተሌ ስለሚያደርገው፥ የሕይወት ዘመኑን እምብዛም አያስባቸውም።
1ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም ለሰዎች ከባድ ነው። 2ለራሱ የሚመኘውን አንዳች ላያጣ እግዚአብሔር ሀብትን፥ ባለጠግነትንና ክብርን ይሰጠዋል፥ የሚደሰትበትን ችሎታ ግን አይሰጠውም። ይልቁንም እነዚህን ነገሮች ሌላው ሰው ይጠቀምባቸዋል። ይህ እንፋሎት፥ ክፉ ስቃይም ነው።3ሰው አንድ መቶ ልጆች ቢወልድና ብዙ ዘመን ቢኖር፥ የዕድሜው ዘመን ቢረዝም፥፥ ልቡ ግን በመልካም ነገር ባይረካ፥ በክብርም ባይቀበር፥ ከዚህ ሰው ይልቅ ሞቶ የተወለደ ሕጻን ይሻላል አልሁ። 4እንዲህ ያለው ሕጻን እንኳን በከንቱ ይወለዳል በጨለማም ይሄዳል፥ ስሙም አይታሰብም።5ይህ ሕጸን ፀሐይን ባያይ ወይም ምንም ባያውቅ፥ ያኛው ባይኖረውም ለዚህኛው ዕረፍት አለው። 6ሰው ሁለት ሺህ ዓመት ያህል እንኳን ቢኖር በመልካም ነገሮች ግን መደሰትን ባያውቅ፥ እንደ ሌላው ሁሉ ወደዚያው ስፍራ ይሄዳል።7የሰው ሁሉ ሥራ አፉን ለመሙላት ነው፥ ፍላጎቱ ግን አይሞላም። 8በርግጥ ከሞኙ ይልቅ የጠቢብ ሰው ብልጫው ምንድነው? ድሃ በሌሎች ሰዎች ፊት እንዴት መመላለስ እንዳለበት ቢያውቅ ምን ብልጫ አለው?9በምኞት ከመቅበዝበዝ በዓይን አይቶ መርካት ይሻላል፥ ይህም ደግሞ እንፋሎትና ንፋስን ለማገድ መሞከር ነው። 10ለነበረው ሁሉ ቀደም ሲል ስያሜ ተሰጥቶታል፥ ሰው ምን እንደሚመስልም አስቀድሞ ታውቋል። ስለዚህ በሁሉ ላይ ብርቱ ፈራጅ ከሆነው ጋር መከራከር አይረባም።11የሚነገር ቃል ሲበዛ ከንቱነትም ይበዛል፥ ታዲያ ይህ ለሰው ምን ይጠቅመዋል? 12እንደ ጥላ በሚያልፍበት ከንቱና የተቆጠረ የሕይወት ዘመኑ ለሰው በሕይወቱ መልካም የሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? እርሱ ካለፈ በኋላ ከፀሐይ በታች ምን ሊሆን እንዳለ ማን ሊነግረው ይችላል?
1ከውድ ሽቶ መልካም ስም ይሻላል፥ ከልደት ቀንም የሞት ቀን ይሻላል። 2ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ሀዘን ቤት መሄድ ይሻላል፥ በሕይወቱ መጨረሻ ሰው ሁሉ ሀዘን ይገጥመዋልና፥ ስለዚህ ሕያዋን የሆኑ ሰዎች ይህንን ልብ ማለት አለባቸው።3ከሣቅ ጥልቅ ሐዘን ይሻላል፥ ከፊት ሐዘን በኋላ የልብ ደስታ ይመጣልና። 4የጠቢብ ልቡ ሐዘን ቤት ውስጥ ነው፥ የሞኞች ልብ ግን በግብዣ ቤት ውስጥ ነው።5የሞኞችን መዝሙር ከመስማት የጠቢብን ተግሳጽ መስማት ይሻላል። 6ከድስጥ ሥር የሚነድ እሾህ እንደሚንጣጣ የሞኞች ሣቅ ደግሞ እንደዚሁ ነው። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።7ቀማኛነት ጠቢቡን ሰው ያለጥርጥር ሞኝ ያደርገዋል፥ ጉቦም ልቡን ያበላሸዋል።8የአንድ ነገር መጨረሻ ከጅማሬው ይሻላል፤ በመንፈሳቸው ትዕግስተኞች የሆኑ ሰዎች በመንፈሳቸው ከሚታበዩት ይሻላሉ። 9በመንፈስህ ለመቆጣት አትቸኩል፥ ቁጣ በሞኞች ልብ ያድራልና።10"ከእነዚህ ይልቅ ያለፉት ዘመናት ለምን ተሻሉ?" አትበል፥ ይህንን የምትጠይቀው ጥበበኛ ስለሆንክ አይደለምና።11ጥበብ ከአባቶቻችን የምንወርሳቸውን ጠቃሚ ነገሮች ያህል መልካም ነው። እርሱ ፀሐይን ለሚያዩ ለእነዚያ ትርፍ ያስገኝላቸዋል። 12ገንዘብ ጥበቃ ሊሰጥ እንደሚችል ጥበብም ጥበቃን ይሰጣል፥ የዕውቀት ብልጫው ግን ጥበብ ላገኟት ሕይወት መስጠቷ ነው።13የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት፡ እርሱ ያጣመመውን የትኛውንም ነገር ማን ሊያቃናው ይችላል?14ጊዜው መልካም ሲሆን በደስታ ኑርበት፥ ቀኑ ሲከፋ ግን ይህን አስብ፡ ሁለቱም አጠገብ ለአጠገብ እንዲኖሩ እግዚአብሔር ፈቅዶላቸዋል። በዚህ ምክንያት ማንም ሰው ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን የትኛውንም ነገር አያውቅም።15ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመኔ ብዙ ነገሮችን ተመልክቻለሁ። ጻድቃን ቢሆኑም የሚጠፉ ጻድቅ ሰዎች አሉ፥ ክፋትን ቢያደርጉም ረጅም ዘመን የሚኖሩ አመጸኞችም አሉ። 16ራስህን አታጽድቅ፥ በራስህም ግምት ጠቢብ አትሁን። ለምን ራስህን ታጠፋለህ?17እጅግ አመጸኛ ወይም ሞኝ አትሁን። ለምን ከቀንህ በፊት ትሞታለህ? 18ይህንን ጥበብ ብትይዝ መልካም ነው፥ ጽድቅንም ከማድረግ እጅህን ባትመልስ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ኃላፊነቱን ሁሉ ይወጣልና።19በአንድ ከተማ ውስጥ ካሉ አሥር አስተዳዳሪዎች ይልቅ በጥበበኛ ሰው ውስጥ ያለች ጥበብ ተጽዕኖዋ ትልቅ ነው። 20መልካምን የሚያደርግና ፈጽሞ ኃጢአትን የማይሠራ አንድም ጻድቅ በምድር ላይ የለም።21የሚነገረውን ቃል ሁሉ አታድምጥ፥ ምናልባት አገልጋይህ ሲረግምህ ትሰማው ይሆናልና። 22በተመሳሳይ፥ ሌሎችን በልብህ ብዙ ጊዜ እንደረገምካቸው አንተ ራስህ ታውቃለህ።23ይህንን ሁሉ በጥበብ አረጋገጥሁ። እኔም፥ "ጠቢብ እሆናለሁ" አልሁ፥ እርሱ ግን መሆን ከምችለው በላይ ነው። 24ጥበብ ሩቅና ጥልቅ ናት። ማን ሊያገኛት ይችላል? 25ለመማርና ለመፈተን፥ ጥበብንና የእውነታን ማብራሪያ ለመፈለግና ክፋት የማይረባ፥ ሞኝነትም ዕብደት መሆኑን ለመረዳት ልቤን መለስሁ።26ልቧ በወጥመድና በመረብ የተሞላ፥ እጆቿም የእግር ብረት የሆኑ የትኛዋም ሴት ከሞት ይልቅ መራራ ናት። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ማንም ቢሆን ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛው ግን በእርሷ ይወሰዳል።27"መርምሬ ያገኘሁትን ተመልከቱ" ይላል አስተማሪው። የእውነታን ፍቺ ለማግኘት በአንደኛው ምርምር ላይ ሌላውን እጨምር ነበር። 28እስካሁን የምፈልገው ይህንን ነው፥ ነገር ግን አላገኘሁትም። በሺህ ሰዎች መካከል አንድ ጻድቅ አገኘሁ፥ በእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ሴት አላገኘሁም።29እግዚአብሔር ሰዎችን ቅን አድርጎ እንደ ፈጠራቸው፥ እነርሱ ግን ብዙ ችግሮችን እየፈለጉ ርቀው እንደ ሄዱ ይህንን ብቻ አገኘሁ።
1ጥበበኛ የሆነ ሰው ማን ነው? በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ሁነቶችን ትርጉም የሚያውቅ ማን ነው? በሰው ውስጥ ያለች ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱም ክባዴ ይለወጣል።2እግዚአብሔር ሊጠብቀው ምሎለታልና የንጉሡን ትዕዛዝ እንድትፈጽም እመክርሃለሁ። 3ንጉሡ ደስ ያለውን ያደርጋልና ከፊቱ በችኮላ አትውጣ፥ ትክክል ላልሆነውም ነገር ድጋፍህን አትስጥ። 4የንጉሥ ቃል ይገዛል፥ ስለዚህ፥ "ምን እያደረግህ ነው?" ማን ይለዋል?5የንጉሡን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ጉዳትን ያርቃል። የጠቢብ ልብ የመተግበሪያ ጊዜንና ተገቢ አካሄድን ያስተውላል። 6የሰው መከራው ብዙ ነውና ለእያንዳንዱ ጉዳይ ትክክለኛ ምላሽና ምላሹን የሚሰጥበት ጊዜ አለ። 7ቀጥሎ የሚሆነውን ማንም አያውቅም። ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል?8መተንፈስን ለማቆም በሕይወት እስትንፋስ ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፥ 9ደግሞም በሞቱ ቀን ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም። በጦርነት ጊዜ ከሠራዊቱ የሚሰናበት ማንም የለም፥ አመጻም ባሪያ የሆኑለትን አይታደጋቸውም። ይህንን ሁሉ አስተዋልሁ፤ ከፀሐይ በታች ለሚሠራው ለሁሉም ዓይነት ሥራ ልቤን ሰጠሁ። አንድ ሰው በሌሎች ላይ ክፉ ለማድረግ አቅም የሚያገኝበት ጊዜ አለ።10ስለዚህ አመጸኞች በይፋ ሲቀበሩ አየሁ። ከተቀደሰው አካባቢ ተወስደው ተቀበሩ፥ የአመጽ ሥራቸውን ይሠሩበት የነበረ ከተማ ሰዎችም አመሰገኗቸው። ይህ ደግሞ ከንቱነት ነው። 11በክፉ ወንጀል ላይ ፍርድ ፈጥኖ በማይሰጥበት ጊዜ፥ ክፋትን እንዲያደርጉ የሰው ልጆችን ልብ ያነሣሣል።12አንድ ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፋትን ቢያደርግና ረጅም ዘመን ቢኖር እንኳን እግዚአብሔርን ለሚያከብሩት፥ አብሯቸው መሆኑን ለሚያከብሩ በጎነት እንደሚሆንላቸው አውቃለሁ። 13ለክፉ ሰው ግን በጎነት አይሆንለትም፤ ሕይወቱም አይረዝምም። እግዚአብሔርን አያከብርምና ዘመኑ ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።14በምድር ላይ የተደረገ ሌላ ከንቱ እንፋሎት አለ። በክፉ ሰዎች ላይ የሚደርሰው በጻድቃኑም ላይ ይደርሳል፥ ለጻድቃኑ የሚደርሰውም ለክፉዎች ሰዎችም ይደርሳል። እኔም፥ ይህ ደግሞ ክፉ እንፋሎት ነው አልሁ። 15ለሰው ከፀሐይ በታች ከመብላት፥ መጠጣትና መደሰት የሚሻል ነገር ስለሌለው ደስታ ይሻላል እላለሁ። ከፀሐይ በታች እግዚአብሔር በሰጠው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሚደክምበት ነገር ደስታ አብሮት ይሆናል።16ጥበብን ለማወቅና በምድር ላይ የሚሠራውን ሥራ ለማስተዋል ልቤን በሰጠሁ ጊዜ ብዙ ጊዜ በቀንም ሆነ በሌሊት ያለ እንቅልፍ በሚሠራው ሥራ 17ከዚያም የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ተመለከትሁ ከፀሐይ በታች የሚሠራውን ሥራ ሰው ሊያስተውለው አይችልም። አንድ ሰው መልሶቹን ለማግኘት ምንም ያህል ቢጥር አያገኛቸውም። ጠቢብ ሰው እንድሚያውቅ ቢያምንም እንኳን በርግጥ አያውቅም።
1ስለ ጻድቃንና ስለ ጥበበኛ ሰዎች፥ ስለ ሥራቸውም፥ ስለ እነዚህ ሁሉ ለመገንዘብ በልቤ አሰብሁ። ሁሉም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ናቸው። አንድ ሰው ፍቅር ወይም ጥላቻ ይገጥመው እንደሆነ ማንም አያውቅም።2ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ አለው። ጻድቃንን እና አመጸኞችን፥ መልካምና ክፉ ሰዎችን፥ ንጹሕ የሆኑትንና ያልሆኑትን፥ መሥዋዕት የሚያቀርበውንና የማያቀርበውን ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ይጠብቃቸዋል። መልካም ሰዎች እንደሚሞቱ ኃጢአተኞችም ደግሞ እንዲሁ ናቸው። የሚምለው ሰው እንደሚሞተው ሁሉ ለመማል የሚፈራው ሰውም ይሞታል።3ከፀሐይ በታች ለተደረገው ሁሉ ክፉ ዕጣ ፈንታ አለው፥ ለሁሉም አንድ መጨረሻ። የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፥ በሕይወት እያሉም ዕብደት በልባቸው አለ። ከዚያ በኋላ ወደ ሙታን ይሄዳሉ።4ከሞተ አንበሳ በሕይወት ያለ ውሻ እንደሚሻል በሕይወት ላለ ሰውም አሁንም ተስፋ አለው። 5ሕያዋን ሰዎች እንደሚሞቱ ያውቃሉ፥ ሙታን ግን ምንም አያውቁም። መታሰቢያቸው ተረስቷልና ምንም ብድራት አይኖራቸውም።6ፍቅራቸው፥ ጥላቻቸውና ቅናታቸው ከብዙ ጊዜ በፊት ጠፍቷል። ከፀሐይ በታች በተደረገ በማንኛውም ነገር ዳግም ስፍራ አይኖራቸውም። 7መንገድህን ሂድ፥ ምግብህን በደስታ ተመገብ፥ በደስተኛ ልብ ወይንህን ጠጣ፥ መልካሙን ሥራህን እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። 8ልብሶችህ ሁልጊዜ ነጭ ይሁኑ፥ ራስህንም በዘይት ተቀባ።9ከፀሐይ በታች እግዚአብሔር በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ፥ ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር በደስታ ኑር። ከፀሐይ በታች ለሆነው ሥራህ ይህ ብድራት ነው። እጅህ ለመሥራት የሚያገኘውን ሁሉ በሙሉ ኃይልህ ሥራ፥ 10በምትሄድበት በመቃብር ስፍራ ሥራ ወይም ገለጻ ወይም እውቀት ወይም ጥበብ በዚያ የለምና።11ከፀሐይ በታች አንዳንድ የሚያስደስቱ ነገሮችን አየሁ፡ ሩጫ ለፈጣኖች አይሆንም። ውጊያ ለብርቱ ሰዎች አይሆንም። እንጀራ ለጥበበኞች ሰዎች አይሆንም። ሀብት ለአስተዋይ ሰዎች አይሆንም። ሞገስ እውቀት ላላቸው ሰዎች አይሆንም። ከዚህ ይልቅ ጊዜና ዕድል በሁሉ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል። 12ዓሳ በሚሞትበት መረብ እንደሚጠመድ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚያዙ ማንም ሰው የሚሞትበትን ጊዜ አያውቅም። የሰው ልጆችም ልክ እንደ እንስሳ ድንገት በሚወድቅባቸው ክፉ ጊዜ ይታሰራሉ።13ደግሞም ከፀሐይ በታች ያስገረመኝን ጥበብ አየሁ። 14ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚኖሩባት አንዲት ከተማ ነበረች፥ አንድ ታላቅ ንጉሥ መጣባት፥ ከበባት፥ በዙሪያዋም ታላቅ ምሽግ ገነባባት። 15በከተማው ውስጥ አንድ ድሃ ጠቢብ ሰው ተገኘ፥ በጥበቡም ከተማይቱን አዳነ። በኋላ ላይ ያንን ድሃ ሰው ማንም አላሰበውም።16እኔም፥ "ጥበብ ከኃይል ይሻላል፥ ነገር ግን የድሃው ጥበብ ተንቋል፥ ቃሎቹም አልተሰሙም" ብዬ ደመደምኩ።17በሞኞች መካከል ከሚጮህ ማንኛውም ገዥ ይልቅ በዝግታ የሚነገሩ የጥበበኞች ሰዎች ቃል ይደመጣል። 18ከጦር መሣሪያዎች ጥበብ ትሻላለች፥ ነገር ግን አንድ ኃጢአተኛ ብዙ መልካም ነገሮችን ሊያበላሽ ይችላል።
1የሞቱ ዝንቦች ሽቶን ያገሙታል፥ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብና ክብርን ሊጎዳ ይችላል። 2የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ ያዘነብላል፥ የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራው። 3ሞኝ መንገድ ላይ በሚሄድበት ጊዜ ማስተዋሉ ያነሰ ነው፥ ሞኝነቱን ለሁሉ ያሳውቃል።4አለቃ በቁጣ ቢነሣብህ ሥራህን አትልቀቅ። ትዕግስት ታላቁን ቁጣ ጸጥ ማድረግ ይችላል።5ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ አለ፥ ያም ከገዝ የሚመጣ ስህተት ነው፡ 6ውጤታማ ሰዎች ዝቅተኛ የሥራ መደብ ሲሰጣቸው ሞኞች የመሪነት ሥራ ተሰጣቸው። 7ባሪያዎች በፈረስ ተቀምጠው፥ ስኬታማ ሰዎች አንደ ባሪያ በእግራቸው ሲሄዱ አየሁ።8ጉድጓድ የሚቆፍር በዚያ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል፥ ካብ የሚያፈርሰውንም እባብ ሊነድፈው ይችላል። 9ድንጋዮችን የሚፈነቅል በእነርሱ ሊጎዳ ይችላል፥ ግንድ የሚጠርብም አደጋ ይደርስበታል።10የብረቱ መቁረጫ ጫፉ ቢደንዝና ሰው ባይስለው ብዙ ኃይል ሊያወጣበት የግድ ነው፥ ጥበብ ግን ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ያዘጋጅለታል። 11ድግምቱ ከመደገሙ በፊት እባብ ቢነድፍ ደጋሚው ምንም አይጠቀምም።12ከጠቢብ ሰው አፍ የሚወጣ ቃል ሞገስ አለው፥ የሞኝ ከንፈር ግን ራሱን ያጠፋዋል።13ከሞኝ አፍ ቃል መውጣት ሲጀምር ሞኝነት አብሮ ይወጣል፥ በመጨረሻም ከአፉ ክፉ ዕብደት ይወጣል። 14ሞኝ ቃሉን ያበዛል፥ የሚመጣው ምን እንደሆነ ግን ማንም አያውቅም። ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ያውቃል?15ወደ ከተማ የሚወስደውን መንገድ እንኳን እስከማያውቁ ድረስ ሞኞችን ሥራቸው ያደክማቸዋል።16ንጉሣችሁ ወጣት ከሆነና መሪዎቻችሁም ግብዣቸውን በማለዳ የሚጀምሩ ከሆኑ በዚያች ምድር መከራ ይሆናል። 17ነገር ግን ንጉሣችሁ ከተከበረው ቤተሰብ የተወለደ፥ መሪዎቻችሁ ለመስከር ሳይሆን ለመበርታት በተገቢው ጊዜ ሲመገቡ ምድሪቱ ደስ ይላታል።18በስንፍና ምክንያት ጣሪያ ይዘብጣል፥ በእጅ ሥራ መፍታትም ቤት ያንጠባጥባል። 19ሰዎች ምግብን ለሣቅ ያዘጋጃሉ፥ ወይን ሕይወትን ደስ ያሰኛል፥ ገንዘብም ፍላጎትን ሁሉ ያሟላል።20በልብህም ቢሆን ንጉሡን አትርገመው፥ በመኝታህም ላይ ባለጸጎችን አትርገም። በሰማይ የሚበር ወፍ ቃልህን ይወስድ ይሆናልና ክንፍ ያለውም ሁሉ ጉዳዩን ሊያሰራጨው ይችላል።
1እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፥ ከብዙ ቀናት በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህ። 2ከሰባት እንዲያውም ከስምንት ሰዎች ጋር ተካፈለው፥ በምድር ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና። 3ደመና ዝናብን ከተሞላ በምድር ላይ ይለቀዋል፥ አንድ ዛፍ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት በዚያው ይኖራል።4ማንም ንፋስን የሚጠባበቅ አይተክልም፥ ደመናንም የሚጠብቅ መከሩን አይሰበስብም። 5ንፋስ ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣ፥ እንዲሁም የሕጻኑ አጥንቶች በእናቱ ማኅፀን ውስጥ እንዴት እንደሚያድግ እንደማታውቅ ሁሉን የፈጠረውን የእግዚአብሔር አሠራር ደግሞ ለማወቅ አትችልም።6በጠዋት ዘርህን ዝራ፤ እስከ ምሽትም ድረስ፥ የሚያስፈልገውን ያህል በእጆችህ ሥራ፤ የትኛው እንደሚበቅል፥ የጠዋቱ ወይም የምሽቱ፥ ይህ ወይም ያኛው፥ ወይም ሁለቱም መልካም ይሆኑ እንደኾነ አታውቅምና። 7በእውነት ብርሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሐይን ማየትም ለዓይን የሚያስደስት ነገር ነው። 8ሰው ረጅም ዘመን ቢኖር በእነዚያ ሁሉ ደስ ይበለው፥ ነገር ግን ብዙዎች ናቸውና ሊመጡ ያሉትን ጨለማ ቀናት ያስብ። የሚመጣውም ሁሉ እንደ እንፋሎት ጠፊ ነው።9አንተ ወጣት፥ በወጣትነትህ ደስ ይበልህ፥ በወጣትነትህም ዘመን ልብህን ደስታ ይሙላው። የልብህን መልካም ምኞትና ዓይንህ የሚያየውን ሁሉ ተከተል። ይሁን እንጂ ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ እወቅ። 10ከልብህ ቁጣን አስወግድ፥ የትኛውንም በሰውነትህ ያለውን ሕመም ቸል በለው፥ ወጣትነትና ብርታቱ እንፋሎት ነውና።
1አስቸጋሪዎቹ ቀናት ሳይመጡ፥ "ደስ አያሰኙኝም" የምትላቸው ዓመታትም ሳይደርሱ፥ 2የፀሐይ፥ የጨረቃና የከዋክብት ብርሃን ሳይጨልም፥ የጠቆረው ደመና ከዝናብ ኋላ ሳይመለስ፥ በወጣትነት ዘመንህ ፈጣሪህን አስብ።3ያ ጊዜ የቤተ መንግሥት ጠባቂዎች የሚርበደበዱበት፥ ብርቱዎች የሚጎብጡበት፥ ጥቂቶች በመሆናቸው የሚፈጩት ሥራቸውን የሚያቆሙበት፥ በመስኮት ወደ ውጪ የሚመለከቱ አጥርተው የማያዩበት፥ ይሆናል።4ያ ጊዜ በጎዳናው ላይ በሮች የሚዘጉበትና የወፍጮ ድምጽ የሚቆምበት፥ ከወፍ ድምጽ የተነሣ ሰዎች የሚደነግጡበትና የሚዘምሩ ልጃገረዶች ድምጻቸው ዝግ የሚልበት ይሆናል።5ያ ጊዜ ሰዎች ከፍታዎችንና በመንገድ ላይ የሚገጥማቸውን አደጋ በማሰብ የሚፈሩበት፥ የለውዝ ዛፍ ሲያብብ፥ አንበጣዎች ተከታትለው ሲሳቡ፥ ተፈጥሯዊ ፍላጎት የሚጠፋበት ጊዜ ነው። ሰው ወደ ዘላለም ቤቱ ይሄዳል፥ አልቃሾችም በጎዳናዎቹ ላይ ይወርዳሉ።6የብር ሰንሰለት ሳይበጠስ ወይም ጎድጓዳው የወርቅ ሳሕን ሳይሰበር ወይም እንስራው በምንጩ አጠገብ ብትንትኑ ሳይወጣ ወይም የውሃ ማውጫው ጉድጓዱ ውስጥ ሳይበጠስ፥ 7አፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስና መንፈስም ወደ ሰጪው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።8አስተማሪው፥ "የሚተን እንፋሎት፥ ሁሉም ነገር የሚጠፋ እንፋሎት ነው" ይላል። 9አስተማሪው ጠቢብ ነበር፥ ለሕዝቡም እውቀትን አስተማረ። ብዙ ምሳሌዎችን መረመረና አጠና፥ በስርዓትም አስቀመጣቸው።10አስተማሪው ግልጽና ቅን የእውነት ቃላትን በመጠቀም ለመጻፍ ፈለገ። 11የጠቢባን ቃል አንደ ከብት መንጃ አርጩሜ ነው። ጠልቀው እንደ ገቡ ሚስማሮች አንድ እረኛ ያስተማራቸውና አስተማሪዎች የሰበሰቧቸው ምሳሌዎችም እንዲሁ ናቸው።12ልጄ ሆይ፥ በይበልጥ አንድ ነገር ተጠንቀቅ፡ ብዙ መጻሕፍት መጻፍ ማለቂያ የለውም። ብዙ ማጥናትም ሰውነትን ያደክማል።13ሁሉም ነገር ከተሰማ በኋላ የጉዳዩ መጨረሻ እግዚአብሔርን እንድትፈራውና ትዕዛዙን እንድትጠብቅ ነው፥ ይህ የሰው ሙሉ ተግባሩ ነውና። 14መልካምም ይሁን ክፉ፥ የተደረገውን ሁሉ፥ ከተሰወረው ነገር ሁሉ ጋር፥ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።
1ከመዝሙሮች የሚበልጥ የሰለሞን መዝሙር። ልጃገረዲቱ ፍቅረኛዋን እንዲህ ትለዋለች፥ 2ኦ በአፍህ መሳም በሳምከኝ፥ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይሻላልና። 3ሽቶህ አስደሳች መዓዛ አለው፤ ስምህ እንደሚፈስ ሽቶ ነው፥ ስለዚህ ልጃገረዶች ወደዱህ። 4ካንተ ጋር ውሰደኝ፥ አብረንም እንሮጣለን። ሴቲቱ ለራሷ ትናገራለች፥ ንጉሡ ወደ ቤቱ ውስጥ አስገባኝ። ሴቲቱ ፍቅረኛዋን እንዲህ ስትል ትናገረዋለች፥ ደስ ብሎኛል፤ ስለ አንተ ደስ ይለኛል፤ በፍቅርህ ሐሴት ላድርግ፤ እርሱ ከወይን ጠጅ ይሻላል። ሌሎቹ ሴቶች ቢያደንቁህ ተፈጥሮአዊ ነው5አንደኛዋ ሴት ለሌላይቱ ስትናገር፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ቢሆንም ውብ ነኝ፥ እናንተ ከኢየሩሳሌም ወንዶች የተወለዳችሁ ሴቶች ልጆች፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች ጥቁር፥ እንደ ሰለሞንም መጋረጃዎች ውብ ነኝ። 6ጥቁር ስለ ሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትመልከቱኝ፥ ምክንያቱም ፀሐይ አጥቁሮኛል። የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ተቆጡኝ፥ የወይን አትክልት ጠባቂም አደረጉኝ፥ የራሴን የወይን ቦታ ግን አልጠበቅሁም። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥7ንገረኝ የምወድህ፥ መንጋህን የምታሰማራው የት ነው? በቀትር ጊዜስ መንጋህን የምታሳርፈው የት ነው? ከባልንጀሮችህ መንጋ ኋላ እንደሚቅበዘበዝ ሰው ለምን እሆናለሁ? ፍቅረኛዋ ሲመልስላት፥8ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽው ሆይ፥ አታውቂ እንደሆነ፥ የመንጋዬን ኮቴ ተከተይ፥ የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።9የኔ ፍቅር፥ በፈርዖን የሰረገላ ፈረሶች መካከል ካለችው ባዝራ ጋር አመሳሰልሁሽ። 10ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፥ አንገትሽም በዕንቁ ሐብል። 11የብር ፈርጥ ያለበት የወርቅ ማጌጫ እሠራልሻለሁ። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥12ንጉሥ ማዕዱ ላይ እያለ፥ የናርዶስ ሽቶዬ መዓዛውን ናኘው። 13ውዴ ለእኔ ልክ ሌሊቱን ሙሉ በጡቶቼ መካከል እንደሚያርፍ እንደ ተቋጠረ ከርቤ ነው። 14ውዴ ለእኔ በዓይንጋዲ የወይን ቦታ ውስጥ እንደ ሂና የአበባ ዕቅፍ ነው። ፍቅረኛዋ ሲናገራት፥15ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ አንቺ ውብ ነሽ፤ እነሆ ያማርሽ ነሽ፤ ዓይኖችሽ እርግቦችን ይመስላሉ። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥16ውዴ ሆይ፥ እነሆ አንተ መልከ መልካም ነህ፥ ያማርክም ነህ። የለመለመው ሣር እንደ አልጋ ያገለግለናል። 17የቤታችን የማዕዘን ተሸካሚ የዝግባ እንጨት፥ የጣሪያችን ማዋቀሪያም የጥድ እንጨት ነው።
1እኔ በሜዳ የሚገኝ አበባ፥ በሸለቆም የሚገኝ አበባ ብቻ ነኝ። ሰውየው ሲናገራት፥ 2ውዴ ሆይ፥ አበባ በእሾህ መካከል እንደሆነ አንቺም በሀገሬ ሴቶች ልጆች መካከል ነሽ። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥3በዱር ዛፍ መካከል እንዳለ የእንኮይ ዛፍ የእኔም ውድ በጎልማሶች መካከል ነው። በታላቅ ደስታ ከጥላው ሥር ተቀመጥኩ፥ የፍሬውም ጣዕም ጣፋጭ ነው። 4ወደ ግብዣው አዳራሽ አመጣኝ፥ በእኔ ላይ ያለው ሰንደቁ ፍቅር ነው። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥5በዘቢብ ጥፍጥፍ ነፍስ ዝሩብኝ፥ በእንኮይ ጭማቂም አበርቱኝ፥ በፍቅር ተይዤ ደክሜአለሁና። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥ 6ግራ እጁ ከአንገቴ ሥር ነው፥ ቀኝ እጁም ያቅፈኛል። ሴቲቱ ለሌላዋ ሴት ስትናገር፥7የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች፥ በፍቅር ግንኙነታችን ወቅት እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን በሜዳ ፍየሎችና በአጋዘኖች ቃል እንድትገቡልኝ እፈልጋለሁ። ሴቲቱ ለራሷ ትናገራለች፥8የውዴ ድምጽ ነው! ኦ፥ በተራራዎች ላይ እየዘለለ፥ በኮረብታዎች ላይ እየተስፈነጠረ ሲመጣ ይታወቀኛል። 9ውዴ የሜዳን ፍየል ወይም ግልገል አጋዘንን ይመስላል፤ እነሆ እርሱ ከቤታችን ግድግዳ በስተኋላ ቆሟል፥ በመስኮቱ በኩል አተኩሮ፥ በፍርግርጉም አጮልቆ ይመለከታል።10ውዴ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ "ውዴ ሆይ ተነሽ፤ የኔዋ ቆንጆ ከእኔ ጋር ነይ። 11ተመልከች፥ ክረምቱ አልፏል፥ ዝናቡም ቆሟል፥ ሄዷልም።12አበቦች በምድር ላይ ታይተዋል፤ ወይን የሚገረዝበትና የወፎች ዝማሬ ጊዜ ደርሶአል፥ የእርግቦችም ድምጽ በምድራችን ተሰምቷል። 13የበለስ ዛፍ አረንጓዴ ፍሬዎቿ በስለዋል፥ ወይኖቹም አብበዋል፥ መዓዛቸውንም ሰጥተዋል። ውዴ ሆይ ተነሽ፥ የኔዋ ቆንጆ ነይ።14በዐለት ሥንጣቂ ውስጥ፥ በድብቁ የተራራማው ቋጢኝ ስንጣቂ ውስጥ ያለሽ እርግቤ ሆይ፥ ፊትሽን ልየው። ድምጽሽን ልስማው፥ ድምጽሽ ጣፋጭ ነውና ፊትሽም ውብ ነው።" ሴቲቱ ለራሷ ስትናገር፥15የወይናችን ቦታ አብቦአልና የወይን ቦታዎችን የሚያበላሹትን ትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን።16ውዴ የእኔ ነው፥ እኔም የእርሱ ነኝ፤ እርሱ መንጋውን በአበቦቹ መካከል በደስታ ያሰማራል። 17ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥ ውዴ ሆይ፥ ተመለስ፣ የንጋቱ ቀዝቃዛ ንፋስ ሳይነፍስ፥ ጥላውም ሳይሸሽ። ተመለስ፤ በጎርበጥባጣዎቹ ኮረብቶች ላይ የሜዳ ፍየልን ወይም ግልገል አጋዘንን ምሰል።
1ሌሊት በመኝታዬ የምወደውን ናፈቅሁት፤ ፈለግሁት፥ ነገር ግን ላገኘው አልቻልኩም። 2እኔም ለራሴ፥ "እነሣለሁ፥ ወደ ከተማው ውስጥ፥ ወደ ጎዳናዎቹና ወደ አደባባዮቹ እሄዳለሁ፤ ውዴንም እፈልገዋለሁ" አልኩ። ፈለግሁት፥ ላገኘው ግን አልቻልኩም።3ጠባቂዎች በከተማው ውስጥ ለጥበቃ ሲዘዋወሩ አገኙኝ። እኔም፥ "ውዴን አይታችሁታል?" ብዬ ጠየቅኋቸው። 4ከእነርሱ ጥቂት እልፍ እንዳልኩኝ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት። ያዝኩት፥ ወደ እናቴ ቤት፥ ወደ ፀነሰችኝም መኝታ ቤት እስካመጣው ድረስ አልለቀውም። ሴቲቱ ለሌላይቱ ሴት ስትናገር፥5እናንተ የኢየሩሳሌም ሰዎች ሴቶች ልጆች፥ በፍቅር ግንኙነታችን እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን በሜዳ ፍየሎችና አጋዘኖች እንድትምሉልኝ እፈልጋለሁ። ወጣቷ ሴት ለራሷ ስትናገር፥6ይህቺ በዕጣንና ከርቤ፥ ነጋዴዎችም በሚሸጡት ልዩ ልዩ ቅመም በተቀመመ ሽቶ ተቀብታ እንደ ጢስ ምሶሶ ከምድረ በዳ የምትወጣ ማናት? 7እነሆ እርሱ የሰለሞን ተንቀሳቃሽ አልጋ ነው፤ ስልሳ የእስራኤል ወታደሮች፥ ስልሳ ጦረኞች ከብበውታል።8እነርሱ በሰይፍ የላቁ ናቸው፥ በጦርነትም የታወቁ። እያንዳንዱ በወገቡ ሰይፍ አለው፥ በሌሊት የሚያሸብሩትን ለመከላከል ታጥቀዋል። 9ንጉሥ ሰለሞን ከሊባኖስ በመጣ እንጨት ሰው ተቀምጦበት የሚሸከሙትን [ለአንድ ሰው መቀመጫ የሚሆን ወንበር የሚይዝ] ሳጥን ለራሱ ሠራ።10ምሶሶዎቹን ከብር፥ ጀርባው ከወርቅ፥ መቀመጫው ከሐምራዊ ጨርቅ ተደርጎ ተሠራ። ውስጡ የተዋበው በኢየሩሳሌም ሰዎች ሴቶች ልጆች ነበር። ወጣቷ ለኢየሩሳሌም ሴቶች ስትናገር፥ 11የጽዮን ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ሂዱ ውጡ፥ ንጉሥ ሰለሞንን ትኩር ብላችሁ እዩት፥ በሕይወቱ በተደሰተባት በዚያች ቀን፥ በሠርጉ ቀን እናቱ የደፋችለትን አክሊል ጭኖ።
1ኦ፥ ወዳጄ ሆይ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥ እነሆም ቆንጆ ነሽ። በመሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እርግቦች ናቸው። ጸጉርሽ ከገለዓድ ተራራ ቁልቁል የሚወርደውን የፍየል መንጋ ይመስላል።2ጥርስሽ በቅርቡ ተሸልቶ ከመታጠቢያው ሥፍራ የሚወጣውን የበግ መንጋ ይመስላል። እያንዳንዱ መንታ ወልዷል፥ በመካከላቸውም መካን የለም።3ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤ አፍሽ ውብ ነው። ጉንጮችሽ በመሸፈኛሽ ውስጥ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላል።4አንገትሽ በረድፍ በተደረደሩ ድንጋዮች ላይ የተገነባውን የዳዊትን የጥበቃ ማማ ይመስላል፥ አንድ ሺህ ጋሻ፥ የወታደሮቹ ሁሉ ጋሻ በእርሱ ላይ ተሰቅሏል። 5ሁለቱ ጡቶችሽ በአበቦች መካከል የተሰማሩ ሁለት የአጋዘን ግልገሎችን፥ መንታም የተወለዱ የሜዳ ፍየሎችን ይመስላሉ።6ጎሕ እስኪቀድና ጥላው እስኪሸሽ ድረስ፥ ወደ ከርቤው ተራራ፥ ወደ ዕጣኑም ኮረብታ እሄዳለሁ። 7ውዴ ሆይ፥ ሁለመናሽ ውብ ነው፥ እንከንም የለብሽም።8ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ። አዎን፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፥ ከአማና ጫፍ፥ ከሳኔርና ከኤርሞን ጫፍ፥ ከአንበሶች ዋሻ፥ የነብሮች ዋሻ ከሆነውም ተራራ ነይ።9እህቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ልቤን ሰርቀሽዋል፤ በአንድ አፍታ ዕይታሽ ብቻ፥ በአንድ ሐብልሽ ብቻ ልቤን ሰርቀሽዋል።10እህቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት ያማረ ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ ይሻላል፥ የሽቶሽ መዓዛም ከቅመሞች ሁሉ። 11ሙሽራዬ ሆይ፥ ከንፈሮችሽ ማር ያንጠባጥባሉ፥ ማርና ወተት ምላስሽ ሥር ናቸው። የልብሶችሽ መዓዛ የሊባኖስን መዓዛ ይመስላል።12እህቴ ሙሽራዬ የተቆለፈበት የመናፈሻ ቦታ ናት፥ የተቆለፈበት የመናፈሻ ቦታ፥ የታተመበትም ምንጭ። 13ቅርንጫፎችሽ የሮማን ዛፍ ከተመረጠ ፍሬ ጋር፥ ሂናና የናርዶስ ተክል፥ 14ናርዶስና ቀጋ፥ ጠጅ ሣርና ቀረፋ ከልዩ ልዩ ቅመሞች ጋር፥ ከርቤና እሬት ምርጥ ከሆኑት ቅመሞች ሁሉ ጋር አሉባቸው።15አንቺ የአትክልት ሥፍራ ምንጭ፥ የንጹህ ውሃ ጉድጓድ፥ ከሊባኖስ ወደ ታች የሚወርድ ምንጭ ነሽ። ወጣቷ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥ 16የሰሜን ንፋስ ሆይ ንቃ፤ የደቡቡም ንፋስ ና፤ ቅመሞቹ መዓዛቸውን እንዲሰጡ በአትክልት ሥፍራዬ ላይ ንፈስ። ውዴ ወደ አትክልቱ ሥፍራ ይምጣ፥ ከምርጡም ፍሬ ጥቂት ይብላ።
1እህቴ፥ ሙሽራዬ፥ ወደ አትክልቴ ቦታ መጣሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ሰብስቤአለሁ። የማር እንጀራዬን ከወለላው ጋር በልቻለሁ፤ ወይኔን ከወተቴ ጋር ጠጥቻለሁ። ጓደኞች ለአፍቃሪዎች ሲናገሩ፥ ጓደኞቻችን ሆይ ብሉ፤ ጠጡ፥ በፍቅርም ስከሩ። ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥2እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን በሕልም ነቅቷል። የውዴ ድምጽ ነው፥ በሩን ያንኳኳል፥ "እህቴ፥ ውዴ፥ እርግቤ፥ እንከን የሌለብሽ ሆይ፥ ራሴ በጤዛ ርሷል ፀጉሬም በሌሊቱ እርጥበት፥ ስለዚህ ክፈችልኝ" እያለ።3"ልብሴን አውልቄአለሁ፤ እንደገና መልበስ አለብኝ? እግሬን ታጥቤአለሁ፤ ማቆሸሽ አለብኝ?" 4ውዴ በበሩ መካፈቻ ቀዳዳ በኩል እጁን አስገባ፥ ልቤም ስለ እርሱ ታወከ።5ለውዴ በሩን ልከፍትለት ተነሣሁ፥ እጆቼ ከርቤን አንጠባጠቡ፥ ጣቶቼ በበሩ እጀታ ላይ በከርቤ ረጠቡ።6ለውዴ በሩን ከፈትኩለት፥ ውዴ ግን ተመልሶ ሄዶ ነበር። ልቤ ደነገጠ፤ እኔም ተከፋሁ። ፈለግሁት፥ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም።7ጠባቂዎቹ በከተማ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤ መቱኝ፥ አቆሰሉኝም፤ በቅጥሩ ላይ ያሉት ጠባቂዎችም ካባዬን ወሰዱብኝ። ወጣቷ ለከተማው ሴቶች ስትናገር፥8እናንተ የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች፥ ውዴን ካገኛችሁት ለእርሱ ካለኝ ፍቅር የተነሣ መታመሜን ልትነግሩት ቃል እንድትገቡልኝ እፈልጋለሁ። የከተማው ሴቶች ለወጣቷ ሲናገሩ፥9አንቺ በሴቶች መካከል የተዋብሽዋ ሆይ፥ ውድሽ ከሌላው አፍቃሪ ወንድ የተሻለው እንዴት ነው? እንዲህ ያለውን መሐላ እንድናደርግ የጠየቅሽን ውድሽ ከሌላው አፍቃሪ የተሻለው ለምንድነው? ወጣቷ ለከተማው ሴቶች ስትናገር፥10ውዴ ደስተኛና ቀይ ነው፥ ከአሥር ሺዎችም የላቀ ነው። 11ራሱ ንጹህ ወርቅ ነው፤ ፀጉሩም ዞማና እንደ ቁራ የጠቆረ ነው።12ዓይኖቹ በጅረት አጠገብ እንዳሉ እርግቦች፥ በወተት እንደ ታጠቡ፥ በማስቀመጫቸው ያሉ ዕንቁዎችን ይመስላሉ።13ጉንጮቹ የሽቶ መዓዛ የሚሰጡ የልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም መደብ ይመስላሉ። ከንፈሮቹ ከርቤን የሚያንጠባጥቡ አበቦች ናቸው።14ክንዶቹ የዕንቁ ፈርጥ ባለበት ወርቅ ተሸፍኗል፤ ሆዱ በሰንፔር ያጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው።15እግሮቹ በንጹህ የወርቅ መሠረት ላይ የቆሙ፥ የእምነ በረድ ምሶሶዎች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባኖስ፥ እንደ ተመረጠም ዝግባ ነው።16አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፤ እርሱ ፍጹም ውብ ነው። የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ጓደኛዬም እርሱው ነው።
1በሴቶች መካከል እጅግ የተዋብሽዋ ሆይ፥ ውድሽ ወዴት ሄደ? ካንቺ ጋር እንድንፈልገው ውድሽ የሄደው በየትኛው አቅጣጫ ነው? ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥2በአትክልቱ ሥፍራ መንጋውን ሊያሠማራ፥ አበቦችንም ሊሰበስብ፥ ውዴ ወደ አትክልቱ ሥፍራ፥ ወደ ቅመማ ቅመሞቹ መደቦች ወርዷል። 3እኔ የውዴ ነኝ፥ ውዴም የእኔ ነው፤ በአበቦቹ መካከል መንጋውን በደስታ ያሰማራል። የሴቲቱ አፍቃሪ እንዲህ ይላታል፥4ውዴ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ቆንጆ ነሽ፥ እንደ ኢየሩሳሌም ውብ ነሽ፥ ሰንደቁን እንደያዘ ሠራዊት ታስፈሪያለሽ።5አድክመውኛልና ዓይኖችሽን ከእኔ መልሺ። ፀጉርሽ ከገለዓድ ተራራ ቁልቁል የሚወርደውን የፍየል መንጋ ይመስላል።6ጥርሶችሽ ከመታጠቢያ ሥፍራቸው የሚመጡትን የሴት በግ መንጋ ይመስላሉ። እያንዳንዱ መንታ ወልዷል፥ በመካከላቸውም መካን የለም። 7በመሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጮችሽ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። የሴቲቱ አፍቃሪ ለራሱ ሲናገር፥8ስልሳ ንግሥቶች፥ ሰማንያ ቁባቶች፥ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ልጃገረዶች አሉ። 9እርግቤ፥ እንከን የሌለባት፥ ብቸኛዋ ናት፤ ለእናቷ ልዩ ልጅ፥ ለወለደቻት ሴትም የተመረጠች ነች። የሀገሬ ሴቶች ልጆች አይተው የተባረክሽ ነሽ አሏት፤ ንግሥቶችና ቁባቶችም ደግሞ አይተው አመሰገኗት፤ ንግሥቶቹና ቁባቶቹ እንዲህ አሏት፦10የንጋት ብርሃን መስላ የምትወጣ፥ እንደ ጨረቃ ያማረች፥ እንደ ፀሐይ ያበራች፥ ሰንደቅ እንደ ያዘ ሠራዊት የምታስፈራ ይህቺ ማን ናት? የሴቲቱ አፍቃሪ ለራሱ ሲናገር፥11በሸለቆው ውስጥ አዲስ የበቀለውን ለማየት፥ ወይኑ አፍርቶ እንደሆነ፥ ሮማኑም አብቦ እንደሆነ ለማየት፥ የለውዝ ተክል ወዳለበት ጥሻ ወረድሁ። 12በልዑሉ ሠረገላ እንደ ተቀመጥኩ ስለ ተሰማኝ፥ በጣም ደስ አለኝ። የሴቲቱ አፍቃሪ እንዲህ ይላል፥13አንቺ ፍጹሟ ሴት፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ አተኩሬ እንዳይሽ ተመለሽ፥ እባክሽ ተመለሽ። ወጣቷ ሴት ፍቅረኛዋን እንዲህ ትለዋለች፥ በሁለት ረድፍ ጨፋሪዎች መካከል የምጨፍር ይመስል፥ ፍጹሟን ሴት ለምን ትክ ብለህ ታየኛለህ?
1አንቺ የልዑል ልጅ! እግሮችሽ በነጠላ ጫማ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ? የዳሌዎችሽ ቅርጽ በእውቅ አንጥረኛ እጅ የተሠሩ ዕንቁዎችን ይመስላሉ።2እንብርትሽ ክብ ጽዋ ይመስላል፤ ድብልቅ ወይን በፍጹም አይጉደለው። ሆድሽ በአበቦች የተከበበ የስንዴ ክምር ይመስላል።3ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ የሜዳ ፍየሎችን፥ ሁለት የአጋዘን ግልገሎችን ይመስላሉ። 4አንገትሽ በዝሆን ጥርስ የተሠራ የጥበቃ ማማ ይመስላል፤ ዓይኖችሽ በባትረቢ በር አጠገብ በሐሴቦን ያሉትን ኩሬዎች ይመስላሉ። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ የሚመለከተውን በሊባኖስ ያለውን የመጠበቂያ ማማ ይመስላል።5ራስሽ በአንቺ ላይ የቀርሜሎስን ተራራ ይመስላል፤ በራስሽ ላይ ያለው ጸጉር ጥቁር ሐምራዊ ነው። ንጉሡ በረጅሙ ጸጉርሽ ተይዞ ታስሮአል። 6ተወዳጇ ሆይ፥ እንዴት የምታስደስቺ፥ ውብና ያማርሽ ነሽ!7ቁመትሽ የቴምር ዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም እንደ ተከማቹ ፍሬዎች ናቸው። 8እኔም፥ "በዚያ የዘንባባ ዛፍ ላይ እወጣለሁ፤ ቅርንጫፎቹንም እይዛለሁ" ብዬ አሰብኩ። ጡቶችሽ የወይን ክምችቶች ይሁኑ፥ የአፍንጫሽ እስትንፋስ መዓዛውም እንደ እንኮይ ይሁኑ።9አፍሽ እንደ ምርጥ የወይን ጠጅ ይሁን፥ በዝግታም በውዴ ከንፈርና ጥርስ እየፈሰሱ ይንቆርቆሩ። ወጣቷ ፍቅረኛዋን እንዲህ ትለዋለች፥10እኔ የውዴ ነኝ፥ እርሱም ይመኘኛል። 11ውዴ ሆይ ና፥ ወደ ገጠር እንሂድ፥ በመንደሮቹም እንደር።12ወደ ወይኑ ቦታ ለመሄድ ማልደን እንነሣ፤ ወይናቸው አፍርቶ፥ አበባቸውም ፈክቶ፥ ሮማኑም አብቦ እንደሆነ እንይ። በዚያም ፍቅሬን እሰጥሃለሁ።13ትርንጉዎች መዓዛቸውን ሰጡ፤ በምንቆይበት ቤት ደጃፍ ሁሉም ዓይነት የተመረጡ ፍሬዎች አሉ፥ አዲስና የቆዩ፥ ውዴ ሆይ፥ ለአንተ አስቀምጫቸዋለሁ።
1ምነው የእናቴን ጡቶች እንደጠባ እንደ ወንድሜ በሆንክ። ከዚያም በውጭ ባገኘሁህ ጊዜ ሁሉ በሳምኩህና፥ ማንም ባልናቀኝ ነበር።2በመራሁህና ወደ እናቴ ቤት ባመጣሁህ፥ አንተም ባስተማርከኝ ነበር። የምትጠጣውን ጣፋጭ ወይን ጠጅ በሰጠሁህ፥ ከሮማኖቼም ጭማቂ ጥቂቱን። 3ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥ ግራ እጁ ይዞኛል፤ ቀኝ እጁም አቅፎኛል። ሴቲቱ ለሌሎች ሴቶች ስትናገር፥4የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፥ በፍቅር ግንኙነታችን ጊዜ እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን እንድትምሉልኝ እፈልጋለሁ። የኢየሩሳሌም ሴቶች ሲናገሩ፥5በውዷ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምትመጣ ይህቺ ማን ናት? ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥ ከእንኮዩ ዛፍ ጥላ ሥር አነቃሁህ፤ በዚያ እናትህ ፀነሰችህ፤ በዚያም አንተን ወለደችህ፤ ተገላገለችህ።6በልብህ ላይ እንደ ማኅተም አስቀምጠኝ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ ላይ፥ ፍቅር እንደ ሞት ብርቱ ነውና። የታማኝነቷም ጠንካራ ስሜት እንደ ሲዖል ጨካኝ ነው፤ ነበልባሏ ይነዳል፤ የምትንቦገቦግ ነበልባል ናት፥ ነበልባሏ ከሌላ ከየትኛውም እሳት ይልቅ የጋለ ነው።7የማዕበል ውሃ ፍቅርን ለማጥፋት አይችልም፥ ጎርፍም ሊያሰጥመው አይችልም። ሰው በቤቱ ያለውን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ብሎ ቢሰጥ ስጦታው ፈጽሞ ይናቃል። የወጣቷ ወንድሞች እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፥8ታናሽ እህት አለችን፥ ጡቶቿም ገና አላደጉም። ለጋብቻ በምትሰጥበት በዚያን ቀን ለእህታችን ምን ልናደርግላት እንችላለን?9እርሷ ቅጥር ብትሆን፥ በላይዋ ላይ የጥበቃ ማማ እንሠራባታለን። በር ብትሆን በዝግባ ሳንቃ እናስውባታለን። ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥10እኔ ቅጥር ነኝ፥ አሁን ግን ጡቶቼ እንደ ተመሸጉ ግንቦች ናቸው፤ ስለዚህ በዓይኖቹ ፊት በሚገባ አድጌአለሁ። ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥11ሰለሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፤ እርሱም የወይኑን ቦታ ለሚንከባከቡት አከራየው። እያንዳንዱ ስለ ፍሬው አንድ አንድ ሺህ ሰቅል ብር ያመጣለት ነበር። 12የእኔ የወይን ቦታ የእኔው የግሌ ነው፤ ወዳጄ ሰለሞን ሆይ፥ አንድ ሺህ ሰቅሉ ያንተ ይሆናል፥ ሁለት መቶ ሰቅሉ ፍሬውን ለሚንከባከቡት ነው። የሴቲቱ አፍቃሪ ሲናገራት፥13በአትክልቱ ቦታ የምትኖሪ ሆይ፥ ጓደኞቼ ድምጽሽን እየሰሙት ነው፤ እኔም ከሚሰሙት አንዱ ልሁን። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥14ውዴ ሆይ፥ ፍጠን፤ በቅመማ ቅመም ተራራዎች ላይ የአጋዘንን ወይም የሜዳ ፍየል ግልገልን ምሰል።
1የይሁዳ ነገሥታት በሆኑት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ።2ስሙ፣ ምድርም አድምጪ፤ "ልጆችን ወለድሁ አሳደግሁም፣ እነርሱም አመጹብኝ።" ሲል እግዚአብሔር ተናግሮአልና። 3በሬ የገዢውን፣ አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቀም፥ እስራኤል አልተገነዘበም"4ወዮላችሁ! ኃጢአተኛ ወገንና በደል የተሞላበት ሕዝብ፣ የክፉ አድራጊዎች ልጆች፣ ርኵሰትን የምታደርጉ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔርን ትተዋል፣ የእስራኤልንም ቅዱስ አቃልለዋል ወደ ኋላቸውም እየሄዱ ተለይተዋል።5አሁን ድረስ ለምን ትቀሰፋላችሁ? አሁንም አሁንም ዓመፃ ለምን ትጨምራላችሁ? ራስ ሁሉ ለሕመም፣ ልብም ሁሉ ለድካም ሆኗል።6ከእግር መርገጫ አንስቶ እስከ ራስ ድረስ ያልታመመ የለውም፤ ቍስልና እበጥ፣ የሚደማ ቊስል ነው፤ አልፈረጠም፣ አልተጠገነም፣ በዘይትም አልለዘበም።7ምድራችሁ ባድማ ናት፤ ከተሞቻችሁ በእሳት ተቃጠሉ፤ እርሻችሁንም በፊታችሁ እንግዶች ይበሉታል፤ ባዕድ እንዳፈረሳት ምድር ባድማ ሆነች።8የጽዮንም ሴት ልጅ በወይን ቦታ እንዳለ ዳስ፣ በዱባ አትክልትም እንዳለ ጎጆ፣ እንደተከበበችም ከተማ ሆና ቀረች።9የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጥቂት ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆንን፣ እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር።10የሰዶም አለቆች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፣ የአምላካችንን ሕግ አድምጡ። 11"የመሥዋዕታችሁ ብዙ ጋጋታ ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?" ይላል እግዚአብሔር። "የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤያለሁ፤ የበሬና የበግ ጠቦት የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም።12በእኔ ፊት ልትታዩ ብትመጡ፣ ይህን የመቅደሴን አደባባይ መርገጣችሁን ከእጃችሁ የሚሻ ማን ነው?13ምናምንቴውን ቍርባን ጨምራችሁ አታምጡ፤ ዕጣን በእኔ ዘንድ አጸያፊ ነው፤ መባቻችሁንና ሰንበታችሁን በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወድድም - እነዚህን የረከሱ ጉባዔዎች አልታገሥም።14መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፥ ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ።15ስለዚህም እጃችሁን በጸሎት ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፣ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል።16ታጠቡ፣ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ መሆንን ተዉ፤17መልካም ማድረግን ተማሩ፣ ፍርድን ፈልጉ፣ የተጨቆነውን እርዱ፣ አባት ለሌለው ፍረዱለት፣ ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።"18"አሁን ኑና በአንድ ላይ እንዋቀስ" ይላል እግዚአብሔር፤ "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን፣ እንደ በረዶ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ፣ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።19እሺ ብትሉ ብትታዘዙ፣ የምድርን በረከት ትበላላችሁ።20ነገር ግን እምቢ ብትሉ፣ ብታምፁም፣ ሰይፍ ይበላችኋል፣" የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።21ፍርድ ሞልቶባት የነበረችው የታመነችይቱ ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ ሞልቶባት ነበር፣ አሁን ግን ገዳዮች ሞልተውባታል።22ብርሽ ወደ ዝገት ተለወጠ፣ የወይን ጠጅሽ ከውሃ ጋር ተደባለቀ።23አለቆችሽ አመጸኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፣ ዋጋም ለማግኘትም ይሮጣሉ። ለድሀ አደጉ አይፈርዱም፣ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም።24ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወዮላቸው! የሚቋቋሙኝ ላይ ቍጣዬን እፈጽማለሁ፣ በጠላቶቼ ላይ እበቀላለሁ።25እጄንም በአንቺ ላይ አመጣለሁ፣ ዝገትሽንም በጣም አነጻለሁ፣ አለመንጻትሽንም ሁሉ አወጣለሁ፤26ፈራጆችሽንም እንደ ቀድሞ፣ አማካሪዎችሽንም እንደ መጀመሪያው ጊዜ መልሼ አስነሣለሁ፤ ከዚያም በኋላ የጽድቅ ከተማ፣ የታመነችም ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።"27ጽዮን በፍርድ፣ ከእርሷም በንስሃ የሚመለሱ በጽድቅ ይድናሉ።28በደለኞችና ኃጢአተኞች ግን በአንድነት ይሰበራሉ፣ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ።29"በተመኛችኋት የተቀደሰች የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፣ በመረጣችኋትም አትክልት ስፍራ ላይ እፍረት ይይዛችኋልና፤30ቅጠልዋ እንደ ረገፈ ዛፍ፣ ውሃም እንደሌለባት አትክልት ትሆናላችሁና።31ኃይለኛውም እንደ ተልባ ጭረት፣ ሥራውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ አብረውም ይቃጠላሉ፣ እነርሱንም የሚያጠፋ የለም።"
1የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ ያያቸው ነገሮች።2በኋለኞቹ የፍጻሜ ቀናት፣ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ከፍታ ላይ ጸንቶ ይቆማል፣ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይጎርፋሉ።3ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፣ "ኑ፣ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ።"4በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፣ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፣ ጦርነትንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።5እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ፣ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ።6የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፣ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፣ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ፣ የሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃል።7ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፣ ለመዛግብቶቻቸውም ፍጻሜ የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፣ ለሠረገሎቻቸውም ፍጻሜ የለውም።8ምድራቸው ደግሞ በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸውም ላደረጉት ለእጃቸው ሥራ ይሰግዳሉ።9ታናሹም ሰው ዝቅ ብሎአል፣ ግለሰቦችም ይዋረዳሉ፤ ስለዚህ አትቀበላቸው።10ከእግዚአብሔር ማሸበርና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግቡ፣ በመሬትም ውስጥ ተሸሸጉ።11ከፍ ያለችውም የሰው ዓይን ትዋረዳለች፣ የሰዎችም ኵራት ተጎትታ ትወድቃለች፣ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ይላል።12የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፣ እርሱም ይዋረዳል፤13ደግሞም በረጅሙ ከፍ ባለው በሊባኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፣ በባሳንም ዛፍ ሁሉ ላይ ይሆናል፣14በረጅሞቹም ተራራዎች ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ኮረብቶች ሁሉ ላይ፣15በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፣ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፣16በተርሴስም መርከቦች ሁሉ ላይ፣ በሚያማምሩ ጣዖታትም ሁሉ ላይ ይሆናል።17የሰው ሁሉ ክብር ይዋረዳል፣ የሰውም ኵራት ይወድቃል፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።18ጣዖቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ።19እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ፣ ሰዎችን ከማስደንገጡና ከግርማው ክብሩ የተነሣ፣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ይገባሉ።20በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላሉ።21እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ይገባሉ።22እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፣ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል?
1ተመልከቱ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፍንና ብርታትን፡ የእንጀራን ድጋፍ ሁሉ የውኃውንም ድጋፍ ሁሉ ይወስዳል፤2ኃያሉንም፣ ተዋጊውንም፣ ፈራጁንም፣ ነቢዩንም፣ ምዋርተኛውንም፣ ሽማግሌውንም፤3የአምሳ አለቃውንም፣ ከበርቴ የሆነውን ዜጋ፣ አማካሪውንም፣ የብልኃት ሠራተኛውንም፣ አስማት አዋቂውንም ይነቅላል።4"አለቆቻቸው እንዲሆኑ ተራ ወጣቶችን አስነሣባቸዋለሁ፣ ብላቴናውም ይገዛቸዋል።5ሕዝቡም ይጨቆናሉ፣ ሰው በሰው ላይ፣ ሰውም በባልንጀራው ላይ ይገፋፋል፤ ብላቴናውም በሽማግሌው ላይ የተጠቃውም በከበርቴው ላይ ይኰራል።6ሰውም በአባቱ ቤት ውስጥ ወንድሙን ይዞ፣ 'አንተ ልብስ አለህ፤ አለቃም ሁንልን፣ ይህችም ባድማ ከኃላፊነትህ በታች ትሁን' ይለዋል።7በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ይላል፣ 'እኔ በቤቴ ውስጥ እንጀራ ወይም ልብስ የለኝምና ባለ መድኃኒት አልሆንም። በሕዝቡም ላይ አለቃ አታደርጉኝም" ይላል።8ንጉሣዊ ሥልጣኑን ያረክሱ ዘንድ ንግግራቸውና ሥራቸው በእግዚአብሔር ላይ ነውና ኢየሩሳሌም ተፈታች ይሁዳም ወደቀ።9የፊታቸውም እፍረት ይመሰክርባቸዋል፤ እንደ ሰዶምም ኃጢአታቸውን ያወራሉ፤ አይሠውሩአትም። በራሳቸው ላይ ጥፋትን ሠርተዋልና ለነፍሳቸው ወዮ!10የሥራውን ፍሬ ይበላልና፣ ጻድቁን መልካም ይሆንልሃል በሉት።11እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደረግበታልና ለበደለኛ ወዮ! ክፉም ደርሶበታል።12ሕዝቤን አስገባሪዎቻቸው ይገፉአቸዋል፣ ሴቶችም ይሠለጥኑባቸዋል። ሕዝቤ ሆይ፣ መሪዎቻችሁ ያስቱአችኋል የምትሄዱበትንም መንገድ አቅጣጫ ያጠፋሉ።13እግዚአብሔር በፍርድ ቤት ሊፈርድ ተነሥቶአል፣ በሕዝቡም ላይ ሊፈርድ ቆሞአል።14እግዚአብሔር ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከአለቆቻቸው ጋር ይፋረዳል፡ "የወይኑን ቦታ የበላችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድሆች የበዘበዛችሁት በቤታችሁ አለ፤15ሕዝቤንስ ለምን ታደቅቁአቸዋላችሁ? የድሆችንስ ፊት ለምን ትፈጫላችሁ?" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።16ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ የጽዮን ቈነጃጅት ኰርተዋልና፣ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፣ ፈንጠርም እያሉ፣ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉ።17ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት አናት በበሽታ ቡሀነት ይመታል፣ እግዚአብሔርም መላጣ ያደርጋቸዋል።18በዚያም ቀን ጌታ የእግር አልቦውን ክብር፣ መርበብንም፣ ጨረቃ የሚመስለውንም ጌጥ፣19የጆሮ እንጥልጥሉንም፣ አንባሩንም፣ መሸፈኛውንም፣20ቀጸላውንም፣ የቁርጭምጭሚት ሰንሰለቱንም፣ መቀነቱንም፣ የሽቱውንም ዕቃ።21አሸንክታቡንም፣ የእጅና የአፍንጫ ቀለበቱንም ያስወግዳል፤22የዓመት በዓል ልብሶችን፣ መጐናጸፊያውንም፣ መሸፈኛውንም፣ ከረጢቱንም፤23የእጅ መስተዋቱንም፣ ከጥሩ በፍታ የተሰራውንም ልብስ፣ ራስ ማሰሪያውንም፣ ዓይነ ርግቡንም ያስወግዳል።24በሽቱ ፋንታ ግማት፣ በመታጠቂያውም ፋንታ ገመድ፣ ጠጕርንም በመንቀስ ፋንታ ቡሀነት፣ በመጐናጸፊያ ፋንታ ማቅ፣ በውበትም ፋንታ ጠባሳ ይሆናል።25ጕልማሶችሽ በሰይፍ፣ ኃያላንሽም በውጊያ ይወድቃሉ።26በሮችዋ ያዝናሉ ያለቅሱማል፤ እርስዋም ብቻዋን በምድር ላይ ትቀመጣለች።
1በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች "የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ ውርደታችንንም አርቅ" ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።2በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጥቋጥ ውብና የከበረ ይሆናል፣ ከእስራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱን ፍሬ ለትምክሕትና ለውበት ይሆናል።3ከዚያም፣ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ባጠበ ጊዜ፣ የኢየሩሳሌምንም ደም በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ ከመካከልዋ ባነጻ ጊዜ፣ 4በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፣ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፣ ቅዱስ ይባላል።5እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ማደሪያ ሁሉ በጉባኤያቸውም ላይ፣ በቀን ዳመናንና ጢስን፣ በሌሊትም የሚቃጠለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብርም ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል።6በቀን ከሙቀት ለጥላ፣ ከዐውሎ ነፋስና ከዝናብም ለመጠጊያና ለመሸሸጊያ ጎጆ ይሆናል።
1አሁን ስለ ወዳጄና ስለ ወይን ቦታው ለወዳጄ ቅኔ እቀኛለሁ። ለወዳጄ በለመለመው ኮረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው።2በዙሪያው ቈፈረ፣ ድንጋዮችንም ለቅሞ አወጣ፣ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት። በመካከሉም ግንብ ሠራ፣ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማሰበት። ወይንንም ያፈራ ዘንድ ጠበቀ፣ ዳሩ ግን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ።3ስለዚህ አሁን፣ እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤ በእኔና በወይኑ ቦታዬ መካከል ፍረዱ።4ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ በተጨማሪ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? መልካም ወይንን ያፈራል ብዬ ስትማመን፣ ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?5አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን አስታውቃችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፤ ለማሰማርያም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፣ ለመራገጫም ይሆናል።6ባድማ አደርገዋለሁ፤ አይቈረጥም፣ አይኰተኰትም፤ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፤ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ዳመናዎችን አዝዛለሁ።7የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፣ የደስታውም አትክልት የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ይጠብቅ ነበር፣ እነሆም ግድያ ሆነ፤ ጽድቅንም ይተማመን ነበር፣ ይልቅ እርዳታ የሚለምን ጩኸት ሆነ።8ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፣ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!9የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ ታላላቆቹና መልካም የሆኑት ቤቶች ሳይቀሩ ባድማ ይሆናሉ፣ የሚኖርባቸውም አይገኝም።10ከወይኑ ቦታ ዐሥር ጥማድ በሬ ካረሰው አንድ የባዶስ መስፈሪያ ብቻ ይወጣል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር አንድ የኢፍ መስፈሪያ ብቻ ይሰጣል።11ጠንካራ መጠጥን ለማፈላለግ በጠዋት ለሚነቊ፣ የወይን ጠጅም እስኪያቃጥላቸው እስከ ሌሊት ድረስ ለሚዘገዩ ወዮላቸው!12መሰንቆና በገና፣ ከበሮና እምቢልታም፣ የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፣ እንዲሁም እጁ ያደረገችውን አላስተዋሉም።13ስለዚህ ሕዝቤ ባለማወቃቸው ወደ ምርኮ ሄዱ፣ መሪዎቻቸውም ተራቡ፣ ሕዝባቸውም የሚጠጡት የላቸውም።14ስለዚህም ሲኦል የመዋጥ ፍላጎትዋን አስፍታለች፣ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ ከበርቴዎቻቸውና አዛውንቶቻቸው፣ ባለጠጎቻቸውም ደስተኞቻቸውም ወደ ሲዖል ይወርዳሉ።15ሰውም ይጐሰቍላል፣ ሰውም ይዋረዳል፣ የትዕቢተኞችም ዓይን ትዋረዳለች።16የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍርድ ከፍ ከፍ ብሎአል፣ ቅዱሱም አምላክ በጽድቅ ተቀድሶአል።17የበግ ጠቦቶች በገዛ መሰማርያቸው ውስጥ፣ እንዲሁም በባለጠጋ ሰዎች ጥፋት ውስጥ ይሰማራሉ፣ ጠቦቶችም ይግጣሉ።18በደልን በምናምንቴ ገመድ፣ ኃጢአትንም በሰረገላ ማሰሪያ ወደ ራሳቸው ለሚስቡ፣ እናይ ዘንድ ይቸኵል፣19"ሥራውንም ያፋጥን፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር ትቅረብ፣ ትምጣ ለሚሉ ወዮላቸው!"20ክፉውን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ለሚሉ፤ ጨለማውን ብርሃን፣ ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፤ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!21በገዛ ዓይናቸው ዘንድ ጥበበኞች፣ በነፍሳቸውም አስተዋዮች ለሆኑ ወዮላቸው!22የወይን ጠጅ ለመጠጣት ኃያላን፣ የሚያሰክረውንም ብርቱ መጠጥ ለማደባለቅ ጨካኞች ለሆኑ፤23በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፣ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!24ስለዚህ የእሳት ወላፈን ቃርሚያን እንደሚበላ፣ እብቅም በነበልባል ውስጥ እንደሚጠፋ፣ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፣ ቡቃያቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፣ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ገፍተዋልና፣ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።25ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዶአል፣ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ ቀጥቷቸዋል፤ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፣ ሬሳቸውም በአደባባይ ላይ እንደ ጕድፍ ሆኖአል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ በድጋሚ ለመምታት ገና ተዘርግታለች።26ለአሕዛብም በሩቅ ምልክትን ያቆማል፣ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል። ተመልከቱ፣ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ።27በመካከላቸው ደካማና ስንኵል የለባቸውም፣ የሚያንቀላፋና የሚተኛም የለም፤ የወገባቸውም መቀነት አይፈታም፣ የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም፤28ፍላጾቻቸው ተስለዋል፣ ቀስቶቻቸውም ሁሉ ተለጥጠዋል፤ የፈረሶቻቸውም ኮቴ እንደ ቡላድ፣ የሰረገሎቻቸውም መንኰራኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ነው።29ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፣ እንደ አንበሳ ደቦሎችም ያገሣሉ። ንጥቂያንም ይዘው ያገሣሉ፣ ይወስዱትማል፣ የሚታደግም የለም።30በዚያም ቀን እንደ ባሕር መትመም ይተምሙባቸዋል፤ ወደ ምድርም ቢመለከቱ፣ ጨለማና መከራ ይመለከታል፤ ብርሃንም በደመናዎችዋ ውስጥ ጨልሞአል።
1ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት፣ እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፣ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።2ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፣ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፣ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።3አንዱም አንደኛውን በመጥራት፣ "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር! ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች" እያለ ይጮኽ ነበር።4የመድረኩም መሠረት ከሚጮኹት ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፣ ቤቱም ጢስ ሞላበት።5ከዚያ እኔ፣ "ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፣ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ፣ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!" አልሁ።6ከዚያም ከሱራፌል አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፤ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ።7በዚያም አፌን ዳሰሰበትና። "ተመልከት፣ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፣ ኃጢአትህም ተሰረየልህ።" አለኝ።8የጌታንም ድምፅ፣ "ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?" ሲል ሰማሁ። እኔም፣ "እኔ አለሁ፤ እኔን ላከኝ።" አልሁ።9እርሱም፣ "ሂድና ይህን ሕዝብ፣ ትሰማላችሁ፣ አታስተውሉምም፤ ታያላችሁ፣ አትመለከቱምም" በላቸው።10በዓይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ፣ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፣ ጆሮአቸውንም አደንቍር፣ ዓይናቸውንም አሳውር" አለኝ።11ከዚያም እኔ፣ "ጌታ ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ነው?" አልሁ። እርሱም ሲመልስ፣ "ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፣ ቤቶችም ሰው የሌለባቸው እስኪሆኑ፣ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ፣12እግዚአብሔርም ሰዎችን እስኪያርቅ፣ በምድርም መካከል ውድማው መሬት እስኪበዛ ድረስ ነው።" አለ።13በእርስዋም ዘንድ አንድ ዐሥረኛ ሰው ቀርቶ እንደ ሆነ እነርሱ ደግሞ በድጋሚ ይቃጠላሉ፤ በተቈረጡ ጊዜ ጉቶቻቸው እንደ ቀሩ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሆኖ፣ ጉቶው የተቀደሰ ዘር ይሆናል።"
1በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን፣ የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ፣ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፣ ሊያሸንፉአትም አልቻሉም።2ለዳዊትም ቤት፣ ሶርያ ከኤፍሬም ጋር እንደተባበሩ ወሬ ተነገረ። የእርሱም ልብ፣ እንዲሁም የሕዝቡም ልብ፣ የዱር ዛፍ በነፋስ እንድትናወጥ ተናወጠ።3ከዚያም እግዚአብሔር ኢሳይያስን፣ "አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኵሬ መስኖ ጫፍ ውጡ።4እንዲህም በለው፣ 'ተጠንቀቅ፣ ዝምም በል፣ ስለ እነዚህ ስለሚጤሱ ስለ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፣ ስለ ሶርያና ስለ ረአሶን፣ ስለ ሮሜልዩም ልጅ ቍጣ አትፍራ፣ ልብህም አይድከም።5ሶርያና ኤፍሬም የሮሜልዩም ልጅ፣ 6"ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቃትም፣ እንስበራትም፣ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥባት" ብለው ክፋት ስለ መከሩብህ፤7ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም፣8የሶርያ ራስ ደማስቆ ስለሆነ፣ የደማስቆም ራስ ረአሶን ስለሆነ አይከናወንም። በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ ኤፍሬም ይሰባበራልና ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ አይሆንም፤9የኤፍሬምም ራስ ሰማርያ ነው፣ የሰማርያም ራስ የሮሜልዩ ልጅ ነው። በእምነት ባትጸኑ፣ በእርግጥም በዋስትና አትጸኑም።"10እግዚአብሔርም ደግሞ አካዝን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣11"ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ቢሆን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ምልክትን ለምን።"12አካዝ ግን፣ "አልለምንም፣ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም" አለ።13ስለዚህ ኢሳይያስ ሲመልስ፣ "እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፣ ስሙ። በውኑ የሰውን ትእግሥት መፈታተናችሁ ቀላል ነውን? ዩአምላኬን ትእግሥት ደግሞ ልትፈታተኑ ይገባችኋልን?14ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ ተመልከቱ፣ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።15ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ ሲያውቅ ቅቤና ማር ይበላል።16ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ከማወቊ በፊት፣ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች።17እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።"18በዚያም ጊዜ እግዚአብሔር በግብጽ ወንዝ ርቀት ያለውን ዝምብ፣ በአሦርም አገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል።19ሁሉም ይመጡና በበረሃ ሸለቆ፣ በድንጋይም ዋሻ ውስጥ በእሾህ ቍጥቋጦ ሁሉ ላይ፣ በማሰማርያውም ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ።20በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይላጫል።21በዚያም ቀን፣ ሰው አንዲት ጊደርንና ሁለት በጎችንም በሕይወት ያቆያል፣ 22ደግሞም ከሚሰጡት ወተት ብዛት የተነሣ ቅቤ ይበላል፤ በአገሪቱም መካከል የቀረ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል።23በዚያም ቀን፣ ሺህ ብር የተገመተ ሺህ የወይን ግንድ በነበረበት ስፍራ ሁሉ ለኵርንችትና ለእሾህ ብቻ ይሆናል።24ኵርንችትና እሾህ በምድር ሁሉ ላይ ነውና በፍላጻና በቀስት ወደዚያ ይገባሉ።25በመቈፈርያም ወደ ተቈፈሩ ኮረብቶች ሁሉ ከኵርንችትና እሾህ ፍርሃት የተነሣ ወደዚያ አትሄድም፤ ነገር ግን የበሬ ማሰማርያና የበግ መራገጫ ይሆናል።
1እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ታላቅ ሰሌዳ ወስደህ፣ 'ምርኮ ፈጠነ፣ ብዝበዛ ቸኰለ' ብለህ ጻፍበት።2የታመኑትን ሰዎች፣ ካህኑን ኦርዮንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ምስክሮች አድርግልኝ" አለኝ።3ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፣ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች።4ከዚያም እግዚአብሔር፣ "ሕፃኑ 'አባባ' እና 'እማማ' በማለት መጣራት ከማወቊ በፊት የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን ምርኮ ፈጠነ፣ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው፤" አለኝ።5እግዚአብሔር በድጋሚ ተናገረኝ፣ እንዲህም አለኝ፣6"ይህ ሕዝብ በቀስታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ውኃ ጠልቶአልና፣ ረአሶንንና የሮሜልዩንም ልጅ ወዶአልና፣7ስለዚህ እግዚአብሔር ብርቱና ብዙ የሆነውን የወንዝ ውኃ፣ የአሦርን ንጉሥና ክብሩን ሁሉ፣ ያመጣባቸዋል። መስኖውንም ሁሉ ሞልቶ ይወጣል፣ በዳሩም ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤8እስከ አንገት እስኪደርስ ድረስ እየጐረፈ ወደ ይሁዳ ይገባል፣ እያጥለቀለቀም ያልፋል። አማኑኤል ሆይ፣ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች።"9አሕዛብ ሆ፣ እወቁና ደንግጡ፣ እናንተም አገራችሁ የራቀ ሁሉ፣ አድምጡ፤ ታጠቁም፣ ደንግጡ፤ ታጠቁ፤ ደንግጡ።10ዕቅድን አብጁ፣ ነገር ግን አይከናወንም፤ ትእዛዙን ተናገሩ፣ ነገር ግን አይከናወንም፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።11እግዚአብሔር በጽኑ እጁ ጭምር እንዲህ ተናገረኝ፣ በዚህም ሕዝብ መንገድ አንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ፣ እንዲህም አለኝ።12ይህ ሕዝብ፣ አድማ ነው የሚሉትን ሁሉ፣ አድማ ነው አትበሉ፤ ማስፈራታቸውንም አትፍሩ፣ አትደንግጡ።13ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፤ የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።14እርሱም ለመቅደስ ይሆናል፤ ነገር ግን ለሁለቱ ለእስራኤል ቤቶች ለዕንቅፋት ድንጋይና ለማሰናከያ ዓለት ይሆናል። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለወጥመድና ለአሽክላ ይሆናል።15ብዙዎችም በእርሱ ይሰናከላሉ፣ ይወድቁማል፣ ይሰበሩማል፣ ይጠመዱማል፣ ይያዙማል።16ምስክሬን እሰር፣ በደቀ መዛሙርቶቼም መካከል ሕጉን አትም።17ከያዕቆብም ቤት ፊቱን የሰወረውን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፣ እጠብቀዋለሁም።18ተመልከቱ፣ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።19እነርሱ፣ "የሚጮኹትንና ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ" ባሉአችሁ ጊዜ፣ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?20ስለዚህ ለሕግና ለምስክር ትኩረት ልትሰጡ ይገባል! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ፣ የንጋት ብርሃን ስለሌላቸው ነው።21እነርሱም ተጨንቀውና ተርበው ያልፋሉ። በተራቡም ጊዜ፣ ተቈጥተው ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይረግማሉ፣ ፊታቸውን ወደ ላይያቀናሉ።22ወደ ምድርም ይመለከታሉ፣ ተመልከቱ፣ መከራና ጨለማ፣ የሚያስጨንቅም ጭጋግ አለ። ወደ ድቅድቅም ጨለማ ይሰደዳሉ።
1ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም። በመጀመሪያው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ፣ በኋለኛው ዘመን ግን በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል።2በጨለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን በራላቸው።3ሕዝቡን አብዝተሃል፣ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፣ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል።4በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር የአስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል።5የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ፣ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፣ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል።6ሕፃን ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።7ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፣ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።8ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃልን ሰደደ፣ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።9በትዕቢትና በልብ ኵራት የሚናገሩ በኤፍሬምና በሳርያ የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ። 10"ጡቡ ወድቆአል፣ ነገር ግን በተወቀረ ድንጋይ እንሠራለን፤ የሾላ ዛፎች ተቈርጠዋል፣ ነገር ግን ዝግባን እንተካባቸዋለን" የሚሉት ሁሉ ያውቃሉ።11ስለዚህ እግዚአብሔር በረአሶን ላይ በጽዮን ተራራ ተቋቋሚ ያስነሣበታል፣12ጠላቶቹን ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፤ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።13ሕዝቡ ግን ወደ ቀሠፋቸው አልተመለሱም፣ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን አልፈለጉም።14ስለዚህ እግዚአብሔር ራስና ጅራትን፣ የሰሌኑን ቅርንጫፍና እንግጫውን በአንድ ቀን ከእስራኤል ይቆርጣል።15ሽማግሌውና ከበርቴው እርሱ ራስ ነው፤ በሐሰትም የሚያስተምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።16ይህን ሕዝብ የሚመሩ ያስቱአቸዋል፤ በእነርሱ የሚመሩትም ይዋጣሉ።17ስለዚህም ሰው ሁሉ ዝንጉና ክፉ ሠሪ ነውና፣ አፍም ሁሉ ስንፍናን ይናገራልና ስለዚህ ጌታ በጕልማሶቻቸው ደስ አይለውም፥ ለድሀ አደጎቻቸውና ለመበለቶቻቸውም አይራራም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።18ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፥ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል።19በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ ራርቶ አያድንም።20ሰው ከቀኙ በኩል ሥጋ ቆርጦም ይራባል፤ ሥጋውን በግራ በኩል ይበላል አይጠግብምም። እያንዳንዱም የገዛ ራሱን ክንድ ሥጋ ይበላል፤21ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤ እነርሱም በአንድነት የይሁዳ ጠላቶች ይሆናሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ልትመታ ትዘረጋለች።
1መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፣ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፣ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፣ 2የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፣ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!3በፍርድ ቀን፣ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን? ለእርዳታስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ብልጥግናችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ?4ከእስረኞች በታች ይጐነበሳሉ፣ ከተገደሉትም በታች ይወድቃሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ልትመታ ተዘርግታለች።5ለቍጣዬ በትር ለሆነ፣ የመዓቴም ጨንገር በእጁ ላለ ለአሦር ወዮለት!6እርሱንም በዝንጉ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፣ ምርኮውንና ብዝበዛውንም ይወስድ ዘንድ እንደ አደባባይም ጭቃ የተረገጡ ያደርጋቸው ዘንድ በምቈጣቸው ሰዎች ላይ አዝዘዋለሁ።7እርሱ እንዲሁ አያስብም፣ በዚህ ሁኔታ አይወጥንም። ነገር ግን በልቡ በርካታ አሕዛብን ለማጥፋትና ለመቍረጥ በልቡ አለ።8እንዲህ ብላልና፣ "መሳፍንቴ ሁሉ ነገሥታት አይደሉምን? 9ካልኖ እንደ ከርከሚሽ አይደለችምን? ሐማትስ እንደ አርፋድ አይደለችምን? ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደለችምን?10የተቀረጹ ምስሎቻቸው ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ ምስሎች የበለጡትን የጣዖቶችን መንግሥታት እጄ እንደረታች፣11በሰማርያና በጣዖቶችዋም እንዳደረግሁ፣ እንዲሁስ በኢየሩሳሌምና በጣዖቶችዋ አላደርግምን?"12ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ፣ "የአሦርን ንጉሥ የኩሩ ልብ ፍሬን የዓይኑንም ከፍታ ትምክሕት እቀጣለሁ።"13እርሱ እንዲህ ብሎአልና፣ "አስተዋይ ነኝና በእጄ ኃይልና በጥበቤ አደረግሁት፤ የአሕዛብን ድንበሮች አራቅሁ፣ ሀብታቸውንም ዘረፍሁ፣ እንደ ጀግናም ሆኜ በምድር የተቀመጡትን አዋረድሁ፤14እጄም የአሕዛብን ባለጠግነት እንደ ወፍ ቤት አገኘች፤ የተተወም እንቍላል እንደሚሰበሰብ፣ እንዲሁ እኔ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ። ክንፉን የሚያራግብ አፉንም የሚከፍት የሚጮኽም የለም።"15በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ስለ ራሱ ይመካልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ላይ ራሱን ይክባልን? ይህስ፣ በትር የሚያነሣውን እንደ መነቅነቅ ዘንግም እንጨት ያይደለውን እንደ ማንሣት ያህል ነው።16ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወፍራሞች ጦረኞቹ ላይ ክሳትን ይልካል፤ ከክብሩም በታች ቃጠሎው እንደ እሳት መቃጠል ይነድዳል።17የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት፣ ቅዱሷም እንደ ነበልባል ይሆናል፤ እሾሁንና ኵርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል ይበላውማል።18ከነፍስም እስከ ሥጋ ድረስ የዱሩንና የሚያፈራውን እርሻ ክብር ይበላል፣ ይህም የታመመ ሰው እንደሚሰለስል ይሆናል።19ታናሽ ብላቴናም ይጽፋቸው ዘንድ እስኪችል ድረስ የቀሩት የዱር ዛፎች በቍጥር ጥቂት ይሆናሉ።20በዚያም ቀን፣ የእስራኤል ቅሬታ ከያዕቆብም ቤት ያመለጡት ከእንግዲህ ወዲህ በመቱአቸው ላይ አይደገፉም፣ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ።21የያዕቆብም ቅሬታ ወደ ኃያል አምላክ ይመለሳሉ።22እስራኤል ሆይ፣ የሕዝብህ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይመለሳል። ጽድቅ የተትረፈረፈበትም ጥፋት ተወስኖአል።23የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ያለቀ የተቈረጠ ጥፋትን በምድር ሁሉ መካከል ይፈጽማል።24ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ አሦርን አትፍራ። አሦር በበትር ይመታሃል፣ ግብጽም እንዳደረገ ዘንጉን ያነሣብሃል።25ቍጣዬ እስኪፈጸም መዓቴም እስኪያጠፋቸው ድረስ በጣም ጥቂት ጊዜ ቀርቶአልና አትፍራው።"26የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ምድያምን በሔሬብ ዓለት በኩል እንደ መታው ጅራፍ ያነሣበታል፤ በትሩንም በባሕር ላይ ያነሣል፣ በግብጽም እንዳደረገ ያነሣዋል።27በዚያም ቀን፣ ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከአንገትህ ላይ ይወርዳል፤ ቀንበሩም ከአንገትህ ከፍተኛ ውፍረት የተነሣ ይሰበራል።28ጠላት ወደ አንጋይ መጥቶአል፤ በመጌዶን በኩል አልፎአል፤ በማክማስ ውስጥ ዕቃውን አኑሮአል፤29በመተላለፊያ አልፎአል፤ በጌባ ማደሪያው ነው፤ ራማ ደንግጣለች፤ የሳኦል ጊብዓ ኰብልላለች።30አንቺ የጋሊም ልጅ ሆይ፥ በታላቅ ድምፅሽ ጩኺ፤ ላይሳ ሆይ፥ አድምጪ! አንቺ ምስኪን ዓናቶት ሆይ፣ መልሽላት!31መደቤና እየሸሸች ናት፣ በግቤርም የሚኖሩ ቤተሰቦቻቸውን አሽሽተዋል።32ዛሬ በኖብ ይቆማል፤ በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ ቡጢውን ይንጣል።33ተመልከቱ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅርንጫፎቹን በሚያስፈራ ኃይል ይቈርጣል፤ በቁመት የረዘሙትም ይቈረጣሉ፣ ከፍ ያሉትም ይዋረዳሉ።34ጭፍቅ የሆነውንም ዱር በመጥረቢያ ይቈርጣል፣ ሊባኖስም በኃያሉ እጅ ይወድቃል።
1ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፣ የሥሩም ቍጥቋጥ ፍሬን ያፈራል።2የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኃይል መንፈስ፣ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።3እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል፤ ዐይኑም እንደምታይ አይፈርድም፣ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤4ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፣ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል። በአፉም በትር ምድርን ይመታል፣ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።5የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፣ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።6ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል፣ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል፣ ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ትንሽም ልጅ ይመራቸዋል።7ላምና ድብ አብረው ግጦሽ ይውላሉ፣ ግልገሎቻቸውም በአንድነት ያርፋሉ። አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።8ሕፃን በእባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፣ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል።9በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ አይጐዱም አያጠፉምም፤ ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።10በዚያም ቀን፣ ለአሕዛብ ምልክት ሆኖ ይቆማል። የእሴይን ሥር አሕዛብ ይፈልጉታል፣ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።11በዚያም ቀን፣ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብጽ፣ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፣ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፣ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደ ገና እጁን ይገልጣል።12ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፣ ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል፣ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።13የኤፍሬምንም ምቀኝነት ያቆማል፣ ይሁዳንም የሚጠሉ ይቆረጣሉ። ኤፍሬምም በይሁዳ አይቀናም፣ ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።14በምዕራብም በኩል በፍልስጥኤማውያን ጫንቃ ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፣ የምሥራቅንም ልጆች በአንድነት ይበዘብዛሉ። በኤዶምያስና በሞዓብም ላይ እጃቸውን ይዘረጋሉ፣ የአሞንም ልጆች ለእነርሱ ይታዘዛሉ።15እግዚአብሔርም የግብጽን ባሕር ያጠፋል፤ በትኩሱም ነፋስ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ያነሣል፣ ሰባት ፈሳሾች አድርጎም ይከፋፍለዋል፣ ስለዚህም በጫማ ሊሻገሩት የሚችሉት ይሆናል።16ከግብጽም በወጣ ጊዜ ለእስራኤል እንደ ነበረው ሁሉ ለቀረውም ሕዝብ ቅሬታ ከአሦር የሚወጣበት ጐዳና እንዲሁ ይሆናል።
1በዚያም ቀን፣ "እግዚአብሔር ሆይ፣ አመሰግንሃለሁ። ተቈጥተኸኛልና፣ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፣ አጽናንተኸኛልምና።2ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፣ አዎን፣ በእርሱ ታምኜ አልፈራም። መድኃኒቴም ሆኖአልና" ትላለህ።3ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።4በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፣ "እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ ተናገሩ።5ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ የታወቀ እንዲሆን አድርጉ።6አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፣ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።"
1የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ያየው ስለ ባቢሎን የተነገረ ሸክም።2ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምልክትን አቁሙ፣ ድምፅንም ከፍ አድርጉባቸው፤ በአለቆችም ደጆች እንዲገቡ እጃችሁን አንስታችሁ አሳዩ።3ቍጣዬን ይፈጽሙ ዘንድ ቅዱሳኔን አዝዣለሁ፣ እኔ ኃያላኔንና በታላቅነቴ ደስ የሚላቸውን ጠርቻለሁ።4በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ! የተከተማቹት የአህዛብ መንግሥታት የውካታ ጫጫታ አለ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊትን ለሰልፍ አሰልፎአል።5እግዚአብሔርና የቍጣው የጦር ዕቃ ምድርን ሁሉ ያጠፉአት ዘንድ ከሩቅ አገር፣ ከሰማይ ዳርቻ ይመጣሉ።6የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፣ አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።7ስለዚህ፣ እጅ ሁሉ ትዝላለች፣ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል፤8ይደነግጣሉ፤ ምጥና ሕማም ይይዛቸዋል፣ እንደምትወልድ ሴትም ያምጣሉ። አንዱም በሌላው ይደነቃል፣ ፊታቸውም የነበልባል ፊት ነው።9ተመልከቱ፣ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፣ ኃጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።10የሰማይም ከዋክብትና ሠራዊቱ ብርሃናቸውን አይሰጡም፣ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፣ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።11ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ። የእብሪተኞችንም ኵራት፣ የጨካኞቹንም ትዕቢት አዋርዳለሁ።12የቀሩትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፣ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል።13ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት፣ በጽኑ ቍጣ ቀንም ሰማያትን አነቃንቃለሁ፣ ምድርም ከስፍራዋ ትናወጣለች።14እንደ ተባረረም ሚዳቋ፣ ማንም እንደማይሰበስበው እንደ በግ መንጋ፣ ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፣ ሁሉም ወደ አገሩ ይሸሻል።15የተገኘ ሁሉ ይገደላል፣ የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይሞታል።16ሕፃናቶቻቸውም በዐይናቸው ፊት እስኪቆራረጡ ድረስ ይጨፈጨፋሉ። ቤቶቻቸውም ይበዘበዛሉ፣ ሚስቶቻቸውም ተይዘው ይነወራሉ።17ተመልከቱ፣ ብር የማይሹትን፣ ወርቅም የማያምራቸውን ሜዶናውያንን በላያቸው አናውጣለሁ።18ፍላጾቻቸውም ጎበዞችን ይወጋሉ። ጨቅላዎችን አይምሩም፣ ዓይኖቻቸውም ለሕፃናት አይራሩም።19እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፣ የመንግሥታት ክብር፣ የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች።20ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ማንም ሰው አይኖርባትም፤ ዓረቦቹ ድንኳንን በዚያ አይተክሉም፣ እረኞችም መንጎቻቸውን በዚያ አያሳርፉም።21በዚያም የምድረ በዳ አራዊት ያርፋሉ። ጕጕቶችም በቤቶቻቸው ይሞላሉ፤ ሰጎኖችና የበረሃ ፍየሎች በዚያ ይኖራሉ።22ጅቦችም በግንቦቻቸው፣ ቀበሮችም በሚያማምሩ አዳራሾቻቸው ይጮኻሉ። ጊዜዋም ለመምጣት ቀርቦአል ቀንዋም አይዘገይም።
1እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፣ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፣ በገዛ አገራቸውም ያኖራቸዋል። መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፣ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል።2አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል። የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል። የማረኩአቸውን ይማርካሉ፣ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ።3በዚያም ቀን፣ እግዚአብሔር ከኀዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል።4ይህንም ምሳሌ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ፣ "አስጨናቂ እንዴት በፍጻሜው ዐረፈ፣ ኩሩውስ እንዴት ጸጥ አለ!" ይላሉ።5እግዚአብሔር የአሕዛብ ገዢዎችን በትር በመዓትና በማያቋርጥ መምታት መታ፣ 6አሕዛብንም ባልተከለከለ መከራ፣ በቍጣው የገዛውን የኀጥኣንን በትር የአለቆችንም ዘንግ እግዚአብሔር ሰብሮአል።7ምድርም ሁሉ ዐርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች፤ በዝማሬ ክብረ-በዓላቸውን ማድረግ ጀምረዋል።8ጥድና የሊባኖስ ዝግባ፣ 'አንተ ከተዋረድህ ጀምሮ ማንም ይቈርጠን ዘንድ አልወጣብንም' ብለው በአንተ ደስ አላቸው።9ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፣ የምድርን ታላላቆች ሁሉ፣ ለአንተ አንቀሳቀሰች፣ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች።10እነዚህ ሁሉ ተናግረው፣ 'አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃል። እኛን መስለሃል። ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፤11በበታችህም ብል ተነጥፎአል። ትልም ይሸፍንሃል' ብለው ይመልሱልሃል።12አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፣ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፣ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ!13አንተ በልብህ፣ 'ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፣ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፣ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤14ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፣ በልዑልም እመሰላለሁ' አልህ።15ነገር ግን ወደ ሲኦል፣ ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።16የሚያዩህ አፍጥጠው ይመለከቱሃልና። በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፣ መንግሥታትንም ያናወጠ፥17ዓለሙን ሁሉ ባድማ ያደረገ፣ ከተሞችንም ያፈረሰ ምርከኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል።18የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ፣ በየመቃብራቸው በክብር አንቀላፍተዋል።19አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ በሰይፍም የተወጉት፣ ተገድለውም ወደ ጕድጓዱ ድንጋዮች የወረዱት ከድነውሃል፤ እንደ ተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።20ምድርህን አጥፍተሃልና፣ ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም፤ የክፉዎች ዘር ለዘላለም የተጠራ አይሆንም።"21እንዳይነሡም፣ ምድርንም እንዳይወርሱ፣ የዓለሙንም ፊት በከተሞች እንዳይሞሉ ስለ አባቶቻቸው በደል ለልጆቹ ሞትን አዘጋጁላቸው።22"በእነርሱ ላይ እነሣለሁ" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ከባቢሎን ስምንና ቅሬታን፣ ዘርንና ትውልድንም እቈርጣለሁ ይላል እግዚአብሔር።23"የጃርት መኖርያ የውኃም መቋሚያ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።24የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፣ "እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፣ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።25አሦርን በምድሬ ላይ እሰብረዋለሁ፣ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ። ከዚያም ቀንበሩ ከእነርሱ ላይ ይነሣል፣ ሸክሙም ከጫንቃቸው ላይ ይወገዳል።"26በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው አሳብ ይህ ነው፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት።27የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን አስቦአል፤ የሚያስጥለውስ ማን ነው? እጁም ተዘርግታለች፤ የሚመልሳትስ ማን ነው?28ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት ይህ ዐዋጅ ወጣ።29ፍልስጥኤም ሆይ፣ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፣ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።30የድሆችም የበኵር ልጆች ይሰማራሉ፣ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፤ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፣ ቅሬታህም ይገደላል።31አንተ በር ሆይ፣ ወዮ በል አንቺም ከተማ ሆይ፣ ጩኺ፤ ፍልስጥኤም ሆይ፣ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይመጣል ከጭፍራውም ተለይቶ የሚቀር የለም።32ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መመለስ ይገባል? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደ መሠረተ፣ የሕዝቡም ችግረኞች በእርስዋ ውስጥ እንደሚጠጉ ነው።
1ስለ ሞዓብ የተነገረ ሸክም፣ በእርግጥ፣ የሞዓብ ዔር በሌሊት ፈርሶ ጠፋ፤ ቂር የሚባልም የሞዓብ ምሽግ በሌሊት ፈርሶ ጠፋ።2ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባው በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቶአል።3በየመንገዳቸውም በማቅ ታጥቀዋል፤ በየሰገነቶቻቸውና በየአደባባዮቻቸው እንባ እጅግ እያፈሰሱ ሁሉም አልቅሰዋል።4ሐሴቦንና ኤልያሊ ለእርዳታ ጮኹ፤ ድምፃቸው እስከ ያሀጽ ድረስ ይሰማል። ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፤ ነፍስዋ በውስጥዋ ተንቀጠቀጠች።5ልቤ ስለ ሞዓብ ጮኸ፤ ከእርስዋም የሚሸሹ ወደ ዞዓር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኰበለሉ፤ በሉሒት ዓቀበት ላይ እያለቀሱ ይወጣሉ፣ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኸት ያነሣሉ።6የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፤ ሣሩም ደርቋል፣ ለጋውም ጠውልጓል፥ ልምላሜውም ሁሉ የለም።7ስለዚህ የሰበሰቡትን ሀብትና መዝገባቸውን ወደ አኻያ ዛፍ ወንዝ ማዶ ይወስዱታል።8ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ብኤርኢሊም ደረሰ።9የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ በዲሞንም ላይ ሥቃይን እጨምራለሁ፣ ከሞዓባውያንም በሚያመልጡ፣ ከምድርም በሚቀሩ ላይ አንበሳን አመጣለሁ።
1በምድርም ላይ ለሠለጠነው አለቃ የበግ ጠቦቶችን በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ስደዱ።2እንደሚበርር ወፍ፣ እንደ ተበተኑም ጫጩቶች፣ እንዲሁ የሞዓብ ሴቶች ልጆች በአርኖን መሻገሪያዎች ይሆናሉ።3"መመሪያን ስጪ፣ ፍርድን አድርጊ፣ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አድርጊ፤ የተሰደዱትን ሸሽጊ፣ የሸሹትን አትግለጪ።4ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ጋር ይኑሩ፤ ከሚያጠፋቸው ፊት መጋረጃ ሁኛቸው።" ጭቆናው ይቆማልና፣ ጥፋትም ይቆማልና፣ ይጨቍኑ የነበሩ ከምድር ይጠፋሉና።5ዙፋንም በኪዳን ታማኝነት ይመሠረታል፤ ከዳዊት ድንኳን የሆነው በታማኝነት በዚያ ይቀመጣል። ፍርድን የሚሻ ጽድቅንም የሚያደርግ እንደመሆኑ ይፈርዳል።6ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ እብሪተኝነቱ፣ ስለ ኵራቱና፣ ስለ ቁጣው ሰምተናል። ትምሕክቱ ባዶ ቃላት ናቸው።7ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ያለቅሳል፤ ሁሉም ያለቅሳል። ፈጽሞ ስለሚጠፋው ስለ ቂርሐራሴት የዘቢብ ጥፍጥፍ ታለቅሳላችሁ።8የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች ደርቀዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ተበትነዋል። ቍጥቋጦቹም ተንሰራፍተው ወደ ባሕር ሄደው ነበር።9በእርግጥ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለቅሳለሁ። ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፣ በእምባዬ አረሰርሳችኋለሁ። በበጋሽ ፍሬና በመከር ላይ የደስታን ጩኸት ትቻለሁና።10ደስታና ሐሤትም ከፍሬያማው የእርሻ ደን ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና የደስታ እልልታ የለም። በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።11ስለዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ አንጀቴም ስለ ቂርሔሬስ እንደ መሰንቆ ትጮኻለች።12ሞዓብም መጥቶ በኮረብታ መስገጃ ላይ ራሱን በደከመና ለጸሎት ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ፣ ጸሎቱ ምንም ነገር አያሳካም።13እግዚአብሔር በሞዓብ ላይ አስቀድሞ የተናገረው ነገር ይህ ነው።14አሁን ግን እግዚአብሔር፣ "በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብርና የሕዝቡ ሁሉ ብዛት ይዋረዳል፣ ቅሬታውም እጅግ ያነሰና የተጠቃ ይሆናል" ይላል።
1ስለ ደማስቆ የተነገረ ሸክም። እነሆ፣ ደማስቆ ከእንግዲህ ከተማ አትሆንም፤ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።2የአሮኤር ከተሞች ይጣላሉ። ለመንጋ ማሰማሪያ ሆናሉ፣ የሚያስፈራቸውም የለም።3የተመሸጉ ከተሞች ከኤፍሬም ይጠፋሉ፣ መንግሥትም ከደማስቆ፤ የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።4በዚያም ቀን የያዕቆብ ክብር ይከሳል፣ የሥጋውም ውፍረት ይሸበሸባል።5አጫጅ የቆመውን እህል በእጁ ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ ይሆናል። በራፋይም ሸለቆ ቃርሚያ እንደሚለቅም እንዲሁ ይሆናል።6ወይራ በተመታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እንደሚቀር፥ አራት ወይም አምስት በዛፊቱ ጫፍ እንደሚገኝ፣ በእርሱ ዘንድ ቃርሚያ ይቀራል ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።7በዚያ ቀን ሰው ወደ ፈጣሪው ይመለከታል፣ ዐይኖቹም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።8እጁም የሠራችውን መሠዊያ አይመለከትም፣ ጣቶቹም ወደ አበጁአቸው፣ ወደ አሼራ ዐምዶች ወይም ወደ ፀሐይ ምስሎች አያይም።9በዚያም ቀን በእስራኤል ልጆች ፊት የአሞራውያንና የኤውያውያን ከተሞች እንደ ተፈቱ እንዲሁ ከተሞችህ ይፈታሉ ባድማም ይሆናሉ።10የደኅንነትህን አምላክ ረስተሃልና፣ የብርቱነትህንም ዐለት አላሰብክምና። ስለዚህ ያማረውን ተክል ተክለሃል፣ እንግዳንም ዘር ዘርተሃል11በዚያ ቀን ተክለህ ታጥርለትና ታበቅለዋለህ። ብዙም ሳይቆይ ዘርህ ያብባል፣ ነገር ግን መከሩ የሚሆነው በኀዘንና በጥልቅ ኃዘን ነው።12ወዮላችሁ! እንደ ባሕር ሞገድ ድምፅ ለሚጮኹ፣ እንደ ኃይለኛም ውኃ ጩኸት ለሚጮኹ አሕዛብ!13አሕዛብ እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፣ እግዚአብሔር ግን ይገሥጻቸዋል። እነርሱም ወደ ሩቅ ይሸሻሉ፣ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ፣ በነፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረው ትቢያ ይበተናሉ።14በመሸ ጊዜ፣ ተመልከቱ፣ ድንጋጤ አለ፤ ከማለዳም በፊት አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች እድል ፈንታ፣ የበዘበዙን ዕጣ ይህ ነው።
1ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የክንፎች ድምፅ ለሚሰማባት አገር ወዮላት፤ 2መልእክተኞችን ከደንገል በተሠራ ጀልባ በአባይ ወንዝ ላይ ለምትልከው አገር፤ ሕዝብዋ ረጃጅሞችና ቆዳቸው ለስላሳ፣ አገራቸው በወንዞች የተከፋፈለች፣ ጠንካሮችና ኃያላን በመሆናቸው በዓለም ሁሉ ወደሚፈሩት ሕዝቦች እናንት ፈጣን መልእክተኞች ሂዱ!3በዓለም የምትኖሩ ሁሉ እና በምድር የምትኖሩ፣ በተራሮች ጫፍ ላይ የተተከለ የሰንደቅ ዓላማ ምልክት ሲውለበለብ አስተውሉ፤ መለከት ሲነፋ ስሙ።4እግዚአብሔር ያለኝ ነገር እንዲህ ነው፣ "በቀትር ጊዜ በጸጥታ እንደምታበራ ፀሐይ፣ በመከርም ወራት በሞቃት ሌሊት እንደሚታይ ጤዛ ከሰማያዊ መኖሪያዬ ጸጥ ባለ መንፈስ ቊልቊል እመለከታለሁ።" 5የወይን መከር ከመሰብሰቡ በፊት አበቦች ረግፈው የወይን ፍሬ በሚበስልበት ጊዜ የወይን ሐረግ ቅርንጫፎች በስለት ተቈርጠው እንደሚጣሉ እርሱ የዚያችን አገር ሕዝብ ያጠፋል።6በአንድነት ለተራራ ወፎችና ለምድረ በዳ አራዊት ይተዋሉ። በበጋ ወፎች፣ በክረምትም አራዊት ይቀራመቷቸዋል።7የሠራዊት አምላክ በዓለም ሁሉ የመፈራት ግርማ ካላቸው፣ ቆዳቸው ለስላሳ፣ ቁመታቸው ረጅም ኀያላንና ብርቱዎች ከሆኑት፣ በወንዞች የተከፋፈለች ምድር ካላቸው ከእነዚያ ሕዝብ መባ የሚቀበልበት ጊዜ ይመጣል፤ እነርሱም የሠራዊት አምላክ ወደሚመለክባት ወደ ጽዮን ኰረብታ ይመጣሉ።
1ስለ ግብጽ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል የሚከተለው ነው። ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ሆኖ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጻውያን ጣዖቶች በእርሱ ፊት ይናወጣሉ፤ የግብጽ ሕዝብም በፍርሃት ይቀልጣሉ። 2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "ግብጻዊያንን በግብጻዊያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድም በወንድሙ ላይ፣ ጐረቤትም በጐረቤቱ ላይ በጠላትነት እንዲነሣ አደርጋለሁ፤ ከተሞች በከተሞች ላይ፣ ነገሥታት በነገሥታት ላይ በጠላትነት ተነሥተው ይዋጋሉ።3የግብጻውያን መንፈስ በውስጡ ይዳከማል። የጣዖቶቻቸውን የጠንቋዮቻቸውን የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን ምክር ቢፈልጉም ምክሩን እደመስሳለሁ። 4እነርሱን በጭካኔ ለሚገዛቸው ጌታ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።"5በዓባይ ውስጥ ያለው ውሃ ይደርቃል፣ ወንዙም እየደረቀ ሄዶ ባዶ ይሆናል 6ወንዞቹ ይገማሉ፤ የግብጽ ምንጭ እየጐደለ ይደርቃል፤ ደንገሎቹና ቄጤማዎቹ ይጠወልጋሉ።7በዓባይ ወንዝ ዳርቻ ያለው ቄጤማ ሁሉ ይደርቃል፤ በወንዙ አጠገብ የተዘራውም ሰብል ሁሉ ደርቆ ወደ አፈርነት በመለወጥ ነፋስ ይወስደዋል። 8ዓሣ አጥማጆችና መንጠቆአቸውን ወደ አባይ ወንዝ የሚጥሉ ሁሉ ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ መረቦቻቸውንም በውሃ ላይ የሚዘረጉ ተስፋ ይቈርጣሉ፤9የተበጠረውን የተልባ እግር የሚሠሩ እና ቀጭን ሐር የሚሠሩ ያፍራሉ። 10የግብጽ ሸማኔዎች ግራ ይጋባሉ፤ ደመወዝተኞችም በውስጣቸው ያዝናሉ።11በጾዓን ያሉ ልዑላን ፍጹም ሞኞች ናቸው። ጠቢባን የሆኑት የፈርዖን አማካሪዎች ምክር ትርጉም የለሽ ይሆናል። ለፈርዖን "እኔ የብልኅ ሰው ልጅ ነኝ የጥንት ነገሥታት ልጅ ነኝ እንዴት ይላሉ?"12እንግዲያው እነዚያ ጠቢባን ወዴት ናቸው? የሠራዊት አምላክ በግብጽ ላይ ያቀደውን ይንገሩህ፣ ደግሞም ያሳውቁህ።13የጾዓን ልዑላን ሞኞች ሆኑ፤ የሜምፊስ ልዑሎችም ተታለሉ፤ የነገዶችዋ ማእዘናት የሆኑት ግብጽን አሳትዋት። 14የተቀያየጠ ምክር እንዲሰጡ ያደረጋቸውም እግዚአብሔር ነው፤ በመጨረሻም ግብጽ በሁሉ ነገር በመሳሳት የገዛ ትውከቱ አዳልጦት እንደሚጥለው ሰካራም ትንገዳገዳለች። 15በግብጽ ራስም ሆነ ጭራ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ ቢሆን ወይም ቄጤማ የሆነ ምንም ነገር ማድረግ አይችልም።16በዚያ ቀን፣ ግብጻዊያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ። በእነርሱ ላይ ከሚነሣው የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የቅጣት እጅ አንጻር ይሸበራሉ፣ ደግሞም ይፈራሉ። 17ይሁዳ ለግብጽ ሕዝብ የምታንገዳግድ ትሆናለች። ማንኛውም ሰው ስለ እርሷ ሲያስታውሳቸው፣ ከእግዚአብሔር የመቅጣት እቅድ የተነሣ ይሸበራሉ።18በዚያን ቀን በግብጽ ምድር ውስጥ የሚገኙ አምስት የዕብራውያን ቋንቋ የሚናገሩ ከተሞች ይኖራሉ፤ በዚያም የሚኖሩ ሕዝቦች በሠራዊት አምላክ ስም ይምላሉ፤ ከእነዚህ ከተሞች አንዲቱ የፀሐይ ከተማ ተብላ ትጠራለች።19በዚያን ቀን በግብጽ ምድር መካከል ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ እንዲሁም በግብጽ ጠረፍ ላይ ለእግዚአብሔር የተለየ የድንጋይ ዐምድ ይተከላል። 20እነርሱም የሠራዊት አምላክ በግብጽ ምድር ለመኖሩ ምልክትና ምስክር ይሆናሉ። ከጭቆና የተነሣ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በሚጠይቁበት ጊዜ፣ የሚታደጋቸውን አዳኝ ይልክላቸዋል፣ እርሱም ከጠላቶቻቸው ያድናቸዋል።21እግዚአብሔር ለግብጽ ሕዝብ የታወቀ ይሆናል፤ ደግሞም በዚያን ጊዜ እነርሱ ያውቁታል። መሥዋዕትና መባም ያቀርቡለታል፣ ለእግዚአብሔርም ስእለት ይሳላሉ፤ ስእለታቸውንም ሁሉ ይፈጽማሉ። 22እግዚአብሔር ግብጻውያንን ይቀጣል፤ ነገር ግን መልሶ ይፈውሳቸዋል፤ ወደ እርሱ ይመለሳሉ፤ እርሱም ጸሎታቸውን ሰምቶ ይፈውሳቸዋል።23በዚያን ጊዜ በግብጽና በአሦር መካከል አውራ ጎዳና ይከፈታል፤ አሦራዊያን ወደ ግብጽ፣ ግብጻዊያንም ወደ አሦር ይመጣሉ፤ ደግሞም ግብጻዊያን ከአሦራዊያን ጋር ያመልካሉ።24በዚያን ቀን፣ እስራኤል ከግብጽና ከአሦር ጋር ሦስተኛ አገር ትሆናለች፤ እነዚህም ሕዝቦች በዓለም መካከል በረከት ይሆናሉ። 25የሠራዊት አምላክም፣ "እናንተ በግብጽ የምትኖሩ ሕዝቤ፣ የፈጠርኳችሁ አሦራውያንና የመረጥኳችሁ የእስራኤል ሕዝብ የተባረካችሁ ሁኑ" ይላቸዋል።
1የአሦር ንጉሥ ሳርጎን ተርታንን በሰደደ ጊዜና ወደ አዛጦን በመጣ ጊዜ አዛጦንም ወግቶ በያዛት ጊዜ፥2በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ "ሂድና ማቅህን ከወገብህ አውጣ፣ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ" ብሎ ተናገረው። እንዲህም አደረገ፣ ራቁቱንም ባዶ እግሩንም ሄደ።3እግዚአብሔርም አለ፣ "ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፣4በዚህ መንገድ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፣ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፣ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፣ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል።5እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል፤6በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚኖሩ፣ "በእርግጥ፣ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?" ይላሉ።
1በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ዐዋጅ። ዐውሎ ነፋስ ከኔጌቭ እንደሚወጣ፣ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር በምድረ በዳ አልፎ ይወጣል።2የሚረብሽ ራእይ ተነገረኝ፤ ወንጀለኛው በወንጀል ይሠራል፣ አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፣ ወደ ላይ ውጪ፣ ሜዶን ሆይ ክበቢ፤ ትካዜውን ሁሉ አስቀርቻለሁ።3ስለዚህ ወገቤ በሕመም ተሞላ፤ እንደምትወልድ ሴት ምጥ ያዘኝ፤ ከሰማሁት የተነሣ ጎበጥኩ፤ ካየሁት ነገር የተነሣ ተረበሽኩ።4ልቤ ተርበደበደ፣ መንቀጥቀጥ አስፈራኝ፤ የተመኘሁት ሌሊት የሚያንቀጠቅጠኝ ሆነብኝ።5ማዕዱን ያዘጋጃሉ፣ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፣ ይበሉማል፣ ይጠጡማል፤ እናንተ ልዑላን ሆይ፣ ተነሡ፣ ጋሻውን በዘይት ቀቡ።6ጌታ ያለኝ እንዲህ ነው፣ "ሂድ፣ ጉበኛም አቁም፣ የሚያየውንም ይናገር።7በከብት የሚቀመጡትን፣ ሁለት ሁለት እየሆኑ የሚሄዱት ሠረገሎች፥ በአህዮች የሚጋልቡትንና በግመሎች የሚጋልቡትን ባየ ጊዜ፣ በጽኑ ትጋት አስተውሎ ተግቶም ያድምጥ።"8ያየውም። ጌታ ሆይ፥ ቀኑን ሁሉ ዘወትር በማማ ላይ ቆሜአለሁ፥ ሌሊቱንም ሁሉ በመጠበቂያዬ ላይ ተተክያለሁ፣"9እነሆም፣ በፈረሶች የሚቀመጡ፣ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፣ "ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች፣ የተቀረጹም የአማልክቶችዋ ምስሎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ" አለ።10እናንተ በአውድማዬ ላይ የተወቃችሁ የአውድማዬ ልጆች ሆይ! ከእስራኤል አምላክ፣ ከሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሰማሁትን ነገርኋችሁ።11ስለ ኤዶምያስ የተነገረ ዐዋጅ። አንዱ ከሴይር ይጣራል፣ "ጕበኛ ሆይ፣ ከሌሊቱ ምን ያክል ሰዓት ቀረ? ጕበኛ ሆይ፣ ከሌሊቱ ምን ያክል ሰዓት ቀረ?" ብሎ ጠራኝ።12ጕበኛውም እንዲህ አለ፣ "ማለዳው ይመጣል፣ ድግሞም ምሽቱ፤ ብትጠይቁ፣ ጠይቁ፤ ተመልሳችሁም ኑ" አለ።13ስለ ዓረብ የተነገረ ዐዋጅ። የዴዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፣ በዓረብ ዱር ውስጥ ታድራላችሁ።14በቴማን የምትኖሩ ሆይ፣ ወደ ተጠሙት ሰዎች ውኃ አምጡ፣ እንጀራ ይዛችሁ የሸሹትን ሰዎች ተቀበሉአቸው።15ከሰይፍ፣ ከተመዘዘው ሰይፍ፣ ከተለጠጠውም ቀስት ከጽኑም ሰልፍ ሸሽተዋልና።16ጌታ ያለኝ እንዲህ ነውና፣ "ምንደኛ ለአንድ ዓመት እንደሚቀጠር፣ በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፤17ከቀስተኞች ቍጥር ጥቂቶቹ ብቻ፣ የቄዳር ልጆች ኃያላን፣ ያንሳሉ፤" የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
1ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ዐዋጅ፤ እናንተ ሁላችሁ ወደ ቤት ሰገነት መውጣታቸሁ ምን ሆናችኋል?2ጩኸትና ፍጅት የተሞላብሽ ከተማ፣ ደስታ ያለሽ ከተማ ሆይ፣ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉም፣ በሰልፍም የሞቱ አይደሉም።3ገዚዎችሽ ሁሉ በአንድነት ሸሹ፣ ያለ ቀስትም ተማረኩ፤ ከሩቅ ሸሽተው ከአንቺ ዘንድ የተገኙት ሁሉ በአንድነት ታሰሩ።4ስለዚህም፣ "ወደ እኔ አትመልከቱ፣ መራራ ልቅሶ አለቅሳለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት ታጽናኑኝ ዘንድ አትድከሙ" አልሁ።5ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የድንጋጤና የመረገጥ የድብልቅልቅም ቀን፣ የቅጥርም መፍረስ ወደ ተራራም መጮኽ በራእይ ሸለቆ ውስጥ ሆኖአል።6ኤላምም ከሰዎች ሠረገለኞችና ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ አፎቱን ተሸከመ፣ ቂርም ጋሻውን ገለጠ።7መልካሞቹንም ሸለቆችሽን ሠረገሎች ሞሉባቸው፣ ፈረሰኞችም መቆሚያቸውን በበር ላይ አደረጉ።8የይሁዳንም መጋረጃ ገለጠ፤ በዚያም ቀን በዱር ቤት የነበረውን የጦር ዕቃ ተመለከትህ።9የዳዊትም ከተማ ፍራሾች እንደ በዙ አይታችኋል፣ የታችኛውንም ኵሬ ውኃ አከማችታችኋል።10የኢየሩሳሌምን ቤቶች ቈጥራችሁ ቅጥሩንም ለማጥናት ቤቶችን አፈረሳችሁ።11በአሮጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መጠባበቂያ ማከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፣ ቀድሞ የሠራውንም አላሰባችሁም።12በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ ራስን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራ።13ነገር ግን ተመልከቱ፣ ሐሜትና ደስታ በሬውንና በጉንም ማረድ፣ ሥጋንም መብላት፣ የወይን ጠጅንም መጠጣት ሆነዋል። እናንተ፣ ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ብላችኋል።14ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተገለጠ፡- "እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።15የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በቤቱ ውስጥ ወደ ተሾመው ወደዚህ አዛዥ ወደ ሳምናስ ሂድ እንዲህም በለው፣16"መቃብር በዚህ ያስወቀርህ ከፍ ባለው ስፍራ መቃብር ያሠራህ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖርያ ያሳነጽህ በዚህ ምን አለህ? በዚህስ በአንተ ዘንድ ማን አለ?"17እነሆ፣ እግዚአብሔር ወርውሮ ይጥልሃል፣ ኃያል ሰውም አጠንክሮ ይወረውርሃል፤ በኃይል ይጎትትሃል።18ጠቅልሎም ያንከባልልሃል ወደ ሰፊይቱም ምድር እንደ ኳስ ይጥልሃል። በዚያ ትሞታለህ በዚያም የክብርህ ሰረገላዎች ይሆናሉ። አንተ የጌታህ ቤት እፍረት ትሆናለህ!19ከአዛዥነትህና ከጣቢያ ሥራህ አሳድድሃለሁ። ከሹመትህም ትወርዳለህ።20በዚያም ቀን ባሪያዬን የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፥21መጐናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፣ በመታጠቂያህም አስታጥቀዋለሁ፣ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።22የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም።23በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ችንካር እተክለዋለሁ፣ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል።24የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ ልጆቹንም የልጅ ልጆቹንም፣ ከጽዋ ዕቃ ጀምሮ እስከ ማድጋ ዕቃ ድረስ፣ ታናናሹን ዕቃ ሁሉ ይሰቅሉበታል።25በዚያ ቀን፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በታመነው ስፍራ የተከለው ችንካር ይወልቃል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፣ በእርሱም ላይ የተሰቀለው ሸክም ይጠፋል እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
1ስለ ጢሮስ የተነገረ ሸክም። የተርሴስ መርከቦች ሆይ፣ አልቅሱ፤ ፈርሶአልና ቤት የለም፣ መግቢያም የለም፤ ከኪቲም አገር ጀምሮ ተገልጦላቸዋል።2እናንተ በደሴት የምትኖሩ፣ በባሕርም የምትሻገሩ የሲዶና ነጋዴዎች፣ ወኪሎቻችሁ የሚያቀርቡላችሁ፣ ጸጥ በሉ።3የሺሖር ዘርና የዓባይ ወንዝ መከር በብዙ ውኆች ላይ ገቢዋ ነበረ፤ እርስዋም የአሕዛብ መናገጃ ነበረች።4እፈሪ፣ ሲዶና ሆይ፣ ባሕር ተናግሯልና፣ የባሕሩ ኃያል ተናግሯል። እንዲህ አለ፣ "አላማጥሁም፣ አልወለድሁምም፤ ጐበዛዝትንም አላሳደግሁም፤ ወጣት ሴቶችንም አላሳደግሁም" ብሎ ተናግሮአልና እፈሪ።5ወሬዋ ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ፣ በጢሮስ ወሬ ስለ እርሷ ምጥ ይይዛቸዋል።6ወደ ተርሴስ ተሻገሩ፤ እናንተ በደሴት የምትኖሩ አልቅሱ።7ደስተኛዋ ከተማ፣ ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ የነበርሽ፣ ይህ ደርሶብሻልን፣ እንግዳ በሆነ ስፍራዎች ለመኖር እግሮችዋ ወደ ሩቅ ያፈለሱአት የደስታችሁ ከተማ ይህች ናትን?8አክሊል ባስጫነች ከተማ ነጋዴዎችዋ ልዑላን በሆኑ፣ በእርስዋም የሚሸጡና የሚለውጡ የምድር ክቡራን የሆኑባት ጢሮስ ላይ ይህን የወጠነ ማን ነው?9የክብርን ሁሉ ትዕቢት ይሽር ዘንድ የምድርንም ክቡራን ሁሉ ያስንቅ ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖታል።10የተርሴስ ልጅ ሆይ፣ የሚከለክልሽ የለምና እንደ ዓባይ ወንዝ በአገርሽ ላይ እረሺ።11እግዚአብሔር በባሕር ላይ እጁን ዘረጋ፣ መንግሥታትንም አናወጠ፤ ምሽጎችዋንም ያጠፉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለ ከነዓን አገር አዘዘ።12እርሱም፣ "አንቺ የተበደልሽ የሲዶና ድንግል ልጅ ሆይ፣ ተነሺ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በድጋሚ ደስ አይልሽም፤ ወደ ኪቲም ተሻገሪ፣ በዚያም ደግሞ አታርፊም አለ።13ተመልከቱ የከለዳውያን ሰዎች። ይህ ሕዝብ መኖሩ ይቆማል፤ አሦራውያን ለምድረ በዳ አራዊት ሰጥተውታል። የወረራ ግንቦቻቸውን ሠሩ፥ አዳራሾችዋንም አፈረሱ፣ የጥፋት ባድማም አደረጓት።14እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፣ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ።15በዚያም ቀን፣ ጢሮስ እንደ ንጉሥ ቀናት ሁሉ ሰባ ዓመት ያህል የተረሳች ትሆናለች። ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢሮስ በጋለሞታ ዘፈን እንደሚሆን እንዲሁ ይሆናል።16አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፣ መሰንቆ ያዢ፣ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ ዘፈንሽንም አብዢ።17ከሰባ ዓመትም በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይረዳታል፣ ወደ ተቀጠረችበት ትመለሳለች። ደግሞም በምድር ፊት ላይ ከሆኑ ከዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር ትገለሙታለች።18ንግድዋና ዋጋዋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል። ንግድዋም በልተው ይጠግቡ ዘንድ ማለፊያም ልብስ ይለብሱ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩ ይሆናል እንጂ በዕቃ ቤትና በግምጃ ቤት ውስጥ አይከተትም።
1ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር ምድርን ባዶ ያደርጋታል፣ ባድማም ያደርጋታል፣ ይገለብጣትማል፣ በእርስዋም የሚኖሩትን ይበትናል።2እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ፣ እንደ ባሪያውም እንዲሁ ጌታው፣ እንደ ባሪያይቱም እንዲሁ እመቤትዋ፣ እንደሚገዛም እንዲሁ የሚሸጠው፣ እንደ አበዳሪውም እንዲሁ ተበዳሪው፣ እንደ ዕዳ አስከፋዩም እንዲሁ ዕዳ ከፋዩ ይሆናል።3ምድር ፈጽሞ ትጠፋለች፣ ፈጽማም ትበላሻላች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሮአልና።4ምድር ደረቀች ረገፈችም፤ ዓለም ተናወጠች ረገፈችም፤ የምድርም ስመ-ጥር ሕዝብ ደከሙ።5ሕጉን ተላልፈዋልና፣ ሥርዓቱንም ለውጠዋልና፣ የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና፣ ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች።6ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች፣ የሚኖሩባትም ጥፋተኞች ይሆናሉ። ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይቃጠላሉ፣ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።7አዲስ የወይን ጠጅ ይደርቃል፣ የወይን ንግድ ደከመች፣ ልባቸው ደስ ያለው ሁሉ ተከዙ።8የከበሮው ደስታ ቆሟል፣ የደስተኞች ድምፅ ዝም ብሎአል፣ የመሰንቆ ደስታ ቀርቶአል።9እየዘፈኑም የወይን ጠጅን አይጠጡትም፣ የሚያሰክርም መጠጥ ለሚጠጡት መራራ ይሆናል።10የተቃወሰችው ከተማ ፈረሰች፤ ቤት ሁሉ ተዘግቶ ባዶ ሆነ።11ስለ ወይኑም ጠጅ በአደባባይ ለቅሶ ይሆናል፤ ደስታ ሁሉ ጨልሞአል፥ የምድርም ደስታ ጠፍቷል።12ከተማይቱም ባድማ ሆናለች፣ በርዋም በጥፋት ተመትቶአል።13የወይራን ዛፍ እንደ መምታት፣ ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም፣ እንዲሁ በምድር መካከል በአሕዛብም መካከል ይሆናል።14እነዚህ ድምፃቸውን አሰምተው እልል ይላሉ፣ ስለ እግዚአብሔር ክብርም ከባሕር በደስታ ይጮኻሉ።15ስለዚህ እግዚአብሔርን በምሥራቅ፣ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ።16"ለጻድቁ ክብር ይሁን!" የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፣ "ባከንሁ፣ ባከንሁ፣ ወዮልኝ! ወንጀለኞች ወንጅለዋል፤ አዎን፣ ወንጀለኞች እጅግ ወንጅለዋል" አልሁ።17በምድር ላይ የምትኖር ሆይ፣ ፍርሃትና ገደል ወጥመድም በአንተ ላይ አሉ።18ከፍርሃት ድምፅ የሸሸ፣ በገደል ይወድቃል፤ ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል። የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋል፣ የምድርም መሠረት ተናውጣለች።19ምድር ፈጽሞ ትሰባበራለች፣ ምድር ፈጽማ ደቀቀች፤ ምድር በኃይል ትነዋወጣለች።20ምድር እንደ ሰካራም ሰው ትንገዳገዳለች፣ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች። መተላለፍዋ ይከብድባታል፣ ትወድቃለች ደግማም አትነሣም።21በዚያም ቀን እንደዚህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በከፍታ ያለውን ሠራዊት በከፍታ ላይ፣ በምድርም ያሉትን ነገሥታት በምድር ላይ ይቀጣቸዋል።22ግዞተኞች በጕድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ፣ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፣ ከብዙ ቀንም በኋላ ይፈረድባቸዋል።23ከዚያም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ይነግሣልና፣ በሽማግሌዎቹም ፊት ክብር ይሆናልና ጨረቃ ያፍራል፣ ፀሐይም ይዋረዳል።
1እግዚአብሔር፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር፣ ከጥንት የታቀዱትን በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ።2ከተማይቱን የድንጋይ ክምር፣ የተመሸገችውን ከተማ ውድማ እንድትሆን፣ የኀጥአንንም አዳራሽ ከተማ እንዳትሆን አድርገሃል፤ ከቶ አትሠራም።3ስለዚህ ኃያላኑ ወገኖች ያከብሩሃል፤ የጨካኞች አሕዛብ ከተማም ትፈራሃለች።4የጨካኞችም ቍጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፣ ለድሀው መጠጊያ፣ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መጠጊያ፣ ከውሽንፍር መሸሸጊያ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።5እንደ በረሃ ሙቀት፣ የኀጥአንን ጩኸት ዝም ታሰኛለህ፤ ሙቀትም በደመና ጥላ እንዲበርድ እንዲሁ የጨካኞች ዝማሬ ይዋረዳል።6የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፣ የተመረጠ የወይን ጠጅ፣ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፣ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።7በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል።8ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፣ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።9በዚያም ቀን፣ "ተመልከቱ፣ አምላካችን ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፣ ያድነንማል። እግዚአብሔር ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን" ይባላል።10የእግዚአብሔርም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፣ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በስፍራው ይረገጣል።11ዋናተኛ ለመዋኘት እጁን እንደሚዘረጋ፣ እንዲሁ በመካከሉ እጁን ይዘረጋል፤ ነገር ግን ምንም ያክል እጆቹ ቢወራጭም እግዚአብሔር ትዕቢቱን ያዋርዳል።12ከፍ ያሉት የተመሸገው ቅጥርህን እስከ ትቢያ ድረስ ዝቅ ያደርገዋል።
1በዚያም ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ላይ ይዘመራል። የጸናች ከተማ አለችን፤ ለቅጥርና ለምሽግ መድኃኒትን አድርጎባታል።2እውነትን የሚጠብቅ ጻድቅ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮችን ክፈቱ።3በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትጸና አእምሮ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።4ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።5በኩራት የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፤ የተመሸገችውን ከተማ ወደ ምድር ያዋርዳል፤ እስከ መሬት ድረስ ያወርዳታል፤ እስከ አፈርም ድረስ ያርዳታል።6በድሆች እንዲሁም በችግረኞች ረገጣ የምትረገጥ ትሆናለች።7የጻድቃን መንገድ ደልዳላ ናት፣ አንተ ጻድቅ የሆንህ የጻድቃንን መንገድ ታቃናለህ።8አዎን፣ በፍርድህ መንገድ ጠብቀንሃል፤ ስምህም መታሰቢያህም ምኞታችን ነው።9ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች። ፍርድህ ወደምድር በመጣ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና።10ለኃጢአተኛ ሞገስ ይደረግለት፣ ነገር ግን ጽድቅን አይማርም። በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋል፤ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያይም።11እግዚአብሔር ሆይ፣ እጅህ ከፍ ብላ ተነሣች፣ ነገር ግን አላስተዋሉም። ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ ምክንያቱም እሳትም ጠላቶችህን ትበላቸዋለች።12እግዚአብሔር ሆይ፣ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ።13አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፣ ከአንተ በተጨማሪ ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤ ነገር ግን የአንተን ስም ብቻ እናስባለን።14እነርሱ ሞተዋል፣ በሕይወት አይኖሩም፤ ሞተዋል፣ አይነሡም፤ በእርግጥ፣ አንተ በፍርድ መጥተህ አጥፍተሃቸዋል፣ መታሰቢያቸውን ሁሉ እንዲጠፋ አድርገሃል።15እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝብን አበዛህ፣ ሕዝብን አበዛህ፤ አንተም ተከበርህ፣ የአገሪቱን ዳርቻ ሁሉ አሰፋህ።16እግዚአብሔር ሆይ፣ በመከራ ጊዜ ተመለከቱህ፤ ቅጣትህ በእነርሱ ላይ በሆነ ጊዜ ድግምታቸውን ሳይቀር በክፉው ላይ ተናገሩ።17የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትታመምና በምጥ እንደምትጮኽ፣ አቤቱ፣ እንዲሁ በፊትህ ሆነናል።18እኛ ፀንሰናል፣ ምጥም ይዞናል፣ ነገር ግን ነፋስን እንደምንወልድ ሆነናል፤ ድነትን ወደምድር አላመጣንም፣ በዓለምም የሚኖሩ አልወደቊም።19ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፣ ጠልህ የመድሃኒት ጠል ነውና፣ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።20ሂድ ሕዝቤ ሆይ፣ ወደ ክፍሎችህ ግባና ደጅህን በኋላህ ዝጋ፤ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።21ተመልከት፣ በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቍጣውን ያመጣባቸው ዘንድ፣ እነሆ፣ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፣ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።
1በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራ፣ በታላቅ፣ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፥ በባሕርም ውስጥ ያለውን አውሬ ይገድላል።2በዚያም ቀን፣ ለተወደደው የወይን ቦታ ተቀኙለት።3"እኔ፣ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፤ ሁልጊዜ አጠጣዋለሁ፤ ማንም እንዳይጐዳው በሌሊትና በቀን እጠብቀዋለሁ።4እሾህና ኵርንችት ለሰልፍ በመኖራቸው አልተቈጣሁም! በውጊያ በእነርሱ ላይ ተራምጄ፣ በአንድነት ባቃጠልኋቸው ነበር።5ከለላነቴን ካልያዙና ከእኔ ጋር ሰላም ካላደረጉ፣ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርጉ።6በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፣ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።"7በውኑ የመቱትን እንደ መታ እንዲሁ እርሱን መታውን? ወይስ እነርሱ እንደ ተገደሉበት መገደል ያዕቆብና እስራኤል ተገድሎአልን?8ያዕቆብና እስራኤልን ለማባረር በታገልክበት መጠን፣ እርሱ ነዳቸው ሰደዳቸው ቀሠፋቸው፤ የምሥራቅ ነፋስ በሚነፍስበት ቀን በጠንካራ ዐውሎ ነፋስ አስወገዳቸው።9ስለዚህም በዚህ መንገድ፣ የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፣ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፣ ይህም ከኀጢአት የመመለስ ፍሬ ሁሉ ነው።10የተመሸገችው ከተማ ጠፋች፣ እንደ ምድረ በዳ የተፈታችና የተተወች መኖሪያ ናት። በዚያም ጥጃ ይሰማራል፣ በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።11ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ። ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።12በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ምንጭ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ሕዝቦች ሆይ፣ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።13በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፣ በአሦርም የጠፉ፣ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፣ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።
1ለኤፍሬም ሰካሮች ትዕቢት አክሊል፣ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ በወፍራም ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮ!2እነሆ፣ በጌታ ዘንድ ኃያል ብርቱ የሆነ አለ። እንደ በረዶ ወጨፎ፣ እንደሚያጠፋም ወጀብ፣ እንደሚያጥለቀልቅም እንደ ታላቅ ውኃ ፈሳሽ በጠነከረ እጅ ምድርን ያጠቃል።3የኤፍሬም ሰካሮች ትዕቢት አክሊል በእግር ይረገጣል፤4በወፍራሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ፣ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ ሰው ባያት ጊዜ በእጁ እንዳለች ይበላታል።5በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፤6በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥም የፍርድ መንፈስ፣ ሰልፉን ወደ በር ለሚመልሱም ኃይል ይሆናል።7እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ። ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፣ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ። ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፤ በራእይ ይስታሉ፣ በፍርድም ይሰናከላሉ።8በእውነት፣ ገበታው ሁሉ ትውከትን ተሞልቷል፤ ንጹሕ ስፍራ እንኳ የለም።9እውቀትን ለማን ያስተምረዋል፣ ወይስ መልእክቱን ለማን ያስረዳል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?10ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ሥርዓት በሥርዓት ላይ፣ ደንብ በደንብ ላይ፣ እዚህ ጥቂት፣ ጥቂት በዚያ ነው።11በእርግጥ፣ በፌዘኛ አፍ በሌሎችም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤12"ይህች እረፍት ናት፣ የደከመውን አሳርፉ፤ ይህችም የምታድስ ማረፊያ ናት" አላቸው፤ እነርሱ ግን አልሰሙም።13ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ እንዲሰበሩም ተጠምደውም እንዲያዙ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ሥርዓት በሥርዓት ላይ፣ ሥርዓት በሥርዓት ላይ፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።14ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ይህንን ሕዝብ የምትገዙ ፌዘኞች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።15እናንተም፣ "ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፣ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ስለዚህ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፣ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም" አላችሁ።16ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። "ተመልከቱ፡ በጽዮን የመሠረት ድንጋይን አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን ድንጋይ፣ የከበረውን፣ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ። የሚያምን እርሱ አያፍርም።17ለገመድ ፍርድን፣ ለቱንቢም ጽድቅን አደርጋለሁ። በረዶውም የሐሰትን መሸሸጊያ ይጠርጋል፣ ውኆችም መሰወሪያውን ያሰጥማሉ።18ከሞትም ጋር ያደረጋችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፣ ከሲኦልም ጋር የተማማላችሁት መሐላ አይጸናም። የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ ትረገጡበታላችሁ።19ባለፈም ጊዜ ይወስዳችኋል፤ ማለዳ ማለዳ ቀንና ሌሊት ያልፋል፤ መልእክቱ በገባቸው ጊዜ ድንጋጤ ይሆናል።20ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፤ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ ብርድልብሱ እጅግ ጠባብ ነው።"21እግዚአብሔርም ሥራውን፣ ማለትም እንግዳ የሆነ ሥራውን ይሠራ ዘንድ፣ አድራጎቱንም ማለት ያልታወቀውን አድራጎቱን ያደርግ ዘንድ በፐራሲም ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፣ በገባዖንም ሸለቆ እንደ ነበረ ይቈጣል።22አሁንም እስራት እንዳይጸንባችሁ አታፊዙ። በምድር ሁሉ ላይ የሚጸናውን የጥፋት ትእዛዝ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና።23በትኩረት አድምጡና ድምፄን ስሙ፤ ልብ አድርጉ ንግግሬንም ስሙ።24በውኑ ገበሬ ሊዘራ ሁልጊዜ ያርሳልን? ወይስ ሁልጊዜ እርሻውን ይጎለጉላልን?25እርሻውን ባስተካከለ ጊዜ ጥቁሩን አዝሙድ፣ ከሙኑንም፣ ስንዴውንም፣ በተርታ፣ ገብሱንም በስፍራው፣ አጃንም በደረጃው የሚዘራ አይደለምን?26አምላኩ ያስታውቀዋል፣ በብልሃት ያስተምረውማል።27በተጨማሪም፣ ጥቁሩ አዝሙድ በተሳለች መሄጃ አያስኬድም፣ የሰረገላም መንኰራኵር በከሙን ላይ አይዞርም፤ ነገር ግን ጥቁሩ አዝሙድ በሽመል ከሙኑም በበትር ይወቃል።28የእንጀራ እህል ይደቅቃል፣ ነገር ግን ለዘላለም አያኬደውም፤ የሰረገላውን መንኰራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቅቀውም።29ይህም ደግሞ ድንቅ ምክር ከሚመክር በግብሩም ማለፊያ ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል።
1ዳዊት ሰፍሮባት ለነበረችው ከተማ ለአርኤል፣ ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፣ በዓላትም ተመልሰው ይምጡ።2ነገር ግን አርኤልንም እከብባለሁ፣ ለቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ ለእኔም እንደ አርኤልም ትሆንልኛለች።3በዙሪያሽም እሰፍራለሁ፣ በቅጥርም ከብቤ አስጨንቅሻለሁ፣ አምባም በላይሽ አቆማለሁ።4ትዋረጂማለሽ፣ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፣ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፤ ድምፅሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፣ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ በደካማነት ይጮኻል።5ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፣ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል። በድንገት፣ በፍጥነትም ይሆናል።6የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፣ በምድርም መናወጥ፣ በታላቅም ድምፅ፣ በዐውሎ ነፋስም፣ በወጨፎም፣ በምትባላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።7በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፣ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፣ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል። ሊያስጨንቋት እርሷንና ምሽጎቿን ያጠቃሉ።8የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ እንደሚያይ፣ ነገር ግን ሲነቃ ሆዱ ባዶ እንደሆነው ያክል ነው። የተጠማም ሰው በሕልሙ እየጠጣ እንደሚያይ፣ ነገር ግን ሲነቃ ጥሙ ሳይቆርጥለት ይዝላል። እንዲሁ የጽዮንን ተራራ የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት ይሆናል።9ለራሳችሁ ተደነቁ፣ ተገረሙም፤ ራሳችሁን አሳውሩ፣ የታወራችሁ ሁኑ! በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ሰከሩ፤ በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገደገዱ።10እግዚአብሔር የጥልቅ እንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል። ዐይኖቻችሁን አጨፍኗል፣ ራሶቻችሁን ደግሞ ነቢያት አጨፍነውባችኋል።11ራእይ ሁሉ እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ። ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ። ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል፤12ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ "ይህን አንብብ" ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፣ "ማንበብ አልችልም" ይላቸዋል።13ጌታም አለ፣ "ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፣ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፣ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው። የሚያከብሩኝ ሰዎች ባስተማሩት ትእዛዝ ነው።14ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል ለማድረግ እቀጥላለሁ፤ ድንቅ ነገርን በድንቅ ነገር ላይ አደርጋለሁ። የጥበበኞቻቸውም ጥበብ ትጠፋለች፣ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።"15ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፣ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፣ "ማን ያየናል፣ ወይስ ማን ያውቀናል?" ለሚሉ ወዮላቸው!16ነገሮችን ገለባብጣችኋል! የተሠራው ነገር የሠራውን "አልሠራኝም፣" ይለው ዘንድ ሸክላ ሠሪው እንደ ጭቃው ሊቆጠር ይገባልን? ወይስ የተበጀው ነገር ያበጀውን "አታስተውልም" ይለዋልን?17ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈጠር ጥቂት የቀረው አይደለምን?18በዚያም ቀን ደንቆሮች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፣ የዕውሮችም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተለይተው ያያሉ።19የተጨቆኑ ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ፣ በሰዎች መካከል ያሉ ድሆችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ።20ጨካኙ ይቋረጣልና፣ ፌዘኛውም ይጠፋልና። ክፋትን ማድረግ የሚወድዱ ይወገዳሉ።21እነዚህም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ። በበርም ለሚገሥጸው ወጥመድ የሚያኖሩ፣ ጻድቁንም በከንቱ ውሸት የሚያስቱ ናቸው።22ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፣ "ያዕቆብ ከእንግዲህ አያፍርም፣ ፊቱም አይገረጣም።23ነገር ግን የእጄ ሥራ የሆኑትን ልጆቹን ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ። የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፣ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።24በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያገኛሉ፣ የሚያጕረመርሙም ትምህርትን ይቀበላሉ።"
1"ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው፣" ይላል እግዚአብሔር። "ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ዕቅድ ይመክራሉ፣ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ይጨምሩ ዘንድ በመንፈሴ ያልተመራውን የትብብር ኪዳን ያደርጋሉ።2ከእኔም ምሪትን ሳይጠይቁ ወደ ግብጽ ይሄዱ ዘንድ ይወጣሉ። በፈርዖን ኃይል ይጸኑ ዘንድ በግብጽም ጥላ ይታመኑ ዘንድ ይፈልጋሉ።3ስለዚህ የፈርዖን ከለላ እፍረት፣ በግብጽም ጥላ መታመን ውርደት ይሆንባችኋል።4አለቆቻቸው በጣኔዎስ ቢሆኑ እንኳን፣ መልክተኞቻቸውም ወደ ሓኔስ ቢደርሱ እንኳን።5ሁላቸው ይጠቅሙአቸው ዘንድ ስለማይችሉ፣ እፍረትና ስድብ እንጂ ረድኤትና ረብ ስለማይሆኑ ሕዝብ ያፍራሉ።6በኔጌቭ ስላሉ አውሬዎች የተነገረ ሸክም፦ ተባትና እንስት አንበሳ እፉኝትም ነዘር እባብም በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።7የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምናምን ነው፤ ስለዚህ ስሙን፣ ተረጋግጦ የሚቀመጥ ረዓብ ብዬ ጠርቼዋለሁ።8አሁንም ሂድ፣ ለሚመጣውም ዘመን ለምስክርነት እንዲሆን በሰሌዳ ላይ በመጽሐፍም ውስጥ ጻፍላቸው።9እነዚህ ዓመፀኛ ሕዝብ ናቸውና፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ለመስማት የማይወድዱ የሐሰት ልጆች ናቸውና።10ለባለ ራእዮች፣ "አትመልከቱ፤" ይላሉ፣ ለነቢያትም፣ "የለዘበውን ነገር፣ አታላዩን ነገር እንጂ፣ ቀጥተኛውን እውነት አትንገሩን፤11ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፤ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፤ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ" ይሉአቸዋል።12ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፣ "ይህችን ቃል አቃልላችሁ፣ በግፍና በጠማምነት ታምናችኋልና፣ በእርሱም ተደግፋችኋልና፣13ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፣ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።"14የሸክላ ሠሪ ማድጋ እንደሚሰበር ይሰብረዋል፤ ሳይራራም ያደቅቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት ወይም ውኃ ከጕድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።15የእስራኤል ቅዱስ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል። እናንተም እንቢ አላችሁ።16ነገር ግን፣ 'አይሆንም፣ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም' አላችሁ፣ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፣ 'በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን' አላችሁ፣ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።17ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ እናንተም በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፣ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፣ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ትሸሻላችሁ።"18ይሁን እንጂ እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፣ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብሩካን ናቸው።19በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ፣ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅሱም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራላችኋል፣ በሰማችሁም ጊዜ ይመልስላችኋል።20ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም፣ አስተማሪህ ከእንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፣ ነገር ግን አስተማሪህን በገዛ ራስህ ዐይኖች ታያለህ።21ወደ ቀኝም ወደ ግራም ብትዞር ከበስተኋላህ ጆሮችህ "መንገዱ ይህች ናት፣ በእርስዋም ሂድ" የሚለውን ቃል ይሰማሉ።22በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስ ጨርቅ ትጥላቸዋለህ። "ከዚህ ውጡ" ትላቸውማለህ።23በምድርም ለተዘራው ዘርህ ዝናብ ይሰጣል፣ ከምድርም ፍሬ የሚወጣ እንጀራ ወፍራምና ብዙ ይሆናል። እህሉም ብዙ ይሆናል። በዚያም ቀን ከብቶችህ በሰፊ መስክ ይግጣሉ።24መሬትንም የሚያርሱ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በወንፊት የነጻውን ጨው ጨው የሚለውን ገፈራ ይበላሉ።25በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ በረጅሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ።26እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፣ መቅሰፍቱ ያቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፣ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፣ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።27ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር ስም ከሚነድድ ቍጣ ከሚትጐለጐልም ጢስ ጋር ከሩቅ ይመጣል፤ ከንፈሮቹም ቍጣን የተሞሉ ናቸው፣ ምላሱም እንደምትበላ እሳት ናት።28እስትንፋሱም አሕዛብን በአጥፊ ወንፊት ሊነፋቸው እንደሚያጥለቀልቅ እስከ አንገትም እንደሚደርስ ወንዝ ነው፣ በሕዝብም መንጋጋ የሚያስት ልጓም ይሆናል።29ዝማሬ በተቀደሰች የዐውደ ዓመት ሌሊት እንደሚሆን ዝማሬ ይሆንላችኋል፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ እስራኤል አምባ ይመጣ ዘንድ እንቢልታ ይዞ እንደሚሄድ ሰው የልብ ደስታ ይሆንላችኋል።30እግዚአብሔርም ክቡር ድምፁን ያሰማል፣ የክንዱንም መውረድ በሚነድድ ቍጣውና በምትባላ እሳት ነበልባል፣ በዐውሎ ነፋስም በወጨፎም፣ በበረዶ ጠጠርም ይገልጣል።31አሦርም በበትር ከመታው ከእግዚአብሔር ድምፅ የተነሣ ይደነግጣል።32እግዚአብሔር በላዩ በሚያወርድበት የታዘዘበቱ የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ ይዋጋቸዋል።33ከጥንት ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች። በእርግጥ፣ ለንጉሥም ተበጅታለች፣ እግዚአብሔርም ጥልቅና ሰፊ አድርጎአታል። እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
1ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፣ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፣ (እጅግ ብርቱዎችም) ስለ ሆኑ፣ በፈረሰኞች ለሚታመኑ (የማይቆጠሩ ስለሆኑ) ፣ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ እግዚአብሔርንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!2እርሱ ደግሞ ጠቢብ ነው፣ ክፉንም ነገር ያመጣል፣ ቃሉንም አይመልስም። በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።3ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፣ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም። እግዚአብሔርም እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፣ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።4እግዚአብሔር የሚለኝ እንዲህ ነውና፣ "አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሳ፣ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ፣ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፣ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።5እንደሚበርር ወፍ፣ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፥ በላይዋ ሲያልፍ ይታደጋታል ያድናታልም።6እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፣ አጥብቃችሁ ወደ ዐመፃችሁበት ተመለሱ።7በዚያም ቀን እያንዳንዳቸው እጆቻቸው ለኃጢአት የሠሩላቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ይጥላሉና።8አሦርም በሰይፍ፣ የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፣ የሰውም ያልሆነ ሰይፍ ይበላዋል፤ ከሰይፍም ይሸሻሉ ጐበዛዝቱም ገባሮች ይሆናሉ።9አምባው ከፍርሃት የተነሣ ያልፋል፣ መሳፍንቱም ከዓላማው የተነሣ ይደነግጣሉ፤" ይላል እሳቱ በጽዮን፣ እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።
1ተመልከቱ፣ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፣ መሳፍንትም በፍርድ ይገዛሉ።2ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ፣ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፣ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፣ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ድንጋይ ጥላ ይሆናል።3ከዚያም፣ የሚያዩትም ሰዎች ዓይኖች አይደበዝዙም፣ የሚሰሙትም ጆሮች በትኩረት ያደምጣሉ።4ጥንቃቄ የሌላቸው ሰዎች ልብ እውቀትን ታስተውላለች፣ የተብታቦችም ምላስ በቀላሉ አድርጋ ትናገራለች።5ከእንግዲህ ወዲህ ሰነፍ ከበርቴ ተብሎ አይጠራም፣ አታላዩም የተገራ አይባልም።6ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፣ ልቡም ዝንጉነትን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔርም ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ፣ የተራበችውንም ሰውነት ባዶ ያደርግ ዘንድ፣ ከተጠማም ሰው መጠጥን ይቈርጥ ዘንድ በደልን ይሠራል።7የንፉግም ዕቃ ክፉ ናት። ችግረኛ ትክክል ነገርን በተናገረ ጊዜ እንኳ እርሱ በሐሰት ቃል ድሀውን ያጠፋ ዘንድ ክፉን አሳብ ያስባል።8ነገር ግን፣ ከበርቴው ሰው ለመከበር ያስባል፤ በመከበርም ጸንቶ ይኖራል።9እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፣ ተነሡ፣ ድምፄንም ስሙ፤ እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ንግግሬን አድምጡ።10እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፣ ወይንን መሰብሰብ ይቀራልና፣ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ።11እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፣ ተጠንቀቁ፤ ተማምናችሁም የምትቀመጡ ሆይ፣ ተንቀጥቀጡ፤ የቅምጥል ልብሳችሁን አውልቁ፣ ዕራቁታችሁን ሁኑ፣ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ።12ስለ ተወደደችውም እርሻ፣ ስለሚያፈራውም ወይን ደረታችሁን ድቁ።13በሕዝቤ ምድር ላይ፣ በደስታ ከተማ ባሉት በደስታ ቤቶች ሁሉ ላይ እሾህና ኵርንችት ይወጣባቸዋል፤14አዳራሹ ወና ትሆናለችና፣ የብዙ ሰውም ከተማ ትለቅቃለችና፣ አምባውና ግንቡም ለዘላለም ዋሻ፣ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፣ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናልና፤15ይህም፣ መንፈስ ከላይ እስኪፈስስልን፣ ምድረ በዳውም ፍሬያማ እርሻ እስኪሆን፣ ፍሬያማውም እርሻ ጫካ ተብሎ እስኪቈጠር ድረስ ይሆናል።16ከዚያ በኋላ ፍርድ በምድረ በዳ ይኖራል፤ ጽድቅም በፍሬያማው እርሻ ያድራል።17የጽድቅም ሥራ ሰላም፣ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።18ሕዝቤም በሰላም ማደሪያ፣ በታመነም ቤት በጸጥተኛ ማረፊያ ይቀመጣል።19በረዶ ግን በዱር ላይ ይወርዳል፣ ከተማም ፈጽማ ትዋረዳለች፣20እናንተ የበሬና የአህያ እግር እየነዳችሁ በውኃ ሁሉ አጠገብ የምትዘሩ ትባረካላችሁ።
1አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣ በአንተም ላይ ወንጀል ሳይደረግ ወንጀል የምታደርግ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ ትጠፋለህ፣ አሳልፎ መስጠትንም በተውህ ጊዜ አሳልፈው ይሰጡሃል።2እግዚአብሔር፣ ማረን፤ አንተን ተማምነናል፤ በየጠዋቱ ክንድ፣ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን።3ከታላቅ ጫጫታ ወገኖች ሸሹ፣ ስትነሣም አሕዛብ ተበትነዋል።4አንበጣ እንደሚሰበስብ፣ ምርኮአችሁ ትሰበሰባለች፣ ኩብኩባም እንደሚዘልል፣ ሰዎች ይዘልሉበታል።5እግዚአብሔር ገነነ። እርሱ በአርያም ይኖራል። ጽዮንን በፍትህና በጽድቅ ሞላት።6የዘመንህም ጸጥታ፣ የመድኃኒት ብዛት፣ ጥበብና እውቀት ይሆናል፤ እግዚአብሔርን መፍራት መዝገቡ ነው።7ተመልከቱ፣ ባለሥልጣናቶቻቸው በጎዳና ይጮኻሉ፤ የሰላም መልእክተኞች መራራ ለቅሶ ያለቅሳሉ።8መንገዶች ተራቆቱ፣ ተላላፊም ቀረ፤ እርሱም ቃል ኪዳንን አፈረሰ፣ ከተሞችንም ናቀ ሰውንም አልተመለከተም።9ምድሪቱ አለቀሰች ከሳችም፤ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ።10"አሁን እነሣለሁ" ይላል እግዚአብሔር፤ "አሁን እከበራለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ።"11ገለባን ትፀንሳላችሁ፣ እብቅንም ትወልዳላችሁ፤ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት።12አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፣ ተቈርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።13እናንተ በሩቅ ያላችሁ፣ የሠራሁትን ስሙ፣ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኃይሌን እወቁ።"14በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፣ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ፤ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለምም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ?15በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፤ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ፥ መማለጃ ጉቦን ከመጨበጥ እጁን የሚያርቅ፣ ደም የማፍሰስ ወንጀልን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቍር፣ ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው።16እርሱ ከፍ ባለ ስፍራ ይቀመጣል፣ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፣ እንጀራም ይሰጠዋል፣ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።17ዓይኖችህ ንጉሥን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ሰፊ ምድርን ያዩአታል።18ልብህም፣ ጸሐፊ ወዴት አለ? ገንዘቡንስ መዛኝ ወዴት አለ? ግንቦቹንስ የቈጠረ ወዴት አለ? ብሎ የሚያስፈራ ነገር ያስባል።19ጨካኝን ሕዝብ፣ ቋንቋው ለማስተዋል ጥልቅ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ፣ አታይም።20የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፣ ዓይኖችህ የሰላም ማደሪያ፣ ካስማውም ለዘላለም የማይነቀል፣ አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ፣ የማይወገድ ድንኳን የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ።21ይልቅ፣ እግዚአብሔር በዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ ከእኛ ጋር በግርማ ይሆናል። የሚቀዘፉ መርከቦች አይጓዙባትም፣ ታላላቆችም መርከቦች አያልፉባትም።22እግዚአብሔር ፈራጃችን ነውና፣ እግዚአብሔር ሕግን የሰጠን ነውና፣ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።23ገመዶችህ ላልተዋል፣ ደቀላቸውንም አላጸኑም፣ ሸራውንም መዘርጋት አልቻሉም፤ በዚያም ጊዜ የብዙ ምርኮ ብዝበዛ ተከፈለ፤ አንካሶች እንኳ ብዝበዛውን በዘበዙ።24በዚያም የሚኖር፣ "ታምሜአለሁ፣" አይልም፤ በእርስዋም ለሚቀመጡ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።
1እናንተ አሕዛብ ሆይ፣ ቅረቡ፣ ስሙ፤ እናንተ ሕዝቦች ሆይ፣ አድምጡ! ምድርና ሞላዋ፣ ዓለምና ከእርስዋ የሚወጣ ሁሉ ይስሙ።2የእግዚአብሔር ቍጣ በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ መዓቱም በሠራዊታቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ፈጽሞ አጠፋቸው፣ ለመታረድም አሳልፎ ሰጣቸው።3ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ፣ የሬሳቸውም ግማት በሁሉ ቦታ ይሸታል፣ ተራሮችም በደማቸው ይርሳሉ።4የሰማይም ሠራዊት ሁሉ ይበሰብሳሉ፣ ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ፣ ከወይንና ከበለስም ቅጠል እንደሚረግፍ፣ ሠራዊታቸው ሁሉ ይረግፋል።5ሰይፌ በሰማይ ሆና እስክትረካ ድረስ ጠጥታለች፤ ተመልከቱ፣ በኤዶምያስና በረገምሁት ሕዝብ ላይ አሁን ለፍርድ ትወርዳለች።6የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፣ በስብም፣ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፣ በአውራም በግ ኵላሊት ስብ ወፍራለች። እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፣ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና።7ጎሽ ከእነርሱ ጋር፣ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትረካለች፣ አፈራቸውም በስብ ትወፍራለች።8የእግዚአብሔር የበቀሉ ቀን፣ ስለ ጽዮንም ክርክር የብድራት ዓመት ነው።9የኤዶምያስም ምንጮች ዝፍት ሆነው ይለወጣሉ፣ አፈርዋም ዲን ይሆናል፣ መሬትዋም የሚቀጠል ዝፍት ትሆናለች።10በሌሊትና በቀንም ይቃጠላል፣ ጢስዋም ለዘላለም ይወጣል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፤ ለዘላለም ዓለም ማንም አያልፍባትም።11ነገር ግን፣ ጭልፊትና ጃርት ግን ይኖሩባታል፤ ጕጕትና ቍራም መረባቸውን ይሠሩባታል። በላይዋም የመፍረስ ገመድና የባዶነት ቱንቢ ይዘረጋባታል።12መሳፍንቶችዋን ወደ መንግሥት ይጠራሉ፣ ነገር ግን ማንም አይገኝባትም፤ አለቆችዋም ሁሉ ምናምኖች ይሆናሉ።13በቤተ መንግሥቶቿ እሾህ፣ በቅጥሮችዋም ሳማን፣ አሜከላ ይበቅሉባታል፤ የቀበሮም ማደሪያና የሰጐን ስፍራ ትሆናለች።14የምድረ በዳም አራዊት ከተኵሎች ጋር ይገናኛሉ፣ አጋንንትም እርስ በርሳቸው በጩኸት ይጠራራሉ፤ ጅንም በዚያ ትኖራለች ለእርስዋም ማረፊያ ታገኛለች።15በዚያም ዋሊያ ቤትዋን ትሠራለች፣ እንቍላልም ትጥላለች ትቀፈቅፈውማለች ልጆችዋንም በጥላዋ ትሰበስባለች፤ በዚያም ደግሞ አሞራዎች እያንዳንዳቸው ከባልንጀሮቻቸው ጋር ይሰበሰባሉ።16በእግዚአብሔር የመጽሐፍ ጥቅልል ውስጥ ፈልጉ፣ አንዳቸውም አይጠፉም። አፌ አዝዞአልና፣ መንፈሱም ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፣ ባልንጀራውንም የሚያጣ የለም።17እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፣ እጁም በገመድ ከፈለችላቸው፤ ለዘላለም ይገዙአታል፣ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይቀመጡባታል።
1ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፣ በረሀውም ሐሤት ያደርጋል እንደ ጽጌ ረዳም ያብባል።2እጅግ ተትረፍርፎ ያብባል፣ በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።3የደከሙትን እጆች አበርቱ፣ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ።4ፈሪ ልብ ላላቸው፣ "ተመልከቱ፣ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፣ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፣ አትፍሩ" በሉአቸው።5በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ያያል፣ የደንቆሮችም ጆሮ ይሰማል።6በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፣ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፣ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።7ደረቂቱ ምድር ኵሬ፣ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸምበቆ ደንገልም ይሆንበታል።8በዚያም ጐዳናና መንገድ ይሆናል እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል። ንጹሐንም ያልሆኑ አይጓዙበትም። ነገር ግን ለሚጓዙበት ይሆናል፤ ተላላፊዎችና ሰነፎች አይጓዙበትም።9አንበሳም አይኖርበትም፣ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፣ ከዚያም አይገኙም፤ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፤10እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፣ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
1እንዲህም ሆነ፣ በንጉሡ ሕዝቅያስ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጥቶ ያዛቸው።2ከዚያም፣ የአሦርም ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፣ እርሱም በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛይቱ ኵሬ መስኖ አጠገብ ቆመ።3የቤቱም አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እርሱ ወጡ።4ራፋስቂስም እንዲህ አላቸው፣ "ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፣ "ይህ የምትታመንበት መተማመኛ ምንድር ነው?5እኔ፣ ለሰልፍ የሆነው ምክርህና ኃያልህ ከንቱ ነገር ነው አልሁ፤ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው?6ተመልከት፣ እየታመንክ ያለኸው በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብጽ ነው። ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል ያቈስለውማል። የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ አንዲሁ ነው።7አንተም፣ "በአምላካችን በእግዚአብሔር እንታመናለን ብትለኝ፣ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን፣ "በዚህ መሠዊያ ፊት ስገዱ" ብሎ የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ይስፈረሰ ይህ አይደለምን?8አሁን እንግዲህ፣ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር በመልካም ተደራደር። የሚጋልቡባቸውንም ሰዎች ማግኘት ቢቻልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።9ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሶኞች በግብጽ ስትታመን፣ ከጌታዬ ባሪያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ትቃወም ዘንድ እንዴት ይቻልሃል?10አሁንም በውኑ ያለ እግዚአብሔር ትእዛዝ ይህን አገር አጠፋ ዘንድ ወጥቻለሁን? እግዚአብሔር፣ "ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው" አለኝ።11ከዚያም ኤልያቄምና ሳምናስ፣ ዮአስም ራፋስቂስን፣ "እኛ እንሰማለንና እባክህ፣ በሶርያ ቋንቋ ለባሪያዎችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን" አሉት።12ራፋስቂስ ግን፣ "ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ አንተና ወደ ጌታህ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ዐይነምድራቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን?" አላቸው።13ራፋስቂስም ቆሞ በታላቅ ድምፅ በአይሁድ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጮኸ፣ "የታላቁን የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ፤14ንጉሡ እንዲህ ይላል፣ 'ያድናችሁ ዘንድ አይችልምና ሕዝቅያስ አያታልላችሁ።15ሕዝቅያስም፣ "እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም" ብሎ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።16ሕዝቅያስንም አትስሙ፣ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፦ 'ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ውጡ። እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፣ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ።17ይህም መጥቼ ምድራችሁን ወደምትመስለው ምድር፣ እህልና የወይን ጠጅ፣ እንጀራና ወይን ወዳለበት ምድር እስካፈልሳችሁ ድረስ ነው።'18ሕዝቅያስም፣ 'እግዚአብሔር ያድነናል' ብሎ እንዳያታልላችሁ ተጠንቀቁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት አገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋልን?19የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?20እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ከእጄ ያድን ዘንድ ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ አገሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?"21ነገር ግን ንጉሡ አንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና ሕዝቡ ዝም አሉ፣ አንዳችም አልመለሱለትም።22ከዚያም የቤቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፣ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።
1እንዲህም ሆነ፣ ንጉሡ ሕዝቅያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፣ ማቅም ለበሰ፣ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገባ።2የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን፣ ጸሐፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።3እነርሱም፣ "ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፣ 'ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል፣ እናታቸው ግን ለመውለድ ኃይል የላትም።4ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደ ሆነ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፣ ስለዚህ አሁን ድረስ እዚህ ላለው ቅሬታ ጸልይ" አሉት።5ስለዚህ የንጉሡ የሕዝቅያስ ባሪያዎች ወደ ኢሳይያስ መጡ፣6ኢሳይያስም እንዲህ አላቸው፣ ለጌታችሁ እንዲህ በሉት፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የአሦር ንጉሥ ባሪያዎች ስለ ሰደቡኝ፣ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ።7ተመልከት፣ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፣ ወሬንም ይሰማል፣ ወደ ምድሩም ይመለሳል። በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ" በሉት" አላቸው።8ከዚያም የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበርና ራፋስቂስ ተመልሶ በልብና ሲዋጋ አገኘው።9እርሱም፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ እና ግብጽ ሊወጉህ መጥቶአል የሚል ወሬ ሰማ። በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፦10እንዲህ ሲል፣ "ለይሁዳ ንጉሠ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ 'ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም ብሎ የምትታመንበት አምላክህ አያታልልህ።'11ተመልከት፣ የአሦር ነገሥታት በምድር ሁሉ ላይ ያደረጉትን፣ እንዴትስ ፈጽመው እንዳጠፉአቸው ሰምተሃል። አንተስ ትድናለህን?12አባቶቼ ያጠፉአቸውን ጎዛንን፣ ካራንን፣ ራፊስን፣ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?13የሐማት ንጉሥ፣ የአርፋድ ንጉሥ፣ የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፣ የሄናና የዒዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?"14ሕዝቅያስም ደብዳቤውን ከመልእክተኞች እጅ ተቀብሎ አነበበው። ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው።15ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጸለየ፣16"አቤቱ፣ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፣ አንተ ብቻህን የምድር መንግሥታት ሁሉ አምላክ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን ፈጥረሃል።17አቤቱ፣ ጆሮህን አዘንብልና ስማ። አቤቱ፣ ዐይኖችህን ክፈትና እይ፤ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬም ቃል ስማ።18አቤቱ፣ በእውነት የአሦር ነገሥታት ዓለሙን ሁሉ አገሮቻቸውንም አፍርሰዋል፣19አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፣ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።20እንግዲህም አምላካችን አቤቱ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድነን።"21ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላከ፣ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ ለምነሃልና22እግዚአብሔር ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣ ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል ንቃሃለች፣ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።23የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግህበት ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው።24አንተም፣ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፣ ወደ ሊባኖስ ጥግ ላይ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፣ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ።25ቈፈርሁም ውኃም ጠጣሁ የግብጽንም ወንዞች ሁሉ በእግሬ ጫማ አደርቃለሁ ብለህ በባሪያዎችህ እጅ በጌታ ላይ ተገዳደርህ።'26እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፣ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።27ስለዚህ የሚኖሩባቸው ሰዎች እጃቸው ዝሎአል፣ ደንግጠውም ታውከዋል። እንደ ምድረ በዳ ሣር፣ እንደ ለመለመም ቡቃያ፣ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፣ ሳይሸት ዋግ እንደ መታው እህል ሆነዋል።28ነገር ግን እኔ መቀመጫህንና መውጫህን፣ መግቢያህንም በእኔም ላይ የተቈጣኸውን ቍጣ አውቄአለሁ።29ቍጣህና ትዕቢትህ ወደጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፣ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።"30ይህም ምልክት ይሆንሃል፦ በዚህ ዓመት የገቦውን፣ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ። በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ ታጭዱማላችሁ፣ ወይንም ትተክላላችሁ ፍሬውንም ትበላላችሁ።31ያመለጠው የይሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፣ ወደ ላይም ያፈራል።32ከኢየሩሳሌም ቅሬታ፣ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይወጣሉና።' የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።"33ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፣ "ወደዚህች ከተማ አይመጣም፣ ፍላጻንም አይወረውርባትም። በጋሻም አይመጣባትም፣ የአፈርንም ምሽግ አይደለድልባትም።34በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፤ ወደዚችም ከተማ አይመጣም፤ ይላል እግዚአብሔር።35ስለ እኔም፣ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት፣ ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ።"36የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፣ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ። ማለዳም በተነሡ ጊዜ፣ እነሆ፣ ሁሉ በየሥፍራው በድኖች ተረፍርፈው ነበሩ።37የአሦርም ንጉሥ ሰናክሬም ተነሥቶ ሄደ፣ ተመልሶም በነነዌ ተቀመጠ።38ኋላ ላይ፣ በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ፣ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት። ወደ አራራትም አገር አመለጡ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
1በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ለሞት እስኪደርስ ድረስ ታመመ። ስለዚህ፣ ነቢዩ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል' አለው።2ከዚያም፣ ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፣3"አቤቱ፣ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ።" ሕዝቅያስም እየጮኸ አለቀሰ።4ከዚያም የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ፣5"ሂድ፣ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፣ 'የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፣ እንባህንም አይቻለሁ። ተመልከት፣ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት አጨምራለሁ።6አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፣ ይህችንም ከተማ እጋርዳታለሁ።7እግዚአብሔርም የተገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል፦8ተመልከት፣ በአካዝ የጥላ ስፍረ-ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋር የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።" ስለዚህ ፀሐይም በጥላ ስፍረ-ሰዓት ላይ የወረደበት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።9የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ታምሞ ከደዌው በተፈወሰ ጊዜ የጻፈው ጽሕፈት ይህ ነው፦10"እኔ፣ በሕይወት ዘመኔ መካከል ወደ ሲኦል በሮች እገባለሁ፤ የቀረው ዘመኔ ጐደለብኝ አልሁ።11ደግሞም፣ በሕያዋን ምድር እግዚአብሔርን አላይም፤ በዓለምም ከሚኖሩ ጋር ሰውን እንግዲህ አልመለከትም አልሁ።12ማደሪያዬ ተነቀለች፣ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፤ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፤ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፤ ከማለዳም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።13እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፤ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፤ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።14እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፣ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፤ ዓይኖቼ ወደ ላይ ከማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፣ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።15ምን እላለሁ? እርሱ ተናግሮኛል፣ እርሱ ራሱም ይህን አድርጎአል፤ በዘመኔ ሁሉ ስለ ነፍሴ ምሬት ቀስ ብዬ እሄዳለሁ።16ጌታ ሆይ፣ የላክኸው መከራ ለእኔ መልካም ነው፤ ሕይወቴ ተመልሶ ይሰጠኝ፤ አንተም ፈወስኸኝ ወደ ሕይወትም መለስኸኝ።17ታላቅ ምሬት ለጥቅሜ ሆነ። አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጕድጓድ አዳንሃት፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጥለሃልና።18ሲኦል አያመሰግንህምና፤ ሞትም አያከብርህምና፤ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም።19እኔ ዛሬ አንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፤ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል።20እግዚአብሔር ያድነኛል፣ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው ዕቃ እንዘምራለን።"21አሁን ኢሳይያስም፣ "የበለስ ጥፍጥፍ አምጥተው በእባጩ ላይ ይለብጡት፣ እርሱም ይፈወሳል" ብሎ ነበር።22ሕዝቅያስም፣ "ወደ እግዚአብሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድር ነው?" ብሎ ነበር።
1በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን፣ ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።2ሕዝቅያስም በእነዚህ ነገሮች ደስ አለው፣ ግምጃ ቤቱንም፣ ብሩንና ወርቁንም፣ ቅመሙንና የከበረውንም ዘይት፣ መሣርያም ያለበትን ቤት ሁሉ፣ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።3ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ "እነዚህ ሰዎች ምን አሉህ? ከወዴትስ መጡ?" አለው። ሕዝቅያስም፣ "ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ" አለው።4እርሱም፣ "በቤትህ ያዩት ምንድር ነው?" አለው። ሕዝቅያስም፣ "በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም" አለው።5ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፣ "የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።6'ተመልከት፣ በቤትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ፣ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል። ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።7ከአንተም ከሚወለዱት ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ" አለው።8ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፣ "የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው" አለው። ደግሞም፣ "በዘመኔ ሰላምና እውነት ይሁን" አለ።
1"አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ" ይላል አምላካችሁ።2ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፣ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፣ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ።3የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪ ቃል፣ "የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ አዘጋጁ፤ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካክሉ።"4ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፣ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፣ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤5የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፣ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፣ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።6አንድ ድምጽ፣ "ጩኽ" ይላል፣ "ምን ብዬ ልጩኽ?" አልሁ። "ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፣ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።7የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው።8ሣሩ ይደርቃል፣ አበባውም ይረግፋል፣ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።"9የምስራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፣ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ፣ የምስራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ድምፅሽን በኃይል አንሺ፣ አንሺ፣ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች፣ "እነሆ፣ አምላካችሁ!" ብለሽ ንገሪ።10ተመልከቱ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይመጣል። ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል፤ እነሆ፣ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው።11መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።12ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፣ ሰማይንም በስንዝር የለካ፣ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?13የእግዚአብሔርን መንፈስ ያዘዘ፣ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው?14ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው?15ተመልከቱ፣ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፣ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ ተመልከቱ፣ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል።16ሊባኖስ ለማንደጃ፣ እንስሶችዋም ለሚቃጠል መሥዋዕት አይበቁም።17አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምናምን እንደሚያንሱ፣ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል።18እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?19የተቀረጸውንስ ምስል! ሠራተኛ ሠርቶታል፤ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፣ የብሩንም ሰንሠለት አፍስሶለታል።20ለዚህ መባዕ ገንዘቡ ያልበቃው ድሀ የማይነቅዘውን እንጨት ይመርጣል፤ ምስሉም እንዳይናወጥ ያቆመው ዘንድ ብልህ ሠራተኛን ይፈልጋል።21አላወቃችሁምን? ወይስ አልሰማችሁምን? ከጥንትስ አልተወራላችሁምን? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?22እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፣ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥23አለቆችንም እንዳልነበሩ፣ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያሳንሳቸው እርሱ ነው።24ተመልከቱ፣ ገና እንደ ተተከሉና እንደ ተዘሩ፣ በምድርም ሥር ገና እንደ ሰደዱ ወዲያውኑ ነፈሰባቸው፣ እነርሱም ደረቁ፣ ዐውሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው።25"እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ?" ይላል ቅዱሱ።26ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፣ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።27ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ፣ "መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፣ ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች" ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?28አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፣ አይታክትም፣ ማስተዋሉም ወሰን የለውም።29ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።30ብላቴኖች ይደክማሉ፣ ይታክቱማል፣ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤31እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።
1"ደሴቶች ሆይ በፊቴ ዝም ብላችሁ አድምጡ፣ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፤ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፤ ለፍርድ ለአንድነት እንቅረብ።2ከምሥራቅ አንዱን ያስነሣ፣ በጽድቅም ወደ አገልግሎቱ የተጠራው ማን ነው? አሕዛብንም አሳልፎ በፊቱ ሰጠው፣ ነገሥታትንም አስገዛለት፤ ለሰይፉ እንደ ትቢያ ለቀስቱም እንደ ተጠረገ እብቅ አድርጎ ሰጣቸው።3አሳደዳቸው፣ እግሮቹም አስቀድመው ባልሄዱባት ፈጣን መንገድ በደኅነት አለፈ።4ይህን የሠራና ያደረገ፣ ትውልድንም ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ፣ እግዚአብሔር፣ ፊተኛው በኋላኞችም ዘንድ የምኖር እኔ ነኝ።5ደሴቶች አይተው ፈሩ፣ የምድርም ዳርቾች ተንቀጠቀጡ፤ ቀረቡም ደረሱም።6ሁሉም እያንዳንዱ ባልንጀራውን ይረዳው ነበር፣ ወንድሙንም፣ 'አይዞህ' ይለው ነበር።7አናጢውም አንጥረኛውን፣ በመዶሻም የሚያሳሳውን መስፍ መችውን አጽናና፣ ስለ ብየዳ ሥራውም፣ 'መልካም ነው' አለ፤ እንዳይንቀሳቀስም በችንካር አጋጠመው።8አንተ ግን፣ ባሪያዬ እስራኤል፣ የመረጥሁህ ያዕቆብ፣ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፣9አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ፣ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፣ 'አንተ ባሪያዬ ነህ፤' መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ።10እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፣ እረዳህማለሁ፣ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።11ተመልከት፣ እነሆ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፣ ይዋረዱማል፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፣ ይጠፉማል።12የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፣ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ።13እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፣ 'አትፍራ፣ እረዳሃለሁ' ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።14አንተ፣ ትል ያዕቆብ፣ የእስራኤልም ሰዎች ሆይ፣ አትፍሩ፤ እረዳሃለሁ፤" ይላል እግዚአብሔር፣ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።15"ተመልከቱ፣ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ሁለት ጎን ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፤ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፣ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።16ታበጥራቸዋለህ፣ ነፋስም ይጠርጋቸዋል፣ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል። አንተም በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፣ በእስራኤልም ቅዱስ ትመካለህ።17ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፣ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ እግዚአብሔር እሰማቸዋለሁ፣ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።18በወናዎቹ ኮረብቶች ላይ ወንዞችን፣ በሸለቆችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ መቆሚያ፣ የጥማትንም ምድር ለውኃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።19የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንደ ሠራች፣ የእስራኤልም ቅዱስ እንደ ፈጠረው ያዩ ዘንድ ያውቁም ዘንድ ያስቡም ዘንድ በአንድነትም ያስተውሉ ዘንድ፣ 20በምድረ በዳ ዝግባውንና ግራሩን ባርሰነቱንና የዘይቱን ዛፍ አበቅላለሁ፣ በበረሀውም ጥዱንና አስታውን ወይራውንም በአንድነት አኖራለሁ።21ክርክራችሁን አቅርቡ፣" ይላል እግዚአብሔር፤ "ማስረጃችሁን አምጡ፣" ይላል የያዕቆብ ንጉሥ።22የገዛ ራሳቸውን ሙግት ያምጡ፣ የሚሆነውንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፣ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ተናገሩ፣ የሚመጡትንም አሳዩን።23አማልክትም መሆናችሁን እናውቅ ዘንድ፣ በኋላ የሚመጡትን ተናገሩ፤ እንደነግጥም ዘንድ በአንድነትም እናይ ዘንድ መልካሙን ወይም ክፉውን አድርጉ።24ተመልከቱ፣ እንዳልነበረ ናችሁ፣ ሥራችሁም ከንቱ ነው፤ የሚመርጣችሁም አስጻያፊ ነው።25አንዱን ከሰሜን አነሣሁ፣ እርሱም መጥቶአል፤ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፤ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል።26እናውቅ ዘንድ ከጥንት የተናገረው። "እውነት ነው" እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፣ የሚገልጥም የለም፣ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም።27በመጀመሪያ ለጽዮን፣ "ተመልከቱ እዚህ ናቸው፤" እላለሁ፤ ለኢየሩሳሌምም የምስራች ነጋሪን እሰጣለሁ።28ብመለከት፣ ማንም አልነበረም፤ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም።29ተመልከቱ፣ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፣ ሥራቸውም ምንምን ናት፤ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ነፋስና ኢምንት ናቸው።
1እነሆ፣ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ። እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።2አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፣ ድምፁንም በጎዳናዎች አያሰማም።3የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል።4በምድርም ፍትሕን እስኪያደርግ ድረስ ይበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም ሕጉን ይጠብቃሉ።5ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፣ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፣ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፣ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣6"እኔ፣ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፣ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ። እጠብቅሃለሁ፣ ለአሕዛብ ብርሃን እንደሆንክ ሁሉ፣ ለሕዝቡም እንደ ኪዳን አደርግሃለሁ።7የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ፣ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።8እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።9ተመልከቱ፣ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፣ አዲስ ክስተቶችንም እናገራለሁ። አስቀድሞም ሳይከሰት ስለ እነርሱ አስታውቃችኋለሁ።"10ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርስዋም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፣ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፣ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፣ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።11ምድረ በዳውና ከተሞቹ የቄዳርም ሰዎች የሚቀመጡባቸው መንደሮች ድምፃቸውን በደስታ ያንሡ! በሴላ የሚኖሩ እልል ይበሉ፤ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።12ለእግዚአብሔር ክብርን ይስጡ፣ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ።13እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይወጣል፤ እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል፣ በጠላቶቹም ላይ ኃይሉን ያሳያል።14ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፤ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።15ተራሮችንና ኮረብቶችን አፈርሳለሁ፣ ቡቃያዎቻቸውንም ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ደሴቶች አደርጋለሁ፣ ኵሬዎችንም አደርቃለሁ።16ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፣ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፣ አልተዋቸውምም።17በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፣ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፣ "አምላኮቻችን ናችሁ" የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፈጽመውም ያፍራሉ።18እናንተ ደንቆሮች፣ ስሙ፤ እናንተም ዕውሮች፣ ታዩ ዘንድ ተመልከቱ።19ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው?20ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትገነዘቡትም፤ ጆሮአችሁም ተከፍተዋል፣ ነገር ግን አትሰሙም።21እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።22ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁላቸው በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል፣ በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ብዝበዛ ሆነዋል የሚያድንም የለም፣ ምርኮም ሆነዋል፣ ማንም፣ "መልሷቸው!" የሚል የለም።23ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፣ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው?24ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ይሄዱ ዘንድ ያልወደዱት ለሕጉም ያልታዘዙለት እግዚአብሔር እርሱ አይደለምን?25ስለዚህ፣ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰበት። በዙሪያም አነደደው እርሱ ግን አላወቀም፣ አቃጠለውም እርሱ ግን ልብ አላደረገም።
1አሁንም ያዕቆብ ሆይ፣ የፈጠረህ፣ እስራኤልም ሆይ፣ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፣ አንተ የእኔ ነህ።2በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፣ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።3እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፣ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።4በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፣ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።5እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፣ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።6ሰሜንን፣ 'መልሰህ አምጣ፣' ደቡብንም፣ 'ማናቸውንም አትከልክል፤' ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣ 7በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፣ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ።8ዓይኖች ያሉአቸውን ዕውሮችን ሕዝብ፣ ጆሮችም ያሉአቸውን ደንቆሮቹን አውጣ።9አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ፣ ወገኖችም ይከማቹ። ከመካከላቸው፤ ይህን የሚናገር፣ የቀድሞዎቹንስ ክስተቶች የሚያሳየን ማን ነው? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፣ ሰምተውም 'እውነት ነው' ይበሉ።10"ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፣ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ" ይላል እግዚአብሔር። ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም።11እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።12ተናግሬአለሁ፣ አድኜማለሁ፣ አውጄማለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም። ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፣" ይላል እግዚአብሔር። "እኔም አምላክ ነኝ።"13ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ፣ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፣ የሚከለክልስ ማን ነው?"14የእስራኤል ቅዱስ፣ የሚቤዣችሁ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ "ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፣ ከለዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።15ቅዱሳችሁ፣ የእስራኤል ፈጣሪ፣ ንጉሣችሁ፣ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።"16እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው (በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል፤17እግዚአብሔር ሠረገላውንና ፈረሱን፣ ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል። እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፤ መቼም አይነሡም፤ ቀርተዋል፣ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል።)18"የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፣ የጥንቱንም ነገር አታስቡ።19ተመልከቱ፣ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፣ አታዩትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ።20የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል። 21ምስጋናዬን እንዲናገሩ ለእኔ የፈጠርሁት ሕዝብ፣ የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን በበረሀም ወንዞችን ሰጥቻለሁና።22ያዕቆብ ሆይ፣ አንተ ግን አልጠራኸኝም፣ አንተም እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ዘንድ ደክመሃል።23ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም፣ በሌላም መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቍርባን አላስቸገርሁህም፣ በዕጣንም አላደከምሁህም።24ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን በገንዘብ አልገዛህልኝም፣ በመሥዋዕትህም ስብ አላጠገብኸኝም፤ ነገር ግን በኃጢአትህ አስቸገርኸኝ፣ በበደልህም አደከምኸኝ።25አዎን፣ መተላለፍህን፣ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ፤ ኃጢአትህንም ከእንግዲህ አላስብም።26የተከሰተውን አሳስበኝ። በአንድነትም ሆነን እንከራከር፤ ስለ ንጹህነትህ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር።27የመጀመሪያው አባትህ ኃጢአት ሠርቶአል፣ መምህሮችህም በድለውኛል።28ስለዚህ የመቅደሱን ቅዱሳን አለቆች አረከስሁ፣ ያዕቆብንም እርግማን፣ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ።"
1አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ፣ የመረጥሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማ።2የፈጠረህ፣ ከማኅፀንም የሠራህ፣ የሚረዳህም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ይሹሩን ሆይ፣ አትፍራ።3በተጠማ ላይ ውኃን፣ በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ፣ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ፥4በፈሳሾችም አጠገብ እንደሚበቅሉ እንደ አኻያ ዛፎች በሣር መካከል ይበቅላሉ።5ይህ፣ 'እኔ የእግዚአብሔር ነኝ' ይላል፤ ሌላኛውም በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ይህም፣ 'እኔ የእግዚአብሔር ነኝ' ብሎ በእጁ ይጽፋል፣ በእስራኤልም ስም ይጠራል።"6የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው - የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እኔ ፊተኛ ነኝ፣ እኔም ኋለኛ ነኝ፣ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።7እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፣ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ።8አትፍሩ አትደንግጡም። ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፦ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ሌላ ዐለት የለም፤ ማንንም አላውቅም።"9የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ የወደዱትም ነገር አይረባቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያዩምና አያውቁም፤ ስለዚህ እንዲያፍሩ ይደረጋሉ።10አምላክን የሠራ ወይስ ለምንም የማይረባ ምስልን የቀረጸ ማን ነው?11ተመልከቱ፣ ባልንጀሮቹ ሁሉ ያፍራሉ፤ ሠራተኞቹም ከሰዎች ወገን ብቻ ናቸው። ሁላቸው ተሰብስበው ይቁሙ፤ ይፈራሉ በአንድነትም ያፍራሉ።12ብረት ሠሪ መጥረቢያውን ይሠራል፣ በፍምም ውስጥ ያደርገዋል፣ በመዶሻም መትቶ ቅርጽ ይሰጠዋል። በክንዱም ኃይል ይሠራዋል፣ እርሱም ይራባል፣ ይደክምማል፣ ውኃም አይጠጣም ይታክትማል።13አናጢውም ገመድ ዘርግቶ በበረቅ ይለካዋል፣ በመቅረጫም ይቀርጸዋል። በመለኪያም ይለካዋል። በቤትም ውስጥ ይቀመጥ ዘንድ በሰው አምሳልና በሚስብ የሰው ውበት ያስመስለዋል።14የዝግባን ዛፎች ይቈርጣል፣ የዞጲንና የኮምቦልን ዛፍ ይመርጣል። ከዱር ዛፎችም መካከል ይጠነክር ዘንድ ይተወዋል፤ የጥድንም ዛፍ ይተክላል ዝናብም ያበቅለዋል።15ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፣ አዎን፣ አንድዶ እንጀራ ይጋግርበታል። ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፣ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል።16ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፣ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል። ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል። ራሱን ያሞቅና፣ "እሰይ ሞቅሁ፣ እሳቱን አይቻለሁ" ይላል።17የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፣ "አምላኬ ነህና፣ አድነኝ" ይላል።18አያውቁም፣ አያስቡም፣ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፣ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን ታውረዋል።19በልቡም ማንም አያስብም፣ "ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፣ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፣ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ። የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም።"20አመድ ይበላል፤ የተታለለ ልብ አስቶታል። ነፍሱን ለማዳን አይችልም፣ ወይም፣ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ" አይልም።21ስለ እነዚህ ነገሮች አስብ፣ ያዕቆብ ሆይ፣ አንተም እስራኤል፣ ባሪያዬ ነህና ይህን አስብ፤ እኔ ሠርቼሃለሁ፤ አንተም ባሪያዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ዘንድ ያልተረሳ ትሆናለህ።22መተላለፍህን እንደ ደመና፣ ኃጢአትህንም እንደ ጭጋግ ደምስሼአለሁ፤ ተቤዥቼሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ።23ሰማያት ሆይ፣ እግዚአብሔር አድርጎታልና ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፣ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፣ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች፣ አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፣ እልል በሉ።24ከማኅፀን የሠራህ፣ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሁሉን የፈጠርሁ፣ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?25የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፣ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፣ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ፣ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤26እኔ፣ እግዚአብሔር! የባሪያዬን ቃል አጸናለሁ፣ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌምን፣ 'የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፣' የይሁዳንም ከተሞች፣ 'ድጋሚ ትታነጻላችሁ፣ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ' እላለሁ፤27ቀላዩንም፣ 'ደረቅ ሁን፣ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ' እላለሁ፤28ቂሮስንም፣ 'እርሱ እረኛዬ ነው፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፣ - 'ትታነጺያለሽ፣ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል' ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል" እላለሁ።
1እግዚአብሔር ለቀባሁት፣ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፣ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦2"በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፤ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤3በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ፣ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።4ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፤ አንተ ግን አላወቅኸኝም።5እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤ 6በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።7ብርሃንን ሠራሁ፣ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ ደኅንነትን እሠራለሁ፣ ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።8እናንተ ሰማያት ከላይ አንጠባጥቡ፣ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ! ምድርም ትከፈት መድኃኒትንም ታብቅል፣ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል። እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።9ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው! ጭቃ የሚሠራውን፣ 'ምን ትሠራለህ?' ወይስ 'ሥራህ - እጅ የለውም' ይላልን?10አባቱን፣ 'ምን ወልደሃል?' ወይም ሴትን፣ 'ምን አማጥሽ?' ለሚል ወዮ!11የእስራኤል ቅዱስ፣ ሠሪውም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስለሚመጣው ነገር ጠይቁኝ፣ ስለ ልጆቼና ስለ እጄ ሥራም እዘዙኝ።'12'እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ። እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቼአለሁ፣ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።13እኔ ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ፣ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ። እርሱ ከተማዬን ይገነባል፣ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፣" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።14እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፣ "የግብጽ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ። እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፣ ለአንተም እየሰገዱ። 'በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፣ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም' ብለው ይለምኑሃል።"15የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፣ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።16ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል፤ ጣዖታትንም የሚሠሩ በአንድነት ወደ ውርደት ይሄዳሉ።17እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘላለማዊ መድኃኒት ያድነዋል፤ እናንተም ለዘላለም አታፍሩምና አትዋረዱም።18ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፣ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፣ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፣ እንዲህ ይላል፣ "እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።19በስውር ወይም በጨለማ ምድር ስፍራ አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፣ 'በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም!' እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ፣ ቅንንም አወራለሁ።20እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ ኑ! ተሰብስባችሁ ኑ፣ በአንድነትም ቅረቡ! የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።21ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ! ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፣ ከእኔም በቀር ማንም የለም።22እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፣ እኔ አምላክ ነኝና፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።23'ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፣ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፣ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።24ስለ እኔም፣ "በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፣ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ።" በእርሱም ላይ የተቈጡ ሁሉ ያፍራሉ።25የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ ይመካሉም ይባላል።
1ቤል ተዋረደ፣ ናባው ተሰባበረ፤ ጣዖቶቻቸው በእንስሳና በከብት ላይ ተጭነዋል። ሸክሞቻችሁ ለደካማ እንስሳ ከባድ ጭነት ሆነዋል።2ተጐነበሱ በአንድነትም ተዋረዱ፤ ሸክሙን ለማዳን አልቻሉም፣ ራሳቸው ግን ተማረኩ።3እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፣ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁ፣ ስሙኝ።4እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፣ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ፤ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ።5በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?6ወርቁን ከኮረጆ የሚያፈስሱ ብሩንም በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፣ እርሱም አምላክ አድርጎ ይሠራ ዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል ይሰግዱለትማል።7በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል፤ በስፍራውም ያደርጉታል፣ በዚያም ይቆማል፣ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም።8ስለእነዚህ ነገሮች አስቡና አልቅሱ፤ ተላላፊዎች ሆይ፣ ንስሐ ግቡ! ልባችሁንም መልሱ።9እኔ አምላክ ነኝና፣ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።10በመጀመሪያ መጨረሻውን፣ ከጥንትም ያልተደረገውን ሳይሆን በፊት እነግራለሁ፤ "ምክሬ ትጸናለች፣ ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ፤" እላለሁ።11ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን፣ ከሩቅም አገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራዋለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤ እፈጽማለሁ፤ አስቤአለሁ አደርግማለሁ።12እናንተ ጽድቅን ከማድረግ የራቃችሁ፣ እልከኞች፣ ስሙኝ።13ጽድቄን አቀርባለሁ፤ አይርቅም መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
1አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፣ ውረጂ በመሬት ትቢያም ላይ ያለ ዙፋን ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፤ ከዚህ በኋላ ቅልጣናምና ቅምጥል አትባይምና።2ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፤ መሸፈኛሽን አውጪ፣ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣዪው፤ ባትሽን ግለጪ፣ ወንዙን ተሻገሪ።3ኀፍረተ ሥጋሽ ይገለጣል እፍረትሽም ይታያል፤ አዎን፣ እኔ እበቀላለሁ፥ ለማንም አልራራም።4ታዳጊያችን፣ ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ቅዱስ ነው።5የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፣ ከዚህ በኋላ፣ የመንግሥታት እመቤት አትባይምና ዝም ብለሽ ተቀመጪ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ።6በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፣ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለእነርሱ ምንም ምሕረት አላደረግሽም፣ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።7አንቺም፣ "እኔ ለዘላለም እመቤት እሆናለሁ" ብለሻል፤ ይህንም በልብሽ አላደረግሽም ፍጻሜውንም አላሰብሽም።8አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ "እኔ እኖራለሁ፣ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም የወላድ መካንነትንም አላውቅም" የምትዪ ይህን ስሚ፤9አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች፦ የወላድ መካንነትና መበለትነት፣ በድንገት ይመጡብሻል፤ ስለ መተቶችሽ ብዛትና ስለ አስማቶችሽ ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል።10በክፋትሽ ታምነሻል፤ "የሚያየኝ የለም" ብለሻል፤ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፣ ነገር ግን በልብሽ፣ "እኔ እኖራለሁ፣ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።" ብለሻል።11ስለዚህ ምክንያት ክፉ ነገር ይመጣብሻል፤ በምዋርትሽም እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም። ጉዳት ይውድቅብሻል ታስወግጅውም ዘንድ አይቻልሽም፤ የማትውቂያትም ጕስቍልና ድንገት ትመጣብሻለች።12ምናልባትም መጠቀም ትችዪ ወይም ታስደነግጪ እንደ ሆነ፣ ከአስማቶችሽና ከሕፃንነትሽ ጀምረሽ ከደከምሽበት ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ።13በምክርሽ ብዛት ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፣ ከዋክብትንም የሚመለከቱ፣ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነሥተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ።14ተመልከቱ፣ እንደ እብቅ ይሆናሉ። እሳትም ያቃጥላቸዋል። ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኃይል አያድኑም። እርሱም ሰው እንደሚሞቀው ፍም፣ ወይም በፊቱ ሰው እንደሚቀመጥበት እሳት ያለ አይደለም!15የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፤ ከሕፃንነትሽ ጀምረው ከአንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፣ የሚያድንሽም የለም።
1እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ ከይሁዳም ዘር የወጣችሁ፣ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፣ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ።2በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ፣ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ፤ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ይህን ስሙ።3የቀድሞውን ነገር ከጥንት ተናግሬአለሁ፣ ከአፌም ወጥቶአል፣ አሳይቼውማለሁ፤ ድንገት አድርጌዋለሁ ተፈጽሞማል።4አንተ እልከኛ፣ አንገትህም የብረት ጅማት፣ ግምባርህም ናስ እንደሆነ አውቄአለሁ፤5ስለዚህ፣ አንተ፣ 'ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፣ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ' እንዳትል፣ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር ሳይሆንም አሳይቼህ ነበር።6ስለ እነዚህ ነገሮች ሰምተሃል፤ ይህን ሁሉ ማረጋገጫ ተመልከት፤ እናንተም የምትናገሩት አይደላችሁምን? የተሰወሩትን ያላወቅሃቸውንም አዲሶች ነገሮችን ከዚህ ጀምሬ አሳይቼሃለሁ።7እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፤ አንተም፣ እነሆ፣ 'አውቄአቸዋለሁ' እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም።8አልሰማህም፣ አላወቅህም፣ ጆሮህ ከጥንት አልተከፈተችም። አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደተጠራህ አውቄአለሁና።9ስለ ስሜ ቍጣዬን አዘገያለሁ፣ እንዳላጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ።10ተመልከት፣ አንጥሬሃለሁ፣ ነገር ግን እንደ ብር አይደለም፤ በመከራም እቶን ፈትኜሃለሁ።11ስለ እኔ፣ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ፣ ስሜ እንዲነቀፍ የምፈቅደው እንዴት ነው? ክብሬንም ለሌላ አልሰጥም።12ያዕቆብ ሆይ፣ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ፣ እኔም ኋለኛው ነኝ።13አዎን፣ እጄ ምድርን መሥርታለች፣ ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፤ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ።14እናንተ ሁሉ፣ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? እግዚአብሔር የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፣ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል።15እኔ፣ እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አምጥቼዋለሁ፥ መንገዱም ትሳካለታለች።16ወደ እኔ ቅረቡ፣ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፣ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ" ልከውኛል።17ታዳጊህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። "እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ፣ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።"18ትእዛዜን ብትፈጽም ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤19ዘርህም እንደ አሸዋ፣ የሆድህም ትውልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፣ ስሙም ከፊቴ ባልጠፋና ባልፈረሰ ነበር።20ከባቢሎን ውጡ! ከከለዳውያንም ኰብልሉ! በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፣ ይህንም ንገሩ፣ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፣ 'እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ታድጎታል' በሉ።21በምድረ በዳ በኩል በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፤ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፣ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ።22ለክፉዎች ሰላም የላቸውም" ይላል እግዚአብሔር።
1ደሴቶች ሆይ፣ ስሙኝ! እናንተም በሩቅ ያላችሁ አሕዛብ፣ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ከማኅፀን በስም ጠርቶኛል፣ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ።2አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፣ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል፣ በሰገባውም ውስጥ ሽጎኛል።3እርሱም፣ "እስራኤል ሆይ፣ አንተ ባሪያዬ ነህ፣ በአንተም እከበራለሁ" አለኝ።4እኔ ግን፣ በከንቱ ደከምሁ፣ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጕልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ፣ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው አልሁ።5አሁንም በእግዚአብሔር ዓይን ከብሬአለሁና፣ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ፣ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የሠራኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።6እርሱ እንዲህ ይላል፣ "የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ፣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመስል፣ ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ" ይላል።7የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፣ እግዚአብሔር፣ ሰዎች ለሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው ለገዥዎች ባሪያ እንዲህ ይላል፣ "ስለ ታማኙ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፣ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።"8እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፣ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ እጠብቅህማለሁ፣ ምድርንም ታቀና ዘንድ፣ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ፥9የተጋዙትንም፣ 'ውጡ፤' በጨለማም የተቀመጡትን፣ 'ራሳችሁን ግለጡ' ትል ዘንድ ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ። በመንገድም ላይ ይሰማራሉ፣ ማሰማርያቸውም በወና ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል።10የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፣ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፣ አይጠሙም፣ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።11ተራሮቼንም ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፣ ጎዳኖቼም ከፍ ከፍ ይላሉ።"12ተመልከቱ፣ እነዚህ ከሩቅ፣ አንዳንዶቹም፣ ከሰሜንንና ከምዕራብ፣ እነዚህም፣ ከሲኒም አገር ይመጣሉ።13እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፣ ለችግረኞቹም ራርቶአልና ሰማያት ሆይ፣ ዘምሩ፣ ምድር ሆይ፣ ደስ ይበልሽ ተራሮችም ሆይ፣ እልል በሉ።14ጽዮን ግን፣ "እግዚአብሔር ትቶኛል፣ ጌታም ረስቶኛል" አለች።15"በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም።16ተመልከቱ፣ እኔ በእጄ መጻፍ ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።17ልጆችሽ ተመልሰው ይፈጥናሉ፤ ያፈረሱሽና ያወደሙሽ ከአንቺ ዘንድ ይወጣሉ።18ዓይንሽን አንሥተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፣ እንደ ሙሽራም ትጐናጸፊአቸዋለሽ፣ ይላል እግዚአብሔር።19ባድማሽና ውድማሽ ወናም የሆነው ምድርሽ ከሚኖሩብሽ የተሣ ዛሬ ጠባብ ትሆናለችና፣ የዋጡሽም ይርቃሉና።20የወላድ መካን ከሆንሽ በኋላ የተወለዱልሽ ልጆችሽ በጆሮሽ፣ 'ስፍራ ጠብቦናልና፣ እንቀመጥ ዘንድ ቦታ አስፊልን' ይላሉ።21አንቺም በልብሽ፣ 'የወላድ መካን ሆኛለሁና፣ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁና ተቅበዝበዤ አለሁምና እነዚህን ልጆች ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፣ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ከወዴት መጡ?" ትያለሽ።22ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፣ ዓላማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በብብታቸው ያመጡአቸዋል። ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል።23ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፣ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግምባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።"24በውኑ ብዝበዛ ከኃያል እጅ ይወሰዳልን፣ ወይስ የጨካኙ ምርኮኞች ያመልጣሉን?25እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፣ "አዎን፣ በኃያላን የተማረኩ ይወሰዳሉ፣ የጨካኞችም ብዝበዛ ያመልጣል፤ ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፣ ልጆችሽንም አድናለሁ።26አስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን አስበላቸዋለሁ፣ እንደ ጣፋጭም ወይን ጠጅ ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መድኃኒትሽና ታዳጊሽ፣ የያዕቆብ ኃያል እንደ ሆንሁ ያውቃል።"
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፣ ስለ ኃጢአታችሁ ተሽጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።2እኔ በመጣሁ ጊዜ ሰው ስለ ምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለ ምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝምን? እነሆ፣ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዓሦቻቸው ይገማሉ በጥማትም ይሞታሉ።3ሰማያትን ጥቍረት አለብሳቸዋለሁ፣ መጋረጃቸውንም ማቅ አደርጋለሁ።"4የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፣ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።5ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶአል፣ እኔም ዓመፀኛ አልነበርሁም ወደ ኋላዬም አልተመለስሁም።6ጀርባዬን ለገራፊዎች፣ ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠሁ፣ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።7ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና፣ ስለዚህ አልተዋረድሁም፤ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፣ እንዳላፍርም አውቃለሁ።8የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው። ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፤ የሚከስሰኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።9ተመልከቱ፣ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል። ማን ይፈርድብኛል? ተመልከቱ፣ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ ብልም ይበላቸዋል።10ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ፣ በጨለማም የሚሄድ፣ ብርሃንም የሌለው፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም የሚታመን፣ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?11ተመልከቱ፣ እሳት የምታነድዱ የእሳትንም ወላፈን የምትታጠቁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ነበልባል ባነደዳችሁትም ወላፈን ሂዱ፤ ይህ ከእጄ ይሆንባችኋል፦ በኀዘን ትተኛላችሁ።
1እናንተ ጽድቅን የምትከተሉ እግዚአብሔርንም የምትሹ፣ ስሙኝ፤ ከእርሱ የተቈረጣችሁበትን ድንጋይ ከእርሱም የተቈፈራችሁበትን ጕድጓድ ተመልከቱ።2ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፣ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፣ ባረክሁትም አበዛሁትም።3አዎን፣ እግዚአብሔር ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርስዋም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፤ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔደን፣ በረሀዋንም እንደ እግዚአብሔር ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።4ወገኔ ሆይ፣ አድምጠኝ፤ ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ! ሕግ ከእኔ ይወጣልና፣ ፍርዴም ለአሕዛብ ብርሃን ይሆናልና።5ጽድቄ ፈጥኖ ቀርቦአል፣ ማዳኔም ወጥቶአል፣ ክንዴም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ ደሴቶች እኔን በመተማመን ይጠባበቃሉ፣ በክንዴም ይታመናሉ።6ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሡ፣ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፣ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፣ የሚኖሩባትም እንዲሁ ይሞታሉ። ማዳኔ ግን ለዘላለም ይሆናል፣ ጽድቄም አይፈርስም።7ጽድቅን የምታውቁ ሕጌም በልባችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፣ ስሙኝ፤ የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ፣ በስድባቸውም አትደንግጡ።8እንደ ልብስም ብል ይበላቸዋል፣ እንደ በግ ጠጕርም ትል ይበላቸዋል፤ ጽድቄ ግን ለዘላለም ማዳኔም ለትውልድ ሁሉ ይሆናል።"9የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፣ ተነሥ፣ ተነሥ፣ ኃይልንም ልበስ። በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?10ባሕሩንና የታላቁን ጥልቅ ውኃ ያደረቅኸው፣ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጠሊቁን ባሕር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?11እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ ወደ ጽዮንም ይመጣሉ፤ የዘላለምም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፣ ኀዘንና ልቅሶም ይሸሻል።12"እኔ፣ የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፤ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ትፈራ ዘንድ አንተ ማን ነህ?13ሰማያትንም የዘረጋው ምድርንም የመሠረተውን ፈጣሪህን እግዚአብሔርን ረስተሃል፤ ያጠፋ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሃል፤ የጨቋኙ ቍጣ የት አለ?14ምርኮኛ ፈጥኖ ይፈታል፣ አይሞትም ወደ ጕድጓድም አይወርድም፣ እንጀራም አይጐድልበትም።15ሞገዱም እንዲተምም ባሕርን የማናውጥ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፣ ስሜም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።16ሰማያትን እዘረጋ ዘንድ ምድርንም እመሠርት ዘንድ፣ ጽዮንንም፣ 'አንቺ ሕዝቤ ነሽ' እል ዘንድ ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፣ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ።"17ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ንቂ፣ ንቂ፣ ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል፣ ጨልጠሽውማል።18ከወለደቻቸው ልጆች ሁሉ የሚመራት የለም፣ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም።19እነዚህ ሁለት ነገሮች ሆነውብሻል፣ ማንስ ያስተዛዝንሻል? መፈታትና ጥፋት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እንዴትስ አድርጌ አጽናናሻለሁ?20ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደተያዘ ሚዳቋ በአደባባይ ሁሉ ራስ ላይ ተኝተዋል፤ በእግዚአብሔር ቍጣና በአምላክሽ ተግሣጽ ተሞልተዋል።21አሁን ግን ይህንን ስሚ፣ ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ አንቺ የተጨቆንሽ።22ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ የሚያንገደግድን ጽዋ የቍጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።23ነፍስሽንም፣ 'እንሻገር ዘንድ ዝቅ በዪ፣ በሚሉአት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፤' ጀርባሽንም ለሚሻገሩት እንደ መሬትና እንደ መንገድ አደረግሽላቸው።"
1ጽዮን ሆይ፣ ተነሺ፣ ተነሺ፣ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።2ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ትቢያን አራግፊ፤ ተነሺና ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።3እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "በከንቱ ተሽጣችሁ ነበር፣ ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ።"4ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብጽ ወረደ፣ አሦርም ቅርብ ጊዜ ላይ ያለ ምክንያት በደለው።5ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ስሜም ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ይሰደባል።6ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል፤ ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ፤ አዎን፣ እኔ ነኝ!"7የምስራች የሚናገር፣ ሰላምንም የሚያወራ፣ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፣ መድኃኒትንም የሚያወራ፣ ጽዮንንም፣ "አምላክሽ ነግሦአል!" የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።8አድምጪ፣ ጕበኞችሽ ጮኸዋል፤ እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፣ በአንድነትም ይዘምራሉ።9እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፤ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፣ በአንድነትም ዘምሩ።10እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።11እናንተ የእግዚአብሔር ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፣ ትታችሁ ውጡ፣ ትታችሁ ውጡ፤ ከዚያ ውጡ፣ ርኩስን ነገር አትንኩ፣ ከመካከልዋ ውጡ፣ ንጽሐን ሁኑ።12እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፣ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም።13ተመልከቱ፣ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፣ እጅግ ታላቅም ይሆናል።14ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፣ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፣ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤15ያልተነገረላቸውንም ያያሉና፣ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።
1የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?2በፊቱ እንደ ቡቃያ፣ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፣ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።3የተናቀ ከሰውም የተጠላ፣ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው። ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፣ እኛም አላከበርነውም።4በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።5እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።6እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።7ተጨቆነ፣ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፣ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።8በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?9ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፣ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፣ በአፉም ተንኮል አልተገንበትም ነበር።10እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፣ ዕድሜውም ይረዝማል፣ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።11ከነፍሱ መከራ በኋላ፣ ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፣ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።12ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፣ ከብዙ ኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፣ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፣ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
1"አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፣ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፣ እልል በዪ፣ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፣" ይላል እግዚአብሔር።2የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፣ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።3በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፣ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፣ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና።4አታፍሪምና አትፍሪ፤ አተዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፣ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።5ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፣ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዲጊሽ ነው፣ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።6እግዚአብሔር እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች በልጅነትዋም እንደ ተጣለች ሚስት ጠርቶሻል፣ ይላል አምላክሽ።7"ለጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፣ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ።8በጥቂት ቍጣ ለቅጽበት ዓይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፣ በዘላለምም ቸርነት እምርሻለሁ፣ ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።9ይህ ለእኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፣ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልገሥጽሽም ምያለሁ።10ተራሮች ይፈልሳሉ፣ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፣ ይላል መሐሪሽ እግዚአብሔር።11አንቺ የተቸገርሽ በዐውሎ ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፣ ተመልከቺ፣ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፣ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ።12የግንብሽንም ጕልላት በቀይ ዕንቍ፣ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቍ፣ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።13ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፣ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።14በጽድቅ ትታነጺያለሽ፤ ከግፍ ራቂ፣ አትፈሪምም፣ ድንጋጤም ወደ አንቺ አትቀርብም።15ተመልከቺ፣ ይሰበሰባሉ፣ ነገር ግን ከእኔ ዘንድ አይሆንም፤ በአንቺም ላይ ችግር የሚፈጥሩ ሁሉ ይሸነፋሉ።16ተመልከቺ፣ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ ብረት ሠሪን እኔ ፈጥሬአለሁ፤ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ።17በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፣ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፣" ይላል እግዚአብሔር።
1"እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፣ ወደ ውኃ ኑ፣ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።2ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፣ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? በጥንቃቄ አድምጡኝ በረከትንም ብሉ፣ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።3ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ! ስሙ፣ ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች! የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፣ የዘላለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።4ተመልከቱ፣ ለአሕዛብ ምስክር፣ ለወገኖችም አለቃና አዛዥ እንዲሆን ሰጥቼዋለሁ።5ተመልከቱ፣ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፤ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣሉ።"6እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፣ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤7ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፣ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።8አሳቤ እንደ አሳባችሁ፣ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ፣ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር።9ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።10ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፣ ምድርን እንደሚያረካት፣ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፣ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፣11ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።12እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ እልልታ ያደርጋሉ፣ የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ።13በእሾህም ፋንታ ጥድ፣ በኩርንችትም ፋንታ ባርሰነት፣ ይበቅላል፤ ለእግዚአብሔርም መታሰቢያን ለዘላለምም የማይጠፋ፣ ምልክት ይሆናል።"
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ማዳኔ ሊመጣ፣ ጽድቄም ሊገለጥ ቀርቦአልና ፍርድን ጠብቁ ጽድቅንም አድርጉ።2ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፣ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።"3ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፣ "በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል" አይበል፤ ጃንደረባም፣ "ተመልከቱ፣ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል።"4እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፣5"በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።"6ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፣ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፣7"ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፣ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ።8ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር፣ ወደ ተሰበሰቡት ዘንድ ሌሎችን እሰበስብለታለሁ" ይላል።9እናንተ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ፣ እናንተም የዱር አራዊት ሁሉ፣ ትበሉ ዘንድ ቅረቡ!10ጕበኞቹ ዕውሮች ናቸው፣ ሁሉ ያለ እውቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ ማንቀላፋትንም ይወድዳሉ።11መብል ወዳጆች ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ እነርሱም ያስተውሉ ዘንድ የማይችሉ እረኞች ናቸው፤ ሁሉ ወደ መንገዳቸው፣ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል።12"ኑ፣ የወይን ጠጅ እንውሰድ፣ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፣ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል" ይላሉ።
1ጻድቅ ይጠፋል፣ በልቡም ነገሩን የሚያኖር የለም፤ ምሕረተኞችም ይወገዳሉ፣ ጽድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።2ወደ ሰላም ይገባል፤ በቅንነት የሄደ በአልጋው ላይ ያርፋል።3እናንተ የአስማተኛይቱ ልጆች፣ የአመንዝራውና የጋለሞታይቱ ዘር፣ ወደዚህ ቅረቡ።4በማን ታላግጣላችሁ? በማንስ ላይ አፋችሁን ታላቅቃላችሁ? ምላሳችሁንስ በማን ላይ ታስረዝማላችሁ?5እናንተ በአድባር ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፣ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፣ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን?6በሸለቆው ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች እድል ፈንታሽ ናቸው፣ እነርሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፣ የእህልንም ቍርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣምን?7ከፍ ባለውም በረዘመውም ተራራ ላይ መኝታሽን አደረግሽ፣ መሥዋዕትንም ትሠዊ ዘንድ ወደዚያ ወጣሽ።8ከመዝጊያውና ከመቃኑ በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ፤ እኔን ትተሽ ለሌላ ተገልጠሻል፣ ወጥተሽ መኝታሽን አስፍተሻል፤ ቃል ኪዳንም ተጋባሻቸው፣ ባየሽበትም ስፍራ ሁሉ መኝታቸውን ወደድሽ።9ዘይትም ይዘሽ ወደ ንጉሡ ሄድሽ፣ ሽቱሽንም አበዛሽ፣ መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፣ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ።10በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፣ ነገር ግን፣ "ተስፋ የለም" አላልሽም፤ የጕልበትን መታደስ አገኘሽ፣ ስለዚህም አልዛልሽም።11"ሐሰትን የተናገርሺው እኔንም ያላሰብሺው በልብሽም ነገሩን ያላኖርሺው ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔ ብዙ ጊዜ ዝም አልሁ፣ አንቺም አልፈራሽም።12እኔ ጽድቅሽን እናገራለሁ፣ ሥራሽም አይረባሽም።13ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፣ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።14እርሱም፣ 'ጥረጉ፣ መንገድን አዘጋጁ! ከሕዝቤም መንገድ ዕንቅፋትን አውጡ!" ይላል።15ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፣ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፣ "የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።16መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘላለም አልጣላም፣ ሁልጊዜም አልቈጣም።17ስለ ኃጢአቱ ጥቂት ጊዜ ተቈጥቼ ቀሠፍሁት፣ ፊቴን ሰውሬ ተቈጣሁ፤ እርሱም በልቡ መንገድ እያፈገፈገ ሄደ።18መንገዱን አይቻለሁ እፈውሰውማለሁ፣ እመራውማለሁ፣ ለእርሱና ስለ እርሱም ለሚያለቅሱ መጽናናትን እመልሳለሁ።19የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ። በሩቅም በቅርብም ላለው ሰላም ሰላም ይሁን፣ እፈውሰውማለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።20ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፣ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና።21ለክፉዎች ሰላም የላቸውም" ይላል አምላኬ።
1"በኃይልህ ጩኽ፣ አትቈጥብ፣ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፣ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።2ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ፤ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝብ እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል። ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።3'ስለ ምን ጾምን፣' አንተም 'አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፣ አንተም አላወቅህም?' ይላሉ። ተመልከቱ፣ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፣ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።4ተመልከቱ፣ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።5እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፣ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?6እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የክፋት በደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፣ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፣ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፣ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?7እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፣ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፣ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፣ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?8የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፣ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፣ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፣ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።9የዚያን ጊዜ ትጠራለህ፣ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፣ "እነሆኝ" ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፣ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፣10ባታንጐራጕርም፣ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፣ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፣ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።11እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል። አንተም እንደሚጠጣ ገነት፣ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።12ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፣ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፣ "ቅጥሩን ጠጋኝ፣" "የመኖሪያ መንገድን አዳሽ" ትባላለህ።13ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፣ ሰንበትንም ደስታ፣ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው።14"በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፤ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።"
1ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፣ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም፤2ነገር ግን፣ በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፣ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።3እጃችሁ በደም ጣታችሁም በበደል ረክሳለች፣ ከንፈራችሁም ሐሰትን ተናግሮአል፣ ምላሳችሁም ኃጢአትን አሰምቶአል።4በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በምናምንቴ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፤ ጕዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል።5የእባብን እንቍላል ቀፈቀፉ፣ የሸረሪትንም ድር አደሩ። እንቍላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፣ እንቍላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል።6ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፣ በሥራቸውም አይሸፈኑም፤ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፣ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው።7እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፣ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው። ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።8የሰላምን መንገድ አያውቁም፣ በአካሄዳቸውም ፍርድ የለም፤ መንገዳቸውን አጣምመዋል፣ የሚሄድባትም ሁሉ ሰላምን አያውቅም።9ስለዚህ ፍርድ ከእኛ ዘንድ ርቆአል፣ ጽድቅም አላገኘንም፤ ብርሃንን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር። እነሆም፣ ጨለማ ሆነ፤ ጸዳልን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፣ ነገር ግን በጨለማ ሄድን።10እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፣ ዓይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፣ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።11ሁላችን እንደ ድቦች እንጮኻለን፤ እንደ ርግብ እንለቃቀሳለን፤ ፍርድን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር። እርሱም የለም፤ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል።12ዓመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፣ ኃጢአታችን መስክሮብናልና፣ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፣ በደላችንን እናውቃለንና።13ዐምፀናል፣ ሐሰትን ተናግረናል፣ አምላካችንንም ከመከተል ተመልሰናል፤ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፣ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።14ፍርድም ወደ ኋላ ተመልሶአል፣ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፣ ቅንነትም ሊገባ አልቻለምና።15እውነትም ታጥቶአል፣ ከክፋትም የራቀ ሰው ለብዝበዛ ሆኖአል። እግዚአብሔርም አየ፣ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ።16ሰውም እንደሌለ አየ፣ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፣ ጽድቁም አገዘው።17ጽድቅንም እንደ ጥሩር ለበሰ፣ በራሱም ላይ የማዳንን ራስ ቍር አደረገ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፣ በቅንዓትም መጐናጸፊያ ተጐናጸፈ።18እንደ ሥራቸው መጠን እንዲሁ ቍጣን ለባላጋራዎቹ፣ ፍዳንም ለጠላቶቹ ይከፍላል፤ ለደሴቶችም ፍዳቸውን ይከፍላል።19እርሱ የእግዚአብሔር ነፋስ እንደሚነዳው እንደ ጐርፍ ፈሳሽ ይመጣልና በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፣ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።20"ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፣ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፣ ይላል እግዚአብሔር።21ከእርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል እግዚአብሔር፣ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ ከአፍህ ከዘርህም አፍ ከዘር ዘርህም አፍ አያልፍም፣" ይላል እግዚአብሔር።
1ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፣ አብሪ።2እነሆ፣ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል፣ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤3አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።4ዓይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ። እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፣ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።5በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፣ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፣ አይተሽ ደስ ይልሻል፣ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል።6የግመሎች ብዛት፣ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፣ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፣ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ።7የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፣ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፣ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።8ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፣ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ እነማን ናቸው?9እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።10በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፣ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል።11በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ፤ ሰዎች የአሕዛብን ብልጥግና የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊትና ቀን አይዘጉም።12ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፣ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።13የመቅደሴንም ስፍራ ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፣ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፣ ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።14የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፣ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።15ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።16የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ፣ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃይል፣ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።17በናስ ፋንታ ወርቅን፣ በብረትም ፋንታ ብርን፣ በእንጨትም ፋንታ ናስን፣ በድንጋይም ፋንታ ብረትን አመጣለሁ። አለቆችሽንም ሰላም፣ የበላይ ገዢዎችሽንም ጽድቅ አደርጋለሁ፤18ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፣ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ19ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፣ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም።20እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፣ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃሽም አይቋረጥም።21ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እከብር ዘንድ የአታክልቴን ቡቃያ፣ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ።22ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሹ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር በዘመኑ ይህን አፋጥነዋለሁ።
1የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፣ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።2የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፣ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤3እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፣ በአመድ ፋንታ አክሊልን፣ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፣ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።4ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ፤ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ። ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ይሠራሉ።5መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ፣ ሌሎች ወገኖችም አራሾችና ወይም ጠባቂዎች ይሆኑላችኋል።6እናንተ ግን የእግዚአብሔር ካህናት ትባላላችሁ፣ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፣ በክብራቸውም ትመካላችሁ።7በእፍረታችሁ ፋንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፣ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፈንታችሁ ደስ ይላቸዋል፤ ስለዚህ በምድራቸው ሁሉ እጥፍ ይገዛሉ፣ የዘላለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።8እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ፣ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፣ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።9ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፣ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል።10አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፣ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፣ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፣ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፣ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።11ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፣ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፣ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።
1ስለ ጽዮን ዝም አልልም፣ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፣ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።2አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ።3በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል፣ በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።4ከእንግዲህ ወዲህ፣ "የተተወች" አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፣ "ውድማ" አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፣ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፣ "ደስታዬ የሚኖርባት" ትባያለሽ ምድርሽም፣ "ባል ያገባች" ትባላለች።5ጕልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል። ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፣ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።6ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ጕበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፣ 7ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ።8እግዚአብሔር፣ "ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፣ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም።9ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል፣ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፣ ያከማቹትም በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል" ብሎ በቀኙና በኃይሉ ክንድ ምሎአል።10እለፉ፣ በበሮች በኩል እለፉ! የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፤ አዘጋጁ፣ ጐዳናውን አዘጋጁ፣ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፤ ለአሕዛብም ዓለማ አንሡ!11ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር ለምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል፣ "ለጽዮን ልጅ፣ እነሆ፥ መድኃኒትሽ ይመጣል፤ እነሆ፣ ዋጋው ከእርሱ ጋር ሥራውም በፊቱ አለ" በሉአት።12እግዚአብሔር፣ "የተቤዣቸው፣ የተቀደሰ ሕዝብ" ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አንቺም፣ "የተፈለገች ያልተተወችም" ከተማ ትባያለሽ።
1ይህ ከኤዶምያስ፣ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፣ አለባበሱ ያማረ፣ በጕልበቱ ጽናት በራስ መተማመን የሚራመድ ማን ነው? በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።2ቀሚስህ ስለ ምን ቀላ፣ ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ?3መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፣ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፣ ልብሴንም ሁሉ አስድፌአለሁ።4የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፣ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና።5ተመለከትሁ፣ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፣ ቍጣዬም እርሱ አገዘኝ።6በቍጣዬም አሕዛብን ረገጥሁ በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፣ ደማቸውንም ወደ ምድር አፈሰስሁት።7እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ።8እርሱም፣ "በእውነት ሕዝቤ፣ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች ናቸው" አለ፤ መድኃኒትም ሆነላቸው።9በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፣ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፣ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።10እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ። ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆነባቸው፣ እርሱም ተዋጋቸው።11እርሱም እንዲህ ብሎ የቀደመውን ዘመን አሰበ። "የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለ? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለ?12የከበረውንም ክንድ በሙሴ ቀኝ ያስሄደ፣ ለራሱም የዘላለምን ስም ያደርግ ዘንድ ውኃውን በፊታቸው የከፈለ፣13በምድረ በዳም እንደሚያልፍ ፈረስ፣ በቀላይ ውስጥ ያለ ዕንቅፋት ያሳለፋቸው ወዴት ነው ያለ?14ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፣ እንዲሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው። እንዲሁም ለራስህ የከበረ ስም ታደርግ ዘንድ ሕዝብን መራህ።15ከሰማይ ቁልቊል ተመልከት፣ ከቅዱስነትህና ከክብርህም ማደሪያ ጐብኝ፤ ቅንዓትህና ኃይልህስ ወዴት ነው? ለእኔም የሆነው የልብህ ናፍቆትና ርኅራኄህ ተከለከለ።16አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን፣ አንተ አባታችን ነህ፤ 'አቤቱ፣ አንተ አባታችን ነህ፣' ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።17አቤቱ፣ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።18የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፤ ጠላቶቻችንም ረግጠውታል።19ከዘላለም እንዳልገዛኸን በስምህም እንዳልተጠራን ሆነናል።
1"ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ! ተራሮችም ምነው ቢናወጡ!2እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አሕዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ!3ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፣ ወረድህ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።4ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላቸው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም በጆሮአቸውም አልተቀበሉም ዓይንም አላየችም።5ጽድቅን የሚያደርገውን በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እነሆ፣ እነተ ተቈጣህ እኛም ኃጢአት ሠራን፤ ስለዚህም ተሳሳትን።6ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፣ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፣ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።7ስምህንም የሚጠራ፣ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፣ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል።8አሁን ግን፣ አቤቱ፣ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፣ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።9አቤቱ፣ እጅግ አትቈጣ፣ ለዘላለምም ኃጢአትን አታስብ፤ እነሆ፣ እባክህ፣ ተመልከት፣ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነን።10የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየሩሳሌምም ውድማ ሆናለች።11አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፣ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈርሶአል።12አቤቱ፣ በውኑ በዚህ ነገር ትታገሣለህን? ዝምስ ትላለህን? አጥብቀህስ ታስጨንቀናለህን?
1ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ፣ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ፤ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ፣ 'እነሆኝ! እነሆኝ!' አልሁት።2መልካም ባልሆነው መንገድ፣ አሳባቸውን እየተከተሉ፣ ወደሚሄዱ ወደ ዓመፀኛ ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆቼን ዘረጋሁ!3ይህ ሕዝብ ዘወትር የሚያስቈጡኝ ናቸው፤ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ በጡብም ላይ የሚያጥኑ፣4በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፣ በስውርም ስፍራ የሚያድሩ፣ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። የረከሰው መረቅ በዕቃቸው ውስጥ አለ።5እነርሱም፣ 'ርቀህ ቁም፣ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና ወደ እኔ አትቅረብ' ይላሉ፤ እነዚህ በአፍንጫዬ ዘንድ ጢስ ቀኑንም ሁሉ የምትነድድ እሳት ናቸው።6እነሆ፣ በፊቴ ተጽፎአል። ኃጢአታችሁና የአባቶቻችሁን ኃጢአት በአንድ ላይ ወደ ብብታቸው ፍዳ አድርጌ አመልሳለሁ እንጂ ዝም አልልም፣" ይላል እግዚአብሔር፤7"በተራሮችም ላይ ስላጠኑ፣ በኮረብቶችም ላይ ስለ ሰደቡኝ፣ ስለዚህ አስቀድመው የሠሩትን ሥራቸውን በብብታቸው እሰፍራለሁ።"8እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፣ በረከት በእርስዋ ላይ አለና አታጥፉት" እንደሚባለው፣ ሁሉን እንዳላጠፉ ስለባሪያዎቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።'9ከያዕቆብ ዘርን ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፤ እኔም የመረጥኋቸው ይወርሱአታል፣ ባሪያዎቼም በዚያ ይኖራሉ።10ሳሮንም የበጎች ማሰማርያ፣ የአኮርም ሸለቆ የላሞች መመሰግያ ለፈልጉኝ ሕዝቤ ይሆናል።11እናንተን ግን እግዚአብሔርን የተዋችሁትን፣ ቅዱሱንም ተራራዬን የረሳችሁትን፣ ጉድ ለተባለ ጣዖትም ማዕድ ያዘጋጃችሁትን፣ እድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን የቀዳችሁትን -12እድላችሁን ለሰይፍ አደርገዋለሁ፣ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጋችሁ፣ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝምና፣ በተናገርሁም ጊዜ አልሰማችሁኝምና።"13ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ይበላሉ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ደስ ይላቸዋል እናንተ ግን ታፍራላችሁ፤14ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፣ እናንተ ግን ከልባችሁ ኀዘን የተነሣ ትጮኻላችሁ፣ መንፈሳችሁም ስለ ተሰበረ ወዮ ትላላችሁ።15ስማችሁንም ለተመረጡት ሕዝቤ እርግማን አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፣ ጌታ እግዚአብሔርም ይገድላችኋል፣ ባሪያዎቹንም በሌላ ስም ይጠራቸዋል።16እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፣ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፤ የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአልና፣ ከዓይኔም ተሰውሮአልና።17ተመልከቱ፣ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁና፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፣ ወደ ልብም አይገቡም።18ነገር ግን በፈጠርሁት ደስ ይበላችሁ፣ ለዘላለምም ሐሤት አድርጉ፤ ተመልከቱ፣ ኢየሩሳሌምን ለሐሤት፣ ሕዝብዋንም ለደስታ እፈጥራለሁና።19እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤት አደርጋለሁ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ አይሰማባትም።20ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን, ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጕልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና, ኃጢአተኛውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተረገመ ይሆናልና።21ቤቶችንም ይሠራሉ ይቀመጡባቸውማል፤ ወይኑንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ።22ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፣ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፣ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋልና።23እነርሱ ከነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም ለጥፋትም አይወልዱም።24እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ አመልስላቸዋለሁ፣ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።25ተኵላና ጠቦት በአንድነት ይሰማራሉ፣ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፣ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፣ አያጠፉምም፣" ይላል እግዚአብሔር።
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሰማይ ዙፋኔ ነው፣ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?2እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፣ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።3በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል፤4እኔ ደግሞ የተሳለቀባቸውን እመርጣለሁ፣ የፈሩትንም ነገር አመጣባቸዋለሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገርን አደረጉ፣ ያልወደድሁትንም መረጡ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፣ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝምና።"5በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ "የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ፣ ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር' ብለዋል፤ ነገር ግን ያፍራሉ።6የጩኸት ድምፅ ከከተማ፣ ድምፅም ከመቅደስ፣ በጠላቶቹ ላይ ፍዳን የሚያመጣ የእግዚአብሔር ድምፅ ተሰምቶአል።7ሳታምጥ ወለደች፤ ምጥም ሳያገኛት ወንድ ልጅን ወለደች።8ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳልን? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።9በውኑ ወደ መውለድ የማደርስ እኔ አላስወልድምን? ይላል እግዚአብሔር፤ የማስወልድስ ማኅፀንን እኔ እዘጋለሁን?" ይላል አምላክሽ።10እናንተ የምትወድዱአት ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋር ሐሤትን አድርጉ፣ ስለ እርስዋም ደስ ይበላችሁ፤ እናንተም የምታለቅሱላት ሁሉ፣ ከእርስዋ ጋር በደስታ ሐሤትን አድርጉ፣11ትጠቡ ዘንድ ከማጽናናትዋም ጡት ትጠግቡ ዘንድ፤ እጅግ ጠጥታችሁ በክብርዋ ሙላት ደስ ይላችሁ ዘንድ።12እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "እነሆ፣ ሰላምን እንደ ወንዝ፣ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ከዚያም ትጠባላችሁ፣ በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጕልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሉአችኋል።13እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፣ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ።"14ታያላችሁ፣ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፣ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የእግዚአብሔርም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፣ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።15ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር መዓቱን በቍጣ፣ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፣ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።16እግዚአብሔርም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በእግዚአብሔርም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።17በመካከላቸው ያለውን አንዱን ተከትለው ወደ ገነቱ ይገቡ ዘንድ ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የእሪያንም ሥጋ አስጸያፊ ነገርንም አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።18ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቄአለሁና፤ አሕዛብንና ልሳናትን ሁሉ የምሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል፣ እነርሱም ይመጣሉ ክብሬንም ያያሉ።19በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፣ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፣ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ ወደ ፉጥ ወደ ሉድ ወደ ሞሳሕ ወደ ቶቤል ወደ ያዋን በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፣ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።20የእስራኤል ልጆች ቍርባናቸውን በጥሩ ዕቃ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚያመጡ፣ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፣ በፈረሶችና በሰረገሎች፣ በአልጋዎችና በበቅሎች በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፣ ከአሕዛብ ሁሉ ወደ ተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፣ ይላል እግዚአብሔር።21ካህናትና ሌዋውያን እንዲሆኑ ከእነርሱ እወስዳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።22እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።23እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ዘወትር ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።24ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፣ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።"
1ይህ የኬልቅያስ ልጅ የሆነው የኤርምያስ ቃል ነው፤ እርሱ በብንያም ምድር ከነበሩት ካህናት አንደኛው ነበር። 2የአሞጽ ልጅ በሆነው በይሁዳ ንጉሥ ዐሥራ ሦስተኛ ዓመት አገዛዝ ዘመን ላይ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ። 3ቃሉ የመጣው በይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ በሆነው ኢዮአቄም ዘመን፣ የኢዮስያስ ልጅ በሆነው የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የዐሥራ አንደኛው አመት አገዛዝ አምስተኛ ወር ድረስ፣ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ምርኮኛ ሆነው ሲወሰዱ ነበር።4የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ 5"በማኅፀን ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብ ነቢይ አድርጌሃለሁ።" 6እኔም፣ "ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ ገና ብላቴና በመሆኔ እንዴት እንደምናገር አላውቅም" አልሁ።7ነገር ግን እግዚአብሔር "'ገና ብላቴና ነኝ' አትበል። ወደምልክህ ሁሉ ልትሄድ ይገባል፣ የማዝዝህንም ሁሉ ልትናገር ይገባል! 8ላድንህ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ - ይህ የእግዚአብሔር ንግግር ነው።" አለኝ።9እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፣ እንዲህም አለኝ "ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፤ 10ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾሜሃለሁ" አለኝ።11የእግዚአብሔር ቃል "ኤርምያስ ሆይ፥ ምን ታያለህ?" እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም "የለውዝ በትር አያለሁ" አልሁት። 12እግዚአብሔርም "መልካም አይተሃል፣ እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና" አለኝ።13የእግዚአብሔር ቃል ለሁለተኛ ጊዜ "ምን ታያለህ?" እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም "ፊቱ ከሰሜን አቅጣጫ የሆነ የሚፈላ ማሰሮ አያለሁ" አልሁ። 14እግዚአብሔርም "በዚህች ምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ከሰሜን አቅጣጫ ክፉ ነገር ይገለጣል" አለኝ።15በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁና ይላል እግዚአብሔር። እነርሱም ይመጣሉ፣ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም መግቢያ በራፍ ላይ፣ በዙሪያዋ ባሉት በአጥሮቿ ሁሉ ላይ፣ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያኖራሉ። 16እኔን ስለተዉበት ክፋታቸው ሁሉ፣ ለሌሎችም አማልክት ስላጠኑ፣ በገዛ እጃቸው ለሠሯቸውም ስለሰገዱላቸው፣ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።17አንተ ራስህን አዘጋጅ! ተነሥና ያዘዝሁህን ሁሉ ንገራቸው። በእነርሱ ፊት አትፍራ፣ አሊያ እኔ በእነርሱ ፊት አስፈራሃለሁ! 18ተመልከት! ዛሬ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በይሁዳም ነገሥታት -በአለቆችዋና በካህናትዋ ላይ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ እንደ ብረትም ዓምድ እንደ ናስም ቅጥር አድርጌሃለሁ። 19ይዋጉሃል፣ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም" ይላል እግዚአብሔር።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ መጣ፣ እንዲህም አለኝ፣ 2"ሂድና በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ። እንዲህም በል 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወጣትነትሽ የነበረሽን የኪዳን ታማኝነት፣ በታጨሽበት ጊዜ የነበረሽን ፍቅር፣ ዘር ባልተዘራበት ምድረ በዳ እንደ ተከተልሽኝ ስለአንቺ አስታውሳለሁ። 3እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረ፣ የእርሻው መከር በኩራትም ነበረ! ከበኩራቱ የበሉት ሁሉ ኃጢአት አድርገዋል! ክፉም ነገር ይመጣባቸዋል ይላል እግዚአብሔር።'"4የያዕቆብ ቤትና የእስራኤልም ቤት ቤተሰቦች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 5እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "አባቶቻችሁ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው እኔን ከመከተል የራቁት፣ ከንቱ ጣዖታትንም የተከተሉት፣ እና ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት? 6እነርሱም 'ከግብጽ ምድር ያወጣን እግዚአብሔር፣ በምድረ በዳ ጉድጓድ ወዳለበት የአረባህ ምድር፣ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ?' አላሉም።7ነገር ግን ፍሬዋንና ሌሎች መልካም ነገሮቿን እንድትበሉ ወደ ቀርሜሎስ ምድር አገባኋችሁ! ይሁን እንጂ በመጣችሁ ጊዜ፣ ምድሬን አረከሳችሁ፣ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ! 8ካህናቱም 'እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ የኦሪቶች ሊቅ የሆኑትም ስለ እኔ ግድ አላላቸውም! እረኞችም በደሉኝ፥ ነቢያትም ለበኣል ትንቢት ተናገሩ፣ ትርፍ የሌለውንም ነገር ተከተሉ።9ስለዚህ እከስሳችኋለሁ - የልጆቻችሁንም ልጆች እከስሳለሁ። 10ወደ ኪቲም ደሴቶች እለፉና ተመልከቱ። ወደ ቄዳርም መልእክተኞችን ላኩና እንደዚህ ያለ ነገር ህኖ እንደ ሆነ መርምራችሁ እዩ። 11አማልክት ባይሆኑ እንኳን አማልክት ያልሆኑትን አማልክቱን የለወጣቸው አንድ ሕዝብ አለን? ነገር ግን ሕዝቤ ሊረዳቸው ለማይችለው ነገር ክብሩን ለወጠ።12ሰማያት ከዚህ የተነሣ ተደነቁ! ተንቀጥቀጡ እና ደንግጡ ይላል እግዚአብሔር። 13ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች በእኔ ላይ አድርገዋልና፦ ውሃ ለመያዝ የማይችሉትን የተቀደዱ ጉድጓዶች ለራሳቸው በመቆፈር እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል!14እስራኤል ባርያ ነውን? ወይስ በቤት የተወለደ አይደለምን? እናስ ብዝበዛ የሆነው ለምንድነው? 15የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ። ብዙ ድምጽ በማሰማት ምድሩን አስፈሪ አደረጉት! ከተሞቹም የሚኖርባቸው እንዳይኖር ሆኖ ተደመሰሰ። 16የሜምፎስና የጣፍናስ ልጆች የራስ ቅልሽን ላጭተው ባርያዎችን ከአንቺ ወሰዱ! 17ይህን ሁሉ በራስሽ ላይ ያደረግሽው በመንገድ ላይ ሲመራሽ አምላክሽን እግዚአብሔርን ስለተውሽ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር አምላክሽ።18አሁንስ በግብጽ መንገድ ሄደሽ የሺሖርን ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው? በአሦርስ መንገድ ሄደሽ የኤፍራጥስንም ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው? 19ክፋትሽ ይገሥጽሻል፣ ክዳትሽም ይቀጣሻል፤ አምላክሽንም እግዚአብሔርን መተውሽ እኔንም መፍራት ማቆምሽ ክፉና መራራ ነገር እንደ ሆነ እወቂ፥ ተመልከቺ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።20ከጥንት ጀምሮ የነበረብሽን ቀንበር ሰብሬአለሁና፣ እስራትሽንም ቈርጫለሁ። እንዲህም ሆኖ አንቺ 'አላገለግልም!' አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ተጋደምሽ፣ አንቺ አመንዝራ። 21እኔ ራሴ ግን የተመረጠች ወይን፣ ፈጽሞ እውነተኛ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር። አንቺ ግን ክፉ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ? 22በወንዝ ብትታጠቢ ወይም በብርቱ ሳሙና ብትታጠቢ፣ በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።23'አልረከስሁም! በአሊምንም አልተከተልሁም' እንዴት ትያለሽ? በሸለቆዎች ያለውን ባህርይሽን ተመልከቺ! ያደረግሽውንም ተገንዘቢ፣ በመንገዷ ላይ እንደ ተለቀቀች ፈጣን ግመል ሆነሻል፤ 24በምኞትዋ ከንቱ ነፋስን እንደምታሸትት፣ ምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ! ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚፈልጋት ሁሉ ራሱን አያደክምም። ወደ እርሷ ሄደው በትኩሳቷ ወራት ያገኟታል። 25እግርሽን ባዶ ከመሆን፣ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ! አንቺ ግን 'ተስፋ-ቢስ ነው! አይሆንም፣ እንግዶችን ወድጄአለሁና እከተላቸዋለሁ!' አልሽ።26ሌባ ሲያዝ እንደሚያፍረው ሁሉ፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት፣ እነርሱ፣ ንጉሦቻቸው፣ አለቆቻቸው፣ ካህናቶቻቸውና ነብያቶቻቸውም ያፍራሉ። 27ለዛፉ፣ 'አንተ አባቴ ነህ፣' ድንጋዮንም 'አንተ ወለድከኝ' ይላሉ። ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ። በመከራቸው ጊዜ ግን 'ተነሥና አድነን!' ይላሉ። 28ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቊጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ!29ስለዚህ እኔ እንዳጠፋሁ አድርጋችሁ የምትከስሱኝ ለምንድር ነው? ሁላችሁ በእኔ ላይ ኃጢአት ሠርታችሁብኛል ይላል እግዚአብሔር። 30ሕዝባችሁን በከንቱ ቀጥቼአቸዋለሁ፤ ተግሣጽን አልተቀበሉም፤ እንደሚሰብር አንበሳ ሰይፋችሁ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል! 31ከዚህ ትውልድ የሆናችሁ እናንተ! የእግዚአብሔር ቃል ለሆነው ለቃሌ ትኩረት ስጡ! በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ፣ ወይስ የጥልቅ ጨለማ ምድር ሆንሁባትን? ሕዝቤስ ስለ ምን 'እኛ እንቅበዝበዝ፣ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም' ይላል?32ደናግሏ ጌጥዋን፣ ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ለማይቈጠሩ ቀናት ረስቶኛል። 33ፍቅርን ለመሻት መንገድሽን እንዴት በደህና ታቀኛለሽ። እንደውም መንገድሽን ለክፉዎች ሴቶች እንኳ አስተምረሻል። 34የንፁሐን ሕይወት የሆነው ደም፣ የድሆችም ደም በልብሶችሽ ላይ ተገኝቷል። እነዚህ ሰዎች በስርቆሽ ተግባር የተያዙ አልነበሩም።35ይልቊን፣ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ፣ 'ወቀሳ የለብኝም፤ በእውነት የእግዚአብሔር ቊጣ ከእኔ ተመልሶአል' አልሽ። ነገር ግን ተመልከቺ! 'ኃጢአት አልሠራሁም' ብለሻልና ይፈረድብሻል። 36መንገድሽን ትለዋውጪ ዘንድ ነገሩን ለምን ታቀልያለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ ያሳፍርሻል። 37እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።
1በሰው ዘንድ፣ 'ሰው ሚስቱን በፍቺ ቢያባርራት፣ ከእርሱም ሄዳ የሌላ ሰው ሚስት ትሆናለች። በድጋሚ ወደ እርሷ ሊመለስ ይገባዋልን? እርሷ ፈጽሞ የረከሰች አይደለችምን?' ይባላል። ያቺ ሴት ማለት ይህች ምድር ናት! አንቺ እንደ ሴተኛ አዳሪ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፣ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር። 2ዓይንሽን ወደ ተራቆቱት ኮረብቶች አንሺና ተመልከቺ! ያልተነወርሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ዘላን በምድረ በዳ እንደሚቀመጠው፣ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ አፍቃሪዎችሽን ትጠብቂያቸው ነበር። በዘማዊነትሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።3ስለዚህ የጸደይ ዝናብ ተከለከለ፣ የኋለኛውም ዝናብ አልመጣም። ነገር ግን እንደ ዘማዊት ሴት ፊት፣ ፊትሽ የእብሪተኛ ነበር። ልታፍሪም እንቢ ብለሻል። 4ከእንግዲህ ወዲህ 'አባቴ! የወጣትነቴ የቅርብ ወዳጅ ነህ።' ብለሽ ወደ እኔ አልጮኽሽልኝምን? 5እስከ ለዘላለም ትቆጣለህን? ቊጣህንስ እስከ ፍጻሜ ድረስ ትጠብቀዋለህን?' ብለሽ ተናገርሽ። ተመልከቺ! ክፋትን እንደምትፈጽሚ ተናገርሽ፣ አደረግሸውም። ስለዚህ ማድረግሽን ቀጥይ!"6እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ "እስራኤል እኔን መክዳቷን ታያለህ? ከፍ ወዳለው ተራራ ሁሉ፣ ወደለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፣ በዚያም እንደ ዘማዊት ሴት ሆነች። 7'ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ፣ ወደ እኔ ትመለሳለች' ብዬ ነበር፤ ነገር ግን አልተመለሰችም። ከዚያም እምነት የለሿ እኅቷ ይሁዳ እርሷ ያደረገችውን አየች።8ስለዚህ፣ ለእነዚህ ምክንያቶች ሁሉ ማመንዘሯን አየሁ። ከዳተኛይቱ እስራኤል! ፈትቼያት አባርሬያታለሁ፣ ደግሞም የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ። አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን አልፈራችም፣ እርስዋም ደግሞ ሄዳ ዝሙትን ፈጸመች። 9በዝሙትዋ ምድሪቱ መርከሷ ምንም አልመሰላትም፣ ስለዚህ ከድንጋይና ከግንድ ጣዖታትን አደረጉ። 10ከዚያም ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣ እምነት-የለሿ ይሁዳ በውሸት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም!"-ይላል እግዚአብሔር።11ከዚያም እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ከእምነት-የለሿ ይሁዳ ይልቅ እምነት-የለሿ እስራኤል ጸደቀች! 12ሂድና ይህን ቃል ለሰሜን ተናገር። 'እምነት የለሿ እስራኤል ሆይ፥ ተመለሽ! ይላል እግዚአብሔር፤ ለሁልጊዜ አልቈጣብሽምና። እኔ ታማኝ ስለሆንኩ - ለዘላለም እንደተቆጣሁ አልቆይም ይላል እግዚአብሔር።13በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኃጢአትሽን ዕወቂ ይላል እግዚአብሔር። 14አግብቻችኋለሁና እምነት-የለሽ የሆናችሁት ሕዝቦች፣ ተመለሱ! ይላል እግዚአብሔር፤ አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ! ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ! 15እንደ ልቤም የሆኑ እረኞችን እሰጣችኋለሁ፣ እነርሱም በዕውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።16በእነዚያ ቀናት ትበዛላችሁ፣ በምድሪቱም ላይ ታፈራላችሁ ይላል እግዚአብሔር። "የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት!" ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይናገሩም። ከእንግዲህ አያስቡትምና፣ ወይም አያስተውሉትምና ይህ ጉዳይ ከእንግዲህ በልባቸው አይመጣም። ከእንግዲህ ወዲህም ይህ ንግግር አይኖርም።'17በዚያም ዘመን ስለ ኢየሩሳሌም 'ይህች የእግዚአብሔር ዙፋን ናት' ብለው ይናገራሉ፣ ደግሞም ሌሎች አሕዛብ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ኢየሩሳሌም ላይ ይሰበሰባሉ። ከእንግዲህም ወዲህ በእልከኛ ልባቸው አይሄዱም። 18በእነዚያም ቀናት፣ የይሁዳ ቤት ከእስራኤል ቤት ጋር ይሄዳል። በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።19እኔ ግን 'እንደ ወንድ ልጄ ላከብርሽና በሌሎች አሕዛብ ካለው ይልቅ የበለጠ ውብ የሆነውን አስደሳቹን ምድር ልሰጥሽ እንዴት ፈለግሁ!' ብዬ ነበር። "አባቴ" ብለሽ ትጠሪኛለሽ። እኔንም ከመከተል አትመለሽም' ብዬ ነበር። 20ነገር ግን ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሴት፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት የሆናችሁት ከዳችሁኝ ይላል እግዚአብሔር።21"የእስራኤል ልጆች መንገዳቸውን ቀይረዋልና፣ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተውኛልና በወና ኮረብቶች ላይ የልመናቸውና ልቅሶአቸው ድምፅ ተሰማ። 22ከዳተኞች ሕዝቦች ሆይ ተመለሱ! ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ!" እነሆ! አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና ወደ አንተ እንመጣለን።23የኮረብቶችና የብዙ ተራሮች ሐሰት ብቻ መጥቷል። በእርግጥም የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ነው። 24ይሁን እንጂ አሳፋሪ ጣዖታት ለበጎቻቸውና ላሞቻቸው፣ ለወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው አባቶቻችን የሠሩትን በልተውባቸዋል። 25በእፍረት እንጋደም። በአምላካችን እግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና እፍረታችን ይሸፍነን። ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፣ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና!"
1እስራኤል ሆይ፣ ብትመለሺ፣ የምትመለሺው ወደ እኔ ይሁን፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ከፊቴ ርኩሰትሽን ብታስወግጂ፣ በድጋሚም ከእኔ ባትርቂ 2'ሕያው እግዚአብሔርን!' ብለሽ በእውነትና በፍትሕ፣ በጽድቅም ብትምይ፥ አሕዛብ በረከቴን ይጠይቃሉ፣ እኔንም ያመሰግኑኛል። 3ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ጥጋቱን እርሻ እረሱ፣ በእሾህም ላይ አትዝሩ።4እናንተም የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፣ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቊጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ። 5ይሁዳ ውስጥ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩ። "በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ" በሉ፤ ጮኻችሁም "ሁላችሁ ተሰብሰቡ። ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ" በሉ። 6ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ሰንደቅ ዓላማን አንሡ፤ ሽሹ፥ አትዘግዩ።7አንበሳ ከጥቅጥቅ ዱር እየወጣ ነው፣ አሕዛብንም የሚያጠፋ እየወጣ ነው። ምድርሽን ለማሸበር፣ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል። 8ከዚህ የተነሣ፣ ራስሽን በማቅ ልብስ ሸፍኚ፣ ሙሾ አውጪ፣ አልቅሺም። የእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና።9በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይሞታል። ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ። 10እኔም "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ፥ 'ሰላም ይሆንላችኋል' በማለት ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን በእርግጥም ፈጽመህ አታልለሃል። ሆኖም 'ሰይፉ እስከ ነፍስ ድረስ ያጠቃል።"11በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም፣"የሚያቃጥል ነፈሳስ በምድረበዳ ካሉት ወና ኮረብቶች ወደ ሕዝቤ ሴት ልጅ ይመጣል። እነርሱን አያበጥርም ወይም አያጠራም። 12ከዚያም ይልቅ እጅግ ብርቱ የሆነ ነፋስ በትእዛዜ ይመጣል፣ ደግሞም እኔ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።13ተመልከቱ እንደ ደመና ያጠቃል፣ ሠረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው። ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን! 14ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። እንዴት ኃጢአት እንደምትሠሪ ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው? 15የተናጋሪ ድምፅ ከዳን ይናገራል። የሚመጣውም ጥፋት ከኤፍሬምም ተራሮች ይሰማል።16አሕዛብ ይህንን እንዲያስቡ አድርጉ፦ ተመልከቱ፣ ወራሪዎች በይሁዳ ከተሞች ላይ የጦርነት ጩኸት ለመጮኽ ከሩቅ ምድር እየመጡ ነው ብላችሁ አውሩ። 17በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና የለማ እርሻን ከብበው እንደሚጠብቊ ይሆናሉ ይላል እግዚአብሔር። 18ባሕርይሽና ሥራሽ ይህን አድርጎብሻል። ይህ ቅጣትሽ ይሆናል። እንዴት አስጨናቂ ይሆናል! የገዛ ልብሽም ይመታል።19ልቤ! ልቤ! በልቤ ተጨንቄያለሁ። ልቤ በውስጤ ታውኮብኛል። የመለከትን ድምፅና የጦርነት ማንቂያን ሰምቻለሁና ዝም ልል አልችልም። 20በጥፋት ላይ ጥፋት ተጠርቶአል፣ መላዋ ምድርም ተበዝብዛለች። በድንገትም ድንኳኔንና መጋረጃዬን አጠፉ።21መስፈርቱን የምመለከተው እስከመቼ ነው? የመለከቱንስ ድምፅ እሰማ ይሆን? 22ሕዝቤ ተሞኝተዋልና አላወቁኝም። ሰነፍ ሕዝብ ናቸው፣ ማስተዋልም የላቸውም። ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፣ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።23ምድሪቱን አየሁ፣ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ለሰማያትም ብርሃንም አልነበረባቸውም። 24ተራሮችን አየሁ። እነሆም፣ ይንቀጠቀጡ ነበር፣ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ። 25አየሁ። እነሆ፣ ሰው አልነበረም፣ የሰማይም ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር። 26ተመለከትሁ። እነሆ፣ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፣ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቊጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር።27እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል "ምድር ሁሉ ትጠፋለች፣ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋቸውም። 28ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፣ ከላይ ያለው ሰማይ ይጠጨልማል። ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከመፈጸምም አልመለስም። 29ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጫጫታ የተነሣ እያንዳንዱ ከተማ ሁሉ ይሸሻሉ፤ ወደ ጫካም ይገባሉ። እያንዳንዱ ከተማ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ። ከተሞቹ ይተዋሉ፣ የሚኖርባቸው ሰው አይኖርምና።30አንቺም ባድማ ሆንሽ፥ ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም አጌጥሽ፣ ዓይንሽንም ተኳልሽ፣ የሚመኙሽ ወንዶች ገፉሽ። ይልቊን፣ ነፍስሽን ይሹአታል። 31ስለዚህ የምጥ፣ የበኩር ልጅ እንደሚወለድበት ያለ የጭንቅ ድምጽ፣ የጽዮን ሴት ልጅን ድምጽ ሰምቻለሁ። ለመተንፈስ ትታገላለች። እጆቿንም ትዘረጋለች፣ ከገዳዮቹ የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና 'ወዮልኝ!' አለች።
1በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፤ በአደባባዮችዋም ፈልጉ። ከዚያም ተመልከቱ፣ ስለዚህም አስቡ፦ ፍትሕን የሚያደርገውን በታማኝነትም ለማድረግ የሚሞክረውንም ሰው ታገኙ እንደሆነ፣ ይቅር እላታለሁ። 2እነርሱም 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ቢሉ የሚምሉት በሐሰት ነው። 3እግዚአብሔር ሆይ፣ ዓይንህ ታማኝነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፣ ነገር ግን አላመማቸውም። ሙሉ ለሙሉ አሸንፈሃቸዋል፣ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ። ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ።4ስለዚህ እኔም "እነዚህ ድሆች ብቻ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው። የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ ሰነፎች ናቸው፤ 5ወደ ጠቃሚዎቹ ሕዝቦች እሄዳለሁ የእግዚአብሔርን መልእክት እናገራቸዋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና። ነገር ግን እነርሱ በሙሉ ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፣ ለእግዚአብሔር ያሰራቸውንም ሰንሰለቶች ቈርጠዋል። 6ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፣ የክዳታቸውም ብዛት አይቆጠርምና አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፣ የበረሀም ተኵላ ያጠፋቸዋል፣ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፣ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።7እነዚህን ሰዎች ይቅር የምላቸው ለምንድነው? ልጆችሽ ትተውኛል አማልክትም ባልሆኑትም ምለዋል። ሞልቼ መገብኳቸው፣ እነርሱ ግን አመነዘሩ የምንዝርና ቤትን ምልክቶችንም ወሰዱ። 8በትኩሳት እንዳሉ ፈረሶች ሆኑ፤ ወዳጅነት ፈልገው ተንከላወሱ። እያንዳንዱ ሰው ወደባልንጀሮቻቸው ሚስቶች አሽካኩ። 9ስለዚህ ልቀጣ አይገባኝምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?10ወደ ወይን ከፍታዋ ወጥታችሁ አፍርሱ። ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፏቸው። ወይኖቻቸውን ቊረጡ፣ እነዚህ ወይኖች ከእግዚአብሔር አልመጡምና። 11የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ ፈጽሞ ከድተውኛልና ይላል እግዚአብሔር። 12እነርሱም ከድተውኛል። 'እርሱ እውነተኛ አይደለም። ክፉ ነገርም አይመጣብንም፣ ሰይፍንና ራብንም አናይም' አሉ። 13ነብያትም የነፋስን ያህል ጥቅም የለሽ ሆነዋል የእግዚአብሔርንም ቃል ለእኛ የሚነግረን የለም። ዛቻቸው በራሳቸው ላይ ይምጣባቸው።14ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል "በዚህ ቃል ተናግራችኋልና ተመልከት፣ በአፍህ ውስጥ ቃሌን አኖራለሁ። እንደ እሳት ይሆናል፣ ይህም ሕዝብ እንደ እንጨት ይሆናል! እሳቱም ይበላቸዋል። 15ተመልከቱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው! ቋንቋቸውንም የማታውቋቸው፣ የሚናገሩትንም የማታስተውሉት ሕዝብ ነው።16የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው። ሁሉም ኃያላን ናቸው። 17መከሮቻችሁንና እንጀራችሁን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም ይበሏቸዋል፤ በጎችንና ላሞቻችሁንም ይበላሉ፤ ወይናችሁንና በለሶቻችሁንም ይበላሉ። የምትታመኗቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ።18ነገር ግን በዚያ ዘመን እንኳን ይላል እግዚአብሔር፣ ፈጽሜ ላጠፋችሁ አላስብም። 19እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ እስራኤል እና ይሁዳ፣ 'አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለምን አደረገብን?' ስትሉ፣ አንተ ኤርምያስ ያን ጊዜ፣ 'እግዚአብሔርን እንደተዋችሁ እና በምድራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፣ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች በባርነት ትገዛላችሁ' ትላቸዋለህ።20ይህን ለያዕቆብ ቤት አውሩ፣ በይሁዳም ይሰማ። 21ይህን ስሙ፣ እናንተ ሰነፎች! ጣዖታት ፈቃድ የላቸውምና፤ ዐይን አለባቸው፣ ነገር ግን ሊያዩ አይችሉም። ጆሮዎችም አሉባቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም። 22እኔን አትፈሩኝምን? በፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ የአሸዋን ድንበር እንዳይተላለፈው በማይቋረጥ ትእዛዝ በባሕሩ ላይ አድርጌአለሁ። የባህሩ ነውጥ ቢጮኽም አያቋርጠውም።23ነገር ግን ይህ ሕዝብ ግን ዐመፀኛ ልብ አለው። በዐመፅ ሸፍቶ ሄዷል። 24በልባቸውም፣ 'የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በትክክለኛው ጊዜ የሚሰጠውን፣ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም። 25በደላችሁ እነዚህ እንዳይሆኑ አስቀርታለች። ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ወደ እናንተ እንዳይመጣ አስቆመ።26በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል። አንድ ሰው ወፎችን ለመያዝ ሲያደባ እንደሚመለከቱ፣ ወጥመድን ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ። 27ዋሻ ወፎችን እንደሚሞላ፣ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች። እንዲሁም ተልቀዋል፣ ባለ ጠጎችም ሆነዋል። 28ወፍረዋል፣ በደህንነታቸውም ያብረቀርቃሉ። ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል። ለሰዎች፣ ወይም ለወላጅ አልባዎች ነገር አልተምዋገቱላቸውም። ለችግረኞች ፍትሕን ባያደርጉም እንኳን በልጽገዋል። 29ስለእነዚህ ነገሮች አልቀጣምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ ለራሴ አልበቀልምን?30በምድር ላይ የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር ሆናለች፤ 31ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፣ ካህናትም በገዛ ኃይላቸው ይገዛሉ። ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፣ ነገር ግን በፍጻሜው ምን ይፈጠራል?
1እናንተ የብንያም ሕዝቦች፣ ከኢየሩሳሌም በመሸሽ ደህንነትን አግኙ። በቴቁሔ መለከትን ንፉ። ታላቅ ጥፋት የሆነ ክፉ ነገር ከሰሜን እየመጣ ነውና በቤትሐካሬም ላይ ምልክትን አንሡ። 2የተዋበችውና ሰልካካዋን የጽዮንን ልጅ እደመስሳለሁ። 3እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርስዋ ይሄዳሉ፣ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፣ እያንዳንዱም እረኛ በገዛ እጁ መንጋውን ይጠብቃል።4ነገሥታት "ለአማልክቶቻችሁ እንድትዋጉ ራሳችሁን አስገዙ። ተነሡ፣ በቀጥርም እናጥቃ። ቀኑ እየመሸ መሆኑ፣ የማታውም ጥላ እየረዘመ መሆኑ እጅግ መጥፎ ነው። 5ነገር ግን በሌሊትም እናጥቃ፣ አምባዎችዋንም እናፍርስ።6የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ የከበባ አፈርን ደልድሉ፤ ይህች በግፍ የተሞላች ከተማ በመሆኗ ለማጥቃት ትክክለኛዋ ከተማ ነች። 7ጕድጓድ ውኃ ማፍለቊን እንደሚቀጥል፣ እንዲሁ ይህች ከተማ ክፋትን ማፍለቋን ትቀጥላለች። ዐመጽና ሥርዓተቢስነት በእርስዋ ዘንድ ይሰማል። መከራና መቅሠፍትም ሳይቋረጥ በፊቴ አለ። 8ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ከአንቺ እንዳልለይ፣ አንቺንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ፣ ተግሣጽን ተቀበዪ።"9የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፣ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን በእርግጥ ይቃርሟቸዋል፤ በድጋሚ እጅህን ዘርግተህ ወይንን ከግንዱ እንደሚለቅም አድርግ። 10ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ፣ ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? ተመልከቱ! ጆሮአቸው ያልተገረዘ ነው፤ በትኩረት ለመስማት አይችሉም! ተመልከቱ! የእግዚአብሔር ቃል ሊያቀናቸው መጥቶባቸዋል፣ ነገር ግን አይፈልጉትም።"11ነገር ግን በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ። በውስጤ ይዤ ልታገሠው ደክሜአለሁ። እንዲህ አለኝ፣ "በጎዳና ሕፃናት ላይ፣ እንዲሁም በወጣቶችም ስብስብ ላይ አፍስሰው። እያንዳንዱ ባል ከሚስቱ ጋር እድሜ ጠገቡ ሽማግሌም ከጎበዙ ጋር ይወሰዳልና። 12ቤቶቻቸው እርሻዎቻቸውም ሚስቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሆናሉ። በምድር የሚገኙ ነዋሪዎችን አጠቃለሁና ይላል እግዚአብሔር።13ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ እያንዳንዳቸው በኃቅ ላልሆነ ትርፍ ስስታሞች ናቸው። ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ እያንዳንዳቸው በተንኰል ይመላለሳሉ። 14የሕዝቤንም ስብራት የሚፈውሱት ግን በጥቂቱ ነው፣ ሰላም ሳይኖር 'ሰላም ሰላም!' ይላሉ። 15ርኩስን ነገር ስለሠሩ አፍረዋልን? በጭራሽ አልፈሩም፣ ማንኛውንም እፍረት አላወቁም። ስለዚህ በምቀጣቸው ጊዜ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ። ይገለበጣሉ፣" ይላል እግዚአብሔር።16እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በመንገድ ማቋረጫ ላይ ቁሙና ተመልከቱ፣ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ። 'መልካሚቱ መንገድ ወዴት ናት?' በሉና በእርስዋ ላይ ሄዳችሁ ለነፍሳችሁ ዕረፍትን አግኙ። ሕዝቡ ግን፣ 'አንሄድባትም' አሉ። 17እኔም የመለከቱን ድምፅ እንዲያደምጡ ጠባቂ ጉበኞችን ሾምሁላችሁ። እነርሱ ግን፣ 'አናደምጥም' አሉ። 18አሕዛብ ሆይ፥ አድምጡ! ተመልከቱ፣ በእነርሱ ላይ የሚደርስባቸውን ትመሰክራላችሁ። 19ምድር ሆይ፣ ስሚ! ተመልከቺ፣ የአሳባቸው ፍሬ የሆነ ጥፋትን በዚህ ህዝብ ላይ ላመጣ ነው። ለቃሌ ወይም ለህጌ ምንም ትኩረት አልሰጡም፣ ነገር ግን ከዚያ ይልቅ አጣጣሉት።"20ከሳባ የሚቀርበው ዕጣን ለእኔ ምን ማለት ነው? ወይስ ከሩቅም አገር የሆነው ጣፋጭ ሽታ ምንድነው? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፣ እንዲሁም መስዋዕቶቻችሁን አልቀበለውም። 21ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ በዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ። አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል። ነዋሪዎችና ጎረቤቶቻቸው ይጠፋሉ። 22እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ሕዝብ ከሰሜን ምድር ይመጣል። ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻ ይነሣል።23ቀስትንና ጦርን ያነሣሉ። ጨካኞች ናቸው፣ ምሕረትንም የላቸውም። ድምፃቸው እንደ ባሕር ጩኸት ነው፣ በጽዮን ሴት ልጅ ላይ እንደሚዋጉ በፈረሶችም ላይ ይጋልባሉ።" 24ስለ እነርሱ ወሬውን ሰምተናል። እጃችን በጭንቀት ዝላለች። ምጥ ወላድን ሴት እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞናል።25የጠላት ሰይፍና ሽብር ስለከበባችሁ ወደ ሜዳ አትውጡ፣ በመንገድም ላይ አትሂዱ። 26የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣ ማቅ ልበሺና ለብቸኛ ልጅ መቀበሪያ አፈር ውስጥ ተንከባለዪ። አጥፊው በድንገት ይመጣብናልና ለራስሽ መራራ የሆነ የቀብር ለቅሶን አድርጊ።27"ኤርምያስ፣ መንገዳቸውን እንድትመረምርና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል ብረትን እንደሚፈትን አድርጌሃለሁ። 28እነርሱ ሁሉ ሌሎችን የሚወነጅሉ እጅግ ዐመፀኞች ናቸው። በብልሹነት የሚመላለሱ ናስና ብረት ናቸው። 29ወናፍ በሚያቃጥላቸው እሳት አናፋ፣ እርሳሱም በእሳቱ ቀለጠ። ክፋት ስላልተወገደ፣ የማጥራቱ ሥራ በመካከላቸው ይቀጥላል። 30እግዚአብሔር ጥሎአቸዋልና የተጣለ ብር ብለው ይጠሯቸዋል።"
1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፣ 2በእግዚአብሔር ቤት በራፍ ላይ ቁም! እንዲህ በል፣ 'ይሁዳ ሁሉ ሆይ፣ እግዚአብሔርን ልታመልኩ በእነዚህ በራፎች የምትገቡ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።3የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መንገዳችሁንና ሥራችሁን መልካም አድርጉ፣በዚህም ስፍራ መኖር እንድትቀጥሉ አደርጋችኋለሁ። 4ራሳችሁን አታላይ በሆኑ ቃሎች ላይ ታምናችሁ፣ "የእግዚአብሔር መቅደስ! የእግዚአብሔር መቅደስ! የእግዚአብሔር መቅደስ!" አትበሉ።5መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ መልካም ብታደርጉ፤ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፤ 6በምድሪቱ የሚቆየውን እንግዳ፣ ወላጅ አልባውን፣ ወይም መበለቲቱንም ባትበዘብዙ፣ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፣ ለገዛ ጉዳታችሁ እንዲሆንባችሁ ሌሎች አማልክትን ባትከተሉ፤ 7ያን ጊዜ ከጥንቱ ጊዜ ጀምሮ እስከ ለዘላለም ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳድራችኋለሁ።8እነሆ! በማይረዳችሁ የሐሰት ቃል እየታመናችሁ ናችሁ። 9ትሰርቃላችሁ፣ ትገድላላችሁ፣ ታመነዝራላችሁ? ደግሞም በሐሰትም ትምላላችሁ፣ ለበኣልም ታጥናላችሁ፣ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ትከተላላችሁ? 10ከዚያም መጥታችሁ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ፣ እነዚህን ሁሉ ጥፋቶች ማድረግ እንድትችሉ "ድነናል፣" አላችሁ። 11ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ ፊት የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? ነገር ግን፣ እነሆ፣ እኔ አይቻለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።12'ስለዚህ በቀድሞ ዘመን ስሜን ከመጀመሪያ ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደ ነበረው ስፍራዬ ሂዱ፣ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ያደረግሁበትን እዩ። 13ስለዚህ አሁንም፣ ይህን ሥራችሁን ሁሉ ስላደረጋችሁ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ ተናገርኳችሁ፣ እናንተ ግን አልሰማችሁም። በጠራኋችሁም ጊዜ፣ አልመለሳችሁም። 14ስለዚህ፣ በሴሎ እንዳደረግሁ፣ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት በምትታመኑበት ቤት፣ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ። 15የኤፍሬምንም ዘር የሆኑትን ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፣ እንዲሁ ከፊቴ እጥላችኋለሁ።16ደግሞም አንተ፣ ኤርምያስ አልሰማህምና ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፣ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፣ አትማልድላቸው። 17እነርሱ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የሚያደርጉትን አታይምን? 18ያስቈጡኝ ዘንድ፣ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ፣ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፣ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፣ ሴቶችም ዱቄት ያቦካሉ።19በእውነት እኔን ያስቈጣሉን? ይላል እግዚአብሔር፤ ለእነርሱስ እፍረት እንዲሆንባቸው የሚያስቆጡት ራሳቸውን አይደለምን? 20እንግዲያው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ ይፈስሳል፣ በሰውና በአውሬው ላይ፣ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል። ይነድዳል፣ መቼም አይጠፋም።'21የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ለመሥዋዕታችሁ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን ጨምሩ፣ ከዚያም ላይ ሥጋውን ጨምሩ። 22አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ቀን፣ የትኛውንም ነገር ከእነርሱ አልጠየቅሁም። ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት አላዘዝኋቸውምም። 23ይህንን ትእዛዝ ብቻ ሰጠኋቸው፣ "ቃሌን ስሙ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ። መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።"24ነገር ግን በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደ ፊትም ሳይሆን ወደ ፊታቸው ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም። 25አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አገልጋዮቼን፣ ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር። እነርሱን ተግቼ ላክሁባችሁ። 26ነገር ግን አልሰሙኝም። ምንም ትኩረት አልሰጡም። ይልቊን፣ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።27እነዚህን ቃሎች ሁሉ ንገራቸው፣ ነገር ግን አይሰሙህም። እነዚህን ነገሮች አውጅላቸው፣ ነገር ግን አይመልሱልህም። 28የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፣ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው። እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ተቈርጦአል በላቸው።29ፀጕርሽን ቍረጪ፣ ተላጪው፣ ጣዪውም። በወናዎች ኮረብቶችም ላይ ሙሾን አውጪ። እግዚአብሔር በቍጣው ይህንን ትውልድ ጥሎአልና፣ ትቶታልምና ። 30የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉን ነገር ሠርተዋል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል።31ከዚያም ቶፌት ውስጥ በቤን ሄኖም ሸለቆ መስገጃዎችን ገነቡ። እኔም ያላዘዝሁትንና ፈጽሞ በልቤ ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ ይህንን አድርገዋል። 32ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ቶፌት ወይም የቤን ሄኖም ሸለቆ ተብሎ ዳግመኛ አይጠራም። የእርድ ሸለቆ ይባላል፤ የሚተርፍ ስፍራ እስኪታጣ ድረስ በቶፌት በድኖችን ይቀብራሉ ይላል እግዚአብሔር።33የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል፣ የሚያስፈራራቸውም አይኖርም። 34ምድሪቱም ወና ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ አጠፋለሁ።
1በዚያን ዘመን፥ የይሁዳን ነገሥታት አጥንትና የመኳንንቶቹን አጥንት፥ የካህናቱን አጥንትና የነቢያቱን አጥንት፥ የኢየሩሳሌምንም ሰዎች አጥንት ከመቃብራቸው ያወጣሉ ይላል እግዚአብሔር። 2በተከተሉአቸው፣ ባገለገሏቸውና በፈለጉአቸው፣ ባመለኳቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል። አጥንቶቻቸው አይሰባሰቡም ወይም በድጋሚ አይቀበሩም። በምድር ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ። 3እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩት፣ ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ቅሬታዎች ሁሉ፣ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር።4እንዲህም ትላቸዋለህ፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የትኛውም የወደቀ ሰው አይነሣምን? የጠፋስ ለመመለስ አይሞክርምን? 5ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘላቂ በሆነ አለመታመን ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ንስሃ ለመግባትም እንቢ ብሎአል።6አደመጥሁ ሰማሁም፣ ትክክለኛ ነገር አልተናገሩም፤ ማንም ስለ ክፋቱ ንስሃ አልገባም፣ ማንም "ምን አድርጌአለሁ?" አላለም። ወደ ጦርነት እንደሚሮጥ ፈረስ ሁላቸውም በየመንገዳቸው ሄዱ። 7ሽመላ በሰማይ ትክክለኛ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም ያውቃሉ። እነርሱ ወደ ሚሰደዱበት የሚሄዱት በትክክለኛ ጊዜ ነው፣ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።8እናንተስ፣ "ጥበበኞች ነን! የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው" እንዴት ትላላችሁ? በእርግጥ ተመልከቱ! የአታላይ ጸሐፊ ብዕር ማታለልን አድርጎአል። 9ጥበበኞች ያፍራሉ። ደንግጠውማል ተጠምደዋል። ተመልከቱ! የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፣ ስለዚህ ጥበባቸው ምን ጥቅም አለው? 10ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስታሞች ናቸውና፣ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ ያታልላሉና፣ ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።11ቀላል ነገር እንደሆነ በማድረግ የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ። ሰላም ሳይሆን፣ "ሰላም፣ ሰላም" ይላሉ። 12አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም። ትሕትናም አልነበራቸውም። ስለዚህ በሚቀጡ ጊዜ ቀድሞውኑ ከወደቊት ጋር ይወድቃሉ ይላል እግዚአብሔር። 13ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ላይ ፍሬ፣ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም። ቅጠልም ይረግፋልና የሰጠኋቸውም ያልፋልና።14ለምን ዝም ብለን እንቀመጣለን? በአንድነት ኑ፤ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንሂድ፣ በዚያም በሞት ዝምተኞች እንሆናለን። እግዚአብሔር ዝም ያሰኘናልና። ስለ በደልነው መርዝ አጠጥቶናል። 15ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ነገር ግን መልካም ነገር አልተገኘም። የፈውስ ጊዜን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ነገር ግን ሽብር እንደሆነ ተመልከቱ።16የፈረሰኞች ድምጽ ከዳን ተሰማ። ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የሚኖሩባትንም ሊበሉ ይመጣሉና። 17ተመልከቱ፣ አስማት የማይከለክላቸውን እባቦችንና እፉኝቶችን እሰድድባችኋለሁ። እነርሱም ይነድፉአችኋል" ይላል እግዚአብሔር።18ኅዘኔ ፍጻሜ የለውም፣ ልቤም ታምሞአል። 19ተመልከቱ! እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የሕዝቤ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ምድር ተሰማ። በተቀረጹ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱ ጣዖታት ያስቈጡኝ ስለ ምንድር ነው?20መከሩ አልፎአል፣ በጋው አብቅቷል። እኛ ግን አልዳንነም። 21በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ። በደረሰባት ነገር በጭንቀት አለቅሳለሁ፤ ጠቁሬማለሁ። 22በገለዓድ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ፈዋሽ የለምን? የሕዝቤ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?
1ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፣ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ! 2ሁሉም አመንዝሮች፣ የከዳተኞች ጉባኤ በመሆናቸው ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ! 3"አታላይ ቀስታቸው በሆነው በምላሳቸው ሐሰት ተናገሩ፣ ነገር ግን በምድር ላይ በታማኝነት ግሩም አይደሉም። ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉ። እኔንም አላወቁምና፣" ይላል እግዚአብሔር።4እያንዳንዱ ወንድም ሁሉ ያታልላልና፣ እያንዳንዱ ጎረቤትም ሁሉ ሐሜተኛ ስለሆነ እናንተ ሁሉ ከጎረቤቶቻችሁ ተጠንቀቁ፣ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ። 5እያንዳንዱ ሰውም ሁሉ ጎረቤቱን ያታልላል በእውነትም አይናገርም። ምላሶቻቸው የማታለል ነገሮችን ያስተምራል። በደልንም በማድረግ ይደክማሉ። 6በማታለል መካከል ትኖራላችሁ፣ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፣ ይላል እግዚአብሔር።7ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ እፈትናቸዋለሁ። እመረምራቸዋለሁ። ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው? 8ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ያልታመኑ ነገሮችን ይናገራሉ። ከጎረቤቶቻቸው ጋር በአንደበታቸው በሰላም ይናገራሉ፣ በልባቸው ግን ያደቡበታል። 9በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀጣቸውምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህስ ባለ ሕዝብ ላይ አልበቀልምን?10ለተራሮች የልቅሶና የዋይታን ዝማሬ እዘምራለሁ፣ ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም የቀብር ዋይታን እዘምራለሁ። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የየትኛውንም ከብት ድምፅ አይሰሙም። የሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሁሉ ሸሽተው ሄደዋል። 11ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርባት ወና አደርጋቸዋለሁ። 12ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ለሌሎች እንዲነግር የእግዚአብሔር አፍ ምን ተናገረው? ምድሪቱስ ስለምን ጠፋች? ማንም እንደማያልፍባት እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተደመሰሰች?13እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ "በፊታቸው የሰጠኋቸውን ሕጌን ስለተዉ፣ ድምጼንም አልሰሙምና ወይም አልተጓዙበትምና። 14አባቶቻቸው እንዳስተማሯቸው በልባቸውን ምኞት ተመላልሰዋልና፣ በኣሊምን ተከትለዋልና።15ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የተመረዘንም ውኃ አጠጣዋለሁ። 16እነርሱና አባቶቻቸውም ባላወቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፣ እስካጠፋቸውም ድረስ በበስተኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።"17የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህንን አስቡ፦ የቀብር አስለቃሾችን ጥሩ፤ ይምጡ። ወደ ብልሃተኛ አልቃሾች ላኩ። 18ይፍጠኑና ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ የለቅሶ ዝማሬን ይዘምሩልን።19'እንዴት ተበዘበዝን። ቤቶቻችን ስለፈረሱ ምድሪቱንም ትተናልና እንዴት አፈርን!' የሚል የልቅሶ ድምፅ በጽዮን ተሰምቶአል። 20ስለዚህ እናንተ ሴቶች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ ከአፉ ለሚወጣው ቃል ትኩረት ስጡ። ከዚያም ለሴቶች ልጆቻችሁም የልቅሶውን ዝማሬ አስተምሩ፣ ለእያንዳንዷም የጎረቤታችሁ ሴት የቀብሩን ሙሾ አስተምሩ።21ሞት ወደ መስኮታችን መጥቷልና፤ ወደ ቤተ መንግሥቶቻችን ሄዷል። ሕፃናቱን ከውጪ፣ ወጣቶቹንም ከከተማይቱ አደባባይ ያጠፋል። 22'የሰውም ሬሳ በሜዳ ላይ እንደ ጕድፍ፣ ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል፣ ማንምም አይሰበስበውም።23እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ጠቢብ በጥበቡ እንዲመካ አትፍቀዱ፣ ወይም ጦረኛ በኃይሉ አይመካ። ባለ ጠጋም በብልጥግናው እንዲመካ አትፍቀዱ። 24ሰው በየትኛውም ነገር የሚመካ ከሆነ፣ በዚህ ይሁን፣ ማስተዋል ያለውና የሚያውቀኝ በመሆኑ። የኪዳን ታማኝነት፣ ፍትሕንና ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፣ ይላል እግዚአብሔር።25ተመልከቱ፣ በሰውነታቸው ብቻ የተገረዙትን እቀጣለሁ። 26ግብጽንና ይሁዳን፣ የአሞን ሕዝቦች የሆኑትን ኤዶምያስና ሞዓብንም፣ እንዲሁም በምድረ በዳም የተቀመጡትን ፀጉራቸውን የተላጩትን ሁሉ፣ ባለመገረዛቸው ምክንያት የምቀጣበት ዘመን እነሆ ይመጣል። እነዚህ ሁሉ ሕዝቦች ያልተገረዙ ናቸውና፣ ደግሞም የእስራኤል ልብ አልተገረዘምና" ይላል እግዚአብሔር።
1እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ የተናገረውን ቃል ስሙ። 2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፣ ከሰማይ በሚሆኑት ምልክቶችም አትፍሩ፣ አሕዛብ እነዚህን ይፈራሉና።3የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና። አንድ ሰው ዛፍን ከጫካ ይቈርጣል፤ የሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይህንን ይሠራል። 4ከዚያም በብርና በወርቅ ያስጌጡታል። እንዳይወድቅም በመዶሻና በሚስማር ይቸነክሩታል። 5እነዚህ ጣዖታት ምንም ማለት ስለማይችሉ፣ በዱባ ማሳ ላይ እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው። ጨርሶ መራመድ ስለማይችሉ ሊይሸከሟቸው ይገባል። ክፉ መሥራት አይቻላቸውምና፣ ደግምም የትኛውንም መልካም ነገር ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።6እግዚአብሔር ሆይ እንደ አንተ ያለ የለም። አንተ ታላቅ ነህ፣ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው። 7የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፣ የማይፈራህ ማነው? በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል ወይም በታማኝ መንግሥታቸውም ሁሉ መካከል እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፣ አንተ ይህ ይገባሃል።8እነርሱ ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው፣ ደንዝዘዋል፣ ደንቍረውማል፤ እንጨት ብቻ እንጂ ምንም ላልሆኑ ጣዖቶቻቸው ደቀመዛሙርት ናቸው። 9ከጠርሴስ አንጥረኛ የቀጠቀጠውን ብር፣ ከአፌዝም ወርቅ ያመጣሉ። ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው። ብልሃተኞች ሰዎቻቸው እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይሠራሉ። 10እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው። እርሱም ሕያው አምላክና የዘላለም ንጉሥ ነው። ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፣ አሕዛብም ቊጣውን መቋቋም አይችሉም።11እናንተም "ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ" ትሏቸዋላችሁ። 12ምድርን በኃይሉ የፈጠረው፣ ደረቊን ምድር በጥበቡ የመሠረተው ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው። 13ድምፁ በሰማይ የውኾችን ድምፅ ይፈጥራል፣ ከምድርም ጠርዝ ደመናትን ከፍ ያደርጋል። ለዝናቡም መብረቅን ያደርጋል፣ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።14እያንዳንዱ ሰው እውቀት አጥቶ አላዋቂ ሆኗል። እያንዳንዱ አንጥረኛ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፣ ሕይወትም የለባቸውምና በቀረጸው ጣዖት አፍሮአል። 15እነርሱ ጥቅም የለሽ፣ የቀልደኞች ሥራ ናቸው፤ በሚቀጡበት ጊዜ ይጠፋሉ። 16የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፣ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስሙ ነው።17በከበባ ውስጥ የምትኖሩ እናንተ ሕዝቦች፣ ዕቃችሁን ሰብስቡና ምድሪቱን ትታችሁ ውጡ። 18እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "ተመልከቱ፣ በዚህ ጊዜ በምድሪቱ የሚኖሩትን ልወረውራቸው ነው። አስጨንቃቸዋለሁ፣ እንደዚያም ሆኖ ያገኙታል።19ስለ ተሰበረው አጥንቴ ወዮልኝ! ቍስሌም መርቅዟል። ስለዚህ እኔ፣ "በእውነት ይህ የመከራ ጩኸቴ ነው ልሸከመውም ይገባኛል" አልሁ። 20ድንኳኔ ተበዘበዘ፣ አውታሬም ሁሉ ለሁለት ተቈረጠ። ልጆቼም ከእኔ ወሰዷቸው፣ ስለዚህ ከእንግዲህ የሉም። ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም።21እረኞች ደንቆሮዎች ሆነዋል። እግዚአብሔርን አልፈለጉትምና። ስኬት አልሆነላቸውም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል። 22የወሬን ድምፅ ስሙ፣ "ተመልከቱ! እየመጣ ነው! የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ጽኑ የምድር ነውጥ መጥቶአል።"23እግዚአብሔር ሆይ፣ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይመጣ አውቃለሁ። የሚራመድ የትኛውም ሰው የገዛ አካሄዱን አያቀናም። 24እግዚአብሔር ሆይ እንዳታጠፋኝ በቊጣህ ሳይሆን በፍትህ ቅጣኝ። 25በማያውቁህ አሕዛብ፣ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አፍስስ። ያዕቆብን በልተውታልና፣ ፈጽመው ሊያጠፉት ውጠውታልና ማደሪያውንም አፍርሰዋልና።
1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ። 2የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስማ፣ ለእያንዳንዳቸው የይሁዳ ሰዎች፣ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩትም ተናገር፥3እንደዚህም በላቸው 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይሰማ ሰው ርጉም ይሁን። 4ከግብጽ አገር ከሚቀልጠው የብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝሁበት ኪዳን ይህ ነው። "ድምፄን ስሙ፣ ያዘዝኋችሁንም ነገሮች ሁሉ አድርጉ፣ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁና።" 5ይህም ዛሬ የምትኖሩባትን ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ የማልሁትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው።" ከዚያ እኔ ኤርምያስ "አዎን፣ እግዚአብሔር ሆይ!' ብዬ መለስሁለት።6እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ "ይህችን ቃል ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ተናገር። እንዲህ በል፣ 'የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ ፈጽሙትም። 7አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ "ቃሌን ስሙ" በማለት በጽናት አስጠንቅቄአቸው ነበር። 8እነርሱ ግን አልሰሙም ወይም ትኩረት አልሰጡም። እያንዳንዱ ሰው በክፉ ልባቸው እልከኝነት ሄዱ። ስለዚህ እንዲመጡባቸው ያዘዝኋቸውን እርግማን ሁሉ አመጣሁ። ሕዝበ ግን እንደዚያም ሆኖ አልታዘዙም።"9ቀጥሎ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ "በይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ዘንድ አድማ ተገኝቶአል። 10ቃሌንም ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወዳሉ፣ ይልቊንም ያመልኩአቸው ዘንድ እንግዶችን አማልክት ወደተከተሉ ወደ አባቶቻቸው ኃጢአት ተመለሱ። የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።11ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ሊያመልጡት የማይችሉትን ጥፋት አመጣባቸዋለሁ። ከዚያም ወደ እኔ ይጮኻሉ፣ እኔ ግን አልሰማቸውም። 12የይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ሄደው ወደሚሰዉላቸው አማልክት ይጮኻሉ፤ ነገር ግን በጥፋታቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም። 13ይሁዳ፣ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ጨምረዋል። በኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ልክ አሳፋሪ መሠዊያ፣ ለበዓለም የማጠኛ መሠዊያ አድርጋችኋል።14ስለዚህ አንተ ራስህ፣ ኤርምያስ፣ ለዚህ ሕዝብ ልትጸልይ አይገባም። ስለእነርሱ አታልቅስ ወይም አትጸልይ። በጥፋታቸው ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና። 15እጅግ ብዙ ክፉ ፍላጎት የነበረው ተወዳጁ ሕዝቤ በቤቴ ውስጥ ያለው ለምንድነው? ለመስዋዕታችሁ የተጠበቀው ሥጋ ክፋትን አድርጋችኋልና ሊረዳችሁ አይችልም፣ ከዚያም በዚያ ደስተኛ አትሆኑም። 16በጥንቱ ጊዜ እግዚአብሔር በተወዳጅ ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራሽ። ሆኖም ግን እንደ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፣ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል።17ለበኣልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።18እግዚአብሔርም እነዚህን ነገሮች አውቃቸው ዘንድ አስታወቀኝ፤ አንተ እግዚአብሔር ሥራቸውን እንዳይ አደረግኸኝ። 19እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ የበግ ጠቦት ሆንሁ። እነርሱም፣ "ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ! ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው" ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር። 20ይሁን እንጂ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አእምሮንና ልብን ይመረምራል፣ በቅንም ይፈርዳል። ጉዳዬን አቅርቤልሃለሁና በእነርሱ ላይ በቀልህን እመሰክራለሁ።21ስለዚህም 'በእጃችን እንዳትሞት በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር' ብለው ነፍስህን ስለሚሹ ስለ ዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። 22ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህንን ይላል፣ 'ተመልከት፣ እቀጣቸዋለሁ። ኃያላን ወጣቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በረሃብ ይሞታሉ። 23በምቀጣቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚቀር የለም።
1እግዚአብሔር ሆይ፣ ከአንተ ጋር በተሟገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ። የማጉረመርምበትን ምክንያት በእርግጥ ልነግርህ ይገባኛል። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይሳካል? እምነት-የለሽ የሆኑት ሁሉ ተሳክቶላቸዋል። 2አንተ ተክለሃቸዋል፣ እነርሱም ሥር ሰድደዋል። ፍሬ ማፍራታቸውን ቀጥለዋል። በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፣ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።3ይሁን እንጂ አንተ እግዚአብሔር ታውቀኛለህ። አይተኸኛል፣ ልቤንም ፈትነሃል። እንደ ሚታረዱ በጎች ለያቸው። ለመታረድም ቀን ነጥላቸው። 4ምድሪቱ የምታለቅሰው፣ የአገሩ ሣርስ ሁሉ ከነዋሪዎቹ ክፋት የተነሣ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? አራዊት እና ወፎች ተወስደዋል። በእርግጥም ሕዝቡ "በእኛ ላይ የሚሆነውን እግዚአብሔር አያውቅም፤" ብለዋል።5"አንተ ኤርምያስ ከእግረኛ ወታደሮች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፣ ከፈረሶች ጋር መወዳደር እንዴት ትችላለህ? በአስተማማኝ የገጠር ምድር ውስጥ ብትሰናከል፣ በዮርዳኖስ ጥሻዎች ውስጥ እንዴት ትሆናለህ? 6ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አሳልፈው ሰጥተውሃልና፣ ጮኸው ክደውሃልና። መልካም ነገሮችንም ቢናገሩህ አትታመናቸው።7ቤቴን ትቼአለሁ፣ ርስቴንም ጥያለሁ። ተወዳጁን የገዛ ሕዝቤን በጠላቶቹ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ። 8ርስቴ በጥሻ እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን አንሥታብኛለችና ስለዚህ ጠልቻታለሁ። 9ርስቴ እንደ ጅብ ሆነችብኝ፣ ዝንጕርጕር አሞሮችም ለማጥመድ በላይዋ ይዞራሉ። ሂዱ፣ የምድር አራዊትን ሁሉ ከሜዳ ሰብስቡና ይበሉም ዘንድ አምጡአቸው።10ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን ደምስሰዋል። እድል ፈንታዬ የሆነውን ምድር ሁሉ ረግጠዋል፤ የምደሰትበትን እድል ፈንታ ወና ምድረ በዳ አድርገውታል። 11ባድማ አድርገውታል። ፈርሳለችና አለቅስላታለሁ። ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም።12በወና ኮረብቶች ሁሉ ላይ አጥፊዎች መጥተዋል፣ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከአንደኛው የምድር ዳር ጀምሮ እስከ ሌላኛው የምድር ዳር ድረስ ይበላልና። በሕይወት ላለ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ደህንነት የለም። 13ስንዴን የዘሩ ቢሆንም እሾህን አጨዱ። በሥራቸው ደከሙ፣ ምንም አላገኙም። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባገኛችሁት ፍሬ ታፍራላችሁ።14ሕዝቤ እስራኤል እንዲወርስ ያደረግሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ከገዛ ምድራቸው የምነቅላቸው እኔ ነኝ፣ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ። 15ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እራራላቸዋለሁ፣ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።16በበኣል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩት ሁሉ እነዚያው ሕዝቦች 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ በጥንቃቄ ቢማሩ፣ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ። 17ነገር ግን ማናቸውም ባይሰሙኝ ያንን ሕዝብ ፈጽሜ እነቅለዋለሁ። በእርግጥም ይነቀላል፣ ይጠፋማል" ይላል እግዚአብሔር።
1እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "ሂድ፣ ከተልባ እግር የተሠራ የውስጥ ሱሪ ግዛና ወገብህን ታጠቅ፤ ነገር ግን አስቀድመህ በውኃ ውስጥ አትንከረው። 2ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳለው የውስጥ ሱሪን ገዛሁና ወገቤን ታጠቅሁበት። 3ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጣና እንዲህ አለኝ፣ 4በወገብህ ያለውን የገዛሃውን መታጠቂያ ወስደህ ተነሥና ወደ ኤፍራጥስ ሂድ። በዚያም በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽገው" አለኝ።5እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ ሄድሁና በኤፍራጥስ ሸሸግሁት። 6ከብዙ ቀንም በኋላ፣ እግዚአብሔር፣ "ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ። በዚያም እንድትሸሽገው ያዘዝሁህን የውስጥ ሱሪ ከዚያ ውሰድ" አለኝ። 7እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄድሁ ቆፈርሁም፣ ከሸሸግሁበትም ስፍራ የውስጥ ሱሪውን ወሰድሁ። ነገር ግን እነሆ! የውስጥ ሱሪው ተበላሽቶ ነበር፣ ለምንም የማይጠቅም ሆኖ ነበር።8ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ በድጋሚ መጣና እንዲህ አለኝ፣ 9"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲሁ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ታላቅ እብሪት አጠፋለሁ። 10ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፣ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፣ ያመልኩአቸውና ይሰግዱላቸው ዘንድ ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንዳማይረባ እንደሆነው እንደዚ የውስጥ ሱሪ ይሆናሉ። 11የውስጥ ሱሪው በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፣ እንዲሁ ሕዝብና ስም ምስጋናና ክብር ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን አልሰሙኝም።12ስለዚህ ይህንን ቃል ለእነርሱ ልትናገር ይገባል፣ 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ ይሞላል።' እነርሱም 'ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ እንዲሞላ በውኑ እኛ አናውቅምን?' ይሉሃል። 13ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፣ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት፣ ካህናቱን፣ ነቢያቱንና በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።' 14ሰውንም በሰው ላይ፣ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፣ እቀጠቅጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራም፣ አላዝንላቸውም፣ አልምርም።"15ስሙ፣ አድምጡም። እግዚአብሔር ተናግሮአልና እብሪተኞች አትሁኑ። 16ሳትጨልም እግራችሁም በጨለመችው ተራራ ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨለማ ሳይለውጠው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ። 17ይህን ባትሰሙ፣ ስለ ትዕቢታችሁ ብቻዬን አለቅሳለሁ። የእግዚአብሔርም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ ታነባለች፣ እንባንም ታፈስሳለች።18ለንጉሡና ንግሥቲት ለሆነችው እናት፣ 'የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ' በል። 19የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፣ የሚከፍታቸውም የለም። ይሁዳ ሁሉ ተማርኮአል፣ ፈጽሞ ተማርኮአል።20ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፤ ለአንቺ የሰጠው መንጋ፣ ለአንቺ የተዋበው መንጋሽ ወዴት አለ? 21ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን እግዚአብሔር በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አንቺንም የሚይዝሽ የምጥ ስቃይ ጅማሬ አይደለምን?22በልብሽም፣ 'እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ?' ብትዪ፣ የቀሚስሽ ዘርፍ ተገልጦ የተገፈፍሽው ከብዙ ኃጢአትሽ የተነሣ ነው። 23የኩሽ ሕዝቦች የቆዳ ቀለማቸውን፣ ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? ከሆነ፣ በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ መልካምን ማድረግ ትችላላችሁ። 24ስለዚህ እንደሚያልፍ እብቅ በምድረ በዳ ነፋስ እበትናቸዋለሁ።25ረስተሽኛልና፣ በሐሰትም ታምነሻልና የሰጠኹሽ፣ የደነገግሁልሽም እድል ፈንታ ይህ ነው፣ ይላል እግዚአብሔር። 26ስለዚህም የቀሚስሽን ዘርፍ እኔ ራሴ በፊትሽ እገልጣለሁ፣ የእፍረት አካልሽም ይታያል። 27አስጸያፊ ሥራሽን፣ ምንዝርናሽን፣ ማሽካካትሽን፣ የግልሙትናሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ በሜዳም የሆኑትን እነዚህን አስፀያፊ ነገሮች እንዲታዩብሽ አደርጋለሁ! ወዮልሽ፣ ኢየሩሳሌም! አልነፃሽም። ይህስ እስከ መቼ ይቀጥላል?"
1ስለ ድርቅ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፣ 2"ይሁዳ ታልቅስ፣ ደጆችዋም ይውደቊ። ስለ ምድራቸው እያለቀሱ ናቸው፤ ለኢየሩሳሌም የሚያለቅሱት ከፍ ብሎአል። 3ኃያላኖቻቸውም አገልጋዮቻቸውን ለውኃ ሰደዱ። ወደ ጕድጓድ ሲመጡ ውኃ ሊያገኙ አልቻሉም። ሁሉም ሳይሳካላቸው ተመለሱ፤ አፍረውና ተዋርደው ራሳቸውን ተከናነቡ።4ከዚህ የተነሣ በምድሪቱ ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ሆነ። አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ። 5ዋላ በምድረ በዳ ወልዳ ሣር ባለመኖሩ ግልገልዋን ተወች። 6የሜዳ አህዮችም በወና ኮረብታ ላይ ቆመው እንደ ቀበሮ ወደ ነፋስ አለከለኩ። ልምላሜ የለምና ዓይኖቻቸው ፈዘዙ።7ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም፣ እግዚአብሔር ስለ ስምህ ሥራ። ያልታመንንባቸው ተግባራቶቻችን ጨምረዋልና፣ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናል። 8የእስራኤል ተስፋ ሆይ፣ በጭንቀት ጊዜ የምታድነው አምላክ ወደ ማደሪያ ዘወር እንደሚል መንገደኛ በምድሪቱ ላይ ለምን እንደ እንግዳ ትሆናለህ? 9ግራ እንደተጋባ ሰው፣ ያድንም ዘንድ እንደማይችል ኃያል ለምን ትሆናለህ? አንተ ግን፣ በመካከላችን ነህ፣ እግዚአብሔር ሆይ እኛም በስምህ ተጠርተናል። አትተወን።10እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፣ "መቅበዝበዝን ወድደዋልና፣ እግራቸውንም እንዲህ ከማድረግ አልከለከሉም፤" ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አላለውም። አሁን በደላቸውን ያስባል ኃጢአታቸውንም ይቀጣል። 11እግዚአብሔርም፣ "ለዚህ ሕዝብ መልካም እንዲሆንላቸው አትጸልይላቸው። 12ቢጾሙ ጸሎታቸውን አልሰማም፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም። በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ አለኝ።13ከዚያም፣ "ኦ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮ! እነሆ! ነቢያት ለሕዝቡ፣ 'በዚህ ስፍራ በእውነት ሰላምን እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፣ ራብም አያገኛችሁም ይሉአቸዋል" እያሉ ናቸው። 14እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ነቢያቱ በስሜ የውሸት ትንቢት ይናገራሉ። አልላክኋቸውም፣ አላዘዝኋቸውም፣ አልተናገርኳቸውምም። ነገር ግን፣ የውሸት ራእይና ጥቅም የለሽ የሆነ ከንቱ ምዋርትን፣ የልባቸውንም ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።"15ስለዚህ እግዚአብሔር፣ "በዚህች አገር ሰይፍና ራብ አይሆንም ስለሚሉ፣ ነገር ግን በስሜ ትንቢት ስለሚናገሩ ስላልላክኋቸው ነቢያት እንዲህ ይላል፦ እነዚህ ነብያት በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ። 16ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይበተናሉ፤ ክፋታቸውንም አፈስስባቸዋለሁ እነርሱንና ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም።17ይህንን ቃል ንገራቸው፦ 'ዐይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ። ድንግሊቱ የሕዝቤ ልጅ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ። 18ወደ ሜዳ ብወጣና ባይ! በሰይፍ የሞቱ አሉ። ወደ ከተማም ብገባ፣ ያኔም በራብ የታመሙ አሉ። ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቋት አገር ሄደዋል።"19በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ጽዮንንስ ጠልተሃታልን? ፈውስ በማይኖረን ጊዜ ስለ ምን መታኸን? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፣ መልካምም አልተገኘም፤ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ተመልከቱ፣ ያለው ግን ድንጋጤ ብቻ ነው። 20እግዚአብሔር ሆይ፣ በአንተ ላይ ኃጢአትን ሠርተናልና ክፋታችንንና የአባቶቻችንን በደል እናውቃለን።21አትጣለን! ስለ ስምህ፣ የክብርህንም ዙፋን አታስነውር። ከእኛ ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ እንጂ አታፍርስ። 22በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል የጸደይን ዝናብ ከሰማይ ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ይህንን የምታደርግ አምላካችን እግዚአብሔር አንተ አይደለህምን? እነዚህን ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን ተስፋ እናደርጋለን።
1እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፣ "ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም እንኳን፣ ለዚህ ሕዝብ አላደላም። እንዲወጡ ከፊቴ አባርራቸው። 2እነርሱም፣ 'ወዴት እንሂድ?' ቢሉህ፣ ያኔ አንተ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሞት የተወሰኑት ወደ ሞት፣ ለሰይፍም የተወሰኑት ወደ ሰይፍ፣ ለራብም የተወሰኑት ወደ ራብ፣ ለምርኮም የተወሰኑት ወደ ምርኮ' ትላቸዋለህ።3አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፣ እነርሱም አንዳንዶችን የሚገድል ሰይፍ፣ አንዳንዶችን የሚጎትቱ ውሾችን፣ አንዳንዶችን የሚበሉ የሰማያትን ወፎች፣ የምድርንም አራዊት ናቸው ይላል እግዚአብሔር። 4የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ ለምድር መንግሥታት ሁሉ መጨነቂያ አደርጋቸዋለሁ።5ኢየሩሳሌም ሆይ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ዘወር የሚል ማነ ነው? 6አንቺ እኔን ጥለሻል፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል። ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ እመታሽና አጠፋሻለሁ። ለአንቺ ምሕረት ማድረግ አድክሞኛል። 7በአገርም ደጆች ውስጥ በመንሽ አበጥራቸዋለሁ። ልጆቻቸውንም እነጥቃለሁ። ከመንገዳቸውም አልተመለሱምና ሕዝቤን አጠፋለሁ።8መበለቶቻቸውን ከባሕር አሸዋ ይልቅ አበዛለሁ። በቀትር ጊዜ ላይ በብላቴኖች እናት ላይ አጥፊውን እልካለሁ። ድንጋጤና ሽብር በድንገት እንዲወድቅባቸው አደርጋለሁ። 9ሰባት የወለደች ትደክማለች። ታለከልካለች። ገና ቀን ሳለ ፀሐይዋ ትገባባታለች። የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁና ታፍራለች፣ ትዋረድማለች።10እናቴ ሆይ፣ ወዮልኝ! በምድሪቱ ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና። አላበደርሁም፣ ከማንም አልተበደርኩም፣ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል። 11እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ "በእውነት ለደኅንነትህ አልታደግህምን? በእርግጥ በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላቶችህ እንዲለምኑህ አደርጋለሁ። 12ሰው ብረትን ይሰብራልን? በተለይ ከሰሜን የሆነውን ከናስ ጋር የተቀየጠውን ብረት የሚሰብር አለን?13ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለመበዝበዝ በነፃ እሰጣለሁ። ይህንንም የማደርገው በድንበሮችህ ሁሉ ስለፈጸምከው ኃጢአትህ ሁሉ ነው። 14ከዚያም፣ ጠላቶችህ ወደማታውቀው ምድር እንዲወስዱህ አደርጋለሁ፣ የምታቃጥላችሁ እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና።15አንተ ራስህ ታውቃለህ፣ እግዚአብሔር ሆይ! አስበኝ እርዳኝም። የሚያሳድዱኝንም ተበቀላቸው። በትእግሥትህ አታርቀኝ። ስለ አንተ ነቀፌታን እንደ ጠገብሁ እወቅ። 16ቃሎችህ ተገኝተዋል እኔም በልቼያቸዋለሁ። የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃሎችህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆኑልኝ።17በሚፈነድቁትና በደስተኞች ዙሪያ አልተቀመጥሁም። በቍጣህ ሞልተኸኛልና በኃይለኛው እጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ። 18ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ፣ ቍስሌስ ስለ ምን ፈውስን የማይቀበልና የማይሽር ሆነ? በውኑ እንደ አታላይ ምንጭ፣ እንደደረቅ ውኃ ትሆናለህን?19ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ኤርምያስ ሆይ፣ ንስሃ ብትገባ፣ እንደ ቀድሞው እመልስሃለሁ፣ በፊቴም ቆመህ ታገለግለኛለህ። የተዋረደውንም ከከበረው ብትለይ፣ እንደ አፌ ትሆናለህ። ሕዝቡ ወደ አንተ ይመለሳሉ፣ አንተ ራስህ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም። 20ለዚህም ሕዝብ የማይጣስ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፣ ይዋጉሃል። ነገር ግን እኔ ላድንህ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም ይላል እግዚአብሔር። 21ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፣ ከጨካኞችም ቡጢ እቤዥሃለሁ።
1ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ 2"በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አይኑርህ። 3እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ስለ ተወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፣ ስለወለዱአቸውም ስለ እናቶቻቸው፣ በዚህችም ምድር እንዲወለዱ ስላደረጉ አባቶቻቸው እንዲህ ይላል፣ 4በበሽታ ሞት ይሞታሉ። አይለቀስላቸውም ወይም አይቀበሩም። በመሬትም ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ። በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፣ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናሉ።'5እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ልቅሶ ወዳለበት የትኛውም ቤት አትግባ። ታለቅስም፣ ታዝንም ዘንድ አትሂድ። ሰላሜን፣ ቸርነትና ምሕረትን፣ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና! 6ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ። አይቀበሩም፣ ሰዎችም አያለቅሱላቸውም። ስለ እነርሱም ገላን አይነጩላቸውም ራስንም አይላጩላቸውም።7ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የእዝን እንጀራን ሊካፈሉ አይገባም፣ ለአባታቸውና ለእናታቸውም ማንም የመጽናናት ጽዋ ሊሰጧቸው አይገባም። 8ትበላና ትጠጣ ዘንድ ከእነርሱ ጋር ለመቀመጥ ወደ ግብዣ ቤት አትግባ።' 9የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'ተመልከት፣ በዐይናችሁ ፊት በዘመናችሁም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስቆማለሁ።'10ከዚያም ለዚህ ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፣ 'እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገር ለምን ተናገረብን? በደላችንስ ምንድር ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድር ነው? ሲሉህ፣ 11እንዲህ በላቸው፣ 'አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ሌሎችን አማልክት ተከተሉ አመለኩአቸውም ሰገዱላቸውም። እነርሱም ትተውኛል፣ ሕጌንም አልጠበቁም።12ነገር ግን፣ እናንተ ራሳችሁ ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ ተመልከቱ፣ እያንዳንዱ ሰው በክፉ ልብ እልከኝነት ሄዷል፣ እኔንም የሚሰማ የለም። 13ስለዚህ ከዚህች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወዳላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፣ ሞገስን አላደርግላችሁምና በዚያ ሌሎችን አማልክት ቀንና ሌሊት ታመልካላችሁ።14ስለዚህ ተመልከቱ! ከእንግዲህ 'የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!' የማይባልበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር። 15ነገር ግን፣ የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር፣ ካሳደዳቸውም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።16ተመልከቱ! ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ሕዝቡን ሊያወጡ ያጠምዱአቸዋል። ከዚህም በኋላ ብዙ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፣ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያጠምዷቸዋል። 17ዓይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነውና፤ ከፊቴም ሊሰወሩ አይችሉም። በደላቸውም ከዓይኔ ሊሰወር አይችልም። 18በተጠሉ ጣዖቶቻቸው ሬሳዎች ምድሬን አርክሰዋልና፣ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና፣ አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።"19እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ምሽጌ፣ አምባዬ፣ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ። አሕዛብ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ ሄደው፣ "በእርግጥ አባቶቻችን ውሸትን ወርሰዋል። ባዶ ናቸው፤ በእነርሱ ዘንድ ትርፍ የለም ይላሉ። 20በውኑ ሕዝቦች አማልክት ያልሆኑትን ለራሳቸው አማልክትን አድርገው ይሠራሉን? 21ስለዚህ ተመልከቱ! በዚህ ጊዜ አስታውቃቸዋለሁ፣ እጄንና ኃይሌን አስታውቃቸዋለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ስሜ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ያውቃሉ።"
1"የይሁዳ ኃጢአት የሾለ አልማዝ ባለው የብረት ብዕር ተጽፎአል። በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶች ላይ ተቀርጾአል። 2ልጆቻቸውም ከለመለሙ ዛፎች በታችና በከፍተኞቹ ኮረብቶች ላይ ያሉትን መሠዊያቸውንና አሼራ የምትባለውን ጣዖታቸውን ያስባሉ።3በገጠር ባሉት ተራሮች ላይ ያሉትን መሠዊያዎቻቸውን ያስታውሳሉ። ባለጠግነታችሁንና መዝገባችሁን ሁሉ፣ የኮረብታውን መስገጃዎቻችሁንም በኃጢአታችሁ ምክንያት እንዲበዘበዙ አደርጋለሁ። 4አናንተም የሰጠኋችሁን ርስት ትለቅቃላችሁ። በማታውቋትም ምድር ለጠላቶቻችሁ ባሪያ አደርጋችኋለሁ፤ ለዘላለም የሚነድደውን እሳት በቍጣዬ አንድዳችኋልና።5እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በሰው የሚታመን፣ ሥጋ ለባሹንም ብርታቱ የሚያደርግ፣ ልቡን ግን ከእግዚአብሔር የሚመልስ ሰው ርጉም ነው። 6በአረብ ምድር እንዳለ ትንሽ ቍጥቋጦ ይሆናል፣ የሚመጣውንም መልካም ነገር አያይም። ሰውም በሌለበት ዐለታማ ምድር ውስጥ ደረቅ በሆነ ምድረ በዳ ይቀመጣል።7ነገር ግን በእግዚአብሔር የታመነ፣ የልበ-ሙሉነቱ ምክንያት እግዚአብሔር ነውና ቡሩክ ነው። 8በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፣ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ተክል ይሆናልና። ሙቀት ሲመጣ አያይም፣ ቅጠሉ ይለመልማልና። ከዚያም፣ በድርቅ ዓመት ላይ አይሠጋም፣ ማፍራቱንም አያቋርጥም።9ልብ ከየትኛውም ነገር ይልቅ ተንኰለኛ ነው። በሽተኛ ነው፤ ማንስ ያስተውለዋል? 10ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፣ እንደ ሥራው ፍሬ ልሰጥ ልብን የምመረምር፣ ኵላሊትንም የምፈትን እግዚአብሔር እኔ ነኝ። 11ያልጣለችውን እንቁላል እንደምታቅፍ ቆቅ፣ እንዲሁ አንድ ሰው ያለፍትህ ባለጠጋ ይሆን ይሆናል። ነገር ግን በእኩሌታ ዘመኑ ላይ ብልጥግናው ይተወዋል፣ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።12የመቅደሳችን ስፍራ ከመጀመሪያም ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው። 13እግዚአብሔር የእስራኤል ተስፋ ነው። አንተን የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ። ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይቆረጣሉ። 14እግዚአብሔር ሆይ፣ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ! አድነኝ እኔም እድናለሁ። አንተ የምስጋናዬ ዝማሬ ነህና።15ተመልከቱ፣ 'የእግዚአብሔር ቃል ወዴት ነው? ይምጣ!' ይሉኛል። 16እኔም አንተን ተከትዬ እረኛ ከመሆን አልሮጥሁም። የመከራንም ቀን አልታገሥሁም። ከከንፈሬ የመጣውን አንተ ታውቃለህ። በህልውናህ ፊት ተነግረዋል።17መሸበሪያ አትሁንብኝ። በመከራ ቀን አንተ መጠጊያዬ ነህ። 18አሳዳጆቼ ይፈሩ፣ እኔ ግን አልፈር። እነርሱ ይደንግጡ፣ እኔ ግን አልደንግጥ። የጥፋትን ቀን አምጣባቸው፣ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው።19እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ "ሂድና የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት የሕዝቡ በር፣ ከዚያም በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም። 20እንዲህም በላቸው፣ 'በእነዚህ በሮች የምትገቡ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፣ የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።21እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ለራሳችሁ ሕይወት ተጠንቀቁ፥ በኢየሩሳሌምም በሮች እንድታገቡ በሰንበት ቀን ሸክምን አትሸከሙ። 22በሰንበት ቀን ከቤቶቻችሁ ሸክምን አታውጡ። የትኛውንም ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፣ ነገር ግን አባቶቻችሁንም እንዳዘዝሁት የሰንበትን ቀን ቀድሱ።" 23እነርሱ ግን ትኩረት ሰጥተው አልሰሙም፣ እንዳይሰሙና ተግሣጽን እንዳይቀበሉ አንገታቸውን አደነደኑ።24እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ ይሆናል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ደግሞም በሰንበት ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም አታምጡ፣ ይልቊንም የሰንበትን ቀን ለእግዚአብሔር ቀድሱ የትኛውንም ሥራ አትሠሩበት፤ 25በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መሳፍንት በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ እየተቀመጡ በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፣ እነርሱና መሳፍንቶቻቸው የይሁዳም ነዋሪዎች በኢየሩሳሌምም የሚቀመጡ ይመጣሉ። ይህችም ከተማ ለዘላለም የሰው መኖሪያ ሆና ትቀራለች።26የሚቃጠለው መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን የእህሉንም ቍርባን ዕጣኑንም የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞች ከኢየሩሳሌምም ዙሪያ ከብንያምም አገር ከቈላውም ከደጋውም ከኔጌቭም ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ። 27ነገር ግን የሰንበትን ቀን ልትቀድሱ፣ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች ልትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፣ እሳትን በበሮችዋ ላይ እለኩሳለሁ፣ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ትበላለች፣ እሳቱም አይጠፋም።
1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል እንዲህ አለው፣ 2"ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፣ በዚያም ቃሌን አሰማሃለሁና። 3ስለዚህም ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ወረድሁ፣ ሸክላ ሠሪውም ሥራውን በመንኵራኩር ላይ ይሠራ ነበር። 4ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፣ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።5የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ 6"የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? ይላል እግዚአብሔር። ተመልከቱ! ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፣ እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ ውስጥ አላችሁ። 7በአንድ ወቅት፣ አባርር፣ አፈርስ፣ ወይም አጠፋ ዘንድ ስለ ሕዝብ ወይም ስለ መንግሥት አንዳች ነገር እናገር ይሆናል። 8ነገር ግን ያንን የተናገርኩበት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፣ ያኔ እኔ ላደርግበት ያሰብሁትን ክፉ ነገር እተወዋለሁ።9በሌላ ጊዜ፣ ስለ ሕዝብ ወይም ስለ መንግሥት እንደምሠራው ወይም እንደምተክለው እናገራለሁ። 10ነገር ግን ድምፄን ባለመስማት በፊቴ ክፉን ነገር ቢያደርግ፣ ያኔ እኔ ላደርግለት የተናገርሁትን መልካም ነገር አቆማለሁ።11አሁን እንግዲህ፣ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ተናገርና እንዲህ በላቸው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ ክፉ ነገር ልፈጥርባችሁ ነው። እቅድንም ላወጣባችሁ ነው። መንገዶቻችሁ እና ልምምዶቻችሁ መልካምን እንዲያመጡላችሁ፣ እያንዳንዱ ሰው ከክፉ መንገዱ ንስሃ ይግባ' 12እነርሱ ግን፣ 'ይህ ጥቅም የለውም። እንደ እቅዶቻችን እናደርጋለን። እያንዳንዳችን ክፉ የሆነው ልባችን እንደተመኘው እልከኝነትን እናደርጋለን' አሉ።13ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እንዲህ ያለውን ነገር ማን ሰምቷል ብላችሁ አሕዛብን ጠይቊ። የእስራኤል ድንግል አስደንጋጭ ነገርን አድርጋለች። 14በውኑ የሊባኖስ በረዶ በሜዳ ያሉትን ድንጋያማ ኮረብቶች ይተዋልን? ወይስ ከሩቅ የምትመጣው ቀዝቃዛይቱ ፈሳሽ ውኃ ትደርቃለችን?15ሕዝቤ ግን ረስተውኛል። ጥቅም ለሌላቸው ጣዖታት ሠውተዋል፤ ከመንገዳቸውም ተሰናክለዋል፤ በአነስተኞቹ መንገዶች ለመሄድ ሲሉ የቀደሙትን መንገዶች ትተዋል። 16ምድራቸው ለመደንገጪያና ለዘላለም ማፍዋጫ ይሆናል። የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፣ ራሱንም ይነቀንቃል። 17እንደ ምሥራቅ ነፋስ በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ። በጥፋታቸውም ቀን ፊቴን ሳይሆን ጀርባዬን አሳያቸዋለሁ።"18እነርሱም፣ "ሕግ ከካህናት፣ ወይም ምክር ከጠቢባን፣ ወይም ቃልም ከነቢያት አይጠፋምና ኑ፣ በኤርምያስ ላይ እናሲር። ኑ፣ በቃላችን እናጥቃው፣ የሚናገረውንም ሁሉ ትኩረት አንስጠው" አሉ። 19እግዚአብሔር ሆይ፣ አድምጠኝ! የጠላቴንም ድንፋታ ስማ። 20ጕድጓድ ቈፍረውልኛልና መልካም ስለሆንኩላቸው ከእነርሱ የሚሆን ጥፋት ክፍያዬ ይሆናልን? ለደህንነታቸው ለመናገር፣ ከእነርሱ ቊጣህን ለመመለስ በፊት እንደቆምኩ አስታውስ።21ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፣ ለሰይፍም ኃይል አሳልፈህ ስጣቸው። ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፣ ወንዶቻቸውም ይገደሉ፣ ወጣቶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ። 22ሊይዙኝ ጕድጓድ ቆፍረዋልና፣ ለእግሮቼም ድብቅ ወጥመድ አኑረዋልና በላያቸው ጭፍራን በድንገት ባመጣህ ጊዜ፣ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ። 23አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይገድሉኝ ዘንድ በላዬ ያቀዱትን ዕቅድ ሁሉ ታውቃለህ። በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር አትበል። ኃጢአታቸውንም ከአንተ ዘንድ አትደምስስ። ይልቅ፣ በፊትህ ይውደቁ። በቍጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።
1እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ሂድና ከሸክላ ሠሪ ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ። 2የገል በር በሚከፈትበት ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፣ በዚያም የምነግርህን ቃል ተናገር። 3እንዲህም በል፣ 'ይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ! የሰማውን ሰው ጆሮ የሚያስጨንቅ ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ አመጣለሁ።4ይህንን የማደርገው ስለተዉኝና ይህንን ስፍራ የባዕድ አማልክት አድርገውታልና ነው። እነርሱና አባቶቻቸው ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት አጥነዋል፣ የይሁዳም ነገሥታት ይህንን ስፍራ በንጹህ ደም ሞልተዋል። 5እኔም ያላዘዝሁትን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ወንዶች ልጆቻቸውን ለበኣል በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋል። ይህንን እንዲያደርጉ አልተናገርኳቸውም፣ በልቤም አላሰብሁትም።6ስለዚህም፣ ተመልከቱ፣ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ የማይባልበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር። 7በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን እቅድ ከንቱ አደርጋለሁ። በጠላቶቻቸው ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን ደግሞ በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ። ከዚያም ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ። 8ከዚያም ይህችን ከተማ አጠፋና መደነቂያ አደርጋታለሁ፣ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፣ ከንፈሩንም ይመጥጣል። 9የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፣ ሁሉም ጠላቶቻቸውንና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የጎረቤቶቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።10ከዚያም ገምቦውን ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ። 11እንዲህም ትላቸዋለህ፣ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪውን ዕቃ ኤርምያስ እንደሰባበረው፣ ደግሞም በድጋሚ ይጠገን ዘንድ እንደማይቻል፣ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀብሩበትም ስፍራ እስከማይኖር ድረስ በቶፌት ይቀበራሉ።12ይህችንም ከተማ እንደ ቶፌት ሳደርግ ለዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የማደርገው ይህንኑ ነው ይላል እግዚአብሔር። 13የረከሱትም የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፣ እነዚያ በሰገነታቸው ላይ ለሰማይ ከዋክብት ሁሉ ያጠኑባቸው ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ፣ እንደ ቶፌት ስፍራ ይሆናሉ።"14ከዚያም ትንቢት እንዲናገር እግዚአብሔር ልኮት ከበረው ስፍራ፣ ከቶፌት ኤርምያስ መጣ። በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ እንዲህ አለ፣ 15"የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና፣ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።"
1በእግዚአብሔርም ቤት የተሾመው አለቃ የካህኑ የኢሜር ልጅ ጳስኮር ኤርምያስ በዚህ ነገር ትንቢት ሲናገር ሰማ። 2ስለዚህ ጳስኮር ነቢዩን ኤርምያስን መታው፣ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ባለው በላይኛው የብንያም በር በእግር ግንድ አሰረው።3በቀጣዩ ቀን ጳስኮር ኤርምያስን ከግንድ እስር አወጣው። ከዚያም ኤርምያስ እንዲህ አለው፣ "እግዚአብሔር ስምህን፣ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም። 4እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'ተመልከት፣ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉና ዓይኖችህም ያንን ያያሉ። ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እርሱም በባቢሎን ምርኮኛ ያደርጋቸዋል ወይም በሰይፍ ይገድላቸዋል።5የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እነዚህን ነገሮች በጠላቶቻችሁ እጅ አኖራለሁ፣ እነርሱም ይይዟቸዋል። እነርሱም ይወስዷቸዋል ደግሞም ወደ ባቢሎን ያመጧቸዋል። 6አንተ ግን፣ ጳስኮር ሆይ፣ በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ። ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ ደግሞም በዚያ ትሞታለህ። አንተና የሚያታልሉ ነገሮችን የተነበይክላቸው ወዳጆችህ ሁሉ በዚያ ትቀበራላችሁ።"7እግዚአብሔር ሆይ፣ አሳመንኸኝ፣ እኔም አምኛለሁ። ያዝኸኝ ደግሞም አሸነፍኸኝ። መላገጫ ሆኛለሁ። ሕዝቡ በየቀኑ፣ ቀኑን ሁሉ ይሳለቊብኛል። 8በተናገርሁ ቍጥር፣ 'ግፍና ጥፋት' ብዬ እጮኻለሁ። የእግዚአብሔርም ቃል ቀኑን ሁሉ ነቀፌታና ዋዛ ሆኖብኛልና። 9እኔም፣ 'ከእንግዲህ ወዲህ የእግዚአብሔርን ስም አላስብም። ከእንግዲህ ወዲህም ስሙን አላውጅም' ብል፣ ያን ጊዜ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደሚነድድ፣ በልቤ ውስጥ እንዳለ እሳት ሆነብኝ። ስለዚህ ልሸከመው ታገልሁ፣ ነገር ግን አልቻልሁም።10በዙሪያዬ ካሉ ብዙ ሰዎች የሚያሽብር አሉባልታን ሰምቻለሁ። የቅርቤ ሰዎች የሆኑት ውድቀቴን ለማየት ጠበቊ፣ 'ምናልባት እንበረታበት እንደ ሆነ፣ ከዚያም እንበቀለው እንደ ሆነ 'ክሰሱት፣ እኛም እንከስሰዋለን' ይላሉ። 11እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያል ጦረኛ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ። አያሸንፉኝም። አይከናወንላቸውምና፣ በእጅጉ ያፍራሉ። መቼም የማይረሳ በሚሆን እፍረት የማያበቃ እፍረት ያፍራሉ።12ጻድቅን የምትመረምር፣ አእምሮንና ልብን የምትመለከት የሠራዊት ጌታ ሆይ፣ ክርክሬን አሳይቼሃለሁና በላያቸው በቀልህን ልይ። 13ለእግዚአብሔር ዘምሩ! እግዚአብሔርን አመስግኑ! የተጨቆኑትን ሰዎች ሕይወት ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና።14የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን። እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን። 15'ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል' ብሎ ለአባቴ የነገረው ሰው የተረገመ ይሁን።16ያም ሰው እግዚአብሔር ያለምሕረት እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን። በማለዳም እርዳታ የሚለምን ጩኸትን በቀትርም የጦርነት እሪታን ይስማ። 17እግዚአብሔር በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና ወይም እናቴን መቃብሬ አላደረገኝምና፣ ይህ ይከሰት። 18ችግርንና ጣርን አይ ዘንድ፣ ዘመኔም በእፍረት ይሞላ ዘንድ ለምን ከማኅፀን ወጣሁ?
1ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። 2"የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፣ እባክህ፣ እግዚአብሔርን ጠይቅ። ምናልባት ከእኛ ይመለስ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአምራቱ ሁሉ ያደርግ ይሆናል።"3ስለዚህ ኤርምያስ እንዲህ አላቸው፣ "ለሴዴቅያስ እንዲህ በሉት፣ 4'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ የባቢሎንን ንጉሥ ከቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን ዕቃ ጦራችሁን እመልሰዋለሁ! እነዚያንም ወደዚህች ከተማ አማከይ እሰበስባቸዋለሁ። 5ያን ጊዜ እኔ ራሴ በተዘረጋች እጅና በብርቱ ክንድ፣ በቍጣና በመዓት በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ።6በዚህችም ከተማ የሚኖሩትን፣ ሰዎችንና እንስሶችን እመታለሁ፣ በጽኑም መቅሰፍት ይሞታሉ። 7ከዚህ በኋላ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስን፣ ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትንም ባሪዎቹንና ሕዝቡን፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ከዚያም እርሱ በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል። አያዝንላቸውም፣ አይራራላቸውም፣ ወይም አያዝንላቸውም።'8ከዚያም ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ልትል ይገባል፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አደርጋለሁ። 9በዚህች ከተማ ውስጥ የሚቆይ የትኛውም ሰው በሰይፍ፣ በራብ፣ በመቅሠፍትም ይሞታል፤ ነገር ግን ወጥቶ ወደ ከበቡአችሁ ወደ ከለዳውያን የሚገባ ግን በሕይወት ይኖራል። በሕይወትም ያመልጣል። 10መልካምን ሳይሆን ጥፋትን ለማምጣት ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ተሰጥታለች፣ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።'11የይሁዳ ንጉሥ ቤትን በተመለከተ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 12የዳዊት ቤት ሆይ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'በማለዳ ፍርድን አድርጉ። የተዘረፈውንም ከአጨቋኙ እጅ አድኑ፣ አሊያ ቍጣዬ እንደ እሳት ይወጣና ያቃጥላል። ከሥራችሁ ክፋት የተነሣ ሊያጠፋው የሚችል ማንም አይኖርም።13ተመልከቱ፣ የሸለቆው ነዋሪዎች! በሜዳው ላይ ያለው ዓለት ሆይ በእናንተ ላይ ነኝ ይላል እግዚአብሔር። "ሊያጠቃን በእኛ ላይ የሚወርድ ማነው?" ወይም "ወደ ቤታችን የሚገባ ማን ነው?" ለምትሉት፣ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ። 14የሥራችሁ ፍሬ በእናንተ ላይ እንዲመጣባችሁ መድቤያለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፣ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድና በዚያም ይህን ቃል ተናገር። 2እንዲህም በል፣ 'በዳዊት ዙፋን የምትቀመጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። አንተና የእርሱ ባርያዎች የሆናችሁ፣ በእነዚህም በሮች የመትገቡት ሕዝቦቹ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፣ የተዘረፈውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ። በምድራችሁ ያለውን እንግዳ፣ ወይም የትኛውንም ወላጅ አልባ ወይም መበለቲቱን አትበድሉ። አታምፁባቸው፣ ወይም በዚህ ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።4እነዚህንም ነገሮች ብታደርጉ፣ ያን ጊዜ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡ ነገሥታት በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ። እርሱም፣ ባርያዎቹም፣ ሕዝቡም እንዲሁ ይገባሉ! 5ነገር ግን ከእኔ የተነገሩትን እነዚህን ቃሎች ባትሰሙ፣ ይህ ንጉሣዊ ቤተመንግሥት እንደሚጠፋ በራሴ ምያለሁ" ይላል እግዚአብሔር።6እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፣ 'አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድ፣ ወይም እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ። ነገር ግን፣ በእርግጥ ምድረ በዳ፣ ማንም እንደማይቀመጥባቸው ከተሞች አደርግሃለሁ። 7እንዲመጡባችሁ አጥፊዎችን በእናንተ ላይ አዘጋጅቻለሁ! የተመረጡትንም የዝግባ ዛፎቻችሁን ይቈርጣሉ፣ በእሳትም ውስጥ ይጥሉአቸዋል።8ከዚያም ብዙ አሕዛብ በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ። ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፣ "እግዚአብሔር በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደረገ?" ይላሉ። 9ሌላኛውም፣ "የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ ስላመለኩአቸውም ነው" ብለው ይመልሳሉ።10ለሞተው አታንቡ። አታልቅሱለትም። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና፣ የተወለደባትንም አገር አያይምና ወደምርኮ ለሚሄደው በእርግጥ አልቅሱ።11በአባቱ በኢዮአስ ፋንታ ስለ ነገሠው ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። 12'በተማረከባት አገር ይሞታል እንጂ ወደዚህ አይመለስም፣ ይህችንም አገር ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።'13ቤቱን ያለ ጽድቅ ሰገነቱንም በግፍ ለሚሠራ፣ ሌሎችንም አሠርቶ፣ ክፍያ ለማይሰጣቸው። 14'ለራሴ ሰፊ የላይኛ ቤት፣ ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፣ መስኮትንም ለሚያወጣ፣ በዝግባም ሥራ ለሚያስጌጥ፣ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት።'15የዝግባ እንጨት እንዲኖርህ ስለፈለግህ መልካም ንጉሥ የሚያደርግህ ይህ ነውን? በውኑ አባትህ አይበላምና አይጠጣም ነበርን፣ ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ ነገሮች መልካም ሆነውለት አልነበረምን። 16ለድሀውና ችግረኛው ፍርድን ይፈርድ ነበር። በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። እኔን ማወቅ ማለት ይህ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር።17ዓይንህና ልብህ ግን ለስስት፣ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ፣ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ካልሆነ በቀር ሌላ ነገር የለውም። 18ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ "ወዮ፣ ወንድሜ ሆይ!" ወይም፣ "ወዮ፣ እኅቴ ሆይ!' እያሉ አያለቅሱለትም፣ ወይም 'ወዮ፣ ጌታዬ!' አሊያም 'ወዮ፣ ግርማዊነትዎ!' እያሉ አያለቅሱለትም። 19በአህያ ቀብር ይቀበራል፣ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል።20ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ። በባሳን ድምፅሽን አንሺ። ውሽሞችሽ ሁሉ ይጠፋሉና ከበዓባሪም ተራሮች ሆነሽ ጩኺ። 21በደኅንነትሽ ጊዜ ተናገርሁሽ፣ አንቺ ግን 'አልሰማም' አልሽ። ከወጣትነትሽ ጀምሮ ቃሌን አለመስማትሽ ልማድሽ ነው።22በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፣ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ። በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትዋረጂማለሽ። 23አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፣ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ፣ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታጓሪያለሽ።"24"እኔ ሕያው ነኝና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ ማኅተም ቢሆን ኖሮ እንኳ፣ ከዚያ እነቅልህ ነበር፤ ይላል እግዚአብሔር። 25ነፍስህንም ለሚሹት ለምትፈራቸውም እጅ፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ለከለዳውያንም እጅ እሰጥሃለሁ። 26አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፣ በዚያም ትሞታላችሁ።27ይመለሱባትም ዘንድ ወደሚመኟት ወደዚያች ምድር ተመልሰው አይመጡም። 28በውኑ ይህ ሰው ኢዮአቄም የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ለአንዳች የማይረባ የሸክላ ዕቃ ነውን? እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለ ምን ተጥለው ወደቁ?29ምድር ሆይ፣ ምድር ሆይ፣ ምድር ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ! 30እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና። መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።"
1"የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።" 2ስለዚህ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፣ "በጎቼን በትናችኋል ደግሞም አባርራችኋቸዋል። በጭራሽ አልተንከባከባችኋቸውም። ይህንን እወቊ! ለሥራችሁ ክፋት መልሼ እከፍላችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር3እኔ ራሴ የመንጋዬን ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ እሰበስባለሁ፣ ፍሬያማ ወደሚሆኑበትና ወደሚበዙበት ወደ መሠማሪያቸው እመልሳቸዋለሁ። 4ከዚያም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይፈሩና እንዳይደነግጡ የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ። ከእነርሱ አንዳቸውም አይጐድሉም፣ ይላል እግዚአብሔር።5ተመልከቱ፣ ለዳዊት ጻድቅ ቅርንጫፍን የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር። እርሱም እንደ ንጉሥ ይገዛል፤ ብልፅግናን ያመጣል፣ በምድሪቱም ላይ ፍትህንና ጽድቅን ይፈጽማል። 6በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፣ እስራኤልም በአስተማማኝ ደህንነት ይቀመጣል። የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው ተብሎ ነው።7ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ከእንግዲህ 'የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!' የማይባልበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር። 8ይልቊን፣ 'የእስራኤልን ቤት የዘር-ሐረግ ከሰሜን ምድርና ከተሰደዱባቸው ምድሮች ሁሉ ያወጣና የመራ ሕያው እግዚአብሔርን!' ይባላል፤ እነርሱም በገዛ ራሳቸው ምድር ይቀመጣሉ።"9ስለ ነቢያት፣ ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል፣ አጥንቶቼም ሁሉ ታውከዋል። ከእግዚአብሔር እና ከቅዱስ ቃሉም የተነሣ እንደ ሰካራም ሰው፣ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈውም ሆኛለሁ። 10ምድር በአመንዝሮች ተሞልታለችና። ከዚህ መርገም የተነሣ ምድር አለቀሰች። የምድረ በዳ ማሰማርያዎች ደርቀዋል። የእነዚህ ነብያት አካሄድ ክፉ ነው፤ ኃይላቸውም በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ አልዋለም።11"ነብያትና ካህናትም ረክሰዋል። እንደውም፣ በቤቴ ውስጥ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ! ይላል እግዚአብሔር። 12ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች ድጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች። እነርሱም ይገፈተሩበታል። በውስጧም ይወድቁባታል። እኔም በምቀጣቸው ዓመት ክፉ ነገርን እልክባቸዋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።13በሰማርያ ነቢያት ላይ የሚያስቀይም ነገርን አይቻለሁ። በበኣል ትንቢት ይናገራሉ፣ ደግሞም ሕዝቤንም እስራኤልን ያስታሉ። 14በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥ ነገሮችን አይቻለሁ፦ ያመነዝራሉ ደግሞም በሐሰት ይመላለሳሉ። የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ማንም ከክፋቱ አልተመለሰም። ሁሉም እንደ ሰዶም ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ!" 15ስለዚህ ነብያትን በተመለከተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኵሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና እሬትን አበላቸዋለሁ የተመረዘንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።"16የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ። ሐሰተኝነትን ያስተምሩአችኋል! ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ አሳባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ። 17ያለማቋረጥ ለሚንቁኝ እንዲህ ይላሉ፣ 'እግዚአብሔር ሰላም ይሆንላችኋል ብሎአል።' በገዛ ራሱ የልብ እልከኝነት ለሚሄድ ሁሉ፣ 'ክፉ ነገር አያገኛችሁም።' ይላሉ። 18ይሁን እንጂ ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነው? ለቃሉ አትኩሮት ሰጥቶ የሰማ ያደመጠስ ማን ነው?19ተመልከቱ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እየመጣ ያለ ዐውሎ ነፋስ አለ! የእርሱም ቍጣና የሚገለባብጥ ዐውሎ ነፍስ ወጥቶአል። በዓመፀኞች ራስ ላይ ይገለባበጣል። 20የእግዚአብሔር ቍጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም። በመጨረሻው ዘመን፣ ትገነዘቡታላችሁ።21እነዚህን ነብያት እኔ አልላክኋቸውም። በድንገት ተገኙ። ምንም አልነገርኳቸውም፣ ነገር ግን እንደዚያም ሆኖ ትንቢትን ተናገሩ። 22በምክሬ ግን ቆመው ቢሆን ኖሮ፣ ለሕዝቤ ቃሌን ባሰሙ ነበር፤ ከክፉም ቃሎቻቸው እንዲሁም ከብልሹ ሥራቸው በመለሱአቸው ነበር።23እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝ ደግሞም የራቀ አምላክ አይደለሁም? ይላል እግዚአብሔር። 24ሰው ላየው እንዳልችል በስውር ሊሸሸግ ይችላልን? ሰማይንና ምድርንስ አልሞላምን? ይላል እግዚአብሔር።25በስሜ ሐሰትን የሚናገሩት የነብያት ያሉትን ነገር ሰምቻለሁ። እነርሱም 'ህልም አልሜ ነበር! ህልም አልሜ ነበር!' ብለዋል። 26ሐሰትን ከአሳባቸው በሚተነብዩ፣ የልባቸውንም ማታለል በሚተነብዩ ነቢያት ይህ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው? 27በሚናገሯቸው ሕልሞች ሕዝቤ ስሜን እንዲረሳ ለማድረግ ያቅዳሉ፣ እያንዳንዱ ለጎረቤቱ ልክ አባቶቻቸው ለበኣል ሲሉ ስሜን እንደ ረሱ ያደርጋሉ።28የሚያልም ነቢይ ሕልሙን ይናገር። ነገር ግን ቃሌን የነገርኩት፣ ቃሌን በእውነተኝነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግዚአብሔር። 29ቃሌ እንደ እሳት፣ ድንጋዩም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር። 30ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ እኔ ቃልን ከሌላኛው ሰው ሰርቆ ቃሉ ከእኔ ዘንድ መጥቷል በሚሉት ነብያት ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር።31ተመልከቱ፣ ትንቢትን ለማወጅ ምላሳቸውን በሚጠቀሙት ነብያት ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር። 32ተመልከቱ፣ በሐሰት በሚያልሙ፣ ከዚያም በሚናገሩትና በዚህም መልኩ በሐሰታቸውና በትምክህታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር። እኔም አልላክኋቸውምና ትእዛዛትንም አልሰጠኋቸውምና በእነርሱ ላይ ነኝ። ስለዚህም ለዚህ ሕዝብ በእርግጥም አይጠቅሟቸውም ይላል እግዚአብሔር።33ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፣ 'የእግዚአብሔር ዐዋጅ ምንድር ነው?' ብለው ቢጠይቊህ፣ 'እናንተን ትቻችኋለሁና የምን ዐዋጅ ነው?' ይላል እግዚአብሔር ልትላቸው ይገባል። 34'የእግዚአብሔር ዐዋጅ ይህ ነው፣' የሚሉትን ነብያትን፣ ካህናትን እና ሕዝቡን በተመለከተ፣ ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ።35እያንዳንዱ ሰው ለጎረቤቱ፣ እንዲሁም እያንዳንዱ ሰው ለወንድሙ፣ 'እግዚአብሔር የመለሰው ምንድር ነው?' ደግሞስ 'እግዚአብሔር ምን ዐወጀ?' ማለትህን ቀጥል። 36ከእያንዳንዱ ሰው የሆነው እያንዳንዱ ዐዋጅ የገዛ ራሱ መልእክት ይሆንበታልና፣ እንዲሁም የሕያው እግዚአብሔርን ቃል ለውጣችኋልና፣ ስለ እግዚአብሔር ዐዋጅ ከእንግዲህ ልትናገሩ አይገባችሁም።37ለነቢዩ የምትጠይቀው ይህንን ነው፣ 'እግዚአብሔር ምን መለሰልህ? እግዚአብሔር ምን ዐወጀ?' 38ከዚያም፣ ከእግዚአብሔር የሆነውን ዐዋጅ ትናገራለህ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን ይላል፣ "ይህ የእግዚአብሔር ዐዋጅ ነው አትበሉ።" ብዬ ትእዛዝን የላክሁባችሁ ቢሆንም፣ እናንተ ግን "የእግዚአብሔር ዐዋጅ ይኸውላችሁ፣" አላችሁ። 39ስለዚህም፣ ተመልከቱ፣ አንሥቻችሁ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ከሰጠሁት ከተማ ጋር ከእኔ ዘንድ ልወረውራችሁ ነው። 40ከዚያም የማይረሳ ዘላለማዊ እፍረትን እና ስድብን አኖርባችኋለሁ።"
1እግዚአብሔር አንድ ነገር አሳየኝ። እነሆ፣ በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር። (ይህ ራእይ የታየው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ የይሁዳንም አለቆች፣ ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ ነበር።) 2በአንደኛው ቅርጫት አስቀድሞ እንደበሰለ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፤ ነገር ግን በሁለተኛው ቅርጫት ውስጥ ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበረበት። 3እግዚአብሔርም፣ "ኤርምያስ ሆይ፣ ምንታያለህ?" አለኝ። እኔም፣ "በለስን። እጅግ መልካም የሆነ በለስ፣ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ በለስ አያለሁ።" አልሁ።4የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ 5"የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፣ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለጥቅማቸው እመለከተዋለሁ። 6ዓይኔንም ለመልካም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፣ ወደዚህችም ምድር እመልሳቸዋለሁ። እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም። እተክላቸዋለሁ፣ እንጂ አልነቅላቸውም። 7ከዚያም፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ እንዲመለሱ፣ ሕዝብ ይሆኑኛል፣ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።8ነገር ግን ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉው በለስ፣ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን አለቆቹንም በዚህችም አገር የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቅሬታ በግብጽም አገር የሚቀመጡትን እጥላቸዋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። 9በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፣ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። 10ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ከሰጠኋቸው ምድር እስኪጠፉ ድረስ በመካከላቸው ሰይፍንና ራብን፣ ቸነፈርንም እሰድዳለሁ።"
1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፣ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። 2ይህንም ቃል ነቢዩ ኤርምያስ ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ።3"ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ አሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ ሲመጣ ነበር። እነግራችሁም ነበር። እነግራችሁ ነበር፣ ነገር ግን አልሰማችሁም። 4እግዚአብሔርም ባርያዎቹን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላከ። እነርሱም ለመውጣት ጉጉዎች ነበሩ፣ ነገር ግን እናንተ አላደመጣችሁም ትኩረትም አልሰጣችሁትም።5እነዚህ ነብያት፣ 'እያንዳንዱ ሰው ከክፉ መንገዱና ከሥራችሁ ብልሹነት ተመለሱና እግዚአብሔር ከጥንት ጊዜያት ጀምሮ ቋሚ ስጦታ አድርጎ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ተቀመጡ። 6ታመልኩአቸው፣ ትሰግዱላቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፣ ክፉም እንዳያደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ አለ።7ለእናንተ ጕዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ ታስቈጡኝ ዘንድ አልሰማችሁኝም፣ ይላል እግዚአብሔር። 8ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ቃሌን አልሰማችሁምና፣ 9ተመልከቱ፣ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባርያዬ ከሆነው ከባቢሎን ንጉሥ ናብከደነዖር ጋር ለመሰብሰብ ትእዛዝን እልካለሁ፤ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፣ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ። ለማጥፋትም እለያቸዋለሁ። ለመጨነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።10ከእነርሱም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ፣ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አጠፋለሁ። 11ከዚያም ይህች ምድር ሁሉ ባድማና መደነቂያ ትሆናለች፣ ከዚያም እነዚህ አሕዛብ ለባቢሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገዛሉ።12ሰባው ዓመትም የሚፈጸምበት ጊዜ ይመጣል፣ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ፣ የከለዳውያንን ምድር ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፣ የማያበቃ ባድማ አደርጋታለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። 13በዚያችም ምድር ላይ የተናገርሁትን ቃሌን ሁሉ፣ እንዲሁም፣ ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ የተነበየውን በዚህች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ በዚያች ምድር አመጣለሁ። 14ብዙ ሌሎች አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ከእነዚህ ሕዝቦች ውስጥ ባርያዎችን ያደርጋሉ። እኔም ስለ አደራረጋቸውና ስለ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።"15የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፣ አንተን ለምሰድድባቸው አሕዛብ ሁሉ አጠጣቸው። 16ከምሰድድባቸውም ሰይፍ የተነሣ ይጠጣሉ፣ ይሰናከላሉ፣ በእብደት ይለፈልፋሉ።17ስለዚህ ጸዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ወሰድሁ፣ ከዚያም እግዚአብሔርም እኔን ለላከባቸው አሕዛብ ሁሉ አጠጣኋቸው። 18በዚህ ዛሬ እንደሆኑት ሁሉ ባድማና መደነቂያ፣ ማፍዋጫም፣ እርግማንም አደርጋቸው ዘንድ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣ ነገሥታትዋንም፣ አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።19ሌሎች ሕዝቦችም እንዲሁ ሊጠጡት ይገባል፦ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንና ባርያዎቹ፤ አለቆቹና ሕዝቦቹ ሁሉ፤ 20የተደባለቀ ቅርስ ሕዝቦች ሁሉ፣ የዖፅ ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፣ አስቀሎና፣ ጋዛ፣ አቃሮን የአዞጦን ቅሬታ ሁሉ፤ 21ኤዶምያስ፣ ሞዓብ፣ እና የአሞንም ሕዝቦች፤22የጢሮስና ሲዶና ነገሥታ፣ በባህሩ ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትም፣ 23ድዳን፣ ቴማን፣ ቡዝን፣ በራሳቸው ጎንና ጎን ጠጕራቸውን የሚቈርጡትን ሁሉ።24እነዚህም ሕዝቦች እንዲሁ ሊጠጡት ይገባል፦ የዓረብ ነገሥታት ሁሉ፣ በምድረ በዳ የሚኖሩት የድብልቅ ቅርስ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣ 25የዘምሪ ነገሥታት ሁሉ፣ የኤላም ነገሥታት ሁሉ፣ የሜዶን ነገሥታት ሁሉ፤ 26የቀረቡና የራቁ፣ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፣ በምድር ገጽ ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታት ሁሉ አጠጣኋቸው። በመጨረሻም፣ የባቢሎን ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።27"'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምሰድደው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፣ ስከሩ፣ አስታውኩ፣ ውደቁ፣ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡ' በላቸው፤ አለኝ። 28እንዲጠጡ ጽዋውን ከእጅህ ለመቀበል እንቢ ቢሉ፣ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእርግጥ ትጠጡታላችሁ፤ በላቸው። 29ተመልከቱ፣ ስሜ በተጠራባት ከተማ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፣ እናንተ ራሳችሁ ያልተቀጣችሁ ትሆናላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ከቅጣት ነፃ አትሆኑም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።'30ስለዚህ፣ አንተ ራስህ፣ ኤርምያስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ትተነብይባቸዋለህ፣ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ 'እግዚአብሔር ከበላይ ሆኖ ይጮኻል፣ ከቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል። በማደሪያው ላይ እጅግ ይጮኻል፣ ወይንን ሲሚጠምቁ እንደሚዘምሩት በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል። 31እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል። ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር በፍትህ ይፋረዳል። ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።'32የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ጥፋት ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፣ ደግሞም ጽኑም ዐውሎ ነፍስ ከሩቅ የምድር ዳርቻ ይነሣል። 33ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ግዳዩች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበዛሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይሰበሰቡም፣ ወይም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።34እረኞች አልቅሱ፣ ለእርዳታም ጩኹ! በመንጋው ውስጥ አውራ የሆናችሁት ሕዝቦች በመሬት ላይ ተንከባለሉ። ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ መጥቷልና። እንደ ተመረጡ በጎች ትወድቃላችሁ። 35ወደእረኞች ለመሸሸግ ማምለጥ ይቀራል። 36እግዚአብሔር ማሰማርያቸውን አጥፍቶአልና የእረኞች ጩኸት ድምፅ፣ የመንጋ አውራዎችም ልቅሶ ሆኖአል።37ከእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ የተነሣ የሰላም ማሰማሪያ ይፈርሳል። 38እንደ ታዳጊ አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፣ ከአስጨናቂውም ሰይፍና ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ምድራቸው አስፈሪ ሆናለችና።"
1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ መጣና እንዲህ አለ፣ 2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በቤቴ አደባባይ ቁም፣ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ንገራቸው። እንድትነግራቸው ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ንገራቸው። አንዲትም ቃል አትጉደል! 3ምናልባት ይሰሙ፣ ከክፉ መንገዳቸውም ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ስለ ሥራቸው ክፋት ያሰብሁባቸውን ክፉ ነገር እተዋለሁ።4ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ትሄዱ ዘንድ ባትሰሙኝ፣ 5በጽናት ወደ እናንተ የላክኋቸውን የባሪያዎቼን የነቢያትን ቃል ባትሰሙ፣ ነገር ግን አላደመጣችኋቸውም! 6ያኔ ይህንን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፤ ይህችንም ከተማ ለምድር አሕዛብ ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።"7ኤርምያስ በእግዚአብሔር ቤት ይህንን ቃል ሲናገር ካህናቱ፣ ነቢያቱ፣ ሕዝቡም ሁሉ ሰሙ። 8ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘውን ነገር ሁሉ በፈጸመ ጊዜ፣ ካህናት፣ ነቢያትና ሕዝቡም ሁሉ፣ ያዙትና "በእርግጥ ትሞታለህ! 9በእግዚአብሔር ስም ተንብየህ ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆናል፣ ይህችም ከተማ ነዋሪ የማይገኝባት ወና ትሆናለች ብለህ ለምን ትንቢት ተናገርህ?" አሉት። ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በኤርምያስ ላይ በዐመጽ ተሰብስበው ነበር።10ከዚያም የይሁዳ አለቆች ይህን ሰሙና ከንጉሥ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄዱ። በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ። 11ካህናቱና ነብያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ ተናገሩ። እንዲህም አሉ፣ "በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው!" አሉ። 12ስለዚህ ኤርምያስ ለአለቆችና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ "በሰማችሁት ቃል ሁሉ፣ በዚህች ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እናገር ዘንድ እግዚአብሔር ልኮኛል።13አሁንም መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ፣ እግዚአብሔርም የተናገረባችሁን ጥፋት እንዲተው፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ ስሙ። 14ተመልከቱኝ! እኔ ራሴ በእጃችሁ ነኝ። በዐይናችሁ ፊት መልካምና ቅን የመሰላችሁን አድርጉብኝ። 15ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነት እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚህች ከተማ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በእርግጥ እወቁ።"16አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፣ "ይህ ሰው በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ተናግሮናልና ሊሞት አይገባውም" አሉ። 17ከዚያም ከምድሪቱ ሽማግሌዎች ሰዎች ተነሥተው ለመላው የሕዝቡ ጉባኤ ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ።18እነርሱም፣ "ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ይተነብይ ነበረ። ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ ተንብዮ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፣ የቤተመቅደሱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል' ብሎ ተናገረ። 19በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ እግዚአብሔርን አልፈራምን? ወደ እግዚአብሔርስ አልተማለሉምን? እግዚአብሔርስ የተናገረባቸውን ክፉ ነገር አይተውምን? እኛም በገዛ ሕይወታችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለንን?"20ደግሞም በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፣ እርሱም የቂርያትይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፤ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ ከኤርምያስ ቃል ጋር የተስማማ ትንቢት ተናገረ። 21ነገር ግን ንጉሡ ኢዮአቄም እና ወታደሮቹ ሁሉ እንዲሁም አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ሞከረ፤ ነገር ግን ኦርዮም ይህን ሲሰማ ፈርቶ ሸሸ ወደ ግብጽም ገባ።22ንጉሡም ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንን ከእርሱም ጋር ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፤ 23ኦርዮንን ከግብጽ አውጥተው ወደ ንጉሡ ኢዮአቄም ይዘውት መጡ። ከዚያም ኢዮአቄም በሰይፍ ገደለውና ሬሳውን ተራ በሆኑ ሰዎች መቃብር ውስጥ ጣለው። 24ነገር ግን በሕዝቡ እጅ እንዳይሰጥና እንዳይገድሉት የሳፋን ልጅ የአኪቃም እጅ ከኤርምያስ ጋር ነበረች።
1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ። 2እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "እስራትና ቀንበር ለራስህ ሥራ። በአንገትህም ላይ አድርግ። 3ከዚያም ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ፣ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፣ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፣ ወደ አሞንም ልጆች ንጉሥ፣ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፣ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ላካቸው። 4ለጌቶቻቸውም እንዲነግሩ እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ 'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለጌቶቻችሁ ልትነግሯቸው የሚገባው ይህንን ነው፣5እኔ ራሴ ምድሪቱን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ ፈጥሬአለሁ። በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን ጭምር ፈጥሬያለሁ። በዐይኔም ዘንድ ትክክል ለሆነው ለማንኛውም ሰው እሰጣታለሁ። 6አሁንም፣ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለባርያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣታለሁ። እንዲሁም ያገለግሉት ዘንድ በሜዳዎች ያሉትን ሕያዋን ነገሮችን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ። 7የገዛ ራሱም ምድር ፍጻሜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጅ ልጅ ልጁም ይገዛሉ። ከዚያም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን ያስገዙታል።8ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማያገለግለውን፣ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፣ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፣ በመቅሰፍትም እቀጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።9እናንተ ደግሞ! 'ለባቢሎን ንጉሥ አታገልግሉ' የሚሉአችሁን ነቢያቶቻችሁን፣ ሟርተኞቻችሁን፣ ሕልም አላሚዎቻችሁንና ቃላተኞቻችሁን፣ መተተኞቻችሁንም መስማት አቊሙ። 10ከምድራቸሁ አርቀው ሊልኳችሁ፣ እኔም እንዳሳድዳችሁ፣ እናንተም እንድትሞቱ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና። 11ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚያገለግለውን ሕዝብ በአገሩ ላይ እተዋቸዋለሁ፤ እነርሱም ያርሱአታል ቤቶችንም ይሠሩባታል።"12ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም በዚህ ቃል ተናገርሁ ይህንንም መልእክት ሰጠሁት፣ "ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉና ለእርሱና ለሕዝቡ አገልግሉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ። 13ለባቢሎን ንጉሥ ይገዛ ዘንድ እንቢ ስላለ ሕዝብ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፣ አንተና ሕዝብህ በሰይፍና በራብ በመቅሰፍትም ለምን ትሞታላችሁ?14ሐሰተኛን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፣ 'ለባቢሎን ንጉሥ አታገልግሉ' የሚሉአችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ። 15'እኔ አልላክኋቸውምና፤ ነገር ግን እኔ እንዳሳድዳችሁ፣ እናንተና ትንቢት የሚናገሩላችሁ ነቢያትም እንድትጠፉ በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገራሉ፣' ይላል እግዚአብሔር።"16ይህንን ለካህናትና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተንብየውላችሁ 'ተመልከቱ! የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ አሁን ከባቢሎን ይመለሳል!' የሚሉአችሁን የነቢያቶቻችሁን ቃል አትስሙ። እነርሱ ውሸትን ይተነብዩላችኋል። 17እነርሱንም አትስሟቸው። የባቢሎንን ንጉሥ ልታገለግሉና በሕይወት ልትኖሩ ይገባችኋል። ይህችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆናለች? 18እነርሱ ግን ነቢያት ከሆኑ፣ የእግዚአብሔርም ቃል በእውነት ወደእነርሱ ቢመጣ፣ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀረችው ዕቃ ወደ ባቢሎን እንዳትሄድ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር ይለምኑ።19የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ከበርቴዎች ሁሉ ማርኮ 20ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ ስላልወሰዳቸው ዓምዶች ስለ ኵሬውም፣ ስለ መቀመጫዎቹም በዚህችም ከተማ ስለ ቀረች ዕቃ ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።21በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀረችው ዕቃ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 22'እነርሱ ወደ ባቢሎን ትወሰዳለች እስከምጐበኛትም ቀን ድረስ በዚያ ትኖራለች፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ከዚያም አወጣታለሁ ወደዚህም ስፍራ እመልሳታለሁ።"
1በዚያም ዓመት በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ነቢዩ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ። 2"የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ይናገራል፣ የባቢሎን ንጉሥ ያኖረውን ቀንበር ሰብሬአለሁ።3የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከዚህች ስፍራ ወደ ባቢሎን ያጋዛትን የእግዚአብሔርን ቤት የሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደዚህች ስፍራ እመልሳታለሁ። 4ከዚያም ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚህች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።"5ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱና በእግዚአብሔር ቤት በቆሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለነቢዩ ሐናንያ ተናገረ። 6ነብዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግ! የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ምርኮውንም ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ እግዚአብሔር የተናገረውን ትንቢት ይፈጽም። 7ይሁን እንጂ፣ በጆሮህና በሕዝብህ ጆሮ ሁሉ የምናገረውን ይህን ቃል ስማ።8ከጥንት ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩ ነብያት በብዙ አገርና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ሰልፍና ስለ ክፉ ነገር፣ ስለ መቅሰፍትም ትንቢት ተናገሩ። 9ስለዚህም ሰላም እንደሚኖር የተናገረ ነቢይ፣ የነቢዩ ቃል በተፈጸመ ጊዜ፣ ያኔ እግዚአብሔር በእውነት የሰደደው ነቢይ እንደ ሆነ ይታወቃል።"10ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ወስዶ ሰበረው። 11ከዚያም ሐናንያ በሕዝብ ሁሉ ፊት፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልክ እንደዚሁ፣ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከአሕዛብ ሁሉ አንገት እሰብራለሁ" አለ። ከዚያም ነብዩ ኤርምያስ መንገዱን ሄደ።12ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ከሰበረ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣ 13"ሂድና ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ የእንጨት ቀንበርን ሰብረሃል፣ እኔ ግን በእርሱ ፋንታ የብረትን ቀንበር እሠራለሁ።' 14የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እንዲያገለግሉ የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ። እነርሱም ያገለግሉታል። እንዲገዛቸውም የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።"15ቀጥሎ፣ ነብዩ ኤርምያስ ነብዩን ሐናንያን፣ "ሐናንያ ሆይ፣ አድምጥ! ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ እግዚአብሔር አልላከህም። 16ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት ከምድር ላይ እሰድድሃለሁ። በእግዚአብሔር ላይ ዐመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ።" አለው። 17ነብዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።
1ነቢዩ ኤርምያስ ከምርኮ ሽማግሌዎች መካከል ወደ ተረፉት፣ ወደ ካህናቱም፣ ወደ ነቢያቱም፣ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃል ይህ ነው። 2ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን፣ እቴጌይቱ እናቱ፣ ከፍተኛ መኮንኖቹ፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም አለቆች፣ ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው። 3ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን እንዲህ ሲል ላከው።4ጥቅሉ እንዲህ ይላል፣ "የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ላስማረክኋቸው ምርኮኞች ሁሉ እንዲህ ይላል፣ 5'ቤት ሠርታችሁ ኑሩባቸው፣ አታክልትም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ፤6ሚስቶችን ውሰዱ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ከዚያም ለወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችን ውሰዱ፣ ሴቶች ልጆቻችሁንም ለባሎቻቸው ስጡ። እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ። 7በእርስዋም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፣ ከእኔ ዘንድ ማልዱ።'8የእስራኤልም አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'በመካከላችሁ ያሉት ነቢያቶቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፣ እናንተም ራሳችሁ የምታልሙትን ሕልም አትስሙ። 9በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና። እኔም አልላክኋቸውም። ይላል እግዚአብሔር።'10እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ባቢሎን ለሰባ ዓመታት በገዛቻችሁ ጊዜ፣ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ እረዳችኋለሁ፣ ደግሞም መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ። 11ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ ራሴ አውቃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የጥፋት አይደለም።12እናንተም ወደ እኔ ትጠራላችሁ፣ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፣ እኔም እሰማችኋለሁ። 13እናንተ ትሹኛላችሁ፣ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። 14ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፤ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ከበተንሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።'15እናንተም፣ እግዚአብሔር በባቢሎን ነቢያትን አስነሥቶልናል ብላችኋልና፣ 16እግዚአብሔር በዳዊት ዙፋን ስለ ተቀመጠ ንጉሥ፣ በዚያች ከተማ ለቆዩት ሕዝቦች ሁሉ፣ ከእናንተም ጋር ስላልተማረኩት ወንድሞቻችሁ፣ እንዲህ ይላል። 17የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ሰይፍንና ራብን፣ በሽታንም እሰድድባቸዋለሁ። ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉ በለስ አደርጋቸዋለሁ።18በሰይፍም፣ በራብም፣ በመቅሠፍትም አሳዳድዳቸዋለሁ፣ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለመጠላት፣ ለመደነቂያ፣ ለማፍዋጫም፣ ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። 19ይህም የሆነው ቃሌን ስላልሰሙ ነው፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ ሰድጃለሁና፤ በተደጋጋሚ ላክኋቸው፣ እናንተ ግን አልሰማችሁም፣ ይላል እግዚአብሔር።'20ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኋችሁ ምርኮኞች ሁሉ ሆይ፣ እናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ 21'የእስራኤል አምላክ፣ እኔ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ስለሚናገሩላችሁ ስለ ቆላያ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ መዕሤያ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ እላለሁ፦ ተመልከቱ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። በዓይኖቻችሁም ፊት ይገድላቸዋል።22ከዚያም በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ ስለ እነዚህ ሰዎች እርግማንን ይናገራሉ። እርግማኑም፦ እግዚአብሔር የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ ያድርግህ የሚል ነው። 23በእስራኤል ዘንድ ስንፍና አድርገዋልና፣ ከጎረቤቶቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፣ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና ይህ ይሆናል። እኔም አውቃለሁ ምስክርም ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር።"24"ለኔሔላማዊው ለሸማያ እንዲህ በል፦ 25'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፣ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፣ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በገዛ ስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፣ 26"እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በእግር ግንድና በሠንሰለት ታኖረው ዘንድ በእግዚአብሔር ቤት አለቃ እንድትሆን እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።27አሁንስ፣ ትንቢት ተናጋሪውን የዓናቶቱን ሰው ኤርምያስን ስለ ምን አትገሥጸውም? 28እርሱ፣ 'ጊዜው የረዘመ ነው። ቤት ገንቡና በውስጡ ኑሩበት፣ አትክልትንም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ' ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢሎን ልኮአል።" 29ካህኑም ሶፎንያስ ይህን ደብዳቤ ነብዩ ኤርምያስ እየሰማ አነበበው።30የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣ 31"'እግዚአብሔር ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ እንዲህ ይላል፣ ብለህ ወደ ምርኮኞች ሁሉ ላክ፦ 'እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችኋልና፣ በሐሰትም እንድትታመኑ አድርጎአችኋልና፤ 32ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ ኔሔላማዊውን ሸማያንና ዘሩን እቀጣለሁ። እኔም የማደርግላችሁን መልካሙን ነገር የሚያይ አንድም የእርሱ ሰው በመካከላችሁ አይኖርም። ለሕዝቤ የማደርገውን አንዱንም መልካም ነገር አያይም ይላል እግዚአብሔር። እርሱ በእኔ፣ በእግዚአብሔር ላይ በእምነት ያልሆነ ነገርን ተናግሯልና።"
1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣ 2"የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የነገርኩህን ቃል ሁሉ በጥቅልል ላይ ጻፈው። 3ተመልከት፣ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስባት ዘመን ይመጣልና፣ ይላል እግዚአብሔር። ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፣ እነርሱም ይገዙአታል።4እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣ 5"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የሚያስፈራ ድምፅ ሰምተናል፤ የፍርሃት ነው እንጂ የሰላም አይደለም።6ጠይቁ፣ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ። እያንዳንዱ ወጣት ሰው እጁን በወገቡ ላይ ያደረገው ለምንድነው? እንደ ወላድ ሴት፣ ፊታቸው ሁሉ ወደ ጥቁረት የተለወጠው ለምንድነው? 7ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ይሆናልና፣ እርሱንም የሚመስል የለምና። ያ የያዕቆብ የመከራ ዘመን ነው፣ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል።8በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፣ እስራትህንም እበጥሳለሁ፣ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ለሌላ አትገዛም። 9ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣ በእነርሱ ላይ ንጉሥ ለማደርግላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ያገለግላሉ።10ስለዚህ፣ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተም እስራኤል ሆይ፣ አትደንግጥ። ተመልከቱ፣ አንተን ከሩቅ፣ ዘርህንም ከምርኮ አገር አድናለሁና። ያዕቆብም ይመለሳል ሰላምም ይሆናል፤ ደህንነቱም ይጠበቃል፣ ከዚያም በኋላ ማንም አያስፈራውም። 11አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፣ ይላል እግዚአብሔር። አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብ ፍጹም ማብቂያቸው እንዲመጣ አደርጋለሁ። አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፣ በፍትህ እቀጣሃለሁ፣ ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም።'12እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስብራትህ የማይፈወስ፣ ቍስልህም ያመረቀዘ ነው። 13ጉዳይህን የሚሟገትልህ የለም፣ ቍስልህንም የሚፈውስ መድኃኒት የለህም።14አፍቃሪዎችሽ ሁሉ ረስተውሻል። አይፈልጉሽምም፣ በደልሽ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትሽም ስለ በዛ፣ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ አሠሪ ቅጣት አቍስዬሻለሁና። 15ሕመምሽ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትሽ ለምን ትጮያለሽ? በደልሽ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትሽም ስለ በዛ፣ ይህን አድርጌብሻለሁ።16ስለዚህ የሚበሉሽ ሁሉ ይበላሉ፣ ጠላቶችሽም ሁሉ ወደ ምርኮ ይወሰዳሉ። የዘረፉሽም ይዘረፋሉ፣ የበዘበዙሽንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ። 17እኔ ጤናሽን እመልስልሻለሁ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ይህንንም የማደርገው፦ ማንም የማይሻት፤ የተጣለች ጽዮን" ብለው ጠርተውሻልና።18እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ለቤቱም እራራለሁ። ከተማይቱም በፍርስራሽ ጉብታዋ ላይ ትሠራለች፣ ምሽጉም እንደ ዱሮው ይሆናል። 19ከዚያም ከእርሱ ዘንድ የምስጋናና የዘፋኞች ድምፅ ይወጣል፣ እኔም አበዛቸዋለሁ አላሳንሳቸውም፤ እንዳይዋረዱ እኔ አከብራቸዋለሁ።20ከዚያም ሕዝቦቻቸው እንደ ቀድሞ ይሆናሉ፣ ማኅበራቸውም በፊቴ ጸንቶ ይኖራል፤ የሚያስጨንቋቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ። 21መሪያቸው ከእነርሱ ውስጥ ይወጣል። እኔ ሳቀርበውና እርሱም ሲቀርበኝ ከመካከላቸው ይወጣል። ይህንን ባላደርግ፣ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር። 22እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።23ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፣ ቍጣው ወጥቷል። ሳይቋረጥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፋስ ወጥቶአል። የክፉዎችንም ራስ ይገለባብጣል። 24የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም። በመጨረሻው ዘመን ታስተውሉታላችሁ።"
1"በዚያን ዘመን፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።" 2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እስራኤልን ለማረድ ከመጣው ሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ።" 3እግዚአብሔር በኃላፊው ጊዜ ተገለጠልኝና እንዲህ አለኝ፣ "እስራኤል ሆይ፣ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ። ስለዚህ በኪዳን ታማኝነት ወደራሴ ሳብሁሽ።4የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ እንደ ገና እገነባሻለሁ አንቺም ትገነቢያለሽ። እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ወደ ደስታ ጭፈራሽ ትወጫለሽ። 5እንደ ገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ የወይን ቦታዎችን ትተክያለሽ፤ ገበሬዎች ይተክላሉ፣ ፍሬውንም በመልካም ይጠቀሙበታል። 6በኤፍሬምም ተራሮች ላይ ያሉ ተመልካቾች፣ 'ተነሡ፣ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ.' ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና።"7እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "ስለ ያዕቆብ በደስታ ጩኹ! ስለ አሕዛብም አለቆች በደስታ ጩኹ! ምስጋና ይሰማ። 'እግዚአብሔር ሕዝቡን፣ የእስራኤልን ቅሬታ አድኖአል' በሉ።8ተመልከቱ፣ ከሰሜን ምድር አመጣቸዋለሁ። ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ። በመካከላቸውም ዕውሩና አንካሳው፣ ያረገዙ ሴቶችና ሊወልዱ ያሉ ሴቶች በአንድነት ይሆናሉ። ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ። 9በልቅሶ መጡ፤ ልመናቸውን ሲያደርጉ እመራቸዋልሁ። በወንዝ ዳር በቀጥተኛ መንገድ አስኬዳቸዋለሁ። በእርሱም አይሰናከሉም፣ እኔ ለእስራኤል አባት እሆናለሁና፣ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።"10"አሕዛብ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩ። እናንተ አህዛብ፣ "እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስባታል፣ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቃታል" በሉ። 11እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶታል፣ ከበረታበትም እጅ አድኖታል።12ከዚያም ይመጡና በጽዮን ተራራ ይፈነድቃሉ። ወደ እግዚአብሔርም መልካምነት፣ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ፣ ወደ ዘይትም፣ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ይሰበሰባሉ። ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፣ ከእንግዲህም ወዲህ ኃዘን አይሰማቸውም።13በዚያን ጊዜ ደናግሉ በዘፈን ደስ ይላቸዋል፣ ወጣቶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ይሆናሉ። ለቅሷቸውን ወደ ክብረ-በዓል እለውጣለሁና። እራራላቸዋለሁ፣ ከኅዘናቸውም ይልቅ እንዲፈነድቁ አደርጋቸዋለሁ። 14ከዚያም የካህናቱን ነፍስ በብዛት አረካታለሁ። ሕዝቤም መልካምነቴን ይጠግባል ይላል እግዚአብሔር።"15እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ። ስለ ልጆችዋ የምታለቅሰው ራሔል ናት። ከእንግዲህ አይኖሩምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።"16እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ድምፅሽን ከለቅሶ፣ ዐይንሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ምክንያቱም ለመከራሽ ካሳ አለ፤ ልጆችሽ ከጠላት ምድር ይመለሳሉ። 17ለፍጻሜሽ ተስፋ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ልጆችሽም ወደ ዳርቻቸው ይመለሳሉ።"18"ኤፍሬም፣ 'ቀጣኸኝ፣ እኔም ተቀጣሁ። እንዳልተገራ ወይፈን መልሰህ አምጣኝ፣ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና እኔም እመለሳለሁ። 19ወደ አንተ ከተመለስሁ በኋላ፣ ተጸጸትሁ፤ ከሠለጠንሁም በኋላ፣ በኃዘን ጭኔን መታሁ፤ በወጣትነቴ በደልን ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፣ ተዋረድሁ።' 20ኤፍሬም ለእኔ የከበረ ልጅ አይደለምን? ወይስ የምደሰትበት ሕጻን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር፣ እንደዚያም ሆኖ በፍቅር አስበዋለሁ። በዚህ መልኩ ልቤ ትናፍቀዋለች። በእርግጥም እራራለታለሁ ይላል እግዚአብሔር።"21ለራስሽ የመንገድ ምልክት አድርጊ። ለራስሽም መንገድን የሚመሩ ዓምዶችን ትከዪ። አሳብሽንም ልትሄጂበት ወደሚገባው ትክክለኛ መንገድ አድርጊ። የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ ተመለሺ! ወደ እነዚህም ወደ ከተሞችሽ ተመለሺ። 22አንቺ እምነት የለሽ ልጅ ሆይ፣ እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና፤ ብርቱ ወንዶችን ለመጠበቅ ሴቶች ይከብባሉ።23የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሕዝቡን ወደ ምድራቸው ባመጣኋቸው ጊዜ፣ በይሁዳ ምድርና በከተሞችዋ እንዲህ ይላሉ፣ 'እርሱ የሚኖርብሽ የጽድቅ ማደሪያ፣ የቅድስና ተራራ ሆይ፣ እግዚአብሔር ይባርክሽ።' 24ይሁዳና ከተሞቹ ሁሉ በአንድነት በእርስዋ ይኖራሉ። ገበሬዎችና እረኞች ከመንጎቻቸው ጋር በዚያ ይገኛሉ። 25ለደከሙት የሚጠጡትን ውሃ እሰጣለሁና፣ በጥማት የሚሰቃዩትን ሁሉ በእርካታ እሞላለሁ። 26ከዚህም በኋላ ነቃሁ፣ እንቅልፌ የሚያነቃ እንደሆነ አስተዋልኩኝ።27"ተመልከቱ፣ የእስራኤልን ቤትና የይሁዳን ቤት በሰውና በእንስሳ ዘር የምዘራበት ዘመን፣ እንደሚመጣ ተመልከቱ ይላል እግዚአብሔር። 28እንዲህም ይሆናል፣ አፈርሳቸውና፣ ክፉ አድርግባቸው ዘንድ እንደ ተጋሁባቸው፣ ነገር ግን በሚመጡት ዘመናት፣ እንዲሁ እሠራቸውና፣ እተክላቸው ዘንድ እተጋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።29በዚያ ዘመን ሰው ዳግመኛ እንዲህ አይልም፣ 'አባቶች መራራ የወይን ፍሬ በሉ፣ ነገር ግን የልጆች ጥርሶች ጠረሱ።' 30ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፤ መራራውን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ ይጠርሳሉ።31ተመልከቱ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር። 32ከግብጽ ምድር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም። ምንም እንኳን እኔ ባላቸው ብሆንም፣ እነርሱ ኪዳኔ ላይ ዐምጸዋልና፣ ይላል እግዚአብሔር።33ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ግን ይህ ነውና፣ ይላል እግዚአብሔር፦ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፣ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል። 34ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን፣ 'እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፣ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፣ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።"35እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ፀሐይን በቀን የጨረቃንና የከዋክብትን ሥርዓት በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። እንዲተምሙም የባሕርን ሞገዶች የሚያናውጥ እርሱ ነው። ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እንዲህ ይላል፣ 36"እነዚህ ቋሚ ነገሮች ከእይታዬ ቢወገዱ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ በዚያን ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እንዳይሆን ለዘላለም ይቀራል።"37እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ከፍ ያሉት ሰማያት ሊለኩ ቢችሉ፣ የምድርም መሠረት ከታች ቢመረመር፣ በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ዘር ሁሉ እጥላለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።"38"ተመልከቱ፣ ከሐናንኤል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ ከተማ ለእግዚአብሔር የሚሠራበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር። 39የተለካበትም ገመድ ወደ ጋሬብ ኮረብታ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዳል፣ ወደ ጎዓም ይዞራል። 40የሬሳም ሸለቆ ሁሉ የአመድም እርሻ ሁሉ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረሰ በር ማዕዘን ድረስ ለእኔ፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል። ከእንግዲህም ወዲህ ለዘላለም አይነቀልም አይፈርስምም።"
1በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዐሥረኛው ዓመት፣ በናቡክደነፆር በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። 2በዚያን ጊዜ፣ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩም ኤርምያስ በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር።3የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በእስር አቆይቶት እንዲህ አለው፣ "ለምን እንዲህ ብለህ ትንቢት ትናገራለህ፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፣ እርሱም ይይዛታል። 4የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፣ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፣ አፉ ለአፉ ይናገረዋል፣ ዐይኑም የንጉሡን ዐይን ያያል። 5ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ይሄዳል፣ እኔም እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይሆናል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ከከለዳውያን ጋር ብትዋጉ አይሳካላችሁም።"6ኤርምያስም እንዲህ አለ፣ "የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ 7'ተመልከቱ፣ የአጐትህ የሰሎም ልጅ አናምኤል ወደ አንተ መጥቶ፣ "ትገዛው ዘንድ መቤዠቱ የአንተ ነውና በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ ይልሃል።"8ከዚያም፣ እግዚአብሔር እንደተናገረው ቃል፣ የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ እንዲህ አለኝ፣ 'በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፣ እባክህ ግዛ፤ የርስት መብቱ የአንተ ነውና፣ የመቤዠቱ መብትም የአንተ ነውና ለአንተ ግዛው።' ያን ጊዜ ይህ የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ አወቅሁ። 9ስለዚህ፣ በዓናቶት ያለውን እርሻ ከአጐቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፣ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘንሁለት።10በውሉም ወረቀት ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፣ ምስክሮችም እንዲመሰክሩ አስደረግሁ። ከዚያም ብሩን በሚዛን መዘንሁለት። 11ቀጥሎ፣ የታተመውንና የተከፈተውን የግዢ ውል ወረቀት ወሰድሁ፤ 12የአጐቴም ልጅ አናምኤል፣ የውሉንም ወረቀት የፈረሙ ምስክሮች፣ በግዞትም ቤት አደባባይ የተቀመጡ አይሁድ ሁሉ እያዩ የውሉን ወረቀት ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።13በፊታቸውም እንዲህ ብዬ ባሮክን አዘዝሁት። 14'የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፡- የታተመውንና የተከፈተውን ይህን የውል ወረቀት ውሰድ። ብዙ ቀን እንደተጠበቊ እንዲቆዩ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው። 15የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህች ምድር ቤትን፣ እርሻን፣ የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።'16ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፣ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፣ 17'ወዮ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ተመልከቱ! አንተ ብቻህን ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል። ለአንተም እንደሚያቅትህ የተናገርከው ነገር የለም። 18ለብዙ ሺህ ምሕረት ታደርጋለህ፣ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ጭን ላይ ትመልሳለህ። ስምህ ታላቅና ኃያል አምላክ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።19በጥበብ ታላቅ በአደራረግም ብርቱ ነህ፣ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይኖችህ በሰዎች መንገድ ሁሉ ላይ ተገልጠዋል። 20እስከ ዛሬም ድረስ ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብጽ ምድር አድርገሃል። እስከዛሬ ድረስ፣ በዚህ በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች ሁሉ መካከል ስምህን አግንነሃል። 21በምልክትና በድንቅ ነገር፣ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ በታላቅም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብጽ ምድር አውጥተሃልና።22ከዚያም ትሰጣቸውም ዘንድ ለአባቶቻቸው የማልህላቸውን፣ ወተትና ማርን የምታፈስሰውን ምድር፣ ሰጠሃቸው። 23እነርሱም ገብተው ወረሱአት። ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም ለሕግህም በመታዘዝ አልሄዱም። ይደረግ ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፣ ስለዚህ ይህን ጥፋት ሁሉ አመጣህባቸው።24ተመልከቱ! የአፈር ድልድል ሊይዙአት እስከ ከተማይቱ ድረስ ቀርበዋል። ከሰይፍ፣ ከራብና፣ ከመቅሠፍት የተነሣ፣ ከተማይቱ ለሚዋጓት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች። እንደሚሆን የተናገርኸው ሆኖአልና፣ ደግሞም ተመልከቱ፣ አንተ ታየዋለህ። 25ከዚያም አንተ ራስህ፣ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ምንም እንኳን ይህች ከተማ ለከለዳውያን እጅ ተላልፋ የምትሰጥ ቢሆንም፣ እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ" አልኸኝ።26ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣ 27"ተመልከቱ! የሰው ዘር ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እፈጽመው ዘንድ የሚያቅተኝ ነገር አለን? 28ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ይህችን ከተማ ለከለዳውያን እጅና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እርሱም ይይዛታል።29ይህችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን መጥተው በእሳት ያነድዱአታል፣ ያስቈጡኝም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበኣል ካጠኑባቸው፣ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቊርባን ካፈሰሱባቸው ቤቶች ጋር ያቃጥሉአታል። 30የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች ከወጣትነታቸው ጀምሮ በዐይኔ ፊት ክፉ ነገርን ብቻ አድርገዋል። የእስራኤልም ልጆች እኔን በእጃቸው ሥራ ከማስቈጣት በቀር ሌላ ሥራ አላደረጉምና፣ ይላል እግዚአብሔር።31ከፊቴ አስወግዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከገነቧት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ቍጣዬንና መዓቴን ለማነሣሣት ሆናለችና። ስለዚህም ከፊቴ አስወግዳታለሁ። 32ምክንያቱም እኔን ያስቈጡኝ ዘንድ፣ እነርሱና ነገሥታቶቻቸው፣ አለቆቻቸውም፣ ካህናቶቻቸውም፣ ነቢያቶቻቸውም፣ የይሁዳም ሰዎች፣ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ፣ ስላደረጉት ስለ እስራኤል ልጆችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው።33ምንም እንኳን በጉጉት ያስተማርኳቸው ቢሆንም፣ ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ። ላስተምራቸው ሞከርኩ፣ ነገር ግን ተግሣጽን ይቀበሉ ዘንድ አንዳቸውም እንኳን አልሰሙም። 34ከዚያም፣ ያረክሱት ዘንድ፣ ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኩሰታቸውን አኖሩ። 35ቀጥሎም ይሁዳን ኃጢአት እንዲሠራ ለማድረግ፣ ይህንን ርኩሰት ያደርጉ ዘንድ፣ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ፣ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።36አሁን እንግዲህ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ አንተ ስለ እርስዋ፣ 'በሰይፍና በራብ በመቅሰፍትም ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ተሰጥታለች' ስለምትላት ከተማ እንዲህ ይላል። 37ተመልከቱ፣ በቍጣዬ፣ በመዓቴና በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ። ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፣ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ።38ከዚያም እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፣ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። 39ለእነርሱም፣ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘላለም እንዲፈሩኝ አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ። 40ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፣ ከእነርሱ ጋር የዘላለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ። መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ። ከዚህ የተነሣ እኔን ከመከተል አይመለሱም።41ከዚያም ለእነርሱ መልካምን በማድረግ ደስ ይለኛል። በታማኝነት በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ። 42እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እንዳመጣሁ፣ እንዲሁ እንደማደርግላቸው የተናገርሁላቸውን በጎነት ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።43ከዚያም፣ እናንተ፣ "ይህች ያለ ሰውና ያለ እንሰሳ ያለች ባድማ ምድር ናት። ለከለዳውያንም እጅ ተሰጥታለች።" በምትሉአት ምድር እርሻን ይገዛሉ። 44ምርኮኞቻቸውንም እመልሳለሁና፣ በብንያም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፣ በይሁዳም ከተሞች በደጋውም ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች፣ በደቡብም ባሉ ከተሞች፣ ሰዎች እርሻውን በብር ይገዛሉ በውሉም ወረቀት ፈርመው ያትማሉ ምስክሮችንም ይጠራሉ።"
1ኤርምያስ ገና በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛ ጊዜ መጣለትና እንዲህ አለው፣ 2"ስሙ እግዚአብሔር የሆነ፣ ያደረገው እግዚአብሔር፣ ያጸናውም ዘንድ የሠራው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። 3'ወደ እኔ ጩኽ፣ እኔም እመልስልሃለሁ። አንተም የማታስተውለውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ።'4የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ ለአፈር ድልድልና ለምሽግ ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፣ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና። 5'ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፊቴን ከዚህች ከተማ ስሰውር፣ ከለዳውያን ለመዋጋትና በቊጣዬ፣ እንዲሁም በመዓቴ በምገድላቸው ሰዎች ሬሳዎች ሊሞሏቸው እየመጡ ናቸው።6ነገር ግን ተመልከቱ፣ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፣ እፈውሳቸውማለሁ፤ መትረፍረፍንም አመጣላቸዋለሁ፣ ሰላምንና የታማኝነትን ብዛት አመጣላቸዋለሁ። 7የይሁዳን ምርኮና የእስራኤልን ምርኮ መልሼ አመጣለሁ፣ ቀድሞም እንደ ነበሩ አድርጌ እሠራቸዋለሁ። 8እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ። እኔንም የበደሉበትን ያመፀብኝንም ኃጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ። 9ይህችም ከተማ እኔ የምሠራላቸውን በጎነት ሁሉ በሚሰሙ እኔም ስላመጣሁላቸው መልካምነትና ሰላም ሁሉ በሚፈሩና በሚደነግጡ አሕዛብ ሁሉ ፊት ለደስታ ስም ለምስጋናም ለክብርም ትሆናለች።10እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ እናንተ፣ "ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚህች ስፍራ፣ የሚቀመጥባቸው በሌላ፣ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ጥፋት ሆኗል።" 11የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፣ "እግዚአብሔር ቸር ነውና፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ" የሚሉ ድምፅ በድጋሚ ይሰማል። ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት አምጡ፣ የምድርን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፣' ይላል እግዚአብሔር።12የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ባድማ ሆኖ፣ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ፣ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉት የእረኞች መኖሪያ ይሆናል። 13በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፣ በቈላውም ባሉ ከተሞች፣ በደቡብም ባሉ ከተሞች፣ እንዲሁም በብንያምም ምድር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፣ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፣' ይላል እግዚአብሔር።14'ተመልከቱ! ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፤ ይላል እግዚአብሔር። 15በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፣ እርሱም ፍትህንና ጽድቅን በምድር ላይ ያደርጋል። 16በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም በአስተማማኝ ሁኔታ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም፣ "እግዚአብሔር ጽድቃችን" ተብሎ ነው።17እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ 'በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዳዊት ዘንድ አይታጣም፤ 18የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የሚያቀርብ፣ የእህሉንም ቍርባን የሚያቃጥል፣ ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ከሌዋውያን ካህናት ዘንድ በእኔ ፊት አይታጣም።"19የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣ 20"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ቀንና ሌሊት በወራቱ እንዳይሆን የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፣ 21ያኔ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ ከእንግዲህ እንዳይሆንለት ከባሪዬ ከዳዊት ጋር፣ ከአገልጋዮቼም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈርሳል። 22የሰማይ ሠራዊት መቍጠር፣ የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፣ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።"23የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣ 24"ይህ ሕዝብ፣ 'እግዚአብሔር መርጧቸው የነበሩትን ሁለቱን ወገን ጥሎአቸዋል፤' ያለውን ነገር አትመለከትምን? በዚህ መልኩ በፊታቸው ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ እንዳይሆን ሕዝቤን አቃልለዋል።25እኔ፣ እግዚአብሔር እንዲህ እላለሁ፣ 'የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔ የማይኖሩ ከሆነ፣ ወይም የሰማይንና የምድርንም ሥርዓት ያልጠበቅሁ እንደሆነ፣ 26ያን ጊዜ በአብርሃም፣ በይስሐቅና፣ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዦች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እንዳልወስድ፣ የያዕቆብንና የባሪያዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ። ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፣ እምራቸውማለሁና።"
1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። ይህ ቃል የመጣው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ፣ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ ነበር። 2'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር እንዲህም በለው፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። በእሳትም ያቃጥላታል። 3አንተም በእርግጥ ትያዛለህ፣ በእጁም ተላልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም። ዐይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፤ ወደ ባቢሎን ስትሄድ፣ እርሱ ከአንተ ጋር አፍ ለአፍ ይነጋገራል።'4የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ! ስለ አንተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'በሰይፍ አትሞትም። 5በሰላም ትሞታለህ። እንደ አባቶችህ የቀብር መቃጠል፣ ከአንተ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት፣ እንዲሁ አካልህን ያቃጥላሉና። "ወየው፣ ጌታ ሆይ!" እያሉ ያለቅሱልሃል። አሁን እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።"6ነቢዩ ኤርምያስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ነገረው። 7የባቢሎንም ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳን ከተሞች ሁሉ፦ ለኪሶንና ዓዜቃን ወጋ። እነዚህ የይሁዳ ከተሞች የተመሸጉ ከተሞች ሆነው ቀሩ።8ንጉሡ ሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ነፃነትን ለማወጅ ስምምነት ካደረገ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። 9እያንዳንዱ ሰው እስራኤላዊ የሆነውን ወንድ ባርያውንና ሴት ባርያውን ነፃነት ሊለቅ ይገባል። ማንም ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በይሁዳ ውስጥ መሰል እስራኤላዊን ባርያ ሊያደርግ አይገባም።10ስለዚህም ስምምነቱን የተቀላቀሉት መሪዎች ሁሉ እና ሕዝቡ ታዘዙ። እያንዳንዱ ሰው ወንድ እና ሴት ባርያዎቻቸውን ከእንግዲህ ወዲህ ባርያ ላያደርጓቸው ነፃ አደረጓቸው። እነርሱም ሰሙ፣ ሰደዷቸውም። 11ነገር ግን ከዚህ በኋላ አሳባቸውን ቀየሩ። ነፃነት የለቀቋቸውን ባርያዎቻቸውን መልሰው አመጡ። በድጋሚ ባርያዎች እንዲሆኑ አስገደዷቸው።12ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣ 13"የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ። 14"ሰባት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፣ ራሱን የሸጠላችሁን፣ ስድስትም ዓመት የተገዛላችሁን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ ነፃነት ልታወጡት ይገባል። ነፃ አድርጋችሁ ስደዱት።" ነገር ግን አባቶቻችሁ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።15እናንተም ዛሬ ተመልሳችሁ ሰው ሁሉ ባልንጀራውን አርነት ለማውጣት ዐዋጅ በመንገር ለዐይኔ ትክክል የሆነውን ነገር አድርጋችሁ ነበር። በስሜም በሚጠራበት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድርጋችሁ ነበር። 16ነገር ግን ያን ጊዜ ተመልሳችሁ ስሜን አስነቀፋችሁ፤ እያንዳንዳችሁም በፈቃዳቸው እንዲሄዱ ነፃነት ያወጣችኋቸውን ወንድና ሴት ባርያዎቻችሁን አስመለሳችሁ። በድጋሚ ወንዶችና ሴቶች ባርያዎች እንዲሆኑላችሁ አስገደዳችኋቸው።'17ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እናንተ ራሳችሁ አልሰማችሁኝም። እያንዳንዳችሁ፣ ለወንድሞቻችሁና ለመሰል እስራኤላውያን ነፃነትን ልታውጁ በተገባ ነበር። ስለዚህ ተመልከቱ! እኔ ለሰይፍ፣ ለመቅሰፍት፣ ለራብም የነፃነት ዐዋጅ እናገርባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል አስደንጋጭ ነገር አደርጋችኋለሁ። 18ከዚያም ቃል ኪዳኔን የተላለፉትን ሰዎች፣ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳንን ቃል ያልፈጸሙትን እቀጣለሁ፤ 19ከዚያም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን አለቆች ጃንደረቦችን ካህናትንም፣ በእንቦሳም ቍራጭ መካከል ያለፉትን የአገሩን ሕዝብ ሁሉ።20ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል። 21የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና አለቆቹን ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት እጅ፣ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። 22ተመልከቱ፣ ትእዛዝ እሰጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ጦርነትን እንዲከፍቱባትና እንዲወስዷት፣ እንዲያቃጥሏትም ወደዚህች ከተማ እመልሳቸዋለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።"
1በይሁዳ ንጉስ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣ 2"ወደ ሬካባውያን ወገን ሄደህ አነጋግራቸው። ወደ ቤቴ፣ ከክፍሎቹ ወደ አንዲቱ፣ አግባቸው የወይን ጠጅም አጠጣቸው።"3የከባስንን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን፣ እንዲሁም ወንድሞቹን፣ ልጆቹንም ሁሉ፣ ብሎም የሬካባውያንን ወገን ሁሉ ወሰድኋቸው። 4ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ ወሰድኳቸው። እነዚህ ክፍሎች የእግዚአብሔር ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ በላይ ባለው የአለቆች ክፍል አጠገብ ነበሩ።5በሬካባውያንም ልጆች ፊት የወይን ጠጅ የሞላባቸውን ማድጋዎችንና ጽዋዎችን አኑሬ፣ "ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጡ፤" አልኳቸው። 6እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፣ "የትኛውንም የወይን ጠጅ አንጠጣም፣ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ 'እናንተና ልጆቻችሁ ለዘላለም የወይን ጠጅ አትጠጡ' ብሎ አዝዞናልና። 7እንደ እንግዶች በምትኖሩባት ምድር ላይ ብዙ ዘመን እንድትኖሩ፣ በዕድሜአችሁ ሙሉ በድንኳን ውስጥ ተቀመጡ እንጂ ቤትን አትሥሩ፣ የትኛውንም ዘር አትዝሩ፣ የትኛውንም ወይን አትትከሉ፣ ይህ ለእናንተ አይደለም።'8እኛም የአባታችንን የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብን ቃል ባዘዘን ነገር ሁሉ ታዝዘናል፤ እኛም፣ ሚስቶቻችንም፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም፣ ዕድሜአችንን ሙሉ የወይን ጠጅ አልጠጣንም። 9የምንቀመጥበትንም ቤት አልሠራንም፣ የወይን ቦታና እርሻ ዘርም የለንም። 10በድንኳንም ውስጥ ኖረናል፣ አድምጠናል፣ አባታችንም ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ አድርገናል። 11ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ምድሪቱን ባጠቃ ጊዜ፣ 'ኑ ከከለዳውያን ሠራዊትና ከሦርያ ሠራዊት ፊት የተነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ' አልን። ስለዚህ በኢየሩሳሌም እየኖርን ነን።"12ከዚያም የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣ 13"የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፣ 'ሂድና ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ተናገር እንዲህም በላቸው፣ "ቃሌን ትሰሙ ዘንድ ተግሣጽን አትቀበሉምን? ይላል እግዚአብሔር። 14ልጆቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዛቸው ቃል እስከ ዛሬ ድረስ ተፈጸመ። ለአባታቸውም ትእዛዝ ታዝዘዋል። እኔ ግን በተደጋጋሚ ተናግሬአችኋለሁ፣ ሆኖም አልሰማችሁኝም።15'እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፣ ሥራችሁንም አሳምሩ፤ ታመልኩአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፣ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ በተደጋጋሚ ባርያዎቼን፣ ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር። እናንተ ግን ጆሯችሁን አላዘነበላችሁም፣ ወይም እኔንም አልሰማችሁኝም። 16የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ልጆች አባታቸው ያዘዛቸውን ትእዛዝ ፈጽመዋልና፣ ይህ ሕዝብ ግን ሊሰማኝ አልፈለገም።"17ስለዚህ፣ የእስራኤል አምላክና የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፣ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና የተናገርሁባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ፣ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።"18ኤርምያስም ለሬካባውያን ቤተሰብ እንዲህ አላቸው፣ "የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለአባታችሁ ለኢዮናዳብ ትእዛዝ ታዝዛችኋልና፣ ትእዛዙንም ሁሉ ጠብቃችኋልና፣ ያዘዛችሁንም ፈጽማችኋልና፤ 19ስለዚህ፣ 'በፊቴ የሚቆም ሰው፣ ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን ለዘላለም አይታጣም።" ይላል የሠራዊት አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
1እንዲህም ሆነ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፣ እንዲህም አለው፣ 2"ለራስህ አንድ የመጽሐፍ ጥቅልል ውሰድና በእስራኤልና በይሁዳ ላይ፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት። ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለአንተ የተናገርሁትን ጻፍበት። 3ምናልባት የይሁዳ ሕዝብ እኔ አደርግባቸዋለሁ ያልሁትንና ያሰብሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል። ከክፋ መንገዳቸው ይመለሱ፣ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ዘንድ።4ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራ፣ ባሮክም ከኤርምያስ አፍ እግዚአብሔር ለእርሱ የተናገረውን ቃል ሁሉ በመጽሐፉ ጥቅልል ላይ ጻፈ። 5ቀጥሎም ኤርምያስ ለባሮክ እንዲህ ሲል አዘዘው። "እኔ በእስር ላይ ስለሆንኩ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ አልችልም። 6ስለዚህ አንተ መሄድና ከአፌም የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል ልታነብብ ይገባል። በጾም ቀን፣ በእግዚአብሔር ቤት ሕዝቡ እየሰሙ አንብብ፣ ደግሞም ከከተሞቻቸው የሚወጡ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እየሰሙ አንብበው። እነዚህን ቃሎች አውጅላቸው።7ምናልባት የምሕረት ልመናቸው በእግዚአብሔር ፊት ትመጣ ይሆናል። እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና፣ ሁሉም ከክፉ መንገዱ ይመለስ ይሆናል።" 8ስለዚህ የኔርያም ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። በእግዚአብሔርም ቤት የእግዚአብሔርን ቃል በመጽሐፉ አነበበ።9በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ለመጾም አዋጅ ነገሩ። 10ባሮክም የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ በእግዚአብሔር ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ጓዳ ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙ መጽሐፉን አነበበ።11የሳፋንም ልጅ የገማርያ ልጅ ሚክያስ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ከመጽሐፉ ጥቅልል ሰማ። 12ወደ ንጉሡ ቤት ወደ ጸሐፊው ክፍል ወረደ። በዚያም፣ አለቆች ሁሉ፦ ጸሐፊው ኤሊሳማ፣ የሸማያ ልጅ ድላያ፣ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፣ የሳፋን ልጅ ገማርያ፣ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ፣ እንዲሁም አለቆቹ ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።13ሚክያስም ሕዝቡ እየሰሙ ባሮክ ከመጽሐፉ ባነበበ ጊዜ የሰማውን ቃል ሁሉ ነገራቸው። 14አለቆቹም ሁሉ፣ "በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ጥቅልል በእጅህ ይዘህ ና" የሚል መልእክት በኵሲ ልጅ፣ በሰሌምያ ልጅ፣ በናታንያ ልጅ፣ በይሁዲ እጅ፣ ወደ ባሮክ ላኩ። ስለዚህ የኔርያ ልጅ ባሮክ ጥቅልሉን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ ሄደ። 15ከዚያም፣ "ተቀመጥና እየሰማንህም ይህንን አንብብልን፤" አሉት። ባሮክም በጆሮአቸው አነበበው።16እነዚህን ቃሎች ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈሩና እርስ በእርሳቸው ተመካከሩ፣ ባሮክንም፣ "ይህን ቃል ሁሉ በእርግጥ ለንጉሡ ልንናገር ይገባል" አሉት። 17ከዚያም ባሮክን፣ "ይህን ሁሉ ቃላት ከኤርምያስ አፍ እንዴት እንደ ጻፍኸው ንገረን" ብለው ጠየቁት። 18ባሮክም፣ "ይህን ቃል ከአፉ ይነግረኝ ነበር፣ እኔም በመጽሐፍ ጥቅልል ላይ በቀለም እጽፍ ነበር" ብሎ መለሰላቸው። 19አለቆቹም ለባሮክ፣ "አንተና ኤርምያስ ሄዳችሁ ተሸሸጉ። የት እንደሆናችሁ ማንም አይወቅ" አሉት።20ወደ ንጉሡም ሸንጎ ገቡና ቃሉን ሁሉ ንጉሡ እየሰማ ተናገሩ። ነገር ግን አስቀድመው ጥቅልሉን በጸሐፊው በኤሊሳማ ክፍል አኑረውት ነበር። 21ከዚያም ንጉሡ ጥቅልሉን ያመጣ ዘንድ ይሁዲን ላከ። እርሱም ከጸሐፊው ከኤሊሳማ ክፍል ወሰደው። ከዚያም ይሁዲ ንጉሡና በንጉሡ አጠገብ የቆሙት አለቆች ሁሉ እየሰሙ አነበበው። 22ያኔ፣ ንጉሡ በዘጠነኛው ወር በክረምት ቤት ተቀምጦ ነበር፣ በፊቱም በምድጃ ውስጥ እሳት ይነድድ ነበር።23ይሁዲ ሦስት ወይም አራት ዓምድ ያህል ባነበበ ቍጥር፣ ንጉሡ በካራ እየቀደደ ጥቅልሉ በምድጃ ውስጥ ባለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ጣለው። 24ነገር ግን ንጉሡ ወይም ይህንን ቃል ሁሉ የሰሙ ባሪያዎቹ ሁሉ አልፈሩም፣ ልብሳቸውንም አልቀደዱም።25ነገር ግን ኤልናታን፣ ድላያና፣ ገማርያ ጥቅልሉን እንዳያቃጥል ንጉሡን ለመኑት፣ እርሱ ግን አልሰማቸውም። 26ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነብዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልን፣ የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን፣ የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፣ እግዚአብሔር ግን ሰውሯቸው ነበር።27ከዚያም ንጉሡ ጥቅልሉንና ባሮክ ከኤርምያስ አፍ እየቀዳ የጻፈውን ቃል ካቃጠለ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ። 28"ዳግመኛ ሌላ ጥቅልል ውሰድ፣ የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአቄም ባቃጠለው ጥቅልል ላይ የነበረውን የቀድሞውን ቃል ሁሉ ጻፍበት። 29ከዚያም፣ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምን እንዲህ በለው፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ አንተ፣ "የባቢሎን ንጉሥ በእርግጥ ይመጣል ይህችንም አገር ያፈርሳታል ከሰውና ከእንስሳም ባዶ ያደርጋታል" ብለህ ለምን ጻፍህበት? ብለህ ይህን ጥቅልል አቃጥለሃል።"30ስለዚህ፣ ስለ አንተ፣ የይሁዳ ንጉሥ፣ ስለ ኢዮአቄም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም። ሬሳውም በቀን ለትኩሳት፣ በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል። 31ስለ ኃጢአታቸውም እርሱንና ዘሩን፣ ባሪያዎቹንም እቀጣለሁ። እነርሱም አልሰሙምና የተናገርሁባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ በእነርሱ ላይና፣ በኢየሩሳሌም በሚቀመጡ፣ በይሁዳም ሰዎች ላይ አመጣለሁ።32ሰለዚህ ኤርምያስ ሌላ ጥቅልል ወሰደ ለኔርያም ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው። እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ እየቀዳ ጻፈበት። በተጨማሪም፣ ከቀድሞው ቃል ጋር የሚመሳሰል ብዙ ቃል ተጨመረበት።
1የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ። 2ነገር ግን ሴዴቅያስም ሆነ ባርያዎቹ፣ የአገሩም ሕዝብ በነቢዩ በኤርምያስ እጅ የተናገረውን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።3ስለዚህ፣ ንጉሡ ሴዴቅያስ፣ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ። እነርሱም "ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ" አሉት። 4በግዞት ቤት ገና አላገቡትም ነበርና ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ይወጣና ይገባ ነበር። 5የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፣ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።6ከዚያም፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣ 7"የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ትጠይቁ ዘንድ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ 'ተመልከቱ፣ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደገዛ ምድሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል። 8ከለዳውያንም ይመለሳሉ። ይህችን ከተማ ይዋጉአታል፣ ይይዟትማል፣ በእሳትም ያቃጥሉአታል።'9እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለማይሄዱ 'ከለዳውያን በእርግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄዳሉ' ብላችሁ ራሳችሁን አታታልሉ። 10እናንተም የሚዋጉትን የከለዳውያንን ሠራዊት ሁሉ አሸንፋችሁ ቢሆን እንኳን፣ ከእነርሱም የቆሰሉት ብቻ በድንኳኖቻቸው ቀርተው ቢሆን ኖሮ፣ይህችን ከተማ በእሳት ባቃጠሉአት ነበር።11ስለዚህ የከለዳውያን ሠራዊት ከፈርዖን ሠራዊት ፊት የተነሣ ከኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ፣ 12ያኔ ኤርምያስ ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ። እርሱ የርስቱን እድል ፈንታ በዚያ ከሕዝቡ መካከል ይቀበል ዘንድ ፈለገ። 13በብንያምም በር በነበረ ጊዜ፣ የዘበኞች አለቃ በዚያ ነበር። ስሙም የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የሪያ ነበረ። እርሱም "ወደ ከለዳውያን መኰብለልህ ነው" ብሎ ነቢዩን ኤርምያስን ያዘው።14ኤርምያስ ግን፣ "ይህ እውነት አይደለም። ወደ ከለዳውያን መኰብለሌ አይደለም" አለ። ነገር ግን የሪያ አልሰማውም። ኤርምያስንም ይዞ ወደ አለቆች አመጣው። 15አለቆችም በኤርምያስ ላይ ተቈጡ። መቱትና የጸሐፊውንም የዮናታንን ቤት እስር ቤት አድርገውት ነበርና በዚያ አኖሩት።16ስለዚህ ኤርምያስ ብዙ ቀናት በተቀመጠበት ከምድር በታች ባለ ክፍል ተጣለ፤ 17ከዚያም ንጉሡ ሴዴቅያስ አንድ ሰው ልኮ ወደ ቤተመንግሥት አስመጣው። ንጉሡም በቤቱ፣ "በውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?" ብሎ በድብቅ ጠየቀው። ኤርምያስም፣ "አዎን አለ፦ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ" አለ።18ከዚያም ኤርምያስ ንጉሡን ሴዴቅያስን፣"በእስር ቤት የጣላችሁኝ አንተን፣ ወይስ ባርያዎችህን፣ ወይስ ሕዝብህን ምን በድያችሁ ነው? 19የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች ምድር አይመጣባችሁም ብለው ትንቢት ይናገሩላችሁ የነበሩ ነቢያቶቻችሁ ወዴት አሉ? 20ንጉሡ ጌታዬ ሆይ፣ እንድትሰማኝ እለምንሃለሁ! ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ። በዚያ እንዳልሞት ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ።"21ስለዚህ ንጉሡ ሴዴቅያስ አዘዘ። አገልጋዮቹም ኤርምያስን በግዞት ቤት አደባባይ አኖሩት። እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከጋጋሪዎች መንገድ ይሰጡት ነበር። ስለዚህ ኤርምያስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀምጦ ነበር።
1ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን ቃል የማታን ልጅ ስፋጥያስ፣ የጳስኮርም ልጅ ጎዶልያስ፣ የሰሌምያም ልጅ ዮካል፣ የመልክያም ልጅ ጳስኮር ሰሙ። ኤርምያስ እንዲህ ሲል ነበር፣ 2"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህች ከተማ የሚቀመጥ ማንኛውም ሰው በሰይፍ፣ በራብ፣ በመቅሠፍትም ይሞታል። ወደ ከለዳውያን የሚወጣ ግን በሕይወት ይኖራል። ሕይወቱንም ያስመልጣል፣ በሕይወትም ይኖራል። 3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህች ከተማ በባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ በእርግጥ ትሰጣለች፣ እርሱም ይይዛታል።"4ስለዚህ አለቆቹ ለንጉሡ እንዲህ አሉት፣ "ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚህች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው ይገደል። ይህ ሰው ጥፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አያበጅለትምና እነዚህን ቃሎች እየተናገረ ነው። 5ስለዚህ ንጉሡ ሴዴቅያስ፣ "ተመልከቱ፣ እናንተን የሚቋቋም ንጉሥ የለምና፣ በእጃችሁ ነው" አለ።6ከዚያም ኤርምያስን ወሰዱትና ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጕድጓድ ጣሉት። ጉድጓዱ በእስር ቤቱ አደባባይ ነበረ። ኤርምያስንም በገመድ አወረዱት። በጕድጓድም ውስጥ ውኃ አልነበረበትም፣ ነገር ግን ጭቃማ ነበርና ኤርምያስ ጭቃው ውስጥ ገባ።7ኩሻዊ የሆነው አቤሜሌክ በንጉሡም ቤት ከነበሩት ጃንደረቦች አንዱ ነበር። ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር። 8ስለዚህ አቤሜሌክ ከንጉሡ ቤት ወጥቶ ከንጉሡ ጋር ተነጋገረ። 9"ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች ነቢዮን ኤርምያስን በጕድጓድ ውስጥ በመጣላቸው ክፉ አድርገዋል። በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ ስለሌለ በዚያ በራብ እንዲሞት ወደ ጉድጓድ ጥለውታል።"10ከዚያም ንጉሡ ለኩሻዊው አቤሜሌክ ትእዛዝ ሰጠ። "ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፣ ነብዩ ኤርምያስ ሳይሞት በፊት ከጕድጓድ አውጣው" ብሎ አዘዘው። 11ስለዚህ አቤሜሌክ ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደና ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደ ነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ። ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደና ወደ ኤርምያስ ወደ ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አወረደው።12ኩሻዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን፣ "ይህን አሮጌ ጨርቅና እላቂውን ልብስ በብብትህ እና ከገመዱ በታች አድርግ" አለው። ስለዚህ ኤርምያስ እንዲሁ አደረገ። 13ከዚያም ኤርምያስን በገመዱ ጐተቱት። በዚህ መልኩ ከጕድጓድ አወጡት። ስለዚህ ኤርምያስ በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ።14ከዚያም ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ በእግዚአብሔር ቤት ወደ ነበረው፣ ወደ ሦስተኛው መግቢያ፣ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው። ንጉሡም ኤርምያስን፣ "አንዲት ነገር ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። መልሱን አትደብቅብኝ" አለው። 15ኤርምያስም ሴዴቅያስን፣ "ብመልስልህ፣ በእርግጥ አትገድለኝምን? ምክር ብሰጥህም፣ አትሰማኝም" አለው። 16ንጉሡ ሴዴቅያስ ግን "እኛን የፈጠረንን ሕያው እግዚአብሔርን፣ አልገድልህም፣ ወይም ነፍስህን ለሚሹ ለእነዚህ ሰዎች እጅ አሳልፌ አልሰጥህም" ብሎ በድብቅ ለኤርምያስ ማለ።17ስለዚህ ኤርምያስ ሴዴቅያስን፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ብትወጣ፣ በሕይወት ትኖራለህ፣ ይህችም ከተማ አትቃጠልም። አንተና ቤተሰብህ በሕይወት ትኖራላችሁ። 18ነገር ግን ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፣ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች። በእሳትም ያቃጥሉአታል፣ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም" አለው።19ንጉሡ ሴዴቅያስም ኤርምያስን፣ "ነገር ግን ወደ ከለዳውያን ክፉኛ እንዲያፌዙብኝ፣ በኰበለሉት በአይሁድ እጅ አሳልፈው ይሰጡኛል ብዬ እፈራለሁ" አለው።20ኤርምያስም እንዲህ አለው፣ "ለእነርሱ አሳልፈው አይሰጡህም። እኔ እየነገርኩህ ያለሁትን የእግዚአብሔርን መልእክት ታዘዝ፤ ነገሮችም መልካም ይሆኑልሃል፣ በሕይወትም ትኖራለህ። 21ነገር ግን ትወጣ ዘንድ እንቢ ብትል፣ እግዚአብሔር ያሳየኝ ይህንን ነው፦22ተመልከት! በይሁዳ ንጉሥ ቤት የቀሩትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ያወጣሉ። እነዚያም ሴቶች ለአንተ፣ "ወዳጆችህ አታልለውሃል፤ አበላሽተውህማል። እግሮችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ሰጥመዋል፣ ወዳጆችህም ይሸሻሉ።' 23ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፣ አንተም ራስህ አታመልጥም። በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።"24ከዚያም ሴዴቅያስ ኤርምያስን እንዲህ አለው፣ "እንዳትሞት ስለእነዚህ ቃሎች ለማንም አትናገር። 25አለቆቹ ግን እኔ ከአንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ ከሰሙ፣ ወደ አንተ መጥተው፣ 'ለንጉሡ የነገርከውን ንገረን። ከእኛም አትሸሽገን፣ አሊያ እንገድልሃለን። ንጉሡ ደግሞ ያለህን ንገረን' ቢሉህ፣ 26ያን ጊዜ 'በዚያ እሞት ዘንድ ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ' ብዬ በንጉሡ ፊት ለመንሁ" በላቸው።27ከዚያም አለቆቹ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፣ ንጉሡም እንዳዘዘው እንደዚህ ቃል ሁሉ ነገራቸው። በኤርምያስና በንጉሡ መካከል የነበረው ውይይት አልተሰማምና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ። 28ስለዚህ፣ ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ቀን ድረስ ኤርምያስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀመጠ።
1ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ፣ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ከበቡአት። 2በሴዴቅያስም በዐሥራ አንደኛው ዓመትና በአራተኛው ወር ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማይቱ ተሰበረች። 3ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ፣ ኤርጌል ሳራስር፣ ሳምጋርናቦና፣ ዋና አለቃው ሠርሰኪም፤ ኤርጌል ሳራስር በከፍተኛ ደረጃ ያለ አለቃ ነበርና ከቀሩት የባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።4የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ ሰልፈኞቹም ሁሉ፣ ባዩአቸው ጊዜ ሸሹ። በሌሊትም በንጉሡ አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥር መካከል ከነበረው ደጅ ከከተማይቱ ወጡ። ንጉሡ በዓረባ መንገድ ወጣ። 5ነገር ግን የከለዳውያን ሠራዊት ተከታተላቸውና ሴዴቅያስን በኢያሪኮ ሜዳ አቅራቢያ ባሉት የዮርዳኖስ ሸለቆ ሜዳዎች ላይ አገኙት። ከዚያም ይዘውት በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፣ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።6የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በገዛ ዐይኑ ፊት በሪብላ አረዳቸው። እርሱም የይሁዳን ከበርቴዎች ሁሉ ገደለ። 7ከዚያም የሴዴቅያስን ዐይን አወጣና ወደ ባቢሎን ሊወስደው በመዳብ ሰንሰለት አሰረው።8ከዚያም ከለዳውያን የንጉሡንና የሕዝቡን ቤቶች በእሳት አቃጠሉ። የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ። 9የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ፣ ወደ እርሱም የኰበለሉትን ሰዎች፣ የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው። 10አንዳች የሌላቸውን የሕዝቡን ድሆች ግን የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን በይሁዳ አገር ተዋቸው። የወይኑን ቦታና እርሻውን በዚያው ቀን ሰጣቸው።11የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ፣ 12"ውሰደውና በመልካም ተንከባከበው። አትጉዳው። የሚነግርህንም የትኛውንም ነገር አድርግለት።" ብሎ የዘበኞቹን አለቃ ናቡዘረዳንን አዘዘ። 13ስለዚህ የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ላከ፣ የጃንደረቦች አለቃ ናቡሽዝባን፣ ዋናው አለቃ ራፋስቂስም ኤርጌል ሳራስርም፣ ራብማግም የባቢሎንም ንጉሥ ዋና ዋና አለቆች ሁሉ ሰዎችን ላኩ። 14ሰዎቻቸውም ኤርምያስን ከግዞት ቤት አደባባይ አወጡት፣ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ ስለዚህ ኤርምያስ በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።15በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፣ 16"ለኩሻዊው ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፣ 'የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ለበጎነት ሳይሆን ለጥፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ። በዚያም ቀን በፊትህ እውነት ሆኖ ይፈጸማል።17ነገር ግን በዚያ ቀን እታደግሃለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም። 18በእርግ አድንሃለሁ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም። በእኔ ታምነሃልና፣ ይላል እግዚአብሔር።"
1ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች መካከል የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን፣ከራማ ከለቀቀው በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጥቶ የነበረው ቃል ይህ ነው። ኤርምያስ ተወስዶ የነበረው ወደዚህ ቦታ የነበረ ሲሆን፣ እርሱም በሠንሰለት ታስሮ ነበር። እርሱ በምርኮ ከተወሰዱት የኢየሩሳሌም እና ይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ መካከል አንዱ ነበር። 2የዘበኞቹም አለቃ ኤርምያስን ወሰደውና እንዲህ አለው፣ "አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተናገረ።3ስለዚህ እግዚአብሔር ነገሩን አመጣው። እናንተ ሕዝቦች በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፣ እንደ ተናገረው አደረገ። ይህ ነገር እየሆነባችሁ ያለው፣ ቃሉን አልሰማችሁምና ነው። 4አሁን ግን ተመልከት! እጅህ የታሰረችበትን ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁልህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት በዐይኖችህ ዘንድ መልካም መስሎ ቢታይህ፣ ና፣ እኔም እንከባከብሃለሁ። ነገር ግን ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣቱ በዐይኖችህ ዘንድ መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፣ አትምጣ። በፊትህ ያለችውን ምድር ሁሉ ተመልከት። በዐይኖችህ ዘንድ ልትሄድበት መልካም መስሎ ወደሚታይህና ትክክል ወደሚመስልህ ስፍራ ሂድ።"5እርሱም ገና መልስ ሳይሰጥ፣ ናቡከደነፆር "የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ተመለስ። ከእርሱም ጋር በሕዝቡ መካከል ተቀመጥ ወይም ልትሄድበት ደስ ወደሚያሰኝህ ስፍራ ሁሉ ሂድ" አለው። የዘበኞቹም አለቃ የምግብ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው። 6ስለዚህ ኤርምያስ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ ሄደ። ከእርሱም ጋር በአገሩ ውስጥ በቀሩት ሕዝብ መካከል ተቀመጠ።7በየገጠሩ የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድር ላይ እንደ ሾመ ሰሙ። እንዲሁም ወደ ባቢሎን ያልተማረኩ የምድሪቱ ድሆች የሆኑት ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ እንደሾመው ሰሙ። 8ስለዚህ ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ። እነዚህም ሰዎች የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናንና ዮናታን፣ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፣ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች፣ የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ፣ እነርሱና ሰዎቻቸው ነበሩ።9የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው ማለ፣ እንዲህም አላቸው፣ "ለከለዳውያን አለቆች ለማገልገል አትፍሩ። በምድሪቱ ላይ ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ አገልግሉ፣ መልካምም ይሆንላችኋል። 10ተመልከቱ፣ ወደ እኛ ከሚመጡት ከለዳውያን ጋር ለመገናኘት ምጽጳ ውስጥ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይንን፣ የበጋ ፍሬንና፣ ዘይትን በየዕቃዎቻችሁ አከማቹ። በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ውስጥ ኑሩ።"11በሞዓብ፣ በአሞንም ልጆች መካከል፣ እንዲሁም በኤዶምያስና በእያንዳንዱ ምድር ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፣ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው ሰሙ። 12ስለዚህ አይሁድ ሁሉ ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ። ጎዶልያስ ወዳለበት፣ ወደ ይሁዳ ምድር፣ ወደ ምጽጳ መጡ። ወይንና የበጋንም ፍሬ በመሰብሰብ እጅግ ብዙ አከማቹ።13የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ በየገጠሩም የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ። 14"የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ ይገድልህ ዘንድ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ሰደደ ታውቃለህን?" አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።15ስለዚህ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ምጽጳ ላይ ጎዶሊያስን እንዲህ በማለት በሚስጢር አነጋገረው፣"ሄጄ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንድገድለው ፍቀድልኝ። ማንም አይጠረጥረኝም። ሊገድልህ የሚገባው ለምንድነው? ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፣ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ለምን ትፈቅዳለህ?" 16ነገር ግን የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን፣ "በእስማኤል ላይ ሐሰት ተናግረሃልና ይህን ነገር አታድርግ" አለው።
1በሰባተኛውም ወር ከመንግሥት ወገንና፣ ከንጉሡ ዋና ዋና አለቆች አንዱ የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ። በዚያም በምጽጳ በአንድ ላይ እንጀራ በሉ። 2የናታንያም ልጅ እስማኤል፣ ከእርሱም ጋር የነበሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ። የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን እስማኤል ገደለው። 3ከዚያም እስማኤል ከጎዶልያስ ጋር በምጽጳ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፣ በዚያም የተገኙትን የከለዳውያንን ሰልፈኞች ሁሉ ገደላቸው።4ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ ሁለት ቀን ሆነ፣ ነገር ግን ማንም አላወቀም ነበር። 5ጢማቸውን ላጭተው፣ ልብሳቸውንም ቀድደው፣ ገላቸውንም ነጭተው፣ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው እየያዙ፣ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬም፣ ከሴሎና፣ ከሰማርያ መጡ።6የናታንያም ልጅ እስማኤል ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሊገናኛቸው ሄደ። ባገኛቸውም ጊዜ፣ "ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ!" አላቸው። 7ወደ ከተማም መካከል በመጡ ጊዜ፣ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰዎች አረዷቸውና በጉድጓድ ውስጥ ጣሉአቸው።8ነገር ግን በመካከላቸው እስማኤልን፣ "የምንሰጥህ በሜዳ የተሸሸገ ስንዴ፣ ገብስ፣ ዘይትና፣ ማር ስላለን አትግደለን" የሚሉት ዐሥር ሰዎች ነበሩ። እርሱም ከሌሎች ወዳጆቻቸው ጋር አልገደላቸውም። 9ጉድጓዱ እስማኤል ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ነበር። ይህ ጥልቅ ጉድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጉድጓድ ነበረ። የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት።10ቀጥሎ እስማኤል በምጽጳ የነበረውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆች፣ የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በምጽጳ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ ማረካቸው። ስለዚህ የናታንያም ልጅ እስማኤል ማርኮ ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።11የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል ያደረገውን ክፋት ሁሉ ሰሙ። 12ስለዚህ ሰዎቻቸውን ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ። በገባዖንም ባለው በታላቁ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ አገኙት።13ከዚያም ከእስማኤል ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆችን ሁሉ ሲያዩ እጅግ ደስ አላቸው። 14ስለዚህ እስማኤል ከምጽጳ የማረካቸው ሕዝብ ሁሉ ዞረው ወደ ቃሬያም ልጅ ወደ ዮሐናን ሄዱ።15ነገር ግን የናታንያ ልጅ እስማኤል ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ። ወደ አሞንም ሕዝቦች ሄደ። 16የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምጽጳ ከገደለው በኋላ ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ያስመለሱአቸውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፣ ከገባዖን ያስመለሱአቸውን ሰልፈኞች፣ ሴቶችንም፣ ልጆችንም፣ ጃንደረቦችንም፣ ወሰዱ።17ከዚያም ሄደው ለተወሰነ ጊዜ በቤተልሔም አቅራቢያ ባለው በጌሮት ከመዓም ተቀመጡ። ሊሄዱ የነበረው ወደ ግብጽ ነበር። 18ይህም ከከለዳውያን ፍርሃት የተነሣ ነበር። የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን እስማኤል ስለ ገደለው ፈሯቸው።
1ከዚያም የጭፍራ አለቆች ሁሉ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ የሆሻያም ልጅ ያእዛንያ፣ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ያሉት ሕዝብ ወደ ነብዩ ኤርምያስ ቀረቡ። 2እንዲህም አሉት፣ "ልመናችን በፊትህ ይድረስ። እንዳየኸው ከብዙዎቹ መካከል የቀረነው ጥቂቶች ነንና፣ 3የምንሄድበትን መንገድና፣ የምናደርገውን ነገር እንዲያሳየን ስለ እኛና ስለዚህ ቅሬታ ሕዝብ ወደ አምላክህ እግዚአብሔር ጸልይ" አሉት።4ስለዚህ ነቢዩ ኤርምያስ፣ "ሰምቻችኋለሁ። ተመልከቱ፣እንደጠየቃችሁት ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ። እግዚአብሔርም የሚመልስላችሁን ሁሉ እነግራችኋለሁ። ከእናንተ ምንም አልሸሽግም፤" አላቸው። 5እነርሱም ለኤርምያስ፣ "አምላክህ እግዚአብሔር ወደ እኛ የላከውን ነገር ሁሉ ባናደርግ፣ እግዚአብሔር በመካከላችን እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን። 6የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፣ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ እንሰማለን አሉት።"7ከዚያም ከዐሥር ቀን በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። 8ስለዚህ ኤርምያስ የቃሬያንም ልጅ ዮሐናንን ከእርሱም ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡንም ሁሉ ጠራ። 9እንዲህ አላቸው፣ "ጸሎታችሁን በፊቱ አቀርብ ዘንድ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 10'በእናንተ ላይ ያመጣሁባችሁን ጥፋት እመልሳለሁና ተመልሳችሁ በዚህች ምድር ብትኖሩ፣እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፣ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም።11የምትፈሩትን የባቢሎን ንጉሥ አትፍሩ። አድናችሁ ዘንድ፣ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ፣ ይላል እግዚአብሔር። 12ምሕረትን እሰጣችኋለሁና። እርሱ እንዲምራችሁ ወደ ምድራችሁም እንዲመልሳችሁ እኔ እራራላችኋለሁ።13እናንተ ግን፣"በዚህች ምድር አንቀመጥም" ብትሉ፣ የእኔን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፣ 14እናንተም፣ "አይሆንም! የትኛውንም ጦርነት ወደማናይባት፣ የመለከትም ድምፅ ወደማንሰማባት፣ ወደማንራብባት ወደ ግብጽ ምድር እንሄዳለን። በዚያ እንኖራለን" ብትሉ፣15አሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ እናንተ የይሁዳ ቅሬታ የሆናችሁ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ወደ ግብጽ እንድትገቡ፣ በዚያም እንድትኖሩ በእርግጥ ፊታችሁን ብታቀኑ፣ 16ያኔ የምትፈሩት ሰይፍ በዚያ በግብጽ ምድር ያገኛችኋል። የምትደነግጡበት ረሃብ በዚያ በግብጽ ይደርስባቸኋል። በዚያም ትሞታላችሁ። 17ስለዚህ ወደ ግብጽ እንዲገቡ፣ በዚያም እንዲኖሩ ፊታቸውን የሚያቀኑ ሰዎች ሁሉ በሰይፍ፣ በረሃብ፣ ወይም በመቅሠፍት፣ ይሞታሉ። እኔም ከማመጣባቸው ክፉ ነገር ማንም አይተርፍም፣ ማንም አያመልጥም።18የእስራኤል አምላክ፣የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላልና፦ ቊጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፣ እንዲሁ ወደ ግብጽ የምትገቡ ከሆነ መዓቴ ይፈስስባችኋል። እናንተም ለእርግማንና ለመደንገገጪያ፣ ለመረገሚያና ለመዋረጂያ ትሆናላችሁ። ደግሞም ይህንን ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም።" 19ከዚያም ኤርምያስ እንዲህ አለ፣ "እናንተ የይሁዳ ቅሬታዎች፣ እግዚአብሔር፣ ወደ ግብጽ አትሂዱ ብሎ ተናግሯችኋልና ዛሬ ምስክር እንደሆንኩባችሁ በእርግጥ እወቁ።20'ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። አምላካችንም እግዚአብሔር የሚናገርህን ሁሉ ንገረን፣ እኛም እንፈጽመዋለን' ብላችሁ ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካችሁ ስትልኩኝ የሕይወት ዋጋ የሚያስከፍላችሁን ነገር አድርጋችኋልና። 21እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፣ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም። 22ስለዚህ፣ አሁንም ሄዳችሁ እንድትኖሩበት በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍ፣ በራብ፣ በቸነፈር እንድትሞቱ በእርግጥ እወቁ።"
1ኤርምያስ አምላካቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ የላከውን ይህንን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፣ለሕዝቡ ሁሉ ተናግሮ ጨረሰ። 2የሆሻያ ልጅ ዓዛርያስ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፣ "ሐሰትን እየተናገርክ ነህ። አምላካችን እግዚአብሔር፣ 'በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብጽ አትግቡ ብሎ አልላከህም፤' 3ነገር ግን ከለዳውያን እንዲገድሉን ወደ ባቢሎንም እንዲማርኩን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ የኔርያ ልጅ ባሮክ በላያችን ላይ አነሣሥቶሃል" አሉት።4ስለዚህ የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ የጦር ሠራዊቱ አለቆች ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይኖሩ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም። 5የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመኖር ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ። 6እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችን፣ የንጉሡንም ሴቶች ልጆች፣ የዘበኞቹንም አለቃ ናቡዘረዳን፣ ከሳፋን ልጅ፣ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያስ ጋር የተዋቸውን ሰዎች ሁሉ፣ ነቢዩንም ኤርምያስን የኔርያንም ልጅ ባሮክን ወሰዱ። 7የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልሰሙ ወደ ግብጽ ምድር ሄዱ፣ እስከ ጣፍናስ ድረስ መጡ።8ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል በጣፍናስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣ 9"ታላላቆችን ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፣ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ ባለው በፈርዖን የጡብ ቤት ደጅ መግቢያ ሸሽጋቸው።" 10ከዚያም እንዲህ በላቸው፣ "የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አገልጋዬ ለማድረግ መልእክተኛ እልክበታለሁ። ዙፋኑንም አንተ፣ ኤርምያስ በሸሸግሃቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ። ናቡከደነፆር ማለፊያ ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል።11መጥቶም የግብጽን ምድር ያጠቃል። ለሞት የተመደበውን ለሞት ይሰጣል። ለምርኮም የተመደበው ለምርኮ ይወሰዳል። ለሰይፍ የተመደበው ለሰይፍ ይሰጣል። 12ከዚያም፣ በግብጽ አማልክት ቤቶች ላይ እሳትን አነድዳለሁ። ናቡከደነፆር ያቃጥላቸዋል ወይም ይማርካቸዋል። እረኞች ከደበሏቸው ተባይን እንደሚያራግፉ፣ እንዲሁ የግብጽን አገር ያጸዳል። ከዚያም ስፍራ በድል ይወጣል። 13በግብጽም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል። የግብጽንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።"
1በግብጽ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ በሜምፎስም በጳትሮስም አገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። 2"የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ያመጣሁትን ክፉ ነገር ሁሉ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል። ተመልከቱ፣ ዛሬ ጠፍተዋል። የሚኖርባቸው የለም። 3ይህም የሆነው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ ያስቀይሙኝ ዘንድ ስላደረጉት ክፋት ነው። እነዚህም አማልክት እነርሱ ራሳቸው፣ አንተም ራስህ፣ እንዲሁም አባቶቻቸው የማያውቋቸው ናቸው።4ስለዚህ በተደጋጋሚ ባርያዎቼን ነብያትን ሁሉ ሰደድሁባችሁ። 'እንደነዚህ ያሉ የጠላኋቸውን ርኩስ ነገሮች ማድረጋችሁን አቊሙ' ልላቸው ላክኋቸው። 5ነገር ግን አልሰሙም። ከክፋታቸው ተመልሰው ለሌሎች አማልክት እንዳያጥኑ አትኩሮታቸውን ለመስጠት አልፈለጉም። 6ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ፈሰሱ፣ ደግሞም እንደ እሳት ተቀጣጠሉ። ዛሬም እንደ ሆነው ፈረሱ፣ ባድማም ሆኑ።"7አሁንም ቢሆን፣ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወንድንና ሴትን፣ ብላቴናንና ሕፃንን ከይሁዳ እንድታጠፉ ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ? ከመካከላችሁ የአንዳችሁም ቅሬታ አይተርፍም። 8ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ፣ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፣ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?9በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያደረጉትን የአባቶቻችሁን ክፋት፣ የይሁዳንም ነገሥታት ክፋት፣ የሚስቶቻቸውንም ክፋት፣ የእናንተንም ክፋት፣ የሚስቶቻችሁንም ክፋት ረስታችሁታልን? 10እስከ ዛሬ ድረስ ትሑታን አልሆኑም። በእነርሱና በአባቶቻቸውም ፊት ያኖርሁትን ሕጌን ወይም ሥርዓቴን አላከበሩም፣ አልሄዱበትም።"11ስለዚህም የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፦ "ተመልከቱ፣ በእናንተ ላይ ጥፋትን ለማድረግ እና ይሁዳን ሁሉ ላጠፋ ፊቴን በላያችሁ ላይ አደርጋለሁ። 12ወደ ግብጽ ሄደው በዚያ እንዲኖሩ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ቅሬታ እወስዳለሁና። ይህን የማደርገው ሁሉም በግብጽ ምድር እንዲጠፉ ነው። እነርሱ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ። ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለመደነቂያ፣ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።13ኢየሩሳሌምን በሰይፍ፣ በረሃብ እና በመቅሠፍት እንደ ቀጣሁ፣ እንዲሁ በግብጽ ምድር የሚኖሩትን እቀጣለሁ። 14በዚያ ለመኖር ወደ ግብጽ ምድር ከሄዱ እንኳን ወደ ይሁዳ አገር ተመልሰው በዚያ ይኖሩ ዘንድ ከሚወድዱ ከይሁዳ ቅሬታ ወገን የሚያመልጥና የሚቀር፣ ወደዚያም የሚመለስ የለም። ከዚህ ከሚያመልጥ በቀር ማንም አይመለስም።"15ከዚያም ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ፣ በዚያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፣ በግብጽ ምድር በጳጥሮስ የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፣ ታላቅ ጉባኤ ሆነው እንዲህ ሲሉ ለኤርምያስ መለሱለት። 16እነርሱም እንዲህ አሉ፣ "በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማህም። 17እኛና አባቶቻችን፣ ነገሥታቶቻችን፣ አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞች በኢየሩሳሌም አደባባይ እናደርገው እንደ ነበረ፣ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ የመጠጥንም ቊርባን እንድናፈስስላት ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን። ያን ጊዜ እንጀራ እንጠግባለን፣ ደግሞም የትኛውም ጥፋት ሳይደርስብን እንበለጽጋለን።18ለሰማይ ንግሥት ማጠንን ለእርስዋም የመጠጥን ቍርባን ማፍሰስን ከተውን ወዲህ ግን፣በድህነት ተሰቃይተናል፣ ደግሞም በሰይፍና በረሃብ አልቀናል።" 19ሴቶቹም እንዲህ አሉ፣ "እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት፣ የመጠጥንም ቍርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፣ ባሎቻችን ሳያውቊ ምስልዋን ለማበጀት እንጐቻ አድርገንላት ኖሮአልን? የመጠጥንም ቍርባን አፍስሰንላት ኖሮአልን?"20ኤርምያስም ይህን ቃል ለመለሱለት ሕዝብ ሁሉ፣ ለወንዶቹና ለሴቶቹ፣ ለሕዝቡም ሁሉ፣ መለሰላቸው እንዲህም አለ፣ 21"እናንተና አባቶቻችሁ፣ ነገሥታቶቻችሁና አለቆቻችሁም፣ የምድርም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን እግዚአብሔር ያሰበው በልቡም ያኖረው አይደለምን?22ከክፉ ልምምዳችሁ የተነሣ፣ ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኵሰት እግዚአብሔር ይታገሥ ዘንድ አልቻለም። ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ፣ መደነቂያ፣ መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነው የሚኖርባት የለም። 23እጣን ስላጠናችሁና በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁ፣ ድምፁንም ስላልሰማችሁ፣ በሕጉ፣ በሥርዓቱና በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፣ ዛሬ እንደሆነው ይህች ክፉ ነገር አግኝታችኋለች።"24ከዚያም ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ፣ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፣ "በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 25የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ፣ "ለሰማይ ንግሥት እንድናጥን፣ የመጠጥንም ቍርባን እንድናፈስስላት የተሳልነውን ስእለታችንን በእርግጥ እንፈጽማለን።" ብላችሁ በእጃችሁ አደረጋችሁት፤ እንግዲህ ስእለታችሁን አጽኑ፣ ፈጽሙትም።'26ስለዚህ፣ እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ 'ተመልከቱ፣ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፣ "ሕያው እግዚአብሔርን!" ተብሎ እንዳይጠራ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፤" ይላል እግዚአብሔር። 27ተመልከቱ፣ ለመልካም ሳይሆን ለጥፋት እተጋባቸዋለሁ። በግብጽ ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ። 28ከዚያም ከሰይፍ የሚያመልጡ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሆነው ከግብጽ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ። ሊቀመጡም ወደ ግብጽ ምድር የገቡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማናችን ቃል እንዲጸና ያውቃሉ።29ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚህች ስፍራ እንድቀጣችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፣' ይላል እግዚአብሔር። 30እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው፣ ነፍሱንም ለሚፈልገው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። ሁኔታው የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራንን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚፈልጉ እጅ አሳልፌ እንደሰጠሁት ይሆናል።"
1ኤርምያስ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ የነገረው ቃል ይህ ነበር። ይህም የሆነው በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ኤርምያስ እየነገረው በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ ነበር፤ እርሱም እንዲህ አለ፣ 2"ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፦ 3አንተ፣ 'እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ። በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፤ ዕረፍትንም አላገኘሁም' ብለሃል።4ልትለው የሚገባህ ይህንን ነው፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ የሠራሁትን፣ አሁን እያፈረስኩ ነው። የተከልሁትንም፣ እየነቀልሁ ነው። ይኽም በምድር ሁሉ ላይ እውነት ነው። 5ነገር ግን ለራስህ ታላቅ ነገር ተስፋ ታደርጋለህን? ያንን ተስፋ አታድርግ። በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ክፉ ነገርን እንደማመጣ ትመለከታለህና አትፈልገው፣ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።"
1ስለ አሕዛብ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። 2ስለ ግብጽ፦ "ይህ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በከርከሚሽ ስለ ነበረው ሠራዊት ነው። በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታው ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ኒካዑ ሠራዊት፦ 3ትንንሾቹን እና ትልልቆቹን ጋሻዎች አዘጋጁና ወደ ውጊያ ሂዱ። 4ፈረሰኞች ሆይ፣ ፈረሶችን ለጉሙና ውጡ፣ ራስ ቍርንም ደፍታችሁ ቁሙ። ጦርንም ሰንግሉ፣ የጦር ዕቃንም ልበሱ።5በዚህ የማየው ምንድነው? ወታደሮቻቸው ተሸንፈዋልና፣ በፍርሃት ተሞልተው ወደ ኋላ ተመለሱ። ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሸሹ። ድንጋጤ በሁሉ ቦታ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር። 6ፈጣኑ ሊሸሽ አይችልም፣ ወታደሮችም ሊያመልጡ አይችሉም። በሰሜን ተሰናከሉ፣ በኤፍራጥስ ወንዝ በኩል ደግሞ ወደቁ።7ይህ እንደ አባይ ወንዝ የሚነሣ፣ ውኃውም እንደ ወንዝ የሚናወጥለት ማን ነው? 8ግብጽ እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፣ ውኃውም እንደ ወንዙ ይናወጣል። እርሱም፣' እነሣለሁ ምድርንም ሁሉ እከድናለሁ። ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ ብሎአል። 9ፈረሶች ሆይ፣ ውጡ። ሠረገሎችም ሆይ፣ ንጐዱ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፋጥ ኃያላን፣ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ።'10ያ ቀን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፣ ደግሞም ጠላቶቹን እርሱ ራሱ ይበቀላቸዋል። ሰይፍ በልቶ ይጠግባል። ደማቸውንም ተሞልቶ ይጠጣል። ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።11ድንግሊቱ የግብጽ ሴት ልጅ ሆይ፣ ወደ ገለዓድ ውጪና መድኃኒት ውሰጂ። መድኃኒትን በራስሽ ላይ ማብዛትሽ ጥቅም የለሽ ነገር ነው። ለአንቺ የሚሆን ፈውስ የለም። 12ወታደሩ በወታደሩ ላይ ተሰናክሎ፣ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ እፍረትሽን ሰምተዋል። ምድር በለቅሶሽ ተሞልታለች።"13የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጥቶ የግብጽን ምድር ሲያጠቃ እግዚአብሔር ለነብዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው። 14"ለግብጽ ተናገሩ፣ በሚግዶልና በሜምፎስ ይሰማ። በጣፍናስ 'ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፣ ተነሥተህ ተዘጋጅ' ብለዋል።15የከፍታ አምላክሽ ለምን ሸሸ? በበሬ የተመሰለው ጣዖትሽስ ለምን አይቆምም? እግዚአብሔር ገፍትሮ ጥሎታል። 16እርሱ የሚሰናከሉትን ቊጥር ያበዛል። እያንዳንዳቸው ወታደሮች አንዱ በሌላው ላይ ይወድቃል። እነርሱም፣ "ተነሡ። ወደቤት እንጂድ። ወደገዛ ሕዝባችን፣ ወደ ተወለድንባት ምድር እንሂድ። ይህንን እየቀጠቀጠን ያለውን ሰይፍ ትተን እንሂድ።" ይላሉ። 17በዚያም፣ 'የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ያገኘውን ዕድል የሚያሳልፍ ኁከተኛ ብቻ ነው" ብለው ይናገራሉ።18"እኔ ሕያው ነኝና በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፣ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፣ እንዲሁ በእውነት ይመጣል፣ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ። 19አንቺ በግብጽ የምትቀመጪ ልጅ ሆይ፣ ለምርኮ የምትሄጂበትን ዕቃ አዘጋጂ። ሜምፎስ የምትሸበር ትሆናለችና፣ ማንም በዚያ የማይኖርባት እንድትሆን ትፈራርሳለችና።20ግብጽ እጅግ የተዋበች ጊደር ናት፣ ነገር ግን ከሰሜን በኩል የሚያሰቃይ መዥገር ይመጣባታል። 21በመካከሏም ያሉ ቅጥረኛ ወታደሮች እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፣ ነገር ግን እነርሱም እንዲሁ ይመለሱና ይሸሻሉ። የጥፋታቸው ቀን እየመጣባቸው ነውና፣ የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና በአንድነት አይቆሙም። 22ጠላቶቿ በእርሷ ላይ ይሰለፉባታልና ግብጽ እንደ እባብ ድምፅ ትጮኻለች፣ በደረቷም ተስባ ትሸሻለች። በመጥረቢያ እንደሚቆርጡ እንደ እንጨት ቈራጮች ሆነው ይመጡባታል።23በጣም ጥቅጥቅ ያሉ ቢሆኑም እንኳን ጫካዎቿን ይቈርጣሉ፣ ይላል እግዚአብሔር። ጠላቶቿ ሊቆጠሩ እስከማይችሉ ድረስ ከአንበጣ ይልቅ ብዙ ይሆናሉና። 24የግብጽ ሴት ልጅ እንድታፍር ትደረጋለች። ከሰሜን ለሚሆኑ ሕዝቦች እጅ ተላልፋ ትሰጣለች።"25የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የኖእ አሞንን፣ ፈርዖንንም፣ ግብጽንና አማልክቶችዋን፣ ፈርዖን ነገሥታቶችዋንና በእነርሱም የሚታመኑትን እቀጣለሁ። 26ነፍሳቸውንም በሚፈልጉ ሰዎች እጅ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡክደነፆር እንዲሁም በባርያዎቹም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ከዚያም በኋላ አንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች፣" ይላል እግዚአብሔር።27"ነገር ግን፣ አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ። አንተም እስራኤል ሆይ፣ አትደንግጥ። እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረከባት ምድር አድናለሁ። ከዚያም፣ ያዕቆብ ይመለሳል፣ ሰላም ያገኛል፣ በዋስትናም ይቀመጣል፣ የሚያስፈራራው ማንም አይገኝም። 28አንተ፣ ባርያዬ ያዕቆብ፣ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተን ያሰደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና አትፍራ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን አንተን ፈጽሜ አላጠፋህም። በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም።"
1ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ይህ ቃል ወደ እርሱ የመጣው ፈርዖን ጋዛን ሳይመታ በፊት ነው። 2"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ውኃ ከሰሜን ይነሣል። እነርሱም እንደሚያጥለቀልቅ ፈሳሽ ይሆናሉ! ከዚያም በምድሪቱና በመላዋ ሁሉ፣ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ይጐርፋሉ! ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለእርዳታ ይጮኻል፣ በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።3ከኃይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፣ ከሰረገሎቹና ከጎማዎቻቸውም መሸከርከር ሁከት የተነሣ፣ አባቶች በገዛ ራሳቸው ድካም ምክንያት ልጆቻቸውን አይረዱም። 4ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የቀሩትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና የሚቆርጥ ቀን ስለሚመጣ ነው። እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ቅሬታ ያጠፋልና።5ራሰ ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቶአል። አስቀሎናን በተመለከተ፣ በሸለቋቸው የተተዉት ሕዝብ ዝም እንዲሉ ይደረጋሉ። እስከ መቼ ድረስ በለቅሶ ራሳችሁን ትነጫላችሁ? 6ወዮ፣ የእግዚአብሔር ሰይፍ! ዝም እስከምትል ምን ያክል ትቆያለህ? ወደ ሰገባህ ተመለስ! ቊም ደግሞም ጸጥ በል። 7እግዚአብሔር አዝዞሃልና እንዴት ዝም ልትል ትችላለህ። በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ ጥቃት እንድትፈጽም አዘጋጅቶሃልና።"
1ስለ ሞዓብ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ናባው ጠፍታለችና ወዮላት። ቂርያታይም ተይዛለች አፍራለችም። ምሽጓ ተደምስሷል፣ ተዋርዷልም። 2ከእንግዲህ ወዲህ ሞዓብ ትምክሕት የላትም። በሐሴቦን ያሉ ጠላቶቿ በእርሷ ላይ ጥፋትን አሲረዋል። 'ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት። ማድሜንም እንዲሁ ትጠፋለች፣ ሰይፍም ይከታተልሻል።' ብለዋል።3አድምጡ! መፍረስና ታላቅ ጥፋት ያለበት የጩኸት ቃል ከሖሮናይም ተሰማ። 4ሞዓብ ጠፍታለች። ልጆችዋም ጩኸታቸውን አሰምተዋል። 5በሉሒት ኮረብታ ለቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉ፣ ከጥፋቱም የተነሣ፣ በሖሮናይምም ቍልቍለት ጩኸትን ሰምተዋል።6ሸሹ! ሕይወታችሁን አድኑና በምድረ በዳ እንዳለ ቊጥቋጦ ሁኑ። 7በሥራሽና በኃብትሽ ታምነሻልና፣ አንቺ ደግሞ ትያዢያለሽ። ከዚያም፣ ካሞሽ ከካህናቱና ከመሪዎቹ ጋር በአንድነት ወደ ምርኮ ይሄዳል።8አጥፊው ወደየከተማው ሁሉ ይመጣል፣ አንዲትም ከተማ አታመልጥም። ስለዚህ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ሸለቆው ይጠፋል፣ ሜዳውም ይበላሻል። 9በእርግጥም በርራ እንድትጠፋ ለሞዓብ ክንፍ ስጡአት። ከተሞችዋ በውስጣቸው አንድም የማይኖርባቸው ወና ይሆናሉ። 10የእግዚአብሔርን ሥራ በስንፍና የሚሠራ ርጉም ይሁን! ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚከለክል ርጉም ይሁን!11ሞዓብ ከወጣትነቱ ጀምሮ ደህንነት ይሰማው ነበር። እርሱ ከዕቃ ወደ ዕቃ ተገላብጦ እንደማያውቀው ወይኑ ነው። ወደ ምርኮም ሄዶ አያውቅም። ስለዚህ ጣዕሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ መልካም ነው፣ መዓዛውም አልተለወጠም። 12ስለዚህ ተመልከቱ፣ የሚያገላብጡትን ሰዎች የምልክበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም እያፈሰሱ ጋኖቹን ባዶ ያደርጋሉ፣ መስቴዎቹንም ይሰብራሉ።13የእስራኤል ቤት ከታመነበት ቤተል እንዳፈረ ሁሉ፣ እንዲሁ ሞዓብ ከታመነበት ካሞሽ ያፍራል። 14እናንተ፣ 'እኛ ወታደሮች ነን፣ ጽኑዓን ተዋጊዎች ነን' እንዴት ትላላችሁ?15ሞዓብ ይፈርሳል፣ ከተሞቹም ጥቃት ይፈጸምባቸዋል። የተመረጡትም ጕልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል። ይህ የንጉሡ አዋጅ ነው! ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። 16የሞዓብ ጥፋት ሊመጣ ቀርቦአል፤ መከራውም እጅግ ይፈጥናል። 17በሞዓብ ዙሪያ ያላችሁ ሁሉ፣ አልቅሱ። ዝናውንም የምታውቁ ሁሉ፣ 'ብርቱው በትር፣ የከበረው ሽመል ተሰብሯልና ወዮለት' ብላችሁ አልቅሱለት።18በዲቦን የምትኖሪ ሴት ልጅ ከክብር ስፍራሽ ውረጂና በደረቅ መሬት ላይ ተቀመጪ። ሞዓብን የሚያጠፋው፣ ምሽግሽንም የሚሰብረው ወጥቶብሻልና። 19በአሮዔር የምትኖሩ ሕዝቦች በመንገድ አጠገብ ቆማችሁ ተመልከቱ። እየሸሹ ያሉትንና የሚያመልጡትን ጠይቊ። 'ምን ተፈጠረ?' በሉ። 20ሞዓብም ፈራርሷልና አፈረ። አልቅሱ፣ ጩኹ፣ ለእርዳታም ተጣሩ። ሞዓብ እንደ ተዘረፈ በአርኖን አጠገብ ለሰዎች አውሩ።21አሁን በኮረብታማው ገጠር ላይ ባሉት በሖሎን፣ በያሳ፣ በሜፍዓት ላይ፣ 22በዲቦን፣ በናባው፣ በቤት ዲብላታይም ላይ፣ 23በቂርያታይም፣ በቤትጋሙል፣ 24በቤትምዖን ላይ፣ በቂርዮት፣ በባሶራ፣ እና በሞዓብ ምድር ባሉ የቅርብና ሩቅ ከተሞች ሁሉ ላይ ቅጣት መጥቶአል። 25የሞዓብ ቀንድ ተቈረጠ፤ ክንዱም ተሰበረ፣ ይላል እግዚአብሔር።26በእኔ በእግዚአብሔር ላይ ኰርቷልና አስክሩት። እንግዲህ ሞዓብ በገዛ ራሱ ትውከቱ ላይ በጥላቻ እጆቹን ያጨበጭባል፣ ደግሞም መሳለቂያ ይሆናል። 27እስራኤል ለአንተ መሳለቂያህ አልሆነምን? ወይስ ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ሁሉ ራስህን እንድትነቀንቅ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን?28እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፣ ከተሞችን ትታችሁ በቋጥኝ ውስጥ ተቀመጡ። በዐለታማ ገደል አፋፍ ቤትዋን እንደምትሠራ ርግብ ሁኑ። 29እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ ትምክህቱም፣ ስለ ኩራቱም፣ ራሱን ስለማክበሩም፣ ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል።30ምንም ሆኖ የማይቆጠረውን የድንፋታ ንግግሩን እኔ ራሴ አውቃለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ፉከራው ምንም አልሠራም። 31ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፣ በኃዘኔታ ለመላዋ ሞዓብ እጮኻለሁ። ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ። 32አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ፣ ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ! ቅርንጫፎችሽ የጨው ባሕርን ተሻግረው ወደ ኢያዜር ባሕር ደርሰዋል። አጥፊዎች በሰብልሽና በወይንሽ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።33ክብረ-በዓላዊ ሐሤትና ፍንደቃ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል። የወይን ጠጁን ከመጥመቂያው አጥፍቻለሁ። ጠማቂውም በደስታ እልልታ አይጠምቅም። እልልታቸውም የደስታ እልልታ አይሆንም።34ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤልያሊና፣ እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፤ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፤ የኔምሬም ውኃዎች ደርቀዋልና። 35በኮረብታው መስገጃ ላይ የሚሠዋውን ለአማልክቱም የሚያጥነውን ከሞዓብ ፍጻሜያቸውን አደርጋለሁ ይላል እግዚአብሔር።36ልቤ ለሞዓብ እንደ እንቢልታ ይጮኻል። ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ይጮኻል። ያገኙት ትርፋቸው ጠፍቶባቸዋልና። 37ራስ ሁሉ መላጣ፣ ጢምም ሁሉ የተላጨ ነውና። በእጅም ሁሉ ላይ ክትፋት በወገብም ላይ ማቅ አለና።38በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ፣ በእያንዳንዱም የተደላደለ ጣራ እና በሁሉም የሞዓብ አደባባዮች ላይ ለቅሶ አለ። ሞዓብን ማንም እንደማይፈልጋቸው የሸክላ ዕቃዎች ሰብሬአለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር። 39እንዴት ተገለበጠ! ከለቅሶም የተነሣ ሞዓብ እያፈረ ጀርባውን እንዴት መለሰ! ብላችሁ አልቅሱ። ስለዚህ ሞዓብ በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና ድንጋጤ ይሆናል።"40እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ጠላት እንደ ንስር እየበረረ፣ ክንፉንም በሞዓብ ላይ እየዘረጋ ይመጣል። 41ከተሞቹ ተይዘዋል፣ ምሽጎቹም ተይዘዋል። በዚያም ቀን የሞዓብ ወታደሮች ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።42ስለዚህ ሞዓብ በእኔ በእግዚአብሔር ላይ እብሪተኛ ሆኗልና ሕዝብ ከመሆን ይጠፋል። 43በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፣ ፍርሃትና ጉድጓድ፣ ወጥመድም በእናንተ ላይ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር። 44በፍርሃት የሸሸ በጕድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጉድጓድም የወጣ በወጥመድ ይያዛል፤ በሞዓብ ላይ የምበቀልበትን ዓመት አመጣበታለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።45የሸሹ ያለ ምንም ብርታት ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፤ እሳት ከሐሴቦን፣ ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአልና፣ የሞዓብንም ማዕዘን የሤትንም ልጆች አናት በልቶአልና።46ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ተደምስሰዋል፣ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፣ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና። 47ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የሞዓብን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።" የሞዓብ ፍርድ እዚህ ላይ ያበቃል።
1ስለ አሞን ልጆች፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እስራኤል ልጆች የሏትምን? ወይስ የትኛውንም ነገር ከእስራኤል የሚወርስ የላትምን? ሚልኮም ጋድን ለምን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቿ ላይ ስለ ምን ተቀመጠ? 2ስለዚህ ተመልከቱ፣ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የጦርነት ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፣ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ። እስራኤልም የወረሷትን ትወርሳለች፣" ይላል እግዚአብሔር።3"ሐሴቦን ሆይ፣ ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺላት! እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ጩኹ! ማቅ ልበሱ። ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፣ ማቅም ታጠቁ፣ አልቅሱም፣ በቅጥሮችም መካከል ተሯሯጡ። 4ማን ይመጣብኛል ብለሽ በብርታትሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፣ በሸለቆችሽ፣ ውኃ በሚያረካቸው ሸለቆችሽ፣ ስለ ምን በብርታትሽ ትመኪያለሽ?5ተመልከቺ፣ ሽብርን አመጣብሻለሁ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ይህ ሽብር በዙሪያሽ ከከበቡሽ ሁሉ ዘንድ ይሆናል። እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትበተናላችሁ። የሚሸሹትንም የሚሰበስብ አይኖርም። 6ነገር ግን ከዚያ በኋላ የአሞንን ልጆችን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።"7ስለ ኤዶምያስ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በውኑ በቴማን ከእንግዲህ ጥበብ አይገኝምን? ማስተዋል ካላቸውስ መልካም ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸው ተበላሽቷልን? 8ሽሹ! ተመለሹ! እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ፣ በጥልቅ ውስጥ ተቀመጡ። የዔሳውን ጥፋት እርሱን በምቀጣበት ጊዜ አመጣበታለሁና9የወይን አዝመራ ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ቃርሚያውን አይተውልህምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፣ የሚሠርቁት እስኪበቃቸው ድረስ አይደለምን? 10እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት። የተሸሸገበትንም ስፍራዎች ገለጥሁ። ስለዚህ ይሸሸግ ዘንድ አይችልም። ልጆቹ፣ ወንድሞቹ፣ እንዲሁም ጎረቤቶቹ ጠፍተዋል፤ እርሱም የለም። 11ድሀ አደጎችህን ተዋቸው። እኔም ለሕይወታቸው እንክብካቤ አደርጋለሁ፤ መበለቶችህም በእኔ ሊታመኑ ይችላሉ።"12እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "ተመልከቱ ያልተገባቸው ሰዎች ጽዋውን በእርግጥም ሊጠጡት ይገባቸዋል። አንተም ሳትቀጣ የምትቀር ይመስልሃልን? በእርግጥ ትጠጣለህ እንጂ ያለ ቅጣት አትቀርም። 13ባሶራ መደነቂያና መሰደቢያ፣ መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። ከተሞችዋም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።14ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ፣ መልእክተኛም በአሕዛብም መካከል ተልኳል፣ 'ተሰብሰቡ፣ እርስዋንም አጥቊ። ለጦርነትም ተነሡ' ይላል። 15"ተመልከቱ፣ በንጽጽር ስትታይ በአሕዛብ ዘንድ የተጠቃህ፣ በሰዎችም ዘንድ የተናቅህ አድርጌሃለሁ።16በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ፣ ድፍረትህና የልብህ ኵራት አታልለውሃል። ቤትህን ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፣ ከዚያ አወርድሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።17ኤዶምያስም የሚያልፉባት ሁሉ እስኪደነቁ ድረስ መሸበሪያ ትሆናለች። ስለ መጣባትም መቅሠፍት ሁሉ እንዲህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ተደናግጠው ያፍዋጩባታል። 18"ሰዶምና ገሞራ፣ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ከተሞች እንደ ተገለበጡ፣" ይላል እግዚአብሔር፣ "እንዲሁ በዚያ ሰው አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።19ተመልከቱ፣ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት እንደ አንበሳ ይወጣል፤ የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?20"ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፣ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ አድም። በእውነት ትንንሽ መንጎች ሳይቀሩ ይጐተታሉ። በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል።21ከመውደቃቸው ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች። የጩኸታቸውም ድምፅ በቀይ ባሕር ተሰማ። 22ተመልከቱ፣ አንዱ መጥቶ እንደ ንስር ወጥቶ ያጠቃል፣ እያንዣበበ ክንፉን በባሶራ ላይ ይዘረጋል። ያን ጊዜ በዚያ ቀን፣ የኤዶምያስ ወታደሮች ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።"23ስለ ደማስቆ፣ "ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ። ቀለጡ! ሊረጋጋ በማይችል ባሕር ላይ ኅዘን አለ። 24ደማስቆ እጅግ ደከመች። ትሸሽም ዘንድ ዘወር አለች፤ ሽብር ያዛት፣ እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት። 25ሕዝቦቿም፣ 'የተመሰገነችው ከተማ፣ የደስታዬ ከተማ፣ ስፍራውን ሳትለቅቅ እንዴት ቀረች?' ይላሉ።26ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፣ በዚያም ቀን ተዋጊዎቿ ሁሉ ይጠፋሉ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።" 27"በደማስቆም ቅጥር ላይ እሳት አነድዳለሁ፣ የወልደ አዴርንም አዳራሾች ትበላለች።"28የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታ ስለ ቄዳርና ስለ አሶር መንግሥታት፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፣ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ። 29ጦር ሠራዊቱ ድንኳናቸውንና መንጋቸውን ይወስዳል፤ መጋረጆቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ። በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው፣ 'ሽብር በዙሪያቸው ሁሉ አለ!"30ሽሹ! በሩቅ ቦታም ተቅበዝበዙ! እናንተ በአሶር የምትኖሩ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፣ አሳብም አስቦባችኋልና በጥልቅ ውስጥ ተቀመጡ፣ ይላል እግዚአብሔር። ሽሹ! ዙሩና ተመለሱ! 31ዕርፊት ወዳለበት በዋስትናም ወደ ተቀመጠው፣ ደጅና መወርወሪያ ወደሌለው ብቻውንም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ውጡ፣ ተነሡ! አጥቊ!።32ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ፣ የእንስሶቻቸውም ብዛት በጦርነት ይማረካል። ጠጉራቸውንም በዙሪያ የሚላጩትን ሰዎች ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከየዳርቻቸውም ሁሉ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። 33አሶርም የቀበሮ መኖሪያና የዘላለም ባድማ ትሆናለች። በዚያም ሰው አይኖርም፣ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም።"34ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ይህ የሆነው በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ ነው። እንዲህም አለ፣ 35"የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዋና የኃይላቸው መሣሪያ የሆነውን የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ። 36ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፣ የኤላምን ሕዝብ ወደ እነዚያ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ። ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች የማይበተኑበት ሕዝብ አይገኝም።37ስለዚህ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን በሚሹአት ፊት ኤላምን አስደነግጣለሁ። ክፉ ነገርን እርሱም ጽኑ ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር። እስካጠፋቸውም ድረስ በኋላቸው ሰይፍ እሰድድባቸዋለሁ። 38ከዚያም፣ ዙፋኔንም በኤላም አኖርና ንጉሡን ከእነአለቆቹ አጠፋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። 39ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
1እግዚአብሔር ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣ 2"በአሕዛብ መካከል ተናገሩና እንዲሰሙ አድርጉ። ዓላማውን አንሡና እንዲሰሙ አውሩ። አትደብቁት። 'ባቢሎን ተወሰደች። ቤል አፈረ። ሜሮዳክ ደነገጠ። ጣዖቶችዋ አፈሩ። ምስሎችዋ ደነገጡ' በሉ።3ሕዝብ ከሰሜን ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፣ የሚቀመጥባት እንዳይገኝባት። ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ በውስጥዋ አይኖሩም። ሸሽተው ሄደዋል። 4በእነዚያም ወራት፣ በዚያም ጊዜ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ሆነው እያለቀሱና አምላካቸውን እግዚአብሔርን እየፈለጉ ይመጣሉ። 5ፊታቸውንም ወደጽዮን አቅንተው ይሄዳሉ። ከቶ በማይረሳ በዘላለም ቃል ኪዳን ወደ እግዚአብሔር ሄደው ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያገኛኛሉ።6ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል። እረኞቻቸው በተራሮች ላይ አስተው አቅበዘበዟቸው፤ ከኮረብታ ወደ ኮረብታ አለፉ። ሄዱ፣ የኖሩበትንም በረታቸውን ረሱ። 7ሲሄዱባቸው ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው። ጠላቶቻቸውም፣ 'በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፣ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ፣ ኃጢአት ስለ ሠሩ እኛ አልበደልንም' አሉ።8ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ ወደ ከከለዳውያን ድር ውጡ፤ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ። 9ተመልከቱ፣ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አስነሣለሁ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ። በእርስዋም ላይ ይሰለፋሉ። ባቢሎን ከዚያ ስፍራ ትወሰዳለች። ፍላጾቻቸውም ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ተካነ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው። 10የከላውዴዎንም ምድር ትበዘበዛለች። የሚበዘብዙአትም ሁሉ ይጠግባሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።11ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ፣ ደስ ይበላችሁ፤ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ሐሤት እያደረጋችሁ ዝለሉ፤ እንደ ብርቱ ፈረሶች አሽካኩ። 12እንዲሁ እናታችሁ በእጅጉ ታፍራለች፤ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች። ተመልከቱ፣ በአሕዛብ መካከል አነስተኛይቱ ትሆናለችና፣ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፣ በረሀም ትሆናለች። 13ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይኖርባትም። በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፣ በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።14በባቢሎን ላይ በዙሪያዋ ተሰለፉ። እናንተ ቀስትን የምትገትሩ ሰዎች ሁሉ። በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርታለችና ወርውሩባት ፍላጾችንም አትመልሱ። 15የእግዚአብሔር በቀል ነውና ድል እያደረጋችሁ በዙሪያዋ ጩኹባት። እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ፣ ቅጥሮችዋም ፈረሱ ይህ የእግዚአብሔር በቀል ነውና። እርስዋን ተበቀሉ! እንደ ሠራችውም ሥሩባት።16ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ። ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።17እስራኤል ባዝኖ የተበተነ በግ እና አንበሶች ያሳደዱት ነው። መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፤ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው። 18ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ የአሦርን ንጉሥ እንደ ቀጣሁ፣ እንዲሁ የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እቀጣለሁ።19እስራኤልንም ወደ ማሰማርያ ምድሩ እመልሳለሁ፤ በቀርሜሎስና በባሳንም ላይ ይሰማራል። በኤፍሬም ተራራና በገለዓድ ላይ ይጠግባል። 20በእነዚያም ቀኖች፣ በዚያ ጊዜ፣ እነዚህን ያስቀረኋቸውን ይቅር እላቸዋለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የእስራኤል በደል የይሁዳም ኃጢአት ይፈለጋል ምንም አይገኝም።"21"በምራታይም ምድር ላይ፣ በፋቁድም በሚኖሩት ላይ ተነሥና ውጣ፤ ግደላቸው ፈጽመህም አጥፋቸው፤ ይላል እግዚአብሔር፣ እንዳዘዝሁህም ሁሉ አድርግ። 22የሰልፍና የታላቅ ጥፋት ውካታ በምድሪቱ ላይ አለ።23የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ደቀቀ እንዴትስ ተደመሰሰ። ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት መሸበሪያ ሆነች። 24ባቢሎን ሆይ፣ አጥምጄብሻለሁ። አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል።25እግዚአብሔር ዕቃ ቤቱን ከፍቶ የቍጣውን ዕቃ ጦር አውጥቶአል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በከለዳውያን ምድር ይሠራ ዘንድ ሥራ አለውና። 26ከየበኩሉ በእርስዋ ላይ ጥቃትን ፈጽሙ። ጎተራዎችዋንም ክፈቱ። እንደ ክምርም አድርጓት፣ ፈጽማችሁም አጥፉአት። አንዳችም አታስቀሩላት።27ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ። ወደ መታረድም ስፍራ ላኳቸው። ቀናቸው፣ የመቀጣታቸው ጊዜ፣ ደርሶአልና ወዮላቸው! 28የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል፣ የመቅደሱንም በቀል በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን አገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።"29ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው። በዙሪያዋ ስፈሩባት፣ አንድም አያምልጥ። በእስራኤል ቅዱስ ላይ በእግዚአብሔር ላይ ኰርታለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት። እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት። 30ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፣ በዚያም ቀን ሰልፈኞችዋ ሁሉ ይጠፋሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።"31ትዕቢተኛው ሆይ፣ አንተን የምቀጣበት ጊዜ፣ ቀንህ ደርሶአልና በአንተ ላይ ነኝ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። 32ስለዚህ ትዕቢተኞቹ ተሰናክለው ይወድቃሉ። የሚያነሣቸው ማንም አይኖርም። በከተሞቻቸውም ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፤ በዙሪያቸው ያለውን ሁሉ ትበላለች።33የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ተጨቊነዋል። የማረኳቸውም ሁሉ አሁን ድረስ በኃይል ይዘዋቸዋል፤ ይለቅቁአቸውም ዘንድ እንቢ ብለዋል። 34የሚቤዣቸው ብርቱ ነው። ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። ምድርንም ያሳርፍ ዘንድ፣ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ሙግታቸውን ፈጽሞ ይሟገታል።35ሰይፍ በከለዳውያንና በባቢሎን በሚኖሩ ላይ፣ በአለቆችዋና በጥበበኞችዋ ላይ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር። 36ጥንቆላን በሚናገሩት ላይ ሰይፍ አለ፣ ራሳቸውን ሰነፎች አድርገው ይገልጣሉ። ሰይፍም በጦረኞችዋ ላይ አለ፣ እነርሱም በሽብር ይሞላሉ። 37ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ በመካከልዋም ባሉት በልዩ በልዩ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፣ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ። ሰይፍ በቤተ መዛግብቷ ላይ አለ፣ ለብዝበዛም ይሆናል።38እርስዋ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናት፣ እነርሱም በጣዖታት ይመካሉና ድርቅ በውኆችዋ ላይ ይሆናል እነርሱም ይደርቃሉ። 39ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊት ከተኵላዎች ጋር ይኖሩባታል፣ ሰጐኖችም ይኖሩባታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘላለም አይኖርባትም፣ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም። 40ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፣ ይላል እግዚአብሔር፣ እንዲሁ ሰው በዚያ አይኖርም የሰውም ልጅ አይኖርባትም።"41"ተመልከቱ፣ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፣ ታላቅ ሕዝብና ብዙ ነገሥታትም ከምድር ሩቅ ዳርቻዎች ይነሣሉ። 42ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ። ጨካኞች ናቸው ምሕረትም አያደርጉም። ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፣ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ። 43የባቢሎን ንጉሥ ወሬአቸውን ሰምቶአል፣ እጁም ዝላ ደክማለች። ጭንቀትም ይዞታል፣ ምጥ ወላድ ሴትን እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞታል።44ተመልከቱ! ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት ውስጥ እንደ አንበሳ ይወጣል። የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ። እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?45ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፣ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ። በእውነት የመንጋ ትናንሾች ሳይቀሩ ይጎተታሉ። በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል። 46ከባቢሎን መያዝ ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፤ ጩኸትም በአሕዛብ መካከል ዘንድ ተሰማ።"
1"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ተመልከቱ፣ በባቢሎን ላይና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ አጥፊውን ነፋስ አስነሣለሁ። 2በባቢሎንም ላይ የውጪ ሰዎች እልካለሁ። እነርሱም ይበትኗታል፣ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፤ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል።3በወርዋሪው ላይ በጥሩርም በሚነሣው ላይ ቀስተኛው ቀስቱን ይገትር፤ ለጐበዛዝትዋ አትዘኑ፣ መላውን ሠራዊትዋንም አጥፉ። 4የቆሰሉት ሰዎች በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፣ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉና።5ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፣ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላኩ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ አልተጣለም። 6ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ራሳችሁን አድኑ። በበደልዋ አትጥፉ። የእግዚአብሔር የበቀል ጊዜ ነውና። እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታል።7ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፣ አሕዛብም ከጠጅዋ ጠጥተዋል፤ ስለዚህ አሕዛብ እብድ ሆነዋል። 8ባቢሎን በድንገት ወድቃ ጠፍታለች። ለእርሷ አልቅሱላት! ትፈወስም እንደ ሆነ ለቊስልዋ መድኃኒት ውሰዱላት።9'ባቢሎንን ለመፈወስ ተመኘን፣ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም። ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፣ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ ምድራችን እንሂድ።' 10እግዚአብሔር ጽድቃችንን አውጥቶአል። ኑ፣ በጽዮን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ሥራ እንናገር።'11ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አዘጋጁ። እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚብሔር በቀል፣ የመቅደሱ መጥፊያ በቀል ነውና። 12በባቢሎን ቅጥር ዓላማውን አንሡበት፣ ጥበቃን አጽኑ። ተመልካቾችን አቁሙ፣ ከከተማዋ የሚወጡትን ለመያዝ ድብቅ ጦር አዘጋጁ። እግዚአብሔር በባቢሎን በሚኖሩት ላይ የተናገረውን አስቦአልና፣ አድርጎአልምና።13አንቺ በብዙ ውኃ አጠገብ የተቀመጥሽ፣ በመዝገብም የበለጠግሽ፣ እንደ ስስትሽ መጠን ፍጻሜሽ ደርሶአል። 14የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ምሏል፣ 'በእውነት ሰዎችን እንደ አንበጣ እሞላብሻለሁ፣ እነርሱም የጦርነት ጩኸት ያነሡብሻል።'15ምድርን በኃይሉ ፈጠረ፤ ዓለሙን በጥበቡ መሠረተ። ሰማያትንም በማስተዋሉ ዘረጋ። 16ድምጹን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፣ ከምድርም ዳር ደመናትን ከፍ ያደርጋል። ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፣ ነፍስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።17ሰው ሁሉ እውቀት አጥቶ እንደ እንስሳ ሆኗል፤ እያንዳንዱ አንጥረኛ ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል። ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፤ እስትንፋስም የላቸውምና። 18እነርሱም ምናምንቴና፣ የቀልድ ሥራ ናቸው፤ በሚቀጡበት ጊዜ ይጠፋሉ። 19የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፣ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።20አንቺ መዶሻዬና የጦር መሣሪያዬ ነሽ። በአንቺ አሕዛብን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም መንግሥታትን አጠፋለሁ። 21በአንቺ ፈረሱንና ሠረገላውን እሰባብራለሁ፤22በአንቺም በላዩ የሚቀመጡትን ወንድ እና ሴት እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እሰባብራለሁ። በአንቺም ጐልማሳውንና ልጃገረዲቱን እሰባብራለሁ። 23በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አለቆችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ።24በጽዮን በዓይናችሁ ፊት ስለሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ፍዳቸውን እከፍላለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።25"ተመልከት፣ አንተ ምድርን ሁሉ የምታጠፋ አጥፊ ተራራ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር። እጄንም እዘረጋብሃለሁ፣ ከድንጋዮችም ላይ አንከባልልሃለሁ። የተቃጠለም ተራራ አደርግሃለሁ። 26ከአንተም ለማዕዘንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይ አይወስዱም፣ ለዘላለምም ባድማ ትሆናለህ፣ ይላል እግዚአብሔር።27"በምድር ላይ ዓላማን አንሡ። በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ። እንዲያጠቋት አሕዛብን አዘጋጁባት፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ሰብስቡባት፣ አለቃንም በላይዋ አቁሙ። እንደ ጠጉራም አንበጣ ኩብኩባ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ። 28አሕዛብን የሚዶንንም ነገሥታት አለቆችንም ሹማምቶችንም ሁሉ የግዛታቸውንም ምድር ሁሉ አዘጋጁባት።29ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጣለች ታመመችም።30የባቢሎን ወታደሮች መዋጋትን ትተዋል፤ በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል። ኃይላቸውም ጠፍቶአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል። ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፣ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል። 31ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች መልካምዎችዋም እንደ ተያዙ፣ ቅጥርዋም በእሳት እንደ ተቃጠለ፣ ሰልፈኞችም እንደ ደነገጡ 32ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ወሬኛው ወሬኛውን፣ መልእክተኛውም መልእክተኛውን ሊገናኝ ይሮጣል።"33የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ አውድማ እንደ ተረገጠ ጊዜ፣ እንዲሁ የባቢሎን ልጅ ናት። ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስላታል።34ኢየሩሳሌም፣ 'የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ። አድርቆ አሟጠጠኝ፣ እንደ ባዶ የሸክላ ዕቃም አደረገኝ። እንደ ዘንዶም ዋጠኝ። ከሚጣፍጠውም ምግቤ ሆዱን ሞላ። እኔንም ወደ ውጪ ጣለኝ።' አለች። 35የጽዮን ነዋሪዎች እንዲህ ይላሉ፣ 'በእኔና በሥጋዬ የተደረገ ግፍ በባቢሎን ላይ ይሁን።' ኢየሩሳሌምም፣ 'የሚፈስሰው ደሜ ጥፋት በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ ይሁን" ትላለች።36ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቺ፣ እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ። ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ፣ ምንጭዋንም አደርቀዋለሁ። 37ባቢሎንም የድንጋይ ቊልልና የቀበሮ ማደሪያ፣ መደነቂያም ማፍዋጫም ትሆናለች፤ የሚቀመጥባትም ሰው አይገኝም።38በአንድነትም እንደ አንበሶች ያገሣሉ። እንደ አንበሳም ደቦሎች ያጕረመርማሉ። 39በስስት በሞቃቸው ጊዜ ደስ እንዲላቸው፣ ለዘላለምም አንቀላፍተው እንዳይነቁ፣ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ፣ አሰክራቸውማለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። 40እንደ ጠቦቶችና እንደ አውራ በጎች እንደ አውራ ፍየሎችም ወደ መታረድ አወርዳቸዋለሁ።"41"ባቢሎን እንዴት ተያዘች! የምድርም ሁሉ ምስጋና እንዴት ተወሰደች። ባቢሎንም በአሕዛብ መካከል መደነቂያ እንዴት ሆነች። 42ባሕር በባቢሎን ላይ ወጣ! በሞገዱም ብዛት ተከደነች።43ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፣ ሰውም የማይኖርበት፣ የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ። 44በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ፤ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፣ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይሰበሰቡም። የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል።"45"ሕዝቤ ሆይ፣ ከመካከልዋ ውጡ። እያንዳንዳችሁም ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ራሳችሁን አድኑ። 46በምድርም ከሚሰማ ወሬ የተነሣ አትፍሩ፣ ልባችሁም የዛለ አይሁን፤ በአንድ ዓመት ወሬ ይመጣል፣ ከዚያም በኋላ በሌላው ዓመት ወሬ፣ በምድርም ላይ ግፍ ይመጣል፣ አለቃም በአለቃ ላይ ይነሣል።47ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል። ምድርዋም ሁሉ ታፍራለች፣ ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ። 48አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና ሰማይና ምድር በእነርሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢሎን እልል ይላሉ፣ ይላል እግዚአብሔር። 49ባቢሎንም ከእስራኤል ተወግተው የሞቱት እንዲወድቁ እንዳደረገች፣ እንዲሁ በባቢሎን ከምድሩ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ይወድቃሉ።"50"ከሰይፍ ያመለጣችሁ፣ ሂዱ! ተረጋግታችሁ አትቁሙ። እግዚአብሔርን ከሩቅ ጥሩት፤ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ። 51ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብተዋልና ነውር ፊታችንን ከድኖታል።"52"ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ የተቀረጹትን ምስሎችዋ የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጉት ያንቋርራሉ። 53ባቢሎን ምንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፣ የኃይልዋንም ምሽጎች ብታጸና፣ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፣ ይላል እግዚአብሔር።"54ከባቢሎን ጩኸት፣ ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰምቶአል። 55እግዚአብሔር ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፣ ከእርስዋም ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፤ ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኆች ይተምማል፣ የድምፃቸውም ጩኸት በብርቱ ተሰምቶአል። 56አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፣ ኃያላኖችዋ ተያዙ፣ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እግዚአብሔር ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፣ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።57"መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋን፣ አለቆችዋንና ሹማምቶችዋን፣ ወታደሮችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘላለምም አንቀላፍተው አይነቁም፣ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።" 58"የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰፊው የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ረጃጅሞችም በሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ የወገኖችም ድካም ከንቱ ትሆናለች፣ የአሕዛብም ሥራ ሁሉ ለእሳት ትሆናለች፤ እነርሱም ይደክማሉ።"59የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው፣ ያን ጊዜ ሠራያ የቤት አዛዥ ነበረ። 60በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፣ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፣ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው።61ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፣ "ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ ይህ ቃል ሁሉ መነበቡን እርግጠኛ ሁን። 62አንተም ደግሞ፣ 'ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፣ ለዘላለምም ባድማ እንድትሆን ታጠፋት ዘንድ በዚህች ስፍራ ላይ ተናግረሃል' በል።63ከዚያም ይህንን ጥቅልል መጽሐፍ ማንበብ ከፈጸምህ በኋላ፣ ድንጋይን እሰርበትና በኤፍራጥስ ወንዝ መሃከል ጣለው። 64አንተ፣ 'እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፣ አትነሣምም" በል። የኤርምያስ ቃል እዚህ ላይ ያበቃል።
1ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም አሚጣል የምትባል ነበረች፤ እርሷ የሊብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። 2ኢዮአቄምም እንዳደረገ ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ። 3ከፊቱም አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በእግዚአብሔር ቍጣ፣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና። ከዚያም ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።4ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ መጥተው ከበቡአት፤ በዙሪያዋም ቅጥር የሚሆን ግድግዳ ገነቡ። 5ስለዚህ ከተማይቱ እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴቅያስ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ድረስ ተከብባ ነበር።6በአራተኛውም ወር፣ በዐመቱ ዘጠነኛ ቀን፣ በከተማይቱ ራብ ጸንቶ ነበር። ለምድሪቱም ሰዎች እንጀራ ታጣ። 7ከተማይቱም ተሰበረች፣ ተዋጊዎች ሁሉ ሸሹ፣ በሁለቱም ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ። ስለዚህ በዓረባ መንገድ ሄዱ። 8ነገር ግን የከለዳውያን ሠራዊት ንጉሡን ተከታተሉት፣ በኢያሪኮም ሜዳ ሴዴቅያስን ያዙ። ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ተበትነው ነበር።9ንጉሡንም ይዘው የባቢሎን ንጉሥ ወዳለባት በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ። 10የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በዐይኖቹ ፊት ገደላቸው፣ የይሁዳንም አለቆች ሁሉ ደግሞ በሪብላ ዐረዳቸው። 11ከዚያም የሴዴቅያስን ዐይኖች አወጣ፣ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው። ወደ ባቢሎንም ወሰደው፣ እስኪሞትም ድረስ በግዞት ቤት አኖረው።12በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ በባቢሎን ንጉሥ ፊት የቆመው የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። 13የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ፣ ታላላቆችን ቤቶች ሁሉ፣ በእሳት አቃጠለ። 14ከዘበኞቹም አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት ሁሉ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ሁሉ ዙሪያዋን አፈረሱ።15የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን የሕዝቡን ድኆች፣ በከተማም ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፣ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፣ የሕዝቡንም ቅሬታ አፈለሰ። 16ነገር ግን የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአገሩ ድኆች ወይን ተካዮችና አራሾች እንዲሆኑ አስቀረ።17ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የናስ ዓምዶች፣ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናሱን ኵሬ ሰባበሩ፣ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ። 18ምንቸቶቹንና መጫሪያዎችንም፣ መኰስተሪያዎችንና ድስቶችን፣ ጭልፋዎችንም የሚያገለግሉበትንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ። 19የዘበኞቹም አለቃ ጽዋዎቹንና ማንደጃዎቹን፣ ድስቶቹንና ምንቸቶችን፣ መቅረዞችንና ጭልፋዎቹን፣ መንቀሎችንም፣ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፣ የብሩንም ዕቃ በብር፣ አድርጎ ወሰደ።20ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፣ አንዱንም ኵሬ፣ ከመቀመጫዎቹም በታች የነበሩትን ዐሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፤ ለእነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አልነበረም። 21ዓምዶቹም የአንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ። የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ። ውፍረቱም አራት ጣት ያህል ነበረ፣ ባዶም ነበረ።22የናሱም ጕልላት በላዩ ነበረ። የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፣ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት። በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት። 23በስተውጭም ዘጠና ስድስት ሮማኖች ነበሩ። በመረበቡም ዙሪያ የነበሩ ሮማኖች ሁሉ አንድ መቶ ነበሩ።24የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን ሦስቱንም በረኞች ወሰደ። 25ከከተማይቱም በሰልፈኞች ላይ ተሹመው ከነበሩት አንዱን ጀንደረባ፣ በከተማይቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፣ የአገሩንም ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፣ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎች ወሰደ።26የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። 27የባቢሎንም ንጉሥ ገደላቸው፣ በሐማትም ምድር ባለችው በሪብላ ገደላቸው። እንዲሁ ይሁዳ ከአገሩ ተማረከ።28ናቡከደነፆር የማረከው ሕዝብ ይህ ነው፤ በሰባተኛው ዓመት፣ 3, 023 አይሁድ፤ 29ናቡከደነፆርም በአሥራ ስምንተኛው ዓመት 832 ሰዎችን ከኢየሩሳሌም ማርኮአል፤ 30በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ 745 የይሁዳ ሰዎችን ማርኳል። የተማረኩት ሰዎች ሁሉ 4, 600 ነበሩ።31እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የዮአኪንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ ከወህኒም አወጣው።32በመልካምም ተናገረውና ዙፋኑን ከእርሱ ጋር በባቢሎን ከነበሩት ነገሥታት ዙፋን በላይ አደረገለት። 33ክፉው ዮርማሮዴክ በወህኒ ውስጥ ዮአኪን ለብሶት የነበረውን ልብስ ለወጠለት፣ ዮአኪንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በፊቴ ሁልጊዜ እንጀራ ይበላ ነበር። 34የባቢሎንም ንጉሥ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ እስኪሞት ድረስ የዘወትር ቀለብ ዕለት ዕለት ይሰጠው ነበር።
1በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን ፈጽማ ብቻዋን ተቀምጣለች! ኃያል የነበረችው አገር እንደ መበለት ሆናለች! በሕዝቦች መካከል እንደ ልዕልት ነበረች፥ አሁን ግን በባርነት ውስጥ ወድቃለች! 2በሌሊት ታለቅሳለች፥ታነባለችም፤እንባዎቿም ጉንጮቿን ከድነዋል። ከፍቅረኞቿ መካከል የሚያጽናናት የለም። ጓድኞቿ ሁሉ አሳልፈው ሰጧት። ጠላቶቿም ሆነዋል።3ከድህነቱና ከመከራዉ የተነሳ ይሁዳ ወደ ምርኮ ሄደች። በሕዝቦች መካከል ኖረች፥ ዕረፍትንም አላገኘችም። በጭንቀቷ ጊዜ አሳዳጆቿ ሁሉ በረቱባት።4ወደ ተቀጠሩት በዓላት የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ። ደጆቿ ሁሉ ባዶ ናችው። ካህናቶቿ ይቃትታሉ። ደናግሎቿ ሐዘንተኞች ናቸዉ፥እራስዋም በፍጹም ጭንቀት ውስጥ አለች። 5ባላንጣዎቿ ጌቶቿ ሆኑ፥ጠላቶቿ በለጸጉ። ስለ ብዙ ኃጢአቷ እግዚአብሔር መከራን አመጣባት። ልጆቿ ለጠላቷ ተማርከው ወደ ግዞት ሄዱ።6የጽዮን ሴት ልጅ ውበቷ ተለያት። ልዑላኖቿ መሰማሪያ እንዳላገኙ አጋዘኖች ሆኑ፥ በአሳዳጆቻቸው ፊት በድካም ሄዱ።7በመከራዋና ቤት አልባ በሆነችባቸው ቀናት፥ ኢየሩሳሌም በቀደሙት ቀናት የነበሯትን የከበሩ ነገሮች ታስባለች፤ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ ማንም የረዳት አልነበረም። ጠላቶቿ ተመለከቷት፥ በጥፋቷም ሳቁ።8ኢየሩሳሌም ታላቅ ኃጢአት ሠርታለች፥ ስለዚህ እንደ አደፈ ነገር ተንቃለች። ዕርቃናዋን ከተመለከቱበት ጊዜ አንስቶ ያከበሯት ሁሉ ናቋት። ታጉተመትማለች፥ ዘወር ለማለትም ትሞክራላች። 9ከቀሚሷ በታች አድፋለች። የወደፊቷን አላሰበችም። አወዳደቋ አስፈሪ ነበር። የሚያጽናት ማንም አልነበረም። «እግዚአብሔር ሆይ፥ መከራዬን ተመልከት፥ ጠላት እጅግ ታላቅ ሆኖአልና» እያለች ትጮኻለች!።10ጠላት በከበረ ነገሯ ሁሉ ላይ እጁን አደረገ። ወደ ጉባዔህ እንዳይገቡ አዝዘህ የነበረ ቢሆንም እንኳን፥ ሕዝቦች ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።11ሕዝቦቿ ሁሉ ምግብ እየፈለጉ ይጮኻሉ። ሕይወታቸውን ለማቆየት የከበረ ኃብታቸውን ስለ ምግብ ይሰጣሉ። የማልጠቀም ሆኟለሁና፥ እግዚአብሔር ሆይ ተመልከት አስበኝም። 12እናንተ መንገደኞች ሁሉ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? እግዚአብሔር እኔን መቅጣት ከጀመረበት ከጽኑ ቁጣው ቀን አንስቶ፥ የደረሰብኝን ሐዘን የሚመስል የማንም የሌላ ሰው ሐዘን ካለ ተመልከቱ፥ እዩም።13ወደ ዉስጥ ወደ አጥንቶቼ ከላይ እሳት ላከ፥ አሸነፋቸዉም። ለእግሮቼ መረብን ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ። ያለማቋረጥ ባዶና ደካማ አደረገኝ። 14የመተላለፌ ቀንበር በእጆቹ በአንድ ላይ ታስረዋል። በአንድ ላይ ተገምደዋል፥በአንገቴም ላይ ተደርገዋል። ብርታቴን ከንቱ አደረገው። ጌታ በእጃቸው አሳልፎ ሰጠኝ፥ መቆምም አልችልም።15ጌታ፥የሚመክቱልኝን ኃያላን ወንዶች ሁሉ ወዲያ ጣላቸው። ጽኑዓን ወንዶቼን ለማድቀቅ ጉባዔን በላዬ ጠራብኝ። ጌታ ድንግሊቱን የይሁዳ ልጅ በወይን መጥመቂያ እንዳለ ወይን ረገጣት።16ስለ እነዚህ ነገሮች አለቅሳልሁ። ሕይወቴን የሚያድሳት አጽናኙ ከእኔ ርቋልና ከዓይኖቼ ውኃ ይፈሳል፥ ከዓይኖቼ። 17ጽዮን እጆቿን እጅግ ዘረጋች፥ የሚያጽናናት ማንም የለም። እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉ ጠላቶቹ እንዲሆኑ አዘዘ። ኢየሩሳሌም በእነርሱ ዘንድ እንደ ርኩስ ነገር ተቆጠረች።18በትዕዛዙ ላይ ዐመጽ አድርጌእለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ ሕዝቦች ሁሉ ስሙ፥ ሐዘኔንም ተመልከቱ። ደናግሎቼና ኃያላን ወንዶቼ ተማርከዉ ሄደዋል። 19ፍቅረኞቼን ጠራኋቸው፥ ነገር ግን ከዳተኞች ሆኑብኝ። ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ ሕይወታችውን ለማኖር ምግብ እየፈለጉ በከተማ ውስጥ ሞቱ።20እግዚአብሔር ሆይ ተጨንቄአለሁና ውስጤም ተንጦአልና ተመልከት። እጅግ ዓመጽ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ታውኮአል። በመንገዶች ላይ ሰይፍ ልጆቻችንን ይነጥቃል፥በቤትም እንደ ሙታን መንደር ነው።21ሲቃዬን ስማ። የሚያጽናናኝ ማንም የለም። ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል። አንተ ስለ አደረግከው ደስ አላቸው። እነርሱም እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ ያወጅክባቸውን ቀን አምጣ። 22ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይታይ። መቃተቴ ብዙ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፤ስለ መተላለፌ ሁሉ እንዳሰቃየኽኝ አሰቃያቸው።
1ጌታ በቁጣው ጥቁር ደመና የጽዮንን ሴት ልጅ ፈጽሞ ከደናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣው ቀን የእግሩን መር ግጫ ችላ አለ። 2ጌታ የያዕቆብን ከተማዎች ሁሉ ዋጠ፥ ርኅራኄም አልነበረውም። በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ የተመሸጉ ከተማዎች ጣለ፤ መንግሥቱ ንና ልዑላኗን አቃለለ፥አዋርዶ ወደ ምድር መትቶ ጣላችው።3በብርቱ ቁጣው የእስራኤልን ብርታት ሁሉ ቆረጠ፥ ከጠላት ፊት ቀኝ እጁን ወደ ኋላ መለሰ፥ በዙሪያው ያለውን ሁሉ እንደሚበላ የሚንቦገቦግ እሳት ያዕቆብን አቃጠለ። 4እንደ ጠላት ቀስቱን በእኛ ላይ ገተረ፥ እንደ ባላጋራ ወርውሮ ሊገድል እጆቹ ተዘጋጅተው በተጠንቀቅ ቆመ። ለዓይን እጅግ የከበሩትን ሰዎች ሁሉ አረደ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ውስጥ ቁጣውን እንደ እሳት አፈሰሰ።5ጌታ እንደ ጠላት ሆነ። እስራኤልን ዋጠ። ቤተ መንግሥቶቿን ሁሉ ዋጠ፤ምሽጎቿን አጠፋ። በይሁዳ ሴት ልጅ ውስጥ ለቅሶንና ሰቆቃን አበዛ። 6ድንኳኑን እንደ አትክልት ቦታ አጠፋ። የታላቁን ጉባዔ ስፍራ አፈረሰ። በቁጣው ትኩሳት ንጉሡንና ካህኑን ንቋልና እግዚአብሔር በጽዮን ታላቁን ጉባዔና ሰንበትን እንዲረሱ አደረገ።7ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን አልተቀበለም። የቤተ መንግሥቶቿን ግንቦች በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ። በታላቅ ጉባዔ ቀን እንደሚሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የድል ድምጽ አሰሙ።8እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ የከተማ ቅጥር ለማፍረስ ወሰነ። የመለኪያውን ገመድ ዘረጋ፥ቅጥሩን ከማፍረስ እጁን አልመለሰም። ምሽጎቿ እንዲያለቅሱ፥ቅጥሮቿ አቅመ አልባ እንዲሆኑ አደረገ። 9በሮቿ ወደ መሬት ሰመጡ፥ የበሮቿን መቀርቀሪያዎች አጠፋ፥ ሰበረም።ንጉሧና ልዑላኖቿ የሙሴ ሕግ በሌለበት በአሕዛብ መካከል ናቸው። ነቢያቶቿም እንኳን ሳይቀሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ራዕይ አላገኙም።10የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች መሬት ላይ ተቀምጥዋል፥ በዝምታም ይቆዝማሉ። በራሳቸው ላይ አቧራ ነሰነሱ፥ የሐዘንም ልብስ ለበሱ። የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ መሬት ዝቅ አደረጉ።11እንባዬ ደረቀ፥ዓይኖቼ ቀሉ፥ የውስጥ ሰዉነቴ ታወከ። ልጆችና የሚያጠቡ ሕጻናት በመንደሮች መንገዶች ላይ ያለ ምንም ተስፋ ደክመዋልና፥ የሕዝቤም ሴት ልጆች ደቅቀዋልና ጉበቴ በመሬት ላይ ተዘረገፈ። 12በከተማይቱ መንገዶች ላይ እንደ ቆሰለ ሰው ዝለው ሳሉ፥ በእናቶቻቸው እቅፍ ነፍሳቸው እየፈሰሰች ሳሉ፥ እናቶቻቸውን፦ «እሕሉና ወይኑ የት አለ?» ይላሉ።13የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ስለ አንቺ ምን ማለት እችላለሁ? የጽዮን ድንግል ሆይ አጽናናሽ ዘንድ ከምን ጋር አመሳስልሻለሁ? ውድቀትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነው። ሊፈውስሽ የሚችል ማነው? 14ነቢያቶችሽ የሚያስትና ከንቱ ራዕይ አይተውልሻል። በረከትሽን ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አለገለጡም፤ ነገር ግን የሚያስት ትንቢትና የሚያጠምድ ራዕይ ተቀበሉ።15በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ እጃቸውን በአንቺ ላይ ያጨበጭባሉ። በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ይዝታሉ፥ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ፥ ደግሞም «'የውበት ሁሉ መጨረሻ'፥ 'የምድር ሁሉ ደስታ' ብለው የሚጠሯት ከተማ ይህቺ ናትን?» ይላሉ። 16ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን እጅግ ይከፍታሉ፥ ያላግጡብሻልም። እያፏጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ «ዋጥናት! በእርግጥም የተጠባበቅናት ቀን ይህቺ ናት! አገኘናት! አየናትም!» ይላሉ።17እግዚአብሔር የወሰነውን አደረገ። ከረዥም ጊዜ በፊት ያወጀውን ቃሉን ፈጸመ። አፈረሰ፥ርኅራኄም አልነበረውም፤ ጠላትሽ በአንቺ ላይ እንዲደሰት ፈቀደ፥ የጠላቶሽን ብርታት ከፍ ከፍ አደረገ።18ልባቸው ወደ ጌታ ጮኽ፤የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ እንባሽ እንደ ወንዝ ቀንና ሌሊት ይፍሰስ። ለራስሽ የእፎይታ ጊዜ አትስጪ። የአይኖችሽን ማፍሰስ አታስቁሚ። 19በሌሊት ተነሺና ጩኺ፥ ከሌሊቱ መጀመሪያ አንስቶ በጌታ ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ። በየመንገዱ ራስ ላይ በረሀብ ደክመው ስለወደቁት ልጆችሽ ሕይወት እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።20እግዚአብሔር ሆይ ተመልከት፥ ጽኑ መከራን ስላመጣህባቸው ስለ እነዚያ ሰዎች ግድ ይበልህ። ሴቶች የራሳቸውን ፍሬ፥ የሚሳሱላቸውን ልጆቻቸውን ይብሉን? ካህኑና ነቢዩ በጌታ መቅደስ ውስጥ ይታረዱን?21ወጣቱና ሽማግሌው በአንድነት በየመንገዶቹ በመሬት ላይ ወደቁ። ደናግሎቼና ኃያላን ወንዶቼ በሰይፍ ወደቁ። በቁጣህ ቀን አረድሃቸው፥በጭካኔ ገደልካቸው፥ ርኅራኄም አልነበረህም። 22በከበረው ጉባዔ ቀን እንደሚሆን ከዙሪያው ሁሉ ሽብርን ጥራህብኝ፤ ማንም አላመለጠም፥ በእግዚአብሔር ቁጣ ቀን የተረፈ ማንምአልነበረም። የተንከባከብኳቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ አጠፋቸው።
1በእግዚአብሔር የቁጣ በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ። 2አባረረኝ፥ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ። 3በእርግጥ ሊቃወመኝ ወደ እኔ ዘወር አለ፥ ቀኑን ሙሉ እጁን በላዬ መለሰ። 4ሥጋዬንና ቆዳዬን ቀደደ፥ አጥንቶቼን ሰበረ።5ቅጥር በዙሪያዬ ገነባብኝ፥ በምሬትና በመከራም ከበበኝ። 6ከሞቱ ረዥም ጊዜ እንደሆናቸው በጨለማ ስፍራ እንድኖር አደረገኝ። 7በዙሪያዬ ቅጥርን ገነባ፥ ማምለጥም አልችልም። የእግሬን ሰንሰለት አከበደ። 8ለርዳታ ብጮኽና ብጣራም ጸሎቴን ዘጋ።9ከጥርብ ድንጋይ በተሰራ ቅጥር መንገዴን ዘጋ፤የምሄድብት የትኛውም መንገድ ጠማማ ሆን። 10መንገዴን ቀየረው። 11ገነጣጠለኝ፥ብቸኛም አደረገኝ።12ቀስቱን ለጠጠ፥ ለፍላጻውም የዒላማ ምልክት አደረገኝ። 13ቀስቱን ለጠጠ፥ ለፍላጻውም የዒላማ ምልክት አደረገኝ። ለሰዎች ሁሉ መሳለቂያ፥ ዘወትርም ለሽሙጥጯ ዝማሬያቸው ምክንያት ሆንኩ። ምሬት ሞላብኝ፥ እሬት እንድጠጣ አስገደደኝ። 14ለሰዎች ሁሉ መሳለቂያ፥ ዘወትርም ለሽሙጥጯ ዝማሬያቸው ምክንያት ሆንኩ። 15ምሬት ሞላብኝ፥ እሬት እንድጠጣ አስገደደኝ።16ጥርሴን በድንጋይ ሰበረ፥ ወደ መሬት ውስጥ ረገጠኝ። 17ሰላምን ከሕይወቴ አስወገድክ፤ ከእንግዲህ መቼም የትኛዉንም ደስታ አላስብም። 18ስለዚህም«ጽናቴ ጠፍቷል፥ በእግዚአብሔር ላይ ያለ ተስፋዬም ሄዷል» አልሁ።19መከራዬንና እሬትና ምሬት ወደ አለበት መጥፋቴን አስባለሁ። 20በእርግጥ አስበዋለሁ፥ተስፋ በመቁረጥ በውስጤ አቀረቀርኩ ። 21ነገር ግን ይህን አስባልሁ፥ ተስፋ ሊኖረኝ የቻለውም ከዚህ የተነሳ ነው።22ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና። 23የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው! 24ለራሴ እንዲህ አልኩ «እግዚአብሔር ዕጣ ክፍሌ ነው» ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ።25ለምጠብቀው፥ ለምትፈልገውም ሕይወት እግዚአብሔር መልካም ነው። 26የእግዚአብሔርን ማዳን በዝምታ መጠበቅ መልካም ነው። 27በወጣትነቱ ቀንበርን ቢሸከም ለሰው መልካም ነው። 28እግዚአብሔር አሸክሞታልና ለብቻው ይቀመጥ ዝምም ይበል። 29ምናልባት ተስፋ ሊኖር ይችላልና አፉን በአፈር ዉስጥ ያኑር።30ለሚመታው ጉንጩን ይስጥ። ዉርደትንም ይጥገብ፤ 31እግዚአብሔር ለዘላለም አይጥለውምና! 32ሐዘንን ቢያመጣም እንኳን ከታላቁ የኪዳኑ ታማኝነት በሚሆን ርኅራኄ ይራራል። 33ምክንያቱም ከልቡ አይጨቁንም፥ወይንም የሰዎችን ልጆች አያሰቃይም።34በምድር ያሉ ምርኮኞችን ሁሉ ከእግሩ በታች ሲያደቅቅ፥ 35በልዑል ፊት የሰውን ፍርድ ሲያጣምም፥ 36ፍትህ ፈላጊውን ሲያፍን- ጌታ አያይምን?37ጌታ ካላዘዘው በቀር የሚናገርና የሚፈጽመው ማን ነው? 38ጥፋትና ስኬት ከልዑል አፍ የሚወጡ አይደሉምን? 39ታዲያ ማንም ሕያው የሆነ ሰው እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል? ማንም ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል?40መንገዳችንን እንፈትን እንመርምርም፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ። 41ልባችንንና እጃችንን በሰማይ ወደ አለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣና እንዲህ ብለን 42እንጽልይ፦ተላልፈናል በአንተም ላይ ዐምፀናል፥ስለዚህ ይቅር አላልከንም። 43ራስህን በቁጣ ሸፈንክ አሳደድከንም። አረድከን፥ አራራህልንምም።44ራስህን በደመና ሸፈንክ፥ስለዚህም ማለፍ የሚችል ጸሎት የለም። 45በአሕዛብም መካከል ቆሻሻና ውዳቂ አደረግኽን ። 46ጠላቶቻችን በእኛ ላይ በማላገጥ አፋቸውን ከፈቱ። 47የአሳር ጉድጓድ ፥የባዶነትና የጥፋት ፍርሃት መጣብን።48ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት ዓይኔ ያለማቋርጥ ውኃ አፈሰሰች። 49ዓይኖቼ ያፈሳሉ አያቆሙምም፥ለለቅሷቸውም ፍጻሜ የለውም፥ 50እግዚአብሔር ውደ ታች እስኪመለከት ከሰማይም እስኪያይ ድረስ።51ከከተማዬ ሴቶች ልጆች የተነሳ ዓይኔ ጽኑ ስቃይ በሕይወቴ ላይ አመጣች። 52ጠላቶቼ ያለ ምንም ምክንያት፥ያለመታከት እንደ ወፍ አደኑኝ። 53ሕይወቴን በጉድጓድ ዉስጥ አጠፉ፥ ድንጋይንም በላዬ ከመሩ። 54ውኆች በራሴ ላይ አለፉ፤እኔም፦ «ተቆርጬአለሁ!» አልኩ።55እግዚአብሔር ሆይ፥ ከጥልቅ ጉድጓድ ስምህን ጠራሁ። 56«እርዳታ ፈልጌ ስጮህ፥እረፍት ፈልጌ ስጣራ ጆሮህን አትሰውር» ባልኩኝ ጊዜ ድምጼን ሰማህ። 57በጠራሁህ ቀን ወደ እኔ ቀርበህ «አትፍራ» አልከኝ።58ጌታ ሆይ በተከሰስሁ ጊዜ ስለ ነፍሴ ተሟገትህ፤ ሕይወቴንም አዳንክ። 59እግዚአብሔር ሆይ እንዴት እንደ ጨቆኑኝ አይተሃል፥ ክርክሬን በጽድቅ ፍረድልኝ። 60በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉ፥የበቀላቸውን ሥራ ሁሉ አይተሃል። 61እግዚአብሔር ሆይ በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉና እሽሙጥጫቸውን ሰምተሃል።62በእኔ ላይ የተነሱብኝን ከንፈሮች ሰምተሃል፤ቀኑን ሁሉ እኔን በመቃወም የሚያስቡትን ጥልቅ አሳቦች ሰምተሃል። 63እግአብሔር ሆይ! ተመልከት፥ በመቀመጣቸውም ሆነ በመነሳታችው የስላቅ ዘፈናቸው ምክንያት ነኝ።64እግዚአብሔር ሆይ እጆቻቸው እንዳደረጉት ክፉ ነገር እንደዚያው መልሰህ ክፈላቸው። 65ፍርሃትን በልባቸው አድርግ፥ ርግማንህንም በላይቸው አድርግ። 66እግዚአብሔር ሆይ! በቁጣህ አሳድዳችው፥ከሰማይት በታች በየስፍራው አጥፋቸው።
1ወርቁ ፈጽሞ ደበዘዘ፤ ንጹሁ ወርቅ ተለወጠ! የተቀደሱት ድንጋዮች በየመንገዱ ዳር ተበተኑ። 2የጽዮን ልጆች የከበሩ፥ከንጹህ ወርቅ በላይ የሚቆጠሩ ነበሩ። አሁን ግን በሸክላ ሠሪ እጅ እንደተሠሩ የሸክላ ዕቃዎች እንጂ ከምንም አልተቆጠሩም።3ቀበሮዎች እንኳን ግልገሎቻቸውን ለማጥባት ጡቶቻቸውን ይገልጣሉ፥የሕዝቤ ሴት ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጎን ጨካኝ ሆነች።4ከጥም የተነሳ የሚጠባው ሕጻን ምላስ ከላንቃው ጋር ተጣበቀ፤ሕጻናት እንጀራ ለመኑ፥ ነገር ግን የሚሰጣችው የለም። 5በውድ ዋጋ የሚገዛ ምግብ ይመገቡ የነበሩ ተጥለዋል፥ በየመንገዱ ተርበዋል፤ቀይ ግምጃ ይለብሱ የነበሩ አሁን በቆሻሻ ክምር መካከል ናቸው።6ምንም እጅ ሳይወድቅባት በድንገት ከተገለበጠች ከሰዶም ኃጢአት ይልቅ የሕዝቤ ሴት ልጅ ኃጢአት ታላቅ ነው።7መሪዎቿ እንደ በረዶ የሚያንጸባርቁ ነበሩ፥እንደ ወተትም ነጭ ነበሩ። ሰውነታቸው ከቀይ ዕንቁ ይልቅ ቀይ ነበረ፥ መልካቸውም እንደ ሰንፔር ነበረ። 8አሁን ጨለማው ገጽታቸውን አጥቁሮታል፥ ቆዳቸው ከመነመኑ አጥንቶቻቸው ጋር ስለተጣበቀም በመንገዶች ላይ ማንነታቸው አልታወቀም።9በሰይፍ የተገደሉት በረሃብ ከሞቱት ይሻላሉ፥አንዳችም ሰብል ከእርሻ በመጥፋቱ በረሃብ ተወግተው ከተወገዱት ይሻላሉ። 10የርኁሩኆቹ ሴቶች እጆች የገዛ ልጆቻቸውን ቀቀሉ፤ በሕዝቤ ሴት ልጅ የጥፋት ቀን እነዚህ ልጆች መብል ሆኑአቸው።11እግዚአብሔር ቁጣውን አረካ። ጽኑ ቁጣውን አፈሰሰ፤ በጽዮን እሳትን አያያዘ፥ መሠረትዋንም በላ።12የምድር ነገሥታት ወይም በዓለም ከሚኖሩ ማናቸውም፥ ባላጋራ ወይም ጠላት በኢየሩሳሌም በሮች ይገባል ብለው አላመኑም። 13ነገር ግን የጻድቅን ደም በመካከልዋ ካፈሰሱ ከነቢያቶቿ ኃጢአትና ከካህናቷ በደል የተነሳ ይህን አደረጉ።14አሁን እነዚያ ነቢያትና ካህናት እንደ ዓይነ ስውራን ሰዎች በየጎዳናዎቹ ይቅበዘበዛሉ። ማንም ልብሶቻቸውን መንካት እስከማይችል ድረስ በደም ረክሰዋል። 15«እናንተ ርኩሳን ለቃችሁ ሂዱ!» እያሉ በነቢያቱና ካህናቱ ላይ ይጮሁባቸዋል።«ለቃችሁ ሂዱ፥ለቃችሁ ሂዱ! አትንኩን!» ይሏቸዋል። ስለዚህ ወደ ሌላ ምድር ይቅበዘበዛሉ፥ ነገር ግን አሕዛብ እንኳን፥«ከእንግዲህ ወድያ በዚህ እንደ እንግዳ መኖር አይችሉም» ይላሉ።16እግዚአብሔር ከማደሪያው በትኖአቸዋል፥ ከእንግዲህ ወድያ ወደ እነርሱ በርኅራኄ አይመለከትም። ማንም ከእንግዲህ ወድያ ካህናቱን በምንም መልኩ አክብሮ አይቀበላቸውም፥ ለሽማግሌዎቹም ግድ አልተሰኙም።17የማይጠቅሙ ረዳቶችን እንኳ ለማግኘት ዓይኖቻችን ድከሙ፤ሊያድነን ወደማይችል ሕዝብ በጉጉት ተመለከቱ። 18በመንገዶቻችን ሁሉ እርምጃዎቻችንን ተከታተሉ። ፍፃሜያችን መጥቶአልና መጨረሻችን ቀርቦአል፥ ቀኖቻችንም አልቀዋል።19አሳዳጆቻችን ከሰማይ ንስሮች ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። በተራሮች ላይ አሳደዱን በምድረ በዳም ሸመቁብን። 20በእግዚአብሔር የተቀባው ንጉሣችን፥ የአፍንጫችን እስትንፋስ፥ በጉድጓቸው ተያዘ፤«በአሕዛብ መካከል በጥበቃው ሥር እንኖራልን» ብለን የተናገርንለት ንጉሣችን ነበር።21በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፥ጽዋው ወደ አንቺም ያልፋልና ደስ ይበልሽ ሐሴትም አድርጊ። ትሰክሪያልሽ፥ እርቃንሽንም ትቀሪያልሽ። 22የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ በደልሽ ተፈጸመ። ከእንግዲህ ወዲያ በምርኮ አያኖርሽም። ነገር ግን የኤዶም ሴትልጅ ሆይ በደልሽን ይቀጣል። ኃጢአትሽንም ይገልጣል።
1እግዚአብሔር ሆይ የሆነብንን አስብ። እፍረታችንን እይ፥ተመልከትም። 2ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለባዕዳን ታልፈው ተሰጡ። 3አባቶች ስለሌሉ፥ እናቶቻችንም መበለቶች ስለሆኑ ወላጅ አልባ ሆን። 4ለመጠጣት ውኃችን የብር ዋጋ ጠየቀ፥ የገዛ እንጨታችንም ተሸጠል ን።5ጠላቶቻችን ያሳድዱናል፥ አንገታችንም ላይ ደርሰዋል። እኛ ደክመናል፥ ዕረፍትም የለንም። 6ምግብ ለመጥገብ ለግብፃውያንና ለአሦራውያን እጃችንን ሰጠን። 7አባቶቻችን ኃጢአት ሠሩ፤ እነርሱ የሉም፥እኛ ግን ኃጢአታቸውን ተሸከምን።8ባሮች ይገዙናል፥ ከእጃቸውም የሚያድነን የለም። 9ከምድረ በዳው ሰይፍ የተነሳ እንጀራ ለማግኘት በሕይወታችን ፈረድን። 10ቆዳችን እንደ ምድጃ ሆኖአል፥ ከረሃቡ ትኩሳት የተነሳ ተቃጥሎአል።11በጽዮን ሴቶችን፥ በይሁዳ ከተሞች ደናግላንን ደፈሩ። 12በገዛ እጆቻቸው ልዑላኑን ሰቀሉ፥ሽማግሌዎችንም አላከበሩም።13ኃያላን ወንዶችን ወደ ወፍጮ ቤት አመጡአቸው፥ ወጣት ወንዶችም ከእንጨት በታች ተንገዳግዱ። 14ሽማግሌዎችን ከከተማይቱ ደጅ፥ ኃያላን ወንዶችንም ከዘፈናቸው አስወገዷቸው።15የልባችን ደስታ ተወግዶአል፥ ጭፈራችንም ወደ ለቅሶ ተለውጦአል። 16አክሊል ከራሳችን ወድቋል! ወዮልን! ኃጢአት ሠርተናልና!17ልባችን ታምሞአል፥ዓይኖቻችንም ፈዝዘዋል፤ 18ምክንያቱም ባድማ በሆነችው በጽዮን ተራራ ላይ ቀበሮዎች ፈንጭተውበታልና።19ነገር ግን አንተ እግዚአብሔር ነህ፤ ለዘላለም ትገዛለህ፥ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው። 20ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ለረዥም ዘመናትስ ትተወናለህን? 21እግዚአብሔር ሆይ፥ወደ አንተ መልሰን፥እኛም ንስሐ እንገባልን። ቀኖቻችንን እንደ ጥንቱ ዘመን አድስ፥ 22ፈጽመህ ካልጣልከንና እጅግም ካልተቆጣኽን።
1በሰላሳኛው ዓመት ክአመቱም በአራተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬብሮን አጠገብ ከምርኮኞቹ ጋር አብሬ እየኖርኩኝ ሳለሁ ሰማያት ተክፍተው የእግዚአብሔርን ራዕይ አየሁ። 2ንጉስ ኢዮአኬም በተማረከበት በአምስተኛው ቀን በከለዳዊያን አገር በኬብሮን ወንዝ አጠገብ 3የእግዚአብሔር ቃል ወደ ካህኑ ወደ ኡዝ ልጅ ወደ ሕዝቅኤል በኃይል መጣ። የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች።4እኔም በውስጡ የእሳት ነበልባል ያለበት ዙሪያውና ውስጡ የሚያበራ ታላቅ ደመና የሚመስል አውሎ ነፋስ ከሰሜን አቅጣጫ ሲመጣ አየሁ፣ በደመናው ውስጥ ያለው እሳት ቀለሙ ቢጫ ነበር። 5መካከል ላይ የአራት ህያዋን ፍጡራን ምስል ነበር። ፍጥረታቱ የሰው መልክ ነበራቸው፣ 6ነገር ግን እያንዳንዳቸው አራት አራት ፊቶችና አራት አራት ክንፎች ነበሩዋቸው።7እግሮቻቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፣ ነገር ግን የእግሮቻችው ኮቴ እንደ ነሀስ የሚያበራ የጥጃ ኮቴ ያለ ነበር። 8ከክንፎቻቸው ስር በአራቱም አቅጣጫ የሰው እጅ ነበራቸው። 9በክንፎቻቸው ተነካክተው ወደ ኋላ ሳይገላመጡ ቀጥ ብለው ወደፊት ይራመዱ ነበር።10መልካቸውም በአንድ በኩል የሰው፥ በቀኝ በኩል የአንበሳ፣ በግራ በኩል የበሬና በሌላ በኩል ደግሞ የንስር ነበር። 11መልካቸው ያንን ይመስል ነበር፣ ክንፎቻቸውም ተዘርግተው ነበር፣ በሁለት ክንፎቻቸው እርስ በርሳቸው ተነካክተው ነበር፣ በሁለት ክንፎቻቸው ደግሞ ሰውነታቸውን ይሸፍኑ ነበር። 12እያንዳንዳቸው ሳይገላመጡ ወደፊት ይራመዱ ነበር፣ መንፈስ ወደመራቸው ሳይገላመጡ ይሄዱ ነበር።13ህያዋን ፍጡራን የከሰል ፍም እሳት ወይም ችቦ ይመስሉ ነበር፣ ከህያዋን ፍጡራኑ ጋር ደማቅ እሳት ይንቀሳቀስ ነበር፣ የመብረቅ ብልጭታዎችም ነበሩ። 14ህያዋን ፍጡራኑ በዝግታ ወደ ኋላና ወደ ፊት ይንቀሳቀሱ ነበር፣ እንደ መብረቅም ነበሩ።15ወዲያውም ወደ ህያዋን ፍጥረታቱ ተመለከትኩ፣ በምድር ላይ ከእያንዳንዱ ፍጡር አጠገብ አንዳንድ መንኮራኩር ነበረ። 16የመንኮራኩረቹ መልክ የሚከተለውን ይመስል ነበር፡ እንደ ብርሌ ያንጸባርቁ ነበር፣ አራቱም አንድ አይነት ነበሩ፣ አንዱም በአንዱ ላይ የተስካ ይመስል ነበር።17መንኮራኩሮቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ፍጡራኑ ወደየትኛውም አቅጣጫ ሳይገላመጡ ይሄዱ ነበር። 18ዙሪያውን በዓይን የተሞላ ስለሆነ የመንኮራኩሮቹ ጠርዝ ርጅምና አስፈሪ ነበር።19ህያዋን ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መንኮራኩሮቹ አብረው ይንቀሳቀሱ ነበር፣ ህያዋን ፍጥረታቱ ወደ ላይ ከፍ ሲሉ መንኮራኩሮቹም ከፍ ይሉ ነበር። 20መንፈስ ወደሚሄድበት ሁሉ ይሄዱ ነበር፣ የህያዋን ፍጡራኑ መንፈስ ስላለባቸው መንኮራኩሮቹ አብረው ወደ ላይ ከፍ ይሉ ነበር። 21የፍጡራኑ መንፈስ ስላለባቸው ፍጡራኑ ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም ከአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፣ ሲቆሙ እነርሱም ይቆሙ ነበር፣ ከምድር ወደ ላይ ከፍ ሲሉ እነርሱም ከፍ ይሉ ነበር።22ከህያዋን ፍጡራኑ ራስ በላይ ጠፈር የሚምስል ነገር ነበረ፤ ያም ጠፈር የሚመስል ነገር በህያዋን ፍጡራኑ ራስ በላይ እንደ አስፈሪ በረዶ ዙሪያቸውን ነበረ። 23ከጠፈሩ በታች የእያንዳንዱ ህያው ፍጡር ክንፍ ቀጥ ብሎ ተዘርግቶ የአንደኛው ፍጡር ክንፍ ከሌላው ፍጡር ክንፍ ጋር ተነካክቶ ነበር። እያንዳምዱ ፍጡር ሰውነቱን የሚሸፍንበት ሁለት ክንፍ ነበረው።24ህያዋን ፍጡራኑ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ሁሉ የክንፎቻቸው ድምጽ ይሰማኝ ነበር፣ ድምጹም እንደ ውሃ ጎርፍ፣እንደ ህያው አምላክ ድምጽ፣ እንደ ሠራዊት ድምጽ፣ እንደ ዝናብ ውሽንፍር ነበረ! በሚቆሙበት ጊዜ ክንፎቻችውን ያጥፉ ነበር። 25በሚቆሙበትና ክንፎቻቸውን በሚያጥፉበት ጊዜ ከራሶቻቸው በላይ ካለው ጠፈር ድምጽ ይመጣ ነበር።26ከራሶቻቸው በላይ ከሚገኘው ጠፈር በላይ ዕንቁ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ነበር፣ በዙፋኑም አምሳያ ላይ ሰው የሚመስል ተቀምጦ ነበር።27ከወገብ በላይ በእሳት የጋለ ብረት ከወገቡ በታች ደግሞ እሳት የሚመስል ምስል አየሁ። 28በዝናብ ጊዜ እንደሚታይ ቀስተ ደመና ይመስል ዙሪያውም ደማቅ ብርሀን ነበረ። ባየሁትም ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፣ ወዲያውም የሚያናግረኝ ድምጽ ሰማሁ።
1"የሰው ልጅ ሆይ ተነስና ቁም ክዚያም አነጋግርሃልሁ" አለኝ። 2እየተናገረኝ ሳለ መንፈስ አንስቶ በእግሮቼ አቆመኝ የናገረኝንም ሰማሁ። 3"የሰው ልጅ ሆይ አመፀኛ ወደሆኑትና በእኔ ላይ ወዳመፁት ወደ እስራኤል ህዝብ እልክሃለሁ፦ እነርሱና የቀደሙ አባቶቻችው እስከዚች ቀን ድረስ በድለውኛል!4ልጆቻቸው የተጨማደደ ፊትና ደንዳና ልብ አላቸው። አንተም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ትላቸዋለህ። 5አመጸኛ ቤት ስለሆኑ ወይ ይሰሙሃል አሊያም አይሰሙህም። ነገር ግን ቢያንስ ነቢይ በመካከላቸው እንዳለ ያውቃሉ።6አንተም የሰው ልጅ ሆይ እነርሱንም ሆነ ቃላቸውን አትፍራ። በእሾሆች፣በኩርንችት እና በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም አትፍራ። አመጸኛ ቤቶች ስለሆኑ ቃላቸውን አትፍራ ፊታቸውን አይተህ አትደንግጥ።7እጅግ አመጸኞች ስለሆኑ ቢሰሙህም ባይሰሙህም ቃልን ትነግራቸዋለህ። 8ነገር ግን አንተ የሰው ልጅ የምነግርህን ስማ። አንተም እንደአመጸኞቹ ሰዎች አመጸኛ አትሁን። አፍህን ክፈትና የምሰጥህን ብላ።9ጽሁፍ የተጻፈበት ጥቅል የያዝ እጅ ወደኔ ሲዘረጋ አየሁ። 10በፊቴም ዘረጋው ክፊትና ከኋላው ተጽፎበት ነበር፤ በሀዘን፣ በልቅሶና በዋይታ የተሞላ ነበር።
1የሰው ልጅ ሆይ ያገኘኽውን ብላ ይህን የመጽሀፍ ጥቅል ብላ ሄደህም ለእስራኤል ህዝብ ተናገር። 2አፌንም ከፈትኩ የመጽሀፉን ጥቅል አጎረሰኝና 3"የሰው ልጅ ሆይ በሰጠሁህ በዚህ የመጽሀፍ ጥቅል ሆድህን ሙላ" አለኝ። እኔም በላሁት እንደማርም ጣፈጠኝ።4ከዚያም "የሰው ልጅ ሆይ ወደ እስራኤል ህዝብ ሄደህ ቃሌን ንገራቸው" አለኝ። 5ምክንያቱም የተላከው ቋንቋቸው ወደማይታወቅ ወይም አስቸጋሪ ወደሆን ህዝብ አይደለም፦ 6እንግዳ ቋንቋ ወደሚናገር ታላቅ ህዝብ ወይም የቋንቋቸውን ቃላት መረዳት ወደሚያስቸግር ህዝብ አላኩህም። ወደዚህ ዓይነት ህዝብ ብልክህ ኖሮ ይሰሙህ ነበር። ነገር ግን የእስራኤል ህዝብ እኔን መስማት ስለማይፈልጉ አይሰሙህም። 7የእስራኤል ህዝብ ሁሉ ግንባረ ጠንካራና አንገተ ደንዳና ናቸው።8እነሆ! ፊትህን እንድፊታቸው ግንባርህንም እንደግንባራቸው ጠንካራ አደርገዋለሁ። 9ግንባርህን ከባልጩት ድንጋይ ይልቅ እንደሚጠነክር እንደ አልማዝ አድርጌዋለ! ስለዚህ የእሴራኤል ህዝብ አመጸኞች ስለሆኑ አትፍራቸው ፊታቸውንም አይተህ አትደንግጥ።10ቀጥሎሜ እንዲህ አለኝ "የሰው ልጅ ሆይ የነገርኩህን ቃል ስማ በልብህም ተቀበለው። 11ከዚያም በምርኮ ወዳሉት ህዝብህ ሂድና ቢሰሙህም ባይሰሙህም 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል' በላቸው።"12መንፈስም ከምድር ከፍ አደረግኝ ከኋላዬም የእግዚአብሔር ክብር በማደሪያው ይባረክ የሚል እንደ ምድር መናወጥ ዓይነት ድምጽ ሰማሁ። 13ወዲያውም የህያው ፍጥርታቱ ክንፎች ሲነካካ የሚፈጠረውን ድምጽ፣ አብረዋቸው ያሉትን መንኮራኩሮች ድምጽ፥ እና የምድር መናወጥ ድምጽ ሰማሁ።14መንፈስም አንስቶ ወሰደኝ፤ የእግዚአብሔርም እጅ በእኔ ላይ ከብዶ ስለነበር የምሄደው በምሬትና በጋለ መንፈስ ነበር። 15ከዚያም በኬብሮን ወንዝ አጠገብ ወደሚኖሩት በቴላቢብ ወደሚገኙት ምርኮኞች ሄጄ በድንጋጤና በመደነቅ ተሞልቼ በመካከላቸው ሰባት ቀን ተቀመጥኩ።16ከስባት ቀንም በኋላ እንዲህ ሆነ፥ 17"የሰው ልጅ ሆይ አንተን ለእስራኤል ህዝብ እንደጠባቂ አድርጌሀለሁ፥ ስለዚህ የአፌን ቃል ስማና የእኔን ማስጠንቀቂያ ንገራቸው! 18ኃጢአተኛውን 'በእርግጥ ትሞታለህ' ብለህ ንገረው ብዬህ አንተ ግን ባትነግረው ከክፉ መንገዱም እንዲመለስ ባታስጠነቅቀው እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። 19ነገር ግን ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱ ግን ከክፋቱና ከመጥፎ ተግባሩ ባይመለስ በኃጢአቱ ይሞታል አንተም ነፍስህን ታድናለህ።" ብሎ እግዚአብሔር ሲናገረኝ ሰማሁ።20ደግሞም አንድ ጻድቅ ሰው ጽድቅ ማድረግን ቢተው እኔም በፊቱ መሰናክል ሳስቀምጥ እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል። አንተ ስላላስጠነቀከው እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል፣ ቀድሞ የሰራውንም የጽድቅ ስራ አላስብለትም፣ ነገር ግን አንተን የሞቱ ተጠያቂ አደርግሀለሁ። 21ነገር ግን አንድ ጻድቅ ሰው ኃጢአት መስራቱን እንዲያቆም ብታስጠነቅቀው ከማስጠንቀቂያው የተነሳ በእርግጥኝነት በህይወት ይኖራል፣ አንተም የራስህን ህይወት ታድናለህ።"22ደግሞም የእግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣ፣ እግዚአብሔርም ፣ "ተነሳ! ወደ ሜዳማው ቦታ ሂድ፣ በዚያ የምነግርህ ነገር አለ" አለኝ። 23እኔም ተነስቼ ወደ ሜዳማው ቦታ ሄድኩ፥ በዚያም በኬብሮን ወንዝ አጠገብ ያየሁት ዓይነት የእግዚአብሔር ክብር ነበረ፣ ስለዚህም በግንባሬ ተደፋሁ።24የእግዚአብሔርም መንፈስ መጥቶ በእግሮቼ አቆመኝና እንዲህ ሲል ተናገረኝ "ወደ ቤትህ ሂድና በር ዘግተህ ተቀመጥ፣ 25ምክንያቱም አሁን የሰው ልጅ ሆይ በመካከላቸው እንዳትንቀሳቀስ በገመድ ያስሩሀል።26አመጸኛ ህዝብ ስለሆኑ እንዳትገስፃቸው እኔ ምላስህን ከላንቃህ ጋር አጣብቀዋለሁ አንተም ዲዳ ትሆናለህ። 27ነገር ግን እኔ ስናገርህ አፍህን እከፍታለሁ አንተም 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል' ትላቸዋለህ፤ አመጸኛ ህዝብ ስለሆኑ የሚሰማ ይሰማሀል የማይሰማ አይሰማህም!"
1አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ ሸክላ ውሰድና የኢየሩሳሌምን ካርታ ሳልበት። የጦር ከበባ አድርግባት፣ 2ምሽግም ስራባት፣ ዙሪያውን በአፈር ደልድለው፣ ትልቅ ቅጥር ና የጦር ሰፈሮችን አስቀምጥ ፣ ቅጥር መደርመሻ ግንዶች ዙሪያውን አስቀምጥ። 3ክዚያም ብረት ምጣድ ለራስህ ውሰድና በአንተና በከትማይቱ መካከል በብርት አጥር ምሳሌ አቁመው። ትከበባለችና ፊትህንም ወደከትማይቱ አዙር ክበባትም! ይህም ለእስራኤል ህዝብ ምልክት ይሆናል።4ክዚያም በግራ ጎንህ ተኛና የእስራኤልን ህዝብ ኃጢአትም ተሸከም፤ በእስራኤል ህዝብ ፊት በግራ ጎንህ በተኛህበት ቀን ቁጥር ልክ ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ። 5አንድ ቀን የሚቀጡበትን አንድ አመት እንዲወክል እኔ ራሴ መድቤልሀለሁ፡ 390 ቀናት! በዚህ መልኩ የእስራኤልን ህዝብ ኃጢአት ትሸከማለህ።6እነዚህን ቀናት ስትጨርስ በቀኝ ጎንህ ትተኛና የይሁዳን ህዝብ ኃጢአት ለአርባ ቀናት ትሸከማለህ። አንድ ቀን አንድ አመት እንዲወክል መድቤልሀለሁ። 7እጅህን ክልብስህ ውስጥ አውጥተህ ፊትህን ወደተከበበችው ኢየሩሳሌም ከተማ አድርገህ ትንቢት ትናገርባታለህ። 8እነሆ! የሜርኮው ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ከአንድ ጎን ወደ ሌላ ጎን እንዳትዞር ቀንበርን አድርጌብሀለሁ።9ስንዴ፣ገብስ፣ባቄላ፥ ምስር፥ ጤፍና አጃ ወስደህ በአንድ ዕቃ ውስጥ አድርገህ በጎንህ በምትተኛባቸው ቀናት ቁጥር ልክ ዳቦ ትጋግራልህ። ለ390 ቀናት ትመገበዋለህ! 10በየቀኑ ሃያ ሃያ ሰቅል የሚመዝን ዳቦ ትበላለህ። በየጊዜውም ትመገበዋለህ። 11አንድ ስድስተኛ ኢን ውሃም ትጠጣለህ። በየጊዜውም ትጠጣዋለህ።12እንደ ገብስ ቂጣ አድርገህ ትበላዋለህ፣ የምትጋግረው ግን በሰው ዓይነ ምድር ነው። 13እግዚአቤሔር "በበተንኳቸው አህዛብ መካከል የእስራኤል ህዝብ የሚመገቡት ዳቦ ርኩስ ይሆናል።" ይላል።14እኔም "ወየው ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ረክሼ አላውቅም! የሞተ ወይም በአውሬ የተገደለ በልቼ አላውቅም፣ የረከሰ ሥጋም ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም!" አልኩኝ። 15እርሱም "እነሆ በሰው ዓይነ ምድር ፋንታ የከብት ፍግ ስጥቼሀለሁ ዳቦውን በእርሱ መጋገር ትችላለህ" አለኝ።16ደግሞም "የስው ልጅ ሆይ! ከኢየሩሳሌም የእንጀራን በትር እሰብራለሁ፣ ህዝቡም እንጀራን በጭንቅ ውሃም በስስት ይጠጣሉ። 17የምግብና የውሃ እጥረት ስለሚኖር ሰው ወንድሙን በድንጋጤ ይመለከተዋል፣ ከኃጢአታቸው የተነሳ ይመነምናሉ።" አለኝ።
1"ከዚያም የሰው ልጅ ሆይ ጎራዴን እንደጢም መላጫ ተጠቀመህ ራስህንም ጢምህንም ተላጨው፣ በመቀጠልም ሚዛን ተጠቅመህ ጠጉሩን ትከፍለዋለህ። 2የምርኮው ዘመን ሲያበቃ የጠጉሩን አንድ ሶስተኛ በከተማው መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ። አንድ ሶስተኛውንም ወስደህ በክተማይቱ ዙሪያ አስቀምጠህ በሰይፍ ትመታዋለህ። ከዚያም አንድ ሶስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፣ እኔም ህዝቡን አሳድድ ዘንድ ሰይፌን እመዛለሁ።3ነገር ግን ጥቂት ጠጉሮችን ወስደህ በጋቢህ ጫፍ ላይ ትቋጥረዋለህ። 4ክዚያም በርከት ያለ ጠጉር ወስደህ ወደ እሳቱ መሀል ጥለህ በእሳቱ አቃጥለው፤ በእሳት ውስጥ ይቃጠል፤ ከዚያም ውስጥ እሳት ወደ እስራኤል ህዝብ ሁሉ ይወጣል።"5ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህች በሌሎች አገሮች ዙሪያዋን እንድትዋሰን ያደረኳት፣ በአህዛብ መካከል ያለች ኢየሩሳሌም ናት። 6ነግር ግን ከሌሎች አህዛብ ይልቅ ከኃጢእታቸው የተነሳ ትዕዛዛቴን አቃለዋል፣ በዙሪያቸው ካሉ አገሮች ይልቅ ህጌን ተላልፈዋል። ፍርዴን አቃለዋል በህጌም አልኖሩም!"7ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በዙሪያቹ ካሉ አገሮች ይልቅ አመጸኞች ስለሆናችሁና በህጌ ስላልኖራችሁ ተግባራችሁም እንድትዕዛዛቴ ስላልሆነ ይባስ ብሎ የምታደርጉት ሁሉ በዙሪያችሁ እንዳሉት አግሮች ትዕዛዝ ስለሆነ ።" 8ስለዚህም ይላል ጌታ እግዚአብሔር "እነሆ! እኔ እራሴ በእናንተ ላይ እነሳለሁ! አህዛብ ሁሉ ያዩ ዘንድ ፍርዴን በመካከልሽ አመጣለሁ።9ከጸያፍ ተግሮችሽ የተነሳ አድርጌ የማላውቀውን ደግሜም የማላደርገውን ነገር በአንቺ ላይ አደርጋለሁ። 10ስለዚህም በመካከልሽ አባቶች ልጆቻችውን ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፣ ፍርድንም አመጣብሻለሁና የተርፉትን በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ!11ስለዚህም በራሴ እምላለሁ፦ ይህ የጌታ የእግዚአብሄር አዋጅ ነው- ቤተመቅደሴን በሚያስጠሉ ነግሮችና በሚያጸይፉ ተግባራት ሞልታችሁታልና ከቁጥር አጎድላችኋለሁ፤ ፊቴን አልመልስልሽም፣ አልራራልሽምም። 12አንድ ሶስተኛችው ህዝብ በመቅሰፍት ይሞታል በመካከልሽም በረሀብ ያልቃሉ፣ አንድ ሶስተኛው ደግሞ በከበቡሽ ጠላቶች ሰይፍ ይገደላሉ። ቀሪውን አንድ ሶስተኛ ደግሞ በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ አሳድዳቸውም ዘንድ ሰይፌን ከሰገባው እመዛለሁ።13ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፣ በእነርሱም ላይ የነበረኝ ንዴት ይበርዳል። በእነርሱ ላይ የነበረኝ ንዴቴ በተፈጸመ ጊዜ እኔ እግዚአብሄር በቁጣዬ እንደተናገርኳቸው ያውቃሉ። 14ዙሪያሽን በከበቡሽ አህዛብና በአላፊ አግዳሚው ሁሉ የተዋረድሽና አሳፋሪ አድርግሻለሁ።15ስለዚህ ኢየሩሳሌም በሌሎች የምትወገዝና መቀለጃ በዙሪያዋ ላሉ አህዛብ ቁጣና ድንጋጤ ትሆናልች። ፍርዴን በንዴትና በቁጣ በጽኑ ተግሳጽም አመጣባችኋለሁ- እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። 16የርሀብን አስከፊ ቀስቶች እሰድባችኋለሁ፣ ያም እናንተን የማጠፋበት መሳሪያ ይሆናል። ርሀብን አበዛለሁ የእንጀራ በትራችሁንም እሰብራለሁ። 17ልጆች አልባ እንድትሆኑ ርሀብና አደጋን እልክባችኋለሁ። መቅሰፍትና ደም በመካከላችሁ ያልፋል ሰይፍንም አመጣባችኋለሁ -- እኔ እግዚአብሄር ይህን ተናግሬአልሁ!"
1የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ 2"የሰው ልጅ ሆይ ፊትህን ወደ እስራኤል ተራሮች አዙርና ትንቢት ተናገር። 3እንዲህም በላቸው 'የእስራኤል ተራሮች ሆይ የጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮች፣ ለኮረብቶች፣ ለሸንተረሮችና ለሸለቆዎች እንዲህ ይላል፡ እነሆ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ ከፍታችሁን ሁሉ አጠፋለሁ።4መሰዊያዎቻችሁ ባድማ ይሆናሉ የዕጣን መሰዊያዎቻችሁም ይደመሰሳሉ የሞቱ ሰዎቻችሁን ሬሳዎች በጣዖቶቻቸው ፊት እጥላለሁ። 5የእስራኤልን ህዝብ ሬሳዎችን በጣዖቶቻችው ፊት አጋድማለሁ፣ አጥንቶቻችሁንም በመሰዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ።6መሰዊያዎቻችሁ የተጣሉና ባድማ እንዲሆኑ የምትኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ የተጣሉ የማምለኪያ ኮረብቶቻቸው ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፣ እንዳልነበሩም ሆነው ይጠፋሉ፤ የዕጣን መሰዊያዎቻችሁ ይወገዳሉ ሥራቼሁ ሁሉ ተጠርጎ ይጠፋል። 7የሰዎች ሬሳ በመካከላችሁ ይወድቃል ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቃላችሁ!8ነገር ግን ቅሬታዎችን አስቀራለሁ፣ እናንተ በየአገሩ ስትበተኑ ከአህዛብ መካከል ከሰይፍ የሚያመልጡ ይኖራሉ። 9እነዚያ ያመለጡትም በምርኮ አገር ሆነው ከእኔ ዘወር ካለው አመንዝራ ልባቸውና ወደ ጣዖታቶቻቸው ከሚያየው አመንዝራ ዓይናቸው የተነሳ ምን ያህል እንዳዝንኩ ስለእኔ ያስባሉ። ባደረጉት ክፋትና ርኩሰት መጸጸታቸው ከፊታቸው ይነበባል። 10ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ። ይህን ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ ብዬ አስቀድሜ የተናገርኩት በዓላማ ነው።11ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ ከፈጸሙት አስነዋሪ ተግባር የተነሳ የእስራኤል ህዝብ በሰይፍ፣ በረህብና በቸነፈር ይጠፋሉና በእጅህ እያጨበጭችብክ በእግርህም መሬቱን እየመታህ "ወዮ" እያልክ ጩህ! 12በሩቅ ያለው በቸነፈር በቅርብ ያለው በሰይፍ ይጠፋሉ። ከዚያ የተረፉት ደግሞ በርሀብ ያልቃሉ፤ በዚህ መንገድ ቁጣዬን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።13በጣዖቶቻቸው መካከል፣ በመሰዊያዎቻቸው ዙሪያ፣ ከፍ ባሉ ተራሮቼ አናት ላይ፣ እንዲሁም በለመለመ ዛፍ ሁሉና በግዙፍ ዋርካ ስር- ለጣዖቶቻቸው በሚያጤኑበት ሥፍራ ሁሉ የተገደሉ ሰዎቻቸው ተጥለው ሲያዩ ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ። 14በገዛ እጄ እመታችኋለሁ የሚኖሩብትን ስፍራ ሁሉ ከምድረ በዳ እስከ ዲብላህ ድረስ ምድሪቱን የተጣለችና ባድማ አደርጋታለሁ።"
1የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ 2"አንተ የሰው ልጅ ሆይ -- ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር የሚለው እንዲህ ነው፣ 'መጨረሻ! በምድሪቱ አራቱም ማዕዘን መጨረሻ መጥቷል!3ቁጣዬን ስለላኩባችሁ መጨረሻችሁ ቀርቧል፣ እኔም እንደመንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ፤ ክፉ ሥራችሁን ሁሉ በእናንተ ላይ እመልስባችኋለሁ። 4በርህራሄ አላያችሁም ምህረትም አላደርግላችሁም፤ ነገር ግን መንግዳችሁን እመልስባችኋለሁ፣ ጥፋታችሁ በመካከላችሁ ይሆናል፥ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቃላችሁ!5ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ መዓት! በመዓት ላይ መዓት! እነሆ እየመጣ ነው! 6መጨረሻ በእርግጥ እየመጣ ነው፤ መጨረሻው ወደ እናንተ እየተራመደ ነው! እነሆ እየመጣ ነው! 7በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ ፍርድ እየመጣ ነው። ጊዜው ደርሷል፤ የጥፋት ቀን ቀርቧል፤ ተራሮች ከእንግዲህ ለደስታ አይሆኑም።8በቅርቡ እንደ መንገዳችሁ በምፈረድባችሁ ጊዜና ክፋታችሁን በመለስኩባችሁ ጊዜ መዓቴን አፈስባችኋለሁ ቁጣዬም በላያችሁ ይሆናል። 9ዓይኔ አይራራላችሁም ምህረትም አላደርግላችሁም። እንዳደርጋችሁብኝ አደርግባችኋለሁ፤ የምቀጣችሁ እኔ እንደሆንኩ ታውቁ ዘንድ ክፋታችሁም በመካከላችሁ ይሆናል።10እነሆ ቀኑ እየደረሰ ነው። ጥፋት ወጥቷል። በትሩ በትዕቢት አበባ ፈክቷል። 11አመጽ ወደ ኃጢአት በትርነት አድጓል-- አንዳቸውም፣ ከህዝባቸውም ማንም፣ የትኛውም ሀብታቸው፣ የትኛው ጠቃሚ ነገራቸው አይተርፍም።12ቀኑ እየመጣ ነው፤ ቀኑ እየቀረበ ነው። ቁጣዬ በህዝቡ ሁሉ ላይ ስለሆነ ንብረት የገዛ አይደሰት፣ የሸጠም አይዘን! 13ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ሻጭ የሸጠውን አያስመልስም፣ ራዕዩ ለመላው ህዝብ ነው። በኃጢአቱ የሚጸና አይበረታምና አይመለሱም።14መለከት ነፉ የሚያስፈልገውን ሁሉ አዘጋጁ ነገር ግን ቁጣዬ በህዝቡ ሁሉ ላይ ነውና ለጦርነት የከተተ አንድም የለም! 15በውጭ ሰይፍ በውስጥ ደግሞ ረሀብና ቸነፈር አለ። በእርሻ ቦታ ያሉ በስይፌ ይወድቃሉ፥ ረሀብና ቸነፈር ደግሞ በከተማ ያሉትን ይፈጃል። 16ነገር ግን ከእነርሱ ጥቂቶች ተርፈው ወደ ተራሮች ይሄዳሉ። ሁሉም ስለኃጢአታቸው እያንዳንዱም ስለስንፍናው እንደ ደሸለቆ እርግብ ያለቅሳሉ።17እጅ ሁሉ ይቀልጣል ጉልበትም ሁሉ እንደ ውሀ ይደክማል፣ 18ማቅም ይለብሳሉ ድንጋጤም ይከባቸዋል፤ ፊት ሁሉ በእፍረት ይሸፈናል ራስም ሁሉ ጠጉር አልባ ይሆናል። 19ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ ወርቃቸውም እንደ ጕድፍ ይሆናል በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ያድናቸው ዘንድ አይችልም። እርሱ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም ሆዳቸውንም አይሞሉም20የክብሩ ጌጦችንም በማንአለብኝነት ወስደው ክፋታቸውንና የፈጸሙትን አመጻ የሚያሳዩ የምንዝርና ምስሎችን አበጁ፣ ስለዚህ እኔ እነዚህን ምስሎች ርኩስ እድርጌባቸዋለሁ። 21በባዕድም እጅ ለንጥቂያ፥ በምድር ኃጢአተኞችም እጅ ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ እነርሱም ያረክሱአቸዋል። 22የተቀድሰውን ቦታዬን ባረከሱ ጊዜ ፊቴንም አዞርባቸዋለሁ፥ ወንበዴዎችም ይገቡባታል ያረክሱትማል።23ምድሪቱ ደም ባመጣው ፍርድ፥ ከተማዪቱም በግፍ ተሞልታለችና ሰንሰለት ሥራ። 24ስለዚህም ከአሕዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚከፉትን አመጣለሁ ቤቶቻቸውንም ይወርሳሉ፣ መቅደሶቻቸው ስለሚረክሱ የኃያላንንም ትዕቢት ወደ ፍጻሜ አመጣለሁ። 25ፍርሀት ይመጣል! ሰላምን ይሻሉ ነገር ግን ምንም ሰላም አይገኝም።26ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ወሬም በወሬ ላይ ይመጣል! ከነቢዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ ነገር ግን ከካህኑም ዘንድ ህግ፥ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል። 27ንጉሡም ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝብ እጆቼ በፍርሀት ይንቀጥቀጣሉ። እንደ መንገዳቸውም መጠን ይህን አደርግባቸዋለሁ! እኔ እግዚአብሔር እንድሆንኩ እስኪያውቁ ድረስ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ ።
1በስድስተኛውም ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእግዚአብሔር እጅ እንደገና በእኔ ላይ ወደቀች። 2እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ የሰው አምሳያ ነበረ ከወገቡም በታች እሳት ይመስል ነበረ፥ ከወገቡም በላይ የቀለጠ ብረት የሚመስል የሚያብለጨልጭ ነበር።3ከዚያም እጅ የሚመስል ነገር ዘረጋ በራስ ጠጕሬም ያዘኝ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፥ በእግዚአብሔርም ራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ አመጣኝ በዚያም ቅንዓት የሚያነሣሣ የቅንዓት ጣዖት ተተክሎ ነበር። 4እነሆም፥ በቈላው እንዳየሁት ራእይ አይነት የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበረ።5እርሱም፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ዓይንህን ወደ ሰሜን አንሣ አለኝ።" ዓይኔንም ወደ ሰሜን መንገድ አነሣሁ እነሆም፥ በመሠዊያው በር በሰሜን በኩል መግቢያው ላይ የቅንዓት ጣዖት ነበረ። 6የእግዚአብሔርም መንፈስ፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ አየህ የሚያደርጉትን? ይህ ከመቅደሴ ያርቁኝ ዘንድ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚያደርጉት ታላቁን ርኵሰት ነው! ግን ዞረህ ስታይ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኵሰት ታያለህ አለኝ!"7ወደ አደባባዩም መግቢያ አመጣኝ ፥ በግንቡ ውስጥ ቀዳዳ እንዳለ አየሁ። 8እርሱም፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ግንቡን ንደለው አለኝ ግንቡንም በነደልሁት ጊዜ መግቢያ በር አገኘሁ። 9እርሱም፦ "ግባና የሚያደርጉትን የከፋ ርኵሰት እይ አለኝ።10እኔም ገባሁና እነሆ፥ በግንቡ ዙሪያ ላይ የሚሳብና አስቀያሚ አውሬ ምስል አየሁ! በግንቡም ዙሪያ የእስራኤል ቤት ጣዖታት ሁሉ ተስለው አየሁ። 11ሰባ እስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በዚያ ቆመው ነበር፥ በመካከላቸውም የሳፋን ልጅ ያእዛንያ ቆሞ ነበር፥ በምስሎቹም ፊት ቆመው ነበር ። እያንዳንዱ ሰው በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ የዕጣኑም ጢስ ሽቱ ይወጣ ነበር።12እርሱም፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በጨለማ የሚያደርጉትን አየህ? 'እግዚአብሔር አያየንም እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል' ብለው ሁሉም ሰው ይህን የሚያድርገው በየራሱ ስውር ቦታ ከጣዖቱ ጋር ሆኖ ነው። 13እርሱም፦ "ደግሞ ወደኋላ ዙርና እያደረጉ ያለውን ከዚህ የበለጠውን ሌላ ታላቅ ርኵሰት እይ" አለኝ።14ከዚያም ወደ በሰሜን አቅወጣጫ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፣ እነሆም! ሴቶች ለተሙዝ እያለቀሱ በዚያ ተቀምጠው ነበር። 15እርሱም፦ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን ታያለህ? ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ርኵሰት ታያለህ አለኝ።16ደግሞም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሀያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ጀርባቸው ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ሆኖ ሸሚሽ ለተሰኘው ጣዖት ይሰግዱ ነበር።17እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን ታያለህ? በዚህ የሚያደርጉት ይህ ርኵሰት ለይሁዳ ቤት እንድ ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱን በግፍ ሞልተዋታል ያስቈጡኝም ዘንድ ተመልሰዋል፥ ቅርንጫፎችንም ወደ አፍንጫዎቻቸው አቅርበዋል። 18ስለዚህ እኔ ደግሞ በመካከላቸው እንቀሳቀሳለሁ ዓይኔ አይራራም ፣አላዝንላቸውም። ወደ ጆሮዬም በታላቅ ድምፅ ቢጮኹ አልሰማቸውም አለኝ።
1ከዚያም "ጠባቂዎች የሚያጠፋ መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ወደ ከተማይቱ ይቅረቡ" ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ። 2እነሆም፥ እያንዳንዳቸው አጥፊውን መሣሪያ በእጃቸው ይዘው ስድስት ሰዎች በሰሜን አቅጣጫ ካለው ከላይኛው በር በኩል መጡ፣ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰ የጸሐፊም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።3የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ከኪሩብ ላይ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄደ። በፍታም የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ። 4እግዚአብሔርም "በኢየሩሳሌም ከተማ መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት አድርግ" አለው።5እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ "እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም! ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም 6ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ! ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ። ከመቅደሴም ጀምሩ!" አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።7እርሱም "ቀጥሉ! ቤቱን አርክሱ፥ አደባባዮቹንም በሬሳ" አላቸው። እነርሱም ወጥተው በከተማይቱ ላይ ጥቃት ፈጸሙ። 8ጥቃቱን እየፈጸሙ ሳሉ እኔ ብቻዬን እንደቀረሁ ሳይ በግምባሬ ተደፍቼ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ቅሬታ ሁሉ ታጠፋለህን?" ብዬ ጮኽሁ።9እርሱም፦ "'እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል እግዚአብሔርም አያይም!' እያሉ የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኃጢአት እጅግ በዝቶአል ምድሪቱም ደም፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች ። 10እኔም ደግሞ ዓይኔ አትራራላቸውም አላዝንምም። ይልቁኑ መንገዳቸውን በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ" አለኝ። 11እነሆም፥ በፍታ የለበሰው የቀለም ቀንድም በወገቡ የያዘው ሰው ተመልሶ መጣና "ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ" የሚል ሪፖርት አቀረበ።
1ከዚያም በኪሩቤል ራስ ላይ ወደ ነበረው ጠፈር ተመለከትኩ። በላያቸው እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ እንደ ዙፋን የሚመስል መልክ ተገለጠ። 2እግዚአብሔርም በፍታም የለበሰውን ሰው "በመንኰራኵሮች መካከል ከኪሩብ በታች ግባ፥ ከኪሩቤልም መካከል ካለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ በከተማይቱም ላይ በትነው" አለው። ሰውዬውም እያየሁት ገባ።3ሰውዬውም ሲገባ ኪሩቤል በቤቱ ቀኝ በኩል ቆመው ነበር፥ ደመናም ውስጠኛውን አደባባይ ሞላው። 4የእግዚአብሔር ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መድረክ ላይ ቆመ፤ ቤቱም በደመናው ተሞላ፥ አደባባዩም በእግዚአብሔር ክብር ፀዳል ተሞላ። 5ሁሉንም የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ጽምፅ እንዲሁ የኪሩቤል ክንፎችን ድምፅ ክውጭው አደባባይ ሰማሁ።6እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን ሰው "ከመንኰራኵሮች ከኪሩቤል መካከል እሳት ውሰድ" ብሎ ባዘዘው ጊዜ ሰውዬው ገብቶ በአንደኛው መንኰራኵር አጠገብ ቆመ። 7ኪሩብም ከኪሩቤል መካከል እጁን በኪሩቤል መካከል ወዳለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ ወሰደ፥ በፍታም በለበሰው ሰው እጅ አኖረው እርሱም ይዞ ወጣ። 8በኪሩቤልም ከክንፎቻቸው በታች የሰው እጅን መሳይ አየሁ።9እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ በኪሩቤል አጠገብ አራት መንኰራኵሮች ነበሩ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ፥ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ አጠገብ ነበረ። የመንኰራኵሮቹም መልክ እንደ ቢረሌ ድንጋይ ነበረ። 10የአራቱም መልክ አንድ ይመስል ነበር፥ መልካቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበረ። 11ሲንቀሳቀሱም ወደየትኛውም አቅጣጫ ይሄዱ ነበር፤ ፊት ለፊት ስለሚሄዱ ሲሄዱ አይገላመጡም ነበር። ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር።12ሰውነታቸው ሁሉ ማለትም ጀርባቸው፣ እጃቸውና ክንፋቸው በዓይን ተሞልቶ ነበር፣ አራቱ መንኰራኵሮችም ዙሪያቸውን በዓይኖች ተሞልተው ነበር። 13መንኰራኵሮችም እኔ እየሰማሁ "ተሽከርካሪዎች" ተብለው ተጠሩ። 14ለእያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛውም የሰው ፊት፥ ሦስተኛው የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም የንስር ፊት ነበረ።15ከዚያም ኪሩቤል ማለትም በኮቦር ወንዝ ያየኋቸው ህያዋን ፍጥረታት ከፍ ከፍ አሉ 16።ኪሩቤል በተንቀሳቀሱ ጊዜ ሁሉ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፤ ኪሩቤልም ከምድር ከፍ ከፍ ይሉ ዘንድ ክንፎቻቸውን ሲዘረጉ መንኰራኵሮች ደግሞ ከአጠገባቸው ፈቀቅ አይሉም ነበር። 17የህያዋኑ ፍጥረታት መንፈስ በመንኰራኵሮች ውስጥ ስለነበረ ኪሩቤል ሲቆሙ መንኮራኩሮችመ ይቆሙ ነበር፥ ከፍ ከፍ ሲሉም መንኮራኩሮቹም ከእነርሱ ጋር ከፍ ከፍ ይሉ ነበር።18የእግዚአብሔርም ክብር ከቤቱ መድረክ ላይ ወጥቶ በኪሩቤል ላይ ቆመ። 19ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ እኔም እያየሁ ከምድር ከፍ ከፍ አሉ በወጡም ጊዜ መንኰራኵሮች በአጠገባቸው እንደዚያው አደረጉ። በእግዚአብሔርም ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ወረደ።20እነኚህም በኮበር ወንዝ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየኋቸው ህያዋን ፍጥረታት ስለነበሩ ኪሩቤልም እንደ ነበሩ አውቄ ነበር። 21ለእያንዳንዱ አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበሩት፥ የሰውም እጅ አምሳያ ከክንፎቻቸው በታች ነበረ። 22ፊቶቻቸውም በኮቦር ወንዝ በራዕይ ያየኋቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር ፣ እያንዳንዱም አቅንቶ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።
1መንፈስም አነሣኝ ወደ ምስራቅ መውጫ ወደሚመለከት ወደ እግዚአብሔር ቤት ምሥራቅ በር አመጣኝ። እነሆም፥ በበሩ መግቢያ ሀያ አምስት ሰዎች ነበሩ፥ በመካከላቸውም የሕዝቡን አለቆች የዓዙርን ልጅ ያእዛንያንና የበናያስ ልጅ ፈላጥያን አየሁ።2እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ክፋትን የሚያስቡ በዚህችም ከተማ ክፉን ምክር የሚመክሩ ሰዎች ናቸው። 3እነርሱም 'ቤቶችን የምንሠራበት ዘመን አይደለም። ይህች ከተማ ድስት እኛም ሥጋ ነን' ብለዋል። 4ስለዚህ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገርባቸው፣ ትንቢት ተናገር።5የእግዚአብሔርም መንፈስ በኔ ላይ ሆኖ እንዲህ አለኝ፥ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ተናገር። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን ነገር ተናግራችኋል፥ እኔም የልባችሁን አሳብ አውቃለሁ። 6በዚህች ከተማ ውስጥ ብዙ ሰዎችን ገድላችኋል ጎዳናዎችዋንም በሬሳዎቻቸው ሞልታችኋል። 7ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአየሩሳሌም ከተማ መካከልም ሬሳዎቻቸው ያኖራችኋቸው የገደላቹኋቸው ሰዎች ሥጋው ሲሆኑ፥ ይህችም ከተማ ድስቱ ናት። እናንተን ግን ከከተማዋ መካከል ተነቅላችሁ ትወጣላችሁ።8ሰይፍን ፈርታችኋል እኔም ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦ 9ከከተማይቱ መካከል አወጣችኋለሁ፥ በእንግዶችም እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ በላያችሁም ፍርድ አመጣባችኋለሁ። 10በሰይፍ ትወድቃላችሁ በእስራኤልም ድንበር ውስጥ እፈርድባችኋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።11ይህች ከተማ የማብሰያ ድስት አትሆንላችሁም እናንተም በመካከልዋ ሥጋ አትሆኑም፣ እኔም በእስራኤል ድንበር ውስጥ እፈርድባችኋለሁ። 12እኔም በትዕዛዙ ያልሄዳችሁለት ፍርዱንም ያላደረግችሁለት እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። ይልቁኑ በዙሪያችሁ እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ሕግ አድርጋችኋል።13እንዲህም ሆነ ትንቢትም በተናገርሁ ጊዜ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፣ እኔም በግምባሬ ተደፍቼ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! በውኑ የእስራኤልን ቅሬታ ፈጽመህ ታጠፋለህን?" ብዬ በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ።14የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ 15"የሰው ልጅ ሆይ፥ ወንድሞችህ! አዎ ወንድሞችህ! ዘመዶችህ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ! 'እነርሱ ከእግዚአብሔር የራቁ ናቸው! ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች' የሚሉአቸው ናቸው።16ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው፣ 'ምንም እንኳ እኔ በሩቅ ወዳሉ አሕዛብ ባርቃቸውና ወደ አገሮችም ብበትናቸውም በሄዱባቸው አገሮች ለጥቂት ጊዜ ቤተ መቅደስ ሆኜላቸዋለሁ' ። 17ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው 'ከአሕዛብ ዘንድ አከማቻችኋለሁ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ፥ የእስራኤልንም ምድር እሰጣችኋለሁ። 18ወደዚያም ይመጣሉ፥ ጸያፉንና ርኩሱንም ነገር ሁሉ ከዚያች ምድር ያስወግዳሉ።19ወደኔ ሲቀርቡ አንድ ልብ እሰጣቸዋለሁ፥ በውስጣቸውም አዲስ መንፈስ አስቀምጣለሁ፤ 20ከሥጋቸውም ውስጥ ድንጋዩን ልብ አውጥቼ የሥጋን ልብ እሰጣቸዋለሁ፣ ይህም በትእዛዜም እንዲሄዱና ፍርዴንም እንዲጠብቁና እንዲያደርጉት ነው። በዚያን ጊዜ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። 21በልባቸው ወደ ጸያፍና ርኩስ ነገሮቻቸው በሚሄዱት ላይ መንገዳቸውን ወደራሳቸው እመልሳለሁ። ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው። "22ኪሩቤልም ክንፎቻቸውንና በአጠገባቸው የነበሩትን መንኰራኵሮች ከፍ አደረጉ፣ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ። 23የእግዚአብሔርም ክብር ከከተማይቱ ውስጥ ተነሥቶ በከተማይቱ ምሥራቅ በኩል ባለው ተራራ ላይ ቆመ።24መንፈስም አነሣኝ፥ ከእግዚአብሔርም ዘንድ በሆነ ራእይ ምርኮኞቹ ወዳሉበት ወደ ከላውዴዎን ምድር አመጣኝ። ያየሁትም ራእይ ከእኔ ተለየ። 25ከዚያም እግዚአብሔር ያሳየኝን ነገር ሁሉ ለምርኮኞች ነገርኳቸው።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ የምትኖረውዓመጸኞች ከመሆናቸው የተነሳ አይን እያላቸው በማያዩ ጆሮ እያላቸው በማይሰሙ በዓመፀኛ ሰዎች መካከል ነው!3አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፥ ለስደት ተዘጋጅ ምክንያቱም በፊታቸውም በጠራራ ፀሀይ ከስፍራህ ወደ ሌላ ስፍራ ተማርከህ እንድትሄድ አደርጋለ። ምናልባት ይህን ሲያዩ ዓመፀኛ ቤት እንደ ሆኑ ያስተውሉ ይሆናል።4እቃዎችህን ሰብስበህ በቀን በፊታቸው ለስደት ተዘጋጅ፤ በማታም ጊዜ በፊታቸው ልክ ስደተኞች እንደሚያደርጉት ሂድ። 5እያዩህም ግንቡን ፈንቅለውና በእዚያ በኩል ውጣ። 6እያዩህም እቃዎችህን በጫንቃህ ላይ ተሸከምና በጨለማ ውጣ። ለእስራኤልም ህዝብ ምልክት አድርጌሃለሁና ምድሪቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።7እንዳዘዘኝም አደረግሁ። በቀንም የስደት እቃዬን ወስጄ ማታ ላይ ግንቡን በእጄ ፈነቀልኩና በጨለማ አወጣቼ እያዩኝ በጫንቃዬ ላይ ተሸከምሁት።8በነጋታውም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 9"የሰው ልጅ ሆይ፥ ዓመፀኛው የእስራኤል ቤት 'የምታደርገው ምንድር ነው?' ብለው ጠየቁህን? 10አንተም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ይህ ትንቢታዊ ጉዳይ በኢየሩሳሌም የሚኖረውን አለቃና በመካከላቸውም የሚኖሩትን የእስራኤል ቤትን ሁሉ የሚመለከት ነው' በላቸው።11ደግሞም፦ እኔ ምልክታችሁ ነኝ እኔ እንዳደረግሁ እንዲሁ ይደረግባቸዋል፥ እነርሱም በስደት ወደ ምርኮ ይሄዳሉ በላቸው። 12በመካከላቸውም የሚኖረው አለቃ ንብረቱን በጫንቃው ላይ ተሸክሞ ግንቡን ፈንቅሎ በጨለማ ይወጣል። ንብረታቸውን ለማውጣት ግንቡን ይፈነቅላሉ። አለቃውም በዓይኑ ምድሪቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል። 13መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ከለዳውያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል።14ሊረዱትም በዙሪያው ያሉትን ሁሉና ወታደሮቹን ሁሉ በየእቅጣጫው እበትናቸዋለሁ፣ከኋላቸውም ሰይፍ እልክባቸዋለሁ። 15በአሕዛብም መካከል በበተንኋቸው ጊዜ፥ በአገሮችም በዘራኋቸው ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 16ነገር ግን በሚሄዱባቸውም አሕዛብ መካከል ርኵሰታቸውን ሁሉ እንዲመዘግቡ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም ጥቂቶች ሰዎችን ከእነርሱ አተርፋለሁ፣ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።17የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ 18"የሰው ልጅ ሆይ፥ እንጀራህን በመረበሽ ብላ ውኃህንም በመንቀጥቀጥና በኀዘን ጠጣ።19ለምድሪቱም ሕዝብ 'ጌታ እግዚአብሔር ስለኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና ስለ እስራኤል ምድር እንዲህ ይላል 'ክሚኖሩባት ሰዎች አመጽ የተንሳ ምድሪቱ ሞላዋ ስለምትጠፋ እንጀራቸውን በመረበሽ ወኃቸውንም በድንጋጤ ይጠጣሉ። 20ሰዎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ባድማ ይሆናሉ ምድሪቱም ውድማ ትሆናለች እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።21የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ, 22"የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር የሚነገረው'ዘመኑ ረዝሞአል ራእዩም ሁሉ ጠፍቶአል' የሚለው ምሳሌ ምንድር ነው? 23ስለዚህ እንዲህ በላቸው 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ክዚህ በኋላ የእስራኤል ህዝብ እንዳይጠቀሙበት ይህን ምሳሌ አስቀረዋለሁ ።' ከዚያም እንዲህ በላቸው "ዘመኑ ቀርቦአል እያንዳንዱ ራዕይም ይናገራል!'24ምክንያቱም ከዚህ በኋላ በእስራኤል ቤት መካከል ከንቱ ራእይና ውሸተኛ ምዋርት አይሆንም። 25እኔ እግዚአብሔር ነኝና! እናገራለሁ የተናገርኩትንም ቃል እፈጽማለሁ። ነገሩ ከእንግዲህ አይዘገይም። እናንተ ዓመፀኛ ቤት ሆይ፥ በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ እፈጽመውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"26የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል እንደገና መጣ፣ 27"የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ የእስራኤል ቤት 'ይህ ያየው ራእይ ገና ስለወደፊቱ ነው ስለሩቅ ዘመንም ትንቢት ይናገራል' ብለዋል። 28ስለዚህ እንዲህ በላቸው 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከዚህ በኋላ አይዘገይም' ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው!"
1የእግዚአብሔርም ቃል እንደገና ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት በሚናገሩ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፥ ከገዛ ልባቸውም ትንቢት የሚናገሩትን 'የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! 3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምንምን ሳያዩ የገዛ መንፈሳቸውን ለሚከተሉ ለሰነፎች ነቢያት ወዮላቸው! 4እስራኤል ሆይ፥ ነቢያትህ በምድረ በዳ እንደሚኖሩ ቀበሮች ናቸው።5፥ በእግዚአብሔርም ቀን በሰልፍ ትቆሙ ዘንድ ልትጠግኑት ወደ ፈረሰው ቅጥር አልወጣችሁም ። 6እግዚአብሔር ሳይልካቸው "እግዚአብሔር እንዲህና እንዲህ ይላል" የሚሉ ሰዎች ውሸተኛ ትንቢትንና ውሸተኛ ራዕይን አይተዋል። ያም ሆኖ ግን ቃላቸው እንደሚፈጸም ተስፋ ያደርጋሉ። 7እኔም ሳልናገር "እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል" የምትሉ እናንተ ከንቱ ራእይን ያያችሁ ውሸተኛንም ትንቢትን መናገራቼሁ አይደለምን?8ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ ውሸት ስለተናገራችሁ ጌታ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚናገረው ይህ ነው፡ 9እጄም ከንቱ ራእይን በሚያዩ፥ የውሸት ትንቢት በሚናገሩ ነቢያት ላይ ይሆናል። እነርሱም በሕዝቤ ጉባኤ ውስጥ አይገኙም፥ በእስራኤልም ቤት መዝገብ ላይ አይጻፉም፥ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ!10በዚህም ምክንያት ሰላም ሳይኖር "ሰላም ነው!" እያሉ ሕዝቤን መረን ሰደዋል፣ ገለባ በሌለበት ጭቃ የተመረገ ቅጥር ይገነባሉ። 11ቅጥሩን ገለባ በሌለበት ጭቃ ለሚመርጉት ሰዎች እንዲህ በላቸው 'ቅጥሩ ይወድቃል፤ የሚያሰጥም ዝናብ ይዘንባል፥ ቅጥሩኔ ለማፍረስ ታላቅም የበረዶ ድንጋይ እልካለሁ፥ እንዲያደቀውም ዐውሎ ነፋስን እልካለሁ። 12እነሆ፥ ግንቡ በወደቀ ጊዜ። የመረጋችሁት ጭቃ ወዴት አለ? አይሉአችሁምን?13ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'በመዓቴ ዐውሎ ነፋስ አመጣለሁ ፥ በቍጣዬም ዶፍ ዝናብ ይዘንባል! በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ፈጽሞ ያወድመዋል። 14ገለባም በሌለበት ጭቃ የመረጋችሁትን ቅጥር አፈርሳለሁ ወደ ምድርም እጥለዋለሁ፥ መሠረቱም ይታያል። እርሱም ይናዳል እናንተም በመካከሉ ትጠፋላችሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።15በመዓቴም ግንቡንና ገለባ በሌለው ጭቃ የመረጉትን ሰዎችአጠፋለሁ። ግንቡም ሆነ መራጊዎቹ የሉም እላችኋለሁ። 16እነርሱም ስለ ኢየሩሳሌም ትንቢት የሚናገሩ የሰላምን ራእይ የሚያዩላት የእስራኤል ነቢያት ናቸው። ሰላምም የለም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር"17አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ከገዛ ልባቸው ትንቢት በሚናገሩ በሕዝብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊትህን አድርግ ትንቢትም ተናገርባቸው፥ 18እንዲህም በል፣ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስን ለማጥመድ በመላ እጆቸው የጥንቆላ መከዳ ለሚሰፉ ለራሶቻቸውም የተለያየ መጠን ያላቸው ሽፋን ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤንም ነፍስ ብታጠምዱ በውኑ ነፍሳችሁን ታድናላችሁን?19ውሸታችሁን ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ ለጭብጥ ገብስና ለቍራሽ እንጀራ ብላችሁ መሞት የማይገባቸውን ለመግደል በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን በሕይወት በማኖር በሕዝቤ ፊትአርክሳችሁኛል።20ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦እነሆ፥ እኔ ነፍሳትን እንደ ወፍ በምታጠምዱባት በአስማት መተቶቻችሁ ላይ ነኝ፥ ከክንዳችሁም ወስጄ እቀደዋለሁ፥ እንደ ወፍም ያጠመዳችኋቸውን ህዝብ ነጻ አወጣለሁ።21ሽፋኖቻችሁንም እቀድዳለሁ ሕዝቤንም ከእጃችሁ አድናለሁ፥ ከዚያም ወዲያ በእጃችሁ አይጠመዱም እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።22እኔም እንዲያዝን የማልፈልገውን የጻድቁን ልብ በውሸታችሁ አሳዝናችኋልና፥ በተቃራኒው ደግሞ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዳይኖር የኃጢአተኛውን ተግባር አበረታታችኋልና 23ሕዝቤን ከእጃችሁ ስለማድን ክእንግዲህ ከንቱን ራእይ አታዩም የውሸት ትንቢትም አትናገሩም፥ ምክንያቱም እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
1ከእስራኤልም ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑ ሰዎች ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። 2ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 3የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን በልባቸው አኑረዋል የበደላቸውንም መቅሠፍት በፊታቸው አቁመዋል ታዲያ እኔ ከእነርሱ ጥያቄ መቀበል አለብኝ?4ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ። 5ይህንንም የማደርገው ሁሉም በጣዖቶቻቸው ምክንያት ከእኔ በጣም በራቀው በልባቸው የእስራኤልን ቤት እንደገና ለመመለስ ነው!' ብለህ ንገራቸው።6ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፣ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ንስሐ ግቡ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ፥ ፊታችሁንም ከርኵሰታችሁ ሁሉ መልሱ።7ከእስራኤልም ቤት፥ በእስራኤልም ዘንድ ከሚቀመጡ መጻተኞች ማንም፥ ከእኔ ተለይቶ ጣዖቶቹን በልቡ ያኖረ፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ ያቆም ሰው ሁሉ፥ ጥያቄ ይዞ ወደ ነቢዩ ቢመጣ ፥ እኔ እግዚአብሔር እራሴ እመልስለታለሁ! 8ፊቴንም እዞርበታለሁ ከሕዝቤም መካከል አጠፋውና መቀጣጫና ምሳሌም አደርገዋለሁ ፣ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ!9ነቢዩም ስቶ ሳለ መልዕክትን ቢናገር፥ እኔ እግዚአብሔር ያንን ነቢይ አስተዋለሁ፥ እጄንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ ከሕዝቤም ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ። 10ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ የነቢዩ ኃጢአት መልዕክት ፍለጋ ወደእርሱ የሄደ ሰው ኃጢአት አንድ ይሆናል። 11በዚህም ምክንያት ከዚህ በኋላ የእስራኤል ቤት ከእኔ ርቀው አይቅበዘበዙም በኃጢአታቸውም ሁሉ አይረክሱም። እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"12የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 13የሰው ልጅ ሆይ፥ ምድር በማመፅ በእኔ ላይ ኃጢአት ብትሠራ፥ እኔም እጄን ብዘረጋባት የእንጀራዋንም በትር ብሰብር ራብን ብሰድድባት ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ባጠፋ፥ 14እነዚህም ሦስት ሰዎች፥ ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብም፥ በመካከልዋ ቢገኙ እነርሱ በጽድቃቸው ሊያዱኑ የሚችሉት የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ነበር፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦15ክፉዎቹን አራዊት በምድር ባሳልፍ እነርሱም ልጆችዋን ቢያጠፉ ስለ አራዊትም ማንም እንዳያልፍባት ባድማ ብትሆን፥ 16እነዚህም ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦17ወይም በዚያች ምድር ላይ ሰይፍ አምጥቼ። ሰይፍ ሆይ፥ በምድሪቱ ላይ እለፊ ብል፥ ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ባጠፋ፥ 18እነዚህም ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦19ወይም በዚያች ምድር ላይ ቸነፈር ብሰድድ ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ለማጥፋት መዓቴን በደም ባፈስስባት፥ 20ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና በጽድቃቸው ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦21ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ይልቁንስ ሰውንና እንስሳን ከእርስዋ አጠፋ ዘንድ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን፥ ሰይፍንና ራብን ክፉዎችንም አውሬዎች ቸነፈርንም፥ በመስደድ ነገሮች እንዲከፉ አደርጋለሁ።22ነገር ግን፥ እነሆ! ከወንዶችና ሴቶች ልጆች ጋር የሚያመልጡ ቅሬታዎች ይተርፉላታል። እነሆ! ወደ እናንተ ይወጣሉ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ በኢየሩሳሌምም ላይ ስላመጣሁት ቅጣት በምድሪቱም ላይ ስላመጣሁባት ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ ። 23መንገዳቸውንና ሥራቸውን ባያችሁ ጊዜ ያጽናኑአችኋል ያደረግሁባትንም ሁሉ በከንቱ እንዳላደረግሁባት ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ የወይን ግንድ፥ በዱር ዛፎች መካከል ካለ ቅርንጫፎቼ ካሉት ማንኛውም ዛፍ ብልጫው ምንድር ነው? 3በውኑ ሥራ የሚሠራበትን እንጨት ከወይን ግንድ ይወስዳሉን? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ችካል ከእርሱ ይወስዳሉን? 4እነሆ፥ ለመቃጠል በእሳት ላይ ቢጣል ፥ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹንና በልቶአል፥ መካከሉንም ቢያቃጥለው በውኑ ለሥራ ይጠቅማልን?5እነሆ፥ ደህና ሳለ ለሥራ ካልጠቀመ፥ ይልቁንስ እሳት ከበላው እርሱም ከተቃጠለ በኋላ ለምንም አይጠቅምም! 6ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካከል ካሉት ዛፎች ይልቅ የወይን ግንዱን እሳት ይበላው ዘንድ እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳልፌ እሰጣለሁ።7ፊቴንም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ ከእሳትም ይወጣሉ፥ እሳት ግን ይበላቸዋል ፊቴንም በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 8ዓመፅን አድርገዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!"
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2የሰው ልጅ ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ርኵሰትዋን አስታውቃት፥ 3እንዲህም በል፣ "ጌታ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይላል፡ ዘርሽና ትውልድሽ ከከነዓን ምድር ነው አባትሽ አሞራዊ ነበረ እናትሽም ኬጢያዊት ነበረች።4በተወለድሽ ጊዜ እናትሽ እትብትሽን አልቆረጠችም ፣ በውኃ አላጠበችሽም ወይም በጨው አላሸችሽም፣ በጨርቅም አልጠቀለለችሽም። 5ከእነዚህ ነገሮች አንዱን እንኳ ሊያደርግልሽ ማንም አልራራልሽም! በተወለድሽበት ቀን በሜዳ ላይ ተጣልሽ።6እኔ ግን በአንቺ ዘንድ ባለፍሁ ጊዜ በደምሽም ውስጥ ተለውሰሽ አየሁ፤ ስለዚህም በደምሽ እንዳለሽ "በሕይወት ኑሪ!" አልሁሽ። 7በእርሻ ላይ እንዳለ ቡቃያ አሳደግሁሽ። አንቺም አደግሽ ታላቅም ሆንሽ፥ በእጅጉም አጌጥሽ። ጡቶችሽም አጐጠጐጡ ጠጕርሽም አደገ፥ ነገር ግን ዕርቃንሽን ሆነሽ፥ ተራቍተሽም ነበር።8እንደገና በአንቺ ዘንድ ባለፍሁና ባየሁሽ ጊዜ፥ እነሆ፥ ጊዜሽ የፍቅር ጊዜ ነበረ እኔም መጐናጸፊያዬን በላይሽ ዘርግቼ እራቁትነትሽን ሸፈንኩ።ከዚያም ማልሁልሽ ከአንቺም ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ አንቺም ለእኔ ሆንሽ።9በውኃም አጠብሁሽ ከደምሽም አጠራሁሽ በዘይትም ቀባሁሽ። 10በወርቅ የተንቆጠቆጠ ልብስም አለበስሁሽ ከቆዳ የተሰራ ጫማ አደረግሁልሽ፤ በጥሩ በፍታ አስታጠቅሁሽ በሐርም ከደንሁሽ። 11በጌጥም አስጌጥሁሽ በእጅሽም ላይ አንባር በአንገትሽም ላይ ድሪ አደረግሁልሽ። 12በአፍንጫሽም ቀለበት በጆሮሽም ጕትቻ በራስሽም ላይ የክብር አክሊል አደረግሁ።13በወርቅና በብር አጌጥሽ፤ ልብስሽም ጥሩ በፍታና ሐር ወርቀ ዘቦም ነበረ፤ አንቺም መልካምን ዱቄትና ማርን ዘይትንም በላሽ እጅግ በጣም ውብ ነበርሽ ከዚያም ንግሥት ሆንሽ። 14ባንቺ ላይ ካኖርኋት ከክብሬ የተነሣ ውበትሽ ፍጹም ነበረና ዝናሽ በአሕዛብ መካከል ወጣ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦15ነገር ግን በውበትሽ ታምነሻል ስለ ዝናሽም አመንዝረሻል ምንዝርናሽንም ከመንገድ አላፊ ሁሉ ጋር አበዛሽ። የእነርሱም ንብረት ሆንሽ! 16ከልብስሽም ወስደሽ በኮረብቶች ላይ በዝንጕርጕር ልብስ ያስጌጥሻቸውን መስገጆች ለራስሽ ሠራሽ በዚያም ገለሞትሽ። እንዲህም ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልነበረም፥ ከእንግዲህም ወዲያ አይሆንም።17ከሰጠሁሽም ከወርቄና ከብሬ የተሠራውን የክብርሽን ዕቃ ወስደሽ የወንድ ምስሎች ለራስሽ አድርገሻል አመንዝረሽባቸውማል። 18ወርቀዘቦውን ልብስሽንም ወስደሽ ደረብሽላቸው፥ ዘይቴንና ዕጣኔንም በፊታቸው አኖርሽ። 19የሰጠሁሽንም እንጀራዬን ያበላሁሽንም መልካሙን ዱቄትና ዘይቱን ማሩንም ጣፋጭ ሽታ አድርገሽ በፊታቸው አኖርሽ፥ ይህ በእርግጥ ሆኖአል! ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦20ለእኔም የወለድሻቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽን ወስደሽ መብል ይሆኑ ዘንድ ለጣዖታቱ ሠዋሽላቸው። በውኑ የግልሙትና ተግባርሽ እንደ ቀላል የሚታይ ነገር ነውን? 21ልጆቼን አረድሽ ለእነርሱም የሚቃጠል መስዋዕት አድርገሽ አቀረብሽ 22በዚህ ሁሉ የርኵሰትና የግልሙትና ተግባርሽ ወቅት ዕርቃንሽን ተራቍተሽ በደምሽም ተለውሰሽ የነበርሽበትን የሕፃንነትሽን ወራት አላሰብሽም።23ወዮ! ወዮልሽ! ይላል ጌታ እግዚአብሔር 24ከክፋትሽም ሁሉ በኋላ የጣዖት ማምለኪያ ስፍራ፥ በየአደባባዩም አጸዶችን ሠራሽ።25በየመንገዱ ራስ ከፍ የማምለኪያ አጸዶችን ሠራሽ፥ ለመንገድ አላፊም ሁሉ እግርሽን በመግለጥና በርካታ የግልሙትና ተግባራት በመፈጸም ውበትሽን አረከስሽ ። 26እጅግ የሴሰኝነት ፍላጎት ካላቸው ከጐረቤቶችሽ ከግብጻውያን ጋር አመነዘርሽ፥ እኔንም ታስቈጭ ዘንድ ግልሙትናሽን አበዛሽ።27ስለዚህ፥ በእጄ አደቅሻለሁ እህልንም ከአንቺ ዘንድ አጠፋለሁ። ለሚጠሉሽም ከክፉ ምኞትሽ የተነሣ ለውርደት ለሚዳርጉሽ ለፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች ፈቃድ አሳልፌ ሰጥቼሻለሁ። 28አልጠግብ ብለሽ ከአሦራውያን ጋር ደግሞ ገለሞትሽ። ያም ሆኖ ግን አሁንም አልበቃሽም። 29እስከ ነጋዴዎች ምድር እስከ ከላውዴዎን ድረስ ግልሙትናሽን አበዛሽ። አሁንም ግን ገና አልጠገብሽም።30የማታፍረውን የጋለሞታን ሥራ ሁሉ ሠርተሻልና ልብሽ ምንኛ ደካማ ነው? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦ 31በየመንገዱ ራስ የምንዝርናሽን ስፍራ ሠርተሻል በየአደባባዩም ከፍ ያለውን ቦታሽን አድርገሻል። ዋጋዋን እንደምትንቅ እንደ ጋለሞታ አልሆንሽም።32አንቺ ዘማዊ ሴት በባልሽ ፋንታ ሌሎች እንግዳ ሰዎች ተቀበልሽ። 33ሰዎች ለጋለሞቶች ሁሉ ዋጋ ገንዘብ ይከፍላሉ አንቺ ግን ለውሽሞችሽ ገንዘብ ትከፍያለሽ፥ ከአንቺም ጋር ለማመንዘር ከአካባቢው ሁሉ ወድ እንቺ እንዲምጡ ማባበያ ትሰጫቸዋለሽ። 34ግልሙትናሽ ከሌሎች ሴቶች ፈጽሞ የተለየ ነው፥ ምክንያቱም ማንም ከአንቺ ጋር ልትኛ ብሎ የሚጠይቅሽ የለም። ይልቁኑ አንቺ ትከፍያቸዋለሽ እንጂ የሚክፍልሽ የለም።35ስለዚህ፥ ጋለሞታ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ! 36ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከውሽሞችሽና ከአጽያፊ ጣዖታትሽ ጋር ባደረግሽው ግልሙትና አማካኝነት ክፉ ምኞትሽን በማፍሰስሽና ኀፍረተ ሥጋሽንም በመግለጥሽ እንዲሁም ለጣዖታትሽ በሰጠሻቸው በልጆችሽ ደም ምክንያት፥ 37እነሆ፥ ከእነርሱ ጋር ደስ ያለሽን የወደድሻቸውንም ውሽሞችሽና የጠላሻቸው ሁሉ ከሁሉም አቅጣጫ በአንቺ ላይ እንዲነሱ እሰበስባቸዋለሁ። እራቁትነትሽን እንዲያዩ በፊታቸው ኀፍረተ ሥጋሽን እገልጣለሁ።38ስለምንዝርናሽና ደም ማፍሰስሽ እቀጣሻለሁ፥ በቁጣዬና በቅንዓቴ ደም መፋሰስን አመጣብሻለሁ። 39በእጃቸውም አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ የምንዝርናሽንም ስፍራ ያፈርሳሉ ከፍ ያለውንም ቦታሽን ይገለብጣሉ ልብስሽንም ይገፉሻል የክብርሽንም ጌጥ ይወስዳሉ፥ ዕርቃንሽን አድርገው ዕራቁትሽን ይተዉሻል።40ህዝብንም ያስነሱብሻል በድንጋይም ይወግሩሻል፥ በሰይፋቸውም ይሰነጥቁሻል። 41ቤቶችሽንም በእሳት ያቃጥላሉ በብዙም ሴቶች ፊት ብዙ ቅጣቶችን ይፈጽሙብሻል፥ ግልሙትናሽንም አስተውሻለሁ፥ ከእንግዲህ ለእነርሱ ዋጋ አትሰጭም! 42መዓቴንም በአንቺ ላይ እጨርሳለሁ ቅንዓቴም ከአንቺ ይርቃል፥ እኔም እረካለሁ፣ከዚያ በኋላም አልቈጣም።43በእንዚህ ነገርች ሁሉ ስታስቆጪኝ የሕፃንነትሽን ወራት አላሰብሽምና፥ ስለዚህ፥ እነሆ፥ እኔ እራሴ ለፈጸምሽው ጥፋት ቅጣትን በአንቺ ላይ አመጣለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ከዚህ በኋላ በአስነዋሪ መንገድሽ በክፋት አትሄጂም።44እነሆ፥ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፥ "ልክ እንደ እናቲቱ ሴት ልጂቱ እንደዛው ናት" እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል። 45አንቺ ባልዋንና ልጆችዋን የጠላች የእናትሽ ልጅ ነሽ፤ ደግሞም ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን የጠሉ የእኅቶችሽ እኅት ነሽ። እናታችሁ ኬጢያዊት ነበረች አባታችሁም አሞራዊ ነበረ።46ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ሰሜን የምትኖረው ሰማርያ ናት ታናሺቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ምዕራብ የምትኖረው ሰዶም ናት።47አንቺ ግን በመንገዳቸው አልሄድሽም እንደ ርኵሰታቸውም አላደረግሽም የእነርሱ ድርጊት ለአንቺ ጥቂት ነበረና። ይልቁኑ በመንገድሽ ሁሉ ከእነርሱ የከፋሽ ሆንሽ። 48በህያውነቴ እምላለሁ አንቺና ሴቶች ልጆችሽ ያደርጋችሁትን ክፋት ያህል ሰዶምና ሴቶች ልጆችዋ አላደረጉም! ይላል ጌታ እግዚአብሔር።49እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፡ በሥራ ፈትነት የበረታች፣ ስለምንም ነገር የማይሰማት ግድ የለሽት ነበረች። የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላበረታችም ። 50ትዕቢተኛ ነበረች በፊቴም ርኩስ ነገርችን አደረገች፣ እንዳየሽውም አጠፋኋቸው።51ሰማርያም የኃጢአትሽን እኵሌታ እንኳ አልሠራችም ፤ አንቺ ግን ከእኅቶችሽ ይልቅ ርኵሰትሽን አበዛሽ፥ በሠራሽውም ርኵሰት ሁሉ እህቶችሽ ካንቺ እንድሚሻሉ አሳየሽ። 52አሁንም ለእኅቶችሽ ስለ ፈረድሽ እፍረትሽን ተሸከሚ ከእነርሱ የባሰ ኃጢአት ሠርተሻልና ከአንቺ ይልቅ የተሻሉ ሆነው ታይተዋል። እህቶችሽ ካንቺ እንድሚሻሉ በማሳየትሽ እፈሪ ።53የሰዶምና የሴቶች ልጆችዋን ምርኮ፥ የሰማርያንና የሴቶች ልጆችዋንም ምርኮ እመልሳለሁ፤ ነገር ግን የአንቺ ምርኮ በእነርሱ መካከል ይሆናል። 54በእዚህም ነገሮች ቀመር እፍረትሽን ታሳዪአለሽ ስለ አደረግሽውም ሁሉ ታፍሪያለሽ፣ በዚህም ምክንያት ለእነርሱ መጽናኛ ትሆኚያለሽ። 55እኅቶችሽም ሰዶምና ሴቶች ልጆችዋ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ፥ ሰማርያና ሴቶች ልጆችዋም ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ። ከዚያም አንቺና ሴቶች ልጆችሽ ወደ ቀድሞ ሁኔታችሁ ትመለሳላችሁ።56ኩሩ በነበርሽ ጊዜ ስለ እኅትሽ ሰዶም ተናግረሽ አታውቂም ነበር፥ 57ክፋትሽ ከመገለጡ በፊትማለት ነው። አሁን ግን ለኤዶም ሴቶች ልጆችና በጎረቤቶችዋ ላሉ የፍሊስጤማውያን ልጆች ሁሉ፥ የውርደት ምሳሌ ሆነሻል። ሰው ሁሉ ይንቅሻል። 58ምንዝርነትሽንና ርኵስነትሽን ይገለጣል ፥ ይላል እግዚአብሔር፦59ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ቃል ኪዳንን ለማፍረስ መሐላን በሚንቅ ሁሉ ላይ የማደርገውን በአንቺም ላይ አደርጋለሁ።60ነገር ግን በሕፃንነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳኔን እኔ እራሴ አስባለሁ የዘላለምንም ቃል ኪዳን ከአንቺ ጋር እገባለሁ። 61እኅቶችሽንም ታላቂቱንና ታናሺቱን በተቀበልሽ ጊዜ መንገድሽን ታስቢያለሽ ታፍሪማለሽ። ለአንቺም ልጆች ይሆኑ ዘንድ እሰጣቸዋለሁ፥ ይህን የማደርገው ግን ስለ ቃል ኪዳንሽ አይደለም።62ቃል ኪዳኔን ከአንቺ ጋር አጸናለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ! 63በዚህም ምክንያት ስላደረግሽውም ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ ያደርግሽውን ሁሉ አስበሽ ታፍሪያለሽ ከዚያም ወዲያ ለምናገር አፍሽን አትከፍቺም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
1የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ 2የሰው ልጅ ሆይ፥ በእንቈቅልሽ አጫውት እንዲህም ብለህ ለእስራኤል ቤት ምሳሌ ንገራቸው ፥ 3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ክንፍ ረጅምም ማርገብገቢያ ያለው ላባም የተሞላ፥ መልከ ዝንጕርጕር ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፥ የዛፍ ቅርንጫፍን ጫፍ ወሰደ። 4የቅርንጫፉን ጫፍ ወደ ከነዓንም ምድር ወሰደው በነጋዶችም ከተማ ተከለው።5ከዚያም ምድር ዘር ወሰደ በፍሬያማ እርሻም ተከለው። በብዙም ውኃ አጠገብ እንደ አኻያ ዛፍ አኖረው። 6በበቀለም ጊዜ ቁመቱ ያጠረ አረጉም ወደ እርሱ የሚመለስ ሥሩም በበታቹ የነበረ ሰፊ ወይን ሆነ።7ታላቅ ክንፍና ብዙ ላባም ያለው ሌላ ታላቅ ንስር ነበረ። እነሆም፥ ውሀ ያጠጣው ዘንድ ይህ ወይን ሥሩን ወደ እርሱ አዘነበለ አረጉንም ከተተከለበት ከመደቡ ወደ እርሱ ሰደደ። 8አረግም ያወጣ ፍሬም ያፈራ የከበረም ወይን እንዲሆን በመልካም ላይ በብዙም ውኃ አጠገብ ተተክሎ ነበር።9ለህዝቡም እንዲህ በል፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ ይከናወንለት ይሆንን? ይደርቅስ ዘንድ፥ አዲስ የበቀለውስ ቅጠሉ ይጠወልግ ዘንድ ሥሩን አይነቅለውምን? ፍሬውንስ አይለቅመውምን? የትኛውም ጠንካራ ክንድ ወይም ብዙ ህዝብ ሥሩን ሊነቅል አይችልም። 10እነሆ፥ ከተተከል በኋላስ ይከናወንለት ይሆንን? የምሥራቅ ነፋስ ባገኘው ጊዜ ፈጽሞ አይደርቅምን? በተተከለበት መደብ ላይ ይደርቃል።11የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 12"ለዓመፀኛ ቤት፥ 'የዚህ ነገር ትርጓሜ ምን እንደ ሆነ አታውቁምን? እነሆ፥ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፥ ወደ እርሱም ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።13ከንጉሳዊያን ዘር የሆነውን ወስዶ ቃል ኪዳን ከእርሱ ጋር አደረገ አማለውም። የምድሪቱንም ኃያላን ወሰደ 14ይኸውም ቃል ኪዳኑን በመጠበቅ እንድትጸና እንጂ መንግሥቱ እንድትዋረድና ከፍ እንዳትል ነው።15የኢየሩሳሌም ንጉስ ግን በእርሱ ላይ ሸፈተ ፈረሶችንና ብዙንም ሕዝብ ይሰጡት ዘንድ መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ላከ። በውኑ ይከናወንለት ይሆንን? ይህንስ ያደረገ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንንስ አፍርሶ ያመልጣልን? 16በህያውነቴ እምላለሁ! ባነገሠውና መሐላውን በናቀበቱ፥ ቃል ኪዳኑንም ባፈረሰበቱ ንጉሥ ምድር ይሞታል። በባቢሎን መካከል ይሞታል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦17የባቢሎን ሠራዊት ብዙዎችን ነፍሳት ለማስወገድ አፈርን በደለደሉ ምሽግም በሠሩ ጊዜ፥ ፈርዖን ከብዙ ሠራዊቱና ከታላቁ ጉባኤው ጋር የኢየሩሳሌምን ንጉሥ በሰልፍ አይረዳውም። 18ይህም የሚሆነው መሐላውን ንቆ ቃል ኪዳኑንን በማፍረሱ ነው። ለቃል ኪዳን እጁን ዘርጋ፥ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች አደረገ። ስለዚህ አያመልጥም።19ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በህያውነቴ እምላለሁ የናቀው መሐላዬን ያፈረሰስ ቃል ኪዳኔን አይደለምን? ስለዚህ ቅጣትን በርሱ ላይ አመጣለሁ! 20መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ በማጥመጃ መረቤም ይያዛል። ወደ ባቢሎንም አመጣዋለሁ በእኔም ላይ ስላደረገው ዓመፅ በዚያ በእርሱ ላይ እፈርዳለሁ። 21ጭፍሮቹም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ የቀሩትም ሁሉ በየአቅጣጫው ይበታተናሉ። እኔም እግዚአብሔር እንደሆንኩ ይህም እንደሚሆን እንደ ተናገርሁ ታውቃላችሁ!'22ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'እኔ እራሴ ከረጅሙ ዝግባ ጫፍ ላይ ቀንበጥን እወስዳለሁ ከለምለም ቅርንጫፎቹ አርቄ እተክለዋለሁ። ቀንጥቤ እኔ እራሴ በረጅምና በታላቅ ተራራ ላይ እተክለዋለሁ! 23ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፥ ቅርንጫፎችም ያወጣል ፍሬም ያፈራል የከበረም ዝግባ ይሆናል በበታቹም በክንፍ የሚበርሩ ወፎች ሁሉ ያርፋሉ፥ በቅርንጫፎቹም ጥላ ውስጥ ጎጆአቸውን ይሰራሉ።24በዚያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ። ረጅሙን ዛፍ ዝቅ አደርጋለሁ፥ አጭሩንም ዛፍ ከፍ አድርጋለሁ! የለመለመውንም ዛፍ አደርቃለሁ፥ የደረቀውንም ዛፍ አለመልማለሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ይህ እንደሚሆን ተናግሬአለሁ እኔም አድርጌዋለሁ።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2"ስለ እስራኤል ምድር፥ 'አባቶች መራራ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ' ብላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድር ነው?3በህያውነቴ እምላለሁ እንግዲህ ወዲህ ይህን ምሳሌ በእስራኤል የምትናገሩብት ሁኔታ አይኖርም ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 4እነሆ፥ ነፍስ ሁሉ የእኔ ነው! የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች የልጅም ነፍስ የእኔ ናት! ኃጢአት የሚሰራ ሰው ይሞታል!5ሰውም ጻድቅ ቢሆን ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥ 6በተራራም ላይ ባሉ የጣዖት አምልኮ ስፍራ ባይበላ ዓይኞቹንም ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ በወር አበባ ላይ ወዳለች ሴት ባይቀርብ7ሰውንም ባያስጨንቅ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ የሌባ ተቀባይ ባይሆን ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ የተራቈተውንም ቢያለብስ8በአራጣ ባያበድር፥ የማይገባ ትርፍን ባይወስድ፥ ፍትህን ቢያደርግ፥ በሰውና በሰው መካከልም መተማመንን ቢፈጥር 9በትእዛዜም ቢሄድ፥ እውነትንም ለማድረግ ፍርዴን ቢጠብቅ፥ ይህ ሰው ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል! ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦10እርሱም ቀማኛና ደም አፍሳሽ ልጅ ከዚህም ሁሉ አንዳቸውን የሚያደርገውን ቢወልድ፥ 11እርሱም ጻድቅ አባቱ የሠራውን ሁሉ ባይሠራ በተራራምላይ ባሉ የጣዖት አምልኮ ስፍራ ላይ ቢበላ የባልንጀራውንም ሚስት ቢያረክስ፥12ድሀውንና ችግረኛውንም ቢያስጨንቅ ቢቀማም መያዣውንም ባይመልስ ዓይኖቹንም ወደ ጣዖታት ቢያነሣ ወይም ርኩስን ነገር ቢያደርግ፥ 13በአራጣ ቢያበድር፥ የማይገባ ትርፍ ቢወስድ፥ በውኑ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም! ይህን ርኵሰት ሁሉ አድርጎአልና ፈጽሞ ይሞታል ደሙም በላዩ ላይ ይሆናል።14እነሆም፥ ልጅ ቢወልድ፥ እርሱም አባቱ የሠራውን ኃጢአት አይቶ ቢፈራ እንዲህም ባይሠራ፥ 15በተራራ ባሉ የጣዖት አምልኮ ስፍራዎች ላይ ባይበላ ዓይኖቹንም ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ የባልንጀራውንም ሚስት ባያረክስ፥16ሰውንም ባያስጨንቅ መያዣውን ባይወስድ ባይቀማም ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ ለተራቈተውም ልብስን ቢያለብስ፥ 17እጁንም ድሀን ከመበደል ቢመልስ፥ በአራጣ ባያበድር የማይገባ ትርፍንም ባይወስድ፤ ፍርዴንም ቢያደርግ በትእዛዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ በአባቱ ኃጢአት አይሞትም።18አባቱ ግን ፈጽሞ በድሎአልና፥ ወንድሙንም ዘርፏልና፥ በሕዝቡም መካከል ክፉን ነገር አድርጎአልና እነሆ፥ እርሱ በበደሉ ይሞታል።19እናንተ ግን፥ 'ልጅ የአባቱን ኃጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን ባደረገ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና ባደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል! 20ኃጢአትን ያደረገ ሰው ይሞታል። ልጅ የአባቱን ኃጢአት አይሸከምም፥ አባትም የልጁን ኃጢአት አይሸከምም። የጻድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፥ የኃጢአተኛውም ኃጢአት በራሱ ላይ ይሆናል።21ኃጢአተኛውም ካደረጋት ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም። 22የበደለው በደል ሁሉ አይታሰብበትም በሠራው ጽድቅ በሕይወት ይኖራል።23በውኑ ከመንገዱስ ቢመለስና በሕይወት ቢኖር እንጂ በኃጢአተኛ ሞት እደሰታለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር24ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ ኃጢአትንም ቢሠራ ኃጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራት ጽድቅ ሁሉ አትታሰብለትም ባደረገው ዓመፅና በሠራት ኃጢአት በዚያች ይሞታል።25እናንተ ግን፥ 'የጌታ መንገድ የቀናች አይደለችም' ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንግዲህ ስሙ! በውኑ መንገዴ የቀናች አይደለችምን? ይልቅስ የእናንተ መንገድ ያልቀናች አይደለችምን? 26ጻድቁ ከጽድቁ ቢመለስ፥ ኃጢአትንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያም ቢሞት፥ እርሱ ባደረገው በደል ይሞታል።27ኃጢአተኛውም ከሠራው ኃጢአት ቢመለስ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ነፍሱን ያድናል። 28አስቦ ከሠራው በደል ሁሉ ተመልሶአልና ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።29ነገር ግን የእስራኤል ቤት፥ 'የጌታ መንገድ የቀናች አይደለችም!' ይላል። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ መንገዴ የቀናች ያልሆነው እንዴት ነው? የእናንተ መንገድስ የቀናች የሆነችው እንዴት ነው? 30የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለዚህ በመካከላችሁ በእያንዳንዱ ሰው እንደ መንገዱ እፈርድበታለሁ! ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።31የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ ምን ትሞታላችሁ? 32የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።
1አንተም በእስራኤል አለቆች ላይ ይህን ሙሾ አሙሽ፥ እንዲህም በል፥ 2'እናትህ ማን ነበረች? አንበሳ ነበረች ከአንበሳ ደቦል ጋር ተጋደመች ግልገሎችዋን አሳደገች። 3ከግልገሎችዋም አንዱን ደቦል አንበሳ እንዲሆንና ጠላቶቹን የሚቆራርጥ እንዲሆን አሳደገችው። ሰዎችንም በላ። 4አሕዛብም ወሬውን ሰሙ እርሱም በወጥመዳቸው ተያዘ፥ በሰንሰለትም አድርገው ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት።5እርስዋም ይመለሳል ብላ ብትጠብቅም ተስፋዋ እንደ ጠፋ ባየች ጊዜ፥ ከግልገሎችዋ ሌላን ወስዳ ደቦል አንበሳ እንዲሆን አሳደገችው። 6ደቦል አንበሳውም በአንበሶች መካከል ተመላለሰ ደቦል አንበሳም ሆነ ንጥቂያም ተማረ፥ ሰዎችንም በላ። 7መበለቶቻቸውን አስነወረ፥ ከተሞቻቸውንም አፈረሰ ከግሣቱም ድምፅ የተነሣ ምድሪቱና በሞላ ሰው አልባ ሆነች።8አሕዛብም ከየአገሩ ሁሉ ተሰበሰቡ፤ መረባቸውንም በእርሱ ላይ ዘረጉ በወጥመዳቸውም ተያዘ። 9በሰንሰለትም አድርገው በሳጥን አድርገው ወደ ባቢሎን ንጉሥ አመጡት። ድምፁም በእስራኤል ተራሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እንዳይሰማ ወደ አምባ አመጡት።10እናትህ በውኃ አጠገብ በደምህ ውስጥ እንደ ተተከለች ወይን ነበረች። ከውኃም ብዛት የተነሣ ፍሬያማና በቅርንጫፍ የትሞላች ነበረች ። 11ለእርስዋም ብርቱዎች በትሮች ነበሩአት እነርሱም ለነገሥታት በትሮች ነበሩ። ቁመቷም በዛፎች ቅርንጫፎች መካከል ከፍ አለ።12ነገር ግን በመዓት ተነቀለች ወደ መሬትም ተጣለች የምሥራቅም ነፋስም ፍሬዋን አደረቀ። ብርቱዎች ቅርንጫፎቿተሰበሩና ደረቁ፥ እሳትም በላቻው። 13አሁን በምድረ በዳ፥ በደረቅና ውሀ በሌለው መሬት ተተክላለች።14ከቅርንጫፎቿ እሳት ወጥቶ ፍሬዋ በላ፥ ጠንካራ ቅርንጫፍ የለባትም የነገሥታትም በትር ሊሆን የሚችልም የለም።' ይህ ሙሾ ነው፥ የልቅሶ ዝማሬም ይሆናል።
1እንዲህም ሆነ በሰባተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን የእስራኤል ሽማግሌዎች እግዚአብሔርን ሊጠይቁ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ።2የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 3"የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ሽማግሌዎች ተናገር፥ እንዲህም በላቸው። 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ትጠይቁ ዘንድ መጥታችኋልን? በህያውነቴ እምላለሁ በእናንተ አልጠየቅም! ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦4ትፈርድባቸዋለህን? የሰው ልጅ ሆይ፥ በውኑ ትፈርድባቸዋለህን? የአባቶቻቸውን ርኵሰት አስታውቃቸው! 5እንዲህም በላቸው፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን በመረጥሁበት ለያዕቆብም ቤት ዘር እጄን አንስቼ በማልሁበት ቀን በግብጽም ምድር በተገለጥሁላቸውና። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ ብዬ በማልሁላቸው ጊዜ፥ 6በዚያ ቀን ከግብጽ ምድር በጥንቃቄ ወደመረጥኩላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ የምድርም ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ምድር እንደማወጣቸው ማልሁላቸው!7እኔም፥ "ከእናንተ እያንዳንዱ ርኩስ ነገርንና የግብጽን ጣዖታት ከዓይኑ ፊት ያስወግድ። ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።" አልኋቸው።8እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ሊሰሙኝም አልወደዱም። እያንዳንዱ ርኩስ ነገሮችን ከአይኑ ፊት አላስወገደም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም በዚህም ጊዜ። በግብጽ ምድር መካከል ቍጣዬን ልፈጽምባቸው መዓቴንም ላፈስባቸው ወሰንኩ። 9ነገር ግን በመካከላቸው በሚኖሩበት ህዝብ መካከል እንዳይረክስ ስለ ስሜ ሰራሁ። ከግብጽ ምድር በማውጣት ራሴን በአይናቸው ፊት ገለጥኩላቸው።10ከግብጽም ምድር አወጣኋቸው ወደ ምድረ በዳም አመጣኋቸው። 11ሰው ቢያደርገው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዓቴንም ሰጠኋቸው፥ ፍርዴንም አስታወቅኋቸው። 12ለራሴ የለየኋቸው እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ምልክት እንዲሆን ሰንበታቴን ሰጠኋቸው።13ነገር ግን የእስራኤል ቤት በምድረ በዳ ዐመፁብኝ። በትዕዛዜም አልሄዱም፤ ይልቁኑ ሰው ቢያደርገው በሕይወት የሚኖርበትንም ፍርዴን ጣሉ። ሰንበታቴንም ፈጽመው አረከሱ፥ ስለዚህም አጠፋቸው ዘንድ ቍጣዬን በምድረ በዳ አፈስስባቸዋለሁ አልሁ። 14ነገር ግን በፊታቸው ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።15ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው የምድር ሁሉ ጌጥ ወደምትሆን ልሰጣቸው ወዳሰብኩት ምድር አላመጣቸውም ብዬ በምድረ በዳ ማልሁባቸው። 16ይህን የማልኩት ልባቸው ጣዖቶቻቸውን ስለተከተሉ፥ ፍርዴንም ስለጣሉ ፥ በሥርዓቴም ስላልሄዱ፥ ሰንበታቴንም ስላረከሱ ነው። 17ነገር ግን ዓይኔ ራራችላቸው እኔም አላጠፋኋቸውም፥ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልፈጀኋቸውም።18ለወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው በምድረ በዳ እንዲህ አልኋቸው፥ "በአባቶቻችሁ ሥርዓት አትሂዱ፤ ወጋቸውንም አትጠብቁ በጣዖቶቻቸውም አትርከሱ። 19እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ! በትእዛዜ ሂዱ ፍርዴንም ጠብቁ አድርጓትም! 20በእናንተና በእኔ መካከል ምልክት እንዲሆኑና እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ እንድታውቁ ሰንበታቴን ጠብቁ።"21ነገር ግን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ዐመፁብኝ። በሥርዓቴም አልሄዱም ወይም ሰው ቢፈጽመው በሕይወት የሚኖርባትን ፍርዴን አልጠበቁም። ሰንበታቴንም አረከሱ ስለዚህም በምድረ በዳ መዓቴን ላፈስባቸው ቍጣዬንም ልፈጽምባቸው ወሰንክ። 22ነገር ግን እጄን መለስሁ፥ በፊታቸውም ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።23ደግሞም ወደ አሕዛብ ልበትናቸው ፥ በአገሮችም መካከልም ለነቀፋ ላደርጋቸው በምድረ በዳ እጄን አንስቼ ማልሁባቸው። ፍርዴን አላደረጉምና 24ሥርዓቴንም ጥሰዋልና ሰንበታቴንም አርክሰዋልና ዓይናቸውም የአባቶቻቸውን ጣዖታቶች ተከትለዋልና ይህን ላደርግባቸው ወሰንኩ።25ደግሞም መልካም ያልሆነውን ሥርዓት በሕይወት የማይኖሩበትንም ህግ ሰጠኋቸው። 26እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ እንዲያውቁ አጠፋቸው ዘንድ፥ ማኅፀን የሚከፍተውን በኩር ሁሉ በእሳት ባሳለፉ ጊዜ፥ በመባቸው አረከስኋቸው።27ስለዚህ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ በዚህም ደግሞ አባቶቻችሁ ባደረጉት ዓመፅ አስቈጡኝ። 28እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ በኮረብታ ላይ ያለውን የጣዖት ማምለኪያ ሁሉና ቅጠልማውንም ዛፍ ባዩ ጊዜ፥ በዚያ መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቈጣኝን ቍርባናቸውን አቀረቡ። በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ። 29እኔም፥ "እናንተ ወደ እርሱ የምትሄዱበት ኮረብታማ ሥፍራ ምንድር ነው?" አልኋቸው። እስከ ዛሬም ድረስ ስሙ ባማ ተብሎ ተጠርቶአል።30ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደ አባቶቻችሁ ልማድ ለምን ትረክሳላችሁ? ለምን እንደአመንዝራ የሚያጸይፍ ተግባር ታከናውናላችሁ? 31ቍርባናችሁን ስታቀርቡ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ስታሳልፉ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ትረክሳላችሁ። ታዲያ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ከእናንተስ ዘንድ እጠየቃለሁን? በህያውነቴ እምላለሁ ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም-ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 32እናንተ "እንጨትና ድንጋይ እንድሚያመልኩት ወገኖች እንደ ሌሎች አሕዛብ እንሁን" ብላችሁ ያሰባችሁት ሀሳብ ይፈጸማል።33በህያውነቴ እምላለሁ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በእናንተ ላይ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር! 34ከአሕዛብም ዘንድ አወጣችኋለሁ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ በፈሰሰችም መዓት እሰበስባችኋለሁ። 35ወደ አሕዛብም ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ በዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ።36በግብጽ ምድረ በዳ በአባቶቻችሁ ላይ እንደፈረድኩ እንዲሁ በእናንተ ላይ እፋረዳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 37ከበሬም በታች አሳልፋችኋለሁ ወደ ቃል ኪዳንም እስራት አገባችኋለሁ፤ 38ከእናንተም መካከል ዓመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ። በእንግድነት ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፥ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም። እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ!39ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እያንዳንዳችሁ ወደየጣዖቶቻችሁ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ እኔኔ መስማት ካልፈለጋችሁ እነርሱን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቍርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።40ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል- በቅዱሱ ተራራዬ፥ ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ፥ በዚያ የእስራኤል ቤት ሁሉ ሁላቸው በምድራቸው ያመልኩኛል። በዚያም ቍርባናችሁን በኵራታችሁንም የቀደሳችሁትንም ነገር ሁሉ በደስታ እቀበላለሁ። 41ከአሕዛብም ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፥ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ።42ለአባቶቻችሁም እሰጣት ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ወደ እስራኤል አገር ባገባኋችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 43በዚያም የረከሳችሁባትን መንገዳችሁንና ሥራችሁን ሁሉ ታስባላችሁ ስለ ሠራችሁትም ክፋት ሁሉ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ። 44ስለዚህም የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንደ ክፉ መንገዳችሁና እንደ ርኩስ ሥራችሁ ሳይሆን ስለ ስሜ ብዬ ይህን ባደረኩላችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።45የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 46"የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ደቡብ አቅና በደቡብ ላይ ተናገር፤ በኔጌብ ዱር ላይ ትንቢት ተናገር 47ለኔጌብም ዱር፥ 'የእግዚአብሔርን ቃል ስማ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ። በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል። የሚንበለበለው እሳትም አይጠፋም፤ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ያለው ገጽታ ሁሉ ይቃጠላል።48እሳቱን ስለኩሰውና ሳይጠፋ በሚነድበት ጊዜ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያያል።'" 49እኔም፥ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! እነርሱ ስለ እኔ፥ "ይሄ ምሳሌን ብቻ ተናጋሪ አይደለም እንዴ?" ይላሉ አልሁ።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም አቅና በመቅደሶችም ላይ ተናገር፤ በእስራኤልም ምድር ላይ ትንቢት ተናገር። 3ለእስራኤልም ምድር እንዲህ በል፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ሰይፌንም ከሰገባው እመዝዘዋለሁ፥ ጻድቁንና ክፉውንም ከእናንተ ዘንድ አጠፋለሁ።4እኔም ጻድቁንና ክፉውን ከእናንተ ዘንድ ስለማጠፋ፥ ሰይፌ ከደቡብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ባለ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል። 5ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ያውቃል፥ ስይፌም ከእንግዲህ አይመለስም!6ስለዚህም፥ አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ አልቅስ ወገብህን በማጕበጥ በፊታቸው ምርር ብለህ አልቅስ። 7እነርሱም 'ስለ ምን ታለቅሳለህ?' ብለው ይጠይቁሀል፥ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፥ 'ስለሚምጣው ክፉ ዜና ነው፥ ምክንያቱም ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስም ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበትም እንደ ውኃ ይፈስሳል። እነሆ፥ ይመጣል ይፈጸምማል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር'"8የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 9የሰው ልጅ ሆይ፥ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር ሰይፍ! ሰይፍ! የተሳለና የተወለወለ ሰይፍ በል።10ለታላቅ ግድያ ተስሎአል! እንደመብረቅም እንዲያብረቀርቅ ይወለወላል! በልጄን በትረ መንግስት ደስ ሊለን ይገባልን? የሚመጣው ስይፍ የዚህ አይነቱን በትር ይጠላል። 11ሰይፉም እንዲወለወልና በእጅ እንዲያዝ ይሰጣል! ሰይፉ የትሳል ነው! ለገዳይም ሊስጥ ተወልውሎ ተዘጋጅቷል!'12የሰው ልጅ ሆይ፥ ሰይፉ እየመጣ ያለው በሕዝቤ ላይ ነውና፥ ለሰይፉም የሚሰጡት የእስራኤል አለቆች ሁሉ ናቸውና ለእርዳታ ተጣራ፥ አልቅስ! ሕዝቤ ነበሩና ስለዚህ ጭንህን በምሬት ጽፋ! 13ፈተና ደርሶአል፥ በትረ መንግስት ቢጸና ምን ዋጋ አለው? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦14ስለዚህ፥ አንተ የሰው ልጅ፥ ትንቢት ተናገር፥ እጅህን አጨብጭብ ሰይፍ ለሶስተኛ ጊዜ ጥቃት ይፈጽማልና! ለሚታረዱ የተዘጋጅ ስይፍ! ሰውነታቸውን ሁሉ ሊወጋ ለሚታረዱ ለብዙዎች ሰዎች የተመደበ ሰይፍ ነው!15ልባቸው እንዲቀልጥ መሰናክላቸውም እንዲበዛ የሚገድለውን ሰይፍ በበሮቻቸው ሁሉ ላይ አድርጌአለሁ! ወዮ! እንድመብረቅ ሆኗል እንዲገድልም ነጻ ተለቋል። 16ሰይፍ ሆይ ተዘጋጅ! ስለትህ ወደፈቀደው ወደ ቅኝም ወደ ግራም ምታ። 17እኔ ደግሞ በእጄ አጨበጭባለሁ መዓቴንም እፈጽማለሁ! እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።"18የእግዚአብሔርም ቃል እንደገና ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 19"አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣ ዘንድ ሁለት መንገዶችን አድርግ። ሁለቱም መንገዶች ከአንድ ምድር ይነሳሉ፥ የመንገድ ምልክቱም አንደኛው መንገድ ወደ ከተማ እንድሚወስድ ያሳያል። 20አንዱ መንገድ የባቢሎን ጦር ወደ አሞናዊያን ከተማ ወድ ረባት እንድሚወስድ አመልክት። ሌላኛው መንገድ ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸገች ወደ ኢየሩሳሌም እንድሚወስድ አመልክት።21የባቢሎን ንጉሥ የጥንቆላ ምሪት ለማግኘት በመንታ መንገድ መታጠፊያ ላይ ይቆማል። ፍላጾችን ይወዘውዛል፥ ከጣዖታቱም ምሪት ይጠይቃል። ጉበትም ይመለከታል። 22የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ። 23በኢየሩሳሌም ላሉ ለባቢሎናዊያን መሐላን ማሉ ዓይን ፊት የሐሰት ምዋርት ይመስላል፥ ነገር ግን ንጉሱ እንዲያዙ ለማድረግ ስምምነታችሁን አፍርሳችኋል ብሎ ይከሳቸዋል።24ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃጢአታችሁን እንዳስብ ስላደርጋችሁኝ መተላለፋችሁ ይገለጣል! ኃጢአታችሁም በሥራችሁ ሁሉ ይታያል! በዚህም ምክንያት በጠላቶቻችሁ እጅ እንደተያዛችሁ ስውን ሁሉ ታሳስባላችሁ!25አንተም የምትቀጣበት ቀን የደረስብህ ፥ አመጻ የማድረጊያ ዘመን ያበቃብህ፥ አመጸኛና ክፉ የእስራኤል አለቃ ሆይ፥ 26ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መጠምጠሚያውን አውልቅ፥ ዘውዱንም ከራስህ ላይ አንሳ! ከእንግዲ ነገሮች እንደነበሩ አይቀጥሉም! የተዋረደውን ከፍ አድርግ፥ ከፍ ያለውንም አዋርድ። 27ባድማ፥ ባድማ፥ ሁሉንም ባድማ አደርጋለሁ! የሚገባው ሰው እስኪመጣና ለእርሱ እስከምሰጠው ድረስ ንግስና ከእንግዲህ አይኖርም።28አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ 'ጌታ እግዚአብሔር ስለሚመጣባቸው ውርደት ለአሞን ልጆች እንዲህ ይላል፡ ሰይፍ፥ ሰይፍ ተመዟል! ለማጥፋትና ለመግደል ተስሏል፤ እንደመብረቅም ያብለጨልጫል! 29ነቢያት ባዶ ራዕይ እያዩልህና ምዋርት እያሟረቱልህ ሳለ ይህ ሰይፍ ሊገደሉ ባሉት የሚቀጡበት ቀን በደረሰባቸው የእመጽ ዘመናቸው ባበቃባቸው ሰዎች አንገት ላይ ያርፋል።30ሰይፉን ወደ ሰገባውም መልሰው። በተፈጠርህበት ስፍራ በተወለድህባትም ምድር እፈርድብሃለሁ! 31ቍጣዬንም አፈስስብሃለሁ! የመዓቴም እሳት አናፋብሃለሁ፥ በማጥፋት ለተካኑ ለጨካኞች ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ!32ለእሳት ማገዶ ትሆናለህ! ደምህም በምድሪቱ መካከል ይፈሳል፥ መታሰቢያም አይኖርህም፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 2"አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትፈርዳለህን? ደም በምታፈስስ ከተማ ላይ ትፈርዳለህን? ርኵሰትዋን ሁሉ አስታውቃት። 3እንዲህም ልትላት ይገባል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ ይህች ጊዜዋ እንዲደርስ በመካከልዋ ደምን የምታፈስ፤ እንድትረክስም ጣዖታትን የምታደርግ ከተማ ናት!4ስላፈሰስሽው ደም በደለኛ ነሽ ፥ ባደረግሽውም ጣዖታት ረክሰሻል! ቀንሽን አቀረብሽ ዘመንሽንም አሳጠርሽ። ስለዚህ ለአሕዛብ መሰደቢያ ለአገሮችም ሁሉ መሳለቂያ አደርግሻለሁ። 5አንቺ ስምሽ የረከሰ ግራ መጋባት የሞላብሽ ሆይ፥ በቅርብም በሩቅም ያሉ ይሳለቁብሻል።6እነሆ፥ የእስራኤል አለቆች እያንዳንዳቸው በኃይላቸው መጠን ደም ያፈስሱ ዘንድ በአንቺ ውስጥ ነበሩ። 7በውስጥሽ አባቶችንና እናቶችም አቃለሉ፥ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ። በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ። 8ቅዱሳቴንም ናቅሽ ሰንበታቴንም አረከስሽ! 9ደምን ያፈስሱ ዘንድ ቀማኞች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ በተራሮችም ላይ በሉ። በመካከልሽ ክፋትን አደረጉ።10በአንቺ ውስጥ የአባቶቻቸውን ኀፍረተ ሥጋ ገለጡ በአንቺም ውስጥ በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት አዋረዱ። 11በባልንጀራቸው ሚስቶች ጋር ርኵሰትን ያደርጉ፥ የልጆቻአውን ሚስቶች ያረከሱ፥ የገዛ አባቶቻቸውን ሴት ልጆች እህቶቻችውን ያስነወሩ፥ እንዲህ ያሉ ስዎች ሁሉ በአንቺ ውስጥ አሉ። 12በአንቺ ውስጥ ደምን ለማፍሰስ ጉቦን ይቀብላሉ። አንቺም አራጣና አላስፈላጊ ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽን በጭቆና ጎዳሻቸው ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።13ስለዚህ፥ እነሆ፥ ያለቅንነት የሰበሰብሽውን ሀብት በመካከልሽ ያለውን ደም ማፍስስ በእጄ እቀጣለሁ። 14በውኑ እኔ ይህን በማደርግብሽ ወራት ልብሽ ይታገሣልን? ወይስ እጅሽ ትጸናለችን? እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ አደርገውማለሁ። 15ወደ አሕዛብም እበትንሻለሁ ወደ አገሮችም እዘራሻለሁ። በዚህ መንገድ ርኵሰትሽን ከአንቺ ዘንድ አጠፋለሁ። 16በአሕዛብም ፊት አንቺ የረከሽ ትሆኚያለሽ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂአለሽ።17ቀጥሎም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 18የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ለእኔ እንደ ዝቃጭ ሆኑብኝ። እነርሱ ሁሉ በእንቺ ውስጥ የመዳብና የቆርቆሮ ፥ የብረትና የእርሳስ ተረፍ ምርት ናቸው። እነርሱ በማቅለጫ ውስጥ የብር ዝቃጭ ናቸው። 19ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁላችሁ ዝቃጭ ሆናችኋልና ስለዚህ፥ እነሆ፥ በኢየሩሳሌም ውስጥ እሰበስባችኋለሁ።20እንዲያቀልጡት እሳት ያናፉበት ዘንድ ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቈርቈሮንም በከውር እንደሚሰበስቡ፥ እንዲሁ አቀልጣችኋለሁ። ስለዚህ በቍጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ እሳትም አናፋባችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ። 21ስለዚህም አሰበስባችሁማለሁ የመዓቴንም እሳት አናፋባችኋለሁ በውስጡም ትቀልጣላችሁ። 22ብርም በማቅለጫ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጧ ትቀልጣላችሁ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።23የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 24የሰው ልጅ ሆይ እንዲህ በላት 'አንቺ ያልነጻሽ ምድር ነሽ። በቍጣ ቀን ዝናብ የለም! 25በውስጥዋ ያሉ ነቢያት እንደሚጮኽና እንደሚናጠቅ አንበሳ አንድ ሆነው ተማምለው ህይወት ያጠፋሉ፥ ከፍ ያለ ብልጥግና ይወስዳሉ! በውስጥዋም መበለቶችን ያበዛሉ!26ካህናቶችዋም ሕጌን አቃለዋል ቅድሳቴንም አርክሰዋል። ቅዱስ በሆነና ቅዱስ ባልሆነ መካከልም አይለዩም፥ በንጹሕና በርኩስ መካከል ያለውን ልዩነት አያስተምሩም። ፊታቸውንም ከሰንበታቴ መለሱ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ። 27በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው። የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈሳሉ ህይወትንም ያጠፋሉ። 28እግዚአብሔርም ሳይናገር ነቢያቶችዋ፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል" እያሉ ከንቱን ራእይ በማየት የሐሰትንም ምዋርት ለእነርሱ በማምዋረት ያለ ገለባ በጭቃ ይመርጓቸዋል።29የምድሪቱም ሕዝብ በማስፈራራት ግፍ አደረጉ ዘረፋ ፈጸሙ፥ ድሆችንና ችግረኞችን አስጨነቁ፥ ያለ ፍትህ መጻተኛውንም በደሉ።30ቅጥርን የሚጠግንን፥ ምድሪቱንም እንዳላጠፋት በፈረሰበት በኩል በፊቴ የሚቆምላትን ሰው በመካከላቸው ፈለግሁ፥ ነገር ግን አንድም ሰው አላገኘሁም። 31ስለዚህ ቍጣዬን አፈስባቸዋልሁ፥ በመዓቴም እሳት አጠፋቸዋለሁ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"
1የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 2የሰው ልጅ ሆይ፥ የአንዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ። 3በግብጽ አገር በኰረዳነታቸው ዕድሜ አመነዘሩ በዚያ ገለሞቱ። በዚያ ጡቶቻቸው ምዋሸሹ በዚያም የድንግልናቸው ጡቶች ተዳበሱ። 4ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የታናሽ እኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ። ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ኦሖላ ሰማርያ ናት ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።5ኦሖላም የእኔ ሆና እያለ ገለሞተችብኝ፤ ውሽሞችዋንም ኃያላኑን ጎረቤቶችዋን አሦራውያንን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው። 6እነርሱም ሰማያዊ ሐር የለበሱ አለቆችና ሹማምቶች፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ በፈረስ ላይ የሚቀመጡ ፈረሰኞች ነበሩ። 7ስለዚህ ራሷን ለተመረጡ ለአሦር ሰዎች ሁሉ ለግልሙትና ሰጠቻቸው ፥ በሴሰኝነት በተከተለቻቸውም ጣዖቶቻቸው ሁሉ ረከሰች።8በግብጽም የነበረውን ግልሙትናዋን አልተወችም በዚያ በኰረዳነትዋ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ተኝተው ነበር፥ የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር፥ ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር። 9ስለዚህ በፍቅር በተከተለቻቸው በውሽሞችዋ በአሦራውያን እጅ አሳልፌ ሰጠኋት። 10እነርሱም ኅፍረተ ሥጋዋን ገለጡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፥ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ በሌሎች ሴቶች ዘንድ መተረቻ ሆነች ስለዚህም ፈረዱባት።11እኅትዋም ኦሖሊባ ይህን አየች ሆኖም ከእርስዋ ይልቅ በሴሰኝነቷ በረታች፥ ግልሙትናዋም ከእኅትዋ ግልሙትና ይልቅ በዛ። 12አለቆችንና ሹማምቶችን ጎረቤቶችዋን ጌጠኛ ልብስ የለበሱትን በፈረሶች ላይ የሚቀመጡትን ፈረሰኞች፥ ሁሉም መልከ መልካሞችን ጐበዛዝት አሦራውያንን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው። 13የረከሰችም እንደ ሆነች አየሁ። የሁለቱም አእህትማማቾች ሁኔታ አንድ ነው።14ግልሙትናዋንም አበዛች! በቀይ ቀለምም የተሳለውን የከለዳውያንን ስዕል፥ በግድግዳ ላይ የተሳሉትን ሰዎች አየች። 15በወገባቸው ዝናር የታጠቁ ራሳቸውንም በቀለማዊ መጠምጠሚያ የጠመጠሙ ነበሩ! ሁሉም የከለዳዊያን ተወላጆችና የሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር።16ባየቻቸውም ጊዜ ለክፉ ተመኘቻቸው፥ ወደ ከላውዴዎን ምድር ወደ እነርሱ መልእክተኞችን ላከች። 17የባቢሎንም ሰዎች ወደ እርስዋ ወደ ሴሰኝነት መኝታ መጡ በግልሙትናቸውም አረከሱአት እርስዋም ከእነርሱ ጋር ረከሰች በውርደትም ከእነርሱ ተለየች።18ግልሙትናዋንም ገለጠች ኅፍረተ ሥጋዋንም አሳየች ነፍሴም ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ ነፍሴ ከእርስዋ ተለየች። 19ነገር ግን በግብጽ ምድር የገለሞተችበትን የኰረዳነትዋን ዘመን በማሰላሰል ግልሙትናዋን አበዛች።20የወንድ ብልቶቻቸው እንደ አህዮች የወንድ ዘራቸውም እንደ ፈረሶች ዘር የሆነውን ውሽሞቿን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው። 21ስለ ኰረዳነትሽ ምክንያት ግብጻውያን ጡቶችሽን የዳበሱበትን ጊዜ የኰረዳነትሽን ሴሰኝነት ተመኘሽ።22ስለዚህ፥ ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'የተለየሻቸውን ውሽሞችሽን አስነሣብሻለሁ! ከሁሉም አቅጣጫ በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ! 23እነርሱም የባቢሎን ሰዎች ከለዳውያንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር አሦራውያን ሁሉ፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ አለቆችና ሹማምቶች ሁሉ፥ መሳፍንቶችና አማካሪዎች ሁሉ፥ በፈረስ ላይ የተቀመጡ ናቸው።24በመሣሪያና በሰረገላ በመንኰራኵርም በብዙ ሠራዊትም ይመጡብሻል! ታላላቅና አነስተኛ ጋሻና ራስ ቍርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል! እንዲቀጡሽ እድልን እሰጣቸዋለሁ፥ በተግባራቸውም ይቀጡሻል! 25ቅንዓቴንም በአንቺ ላይ ስለማደርግ በመዓትም ስለሚገናኙሽ አፍንጫሽንና ጆሮሽንም ከአንቺ ይቈርጣሉ፥ ከአንቺም የቀረ በሰይፍ ይወድቃል ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽንም ማርከው ይወስዳሉ፥ ከአንቺም የቀረውን እሳት ትበላቸዋለች!26ልብስሽንም ይገፍፉሻል ጌጣጌጥሽንም ይወስዳሉ! 27አሳፋሪ ባህሪሽን፥ ከግብጽ ምድር ያመጣሽውን ግልሙትናሽንም ከአንቺ አስወግዳለሁ። ዓይንሽንም ወደ እነርሱ በናፍቆት አታነሺም ግብጽንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም።28ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ 'እነሆ፥ በጠላሻቸው እጅ፥ በተለየሻቸውም እጅ አሳልፌ እሰጥሻለሁ! 29እነርሱም በጥላቻ ይገናኙሻል፥ ንብረትሽን ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን ይተዉሻል። የግልሙትናሽም ነውር፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽም ሁሉ ይገለጣል።30ከአሕዛብ ጋር ስላመነዘርሽ በጣዖቶቻቸውም ስለ ረከስሽ ይህ ነገር ይደርስብሻል። 31በእኅትሽ መንገድ ሄደሻል ስለዚህ የቅጣት ጽዋዋን በእጅሽ እሰጥሻለሁ።32ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'የጠለቀውንና የሰፋውን ብዙም የሚይዘውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ መሳቂያና መሳለቂያም ትሆኛለሽ!33በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፥ በድንጋጤና በጥፋት ጽዋ፥ በስካርና በውርደት ትሞያለሽ! 34ትጠጪዋለሽ ትጨልጪውማለሽ መጠጫውንም ትሰባብሪዋለሽ በስብርባሪውም ጡትሽንም ትሸነትሪዋለሽ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር፦35ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ረስተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ የሴሰኝነትሽንና የግልሙትናሽን ውጤት ተሸከሚ።36እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ አሳፋሪ ተግባራቸውን አስታውቃቸው 37አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና! ከጣዖቶቻቸውም ጋር አመንዝረዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን ለእሳት መቃጠል አሳልፈዋቸዋልና።38ይህን በእኔ ላይ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል ሰንበታቴንም ሽረዋል! 39ልጆቻቸውንም ለጣዖቶቻቸው በሠዉበት በዚያው ቀን ያረክሱት ዘንድ ወደ መቅደሴ ገቡ! እነሆም፥ በቤቴ ውስጥ ያደረጉት ይህ ነው።40ደግሞ ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች መልእክተኛ ልከሻቸዋል። እነርሱም መጥተዋል! እነሆም መጡ፥ አንቺም ታጠብሽና ዓይኖችሽን ትኩለሽ አጊጠሽም ጠብቅሻቸው። 41ከፊት ለፊቱ ገብታ በተዘጋጀበት በክብር አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፥ ዕጣኔንና ዘይቴንም አኖርሽበት።42በጭንቀት የተሞላ የህዝብ ድምፅ በአንቺ ዘንድ ነበረ፥ ሰካራሞችም ከሌሎች ምናምንቴ ሰዎች ጋር ከምድረ በዳ መጡ። በእጅሽም ላይ አንባር በራስሽም ላይ የተዋበ አክሊል አደረጉ።43እኔም በምንዝር ስለሻገተችው ፥ 'አሁን ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ታመነዝራለች' አልሁ።' 44ወደ ጋለሞታም እንደሚገቡ ወደ እርስዋ ገቡ እንዲሁ ይሴስኑ ዘንድ በግልሙትና በደለኛ ወደሆኑት ወደ ኦሖላና ወደ ኦሖሊባ ገቡ። 45ሴቶቹ አመንዝሮች ናቸውና፥ በእጃቸውም ደም አለና ጻጽቃን ሰዎች ለአመንዝሮቹና ለደም አፍሳሾቹ የተመደበውን ቅጣት ያስተላልፉባቸዋል።46ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ጦር አመጣባቸዋለሁ፥ ለመበተንና ለመበዝበዝም አሳልፌ አሰጣቸዋለሁ። 47ሠራዊቱም በድንጋይ ይወግሩአቸዋል በሰይፋቸውም ይቈርጡአቸዋል። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ይገድላሉ፥ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።48ከእንግዲህ ሴቶች ሁሉ የሴሰኝነት ተግባር እንዳይፈጽሙ ሴሰኝነትን ከምድሪቱ ላይ አጠፋለሁ። 49ሴሰኝነታችሁንም በላያችሁ ላይ ይመልሳሉ። እናንተም ኃጢአታችሁንና ጣዖቶቻችሁን ትሸከማላችሁ በዚህ መንገድ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
1በዘጠነኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ በዚህ ቀን የባቢሎን ንጉሥ ኢየሩሳሌምን ከቧልና የዚህን ቀን፥ የዛሬን ቀን ስም ጻፍ ።3ለዓመፀኛውም ቤት ምሳሌን ተናገር እንዲህም በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ድስቱን ጣድ! ጣደው! ውኃም ጨምርባት! 4የምግብ ፍራፍሬዎችን በውስጡ ጨምር፥ ጭኑንና ወርቹን በእርስዋ ውስጥ ሰብስብ፥ የተመረጡትንም አጥንቶች ሙላባት! 5ከመንጋው የተመረጠውን ውሰድ፥ አጥንቶቹም እንዲበስሉ እንጨት በበታችዋ ማግድ አጥንቶቹም በውስጥዋ ቀቅል።6ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዝገት ላለባት ዝገትዋም ለማይለቃት ምንቸት፥ ለደም ከተማ ወዮላት! ጥቂት ጥቂት ከውስጡ ውሰድ፥ ነገር ግን ዕጣ አታውጣላት።7ደምዋ በውስጥዋ አለና! በተራቈተ ድንጋይ ላይ አደረገችው እንጂ በአፈር ይከደን ዘንድ በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም 8ይህም መዓትን አመጣባት። ደምዋም እንዳይከደን በተራቈተ ድንጋይ ላይ አፈሰስኩት!9ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለደም ከተማ ወዮላት! እኔ ደግሞ የማገዶውን ክምር አሳድጋለሁ። 10እንጨቱን ጨምር! እሳቱን አንድድ! ሥጋውን ቀቅል መረቁን አጣፍጠው! አጥንቶቹም በደንብ ይቃጠሉ።11እንድትሞቅና እንድትግል በውጧ ያለው ርኵሰትዋ በውስጥዋ ይቀልጥ ዘንድ ዝገትዋም ይጠፋ ዘንድ ባዶዋን ድስት በፍም ላይ ጣዳት። 12በከንቱ ደከመች ሆኖም ዝገትዋ በእሳት ስንኳ አልለቀቀም።13አሳፋሪው ተግባርሽ በርኵሰትሽ ውስጥ ነው። እኔ ባነጻሽም አልነጻሽም። መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ ከርኵሰትሽ አትነጺም።14እኔ እግዚአብሔር ይሆናል ብዬ ተናግሬአለሁ ፥ እኔም አደርገዋለሁ! አልመለስም፥ ፥ አልጸጸትምም። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል! ይላል ጌታ እግዚአብሔር።"15የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 16"የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ የዓይንህን አምሮት በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ አንተም ማዘንም ሆነ ማልቀስ የለብህም እንባህንም አታፍስስ። 17በቀስታ ተክዝ። ለምዋቾችም የቀብር ሥርዓትም አታዘጋጅ። መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፥ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፥ ጢምህን አትሸፍን ወይም ሚስቶቻቸው በመሞታቸው ምክንያት እያዘኑ ያሉ ሰዎችን እንጀራ አትብላ።18እኔም በማለዳ ለሕዝቡ ተናገርሁ፥ ምሽት ላይም ሚስቴ ሞተች። በነጋውም እንደ ታዘዝሁ አደረግሁ።19ሕዝቡም፥ "ይህ የምታደርገው ነገር ምን እንደ ሆነ አትነግረንምን?" አሉኝ። 20እኔም እንዲህ አልኋቸው፥ "የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 21ለእስራኤል ቤት ተናገር እንዲህም በል፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የኃይላችሁ ትምክሕት፥ የዓይናችሁ አምሮት፥ ክፉ ምኞታችሁ መቅደሴን አርክሰዋል! ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።22እኔም እንዳደረግሁ እናንተ ታደርጋላችሁ ጢማችሁን አትሸፍኑም የኃዘንተኛ ሰዎችንም እንጀራ አትበሉም! 23ይልቁኑ መጠምጠሚያችሁም በራሳችሁ ጫማችሁም በእግራችሁ ይሆናል፤ አታዝኑም ወይም አታለቅሱምም በኃጢአታችሁም ትሰለስላላችሁና እያንዳንዱ ሰው ስለወንድሙ ያቃስታል። 24ይህ በሚሆንባችሁ ጊዜ ሕዝቅኤልም ምልክት ይሆናችኋል እርሱ እንዳደረገ ሁሉ እናንተ ታደርጋላችሁ። ከዚያም እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።25አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ደስታቸው፥ ትምክህታቸው የሆነውን መቅደሳቸውንና የሚያዩትና የተመኙትን በያዝኩ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በወሰድሁባቸው ቀን፥ 26በዚያ ቀን ያመለጠ ሰው ይህን ሊነግርህ ይመጣል። 27በዚያ ቀን አፍህ አምልጦ ለመጣው ይከፈታል፥ አንተም ትናገራለህ ከዚያ ወዲያም ዝም አትልም። ምልክትም ትሆናቸዋለህ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ አሞን ልጆች አቅንተህ ትንቢት ተናገርባቸው።3ለአሞንም ሰዎች እንዲህ በል፥ 'የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ የይሁዳም ቤት በተማረኩ ጊዜ ስለ እነርሱ "እሰይ!" ብላችኋል። 4ስለዚህ፥ እነሆ፥ ርስት አድርጌ ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ አሳልፌ አሰጣችኋለሁ፥ እነርሱም በእናንተ ላይ ምሽግን ይሰራሉ ፥ ድንኳኖቻቸውንም በእናንተ ዘንድ ይተክላሉ። ፍሬያችሁን ይበላሉ ወተታችሁንም ይጠጣሉ! 5የአሞንን ከተማ ለግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።6ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ በእጃችሁ አጨብጭባችኋልና፥ በእግራችሁም አሸብሽባችኋልና፥ በእስራኤልም ምድር ላይ በነፍሳችሁ ንቀት ሁሉ ደስ ብሏችኋልና 7ስለዚህ፥ እነሆ፥ በእጄን እመታችኋለሁ፥ ለአሕዛብም ለብዝበዛ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ ከአሕዛብም ለይቼ እቈርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም አጠፋሃለሁ እፈጅህማለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።8ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ሞዓብና ሴይር እነሆ፥ "የይሁዳ ቤት ያው እንደ ሌሎቹ አሕዛብ ሁሉ ነው!" ብለዋልና 9ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሞዓብን ጫንቃ ከከተሞቹ፥ በዳርቻው ካሉት የምድሩ ትምክሕት ከሆኑት ከተሞቹ፥ ከቤትየሺሞት፥ ከበኣልሜዎን፥ 10ከቂርያታይም፥ ከአሞን ልጆች ጋር ለምሥራቅ ልጆች እከፍታለሁ። የአሞን ህዝብ በአሕዛብ መካከል ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰቡ ርስት አድርጌ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። 11በሞዓብም ላይ ፍርድን አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።12ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ኤዶምያስ በይሁዳ ቤት ላይ በቀል አድርጎአል፥ ይህን በማድረጉም ስህተት ፈጽሟል። 13ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እጄን በኤዶምያስ ላይ እዘረጋለሁ ከእርስዋም ዘንድ ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ። ከቴማንም ጀምሮ እስከ ድዳንም ድረስ ባድማ አደርጋታለሁ፥ በሰይፍም ይወድቃሉ።14በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምያስን እበቀላለሁ እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴም መጠን በኤዶምያስ ያደርጋሉ በቀሌንም ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!'15ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ፍልስጥኤማውያን በንቀት በቀልን አድርገዋልና፥ ይሁዳንም ከውስጣቸው ለማጥፋት ደጋግመው ሞክረዋልና 16ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን በፍልስጥኤማውያን ላይ እዘረጋለሁ፥ ከሊታውያንንም እቈርጣለሁ፥ የባሕሩንም ዳር ቅሬታ አጠፋለሁ። 17በመዓት መቅሠፍትም ታላቅ በቀል አደርግባቸዋለሁ በቀሌንም በላያቸው ባደረግሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1እንዲህም ሆነ በአሥራ አንደኛው ዓመት ከወሩ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፡ 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢየሩሳሌም ላይ። 'እሰይ፥ የአሕዛብ በር የነበረች ተሰብራለች ወደ እኔም ተመልሳለች እርስዋ ፈርሳለችና እኔ እሞላለሁ!' ብላለች።3ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ "ጢሮስ ሆይ፥ እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ባሕርም ሞገድዋን እንደምታወጣ እንዲሁ ብዙ ህዝቦችን በአንቺ ላይ አስነሳልሁ። 4የጢሮስንም ቅጥሮች ያጠፋሉ ግንቦችዋንም ያፈርሳሉ ትቢያዋንም ከእርስዋ እጠርጋለሁ፥ የተራቈተ ድንጋይም አደርጋታለሁ።5በባሕር ውስጥ የመረብ ማስጫ ትሆናለች እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር ለአሕዛብም ብዝበዛ ትሆናለች። 6በሜዳ ያሉትም ሴቶች ልጆችዋ በሰይፍ ይገደላሉ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።7ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች ከፈረሰኞችም ከብዙ ሕዝብ ጋር በጢሮስ ላይ አመጣለሁ። 8በሜዳ ያሉትን ሴቶች ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፥ ምሽግም ይሠራብሻል አፈርንም ይደለድልብሻል ጋሻም ያነሣብሻል።9ማፍረሻውን በቅጥርሽ ላይ ያደርጋል፥ መሳሪያውም ግንቦችሽንም ያፈርሳል! 10ከፈረሶቹም ብዛት የተነሣ ትቢያቸው ይከድንሻል! ሰዎችም በፈርሰ ቅጥር በኩል ወደ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ ሲገባ፥ ከፈረሰኞችና ከመንኰራኵሮች ከሰረገሎችም ድምፅ የተነሣ ቅጥርሽ ይናወጣል። 11በፈረሶቹ ኮቴ ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረመርማል፤ ሕዝብሽንም በሰይፍ ይገድላል፥ የብርታትሽም ሐውልት ወደ ምድር ይወድቃል።12በዚህ መንገድ ብልጥግናሽንም ሸቀጥሽንም ይዘርፋሉ! ቅጥርሽንም ያፈርሳሉ፥ ተድላ የምታደርጊባቸውን ቤቶችሽን ያጠፋሉ ድንጋይሽንና እንጨትሽን መሬትሽንም በባሕር ውስጥ ይጥላሉ። 13የዝማሬ ጩኸትሽን ዝም አሰኛለሁ የክራሮች ድምፅ ከዚያ ወዲያ አይሰማም! 14የተራቈተ ድንጋይ አደርግሻለሁ የመረብም ማስጫ ትሆኛለሽ። ከእንግዲህ እንደገና አትገነቢም እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር!15ጌታ እግዚአብሔር ጢሮስን እንዲህ ይላታል፥ 'በውስጥሽ እልቂት በሆነ ጊዜ በውድቀትሽ ጩኸትና በቆሰሉ ሰዎች የሥቃይ ድምጽ የተወጉት ባንቋረሩ ጊዜ፥ ፥ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሣ ደሴቶች አይነዋወጡምን? 16የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ መጐናጸፊያቸውን ያወጣሉ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ መንቀጥቀጥን ለብሰው በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ ስለአንቺም ይፈራሉ።17በአንቺም ላይ ሙሾ ያሞሻሉ፥ እንዲህም ይሉሻል። የመርከበኞች መኖሪያ የነበርሽ እንዴት ወደምሽ! ዝናሽ የወጣ ጠንካራ ከተማ አሁን ግን ከባህር ጠፋሽ! በአንድ ወቅት በእርሷ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አስፍሪነታቸው በዙሪያቸው ባሉ ሁሉ ላይ ነበር። 18አሁን በውድቀትሽ ቀን የባህር ዳርቻዎችይንቀጠቀጣሉ፥ በባሕርም ውስጥ ያለ ደሴቶች ከመጥፋትሽ የተነሣ ይደነግጣሉ።19ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፡ ሰው እንደሌለባቸው ከተሞች ባድማ ከተማ ባደረግሁሽ ጊዜ፥ ቀላያትንም ባንቺ ላይ ባስነሳሁብሽ ጊዜ ብዙ ውኆችም በከደኑሽ ጊዜ፥ 20ያኔ ወደ ጉድጓድ እንደወረዱ ሰዎች ወደ ጥንት ሰዎች አወርድሻለሁ፤ እንደ ጥንት ዘመን ፍርስራሾች በምድር ጥልቅ ውስጥ እንድትኖሪ አደርግሻልችሁ። ከዚህ የተነሳ ሰዎች ወደሚኖሩበት21ጥፋትን አመጣብሻለሁ ለዘላለምም ትጠፊያለሽ፤ ይፈልጉሻል ነገር ግን ለዘላለም አያገኙሽም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 2"አንተ የሰው ልጅ ሆይ እንግዲህ ፥ ስለ ጢሮስ ሙሾ ጀምር ጢሮስንም እንዲ በላት 3'አንቺ በባሕር መግቢያ የምትኖሪ በብዙም ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ህዝቦች ጋር ንግድን የምታደርጊ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ። 'በውበት ፍጹም ነኝ ብለሻል!4ዳርቻሽ በባሕር ውስጥ ነው የሰሩሽ ፍጹም ውብ አድርገውታል። 5ሳንቃዎችሽን ሁሉ ከሳኔር ጥድ ሠርተዋል፥ ደቀልንም ሊሰሩልሽ ከሊባኖስ ዝግባ ወስደዋል።6ከባሳን ዛፍ መቅዘፊያሽን ሠርተዋል፥ በዝሆን ጥርስ ከታሸበ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍ የመርከብ ወለሎችሽን ሠርተዋል። 7የመርከብሽ ሸራ ልክ እንደ ሰንደቅ ዓላማሽ የግብጽ ባለብዙ ቀለማት በፍታ ጨርቆች ነበሩ።8የሲዶናና የአራድ ሰዎች ቀዛፎችሽ ነበሩ፤ የጢሮስ ጥበበኞችሽ በአንቺ ዘንድ ነበሩ የመርከቦችሽም መሪዎች ነበሩ። 9ልምድ ያላቸው ጥበበኞች መጋጠሚያዎችሽን ሞልተዋል። የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው የንግድ እቃዎችሽን ለንግድ ያጓጉዙልሻል።10ፋርስና ሉድ ፉጥም በሠራዊትሽ ውስጥ ነበሩ፥ ጋሻና ራስ ቍርም በአንቺ ውስጥ ያንጠለጥሉ ነበር፥ እነርሱም ውበትሽን አሳዩ። 11በሠራዊትሽ ውስጥ የነበሩት የአራድ እና የኤሌክ ሰዎች በቅጥሮችሽ በዙሪያ ነበሩ፥ ገማዳውያንም በግንቦችሽ ውስጥ ነበሩ! ጋሻቸውንም ዙሪያውን በቅጥርሽ ላይ አንጠለጠሉ! ውበትሽንም ፍጹም አደረጉት!12በብዙ ዓይነት ማለትም በብር፥ በብረት ፥ በቈርቈሮና በእርሳስ ካለሽ ብልጥግና ብዛት የተነሣ ተርሴስ የንግድ ደንብኛሽ ነበረች። ሸቀጥሽን ይገዙና ይሸጡ ነበር። 13ያዋንና ቶቤል ሞሳሕም ባሮችንና ከናስ የተሰሩ እቃዎችን ይነግዱ ነበር። ንግድሽን የሚመሩት እነርሱ ነበሩ።14ከቤተ ቴርጋማም መጋዣዎችን፥ የጦር ፈረሶችንና በበቅሎዎችን ወደ ንግድሽ አመጡ። 15የድዳን ሰዎች በብዙ ዳርቻዎችሽ የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ። ንግድ በእጅሽ ነበረ፤ በሸቀጥሽ ምላሽ የዝሆን ጥርስና ዞጲ ይልኩልሽ ነበር።16ሶርያ የብዙ ምርቶችሽ ተጠቃሚ ነበረች። በልዋጩም የከበረ ድንጋይ፥ የወይን ጠጅ፥ ባለ ብዙ ቀለም ልብሶች፥ ያማሩ ጨርቆች፥ በዛጎል እና ቀይ ዕንቍም ያቀርቡ ነበር። 17ይሁዳና የእስራኤል ምድር የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ። የሚኒትን ስንዴ ጣፋጭም እንጐቻ፥ ማር ዘይትም በለሳንም ያቀርቡ ነበር። 18ደማስቆ የምርትሽ ሁሉ፥ ተዝቆ የማያልቅ ሀብትሽ እንዲሁም የኬልቦን የወይን ጠጅና የዘሀርን የበግ ጠጕር ይነግዱ ነበር።19ዌንዳንና ያዋን ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር። ቀልጦ የተሠራ ብረት፥ ብርጕድና ቀረፋም ያቀርቡ ነበረ። ይህም ላንቺ ንግድ ሆነልሽ 20ድዳን የግላስ ንግድ ከአንቺ ጋር ነበራት። 21ዓረብና ሌሎች የቄዳር አለቆች ሁሉ የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ፤ ጠቦቶች፥ አውራ በጎችና ፍየሎችን ለንግድ ያቀርቡልሽ ነበር።22የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች ምርጥ የሆነ የቅመም ሽቱ ሁሉና ብዙ ዓይነት የከበሩ ድንጋዮች ሊሸጡልሽ ይመጡ ነበር። ወርቅም ይነግዱ ነበር። 23ካራንና ካኔ ዔድንም ከሳባ፥ ከአሦርና ከኪልማድ በመሆን የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ።24እነዚህ ባማረ ልብስ በሰማያዊ ካባ በወርቀ ዘቦም፥ በዝግባ በተሠራች በገመድም በታሰረች በግምጃም በተሞላች ሳጥን ይነግዱ የነበሩ ናቸው። 25የተርሴስ መርከቦች የሸቀጥሽ ማጓጓዣዎች ነበሩ። አንቺም በባህር መካከል ተሞልተሽ በጭነትም ከብደሽ ነበር።26ቀዛፊዎችሽ ወደ ስፊ ባህሮች አመጡሽ፤ የምሥራቅ ነፋስም በባህሮቹ መካከል ሰበረሽ። 27በውድቀትሽ ቀን ብልጥግናሽ፥ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃዎችሽ፤ የመርከብ ነጂዎችሽ፥ መርከበኞችሽም መርከብ ሠሪዎችሽ፤ ነጋዴዎችሽ ሁሉ በአንቺም ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በውስጥሽ ካሉት ሠራተኞች ጋር ወደ ባሕር ጥልቅ ይወድቃሉ።28ከመርከብ መሪዎች ጩኸት ድምፅ የተነሣ በባህር አጠገብ ያሉ ከተሞች ይንቀጠቀጣሉ። 29ቀዛፊዎችም ሁሉ መርከበኞችም መርከብ መሪዎችም ሁሉ ከመርከቦቻቸው ወርደው በመሬት ላይ ይቆማሉ። 30ከዚያም ድምፃቸውን እንድትሰሚ ያደርጉሻል ምርር ብለውም ይጮኻሉ፥ ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ይነሰንሳሉ፥ በአመድም ውስጥ ይንከባለላሉ31ስለ አንቺም የራሳቸውን ጠጕር ይላጫሉ ማቅም ይታጠቃሉ በምሬትም ስለአንቺ ያነባሉ ይጮኸሉ። 32በትካዜያቸውም ልቅሶ ያነሡልሻል፥ ስለ አንቺም ሙሾ ያሞሻሉ እንዲህም ይላሉ። በባሕር መካከል ጠፍቶ እንደ ቀረ እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው? 33ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ ብዙ አሕዛብን ያጠግብ ነበር በብልጥግናሽና በንግድሽ ብዛት የምድርን ነገሥታት ባለ ጠጎች አድርገሻል።34ነገር ግን በጥልቅ ውኃ ውስጥ በባህር በተሸፈንሽ ጊዜ ንግድሽና ሠራተኞችሽ ሁሉ ሰጠሙ! 35በባህር ዳርቻ የሚኖሩ ሁሉ ተደንቀውብሻል፥ ነገሥታቶቻቸውም በፍርሀት ተንቀጥቅጠዋል። ፊታቸውም ደንግጧል። 36የአሕዛብ ነጋዴዎች አፍዋጩብሽ፤ ለድንጋጤ ሆነሻል፥ ከእንግዲህ በኋላም አትኖሪም።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2የሰው ልጅ ሆይ፥ የጢሮስን ገዥ እንዲህ በለው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርቶአል፥ አንተም "እኔ አምላክ ነኝ! በባሕር መካከል በአማልክት ወንበር ላይ እቀመጣለሁ!" ብለሃል። ነገር ግን አንተ ሰው እንጂ እግዚአብሔር ባትሆንም ልብህን እንደ አምላክ ልብ አደረግህ። 3እነሆ፥ ከዳንኤል ይልቅ ጥበበኛ እንደሆንክ ምንም ሚስጢር ከአንተ እንደማይሰወር አሰብክ።4በጥበብና በማስተዋል ራስህን አበልጽገሀል፥ ወርቅና ብርም በግምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብስበሃል! 5በታላቅ ጥበብና በንግድህ ብልጥግናህን አብዝተሃል ከብልጥግናህም የተነሳ ልብህ ኰርቶአል!6ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህን እንደ አምላክ ልብ አድርገሃልና 7ስለዚህ፥ እነሆ፥ እንግዳ ሰዎችን፥ የአሕዛብን ጨካኝ ሰዎችን አመጣብሃለሁ! ሰይፋቸውንም በጥበብህ ውበት ላይ ይመዝዛሉ፥ ክብርህንም ያዋርዳሉ!8ወደ ጕድጓድ ያወርዱሃል፥ በባህር ልብ ውስጥ የሞቱትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ። 9በውኑ በገዳይህ ፊት፥ "እኔ አምላክ ነኝ" ትላለህን? አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም፥ በሚቆራርጡህ እጅ ትወድቃለህ። 10በእንግዶች ሰዎች እጅ ያልተገረዙትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር!"11የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 12የሰው ልጅ ሆይ፥ በጢሮስ ንጉሥ ላይ ሙሾ አሞሽተህ እንዲህ በለው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ጥበብን የተሞላህ የፍጽምና መደምደሚያ በውበትህም ፍጹም ነበርክ! 13በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ! በከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅ፥ ተሽፍነህ ነበረ። እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች በወርቅ ዕቃ በፊትህ ተቀምጠው ነበር። አነዚህም በተፈጠርህበት ቀን እንድትለብሳቸው ተዘጋጅተው ነበር!14የሰውን ዘር እንዲጋርድ እንደቀባሁት ኪሩብ በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አኖርሁህ! ትመላለስባቸው በነበሩ የእሳት ድንጋዮች መካከል ነበርክ። 15ከተፈጠርህበት ቀን ጀምረህ በደል እስኪገኝብህ ድረስ በመንገድህ ፍጹም ነበርህ።16በንግድህ ብዛት በአምጽ ተሞላህ ስለዚህም ኃጢአትን ሠራህ! ስለዚህ እንደ ርኩስ ነገር ከእግዚአብሔር ተራራ ጣልሁህ የምትጋርድ ኪሩብ ሆይ፥ ከእሳት ድንጋዮች መካከል አጠፋሁህ። 17በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ! ወደ ምድርም ጣልሁህ! ያዩህም ዘንድ በነገሥታት ፊት አስቀመጥኩህ።18በበደልህ ብዛት ቅን ባልሆነው ንግድህም ቅዱስ ስፍራህን አረከስህ! ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርስዋም ትበላሀለች። በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አደርግሀለሁ። 19በአሕዛብም ውስጥ የሚያውቁህ ሁሉ ይደነቁብሃል፤ ይደነግጣሉ ፥ አንተም እስከ ዘላለምም አትገኝም።20የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 21"የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሲዶና አቅንተህ ትንቢት ተናገርባት! እንዲህም በል፥ 22'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሲዶና ሆይ፥ እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ፍርድን በውስጥሽ በማደርግበት ጊዜ ህዝብሽ እኔ እግዚአብሔር እንድሆንኩ እንዲያውቁ በመካከልሽ ክብሬን እገልጣለሁ። ቅዱስ መሆኔም ይገለጣል።23ቸነፈርንም በአንቺ ላይ፥ ደምንም በጎዳናሽ ላይ እሰድዳለሁ፥ በሰይፍ የታረዱ በመካከልሽ ይወድቃሉ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ! 24እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ እንዲያውቁ ከእንግዲህም ወዲያ ለእስራኤል ቤት የሚወጋ እሾህ፥ በዙሪያቸውም ካሉ ከናቋቸው ሁሉ የሚያቈስል ኵርንችት አይሆንም25ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤልን ቤት ከተበተኑባቸው አሕዛብ ዘንድ በሰበሰብሁ ጊዜ፥ በአሕዛብም ፊት በተቀደስሁባቸው ጊዜ፥ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድራቸው ይቀመጣሉ። 26በውስጧም ተዘልለው ይቀመጡባታል ቤቶችንም ይሠራሉ ወይኑንም ይተክላሉ በዙሪያቸውም ባሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን ባደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1በአሥረኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሁለተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ አድርግ፥ በእርሱና በግብጽ ሁሉ ላይም ትንቢት ተናገር፥ 3እንዲህም በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወንዞች መካከል የምትተኛና። ወንዙ የእኔ ነው ለራሴም ሠርቼዋለሁ የምትል ታላቅ የባህር ውስጥ ፍጥረት፥ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ።4በመንጋጋህ መቃጥን አገባብሃለሁ፥ የወንዞችህንም ዓሦች ወደ ቅርፊትህ አጣብቃለሁ በቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁ ዓሦች ሁሉ ጋር ከወንዞችህም መካከል አወጣሃለሁ። 5አንተንና የወንዞችህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥላለሁ፥ በምድርም ፊት ላይ ትወድቃለህ እንጂ አትከማችም አትሰበሰብም። መብልም አድርጌ ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እሰጥሀለሁ።6ለእስራኤል ቤት የሸንበቆ በትር ሆነዋልና በግብጽም የሚኖሩ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 7በእጅ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህና ተሰነጣጥቅህ ትከሻቸውን ትወጋለህ፤ በተደገፉብህም ጊዜ እግራቸውን ትሰባብራለህ ወገባቸውንም እንዲንቀጠቀጥ ታደርጋለህ።8ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሰይፍ አመጣብሃለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከአንተ ዘንድ አጠፋለሁ። 9የባህር ጭራቁ "ወንዙ የእኔ ነው የሠራሁትም እኔ ነኝ" ብሏልና የግብጽ ምድር ባድማና ውድማ ትሆናለች፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ አንተ። 10ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፥ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።11የሰው እግር አያልፍባትም የእንስሳም ኮቴ አያልፍባትም፥ እስከ አርባ ዓመትም ድረስ ማንም አይኖርባትም። 12ባድማም በሆኑ ምድሮች መካከል የግብጽን ምድር ባድማ አደርጋታለሁ፥ በፈረሱትም ከተሞች መካከል ከተሞችዋ አርባ ዓመት ፈርሰው ይቀመጣሉ ግብጻውያንንም ወደ አሕዛብ እበትናቸዋለሁ በአገሮችም እዘራቸዋለሁ።13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከአርባ ዓመት በኋላ ግብጻውያንን ከተበተኑባቸው አሕዛብ ዘንድ እሰበስባለሁ 14የግብጽንም ምርኮ እመልሳለሁ፥ ወደ ተወለዱባትም ምድር ወደ ጳትሮስ እመልሳቸዋለሁ በዚያም የተዋረደች መንግሥት ይሆናሉ።15ከሌሎች መንግሥታት ሁሉ ይልቅ የተዋረደች ትሆናለች ከእንግዲህ ወዲያ ከአሕዛብ መካከል ከፍ አትልም።ከእንግዲህም በአሕዛብም ላይ እንዳይገዙ አሳንሳቸዋለሁ። 16ግብጻውያን ከእንግዲህ ለእስራኤል ቤት የትምክህት ምክንያት አይሆኑም። ይልቁኑ እስራኤል ለእርዳታ ፊቷን ወደ ግብጽ ባዞረች ጊዜ የፈጸመችውን በደል የሚያሳስቡ ይሆናሉ።እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።17እንዲህም ሆነ በሀያ ሰባተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 18የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በጢሮስ ላይ ጽኑ ሥራ ለማሰራት ሠራዊቱን ሰበሰበ። ራስ ሁሉ ተላጭቶ ጫንቃም ሁሉ ተልጦ ነበር፥ ነገር ግን በላይዋ ስላገለገለው አገልግሎት እርሱና ሠራዊቱ ምንም አይነት ደመወዝ ከጢሮስ አልተቀበሉም።19ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የግብጽን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጠዋለሁ፥ ብዛትዋንም ይወስዳል ምርኮዋንም ይማርካል ብዝበዛዋንም ይበዘብዛል ይህም ለሠራዊቱ ደመወዝ ይሆናል። 20ለእኔ ለሠሩት ሥራ ደመወዝ አድርጌ የግብጽን ምድር ሰጥቼዋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦21በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድን አበቅላለሁ፥ በመካከላቸውም ለአንተ የተከፈተ አፍን እሰጣለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዋይ! በሉ፥ ለቀኑ ወዮ! ቀኑ ቅርብ ነው፥ 3የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፥ የደመና ቀን፥ ለአሕዛብም ክፉ ወቅት ይሆናል።4ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ የተገደሉት ሰዎች በግብጽ ውስጥ ሲወድቁ ሀብቷን ሲወስዱ መሠረትዋም ሲፈርስ በኢትዮጵያ ውስጥ ሁከት ይሆናል! 5ኢትዮጵያ፥ ፉጥና ሉድም እንግዶችም የቃል ኪዳንም ህዝቦች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ግብጽን የሚደግፉ ይወድቃሉ፥ የኃይልዋም ትምክህት ይወርዳል። ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔ ድረስ ወታደሮቻቸው በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር! 7ባድማም በሆኑ አገሮች መካከል ይሸበራሉ፥ ከተሞቻቸውም እንደ ፈረሱት ከተሞች ይሆናሉ።8እሳትንም በግብጽ ባነደድሁ ጊዜ ረዳቶችዋም ሁሉ በጠፉጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ! 9በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ በግብጽም ጥፋት ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል። እነሆ፥ ይመጣልና!10ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ የግብጽን ህዝብ ፍጻሜ አመጣለሁ። 11የአህዛብ ድንጋጤ የሆኑት እርሱና ሠራዊቱ ምድሪቱን ለማጥፋት ይመጣሉ፤ ሰይፋቸውንም በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ ምድሪቱንም በሞቱ ሰዎች ይሞላሉ!12ወንዞችን ደረቅ መሬት አደርጋለሁ ምድሪቱንም ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ። ምድሪቱንና ሙላዋንም በእንግዶች እጅ ባድማ አደርጋለሁ! እኔ እግዚአብሔር ተናግሬያለሁ!13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶችን አጠፋለሁ እርባና ቢስ የሆኑትን የሜምፎስ ጣዖታት እሽራለሁ። ከእንግዲህ ወዲያ በግብጽ ምድር አለቃ አይገኝም ፥ በግብጽም ምድር ላይ ሽብርን አደርጋለሁ! 14ጳትሮስንም አፈርሳለሁ፥ በጣኔዎስም እሳትን አነድዳለሁ፥ በኖእ ላይም ፍርድን አደርጋለሁ።15በግብጽም ምሽግ በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፥ የኖእንም ህዝብ አጠፋለሁ። 16ከዚያም በግብጽ እሳትን አነድዳለሁ። ሲንም ትጨነቃለች ኖእም ትሰበራለች፥ ሜምፎስም በየቀኑ ጠላቶች ይነሱባታል!17የሄልዮቱና የቡባስቱም ወጣቶች በሰይፍ ይወድቃሉ ከተሞቻቸውም ይማረካሉ። 18በዚያ የግብጽን ቀንበር በሰበርሁ ጊዜ በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል የኃይልዋም ትዕቢት ይጠፋል። ደመናም ይጋርዳታል፥ ሴቶች ልጆችዋም ይማረካሉ። 19እንዲሁ በግብጽ ላይ ፍርድን አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።20እንዲህም ሆነ በአሥራ አንደኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 21የሰው ልጅ ሆይ፥ የግብጽን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬያለሁ።። እነሆም፥ እንዲድን በጨርቅ አልታሰረም በመቃም አልታሰረለትም ስለዚህም ሰይፍን ለመያዝ የሚያስችል ጥንካሬ የለውም።22ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነስቻለሁ! ጠንካራውንም የተሰበረውንም ክንዱን እሰብራለሁ፥ ሰይፉንም ከእጁ አስጥላለሁ። 23ግብጻውያንንም ወደ አሕዛብ እበትናለሁ ወደ አገሮችም እዘራቸዋለሁ። 24የፈርዖንን ክንድ ለመስበር የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ። በባቢሎን ንጉሥ ፊት ለሞት እንድሚያጣጥር ሰው ያጓራል።25የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አጸናለሁ የፈርዖን ክንድ ግን ይወድቃል። ሰይፌንም በባቢሎን ንጉሥ እጅ በሰጠሁ ጊዜ እርሱም በሰጠሁት ሰይፍ የግብጽን ምድር በሚመታ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 26ግብጻውያንንም ወደ አሕዛብ እበትናለሁ ወደ አገሮችም እዘራቸዋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1እንዲህም ሆነ በአሥራ አንደኛው ዓመት በሦስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2የሰው ልጅ ሆይ፥ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንንና በዙሪያው ያሉትን አገልጋዮቹን እንዲህ በላቸው። 'በታላቅነትህ ማንን ትመስላለህ?3እነሆ፥ አሦር ጫፉ እንደ ተዋበ፥ ችፍግነቱ ጥላ እንደ ሰጠ፥ ቁመቱም እንደ ረዘመ፥ ራሱም በደመናዎች መካከል እንደ ነበረ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ነበረ። 4ውኆችም አበቀሉት፥ ቀላይም ግዙፍ አደረገው። ወንዞችም በተተከለበት ዙሪያ ይጐርፉ ነበር፥ መስኖዎቻቸውን በሜዳ ወዳሉ ዛፎች ይሰዳሉ።5ቁመቱ ከምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ከፍ ያለ ነበር አለ፤ ቅርንጫፎቹም ከብዙ ውኆች የተነሣ ረዘሙ። 6የሰማይ ወፎች ሁሉ ጎጆቻቸውን በቅርንጫፎቹ ላይ አደረጉ፥ የምድርም አራዊት ሁሉ ከጥላው በታች ተዋለዱ። ታላላቅ ህዝቦች ከጥላውም በታች ኖሩ። 7ሥሩም በብዙ ውኃ አጠገብ ነበረና በታላቅነቱና በቅርንጫፎቹ ርዝመት የተዋበ ነበረ።8በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አልተካከሉትም! ጥዶችም ቅርንጫፎቹን አይመስሉትም አስታ የሚባለውም ዛፍ ቅርንጫፎቹን አይተካከሉም! በእግዚአብሔርም ገነት ካሉ ዛፎች በውበቱ ሊተካከለው አልቻለም! 9በቅርንጫፎቹ ብዛት ውብ አደረግሁት፤ በእግዚአብሔርም ገነት በዔድን የነበሩ ዛፎች ሁሉ ቀኑበት።10ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቁመቱ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ ጫፎቹንም ከቅርንጫፎች በላይ አድርጎአልና፥ 11ልቡም በቁመቱ ልክ ኰርቶአልና ከአሕዛብ ሁሉ በላይ ኃይለኛ ገዢ እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ! ይህም ገዢ ይቃወመዋል እንደ ክፋቱም መጠን ያሳድደዋለሁ።12የአህዛብ ድንጋጤ የሆኑ የሌላ አገር ሰዎች፥ አስወግዱት ፈጽሞም ጣሉት። ቅርንጫፎቹ በተራሮችና ላይና በሸለቆች ውስጥ ወደቁ፥ ቅርንጫፎቹም በምድር ፈሳሾች ሁሉ ላይ ተሰባበሩ። የምድርም አሕዛብ ሁሉ ከጥላው ወጥተው ጥለውት ሄዱ።13የሰማይ ወፎች ሁሉ በግንዱ ላይ ይቀመጣሉ የምድርም አራዊት ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ይቀመጣሉ። 14ይህም የሆነው ወደ ጕድጓድ በሚወርዱ በሰው ልጆች መካከል ሁላቸው ለታችኛው ምድር ለሞት አልፈው ተሰጥተዋልና ውሀ ሲጠጡ ከነበሩት ዛፎች ውስጥ አንዳቸውም ረጅም ሆነው እንዳያድጉ፥ ጫፎቻቸውም ከቅጠሎች በላይ እንዳይሆኑ፥ በውኃ አጠገብ ያሉ ዛፎች ሁሉ ከእንግዲህ በቁመታቸው እንዳይረዝሙ ነው።15ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ሲኦል በወረደበት ቀን ልቅሶን ወደ ምድር አመጣሁ። በቀላያትም ሸፈንኩት፥ የውቅያኖስ ፈሳሾቹንም ከለከልሁ። ታላላቆችም ውኆች ከለከልኩ፥ ሊባኖስንም ስለ እርሱ አሳዘንሁት! የዱርም ዛፎች ሁሉ ስለ እርሱ አለቀሱ።16ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣልሁት ጊዜ ክአውዳደቁ ድምፅ የተነሣ በአሕዛብ ላይ መንቀጥቀጥን አመጣሁ! በምድር ዝቅተኛ ቦታ የኤደን ዛፎችን ሁሉ አጽናናለሁ! እነርሱም ውኃ የሚጠጡ ፥ ምርጦችና መልካካሞች የሊባኖስ ዛፎች ናቸው።17ክንዱም ወደ የነበሩት በአሕዛብም መካከል በጥላው ሥር የተቀመጡት፥ በሰይፍ ወደ ተገደሉት ሰዎች ወደ ሲኦል ከእርሱ ጋር ወርደዋልና። 18በክብርና በታላቅነት በዔድን ዛፎች መካከል ማን ይመስልህ ነበር? ነገር ግን ከዔድን ዛፎች ጋር ወዳልተገረዙት መካከል ወደ ታችኛው ምድር ያወርዱሃል፤ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ትኖራለህ! እነርሱም ፈርዖንና አገልጋዮቹ ናቸው ይላል ጌታ እግዚአብሔር!"
1እንዲህም ሆነ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 2የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፥ እንዲህም በለው፥ 'በእህዛብ መካከል እንደ አንበሳ ደቦል በባህር እንዳለ አስፈሪ ፍጥረት ነበርክ፤ ውሃውን አናወጥከው፥ ውሆችን በእግርህ በጥብጠህ አጨቀየሀቸው።3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ አሕዛብ ጉባኤ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፥ እነርሱም በመረቤ ይይዙሀል! 4በምድርም ላይ እተውሃለሁ፥ በምድረ በዳም ፊት እጥልሃለሁ፥ የሰማይንም ወፎች ሁሉ አሳርፍብሃለሁ፥ የተራቡ ምድርን አራዊት በአንተ አጠግባቸዋለሁ።5ሥጋህን በተራሮች ላይ አደርጋለሁ ሸለቆቹንም በትል በተሞላ ሬሳህ እሞላለሁ! 6ደምህንም በተራሮች ላይ አፈሳለሁ መስኖችም በደምህ ይሞላሉ።7መብራትህን ባጠፋህ ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፥ ከዋክብቶችንም አጨልማለሁ። ፀሐይንም በደመና እሸፍናለሁ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም! 8የሰማይን ብርሃኖች ሁሉ በላይህ አጨልማለሁ፥ በምድርህም ላይ ጨለማ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦9በአዛብ መካከል ጥፋትህን በማመጣ ጊዜ የማታውቃቸውን የብዙ ሕዝብን ልብ አስደነግጣለሁ። 10ብዙም አሕዛብን ስለዘንተ አስደንቃለሁ፤ ሰይፌንም በፊታቸው ባወዛወዝሁ ጊዜ ነገሥታቶቻቸው ስለ አንተ እጅግ አድርገው ይፈራሉ። በውድቀትህም ቀን እያንዳንዱ በአንተ ምክንያት ይንቀጠቀጣል።11ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል። 12አገልጋዮችህ የአህዛብ ድንጋጤ በሆኑ ጦርኞች ሥይፍ እንዲወድቁ አደርጋልሁ! የግበጽንም ትዕቢት ያውርዳሉ ህዝቧንም ሁሉ ያጠፋሉ!13እንስሶችን ከብዙ ውኃ አጠገብ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ የሰው እግርም ሆነ የእንስሳት ኮቴ ውሃውን አያደፈርስም! 14በዚያን ጊዜ ውኃቸውን አረጋጋለሁ፥ እንደ ዘይትም እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦15ሙሉ የነበረውን የግብጽን ምድር ባድማና ውድማ ባደረግሁ ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በቀሠፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ! 16የአሕዛብ ቈነጃጅት ያለቅሱበታል ያለቅሱባታልና ሙሾ ይሆናል፥ ነው ስለ ግብጽና ስለአገልጋዮቿ ሁሉ ያለቅሳሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦17እንዲህም ሆነ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 18የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ አገልጋዮች አልቅስ፥ እርስዋንና የብርቱዎችን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።19እንዲህ ብለህ ጥይቃቸው፥ 'ከማንም ይልቅ በውበት ትበልጣላችሁን? ውረዱና ካልተገረዙትም ጋር ተኙ! 20በሰይፍ በተገደሉት መካከል ይወድቃሉ፤ ጥላቶቿ እርሷንና አገልጋዮቿን ይይዛሉ! 21በሲኦል የኃያላን አለቆች ስለ ግብጽ ፥ "ወደዚህ ወደ ሲዖል መጥተዋል! በሰይፍ ከተገድሉ ካልተገርዙት ጋር ይተኛሉ!' ብለው ይናገራሉ።22አሦርና ጉባኤዋ ሁሉ በዚያ አሉ መቃብሮችም ከበዋታል፤ ሁሉም በሰይፍ የተገደሉ ናቸው። 23መቃብራቸው በጕድጓዱ በውስጠኛው ክፍል የሆኑትም ከእርሷ ጉባኤ ሁሉ ጋር በዚያ አሉ! መቃብሯ በተገደሉ፥ በሰይፍ በወደቁ እንዲሁም በሕያዋን ምድር ፍርሀትን ባመጡ ተከቧል።24ኤላምም ከአገልጋዮቿ ጋር በዚያ አለች፤ መቃብሮቿም ከበዋታል። ሁሉም የተገደሉ ናቸው። እነርሱም በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ ፥ ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር የወረዱ፥ በህያዋን ምድር ሽብርን ያመጡና ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን የተሸከሙ ናቸው። 25በተገደሉት መካከል ለኤላምና ለአገልጋዮቻ መኝታን አድርገውላታል፤ መቃብርዋ በዙሪያዋ ነው! ሁሉም ያልተገረዙና በህያዋን ምድር ሽብርን በማምጣታቸው በሰይፍ የተገደሉ ናቸው! ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል። ኤላምም በተገደሉትም መካከል ነች።26ሞሳሕና ቶቤል ብዛታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው ሁሉም ያልተገረዙ ሲሆኑ በሕያዋን ምድር ሽብር ያመጡ ስለነበር በሰይፍ የተገደሉ ናቸው! 27በሕያዋንም ምድር ኃያላኑን ያስፈሩ ነበርና መሣሪያቸውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወረዱ፥ ሰይፋቸውንም ከራሳቸው በታች ካደረጉ፥ ካልተገረዙ ኃያላን ጋር አልተኙምን? በህያዋን ምድር አስፈሪ ተዋጊዎች በመሆናቸው ጋሻቸውም በአጥንታቸው ላይ ነው ።28አንቺም ግብጽ ባልተገረዙት መካከል ትሰበሪያለሽ! በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ትተኚያለሽ። 29ኤዶምያስ ከነገሥታቶችዋና ከአለቆችዋ ሁሉጋር በዚያ አሉ። ኃያላን ነበሩ፥ ነገር ግን አሁን በሰይፍ ከተገደሉትና ካልተገረዙት ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ይተኛሉ ።30የሰሜን አለቆች ሁሉ ከሙታን ጋር የወረዱ ከሲዶናውያንም በዚያ አሉ! ኃያላን ነበሩ፥ አሁን ግን በዚያ በእፍረት ፥ በሰይፍ ከተገደሉት ጋር ሳይገረዙ ተኝተዋል። እፍረታቸውን ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር ይሸከማሉ።31ፈርዖንም ይመለከታል በሠይፍ ስለተገደሉት አገልጋዮቹ ይጽናናል ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 32መፈራቱን በሕያዋን ምድር አድርጌአለሁ፥ ነገር ግን በሰይፍ በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ይተኛል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!"
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ለሕዝብህ ልጆች ተናገር እንዲህም በላቸው፥ 'ሰይፍን በምድር ላይ ባመጣሁ ጊዜ፥ የምድር ሕዝብ ከመካከላቸው ሰውን ወስደው ለራሳቸው ጕበኛ ያድርጉ። 3ሰይፍ በመጣ ጊዜ ይመልከት ቀንደ መለከቱንም በመንፋት ህዝቡን ያስጠንቅቅ! 4ህዝቡም የመለከቱን ድምፅ ሰምተው ባይጠነቀቁ ፥ ሰይፍ መጥቶ ቢገድላቸው እያንዳንዱ ሰው ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል።5አንድ ሰው የመለከቱን ድምፅ ሰምቶ ባይጠነቀቅ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ ነገር ግን ቢጠነቀቅ የራሱን ህይወት ያድናል። 6ጕበኛው ግን ሰይፍ ሲመጣ ቢያይ መለከቱንም ባይነፋ ሕዝቡንም ባያስጠነቅቅ ሰይፍም መጥቶ አንድን ሰው ቢገድል እሱ በኃጢአቱ ይሞታል፥ደሙን ግን ከጕበኛው እጅ እፈልጋለሁ።7አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ እኔን ወክለህ አስጠንቅቃቸው። 8ኃጢአተኛውን "ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ!" ባልኩት ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ እንዲመለስ ለማስጠንቀቅ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። 9ነገር ግን ከመንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱ ግን ከመንገዱ ባይመለስ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።10አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤልን ቤት እንዲህ በላቸው፥ 'እናንተ በደላችንና ኃጢአታችን በላያችን አሉ እኛም ሰልስለንባቸዋል እንዴትስ በሕይወት እንኖራለን? ብላችኋል' ። 11'እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ የእስራኤል ቤት ሆይ ንስሀ ግቡ! ስለ ክፉ መንገዳችሁ ንስሀ ግቡ ለምን ትሞታላችሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር?' በላቸው።12አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ህዝብህን እንዲህ በላቸው፥' ጻድቅ ቢበድል ጽድቁ አያድነውም! ኃጢአተኛም ከኃጢአቱ ቢመለስ በኃጢአቱ አይጠፋም። ጻድቁም ኃጢአት ቢስራ በጽድቁ በሕይወት ሊኖር አይችልም። 13እኔ ጻድቁን፥ "በእርግጥ በሕይወት ይኖራል!" ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ በጽድቁ ታምኖ ኃጢአት ቢሠራ በሠራው ኃጢአት ይሞታል እንጂ ጽድቁ አላስብለትም።14እኔም ኃጢአተኛውን። በእርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ፥ 15ኃጢአተኛውም የብድር መያዣን ቢመልስ የነጠቀውንም ቢመልስ ሕይወት በሚሰጡ ትእዛዛት ቢራመድ ከዚያም በኋላ ኃጢአት ባይሠራ፥ በእርግጥም በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም። 16የሠራው ኃጢአት ሁሉ አይታሰብበትም። ፍርድንና ቅን ነገርን አድርጎአል በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።17ነገር ግን ሕዝብህ ፥ "የጌታ መንገድ የቀና አይደለም!" ይላሉ ነገር ግን ቅን ያልሆነው የእናንተ መንገድ ነው! 18ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ኃጢአትን ቢሠራ በኃጢአቱ ይሞታል! 19ኃጢአተኛውም ከኃጢአቱ ተመልሶ ፍርድንና ቅን ነገርን ቢያደርግ ባደረጋቸው ነገሮች ምክንያት በሕይወት ይኖራል። 20እናንተ ግን፥ "የጌታ መንገድ የቀና አይደለም!" ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።21እንዲህም ሆነ በተማረክን በአሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ "ከተማይቱ ተያዘች!"አለኝ። 22ሰውዬው ከመምጣቱ በፊት ባለው ምሽት የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ ሰውዬው በምሽት ወደ እኔ በመጣ ጊዜ አፌ ተከፍቶ ነበር። ስለዚህም አፌ ተከፍቶ ነበር ከዚያም በኋላ እኔ ዲዳ አልሆንሁም።23የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 24የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር ባሉ በባድማ ስፍራዎች የተቀመጡ፥ 'አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ እኛም ብዙዎች ነን ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች' ይላሉ።25ስለዚህ እንዲህ በላቸው፥'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፥ ዓይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፥ የስዎችንም ደም ታፈስሳላችሁ። በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን? 26በሰይፋችሁ ተማምናችሁ፥ ርኩስ ነገርን ታደርጋላችሁ፥ የባልንጀሮቻችሁንም ሚስቶች ታስነውራላችሁ። በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?27እንዲህም በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በባድማ ስፍራዎች ያሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ በምድረ በዳ ያለውን ለአራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ፥ በአምባዎችና በዋሾች ያሉ በቸነፈር ይሞታሉ። 28ምድሪቱንም ባድማና ውድማ አደርጋታለሁ በኃይሏም መመካቷ ይቀራል፥ የእስራኤልም ተራሮች ማንም የማያልፍባቸው በረሀ ይሆናሉ፥ ። 29ስላደረጉትም ርኵሰት ሁሉ ምድሪቱን ባድማና ውድማ ባደርግሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።30አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ሕዝብህ በቅጥር አጠገብና በቤት ደጆች ውስጥ ስለ አንተ ይናገራሉ፥ እርስ በርሳቸውም፥ አንዱ ከአንዱ ጋር፥ 'ወደ ነቢዩ እንሂድና እግዚአብሔር ያለው ቃል ምን እንደ ሆነ እንስማ!' እያሉ ይነጋገራሉ። 31ስለዚህ ሕዝቤ ብዙ ጊዜ እንደሚያደርጉት መጥተው በፊትህ ይቀመጣና ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም። ትክክለኛው ቃል በፍቸው ነው ፥ ልባቸው ግን ቅንነት የሌለበትን ትርፍ ትከተላለች።32እነሆ፥ አንተ መልካም ድምፅ እንዳለው እንደሚወደድ መዝሙር ማለፊያም አድርጎ እንደሚጫወቱት በገና ሆነህላቸዋል ስለዚህም ቃልህን ይሰማሉ ነገር ግን አንዳቸውም አያደርጉትም። 33እነሆ፥ ይህ ይመጣል በመጣም ጊዜ እነርሱ ነቢይ በመካከላቸው እንደ ነበረ ያውቃሉ።"
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን? 3ጮማውን ትበላላችሁ ጠጕሩንም ትለብሳላችሁ! ከመንጋው መካከል የወፈሩትን ታርዳላችሁ! በጎቹን ግን ፈጽሞ አታሰማሩም።4የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው። 5ያለ እረኛም በማጣት ተበተኑ፥ ከተበተኑም በኋላ ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ። 6በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በምድርም ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል። የሚፈልጋቸውም የለም።7ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ 8ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያና፥ ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና9ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ 10ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ በጎቼንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያሰማሩም በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።11ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ አሰማራቸውማለሁ። 12እረኛ በተበተኑት በጎች መካከል ባለ ጊዜ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ። 13ከአሕዛብም መካከል አወጣቸዋለሁ ከአገሮችም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም እሰበስባቸዋለሁ። በእስራኤልም ተራሮች ላይ በፈሳሾችም አጠገብ በምድርም ላይ ሰዎች በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።14በመልካም ማሰማርያ እሰማራቸዋለሁ የእስራኤል ረጃጅም ተራሮች የግጦሽ ቦታቸው ይሆናል። በዚያ በለመለመ መስክ በመልካምም የግጦሽ ሥፍራ ያርፋሉ፥ በእስራኤልም ተራሮች ላይ ይግጣሉ። 15እኔ ራሴ በጎቼን አሰማራለሁ አስመስጋቸውማለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦ 16የጠፋውንም እፈልጋለሁ የባዘነውንም እመልሳለሁ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አጸናለሁ የወፈረውንና የበረታውንም አጠፋለሁ! በመልካም አሰማራለሁ።17ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተም መንጋዬ ሆይ፥ እነሆ፥ በበግና በበግ መካከል፥ በአውራ በግና በአውራ ፍየልም መካከል፥ እፈርዳለሁ። 18የቀረውን ማሰማርያችሁን በእግራችሁ የረገጣችሁት፥ በመልካሙ ማሰማርያ መሰማራታችሁ አልበቃ ብሏችሁ ነው? የቀረውንስ ውኃ በእግራችሁ ያደፈረሳችሁት፥ ጥሩውን ውኃ መጠጣታችሁ አልበቃ ብሏችሁ ነው? 19በጎቼም በእግራችሁ በረገጣችሁት ይሰማራሉ በእግራችሁም ያደፈረሳችሁትን ይጠጣሉ።20ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፥ እነሆ፥ እኔ በወፈሩት በጎችና በከሱት በጎች መካከል እፈርዳለሁ። 21ይህም እስክትበትኑአቸው ድረስ በእንቢያና በትከሻ ስለምትገፉአቸው የደከሙትንም ሁሉ በቀንዳችሁ ስለምትወጉአቸው ነው።22ስለዚህ መንጋዬን አድናለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ለንጥቂያ አይሆኑም። በበግና በበግ መካከልም እፈርዳለሁ። 23በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው! ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል። 24እኔም እግዚአብሔር አምላክ እሆናቸዋለሁ ባሪያዬም ዳዊት በመካከላቸው አለቃ ይሆናል እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።25የሰላምን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እገባለሁ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አጠፋለሁ፥ በጎቼም ተጠብቀው በምድረ በዳ ይኖራሉ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ። 26በእነርሱና በዙሪያ ባሉ ኮረብቶቼ በረከቴን አፈሳለሁ፥ ዝናቡንም በጊዜው እልካለሁ። ይህም የበረከት ዝናብ ይሆናል። 27የምድረ በዳም ዛፍ ፍሬውን ይሰጣል ምድርም ቡቃያዋን ትሰጣለች፥ በጎቼ በምድራቸው ተዘልለው ይኖራሉ የቀንበራቸውንም ማነቆ በሰበርሁ ጊዜ ከሚገዙአቸውም እጅ ባዳንኋቸው ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።28እንግዲህም ለአሕዛብ ንጥቂያ አይሆኑም የምድርም አራዊት አይበሉአቸውም ተዘልለውም ይቀመጣሉ የሚያስፈራቸውም የለም። 29መልካም የእርሻ ቦታ አዘግዝጅላቸዋልሁ፥ ከእንግዲህም ከራብ የተነሣ በምድሪቱ አያልቁም አሕዛብም ከእንግዲህ ወዲህ አይሰድቧቸውም።30እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ከእነርሱ ጋር እንዳለሁ ያውቃሉ። የእስራኤል ቤት ሕዝቤ እነርሱ ህዝቤ ናቸው ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 31እናንተም በጎቼ፥ የማሰማርያዬ በጎች፥ ህዝቤ ናችሁ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር"
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርበት፥ 3እንዲህም በለው 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሴይር ተራራ ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ፥ በእጄ እመታሀለሁ ባድማና ድንጋጤ አደርግሃለሁ።4ከተሞችህንም አፈራርሳቸዋለሁ፥ አንተም ባድማ ትሆናለህ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ። 5ለእስራኤልን ህዝብ ሁል ጊዜ ጥላቻ ስላለህ በመከራቸውም ጊዜ በጽኑ ቅጣት በተቀጡበት ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና 6ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ለደም መፋሰስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደም መፋሰስም ያሳድድሃል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ደም መፋሰስን ስላልጠላህ ደም መፋሰስ ያሳድድሃል።7በእርሱ የሚያልፈውንም ሆነ ወደ እርሱ የሚመለስ እንዳይኖሬ በማድረግ የሴይርን ተራራ ውድማ አደርገዋለሁ ። 8ተራሮቹንም በተገደሉት ሰዎች እሞላለሁ በኮረብቶችህና በሸለቆችህ በፈሳሾችህም ሁሉ ላይ በሰይፍ የተገደሉት ሁሉ ይወድቃሉ። 9ለዘላለምም ባድማ አደርግሃለሁ ከተሞችህም ሰው የማይኖርባቸው ይሆናሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።10አንተ፥ "እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋሬ ቢሆንም እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች እነዚህም ሁለቱ አገሮች ለእኔ ይሆናሉ እኛም እንወርሳቸዋለን" ብለሃል። 11ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና እንደ ቍጣህ መጠን እነርሱንም ጠልተህ እንዳደረግኸው እንደ ቅንዓትህ መጠን እኔ አደርግብሀለሁ፥ በፈረድሁብህም ጊዜ በእነርሱ ዘንድ የታወቅሁ እሆናለሁ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ።12ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቃለህ። በእስራኤል ተራሮች ላይ "ፈርሰዋል! መብልም ሆነው ለእኛ ተሰጥተዋል" ብለህ የተናገርኸውን ስድብ ሁሉ ሰምቻለሁ። 13በአፋህም በእኔ ላይ የተናገርከውን ትምክህት የተሞላ ንግግር ሰምቻለሁ፤ በኔ ላይ ብዙ ነገሮችን ተናገርክ።፥ እኔም ሰምቼዋለሁ።14ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። ምድር ሁሉ ደስ ሲላት አንተን ባድማ አደርግሃለሁ። 15የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ አንተ ደስ እንዳለህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ። የሴይር ተራራ ሆይ፥ አንተና ኤዶምያስ ሁሉ ሁለንተናውም ባድማ ትሆናላችሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው ፥ 'የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!' 2ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጠላት በእናንተ ላይ "እሰይ! የጥንት ከፍታዎች ለእኛ ርስት ሆነዋል" ብሎአል። 3ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ባድማ በመሆናችሁና ከሁሉም አቅጣጫ ከመጣባችሁ ጥቃት የተነሳ ለሌሎች አሕዛብ ርስት ሆናችኋል፤ የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫም ሆናችኋል።4ስለዚህ፥ እናንተ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለፈሳሾችና ለሸለቆች ለምድረ በዳዎች ባዶ ለሆኑትም በዙሪያ ላሉት ለቀሩት አሕዛብ ምርኮና መሳቂያ ለሆኑት ከተሞች እንዲህ ይላል 5ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በወሰዱ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ 6ስለዚህ ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፥ ለተራሮችና ለኮረብቶችም ለፈሳሾችና ለሸለቆችም እንዲህ በል። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የአሕዛብን ስድብ ስለ ተሸከማችሁ በቅንዓቴና በመዓቴ ተናግሬአለሁ7ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ ስድባቸውን በእርግጥ ይሸከማሉ ብዬ ምያለሁ።8እናንተ የእስራኤል ተራሮች ግን ወደ እናንተ ተመልሰው የሚመጡበት ቀን ቀርቧልና፥ ቅርንጫፎቻችሁን ታቈጠቍጣላችሁ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤልም ፍሬአቸሁን ትሰጣላችሁ። 9እነሆ፥ እኔ ለእናንተ ነኝና ወደ እናንተም እመለከታለሁ፥ እናንተም ትታረሳላችሁ ይዘራባችሁማል።10ስለዚህም እናንተ ተራሮች ሆይ በእስራኤል ቤት ሁሉ ሰዎችን አበዛባችኋለሁ። ሁሉም! ከተሞች የሰዎች መኖሪያ ይሆናሉ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ። 11እናንተ ተራሮች ሆይ ሰውንና እንስሳውንም አበዛባችኋለሁ፥ እነርሱም ይበዛሉ ያፈሩማል። ቀድሞ እንደነበራችሁት የሰዎች መኖሪያ አደርጋችኋለሁ፥ ከቀድሞ ይልቅ አበለጥጋችኋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 12በእናንተ ላይ እንዲረማመዱ የሕዝቤን የእስራኤልን ሰዎችን አመጣቸዋለሁ። እነርሱም ይወርሱዋቸዋል ርስትም ትሆኑላቸዋላችሁ፥ ከእንግዲህም የልጆቻቸው ሞት ምክንያት አትሆኑም።13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነርሱ "እናንተ ሰው በሊታ ናችሁ የሕዝባችሁም ልጆች አልቀዋል" ብለዋችኋልና 14ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ሰው በሊታ አትሆኑም፥ ዳግመኛም ሕዝብችሁን በሚሞቱ ሰዎች ምንንያት እንዲያለቅሱ አታደርጉም ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 15ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አላሰማብሽም፤ ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም፥ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።16የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 17"የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት በምድራቸው በተቀመጡ ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው አረከሱአት፥ መንገዳቸውም በፊቴ እንደ መርገም አደፍ ነበረ። 18በምድሪቱም ላይ ስላፈሰሱት ደም በጣዖቶቻቸውም ስላረከሱአት መዓቴን አፈሰስሁባቸው።19ወደ አሕዛብም በተንኋቸው ወደ አገሮችም ተዘሩ እንደ መንገዳቸውና እንደ ሥራቸው መጠን ፈረድሁባቸው። 20ወደ ሌሎች ሕዝቦች ሄዱ። በሄዱም ጊዜ ሰዎች ስለነርሱ 'አሁን እነዚህ ከአገራቸው የተፈናቅሉ የእግዚአብሔር ሕዝብ እነዚህ ናቸው?' በማለታቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ። 21እኔ ግን የእስራኤል ቤት በመጡባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሱት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ራራሁላቸው።22ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህን የማደርገው በሄዳችሁበት በአሕዛብ መካከል ሁሉ ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እናንተ አይደለም። 23በአሕዛብም ዘንድ የረከሰውን፥ በመካከላቸው ያረከሳችሁትን ስሜን እቀድሰዋለሁ። በዓይናቸውም ዘንድ በተቀደስሁባችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦24ከአሕዛብም መካከል እወስዳችኋለሁ ከየአገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ ወደ ገዛ ምድራችሁም አመጣችኋለሁ። 25ከእርኩሰታችሁ ሁሉ እንድትነጹም ጥሩ ውኃን እረጭባችኋለሁ። ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ።26አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። 27መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም መሄድ አስችላችኋለሁ ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ። 28ለአባቶቻችሁም በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ ሕዝቤ ትሆናላችሁ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።29ከርኵሰታችሁም ሁሉ አድናችኋለሁ እህልንም እጠራዋለሁ አበዛውማለሁ ከእንግዲህም ራብን አላመጣባችሁም። 30ደግሞም የራብን ስድብ በሕዝቦች መካከል እንዳትሸከሙ የዛፍን ፍሬና የእርሻውን ቡቃያ አበዛለሁ። 31ከዚያም ክፉውን መንገዳችሁንና መልካም ያይደለውን ሥራችሁንም ታስባላችሁ፥ ስለ በደላችሁና ስለ ርኵሰታችሁም ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።32ይህን ያደረኩት ስለ እናንተ ብዬ እንዳይደለ እወቁ-ይላል ጌታ እግዚአብሔር። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ መንገዳችሁ እፈሩና ተዋረዱ። 33ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ክእርኩሰታችሁ ሁሉ ባነጻኋችሁበት ቀን በከተሞቻችሁ እንድትኖሩ የፈረሱትንም ሥፍራዎች እንደገና እንድትጠግኑ አደርጋችኋለሁ። 34ባድማ የነበረች ምድር በመንገደኛ ሁሉ ዓይን ባድማ ባል ድረስ ትታረሳለች።35ሰዎችም፥ "ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች የፈረሱት ባድማ የሆኑት የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል" ይላሉ። 36በዙሪያችሁም ያሉ አሕዛብ እኔ እግዚአብሔር የፈረሱትን ስፍራዎች እንደ ሠራሁ ውድማ የሆነውንም እንደገና እንደተከልሁ ያውቃሉ፥ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርገዋለሁ።37ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ እንደመንጋ እንዳበዛቸው የእስራኤል ቤት ይጠይቁኛል። 38ለእግዚአብሔሬእንደ ተለዩ በጎች፥ በበዓላቶችዋ ቀን እንደሚሆኑ እንደ ኢየሩሳሌም በጎች፥ እንዲሁ የፈረሱት ከተሞች በሰዎች መንጋ ይሞላሉ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ አጥንቶችም በሞሉባት ሸለቆ መካከል አኖረኝ። 2ዙሪያውን በመካከላቸው እንዳልፍ አደረገኝ፥ እነሆ በሸለቆው ውስጥ እጅግ ብዙ ነበሩ፥ እነሆም፥ እጅግ ደርቀው ነበር። 3እርሱም፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች እንደገና በሕይወት ሊኖሩ ይችላሉን?" አለኝ። እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ይህን የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ!" አልሁ።4እርሱም እንዲህ አለኝ፥ "በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፥ 'እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ። 5ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል። እነሆ፥ መንፈስን አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ። 6ጅማትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።7እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ ስናገርም ፥ እነሆ የሚያናውጥ ድምፅ ሆነ፥ አጥንቶችም አጥንት ከአጥንት ጋር ተቀራረቡ። 8እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ጅማት ነበረባቸው ሥጋም ወጣ ቁርበትም በላያቸው ተዘረጋ፥ ህይወት ግን አልነበራቸውም።9እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስም 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦' መንፈስ ቅዱስ! ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው" በል አለኝ። 10እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ! እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።11እርሱም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው። እነሆ! አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል። 12ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር እመልሳችኋለሁ!13ሕዝቤ ሆይ፥ መቃብራችሁን በከፈትሁ ጊዜ ከመቃብራችሁም ባወጣኋችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 14መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ባወቃችሁ ጊዜ በገዛ ምድራችሁም እንድታርፉ አደርጋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ አደርገውማለሁ ይላል እግዚአብሔር።15የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 16"አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ አንድ በትር ውሰድና። 'ለይሁዳና ለባልንጀሮቹ ለእስራኤል ልጆች'ብለህ በላዩ ጻፍ። 'ሌላም በትር ውሰድና 'ለኤፍሬም በትር ለዮሴፍና ለባልንጀሮቹ ለእስራኤል ቤት ሁሉ' ብለህ በላዩ ጻፍ። 17ከዚያም በእጅህ ውስጥ አንድ እንዲሆኑ ሁልቱንም በትሮች በአንድ ላይ ያዛቸው።18ሕዝብህም ፥ 'ይህ የምታደርገው ነገር ምን ማለት እንደሆነ አትነግረንምን? ብለው በተናገሩህ ጊዜ፥ 19አንተ። 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን በትር ባልንጀሮቹንም የእስራኤልን ነገዶች እወስዳለሁ፥ ከይሁዳ በትር ጋር አጋጥማቸዋለሁ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፥ በእጄም ውስጥ አንድ ይሆናሉ' በላቸው። 20የጻፍክባቸውንም በትሮች በዓይናቸው ፊት በእጅህ ያዛቸው።21ከዚያም እንዲህ በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ከአሕዛብ መካከል የምወስድበት ጊዜ ደርሷል ከአካባቢው አገሮች ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ። 22በምድሪቱም ውስጥ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፥ አንድ ንጉሥም በሁላቸው ላይ ይነግሣል ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፥ ከዚያ ወዲያም ሁለት መንግሥቶች ሆነው አይለዩም። 23ከዚያ ወዲያም በጣዖቶቻቸውና በርኵሰታቸው በመተላለፋቸውም ሁሉ አይረክሱም፥ ኃጢአትም ከሠሩባት ዓመፅ ሁሉ አድናቸዋለሁ አነጻቸውማለሁ ሕዝብም ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።24ባሪያዬም ዳዊት በላያቸው ይነግሳል። ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል። 25አባቶቻችሁም በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል።26ከእነርሱ ጋር የሰላምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለምም ቃል ኪዳን ይሆናል። እኔም አጸናቸዋለሁ አበዛቸውማለሁም መቅደሴንም ለዘላለም በመካከላቸው አኖራለሁ። 27ማደሪያዬም በእነርሱ ዘንድ ይሆናል፤ ይሆናል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል። 28መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ፥ እኔ እስራኤልን ለራሴ የለየሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ።
1የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ 2"የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን በጎግ ላይና በማጎግ ምድር ላይ፥ በሞሳሕና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ አቅናበት፥ ትንቢትም ተናገርበት፥ 3እንዲህም በል፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሳሕና የቶቢል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ።4እመልስህማለሁ በመንጋጋህም ልጓም አገባብሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህንም ሁሉ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን ሰይፍንም ያያዙትን ሁሉ፥ ታላቁን ወገን አወጣለሁ! 5ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱት ፋርስን ኢትዮጵያና ፉጥ ከእነርሱ ጋር ናቸው! 6ጋሜርንና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻም ያለውን የቴርጋማን ቤትና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ ብዙዎች ሕዝቦች ከእነርሱ ጋር ናቸው።7ተዘጋጅ! አዎ፥ ራስህንና ሠራዊትህን አዘጋጅ አለቃም ሁናቸው። 8ከብዙ ቀናትም በኋላ ትጠራልህ ክተወሰኑ ዓመታት በኋላ ክሠይፍ እያገገመች ወዳለችው፥ ከብዙ ሕዝቦችም መካከል ተሰብስበው ያለማቋረጥ ባድማ በነበሩት በእስራኤል ተራሮች ላይ ዳግም ወደ ተሰበሰቡ ትሄዳለህ። የምድሪቱ ሕዝብ ግን ከሕዝቦች መካከል ወጥተው ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል። 9አንተም ትወጣለህ፥ እንደ ዐወሎ ነፋስም ትመጣለህ አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ምድሪቱን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።10ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን በልብህ ታቅዳለህ፥ 11ክፉ አሳብንም ታስባለህ።' እንዲህም ትላለህ፥ 'ቅጥር ወደሌላቸው መንደሮች እወጣለሁ ተዘልለው ወደሚኖሩ፥ ሁላቸው ሳይፈሩ ያለ ቅጥርና ያለ መወርወሪያ ያለ መዝጊያም ወደሚቀመጡ እገባለሁ 12ባድማም በነበሩና በቅርቡ ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከብትና ዕቃንም ይዘው ከአሕዛብም በተሰበሰቡ ሰዎች በምድርም መካከል በሚኖሩ ሕዝብ ላይ እጄን እዘረጋናምርኮን እማርካለሁ ብዝበዛንም እበዘብዛለሁ ።13ሳባና ድዳን የተርሴስም ነጋዴዎች ከወጣት ጦረኞቻችው ሁሉ ጋር እንዲህ ይሉሀል፥ 'የመጣኸው ምርኮን ለመማረክ ነው? ጦርህን የሰበሰብከው ብዝበዛን ለመበዝበዝ ብርንና ወርቅንስ ለመውሰድ፥ ከብትንና ዕቃንስ ለመውሰድ እጅግም ብዙ ምርኮ ለመማረክ ነው?'።14ስለዚህም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር ጎግንም እንዲህ በለው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል ሳይፈራ በተቀመጠ ጊዜ አንተ ስለእነርሱ አታውቀውምን? 15አንተም፥ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላቸው በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፥ ታላቅ ወገንና ብርቱ ሠራዊት፥ ከሰሜን ዳርቻ ከስፍራችሁ ትመጣላችሁ። 16ደመና ምድርን እንድሚሸፍን ህዝቤን ታጠቃለህ። ጎግ ሆይ እንዲህ ይሆናል በዓይናቸው ፊት በተቀደስሁብህ ጊዜ አሕዛብ ያውቁኝ ዘንድ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።17ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእነርሱ ላይ እንደማመጣህ በዚያች ዘመን ብዙ ዓመት ትንቢት በተናገሩ በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያቶች በቀደመው ዘመን ስለ እርሱ የተናገርሁ አንተ አይደለህምን? 18በዚያም ቀን ጎግ በእስራኤል ምድር ላይ በመጣ ጊዜ መቅሠፍቴ በመዓቴ ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦19በቁጣዬ ትኩሳትና በመዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፥ በእርግጥ በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ጽኑ የምድር መናወጥ ይሆናል። 20የባሕር ዓሣዎችና የሰማይ ወፎች የምድረ በዳም አራዊት በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በምድርም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ። ተራሮችም ይገለባበጣሉ ገደላገደሎችም ይወድቃሉ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።21በተራሮቼም ሁሉ በእርሱ ላይ ሰይፍን እጠራለሁ፥ የሰውም ሁሉ ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦ 22በቸነፈር፥ በደም ፥በዶፍ ዝናብና የድንጋይ እሳት እፈርድባቸዋለሁ። ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ። 23ታላቅነቴንና ቅዱስ መሆኔን አሳያለሁ በብዙ አሕዛብም ዓይን የታወቅሁ እሆናለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
1አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ የሞሳሕና የቶቤል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ 2እመልስሃለሁ፥ እነዳህማለሁ፥ ከሰሜንም ዳርቻ እጐትትሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች አመጣሃለሁ። 3ከግራ እጅህም ቀስትህን አስጥልሃለሁ፥ ከቀኝ እጅህም ፍላጾችህን አስረግፍሃለሁ።4የአንተና የጭፍሮች ሁሉ ከአንተም ጋር ያሉ ሠራዊትና ወታደሮች ሬሳ ይገኛል። ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ። 5አንተ በምድር ፊት ላይ ትወድቃለህ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 6በማጎግም ላይ ሳይፈሩም በደሴቶች በሚቀመጡ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።7ቅዱሱም ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል እንዲታወቅ አደርጋለሁ፥ ቅዱሱንም ስሜን ከእንግዲህ ወዲህ እንዲረክስ አልፈቅድም፤ አሕዛብም እግዚአብሔር፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 8ያልሁት ቀን እነሆ፥ ይመጣል ይሆንማል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር ።9በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ይወጣሉ፥ የጦር መሣሪያዎችን፥ አላባሽ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትንና ፍላጻዎችን፥ ጎመድንና ጦርንም ያቃጥላሉ፥ ለሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል። 10በጦር መሣሪያው እሳትን ያነድዳሉ እንጂ እንጨትን ከምድረ በዳ አይወስዱም ከዱርም አይቈርጡም የገፈፉአቸውንም ይገፍፋሉ የበዘበዙአቸውንም ይበዘብዛሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦11በዚያም ቀን በእስራኤል ዘንድ በባሕር ምሥራቅ የሚያልፉበትን ሸለቆ የመቃብርን ስፍራ ለጎግ እሰጣለሁ፥ የሚያልፉትንም ይከለክላል በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ይቀብራሉ የሸለቆውንም ስም ሐሞንጎግ ብለው ይጠሩታል።12ምድሩንም ያጸዱ ዘንድ የእስራኤል ቤት ሰዎች ሰባት ወር ይቀብሩአቸዋል፥ 13የምድሪቱም ሰዎች ሁሉ ይቀብሩአቸዋል፥ እኔ የምከብርበት የማይረሳ ቀን ይሆንላችኋል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦14ምድርንም ለማጽዳት በምድሩ ላይ ወድቀው የቀሩትን የሚቀብሩ፥ ዘወትር በምድሩ ላይ የሚዞሩትን ሰዎች ይመድባሉ ስራውንም ከሰባት ወርም በኋላ ይጀምራሉ። 15በምድሩ ላይ እንዲዞሩ የተመደቡት በሚያልፉብት ጊዜ የሰውን አጥንት ካዩ ፥ ቀባሪዎች መጥተው በሐሞን ጎግ ሸለቆ እስኪቀብሩት ድረስ ምልክት አድርገው ያልፋሉ። 16ስሟ ሐሞና የሚሰኝ ከተማ በዚያ ትገኛለች። በዚህ መንገድ ምድሪቱን ያጸዳሉ።17አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለወፎች ሁሉና ለምድር አራዊት ሁሉ እንዲህ በላቸው፥ 'ኑ፥ ተከማቹ፥ ሥጋንም ትበሉ ዘንድ ደምንም ትጠጡ ዘንድ በእስራኤል ተራሮች ላይ ወደማርድላችሁ ታላቅ መሥዋዕት፥ ከየስፍራው ሁሉ ተሰብሰቡ። 18የኃያላኑን ሥጋ ትበላላችሁ የምድርንም አለቆች፥ የአውራ በጎችንና የጠቦቶችን፥ የፍየሎችንና የወይፈኖችን፥ የባሳንን ፍሪዳዎች ሁሉ፥ ደም ትጠጣላችሁ።19እኔም ከማርድላችሁ መሥዋዕት እስክትጠግቡ ድረስ ጮማ ትበላላችሁ እስክትሰክሩም ድረስ ደም ትጠጣላችሁ። 20በሰደቃዬም ከፈረሶችና ከፈረሰኞች፥ ከኃያላንና ከሰልፈኞች ሁሉ ትጠግባላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።21ክብሬንም በአሕዛብ መካከል አኖራለሁ አሕዛብም ሁሉ ያደርግሁትን ፍርዴን፥ በላያቸውም ያኖርኋትን እጄን ያያሉ። 22ከእንግዲህም ወዲያ የእስራኤል ቤት እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።23አሕዛብም የእስራኤል ቤት እኔን ባቃለሉበት በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ተማረኩ ያውቃሉ፥ ስለ በደሉኝ እኔም ፊቴን ከእነርሱ ስለ ሸሸግሁ፥ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ እነርሱም ሁሉ በሰይፍ ወደቁ። 24እንደ ርኵሰታቸውም እንደ መተላለፋቸውም መጠን አደረግሁባቸው ፊቴንም ከእነርሱ ሸሸግሁ።25ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሁን የያዕቆብን ምርኮ እመልሳለሁ ለእስራኤልም ቤት ሁሉ እራራለሁ፥ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀናለሁ። 26እፍረታቸውንና እኔን የካዱበትን ክህደት ይረሳሉ። ማንም ሳያስፈራቸው በምድራቸው ተዘልለው በተቀመጡ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ይረሳሉ። 27ከአሕዛብም ዘንድ በመለስኋቸው ጊዜ ከጠላቶቻቸውም ምድር በሰበሰብኋቸው ጊዜ በብዙ አሕዛብም ፊት እቀደሳለሁ።28እኔም ወደ አሕዛብ አስማርኬአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። ከእነርሱም አንድንም ሰው በአሕዛብ መካከል አልተውኩም። 29ፊቴንም ከእነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አልሸሽግም መንፈሴን በእስራኤል ቤት ላይ አፍስሻለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
1በተማረክን በሀያ አምስተኛው ዓመት በዓመቱ መጀመሪያ ከወሩ በአሥረኛው ቀን፥ ከተማይቱ ከተመታች በኋላ በአሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ። 2በእግዚአብሔር ራእይ ወደ እስራኤል ምድር አመጣኝ እጅግም በረዘመ ተራራ ላይ አኖረኝ፥ በዚያም ላይ በደቡብ ወገን እንደ ከተማ ሆኖ የተሠራ ነገር ነበረ።3ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆም፥ መልኩ እንደ ናስ መልክ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ነበረ እርሱም በከተማይቱ በር አጠገብ ቆሞ ነበር። 4ሰውዬውም፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ወደዚህ ያመጣሁህ ይህን ላሳይህ ስለሆን በዓይንህ እይ በጆሮህም ስማ በማሳይህም ሁሉ ላይ ልብ በል የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር አለኝ።5እነሆም፥ በቤተመቅደሱ ዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ ርዝመቱ ስድስት ክንድ የሆነ የመለኪያ ዘንግ ነበር። እያንዳንዱም ክንድ አንድ ክንድ ከስንዝር ነበረ። ሰውዬውም ቅጥሩን ለካ፤ የቅጥሩም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመቱንም አንድ ዘንግ ነበረ። 6ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተውም በር ሄዶ በደረጃዎቹ ወጣ፥ የመድረኩንም ወለል ለካ፥ ወርዱን አንድ ዘንግ ነበር። 7የዘበኞቹም ጓዳ ሁሉ ርዝመቱ አንድ ዘንግ፥ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበረ በዘበኞቹም ጓዳዎች መካከል አምስት ክንድ ርቀት ነበረ በበሩም ደጀ ሰላም በስተ ውስጥ በኩል የሚገኝ የበሩ የመድረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።8የበሩን መተላለፊያ ደጅ ለካ ርዝመቱም አንድ ዘንግ ነበር። 9የበሩን መተላለፊያ ደጅ ለካ፥ ጥልቀቱ አንድ ዘንግ ነበረ። የግንቡንም አዕማድ ወርድ ሁለት ክንድ ነበረ። አድርጎ ለካ ።ይህም በቤተመቅደሱ ትይዩ የሚገኘው ድጅ መተላለፊያ ነበረ። 10በበሩ አጠገብ የሚገኙት የዘበኛ ጓዳዎች በበሩ በሁለቱም በኩል ሦስት ሦስት ነበሩ፥ የሁሉም መጠን እኩል ነበረ በሁሉም አቅጣጫ የሚለያቸው ግንብም እኩል መጠን ነበረው።11ቀጥሎም ሰውዬው የበሩን መግቢያ ወርድ ለካ አሥር ክንድ ሆነ፤ የበሩንም መግቢያ ርዝመት ለካ አሥራ ሦስት ክንድ ሆነ። 12በእያንዳንዱ በዘበኛ ጓዳ ፊት ከፍታው አንድ ክንድ የሆነ መከለያ ነበረ። የዘበኛ ጓዳዎቹም በሁሉም አቅጣጫ ስድስት ክንድ ከፍታ ነበራቸው። 13ከአንዱም የዘበኛ ጓዳ ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበሩን ወርድ ሀያ አምስት ክንድ ለካ ይህም ከመጀምሪያው የዘበኞች ጓዳ መግቢያ እስከ ሌላኛው መግቢያ ድረስ ነው።14ቀጥሎም በዘበኞች ጓዳ መካከል የሚያልፈውን ግንብ ለካ፤ ስድስት ክንድም ሆነ። እስከ መግቢያው መተላለፊያ ድረስ ለካ ። 15ከበሩም መግቢያ ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው የበሩ መተላለፊያ መጨረሻ ድረስ አምሳ ክንድ ነበረ። 16በዘበኛ ጓዳዎቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ ትንንሽ መስኮቶች ነበሩዋቸው። በበሩም ደጅ መተላለፊያ እንደዚያው ነበር። ሁሉም መስኮቶች በውስጥ በኩል ነበሩ። በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።17ቀጥሎም ሰውዬው ወደ ውጭውም አደባባይ አመጣኝ። እነሆም፥ በአደባባዩ ዙሪያ ክፍሎችና ወለል ነበሩ። በወለሉም ላይ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ። 18ወለሉም እስከ በሮቹ ይደርስ ነበር ስፋቱም እንደ በሮቹ ርዝመት መጠን ነበረ። ይህም ታችኛው ወለል ነበር። 19ከታችኛውም በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው በር ፊት ድረስ ያለውን ርቀት ለካ፤ በምስራቅ በኩል አንድ መቶ ክንድ በሰሜኑም በኩል ተመሳሳይ ነበረ።20ቀጥሎም ከውጭው አደባባይ በሰሜን በኩል ያለውን በር ርዝመትና ስፋት ለካ። 21በበሩ በዚህና በዚያ የዘበኛ ጓዳዎቹም ነበሩ፥ በሩና መተላለፊያው ከዋናው በር ልኬታቸው እኩል ነበር- ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።22መስኮቶቹም ፥መተላለፊያዎቹና የዘንባባ ዛፎቹ ወደ ምሥራቅ እንደሚመለከተው በር ጋር ይዋሰኑ ነበር። ወደ እርሱና ወደ መተላለፊያዎቹ የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ። 23በውስጠኛውም አደባባይ በሰሜኑና በምሥራቁ በኩል በሌላው በር አንጻር በር ነበረ፤ ሰውዬውም ከአንዱ በር እስከ በር ድረስ ለካ። ርቀቱም አንድ መቶ ክንድ ነበር።24ቀጥሎም ሰውዬው ወደ ደቡቡ መግቢያ አመጣኝ፥ እነሆም፥ ግንቡና መተላለፊያዎቹ ከሌላኛው መውጪያው በር ጋር እኩል ልኬት ነበራቸው። 25በመግቢያውና በመተላለፊያዎቹ እንደዚያኛው በር አይነት ትንንሽ መስኮቶች ነበሩዋቸው። የድቡቡ በርና መተላልፊያው ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ።26ወደ በሩና መተላለፊያዎቹ የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፥ በግንቡም አዕማድ ላይ በሁለቱም ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር። 27በደቡብ በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባ መግቢያ ነበረ፥ ሰውዬውም ከዚህኛው በር እስከ ደቡቡ መግቢያ ድረስ ለካ፥ ርቀቱ መቶ ክንድ ነበረ።28ቀጥሎም ሰውዬው ከሌላኛው በር እኩል ልኬት ባለው በደቡብ በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አገባኝ ። 29የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድና መተላለፊያዎቹ ከመጀመሪያዎቹ መግቢያዎች እኩል ነበሩ፤ በመተላለፊያዎቹ ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ።ውስጠኛው መግቢያና መተላለፊያው ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ። 30በውስጠኛው ግንብ ዙሪያውም መተላለፊያዎች ነበሩ። ርዝመታቸውም ሀያ አምስት ክንድ ወርዳቸውም አምስት ክንድ ነበረ። 31መተላለፊያዎቹም ወደ ውጭው አደባባይ ይመለከቱ ነበር በግንቡም አዕማድ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ።32ቀጥሎም ከሌሎቹ መግቢያዎች እኩል ልኬት ባለው በምስራቁ በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አገባኝ። 33የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድ መተላለፊያዎቹ ሌኬታቸው ከሌሎቹ መግቢያዎች እኩል ነበር በዙሪያም መስኮቶች ነበሩ። መግቢያውና መተላልፊያው ርዝመቱም አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ። 34መተላለፊያዎቹም በስተ ውጭ ወዳለው አደባባይ ይመለከቱ ነበር በግንቡም አዕማድ ላይ በዚህና በዚያ ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።35በሰሜንም ወዳለው በር አመጣኝ፥ በሩንም ለካው፤ ልኬቱም ከሌሎቹ በሮች እኩል ነበር። 36የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድ መተላለፊያዎቹ ልኬታቸው ከሌሎቹ በሮች እኩል ነበር በዙሪያውም መስኮቶች ነበሩ። ርዝመቱም አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ። 37መተላለፊያውም ወደ ውጭው አደባባይ ይመለከቱ ነበር በግንቡም አዕማድ ላይ በዚህና በዚያ ወገን የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩት።38በእያንዳኔዱ ውስጠኛ መግቢያ በር ያላቸው ክፍሎች ነበሩ። ይህም የሚቃጠለውን መሥዋዕት የሚያጥቡበትነበር። 39የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የኃጢአቱንና የበደሉንም መሥዋዕት ያርዱባቸው ዘንድ፥ በበሩ መተላለፊያ በዚህ ወገን ሁለት ገበታዎች፥ በዚያም ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ።40በሰሜን በኩል ባለው በር በስተ ውጭው፥ በመወጣጫው ደረጃዎች አጠገብ፥ በአንድ ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ፥ በሌላውም ወገን በበሩ መተላለፊያ በኩል ሁለት ገበታዎች ነበሩ። 41በበሩ በሁለቱም ወገን አራት ገበታዎች ነበሩ፤ በስምንቱም ገበታዎች እንስሳትን ይሰው ነበር።42ለሚቃጠለውም መሥዋዕት ርዝመታቸው አነድ ክንድ ተኩል ወርዳቸውም አንድ ክንድ ተኩል ቁመታቸውም አንድ ክንድ የሆኑ ከተጠረበ ድንጋይ የተሠሩ አራት ገበታዎች ነበሩ። በእነርሱም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን የሚያርዱበትን መሳሪያ ያኖሩባቸው ነበር። 43በዙሪያውም በመተላለፊያው አንድ ጋት የሚርዝም መስቀያዎችነበሩ፥ የመስዋዕቱም ሥጋ የሆነ ክፈፍ በገበታዎቹም ላይ ይቀመጡ ነበር።44በውስጠኛው አደባባይ ከውስጠኛው መግቢያም አጠገብ የዘማሪያን ክፍሎች ነበሩ። ከክልሎቹ አንዱ በሰሜን በኩል ነበረ፥ ሌላውም በስተደቡብ ነበረ። 45ሰውዬውም፥ "ይህ ወደ ደቡብ የሚመለከት ቤት በመቅደሱ ውስጥ ለማገልገል ተረኛ ለሆኑለሚተጉ ካህናት ነው።46ወደ ሰሜንም የሚመለከተው ቤት በመሠዊያው ዙሪያ ለሚያገለግሉ ካህናት ነው። እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል ያገለግሉት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው" አለኝ። 47ቀጥሎም አደባባዩን ለካ፥ አራት ማዕዘን ሆኖ ርዝመቱን መቶ ክንድ ወርዱንም መቶ ክንድ ነበረ መሠዊያውም በቤቱ ፊት ነበረ።48ከዚያም ሰውዬው ወደ ቤቱ መተላለፊያ አመጣኝ፥ የግንብ አዕማዱንም ለካ፤ ወርድ በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ ነበረ። መግቢያው ራሱ ወርዱ አሥራ አራት ክንድ ነበረ፥ በበሩም በዚህ ወገንና በዚያ ወገን የነበሩት ግንቦች ስፋት ሦስት ሦስት ክንድ ነበር። 49የቤተ መቅደሱ መተላለፊያ ርዝመት ሀያ ክንድ ወርዱም አሥራ ሁለት ክንድ ነበረ። ወደ እርሱም የሚያደርሱ ደረጃዎች በሁለቱም አቅጣጫ የቆሙ አዕማድ ነበሩ።
1ከዚያም ሰውዬው ወደ መቅደሱም ቅዱስ ስፍራ አገባኝ፥ የግንቡንም አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድስት ክንድ በዚያም ወገን ስድስት ክንድ አድርጎ ለካ። 2የመግቢያውም ወርድ አሥር ክንድ ነበረ፥ የመግቢያውም መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ ነበሩ።ቀጥሎም ሰውዬው ቅዱስ ስፍራውን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሀያ ክንድአድርጎ ለካ።3ከዚያም ሰውዬው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ገባ፥ የመግቢያውንም የግንብ አዕማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድርጎ ለካ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበረ። የመግቢያውም ግንብ ወርድ በዚህ ወገን ሰባት ክንድ በዚያም ወገን ሰባት ክንድ ነበረ። 4የክፍሉንም ርዝመት ወደ መቅደሱ ፊት ለፊት ሀያ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካና፥ "ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው" አለኝ።5የመቅደሱንም ግንብ ስድስት ክንድ አድርጎ። በመቅደሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉትን የጓዳዎቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ ነበረ። 6ጓዳዎቹም አንዱ ከአንዱ በላይ በሦስት ደርብ ነበሩ፥ በእያንዳንዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳዎች ነበሩ። በመቅደሱም ግንብ ዙሪያ ድጋፍ የሆኑ መደርደሪያዎች ነበሩ፥ ምክንያቱም በመቅደሱ ግንብ ውስጥ ድጋፎች አልነበሩም። 7ላይኞቹ ጓዳዎች ከታችኞቹ ጓዳዎች ይበልጡ ነበር ከታችኛውም ደርብ ወደ መካከለኛው ከመካከለኛውም ደርብ ወደ ላይኛው የሚወጣበት ደረጃ ነበረ።8በመቅደሱም ዙሪያ የጓዳዎቹም መሠረት የሆነ ከፍ ያለ ወለል እንዳለ አየሁ ቁመቱም ሙሉ ዘንግ የሚያህል ስድስት ክንድ ነበረ። 9የጓዳዎቹም የውጭው ግንብ ውፍረት አምስት ክንድ ነበረ። በመቅደሱም ጓዳዎች ውጭ የቀረ አንድ ባዶ ስፍራ ነበረ።10በዚህም ባዶ ስፍራ በአንድ ወገን የካህናት በረንዳዎች ነበሩ፤ የባዶውም ስፍራ ወርድ በዙሪያ አምስት ክንድ ነበረ። ይህም ባዶ ሥፍራ በመቅደሱ ዙሪያ ወርዱ ሀያ ክንድ ነበረ። 11በዚህም በባዶው ስፍራ አንዱ በሰሜን በኩል አንዱም በደቡብ በኩል የጓዳዎች መግቢያ ነበረ። የባዶውም ስፍራ ዙሪያ ወርድ አምስት ክንድ ነበረ።12በምዕራብም በኩል ባለው ግቢ አንጻር ያለው ህንጻ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግቢውም ዙሪያ የነበረ ግንብ ውፍረቱ አምስት ክንድ ርዝመቱም ዘጠና ክንድ ነበረ። 13የመቅደሱንም ርዝመት መቶ ክንድ፥ የልዩውን ስፍራና ግቢውን ከግንቡ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 14ደግሞም ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት የሚገኘው ግቢ የፊት ለፊት ወርዱ አንድ መቶ ክንድ ነበር።15ቀጥሎም ሰውዬው ከቤተ መቅደሱ በስተዋላ ያለውን ህንጻ የምዕራብ ክፍል በዚህና በዚያ ከነበሩት ፎቆች ጋር እንዲሁም ቅዱስ ስፍራውና መድረኩን አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 16ውስጠኛዎቹ ግድግዳዎች፥ ጠባቦቹን ጨምሮ መስኮቶቹ እንዲሁም በሶስት ደረጃዎች ያሉ ፎቆች በእንጨት ተለብጠው ነበር። 17ከደጁም በላይ እስከ ውስጠኛው ክፍል ድረስ፥ በውጭም ግንቡ ሁሉ ውስጡም ውጭውም ተለብጦ ነበር።18በኪሩቤልና በዘንባባ ዛፎች ተውቦ ነበር የዘንባባውም ዛፍ ከኪሩብና ከኪሩብ መካከል ነበረ እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው። 19የሰው ፊት የሚመስለው በአንድ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር፥ የአንበሳ ፊት የሚመስለው ደግሞ በሌላ ወገን ወዳለው የዘንባባ ዛፍ ይመለከት ነበር። ይህም በዙሪያ ያሉትን ቤቶች አስውቦ ነበር። 20ከመሬት አንሥቶ እስከ ደጁ አናት ድረስ እና በመቅደሱ ላይ በኪሩቤልና በዘንባባ ዛፎች ተውበው ነበር።21የመቅደሱ መቃኖችም አራት ማዕዘን ነበሩ፥ ሁሉም ለእርስ በእርስ ትይዩ ነበሩ። 22ከቅዱሱ ሥፍራ ፊት ለፊት የሚገኘው ከእንጨት የተሰራው መስዋዕት ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ወርዱም ሁለት ክንድ ነበር። ማዕዘኖቹም እግሩም አገዳዎቹም ከእንጨት ተሠርተው ነበር። ሰውዬውም ፥ "ይህች በእግዚአብሔር ፊት ያለችው ገበታ ናት" አለኝ። 23ለተቀደሰው ስፍራና ለቅድስተ ቅዱሳኑ ሁለት መዝጊያዎች ነበሩአቸው። 24ለእያንዳንዱ መዝጊያም ሁለት ተዘዋዋሪ ሳንቃዎች ነበሩት ለአንዱ መዝጊያ ሁለት ለሌላውም መዝጊያ ሁለት ሳንቃዎች ነበሩት።25ግንቦቹን እንዳስዋቡት ዓይነት በእነዚህ በቅዱስ ስፍራው መዝጊያዎች ላይ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸው ነበር፣ በስተ ውጭም ባለው በደጀ ሰላሙ ፊት የእንጨት ጣራ ነበረ። 26በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ ጠባብ መስኮቶችና የተቀረጹ የዘንባባ ዛፎች ነበሩበት። እነዚህም የመቅደሱም ጓዳዎች ነበሩ ፥ እነርሱም ተንጠልጣይ ጣሪያዎችም ነበሯቸው።
1በመቀጠልም ሰውዬው በውጭ በሰሜን አቅጣጫ ወደሚገኘው አደባባይ አወጣኝ፥ በልዩውም ስፍራ አንጻርና በሰሜን በኩል ባለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳሉ ክፍሎች አመጣኝ ። 2ክፍሎቹም በፊት ለፊት ገጽታቸው መቶ ክንድ ስፋታቸውም አምሳ ክንድ ነበረ። 3ከእነዚህ ክፍሎች አንዳንዶቹ ፊታቸው ወደ ግቢው ወስጥ ነበር ከቤተመቅደሱም ሃያ ክንድ ይርቁ ነበር። ባለ ሶስት ደርብ ክፍሎችም ነበሩ። ከላይ ያለው ክፍል ወደታችኛው ክፍሎች ይመለከትና ለእነርሱ ክፍት ነበር መላለፊያ መንገድም ነበረው። የተወሰኑት ክፍሎች ወደ ወደውጪኛው አደባባይ ይመለከቱ ነበረ።4ከክፍሎቹም ፊት በስተ ውስጥ ወርዱ አሥር ክንድ ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ መተላለፊያ ነበረ። የክፍሎቹም መዝጊያዎች ወደ ሰሜን ይመለከቱ ነበር። 5ነገር ግን መተላለፊያው ከህንጻው መካከለኛና ከታችኛው ክፍል በላይ ቦታቸውን የያዘ በመሆኑ የላይኞቹ ክፍሎች ትንንሽ ነበሩ። 6በሦስት ደርብ በመስራታቸውና በአደባባዩም እንዳሉት አዕማድ ያሉ፥ አዕማድ ስላልነበሯቸው ላይኞቹ ደርቦች ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ7የውጪው ግንብ ከክፍሎቹና ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ከሚገኘው ክውጭው አደባባይ ትይዩ ይገኛል ፥ ርዝመቱም አምሳ ክንድ ነበረ። 8በውጪኛው አደባባይ ርዝመቱ ሃምሳ ክንድ ሲሆን በመቅደሱ ፊት የነበሩት ክፍሎች ደግሞ ርዝመታቸው መቶ ክንድ ነበረ። 9ከእነዚህም ዕቃ ቤቶች በታች በስተ ምሥራቅ በኩል፥ ከውጭው አደባባይ የሚጀምር መግቢያ ነበረ።10በምስራቅ በኩል የውጭውን አደባባይ ተከትሎ ከቤተመቅደሱ ውስጠኛ አደባባይ ፊት ለፊት ክፍሎች ነበሩ። 11በስተ ፊታቸውም የነበረ መንገድ በርዝመቱና በወርዱ በሰሜን በኩል ከነበሩት ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆን መግቢያዎቻቸውም በቁጥር እኩል ነበሩ። 12በደቡብም በኩል ልክ በሰሜን በኩል እንዳለው ወደ ክፍሎቹ የሚያስገቡ መግቢያዎች አሉ። በውስጥ በኩል ያለው መተላለፊያ ከበላዩ መግቢያ ያለው ሲሆን መተላለፊያው ወደተለያዩ ክፍሎች ያመሩ ነበር። በምስራቅ በኩል ወደ መተላለፊያው አንደኛው ጫፍ የሚያመራ መግቢያ ነበር።13ከዚያም እንዲህም አለኝ፥ "በውጭኛው አደባባይ ፊት ለፊት የሚገኙት የሰሜንና የደቡብ ክፍሎች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ ካህናት ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው የተቀደሱ ክፍሎች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ስለሆን በዚያ የተቀደሰውን ነገር የእህሉን ቍርባን የኃጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያስቀምጣሉ። 14ካህናቱም አንድ ጊዜ ወደዚያ ከገቡ ሲያገለግሉ የሚለብሷቸው ልብሶች ቅዱስ በመሆናቸው ሳያወልቁ ከተቀደሰው ሥፍራ ወደውጭኛው አደባባይ መውጣት የለባቸውም። ስለዚህም ወደ ሕዝቡ ከመጠጋታቸው በፊት ሌላ ልብስ መልበስ አለባቸው።15ውስጠኛውንም ቤት ለክቶ በፈጸመ ጊዜ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በር አወጣኝና ዙሪያውን ሁሉ ለካ።16የምሥራቁን ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 17የሰሜኑንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 18የደቡቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 19ዞረም፥ የምዕራቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።20በአራቱ ወገን ለካው። የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን ይለይ ዘንድ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበረ።
1ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በር አመጣኝ። 2እነሆም፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከምሥራቅ በኩል መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ያለ ነበር፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር ታበራ ነበር።3ያየሁትም ራእይ ከተማይቱን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ እንዳየሁትና በኮበር ወንዝ እንዳየሁት አይነት ራእይ ነበረ- እኔም በግምባሬ ተደፋሁ! 4የእግዚአብሔርም ክብር ወደ ምሥራቅ በሚመለከት በር ወደ መቅደሱ ገባ። 5መንፈሱም አነሣኝ ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አገባኝ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር መቅደሱን ሞልቶት ነበር።6ሰውዬው በአጠገቤ ቆሞ ሳለ ከመቅደሱ ውስጥ የሚናገረኝን ሌላ ሰው ሰማሁ። 7እንዲህም አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ነው፤ ዳግመኛም የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በግልሙትናቸውና በጣዖት ማምለኪያ ቦታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም፡፡ 8ከእንግዲህ ግንብ ብቻ በመካከል በማድርግ የጣዖቶቻቸውን መድረክ በመድረኬ አጠገብ፥ የጣዖቶቻቸውን መቃኖች በመቃኔ አጠገብ በማስቀመጥ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም። በሠሩትም ርኵሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ ስለዚህ በቍጣዬ አጠፋኋቸው።9አሁንም ግልሙትናቸውንና የነገሥታቶቻቸውን ሬሳ ከፊቴ ያርቁ፥ እኔም ለዘላለም በመካከላቸው አድራለሁ!10አንተም የሰው ልጅ፥ ከኃጢአታቸው የተነሣ ያፍሩ ዘንድ ለእስራኤል ቤት ራስህ ልትነግራቸው ይገባል። ስለዚህ የቤቱ ዝርዝር መግለጫ ማሰብ አለባቸው። 11ከሠሩትም ሥራ ሁሉ የተነሣ ቢያፍሩ፥ የቤቱን መልክና ምሳሌውን መውጫውንም መግቢያውንም ሥርዓቱንም ሕጉንም ሁሉ አስታውቃቸው። የቤቱን አሰራርና ሕጉን ሁሉ ይጠብቁ ዘንድ ያደርጉትም ዘንድ በፊታቸው ጻፈው።12የቤቱ ሥርዓት ይህ ነው፡ ከተራራው ራስ ጅምሮ በዙሪያው ያለ ዳርቻ ሁሉ እጅግ የተቀደስ ይሆናል። አስተውል! የቤቱ ሥርዓት ይህ ነው።13የመሠዊያውም ልክ በረጅም ክንድ ይህ ነው፥ ይህም ማለት አንድ ክንድ ከጋት ነው። በመሰዊያው ዙሪያ ያለው አሸንዳ ቁመቱ አንድ ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። የዙሪያው ጠርዝ አንድ ስንዝር ነው። ይህም የመሰዊያው መሠረት ነው። 14በመሬቱም ላይ ካለው አሸንዳ ጀምሮ እስከ ታችኛው የመስዊያው እርከን ድረስ ሁለት ክንድ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። ከመሰዊያው ትንሹ ጠርዝ እስከ ትልቁ ጠርዝ ድረስ አራት ክንድ፥ የሰፊው ጠርዝ ስፋትም አንድ ክንድ ነው።15ለሚቃጠል መስዋዕት የሚያገለግለው በመሰዊያው ላይ ያለው ምድጃ አራት ክንድ ነው፥ በምድጃውም ላይ ጫፋቸው ወደላይ የቆመ ቀንዶች አሉበት። 16ምድጃውም አራት ማዕዘን ሆኖ ርዝመት አሥራ ሁለት ክንድ ወርዱም አሥራ ሁለት ክንድ ነው። 17ጠርዙም በአራቱም ማዕዘን አሥራ አራት ክንድ ወርዱም አሥራ አራት ክንድ ነው፥ በዙሪያውም ያለው ክፈፍ ግማሽ ክንድ ነው። አሽንዳውም ወደምስራቅ ከሚያመለክቱት ደረጃዎቹ ጋር ዙሪያውን አንድ ክንድ ነው።18ቀጥሎም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ ደሙንም ይረጩበት ዘንድ መሰዊያውን በሚሠሩበት ቀን የመሠዊያው ሕግ ይህ ነው። 19ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ከሳዶቅ ዘር ለሚሆኑ ለሌዋውያኑ ካህናት ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦20ከደሙም ትወስዳለህ፥ በአራቱ ቀንዶቹም በእርከኑም በአራቱ ማዕዘን ላይ በዙሪያውም ባለው ክፈፍ ላይ ትረጨዋለህ እንዲሁ ታነጻዋለህ ታስተሰርይለትማለህ። 21ለኃጢአትም መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትወስዳለህ፥ በመቅደሱም ውጭ በተዘጋጀለት ስፍራ ታቃጥለዋለህ።22በሁለተኛውም ቀን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ነውር የሌለበትን አውራ ፍየል ታቀርባለህ፤ ካህናቱም በወይፈኑ ደም እንዳነጹት እንዲሁ መሠዊያውን ያነጹበታል። 23ማንጻቱንም ከፈጸምህ በኋላ ነውር የሌለበትን ወይፈንና ከመንጋው የወጣውን ነውር የሌለበትን አውራ በግ ታቀርባለህ። 24በእግዚአብሔርም ፊት ታቀርባቸዋለህ፥ ካህናቱም ጨው ይጨምሩባቸዋል፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር ያቀርቡአቸዋል።25ለሰባት ቀንም በየዕለቱ ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ ፍየልን ታቀርባለህ፥ ካህናቱም ነውርም የሌለባቸውን አንድ ወይፈን ከመንጋውም የወጣውን አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ። 26ሰባት ቀን ለመሠዊያው ያስተሰርያሉ ያነጹትማል፥ እንዲሁም ይቀድሱታል። 27እነዚህ ቀኖችንም መፈጸም አለባቸው፥ በስምንተኛውም ቀን ከዚያም በኋላ ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን የደኅንነትንም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
1ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር እንደገና አመጣኝ በሩም በጣም ተዘግቶ ነበር። 2እግዚአብሔርም፥ "ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ማንም አይገባበትም፥ በጥብቅ የተዘጋውም ለዚህ ነው 3የእስራኤል አለቃ በውስጡ ተቀምጦ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላል። በበሩ ደጀ ሰላም መንገድ ይገባል በዚያም መንገድ ይወጣል።4ቀጥሎም ከቤቱ ፊት ለፊት በሰሜኑ በር በኩል አመጣኝ። እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶት ነበር፥ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ። 5እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ ልብ አድርግ ሁሉ በዓይንህም ተመልከት በጆሮህም ስማ። የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ በል።6ለዓመፀኛው ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፥ "ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ 7እንጀራዬን፥ ስብንና ደምን፥ በምታቀርቡበት ጊዜ በመቅደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴንም ያረክሱ ዘንድ በልባቸውና በሥጋቸው ያልተገረዙትን እንግዶችን ሰዎች አግብታችኋልና፥ እነርሱም በርኵሰታችሁ ሁሉ ላይ ይጨመሩ ዘንድ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና ርኵሰታችሁ ሁሉ ይብቃችሁ።8የተቀደሰውን ሥፍራዬን ኃላፊነት ለሌሎች ሰጣችሁ እንጂ ስለእኔ ያለባችሁን ግዴታ አልተወጣችሁም። 9ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ካሉት ሁሉ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ እንግዳ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ።10ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስራኤልም በሳቱ ጊዜ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋውያን ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ። 11እነርሱ የመቅደሴ በሮች ጠባቂዎች በመቅደሴም ውስጥ አገልጋዮች ናቸው። ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን ያርዳሉ፥ ያገለግሉአቸውም ዘንድ በፊታቸው ይቆማሉ። 12ነገር ግን በጣዖቶቻቸውም ፊት መስዋዕት በማቅረባቸው ለእስራኤልም ቤት የኃጢአት ዕንቅፋት ሆነዋል። ስለዚህ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ ብዬ እጄን አንስቼ ምያለሁ ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!13ካህናትም ይሆኑኝ ዘንድ ወደ እኔ አይቀርቡም፥ ወደ ተቀደሰውም ነገሬና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ነገር አይቀርቡም እፍረታቸውንና የሠሩትንም ርኵሰታቸውን ይሸከማሉ። 14ነገር ግን ለአገልግሎቱ ሁሉና በእርሱ ውስጥ ለሚደረገው ሁሉ የቤቱ ሥርዓት ጠባቂዎች አደርጋቸዋለሁ።15ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ከእኔ በራቁ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዓት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ ስቡንና ደሙንም ወደ እኔ ያቀርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 16ወደ መቅደሴም ይገባሉ ያገለግሉኝም ዘንድ ወደ ገበታዬ ይቀርባሉ ሥርዓቴንም ይጠብቃሉ።17ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በርና ወደ ቤቱ ውስጥ የሱፍ ልብስ ለብሰው መግባት የለባቸውም። 18በራሳቸው ላይ የተልባ እግር መጠምጠሚያ ይሁን፥ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን የሚያልብ ልብስ መልበስ የለባቸውም።19ወደ ውጭውም አደባባይ ወደ ሕዝብ ሲወጡ ሲያገለግሉ ለብሰውት የነበረውን ልብስ ማውለቅ አለባቸው፤ በተቀደሰ ልብሳቸው ነክተው ሕዝቡንም እንዳይቀድሱ አውልቀው በተቀደሰውም ክፍል ውስጥ ያስቀምጡት።20ራሳቸውንም አይላጩ የራሳቸውንም ጠጕር ይከርከሙ እንጂ ጠጕራቸውን አያሳድጉ። 21ካህናቱም ሁሉ በውስጠኛው አደባባይ ሲገቡ የወይን ጠጅ አይጠጡ። 22መበለቲቱንና የተፈታችይቱን አያግቡ ነገር ግን ከእስራኤል ቤት ዘር ድንግሊቱን ወይም የካህን ሚስት የነበረችይቱን መበለት ብቻ ያግቡ።23በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ያለውን ልዩነት ለሕዝቤ ያስተምራሉ፥ ንጹሁን ንጹሕ ካልሆነው መለየት እንዲችሉ ያደርጓቸዋል። 24ክርክርም በሚያጋጥም ጊዜ በህጌ መሰረት ይፍረዱ፤ ፍትሀዊ መሆን አለባቸው። በበዓላቴ ሁሉ ሕጌንና ሥርዓቴን ይጠብቁ፥ ሰንበታቴንም ይቀድሱ።25እንዳይረክሱም የአባት ወይም የእናት ወይም የወንድ ልጅ ወይም የሴት ልጅ ወይም የወንድም ወይም ከወንድ ጋር ያሌተኛች እኅት ካልሆን በስተቀር ወደ ሰው ሬሳ አይቅረቡ፤ ያለዚያ ይረክሳሉ። 26ካህን ከርከሰ ህዝቡ ሰባት ቀን ይቈጠርለት። 27በመቅደስም ውስጥ ያገለግል ዘንድ ወደ ውስጠኛው አደባባይ ወደ መቅደሱ ከመግባቱ በፊት፥ የኃጢአትን መሥዋዕት ለራሱ ያቅርብ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦28ይህም ርስት ይሆንላቸዋል፡ እኔ ርስታቸው እሆንላቸዋለሁ! ስለዚህ በእስራኤል ዘንድ ግዛት አትሰጡአቸው እኔ ግዛታቸው ነኝ። 29የእህሉን ቍርባንና የኃጢአትን መሥዋዕት የበደልንም መሥዋዕት ይበላሉ በእስራኤልም ለእግዚአብሔር የተለየው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።30ከበኵራቱ ሁሉ የተሻለው ከየዓይነቱ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፥ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የዱቄታችሁን በኵራት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ። 31ካህናቱ የሞተ ወይም በአውሬ የተሰበረ ፥ ወፍ ወይም እንስሳ ቢሆን፥ አይበሉም።
1ርስትም አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ለእግዚአብሔር መባ ታቀርባላችሁ። ይህም መባ የምድሪቱ የተቀደሰ ሥፍራ ሲሆን ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል በዳርቻው ሁሉ ዙሪያውን የተቀደሰ ይሆናል። 2ከእርሱም ርዝመቱ አምስት መቶ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ አራት ማዕዘን የሆነ ቦታ ለመቅደሱ ይሆናል በዙሪያውም ባዶ ስፍራ የሚሆን አምሳ ክንድ ይሆናል።3ከዚያ ቦታ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም አሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ትለካለህ፤ እርሱም ቅዱስ ስፍራና ቅድስተ ቅዱሳን ይሆንልሀል። 4ከምድሪቱም እግዚአብሔርን ለሚያገለግሉና ሊያገለግሉትም ወደ እግዚአብሔር ለሚቀርቡት ለካህናት የተለየ ክፍል ይሆናል። ለቤቶቻቸውም የሚሆን ስፍራ ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል። 5ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገልጋዮች ለሌዋውያን ይሆናል፥ ለሚቀመጡባቸውም ከተሞች ለራሳቸውም የርስት ይዞታ ይሆናል።6ለከተማ የሚሆን ሥፍራም ከተቀደሰው የዕጣ ክፍል አጠገብ ወርዱ አምስት ሺህ ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ የሆነውን ስፍራ ትለያላችሁ። ይህም ከተማ ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል። 7ለአለቃ ይዞታ የሆነው የዕጣ ክፍል በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ አጠገብ በዚህና በዚያ ይሆናል። በምዕራብና በምሥራቅ ይሆናል። ርዝመቱም እንደ አንድ ነገድ ዕጣ ክፍል ሆኖ ከምድሩ ከምዕራቡ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ዳርቻ ድረስ ይሆናል።8ይህም ለእስራኤል አለቃ ይዞታ ይሆንለታል። አለቆቼም ለእስራኤል ቤት ምድሪቱን እንደ ነገዳቸው መጠን ይሰጡአቸዋል እንጂ ሕዝቤን ከእንግዲህ ወዲህ አያስጨንቋቸውም።9ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል አለቆች ሆይ፥ ይብቃችሁ ግፍንና ብዝበዛን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ! ሕዝቤን መቀማት አቁሙ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር! 10እውነተኛ ሚዛን እውነተኛም የኢፍ መስፈሪያ እውነተኛውም የባዶስ መስፈሪያ ይሁንላችሁ። 11የኢፍና የባዶስ መስፈሪያ መጠናቸው እኩል ሆኖ የባዶስ መስፈሪያ የቆሮስ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ ይሆናል ፥ መስፈሪያው እንደ ቆሮስ መስፈሪያ ይሁን። 12ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ይሁን ሀያ ሰቅል፥ ሀያ አምስት ሰቅል፥ አሥራ አምስት ሰቅል፥ ምናን ይሁንላችሁ።13የምታቀርቡት መባ ይህ ነው ከአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ስድስተኛ፥ ከአንድም ቆሮስ መስፈሪያ ገብስ የኢፍ መስፈሪያ አንድ ስድስተኛ ትሰጣላችሁ። 14የዘይቱም ደንብ፥ ከእያንዳንዱ የቆሮስ መስፈሪያ የባዶስን አንድ አሥረኛ ወይም ለእያንዳንዱ ቆሮስ ምክንያቱም አሥር የባዶስ መስፈሪያ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ነው። 15ውኃም ካለበት ከእስራኤል አውራጃ ከመንጋው ከሁለቱ መቶ አንዱን የበግ ጠቦት ትሰጣላችሁ ይህ ያስተሰርይላችሁ ዘንድ ለእህል ቍርባንና ለሚቃጠል መሥዋዕት ለደኅንነትም መሥዋዕት ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦16የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ይህን መባ ለእስራኤል አለቃ ይሰጣሉ። 17በየበዓላቱም በየመባቻውም በየሰንበታቱም በእስራኤልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የመጠጡንም ቍርባን በየመደቡ ማዘጋጀት የአለቃው ይሆናል። እርሱ የእስራኤል ቤት ወክሎ የኃጢአቱን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርባል።18ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ ስለ መቅደሱም የኃጢአት መስዋዕት ታቀርባላችሁ። 19ካህኑም ከኃጢአቱ መሥዋዕት ደም ወስዶ በመቅደሱ መቃኖችና በመሠዊያው እርከን በአራቱ ማዕዘን በውስጠኛውም አደባባይ በበሩ መቃኖች ላይ ይርጨው.20ይህንንም ከወሩ በሰባተኛው ቀን ስለ ሳተውና ስላላወቀው ታደርጋለህ። በዚህ መንገድ ለቤተ መቅድሱ ታስተስርያላችሁ።21በመጀመሪያ ወር ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታደርጋላችሁ። የሰባት ቀንም በዓል ይሆናል። የቂጣ እንጀራም ትበላላችሁ። 22በዚያም ቀን አለቃው ለራሱና ለአገሩ ሕዝብ ሁሉ የኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ያቀርባል።23በበዓሉም በሰባቱ ቀኖች የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርብ፡ ሰባቱንም ቀኖች በየዕለቱ ነውር የሌለባቸውን ሰባት ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ያቅርብ ለኃጢአትም መሥዋዕት በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቅርብ። 24ለአንድም ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአንድም አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአንድም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ለእህል ቍርባን ያቅርብ።25አለቃው በሰባተኛውም ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን በበዓሉ ሰባት ቀኖች፥ የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የእህሉንም ቍርባን ከዘይቱ ጋር እንዲሁ ያቅርብ።
1ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ሥራ በሚሠራበት በስድስቱ ቀን ተዘግቶ ይቈይ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በመባቻ ቀን ይከፈት። 2አለቃውም በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገድ ገብቶ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት እስኪያቀርርቡ ድረስ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም። ከዚያም በበሩ መድረክ ላይ ሰግዶ ይውጣ ፥ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ።3የአገሩም ሕዝብ በዚያ በር መግቢያ በእግዚአብሔር ፊት በሰንበታትና በመባቻ ይስገዱ። 4አለቃውም በሰንበት ቀን ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸው ስድስት የበግ ጠቦቶች ነውርም የሌለበት አንድ አውራ በግ ይሁን 5የእህሉም ቍርባን ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ይሁን፥ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባን የሚቻለውን ያህል ይሁን፥ ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ።6በመባቻም ቀን ከመንጋው መካከል ነውር የሌለበትን አንድ ወይፈን፥ ነውር የሌለባቸውንም ስድስት ጠቦቶችና አንድ አውራ በግ ያቅርብ 7ለወይፈኑም አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለአውራውም በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ለጠቦቶቹም እንደ ተቻለው ያህል፥ የእህል ቁርባን እንዲሁም ለአንዱም የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቁርባን አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ያቅርብ። 8አለቃውም በሚገባበት ጊዜ በበሩ ደጀ ሰላም መንገድ ይግባ በዚያውም ይውጣ።9የአገሩ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ እግዚአብሔር ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የሚገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፥ በደቡብም በር የሚገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ። በፊት ለፊት ይውጣ እንጂ በገባበቱ በር አይመለስ። 10በሚገቡበት ጊዜ አለቃው በመካከላቸው ይግባ በሚወጡበትም ጊዜ ይውጣ።11በበዓላትም የእህሉ ቍርባን ለወይፈኑ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለአውራ በጉ አንድ የኢፍ መስፈሪያ፥ ለጠቦቶቹም እንደሚቻለው ያህል፥ ለኢፍ መስፈሪያም አንድ የኢን መስፈሪያ ዘይት ይሆናል። 12አለቃውም በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም በፈቃዱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን የደኅንነቱን መሥዋዕት፥ ባቀረበ ጊዜ፥ የምሥራቁን በር ይክፈት፥ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርብ ከዚያም በኋላ ይውጣ፥ ከወጣም በኋላ በሩን ይዝጋ።13በየዕለቱም ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት በግ ጠቦት ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ ይህንንም በየማለዳው ታደርጋላችሁ። 14ከእርሱም ጋር እንደ ቋሚ ሥርዓት የእህልን ቍርባን፥ በኢን መስፈሪያ ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ስድስተኛ እጅ መልካም ዱቄትን፥ በየማለዳው ታቀርባላችሁ። 15እንዲሁ ዘወትር ለሚቃጠለው መሥዋዕት ጠቦቱንና የእህሉን ቍርባን ዘይቱንም በየማለዳው ያቅርብ።16ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አለቃው ከልጆቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ የልጁ ውርስ ይሆናል። የልጆቹ ንብረት ውርስ ይሆንላቸዋል። 17ነገር ግን ከባሪያዎቹ ለአንዱ ከርስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነጻነት ዓመት ድረሰ ለእርሱ ይሁን፥ ከዚያም በኋላ ለአለቃው ይመለስ። ርስቱ ግን ለልጆቹ ይሁን። 18አለቃውም ሕዝቡን ከይዞታቸው ያወጣቸው ዘንድ ከርስታቸው በግድ አይውሰድ ሕዝቤ ሁሉ ከይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆች ርስትን ይስጥ።19ከዚያም ሰውዬው ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ለካህናት ወደሚሆን ወደ ተቀደሱ ክፍሎች እነሆም፥ በስትምዕራብ በኩል አንድ ስፍራ ነበረ። 20እርሱም፥ "ካህናቱ ሕዝቡን ለመቀደስ ወደ ውጭው አደባባይ እንዳያወጡ የበደሉን መሥዋዕትና የኃጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፥ የእህሉንም ቍርባን የሚጋግሩበት ስፍራ ይህ ነው አለኝ።21በውጭው አደባባይ አወጣኝ በአደባባይም ወዳለው በአራቱ ማዕዘን በኩል አሳለፈኝ እነሆም፥ በእያንዳንዱ የአደባባዩ ማዕዘን ሌላ አደባባይ እንዳለ አየሁ። 22በአደባባዩ በአራቱ ማዕዘን ርዝመቱ አርባ ክንድ ወርዱም ሠላሳ ክንድ የሆነ አደባባይ ነበረ። በማዕዘኑ ላሉ ለእነዚህ ለአራቱ ስፍራዎች አንድ ልኬቱ እኩል ነበረ። 23በአራቱም ዙሪያ ሁሉ ግንብ ነበረ፥ በግንቡም ሥር በዙሪያው የመቀቀያ ቦታ ነበረ። 24ሰውዬውም፥ "እነዚህ የቤቱ አገልጋዮች የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው ስፍራዎች ናቸው አለኝ።
1ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ እነሆም፥ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና ውኃውም ከመስዊውው በስተቀኝ በኩል ወደ ቤተመቅደሱ ደቡብ አቅጣጫ ይወርድ ነበር። 2በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ በስተ ውጭ ባለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር መራኝ እነሆም፥ ውኃው ከበሩ ምዕራብ ወገን ይፈስስ ነበር።3ሰውዬውም ገመዱን በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃም እስከ ቍርጭምጭሚት ደረሰ። 4ደግሞ አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ጕልበት ደረሰ። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ። 5ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፥ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ።6ሰውዬውም፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን?" አለኝ። አመጣኝም፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ። 7በተመለስሁም ጊዜ፥ እነሆ፥ በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ። 8እርሱም እንዲህ አለኝ፥ "ይህ ውኃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይወጣል ወደ ዓረባም ይወርዳል ወደ ጨው ባሕሩም ወደ መልካም ውሃነቱ ይመልሰዋል።9ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በመጣበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ። ጨዋማ ባህርን መልካም ያደርጋል። ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል። 10የዓይንጋዲ አጥማጆችም በወንዙ ዳር ይቆማሉ በዓይንጋዲ መረብ መዘርጊያ ቦታ ይገኛል። በጨው ባህርም ዓሣዎች እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።11ነገር ግን የጨው ባህር እረግረጉና እቋሪው ሥፍራ ጨው ለመስጠት ጨዋማ እንደ ሆነ ይኖራል እንጂ አይቀየርም። 12በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል። ቅጠሉም አይረግፍም ፍሬውም አይቋረጥም። ውኃውም ከመቅደስ የሚመጣ በመሆኑ ዛፎቹ በየወሩ ፍሬ ያፈራሉ። ፍሬውም ለመብል ቅጠሉም ለመድኃኒት ይሆናል።13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ርስት አድርጋችሁ ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ምድሪቱን የምትከፍሉበት እንደዚህ ነው፡ ለዮሴፍ ሁለት እድል ፈንታ ይሰጠዋል። 14ለአባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ ምዬ ነበርና እናንተ እያንዳንዳችሁ እኩል አድርጋችሁ ትካፈላላችሁ። በዚህም መንገድ ይህች ምድር ርስት ትሆናችኋለች።15የምድሪቱም ድንበር ይህ ነው። በሰሜኑ ወገን ከታላቁ ባሕር ጀምሮ በሔትሎን መንገድ ወደ ጽዳድ መግቢያ 16ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን። 17ስለዚህም ድንበሩ ከባሕሩ በደማስቆ ድንበር ላይ ያለው ሐጸርዔናን ሐማት ድንበር ይሆናል። ይህ የሰሜኑ ድንበር ነው።18የምሥራቁም ድንበር በሐውራን በደማስቆና በገለዓድ በእስራኤልም ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል። ይህም ድንበር እስከ ታማር ድረስ ይሄዳል። 19የደቡቡም ድንበር ከደቡብ ታማር ጀምሮ እስከ ሜርባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብጽ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል። የደቡቡ ድንበር ይህ ነው። 20የምዕራቡም ድንበር ከታላቁ ባሕር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ አንጻር ድረስ ይሆናል። የምዕራቡ ድንበር ይህ ነው።21እንዲሁ ይህችን ምድር እንደ እስራኤል ነገድነታችሁ ለእናንተ ትካፈላላችሁ። 22ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጡ በእናንተም መካከል ልጆችን ለሚወልዱ ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል እንዳሉ እንደአገር ልጆች ላሉ መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ትካፈሉአታላችሁ ። በእስራኤልም ነገዶች መካከል ለርስት ክፍፍል ዕጣ ትጣላላችሁ። 23መጻተኛውም በማናቸውም ነገድ መካከል ቢቀመጥ በዚያ ርስቱን ትሰጡታላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦
1የነገዶችም ስም ይህ ነው። የዳን ነገድ አንድ የዕጣ ክፍል ይወስዳል፡ ድንብሩም በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ በደማስቆም ድንበር ባለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ካለው ከሰሜን ድንበር ይጀምራል። ወርዳቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። 2ከዳንም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለአሴር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 3ከአሴርም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለንፍታሌም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።4ከንፍታሌም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለምናሴ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 5ከምናሴም ደቡብ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለኤፍሬም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 6ከኤፍሬምም ደቡብ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለሮቤል አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 7ከሮቤልም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለይሁዳ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።8ከይሁዳም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለመባ የሆነ የዕጣ ክፍል ይሆናል ወርዱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ከዕጣ ክፍሎች እንደ አንዱ ይሆናል፥ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል። 9ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት መሬት ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ወርዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆናል።10ይዚህም ቅዱስ ስፍራ አገልግሎት ይህ ነው፡ ለካህናቱ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብም በኩል ወርዱ አሥር ሺህ፥ በምሥራቅም በኩል ወርዱ አሥር ሺህ፥ በደቡብም በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ የሆነ ቦታ ይለይላቸዋል። የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይሆናል። 11ይህም የእስራኤል ልጆች በሳቱ ጊዜ፥ ሌዋውያን እንደ ሳቱት ላልሳቱት ሥርዓቴንም ለጠበቁት ከሳዶቅ ልጆች ወገን ለተቀደሱት ካህናት ይሆናል። 12ለእነርሱም የሚሆነው መባ እስከ ሌዋውያን ድንበር የሚደርስ የዚህ የተቀደሰ ሥፍራ ክፍል ነው።13የሌዋውያን መሬት በካህናቱም ድንበር አንጻር ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም አሥር ሺህ የሆነ ዕጣ ይሆናል። የእነኚህ ኩታ ገጠም መሬቶች ጠቅላላ ርዝመት ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል። 14ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ነውና ከእርሱ ምንም አይሸጡም አይለውጡምም፥ የምድሩም በኵራት አይፋለስም።15የቀረው ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ስፋትና አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት ያለው ስፍራ ለከተማይቱ የጋራ ጉዳይ ፥ ለመኖሪያና ለማስማርያም ይሆናል ከተማይቱም በመካከሉ ትሆናለች። 16የከተማይቱም ልኬት ይህ ነው፡ በሰሜን በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በደቡብም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በምሥራቅም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ፥ በምዕራብም በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ይሆናል።17ለከተማይቱም በሰሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደቡብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምሥራቅም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምዕራብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ጥልቀት ያለው ማሰማርያ ይኖራታል። 18ቀሪው የተቀደሰው በተቀደሰው የመሬት መባ ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ አሥር ሺህ ወደ ምዕራብም አሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። ድንበሩም በተቀደሰው የመሬት የተያያዘ ይሆናል። ፍሬውም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል።19ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከተማይቱን የሚያገለግሉ ምድሪቱን ያርሱታል። 20መባው ሁሉ ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ወርዱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል ። በዚህም መንገድ የተቀደሰውን የመሬት መባና የከተማይቱን ይዞታ ታደርጋላችሁ።21በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ሥፍራ ለአለቃው ይሆናል። በምስራቅ በኩል ያለው የአለቃው ኩታ ገጠም መሬት ከተቀደሰው የመሬት መባ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል ደግሞ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወደ ምዕራቡ ድንበር ይዘልቃል። የተቀደሰውም የመሬት መባውና የቤተ መቅደሱ የተቀደሰ ስፍራ በመካከል ይሆናል። 22የአለቃውም ይዞታው ከሌዋውያን ርስትና ክከተማይቱ ይዞታ መካከል ይሆናል፤ በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበርም መካከል ይሆናል።23ለቀሩትም ነገዶች ድርሻቸው ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። የብንያም ነገድ አንድ የዕጣ ክፍል ይቀበላል። 24ከብንያምም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለስምዖን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 25ከስምዖንም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለይሳኮር አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 26ከይሳኮርም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለዛብሎን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።27ከዛብሎንም ደቡባዊ ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለጋድ አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል። 28ከጋድም ድንበር ቀጥሎ በደቡብ በኩል ድንበሩ ከታማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብጽ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ይሆናል። 29ርስት አድርጋችሁ ለእስራኤል ነገዶች በዕጣ የምታካፍሉአት ምድር ይህች ናት፥ ይህም ርስታቸው ይሆናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።30የከተማይቱም መውጫዎች እነዚህ ናቸው፡ በሰሜን ወገን ልኩ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ነው። 31የከተማይቱ በሮች ሦስት ሲሆኑ እንደ እስራኤል ነገዶች ስም በሰሜን በኩል አንዱ የሮቤል በር አንዱም የይሁዳ በር አንዱም የሌዊ በር ይሆናሉ። 32በምሥራቁም ወገን አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ በሚረዝመው ሥፍራ፥ ሦስትም በሮች አሉ፡ አንዱ የዮሴፍ በር አንዱም የብንያም በር አንዱም የዳን በር ይሆናሉ።33በምስራቅ ወገን አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ በሚረዝመው ሥፍራ፥ ሦስት በሮች አሉ፡ አንዱ የስምዖን ፥አንዱ የይሳኮር፥ እና አንዱም የዛብሎን በር ናቸው። 34በምዕራቡም ወገን ልኬቱ አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ሲሆን፥ በዚያ ሦስት በሮች አሉ፡ አንዱ የጋድ፥ አንዱም የአሴር፥ ሌላውም የንፍታሌም በር ናቸው። 35የከተማይቱ ዙሪያም አሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማይቱ ስም "እግዚአብሔር በዚያ አለ" ተብሎ ይጠራል።
1በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በሦሥተኛው ዓመት፥አቅርቦቶቿን ሁሉ ለማስቆም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ከበባትም። 2ጌታም ለናቡከደነፆር በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአቄም ላይ ድል ሰጠው፥እርሱም ከእግዚአብሔር ቤት የተቀድሱ ዕቃዎች ጥቂቱን ሰጠው። እርሱም ወደ ባቢሎን ምድር፥ ወደ አምላኩ ቤት አመጣቸው፥የተቀደሱትንም ዕቃዎች በአምላኩ ግምጃ ቤት ውስጥ አኖራቸው።3ንጉሡም ዋና አለቃውን አስፋኔዝን፥ ከነገሥታቱና ከመሳፍንቱ ቤተስብ የሆኑትን፥ ከእስራኤል ሰዎች አንዳንዶችን፦ 4ነውር የሌለባቸውን ወጣት ወንድች፥ መልከ መልካሞችን፥ ጥበበኞችን፥ በዕውቀትና በማስተዋል የተሞሉትንና በንጉሡ ቤት ለማገልገል ብቁዎች የሆኑትን እን ዲያመጣ ተናገረው። የባቢሎናውያንን ሥነ ጽሑፍና ቋንቋ እንዲያስተምራቸው ተናገረው። 5ንጉሡ ከምግቡና ከሚጠጣው ወይን በየዕለቱ ድርሻ መደበላቸው። እነዚህ ወጣት ወንዶች ለሦሥት ዓመት መሠልጠንና ከዚያ በኋላ ንጉሡን ማገልገል ይጠበቅባቸዋል።6ከእነዚህም መካከል አንዳንድ የይሁዳ ሰዎች፥ ዳንኤል፥ አናንያ፥ ሚሳኤልና አዛሪያ ነበሩ። 7ዋና አለቃውም ስም አወጣላቸው፦ ዳንኤልን ብልጣሶር፥ አናንያን ሲድራቅ፥ ሚሳኤልን ሚሳቅ፥ አዛሪያንም አብድናጎ ብሎ ጠራቸው።8ነገር ግን ዳንኤል በንጉሡ ምግብና በሚጠጣውም ወይን ራሱን እንዳያረክስ በውስጡ አሰበ። ራሱን እንዳያረክስ ከዋናው አለቃ ፈቃድ ጠየቀ። 9ዋና አለቃው ለእርሱ ባለው አክብሮት አማካይነት እግዚአብሔር ለዳንኤል ሞገስንና ጸጋን ሰጠው። 10ዋና አለቃውም ዳንኤልን አለው፥ «እኔ ጌታዬን ንጉሥን እፈራለሁ። ምን ዓይነት ምግብና መጥጥ ማግኘት እንዳለባችሁ አዞኛል። በእናንተ እድሜ ካሉ ወጣቶች ይልቅ ከስታችሁ ስለ ምን ይመለከታል? ንጉሡ ከእናንተ የተነሳ በሞት ይቀጣኝ ይሆናል።»11ዳንኤልም ዋናው አለቃ በዳንኤል፥በአናንያ፥በሚሳኤልና በአዛሪያ ላይ ለሾመው መጋቢ ተናገረ። 12እርሱም አለ፥«እባክህ፥እኛን አገልጋዮችህን ለአሥር ቀናት ፈትነን። የምንመገብው ጥቂት አትክልትና የምንጠጣው ውኃ ብቻ ስጠን። 13ከዚያም የእኛን ፊት የንጉሡን ምግብ ከሚመገቡ ወጣቶች ጋር አስተያይ፥ባየኽውም መሠረት በአገልጋዮችህ ላይ አድርግ።»14መጋቢውም ይህን ለማድረግ ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ለአሥር ቀናትም ፈተናቸው። 15ከአሥርም ቀን በኋላ የንጉሡን መብል ከተመገቡ ወጣቶች ይልቅ ጤነኞችና የተሻለ የተመገቡ ሆነው ታዩ። 16ስለዚህ መጋቢው የተመደበላቸውን የተመረጠ ምግብና ወይን አስቀርቶ አትክልት ብቻ ሰጣቸው።17ለእነዚህ አራት ወጣቶች፥ እግዚአብሔር በሁሉም ሥነ ጽሑፍና በጥበብ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፥ ዳንኤልም ሁሉንም ዐይነት ራዕይና ሕልም መረዳት ይችል ነበር። 18እንዲያስገቡአቸው ንጉሡ የመደበው ጊዜ እንዳበቃ፥ዋናው አለቃ በናቡከደነፆር ፊት አቀረባቸው።19ንጉሡም ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ፥አብረዋቸው ከነበሩት ሁሉ መካከል ከዳንኤል፥ሐናንያ፥ ሚሳኤልና አዛርያ ጋር የሚወዳድር ማንም አልነበረም። በንጉሡ ፊት ቆሙ፥ ሊያገለግሉት ዝግጁዎች ነበሩ። 20ንጉሡ በጠየቃቸው የጥበብና የማስተዋል ጥያቄዎች ሁሉ፥በግዛቱ ሁሉ ከሚገኙ አስማተኞችና ሙታን ሳቢዎች አሥር እጥፍ በልጠው ተገኙ። 21ዳንኤልም እስከ ንጉሥ ቂሮስ የመጀመሪያ ዓመት ድረስ እዚያው ነበረ።
1ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አለመ፤ አእምሮው ታወከ፥ ሊተኛም አልቻለም። 2ከዚያም አስማተኞችና ሙታን ሳቢዎች እንዲመጡ አዘዘ፤ ጠንቋዮችንና ጠቢባንን ደግሞ ጠራ፤ ስለ ሕልሙ እንዲነግሩት ፈለጋቸው፤ ስለዚህ ገቡና በንጉሡ ፊት ቆሙ።3ንጉሡ አላቸው፥«ሕልም አልሜአልሁ፥ሕልሙም ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ አእምሮዬ ተጨንቋል።» 4ከዚያም ጠቢባኑ በአረማይክ፥ «ንጉሥ ሆይ ለዘላለም ንገሥ! ሕልሙን ለእኛ ለባሪያዎችህ ተናገር፥ እኛም ፍቺውን እናስታውቅሃለን» ብለው ለንጉሡ ተናገሩ።5ንጉሡም ለጠቢባኑ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፥«ሕልሙን ካልገለጣችሁልኝና ካልተረጎማችሁት፥ ሰውነታችሁ እንዲቆራረጥና ቤታችሁም የቆሻሻ ክምር እንዲሆን ወስኜአለሁ። 6ነገር ግን ሕልሙንና ትርጉሙን ከነገራችሁኝ፥ ከእኔ ዘንድ ሥጦታ፥ ሽልማትና ታላቅ ክብር ትቀበላላችሁ። ስለዚህ ሕልሙንና ትርጉሙን ንገሩኝ።»7እነርሱም እንደገና እንዲህ ሲሉ መለሱ፥ «ንጉሡ ሕልሙን ለአገልጋዮቹ ይንገር፥ እኛም ትርጉሙን እንነግርሃለን።» 8ንጉሡም መለሰላቸው፥ «ይህን ጉዳይ በተመለከተ ውሳኔዬ ምን ያህል ጽኑ እንደሆነ ስላወቃችሁ ተጨማሪ ጊዜ ማግኘት እንደምትፈልጉ በእርግጥ አውቃለሁ። 9ነገር ግን ሕልሙን ባትነግሩኝ፥ ሁላችሁን አንድ ቅጣት ይጠብቃችኋል። ሐሰት የሆኑ አሳች አሳቦችን ለማዘጋጅት ወስናችኋል፥ አሳቤንም እስክለውጥ ድረስ ልትነግሩኝ በአንድነት ተስማምታችኋል። ስለዚህ ሕልሙን ንገሩኝ፥ ያን ጊዜም ልትተረጉሙልኝ እንደምትችሉ አውቃለሁ።»10ጠቢባኑም ለንጉሡ እንዲህ ሲሉ መለሱ፥«የንጉሡን ጥያቄ ሊመልስ የሚችል ሰው በምድር አይገኝም። አስማተኞችን፥ ሙታን ሳቢዎችን ወይም ጠቢባንን እንዲህ ዓይነት ጥያቄ የጠየቀ ታላቅና ኃያል ንጉሥ የለም። 11ንጉሡ የሚጠይቀው ነገር አስቸጋሪ ነው፥ በሰዎች መካከል ከማይኖሩት አማልክት በስተቀር ይህንን ለንጉሡ መንገር የሚችል ማንም የለም።12ይህም ንጉሡን አስቆጣው እጅግም አበሳጨው፥ በባቢሎንም በጥበባቸው የሚታወቁትን ሁሉ እንዲያጠፉአቸው አዘዘ። 13ስለዚህም አዋጁ ወጣ፤ በጥበባቸው የሚታወቁት ሁሉ ሊገድሉ ሆነ፥ ዳንኤልንና ጓደኞቹንም ሊገድሉአቸው ፈለጉአቸው።14በዚያን ጊዜ ዳንኤል በባቢሎን በጥበባቸው የሚታወቁትን ሁሉ ሊገድል ለመጣው ለንጉሡ የዘበኞች አዛዥ ለአርዮክ በጥንቃቄና በማስተዋል መለሰለት። 15ዳንኤልም «የንጉሡ አዋጅ ለምን አስቸኳይ ሆነ?» ሲል የንጉሡን አዛዥ ጠየቀው፤ አርዮክም የሆነውን ለዳንኤል ነገረው። 16በዚያን ጊዜ ዳንኤል ገባና ትርጉሙን ለንጉሡ የሚያስታውቅበት ቀጠሮ ከንጉሥ እንዲሰጠው ጠየቀ።17በዚያን ጊዜ ዳንኤል ወደ ቤቱ ሄደና የሆነውን ለአናንያ፥ ለሚሳኤልና ለአዛርያ ነገራቸው። 18እርሱም እነርሱም በጥበባቸው ከሚታወቁት ከተቀሩት የባቢሎን ሰዎች ጋር አብረው እንዳይገደሉ፥ ስለዚህ ምሥጢር ከሰማይ አምላክ ምሕረት እንዲለምኑ አጥብቆ ነገራቸው።19በዚያች ሌሊት ምሥጢሩ ለዳንኤል በራዕይ ተገለጠለት። በዚያን ጊዜ ዳንኤል የሰማይን አምላክ አመሰገነ፥ አለም፦20«ጥበብና ኃይል የእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ ይሁን።»21ጊዜዎችንና ወቅቶችን ይለውጣል፤ነገሥታትን ይሽራል በዙፋናቸውም ነገሥታትን ያስቀምጣል። ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል። 22እርሱ በጨለማ ያለውን ያውቃልና ብርሃንም ከእርሱ ጋር ነውና የጠለቁትንና የተሰወሩትን ነገሮች ይገልጣል።23የአባቶቼ አምላክ ስለ ሰጠኽኝ ጥበብና ኃይል አመሰግንሃለሁ፥እባርክሃለሁም። የለመንህን ነገር አስታውቀኽኛል፥ንጉሡን ያሳሰበውን ነገር አስታውቀኽናል።24ከዚህም በኋላ ዳንኤል የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ እንዲገድል ንጉሡ ኃላፊነት ወደ ሰጠው ወደ አርዮክ ሄደ። ሄዶም አለው፦«በባቢሎን የሚገኙትን ጠቢባን አትግድል። ወደ ንጉሡ ይዘኽኝ ግባ እኔም የሕልሙን ትርጉም ለንጉሥ እናገራለሁ።»25ከዚያም አርዮክ በፍጥነት ዳንኤልን ወደ ንጉሡ አስገባና አለ፦«የንጉሡን ሕልም ትርጉም የሚገልጥ ሰው ከይሁዳ ምርኮኞች መካከል አግኝቼአለሁ። 26ንጉሡም (ብልጣሶር ተብሎ የሚጠራውን) ዳንኤልን አለው፦«ያየሁትን ሕልምና ትርጉሙን ልትነግረኝ ትችላለህን?»27ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፦«ንጉሡ የጠየቀው ምሥጢር ጥበብ ባላቸው፥ በሙታን ሳቢዎች፥ በአስማተኞችና በኮከብ ቆጣሪዎችም ሊገለጥ አይችልም። 28ነገር ግን ምሥጢር የሚገልጥ አምላክ በሰማያት ውስጥ አለ፤ ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ! እርሱም በሚመጡት ዘመናት ሊሆን ያለውን አስታውቆሃል። በአልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለህ ያየኽው ሕልምህና የአእምሮህ ራዕዮች እነዚህ ናቸው፦29ንጉሥ ሆይ! በአልጋህ ላይ ሆነህ ሊሆኑ ስላሉ ነገሮች ታስብ ነበር፤ ምሥጢርንም የሚገልጠው ሊሆን ያለውን አስታውቆሃል። 30እኔ ከሌሎች ሰዎች የሚበልጥ ጥበብ ስላለኝ ይህ ምሥጢር አልተገለጠልኝም። ንጉሥ ሆይ! ይህ ምሥጢር ለእኔ የተገለጠው አንተ ትርጉሙን ትረዳ ዘንድና የውስጥ አሳብህንም ታውቅ ዘንድ ነው።31ንጉሥ ሆይ! ትልቅ ምስል አየህ ተመለከትህም። ምስሉም እጅግ ታላቅና አንጸባራቂ ነበር፥ በፊትህም ቆሞ ነበር። ማንጸባረቁም አስፈሪ ነበር። 32የምስሉ ራስ ከወርቅ የተሠራ ነበር። ደረቱና ክንዶቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ። ወገቡና ጭኖቹ ከናስ፥ 33እግሮቹም ከብረት የተሠሩ ነበሩ። መርገጫ እግሮቹ ከፊሉ ከብረት ከፊሉ ከሸክላ የተሠሩ ነበሩ።34የሰው እጆች ሳይነኩት ድንጋይ ሲፈነቀል፥ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትንም የምስሉን መርገጫ እግሮች ሲመታቸውና ሲያደቃቸው ተመለከትህ። 35ከዚያም ብረቱ፥ሸክላው፥ ናሱ፥ ብሩና ወርቁ ወዲያው እንክትክታቸው ወጣ፤ በመከርም ወቅት በአውድማ ላይ እንዳል እብቅ ሆኑ። ነፋሱም ጠርጎ ወሰዳችው ምልክታቸውም አልቀረም። ነገር ግን ምስሉን የመታው ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ ምድርንም ሞላ።36ሕልምህ ይህ ነበር። አሁን ትርጉሙን ለንጉሥ እንናግራለን። 37አንተ ንጉሥ ሆይ! የሰማይ አምላክ መንግስትን፥ ኃይልን፥ብርታትንና ክብርን የሰጠህ የነገሥታት ንጉሥ ነህ። 38የሰው ልጆች የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ በእጅህ ሰጠህ። የምድር እንሰሳትንና የሰማያት ወፎችን በእጅህ ሰጠህ፤ በእነርሱ ሁሉ ላይም ግዢ አደረገህ። አንተ የምስሉ የወርቅ ራስ ነህ።39ከአንተም በኋላ ከአንተ የሚያንስ ሌላ መንግሥት ይነሳል፤ከዚያም በኋላ በምድር ሁሉ ላይ የሚገዛ ሦሥተኛ የናስ መንግሥት ይነሳል።40ብረት ሌሎች ነገሮችን እንደሚሰባብርና ሁሉን ነገር እንደሚያደቅቅ፥እንዲሁ እንደ ብረት ብርቱ የሆነ አራተኛ መንግሥት ይነሳል። እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያደቅቃቸዋል ይፈጫቸዋልም።41እግሮቹና ጣቶቹ በከፊል ከሸክላ በከፊል ከብረት ተሠርተው እንዳየህ እንዲሁ የተከፋፈለ መንግሥት ይሆናል፤ ለስላሳ ሸክላ ከብረት ጋር ተደባልቆ እንዳየህ እንዲሁ የተወሰነ የብረት ብርታት ይኖረዋል። 42የእግሮቹ ጣቶች በከፊል ከብረት በከፊል ከሸክላ ተሠርተው እንዳየህ መንግሥቱ በከፊል ብርቱ በከፊል ደካማ ይሆናል። 43ብረትና ለስላሳ ሸክላ ተደባልቀው እንዳየህ እንዲሁ ሕዝቡም ድብልቅ ይሆናል፤ብረትና ሸክላ እ ንደማይዋሓድ እነርሱም አብረው አይዘልቁም።44በእነዚያ ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋና በሌላ ሕዝብ የማይሸንፍ መንግሥት ያቆማል። ሌሎቹን መንግሥታት ይፈጫቸዋል ፈጽሞም ያጠፋቸዋል፤ እርሱ ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። 45የሰው እጆች ሳይነኩት ድንጋይ ከተራራ ሲፈነቀል እንዳየህ እንዲሁ ነው። እርሱም ብረቱን፥ ናሱን፥ ሸክላውን፥ ብሩንና ወርቁን አደቀቃቸው። ንጉሥ ሆይ! ከዚህ በኋላ ሊሆን ያለውን ታላቁ አምላክ አስታውቆሃል። ሕልሙ እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው።46ንጉሥ ናቡከደነፆርም በዳንኤል ፊት በግንባሩ ተደፋ አከበረውም፤ መሥዋዕትና ዕጣን እንዲይቀርቡለት አዘዘ። 47ንጉሡ ዳንኤልን እንዲህ አለው፦«ይህን ምሥጢር መግለጥ ችለሃልና፥ ምሥጢርን ሁሉ የሚገልጠው አምላክህ በእውነት የአማልክት አምላክ፥ የነገሥታት ጌታ ነው።»48ከዚያም በኋላ ንጉሡ ዳንኤልን እጅግ አከበረው፥ብዙ አስደናቂ ሥጦታዎችንም ሰጠው። በባቢሎን ክፍለ አገር ሁሉ ላይ ገዢ አደረገው። በባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ላይ ዋነኛ አስተዳዳሪ ሆነ። 49ዳንኤልም ለንጉሡ ጥያቄ አቀረበ፥ ንጉሡም ሲድራቅን፥ሚሳቅንና አብድናጎን በባቢሎን ክፍለ አገር ላይ አስተዳዳሪዎች አድርጎ ሾማቸው። ዳንኤል ግን በንጉሡ ቤተ መንግሥት ተቀመጠ።
1ንጉሡ ናቡከደነፆር ርዝመቱ ስድሳ ክንድ ስፋቱ ስድስት ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አሠራ። በባቢሎንም ክፍለ አገር በዱራ ሜዳ አቆመው። 2ከዚያም ናቡከደነፆር አማካሪዎችን፥ የግምጃ ቤት ኃላፊዎችን፥ ዳኞችን፥ የአጥቢያ ፈራጆችንና የክፍላተ አገር ከፍተኛ ባለ ሥልጣናትን ሁሉ ጨምሮ የክፍለ አገር አስተዳዳሪዎች፥ የክልል አስተዳዳሪዎችና የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ላቆመው ምስል ምረቃ እንዲመጡ፥ በአንድ ላይ እንዲሰበሰቡ መልእክት ላከ።3በዚያን ጊዜም አማካሪዎችን፥ የግምጃ ቤት ኋላፊዎችን፥ ዳኞችን፥ የአጥቢያ ፈራጆችንና የክፍላተ አገር ከፍተኛ ባለ ሥልጣናትን ጨምሮ የክፍለ አገር አስተዳዳሪዎች፥ የክልል አስተዳዳሪዎችና የአካባቢ አስተዳዳሪዎች ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ በአንድነት ተሰበሰቡ። በፊቱም ቆሙ። 4ከዚያም አዋጅ ነጋሪ እየጮኽ እንዲህ አለ፡- «አሕዛብ፥ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ የምትናገሩ ሁሉ፥ 5የመለከትና የእንቢልታ፥ የመስንቆና የክራር፥ የበገናና የዋሽንት፥ የዘፈንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ንጉሥ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል ወድቃችሁ እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል።6ማንም የማይወድቅና የማይሰግድ፥ በዚያው ጊዜ በሚንቦገቦገው የእሳት እቶን ውስጥ ይጣላል።» 7ስለዚህም አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመስንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዋሽንቱን፥ የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ አሕዛብ ሁሉ፥ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል ወድቀው ሰገዱ።8በዚህ ጊዜም አንዳንድ ከለዳውያን መጥተው አይሁድን ከሰሱ። 9ለንጉሡ ናቡከደነፆርም እንዲህ አሉ፦ «ንጉሥ ሆይ ለዘላለም ኑር! 10ንጉሥ ሆይ፥አንተ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመስንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዋሽንቱን፥ የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ የሰማ ማንኛውም ሰው ለወርቁ ምስል እንዲውድቅና እንዲሰግድ ትዕዛዝ አውጥተህ ነበር።11ማንም ያልወደቀና ያላመለከ በሚንቦገቦገው የእሳት እቶን ውስጥ ሊጣል ይገባዋል። 12አሁን ግን በባቢሎን ክፍለ አገር ጉዳይ ላይ የሾምካቸው፥ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ የሚባሉ አንዳንድ አይሁድ አሉ። ንጉሥ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች አንተን ከምንም አይቆጥሩም። አማልክትህን አያመልኩም፥ አያገለግሉምም ወይም ላቆምከው የወርቁ ምስል አይሰግዱም።»13በዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በቁጣና በብስጭት ተሞላ፤ ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብድናጎን ወደ እርሱ እንዲያመጡአቸው አዘዘ። ስለዚም እነዚህን ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው። 14ናቡከደነፆርም አላቸው፦«ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ አማልክቴን አለማምለካችሁ ወይም ላቆምኩት የወርቅ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን?15አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን፥የመስንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዋሽንቱን፥ የዘፈኑንም ድምፅ ሁሉ በሰማችሁ ጊዜ ለመውደቅ እና ላሠራሁት ምስል ለመስግድ ዝግጅዎች ከሆናችሁ ሁሉም መልካም ይሆናል። ካላመለካችሁ ግን ወዲያው ወደ ሚንቦገቦገው የእሳት እቶን ትጣላላችሁ። ከእጄስ ሊያድናችሁ የሚችል አምላክ ማነው?»16ሲድራቅ፥ሚሳቅና አብድናጎም ለንጉሡ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦«ናቡከደነፆር ሆይ በዚህ ጉዳይ መልስ ልንሰጥህ አያስፈልገንም። 17መልስ መስጠት የሚገባን ከሆነ፥ የምናገለግለው አምላካችን ከሚንቦገቦገው የእሳት እቶን ሊያድነን ይችላል፥ ንጉሥ ሆይ፥ ከእጅህም ያድነናል። 18ነገር ግን ንጉሥ ሆይ ባያድነን እንኳን፥አማልክትህን እንደማናመልክና ላቆምከውም የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ በአንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።19በዚያን ጊዜ ናቡከደነፆር በቁጣ ተሞላ፤ በሲድራቅ፥ በሚሳቅና በአብድናጎ ላይ ፊቱ ተለወጠባቸው። የእቶኑ እሳት ብዙውን ጊዜ ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ እንዲነድድ አዘዘ። 20ከዚያም ከሠራዊቱ ጥቂት በጣም ብርቱ ሰዎችን፥ ሲድራቅን፥ሚሳቅንና አብድናጎን አሥረው ወደ ሚንቦገቦገው የእቶኑ እሳት እንዲጥሉአችው አዘዘ።21እነርሱም መጎናጸፊያቸውን፥ ቀሚሳቸውን፥ ጥምጥማቸውንና ሌሎች ልብሶቻቸውን እንደ ለበሱ ታስረው ወደ ሚንቦገቦገው የእቶን እሳት ተጣሉ። 22የንጉሡ ትእዛዝ ጥብቅ ስለነበረና የእቶኑ እሳት እጅግ ነዶ ስለነበረ፥ ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብድናጎን የወሰዱአቸውን ሰዎች ነበልባሉ ገደላቸው። 23እነዚህ ሦሥት ሰዎች እንደ ታሰሩ በሚንቦገቦገው የእቶን እሳት ውስጥ ወደቁ።24ከዚያም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ፥ ፈጥኖም ተነሣ። አማካሪዎቹንም፦ «ሦሥት ሰዎችን አስረን እሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?» ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ለንጉሡ፦ «ንጉሥ ሆይ እርግጥ ነው» ብለው መለሱ። 25እርሱም፦ «እኔ ግን ያልታሰሩ አራት ሰዎች በእሳት ውስጥ ሲመላለሱ አያልሁ፥ጉዳትም አላገኛቸውም። የአራተኛው ማንጸባረቅ የአማልክትን ልጅ ይመስላል።» አለ።26ከዚያም ናቡከደነፆር ወደ እሳቱ እቶን በር ቀረቦ፦ «የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ ኑ ውጡ! ወደዚህ ኑ!» ብሎ ተጣራ። በዚያን ጊዜም ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብድናጎ ከእሳቱ ውስጥ ወጡ። 27በአንድነት የተሰበሰቡት የክፍላተ አገር አስተዳዳሪዎች፥ የክልል አስተዳዳሪዎች፥ ሌሎች አስተዳዳሪዎችና የንጉሡ አማካሪዎች እነዚህን ሰዎች ተመለከቱ። እሳቱ ሰውነታቸውን አልጎዳውም፥ የራሳችው ጸጉር አልተቃጠለም፥ መጎናጸፊያቸው አልተጎዳም፥ የእሳቱም ሽታ በላያቸው አልነበረም።28ናቡከደነፆርም እንዲህ አለ፦«መልአኩን የላከውንና ለአገልጋዮቹ መልእክቱን የሰጠውን የሲድራቅን፥የሚሳቅንና የአብድናጎን አምላክ እናመስግን። በእርሱ በመታመን ትእዛዜን ችላ ብለዋል፥ ከአምላካቸውም ሌላ ማንኛውንም ሌላ አምላክ ከማምለክ ወይም ለእርሱ ከመስገድ ይልቅ ሰውነ ታቸውን አሳልፈው መስጠትን መርጠዋል።29ስለዚህ እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና፥በሲድራቅ፥ሚሳቅና አብድናጎ አምላክ ላይ ክፉ የሚናገር ማንኛውም ሕዝብ፥አገር ወይም ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ይቆራረጣሉ፥ቤቶቻቸውም የቆሻሻ ክምር ይሆናሉ ብዬ አዝዤአለሁ። 30ከዚያም ንጉሡ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብድናጎን በባቢሎን አውራጃ ሾማቸው።
1ከንጉሥ ናቡከደነፆር፥በምድር ሁሉ ለሚኖሩ አሕዛብ፥ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ሁሉ፦ «ሰላማችሁ ይብዛ። 2ልዑል አምላክ ስላደረገልኝ ምልክቶችና ድንቆች እነግራችሁ ዘንድ መልካም ሆኖ ታየኝ። 3ምልክቶቹ እንዴት ታላላቅ ናቸው! ድንቆቹም እንዴት ብርቱዎች ናቸው! መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።4እኔ ናቡከደነፆር በቤቴ ደስ ብሎኝ፥ በቤተ መንግሥቴም በብልጽግና ፍሥሐ እያደረግሁ እኖር ነበር። 5ነገር ግን የአስፈራኝን ሕልም አለምሁ፤ ተኝቼም ሳለሁ ያየኋቸው ምስሎችና የአእምሮዬ ራዕዮች አወኩኝ። 6ስለዚህ ሕልሙን ይተረጉሙልኝ ዘንድ የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ በፊቴ እንዲያቀርቧቸው ትእዛዝ አወጣሁ።7በዚያን ጊዜ አስማተኞች፥ሙታን ሳቢዎች፥ጠቢባንና ኮከብ ቆጣሪዎች መጡ፤ ሕልሙንም ነገርኳችው፥ ነገር ግን ሊተረጉሙልኝ አልቻሉም። 8በመጨረሻም፥ እንደ አምላኬ ስም ብልጣሶር ተብሎ የተጠራውና የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ዳንኤል ገባ። ሕልሙን ነገርኩት። 9«የአስማተኞች አለቃ ብልጣሶር ሆይ፦የቅዱሳን አማልክት መንፈስ እንዳለብህና የሚያስችግርህ ምሥጢር እንደሌለ አውቄአልሁና፤ በሕልሜ ምን እንዳየሁና ትርጉሙ ምን እንደሆነ ንገረኝ አልኩት።10በአልጋዬ ላይ ትኝቼ ሳልሁ በአእምሮዬ ያየኋቸው ራዕዮች እነዚህ ነበሩ፦ ተመለከትኩ፥ በምድርም መካከል ዛፍ ነበረ፥ቁመቱም እጅግ ታላቅ ነበረ። 11ዛፉ አደገ፥በረታም። ጫፉ ሰማይ ደረሰ፥ እስከ መላው ዓለም ዳርቻ ድርስም ይታይ ነበረ። 12ቅጠሎቹ ያማሩ፥ ፍሬዎቹም የተት ረፈረፉ ነበሩ፤ ለሁሉ የሚሆን ምግብም በላዩ ነበረበት። የዱር አራዊት ከበታቹ ጥላ አግኝተው ነበር፥ የሰማያት አእዋፍም በቅርንጫፎቹ ይኖሩ ነበር። ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ከእርሱ ይመገቡ ነበር።13በአልጋዬ ላይ ተኝቼ ሳለሁ በአእምሮዬ አየሁ፥ አንድ ቅዱስ መልእክተኛም ከሰማያት ወረደ። 14እርሱም ጮኽ፥ እንዲህም አለ፦ ዛፉንና ቅርንጫፎቹን ቁረጡ፥ ቅጠሎቹን አራግፉ፥ ፍሬውንም በትኑ። አራዊቱ ከሥሩ፥ አእዋፍም ከቅርንጫፎቹ ይሽሹ።15የሥሮቹን ጉቶ፥ በሜዳው ለምለም ሳር መካከል በብረትና በናስ ማሰሪያ እንደታሰረ በመሬት ውስጥ ተውት። በሰማያት ጠል ይረስርስ፥ በምድር ዛፎች መካከል ከአራዊት ጋር ይኑር።16አእምሮው ከሰው አእምሮ ይለወጥ፥ ሰባት ዓመታትም እስኪያልፉ ድረስ የአውሬ አእምሮ ይሰጠው።17በመልእክተኛው በተነገረው አዋጅ ይህ ውሳኔ ሆነ። ልዑሉ በሰዎች መንግሥታት ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለተናቁ እጅግ ትሑታን ለሆኑ ሰዎች እንኳን ሳይቀር፥ ሊያነግሠው ለወደደው ለማንም እንደሚስጥ ሕያዋን ሁሉ ያውቁ ዘንድ ይህ የቅዱሱ ውሳኔ ነው። 18እኔ ንጉሡ ናቡከደነፆር ይህን ሕልም አልሜአለሁ። አሁንም አንተ ብልጣሶር፥ በመንግሥቴ ካሉ ጠቢባን ሰዎች አንዳቸውም ሊተረጉሙልኝ አልቻሉምና ትርጉሙን ንገረኝ። አንተ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ልትተረጉም ትችላለህ።»19በዚያን ጊዜ ብልጣሶር የተባለው ዳንኤል፥ ለትንሽ ጊዜ እጅግ ታወከ፥ ሐሳቡም አስደነገጠው። ንጉሡም አለው፦ «ብልጣሶር ሆይ ሕልሙ ወይም ትርጉሙ አያስደንግጥህ።» ብልጣሶርም እንዲህ ሲል መለስ፥ «ጌታዬ ሆይ፥ ሕልሙ ለሚጠልህ፥ ትርጉሙም ለጠላቶችህ ይሁን።20ያየኽው ዛፍ፥ ያድግ የነበረውና የበረታው፥ ጫፉም ወደ ሰማያት የደረሰው፥ እስከ መላው ዓለም ዳርቻ ድረስ የታየው፥ 21ቅጠሎቹያምሩ የነበሩት፥ ፍሬዎቹም የተትረፈረፉት፥ ስለዚህም ለሁሉ የሚሆን መብል የነበረበት፥ ከበታቹም የምድር አራዊት ጥላ ያገኙበት፥ የሰማያት አእዋፍም ይኖሩበት የነበረ፥ 22ያ ዛፍ፥ እጅግ ኃያል የሆንከው ንጉሥ አንተ ነህ። ታላቅነትህ እስከ ሰማያት፥ ሥልጣንህም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ።23አንተ ንጉሥ ሆይ፥ አንድ ቅዱስ መልእክተኛ ከሰማይ ሲወርድና እንዲህ ሲል አየህ፦«ዛፉን ቁረጡና አጥፉት፥ ነገር ግን የሥሮቹን ጉቶ በሜዳው ለምለም ሣር መካከል በብረትና በናስ ማሰሪያ እንደታሰረ በመሬት ውስጥ ተውት። በሰማያት ጠል ይረስርስ። ሰባት ዓመታት እስኪያልፉ ድረስ ከአራዊት ጋር በሜዳ ይኑር።24ንጉሥ ሆይ ትርጉሙ ይህ ነው። ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ይህ በአንተ ላይ የወጣ የልዑሉ አዋጅ ነው። 25ከሰዎች መካከል ተለይተህ ትባረራለህ፥ በሜዳም ከአራዊት ጋር ትኖራለህ። እንደ በሬ ሣር እንድትበላ ትደረጋለህ፥ በሰማያትም ጠል ትረሰርሳለህ፥ ልዑሉ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እንደሚገዛና እንዚህንም መንግሥታት እርሱ ለወደደው ለማንም ሊሰጣቸው እንደሚችል እስክታውቅ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል።26የዛፉን የሥሩን ጉቶ ይተዉት ዘንድ እንደታዘዘው፥ እንዲሁ ሰማይ እንደሚገዛ ከተማርህ በኋላ መንግሥትህ ይመለስልሃል። 27ስለዚህ ንጉሥ ሆይ ምክሬ በፊትህ ተቀባይነት ያግኝ። ኃጢአት ማድረግህን አቁምና ትክክል የሆንውን ሥራ።28እነዚህ ነገሮች ሁሉ በናቡከደነፆር ላይ ደረሱ።29ከዐሥራ ሁለት ወሮች በኋላ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ሰገነት ላይ ሲመላለስ፣ 30“ይህች ለንግሥናዬ መኖሪያ፣ ለክብሬም ግርማ እንድትሆን የመሠረትኋት ባቢሎን አይደለችምን?” አለ።31ንጉሡ ይህን ገና ተናግሮ ሳይጨርስ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ፣ “መንግሥትህ ከአንተ እንደ ተወሰደ ተነግሮአል፤ 32ከሰዎች ትገለላለህ፤ መኖሪያህ ዱር ውስጥ ከአራዊት ጋር ይሆናል። እንደ በሬ ሣር ትበላለህ። ልዑል በሰዎች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና እርሱ ለፈለገው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ሰባት ዓመታት ያልፉብሃል።”33ይህ ቃል ናቡከደነፆር ላይ የተፈጸመው ወዲያውኑ ነበር፤ ከሰዎች ተገለለ፤ እንደ በሬ ሣር በላ፤ ሰውነቱ ከሰማይ በሚወርድ ጠል ረሰረሰ፤ ጠጉሩ እንደ ንስር ላባ፣ ጥፍሩም እንደ ወፍ ጥፍር ሆነ።34ጊዜው ከተፈጸመ በኋላ እኔ ናቡከደነፆር ዐይኖቼን ወደ ሰማይ አነሣሁ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ። “ልዑልንም ባረክሁት ለዘላለም የሚኖረውን እርሱን አመሰገንሁት አከበርሁት። እርሱ ለዘላለም ይነግሣልና መንግሥቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ዘመን ነው።35የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ኢምንት ይቆጠራሉ፤ በሰማይ ሰራዊትና በምድር ሕዝቦች መካከል የወደደውን ያደርጋል። የሚያስቆመው ወይም የሚከራከረው የለም። “ለምን እንዲህ አደረግህ?” የሚለውም የለም።36አእምሮዬ እንደ ተመለሰልኝ ወዲያውኑ ከመንግሥቴ ክብር ግርማዊነቴና ሞገስ ተመለሰልኝ። አማካሪዎቼና ሹማምንቴ ፈለጉኝ። ወደ ዙፋኔ ተመለስሁ፤ የበለጠ ታላቅነትም ተሰጠኝ። 37እኔ ናቡከደነፆር አሁን የሰማይን ንጉሥ እባርካለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። ሥራዎቹ ትክክል መንገዶችም ጽድቅ ናቸው። በትዕቢታቸው የሚራመዱትን ያዋርዳል።
1ንጉሥ ቤልሻዛር በሺህ ለሚቆጠሩ መኳንንቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፣ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር። 2ቤልሻዘር የወይን ጠጅ እየጠጣ ሳለ፣ አባቱ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ያመጣቸውን የወርቅና የብር መጠጫዎችን እርሱና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ይጠጡባቸው ዘንድ እንዲያመጡለት አዘዘ።3አገልጋዮቹም እነዚያን ከኢየሩሳሌም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተወሰዱትን የወርቅ ዕቃዎች አመጡ፤ ንጉሡና መኳንንቱ፣ ሚስቶቹና ቁባቶቹም ጠጡባቸው። 4የወይን ጠጁንም እየጠጡ የወርቅና የብር፣ የናስ፣ የብረት፣ የዕንጨትና የድንጋይ አማልክቶቻቸውን አመሰገኑ።5በዚያን ቅጽበት የሰው እጅ ጣቶች ታዩ፤ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በመቅረዙ ትይዩ ባለው በግድግዳው ልስን ላይ ጻፉ፤ ንጉሡም ይጽፍ የነበረውን እጅ አየ፤ 6በዚያን ጊዜ የንጉሡ ፊት ተለዋወጠ በድንጋጤም ተሞላ፤ እጆቹና እግሮቹ ከዱት፤ ጉልበቶቹም ተብረከረኩ።7ንጉሡም ድምፁን ከፍ አድርጎ አስማተኞችን፣ ኮከብ ቆጣሪዎችንና መተተኞችን እንዲያስገቡለት አዘዘ፤ ለባቢሎናውያኑ ጠቢባን ንጉሡ እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ጽሕፈት አንብቦ ትርጉሙን የሚነግረኝን ሐምራዊ መጎናጸፊያ አለብሰዋለሁ፤ የወርቅ ሐብልም በዐንገቱ አጠልቅለታለሁ፤ በመንግሥቴም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕረግ ይይዛል።”8ከዚያም የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፤ ነገር ግን ጽሕፈቱን ሊያነብም ሆነ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ለንጉሡ ሊነግር የሚችል ማንም አልነበረም። 9ንጉሥ ቤልሻዘር ፈራ ፊቱም እጅግ ተለወጠ፤ መኳንንቱም ግራ ግብቶአቸው ተደናገጡ።10ንግሥቲቱም የንጉሡንና የመኳንንቱን ድምፅ ሰምታ ወደ ግብዣው አዳራሽ ገባች፤ እንዲህም አለች፤ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፣ አትደንግጥ፣ ፊትህም አይለዋወጥ11በመንግሥትህ ውስጥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት አንድ ሰው አለ፤ ይህ ሰው በአባትህ ዘመን እንደ አማልክት ጥበብና ማስተዋል ዕውቀትም የሞላበት ሆኖ ተገኝቶአል፤ አባትህ ንጉሥ ናቡከደነፆርም የጠንቋዮች፣ የአስማተኞች፣ የኮከብ ቆጣሪዎችና የመተተኞች አለቃ አደረገው። 12ንጉሡ ብልጣሶር ብሎ የጠራው ይህ ዳንኤል መልካም መንፈስ፥ ዕውቀትና ማስተዋል ያለው ሆኖ ተገኘ፤ ሕልምን የመተርጎም፣ እንቆቅልሽን የመፍታትና የተሰወረውን የመግለጥ ልዩ ችሎታም ነበረው። ስለዚህ ዳንኤልን አስጠራ፣ እርሱም የጽሕፈቱን ትርጉም ይነግርሃል።”13ዳንኤልንም ወደ ንጉሥ አቀረቡት፤ ንጉሡም እንዲህ አለው፤ “ንጉሡ አባቴ ከይሁዳ ማርኮ ካመጣቸው መካከል አንዱ የሆንኸው ዳንኤል አንተ ነህን? 14የአማልክት መንፈስ በውስጥህ እንዳለ፣ ዕውቀት፣ ማስተዋልና ልዩ ጥበብ እንዳለህ ሰምቻለሁ፤15ይህን ጽሕፈት አንብበው ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይነግሩኝ ዘንድ ጠቢባንና አስማተኞች በፊቴ ቀርበው ነበር፣ ነገር ግን ሊገልጡት አልቻሉም። 16አንተ ግን መተርጎምና አስቸጋሪ የሆነውን ነገር መፍታት እንደምትችል ሰምቻለሁ። ይህን ጽሕፈት አንብበ ትርጉሙን ብትነግረኝ፣ ሐምራዊ መጎናጸፊያ ያለብሱሃል፣ የወርቅ ሐብል በዓንገትህ ያጠልቁልሃል፣ በመንግሥት ሥልጣንም ሦስተኛውን ማዕረግ እንድትይዝ ትደረጋለህ።”17ዳንኤልም ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ስጦታዎችህን ለራስህ አድርግ፤ ሽልማቶችህንም ለሌላ ሰው ስጥ፤ ይሁን እንጂ ጽሕፈቱን ለንጉሡ አነባለሁ፤ ትርጉሙ ምን እንደሆነም እነግረዋለሁ።”18“ንጉሥ ሆይ፤ ልዑል አምላክ ለአባትህ ለናቡከደነፆር ገናናነትንና ታላቅነትን፣ ክብርንና ግርማን ሰጠው። 19ከሰጠው ታላቅ ሥልጣን የተነሣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣ ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችም ሁሉ ተንቀጠቀጡለት ፈሩትም። ንጉሡም ሊገድል የፈለገውን ይገድል፣ ሊያድን የፈለገውን ሊያድን፣ ሊሾም ይፈለገውን ይሾም፣ ሊያዋርድ የፈለገውንም ያዋርድ ነበር።20ነገር ግን ልቡ በትዕቢት በጸናና በእብሪት በተሞላ ጊዜ ከዙፋኑ ተወገደ፤ ክብሩም ተገፈፈ። 21ከሰው መካከል ተሰደደ፤ የእንስሳም አእምሮ ተሰጠው፤ ከዱር አህዮች ጋር ኖረ፤ እንድች በሬም ሣር በላ፤ ልዑል አምላክ በሰዎች መንግሥት ላይ እንደሚገዛና እነርሱምን ለወደደው እንደሚሰጥ እስኪያውቅ ድረስ ሰውነቱ በሰማይ ጠል ረሰረሰ።22“ቤልሻዘር ሆይ፤ አንተ ልጁ ሆነህ ይሁ ሁሉ ብታውቅም፣ ራስህን ዝቅ አላደረግህም፤ 23ይልቁንም በሰማይ አምላክ ላይ በመታበይ ራስህን ከፍ ከፍ አደረግህ፤ የመቅደሱን መጠጫዎች አስመጣህ፤ አንተና መኳንንትህ፣ ሚስቶችህና ቁባቶችህም የወይን ጠጅ ጠጣችሁባቸው፣ ማየት፣ መስማት፣ ማስተዋልም የማይችሉትን የብርና የወርቅ የናስና የብረት፣ የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን አመሰገንህ። ሕይወትህንና መንገድህን ሁሉ በእጁ የያዘውን አምላክ ግን አላከበርህም። 24ስለዚህ እርሱ ጽሕፈቱን ይጻፈውን እጅ ላከ።25የተጻፈውም ጽሕፈት፣ ‘ማኔ፣ ቴቄል፣ ፋሬስ’ ይላል26የቃሉም ትርጉም ይህ ነው፤ ‘ማኔ’ ማለት እግዚአብሔር የመንግሥትህን ዘመን ቆጠረው፣ ወደ ፍጻሜም አደረሰው ማለት ነው።27‘ቴቄል’ ማለት በሚዛን ተመዝነህ ቀለህም ተገኘህ ማለት ነው። 28‘ፋሬስ’ ማለት መንግሥትህ ተከፈለ፣ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ ማለት ነው።”29ከዚህ በኋላ በቤልሻዘር ትእዛዝ ዳንኤልን ሐምራዊ መጎናጸፊያ አለበሱት፣ የወርቅ ሐብል በዐንገቱ ኣይ አጠለቁለት፣ በመንግሥቱም ሥልጣን ሦስተኛውን ማዕረግ እንዲይዝ እንዲያደርጉት በዐዋጅ አዘዘ። 30በዚያኑ ሌሊት የባቢሎናውያን ንጉሥ ቤልሻዘር ተገደለ፤ 31የሥልሳ ሁለት ዓመት ዕድሜ የነበረው ሜዶናዊው ዳርዮስም መንግሥቱን ወሰደ።
1ዳርዮስ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ እንዲገዙ አንድ መቶ ሃያ መሳፍንትን መሾም ፈለገ፤ 2በእነዚህም ላይ ሦስት የበላይ አስተዳዳሪዎችን አደረገ፣ ከእነርሱም አንዱ ዳንኤል ነበረ። ንጉሡ ጉዳት እንዳይደርስበት መሳፍንቱ ተጠሪነታቸው ለሦስቱ የበላይ አስተዳዳሪዎች እንዲሆን ተደረገ። 3ከመሳፍንቱና ከበላይ አስተዳዳሪዎቹ ሁሉ ይልቅ ዳንኤል ልዩ የጥበብ መንፈስ የሞላበት ሆኖ በመገኘቱ፣ ንጉሡ በመላው ግዛቱ ላይ ሊሾመው አሰበ።4በዚህ ምክንያት የበላይ አስተዳዳሪዎቹና መሳፍንቱ ዳንኤል በሚያከናውነው የመንግሥት ሥራ እንከን ለማግኘት ፈለጉ፤ ነገር ግን ዳንኤል ታማኝ ጠንቃቃና በሥራው እንከን የሌለበት ስለነበር በእርሱ ላይ ስህተት ሊያገኙ አልቻሉም። 5እነዚህም ሰዎች፣ “ከአምላኩ ሕግ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ካልሆነ በቀር፣ ይህን ሰው የምንከስበት ምንም ሰበብ አናገኝበትም” አሉ።6ከዚያም የበላይ አስተዳዳሪዎቹና አሳፍንቱ ዕቅድ ካወጡ በኋላ በአንድነት ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ንጉሥ ዳርዮስ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ! 7ንጉሥ ሆይ፤ እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ ሌላ አምላክ መጸለይ እንደሌለበት ንጉሡ ዐዋጅ እንዲያወጣ ትእዛዙም እንዲፈጸም፤ ይህንም የተላለፈ ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል፣ የመንግሥት የበላይ አስተዳዳሪዎች፣ መኳንንት፣ መሳፍንት፣ አማካሪዎችና አገረ-ገዦች ሁሉ በአንድነት ተስማምተዋል፤8ንጉሥ ሆይ፤ ይህን ዐዋጅ አውጣ፤ እንደማይሻረውና እንደማይለወጠው የሜዶንና የፋርስ ሕግ እንዲሆን ትእዛዙን በጽሑፍ አድርገው።” 9ስለዚህ ንጉሡ ዳርዮስ ዐዋጁ ተጽፎ እንዲወጣ አደረገ።10ዳንኤልም ዐዋጁ እንደወጣ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፤ መስኮቶቹን በኢየሩሳሌም አንፃር ተከፍተው ባሉበት በሰገነቱ ቀድሞ ያደርግ እንደነበረው በቀን ሦስት ጊዜ ተንበርክኮ ጸለየ አምላኩንም አመሰገነ። 11ሰዎቹም በአንድ ላይ ሄደው ዳንኤልን ሲጸልይና አምላኩን ሲማጸን አገኙት።12ወደ ንጉሡም ሄደው፤ “ንጉሥ ሆይ፤ በሚቀጥሉት ሠላሳ ቀናት ማንም ሰው ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ወደ ሰውም ሆነ ወደ ማንኛውም አምላክ ቢጸልይ በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ እንደሚጣል ዐዋጅ አውጥተህ አልነበረምን?” ሲሉ እርሱ ስላወጣው ዐዋጅ ጠየቁት። ንጉሡም፤ “ዐዋጁ እንደማይሻረው እንደ ሜዶንና እንደ ፋርስ ሕግ የጸና ነው” ሲል መለሰ።13እርሱም ንጉሡን፤ “ንጉሥ ሆይ፤ ከይሁዳ ምርኮኞች አንዱ የሆነው ዳንኤል፣ አንተም ሆነ በጽሑፍ ያወጣኸውን ዐዋጅ አያከብርም፤ አሁንም በቀን ሦስት ጊዜ ወደ አምላኩ ይጸልያል” አሉት። 14ንጉሡ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ ዳንኤልንም ከዚህ ትእዛዝ የሚያድንበትን መንገድ አሰላሰለ፤ ፀሐይ እስክትጠልቅም ድረስ የተቻለውን ሁሉ አደረገ።15ከዚያም ሰዎቹ በአንድ ላይ ወደ ንጉሡ ቀርበው፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በሜዶንና በፋርስ ሕግ መሠረት፣ አንድ ንጉሥ የጣው ዐዋጅም ሆነ ትእዛዝ ሊለወጥ እንደማይችል ዕወቅ” አሉት።16 ስለዚህ ንጉሡ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም ዳንኤልን አመጡት፤ ወደ አንበሶቹም ጉድጓድ ጣሉት። ንጉሡም ዳንኤልን፣ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ያድንህ” አለው።17ድንጋይ አምጥተው በጉድጓዱ አፍ ላይ ገጠሙበት፤ ንጉሡም በዳንኤል ላይ የተፈጸመው እንዳይለወጥ በራሱ የቀለበት ማሕተምና በመሳፍንቱ ቀለበቶች አተመበት። 18ንጉሡም ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፤ በዚያም ሌሊት ምግብ ሳይበላ፣ የሚያዝናናውም ነገር ሳይቀርብለት ዐደረ፤ እንቅልፍም ከእርሱ ራቀ።19በማለዳም ገና ጎሕ ሲቀድ፣ ንጉሡ ተነሥቶ ወደ አንበሶቹ ጉድጓድ እየተጣደፈ ሄደ። 20ወደ ጉድጓዱም ቀርቦ በሐዘን ድምፅ ዳንኤልን፣ “የሕያው አምላክ አገልጋይ ዳንኤል ሆይ፤ ሁልጊዜ የምታመልከው አምላክህ ከአንበሶቹ ሊያድንህ ችሎአልን?” ብሎ ጠየቀው።21ዳንኤልም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፤ 22ንጉሥ ሆይ፤ በፊቱ ቅን ሆኜ ስለተገኘሁ፣ በአንተም ፊት በደል ስላልተገኘብኝ አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ፤ እነርሱም አልጎዱኝም።”23ንጉሡ እጅግ ተደሰተ፤ ዳንኤልን ከጉድጓድ እንዲያወጡት አዘዘ። ዳንኤል በአምላኩ ታምኖ ነበርና ከጉድጓድ በመጣ ጊዜ፣ አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም።24በንጉሡ ትእዛእ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ተደረገ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶቹ ጉድጓድ ውስጥ ተጣሉ። ወደ ጉድጓዱም መጨረሻ ገና ሳይደርሱ አንበሶቹ ቦጫጩቋቸው፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ። 25ከዚያ በኋላ ንጉሥ ዳርዮስ፣ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሕዝቦች፣ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ሰዎች ሁሉ እንዲህ የሚል መልእክት ጻፈ፤ “ሰላም ይብዛላችሁ!26በማንኛውም የመንግሥቴ ግዛት ሰው ሁሉ፣ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር ይህን ዐዋጅ አውጥቻለሁ። “እርሱ ለዘላለም የሚኖር ሕያው አምላክ ነውና መንግሥቱም አይጠፋም፤ ለግዛቱም መጨረሻ የለውም 27እርሱ ይታደጋል፣ ያድናልም በሰማይና በምድር ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋል ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ አድኖታል።28ስለዚህ ዳንኤል በዳርዮስ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ ዘመነ መንግሥት ሁሉ ኑሮው ተሳካለት።
1የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዘር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልም አለመ፤ ራእይም አየ፤ የሕልሙንም ዋና ሃሳብ ጻፈው። 2ዳንኤል እንዲህ አለ፤ “ኣቱ የሰማይ ነፋሳት ታላቁን ባሕር ሲያናውጡት ሌሊት በራእይ አየሁ፤ 3እርስ በርሳቸው የማይመሳሰሉ አራት ታላላቅ አራዊት ከባሕሩ ወጡ።4የመጀመሪያው አንበሳ ይመስል ነበር፤ የንስርም ክንፎች ነበሩት፤ ክንፎቹ እስኪነቃቀሉ ድረስ ትመለከትሁ፤ እንደ ሰው በሁለት እግር እንዲቆም ከመድር ከፍ ከፍ ተደረገ፤ ሰብዓዊ አእምሮ ተሰጠው። 5እነሆም ሁለተኛው አውሬ ድብ ይመስል ነበር፤ በአንድ ጎኑ ከፍ ብሎአል፤ በአፉ ውስጥ በጥርሶቹ መካከል ሦስት የጎድን አጥንቶች ነበርት። እርሱም፤ “ተነሥ እስክትጠግብ ድረስ ሥጋ ብላ” ተባለ።6ከዚህ በኋላ ተመለክትሁ፤ በፊቱ በኩል ነብር የሚመስል ሌላ አውሬ ነበር፤ በጀርባውም በኩል የወፍ ክንፍ የሚመስሉ አራት ክንፎች ነበርት፤ ይህ አውሬ አራት ራስ ነበረው፤ ለመግዛትም ሥልጣን ተሰጠው። 7ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኃይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከእርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፤ አሥር ቀንዶች ነበሩት።8 ስለ ቀንዶቹ ሳስብ ሳለሁ፣ ከመካከላቸው አንድ ሌላ ትንሽ ዘንድ ብቅ ሲል አየሁ፤ ከመጀመሪያዎቹ ቀንዶች ሦስቱ ከፊቱ ተነቃቀሉ፤ ይህም ቀንድ የሰው ዐይኖችን የሚመስሉ ዐይኖች፣ በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበረው።9እኔም ስመለከት፣ ዙፋኖች ተዘረጉ፣ ጥንታዌ ጥንቱም ተቀመጠ፣ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፣ የሩስም ጠጉር እንደ ጥጥ ነጭ ነበረ፣ ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኩራኩሮቹም ሁሉ እንደሚነድ እሳት ነበር፥10 የእሳት ወንዝ ከፊት ለፊት ፈልቆ ይፈስ ነበር ሺህ ጊዜ ሺዎች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍ በፊቱ ቆመዋል፤ የፍርድ ጉባዔ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ።11ቀንዱም ከሚናገረው የትዕቢት ቃል የተነሣ፣ መመልከቴን ቀጠልሁ፣ አውሬው እስኪታረድና እካሉድቆ ወደሚንበለበለው እሳት እስኪጣል ድረስ ማየቴን አላቋርጥሁም። 12ሌሎቹም አራዊት ሥልጣናቸው ተገፎ ነበር፤ ነገር ግን ለተወሰነ ጊዜና ወቅት በሕይወት እንዲኖሩ ተፈቀደላቸው።13ሌሊት ባየሁት ራእይ የሰውን ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመና ጋር ሲመጣ አየሁ፤ ወደ ጥንታዌ ጥንቱ መጣ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። 14ሥልጣን፣ ክብርና ታላቅ ኃይል ተሰጠው፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፤ መንግሥታትና ሕዝቦች ሰገዱለት፤ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው።15እኔ ዳንኤል በመንፈሴ ታወክሁ፤ ያየሁትንም ራእይ እጅግ አስጨነቀኝ። 16በዚያ ከቆሙት ወደ አንዱ ቀርቤ የዚህ ሁሉ ትርጕም ምን እንደ ሆነ ጠየቅሁት።17“አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ መንግሥታት ናቸው፤ 18ነገር ግን የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፣ ለዘላለምም ይይዙታል።19ከዚያም የሚያደቅቀውንና የሚበላውን የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ የሚረጋግጠውን የብረት ጥርሶችና የናስ ጥፍሮች የነበሩትን ከሌሎች የተለየና እጅግ አስፈሪ የሆነውን የአራተኛውን አውሬ ምንነት የበለጠ ማወቅ ፈለግሁ። 20ደግሞም በራሱ ላይ ስላሉት አሥር ቀንዶች፣ ከመካከላቸው ብቅ ስላለው ቀንድና ከዚሁ ቀንድ ፊት ስለተነቃቀሉት ሦስት ቀንዶች፣ እንደዚሁም ከሌሎች ስለበለጠው የሰው ዓይኖች የሚመስሉ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ስለነበሩት ስለዚሁ ቀንድ ማወቅ ፈለግሁ።21እየተመለክትኩም ሳለሁ ይህ ቀንድ በቅዱሳን ላይ ጦርነት ዐውጆ አሸነፋቸው። 22ይህም የሆነው ጥንታዌ ጥንቱ እስኪመጣና ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪፈርድላቸው ድረስ ነበር፤ ኪዝያም የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን የሚወርሱበት ዘመን መጣ።23እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “አራተኛው አውሬ በምድር ላይ የሚነሣ አራተኛው መንግት ነው። ከሌሎች መንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፤ መላውንም ምድር እየረገጠና እያደቀቀ ይበላል። 24ዐሥሩ ቀንዶች ከዚህ መንግሥት የሚወጡ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከዚያም በኋላ ከእነርሱ የተለየ ሌላ ንጉሥ ይነሣል፤ ሦስቱንም ነገሥታት ያንበረክካል።25በልዑል ላይ የዓመፅ ቃል ይናገራል፤ የልዑልንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ ለበዓላት የተመደበውን ጊዜና ሕግን ለመለወጥ ይሞክራል፤ እነዚህም ነገሮች ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘመን እኩሌታም ለእርሱ ዐልፈው ይሰጣሉ። 26ነገር ግን የፍርድ ዙፋን ይዘረጋል፤ ሥልጣኑም ይወሰድበታል፤ ፈጽሞ ለዘላለም ይደመሰሳል።27ከዚያም ከሰማይ በታች ያሉ መንግሥታት ልዕልና፣ ሥልጣንና ታላቅነት ለልዑሉ ሕዝብ ለቅዱሳን ይሰጣል። መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ይሆናል፤ ገዦች ሁሉ ያመልኩታል ይታዘዙታልም። 28የነገሩ ፍጻሜ ይህ ነው፤ እኔም ዳንኤል በሃሳቤ እጅግ ተጨነቅሁ፤ መልኬም ተለወጠ፤ ይሁን እንጂ ነገሩን በልቤ ጠበቅሁት።
1ንጉሥ ቤልሻዘር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት አስቀድሞ ከተገለጠልን ራእይ በኋላ እኔ ዳንኤል ሌላ ራእይ አየሁ። 2በራእዩም በኤሳም አውራጃ በሱሳ ግንብ ራሴን አየሁት፤ በራእዩም በኡባል የውሃ መውረጃ አጠገብነበርሁ፤3ዓይኔን አንስቼ ስመለከት እነሆ፣ ሁለት ቀንዶች ያሉት አውራ በግ በወንቁ አጠገብ ቆሞ አየሁ፤ ቀንዶቹም ረጃጅሞች ነበር፤ ከቀንዶቹም አንዱ ከሌላው ይረዝማል፤ ረጅሙ ቀንድ የበቀለው ዘግይቶ ቢሆንም ከአጭሩ ይልቅ በርዝመቱ የላቀ ነበር። 4አውራ በጉም ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ በቀንዱ ሲጎሽም አየሁ። ምንም ዐይነት እንስሳ ሊቋቋመው አልቻለም፤ ከእጁም ሊያድን የሚችል አልነበረም፤ የፈለገውን ሁሉ አደረገ፤ ታላቅም ሆነ።5ስለዚህ ነገር እያሰብሁ ሳለሁ፣ በዐይኖቹ መካከል ትልቅ ቀንድ ያለው አውራ ፍየል፣ መሬት ሳይነካ ምድርን ሁሉ እያቋረጠ በድንገት ከምዕራብ መጣ፤ 6በወንዙ አጠገብ ቆሞ ወዳየሁት፣ ሁለት ቀንድ ወዳለው አውራ በግ ተንደርዶ መጣበት፤ በታላቅ ቁጣም መታው።7እየወጋውና ሁለቱን ቀንዶቹን እየሰበረ፣ በጭካኔ አውራውን በግ ሲጎዳው አየሁ፤ አውራ በጉም ለመቋቋም ጉልበት አልነበረውም። ፍየሉ በምድር ላይ ጥሎ ረገጠው፤ አውራ ብጉንም ከፍየሉ እጅ ለማዳን የሚችል አልነበረም። 8ፍየሉም ታላቅ ሆነ፤ ነገር ግን በኃይሉ በበረታ ጊዜ፣ ትልቁ ቀንዱ ተሰበረ፤ በቦታውም ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት የሚያመለክቱ አራት ታላላቅ ቀንዶች በቀሉ።9ከእነዚህም ቀንዶች መካከል በአንዱ ላይ አንድ ትንሽ ቀንድ በቀለ፤ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ተከበረችው የእስራኤል ምድር በኃይል አደገ። 10ከሰማይ ሠራዊት ጋር ጦርነት እስኪገጥም ድረስ አደገ፤ ከሰማይና ከክዋክብት ሠራዊት የተወሰኑትን ወደ ምድር ጣለ፣ ረጋገጣቸውም።11ከሰማይ ሠራዊት አለቃ ጋር እስኪተካከል ድረስ ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፤ የልዑሉንም የዘወትር መሥዋዕት ወሰደበት፤ የመቅደሱንም ስፍራ አረከሰ። 12ከዐመፅ የተነሳም የቅዱሳን ሠራዊት ለፍየሉ ቀንድ አልፎ ተሰጠ፤ የሚቃጠል መሥዋዕቱም እንዲቆም ተደረገ። እውነትን ወደ ምድር ይጥላል የሚያደርገውም ሁሉ ይከናወንለታል።13ከቅዱሳኑም አንዱ ሲናገር ሰማሁ፤ ሌላውም ቅዱስ እንዲህ አለው፤ “ስለ ዘወትሩ መሥዋዕት፣ ለጥፋት ምክንያት ስለሆነው ዐመፅ፣ ከእግር በታች እንዲረገጡ ዐልፈው ስለሚሰቱት መቅደስና ሠራዊት የታየው ራእይ የሚፈጸመው መቼ ነው?” 14እርሱም፣ “እስከ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ምሽቶችና ማለዳዎች ድረስ ይቆያል፤ ከዚያም መቅደሱ እንደገና ይነጻል” አለኝ።15እኔ ዳንኤል ራእዩን ስመለከትና ሳስተውል ሳለ፣ ሰውን የሚመስል ከፊት ለፊቴ ቆመ፤ 16ከኡባልም፣ “ገብርኤል ሆይ፤ ለዚህ ሰው የራእዩን ትርጕም ንገረው” ብሎ የሚጮህ የሰው ድምፅ ሰማሁ። 17እኔ ወደቆምሁበት እየቀረበ ሲመጣ፣ ደንግጬ በግንባሬ ተደፋሁ፣ እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ራእዩ ስለ ዘመኑ ፍጻሜ እንደሆነ አስተውል” አለኝ።18እየተናገረኝ ሳለ፣ በምድር ላይ በግንባሬ ተደፋሁ፤ በከባድ እንቅልፍም ተዋጥሁ፣ እርሱ ግን ዳሰሰኝና በእግሮቼ አቆመኝ። 19እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ራእዩ በመጨረሻው ዘመን ሊሆን ያለውን የሚያመለክት ስለሆነ፣ በኋላ በቁጣው ዘመን ምን እንደሚሆን እነግርሃለሁ።20ያየኸው ሁለት ቀንዶች የነበሩት አውራ በግ፣ የሜዶንና የፋርስን መንግሥታት ያመለክታል። 21ተባዕቱ ፍየል የግሪክ ንጉሥ ሲሆን፣ በዐይኖቹም መካከል ያለው ትልቁ ቀንድ የመጀመሪያው ንጉሥ ነው።22የተሰበረውን ቀንድ የተኩት አራቱ ቀንዶቹ፣ ከመንግሥቱ የሚወጡትን አራት መንግሥታትን ያመለክታሉ፣ ነገር ግን ከእርሱ ጋር የሚተካከል ኃይል አይኖራቸውም። 23“በዘመነ መንግሥታቸው በስተ መጨረሻ፣ ዐመፀኞች ፍጹም እየከፉ በሚሄዱበት ጊዜ፣ አስፈሪ ፊት ያለው አታላይ ንጉሥ ይነሣል።24እጅግ ብርቱ ይሆናል፤ ነገር ግን በገዛ ኃይሉ አይደለም። አሠቃቂ ጥፋት ይፈጽማል፤ የሚያደርገው ሁሉ ይከናወንለታል፤ ኃያላን ሰዎችንና ቅዱሳኑን ሕዝብ ያጠፋል። 25እጅግም ተንኮለኛ ስለሆነ በማታለል ይበለጽጋል፤ በልዑላን ልዑልም ላይ ይነሣል፤ ይሁን እንጂ እርሱም ይጠፋል ነገር ግን በሰው ኃይል አይደለም።26የተሰጠህ የምሽቱና የማለዳው ራእይ እውነት ነው፤ ነገር ግን ከብዙ ዘመን በኋላ የሚሆነውን ስለሚያመለክት ራእዩን ዘግተህ አትምበት።”27እኔ ዳንኤል ዐቅሜ ተሟጦ ነበር፤ ለብዙ ቀናት ታመምሁ፣ ተኛሁም። ከዚያም በኋላ ተነሥቼ ወደ ንጉሡ ሥራ ሄድሁ። ባየሁት ራእይ ተደናግጬ ነበር፤ ነገሩም የገባው ማንም አልነበረም።
1የሜዶናዊው የአርጤክስስ ልጅ ዳርዮስ በባቢሎን በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት 2በዘመነ መንግሥቱ በመጀመሪያው ዓመት፣ እኔ ዳንኤል ለነቢዩ ኤርምያስ በተሰጠው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት፣ የኢየሩሳሌም መፈራረስ ሰባ ዓመት እንደሚቆይ ከቅዱሳት መጻሕፍት አስተዋልሁ።3ስለዚህ ማቅ ለብሼ በራሴም ላይ ዐመድ ነስንሼ በጾምና በጸሎት፣ በምልጃም ፊቴን ውደ ጌታ አምላክ አቀናሁ። 4ወደ እምላኬ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፣ ተናዘዝሁም፤ “ከሚወዱህና ትእዛዝህን ከሚፈጽሙ ሁሉ ጋር የፍቅር ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ ታላቅና የተፈራህ አምላክ ጌታ ሆይ፤5እኛ ኃጢአት ሠርተናል፣ በድለናልም፣ ክፋትን አድርገናል፣ ዐምፀናልም፣ ከትእዛዝህና ከሕግህ ዘወር ብለናል። 6ለንጉሦቻችን፣ ለልዑሎቻችንና ለአባቶቻችን እንዲሁም ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በአንተ ስም የተናገሩትን አገልጋዮችህን ነቢያትን አልሰማንም።7“ጌታ ሆይ፤ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን በአንተ ላይ ስለ ሠራነው ታላቅ ክፋት እኛን በበተንህባቸው አገሮች ሁሉ የምንገኝ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምና የመላው እስራኤል ሕዝብ፣ በሩቅም ሆነ በቅርብ ያለን በዚህ ቀን ኀፍረት ተከናንበናል። 8እግዚአብሔር ሆይ፤ እኛና ንጉሦቻችን፣ ልዑሎቻችንና አባቶቻችን በአንተ ላይ ኃጢአት ስለ ሠራን ኀፍረት ተከናንበናል።9ምንም እንኳ በእርሱ ላይ ያመፅን ብንሆን፣ ጌታ አምላካችን ይቅር ባይና መሐሪ ነው። 10እግዚአብሔር አምላካችንን አልታዘዝነውም፤ ደግሞም በአገልጋይቹ በነቢያት በኩል የሰጠንን ሕግ አልጠበቅንም፤ 11መላው እስራኤል አንተን ባለመታዘዝ ሕግህን ተላልፎአል፤ ዘወርም ብሎአል።በአንተ ላይ ላይ ኃጢአትን ስለ ሠራን፣ በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ ሕግ የተጸው መሐላና ርግማን ፈሰሰብን።12ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ በማምጣት፣ የተነገረውን ቃል ፈጸምህብን፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተደረገውን የሚያህል ከሰማይ በታች ከቶ የለም። 13በሙሴም ሕግ እንደ ተጻፈው፤ ይህ ሁሉ ጥፋት በእኛ ላይ ደረሰ፤ ሆኖም ከኃጢአታችን በመመለስና እውነትህን በመከተል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ምሕረትን አልፈለግንም። 14አምላካችን እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ ጻድቅ ነውና፣ በእኛ ላይ እግዚአብሔር ጥፋት ከማምጣት አልተመለሰም፣ እኛም አልታዘዝነውም።15አሁንም ሕዝብህን ከግብፅ ምድር በብርቱ እጅ ያወጣህ፣ እስከዚህም ቀን ድረስ ስምህ እንዲታወቅ ያደረግህ፤ ጌታ አምላካችን ሆይ፤ ኃጢአት ሠርተና፣ አንተንም በድለናል። 16ጌታ ሆይ እንዳደረግኸው የጽድቅ ሥራህ ሁሉ፣ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም፣ ከቅዱሱም ተራራህ ቁጣህን መልስ፣ በእኛ ኃጢአትና በአባቶቻችን በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ህዝብህ በዙሪያችን ባሉት ዘንድ መሣለቂያ ሆነዋል።17አሁንም አምላካችን ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ልመና ስማ። ጌታ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል ፊትህን ወደፈረሰው መቅደስ መልስ። 18አምላክ ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፣ ዐይንህን ገልጠህ መጥፋታችንንና ስምህ የተጠራበትን ከተማ ተመልከት። ልመናችንን የምናቀርበው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን፣ ስለ ታላቅ ምሕረትህ ነው። 19ጌታ ሆይ፣ አድምጥ! ጌታ ሆይ፤ ይቅር በል! ጌታ ሆይ፤ ስማ! አድርግም፤ ስምህ በከተማንህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና አምላኬ ሆይ፣ ስለ ስምህ ስትል አትዘግይ።”20እኔም እየተናገርሁና እየጸለይሁ፣ የራሴንና የሕዝቤን የእስራኤልን ኃጢአት እየተናዘዝሁ፣ ስለ ቅዱስ ተራራውም እግዚአብሔር አምላኬን እየለመንህ 21እየጸለይሁም ሳለሁ፣ በመጀመሪያው ራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል፣ በሠርክ መሥዋዕት ጊዜ በፍጥነት እየበረረ ወደ እኔ መጣ።22እርሱም እንዲህ ብሎ አስረዳኝ፤ “ዳንኤል ሆይ፣ አሁን ጥበብንና ማስተዋልን ልሰጥህ መጥቻለሁ 23አንተ እጅግ የተወደድህ ስለሆንህ፣ ገና መጸለይ ስትጀምር መልስ ተሰጥቶአል፣ አኔም ይህን ልነግርህ መጣሁ። ስለዚህ መልእክቱን ልብ በል፤ ራእዩንም አስተውል።24ዐመፃን ለማስቆም፣ ኃጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተሰረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራእይንና ትንቢትን ለማተምና እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል። 25ይህንን ዕወቅ አስተውለውም፤ ኢየሩሳሌምን ለማደስና ለመጠገን ዐዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ገዢው መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስልሳ ሁለት ሱባዔ ይህናል። ኢየሩሳሌም ከጎዳናዎቿና ከቅጥሮቿ ጋር ትታደሳለች፤ ይህ የሚሆነው ግን በመከራ ጊዜ ነው።26ከሥልሳ ሁለት ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፤ ምንም አይቀረውም። የሚመጣው አለቃ ሰዎችም ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሱን ይመደስሳል። ፍጻሜውም እንደ ጎርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ ጥፋትም ታውጇል።27አለቃው ከብዙዎች ጋር ለአንድ ሱባዔ ቃል ኪዳኑን ያጸናል፤ በሱባዔውም እኩሌታ መሥዋዕትና ቁርባን ማቅረብን ያስቀራል። በርኵሰቱ ጫፍ ላይ ጥፋቱን የሚፈጽመው ይገለጣል። የታወጀው ፍርድ ጥፋትን በሚያመጣው ላይ የሚፈስ ይሆናል።
1 የፋርስ ንጉስ ቂሮስ በነገሰ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ዳንኤል ራዕይ ታየው መልዕክቱ እውነት ነው፤ ስለ ታላቅ ጦርነትም የሚገልፅ ነበር፡፡ መልእክቱንም ይገነዘብ ዘንድ በራዕዩ ማስተዋል ተሰጠው፡፡2በዚያ ጊዜ እኔ ዳንኤል ለሦስት ሳምንት አለቀስኩ፤ 3ሦስቱም ሳምንት እስኪፈፀም ድረስ ጥሩ ምግብ አልበላሁም፤ ስጋም ሆነ የወይን ጠጅ ወደ አፌ አልገባም፤ ቅባትም አልተቀባሁም፡፡4በመጀመሪያው ወር አያ አራተኛው ቀን፤ በታላቁ በጤግሮስ ወንዝ ዳር ቆሜ፤ 5ቀና ብዬ ስመለከት፣ በፊቴ በፍታ የለበሰ እና በወገቡም ላይ ምርጥ የወርቅ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ፡፡ 6አካሉ እንደ እንቁ፣ ፊቱ እንደ መብረቅ፣ ዐይኖቹ እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹ እንደ ጋለ ናስ የሚያብረቀርቁ ድምፁም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበር፡፡7ራዕዩን ያየሁት እኔ ዳንኤል ብቻ ነበርሁ፤ ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች አላዩም፤ ነገር ግን ታላቅ ፍርሃት ስለ ወደቀባቸው ሸሽተው ተደበቁ፡፡ 8ስለዚህ ይህን ታላቅ ራዕይ እያየሁ ብቻዬን ቀረሁ፤ ምንም ጉልበት አልነበረኝም፤ መልኬ እጅጉን ገረጣ፤ ኃይልም አጣሁ፡፡ 9ከዚያም የቃሉን ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉንም ድምፅ በሰማሁ ጊዜ፣ በግንባሬ በምድር ላይ ተደፍቼ በከባዱ እንቅልፍ ተኛሁ፡፡10እነሆም አንድ እጅ ዳሰሰኝ፤ እየተንቀጠቀጥሁም በእጄና በጉልበቴ አቆመኝ፤ 11እርሱም፤ “ እጅግ የተወደድህ ዳንኤል ሁይ፣ አሁን ወደ አንተ ተልኬአለሁና የምነግርህን አስተውል፤ ቀጥ ብለህም ቁም አለኝ፡፡ ይህን ሲለኝም፤ እየተንቀጠቀጥሁ ተነስቼ ቆምሁ፡፡12ደግሞም እንዲ አለኝ፤ “ዳንኤል ሁይ፣ አትፍራ ማስተዋልን ለማግኘትና በአምላክህም ፊት ራስህን ለማዋረድ ከወሰንክበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ቃልህ ተሰምቷል፤ እኔም የቃልህን መልስ ይዤ መጥቻለሁ፡፡ 13ነገር ግን የፋርስ መንግስት አለቃ ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል ሊረዳኝ ወጣ፡፡14ራዕዩ ሊፈፀም ገና ብዙ ዘመን ስለሚቀረው ወደፊት በህዝብህ ላይ የሚሆነውን ልገልፅልህ አሁን ወደአንተ መጥቻለሁ፡፡” 15ይህን እየተናገረኝ ሳለ፣ ፊቴን ወደ ምድር አቀረቀርሁ፣ የምናገረውንም አጣሁ፡፡16ከዛም የሰው ልጅ የሚመስል ከንፈሮቼን ዳሰሰ፣ እኔም አፌን ከፈትኩ፣ መናገርም ጀመርኩ፤ በፊቴ የነበረውንም እንዲህ አልኩት፤ “ ጌታዬ ሆዬ ከራዕዩ የተነሳ ተሰቃይቻለሁ ሃይልም አጣሁ፤ 17ጉልቤቴ ከዳኝ፤ መተንፈስም አቅቶኛል፣ እኔ አገልጋይህ ከአንተ ጋር መነጋገር እንዴት እችላለሁ?”18እንደገናም ሰው የሚመስለው ዳሰሰኝ አበረታኝም፡፡ 19እርሱም፤ “እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ፤ አትፍራ፤ ሰላም ላንተ ይሁን፤ በርታ፤ ፅና” አለኝ፡፡ እየተናገረኝም ሳለ፣ በረታሁና፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አበረትተኸኛልና ተናገር” አልሁት፡፡20እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ለምን ወደ አንተ እንደ መጣሁ ታውቃለህ? የፋርስን መንግሥት ለመውጋት እመለሳለሁ፤ እኔም ስሄድ የግሪክ አለቃ ይመጣል። 21አስቀድሜ ግን በእውነት መጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ ከእነዚህ አለቆች ጋር ለመዋጋት ከአለቃችሁ ከሚካኤል በስተቀር የሚረዳኝ የለም።
1እኔም፣ ሜዶናዊ ዳርዮስ በነገሠ በመጀመሪው ዓመት እርሱን ለማገዝና ለማበርታት በአጠገቡ ቆሜ ነበር፡፡ 2አሁንም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ እነሆ ሦስት ሌሎች ነገስታት በፋርስ ይነሳሉ፤ አልተኛውም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ እጅግ ባለጠጋ ይሆናል፡፡ በባለጠግነቱም እጅግ በበረታ ጊዜ ሌላውን ሁሉ አሳድሞ በግሪክ መንግስት ላይ ያስነሣል፡፡3ከዚያም በታላቅ ኃይል የሚገዛና የወደደውንም ሁሉ የሚያደርግ ሃይል ንጉስ ይነሣል፡፡ 4በኃይሉ እየገነነ ሳለም፣ መንግስቱ ይፈርሳል፤ ወደ አራቱ የሰማይ ነፍሳትም ይከፋፈላል፡፡ መንግስቱ ተወስዶ ለሌሎች ስለሚሰጥ ለዘሩ አይተላለፉም፤ ኃይሉም እንደ መጀመሪያው አይሆንም5የደቡብ ንጉስ ይበረታል፤ ነገር ግን ከጦር አዛዦቹ አንዱ ከእርሱ የበለጠ የበረታ ይሆናል፣ ግዛቱም ታላቅ ይሆናል፡፡ 6ከጥቂት ዓመታት በኋላም አመቺ ጊዜ ሲያገኙ አንድነት ይፈጥራሉ፡፡ የደቡብ ንጉስ ሴት ልጅ ስምምነት ለማድረግ ወደ ሰሜኑ ንጉስ ትሄዳለች፤ ነገር ግን ኃይሏን ይዞ መቆየት አትችልም፤ በእነዚያ ቀናት እርሷ ከቤተ መንግስት አጃቢቿ፣ ከአባቷና ከደጋፊዎቿ ጋር አልፋ ትሰጣለች፡፡7ከዘመዶቿ አንዱ ስፍራዋን ሊይዝ ይነሳል፤ የሰሜኑን ንጉስ ሰራዊት ይወጋል፤ ምሽጎቹንም ጥሶ ይገባል፤ ከእነርሱም ጋር ተዋግቶ ድል ያደርጋል፡፡ 8አማልክታቸውን፤ የብረት ምስሎቻቸውን፣ ከክብርና ከወርቅ የተሰሩ የክብሩ ዕቃዎቻቸውን ይማርካሉ፤ ወደ ግብፅም ይወስዳል፡፡ ለጥቂት ዓመታም ከሰሜኑ ንጉስ ጋር ከመዋጋት ይቆጠባል፡፡ 9የሰሜኑም ንጉስ፣ የደቡቡን ንጉስ ግዛት ይወራል፤ ነገር ግን አፈግፍጎ ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል፡፡10ወንዶች ልጆቹም ለጦርነት ይዘጋጃሉ፤ እስከ ጠላት ምሽግ ደርሶ የሚዋጋና ሊቋቋሙት እንደማይቻል ጎርፍ የሚጠራርግ ታላቅ ሰራዊት ይሰበስባሉ፡፡11ከዚያም የደቡቡ ንጉስ በቁጣ ወጥቶ የሰሜኑን ንጉስ ይወጋል፡፡ የሰሜኑ ንጉስ ታላቅ ሰራዊት ቢያሰባስብም ሰራዊቱ ለደቡብ ንጉስ አልፎ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ 12ሰራዊቱ በሚማረክበት ጊዜ ልቡ በትዕቢት ይሞላል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችንም ይገድላል፤ ነገር ግን በድል አድራጊነቱ አይጸናም፡፡13የሰሜን ንጉስ ከመጀመሪው የሚበልጥ ታላቅ ሰራዊት ያሰባስባል፤ ከብዙ አመታ በኋላ በትጥቅ እጅግ ከተደራጀ ታላቅ ሰራዊት ጋር ተመልሶ ይመጣል፡፡14በዚያም ዘመን ብዙዎች በደቡብ ንጉስ ላይ ይነሣሉ፡፡ ራዕዩ ይፈጸም ዘንድ ከህዝብህ መካከል ዐመፀኛ የሆኑ ሰዎች ይከሣሉ፤ ነገር ግን ተሰነካክለው ይወድቃሉ፡፡15የሰሜኑም ንጉስ መጥቶ የዐፈር ድልድል ይክባል፤ የተመሸገእውንም ከተማ ይይዛል፡፡ የደቡቡ ሰራዊትም ለመቋቋም ኋይል ያጣል፤ የተመረጡት ተዋጊዎቻቸው እንኳ ፀንተው መዋጋት አይችሉም፡፡16ነገር ግን የሰሜኑ ንጉስ በደቡቡ ንጉስ ላይ ደስ ያሰኘውን ያደርጋል፤ ማንም ሊቋቋመው አይችልም፡፡ በመልካሚቱ ምድር ላይ ይገዛል እርሷን ለማይፋትም ኋይል ይኖረዋል፡፡17የሰሜኑ መንግስት ያለውን ሠራዊት ሁሉ ይዞ ለመምጣት ይወስናል፤ ከደቡቡም ንጉስ ጋር ይስማል፣ የደቡቡንም መንግስት ለመጣል ሴት ልጁን ይድርለታል፤ ይሁን እንጂ ዕቅዱ አይሳካለትም፤ ያሰበውም ነገር አይጠቅመውም፡፡ 18ከዚህም በኋላ በባሕር ጠረፍ ወዳሉት አገሮች ፊቱን በመመለስ ብዙዎቹን ይይዛል፤ ነገር ግን አንድ አዛዥ ትዕቢቱን ያከሸፍበታል፤ በራሱም ላይ ይመልስበታል፡፡ 19በገዛ አገሩ ወዳሉት ምሽጎችም ፊቱን ይመልሳል፤ ነገር ግን ተሰናክሎ ይወድቃል፤ ደግሞም አይታይም፡፡20በእርሱ ቦታ የሚተካውም የመንግስቱን ክብር ለማስጠበቅ የሚውል ግብር እንዲከፍል የሚያስገድድ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ በቁጣ ወይም በጦርነት ሳይሆን በጥቂት ዓመታ ውስጥ ይደመሰሳል፡፡ 21በእርሱም ፋንታ የተናቀ ሰው የነግሣል፤ ለእርሱም ሕዝቡ ንጉሳዊ ክር አይሰጡትም፣ በቀስታ ይገባና በተንኮል መንግስቱን ይዛል፡፡ 22ከፊቱ የሚቆመው ሰራዊት እንደ ጎርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል፡፡ ሰራዊቱና የቃል ኪዳኑም አለቃ ሳይቀር ይደመሰሳሉ፡፡23ከእርሱ ጋር ስምምነት ከተደረገ በኋላ የማታለል ስራውን ይሰራል፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር በብርታት እየጨመረ ይሄዳል 24የበለጸጉትን ክፍለ አገሮች በሰላ ሳሉ በድንገት ይወሯቸዋል፤ አባቶቹም ሆኑ አያቶቹ ያላደረጉትን ነገር ያደርጋሉ፤ ብዝበዛውን ምርኮውንና የተገኘውን ሀብት ሁሉ ለተከታዮቹ ያካሏቸዋል፤ ምሽጎችን ለመጣል ያሤራል፤ ይህን የሚያደርገውም ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡25“ታላቅ ሠራዊት አደራጅቶ ኀይሉንና ብርታቱን በደቡብ ንጉስ ላይ ይነሳሳል፤ የደቡብ ንጉሱም ብርቱ የሆነ ኃይል ሰራዊት ይዞ ጦርነትን ያውጃል፤ ከር ግን ከተዶለተበት ሴራ የተነሳ መቋቋም አይእል፣፡፡ 26ከንጉስ ማዕድ አብረውት ሲበሉ የነበሩት፤ ብዙዎቹም በጦርነት ይገደላሉ፡፡ 27አንዳቸው በሌላኛው ላይ ልባቸው ወደ ክፋት ያዘነበለው ሁለት ነገስታት፣ በአንድ ገበታ አብረው ይቀመጣሌ፤ እርስ በእርሳቸውም በከንቱ ውሸት ይነጋገራሉ፤ ምክንያቱም ፍፃሜ የሚሆነው በተወሰነው ጊዜ ነው28የሰሜን ንጉስ ብዙ ሃብት ይዞ ወደ ሀዛ አገሩ ይመለሳ፤ ነገር ግ ልቡ በተቀደሰው ኪዳን ላይ ይነሣሣል፤ የወደደውን ያደርጋል፣ ከዚያም ወደ ገዛ አገሩ ይመለሳል፡፡29በተወሰነው ጊዜ ይመለስና ደቡቡን እንደ ገና ይወርራል፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ውጤቱ ከበፊቱ የተለየ ይሆናል፡፡ 30የኪቲም መርከቦች ይቃወሙታል፤ ልቡም ይሸበራል፡፡ ወደ ኋላም ይመለሳል፤ ቁጣውን በተቀደሰው ኪዳን ላይ ይወርዳል፤ ተመልሶም የተቀደሰውን ኪዳ የተዉትን ይንከባከባል፡፡31የጦ ሠራዊቶቹም ቤተ መቅደሱንና ቅጥሩን ያረክሳሉ፤ የዘውትሩንም መስዋዕት ያስቀራሉ፤ በዚያም ፍፁም ጥፋትን የሚያመጣውን የጥፋት ርኩሰት ይተክላሉ፤ 32ኪዳኑን የሚተላለፉትን በማታለል ይስታል ይረክስባቸዋልም፤ አምላካቸውን የሚያውቁ ሕዝብ ግን ደንተው ይቃወሙታል፤ ርምጃም ይወስዳሉ፡፡33“ለጊዜው በሰይፍ ቢወድቁም፣ ቢቃጠሉም፣ ቢማረኩና ቢዘረፉም፣ ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ብዙዎችን ያስተምራሉ፡፡ 34በሚወድቁበት ጊዜ መጠነኛ ርዳታ ይገኛሉ፤ እውነተኛ ያልሆኑ ብዙ ሰዎችም ይተባበሯቸዋል፡፡ 35ጥበበኛ ከሆኑ ሰዎች አንዳንዶቹ ይሰናከላሉ፣ ይህም እስከ ፍፃሜ ዘመን ድረስ የጠሩ፣ የነጠሩና እንከን የሌለባቸው ይሆን ዘንድ ነው፤ የተወሰነው ጊዜ ገና አልደረሰምና፡፡36ንጉሱ እንዳለው ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ራሱን እጅግ ከፍ በማድረግ በአማልክት አማላክ ላይ አስገራሚ ነገሮችን ይናገራል፤ የቁጣውም ዘመን እስኪፈጸም ይሳካለታል፤ የተወሰነ ነገር ሁሉ መሆን አለበትና። 37ሴቶች ለሚወዱትም ሆነ ለአባቶቹ አምላክ ትክብርን አይሰጥም፤ ማንኛውንም አምላክ አያከብርም፤ ነገር ግን ራሱን ከእነዚህ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል።38በእነርሱም ምትክ የምሽጎችን አምላክ ያደብራል፤ አባቶቹ የማያውቁትን አምላክ በወርቅ፣ በብር፣ በከበሩ ድንጋዮችና በውድ ስጦታዎች ያከብራል። 39በባዕድ አምላክ ርዳታ ጽኑ ምሽቶችን ይወጋል፤ ለእርሱ የሚገዙትን በእጅጉ ያከበራቸዋል፤ በብዙ ሕዝብ ልያ ገዦች ያደርጋቸዋል፤ ምድሩንም በዋጋ ያከፋፍላቸዋል።40“በመጨረሻው ዘመን የደቡብ ንጉሥም ጦርነት ያውጅበታል፤ የሰሜን ንጉሥም በፈረሰኞችና በሰርጎች በብዙ መርከቦችም እንደ ማዕበል ይመጣበታል፤ ብዙ አገሮችን ይወራል፤ እንደ ጎርም እየጠራረገ በመካከላቸው ያልፋል። 41የከበረችውንም ምድር ይወራል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩእስራኤላውያንም ተሰነካክለው ይወድቃሉ፣ ነገር ግን ከኤዶም፣ ከሞዓብ ብዙ ሰዎች እንዲሁም ከአሞን የቀሩት ሕዝብ ከእጁ ያመልጣሉ።42ሥልጣኑን በብዙ አገሮች ላይ ያንሰራፋል ግብፅም አታመልጥ። 43የወርቅና የብር ክምችትን፣ እንዲሁም የግብፅን ሀብት ሁሉ በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል፤ የሊቢያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይገዙታል።44ነገር ግን ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣ ወሬ ያስደነግጠዋል፤ ብዙዎችንም ለማጥፋትና ለመደምሰስ በታላቅ ቁጣ ይወጣል። 45ንጉሣው ድንኳኖቹን በባሕሮች መካከል ውብ በሆነው ቅዱስ ተራራ ላይ ይተክላል፤ ይሁን እንጂ ወደ ፍጻሜው ይመጣል፤ ማንም አይረዳውም።
1በዚያን ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። መንግሥታት ከተመሠረቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የመከራ ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በዚያን ጊዜ ስማቸው በመጽሐፉ ተጾጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ ይድናሉ። 2በምድር አፈር ውስጥ ካንቀላፉት ብዙዎች ይነቃሉ፤ አንዳንዶቹ ለዘላለም ሕይወት፣ ሌሎቹም ለውርደትና ለዘላለም ጉስቁልና ይነሣሉ።3ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ክዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ። 4ዳንኤል ሆይ፣ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ አትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ ዕውቀትም ይበዛል።5እኔም ዳንኤል ተመለከትሁ፤ እነሆ ከፊት ለፊቴ ሌሎች ሁለት ቆመው ነበር፤ አንዱ ከወንዙ በዚህኛው ዳር፣ ሌላው ደግሞ ከወንዙ በዚያኛው ዳር። 6ከእነርሱም አንዱ፣ ከወንዙ በላይ የነበረውንና በፍታ የለበሰውን ሰው፣ እነዚህ አስደናቂ ነገሮች ሊፈጽሙ ምን ያህል ጊዜ ይቀራል?” አለው።7ከወንዙ ውሃ በላይ የነበረው በፍታ የለበሰው ሰው፣ ቀኝ እጁንና ግራ እጁን ወደ ሰማይ አንሥቶ፣ “ለዘመን፣ ለዘመናት፣ ለዘምንም እኩሌታ ማለትም ለሦስት ዓመት ተኩል ይሆናል፤ የተቀደሰው ሕዝብ ኃይል መስበር ሲያከትም፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ይፈጸማሉ” ብሎ ለዘላልም በሚኖረው በእርሱ ሲምል ሰማሁ።8እኔም ሰማሁ፤ ነገር ግን አላስተዋልሁትም፤ ስለዚህ፣ ጌታዬ፣ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ ምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅሁ። 9እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ቃሉ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የተዘጋና የታተመ ስለሆነ ሂድ፤10ብዙዎቹ ይነጻሉ፤ ይጠራሉ እንከን አልባምይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይድናሉ፤ ከክፉዎች አንዳቸውም አያስተውሉም፣ ጠቢባን ግን ያስተውላሉ። 11“የዘወትሩ መሥዋዕት ከተቋረጠበትና ፍጹም ጥፋት የሚያመጣው አስጸያፊ ርኵሰት ከተተከለበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ቀን ይሆናል።12የሚታገሥና እስከ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሰለሳ አምስት ቀን ፍጻሜ የሚደርስ የተባረከ ነው።13“አንተ ግን እስከ ፍጻሜ ድረስ ሂድ፣ ታርፋለህ፤ በቀኖች መጨረሻም ተንሥተህ የተመደበልህን ርስት ትቀበላለህ።”
1በይሁዳ ነገሥታት በዖዚያን፥ በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን፤በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብዔር ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። 2እግዚአብሔር በሆሴዕ አማካይነት መናገር በጀመረ ጊዜ እንዲህ አለው፦«ምድሪቱ እኔን በመተው ታላቅ ምንዝርናን እያደረገች ነውና፥ሂድ፥የምንዝርናዋ ፍሬዎች የሆኑ ልጆች ያሏትን ሴተኛ አዳሪዋን ሚስትህ አድርገህ ውሰድ።»3ስለዚህም ሆሴዕ ሄዶ የዴቤላይምን ሴት ልጅ ጎሜርን አገባ፤እርስዋም ጸነሰች፥ ወንድ ልጅም ወለደችለት። 4እግዚአብሔርም አለው፦ «ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኢይዝራኤል ስለነበረው ደም ማፍሰስ የኢዩን ቤት እቀጣለሁና፥ የቤተ እስራኤልንም መንግሥት እንዲያከትም አደርጋለ ሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው። 5ይህም በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ የእስራኤልን ቀስት በምሰብርበት ቀን ይፈጸማል።»6ጎሜር እንደገና ጸነሰች፥ ሴት ልጅም ወለደች። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ «ቅንጣት ታህል ይቅር እላቸው ዘንድ ከእንግዲህ ወዲያ የእስራኤልን ቤት አልምርምና ስሟን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት። 7ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር አምላካችው በራሴ አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት፥ በሰይፍ፥ በጦርነት፥ በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች አላድናቸውም።»8ጎሜር፥ ሎሩሃማን ጡት ካስጣለቻት በኋላ ጸነሰች፥ሌላ ወንድ ልጅም ወለደች። 9በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦«ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላካችሁ አይደለሁምና ስሙን ሎዓሚ ብለህ ጥራው ።»10ነገር ግን የእስራኤል ቤት ቁጥር ሊለካ ወይም ሊቆጠር እንደማይችል የባሕር አሸዋ ይሆናል። «ሕዝቤ አይደላችሁም» በተባሉበት ቦታ፥«የሕያው አምላክ ሕዝብ ናችሁ» ይባላሉ። 11የይሁዳ ሕዝብና የእስራኤል ሕዝብ በአንድነት ይሰበሰባሉ። የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና፥ ለራሳቸው አንድ መሪ ይሾማሉ፥ ከምድሪቱም ይውጣሉ።
1ወንድሞቻችሁን «ሕዝቤ!»፥ እኅቶቻችሁንም «የተራራላችሁ» በሏቸው።2እርሷ ሚስቴ አይደለችምና እኔም ባሏ አይደለሁምና ከእናታችሁ ጋር ተምዋግቱ፥ ተምዋገቱ። ሴተኛ አዳሪነቷን ከፊቷ፥ምንዝርናዋንም ከጡቶቿ መካከል ታስወግድ። 3አለበለዚያ እርቃንዋን እስክትቀር እገፋታልሁ፥እንደ ተወለደችበትም ቀን እርቃንዋን እገልጣለሁ። እንደ ምድረ በዳ እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፥ተጠምታ እንድትሞት አደርጋለሁ።4የሴተኛ አዳሪነት ልጆች ናቸውና ለልጆቿ ቅንጣት ምሕረት የለኝም። 5ምክንያቱም እናታቸው ሴተኛ አዳሪ ናትና፥ የጸንሰቻቸውም በአሳፋሪ ተግባር ነውና። እርሷም ፦«እንጀራዬንና ውኃዬን፥ሱፌንና ሐሬን፥ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛልና ከውሽሞቼ ኋላ እሄዳለሁ» አለች።6ስለዚህ መንገድዋን በእሾህ ለመዝጋት አጥር እሠራለሁ። መንገድዋንም እንዳታግኝ ቅጥር እገነባባታለሁ። 7ውሽሞችዋን ትከታተላቸዋለች ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች ነገር ግን አታገኛቸውም። ከዚያም በኋላ ፦«አሁን ካለሁበት የበፊቱ ይሻላልና ወደ መጀመሪያው ባሌ እመለሳለሁ» ትላለች።8እህሉን፥አዲሱን ወይን ጠጅና ዘይቱን የሰጠኋት፣ በአልን ያገለገሉበትን ብርና ወርቅ ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንኩ አላወቀችም። 9ስለዚህ እህሏን በመከር ጊዜ፥ አዲሱንም የወይን ጠጄን በወቅቱ መልሼ እወስዳለሁ። እርቃኗንም የምትሸፍንበትን ሱፌንና ሐሬን መልሼ እወስዳለሁ።10ከዚያም ውሽሞችዋ እያዩ እርቃንዋን እስክትቀር ድረስ እገፋታለሁ፥ ከእጄም ማንም አያስጥላትም። 11ሁሉንም ክብረ በዓላቷን፦ የደስታ በዓላቷን፥የአዲስ ጨረቃ ክብረ በዓላቷን፥ ሰንበታቷንና ዓመታዊ በዓላቷን አስቀራለሁ።12«ውሽሞቼ የሰጡኝ ክፍያዎቼ ናቸው» የምትላቸውን ወይንዋንና የበለስ ዛፎችዋን አጠፋለሁ። ጫካ አደርጋቸዋለሁ፥ የዱር አራዊትም ይበሉዋቸዋል። 13ለበአል አማልክት ዕጣን ስላጠነችባቸው፥ በቀለበቶችዋና በጌጣ ጌጦቿ ራስዋን ስላስዋበችባቸው እና እኔን ረስታ ከውሽሞቿ ኋላ ስልሄደችባችው የደስታ በዓላት እቀጣታለሁ።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።14ስለዚህ አመልሳታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳ እወስዳታለሁ፥ በፍቅርም አነጋግራታለሁ። 15የወይን ተክሏን፥ የተስፋ በርም እንዲሆናት የአኮርን ሸለቆ መልሼ እሰጣታለሁ። በዚያም በወጣትነቷ ቀናት፥ ከግብጽ ምድር በወጣችባቸው ቀናት እንዳደረገችው ትመልስልኛለች።16የእግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፦«በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ ከእንግዲህ ወዲያም በአሌ ብለሽ አትጠሪኝም። 17የበአልን አማልክት ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁና ስሞቻቸው ከእንግዲህ ወዲያ አይታሰቡም።18በዚያን ቀን ከዱር አራዊት፥ ከሰማይ አእዋፍና በምድር ከሚንቀሳቀሱት ነገሮች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። ቀስትን፥ ሰይፍንና ጦርነትን ክምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ በሰላምም እንድትጋደሙ አደርጋችኋለሁ።19ለዘላለም ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ። በጽድቅ፥ በፍትሕ፥ በኪዳን ታማኝነትና በምሕረት ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ። 20በታማኝነት ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ። አንቺም እኔን እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።21የእግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፦ በዚያን ቀን እመልሳልሁ። «ለሰማያት እመልሳለሁ፥ እነርሱም ለምድር ይመልሳሉ። 22ምድርም ለእህሉ፥ ለአዲሱ ወይን ጠጅና ለዘይቱ ትመልሳለች፥ እነርሱም ለኢይዝራኤል ይመልሳሉ።23ስለ ራሴ ስል በምድሪቱ ላይ እተክላታልሁ፥ ሎሩሃማንም እምራታለሁ። ሎዓሚንንም፦ አንተ ዓሚ አታህ ነህ እለዋለሁ፤ እነርሱም አንተ አምላካችን ነህ ይሉኛል።»
1እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦«እንደገና ሂድ፥ ባልዋ የሚወዳትን ነገር ግን አመንዝራ የሆነችውን ሴት ውደድ። ወድ ሌሎች አማል ክት ዘወር ቢሉና የዘቢብ እንጎቻ ቢወዱም እንኳን፥ እኔ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደምወድ ውደዳት።» 2ስለዚህ በአሥራ አምስት የብር ሳንቲሞችና በአንድ ቆሮስ ተኩል ገብስ ገዛኋት። 3እኔም፦ «ከእኔ ጋር ብዙ ቀናት ኑሪ፥ ሴተኛ አዳሪ ወይም የሌላ የማንም ሰው አትሁኚ፥እኔም እንዲዚሁ ከአንቺ ጋር እሆናለሁ» አልኳት።4የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ፥ ያለ መስፍን፥ ያለ መሥዋዕት፥ ያለ ድንጋይ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድ ወይም ያለ ቤተሰብ ጣዖት ለብዙ ቀናት ይኖራሉ። 5ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሰዎች ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔር አምላካቸውንና ንጉሣቸውን ዳዊትንም ይፈልጋሉ። በመጨረሻዎቹም ቀናት በእግዚአብሔርና በበረከቱ ፊት እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።
1የእስራኤል ሕዝብ ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። እውነተኛነት፥ ለኪዳን ታማኝነት፥ እግዚአብሔርን ማወቅ በምድሪቱ የለምና እግዚ አብሔር በምድሪቱ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለው። 2መርገም፥ መዋሽት፥ መግደል፥ መስረቅና ማመንዘር በዚያ አለ። ሕዝቡ ስምምነቶችን ሁሉ ያፈርሳሉ፥ ሳያቋርጡ ደም ይፋሰሳሉ።3ስለዚህ ምድሪቱ ደረቀች፥ በእርሷ የሚኖሩ ሁሉ መነመኑ፥ የዱር አራዊትና የሰማይ አእዋፍ፥ የባሕርም ዓሦች እንኳን አለቁ።4ነገር ግን ማንም ሙግቱን አያቅርብ፥ማንም ሌላውን ማንንም አይክሰስ። ምክንያቱም እኔ የምከስው እናንተን ካህናቱን ነውና። 5እናንተ ካህናት በቀን ትሰናከላላችሁ፥ ነቢያቶቹም ከእናንተ ጋር በሌሊት ይሰናከላሉ፥ እናታችሁንም አጠፋታለሁ።6ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል። እናንተ ካህናት ዕውቀትን ጥላችኋልና እኔም እጥላችኋለሁ። እኔ አምላካችሁ ብሆንም ሕጌን ረስታችኋል፥ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ። 7ካህናቱ በበዙ መጠን የሚሠሩብኝ ኃጢአት በዝቶአል። ክብራቸውን ወደ ውርድት እለውጠዋለሁ።8የሕዝቤን ኃጢአት ይመገባሉ፥ ክፋታቸውም እንዲበዛ ይቋምጣሉ። 9በካህናቱ ላይ እንደሚሆን እንዲሁ በሕዝቡም ላይ ይሆናል፦ ስለ ልማዶቻቸው እቀጣቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም አከፍላቸዋለሁ።10ከእኔ ከእግዚአብሔር ርቀው ሄደዋልና ትተውኛልምና፤ይበላሉ ግን አይጠግቡም፥ ያመነዝራሉ ግን አይበዙም።11ሴሰኝነት፥ የወይን ጠጅና አዲስ የወይን ጠጅ ማስተዋላቸውን ወስዶታል። 12የእንጨት ጣዖቶቻችውን ያማክራሉ፥ በትሮቻቸውም ይተነብዩላቸዋል። የሴሰኝነት መንፈስ አስቶአቸዋል፥ እኔን አምላካቸውንም ትተውኛል።13በተራሮች ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፥ ጥላው መልካም ነውና ከባሉጥ፥ ከኮምቦልና ከአሆማ ዛፍ በታች በኮረብቶች ላይ ያጥናሉ። ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰት ይፈጽማሉ፥ የልጆቻችሁ ሚስቶች ያመነዝራሉ። 14ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰትን በወደዱ ጊዜ፥ ወይም የልጆቻችሁ ሚስቶች ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም። ምክንያቱም ወንዶቹ ራሳቸውን ለሴተኛ አዳሪዎች ሰጥተዋልና፥ እንዲሁም ከቤተ ጣዖት ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ርኩሰትን ለመፈጸም መሥዋዕት ይሰዋሉና። ስለዚህ ይህ የማያስተውል ሕዝብ ይጠፋል።15እስራኤል ሆይ አንቺ ብታመነዝሪም፥ ይሁዳ በደለኛ አይሁን። እናንተ ሰዎች፥ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ። ሕያው እግዚአብሔርን ብላችሁም አትማሉ። 16እስራኤል እንደ እልኽኛ ጊደር በእልኽኝነት ሄዳለችና፤ እንዴት እግዚአብሔር በለመለመ መስክ እንዳ ሉ ጠቦቶች ያሰማራታል?17ኤፍሬም ራሱን ከጣዖታት ጋር አጣምሮአል፤ብቻውን ተውት። 18አስካሪ መጠጣቸው ባላቀ ጊዜ እንኳን ማመንዘራቸውን አያቆ ሙም፤ገዢዎቿም ነውራቸውን እጅግ ይወዳሉ። 19ነፋሱ በክንፎቹ ይጠቀልላታል፥ ከመሥዋዕቶቻቸውም የተነሳ ይፍራሉ።
1በእናንተ በሁላችሁ ላይ ፍርድ እየመጣ ነውና፤ ካህናት ሆይ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት ሆይ ልብ በሉ! የንጉሡ ቤት ሆይ ስሙ! እናንተ፥ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል። 2ዓመጸኞች በማረድ እጅግ በርትተዋል፥ ሁሉንም እገራቸዋለሁ።3ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፥ እስራኤልም ከእኔ አልተሰወረችም። ኤፍሬም፥ አንተ አሁን እንደ ሴተኛ አዳሪ ሆነሃል፤ እስራኤልም ረክሳልች። 4ሥራቸው ወደ እኔ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፥ የአመንዝራነት መንፈስ በውስጣቸው አለ፥ እኔን እግዚአብሔርን አላወቁኝም።5የእስራኤል ትዕቢት ይመሰክርባታል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በበደላቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ከእነርሱ ጋር ትሰናከላለች። 6በጎቻቸውንና ከብቶቸውን ይዘው እግዚአብሔርን ፍልጋ ይሄዳሉ፥ ነገር ግን ከእነርሱ ተለይቶ ተመልሷልና አያገኙትም። 7ዲቃሎች ልጆችን ወልደዋልና ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም። አሁንም የወር መባቻ በዓላቱ እነርሱን ከእርሻቸው ጋር ይበሉአቸዋል።8በጊብዓ መለከትን፥በራማም እንቢልታን ንፉ። «ቢንያም ሆይ እንከተልሃለን!» እያላችሁ የጦርነት ድምጽ አሰሙ። 9በቁጣው ቀን ኤፍሬም የፈረሰ ይሆናል። በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ሊሆን ያለውን አውጄአለሁ።10የይሁዳ መሪዎች የድምበር ድንጋይ እንደሚነቅሉት ናቸው። ቁጣዬን በላያቸው እንደ ውኃ አፈስሳለሁ። 11ለጣዖታት ሊሰግድ ወስኖአልና ኤፍሬም ደቀቀ፥ በፍርድ ደቀቀ።12እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፥ለይሁዳም ቤት እንደ ነቀዝ እሆናለሁ። 13ኤፍሬም በሽታውን ባየ ጊዜ፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ፤ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ይሁዳም ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኞችን ላከ። ነገር ግን እርሱ ሊያድናችሁ፥ ቁስላችሁንም ሊፈውስ አልቻለም።14ስለዚህ በኤፍሬም ላይ እንደ አንበሳ፥ በይሁዳም ላይ እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁ። እኔ፥ አዎ እኔ፥ እገነጣጥላለሁ፥ እሄዳለሁ፥ እወስዳቸዋለሁ፥ የሚያድናቸውም ማንም የለም። 15በደላቸውን እስኪያውቁና ፊቴን እስኪፈልጉ ድርስ፥ በመከራቸው አጥብቀው እስኪፈልጉኝ ድረስ፥ እሄዳለሁ፥ ወድ ስፍራዬም እመለሳለሁ።
1ኑ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ። እርሱ ገነጣጥሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ይፈውሰናል፤ እርሱ አቁስሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ቁስላችንን አስሮ ይጠግናል። 2ከሁለት ቀን በኋላ ያበረታናል፥ በሦሥተኛው ቀን ያሥነሣናል፥ እኛም በፊቱ እንኖራለን። 3አወጣጡ እንደ ንጋት የታመነ ነው፤ እንደ ካፊያ፥ ምድሪቱን እንደሚያጠጣ እንደ ጸደይ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።4ኤፍሬም ሆይ ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ ምን ላድርግልህ? ታማኝነታችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በጠዋት እንደሚጠፋ ጤዛ ነው። 5ስለዚህ በነቢያቱ ቆራረጥኋቸው፥ በአፌም ቃል ገደልኋቸው። ፍርዶችህ እንደሚያንጸባርቅ ብርሃን ናቸው።6ታማኝነትን እሻለሁና፥መሥዋዕትንም አይደለም፥ከሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ይልቅ እኔን እግዚአብሔርን ማወቅን እሻለሁ። 7እንደ አዳም ኪዳኑን አፍርሰዋል፤ ለእኔ ያልታመኑ ነበሩ።8ገልዓድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ነው፥ በደም ዱካ ተሞልቷል። 9የቀማኞች ቡድን የሚዘርፉትን አድብተው እንደሚጠባበቁ፥ ካህናቱም በሴኬም መንገድ ላይ ሰው ለመግደል በቡድን ተደራጅተዋል፤ አሳፋሪም ወንጀል ይፈጽማሉ።10በእስራኤል ቤት የሚያሰቅቅ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬም ምንዝርና አለ፥ እስራኤልም ተበክሏል። 11የሕዝቤን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ፥ ይሁዳ ሆይ ለአንተም መከር ተቀጥሮልሃል።
1ማታለልን ይለማመዳሉና እስራኤልን ለመፈወስ በፈለግሁ ጊዜ ሁሉ የኤፍሬም ኃጢአት፥ የሰማሪያም ክፋት ይገለጣል፤ ሌባ ወደ ውስጥ ይገባል፥ የቀማኞች ቡድን በመንገድ ላይ አደጋ ያደርሳል። 2ክፋታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ በልባቸው አይገነዘቡም። ሥራቸው ከቦአቸዋል፥ በፊቴም ናቸው።3በክፋታቸው ንጉሡን፥ በሐሰታቸውም አለቆቹን ደስ ያሰኛሉ። 4የተቦካው ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ እሳቱን መቆስቆስ እንድሚያቆም፥ ጋጋሪ እንደሚያነድበት ምድጃ፥ ሁሉም አመንዝራ ናቸው። 5በንጉሣችን ቀን አለቆች በወይን ጠጅ ትኩሳት ታመሙ። እርሱም ለፌዘኞች እጁን ዘረጋ።6እንደ ምድጃ በሆነ ልባቸው፥ አታላይ እቅዶቻችውን ይወጥናሉ። ቁጣቸው ሌሊቱን ሁሉ ይጤሳል፥ በማለዳም እንደሚንቀለቀል እሳት እጅጉን ይነድዳል። 7ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፥ ግዢዎቻቸውንም ይበላሉ። ነገሥታቶቻቸው ሁሉ ወደቁ፥ ከመካከላቸውም ማንም ወደ እኔ አልተጣራም።8ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቅ፥ ኤፍሬም ያልተገለበጠ ቂጣ ነው። 9እንግዶች ጉልበቱን በሉት፥ እርሱ ግን አላወቀም። ሽበትም ወጣበት፥ እርሱ ግን አላወቀም።10የእስራኤል ትዕቢት ይመሰክርበታል፤ ነገር ግን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም። 11ኤፍሬም ማስተዋል እንደሌላትና ተላላ እንደ ሆነች ርግብ ነው፤ ወደ ግብጽ ይጣራል፥ ወደ አሦርም ይበራል።12ሲሄዱ መሬቤን እዘረጋባቸዋለሁ፥ እንደ ሰማይ አዕዋፍ አወርዳቸዋለሁ። እንደ መንጋ በሚተምሙብት እቀጣቸዋለሁ። 13ወዮ ለእነርሱ! ከእኔ ርቀው ሄደዋልና። ጥፋት ይመጣባቸዋል! በእኔ ላይ አምፀዋል! ላድናቸው ወደድሁ፥ እነርሱ ግን ሐሰትን ተናገሩብኝ።14ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፥ ነገር ግን በአልጋዎቻችው ላይ ያለቅሳሉ። እህልና አዲስ ወይን ጠጅ ለማግኘት ራሳቸውን ለይተዋል፥ ከእኔም ዘወር ብለዋል። 15እኔ ባሠለጠናቸውም፥ ክንዶቻችውንም ባበረታ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን አሴሩብኝ።16ተመልሰዋል፥ ነገር ግን ወደ እኔ ወደ ልዑሉ አልተመለሱም። ዒላማውን እንደ ሳተ ቀስት ናቸው። ከምላሳቸው ነውረኛነት የተነሳ አለቆቻችው በሰይፍ ይወድቃሉ። ይህም በግብጽ ምድር ለመሳለቂያ ይሆንባቸዋል።
1«መለከትን በከንፈሮችህ ላይ አድርግ። በእኔ በእግዚአብሔር ቤት ላይ ንስር እየመጣ ነው። ሕዝቡ ኪዳኔን አፍርሰዋልና በሕጌም ላይ አምጸዋልና ይህ ይሆናል። 2'አምላኬ፥ በእስራኤል ያለን እኛ እናውቅሃለን' እያሉ ወደ እኔ ይጮሃሉ። 3ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ጥሎአል፥ ጠላትም ያሳድደዋል።4ነገሥታትን አነገሡ፥ በእኔ ግን አይደለም። እኔም ሳላውቅ መሳፍንቶችን አደረጉ። በብራቸውና በወርቃቸው ለራሳቸው ጣዖታትን ሠሩ፥ ነገር ግን ለጥፋታቸው ብቻ ነበር።» 5ነቢዩ፦«ሰማርያ ሆይ ጥጃህን ወዲያ ጥሎታል» አለ። እግዚአብሔር፦«ቁጣዬ በዚህ ህዝብ ላይ ነድዶአል። ሳይነጹ እስከ መቼ ይኖራሉ? አለ።6ይህ ጣዖት ከእስራኤል የመጣ ነው፤ ባለሙያ ሠራው፥ እርሱ አምላክ አይደለም! የሰማርያ ጥጃ ይደቅቃል። 7ሕዝቡ ነፋስን ዘርተዋል፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ። ያልተሰበሰበው እህል ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም። ለማፍራት ቢደርስም እንኳን እንግዶች ይበሉታል።8እስራኤል ተውጦአል፤ በአሕዛብም መካከል እንደማይጠቅም ነገር ወድቀዋል። 9ሁሌ ብቻውን እንደሚሆን የዱር አህያ፥ወደ አሦር ሄደዋልና። ኤፍሬም ለራሷ ወዳጆችን ገዛች። 10በአሕዛብ መካከል ወዳጆችን ቢገዙም፥ እኔ እሁን አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ። ከመሳፍንቱ ንጉሥ ጭ ቆና የተነሳም ሊመነምኑ ይጅምራሉ።11ኤፍሬም ለኃጢአት ማስተሰሪያ መሠዊያ ቢያበዛም፥በዚያ ፈንታ ግን የኃጢአት መሥሪያ መሠዊያዎች ሆኑ። 12ሕጌን አሥር ሺህ ጊዜ ያህል ፃፍሁላቸው፥ እነርሱ ግን እንግዳ እንደ ሆነ ነገር ተመለከቱት።13መሥዋዕቴን ይሠዋሉ፤ ሥጋ ይሠዋሉ፥ ይበሉታልም፤ እኔ እግዚአብሔር ግን አልተቀበልኳቸውም። አሁን ክፋታቸውን አስባለሁ፥ ኃጢአታቸውንም እቀጣለሁ። ወደ ግብጽ ይመለሳሉ። 14እስራኤል፥ እኔን ሠሪውን ረሳ፥ አብያተ መንግሥትንም ገነባ። ይሁዳ ብዙ ከተሞችን አጸና፥ እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ ምሽጎቹንም ታጠፋለች።
1እስራኤል ሆይ፥ አንተ የታመንክ አይደለህምና፥ አምላክህንም ትተሃልና፤ ሌሎች ሕዝቦች ደስ እንደሚላቸው፥ ደስ አይበልህ። በአውድዎች ሁሉ ላይ ሴተኛ አዳሪ የምትጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ወድደሃል። 2ነገር ግን አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፥ አዲሱ የወይን ጠጅም ይጥላታል።3በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይኖሩም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ ደግሞም አንድ ቀን በአሦር የረከሰ ምግብ ይበላሉ። 4ለእግዚአብሔር የወይን ጠጅ ቁርባን አያፈሱም፤ ደስም አያሰኙትም። መስዋዕታቸው እንደ ሐዘንተኞች ምግብ ይሆንባቸዋል፦ የሚበሉት ሁሉ ይረክሳሉ። ምግባቸው ለእነርሱ ብቻ የሚሆን ነውና ወደ እግዚአብሔር ቤት ሊመጣ አይችልም።5በእግዚአብሔር በዓል ቀን፥ በዓመት በዓል ቀን ምን ታድርጋላችሁ? 6ተመልከቱ፥ ከጥፋት ቢያመልጡ እንኳን ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ክምችታቸውን ሳማ ይውጠዋል፥ድንኳኖቻቸውንም እሾህ ይሞላዋል።7የቅጣት ቀን እየመጣ ነው፥የበቀል ቀን እየመጣ ነው። እስራኤል ሁሉ ይህን ይወቅ። ከክፋትህና ከጠላትነትህ የተነሳ፤ ነቢዩ ሞኝ፥ በመንፈስ የሚነዳውም ሰው እብድ ሆኖእል።8ከአምላኬ ጋር የሆነው ነቢይ የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ ነገር ግን የወፍ ወጥመድ በመንገዱ ሁሉ ነው፥በአምላኩም ቤት ጠላትነት አለበት። 9በጊብዓ ዘመን እንደነበረው ራሳቸውን እጅግ አርክሰዋል። እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይቀጣል።10እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥«እስራኤልን ያገኘሁበት ጊዜ፥ በምድረ በዳ ወይን እንደማግኘት ነበረ። እንደ በለስ ዛፍ የፍሬ ጊዜ የመጀመሪያ እሸት አባቶቻችሁን አገኘሁ።ነገር ግን ወደ ብዔልፌጎር ሄዱ፥ራሳቸውንም ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ሰጡ።እንደወደዱት ጣዖት እነርሱም የተጠሉ ሆኑ።11የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይሄዳል።መውለድ፥ ማርገዝና መፀነስ የለም። 12ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳን፥ አንዳቸውም እሰከማይቀሩላቸው ድረስ እወስድባቸዋለሁ። ከእነርሱ ዘወር ባልሁ ጊዜ፥ ወዮ ለእነርሱ!13ኤፍሬም እንደ ጢሮስ በለምለም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፥ ነገር ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለሚያርዳቸው አሳልፎ ይሰጣል። 14እግዚአብሔር ሆይ ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፍ ማኅፀንና ወተት የማይሰጡ ጡቶች ስጣቸው።15በጌልጌላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሳ፥ በዚያ እነርሱን መጥላት ጀመርኩ። ከክፉ ሥራቸው የተነሣ፥ ከቤቴ አስወጣቸዋለሁ። ከእንግዲህ ወዲያ አልወዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመጸኞች ናቸው።16ኤፍሬም በበሽታ ተመታ፤ሥራቸውም ደረቀ፥ ፍሬም አይሰጡም። ልጆች ቢወልዱም እንኳን፥ የተወደዱ ልጆቻቸውን እገድላለሁ።» 17አልታዘዙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል። በሕዝቦች መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።
1እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ ያማረ ወይን ነው። ፍሬው በበዛ መጠን፥ መሠዊያ አብዝቶ ሠራ። ምድሩ አብዝቶ ባፈራ መጠን፥የተቀደሱ አ ምዶቹን አሳመረ። 2ልባቸው አታላይ ነው፥ አሁን በደላቸውን ሊሸከሙ ይገባል። እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ያፈርሳል፤ የተቀደሱ አምዶቻቸውን ያጠፋል።3አሁንም እነርሱ፦ «እግዚአብሔርን ስላልፈራን፥ ንጉሥ የለንም፤ ንጉሥሥ ምን ሊያደርግልን ይችል ነበር?» ይላሉ። 4ባዶ ቃላትን ይናገራሉ፥ በሐሠት መሃላም ኪዳን ያደርጋሉ። ስለዚህ ፍትሕ፥ በእርሻ ትልም ላይ እንደሚወጣ መርዛማ አረም ይወጣል።5የሰማሪያ ነዋሪዎች ከቤትአዌን ጥጃዎች የተነሳ ይፈራሉ። በእነርሱና በውብታቸው ደስ ይሰኙ የነበሩ እነዚያ ጣዖት አምላኪ ካህናት እንደሚያልቅሱላቸው፣ ሕዝቡም ያለቅሱላቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ በዚያ የሉምና። 6ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ ወደ አሦር ይወሰዳሉ። ኤፍሬም ይዋረዳል፥ እስራኤልም የጣዖታትን ምክር በመከተሉ ያፍራል።7የሰማርያ ንጉሥ፥ በውኃ ላይ እንዳለ የእንጨት ፍቅፋቂ ይጠፋል። 8የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት፥ የክፋት ቅዱስ ቦታዎች ይጠፋሉ። እሾህና አሜክላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ። ሕዝቡ ተራሮችን፥ «ሸፍኑን!»፥ ኮረብታዎችንም፥ «ውደቁብን!» ይላሉ።9እስራኤል ሆይ ከጊብዓ ዘመን አንስቶ ኃጢአት ሠራችሁ፥ በዚያም ጸንታችኋል። በጊብዓ ክፉ አድራጊዎች ላይ ጦርነት በድንገት አልደረሰባቸውምን?10በወደድሁ ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ። ሕዝቦች በአንድነት ይሰበሰቡባቸዋል፥ ስለ ድርብ ኃጢአታቸውም ያስሯቸዋል። 11ኤፍሬም እህል ማበራየት የምትወድ የተገራ ጊደር ነች፥ ስለዚህ በሚያምር ጫንቃዋ ላይ ቀንበር አኖራለሁ። በኤፍሬም ላይ ቀንበር አኖራለሁ፥ ይሁዳ ያርሳል፥ ያዕቆብም ብቻውን መከስከሻውን ይጎትታል።12ጽድቅን ለራሳችሁ ዝሩ፥ የኪዳኑን ታማኝንት ፍሬም እጨዱ። እስኪመጣ፥ ጽድቅንም እስኪያዝንብባችሁ ድረስ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና፤ ያልታረሰ መሬታችሁን አለስልሱ። 13ክፋትን አረሳችሁ፥ግፍንም አጨዳችሁ። በስልታችሁና በወታደሮቻችሁ ብዛት ታምናችኋልና፥ የመታለልን ፍሬ በላችሁ።14ስለዚህ በሕዝብህ መካከል የጦርነት ሽብር ይነሣል፥ የተመሸጉ ከተሞችህም ሁሉ ይጠፋሉ። እናቶች ከልጆቻችው ጋር እንደተከሰከሱበት፥ ስልማን በሰልፍ ቀን ቤትአርብኤልን እንዳጠፋበት ጊዜ ይሆናል። 15ስለዚህ ቤቴል ሆይ፥ ከታላቅ ክፋትሽ የተነሣ በአንቺም ላይ እንዲሁ ይሆናል። ንጋት ላይ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።»
1እስራኤል ወጣት በነበረበት ጊዜ ወደድኩት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት። 2አብዝቶ በተጠሩ መጠን፥ አብዝተው ራቁ። ለበአል አማልክት ሠው፥ ለጣዖታትም አጠኑ።3ሆኖም ግን ኤፍሬምን መራመድ ያስተማርኩት እኔ ነበርኩ። ክንዶቻቸውን ይዤ ያነሳኋቸው እኔ ነበርኩ፥ እነርሱ ግን የተጠነቀቅሁላቸው እኔ እንደሆንሁ አላወቁም። 4በሰው ገመድ፥ በፍቅርም ማሰሪያ መራኋቸው። የመንጋጋዎቻቸውን ማሰሪያ እንደሚያላላ ሆንኩላቸው፥ ዝቅ ብዬም መገብኳቸው።5ወደ ግብጽ ምድር አይመለሱምን? ወደ እኔ መመለስን እምቢ በማለታቸው አሦር አይገዛቸውምን? 6ሰይፍ በከተሞቻቸው ላይ ይወድቃል፥ የበሮቻቸውንም መቀርቀሪያ ያጠፋል፤ከገዛ ራሳቸው ዕቅድ የተነሳ ያጠፋቸዋል። 7ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ለማለት ቆርጦአል። በከፍታ ወደ አለሁት ወደ እኔ ቢጣሩ እንኳ፥ማንም አይረዳቸውም።8ኤፍሬም ሆይ እንዴት እተውሃለሁ? እስራኤል ሆይ እንዴት አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተለውጦአል፤ መላው ርኅራኄዬ ተነሣሥቷል። 9ጽኑ ቁጣዬን አላመጣም፤ ኤፍሬምን ዳግመኛ አላጠፋም። እኔ አምላ ክ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥በመካከልህ ቅዱሱ ነኝና፥በቁጣ አልመጣም።10እነርሱም ከእኔ ከእግዚአብሔር በኋላ ይመጣሉ። እንደ እንበሳ አገሳለሁ። በእርግጥ አገሳለሁ፥ ሕዝቡም ከምዕራብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ። 11ከግብጽ እንደ ወፍ፥ ከአሦርም ምድር እንደ ርግብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ። በየቤቶቻቸውም አኖራቸዋለሁ።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።12«ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በማታለል ከበበኝ። ይሁዳ ግን እስካሁን ከእኔ ከአምላኩ ጋር ጸንቷል፥ ለእኔም ለቅዱሱ የታመነ ነ ው።»
1ኤፍሬም ነፋስ ይመገባል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል። ሐሰትንና ዓመፅን ያለማቋረጥ ያበዛል። ከአሦር ጋር ኪዳን ያደርጋሉ፥ የወይራ ዘይትም ወደ ግብጽ ይወስዳሉ። 2እግዚአብሔር ከይሁዳ ጋር ሙግት አለው፥ ያዕቆብንም ስላደረገው ይቀጣዋል፥ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።3ያዕቆብ በማሕፀን ውስጥ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፥ በጎልማስነቱም ከአምላክ ጋር ታገለ።ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ። 4አልቅሶም በፊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለመነው። በቤቴል ከአምላክ ተገናኘ፥ በዚያም አምላክ ከእርሱ ጋር ተነጋገረ።5እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤የሚጠራበት ስሙም «እግዚአብሔር» ነው። 6ስለዚህ ወደ አምላካችሁ ተመለሱ። ለኪዳኑ ታማኝነትን፥እንዲሁም ፍትሕን ጠብቁ፤ሁል ጊዜም አምላካችሁን ተስፋ አድርጉ።7ነጋዴዎቹ ሐሰተኛ ሚዛኖችን በእጆቻቸው ይዘዋል፤ ማጭበርበርን ይወዳሉ። 8ኤፍሬምም፦ «በእርግጥ እጅግ ባለጠጋ ሆኜአለሁ፥ ሀብትንም አግኝቼአለሁ። በሥራዬ ሁሉ ኃጢአት የሚሆን ምንም ዓይነት በደል አያገኙብኝም» ይላል።9ከግብጽ ምድር አንስቶ ከአናንተ ጋር የሆንኩ አምላካችሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እንደ ዓመት በዓላት ቀናት ዳግመኛ በድንኳኖች እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ። 10ለነቢያቶቹም ተናገርሁ፥ ስለ እናንተም ብዙ ራዕዮችን ሰጠኋቸው። በነቢይቶቹም አማካይነት ምሳሌዎችን ሰጠኋችሁ።»11በገለዓድ ኃጢአት ካለ፥ በእርግጥ ሕዝቡ ከንቱ ነው። በጌልጌላ ወይፈኖችን ይሰዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸው በታረሰ መሬት ላይ እንዳለ የድ ንጋይ ክምር ይሆናሉ።12ያዕቆብ ወደ ሶሪያ ምድር ሸሸ፤ እስራኤልም ሚስት ለማግኝት አገለገለ፥ ሚስትም ለማግኘት የበጎችን መንጋ ይጠብቅ ነበረ።13እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፥ በነቢይም አማካይነት ተጠነቀቀለት። 14ነገር ግን እግዚአብሔር ይቆጣ ዘነድ ኤፍሬም ክፉኛ አነሳሳው። ስለዚህ ጌታው የደሙን በደል በእርሱ ላይ ይደርጋል፥ አሳፋሪም ስለ ሆነው ሥራው የሚገባውን ይከፍለዋል።
1«ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ መንቀጥቀጥ ነበረ። በእስራኤል መካከል ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፥ ነገር ግን በአልን በማምለኩ በደለኛ ሆነ፥ ሞተም። 2አሁንም አብዝተው ኃጢአት ሠሩ። ከብራቸው የተቀረጸ ምስል ሠሩ፥ ጣዖታት በሚቻለው መጠን በጥበብ ተሠርተዋል፥ ሁሉም የባለ ሙያ ሥራ ናቸው። ሕዝቡ ስለ እነርሱ እንዲህ ይላሉ፦ 'እነዚህ የሚሠው ሰዎች ጥጃዎችን ይስማሉ።'3ስለዚህ እንደ ማለዳ ደመና፥በጠዋት እንደሚጠፋ ጤዛ፥ከአውድማ ላይ በነፋስ እንደሚወሰድ እብቅ፣ከጪስ ማውጫ እንደሚወጣ ጢስ ናቸ ው።4ነገር ግን ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ አታውቅም። 5በምድረ በዳ፥ በታላቅም የድርቀት ምድር አውቅሁህ። 6መሰማሪያ ባገኘህ ጊዜ ጠገብህ፥ በጠገብህም ጊዜ ልብህ ታበየ፤ከዚህም የተነሳ ረሳኽኝ።7እንደ አንበሳ ሆንኩባቸው፥እንደ ነብርም በመንገዳቸው አደባለሁ። 8ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ አጠቃቸዋለሁ። ደረታቸውን ቀድጄ ከፍታለሁ፥በዚያም እንደ አንበሳ እበላቸዋለሁ፥ እንደ ዱር አራዊትም እገነጣጥላቸዋለሁ።9እስራኤል ሆይ በረዳትህ በእኔ ላይ ዓምፀሃልና ጥፋትህ እየመጣ ነው። 10በከተማዎችህ ሁሉ ያድንህ ዘንድ ንጉሥህ አሁን ወዴት ነው? ስለ እነርሱ፥ 'ንጉሥና መሳፍንቶች ስጠኝ' ብለህ የተናገርክላቸው፥ ገዢዎችህ ወዴት ናቸው? 11በቁጣዬ ንጉሥ ሰጠሁህ፥ በመዓቴም አስወገድኩት።12የኤፍሬም ክፋት ተደብሮአል፥በደሉም ተደብሮአል። 13የምጥ ሕመም ይመጣበታል፥ እርሱ ግን ጥበብ የጎደለው ልጅ ነው፤ ምክንያቱም የሚወለድበት ጊዜ ቢደርስም ከማኅጸን አይወጣም።14በእርግጥ ከሲዖል ኃይል አድናቸዋለሁን? በእርግጥ ከሞትስ አድናቸዋለሁን? ሞት ሆይ መቅሰፍቶችህ ወዴት አሉ? ወደዚህ አምጣቸው። ሲዖል ሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ወደዚህ አምጣው። ርህራኄ ከዓይኖቼ ተሰወረ።15ኤፍሬም በወንድሞቹ መካከል ባለጸጋ ቢሆንም እንኳን፥ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፤ የእግዚአብሔር ነፋስ ከምድረ በዳ ይነፍሳል። የኤፍሬም ምንጭ ይደርቃል፥ ጉድጓዱም ውኃ አይኖረውም። ጠላቱ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን ግምጃ ቤቱን ይበዘብዛል።16በአምላኳ ላይ ዐምፃለችና ሰማሪያ በደለኛ ትሆናለች። በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ብላቴኖቻቸውም ይከሰከሳሉ፥ እርጉዝ ሴቶቻቸውም ይቀደዳሉ።
1እስራኤል ሆይ ከክፋትህ የተነሳ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። 2የኑዛዜ ቃላት ያዝና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። እንዲህም በሉት፦«የከንፈሮቻችንን ፍሬ ምስጋናችንን እንሰዋልህ ዘንድ፤ክፋታችንን አስወግድ፥በቸርነትም ተቀበለን።3አሦር አያድነንም፤ ለጦርነትም ፈረሶችን አንጋልብም። ወይም ከእንግዲህ የእጆቻችንን ሥራዎች 'እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ' አንላቸውም፤ አባት አልባው እንኳ በአንተ ዘንድ ርኅራኄን ያገኛልና።4ከተውኝም በኋላ ወደ እኔ በተመለሱ ጊዜ እፈውሳቸዋለሁ፤ እንዲያው እወዳቸዋለሁ፥ ቁጣዬ ከእርሱ ተመልሶአልና። 5እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤ እንደ አበባ ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ዝግባ ሥር ይሰዳል። 6ቅርንጫፎቹ ይዘረጋሉ፤ ውበቱ እንደ ወይራ ዛፎች፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባዎች ይሆናል።7ከጥላው በታች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ይመለሳሉ፤እንደ እህል ይለመልማሉ፥ እንደ ወይንም ያብባሉ።ዝናውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል። 8ኤፍሬም፦ 'ከእንግዲህ ከጣዖታት ጋር ምን አለኝ?' ይላል። እኔ እመልስለታለሁ፥እጠነቀቅለታለሁም። እኔ ቅጠሎቹ ሁል ጊዜ ለመለም እን ደሆኑ እንደ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህም ከእኔ ይመጣል።»9እነዚህን ነገሮች ያስተውል ዘንድ ጠቢብ የሆነ ማን ነው? ያውቃቸው ዘንድ እነዚህን ነገሮች የሚያስተውል ማን ነው? የእግዚአብሔር መንገዶች ትክክል ናቸው፥ ጻድቃንም ይሄዱባቸዋል፥ ዓመፀኞች ግን ይሰናከሉባቸዋል።
1ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። 2እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ፤በምድሪቱም የምትኖሩ ሁላችሁ አድምጡ። ይህ፥ከዚህ በፊት በእናንተ ወይም በአባቶቻችሁ ዘመን ሆኖ ያውቃልን? 3ይህንን ለልጆቻችሁ ንገሩ፥ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው ይንገሩ፥የእነርሱም ልጆች ለሚቀጥለው ትውልድ ይንገሩ።4ከአንበጣ መንጋ የተረፈውን ትላልቁ አንበጣ በላው፥ከትልቁ አንበጣ የተረፈውን ፌንጣ በላው፥ ከፌንጣ የተረፈውን አባ ጨጓሬ በላው።5እናንተ ሰካራሞች ተነሡና አልቅሱ! አዲሱ የወይን ጠጅ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ዋይ በሉ። 6ቁጥር የሌለው ሕዝብ በምድሬ ላይ መጥቶአልና። ጥርሶቹ የአንበሳ ጥርሶች ናቸው፤የሴት አንበሳም ጥርሶች አሉት። 7የወይን ቦታዬን አስደንጋጭ ስፍ ራ አደረገው፤የበለስ ዛፌን መልምሎ ባዶውን አስቀረ። ቅርፊቱን ላጠው፥ጣለውም፤ቅርንጫፎቹም ነጡ።8ለልጅነት ባሏ ሞት ማቅ እንደ ለበሰች ድንግል አልቅሱ። 9የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከእግዚአብሔር ቤት ተወግዷል፤የእ አብሔርም አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ። 10እርሻው ጠፍቷል፥ምድሪቱም አለቀሰች። እህሉ ወድሟል፥አዲሱ ወይን ደርቋል፥ዘይቱም ተበላሽቷል።11እናንተ ገበሬዎችና የወይን አትክልተኞች ስለ ስንዴዉና ስለ ገብሱ እፈሩ። የእርሻው መከር ጠፍቷልና። 12ወይኑ ጠውልጓል፥የበለስም ዛፎች ደርቀዋል፤የሮማን፥የተምርና የእንኮይ ዛፎች፥የእርሻው ዛፎች ሁሉ ጠውልገዋል። ደስታም ከሰው ልጆች ርቋል።13የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና፥እናንተ ካህናት ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ! ፥እናንተ የመሠዊያው አገልጋዮች ዋይ በሉ። እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች ኑ ሌሊቱን በሙሉ ማቅ ላይ ተኙ። 14ቅዱስ ጾም አውጁ፥የተቀደሰም ጉባዔ ጥሩ። ሽማግሌዎችንና በምድሪቱ የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።15የእግዚአብሔር ቀን ደርሷልና፥ወዮ ለዚያ ቀን! ከእርሱ ጋር ጥፋት ሁሉን ከሚችል አምላክ ይመጣል። 16ምግብ ከዓይናችን ፊት፥ ደስታና ሐሴት ከአምላካችን ቤት አልተወገደምን? 17ዘሩ በምድር ውስጥ በስብሷል፤እህሉ ደርቋልና ጎተራዎቹ ባዶ ሆነዋል፥ጎታዎቹም ፈርሰዋል።18እንስሳት ምንኛ ጮኹ! መሰማሪያ የላቸውምና የቀንድ ከብት መንጎች ተሰቃዩ። የበግ መንጎችም ተሰቃዩ። 19እሳቱ የምድረ በዳውን ማሰማሪያ በልቷልና፥ነበልባሉም የጫካውን ዛፎች ሁሉ አቃጥሎአልና፤እግዚአብሔር ሆይ ወደ አንተ እጮሃለሁ። 20ጅረቶች ሁሉ ስለደረ ቁና እሳ ት የምድረ በዳውን ማሰማሪያ ስለ በላው፥የዱር እንስሳት እንኳን ወደ አንተ አለኽልኹ።
1በጽዮን መለከት ንፉ፥ በቅዱስ ተራራዬም ላይ የማስጠንቀቂያ ድምጽ አሰሙ! የእግዚአብሔር ቀን መጥቷልና፥በእርግጥም ቅርብ ነውና፤የም ድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ በፍርሃት ይንቀጥቀጡ። 2እርሱም የጨለማና የጭጋግ ቀን፥የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። ንጋት በተራሮች ላይ እንደሚዘረጋ፥ታላቅና ኃያል ሠራዊት እየመጣ ነው። እርሱን የመሰለ ሠራዊት ከቶ አልነበረም፥ከብዙ ትውልድ በኋላ እንኳን ዳግመኛ አይኖርም።3በስተፊቱ እሳት ሁሉን ነገር ይበላል፥በስተኋላውም ነበልባል ይንቦገቦጋል። በስተፊቱ ምድሪቱ የዔደን ገነትን ትመስላለች፥በስተኋላው የሚገኘ ው ግን ባዶ ምድረ በዳ ነው።በእርግጥ፥ምንም ከእርሱ አያመልጥም።4የሠራዊቱ ገጽታ እንደ ፈረስ ነው፥እንደ ፈረሰኛም ይሮጣሉ። 5በተራሮች ራስ ላይ እንደሚሄድ የሰረገላ ድምጽ፥ገለባውን እንደሚበላ የእሳት ነበለባል ድምጽ እያሰሙ፥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኃያል ሠራዊት ያኮበኩባሉ።6በፊታቸው ሰዎች ይታወካሉ፥የሁሉም ፊት ይገረጣል። 7እንደ ብርቱ ተዋጊዎች ይሮጣሉ፥እንደ ወታደሮችም በቅጥሩ ላይ ይዘላሉ፤እያን ዳንዱ እርምጃውን ጠብቆ ፥ሰልፋቸውንም ሳያፈርሱ፤ ይተማሉ።8እያንዳንዱ መንገዱን ይሄዳል፥እርስ በእርሳቸው ሳይገፋፉ ይተማሉ፤ምሽጎችን ሰብረው ያልፋሉ፥ነገር ግን ከመስመራቸው አይወጡም።9ከተማን በድንገት ያጠቃሉ፥በቅጥር ላይ ይሮጣሉ፥ቤቶች ላይ ይወጣሉ፥እንደ ሌቦችም በመስኮቶች ያልፋሉ።10ምድር በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፥ሰማያትም ይናወጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ከዋክብትም ማብራታችውን ያቆማሉ። 11ተዋጊዎቹ እጅግ ብዙ ናቸውና፥ትእዛዙን የሚፈጽሙ ኃያላን ናቸውና፤ እግዚአብሔር በሠራዊቱ ፊት ድምጽን ያሰማል። የእግዚአብሔር ቀን ታላቅና የሚያስፈራ ነውና፤ ማን ሊቆም ይችላል?12«አሁንም እንኳን» ይላል እግዚአብሔር፥«በፍጽም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ፤ጹሙ፥አልቅሱ፥እዘኑም።» 13ልብሳችሁን ብቻ ሳይሆን ልባችሁንም ቅደዱ፤ ወደ አምላካችሁም ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ። እርሱ ቸርና መሐሪ፥ለቁጣ የዘገየ፥ፍቅሩ የተትረፈረፈ ነውና፤ስቃይ ካለብት ከዚህ ቅጣት መመለስ ይፈልጋል።14ምናልባት ይመለስና ይራራ እንደሆነ፥ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን የሚሆን በረከት በስተኋላው ያተርፍ እ ንደሆነ ማን ያውቃል?15በጽዮን መለከት ንፉ፥የተቀደሰ ጾም አውጁ፥ የተቀደሰም ጉባዔ ጥሩ። 16ሕዝቡን ሰብስቡ፥የተቀደሰ ጉባዔ ጥሩ። ሽማግሌዎችን፥ልጆችን፥ የሚጠቡትንም ሕጻናት ሰብስቡ። ሙሽራው ከእልፍኛቸው፥ሙሽራይቱም ከጫጉላ ቤታቸው ይውጡ።17የእግዚአብሔር አገልጋዮች፥ ካህናቱ፥ በቤት መቅደሱ መግቢያ ደጅና በመሠዊያው መካከል ያልቅሱ። እንዲህም ይበሉ፦«እግዚአብሔር ሆይ ለሕዝብህ ራራ፥አሕዛብ ይገዙአቸው ዘንድ ርስትህን ለእፍረት አሳልፈህ አትስጥ።በአሕዛብ መካከል አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይበሉ።»18እግዚአብሔርም ስለ ምድሩ ቀና፥ለሕዝቡም ራራ። 19እግዚአብሔርም ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦«እነሆ፥ እህል፥አዲስ ወይንና ዘይት እልክላችኋለሁ። እናንተም በእነርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል ለውርደት አላደርጋችሁም።20የሰሜንን ጥቃት ፈጻሚዎች ከእናተ አርቃለሁ፥ ወደ ደረቅና ወደ ተተወ ምድር እሰድዳቸዋለሁ። የሠራዊቱ ፊተኛ ጦር ወደ ምሥራቅ ባሕር፥ የሠራዊቱ ኋለኛ ጦር ወደ ምዕራብ ባሕር ይሄዳል። ግማቱ ይውጣል፥ክርፋቱም ይነሳል፤ታላላቅ ነገሮችንም አደርጋለሁ።»21እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን አድርጓልና፤ ምድር ሆይ አትፍሪ፥ ደስ ይበልሽ፥ ሐሴትም አድርጊ። 22የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳ ማሰማሪያዎች ለምልመዋልና፥ ዛፎች ፍሬያቸውን አፍርተዋልና፥ የበለስ ዛፎችና ወይኖች ሙሉ ፍሬያቸውን ሰጥተዋልና፤አትፍሩ። 23የበልግን ዝናብ እንደሚገባ ይሰጣአችኋልና፥እንደ ቀድሞ ዘመን የበልግ ዝናብንና የፀደይን ዝናብ ያካፋላችኋልና፤ የጽዮን ሰዎች ሆይ፥ደስ ይበላችሁ፥ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ሐሴት አድርጉ።24አውድማዎቹ በስንዴ ይሞላሉ፥መጥመቂያዎችም አዲስ ወይን ጠጅና ዘይት ያፈስሳሉ። 25በመካከላችሁ የላኩት ታላቁ ሠራዊቴ፥ የአንበጣ መንጋ፥ ትልቁ አንበጣ፥ ፌንጣና አባ ጮጋሬ የበሏቸውን የምርት ዓመታት እመልስላችኋለሁ።26ተትረፍርፎ ትበላላችሁ፥ ትጠግባላችሁም፤ በመካከላችሁም ተዓምራት ያደረገውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ እፍረትን በሕዝቤ ላይ ከቶውኑ አላመጣም። 27እኔ በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንኩ፥ ሌላም እንደሌለ፥ ከእንግዲህም ወዲይ እፍረትን በሕዝቤ ላይ ከቶውን እንደማላመጣ ታውቃላችሁ።28ከዚያም በኋላ እንደዚህ ይሆናል፡- መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፥ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ። ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፥ጎልማሶቻችሁም ራእይ ያያሉ። 29በእነዚያ ወራት በወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ላይም መንፈሴን አፈሳለሁ።30በሰማያት ድንቆችን፥በምድርም ደም፥እሳትና የጢስ ዓምድ አሳያለሁ። 31ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት፥ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።32የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል። እግዚአብሔር እንደ ተናገርው፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚያመልጡ ይኖራሉ፤ከትሩፋኑም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኛሉ።
1እነሆ፥ በዚያ ወራትና በዚያ ጊዜ፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜ፥ 2አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፥ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ። በአሕዛብ መካከል ከበተኑአቸው ከሕዝቤና ከርስቴ ከእስራኤል የተነሳ፥ ምድሬን ከመከፋፈላቸው የተነሳ፤ በዚያ እፈር ድባቸዋለሁ። 3በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ወንድ ልጅን በሴተኛ አዳሪ ለወጡ፥ ሴት ልጅንም ለወይን ጠጅ ሸጡ፥ ጠጡም።4ጢሮስና ሲዶና የፍልስጤምም ክፍለ አገራት ሁሉ፥አሁን በእኔ ላይ መቆጣታችሁ ለምንድ ነው? ብድራትን ትመልሱልኛላችሁን? ብድራትን ብትመልሱልኝ፥ወዲያው ብድራታችሁን በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ። 5ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፥የከበረውንም ሀብቴን ወደ ቤተ መቅ ደሳችሁ አግዛችኋል። 6ከግዛታቸው ልታርቋቸው፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለግሪኮች ሸጣችኋል።7እነሆ እነርሱን የሸጣችሁብትን ሥፍራ እንዲለቁ አደርጋቸዋለሁ፥ ብድራታችሁንም በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ። 8ወንዶችና ሴቶች ልጆ ቻችሁን በይሁዳ ሰዎች እጅ እሸጣለሁ። እነርሱም በሩቅ ላለ ሕዝብ፥ለሳባ ሰዎች ይሸጡአቸዋል። እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።9ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፦ ለጦርነት ተዘጋጁ፥ኃያላን ሰዎችን አነሣሡ፥ ይቅረቡ፥ ተዋጊዎችም ሁሉ ይውጡ። 10ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁን ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፤ ደካማውም «እኔ ብርቱ ነኝ» ይበል።11እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ፈጥናችሁ ኑ፥ በአንድነትም ተሰብሰቡ። እግዚአብሔር ሆይ ኃያላን ተዋጊዎችህን ወደዚያ አውርድ።12በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ልፈርድ በዚያ እቀመጣለሁና፤ አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ ይምጡ። 13መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ላኩ፥ የወይኑ መጭመቂያ ሞልቶ እየፈሰሰ ነውና ኑ ወይኑን ርገጡ፥ ክፋታቸው በዝቶአልና።14የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ውስጥ ቀርቦአልና፤ ሁካታ፥ በፍርድ ሸለቆ ውስጥ ሁካታ አለ። 15ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይከለክላሉ።16እግዚአብሔር ከጽዮን ይጮኻል፥ከኢየሩሳሌም ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማል። ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፥ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መጠለያ፥ ለእስራኤልም ሕዝብ መመሸጊያ ይሆናል። 17«ስለዚህ በተቀደሰ ተራራዬ በጽዮን የምኖር እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፥ ዳግመኛም ሠራዊት አያልፍባትም።18በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ተራሮች አዲስ ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ወተት ያፈስሳሉ፥የይሁዳ ጅረቶች ሁሉ ውኃ ያጎርፋሉ፥ ከእግዚአብሔር ቤት ምንጭ ይመነጫል፥ የሰጢምንም ሸለቆ ያጠጣል። 19በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋልና፥ በምድራቸው የንጽሐንን ደም አፍስሰዋልና፤ ግብጽ ባድማ፥ ኤዶምም ምድረ በዳ ትሆናለች።20ነገር ግን ይሁዳ ለዘላለም ይኖራል፥ኢየሩሳሌምም ከትውልድ ትውልድ ትኖራለች። 21ያልተበቀልኩትን ደማቸውን እበቀላለሁ፤» እግ ዚአብሔር በጽዮን ይኖራል።
1በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፥ ስለ እስራኤል በራዕይ የተቀበላቸው ነገሮች አነዚህ ናቸው። እነዚህንም ነገሮች በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመነ መንግሥት፥በእስራኤል ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት፥የምድርም መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓ መት አስቀድሞ ተቀበለ። 2እንዲህም አለ፥«እግዚአብሔር ከጽዮን ይጮኻል፥ ከኢየሩሳሌምም ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማል። የእረኞች ማሰማሪያ ዎች ያለቅሳሉ፥የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።»3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ገልዓድን በብረት መሣሪያ አድቅቋልና፤ ስለ ደማስቆ ሦሥት ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስለ አራቱ ፥ ቅጣቴን አልመልስም። 4በአዛሄል ቤት ላይ እሳት እልካለሁ፥ የወልደ አዴርንም ምሽጎች ትበላለች።5የደማስቆን በር መቀርቀሪያዎች እሰብራኣለሁ፥በአዌን ሸለቆ የሚኖረውን ሰውና በቤተ ኤደንም በትረ መንግሥት የያዘውን ሰው ድል ነሳለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል» ይላል እግዚአብሔር።6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ለዔዶም አሳልፈው ሊሰጧቸው ሕዝቡን ሁሉ ማርከው ወስደዋልና፤ ስለ ጋዛ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁን ም ስለ አራቱ ፥ ቅጣቴን አልመልስም። 7በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እልካልሁ፥ምሽጎቹዋንም ይበላል።8በአሽዶድ የሚኖረውንና በአስቀሎና በትረ መንግሥት የያዘውን ሰው አጠፋለሁ። እጄን በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ የቀሩት ፍልስጤማውያንም ይጠፋሉ»ይላል እግዚአብሔር።9እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«የሕዝብን ወገኖች ሁሉ ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋልና የወንድማማችነትንም ኪዳን አፍርሰዋልና፥ ስለ ጢሮስ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አለመልስም። 10በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እልካለሁ፥ምሽጎችዋንም ሁሉ ይበላል።»11እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ ርኅራኄንም ሁሉ ጥሎአልና፥ ቁጣው ሳያቋርጥ ነዶአልና፥ ቁጣው ለዘላለም ነውና፤ 12በቴማን ላይ እሳት እልካለሁ፥ የባሶራንም አብያተ መንግሥት አጠፋለሁ።»13እግዚእብሔር እንዲህ ይላል፦«ድንበሩን ለማስፋት የገለዓድን እርጉዝ ሴቶች ቀድዶአልና፤ ስለ አሞን ሕዝብ ሦሥት ኃጢአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።14በረባት ቅጥሮች ላይ እሳት አነድዳለሁ፥ በጦርነት ቀን ከጩኽት ጋር፥ በአውሎ ነፋስም ቀን ከማዕበል ጋር፤ አብያተ መንግሥትን ይበላል። 15ንጉሣቸው ከአለቆቻቸው ጋር ወደ ምርኮ ይሄዳል» ይላል እግዚአብሔር።
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «አመድ እስኪሆን ድረስ የኤዶምን ንጉሥ አጥንት አቋጥሏልና፤ ስለ ሞዓብን ሦሥት ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።2በሞዓብ ላይ እሳት እልካለሁ፥ የቂርዮትንም ምሽጎች ይበላል። ሞዓብ በጩኽትና በመለከትድምጽ፥ በሁካታ ውስጥ ይሞታል። 3በውስጧ የሚገኝውን ፈራጁን አጠፋለሁ፥ መሳፍንቱን ሁሉ ከእርሱ ጋር እገድላለሁ» ይላል እግዚአብሔር።4እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አለጠበቁምና ስለ ሦሥት የይሁዳ ኃጢአቶች፥ይልቁንም ስል አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም። ሐሰታቸው አስቷቸዋልና፥በዚሁ መንገድ አባቶቻቸውም ሄዱ። 5እሳት በይሁዳ ላይ እልካለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ይበላል።6እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ንጹሑን ስለ ብር፥ ችግረኛውንም ስለ ጥንድ ጫማ ሽጠዋልና ፤ስለ እስራኤል ሦሥት ኃጥአቶች፥ ይልቁንም ስለ አራቱ፥ ቅጣቴን አልመልስም።7ሰዎች በምድር ላይ ትቢያን እንደሚረግጡ፥ የድኾችን ራስ ይረግጣሉ፤ የተጨቆኑትን ይገፋሉ። አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ይተኛሉ፥ ቅዱስ ስሜንም ያረክሳሉ። 8በየመሠዊያው አጠገብ በመያዣነት በተወሰደ ልብስ ላይ ይተኛሉ፥በአምላካቸውም ቤት በመቀጫነት የተወሰደውን ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።9ነገር ግን ቁመታቸው እንደ ዝግባ፥ጥንካሬያቸው እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረውን አሞራዊያንን ከፊታችው አጠፋሁ። ከላይ ፍሬውን፥ ከታችም ሥሩን አጠፋሁ። 10የአሞራውያንን ምድር እንድትወርሱ እናንተን ከግብፅ አወጣሁ፤ በምድረ በዳ አርባ ዓመት መራሁዋችሁ።11ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ፥ናዝራዊያንንም ከጎልማሶቻችሁ መካከል አስነሳሁ። የእስራኤል ህዝብ ሆይ፥ይህ እንደዚህ አይደለም ን? ይላል እግዚአብሔር። 12«እናንተ ግን ናዝራዊያንን የወይን ጠጅ ይጠጡ ዘንድ አሳባቸውን አስለወጣችሁ፥ነቢያቱንም እንዳይተነብዩ አዘዛችኋቸው።13እነሆ፥በእህል የተሞላ ሰረገላ ሰውን እንደሚያደቅቅ እንዲሁ አደቅቃችኋለሁ። 14ፈጣኑ ሰው አያመልጥም፥ብርቱው ለራሱ ብርታትን አይጨምርም፥ኃያልም ራሱን አያድንም።15ቀስተኛው አይቆምም፥ፈጣኑ ሯጭ አያመልጥም፥ፈረሰኛውም ራሱን አያድንም። 16ጅግኖቹ ተዋጊዎች እንኳን በቀን ዕርቃናቸውን ይሸሻሉ፤ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»
1የእስራኤል ሕዝብ፥ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ወገኖች ሁሉ፥እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤ 2ከምድር ወገኖች ሁሉ እናንተን ብቻ መረጥሁ። ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እቀጣችኋለሁ።3ሁለቱ ካልተስማሙ በስተቀር አብረው ይሄዳሉን? 4አንበሳ የሚሰብረውን ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሳልን? የአንበሳ ደቦል ምንም ሳይዝ በዋ ሻው ውስጥ ያጉተመትማልን?5ማታለያ ምግብ ካልተዘጋጀለት በስተቀር ወፍ በምድር ወጥመድ ዉስጥ ይገባልን? አንዳች ሳይዝ ወጥመድ ከምድር ይፈናጠራልን? 6በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? በከተማ ላይ ጥፋት ከመጣ የላከው እግዚአብሔር አይደለምን?7በእርግጥ ጌታ እግዚአብሔር ሊያደርግ ያለውን ለአልጋዮቹ ለነቢያት ካልገለጠ በስተቀር ምንም አያደርግም። 8አንበሳው አገሳ፥የማይፈራ ማነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፥ትንቢት የማይናገር ማነው?9ይህንን በአዛጦንና በግብጽ ምሽጎች አውጁ፥ እንዲህም በሉ፦«በሰማሪያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፥ በውስጧ ምን ዓይነት ታላቅ ግራ መጋባትና ጭቆና እንዳለ ተመልከቱ። 10ቅን ነገርን እንዴት እንደሚያደርጉ አያውቁምና፥ዝርፊያንና ጥፋትን በምሽጎቻቸው አከማችተዋል።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።11ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ጠላት ምድሪቱን ይከብባል፤ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል ይበዘብዛልም። 12እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«እረኛ ከአንበሳ አፍ ሁለት እግር ብቻ፥ወይንም የጆሮ ቁራጭ እንደሚያድን፥ በመከዳ ጠርዝ ብቻ ወይም በትንሽ የአልጋ ልብስ በሰማሪያ የሚኖሩ የእስራኤል ሰዎች ብቻ ይድናሉ»13ስሙ፥በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ፥ ይላል የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር። 14የእስራኤልን ኃጢአት በምቀጣበት ቀን የቤቴልን ም መሠዊያዎች እቀጣለሁ። የመሠዊያው ቀንዶች ይቆረጣሉ፥ወደ ምድርም ይወድቃሉ።15የክረምቱን ቤት ከበጋው ቤት ጋር አጠፋለሁ። በዝሆን ጥርስ የተዋቡ ቤቶች ይጠፋሉ፥ታላላቅ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፥» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
1እናንተ የባሳን ላሞች፥በሰማሪያ ተራራ የምትኖሩ፥ድኾችን የምትጨቁኑ፥ችግረኞችን የምታደቅቁ፥ ባሎቻችሁንም «መጠጥ አምጡልን» የምትሉ ይህን ቃል ስሙ። 2ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ «ተመልከቱ፥ እናንተን በመንጠቆ፥ የቀሩትንም በዓሳ መንጠቆ የ ሚወስዱበት ቀናት ይመጣል።3በከተማው ቅጥር ፍራሽ በኩል ትወጣላችሁ፥እያንዳንዳችሁ በእርሱ በኩል ወደ ፊት ቀጥ ብላችሁ ትሄዳላችሁ፥ወደ ሬማንም ትጣላላችሁ--ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»4ወደ ቤቴል ሂዱና ኃጢአት ሥሩ፥ወደ ጌልጌላ ሂዱና ኃጢአት አብዙ። መሥዋዕታችሁን በየማለዳው፥ አሥራታችሁንም በየሦሥተኛው ቀን አቅርቡ። 5እርሾ ያለበትን የምስጋና መሥዋዕት ሠው፤ እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ ይህ ደስ ያሰኛችኋልና በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን አው ጁ፥ ስለ እነርሱም አውሩ --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»6የጥርስ ንፃትን በከተማዎቻችሁ ሁሉ፥ እንጀራንም ማጣትን በስፍራዎቻችሁ ሁሉ እሰጣችኋለሁ። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም ---- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።» 7ለመከር ሦሥት ወር ሲቀረው ዝናብ ከለከልኋችሁ። በአንዱ ከተማ ላይ እንዲዘንብ፥ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ። በአንዱ ቁራጭ መሬት ላይ ዘነበበት፥ ያልዘነበበት ቁራጭ መሬት ግን ደረቀ።8ሁለት ወይም ሦሥት ከተሞች ውኃ ለመጠጣት ወደ ሌላ ከተማ እየተንገዳገዱ ሄዱ፤ ነገር ግን አልረኩም። ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።» 9በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ። የአትክልቶቻችሁን ብዛት፥ ወይኖቻችሁን፥ የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን ሁሉ አንበጦች በሉት። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»10«በግብጽ ላይ እንዳደረግሁባቸው መቅሰፍት ላክሁባችሁ። ወጣቶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፥ ፈረሶቻችሁንም አስማረክሁ፥ የሠፈራች ሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲደርስ አደረግሁ። እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም --- ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።» 11እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን እንደገለበጣቸው፥ በመካከላችሁ ከተሞችን ገለበጥሁ።እናንተም ከእሳት እንደተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።»12«ስለዚህ እስራኤል ሆይ አስደንጋጭ ነገር አደርግብሃለሁ፥ አስደንጋጭንም ነገር ስለማደርግብህ እስራኤል ሆይ አምላክህን ለመገናኘት ተዘጋጅ! 13እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ነፋስንም የፈጠረ፥ አሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ» ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
1የእስራኤል ቤት ሆይ፥ይህን ቃል ይኽውም በእናንተ ላይ የማሰማውን የሐዘን እንጉርጉሮ ስሙ። 2ድንግሊቱ እስራኤል ወደቀች፤ ከእንግህም ወዲያ አትነሳም፥ በራሷ ምድር ላይ ተተወች፤ የሚያነሳትም ማንም የለም።3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦«ለእስራኤል ቤት ሺህ ታወጣ የነበረች ከተማ መቶ ይቀርላታል፥ መቶም ታወጣ የነበረች ከተማ አሥር ይቀርላታል።»4ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላል፦ «እኔን ፈልጉ፥በሕይወትም ኑሩ! 5ጌልጌላ በእርግጥ ትማረካለችና፥ በቴልም ታዝናለችና፤ ቤቴልን አትፈልጉ፥ወደ ጌልጌላ አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትሂዱ።6እግዚአብሔርን ፈልጉ፥በሕይወትም ኑሩ፤ይህ ካልሆነ በዮሴፍ ቤት ላይ እንደ እሳት ይነሳል። ይበላል፥ በቤቴልም የሚያጠፋው ማንም የለም። 7እነዚያ ሰዎች ፍትህን ወደ መራራ ነገር ለውጠዋልና፥ ጽድቅንም ወደ ምድር ጥለዋልና።8ሰባቱን ከዋክብትና ኦርዮንን የፈጠረ አምላክ፥ ጨለማን ወደ ንጋት ይለውጣል፥ ቀኑን በሌሊት ያጨልማል፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ ያፈሳቸዋል። ስሙ እግዚአብሔር ነው! 9ምሽጉ እንዲፈርስ ድንገትኛ ጥፋትን ያመጣል።10በከተማይቱ በር ላይ የሚያርማቸውን ማንንም ጠሉ፥ እውነትን የሚናገረውን ማንንም ተጸየፉ። 11ድኻውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውን ም ድርሻ ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ብትሠሩም አትኖሩባቸውም። ያማሩ የወይን ተክል ቦታዎች አሉአችሁ፥ የወይን ጠጃቸውን ግን አትጠጡም።12እናንተ ጻድቁን የምታጥቁ፥ ጉቦ የምትቀበሉ፥ በከተማይቱም በር ችግረኛውን የምትገለብጡ፤ በደላችሁ እንዴት ብዙ እንደሆን፥ ኃጢአታችሁም እንዴት ታላቅ እንደሆን እኔ አውቃለሁ። 13ጊዜው ክፉ ነውና፥ አስተዋይ የሆነ ማንም በእንደዚህ ዓይነቱ ጊዜ ዝም ይላል።14በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን ፈልጉ፥ ክፉውንም አይደለም። እርሱም እንደተናገራችሁት ነውና፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር በእርግጥ ከእናንተ ጋር ይሆናል። 15ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በከተማይቱም በር ፍትሕን አጽኑ፤ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።16ሰለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ «በአደባባዮቹ ሁሉ ዋይታ ይሆናል፥ በየመንገዶቹ ወዮ! ወዮ! ይላሉ። ገበሬዎችን ለለቅሶ፥ አልቃሾችንም ለዋይታ ይጠራሉ። 17እኔ በመካከልህ አልፋለሁና፥ በወይን ተክል ቦታዎች ሁሉ ዋይታ ይሆናል» ይላል እግዚአብሔር።18የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም። 19አንድ ሰው ከአንበሳ ሲሸሽ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወደ ቤት ገብቶ እጁን ግድግዳ ላይ ሲያስደግፍ እባብ እንደሚነድፈው ነው። 20የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ አይደለምን? ብሩህ ሳይሆን ደብዛዛ አይደለምን?21ዓመት በዓላችሁን ጠልቼዋለሁ፥ ተጸይፌዋለሁም፤በጉባዔዎቻችሁ ደስ አይለኝም። 22የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁንና የእህል ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝ እንኳን አልቀበላቸውም፤ ወይም ወደ ሰቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት አልመለከትም።23የመዝሙሮችህን ጩኽት ከእኔ አርቅ፤ የበገናህንም ድምጽ አልሰማም። 24በዚያ ፈንታ ፍትሕ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም ሳያቋርጥ እንደሚመነጭ ምንጭ ይፍሰስ።25የእስራኤል ቤት ሆይ በምድረ በዳው ለአርባ ዓመታት መሥዋዕትንና ቁርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን? 26ለራሳችሁ የሠራችኋቸውን ጣዖታት፥ ሞሎክን እንደ ንጉሣችሁ፥ሬፋን እንደ ኮከብ አምላካችሁ አንሥታችሁ ትሸከማችሁ።27ስለዚህ ከደማስቆ ማዶ እስማርካችኋለሁ» ይላል፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ የሆነው እግዚአብሔር።
1በጽዮን በምቾት፥በሰማሪያ ተራሮች ላይ ያለ ስጋት ለሚኖሩ፥የእስራኤል ቤት ለርዳታ ወደ እነርሱ ለሚመጡባችው፥ ለታላላቅ የሕዝብ አለቆች ወዮላቸው! 2መሪዎቻችሁ እንዲህ ይላሉ፦«ወደ ካልኔ ሂዱና ተመልከቱ፥ከዚያም ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ሐማት እለፉ፥ ከዚያም ወደ ፍልስጤም ጌት ውረዱ። እነርሱ ከእናንተ ሁለት መንግሥታት የተሻሉ ናቸውን? የእነርሱ ድንበር ከእናንተ ድንበር ይሰፋልን?»3የጥፋትን ቀን ለምታርቁ፥የግፍንም መንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ! 4ከዝሆን ጥርስ በተሠሩ አልጋዎች ላይ ይተኛሉ፥በመከዳዎቻቸውም ላይ ይዝናናሉ። ከበጎች መንጋ ጠቦትን፥ከበረትም ጥጃን ይበላሉ።5በበገና ድምጽ ጣዕም የሌለው ዜማ ያዜማሉ፥ እንደ ዳዊት በተገኘው የሙዚቃ መሣሪያ መጫወት ይሻሉ። 6በዋንጫ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ፥ ከሁሉ በተመረጠ ዘይት ይቀባሉ፥ ነገር ግን በዮሴፍ መጥፋት አያዝኑም።7ስለዚህ ከመጀመሪያዎቹ ምርኮኞች ጋር ወደ ምርኮ ይሄዳሉ፥ የሚዝናኑቱ ድግሶችና ፈንጠዚያዎች ያከትማሉ። 8እኔ ጌታ እግዚአብሔር በራሴ ምያለሁ፥ ይህ የሠራዊት አምላክ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው፦«የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ ምሽጎቹንም ጠልቼአለሁ። ስለዚህ ከተ ማይቱን በውስጧ ካሉት ሁሉ ጋር አሳላፌ አሰጣለሁ።»9እንዲህም ይሆናል፤ በአንድ ቤት አሥር ሰዎች ቢቀሩ ሁሉም ይሞታሉ። 10የሰው ዘመድ አስከሬኖቹን ለመውሰድ በመጣ ጊዜ፤ አስከሬኖቹን ከቤት አውጥቶ የሚያቃጥላቸው ሰው፥ በቤት ውስጥ ያለውን ሰው፦«ከአንተ ጋር ሌላ ሰው አለን?» ሲለው፤ ሰውዬውም፦ «ማንም የለም» ብሎ በመለሰለት ጊዜ፥ እርሱም፦«ዝም በል፥ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንምና» ይለዋል።11ተመልከቱ፥ እግዚአብሔር ትዕዛዝ ይሰጣል፤ ትልቁም ቤት ይሰባበራል፥ ትንሹም ቤት ይደቅቃል።12ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ሰውስ በዚያ ላይ በበሬዎች ያርሳልን? እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፥ የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራርነት ለውጣችኋል። 13እናንተ ሎዶባርን በማሸነፋችሁ ደስ ያላችሁ፥ «ቃርናይምን በራሳችን ብርታት አልወሰድንምን?» የምትሉ፤14«ነገር ግን፥ የእስራኤል ቤት ሆይ አነሆ ሕዝብን አስነሣባችኋለሁ»፥ ይህ የሠራዊት አምላክ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው። «ከሐማት መግቢያ አንስቶ እስከ ዓረባ ወንዝ ድረስ ያስጨንቋችኋል።»
1ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ። እነሆ፥የጸደይ አዝመራ መብቀል በሚጀምርበት ጊዜ የአንበጣን መንጋ ፈጠረ፥ ተመለከትሁም፥ ከንጉሥ አጨዳ በኋላ ዘግይቶ የበቀለ አዝመራ ነበር። 2የምድሪቱን ሣር በልተው ከጨረሱ በኋላ፤ «ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ይቅር በል፥ ያዕቆብ በዚህ ውስጥ እንዴት ይቆማል? እርሱ ታናሽ ነውና» አልሁ። 3እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ «ይህ አይሆንም» አለ።4ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፦እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር በእሳት ለመፍረድ ጠራ። እርሱም በምድር ውስጥ የሚገኘውን ሰፊና ጥልቅ ውኃ አደረቀ፥ ምድሪቱንም ደግሞ በላ። 5እኔ ግን፦«ጌታ እግዚአብሔር ሆይ እባክህ ተው፥ያዕቆብ በዚህ ውስጥ እንዴት ይቆማል? እርሱ ታናሽ ነውና» አልሁ። 6እግዚአብሔርም ስለዚህ ነገር ተጸጸተ፤ «ይህም ደግሞ አይሆንም» ይላል ጌታ እግዚአብሔር።7እንዲህም አሳየኝ፦ እነሆም ፥ጌታ በእጁ ቱምቢ ይዞ በቅጥሩ አጠገብ ቆሞ ነበር። 8እግዚአብሔርም፦ «አሞጽ ምን ታያለህ?» አለኝ፥ እኔም «ቱምቢ» አልሁኝ። ከዚያም ጌታ፦«ተመልከት፥በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱምቢ አኖራለሁ። ከእንግዲህም ወዲያ አልምራቸውም።9የይስሐቅ ከፍታ ቦታዎች ይጠፋሉ፥ የእስራኤል መቅደሶች ይፈርሳሉ፥ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሳለሁ።»10ከዚያም የቤቴል ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፦«አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሤረ ነው። ምድሪቱም ቃሎቹን ልትሸከም አትችልም። 11አሞጽ እንዲህ ሲል ተናግሮአል፦'ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፥ እስራኤልም በእርግጥ ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል'።»12አሜስያስም፥ አሞጽን እንዲህ አለው፦«ባለ ራዕዩ ሆይ፥ ወደ ይሁዳ ምድር ተመልሰህ ሽሽ፥ በዚያም እንጀራ ብላ ትንቢትም ተናገር። 13ነገር ግን ቤቴል የንጉሡ መቅድስና የመንግሥት መኖሪያ ነውና ከእንግዲህ ወድያ በዚህ ትንቢት አትናገር።»14ከዚያም አሞጽ አሜስያስን እንዲህ አለው፦ «እኔ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም። እኔ እረኛና የዋርካ ዛፎች ጠባቂ ነኝ። 15ነገር ግን እግዚአብሔር የበግ መንጋ ከመጠበቅ ወሰደኝና እንዲህ አለኝ፦'ሂድ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር።'16አሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። አንተ፥ «'በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ በይስሐቅም ቤት ላይ አትናገር' ትላለህ። 17ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦' ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ ሴተኛ አዳሪ ትሆናለች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ምድርህ እየተለካ ይከፋፈላል፥ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፥ እስራኤልም በእርግጥ ከምድሩ ተማርኮ ይጋዛል።»
1ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ የበጋ ፍሬ ቅርጫት ተመለከትሁ! 2እርሱም፥ «አሞጽ፥ ምን ታያለህ?» አለኝ። እኔም፥ «የበጋ ፍሬ ቅርጫት» አልሁት። ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ «በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፍጻሜ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልምራቸውም። 3የቤተ መቅደሱ ዝማሬ ዋይታ ይሆናል። የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፥ በዚያን ቀን፥ «አስከሬኑ ብዙ ይሆናል፤ በሁሉ ሥፍራ በዝምታ ይጥሏቸዋል።»4እናንተ ችግረⶉችን የምትረግጡና የምድሪቱን ድኾች የምታጠፉ ስሙ። 5እንዲህ ይላሉ፦«እህል እንሸጥ ዘንድ የወር መባቻው መቼ ያልፋል? በሐሰተኛ ሚዛን እያታለልን፥ መስፈሪያውን እያሳነስን፥ ዋጋውን ከፍ እያደረግን፥ ስንዴ ለገበያ እናቀርብ ዘንድ፥ 6የስንዴውን ግርድ እንሸጥና ደኻውን በብር፥ ችግረኛውንም በጥንድ ጫማ እንገዛ ዘንድ ሰንብት መቼ ያልፋል?»7እግዚአብሔር በያዕቆብ ክብር እንዲህ ሲል ምሎአል፦ «በእርግጥ የትኛውንም ሥራቸውን ፈጽሞ አልረሳም።» 8በዚህ ነገር፥ ምድር አትናወጥምን፥ በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ አያለቅሱምን? ሁለመናዋ እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፥ እንደ ግብጽ ወንዝም ወደ ላይ ይወረወራል፥ተመልሶም ይወርዳል።9«በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል» ፥የእግዚአብሔር አዋጅ እንዲህ ይላል፥ «ፀሐይ በቀን እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፥ በቀንም ብርሃን እያለ ምድርን አጨልማታለሁ»። 10ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፥ መዝሙራችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ። ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፥ ጸጉራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ። ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ፥ እንደ መራራም ቀን አደርገዋለሁ።11ተመልከቱ፥ቀኖቹ እየቀረቡ ናቸው» ፥የእግዚአብሔር አዋጅ እንዲህ ይላል፥ «ረሓብን በምድር ላይ እሰድዳለሁ፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት ረሓብ እንጂ እንጀራን የመራብ ወይም ውኃን የመጠማት አይደለም። 12የእግዚአብሔርን ቃል ፍለጋ ከባሕር ወደ ባሕር ይንከ ራተታሉ፥ ከሰሜን ወደ ምሥራቅ ይሮጣሉ፤ ነገር ግን አያገኙትም።13በዚያን ቀን ያማሩ ደናግላንና ወጣቶች ከውኃ ጥም የተነሳ ይዝላሉ። 14'ዳን ሆይ ሕያው አምላክህን' ድግሞም 'ሕያው የቤርሳቤህ አምላክ' እያሉ በሰማርያ ኃጢአት የሚምሉ ፤ይወድቃሉ፥ዳግመኛም አይነሱም።»
1ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፥ እንዲህም አለ፦«መሠረቶቹ እንዲናወጡ የአምዶቹን የላይኛውን ጫፍ ምታ። በራሶቻቸው ሁሉ ላይ ሰባብራቸው፥ ከእነርሱም የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ። ከእነርሱ ማንም አያመልጥም፥ ማንም አይተርፍም። 2ቆፍረው ወደ ሲዖል ቢወርዱም፥ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች። ወደ ሰማይ ቢወጡም፥ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ።3በቀርሜሎስ ራስ ላይ ቢሸሸጉም፥ በርብሬ ከዚያ እወስዳቸዋለሁ። በባሕሩ ሥር ከዓይኔ ቢደበቁም፥ በዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል። 4በጠላቶቻቸው ፊት እየተነዱ ወደ ምርኮ ይጋዛሉ፤ በዚያም ሰይፍን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይገድላቸዋል። ዓይኔን ለክፉ በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ለመልካምም አይደለም።»5ጌታ፥ የሠራዊቱ እግዚአብሔር ምድርን ይዳስሳል፥ እርስዋም ትቀልጣለች፥ በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሁሉ፤ ሁለመናዋ እንደ ወንዝ ወደ ላይ ይወረወራል፥ እንደ ግብጽም ወንዝ ተመልሶ ይሰምጣል። 6አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ግምጃ ቤቱን በምድር የመሠረተ እርሱ ነው። የባሕርን ዉኆች ይጠራቸዋል፥ በምድርም ፊት ላይ ያፈስሳቸዋል፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው።7የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር። እስራኤልን ከግብጽ፥ፍልስጤማያንን ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን? 8እነሆ፥ የጌታ እግዚአብሔር ዓይኖች በኃጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፥ ከምድርም ገጽ አጠፋዋለሁ፣ የያቆብን ቤት ግን ፈጽሜ አላጠፋም፤ ይላል እግዚአብሔር።»9እነሆ፥አዝዛለሁ፥ ሰው በወንፊት እህል እንደሚነፋ፥ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እነፋለሁ፤ ነገር ግን አንዲትም ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም። 10«ጥፋት አይደርስብንም ወይም አያገኘንም» የሚሉ፤ የሕዝቤ ኃጢአተኞች ሁሉ በሰይፍ ይሞታሉ።11«በዚያን ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሳለሁ፥ ሽንቁሩንም እዘጋለሁ። ፍራሽዋንም አነሳለሁ፥ በቀድሞ ዘመን እንደነበረች እን ደገና እሠራታለሁ፤ 12ይኼውም የኤዶምን ቅሬታ፥ በስሜም የተጠሩትን አሕዛብ ሁሉ ይወርሱ ዘንድ ነው፥ ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።»13እነሆ፥ አራሹ አጫጁ ላይ፥ ወይን ጠማቂው ዘሪው ላይ የሚደርስበት ጊዜ ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። ተራሮቹ ጣፋጩን ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ይፈስባቸዋል።14ሕዝቤን እስራኤልን ከተማረከበት እመልሰዋለሁ። የፈረሱትን ከተሞች ሠርተው ይኖሩባቸዋል፥ ወይንንም ተከለው የወይን ጠጃቸውን ይጠጣሉ፥አትክልትም ተክለው ፍርውን ይበላሉ። 15በምድራቸው ላይ እተክላቸዋለሁ፥ ከሰጠኋቸውም ምድር ከቶውን ዳግመኛ አይነቀሉም» ይላል አምላካችሁ እግዚአብሔር።
1የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፥ መልእክተኛውም በአሕዛብ መካከል ተልኮ፥«ተነሡ! እርሷን ለመውጋት እንነሣ» ብሎአል። 2አነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ታናሽ አደርግሃለሁ፥እጅግ የተናቅህ ትሆናለህ።3አንተ በዓለት ስንጣቂ ውስጥ፥በከፍታ ሥፍራ በሚገኝ ቤት የምትኖር፥ በልብህም «ማን ወደ ምድር ያወርደኛል?» የምትል ሆይ፥የልብህ ኩራት አታልሎሃል። 4እንደ ንስር እጅግ ከፍ ከፍ ብትል እንኳ፥ጎጆህም በከዋክብት መካከል ቢሆን እንኳ፥እኔ ከዚያ አወርድሃለሁ ይላል እግዚአብ ሔር።5ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፥ዘራፊዎች በሌሊት ቢመጡ (አንተ እንዴት ተቆረጥህ!) ፥የሚበቃቸውን ያህል ብቻ የሚሰርቁ አይደለምን? ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ አያስቀሩምን? 6ዔሳው ምንኛ ተበረበረ፥የተደበቀ ሀብቱ ምንኛ ተዘረፈ?7የተማማልሃቸው ሰዎች፥በጉዞህ ወደ ድንበር ይሰድዱሃል።ከአንተ ጋር መልካም ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች አታለሉህ፥አሸነፉህም። እንጀራህን የበሉ ከበታችህ ወጥመድ ዘረጉብህ። በእርሱም ዘንድ ማስተዋል የለም። 8በዚያ ቀን ከኤዶም ጥበበኞችን፥ ከዔሳውም ተራራ ማስተዋልን አላጠፋምን? ይላል እግዚአብሔር። 9ቴማን ሆይ፥ ሰው ሁሉ ከዔሳው ተራራ ታርዶ ይጠፋ ዘንድ፤፡ኃያላንህ ይደነግጣሉ።10በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስለ ተፈጸመ ግፍ፥እፍረት ይከድንሃል፥ለዘላለምም ትጠፋለህ። 11እንግዶች ሀብቱን በዘረፉበት፥ባዕዳንም በበሮቹ በገቡበት፥በኢየሩሳሌምም ላይ ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን፤አንተም ገለልተኛ ሆነህ በቆምህበት ቀን፥ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆነሃል።12ነገር ግን ወንድምህ በገጠመው ክፉ ቀን ሐሴት ማድረግ አይገባህም ነበር፥በጥፋታቸው ቀን በይሁዳ ሕዝብ ላይ መደሰት አይገ ባህም ነበር፤በጭንቀታቸው ቀን ትኩራራ ዘንድ አይገባህም ነበር። 13በጥፋታቸው ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ አይገባህም ነበር፥በጥፋታቸው ቀን በመ ከራቸው ሐሴት ማድረግ አይገባህም ነበር፤በጥፋታቸው ቀን ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር። 14የሸሹትን ለመግደል በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትቆም ዘንድ አይገባህም ነበር፤በጭንቀት ቀን የተረፉለትን አሳልፈህ መስጠት አይገባህም ነበር።15የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና። እንዳደረግኽው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ሥራህ በገዛ ራስህ ላይ ይመለሳል። 16በቅዱስ ተራራዬ ላይ እንደጠጣችሁ፥ አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ። ይጠጣሉ፥ ይጨልጡማል፤ ከዚህ በፊት እንዳልሆኑት ይሆናሉ።17በጽዮን ተራራ ያመለጡ ይገኛሉ፥ እርሱም ቅዱስ ይሆናል፤ የያዕቆብም ቤት የገዛ ራሱን ርስት ይወርሳል። 18የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍ ቤት ነበልባል፥ የዔሳውም ቤት ገለባ ይሆናሉ፤ያቃጥሉታል፥ይበሉታልም። ከኤሳው ቤት የሚተርፍ አይኖርም፥እግዚአብሔር ተናግሮአልና።19የኔጌብ ሰዎች የዔሳውን ተራራ ይወርሳሉ፥የቆላውም ሰዎች፦የፍልስጥኤማውያንን ምድር፥የኤፍሬምን ምድር፥ የሰማሪያንም ምድር ይወርሳሉ፤ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል።20የእስራኤል ሕዝብ ሠራዊት ምርኮኞች የከንዓንን ምድር እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳሉ። በስፋራድም የሚኖሩ የእስራኤል ምርኮኞች የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ። 21በዔሳው ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ ነጻ አውጪዎች ወድ ጽዮን ተራራ ይወጣሉ፤ መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።
1የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፤2«ተነሣና ወደ ታላቋ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፏቷ ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርሷ ላይ ስበክ፡፡»3ዮናስ ግን ከያህዌ ፊት ኮበለለ፤ ወደ ተርሴስ ለመሄድም ተነሣ፡፡ ወደ ኢዮጴ ወረደ፡፡ ወደ ተርሴስ በምትሄድ መርከብ ተሳፈረ፡፡4ያህዌ ግን በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስ ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቧን አናወጠ፤ ወዲያውኑ የምትሰበር መስሎ ታየ፡፡5መርከበኞቹ በጣም ፈሩ፤ እያንዳንዱ ሰው ወደ አምላኩ ጮኸ ፡፡ የመርከቧ ክብደት እንዲቀልል በውስጧ የነበረው ሸክም ወደ ባሕሩ ተጣለ፡፡ ዮናስ ግን ወደ መርከቧ ታችኛ ክፍል ሄዶ ተኛ፤ ከባድ እንቅልፍ ላይም ነበር፡፡6የመርከቧ አዛዥ ወደ እርሱ መጥቶ፣ «እንዴት ትተኛለህ? ተነሥና አምላክህን ጥራ! ምናልባትም አምላክህ ያስበንና ከጥፋት ያድነን ይሆናል፡፡ አለው፡፡7እርስ በርሳቸውም፣ ይህ ክፉ ነገር የደረሰብን በማን ኃጢአት መሆኑን እንድናውቅ ኑ፣ ዕጣ እንጣጣል» ተባባሉ፡፡ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ፡፡8ከዚያም ዮናስን፣ «ይህ ክፉ ነገር የደረሰብን በማን ምክንያት እንደ ሆነ እባክህ ንገረን፡፡ ሥራህ ምንድነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ?» አሉት፡፡9ዮናስም፣ «እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና ደረቁን ምድር የፈጠረውን የሰማይን አምላክ ያህዌን አመልካለሁ» አላቸው፡፡10እርሱ ራሱ ነግሮአቸው ስለ ነበር ከያህዌ ፊት እየኮበለለ እንደ ነበር አወቁ፤ ስለዚህ የበለጠ ፈርተው፣ «ለመሆኑ፣ ምን እያደረግህ ነው?» አሉ፡፡11ባሕሩ ይበልጥ እየተናወጠ በመሄዱ፣ ሰዎቹ ዮናስን፣ «ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን አንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?» አሉት፡፡12ዮናስም፣ «አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ያኔ ባሕሩ ጸጥ ይልላችኃል፤ ይህ ታላቅ ማዕበል የመጣባችሁ በእኔ ምክንያት እንደ ሆነ አውቃለሁ» አላቸው፡፡13ሰዎቹ ግን ወደ መሬት ለመመለስ የሚቻላቸውን ያህል ቀዘፉ፤ ይሁን እንጂ ባሕሩ የባሰ ይናወጥ ጀመረ፡፡14ስለዚህም፣ «ያህዌ ሆይ፣ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት እንዳታጠፋን እንለምንሃለን፤ የዚህ ሰው ሞት እኛ ላይ አይሁንብን፤ ምክንያቱም አንተ ያህዌ የወደድኸውን አድርገሃል» በማለት ወደ ያህዌ ጮኹ፡፡15ዮናስንም አንሥተው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም መናወጡ ቆመ፡፡16ሰዎቹም ያህዌን እጅግ ፈሩ፡፡ ለያህዌ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ለእርሱም ስእለትን ተሳሉ፡፡17እግዚአብሔር ግን ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ዓሣው ሆድ ውስጥ ኖረ፡፡
1ከዚያም ዮናስ ዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ ያህዌ ጸለየ፡፡2እንዲህ አለ፤ «ተጨንቄ ሳለሁ ወደ ያህዌ ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ እርሱ እንዲረዳኝ ከጥልቁ መቃብር ጮኽኩ አንተም ጩኸቴን ሰማህ፡፡3ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕሩ መሠረት ጣልኸኝ፤ ፈሳሾች ዙሪያዬን ከበቡኝ፣ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላየ አለፈ፡፡4እኔም፣ ከፊትህ ጠፋሁ፤ ሆኖም፣ እንደ ገና ወደ ቅዱስ መቅደስህ እመለከታለሁ» አልሁ፡፡5ሕይወቴን ለማጥፋት ውሆች ሸፈኑኝ፤ ጥልቁም በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕር ዐረም ራሴ ላይ ተጠመጠመ፡፡6ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ አንተ ሕይወቴን ከጥልቁ አወጣህ!7ነፍሴ በዛለች ጊዜ ያህዌን አሰብሁት፤ ጸሎቴ ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ መጣ፤፤8ልባቸውን ከንቱ አማልከት ላይ የሚያደርጉ ለእነርሱ ያለህን ጸጋ ያጣሉ፡፡9እኔ ግን፣ በምስጋና መዝሙር መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እፈጽማለሁ፡፡ ድነት ከያህዌ ዘንድ ነው፡፡10ከዚም ያህዌ ዓሣውን አዘዘ ዮናስንም ደረቁ ምድር ላይ ተፋው፡፡
1የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ዮናስ መጣ፤2«ተነሥተህ ወደ ታላቋ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የምነግርህንም መልእክት ስበክላት፡፡»3ስለዚህም ዮናስ ለያህዌ ቃል በመታዘዝ ወደ ነነዌ ሄደ፡፡ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷን ዳር እስከ ዳር ለማዳረስ ሦስት ቀን ይወስድ ነበር፡፡4ዮናስ ወደ ከተማዋ ገባ፤ ከአንድ ቀን ጉዞ በኃላ፣ «ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች» ብሎ ዐወጀ፡፡5የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ጾምንም ዐወጁ፡፡ ከታላቁ እስከ ታናሹ ድረስ ሁሉም ማቅ ለበሱ፡፡6ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ በደረሰ ጊዜ፣ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱን አወለቀ፣ ማቅም ለብሶ ዐመድ ላይ ተቀመጠ፡፡7ከዚያም እንዲህ የሚል ዐዋጅ በነነዌ አስነገረ፤ «በንጉሡና በመኳንንቱ» ሥልጣን ከነነዌ የወጣ ዐዋጅ፤ ሰውም ሆነ እንስሳ፣ የከብት መንጋም ሆነ የበግ ምጋ ምንም ነገር አይቅመስ አይብላ ውሃም አይጣጣ፡፡8ሰውም ሆነ እንስሳ ማቅ ይልበስ፤ አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጮኽ፡፡ ሰው ሁሉ ከክፉ መንገዱ ይመለስ፤ ግፍ መሥራቱንም ይተው፡፡9እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቁጣው ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?»10እግዚአብሔርም ያደረጉትን፣ ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውንም አየ፡፡ በእነርሱ ላይ ሊያመጣ ያሰበውንም ጥፋት አላመጣም፡፡
1ይህ ግን ዮናስን ደስ ስላላሰኘው በጣም ተቆጣ፡፡2እንዲህ በማለትም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ «ያህዌ ሆይ፣ ገና በአገሬ ሳለሁ ያልሁት ይህንኑ አልነበረምን? አንተ ቸርና ርኅሩኅ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየህ ምህረትህም የበዛ፣ ጥፋትን ከማምጣት የምትመለስ አምላክ መሆንህን ስለማውቅ ወደ ተርሴስ ለመኮብለል የሞከርኩት በዚሁ ምክንያት ነበር፡፡3አሁንም ያህዌ ሆይ፣ ሕይወቴን እንድትወስድ እለምንሃለሁ፣ በሕይወት ከመኖር መሞት ይሻለኛል» አለ፡፡4ያህዌ ግን፣ «መቆጣትህ ተገቢ ነውን?» አለው፡፡5ከዚያም ዮናስ ከከተማዋ ወጥቶ በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፡፡ በዚያም ለራሱ ዳስ ሠርቶ በከተማዋ የሚደርሰውን ለማየት ከጥላው ሥር ተቀመጠ፡፡6ያህዌ አምላክም አንድ ተክል አብቅሎ፣ የዮናስ ራስ ጥላ እንዲሆንና ትኩሳቱም እንዳያስጨንቀው ከበላዩ እንዲያድግ አደረገ፤ ዮናስም ስለ ተክሉ በጣም ደስ አለው፡፡7ነገር ግን በሚቀጥለው ጠዋት ፀሐይ ስትወጣ አንድ ትል አዘጋጅቶ ያንን ተክል እንዲያጠቃ አደረገ፤ ተክሉም ጠወለገ፡፡8ፀሐይ ስትወጣ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አመጣ፡፡ ፀሐዩ የዮናስንም ራስ አቃጠለ እርሱም ተዝለፈለፈ፡፡ ያኔ ዮናስ መሞት ፈልጐ፣ «ከመኖር መሞት ይሻለኛል» አለ፡፡9እግዚአብሔርም ዮናስን፣ «ስለ ተክሉ መቆጣትህ ተገቢ ነውን?» አለው፡፡ ዮናስም፣ «አዎን፣ እንዲያውም እስከ ሞት ድረስ መቆጣት ይገባኛል» አለ፡፡10ያህዌ እንዲህ አለ፣ «አንተ እንዲበቅል ወይም እንዲያድግ ላልደከምህበት ተክል ይህን ያህል አዝነሃል፤ በአንድ ሌሊት በቀለ፤ በአንድ ሌሊትም ደረቀ፡፡11ታዲያ፣ እኔ ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር የማይችሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ በላይ ሰዎችና እንስሶች ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን የለብኝምን? ፡፡»
1በይሁዳ ንጉሦች በአዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የያህዌ ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፡፡2እናንት ሕዝቦች ስሙ ምድርና በውስጧ የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፡፡ ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣ ጌታ ያህዌም ይመሰክርባችኃል፡፡3ተመልከቱ፤ ያህዌ ከመኖሪያው ስፍራ ይመጣል፤ ‹ወርዶም፣ በምድር ከፍታዎች ላይ ይራመዳል፡፡4ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ ሸለቆዎች ይሰነጠቃሉ እሳት ፊት እንዳለም ሰም በገደል ላይ እንደሚወርድ ውሆች ይሆናሉ፡፡5ይህ ሁሉ የሚሆነው ከያዕቆብ ዐመፅ ከእስራኤልም ቤት ኃጢአት የተነሣ ነው፡፡ የያዕቆብ ዐመፅ ምክንያት ምን ነበር? ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ ኮረብታ መስገጃ ምንድው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?6ስለዚህ ሰማርያን ሜዳ ላይ እንዳለ ፍርስራሽ ክምር፣ ወይን እንደሚተከልባትም ቦታ አደርጋታለሁ፡፡ የከተማዋን ፍርስራሽ ድንጋይ ወደ ሸለቆው አወርዳለሁ፤ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ፡፡7ምስሎቿ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ ለእርሷ የተሰጡ ስጦታዎችም ይቃጠላሉ፡፡ ጣዎቶችዋም ሁሉ ለጥፋት ይሆናሉ፡፡ እነዚህን የሰበሰበችው ለዝሙት ሥራዋ ካገኘችው ገጸ በረከት እንደ ነበር ሁሉ አሁንም ገጸ በረከትዋ የዝሙት አዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል፡፡8በዚህ ምክንያት ዋይ ዋይ እያልሁ አለቅሳለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ እንደ ጉጉትም አለቅሳለሁ፡፡9ቁስሏ የማይፈወስ ነውና ለይሁም ተርፏል፡፡ ወደ ሕዝቤ ደጅ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ደርሷል10በጌት አታውሩ፣ ከቶም አታልቅሱ በቤትዓፍራ ትቢያ ላይ እንከባለላለሁ11እናንት በሻፊር የምትሮሩ ዕርቃናችሁን ሆናችሁ እለፉ፡፡ በጸዓናን የሚኖሩ ከዚያ አይወጡም፡፡ ቤትዔጼል ሐዘን ላይ ስለሆነች መጠጊያ ልትሆን አትችልም፡፡12የማሮት ነዋሪዎች መልካም ዜና ለመስማት እጅግ ጓጉተዋል፤ ምክንያቱም ከያህዌ ዘንድ ጥፋት እስከ ኢየሩሌም ደጆች መጥቷል፡፡13እናንት በለኪሶ የምትኖሩ የሰረገሎችን ፈረሶች ለጉሙ፣ ለጽዮን ሴት ልጅ ኃጢአት መጀመሪያ እናንተ ነበራችሁ፡፡ የእስራኤልም በደል አንተ ዘንድ ተገኝቷል፡፡14ስለዚህ እናንተ ለሞሬሴት ጌት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጣላችሁ፤ የአክዚብም ከተሞች የእስራኤልን ንጉሦች ያታልላሉ፡፡15እናንት በመሪሳ የምትኖሩ ወራሪ አመጣባችኃለሁ፡፡ የተከበሩ የእስራኤል መሪዎች በዓዶላም ዋሻ ይሸሸጋሉ፡፡16ደስ ትሰኙባቸው ለነበሩ ልጆቻችሁ በማዘን ራሳችሁን ተላጩ ጡራችሁን ተቆረጡ ራሳችሁን እንደ ንስር ራስ ተመለጡት ምክንያቱም ልጆቻችሁ በምርኮ ከእናንተ ይወሰዳሉና፡፡
1ክፉ ነገር ለማድረግ ለሚያቅዱ መኝታቸው ላይ ሆነው ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው፡፡ ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን ሥራ ላይ ያውሉታል፡፡2የዕርሻ ቦታ ሲፈልጉ፣ ቀምተው ይወስዳሉ ቤት ሲፈልጉ ነጥቀው ይወስዳሉ፡፡ የሰው መብት ረግጠው ሀብቱን ይዘርፋሉ3ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት አመጣለሁ ከዚህም ልታመልጡ አትችሉም፡፡ ያ የመከራ ጊዜ ስለሚሆን ከእንግዲህ በእብሪት አትኖሩም፡፡4በዚያ ቀን ጠላቶቻችሁ ይሳለቁባችኃል በሐዘን እንጉርጉሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኃል እኛ እስራኤላውያን ፈጽሞ ጠፍተናል ያህዌ የሕዝቤን ንብረት ወስዶ ርስታችንንም ለከሐሂዲዎች አከፋፈለ5ስለዚህ እናንተ ባለጸጐች በያህዊ ጉባኤ ውስጥ ርስት በዕጣ የሚከፋፈሉ ልጆች አይኖሯችሁም፡፡6«ትንቢት አትናገር» ምንም ውርደት አይደርስብንም፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር ይላሉ፡፡7የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ እንደህ መባል ነበረበትን? የያህዌ ትዕግሥት አልቋልን? እነዚህስ የእርሱ ድርጊቶች ናቸውን? አካሄዳቸው ቀና ለሆነ ሰዎች ቃሎቼ መልካም አያደርጉምን?8በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ በጠላትነት ተነሥታችኃል ከጦርነት በኃላ ሰላም ነው ብለው ወደሚያስቡት እንደሚመለሱ ወታደሮች ምንም ሳይጠራጠሩ የሚያልፉ ሰዎችን ልብስ ገፋችኃል፡፡9የወገኔን ሴቶች ከሚወዱት ቤታቸው አባረራችሁ በረከቴን ለዘላለም ከልጆቻቸው ወሰዳችሁ፡፡10በርኩሰት ምክንያት ከባድ ጥፋት ስለሚመጣ እዚህ ቦታ መቆየት አትችሉም፤ ስለዚህ ተነሥታችሁ ሂዱ፡፡11አንድ ሰው በሐሰት መንፈስ ተነሣሥቶ «ስለ ወይን ጠጅና ጠንካራ መጠጥ ትንቢት እናገራለሁ» ቢል፤ በእነዚህ ሰዎች ዘንድ እንደ ነቢይ ይቆጠራል፡፡12ያዕቆብ ሆ በእርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልን ትሩፍ ጉረኖ ውስጥ እንዳለ በጐች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ አመጣቸዋለሁ፡፡ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታላቅ ጩኸት ይሆናል፡፡13መንገዳቸውን የሚከፍትላቸው መሪ ከእነርሱ ፊት ፊት ይሄዳል እነርሱም ተግተልትለው በበሩ ይወጣሉ ንጉሣቸው ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ ያህዌ መሪያቸው ይሆናል፡፡
1ከዚያም እኔ እንዲህ አልሁ፤ «እናንተ የያዕቆብ መሪዎች የእስራኤልም ቤት ገዦች አድምጡ፤ ፍትሕን ማወቅ ይገባችሁ አልነበረምን?2እናንተ ግን መልካሙን ጠላችሁ ክፉን ወደዳችሁ ቆዳቸውን ገፈፋችሁ ሥጋቸውን ከአጥንታቸው ጋጣችሁ የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ ቆዳቸውን ገፈፋችሁ ዐጥንቶቻቸውን ሰባበራችሁ፤ በመጥበሻ እንደሚጠበስ በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቆራረጣችኃቸው፡፡3እናንተ መሪዎች ወደ ያህዌ ትጮኻላችሁ እርሱ ግን አይሰማችሁም፡፡ ከክፉ ሥራችሁ የተነሣ በዚያ ጊዜ ፊቱን ከእናንተ ይሰውራል፡፡4ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት ያህዌ እንዲህ ይላል፤5«ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን፣ «ብልጽግና ይሆናል» ይላሉ፤ ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ግን፣ ‹ጦርነት ይመጣባችኃል› እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፡፡6ስለዚህ ራእይ የማታዩበት ሌሊት ይሆንባችኃል ሌሊት ስለሚሆንባችሁ ንግርት አታደርጉም፡፡ በነቢያት ላይ ፀሐይ ትጠልቅባቸዋለች ቀኑ እነርሱ ላይ ይጨልማል፡፡7ባለ ራእዮች ያፍራሉ ንግርተኞችም ይዋረዳሉ ከእኔ ዘንድ መልስ የለምና ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍናሉ፡፡8እኔ ግን፣ ለያዕቆብ በደሉን ለእስራኤል ኃጢአቱን እንድናገር በያህዌ መንፈስ ኃይል ተሞልቻለሁ ፍትሕና ብርታትንም ተሞልቻለሁ፡፡9እናንት የያዕቆብ ቤት መሪዎች ፍትሕ የምትጠሉ፣ ቀና የሆነውን የምታጣምሙ የእስራኤል ቤት ገዦች ይህን ስሙ፡፡10ጽዮንን ደም በማፍሰስ ኢየሩሳሌምን በርኩሰት የምትገነቡ ስሙ11መሪዎቻችሁ በጉቦ ይፈርዳሉ ካህናቶቻችሁ በዋጋ ያስተምራሉ ነቢያቶቻችሁ በገንዘብ ንግርት ይናገራሉ፡፡ ያም ሆኖ በያህዌ በመተማመን፣ «ያህዌ ከእኛ ጋር ስለሆነ ክፉ ነገር አይደርስብንም» ይላሉ፡፡12ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች የቤተ መቅደሱ ኮረብታ ጥቅጥቅ ያለ ደን ይሆናል፡፡
1በመጨረሻው ዘመን የያህዌ ቤት ተራራ ሌሎች ተራቶች ላይ ይመሠረታል ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ይላል ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ፡፡ ብዙ ሕዝቦች መጥተው እንዲህ ይላሉ2«ኑ ወደ ያህዌ ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንሂድ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል እኛም በመንገዱ እንሄዳለን፡፡ ሕግ ከጽዮን፣ የያህዌም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣል፡፡3እርሱ በብዙ ሕዝብ መካከል ይፈርዳል በሩቅ ባሉ ሕዝቦችም ላይ ይበይናል፡፡ ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጉታል፡፡ መንግሥት በመንግሥት ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ከእንግዲህ የጦር ትምህርት አይማሩም፡፡4ይልቁን፣ እያንዳንዱ ሰው ከገዛ ወይኑ ሥር ከገዛ በለሱም ሥር ይቀመጣል፡፡ የሰራዊት አምላክ ያህዌ ተናግሮአልና የሚያስፈራቸው አይኖርም፡፡5ሕዝቦች ሁሉ በአምላኮቻቸው ስም ይሄዳሉ፡፡ እኛ ግን በአምላካችን በያህዌ ስም ለዘላለም እንሄዳለን6በዚያ ቀን ይላል ያህዌ፣ አንካሳውን እሰበስባለሁ ስደተኞችና ሐዘንተኞች ያደረግኃቸውን እሰበስባለሁ፡፡7አንካሳውን ወደ ተረፉት ወገኖች የተገፉትንም ወደ ብርቱ ሕዝብ እመልሳለሁ፤ እኔ ያህዌ በጽዮን ተራራ ከዘላለም እስከ ዘላለም እነግሣለሁ፡፡8አንተ የመጠበቂያው ማማ፣ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ የቀድሞው ግዛትህ፣ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ይመለስልሃል፡፡9አሁንስ እንደዚህ የምትጮኺው ለምንድነው? በመካከልሽ ንጉሥ የለምን? ምጥ እንደ ያዛት ሴት የምትጨነቂው መካሪሽ ስለጠፋ ነውን?10የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ምጥ እንደያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁን ከከተማ ወጥተሸ ሜዳ ላይ ስፈሪ ወደ ባቢሎንም ትሄጃለሽ፡፡ በዚያም ከጠላት እጅ ትድኛለሽ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ ይታደግሻል፡፡11አሁን ግን፣ ብዙ ሕዝቦች አንቺ ላይ ተሰብስበዋል እነርሱም፣ «የረከሰች ትሁን፤ እኛም መፈራረስዋን እንይ» ብለዋል፡፡12ነቢዩ እንዲህ ይላል፤ «የያህዌን ሐሳብ አያወቁም የእርሱንም ዕቅድ አያስተውሉም፤ እርሱ ዐውድማ ላይ እንደ ነዶ ይሰበስባቸዋል፡፡»13ያህዌ እንዲህ ይላል፤ «ቀንድሽን እንደ ብረት፣ ሰኮናሽን እንደ ናስ አደርጋለሁ ብዙ ሕዝቦችን ታደቂያለሽ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ተነሥተሸ አበራዪ፡፡ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብት ለራሴ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ አቀርባለሁ፡፡»
1አንቺ የወታደር ከተማ ሰራዊትሽን አሰልፊ ከበባ ተደርጐብናልና የእስራኤልን ገዥ ጉንጩን በበትር ይመቱታል፡፡2አንቺ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፣ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ ጅማሬው ከጥንት ከዘላለም ዘመናት የሆነ የእስራኤል ገዥ ከአንቺ ይወጣልኛል፡፡3ስለዚህ ያማጠችው ልጅ እስክትወልድ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ይተዋቸዋል የተቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ፡፡4በያህዌ ብርታት፣ በአምላኩ በያህዌ ስም ክብር ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል፡፡ በዚያ ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ ተደላድለው ይኖራሉ፡፡5እርሱ ሰላማችን ይሆናል፡፡ አሦራውያን ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ምሽጐቻችንም ሲገሠግሡ ሰባት እረኞችን፣ እንዲሁም ስምንት መሪዎችን እናስነሣባቸዋልን፡፡6እነዚህ ሰዎች የአሦርን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩዱንም ምድር እጃቸው ላይ ባለው ሰይፍ ይገዛሉ፡፡ ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ድንበራችንም ሲገሠግሡ እርሱ ከአሦራውያን ይድነናል፡፡7የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝብ መካከል ከያህዌ ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣ ሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ ሰውን እንደማይጠብቅ፣ በሰው ልጆችም እንደማይተማመን ሰው ይሆናል፡፡8የያዕቆብ ትሩፍ በሕዝቦች መካከል፣ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይሆናል፤ በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በበጐች መካከል እንዳለ አንበሳ ደቦል ይሆናል፡፡ በእግሩ እየረጋገጠ ይቦጫጭቃቸዋል፤ የሚያድናቸውም አይኖርም፡፡9እጅህ በጠላቶችህ ላይ ከፍ ከፍ በማለት ያጠፋቸዋል፡፡10በዚያ ቀን ይላል ያህዌ «ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ ሠረገሎቻችሁንም እደመስሳለሁ፡፡11የምድራችሁን ከተሞች አጠፋለሁ ምሽጐቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ፡፡12በምድራችሁ ያለውን ጥንቆላ አጠፋለሁ ከእንግዲህ አታሟርቱም፡፡13የተቀረጹ ምስሎቻችሁንና የድንጋይ ዐምዶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፡፡ ከእንግዲህ የእጆቻችሁን ሥራ አታመልኩም፡፡14የአሼራ ምሰሶዋችሁን ከምድራችሁ እነቅላለሁ ከተሞቻችሁንም አጠፋለሁ፡፡15ያልታዘዙኝን ሕዝቦች በቀጣዬና በመዓቴ እበቀላሁ፡፡»
1እንግዲህ ያህዌ የሚናገረውን አድምጡ፤ «ተነሡ፤ ያላችሁንም ቅርታ በተራሮች ፊት አቅርቡ ኮረብቶችም የምትሉትን ይስሙ፡፡2እናንተ ተራሮች እናንተ ጸንታችሁ የቆማችሁ የምድር መሠረቶች ያህዌ የሚያቀርበውን ክስ አድምጡ፤ እርሱ ከእስራኤል ጋር ይፋረዳል፡፡»3«ሕዝቤ ሆይ፣ ምን አደረግሁህ? ያታከትሁህስ በምንድነው? እስቲ መስክርብኝ!4እኔ ከግብፅ ምድር አወጣሁህ ከባርነት ቤትም ታደግሁህ፡፡ ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን ወደ አንተ ላክሁ፡፡5ሕዝቤ ሆይ፣ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደብህን የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፣ ከሺጡም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ ስትሄድ፣ እኔ፣ ያህዌ ያደረግሁትን የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ አስታወስ፡፡6ለልዑል አምላክ ለመስገድ በምመጣበት ጊዜ፣ ለያህዌ ምን ይዤ ልምጣ? የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲሆኑ የአንድ ዓመት ጥጃ ይዤ ልምጣን?7በሺህ የሚቆጠሩ ዐውራ በጐችን ወይስ የአሥር ሺህ ወንዞች የሚያህል ዘይት ባቀርብለት ያህዌ ይደሰት ይሆን? ስለ መተላለፌ የበኩር ልጄን፣ ስለ ኃጢአቴስ የአካሌን ፍሬ ልስጥን?8ሰው ሆይ፣ መልካሙን፣ ያህዌ ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል ፍትሕ አድርግ፤ ደግነትን ውደድ፤ ከአምላክህ ጋር በትሕትና ተመላለስ፡፡9የያህዌ ድምፅ ከተማዋን ይጣራል አሁን እንኳ ጥበብ ስምህን ትገነዘባለች በትሩን አስታውስ፤ በቦታው ያደረገው ማን እንደ ሆነ አስታውስ፡፡10ክፉው ቤት ውስጥ በግፍ የተገኘ ሀብት አስጸያፊ የሆነ ሐሰተኛ መስፈሪያ አለ፡፡11ዐባይ ሚዛን የሚጠቀመውን ሰው፣ ሐሰተኛ መመዘኛ በከረጢት የቋጠረውን ሰው ንጹሕ ላድርገውን?12ባለ ጠጐች በግፍ ተሞልተዋል በዚያ የሚኖሩ ሐሰት ተናግረዋል ምላሳቸው አታላይ ናት፡፡13ስለዚህ በጽኑ ቁስል መታሁህ ከኃጢአትህ የተነሣም አፈረስሁህ፡፡14ትበላለህ ግን አትጠግብም ሁሌም ባዶነት ውስጥህ ይኖራል፡፡ ታከማቻለህ ግን አይጠራቀምልህም ያጠራቀምኸውን ለሰይፍ እዳርጋለሁ፡፡15ትዘራለህ ግን አታጭድም የወይራ ፍሬ ትጨምቃለህ፤ ግን ዘይት አትቀባም፤ ወይን ትጨምቃህ ግን ጠጅ አትጠጣም፡፡16የዖምሪን ሥርዐት የአክዓብን ቤት ተግባርም አጥብቀህ ይዘሃል በምክራቸው መሠረት ኖረሃል፡፡ ስለዚህ አንተንና ከተማህን ለውድመት ሕዝብህንም ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ ትሸከማለህ፡፡
1ለእኔ ወዮልኝ! የመከር ጊዜ ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ካበቃ በኃላ እርሻ ውስጥ እንደ ቀረው ፍሬ ሆኛለሁ ከዚያ የሚበላ ወይን ፍሬ አይገኝም የምጓጓለትና ቶሎ ቀድሞ የሚደርሰው በለስ አይኖርም፡፡2ከምድሩ ታማኝ ሰዎች ጠፍተዋል በሰው ልጆች መካከልም ቅን ሰው የለም፡፡ ሁሉም ደም ለማፍሰስ ያደባል እያንዳንዱም የገዛ ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል፡፡3እጆቻቸው ሌሎችን ለመጉዳት ሠልጠነዋል፤ ገዦቻቸው ገንዘብ ይፈልጋሉ ፈራጁ ጉቦ ይጠብቃል፤ ኃይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ፡፡4ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜኬላ እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኩርንችት ነው፡፡ ነቢያቶቻችሁ አስቀድመው የተናገሩለት ቀን እናንተ የምትቀጡበት ቀን ነው፡፡ የሚሸበሩበት ቀን ደርሶአል፡፡5ጐረቤትህን አትመን፣ ወዳጅህም ላይ አትተማመን፡፡ በዕቅፍህ ከምትተኛዋ እንኳ ለምትናገረው ተጠንቀቅ፡፡6ወንድ ልጅ አባቱን ያዋርዳል ሴት ልጅ በእናትዋ ላይ ምራት በአማቷ ላይ ትነሣለች፡፡ የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰቦቹ ይሆናሉ፡፡7እኔ ግን ያህዌን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የመድኃኒቴን አምላክ እጠብቃለሁ አምላኬም ይሰማኛል፡፡8ጠላቴ፣ ሆይ ብወድቅ እንኳ በእኔ ደስ አይበልሽ፤ ከወደቅሁበት እነሣለሁ በጨለማ ብቀመጥ እንኳ ያህዌ ብርሃን ይሆንልኛል፡፡9ያህዌን ስለ በደልሁ እርሱ እስኪፈርድልኝ ድረስ ቁጣውን እታገሣለሁ፡፡ እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል በጽድቁ ሲያድነኝም አያለሁ10ጠላቴም ታያለች፣ «አምላክህ ያህዌ የታል?» ያለች ጠላቴ ታፍራለች፡፡ እኔም የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ትረገጣለች፡፡11ቅጥሮቻችሁን የምትሠሩበት ቀን ይመጣል በዚያን ቀን ድንበራችሁ ይሰፋል!12በዚያ ቀን ሕዝባችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል፤ ከአሦርና ከግብፅ ከተሞች ከግብፅ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ከባሕር እስከ ባህር፣ ከተራራ እስከ ተራራ ድረስ ሕዝባችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል፡፡13ከሚኖሩበት ሰዎች ክፋት የተነሣ ምድሪቱ ወና ትሆናለች፡፡14በለመለመ መስክ መካከል ብቻቸውን ዱር ውስጥ ያሉትን የርስትህ መንጋ የሆኑት ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፡፡ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሰንና በገለዓድ አሰማራቸው፡፡15ከግብፅ እንደ ወጣችሁበት ዘመን ድንቆችን አሳያቸዋለሁ፡፡16ኃይል ያላቸው ቢሆኑም አሕዛብ ይህን አይተው ያፍራሉ፤ እጃቸውን አፋቸው ላይ ያደርጋሉ ጆሮዋቸውም ይደነቁራል፡፡17እንደ እባብ፣ ምድር ላይ እንደሚርመሰመሱም ፍጥረቶች ትቢያ ይልሳሉ፡፡ እየተንቀጠቀጡ ከዋሻዎቻቸው ይወጣሉ አምላካችን ያህዌ ሆይ በፍርሃት ወደ አንተ ይመጣሉ ከአንተ የተነሣ ይሸበራሉ፡፡18ኃጢአትን ይቅር የሚል የርስቱንም ትሩፍ መተላለፍ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? የኪዳን ታማኝነትህን ለእኛ ማሳየት ደስ ስለሚልህ አንተ ለዘላለም አትቆጣም፡፡19እንደ ገና ትራራልናለህ፤ ርኩሰታችንን በእግሮችህ ትረግጣለህ፡፡ ኃጢአታችንን ሁሉ ወደ ባሕሩ ጥልቅ ትጥላለህ፡፡20በቀድሞ ዘመን ለአባቶቻችን በመሐላ እንደ ገባኸው ቃል ለያዕቆብ ታማኝነትን፣ ለአብርሃምም የኪዳን ታማኝነትን ትሰጣለህ፡፡
1ስለ ነነዌ የተነገረ ቃል፤ የአልቆሻዊው የናሆም ራእይ መጽሐፍ ይህ ነው፡፡2ያህዌ ቀናተኛና ተበቃይ ነው፤ ያህዌ የሚበቀል በመዓትም የተሞላ አምላክ ነው፡፡ ያህዌ ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ በጠላቶቹም ላይ ቁጣውን ይወርዳል፡፡3ያህዌ ለቁጣ የዘገየ፣ በኃይሉም ታላቅ ነው፤ በምንም ዐይነት ጠላቶቹን ንጹሕ ናችሁ አይልም፡፡ ያህዌ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፤ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው፡፡4ባሕርን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ እርሱ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል፡፡ ባሳንና ቀርሜሎስ ጠውልገዋል፤ የሊባኖስ አበቦችም ረግፈዋል፡፡5ተራሮች በእርሱ ፊት ተናወጡ፤ ኮረብቶችም ቀለጡ፤ ምድር በፊቱ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖሩ ሰዎችም ሁሉ ተናወጡ፡፡6በቁጣው ፊት ማን መቆም ይችላል? ጽኑ ቁጣውንስ ማን መቋቋም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሶአል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጠቁ፡፡7ያህዌ መልካም ነው፤ በመከራ ጊዜም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑበት ታማኝ ነው፡፡8ጠላቶቹን ግን በኃይለኛ ጐርፍ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ወደ ጨለማም ያሳድዳቸዋል፡፡9እናንተ ሰዎች ያህዌ ላይ የምታሤሩት ምንድነው? እርሱ ፈጽሞ ያጠፋዋል፤ መከራም ዳግመኛ አይነሣም፡፡10እንደ እሾኽ ይጠላለፋሉ፤ በወይን ጠጃቸውም ይሰክራሉ፤ እሳት እንደ ገለባ ይበላቸዋል፡፡11ነነዌ ሆይ፣ ያህዌ ላይ የሚያሤር፣ ክፉ ምክር የሚመክር ከመካከላችሁ ወጥቷል፡፡12ያህዌ እንዲህ ይላል፤ «ኅይለኞችና ቁጥራቸውም እጅግ የበዛ ቢሆን እንኳ ተቆርጠው ይጠፋሉ፤ ከእንግዲህም ሕዝባቸው አይኖም፡፡ ይሁዳ ሆይ፣ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ ከእንግዲህ አላስጨንቅህም፡፡13አሁንም ቀንበራቸውን ከአንተ ላይ እሰብራለሁ፤ ስንሰለትህንም በጥሼ እጥላለሁ፡፡14ነነዌ ሆይ፣ ስለ አንቺ ያህዌ እንዲህ ብሎ አዝዞአል፤ «ስም የሚያስጠራ ትውልድ አይኖራችሁም፡፡ የተቀረጹ ምስሎችና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶችን ከአማልክቶቻችሁ ቤት አጠፋለሁ፡፡ እጅግ ክፉ ነህና መቀበሪያህን እምስልሃለሁ፡፡15የምሥራችን የሚያመጣና ሰላምን የሚያውጅ ሰው እግር በተራራው ላይ ናቸው! ይሁዳ ሆይ፣ በዓላትህን አክብር፤ ስእለትህንም ፈጽም፤ ከእንግዲህ ክፉዎች አይወርሩህም፤ እነርሱ ፈጽሞ ይጠፋሉ፡፡
1እስክትደቅቂ ድረስ የሚረግጥሽ እርሱ እየመጣ ነው፡፡ ስለዚህ ምሽጐችሽን አጠናክሪ መንገድሽን ጠብቂ፤ ወገብሽን ታጠቂ፤ ኃይልሽን ሁሉ አሰባስቢ፡፡2አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣ የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ ያህዌ የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል፡፡3የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፣ ተዋጊዎቹም ሐምራዊ ልብስ ለብሰዋል ዝግጁ በሆኑበት ቀን የሰረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል፡፡4ሰረገሎቹ በየመንገዱ ይከንፋሉ፤ ሰፋፊ በሆኑት መንገዶች በፍጥነት ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡ የሚንቦገቦግ ችቦ ይመስላሉ፤ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ፡፡5እስክትደቂ ድረስ የሚረግጥሽ እርሱ የጦር ሹማምንቱን ይጠራል እነርሱም እየተደነቃቀፉ ወደ ፊት ይመጣሉ፣ ለማጥቃት ወደ ከተማ ቅጥር ይወጣሉ፤ የሚወረወርባቸውን ፍላጻ በትልቁ ጋሻቸው ይከላከላሉ፡፡6በወንዙ በኩል ያሉ በሮች ወለል ብለው ይከፈታሉ ቤተ መንግሥቱም ተደመሰሰ፡፡7ንግሥቲቱ ተማርካ ዕርቃኗን ተወሰደች ሴት አገልጋዮቿ ደረታቸውን እየደቁ እንደ ርግብ ያላዝናሉ፡፡8ነነዌ ውሃ መያዝ እንደማይችል ኩሬ ናት፤ ሕዝቧም እንደ ፈጣን ወራጅ ውሃ ፈጥኖ ይሸሻል፡፡ ሌሎች «ቁሙ ቁሙ» ብለው ይጮኻሉ ዞር ብሎ የሚያይ ግን የለም፡፡9የነነዌ ሀብት ስፍር ቁጥር የለውም የከበሩ ድንጋዮቿ የተትረፈረፉ ናቸው ስለዚህ ብሩን ዝረፉ፣ ወርቁንም ንጠቁ፡፡10ነነዌ ባዶ ሆነች፣ ተራቆተች፡፡ የሰዎች ልብ ቀለጠ፤ የሰው ሁሉ ጉልበት ተብረከረከ ሁሉም ተጨንቀዋል፤ ፊታቸው ገርጥቷል፡፡11የአንበሶች ዋሻ፣ የአንበሳ ደቦሎች የሚመገቡበት፣ ወንድ አንበሳና እንስት አንበሳ ምንም ሳይፈሩ ወዲያ ወዲህ ይሉበት የነበረ ቦታ የታል?12አንበሳ ለግልገሎቹ የሚበቃውን ያህል ገደለ፤ ለእንስቶቹ የሚበቃውንም ያህል አድኖ ያዘ የገደለውን በዋሻው፣ የነጠቀውንም በመኖሪያ ቦታው ሞልቶአል፡፡13የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ሰረገሎችን አቃጥላለሁ፤ ደቦል አንበሶችህን ሰይፍ ይበላቸዋል፡፡ የዘረፍኸውን ከምድርህ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ የመልእክተኞችህ ድምፅ አይሰማም፡፡»
1ደም ለሞላባት ከተማ ወዮላት! ሐሰትና የተዘረፈ ንብረት ሞልቶበታል፡፡2አሁን ግን የአላንጋ ድምፅና የመንኰራኩር ኳኳታ ድምፅ፣ የፈጣን ፈረስ ኮቴ፣ የሰረገሎች መንጓጓት ይሰማል፡፡3የሚያብረቀርቅ ሰይፍና የሚያንጸባርቅ ጦር የያዙ ፈረሰኞች ጥቃት ያደርሳሉ፤ የሞተው ብዙ ነው፤ ሬሳ በሬሳ ተከምሮአል እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ አጥቂዎቹ በሞቱት ሰዎች ሬሳ ይሰናከላሉ፡፡4ይህ ሁሉ የሆነው ገደብ በሌለው የአመንዝራዋ ፍትወት ምክንያት ነው፤ እርሷ በዝሙቷ መንግሥታን፣ በጥንቆላዋም ሕዝቦችን ባሪያ አድርጋለች፡፡5የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ «እኔ በጠላትነት ተነሥቼብሻለሁ ዕርቃንሽን ለሕዝቦች፣ ኅፍረተ ሥጋሽን ለመንግሥታት አሳያለሁ፡፡6በጣም የሚያስጸይፍ ቆሻሻ እደፋብሻለሁ፤ እንቅሻለሁ፤ ሰው ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ፡፡7የሚያይሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሸ፣ «ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል? የሚያጽናናትንስ ከወዴት አገኛለሁ?» ይላል፡፡8ነነዌ ሆይ፣ ለመሆኑ አንቺ ዐባይ ወንዝ አጠገብ ከተሠራችውና በውሃ ከተከበበችው፣ ወንዙ መከላከያ፣ ባሕሩ ራሱ ቅጥራ ከሆነለት ከቴብስ ትበልጫለሽን?9ኢትዮጵያና ግብፅ ወሰን የለሽ ኃይሏ ነበሩ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ፡፡10ያም ሆኖ፣ ቴብስ ተጋዘች፤ በምርኮም ተወሰደች ሕፃናቷ በየመንገዱ ማእዘን ላይ ተፈጠፈጡ፤ በመኳንንቷ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ፡፡11አንቺ ደግሞ ትሰክሪያለሽ መደበቅ ትሞክሪያለሽ ከጠላቶችሽ መሸሸጊያም ትፈልጊያለሽ፡፡12ምሽጐችሽ ሁሉ ቀድሞ እንደ ደረሰ፣ ሲነቀነቅ በላተኛው አፍ ውስጥ እንደሚወድቅ የበለስ ፍሬ ሆነዋል፡፡13ወታደሮችሽ እንደ ሴት ፈሪዎች ሆነዋል የምድርሽ በሮች ወለል ብለው ለጠላቶችሽ ተከፍተዋል፡፡ መዝጊያዎቻቸውን እሳት በልቷቸዋል፡፡14ለከበባው ውሃ ቅጂ፣ ምሽጐችሽን አጠናክሪ፤ ጭቃ ረግጠሸ የሸክላ መሥሪያ አዘጋጂ፤ ጡብም ሥሪ፡፡15በዚያ እሳት ይበላሻል፤ ሰይፍ ያጠፋሻል፤ አንበጣ ማንኛውንም ነገር እንደሚጠፉ ያጠፋሻል፡፡ ስለዚህ እንደ አንበጣ እርቢ እንደ ኩብኩባም ተባዢ፡፡16ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይበልጥ አብዝተሻል፤ ይሁን እንጂ፣ ምድሪቱን እንደ አንበጣ ጋጡ፤ ከዚያም በርረው ሄዱ፡፡17መኳንንቶችሽ የአንበጦችን ያህል ብዙ ናቸው፣ የጦር መሪዎችሽ በብርድ ቀን ቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ የኩብኩባ መንጋ ናቸው፡፡ ፀሐይ ሲወጣ ግን በርረው ይሄዳሉ፤ የት እንደሚሄዱም አይታወቅም፡፡18የአሦር ንጉሥ ሆይ፣ እረኞችህ አንቀላፉ መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፡፡ ሕዝብህ ሰብሳቢ አጥተው በየተራሮች ተበትነዋል፡፡19ቁስልህን መፈወስ የሚችል የለም፤ ቁስልህ እጅግ ጽኑ ነው፡፡ ስለ አንተ የሚሰማ ሁሉ በውድቀትህ ደስ ብሎት ያጨበጭባል፡፡ ወሰን ከሌለው ጭካኔህ ማን ያመለጠ አለ?
1ነቢዩ ዕንባቆም የተቀበለው መልእክት፤2«ያህዌ ሆይ፣ ለርዳታ ወደ አንተ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? «ግፍ በዛ!» በማለት ወደ አንተ ጮኽሁ፤ አንተ ግን አላዳንኸኝም፡፡3ርኩሰትና በደልን ለምን እንዳይ አደረግኸኝ? ጥፋና ዐመፅ በፊቴ ናቸው፤ ፀብና ጭቅጭቅም እየበዛ ነው!4ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፤ ፍትሕ ተዛብቶአል፡፡ ክፉዎች ጻድቃንን ከብበዋል ስለዚህ ፍርድ ተጣሟል፡፡» ያህዌ እንዲህ በማለት ለዕንባቆም መለሰ5«ቢነገራችሁ እንኳ የማታምኑትን አንድ ነገር በዘመናችሁ ስለማደርግ፣ ልብ አድርጋችሁ አሕዛብን እዩ፤ ተመልከቱ፤ እጅግም ተደነቁ፡፡6ጨካኞቹንና ችኩሎቹን ከለዳውያንን ላስነሣ ነው፤ የራሳቸው ያልሆኑ ቤቶችን ለመውሰድ በምድሪቱ ስፋትና ርዝመት ይገሠግሣሉ፡፡7እነርሱ አስፈሪና አስደንጋጭ ናቸው፤ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል፡፡8ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች፣ ከማታም ተኩላ ይልቅ፣ አስፈሪዎች ናቸው፡፡ ፈረሶቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኩል ንስር ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፡፡9ሁሉም ለዐመፅ ሥራ ይመጣሉ፤ ሰራዊታቸው እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ይገሠግሣል፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባል፡፡10ነገሥታት ላይ ይሳለቃሉ፤ ገዥዎች ላይ ያፌዛሉ፡፡ በምሽጐች ላይ በመሳቅ ዐፈር ቆልለው ይይዟቸዋል፡፡11ከዚያም እንደ ነፋስ አልፈው ይሄዳሉ፤ ጉልበታቸውን አምላካቸው ያደረጉ እነዚያን በደለኞች ይጠራርጋቸዋል፡፡ ዕንባቆም ለያህዌ ያቀረበው ሌላው ጥያቄ12አንተ የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ፣ አንተ ከዘላለም ጀምሮ ያለህ አይደለህምን? እኛ አንሞትም፡፡ እንዲፈርዱ ያህዌ ሾሟቸዋል፤ አንተ ዐለት ሆይ፣ ይቀጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጠሃቸው፡፡13ዐይኖችህ እጅግ የነጹ በመሆናቸው ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ዝም ብለህ አታይም፤ ታዲያ፣ እነዚያን ዐመፀኞች ለምን ዝም ብለህ ትመለከታለህ? ዐመፀኛው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሰው ሲውጠውስ ለምን ዝም ትላለህ?14ሰዎችን ባሕር ውስጥ እንዳለ ዓሣ፣ መሪ እንደሌላቸው በደረታቸው እየተሳቡ እንደሚሄዱ ፍጥረታት የምታደርጋቸው ለምንድነው?15ዓሣ በመንጠቆ እንደሚያዝ ሁሉንም በመንጠቆ ይይዟቸዋል፤ ሰዎችን በመረቦቻቸው ይዘው ይሰበሰቧቸዋል፡፡ ደስ የሚሰኙትና ሐሤት የሚያደርጉት ከዚህ የተነሣ ነው፡፡16የስቡ እንስሳት ድርሻዎቻቸው፣ የጣፈጠውም ሥጋ ምግባቸው ሆናልና ስለዚህ ለመረቦቻቸው ይሠዋሉ፤ ለአሸክላዎቻቸውም ያጥናሉ፡፡17ታዲያ፣ መረቦቻቸውን ባዶ እያደረጉ፣ ያለ አንዳች ርኅራኄ ሕዝቦችን መግደል መቀጠል አለባቸውን?»
1በጥበቃ ቦታዬ እቆማለሁ፤ በመጠበቂያው ግንብ ላይ ቦታዬን እይዛለሁ፤ ምን እንደሚለኝና ለጥያቄዬ ምን መልስ እንደሚሰጥ እጠባበቃለሁ፡፡2ያህዌ እንዲህ በማለት መለሰልኝ፤ «ይህን ራእይ ጻፈው፤ በቀላሉ እንዲነበብ አድርገህም በጽላት ቅረጸው፡፡3ራእዩ የሚናገረው ገና ወደ ፊት ስለሚሆነው ነው፡፡ በመጨረሻም ይፈጸማል እንጂ፣ በፍጹም አይዋሽም፡፡4ተመልከት! ጠማማ ሐሳብ ያለው ሰው ታብዮአል፡፡ ጻድቁ ግን በእምነቱ ይኖራል፡፡5ዐርፎ እንዳይቀመጥ ወይን ጠጅ ዕብሪተኛውን ወጣት አስቶታል ይልቁን ምኞቱን እንደ መቃብር አስፍቶአል እንደ ሞት በቃኝ ማለትን አያውቅም፡፡ ሕዝቦችን ሁሌ ወደ ራሱ ይሰበስባል ሰዎችንም ሁሉ ማርኮ ይወስዳል፡፡6ታዲያ፣ በእንዲህ ዐይነቱ ሰው ላይ በማፌዝና በመዘባበት እንዲህ እያሉ ሁሉም አይሣለቁበትምን? ‹የተሰረቀውን ለራሱ ለሚያከማች፣ ራሱን በዐመፅ ባለጠጋ ለሚያደርግ ወዮለት! ይህ የሚቀጥለውስ እስከ መቼ ነው?7በአንተ የተመረሩ ድንገት አይነሡብህምን፣ አንተን የማያስደነግጡስ አይነቁብህምን? በእጃቸውም ትወድቃለህ፡፡8አንተ ብዙ ሕዝብ ስለ ዘረፍህ የተረፉት ሕዝቦች ይዘርፉሃል፡፡ የሰው ደም አፍስሰሃል አገሮች፣ ከተሞችና የሚኖሩባቸው ሰዎች ሁሉ ላይ ግፍ ሠርተሃል፡፡9በማጭበርበር በተገኘ ሀብት ቤቱን ለሚገነባ ከክፉ ለማምለጥ ቤቱን በከፍታ ላይ ለሚሠራ ወዮለት!10ብዙ ሰዎችን ለማጥፋት ደባ ፈጽመሃል በገዛ ቤትህ ላይ ውርደትን፣ በራስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል፡፡11ድንጋዮች በቅጥሩ ውስጥ ይጮኻሉ፣ ከዕንጨት የተሠሩ ተሸካሚዎችም እንዲህ በማለት ይመልሱላቸዋል፣12«ደም በማፍሰስ ከተማን ለሚሠራ፣ በወንጀልም አገርን ለሚመሠርት ወዮለት!»13ሰዎች ለእሳት ማገዶ እንዲሆን እንዲለፉ፣ ሕዝቦችም በከንቱ እንደደከሙ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ወስኖ የለምን?14ያም ሆኖ፣ ውሃ ባሕርን እንደሚሞላ ሁሉ ምድርም የያህዌን ክብር በማወቅ ትሞላለች፡፡15ኅፍረተ ሥጋቸውን ለማየት ባልንጀሮቹን ለሚያጠጣ፣ እስኪሰክሩም ድረስ ወይን ለሚያቀርብላቸው ወዮለት!»16በክብር ፈንታ ውርደት ትሞላለህ፤ አሁን ተራው የአንተ ነውና ጠጣ፤ ኀፍረተ ሥጋህም ይገለጥ፤ በያህዌ ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ በተራው ይመልስብሃል ክብርህን ውርደት ይሸፍነዋል፡፡17ሊባኖስ ላይ ያሠራኸው ግፍ ያጥለቀልቅሃል፤ እንስሶች ላይ የፈጸምኸው ጥፋት ያስደነግጥሃል፡፡ የሰው ደም አፍስሰሃል፤ አገሮች፣ ከተሞችና የሚኖሩባቸው ሰዎች ሁሉ ላይ ግፍ ሠርተሃል፡፡18ታዲያ፣ የቀረጽኸው ምስል ምን ይጠቅምሃል? ምስሉን የቀረጸው፣ ከቀለጠ ብረት ጣዖት የሠራ ሰው የሐሰት መምህር ነው፤ እነዚያን የማይናገሩ አማልክት ሲሠራ በገዛ እጅ ሥራው ተማምኖአልና፡፡19ዕንጨቱን ንቃ! ሕይወት የሌለውንም ድንጋይ ተነሣ ለሚል ወዮለት ለመሆኑ፣ እነዚህ ነገሮች ማስተማር ይችላሉን? በወርቅና በብር ተለብጦአል፤ እስትንፋስ ግን የለውም፡፡20ያህዌ ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል!»
1የነቢዩ ዕንባቆም ጸሎት2ያህዌ ሆይ፣ ስላደረግኸው ድንቅ ሥራ ሰዎች ፈራሁ፤ የቀድሞ ዘመን ሥራህን በዚህ ዘመንም አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፡፡ በቁጣህ ውስጥ እንኳ ምሕረት ርኅራኄኅን አስብ፡፡3እግዚአብሔር ከቴማን፣ ቅዱሱንም ከፋራን ተራራ መጣ! ሴላ፡፡ ክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ ምድር በምስጋናው ተሞላች፡፡4ኃይሉ ከተሰወረበት እጁ የወጡ ሁለት ጨረሮች እንደ መብረቅ ደምቀዋል፡፡5መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው፡፡6እርሱ ሲቆም ምድር ትናወጣለች፤ እርሱ ሲመለከት ሕዝቦች ይንቀጠቀጣሉ፡፡ የዘላለም ተራሮች እንኳ ተፈረካከሱ የጥንት ኮረብቶችም ዝቅ አሉ፡፡ መንገዱ ዘላለማዊ ነው፡፡7የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣ የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ፡፡8ያህዌ ወንዞች ላይ ተቆጥቷልን? መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን? ወይስ በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሰረገሎችህ በጋለብህ ጊዜ ባሕር ላይ ተቆጥተህ ነበርን?9ቀስትህን ከሰገባው አወጣህ፤ ፍላጻህንም ለመወርወር አዘጋጀህ፡፡ ሴላ፡፡ ምድርን በወንዞች ከፈልህ፡፡10ተራሮች አዩህ፤ በፍርሃትም ተጨማደዱ የውሃ ወጀብ በላያቸው አለፈ፤ ጥልቁ ባሕር ድምፁን አሰማ ማዕበሉም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ፡፡11ከሚወረወሩ ፍላጾች ብርሃን፣ ከሚያብረቀርቀው የጦርህ ነጸብራቅ የተነሣ ፀሐይና ጨረቃ በቦታቸው ቆሙ፡፡12በቁጣህ በምድር ላይ ተመላለስህ፤ በመዓትህ ሕዝቦችን አደቀቅህ፡፡13ሕዝብህን ለማዳን፣ የቀባኸውንም ለመታደግ ወጣህ፡፡ ዕርቃኑን ታስቀረው ዘንድ የዐመፃን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፡፡ ሴላ፡፡14እንደ ዐውሎ ነፋስ ሊበታትን የመጣውን፣ ምስኪኑን በስውር ለመዋጥ የመጣውን ሰራዊት አለቃ ራስ በገዛ ፍላጻው ወጋህ፡፡15በፈረሶችህ ባሕሩ ላይ ተራመድህ፤ ታላላቅ ውሆችን ከመርህ፡፡16እኔ ሰማሁ ውስጤም ተናወጠ፤ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፡፡ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼም ከታች ይርዳሉ ወራሪዎቻችን ላይ መከራ የሚመጣበትን ቀን በትዕግሥት እጠብቃለሁ፡፡17ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፣ ወይን ዛፍ ላይ ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራ ዛፍ ምንም ፍሬ ባይሰጥ፣ ከእርሻዎች ሰብል ቢጠፋ፣ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፣ በረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፣18ይህም ሁሉ ቢሆን፣ እኔ በያህዌ ደስ ይለኛል በመድኃኒቴም አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ፡፡19ጌታ ያህዌ ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋሊያ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎቼም ላይ ይመራኛል፡፡ - ለመዘምራን አለቃ በባለ አውታር መሣሪያዎች የተዘመረ፡፡
1ይህ በይሁዳ ንጉሥ በአሞን ልጅ በኢዮስያስ ዘመን፣ ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጐዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኩሲ ልጅ፣ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የያህዌ ቃል ነው፡፡2«ማንኛውንም ነገር ከምድር ገጽ ፈጽሜ አጠፋለሁ! ይላል ያህዌ3ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ የሰማይን ወፎችና የባሕር ዓሦች አጠፋለሁ፡፡ ሰውን ከምድር ገጽ በማስወግድበት ጊዜ ክፉዎች የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ ይላል ያህዌ፡፡4እጄን በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፡፡ የበአልን አምልኮ ርዝራዥ፣ የጣዖቶቹንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ከዚህ ቦታ አጠፋለሁ ስም ሁሉ ከዚህ ቦታ አጠፋለሁ፤5በየቤቶቹ ጣራ የሰማይን ሰራዊት የሚያመልኩትን፣ በያህዌ ስም እየማሉ ደግሞም በሜልኮም የሚምሉትን ሕዝብ አጠፋለሁ፡፡6ያህዌን ከመከተል ወደ ኃላ የሚሉትን፣ ያህዌን የማይፈልጉትንም ሆነ ከእርሱ ምሪት የማይፈልጉትን አጠፋለሁ፡፡»7የያህዌ ቀን እየቀረበ ነውና በጌታ ያህዌ ፊት ጸጥ በሉ፤ ያህዌ መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውንም እንግዶች ቀድሷል፡፡8በያህዌ የመሥዋዕት ቀን መኳንንቱንና የንጉሡን ልጆች፣ እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ፡፡9በዚያን ቀን፣ በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን ሁሉ፣ የጌቶቻቸውን ቤት በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትንም ሁሉ እቀጣለሁ፡፡10በዚያን ቀን ይላል ያህዌ፣ ከዓሣው በር ጩኸት፣ ከሁለተኛው አደባባይ ዋይታ፣ ከኮረብቶችም ታላቅ የጥፋት ድምፅ ይሰማል፡፡11እናንት በገበያው ቦታ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ ነጋዴዎች ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይጠፋሉ፡፡›12በዚያ ዘመን፣ ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ወይን ጠጅ የሚያዘወትሩንና በልባቸው፣ «ክፉም ሆነ መልካም ያህዌ ምንም አያደርግም» የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ፡፡»13ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ ቤት ይሠራሉ፤ ሆኖም፣ አይኖሩበትም፤ ወይን ይተክላሉ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም፡፡14ታላቁ የያህዌ ቀን ቀርቧል፤ እጅግ እየፈጠነ ነው፤ የያህዌ ቀን ድምፅ ጦረኞች አምርረው የሚያለቅሱበት ይሆናል፤15ያ ቀን የቁጣ፣ የመከራና የጭንቀት፣ የጥፋትና የመፍረስ፣ የጨለማና የጭጋግ፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፡፡16በዚያ ቀን በተመሸጉት ከተሞችና በረጃጅም ግንቦች ላይ የጦር መለከትና የማስጠንቀቂያ ድምፅ ይሰማል፡፡17እንደ ዕውሮች እስኪደናበሩ ድረስ በሰዎች ላይ ታላቅ ጭንቀት አመጣለሁ፤ ያህዌ ላይ ኃጢአት አድርገዋልና ደማቸው እንደ ውሃ ይፈስሳል፤ ሬሳቸውም እንደ ጉድፍ የትም ይጣላል፡፡18ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ያህዌ ቁጣውን በሚገልጥበት ቀን የቁጣው እሳት ምድርን ሁሉ ይበላል፤ ይህም የሆነው በምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ በድንገት ጥፋት ስለሚመጣ ነው፡፡»
1እናንት ዕፍረት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፣ በአንድነት ተሰብሰቡ ተከማቹም፤2የወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣ ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣ የያህዌ ቁጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣና የያህዌ መዓት ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ፡፡3እናንተ ትእዛዙን የምትፈጽሙ በምድር ያላችሁ ትሑታን ሁሉ ያህዌን ፈልጉ፤ ጽድቅንና ትሕትናንም ፈልጉ፤ በያህዌ ቀን ምናልባት ጥበቃ ታገኙ ይሆናል፡፡4ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤ አስቀሎናም ትፈራርሳለች፤ አሸዶድ በቀትር ባዶ ትሆናለች፤ አቃሮንም ትነቀላለች፡፡5እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ የከሌታውያን ሰዎች ሆይ፣ የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፣ ያህዌ እናንተ ላይ ተናግሯልና ወዮላችሁ፤ ከእናንተ ማንም እስከማይተርፍ ድረስ አጠፋችኃለሁ፡፡6የባሕሩ ዳርቻ የእረኞች መሰማርያና የበጐች በረት ይሆናል፡፡7የባሕሩ ዳርቻ ከይሁዳ ቤት ለተረፉት ይሆናል፤ እነርሱም በዚያ መንጐቻቸውን ያሰማሩበታል፡፡ በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ በምሽት ይተኛሉ፤ አምላካቸው ያህዌ ይጠብቃቸዋል፤ ሀብታቸውንም ይመልሳል፡፡8በሕዝቤ ላይ የደረሰውን የሞዓብን ሕዝብ ፌዝና የአሞናውያንን ንቀት ሰምቻለሁ፤ ሕዝቤን ሰድበዋል፤ ርስታቸውን ለመውሰድም ዝተዋል፡፡9ስለዚህ ይላል የሰራዊት ጌታ፣ የእስራኤል አምላክ ያህዌ፣ የሞዓብ ሕዝብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያንም እንደ ገሞራ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘላለም ጠፍ እንደሚሆኑ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ከሕዝቤ የተረፉት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ፡፡10ከትዕቢታቸው የተነሣ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሕዝብ ላይ በማፌዛቸውና እነርሱንም በመስደባቸው የሞዓብና የአሞን ሕዝብ ላይ ይህ ይሆናል፡፡11እርሱ የምድሪቱን አማልክት በሚያጠፋበት ጊዜ፣ ያህዌ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፡፡ በባሕሩ ጠረፍና በየምድራቸው የሚኖሩ ሁሉ በያሉበት ያመልኩታል፡፡12እናንተ ኢትዮጵያውያንም በሰይፌ ትገደላላችሁ፣13የእግዚአብሔር እጅ ሰሜንን ይመታል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ ነነዌን ባድማ ያደርጋል፤ እንደ ምድረ በዳም ትደርቃለች፡፡14የአራዊት መንጋዎች፣ የአሕዛብ እንስሶች ሁሉ አሦር ውስጥ ያርፋሉ፤ ወፎችና ልዩ ልዩ ዐይነት ጉጉቶች በጉልላትዋ ላይ ይሰፍራሉ፡፡ ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎች ተገልጠዋልና ቁራዎች በየደጃፎቻቸው ይጮኻሉ፡፡15ይህች በልቧ «እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ማንም የለም» ያለች ያለ አንዳች ፍርሃት ተደላድላ ትኖር የነበረች ከተማ ነች፡፡ ታዲያ፣ እንዴት የዱር አራዊት የሚኖሩባት ባድማ ሆና ቀረች? በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል!
1ለዐመፀኛዋ፣ ለጨቋኛና ለረከሰች ከተማ ወዮላት፡፡2እርሷ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልሰማችም፤ የያህዌንም ተግሣጽ አልተቀበለችም፤ በያህዌ አትታመንም፤ ወደ አምላኳም አትቀርብም፡፡3መሪዎቿ እንደሚያገሡ አንበሶች፣ ዳኞችዋም ለነገ ሳያስተርፉ ያገኙት ሁሉ በልተው እንደሚጨርሱ እንደ ተራቡ የማታ ተኩላዎች ናቸው፡፡4ነቢያቶችዋ ትዕቢተኞችና ተንኰለኞች ናቸው፡፡ ካህናትዋ የተቀደሰውን አርክሰዋል፤ ሕጉንም ተላልፈዋል፡፡5ጻድቁ ያህዌ በእርሷ ውስጥ አለ፤ እርሱ ፈጽሞ አይሳሳትም፤ በየማለዳው ፍርዱን ይሰጣል፤ በየቀኑም ይህን ከማድረግ አይቆጠብም፤ ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም፡፡6ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ ምሽጐቻቸውንም ደምስሻለሁ፡፡ ማንም እንዳያልፍባቸው መንገዶቻቸውን አፈራርሻለሁ፡፡ ከተሞቻቸው ስለ ተደመሰሱ ከእንግዲህ የሚኖርባቸው አይኖርም፡፡7እኔም፣ «በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፣ እርምትም ተቀበዪ፤ ላደርግብሽ እንዳሰብኩት ከመኖሪያሽ አትነቀዪ አልኩ፡፡ እነርሱ ግን በሚያደርጉት ሁሉ ክፋትን እያበዙ ሄዱ፡፡8ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ «እስከምፈርድበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፤ ምድሪቱ ሁሉ በቁጣዬ እሳት እንድትጠፋ አሕዛብን ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትን ለማከማቸት፤ ቁጣዬንና ጽኑ መዓቴን እነርሱ ላይ ለማፍሰስ ወስኛለሁ፡፡9በዚያ ጊዜ ሰዎች የያህዌን ስም እንዲጠሩ፣ አንድ ልብ ሆነውም እንዲያገለግሉት ንጹሑን አንደበት እሰጣቸዋለሁ፡፡›10ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ያሉት እኔን የሚያመልኩ የተበተኑ ሕዝቤ ለእኔ የሚገባውን ቁርባን ያመጡልኛል፡፡11በዚያ ቀን በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ አታፍሩም፤ በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን ከመካከላችሁ ስለማስወግድ ከእንግዲህ ወዲያ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም፡፡12ሆኖም፣ የዋሃንንና ትሑታንን አስቀራለሁ፤ እናንተም በያህዌ ስም ትተማመናላችሁ፡፡13የእስራኤል ትሩፋን ከእንግዲህ ፍርድ አያጐድሉም፤ ሐሰትንም አይናገሩም፤ በአንደበታቸው ሐሰት አይገኝም፡፡ ይበላሉ፤ በሰላምም ያርፋሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም፡፡»14የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፣ እልል በዪ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፣ በፍጹም ልብሽ ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፡፡15ያህዌ ቅጣትሽን አስወግዷል፤ ጠላቶችንም አስወጥቷል፤ የእስራኤል ንጉሥ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ ከእንግዲህ ክፉን አትፈሪም፡፡16በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን እንዲህ ይሏታል፤ «ጽዮን ሆይ አትፍሪ፤ እጆችሽም አይዛሉ፡፡17አንቺን ለማዳን ብርቱ የሆነው አምላክሽ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩም ያሳርፍሻል፡፡ በዝማሬ በአንቺ ደስ ይለዋል፡፡18ለታወቁ ክብረ በዓላት ሐዘንን ከአንቺ አርቃለሁ፤ በመካከልሽ ሸክምና ዕፍረት ሆነውብሻል፡፡19በዚያ ቀን የበደሉሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ያነከሱትን እታደጋለሁ፤ የተጣሉትንም እሰበስባለሁ፡፡ ዕፍረታቸውን አስወግጄ በምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለክብር አደርጋቸዋለሁ፡፡20በዚያ ቀን እመራችኃለሁ፤ በዚያ ቀን በአንድነት እሰበስባችኃለሁ፡፡ እኔ እንደ ሰበሰብኃችሁ፣ ምርኮአችንም እንደ ሰበሰብሁ ስታዩ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ያመሰግኗችኃል፤ ያከብራችኃል ይላል ያህዌ፡፡
1ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር መጀመሪያ ቀን በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዢ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህኑ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ የያህዌ ቃል መጣ።2የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ይህ ሕዝብ “እኛ የምንመጣበት ወይ የያህዌን ቤት የምንሠራበት ጊዜ ገና ነው” ይላል።3የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩ መጣ፤ እንዲህም አሉ፣4“ይህ ቤት ፈራርሶ እያለ፣ እናንተ ራሳችሁ ባማሩ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?5ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ እስቲ፣ የሠራችሁትን ቤት አስቡ!6ብዙ ዘራችሁ፤ ግን ጥቂት አጭዳችሁ፤ በላችሁ ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዝ ተቀበላችሁ ግን ብዙ ቀዳዶች በሞሉበት መያዣ የማስቀመጥ ያህል ሆነባችሁ!7የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ እስቲ የሠራችሁትን አስቡ!8ወደ ተራራ ውጡ፤ እንጨትን አምጡና ቤቴን ሥሩ፤ ያኔ እኔ በእርሱ ደስ ይለኛል፣ እከብርበታለሁ! ይላል ያህዌ።9ብዙ ጠበቃችሁ፤ ግን እኔ እፍ ስላልሁበት ወደ ቤት ያመጣችሁት ግን ጥቂት ነው፤ እንዲህ ያደረግሁት ለምን ይመስላችኋል? የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል! ምክንያቱም የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ፣ ሰው ሁሉ በገዛ ራሱ ቤት እጅግ ደስ በመሰኘቱ ነው።10ከዚህ የተነሣ ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች።11እኔ በምድሪቱና በተራሮች፤ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፤ በዘይቱና ምድር በምትሰጠው ሁሉ ላይ፣ በሰዎችና በእንስሳት፣ በእጆቻችሁ ሥራ ሁሉ ላይ ድርቅ አመጣለሁ!12ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህኑ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ ከተረፉት ሕዝብ ሁሉ ጋር የአምላካቸው የያህዌን ድምጽ ሰሙ፤ አምላካቸው ያህዌ ልኮታልና ለነቢዩ ሐጌ ቃል ታዘዙ። ሕዝቡም ያህዌን ፈሩ።13ከዚያም የያህዌ መልእክተኛ ሐጌ ለሕዝቡ የያህዌን መልእክት እንዲህ በማለት ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ! ይህ የያህዌ ቃል ነው!14ስለዚህ ሄደው የአምላካቸውን የሠራዊት ጌታ የያህዌን ቤት እንዲሠሩ የይሁዳን ገዢ የሰላትያል ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስና የኢዮሴዴቅ ልጅ የካህኑ ኢያሱን መንፈስ፣ እንዲሁም ከምርኮ የተረፉትን ሰዎች ሁሉ መንፈስ ያህዌ አነሣሣ።15ይህ የሆነው በንጉሥ ዳርዮስ ሁለተኛ ዓመት በስድስተኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን ነው።
1በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በሃያ አንደኛው ቀን የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል መጣ እንዲህም አለ፤ 2“ለይሁዳ ገዢ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤልና ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለካህኑ ኢያሱ፣ እንዲሁም ከምርኮ ለተረፉት ሰዎች ተናገሩ እንዲህም በሏቸው3የዚህን ቤት የቀድሞ ክብር ያየ በመካከላችሁ ማን አለ? አሁንስ እንዴት ሆኖ ይታያችኋል? በዓይኖቻችሁ ፊት እንደ ተራ ነገር ቀልሎ የለምን?4አሁንም ዘሩባቤል ሆይ፣ በርታ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው አንተም የኢዮሴዴቅ ልጅ ሊቀ ካህኑ ኢያሱ በርታ፤ በምድሪቱ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ በርቱ! - ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ተነሡ ሥሩ! ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው5ከግብፅ በወጠችሁ ጊዜ በገባሁላችሁ ኪዳን፣ በመካከላችሁም ባለው መንፈሴ አትፍሩ!6የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ በቅርብ ጊዜ ሰማያትንና ምድርን፣ ባሕርንና ደረቁን ምድር አናውጣለሁ!7ሕዝቦችን ሁሉ አናውጣለሁ፤ ሕዝቦች የከበሩ ነገሮቻቸውን ወደ እኔ ያመጣሉ፤ ይህንንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ! ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።8ብርና ወርቁ የእኔ ነው! ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።9የወደፊቱ የዚህ ቤት ክብር ከመጀመሪያው ይበልጣል ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፤ በዚህ ቦታ ሰላም እሰጣለሁ - ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።”10ዳርዮስ በነገሠ ሁለተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል መጣ፤ እንዲህም አለ፣ 11“የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ሕጉ ምን እንደሚል ካህናቱን ጠይቁ፤ 12አንድ ሰው ለያህዌ የተቀደሰውን ሥጋ በልብሱ እጥፋት ቢይዝ፣ በልብሱ እጥፋት እንጀራ ወይም ወጥ፣ የወይን ጠጅ ወይም ዘይት ወይ ሌላ ምግብ ቢነካ፣ ያ ምግብ ይቀደሳልን?” ካህናቱም፣ “የለም፣ አይቀደስም” በማለት መለሱ።13ሐጌም፣ “ሬሳ በመንካቱ የረከሰ ሰው ከእነዚህ አንዱን ቢነካ ይረክሳሉን?” አለ። ካህናቱም፣ “አዎን፣ ይረክሳሉ” በማለት መለሱ። 14ስለዚህ ሐጌ መልሶ፣ “ ይህም ሕዝብ በፊቴ እንዲሁ ነው! - ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው፤ የእጃቸው ሥራና ለእኔ የሚያቀርቡት ሁሉ የረከሰ ነው።15እንግዲህ ከዘሬ ጀምራችሁ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመነባበሩ በፊት የነበረውን ሁኔታ ልብ በሉ፤ 16ለምሆኑ ያኔ እንዴት ነበር? አንድ ሰው ሃያ መስፈሪያ እህል ጠብቆ ወደ ክምሩ ሲሄድ አሥር ብቻ አገኘ። አምሳ ማድጋ ወይን ጠጅ ለመቅዳት ወደ መጭመቂያው ሲሄድ ሃያ ብቻ አገኘ። 17እናንተንና የእጆቻችሁን ሥራ ሁሉ በዋግና በአረማሞ መታሁ፤ ያም ሆኖ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም - ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።18ከዚህ ቀን ጀምሮ ማለትም የያህዌ ቤተመቅደስ መሠረት ከተጣለበት ከዘጠነኛው ወር ሃያ አራተኛው ቀን ጀምሮ ወደፊት ቁጠሩ፤ ልብ አድርጋችሁ አስቡት! 19በጎተራው የቀረ ዘር ይኖራልን? የወይኑና የበለሱ፣ የሮማኑና የወይራው ዛፍ ፍሬ አላፈሩም! ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ!”20በዘጠነኛው ወር በወሩም ሃያ አራተኛ ቀን የያህዌ ቃል በድጋሚ ወደ ሐጌ መጣ፤ እንዲህም አለ፣ 21“ለይሁዳ ገዥ ለዘሩባቤል እንዲህ በለው፤ “ሰማያትንና ምድርን አናውጣለሁ።22የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ የሕዝቦችን መንግሥት ብርታት አጠፋለሁ! ሰረገሎችንና በላያቸው ያሉትን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችና ጋላቢዎቻቸውን በገዛ ወንድሞቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።23በዚያ ቀን - የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ እንዲህ የሚል ይሆናል- የሰላትያል ልጅ ባርያዬ ዘሩባቤል ሆይ፣ እኔ እወስድሃለሁ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። እኔ መርጬሃለሁና ቀለበቴ ላይ እንደ ማህተም አደርግሃለሁ፤ ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
1ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ የሚል የያህዌ ቃል መጣ፤ 2“ያህዌ በአባቶቻችሁ እጅግ ተቆጥቶ ነበር! 3ለሕዝቡ ተናገር፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ወደ እኔ ተመለሱ! ይህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ።4“የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ “ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ!” በማለት በቀድሞ ዘመን ነቢያት እንደ ሰበኩላቸው አባቶቻችሁ አትሁኑ። እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።5ለመሆኑ፣ አባቶቻችሁ ወዴት አሉ? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን?6ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? እነርሱም ንስሐ በመግባት እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ ያህዌ በወሰነው መሠረት ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።7ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሳባጥ በመባለው በአሥራ አንደኛው ወር በሃያ አራተኛው ቀን ያይህዌ ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ መጣ። 8እነሆም በሌሊት ራእይ አየሁ፤ አንድ ሰው ቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በሸለቆው ውስጥ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፤ ከበስተ ኋላውም ቀይ፣ ቀይ ቡናማና ነጭ ፈረሶች ቆመው ነበር። 9እኔም፣ “ጌታ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁ። ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክም፣ “እነዚህ፣ ምን እንደ ሆኑ፣ አሳይሃለሁ” አለኝ።10ዛፎች መካከል ቆሞየነበረውም ሰው “እነዚህ በምድር ሁሉእንዲመላለሱ ያህዌ የላካቸው ናቸው”በማለት መለሰ። 11ከዚያም፣ በባርሰነትዛፎች መካከል ቆሞ ለነበረው የያህዌመልአክ፣ “በምድር ሁሉ ተመላለስን፤እነሆ መላዋ ምድር አርፋ ተቀምጣለች”አሉት።12ያኔ የያህዌ መልአክ መልሶ፣ “የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በእነዚህ ሰባ ዓመቶች ውስጥ የተቆጣሃቸውን ኢየሩሳላምንና የይሁዳን ከተሞች የማትራራላቸው እስከ መቼ ነው?” አለ። 13ያህዌም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ ለነበረው መልአክ ደስ በሚያሰኝ የሚያጽናና ቃል መለሰለት።14ስለዚህ፣ ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፤ “እንዲህ ብለህ ተናገር፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ ለኢየሩሳሌምና ለጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ!15ተደላድለውና ተመቻችተው በተቀመጡ ሕዝቦች ላይ በጣም ተቆጥቻለሁ። እኔ የተቆጣሁት በመጠኑ ቢሆንም፣ እነርሱ ግን ጥፋት እንዲባባስ አድርገዋል።16ስለዚህ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ በምሕረቴ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሻለሁ። በውስጧ ቤቴ እንደ ገና ይሠራል፤ መለኪያ ገመድም በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋል! ይህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።17ደግሞም፣ እንዲህ በማለት ተናገር፣ ‘የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ከተሞቼ እንደ ገና በመልካም ነገሮች ይሞላሉ፤ ያህዌ እንደ ገና ጽዮንን ያጽናናል፤ እንደ ገና ኢየሩሳሌምን ይመርጣታል።18ከዚያ ዐይኖቼን ወደ ላይ አንሥቼ አራት ቀንዶች ተመለከትሁ! 19ከእኔ ጋር እየተነጋገረ ለነበረውም መልአክ፣ “እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። እርሱም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበተኑ ቀንዶች ናቸው” አለኝ።20ከዚያም ያህዌ አራት የእጅ ባለ ሙያዎች አሳየኝ። 21እኔም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበተኑ አራት ቀንዶች ናቸው፤ እነዚህ ሰዎች የመጡት ግን እነርሱን ለማስወጣትና ሕዝቡን ለመበታተን በይሁዳ ምድር ላይ ቀንዳቸውን ያነሡትን ሕዝቦች ቀንዶች ሰባብሮ ለመጣል ነው” በማለት መለሰልኝ።
1እንደ ገና ዐይኖቼን ወደ ላይ አንሥቼ በእጁ መለኪያገመድ የያዘ ሰው አየሁ።2እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው?” አልሁት። እርሱም መልሶ፣ “የኢየሩሳሌም ስፋትና ርዝመት ምን ያህል እንደ ሆነ ለመለካት ነው” አለኝ።3ከዚያም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክ ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ። 4ሁለተኛው መልአክ፣ ሩጥና ለዚያ ወጣት እንዲህ ብለህ ንገረው፣ ‘በውስጧ ካለው ሕዝብና እንስሶች ባት የተነሣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች።5ምክንያቱም እኔ ራሴ፣ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር በመካከልዋም ክብር እሆናለሁ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።6ኑ! ኑ! ከሰሜን ምድር አምልጡ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሶች በትኛችኋለሁ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።7እናንት ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሩ፣ ወደ ጽዮን አምልጡ!”8የሰራዊት ጌታ ያህዌ ካከበረኝና በዘረፉአችሁ ሕዝቦች ላይ ከላከኝ በኋላ፣ እናንተን የሚነካ የእግዚአብሔርን ዐይን ይነካል! ያህዌ ይህን ካደረገ በኋላ፣ 9“እኔ ራሴ እጄን በእነርሱ ላይ አንሣለሁ፤ ባርያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል” ያኔ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።10እኔ ራሴ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና የጽዮን ልጅ ሆይ በደስታ ዘምሪ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። 11ከዚያም ቀን ብዙ ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ፤ በመካከልሽ እኖራለሁ” እናንተም ወደ እናንተ የላከኝ ያህዌ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።12ያህዌም በተቀደሰች ምድር ይሁዳን ርስቱ ያደርገዋል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደ ገና ለራሱ ይመርጣታል። 13ከተቀደሰ ማደሪያው ተነሥቷልና፤ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በያህዌ ፊት ጸጥ በል!
1ከዚያም ሊቀ ካሁኑ ኢያሱ በያህዌ መልአክ ፊት ቆሞ ያህዌ አሳየኝ፤ እርሱን በኃጢአት ልመክሰሰ ሰይጣን በቀኙ በኩል ቆሞ ነበር። 2የያህዌ መልአክ ሰይጣንን፣ “አንተ ሰይጣን ያህዌ ይገሥጽህ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠ ያህዌ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይድለምን?” አለው። 3መልአኩ ፊት ቆሞ በነበረ ጊዜ ኢያሱ ያደፉ ልብሶች ለብሶ ነበር።4ስለዚህ መልአኩ በፊቱ ቆመው የነበሩትን፣ “ያደፉ ልብሶቹን አውልቁለት” አላቸው። ከዚያም ኢያሱን፣ “እነሆ፣ ርኩሰትህን ከአንተ አስወግጃለሁ፤ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ” አለው። 5መልአኩም፣ “ራሱ ላይ ንጹሕ መጠምጠሚያ ያድርጉለት! አለ። እነርሱም የያህዌ መልአክ አጠገቡ ቆሞ እያለ በኢያሱ ራስ ላይ ንጹሕ መጠምጠሚያ አደረጉለት፤ ንጹሕ ልብስም አለበሱት።6በመቀጠል የያህዌ መልአክ ለኢያሱ ይህን ማስጠንቀቂያ ሰጠው፤ 7“የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ያኔ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ በእነዚህ በፊቴ በቆሙት መካከል እንድትገባና እንድትወጣ አደርግሃለሁ።8ሊቀ ካሁኑ ኢያሱ ሆይ ስማ፤ ከአንተ ጋር ያሉት ጓደኞችህም ፊት ለሚመጡት ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፤ እነሆ፣ ባርያዬን ቁጥቋጡን አመጣለሁ።9ኢያሱ ፊት ያኖሩትን ድንጋይ ተመልከቱ። በዚያ አንድ ድንጋይ ላይ ሰባት ዐይኖች አሉ፤ በእርሱም ላይ ቅርጽ እቀርጻለሁ፤ የዚህችንም ምድር ኀጢአት በአንድ ቀን አስወግዳለሁ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።10በዚያን ቀን እያንዳንዱ ሰው በገዛ ወይኑና በለስ ዛፉ ሥር እንዲቀመጥ ባልንጀራውን ይጋብዛል” ይላል ያህዌ።
1ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ተመልሶ፣ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው አንቃኝ። 2እርሱም፣ “ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም፣ “በዐናቱ ላይ፣ የዘይት ማሰሮ ያለበት ሁለመናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ አየሁ። መቅረዙም ላይ በእያንዳንዱ ጫፍ ሰባት ክሮች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበር። 3ደግሞም አንዱ ከዘይት ማሰሮው በስተ ቀኝ፣ ሌላውም በስተ ግራ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”4እኔም፣ ያነጋገረኝ የነበረውን መልአክ፣ “ጌታዬ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት። 5ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክም መልሶ፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅም?” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” አልሁት።6ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለዘሩባቤል የመጣው የያህዌ ቃል ይህ ነው፤ ‘በመንፈሴ እንጂ፣ በኀይልና በብርታት አይደለም፤ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። 7አንተ ታላቅ ተራራ ምንድነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎች “ሞገስ! ሞገስ ይሁንለት!” ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።8የያህዌ ቃል ወደ እኔ መጣ፤ 9“የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤት መሠረት እንደ ጣሉ ሁሉ፣ የእርሱ እጆች ይፈጽሙታል። ያኔ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። 10የጥቂቱን ቀን ነገሮች የናቀ ግን ነው? እነዚህ ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ በጣም ደስ ይላቸዋል። እነዚህ ሰባት መብራቶች በምድር ሁሉ የሚመላለሱ የያህዌ ዐይኖች ናቸው። 11ከዚያም መልአኩን፣ “ከመቅረዙ ግራና ቀኝ የቆሙት እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድን ናቸው?” በማለት ጠየቅሁት።12እንደ ገናም፣ “በሁለት የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈስሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅንርንጫፎችስ ምንድን ናቸው?” አልሁት። 13እርሱም፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅም?” አለኝ፤ እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” አልሁት።14እርሱም፣ “እነዚህ የምድርን ሁሉ ጌታ ለማገለል የሚቆሙ ሁለቱ የወይራ ዛፎች ናቸው” አለኝ።
1ከዚያም ዘወር ብዬ ዐይኖቼን አነሣሁ፤ እነሆም፣ የሚበር መጽሐፍ ተመለከትሁ! 2መልአኩም፣ “ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም፣ “ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ አሥር ክንድ የሆነ መጽሐፍ ሲበር ይታየኛል” በማለት መለስሁ።3እርሱም፣ “ይህ በምድር ሁሉ ላይ የሚመጣ መርገም ነው፤ የሚሰርቅ ሁሉ፣ በአንዱ በኩል በተጻፈው መሠረት ይጠፋል፤ በሐሰት የሚምል ሁሉ እንደ ተናገረው ቃል በሌላው ወገን በተጻፈው መሠረት ይጠፋል።4እኔ መርገሙን አመጣዋለሁ፤ ይህ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ዐዋጅ ነው። ወደ ሌባው ቤትና በስሜ በሐሰት ወደሚምለው ሰው ቤት ይገባል፤ በዚያም ይቀመጣል፤ ቤቱን፣ እንጨቱንና ድንጋዩን ያጠፋል።5ከዚያም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክ መጥቶ፣ “ዐይንህን አንሥተህ እየመጣ ያለውን ተመልከት! አለኝ። 6እኔም፣ “ምንድን ነው?” አልኩት። እርሱም፣ “ይህ እየመጣ ያለውን ኢፋ የያዘ መስፈሪያ ነው፤ ይህ የምድሪቱ ሁሉ በደል ነው” አለኝ። 7ከዚያም ከእርሳስ የተሠራው ክዳን ተነሣ፤ የአፍ መስፈሪያው ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር!8መልአኩም፣ “ይህች ዐመፃ ናት!” ብሎ መልሶ ወደ መስፈሪያው አስገባትና የእርሳሱን ክዳን አጋው። 9እነሆም፣ ዐይኔን አንሥቼ ሁለት ሴቶች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁ፤ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበር፤ የሽመላ ክንፎችን የመሰሉ ክንፎች ነበሯቸው። መስፈሪያውን በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።10በእኔም ጋር እየተነጋገረ የነበረውን መልአክ፣ “መስፈሪያውን ወዴት እየወሰዱት ነው?” አልሁት። 11እርሱም፣ “ቤተ መቅደስ ሊሠሩለት ወደ ባቢሎን ምድር ይወስዱታል፤ ቤተ መቅደሱ ዝግጁ ሲሆን፣ እዚያ በተዘጋጀለት ቦታ ይቀመጣል” አለኝ።
1ከዚያም ዘወር ብዬ ዐይኖቼን ወደ ላይ ሳነሣ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራሮች መካከል ሲመጡ አየሁ፤ ሁለቱ ተራሮች የናስ ተራሮች ነበር። 2የመጀመሪያው ሰረገላ ቀይ ፈረሶች ነበሩት፤ ሁለተኛው ሰረገላ ጥቁር ፈረሶች ነበሩት። 3ሦስተኛው ሰረገላ ነጭ ፈረሶች ነበሩት፤ አራተኛው ሰረገላ ዝንጉርጉር ፈረሶች ነበሩት። 4እኔም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረውን መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው?” አልሁት።5መልአኩም እንዲህ አለኝ’ “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ቆመው ከነበሩበት ቦታ የወጡ አራቱ የሰማይ ነፋሶች ናቸው!” አለኝ። 6ጥቁር ፈረሶች ያሉት ወደ ሰሜን፣ ነጭ ፈረሶች ያሉት ወደ ምዕራብ፣ ዝንጉርጉር ፈረሶች ያሉት ወደ ደቡብ ይሄዳሉ።7ጠንካሮች ፈረሶች ሲወጡ፣ በምድር ሁሉ ፊት ለመመላለስ አቆብቁበው ነበር፤ ስለዚህም መልአኩ፣ “ወደ ምድር ሁሉ ሂዱ!” አላቸው። እነርሱም ወጥተው ወደ ምድር ሁሉ ሄዱ። 8ከዚያም ወደ እኔ ጮኾ እንዲህ አለኝ፤ “ወደ ሰሜን እየሄዱ ያሉትን ተመልከት፣ መንፈሴን በሰሜን ምድር አሳርፈውታል።”9የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 10ከምርኮኞቹ ከሔልዳይና፥ ከጦቢያ፣ ከዮዳኤም ወርቅና ብር ወስደህ በዚያው ቀን ከምርኮ ወደ መጣው ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ። 11ወርቁንና ብሩን ወስደህ አክሊል ሥራ በኢዮሴዴቅ ልጅ በሊቀ ካህኑ ኢያሱ ራስ ላይ አድርገው።12እንዲህም በለው፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ እነሆ፣ ስሙ ቁጥቋጥ የተባለው ሰው ይህ ነው! እርሱም በቦታው ይንሰራፋል፤ የያህዌንም ቤተ መቅደስ ይሠራል!13የያህዌን ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው፤ ክብሩን ይጎናጸፋል፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል። በዙፋኑ ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ስምምነት ይኖራል።14ለሔልዳይና፣ ለጦቢያና ለዮዳኤ ክብር አክሊል ቤተ መቅደሱ ውስጥ ይቀመጣል፤ ለሶፎንያስ ልጅ ቸርነት መታሰቢያ ይሆናል። 15ያኔ በሩቅ ያሉት መጥተው የያህዌን ቤተ መቅደስ ይሠራሉ፤ ወደ እናንተ የላከኝ ያህዌ እንደ ሆነም ታውቃላችሁ፤ የአምላካችሁን የያህዌን ድምፅ ከልባችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል!”
1ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ካሴሉ በተባለው በዘጠነኛው ወር የያህዌ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ። 2የቤቴል ሰዎች እግዚአብሔርን ለመለመን ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን አብረዋቸው ከነበሩ ሰዎች ላኩ። 3በሰራዊት ጌታ በያህዌ ቤት የነበሩትን ካህናትና ነቢያት፣ “ብዙ ዓመት እንዳደርግሁት በአምስተኛው ወር ማዘንና መጾም ይገባኛልን?” አሏቸው።4ስለዚህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤5“በምድሩ ላሉት ሕዝብ ሁሉ፣ ለካህናቱም እንዲህ በላቸው፤ በእነዚህ ሰባ ዓመታት አምስተኛና ሰባተኛ ወሮች የጾማችሁትና ያዘናችሁት በእውነት ለእኔ ነውን?6የምትበሉትና የምትጠጡትስ ለራሳችሁ አይደለምን?7በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች በሰላምና በብልጽግና ትኖር በነበረ ጊዜ የኔጌቭና የምዕራብ ተራሮች ግርጌ የሰው መኖሪያ በነበሩ ዘመን በቀደሙት ነቢያት የተነገረው የያህዌ ቃል ይኸው አልነበረምን?”8የያህዌ ቃል እንደ ገና ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፣9“የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ‘በእውነተኛ ፍትሕና የኪዳን ታማኝነት፣ በምሕረትም ፍረዱ። እያንዳንዱ ሰው ለወንድሙ እንዲህ ያድረግ።10መበለቶችንና ድኻ አደጎችን፣ መጻተኞችንና ድኻውን አታስጨንቋቸው፤ በልባችሁም አንዳችሁ በሌላው ክፉ አታስቡ!11እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ በእልኽኝነት ትከሻቸውን አሳበጡ። እንዳይሰሙ ጆሮአቸውን ደፈኑ። 12ሕጉንና የሰራዊት ጌታ የያህዌን ቃል ላለመስማት ልባቸውን እንደ ዐለት አጠነከሩ። በቀደሙት ዘመኖች በመንፈሱ፣ በነቢያትም አንደበት እነዚህን መልእክቶች ወደ ሕዝቡ ላከ። ሕዝቡ ግን መስማት አልፈለጉም፤ ስለዚህ ያህዌ በእነርሱ ላይ በጣም ተቆጣ።13እርሱ ሲጠራቸው አልሰሙም። በተመሳሳይ መንገድ፣ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ “ወደ እኔ ይጣራሉ፤ እኔ ግን አልሰማም።” 14አይተዋቸው ወደማያውቁ ሕዝቦች ሁሉ በዐውሎ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፤ ምድሪቱም በኋላቸው ባድማ ትሆናለች። ሕዝቡ መልካሚቱ ምድራቸውን ባድማ አድርገዋልና ማንም በምድሪቱ አያልፍም ወደዚያም አይመለስም።”
1የሰራዊት ጌታ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ “ስለ ጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ፤ ስለ እርሷ በታላቅ ቁጣ ነድጃለሁ!3የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል ወደ ጽዮን እመለሳለሁ፤ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌም የእውነት ከተማ ትባላለች፤ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ተራራም ቅዱሱ ተራራ ይባላል!4የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል ሽማግሌዎችና አሮጊቶች እንደ ገና በኢየሩሳሌም አደባባዮች ይሆናሉ፤ እያንዳንዱ ሰው በጣም ስለሚያረጅ በእጁ ምርኩዝ ይይዛል።5የከተማዋ አደባባዮች በሚቦርቁ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።6የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ በዚያን ጊዜ ይህ ከተቀሩት ሕዝብ የማይቻል መስሎ ቢታይ እንኳ፣ በእኔ ዐይን ፊት የማይቻል ይመስላልን? ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።7የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል። እነሆ እኔ ሕዝቤን ከፀሐይ መውጫና ከፀሐይ መጥለቂያ ምድር አድናለሁ!8እንደ ገና አመጣቸዋለሁ፤ በኢየሩሳሌም መካከልም ይኖራሉ፤ እንደ ገና ሕዝቤ ይሆናሉ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላካቸው እሆናለሁ!9የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ እናንተ ከነቢያት አፍ የወጡ ቃሎችን አሁን እየሰማችሁ ያላችሁ፣ የእኔ ቤት፣ የሰራውቲ ጌታ የእኔ የያህዌ ቤት መሠረት በተጣለ ጊዜ ቤተ መቅደሱ መሠራት እንዲችል እጆቻችሁን አበርቱ።10ከእነዚያ ቀኖች በፊት ማንም እህል አልሰበሰበም ነበር፤ ለሰውም ሆነ ለእንስሳት የሚጠቅም ነገር አልነበረም፤ ከጠላት የተነሣ ለሚወጣም ሆነ ለሚገባ ሰው ሰላም አልነበረም ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው በባልንጀራው ላይ እንዲነሣ አድርጌ ስለ ነበር ነው።11አሁን ግን እንደ ቀድሞው ዘመን አይሆንም፤ ከተረፈው ሕዝብ ጋር እሆናለሁ፤ ይህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።12የሰላም ዘር ይዘራል፤ ያንሰራራው ወይን ፍሬውን ይሰጣል፤ ምድሪቱም አዝመራዋን ታበረክታለች፤ ሰማያት ጠል ይሰጣሉ፤ የተፈረው ሕዝብ ይህን ሁሉ እንዲወርስ አድርጋለሁ።13የይሁዳና የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለሌሎች ሕዝቦች የመርገም ምሳሌ ሆናችሁ ነበር። ስለዚህ አድናችኋለሁ፤ በረከትም ትሆናላችሁ። አትፍሩ፤ እጃችሁም ይበርታ!14የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ አባቶቻችሁ ቁጣዬን ባነሳሡ ጊዜ ያላንቻች ርኅራኄ ጥፋት ላመጣባቸው እንደ ወሰንሁ፣ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ 15አሁን ደግሞ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ እንደ ገና መልካም ለማድረግ ወስኛለሁ፤ አትፍሩ!16እናንተ ማድረግ ያለባችሁ እነዚህን ነው፤ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባዮቻችሁም እውነትን፣ ፍትሕንና ሰላምን አስፍኑ። 17በባልንጀራችሁ ላይ በልባችሁ ክፋትን አታውጠንጥኑ፤ የሐሰት መሓላን አትውደዱ፣ ምክንያቱም እኔ እነዚህን ሁሉ እጠላለሁ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።”18እንደ ገናም የሰራዊት ጌታ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 19አሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ የአራተኛው ወር፣ የአምስተኛው ወር፣ የሰባተኛውና የአሥረኛው ወር ጾሞች ለይሁዳ ቤት የደስታ፣ የተድላና የሐሤት በዓሎች ይሆናሉ! ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ!20የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ያላል፤ በተለያዩ ብዙ ከተሞች ያሉት እንኳ ሳይቀሩ እንደ ገና ሰዎች ይመጣሉ። 21የአንዱ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ሌላው ከተማ እየሄዱ፣ “ያህዌን ለመለመንና የሰራዊት ጌታ ያህዌን ለመፈለግ ኑ በፍጥነት እንሂድ፤ እኛ ራሳችንም ደግሞ እንሄዳለን” ይላሉ። 22ብዙ ሕዝብና ኀያላይ መንግሥታት የሰራዊት ጌታ ያህዌን ለመፈለግ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ፤ የያህዌንም ሞገስ ይለምናሉ!23የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል በእነዚያ ቀኖች ከየወገኑና ከየቋንቋው አሥር ሰዎች የእናንተን ልብስ ዘርፍ አጥብቀው በመያዝ፣ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና፤ ከእናንተ ጋር እንሂድ! ይላሉ።
1ይህ በሴድራክና በደማስቆ ላይ የተነገረ የያህዌ ቃል ዐዋጅ ነው። የያህዌ ዐይኖች በሰው ልጆች ሁሉ እና በእስራኤል ነገዶች ሁሉ ላይ ናቸው። 2ይህ ዐዋጅ ደማስቆን የምታዋስናትን ሐማትንም ይመለከታል፤ በጣም ጥበበኞች ቢሆኑም ጢሮስንና ሲዶናንም ይመለከታል።3ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ ብሩን እንደ ዐፈር፣ ንጹሑን ወርቅ እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቆልላለች። 4እነሆ፣ ጌታ ሀብቷን ይወስዳል፤ በባሕሩ ላይ ያላትንም ኀይል ይደመስሳል፤ እርሷም ፈጽማ በእሳት ትጸፋለች።5አስቀሎና አይታ ትፈራለች! ጋዛም እጅግ ትሸበራለች! የአቃሮና ተስፋ ይጨነግፋል! ንጉሥ ከጋዛ ይጠፋል፤ አስቀሎና ከእንግዲህ መኖሪያ አትሆንም! 6ባዕዳን ቤታቸውን በአሽዶድ ያደርጋሉ፤ የፍልስጥኤማውያንን ትዕቢት አጠፋለሁ። 7ደሙን ከአፋቸው፣ የተከለከለውንም ምግብ ከጥርሶቻቸው መካከል አወጣለሁ። ያኔ እንደ ይሁዳ ነገድ የአምላካችን ትሩፋን ይሆናሉ፤ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።8እኔ ግን ቤቴን ከዘራፊዎች እጠብቃለሁ፤ ጨቋኝ እንግዲህ ምድሬን አይወርስም፤ አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና!9አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፣ በደስታ ጩኺ! እነሆ ንጉሥሽ በጽድቅ ወደ አንቺ መጥቶ ያድንሻል። እርሱ ትሑት ነው፤ በእህያ ላይ ይቀመጣል፤ በአህያ ግልገል በውርንጫዋ ላይ ይቀመጣል።10ከዚያም ከኤፍሬም ሰረገላን፣ ከኢየሩሳሌም ፈረስን አጠፋለሁ፤ ቀስት ከጦርነት ይሰበራል፤ ሰላምን ለሕዝቦች ይናገራል፤ ግዛቱ ከባሕር እስከ ባሕር ይሆናል፤ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ይሆናል!11ለአንቺ ደግሞ፣ ከአንቺ ጋር ካደረግሁት የደም ኪዳን የተነሣ እስረኞችሽን ውሃ ከሌለበት ጉድጓድ ነጻ እለቃቸዋለሁ። 12እናንተ የተስፋ እስረኞች ወደ ምሽጋችሁ ተመለሱ! አሁንም ቢሆን ዕጥፍ አድርጌ እንደምመልስላችሁ እናገራለሁ፤ 13እንደ እኔ ቀስት ይሁዳን አጉብጫለሁ። ኤፍሬምን በፍላጻ ሞልቻለሁ። ጽዮን ሆይ፣ ልጆችሽን አስነሣለሁ፤ ግሪክ ሆይ በአንቺ ልጆች ላይ ይነሣሉ፤ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ!14ያህዌ ለእነርሱ ይገለጣል፤ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይፈነጠራል! ጌታ ያህዌ መለከት ይነፋል፤ በቴማን ዐውሎ ነፋስ ይገሰግሣል። 15የሰራዊት ጌታ ያህዌ ይከልላቸዋል፤ ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ። ይጠጣሉ፤ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ መሠዊያው ላይ እንዳሉ ዕቃዎች፣ እንደ መሠዊያው ማእዘኖች በወይን ይሚላሉ።16በዚያ ቀን አምላካቸው ያህዌ ያድናቸዋል፤ ሕዝቡን የራሱ መንጋ ያደርጋቸዋል። አክሊል ላይ እንዳለ ዕንቁ፣ በገዛ ምድሩ ላይ ያብለጨልጫሉ። 17ምንኛ መልካም፣ ምንኛ ቆንጆ ይሆናሉ! እህል ወጣቶችን፣ ጣፋጭ ወይን ጠጅ ቆነጃጅቱን ያሳምራል!
1የበልግ ወራት ዝናብ እንዲሰጣችሁ ጠይቁ፣ ዝናብ ያዘለ ደመናን የሚልክ ያህዌ ነው እርሱ ዝናብንና የመስክ አትክልትን ለሁሉም ይሰጣል።2የቤተ ሰብ ጣዖቶች ውሸት ይናገራሉ፤ ሟርተኞች የሐሰት ራእይ ያያሉ አሳሳች ሕልም ይናገራሉ፤ ባዶ መጽናኛ ይሰጣሉ ስለዚህ ሕዝቡ እንደ በጎች ይባዝናሉ፣ እረኛ በማጣጥም ይጨነቃሉ።3ጽኑ ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነዶአል፤ መሪዎችንም እቀጣለሁ። የሰራዊት ጌታ ያህዌ ለመንጋው ለይሁዳ ቤት ይጠነቀቃል፤ በጦርነት ጊዜ እንደ ኩሩ የጦር ፈረሱ ያደርጋቸዋል!4ከይሁዳ ሕዝብ የማእዘን ድንጋይ ይወጣል፤ ከእነርሱ የድንኳን ካስማ ይገኛል፤ ከእነርሱ የጦር ቀስት ይመጣል፤ ከእነርሱ ገዥ ሁሉ ይወጣል። 5በጦርነት ጊዜ ጠላቶቹን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንደሚረግጥ ሰራዊት ይሆናሉ፤ ያህዌ ከእነርሱ ጋር ስለሆነ ተዋግተው የጦር ፈረሰኞችን ያሸንፋሉ።6የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ እምራቸዋለሁ፤ ወደ ቦታቸውም እመልሳቸዋለሁ። ከዚህ በፊት በፍጹም ጥዬአቸው እንደማላውቅ ይሆናሉ፤ እኔ አምላካቸው ያህዌ ነኝ፤ ጸሎታቸውንም እሰማለሁ።7በዚያ ጊዜ ኤፍሬም እንደ ብርቱ ጦረኛ ይሆናል፤ ወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ልባቸውን ደስ ይለዋል፤ ልጆቻቸውም አይተው ሐሤት ያደርጋሉ። ልባቸው በእኔ ሐሤት ያደርጋል!8በፉጨት ጠርቼ እሰበስባቸዋለሁ፤ በእርግጥ እታደጋቸዋለሁ፤ እንደ ቀድሞው ዘመን ይበዛሉ! 9በሕዝቦች መካከል ብበትናቸው እንኳ፣ በሚኖሩባቸው ሩቅ አገሮች ሆነው ያስታውሱኛል፤ እነርሱና ልጆቻቸው ተርፈው ይመለሳሉ። 10ከግብፅ ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ ከአሦርም እሰበስባቸዋልሁ። ቦታ እስኪጠባቸው ድረስ በገልዓድና በሊባኖስ አሰፍራቸዋለሁ።11በመከራቸው ባሕር ውስጥ አልፋለሁ፤ ምክንያቱም የባሕሩን ማዕበል እመታለሁ፤ የዐባይም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል። የአሦር ግርማ ይወገዳል፤ የግብፅ በትረ መንግሥት ከግብፃውያን ይወገዳል። 12በእኔ በራሴ አበረታቸዋለሁ፤ በስሜ ይመላለሳሉ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
1ሊባኖስ ሆይ፣ እሳት ዝግባሽን እንዲበላው በሮችሽን ክፈቺ!2የጥድ ዛፍ ሆይ፣ ዝግባ ውድቋልና አልቅስ! ግርማ የነበራቸው ዛፎች ጠፍተዋል! ጥቅጥቅ ያለው ደን ተመንጥሯልና እናንት የባሳን ወርካዎች ሆይ አልቅሱ።3ክብራቸው ጠፍቷልና እረኞች ሆይ ጩኹ!4አምላኬ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ “ለእርስ የተለዩትን በጎች እንደ እረኛ አሰማራ! 5የሚገዟቸው ያርዷቸዋል ሳይቀጡም ይቀራሉ፤ የሚሸጧቸውም፣ “ሀብታም ሆኛለሁና ያህዌ ይመስገን” ይላሉ። እረኞቻቸው እንኳ አይራሩላቸውም። 6ከእንግዲህ እኔም በምድሪቱ ለሚኖረው ሕዝብ አልራራም! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። እኔ ራሴ ሰውን ሁሉ ለባልንጀራውና ለንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እነርሱ ምድሪቱን ያስጨንቃሉ። ይሁዳንም ከእጃቸው አልታደገውም።”7ስለዚህ እኔ ለእርድ ለተለዩትና ለተጨቆኑት እረኛ ሆንሁ። ሁለት በትሮች ወስጄ እንዱን፣ “ሞገስ” ሌላውንም፣ “አንድነት” ብዬ ጠራኋቸው። መንጋውንም አሰማራሁ። 8በአንድ ወር ውስጥ ሦስቱን እረኞች አስወገድሁ፤ ትዕግሥቴ አለቀ፤ እነርሱም እንዲሁ እኔን ጠሉኝ። 9ከዚያም ለበጎቹ ባለቤቶች፣ “ከእንግዲህ እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱ በጎች ይሙቱ፤ የሚጠፉት በጎች ይጥፉ። የቀሩትም አንዱ የሌላውን ሥጋ ይብላ” አልኋቸው።10ከዚያም፣ ከነገዶቼ ሁሉ ጋር ያደረግሁት ኪዳን መቋረጡን ለማመልከት፣ “ሞገስ” የተባለው በትሬን ሰበርሁ። 11በዚያ ቀን ኪዳኑ ፈረስ፣ ብጎቹን ያስጨነቁትና ሲመለከቱኝ የነበሩትም ያህዌ እንደ ተናገረ አወቁ። 12እኔም፣ “መልካም መስሎ ከታያችሁ ደመወዜን ክፈሉኝ፤ ካልመሰላችሁም ተዉት” አልኋቸው። ስለዚህ ሰላሣ ብር ከፈሉኝ።13ያህዌም፣ “ሊከፍሉህ የተስማሙትን ጥሩ ዋጋ ሰላሣ ብሩን ግምጃ ቤት ውስጥ አኑረው” አለኝ። ስለዚህም ሰላሣውን ብር ወስጄ በሃህዌ ቤት ባለው ግምጃ ቤት ውስጥ አኖሩሁት። 14ከዚያም በይሁዳና በእስራኤል መካከል የነበረው ወንድማማችነት መፍረሱን ለማመልከት፣ “አንድነት” የተባለው ሁለተኛውን በትሬን ሰበርሁት።15ያህዌም እንዲህ አለኝ፤ “እንደ ገና የሰነፍ እረኛ ዕቃ ውሰድ፣ 16እነሆ እኔ በምድሪቱ ላይ እረኛ ላስነሣ ነው። እርሱም ለጠፋው በግ አያስብም፤ የባዘነውን በግ አይፈልግም፤ የተሰበረውን አይጠግንም፤ ጤነኛውን አይመግብም፤ ሆኖም፣ የሰባውን ሥጋ ይበላል፤ ሰኮናው እንኳ ሳይቀር ይቀለጣጥማል።17መንጋውን ለሚተው እረኛ ወዮለት! ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዐይኑን ይውጋ! ክንዱ ፈጽማ ትሰልል፤ ቀኝ ዐይኑም ጨርሳ ትታወር!”
1ስለ እስራኤል የተነገረው የያህዌ ቃል ዐዋጅ ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፣ ምድርን የመሠረተ፣ የሰውን መንፈስ የሠራ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ 2“ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ የሚያንገዳግድ ጽዋ አደርጋታለሁ። ኢየሩሳሌም በምትከበብበት ጊዜ ይሁዳም ላይ እንደዚያው ይሆናል። 3በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን አሕዛብ ሁሉ ላይ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ። ያንን ድንጋይ ማንቀሳቀስ የሚሞክር ሁሉ ክፉኛ ይጎዳል፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ በዚያች ከተማ ላይ ይሰበሰባሉ።4በዚያ ቀን፣ ፍረሱን ሁሉ በሽብር፣ የተቀመጠበትንም ሁሉ በእብደት እመታለሁ። የይሁዳን ቤት በምሕረት አያለሁ፤ የጠላትን ፈረስ ሁሉ አሳውራለሁ። 5በዚያ ጊዜ የይሁዳ መሪዎች በልባቸው፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ አምላካቸው ስለ ሆነ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ብርታታችን ናቸው!” ይላሉ።6በዚያ ቀን የይሁዳን መሪዎች በእንጨት ክምር ውስጥ እንዳለ የእሳት ምድጃ በነዶም መካከል እንዳለ ችቦ ነበልባል አደርጋለሁ፤ በቀኝና በግራ ዙሪያውን ያሉትን ሕዝቦች ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌምም እንደ ገና ከምድሯ ትኖራልች።7የዳዊት ቤትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከይሁዳ ክብር እንዳይበልጥ፣ በዚያ ቀን ያህዌ በመጀመሪያ የይሁዳን መኖሪያዎች ያድናል። 8በዚያ ቀን ያህዌ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከለላ ይሆናል፤ በዚያ ቀን በመካከላቸው ያለው ደካማው እንደ ዳዊት፣ የዳዊት ቤትም በፊታቸው እንደ አምላክ፣ እንደ ያህዌም መልአክ ይሆናል። 9በዚያ ቀን ኢየሩሳሌም ላይ የሚነሡ ሕዝቦችን ሁሉ ማጥፋት እጀምራለሁ።10በዚያ ቀን በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ ወጉኝ ወደ እኔ ይመለክታሉ፤ እነርሱም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ሰው ያለቅሱልኛል፤ ለበኩር ልጁ ሞት እንደሚያለቅስ ሰው ምርር ብለው ያለቅሳሉ። 11በዚያ ቀን ኢየሩሳሌም ውስጥ የሚሆነው ለቅስ በመጊዶ ሜዳ ለሐዳድ ሪሞን እንደ ተለቀሰው ታላቅ ለቅሶ ይሆናል።12ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ የእያንዳንዱ ወገን ቤተ ሰብ ለየራሱ ያለቅሳል። የዳዊት ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የናታን ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ 13የሌዊ ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የሰማኢ ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ 14የቀሩትም ወገኖች ወንዶች ሁሉ ከነሚስቶቻቸው ያለቅሳሉ።
1በዚያ ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችን ኀጢአትና ርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል። 2በዚያ ቀን ከእንግዲህ አስታዋሽ እንዳይኖራቸው የጣዖቶችን ስሞች ከምድሪቱ አጠፋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። ሐሰተኛ ነቢያትንና ርኵሳን መናፍስቶቻቸውም ከምድሪቱ ይወገዳሉ።3ማንም ትንቢት ቢናገር ወላጅ አባት እናቱ፣ “በያህዌ ስም ሐሰት ተናግረሃልና ትሞታለህ!” ይሉታል። ትንቢት ሲናገርም የገዛ ወላጆቹ ይወጉታል።4በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ስለሚናገረው ትንቢት ራእይ ያፍራል። እነዚህ ነቢያት ሕዝቡን ለማታለል ከእንግዲህ ጠጕራም ልብስ አይለብስም። 5እያንዳንዱ፣ “እኔ ገበሬ እንጂ፣ ነቢይ አይደለሁም፤ ከልጅነቴ ጀምሮ ኑርዬ የተመሠረተውም በዚሁ ነበር!” ይላል። 6ሌላውም መልሶ፣ “ታዲያ፣ ክንዶችህ” መካከል ያሉት እነዚህ ቁስሎች ምንድናቸው?” በማለት ቢጠይቀው፣ “በባልንጀሮቼ ቤት ሳለሁ ያቆሰልሁት ነው” በማለት ይመልሳል።7“ሰይፍ ሆይ፣ በእረኛ፣ ለእኔ ቅርብ በሆነው ላይ ተነሣ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። እረኛውን ምታው በጎቹም ይበተናሉ! እኔም ክንዴን በታናናሾች ላይ አዘራለሁ።8የምድሩ ሁሉ ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል! ሰዎች ይሞታሉ አንድ ሦስተኛው ብቻ ይተርፋል ያላል ያህዌ።9እንደ ብር እንደነጹ፣ ያንን አንድ ሦስተኛ ሕዝብ በእሳት ውስጥ አሳልፋለሁ፤ ወርቅ እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ። ስሜን ይጠራሉ፣ እኔም እመልስላቸዋለሁ ‘ይህ ሕዝቤ ነው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ “ያህዌ አምላኬ ነው!” ያላሉ።
1እነሆ፣ ብዝበዛሽን በውስጥሽ የሚከፋፈሉበት ቀን ይመጣል። 2ሕዝብን ሁሉ ለጦርነት ኢየሩሳሌም ላይ አስነሣለሁ፤ ከተማዋም ትያዛለች። ቤቶች ይበዘበዛሉ፣ ሴቶች ይነወራሉ። የከተማው ግማሽ ሕዝብ በምርኮ ይወሰዳል፤ የተቀረው ሕዝብ ግን ከከተማው አይጠፋም።3ነገር ግን በጦርነት ጊዜ እንደሚዋጋ ያህዌ እነዚያን ሕዝቦች ይዋጋል። 4በዚያ ጊዜ እግሮቹ ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ባለው ደብረ ዘይት ተራራ ይቆማሉ። የደብረ ዘይት ተራራ በመካከሉ ባለው ታላቅ ሸለቆ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ለሁለት ይከፈልና እኩሌታው ወደ ሰሜን፣ እኩሌታው ወደ ደቡብ ይሄዳሉ።5እናንተም በያህዌ ተራሮች መካከል ባለው ሸለቆ በኩል ታመልጣላችሁ፤ በእነዚህ ተራሮች መካከል ያለው ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳል። በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ። ያኔ አምላኬ ያህዌ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር ቅዱሳኑ ይመጣሉ።6በዚያ ቀን ብርሃን አይኖርም፣ ብርድና ውርጭም አይኖርም። 7በዚያ በእግዚአብሔር ብቻ በሚታወቅ ቀን ቀንም ሆነ ማታ ከኢየሩሳሌም ይፈስሳል። 8ክረምትም ሆነ በጋ እኩሌታው ወደ ምሥራቅ ባሕር፣ እኩሌታው ወደ ምዕራብ ባሕር ይፈስሳል።9ያህዌ በመላው ምድር ይነግሣል። በዚያ ቀን አንድ አምላክ ያህዌ ብቻ ይሆናል፤ ስሙም አንድ ይሆናል። 10ከጌባ አንሥቶ በኢየሩሳሌም ደቡብ እስካለችው ሬሞን ድረስ ምድር ሁሉ እንደ አረባ ትሆናለች። ኢየሩሳሌም ከፍ እንዳለች ትዘልቃለች። ከብንያም በር አንሥቶ የመጀመሪያው በር እስከ ነበረበት እስከ ማእዘኑ በር ድረስ፣ ከሐናንኤል ግንብ እስከ ንጉሡ ወይን መርገጫ ድረስ በቦታዋ ትኖራለች። 11ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ይኖራል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ ጥፋት አይመጣባቸውም፤ ኢየሩሳሌም በሰላም ትኖራለች።12ኢየሩሳሌምን በወጉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያህዌ የሚያመጣባቸው መቅሠፍቶች እነዚህ ናቸው፤ በእግራቸው ቆመው እያለ ሥጋቸው ይበሰብሳል። ዐይኖቻቸው ጉድጓዶቻቸው ውስጥ እያሉ ይበሰብሳሉ፤ ምላሳቸው አፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል። 13በዚያ ቀን ከያህዌ ዘንድ ታላቅ ፍርሃት ይመጣባቸዋል። እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ አንዱ ሌላውን ይወጋል።14ይሁዳም ኢየሩሳሌምን ይወጋል። የአካባቢውን ሕዝቦች ሁሉ ሀብት ይሰበስባሉ፤ ወርቅ፣ ብርና ልብስ በብዛት ይኖራል። 15ፈረሶችና በቅሎዎች ላይ፣ ግመሎችና አይሆች ላይ መቅሠፍት ይወርዳል፤ ይኸው መቅሠፍት በየሰፈሩ ያሉ እንስሳትንም ሁሉ ይመታል።16ኢየሩሳሌምን ከወጓት ሕዝቦች ከሞት የተረፉት ለንጉሡ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ለመስገድና የዳስን በዓል ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ። 17በምድር ካሉ ሕዝቦች ሁሉ ለንጉሡ፣ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጣ ካለ፣ ያህዌ ደግሞ ዝናብ አያዘንብላቸውም። 18የግብፅ ሕዝብ የማይወጣ ከሆነ ዝናብ አያገኝም። የዳስ በዓልን ለማክበር በማይወጡ ሕዝቦች ላይ መቅሠፍት ከያህዌ ዘንድ ይመጣባቸዋል።19የዳስ በዓልን ለማክበር በማይወጣው ግብፅና ማንኛውም ሕዝብ ላይ የሚመጣው ቅጣት ይህ ይሆናል።20በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኩራ ላይ፣ “ለእግዚአብሔር የተቀደሰ” የሚል ጽሑፍ ይቀረጻል፤ በእግዚአብሔር ቤት ያሉት መታጠቢያዎች መሠዊያው ፊት እንዳሉት ሳህኖች የተቀደሱ ይሆናሉ፤ 21በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉት ምንቸቶች ሁሉ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ይቀደሳሉ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡ ሁሉ በእነርሱ በማብሰል ይበሉባቸዋል። በዚያ ቀን በሰራዊት ጌታ በያህዌ ቤት ውስጥ ከእንግዲህ ነጋዴዎች አይኖሩም።
1በሚልክያስ በኩል ወደ እስራኤል የመጣው የያህዌ ቃል ዐዋጅ ይህ ነው።2“እኔ ወድጃችኋለሁ” ይላል ያህዌ። እናንተ ግን፣ “እንዴት ወደድኸን?” ብላችኋል? “ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ያዕቆብን ወደድሁ3ዔሳውን ግን ጠላሁ። ተራራውን ባድማ አደረግሁ፤ ርስቱንም የምድረ በዳ ቀበሮዎች መኖሪያ አደረግሁ።”4ኤዶምያስ፣ “ብንደመሰስ እንኳ፣ የፈረሰውን መልስን እንሠራዋለን” ይል ይሆናል፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ “እነርሱ የሠሩ ይሆናል፤ እኔ ግን መልሼ አፈርሳለሁ።” ሌሎች ሰዎች፣ “የዐመፀኞች አገር፤ ያህዌ ለዘላለም የተቆጣው ሕዝብ” በማለት የጠሯቸዋል። 5የገዛ ዓይኖቻችሁ ይህን ያያሉ። ከእስራኤል ዳርቻዎች ወዲያ እንኳ ያህዌ ትልቅ ነው ትላላችሁ”6ለእናንተ ስሜን ለታቃልሉ ካህናት “ልጅ አባቱን ያከብራል፤ አገልጋይም ጌታውን ያከብራል። እኔ አባት ከሆንሁ፣ ታዲያ፣ ክብሬ የታለ? ጌታስ ከሆንሁ፣ መፈራቴ የታለ? ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። እናንተ ግን፣ “ስምህን ያቃለልነው በመንድነው?” ብላችኋል። 7መሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ በማቅረብ ነው። እናንተ፣ “ያረከስንህ በምንድነው” ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተናቀ ነው በማለታችሁ ነው።8የታወረውን እንስሳ መሥዋዕት ማቅረብ፣ በደል አይደለም? አንካሳውንና በሽተኛውን መሥዋዕት ማቅረብስ በደል አይደለም? እስቲ ያንኑ ለባለሥልጣን አቅርቡት፣ ይቀበላችኋልን? ወይስ በእናንተ ደስ ይለዋልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። 9አሁን ግን እንዲራራልን የእግዚአብሔርን ፊት ፈልጉ። ለመሆኑ፣ እንዲህ ዓይነቱን መሥዋዕት ይዛችሁ ስትቀርቡ እርሱ ይቀበላችኋልን? ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ።10መሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳት እንዳታነዱ፣ ምነው ከእናንተ አንዱ የቤተመቅደሱን ደጆች በዘጋ ኖሮ! በእናንተ ደስ አልሰኝም፤ ከእጃችሁም ማንኛውንም መሥዋዕት አልቀበልም ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።11ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ በሕዝቦች መካከል ስሜ ታላው ይሆናል፤ በየቦታው ሁሉ በስሜ ዕጣንና ንጹሕ መሥዋዕት ይቀርባል። በሕዝቦች መካከል ስሜ ታላቅ ይሆናል” የሠራዊት ጌታ ያህዌ። 12እናንተ ግን “የእግዚአብሔር ማዕድ የረከሰ ነው በማለት ታረክሱታላችሁ፤ ምግቡም የተናቀ ነው” በማለት ታቃልሉታላችሁ።13ደግሞም፣ “ይህ ድካም ነው” በማለት ፣ “በንቀት ጢቅ አላችሁበት” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። በዱር እንስሳ ተወስዶ የነበረውን ወይም አንካሳና በሽተኛውን መሥዋዕት ለማቅረብ ታመጣላችሁ። ታዲያ፣ ይህን ከእናንተ እጅ ልቀበል?” ይላል ያህዌ። 14“መንጋው ውስጥ ያለውን ተባዕት በግ መሥዋዕት ለማቅረብ ተስሎ ሳለ ለእኔ ነውር ያለበትን እንስሳ የሚያቀርብ አታላይ ርጉም ይሁን! እኔ’ኮ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በአሕዛብ መካከል ይከበራል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
1አሁንም፣ እናንተ ካህናት ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው። 2“የማትሰሙና ለስሜ ክብር ለመስጠት በልባችሁም የማታኖኑት ከሆነ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፣ “መርገም እልክባችኋለሁ፤ በረከታችሁን እረግማለሁ። ትእዛዜን በልባችሁ አላኖራችሁምና በእርግጥ ረግሜአችኋለሁ።3ዘራችሁን እገሥጻለሁ፤ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ ፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ እናንተም ከእርሱ ጋር ትጠፋላችሁ። 4ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ያዘዝሁ እኔ መሆኔንም ታውቃላችሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።5“ከእርሱ ጋር ያደረግሁት ኪዳን የሕይወትና የሰላም ኪዳን ነበር፤ እነዚህን ለእርሱ ሰጠሁት፤ አከበርኩት፤ እርሱ አከበረኝ፤ በስሜ ፊት በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ቆመ። 6እውነተኛ ትምህርት በአንደበቱ ነበር፤ በከንፈሮቹ ምንም ሐሰት አልተገኘም። በሰላምና በጽድቅ ከእኔ ጋር ተመላለሰ፤ ብዙዎችንም ከኅጢአት መለሰ። 7የካህኑ ከንፈሮች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ እርሱ የሠራዊት ጌታ የያህዌ መልዕክተኛ ስለሆነ ሰዎች ከአፉ ትምህርት መፈለግ ይኖርባቸዋል።8እናንተ ግን ከእውነተኛው መንገድ ወጥታችኋል። ሕጉን በተመለከተም ብዙዎችን አሰናክላችኋል፤ የሌዊን ኪዳን አፍርሳችኋል።” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። 9“መንገዴን አልጠበቃችሁም፤ ትምሕርቱን በተመለከተ አድልዎ አድርጋችኋል፤ ስለዚህ እኔም በሰዎች ሁሉ ፊት እንድትዋረዱና እንድትናቁ አደርጋለሁ።”10ለሁላችንም ያለን አንድ አባት አይደለምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? ታዲያ፣ እያንዳንዱ ሰው ለወንድሙ ታማኝ ባለመሆን የአባቶቻችንን ኪዳን ያረከስነው ለምንድንው? 11ይሁዳ አልታመነም። በእስራኤልና በኢየሩሳሌም አስጸያፊ ነገር ተፈጽሞአል። 12እንዲህ የሚያደርገውን ሰው፣ ሌላው ቀርቶ ለሠራዊት ጌታ ለያህዌ መሥዋዕት የሚያመጣ እንኳ ቢሆን፣ ያህዌ ከያዕቆብ ድንኳኖች ያስወግደው።13እናንተ ይህንንም አድርጋችኋል፣ የያህዌን መሠዊያ በእንባ አጥለቅልቃችኋል፤ እርሱ ቁርባናችሁን ስለማይመለከት ወይ በደስታ ከእጃችሁ ስለማይቀበለው ትጮኻላችሁ ታለቅሳላችሁም።14እናንተም፣ “ይህ ለምን ሆነ?” በማለት ትጠይቃላችሁ። እንዲህ የሆነው ያህዌ በአንተና በወጣትነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለሆነ ነው፤ የቃል ኪዳን ጓደኝህና ሚስትህ ብትሆን እንኳ አንተ ለእርሷ ታማኝ አልነበርክም። 15በመንፈሱ ክፋይ እግዚአብሔር አንድ አላደረጋቸውምን? እርሱ አንድ ያደረጋችሁ ለመንድነው? ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የሚሆን መሥዋዕት ስለፈለገ ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ከወጣትነት ሚስታችሁ ጋር ያላችሁንም ታማኝነት አታጉድሉ። 16“እኔ መፋታትን እጠላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ ያህዌ፤ “ልብሱን በግፍ ሥራ የሚሸፍነውንውም ሰው እጠላለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። “ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ታማኝነታችሁንም አታጉድሉ።”17በቃላችሁ ያህዌን አታክታችኋል። እናንተ ግን፣ “እርሱን ያታከትነው በምንድነው?” ብላችኋል። “ክፉ የሚያደርግ ሁሉ በያህዌ ፊት መልካም ነው፤ እርሱም በክፉዎች ደስ ይለዋል፤ ወይም፣ “የፍትህ አምላክ ወዴት ነው?” በመለታችሁ ነው።
1“እነሆ፣ መልእክተኝዬን እልካለሁ፤ እርሱም መንገዴን በፊቴ ያዘጋጃል። እናንተ የምትፈልጉትም ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ የመጣል። ደስ የምትሰኙበትን የቃል ኪዳኑ መልእክተፍኛ ለመጣ ነው” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።2እርሱ የሚመጠበትን ቀን ማን መቋቋም ይችላል? እርሱ ሲገለጥ ማን ፊቱ መቆም ይችላል? ምክናቱም እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳት፣ እንደ ለብስ አጠቢ ሳሙና ነው። 3ብር እንደሚያጠራና እንደ እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች ያጠራል እንደወርቅና እንደብር ያጠራቸዋል፤ እነርሱም የጽድቅን ቁርባን ለያህዌ ያመጣሉ።4ያኔ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ቁርባን እንደ ቀድሞ ዘመን፣ እንደጥንቱም ዘመን ያህዌን ደስ ያሰኘዋል። 5“በዚያ ጊዜ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ። በመተተኞችና በአመንዝራዎች ላይ፣ በሐሰተኛ ምስክሮችና የሠራተኞቻቸውን ደመወዝ በሚከለክሉ ላይ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቁን ላይ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ ላይ፣ እኔንም በማያከብሩ ላይ በፍጥነት እመሰክርባቸዋለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።6እኔ ያህዌ አልተለወጥሁም፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች አልጠፋችሁም።7ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ብላችኋል፤ እነርሱንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። እናንተ ግን፣ “የምንመለሰው እንዴት ነው?” ብላችኋል።8ሰው ከእግዚአብሔር ይሰርቃልን? እናንተ ግን ከእኔ ሰርቃችኋል፤ ያም ሆኖ ግን፣ “ከአንተ የሰረቅነው እንዴት ነው?” ብላችኋል። በዐሥራትና በበኩራት ነው። 9እናንተም ሆናችሁ መላው ሕዝብ ከእኔ ሰርቃችኋልና የተረገማችሁ ናችሁ።10በቤቴ መብል እንዲኖር ሙሉ አስራት ወደጎተራ አስገቡ። “በቂ ቦታ እስከማይኖራችሁ ድረስ የሰማይን መስኮት ከፍቼ በረከትን ባላፈስስላችሁ በዚህ አሁን ፈትኑኝ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። 11የምድራችሁን ፍሬ እንዳያጠፋ እህላችሁን የሚያጠፉትን እገሥጻለሁ። እርሻ ላይ ያለው የወይን ተክላችሁም ፍሬ አልባ አይሆንም” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። 12የምድር ደስታ ስለምትሆኑ ሕዝቦች ሁሉ ቡሩካን ብለው ይጠሯችኋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።13“እኔ ላይ የድፍረት ቃል ተናግራችኋል” ይላል ያህዌ። እናንተ ግን፣ “በአንተ ላይ የተናገርነው ምንድነው?” ትላላችሁ። 14“እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው ብላችኋል። የእርሱን ትእዛዞች መጠበቅ፣ ወይም በሠራዊት ጌታ በያህዌ ፊት ሐዘንተኞች ሆነን መመላለሳችን ጥቅሙ ምንድነው?” ብላችኋል።15ስለዚህም አሁን እብሪተኞችን ቡሩካን እንላቸዋለን። ክፉ አድራጊዎችን መበልጸግ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን የሚፈታተኑትም ያመልጣሉ።16ከዚያም ያህዌን የሚፈሩ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። እግዚአብሔርም ሰማ፤ አደመጠም፤ ያህዌን ስለሚፈሩትና ስሙንም ስለሚያከብሩት ሰዎች በፊቱ መታሰቢያ እንዲሆን ተጻፈ።17“እነርሱ የእኔ ይሆናሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፣ “እኔ በምሠራበት ቀን ርስቴ ይሆናሉ። ለሚያገለግለው ልጁ እንደሚራራ ሰው እኔም እራራላቸዋለሁ። 18በጻድቁና በዐመፀኛው መካከል፣ እግዚአብሔርን በሚያመልኩና እርሱን በማያመልኩ መካከል እንደገና ትለያላችሁ።
1“እብሪተኞችና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ገለባ የሚሆኑበት እንደምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል። የሚመጣው ቀን ያነዳቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፤ “ሥርም ሆን ቅርንጫፍ አይተውላቸውም።2ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን ፈውስ በክንፎቹ የያዘ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላቸዋል። እናንተም ከጋጥ እንደተለቀቁ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።3እኔ በምሠራበት ቀን ዐመፀኛውን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ጫማ በታች ዐመድ ይሆናሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።4ለእስራኤል ሁሉ ሕጎችና ሥርዐቶች ይሆኑ ዘንድ ለአገልጋዬ ለሙሴ በኮሬብ የሰጠሁትን ትምህርቶች አስታውሱ። 5ታላቁና አስፈሪው የያህዌ ቀን ከመምጣቱ በፊት ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ። 6መጥቼ ምድርን ፈጽሜ እንዳላጠፋ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የልጆችንም ልብ ውደ አባቶች ይመልሳል።
1የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ መጽሐፍ፡፡2አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና የይሁዳን ወንድሞች ወለደ፤3ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤4አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤5ሰልሞንም ከረዐብ ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፡፡6ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤7ሰሎሞንም ሮበዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አብያን ወለደ፤ አብያም አሳፍን ወለደ፤8አሳፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤9ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤10ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞጽን ወለደ፤ አሞጽም ኢዮስያስን ወለደ፤11ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ፡፡12ከባቢሎን ምርኮ በኋላም፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤13ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤14አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤15ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤ 16ያዕቆብም ክርስቶስ ተብሎ የሚጠራውን ኢየሱስን የወለደችውን፣ የማርያምን ባል ዮሴፍን ወለደ፡፡17ከአብርሃም እስከ ዳዊት፣ የነበሩት ትውልዶች ሁሉ ዐሥራ አራት፤ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ድረስም እንደዚሁ ዐሥራ አራት፤ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ድረስ የነበሩትም ዐሥራ አራት ትውልዶች ናቸው፡፡18የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሚከተለው መንገድ ተፈጸመ፡- እናቱ ማርያም ዮሴፍን ልታገባው ታጭታ ነበር፤ ነገር ግን ሳይጋቡ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች፡፡19ዮሴፍ ጻድቅ ነበረ፤ በመሆኑም እርሷን በሕዝብ ፊት ሊያዋርዳት አልፈለገም፡፡ ስለዚህ ከእርሷ ጋር የነበረውን የዕጮኛነቱን ግንኙነት በምስጢር ለማቋረጥ ወሰነ፡፡20ዮሴፍ ስለ እነዚህ ነገሮች እያሰበ ሳለ፣ የጌታ መልአክ፣ "የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፣ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ፤ ምክንያቱም እርሷ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነው።21እርሷ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ ሕዝቡንም ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ" በማለት ተገለጠለት።22-23ይህ ሁሉ የሆነው፣ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ብለው ይጠሩታል፤ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው" ብሎ ጌታ በነቢይ የተናገረው እንዲፈጸም ነው።24ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቃ፣ የጌታ መልአክ አዝዞት እንደ ነበረውም አደረገ፡- ማርያምን እን ደሚስቱ ወሰዳት፡፡25(ይሁን እንጂ፣ ልጅ እስከምትወልድ ድረስ ከእርሷ ጋር ግንኙነት አላደረገም፡፡) የሕፃኑንም ስም ኢየሱስ አለው፡፡
1በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ኢየሱስ በቤተ ልሔም ይሁዳ ከተወለደ በኋላ፣ ጠቢባን ሰዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ እንደዚህም በማለት ጠየቁ፤2‹‹የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት ነው? የእርሱን ኮከብ በምሥራቅ አየን፣ ልንሰግድለትም መጥተናል፡፡››3ንጉሡ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ ተረበሸ፤ መላው ኢየሩሳሌምም ከእርሱ ጋር ታወከ፡፡4ሄሮድስ የካህናቱን አለቆችና የሕዝቡን የሕግ መምህራን ሰብስቦ፣ ‹‹ክርስቶስ የሚወለደው የት ነው?›› በማለት ጠየቀ፡፡5‹‹በቤተ ልሔም ይሁዳ›› አሉት፤ በነቢዩ የተጻፈው ይህ ነውና፡6በይሁዳ ምድር የምትገኚ አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፣ ሕዝቡን እስራኤልን የሚጠብቅ ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልና፡፡7ከዚያም በኋላ ሄሮድስ ኮከቡ በትክክል በምን ሰዓት ታይቶ እንደ ነበር ሊጠይቃቸው ጠቢባኑን በምስጢር ጠራቸው፡፡8ወደ ቤተ ልሔምም ላካቸው፤ ‹‹ሂዱና ሕፃኑን በጥንቃቄ ፈልጉ፡፡ ስታገኙት እኔም ደግሞ እንድመጣና እንድሰግድለት ንገሩኝ›› አላቸው፡፡9ንጉሡ የተናገረውን ከሰሙ በኋላ ሄዱ፤ በምሥራቅ አይተውት የነበረውም ኮከብ ሕፃኑ በነበረበት ላይ እስኪደርስና እስኪቆም ድረስ በፊታቸው ይሄድ ነበር፡፡10ጠቢባኑ ኮከቡን ባዩት ጊዜ፣ እጅግ በጣም ተደሰቱ፡፡11ወደ ቤት ገብተው ሕፃኑንም ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት፡፡ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፣ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት፡፡12እግዚአብሔር ጠቢባኑን ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ በሕልም አስጠነቀቃቸው፤ ስለዚህም በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ፡፡13ጠበባኑ ከሄዱ በኋላ፣ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣ "ተነሥ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፡፡ እኔ እስክነግርም ድረስ እዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልጋልና" አለው፡፡14በዚያ ሌሊት ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ ግብፅ ሄደ፡፡15ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ እዚያው ቈየ፡፡ በዚህም ጌታ፣ ‹‹ልጄን ከግብፅ ጠራሁት›› ብሎ በነቢዩ የተናገረው ቃል ተፈጸመ፡፡16ከዚያም ሄሮድስ ጠቢባኑ እንደ ተሣለቁበት ሲገነዘብ በጣም ተናደደ፡፡ በቤተ ልሔምና በዚያ አውራጃ የነበሩ ወንድ ሕፃናትን፣ እንደዚሁም ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን ሁሉ ከጠቢባኑ በትክክል በተረዳው ጊዜ መሠረት ልኮ አስፈጀ፡፡17በዚያም በነቢዩ ኤርምያስ ተነግሮ የነበረው፡-18‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፣ ልቅሶና መሪር ዋይታ፣ ራሔል ስለ ልጆቿ በማልቀስ፣ ለመጽናናትም እምቢ አለች፣ በሕይወት የተረፈ የለምና›› የሚለው ተፈጸመ፡፡19ሄሮድስ ሲሞት፣ እነሆ፣ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣20‹‹ሕፃኑን ሊገድሉት የፈለጉት ስለ ሞቱ፣ ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ›› አለው፡፡21ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል አገር ሄደ፡፡22አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ስፍራ ተተክቶ ይሁዳን ይገዛ እንደ ነበረ ሲሰማ ግን ወደዚያ ለመሄድ ፈራ፡፡ እግዚአብሔር በሕልም ካስጠነቀቀው በኋላ፣ ወደ ገሊላ አውራጃ ሄደ፤23ናዝሬት በምትባል ከተማ ውስጥም ኖረ፡፡ ይህ በነቢዩ ተነግሮ የነበረውን፣ ናዝራዊ ተብሎ ይጠራል የሚለውን እንዲፈጸም አደረገ፡፡
1በእነዚያ ቀኖች መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ ፤2"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ እየሰበከ መጣ።3በነቢዩ ኢሳይያስ፦ "ምድረ በዳ ውስጥ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፣ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናዎቹንም አስተካክሉ" ተብሎ የተነገረለት ይህ ነውና።4ዮሐንስ ይለብስ የነበረው የግመል ጠጕር፣ በወገቡ የሚታጠቀውም የቆዳ ጠፍር ነው፤ ምግቡም አንበጣና የዱር ማር ነበረ።5በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌም፣ መላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።6ሕዝቡ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ እጅ ተጠመቁ።7ነገር ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፣ "እናንተ የመርዛማ እባቦች ልጆች ከሚመጣው ቊጣ ለማምለጥ ማን አስጠነቀቃችሁ?8ለንስሐ የሚጠቅም ፍሬ ይኑራችሁ።9ለራሳችሁም አብርሃም አባታችን አለን" ብላችሁ አታስቡ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች እንኳ ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና።10አሁን መጥረቢያው በዛፎቹ ሥር ተቀምጦአል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል በእሳት ውስጥም ይጣላል።11እኔ ለንስሐ የማጠምቃችሁ በውሃ ነው፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቃል፤ ጫማውን መሸከምም እንኳ አይገባኝም። እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።12ዐውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን በጎተራ ውስጥ ለመክተት መንሹ በእጁ ነው። ገለባውን ግን ፈጽሞ በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።13ከዚያም ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ።14ነገር ግን "እኔ አንተ እንድታጠምቀኝ ሲገባ፣ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?" በማለት ሊያስቆመው ሞከረ።15ኢየሱስም መልሶ፣ "አሁን ይህን ፍቀድ፤ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ለእኛ ተገቢ ነውና" አለው። ከዚያም በኋላ ዮሐንስ ፈቀደለት።16ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ፣ ወዲያውኑ ከውሃ ውስጥ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ። የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ መልክ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲቀመጥ አየ።17እነሆ፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው። "በእርሱ እጅግ ደስ ይለኛል" የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።
1ከዚያም በኋላ በዲያብሎስ ሊፈተን መንፈስ ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ መራው፡፡2ኢየሱስ ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ፡፡3ፈታኙ ወደ እርሱ መጣና፣ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እንጀራ እንዲሆኑ እነዚህን ድንጋዮች እዘዛቸው›› አለው፡፡4ኢየሱስ ግን መለሰና፣ ‹‹ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል" አለው፡፡5ከዚያም ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ወሰደው፤ በቤተ መቅደስ ሕንጻ ዐናት ላይም አቁሞ፣6የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ ‹እንዲጠብቁህ መላእክቱን ይልካል፣› እና ‹‹እግርህ ድንጋይ እንዳይመታው፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል›› ተብሎ ተጽፎአል አለው፡፡7ኢየሱስም፣ ‹‹‹ጌታ አምላክህን አትፈታተን› ተብሎም ተጽፎአል›› አለው፡፡8እንደ ገናም ዲያብሎስ ወደ አንድ ተራራ ወሰደውና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ከሙሉ ክብራቸው ጋር አሳየው፡፡9‹‹ብትወድቅና ብትሰግድልኝ፣ እነዚህን ሁሉ እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡10ከዚያም ኢየሱስ፣ አንተ ሰይጣን ከዚህ ሂድ! ‹ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፣ እርሱንም ብቻ አምልክ››› ተብሎ ተጽፎአልና አለው፡፡11ከዚያ በኋላ ዲያብሎስ ተወው፤ እነሆም፣ መላእክት መጡና ኢየሱስን አገለገሉት፡፡12ኢየሱስ የዮሐንስን መያዝ ሲሰማ፣ ወደ ገሊላ ሄደ፡፡13ናዝሬትን ትቶ በመሄድ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በገሊላ ባሕር አጠገብ ባለው በቅፍርናሆም ኖረ፡፡14ይህ የሆነው፣ በነቢዩ ኢሳይያስ ተነግሮ የነበረው እንዲፈጸም ነው፤ ይኸውም፡-15‹‹የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፣ በባሕሩ አቅጣጫ፣ ከዮርዳኖስ ማዶ፣ የአሕዛብ ገሊላ!16በጨለማ ውስጥ የኖረ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፣ በሞት ጥላና ምድር ውስጥ ለሚኖሩትም፣ ብርሃን ወጣላቸው›› የሚለው ነው፡፡17ኢየሱስ ከዚያ ጊዜ አንሥቶ፣ ‹‹መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡18ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ እየሄደ ሳለ፣ ሁለት ወንድማማቾችን አየ፤ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ ዓሣ አጥማጆች ስለ ነበሩ፣ ወደ ባሕሩ መረብ እየጣሉ ነበር፡፡19ኢየሱስ፣ ‹‹ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ›› አላቸው፡፡20እነርሱም ወዲያውኑ መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡21ኢየሱስ ከዚያ ዐለፍ እንዳለም ሁለት ሌሎች ወንድማማቾችን፣ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን አየ፤ ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ውስጥ መረቦቻቸውን ያበጃጁ ነበር፡፡ ኢየሱስም ጠራቸው፡፡22ወዲያውኑ ጀልባዋንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት፡፡23ኢየሱስ በምኵራቦቻቸው ውስጥ እያስተማረ፣ የመንግሥትን ወንጌልም እየሰበከና በሕዝቡ መካከል ያሉ በሁሉም የደዌና የበሽታ ዐይነት የሚሠቃዩትን እየፈወሰ በመላው ገሊላ ተዘዋወረ፡፡24ስለ እርሱ በሶርያ ምድር ሁሉ ተወራ፤ ሕዝቡም የታመሙትን ሁሉ፣ በልዩ ልዩ ደዌና ሕመም የሚሠቃዩትን፣ በአጋንንት የተያዙትንና የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡25ከገሊላ፣ ከዐሥሩ ከተሞች፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፡፡
1ኢየሱስ ሕዝቡን ሲያይ፣ ወደ ተራራ ወጣ፤ እዚያም ሲቀመጥ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ መጡ።2እንደዚህ እያለም አስተማራቸው፤3በመንፈስ የደኸዩ የተባረኩ ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።4የሚያዝኑ የተባረኩ ናቸው፤ ይጽናናሉና።5የዋሆች የተባረኩ ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።6ለጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ የተባረኩ ናቸው፤ ይጠግባሉና።7የሚምሩ የተባረኩ ናቸው፤ ይማራሉና።8ልበ ንጹሖች የተባረኩ ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና።9የሚያስታርቁ የተባረኩ ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።10ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ የተባረኩ ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።11ሰዎች ሲሰድቧችሁና ሲያሳድዷችሁ፣ ወይም በእኔ የተነሣ ክፉውን ሁሉ በእናንተ ላይ በሐሰት ሲናገሩ ብፁዓን ናችሁ።12በሰማይ ዋጋችሁ ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፣ ሐሤትም አድርጉ። ሰዎች ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት በዚህ መንገድ አሳድደዋቸዋልና።13እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ካጣ፣ እንደ ገና ጨው እንዴት መሆን ይችላል? ወደ ውጭ ተጥሎ በእግር ከመረገጥ በቀር ፈጽሞ ለምንም አይጠቅምም።14እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ የተመሠረተች ከተማ ልትሰወር አትችልም።15ሰዎች መብራት አብርተው ቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ በቅርጫት ሥር አያስቀምጡትም።16መልካሙን ሥራችሁን እንዲያዩና በሰማይ ያለ አባታችሁን እንዲያከብሩት መብራታችሁ እንዲሁ በሰዎች ፊት ይብራ።17ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ የመጣሁት ልሽራቸው ሳይሆን ልፈጽማቸው ነው።18ምክንያቱም፣ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ፣ ሁሉ እስኪፈጸምም ድረስ፣ ከሕግ እንዷ ፊደል ወይም ቅንጣት ከቶ አታልፍም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።19እንግዲህ ከእነዚህ ትእዛዞች ትንሿን የሚሽርና ለሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ የሚያስተምር፣ በመንግሥተ ሰማይ ታናሽ ይባላል። የሚጠብቃቸውና የሚያስተምራቸው ግን በመንግሥተ ሰማይ ታላቅ ይባላል።20ምክንያቱም፣ ጽድቃችሁ ከሕግ መምህራንና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ልቆ ካልተገኘ መንግሥተ ሰማይ ከቶ አትገቡም እላችኋለሁ።21ለቀደሙት፣ 'አትግደል፣ የገደለ ይፈረድበታል' እንደ ተባለ ሰምታችኋል።22እኔ ግን፣ 'ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ይፈረድበታል፣ ወንድሙን፣ 'አንተ የማትረባ!' የሚለው የሸንጎ ፍርድ፣ 'ቂል' የሚለውም የገሃነመ እሳት ፍርድ ይፈረድበታል።23እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ልታቀርብ ከሆነና ወንድምህ አንዳች ነገር በአንተ ላይ እንዳለው ካስታወስህ፣24መባህን በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ፣ በቅድሚያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ፣ ከዚያም ተመልሰህ መጥተህ መባህን አቅርብ።25ባላጋራህ ለዳኛው፣ ዳኛውም ለአሳሪው አሳልፎ እንዳይሰጥህና በወህኒ ውስጥ እንዳትጣል፣ ወደ ፍርድ ቤት ዐብረኸው እየሄድህ ሳለ ከሚከስስህ ባላጋራህ ጋር በፍጥነት ተስማማ።26እውነት እነግርሃለሁ፣ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ ፈጽሞ አትወጣም።27"አታመንዝር" እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤28እኔ ግን፣ ሴትን ተመኝቷት የሚመለከት ሁሉ በልቡ አመንዝሯል እላችኋለሁ።29የቀኝ ዐይንህ ቢያሰናክህል አውጥተህ ጣለው፤ መላ ሰውነትህ በገሃነም ከሚቃጠል፣ ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱ ቢጠፋ ይሻልሃልና።30የቀኝ እጅህም ቢያሰናክልህ ቆርጠህ ጣለው፤ መላ ሰውነትህ ገሃነም ውስጥ ከሚገባ ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱ ቢጠፋ ይሻልሃል።31'ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ የፍቺ ማረጋገጫ ይስጣት' ተብሎአል።32እኔ ግን፣ 'በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ እንድታመንዝር ያደርጋታል፤ ከተፈታች በኋላ የሚያገባትም ምንዝርና ይፈጽማል።33ደግሞም ለቀደሙት፣ በሐሰት አትማል፣ መሐላዎችህንም ለጌታ ስጥ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።34እኔ ግን ከቶ አትማሉ፤ በሰማይም፣ የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤35በምድርም፣ እግሩ የሚያርፍባት ናትና፤ በኢየሩሳሌምም፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና።36በራሳችሁም አትማሉ፤ አንዷን ጠጕር ነጭ ወይም ጥቍር ማድረግ አትችሉምና።37ነገር ግን ንግግራችሁ 'አዎ፣ አዎ'፣ ወይም 'አይደለም፣ አይደለም' ይሁን። ከዚህ የወጣ ሁሉ ከክፉው ነው።38ዐይን ስለ ዐይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፣39እኔ ግን እላችኋለሁ፣ 'ክፉውን ሰው አትቃወሙት፣ ይልቁን የቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውንም አዙርለት።40ማንም ሰው ሊከስስህና ኮትህን ሊወስድ ቢመኝ፣ ካባህንም ይውሰድ።41አንድ ምዕራፍ እንድትሄድ ማንም ሰው ቢያስገድድህ፣ ዐብረኸው ሁለት ምዕራፍ ሂድ።42ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፣ ከአንተ መበደር ከሚፈልገውም ፊትህን አታዙር።43ባልንጀራህን ውደድ፣ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።44እኔ ግን ጠላቶችህን ውደድ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ ብዬ እነግራችኋለሁ።45ይኸውም በሰማያት ያለ አባታችሁ ልጆች እንድትሆኑ ነው። እርሱ ፀሐይን በክፉዎችና በደጎች ላይ ያወጣል፤ ዝናብም በጻድቃንና በኅጥኣን ላይ ያዘንባል።46የሚወድዷችሁን ብትወዱ፣ ምን ዋጋ ታገኛላችሁ? ቀራጮች እንኳ እንደዚህ ያደርጉ የለምን?47ለወንድሞቻችሁ ብቻ ሰላምታ ብታቀርቡ፣ ከሌሎች የበለጠ የምታደርጉት ምንድን ነው? አሕዛብስ እንኳ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?48እንግዲህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።
1ሰዎች እንዲያዩአችሁ የጽድቅ ተግባሮቻችሁን በፊታቸው ከማከናወን ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ከሰማይ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም፡፡2ስለዚህ አንተ ምጽዋት ስትሰጥ ግብዞች የሰዎችን ከበሬታ ለማግኘት በምኵራቦችና በጐዳና ላይ እንደሚያደርጉት፣ በፊትህ ጥሩንባ አታስነፋ፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡3አንተ ግን ምጽዋት ስትሰጥ፣ የቀኝ እጅህ የሚያደርገውን የግራ እጅህ እንዲያውቅ አታድርግ፤4ይኸውም ምጽዋትህ በስውር የሚሰጥ እንዲሆንና ከዚያም በስውር የሚያይ አባትህ ዋጋህን እንዲከፍልህ ነው፡፡5ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ግብዞች ሕዝብ እንዲያያቸው በምኵራቦችና በጐዳና ማእዘኖች ላይ ቆመው መጸለይ ይወዳሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡6አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ጓዳህ ገብተህ በር ዝጋና በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡7ስትጸልይም አሕዛብ እንደሚያደርጉት ረብ የለሽ ድግግሞሽ አታድርግ፤ አሕዛብ በንግግራቸው ብዛት ምክንያት የሚሰሙ ይመስላቸዋልና፡፡8ስለዚህ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤ እናንተ ከመለመናችሁ በፊት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ አባታችሁ ያውቃልና፡፡9እንግዲህ እንደዚህ ጸልዩ፡- ‹በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ፡10መንግሥትህ ትምጣ፡፡ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን፡፡11የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፡፡12በደላችንን ይቅር በለን፣ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፡፡13ወደ ፈተና አታግባን፣ ከክፉው አድነን እንጂ፡፡› [መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም የአንተ ነውና፣ ለዘላለም፣ አሜን፡፡]14የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ብትሉ፣ የሰማይ አባታችሁ እናንተንም ይቅር ይላችኋል፡፡15የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ካላላችሁ ግን፣ የሰማይ አባታችሁ የእናንተን ኀጢአት ይቅር አይልም፡፡16ስትጾሙም ግብዞች እንደሚያደርጉት ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ እንደ ጾመኛ ለመታየት ግብዞች ፊታቸውን ያጠወልጋሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡17አንተ ግን ስትጾም ራስህን ተቀባ፣ ፊትሀንም ታጠብ፣18ይኸውም፣ በስውር ላለው የሰማይ አባትህ ብቻ እንጂ ለሰዎች ጾመኛ መስለህ እንዳትታይ ነው፡፡ በስውር የሚያይ የሰማይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡19ብልና ዝገት በሚበላውና ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት በምድር ላይ ሀብትን ለራሳችሁ አታከማቹ፡፡20ይልቁን ብልም ሆነ ዝገት በማያጠፋበት፣ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብትን ለራሳችሁ አከማቹ፡፡21ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛልና፡፡22ዐይን የሰውነት መብራት ነው፡፡ ስለሆነም ዐይንህ ጤናማ ከሆነ፣ መላ ሰውነትህ በብርሃን ይሞላል፡፡23ዐይንህ ጤናማ ካልሆነ ግን፣ መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል፡፡ እንግዲህ በውስጥህ ያለው መብራት በእውነት ጨለማ ከሆነ፣ ጨለማው እንዴት ከባድ ይሆን24! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡25ስለዚህ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ ወይም ምን እንደምትጠጡ፡- ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን?26አየር ላይ የሚበርሩ ወፎችን ተመልከቱ! እነርሱ እህል አይዘሩም ወይም አያጭዱም፣ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ፣ የሰማይ አባታችሁ ይመግባቸዋል፡፡ ከወፎች ይልቅ እናንተ እጅግ የሚበልጥ ዋጋ ያላችሁ አይደላችሁምን?27ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ቀን መጨመር የሚችል ይገኛልን?28ስለ ልብስስ የምትጨነቁት ለምንድን ነው?29ነገር ግን እነግራችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ክብሩ ሁሉ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡30እግዚአብሔር ዛሬ የሚታየውንና ነገ እሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንደዚህ ካለበሰ፣ እናንት እምነት የጐደላችሁ! እናንተንማ እንዴት እጅግ የበለጠ አያለብሳችሁም?31እንግዲህ ‹ምን እንበላለን?› ወይም ‹ምን እንጠጣለን?› ወይም ‹ምን እንለብሳለን?› ብላችሁ አትጨነቁ፡፡32አሕዛብ እነዚህን ሁሉ ይፈልጋሉና፤ የሰማይ አባታችሁ እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል፡፡33ነገር ግን በመጀመሪያ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ፤ ከዚያም እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡34ስለዚህ ለነገ አትጨነቁ፤ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና፡፡ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል፡፡
1አትፍረዱ፥ እናንተም አይፈረድባችሁም።2በምትፈርዱበት ፍርድ፥ ይፈረድባችኋል፤በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ፥ ለእናንተም ይሰፈርላችኋል።3በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታስተውል፥ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ የምታየው ለምንድን ነው?4በአንተ ዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ፣ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ ማለት እንዴት ትችላለህ?5አንተ ግብዝ! በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ በደንብ አይተህ ለማውጣት፣ በመጀመሪያ በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ አስወግድ።6በእግራቸው እንዳይረግጡትና እናንተንም እንዳይቦጫጭቁዋችሁ፤ ቅዱስ የሆነውን ለውሾች አትስጡ፥ እንቁዎቻችሁንም ለዐሳማዎች አትጣሉ።7ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፥ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።8የሚለምን ሰው ሁሉ ይቀበላልና፣ የሚፈልግ ሰውም ያገኛል፥ ለሚያንኳኳም ሰው ይከፈትለታል።9ከእናንተ መካከል ልጁ እንጀራ ሲለምነው፣ ድንጋይ የሚሰጠው፣10ዐሣ ሲለምነው፣ እባብ የሚሰጠው? ምን ዐይነት ሰው ነው?11እንግዲህ፥ እናንተ ክፉዎች የሆናችሁ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ የሚኖር አባታችሁ ለሚለምኑት አብዝቶ መልካም ስጦታን እንዴት አይስጣቸውም?12ስለዚህ፣ ማንኛውንም ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፣ እናንተም ልታደርጉላቸው ይገባል፤ ምክንያቱም ሕጉም ነቢያቱም የሚያስተምሩት ይህንኑ ነው፡፡13በጠባቡ በር ግቡ፣ ምክንያቱም ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ሰፊ፣ የሚሄዱበትም ብዙዎች ናቸው፡፡14በሩ ጠባብ፣ ወደ ሕይወት የሚወስደውም መንገድ ቀጭን ስለ ሆነ፣ የሚያገኙት ጥቂቶች ናቸው፡፡15የበግ ቆዳ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፣ በትክክል ግን ነጣቂ ተኩላዎች ከሆኑ፣ ከሃሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ።16በሚያፈሩት ፍሬ ታውቋቸዋላችሁ፡፡ሰው ከእሾኽ የወይን ፍሬ፣ ወይም ከኩርንችት በለስ ሊሰበስብ ይችላልን?17እንደዚያው፥ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፣ መጥፎ ዛፍ መጥፎ ፍሬ ያፈራል።18መልካም ዛፍ ሆኖ መጥፎ ፍሬ የሚያፈራ፣ ወይም መጥፎ ዛፍ ሆኖ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም።19ማንኛውም መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፣ ወደ እሳትም ይጣላል።20እንግዲህ በሚያፈሩት ፍሬ ታውቋቸዋላችሁ።21በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እንጂ፣" ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣" እያለ የሚጠራኝ ሁሉ፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባ አይደለም፡፡22በዚያ ቀን ብዙዎች፣ "ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣ በስምህ ትንቢት ተናግረን አልነበረም እንዴ፣ በስምህ አጋንንት አስወጥተን አልነበረም እንዴ፣ በስምህስ ብዙ ታላላቅ ነገሮችን አድርገን አልነበረም እንዴ?" ይሉኛል፡፡23እኔም፣ “እናንት ክፉ አድራጊዎች፣ የት ዐውቃችሁና ነው? ከእኔ ራቁ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ”24ስለዚህ፣ ቃሎቼን የሚሰማና የሚታዘዛቸው ልክ ቤቱን በድንጋይ ላይ የመሠረተ አስተዋይ ሰውን ይመስላል፡፡25ዝናብ ዘነበ፣ ጎርፍም ጎረፈ፣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት መታው፤ ይሁን እንጂ ቤቱ በዐለት ላይ ስለ ተመሠረተ፣ አልወደቀም፡፡26ሆኖም ቃሌን ሰምቶ የማይታዘዝ፣ ቤቱን በአሸዋ ላይ የመሠረተ ሞኝ ሰውን ይመስላል፡፡27ዝናብ ዘነበ፣ ጎርፍ ጎረፈ፣ ነፋስም ነፈሰ፣ ያንንም ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም ከባድ ሆነ ።28ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ተናግሮ ሲጨርስ፣ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡29ያስተማረውም እንደ ባለስሥልጣን እንጂ ፣እንደ ጽሐፍት አልነበረም።
1ኢየሱስ ከተራራው በወረደ ጊዜ፣ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።2እነሆ፣ አንድ ለምጻም ወደ እርሱ መጣ፣ “ጌታ ሆይ፣ ፈቃደኛ ከሆንህ፣ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት በፊቱ ሰገደለት።3ኢየሱስም፣ “ፈቃደኛ ነኝ ንጻ” በማለት እፉን ዘርግቶ ዳሰሰው። ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።4ኢየሱስ፣ “ተጠንቀቅ! ለማንም አትናገር። ዝም ብለህ ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ፣ምስክር እንዲሆናቸውም ሙሴ ያዘዘውን ስጦታ አቅርብ”አለው።5ኢየሱስ ወደቅፍርናሆም በገባ ጊዜ፣ አንድ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ መጥቶ፣6ጌታ ሆይ፣ "አገልጋዬ በከባድ ሕመም ሽባ ሆኖ ቤቴ ተኝቷል" በማለት ለመነው።7ኢየሱስ፣ "መጥቼ እፈውሰዋለሁ” አለው።8የመቶ አለቃውም መልሶ፣“ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፣ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር አገልጋዬም ይፈወሳል” አለው፡፡9እኔ ደግሞ ከሌላው ሥልጣን ሥር ያለሁና በእኔም ሥልጣን ሥር ወታደሮች ያሉኝ ሰው ነኝ። አንዱን “ሂድ” ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም “ና” ብለው ይመጣል፣ አገልጋዬንም 'ይህን አድርግ' ብለው ያደርጋል"፡፡10ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ በጣም ተደነቀ፣ ይከተሉት ለነበሩት ሰዎችም “እውነት ነው የምነግራችሁ፣ በእስራኤል እንኳ እንደዚህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም” አላቸው፡፡11እነግራችኋለሁ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፣ በእግዚአብሔር መንግሥትም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በማዕድ ይቀመጣሉ።12የመንግሥት ልጆች ግን ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ ውጪው ጨለማ ይጣላሉ፡፡13ኢየሱስም የመቶ አለቃውን፣ “ሂድ! እንደ እምነትህ ይሁንልህ" አለው። አገልጋዩም በዚያው ሰዓት ተፈወሰ ፡፡14ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ የጴጥሮስን አማት በትኩሳት ታማ ተኝታ አገኛት።15ኢየሱስ እጅዋን ነካት፣ ትኩሳቱም ለቀቃት፣ ተነሥታም ታገለግለው ጀመር።16በመሸ ጊዜ፣ ሕዝቡ አጋንንት የያዙአቸውን ብዙዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፣ እርሱም በቃሉ፣ መናፍስቱን አስወጣቸው፤ ታመው የነበሩትንም ሁሉ ፈወሳቸው።17በዚህ ዐይነት፣ በነቢዩ ኢሳይያስ፣ “እርሱ ሕመማችንን ተቀበለ ደዌዎቻችንን ተሸከመ” ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ።18ኢየሱስም በዙሪያው ያሉትን ሕዝብ ባየ ጊዜ፣ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ።19ከዚያም አንድ ጸሐፊ ወደ እርሱ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ፣ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው።20ኢየሱስም "ቀበሮዎች ጉድጓድ የሰማይ ወፎችም ጎጆዎች አሏቸው። የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያሳርፍበት ምንም ስፍራ የለውም"አለው።21ከደቀመዛሙርቱም ሌላው፣ "ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ እንድሄድና አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ አለው።"22ኢየሱስ ግን፣ “ተከተለኝ፣ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው” አለው።23ኢየሱስ ወደ ጀልባ በገባ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱም ተከትለውት ገቡ።24እነሆም፣ በባሕሩ ላይ ታላቅ ማዕበል ተነሥቶ ጀልባዋ በማዕበል ተሸፈነች። ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር።25ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ መጥተው፣ "ጌታ ሆ፣ እድነን ልንጠፋ ነው" በማለት ቀሰቀሱት።26ኢየሱስ፣ "እናንተ እምነት የጐደላችሁ ስለምን ፈራችሁ?”አላቸው። ከዚያም ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠፀ፣ ከዚያ በኋላ ታላቅ ጸጥታ ሆነ።27ሰዎቹም ተገርመው፣ "ይህ ምን ዓይነት ሰው ነው? ነፋሳትና ባሕሩም እንኳ ይታዘዙለታል" አሉ።28ኢየሱስም ወደ ማዶ ወደ ጌርጌሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፣ አጋንንት የተቆጣጠራቸው ሁለት ሰዎች ተገናኙት። የመጡትም ከመቃብር ነበርና በዚያ ማንም ማለፍ እስከማይችል ድረስ በጣም ኅይለኞች ነበሩ።29እነሆም፣ እየጮኹ፣ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ፣ እኛ ከአንተ ምን ጉዳይ አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?" አሉ።30ከዚያ አካባቢ ብዙ ሳይርቅ በግጦሽ ላይ ያሉ ብዙ ዐሳማዎች ነበሩ።31አጋንንቱም ኢየሱስን፣ "የምታወጣን ከሆነ ወደዚያ የዐሳማዎች መንጋ ስደደን" ብለው መለመናቸውን ቀጠሉ።32ኢየሱስም፣ "ሂዱ!"አላቸው። አጋንንቱም ወጥተው ዐሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ እነሆም፣ የዐሳማዎቹ መንጋ ሁሉ ወደ ታች ቁልቁለቱን እየተጣደፉ ወደ ባሕሩ ወርደው ውሃው ውስጥ ገብተው ጠፉ፡፡33እነዚያም ዐሳማዎቹን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች ሸሽተው ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ሁሉ ፣ በአጋንንት ተይዘው ስለ ነበሩት ሰለ ሁሉቱ ሰዎችም አወሩ።34የከተማውም ሕዝብ ሁሉ ኢየሱስን ለማየት መጡ። ባዩትም ጊዜ አካባቢያቸውን ለቆ አንዲሄድ ለመኑት።
1ኢየሱስ ወደ ጀልባ ገባ፤ ባሕሩንም አቋርጦ ወደ ገዛ ከተማው መጣ።2እነሆ፣ በምንጣፍ የተኛ አንድ ሽባ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን በማየት ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፣ አይዞህ፤ ኅጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው፡፡3አንዳንድ ጸሐፍት ግን እርስ በርሳቸው፣ "ይህ ሰው እኮ እየተሳደበ ነው" ተባባሉ ።4ኢየሱስም ዐሳባቸውን ዐውቆ፣ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?”5ለመሆኑ የሚቀለው፣'ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል' ነው፣ ወይስ 'ተነሣና ሂድ ማለት ነው?'6ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ዕወቁ" አለ፡፡ ሽባውንም፣ "ተነሣና፣ምንጣፍህን ይዘህ ወደ ቤት ሂድ" አለው፡፡7ከዚያም ሰውየው ተነሥቶ ወደ ቤቱ ሄደ።8ሕዝቡም ይህን ባዩ ጊዜ ተገርመው፣ ለሰው እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ።9ኢየሱስም ከዚያ አለፍ እንዳለ፣ ማቴዎስ የሚባለውን ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያ ቦታ ላይ ተቀምጦ አየውና "ተከተለኝ" አለው።እርሱም ተነሥቶ ተከተለው፡፡10ኢየሱስም በቤቱ ውስጥ ለመመገብ በተቀመጠ ጊዜ፣ ቀረጥ የሚሰበስቡ ብዙ ሰዎችና ኃጢአተኞች መጥተው፣ ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርት ጋር አብረው ተመገቡ።11ፈሪሳውያንም ይህን ሲያዩ፣ደቀ መዛሙርቱን "ለምንድን ነው መምህራችሁ፣ ከግብር ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላው?" አሏቸው፡፡12ኢየሱስም ይህንን ሲሰማ ፣"ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፡፡13'ሂዱና' ምሕረት እንጂ መሥዋዕትን አልፈልግም' የሚለውን ተማሩ፣ እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኅጥአንን ወደ ንስሓ ለመጥራት" ነው አለ።14ከዚያም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣" እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ እንጾማለን ፣የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?" አሉት።15ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ሰርገኞች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሆኖም ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፣በእነዚያ ቀናት ይጾማሉ።16ማንም ሰው በአሮጌ ልብስ ላይ ዐዲስ ቊራጭ ጨርቅ አይለጥፍም፤ ምክንያቱም አሮጌውን ልብስ ይቦጭቀዋል፣ ልብሱም የባሰ ይጐዳል።17ሰዎች ዐዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ ውስጥ አያስቀምጡም፤ እንደዚያ ካደረጉ አቁማዳው ይፈነዳል፣ የወይን ጠጁ ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይቀደዳል። ይልቁንም ዐዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ውስጥ ያስቀምጡታል፣ ሁለቱም ይጠበቃሉ፡፡"18ኢየሱስ ይህን እየተናገራቸው እያለ፣ አንድ ሹም እየሰገደ ወደ እርሱ መጣ። “ልጄ አሁን ገና ሞተች፣ ነገር ግን ና ና እጅህን ጫንባት በሕይወትም ትኖራለች አለው”።19ኢየሱስም ተነሥቶ ተከትሎት ሄደ፤ ደቀ ዛሙርቱም ደግሞ አብረውት ሄዱ።20አንዲት ለዐሥራ ሁለት ዓመት ከባድ የደም መፍሰስ የነበረባት ሴት፣ ከኢየሱስ ኋላ መጥታ የልብሱን ጠርዝ ነካች፤21"የልብሱን ጫፍ ብቻ ብነካ ደኅና እሆናለሁ" ብላ ነበርና።22ኢየሱስም ዞር ብሎ አያትና፣ “ልጄ ሆይ፣ አይዞሽ እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ሴቲቱም ወዲያውኑ ደኅና ሆነች።23ኢየሱስም ወደ ሹሙ ቤት በገባ ጊዜ፣ዋሽንት የሚነፉትንና የሚንጫጩትን አይቶ፣24"ወደዚያ ዞር በሉ፣ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም"አላቸው። እነርሱ ግን በማፌዝ ሳቁበት።25ሕዝቡን ወደ ውጭ ባስወጡ ጊዜ፥ ኢየሱስ ወደ ክፍሉ ገብቶ እጅዋን ያዘ፤ልጅቱም ተነሣች።26ወሬውም በዚያ አካባቢ ሁሉ ተዳረሰ።27ኢየሱስም በዚያ ሲያልፍ፣ ሁለት ዐይነ ስውሮች ተከተሉት፣ ያለ ማቋረጥም፣ "የዳዊት ልጅ ማረን!" እያሉ ይጮኹ ነበር።28ኢየሱስም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ፣ ዐይነ ስውሮቹ ወደ እርሱ መጡ። ኢየሱስም፣ "ይህን ለማድረግ እንደምችል ታምናላችሁ?" አላቸው። እነርሱም "አዎን፣ ጌታ ሆይ" አሉት፡፡29ከዚያም ኢየሱስ ዐይኖቻቸውን ዳስሶ፣ "እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ" አላቸው።30ዐይኖቻቸውም ተከፈቱ። ከዚያም ኢየሱስ፣"ይህንን ማንም እንዳያውቅ" ብሎ በጥብቅ አዘዛቸው።31ሁለቱ ሰዎች ግን ሄደው ወሬውን በየቦታው አዳረሱት።32ሁለቱ ሰዎች እየሄዱ እያሉ እነሆ፣ በጋኔን የተያዘ ዲዳ ወደ ኢየሱስ አመጡ።33ጋኔኑም ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ። ሕዝቡም ተገርመው፣ "እንዲህ ያለ ከዚህ በፊት በእስራኤል አልታየም" አሉ።34ፈሪሳውያን ግን "አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው" ይሉ ነበር።35ኢየሱስ ወደ ከተሞችና መንደሮች ሁሉ ሄደ፣ በየምኩኲራቦቻቸውም ማስተማሩን፣ የመንግሥትን ወንጌል መስበኩንና፣ ማንኛውንም ዐይነት በሽታና ደዌ መፈወሱን ቀጠለ።36ሕዝቡንም ሲያይ፣ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው ነበርና ራራላቸው።37ለደቀ መዛሙርቱም፣ "መከሩ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን ጥቂት ናቸው።38ስለዚህ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ፣ ወደ መከሩ ጌታ አጥብቃችሁ ጸልዩ" አላቸው።
1ሁለቱን ደቀ መዛሙርት በአንድ ላይ ጠርቶ፣ ርኩሳን መናፍስትን እንዲያወጡ፣ ሁሉንም ዐይነት በሽታና ደዌ እንዲፈውሱ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡2የዐስራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ የመጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣3ፊልጶስና በርተሎሜዎስ፣ ቶማስና ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ፣4ቀነናዊው ስምዖን፣አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።5ኢየሱስ እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን "አሕዛብ ወደሚኖሩበት የትኛውም ቦታ አትሂዱ፤ ወደ የትኛውም የሳምራውያን ከተማ አትግቡ።6ከዚያ ይልቅ ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት በጐች ሂዱ።7መንግሥተ ሰማይ ቀርባለች፣ ብላችሁ ስበኩ" ብሎ አስተምሮ ላካቸው።8ሕሙማንን ፈውሱ፣ ሙታንን አስነሡ፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ አጋንንትንም አስወጡ፣ በነጻ ተቀብላችኋል በነጻ ስጡ።9በቦርሳችሁ ወርቅ ብር ወይም ናስ አትያዙ፤10ለሠራተኛ ቀለቡ የሚገባው ስለ ሆነ፣ ለመንገዳችሁ ሻንጣ ወይም ትርፍ ልብስ፣ ወይም ጫማ፣ ወይም በትር አትያዙ።11ወደ የትኛውም ከተማ ወይም መንደር ስትገቡ፣ በዚያ ተገቢ የሆነው ሰው ማን እንደሆን እወቁ፤ ለቃችሁ እስከምትሄዱ ድረስ በዚያው ቆዩ።12ወደ ቤት ስትገቡ፣ ሰላምታ ስጡ።13ቤቱ የሚገባው ከሆነ ሰላማችሁ ይደርሰዋል፤ የማይገባው ከሆነ ግን ሰላማችሁ ይመለስላችኋል።14እናንተን የማይቀበላችሁን፣ ወይም ቃላችሁን የማይሰማውን በተመለከተ ግን፣ ከዚያ ቤት ወይም ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን አቧራ አራግፉ።15እውነት እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ይቀልላቸዋል።16ተመልከቱ፣ እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ። ስለዚህ፣ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።17ከሰዎች ተጠበቁ፣ ወደ ፍርድ ሸንጎ ያቅርቧችኋል፣ በምኲራባቸውም ይገርፏችኋል።18ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን፣ በእኔም ምክንያት ወደ ገዥዎችና ነገሥታት ፊት ትቀርባላችሁ።19ለፍርድም ሲያቀርቧችሁ፣ በዚያች ሰዓት የምትናገሩት ስለሚሰጣችሁ፣ ምን ወይም እንዴት እንደምትናገሩ አትጨነቁ።20በእናንተ ውስጥ የሚናገረው የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ የምትናገሩት እናንተ አይደላችሁም።21ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን፣ ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ተነሥተው ያስገድሏቸዋል።22ከስሜ የተነሣ በሰው ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ ነገር ግን ማንም እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል።23በዚህች ከተማ በሚያሳድዷችሁ ጊዜ ወደሚቀጥለው ከተማ ሽሹ። እውነት እላችኋለሁ፣ የሰው ልጅ ከመምጣቱ በፊት፣ የእስራኤልን ከተሞች አታዳርሱም።24ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ወይም አገልጋይ ከጌታው በላይ አይደለም።25ለደቀ መዝሙር ልክ እንደ መምህሩ፣ ለአገልጋይም ልክ እንደ ጌታው መሆን ይበቃዋል።26እንግዲህ አትፍሯቸው፤ የማይገለጥ የተሰወረ፣ የማይታወቅ የተደበቀ ምንም የለም።27በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን፣ በሹክሹክታ የምትሰሙትንም በአደባባይ ተናገሩት፡፡28ሥጋን እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ከዚያ ይልቅ ነፍስንም፣ ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ፡፡29ሁለት ድንቢጦች በትንሽ ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ሆኖም አንዷም ብትሆን አባታችሁ ሳያውቅ በመሬት ላይ አትወድቅም፡፡30የእናንተ ግን የራሳችሁ ጠጉር እንኳን ሳይቀር የተቈጠረ ነው፡፡31አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች የበለጠ ዋጋ አላችሁ፡፡32ስለዚህ በሰዎች ፊት ለሚመሰክርልኝ፣ እኔም በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፡፡33በሰው ፊት የሚክደኝን ግን፣ እኔም ደግሞ በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ፡፡34በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ፣ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም፡፡35ሰውን በአባቱ ላይ፣ ሴት ልጅን በእናቷ ላይ፣ ምራትን በአማቷ ላይ ለማነሣሣት መጥቻለሁ፡፡36የሰውም ጠላቶቹ የገዛ ቤተ ሰቦቹ ይሆናሉ፡፡37አባትን ወይም እናትን ከእኔ የበለጠ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም፤ እንዲሁም ወንድ ልጅን፣ ወይም ሴት ልጅን ከእኔ የበለጠ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም።38መስቀሉን ተሸክሞ፣ ከኋላዬ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም፡፡39ሕይወቱን የሚያገኛት ያጣታል፤ ስለ እኔ ብሎ ሕይወቱን የሚያጣት ግን ያገኛታል፡፡40እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፡፡41ነቢይ ስለ ሆነ ነቢይን የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅ ስለ ሆነ ጻድቅን የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል፡፡42እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ታናናሾች ለአንዱ፣ ደቀ መዝሙሬ ስለ ሆነ፣ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ማንም፣ በምንም ዐይነት ዋጋውን አያጣም፡፡
1እንዲህም ሆነ፣ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት አዝዞ ከጨረሰ በኋላ፣ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ ሄደ፡፡2ዮሐንስ በወህኒ ቤት ሆኖ የክርስቶስን ሥራዎች በሰማ ጊዜ፣ በደቀ መዛሙርቱ መልእክት ላከበት፡፡3እንዲህም አለው፣ "የሚመጣው አንተ ነህ፣ ወይስ መጠበቅ ያለብን ሌላ ሰው አለ?"4ኢየሱስም መለሰ እንዲህም አላቸው፤ “ሂዱና፣ ለዮሐንስ የምታዩትንና የምትሰሙትን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤5ዕውሮች ብርሃናቸውን እያገኙ፣ አንካሶች እየተራመዱ፣ ለምጻሞች እየነጹ፣ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ፣ ሙታን እየተነሡ፣ ድኾችም የምሥራች እየሰሙ ነው፡፡6በማንኛውም ሁኔታ በእኔ የማይሰናከል ሁሉ የተባረከ ነው" ።7እነዚህ ሰዎች እንደ ሄዱ፣ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ መናገር ጀመረ፣ እንዲህም አለ፣ "ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆን?8ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ? የሚያምር ልብስ የለበሰውን? በርግጥ፣ ጥሩ ልብስ የሚለብሱ የሚኖሩት በቤተ መንግሥት ነው፡፡9ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን ነውን? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጠውን ነው፡፡10እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ስለ እርሱ ነው፦ 'መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡'11እውነት እላችኋለሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም። በመንግሥተ ሰማይ ግን፣ ታናሹ ሰው ከእርሱ ይበልጣል፡፡12ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በዐመፅ ትቸገራለች፣ ዐመጸፀኞች ግን በኅይል ይወስዷታል፡፡13እስከ ዮሐንስ ዘመን ድረስ ሕጉም፣ ነቢያቱም ሁሉ ትንቢት ሲናገሩ ነበርና፡፡14እንግዲህ ልትቀበሉት ፈቃደኞች ከሆናችሁ፣ የሚመጣው ኤልያስ እርሱ ነው፡፡15የሚሰማ ጆሮ ያለው፣ ይስማ።16ይህን ትውልድ ከምን ጋር ላነጻጽረው? በገበያ ተቀምጠው፣ እየተቀባበሉ እንደሚዘፍኑ ልጆች ነው፡፡17'ዋሽንት ነፋንላችሁ፣ አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወጣንላችሁ እናንተም አላለቀሳችሁም' ይላሉ።18ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላና የወይን ጠጅ ሳይጠጣ በመምጣቱ፣'ጋኔን አለበት' አሉት።19የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ በመምጣቱ፣ 'ተመልከቱ ይህ ሰው በላተኛና ጠጪ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና፣ የኃጢአተኞች ወዳጅ ነው!' አሉት ነገር ግን ጥበብ በሥራዋ ትክክል ሆነች፡፡20ኢየሱስም ብዙ ታላላቅ ሥራዎች ያደረገባቸውን ከተማዎች፣ ንስሓ ባለመግባታቸው ይገሥጻቸው ጀመር፡፡21ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ታላላቅ ሥራዎች በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ ማቅ ለብሰውና፥ ዐመድ ነስንሰው ድሮ ንስሓ በገቡ ነበር፡፡22ነገር ግን በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ፣ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል፡፡23አንቺ ቅፍርናሆም፣ እስከ ሰማይ የወጣሽ ይመስልሻልን? በፍጹም፤ ወደ ሲኦል ትወርጂያለሽ፡፡ ለአንቺ እንደተደረጉት ትልልቅ ነገሮች በሰዶም ተደርገው ቢሆን ፣ እስከ አሁን በኖረች ነበር፡፡24ነገር ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን፣ ከእናንተ ይልቅ ለሰዶም ይቀልላታል፡፡25በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ ይህን ከዐዋቂዎችና ከአስተዋዮች ሰውረህ እንደ ሕፃናት ላልተማሩት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።”26አዎ፣ አባት ሆይ፣ በፊትህ እጅግ ደስ የሚያሰኝህ ይህ ሆኖአልና፡፡27ከአባቴ ሁሉ ተሰጥቶኛል፣ ከአባት በቀር ማንም ልጅን የሚያውቀው የለም፤ ከልጅም በቀር፣ ልጁም ሊገልጥለት ከሚፈልገው በቀር፣ አባትን የሚያውቅ ማንም የለም፡፡28እናንተ ደካሞች፣ ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋላሁ፡፡29ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህና በልቤ ትሁት ነኝ፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡፡30ቀንበሬ ቀላል፣ ሸክሜም የማይከብድ ነው፡፡
1በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት በእርሻ መካከል ሄደ። ደቀ መዛሙርቱም ተርበው ስለ ነበር፣ እሸቱን እየቀጠፉ ይበሉ ጀመር፡፡2ፈሪሳውያንም ያንን ባዩ ጊዜ፣ “ኢየሱስን፣ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት የሚያደርጉትን የማይገባ ነገር ተመልከት” አሉት፡፡3ኢየሱስ ግን፣ "ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ከቶ አላነበባችሁምን?4ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፣ ለካህናት ብቻ እንጂ ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ያልተፈቀደውን የተቀደሰ እንጀራ እንዴት እንደበላ?" አላቸው።5በሰንበት ካህናት በቤተ በመቀደስ ሥራ እንድሚሠሩና፣ ሰንበትን እንደሚያረክሱ፣ በደልም እንደማይሆንባቸው ከሕጉ አላነበባችሁምን?6እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ከቤተ መቅደስ የሚበልጠው እዚህ አለ፡፡7“መሥዋዕትን ሳይሆን ምሕረትን እፈልጋለሁ” የሚለውን ብታውቁ ኖሮ፣ በደል የሌለባቸውን አትፈርዱባቸውም ነበር፡፡8የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።"9ከዚያም ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ፣ ወደ ምኲራባቸው ገባ።10እነሆ፣ እጁ ሽባ የሆነ አንድ ሰው ነበረ፡፡ ፈሪሳውያንም ኢየሱስን በኅጢአት ለመክሰስ፣ "ሕጉ በሰንበት መፈወስን ይፈቅዳልን?" ብለው ጠየቁት፡፡11ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ከእናንተ መካከል አንድ በግ ብቻ ብትኖረውና፣ ያቺም በግ ጉድጓድ ውስጥ ብትገባበት፣ በሰንበት የማያወጣት ማን ነው?12ታዲያ ሰውማ ፣ ከበግ ይልቅ ምን ያህል ዋጋ ይኖረዋል! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዷል ፡፡"13ከዚያም ኢየሱስ፣ ሰውየውን፣ “እጅህን ዘርጋ” አለው፡፡ እጁንም ዘረጋ፣ እንደ ሌላውም እጅ ጤነኛ ሆነ፡፡14ነገር ግን ፈሪሳውያን ሄደው አሤሩበት፣ እርሱን የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡15ኢየሱስ ይህን እንዳወቀ፣ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤ እርሱም ሁሉንም ፈወሳቸው፡፡16ሰዎቹን ስለ እርሱ ለሌሎች እንዳይገልጹ አዘዛቸው፣17ይህም የሆነው በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፤18እነሆ፣ እኔ የመረጥኩት አገልጋዬ፤ የምወደው ነፍሴም ደስ የተሰኘችበት። መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ፍትሕን ለአሕዛብ ያውጃል።19አይጨቃጨቅም ወይም አይጮህም፤ ወይም ማንም ድምፁን በጐዳናዎች ላይ አይሰማም።20ፍርድን ለድል እስኪያበቃ ድረስ፤ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤሰውንም የጧፍ ክር አያጠፋም፣21አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።"22ከዚያም በአጋንንት የተያዘን ዐይነ ስውርና ዲዳ ሰው ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም ፈወሰው፤ ዲዳውም ተናገረ፣ አየም።23ሕዝቡም በመገረም፣ "ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆን እንዴ?" አሉ፡፡24ነገር ግን ፈሪሳውያን ይህን ተአምር በሰሙ ጊዜ “ይህ ሰው በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል ካልሆነ በቀር አጋንንቱን አያወጣም ነበር" አሉ፡፡25ኢየሱስም ዐሳባቸውን ዐውቆ ፣“እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ይወድቃል፤ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማ ወይም ቤት ሁሉ አይጸናም፡፡26ሰይጣን ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፣ እርስ በርሱ ተከፋፍሏል፣ መንግሥቱስ እንዴት ይቆማል?27እኔ አጋንንትን የማወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ተከታዮቻችሁ በማን ሊያወጡ ነው? ከዚህ የተነሣ እነርሱው ይፈርዱባችኋል፡፡28ነገር ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆነ፣ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥታለች፡፡29ማንም ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ቤቱ ገብቶ ንብረቱን እንዴት መዝረፍ ይችላል?፡፡ ካሰረው በኋላ ግን፣ ንብረቱን ይዘርፋል።30ከእኔ ጋር ያልሆነ ተቃዋሚዬ ነው፣ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል፡፡31ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ማንኛውም ኅጢአትና ስድብ ለሰዎች ይቅር ይባልላቸዋል ፤መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ግን ይቅር አይባልም፡፡32በሰው ልጅ ላይ ማንኛውንም ቃል የሚናገር ይቅር ይባልለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ግን፣ በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ይቅር አይባልም።33እንግዲህ ዛፍ የሚታወቀው በፍሬው ስለ ሆነ ዛፉን መልካም አድርጉ፤ ፍሬውም መልካም ይሆናል፣ ወይም ዛፉን መጥፎ አድርጉ ፍሬውም መጥፎ ይሆናል፡፡34እናንተ የእባብ ልጆች ክፉዎች ስለ ሆናችሁ፣ እንዴት መልካም ልትናገሩ ትችላላችሁ? ምክንያቱም በልብ ውስጥ የሞላውን አፍ ይናገረዋል፡፡35. መልካም ሰው በልቡ ውስጥ ካለው መልካም መዝገብ፣ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ልቡ ውስጥ ካለው ክፉ መዝገብ ክፉውን ይወጣል።36ለእናንተም እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ሰዎች ስለ ተናገሯቸው ከንቱ ንግግሮች መልስ ይሰጣሉ፡፡37ምትናገሩት ትጸድቃላችሁ፣ በምትናገሩትም ይፈረድባችኋልና፡፡38አንዳንድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን መልሰው ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፣ ምልክት እንድታሳየን እንፈልጋለን" አሉት።39ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፣ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምንም አይሰጠውም፡፡40ዮናስ በትልቅ ዐሣ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፣ የሰው ልጅም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ ይሆናል፡፡41የነነዌ ሰዎች በዮናስ ስብከት ንስሓ በመግባታቸው፣ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፡፡ ደግሞም ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ፡፡42የደቡብ ንግሥት፣ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻዎች መጥታለችና፣ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፡፡ደግሞም ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ፡፡43ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ፣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለባቸው ቦታዎች ያልፋል፣ ነገር ግን አያገኝም።44ከዚያም፣ 'ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ' ይላል። ሲመለስም ቤቱ ጸድቶ ተዘጋጅቶ ያገኘዋል፡፡45ከዚያም ይሄድና ከእርሱ ይልቅ የከፉትን ሰባት ሌሎች መናፍስትን ይዞ ይመጣል፣ ሁሉም በዚያ ለመኖር ይመጣሉ፡፡ የዚያም ሰው የመጨረሻው ሁኔታ ከመጀመሪያው የከፋ ይሆናል፡፡ በዚህ ክፉ ትውልድ ላይ የሚሆነውም እንደዚሁ ነው፡፡46ኢየሱስም ለሕዝቡ እየተናገረ እያለ፣ እናቱና ወንድሞቹ ሊያናግሩት ፈልገው፣ በውጭ ቆመው ነበር።47አንድ ሰውም፣ "እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ሊያነጋግሩህ በውጭ ቆመዋል" አለው።48ኢየሱስም መልሶ ለነገረው ሰው፣ "እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?" አለው።49ከዚያም እጁን ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፣ "እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው!50በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፣ ወንድሜ፣ እኅቴ እናቴም ነውና" አለ።
1በዚያ ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕር ዳርቻ ተቀመጠ።2በጣም ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ተሰበሰቡ፣ ስለዚህ ጀልባ ውስጥ ገብቶ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ቆመው ነበር።3ከዚያም ኢየሱስ በምሳሌ ብዙ ነገር ነገራቸው። እንዲህም አለ፤ "ዘሪ ለመዘራት ወጣ።4ሲዘራም፣ አንዳንዱ ዘር በመንገድ አጠገብ ወድቆ፣ ወፎች መጥተው በሉት።5ሌላውም ዘር በቂ አፈር በሌለበት በዐለታማ መሬት ላይ ወደቀ። አፈሩም ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ።6ፀሐይ ሲወጣ ግን፣ሥር ስላልነበረው ጠውልጎ ደረቀ።7ሌላው ዘር ደግሞ በእሾኽማ ቊጥቋጦ መካከል ወደቀ፣ እሾኹም አድጎ አነቀው።8ሌላው ዘር በመልካም መሬት ላይ ወድቆ ፍሬ አፈራ፤ አንዳንዱ መቶ፣ አንዳንዱ ሥልሳ፣ አንዳንዱም ሠላሳ ፍሬ አፈራ።9ጆሮ ያለው ይሰማ።"10ደቀ መዛሙርቱም መጡና ኢየሱስን፣ “ለምንድን ነው ለሕዝቡ በምሳሌ የምትናገረው?" አሉት።11ኢየሱስም መልሶ፣ "ለእናንተ የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር ማወቅ ተሰጥቷችኋል፣ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም" አላቸው።12ምክንያቱም ላለው ሁሉ የበለጠ ይሰጠዋል፤ ይበዛለትማል። የሌለው ግን ያለው እንኳ ይወሰድበታል።13ስለዚህ ለእነርሱ በምሳሌ እነግራቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ቢያዩ እንኳ እያዩ አይደለም፣ ቢሰሙም እየሰሙ አይደለም፣ ወይም አያስተውሉም።14በእነርሱ ላይ እንዲህ የሚለው የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጸመ ፦ መስማትን ትሰማላችሁ፣ ነገር ግን በምንም መንገድ አታስተውሉም፣ ማየትን ታያላችሁ፣ ግን ምንም አትገነዘቡትም።15በዐይናቸውም እንዳይመለከቱ፣ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ጆሯቸው ለመስማት ተደፍኗል፣ ዐይናቸውም ተጨፍኗል። እንዳይመለሱና እኔም እንዳልፈውሳቸው የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗል።16የእናንተ ዐይኖች ግን ስለሚያዩ፣ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ የተባረኩ ናቸው።17እውነት እላችኋለሁ፣ ብዙ ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ለማየት ተመኝተው አላዩም፤ የምትሰሙትን ለመስማት ተመኝተው አልሰሙም።18እንግዲህ የዘሪውን ምሳሌ ስሙ።19ማንም የመንግሥትን ቃል ሰምቶ ባያስተውል፣ ክፉው ይመጣል በልቡም የተዘራውን ይነጥቃል። ይህም በመንገድ ዳር የተዘራውን ይመስላል።20በዐለት ላይ የተዘራው ፣ቃሉን የሚሰማና ወዲያውኑ በደሰታ የሚቀበለው ነው፤21ሆኖም በራሱ ሥር ስለሌለው፣ የሚቆየው ለአጭር ጊዜ ነው። በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሚነሣበት ጊዜ፣ ወዲያውኑ ይሰናከላል።22በእሾኽ ተክሎች መካከል የተዘራው፣ ቃሉን የሚሰማ ሆኖ የዓለም ዐሳብ፣ የብልጥግናም አሳሳችነት ቃሉን ያንቁታል፣ ፍሬ ቢስም ይሆናል።23በመልካም መሬት ላይ የተዘራው፣ ቃሉን የሚሰማና የሚረዳ ነው፤ በርግጥ የሚያድገውና ፍሬ የሚሰጠውም ይህኛው ነው፤ አንዱ መቶ፣ አንዱም ሥልሳ፣ አንዱም ሠላሣ እጥፍ ያፈራል።24ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህ አለ፤ “መንግሥተ ሰማይ በዕርሻው ላይ መልካም ዘር የዘራ ሰው ትመስላለች።25ሰዎቹ በተኙ ጊዜ ግን፣ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው መካከል እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ።26ቅጠሉም በለመለመና ፍሬ ማፍራት በጀመረ ጊዜ፣ እንክርዳዱ ደግሞ አለ።27የዕርሻው ባለቤት አገልጋዮች መጥተው፣ "ጌታ ሆይ፣ በዕርሻው ላይ መልካም ዘር ዘርተህ አልነበረምን? ታዲያ እንክርዳድ የበቀለው እንዴት ነው?"አሉት።28እርሱም፣ “ጠላት ይህን አደረገ" አላቸው። አገልጋዮቹም መልሰው፣"ስለዚህ ሄደን እንድንነቅለው ትፈልጋለህን?" አሉት።29የዕርሻውም ባለቤት፣ 'አይሆንም፣ እንክርዳዱን በምትነቅሉበት ጊዜ ስንዴውንም አብራችሁ ልትነቅሉት ትችላላችሁ 'አላቸው።30እስከ መከር ድረስ አብረው ይደጉ። በመከሩ ጊዜ ለኣጫጆቹ፣ "መጀመሪያ እንክርዳዱን ነቅላችሁ እንዲቃጠል አንድ ላይ ሰብስቡ። ስንዴውን ግን ሰብስባችሁ ወደ ጎተራዬ አስገቡት እላቸዋለሁ" አላቸው።31ኢየሱስም ሌላ ምሳሌ ነገራቸው። እንዲህም አለ፤ “መንግሥተ ሰማይ ሰው ወስዶ በዕርሻው ላይ የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች።32በርግጥ ይህች ዘር ከሌሎች ዘሮች ሁሉ ታንሳለች። በምታድግበት ጊዜ ግን የሰማይ ወፎች በቅርንጫፎቿ እስኪሰፍሩባት ድረስ፣ ከሌሎች ዛፎች ትበልጣለች፡፡33ከዚያም ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ ሴት ወስዳ ኩፍ እስኪል ድረስ ከሦስት እጅ ዱቄት ጋር የደባለቀችውን እርሾ ትመስላለች።”34ኢየሱስም ለሕዝቡ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፣ ያለ ምሳሌም ምንም አልነገራቸውም።35ይህም ፦ "አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፣ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ የተሰወረውን እገልጣለሁ" ተብሎ በነቢዩ የተነገረው እንዲፈጸም ነው።36ኢየሱስ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ መጥተው "በዕርሻው የነበረውን የእንክርዳዱን ምሳሌ አስረዳን" አሉት።37ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አለ፤ “መልካሙን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው።38ዕርሻው ይህ ዓለም ነው፣ መልካሙ ዘር የመንግሥቱ ልጆች ናቸው። እንክርዳዱ የክፉው ልጆች ናቸው፤39ዘሩን የዘራው ጠላት ዲያብሎስ ነው። መከሩ የዓለም መጨረሻ ሲሆን፣ አጫጆቹም መላእክት ናቸው።40ስለዚህ እንክርዳዱ ተሰብስቦ በእሳት እንደሚቃጠል፣ በዓለም መጨረሻም እንዲሁ ይሆናል።41የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፣ ከመንግሥቱ ለኅጢአት ምክንያት የሆኑ ነገሮችን ሁሉና፣ ክፉ አድራጊዎችን ይሰበስቧቸዋል፣42ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት፣ ወደ እቶን እሳትም ይጥሏቸዋል።43ከዚያም ፃድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ። ጆሮ ያለው ይስማ።44መንግሥተ ሰማይ በዕርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት ትመስላለች፣ አንድ ሰውም አግኝቶ ደበቃት፤ ከደስታውም የተነሳ ያለውን ንብረት ሁሉ ሸጦ ያንን ዕርሻ ገዛው።45ደግሞም፣ መንግሥተ ሰማይ የከበሩ ዕንቈች የሚፈልግ ነጋዴን ትመስላለች።46በጣም ትልቅ ዋጋ ያለው ዕንቊ ባገኘ ጊዜ፣ ሄዶ ያለውን ንበረት ሁሉ ሸጠና ገዛው።47እንዲሁም፣መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር የተጣለችና ሁሉም ዓይነት ፍጥረታት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች።48መረቡዋ ስትሞላ፣ ዓሣ አጥማጆቹ ወደ ዳር አወጡት። ተቀምጠውም መልካም መልካሙን ሰብስበው በዕቃ አደረጉ፣ የማይጠቅመውን ግን አውጥተው ጣሉት።49በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፣ መላእክት መጥተው ከጻድቃን መካከል ክፉዎችን ይለያሉ።50ከዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት፣ ወደሚነደው እቶን እሳት ይጥሏቸዋል።51ይህን ሁሉ ተረድታችኋል?" አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም፣ “አዎን” አሉት።52ከዚያም ኢየሱስ፣ “ ስለዚህ የመንግሥተ ሰማይ ደቀ መዝሙር የሆነ ጸሐፊ ሁሉ፣ ከሀብቱ መካከል አሮጌውንና ዐዲሱን ያወጣ የቤት ጌታን ይመስላል አላቸው"።53ከዚያም ኢየሱስ እነዚህን ምሳሌዎች በጨረሰ ጊዜ፣ ከዚያ ስፍራ ሄደ።54ኢየሱስ ወደ ራሱ አገር መጥቶ፣ በምኲራቦቻቸው ሕዝቡን አስተማረ፣ ከዚህም የተነሣ ተገርመው፣ "ይህ ሰው ይህን ጥበቡንና እነዚህን ተአምራት ከየት አገኘ?55ይህ ሰው የአናጢው ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም አይደለችም ወይ? ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳስ ወንድሞቹ አይደሉም ወይ?56እኅቶቹስ ከእኛው ጋር አይደሉም ወይ? ታዲያ ይህ ሰው እነዚህን ነገሮች ሁሉ ከየት አገኛቸው?" አሉ።57በእርሱም ተሰናከሉበት። ኢየሱስ ግን፣ "ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤተ ሰቡ በቀር መከበሩ አይቀርም" አላቸው።58በአለማናቸውም ምክንያት ፣በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።
1በዚያን ጊዜ፣ የአራተኛው ክፍል ገዢ የነበረው ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ሰማ።2አገልጋዮቹንም፣ "ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው። ስለዚህ ይህ ሁሉ ኅይል በእርሱ የሚሠራው ከሞት ስለ ተነሣ ነው" አላቸው።3ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት፣ ይዞ አሳስሮት ነበርና፡፡4ምክንያቱም ዮሐንስ፣ "እርሷን ማግባትህ ተገቢ አይደለም" ይለው ነበር።5ሄሮድስ ሊያስገድለው ፈልጎ፣ ሕዝቡን ፈራ፣ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያዩት ነበር።6ነገር ግን በሄሮድስ የልደት ቀን፣ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከል ስትጨፍር፣ ሄሮድስን ደስ አሰኘችው።7በዚህም ምክንያት፣ የምትጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰጣት በመሓላ ቃል ገባላት።8በእናቷም ተመክራ፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ እዚሁ፣ በሳሕን አድርገህ ስጠኝ” አለችው።9ንጉሡ በጥያቄዋ በጣም ዐዘነ፣ ነገር ግን በመሓላውና ከእርሱ ጋር እራት ላይ በነበሩት ምክንያት፣ የተናገረው እንዲፈጸም አዘዘ።10ሰው ልኮ፣ በወህኒ ቤት የዮሐንስን ራስ አስቈረጠ።11ከዚያም ራሱ በሳሕን ተደርጎ ለልጅቱ ተሰጣት፣ እርሷም ለእናቷ ወስዳ ሰጠች።12ከዚያም የእርሱ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣ በድኑን ወስደው ቀበሩት። ከዚህ በኋላ ሄደው ለኢየሱስ ነገሩት።13ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ በጀልባ ገለል ወዳለ ቦታ ሄደ። ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ፣ ከየከተሞቹ በእግር ተከተሉት።14ከዚያም ኢየሱስ ቀድሞአቸው መጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና ራራላቸው፣ ሕመምተኞቻቸውንም ፈወሰ።15በመሸም ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ መጡና፣ “ቀኑ መሽቷል ይህም ስፍራ ምድረ በዳ ነው ። ሕዝቡን ወደ መንደሮች እንዲሄዱና፣ ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ አሰናብት" አሉት።16ኢየሱስ ግን፣ "መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተው የሚበሉትን ስጧቸው" አላቸው።17እነርሱም፣ “ እኛ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዐሣ ብቻ ነው" አሉት።18ኢየሱስም፣ "እነርሱኑ ወደ እኔ አምጡአቸው" አለ።19ከዚያም ኢየሱስ ሣሩ ላይ እንዲቀምጡ ሕዝቡን አዘዘ። ዐምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዐሣ ወሰደ፣ ወደ ሰማይ አሻቅቦ እያየ፣ አመሰገነ፤ እንጀራውንም ቈርሶ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ።20ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚያም የተረፈውን ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ ቊርስራሽ ሰበሰቡ።21የበሉትም፣ ከሴቶችና ከልጆች ሌላ፣ ዐምስት ሺ ያህል ወንዶች ነበሩ።22እርሱም ሕዝቡን እያሰናበተ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱን ወዲያው ወደ ጀልባ ገብተው፣ ከእርሱ በፊት ወደ ማዶ እንዲሄዱ አዘዛቸው።23ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ፣ ብቻውን ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። በመሸ ጊዜ፣ በዚያ እርሱ ብቻውን ነበር።24ጀልባዋ በባሕሩ መካከል እያለች፤ ከተቃራኒ አቅጣጫ ይነፍስ ስለ ነበር፣ በማዕበሉ ክፉኛ ትንገላታ ነበር።25ከምሽቱ በአራተኛው ክፍል፣ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ እየመጣ ነበር።26ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ እየተራመደ ሲያዩት፣ እጅግ ደንግጠው፣ “መንፈስ ነው”ብለው በፍርሀት ጮኹ።27ኢየሱስ ግን ወዲያውኑ፣ “አይዟችሁ! እኔ ነኝ! አትፍሩ” ብሎ ተናገራቸው።28ጴጥሮስም መልሶ፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተስ ከሆንህ፣ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ" አለው።29ኢየሱስም፣ “ና" አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወጥቶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ፣ በውሃው ላይ ተራመደ።30ነገር ግን ጴጥሮስ ነፋሱን አይቶ በመፍራት፣ መስጠም በጀመረ ጊዜ ፣ “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ” ብሎ ጮኸ።31ኢየሱስም ያኔውኑ እጁን ዘርግቶ ጴጥሮስን ያዘውና፣ “አንተ እምነት የጎደለህ፣ ለምን ትጠራጠራለህ?” አለው።32ከዚያም ኢየሱስና ጴጥሮስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ፣ ነፋሱ መንፈሱን አቆመ።33በጀልባው ውስጥ የነበሩት ደቀ መዛሙርትም ኢየሱስን፣ “አንተ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።34ከተሻገሩም በኋላ፣ ጌንሳሬጥ ወደ ተባለ አገር መጡ።35በዚያም ስፍራ የነበሩ ሰዎች ኢየሱስ መሆኑን ባወቁ ጊዜ፣ በአካባቢው ወዳለ ስፍራ ሁሉ መልእክት ላኩና፣ የታመመውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ።36የልብሱን ጫፍ ብቻ ለመንካት ለመኑት፣ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ።
1ከዚያም አንዳንድ ፈሪሳውያንና የአይሁድ የሕግ መምህራን ከኢየሩሳሌም ኢየሱስን ለማነጋገር መጥተው እንዲህ አሉ፤2"ደቀ መዛሙርትህ የሽማግሌዎችን ወግ የሚጥሱት ለምንድነው? ምግብ ከመብላታቸው በፊት እንደ ወጉ እጃቸውን አይታጠቡምና።"3ኢየሱስም መለሰና፣ "እናንተስ ስለ ወጋችሁ ስትሉ ለምን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትተላለፋላችሁ?" አላቸው፡፡4እግዚአብሔር፣ ‹አባትህንና እናትህን አክብር፣› ‹ስለ አባቱ ወይም ስለ እናቱ ክፉ የሚናገር በርግጥ ይሞታል› ብሏልና፡፡5እናንተ ግን፣ "አባቱን ወይም እናቱን፣ 'ከእኔ የተቀበላችሁት ማንኛውም እርዳታ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው ትላላችሁ፡፡'6ያ ሰው አባቱን ማክበር አያስፈልገውም። ስለ ወጋችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፡፡7እናንተ ግብዞች፣ ኢሳይያስ ስለ እናንተ፣8'ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤9የሰዎችን ትእዛዝ እንደ ሕግ በመቊጠር የራሳቸውን ትምህርት ስለሚያስተምሩ፣ እኔን በከንቱ ያመልኩኛል›› ብሎ ትንቢት በመናገሩ መልካም አድርጓል።10ከዚያ ሕዝቡን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ "አድምጡ አስተውሉም፡-11ወደ አፍ የሚገባ ሰውን ምንም አያረክስም፡፡ ይልቁንም ከአፍ የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ነው" አላቸው፡፡12ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ኢየሱስን፣ ‹‹ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሲሰሙ እንደ ተሰናከሉ ዐወቀሃል?›› አሉት፡፡13ኢየሱስም መለሰና፣ ‹‹አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል፤14እነርሱን ተዉአቸው፤ ዐይነ ስውር መሪዎች ናቸው፡፡ አንድ ዐይነ ስውር ሌላውን ዐይነ ስውር ቢመራው ሁለቱም ተያይዘው ጕድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡››15ጴጥሮስ መልሶ ኢየሱስን፣ ‹‹ይህን ምሳሌ አብራራልን›› አለው፡፡16ኢየሱስ፣ ‹‹እናንተ ደግሞ አሁንም አታስተውሉምን?17ወደ አፍ የሚገባው ሁሉ ወደ ሆድ እንደሚሄድና ከዚያም ዐይነ ምድር ሆኖ ወደ ውጭ እንደሚጣል አታስተውሉምን?18ዳሩ ግን ከአፍ የሚወጣ ከልብ ይወጣል፡፡ እነዚህ ነገሮች ሰውን ያረክሳሉ፡፡19ከልብ ክፉ ዐሳብ፣ ነፍስ መግደል፣ ምንዝርና፣ ዝሙት፣ ስርቆት፣ የሐሰት ምስክርነትና ስድብ ይወጣሉ፤20ሰውን የሚያረክሱት እነዚህ ናቸው፡፡ ነገር ግን ባልታጠበ እጅ መብላት ሰውን አያረክስም፡፡"21ቀጥሎም ኢየሱስ ከዚያ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና ከተሞች አካባቢ ሄደ፡፡22እነሆም፣ አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከዚያ አካባቢ ወጣችና ጮኽ ብላ እንዲህ አለች፣ ‹‹የዳዊት ልጅ፣ ጌታ ሆይ፣ ማረኝ፡፡ ልጄ በጋኔን ተይዛ በጣም እየተሠቃየች ነው፡፡››23ኢየሱስ ግን አንድም ቃል አልመለሰላትም፡፡ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው፣ ‹‹ይህች ሴት ትጮኽብናለችና ሸኛት›› ብለው ለመኑት፡፡24ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ፣ ‹‹እንደ በግ ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት ሰዎች ካልሆነ በቀር ወደ ማንም አልተላክሁም›› አለ፡፡25ነገር ግን ሴቲቱ "ጌታ ሆይ፣ እርዳኝ" በማለት መጥታ በፊቱ ሰገደች፡፡26ኢየሱስ መልሶ፣ "የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለቡችሎች መጣል ትክክል አይደለም" አለ፡፡27ሴቲቱ፣ "አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ ከሚወድቀው የተወሰነውን ትርፍራፊ ይበላሉ" አለች፡፡28ከዚያም ኢየሱስ መልሶ፣ "አንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው፤ ልክ እንደ ተመኘሽው ይሁንልሽ" አላት፡፡ ልጇም በዚያች ሰዓት ተፈወሰች፡፡29ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ወደ ገሊላ ባሕር አቅራቢያ ሄደ፡፡ ከዚያም ወደ አንድ ኮረብታ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ፡፡30ብዙ ሕዝብም ወደ እርሱ መጡ፤ አንካሶችን፣ ዐይነ ስውሮችን፣ ዲዳዎችንና ጕንድሾችን፣ እንዲሁም ሌሎች ታመው የነበሩ ብዙዎችን ይዘው መጡ፡፡ በኢየሱስ እግር አጠገብም አስቀመጧቸው፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡31ስለዚህ ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ፣ ጕንድሾች ሲፈወሱ፣ አንካሶች ሲራመዱ፣ ዐይነ ስውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፡፡ የእስራኤልንም አምላክ አመሰገኑ፡፡32ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ "ለሕዝቡ አዝንላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ከእኔ ጋር ሦስት ቀን ቈይተዋል፣ የሚበሉትም የላቸውም፡፡ በመንገድ ላይ ዝለው እንዳይወድቁ ሳይበሉ ዝም ብዬ አላሰናብታቸውም" አለ፡፡33ደቀ መዛሙርቱ፣ "በዚህ በረሓ ይህን የሚያህል ብዙ ሕዝብ የሚያጠግብ እንጀራ ከየት እናገኛለን?" አሉት፡፡34ኢየሱስ፣ "ስንት እንጀራ አላችሁ?" አላቸው፡፡ "ሰባት እንጀራና ጥቂት ትናንሽ ዐሣ አለ" አሉት፡፡35ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን መሬት ላይ እንዲቀመጡ አዘዛቸው፡፡36ኢየሱስ ሰባቱን እንጀራና ዐሣዎቹን ይዞ ካመሰገነ በኋላ እንጀራውን ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጧቸው፡፡37ሕዝቡ ሁሉ በሉና ጠገቡ፡፡ ትርፍራፊውንም ሰበሰቡ፤ ትርፍራፊውም ሰባት ቅርጫት ሙሉ ነበር፡፡38የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡39ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን አሰናበተና በጀልባም ገብቶ መጌዶን ወደ ተባለ ክፍለ አገር ሄደ፡፡
1ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም መጥተው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው በመጠየቅ ኢየሱስን ፈተኑት፡፡2ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "በመሸ ጊዜ ሰማዩ ቀልቷልና ዝናብ አይኖርም ትላላችሁ3በነጋ ጊዜም፣ ‹ዛሬ ሰማዩ ስለ ጠቈረ ይዘንባል› ትላላችሁ፤ የዘመኑን ምልክት ግን መለየት አትችሉም፡፡4ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም፡፡" ከዚያም ኢየሱስ ትቶአቸው ሄደ፡፡5ደቀ መዛሙርቱ ወደ ማዶ ተሻገሩ፤ እንጀራ መያዝን ግን ረሱ፡፡6ኢየሱስ፣ "ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም" አላቸው፡፡7ደቀ መዛሙርቱ፣ "እንጀራ ስላልያዝን ነው" ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፡፡8ኢየሱስ ይህን ዐውቆ፣ "እናንተ እምነተ ጎደሎዎች፣ እንጀራ ስላልያዝን ነው ብላችሁ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ?"9ዐምስት እንጀራ ለዐምስቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንደ ሰበሰባችሁ አሁንም አታስተውሉም ወይም አታስታውሱም?10ወይም ደግሞ ሰባቱ እንጀራ ለአራቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንዳነሣችሁስ አታስታውሱምን?11እኔ የነገርኋችሁ ስለ እንጀራ እንዳልነበረ እንዴት ነው የማታስተውሉት? ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያ እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም፡፡"12ከዚያም እርሱ ሲነግራቸው የነበረው ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንዲጠበቁ እንጂ፣ ስለ እንጀራ እርሾ እንዳልነበረ ተረዱ፡፡13ኢየሱስም ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ክልል በመጣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፣ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ነው ይላሉ?" በማለት ጠየቃቸው፡፡14እነርሱ፣ እንዲህ አሉ፤ "አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ የቀሩትም ኤርምያስ፣ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ፡፡"15"እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?" አላቸው፡፡16ስምዖን ጴጥሮስ፣ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት መልስ ሰጠ፡፡17ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለው፣ "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ አንተ የተባረክህ ነህ፤ ይህን የገለጠልህ የሰማዩ አባቴ ነው እንጂ፣ ሥጋና ደም አይደለም፡፡18ደግሞም አንተ ጴጥሮስ ነህም እላለሁ፤ በዚህም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም፡፡19እኔ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፡፡ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈታውም ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡››20ከዚያም ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ለማንም እንዳይናገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፡፡21ከዚያን ጊዜ አንሥቶ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ፣ በሽማግሌዎችና በካህናት አለቆች፣ በፈሪሳውያንና በሕግ መምህራንም እጅ ብዙ መከራ መቀበልና መገደል፣ በሦስተኛውም ቀን መነሣት እንዳለበት ለደቀ መዛሙርቱ ይነግራቸው ጀመር፡፡22ከዚያም ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ገለል አድርጎ፣ "ጌታ ሆይ፣ ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ይህም ከቶ አይሁንብህ" በማለት ገሠጸው፡፡23ኢየሱስ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን፣ "ከፊቴ ዞር በል፣ ሰይጣን! ስለ ሰው እንጂ ስለ እግዚአብሔር ነገር ደንታ የለህምና አንተ ለእኔ እንቅፋት ነህ" አለው፡፡24ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር፣ ራሱን መካድ፣ የራሱን መስቀል መሸከምና እኔን መከተል አለበት፡፡25ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣዋል፤ ስለ እኔ ሕይወቱን የሚያጣ ግን ያገኘዋል፡፡26ሰው ሙሉውን ዓለም የራሱ ቢያደርግ ሕይወቱን ግን ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰው በሕይወቱ ፈንታ ምን መስጠት ይችላል?27የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ከመላእክቱ ጋር ይመጣልና፡፡ ከዚያም ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፡፡28እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆማችሁት መካከል የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ፡፡"
1ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙን ይዞ ብቻቸውን ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው፡፡2በፊታቸውም መልኩ ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን አንጸባረቀ፡፡3እነሆ፣ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡4ጴጥሮስ መልሶ ኢየሱስን፣ "ጌታ ሆይ፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትፈልግ እኔ እዚህ ሦስት ዳሶችን፡- አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እሠራለሁ" አለው፡፡5እርሱ ገና እየተናገረ እያለ፣ እነሆ፣ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም፣ "በእርሱ እጅግ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ ነበረ፡፡6ደቀ መዛሙርቱ ድምፁን በሰሙ ጊዜ ፈሩ፣ በግንባራቸውም ወደቁ፡፡7ከዚያም ኢየሱስ መጥቶ ዳሰሳቸውና፣ ‹‹ተነሡ አትፍሩ›› አላቸው፡፡8ከዚያም እነርሱ ቀና ብለው ተመለከቱ፣ ነገር ግን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡9ከተራራ ሲወርዱም ኢየሱስ፣ "የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ይህን ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ" ብሎ አዘዛቸው፡፡10ደቀ መዛሙርቱ፣ "እንግዲያው የአይሁድ ሕግ መምህራን መጀመሪያ ኤልያስ መምጣት አለበት ለምን ይላሉ?" በማለት ጠየቁት፡፡11ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፤ "ኤልያስ በርግጥ ይመጣል፣ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል፡፡12ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ኤልያስ አስቀድሞ መጥቷል፤ ነገር ግን አላወቁትም፡፡ በዚህ ፈንታ የፈለጉትን ነገር ሁሉ አደረጉበት፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የሰው ልጅ በእነርሱ እጅ መከራ ይቀበላል፡፡››13በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ የተናገራቸው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነበረ ተረዱ፡፡14ወደ ሕዝቡ በመጡ ጊዜ አንድ ሰው መጥቶ በፊቱ ተንበረከከ፤ እንዲህም አለው፤ 15"ጌታ ሆይ፣ ልጄን ማረው፣ የሚጥል በሽታ ይዞት በኀይል ይሠቃያል፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ወይም በውሃ ውስጥ ይጥለዋልና፡፡16ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት፤ ነገር ግን እነርሱ ሊፈውሱት አልቻሉም፡፡›17ኢየሱስ መልሶ፣ "የማታምኑና ምግባረ ብልሹ ትውልድ፣ እስከ መቼ ድረስ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ? እስከ መቼስ እናንተን መታገሥ አለብኝ? እስቲ ወደ እኔ አምጡት" አለ፡፡18ኢየሱስ ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፤ ልጁም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ፡፡19ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "እኛ ልናወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?" አሉ፡፡20ኢየሱስ፣ ‹‹በእምነታችሁ ማነስ ምክንያት፤ እውነት እላችኋለሁና፣ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት እንኳ ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ማዶ ሂድ ብትሉት ይሄዳል፡፡ ማድረግ የሚሳናችሁ ምንም ነገር አይኖርም፡፡21122በገሊላ እያሉ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ "የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፤23እነርሱም ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል" አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በጣም ዐዘኑ፡፡24ወደ ቅፍርናሆም በመጡ ጊዜ ግማሽ ሰቅል ቀረጥ የሰበሰቡ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ መጥተው፣ "መምህራችሁ ግማሽ ሰቅሉን ቀረጥ አይከፍልምን?" አሉ፡፡25እርሱ፣ "አዎ" አለ፡፡ ጴጥሮስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ግን ኢየሱስ መጀመሪያ እርሱን ተናገረው፤ "ስምዖን ሆይ፣ ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥ ወይም ግብር የሚሰበስቡት ከማን ነው? ከዜጎቻቸው ወይስ ከውጭ አገር ሰዎች?" አለው፡፡26ጴጥሮስ፣ "ከውጭ አገር ሰዎች" ባለ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "እንግዲያስ ዜጎቹ ከክፍያ ነጻ ናቸው፡፡27ነገር ግን ቀረጥ ሰብሳቢዎቹን ኃጢአት እንዲሠሩ እንዳናደርጋቸው ወደ ባሕር ሄደህ መንጠቆ ጣል፤ በመጀመሪያ የምታጠምደውን ዐሣ አፍ ስትከፍት አንድ ሰቅል ታገኛለህ፤ ያንን ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ክፈል፡፡››
1በዚያው ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው?" አሉ2ኢየሱስ አንድ ትንሽ ልጅ ጠርቶ በመካከላቸው አቆመው፤3እንዲህም አለ፡- "እውነት እላችኋለሁ፤ ንስሐ ካልገባችሁና እንደ ልጆች ካልሆናችሁ በምንም መንገድ ወደ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም፡፡4ስለዚህ እንደዚህ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሰው ሁሉ፣ እንዲሁ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ይበልጣል፡፡5እንደዚህ ያለውን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፡፡6ነገር ግን በእኔ ከሚያምነው ከእነዚህ ልጆች አንዱን ኀጢአት እንዲሠራ የሚያደርግ ማንም፣ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቁ ባሕር ቢሰጥም ይሻለዋል፡፡7የመሰናክል ምክንያት በመሆኗ ለዓለም ወዮላት! መሰናክል መምጣቱ ግድ ነው፤ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣ ሰው ወዮለት!8እጅህ ወይም እግርህ ቢያሰናክልህ፣ ቈርጠህ ከአንተ ጣለው፡፡ ሁለት እጆች ወይም እግሮች ኖረውህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል የአካል ጉዳተኛ ወይም አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃል፡፡9ዐይንህ እንድትሰናከል ቢያደርግህ፣ አውጥተህ ከአንተ ጣለው፡፡ ሁለት ዐይኖች ኖረውህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻላል፡፡10ከእነዚህ ከታናናሾች ማንኛውንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክታቸው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ሁልጊዜ ያያሉና፡፡ 11 (2) ብዙ ምንጮች፣ አንዳንድ የጥንት የሆኑ ቊ. 11ን ያስገባሉ፡፡11112ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት፣ ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፣ ዘጠና ዘጠኙን በኮረብታው ጥግ ትቶ የጠፋውን ሊፈልግ አይሄድምን?13በሚያገኘውም ጊዜ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል፡፡14በተመሳሳይ መንገድ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ የሰማዩ አባታችሁ ፈቃድ አይደለም፡፡15ወንድምህ ቢበድልህ፣ ሂድና አንተና እርሱ ብቻ ሆናችሁም ጥፋቱን አሳየው፡፡ ቢሰማህ፣ ወንድምህን የራስህ ታደርገዋለህ፡፡16ባይሰማህ ግን፣ ቃል ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ይጸናልና፣ ከአንተ ጋር አንድ ወይም ሁለት ተጨማሪ ወንድሞችን ይዘህ ሂድ፡፡17እነርሱንም አልሰማም ቢል፣ ጉዳዩን ለቤተ ክርስቲያን ንገር፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ደግሞ አልሰማም ቢል፣ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቊጠረው፡፡18እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር የምታስሩት ነገር ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱትም ነገር ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡19በተጨማሪም እላችኋለሁ፣ ከእናንተ ሁለቱ በምድር ስለሚለምኑት ስለ ማንኛውም ነገር ቢስማሙ፣ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላቸዋል፡፡20ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት ቦታ እዚያ በመካከላቸው እገኛለሁና፡፡21ከዚያም ጴጥሮስ መጥቶ ኢየሱስን፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን?›› አለው፡፡22ኢየሱስም፣ ‹‹ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ፣ ሰባት ጊዜ አልልህም›› አለው፡፡23ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ከአገልጋዮቹ ጋር ሒሳብ ሊተሳሰብ የፈለገ ንጉሥን ትመስላለች፡፡24መተሳሰቡን እንደ ጀመረ፣ የዐሥር ሺህ መክሊት ዕዳ ያለበትን አገልጋይ ወደ እርሱ አመጡ፡፡25ነገር ግን የሚከፍልበት መንገድ ስላልነበረው፣ ጌታው ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ያለውም ሁሉ ተሸጦ ክፍያው እንዲፈጸም አዘዘው፡፡26ስለዚህ አገልጋዩ ወድቆ በፊቱ ተንበረከከ እንዲህም አለ፤ ‹ጌታዬ ሆይ፣ ታገሠኝ፣ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፡፡›27ስለዚህ የዚያ አገልጋይ ጌታ ስለ ራራለት፣ ተወው፤ ዕዳውንም ሠረዘለት፡፡28ነገር ግን ያ አገልጋይ ወጥቶ አብረውት ከሚሠሩት አገልጋዮች መቶ ዲናር ያበደረውን አንዱን አገልጋይ አግኝቶ ያዘው፤ ጕሮሮውን አነቀውና፣ ‹‹ያለብህን ዕዳ ክፈለኝ›› አለው፡፡29ነገር ግን የሥራ ባልደረባው፣ ‹‹ታገሠኝ፣ እከፍልሃለሁ›› በማለት ወድቆ ለመነው፡፡30የመጀመሪያው አገልጋይ ግን አሻፈረኝ አለ፤ በዚህ ፈንታ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍለው ድረስ በእስር ቤት ጣለው፡፡31የሥራ ጓደኞቹ የሆኑት አገልጋዮች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ፣ በጣም ተበሳጩ፤ መጥተውም ለጌታቸው የሆነውን ሁሉ ነገሩት፡፡32ከዚያም የዚያ አገልጋይ ጌታ ጠራው፣ እንዲህም አለው፤ 'አንተ ክፉ አገልጋይ፣ ስለ ለመንኸኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውሁልህ፡፡33እኔ አንተን እንደማርሁህ፣ የሥራ ባልደረባህ የሆነውን አገልጋይ ልትምረው አይገባህም ነበርን?'34ጌታው ተቈጥቶ ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ለሚያሠቃዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡35ስለዚህም ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልብ ይቅር ባይል የሰማዩ አባቴ እንዲሁ ያደርግበታል፡፡"
1እንዲህም ሆነ፤ ኢየሱስ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ገሊላን ትቶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ ጠረፍ መጣ፡፡2ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፤ እዚያም ፈወሳቸው፡፡3ፈሪሳውያን እንዲህ በማለት ሊፈትኑት ወደ እርሱ መጡ፤ "በማንኛውም ምክንያት ሰው ሚስቱን ቢፈታ ሕጋዊ ነውን?"4ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፣ "ከመጀመሪያው የፈጠራቸው እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸውና5ደግሞም፣ 'በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ አንድ ሥጋም ይሆናሉ' የተባለውን አላነበባችሁምን?6ስለዚህ እነርሱ ከእንግዲህ አንድ ሥጋ እንጂ ሁለት አይደሉም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር አንድ ላይ ያጣመረውን፣ ማንም አይለየው፡፡››7እነርሱ፣ "ታዲያ የፍቺ የምስክር ወረቀት ሰጥተን ከዚያ በኋላ እንድናባርራት ሙሴ ለምን አዘዘን?" አሉት፡፡8ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ "ከልባችሁ ድንዳኔ የተነሣ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ሙሴ ፈቀደላችሁ፤ ነገር ግን ከመጀመሪያው እንደዚያ አልነበረም፡፡9እኔ እላችኋለሁ፣ ከዝሙት በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል፡፡"10ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ "የባልና የሚስት ጉዳይ እንዲህ ከሆነ ማግባት ጥሩ አይደለም" አሉት፡፡11ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ "እንዲቀበሉት የተፈቀደላቸው እንጂ፣ ሁሉም ሰው ይህን ትምህርት አይቀበለውም፡፡12በተፈጥሮ ከእናታቸው ማኅፀን ስልብ ሆነው የተወለዱ አሉና፡፡ ሰዎች የሰለቧቸውም ይገኛሉ፡፡ ስለ መንግሥተ ሰማያት ሲሉም ራሳቸውን ስልብ ያደረጉ አሉ፡፡ ይህን ትምህርት መቀበል የሚችል፣ ይቀበለው፡፡››13በዚያን ጊዜ እጁን ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሰዎች ልጆችን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው፡፡14ኢየሱስ ግን፣ "ልጆቹን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም እንዲመጡ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና" አለ፡፡1515 እጁንም በልጆቹ ላይ ጫነባቸው፤ ከዚያም ያን ቦታ ትቶ ሄደ፡፡16እነሆ፣ አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ ‹‹መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ማድረግ አለብኝ?›› አለ፡፡17ኢየሱስ፣ ‹‹ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም አንድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ትእዛዛትን ጠብቅ›› አለው፡፡18ሰውዬው፣ ‹‹የትኞቹን ትእዛዛት? አለ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "አትግደል፤" "አታመንዝር" "አትስረቅ፤" "በሐሰት አትመስክር፤"19"አባትህንና እናትህን አክብር፤" እንዲሁም፣ "ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡"20ወጣቱ፣ "እነዚህን ነገሮች ሁሉ ፈጽሜአለሁ፣ ሌላስ ምን ያስፈልገኛል?" አለው፡፡21ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "ፍጹም ለመሆን ብትፈልግ፣ ሂድና ያለህን ሽጠህ ለድኾችም ስጠው፤ በሰማይም ሀብት ይኖርሃል፡፡ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ፡፡››22ነገር ግን ወጣቱ ኢየሱስ የተናገረውን በሰማ ጊዜ፣ ብዙ ንብረት ነበረውና ዐዝኖ ሄደ፡፡23ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ከባድ ነው፡፡24ደግሜ እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከመግባት፣ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፡፡"25ደቀ መዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ተደነቁና፣ "ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?" አሉ፡፡26ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተመልክቶ፣ "ይህ ለሰዎች የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል" አለ፡፡27ከዚያም ጴጥሮስ መልሶ፣ "ተመልከት፣ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ ታዲያ ምን እናገኛለን?" አለ፡፡28ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ እኔን የተከተላችሁኝ፣ በዐዲሱ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም በዐሥራ ሁለት ዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶችም ላይ ትፈርዳላችሁ፡፡29ስለ ስሜ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን፣ ወይም ርስትን የተወ ሁሉ፣ መቶ እጥፍ ይቀበላል፣ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል፡፡30ነገር ግን አሁን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች ይሆናሉ፤ ኋለኞች የሆኑ ብዙዎችም ፊተኞች ይሆናሉ፡፡
1መንግሥተ ሰማይ ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤትን ትመስላለች።2በቀን አንዳንድ ዲናር ሊከፍላቸው ከሠራተኞቹ ጋር ከተስማማ በኋላ፣ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ላካቸው።3ደግሞም በሦስት ሰዓት ገደማ ወጥቶ በገበያ ቦታ ሥራ ፈትተው የቆሙ ሌሎች ሠራተኞችን አየና፣4'እናንተ ደግሞ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሂዱ፤ የሚገባችሁንም እከፍላችኋለሁ' አላቸው። ስለዚህ እነርሱም ሊሠሩ ሄዱ።5ደግሞ በስድስት ሰዓትና በዘጠኝ ሰዓት ገደማ ወጥቶ እንደዚሁ አደረገ።6አሁንም በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ገደማ ወጥቶ ሥራ ፈትተው የቆሙ ሌሎችን አገኘ። እነርሱንም፣ 'ቀኑን ሙሉ ሥራ ፈትታችሁ እዚህ ለምን ቆማችኋል?' አላቸው።7'ማንም ስላልቀጠረን ነው' አሉት። 'እናንተም ደግሞ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሂዱ' አላቸው።8ቀኑ በመሸ ጊዜ፣ የወይኑ አትክልት ባለቤት ሥራ አስኪያጁን፣ 'ሠራተኞቹን ጥራ ከኋለኞቹ አንሥተህ እስከ ፊተኞቹ የሠሩበትን ገንዘብ ክፈላቸው' አለው።9በዐሥራ አንደኛው ሰዓት የተቀጠሩት ሠራተኞች በመጡ ጊዜ፣ እያንዳንዳቸው አንዳንድ ዲናር ተቀበሉ።10ፊተኞቹ ሠራተኞች በመጡ ጊዜ፣ የበለጠ የሚቀበሉ መሰላቸው፤ ነገር ግን እነርሱም ደግም እያንዳንዳቸው አንዳንድ ዲናር ተቀበሉ።11ገንዘባቸውን በተቀበሉ ጊዜ፣ በወይኑ አትክልት ባለቤት ላይ አጕረመረሙ።12እንዲህም አሉ፤ 'እነዚህ በመጨረሻ የመጡ ሠራተኞች በሥራ ላይ አንድ ሰዓት ብቻ አሳልፈዋል፤ ነገር ግን አንተ የዕለቱን ሸክምና የሚለበልበውን ሙቀት ከተሸከምነው ከእኛ ጋር እኩል አድርገሃቸዋል።'13ባለቤቱ ግን መልሶ ከእነርሱ አንዱን እንዲህ አለው፤ "ወዳጄ ሆይ፣ አልበደልኩህም። ከእኔ ጋር በአንድ ዲናር አልተስማማህምን?14የሚገባህን ተቀብለህ መንገድህን ሂድ፤ ለእነዚህ በመጨረሻ ለተቀጠሩት ሠራተኞች ልክ እንደ አንተው ልሰጣቸው ደስ ይለኛል።15በገዛ ንብረቴ የፈለግሁትን ማድረግ አይገባኝምን? ወይስ እኔ ደግ ስለ ሆንሁ ትመቀኛለህን?16ስለዚህ ኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ።"17ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ስለ ነበር፣ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ወሰደ፤ በመንገድ ላይም እንዲህ አላቸው፦18እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለሕግ መምህራን ተላልፎ ይሰጣል። ሞትም ይፈርዱበታል፤19እንዲዘብቱበት፣ እንዲገርፉት፣ እንዲሰቅሉትም ለአሕዛብ ይሰጡታል። ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ይነሣል።"20በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆቿ ጋር ወደ ኢየሱስ መጣች፤ በፊቱ ተንበርክካም ከእርሱ አንድ ነገር ለመነች።21ኢየሱስ፣ "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት። እርሷም፣ "በመንግሥትህ እነዚህ ሁለት ልጆቼ አንዱ በቀኝህ፣ አንዱም በግራህ እንዲቀመጡ እዘዝ" አለችው።22ኢየሱስ ግን መልሶ፣ "የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?" አለ። እነርሱ፣ "እንችላለን" አሉት።23ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "በርግጥ ጽዋዬን ትጠጣላችሁ። በቀኜና በግራዬ መቀመጥን የምሰጥ ግን እኔ አይደለሁም፤ ነገር ግን በአባቴ ለተዘጋጀላቸው ለእነርሱ ነው።"24ሌሎቹ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ይህን በሰሙ ጊዜ፣ በሁለቱ ወንድማማች ላይ ተቈጡ።25ነገር ግን ኢየሱስ ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ "የአሕዛብ አለቆች ሕዝባቸውን ጨቊነው ይገዛሉ፤ የበላዮቻቸውም ይሠለጥኑባቸዋል።26በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መደረግ የለበትም። ይልቁንም፣ ከእናንተ መካከል ታላቅ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን፤27ከእናንተም ፊተኛ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን።28የሰው ልጅ ሊያገለግል፣ ሕይወቱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ እንጂ፣ እንዲያገለግሉት አልመጣም።"29ከኢያሪኮ እንደ ወጡ፣ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስን ተከተሉት።30እነሆ፣ ሁለት ዐይነ ስውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው ነበር፤ ኢየሱስ ሲያልፍ በሰሙ ጊዜ ጮኽ ብለው፣ "ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ማረን" አሉ።31ሕዝቡ ግን ዝም እንዲሉ በመንገር ገሠጿቸው። ይሁን እንጂ፣ እነርሱ አብዝተው በመጮኽ፣ "ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ ማረን" አሉ።32በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ቆም ብሎ ጠራቸውና፣ "ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?" አለ።33እነርሱም፣ "ጌታ ሆይ፣ ዐይኖቻችን እንዲከፈቱ ነው" አሉት።34ከዚያም ኢየሱስ ራርቶ፣ ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ። እነርሱም ወዲያውኑ አይተው ተከተሉት።
1ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም እንደቀረቡ፣ በደብረ ዘይት ወዳለው ወደ ቤተ ፋጌ መጡ፤2ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ በማለት ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤ “ወደሚቀጥለው መንደር ሂዱ፤ አህያም ከነውርንጫዋ ታስራ ታገኛላችሁ። ፈትታችሁ ወደ እኔ አምጧቸው፤3ማንም ስለዚያ አንዳች ቢናገራችሁ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ፈጥኖ ይሰዳቸዋል።”4-5ይህ የሆነው፣ “እነሆ፣ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሯት” ተብሎ በነቢዩ የተተነበየው ይፈጸም ዘንድ ነው።6ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሄደው ልክ ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ።7አህያይቱንና ውርንጫዋን አመጡ፤ ልብሳቸውንም አደረጉባቸውና ኢየሱስ ተቀመጠባቸው።8ከሕዝቡ አብዛኞቹ ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፣ ሌሎችም የዘንባባ ዝንጣፊ እየቈረጡ በመንገድ ላይ አደረጉ።9ከኢየሱስ ፊት ይሄዱ የነበሩትና የተከተሉትም ሕዝብ፣ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው። ሆሣዕና በአርያም ይሁን!” በማለት ጮኹ።10ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ከተማይቱ በሞላ ታወከችና፣ “ይህ ማን ነው?” አለች።11ሕዝቡ፣ “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የሆነው ነቢዩ ኢየሱስ ነው” ብለው መለሱ።12ከዚያም ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደ። በቤተ መቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን አስወጣ። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና ወንበሮች ገለበጠ።13እንዲህም አላቸው፤ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል። እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት።"14ከዚያም ዐይነ ስውሮችና ሽባዎች ወደ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።15ነገር ግን የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን እርሱ ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች ባዩና በቤተ መቅደስ ልጆች፣ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ” በማለት ሲጮኹ በሰሙ ጊዜ፣ ተቈጡ።16“ሕዝቡ የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት። ኢየሱስ፣ “አዎ! ነገር ግን ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።17ከዚያም ኢየሱስ ትቷቸው ከከተማው ወጣና ወደ ቢታንያ ሄዶ በዚያ ዐደረ።18ኢየሱስ ጠዋት ወደ ከተማው እንደተመለሰ፣ ተራበ።19በመንገድ ዳር አንዲት የበለስስ ተክል አየና ወደ እርሷ ሄደ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። “ሁለተኛ ከቶ ፍሬ አይገኝብሽ” አላት። የበለስ ተክሊቱም ወዲያውኑ ደረቀች።20ደቀ መዛሙርቱ ባዩአት ጊዜ ተደንቀው፣ “የበለስ ተክሊቱ እንዴት ወዲያውኑ ደረቀች?” አሉ።21ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፣ እምነት ቢኖራችሁና ባትጠራጠሩ፣ በዚች የበለስ ተክል የሆነባትን ብቻ ሳይሆን፣ ይህን ኮረብታ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት እንኳ ይሆናል።22አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ።”23ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ መጥተው፣ “በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉ።24ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ደግሞ አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ። ያንን ከነገራችሁኝ እኔ ደግሞ በማን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ እነግራችኋለሁ።25የዮሐንስ ጥምቀት ከየት መጣ ከሰማይ ነውን ወይስ ከሰዎች?” እርስ በርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋገሩ፤ “ከሰማይ ነው ብንለው፣ ‘ለምን አታምኑትም?’ ይለናል።26ነገር ግን ‘ከሰው ነው ብንል፣ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ስለሚያዩት ሕዝቡን እንፈራለን።”27ከዚያም መልሰው ኢየሱስን፣ “አናውቅም” አሉት። እርሱ ደግሞ፣ “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።28ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፣ ወደ መጀመሪያው ሄዶ፣ ልጄ ሆይ፣ ዛሬ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሄደህ ሥራ’ አለው።29ልጁ መልሶ፣ ‘አልሄድም’ አለ፤ በኋላ ግን ዐሳቡን ለውጦ ሄደ።30ሰውዬውም ወደ ሁለተኛው ልጅ ሄዶ ይህንኑ ነገረው። ይህኛው ልጅ መልሶ፣ ‘እሄዳለሁ፣ አባዬ’ አለ። ነገር ግን አልሄደም።31ከሁለቱ ልጆች የአባቱን ትእዛዝ የፈጸመው የትኛው ነው? እነርሱ፣ "የመጀመሪያው” አሉ። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ቀድመዋችሁ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባሉ።32ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ ወደ እናንተ መጥቶ ነበርና፤ እናንተ ግን አላመናችሁትም፤ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ግን አመኑት። እናንተም ይህ ሲሆን አይታችሁ ታምኑት ዘንድ በኋላ እንኳ ንሰሐ አልገባችሁም።33ሌላም ምሳሌ ስሙ። ሰፊ መሬት ያለው አንድ ሰው ነበር። የወይን አትክልት ተከለ፤ ዐጥር አጠረለት፤ የወይን መጥመቂያ ማሰለት፤ መጠበቂያ ማማ ሠራለት፤ ለወይን ገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።34የወይን ፍሬ የሚሰበሰብበት ጊዜ እንደ ደረሰ፣ ፍሬውን እንዲቀበሉ ጥቂት አገልጋዮችን ላከ።35የወይኑ ገበሬዎች ግን አገልጋዮቹን ያዙ፤ አንዱን ደበደቡት፣ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውንም በድንጋይ ወገሩት።36ባለቤቱ እንደ ገና ከፊተኞቹ የበዙ ሌሎች አገልጋዮችን ላከ፤ ነገር ግን የወይን ገበሬዎቹ ያንኑ አደረጉባቸው።37ከዚያ በኋላ ባለቤቱ፣ ‘ልጄንስ ያከብሩታል’ በማለት የገዛ ልጁን ላከ።38የወይን ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ፣ እርስ በርሳቸው፣ 'ይህ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ።39ስለዚህ ያዙትና ከወይኑ አትክልት ስፍራ ወደ ውጭ ጣሉት፤ ገደሉትም።40እንግዲህ የወይኑ አትክልት ባለቤት በሚመጣበት ጊዜ እነዚያን የወይን ገበሬዎች ምን ያደርጋቸዋል?”41ሕዝቡ እንዲህ አሉት፤ “እነዚያን ክፉ ሰዎች እጅግ በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ ያጠፋቸዋል፤ ከዚያም የወይኑን አትክልት ስፍራ ወይኑ በሚያፈራበት ጊዜ ገንዘቡን ለሚከፍሉ ለሌሎች የወይን ገበሬዎች ያከራየዋል።”42ኢየሱስ እነርሱን፣ “ 'ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነ። ይህ ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው ተብሎ የተጻፈውን ፈጽሞ አላነበባችሁም?’43ስለዚህ እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰድና ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች።44በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይሰባበራል። ድንጋዩ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ይፈጨዋል።”45የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ፣ የተናገረው ስለ እነርሱ እንደ ሆነ ተረዱ።46ነገር ግን ሊይዙት በፈለጉ ጊዜ ሁሉ፣ ሰዎቹ እንደ ነቢይ ይቈጥሩት ስለ ነበር ሕዝቡን ፈሩ።
1ኢየሱስም ደግሞ እንዲህ በማለት በምሳሌ መለሰላቸው፤2"መንግሥተ ሰማይ ለልጁ የሰርግ ድግስ የደገሰ ንጉሥን ትመስላለች፡፡3ወደ ሰርጉ እንዲመጡ ወደ ጋበዛቸው ሰዎች አገልጋዮቹን ላከ፤ እነርሱ ግን መምጣት አልፈለጉም፡፡4እንደ ገና ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንዲህ በማለት ላከ፤ "እነሆ፣ እራት አዘጋጅቻለሁ፤ በሬዎቼንና የሰቡ ወይፈኖቼን አርጃለሁ፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአልና ወደ ሰርግ ግብዣው ኑ በሏቸው፡፡' "5ሰዎቹ ግን ግብዣውን ከልብ አልተቀበሉትም፡፡ አንዳንዶቹ ወደ እርሻዎቻቸው፣ ሌሎች ደግሞ ወደ ሥራ ቦታቸው ሄዱ፡፡6አንዳንዶቹ የንጉሡን አገልጋዮች ደበደቡአቸው፤ አዋረዱአቸው፤ ገደሉአቸው፡፡7ንጉሡ ግን ተቈጣ፤ ወታደሮቹን ላከ፤ እነዚያን ነፍሰ ገዳዮች ገደለ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ፡፡8ከዚያም ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፤ 'ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎች ግን የሚገባቸው ሆነው አልተገኙም፡፡9ስለዚህ ወደ ዐውራ መንገድ ማቋረጫ ሄዳችሁ የምታገኙአቸውን ያህል ሰዎች ወደ ሰርጉ ግብዣ ጥሩ፡፡10ሰዎቹም ወደ ዐውራው መንገድ ሄደው መልካምም ሆኑ መጥፎዎች ያገኙአቸውን ሁሉ አንድ ላይ ሰበሰቡ፡፡ ስለዚህ የግብዣው አዳራሽ በተጋባዦች ተሞላ፡፡11ንጉሡ ተጋባዦቹን ለማየት ሲመጣ ግን፣ የሰርግ ልብስ ያልለበሰ ሰው አየ፡፡12ንጉሡ እንዲህ አለው፤ ‹ወዳጄ፣' የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?› ሰውየውም ዝም አለ፡፡13ከዚያም ንጉሡ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አላቸው፤ እጅና እግሩን አስራችሁ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት፡፡'14የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡"15ከዚያም ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስን እንዴት በንግግሩ ማጥመድ እንደሚችሉ ዕቅድ አወጡ፡፡16ከዚያም ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ደቀ መዛሙርታቸውን ወደ እርሱ ላኩ፡፡ ኢየሱስንም እንዲህ አሉት፤ "መምህር ሆይ፣ አንተ በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ የምታስተምር እውነተኛ ሰው መሆንህን እናውቃለን፤ ሰውን በመፍራት ዐሳብህን አትለውጥም፤ በሰዎች መካከል አድልዎ አታደርግም፡፡17እስቲ ንገረን ምን ይመስልሃል? ለቄሳር ግብር መስጠት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?"18ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ "እናንት ግብዞች የምትፈትኑኝ ለምንድን ነው?19እስቲ የግብሩን ገንዘብ አሳዩኝ" አላቸው፡፡ እነርሱም ዲናሩን አመጡለት፡፡20ኢየሱስም፣ "ይህ የማን መልክና ስም ነው?›› አላቸው፡፡21እነርሱም፣ "የቄሣር፣" አሉት፡፡ ከዚያም ኢየሱስ፣ "እንግዲያስ የቄሣር የሆነውን ለቄሣር ስጡ፤ የእግዚአብሔር የሆነውን ለእግዚአብሔር ስጡ" አላቸው፡፡22ያንን ሲሰሙ ተገረሙ፡፡ ትተውትም ሄዱ፡፡23በዚያው ቀን ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ጥቂት ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጡ፡፡24"መምህር ሆይ፣ ‹አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሞተ ሚስቱን ወንድሙ እንዲያገባና ለወንድሙ ልጅ እንዲወልድለት ሙሴ ተናግሮአል›25ሰባት ወንድማማች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፡፡ ሚስቱ የወንድምየው ሆነች፡፡26ሁለተኛውና ሦስተኛውም እስከ ሰባተኛው ድረስ ያንኑ አደረጉ፡፡27ከሁሉም በኋላ ደግሞ ሴትየዋ ሞተች፡፡28እንግዲህ ሰባቱም ወንድማማች አግብተዋት ነበርና በትንሣኤ ቀን የማንኛው ሚስት ልትሆን ነው?" በማለት ጠየቁት፡፡29ኢየሱስ ግን እንዲህ በማለት መለሰላቸው፤ "መጻሕፍትንም ሆነ የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታወቁ ተሳስታችኋል፡፡30ምክንያቱም በትንሣኤ ቀን እንደ ሰማይ መላእክት ይሆናሉ እንጂ፣ አያገቡም፣ ደግሞም አይጋቡም፡፡31ትንሣኤ ሙታንን በተመለከተ፣ እግዚአብሔር32"እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ" በማለት ለእናንተ የተናገረውን አላነበባችሁምን? እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ እንጂ፣ የሙታን አምላክ አይደለም፡፡"33ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡34ኢየሱስ ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው ፈሪሳውያን ሲሰሙ፣ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡35ከእነርሱ መካከል ሕግ ዐዋቂ የሆነ አንዱ እርሱን ለመፈተን፣36"መምህር ሆይ፣ ከሕጉ ሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው ነው" ብሎ ጠየቀው፡፡37ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ "እግዚአብሔር አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ ዐሳብህ ውደድ፡፡"38ከሁሉም የሚበልጠው የመጀመሪያው ትእዛዝ ይህ ነው፡፡39ሁለተኛውም ትእዛዝ ያንኑ ይመስላል፤ 'ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡'40ሕግና ነቢያት ሁሉ የትመሠረቱት በእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ላይ ነው፡፡41ፈሪሳውያን በአንድነት ተሰብስበው እያለ ኢየሱስ አንድ ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡42"ስለ ክርስቶስ ምን ታስባላችሁ? ለመሆኑ የማን ልጅ ነው?" አላቸው፡፡ "የዳዊት ልጅ ነው" አሉት፡፡43ኢየሱስም፣ "ታዲያ፣ ዳዊት፣ በመንፈስ፣44ጌታ ጌታዬን ‹ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ' በማለት እንዴት ጌታ ብሎ ይጠራዋል?45ዳዊት ክርስቶስን 'ጌታ' በማለት ከጠራው እንዴት የዳዊት ልጅ ሊሆን ይችላል?"46ማንም አንዲት ቃል ሊመልስለት አልቻለም፤ ከዚያ ቀን ጀምሮ ጥያቄ ሊያቀርብለት የደፈረ አልነበረም፡፡
1ከዚያም ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ሲል ተናገረ፤2"የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል፡፡3ስለዚህ የሚያዝዙአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ አክብሩትም፡፡ እነርሱ የሚያደርጉትን ግን አታደርጉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው የሚናገሩትን አያደርጉትም፡፡4ለመሸከም የሚያስቸግር ከባድ ሸክም አንሥተው በሰዎች ትከሻ ላይ ይጭናሉ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ግን መሸከም ቀርቶ በጣታቸው ሊያነሡት እንኳ አይፈልጉም፡፡5ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት በሰዎች ለመታየት ነው፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ፡፡6ግብዣ ላይ የከበሬታ ቦታዎችንና በምኵራብ ውስጥ የተለየ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ፤7በገበያ ቦታ ሰዎች የተለየ ክብር እንዲሰጧቸውና፣ 'መምህር ሆይ› በማለት እንዲጠሩአቸው ይፈልጋሉ፡፡8እናንተ ግን ያላችሁ አንድ መምህር ብቻ ስለሆነና ሁላችሁም ወንድማማች ስለሆናችሁ ‹መምህር› ተብላችሁ አትጠሩ፡፡9በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ፤ ምክንያቱም በሰማይ የሚኖር አንድ አባት ብቻ አላችሁ፡፡10‹ሊቅም› ተብላችሁ አትጠሩ፤ ምክንያቱም ያላችሁ አንድ ሊቅ ብቻ ነው፤ እርሱም ክርስቶስ ነው፡፡11ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነው አገልጋያችሁ ይሁን፡፡12ራሱን ከፍ የሚያደርግ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል፡፡13እናንተ፣ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ግን ወዮላችሁ! በሰዎች ፊት መንግሥተ ሰማይን ትዘጋላችሁ፡፡ እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ፡፡ 141እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ለታይታ ረጅም ጸሎታችሁን በማድረግ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ ወዮላችሁ! ስለዚህ የበለጠውን ፍርድ ትቀበላላችሁ፡፡ እናንተ ግብዞች የአይሁድ ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ!15አንድን ሰው ተከታያችሁ ለማድረግ በባሕርና በምድር ትሄዳላችሁ፤ ተከታያችሁ ካደረጋችሁት በኋላ፣ ከእናንተ እጥፍ የሚከፋ የገሃነም ልጅ ታደርጉታላችሁ፡፡16እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች ወዮላችሁ፤ አንድ ሰው 'በቤተ መቅደሱ ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ባለው ወርቅ ቢምል ግን፣ በመሐላው ይጠመዳል' ትላላችሁ፡፡17እናንተ የታወራችሁ ሞኞች፣ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ወርቁ ወይስ ወርቁን የሚቀድሰው ቤተ መቅደሱ?18አንድ ሰው በመሠዊያው ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ መሠዊያው ላይ ባለው ስጦታ ቢምል ግን በመሐላው ይጠመዳል ትላላችሁ፡፡19እናንተ ዕውሮች፤ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ስጦታው ወይስ ስጦታውን የሚቀድሰው መሠዊያ?20ስለዚህ በመሠዊያው የሚምል በመሠዊያውና እርሱ ላይ ባሉ ነገሮች ሁሉ ይምላል፡፡21በቤተ መቅደሱ የሚምል በቤተ መቅደስና እርሱ ውስጥ በሚኖረው ይምላል፡፡22በሰማይ የሚምል በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል፡፡23እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፣ ከአዝሙድ፣ ከእንስላልና ከከሙን ዐሥራት ብታወጡም፣ የሕጉን ዋና ዋና ነገሮች ማለትም ፍትሕን፣ ምሕረትንና እምነትን ሥራ ላይ አታውሉም፡፡ ሌላውን ችላ ሳትሉ እነዚህን መፈጸም ነበረባችሁ፡፡24እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች፣ ትንኝን አውጥታችሁ ትጥላላችሁ፤ ግመልን ግን ትውጣላችሁ!25እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የጽዋውንና የሳሕኑን ውጫዊ ክፍል ታጠራላችህ፤ ውስጡ ግን ቅሚያና ስስት ሞልቶበታል፡፡26አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፣ ውጫዊ አካሉም ንጹሕ እንዲሆን በመጀመሪያ የጽዋውንና የሳሕኑን ውስጥ አጽዳ፡፡27እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ከውጭ ሲያዩት እንደሚያምር፣ ውስጡ ግን የሞቱ ሰዎች አጥንትና ርኵሰት እንደ ሞላበት መቃብር ናችሁ፡፡28በተመሳሳይ መንገድ እናንተም ከውጭ ለሰዎች ጻድቃን ትመስላላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ርኲሰት ሞልቶበታል፡፡29እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፣ የጻድቃንን መቃብር ስለምታስጌጡ፣30በአባቶቻችን ዘመን ኖረን ቢሆን ኖሮ፣ የነቢያትን ደም በማፍሰስ አንተባበራቸውም ነበር ትላላችሁ፡፡31ስለሆነም የነቢያት ገዳይ ልጆች መሆናችሁን እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡32እናንተ ራሳችሁም አባቶቻችሁ የጀመሩትን ኃጢአት ትፈጽማላችሁ፡፡33እናንተ እባቦች፣ እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?34ስለዚህ ነቢያትን፣ አስተዋይ ሰዎችንና የአይሁድ ሕግ መምህራንን ወደ እናንተ እልካለሁ፡፡ አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፣ ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹን በምኵራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፣ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፡፡35ከጻድቁ ከአቤል አንሥቶ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካካል እስከ ገደላችሁት የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደም ድረስ፣ በምድር ላይ በፈሰሰው ጻድቃን ደም ሁሉ ትጠየቃላችሁ፡፡36እውነት እላችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይሆናሉ፡፡37ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ ወደ አንቺ የተላኩትን በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን መሰብሰበ ብዙ ጊዜ ፈልጌ ነበር፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም!38ስለሆነም ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀራል፡፡39'በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው' እስክትሉ ድረስ ከአሁን ጀምሮ አታዩኝም እላችኋለሁ፡፡
1ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ እየሄደ ሳለ፤ ደቀ መዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ሕንጻ ሊያሳዩት ወደ እርሱ መጡ፡፡2እርሱ ግን፣ "እነዚህን ሁሉ ነገሮች ታያላችሁ? እውነት እላችኋለሁ፣ ይፈርሳል እንጂ፣ አንድ ድንጋይ እንኳ በሌላ ድንጋይ ላይ እንደ ተነባበረ አይቀርም" በማለት መለሰላቸው፡፡3በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ መጥተው፣ "እስቲ ንገረን፤ ይህ ሁሉ የሚሆነው መቼ ነው? የአንተ መምጣትና የዓለም መጨረሻስ ምልክቱ ምንድን ነው?" አሉት፡፡4ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡5ምክንያቱም ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ፤ 'እኔ ክርስቶስ ነኝ' እያሉ ብዙዎችን ያሳስታሉ6ጦርነትንና የጦርነትን ዜና ትሰማላችሁ፤ በፍጹም እንዳትታወኩ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ ግድ ነው፤ ቢሆንም፣ መጨረሻው ገና ነው፡፡7ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፡፡ በተለያየ ቦታ ራብና የምድር መናወጥ ይሆናል፡፡8እነዚሀ ሁሉ ግን የምጥ ጣር መጀመሪያ ብቻ ናቸው፡፡9ከዚያም ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሏችኋልም፡፡ ስለ ስሜ ሕዝቦች ሁሉ ይጠሏችኋል፡፡10ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ ይካካዳሉ፤ እርስ በርስ ይጠላላሉ፡፡11ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፣ ብዙዎችን ያሳስታሉ፡፡12ዐመፅ ስለሚበዛ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል፡፡13እስከ መጨረሻ የሚታገሥ ግን ይድናል፡፡14ለሕዝቦች ሁሉ ምስክር እንዲሆን የመንግሥቱ ወንጌል ለመላው ዓለም ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል፡፡15ስለዚህ በነቢዩ ዳንኤል የተነገረለት የጥፋት ርኲሰት በተቀደሰው ቦታ ቆሞ ስታዩ፣ (ያኔ አንባቢው ያስተውል)16በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣17ጣራ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ያለውን ምንም ነገር ከቤቱ ለመውሰድ አይመለስ፣18በእርሻ ያለ ልብሱን ለመውሰድ አይመለስ፡፡19ልጆች ላሉአቸውና ለሚያጠቡ እናቶች ግን ወዮላቸው!20ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፡፡21ምክንያቱም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስና ከዚያም በኋላ ፈጽሞ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል፡፡22እነዚያ ቀኖች ባያጥሩ ኖሮ፣ ማንም ሥጋ ለባሽ አይድንም ነበር፤ ለተመረጡት ሲባል ግን እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ፡፡23ስለዚህ ማንም "እነሆ ክርስቶስ፣ እዚህ ነው" ወይም፣ 'ክርስቶስ እዚያ ነው' ቢላችሁ አትመኑ፡፡24ምክንያቱም ብዙዎችን ለማሳሳት ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት መጥተው ታላላቅ ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋሉ፤ ከተቻለም የተመረጡትን እንኳ ያሳስታሉ፡፡25ይህ ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፡፡26ስለዚህ፣ ‹ክርስቶስ በምድረ በዳ ነው› ቢሏችሁ ወደ ምድረ በዳ አትሂዱ ወይም ቤት ውስጥ ነው ቢሏችሁ አትመኑ፡፡27መብረቅ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በአንዴ እንደሚታይ የሰው ልጅ ሲመጣ እንደዚያው ይሆናል፡፡28የሞተ እንስሳ ባለበት ሁሉ፣ በዚያ አሞሮች ይሰበሰባሉ፡፡29ከእነዚህ የመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉ፡፡30ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ የምድር ነገዶች ሁሉ አምርረው ያለቅሳሉ፡፡ የሰው ልጅንም በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፡፡31መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም፣ ከአንድ የሰማይ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ ከአራቱም ነፋሳት ምርጦቹን ይሰበስቧቸዋል፡፡32ከበለስ ዛፍ ተማሩ፡፡ ቅርንጫፎቿ ሲለመልሙና ቅጠሎች ብቅ ብቅ ሲሉ በጋ መቅረቡን ታውቃላችሁ፡፡33እናንተም እነዚህን ሁሉ ስታዩ እርሱ መቅረቡን፣ እንዲያውም በደጅ መሆኑን ዕወቁ፡፡34እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም፡፡35ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም፡፡36ስለዚያች ቀንና ሰዓት ግን ማንም አያውቅም፤ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ አያወቁም፤ አብ ብቻ እንጂ ወልድ እንኳ ቢሆን አያውቅም፡፡37በኖኅ ዘመን እንደ ነበረው፣ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል፡፡38ከጥፋት ውሃ በፊት እንደ ነበረው ዘመን፣ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባ ድረስ ይበሉና ይጠጡ፣ ያገቡና ይጋቡ ነበር።39ጐርፉ መጥቶ እስኪያጠፋቸው ድረስ ምንም አላወቁም፣ የሰው ልጅ ሲመጣም እንዲሁ ይሆናል፡፡40በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሌላው ይቀራል፡፡41ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች፡፡42ስለዚህ ጌታችሁ በምን ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተጠንቀቁ፡፡43ይህን ግን ዕወቁ፤ ሌባው በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ የቤቱ ባለቤት ቢያውቅ ኖሮ ይጠነቀቅ ነበር፤ ቤቱ አይዘረፍም ነበር፡፡44የሰው ልጅ ባልጠበቃችሁት ሰዓት ስለሚመጣ እናንተም ብትሆኑ ተዘጋጅታችሁ መጠበቅ አለባችሁ፡፡45በተገቢው ጊዜ ለቤተ ሰቦቹ ምግባቸውን ለመስጠት ጌታው በቤቱ ላይ ኀላፊነት የሰጠው ታማኝና አስተዋይ አገልጋይ ማን ነው?46ጌታው ሲመጣ ያንን እያደረገ የሚያገኘው አገልጋይ የተባረከ ነው፡፡47እውነት እላችኋለሁ የምላችሁ፣ ጌታው ባለው ነገር ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ይሾመዋል፡፡48ይሁን እንጂ፣ አንድ ክፉ አገልጋይ በልቡ፣ ‹‹ጌታዬ ከመምጣት ዘግይቶአል ብሎ ቢያስብ፣49አገልጋይ ጓደኞቹን መደብደብና ከሰካራሞች ጋር መብላት መጠጣት ቢጀምር50የዚያ አገልጋይ ጌታ አገልጋዩ ባልጠበቀው ቀንና በማያውቀው ሰዓት ይመጣበታል፡፡51ጌታው ለሁለት ይሰነጥቀዋል፤ ዕጣ ፈንታውን ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፣ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡
1መንግሥተ ሰማይ መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ለመቀበል የወጡ ዐሥር ድንግሎችን ትመስላለች።2ዐምስቱ ሞኞች፣ ዐምስቱ ልባሞች ነበሩ።3ሞኞቹ ድንግሎች መብራታቸውን ይዘው ሲሄዱ ምንም ዘይት አልያዙም ነበር።4ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር ዘይትም ይዘው ነበር።5ሙሽራው በዘገየ ጊዜ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ሁሉም ተኙ።6ዕኩለ ሌሊት ላይ ግን፣ “ሙሽራው መጥቶአልና ወጥታችሁ ተቀበሉት!” የሚል ሁካታ ሆነ።7ያኔ እነዚያ ድንግሎች ሁሉ ተነሥተው መብራታቸውን አዘጋጁ።8ሞኞቹም ልባሞቹን፣ “መብራታችን እየጠፋ ስለ ሆነ፣ ከዘይታችሁ ጥቂት ስጡን” አሏቸው።9ልባሞቹ ግን፣ “ለእኛና ለእናንተ የሚበቃ ስለሌለን፣ ወደ ሻጮች ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ” በማለት መለሱአቸው።10ለመግዛት ሲሄዱ፣ ሙሽራው መጣ፤ ተዘጋጅተው የነበሩት ግብዣው ላይ ለመገኘት ከእርሱ ጋር ሄዱ፤ በሩም ተዘጋ።11በኋላ ሌሎቹ ድንግሎች መጥተው፣ “ጌታው፣ በሩን ክፈትልን” አሉ።12እርሱ ግን መልሶ፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ አላውቃችሁም” አላቸው።13ስለዚህ ቀኑን ወይም ሰዓቱን አታውቁምና ነቅታችሁ ጠብቁ።14ነገሩ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ ያሰበ ሰውን ይመስላልና፤ አገልጋዮቹን ጠርቶ በሀብት በንብረቱ ሁሉ ላይ ኀላፊነት ሰጣቸው።15እንደ ዐቅማቸው መጠን ለአንዱ ዐምስት መክሊት፣ ለሌላው ሁለት፣ ለሌላው ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸውና ሄደ።16ዐምስት መክሊት የተቀበለው ወዲያውኑ ሄዶ ነገደበት፤ ሌላ ዐምስት አተረፈ።17ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንደዚያው ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ።18አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ግን ሄዶ ጉድጓድ ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።19ከብዙ ጊዜ በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ መጣና ተሳሰባቸው።20ዐምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ሌላ ዐምስት መክሊት ጨምሮ አመጣና፣ “ጌታ ሆይ፣ ዐምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እኔ ግን ሌላ ዐምስት መክሊት አተረፍሁ” አለ።21ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ።' አለው።22ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው አገልጋይም መጥቶ፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር። ሌላ ሁለት መክሊት አትርፌአለሁ’ አለ።23ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።24ከዚያም አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ መጥቶ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ።25ስለዚህ ፈራሁ፤ መክሊትህን መሬት ውስጥ ቀበርሁት። መክሊትህ ይኸውልህ' አለው።26ጌታው ግን መልሶ፣ 'አንተ ዐመፀኛና ሰነፍ አገልጋይ፤ ካልዘራሁበት የማጭድ፣ ካልበተንሁበት የምሰበስብ መሆኔን ታውቃለህ።27ስለዚህ ገንዘቤን በባንክ ማስቀመጥ ይገባህ ነበር፤ እኔ ስመጣ ከነወለዱ እወስደው ነበር' አለው።28ስለዚህ መክሊቱን ከእርሱ ወስዳችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት።29ላለው የበለጠ እንዲያውም የተትረፈረፈ ይሰጠዋል። ምንም ከሌለው ግን፣ ያው ያለው ነገር እንኳ ይወሰድበታል።30ይህን የማይረባ አገልጋይ አውጡና ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት” አለ።31የሰው ልጅ በክብሩ ከመላእክቱ ሁሉ ጋር ሲመጣ፣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።32አሕዛብ ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ ሕዝቡን ይለያቸዋል።33በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን በግራው ያደርጋቸዋል።34ከዚያም ንጉሡ በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ 'እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።35ተርቤ ነበር ምግብ ሰጣችሁኝ፤ ተጠምቼ ነበር የምጠጣው ሰጣችሁኝ፤ እንግዳ ሆኜ ነበር አስተናገዳችሁኝ፤36ተራቊቼ ነበር አለበሳችሁኝ፤ ታምሜ ነበር ተንከባከባችሁኝ፤ ታስሬ ነበር ጠየቃችሁኝ' ይላቸዋል።37ከዚያም ጻድቃን እንዲህ ብለው ይመልሱለታል፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ያገኘንህና ያበላንህ ወይስ ተጠምተህ ያጠጣንህ መቼ ነው?3838 እንግዳ ሆነህ ያየንህና ያስተናገድንህ መቼ ነው? ወይም ተራቊተህ ያለበስንህ መቼ ነው?39ታምመህ የተንከባከብንህ ወይስ ታስረህ የጠየቅንህ መቼ ነው?’40ንጉሡም መልሶ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ለእነዚህ ታናናሽ ወንድሞቼ ያደረጋችሁትን ለእኔ አድርጋችሁታል።’41ከዚያም በግራው ያሉትን፣ ‘እናንተ ርጉማን ከእኔ ራቁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ገሃነም እሳት ሂዱ።42ምክንያቱም ‘ተርቤ ነበር አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ ነበር አላጠጣችሁኝም፤43እንግዳ ሆኜ ነበር አልተቀበላችሁኝም፤ ተራቊቼ ነበር አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜ፣ ታስሬ ነበር፣ እናንተ ግን አልተንከባከባችሁኝም’ ይላቸዋል።44እነርሱም መልሰው እንዲህ ይሉታል፤ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ወይም ተጠምተህ ወይም እንግዳ ሆነህ ወይም ተራቊተህ ወይም ታምመህ ወይም ታስረህ ያላገለገልንህ መቼ ነው?’45እርሱም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ አለማድረጋችሁ ለእኔ አለማድረጋችሁ ነው’ ይላቸዋል።46እነዚህ ወደ ዘላለም ቅጣት፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።"
1ኢየሱስ እነዚህን ቃሎች ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤2"ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንደሚሆን ታውቃላችሁ፣ የሰው ልጅም ተሰቅሎ እንዲገደል ተላልፎ ይሰጣል፡፡"3ከዚያ የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ቀያፋ በሚሉት ሊቀ ካህናት ግቢ ውስጥ ተሰበሰቡ፤4ኢየሱስን በረቀቀ ዘዴ ለማሰርና ለመግደል ተማከሩ፡፡5ምክንያቱም፣ በሕዝቡ መሓል ረብሻ እንዳይነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም እያሉ ነበር፡፡6ኢየሱስ በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት7ማዕድ ላይ ተቀምጦ እያለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ ያለበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣችና ራሱ ላይ አፈሰሰች፡፡8ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲያዩ በጣም ተቈጥተው፣ "ይህ ብክነት ምንድን ነው?9ይህ እኮ ከፍ ባለ ዋጋ ተሸጦ ገንዘቡን ለድኾች መስጠት ይቻል ነበር" አሉ፡፡10ኢየሱስም ይህን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፣ "ይህችን ሴት ለምን ታስቸግሯታላችሁ? ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች፡፡11ድኾች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልሆንም፡፡12ይህን ሽቱ እኔ ላይ ባፈሰሰች ጊዜ ለቀብሬ አድርጋዋለች፡፡13እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ወንጌል በመላው ዓለም ሲሰበክ ለእርሷ መታሰቢያ እንዲሆን ይህች ሴት ያደረገችውም ይነገርላታል።"14ከዚያም የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆቹ ሄዶ፣15"እርሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ለእኔ ምን ትሰጡኛላችሁ?" አላቸው፡፡ እነርሱም ሠላሣ ጥሬ ብር ተመኑለት፡፡16ከዚያ ጊዜ ወዲህ እርሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን ምቹ ጊዜ ይጠባበቅ ጀመር፡፡17በቂጣ በዓል በመጀመሪያው ግን ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "የፋሲካን እራት እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?" አሉት፡፡18እርሱም፣ "ከተማው ውስጥ ወዳለ አንድ ሰው ሂዱና፣ 'መምህሩ "ጊዜዬ ደርሷል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በአንተ ቤት ማክበር እፈልጋለሁ' ይልሃል በሉት'" አላቸው፡፡19ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንደ ነገራቸው አደረጉ፤ የፋሲካንም እራት አዘጋጁለት፡20ምሽት ላይ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ለመብላት ተቀመጠ፡፡21በመብላት ላይ እያሉ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል" አላቸው፡፡22እነርሱ በጣም ዐዘኑ፤ እያንዳንዱም፣ "እኔ እሆንን?" በማለት ይጠያየቁ ጀመር፡፡23እርሱም፣ "አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር እጁን ወደ ሳሕኑ የሚሰደው ነው፡፡24የሰው ልጅ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈው ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ግን ወዮለት! ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር" በማለት መለሰላቸው፡፡25አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳ፣ "መምህር ሆይ፣ እኔ ነኝ እንዴ?" አለው፤ እርሱም፣ "አንተው ራስህ ብለኸዋል" አለው፡፡26በመብላት ላይ እያሉ፣ ኢየሱስ እንጀራ አንሥቶ ባርኮ ቈረሰ፡፡ "እንካችሁ ውሰዱ፣ ብሉት፤ ይህ ሥጋዬ ነው" ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡27ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነና ሰጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ "ሁላችሁም ጠጡት28ይህ ለብዙዎች ኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የኪዳኑ ደሜ ነው፡፡29እንደ ገና በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር እስክጠጣው ድረስ ከእንግዲህ ከዚህ ወይን ፍሬ እንደማልጠጣ ግን እነግራችኋለሁ፡፡"30መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ፡፡31ያኔ ኢየሱስ፣ "በዚህ ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ምክንያት ትሰናከላላችሁ፤ ምክንያቱም፣ 'እረኛውን እመታለሁ በጎቹም ይበተናሉ' ተብሎ ተጽፎአል፡፡32ከተነሣሁ በኋላ ግን ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ" አላቸው፡፡33ጴጥሮስ ግን፣ "ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እንኳ እኔ አልሰናከልም" አለው፡፡34ኢየሱስም፣ "እውነት እልሃለሁ ፣ በዚህች ሌሊት ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ" አለው፡፡35ጴጥሮስም፣ "ከአንተ ጋር መሞት ቢኖርብኝ እንኳ አልክድህም" አለ፡፡ ሌሎችም ደቀ መዛሙርት ሁሉ እንደዚያው አሉ፡፡36ከዚያም ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደሚሉት ቦታ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱንም፣ "ወደዚያ ሄጄ እስክጸልይ ድረስ እዚህ ሁኑ" አላቸው፡፡37ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዴዎስ ልጆች ይዞ ሄደ፤ ያዝንና ይጨነቅም ጀመር፡፡ ከዚያም፣38"ነፍሴ፣ እስከ ሞት ድረስ በጣም ዐዝናለች፡፡ እዚህ ሆናችሁ ከእኔ ጋር ትጉ" አላቸው፡፡39ጥቂት ራቅ ብሎ በመሄድ በግንባሩ ወድቆ ጸለየ፤ "አባት ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ፤ ይሁን እንጂ፣ የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን" አለ፡፡40ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም፣ "ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት ያህል እንኳ መትጋት አልቻላችሁምን?41ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፡፡ መንፈስ በእርግጥ ፈቃደኛ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው" አለው፡፡42ለሁለተኛ ጊዜ ጥቂት ፈቀቅ ብሎ ጸለየ፤ "አባት ሆይ፣ እኔ ካልጠጣሁት በቀር ይህ የማያልፍ ከሆነ፣ ፈቃድህ ይሁን" አለ፡፡43እንደ ገና ሲመጣ ዐይኖቻቸው ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፡፡44እንደ ገና ትቶአቸው ሄዶ ለሦስተኛ ጊዜ ያንኑ ቃል ጸለየ፡፡45ከዚያም ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፣ "አሁንም ዐርፋችሁ ተኝታችኋል? ጊዜው ደርሷል፤ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፡፡46እንግዲህ ተነሡ እንሂድ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል" አላቸው፡፡47ገና እየተናገረ እያለ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፣ ከእርሱም ጋር ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች የመጡ ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡48በዚህ ጊዜ አሳልፎ የሚሰጠው፣ "እኔ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት" የሚል ምልክት ሰጣቸው፡፡49ወዲያውኑ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ "መምህር ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!" ብሎ ሳመው፡፡50ኢየሱስም፣ "ወዳጄ፣ የመጣህበትን ጉዳይ ፈጽም" አለው፡፡ ከዚያም መጡ ኢየሱስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፣ ያዙትም።51ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፍ አወጣ፤ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ጆሮ መትቶ ቈረጠ፡፡52ያኔ ኢየሱስ፣ "ሰይፍህን ወደ ቦታው መልስ፤ ሰይፍ የሚያነሡ በሰይፍ ይጠፋሉ፡፡53አባቴን ብጠይቅ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ መላእክት የማይልክልኝ ይመስልሃል?54እንደዚያ ከሆነ ይህ እንደሚሆን የሚናገረው መጽሐፉ ቃል እንዴት ይፈጸማል?" አለው፡፡55በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡ፣ "ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ መጣችሁ? በየቀኑ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ እያስተማርሁ ነበርሁ፡፡ እናንተም አልያዛችሁኝም ነበር፡፡56የነቢያት መጽሐፍ እንዲፈጸም ይህ ሆኗል" አላቸው፡፡ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ፡፡57ኢየሱስን የያዙ ሰዎች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ሽማግሌዎቹ ተሰብስበው ወደ ነበሩበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ቤት ወሰዱት፡፡58ጴጥሮስ ግን ከሩቅ ሆኖ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ተከተለው፤ ወደ ውስጥ ገብቶም የሚሆነውን ለማየት ከጠባቂዎቹ ጋር ተቀመጠ፡፡59እርሱን ለማስገደል የካህናት አለቆቹና ሸንጎው ሁሉ በኢየሱስ ላይ በሐሰት የሚመሰክሩበትን ሰዎች እየፈለጉ ነበር፡፡60ምንም እንኳ ብዙ የሐሰት ምስክሮች ቢመጡም፤ በቂ ማስረጃ አላገኙም፡፡ በኋላ ግን ሁለት ሰዎች ወደ ፊት መጥተው፣61"ይህ ሰው፣ 'የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ እንደ ገና ልሠራው እችላለሁ' ብሏል" አሉ፡፡62ሊቀ ካህናቱ ተነሥቶ፣ "መልስ የለህም? በአንተ ላይ እየመሰከሩብህ ያለው ምንድን ነው?" አለው፡፡63ኢየሱስ ግን ዝም አለ፡፡ ሊቀ ካህናቱም፣ "በሕያው እግዚአብሔር አዝሃለሁ፤ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን አለመሆንህን ንገረን" አለው፡፡64ኢየሱስም፣ "አንተው ራስህ አልህ፤ ግን ልንገርህ፣ ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያለህ" በማለት መለሰለት፡፡65ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀደደና፣ "እግዚአብሔርን ተሳድቧል፤ ታዲያ፣ ምስክር የምንፈልገው ለምንድን ነው? አሁን ስድቡን ሰምታችኋል66ለመሆኑ፣ ምን ታስባላችሁ?" አለ፡፡ እነርሱም መልሰው፣ "ሞት ይገባዋል" አሉ፡፡67ከዚያም ፊቱ ላይ ተፉበት፣ በጡጫና በጥፊ መቱት፤68"አንተ ክርስቶስ እስቲ ትንቢት ተናገር፡፡ ለመሆኑ፣ በጥፊ የመታህ ማን ነው?" አሉት፡፡69በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እደጅ ግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት አገልጋይ ልጅ ወደ እርሱ መጥታ፣ "አንተም ደግሞ ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርህ" አለችው፡፡70እርሱ ግን፣ "ምን እየተናገርሽ እንደ ሆነ አላውቅም" በማለት በሁሉም ፊት ካደ፡፡71ከግቢው ወደሚያስወጣው በር እየሄደ እያለ፣ ሌላ አገልጋይ ልጅ አየችውና እዚያ ለነበሩት፣ "ይህኛውም ሰውየ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበረ" አለች፡፡72እርሱም፣ "ሰውየውን አላውቀወም" በማለት በመሐላ ጭምር በድጋሚ ካደ፡፡73ጥቂት ቆየት ብሎ እዚያ ቆመው የነበሩት መጥተው ጴጥሮስን፣ "በርግጥ አንተም ብትሆን ከእነርሱ አንዱ ነህ፤ አነጋገርህ ራሱ ያጋልጥሃል" አሉት፡፡74ከዚያም፣ "ሰውየውን ጨርሶ አላውቀውም" በማለት ይራገምና ይምል ጀመር፤ ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ፡፡75ጴጥሮስ "ዶሮ ሳይጮኽ ሦስቴ ትክደኛለህ" በማለት ኢየሱስ የተናገረውን አስታወሰ፡፡ ከዚያ ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡
1ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስን ለመግደል ተማከሩ።2አስረው ወሰዱትና ለአገሩ ገዢው ለጲላጦስ አስረከቡት።3አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ኢየሱስ እንደ ተፈረደበት ባየ ጊዜ ተጸጸተ፣ ሠላሣውን ጥሬ ብር ለካህናት አለቆቹና ለሽማግሌዎቹ መልሶ፣4"ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠት በድያለሁ" አለ። እነርሱ ግን፣ “ታዲያ፣ እኛን ምን አገባን? የራስህ ጉዳይ ነው” አሉት።5ከዚያም ጥሬ ብሩን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ወረወረና ወጥቶ ራሱን ሰቀለ።6የካህናት አለቆቹ ጥሬ ብሩን ወስደው፣ “ይህ የደም ዋጋ ስለ ሆነ፣ ከቤተ መቅደሱ ገንዘብ ጋር መቀላቀል ተገቢ አይደለም” አሉ።7እርስ በርሳቸው ተነጋግረው የእንግዶች መቀበሪያ እንዲሆን የሸክላ ሠሪውን መሬት ገዙበት።8ከዚህ የተነሣ ያ መሬት እስከዚህ ጊዜ ድረስ፣ “የደም መሬት” ተባለ።9በነቢዩ ኤርምያስ፣ “የእርሱ ዋጋ እንዲሆን የእስራኤል ልጆች የተመኑለትን ሠላሣ ጥሬ ብር ወሰዱ፣10እግዚአብሔር እንደ አዘዘኝ ለሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉት” ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ።11ኢየሱስ በአገረ ገዢው ፊት ቆመ፤ አገረ ገዢውም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህ እንዴ?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተ እንዳልኸው ነው” በማለት መለሰለት።12የካህናት አለቆችና፣ ሽማግሌዎቹ፣ ሲከሱት ምንም አልመለሰም።13በዚህ ጊዜ ጲላጦስ፣ “በአንተ ላይ የሚያቀርቡትን ክስ ሁሉ አትሰማምን?” አለው።14እርሱ ግን አንድ ቃል እንኳ ስላልመለሰለት አገረ ገዡ በጣም ተደነቀ።15በዓል ሲመጣ አገረ ገዢው ሕዝቡ የሚፈልጉትን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው።16በዚያን ጊዜ በርባን የሚሉት ከባድ ወንጀለኛ በእስር ቤት ውስጥ ነበር።17ተሰብስበው እያለ ጲላጦስ፣ “ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ፣ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን?” አላቸው።18ምክንያቱም አሳልፈው የሰጡት በቅናት መሆኑን ያውቅ ነበር።19በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ እያለ ሚስቱ፣ “በዚያ ንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ፤ እርሱን በተመለከተ በዚህ ሌሊት በሕልሜ ብዙ መከራ ተቀብያለሁ” የሚል ቃል ላከችበት።20የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ በርባን እንዲፈታና ኢየሱስ እንዲገደል እንዲጠይቁ ሕዝቡን ቀሰቀሱ።21አገረ ገዢው፣ “ከሁለቱ የትኛውን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፣”በርባንን” አሉ።22ጲላጦስም፣ “ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስንስ ምን ላድርገው?” አላቸው። ሁሉም፣ “ስቀለው” በማለት መለሱ።23እርሱም፣ “ለምን፣ የሠራው ወንጀል ምንድንነው?” አላቸው። እነርሱ ግን፣ “ስቀለው” እያሉ የበለጠ ጮኹ።24ስለዚህ ምንም ማድረግ እንዳልቻለና እንዲያውም ዐመፅ እየተነሣ መሆኑን ጲላጦስ ባየ ጊዜ፣ በሕዝቡ ፊት እጁን በውሃ ታጥቦ፣ “እኔ ከዚህ ንጹሕ ሰው ደም ነጻ ነኝ፤ ከእንግዲህ ኀላፊነቱ የእናንተው ነው” አለ።25ሕዝቡ ሁሉ፣ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” አሉ።26ከዚያም በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቅሉት ሰጣቸው።27የአገረ ገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱትና ወታደሮቹን ሁሉ ሰበሰቡ።28ልብሱን ገፍፈው ቀይ ልብስ አለበሱት።29ከዚያም የእሾኽ አክሊል ሠርተው በራሱ ላይ ደፉ፣ በቀኝ እጁ በትር አስያዙት፤ በፊቱ ተንበርክከውም፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ አሾፉበት።30ፊቱ ላይም ተፉበት፤ በትሩን ወስደው ራሱን መቱት።31ካፌዙበትም በኋላ ልብሱን አውልቀው የራሱን ልብስ አለበሱትና እንዲሰቀል ወሰዱት።32እንደወጡ ስምዖን የሚሉት የቀሬና ሰው አገኙ፤ መስቀሉን እንዲሸከም አስገደዱት።33ጎልጎታ ወደሚባል ቦታ መጡ፤ ትርጕሙም “የራስ ቅል” ማለት ነው።34ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሰጡት፤ እርሱ ግን ቀምሶ ሊጠጣው አልፈለገም።35በሰቀሉት ጊዜ ዕጣ በመጣጣል ልብሶቹን ተከፋፈሉ፤36ተቀምጠው ይጠብቁትም ጀመር።37ከራሱ በላይ፣ “ይህ የአይሁድ ንጉሥ ኢየሱስ ነው” የሚል የክስ ጽሕፈት አኖሩ።38ሁለት ወንበዴዎች አንዱ በቀኙ ሌላው በግራው በኩል ከእርሱ ጋር ተሰቅለው ነበር።39የሚያልፉ ሰዎችም ሰደቡት፤ ራሳቸውን እየነቀነቁም40“ቤተ መቅደሱን የምታፈርስና በሦስት ቀን የምትሠራ ራስህን አድን። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ” ይሉት ነበር።41በተመሳሳይ መንገድ የካህናት አለቆች፣ ከአይሁድ የሕግ መምህራንና ከሽማግሌዎቹ ጋር አብረው፣42“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አልቻለም። እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ነው፣ ከመስቀል ይውረድ፣ ከዚያም እኛ እናምንበታለን።43በእግዚአብሔር ተማምኖአል፤ እርሱ ከወደደ ያድነው፤ ምክንያቱም፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሏል" እያሉ ያፌዙበት ነበር።44ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም እንዲሁ ይሰድቡት ነበር።45ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ምድሩን ሁሉ የሚሸፍን ጨለማ ሆነ።46በዘጠኝ ሰዓት ኢየሱስ፣ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰባቅታኒ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጒሙም፣ “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ” ማለት ነው።47እዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ፣ “ኤልያስን እየተጣራ ነው” አሉ።48ወዲያውኑ ከእነርሱ አንዱ ሮጦ ሄደና ስፖንጁን የኮመጠጠ ወይን ጠጅ ውስጥ ነክሮ በሸንበቆ በትር አድርጎ እንዲጠጣ ሰጠው።49የተቀሩትም፣ "እስቲ ተዉት፤ ኤልያስ መጥቶ ሲያድነው እናያለን” አሉ።50ከዚያም ኢየሱስ በድጋሚ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን ሰጠ።51የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተከፈለ፤ ምድር ተናወጠ፤ ዐለቶችም ተሰነጠቁ፤52መቃብሮች ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው የነበሩ ብዙ ቅዱሳን ተነሡ።53ከትንሣኤው በኋላ ከመቃብር ወጡ፤ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩ።54የመቶ አለቃውና ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩ ሰዎች የምድር መናወጡንና የሆኑትን ነገሮች ሲያዩ በጣም ፈርተው፣ "በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው" አሉ።55እርሱን ለመርዳት ከገሊላ ጀምሮ ኢየሱስን ተከትለው የነበሩ ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር።56ማርያም መግደላዊት፣ የያዕቆብና የዮሴፍ እናት ማርያም፣ እንዲሁም የዘብዲዎስ ልጆች እናት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።57ምሽት ላይ ዮሴፍ የሚሉት አንድ ሀብታም ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱ ራሱ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር።58ወደ ጲላጦስ መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ። ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ።59ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ፤ በንጹሕ ናይለን ጨርቅ ጠቀለለውና60ለራሱ ከዐለት በሠራው መቃብር ውስጥ አኖረው። ከዚያም ትልቅ ድንጋይ አንከባልሎ መቃብሩ ደጃፍ ላይ አድርጎ ሄደ።61ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም መቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው በዚያ ነበሩ።62በሚቀጥለው ቀን ከዝግጅት በኋላ የካህናት አለቆቹና ፈሪሳውያን በአንድነት ከጲላጦስ ጋር ተሰበሰቡ።63እንዲህም አሉ፣ "ጌታ ሆይ፣ ያ አሳሳች በሕይወት በነበረ ጊዜ፣ 'ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ' ብሎ እንደ ነበር ትዝ አለን።64ስለሆነም፣ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ መቃብሩ በጥንቃቄ እንዲጠበቅ እዘዝ፤ አለበለዚያ ግን፣ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ሥጋውን ይሰርቁና ለሕዝቡ፣ ‘ከሞት ተነሣ’ ይላሉ፤ የኋላው ስሕተት ከመጀመሪያው የከፋ ይሆናል” አሉት።65ጲላጦስም፣ “ጠባቂ ወስዳችሁ፣ የሚቻላችሁን ያህል በጥንቃቄ እንዲጠበቅ አድርጉ” አላቸው።66ስለዚህ ሄደው መቃብሩ በጥንቃቄ እንዲጠበቅ አደረጉ፤ ድንጋዩን አተሙ፤ ጠባቂ አኖሩ።
1ሰንበት እንዳለፈ፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ማለዳ፣ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም ወደ መቃብሩ መጡ።2የጌታ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ነበርና ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ መጥቶም ድንጋዩን አንከባልሎ በላዩ ተቀመጠ።3መልኩ እንደ መብረቅ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር።4ጠባቂዎቹ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ እንደ ሞተ ሰውም ሆኑ።5መልአኩም እንዲህ በማለት ተናገረ፤ "አትፍሩ፤ ተሰቅሎ የነበረውን ክርስቶስን እንደምትፈልጉ አውቃለሁ።6እንደ ተናገረ ተነሥቷል እንጂ፣ እዚህ የለም፤ ኑና የነበረበትን ቦታ እዩ።7በፍጥነት ሄዳችሁ፣ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ በማለት ንገሩ፤ 'እርሱ ከሞት ተነሥቷል፤ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል። እዚያ ታዩታላችሁ።' እንግዲህ ነግሬአችኋለሁ።”8ሴቶቹ ፈጥነው በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር ከመቃብሩ እየሮጡ ሄዱ።9እነሆ ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ሴቶቹም እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት።10ከዚያም ኢየሱስ፣ "አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሩ፤ እዚያ ያዩኛል" አላቸው።11ሴቶቹ እየሄዱ እያሉ፣ ከጠባቂዎች ጥቂቱ ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ሁሉ ለካህናት አለቆቹ ነገሩ።12ካህናቱ ከሽማግሌዎቹ ጋር ተገናኝተው የሆነውን ሁሉ ሲናገሩ፣ ለወታደሮቹ ብዙ ገንዘብ በመስጠት፣13“እኛ ተኝተን እያለ ፣ ሌሊት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መጥተው አስክሬኑን ሰረቁ” ብለው እንዲናገሩ ነገሩዋቸው።14ይህ ወሬ ወደ አገረ ገዢው ከደረሰ፤ እኛ እናሳምነዋለን፣ እናንተም ከሥጋት ነጻ ትሆናላችሁ" አሏቸው።15ወታደሮቹ ገንዘቡን ተቀብለው ፣ እንደ ተነገራቸው አደረጉ። ይህ ወሬ እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁድ መሐል በሰፊው ተሰራጭቷል።16ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ወደ ገሊላ ኢየሱስ ወደ ነገራቸው ተራራ ሄዱ።17ባዩት ጊዜ ሰገዱለት፤ አንዳንዶቹ ግን ተጠራጥረው ነበር።18ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጥቶ፣ “በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠኝ።19ስለዚህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ፣ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስም ስም እያጠመቃችኋቸው፤20እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲያደርጉ እያስተማራችኋቸው፤ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
1ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፡፡2በነብዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈው እነሆ! መንገድን የሚያዘጋጅላችሁን መልዕክተኛዬን በፊታችሁ እልካለሁ፤3መንገድን አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ ብሎ በምድረበዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ፡፡4በምድረበዳ እያጠመቀና ለኃጢአት ይቅርታ የንሰሐን ጥምቀት እየሰበከ መጣ፡፡5ሁሉና በኢየሩሳሌም ያሉ ሁሉ ወደ እርሱ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እየመጡ ኃጢአታቸውን በመናዘዝ ይጠመቁ ነበር፡፡6የግመል ጠጉር ይለብስና ወገቡን በቆዳ መታጠቂያ ይታጠቅ፣ አንበጣና የበረሃ ማርም ይበላ ነበር፡፡7የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት የማልበቃ ከእኔ ይልቅ ታላቅ የሆነ እርሱ ከበስተኋላዬ ይመጣል፡፡8በውሃ አጥምቄአችኋለሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር፡፡9ቀናት ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት በመምጣት በዮርዳኖስ ውስጥ በዮሐንስ ተጠመቀ፡፡10እንደወጣም ሰማይ ሲከፈት፣ መንፈስ ቅዱስም እንደ እርግብ በእርሱ ላይ ሲወርድ አየ፤11ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምጽም ከሰማያት መጣ፡፡12መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድረበዳ መራው፡፡13በሰይጣን እየተፈተነም በምድረበዳ ለአርባ ቀን ቆየ፡፡ ከዱር አራዊትም ጋር ነበረ፤ መላዕክትም አገለገሉት፡፡14ታልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል እየሰበከ ወደ ገሊላ መጣ፡፡15ተፈጸመ፤የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ ይል ነበር፡፡16ባህር ዳር ሲያልፍ ሳለ ስምዖን ጴጥሮስንና ወንድሙን እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባህር ሲጥሉ አያቸው፤ አሳ አጥማጆች ነበሩና፡፡17በኋላዬ ኑና ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ አላቸው፡፡18መረቦቻቸውን ትተው ተከተሉት፡፡19እልፍ እንዳለም የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን እነርሱም በጀልባቸው ውስጥ መረቦቻቸውን ሲጠግኑ አያቸው፡፡20ጠራቸው፤ እነርሱም ዘብዴዎስ አባታቸውን ከተቀጣሪ ሰራተኞቻቸው ጋር በጀልባው ውስጥ ትተው ተከተሉት፡፡21ቅፍርናሆም ሔዱ፡፡ ወዲያው በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማራቸው፡፡22ጸሐፍት ሳይሆን ትምህርቱ እንደ ባለሥልጣን ስለነበረ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡23ርኩስ መንፈስ ያለበት አንድ ሰው በምኩራባቸው ነበረ፡፡24የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደሆንክ አውቄሃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ብሎ ጮኸ፡፡25ዝም በል! ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሰጸው፡፡26መንፈስ መሬት ላይ ጥሎ ካንፈራገጠው በኋላ በታላቅ ድምጽ ጮኾ ወጣ፡፡27ሁሉ በጣም ተገረሙና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው? ርኩሳን መናፍስትን እንኳን በሥልጣን ያዛቸዋልና እነርሱም ይታዘዙለታል በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ፡፡28እርሱም በገሊላ አውራጃና በዙሪያው ባሉ ሀገራት ሁሉ ዝናው ወጣ፡፡29እንደወጡ ወዲያው ከዮሐንስና ከያዕቆብ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት መጡ፡፡30ጊዜ የስምዖን አማት አተኵሷት ተኝታ ነበርና ወዲያው ስለ እርስዋ ነገሩት፡፡31እጇን ይዞ አስነሳት፤ ወዲያውኑ ትኵሳቱ ለቀቃትና አገለገለቻቸው፡፡32ጠልቃ በመሸ ጊዜም ብዙ በሽተኞችንና በአጋንንት የተያዙትን ወደ እርሱ አመጧቸው፡፡33ሰው ሁሉ በአንድነት በቤቱ ደጃፍ ተከማችቶ ነበር፡፡34በተለያየ በሽታ የታመሙትን ፈወሳቸው፤ ብዙ አጋንንንትንም አወጣ፡፡ አጋንንቱ ማን መሆኑን አውቀውት ነበርና እንዳይገልጡት አዘዛቸው፡፡35እጅግ በማለዳ ተነስቶ ለብቻው ወደ ምድረበዳ ሔደና ጸለየ፡፡36ከእርሱ ጋር የነበሩትም ተከተሉት፡፡37ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት፡፡38የምሥራቹን ቃል እንድሰብክ ወደ ሌሎቹ ከተሞች ደግሞ እንሂድ፣ ስለዚህ ጉዳይ መጥቻለሁና አላቸው፡፡39ወዳሉ ምኩራቦቻቸው ሁሉ እየገባ ሰበከላቸው፣ አጋንንትንም አወጣ፡፡40ለምጻም ወደ እርሱ መጥቶ ሰገደለትና ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው፡፡41አዘነለት፤ እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና እፈቅዳለሁ፣ ንጻ! አለው፡፡42ለምጹ ለቀቀውና ንጹህ ሆነ፡፡43ለማንም እንዳይናገር አጥብቆ አዘዘውና ወዲያው ሲያሰናብተው ሳለ44ግን ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለመንጻትህ ምሥክር እንዲሆንባቸው ሙሴ ያዘዘውን መስዋዕት አቅርብ አለው፡፡45ግን ሄደና ኢየሱስ በግልጽ ወደ ከተማ ለመግባት እስኪሳነው ድረስ ስለዚህ ነገር አብዝቶ ሊያወራና ሊያሰራጭ ጀመረ፡፡ በመሆኑም በምድረበዳ አካባቢዎች እንዲቆይ ሆነ፤ ሰዎችም ከየአቅጣጫው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፡፡
1ቀናት በኋላ ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ በቤት እንዳለ ወሬው ተሰማ፡፡2ሰዎችም ተሰበሰቡ፤ከዚህ የተነሣ በበሩ መግቢያም እንኳ በቂ ቦታ አልነበራቸውም፡፡ ኢየሱስም የእግዚአብሔርን ቃል ነገራቸው፡፡3ሰዎችም አንድ ሽባ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡4ብዛት ምክንያት ወደ እርሱ መቅረብ ስላልቻሉ፣ኢየሱስ ባለበት አቅጣጫ ጣሪያውን ነደሉት፡፡ በቀዳዳውም ሽባው ያለበትን ዐልጋ ወደ ታች አወረዱት፡፡5እምነታቸውን አይቶ ሽባውን ሰው፣ "አንተ ልጅ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል" አለው፡፡6ግን አንዳንድ ጸሓፍት በዚያ ተቀምጠው ነበር፡፡ ይህ ሰው እንዲህ ብሎ የሚናገረው ለምንድን ነው? እርሱ እግዚአብሔርን ይሳደባል፤7ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ይቅር ማለት የሚችል ማን ነው? እያሉ በልባቸው ያጉረመርሙ ነበር፡፡8ኢየሱስ በውስጣቸው እያጉረመረሙ እንደሆነ በመንፈሱ ዐውቆ፣ "በልባችሁ የምታጉረመርሙት ለምንድን ነው? አላቸው፡፡9ለሽባው ሰው የትኛውን ማለት ይቀላል? ኀጢኣትህ ተሰርዮልሃል ወይስ ተነሣ ዐልጋህን ተሸክመህ ሂድ ማለት?10እንጂ የሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢኣትን የማስተሰረይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፣11እልሃለሁ፤ ተነሣ! ዐልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ" አለው፡፡12እርሱም ተነሣ፤ ወዲያውኑም ዐልጋውን ተሸክሞ በሁሉም ፊት ወጥቶ ሄደ፡፡በዚያ የነበሩትም ሁሉም ተገርመው ስለ ነበር እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም በማለት እግዚአብሔርን አከበሩ፡፡13ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሄደ፡፡ሕዝቡም በሙሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ አስተማራቸውም፡፡14ሲያልፍም የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን ቀረጥ በመሰብሰቢያ ቦታው ተቀምጦ አየውና "ተከተለኝ" አለው፡፡ ተነሥቶም ተከተለው፡፡15በእርሱ(በሌዊ) ቤት ተቀምጦ እየበላ ነበር፡፡ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞችም ከኢየሱስና ከደቀመዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙዎቹም ተከትለውት ነበርና፡፡16ጸሓፍትም ከኀጢአተኞችና ከቀራጮች ጋር ሲበላ ሲያዩት ደቀመዛሙርቱን፣ "እርሱ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላውና የሚጠጣው እንዴት ነው" አሏቸው፡፡17ይህን ሲሰማ፣ "ሕሙማን እንጅ ጤናሞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም" ፤ እኔ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው፡፡18ደቀመዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጾሙ ነበር፡፡ ወደ እርሱም መጥተው የዮሐንስ ደቀመዛሙርትና የፈሪሳውያን ደቀመዛሙርት የሚጾሙት ነገር ግን የአንተ ደቀመዛሙርት የማይጾሙት ለምንድን ነው? አሉት፡፡19እንዲህ አላቸው፡፡ሙሽራው አብሮአቸው ሳለ ሚዜዎቹ ይጾማሉ? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እስካለ ሊጾሙ አይችሉም፡፡20ግን ሙሽራው የሚወሰድበት ቀን ይመጣል፡፡ በዚያን ጊዜ በዚያ ቀን ይጾማሉ፡፡21አዲስ እራፊ ጨርቅ በዐሮጌ ልብስ ላይ አየይጥፍም፤ ያለበለዚያ የተጣፈው እራፊ ይቀደዳል፡፡ ቀዳዳውም የባሰ ይሆናል፡፡22የወይን ጠጅ በዐሮጌ ዐቁማዳ ውስጥ የሚያስቀምጥ ማንም ለም፡፡ አለበለዚያ የወይን ጠጁ ዐቁማዳውን ያፈነዳዋል፤የወይን ጠጁና ዐቁማዳውም ይበላሻሉ፡፡ ነገር ግን አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ ዐቁማዳ ውስጥ ያስቀምጣሉ፡፡23በሰንበት ቀን በእህል ማሳ መካከል ያልፍ ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱም ሲያልፉ እሸት መቅጠፍ ጀመሩ፡፡24ፈሪሳውያንም እነሆ በሕግ ያልተፈቀደውን በሰንበት የሚያደርጉት ለምንድን ነው? አሉት፡፡25እንዲህ አላቸው፡፡ ዳዊት በተራበና በተቸገረ ጊዜ ለራሱና አብረውት ለነበሩት ምን እንዳደረገ፣ አብያታር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደገባ፤26ብቻ የተፈቀደውን ገጸ ኅብስት እንደ በላ፣ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደሰጣቸው ፈጽሞ አላነበባችሁምን? እንዲህም አላቸው፡፡27የተፈጠረው ለሰው ነው እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፡፡28የሰው ልጅ የሰንበትም እንኳ ጌታ ነው፡፡
1ምኩራብም ደግሞ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለችበት ሰው ነበረ፡፡2ሰውየውን በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደሆነ ተመለከቱት፡፡3የሰለለችበትን ሰውየም ተነሥ አለው፡፡4ሕዝቡንም በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ ማድረግ? ሕይወትን ማዳን ወይስ ማጥፋት? አላቸው፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ ዝም አሉ፡፡5በቁጣ ሲመለከት፣ በልባቸው ድንዳኔ ዐዝኖ፣ ሰውየውን እጅህን ዘርጋ አለው፤ ዘረጋውም፤ ዳነም፡፡6ወጡ፤ ወዲውም እንዴት ሊያጠፉት እንደሚችሉ ከሄሮድስ ወገኖች ጋር በእርሱ ላይ ተማከሩ፡፡7ከደቀ ዛሙርቱ ጋር ወደ ባሕሩ ሄደ፤ ከገሊላም እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከትለው፤ ከይሁዳና8ከኤዶምያስና ከዮርዳኖስ ማዶ፣ ከጢሮስና ከሲዶና ምን ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገ በመስማት እጅግ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ መጣ፡፡9የተነሣ እንዳያጨናንቁት ትንሽ ጀልባ እንዲያቆዩለት ለደቀ መዛሙርቱ ተናገረ፤10ፈውሶ ነበርና፡፡ በብዙ ደዌ የሚሠቃዩ ሁሉ ሊዳስሱት ይጋፉት ነበር፡፡11መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ወደቁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉም ጮኹ፡፡12ግን ማንነቱን እንዳይገልጡት አጥብቆ አዘዛቸው፡፡13ወደ ተራራውም ወጣ፤ የሚፈልጋቸውንም ወደ እርሱ ጠራ፤ እነርሱም ወደ እርሱ ሄዱ፡፡14ጋር እንዲሆኑ፣ ለመስበክ እንዲልካቸውና15ለማስወጣት ሥልጣን እንዲኖራቸው16ሁለት ሾመ፤ ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው ስምዖን፣17ልጅ ያዕቆብና የያዕቆብ ወንድም ዮሐንስ፤ እነርሱንም ቦአኔርጌስ ብሎ ጠራቸው፤ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤18እንድርያስና ፊልጶስ፣ በርተሎሜዎስና ማቴያስ፣ ቶማስና የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታዴዎስ፣ ቀናተኛው ስምኦንና19የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ፡፡20ኢየሱስ ወደ አንድ ቤት ውስጥ ገባ፡፡ መብላት እንኳ እስከማይችሉ ድረስ እንደ ገና ብዙ ሕዝብ መጥቶ ተሰበሰበ፡፡21ዘመዶቹም በሰሙ ጊዜ ይዘውት ሊሄዱ ወደ እርሱ መጡ፤ ዐብዶአል ብለው ነበርና፡፡22የወረዱ ጻፎችም ብዔልዜቡል አለበት፤ አጋንንንትን የሚያስወጣውም በአጋንንት አለቃ ነው አሉ፡፡23እርሱ ጠርቶአቸውም በምሳሌ ነገራቸው፤ ሰይጣን እንዴት ሰይጣንንን ማስወጣት ይችላል?24መንግሥትም እርስ በርሱ ቢከፋፈል፣ ያ መንግሥት መቆም አይችልም፤25ቤትም እርስ በርሱ ቢለያይ፣ ያ ቤት ጸንቶ ሊቆም አይችልም፡፡26ሰይጣንም እርስ በርሱ ቢቀዋወምና ቢለያይ፣ ፍጻሜው ይሆናል እንጂ መቆም አይችልም፡፡ በመጀመሪያ ኀይለኛውን ሰው ካላሰረና ከዚያም ንብረቱን ካልዘረፈ በቀር፣ 27ወደ ኀይለኛው ቤት መግባትና ንብረቱን መዝረፍ የሚችል የለም፡፡28እላችኋለሁ፤ ለሰው ልጆች ኀጢአታቸው ሁሉ፣ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይቅር ይባላል፤29ቅዱስን የሚሳደብ ግን ፈጽሞ ይቅርታ አያገኝም፤ ይልቁንም የየዘለዓለም ኀጢአት ዕዳ አለበት፤30ርኩስ መንፈስ አለበት ብለዋል፡፡31ወንድሞቹም መጡ፤ ውጭ ቆመውም እንዲጠሩት ወደ እርሱ ላኩ፡፡32ብዙ ሰው ተቀምጦ ነበር፤ ሰዎችም እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ውጭ ይፈልጉሃል አሉት፡፡33መለሰላቸው፤ አላቸውም፣ እናቴና ወንድሞቼ ማን ናቸው?34ዙሪያ የተቀመጡትን ተመልክቶም፣ እነሆ እናቴና ወንድሞቼ! ምክንያቱም35ፈቃድ የሚፈጽም ሁሉ ወንድሜ፣ እኅቴና እናቴ ነው፡፡
1በባህር አጠገብ ማስተማር ጀመረ፡፡ ከህዝቡ መብዛት የተነሳ በባህር ላይ ባለ ጀልባ ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ህዝቡም ሁሉ በባህሩ ዳርቻ ላይ ተሰብስበው ነበር፡፡2ነገርም በምሳሌ አስተማራቸው፡፡ በትምህርቱም እንዲህ አላቸው፡፡3ስሙ ዘሪ ሊዘራ ወጣ፡፤4በሚዘራበትም ጊዜ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ ወፎችም መጥተው ለቀሙት፡፡5ደግሞ ብዙ አፈር በሌለው በድንጋያማ መሬት ላይ ወደቀ፡፡ መሬቱ ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤6በወጣ ጊዜም ጠወለገ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ፡፡7ደግሞም አንዳንዱ በእሾህ መካከል ወደቀ እሾሁም አድጎ አነቀው ፍሬም አላፈራም፡፡8አንዳንዱ በመልካም መሬት ላይ ወደቀ አደገ እየበዛ ሄደ ፍሬም አፈራ ሶስት እጥፍ ስልሳ እጥፍ እና መቶ እጥፍ ፍሬ ሰጠ፡፡9እንዲህም አለ ጆሮ ያለው ይስማ፡፡10በሆነ ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ ጋር አብረው የነበሩት ስለ ምሳሌዎቹ ጠየቁት፡፡11አላቸው ለእናንተ የእግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር ተሰጥቷችኋል፡፡ በውጭ ላሉት ግን እንዲህ አይደለም12እንዳያዩ ሰምተውም እንዳያስተውሉ እንደገና ተመልሰው ይቅር እንዳይባሉ ሁሉም ነገር በምሳሌ ይሆንባቸዋል፡፡13አላቸው እናንተ ይህ ምሳሌ አልገባችሁምን? ሌሎቹን ምሳሌዎች ሁሉ እንዴት ትረዳላችሁ?14ዘሪው ቃሉን ዘራ፡፡15በመንገድ ዳር የወደቁት እነዚህ ናቸው ቃሉ በሚዘራበት ጊዜና ቃሉን እንደሰሙ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል፡፡16በድንጋያማ መሬት ላይ የወደቁት አነዚህ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ በደስታ ይቀበሉታል17ሥር የላቸውምና ለጊዜው ይቀበሉታል ከዚያም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሚነሳበት ጊዜ ወዲያወኑ በቃሉ ይሰናከሉበታል፡፤18ቦታ የወደቁት እነዚህ ቃሉን የሰሙ ናቸው19አለም ሀሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌሎች ነገሮች ምኞት ይገቡና ዘሩን ያንቁታል ፍሬ የማያፈራም ይሆናል፡፡20መሬት የወደቁት እነዚህ ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት ናቸው ሰላሳ እጥፍ ስልሳ እጥፍ እና መቶ እጥፍ የሚያፈሩ ናቸው፡፡21አላቸው፡- መብራትን ከፍ ባለ ማስመጫ ላይ እንጂ ከእንቅብ በታች ወይም አልጋ ሥር ያስቀምጡታልን?22ሳይገለጥ የሚቀር ነገር የለም በሚስጢር የተደረገ ወደ ብርሃንም የማይወጣ የለም፡፡23ያለው ይስማ እንዲህም አላቸው24-25አስተውሉ መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል ለእናንተም የበለጠ ይሰጣችኋል፡፡ ላለው የበለጠ ይጨመርለታል ከሌለው ግን ያ ያለው እንኳ ይወሰድበታል፡፡26አለ የእግዚአብሔር መንግሥት በመሬት ላይ ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች፡፡27ሲመሽ ይተኛል ሲነጋም ይነቃል፡፡ እንዴት እንደሆነ ባላወቀው መልኩ ዘሩ አቆትቁጦ በቀለ፡፤28ምድር የራሷን ሰብል ፍሬ አፈራች መጀመሪያ ቅጠሉ ቀጥሎም ዛላው በመጨረሻም በዛላው ውስጥ ሙሉ ፍሬ አፈራች፡፡29ግን ፍሬው በደረሰ ጊዜ መከር ነውና ወዲያውኑ ማጭድ አዘጋጀ፡፡30እንዲህ አለ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እንመስላታለን? ወይም በምን ምሳሌ እንገልጻታለን?31ቅንጣት ትመስላለች፡፡ በምድር ላይ በተዘራ ጊዜ ሲዘራ ምንም እንኳ በምድር ካሉ ዘሮች ሁሉ ያነሰ ቢሆንም32ጊዜ ያድጋል ቅርንጫፍም ያወጣል የሰማይ ወፎች ከጥላው ሥር እስኪጠለልቡበት ድረስ ከተክሎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ይሆናል፡፡33ሊሰሙ በሚችሉት መጠን ቃሉን በብዙ ምሳሌዎች ተናገራቸው34ምሳሌ ምንም አልተናገራቸውም፡፡ ለደቀመዛሙርቱ ግን ለብቻቸው ሁሉንም ነገር ገለጸላቸው፡፡35ቀን በመሸ ጊዜ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው፡፡36ህዝቡንም ትተው በጀልባ ወሰዱት፡፡ ሌሎችም ጀልባዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡37የነፋስ ማዕበልም ተነሳ ጀልባው እስኪጥለቀለቅ ድረስ ማዕበል ጀልባውን መታው፡፡38ከጀልባው በስተኋለኛው ክፍል ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፡፡ ቀስቅሰውም መምህር ሆይ ስንጠፋ አይገድህምን አሉት፡፡39እርሱም ተነሳ ነፋሱንም ገሰጸው ባህሩንም ዝም በል ጸጥ በል አለው፡፡ ነፋሱም ተወ ታላቅ ጸጥታም ሆነ፡፡40ስለምን ፈራችሁ? እምነት የላችሁምን እምነታችሁስ ወዴት አለ አላቸው፡፡41ፈርተው እርስ በእርሳቸው ነፋሱና ባህሩ እንኳ የሚታዘዙለት እንግዲህ ይህ ማነው? ተባባሉ፡፡
1ባሕሩ ሌላ ዳርቻ፣ ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጡ፡፡2ከጀልባዋ ውስጥ ሲወጣም ወዲያውኑ ርኩስ መንፈስ ያለበት አንድ ሰው ከመቃብር ሥፍራ ወጥቶ ተገናኘው፤3በመቃብር ስፍራ አድርጎ ነበር፤ እርሱን በሰንሰለት ሊያስረው የሚችል ሰው አልነበረም፤4ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ስለ ነበር፣ ሰንሰለቶቹን ይበጣጥሳቸው፣ እግር ብረቶቹንም ይሰባብራቸው ነበር፤ እርሱን ለመያዝ የሚያስችል ጥንካሬ ያለው ሰውም አልነበረም፡፡5ቀንና ሌሊት በመቃብሮቹና በተራራዎቹ ዘንድ ሰውነቱን በድንጋይ እየቈረጠ ይጮኽ ነበር፡፡6ከሩቅ ሲያየው፣ ሮጠና ሰገደለት፤7በመጮኽም፣ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፣ አታሠቃየኝ አለ፡፡8ርኩስ መንፈስ ከሰውየው ውጣ ብሎት ነበርና፡፡9ማን ነው ብሎም ጠየቀው፤ ብዙ ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለው፡፡10እንዳያባርራቸውም አጥብቆ ለመነው፡፡11በተራራው ጥግ ትልቅ የእሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር፡፡12በእነርሱ ውስጥ እንድንገባ ወደ እሪያዎቹ ስደደን በማለትም ለመኑት፡፡13እዲሄዱ ፈቀደላቸው፡፡ ርኩሳን መናፍስቱም ወጡ፣ በእሪያዎቹም ውስጥ ገቡ፤ ሁለት ሺ ያህል እሪያ ያለበት መንጋም በቁልቁለቱ ላይ ወደ ባሕሩ እየተንጋጋ ሄደ፤ በባሕሩም ውስጥ ሰመጠ፡፡14የሚጠብቁትም ሸሹ፤ በከተማውና በአገሩ ውስጥም አወሩት፡፡ የሆነውንም እንዴት እንደ ነበረ ለማየትም ሰዎች መጡ፡፡15ኢየሱስም መጥተው አጋንንት ያደሩበትን፣ ሌጌዎንም እንኳ የነበረበትን ሰው ተቀምጦ፣ ልብስ ለብሶና ልቡም ተመልሶለት አይተው ፈሩ፡፡16ሰዎችም አጋንንት ባደሩበት ሰውየ ላይ የታየው እንዴት እንደ ሆነና በእሪያዎቹ የሆነውም እንዴት እንደ ነበረ ነገሯቸው፡፡17ኢየሱስንም ከአገራቸው እንዲወጣ ይለምኑት ጀመር፡፡18ጀልባዋ ውስጥ እየገባ ሳለ፣ በአጋንንት ተይዞ የነበረው ሰው ከአንተ ጋር ልኑር ብሎ ለመነው፡፡19አልፈቀደለትም፤ ይልቁንም ወደ ቤትህ፣ ወደ ዘመዶችህ ሂድ፣ ጌታ ለአንተ እንዴት ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገልህ፣ እንዴትም ምሕረቱን ባንተ ላይ እንዳሳየ ንገራቸው አለው፡፡20ሄደና ኢየሱስ እንዴት ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገለት ዐሥር ከተማ በሚባለው ውስጥ ማሠራጨት ጀመረ፤ ሰዎችም ሁሉ ተደነቁ፡፡21በጀልባዋ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይሄድ በነበረ ጊዜም ደግሞ፣ እጅግ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፤ እርሱም በባሕሩ አቅራቢያ ነበረ፡፡22ከምኵራብ ኀላፊዎች አንዱ፣ ኢያኢሮስ የሚባል መጣ፣ እርሱንም አይቶ በእግሩ ሥር ወደቀ፤23ልጄ ልትሞት ነው፤ እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ትጭንባት ዘንድ እለምንሃለሁ በማለትም አጥብቆ ለመነው፡፡24ዐብሮት ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ ይጋፉትም ነበር፡፡25ሁለት ዓመት ደም ይፈስባት የነበረ፣26ብዙ ችግር የደረሰባት ብትሆንና ያላትን ሁሉ ብትከፍልም፣ ምንም ያልተሻላት፣ ይልቁንም የባሰባት27ሴት ስለ ኢየሱስ ሰምታ ከሕዝቡ በስተኋላ መጣች፣ የኢየሱስንም ልብስ ነካች፡፡28ላት፣ ይልቁንም የባሰባት 27አንድ ሴት ስለ ኢየሱስ ሰምታ ከሕዝቡ በስተኋላ መጣች፣ የኢየሱስንም ልብስ ነካች፡፡ 28ልብሱን ብቻ ከነካሁ እድናለሁ ብላለችና፡፡29የሚፈስሰው ደሟ ቆመ፤ ከሕማሟ እንደ ተፈወሰችም በሰውነቷ ታወቃት፡፡30ኢየሱስ ኀይል ከእርሱ መውጣቱን በራሱ በመረዳት፣ ዙሪያውን ወደ ሕዝቡ ተመለከተ፤ ልብሴን የነካው ማን ነው? ብሎም ተናገረ፡፡31መዛሙርቱም ሕዝቡ ሲጋፉህ ታያለህ፣ የነካኝ ማን ነውም? ትላለህ፡፡32ይህን ያደረገችውንም ለማየት ዙሪያውን ተመለከተ፡፡33ሴትዮዋ ግን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ፣ ለእርሷ የተደረገውንም በማወቅ መጣችና በፊቱ ወደቀች፤ እውነቱንም ሁሉ ነገረችው፡፡34እርሱም፡- ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፣ ከሕማምሽም ተፈወሺ አላት፡፡35ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ ከምኵራቡ ኀላፊ ቤት ሰዎች መጡ፤ ልጅህ ሞታለች፤ መምህሩን ለምን ታስቸግረዋለህ ብለውም ተናገሩ፡፡36ኢየሱስ የተናገሩትን ሰምቶ የምኵራቡን ኀላፊ “አትፍራ፤ እመን ብቻ” አለው፡፡37ኢየሱስ ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብና ከያዕቆብ ወንድም ከዮሐንስ በቀር ማንም እንዲከተለው አልፈቀደም፡፡38ወደ ምኵራቡ ኀላፊ ቤት መጡ፤ ኢየሱስ ያዘኑ፣ የሚያለቅሱና የዋይታ ጩኸት የሚያሰሙ ሰዎችን ተመለከተ፡፡39ወደ ውስጥ ገባና “ለምን ታዝናላችሁ? ለምንስ ታለቅሳላችሁ? ልጅቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው፡፡40ሰዎቹ በኢየሱስ ሣቁበት፤ እርሱ ግን ሁሉንም ወደ ውጭ አስወጣቸው፡፡ የልጅቱን አባትና እናት፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ይዞ ልጅቱ ወደ ነበረችበት ክፍል ገባ፡፡41ከዚያም ልጅቱን በእጁ ይዞ “ታሊታ ኩም!” ትርጉሙ “ትንሿ ልጅ ተነሺ እልሻለሁ” ማለት ነው፡፡42ወዲያው ልጅቱ ተነሣች፤ መራመድም ጀመረች፡፡ (ዐሥራ ሁለት ዓመቷ ነበርና) በዚህ ሰዎቹ በጣም ተገረሙ፡፡43ከዚያም ኢየሱስ ስለዚህ ጕዳይ ማንም ማወቅ እንደሌለበት ለሰዎቹ ጥብቅ ትእዛዛትን ሰጣቸው፤ የምትበላውንም ስጧት አለ፡፡
1ከዚያ ወጥቶ ወደ ገዛ ምድሩ መጣ፤ ደቀመዛሙርቱም ተከተሉት፡፡2ሰንበት በሆነ ጊዜም በምኩራብ ውስጥ ሊያስተምር ጀመረ፡፡ የሰሙትም ሁሉ ይህ ሰው እነኚህን ነገሮች ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ ሰው የተሰጠችውስ ጥበብ እንደምን ያለች ናት፤ በእጆቹ የሚደረጉት እነዚህ ታላላቅ ነገሮችስ ምን ትርጉም ይኖራቸው ይሆን?3ይህ አናጺው የማርያም ልጅ፤ የያዕቆብና የዮሳ፣ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እህቶቹስ ቢሆኑ እዚህ ከእኛ ጋር አይደሉምን? በማለት ተደነቁ፤ ተሰናከሉበትም፡፡4ኢየሱስም ነብይ በሀገሩ፣ በወገኑና በገዛ ቤተሰቡ ካልሆነ በስተቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው፡፡5ላይ እጆቹን ጭኖ ከመፈወስ በስተቀር በዚያ ታላቅ ተአምራት አላደረገም፡፡6ምክንያት ተደነቀ፡፡ በየመንደሮቹም እያስተማረ ዞረ፡፡7አሥራ ሁለቱን ወደ ራሱ ጠራና ሁለት ሁለት አድርጎ ይልካቸው ጀመር፤ በእርኩሳን መናፍስት ላይም ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡8ለጉዞአቸውም ከበትራቸው በቀር ምግብ፣ የመንገድ ሻንጣም ሆነ በገንዘብ ቦርሳቸው ውስጥ ገንዘብ እንዳይዙ አዘዛቸው፡፡9በስተቀር ቅያሪ ልብስ አትያዙ አላቸው፡፡10ከዚያ እስክትወጡ ድረስ በምትገቡበት ቤት በዚያ ቆዩ አላቸው፡፡11ቦታ ሁሉ ከማይቀበሏችሁና ከማይሰሟችሁ ሰዎች ምሥክር ይሆንባቸው ዘንድ በጫማችሁ ሥር ያለውን አቧራ አራግፉ፡፡12ደቀ መዛሙርቱም ወጥተው ሰዎች ንሰሐ እንዲገቡ ሰበኩላቸው፡፡13ብዙ አጋንንትን አስወጡ፤ ታመው የነበሩ ብዙዎችንም ዘይት ቀብተው ፈወሱአቸው፡፡14ዝናው ወጥቶ ነበርና ንጉሡ ሔሮድስ በሰማ ጊዜ አጥማቂው ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል፤ ስለዚህ እነዚህ ታላላቅ ነገሮች የሚደረጉትም በእርሱ ነው አለ፡፡15ግን ሌሎች ኤልያስ ነው አሉ፡፡ ሌሎቹም ነብይ ወይም ከነብያት አንዱ ነው አሉ፡፡16ነገር ግን ሔሮድስ ይህንን ሁሉ በሰማ ጊዜ እኔ አንገቱን ያስቆረጥኩት ዮሐንስ ተነሥቶአል አለ፡፡17ባገባት በወንድሙ በፊሊጶስ ሚስት በሄሮድያስ ምክንያት ራሱ ልኮ ዮሐንስን በመያዝ በወህኒ አኑሮት ነበርና፡፡18ዮሐንስም ሔሮድስን የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አይገባም ይለው ነበር፡፡19ሔሮድያዳ ዮሐንስን ትቃወምና ልትገድለው ትፈልግ ነበር፣አልቻለችምም፡፡20ሔሮድስ ዮሐንስን ይፈራው ነበር፡፡ ቅዱስና ጻድቅ እንደሆነ በማወቁም ይጠነቀቅለት ነበር፡፡ በሚሰማው ጊዜ ግራ እየተጋባም ቢሆን በደስታ ይሰማው ነበር፡፡21ምቹ ቀን በመጣ ጊዜም ልደቱን አስመልክቶ ሔሮድስ ለመኳንንቱ፣ ለሹማምንቱና ለገሊላ ታላላቅ ሰዎች የእራት ግብዣ አዘጋጀላቸው፡፡22የሄሮድያዳ ልጅ ራሷ ገብታ በዘፈነች ጊዜም ሔሮድስንና ከእርሱ ጋር በማዕድ የተቀመጡትን አስደሰተቻቸው፡፡ ንጉሱም ልጃገረዲቱን የምትፈልጊውን ሁሉ ጠይቂኝ እሰጥሻለሁ አላት፡፡23ማናቸውንም የምትፈልጊውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴን ግማሽም ቢሆን እሰጥሻለሁ ብሎ ማለላት፡፡24እርስዋም ወጥታ ወደ እናቷ በመሄድ ምን ልጠይቀው? ብትላት የአጥማቂው የዮሐንስን ራስ አለቻት፡፡25እርስዋም ወደ ንጉሱ ፈጥና በመምጣት የአጥማቂውን የዮሐንስን ራስ በሳህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ አለችው፡፡26ንጉሡም እጅግ አዘነ፡፡ ነገር ግን በመሐላዎቹና በማዕድ በተቀመጡት ምክንያት አልተቃወማትም፡፡27ንጉሡም ወዲያውኑ ከጠባቂዎቹ አንደኛውን ወታደር ልኮ ራሱን እንዲያመጣ አዘዘው፡፡ እርሱም ሔደና በወህኒ የዮሐንስን ራስ ቆረጠው፤28በሳህን አምጥቶም ለልጃገረዲቱ ሰጣት፣ ልጃገረዲቱም ለእናቷ ሰጠቻት፡፡29ደቀመዛሙርቱም ይህንን በሰሙ ጊዜ መጡና አስከሬኑን ወስደው በመቃብር አኖሩት፡፡30ሐዋርያቱም ወደ ኢየሱስ ተመልሰው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ነገር ሁሉ ነገሩት፡፡31እርሱም እናንተ ራሳችሁ ወደ ምድረበዳ ኑና ጥቂት ጊዜ ዕረፉ አላቸው፡፡ ወደ እነርሱ የሚመጡና የሚሔዱ ብዙዎች ነበሩና ለመብላት እንኳን ጊዜ አጥተው ነበር፡፡32በጀልባ ገብተው ወደ ምድረበዳው ፈቀቅ ብለው ሔዱ፡፡33ሲሔዱም ሕዝቡ አዩአቸውና ብዙዎቹ አወቁአቸው፤ እነርሱም ከየከተሞቹ ሁሉ በአንድነት በሩጫ ቀደሟቸው፡፡34ወደዚያ በመጣም ጊዜ ብዙ ሕዝብ አይቶ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ይመስሉ ነበርና አዘነላቸው፡፡ ብዙ ነገሮችንም ያስተምራቸው ጀመር፡፡35ቀኑ በመሸ ጊዜም ደቀመዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው ሥፍራው ምድረበዳ ነው፣ ቀኑም መሽቶአል፤36በአቅራቢያው ወደሚገኙ ከተሞችና መንደሮች ሔደው ለራሳቸው አንዳች የሚበሉትን እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብታቸው አሉት፡፡37እርሱ ግን መልሶ እናንተ የሚበሉትን ስጧቸው አላቸው፡፡ እነርሱም እንሂድና ይበሉ ዘንድ የአንድን ሰው የስድስት ወር ገቢ በሚያህል ገንዘብ እንጀራ ገዝተን እንስጣቸውን? አሉት፡፡38እርሱም ምን ያህል እንጀራ እንዳላችሁ ሂዱና እዩ አላቸው፡፡ ባወቁ ጊዜም ያለው አምስት እንጀራና ሁለት ዓሳ ነው አሉት፡፡39እርሱም ሁሉን በአረንጓዴው ሣር ላይ በቡድን በቡድን እንዲያስቀምጡ አዘዛቸው፡፡40እነርሱም በመቶዎችና በሃምሳዎች እየሆኑ በረድፍ ተቀመጡ፡፡41እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሳ ተቀብሎ ወደ ሰማይ በመመልከት ባረከውና ቆርሶ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡት ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ ሁለቱን ዓሳም ለሁሉም አካፈላቸው፡፡42ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡43አሥራ ሁለት ትላልቅ መሶብ ሙሉ ቁርስራሽ፣ እንዲሁም ከዓሳው ሰበሰቡ፡፡44እንጀራውን የበሉት እነዚያ 5000 ወንዶች ነበሩ፡፡45ወዲያውኑ እርሱ ራሱ ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀመዛሙርቱ በጀልባ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተሳይዳ ቀድመውት እንዲሻገሩ ግድ አላቸው፡፡46ከተለያቸው በኋላም ሊጸልይ ወደ ተራራ ፈቀቅ አለ፡፡47በመሸም ጊዜ ጀልባዋ በባህር ላይ ነበረች፤ እርሱም ብቻውን በምድር ላይ ነበር፡፡48ነፋሱ ከፊት ለፊታቸው እየተቃወማቸው ሳለ ለመቅዘፍ ሲጨነቁ አያቸውና ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባህሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይፈልግ ነበር፡፡49ነገር ግን በባህሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ ምትሃት ነው ብለው ስላሰቡ ጮኹ፡፡50ሁሉም አይተውት ስለነበረ ታወኩ፡፡ እርሱ ግን ወዲያው ተናገራቸውና አይዞአችሁ! እኔ ነኝ አትፍሩ! አላቸው፡፡51ወደ እነርሱ ወጥቶም ወደ ጀልባይቱ ገባ፤ ነፋሱም ተወ፡፡52እነርሱም በራሳቸው ያለመጠን ተገረሙ፤ ልባቸው ደንዝዞ ነበርና ስለ እንጀራው አላስተዋሉም፡፡53በተሻገሩ ጊዜም ወደ ጌንሳሬጥ አገር ወደ ባህሩ ዳርቻ መጡ፡፡54ከጀልባዋ በወጡ ጊዜም ሕዝቡ ወዲያው አወቁትና55በዙሪያው ወዳሉ መንደሮች በሞላ በመሮጥ ህሙማንን በአልጋ ተሸክመው እርሱ እንዳለ ወደሰሙበት ወደዚያ አመጧቸው፡፡56በየትኛውም እርሱ በገባባቸው መንደሮች ወይም ከተማዎች ወይም ሀገሮች ህሙማንን በገበያ ሥፍራዎች ያስቀምጧቸው፣ ቢቻላቸው ሊዳስሱት ካልሆነም የልብሱን ጫፍ ለመንካት ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ይድኑ ነበር፡፡
1ፈሪሳውያንና ከኢየሩሳሌም የመጡ አንዳንድ ጸሓፍት በአንድ ላይ ተሰብስበው ወደ ኢየሱስ መጡ፡፡2ከደቀመዛሙርቱ አንዳንዶቹ በረከሰ እጅ ማለትም ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ፡፡3(ፈሪሳውያንና ሁሉም አይሁድ የአባቶችን ወግ ስለሚጠብቁ እጆቻቸውን ካልታጠቡ በቀር አይበሉም ነበር)4ከገበያ ስፍራ ሲመጡ እጃቸውን ካልታጠቡ በቀር አይበሉም ነበር ፤እንዲሁም ዋንጫዎችን፣ ማሰሮዎችንና የናስ እቃዎችን ማጠብን የመሳሰሉ ሌሎች በርካታ ወጎችን ይጠብቁ ነበር፡፡5ፈሪሳውያንና ጸሓፍት "ደቀመዛሙርትህ በአባቶች ወግ መሰረት የማይጓዙት፣ ነገር ግን ባልታጠበ እጅ የሚበሉት ለምንድን ነው?" ብለው ጠየቁት ፡፡6እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፡፡ ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች በተናገረው ትንቢት፣ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ብቻ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤7ሰው ሠራሽ ሥርዐት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል˝ ተብሎ የተጻፈው ትክክል ነው፡፡8እናንተ የእግዚአብሔርን ሕግ ትታችሁ የሰዎችን ወግ ታጠብቃላችሁ፡፡9እንዲህም አላቸው፡፡ ወጋችሁን ለመጠበቅ ስትሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ትሽራላችሁ፡፡10ሙሴ፣ «አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ሞትን ይሙት» ብሏልና፡፡11እናንተ ግን አንድ ሰው እናቱን ወይም አባቱን፣ «ከእኔ ልታገኙ የሚገባችሁን እርዳታ ቁርባን አድርጌዋለሁ፤ ማለትም ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ» ቢላቸው፣12ከዚህ በኋላ ለአባቱና ለእናቱ ምንም ነገር እንዲያደርግ አትፈቅዱለትም፡፡ ለሌሎች በምታስተላልፉት ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፡፡13ይህን የመሳሰሉ ብዙ ነገሮችንም ታደርጋላችሁ፡፡14ደግሞም ሕዝቡን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ ሁላችሁም ስሙኝ ፤ አስተውሉም፡፡15ከውጭ ወደ ውስጡ ገብቶ ሰውን የሚያረክስ ምንም ነገር የለም፡፡16ነገር ግን ከውስጡ የሚወጡ ነገሮች እነርሱ ሰውን ያረክሱታል፡፡17ከሕዝቡ ተለይቶ ወደ ቤት እንደ ገባም ደቀመዛሙርቱ ስለ ምሳሌው ጠየቁት፡፡18እርሱም፣ «እናንተም አልተረዳችሁምን? ከውጭ ወደ ውስጡ ገብቶ ሰውን የሚያረክሰው ምንም ነገር እንደሌለ አታስተውሉምን?» አላቸው፡፡19ምክንያቱም ፣ወደ ውስጡ (ዐፉ) የሚገባው ነገር ወደ ሆዱ እንጂ ወደ ልቡ የሚገባ ስላልሆነ ከሰውነቱ የሚወጣ አይደለምን? ይህን በማለቱ ምግብ ሁሉ ንጹሕ መሆኑን ተናገረ፡፡2020እንዲህም አለ፤ ከሰው የሚወጣ ያ ሰውን ያረክሰዋል፡፡21ከውስጥ ከሰው ልብ ክፉ ሐሳብ፣ ዝሙት፣ መስረቅ፣ መግደል፣22ምንዝር፣ ስግብግብነት፣ ክፋት፣ ማታለል፣ መዳራት፣ ምቀኝነት፣ ስም ማጥፋት፣ ትእቢት፣ ስንፍና ይወጣሉ፡፡23እነዚህ ክፉ ነገሮች ሁሉ ከውስጥ ይወጣሉ፡ ሰውንም ያረክሱታል፡፡24ከዚያም ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ሲዶና አካባቢ ሄደ፡፡ ያለበትን ማንም እንዳያውቅም ወደ አንድ ቤት ገባ ፤ሆኖም ሊደበቅ አልቻለም፡፡25ወዲያውኑም ስለ እርሱ የሰማችና ትንሽ ልጅዋ በእርኩስ መንፈስ የተያዘችባት አንዲት ሴት ወደ እርሱ መጥታ በእግሩ ሥር ተደፋች፡፡26ሴቲቱ ዝርያዋ ከሲሮፊኒቃዊት ወገን የሆነ ግሪካዊት ነበረች፡፡ እርስዋም ኢየሱስ በልጅዋ ውስጥ ያለውን ጋኔን እንዲያወጣላት ለመነቸው፡፡27እርሱም «በመጀመሪያ ልጆች ይጥገቡ፤ የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለውሾች መስጠት ተገቢ አይደለምና» አላት፡፡28እርስዋ ግን «አዎን ጌታ ሆይ፤ ውሾችም እኮ ከገበታ ሥር የሚወዳድቀውን የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ፡፡» ብላ መለሰችለት፡፡29ኢየሱስም ፣ እንዲህ በማለትሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቷል አላት፡፡30ወደ ቤትዋም ሄደች፤ልጅዋም አጋንንቱ ለቅቋት ዐልጋው ላይ ተኝታ አገኘቻት፡፡31ደግሞም ከጢሮስ አካባቢ ተነሥቶ በሲዶና በኩል አድርጎ በዐሥሩ ከተሞች ዐልፎ ወደ ገሊላ ባሕር መጣ፡፡32እጁን እንዲጭንበትና እንዲፈውሰው አንድ መስማት የተሳነውና ኮልታፋ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡33እርሱም ከሕዝቡ ለይቶ ወደ ገለልተኛ ስፍራ ወሰደው፤ጣቶቹን በጆሮዎቹ ውስጥ አስገብቶ እንትፍ አለበት፤ምላሱንም ነካው፡፡34ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ተመለከተና በረጅሙ ተንፍሶ «ኤፍታህ» አለው፡፡ ይህም ተከፈት ማለት ነው፡፡35ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤ የታሰረውም ምላሱ ተፈታ፡፡ ጥርት አድርጎም ተናገረ፡፡36ኢየሱስም ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤ ሆኖም አጥብቆ ባዘዛቸው መጠን አብልጠው አሰራጩት ፡፡37እነርሱም ከልክ በላይ ተደንቀው ፣ ሁሉንም ነገር ደኅና አድርጓል፤እርሱ መስማት የተሣነው እንዲሰማ ኮልታፋውም እንኳ እንዲናገር ያደርጋል አሉ፡፡
1በእነዚያ ቀናት እንደገና ብዙ ህዝብ በተሰበሰበና የሚበሉት ባጡ ጊዜ2ኢየሱስም ደቀመዛሙርቱን ወደእርሱ ጠርቶ ህዝቡ ከኔ ጋር ሶስት ቀናት ቆይተዋል የሚበሉትም የላቸውምና እራራላቸዋለሁ3ሳይበሉ ብሰዳቸውም በመንገድ ላይ ይደክማሉ አንዳንዶቹም ከሩቅ ሥፍራ ነው የመጡት አላቸው፡፡4ደቀመዛሙርቱም በዚህ ምድረበዳ እነዚህን ሁሉ የሚያጠግብ እንጀራ እንዴት ይገኛል ብለው መለሱለት፡፡5ስንት እንጀራ አላችሁ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ሰባት አሉት ፤6ህዘቡን በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ ሰባቱንም እንጀራ ተቀብሎ እግዚአብሔርን ካመሰገነ በኋላ ቆርሶ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው እነርሱም ለህዝቡ አቀረቡላቸው፡፤7ጥቂትም ትናንሽ አሦች ነበሯቸው ባርኮም ያንንም አንዲያቀርቡላቸው አዘዘ፡፡8ሕዝቡም በልተውም ጠገቡ፡ ደቀመዛሙርቱም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰባት ታላላቅ መሶብ አነሱ፡፡9የህዝቡም ቁጥር ቁጥራቸውም አራት ሺ ያህል ነበር፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ህዝቡን አሰናበታቸው ፡፡10ወዲያውም ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ጀልባ ገብተው ወደ ዳልማኑታ አውራጃ አካባቢ ሄዱ፡፡11ፈሪሳውያንም ወደ ኢየሱስ እርሱ መጥተው ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ምልክትን እንዲያሳያቸው በመፈለግ ሊፈትኑት ይጠይቁት ጀምር፡፡12ኢየሱስም እርሱም በመንፈሱ እጅግ ተበሳጭቶ በዚህ ዘመን ያለ ህዝብ ለምን ምልክት ይፈልጋል እዉነት እላችኋለሁ እናንተ ሰዎች አይሰጣችሁም አላቸው፡፡13ትቶአቸው እንደገና ወደ ጀልባ ገብቶ ወደ ባህሩ ማዶ ተሻገረ፡፡14ደቀመዛሙርቱም እንጀራ መያዝን ረሱ፡፡15በጀልባ ውስጥም ከአንድ እንጀራ በቀር ምንም አልያዙም ነበር።16ኢየሱስ ከፈሪሳዊያንና ከንጉሥ ሄሮድስ እርሾ ተጠንቀቁ ብሎ አሳሰባቸው፡፡ እንጀራ ስላልያዝን ነው ብለው እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ ፡፡17ኢየሱስም ይህን አውቆ እንጀራ ስለሌላችሁ ለምን ትነጋገራላችሁ፡፡ እስከአሁን አልገባችሁምን ወይም እስከአሁን አታስተውሉምን ልባችሁ ደንዝዞአልን18አይን እያላችሁ አታዩምን ጆሮ እያላችሁ አትሰሙምን አታስታውሱምን19አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺ ባካፈልኩ ጊዜ ስንት መሶብ ቁርስራሽ ሰበሰባችሁ ብሎ ጠየቃቸው እነርሱም አሥራ ሁለት ብለው መለሱለት፡፡20ሰባቱን ለአራት ሺ ባካፈልኩ ጊዜስ ስንት ቅርጫት ቁርስራሽ አነሳችሁ አላቸው ሰባት አሉት ፡፡21ገና አታስተውሉምን አላቸው፡፡22ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም አይነ ስውር የሆነን ሰው ወደ እርሱ አምጥተው እንዲዳስሰው ለመኑት፡፡23የአይነስውሩንም ሰው እጅ ይዞ ከመንደሩ ውጭ ወሰደው፡፡ በአይኖቹም ላይ እንትፍ ብሎና እጁን ጭኖ አሁን ይታይሀልን ብሎ ጠየቀው፡፡24ቀና ብሎ ተመለከተና ሰዎች ሲራመዱ እንደዛፍ ሆነው ይታየኛል አለው፡፡25እንደገናም እጁን በአይኑ ላይ በጫነበት ጊዜ በሚገባ ተመለከተ የአይኑም ብርሀን ተመለሰለት ሁሉንም ነገር አጥርቶ አየ፡፡26ኢየሱስም ወደ መንደሩ እንኳ እንዳትገባ ብሎ ወደ ቤቱ አሰናበተው፡፡27ኢየሱስም ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ፊሊጶስፕ ቂሳሪያ ዙሪያ ወዳሉ መንደርሮች ሄዱ፡ በመንገድም ላይ ሳሉ ሰዎች እኔን ማነው ይላሉ ብሎ ጠየቃቸው28እነርሱም መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ አንዳንች ግን ከነቢያት አንዱ ብለው መለሱለት፡፡29እንደገናም እናንተስ እኔ ማን እንደሆንኩ ትላለችሁ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ጴጥሮስም አንተ መሲሁ ነህ በማለት መለሰለት፡፡30ስለእርሱ ለማንም እንዳይናገሩ አስጠነቀቃቸው፡፡31የሰው ልጅ ብዙ መከራ እንደሚቀበል በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጻፎች እንደሚነቀፍና እንደሚገደል በሦስተኛውም ቀን እንደገና እንደሚነሳ እንዳለው ያስተምራቸው ጀመር፡፡32ይህንንም በግልጽ ተናገረ፡፡ ጴጥሮስም ወስዶ ሊገስጸው ጀመረ፡፡33ኢየሱስም ዞር ብሎ ደቀመዛሙርቱን አየና ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና ብሎ ጴጥሮስን ገሰጸው፡፡34ህዘቡንና ደቀመዛሙርቱንም ወደ እርሱ ጠርቶ ሊከተለኝ የሚወድ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፡፡35ህይወቱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠጣፋታልና ነፍሱን ግን ስለኔ ወይም ስለወንጌል የሚያጣ ያገኛታልና፡፡36ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል፡፡37ወይስ ሰው ስለነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል፡፡38በዚህ አመንዝራ ኃጢአተኛ ህዝብ ፊት በእኔና በቃሌ የሚያፍርብኝ ማንም ቢኖር የሰው ልጅም ከቅዱሳን መላዕክቱ ጋር በአባቱ ክብር በሚመጣበት ጊዜ ያፍርበታል፡፡
1ኢየሱስም እውነት እላችኋለሁ፣ በዚህ ከቆሙት አንዳንዶቹ የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል መምጣቷን ሳያዩ የማይሞቱ አሉ አላቸው፡፡2ከስድስት ቀን በኋላም ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ለብቻቸው ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ላይ አመጣቸው፡፡3በፊታቸውም ተለወጠባቸው፤ ልብሱም አጣቢ በምድር ላይ ሊያነጻው እስከማይችል ድረስ ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ፡፡4ሙሴና ኤልያስ ታዩአቸው፤ ከኢየሱስ ጋርም ይነጋገሩ ነበር፡፡5ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ረቡኒ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴና አንድ ለኤልያስ ሦስት ዳሶችን እንሥራ አለው፡፡6እጅግ ፈርተው ስለነበረ የሚመልሰውን አያውቅም ነበር፡፡7ከዚያም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ፡፡8ድንገት ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከኢየሱስ በቀር ከእነርሱ ጋር ሌላ ማንንም አላዩም፡፡9ከተራራው ሲወርዱ ሳሉም ይህንን ያዩትን ነገር ሁሉ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሳ ድረስ ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፡፡10እነርሱም ቃሉን ይዘው ከሙታን መነሳት ማለት ምን ማለት ነው ተባባሉ፡፡11እነርሱም ጸሐፍት አስቀድሞ ኤልያስ መምጣት አለበት የሚሉት ለምንድነው ብለው ጠየቁት፡፡12ኢየሱስም ኤልያስማ በርግጥ አስቀድሞ ይመጣል፤ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል፡፡ ስለ ሰው ልጅ ብዙ መከራ እንዲቀበልና እንዲጣል የተጻፈው ታዲያ እንዴት ይሆናል?13እኔ ግን እላችኋለሁ! ኤልያስ መጥቷል፤ ስለ እርሱም አንደተጻፈው የወደዱትን አደረጉበት፡፡14ወደ ደቀመዛሙርቱ በመጡ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ከበዋቸው ጸሓፍትም ሲጠይቋቸው ተመለከቱ፡፡15ወዲያው ሕዝቡ ሁሉ ኢየሱስን ባዩት ጊዜ እጅግ ተገርመው ወደ እርሱ በመሮጥ ሰላምታ ሰጡት፡፡16እርሱም ስለምንድነው የምትጠይቋቸው? ብሎ ጠየቃቸው፡፡17ከሕዝቡም መሐል አንዱ መምህር ሆይ! ዲዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወዳንተ አመጣሁት፡፡18በሚወስደው ቦታ ሁሉ ይጥለውና አረፋ ያስደፍቀዋል፣ ጥርሱን ያንቀጫቅጭና ያደርቀዋል፡፡ እንዲያወጡት ደቀመዛሙርትህን ጠየቅኳቸው፣ እነርሱም አልቻሉም፡፡19ኢየሱስም መልሶ እናንተ የማታምኑ ትውልዶች እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሳችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት አላቸው፡፡20ወደ እርሱም አመጡለት፤ ባየውም ጊዜ ወዲያው መንፈሱ በምድር ላይ በኃይል ጥሎ እያንፈራገጠ አረፋ አስደፈቀው፡፡21ኢየሱስም የልጁን አባት ይህ ከያዘው ምን ያህል ጊዜ ሆነው? ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም ከሕጻንነቱ ጀምሮ ነው፡፡22ብዙ ጊዜ ሊያጠፋው በውሃና በእሳት ላይ ይጥለዋል፤ የሚቻልህ ከሆነ እዘንልንና እርዳን አለው፡፡23ኢየሱስም የሚቻልህ ከሆነ አልክን ለሚያምን ሁሉም ነገር ይቻላል አለው፡፡24ወዲያው የልጁ አባት ጮኸና አምናለሁ፣ እንዳምንም እርዳኝ አለው፡፡25ኢየሱስ ሕዝቡ እየሮጠ ሲመጣ ተመልክቶ እርኩሱን መንፈስ አንተ ዲዳ ደንቆሮም መንፈስ ከእርሱ እንድትወጣ ተመልሰህም እንዳትገባበት አዝሃለሁ ብሎ ገሰጸው፡፡26መንፈሱም ካንፈራገጠው በኋላ ጮኾ ወጣ፡፡ ብዙዎች ሞተ እስኪሉ ድረስም እንደ ሞተ ሰው ሆነ፡፡27ኢየሱስ ግን እጁን ይዞ አስነሳው፤ እርሱም ተነሣ፡፡28ወደ ቤት በገቡ ጊዜም ደቀመዛሙርቱ እኛ ልናስወጣው ያልቻልነው ለምንድነው? ብለው ለብቻው ጠየቁት፡፡29ኢየሱስም እንዲህ ዓይነቱ ወገን በጸሎት ካልሆነ በስተቀር አይወጣም አላቸው፡፡30ከዚያም ወጥተው በገሊላ በኩል አለፉ፤ በዚያ መሆኑን ማንም እንዲያውቅ አይፈልግም ነበር፡፡31ደቀመዛሙርቱንም እንዲህ ሲል አስተማራቸው፤ የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ታልፎ ይሰጣል፣ ይገድሉታልም፣ ከተገደለ ከሶስት ቀን በኋላም ይነሣል አላቸው፡፡32ነገር ግን የተናገራቸውን አላስተዋሉም፤ እንዳይጠይቁትም ፈርተው ነበር፡፡33ወደ ቅፍርናሆም መጡ፤ በቤት ሳሉም መንገድ ላይ ስለምን ጉዳይ ነበር የምትነጋገሩት ብሎ ደቀመዛሙርቱን ጠየቃቸው፡፡34ከእነርሱ ማን ይበልጥ እንደሆነ ተከራክረው ነበርና ዝም አሉ፡፡35ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠራቸው፣ እንዲህም አላቸው፣ ከእናንተ የመጀመሪያ ሊሆን የሚወድ የሁሉ መጨረሻና አገልጋይ ይሁን፤36ትንሽ ልጅ በመካከላቸው አቁሞና አቅፎት እንዲህ አላቸው፤37ማንም እንደዚህ ካሉት ታናናሽ ልጆች አንዱን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፣ እኔንም የሚቀበል የሚቀበለው የላከኝን ነው እንጂ እኔን አይደለም፡፡38ዮሐንስም መምህር ሆይ! አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያስወጣ አየነው፤ ስለማይከተለንም ከለከልነው አለው፡፡39ኢየሱስ ግን በስሜ ተአምራትን አድርጎ ፈጥኖ በእኔ ላይ ክፉ ሊናገር የሚችል የለምና አትከልክሉት፤40የማይቃወመን ሁሉ ከእኛ ጋር ነው አለው፡፡41እውነት እላችኋለሁ የክርስቶስ በመሆናችሁ ምክንያት አንድ ብርጭቆ ውሃ እንድትጠጡ የሚሰጣችሁ ዋጋውን አያጣም፡፡42በእኔ ከሚያምኑ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከእምነቱ የሚያስት ሰው ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታሥሮ በጥልቅ ባህር ላይ ቢጣል ይሻለው ነበር፡፡43እጅህ ለመሰናከልህ ምክንያት የምትሆን ከሆነ ቆርጠህ ጣላት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ እሳቱ ወደማይጠፋበት ወደ ሲዖል ከምትሔድ አካልህ ጎሎ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃልና፡፡4445እግርህ ለመሰናከልህ ምክንያት የሚሆን ከሆነ ቆርጠህ ጣለው፤ ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ሲዖል ወደ እሳቱ ከምትጣል አንድ እግር ኖሮህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃል፡፡4647ዐይንህ ለመሰናከልህ ምክንያት የምትሆን ከሆነ አውጥተህ ጣላት፤48ሁለት ዐይን ኖሮህ ትሉ ወደማይሞትበት፣ እሳቱ ወደማይጠፋበት ከምትገባ አንድ ዐይና ሆነህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ብትገባ ይሻልሃል፡፡49እያንዳንዱ ሰው በእሳት ይቀመማል፡፡50ጨው መልካም ነው፤ የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ግን ምን ታደርጉታላችሁ? በእያንዳንዳችሁ ሕይወት የጨውነት ጣዕም ይኑርባችሁ! እርስ በርሳችሁም በሰላም ኑሩ፡፡
1ኢየሱስም ከዚያ ተነስቶ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወደ ይሁዳ አውራጃዎች መጣ፡፡ ብዙ ህዝብም በአንድ ላይ ሆነው እንደገና ወደ እርሱ መጡ፡፡ እንደልማዱም ያስተምራቸው ጀመር፡፡2ፊሪሳውያንም ወደ ኢየሱስ መጥተው ሊፈትኑት አንድ ሰው ሚስቱን መፍታት ተፈቅዶለታል ሲሉ ጠየቁት፡፡3እርሱም መልሶ ሙሴ ምን ብሎ አዘዛችሁ አላቸው፡፡4እነርሱም የፍቺውን ጽፈት ሰጥቶ ይፍታት ብሎ ደንግጓል አሉት፡፡5ኢየሱስ ግን ሙሴ ስለልባችሁ ድንዛዜ ይህን ትዕዛዝ ሰጣችሁ እንጂ6ከፍጥረት መጀመሪያ ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡፡7በዚህም ምክንያት ሰው እናቱንና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል8ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ ስለዚህም አንድ ሥጋ እንጂ ከእንግዲህ ሁለት አይደሉም9እንግዲህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው አላቸው፡፡10በቤትም ሳሉ ደቀመዛሙርቱ ስለጉዳዩ እንደገና ጠየቁት፡፡11ኢየሱስም ማንም ሚስቱን ፈቶ ሌላይቱን ቢያገባ በሚስቱ ላይ ያመነዝራል፡፡12እንዲሁም እርሷም ራሷ ባሉዋን ትታ ሌላ ሰው ካገባች ታመነዝራለች አላቸው ፡፡13ህዝቡም እንዲዳስሳቸው ህጻናትን ወደ ኢየሱስ ያመጡ ነበር፡፡ ደቀመዛሙርትም ገሰጹዋቸው፡፡14ኢየሱስ ግን ባየ ጊዜ በቁጣ ተሞልቶ ህጻናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተው አትከልክሏቸው፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና አላቸው፡፡15እውነት እላችኋለሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ህጻን ሆኖ የማይቀበላት ሊገባባት አይችልም፡፡16ህጻናቱንም አቅፎ እጁን ጭኖ ባረካቸው፡፡17በመንገድም ሳሉ አንድ ሰው ወደእርሱ ሮጠና በፊቱ ተንበርክኮ ቸር መመህር ሆይ የዘላለምን ህይወት እንድወርስ ምን ማድረግ ይገባኛል? ብሎ ጠየቀው ፡፡18ኢየሱስም ለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር የለም አለው፡፡19ትዕዘዛትን ታወቃለህ አትግደል አትስረቅ አታመንዘር በሀሰት አትመስክር አታታልል አባትህንና እናትህን አክብር አለው፡፡20እርሱም መምህር ሆይ እነኚህን ሁሉ ከልጅነቴ ጀምሮ ጠብቄአለሁ አለው፡፡21ኢየሱስም አይቶ ወደደውና አንዲት ነገር ቀርታሀለች ሂድ ያለህን ሁሉ ሽጥና ለድሆች ስጥ መዝገብም በሰማይ ይቆይሀል መጥተህም ተከተለኝ አለው፡፡22እርሱም ብዙ ሀብት ነበረውና በሰማው ነገር ፊቱ ተቁሮ እያዘነ ሄደ፡፡23ኢየሱስም ዙሪያውን ተመለከተና ደቀመዛሙርቱን ለሀብታሞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው አላቸው፡፡24ደቀመዛሙርቱም በንግግሩ እጅግ ተገረሙ፡፡ ኢየሱስ እርሱ ግን መልሶ ልጆች ሆይ በሀብታቸው ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ከባድ ነው አላቸው፡፡25ሀብታም ሰው ወደ መንግስተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል አላቸው፡፡26ደቀመዛሙርቱም እጅግ ተገርመው እንግዲያውስ ማን ሊድን ይችላል አሉት፡፡27ኢየሱስም ወደ እነርሱ ተመከተና ለሰዎች ይህ አይቻልም ነገር ግን ለእግዚአብሔር ይቻላል ለእግዚአብሔር ሁሉ ይቻላልና አላቸው፡፡28ጴጥሮስም ጌታ ሆይ እኛ ሀሉን ትተን ተከልንህ ይለው ጀመር፡፡29ኢየሱስም እውነት እላችኋለሁ ስለኔና ስለ ወንጌል ቤቱን ወንዱሞቹን ወይም እህቶቹንወይም እናቱን ወይም አባቱን ወይም ልጆቹን ወይም መሬቱን የሚተው30በዚህ ዓለም መቶ እጥፍ ቤቶችን ወንድሞችን እህቶችን እናቶችን ልጆችንና መሬት ከስደት ጋር በሚመጣውም አለም የዘላለምን ህይወት የማይቀበል የለም31ነገር ግን ብዙዎች ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ አላቸው፡፡32ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ሳለ ኢየሱስ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፡፡ እጅግም ተገርመው ነበር የሚከተሉትም በጣም ፈርተው ነበር፡፡ አስራሁለቱን እንደገና ወስዶ ሊደርስበት ያለውን ነገር ይነግራቸው ጀመር፡፡33እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንሄዳለን የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል እነርሱም ሞትን ይፈርዱበታል ለአህዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፡፡34አህዛብም/ፈሪሳዊያን ይቀልዱበታል ይተፉበታል ይገርፉታል ይገድሉታልም ከሶስት ቀን በኋላም ይነሳል እያለ ይነግራቸው ጀመር፡፡35የዘብድዮስ ልጆች ያዕቆብና ዮሀንስ ወደ ኢየሱስ ቀርበው መምህር ሆይ የምንጠይቅህን ሁሉ እንድታደርግልን እንለምንሀለን አሉት፡፡36እርሱም ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋለችሁ አላቸው፡፡37እነርሱም በክብርህ በምትሆንበት ጊዜ አንዳችን በቀኝህ አንዳችን በግራህ እንድንቀመጥ ፍቀድ አሉት፡፡38ኢየሱስ ግን የምትለምኑትን አታውቁም እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ እኔ የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን አላቸው፡፤39እነርሱም እንችላለን አሉት፡፡ ኢየሱስም እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ እኔ የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ40ነገር ግን በግራዬና በቀኜ መሆን ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምሰጠው አይደለም አላቸው፡፡41አሥሩ ደቀማዘሙርትም ይህን በሰሙ ጊዜ በያዕቆብና በዮሀንስ ላይ ተቆጡ፡፡42ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ የአህዛብ አለቆች በሚመሩዋቸው ላይ እንደሚሠለጥኑባቸው ታላላቆቻቸውም እንደሚገዙዋቸው ታውቃላችሁ፡፡43በእናንተ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም ነገር ግን ከእናንተ ማንም የበላይ(ታላቅ) ለመሆን የሚፈልግ የሁሉ አገልጋይ ይሁን44ፊተኛ ለመሆን የሚፈልግም የሁሉ ባሪያ ይሁን45የሰው ልጅም ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊያደርግ እንጂ እንዲያገልግሉት አልመጣም አላቸው፡፡46ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱም ወደ ኢያሪኮ መጡ፡፡ ከደቀመዛሙርቱና ከብዙ ህዝብ ጋር ከኢያሪኮ በመውጣት ላይ ሳለ የጤሚዮስ ልጅ ዓይነ ስወሩ ለማኝ በርጠሚዮስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር፡፡47የናዝሬቱ ኢየሱስ እያለፈ መሆኑን ሲሰማ የዳዊተ ልጅ ኢየሱስ ሆይ እራራልኝ እያለ ጮኸ፡፡48ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሰፁት፡፡ እርሱ ግን አብዝቶ የዳዊት ልጅ ሆይ እራራልኝ ብሎ ጮኸ፡፡49ኢየሱስም ቆመና ጥሩት አለ፡፡ እነርሱም አይዞህ መምህሩ ይጠራሀልና ተነሳ አሉት፡፡50በርጠሚዮስም ልብሱን ጥሎ እየዘለለ ወደ ኢየሱስ መጣ፡፡51ኢየሱስም ምን እንዳደርገልህ ትወዳለህ አለው፡፡ ዓይነ ስውሩም ሰው መምህር ሆይ ማየት እንድችል አለው፡፡52ኢየሱስም መንገድህን ሂድ እምነትህ አድኖሀል አለው፡፡ ወዲያውም አየ ኢየሱስንም ተከትሎ ሄደ፡፡
1ከደብረ ዘይት ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ሁለቱን ላካቸው፡፡2እንዲህም አላቸው፣ ፊት ለፊታችን ወዳለው መንደር ሂዱ፤ወዲያው እንደ ገባችሁም ማንም ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ ውርንጫ መንገድ ዳር ታስሮ ታገኛላችሁ፡፡ ፍቱትና አምጡልኝ፤3ማንም ለምን ይህን ታደርጋላችሁ ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፤ እርሱም ይለቅቀዋል አላቸው፡፡4እነርሱም ሄዱ፤ አንድ ውርንጫ ከቤት ውጭ በመንገድ ዳር ታስሮ አገኙ፤ ፈቱትም፡፡5በአካባቢው ከቆሙት አንዳንዶቹ ሰዎች ለምን ፈታችሁት? አሏቸው፡፡6እነርሱም ልክ ኢየሱስ እንዳላቸው ነገሯቸው፤ ለቀቋቸውም፡፡7ደቀመዛሙርቱም ውርንጫውን ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ ልብሳቸውንም አለበሱት፤ ኢየሱስም ተቀመጠበት፡፡8ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን ፣ሌሎችም ከየቦታው ቅርንጫፎችን ቆርጠው በሚሄድበት መንገድ ላይ አነጠፉ፡፡9ከፊት የቀደሙት ከኋላውም የተከተሉት ሆሳእና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤10የሚመጣው የአባታችን የንጉሥ ዳዊት መንግስት የተባረከ ነው፤ ሆሳእና በአርያም እያሉ ጮኹ፡፡11ኢየሩሳሌም እንደ ደረሰ ወደ ቤተመቅደስ ገባ፡፡ በአካባቢው ያለውን ሁሉ ተመለከተ፤መሽቶም ነበርና ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ሄደ፡፡12በማግስቱም ከቢታንያ እንደ ወጡ ተራበ፤13አንዲት ቅጠሏ ያቆጠቆጠ በለስ ከርቀት አየ፡፡ ምናልባት አንዳች አገኝባት ይሆናል በማለት ወደ እርሷ መጣ፡፡ ሲደርስ ግን በለስ የሚያፈራበት ጊዜ ስላልነበረ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም፡፡14ስለዚህም ማንም ሰው ለዘላለም ምንም ፍሬ አያግኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ ደቀመዛሙርቱም ሰሙት፡፡15ወደ ኢየሩሳሌምም እንደ መጡ ወደ ቤተመቅደስ ገባ፤ በዚያም የሚሸጡትንና የሚገዙትን አባረረ፤የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛ የርግብ ሻጮችንም መቀመጫቸውን ገለበጠባቸው፡፡16ማንም ሰው በቤተ መቅደስ ውስጥ ዕቃ ይዞ እንዳይመላለስ ከለከለ፡፡17አስተማራቸውም፤ ቤቴ የአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው፡፡18ሊቀ ካህናቱና ጸሓፍትም፣ይህን ሲናገር ሲሰሙ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ተደንቀው ስለ ተከተሉት ፈርተው ነበርና እንዴት እንደሚገድሉት ማሰብ ጀመሩ፡፡19ኢየሱስም በየምሽቱ ከከተማ ይወጣ ነበር፡፡20በማለዳ ሲያልፉም በለሲቱ ከሥሯ ደርቃ አገኟት፡፡21ጴጥሮስም አስታውሶ መምህር ሆይ! እነሆ፤የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው፡፡22ኢየሱስም እንዲህ አለው፡፡ በእግዚአብሔር እመን፤23እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም በልቡ ሳይጠራጠር ይህን ተራራ ከዚህ ተነቅለህ ወደ ባሕር ውስጥ ተወርወር ቢልና የተናገረው እንደሚፈጸም በልቡ ቢያምን ይሆንለታል፡፡24ስለዚህ እላችኋለሁ፤የጸለያችሁትንና የለመናችሁትን ነገር ሁሉ እንደምትቀበሉ ብታምኑ ይሆንላችሁማል፡፡25ለጸሎት ስትቆሙ፣ በማንም ላይ ቅርታ ቢኖራችሁ፣ የሰማዩ አባታችሁ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ ይቅር በሉ፡፡26እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ የቅር አይላችሁም፡፡27በድጋሚም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ኢየሱስ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባም ሊቀ ካህናት፣ጸሓፍትና ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሱስ መጥተው፣28እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ወይም እነዚህን ነገሮች እንድታደርግ ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው? አሉት፡፡29ኢየሱስም አንድ ጥያቄ ጠይቃችኋለሁ እናንተም መልሱልኝ፤ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ አላቸው፡፡30መልሱልኝ፤ የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነው? ወይስ ከሰው? አላቸው ፡፡31እነርሱም እርስ በርሳቸው ተመካከሩ፤ ከሰማይ ነው ብንል ታዲያ ለምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤32ነገር ግን ከሰው ነው ብንል ደግሞ ሰዉ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ ነው ብሎ አምኖበታል ብለው ሕዝቡን ፈሩ፡፡33ለኢየሱስም አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ ኢየሱስም እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው፡፡
1ኢየሱስም በምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፡፡ አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤በዙሪያው ዐጥር ሠራ፤ለወይን መጭመቂያ የሚሆን ጕድጓድ ቈፈረ፤ማማም ሠራ፡፡ ለገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ፡፡2በወቅቱ የወይኑን ፍሬ እንዲቀበል አንድ አገልጋይ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፡፡3እነርሱም አገልጋዩን ያዙት፤ ደብድበውም ባዶ እጁን ሰደዱት፡፡4በድጋሚም ሌላ አገልጋይ ላከ፤እነርሱም ፈነከቱት፤ አሳፈሩትም፡፡5ሌላም አገልጋይ ወደ እነርሱ ላከ፤ እርሱንም ገደሉት፡፡ ብዙዎች ሌሎችንም ላከ፤ አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ ሌሎቹንም ገደሉ፡፡6የወይኑ ተክል ባለቤት አንድ ተወዳጅ ልጅ ነበረው፤ልጄን ያከብሩታል በማለት በመጨረሻ እርሱን ላከው፡፡7ገበሬዎቹ ግን እርስበርሳቸው እንዲህ አሉ፡፡ ይህ ወራሹ ነው ኑ እንግደለው ሀብቱ ሁሉ የእኛ ይሆናል ተባባሉ፡፡8ልጁንም ያዙት፤ ገደሉት፤ከወይኑ ቦታ ውጭም ጣሉት፡፡9የወይኑ ተክል ባለቤት በዚህ ጊዜ ምን ያደርጋል? ይመጣና ገበሬዎቹን ያጠፋቸዋል፤የወይን ቦታውንም ለሌሎች ይሰጣቸዋል፡፡10ይህን የመጽሓፍ ቃል አላነበባችሁምን? እነሆ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ድንጋይ ሆነ፤11ይህ ከጌታ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፡፡12ኢየሱስ ምሳሌውን የተናገረው ስለ እነርሱ እንደ ሆነ ስለ ተገነዘቡ እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ፤ነገር ግን ሕዝቡን ስለ ፈሩ፤ትተውት ሄዱ፡፡13እነርሱም በንግግር እንዲያጠምዱት አንዳንድ ፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑ ሰዎችን ላኩ፡፡14ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፤መምህር ሆይ፣ አንተ እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንም በይሉኝታ እንደማታደርግ፣ለሰው ፊትም እንደማታዳላ ነገር ግን የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፡፡ ለቄሳር ግብር መክፈል ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም?15እንክፈል ወይስ አንክፈል? አሉት፡፡ ኢየሱስ ግን ግብዝነታቸውን ዐውቆ ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አላቸው፡፡ እንዳየው አንደ ዲናር አምጡልኝ አላቸው፡፡16እነርሱም አመጡለት፡፡ ኢየሱስም ይህ ምስል ቅርጹም የማን ነው? አላቸው፡፡ እነርሱም የቄሳር ነው አሉት፡፡17ኢየሱስም እንግዲህ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ አላቸው፡፡ እጅግም ተገረሙበት፡18ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ ብለው ጠየቁት፡፡19መምህር ሆይ፣ ሙሴ፣ አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ሚስቱን ትቶ ቢሞት፣ ወንድሙ እርስዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካለት ብሎ ጽፎልናል፡፡20ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው ሚስት አገባ፤ ዘር ሳይተካም ሞተ፡፡21ሁለተኛውም አገባት፤ እርሱም ዘር ሳይተካለት ሞተ፡፡ ሦስተኛውም እንዲሁ፡፡22ሰባቱም ለወንድማቸው ዘር አልተኩም፡፡ ከሁሉም በኋላ ሴቲቱም ደግሞ ሞተች፡፡23ታዲያ ይህች ሴት በትንሣኤ የየትኛው ሚስት ትሆናለች? አሉት፡፡ ሰባቱም አግብተዋት ነበርና፡፡24ኢየሱስም የምትስቱት መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታውቁ አይደለምን?25በትንሳኤ ጊዜ ሰዎች አያገቡም፤ አይጋቡም፤ ነገር ግን በሰማይ እንደ መላእክት ይሆናሉ እንጂ፡፡26ነገር ግን ሙታን እንደሚነሡ በሚነድደው ቁጥቋጦ ውስጥ እኔ የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያእቆብ አምላክ ነኝ ሲል እግዚአብሔር ለሙሴ የተናገረውን አላነበባችሁምን? እጅግ ትስታላችሁ፡፡27እርሱ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፡፡28ከጸሓፍት አንዱ መጣና በአንድነት ሆነው ሲጠይቁት እንዴት በጥሩ ሁኔታ እንደ መላሰላቸው አይቶ፣ ከሕግ ፊተኛው የትኛው ነው? ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው፡፡29ኢየሱስም ፊተኛው፣ እስራኤል ሆይ ስማ! አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤30አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ፣በፍጹም አሳብህ፣ በፍጹምም ኀይልህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡31ሁለተኛዋም ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡ ከእነዚህ የሚበልጥ ምንም ሌላ ትእዛዝ የለም አለው፡፡32ሰውዬውም መምህር ሆይ፣በእውነት መልካም ብለሃል፤ እርሱ አንድ ነው፤ከእርሱም በቀር ሌላ የለም፤ እርሱን በፍጹም ልብ፣ በፍጹም ማስተዋል፣33በፍጹም ኀይል መውደድና ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ ሁሉንም ዓይነት መስዋእትና የሚቃጠል መሥዋእት ከማቅረብ ይበልጣል አለ፡፡34ኢየሱስም ሰውዬው በማስተዋል እንደ መለሰለት ባየ ጊዜ አንተ ከእግዚአብሔር መንግስት የራቅህ አይደለህም አለው፡፡ ከዚያ በኋላ ማንም ሰው ምንም ጥያቄ ሊጠይቀው አልደፈረም፡፡35ኢየሱስም መለሰላቸው፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሲያስተምር፣ ጸሓፍት ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው የሚሉት እንዴት ነው? አለ፡፡36ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው፡፡37ዳዊት ራሱ ጌታዬ ብሎ ይጠራዋል፤ ታዲያ እንዴት ልጁ ይሆናል? ሕዝቡም በደስታ ይሰማው ነበር፡፡38ኢየሱስም እንዲህ አለ፡፡ ከጸሓፍት ተጠንቀቁ፤ የተንዘረፈፈ ልብስ ለብሰው መሄድን ይወድዳሉ፤ እነርሱ በገበያ ቦታ ሰላምታን፣39በምኩራብም የክብር ወንበር፣ በግብዣም የክብር ቦታ ላይ መቀመጥ ይወድዳሉ፡፡40ለይምሰል ጸሎት በማስረዘም የመበለቶችን ቤት ይበዘብዛሉ፡፡ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ፡፡41ኢየሱስም በመባ መቀበያው ፊት ለፊት ተቀመጠ፡፡ ብዙ ሰዎች በመባ መቀበያው ውስጥ ገንዘብ ሲጨምሩ ተመለከተ፡፡ ብዙ ሃብታሞች ብዙ ገንዘብ ይጨምሩ ነበር፡፡42ከዚያም አንዲት ድኻ መበለት መጥታ ሁለት ናስ ጨመረች፤ይህም የብር ሩብ ነው፡፡43እርሱም ደቀመዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ይህች መበለት በመባ መቀበያው ውስጥ ገንዘባቸውን ከጨመሩት ሁሉ አብልጣ ሰጠች፡፡44እነርሱ ከትርፋቸው ሰጥተዋልና፡፡ እርስዋ ግን ከጉድለቷ ሰጠች፤ ያላትን ሁሉ ሰጠች፤ ኑሮዋን እንኳ ሳይቀር ሁሉንም ሰጠች፡፡
1ኢየሱስ ከቤተመቅደስ ሲወጣ ሳለ ከደቀመዛሙርቱ አንዱ መምህር ሆይ፤ እንዴት ያሉ ድንጋዮችና እንዴት ያሉ ሕንጻዎቹ እንደሆኑ ተመልከት! አለው፡፡2እርሱም እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን? ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ እንደዚህ አይቀርም አለው፡፡3ኢየሱስ በደብረዘይት ተራራ ላይ በቤተመቅደሱ ትይዩ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና እንድርያስ4ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚፈጸሙበት ምልክቱስ ምንድነው? ብለው ለብቻው ጠየቁት፤5ኢየሱስም ማንም እንዳያስታችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ አላቸው፡፡6ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ! እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡7ጦርነትንና የጦርነትን ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትታወኩ፤ እነዚህ ነገሮች የግድ መፈጸም አለባቸው፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው፡፡8ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፡፡ በተለያዩ ቦታዎች የምድር መንቀጥቀጥ፣ ረሃብም ይሆናል፡፡ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡9እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ወደ ሸንጎዎቻቸው ያቀርቧችኋል፣ በምኩራቦች ውስጥ ትደበደባላችሁ፡፡ ለእነርሱ ምስክር እንዲሆን በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ፡፡10አስቀድሞ ወንጌል ለሕዝቦች ሁሉ ይሰበካል፡፡11ወደ ፍርድ በሚያቀርቧችሁና አሳልፈው በሚሰጧችሁ ጊዜ አስቀድማችሁ ምን እንደምትናገሩ አትጨነቁ፤ ነገር ግን በዚያች ሰዓት የምትናገሩት ይሰጣችኋልና፤ የሚናገረውም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁም፡፡12ወንድም ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፣ አባትም ልጁን፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን በመቃወም ተነስተው ይገድሏቸዋል፡፡13ስለስሜም በሰዎች ሁሉ ትጠላላችሁ፡፡ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የሚጸና እርሱ ይድናል፡፡14የጥፋትን እርኩሰት በማይገባው ቦታ ቆሙ ስታዩት (አንባቢው ያስተውል) በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤15በቤቱ ጣሪያ ላይ ያለም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይውረድ፣ ወደ ቤትም አይግባ፤16በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመልከት፡፡17ነገር ግን በእነዚያ ወራት ለእርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!18በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፡፡19እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያልሆነ ወደፊትም የማይሆን ታላቅ መከራ በእነዚያ ቀናት ይሆናልና፡፡20ጌታ ቀኖቹን ባያሳጥር ኖሮ ሥጋን የለበሰ ሁሉ አይድንም ነበር፡፡ ነገር ግን ስለመረጣቸው ስለ ምርጦቹ ሲል ቀኖቹን አሳጠረ፡፡21አንድ ሰው እነሆ ክርስቶስ በዚህ ነው ወይም እነሆ በዚያ ነው ቢላችሁ አትመኑት፡፡22ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነብያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸው የተመረጡትን ለማሳት ድንቆችንና ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡23ነገር ግን አስተውሉ፤ እነሆ አስቀድሜ ሁሉንም ነገር ነግሬአችኋለሁ፡፡24ከመከራው በኋላ በእነዚያ ቀናት ፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፣25ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፣ በሰማያት ውስጥ ያሉ ኃይላትም ይናወጣሉ፡፡26እነርሱም የሰው ልጅ በደመና ውስጥ በታላቅ ኃይልና ክብር ሲመጣ ያዩታል፡፡27ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ ለእርሱ የተመረጡትን ከአራቱም ነፋሳት በአንድ ላይ እንዲሰበስቡለት መላዕክትን ይልካቸዋል፡፡28ምሳሌውን ከበለስ ዛፍ ተማሩ፤ ቅርንጫፏ ሲለሰልስ፣ ቅጠሏም ሲያቆጠቁጥ ያን ጊዜ በጋ መቃረቡን ታውቃላችሁ፡፡29እናንተም ደግሞ እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ በምታዩበት ጊዜ የሰው ልጅ በበር ላይ መሆኑን ታውቃላችሁ፡፡30እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም፡፡31ሰማይና ምድር ያልፋል፣ ቃሌ ግን አያልፍም፡፡32ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት በስተቀር የሰማይ መላዕክትም ቢሆኑ፣ ልጅም ቢሆን ማንም አያውቅም፡፡33ጊዜው መቼ እንደሆነ አታውቁምና አስተውሉ፣ ንቁና ጸልዩ፡፡34ነገሩ ለአገልጋዮቹ ሥልጣን፣ ለእያንዳንዳቸውም የሥራ ድርሻ በመስጠት ዘበኛውም ደግሞ እንዲጠብቅ አዝዞት ቤቱን ትቶ ወደ ሩቅ ሀገር የሚሔድን ሰው ይመስላል፡፡3535የቤቱ ጌታ በምሽት፣ ወይም በእኩለ ሌሊት፣ ወይም ዶሮ ሲጮህ፣ ወይም ጠዋት ላይ ምን ጊዜ እንደሚመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ!36በድንገት ሲመጣ እንቅልፍ ላይ ሆናችሁ እንዳያገኛችሁ፡፡37ለእናንተ የምነግራችሁን ለሁሉም እናገራለሁ፣ንቁ!
1ከሁለት ቀን በኋላ የፋሲካና የቂጣ በዓል ነበር፡፡ የካህናት አለቆችና ጸሓፍት እንዴት አድርገው በተንኮል ይዘው ሊገድሉት እንደሚችሉ ያስቡ ነበር፡፡2ነገር ግን የህዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል ቀን አይሁን ተባብለው ነበር፡፡3እርሱም በቢታኒያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በማዕድ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ሽቱ የያዘ የአልባስጥሮስ ጠርሙስ ይዛ መጣች፡፡ ጠርሙሱንም ሰብራ ሽቱውን በኢየሱስ በራሱ ላይ አፈሰሰች ፡፡4ነገር ግን ከመካከላቸው አንዳንዶቹ እንዲህ ያለው የሽቱ ማባከን ያስፈለገው ለምንድነው በማለት የተበሳጩ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ5ይህ ቅባት ከሦስተ መቶ ሽልንግ በላይ ተሸጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበር እያሉ በእርሷ ላይ አጉረመረሙ፡፡6ኢየሱስ ግን ተዋት ለምን ታስቸግሯታላችሁ እርሷ መልካምን ነገር አድርጋልኛለች፡፡7ድሆች ሁሉጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው በፈለጋችሁም ጊዜ መልካም ልታድጉላቸው ትችላላችሁ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም፡፡8እርሷ ከመቃብር በፊት ሰውነቴን ሽቱ በመቀባት የምትችለውን አድርጋለች፡፡9ደግሞም እውነት እላችኋለሁ ይህ ወንጌል በዓለም ዙሪያ በሚሰበክበት ጊዜ ሁሉ ይህች ሴት ያደረገችው ነገር ለመታሰቢያዋ ይነገራል አላቸው፡፡10ከአስራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንዴት አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ ወደ ካህናት አለቆች ሄደ11እነርሱም በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው ገንዘብም ሊሰጡት ቃል ገቡለት፡፡እርሱም አሳልፎ ሊሰጠው አመቺ ጊዜ ይጠብቅ ነበር፡፡12የፋሲካን መስዋዕት በሚያቀርቡበት በቂጣ በዓል የመጀመሪው ቀን ደቀመዛሙርቱ ፋሲካን ትበላ ዘንድ የት እናዛገጅልህ ብለው ጠየቁት፡፡13እርሱም ከደቀመዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ ወደ ከተማ ሂዱ ወዲያውም አንድ ሰው ውሃ ተሸክሞ ታገኛላችሁ ተከትላችሁትም ሂዱና14ወደሚገባበት ቤት ገብታችሁ የቤቱን ባለቤት መምህሩ ከደቀመዛሙርቴ ጋር ፋሲካን እበላ ዘንድ የእንግዳ ክፍሌ የትኛው ነው ብሎሀል ብላችሁ ጠይቁት15እርሱ ራሱ በሰገነት ላይ ያለ በቤት ዕቃ የተደራጀና የተዘጋጀ ሰፊ አዳራሽ ያሳያችኋል በዚያም አዘጋጁልን ፡፡16ደቀመዛሙርቱም ወጥተው ወደ ከተማ መጡ ልክ እንዳላቸውም አገኙ ፋሲካንም አዘጋጁ፡፡17በመሸም ጊዜ ከአስራ ሁለቱ ጋር መጣ፡፡18ተቀምጠውም በመመገብ ላይ ኢየሱስ አውነት እላችኋለሁ በማዕድ ከኔ ጋር ያለ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል አላቸው፡፡19እነርሱም እጅግ አዝነው በየተራ እኔ እሆንን ይሉት ጀምር፡፡20ኢየሱስም ከእኔ ጋር ወደ ወጥ ሳህኑ የሚነክረውና ከአስራሁለቱ አንዱ ነው አላቸው፡፡21የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደተጻፈው ይሄዳል የሰው ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት ባይወለድ ይሻለው ነበር አላቸው፡፡22እየተመገቡም ሳለ እንጀራን አንስቶ ከባረከ በኋላ ቆርሶ ሰጣቸውና ውሰዱና ብሉ ይህ ስጋዬ ነው አላቸው፡፡23እንዲሁም ጽዋውን አንስቶ አመስግኖ ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው ሁሉም ጠጡ፡፡24እርሱም ይህ ለብዙዎች የሚፈስ የቃል ኪዳን ደሜ ነው ፡፡25እውነት እላችኋለሁ በእግዚአብሔር መንግስት እንደገና እንደ አዲስ እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከዚህ ወይን ከዚህ በኋላ አልጠጣም፡፡26መዝሙርም ከዘመሩም በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዱ፡፡27ኢየሱስም እረኛውን እመታለው በጎቹም ይበታተናሉ ተብሎ እንደተጻፈ ሁላችሁ ትሰናከላላችሁ28ከተነሳሁ በኋላ ግን ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው፡፡29ጴጥሮስም ሁሉ ቢሰናከሉ እኔ ግን አልሰናከልም አለው፡፡30ኢየሱስም አውነት እልሃለሁ ዛሬ ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው፡፡31እርሱ ግን እጅግ እየጮኸ እስከሞት እንኳ ቢሆን አልክድህም አለው፡፡ ሌሎቹም እንደዚያው አሉ፡፡32ጌቴ ሴማኒ ወደሚባል ሥፍራም መጡ፡፡ ደቀመዛሙርቱንም እስክ ጸልይ ድረስ በዚህ ተቀመጡ አላቸው፡፡33ኢየሱስም ጴጥሮስን ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ሄደ እጅግ ሊያዝንና ሊተክዝ ጀመረ፡፡34ነፍሴ እስከሞት ድረስ እጅግ አዝናለች በዚህ ሆናችሁ ትጉ ንቁም አላቸው፡፡35ጥቂትም ፈቀቅ ብሎ ሄደ፤ በግንባሩም ተደፍቶ የሚቻል ከሆነ ይህች ሰዓት ሰዓቲቱ እንድታልፍ መጸለይ ጀመረ፡፡36አባት ሆይ ለአንተ ሁሉ ይቻላል ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ነገር ግን የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን አለ፡፡37ወደ እነርሱም መጣ ተኝተውም አገኛቸው ጴጥሮስንም ስምዖን ተኝተሀልን ለአንድ ሰዓት እንኳ ልትተጋ አልቻልክምን፡፡38ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፡፡ መንፈስ ዝግጁ ነው ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው፡፡39ተመልሶም ሄደና ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ፡፡40እንደገና ወደ ደቀመዛሙርቱ በመጣ ጊዜ አሁንም ተኝው አገኛቸው አይናቸው በእንቀልፍ ከብዶ ስለነበር የሚመልሱለትንም አያውቁም ነበር፡፡41ለሦስተኛም ጊዜ ወደ እነርሱ መጣና እንግዲህስ ይበቃል ተኙ እረፉም የሰው ልጅ ለኃጢአተኞች አልፎ ይሰጥ ዘንድ ሰዓቲቱ ደርሳለች ፡፡42ተነሱ እንሂድ እነሆ አሳልፎ የሚሰጠኝ በደጅ ነው አላቸው፡፡43ወዲያውም ገና በመናገር ላይ ሳለ ከአስራ ሁለቱ አንዱ የነበረው የአስቆሮቱ ይሁዳ መጣ ፡፡ ከእርሱም ጋር ከካህናት አለቆች፣ ከጸሓፍትና ከሽማግሌዎች ዘንድ የተላኩ ብዙ ህዝብ ሠይፍና ቆመጥ ይዘው መጡ፡፡44አሳልፎ የሚሰጠውም የምስመው እርሱ ነውና ያዙት በጥንቃቄ ውሰዱት ብሎ ምልክት ሰጥቷቸው ነበር፡፡45በመጣም ጊዜ በቀጥታ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ መምህር ሆይ ብሎ ሳመው፡፡46እነርሱም ይዘው ወሰዱት፡፡47ነገር ግን በዚያ ከቆሙት መካከል አንዱ ሰይፉን መዘዘ፤ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ጆሮም ቆረጠው፡፡48ኢየሱስም መልሶ ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን49በየዕለቱ በቤተ መቅደስ እያስተማርከ ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዘ አልያዛችሁኝም፡፡ ነገር ግን የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆኗል አላቸው፡፡50ሁሉም ትተውት ሸሹ፡፡51እርቃኑን ከበፍታ በተሰራ ጨርቅ የሸፈነ አንድ ወጣት ይከተለው ነበር ሊይዙትም ባሉ ጊዜ52የበፍታ ጨርቁን ነጠላውን ትቶ ራቁቱን አመለጠ፡፡53ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ይዘውት መጡ፡፡ የካህናት አለቆች፣ ሽማግሌዎችና ጸሓፍትም አብረውት መጡ፡፡54ጴጥሮስም እስከ ሊቀካህናቱ ግቢ ድረስ በሩቅ ሆኖ ይከተለው ነበር፡፡ ከዚያም ከጠበቃዊዎች ጋር እሳት እየሞቀ ተቀመጠ፡፡55ሊቀ ካህናቱና ጉባኤው ሁሉ በኢየሱስ ላይ ሞት የሚያስፈርድበት ምክንያት ይፈልጉ ነበር ነገር ግን ሊያገኙ አልቻሉም፡፡56ብዙዎች በሀሰት ቢመሰክሩበትም ምስክርነታቸው እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነበር፡፡57ሦስት ሰዎችም ተነስተው በሀሰት መሰከሩበት እንዲህም አሉ58ይህንን በእጅ የተሰራ ቤተመቅደስ በሶስት ቀን አፍርሼ እንደገና በሶስት ቀን ውስጥ በእጅ ያልተሰራ ሌላ ቤተመቅደስ እሰራለሁ ሲል ሰምተነዋል ፡፡59የእነርሱም ምስክርነት ቢሆን እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነበረ፡፡60ሊቀ ካህናቱም ተነስቶ በመካከል ቆመና ለሚመሰክሩብህ መልስ አትሰጥምን ብሎ ጠየቀው፡፡61ኢየሱስ ግን ዝም አለ መልስም አልሰጠም፡፡ ሊቀ ካህናቱም በድጋሚ የቡሩኩ ልጅ መሲሁ አንተ ነህን ብሎ ጠየቀው62ኢየሱሰም አዎ ነኝ የሰው ልጅ በኃይሉ ቀኝ ተቀምጦ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታዩታላችሁ አለው፡፡63ሊቀካህናቱም ልብሱን ቀደደና ከእንግዲህ ምን ሌላ ምስክር ያስፈልጋል64እግዚአብሔርን ሲሳደብ ሰምታችኋል ታዲያ ምን ታስባለችሁ ፡፡ ሁሉም ሞት ይገባዋል አሉ፡፡65አንዳነዶቹም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ትንቢት ተናገር እያሉ ያሾፉበት ጀመር፡፡ መኮንኖችም በእጃቸው እየጎሰሙ ወሰዱት፡፡66ጴጥሮስም በሊቀ ካህናቱ ግቢ እሳት በመሞቅ ላይ ሳለ67አንዲት የሊቀ ክህናቱ የቤት ውስጥ ሠራተኛ አየችውና አንተ በትክክል ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበርክ አለችው፡፡68እርሱ ግን የምትይውን አላውቀውም ምን እንደምታወሪም አልገባኝም ብሎ ካደ፡፡ ወደ ዋናው በር መግቢያ በሄደ ጊዜ ዶሮ ጮኸ69ሠራተኛይቱም አይታው በዚያ ላሉት ወታደሮች ይህ ከእነርሱ አንዱ ነው አለቻቸው፡፡70እርሱ ግን እንደገና ካደ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በዚያ ከቆሙት መካከል አንዳንዶቹ ጴጥሮስን አንተ የገሊላ ሰው ስለሆንክ በትክክል ከእነርሱ አንዱ ነህ አሉት፡፡71እርሱም የምትሉትን ሰው አላውቀውም ብሎ መማልና መራገም ጀመረ፡፡72ወዲያውም ለሁለተኛ ጊዜ ዶሮ ጮኸ ጴጥሮስም ኢየሱስ ዛሬ ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለውን ቃል አስታወሰ ነገሩንም ባሰበ ጊዜ አለቀሰ፡፡
1ወዲያውኑም በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፣ ከጸሓፍት፣ ከሸንጎም አባሎችም ሁሉ ጋር ተማከሩ፤ ኢየሱስን አስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።2ጲላጦስም፣አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም ሲመልስ አንተ እንዳልከው ነኝ አለው።3የካህናት አለቆችም ብዙ ክስ አቀረቡበት።4ጲላጦስም ስንት ክስ እንዳቀረቡብህ ተመልከት! ምንም አትመልስምን? ብሎ እንደገና ጠየቀው።5ኢየሱስ ግን ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም መልስ አልሰጠም።6በየበዓሉ ሕዝቡ ጲላጦስ እንዲፈታላቸው የጠየቁትን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው።7በዚያም ኹከት ቀስቅሰው ግድያ ከፈጸሙ ሰዎች ጋር የታሰረ አንድ በርባን የሚባል ሰው ነበር።8ሕዝቡም ወደ ጲላጦስ ቀርበው የተለመደውን እንዲያደርግላቸው ጠየቁት።9ጲላጦስም "የአይሁድን ንጉሥ" እንድፈታላችሁ ትፈልጋላቸሁን? አላቸው።10እንዲህ ያለው የካህናት አለቆች ኢየሱስን አሳልፈው የሰጡት በቅናት መሆኑን ያውቅ ስለ ነበር ነው።11የካህናት አለቆች ግን በእርሱ ፈንታ በርባን እንዲፈታላቸው ጲላጦስን እንዲጠይቁ ሕዝቡን ቀሰቀሱ።12ጲላጦስም መልሶ ታዲያ በዚህ የአይሁድ ንጉሥ ብላችሁ በምትጠሩት ሰው ላይ ምን ላድርግበት? አላቸው።13እነርሱም "ስቀለው!" እያሉ እንደገና ጮኹ።14ጲላጦስም "ለምን? ምን በደል ፈጽሟል?" አላቸው። እነርሱም "ስቀለው!" እያሉ አብዝተው ጮኹ።15ጲላጦስም ሰዎቹን ደስ ለማሰኘት ብሎ በርባንን ፈቶ ለቀቀላቸው፤ኢየሱስን ግን አስገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።16ወታደሮቹም ኢየሱስን ፕራይቶሪዮን ወደሚባለው ግቢ ወሰዱት፤ወታደሮቹንም ሁሉ ጠሩ፤17ሐምራዊ ልብስ አለበሱት፤ የእሾኽ አክሊልም በራሱ ላይ ደፉበት፡፡18"የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን!" እያሉ ሰላምታ ይሰጡት ነበር።19በመቃ ዐናቱን እየመቱ፤ ምራቃቸውን ተፉበት፤ በፊቱም ተንበርክከው ሰገዱለት።20አላግጠውበትም ሐምራዊውን ልብስ አወለቁበት፤ የራሱንም ልብስ አልብሰው፤ሊሰቅሉ ወሰዱት።21በመንገድ ሳሉም የቀሬና ሰው የሆነውን የእስክንድርንና የሩፎስን አባት ስምዖንን ከገጠር ሲመጣ አግኝተው፤ የኢየሱስን መስቀል ተሸክሞ ከእነርሱ ጋር እንዲሄድ አስገደዱት።22ከዚያም በኋላ ኢየሱስን ጎልጎታ ተብሎ ወደሚጠራው ቦታ ወሰዱት፤ ትርጉሙም፡- "የራስ ቅል ስፍራ" ማለት ነው።23ከከርቤ ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅም ሰጡት፤ እርሱ ግን አልጠጣውም።24ከዚያም ሰቀሉት፤ ልብሶቹንም ማን ምን እንደሚወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተከፋፈሉ።25ከጧቱ ሦስት ሰዓት ሲሆን ሰቀሉት፡፡26"የአይሁድ ንጉሥ" የሚል የክስ ጽሑፍ በመስቀሉ ዐናት ተጽፎ ነበር።27ከኢየሱስም ጋር ሁለት ወንበዴዎችን አንዱን በቀኙ፣አንዱንም በግራው ሰቀሉ።28መጽሓፍ "ከዐመፀኞች ጋር ተቈጠረ፤" የሚለው ቃል ተፈጸመ።29በአጠገቡ ያልፉ የነበሩትም ሰዎች ራሳቸውን በንቀት እየነቀነቁ እንዲህ በማለት ይሰድቡት ነበር፣ "አንተ ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን የምትሠራ ሆይ!30እስቲ አሁን ራስህን አድን፤ከመስቀልም ውረድ!"31እንደዚሁም የካህናት አለቆች ከጸሓፍት ጋር ሆነው እርስበርሳቸው እንዲህ እያሉ ያፌዙበት ነበር፤ "ሌሎችን አድኖአል፤ ራሱን ማዳን ግን አይችልም" አሉ፡፡32"አይተን እንድናምንበት መሲሑ የእስራኤል ንጉሥ እስቲ አሁን ከመስቀል ይውረድ" ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም ይሰድቡት ነበር።33ከቀኑም ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።34ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ኢየሱስ፣ "ኤሎሄ፣ ኤሎሄ፣ ላማሰበቅታኒ፤" ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ትርጓሜውም "አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?" ማለት ነው።35በዚያም ቆመው ከነበሩት ሰዎች አንዳንዶቹ ሰምተው "እነሆ! ኤልያስን ይጣራል፤" አሉ።36ከእነርሱም አንዱ ሮጠና ሆምጣጤ በሰፍነግ ሞላ፤ "ኤልያስ መጥቶ ያወርደው እንደ ሆነ እንይ" አለ።እንዲጠጣውም በመቃ ላይ አድርጎ ለኢየሱስ ሰጠው፡፡37ከዚያም ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ መንፈሱንም ሰጠ።38የቤተ መቅደሱም መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዶ ከሁለት ተከፈለ።39በመስቀሉ ፊት ለፊት ቆሞ የነበረ የመቶ አለቃ ኢየሱስ እንዴት መንፈሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ፣ "ይህ ሰው በእርግጥ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር፤" አለ።40በሩቅ ሆነው የሚመለከቱ ሴቶችም በዚያ ነበሩ። ከእነርሱም መካከል መግደላዊት ማርያም፣ የታናሹ ያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም፣ሰሎሜም ነበሩ።41እነርሱ ኢየሱስ በገሊላ በነበረበት ጊዜ ይከተሉትና ያገለግሉት ነበር። እንዲሁም ከኢየሱስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሌሎች ብዙ ሴቶችም ነበሩ።42መሽቶ ስለ ነበርና የሰንበት ዋዜማና ለሰንበት የመዘጋጃ ጊዜ ስለ ነበር፡፡43የተከበረ የሸንጎ አባል የነበረ ዮሴፍ የሚባል የአርማትያስ ሰው መጣ። እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚጠባበቅ ሰው ነበር። በድፍረትም ወደ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ለመነው።44ጲላጦስም "እንዴት እንዲህ በቶሎ ሞተ?" ብሎ ተደነቀ። የመቶ አለቃውንም ጠርቶ፣ "ከሞተ ቈይቶአልን?" ሲል ጠየቀው።45የኢየሱስን መሞት ከመቶ አለቃው ከሰማ በኋላ አስከሬኑን እንዲወስድ ለዮሴፍ ፈቀደለት።46ዮሴፍም የከፈን ልብስ ገዛ፤ የኢየሱስን አስከሬን ከመስቀል አውርዶ ገነዘው፤ ከዐለት ተወቅሮ በተዘጋጀ መቃብር ውስጥ አስቀመጠው። ትልቅ ድንጋይም አንከባሎ የመቃብሩን መግቢያ ዘጋ።47መግደላዊት ማርያምና የዮሳ እናት ማርያምምሰ ኢየሱስን የት እንዳኖሩት አዩ።
1ሰንበት ካለፈ በኋላም መጥተው ይቀቡት ዘንድ መግደላዊት ማርያም፣ የያዕቆብ እናት ማርያምና ሰሎሜ ሽቶ ገዙ፡፡2ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ጎህ በቀደደ ጊዜ ወደ መቃብሩ መጡ፡፡3እርስ በርሳቸውም ድንጋዩን ከመቃብሩ መግቢያ ማን ያንከባልልናል ይባባሉ ነበር፡፡4አሻግረው ሲመለከቱም ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና ተንከባሎ አዩት፡፡5ወደ መቃብሩም ገብተው የሚያንጸባርቅ ነጭ ልብስ የለበሰ አንድ ወጣት በስተቀኝ ተቀምጦ አዩና ተገረሙ፡፡6እርሱም አትገረሙ፣ የምትፈልጉት ተሰቅሎ የነበረውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ነው፡፡ ያኖሩበትን ቦታ ተመልከቱ፤ እርሱ በዚህ የለም፣ ተነሥቷል፡፡7ነገር ግን ሂዱ፣ ለጴጥሮስና ለደቀመዛሙርቱም እንደነገራችሁ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፣ በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሯቸው አላቸው፡፡8እነርሱም መገረምና ፍርሃት ወድቆባቸው ነበርና ከዚያ ወጥተው ከመቃብሩ ሸሹ፡፡ ፈርተውም ነበርና ለማንም አንዳች አልተናገሩም፡፡9ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን በማለዳ በተነሳ ጊዜ ሰባት አጋንንት አውጥቶላት ለነበረችው ለመግደላዊት ማርያም አስቀድሞ ታያት፡፡10እርሷም ከኢየሱስ ጋር የነበሩት እያዘኑና እያለቀሱ ሳሉ ሄዳ ነገረቻቸው፡፡11እነርሱም ሕያው እንደሆነና ለእርሷም እንደታያት በሰሙ ጊዜ አላመኑም፡፡12ከእነዚህ ነገሮች በኋላም ከእነርሱ ሁለቱ ወደ ገጠር በመሄድ ላይ ሳሉ ኢየሱስ በሌላ ሰው መልክ ተገለጠላቸው፡፡13እነርሱም ሄደው ለተቀሩት ነገሯቸው፤ እነርሱንም አላመኗቸውም፡፡14ከዚያም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ለራሳቸው ኢየሱስ ተገለጠላቸውና ስለ ልባቸው ጥንካሬና ከትንሳኤው በኋላ ያዩትን ስላላመኗቸው ወቀሳቸው፡፡15እንዲህም አላቸው፣ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት በሙሉ ስበኩ አላቸው፡፡16ያመነና የተጠመቀም ይድናል፣ ያላመነ ግን ይፈረድበታል፡፡17ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፣ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፣18እባቦችን ይይዛሉ፣ የሚገድል ነገር እንኳን ቢጠጡ አይጎዳቸውም፣ እጆቻቸውን በህሙማን ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይፈወሳሉ፡፡19ጌታ ኢየሱስ ይህንን ካላቸው በኋላ ወደ ሰማይ ወጥቶም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፡፡20እነርሱም ወጥተው በየቦታው ሰበኩ፡፡ ጌታም ቃሉን ተከትለው በሚመጡ ምልክቶች እያጸና ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፡፡ አሜን፡፡
1ብዙዎች በእኛ ዘንድ ስለተፈጸሙት ጉዳዮች ታሪኩን በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ ሞክረዋል፣2ይህም የዓይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት በመጀመሪያ ለእኛ ባስተላለፉልን መሠረት ነበር፡፡3ስለሆነም፣ እጅግ የተከበርክ ቴዎፍሎስ ሆይ፣ እኔም የእነዚህን ነገሮች ሂደት ከመጀመሪያው በትክክል ከመረመርኩ በኋላ፣ በቅደም ተከተላቸው መጻፍ መልካም መስሎ ታየኝ፡፡4ይህንንም ያደረግሁት ስለ ተማርኸው ነገር እውነቱን ታውቅ ዘንድ ነው፡፡5በይሁዳ ገዢ፣ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፡፡ ሚስቱም ከአሮን ልጆች የነበረችና ስሟም ኤልሳቤጥ የሚባል ነበር፡፡6ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፣ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ትእዛዛት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየጠበቁ ይኖሩ ነበር፡፡7ነገር ግን ኤልሳቤጥ መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራቸውም፣ በዚህ ጊዜ ደግሞ ሁለቱም አርጅተው ነበር፡፡8በዚህን ጊዜ፣ ዘካርያስ በክፍሉ ተራ የክህነት አገልግሎቱን እየፈጸመ በእግዚአብሔር ፊት የሚሆንበት ጊዜ ደረሰ፡፡9የትኛው ካህን እንደሚያገለግል ለመምረጥ በሚፈጸመው ልምድ መሠረት፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን ዕጣ ደረሰው፡፡10እርሱ ዕጣን በሚያጥንበት ወቅት፣ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ይጸልይ ነበር፡፡11በዚህን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና በዕጣኑ መሠዊያ በስተቀኝ ቆመ፡፡12ዘካርያስ በተመለከተው ጊዜ ደነገጠ፣ ፍርሃትም በእርሱ ላይ ወደቀ፡፡13ነገር ግን መልአኩ፣ “ጸሎትህ ተሰምቶአልና ዘካርያስ ሆይ፣ አትፍራ፡፡ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡14ሐሴትና ደስታ ይሆንልሃል፣ ብዙዎችም በእርሱ መወለድ ሐሴት ያደርጋሉ፡፡15በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና፣ ወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮም በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ይሆናል፡፡16ከእስራኤል ሕዝብም ብዙዎቹ ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመለሳሉ፡፡17በእግዚአብሔርም ፊት በኤልያስ መንፈስና ኃይል ይመላለሳል፡፡ ይህንንም የሚያደርገው የማይታዘዙት በጻድቃን ጥበብ ይሄዱ ዘንድ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች ለመመለስና የተዘጋጁትን ሕዝብ ለእግዚአብሔር ያዘጋጅ ዘንድ ነው” አለው፡፡18ዘካርያስም፣ “እኔ ያረጀሁ በመሆኔና ሚስቴም ዕድሜዋ የገፋ በመሆኑ፣ ይህንን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?” አለ፤19መልአኩም፣ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንን የምሥራች እነግርህ ዘንድ ተልኬያለሁ፡፡20እነሆ፣ እነዚህ ነገሮች እስኪፈጸሙ ድረስ ጸጥ ትላለህ፣ መናገርም አትችልም፡፡ ይህም የሚሆነው በትክክለኛው ጊዜ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንክ ነው፡፡”21በዚህን ጊዜ ሕዝቡ ዘካርያስን እየተጠባበቁ ነበር፣ ለረጅም ጊዜ በቤተ መቅደስ በመቆየቱም ተደነቁ፡፡22በወጣ ጊዜ ግን ሊያነጋግራቸው አልቻለም፤ እነርሱም በቤተ መቅደስ በነበረበት ጊዜ ራእይ እንደ ተገለጠለት ተገነዘቡ፡፡ ለእነርሱ ምልክት ብቻ እየሰጣቸው ጸጥ ብሎ ቆየ፡፡23የአገልግሎቱም ወቅት እንዳበቃ ወደ ቤቱ ለመመለስ ተነሣ፡፡24ከዚህም ወቅት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፤ ለአምስት ወራትም ራሷን ሰወረች፣ እንደዚህም አለች፣25“በሕዝብ ዘንድ የነበረብኝን ነቀፌታ ለማስወገድ ብሎ በሞገስ ተመልክቶኝ እግዚአብሔር ለእኔ ያደረገልኝ ይህንን ነው፡፡”26ስድስት ወሯ በነበረ ጊዜ መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደተባለች የገሊላ ከተማ ተላከ፡፡27የተላከውም ዮሴፍ ለተባለ ከዳዊት ነገድ ለሆነ ሰው ወደ ታጨች አንዲት ድንግል ነበር፡፡ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር፡፡28ወደ እርሷም መጣና እንደዚህ አላት፣ “እጅግ የተከበርሽ ሆይ፣ ሰላም ለአንቺ ይሁን! እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፡፡”29እርሷ ግን በንግግሩ በጣም ግራ ተጋባች፣ ምን ዓይነት ሰላምታ ሊሆን እንደሚችልም በማሰብ ተደነቀች፡፡30መልአኩም፣ “ማርያም ሆይ፤ አትፍሪ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አግኝተሻል፤31እነሆ፣ ፅንስ በማሕፀንሽ ውስጥ ይፀነሳል፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ስሙንም ‘ኢየሱስ’ ትይዋለሽ፡፡32እርሱም ታላቅ ይሆናል፣ የልዑልም ልጅ ይባላል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፡፡33በያዕቆብም ቤት ላይ ለዘላለም ይነግሣል፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፡፡"34ማርያምም ለመልአኩ፣ “ከማንም ወንድ ጋር ተኝቼ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?” አለችው፡፡35መልአኩም እንደዚህ በማለት መለሰላት፣ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑል ኃይልም በአንቺ ላይ ያርፋል፤ ከዚህ የተነሣም የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡36እነሆ፣ ዘመድሽም ኤልሳቤጥ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን ትባል ለነበረችው ለእርሷ ይህ ስድስተኛ ወሯ ነው፡፡37ለእግዚአብሔር የሚሳነው ምንም ነገር የለምና፡፡”38ማርያምም፣ “እነሆ፣ የእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ፤ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ፡፡” ከዚያ በኋላም መልአኩ ትቷት ሄደ፡፡39ከዚያ በኋላ፣ ማርያም ተነሥታ በእነዚያ ቀናት በኮረብታማው አገር በይሁዳ ወዳለች ወደ አንዲት ከተማ በፍጥነት ሄደች፡፡40ወደ ዘካርያስም ቤት ሄደችና ለኤልሳቤጥ ሰላምታ አቀረበችላት፡፡41ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፣ እንደዚህ ሆነ፣ በማሕፀኗ ያለው ፅንስ ዘለለ፣ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፡፡42ድምፅዋን ከፍ በማድረግ ጮክ ብላ፣ “ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ፣ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡43የጌታዬ እናት ወደ እኔ እንድትመጣ ይህ ለምን ሆነ?44እነሆ፣ የሰላምታሽ ድምፅ ወደ ጆሮዬ በመጣ ጊዜ በማሕፀኔ ውስጥ ያለው ሕፃን በደስታ ዘለለ፡፡45ከጌታ የተነገሩላት ነገሮች እንደሚፈጸሙ የምታምን እነሆ እርሷ የተባረከች ናት፡፡”46ከጌታ የተነገሩላት ነገሮች እንደሚፈጸሙ የምታምን እነሆ እርሷ የተባረከች ናት፡፡” 46. ማርያምም፣ “ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፣47መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ሐሴት ታደርጋለች፡፡48የሴት ባሪያውን ውርደት ተመልክቶአልና፡፡ እነሆ፣ ከዚህ በኋላ ትውልድ ሁሉ የተባረከች ይሉኛል፡፡49ብርቱ የሆነ እርሱ ለእኔ ታላቅ ነገር አድርጎልኛልና፣ ስሙም ቅዱስ ነው፡፡50ለሚያከብሩት ምሕረቱ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው፡፡51በክንዱ ብርታትን ገልጾአል፣ ስለ ልባቸው ሐሳብ የሚታበዩትን በትኖአቸዋል፡፡52ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዷቸዋል፣ ዝቅ ያሉትንም ከፍ አድርጓቸዋል፡፡53የተራቡትን በመልካም ነገር አጥግቧቸዋል፣ ባለጠጎችን ግን ባዶአቸውን ሰድዷቸዋል፡፡54ምሕረት ማድረጉን ያስታውስ ዘንድ ለባሪያው ለእስራኤል ረድኤቱን ልኮለታል፣55ይህንንም ያደረገው (ለአባቶቻችን እንደተናገረው) ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም፡፡”56ማርያም ከኤልሳቤጥ ጋር ሦስት ወራት ያህል ተቀመጠች፣ ከዚያ በኋላም ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡57በዚያን ጊዜ ኤልሳቤጥ የምትወልድበት ወቅት ደረሰ፣ ወንድ ልጅም ወለደች፡፡58ጎረቤቶቿና ዘመዶቿ እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዳበዛላት ሰሙ፣ ከእርሷም ጋር ደስ አላቸው፡፡59ልጁን የሚገርዙበት ስምንተኛው ቀን በመጣ ጊዜ፣ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ፈልገው ነበር፡፡60እናትዬዋ ግን መልስ ሰጠቻቸው፣ “አይሆንም፣ ስሙ ዮሐንስ ይሆናል” አለች፡፡61እነርሱም ለእርሷ፣ “ከዘመዶችሽ መካከል በዚህ ስም የተጠራ የለም” አሏት፡፡62በምን ስም እንዲጠራ እንደሚፈልግ አባቱን በምልክት ጠየቁት፡፡63አባቱም ሰሌዳ እንዲያቀርቡለት ጠየቀና፣ “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ፡፡ በዚህም ሁሉም ተደነቁ፡64ወዲያውኑም አንደበቱ ተከፈተ፣ ምላሱም ተፈትቶ ተናገረ፣ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡65በዙሪያቸውም በሚኖሩት ሰዎች ዘንድ ፍርሃት መጣባቸው፣ የእነዚህም ነገሮች ዜና በኮረብታማው በይሁዳ አገር ሁሉ ተሠራጨ፡፡66ዜናውን የሰሙትም ሁሉ፣ የእግዚአብሔር እጅ ከእርሱ ጋር ነበርና “እንግዲህ ይህ ልጅ ምን ሊሆን ይሆን?” እያሉ ነገሩን በልባቸው ጠበቁት፡፡67አባቱም ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ፣68“የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣ የመቤዠት ሥራ በመሥራት ሕዝቡን ረድቶታልና፡፡69ከባሪያው ከዳዊት ዝርያዎች መካከል ለባሪያው ለዳዊት ቤት የድነት ቀንድ አስነሥቶልናል፡፡70ይህም በጥንት ዘመን በነበሩት በቅዱሳን ነቢያቱ እንደ ተናገረው ነው፡፡71ከጠላቶቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ ያድነናል፡፡72ይህንን የሚያደርገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየትና ቅዱስ ኪዳኑን፣73ማለትም ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ለማስታወስ ነው፡፡74መሐላውን የማለውም እኛ ከጠላቶቻችን ድነን በዘመኖቻችን ሁሉ በእርሱ ፊት በመሆን ያለ ፍርሃት፣75በቅድስናና በጽድቅ እርሱን እንድናገለግለው ነው፡፡76አዎን፣ አንተም ሕፃን የእርሱን መንገድን ለማዘጋጀት በጌታ ፊት ስለምትሄድና ሕዝብንም ለመምጣቱ ስለምታሰናዳ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡77ለኃጢአቶቻቸው ይቅርታ የሚያገኙትን የድነት ዕውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፡፡78ይህም ከእግዚአብሔር አምላካችን መልካም ምሕረት የተነሣ ከእርሱ የተነሣ የፀሐይ ብርሃን በእኛ ላይ እንዲያርፍብንና79በጨለማና በሞት ጥላ ላሉት እናበራላቸው ዘንድ ነው፡፡ ይህንንም እግሮቻችንን በሰላም መንገድ ይመራው ዘንድ ያደርገዋል፡፡”80ልጁም አደገ፣ በመንፈሱም ጠነከረ፣ ለእስራኤልም እስኪገለጥ ድረስ በምድረ በዳ ኖረ፡፡
1በዚያን ጊዜ አውግስጦስ ቄሣር በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይቆጠሩ ዘንድ ዐዋጅ አወጣ፡፡2ይህም ቄሬኔዎስ የሶርያ ገዥ በነበረበት ጊዜ የተደረገ የመጀመሪያው የሕዝብ ቆጠራ ነበር፡፡3ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለሕዝብ ቆጠራው ወደየራሱ ከተማ ሄደ፡፡4ዮሴፍም የዳዊት ቤተሰብ ዝርያ ስለነበረ በገሊላ ከነበረችው ከናዝሬት ተነሥቶ የዳዊት ከተማ ወደምትባለው የይሁዳ ከተማ ወደ ነበረችው ወደ ቤተ ልሔም ተጓዘ፡፡5ይመዘገብ ዘንድ ለእርሱ ታጭታ ከነበረችውና የመውለጃዋን ቀን እየተጠባበቀች ከነበረችው ከማርያም ጋር ወደዚያ ስፍራ ሄደ፡፡6እዚያም በነበሩበት ጊዜ የምትወልድበት ወቅት ደረሰ፡፡7የበኩር ልጅዋ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፣ በመታቀፊያ ጨርቅም በሚገባ ጠቀለለችው፡፡ በእንግዳ መቀበያውም ስፍራ ስላልነበረ በእንስሳት መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛቸው፡፡8በዚያው አካባቢ በሌሊት የበግ መንጎቻቸውን እየጠበቁ በመስክ የነበሩ እረኞች ነበሩ፡፡9በድንገትም የእግዚአብሔር መልአክ ለእነርሱ ተገለጠላቸው፣ የእግዚአብሔርም ክብር በእነርሱ ዙሪያ አበራላቸው፤ እነርሱም በጣም ፈሩ፡፡10ከዚያ በኋላ መልአኩ፣ “ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚሆን የምሥራች ይዤላችሁ መጥቻለሁና አትፍሩ፡፡11ዛሬ በዳዊት ከተማ፣ አዳኝ ተወልዶላችኋል፤ እርሱም ክርስቶስ ጌታ ነው፡፡12ለእናንተም ይህ ምልክት ይሰጣችኋል፣ ሕፃን በመታቀፊያ ጨርቅ ተጠቅልሎ፣ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ፡፡”13በድንገትም ከመልአኩ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ፣14“ከፍ ባለ ስፍራ ለሚኖረው ለእግዚአብሔር ክብር፣ በምድርም እርሱ ደስ በሚሰኝባቸው ሕዝቦች መካከል ሰላም ይሁን፡፡” ይሉ ነበር፡፡15መላእክቱም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በሄዱ ጊዜ፣ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ወደ ቤተልሔም እንሂድና፣ እግዚአብሔር ለእኛ የገለጠልንን ይህንን የሆነውን ነገር እንመልከት፡፡” ተባባሉ፡፡16በችኮላ ወደዚያ ሄደው ማርያምንና ዮሴፍን አገኝዋቸው፣ ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ ተመለከቱት፡፡17ይህንን ከተመለከቱ በኋላ ስለዚህ ልጅ የተባለውን ለሕዝቡ አስታወቁ፡፡18ያዳመጡአቸውም ከእረኞቹ በተነገራቸው ነገር ተደነቁ፡፡19ስለሰማችው ነገር ሁሉ ማርያም እያሰላሰለች በልብዋ ትጠብቀው ነበር፡፡20ልክ እንደ ተነገራቸው ስለ ሰሙትና ስላዩት ስለ ማንኛውም ነገር እረኞቹ እግዚአብሔርን እያከበሩና እያመሰገኑ ተመለሱ፡፡21ሕፃኑ የሚገረዝበት ስምንተኛው ቀን በደረሰ ጊዜ በማሕፀን ከመፀነሱ በፊት በመልአኩ በተሰጠው ስም ኢየሱስ ብለው ጠሩት፡፡22በሙሴ ሕግ መሠረት የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርቡት ዘንድ በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ23ይህም፣ “ማሕፀንን የሚከፍት ማንኛውም ወንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል” ተብሎ በሕጉ እንደ ተጻፈው ነው፡፡24በእግዚአብሔር ሕግም በተነገረው መሠረት መሥዋዕት ማለትም ‘ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች’ ያቀርቡ ዘንድ መጡ፡፡25በኢየሩሳሌምም የሚኖር ስሙ ስምዖን የተባለ ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው ጻድቅና የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚያከብር ነበር፤ ለእስራኤል መጽናኛም የሚሆነውን ይጠባበቅ ነበር፣ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር፡፡26እግዚአብሔር የቀባውን ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፡፡27የሕጉ ሥርዓት የሚጠይቀውን ሊያደርጉለት ወላጆቹ ሕፃኑ ኢየሱስን ይዘው በመጡበት ቀን በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ መጣ፡፡28ከዚያም ስምዖን በእጆቹ አቅፎት፣ እግዚአብሔርን እያመሰገነ፣29“ጌታ ሆይ፣ እንግዲህ፣ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው፣30ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና31ይህም ድነት አንተ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፡፡32እርሱም ለአሕዛብ መገለጥ ብርሃን፣ ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው፡፡”33የልጁም አባትና እናት ስለ እርሱ እየተነገረ ባለው ነገር ተደነቁ፡፡34ከዚያ በኋላ ስምዖን ባረካቸውና እናቱን ማርያምን፣ “በጥንቃቄ አድምጪ! ይህ ልጅ በእስራኤል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ምክንያት፣ ክፉም ለተናገሩበት ምልክት የሚሆን ነው፡፡35የብዙዎች የልባቸው ሐሳብ ይገለጥ ዘንድ የአንቺም የራስሽ ልብ በሰይፍ የሚወጋ ይሆናል፡፡”36ሐና የተባለች ነቢይትም በዚያ ነበረች፤ እርሷም ከአሴር ነገድ የሆነ የፋኑኤል ልጅ ነበረች፡፡ ዕድሜዋ እጅግ የገፋ ሲሆን ከጋብቻዋ በኋላ ከባልዋ ጋር ለሰባት ዓመታት ቆይታለች፡፡37ከዚያ በኋላ ለሰማንያ አራት ዓመታት መበለት ሆና ኖራለች፡፡ ከቤተ መቅደስ በፍጹም ሳትለይ ቀንና ሌሊት በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን ታመልክ ነበር፡፡38ልክ በዚያን ሰዓት ወደ እነርሱ መጥታ እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመረች፡፡ የኢየሩሳሌምን መቤዠት ለሚጠባበቁ ለማንኛዎቹም ሰዎች ስለ ልጁ ትናገር ነበር፡፡39እንደ እግዚአብሔር ሕግ እንዲያደርጉ የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም ነገር ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ገሊላ ወደ ራሳቸው ከተማ ወደ ናዝሬት ተመለሱ፡፡40ልጁ አደገ፣ ጠነከረ፣ በጥበብም ጨመረ፤ የእግዚአብሔር ጸጋም በ እርሱ ላይ ነበረ፡፡41ወላጆቹም ለፋሲካ በዓል በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር፡፡42አሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ በተለመደው ጊዜ እንደገና በዓሉን ለማክበር ሄዱ፡፡43ለበዓሉ መቆየት ያለባቸውን ሁሉንም ቀናት ከቆዩ በኋላ ወደ ቤታቸው መመለስ ጀመሩ፡፡ ልጁ ኢየሱስ ግን በኢየሩሳሌም ቀረ፣ ወላጆቹም ይህንን አላወቁም ነበር፡፡44ከእነርሱ ጋር ይጓዙ ከነበሩት መንገደኞች ጋር የነበረ መስሏቸው ስለነበረ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፡፡ ከዚያ በኋላም በዘመዶቻቸውና በወዳጆቻቸው ዘንድ ፈለጉት፡፡45ባላገኙትም ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው በዚያ ሊፈልጉት ጀመሩ፡፡46ከሦስት ቀን በኋላ እያዳመጣቸውና ጥያቄዎችን እየጠየቃቸው በመምህራን መካከል ተቀምጦ በቤተ መቅደስ ውስጥ አገኙት፡፡47ያዳመጡት ሁሉ በማስተዋሉና በሚሰጣቸው መልሶች ተገረሙ፡፡48ባዩትም ጊዜ ተደነቁ፡፡ እናቱም እርሱን፣ “ልጄ ሆይ፣ ለምን እንደዚህ አደረግኸን? አድምጠኝ፣ እኔና አባትህ ተጨንቀን አንተን ስንፈልግህ ነበርን” አለችው።49እርሱም፣ “ለምን ነበር የፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንደሚገባኝ አታውቁምን?”50ነገር ግን እንደዚያ ሲል ምን ማለቱ እንደነበረ አልገባቸውም፡፡51ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር ወደ ናዝሬት ተመለሰ፣ ይታዘዝላቸውም ነበር፡፡ እናቱም ይህንን ሁሉ ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር፡፡52ኢየሱስ ግን በጥበብና በሰውነት ቁመና ማደጉን ቀጠለ፣ በእግዚአብሔርና በሰዎችም ፊት ያለው ሞገስ እየጨመረ ሄደ፡፡
1ጢባርዮስ ቄሣር በነገሠ በአሥራ አምስተኛው ዓመት፣ ጴንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ ገዥ፣ ሄሮድስ የገሊላ አራተኛው ክፍል ገዥ፣ ወንድሙ ፊልጶስ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ የአራተኛው ክፍል ገዥ፣ ሊሳኒዮስም የሳቢላኒስ አራተኛው ክፈል ገዥ2እንደዚሁም ሐናና ቀያፋ ሊቃነ ካህናት በነበሩበት ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ለዘካርያስ ልጅ ለዮሐንስ በምድረ-በዳ መጣ፡፡3ለኃጢአት ይቅርታ የንስሓን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ወንዝ አውራጃ ሁሉ ተመላለሰ፡፡4ይህም በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ፣ “በምድረ-በዳ የሚጣራ ሰው ድምፅ፣ ‘የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናውንም አቅኑ፡፡5ሸለቆ ሁሉ ይሞላል፣ ተራራውና ኮረብታው ደልዳላ ይሆናል፣ ጠማማው መንገድ ቀና ይሆናል፣ ሸካራውም መንገድ የተመቸ ይሆናል፡፡6ሰዎችም ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያሉ፡፡’”7ስለዚህ በእርሱ ለመጠመቅ ይመጣ ለነበረው ከፍተኛ ቁጥር ላለው ሕዝብ ዮሐንስ እንደዚህ አላቸው፣ “እናንተ የመርዘኛ እባብ ልጆች፣ ሊመጣ ካለው ቁጣ እንድትሸሹ ማን አስጠነቀቃችሁ?8ለንስሓ የሚሆን ፍሬ አፍሩ፣ እርስ በርሳችሁም፣ ‘አባታችን አብርሃም አለን’ አትበሉ፣ ምክንያቱም ከእነዚህ ድንጋዮች እንኳን እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል፡፡9መጥረቢያ በዛፎች ግንድ ሥር ተቀምጦአል፤ ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ ወደ እሳት ውስጥ ያጣላል፡፡”10ከዚያ በኋላ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች እንደዚህ ብለው ጠየቁት፣ “እንግዲህ ምን እናድርግ?”11እርሱም እንደዚህ ብሎ መለሰላቸው፣ “አንድ ሰው ሁለት ልብስ ካለው ምንም ለሌለው ለሌላ ሰው ይስጠው፤ ትርፍ ምግብ ያለውም እንደዚሁ ያድርግ፡፡”12ከዚያ በኋላም አንዳንድ ቀረጥ ሰብሳቢዎች ለመጠመቅ መጡና እንደዚህ አሉት፣ “መምህር ሆይ፣ እኛስ ምን ማድረግ ይገባናል?”13እርሱም እንደዚህ አላቸው፣ “መሰብሰብ ከሚገባችሁ ገንዘብ በላይ አትሰብስቡ፡፡”14አንዳንድ ወታደሮችም እንደዚህ ብለው ጠየቁት፣ “እኛስ፣ ምን ማድረግ ይገባናል?” እርሱም እንደዚህ አላቸው፣ “ከማንም ላይ አስገድዳችሁ ገንዘብ አትውሰዱ፣ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፡፡ የምታገኙትም ደመወዝ ይብቃችሁ፡፡”15ሕዝቡ የክርስቶስን መምጣት እየተጠባበቁ ሳሉ፣ ሰዎች ሁሉ በልባቸው እርሱ ክርስቶስ ይሆን እያሉ ስለ ዮሐንስ ይደነቁ ነበር፡፡16እንደዚህ በማለት ዮሐንስ ለሁሉም መልስ ሰጣቸው፣ “እኔ በበኩሌ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፣ የጫማውን ማሠሪያ መፍታት እንኳን የማይገባኝ ከእኔ ይልቅ ብርቱ የሆነ ይመጣል፡፡ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡17አውድማውን ፈጽሞ ያጠራውና ስንዴውን ወደ ጎተራ ያስገባ ዘንድ የሚያበራይበት መንሽ በእጁ ነው፡፡ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል፡፡”18ሌሎች ብዙ ምክሮችንም በመምከር፣ የምሥራቹን ቃል ለሕዝቡ ሰበከላቸው፡፡19የወንድሙን ሚስት ሄሮዳይዳን ስላገባና ስላደረጋቸውም ሌሎች ክፉ ሥራዎች የአራተኛው ክፍል ገዥ የነበረውን ሄሮድስንም ገሰጸው፡፡20ሄሮድስ ግን ከዚህም የባሰ ክፉ ሥራ ሠራ፣ ዮሐንስን ወህኒ ቤት አስገብቶ ቆለፈበት፡፡21ሰዎች ሁሉ በዮሐንስ እየተጠመቁ ሳሉ፣ ኢየሱስም ደግሞ ተጠመቀ፡፡ እየጸለየም ሳለ ሰማያት ተከፈቱ፡፡22መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በአካል በእርሱ ላይ አረፈ፣ በዚህም ጊዜ ከሰማይ፣ “አንተ፣ ውድ ልጄ ነህ፤ በአንተ እጅግ ደስ ይለኛል፡፡” የሚል ድምፅ መጣ፡፡23በዚህን ጊዜ ኢየሱስ ራሱ ማስተማር ሲጀምር ዕድሜው ሰላሳ ዓመት ገደማ ነበር፡፡ (ይገመት እንደነበረው) እርሱ የኤሊ ልጅ የነበረው የዮሴፍ ልጅ24ኤሊም የማቲ ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣ የሚልኪ ልጅ፣ የዮና ልጅ፣ የዮሴፍ ልጅ፣25የማታትዩ ልጅ፣ የአሞጽ ልጅ፣ የናሆም ልጅ፣ የኤሲሊም ልጅ፣ የናጌ ልጅ፣26የማኦት ልጅ፣ የማታትዩ ልጅ፣ የሰሜይ ልጅ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዮዳ ልጅ፣27የዮናን ልጅ፣ የሬስ ልጅ፣ የዘሩባቤል ልጅ፣ የሰላትያል ልጅ፣ የኔር ልጅ፣28የሚልኪ ልጅ፣ የሐዲ ልጅ፣ የዮሳስ ልጅ፣ የቆሳም ልጅ፣ የኤልሞዳም ልጅ፣ የኤር ልጅ፣29የዮሴዕ ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ፣ የዮራም ልጅ፣ የማጣት ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣30የስምዖን ልጅ፣ የይሁዳ ልጅ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዮናም ልጅ፣ የኤልያቄም ልጅ፣31የሜልያ ልጅ፣ የማይናን ልጅ፣ የማጣት ልጅ፣ የናታን ልጅ፣ የዳዊት ልጅ፣32የእሴይ ልጅ፣ የኢዮቤድ ልጅ፣ የቦዔዝ ልጅ፣ የሰልሞን ልጅ፣ የነአሶን ልጅ፣33የአሚናዳብ ልጅ፣ የአራም ልጅ፣ የአሮኒ ልጅ፣ የኤስሮም ልጅ፣ የፋሬስ ልጅ፣ የይሁዳ ልጅ፣34የያዕቆብ ልጅ፣ የይስሐቅ ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ፣ የታራ ልጅ፣ የናኮር ልጅ፣35የሴሮህ ልጅ፣ የራጋው ልጅ፣ የፋሌቅ ልጅ፣ የአቤር ልጅ፣ የሳላ ልጅ፣36የቃይንም ልጅ፣ የአርፋክስድ ልጅ፣ የሴም ልጅ፣ የኖኅ ልጅ፣ የላሜህ ልጅ፣37የማቱሳላ ልጅ፣ የሄኖክ ልጅ፣ የያሬድ ልጅ፣ የመላልኤል ልጅ፣ የቃይናን ልጅ፣38የሄኖስ ልጅ፣ የሴት ልጅ፣ የአዳም ልጅ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፡፡
1ከዚያ በኋላ፣ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ወንዝ ተመለሰ፤ መንፈስም ወደ ምድረ-በዳ መራው፡፡2በዚያም ለአርባ ቀናት በዲያብሎስ ተፈተነ፡፡ በእነዚያም ቀናት ምንም አልበላም፣ ያም ወቅት በተጠናቀቀ ጊዜ ተራበ፡፡3ዲያብሎስም፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ይህ ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዝ” አለው፡፡4ኢየሱስም፣ “’ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፎአል፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡5ከዚያ በኋላም ዲያብሎስ ከፍ ወዳለ ስፍራ ወሰደውና፣ በቅጽበት የዓለም መንግሥታትን ሁሉ አሳየው፡፡6ዲያብሎስም ለእርሱ፣ “እነዚህን ሁሉ መንግሥታት ከክብራቸው ሁሉ ጋር እንድትገዛ እኔ ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ ይህንን ማድረግ የምችለው እገዛቸው ዘንድ ለእኔ ስለተሰጡኝ ነው፣ እኔም ለምፈልገው ለማንኛውም ሰው ልሰጣቸው እችላለሁ፡፡7ስለዚህ በፊቴ ብትሰግድልኝና ብታመልከኝ፣ ይሄ ሁሉ የአንተ ይሆናል አለው።8ኢየሱስ ግን እንደዚህ ብሎ መለሰለት፣ “’እግዚአብሔር አምላክህን አምልክ፣ እርሱንም ብቻ አገልግል’ ተብሎ ተጽፎአል፡፡”9ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቤተ መቅደሱ ሕንፃ እጅግ ከፍተኛ ስፍራ አቆመውና፣10“’ይጠብቁህና ይንከባከቡህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋል’11ደግሞም፣ ‘እግርህም ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ በእጆቻቸው ወደ ላይ ይይዙሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና፣ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ራስህን ከዚህ ላይ ወርውር፡፡” አለው፡፡12ኢየሱስም፣ “’እግዚአብሔር አምላክህን መፈታተን የለብህም’ ተብሎአል፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡13ዲያብሎስም ኢየሱስን መፈተኑን ባበቃ ጊዜ፣ እስከ ሌላ ጊዜ ድረስ ትቶት ሄደ፡፡14ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ በዚያ አካባቢ በነበሩት ስፍራዎች ሁሉ የእርሱ ዝና ተሰራጨ፡፡15በምኩራቦቻቸው አስተማረ፣ ሰዎችም ሁሉ ያመሰግኑት ነበር፡፡16አንድ ቀንም ወዳደገበት ከተማ ወደ ናዝሬት መጣ፡፡ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገባ፣ የእግዚአብሔርንም ቃል ያነብ ዘንድ ቆመ፡፡17የነቢዩ የኢሳይያስ የመጽሐፍ ጥቅልል ተሰጥቶት ስለነበረ፣ ጥቅልሉን ሲከፍተው፣18“ለድሆች የምሥራቹን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለምርኮኞች ነፃነትን፣ ለዕውሮች ብርሃናቸው እንደሚመለስላቸው ፣ የተጨቆኑትም መፈታትን እንደሚያገኙ19የእግዚአብሔርን የሞገስ ዓመት ዐውጅ ዘንድ ልኮኛል፡፡” የሚለውን ስፍራ አገኘ፡፡20ከዚያ በኋላ የመጽሐፉን ጥቅልል ዘጋና ለምኩራቡ አገልጋይ ሰጥቶ ተቀመጠ፡፡21“እናንተ እየሰማችሁ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ተፈጸመ፡፡” እያለ ሊነግራቸው ጀመረ፡፡22በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ የተናገረውን አስተዋሉ፣ ከአንደበቱም በሚወጣው የጸጋ ቃል ሁሉም ተገረሙ፡፡ እነርሱም፣ “ይህ የዮሴፍ ልጅ ነው፣ አይደለም እንዴ?” ይሉ ነበር፡23ኢየሱስም፣ “በእርግጥ ‘ሐኪም ሆይ፣ ራስህን አድን፤ በቅፍርናሆም እንደምታደርግ የሰማነውን በዚህም በትውልድ ከተማህ አድርግ’ የሚለውን ይህንን ምሳሌ ትመስሉብኛላችሁ፡፡”24ደግሞም እንደዚህ አላቸው፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ ማንኛውም ነቢይ በገዛ አገሩ ተቀባይነት የለውም፡፡25ነገር ግን እኔ እውነት እላችኋለሁ፣ ለሦስት ዓመታት ተኩል ሰማይ ተዘግቶ ዝናብ ባልነበረበትና በምድሪቱም ሁሉ ረሃብ በነበረበት በኤልያስ ዘመን በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፡፡26ነገር ግን ኤልያስ በሲዶና አጠገብ በሰራፕታ ትኖር ወደነበረችው መበለት ብቻ እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱም አልተላከም፡፡27በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፣ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንዳቸውም አልተፈወሱም፡፡”28በምኩራብ የነበሩት ሰዎች ሁሉ እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ በቁጣ ተሞሉ፡፡29ተነሥተው ከከተማይቱ እንዲወጣ አስገደዱት፣ ከገደል ጫፍም ገፍትረው ይጥሉት ዘንድ ከተማይቱ ወደ ተመሠረተችበት ወደ ኮረብታው ጫፍ ገፍተው ወሰዱት።30ነገር ግን በመካከላቸው አልፎ ጉዞውን ቀጠለ፡፡31ከዚያ በኋላም በገሊላ ወደምትገኝ ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ሄደ፡፡32በሥልጣን ይናገር ስለነበረ፣ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡33በዚያን ቀን በምኩራብ ውስጥ ርኩስ መንፈስ የነበረበት ሰው ነበረ፤ እርሱም በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡34“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፣ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደሆንክ አውቄሃለሁ፣ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ፡፡”35ኢየሱስም ጋኔኑን፣ “ፀጥ ብለህ ከእርሱ ውጣ!” ብሎ ገሠጸው፡፡ ጋኔኑ በሰዎቹ መካከል በጣለው ጊዜ፣ ምንም ጉዳት ሳያደርስበት ከእርሱ ወጣ፡፡36ሰዎች ሁሉ በጣም ተደነቁ፣ እርስ በርሳቸውም ስለሆነው ነገር መነጋገር ቀጠሉ፡፡ እነርሱም፣ “እነዚህ እንዴት ያሉ ቃላት ናቸው? ርኩሳን መናፍስትን በሥልጣንና በኃይል ያዛቸዋል፣ እነርሱም ይወጣሉ፡፡”37የእርሱም ዝና በአካባቢው ባሉት አውራጃዎች በማንኛውም ስፍራ ወጣ፡፡38ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከምኩራብ ወጥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ፡፡ በዚያን ጊዜ የስምዖን አማት በከፍተኛ ትኩሳት ታማ ነበር፣ እነርሱም ስለ እርሷ ተማፀኑት፡፡39ስለዚህ በአጠገብዋ ቆሞ ትኩሳቱን ገሠጸው፣ ትኩሳቱም ቆመ፡፡ ወዲያውኑም ተነሥታ ልታገለግላቸው ጀመረች፡፡40ፀሐይም በጠለቀች ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ደዌዎች የተያዙትን በሽተኞች ወደ እርሱ አመጡ፡፡ እርሱም እጆቹን በእያንዳንዳቸው ላይ ጭኖ ፈወሳቸው፡፡41አጋንንትም፣ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” እያሉ በመጮኽ ከብዙዎች ወጡ፡፡ ኢየሱስ አጋንንትን ገሠጻቸው፣ እንዲናገሩም አልፈቀደላቸውም፣ ምክንያቱም እርሱ ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና፡፡42ንጋትም በሆነ ጊዜ ወደ ገለልተኛ ስፍራ ሄደ፡፡ ብዙ የሕዝብ አጀብ እየፈለጉት ነበርና፣ እርሱ ወደነበረበት ስፍራ መጡ፡፡ እነርሱንም ትቷቸው እንዳይሄድ ሊያስቀሩት ሞከሩ፡፡43እርሱ ግን እንደዚህ አላቸው፣ “የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ለብዙ ከተሞች መስበክ ይገባኛል፣ ምክንያቱም ወደዚህ የተላክሁት ለዚህ ነው፡፡”44ከዚያ በኋላ በመላው ይሁዳ ባሉት ምኩራቦች መስበኩን ቀጠለ፡፡
1ሕዝቡ ከበውት የእግዚአብሔርን ቃል እያዳመጡ ሳሉ፣ ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ሐይቅ ዳር ቆሞ ነበር፡፡2ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ጥግ በኩል ሲጎተቱ ተመለከተ፡፡ ዓሣ አጥማጆቹ ከጀልባዎቹ ወርደው መረቦቻቸውን እያጠቡ ነበር፡፡3ኢየሱስ የስምዖን ወደ ነበረችው ከጀልባዎቹ ወደ አንዲቱ ገባና ከምድር ጥቂት ፈቀቅ አድርጎ ወደ ውሃ ውስጥ እንዲያስገባት ጠየቀው፡፡ ከዚያ በኋላም በጀልባዋ ውስጥ ተቀምጦ ሕዝቡን ማስተማር ጀመረ፡፡4ንግግሩንም በጨረሰ ጊዜ ለስምዖን፣ “ጀልባይቱን ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ አድርጋትና ዓሣ ለማጥመድ መረቦቻችሁን ጣሉ፡፡” አለው፡፡5ስምዖንም፣ “ጌታ ሆይ፣ ሌሊቱን ሁሉ ስንሠራ አደርን ምንም አላጠመድንም፣ ነገር ግን በቃልህ መረቡን እጥላለሁ፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡6ይህንን ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፣ መረቦቻቸውም ሊቀደዱ ደረሱ፡፡7ስለዚህ እንዲመጡና እንዲረዷቸው በሌላ ጀልባ የነበሩትን ጓደኞቻቸውን በጥቅሻ ጠሩ፡፡ እነርሱም መጥተው ሁለቱንም ጀልባዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው፡፡8ስምዖን ጴጥሮስ ግን ይህንን በተመለከተ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ሥር ዝቅ ብሎ በመንበርከክ፣ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ሰው ነኝና ከእኔ ተለይ” አለው፡፡9እንደዚህም ያለው ስላጠመዷቸው ዓሣዎች እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ተደንቀው ስለነበረ ነው፡፡10በዚያም ከነበሩት መካከል የዘብዴዎስ ልጆች ዮሐንስና ያዕቆብ አብረውት ነበሩ፡፡ ኢየሱስም ለስምዖን፣ “ከእንግዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህና፣ አትፍራ፡፡” አለው፡፡11ጀልባቸውን ወደ ምድር ባመጧት ጊዜ ሁሉንም ትተው ተከተሉት፡፡12ከከተማዎቹ በአንዲቱ በነበረ ጊዜ፣ መላ ሰውነቱ በለምጽ የተመታ ሰው በዚያ ነበረ፡፡ ኢየሱስንም ባየ ጊዜ በፊቱ ወድቆ፣ “ብትፈቅድስ፣ ልታነጻኝ ትችላለህ፡፡” ብሎ ለመነው፡፡13በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ” አለው፡፡ ወዲያውኑም ለምጹ ከእርሱ ተወገደ፡፡14ለማንም እንዳይነግር አስጠነቀቀው፣ ነገር ግን፣ “ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ፣ ሙሴ ባዘዘውም መሠረት ለእነርሱ ምስክር ይሆን ዘንድ ለመንጻትህ መሥዋዕት አቅርብ፡፡” አለው፡15ነገር ግን ስለ እርሱ ያለው ዝና ከዚያም ርቆ ወጣ፤ ብዙም የሕዝብ አጀብ ሲያስተምር ለመስማትና ከሕመሞቻቸው ለመፈወስ በአንድነት ወደ እርሱ መጡ፡፡16እርሱ ግን ወደ ገለልተኛ ስፍራዎች ሄዶ በዚያ ይጸልይ ነበር፡፡17ያስተምር ከነበረባቸውም ከእነዚያ በአንዱ ቀን ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮችና አውራጃዎች እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ከተማ መጥተው በዚያ የተቀመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ነበሩ፡፡ ይፈውስም ዘንድ የእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ ላይ ነበረ፡፡18በዚያን ጊዜ ጥቂት ሰዎች ሰውነቱ የደነዘዘ ሰው በቃሬዛ ይዘው መጡ፤ በኢየሱስ ፊትም ያደርጉት ዘንድ ወደ ውስጥ የሚያስገቡበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡19ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያስገቡ የሚችሉበትን መንገድ አላገኙም፤ ስለዚህ ወደ ቤቱ ጣሪያ ላይ ወጥተው፣ ሰውዬውን በቃሬዛው ላይ እንዳለ በጣሪያው አሳልፈው በሰዎቹ መካከል ከኢየሱስ ፊት አወረዱት፡፡20ኢየሱስ እምነታቸውን ተመልክቶ፣ “አንተ ሰው፣ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው፡፡21ፈሪሳውያንና ጸሐፍት፣ “የስድብ ቃል የሚናገር ይህ ማን ነው? እግዚአብሔር ብቻ ካልሆነ በስተቀር፣ ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችል ማን ነው?” በማለት መጠየቅ ጀመሩ፡፡22ነገር ግን ኢየሱስ ምን እንዳሰቡ አውቆ፣ “በልባችሁ ይህንን ለምን ትጠይቃላችሁ?23የትኛውን ማለት ይቀላል፡- ‘ኃጢአትህ ተሰረየችልህ’ ማለት ወይስ ‘ተነሣና ሂድ’ ማለት?24ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፣ ለአንተ፣ ‘ተነሣና ቃሬዛህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ’ ብዬ እናገራለሁ፡፡"25ከዚያ በኋላ በእነርሱ ፊት ተነሣ፣ ተኝቶበት የነበረውንም ቃሬዛ ተሸክሞ እግዚአብሔርን እያከበረ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡26ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፣ እግዚአብሔርንም አከበሩ፡፡ “በዛሬው ዕለት ያልተለመደ ነገር አየን” እያሉ በፍርሃት ተሞሉ፡፡27እነዚህ ነገሮች ከሆኑ በኋላ፣ ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ በቀረጥ መሰብሰቢያው ስፍራ ተቀምጦ የነበረውን ሌዊ የተባለውን ቀረጥ ሰብሳቢ ተመለከተ፡፡ እርሱንም፣ “ተከተለኝ” አለው፡፡28ስለዚህ ሌዊ ሁሉንም ትቶ ተነሥቶ ተከተለው፡፡29ከዚያ በኋላ፣ ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ታላቅ ግብዣ አደረገለት፣ በዚያም ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና በማዕድ ቀርበው ከእነርሱ ጋር የሚመገቡ ሌሎች ሰዎችም ነበሩ፡፡30ነገር ግን ፈሪሳውያንና ጻሐፍት በደቀመዛሙርቱ ላይ፣ “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከሌሎች ኃጢአተኛ ሰዎች ጋር ለምን ትበላላችሁ ትጠጣላችሁም?” እያሉ ያጉረመርሙባቸው ነበር፡፡31ኢየሱስም እንደዚህ በማለት መለሰላቸው፣ “በመልካም ጤንነት ላይ ያሉ ሐኪም አያስፈልጋቸውም፣ ሐኪም የሚያስፈልጋቸው የታመሙ ብቻ ናቸው፡፡32እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ለንስሐ ለመጥራት ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ ለመጥራት ነው፡፡”33እነርሱም ፣ “የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ይጾማሉ ይጸልያሉም፣ የፈሪሳውያን ደቀመዛሙርትም እንደዚሁ ያደርጋሉ፡፡ የአንተ ደቀመዛሙርት ግን ይበላሉ፣ ይጠጣሉም፡፡” አሉት፡፡34ኢየሱስም ፣ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎቹን እንዲጾሙ ሊያደርጋቸው የሚችል አለን?35ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወቅት ይመጣል በእነዚያ ቀናት ይጾማሉ፡፡”36ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በምሳሌ ተናገራቸው፣ “ማንም ሰው ከአዲስ ልብስ ላይ እራፊ ቀዶ አሮጌ ልብስ አይጥፍም፡፡ እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ፣ ከአዲሱ ልብስ ላይ እራፊ ይቀዳል፣ ነገር ግን ከአዲሱ ልብስ ላይ የተቀደደው እራፊ ከአሮጌው ልብስ ጋር አብሮ አይሄድም፡፡37እንደዚሁም፣ ማንም ሰው በአሮጌው አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ አያስቀምጥም፡፡ እንደዚህ ቢያደርግ፣ አዲሱ ወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፣ ወይን ጠጁም ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይበላሻል፡፡38ነገር ግን አዲስ ወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ይቀመጣል፡፡39ማንም ሰው አሮጌውን ወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ አዲሱን የወይን ጠጅ አይፈልግም፣ ‘አሮጌው ይሻላል’ ይላልና፡፡”
1በሰንበት ቀን በእህል እርሻ መካከል በሚያልፍበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱ እሸት እየቀጠፉና በእጆቻቸው እያሹ እህሉን ይቅሙ ነበር፡፡2ገር ግን ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፣ “በሰንበት ቀን ማድረግ ያልተፈቀደውን የምታደርጉት ለምንድን ነው?” አሏቸው፡፡3ኢየሱስም ለእነርሱ፣ “ዳዊት በተራበ ጊዜ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ያደረጉትን እንኳ አላነበባችሁምን?4ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ከተቀደሰው ኅብስት ጥቂት ወሰደ፤ ካህናትም ብቻ ይበሉ ዘንድ የተፈቀደላቸውን ለራሱ በላ። አብረውት ከነበሩትም ለአንዳንዶቸ ይበሉ ዘንድ ሰጣቸው” አላቸው፡፡5ከዚያ በኋላም፣ “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው” አላቸው፡፡6በሌላም ሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ በዚያ የነበሩትን ሰዎች አስተማራቸው፡፡ በዚያም የቀኝ እጁ የሰለለች አንድ ሰው ነበረ፡፡7አንድ የተሳሳተ ነገር ሲያደርግ ተመልክተው ለመክሰስ ምክንያት ያገኙ ዘንድ በሰንበት ቀን አንድን ሰው ይፈውስ እንደሆነ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት በትኩረት ይመለከቱት ነበር፡፡8እርሱ ግን ምን እንደሚያስቡ አውቆ፣ እጁ የሰለለችበትን ሰውዬ፣ “ተነሣና በሰዎች ሁሉ መካከል ቁም” አለው፡፡ ስለዚህም ሰውዬው ተነሣና በዚያ ስፍራ ቆመ፡፡9ኢየሱስም፣ “ እኔም እናንተን እጠይቃችኋለሁ፡- በሰንበት ሕጋዊ የሚሆነው መልካም ማድረግ ነው ክፉ፣ ሕይወት ማድን ነው ወይስ ማጥፋት?”10ከዚያም ዞር ብሎ ሁሉንም ተመለከታቸውና ለሰውዬው፣ “እጅህን ዘርጋ” አለው፤ ዘረጋውም፣ እጁም ዳነለት፡፡11ከዚያ በኋላም በቁጣ ተሞልተው፣ በኢየሱስ ላይ ምን እንደሚያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፡፡12በዚያም ወቅት ኢየሱስ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፣ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩን ቀጠለ፡፡13በነጋም ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠራ፣ ከእነርሱም ‘ሐዋርያት’ ብሎ የሰየማቸውን አሥራ ሁለቱን መረጠ፡፡14የሐዋርያቱም ስም፣ ስምዖን (ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው) ወንድሙ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊልጶስ፣ በርተሎሚዎስ፣15ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ ያዕቆብ የእልፍዮስ ልጅ፣ ቀናተኛ የተባለው ስምዖን፣16የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና ከዳተኛ የሆነው ይሁዳ አስቆሮቱ ናቸው፡፡17ከዚያ በኋላም ኢየሱስ ከተራራው ወረደና በደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፡፡ ከደቀመዛሙርቱ በርከት ያሉት፣ ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርቻ ብዙ ሰዎች በዚያ ነበሩ፡፡18ወደዚያ የመጡት እርሱን ሊያዳምጡትና ከበሽታዎቻቸው ሊፈወሱ ነበር፡፡ በርኩሳን መናፍስት ሲጨነቁ የነበሩም ሰዎች ተፈወሱ፡፡19የሚፈውስ ኃይል ከእርሱ ይወጣ ስለነበረ፣ በሕዝቡ መካከል ያለ እያንዳንዱ ሰው እርሱን ለመንካት ጥረት ያደርግ ነበር፤ እርሱም ሁሉንም ፈወሳቸ.20ከዚያ በኋላም ወደ ደቀመዛሙርቱ ተመለከተና፣ እንደዚህ አላቸው፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ለእናንተ ናትና፣ እናንተ ድሆች የተባረካችሁ ናችሁ፡፡21አሁን የምትራቡ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ትጠግባላችሁና፡፡ አሁን የምታለቅሱ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ትስቃላችሁና፡፡22ሰዎች በሚጠሏችሁና በሚያገሏችሁ ጊዜ እንደዚሁም በሰው ልጅ ምክንያት ስማችሁን በክፉ ሲያነሱ የተባረካችሁ ናችሁ፡፡23አባቶቻቸው ነቢያትን እንደዚሁ አድርገውባቸው ነበርና ፣ በዚያን ቀን ሐሴት አድርጉ፣ በደስታም ዝለሉ፣ ምክንያቱም በሰማይ በእርግጥ ታላቅ ብድራት ይኖራችኋል፡፡24እናንተ አሁኑኑ መጽናናትን ተቀብላችኋልና፣ ነገር ግን እናንተ ባለጠጎች ወዮላችሁ!25በኋላ ትራባላችሁና፣ እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ! በኋላ ስለምታለቅሱና ዋይ፣ ዋይ ስለምትሉ፣ እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ!26ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መልካም በሚናገሩላችሁ ጊዜ ወዮላችሁ! ምክንያቱም አባቶቻቸው ለሐሰተኛ ነቢያት እንደዚያ ያደርጉላቸው ነበርና፡፡27ለእናንተ ለምታደምጡ ግን እላችኋለሁ፣ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉላቸው፡፡28የሚረግሟችሁን መርቁ፣ ለሚያንገላቷችሁም ጸልዩላቸው።29አንድ ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውንም ጉንጭህን አዙርለት፡፡ አንድ ሰው ነጠላህን የሚወስድብህ ከሆነ፣ እጀ ጠባብህን አትከልክለው፡፡30ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፣ አንድ ሰው የአንተ የሆነውን የሚወስድብህ ከሆነ፣ እንዲመልስልህ አትጠይቀው፡፡31ሰዎች እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን ሁሉ አንተም ለእነርሱ ልታደርግላቸው ይገባሃል፡፡32ኃጢአተኞችም እንኳን የሚወዷቸውን ይወዳሉና የሚወዷችሁን የምትወዱ ከሆነ፣ ምን ምስጋና ትቀበላላችሁ?33ኃጢአተኞችም እንደዚያው ያደርጋሉና መልካም ለሚያደርጉላችሁ ብቻ መልካም የምታደርጉ ከሆናችሁ፣ ምን ምስጋና ትቀበላላችሁ?34እንደሚመልሱላችሁ ለምትጠብቋቸው ብቻ የምታበድሩ ከሆናችሁ፣ ምን ምስጋና አላችሁ? የሰጡትን ያንኑ ያህል ለመቀበል ተስፋ አድርገው፣ ኃጢአተኞችም እንኳን ለኃጢአተኞች ያበድራሉ፡፡35ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ መልካምም አድርጉላቸው፤ ምንም ነገር ስለመቀበል ሳትጨነቁ አበድሯቸው፣ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፡፡ እርሱ ራሱ ለማያመሰግኑና ለክፉ ሰዎች ቸር ነውና፣ እናንተም የልዑል ልጆች ትባላላችሁ፡፡36አባታችሁ መሐሪ እንደሆነ ሁሉ እናንተም መሐሪዎች ሁኑ፡፡37አትፍረዱ አይፈርድባችሁም፤ አትኮንኑ አትኮነኑምም፤ ሌሎችን ይቅር በሉ፣ እናንተም ይቅር ትባላላችሁ፡፡38ለሌሎች ስጡ፣ ለእናንተም የተጠቀጠቀ፣ የተነቀነቀ፣ በእቅፎቻችሁም ተርፎ የሚፈስ መልካም መስፈሪያ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል፡፡ ለሌሎች ለመስፈር በምትጠቀሙበት በዚያው መስፈሪያ ለእናንተም ይሰፈርላችኋል፡፡"39ከዚያም ይህን ምሳሌ ነገራቸው፣ በኋላም፣ “አንድ ዕውር ሌላውን ዕውር ሊመራው ይችላልን? እንደዚያ ቢያደርግ፣ ሁለቱም ጉድጓድ ውስጥ ይገቡ የለምን?40ደቀመዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ነገር ግን አንድ ሰው ፈጽሞ ከተማረ እንደ መምህሩ ይሆናል፡፡41በወንድምህ ዓይን ያለውን ትንሽ ጉድፍ ለምን ትመለከታለህ? ለምንስ በራስህ ዓይን ያለውን ግንድ አትመለከትም? በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳትመለከት፣42ለወንድምህ፣ ‘ወንድሜ ሆይ፣ ዓይንህ ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? አንተ ግብዝ! በመጀመሪያ በዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፣ ከዘያም በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ፡፡43የተበላሸ ፍሬ የሚያፈራ መልካም ዛፍ የለምና፣ መልካም ፍሬም የሚያፈራ የተበላሸ ዛፍ የለም፡፡44እያንዳንዱ ዛፍ የሚታወቀው በሚያፈራው ፍሬ ነውና፤ ከእሾህ የበለስ ፍሬ አይለቀምም፣ ከቀጋ ቁጥቋጦም የወይን ፍሬ አይቆረጥም፡፡45መልካሙ ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ሀብት መልካም የሆነውን ነገር ያወጣል፤ ክፉም ሰው በልቡ ካከማቸው ክፉ ክምችት ክፉ የሆነውን ያወጣል፡፡ በልቡ ሞልቶ ከተረፈው በአፉ ይናገራልና፡፡46ለምንስ ‘ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ’ ትሉኛላችሁ? ለምናገራቸውስ ነገሮች ለምን አትታዘዙም?47ወደ እኔ የሚመጣና ለቃሌ የሚታዘዝ ምን እንደሚመስል እነግራችኋለሁ እነግራችኋለሁ፣48መሬቱን በጥልቁ ከቆፈረ በኋላ መሠረቱን በዓለት ላይ በማድረግ ቤቱን እንደሚገነባ ሰው ነው፡፡ ጎርፍ በመጣ ጊዜ የውሃው ሙላት ያን ቤት ገፋው፣ ሆኖም በሚገባ ተገንብቶ ነበርና አልነቀነቀውም፡፡49ነገር ግን ቃሌን ሰምቶ የማይታዘዘው ሰው ቤቱን ያለ መሠረት በመሬቱ አፈር ላይ እንደ ሠራው ሰው ነው፤ ጎርፉ በመጣ ጊዜ ቤቱን መታው፣ ወዲያውኑም ፈረሰ፣ ውድም ብሎም ጠፋ፡፡”
1ኢየሱስ ለሕዝቡ የሚናገረውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ፣ ወደ ቅፍርናሆም ገባ።2እጅግ የሚወደውና ሞት አፋፍ ላይ የደረሰ አገልጋይ የነበረው አንድ የመቶ አለቃ ነበረ።3ስለ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ መጥቶ አገልጋዩን ከመሞት እንዲያድንለት እንዲለምኑት የአይሁድ ሽማግሌዎችን ወደ እርሱ ላካቸው።4እነርሱ ወደ ኢየሱስ በቀረቡ ጊዜ፣ "ለእርሱ ይህን ልታደርግለት የተገባ ነው፣5ምክንያቱም ሕዝባችንን ይወዳል፣ ምኩራብ የሠራልንም እርሱ ነው" በማለት አጥብቀው ለመኑት።6ስለዚህ ኢየሱስ ዐብሮአቸው መንገዱን ቀጠለ። ነገር ግን ወደ ቤቱ ለመድረስ ጥቂት በቀረው ጊዜ፣ የመቶ አለቃው፣ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት ወዳጆቹን ወደ ኢየሱስ ላካቸው፤ “ጌታ ሆይ፣ አትድከም፣ ምክንያቱም አንተ ወደ ቤቴ ልትገባ የተገባሁ አይደለሁም፤7ከዚህ የተነሣ እኔም ራሴ ወደ አንተ ለመምጣት የምገባ አድርጌ እንኳ ራሴን አልቈጥረውም። ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር አገልጋዬ ይፈወሳል፤8እኔም ደግሞ ባለ ሥልጣን ነኝና፤ በእኔ ሥር ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን 'ሂድ' ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን 'ና' ስለው ይመጣል።9ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ፣ በመቶ አለቃው ተደንቀ፣ ይከተሉት ወደነበሩት ሰዎችም ዞር ብሎ፣ “በእስራኤልም እንኳ እንዲህ ያለ እምነት ያለው ሰው አላገኘሁም” አላቸው።10ከዚያም የተላኩት ሰዎች ወደ መቶ አለቃው ቤት ተመልሰው፣ አገልጋዩን ጤናማ ሆኖ አገኙት።11ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኢየሱስ ናይን ወደ ምትባል ከተማ እየተጓዘ ነበር። ከእርሱም ጋር ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብ ዐብረውት ይሄዱ ነበር።12ወደ ከተማይቱም በቀረበ ጊዜ፣ እነሆ፣ ለእናቱ ብቸኛ ልጅ የነበረ ሰው ሞቶ አስከሬኑን ሰዎች ተሸክመው እየሄዱ ነበር። የልጁ እናት መበለት ነበረች፤ በርከት ያሉ ለቀስተኞችም ተከትለዋት ነበር።13ጌታም ተመልክቷት እጅግ ዐዘነላትና፣ “አታልቅሺ” አላት።14ከዚያም ወደ ቃሬዛው ተጠግቶ ነካው ቃሬዛውን የተሸከሙትም ቆሙ። ኢየሱስ፣ “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ” አለ።15ወጣቱም ተነሥቶ መናገር ጀመረ፤ ከዚያም ኢየሱስ ልጁን ለእናትዮዋ ሰጣት።16ከዚያም ሁሉንም ፍርሀት ያዛቸው። “ታላቅ ነቢይ በመካከላችን ተነሥቶአል" "ደግሞ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጎበኝቶአል” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገኑ።17ይህ የኢየሱስ ዝና በመላው ይሁዳና በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተሰማ።18የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አወሩለት።19ከዚያም ዮሐንስ፣ “የምትመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ብለው እንዲጠይቁት ከእነርሱ ሁለቱን ወደ ኢየሱስ ላካቸው።20ሰዎቹም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ "'የምትመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌ እንጠብቅ?' ብለን እንድንጠይቅህ መጥምቁ ዮሐንስ ልኮናል" አሉ።21በዚያኑ ሰዓት ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ከተለያየ ደዌና በሽታ ፈወሰ። በአጋንንት የተያዙትን ነጻ አወጣ፣ ዐይነ ስውራንም ማየት እንዲችሉ አደረገ።22ኢየሱስ መልእክተኞቹን፣ “ወደ ዮሐንስ ተመልሳችሁ ሂዱና ያያችሁትንና የሰማችሁትን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ ዐይነ ስውራን ያያሉ፣ ሽባዎች ይራመዳሉ፣ ለምጻሞች ይነጻሉ፣ መስማት የተሳናቸው ይሰማሉ፣ ሙታን ይነሣሉ፣ ለድኾችም ወንጌል እየተሰበከ ነው።23በማደርጋቸው ነገሮች በእኔ ሳይሰናከል በእምነቱ የሚጸና ሰው የተመሰገነ ነው” አላቸው።24የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ ይላቸው ጀመር፣ “ምን ልታዩ ወደ በረሐ ወጣችሁ በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን?25ወይስ የወጣችሁት የሚያማምሩ ልብሶች የለበሱትን ለማየት ነውን? እነሆ፣ የሚያማምሩ ልብሶችን ለብሰው በድሎት የሚኖሩ ሰዎች የሚገኙት በአብያተ መንግሥታት ነው።26ልታዩ የወጣችሁት ግን ነቢይን ከሆነ፣ እንግዲያውስ ያያችሁት ነቢይን ብቻ ሳይሆን ከነቢያትም የበለጠውን ነው።27ስለ እርሱ፣ ‘እነሆ፣ በፊታችሁ መንገድን የሚጠርግ መልእክተኛዬን እልካለሁ’ ተብሎ ተጽፏል።28እላችኋለሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ ቢሆንም በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉም የሚያንሰው ይበልጠዋል።29ይህን በሰሙ ጊዜ ቀራጮች እንኳ ሳይቀሩ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔር ጻድቅ እንደ ሆነ ተናገሩ፤ ምክንያቱም እነርሱን ያጠመቃቸው ዮሐንስ ነበር።30በዮሐንስ ያልተጠመቁት ፈሪሳውያንና የአይሁድ የሕግ ዐዋቂዎች ግን በራሳቸው ፈቃድ የእግዚአብሔርን ጥበብ ተቃወሙ።31እንግዲያውስ የዚህን ትውልድ ሰዎች ከምን ጋር አመሳስላቸዋለሁ? ምንስ ይመስላሉ?32እርስ በርሳቸው በገበያ እየተጠራሩ፥ ‘እንቢልታ ነፋንላችሁ እናንተም አልዘፈናችሁም፣ ሙሾ አወጣንላችሁ እናንተም አላለቀሳችሁም’ እንደሚባባሉ ልጆች ናቸው።33መጥምቁ ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላና ወይን ጠጅ ሳይጠጣ ቢመጣ፣ ‘ጋኔን አለበት’ አላችሁት፣34የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ ቢመጣ፦ ‘በላተኛና ጠጪ፣ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ!’ አላችሁት።35ጥበብ ግን በልጆቿ ሁሉ ትክክል እንደ ሆነች ታወቀች።36አንድ ፈሪሳዊም በቤቱ ዐብሮት እንዲመገብ ኢየሱስን ጋበዘው ኢየሱስ ግብዣውን ተቀብሎ ወደ ማዕዱ ቀረበ።37እነሆ፣ በዚያ ከተማ በመጥፎ ምግባሯ የታወቀች እንዲት ሴት ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት ተጋብዞ በማዕድ እንደ ተቀመጠ ተረድታ የአልባስጥሮስ ሽቱ ብልቃጥ ይዛ ወደ ቤቱ ገባችና38ከኢየሱስ በስተኋላ ከእግሩ አጠገብ ቆማ ማልቀስ ጀመረች። ከዚያም በእንባዋ እግሩን ማራስና በፀጉሯም ማበስ ቀጠለች፣ እግሩንም ትስመው በሽቱም ትቀባው ነበር።39ኢየሱስን የጋበዘው ፈሪሳዊ ይህንን ባየ ጊዜ፣ "ይህ ሰው በእርግጥ ነቢይ ቢሆን ኖሮ እየነካችው ያለችው ሴት ምን ዓይነት ሴት እንደ ሆነች ባወቀም ነበር" ብሎ በልቡ ዐሰበ።40ኢየሱስም መልሶ ፈሪሳዊውን፣ “አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ፈሪሳዊውም፣ “መምህር ሆይ፣ ተናገር” አለው።41ኢየሱስ፣ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፣ አንደኛው የአምስት መቶ ዲናር ሌላኛው ደግሞ የሃምሳ ዲናር ዕዳ ነበረባቸው፤42የሚከፍሉት ስላልነበራቸው ሁለቱንም ዕዳቸውን ማራቸው። ስለዚህ ዕዳቸው ከተማረላቸው ከእነዚህ ከሁለቱ ማንኛቸው አብዳሪውን የበለጠ የሚወደው ይመስልሃል? አለው።43ስምዖንም መልሶ፣ “ብዙ የተተወለቱ ይመስለኛል” አለው። ኢየሱስ፣ “በትክክል መልሰሃል” አለው።44ኢየሱስም ወደ ሴትዮይቱ ዞር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፣ “ይህችን ሴት ትመለከታታለህ? እኔ ወደ ቤትህ ገብቼ ለእግሬ ውሃ እንኳን አላቀረብህልኝም፣ እርሷ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች፣ በፀጉሯም አበሰችው፤45አንተ አልሳምኸኝም፣ እርሷ ግን ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም።46አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፣ እርሷ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች፣47ስለዚህ ለበዛው ኃጢአቷ ብዙ ምሕረትን አግኝታለችና አብዝታ ወዳለች። ጥቂት ኃጢአቱ ይቅር የተባለለት ግን ጥቂት ይወዳል” አለው።48ከዚያም ወደ ሴቱቱ ዞር ብሎ፣ “ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል” አላት።49በዚያም ተቀምጠው የነበሩት እርስ በርሳቸው፣ “ኃጢአትን ይቅር የሚል ይህ ማን ነው?” አሉ።50ከዚያም ኢየሱስ ሴቲቱን፣ “እምነትሽ አድኖሻል። በስላም ሂጂ” አላት።
1ከዚያ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ወንጌል እየሰበከና እያወጀ ወደ ልዩ ልዩ ከተሞችና መደሮች መጓዝ ጀመረ። በጒዞውም ወቅት ዐሥራ ሁለቱ፣2እንዲሁም ከርኩሳን መናፍስትና ከሕመማቸው የተፈወሱ አንዳንድ ሴቶች ዐብረውት ሄዱ፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት ማርያም፣3እንደ የሄሮድስ ቤተ መንግሥት አዛዥ የነበረው የኩዛ ሚስት የነበረችው ዮሐና፣ ሶስና ሌሎችም ብዙ ሴቶች ነበሩ፤ እነዚህ ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን በገንዘባቸው ያገለግሉ ነበር።4ከብዙ የተለያዩ ከተሞች የመጡትን ጨምሮ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰቡ ጊዜ፣ በምሳሌ ተጠቅሞ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፤5“አንድ ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ።እንደ ዘራም አንዳንዱ ዘር በመንገድ ዳር ወደቀና ተረገጠ፣ የሰማይ ወፎችም መጥተው በሉት።6ሌላው ዘርም በጭንጫ መሬት ላይ ወደቀ፤ በበቀለም ጊዜ እርጥብ አፈር ስላልነበረው ወዲያው ደረቀ።7ሌላውም ዘር በእሾህ መካከል ወደቀ እሾሁም ከዘሩ ጋር ዐብሮት አደገና አነቀው።8ከዘሩ አንዳንዱ ግን በመልካም ዐፈር ላይ ወደቀ መቶ እጥፍ ፍሬም አፈራ።" ኢየሱስ ይህንን ከተናገረ በኋላ ጮኽ ብሎ፣ "ጆሮ ያለው ይስማ” አለ።9ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ይህ ምሳሌ ምን ማለት እንደ ሆነ ጠየቁት፤10ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር የማወቅ ዕድል ተሰጥቷችኋል፣ ለተቀሩት ሕዝብ ግን 'እያዩ ስለማያዩ፣ እየሰሙም ስለማያስተውሉ' የሚማሩት በምሳሌ ነው።11ትርጕም እንደዚህ ነው፣ ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።12በመንገድ ዳር የወደቁት ሰምተው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ የሰሙትን ቃል ከልባቸው የሚወሰድባቸው ናቸው።13በድንጋይ መካከል የወደቁትም ቃሉን በሰሙ ጊዜ በደስታ የሚቀበሉትና መስማት እንጂ፣ በቃሉ ሥር ስላልሰደዱ ለጊዜው አምነው ፈተና በመጣባቸው ጊዜ፣ እምነታቸውን የሚክዱ ናቸው።14በእሾኽ መካከል የወደቀው ዘር ቃሉን የሰሙ ሰዎች ሲሆኑ፣ በኑሮ ሂደታቸው ወቅት በምድራዊ ሕይወት ዐሳብና በባለጠግነት ምቾት የሚታነቁ በመሆናቸው ፍሬ ወደ ማፍራት የማይመጡ ናቸው።15ነገር ግን በመልካሙ ዐፈር ላይ የወደቁት በመልካምና በቅን ልብ ካደመጡ በኋላ ቃሉን አጥብቀው የሚይዙ በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።16እንግዲህ፣ አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ ጎድጓዳ ነገር ውስጥ ወይም ከአልጋ ሥር አያደርገውም። ከዚያ ይልቅ ሁሉም ሰው ብርሃኑን ማየት ይችል ዘንድ ከፍ ባለ ስፍራ ላይ ያስቀምጠዋል።17ምክንያቱም የሚታወቅ እንጂ የሚደበቅ፣ ታውቆ ወደ ብርሃን የሚወጣ እንጂ ምሥጢር የሚሆን ነገር የለም።18ስለዚህ እንዴት እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ፣ ምክንያቱም ላለው ሁሉ የበለጠ ይሰጠዋል፣ ከሌለው ደግሞ እንዳለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።"19ከዚያም የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ ወደ እርሱ መጡ፣ ነገር ግን ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ወደ እርሱ መቅረብ አልቻሉም።20ስለሆነም፣ ‘እናትህና ወንድሞችህ ሊያነጋግሩህ ፈልገው እየጠበቁህ ናቸው’ የሚል መልእክት አመጡለት።21ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ፣ “እናቴና ወንድሞቼ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት ናቸው” አላቸው።22ከዕለታት አንድ ቀን ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ሲሳፈሩ ኢየሱስ፣ "ሐይቁ ማዶ እንሻገር" አላቸው። ከዚያም እነርሱ መቅዘፍ ጀመሩ።23ነገር ግን እየቀዘፉ ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደውና በታላቅ ነፋስ የታጀበ ማዕበል በሐይቁ ላይ ስለተነሣ ጀልባቸው ውስጥ ውሃ መግባት ጀመረ'፤ታላቅ አደጋም በፊታቸው ተደቀነ።24ከዚያም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ መጥተው፣ "መምህር ሆይ፣ መምህር ሆይ፣ መሞታችን ነው" በማለት ቀሰቀሱት። እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ ነፋሱንና የሚናወጠውን ማዕበል ገሰጸ ጸጥ አደረጋቸው።25ከዚያም ኢየሱስ፣ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። ፍርሃት ይዟቸውና በጣም ተደንቀው እርስ በርሳቸው፣ “ነፋሳትንና ባሕርን የሚያዝ እነርሱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?" ተባባሉ።26ከገሊላ ባሕር በስተ ማዶ በሌላው አንጻር ወደ ነበረው ወደ ጌርጌሴኖን ክልል ደረሱ።27ኢየሱስ ከጀልባው ወርዶ ወደ ምድር በተሻገረ ጊዜ፣ አጋንንት የነበሩበት አንድ ሰው አገኘው። ይህ ሰው ለረጅም ጊዜ ልብስ ለብሶ አያውቅም፤ በመቃብር ስፍራ እንጂ፣ በቤትም ውስጥ አልኖረም።28ኢየሱስን ባየው ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅም ድምፅ፣ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! እኔ ከአንተ ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለው።29እንደዚህም ያለበት ምክንያት ብዙ ጊዜ ይይዘውና ያሠቃየው የነበረውን ርኩስ መንፈስ ከእርሱ እንዲወጣ ኢየሱስ አዞት ስለነበር ነው። ምንም እንኳ በብረት ሰንሰለት የታሰረና በቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገ ቢሆንም፣ እስራቱን ይበጥስ፣ በአጋንንቱም ግፊት ወደ በረሐ እየሄደ ይንከራተት ነበር።30ከዚያም ጊዜም ኢየሱስ፣ “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው፤ እርሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ነበርና ስሜ፣ "ጭፍራ" ነው ብሎ መለሰ።31በውስጡ የነበሩት አጋንንት ወደ ጥልቁ እንዲሄዱ እንዳያዛቸው መለመናቸውን ቀጠሉ።32በዚያም ብዙ ዐሳማዎች በኮረብታው ላይ ለግጦሽ ተሰማርተው ነበር፤ አጋንንቱም ወደ ዐሳማዎቹ ይገቡ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት። ኢየሱስ የለመኑትን እንዲያደርጉ ፈቀደላቸው።33ስለዚህ አጋንንቱ ከሰውዬው ወጥተው ዐሳማዎቹ ውስጥ ገቡ። ዐሣማዎቹን ከኮረብታው ተጣድፈው ቁልቁል ወረዱ፣ ወደ ሐይቁም ውስጥ ገብተው ሰጠሙ።34ዐሳማዎቹን ሲያሰማሩ የነበሩት ሰዎች ይህን በተመለከቱ ጊዜ ወደ ከተማውና ወደ ገጠሮች ሁሉ ሸሽተው በመሄድ ዜናውን አሠራጩ።35ስለዚህ ይህንን የሰሙት ሰዎች የሆነውን ለማየት ወጡ፤ ወደ ኢየሱስም በመጡ ጊዜ አጋንንት የወጡለትን ሰው አገኙት። ሰውዬውም ልብስ ለብሶ ወደ አእምሮውም ተመልሶ በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጦ ሲያዩት፣ ፍርሃት ያዛቸው።36ከዚያም የሆነውን ነገር ያዩ ሰዎች በአጋንንት ቁጥጥር ሥር የነበረው ሰው እንዴት እንደ ዳነ ለሌሎች ተናገሩ።37የጌርጌሴኖን ክልልና የዚያ አካባቢ ሰዎች ሁሉ ታላቅ ፍርሃት ይዟቸው ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ከእነርሱ እንዲሄድ ለመኑት፤ እርሱም ከዚያ ስፍራ ወደ መጣበት ለመመለስ ወደ ጀልባይቱ ገባ።38አጋንንት የወጡለት ሰው ዐብሮት ለመሄድ ኢየሱስን ለመነው።39ኢየሱስ ግን፣ “ወደ ቤተ ሰብህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ ተርክላቸው” ብሎ አሰናበተው። ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ታላላቅ ነገሮች በከተማው ሁሉ እየመሰከረ ጒዞውን ቀጠለ።40ሁሉም ይጠብቁት ነበርና ኢየሱስ ሲመለስ ሕዝቡ ተቀበሉት።41እነሆም ከምኲራብ መሪዎች አንዱ ኢያኢሮስ የተባለ ሰው መጣ፤ እርሱም በኢየሱስ እግር ላይ ወድቆ ወደ ቤቱ ይመጣ ዘንድ ለመነው።42ወደ ቤቱ እንዲመጣ የፈለገው ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆናት እንድያ ልጁ በሞት አፋፍ ላይ ስለነበርች ነው። ነገር ግን ወደዚያ እየሄደ በነበረበት ጊዜ፣ ብዙ ሕዝብ በመጨናነቅ ይጋፉት ነበር።43በዚያም ለዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረች፣ ገንዘቧን ሁሉ ለሐኪሞች ብትከፍልም አንዳቸውም ያልፈወሷት አንዲት ሴት ነበረች።44እርሷ ከኢየሱስ በስተኋላ መጥታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የፈሳት የነበረው ደምም ወዲያው ቆመ።45ኢየሱስ፣ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም አልነካንህም ብለው በተናገሩ ጊዜ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ሕዝቡ እኮ እየገፋፉህና እያጨናነቁህ ነው” አለው።46ኢየሱስ ግን፣ “ከእኔ ኅይል እንደ ወጣ ዐውቄአለሁና አንድ ሰው ነክቶኛል” አለ።47ሴቲቱ ያደረገችውን መደበቅ እንዳልቻለች ባስተዋለች ጊዜ፣ ሴቲቱ እየተንቀጠቀጠች መጣችና በኢየሱስ እግር ሥር ወድቃ በሰዎች ሁሉ ፊት እርሱን ለምን እንደነካችውና እንዴት ወዲያው እንደ ተፈወሰች ተናገረች። ከዚያም ኢየሱስ ሴቲቱን፥48“ልጄ ሆይ እምነትሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ” አላት።49እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ከምኲራብ አለቃው ቤት አንድ ሰው መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች። መምህሩን አታድክመው” አለ።50ኢየሱስ ግን ይህን በሰማ ጊዜ፣ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ፣ እርሷም ትድናለች” አለው።51ከዚያም እርሱ ወደዚያ ቤት በመጣ ጊዜ፣ ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስ፣ ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና ከእናትዋ በስተቀር ማንም ዐብሮት እንዲገባ አልፈቀደም።52በዚያ ስፍራ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ያለቅሱ ዋይ ዋይም ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ ልጅትዋ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አለ።53እነርሱ ግን መሞቷን ዐውቀው ስለ ነበር፣ በንቀት ሳቁበት።54እርሱ ግን የልጅቱን እጅ ይዞ፣ “አንቺ ልጅ ተነሽ” አላት።55ነፍስዋም ተመለሰች፣ ወዲያውኑም ብድግ አለች። እርሱም የምትበላው እንዲሰጧት አዘዘ።56ወላጆቿም ተደነቁ፤ እርሱ ግን ስለሆነው ነገር ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።
1ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይና በሽታዎችን የመፈወስ ሥልጣን ሰጣቸው።2የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩና በሽተኞችን እንዲፈውሱ ላካቸው።3እንዲህም አላቸው፤ “ለጒዞአችሁ በትርም ቢሆን፣ የገንዘብም ቦርሳ ቢሆን፣ ስንቅም ቢሆን፣ ገንዘብ ወይም ቅያሬ ልብስ፣ ምንም ነገር አትያዙ።4ከዚያ ስፍራ እስከምትወጡ በገባችሁበት ቤት በዚያ ቆዩ።5“የማይቀበሏችሁ ቢኖሩ ከዚያ ከተማ ስትወጡ ምስክር እንዲሆንባቸው ከእግሮቻችሁ ጫማ ላይ አቧራውን አራግፉ።”6ከዚያም እነርሱ ከዚያ ተነሥተው የምሥራቹን ወንጌል እየሰበኩ፣ በሄዱባቸውም ስፍራዎች ሁሉ በሽተኞችን እየፈወሱ ያልፉ ነበር።7የአራተኛው ክፍል ገዢ ሄሮድስ እየተደረገ የነበረውን ሁሉ በሰማ ጊዜ፣ በጣም ተሸበረ፣ ምክንያቱም ‘አንዳንዶቹ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቷል፤8በሌሎች ዘንድ ደግሞ ኤልያስ ተገልጧል፤ እንደ ገና ሌሎች ከጥንት ነቢያት አንዱ ሕያው ሆኖ ተነሥቷል’ ይሉ ነበር።9ሄሮድስም “የዮሐንስን ራስ እኔ አስቈርጬዋለሁ፣ እንዲህ ያለ ነገር የምሰማበት ይህ ማን ነው?” አለ። ሄሮድስም ኢየሱስን ለማየት ጥረት ያደርግ ነበር።10የተላኩት በተመለሱ ጊዜ፣ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት። ኢየሱስ ራሱ ሐዋርያቱን አስከትሎ ቤተ ሳይዳ ወደምትባል ከተማ ሄደ።11ነገር ግን፣ ሕዝቡ ስለዚህ ጉዳይ ሰሙና ተከተሉት፣ እርሱም ተቀብሏቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገራቸው፣ መፈወሰ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው።12ቀኑ ወደ መገባደድ ተቃረበ፣ ዐሥራ ሁለቱም ወደ እርሱ መጡና “ያለንበት ቦታ ምንም የሌለበት ምድረ በዳ በመሆኑ ሕዝቡ በአካባቢው ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች ሄደው ማረፊያ ቦታና ምግብ እንዲያገኙ አሰናብታቸው” አሉት።13እርሱ ግን፣ “የሚበሉትን እናንተ ስጧቸው” አላቸው። እነርሱም፣ “ወጣ ብለን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን በስተቀር አሁን ያለን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዐሣ የበለጠ አይደለም” አሉት።14በዚያ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ። እርሱም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ሃምሳ ሃምሳ ሆነው በቡድን እንዲቀመጡ አድርጓቸው” አላቸው።15ስለዚህ እርሱ እንዳላቸው አደረጉ፣ ሕዝቡም ሁሉ ተቀመጡ።16እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዐሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ ከተመለከተ በኋላ ባርኮ፣ ቈርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው።17ሁሉም በልተው ጠገቡ፣ የተራረፈውም የምግብ ፍርፋሪ ተሰበሰበና ዐሥራ ሁለት ቅርጫት ሙሉ ሆነ።18ኢየሱስ ብቻውን ይጸልይ በነበረበት አንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፣ “ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ነው የሚናገሩት?” ብሎ ጠየቃቸው።19እነርሱም፣ “አጥማቂው ዮሐንስ ፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ፣ እንደ ገና ሌሎች ጥንት ከነበሩት ነቢያት አንዱ ከሙታን ተነሥቶ ነው ይላሉ” አሉት።20“እናንተ ግን እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስ፣ “አንተ ከእግዚአብሔር የመጣህ ክርስቶስ ነህ” ብሎ መለሰ።21ነገር ግን ኢየሱስ ይህን ለማንም እንዳይነግሩ በማስጠንቀቅ አዘዛቸው።22በተጨማሪም የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበል እንደሚገባው በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በሕግ መምሕራን ተቀባይነት እንደማያገኝ፣ እንደሚሞትና በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚነሣ በቅድሚያ አስታወቃቸው።23ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ "እኔን መከተል የሚፈልግ ራሱን ይካድ ዕለት ዕለትም መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ።24ሕይወቱን ሊያድን ጥረት የሚያደርግ ሰው ካለ ያጠፋታል፣ ስለ እኔ ብሎ ሕይወቱን የሚጥል ደግሞ ያድናታል።25አንድ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ የራሱን ሕይወት ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል?26በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅ በራሱ፣ በአባቱ፣ እንዲሁም በቅዱሳን መላእክቱ ክብር በሚመጣበት ጊዜ ያፍርበታል።27እኔ ግን በእውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆማችሁት መካከል አንዳንዶቻችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት እስከምታዩ ድረስ ሞትን አትቀምሱም።28ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ገደማ በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን፣ እንዲሁም ያዕቆብን ይዞ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ።29እየጸለየም ሳለ የፊቱ መልክ ተለወጠ ልብሱም በጣም ከመንጣቱ የተነሣ አንፀባረቀ።30እነሆ፣ ሁለት ሰዎች ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር!31እነርሱም በክብር የተገለጡት ሙሴና ኤልያስ ነበሩ። በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ከዚህ ሕይወት ስለ መለየቱ ይነጋገሩ ነበር።32ጴጥሮስና ዐብረውት የነበሩት እንቅልፍ ከብዶባቸው ነበር። ሙሉ በሙሉ በነቁ ጊዜ ግን የኢየሱስን ክብርና ዐብረውት የነበሩትን ሁለቱን ሰዎች አዩ።33እነርሱ ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ለእኛ በዚህ መሆን መልካም ነው፣ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ደግሞ ለኤልያስ ሦስት ዳሶችን ልንሠራ ይገባናል” አለው። ስለ ምን እየተናገረ እንደ ነበረ አላስተዋለም።34ከዚያም እርሱ ይህን እየተናገረ ሳለ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ በዙሪያቸው ከነበረው ደመና የተነሣ ፈሩ።35ከደመናው ውስጥ፣ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።36የድምፁ መሰማት ባበቃ ጊዜ፣ ኢየሱስ ብቻውን ነበረ። እነርሱም ዝም አሉ፤ በነዚያ ቀናት ስላዩአቸው ስለ እነዚያ ነገሮች ምንም ነገር ለማንም አልተናገሩም።37ከተራራው በወረዱ ማግስት ብዙ ሕዝብ ተሰብስበው ወደ እርሱ መጡ።38እነሆም፣ ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው፣ “መምህር ሆይ፣ ብቸኛ የሆነውን አንድ ልጄን ትመለከትልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።39ክፉ መንፈስ በላዩ ሲመጣበት በድንገት ይጮኻል፣ እየጣለ ያንፈራግጠዋል፤ አረፋም በአፉ ይደፍቃል። በጭንቅ ለቅቆት ይሄዳል፣ በሚሄድበት ጊዜ ክፉኛ ያቈስለዋል።40ክፉውን መንፈስ እንዲያወጡለት ደቀ መዛሙርትህን ለመንኋቸው፣ እነርሱ ግን አልቻሉም” በማለት ጮኸ።41ኢየሱስ እንደዚህ በማለት መልስ ሰጠ፣ “ክፉና ጠማማ ትውልድ፣ ከእናንተ ጋር የምኖረውና የምታገሣችሁ እስክ መቼ ነው? ልጅህን ወደዚህ አምጣው።”42ልጁ እየመጣ ሳለ ጋኔኑ ጣለው፣ እጅግም አንፈራገጠው። ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሠጸውና ልጁን ፈወሰው፣ ለአባቱም መልሶ ሰጠው።43ሁሉም በእግዚአብሔር ታላቅነት ተደነቁ። ነገር ግን ሁሉም እርሱ ባደረጋቸው ነገሮች ሁሉ እየተደነቁ ሳሉ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣44"የነገርኋችሁን እነዚህን ነገሮች በጥልቀት አስተውሉ፤ ምክንያቱም የሰውን ልጅ በሰዎች እጅ አሳልፈው ይሰጡታል" አላቸው።45ነገር ግን ተሰውሮባቸው ስለ ነበረ፣ ይህ አባባሉ ምን እንደ ሆነ ስላልተረዱት ሊገባቸው አልቻለም። ስለዚያ አባባል እርሱን መጠየቅ ፈሩ።46ከዚያም ከእነርሱ መካከል ከሁሉም እጅግ ታላቅ የሆነው ማን ነው የሚለውን ጥያቄ በሚመለከት ክርክር ተነሣ።47ኢየሱስ ግን በልባቸው ምን እያሰላሰሉ እንደ ነበሩ ባወቀ ጊዜ፣ አንድ ትንሽ ልጅ ይዞ በአጠገቡ አቆመው፣ እንዲህም አላቸው፤48"እንደዚህ ያለውን ሕፃን በስሜ የሚቀበል፣ እኔን ይቀበላል። እኔን የሚቀበል ከሆነ ደግሞ የላከኝን ይቀበላል። ስለሆነም፣ በመካከላችሁ ከሁላችሁም የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና።”49ዮሐንስ መልሶ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፣ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፣ ከእኛ ጋር ስላልሆነ ከለከልነው።"50ኢየሱስ ግን፣ “አትከልክሉት፣ ምክንያቱም የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነው” አላቸው።51ወደ ሰማይ የሚሄድበት ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ።52ከእርሱ ቀደም ብለው እንዲሄዱ መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ሊያዘጋጁለት ዘንድ ወደ ሳምራውያን መንደር ገቡ።53ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አንቅቶ ስለ ነበር፣ በዚያ የነበሩት ሕዝብ አልተቀበሉትም።54ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ባዩ ጊዜ፣ “ጌታ ሆይ፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝ ትወዳለህን?” አሉት።55እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሰጻቸው።56ከዚያም ወደ ሌላ መንደር ሄዱ።57እየሄዱ ሳሉም አንድ ሰው፣ “ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው።58ኢየሱስ፣ “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፣ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት መጠለያ የለውም” አለው።59ከዚያም ለሌላውን ሰው፣ “ተከተለኝ” አለው። ሰውዬው ግን፣ “ጌታ ሆይ፣ በቅድሚያ እንድሄድና አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው።60እርሱ ግን፣ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፣ አንተ ግን በየስፍራው ሁሉ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት አውጅ” አለው።61ሌላ ሰው ደግሞ፣ “ጌታ ሆይ፣ እከተልሃለሁ ነገር ግን በቅድሚያ የቤተ ሰቤን አባላት እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለው።62ኢየሱስ ግን፣ “ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም” አለው።
1ከዚህ በኋላ ጌታ፣ ሌሎች ሰባ ሰዎችን ሾመ፤ እርሱ ራሱ ሊሄድባቸው ወዳሰባቸው ከተማዎችና ስፍራዎች ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው፤2እንዲህም አላቸው፣ "መከሩ ብዙ ነው፣ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ወደ መከሩ ሠራተኞችን እንዲክ የመከሩን ጌታ በአስቸኳይ ለምኑት።3እንግዲህ ሂዱ፣ እነሆ፣ በተኲላዎች መካከል እንደ በጎች እልካችኋለሁ፡፡4ለመንገዳችሁ ምንም አትያዙ፤ የገንዘብ ቦርሳም ቢሆን የመንገደኛ ሻንጣም ቢሆን፣ ጫማም ቢሆን አትያዙ፣ በመንገድም ላይ ለማንም ሰላምታ አትስጡ፡፡5ወደ ማንኛውም ሰው ቤት ስትገቡ፣ በቅድሚያ 'ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን' በሉ፡፡6በዚያ ቤት ያለው ሰው የሰላም ሰው ከሆነ ሰላማችሁ ያርፍበታል፣ የሰላም ሰው ካልሆነ ደግሞ ሰላማችሁ ይመለስላችኋል፡፡7ያቀረቡላችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በገባችሁበት በዚያው ቤት ቆዩ፣ ምክንያቱም ሠራተኛ ደመወዙን ማግኘት ይገባዋል፡፡ ከቤት ወደ ቤት ግን አትዘዋወሩ፡፡8ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡና እነርሱም ሲቀበሏችሁ፣ ያቀረቡላችሁን ብሉ፡፡9በዚያም ያሉትን ሕመምተኞች ፈውሱ፣ 'የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀርባለች' ብላችሁም ንገሩአቸው፡፡10ነገር ግን ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡ እነርሱ ባይቀበሏችሁ፣ ወደ ጐዳናዎቻቸው ውጡና፣11'በጫማችን ላይ የተጣበቀውን የከተማችሁን አቧራ እንኳ በእናንተ ላይ ምስክር ይሆንባችሁ ዘንድ እናራግፈዋለን! የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ ቀረበ ግን ይህንን እወቁ' በሏቸው፡፡12እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ይቀልላቸዋል፡፡13ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ ዘንድ የተደረጉት ታላላቅ ታምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ የሐዘን ልብስ ለብሰውና ራሳቸውን አዋርደው ከረጅም ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር፡፡14ነገር ግን በፍርድ ወቅት ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።15አንቺስ ቅፍርናሆም፣ እስከ ሰማይ ከፍ እንዳልሽ ታስቢ ይሆን? እንደዚያ አታስቢ፣ እስከ ሲዖል ድረስ ትወርጃለሽ።16እናንተን የሚሰማችሁ እኔን ይሰማኛል፣ እናንተንም የማይቀበል እኔን አይቀበለኝም፣ እኔን የማይቀበል ደግሞ የላከኝን አይቀበልም፡፡17ሰባዎቹም ደስ እያላቸው ተመለሱና፣ ጌታ ሆይ፣ አጋንንት እንኳ በስምህ ታዘዙልን" አሉት፡፡18ኢየሱስ፣ "ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ19እነሆ፣ እባቦችንና ጊንጦችን እንድትረግጡ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፣ በምንም ዓይነት መንገድ ምንም አይጐዳችሁም፡፡20የሆነ ሆኖ መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚህ ብቻ ደስ አይበላችሁ፤ ነገር ግን ስማችሁ በሰማይ ስለ ተጻፈ የላቀ ደስታ ይሰማችሁ።"21በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እጅግ ሐሤት አደረገና፣ "የሰማይና የምድር ጌታ፣ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከሚያስተወሉ ሰውረህ እንደ ሕፃናት ለሆኑት ላልተማሩት ለእነዚህ ስለ ገለጽህላቸው አመሰግንሃለሁ፡፡ አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ በፊትህ ዘንድ መልካም ሆኖአልና።22ሁሉም ነገር ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፣ ከአባትም በቀር ልጁ ማን እንደ ሆነ የሚያውቅ የለም፣ አባትም ማን እንደ ሆነ ከልጁ ወይም ልጁ ሊገልጥለት ከፈለገው ሰው በቀር ማንም የሚያውቅ የለም።"23ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መለስ ብሎ፣ ለእነርሱ ብቻ፣ "እናንተ የምታዩትን የሚያዩ የተባረኩ ናቸው፡፡24ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ ያያችሁትን ለማየት ፈልገው ሳያዩ፣ እናንተም የሰማችሁትን ሊሰሙ ፈልገው ሳይሰሙ ቀርተዋል" አለ።25እነሆ፣ አንድ የአይሁድ የሕግ መምህር ሊፈትነው ፈልጎ ብድግ አለና፣ "መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይገባኛል?" በማለት ጠየቀው፡፡26ኢየሱስ፣ "በሕጉ የተጻፈው ምንድን ነው? የተረዳኸው እንዴት ነው?" አለው።27እርሱም፣ "ጌታ አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣ በሙሉ ኃይልህ፣ በሙሉ ዐሳብህም ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ" ብሎ መለሰ፡፡28ኢየሱስም፣ "በትክክል መልሰሃል፡፡ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ" አለው።29መምህሩ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወዶ፣ ኢየሱስን፣ "ባልንጀራዬ ማን ነው?" ብሎ ጠየቀው፡፡30ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፤ "አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ እየሄደ ሳለ ወንበዴዎች አግኝተውት ንብረቱን ዘረፉት፣ ደበደቡት፣ በሞት አፋፍ ላይ እያለም ጥለውት ሄዱ።31እንደ አጋጣሚ አንድ ካህን በዚያ መንገድ ሲሄድ ሰውዬውን ተመለከተውና በሌላ በኩል አድርጎ አልፎት ሄደ።32በተመሳሳይ ሁኔታ አንድ ሌዋዊም ወደዚያ ስፍራ መጥቶ በሌላ በኩል አድርጎ አልፎ ሄደ።33አንድ ሳምራዊ ግን እየተጓዘ ሳለ ሰውዬው ወደነበረበት መጣ። ባየውም ጊዜ በርኅራኄ ልቡ ተነካ።34ወደ እርሱም ጠጋ ብሎ መድኃኒት ካደረገለት በኋላ ቊስሉን በጨርቅ አሰረለት። እርሱ ይጓጓዝበት በነበረበትም አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ አንድ የእንግዶች ማረፊያ አመጣው፣ እንክብካቤም አደረገለት።35በማግስቱ ሁለት ዲናር ከኪሱ አውጥቶ ለእንግዳ ማረፊያው ኅላፊ ሰጠውና፣ "ተንከባከበው፣ ከዚህ በላይ ወጪ የሚያስወጣህ ከሆነ በምመለስበት ጊዜ ያወጣኸውን ትርፍ ወጪ እመልስልሃለሁ" አለው።36"ከእነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነለት የትኛው ይመስልሃል?" አለው።37መምህሩም፣ "የራራለቱ ነው" አለ። ኢየሱስም፣ "አንተም ሂድና ይህንኑ አድርግ" አለው።38እየተጓዙ ሳሉም ወደ አንድ መንደር ገባ፤ ማርታ የምትባልም አንዲት ሴት በቤትዋ ተቀበለችው"39እርሷም ማርያም የተባለች በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጣ ቃሉን የምትሰማ እኅት ነበረቻት"40ማርታ ግን ምግብ ለማዘጋጀት ባደረገችው ጥረት በጣም ውጥረት በዛባት። ወደ ኢየሱስም ዘንድ መጥታ፣ "ጌታ ሆይ፣ እኔ ብቻዬን ሥራ ስሠራ፣ እኅቴ እኔን ሳትረዳኝና ስትተወኝ አንተ ዝም ትላለህን? እንግዲያውስ እንድታግዘኝ ንገራት" አለችው።41ጌታ ግን፣ "ማርታ፣ ማርታ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፣42የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ነው፡፡ ማርያም በጣም ትክክል የሆነውን ምርጫ መርጣለች፣ ይህም ደግሞ ከእርሷ አይወሰድባትም›› ብሎ መለሰላት፡፡
1ኢየሱስ በአንድ ስፍራ መጸለዩን በፈጸመ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እኛን መጸለይ አስተምረን” አለ።2ኢየሱስም፣ “በምትጸልዩበት ጊዜ፣ 'በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ3የዕለት እንጀራችን በየዕለቱ ስጠን።4እኛን የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን። ወደ ፈተናም አታግባን በሉ'" አላቸው።5ኢየሱስም፣ “ከእናንተ ወዳጅ ያለው በእኩለ ሌሊት ውድ ወዳጁ ዘንድ በመሄድ6‘አንድ ወዳጄ ከሌላ ስፍራ ወደ እኔ መጥቶ የማስተናግድበት ምንም ስለሌለኝ፣ ሦስት እንጀራ አበድረኝ የማይለው ማነው’?7በቤት ውስጥ ያለው ወዳጁ ‘አታስቸግረኝ፤ በሩ ተዘግቶአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል። ለመነሣትና ለአንተ እንጀራ ለመስጠት አልችልም’ ይለዋልን?8ምንም እንኳን ወዳጁ ስለሆናችሁ ተነሥቶ እንጀራ ባይሰጣችሁም ያለ ዕረፍት ስለነዘነዛችሁት ብቻ ተነስቶ የምትፈልጉትን ያህል እንጀራ ይሰጣችኋል፤9ለምኑ ይሰጣችኋል፣ ፈልጉ ታገኛላችሁ፣ አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤10የሚለምን ሰው ሁሉ ይቀበላልና የሚፈልግም ሰው ያገኛል፣ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።11አባት ከሆናችሁት ከእናንተ ዓሣ ሲለምነው በዓሣ ፈንታ እባብ ወይም12ዕንቁላል ሲለምነው በዕንቁላሉ ፈንታ ጊንጥ የሚሰጠው ማን ነው?13ስለዚህ፣ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን የምታውቁ ከሆነ፣ በሰማይ የሚኖረው አባታችሁማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም?”14በኋላ ኢየሱስ ጋኔን እያወጣ ነበር፤ እርሱም ድዳ ነበር። ጋኔኑም በወጣ ጊዜ ድዳው ሰውዬ ተናገረ፤ ሕዝቡም ተደነቁ።15ነገር ግን ከሕዝቡ አንዳንዶቹ፣ “አጋንንትን የሚያወጣው የአጋንንት አለቃ በሆነው በብዔል ዜቡል ነው” አሉ።16ሌሎች ሊፈትኑት ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።17ኢየሱስ ግን ዐሳባቸውን አውቆ፣ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ይፈርሳል፤ እርስ በርሱ የሚለያይ ቤተ ሰብም ይወድቃል።18ሰይጣን ራሱን በራሱ የሚቃረን ከሆነ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? እናንተ ግን እኔን አጋንንትን የሚያወጣው በብዔል ዜቡል ነው ትሉኛላችሁ።19እኔ በቡዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ የእናንተ ተከታዮች የሚያወጧቸው በማን ነው? ከዚህም የተነሣ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።20እኔ ግን በእግዚአብሔር ኃይል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፣ እንግዲያውስ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥቷል።2121 በሚገባ የታጠቀ ብርቱ ሰው ቤቱን በሚጠብቅበት ጊዜ የቤቱ ንብረት ያለ ስጋት ይሆናል፤22ከእርሱ የበረታ ሰው ሲያሸንፈው ግን ያ ከእርሱ የበረታው ሰው መሣሪያውን ይቀማዋል፣ የቤቱንም ሀብት ይበዘብዛል።23ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፣ ከእኔ ጋርም የማይሰበስብ ይበትናል።24ርኩስ መንፈስ ከሰው በሚወጣበት ጊዜ ውሃ በሌለባቸው ስፍራዎች እየተዘዋወረ ማረፊያ ይፈልጋል። ምንም ማረፊያ ሲያጣ ‘ወደ ወጣሁበት ቤት እመለሳለሁ’ ይላል።25በሚመለስበት ጊዜ ያንን ቤት ተጠርጎና ጸድቶ ያገኘዋል።26ከዚያም ከእርሱ ይልቅ የከፉ ሰባት ሌሎችን ከእርሱ ጋር ይዞ ይሄድና ሁሉም በዚያ ሰው ውስጥ ገብተው ይኖራሉ። ከዚያም ያ ሰው በመጨረሻ የሚገጥመው ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ይሆናል።27ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በሚናገርበት ጊዜ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምጿን ከፍ አድርጋ፣ “አንተን የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች የተባረኩ ናቸው” አለችው።28እርሱ ግን፣ “የተባረኩትስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው” አለ።29የሕዝቡም ቊጥር እየጨመረ ሲሄድ፣ እንዲህ ማለት ጀመረ፣ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው። ምልክት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።30ልክ ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆነላቸው፣ የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናልና።31የደቡብ ንግሥት በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ትነሣና ትፈርድበታለች፣ ምክንያቱም የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ።3232 የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይነሡና ይፈርዱበታል፣ ምክንያቱም በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋል፤ እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።33አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ ብርሃኑ በማይታይበት ሰዋራ ስፍራ አያስቀምጠውም ወይም እንቅብ በላዩ ላይ አይደፋበትም። ነገር ግን ወደዚያ ቤት የሚገቡ እንዲታያቸው ከፍ ባለ ስፍራ ላይ ያስቀምጠዋል።34ዓይን የሰውነት መብራት ነው። ዓይንህ ጤናማ ከሆነ፣ መላ ሰውነትህ በብርሃን የተሞላ ይሆናል። ዓይንህ ሕመምተኛ ከሆነ ግን መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል።35ስለዚህ በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ።36እንግዲህ መላ ሰውነትህ ምንም ጨለማ የሌለበትና በብርሃን የተሞላ ከሆነ፣ በዚያን ጊዜ በሙሉ ብርሃኑ መብራት በአንተ ላይ እንደሚያበራ ያህል ይሆናል።37ንግግሩንም ሲያበቃ አንድ ፈሪሳዊ በቤቱ ምግብ ይመገብ ዘንድ ጋበዘው፤ ኢየሱስም ከፈሪሳዊው ቤት ሄዶ ለማዕድ ቀረበ።38ኢየሱስ ወደ ማዕድ ከመቅረቡ በፊት እጁን ባለመታጠቡ ፈሪሳዊው ተደነቀ።39ጌታ ግን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ፣ እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጸዳላችሁ፣ ውስጣችሁ ግን በስስትና በክፋት የተሞላ ነው።40እናንተ ማስተዋል የሌላችሁ ሰዎች፣ ውጪውን የፈጠረ የውስጡንስ አልፈጠረምን?41በውስጥ ያለውን ለድኾች ስጡ፣ ከዚያም ሁሉም ነገር ንጹሕ ይሆንላችኋል።42ነገር ግን እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ካመረታችሁት አዝሙድና ጤና አዳም ዐሥራት እያወጣችሁ ፍትሕንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ንቃችሁ ትተዋላችሁ። ሌላውን ነገር ማድረግ ሳትተዉ ፍትሕ ማድረግንና የእግዚአብሔርን ፍቅር መጠበቅ ያስፈልጋችኋል።43እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! በምኲራቦች የክብር መቀመጫዎችንና በገበያ ስፍራም የከበሬታ ሰላምታን ትወዳላችሁና።44ሰዎች የማን እንደሆኑ ሳያውቁ የሚረማመዱባቸው መቃብሮችን ትመስላላችሁና ወዮላችሁ!"45የአይሁድ የሕግ መምህር የነበረ አንድ ሰው፣ “መምህር ሆይ፣ በምትናገረው ነገር እኛንም እየሰደብኸን ነው” ብሎ መለሰለት።46ኢየሱስም እንዲህ አለ፣ “እናንተም የሕግ መምህራን፣ ለመሸከም የሚከብድ ሸክም በሰዎች ላይ ትጭናላችሁና፣ እናንተ ግን እነዚያን ሸክሞች በአንድ ጣታችሁ እንኳ አትነኳቸውምና ወዮላችሁ!47የገደሏቸው የእናንተ አባቶች ሆነው ሳለ እናንተ ግን የቀደሙ ነቢያትን መቃብር የምታንጹ ናችሁና ወዮላችሁ!።48ከዚህም የተነሣ አባቶቻችሁ በሠሩት ሥራ ምስክሮችና ከእነርሱም ጋር የምትስማሙ ናችሁና፣ ምክንያቱም እናንተ የመታሰቢያ መቃብራቸውን የምታንጹላቸው ነቢያት በእርግጥም በአባቶቻችሁ የተገደሉ ነበር።49በዚህ ምክንያት በእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ ተብሏል፣ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፣ እነርሱም አንዳንዶችን ያሳድዳሉ ይገድሉማል።50ስለሆነም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም ይህ ትውልድ ተጠያቂ ነው’።51ተጠያቂ የሚሆነውም ከአቤል ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ተገደለው እስከ ዘካርያስ ድረስ ለፈሰሰው የነቢያት ደም ነው። አዎን፣ ይህ ትውልድ ተጠያቂ ነው እላችኋለሁ።5252 እናንተ የአይሁድ የሕግ መምህራንም የዕውቀትን ቊልፍ ጨብጣችሁ ሳላችሁ እናንተ ራሳችሁ የማትገቡ፣ ሊገቡ ያሉትን እንዳይገቡ የምትከለክሉ ናችሁና ወዮላችሁ!53ኢየሱስ ከዚያ ለመሄድ እንደተነሣ፣ የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ተቃወሙት፣ ብዙ ጉዳዮችን አስመልክተው ከእርሱ ጋር ተከራረኩ።54ይህንም ያደረጉት ራሱ በተናገረው ቃል ሊያጠምዱት ፈልገው ስለነበረ ነው።
1ይህ እየሆነ ሳለ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ባሉበት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ይላቸው ጀመር። "ግብዝነት ከሆነው የፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ።"2ነገር ግን የሚገለጥ እንጂ ምንም የተሰወረ፣ የሚታወቅ እንጂ ምንም የተደበቀ ነገር የለም፡፡3በጨለማ የተናገራችሁት ማንኛውም ነገር በብርሃን የሚሰማ፣ በጓዳ በጆሮ የተናገራችሁትም በከፍተኛ መድረኮች ላይ የሚታወጅ ይሆናል፡፡4ለእናንተ ለወዳጆቼ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ሥጋን የሚገድሉትን ከዚያ በኋላ ግን ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ።5ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ እኔ እነግራችኋለሁ። ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም እሳት የመጣል ሥልጣን ያለውን እርሱን ፍሩት። አዎን፣ እርሱን ፍሩት ብዬ እላችኋለሁ።6ሁለት ድንቢጦች ዝቅተኛ ዋጋ ባላቸው ሳንቲሞች ይሸጡ የለምን? ሆኖም ከእነርሱ አንዷም እንኳ በእግዚአብሔር ፊት የተዘነጋች አይደለችም።7ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ፀጉሮች እንኳ የተቈጠሩ ናቸው። አትፍሩ፣ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።8በሰዎች ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል፤9በሰዎች ፊት የሚክደኝ ግን በእግዚአብሔር መላእክት ፊት የሚካድ ይሆናል ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡10በሰው ልጅ ላይ የተቃውሞ ንግግር የተናገረ ማንኛውም ሰው ይቅርታ ያገኛል፣ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ግን ይቅርታ አያገኝም፡፡11በምኲራቦች፣ በገዢዎችና በባለ ሥልጣኖች ፊት በሚያቀርቧችሁ ጊዜ ለቀረበባችሁ ክስ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ወይም ምን ማለት እንዳለባችሁ አትጨነቁ፤12መንፈስ ቅዱስ በዚያ ወቅት ምን መናገር እንደሚገባችሁ ይነግራችኋልና"13ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው፣ "መምህር ሆይ፣ ወንድሜ ርስት እንዲያካፍለኝ ንገረው" አለ።14ኢየሱስም፣ "አንተ ሰው፣ በእናንተ ላይ ዳኛ ወይም አደራዳሪ አድርጎ የሾመኝ ማን ነው?" አለው።15ለእነርሱም እንዲህ አላቸው፣ "ስግብግብነት ከሞላባቸው ምኞቶች ራሳችሁን ጠብቁ፣ ምክንያቱም የአንድ ሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት ላይ የተመሠረተ አይደለም"16ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ በማለት ምሳሌ ነገራቸው፤ "የአንድ ሰው ዕርሻ ከፍተኛ ምርት አስገኘለት፤17እርሱም፣ 'የተመረተውን እህል የማከማችበት የለኝምና ምን ማድረግ ይገባኛል?' ብሎ በልቡ ዐሰበ።18እንዲህም አለ፤ 'እንግዲያውስ እንደዚህ አደርጋለሁ፣ ጐተራዎቼን አፍርሼ በምትኩ ትልልቅ ጐተራዎችን እሠራለሁ፣ የተመረተውን እህልና ሌሎች ንብረቶቼንም ሁሉ አከማችባቸዋለሁ።19ነፍሴንም፣ "ነፍሴ ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ ብዙ ሀብት ተከማችቶልሻልና አትጨነቂ ብዪ፣ ጠጪ ደስም ይበልሽ እላታለሁ'" አለ።20እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለው፤ "አንተ ሞኝ ሰው፣ ዛሬ ማታ ከአንተ ልትወሰድ ነፍስህ ትፈለጋለች፣ ያዘጋጀሃቸው ነገሮች ታዲያ ለማን ይሆናሉ?"21በእግዚአብሔር ፊት ባለ ጠጋ ያልሆነ ለራሱ ግን ሀብትን የሚያከማች ሰው ይህን ይመስላል።22ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ምን እንበላለን ብላችሁ ስለ ሕይወታችሁ ወይም ምን እንለብሳለን ብላችሁ ስለ ሰውነታችሁ አትጨነቁ፡፡23ምክንያቱም ሕይወት ከምግብ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና፡፡24የማይዘሩትን ወይም የማያጭዱትን ቁራዎችን ተመልከቱ። መጋዘን ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። ከወፎች ይልቅ እናንተ ምን ያህል የላቀ ግምት ያላችሁ ናችሁ?25ከእናንተስ ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንዲት ቀን መጨመር የሚችል ማን ነው?26ታዲያ፣ ታናሽ የሆነውን ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ ስለ ሌላው ጉዳይ ለምን ትጨነቃላችሁ?27እንዴት እንደሚያድጉ አበቦችን ተመልከቱ፡፡ አይሠሩም ወይም አይፈትሉም። ሆኖም፣ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ ከእነዚህ እንደ አንዱ እንዳልለበሰ እኔ እነግራችኋለሁ።28ዛሬ ታይቶ ነገ ወደ ቆሻሻ ማከማቻ እንደሚጣለው ሣር በሜዳ ላይ ያለውን እግዚአብሔር እንደዚህ የሚያለብሰው ከሆነ፣ እምነታችሁ ትንሽ የሆነውን እናንተንማ ምን ያህል የበለጠ አያለብሳችሁም?29የምትበሉትንና የምትጠጡትን በመፈለግ አትጨነቁ።30በዓለም ውስጥ ባሉት አገሮች የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ እነዚህን ይፈልጋሉና፣ እናንተም እነዚህን እንደምትፈልጉ አባታችሁ ያውቃል።31ነገር ግን የእርሱን መንግሥት ፈልጉ፣ እነዚህም ነገሮች ይጨመሩላችኋል።32አንተ ታናሽ መንጋ፣ መንግሥትን ሊሰጥህ አባትህ እጅግ ደስ ይለዋልና አትፍራ።33ንብረቶቻችሁን ሽጡና ለድኾች ስጡ። በማያረጅ ከረጢት ሌቦች ሊቀርቡትና ብል ሊያጠፋው የማይቻለውን የማያልቀውን ሀብት በሰማይ አከማቹ።34ንብረታችሁ ባለበት ልባችሁም በዚያ ይሆናልና።35የሥራ ልብሳችሁን በአጭር ታጥቃችሁ በተጠንቀቅ ቁሙ፣ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤36በሚመጣበትና በሩን በሚያንኳኳበት ጊዜ ፈጥነው በሩን እንደሚከፍቱለት ጌታቸው ከሠርግ ሲመለስ እንደሚጠባበቁ ሰዎች ሁኑ።37በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው ሲጠብቁ ጌታቸው የሚያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች የተመሰገኑ ናቸው። በእርግጥ እላችኋለሁ፣ እርሱም የሥራ ልብሱን ለብሶ ምግብ ለመመገብ እንዲቀመጡ ያደርጋቸውና ወደ እነርሱ መጥቶ ያገለግላቸዋል።38ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት ወይም በዘጠኝ ሰዓትም እንኳ ቢሆን ሲመጣ ተዘጋጅተው የሚያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች የተመሰገኑ ናቸው።39በተጨማሪ ይህን እወቁ፤ የአንድ ቤት ጌታ ሌባ የሚመጣበትን ሰዓት የሚያውቅ ቢሆን ኖሮ የቤቱ በር እንዲሰበር ባልፈቀደም ነበር፡፡40እናንተም እንደዚሁ ዝግጁ ሁኑ፣ ምክንያቱም የሰው ልጅ የሚመጣበትን ሰዓት አታውቁም።"41ጴጥሮስ፣ "ጌታ ሆይ፣ ይህንን ምሳሌ የተናገርኸው ለእኛ ብቻ ነው ወይስ ለሌሎችም ሰዎች ሁሉ ነው?" አለ።42ጌታም እንዲህ አለ፣ "ታዲያ ለሌሎቹ አገልጋዮቹ የተመደበላቸውን ምግብ በትክክለኛው ጊዜ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው የሾመው ታማኝና ብልህ አስተዳዳሪ ማን ነው?43ጌታው በሚመጣበት ጊዜ ይህን ሲያደርግ የሚያገኘው ያ አገልጋይ የተመሰገነ ነው"44እውነት እላችኋለሁ፣ ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ይሾመዋል።45ያ አገልጋይ ግን በልቡ፣ 'የጌታዬ የመመለሻ ወቅት ይዘገያል' ቢልና ወንድና ሴት አገልጋዮችን መደብደብ፣ መብላትና መጠጣት እንዲሁም መስከር ቢጀምር፣46የዚያ አገልጋይ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላወቀው ሰዓት ይመጣል፣ ይቆራርጠዋል፣ ካልታመኑት ጋርም ይደባልቀዋል።47የጌታውን ፈቃድ ያወቀውና እንደ ፈቃዱ ሆኖ ለመገኘት ያልተዘጋጀውና ፈቃዱን ያልፈጸመው ያ አገልጋይ ከፍተኛ ቅጣት ይቀጣል።48ነገር ግን ያላወቀና ቅጣት የሚያስከትልበትን ተግባር የፈጸመ ጥቂት ይቀጣል። ብዙ ከተሰጠው ከማንኛውም ሰው ብዙ ይጠበቅበታል፣ ከፍ ያለ አደራ ከተሰጠውም፣ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል።49የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኰስ ነው፣ ሆኖም አሁኑኑ ተቀጣጥሎ ባገኘው ደስ ባለኝ ነበር።50ነገር ግን የምጠመቀው ጥምቀት አለኝ፣ ያንንም ጥምቀት እስከምፈጽመው ምን ያህል በጭንቀት እጠባበቀዋለሁ!51በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት እንደ መጣሁ ታስባላችሁን? እንደዚያ አታስቡ፣ እነግራችኋለሁ፣ የመጣሁት ይልቁኑ መለያየትን ላመጣ ነው፡፡52ከእንግዲህ ወዲህ በአንድ ቤት ውስጥ አምስት ሰዎች ቢኖሩ ሦስቱ በሁለቱ ላይ፣ ሁለቱም በሦስቱ ላይ የሚነሡና የሚለያዩ ይሆናሉ፡፡53አባት በልጅ ላይ ልጅም በአባት ላይ፤ አማት በምራት ላይ፣ ምራትም በአማት ላይ ይነሡና ይለያያሉ፡፡54ደግሞም ኢየሱስ ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፤ "በምዕራብ በኩል ደመና ሲያንጃብብ በምትመለከቱበት ጊዜ ወዲያውኑ፣ 'ሊያካፋ ነው' ትላላችሁ፣ እንዳላችሁትም ይሆናል።55የደቡብ ነፋስም ሲነፍስ፣ 'የሚያቃጥል ሙቀት ሊመጣ ነው' ትላላችሁ፣ እንዳላችሁትም ይሆናል።56እናንተ ግብዞች፣ የምድርንና የሰማይን መልክ እንዴት እንደምትተረጒሙ ታውቃላችሁ፣ ታዲያ የአሁኑን ወቅት እንዴት እንደምትተረጒሙ እንዴት አታውቁም?57እናንተ ራሳችሁ ትክክል የሆነውን ለምን አትፈርዱም?58ከባላጋራህ ጋር ወደ ከተማው አስተዳዳሪ በምትሄድበት ጊዜ፣ በመንገድ ላይ ቅራኔህን ለመፍታት ጥረት ማድረግ አለብህና፣ ይህን ባታደርግ ዳኛው ለዕለቱ ተረኛ መኰንን አሳልፎ ይሰጥሃል፣ ተረኛው መኰንንም ወደ ወንጀለኛ ማረፊያ ክፍል ያስገባሃል።59ዕዳህን ሙሉ በሙሉ እስካልከፈልህ ድረስ ከዚያ በፍጹም እንደማትወጣ እኔ እነግርሃለሁ።"
1በዚያን ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ የገሊላ ሰዎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ጲላጦስ ስለ ገደላቸውና ደማቸውንም ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀባቸው ሰዎች ነገሩት፡፡2ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ "እነዚያ የገሊላ ሰዎች ይህ ሁሉ የደረሰባቸው በዙሪያቸው ካሉት ከሌሎች የገሊላ ሰዎች ይልቅ ኅጢአተኞች ስለ ነበሩ ነውን?3አይደለም፤ እናንተም ንስሓ ካልገባችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ ።4ወይም በሰሊሆም ግንብ ተደርምሶባቸው የሞቱ ዐሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ይልቅ ኃጢአተኞች ስለ ነበሩ ነውን?5አይደለም፤ ሁላችሁም ንስሓ ባትገቡ ትጠፋላችሁ።"6ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ተናገረ፤ "አንድ ሰው በወይን አትክልት ቦታው የበለስ ዛፍ ተከለ፤ ፍሬዋንም ፈልጎ ወደ በለሲቱ መጣ፤ ነገር ግን ምንም ፍሬ አላገኘባትም።7እርሱም ለአትክልተኛው እንዲህ አለው፤ "ተመልከት! ሦስት ዓመት ሙሉ ፍሬ ፈልጌ ወደ በለሲቱ መጣሁ፤ ግን ምንም ፍሬ አላገኘሁባትም፡፡ ቊረጣት ስለምን መሬትን ታበላሻለች።"8አትክልተኛውም መልሰና እንዲህ አለ፣ "ለዚህ ዓመት ተዋት ዙሪያዋን ኮትኩቼ ማዳበሪያ አደርግላትና9በሚቀጥለው ዓመት ታፈራ ይሆናል፤ ባታፈራ ግን ቊረጣት።"10ኢየሱስም በሰንበት ቀን በአንዱ ምኲራብ እያስተማረ ነበር።11ለዐሥራ ስምንት ዓመት ርኩስ መንፈስ ያጐበጣት አንዲት ሴት በዚያ ነበረች፡፡ እርስዋም ከመጒበጧ የተነሣ ቀና ብላ መቆም አትችልም ነበር፡፡12ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፣ "ተነሺና ከበሽታሽ ተፈወሺ" አላት።13በእጁ ዳሰሳት፣ ወዲያውኑም ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም14አመሰገነች፡፡ የምኲራቡ አለቃ ግን በሰንበት በመፈወሷ ተቈጣና ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ "ከሳምንቱ ቀኖች ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ ሄዳችሁ በእነዚያ ቀኖች ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይሆንም አላቸው።"15ጌታ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ "እናንት ግብዞች! በሰንበት ቀን ከእናንተ መካከል በሬውን ወይም አህያውን ከታሰረበት በረት አወጥቶ ውኅ የማያጠጣው ማን ነው?16ይህች የአብርሃም ዘር የሆነች ለዐሥራ ስምንት ዓመት በሰይጣን ታስራ የኖረች ሴት በሰንበት ቀን ከበሽታዋ መፈታት አይገባትምን?"17ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በተናገረ ጊዜ፣ ይቃወሙት የነበሩ ሁሉ አፈሩ፣ ሕዝቡ ግን በተደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላቸው።18ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ "የእግዚአብሔር መንግሥት በምን ትመሰላለች? ከምንስ ጋር አነጸጽራታለሁ?19አንድ ሰው የሰናፍጭ ዘር በአትክልት ቦታው እንደተከላት ዛፍዋም አድጋ፣ ወፎች በቅርንጫፎችዋ ላይ ጎጆአቸውን ሠርተው ማረፊያ ያደረጉባት ዛፍ ትመሰላለች።"20እንደ ገናም እንዲህ አለ፤ "የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን ላነጻጽራት እችላለሁ?21የእግዚአብሔር መንግሥት አንዲት ሴት ሊጡን ሁሉ እስኪያቦካ ድረስ በሶሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ የሰወረችውን እርሾ ትመስላለች።"22ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ሳለ በየከተማውና በየገጠሩ እያስተማረ ያልፍ ነበር፡፡23አንድ ሰው፣ "ጌታ ሆይ፤ የሚድኑት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸውን?" ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤24"በጠባብዋ በር ለመግባት ታገሉ፣ ብዙዎች በዚህች በር ሊገቡ ይሞክራሉ ነገር ግን ሊገቡባት አይችሉም።25የቤቱ ጌታ በሩን ይዘጋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ፤ አንኳኩታችሁ፣ 'ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ እንድንገባ ክፈትልን' ትላላችሁ፡፡ እርሱ መልሶ 'ከየት ነው የመጣችሁት? እኔ አላውቃችሁም' ይላችኋል፡፡26ከዚያም እናንተ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ከአንተ ጋር አብረን በልተናል፤ አብረንም ጠጥተናል፤ በአደባባዮቻችንም አስተምረሃል' ትላላችሁ፡፡27እርሱ ግን እንዲህ ይመልሳል፤ 'ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም ፤ እናንተ ዐመፀኞች ከእኔ ራቁ እላችኋለሁ፡፡'28በእግዚአብሔር መንግሥት አብርሃምን፤ይስሐቅን፤ ያዕቆብን፤ ነቢያትንም በምታዩበት ጊዜ፤ እናንተ ግን በውጪ ትጣላላችሁ ከዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡29ብዙ ሰዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ፤ ከሰሜንና ከደቡብ መጥተው በእግዚአብሔር መንግሥት በማዕድ ተቀምጠው ይደሰታሉ፡፡30ይህንም እወቁ ኋለኞች ፊተኞች፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፡፡"31ከዚያ በኋላ፣ አንዳንድ ፈሪሳውያን ወደ እርሱ ቀርበው፣ "ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋልና ከዚህ ወጥተህ ወደ ሌላ ስፍራ ሂድ" አሉት፡፡32ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "ሂዱና ለዚያ ቀበሮ፣ 'ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ በሽታኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛም ቀን ሥራዬን እፈጽማለሁ' ይላል በሉት"33ይሁን እንጂ ዛሬና ነገ ከዚያም በኋላ ነቢይ ከኢየሩሳሌም በቀር በሌላ ስፍራ መሞት ስለሌበት ወደ ኢየሩሳሌም መንገዴን መቀጠል አለብኝ" አለ።34አንቺ ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድዪ፤ መልእክተኞችሽንም የምትወግሪ ነሽ፡፡ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፡፡ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም፡፡35እነሆ፣ ቤታችሁ ባዶ ሆኖ ቀርቶአል፡፡ እላችኋለሁ፣ እናንተ 'በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው' እስከምትሉ ድረስ አታዩኝም፡፡"
1በሰንበት ቀን ኢየሱስ ከፈሪሳዊያን አለቆች ወደ እንዱ ቤት እንጀራ ሊበላ በገባ ጊዜ፣ የሚያደርገውን ለማየት በቅርበት ይጠባበቁት ነበር፡፡2በዚያም በእጅና በእግር ዕብጠት የሚሠቃይ አንድ ሰው በኢየሱስ ፊት ነበር።3ኢየሱስ የአይሁድ ሕግ ዐዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን፣ "በሰንበት ቀን መፈወስ በሕግ ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም? "ብሎ ጠየቃቸው፡፡4እነርሱ ግን ዝም አሉ፡፡ ኢየሱስ የታመመውን ሰው ይዞ ፈወሰውና አሰናበተው፡፡5ቀጥሎም ኢየሱስ፣ "ከእናንተ ልጅ ወይም በሬ በሰንበት ቀን በጒድጓድ ውስጥ ቢወድቁ ወዲያውኑ የማያወጣቸው ማን ነው?" አላቸው።6እነርሱ ለእነዚህ ነገሮች መልስ መስጠት አልቻሉም፡፡7ኢየሱስ በግብዣ ቦታ የከበሬታ ወንበር ለመያዝ ሲሽቀዳደሙ በተመለከት ጊዜ እንዲህ በማለት አንድ ምሳሌ8ነገራቸው፤ "አንድ ሰው ወደ ሰርግ ግብዣ ቢጠራህ በመጀመሪያ በከበሬታ ቦታ አትቀመጥ፣ ምናልባት በዚያ ቦታ የሚቀመጥ ከአንተ ይልቅ ክብር የሚሰጠው ሰው ተጋብዞ ይሆናል፡፡9ሁለታችሁንም የጋበዛችሁ ሰው መጥቶ፣ 'ይህን ቦታ ለሌላ ሰው ልቀቅለት' ይልሃል፣ ከዚያም አንተ በሃፍረት ወደ ዝቅተኛ ቦታ ትሄዳለህ፡፡10ነገር ግን ወደ ግብዣ ስትጠራ በዝቅተኛ ቦታ ተቀመጥ፤ አንተን የጋበዘህ ሰው መጥቶ፤ ወዳጄ ሆይ፣ 'ወደ ከፍተኛ ስፍራ መጥተህ ተቀመጥ' ይልሃል፡፡ ከዚያም በተጋባዦቹ ፊት ሁሉ የተከበርህ ትሆናለህ፡፡11ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ዝቅ ዝቅ ይላል፡፡ ራሱንም ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ደግሞ ከፍ ከፍ ይላል፡፡12ኢየሱስ ደግሞ ጋባዡን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፤ "የምሳ ወይም የራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ መልሰው ይጋብዙኛል በማለት ብድራትን በመፈለግ ወዳጆችህን ወይም ወንድሞችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ሀብታም ጎረቤቶችህን አትጋብዝ፡፡13ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ የአካል ጒዳተኞችን፣ ሽባዎችንና ዐይነ ስውራንን ጥራ፡፡14ይህን በማድረግህ እነርሱ መልሰው ሊከፍሉህ ስለማይችሉ፣ የተባረክህ ትሆናለህ፡፡ በጻድቃን ትንሣኤ ቀንም እግዚአብሔር ብድራትህን ይከፍልሃል፡፡15በማዕድ ተቀምጠው ከነበሩት አንዱ ኢየሱስ የተናገራውን ሰምቶ፣ "በእግዚአብሔር መንግሥት ማዕድ ተቀምጦ እንጀራ የሚበላ ሰው የተባረከ ነው" አለው፡፡16ኢየሱስ ግን እንዲህ አለው፤ "አንድ ሰው ትልቅ የእራት ግብዣ አዘጋጅቶ ብዙ ሰዎችን ጋበዘ፡፡17የግበዣውም ዝግጅት በተጠናቀቀ ጊዜ ወደ እራት ግብዣው ወደ ተጋበዙት ሰዎች፣ 'ሁሉ ተዘጋጅቶአልና ወደ ግብዣው ኑ' ብሎ መልእክተኞችን ላከ፡፡18ነገር ግን እያንዳንዱ ተጋባዥ ከግብዣው ለመቅረት ምክንያት መደርደር ጀመረ፡፡ የመጀመሪያው፤ "መሬት ስለ ገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝባ ይቅርታ አድርግልኝ አለው፡፡19ሌላው፣ 'አምስት ጥማድ በሬዎችን ገዝቻለሁ፣ እነርሱን ልፈትናቸው ስለምሄድ፤ ይቅርታ አድርግልኝ' አለው፡፡20ሌላኛውም ሰው፣ 'ሚስት አግብቼ ሙሽራ ስልሆንሁ፣ ልመጣ አልችልም' አለ፡፡"21አገልጋዩ ለጌታው እነዚህን ነገሮች ነገረው። ከዚያም የቤቱ ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን 'ቶሎ ሄደህ በከተማው አውራ ጐዳናዎች ስላች መንገዶች ሁሉ ያሉ ድኾችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ዐይነ ስውራንን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደዚህ እንዲገቡ ጥራቸው' አለው።22አገልጋዩም አለው፤ 'ጌታ ሆይ፤ ያዘዝኸኝን ሁሉ አድርጌአለሁ፤ አሁንም ትርፍ ቦታ አለ።'23ጌታውም አገልጋዩን፣ 'ወደ ጎዳናዎችና ወደ ገጠር መንገዶች ውጣ፤ ቤቴም እንዲሞላ ያገኘሃቸውን ሁሉ እንዲገቡ ግድ በላቸው።24"እላችኋለሁ፣ በመጀመሪያ ከተጋበዙት ከእነዚያ ሰዎች መካከል አንድ ሰው እንኳ ከእራቴ አይቀምስም' አለው።25ሕዝብም ከኢየሱስ ጋር አብረው እየሄዱ ሳለ፣ እርሱ ዞር ብሎ እንዲህ አላቸው፤26"ማንም ወደ እኔ ሊመጣ የሚወድ አባቱንና እናቱን፣ ሚስቱንና ልጆቹን፣ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፣ እንዲያውም የራሱንም ሕይወት ስንኳ ስለ እኔ ብሎ ካልተወ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡27የራሱንም መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡"28ከእናንተ አንድ ሰው ሕንጻ መሥራት ቢፈልግ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በመጀመሪያ ተቀምጦ የማይተምን ማን ነው?29መሠረቱን ሠርቶ መደመደም ቢያቅተው በዚያ የሚያልፉት ሁሉ ፣30'ይህ ሰው መገንባት ጀምሮ መደምደም አቃተው እያሉ ይዘብቱበታል' ፡፡31ወይም አንድ ንጉሥ ከሌላ ንጉሥ ጋር ሊዋጋ በሚነሣበት ጊዜ ሃያ ሺህ ሰራዊት አስከትቶ የሚመጣበትን በአሥር ሺህ ሰራዊት ለመመከት ተቀምጦ የማይመክር ማን አለ?32መመከት የማይችል ከሆነ የሌላው ሰራዊት ገና ከሩቅ ሳለ መልእክተኛ ልኮ ዕርቅ ይጠይቃል፡፡33እንዲሁም ከእናንተ ማንም ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡34ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው ጣዕም ካጣ እንዴት ተመልሶ እንደ ገና የጨውነት ጣዕም ሊኖረው ይችላል?35ለመሬትም ሆነ ለማዳበሪያነት የማይጠቅም በመሆኑ ወደ ውጪ ይጣላል፡፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!"
1አንድ ቀንም ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ኅጢአተኞች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት መጡ።2ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን፣ "ይህ ሰው ኅጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር ይበላል" በማለት እርስ በርሳቸው አጒረመረሙ።3ኢየሱስ እንዲህ በማለት ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤4"ከእናንተ መካከል መቶ በጎች ያሉት ከዚያም ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋበትን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልግ የማይሄድ ማንነው?5ባገኘውም ጊዜ ከመደሰቱ የተነሣ በጫንቃው ይሸከመዋል።6ወደ ቤቱም ሲመለስ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፣ 'የጠፋብኝን በጌን አግኝቻለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል።7እንዲሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኅጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ እንደሚሆን እነግራችኋለሁ።8ወይስ ዐሥር የብር ሳንቲሞች ያላት ሴት ከዐሥሩ አንዱ ቢጠፋበት፣ እስከምታገኛው ድረስ መብራት አብርታ፣ ቤቷንም ሁሉ ጠርጋ በትጋት የማትፈልግ ሴት ማን ናት?9ባገኘችም ጊዜ ወዳጆቿንና ጎረቤቶቿን ሁሉ በአንድነት ጠርታ፣ 'የጠፋብኝን የብር ሳንቲሜን አግኝቻለሁና ኑ ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ትላቸዋለች።10"እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኅጢአተኛ በእግዚአብሔር መላአክት ፊት ታላቅ ደስታ እንደሚሆን እነግራችኋለሁ።"11ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ "አንድ ሰው ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤12ታናሹ ልጅም አባቱን፣ 'አባቴ ሆይ፣ በኋላ ከሀብትህ ከሚደርሰኝ ድርሻዬን ስጠኝ' አለው። አባቱም ሀብቱን ለሁለቱም ልጆቹ አካፈላቸው።13ከጥቂት ቀናትም በኋላ ታናሹ ልጅ ድርሻውን ይዞ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። እዚያም ገንዘቡን ሁሉ አላግባብ እየጨፈረ አባከነ።14እርሱም ያለውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ በዚያ አገር ጽኑ ራብ ሆነ። ከዚህም የተነሳ ችግር ላይ ወደቀ።15በዚያም አገር ዐሳማ ያረባ ወደ ነበረ ወደ አንዱ ሰው ዘንድ ሄዶ ተቀጠረ። ሰውዬው ዐሳማዎችን እንዲጠብቅለት አሰማራው።16እርሱም የሚበላውን ምግብ የሚሰጠው ስላልነበረ፣ ዐሳማዎቹ ከሚመገቡት መኖ ለመብላት ይፈልግ ነበር።17እርሱም አንድ ቀን ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ አለ፤ 'ምግብ የሚተርፋቸው የአባቴ ቤት ሠራተኞች ስንት ናቸው?18እኔ ግን እዚህ የምበላውን አጥቼ በራብ እሞታለሁ! ተነሥቼ ወደ አባቴ ቤት ልሂድና እንዲህ ልበለው፤ "አባቴ ሆይ፣ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት ኅጢአት አድርጌአለሁ።19ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ መጠራት አይገባኝም፤ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዱ ቊጠረኝ።"20ስለዚህ ታናሹ ልጅ ተነሥቶ ወደ አባቱ መጣ። ልጁ ገና ከሩቅ እየመጣ ሳለ፤ አባቱ አይቶ በርኅራኄ ሮጦ ተቀበለውና ዐቅፎ ሳመው።21ልጁ፣ 'አባቴ ሆይ፣ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት ኅጢአት አድርጌአለሁ። ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም' አለ።22አባቱም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ "ፈጥናችሁ ምርጡን ልብስ አምጡና አልብሱት፣ በጣቱ ቀለበት፣ በእግሩም ጫማ አድርጉለት።23ከዚያም የሰባውን ወይፈን አምጡና ዕረዱት። እንብላ፤ እንደሰት።24ይህ ልጄ ሞቶ ነበረ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶም ነበረ ተገኝቶአል።" ይደሰቱም ጀመር።25ታላቁ ልጅ በዕርሻ ቦታ ነበረ። ወደ ቤትም በተቃረበ ጊዜ፣ ሙዚቃና ጭፈራ ሰማ።26ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ፤ ምን እየሆነ እንዳለ ጠየቀው። አገልጋዩም፣ 'ወንድምህ መጥቶአል።27በደኅና ስለተመለሰም አባትህ የሰባውን ወይፈን አርዶለታል' አለው።28ታላቁ ልጅ ይህን ሰምቶ ተቈጣ፤ ወደ ቤትም ሊገባ አልፈለገም። አባቱም ወጥቶ እንዲገባ ለመነው።29እርሱ ግን አባቱን እንዲህ አለው፤ 'እነሆ፣ ይህን ሁሉ ዘመን እንደ ባሪያ አገለገልሁህ፤ ከትእዛዝህ አንዱንም ሳላጎድል ከአንተ ጋር ኖርሁ፤ ከባልንጀሮቼ ጋር እንድደሰት አንዲት የፍየል ግልገል እንኳ አልሰጠኸኝም፤30ነገር ግን ይህ ልጅህ ገንዘብህን ሁሉ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር አባክኖ ሲመጣ፣ የሰባውን ወይፈን አረድህለት።'31አባቱ እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ ያለኝ ሁሉ የአንተ ነው።32ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበር፤ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአል። ስለዚህ ልንበላና ልንደሰት ይገባናል።'
1ደግሞም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ "አንድ ሀብታም ሰው ነበረ፤ እርሱም በንብረቱ ሁሉ ላይ የሾመው አስተዳዳሪ ነበረው። ይህ አስተዳዳሪ ሀብተ ያባክናል ተብሎ ለሀብታሙ ተነገረው።2ስለዚህ ሀብታሙ ሰው አስተዳዳሪውን ጠርቶ፣ 'ይህ ስለ አንተ የምሰማው ነገር ምንድን ነው? ከዚህ በኋላ ለእኔ አስተዳዳሪ ልትሆን ስለማትችል ንብረቴን አስረክበኝ' አለው።3አስተዳዳሪው እንዲህ ብሎ አሰበ፤ 'እንግዲህ ጌታዬ ከአስተዳደር ሥራዬ ስለሚያሰናብተኝ፣ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ዓቅም ስለሌለኝ፣ ከእንግዲህ መሬት በመቈፈር ለመተዳደር አልችልም፤ መለመንም ያሳፍረኛል።4ከአስተዳዳሪነት ሥራዬ ስሰናበት፣ ሰዎች በቤታቸው እንዲቀበሉኝ ካሁኑ ምን እንደማደርግ ዐውቃለሁ።'5ከዚያም አስተዳዳሪው የጌታውን ተበዳሪዎች አንድ በአንድ ጠርቶ፣ የመጀመሪያውን ሰው 'ያለብህ ዕዳ ምን ያህል ነው?' ብሎ ጠየቀው።6እርሱም፣ 'አንድ መቶ ማድጋ ዘይት አለብኝ' አለ። አስተዳዳሪውም፣ 'በፈረምኸው ውል ላይ ዐምሳ ማድጋ ብለህ ጻፍ' አለው።7ሌላውንም፣ 'አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ?' ብሎ ጠየቀው። እርሱም፣ 'መቶ ኩንታል ስንዴ አለብኝ' አለ፤ በፈረምኸው ውል ላይ ሰማንያ ኩንታል ብለህ ጻፍ' አለው።8ጌታውም እምነት ያጎደው አስተዳዳሪ ያደረገውን ሰምቶ፤ በብልኅነቱ በመደነቅ እንዲህ አለ፤ 'በዚህ ዓለም እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች እግዚአብሔርን ከሚያውቁ ሰዎች ይልቅ በዓለማዊ ሥራቸው ብልኆች ናቸው።9ስለዚህ እላችኋለሁ፣ በዓለም ባላችሁ ሀብት ለራሳችሁ ወዳጆችን አፍሩበት፤ ምክንያቱም ሀብታችሁ ባለቀ ጊዜ በዘላለም ቤቶች ይቀበሉአችኋል።10በጥቂቱ የታመነ ሰው በብዙ ላይ የታመነ ይሆናል፤ በጥቂቱ የሚያምፅ በብዙም ዐመፀኛ ይሆናል።11ስለዚህ በዚህ ዓለም ሀብት ካልታመናችሁ እውነተኛውን ሀብትማ ማን አምኖ ይሰጣችኋል?12እንደዚሁም በሌላ ሰው ሀብት ካልታመናችሁ የራሳችሁን ማን ይሰጣችኋል?13ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይተዋል፤ ሌላውን ይወዳል፤ አለበለዚያም ለአንዱ ራሱን የሰጠ ይሆናል፤ሌላውን ደግሞ ይንቃል። ስለሆነም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።14ገንዘብን የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው፣ በኢየሱስ ላይ አፌዙበት።15እርሱም እንዲህ አላቸው፤ "እናንተ በሰው ፊት ራሳችሁን እንደ ጻድቃን ትቈጥራላችሁ፣ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል። በሰዎች ፊት የከበረ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።"16ሕግና ነቢያት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ሲሠራባቸው ኖረዋል። ከዚያ በኋላ ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል ተሰብኳል። ሰው ሁሉ ወደዚህ ለመግባት ይጋፋል።17ነገር ግን ከሕግ አንድ ነጥብ ዋጋ ከሚያጣ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል።18ማንም ሚስቱን ፈትቶ ሌላይቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ከባሏ የተፋታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል።19ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ "ሐምራዊና ቀጭን የሐር ልብስ የለበሰ በየቀኑም በምቾትና በደስታ የሚኖር ሀብታም ሰው ነበረ።20ሰውነቱ በቊስል የተወረረ አልዓዛር የሚባል ለማኝም በሀብታሙ ሰው ደጅ ይተኛ ነበር።21አልዓዛርም ከሀብታሙ ማዕድ የተረፈውን ፍርፋሪ ሊመገብ ይመኝ ነበር። ውሾች እንኳ እየመጡ ቊስሉን ይልሱ ነበር።22ከጊዜ በኋላ ለማኙ ሞተ፤መላእክትም መጥተው ወደ አብርሃም አጠገብ ወሰዱት። ሀብታሙም ሞተ፤ ተቀበረም።23ሀብታሙ በሲኦል እየተሠቃየ ሳለ፣ ቀና ብሎ አብርሃም አልዓዛርን በዕቅፉ ይዞት አየ።24እርሱም፣ 'አብርሃም አባት ሆይ፣ ራራልኝ በዚህ ነበልባል እየተሠቃየሁ ስለ ሆነ፣ አልዓዛር የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ እባክህ አልዓዛርን' ላክልኝ ብሎ ጮኸ።25አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ "ልጄ ሆይ፣ አንተ በምድር የሕይወት ዘመንህ መልካም ነገሮችን እንደተቀበልህና በደስታ እንደ ኖርህ፤ አልዓዛርም ክፉ ነገሮችን ሲቀበል እንደ ኖረ አስታውስ። አሁን ግን አልዓዛር እዚህ በምቾት ሲኖር፣ አንተ በሥቃይ ላይ ትገኛለህ።26ከሁሉ በላይ ከዚህ ወደ እናንተ ለማለፍ የሚፈልጉ እንዳይሻገሩ እዚያ ያሉትም ወደ እኛ እንዳይመጡ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል አለ።'27ሀብታሙ ሰው እንዲህ አለ፤ 'አባት ሆይ፣ እንግዲያውስ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤተ ሰብ እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤28ምክንያቱም አምስት ወንድሞች አሉኝና እነርሱ ወደዚህ ሥቃይ ቦታ እንዳይመጡ ያስጠንቅቃቸው።'29አብርሃም ግን፣ 'ወንድሞችህ ሙሴና ነቢያት አሏቸው፤ እነርሱንም ይስሙአቸው' ብሎ መለሰለት። ነገር ግን30ሀብታሙ ሰው፣ 'አብርሃም አባት ሆይ፣ እንደዚህ አይደለም፤ አንድ ሰው ከሙታን ተነሥቶ ሄዶ ቢነግራቸው ንስሓ ይገባሉ' አለ።31አብርሃም ግን ሙሴንና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ፣ አንድ ሰው ከሙታን ተነሥቶ ቢነግራቸው እንኳ አያምኑም' አለው።
1ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤ "ወደ ኅጢአት የሚያመሩ ነገሮች መምጣታቸው የማይቀር ነው። ነገር ግን ለኅጢአት ምክንያት ለሚሆነው ሰው ወዮለት።2በእምነት ደካማ ከሆኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከማስናከል ይልቅ ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል።3ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤ ተመልሶ ከተጸጸተ ይቅር በለው፤ በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህና ሰባት ጊዜ ተመላልሶ፤4'ስለ ሠራሁት ኅጢአት ተጸጸትሁ' እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ይቅር ልትለው ይገባል።"5ሐዋርያት ጌታን፣ "እምነት ጨምርልን" አሉት።6ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ "የሰናፍጭን ዘር ያህል እምነት ቢኖራችሁ፤ ይህን የሾላ ዛፍ፣ 'ከመሬት ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል' ብትሉት ይታዘዝላችኋል።7"በዕርሻ ወይም በበጎች እረኝነት የተሰማራ አገልጋይ ካላችሁ፣ አገልጋዩ ከሥራ ደክሞ ሲመለስ፣ ወዲያውኑ "ና ተቀመጥና እራትህን ብላ የሚለው ከእናንተ ማን ነው?"8"እራቴን አዘጋጅልኝ፤ እስክበላና እስክጠጣም ወገብህን ታጥቀህ ቆመህ አስተናግደኝ፤ ከዚያ በኋላ አንተ ደግሞ ትበላለህ ትጠጣለህም አይለውምን?"9ታዲያ አገልጋዩ የታዘዘውን ስለ ፈጸመ ጌታው ያመሰግነዋልን?10እንዲሁም እናንተም የታዘዛችሁትን ሁሉ ከፈጸማችሁ በኋላ የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ 'የፈጸምነውም የታዘዝንውን ግዳጃችንን ብቻ ነው' ማለት አለባችሁ።"11ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ሳለ፣ ሰማርያንና ገሊላን በሚያዋስነው መንገድ ያልፉ ነበር።12ኢየሱስም ወደ አንዲት መንደር በገባ ጊዜ ዐሥር ለምጻሞች አገኙት። እነርሱም ከእርሱ ርቀው ቆሙና13ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ "ኢየሱስ ሆይ፣ መምህር ሆይ፣ እባክህ ማረን" እያሉ ጮኹ።14ኢየሱስ ባያቸው ጊዜ፣ "ሂዱና ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ" አላቸው። እነርሱም እየሄዱ ሳሉ፣ ከለምጻቸው ነጹ።15ከእነርሱ አንዱ ከለምጹ መፈወሱን ባየ ጊዜ፣ ጮክ ብሎ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ።16በኢየሱስ እግር ሥር በግንባሩ ተደፍቶ አመሰገነው። እርሱም የሰማርያ ሰው ነበር።17ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፣ "ዐሥሩም ለምጻሞች ተፈውሰው አልነበረምን? ታዲያ ዘጠኙ የት አሉ?18ከዚህ ከባዕድ ሰው በቀር እግዚአብርሔን ለማመስገን ተመልሶ የመጣ ሌላ የለምን?"19ኢየሱስ ሰውየውን፣ "ተነሥና ሂድ እምነትህ አድኖሃል" አለው።20ፈሪሳውያን ኢየሱስን፣ "የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?" ብለው ለጠየቁት ጥያቄ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ "የእግዚአብሔር መንግሥት የምትታይ አይደለችም።" ወይም'እነሆ፣ እዚህ ናት'21ወይም 'እነሆ፣እዚያ ናት' የምትባል አይደለችም። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናት።"22ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤" ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትናፍቁበት ቀን ይመጣል። ነገር ግን አታዩትም።23ሰዎች፣ 'እነሆ፣ ክርስቶስ እዚህ ነው! ወይም እዚያ ነው!' ይሉአችኋል። ነገር ግን እነርሱን ሰምታችሁ አትፈልጉ፤ አትከተሉአቸውም።24መብረቅ በሰማይ ላይ ሲበርቅ ከዳር እስከ ዳር እንደሚያበራ፣ የሰው ልጅም በሚመጣበት ቀን እንዲሁ ይሆናል።25ነገር ግን ይህ ከመሆኑ በፊት የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል ይገባል። በዚህ ዘመን ሰዎችም ሊናቅና ሊነቀፍ ግድ ነው።26በኖኅ ዘመን እንደሆነው፣ በሰው ልጅ ዘመንም እንዲሁ ይሆናል።27ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡና ነበር። ነገር ግን በዚያን ጊዜ የጥፋት ውሃ መጥቶ ሁሉንም አጠፋቸው።28እንደዚሁም በሎጥ ዘመን ሰዎች ይበሉ፣ ይጠጡ፣ ይሸጡ ይገዙ፣ አትክልት ይተክሉና ቤትም ይሠሩ እንደ ነበረ ይሆናል።29ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን እሳትና ዲን ከሰማይ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋ።30የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀንም እንዲሁ ይሆናል።31በዚያ ቀን በቤቱ ጣሪያ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ ለመውሰድ አይውረድ። በዕርሻም ቦታ ያለ ሰው ወደ ቤቱ አይመለስ።32የሎጥን ሚስት አስታውሱአት። ሕይወቱን ሊያድን በራሱ መንገድ ለመሄድ የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል።33ነገር ግን ሕይወቱን ለጌታ አሳልፎ የሚሰጥ ሁሉ ያድናታል።34ይህን እላችሏለሁ፣ "በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ላይ ይተኛሉ።35ከእነርሱም አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። እንዲሁም ሁለት ሴቶች በአንድ ቦታ አብረው ይፈጫሉ፤36አንድዋ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች። ሁለት ሰዎች በአንድ ዕርሻ ቦታ ያርሳሉ፤አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።"37ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስን፦ 'ጌታ ሆይ፤ ወዴት?' ብለው ጠየቁት። እርሱም፦ "በድን ባለበት አሞራዎች ይሰበባሉ።" ሲል መለሰላቸው።
1ከዚያም ኢየሱስ ሳይታክቱ ዘወትር መጸለይ እንደሚገባቸው እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፤2"በአንድ ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ፤ ሰውንም የማያከብር አንድ ዳኛ ነበረ።3አንዲት ባል የሞተባት ሴትም በዚያ ከተማ ነበረች። እርስዋም ዘወትር ወደ ዳኛው እየመጣች፣ 'ከባላጋራዬ ጋር ስላለኝ ክርክር ፍረድልኝ' ትለው ነበር።4ዳኛውም ለረጅም ጊዜ ሊረዳት ፈቃደኛ አልነበረም። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ ብሎ አሰበ፤5'ምንም እንኳ እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላከብር፣ ይህች ባል የሞተባት ሴት አዘውትራ በመምጣት እንዳታታክተኝ እፈርድላታለሁ።' "6ከዚያም ጌታ እንዲህ አለ፤ "ቅንነት የሌለው ዳኛ የሚናገረውን ስሙ።7ታዲያ እግዚአብሔር ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹት ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?8ደግሞስ አይታገሣቸውምን? እላችኋለሁ በቶሎ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆን?"9ከዚያም ኢየሱስ ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚመኩና ሌሎችንም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ተናገረ፤10"ሁለት ሰዎች ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፤ አንዱ ፈሪሳዊ ሲሆን፣ ሌላው ቀራጭ ነበረ።11ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ በማለት ስለ ራሱ ጸለየ፤ 'እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፣ ዐመፀኛ፣ አመንዝራ፣ ወይም እንደዚህ ቀራጭ እንኳ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ።12በሳምንት ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፣ ከማገኘውም ሁሉ ዐሥራት አወጣለሁ።'13"ቀራጩ ግን ከርቀት ቆሞ ዐይኑን ወደ ሰማይ ሳያነሣ ደረቱን እየመታ፣ 'አምላኬ ሆይ፣ እኔን ኅጢአተኛውን ማረኝ!' ይል ነበር። እላችኋለሁ፣14"ከሌላው ይልቅ ጻድቅ ሆኖ ይህ ሰው ወደ ቤቱ ተመለሰ ፤ ምክንያቱም ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ከፍ ከፍ ይላል።"15እንዲዳስሳቸው ሰዎች ልጆቻቸውን ወደ እርሱ ያመጡ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ ይህን ባዩ ጊዜ ገሠጹአቸው።16ኢየሱስ ግን ሕፃናትን ወደ እርሱ ጠራቸውና፣ "ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተውአቸው አትከልክሏቸውም። የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።17እውነት እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን በየዋህነት ያልተቀበላት ፈጽሞ አይገባባትም" አለው።18ከአለቆች አንዱ ኢየሱስን፣ "ቸር መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባኛል?" ብሎ ጠየቀው።19ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ "ለምን ቸር ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስቀር ቸር የለም።20ትእዛዛትን ሁሉ ታውቃቸዋለህ፤ እነርሱም፣ 'አትግደል፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ እናትህንና አባትህን አክብር የሚሉ ናቸው።"21አለቃውም ፣ "እነዚህንማ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአቸዋለሁ።"22ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ፣ ሰውየውን፣ "እንግዲያውስ ገና አንድ ነገር ማድረግ ይቀርሃል፤ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድኾች ስጣቸው፤ በመንግሥተ ሰማያት ሀብት ይኖርሃል። ከዚያም በኋላ መጥተህ ተከተለኝ" አለው።23ሀብታሙ ሰውዬ ግን በጣም ባለጠጋ ስለ ነበረ፣ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ።24ከዚያም ኢየሱስ ሰውየው እንዳዘነ አይቶ፣ "ሀብታም ለሆኑ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት አስቸጋሪ ነው!25ሀብታም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" አለ።26የሰሙትም ሰዎች፣ "እንግዲያውስ ማን ሊድን ይችላል?" አሉ።27ኢየሱስ፣ "በሰው ዘንድ የማይቻል ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል" ብሎ መለሰ።28ጴጥሮስ፣ "እነሆ፣ እኛ ያለንን ሁሉ ትተን ተከትለንሃል" አለው።29ከዚያም ኢየሱስ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ብሎ ቤቱን ወይም ሚስቱን፣ ወይም ወንድሞቹን፣ ወይም ወላጆቹን ወይም ልጆቹን የተወ30በዚህ ዓለም ብዙ ዕጥፍ በሚመጣውም ዓለም የዘላለምን ሕይወት የማያገኝ ማንም የለም" አላቸው።31ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ከሰበሰበ በኋላ እንዲህ አላቸው፤ "አሁን ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ ስለ ሰው ልጅ በነቢያት አስቀድሞ የተነገሩት ሁሉ ይፈጸማሉ።32እርሱ ለአሕዛብ ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም ያላግጡበታል፤ ያዋርዱታል፤ ይተፉበታልም።33ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሣል።"34ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ ከተናገራቸው ነገሮች አንዱንም አልተረዱም። ይህ ቃልም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለተባሉትም ነገሮች ምንም አልተረዱም።35ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ በቀረበ ጊዜ፣ አንድ ዐይነ ስውር ምጽዋት እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር፤36ሕዝብ ሲያልፉ ሰምቶም እየሆነ የነበረውን ነገር ጠየቀ።37እነርሱም፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ በኩል እያለፈ መሆኑን ነገሩት።38ስለዚህ ዐይነ ስውሩ፣ "የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እባክህ ማረኝ" እያለ ጮኸ።39እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት፣ "ዝም በል!" ብለው ዐይነ ስውሩን ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን የበለጠ ከፍ አድርጎ፣ "የዳዊት ልጅ ሆይ፣ እባክህ ማረኝ" ብሎ ጮኸ።40ኢየሱስ ቆሞ ሰውየውን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዛቸው ። ከዚያም ዐይነ ስውሩ ወደ እርሱ በቀረበ ጊዜ፣ ኢየሱስ፣41"ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?" ብሎ ጠየቀው። "ጌታ ሆይ፣ ማየት እፈልጋለሁ" አለ።42ኢየሱስም፣ "እይ። እምነትህም አድኖሃል" አለው። ዐይነ ስውሩም ወዲያውኑ ማየት ቻለ።43እግዚአብሔርን እያመሰገነ ኢየሱስን ተከተለ። ሕዝቡ ሁሉ ይህን አይተው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
1ኢየሱስ ኢያሪኮ ከተማ ገብቶ እያለፈ ሳለ፣2ዘኬዎስ የሚባል አንድ የቀራጮች አለቃና ሀብታም ሰው ወዳለበት ስፍራ ደረሰ።3ዘኬዎስ ኢየሱስ የትኛው እንደ ሆነ ለማየት ይሞክር ነበር፣4ነገር ግን አጭር ስለ ነበረ፣ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ አሻግሮ ማየት አልቻለም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ በዚያ መንገድ ያልፍ ስለነበር፣ ከሕዝቡ ቀድሞ ሮጠና ሊያየው በእንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ።5ኢየሱስ ወደ ስፍራው በደረሰ ጊዜ፣ ቀና ብሎ ተመለከተና፣ “ዘኬዎስ ሆይ፣ ዛሬ ወደ ቤትህ መሄድ እፈልጋለሁና ቶሎ ውረድ” አለው።6ስለዚህ ዘኬዎስ በፍጥነት ወርዶ በደስታ በቤቱ ተቀበለው።7ይህን የተመለከቱት ሰዎች ሁሉ፣ “በኃጢአተኛ ሰው ቤት ገባ” በማለት አጒረመረሙ።8ዘኬዎስ ተነሥቶ ቆመና ጌታን፣ “ጌታ ሆይ፣ የሀብቴን ግማሽ ለድሆች እሰጣለሁ፣ ያታለልሁት ሰው ካለ፣ የወሰድሁበትን አራት ዕጥፍ እመልስለታለሁ” አለው።9ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ "ዛሬ ድነት ለዚህ ቤት መጥቷል። ምክንያቱም፣ እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነው።10የሰው ልጅ የመጣው የጠፉትን ሰዎች ሊፈልግና ሊያድን ነውና” አለ።11እነርሱ እነዚህን ነገሮች እንደ ሰሙ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየተቃረበ ስለ ነበር ሕዝቡ የእግዚአብሔር መንግሥት ወዲያው የሚገለጥ መሰላቸው።12ስለዚህ ኢየሱስ ንግግሩን በምሳሌ በመቀጠል እንዲህ አለ፣ “አንድ መኰንን የመንግሥት ሹመት ተቀብሎ ሊመጣ ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ነበር።13ከዚያም፣ ከአገልጋዮቹ ዐሥሩን ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና፣ “እስክመጣ ድረስ ይህን ነግዱበት” አላቸው።14ነገር ግን የአገሩ ሰዎች ይጠሉት ስለ ነበር፣ 'ይህ ሰው ተመልሶ በእኛ ላይ ገዥ እንዲሆን አንፈልግም' በማለት ተወካዮቻቸውን ከኋላው ላኩበት።15መኰንኑም ሹመቱን ተቀብሎ ሲመለስ፣ ነግደው ያተረፉትን ትርፍ ለመተሳሰብ ገንዘቡን የሰጣቸው አገልጋዮቹ እንዲጠሩለት አዘዘ።16የመጀመሪያው አገልጋይ ወደፊቱ ቀረበና፣ 'ጌታ ሆይ፣ ምናንህ ተጨማሪ ዐሥር ምናን አትርፎልሃል' አለው።17ጌታውም፣ “ደግ አድርገሃል፣ አንተ ታታሪ አገልጋይ። በጥቂቱ ስለ ታመንህ፣ በዐሥር ከተሞች ላይ ገዥ ትሆናለህ' አለው።18ሁለተኛውም ቀርቦ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ምናንህ ዐምስት አትርፏል' አለው።19ጌታውም፣ 'በዐምስት ከተሞች ላይ ገዥ ሁን' አለው።20ሌላኛውም መጣና፣ 'ጌታ ሆይ፣ በደንብ አድርጌ በጨርቅ ጠቅለዬ ያስቀመጥሁት ምናንህ ይኸውልህ፣21ይህን ያደረግሁት አንተ ጨካኝ ሰው መሆንህን ስላወቅሁ ፈርቼ ነው። አንተ ያላስቀመጥኸውን የምትጠይቅ ያልዘራኸውን የምታጭድ ነህ' አለው።22ጌታውም፣ እንዲህ አለው፤ 'አንተ ክፉ አገልጋይ፣ በአፍህ ቃል እፈርድብሃለሁ። ካላስቀመጥሁበት የምፈልግ፣ ካልዘራሁበት የማጭድ ጨካኝ ሰው መሆኔን ያወቅህ ከሆነ፣23ታዲያ ስመለስ ገንዘቤን ከነትርፉ እንዳገኝ ለምን በባንክ አላስቀመጥኸውም?”24ከዚያም ጌታው በዚያ ለቆሙት ሰዎች፣ “ምናኑን ውሰዱበት፣ ዐሥር ላለውም ጨምሩለት' አላቸው፤25እነርሱም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አስር ምናን አለው እኮ' አሉት።26ጌትየውም፣ 'ላለው ይጨምርለታል፣ ከሌለው ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።27በእነርሱ ላይ ገዥ እንዳልሆን የተቃወሙትን እነዚህን ጠላቶቼን ግን አምጡና በፊቴ ግደሏቸው' አለ።28ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ፣ ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም በማቅናት መንገዱን ቀጠለ።29ደብረ ዘይት በሚባለው ተራራ አጠገብ ወደሚገኝ ቤተ ፋጌና ቢታንያ በተቃረበ ጊዜ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን30እንዲህ ብሎ ላካቸው፤ "ወደሚቀጥለው መንደር ሂዱ። ስትገቡ፣ ማንም ያልተቀመጠበትን አንድ የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ። ፍቱትና አምጡልኝ።31ማንም፣ 'ለምን ትፈቱታላችሁ?' ብሎ ቢጠይቃችሁ፣ 'ለጌታ ያስፈልገዋል' በሉት" አላቸው።32የተላኩትም ወደ ስፍራው በደረሱ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንደ ነገራቸው፣ የአህያውን ውርንጫ ታስሮ አገኙት።33ውርንጫውን እየፈቱ እያለ ባለቤቶቹ፣ 'ውርንጫውን ለምን ትፈቱታላችሁ?' አሉ።34እነርሱም፣ “ለጌታ ያስፈልገዋል” ብለው መለሱለት።35ወደ ኢየሱስ አመጡትና ልብሳቸውን በውርንጫው ጀርባ ላይ አንጥፈው ኢየሱስ እንዲቀመጥበት አደረጉ።36ኢየሱስ በሚሄድበት ጊዜ፣ ከፊቱ ባለው መንገድ ላይ ልብሶቻቸውን ያነጥፉለት ነበር።37ከደብረ ዘይት ተራራ ቁልቁል ወደሚወስደው መንገድ በቀረበ ጊዜ፣ ቊጥራቸው ብዙ የሆነ ደቀ መዛሙርት፣ ስላዩአቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ ደስ እያላቸው፣ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው! በሰማይ ሰላም፣38ክብርም በአርያም ይሁንለት!” እያሉ በከፍተኛ ድምፅ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።39በሕዝቡ መካከል የነበሩ አንዳንድ ፈሪሳውያን፣ “መምህር ሆይ፣ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው” አሉ።40ኢየሱስም፣ “ልንገራችሁ፣ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮችም እንኳ ይጮኻሉ” አላቸው።41ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በተቃረበ ጊዜ እንዲህ በማለት አለቀሰላት፤42“ለአንቺ ሰላም የሚያመጣልሽን ነገር ምነው ዛሬ ባወቅሽ ኖሮ! አሁን ግን ከዐይንሽ ተሰውሮብሻል።43ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው የሚከቡሽና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁሽ ጊዜያት ይመጣሉ።44አንቺንና ልጆችሽንም በምድር ላይ ይፈጠፍጣሉ። እነርሱም ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ አይተዉም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያድንሽ መፈለጉን አላወቅሽምና።”45ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገባና በዚያ ይሸጡ የነበሩትን ያባርራቸው ጀመር፣46ከዚያም፣ “የአባቴ ቤት 'የጸሎት ቤት ይሆናል' ተብሎ ተጽፏል፣ እናንተ ግን የወንበዴዎች መሸሸጊያ አደረጋችሁት” አለ።47ስለዚህ ኢየሱስ በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር። ታዲያ የካህናት አለቆች፣ የሕግ መምህራንና የሕዝቡ መሪዎች ሊገድሉት ፈለጉ።48ነገር ግን ሕዝቡ ከልብ ያደምጡት ስለ ነበር መንገድ አላገኙም።
1አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፣ ኢየሱስ ሕዝቡን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያስተምርና ወንጌልን ይሰብክ በነበረ ጊዜ፣ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ መጡ።2"እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ወይም ይህን ሥልጣን የሰጠህ እርሱ ማን ነው?" አሉት።3እርሱም እንዲህ በማለት መለሰላቸው፤ "እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፣ እስቲ መልሱልኝ።4የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበር ወይስ ከሰዎች?"5እርስ በርሳቸው ተመካከሩና፣ "'ከሰማይ ነው ብንል፣ 'ታዲያ ለምን አላመናችሁትም ይለናል።6ነገር ግን 'ከሰው ነው ብንል' ሕዝቡ ዮሐንስን ነቢይ አድርገው ስለሚቆጥሩ ይወግሩናል" አሉ።7ስለዚህ ከየት እንደ ሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት።8ኢየሱስ፣ "እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም" አላቸው።9ለሕዝቡ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፣ "አንድ ሰው ያዘጋጀውን የወይን ዕርሻ ለወይን ገበሬዎች አከራይቶ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ወደ ሌላ አገር ሄደ።10ምርቱ የሚሰበሰብበት ጊዜ ሲደርስ ከወይኑ የሚገባውን ፍሬ ለማግኘት ወደ ገበሬዎቹ አንድ አገልጋይ ላከ። ነገር ግን የወይኑ ገበሬዎች አገልጋዩን ደብድበው ባዶ እጁን መልሰው ላኩት።11እርሱም አሁንም ሌላ አገልጋይ ላከባቸው፣ ይህንም ደብድበውና አዋርደው ባዶ እጁን መልሰው ላኩት።12እንደ ገና ሦስተኛ አገልጋይ ቢልክባቸው፣ እርሱንም አቈሳስለው አውጥተው ጣሉት።13ስለዚህ የወይኑ ዕርሻ ባለቤት፣ 'ምን ላድርግ? የምወደውን ልጄን እልከዋለሁ። ምናልባት እርሱን ያከብሩት ይሆናል' አለ።14ነገር ግን የወይኑ ገበሬዎች ባዩት ጊዜ፣ 'ወራሹ ይህ ነው። ዕርሻው የእኛ እንዲሆን እንግድለው' ብለው እርስ በርስ ተመካከሩ።15ከዕርሻው ቦታ አወጡትና ገደሉት። እንግዲህ የዕርሻው ባለቤት ምን ያደርግባቸዋል? መጥቶ እነዚህን የወይን ገበሬዎች ይደመስሳቸዋል፣16ዕርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል" አላቸው። እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን ነገር ያርቀው!" አሉ።17ኢየሱስ ግን ተመለከታቸውና፣ 'ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነ' "የሚለው ይህ የመጽሐፍ ቃል ምን ማለት ነው?18በዚህ ድንጋይ የሚደናቀፍ ሁሉ ይሰባበራል። ነገር ግን ድንጋዩ የሚወድቅበት ሁሉ ይደቃል" አለ።19ስለዚህ፣ የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፣ ምክንያቱም ይህን ምሳሌ የተናገረው በእነርሱ ላይ እንደ ሆነ አውቀዋልና።20ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። በዐይነ ቁራኛ እየተከታተሉት፣ ለፍርድና ለገዢው ሥልጣን የሚዳርገውን ስሕተት ከንግግሩ ሊያገኙበት ራሳቸውን ጻድቃን አስመስለው የሚቀርቡ ሰላዮችን ላኩበት።21እነርሱ እንዲህ በማለት ጠየቁት፤ "መምህር ሆይ፣ አንተ በትክክል እንደምትናገርና እንደምታስተምር፣ ደግሞም በማንም እንደማትመራ፣ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንገድ እውነቱን እንደምታስተምር እናውቃለን።22ለቄሣር ግብር መክፈል ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?"23ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ተረዳ፣ እንዲህም አላቸው፣24"አንድ ዲናር አሳዩኝ። በላዩ ያለው የማን ጽሑፍና ምስል ነው?" እነርሱም፣ "የቄሣር ነው" አሉት።25"እንግዲያውስ የቄሣር የሆኑትን ነገሮች ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርን ነገሮች ለእግዚአብሔር ስጡ" አላቸው።26የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም። ምንም እስከማይናገሩ ድረስ በመልሱ ተደነቁ።27የሙታን ትንሣኤ የለም የሚሉ አንዳንድ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ፣28እንዲህ ብለው ጠየቁት፤ "መምህር ሆይ፣ ሙሴ አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ የዚያን ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ለእርሱ እንዲወልድለት ጽፎልናል።29ሰባት ወንድማማች ነበሩ፤ የመጀመሪያው ሚስት አገባና ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤30ሁለተኛውም እንደዚሁ አግብቷት ልጅ ሳይወልድ ሞተ።31ሦስተኛውም አገባት፤ በዚህ ዓይነት ሰባቱም ሴቲቱን አግብተው ልጅ ሳይወልዱ ሞቱ።32በመጨረሻ ሴቲቱም ሞተች።33ታዲያ በትንሣኤ ቀን ይህች ሴት የማንኛቸው ሚስት ትሆናለች? ምክንያቱም ሰባቱም አግብተዋታልና።"34ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "የዚህ ዓለም ሰዎች ያገባሉ፣ ይጋባሉም።35ነገር ግን የሙታን ትንሣኤንና የዘላለም ሕይወትን ለመቀበል የተገባቸው አያገቡም፣ አይጋቡምም።36እንደ መላእክት ስለ ሆኑ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ሊሞቱ አይችሉም። የትንሣኤ ልጆች እንደ መሆናቸው መጠን የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።"37ነገር ግን ሙታን ስለ መነሣታቸው ሙሴ እንኳ በቊጥቋጦው ስፍራ፣ጌታን የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ብሎ በመጥራቱ አሳይቷል።38አሁን እርሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፣ ምክንያቱም ለእርሱ ሁሉም ሕያዋን ናቸው።"39ከሕግ መምህራን አንዳንዶች፣ "መምህር ሆይ፣ ጥሩ አድርገህ መልሰሃል" አሉት።40ደግሞም ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ማንም አልደፈሩም።41ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ "እንግዲህ ሰዎች ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ነው የሚሉት እንዴት ነው?42ዳዊት ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ፣ "ጌታ ለጌታዬ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ43እስከማደርግልህ ድረስ 'በቀኜ ተቀመጥ' ይላልና።44ስለዚህ ዳዊት ክርስቶስን ጌታ ይለዋል፣ታዲያ የዳዊት ልጅ እንዴት ይሆናል?"45ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፣46"ረጅም ቀሚስ ለብሰው መመላለስ ከሚፈልጉ፣ በገበያ ቦታዎችም ልዩ ሰላምታ፣ በምኲራቦች ከፍተኛ ስፍራ፣ በግብዣ ቦታዎችም የከበሬታ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ከሚወዱ የሕግ መምህራን ተጠንቀቁ።47ደግሞም እነርሱ ረጅም የሆኑ የማስመሰል ጸሎቶችን እየጸለዩ የመበለቶችን ቤት አለአግባብ ይበዘብዛሉ። እነዚህ የባሰ ቅጣት ይቀበላሉ።"
1ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታም ሰዎች በመባ መሰብሰቢያ ሣጥን ውስጥ ገንዘብ ሲጨምሩ አየ።2አንዲት ድኻ መበለት ደግሞ ሁለት ሳንቲሞችን ስትጨምር አየ።3ስለዚህ እንዲህ አለ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድኻ መበለት ከሁሉም የበለጠ ሰጠች።4እነዚህ ሁሉ የሰጡት ስጦታ ከተትረፈረፈ ሀብታቸው ነው። ይህች መበለት ግን በድኽነቷ መተዳደሪያዋን ሁሉ ሰጠች።"5አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ በተዋቡ ድንጋዮች እንዴት እንዳማረና እንዳጌጠ ሲናገሩ ሰምቶ እንዲህ አለ፣6"እነዚህ የምታዩአቸው ነገሮች፣ እንዲህ እንደተነባበሩ የማይቆዩበትና የሚፈራርሱበት ጊዜ ይመጣል" አለ።7ስለዚህ፣ "መምህር ሆይ፣ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች እንደሚፈጸሙ ምልክቱስ ምንድን ነው?" በማለት ጠየቁት።8ኢየሱስ፣ "እንዳትስቱ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ብዙዎች 'እኔ ኢየሱስ ነኝ፣ ደግሞም 'ጊዜው አሁን ነው' እያሉ በስሜ ይመጣሉ። አትከተሏቸው።9ስለ ጦርነቶችና ሁከቶች ስትሰሙ አትሸበሩ፣ እነዚህ ነገሮች አስቀድመው መፈጸም ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን መጨረሻው ወዲያው አይሆንም" ብሎ መለሰ።10ከዚያም እንዲህ አላቸው፣ "ሕዝብ በሕዝብ ላይ ይነሣል፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል።11ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል፣ ደግሞም በተለያዩ ቦታዎች ራብና ቸነፈር ይከሠታል። አስፈሪ ሁነቶችና ታላላቅ ምልክቶች ከሰማይ ይገለጣሉ።12ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች አስቀድሞ እናንተን ይይዟችኋል፣ ያሳድዷችኋል፣ ለምኩራቦችና ለወህኒ ቤቶች አሳልፈው በመስጠት ስለ ስሜ በገዦችና በነገሥታት ፊት ያቆሟችኋል።13ይህም ለእናንተ ለመመስከር ዕድልን ይሰጣችኋል።14ስለዚህ፣ አስቀድማችሁ ምን መከላከያ እናቀርባለን በማለት አትናወጡ፣15ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ጠላቶቻችሁ ሊቋቋሙትና ሊቃወሙት የማይችሉትን ቃልና ጥበብ እሰጣችኋለሁ።16ነገር ግን በወላጆች፣ በወንደሞች፣ በዘመዶችና በጓደኞች ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ፣ ከእናንተም አንዳንዶቹን ይገድላሉ።17በስሜ ምክንያት በሰው ሁሉ ትጠላላችሁ።18ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጒር አንዲቱ እንኳ አትጠፋም።19በትዕግሥታችሁም ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ።20ኢየሩሳሌም በሠራዊት ተከብባ ስታዩ ጥፋቷ መቃረቡን እወቁ።21በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣ በከተማይቱ መካከል ያሉትም ለቀው ይሂዱ፣ በገጠር ያሉት ደግሞ ወደ ከተማይቱ አይግቡ።22የተጻፈው እንዲፈጸም እነዚህ ጊዜያት የበቀል ጊዜያት ናቸውና።23በእነዚያ ቀኖች ለእርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቊጣ ይወርዳል።24በሰይፍም ስለት ይወድቃሉ፤ ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ሁሉ ምርኮኞች ተደርገው ይወሰዳሉ፤ የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ፣ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።25በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ምልክቶች ይታያሉ። በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ከባሕርና ከማዕበል ድምፅ የተነሣ ተስፋ በመቊረጥ ይጨነቃሉ።26ከፍርሃትና በዓለም ላይ ሊከሰቱ ያሉትን ነገሮች ከመሥጋት የተነሣ የሚዝሉ ሰዎችም ይኖራሉ። ምክንያቱም የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉና።27ከዚያም የሰው ልጅ በኅይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።28ነገር ግን እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ቀረበ ንቁ፣ ቀና ብላችሁ ተመልከቱ።29ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ነገራቸው፤ “የበለስ ዛፍና ሌሎች ዛፎችን ተመልከቱ።30ቀንበጥ ሲያወጡ፣ በጋ እንደተቃረበ ታውቃላችሁ።31ልክ እንደዚሁም እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ።32እውነቱን እነግራችኋለሁ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት ይህ ትውልድ አያልፍም።33ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።34ልቅ በሆነ አኗኗር፣ በስካርና በጭንቀት ልባችሁ እንዳይከብድ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይመጣባችኋል።35በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይም ይመጣባቸዋል።36ነገር ግን ከሚከሠቱት ከአነዚህ ነገሮች ሁሉ እንድታመልጡና በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትበረቱ ሁልጊዜ ነቅታችሁ ጸልዩ።37ስለዚህ ኢየሱስ በየቀኑ በቤተ መቅደስ ያስተምር፣ ሌሊቱን ደግሞ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ እየወጣ ያሳልፍ ነበር።38በቤተ መቅደስም ሲያስተምር ሰዎች ሁሉ ሊሰሙት በማለዳ ይመጡ ነበር።
1ፋሲካ የተባለው የቂጣ በዓል ተቃርቦ ነበር።2የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ሕዝቡን ይፈሩ ስለ ነበር፣ ኢየሱስን እንዴት አድርገው እንደሚገድሉት ተመካከሩ።3ሰይጣን ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ በሆነው በአስቆሮቱ ይሁዳ ገባበት።4አርሱም ኢየሱስን እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከሕዝብ መሪዎች ጋር ተነጋገረ።5እነርሱም ደስ አላቸው፣ ገንዘብም ሊሰጡት ተስማሙ።6እርሱም ኢየሱስን ለእነርሱ አሳልፎ ለመስጠት ሕዝብ የሌሉበትን ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።7የፋሲካ በግ መሥዋዕት የሚደረግበት የቂጣ በዓል ደረሰ።8ኢየሱስም ጴጥሮስንና ዮሐንስን፣ “ሂዱና የፋሲካ ምግብ እንድንበላ አዘጋጁልን” ብሎ ላካቸው።9እነርሱም፣ “የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” ብለው ጠየቁት።10እንዲህም ብሎ መለሰላቸው፣ “አድምጡ፣ ወደ ከተማው በገባችሁ ጊዜ የውሃ እንስራ ተሸክሞ የሚመጣ ሰው ያገኛችኋል። ይህን ሰው ወደሚገባበት ቤት ተከትላችሁ ግቡ።11ከዚያም ለቤቱ ባለቤት፣ 'መምህሩ እንዲህ ይልሃል፤" የፋሲካን እራት ከደቀ መዛሙርቴ ጋር የምበላበት የእንግዳ ክፍል የት ነው?' በሉት።”12እርሱም በፎቁ ላይ ሰፊና በሚገባ የተሰናዳ ክፍል ያሳያችኋል። ዝግጅቱንም በዚያ አድርጉ።13ስለዚህ ወጥተው ሲሄዱ፣ ሁሉም ነገር እርሱ እንደተናገረው ሆኖ አገኙት። ከዚያም የፋሲካውን ምግብ አዘጋጁ።14ሰዓቱ ሲደርስ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ዐብሮ ተቀመጠ።15ከዚያም እንዲህ አላቸው፤ “መከራ ከመቀበሌ በፊት ይህን የፋሲካ እራት ከእናንተ ጋር ለመብላት በእጅጉ እጓጓ ነበር።16በእግዚአብሔር መንግሥት እስከሚፈጸም ድረስ ከዚህ ምግብ ዳግመኛ እንደማልበላ እነግራችኋለሁና።"17ከዚያም ኢየሱስ ጽዋውን አንሥቶ አመሰገነና እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ውሰዱና ተካፈሉት።18እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከዚህ ወይን ፍሬ ዳግመኛ አልጠጣም።”19እንጀራውን ወሰደ፣ ካመሰገነ በኋላ እንዲህ በማለት ቈርሶ ሰጣቸው፣ “ይህ ለእናንተ የተሰጠው ሥጋዬ ነው። እኔን እያሰባችሁ ተመገቡት።”20በተመሳሳይ ሁኔታም፣ ከእራት በኋላ ጽዋውን አነሣና እንዲህ አለ፣ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ የፈሰሰ በደሜ የሚሆን ዐዲስ ኪዳን ነው።21ነገር ግን እኔን አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር በማዕድ እየበላ መሆኑን ልብ በሉ።22የሰው ልጅስ እንደተወሰነለት ይሆናል። ነገር ግን አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ወዮለት!"23በዚህ ጊዜ እርስ በርሳቸው ይህን ነገር የሚያደርግ ማን እንደ ሆነ ተጠያየቁ።24ከዚያም ከሁሉም የሚበልጥ ማን ሊሆን እንደሚገባው በመካከላቸው ጠብ ተነሣ። እርሱ እንዲህ አላቸው፣25“የአሕዛብ ነገሥታት በሕዝብ ላይ ይገዛሉ፣ በእነርሱ ላይ ሥልጣን ያላቸውንም የተከበሩ ገዦች ይሏቸዋል።26ነገር ግን በእናንተ ዘንድ እንዲህ አይሁን። ይልቅ ከእናንተ ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን። እጅግ ተፈላጊ የሆነ እንደሚያገለግል ሰው ይሁን።27በማዕድ ከተቀመጠውና ከሚያገለግለው የትኛው ታላቅ ነው? በማዕድ የተቀመጠ አይደለምን? እኔ ግን በእናንተ መካከል እንደሚያገለግል ሰው ነኝ።28ነገር ግን እናንተ በፈተናዬ ከእኔ ጋር ጸንታችኋል። አብ ለእኔ መንግሥትን እንደ ሰጠኝ፣29በመንግሥቴ በእኔ ማዕድ እንድትበሉና እንድትጠጡ መንግሥትን እሰጣችኋለሁ።30ደግሞም በዙፋን ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።31ስምዖን ሆይ፣ ስምዖን ሆይ፣ ተጠንቀቅ፤ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥርህ ፈልጎ ጠይቋል።32ነገር ግን እኔ እምነትህ እንዳይጠፋ ጸለይሁልህ። ዳግመኛ ከተመለስህ በኋላ ወንድሞችህን አበርታቸው።”33ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ወደ እስር ቤትም ይሁን ወደ ሞት ከአንተ ጋር ለመሄድ ዝግጁ ነኝ” አለው።34ኢየሱስ፣ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ አላውቀውም ብለህ ሦስት ጊዜ እንደምትክደኝ እነግርሃለሁ” ብሎ መለሰለት።35ከዚያም ኢየሱስ፣ “ያለ ገንዘብ ቦርሣ፣ ወይም ያለ ስንቅ ወይም ያለ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ ያጣችሁት ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱ፣ “ምንም አላጣንም" ብለው መለሱለት።36ከዚያም እንዲህ አላቸው፣ “አሁን ግን የገንዘብ ቦርሣ ያለው ቦርሣውን፣ ደግሞም ስንቁን ይያዝ። ጎራዴ የሌለው ልብሱን ሽጦ ጎራዴ ይግዛ።37እላችኋለሁ፣ 'ከወንበዴዎች እንደ አንዱ ተቈጠረ' ተብሎ ስለ እኔ የተጻፈው መፈጸም አለበት። ይህ ስለ እኔ የተነገረው አሁን እየተፈጸመ ነው።"38ከዚያም እነርሱ፣ “ጌታ ሆይ፣ ተመልከት፣ እዚህ ሁለት ጎራዴዎች አሉ” አሉት። እርሱም “ይበቃል” አላቸው።39ከእራት በኋላ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ እንደሚያደርገው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄደ፣ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት።40እዚያ በደረሱ ጊዜ፣ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጸልዩ” አላቸው።41ከእነርሱ የድንጋይ ውርወራ ያህል ራቅ ብሎ ሄደና ተንበርክኮ፣42“አባት ሆይ፣ ብትወድ ይህን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፣ ነገር ግን የአንተ ፈቃድ እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን” በማለት ጸለየ።43የሚያበረታታው መልአክም ከሰማይ መጣለት።44በጣር ውስጥ ሆኖ በጣም እየቃተተ ጸለየ፣ ላቡም እንደ ትልልቅ የደም ጠብታዎች ወደ መሬት ይንጠባጠብ ነበር።45ከጸሎቱ ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ በመጣ ጊዜ ከሐዘን የተነሣ ተኝተው አገኛቸውና፣46“ለምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሡና ጸልዩ” አላቸው።47ገና እየተናገረ እያለ ብዙ ሰዎች ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ እየመራቸው መጡ። ይሁዳም ሊስመው ወደ ኢየሱስ ቀረበ፤48ነገር ግን ኢየሱስ፣ “ይሁዳ ሆይ፣ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጣለህን?” አለው።49በኢየሱስ ዙሪያ የነበሩት እየሆነ ያለውን ነገር ባዩ ጊዜ፣50“በጎራዴ እንምታቸውን?” አሉ። ከዚያም ከመካከላቸው አንዱ በጎራዴ የሊቀ ካህኑን አገልጋይ ቀኝ ጆሮ መታና ቈረጠው።51ኢየሱስ፣ “ይህ ይብቃ” አለ። የአገልጋዩንም ጆሮ ዳሰሰ፣ ፈወሰውም።52ኢየሱስ ሊያጠቁት ለመጡ የካህናት አለቆችና የቤተ መቅደስ መሪዎች እንዲሁም ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወንበዴን እንደሚይዝ ሰው ጐራዴና ዱላ ይዛችሁ ትመጡብኛላችሁን?53በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ከእናንተ ጋር ሳለሁ አልያዛችሁኝም። ነገር ግን ይህ የእናንተና የጨለማው ሥልጣን ጊዜ ነው።”54ያዙትና ወሰዱት፣ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤትም አመጡት። ጴጥሮስ ግን ከርቀት ተከተለው።55በግቢው መሓል እሳት ካቀጣጠሉና ዐብረው ከተቀመጡ ጴጥሮስ መጥቶ በመካከላቸው ተቀመጠ።56በእሳቱ ብርሃን እንደተቀመጠም አንዲት ገረድ አየችውና በቀጥታ ተመልክታው፣ “ይህ ሰው ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበር” አለች።57ጴጥሮስ ግን፣ “ሴትዮ፣ የምትዪውን ሰው አላውቀውም” ብሎ ካደ።58ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ፣ ሌላ ሰው አየውና፣ “አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ” አለው። ነገር ግን ጴጥሮስ፣ “አንተ ሰው፣ እኔ አይደለሁም” አለ።59ከአንድ ሰዓት ያህል ጊዜ በኋላ፣ ሌላ ሰው፣ “በእውነት ይህ ሰው ደግሞ ገሊላዊ ስለ ሆነ ከእርሱ ጋር ነበረ” በማለት በጥብቅ ተናገረ።60ነገር ግን ጴጥሮስ፣ “አንተ ሰው የምትለውን አላውቅም” አለ። ይህን እየተናገረ እያለ ወዲያው ዶሮ ጮኸ።61ጌታም ዞር አለና ጴጥሮስን ተመለከተው። ጴጥሮስም፣ ጌታ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለውን ቃል አስታወሰ።62ጴጥሮስ ወደ ውጭ ወጣና መራራ ልቅሶ አለቀሰ።63ከዚያም ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች እያላገጡበት ደበደቡት። ዐይኖቹን ከሸፈኑ በኋላ፣64“እስቲ ትንቢት ተናገር። አሁን የመታህ ሰው ማን ነው?” በማለት ጠየቁት።65እየተሳደቡ፣ ሌሎች ብዙ ነገሮችን በኢየሱስ ላይ ተናገሩ።66እንደነጋም የሕዝቡ ሽማግሌዎች፣ ከካህናት አለቆችና ከሕግ መምህራን ጋር ዐብረው ተሰበሰቡ። ከዚያም ኢየሱስን ወደ ሸንጎው ፊት አቀረቡትና፣67“ክርስቶስ ከሆንህ ንገረን” አሉት። እርሱ ግን፣ “እኔ ብነግራችሁ አታምኑም፣68ደግሞም ብጠይቃችሁ አትመልሱም።69ነገር ግን ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ኅይል ቀኝ ይቀመጣል” አላቸው።70ሁሉም በአንድነት፣ “እንግዲህ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነሃ?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እኔ እንደ ሆንሁ እናንተ ትናገራላችሁ” አላቸው። እነርሱ፣71“እንግዲህ ለምን ምስክር እንፈልጋለን? ሲናገር እኛ ራሳችን ከአፉ ሰምተነዋል” አሉ።
1ሕዝቡ በጠቅላላ ተነሥተው ቆሙ፣ ኢየሱስንም በጲላጦስ ፊት አቀረቡት።2“ይህ ሰው ራሱን ክርስቶስ፣ ንጉሥ ነኝ ሲልና ለቄሣር ግብር እንዳይከፈል በመከልከል አገር ሲበጠብጥ አግኝተነዋል” በማለት ይከሱት ጀመር።3ጲላጦስ፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተ አልህ” ብሎ መለሰለት።4ጲላጦስ የካህናት አለቆችንና የተሰበሰቡትን ሕዝብ፣ “በዚህ ሰው ምንም ስሕተት አላገኘሁበትም” አላቸው።5እነርሱ ግን፣ “ከገሊላ ጀምሮ በመላው ይሁዳ፣ እስከዚህ ስፍራም እንኳ እያስተማረ ሕዝቡን ያነሣሣል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ።6ስለዚህ ጲላጦስ ይህን በሰማ ጊዜ ሰውየው ገሊላዊ እንደ ሆነ አጠያየቀ።7ከሄሮድስ ሥልጣን በታች እንደ ሆነ ተረድቶ በዚያው ሰሞን ኢየሱስን በኢየሩሳሌም ወደ ነበረው ሄሮድስ ላከው።8ሄሮድስ ኢየሱስን ባየው ጊዜ በጣም ደስ አለው፣ ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ሊያየው ሲፈልግ ነበር። ስለ እርሱ ሰምቶ የነበረ ሲሆን፣ አንዳንድ ተአምራት ሲያደርግ ለማየትም ተስፋ ነበረው።9ሄሮድስ ኢየሱስን በብዙ ቃሎች ቢጠይቅም፣ ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም።10በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ተነሥተው ቆሙና በኅይለ ቃል ከሰሱት።11ሄሮድስ ከወታደሮቹ ጋር በመሆን ኢየሱስን ሰደበው፣ አላገጠበትም፤ ጥሩ ልብስ ካለበሰው በኋላ መልሶ ወደ ሄሮድስ ላከው።12ከዚያን ቀን ጀምሮ ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ (ከዚያ በፊት አንዱ የአንዱ ጠበኞች ነበሩ)።13ከዚያም ጲላጦስ የካህናት አለቆችን፣ ገዢዎችንና ሕዝቡን አንድ ላይ ጠራ፤14እንዲህም አላቸው፤ “ ይህን ሰው ሰዎችን ለክፉ ድርጊት የሚያነሣሣ አድርጋችሁ ወደ እኔ አመጣችሁት፣ እኔም በፊታችሁ ከጠየቅሁት በኋላ ፣ እነሆ፣ እርሱን በምትከሱባቸው ነገሮች ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።15ሄሮድስም ቢሆን ምንም ነገር አላገኘበትም፤ ምክንያቱም መልሶ ወደ እኛ ልኮታልና፤ እነሆ፣ እርሱን ለሞት የሚያደርስ በዚህ ሰው የተፈጸመ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።16ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።" ጲላጦስም በበዓሉ ለአይሁድ አንድ እስረኛ የመፍታት ግዴታ ነበረበት።1718ነገር ግን እነርሱ በአንድነት፣ “ይህን ሰው አስወግደው፣ በርናባስን ለእኛ ፍታልን!" በማለት ጮኹ።19በርናባስ በከተማይቱ ውስጥ አንድ ዐይነት ዐመፅና ግድያ በመፈጸም የታሰረ ሰው ነበር።20ጲላጦስ ኢየሱስን ሊፈታ ፈልጎ እንደ ገና ሕዝቡን አነጋገራቸው።21ነገር ግን ሕዝቡ፣ “ስቀለው፣ ስቀለው” እያሉ ጮኹ።22ለሦስተኛ ጊዜም እንዲህ አላቸው፤ “ለምን? ይህ ሰው የሠራው ክፋት ምንድን ነው? ለሞት ቅጣት የሚያበቃ ነገር አላገኘሁበትም። ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።”23እነርሱ ግን ኢየሱስ እንዲሰቀል በመጠየቅ ሳያቋርጡ አብዝተው ጮኹ። ጩኸታቸውም ጲላጦስን አሳመነው።24ስለዚህ ጲላጦስ ፍላጎታቸውን ለማሟለት ወሰነ።25እንዲፈታላቸው የጠየቁትን፣ በዐመፅና በግድያ ምክንያት የታሰረውን ሰው ለቀቀላቸው። ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።26እየወሰዱት ሳሉ፣ ከገጠር ይመጣ የነበረ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ያዙና ኢየሱስ ይሸከመው የነበረውን መስቀል አሸከሙት።27እጅግ ብዙ ሕዝብና ለእርሱ የሚያዝኑና የሚያለቅሱ ሴቶች ይከተሉት ነበር።28ኢየሱስም ወደ እነርሱ ዞር ብሎ፣ “የኢየሩሳሌም ሴቶች ሆይ፣ ለእኔ ሳይሆን ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ” አለ።29እነሆ፣ 'መካን የሆኑና ያልወለዱ ማኅፀኖች እንዲሁም ያላጠቡ ጡቶች የተባረኩ ናቸው' የሚሉባቸው ቀኖች ይመጣሉና።30ከዚያም ተራሮችን፣ 'በላያችን ውደቁ፣ ኮረብቶችንም ክደኑን ማለትይጀምራሉ።'31ዛፉ እርጥብ እያለ ይህን ነገር ካደረጉ፣ በሚደርቅበት ጊዜ ምን ይሆናል?"32ሌሎች ሁለት ወንጀለኞችም ከእርሱ ጋር ሊገደሉ ተወሰዱ።33የራስ ቅል ወደሚባል ቦታ በደረሱ ጊዜ፣ እርሱን ከሌሎች ሁለት ወንጀለኞች ጋር ሰቀሉት፥ አንደኛው በቀኙ ሌላኛው በግራው ነበሩ።34ኢየሱስ፣”አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ። ዕጣ ተጣጥለውም ልብሱን ተከፋፈሉ።35“ሌሎችን አዳነ፣ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠ ክርስቶስ ከሆነ አስኪ ራሱን ያድን” በማለት ገዢዎቹ እየዘበቱበት ሳለ ሕዝቡ ቆመው ያዩ ነበር።36ወታደሮቹም ወደ እርሱ ቀርበው፣37“አንተ ንጉሥ ከሆንህ ራስህን አድን” በማለት እያሾፉበት ኮምጣጤ ሰጡት።38“የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ምልክትም ከበላዩ ተደርጎ ነበር።39ከተሰቀሉት ወንጀለኞች አንዱ፣ "አንተ ክርስቶስ ነህን? ራስህንም እኛንም አድን” በማለት ሰደበው።40ሌላኛው ግን እየገሠጸው፣ “ከፍርድ በታች ሆነህ እግዚአብሔርን አትፈራምን? እኛ በዚህ ያለነው እንደ ሥራችን ስለ ሆነ፣ ትክክል ነው፣41ነገር ግን ይህ ሰው ምንም ጥፋት አላደረገም” ብሎ መለሰለት።42ቀጥሎም፣ “ኢየሱስ ሆይ፣ በመንግሥትህ ስትመጣ አስታውሰኝ” አለ።43ኢየሱስ፣ “እውነት እልሃለሁ፣ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ” አለው።44ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር፣ የፀሐይ ብርሃን በመቋረጡ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ጨለማ ሆነ።45ከዚያም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከመሐል ተቀደደ።46ኢየሱስ፣ “አባት ሆይ፣ ነፍሴን በእጅህ አኖራለሁ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህን ከተናገረ በኋላ ሞተ።47መቶ አለቃው የተደረገውን ነገር ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በእውነት ጻድቅ ነበር” በማለት እግዚአብሔርን አከበረ።48ሁኔታውን ለማየት እጅግ ብዙ ሰዎች በመጡ ጊዜ፣ የተደረጉትን ነገሮች አይተው ደረታቸውን እየደቁ ተመለሱ።49ነገር ግን ከገሊላ ጀምሮ የተከተሉት አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ከርቀት ቆመው ይህን ድርጊት ይከታተሉ ነበር።50እነሆ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት መምጣት የሚጠባበቅ፣ ከአይሁድ ከተማ፣ ከአርማቲያ የሆነ ዮሴፍ የሚባል51(በውሳኔያቸውና በድርጊታቸው ያልተስማማ) አንድ መልካምና ጻድቅ ሰው ነበረ።52ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ በመቅረብ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀው።53አስክሬኑን አውርዶ በጥሩ የተልባ እግር ጨርቅ ከፈነውና ማንም ባልተቀበረበት ከድንጋይ በተወቀረ መቃብር ውስጥ አኖረው።54ጊዜው የዝግጅት ቀን የነበረ ሲሆን፣ ሰንበትም እየገባ ነበር።55ከእርሱ ጋር ከገሊላ የመጡ ሴቶች ተከትለውት በመሄድ መቃብሩንና አስከሬኑ እንዴት እንዳረፈ አዩ።56ከዚያም ተመልሰው ቅመማ ቅመምና ቅባቶችን አዘጋጁ። ሰንበት ስለ ነበር በሕጉ መሠረት ዐረፉ።
1በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ሴቶች ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው በጣም ማልደው ወደ መቃብሩ መጡ።2ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት።3ወደ ውስጥ ገቡ፣ ነገር ግን የጌታ ኢየሱስን ሥጋ አላገኙም።4ስለዚህ ነገር ግራ ተጋብተው ሳሉ፣ የሚያብረቀርቅ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በድንገት ከአጠገባቸው ቆመው አገኙ።5ሴቶቹ በፍርሃት ተሞልተውና ወደ መሬት አቀርቅረው ሳሉ፣ ሰዎቹ ፣“ስለምን ሕያውን ከሙታን መካከል ትፈልጋላችሁ?6እርሱ በዚህ የለም፣ ተነሥቷል! ገና በገሊላ ሳለ፣7እንዴት በኃጢአተኞች ሰዎች እጅ ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ እንደሚሰቀልና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ የነገራችሁን አስታውሱ" አሏቸው።8ሴቶቹ ቃሎቹን አስታወሱ፣9ከመቃብሩም ተመለሱና እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለዐሥራ አንዱና ለተቀሩትም ነገሩ።10መግደላዊት ማርያም፣ ዮሐናና የያዕቆብ እናት ማርያም እንዲሁም ሌሎች ሴቶች ሁኔታውን ለሐዋርያት ነገሯቸው።11ነገር ግን ይህ ንግግር ለሐዋርያቱ ቀልድ ስለ መሰላቸው፣ ሴቶቹን አላመኗቸውም፣12ሆኖም ግን ጴጥሮስ ተነሣና እየሮጠ ወደ መቃብሩ ሄደ፣ ከዚያም አጎንብሶ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ የተልባው እግር ጨርቅ ለብቻው ተቀምጦ አየ። ከዚያ በኋላ ጴጥሮስ ምን ተፈጥሮ ይሆን ብሎ እያሰበ ወደ ቤቱ ተመለሰ።13እነሆ፣ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያው ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ርቆ ወደሚገኝ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር እየተጓዙ ነበር።14ስለሆኑት ነገሮች ሁሉ በመንገዳቸው ላይ እርስ በርስ ይነጋገሩ ነበር።15እየተነጋገሩና እየተጠያየቁ በመሄድ ላይ ሳሉ፣ ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተጠግቶ ይሄድ ነበር።16ነገር ግን እርሱን እንዳያውቁት ዐይኖቻቸው ተይዘው ነበር።17ኢየሱስ፣ “እናንተ ሁለታችሁ እየተጓዛችሁ የምትነጋገሩት ስለምንድን ነው?” አላቸው። ያዘኑ መስለው ቆም አሉ።18ስሙ ቀለዮጳ የተባለ ከሁለቱ አንዱ፣ “በኢየሩሳሌም ሰሞኑን የተደረጉትን ነገሮች የማታውቅ አንተ ብቻ ነህን?" ብሎ መለሰለት።19ኢየሱስም፣ “ነገሮቹ ምንድን ናቸው?” አላቸው።20እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት፣ “የካህናት አለቆችና ገዢዎቻችን ኢየሱስ የተባለውን ናዝራዊና ነቢይ እንዴት አድርገው እንደ ፈረዱበትና ለሞትና ለስቅላት አሳልፈው እንደ ሰጡት ነዋ።21እስራኤልን ነጻ ያወጣል ብለን ተስፋ ያደረግነው እርሱን ነበር። አዎን፣ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ይህ ነገር ከሆነ አሁን ሦስተኛ ቀኑ ነው”22ነገር ግን ጠዋት ወደ መቃብሩ የሄዱ ከእኛ ጋር የሆኑ አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን።23ሥጋውን ባላገኙ ጊዜ፣ በመቃብሩ ውስጥ ሥጋውን እንዳላገኙና እርሱ ሕያው ሆኗል ብለው የነገሯቸውን የመላእክት ራእይ አይተናል አሉ።24ከእኛ ጋር ካሉት ወንዶችም አንዳንዶች ወደ መቃብሩ ሄደው ልክ ሴቶቹ እንዳሉት ሆኖ አገኙት። ነገር ግን እርሱን አላዩትም”።25ኢየሱስም፣ “ነቢያት የተናገሩትን ሁሉ ለማመን የዘገያችሁ እናንተ ሞኞች!26ክርስቶስ በእነዚህ ነገሮች መሠቃየቱና ወደ ክብሩ መግባቱ ግድ መሆኑን አታውቁምን?" አላቸው።27ከዚያም ከሙሴ ጀምሮ እስከ ነቢያት መጻሕፍት፣ በመጻሕፍት ሁሉ ስለ እርሱ የተነገረውን ተረጐመላቸው።28ወደሚሄዱበት መንደር በተቃረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ቀደም ቀደም እያለ መሄድ ጀመረ።29ነገር ግን እነርሱ፣ “ቀኑ እየመሸ ጊዜውም እያለፈ ስለ ሆነ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ጎተጎቱት። ስለዚህ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ሊያድር ሄደ።30ለመብላት ከእነርሱ ጋር በማዕድ በተቀመጠ ጊዜ፣ እንጀራውን ወሰደና ከባረከው በኋላ ቈርሶ ሰጣቸው።31በዚህ ጊዜ ዐይኖቻቸው ተከፈቱና አወቁት። እርሱ ግን ከዐይናቸው ተሰወረባቸው።32እርስ በርሳቸው፣ “በመንገድ ላይ አብረን ሳለን ሲያናግረንና መጻሕፍትን ሲከፍት ልባችን በውስጣችን ይቃጠልብን አልነበርምን?” ተባባሉ።33በዚያው ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ዐሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ተሰብስበው እንዲህ እያሉ አገኟቸው፤34“ጌታ በእርግጥ ተነሥቷል፣ ለስምዖንም ታይቷል።”35ከዚያም በመንገድ ላይ የሆነውን ነገርና ኢየሱስ በማዕድ እንጀራን በሚቈርስበት ጊዜ እንዴት እንደ ታያቸው ተናገሩ።36እነዚህን ነገሮች እየተናገሩ እያሉ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው።37እነርሱም ስለ ተሸበሩና በፍርሃት ስለ ተዋጡ መንፈስ ያዩ መሰላቸው።38ኢየሱስ፣ “ለምን ትጨነቃላችሁ? ለምንስ በልባችሁ ጥያቄዎች ይነሣሉ?39እኔው ራሴ ስለ መሆኔ እጆቼንና እግሮቼን እዩ። ዳሳችሁም እዩኝ። በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውም" አላቸው።40ይህን ተናግሮ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው።41ከደስታ የተነሣ ማመን ተስኗቸው ግራ ተጋብተው ሳሉ፣ ኢየሱስ፣ “የሚበላ ጥቂት ነገር ይኖራችኋል?” አላቸው።42የተጠበሰ ዐሣ ሰጡት።43ኢየሱስም ወስዶ በፊታቸው በላው።44እንዲህም አላቸው፤ “ከእናንተ ጋር በነበርሁ ጊዜ በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙራት የተጻፈው ሁሉ መፈጸም እንደሚገባው ነግሬአችሁ ነበር።”45ከዚያም መጻሕፍትን ይረዱ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው።46እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ ክርስቶስ መሠቃየት፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን መካከል መነሣት እንደሚገባው በመጻሕፍት ተጽፏል።47ደግሞም ንስሐና የኃጢአት ይቅርታ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለአሕዛብ ሁሉ በስሙ መሰበክ አለበት።48እናንተ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ናችሁ።49እነሆ፣ የአባቴን ተስፋ በእናንተ ላይ እልካለሁ። ኅይልን ከላይ እስከምትቀበሉ ድረስ በዚህ ከተማ ሆናችሁ ተጠባበቁ።"50ከዚያም ኢየሱስ ወደ ቢታንያ እስከሚቃረቡ ድረስ ይዟቸው ሄደ። እጆቹንም አነሣና ባረካቸው፤51እየባረካቸውም ሳለ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ አለ።52ስለዚህ እነርሱ ሰገዱለት፣ እጅግ ደስ እያላቸውም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።53በቤተ መቅደስም ያለ ማቋረጥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
1በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤2ይህም ቃል ከመጀመሪያው ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፡፡3ሁሉም ነገር የተሠራው በእርሱ አማካይነት ነው፤ ከተሠሩት ነገሮች ሁሉ ያለ እርሱ የተሠራ አንድም ነገር አልነበረም፡፡4በእርሱ ሕይወት ነበረ፤ያም ሕይወት የሰው ሁሉ ብርሃን ነበር፡፡5ብርሃኑ በጨለማ ይበራል፤ ጨለማም ሊያጠፋው አልቻለም፡፡6ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፡፡7ሁሉም በእርሱ እንዲያምኑ እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ።8ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ዮሐንስ ራሱ ብርሃን አልነበረም፡፡9ወደ ዓለም የሚመጣውና ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጭ የሆነው እውነተኛ ብርሃን እየመጣ ነበር፡፡10እርሱ በዓለም ውስጥ ነበር፤ ዓለሙም የተሠራው በእርሱ ነው፤ ዓለም ግን አላወቀውም፤11የራሱ ወደ ሆኑት መጣ፤ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም፡፡12ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን መብት ሰጣቸው፡፡13እነርሱም ከደምና ከሥጋ ወይም ከሰው ፈቃድ አልተወለዱም፤ ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፡፡14ቃል ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋና እውነት የተሞላውን ከአብ ዘንድ ያለውን የአንድያ ልጁን ክብር አየን፡፡15ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ፣ «ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ ይበልጣል፤ 'ከእኔ በፊት ነበርና' ያልኋችሁ ይህ ነው» ይል ነበር፡፡16ከእርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀበልን፤17ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ በኩል መጣ፡፡18በየትኛውም ጊዜ እግዚአብሔርን ያየው አንድም ሰው የለም፤ ነገር ግን በአባቱ ዕቅፍ ያለውና እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነው አንድያ ልጁ እርሱ እግዚአብሔርን እንዲታወቅ አደረገው፡፡19አይሁድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ልከው፣ «አንተ ማን ነህ?» ብለው በጠየቁት ጊዜ፣ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው፡፡20እርሱ በግልጽ ተናገረ አልካደምም፤ ነገር ግን፣ «እኔ ክርስቶስ አይደለሁም» ብሎ መለሰላቸው።21ስለዚህ እነርሱም፣ «ታዲያ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን?» ብለው ጠየቁት፤ እርሱ፣ «አይደለሁም» አላቸው። እነርሱ፣ «ነቢዩ ነህን?» አሉት፤ እርሱ፣ «አይደለሁም» አለ፡፡22ከዚያም እነርሱ፣ «ለላኩን መልስ መስጠት እንድንችል፣ አንተ ማን ነህ? ስለ ራስህስ ምን ትላለህ?» አሉት፡፡23እርሱ፣ «ልክ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለው፡- 'የጌታን መንገድ አስተካክሉ' እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ» አላቸው፡፡24ከፈሪሳውያን የተላኩ ሰዎችም ነበሩ።25እነርሱ፣ «ክርስቶስ፣ ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካልሆንህ፣ ታዲያ ለምን ታጠምቃለህ?» ብለው ጠየቁት፡፡26ዮሐንስ፣ «እኔ በውሃ አጠምቃለሁ፤ ይሁን እንጂ እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሟል፤27ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ነው፤ እኔ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ ነኝ» በማለት መለሰላቸው፤28ይህ ሁሉ የሆንው ዮሐንስ ሲያጠምቅ በነበረበት በዮርዳኖስ ማዶ በምትገኘው በቢታንያ ነበር፡፡29በማግስቱ ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ ተመልክቶ እንዲህ አለ፤ «እነሆ፣ የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ይኸውና!30'ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይበልጣል' ብዬ ስለ እርሱ የነገርኋችሁ እርሱ ነው፡፡31እኔ አላወቅሁትም ነበር፤ ነገር ግን እርሱ ለእስራኤል ይገለጥ ዘንድ እኔ በውሃ እያጠመቅሁ መጣሁ፡፡»32ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየሁ፡፡33እኔ አላወቅሁትም ነበር፤ ነገር ግን በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝ እርሱ፣ 'መንፈስ ሲወርድበትና ሲያርፍበት የምታየው፣ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው እርሱ ነው' አለኝ፡፡34እኔ ይህን አይቻለሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነም መስክሬአለሁ፡፡»35ደግሞም በማግስቱ፣ ዮሐንስ ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ቆሞ ሳለ፣36ኢየሱስን በአጠገባቸው ሲያልፍ አዩት፤ ዮሐንስም፣ «እነሆ፣ የእግዚአብሔር በግ» አለ፡፡37ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ዮሐንስ ይህን ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት፤38ከዚያም ኢየሱስ መለስ ብሎ ሲከተሉት አየና፣ «ምን ትፈልጋላችሁ?» አላቸው፡፡ እነርሱ፣ «ረቢ የት ነው የምትኖረው?» አሉት። ረቢ ማለት 'መምህር' ማለት ነው።39እርሱ፣ «ኑና እዩ» አላቸው፡፡ ከዚያም እነርሱ መጥተው የሚኖርበትን አዩ፤ በዚያም ቀን ዐብረውት ዋሉ፤ ሰዓቱም ዐሥረኛው ሰዓት ያህል ሆኖ ነበርና፡፡40ዮሐንስ ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ፡፡41እርሱ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ጴጥሮስን አገኘውና፣ «መሲሑን አግኝተነዋል» አለው። መሲሕ 'ክርስቶስ ማለት ነው'፡፡42ወደ ኢየሱስም አመጣው፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስን ተመለከተውና፣ «አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ ኬፋ ትባላለህ» አለው። ኬፋ 'ጴጥሮስ ማለት ነው'፡፡43በማግስቱ፣ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ በፈለገ ጊዜ፣ ፊልጶስን አግኝቶ፣ «ተከተለኝ» አለው፡፡44ፊልጶስም ጴጥሮስና እንድርያስ ከሚኖሩበት ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበር፡፡45ፊልጶስ ናትናኤልን አገኘውና፣ «ሙሴ በሕግ፣ ነቢያትም በትንቢት የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስ አግኝተነዋል» አለው፡፡46ናትናኤል፣ «ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?» አለው፡፡ ፊልጶስም መጥተህ እይ አለው፡፡47ኢየሱስ፣ ናትናኤል ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፣ «እነሆ፣ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ!» አለ።48ናትናኤል፣ «እንዴት ታውቀኛለህ?» አለው፡፡ኢየሱስም፣ «ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አየሁህ» ብሎ መለሰለት፡፡49ናትናኤል፣ «አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ!» ብሎ መለሰለት፡፡50ኢየሱስ፣ «ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ገና ከዚህ የሚበልጡ ነገሮችን ታያለህ» ብሎ መለሰለት፡፡51ኢየሱስ፣ «እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማያት ሲከፈቱ መላእክትም በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ» አለ፡፡
1በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች።2ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ተጠርተው ነበር፡፡3የወይን ጠጁ ባለቀ ጊዜ፣ የኢየሱስ እናት ኢየሱስን፣ «የወይን ጠጅ እኮ ዐልቆባቸዋል» አለችው፡፡4ኢየሱስ መልሶ፣ «አንቺ ሴት፣ ከዚህ ጋር እኔ ምን ጉዳይ አለኝ? ጊዜዬ እኮ ገና አልደረሰም» አላት፡፡5እናቱ ለአሳላፊዎቹ፣ እርሱ «የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ» አለቻቸው፡፡6በዚያ፣ ለአይሁድ የመንጻት ሥርዐት የሚያገለግሉ እያንዳንዳቸው ሁለት ወይም ሦስት እንስራ የሚይዙ ስድስት የድንጋይ ጋኖች ነበሩ፡፡7ኢየሱስ፣ «ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው» አላቸው፡፡ እነርሱም እስከ አፋቸው ሞሉአቸው፡፡8ከዚያም ኢየሱስ አሳላፊዎቹን፣ «ጥቂት ቅዱና ለመስተንግዶው ኀላፊ ስጡት» አላቸው፤ እነርሱም እንዳላቸው አደረጉ፡፡9የመስተንግዶው ኀላፊ፣ ወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ ቀመሰው፤ ከየት እንደ መጣ ግን አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አሳላፊዎች ግን ያውቁ ነበር፡፡ እርሱም ሙሽራውን ጠርቶ10«ሰው ሁሉ መልካሙን ወይን ጠጅ በመጀመሪያ ያቀርባል፤ መናኛውን ሰዎች ከሰከሩ በኋላ ነው የሚያቀርበው፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን ድረስ አቈይተሃል» አለው፡፡11ይህ በገሊላ ቃና የተደረገው ተአምር ኢየሱስ ካደረጋቸው ተአምራዊ ምልክቶች የመጀመሪያ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።12ከዚህ በኋላ ከእናቱ፣ ከወንድሞቹና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም ጥቂት ቀናት ቈዩ፡፡13የአይሁድ ፋሲካ ቀርቦ ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡14በቤተ መቅደስ ውስጥ በሬዎችን፣ በጎችንና ርግቦችን ሲሸጡ የነበሩ ሰዎችን አገኘ፡፡ ገንዘብ ለዋጮችም ደግሞ በዚያ ተቀምጠው ነበር፡፡15እርሱም የገመድ ጅራፍ አበጅቶ በጎችንና ከብቶችን ጭምር ሁሉንም ከቤተ መቅደስ አስወጣቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለባበጠ።16ርግብ ሻጮችንም፣ «እነዚህን ከዚህ አስወጧቸው፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት ማድረጋችሁን አቁሙ!» አላቸው።17ደቀ መዛሙርቱ፣ «ለቤትህ ያለኝ ቅናት ይበላኛል» ተብሎ የተጻፈውን አስታወሱ፡፡18ከዚያም የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች፣ «እነዚህን ነገሮች ለማድረግ መብት እንዳለህ ምን ምልክት ታሳየናለህ?» በማለት መለሱለት፡፡19ኢየሱስ፣ «ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ እኔ በሦስት ቀን አስነሣዋለሁ» ብሎ መለሰ፡፡20ከዚያም አይሁድ፣ «ይህን ቤተ መቅደስ ለመገንባት ዐርባ ስድስት ዓመት ፈጅቶአል፤ አንተ በሦስት ቀን መልሰህ ታስነሣዋለህ?» አሉት።21ይሁን እንጂ፣ እርሱ ቤተ መቅደስ ብሎ የተናገረው፣ ስለ ራሱ ሰውነት ነበር።22ከሙታን ከተነሣም በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ይህን እንደ ተናገረ አስታወሱ፤ መጻሕፍትንና ኢየሱስ የተናገረውንም ቃል አመኑ።23በፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ሳለ፣ ያደረጋቸውን ተአምራት አይተው ብዙዎች በስሙ አመኑ።24ሆኖም፣ ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ስለ ነበር፣ እነርሱን አላመናቸውም፤25ደግሞም በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ስለ ነበር፣ ማንም ስለ ሰው እንዲመሰክርለት አያስፈልገውም ነበር።
1ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ፣ ስሙ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ የአይሁድ ሸንጎ አባል ነበር ፤2ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ «መምህር ሆይ፣ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ክሆነ ሰው በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ማንም ማድረግ ስለማይችል፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር መሆንህን እናውቃለን» አለው።3ኢየሱስ፣ «እውነት እልሃለሁ፣ ሰው ዳግም ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም» ብሎ መለሰለት።4ኒቆዲሞስ፣ «ሰው ካረጀ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ወደ እናቱ ማኅፀን ዳግመኛ ገብቶ ሊወለድ ይችላልን?» አለው።5ኢየሱስ መልሶ፣ «እውነት፣ እውነት፣ እልሃለሁ፣ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።6ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።7'ዳግም መወለድ አለባችሁ' ስላልሁህ አትደነቅ፤8ነፋስ ወደ ፈለገው ይነፍሳል፤ ድምፁን ትሰማለህ፣ ነገር ግን ከየት እንደ መጣ፣ ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስም የተወለደ ሁሉ እንደዚሁ ነው።»9ኒቆዲሞስ፣ «ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?» በማለት መለሰ።10ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ሳለ እነዚህን ነገሮች አታውቅምን?11እውነት፣ እውነት፣ እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ እናንተ ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉም።12ስለ ምድራዊው ነገር ነግሬአችሁ ያላመናችሁ፣ ስለ ሰማያዊው ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?13ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር፣ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም።14ሙሴ እባብን በምድረ በዳ እንደ ሰቀለ፣ እንዲሁ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል።15ይህም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው።16በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤17እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ላይ ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።18በእርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል።19የፍርዱ ምክንያት ይህ ነው፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ነበረ፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ፤20ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ ድርጊቱም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።21እውነትን በተግባር ላይ የሚያውል ሰው ግን ሥራው እግዚአብሔርን በመታዘዝ የተፈጸመ መሆኑ በግልጽ እንዲታይ ወደ ብርሃን ይመጣል።»22ከዚህ በኋላ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ አገር ሄዱ፤ በዚያ ከእነርሱ ጋር ቆየ፤ ያጠምቅም ነበር፤23በዚህ ጊዜ ዮሐንስም በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ብዙ ውሃ ስለ ነበረ፣ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም ወደ እርሱ እየመጡ ይጠመቁ ነበር።24ምክንያቱም ዮሐንስ ገና በወኅኒ አልተጣለም ነበር።25ከዚያም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአንድ አይሁዳዊ መካከል ስለ መንጻት ሥርዐት ክርክር ተነሣ።26ደቀ መዛሙርቱ ወደ ዮሐንስም መጥተው፣ «መምህር ሆይ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው ስለ እርሱ የመሰከርክለት ሰው፣ እነሆ እያጠመቀ ነው፤ ሁሉም ወደ እርሱ እየሄዱ ነው አሉት።»27ዮሐንስ መልሶ እንዲህ አለ፤ «ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በቀር ምንም ነገር ሊቀበል አይችልም።28'እኔ ክርስቶስ አይደለሁም' ነገር ግን 'ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ' ማለቴን እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ።29ሙሽሪት ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ አጅቦት ቆሞ የሚሰማው ሚዜው በሙሽራው ድምፅ እጅግ ደስ ይለዋል። አሁን ይህ ደስታዬ ፍጹም ሆኖእል።30እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባል።31ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።32እርሱ ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን ምስክርነቱን ማንም አይቀበልም።33ምስክርነቱን የተቀበለ ሰው የእግዚአብሔርን እውነተኝነት አረጋግጧል።34እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።35አብ ወልድን ይወዳል ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል።36በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ለልጁ የማይታዘዝ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።»
1ፈሪሳውያን ኢየሱስ ከዮሐንስ የበለጠ ብዙ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እንደሚያደርግና እንደሚያጠምቅ ሰሙ፤ ኢየሱስም ይህን ዐወቀ፤2(ያጠምቁ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ እንጂ እርሱ ባይሆንም)፣ ኢየሱስ መስማታቸውን ባወቀ ጊዜ3የይሁዳን ምድር ለቅቆ ወደ ገሊላ ሄደ።4በሰማርያም በኩል ማለፍ ነበረበት።5ከዚያም በሰማርያ ከተማ፣ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደምትገኝ፣ ሲካር ወደምትባል ቦታ መጣ።6በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጒድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስ ከጒዞው ብዛት ደክሞት ስለ ነበር፣ በውሃው ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም እኩለ ቀን አካባቢ ነበር።7አንዲት ሳምራዊት ሴት ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ፣ ኢየሱስ፣ «እባክሽ የምጠጣው ውሃ ስጪኝ» አላት።8ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ለመግዛት ወደ ከተማ ሄደው ነበር።9ሳምራዊቷም ሴት፣ «አንተ አይሁዳዊ ሆነህ፣ እኔን ሳምራዊቷን ሴት እንዴት ውሃ አጠጪኝ ትለኛለህ?» አለችው። አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።10ኢየሱስ፣ «የእግዚአብሔርን ስጦታና ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን እንደሆነ ዐውቀሽ ቢሆን ኖሮ ፣ አንቺው በጠየቅሽው፣ እርሱም ሕያው ውሃ በሰጠሽ ነበር» ብሎ መለሰላት።11ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ «ጌታ ሆይ፣ አንተ መቅጃ የለህም፤ ጒድጓዱም ጥልቅ ነው፤ ታዲያ ሕያዉን ውሃ ከየት ታገኛለህ?12አንተ፣ ይህን ጒድጓድ ከሰጠን፣ ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እርሱ ራሱ፣ ልጆቹና ከብቶቹም ከዚሁ ጒድጓድ ጠጥተዋል።13ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፤ «ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤14እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ፈጽሞ ዳግመኛ አይጠማም፤ ይልቁንም፣ እኔ የምሰጠው ውሃ፣ ከውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል።»15ሴትዮዋም፣ «ጌታዬ፤ ከእንግዲህ እንዳልጠማና ውሃ ለመቅዳት ወደዚህ እንዳልመጣ፣ ይህን ውሃ ስጠኝ» አለችው።16ኢየሱስም፣ «ሂጂ፣ ባልሽን ጥሪና ወደዚህ ተመልሰሽ ነይ» አላት።17ሴትዮዋ፣ «ባል የለኝም» በማለት መለሰች፤ ኢየሱስ፣ 'ባል የለኝም' በማለትሽ ልክ ነሽ፤18አምስት ባሎች ነበሩሽና፤ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ሰው ባልሽ አይደለም፤ ስለዚህ እውነቱን ተናግረሻል» ብሎ መለሰ።19ሴትዮዋ፣ «ጌታ ሆይ፣ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ ይገባኛል፤20አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ ግን ሰው መስገድ ያለበት በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ» አለችው።21ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፤ «አንቺ ሴት፣ በዚህ ተራራም ሆነ በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ እየመጣ መሆኑን እመኚኝ።22እናንተ ሳምራውያን ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ። እኛ ግን፣ ድነት ከአይሁድ ስለ ሆነ፣ ለምናውቀው እንሰግዳለን።23ይሁን እንጂ፣ በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ አሁንም መጥቶአል፤ አብ እንደዚህ በእውነት የሚሰግዱለትን ሰዎች ይፈልጋልና።24እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።»25ሴትዮዋ፣ «ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉንም ነገር ይነግረናል» አለችው።26ኢየሱስ፣ «አሁን እያነጋገርሁሽ ያለሁት እኔ እርሱ ነኝ» አላት።27ልክ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሰው መጡ፤ ኢየሱስ ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተገረሙ፤ ይሁን እንጂ፣ ማንም፣ «ምን ትፈልጋለህ? ወይም ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?» ያለው የለም።28ሴትዮዋ እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ተመለሰች፤ ለሕዝቡም፣29«ያደረግሁትን ነገር ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?» አለች፤30ሕዝቡ ከከተማ ወጥተው እርሱ ወዳለበት መጡ።31በዚህም መሐል ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ «መምህር ሆይ፣ ምግብ ብላ» አሉት።32እርሱ ግን፣ «እናንተ የማታውቁት፣ የምበላው ምግብ አለኝ» አላቸው።33ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ እርስ በርስ፣ «ምግብ ያመጣለት ሰው ይኖር ይሆን?» ተባባሉ።34ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ «የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው።35እናንተ 'መከር ገና አራት ወር ቀርቶታል፤ ከዚያም መከሩ ይመጣል' ትሉ የለምን? ቀና በሉና ዕርሻዎቹን ተመልከቱ፣ መከሩ ደርሷልና እያልኋችሁ ነው፤36የሚያጭድ ደመወዙን ይቀበላል፤ ለዘላለም ሕይወት የሚሆን ፍሬም ይሰበስባል፤ ስለዚህ የሚዘራውም፣ የሚያጭደውም አብረው ይደሰታሉ።37'አንዱ ይዘራል፣ ሌላውም ያጭዳል' የሚለው አባባል እውነት የሚሆነው በዚህ ምክንያት ነው።38እኔ ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ፤ ሌሎች በሥራ ደከሙ፤ እናንተም በእነርሱ ሥራ ገባችሁ።»39ሴትዮዋ፣ «ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ» ብላ ስለ እርሱ በሰጠችው ምስክርነት የተነሣ፣ በዚያች ከተማ ከሚኖሩ ሳምራውያን ብዙዎቹ በእርሱ አመኑ።40ስለዚህ፣ ሳምራውያኑ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ፣ ከእነርሱ ጋር እንዲቈይ ለመኑት፤ እዚያም ሁለት ቀን ቈየ።41ከቃሉም የተነሣ ሌሎች ብዙ ሰዎች አመኑ።42ሴትዮዋንም፣ «የምናምነው አንቺ ስለ ነገርሽን ቃል ብቻ አይደለም፤ እኛ ራሳችን ሰምተነዋል፤ ይህ ሰው በእውነት የዓለም አዳኝ እንደ ሆነ እናውቃለን» ይሏት ነበር።43ከእነዚያ ሁለት ቀናት በኋላም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ገሊላ ሄደ።44ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር ኢየሱስ ራሱ ተናግሮ ነበርና።45ወደ ገሊላ በደረሰ ጊዜ፣ የገሊላ ሰዎች በደስታ ተቀበሉት፤ እነርሱ በፋሲካ በዓል ወደዚያ ሄደው ስለ ነበር፣ በኢየሩሳሌም ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ አይተው ነበር። እነርሱ ደግሞ ወደ በዓሉ ሄደው ነበርና።46ኢየሱስም ውሃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት፣ በገሊላ ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ ዳግመኛ መጣ፤ በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት አንድ ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የሆነ ሹም ነበር፤47እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መምጣቱን በሰማ ጊዜ፣ ወደ እርሱ ሄደና በሞት አፋፍ ላይ የሚገኘውን ልጁን መጥቶ እንዲፈውስለት ለመነው።48ከዚያም ኢየሱስ፣ «እናንተ ሰዎች ምልክቶችንና ድንቆችን ካላያችሁ አታምኑም» አለው።49ሹሙ፣ «ጌታ ሆይ፤ ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ ውረድ» አለው።50ኢየሱስ፣ «ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት ይኖራል» አለው። ሰውየው ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አምኖ ሄደ።51በመንገድ ላይ ሳለም፣ አገልጋዮቹ አገኙትና ልጁ ተሽሎት በሕይወት እንዳለ ነገሩት።52እርሱም ልጁ የተሻለው በስንት ሰዓት ላይ እንደ ነበረ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ «ትኵሳቱ የለቀቀው ትናንት በሰባተኛው ሰዓት ላይ ነበር» አሉት።53አባትየውም፣ ኢየሱስ «ልጅህ በሕይወት ይኖራል» ብሎት የነበረው በዚያ ሰዓት እንደ ነበረ ተገነዘበ፤ ስለዚህ እርሱ ራሱና ቤተ ሰቡ በሙሉ በኢየሱስ አመኑ።54ይህም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ በመጣ ጊዜ ያደረገው ሁለተኛው ምልክት ነው።
1ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።2በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ፣ አምስት ጣሪያ ያላቸው መመላለሻዎች ነበሩ። በዚያ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የሚባል አንድ መጠመቂያ ነበረ።3በእነዚህ መመላለሻዎች ወለል ላይ በጣም ብዙ ሕሙማን፣ ዐይነ ስውሮች፣ አንካሶች ወይም ሽባዎች ተኝተው ነበር።41«ዐልፎ ዐልፎ የጌታ መልአክ መጥቶ ውሃውን በሚያናውጥበት ጊዜ፣ ቀድሞ ወደ መጠመቂያው የገባ ሰው ከሚሠቃይበት ከማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር» የሚለውን ክፍል እንድትተዉት እንመክራለን።5በዚያም ለሠላሳ ስምንት ዓመት ሽባ ሆኖ የኖረ አንድ ሰው ነበረ።6ኢየሱስ ሰውየውን እዚያ ተኝቶ ባየው ጊዜ፣ ለረጅም ጊዜ በዚያ መቆየቱን ዐውቆ፣ «መዳን ትፈልጋለህን?» አለው።7ሕመምተኛውም ሰው መልሶ፣ «ጌታ ሆይ፣ ውሃው በሚናወጥበት ጊዜ መጠመቂያው ውስጥ የሚያስገባኝ ሰው የለኝም፤ ለመግባትም ስሞክር ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል» አለው።8ኢየሱስ፣ «ተነሥ! የተኛህበትን ምንጣፍ ተሸክመህ ሂድ» አለው።9ሰውየው ወዲያውኑ ተፈወሰ፤ የተኛበትንም ምንጣፍ ተሸክሞ ሄደ። ያም ቀን ሰንበት ነበረ።10ስለዚህ የአይሁድ መሪዎች የተፈወሰውን ሰው፣ «ሰንበት ነው፤ ምንጣፍህን ልትሸከም አልተፈቀደልህም» አሉት።11እርሱ ግን፣ «ያ ያዳነኝ ሰው፣ 'የተኛህበትን ምንጣፍ ተሸክመህ ሂድ'» አለኝ ብሎ መለሰላቸው።12እነርሱም፣ «የተኛህበትን ምንጣፍ ተሸክመህ ሂድ» ያለህ ሰው ማን ነው?» ብለው ጠየቁት።13የተፈወሰው ሰው ግን ኢየሱስ ከአጠገቡ ፈቀቅ ስላለና በስፍራው ብዙ ሕዝብ ስለ ነበር፣ ማን እንደ ፈወሰው አላወቀም።14በኋላ ኢየሱስ ያን ሰው በቤተ መቅደስ አግኝቶት፣ «እነሆ፣ ተፈውሰሃል፤ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ኀጢአት አትሥራ» አለው።15ሰውየው ሄዶ የፈወሰው ኢየሱስ መሆኑን ለአይሁድ መሪዎች ነገራቸው።16ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በሰንበት ስላደረገ፣ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር።17ኢየሱስ፣ «አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው፤ እኔም እሠራለሁ» አላቸው።18በዚህ ምክንያት አይሁድ ኢየሱስ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን አባቴ ነው በማለት፣ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ስላደረገ፣ ሊገድሉት አጥብቀው ይፈልጉ ነበር።19ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ «እውነት እላችኋለሁ፣ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድም ያንኑ ያደርጋልና።20አብ ወልድን ይወዳልና፣ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ነገር ያሳየዋል።21አብ ሙታንን እንደሚያስነሣና ሕይወትንም እንደሚሰጣቸው፣ ወልድም ደግሞ ለሚፈልገው ሁሉ ሕይወትን ይሰጣል።22አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶታል፤23ይኸውም፣ ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ ወልድን የማያከብር፣ የላከውን አብንም አያከብርም።24እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ አይፈረድበትም።25እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእኔን፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ አሁንም መጥቶአል፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።26አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና፤27ወልድ የሰው ልጅ ስለ ሆነ፣ አብ የመፍረድን ሥልጣን ለወልድ ሰጥቶታል።28በዚህ አትደነቁ፤ በመቃብር ውስጥ ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤29መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩም ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።30እኔ ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም፤ የምፈርደው በሰማሁት መሠረት ነው፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ የራሴን ፈቃድ ስለማልሻም፣ ፍርዴ ትክክል ነው።31እኔው ስለ ራሴ ብመሰክር፣ ምስክርነቴ እውነት አይደለም።32ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ አለ፤ እርሱ ስለ እኔ የሚሰጠውም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ።33ወደ ዮሐንስ ልካችሁ ነበር፤ እርሱም ስለ እውነት መስክሮአል፤34ይሁን እንጂ፣ እኔ የሰው ምስክርነት የምቀበል አይደለሁም፤ ነገር ግን ይህን የምናገረው እናንተ እንድትድኑ ነው።35ዮሐንስ እየነደደ ብርሃን የሚሰጥ መብራት ነበረ፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በብርሃኑ ሐሤት ልታደርጉ ፈለጋችሁ።36እኔ ያለኝ ምስክርነት ግን ከዮሐንስ ምስክርነት ይበልጣል፡፡ አብ እንድፈጽመው የሰጠኝ፣ እኔም እየሠራሁት ያለሁት ሥራ አብ እንደ ላከኝ ይመሰክራል።37የላከኝ አብ እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል፤ እናንተም ከቶ ድምፁን አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤38እርሱ በላከው አላመናችሁምና ቃሉ በእናንተ አይኖርም።39በእነርሱ የዘላለምን ሕይወት የምታገኙ ስለሚመስላችሁ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ ይመሰክራሉ፤40እናንተ ወደ እኔ መጥታችሁ ሕይወት ማግኘት አትፈልጉም።41እኔ ከሰው ክብር አልቀበልም፤42ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር በእናንተ ውስጥ እንደሌለ ዐውቃለሁ።43እኔ በአባቴ ስም መጥቼ አልተቀበላችሁኝም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ ግን ትቀበሉታላችሁ።44እናንተ አንዳችሁ ከሌላችሁ ክብር የምትቀበሉ፣ ነገር ግን ከአንዱ አምላክ የሚመጣውን ክብር የማትሹ ከሆነ፣ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?45በአብ ፊት የምከሳችሁ እኔ አልምሰላችሁ፤ የሚከሳችሁ ሌላ አለ እርሱም ተስፋ ያደረጋችሁበት ሙሴ ነው።46ሙሴን ብታምኑ ኖሮ፣ እኔን ባመናችሁ ነበር፤ ምክንያቱም እርሱም የጻፈው ስለ እኔ ነው።47ታዲያ እርሱ የጻፈውን ካላመናችሁ፣ ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ?»
1ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የጥብርያዶስ ባሕር ወደሚባለው ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፡፡2ብዙ ሰዎች ሕመምተኞችን በመፈወስ ያደረጋቸውን ተአምራት ስላዩ ተከተሉት፡፡3ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚያ ተቀመጠ፡፡4የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ተቃርቦ ነበር፡፡5ኢየሱስ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ ባየ ጊዜ፣ ፊልጶስን፣ ‹‹ይህ ሁሉ ሕዝብ እንዲበላ እንጀራ ከየት እንግዛ?›› አለው፡፡6ኢየሱስ ይህን ያለው ፊልጶስን ሊፈትን ነበር እንጂ፣ እርሱ ራሱ ሊያደርግ ያሰበውን ያውቅ ነበር፡፡7ፊልጶስ፣ ‹‹ይህ ለእያንዳንዱ ሰው ቍራሽ እንዲደርሰው የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ እንኳ ብንገዛ አይበቃም›› አለ፡፡8ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም የሆነው እንድርያስም ኢየሱስን፣9‹‹አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ አንድ ልጅ እዚህ አለ፤ ነገር ግን ይህ ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምን ይጠቅማል?›› አለው፡፡10ኢየሱስ፣ ‹‹ሕዝቡ እንዲቀመጡ አድርጉ›› አላቸው፡፡ ስፍራውም በሣር የተሸፈነ ነበር፡፡ ስለዚህ ቍጥራቸው አምስት ሺህ የሚያህል ወንዶች ተቀመጡ፡፡11ከዚያም ኢየሱስ እንጀራውንና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ባረከና ለተቀመጡት ዐደለ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ከዓሣውም የሚፈልጉትን ያህል ዐደላቸው፡፡12ሕዝቡ በጠገቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ ‹‹አንዳችም እንዳይጣል የተረፈውን ፍርፋሪ ሰብስቡ›› አላቸው፡፡13ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡ ከበሉ በኋላ የተረፈውን ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ የገብስ እንጀራ ፍርፋሪ ሰበሰቡ፡፡14ከዚያም ሕዝቡ ኢየሱስ ያደረገውን ይህን ምልክት ባዩ ጊዜ፣ ‹‹ይህስ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው›› አሉ፡፡15ኢየሱስም ሊመጡና ይዘው በግድ ሊያነግሡት እንደ ፈለጉ በተረዳ ጊዜ፣ እንደ ገና ለብቻው ወደ ተራራ ጫፍ ወጣ፡፡16በመሸም ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕሩ ወረዱ፤17በጀልባ ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም በባሕር ላይ መጓዝ ጀመሩ፡፡ ጊዜው መሽቶ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፡፡18በዚህ ጊዜ ባሕሩ ከኀይለኛ ነፋስ የተነሣ ይታወክ ነበር፡፡19ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ እነርሱ ወዳሉበት ጀልባ ሲቃረብ አይተውት ፈሩ፡፡20ይሁን እንጂ እርሱ፣ ‹‹እኔ ነኝ አትፍሩ›› አላቸው፡፡21ከዚያም ጀልባዋ ላይ እንዲወጣ ፈቀዱለት፣ ጀልባዋም ወዲያው ወደሚሄዱበት ስፍራ ደረሰች፡፡22በማግስቱም በማዶ ቆመው የነበሩ ሕዝብ አንድም ጀልባ በባሕሩ ላይ እንዳልነበረ አዩ፤ በዚያ የነበረው አንድ ጀልባ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ያልተሳፈረበት ብቻ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም ብቻቸውን ከዚያ ሄደው ነበር፡፡23ይሁን እንጂ ጌታ አመስግኖ ሰዎቹን እንጀራ ካበላበት ስፍራ አጠገብ፣ ከጥብርያዶስ የመጡ አንዳንድ ጀልባዎች እዚያ ነበሩ፡፡24ሕዝቡም፣ ኢየሱስም ሆነ ደቀ መዛሙርቱ እዚያ እንዳልነበሩ በተረዱ ጊዜ፣ ራሳቸው በጀልባዎቹ ተሳፍረው ኢየሱስን ፍለጋ ሄዱ፡፡25በባሕሩ ማዶ ኢየሱስን ባገኙት ጊዜ፣ ‹‹መምህር ሆይ፤ ወደዚህ የመጣኸው መቼ ነው?›› አሉት፡፡26ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ ‹‹እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እኔን የምትፈልጉኝ ምልክቶችን ስላያችሁ ሳይሆን፣ እንጀራውን በልታችሁ ስለ ጠገባችሁ ነው፡፡27ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቁን ወልድ ለሚሰጣችሁ ዘላለም ለሚኖር ሕይወት ሥሩ፤ እግዚአብሔር አብ ማኅተሙን በእርሱ ላይ አትሞአልና፡፡››28ከዚያም፣ ‹‹የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ?›› አሉት፡፡29ኢየሱስ፣ ‹‹የምትሠሩት የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው ማመን ነው›› ብሎ መለሰላቸው፡፡30ስለዚህ እነርሱ እንዲህ አሉት፤ ‹‹አይተን እንድናምንህ ምን ተአምር ትሠራለህ? ምንስ ታደርጋለህ?31‹እንዲበሉ ከሰማይ እንጀራ ሰጣቸው› ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ፡፡››32ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ መና እንድትበሉ ከሰማይ የሰጣችሁ ሙሴ አልነበረም፤ ነገር ግን ከሰማይ እውነተኛ እንጀራ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው፤33ከሰማይ የሚወርድና ለዓለም ሕይወትን የሚሰጥ የእግዚአብሔር እንጀራ ነውና፡፡››34ስለዚህ፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን›› አሉት፡፡35ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ከቶ አይጠማም፡፡36ነገር ግን እኔን አይታችሁ አሁንም ገና ስላላመናችሁብኝ ይህን አልኋችሁ፡፡37አባቴ የሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ እኔም አባቴ የሰጠኝን ከቶ ወደ ውጭ አላባርርም፡፡38ከሰማይ የወረድሁት የራሴን ፈቃድ ለማድረግ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለመፈጸም ነውና፡፡39የላከኝም ፈቃድ፣ እርሱ ከሰጠኝ ሁሉ አንድም ሳይጠፋ፣ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣቸው ነው፡፡40የአባቴ ፈቃድ፣ ወልድን አይቶ በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፡፡ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡››41ከዚያም የአይሁድ መሪዎች፣ ‹‹እኔ ከሰማይ የወረድሁ የሕይወት እንጀራ ነኝ›› በማለቱ አጕረመረሙበት፡፡42እነርሱ፣ ‹‹ይህ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? አባቱንና እናቱንስ የምናውቃቸው አይደሉምን? ታዲያ፣ እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል?›› ተባባሉ፡፡43ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ ‹‹እርስ በርስ ማጕረምረማችሁን ተዉት፡፡44አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ የሚመጣ የለም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡45በነቢያት፣ ‹ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ› ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ከአብ የሰማና የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፡፡46ከእግዚአብሔር ከሆነው በቀር አብን ያየ ማንም የለም፤ እርሱ አብን አይቶታል፡፡47እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡48እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ፡፡49አባቶቻችሁ በበረሐ መና በሉ፣ ሞቱም፡፡50ሰው በልቶት እንዳይሞት፣ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፡፡51ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡ ለዓለም ሕይወት እንዲሆነው የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው፡፡››52አይሁድ በዚህ አባባሉ ተቈጥተው፣ ‹‹ይህ ሰው እንዴት እንድንበላ ሥጋውን ሊሰጠን ይችላል?›› በማለት እርስ በርስ ተከራከሩ፡፡53ከዚያም ኢየሱስ፣ ‹‹እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፣ ደሙንም ካልጠጣችሁ የራሳችሁ የሆነ ሕይወት አይኖራችሁም›› አላቸው፡፡54‹‹ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፤55ሥጋዬ እውነተኛ መብል፣ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና፡፡56ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ፡፡57ሕያው አብ እንደ ላከኝና እኔ ከአብ የተነሣ እንደምኖር፣ የሚበላኝም ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል፡፡58አባቶቻችን በልተውት እንደ ሞቱ ዐይነት ሳይሆን፣ ይህ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ነው፡፡ ይህን እንጀራ የበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡››59ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቅፍርናሆም፣ በምኵራብ ሲያስተምር ነበር፡፡60ከዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ይህን ሲሰሙ፣ ‹‹ይህ ጠንካራ ትምህርት ነው፤ ማን ሊቀበለው ይችላል?›› አሉ፡፡61ኢየሱስ በዚህ ማጕረምረማቸውን በገዛ ራሱ ስላወቀ፣ ‹‹ይህ አሰናከላችሁ እንዴ?62ታዲያ፣ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበረበት ስፍራ፣ ተመልሶ ወደ ላይ ሲወጣ ብታዩ ምን ልትሉ ነው?63ሕይወት የሚሰጠው መንፈስ ነው፤ ሥጋ ለምንም አይጠቅምም፡፡ እኔ የነገርኋችሁ ቃላት መንፈስ ናቸው፤ ሕይወትም ናቸው፡፡64ይሁን እንጂ፣ ከእናንተ መካከል የማያምኑ አንዳንዶች አሉ›› አለ፡፡ ከመጀመሪያው በእርሱ የማያምኑ እነማን እንደ ሆኑና የሚከዳው ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበርና፡፡65ደግሞም፣ ‹‹ከአብ ከተሰጠው በቀር ማንም ወደ እኔ ሊመጣ አይችልም ያልኋችሁ ለዚህ ነው›› አለ፡፡66ከዚህ በኋላ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ትተውት ወደ ኋላቸው ተመለሱ፤ አብረውትም አልተጓዙም፡፡67ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን፣ ‹‹እናንተም ትታችሁኝ ልትሄዱ ትፈልጋላችሁን?›› አላቸው፡፡68ስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤69እኛም አምነናል፤ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ መሆንህንም ዐወቀናል፡፡››70ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ዐሥራ ሁለታችሁንም መርጫችሁ የለም ወይ? ከእናንተም መካከል አንዱ ዲያብሎስ ነው›› አላቸው፡፡71ይህን ያለው ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ስለ ሆነውና ኋላም ኢየሱስን አሳልፎ ስለ ሰጠው፣ ስለ አስቆሮቱ ስምዖን ልጅ፣ ስለ ይሁዳ ነው፡፡
1ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር፣ ወደ ይሁዳ መሄድ አልፈለገም፤ ስለዚህ እዚያው በገሊላ ውስጥ ይመላለስ ነበር፡፡2የአይሁድ የዳስ በዓል የሚከበርበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፡፡3ስለዚህ ወንድሞቹ እንዲህ አሉት፤ ‹‹ተነሥተህ ከዚህ ስፍራ ወደ ይሁዳ አውራጃ ሂድ፤ ደቀ መዛሙርትህም ደግሞ አንተ የምትሠራውን ሥራ ይዩ፡፡4በሕዝብ ፊት መታወቅ የሚፈልግ ሰው የሚሠራውን ሥራ በድብቅ አያደርግም፡፡ እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ፣ ራስህን ለዓለም አሳይ፡፡››5ምክንያቱም ወንድሞቹ እንኳ ገና አላመኑበትም ነበር፡፡6ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ጊዜዬ ገና ነው፡፡ ለእናንተማ ጊዜው ሁሉ የተመቸ ነው፡፡7ዓለም እናንተን ሊጠላችሁ አይችልም፡፡ እኔን ግን በክፉ ሥራው ስለምመሰክርበት፣ ይጠላኛል፡፡8እናንተ ወደ በዓሉ ውጡ፤ እኔ ግን ጊዜዬ ገና ስላልደረሰ፣ ወደ በዓሉ አልሄድም፡፡››9እርሱ ይህን ካላቸው በኋላ፣ በገሊላ ቈየ፡፡10ነገር ግን ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ እርሱም በግልጽ ሳይሆን በስውር ወደዚያው ሄደ፡፡11አይሁድ በበዓሉ ላይ ሊፈልጉት ሄደው፣ ‹‹እርሱ ያለው የት ነው?›› አሉ፡፡12በሕዝቡም መካከል ብዙ ውይይት ተነሥቶ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ፣ ‹‹እርሱ ጥሩ ሰው ነው›› አሉ፤ ሌሎቹም፣ ‹‹አይደለም፣ ሕዝቡን እያሳተ ነው›› አሉ፡፡13ይሁን እንጂ፣ አይሁድን ስለ ፈሩ፣ ስለ እርሱ በግልጽ የተናገረ ማንም አልነበረም፡፡14በበዓሉ አጋማሽ ላይ፣ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ወጥቶ ማስተማር ጀመረ፡፡15አይሁድም እየተደነቁ፣ ‹‹ይህ ሰው እንዴት ይህን ሁሉ ዐወቀ? ትምህርት እንኳ አልተማረም›› ይሉ ነበር፡፡16ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹የማስተምረው ከራሴ አይደለም፤ ነገር ግን ትምህርቴ ከላከኝ ነው›፡፡17ማንም የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ ቢፈልግ፣ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር የመጣ መሆኑን ወይም ከራሴ የምናገር መሆኑን ያውቃል፡፡18ከራሱ የሚናገር የራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላከውን ክብር የሚፈልግ ግን እውነተኛ ነው፤ ሐሰትም የለበትም፡፡19ሙሴ ሕግ ሰጥቶአችሁ አልነበረምን? ነገር ግን ከእናንተ ሕጉን የሚጠብቅ አንድም ሰው የለም፡፡ ለመሆኑ፣ ልትገድሉኝ የምትፈልጉት ለምንድን ነው?››20ሕዝቡ፣ ‹‹ጋኔን አለብህ፤ አንተን ማን ሊገድል ይፈልጋል?›› ብለው መለሱ፡፡21ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹አንድን ሥራ በመሥራቴ ሁላችሁም በዚህ ትደነቃላችሁ፡፡22ሙሴ ግዝረትን ሰጣችሁ፤ ይህም የመጣው ከአባቶች እንጂ ከሙሴ አልነበረም፤ ስለሆነም፣ በሰንበት ቀን ሰውን ትገርዛላችሁ፡፡23ሰውን በሰንበት ቀን ስትገርዙ የሙሴ ሕግ የማይሻር ከሆነ፣ እኔ በሰንበት ቀን የሰውን መላ አካል ስላዳንሁ ለምን በእኔ ላይ ትቈጣላችሁ?24መልክ በማየት ሳይሆን በቅንነት ፍረዱ፡፡››25ከኢየሩሳሌም ከመጡት አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፤ ‹‹ሊገድሉት የሚፈልጉት ይህን ሰው አልነበረም?26ተመልከቱ፤ እንዲህ በግልጽ እየተናገረ ምንም አይሉትም፡፡ ገዦቹ እርሱ በትክክል ክርስቶስ መሆኑን ዐውቀው ይሆን?27እኛ ግን ይህ ሰው ከየት እንደ መጣ እናውቃለን፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ማንም ከየት እንደ መጣ አያውቅም፡፡››28ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ ‹‹እኔን ታውቁኛላችሁ፤ ከየት እንደ መጣሁም ታውቃላችሁ፤ ሆኖም በራሴ አልመጣሁም፤ የላከኝ ግን እውነተኛ ነው፤ እርሱን ደግሞ እናንተ አታውቁትም፡፡29እኔ ከእርሱ ዘንድ ስለ መጣሁ፣ ዐውቀዋለሁ፤ የላከኝም እርሱ ነው፡፡››30እነርሱም በዚህ ጊዜ ሊይዙት ሞከሩ፤ ነገር ግን የነካው አንድም ሰው አልነበረም፤ ምክንያቱም የተወሰነለት ሰዓት ገና ነበር፡፡31ይሁን እንጂ፣ በሕዝቡ መካከል ብዙዎች በእርሱ አመኑ፡፡ ያመኑትም፣ ‹‹ክርስቶስ ሲመጣ ይህ ሰው ከሠራው ተአምር የሚበልጥ ሊሠራ ይችላልን?›› አሉ፡፡32ፈሪሳውያን ሕዝቡ ስለ ኢየሱስ በሹክሹክታ የሚያወሩትን ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሊያስይዙት የጥበቃ ሰዎችን ላኩበት፡፡33ኢየሱስ፣ ‹‹ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ከዚያም ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፡፡34ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፡፡ እናንተ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም›› አላቸው፡፡35ስለዚህ አይሁድ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ ‹‹ይህ ሰው እንዳናገኘው ወዴት ሊሄድ ነው? ተበትነው በግሪክ ወዳሉት ሰዎች ሄዶ እነርሱን ሊያስተምር ይሆን?36‹ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፡፡ እናንተ እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም› ያለውስ ቃል ምን ማለት ነው?››37በታላቁ የበዓሉ ቀን፣ በመጨረሻው ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ድምፁን ከፍ በማድረግ፣ ‹‹የተጠማ ማንም ቢኖር፣ ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ፡፡38ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተናገሩት፣ በእኔ የሚያምን የሕይወት ውሃ ወንዝ ከውስጡ ይፈልቃል›› አለ፡፡39ይህን ያለው ግን በእርሱ የሚያምኑት ወደ ፊት ስለሚቀበሉት፣ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ፣ መንፈስ ቅዱስ ገና አልተሰጠም ነበር፡፡40ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ይህን ቃል ሲሰሙ፣ ‹‹ይህ በእርግጥ ነቢዩ ነው›› አሉ፡፡41ሌሎቹ ደግሞ፣ ‹‹እርሱ ክርስቶስ ነው›› አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግን፣ ‹‹ክርስቶስ ከገሊላ እንዴት ይመጣል!42ቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ ከዳዊት ዘር፣ የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከቤተ ልሔም እንደሚመጣ ተናግረው የለምን?›› አሉ፡፡43ስለዚህ እርሱን በተመለከተ በመካከለቸው መለያየት ተከሠተ፡፡44ከእነርሱ አንዳንዶቹ ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ማንም አልነካውም፡፡45ከዚያም የጥበቃ ሰዎቹ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን ተመልሰው መጡ፤ የላኳቸውም፣ ‹‹ለምንድን ነው ይዛችሁ ያላመጣችሁት?›› አሏቸው፡፡46የጥበቃ ሰዎቹ፣ ‹‹ከዚህ ቀደም እንደዚህ የተናገረ አልነበረም›› አሏቸው፡፡47ፈሪሳውያንም እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተም ሳታችሁን?48ከገዦቹ ወይም ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለ?49ነገር ግን ሕጉን የማያውቅ ይህ ሕዝብ የተረገመ ነው፡፡››50ከፈሪሳውያን አንዱ፣ ከዚህ በፊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ፣51‹‹መጀመሪያ ከሰውየው ሳይሰማና የሚሠራውን ሳያውቅ፣ የእኛ ሕግ በሰው ላይ ይፈርዳልን?›› አላቸው፡፡52እነርሱ፣ ‹‹አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህ ወይ? ነቢይ ከገሊላ እንደማይመጣ መርምረህ ዕወቅ›› አሉት፡፡53ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ (*53 የጥንት ቅጆች በዮሐንስ 7፡53-8፡11 ላይ ያለውን ክፍል አያካትቱም፡፡)
1ኢየሱስ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ።2ጠዋት በማለዳ ተመልሶ ወደ ቤተ መቅደስ መጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱም ተቀምጦ አስተማራቸው።3የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያንም ስታመነዝር የተያዘችን ሴት አምጥተው፤ በመካከላቸው አቆሟት።4ከዚያም ኢየሱስን እንዲህ አሉት፤ «መምህር ሆይ፣ ይህች ሴት ስታመነዝር እጅ ከፍንጅ የተያዘች ናት፤5ሙሴ በሕጉ እንዲህ ያሉትን በድንጋይ እንድንወግር አዞናል፤ አንተስ ስለ እርሷ ምን ትላለህ?»6ይህን ያሉት እርሱን ወጥመድ ውስጥ ለማስገባትና ለመክሰስ ፈልገው ነው፤ ኢየሱስ ግን ጎንበስ ብሎ በጣቱ መሬት ላይ ጻፈ።7ጥያቄ ማቅረባቸውን በቀጠሉ ጊዜም፣ ተነሥቶ ቆመና፣ “ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት ሰው በመጀመሪያ ይውገራት” አላቸው።8ዳግመኛም ጐንበስ ብሎ፣ በጣቱ መሬት ላይ ጻፈ።9ይህንም በሰሙ ጊዜ፣ ከታላቅ ጀምረው አንድ ባንድ ወጥተው ሄዱ። በመጨረሻ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ለብቻው ቀረ።10ኢየሱስ ተነሥቶ በመቆም፣ “አንቺ ሴት፤ የከሰሱሽ ሰዎች የት ናቸው? አንድም የፈረደብሽ የለም?” አላት።11እርሷም፣ “ጌታ ሆይ፣ አንድም የለም” አለች። ኢየሱስ፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁን በኋላ ግን ደግመሽ ኀጢአት አትሥሪ” አላት።12ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ ቢኖር የሕይወት ብርሃን ያገኛል እንጂ፣ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።13ፈሪሳውያንም፣ “አንተው ስለ ራስህ ስለምትመሰክር፤ ምስክርነትህ እውነት አይደለም” አሉት።14ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር እንኳ ምስክርነቴ እውነት ነው። ከየት እንደ መጣሁ፣ ወዴትም እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤ እናንተ ግን እኔ ከየት እንደ መጣሁ ወይም ወዴት እንደምሄድ አታውቁም።15እናንተ በሥጋዊ ዐይን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በማንም አልፈርድም።16ብፈርድም እንኳ፣ ብቻዬን አይደለሁም፤ ከላከኝ አብ ጋር ስለ ሆንሁ፣ ፍርዴ እውነት ነው።17አዎን፤ በሕጋችሁ የሁለት ሰዎች ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ ተጽፎአል።18እኔ ስለ ራሴ እመሰክራለሁ፤ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።”19እነርሱም፣ “አባትህ የት ነው ያለው?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እናንተ እኔንም ሆነ አባቴን አታውቁንም፤ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር” አላቸው።20ይህንም የተናገረው በቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት አጠገብ ሆኖ ሲያስተምር ነበር፤ ሆኖም ሰዓቱ ገና ስላልደረሰ፣ ማንም አልያዘውም።21ደግሞም፣ “እኔ ተለይቻችሁ እሄዳለሁ፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ። እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም” አላቸው።22አይሁድም፣ “ይህ 'እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም' የሚለው ራሱን ሊገድል ዐስቦ ይሆን?” አሉ።23ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ከታች ናችሁ፤ እኔ ግን ከላይ ነኝ። እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ግን ከዚህ ዓለም አይደለሁም።24በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ ያልኋችሁ ለዚህ ነው። ምክንያቱም እኔ ነኝ ስላችሁ ካላመናችሁ፣ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ።”25እነርሱም፣ “ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤”ከመጀመሪያው እንደ ነገርኋችሁ ነኝ።26ብዙ የምናገረውና ስለ እናንተም የምፈርደው አለኝ። ይሁን እንጂ የላከኝ እርሱ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን፣ ያንኑ ለዓለም እናገራለሁ።”27እነርሱ ግን ስለ አብ እየነገራቸው እንደ ነበር አልተረዱም።28ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰውን ልጅ ወደ ላይ ከፍ ስታደርጉት፣ በዚያን ጊዜ እኔው እንደ ሆንሁና ከራሴ አንድም ነገር እንደማላደርግ ታውቃላችሁ። አብ እንዳስተማረኝ ይህን እናገራለሁ።29የላከኝ እርሱ ከእኔ ጋር ነው፤ ብቻዬንም አልተወኝም፤ እኔ ሁልጊዜ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር አደርጋለሁና።”30ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በተናገረ ጊዜ ብዙ ሰዎች በእርሱ አመኑ።31ኢየሱስ በእርሱ ያመኑትን አይሁድ፣ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ፣ በርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤32እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል” አላቸው።33እነርሱም፣ “እኛ የአብርሃም ዘሮች ነን፤ የማንም ባሪያ ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ እንዴት ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ ትለናለህ?” አሉት።34ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው።35ባሪያ ለዘለቄታ በቤት አይኖርም፤ ልጅ ግን ለዘለቄታ ይኖራል።36ስለዚህ ልጁ ነጻ ካወጣችሁ፣ በርግጥ ነጻ ትወጣላችሁ።37የአብርሃም ዘር መሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ቃሌን ስላልተቀበላችሁ፣ ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ።38አባቴ ጋ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።”39እነርሱም መልሰው፣ “አባታችንስ አብርሃም ነው” አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ፣ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር።40አሁን ግን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ለመግደል ትፈልጋላችሁ። አብርሃምኮ ይህን አላደረገም።41እናንተ ግን የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ።” እነርሱም፣ “እኛ በዝሙት የተወለድን አይደለንም፤ አንድ አባት እግዚአብሔር አለን” አሉት።42ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ ስለ መጣሁ፣ በወደዳችሁኝ ነበር፤ በራሴም ፈቃድ አልመጣሁም፤ ነገር ግን እርሱ ላከኝ።43ቃሌን የማትረዱት ለምንድን ነው? ምክንያቱም ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው።44እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት ለማድረግ ትመኛላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያውም ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ እውነት በእርሱ ዘንድ ስለሌለም፣ በእውነት አይጸናም። ሐሰትንም ሲናገር ከራሱ አፍልቆ ይናገራል፤ ምክንያቱም እርሱ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት ነው።45እኔ ግን እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም።46ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ሰው ማን ነው? እውነትን የምናገር ከሆነስ፣ ታዲያ ለምን አታምኑኝም?47ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ፣ ቃሉን አትሰሙም።”48አይሁድም፣ “እንግዲህ ጋኔን ያደረብህ ሳምራዊ ነህ በማለታችን እውነት አልተናገርንምን?” በማለት መለሱለት።49ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “እኔ ጋኔን የለብኝም፤ እኔ አባቴን አከብረዋለሁ እንጂ፣ እናንተ ግን ታዋርዱኛላችሁ።50እኔ የራሴን ክብር አልሻም፤ የሚሻና የሚፈርድ አንድ አለ።51እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ማንም ቢኖር፣ እርሱ ሞትን በፍጹም አያይም።”52አይሁድም፣ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን። አብርሃምም ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን 'ማንም ቃሌን ቢጠብቅ ሞትን አይቀምስም' ትላለህ።53አንተ ከሞተው ከአባታችን፣ ከአብርሃም ትበልጣለህን? ነቢያትም ሞተዋል። ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነኝ ልትል ነው?” አሉት።54ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ራሴን ባከብር፣ ክብሬ ከንቱ ነው፤ እኔን የሚያከብረኝ እናንተ አምላካችን ነው የምትሉት አባቴ ነው።55እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ። እኔ ‘አላውቀውም’ ብል እንደ እናንተው ሐሰተኛ እሆናለሁ። ነገር ግን እኔ ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።56አባታችሁ አብርሃም ቀኔን በማየቱ ደስ አለው፤ አይቶም ሐሤት አደረገ።”57አይሁድም፣ “ገና ዐምሳ ዓመት ያልሞላህ፣ አንተ አብርሃምን አይተሃልን?” አሉት።58ኢየሱስም፣ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ አለሁ” አላቸው።59እነርሱም፣ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ራሱን ሰውሮ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ።
1ኢየሱስ በመንገድ ሲያልፍ ፣ ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ስውር የነበረ አንድ ሰው አየ።2ደቀ መዛሙርቱ፣ “መምህር ሆይ፤ ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ያደረገው የራሱ ኀጢአት ነው ወይስ የወላጆቹ?” አሉት።3ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ፣ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኀጢአት አልሠሩም።4የላከኝን ሥራ ቀን ሳለ መሥራት ይገባናል። ማንም ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት እየመጣ ነው።5በዓለም እስካለሁ፣ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።”6ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ፣ መሬት ላይ እንትፍ ብሎ፣ በምራቁ ጭቃ ሠራ፤ በጭቃውም የሰውየውን ዐይን ቀባ።7ሰውየውንም፣ “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠበ” አለው፣ ‘ሰሊሆም’ የተላከ ማለት ነው። ሰውየውም ወደዚያው ሄዶ ታጠበ፤ ዐይኑም እያየለት ተመልሶ መጣ።8የሰውየው ጐረቤቶችና ቀድሞ ለማኝ ሆኖ ያዩት ሰዎችም፣ “ይህ ሰው ተቀምጦ ሲለምን የነበረው ሰው አይደለምን?” አሉ።9አንዳንዶቹ፣ “እርሱ ነው” አሉ፤ ሌሎችም፣ “ይመስለዋል እንጂ እርሱ አይደለም” አሉ። እርሱ ግን፣ “እኔው ነኝ” አለ።10እነርሱም፣ “ታዲያ፣ ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱልህ?” አሉት።11እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ ሠርቶ ዐይኔን ቀባ፤ ከዚያም፣ ‘ወደ ሰሊሆም ሄደህ ታጠብ’ አለኝ። እኔም ሄጄ ታጠብሁ፤ ዐይኖቼም በሩ።”12እነርሱም፣ “ታዲያ፣ እርሱ የት ነው?” አሉ። እርሱም፣ “እኔ አላውቅም” ብሎ መለሰላቸው።13እነርሱም ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት።14ኢየሱስ ጭቃ ሠርቶ የሰውየውን ዐይን የከፈተው በሰንበት ቀን ነበረ።15ፈሪሳውያንም ዐይኑ እንዴት እንደ ተከፈተለት እንደ ገና ሰውየውን ጠየቁት። እርሱም፣ “ዐይኖቼን ጭቃ ቀባ፤ ታጠብሁና ማየት ቻልሁ” አላቸው።16ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፣ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር፣ ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎቹም፣ “ኀጢአተኛ የሆነ ሰው እንዴት እንደዚህ ያለ ተአምር ይሠራል?” አሉ። ስለዚህ በመካከላቸው መከፋፈል ተፈጠረ።17እንደ ገናም ዐይነ ስውሩን ሰው፣ “ዐይንህን ስለ ከፈተው ሰው ምን ትላለህ?” አሉት። ዐይነ ስውሩም፣ “ነቢይ ነው” አለ።18ፈሪሳውያንም ዐይነ ስውር የነበረው ሰው ዐይኖች መከፈታቸውን አሁንም ስላላመኑ፣ ዐይኑ የበራለትን ሰው ወላጆች አስጠሩ።19ወላጆቹንም፣ “ይህ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደ ነው የምትሉት ሰው ልጃችሁ ነውን? ከሆነስ፣ አሁን እንዴት ማየት ቻለ?” ብለው ጠየቋቸው።20ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “ይህ ልጃችን መሆኑንና ዐይነ ስውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን።21አሁን እንዴት ማየት እንደ ቻለ ግን አናውቅም፤ ዐይኑን የከፈተለት ማን እንደ ሆነም አናውቅም። እርሱን ጠይቁት፤ ጕልማሳ ነው፤ ስለ ራሱ መናገር ይችላል።”22ወላጆቹ እንዲህ ያሉት አይሁድን ስለ ፈሩ ነበር። ምክንያቱም አይሁድ፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው የሚል ሰው ካገኙ፣ ከምኵራብ ሊያስወግዱት ቀደም ብለው ተስማምተው ነበር።23ወላጆቹ፣ “እርሱ ጕልማሳ ነው፤ ራሱን ጠይቁት” ያሉትም በዚህ ምክንያት ነበር።24ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው እንደ ገና አስጠርተው፣ “ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ እኛ ይህ ሰው ኀጢአተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን” አሉት።25ሰውየውም፣ “እኔ እርሱ ኀጢአተኛ መሆኑን አላውቅም። ነገር ግን አንድ ነገር ዐውቃለሁ፤ ዐይነ ስውር ነበርሁ፤ አሁን ግን እያየሁ ነው” አላቸው።26እነርሱም፣ “ያደረገልህ ምንድን ነው? ዐይኖችህንስ የከፈተው እንዴት ነው?” አሉት።27እርሱም፣ “አስቀድሜ ነግሬአችሁ ነበር! እናንተ ግን አትሰሙም። እንደ ገና መስማትስ ለምን ፈለጋችሁ? እናንተም የእርሱ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ትፈልጋላችሁን?” ብሎ መለሰ።28ሰደቡትና እንዲህ አሉ፤ “አንተ የእርሱ ደቀ መዝሙር ነህ፣ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን።29እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ መጣ አናውቅም።”30ሰውየውም፣ “ይህ ሰው ከየት እንደ መጣ አለማወቃችሁ የሚገርም ነው፤ ይሁን እንጂ፣ ዐይኔን የከፈተው እርሱ ነው።31እግዚአብሔር ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱን የሚያደርግ ሰው ሁሉ እግዚአብሔር ይሰማዋል።32ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ፣ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደን ሰው ዐይን የከፈተ ሰው ከቶ አልተሰማም።33ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ፣ አንድም ነገር ማድረግ ባልቻለ ነበር።”34እነርሱም፣ መልሰው “አንተ ሁለንተናህ በኀጢአት የተወለደ፣ አሁን አንተ እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት። ከዚያም ከምኵራብ አስወጡት።35ኢየሱስም ሰውየውን ከምኵራብ እንዳስወጡት ሰማ። ሰውየውንም አግኝቶ፣ “በሰው ልጅ ታምናለህን?” አለው።36እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ አምንበት ዘንድ እርሱ ማን ነው?” አለው።37ኢየሱስም፣ “አይተኸዋል፤ አሁን እንኳ ከአንተ ጋር እየተነጋገረ ያለው እርሱ ነው” አለው።38ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፣ አምናለሁ” አለ። ከዚያም ሰገደለት።39ኢየሱስም፣ “የማያዩ እንዲያዩ፣ የሚያዩም እንዳያዩ፣ ለፍርድ ወደዚህ ዓለም መጣሁ” አለ።40ከእነርሱም ጋር ከነበሩት አንዳንድ ፈሪሳውያን ይህን ሰምተው፣ “እኛም ደግሞ ዐይነ ስውራን ነን ወይ?” አሉት።41ኢየሱስም ፣ “ዐይነ ስውራን ብትሆኑማ፣ ኀጢአት ባልሆነባችሁ ነበር። ነገር ግን፣ ‘እናያለን’ ስለምትሉ፣ ኀጢአታችሁ እንዳለ ይኖራል።”
1“እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ወደ በጎች በረት በበር ሳይሆን፣ በሌላ መንገድ ተንጠላጥሎ የሚገባ እርሱ ሌባና ወንበዴ ነው።2በበር የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።3በር ጠባቂውም ለእርሱ ይከፍትለታል። በጎቹም ድምፁን ይሰማሉ፤ እርሱም የራሱን በጎች በስማቸው ጠርቶ፣ ወደ ውጭ ይመራቸዋል።4የራሱን ሁሉ ካወጣቸው በኋላ፣ ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ድምፁን ስለሚያውቁ ይከተሉታል።5ባዕድ የሆነውን አይከተሉትም፤ ይልቁንም የባዕዱን ድምፅ ስለማያውቁት ይሸሹታል።”6ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ስለ ምን እንደ ሆነ አልገባቸውም።7ኢየሱስም እንደ ገና እንዲህ አላቸው፤ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ።8ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ በጎቹ ግን አላዳመጡአቸውም።9በሩ እኔ ነኝ። ማንም በእኔ በኩል ቢገባ፣ ይድናል፤ ይገባል፣ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል።10ሌባው የሚመጣው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ነው። እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።11መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ለበጎቹ ሲል ነፍሱን ይሰጣል።12እረኛ ያልሆነው ተቀጣሪ በጎቹም የእርሱ ያልሆኑት፣ ቀበሮ መምጣቱን ሲያይ በጎቹን ጥሎ ይሸሻል ። ቀበሮም ነጥቆአቸው ይሄዳል፤ ይበታትናቸውማል።13የሚሸሸውም ተቀጣሪ ስለ ሆነና ለበጎቹ ደንታ ስለሌለው ነው።14መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን ዐውቃቸዋለው፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል።15አብ እንደሚያውቀኝ፤ እኔም አብን ዐውቀዋለው፤ ነፍሴንም ስለ በጎች እሰጣለሁ።16ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ። እነዚያን ደግሞ ማምጣት አለብኝ፤ እነርሱ ድምፄን ይሰማሉ። አንድ መንጋ ይሆናሉ፤ እረኛቸውም አንድ ይሆናል።17አባቴ የሚወደኝ ለዚህ ነው፤ መልሼ ልወስደው እንድችል ነፍሴን እሰጣለሁ ።18ነፍሴን ማንም ከእኔ አይወሰድም፤ ግን እኔው ራሴ እሰጣለሁ ። ለመስጠት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ ለመውሰድም ሥልጣን አለኝ። ይህን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀብያለሁ።”19ከዚህ አባባል የተነሣም በአይሁድ መካከል እንደ ገና መከፋፈል ተፈጠረ።20ብዙዎች፣ “ጋኔን ስላለበት ዐብዶአል፤ ለምን ታዳምጡታላችሁ?” አሉ።21ሌሎችም፣ “ንግግሩ ጋኔን ያለበት ሰው ንግግር አይደለም። ጋኔን ያለበት ሰው የዐይነ ስውርን ዐይን መክፈት ይችላልን?” አሉ።22በኢየሩሳሌምም የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል ደርሶ ነበር።23ጊዜው ክረምት ነበረ፤ ኢየሱስም በቤተ መቅደስ በሰሎሞን መተላለፊያ ይመላለስ ነበር።24ከዚያም አይሁድ ወደ እርሱ ተሰብስበው፣ «እስከ መቼ ድረስ ልባችንን ታንጠለጥላለህ? አንተ ክርስቶስ ከሆንህ፣ በግልጽ ንገረን» አሉት።25ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ነገርኋችሁኮ፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ሥራዎች እነዚህ ስለ እኔ ይመሰክራሉ።26እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።27በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል።28የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለው፤ ፈጽሞም አይጠፉም፤ ነጥቆ ከእጄ የሚያወጣቸው ማንም የለም።29እነርሱን ለእኔ የሰጠ አባቴ ከሌሎች ሁሉ ይበልጣል፤ ስለዚህ ከአብ እጅ ነጥቆ ሊያወጣቸው የሚችል ማንም የለም።30እኔና አብ አንድ ነን።”31አይሁድ ሊወግሩት እንደ ገና ድንጋይ አነሡ።32ኢየሱስም መልሶ፣ «ከአብ የሆነ ብዙ መልካም ሥራ አሳይቻችኋለሁ፤ ከእነዚህ ሥራዎች ውስጥ በየትኛው ምክንያት ትወግሩኛላችሁ?” አላቸው።33አይሁድም መልሰው፣ «የምንወግርህ በየትኛውም መልካም ሥራ ምክንያት አይደለም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ በምትሰነዝረው የስድብ ቃል ምክንያት ነው፤ አንተ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ እያደረግህ ስለ ሆነ ነው» አሉት።34ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ «በሕጋችሁ፣ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ’ ተብሎ አልተጻፈምን?35የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ናችሁ ካላቸው፣ የመጻሕፍት ቃል አይሻርምና፣36እኔ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስላልሁ፣ አብ ቀድሶ ወደ ዓለም የላከውን እንዴት የስድብ ቃል ሰነዘረ ትሉታላችሁ?37እኔ የአባቴን ሥራዎች የማላደርግ ከሆንሁ አትመኑኝ።38ነገር ግን የማደርጋቸው ከሆንሁ፣ በእኔ ባታምኑ እንኳ፣ አብ በእኔ እንዳለ፣ እኔም በአብ እንዳለሁ እንድታውቁና እንድትረዱ፣ በሥራዎቹ እመኑ።»39እነርሱም ኢያሱስን እንደ ገና ለመያዝ ሞከሩ፣ እርሱ ግን ከእጃቸው አምልጦ ሄደ።40ኢየሱስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ፣ ዮሐንስ በመጀመሪያ ሲያጠምቅበት ወደ ነበረው ቦታ እንደ ገና ሄደ፤ በዚያም ቆየ ።41ብዙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጡ። እነርሱም፣ «በርግጥ ዮሐንስ ምንም ተአምር አልሠራም፤ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነው» ይሉ ነበር።42በዚያም ብዙ ሰዎች በኢያሱስ አመኑ።
1አልዓዛር የተባለ አንድ ሰውም ታሞ ነበር። እርሱም ማርያምና እኅትዋ ማርታ በሚኖሩበት መንደር በቢታንያ ይኖር ነበር።2ወንድምዋ የታመመባትም የጌታ ኢየሱስን እግር ሽቱ የቀባችውና በጠጕርዋ ያበሰችው ናት።3ከዚያም እኅትማማቹ፣ ‹‹እነሆ፣ የምትወደው ታሞአልና በፍጥነት ድረስ›› በማለት ወደ ኢየሱስ ላኩበት።4ኢየሱስ መልእክቱን በሰማ ጊዜ፣ ‹‹ይህ የእግዚአብሔር ልጅ እንዲከብርበት ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ነው›› አለ።5ኢየሱስ ማርታንና እኅቷን እንዲሁም አልዓዛርን ይወድ ነበር፡፡6ስለሆነም አልዓዛር መታመሙን በሰማ ጊዜ፣ ኢየሱስ በነበረበት ቦታ ሁለት ተጨማሪ ቀናት ቆየ፡፡7ከዚህ በኋላም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ወደ ይሁዳ ዳግመኛ እንሂድ” አላቸው፡፡8ደቀ መዛሙርቱ፣ “መምህር ሆይ፣ አይሁድ አሁን ሊወግሩህ ነበር፣ እንደ ገና ወደዚያ ተመልሰህ ትሄዳለህን?” አሉት፡፡9ኢየሱስም፣ “በአንድ ቀን ውስጥ አሥራ ሁለት የብርሃን ሰዓታት አሉ አይደለምን? አንድ ሰው በቀን የሚራመድ ከሆነ የቀኑን ብርሃን ስለሚመለከት፣ አይደናቀፍም፡፡10በሌሊት የሚራመድ ከሆነ ግን ብርሃኑ በእርሱ ውስጥ ስለሌለ፣ ይደናቀፋል፡፡”11ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ተናገረ፣ ከእነዚህም ነገሮች በኋላ፣ “ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቷል፣ እኔ ግን ከእንቅልፉ ላነቃው እሄዳለሁ” አላቸው፡፡12ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ፣ “ጌታ ሆይ፣ ተኝቶስ ከሆነ ይድናል” አሉት፡፡13ኢየሱስም የተናገረው አልዓዛር ስለ መሞቱ ነበር፣ እነርሱ ግን ዕረፍት ለማድረግ ስለ መተኛቱ የተናገረ መስሎአቸው ነበር፡፡14ከዚያም ኢየሱስ በግልጽ፣ “አልዓዛር ሞቷል15እናንተ ታምኑ ዘንድ እኔ እዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ብሎኛል” አላቸው፡፡16ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ ባልደረቦቹ ደቀ መዛሙርትን፣ “ከኢየሱስ ጋር እንሞት ዘንድ እኛም ከእርሱ ጋር እንሂድ” አላቸው፡፡17ኢየሱስ በመጣ ጊዜ፣ አልዓዛር በመቃብር ውስጥ አራት ቀን መቆየቱን ተረዳ፡፡18ቢታንያ አሥራ አምስት ኪሎ ሜትር ብቻ የምትርቅ ለኢየሩሳሌም ቅርብ ስፍራ ነበረች፡፡19ስለ ወንድማቸው ሞት ሊያጽናኗቸው ከአይሁድ ብዙዎቹ መጥተው ነበር፡፡20ከዚያም ማርታ ኢየሱስ እንደ መጣ በሰማች ጊዜ፣ ልትቀበለው ወጣች፣ ማርያም ግን በቤት ተቀምጣ ነበር፡፡21ከዚያም ማርታ ኢየሱስን፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትኖር ኖሮ ወንድሜ ባልሞተም ነበር፡፡22አሁንም ቢሆን የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚሰጥህ ዐውቃለሁ” አለችው፡፡23ኢየሱስ፣ “ወንድምሽ ይነሣል” አላት፡፡24ማርታ፣ “በመጨረሻው ቀን በሚሆነው በትንሣኤ ከሞት እንደሚነሣ ዐውቃለሁ” አለችው፡፡25ኢየሱስ፣ “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ፣ በእኔ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡26በእኔ የሚኖርና የሚያምንብኝ ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?” አላት፡፡27እርሷም፣ “አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ዓለም ልትመጣ ያለኸው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ አምናለሁ” አለችው፡፡28ማርታ ይህን ከተናገረች በኋላ እኅቷን ማርያምን በግል ለማነጋገር ትጠራት ዘንድ ሄደችና፣ “መምህሩ እዚህ ነው፣ ሊያነጋግርሽ ይፈልጋል” አለቻት፡፡29ማርያም ይህን እንደ ሰማች በፍጥነት ተነሥታ ወደ ኢየሱስ ሄደች፡፡30ኢየሱስም ማርታን ባገኘበት ስፍራ ነበር እንጂ ገና ወደ መንደሩ አልገባም ነበር፡፡31ከዚያም በቤት ውስጥ ሆነው ማርያምን ሲያጽናኗት የነበሩት አይሁድ ፈጥና ስትወጣ ባዩአት ጊዜ፣ ወደ መቃብር ሄዳ በዚያ ልታለቅስ መስሏቸው ተከተሏት፡፡32ከዚያም ማርያም ኢየሱስ ወደ ነበረበት መጥታ ስታየው በእግሩ ሥር ወድቃ፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ፣ ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለችው፡፡33ኢየሱስ እርሷና ዐብረዋት የነበሩት አይሁድ ሲያለቅሱ ተመልክቶ በመንፈሱ ቃትቶና ተጨንቆ፣34“ወዴት አኖራችሁት?” አላቸው፡፡ እነርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ” አሉት፡፡35ኢየሱስ አለቀሰ፡፡36ከዚያም አይሁድ፣ “አልዓዛርን ምን ያህል ይወደው እንደ ነበረ ተመልከቱ!” አሉ፡፡37ከእነርሱ አንዳንዶቹ ግን፣ “ዓይነ ስውር የነበረውን ሰውዬ ዓይን የከፈተ ይህ ሰው የሞተውን ይህን ሰው እንዳይሞት ማድረግ አይችልም ነበር?” አሉ፡፡38ከዚያም ኢየሱስ አሁንም በውስጡ እየቃተተ ወደ መቃብሩ ሄደ፡፡ መቃብሩ ዋሻ ነበረ፣ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር፡፡39ኢየሱስ፣ “ድንጋዩን አንሡት” አለ፡፡ የሟቹ የአልዓዛር እኅት ማርታም ኢየሱስን፣ “ከሞተ አራት ቀን ስለሆነው፣ በአሁኑ ጊዜ ገላው ይበሰብሳል” አለችው፡፡40ኢየሱስ ማርታን፣ “ብታምኚስ፣ የእግዚአብሔርን ክብር እንደምታዪ አልነገርሁሽምን” አላት፡፡41ስለዚህ ድንጋዩን አነሡት፡፡ ኢየሱስም ሽቅብ እየተመለከተ፣ “አባት ሆይ፣ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤42ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ ዐውቃለሁ፣ ነገር ግን ይህን ያልሁት አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ እዚህ በዙሪያዬ ስለቆመው ሕዝብ ነው” አለ፡፡43ይህን ካለ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “አልዓዛር ሆይ፣ ውጣ!” አለ፡፡44የሞተው ሰው እጁና እግሩ በመገነዣ ጨርቅ እንደ ተጠቀለለ፣ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተሸፈነ ወጣ፡፡ ኢየሱስ፣ “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው፡፡45ከዚያም ወደ ማርያም ከመጡትና ይህን ከተመለከቱት አይሁድ አብዛኛዎቹ በእርሱ አመኑ፤46ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዶቹ ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሯቸው፡፡47ከዚያም ሊቀ ካህናቱና ፈሪሳውያን ጉባዔ ጠርተው፣ “ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶችን እያደረገ ነው፡፡48እንደዚሁ የምንተወው ከሆነ፣ ሮማውያን መጥተው ስፍራችንና አገራችንንም ይወስዳሉ” አሉ፡፡49ሆኖም በዚያ ዓመት ሊቀ ካህን የነበረ ከእነርሱ መካከል ቀያፋ የተባለው አንዱ፣ “እናንተ ምንም አታውቁም፤50አገሪቱ በመላ ከምትጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት የተሻለ እንደሆነ ከግምት ውስጥ አላስገባችሁም” አላቸው፡፡51እርሱ ይህን የተናገረው ከራሱ አልነበረም፣ ይልቁንም በዚያ ዓመት ሊቀ ካህን ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ፣52ደግሞም ስለ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በልዩ ልዩ ስፍራ የተበታተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ይሰበስብ ዘንድ መሞት እንደሚገባው ትንቢት ተናገረ፡፡53ስለዚህ ከዚያ ቀን ጀምሮ ኢየሱስን እንዴት መግደል እንዳለባቸው ዕቅድ አወጡ፡፡54ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ በአይሁድ መካከል በግልጽ መውጣትና መግባቱን ትቶ ኤፍሬም ወደ ተባለው በበረሐው አጠገብ ወዳለው ከተማ ሄደ፡፡ እዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቈየ፡፡55የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ቀርቦ ነበረና ብዙዎች ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካው በፊት ከየገጠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር፡፡56ኢየሱስን እየፈለጉት፣ በቤተ መቅደስ ቆመው ሳሉ፣ “ምን ይመስላችኋል? ወደ በዓሉ አይመጣ ይሆን?” እያሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር፡፡57ሊቀ ካህናቱና ፈሪሳውያኑም ኢየሱስን ይይዙት ዘንድ እርሱ የት እንዳለ ያወቀ ማንኛውም ሰው ጥቆማ እንዲያቀርብ ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡
1የፋሲካ በዓል ሊከበር ስድስት ቀናት ሲቀሩት ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡2ስለዚህ በዚያ እራት አዘጋጁለት፣ አልዓዛር ከኢየሱስ ጋር በማዕድ ከተቀመጡት ጋር ሲሆን ማርታ ደግሞ ታገለግላቸው ነበር፡፡3ማርያም ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ በጣም ውድ የሽቱ ብልቃጥ ወስዳ የኢየሱስን እግር ትቀባ፣ በፀጉሩዋም ታብስ ስለነበር፣ ቤቱ በሽቱው መዓዛ ታወደ፡፡4ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ፣5“ይህ ሽቱ በሦስት መቶ ዲናር ተሸጦ ለድሆች ያልተሰጠው ለምንድን ነው?” አለ፡፡6ይህን ያለው ለድሆች ተገዶላቸው ሳይሆን ሌባ ስለነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢቱን የሚይዘው እርሱ ስለነበረ፣ ከዚያ ውስጥ ለራሱ ጥቂት ይወስድ ነበር፡፡7ኢየሱስ፣ “የያዘችውን ለቀብሬ ቀን እንድታቆየው ፍቀዱላት፤8ድሆች ምንጊዜም ከእናንተ ጋር ይሆናሉ፣ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም” አላቸው፡፡9ብዙ የአይሁድ ሕዝብም ኢየሱስ በዚያ እንደነበረ ተረድተው ነበርና ወደዚያ መጡ፣ የመጡትም ለኢየሱስ ብቻ ብለው ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ጭምር ነበር፡፡10የካህናት አለቆች አልዓዛርን ደግሞ ለመግደል በአንድነት የተንኮል ስምምነት አደረጉ፣11ምክንያቱም ብዙ አይሁድ የሄዱትና በኢየሱስ ያመኑት ከእርሱ የተነሣ ነበር፡፡12በማግስቱ ብዙ ሕዝብ ወደ በዓሉ መጡ። ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መምጣቱን በሰሙ ጊዜ፣13የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው፣ “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው” እያሉ ሊቀበሉት ወጡ፡፡14ኢየሱስ የአህያ ውርንጫ አገኘና ተቀመጠባት፣ ይህንን ያደረገው፣15“የጽዮን ልጅ ሆይ፣ አትፍሪ፣ እነሆ፣ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ተብሎ በተጻፈው መሠረት ነው፡፡16ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ ይህን አልተረዱም ነበር፣ ኢየሱስ በከበረ ጊዜ ግን እነዚህ ነገሮች ስለ እርሱ ተጽፈው እንደነበረና እነርሱም እነዚህን ነገሮች ለእርሱ እንዳደረጉለት ተገነዘቡ፡፡17ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር በጠራውና ከሞት ባስነሣው ጊዜ በዚያ የነበሩት ሕዝብም ለሌሎች መሰከሩላቸው፡፡18ይህን ምልክት እንዳደረገ ሰምተው ነበርና ሊቀበሉት የወጡትም በዚህ ምክንያት ነበር፡፡19ስለዚህ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው፣ “ምንም ማድረግ እንደማትችሉ ተመልከቱ፣ ዓለሙ ተከትሎታል” ተባባሉ፡፡20በበዓሉ ሊያመልኩ ከሄዱት መካከል አንዳንድ የግሪክ ሰዎችም ነበሩ፡፡21እነዚህ በገሊላ ካለችው ከቤተሳይዳ ወደ ሆነው ወደ ፊልጶስ ዘንድ ሄደው፣ “ጌታ ሆይ፣ ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” አሉት፡፡22ፊልጶስ ሄዶ ለእንድርያስ ነገረው፣ እንድርያስና ፊልጶስም ዐብረው ሄዱና ለኢየሱስ ነገሩት፡፡23ኢየሱስም፣ “የሰው ልጅ የሚከብርበት ሰዓት ደርሷል፤24እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የስንዴ ዘር ወደ ምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች፡፡” ብሎ መለሰላቸው፡፡25ሕይወቱን የሚወድ ያጠፋታል፤ ነገር ግን በዚህ ዓለም እያለ ሕይወቱን የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት እንድትጠበቅ ያደርጋታል።26ማንም ሊያገለግለኝ የሚወድ ይከተለኝ፤ እኔ ባለሁበት አገልጋዬም በዚያ ይሆናል። ማንም ቢያገለግለኝ አብ ያከብረዋል።27አሁን ነፍሴ ታውካለች ምን እላለሁ? 'አባት ሆይ፣ ከዚህ ሰዓት አድነኝ' ነገር ግን ስለዚህ ጉዳይ ወደዚህ ሰዓት መጥቻለሁ።28አባት ሆይ፣ ስምህን አክብረው።» ከዚያም ከሰማይ፣ «አክብሬዋለሁ ደግሞም አከብረዋለሁ» የሚል ድምፅ መጣ።።29ባጠገቡ ቆመው የነበሩትና ድምፁን የሰሙት ብዙ ሕዝብ ነጐድጓድ መሰላቸው። ሌሎች ደግሞ «መልአክ ተናግሮታል» አሉ።30ኢየሱስ መልሶ፣ «ይህ ድምፅ የመጣው ስለ እኔ ሳይሆን ስለ እናንተ ነው» አለ።31በዚህ ዓለም ላይ የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዢ ወደ ውጭ ይጣላል።32እኔ ከምድር ከፍ ከፍ በምልበት ጊዜ፣ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ።»33ይህን የተናገረው በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚሞት ለማመልከት ነበር።34ሕዝቡ፣ «ክርስቶስ ለዘላለም እንደሚኖር ከሕጉ ሰምተናል። ታዲያ 'የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ማለት አለበት እንዴት ትላለህ?' ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?» ብለው መለሱለት።35ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ «አሁን ለጥቂት ጊዜ ብርሃን በመካከላችሁ አለ፤ ጨለማ እንዳይውጣችሁ በዚህ ብርሃን ተመላለሱ። በጨለማ የሚመላለስም ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።36የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃኑ እመኑ።» ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ከእነርሱ ተለየ፤ ተሰወረባቸውም።37ምንም እንኳ ኢየሱስ በሕዝቡ ፊት ብዙ ምልክቶችን ቢያደርግም በእርሱ አላመኑም።38ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ፣ «ጌታ ሆይ የተናገርነውን ማን አመነ? የጌታስ ክንድ ለማን ተገለጠ?» በማለት የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው።39በዚህም ምክንያት ማመን አልቻሉም፤ ኢሳይያስ እንደ ገና እንዲህ ብሏልና፤40«ዐይኖቻቸውን አሳውሯል፤ ልባቸውንም አደንድኗል፤ ይህም የሆነው በዐይናቸው ዐይተው በልባቸው አስተውለውና ተመልሰው እንዳልፈውሳቸው ነው።»41ኢሳይያስ እነዚህን ነገሮች የተናገረው የኢየሱስን ክብር ስላየና ስለ እርሱም ስለ ተናገረ ነው፤42የሆነ ሆኖ ከገዢዎች እንኳ ብዙዎች በኢየሱስ አምነዋል፤ ነገር ግን ፈሪሳውያን ከምኵራብ እንዳያግዷቸው በመፍራት ማመናቸውን አልገለጹም።43በእግዚአብሔር ከመመስገን ይልቅ በሰዎች ለመመስገን ወደዱ።44ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ «በእኔ የሚያምን በእኔ ብቻ የሚያምን ሳይሆን በላከኝም ያምናል፤45እንደዚሁም እኔን የሚያይ የላከኝንም ያያል።46በእኔ የሚያምን በጨለማ ውስጥ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤47ማንም ቃሌን ሰምቶ ባያደርገው የምፈርድበት እኔ አይደለሁም፤ ዓለምን ለማዳን እንጂ በዓለም ላይ ልፈርድ አልመጣሁምና።48እኔን የሚቃወምና ቃሌንም የማይቀበል የሚፈርድበት አለ፤ በመጨረሻው ቀን የሚፈርድበት እኔ የተናገርሁት ቃል ነው።49ምክንያቱም ይህ ቃል ከራሴ የተናገርሁት አይደለም፤ ይልቁን ምን እንደምልና እንደምናገር ትእዛዝ የሰጠኝ የላከኝ አብ ነው።50ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደሚያስገኝ አውቃለሁ፤ ስለዚህ የምናገረው ቃል አብ እንደ ነገረኝ የምናገረው ነው።»
1በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ከፋሲካ በዓል በፊት ከዚህ ዓለም ተለይቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ ስላወቀ፣ ቀድሞውኑ የሚወዳቸውን በዓለም ይኖሩ የነበሩትን የራሱን ወገኖች እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።2ዲያብሎስም ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ክፉ ዐሳብ አስገባ።3ኢየሱስ አብ ሁሉን ነገር በእጁ አሳልፎ እንደ ሰጠው፣ ከእግዚአብሔር እንደ መጣ ወደ እግዚአብሔርም ተመልሶ እንደሚሄድ ዐወቀ፤4ከእራት ላይ ተነሣ፤ መጎናጸፊያውንም አስቀመጠ፤ ከዚያም ፎጣ ወስዶ ወገቡ ላይ ከታጠቀ በኋላ5በሳሕን ውስጥ ውሃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብና በያዘውም ፎጣ ማበስ ጀመረ።6ወደ ስምዖን ጴጥሮስ መጣ፤ ጴጥሮስም «ጌታ ሆይ የእኔን እግር ልታጥብ ነውን?» አለው7ኢየሱስም «የማደርገውን አሁን አይገባህም፤ወደፊት ግን ትረዳዋለህ» በማለት መለሰለት8ጴጥሮስም «ፈጽሞ የእኔን እግር አታጥብም» አለው ኢየሱስም «እግርህን ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ አይኖርህም» ሲል መለሰለት9ስምዖን ጴጥሮስም «ጌታ ሆይ እንግዲያስ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንና ራሴንም እጠበኝ» አለው10ኢየሱስም «ገላውን የታጠበ እግሩን ብቻ ከመታጠብ በስተቀር ሌላ ሰውነቱ ንጹህ ነው፤ እናንተ ንጹሓን ናችሁ ነገር ግን ይህን ስል ሁላችሁንም ማለቴ አይደለም»11ኢየሱስ «ሁላችሁም ንጹህ አይደላችሁም» ያለው ኣሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ ያውቅ ስለነበረ ነው12ኢየሱስ እግራቸውን አጥቦ ከጨረሰ በኋላ ልብሱን ለብሶ ተቀመጠ፤ እነርሱንም፣ «ያደረግሁላችሁን ልብ ብላችኋል?13'መምህር' እና 'ጌታ' ትሉኛላችሁ። እንደዚያም ስለሆንሁ አባባላችሁ ትክክል ነው።14እኔ ጌታና መምህር ሆኜ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባል።15እኔ እንዳደረግሁላችሁ እንደዚያው ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ትቼላችኋለሁ።16እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም ወይም የተላከ ሰው ከላኪው አይበልጥም።17እነዚህን ነገሮች ብታውቁና ብታደርጓቸው የተባረካችሁ ናችሁ።18የምናገረው ሁላችሁን በሚመለከት አይደለም፤ የመረጥኋቸውን አውቃለሁና፣ ነገር ግን እንደዚህ የምናገረው እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ የሚለው የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው።19ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ የምነግራችሁ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ እንደሆንሁ እንድታምኑ ነው።20እውነት እውነት እላችኋለሁ እኔን የሚቀበል የላክሁትን ይቀበላል፤ እኔን የተቀበለ ደግሞ የላክኝን ይቀባላል»21ኢየሱስ ይህን በሚናገርበት ጊዜ በመንፈሱ ታወከ፤ «እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል» ብሎ በግልጽ ነገራቸው22ደቀ መዛሙርቱም ስለማን እየተናገረ እንደሆነ ስላልገባቸው እርስ በርስ ተያዩ።23ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነው ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ወደ ደረቱ ተጠግቶ ተቀምጦ ነበር።24ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ወደዚህ ደቀ መዝሙር ጠጋ ብሎ «ንገረን ለመሆኑ ስለ ማን ነው እየተናገረ ያለው?» በማለት ጠየቀው።25ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ የተቀመጠው ደቀ መዝሙርም፣ «ጌታ ሆይ፣ ይህ የምትለው ሰው ማን ነው?» ብሎ ጠየቀው።26ከዚያም ኢየሱስ፣ «ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው ያ ሰው እርሱ ነው» በማለት መለሰለት። ስለዚህ ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው።27ቍራሹንም እንጀራ ከተቀበለ በኋላ፣ ሰይጣን ገባበት። ከዚያም ኢየሱስ፣ «ለማድረግ ያሰብኸውን ፈጥነህ አድርግ» አለው።28ኢየሱስ ለይሁዳ እንደዚያ ለምን እንዳለው በማዕድ ላይ ከተቀመጡት ማንም ያወቀ የለም።29አንዳንዶቹ ይሁዳ ገንዝብ ያዥ ስለ ነበር፣ ኢየሱስ «ለበዓሉ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ግዛ» ወይም ለድኾች ገንዘብ ስጥ ብሎ ነግሮታል ብለው ዐሰቡ።30ይሁዳ ቍራሹን እንጀራ ከተቀበለ በኋላ፣ ፈጥኖ ወጣ ምሽትም ነበረ።31ይሁዳ በሄደ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንዲህ በማለት ተናገረ፤ «አሁን የሰው ልጅ ከብሯል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ከብሯል።32እግዚአብሔር በራሱ ያከብረዋል፣ ደግሞም ፈጥኖ ያከብረዋል።33ልጆች ሆይ፣ ከእንግዲህ ከእናንተ ጋር የምቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው። እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፣ ይሁን እንጂ፣ ለአይሁድ፣ 'እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም' እንዳልኋቸው፣ ለእናንተም የምናገረው እንደዚያ ነው።34እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ዐዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።35እርስ በርሳችሁም ብትዋደዱ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ።»36ስምዖን ጴጥሮስ «ጌታ ሆይ፣ ወዴት ልትሄድ ነው?» ሲል ጠየቀው። ኢየሱስ፣ «ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፣ በኋላ ግን ትከተለኛለህ» በማለት መለሰለት።37ጴጥሮስ፣ «ጌታ ሆይ፣ አሁን ልከተልህ የማልችለው ለምንድን ነው? ስላንተ ሕይወቴን እንኳ አሳልፌ ለመስጠት ቈርጫለሁ» አለው።38ኢየሱስ፣ «ስለ እኔ ሕይወትህን አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት፣ እውነት እልሃለሁ፣ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ» ብሎ መለሰለት።
1«ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔ ደግሞ እመኑ።2በአባቴ ቤት ብዙ የመኖሪያ ስፍራ አለ፤ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ፣ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁ ብዬ አልነግራችሁም ነበር።3ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ ዳግመኛ እመጣለሁ፣ ወደ ራሴም እወስዳችኋለሁ።`4ወዴት እንደምሄድ መንገዱን ታውቃላችሁ።»5ቶማስ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፣ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?» በማለት ጠየቀው።6ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ «እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ አብ ሊመጣ አይችልም።7እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።»8ፊልጶስ ጌታ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየን ያ ለእኛ በቂያችን ነው» አለው።9ኢየሱስ፣ «ፊልጶስ ሆይ፣ ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ኖሬ ገና ኣላወቅኸኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፤ 'እንዴትስ አብን አሳየን' ትላለህ?10እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እየነገርኋችሁ ያለው ቃል ከራሴ የምናገረው አይደለም፤ ይልቁንስ ይህን ሥራ የሚሠራው በእኔ ውስጥ የሚኖረው አብ ነው።11እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ሌላው ቢቀር ከምሠራው ሥራ የተነሣ እመኑኝ።12እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ፣ እኔ ከሠራሁት የሚበልጥ ሥራ ይሠራል።13አብ በልጁ ይከብር ዘንድ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።14ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ፣ እኔ አደርገዋለሁ።15የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።16እኔም ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ እንዲሰጣችሁ አብን እለምናለሁ።17እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየው ወይም ስለማያውቀው አይቀበለውም። ይሁን እንጂ፣ ከእናንተ ጋር ስለሚኖርና በውስጣችሁም ስለሚሆን፣ እናንተ ታውቁታላችሁ።18ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፣ ዳግመኛ ወደ እናንተ እመጣለሁ።19ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ።20በዚያን ቀን እኔ በአብ እንዳለሁ፣ እናንተ በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ ታውቃላችሁ።21ትእዛዜ በውስጡ ያለ የሚያደርገውም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።22የአስቆሮቱ ያልሆነው ይሁዳም ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን የምትገልጠው እንዴት ነው?» ብሎ ጠየቀው።23ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «ማንም ሰው ቢወደኝ ቃሌን ይጠብቃል። አባቴም ይወደዋል፣ ወደ እርሱ እንመጣለን፣ መኖሪያችንንም በእርሱ እናደርጋለን።24የማይወደኝ ማንኛውም ሰው ቃሌን አይጠብቅም። የምትሰሙት ቃል የእኔ ሳይሆን፣ የላከኝ የአብ ቃል ነው።25በመካከላችሁ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች ልብ እንድትሉ ነግሬአችኋለሁ።26የሆነ ሆኖ፣ አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ነገር ሁሉ እንድታስታውሱ ያስችላችኋል።27ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፣ አይፍራም።28'እሄዳለሁ፣ ዳግመኛም ወደ እናንተ እመጣለሁ' ብዬ የነገርኋችሁን ቃል ሰምታችኋል። ከወደዳችሁኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ሊላችሁ ይገባ ነበር፤ ምክንያቱም አብ ከእኔ ይበልጣል።29ይህ ነገር በሚፈጸምበት ጊዜ ታምኑ ዘንድ አሁን ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነገርኋችሁ።30የዚህ ዓለም ገዥ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በላይ ከእናንተ ጋር መነጋገር አልችልም።እርሱ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን የለውም፡31ነገር ግን አብን እንደምወድ ዓለም ሁሉ ያውቅ ዘንድ በሰጠኝ ትዕዛዝ መሠረት አብ ያዘዝኝን አደርጋለሁ። ተነሱ ከዚህ እንሂድ»
1እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬው ደግሞ አባቴ ነው።2እርሱም በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ ያማያፈራውን ማንኛውንም ቅርንጫፍ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ግን ይበልጥ ያፈራ ዘንድ ያጠራዋል።3ከነገርኋችሁ ቃል የተነሣ እናንተ ንጹሓን ናችሁ።4በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ካልኖረ በቀር በራሱ ፍሬ ማፍራት እንደማይችል ሁሉ፣ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።5እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ የምኖርበት ያ ሰው ብዙ ፍሬ ያፈራል። ያለ እኔ ምንም ነገር ልታደርጉ አትችሉም።6ማንም ሰው በእኔ ባይኖር፣ እንደ ቅርንጫፍ ይወገዳል፣ ይደርቃልም፤ ሰዎች ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉታል፣ ይቃጠላልም።7በእኔ ብትኖሩ፣ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ ይሰጣችኋል።8ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።9አብ እንደ ወደደኝ እኔም ወደድኋችሁ፣ በፍቅሬ ኑሩ።10እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደጠበቅሁና በፍቅሩ እንደምኖር ሁሉ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።11ደስታዬ በውስጣችሁ እንዲሆንና ደስታችሁም ፍጹም እንዲሆን እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ።12እኔ የምሰጣችሁ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።13ስለ ወዳጁ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ እንዲሰጥ ግድ ከሚል የሚበልጥ ፍቅር ማንም ሰው የለውም።14ያዘዝኋችሁን ነገር ብታደርጉ ወዳጆቼ ናችሁ።15ከእንግዲህ አገልጋዮች ብዬ አልጠራችሁም፤ ምክንያቱም አገልጋይ ጌታው ምን እያደረገ እንዳለ አያውቅም። ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ እንድታውቁ ስለ ነገርኋችሁ፣ ወዳጆች ብያችኋለሁ።16እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ነገር ግን እኔ መረጥኋችሁ፤ ሄዳችሁ ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬአችሁም ዘላቂ ሆኖ እንዲቆይ ሾምኋችሁ። ይህም አብን በስሜ የምትለምኑትን ማንኛውንም ነገር እንዲሰጣችሁ ነው።17እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።18ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ ዕወቁ።19ከዓለም ብትሆኑ ኖሮ ዓለም የራሱ እንደሆኑት አድርጎ በወደዳችሁ ነበር። ነገር ግን ከዓለም ስላይደላችሁ ከዓለምም ስለ መረጥኋችሁ ዓለም ይጠላችኋል።20'አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም' በማለት የነገርኋችሁን ቃል ልብ በሉ፤ እኔን አሳድደውኝ ከሆነ፣ እናንተንም ያሳድዷችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ከሆነ፣ የእናንተንም ቃል ይጠብቃሉ።21የላከኝን እርሱን ስለማያውቁ፣ በስሜ ምክንያት ይህን ሁሉ ያደርጉባችኋል።22እኔ ባልመጣና ባልነግራቸው ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ ነገር ግን አሁን ለኀጢአታቸው የሚሰጡት ምክንያት የለም።23እኔን የሚጠላ አባቴንም ይጠላል።24ማንም ያልሠራውን ሥራ በመካከላቸው ሠርቼ ባላሳያቸው ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ሥራዬን አይተዋል፤ እኔንና አባቴንም ጠልተዋል።25ይህም የሆነው በሕጋቸው 'በከንቱ ጠሉኝ' ተብሎ የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።26ከአብ የምልክላችሁ አጽናኝ፣ እርሱም ከአብ የሚወጣው የእውነት መንፈስ በሚመጣበት ጊዜ፣ ስለ እኔ ይመሰክራል።27ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእኔ ጋር ስለ ነበራችሁ፣ እናንተም ትመሰክራላችሁ።
1«እነዚህን ነገሮች የምነግራችሁ እምነታችሁ እንዳይናወጥ ነው፡፡2ከምኵራብ ያስወጡአችኋል፤ እናንተን የሚገድል ሁሉ ለእግዚአብሔር መልካም እንዳደረገ የሚያስብበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም፡፡3እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉት አብንም ሆነ እኔን ስለማያውቁ ነው፡፡4ይህን የምነግራችሁ እነርሱ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ፣ ነገሮቹን እንድታስተውሷቸውና እንዴት እንደነገርኋችሁ እንድታስቡ ነው፡፡ አብሬችሁ ስለ ነበርሁ ስለነዚህ ነገሮች ቀደም ሲል አልነገርኋችሁም፡፡5ነገር ግን አሁን ወደ ላከኝ እመለሳለሁ፤ ያም ሆኖ ከእናንተ ማንም 'የት ነው የምትሄደው? ˋ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።6ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ስላልኋችሁ ልባችሁ በሐዘን ተሞልቷል፡፡7ነገር ግን እውነቱን ልንገራችሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ፡፡8አጽናኙ በመጣ ጊዜ ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ዓለምን ይወቅሳል፤9ስለ ኀጢአት በእኔ ባለማመናቸው፤10ስለ ጽድቅ እኔ ወደ አባቴ ስለምሄድና ከእንግዲህ ስለማታዩኝ፣ እንዲሁም11ስለ ፍርድ የዚህ ዓለም ገዢ ስለ ተፈረደበት ነው፡፡12ብዙ የምነግራችሁ ነገር አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ልትረዱአቸው አትችሉም፡፡13ነገር ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ምክንያቱም እርሱ ከራሱ አይናገርም፤ ነገር ግን ከእኔ የሰማውን ሁሉ እነዚያን ይናገራል፤ ደግሞም ሊመጡ ስላሉ ነገሮች ይነግራችኋል፡፡14የእኔ የሆኑትን ነገሮች ወስዶ ስለሚነግራችሁም ያከብረኛል፡፡15የአባቴ የሆነው ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ ነው መንፈስ ቅዱስ የእኔ የሆኑትን ነገሮች ወስዶ ይነግራችኋል ያልኋችሁ፡፡16ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አታዩኝም ደግሞም እንደ ገና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ።»17ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው ‹‹ወደ አባቴ ስለምሄድ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አታዩኝም ደግሞም እንደ ገና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁˋ እያለ የሚነግረን ነገር ምንድን ነው?›› ተባባሉ፡፡18ከዚህም የተነሣ ‹‹ከጥቂት ጊዜ በኋላˋ ሲል ምን ማለቱ ነው። ምን እያለ እንደ ሆነ አናውቅም›› አሉ፡፡19ኢየሱስም ሊጠይቁት በጣም እንደ ፈለጉ አይቶ፣ ‹‹ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አታዩኝም ደግሞም እንደ ገና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁˋ ስላልሁት ነገር እርስ በርሳችሁ ትጠያየቃላችሁን?20እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ ታለቅሳለችሁ ታዝናላችሁም፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተ በሐዘን ትሞላላችሁ፣ ነገር ግን ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል፡፡21አንዲት ሴት የመውለጃዋ ወራት በደረሰ ጊዜ፣ የምጧን ሥቃይ እያሰበች ታዝናለች፤ ነገር ግን ከወለደች በኋላ ሕፃን ወደዚህ ዓለም በመምጣቱ ከሚሰማት ደስታ የተነሣ ጭንቀቷን ፈጽሞ አታስበውም፡፡22ደግሞም አሁን ዐዝናችኋል፤ ነገር ግን ተመልሼ አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም ማንም ከእናንተ ሊወስድ አይችልም፡፡23በዚያም ቀን ምንም ጥያቄ አትጠይቁኝም፤ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከአብ ዘንድ ማንኛውንም ነገር ብትለምኑ አብ ስለስሜ ይሰጣችኋል፡፡24እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፣ ለምኑ፣ ደስታችሁም ሙሉ ይሆን ዘንድ ትቀበላላችሁ፡፡25እስከ አሁን በምሳሌ ስነግራችሁ ነበር፤ ነገር ግን በምሳሌ የማልናገርበትና ለእናንተ ስለ አብ በግልጽ የምናገርበት ጊዜ ይመጣል፡፡26በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ ወደ አብ እለምናለሁ አልላችሁም፤27ምክንያቱም አብ ራሱ እኔን ስለወደዳችሁኝና ከአብ ዘንድ እንደ መጣሁ ስላመናችሁ ይወዳችኋልና ነው፡፡28ከአብ ወደዚህ ዓለም መጥቻለሁ፤ እንደ ገናም ይህን ዓለም ትቼ ወደ አብ እሄዳለሁ፡፡»29ደቀ መዛሙርቱ፣ ‹‹እነሆ፣ አሁን በግልጽ ተናገርህ፤ ምንም በምሳሌ አልተናገርህም፡፡30አሁን ሁሉን እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ አውቀናል። በዚህም ምክንያት አንተ ከአብ እንደ መጣህ እናምናለን» አሉት፡፡31ኢየሱስ፣ ‹‹አሁንስ አመናችሁ ማለት ነው?››32እነሆ፣ እያንዳንዳችሁ እኔን ብቻዬን ትታችሁ ወደየቤታችሁ የምትበታተኑበት ጊዜ እየመጣ ነው፡፡ አዎን፣ በርግጥም መጥቷል፡፡ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስላለ ብቻዬን አይደለሁም፡፡33በስሜ ሰላም እንዲሆንላችሁ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ፡፡ በዓለም ውስጥ ስትኖሩ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዟችሁ፣ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፡፡»
1ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ እያየ፣ ‹‹አባት ሆይ፣ ሰዓቱ ደርሷል፣ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው2ይህም ከአንተ ለተቀበላቸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲሰጣቸው በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በሰጠኸው ሥልጣን ልክ ነው፡፡3ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተን፣ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቁ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡4አባት ሆይ፣ እንዳከናውነው የሰጠኸኝን ሥራ በመፈጸም በምድር ላይ አከበርሁህ፡፡5አሁን አባት ሆይ፣ ዓለም ሳይፈጠር በፊት በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር ከአንተ ጋር አክብረኝ፡፡6ከዓለም ለሰጠኸኝ ለእነዚህ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ፣ ለእኔም ሰጠሃቸው፣ ቃልህንም ጠብቀዋል።7አሁን ከአንተ የተቀበልኋቸው ነገሮች ሁሉ በርግጥ ከአንተ እንደ መጡ አምነዋል፣8የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና። እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ እንደ መጣሁ አውቀዋል አንተ እንደላክኸኝም አምነዋል።9እነርሱ የአንተ ናቸውና አንተ ለሰጠኸኝ ለእነርሱ እንጂ ለዓለም አልጸልይም፡፡10የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው፤ የአንተ የሆነውም ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ እኔ በእነርሱ ከብሬአለሁ፡፡11እኔ ወደ አንተ እመጣለሁና። ከእንግዲህ በዓለም አልኖርም፤ እነርሱ ግን በዓለም ውስጥ ናቸው፡፡ ቅዱስ አባት ሆይ፣ እኔና አንተ አንድ እንደ ሆንን አንድ እንዲሆኑ በሰጠኸኝ በስምህ ጠብቃቸው፡፡12ከእነርሱ ጋር እያለሁ በሰጠኸኝ በስምህ ጠበቅኋቸው፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት የተባለው እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ አንዱም እንዳይጠፋ ጋረድኋቸው፡፡13አሁን ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ይህን በዓለም ሳለሁ የምናገረው፣ ደስታዬ በእነርሱ ሙሉ እንዲሆን ነው፡፡14ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔ ከዓለም እንዳልሆንሁ እነርሱም ከዓለም አይደሉምና ዓለም ይጠላቸዋል፡፡15ከክፉው እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልጸልይም፡፡16እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ እነርሱም ከዓለም አይደሉም፡፡17በእውነት ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው፡፡18አንተ ወደ ዓለም ላክኸኝ፣ እኔም ደግሞ እነርሱን ወደ ዓለም ልኬአቸዋለሁ፡፡19እነርሱ በእውነት እንዲቀደሱ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ ቀድሼአለሁ፡፡20ከእነርሱ ምስክርነት የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑት ሁሉ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልጸልይም፡፡21ይህም አባት ሆይ፣ አንተ በእኔ እኔም በአንተ እንዳለሁ እነርሱም አንድ እንዲሆኑ ነው፡፡ ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ እንዲያምን እነርሱም በእኛ እንዲሆኑ እጸልያለሁ፡፡22እኛ አንድ እንደ ሆንን እነርሱም አንድ እንዲሆኑ የሰጠኸኝን ክብር ሰጥቻቸዋለሁ፤23ይህም እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ ሆነህ እነርሱ በአንድነት ፍጹማን እንዲሆኑና ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ እኔን በወደድህበት ፍቅር እነርሱንም እንደ ወደድሃቸው እንዲያውቅ ነው።24አባት ሆይ፣ የሰጠኸኝ እነዚህ ስለ ወደድኸኝ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የሰጠኸኝን ክብር እንዲያዩ እኔ ባለሁበት እነርሱም ከእኔ ጋር እንዲሆኑ እወዳለሁ፡፡25ጻድቅ አባት ሆይ፣ ዓለም አላወቀህም፤ እኔ ግን አውቅሃለሁ፤ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አውቀዋል፡፡26አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ እኔን የወደድህበት ፍቅር በእነርሱም እንዲሆንና እኔም በእነርሱ እንድሆን ስምህን አስታውቃቸዋለሁ፡፡
1ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ከቄድሮን ሸለቆ ማዶ የአትክልት ስፍራ ወደሚገኝበት ቦታ ሄደ፣ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ አትክልት ስፍራው ገባ፡፡2ኢየሱስ በተደጋጋሚ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደዚያ ስፍራ ይመጣ ስለ ነበር አሳልፎ ሊሰጠው ያለው ይሁዳ ቦታውን ያውቅ ነበር፡፡3ከዚያም ይሁዳ ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን ብዙ ወታደሮችንና ጠባቂዎችን ከተቀበለ በኋላ ፋኖስ፣ ችቦና የጦር መሣሪያ ይዞ ወደ አትክልት ስፍራው መጣ፡፡4ከዚያም እየደረሰበት ያለውን የተረዳው ኢየሱስ ወደ ፊት ወጥቶ፣ ‹‹ማንን ፈለጋችሁ?›› አላቸው፤5እነርሱ፣ ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ብለው መለሱለት፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ነኝ›› አላቸው፡፡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ከወታደሮቹ ጋር ቆሞ ነበር፡፡6ስለዚህ ‹‹እኔ ነኝ›› ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ላይ ወደቁ፡፡7እንደ ገናም፣ ‹‹ማንን ፈለጋችሁ?›› አላቸው። እነርሱም፣ ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ብለው በድጋሚ መለሱለት፡፡8ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ ስለዚህ እኔን የምትፈልጉ ከሆነ እነዚህን እንዲሄዱ ተዉአቸው›› አላቸው፡፡9ይህም ‹‹ከሰጠኸኝ ከእነዚህ አንዱም አልጠፋብኝም›› ተብሎ የተነገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፡፡10ከዚያም ስምዖን ጴጥሮስ የታጠቀውን ሰይፍ መዞ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፡፡ የአገልጋዩም ስም ማልኮስ ነበረ፡፡11ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ‹‹ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፡፡ አብ የሰጠኝን ጽዋ መጠጣት የለብኝም እንዴ?›› አለው፡፡12ስለዚህ ወታደሮቹና አዛዣቸው እንዲሁም የአይሁድ ጠባቂዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፡፡13በዚያን ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ ለሐና አማቹ ስለ ነበረ፣ በመጀመሪያ ወደ ሐና ወሰዱት ፡፡14ቀያፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት ይሻላል ብሎ አይሁድን የመከረው ሰው ነው፡፡15ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር ኢየሱስን ተከትለው ሄዱ፡፡ ሌላኛው ደቀ መዝሙር ከሊቀ ካህናቱ ጋር ይተዋወቅ ስለ ነበረ፣ ከኢየሱስ ጋር ወደ ሊቀ ካህናቱ አደባባይ ገባ፡፡16ጴጥሮስ ግን በውጭ በር ላይ ቆሞ ነበር፡፡ ከሊቀ ካህናቱ ጋር የሚተዋወቀው ያ ደቀ መዝሙር በር የምትጠብቀውን አገልጋይ አናግሮ ጴጥሮስን ወደ ውስጥ አስገባው፡፡17ከዚያም በር ትጠብቅ የነበረችው አገልጋይ ጴጥሮስን፣ ‹‹አንተ ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህም እንዴ?›› አለችው፡፡ እርሱ፣ ‹‹አይደለሁም›› አለ፡፡18ጊዜው ብርድ ስለ ነበረ፣ አገልጋዮችና ጠባቂዎች እሳት አቀጣጥለው ዙሪያውን ከበው እየሞቁ ነበር፡፡ ጴጥሮስም በዚያ ከእነርሱ ጋር ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፡፡19ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ አስተማረው ትምህርት ጠየቀው፡፡20ኢየሱስ፣ ‹‹ለዓለም ሁሉ በግልጽ ስናገር ነበር፤ ሁልጊዜ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በቤተ መቅደስ ሳስተምር ነበር፤ በድብቅ የተናገርሁት ምንም ነገር የለም፣21ታዲያ ለምን ትጠይቀኛለህ? የተናገርኋቸውን ነገሮች ስለሚያውቁ ሲሰሙኝ የነበሩትን ሰዎች ስለተናገርኋቸው ነገሮች ጠይቅ›› ብሎ መለሰለት፡፡22ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ፣ በዚያ ከቆሙት ጠባቂዎች መካከል አንዱ በጥፊ መታውና፣ ‹‹እንደዚህ ነው ለሊቀ ካህናቱ የምትመልሰው?›› አለው፡፡23ኢየሱስ፣ ‹‹አንዳች ክፉ ነገር ተናግሬ ከሆነ መስክርብኝ፤ በትክክል መልሼ ከሆነ ግን ለምን ትመታኛለህ?›› አለው፡፡24ሐናም ኢየሱስን እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው፡፡25ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት እየሞቀ ነበር። ሰዎቹ፣ ‹‹አንተ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አይደለህም እንዴ?›› አሉት። ጴጥሮስ፣ ‹‹አይደለሁም›› ብሎ ካደ፡፡26ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ የሆነ ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች አንዱ፣ ጴጥሮስን፣ ‹‹አንተን በአትክልት ስፍራው ከእርሱ ጋር አላየሁህም እንዴ?›› አለው፡፡27ጴጥሮስ እንደ ገና ካደ፣ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ፡፡28ከዚያም ኢየሱስን ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት። ጊዜው ማለዳ ነበረ፣ ይዘውት የመጡት አይሁድ እንዳይረክሱና ፋሲካን መብላት እንዲችሉ ወደ ገዢው ግቢ መግባት አልፈለጉም።29ስለዚህ ጲላጦስ ወደ ውጭ ወጥቶ፣ «በዚህ ሰው ላይ ያላችሁ ክስ ምንድን ነው?» ብሎ ጠየቃቸው።30እነርሱም፣ «ይህ ሰው ክፉ ባያደርግ ኖሮ ወደ አንተ አናመጣውም ነበር» አሉት።31ስለዚህ ጲላጦስ፣ «እናንተ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት» አላቸው። አይሁድ፣ «እኛ ማንንም ሰው ለመግደል አልተፈቀደልንም» ብለው መለሱለት።32ይህንም ያሉት ኢየሱስ በእንዴት ዓይነት ሞት እንደሚሞት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።33ጲላጦስ ወደ ግቢው ተመልሶ ኢየሱስን ጠራውና፣ «አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?» አለው።34ኢየሱስ፣ «ይህን የምትጠይቀኝ ከራስህ ነው ወይስ ሌሎች እንድትጠይቀኝ ስለ ነገሩህ ነው?» አለው።35ጲላጦስ፣ «እኔ አይሁዳዊ አይደለሁም፤ ነኝ እንዴ? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ የገዛ አገርህ ሰዎችና የካህናት አለቆች ናቸው፣ ምን አድርገህ ነው?» አለው።36ኢየሱስ፣ «የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለም፤ የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም ቢሆን ኖሮ አይሁድ እንዳይዙኝ አገልጋዮቼ ይዋጉልኝ ነበር። በመሠረቱ የእኔ መንግሥት ከምድር አይደለም» ብሎ መለሰለት።37ጲላጦስ፣ «ታዲያ አንተ ንጉሥ ነህ?» አለው፤ ኢየሱስ፣ «እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ተናገርህ፤ የተወለድሁት ወደ ዓለምም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመስከር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል» ብሎ መለሰለት።38ጲላጦስ፣ «እውነት ምንድን ነው?» ካለ በኋላ፣ እንደ ገና ወደ አይሁድ ወጣና፣ «በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።39እንደ ተለመደው በየዓመቱ በፋሲካ በዓል አንድ እስረኛ እለቅላችኋለሁ፣ ታዲያ የአይሁድን ንጉሥ ልፍታላችሁን?» አላቸው።40ከዚያም፣ እነርሱ፣ እንደ ገና ጮኸው «ይህን ሰው አይደለም፣ በርባንን ፍታልን» አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበር።
1ከዚያም ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው።2ወታደሮቹ የእሾኽ አክሊል ጐንጕነው በኢየሱስ ራስ ላይ አደረጉ። ሐምራዊ ልብስም አለበሱት።3ወደ እርሱ መጥተው፣ «የተከበሩ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ!» አሉ በጥፊም መቱት።4ከዚያም ጲላጦስ እንደ ገና ወደ ወጥቶ ሕዝቡን፣ «ምንም ጥፋት እንዳላገኘሁበት እንድታውቁ እነሆ፣ ሰውየውን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ» አላቸው።5ስለዚህ ኢየሱስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶና ሐምራዊ ልብስ ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም፣ «እነሆ፣ ሰውየው!» አላቸው።6የካህናት አለቆችና ጠባቂዎቹ ኢየሱስን ባዩ ጊዜ፣ «ስቀለው፣ ስቀለው» እያሉ ጮኹ። ጲላጦስ፣ «እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት፤ እኔ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም» አላቸው።7አይሁድ፣ «እኛ ሕግ አለን፣ በሕጋችን መሠረትም ይህ ሰው ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጓልና ሞት ይገባዋል» ብለው መለሱ።8ጲላጦስ ይህን ሲሰማ የበለጠ ደነገጠ፤9ወደ ግቢውም ተመልሶ ኢየሱስን፣ «ከየት ነው የመጣኸው?» ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም።10ጲላጦስም ኢየሱስን፣ «አናግረኝ እንጂ፤ ልፈታህም ሆነ ልሰቅልህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም እንዴ?» አለው።11ኢየሱስ፣ «ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር። ስለዚህም ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ኀጢአቱ የከፋ ነው» አለው።12ከዚህ መልሱ የተነሣ ጲላጦስ ሊፈታው ፈለገ፣ ነገር ግን አይሁድ፣ «ራሱን ንጉሥ ብሎ የሚጠራ ቄሣርን የሚቃወም ስለ ሆነ፣ ይህን ሰው ብትለቀው አንተ የቄሣር ወዳጅ አይደለህም» እያሉ ይጮኹ ነበር።13ጲላጦስ እነዚህን ቃላት በሰማ ጊዜ ኢየሱስን ወደ ውጭ አውጥቶ የድንጋይ ንጣፍ፣ በዕብራይስጥ ግን ገበታ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ።14ቀኑ ለፋሲካ በዓል ዝግጅት የሚደረግበትና ሰዓቱም ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር። ጲላጦስ አይሁድን፣ «እነሆ፣ ንጉሣችሁ» አላቸው።15እነርሱም፣ «አስወግደው፣ አስወግደው፣ ስቀለው!» እያሉ ጮኹ። እርሱ፣ «ንጉሣችሁን ልስቀለውን?» አላቸው። የካህናት አለቆችም፣ «እኛ ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ አናውቅም» ብለው መለሱለት።16ስለዚህ ጲላጦስ ኢየሱስን እንዲሰቅሉት ፈቀደላቸው።17ከዚያም ኢየሱስን፣ የሚሰቀልበትን መስቀል አሸክመው የራስ ቅል፣ በዕብራይስጥ ደግሞ ጎልጎልታ ወደሚባል ቦታ ወሰዱት።18በዚያም ስፍራ ሰቀሉት፤ ሁለት ሌሎች ሰዎችንም በኢየሱስ ግራና ቀኝ ሰቀሉ።19ጲላጦስም ጽሑፍ አዘጋጅቶ በኢየሱስ መስቀል ላይ አስቀመጠ። ጽሑፉም፣ «የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ የአይሁድ ንጉሥ» የሚል ነበር።20ኢየሱስ የተሰቀለበት ቦታ ለከተማው ቅርብ ስለ ነበር፣ ብዙ አይሁድ ጽሑፉን ያነቡት ነበር። ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ፣ በላቲንና በግሪክ ቋንቋዎች ነበር።21የአይሁድ የካህናት አለቆችም ጲላጦስን «እርሱ ራሱን 'የአይሁድ ንጉሥ ነኝ' ብሏል ብለህ ነው እንጂ፣ 'የአይሁድ ንጉሥ' ብለህ መጻፍ የለብህም» አሉት።22ጲላጦስም፣ «አንዴ የጻፍሁትን ጽፌአለሁ» አላቸው።23ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ ልብሱን ወስደው ለእያንዳንዳቸው እንዲዳረስ አድርገው አራት ቦታ ቈራረጡት፣ እጀ ጠባቡንም ወሰዱ።24እጀ ጠባቡ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረና እርስ በርሳቸው «ከምንቀደው ዕጣ እንጣጣልና የሚደርሰው ይውሰደው» ተባባሉ። ይህም የሆነው በቅዱስ መጽሐፍ፣ «ልብሴን ተከፋፈሉት በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉበት» የተባለው ቃል እንዲፈጸም ነው።25ወታደሮቹ ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ የኢየሱስ እናት ማርያም፣ የእናቱ እኅት፣ የቀለዮጳ ሚስት ማርያምና መግደላዊት ማርያም በዚያ በኢየሱስ መስቀል አጠገብ ቆመው ነበር።26ኢየሱስ እናቱንና ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር አብረው ቆመው ባየ ጊዜ፣ እናቱን «አንቺ ሴት እነሆ፣ ከአጠገብሽ ያለው እንደ ልጅሽ ይሁንልሽ» አላት ፤27ደቀ መዝሙሩንም፣ «እነኋት፣ በአጠገብህ ያለችው እንደ እናትህ ትሁንልህ» አለው። ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።28ኢየሱስ ሁሉ እንደ ተፈጸመ ዐውቆ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈው እንዲፈጸም፣ «ተጠማሁ» አለ።29በዚያም በሆምጣጤ የተሞላ ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ ወዲያውም በሆምጣጤ የተሞላ ሰፍነግ በሂሶጵ ወደ አፉ አስጠጉለት።30ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከጠጣ በኋላ «ተፈጸመ» አለ። ራሱንም አዘንብሎ ሞተ።31ቀኑ የመዘጋጀት ቀን በመሆኑና ሰንበትም በአይሁድ ዘንድ በጣም የሚከበር ስለነበረ በሰንበት ሥጋቸው በመስቀል ላይ መቆየት ስለሌለበት የሞት ፍርድ የተፈጸመባቸው ሰዎች እግሮቻቸው እየተሰበረ ሥጋቸው ከመስቀል እንዲወርድ አይሁድ ጲላጦስን ለመኑት።32ከዚያም ወታደሮቹ መጥተው ከኢየሱስ ጋር ከተሰቀሉት ሰዎች በመጀመሪያ የአንዱን፣ ቀጥሎም የሌላኛውን ሰው እግሮች ሰበሩ።33ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን ሞቶ ስላገኙት እግሮቹን አልሰበሩም።34ይሁን እንጂ፣ ከወታደሮቹ አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው፣ ወዲያውም ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ።35ይህን ያየው ሰው ስለዚህ መስክሯል፣ ምስክርነቱም እውነት ነው። እናንተም እንድታምኑ የተናገረው እውነት እንደ ሆነ ያውቃል።36እነዚህ ነገሮች የሆኑት «ከዐጥንቱ አንድም አይሰበርም» የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።37ደግሞም በሌላ መጽሐፍ፣ «የወጉትን ያዩታል» ተብሎ ተጽፎአል።38ከእነዚህ ነገሮች በኋላ አይሁድን ፈርቶ በድብቅ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረውና ከአርማትያስ ከተማ የሆነው ዮሴፍ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነ። ጲላጦስም ፈቀደለት። ዮሴፍም መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን ወሰደ።39በአንድ ወቅት በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስም አንድ መቶ ነጥር ያህል የእሬትና የከርቤ ቅልቅል ይዞ መጣ።40ስለዚህ የኢየሱስን አስከሬን ወስደው በአይሁድ ባህል አስከሬን ከመቀበሩ በፊት እንደሚደረገው ልማድ አስከሬኑን ሽቱ በተቀባ በበፍታ ጨርቅ ገነዙት።41ኢየሱስ ከተቀበረበት ቦታ አጠገብ የአትክልት ስፍራ ነበረ፤ በዚያም ማንም ገና ያልተቀበረበት ዐዲስ መቃብር ይገኝ ነበረ።42ቀኑ ለአይሁድ የመዘጋጀት ቀን በመሆኑና መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበር፣ የኢየሱስን አስከሬን በዐዲሱ መቃብር አኖሩት።
1በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ገና ጨለማ እያለ መግደላዊት ማርያም በሌሊት ወደ መቃብሩ መጣች፤ ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አየች።2ስለዚህ ወዲያው እየሮጠች ተመልሳ ወደ ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ደቀ መዝሙር መጥታ፣ «ጌታን ከመቃብሩ አውጥተው ወስደውታል፣ የት እንዳደረጉትም አናውቅም» አለቻቸው።3ከዚያም ጴጥሮስና ሌላኛው ደቀ መዝሙር ወደ መቃብሩ ሄዱ።4አብረው እየሮጡ ሳለ፣ ሌላኛው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደረሰ።5ጐንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ የበፍታ ጨርቁ ተቀምጦ አየ፣ ወደ ውስጥ ግን አልገባም።6ከእርሱም በኋላ ጴጥሮስ ደረሰና ወደ መቃብሩ ውስጥ ገባ። የበፍታ ጨርቁ ተቀምጦ አየ፣7በኢየሱስ ራስ ላይ የነበረውንም ጨርቅ ከበፍታ ጨርቁ ጋር ዐብሮ ሳይሆን ለብቻው እንደ ተጠቀለለ በቦታው ተቀምጦ አየ።8ከዚያም ጴጥሮስ ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደርሶ የነበረው ደቀ መዝሙር ወደ ውስጥ ገባና አይቶ አመነ።9ምክንያቱም እስከዚያን ሰዓት ድረስ ኢየሱስ ከሞት እንደሚነሣ በመጻሕፍት የተነገረውን ቃል አላስተዋሉም ነበር።10ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ወደየቤታቸው ሄዱ።11ነገር ግን መግደላዊት ማርያም እያለቀስች ከመቃብሩ ውጭ ቆማ ነበር፤ እያለቀሰችም ጐንበስ ብላ ወደ መቃብሩ ውስጥ ተመለከተ።12የኢየሱስ አስከሬን ተጋድሞበት በነበረው ቦታ ላይ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክት፣ አንደኛው በራስጌ፣ ሌላው ደግሞ በእግርጌ ተቀምጠው አየች።13እነርሱም፣ «አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ?» አሏት፤ እርሷም፣ «ጌታዬን ስለወሰዱትና ወዴትም እንዳኖሩት ስለማላውቅ ነው።» አለቻቸው።14ይህን ብላ ዞር ስትል፣ ኢየሱስን እዚያው ቆሞ አየችው፤ እርሱ እንደ ሆነ ግን አላወቀችም ነበር።15ኢየሱስ፣ «አንቺ ሴት ለምን ታለቅሽያለሽ፣ ማንንስ እየፈለግሽ ነው?» አላት። እርሷም የአትክልት ስፍራው ጠባቂ መስሏት፣ «ጌታዬ የወሰድኸው አንተ ከሆንህ እባክህ የት እንዳስቀመጥኸው ንገረኝና ልውሰደው።» አለችው።16ኢየሱስም፣ «ማርያም» አላት። ዞር ብላ በአረማይክ ቋንቋ፣ «ረቡኒ» አለችው፤ ትርጓሜውም «መምህር» ማለት ነው።17ኢየሱስም«ገና ወደ አብ አልሄድሁምና አትንኪኝ፣ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ መሄዴ ነው ብለሽ ንገሪአቸው» አላት።18መግደላዊት ማርያምም ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥታ፣ «ጌታን አየሁት» ብላ ኢየሱስ የነገራትን ሁሉ ነገረቻቸው።19በዚያው ቀን ማለትም ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ምሽት ላይ፣ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን ፈርተው በሮቹ ተዘግተው ሳለ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆሞ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን» አላቸው።20ይህንም ብሎ እጁንና ጐኑን አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩት ጊዜ፣ ደስ አላቸው።21እንደ ገናም ኢየሱስ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ አብ እንደ ላከኝ እኔም እልካችኋለሁ» አላቸው።22ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፣ «መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፣23ኀጢአቱን ይቅር ያላችሁት ማንም ይቅር ይባልለታል፣ ኀጢአቱን የያዛችሁበት ማንም ይያዝበታል» አላቸው።24ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ በመጣ ጊዜ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ሌላ ስሙ ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ዐብሮአቸው አልነበረም።25ኋላ ላይ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት፣ «ጌታን አየነው እኮ» አሉት። እርሱም፣ «የምስማር ምልክቱን በእጆቹ ላይ ካላየሁ፣ ጣቶቼንም በምስማር ምልክቱና እጄን በጐኑ ካላስገባሁ አላምንም» አላቸው።26ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ዐብሯቸው ነበረ። በሮቹ ተዘግተው ሳለ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆሞ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን» አላቸው።27ቶማስንም፣ «ጣቶችህን አምጣና እጆቼን ንካ፣ እጆችህንም ወደ ጐኔ አስገባ፣ እመን እንጂ የማታምን አትሁን» አለው።28ቶማስም፣ «ጌታዬና አምላኬ» ብሎ መለሰለት።29ኢየሱስ «አንተ ስላየኸኝ አመንህ፣ ሳያዩ የሚያምኑ የተባረኩ ናቸው» አለው።30ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ብዙ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤31ነገር ግን ይህ የተጻፈው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እንድታምኑና አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንድታገኙ ነው።
1እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ተገለጠላቸው፤ ሁኔታውም እንደዚህ ነበር፦2ስምዖን ጴጥሮስ ዲዲሞስ ከተባለው ከቶማስ፣ ከገሊላ አውራጃ ከቃና መንደር ከሆነው ከናትናኤል፣ ከዘብዴዎስ ልጆችና ከሌሎች ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ጋር ዐብረው ነበሩ።3ስምዖን ጴጥሮስ፣ «ዓሣ ለማጥመድ መሄዴ ነው» አላቸው። እነርሱም፣ «እኛም ከአንተ ጋር እንሄዳለን» አሉት። በጀልባ ተሳፍረው ሄዱ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት ምንም ዐሣ አላጠመዱም።4ቀኑ እየነጋ ሳለ ኢየሱስ መጥቶ በባሕሩ ዳር ቆመ፤ እነርሱ ግን ኢየሱስ እንደ ሆነ አላወቁም ነበር።5ከዚያም ኢየሱስ «ልጆች ሆይ፣ የሚበላ ዐሣ አላችሁን?» አላቸው። «የለንም» ብለው መለሱለት።6ኢየሱስ፣ «መረባችሁን ከጀልባው በቀኝ በኩል ጣሉት ታገኙማላችሁ» አላቸው። እነርሱም እንደተባሉት መረባቸውን ጣሉ፤ ነገር ግን ከዐሣው ብዛት የተነሣ መረቡን ወደ ጀልባው ውስጥ መጐተት አቃታቸው።7ከዚያም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ስምዖን ጴጥሮስን፣ «ጌታ እኮ ነው» አለው። ጴጥሮስ ጌታ እኮ ነው የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፣ መደረቢያውን ልብስ ታጥቆ ወደ ውሃው ውስጥ ዘሎ ገባ።8ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ግን ከምድር የነበራቸው ርቀት ሁለት መቶ ክንድ ያህል ብቻ ስለ ነበር ዐሣ የሞላውን መረብ እየጐተቱ በጀልባ ወደ ዳር መጡ።9ወደ መሬትም በደረሱ ጊዜ፣ በላዩ ላይ ዐሣ የተቀመጠበት ፍምና እንጀራ ተዘጋጅቶ አዩ።10ኢየሱስ፣ «እስኪ ካጠመዳችሁት ዐሣ ጥቂት ወደዚህ አምጡ» አላቸው።11ስምዖን ጴጥሮስም ሄዶ 153 ዐሣ የሞላውን መረብ ወደ ምድር ጐተተ፤ ምንም እንኳ የዐሣው ብዛት ከፍተኛ ቢሆንም፣ መረቡ ግን አልተቀደደም ነበር።12ኢየሱስ፣ «ኑ ቍርስ ብሉ» አላቸው። ኢየሱስ እንደ ሆነ አውቀው ነበርና ከደቀ መዛሙርቱ ማንም፣ «አንተ ማነህ?» ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም።13ኢየሱስ እንጀራውን አንሥቶ ሰጣቸው፤ ዐሣውንም እንደዚያው አደረገ።14ከሞት ከተነሣ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነበር።15ቍርስ ከበሉ በኋላ፣ ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ከእነዚህ የበለጠ ትወደኛለህን?» አለው። ጴጥሮስ፣ «አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ እንደምወድህማ አንተም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱ፣ «ጠቦቶቼን መግብ» አለው።16እንደ ገና ለሁለተኛ ጊዜ፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ትወደኛለህን?» አለው። ጴጥሮስ፣ «አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ እንደምወድህማ አንተም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱስ፣ «በጎቼን ጠብቅ» አለው።17ለሦስተኛ ጊዜ፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ትወደኛለህ?» አለው። ለሦስተኛ ጊዜ «ትወደኛለህ ወይ?» ብሎ ስለ ጠየቀው ጴጥሮስ በጣም ዐዘነ። ቀጥሎም፣ «ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱስም «በጎቼን መግብ።18እውነት፣ እውነት እልሃለሁ፣ ወጣት እያለህ ልብስህን ራስህ ለብሰህ ወደምትፈልገው ቦታ ትሄድ ነበር፤ ስታረጅ ግን ሌላ ሰው ልብስህን አልብሶህ ወደማትፈልገው ቦታ ይወስድሃል፣ በዚያን ጊዜ አንተ እጅህን ከመዘርጋት ውጪ ሌላ ማድረግ የምትችለው ነገር አይኖርም» አለው።19ኢየሱስ ይህን የተናገረው ጴጥሮስ በምን ዓይነት አሟሟት እግዚአብሔርን እንደሚያከብር ለማመልከት ነው። ከዚያም ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ «ተከተለኝ» አለው።20ጴጥሮስም ዞር ብሎ በፋሲካ እራት ላይ እያሉ ወደ ኢየሱስ ደረት ጠጋ ብሎ፣ «አሳልፎ የሚስጥህ ማን ነው?» ብሎ የጠየቀውንና ኢየሱስ ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር ሲከተላቸው አየው።21ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ይህ ሰውስ ምን ይሆናል?» አለው።22ኢየሱስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል? ዝም ብለህ ተከተለኝ» አለው።23በዚህ ምክንያት «ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም» የሚል ወሬ በየ ስፍራው ተሠራጨ። ኢየሱስ ግን ለጴጥሮስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል?» አለው እንጂ ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም አላለውም።24ስለ እነዚህ ነገሮች የመሰከረውና የጻፈው ይህ ደቀ መዝሙር ነው፣ ምስክርነቱም እውነት እንደ ሆነ እናውቃለን።25ከእነዚህ ሌላ ኢየሱስ ያደረጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እያንዳንዱ ነገር ቢጻፍ ኖሮ ለሚጻፉት መጻሕፍት ማስቀመጫ ዓለም እንኳ የሚበቃ አይመስለኝም።
1ቴዎፍሎስ ሆይ፣ ኢየሱስ እስካረገበት ቀን ድረስ ለማድረግና ለማስተማር የጀመረውን ሁሉ የሚናገረውን የመጀመሪያውን መጽሐፍ ጻፍሁ፤2ይህም የሆነው ጌታ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እርሱ የመረጣቸውን ሐዋርያትን ካዘዛቸው በኋላ ነበር፤3ለምርጦቹ ከመከራው በኋላ ሕያው ሆኖ ተገልጦላቸዋል። አርባ ቀን እየታያቸው፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየተናገረ ቆየ።4ከእነርሱም ጋር ዐብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፤ ነገር ግን "ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን ተስፋ ጠብቁ፤5በእርግጥ ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበር፤ እናንተ ግን በጥቂት ቀናት ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ" አለ።6ሐዋርያት በአንድነት ተሰብስበው ሳለ፣ “ጌታ ሆይ፣ ይህ የእስራኤልን መንግሥት የምትመልስበት ጊዜ ነውን?” ብለው ጠየቁት።7እርሱም እንደዚህ አላቸው፤ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ጊዜ ወይም ወቅት ማወቅ እናንተን አይመለከትም።8ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ሲመጣ፣ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”9ጌታ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ፣ ሐዋርያቱ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረው።10ትኵር አድርገው ወደ ሰማይ እየተመለከቱ ሳለ፣ ድንገት ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ።11እነርሱም፣ “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን እዚህ ትቆማላችሁ? ወደ ሰማይ የወጣው ይህ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁበት ሁኔታ ተመልሶ ይመጣል” አሏቸው።12ከዚያም በኋላ፣ የሰንበት ቀን ጕዞ ያህል ከሚያስሄደው፣ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ካለው ከደብረ ዘይት ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ሄዱ።13ሐዋርያት እዚያ ሲደርሱ፣ ወደሚቈዩበት፣ ወደ ላይኛው ሰገነት ወጡ። እነርሱም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ ቶማስ፣ በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ቀናተኛው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ነበሩ።14ሁሉም በአንድነት ሆነው፣ ሴቶቹ፣ የኢየሱስ እናት ማርያምና ወንድሞቹም ጭምር በጸሎት ይተጉ ነበር።15በዚያ ጊዜ ጴጥሮስ 120 ያህል በሚሆኑት ወንድሞች መካከል ቆመ፤ እንደዚህም አለ፤16“ወንድሞች ሆይ፣ ኢየሱስን የያዙትንና መርቶ ያመጣውን ይሁዳን በሚመለከት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ አስፈላጊ ነበር።17ይሁዳ ከእኛ እንደ አንዱ ተቈጥሮና የዚህን አገልግሎት ድርሻም ተቀብሎ ነበርና።18“ይሁዳም ለክፉ ሥራው በተከፈለው ዋጋ መሬት ገዛ። ከዚያም በግንባሩ ተደፋ፤ አካሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ተዘረገፈ።19በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ መሬቱ በቋንቋቸው አኬልዳማ [የደም መሬት] ተብሎ እንደሚጠራ ታወቀ።20በመዝሙር መጽሐፍ፦ መኖሪያው ወና ይሁን፤ የሚኖርበት አንድ ሰውም እንኳ አይገኝ፤ ሹመቱንም ሌላ ሰው ይውሰደው፤ ተብሎ ተጽፎአልና።21ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በመካከላችን በገባበትና በወጣበት ጊዜ ሁሉ ዐብረውን ከቈዩ ሰዎች፣22ይኸውም ዮሐንስ ካጠመቀው ጥምቀት ጀምሮ ኢየሱስ ከእኛ እስካረገበት ቀን ድረስ፣ ከነበሩት ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ሊሆን ይገባል።”23ኢዮስጦስም የሚባለውን፣ በርስያን ተብሎ የሚጠራውን ዮሴፍንና ማትያስን፣ ሁለት ሰዎችን እንዲቀርቡ አደረጉ።24እንደዚህ ብለውም ጸለዩ፤ “ጌታ ሆይ፣ የሰዎችን ሁሉ ልብ አንተ ታውቃለህ፤ ስለዚህ ከእነዚህ ከሁለቱ የትኛውን እንደ መረጥኸው ግለጥ፤25ይኸውም ይሁዳ ወደገዛ ስፍራው ትቶት በሄደው በዚህ አገልግሎትና ሐዋርያነት ውስጥ ስፍራ እንዲያገኝ ነው።”26ሐዋርያት ዕጣዎችን ለእነርሱ ጣሉ፤ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀ፤ እርሱም ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር አንድ ሆኖ ተቈጠረ።
1በበዓለ ኀምሳ ቀን ሁሉም በአንድነት አንድ ስፍራ ላይ ነበሩ።2ድንገት እንደ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ ተቀምጠውበት የነበረውን ቤትም ሞላው።3እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳናት ታዩአቸው፤ በእያንዳንዳቸው ላይም ተቀመጡባቸው።4ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲናገሩ እንደ ሰጣቸውም በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።5በዚያን ጊዜ ከሰማይ በታች ካለው ሕዝብ ሁሉ የመጡ፣ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች፣ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ አይሁድ ነበሩ።6ይህ ድምፅ ሲሰማ፣ ብዙ ሕዝብ በአንድነት ተሰበሰበ፣ እያንዳንዱ ሰውም በገዛ ራሱ ቋንቋ ሲናገሩ በመስማቱ ግራ ተጋባ።7ሕዝቡ ተደነቁ፤ ተገረሙም፤ “እነዚህ የሚናገሩ ሰዎች ሁሉ በእውነት የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? ብለውም ተናገሩ።8እያንዳንዳቸው በተወለድንበት ቋንቋ ሲናገሩ የምንሰማቸው ለምንድን ነው?9የጳርቴና፣ የሜድና የኢላሜጥ ሰዎች፣ በመስጴጦምያም፣ በይሁዳም፣ በቀጰዶቅያም፣ በጳንጦስም፣ በእስያም፣10በፍርግያም፣ በጵንፍልያም፣ በግብፅም፣ በቀሬና በኩል በሚገኙት የሊቢያ ክፍሎች የምንኖርም፣ ከሮም የመጣን፣11አይሁድና ወደ ይሁዲነት የገባን ቀርጤሳውያንና ዐረባውያን የሆንን እኛም፣ እነዚህ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ታላላቅ ሥራዎች በራሳችን ቋንቋዎች ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።"12ሁሉም ተደነቁ፣ ግራ ተጋቡም፤ እርስ በርሳቸውም፣ “ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባባሉ።13ሌሎች ግን፣ “ዐዲስ ወይን ጠጅ ጠጥተው ጠግበው ነው” ብለውም በማፌዝ ተናገሩ።14ነገር ግን ጴጥሮስ ከዐሥራ አንዱ ጋር ቆሞ፣ ድምፁን ከፍ በማድረግ እንደዚህ አላቸው፤ “የይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ፣ ይህ ለእናንተ የታወቀ ይሁን፤ የምናገረውንም አድምጡ።15እነዚህ ሰዎች እናንተ እንደምታስቡት አልሰከሩም፤ ምክንያቱም ገና ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነው።16ነገር ግን በነቢዩ በኢዩኤል ይህ ተነግሯል፦17‘በመጨረሻዎቹ ቀናት ይህ ይሆናል፣’ እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፤ ‘መንፈሴን ሥጋ በለበሱ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፣ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ። ወጣቶቻችሁ ራእይ ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ።18በአገልጋዮቼና በሴት አገልጋዮቼ ላይም በእነዚያ ቀናት መንፈሴን አፈስሳለሁ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገራሉ።19በላይ በሰማይ ድንቆችን፣ ምልክቶችንም በታች በምድር ላይ፣ ደምን፣ እሳትንና የጢስ ደመናን አሳያለሁ።20ታላቁና ገናናው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ወደ ጨለማነት፣ ጨረቃም ወደ ደምነት ይለወጣሉ።21የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።'22የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እነዚህን ቃሎች ስሙ፦ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ በመካከላችሁ እግዚአብሔር በእርሱ በኩል ባደረጋቸው ታላላቅ ተግባራት፣ በተኣምራትና በምልክቶች፣ ከእግዚአብሔር ለእናንተ መገለጡ የተረጋገጠ ሰው ነው።23አስቀድሞ በተወሰነው የእግዚአብሔር ዕቅድና በቀዳሚ ዕውቀቱ መሠረት፣ ዐልፎ ተሰጥቶአል፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ ሰቀላችሁት፤ ገደላችሁትም፤24እግዚአብሔርም የሞትን ጣር ከእርሱ አጥፍቶ አስነሣው፤ ምክንያቱም ሞት እርሱን ይይዘው ዘንድ አልቻለም።25ዳዊት ስለ እርሱ እንዲህ ብሎ ይናገራልና፦ ‘ጌታን ሁልጊዜ በፊቴ አየሁት፤ በቀኜ ነውና አልናወጥም።26ስለዚህ ልቤ ተደሰተ፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ። ሥጋዬም በተስፋ ያድራል።27ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም።28የሕይወትን መንገድ ገለጥህልኝ፤ በፊትህም ደስታን ታጠግበኛለህ።’29ወንድሞች ሆይ፣ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት በግልጽ ልነግራችሁ እችላለሁ፤ እርሱ ሞቶአል፤ ተቀብሮአልም፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ ነው።30ስለዚህ ዳዊት ነቢይ ነበረና ከዘሩ በዙፋኑ ላይ አንድን ሰው እንደሚያስቀምጥ እግዚአብሔር በመሐላ ለእርሱ ቃል ገብቶለት ነበር።31ዳዊት ይህን አስቀድሞ አየ፤ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤም ተናገረ፦ ክርስቶስ በሲኦል አልቀረም፤ ሥጋውም መበስበስን አላየም።32ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው፤ ለዚህም እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን።33ስለዚህ ከሙታን በመነሣትና በእግዚአብሔር ቀኝ በመቀመጥ፣ ከአብ ቃል የተገባውን መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ፣ እናንተ የምታዩትንና የምትሰሙትን ይህን አፈሰሰው።34-35ዳዊት ወደ ሰማይ አልወጣም፤ ነገር ግን እንዲህ ይላል፦ “ጌታ ለጌታዬ፣ ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርጋቸው ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።”36ስለዚህ፣ እናንተ የሰቀላችሁትን ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።"37ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ ልባቸው ተነካና ለጴጥሮስና ለቀሩት ሐዋርያት፣ “ወንድሞች ሆይ፣ ምን እናድርግ?” አሉ።38ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ እያንዳንዳችሁም ለኀጢአታችሁ ይቅርታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ መንፈስ ቅዱስንም በስጦታነት ትቀበላላችሁ።39የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ፣ ጌታ አምላካችን ለሚጠራቸው ሩቅ ላሉት ሁሉም ነውና።”40ጴጥሮስ በሌሎች ብዙ ቃላት መሰከረ፤ “ከዚህ ክፉ ትውልድ ራሳችሁን አድኑ” በማለትም አስጠነቀቃቸው።41ከዚያም ሕዝቡ ቃሉን ተቀብለው ተጠመቁ፤ በዚያም ቀን ሦስት ሺሕ ያህል ሰዎች ተጨመሩ።42እነርሱም ሐዋርያት በሚያስተምሩት ትምህርትና በኅብረት፣ እንጀራውን በመቊረስና በጸሎትም ይተጉ ነበር።43በሰው ሁሉ ላይ ፍርሀት መጣ፤ ብዙ ድንቆችና ምልክቶችም በሐዋርያት እጅ ተደረጉ።44ያመኑት ሁሉ በአንድነት ነበሩ፤ ሁሉም ነገር የጋራ ነበር፤45መሬታቸውንና ንብረታቸውን እየሸጡም ለሁሉም እንደሚያስፈልገው አካፈሉ።46በየቀኑም በአንድ ዐላማ በመቅደስ እየተጉ፣ በቤት ውስጥ እንጀራ እየቈረሱም ምግብን ልባዊ በሆነ ደስታና ትሕትና ዐብረው ይመገቡ ነበር፤47እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ ከበሬታ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን በየቀኑ በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።
1ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ጊዜ፣ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደስ ይወጡ ነበር።2ወደ ቤተ መቅደሱ ከሚገቡ ሰዎች ምጽዋት መለመን እንዲችል፣ ውብ ተብሎ በሚጠራው በቤተ መቅደሱ በር ላይ ሰዎች በየቀኑ በሸክም አምጥተው የሚያስቀምጡት፣ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ዐንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።3ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ቤተ መቅደሱ ሊገቡ ሲሉ ባያቸው ጊዜ፣ ምጽዋት ለመነ።4ጴጥሮስ ዐይኖቹን ምጽዋት በሚለምነው ሰውዬ ላይ በማድረግ፣ ከዮሐንስ ጋር “ወደ እኛ ተመልከት” አለው።5ዐንካሳውም፣ ከእነርሱ አንድ ነገር ለመቀበል በመጠበቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።6ጴጥሮስ ግን፣ “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ። በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተራመድ” አለው።7ጴጥሮስ ቀኝ እጁን ያዘውና ወደ ላይ አነሣው፤ ወዲያውም እግሮቹና የቍርጭምጭሚቱ ዐጥንቶች ጥንካሬ አገኙ።8ዐንካሳው ሰውዬ ወደ ላይ ዘልሎ ቆመ፤ መራመድም ጀመረ፤ ከጴጥሮስና ከዮሐንስ ጋርም እየተራመደ፣ እየዘለለና እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ።9ሰዎች ሁሉ ዐንካሳው እየተራመደ ሲሄድና እግዚአብሔርን ሲያመሰግን አዩት።10ምጽዋት ለመቀበል ውብ በሚባለው የቤተ መቅደሱ በር ላይ ይቀመጥ የነበረው ሰውዬ እንደ ሆነም ዐወቁ፤ በእርሱ ላይ ከሆነው የተነሣም በመደነቅና በመገረም ተሞሉ።11ሰውየው የጴጥሮስንና የዮሐንስን እጅ ይዞ ሳለ፣ የሰሎሞን መመላለሻ በሚባለው ደጅ ሰዎች ሁሉ በኀይል እየተደነቁ በአንድነት ወደ እነርሱ ሮጡ።12ጴጥሮስ ይህን ሲያይ ለሕዝቡ፣ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ለምን ትደነቃላችሁ? ይህን ሰው በገዛ ኀይላችን ወይም በመንፈሳዊነታችን እኛ እንዲራመድ እንዳደረግን ሁሉ፣ ለምን ዐይናችሁን አፍጥጣችሁ ትመለከታላችሁ? በማለት መልስ ሰጠ።13የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ፣ የአባቶቻችን አምላክ አገልጋዩን ኢየሱስን አክብሮታል። እርሱ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትና ጲላጦስ ሊፈታው ወስኖ ሳለ፣ በፊቱ የካዳችሁት ነው።14ቅዱሱንና ጻድቁን ካዳችሁት፤ በእርሱም ፈንታ ነፍሰ ገዳይ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ።15እግዚአብሔር ከሙታን ያስነሣውን፣ የሕይወትን ጌታ ገደላችሁት፤ እኛም የዚህ ምስክሮች ነን።16በእርሱ ስም ማመን አሁን የምታዩትንና የምታውቁትን ይህን ሰው ብርቱ አድርጎታል። አዎ፣ በኢየሱስ ያለው እምነቱ በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤንነት ሰጠው።17አሁን ወንድሞች ሆይ፣ አለቆቻችሁም እንዳደረጉት ባለማወቅ ያደረጋችሁት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ።18ነገር ግን እግዚአብሔር በነቢያቱ ሁሉ አፍ የእርሱ ክርስቶስ መከራ መቀበል እንዳለበት አስቀድሞ የተናገረውን አሁን ፈጸመው።19እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ፣ ከጌታ ዘንድም የመታደስ ዘመን እንዲመጣ ንስሓ ግቡ፤ ተመለሱም፤20ይኸውም ለእናንተ የመረጠውን ክርስቶስ የሆነውን ኢየሱስን እንዲልከው ነው።21እርሱ ሰማያት ሊቀበሉትና ነገሮች ሁሉ እስከሚታደሱበት ዘመን ድረስ ጠብቀው ሊያቈዩት የሚገባ፣ ከጥንት ጀምሮ በነበሩ ቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተነገረለት ነው።22ሙሴ በእርግጥ፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣል። የሚነግራችሁንም ሁሉ ስሙ’ አለ።23ያን ነቢይ የማይሰማ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።24አዎ፣ ከሳሙኤል ጀምሮና ከእርሱም በኋላ የተናገሩ ነቢያት ሁሉ ስለ እነዚህ ቀኖች ተናግረዋል።25እናንተ የነቢያትና ‘በዘርህ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ’ ብሎ ለአብርሃም እንደ ተናገረው፣ ከአባቶቻችሁ ጋር እግዚአብሔር ያደረገው ኪዳን ልጆች ናችሁ።26እግዚአብሔር አገልጋዩን ካስነሣ በኋላ በመጀመሪያ ወደ እናንተ ላከው፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ መልሶ ሊባርካችሁ ነው።
1ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ እየተናገሩ ሳሉ፣ ካህናቱና የቤተ መቅደሱ ሹም፣ ሰዱቃውያንም ወደ እነርሱ መጡ።2እነርሱም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ሕዝቡን ያስተምሩና ከሙታን መነሣቱንም ያውጁ ስለ ነበረ፣ እጅግ ተበሳጩ።3ያዟቸውና በዚያ ጊዜ ምሽት ስለ ነበረ እስከሚቀጥለው ጧት ድረስ በወኅኒ አቈዩአቸው።4ነገር ግን መልእክቱን ከሰሙት ብዙ ሰዎች አመኑ፤ ያመኑት ሰዎች ቍጥርም ዐምስት ሺሕ ያህል ነበረ።5በሚቀጥለው ቀን እንደዚህ ሆነ፤ አለቆቻቸው፣ ሽማግሌዎቻቸውና የሕግ መምህራናቸው በኢየሩሳሌም ውስጥ በአንድነት ተሰበሰቡ።6ሊቀ ካህናቱ ሐና እዚያ ነበረ፤ ቀያፋም፣ ዮሐንስም፣ እስክንድሮስና የሊቀ ካህናቱ ዘመዶች ሁሉ ነበሩ።7ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከላቸው አቁመውም፣ "በማን ሥልጣን ወይም በማንስ ስም ይህን አደረጋችሁ?" ብለው ጠየቋቸው።8ከዚያም ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የሕዝቡ አለቆች፣ ሽማግሌዎችም፣9ለታመመ ሰው የተደረገ መልካም ነገርን በሚመለከት በዚህ ቀን እየተጠየቅን ከሆንን፣ ይህ ሰው በምን ዳነ?10ይህ ለእናንተ ለሁላችሁ፣ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን፤ ይህ ሰው በፊታችሁ እዚህ በጤንነት የቆመው እናንተ በሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔር ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው።11ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፣ ነገር ግን የማእዘን ራስ የሆነ ድንጋይ ነው።12በሌላ በማንም ድነት የለም፤ ልንድንበት የሚገባ በሰዎች መካከል የተሰጠ ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።”13የጴጥሮስንና የዮሐንስን ድፍረት ሲያዩ፣ ያልተማሩና ተራ ሰዎች እንደ ሆኑ ሲያውቁም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ በማወቅ ተደነቁ።14የተፈወሰው ሰውዬ ዐብሯቸው ቆሞ ስላዩት፣ የአይሁድ መሪዎች በእነርሱ ላይ ምንም መናገር አልቻሉም።15ሐዋርያቱ ከሸንጎው ወጥተው እንዲሄዱ ካዘዙ በኋላ፣ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።16እንደዚህም አሉ፤ “በእነዚህ ሰዎች ላይ ምን እናድርግ? በእነርሱ አማካይነት የታወቀ ተአምር የመፈጸሙ እውነታ በኢየሩሳሌም ለሚኖር ሁሉ ታውቆአልና፤ ልንክደው አንችልም።17ሆኖም ይህ በሕዝቡ መካከል የበለጠ እንዳይሠራጭ፣ በዚህ ስም ከእንግዲህ ለማንም እንዳይናገሩ እናስጠንቅቃቸው።”18ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ውስጥ ጠርተው በኢየሱስ ስም ፈጽሞ እንዳይናገሩም፣ እንዳያስተምሩም አዘዟቸው።19ነገር ግን ጴጥሮስና ዮሐንስ መልሰው እንዲህ አሏቸው፤ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ እናንተን መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል እንደ ሆነ እናንተ ፍረዱ።20እኛ ስላየናቸውና ስለ ሰማናቸው ነገሮች ለመናገር ዝም ማለት አንችልም።”21እንደ ገናም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ካስጠነቀቋቸው በኋላ፣ ለቀቋቸው። እነርሱን ለመቅጣት ምንም ምክንያት ለማግኘት አልቻሉም፤ ምክንያቱም ሰዎቹ ሁሉ ለተደረገው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።22ይህ በተአምር የተፈወሰው ሰውዬ ከዐርባ ዓመት በላይ ዕድሜ ነበረው።23ከተለቀቁ በኋላ፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ራሳቸው ሰዎች መጡና የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ያሏቸውን ሁሉ ነገሯቸው።24ሰዎቹ የነገሯቸውን ሲሰሙም፣ ድምፃቸውን በአንድነት ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በውስጣቸው የሚገኘውንም ሁሉ የፈጠርህ ነህ፤25በመንፈስ ቅዱስም በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለሃል፦ ‘አሕዛብ ለምን አጕረመረሙ፣ ሕዝቡስ ከንቱ ነገርን ለምን ዐሰቡ?26በጌታ፣ በእርሱ መሲሕም ላይ የምድር ነገሥታት ተነሡ፣ አለቆችም በአንድነት ተሰበሰቡ።’27በእውነት ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ፣ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በቀባኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ በዚህ ከተማ ውስጥ በአንድነት ተሰብስበዋል።28የተሰበሰቡትም እጅህና ዐሳብህ አስቀድመው የወሰኑት እንዲፈጸም ነው።29ጌታ ሆይ፣ አሁን ወደ ዛቻዎቻቸው ተመልከት፤ ለባሪያዎችህም ቃልህን በሙሉ ድፍረት እንዲናገሩ ስጥ።30ለመፈወስ እጅህን ስትዘረጋው፣ ምልክቶችና ድንቆች በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ስም ይደረጋሉ።"31ጸሎት ሲጨርሱ፣ ተሰብስበውበት የነበረው ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃልም በድፍረት ተናገሩ።32ካመኑት እጅግ ብዙዎች አንድ ልብና አንድ ነፍስ ነበራቸው፤ ከእነርሱ አንድም ሰው፣ ያለው ማንኛውም ነገር የራሱ እንደ ሆነ አልተናገረም፤ ይልቁን ሁሉም ነገሮች የጋራ ነበሩ።33ሐዋርያቱም በታላቅ ኀይል ስለ ጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ ምስክርነታቸውን ያውጁ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።34በመካከላቸው ችግረኛ ሰው አልነበረም፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ ሸጠው የሽያጩን ገንዘብ ያመጡትና፣35በሐዋርያት እግር አጠገብ ያስቀምጡት ነበርና። አከፋፈሉም ይደረግ የነበረው እያንዳንዱ አማኝ በሚያስፈልገው መሠረት ነው።36ሌዋዊ የሆነው፣ ቆጵሮሳዊው ዮሴፍ ሐዋርያት በርናባስ የሚባል ስም ያወጡለት ሰው ነበር (ትርጕሙ የመጽናናት ልጅ ማለት ነው)።37እርሱ የነበረውን መሬት ሸጠው፤ ገንዘቡንም አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አስቀመጠው።
1ሐናንያ የሚባል አንድ ሰውም ከሚስቱ ከሰጲራ ጋራ መሬት ሸጠ፤2የሽያጩን ገንዘብ ከፊል መጠን አስቀረው (ሚስቱም ታውቅ ነበር)፤ ሌላውን የገንዘብ መጠን ግን አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አስቀመጠው።3ጴጥሮስ ግን ሐናንያን እንዲህ አለው፤ “ሐናንያ ሆይ፣ ለመንፈስ ቅዱስ እንድትዋሽና የመሬቱን ዋጋ ከፊል መጠን እንድታስቀር ሰይጣን ልብህን ለምን ሞላው?4መሬቱ ሳይሸጥ የአንተ እንደ ሆነ አይዘልቅም ነበርን? ከተሸጠ በኋላስ በአንተ ቊጥጥር ሥር አልነበረምን? በልብህ ይህን ነገር እንዴት ዐሰብህ? የዋሸኸው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰዎች አይደለም።5እነዚህን ቃሎች ሰምቶ፣ ሐናንያ ወደቀ፤ ሞተም። በሰሙት ሁሉ ላይም ታላቅ ፍርሀት መጣ።6ጐበዛዝቱ ወደ ፊት መጡና ከፈኑት፤ ወደ ውጭ አውጥተውም ቀበሩት።7ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላ፣ ሚስቱ ምን እንደ ሆነ ሳታውቅ ወደ ውስጥ ገባች።8ጴጥሮስ፣ “መሬቱን ይህን ለሚያህል ዋጋ ሸጣችሁት ከሆነ ንገሪኝ” አላት። እርሷም፣ "አዎ፣ ይህን ለሚያህል ነው” አለችው።9ከዚያም ጴጥሮስ፣ “የጌታን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? ተመልከቺ፣ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በር ላይ ነው፤ አንቺንም ወደ ውጭ ያወጡሻል።”10እርሷም ወዲያው በጴጥሮስ እግር ሥር ወደቀች፤ ሞተችም፤ ጐበዛዝቱም ወደ ውስጥ ሲገቡ ሞታ አገኟት፤ ወደ ውጭ አወጧትና በባሏ አጠገብ ቀበሯት።11በቤተ ክርስቲያን ሁሉና እነዚህን ነገሮች በሰሙት ላይ ታላቅ ፍርሀት መጣ።12በሕዝቡ መካከል ብዙ ምልክቶችና ድንቆች በሐዋርያት እጅ ይደረጉ ነበር። ሁሉም በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በአንድነት ነበሩ።13ነገር ግን አንድም ሌላ ሰው እንኳ ከእነርሱ ጋር ለመተባበር ድፍረት አልነበረውም፤ ሆኖም ከሕዝቡ ከፍተኛ አክብሮት ነበራቸው።14አሁንም የበለጡ አማኞች፣ እጅግ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ለጌታ ይጨመሩ ነበር፤15በሽተኞችንም እንኳ ተሸክመው ወደ መንገድ እያመጡ በዐልጋና በቃሬዛ ላይ ያስቀምጧቸው ነበር፤ ይኸውም ጴጥሮስ ሲያልፍ በተወሰኑት ላይ ጥላው እንዲያርፍባቸውነው።16በሽተኞችንና በርኩሳን መናፍስት የሚሠቃዩትን በማምጣት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉ ከተሞች አያሌ ሰዎችም በአንድነት ተሰበሰቡ፤ በሽተኞችም ሁሉ ተፈወሱ።17ነገር ግን ሊቀ ካህናቱና ዐብረውት የነበሩትም ሁሉ ተነሡ (የሰዱቃውያን ወገን የሆነው ማለት ነው)፤ እነርሱም በቅናት ተሞልተው ነበር፤18እጃቸውንም በሐዋርያት ላይ ጫኑ፤ በሕዝብ ወኅኒ ውስጥም አስገብተው አሰሯቸው።19ይሁን እንጂ፣ የጌታ መልአክ በሌሊት የወኅኒውን በሮች ከፈተ፤ ወደ ውጭ አውጥቶአቸውም እንዲህ አላቸው፤20“ሂዱ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ቁሙና የዚህን ሕይወት ቃሎች ሁሉ ለአሕዝቡ ተናገሩ።”21ይህን ሲሰሙም፣ ንጋት ላይ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና አስተማሩ። ነገር ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጡ፤ ሸንጎውንም በአንድነት፣ የእስራኤል ሕዝብ ሽማግሌዎችንም ጠሩ፤ ሐዋርያቱን እንዲያመጧቸውም ወደ ወኅኒው ላኩ።22ነገር ግን የተላኩት መኰንኖች በወኅኒው ውስጥ አላገኟቸውም፤ ተመልሰው በመሄድም እንዲህ ብለው ተናገሩ፣23“ወኅኒው በደኅና እንደ ተቈለፈና ጠባቂዎችም በር ላይ እንደ ቆሙ አግኝተናል፤ በከፈትነው ጊዜ ግን በውስጡ ማንንም አላገኘንም።”24የመቅደሱ ጥበቃ ሹምና ሊቃነ ካህናቱ እነዚህን ቃላት ሲሰሙ፣ እስረኞችን በሚመለከት ምን እንደሚሆን እጅግ ግራ ተጋቡ።25ከዚያም አንድ ሰው መጣና፣ “ወኅኒ ውስጥ ያስገባችኋቸው ሰዎች ቤተ መቅደስ ውስጥ ቆመው ሕዝቡን እያስተማሩ ናቸው” ብሎ ነገራቸው።26ስለዚህ ሹሙ ከመኰንኖች ጋር ሄደ፤ መልሶም አመጣቸው፤ ያመጧቸው ግን በኀይል አልነበረም፤ ሕዝቡ በድንጋይ ይወግሯቸዋል ብለው ፈርተው ነበርና።27አምጥተዋቸው በነበረ ጊዜ፣ በሸንጎው ፊት አቆሟቸው። ሊቀ ካህናቱም ጠየቃቸው፤28እንዲህም አላቸው፤ “በዚህ ስም እንዳታስተምሩ በጥብቅ አስጠንቅቀናችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋታል፤ የዚህን ሰው ደም በእኛ ላይ ለማምጣትም ትፈልጋላችሁ።”29ጴጥሮስና ሐዋርያቱ ግን መልሰው፣ “ለሰው ከመታዘዝ ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።30የአባቶቻችን አምላክ በዕንጨት ላይ በመስቀል የገደላችሁትን፣ ኢየሱስን አስነሣው።31አዳኝና የሁሉ የበላይ እንዲሆን፣ ለእስራኤል ንስሓንና የኀጢአት ይቅርታን ለመስጠት እግዚአብሔር በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።32እኛና እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ነን።”33የሸንጎው አባሎች ይህን ሲሰሙ፣ በጣም ተናደዱ፤ ሐዋርያቱንም ለመግደል ፈለጉ።34ነገር ግን የሕግ መምህር የነበረና ሕዝቡም ሁሉ የሚያከብረው ገማልያል የሚባል አንድ ፈሪሳዊ ተነሥቶ፣ ሐዋርያት ለተወሰነ ጊዜ ውጭ እንዲቈዩ አዘዘ።35ከዚያም እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በእነዚህ ሰዎች ልታደርጉ ያሰባችሁትን በጥንቃቄ ተመልከቱት።36ከጥቂት ጊዜ በፊት ቴዎዳስ ትልቅ ሰው ነኝ በማለት ተነሥቶ ነበርና፤ አራት መቶ ያህል ወንዶችም ተከተሉት። እርሱ ተገደለ፤ ይታዘዙለት የነበሩትም ሁሉ ተበታትነው እንዳልነበሩ ሆኑ።37ከዚህም ሰው በኋላ፣ የገሊላው ይሁዳ በቈጠራው ቀናት ዐምፆ የተወሰኑ ሰዎችን አስከትሎ ሄደ። እርሱም ሞተ፤ እርሱን ይታዘዙት የነበሩትም ተበታተኑ።38አሁንም እነግራችኋለሁ፤ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ፤ እነርሱንም ተዉአቸው፤ ይህ ዐሳብ ወይም ሥራ የሰዎች ከሆነ፣ ይጠፋል።39የእግዚአብሔር ከሆነ ግን፣ ልታጠፏቸው አትችሉም፤ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጋጩም እንኳ እንዳትገኙ።” እነርሱም በዐሳቡ ተስማሙ።40ከዚያም በኋላ፣ ሐዋርያቱን ወደ ውስጥ ጠርተው ገረፏቸው፤ በኢየሱስ ስም እንዳይናገሩም አዘዟቸውና ለቀቋቸው።41እነርሱም ስለ ስሙ ይዋረዱ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ፣ ደስ እያላቸው ከሸንጎው ወጡ።42ከዚያ በኋላ በየቀኑ፣ በቤተ መቅደስና ከቤት ወደ ቤት፣ በተከታታይ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ እንደ ሆነ ያስተምሩና ይሰብኩ ነበር።
1በእነዚህ ወራት፣ የደቀ መዛሙርት ቊጥር እየበዛ በሄደ ጊዜ፣ ከግሪክ የመጡት አይሁድ በዕብራውያን ላይ ማጕረምረም ጀመሩ፤ ምክንያቱም መበለቶቻቸው በየዕለቱ የምግብ ዕደላ ላይ ቸል ተብለውባቸው ነበር።2ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ ጠርተው እንዲህ አሏቸው፤ “የምግብ አገልግሎትን ለመስጠት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል መተው ለእኛ ተገቢ አይደለም።3ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፣ በዚህ ኀላፊነት ላይ ልንሾማቸው የምንችል መልካም አርአያነት ያላቸውን፣ መንፈስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ መካከል ምረጡ።4እኛ ግን፣ ሁልጊዜ በጸሎትና በቃሉ አገልግሎት እንቀጥላለን።”5ንግግራቸው ሕዝቡን ሁሉ ደስ አሰኘ። ስለዚህ እምነትና መንፈስ ቅዱስ የሞላበትን እስጢፋኖስን፣ ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞናን፣ ጳርሜናንና ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ።6አማኞቹ እነዚህን ሰዎች፣ በጸለዩላቸውና ከዚያም እጃቸውን በላያቸው በጫኑት በሐዋርያት ፊት አቀረቧቸው።7ስለዚህም የእግዚአብሔር ቃል አደገ፤ የደቀ መዛሙርት ቊጥርም በኢየሩሳሌም ውስጥ በብዛት ጨመረ፤ ከካህናትም ብዙዎቹ ለእምነት ታዛዦች ሆኑ።8እስጢፋኖስ ጸጋንና ኀይልን ተሞልቶ፣ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ድንቆችንና ምልክቶችን ያደርግ ነበር።9ነገር ግን ነጻ የወጡት ሰዎች ምኵራብ ከሚባለው ምኵራብ፣ ከቀሬናና ከእስክንድርያ፣ ከኪልቅያና ከእስያም የሆኑ ጥቂት ሰዎች ተነሡ። እነዚህ ሰዎች ከእስጢፋኖስ ጋር ይከራከሩ ነበር።10ነገር ግን ሰዎቹ እስጢፋኖስ የተናረገረበትን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም።11ከዚያም፣ “እስጢፋኖስ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተናል” እንዲሉ አንዳንድ ሰዎችን በምስጢር አሳመኑ።12ሰዎቹን፣ ሽማግሌዎቹን፣ የሕግ መምህራኖቹንም አነሣሡ፤ እስጢፋኖስንም ይዘው ወደ ሸንጎው አቀረቡት።13እንዲህ ብለው የሚናገሩ ሐሰተኛ ምስክሮችንም አመጡ፤ “ይህ ሰው ይህን ቅዱስ ስፍራና ሕጉን ተቃውሞ መናገርን አያቆምም።14ምክንያቱም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል፤ ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዐትም ይለውጠዋል ሲል ሰምተነዋል።”15በሸንጎው ውስጥ የተቀመጡት ሁሉ አተኵረው ተመለከቱት፤ ፊቱም እንደ መልአክ ፊት ሆኖ አዩት።
1ሊቀ ካህናቱም፣ “እነዚህ ነገሮች እውነት ናቸውን?” አለ።2እስጢፋኖስ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ አድምጡኝ፤ የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም በካራን ከመኖሩ በፊት በመስጴጦምያ ሳለ ተገለጠለት፤3እግዚአብሔርም፣ 'አገርህንና ዘመዶችህን ተውና እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ' አለው።4ከዚያም በኋላ፣ ጊዜ አብርሃም ከከለዳውያን ምድር ወጥቶ በካራን ኖረ፤ ከዚያም፣ አባቱ ከሞተ በኋላ፣ እግዚአብሔር አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት፣ ወደዚህ ምድር አመጣው።5ከዚህ ምድር ምንም ርስት፣ የእግር ጫማ ለማሳረፍ የሚበቃ እንኳ አልሰጠውም። ነገር ግን አብርሃም ገና ልጅ ያልነበረው ቢሆንም እንኳ፣ እግዚአብሔር ምድሪቱን ርስት አድርጎ ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለዘሮቹ እንደሚሰጥ ቃል ገባ።6እግዚአብሔር ለአብርሃም እንደዚህ እየተናገረው ነበር፤ ይኸውም ዘሮቹ ለተወሰነ ጊዜ በባዕድ ምድር እንደሚኖሩ፣ እዚያ ያሉ ኗሪዎችም በባርነት ውስጥ እንደሚያስገቧቸውና ለአራት መቶ ዓመታት እንደሚያስጨንቋቸው ነው።7‘በባርነት የሚኖሩበትን ሕዝብም እፈርድበታለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይወጣሉ፤ በዚህም ስፍራ ያመልኩኛል’ አለ እግዚአብሔር።8እግዚአብሔር ለአብርሃም የግዝረትን ኪዳን ሰጠው፤ አብርሃምም የይስሐቅ አባት ሆነ ይስሐቅንም በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅ የያዕቆብ አባት ሆነ፤ ያዕቆብም የዐሥራ ሁለቱ አለቆች አባት።9አለቆች በዮሴፍ ላይ በቅናት ተነሣሥተው ወደ ግብፅ ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ፤10ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስና ጥበብ ሰጠው። ፈርዖንም ዮሴፍን በግብፅና በቤቱ ባለው ሁሉ ላይ ገዥ አደረገው።11በመላው ግብፅና በከነዓን ራብና ትልቅ ጭንቀት መጣ፤ አባቶቻችንም ምንም ምግብ አላገኙም።12ነገር ግን ያዕቆብ እህል በግብፅ ውስጥ እንደ ነበረ ሲሰማ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ አባቶቻችንን ላካቸው።13በሁለተኛው ጊዜ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን ገለጠ፤ የዮሴፍ ቤተ ሰብም ከፈርዖን ጋር ተዋወቀ።14ከዘመዶቹ ሁሉ ጋር፣ ሰባ ዐምስት ሰዎች ሆኖ ወደ ግብፅ እንዲመጣ፣ ለአባቱ ለያዕቆብ እንዲነግሩ ዮሴፍ ወንድሞቹን መልሶ ላካቸው።15ስለዚህ ያዕቆብ ወደ ግብፅ ወረደ፤ ከጊዜ በኋላም፣ እርሱና አባቶቻችን በዚያ ሞቱ።16ወደ ሴኬም ተወስደውም አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በብር ገዝቶት በነበረው መቃብር ተቀበሩ።17እግዚአብሔር ለአብርሃም ገብቶት የነበረው የተስፋ ቃል ጊዜ ሲቃረብ፣ ሕዝቡ በግብፅ ውስጥ በቍጥር እያደጉና እየበዙ ሄዱ፤18በግብፅ ሌላ ንጉሥ፣ ስለ ዮሴፍ ያላወቀ ንጉሥ እስከ ተነሣ ድረስ።19ይኸው ንጉሥ ሕዝባችንን አታለለ፤ አባቶቻችንንም አስጨነቀ፤ ሕዝቡም ሕፃናታቸውን በሕይወት እንዳይኖሩ ወደ ውጭ መጣል ነበረባቸው።20በዚያ ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት በጣም ያማረ ነበር፤ በአባቱ ቤትም ሦስት ወር አደገ።21ሙሴ ወንዝ ውስጥ ሲጣል፣ የፈርዖን ሴት ልጅ ወስዳ እንደ ልጇ አሳደገችው።22ሙሴ በግብፃውያን ትምህርት ሁሉ የሠለጠነ፣ በንግግሩና በሥራውም ታላቅ ሰው ነበር።23አርባ ዓመት ሲሆነው ግን ወንድሞቹን፣ የእስራኤልን ልጆች የመጐብኘት ዐሳብ ወደ ልቡ መጣ።24አንድ እስራኤላዊ ሲጠቃ አይቶ፣ ሙሴ ተከላከለለት፤ ያጠቃውንም ግብፃዊ ተበቀለው፤25ሙሴ በእርሱ እጅ እግዚአብሔር እያዳናቸው መሆኑን ወንድሞቹ ያስተውላሉ ብሎ ዐሰበ፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም።26በሚቀጥለው ቀን ሙሴ እየተጣሉ ወደ ነበሩ እስራኤላውያን መጣ፤ እርስ በርስ ሊያስታርቃቸውም ሞከረ፤ ‘እናንተ ሰዎች ሆይ፣ ወንድማማቾች ናችሁ፤ እርስ በርስ ለምን ትጐዳዳላችሁ?’ አለ።27ባልንጀራውን የጐዳው ግን ሙሴን ገፈተረው፤ እንደዚህም አለው፤ 'በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ ያደረገህ ማን ነው?28ግብፃዊውን ትናንት እንደ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?'29ሙሴ ይህን ከሰማ በኋላ ሸሽቶ ሄደ፤ የሁለት ልጆች አባት በሆነበት በምድያም ምድር መጻተኛ ሆነ።30አርባ ዓመት ሲያልፍ፣ በሲና ተራራ ምድረ በዳ፣ በቊጥቋጦ ውስጥ በእሳት ነበልባል መልአክ ታየው።31ሙሴ እሳቱን ሲያይ፣ በሚታየው ተደነቀ፤ ሊመለከተው ሲቀርብም፣ እንዲህ የሚል የጌታ ድምፅ መጣ፤32‘እኔ የአባቶችህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ።’ ሙሴ ተንቀጠቀጠ፣ መመልከትም አልቻለም።33ጌታም ለሙሴ እንዲህ አለው፤ ‘የቆምህበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ጫማህን አውልቅ።34በግብፅ ውስጥ ያሉትን የሕዝቤን ሥቃይ በእርግጥ አይቻለሁ፤ የሥቃይ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁና አሁን ና፤ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ።’35“በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ ያደረገህ ማን ነው?” ባሉት ጊዜ ተቀባይነትን ያሳጡት ይህ ሙሴ፦ እግዚአብሔር ገዥም ታዳጊም አድርጎ የላከው ነው። እግዚአብሔር ሙሴን በቊጥቋጦው ውስጥ በታየው መልአክ እጅ ላከው።36በግብፅና በቀይ ባሕር፣ በአርባ ዓመታቱ ወቅትም በምድረ በዳ ተአምራትንና ምልክቶችን ካደረገ በኋላ፣ ሙሴ ሕዝቡን ከግብፅ አወጣቸው።37‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል’ ብሎ ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው ያው ሙሴ ነው።38ይህ ሰው ሲና ተራራ ላይ ያናግረው ከነበረው መልአክ ጋር በምድረ በዳው በጉባኤ ውስጥ የነበረ ሰው ነው። ሰው ከአባቶችችን ጋር ነበረ፤ ለእኛ ሊሰጥ ሕያው ቃልን የተቀበለ ሰውም ነው።39ይህ አባቶቻችን ለመታዘዝ እንቢ ያሉት ሰው ነው፤ እነርሱም ገፉት፤ በልባቸውም ወደ ግብፅ ተመለሱ።40በዚያ ጊዜ አሮንን እንዲህ አሉት፤ ‘የሚመሩንን አማልክት ሥራልን። ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ይህ ሙሴ፣ ምን እንዳጋጠመው አናውቅም።'41ስለዚህ እስራኤላውያን በእነዚያ ቀኖች ጥጃ ሠርተው ለጣዖቱ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከእጆቻቸው ሥራ የተነሣም ደስ አላቸው።42እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ፤ የሰማይ ከዋክብትን እንዲያመልኩም አሳልፎ ሰጣቸው፤ በነቢያት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣ የታረዱ እንስሳትንና መሥዋዕቶችን አቀረባችሁልኝን?43የሞሎክን ድንኳን፣ ሬምፉም የሚባለውን አምላክ ኮከብም፣ ልታመልኳቸው የሠራችኋቸውን ምስሎችም ተቀበላችሁ፤ እኔም ከባቢሎን ወዲያ እሰድዳችኋለሁ።’44አባቶቻችን የምስክሩ ድንኳን በምድረ በዳ ነበራቸው፤ ይኸውም ባየው ምሳሌ መሠረት መሥራት እንዳለበት እግዚአብሔር ሙሴን ሲያናግረው እንዳዘዘው ያለ ነው።45ይህ አባቶቻችን በተራቸው ከኢያሱ ጋር ወደ ምድሪቱ ያመጡት ድንኳን ነው። እግዚአብሔር በአባቶቻችን ፊት ባስወጣቸው አሕዛብ አገር ውስጥ ሲገቡ፣ ይህ ሆነ። እስከ ዳዊት ዘመን ድረስ እንደዚህ ነበር፤46ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አገኘ፤ ለያዕቆብ አምላክም ማደሪያ ስፍራን ለማግኘት ለመነ።47ነገር ግን ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ሠራለት።48ይሁን እንጂ፣ ልዑሉ በእጅ በተሠሩ ቤቶች ውስጥ አይኖርም፤ ይህም ነቢዩ እንዲህ ብሎ እንደሚናገረው ነው፦49ሰማይ ዙፋኔ፣ ምድርም የእግሬ መርገጫ ነው። ምን ዐይነት ቤት ልትሠሩልኝ ትችላላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ የማርፍበት ስፍራ የት ነው?50እጄ እነዚህን ሁሉ አልሠራችምን?51እናንተ ዐንገተ ደንዳኖች፣ ልባችሁንና ጆሮዎቻችሁን ያልተገረዛችሁ፣ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንዳደረጉትም ታደርጋላችሁ።52ከነቢያት የእናንተ አባቶች ያላሳደዱት የትኛው ነው? እነርሱ ከጻድቁ መምጣት ቀድመው የተናገሩ ነቢያትን ገድለዋል፤ እናንተም አሁን ጻድቁን የምትክዱና የምትገድሉ ሆናችኋል፤53መላእክት ያጸኑትን ሕግ ብትቀበሉም አልጠበቃችሁትም።”54አሁን የሸንጎው አባላት እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ፣ በልባቸው እጅግ ተቈጡ፣ ጥርሳቸውንም በእስጢፋኖስ ላይ አፋጩ።55እስጢፋኖስ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ፣ ወደ ሰማይ አተኵሮ ተመለከተ፣ የእግዚአብሔርንም ክብር አየ፤ ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየው።56እስጢፋኖስ፣ “እነሆ፣ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየሁ” አለ።57የሸንጎው አባላት ግን በታላቅ ድምፅ ጮኹ፤ ጆሮአቸውንም በመድፈን በአንድነት እየሮጡ ወደ እስጢፋኖስ ሄዱ፤58ከከተማው አውጥተውም በድንጋይ ወገሩት፤ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚባል አንድ ወጣት እግር አጠገብ አኖሩ።59እስጢፋኖስን ሲወግሩት፣ ወደ እግዚአብሔር ይጣራ፣ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ነፍሴን ተቀበል” እያለ ይናገርም ነበር።60ተንበረከከና በታላቅ ድምፅ፣ “ጌታ ሆይ፣ ይህን ኀጢአት አትቊጠርባቸው” ብሎ ጮኸ። ይህን ተናግሮም፣ አንቀላፋ።
1ሳውል በእስጢፋኖስ ሞት ተስማምቶ ነበር። በዚያም ጊዜ በኢየሩሳሌም በነበረችዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ አማኞችም ሁሉ ከሐዋርያት በቀር በይሁዳና በሰማርያ ተበታተኑ።2በመንፈሳዊ ነገር የተጉ ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ መሪር ልቅሶም አለቀሱለት።3ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን በጣም ጐዳ፤ ከቤት ወደ ቤት በመሄድም ክርስቲያን ወንዶችንና ሴቶችን ጐትቶ አወጣቸው፤ ወኅኒ ቤት ውስጥም አስገባቸው።4የተበታተኑት አማኞች ግን ቃሉን እየሰበኩ በየቦታው ዞሩ።5ፊልጶስ ወደ ሰማርያ ከተማ ወረደ፣ ለሕዝቡም ክርስቶስን ሰበከላቸው።6እጅግ ብዙ ሰዎች ፊልጶስን ሲሰሙትና ያደረጋቸውንም ምልክቶች ሲያዩ፣ በአንድነት እርሱ ለተናገረው ትኵረት ሰጡ።7ምክንያቱም ከብዙ ሰዎች ርኩሳን መናፍስት እየጮኹ ወጥተው፣ አያሌ ሽባዎችና ዐንካሶችም ተፈውሰው ነበር።8ስለዚህ በዚያች ከተማ ውስጥ ብዙ ደስታ ነበር።9ነገር ግን በዚያች ከተማ ውስጥ ቀደም ሲል የጥንቈላ ሥራ ይሠራ የነበረ ሲሞን የሚባል ሰው ነበረ፤ ተፈላጊ ሰው እንደ ሆነ እየተናገረ የሰማርያን ሰዎች ያስደንቅ ነበር።10ሳምራውያን በሙሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ፣ “ይህ ሰው ታላቅ የሚባለው የእግዚአብሔር ኀይል ነው” እያሉ በሚገባ ያደምጡት ነበር።11በጥንቈላ ሥራው ለረጅም ጊዜ ያስገርማቸው ስለ ነበር አደመጡት።12ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፊልጶስ የሰበከውን ወንጌል ሲያምኑ ግን ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።13ሲሞንም ደግሞ አመነ፤ ከተጠመቀም በኋላ ከፊልጶስ ጋር መሆንን ቀጠለ፤ የተደረጉ ምልክቶችንና ታላላቅ ተኣምራትን ባየ ጊዜም ተደነቀ።14በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያት ሰማርያ የእግዚአብሔርን ቃል የተቀበለች መሆኗን ሲሰሙ፣ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኩላቸው።15እነርሱም እዚያ ወርደው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጸለዩላቸው።16መንፈስ ቅዱስ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በማንኛቸውም ላይ አልወረደም ነበርና፣ እነርሱ በጌታ ኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር።17ከዚያም ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፣ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ።18በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰጥ ሲያይ፣ ሲሞን ገንዘብ አቀረበላቸው።19“እኔም እጁን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንዲችል ይህን ሥልጣን ስጡኝ” አላቸው።20ነገር ግን ጴጥሮስ እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለማግኘት አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ።21ልብህ ለእግዚአብሔር የቀና አይደለምና በዚህ ጉዳይ ውስጥ ዕድል ወይም ድርሻ የለህም።22እንግዲህ ለዚህ ክፋትህ ንስሓ ግባ፤ ምናልባትም ለልብህ ዐሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ጌታን ለምን።23በኀጢአት እስራትና በመራርነት መርዝ ውስጥ እንዳለህ አያለሁና።”24ሲሞንም መልሶ፣ “ከተናገራችኋቸው አንዱም በእኔ ላይ እንዳይፈጸም ወደ ጌታ ጸልዩልኝ” አላቸው።25ጴጥሮስና ዮሐንስ ከመሰከሩና የጌታን ቃል ከተናገሩ በኋላ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ በመንገድም ለብዙ የሰማርያ መንደሮች ወንጌልን ሰበኩ።26የጌታ መልአክ ፊልጶስን፣ “ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ተነሥና ሂድ” አለው። (ይህ መንገድ በበረሓ ውስጥ ነው።)27እርሱም ተነሣና ሄደ። እነሆ፣ በኢትዮጵያውያን ንግሥት በሕንደኬ ሥር ትልቅ ሥልጣን የነበረው አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ነበረ። ሰውዬው በንግሥቲቱ ንብረት ሁሉ ላይ ኀላፊነት ነበረው። ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር።28ከኢየሩሳሌም በመመለስ ላይ ሳለ፣ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ትንቢተ ኢሳይያስን እያነበበ ነበር።29መንፈስ ፊልጶስን፣ “ሂድ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው።30ፊልጶስ ወደ ጃንደረባው ሮጠ፣ ትንቢተ ኢሳይያስንም ሲያነብ ሰማው፤ “የምታነበውን ትረዳዋለህ?” አለው።31ኢትዮጵያዊውም፣ “የሚመራኝ ከሌለ እንዴት ልረዳው እችላለሁ?” አለው። ወደ ሠረገላው እንዲወጣና ዐብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው።32ኢትዮጵያዊው ያነበው የነበረ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይህ ነው፦ “እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤ በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል ጠቦት፣ አፉን አልከፈተም፤33በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ትውልዱን ማን ይናገራል? ሕይወቱ ከምድር ተወግዶአልና።”34ጃንደረባው ፊልጶስን፣ “እባክህ ነቢዩ ስለ ማን ነው የሚናገረው? ስለ ራሱ ወይስ ስለ ሌላ ነው?” አለው።35ፊልጶስም መናገር ጀመረ፤ ከዚህም ከኢሳይያስ መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ሰበከው።36እየሄዱ ሳሉ ውሃ አለበት ዘንድ ደረሱ፤ ጃንደረባው፣ “ተመልከት፣ እዚህ ውሃ አለ፤ እንዳልጠመቅ ምን ይከለክለኛል?” አለ።37ፊልጶስም፣ “በፍጹም ልብህ ካመንህ፣ መጠመቅ ትችላለህ” አለ። ኢትዮጵያዊውም መልሶ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ” አለ።38ኢትዮጵያዊው ሠረገላው እንዲቆም አዘዘና፣ ፊልጶስም ጃንደረባውም ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም አጠመቀው።39ከውሃው ውስጥ ሲወጡ፣ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ከዚያ ወዲያ አላየውም፤ ደስ ብሎትም ጕዞውን ቀጠለ።40ነገር ግን ፊልጶስ በአዛጦን ታየ። በዚያ አገር ውስጥ በማለፍ ቂሣርያ እስኪደርስ ድረስ፣ ለከተሞች ሁሉ ወንጌልን ሰበከ።
1ሳውል ግን በጌታ ደቀ መዛሙርት ላይ ለግድያም እንኳ እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤2የጌታን መንገድ ከሚከተሉት ወንዶችም ሆነ ሴቶች ቢያገኝ፣ ወደ ኢየሩሳሌም አስሮ እንዲያመጣቸው፣ ለምኵራቦች ደብዳቤ እንዲሰጠውም ሊቀ ካህናቱን ጠየቀ።3እየሄደ ሳለ ደማስቆ አጠገብ ሲደርስ፣ በድንገት ከሰማይ ብርሃን በዙሪያው በራበት፤4በምድር ላይ ወደቀ፤ “ሳውል፣ ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ” የሚል ድምፅ ሰማ።5ሳውልም፣ "ጌታ ሆይ፣ ማን ነህ?" ብሎ መለሰ፤ ጌታም፣ “አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ፤6ነገር ግን ተነሥተህ ወደ ከተማው ግባ፤ ማድረግ ያለብህም ይነገርሃል” አለ።7ከዚያም ከሳውል ጋር የተጓዙት ሰዎች ድምፁን እየሰሙ፣ ማንንም ግን ሳያዩና ሳይነጋገሩ ቆሙ።8ሳውል ከወደቀበት ተነሣ፤ ዐይኑን ሲከፍትም ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህም በእጅ እየመሩ ወደ ደማስቆ አስገቡት።9ሦስት ቀን ዕውር ሆኖ ቆየ፤ አልበላም አልጠጣምም።10በዚያ ጊዜ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር በደማስቆ ነበር፤ ጌታም ለእርሱ በራእይ፣ “ሐናንያ” አለው። እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ እነሆኝ” አለ።11ጌታም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ተነሥና ቀጥተኛ ወደሚባለው ጎዳና ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰውን ፈልግ፤ እርሱ እዚያ እየጸለየ ነውና፤12እርሱ እንዲያይ ሐናንያ የሚባል ሰው ሲገባና በእርሱ ላይ እጁን ሲጭንበት በራእይ አይቶአል።”13ሐናንያም መልሶ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፣ ስለዚህ ሰው በኢየሩሳሌም ባሉት ሕዝብህ ላይ ምን ያህል ክፋት እንደ ፈጸመባቸው ከብዙዎች ሰምቻለሁ።14ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከሊቀ ካህናቱ ሥልጣን ተቀብሎአል።”15ጌታ ግን መልሶ እንዲህ አለው፤ “ሂድ፤ እርሱ በአሕዛብ፣ በነገሥታትና በእስራኤል ልጆች ፊት ስሜን ለመሸከም የተመረጠ ዕቃየ ነውና፤16ስለ ስሜ ሲል ምን ያህል መከራ መቀበል እንዳለበትም አሳየዋለሁና።17ስለዚህ ሐናንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁን በሳውል ላይ በመጫንም፣ “ወንድሜ ሳውል ሆይ፣ ስትመጣ በመንገድ ላይ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ እንድታይና መንፈስ ቅዱስን እንድትሞላ ወዳንተ ልኮኛል።”18ወዲያው እንደ ቅርፊት ያለ ነገር ከሳውል ዐይን ወደቀ፤ ማየትም ጀመረ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፤19በላ፣ በረታም። ሳውል በደማስቆ ውስጥ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ብዙ ቀን ቆየ።20ወዲያውም ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በምኵራብ ውስጥ ዐወጀ።21የሰሙትም ሁሉ በመደነቅ እንዲህ አሉ፤ “ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ያጠፋው አይደለምን? የመጣውም አስሮ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊያቀርባቸው ነው።”22ሳውል ግን ለመስበክ በረታ፣ በደማስቆ ይኖሩ የነበሩ አይሁድንም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በማረጋገጥ ግራ አጋባቸው።23ከብዙ ቀን በኋላ፣ አይሁድ ሊገድሉት ዐሰቡ።24ሳውል ግን ዐሳባቸውን ዐወቀባቸው። ሊገድሉት የከተማይቱን በሮች ቀንም ሌሊትም ይጠብቁ ነበር።25ደቀ መዛሙርቱ ግን በግድግዳው በኩል በቅርጫት አወረዱት።26ሳውል ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመገናኘት ሞከረ፤ ነገር ግን ደቀ መዝሙር መሆኑን በመጠራጠር ሁሉም ፈሩት።27ይሁን እንጂ፣ በርናባስ ወስዶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ አቀረበው። ሳውል ጌታን በመንገድ ላይ እንዴት እንዳየው፣ ጌታም እንደ ተናገረው፣ በኢየሱስ ስም ደማስቆ ውስጥ በድፍረት እንዴት እንደ ሰበከም ነገራቸው።28ሳውል ኢየሩሳሌም ውስጥ ሲገባና ከዚያም ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተገናኘ። በጌታ ኢየሱስ ስም በድፍረት ተናገረ፤29ከግሪክ አይሁድ ጋርም ተከራከረ፤ ሊገድሉት ሙከራ ማድረጋቸውን ግን አላቋረጡም።30ወንድሞች ስለዚህ ባወቁ ጊዜ፣ ወደ ቂሣርያ አውርደው ወደ ጠርሴስ ላኩት።31ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሁሉ፣ የገሊላና የሰማርያ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ነበራት፣ ታነጸችም፤ እግዚአብሔርን በመፍራትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት ቤተ ክርስቲያን በቍጥር አደገች።32ጴጥሮስም በየቦታው ሲዘዋወር፣ በልዳ ከተማ ወደሚኖሩ ቅዱሳንም ወረደ።33እዚያም፣ ሽባ በመሆኑ ስምንት ዓመት የአልጋ ቊራኛ የነበረን ኤንያ የሚባለውን አንድ ሰው አገኘ።34ጴጥሮስ፣ “ኤንያ ሆይ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሥና ዐልጋህን አንጥፍ” አለው። ወዲያውም ተነሣ።35በልዳና በሰሮና የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ሰውየውን አዩትና ወደ ጌታ ተመለሱ።36በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟ ትርጕም “ዶርቃ” ማለት ነው። ይች ሴት በመልካም ምግባርና ለድኾች በምታደርጋቸው የርኅራኄ ሥራዎች የተሞላች ነበረች።37በዚያም ወቅት ታመመችና ሞተች፤ ዐጥበውም ሰገነት ላይ አስቀመጧት።38ልዳ በኢዮጴ አጠገብ በመሆኑና ደቀ መዛሙርቱም የጴጥሮስን በዚያ መኖር ስለ ሰሙ፣ “ሳትዘገይ ወደ እኛ ና” ብለው በመለመን ሁለት ሰዎችን ወደ እርሱ ላኩ።39ጴጥሮስም ተነሣና ከተላኩት ጋር ሄደ። እዚያ ሲደርስ፣ ወደ ሰገነቱ አወጡት። መበለታቱም ሁሉ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ትለብሳቸው የነበሩትን ቀሚሶችና ልብሶች እያሳዩትና እያለቀሱ በአጠገቡ ቆሙ።40ጴጥሮስ ሁሉንም ከክፍሉ አስወጣቸውና ተንበርክኮ ጸለየ፤ ከዚያም ወደ አስከሬኑ በመዞር፣ “ጣቢታ ሆይ፣ ተነሺ” አለ። ዐይኖቿን ከፈተች፤ ጴጥሮስንም ስታየው ተነሥታ ተቀመጠች።41ጴጥሮስም እጇን ይዞ አነሣት፤ አማኞችንና መበለታቱን ጠርቶም በሕይወት እንዳለች ሰጣቸው።42ይህ ጉዳይ በመላው ኢዮጴ የታወቀ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ።43ጴጥሮስ በኢዮጴ ቍርበት ፋቂ ከነበረ ስምዖን ከሚባል ሰው ጋር ብዙ ቀን ቆየ።
1በቂሣርያ ከተማ ውስጥ የኢጣሊቄ ክፍለ ሰራዊት በሚባል የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚባል ሰው ነበረ።2እርሱም መንፈሳዊ፣ ከቤተ ሰቡ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ ለአይሁድ ብዙ ገንዘብ የሚሰጥና ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር የሚጸልይ ሰው ነበረ።3ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲመጣ በራእይ በግልጽ ታየው። መልአኩ፣ “ቆርኔሌዎስ!” አለው።4ቆርኔሌዎስ መልአኩን አተኵሮ ተመለከተውና ፈርቶ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፣ ይህ ምንድን ነው?” መልአኩም መልሶ፣ “ጸሎትህና ምጽዋትህ በመታሰቢያነት ወደ እግዚአብሔር ደርሶአል።5ጴጥሮስም ተብሎ የሚጠራውን ስምዖን የሚባለውን ሰውየ ለማስመጣት አሁን ወደ ኢዮጴ ከተማ ሁለት ሰዎችን ላክ።6ሰውየው ቤቱ በባሕሩ አጠገብ ከሚገኝ ስምዖን ከሚባለው ከቆዳ ፋቂው ጋር አለ” አለው።7ያነጋግረው የነበረው መልአክ እንደ ሄደ፣ ቆርኔሌዎስ ከሚያገለግሉት ወታደሮች መካከል እግዚአብሔርን ያመልክ የነበረ አንድ ወታደርንና ከቤት አሽከሮቹ ሁለቱን ጠራ።8ቆርኔሌዎስ የሆነውን ሁሉ ነግሮአቸው ወደ ኢዮጴ ላካቸው።9በሚቀጥለው ቀን ስድስት ሰዓት አካባቢ፣ በጕዞ ላይ ሳሉና ወደ ከተማዋ ሲቃረቡ፣ ጴጥሮስ ሊጸልይ ወደ ሰገነቱ ወጣ።10ራበውና አንዳች ነገር ለመብላት ፈለገ፤ ነገር ግን ሰዎች ምግብ በማዘጋጀት ላይ ሳሉ፣ በተመስጦ ውስጥ ገባ፤11ሰማይ ተከፍቶ፣ ትልቅ ሸማ የሚመስል አንድ መያዣ በአራቱ ጠርዞቹ ተይዞ ወደ ምድር ሲወርድም አየ።12በውስጡም አራት እግር ያላቸው እንስሳት ሁሉና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራን፣ የሰማይ ወፎችም ነበሩበት።13“ጴጥሮስ ሆይ፣ ተነሥና ዐርደህ ብላ” የሚል ድምፅ ለጴጥሮስ መጣ።14ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፣ አይሆንም፤ ምክንያቱም እኔ ርኩስና አስጸያፊ የሆነ ምንም ነገር ፈጽሞ በልቼ አላውቅም” አለ።15እንደገናም ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ጴጥሮስ መጣ፤ “እግዚአብሔር ቅዱስ ያደረገውን ርኩስ ብለህ አትጥራው” የሚል ድምፅ።16ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፤ ከዚያም መያዣው ወዲያው ወደ ሰማይ ተመልሶ ተወሰደ።17ጴጥሮስ ያየው ራእይ ምን ትርጕም ሊኖረው እንደሚችል በጣም ግራ ገብቶት ሳለ፣ ወደ ቤት የሚያስሄደውን መንገድ ጠይቀው ካገኙ በኋላ እነሆ፣ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በበሩ ፊት ለፊት ቆሙ።18ድምፃቸውን ከፍ በማድረግም ጴጥሮስ የሚባለው ስምዖን በዚያ መኖሩንና አለመኖሩን ጠየቁ።19ጴጥሮስ ስለ ራእዩ በማሰብ ላይ ሳለ፣ መንፈስ ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፣ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል።20ተነሥና ውረድ፤ ከእነርሱም ጋር ሂድ። ዐብረሃቸው ለመሄድ አትፍራ፤ ምክንያቱም የላክኋቸው እኔ ነኝ።”21ስለዚህም ጴጥሮስ ወደ ሰዎቹ ወርዶ፣ “የምትፈልጉት ሰው እኔ ነኝ። የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አላቸው።22እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ በአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ዘንድም የተመሰገነ ቆርኔሌዎስ የሚባል ጻድቅ ሰው፣ ወደ ቤቱ ሰው ልኮ እንዲያስመጣህ የእግዚአብሔር መልአክ ነገረው፤ እንዲህ ያደረገውም ከአንተ መልእክትን መስማት እንዲችል ነው።”23ጴጥሮስም እንዲገቡና ከእርሱና ዐብረውት ከነበሩ ሰዎች ጋር እንዲቈዩ በእንግድነት ተቀበላቸው። በማግስቱ ጧት ጴጥሮስ ተነሣና ከእነርሱ ጋር ሄደ፤ በኢዮጴ ከነበሩት ወንድሞችም አንዳንዶቹ ዐብረውት ሄዱ።24በሚቀጥለው ቀን ቂሣርያ ደረሱ። ቆርኔሌዎስ እየጠበቃቸው ነበር፤ ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹንም ጠርቶ እንዲሰበሰቡ አደረገ።25ጴጥሮስ ሲገባ፣ ቆርኔሌዎስ አግኝቶት እግሩ ላይ ወድቆ ሰገደለት።26ነገር ግን ጴጥሮስ አነሣውና፣ “ተነሥ ቁም፤ እኔ ራሴም ሰው ነኝ” አለው።27ጴጥሮስ ከቆርኔሌዎስ ጋር እየተነጋገረ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ የተሰበሰቡ ብዙ ሰዎችን አገኘ።28እንዲህም አላቸው፤ "አይሁዳዊ የሆነ ሰው ከሌላ ሕዝብ ከሆነ ጋር መገናኘት ወይም እርሱን መጎብኘት በሕግ እንደማይፈቀድለት እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር ማንንም ሰው ርኩስ ወይም አስጸያፊ ብዬ መጥራት እንደማይገባኝ ለእኔ አሳይቶኛል።29ሲላክብኝ ሳልከራከር የመጣሁት ከዚህ የተነሣ ነው። ስለዚህ ለምን እንደ ላካችሁብኝ እጠይቃችኋለሁ።"30ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለ፤ “ከአራት ቀን በፊት ልክ በዚህ ሰዓት በዘጠኝ ሰዓት በቤቴ ውስጥ እጸልይ ነበር፤ እነሆም ነጭ ልብስ ለብሶ ፊት ለፊቴ ቆመና፣31‘ቆርኔሌዎስ ሆይ፣ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰምቶአል፤ ምጽዋትህም መታሰቢያ ሆኖልሃል።32ስለዚህ ወደ ኢዮጴ ሰው ላክና ጴጥሮስም የሚባለውን ስምዖንን ወደ አንተ ጠርተህ አስመጣ። እርሱ በቆዳ ፋቂው በስምዖን ቤት በባሕር አጠገብ ተቀምጦአል’ አለኝ።33ስለዚህ ወዲያው ላክሁብህ። አሁን መምጣትህ መልካም አደረግህ። አሁን እንግዲህ እኛ ሁላችን እግዚአብሔር እንድትናገር ያዘዘህን ሁሉ ለመስማት በእግዚአብሔር ፊት እንገኛለን።"34ጴጥሮስም እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ በእውነት ተገንዝቤአለሁ።35ይልቁን በማንኛውም ሕዝብ ውስጥ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የጽድቅ ተግባራትንም የሚፈጽም ሁሉ በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።36እግዚአብሔር በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰላምን የምሥራች ባወጀበት ጊዜ፣ ወደ እስራኤል ሕዝብ የላከውን መልእክት ታውቃላችሁ፦37ዮሐንስ ካወጀው ጥምቀት በኋላ፣ በገሊላ በመጀመር በይሁዳ ሁሉ የታዩትን የተፈጸሙ ሁነቶችን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤38ሁነቶቹም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስና በኀይል እንዴት እንደ ቀባው የናዝሬቱን ኢየሱስን የሚመለከቱ ናቸው። ኢየሱስ መልካም እያደረገና ለዲያብሎስ የተገዙትን እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና።39በዕንጨት ላይ ሰቅለው የገደሉት ይህ ኢየሱስ ከአይሁድ አገርም በኢየሩሳሌምም ለፈጸማቸው ተግባራት ሁሉ እኛ ምስክሮች ነን።40ይህን ሰው እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው፤ እንዲገለጥም አደረገው፤41ይኸውም እግዚአብሔር አስቀድሞ መርጦአቸው ለነበሩ ምስክሮች እንጂ፣ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፦ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ዐብረነው የበላንና የጠጣን እኛው ራሳችን ነን።42ለሕዝቡ እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ላይ እንዲፈርድ፣ እግዚአብሔር የመረጠው ይህ እንደ ሆነ እንድንመሰክር አዘዘን።43በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኀጢአትን ይቅርታ እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ የሚመሰክሩት ስለ እርሱ ነው።”44ጴጥሮስ እነዚህን ነገሮች ገና እየተናገረ ሳለ፣ መልእክቱን በሚሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው።45ከተገረዙት ወገን የሆኑ አማኞች፦ ከጴጥሮስ ጋር የመጡትም ሁሉ ተደነቁ፤ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብም ላይ ወርዶ ነበር።46እነዚህ አሕዛብ በሌሎች ቋንቋዎች ሲናገሩና እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ሰምተዋቸዋልና። ከዚያም በኋላ ጴጥሮስ መልሶ፣47“እንደ እኛ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እነዚህ ሰዎች እንዳይጠመቁ ማን ውሃ ሊከለክላቸው ይችላል?” አለ።48በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁም አዘዛቸው። ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር ጥቂት ቀን እንዲቈይ ጴጥሮስን ለመኑት።
1ሐዋርያትና በይሁዳ የነበሩት ወንድሞች አሕዛብ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ተቀብለው እንደ ነበር ሰሙ።2ጴጥሮስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቶ በነበረ ጊዜ፣ ከመገረዝ ወገን የነበሩት ነቀፉት፤3“ካልተገረዙ ወንዶች ጋር ተባብረሃል፣ አብረሃቸውም በልተሃል!” አሉት።4ጴጥሮስ ግን እንዲህ ብሎ ጉዳዩን በዝርዝር ያብራራላቸው ጀመር፤5እኔ በኢዮጴ ከተማ እጸልይ ነበር፤ በተመስጦም አራት ማዕዘን ያለው ታላቅ ሸማ የመሰለ ዕቃ መያዣ ከሰማይ ሲወርድ ራእይ ዐየሁ፤ ወደ እኔ ወረደ፣6ትኵር ብዬ ተመለክትሁትና ስለ እርሱ ዐሰብሁ። አራት እግር ያላቸው የምድር እንስሳትን፣ አራዊትን፣ የሚሳቡ ፍጥረታትን፣ የሰማይ አዕዋፍንም ዐየሁ።7በዚያን ጊዜ አንድ ድምፅ፣ “ጴጥሮስ ሆይ፣ ተነሣ፣ አርደህም ብላ!” ሲለኝ ሰማሁ።8“ጌታ ሆይ፣ አይሆንም፣ ምክንያቱም ጸያፍ ወይም ርኩስ የሆነ ምንም ነገር ከቶ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም” አልሁ።9ነገር ግን ድምፁ ዳግመኛ ከሰማይ፣ “እግዚአብሔር ንጹሕ ነው ያለውን አንተ ርኩስ ብለህ አትጥራው” ብሎ መለሰ።10ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፤ ከዚያም ሁሉም ነገር እንደ ገና ወደ ሰማይ ተወሰደ።11እነሆ፣ ወዲያውኑ እኛ በነበርንበት ቤት ፊት ለፊት ሦስት ሰዎች ቆመው ነበር፤ እነርሱም ከቂሣርያ ወደ እኔ የተላኩ ናቸው።12መንፈስም ከእነርሱ ጋር እንድሄድ፣ ስለ እነርሱም ልዩነት እንዳላደርግ አዘዘኝ። እነዚህ ስድስት ወንድሞች አብረውኝ ሄዱ፤ ወደ ሰውዬውም ቤት ገባን።13እርሱም መልአክ በቤቱ ቆሞ እንዳየና እንዲህ እንዳለውም ነገረን፤ “ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ላክና ሌላው ስሙ ጴጥሮስ የሆነውን፣ ስምዖንን አስመጣ።14አንተና ቤተ ሰቦችህ ሁሉ የምትድኑበትን መልእክት ይነግርሃል።”15ለእነርሱ መናገር እንደ ጀመረና ልክ በመጀመሪያ በእኛ ላይ እንደ ሆነው፣ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወረደ።16“ዮሐንስ በእርግጥ በውሃ አጥምቆ ነበር፤ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ” ብሎ እንደ ተናገረ፣ የጌታን ቃሎች አስታወስሁ።17እኛ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመንን ጊዜ እንደ ሰጠን ያለ ስጦታ እግዚአብሔር ለእነርሱ ከሰጣቸው እንግዲያ፣ እግዚአብሔርን እቃወም ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?”18እነርሱ እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ መልስ አልሰጡም፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን አመስግነው፣ “እግዚአብሔር ለአሕዛብ ለሕይወት የሚሆን ንስሓን ደግሞ ሰጥቷቸዋል” አሉ።19ስለዚህ በእስጢፋኖስ መሞት የተጀመረው ሥቃይ ከኢየሩሳሌም የበተናቸው እነዚህ አማኞች እስከ ፊንቄ፣ ቆጵሮስና አንጾኪያ ድረስ ሄዱ። ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን መልእክት ለአይሁድ ብቻ እንጂ ለሌላ ለማንም አልተናገሩም።20ነገር ግን ከቆጵሮስና ከቀሬና የነበሩ ሰዎች አንዳንዶቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው ለግሪኮች ተናገሩ፤ ጌታ ኢየሱስንም ሰበኩላቸው።21የጌታም እጅ ከእነርሱ ጋር ነበረ፤ በቍጥ ብዛት ያላቸው ሰዎች አምነው ወደ ጌታ ዘወር አሉ።22ስለ እነርሱ ወሬ በኢየሩሳሌም ባለችው ጉባኤ ተሰማ፤ በርናባስንም እስከ አንጾኪያ ላኩት።23እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ስጦታ ባየ ጊዜ፣ ደስ አለው። ከሙሉ ልባቸው ከጌታ ጋር እንዲኖሩ ሁላቸውንም አበረታታቸው።24ምክንያቱም እርሱ መንፈስ ቅዱስና እምነት የሞላበት በጎ ሰው ነበር፤ ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ።25ከዚያም በርናባስ ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ ወጣ።26ባገኘውም ጊዜ፣ ወደ አንጾኪያ አመጣው። እንዲህም ሆነ፣ አንድ ዓመት ሙሉ በቤተ ክርስቲያን አብረው ተሰበሰቡ፣ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ። ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።27በእነዚያ ቀናትም አንዳንድ ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ።28ከእነርሱ አንዱ አጋቦስ የተባለው፣ ተነሥቶ ቆመና በመላው ዓለም ላይ ታላቅ ራብ እንደሚሆን በመንፈስ አመለከተ። ይህም በቀላውዴዎስ ዘመን ሆነ።29ስለ ሆነም፣ ደቀ መዛሙርቱ እያንዳንዳቸው እንደ ዐቅማቸው በይሁዳ ላሉት ወንድሞች እርዳታ ለመላክ ወሰኑ።30ይህንም አደረጉ፤ በበርናባስና በሳውል እጅ ለሽማግሌዎቹ ገንዘብ ላኩ።
1በዚያን ጊዜ ንጉሡ ሄሮድስ ሊያሠቃያቸው ከቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን ያዛቸው።2የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።3ይህ አይሁድን ደስ እንዳሰኛቸው ካየ በኋላ፣ ጴጥሮስንም ያዘው። ይህ የሆነው በቂጣ በዓል ጊዜ ነበር።4ከያዘውም በኋላ ወደ ወኅኒ አገባው፤ እንዲጠብቁትም እያንዳንዳቸው አራት ወታደሮች ያሏቸው ቡድኖችን መደበ፤ ከፋሲካ በኋላ ወደ ሕዝቡ ሊያቀርበው ዐስቦ ነበር።5ጴጥሮስም በወኅኒው ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ጉባኤው ወደ እግዚአብሔር አጥብቆ ይጸልይ ነበር።6ሄሮድስ ሊያወጣው ባሰበበት በዚያ ሌሊት፣ ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለቶች ታስሮ በሩን በሚጠብቁ ሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር።7እነሆም የጌታ መልአክ በድንገት በአጠገቡ ታየ፣ በክፍሉም ብርሃን በራ። መልአኩ የጴጥሮስን ጎን መትቶ ቀሰቀሰውና፣ “ፈጥነህ ተነሥ” አለው። በዚያን ጊዜ ሰንሰለቶቹ ከእጆቹ ወደቁ።8መልአኩ ጴጥሮስን፣ “ልብስህን ልበስ ጫማህንም አድርግ” አለው። ጴጥሮስም እንዲሁ አደረገ። መልአኩ፣ “መደረቢያህን ልበስና ተከተለኝ” አለው።9ጴጥሮስም መልአኩን ተከትሎ ወደ ውጭ ወጣ። መልአኩ ያደረገው ነገር በእውን እንደ ሆነ ጴጥሮስ አላወቀም። ራእይ ያየ መሰለው።10የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ እንዳለፉ፣ ወደ ከተማይቱ ወደሚያወጣው የብረት በር ደረሱ፤ እርሱም ዐውቆ ተከፈተላቸው። እነርሱም ወጥተው በአንድ መንገድ በኩል ወረዱ፤ መልአኩም ወዲያውኑ ተለየው።11ጴጥሮስም ራሱን ሲያውቅ፣ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅ፣ የአይሁድ ሕዝብም ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንዳዳነኝ አሁን ዐወቅሁ” አለ።12ጴጥሮስ ይህን ከተገነዘበ በኋላ፣ ማርቆስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ዮሐንስ እናት ቤት መጣ፤ በዚያ ብዙ ምእመናን ተሰብስበው እየጸለዩ ነበር።13የደጁን በር ባንኳኳ ጊዜ፣ ሮዴ የሚሏት የቤት ሠራተኛ ልትከፍትለት መጣች።14የጴጥሮስን ድምፅ ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ በሩን መክፈት አቃታት፤ ይልቁን ሮጣ ወደ ቤት ገባች፤ ጴጥሮስ ከበሩ ውጭ መቆሙን ተናገረች።15ምእመናኑም፣ “ዐብደሻል” አሏት። እርሷ ግን እንዲሁ ነው ብላ በዐሳብዋ ጸናች። እነርሱም፣ “የእርሱ መልአክ ነው” አሉ።16ጴጥሮስ ግን ማንኳኳቱን ቀጠለ፤ በሩን በከፈቱ ጊዜ፣ ዐይተውት ተደነቁ።17ጴጥሮስ ዝም እንዲሉ በእጁ ምልክት ሰጣቸው፤ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣውም ነገራቸው። “እነዚህን ነገሮች ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሩ” አላቸው። ከዚያም ቤት ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።18በማግስቱም፣ ጴጥሮስን በሚመለከት ስለ ተከሠተው ነገር በወታደሮች መካከል መደናገጥ ሆነ።19ሄሮድስ ጴጥሮስን ፈልጎ ሊያገኘው አልቻለም፤ ጠባቂዎችን መርምሮ እንዲገደሉ አዘዘ። ከዚያም ጴጥሮስ ከይሁዳ ወደ ቂሣርያ ወርዶ በዚያ ተቀመጠ።20ሄሮድስም በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ እጅግ ተቈጥሮ ነበር። የጢሮስና የሲዶና ሰዎች ተሰብስበው ወደ እርሱ ሄዱ። እንዲረዳቸው የንጉሡን ረዳት ብላስጦስን እሺ አሰኙት። ከዚያም ዕርቀ ሰላም እንዲወርድ ጠየቁ፤ ምክንያቱም አገራቸው ከንጉሡ አገር ምግብ ያገኝ ነበር።21በቀጠሮ ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥት ለብሶ በዙፋን ላይ ተቀመጠና ንግግር አደረገላቸው።22ሕዝቡም፣ “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ፣ የሰው አይደለም!” ብለው ጮኹ።23ሄሮድስ ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሰጠ፣ ወዲያውኑ የጌታ መልአክ ቀሠፈው፤ በትል ተበልቶም ሞተ።24የእግዚአብሔር ቃል ግን እያደገና እየሰፋ ሄደ።25በርናባስና ሳውል ለኢየሩሳሌም የነበራቸውን ተልእኮ ከፈጸሙ በኋላ፣ ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውንም ዮሐንስን ይዘው ሄዱ።
1በአንጾኪያም ባለችው ጉባኤ አንዳንድ ነቢያትና መምህራን ነበሩ። እነርሱም በርናባስ፣ ኔጌር የተባለው ስምዖን፣ የቀሬናው ወንድሙ ምናሔ፣ ሳውልም ነበሩ።2ጌታን እያመለኩና እየጾሙ እያሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ “ለጠራኋቸው ሥራ በርናባስንና ሳውልን ለዩልኝ” አለ።3ጉባኤው ከጾመ፣ ከጸለየና እጅ ከጫነም በኋላ አሰናበታቸው።4በርናባስና ሳውልም ለመንፈስ ቅዱስ ታዘዙና ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ሄዱ።5በስልማና ከተማ በነበሩ ጊዜም፣ በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ። ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ሊረዳቸው አብሯቸው ነበር።6በደሴቲቱም ሁሉ እስከ ጳፉ በሄዱ ጊዜ፣ ስሙ በርያሱስ የተባለ፣ አንድ አይሁዳዊ የሐሰት ነቢይና አስማተኛ አገኙ።7ይህ አስማተኛ አስተዋይ ሰው ከነበረው ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አገረ ገዥ ጋር ተባበረ። ይህ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ስለ ፈለገ፣ በርናባስናን ሳውልን ጠራ።8ነገር ግን፣ “አስማተኛው” ኤልማስ ስሙ ሲተረጎም እንዲሁ ነውና ተቃወማቸው፤ አገረ ገዡን ከእምነቱ ለመመለስ ሞከረ።9ደግሞ ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞላ፤ ትኵር ብሎም ተመለከተውና10እንዲህ አለው፤ “አንተ የዲያብሎስ ልጅ፣ ክፋትና ተንኮል ሁሉ የሞላብህ ነህ። የጽድቅ ሁሉ ጠላት ነህ። የቀናችውን የጌታን መንገድ ማጣመምህን አታቆምምን?11አሁንም ተመልከት፤ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ነችና ትታወራለህ። ለጥቂት ጊዜ ፀሐይን አታይም።” ወዲያውኑ በኤልማስ ጨለማና ጭጋግ ወደቀበት፤ እጁንም ይዘው እንዲመሩት ሰዎችን እየጠየቀ ይዘዋወር ጀመር።12አገረ ገዡ የሆነውን ካየ በኋላ፣ ስለ ኢየሱስ በቀረበው ትምህርት ስለ ተደነቀ፣ አመነ።13ጳውሎስና ጓደኞቹም በመርከብ ከጳፉ ተነሥተው በጵንፍልያ ወዳለችው ወደ ጴርጌን መጡ። ዮሐንስ ግን ትቶአቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።14ጳውሎስና ጓደኞቹ ከጴርጌን ተጕዘው የጲስድያ ወደ ሆነችው አንጾኪያ መጡ። በዚያ በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ።15ሕግና ነቢያት ከተነበቡ በኋላ፣ የምኵራብ አለቆች፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እዚህ ላሉት ሕዝብ የሚሆን የሚያበረታታ መልእክት ካላችሁ፣ ተናገሩ” በማለት መልእክት ላኩላቸው።16ጳውሎስም ቆመና በእጁ ምልክት ሰጥቶ እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሰዎችና እናንተ እግዚአብሔርን የምታከብሩ፣ ስሙ።17የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መርጦ በግብፅ ይኖሩ በነበሩበት ጊዜ፣ ሕዝቡን አበዛላቸው፤ በተዘረጋችም ክንድ መርቶ ከዚያ አወጣቸው።18ለአርባ ዓመታት ገደማ በምድረ በዳ ታገሣቸው።19በከነዓን ምድርም ሰባት ሕዝቦችን ካጠፋ በኋላ፣ ምድራቸውን ለሕዝባችን ርስት አድርጎ ሰጠ።20እነዚህ ሁነቶች ሁሉ በአራት መቶ ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ተፈጸሙ። ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር እስከ ነቢዩ ሳሙኤል ድረስ መሳፍንትን ሰጣቸው።21ከዚህ በኋላ፣ ሕዝቡ ንጉሥ ይንገሥልን ብለው ጠየቁ፤ ስለሆነም፣ እግዚአብሔር ከብንያም ነገድ የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን ለአርባ ዓመታት ሰጣቸው።22ከዚያም እግዚአብሔር እርሱን ከንጉሥነት ከሻረው በኋላ፣ ንጉሣቸው እንዲሆን ዳዊትን አስነሣ። እግዚአብሔር፣ ‘እንደ ልቤ የሆነውን የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤ እርሱ እኔ የምፈልገውን ሁሉ ያደርጋል’ በማለት ስለ ዳዊት ተናግሮ ነበር።23ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠ አዳኝ ኢየሱስን ለእስራኤል አመጣ።24ይህ መሆን የጀመረው ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት፣ ዮሐንስ መጀመሪያ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐን ጥምቀት ባወጀ ጊዜ ነው።25ዮሐንስ ሥራውን እንደ ጨረሰ እንዲህ አለ፤ ‘ማን እንደ ሆንሁ ታስባላችሁ? እኔ እርሱ አይደለሁም። ነገር ግን ስሙ፤ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ በኋላ እርሱ ይመጣል።’26ወንድሞች፣ የአብርሃም ዘር ልጆች፣ እግዚአብሔርንም የምታመልኩ ሆይ፣ የዚህ ድነት መልእክት የተላከው ለእኛ ነው።27በኢየሩሳሌም የሚኖሩ፣ አለቆቻቸውም በእርግጥ ኢየሱስን አላወቁትም፤ በየሰንበቱ የሚነበበውን የነቢያትን ድምፅም በእውነት አልተረዱም፤ ስለ ሆነም በኢየሱስ ላይ ሞት በመፍረድ የነቢያትን ቃል ፈጸሙ።28ምንም እንኳ በእርሱ ላይ ለሞት የሚያበቃ ምክንያት ባያገኙም፣ እንዲገድለው ጲላጦስን ለመኑት።29ስለ እርሱ የተጻፈውን ሁሉ በፈጸሙ ጊዜም፣ ከዕንጨት ላይ አውርደው በመቃብር አኖሩት።30እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው።31ከእርሱ ጋር ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም የወጡት ብዙዎች ለአያሌ ቀናት ዐዩት። እነዚህ ሰዎች አሁን ለሕዝቡ የሚናገሩ የእርሱ ምስክሮች ናቸው።32ስለ ሆነም እኛ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠው ተስፋ የሚናገር የምሥራች እናመጣላችኋለን፤33ኢየሱስን ከሙታን በማስነሣት እግዚአብሔር እነዚህን ተስፋዎች ለእኛ ለልጆቻቸው ጠብቆአል። ይህም ደግሞ በሁለተኛው መዝሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፣ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ ተብሎ የተጻፈ ነው።’34ደግሞም ሥጋው እንዳይበሰብስ ከሙታን እንዳስነሣው፦ ‘የተቀደሰውንና እውነተኛውን የዳዊት በረከት እሰጥሃለሁ’ ብሎ ተናግሯል።35በሌላ መዝሙርም፣ ‘ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ የሚለው ስለዚህ ነው።36ዳዊትም በዘመኑ የእግዚአብሔርን ዐሳብ አገልግሎ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ መበስበስንም ዐየ።37እግዚአብሔር ያስነሣው ኢየሱስ ግን መበስበስን አላየም።38ስለ ሆነም ወንድሞች ሆይ፣ በዚህ ሰው በኩል የኃጢአት ይቅርታ እንደ ተሰበከላችሁ ይህ ለእናንተ የታወቀ ይሁን።39በሙሴም ሕግ እንድትጸድቁበት ከማይቻላችሁ ሁሉ፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ ጸድቆአል።40እንግዲያው ነቢያት እንዲህ ሲሉ የተናገሩለት ነገር እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፦41‘እናንተ የምትንቁ፣ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፣ ጥፉም፤ አንድ ስንኳ ቢነግራችሁ ከቶ የማታምኑትን ሥራ፣ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’”42ጳውሎስና በርናባስ እንደ ወጡ፣ በሚቀጥለው ሰንበት ይህንኑ ቃል ደግመው እንዲናገሩ ሕዝቡ ለመኑአቸው።43የምኵራቡ ስብሰባ እንዳበቃም፣ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ከገቡ ከሚያመልኩ ብዙዎቹ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ እንዲጸኑ የመከሩአቸውን ጳውሎስና በርናባስን ተከተሉአቸው።44በሚቀጥለውም ሰንበት፣ ጥቂቶች ሲቀሩ፣ መላው ከተማ የጌታን ቃል ለመስማት አንድ ላይ ተሰበሰበ።45አይሁድ ሕዝቡን ባዩ ጊዜ፣ ቅንዓት ሞላባቸውና ጳውሎስ የተናገረውን ተቃወሙ፣ ሰደቡትም።46ጳውሎስና በርናባስ በድፍረት ተናገሩ፤ እንዲህም አሉ፤ “የእግዚአብሔር ቃል መጀመሪያ ለእናንተ መነገሩ አስፈላጊ ነበር። ቃሉን ከራሳችሁ ስትገፉትና ለዘላለም ሕይወት የተገባችሁ እንዳልሆናችሁ ራሳችሁን ስትቈጥሩ ዐይተናችሁ፣ ወደ አሕዛብ ዘወር የምንል መሆናችንን ተመልከቱ።47ጌታ፣ ‘እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለድነት ትሆን ዘንድ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ’” በማለት አዞናልና።48አሕዛብ ይህን እንደ ሰሙ ደስ አላቸው። የጌታንም ቃል አከበሩ። ለዘላለም ሕይወት የተመረጡትም አመኑ።49የጌታም ቃል በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ።50አይሁድ ግን የሚያመልኩትን ታዋቂ ሴቶችን፣ የከተማይቱን ታላላቅ ወንዶችንም ቀሰቀሱ። በጳውሎስና በበርናባስ ላይም ስደት አስነሥተው ከከተማቸው ዳርቻ ወዲያ አውጥተው ጣሏቸው።51ጳውሎስና በርናባስ ግን የእግራቸውን ትቢያ አራገፉባቸው። ከዚያም ወደ ኢቆንዮን ከተማ ሄዱ።52ደቀ መዛሙርቱም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር።
1በኢቆንዮንም እንዲህ ሆነ ፤ ጳውሎስና በርናባስ ወደ አይሁድ ምኵራብ አብረው ገብተው፣ ከአይሁድና ከግሪክ ብዙ ሰዎች እስኪያምኑ ድረስ ተናገሩ።2ነገር ግን ማመን ያልፈለጉ አይሁድ የአሕዛብን ልብ በመቀስቀስ በወንድሞች ላይ በክፋት አነሣሡአቸው።3ጳውሎስና በርናባስም በጌታ ኀይል በድፍረት እየተናገሩ ረዘም ላለ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ፤ ጌታም ስለ ጸጋው የሚነገረውን መልእክት በማስረጃ ለመደገፍ ጳውሎስና በርናባስ ምልክትና ድንቅ በእጃቸው እንዲደረግ ሰጠ።4የከተማዋ አብዛኛው ሕዝብ ግን፣ አንዳንዱ አይሁድን በመደገፍ፣ ሌላው ደግሞ ከሐዋርያት ጋር በመቆም ተከፋፈሉ።5አሕዛብና አይሁድ ጳውሎስንና በርናባስን እንዲያንገላቷቸውና በድንጋይም እንዲወግሯቸው አለቆቻቸውን በማሳመን ጥረት ማድረጋቸውን6በተረዱ ጊዜ፣ ወደ ሊቃኦንያ ከተሞች፣ ወደ ልስጥራና ወደ ደርቤ፣ እንዲሁም በአካባቢው ወዳለው ስፍራ ሸሹ፤7በዚያም ወንጌልን ይሰብኩ ነበር።8በእግሩ መቆም የማይችልና ሽባ ከእናቱም ማሕፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር።9ይህ ሰው ጳውሎስ ሲናገር ሰማ። ጳውሎስም ዐይኑን ተከትሎ ይህን ሰው ሲመለከት ለመዳን የሚያስችል እምነት እንዳለው አየ።10ስለዚህ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም” አለው፤ ሰውየውም ብድግ ብሎ ተነሣና ወዲያ ወዲህ ይመላለስ ጀመር።11ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ በሊቃኦንኛ ቋንቋ፣ «አማልክት በሰዎች መልክ ወደ እኛ ወርደዋል» አሉ።12ስለዚህም በርናባስን «ድያ» አሉት፤ ጳውሎስም ዋነኛ ተናጋሪ ስለ ነበር፣ «ሄርሜን» አሉት።13ቤተ ጣዖቱ ከከተማው ውጭ የነበረው የድያ ካህን በሬዎችንና የአበባ ጕንጕን ይዞ ወደ ከተማይቱ በር መጣ፤ እርሱና ሕዝቡም ለእነ ጳውሎስ መሥዋዕት ሊያቀርቡላቸው ፈለጉ።14ነገር ግን ሐዋርያቱ፣ ባርናባስና ጳውሎስ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ልብሳቸውን ቀደው በመጮኽ፣ ፈጥነው ወደ ሕዝቡ መካከል ገቡ፤15እንዲህም አሉ፤ «እናንተ ሰዎች፣ ለምን እነዚህን ነገሮች ታደርጋላችሁ? እኛኮ እንደ እናንተው ዐይነት ስሜት ያለን ሰዎች ነን፤ ወደ እናንተም የመጣነው ከእነዚህ ከንቱ ነገሮች፦ ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ፈጠረ፣ ወደ ሕያው እግዚአብሔር እንድትመለሱ የምሥራች ቃል ይዘን ነው።16እግዚአብሔር ባለፉት ዘመናት አሕዛብን ሁሉ በገዛ መንገዳቸው እንዲሄዱ ተዋቸው።17ይሁን እንጂ፣ ራሱን ያለ ምስክር አልተወም፤ ምክንያቱም መልካም ሥራ በመሥራት የሰማይን ዝናብና ፍሬያማ ወቅቶችን ሰጥቶአችኋል፤ ልባችሁንም በምግብና በርካታ ሞልቷል።"18ጳውሎስና በርናባስ እንደዚህ እየተናገሩም እንኳ፣ ሕዝቡ እንዳይሠዉላቸው መከልከሉ ቀላል አልነበረም።19ይልቁንም አንዳንድ አይሁድ ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጥተው ሕዝቡን በማግባባት ጳውሎስን በድንጋይ ወገሩት፤ የሞተ ስለ መሰላቸውም በመሬት ላይ ጎትተው ከከተማው አወጡት።20ይሁን እንጂ፣ ደቀ መዛሙርቱ አብረውት ቆመው ሳሉ፣ ተነሥቶ ወደ ከተማው ገባ። በማግስቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤ ሄደ።21በዚያም ከተማ ወንጌልን ሰብከው ብዙ ደቀ መዛሙርትን ካፈሩ በኋላ፣ ወደ ልስጥራ፣ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ።22የደቀ መዛሙርቱንም ልብ እያበረቱ በእምነት እንዲጸኑ መከሯቸው። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ውስጥ ማለፍ እንዳለብንም ነገሯቸው።23ጳውሎስና በርናባስ በአማኞች ጉባኤ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ከሾሙ በኋላ፣ ላመኑበት ጌታ በጾምና በጸሎት ዐደራ ሰጡአቸው።24ከዚያም በጲስድያ አድርገው ወደ ጵንፍልያ መጡ።25ቃሉን በጴርጌን ከተናገሩ በኋላም ወደ አጣሊያ ወረዱ።26ለፈጸሙት ሥራ ከዚህ ቀደም ለእግዚአብሔር ጸጋ ወደ ተሰጡበት፣ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።27አንጾኪያ ደርሰው፣ ጉባኤውን በአንድነት ከሰበሰቡ በኋላም፣ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሠራውን ሁሉና ለአሕዛብም የእምነትን በር እንዴት እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።28በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ረጅም ጊዜ ቆዩ።
1አንዳንድ ሰዎች ከአይሁድ ወደ አንጾኪያ ወርደው፣ «በሙሴ ሥርዓት መሠረት ካልተገረዛችሁ መዳን አትችሉም» በማለት ወንድሞችን አስተማሯቸው።2ጳውሎስና በርናባስም ከእነርሱ ጋር ጥልና ክርክር በገጠሙ ጊዜ፣ ጳውሎስና በርናባስ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ በኢየሩሳሌም ወደ ነበሩ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች እንዲወጡ ወንድሞች ወሰኑ።3ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ተልከው፣ በፊንቄና በሰማርያ በኩል አድርገው ሲሄዱ፣ የአሕዛብን መለወጥ እያወጁ ዐለፉ፤ ይህም ወንድሞችን ሁሉ እጅግ ደስ አሰኛቸው።4ወደ ኢየሩሳሌም በመጡ ጊዜም፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች በደስታ ተቀበሏቸው፤ እነ ጳውሎስም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሠራውን ሁሉ ነገሯቸው።5ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑ አንዳንድ ሰዎች ግን ተነሥተው፣ «እነርሱን መግረዝና የሙሴንም ሕግ እንዲጠብቁ ማዘዝ ያስፈልጋል» አሉ።6ስለዚህ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ይህን ጉዳይ ለማየት ተሰበሰቡ።7ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ ቆመና እንዲህ አለ፦ «ወንድሞች ሆይ፣ አሕዛብ የወንጌልን ቃል ከአፌ እንዲሰሙና እንዲያምኑ፣ እግዚአብሔር ከጥቂት ጊዜያት በፊት ከእናንተ መካከል እኔን እንደ መረጠኝ ታውቃላችሁ።»8ልብን የሚያውቅ አምላክ፣ ለእኛ እንዳደረገው ሁሉ፣ ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤9በእኛና በእነርሱ መካከልም ልባቸውን በእምነት በማንጻት ልዩነት አላደረገም።10እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ መሽከም ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?11ነገር ግን እኛም በጌታ በኢየሱስ ጸጋ እንደ እነርሱ እንደምንድን እናምናለን።»12በርናባስና ጳውሎስ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት በአሕዛብ መካከል ስለ ሠራው ምልክትና ድንቅ ሲናገሩ፣ ሕዝቡ ሁሉ በጸጥታ አደመጡ።13ንግግራቸውንም በጨረሱ ጊዜ፣ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ «ወንድሞች ሆይ፣ አድምጡኝ።14እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ሕዝብ ከእነርሱ መካከል ይወስዱ ዘንድ፣ አሕዛብን በመጀመሪያ በጸጋ እንደ ረዳ ስምዖን ተናግሮአል።15የነቢያት ቃል ከዚህ ጋር ይስማማል እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤16ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እመለሳለሁ፤ ፍርስራሹንም መልሼ እተክላለሁ፤ እንደገናም ዐድሳለሁ፤17ይኸውም የተረፉት ሰዎችና በስሜ የተጠሩ አሕዛብ፣ እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ ነው።18እነዚህ ጥንታዊ ነገሮች እንዲታወቁ የሚያደርግ ጌታ የሚለው ይህን ነው።19ስለዚህ የእኔ ዐሳብ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን እንዳናስጨንቃቸው ነው፤20ነገር ግን በጣዖታት ከመርከስ፣ ከዝሙት፣ ከታነቀና ከደም እንዲርቁ እንጻፍላቸው።21ሙሴስ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ በከተሞች ሁሉ በየሰንበታቱ በምኵራብ የሚሰብኩና የሚያነቡ ሰዎች አሉትና።»22ስለዚህ በርስያን የተባለው ይሁዳንና ሲላስን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች አድርገው እንዲመርጡና፣ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ እንዲልኳቸው ለሐዋርያትና ለሽማግሌዎች፣ ከቤተ ክርስቲያን ሁሉ ጋር መልካም መስሎ ታያቸው።23እንዲህም ብለው ጻፉ፤ «ለሐዋርያት፣ ለሽማግሌዎችና ወንድሞች፣ እንዲሁም በአንጾኪያ፣ በሶርያና በኪልቅያ ለሚገኙ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን።24እኛ ያላዘዝናቸው አንዳንድ ሰዎች ከእኛ ዘንድ መጥተው ነፍሳችሁን በሚያስጨንቅ ትምህርት እንዳስቸገሩአችሁ ሰምተናል።25ስለዚህ በአንድ ልብ ሆነን ሰዎችን መርጠን ከወዳጆቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ መላክ ለሁላችንም መልካም መስሎ ታየን፤26እነዚህ ሰዎች ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲሉ ለሕይወታቸው እንኳ ያልሣሡ ናቸው።27ይህንኑ እንዲነግሯችሁ ይሁዳንና ሲላስን ወደ እናንተ ልከናል፤28ከእነዚህ አስፈላጊ ነገሮች በላይ ከባድ ሸክም እንዳንጭንባችሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስና ለእኛ መልካም መስሎ ታይቶናልና፤29ይኸውም ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደም፣ ከታነቀ፣ ከዝሙትም እንድትርቁ ነው። ራሳችሁን ከእነዚህ ብትጠብቁ መልካም ይሆንላችኋል፤ ደኅና ሁኑ።»30ከዚያም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው።31ደብዳቤውንም አንብበው ስለ ተጽናኑ በጣም ደስ አላቸው።32ደግሞም ይሁዳና ሲላስ ነቢያት ስለ ነበሩ፣ወንድሞችን በብዙ ቃል በመምከር አበረታቱአቸው።33በዚያም ጥቂት ጊዜ ከተቀመጡ በኋላ፣ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ላኳቸው ሄዱ።34ሲላስ ግን እዚያው መቆየት መልካም መስሎ ታየው።35ጳውሎስና በርናባስ ግን የጌታን ቃል ባስተማሩበትና በሰበኩበት በአንጾኪያ ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋር ተቀመጡ።36ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ጳውሎስ በርናባስን፣ «ተመልሰን የጌታን ቃል በሰበክንበት ከተማ ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ በምን ሁኔታ እንዳሉም እንወቅ» አለ።37በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነሱ ጋር ይዞ ለመሄድ ፈለገ።38ጳውሎስ ግን ማርቆስን ይዞ መሄድ አልፈለገም፤ ምክንያቱም ማርቆስ ከዚህ ቀደም ከእነርሱ ጋር ለሥራ በመሄድ ፈንታ፣ በጵንፍልያ ተለይቶአቸው ቀርቶ ነበር።39በመካከላቸው ከፍተኛ አለምስማማት ስለ ተፈጠረም፣ ተለያዩ፤ በርናባስም ማርቆስን ይዞ ወደ ቆጵሮስ በመርከብ ሄደ።40ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞች ለጌታ ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ፣ ተለይቶአቸው ሄደ።41ከዚያም አብያተ ክርስቲያናትን እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።
1ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ መጣ፤ እነሆም፣ እናቱ አይሁዳዊት አማኝ የሆነች፣ አባቱ ግን ግሪክ የሆነ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር አገኘ።2በልስጥራና በኢቆንዮን የነበሩ ወንድሞችም ስለ እርሱ ጥሩ ምስክርነት ነበራቸው።3ጳውሎስም እርሱን ይዞ መጓዝ ፈለገ፤ በዚያ አካባቢ ስለ ነበሩ አይሁድ ሲልም ጢሞቴዎስን ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ሁሉም ያውቁ ነበርና።4በየከተሞቹ በሚዞሩበት ጊዜ፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዲጠብቁት በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የጻፉትን መመሪያ ሰጡአቸው።5ስለዚህ አብያተ ክርስቲያናቱ በእምነት እየበረቱ፣ ቍጥራቸውም በየዕለቱ እየጨመረ ነበር።6በእስያ አውራጃ ቃሉን እንዳይሰብኩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው፣ ጳውሎስና ባልደረቦቹ በፍርግያና በገላትያ አውራጃዎች አድርገው ዐለፉ።7ወደ ሚስያ አካባቢ በደረሱ ጊዜ፣ ቢታንያ ለመግባት ሞከሩ፤ የኢየሱስ መንፈስ ግን ከለከላቸው።8ስለዚህ ሚስያን ዐልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።9ጳውሎስም አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ፣ “ወደ መቄዶንያ ተሻግረህ ርዳን” እያለ ሲለምነው ሌሊት በራእይ ታየው።10ራእዩንም ካየ በኋላ፣ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ወንጌልን ለእነርሱ እንድንሰብክ እንደ ጠራን ዐሰብን።11ከጢሮአዳ ተነሥተንም ቀጥታ በመርከብ ወደ ሳሞትራቄ ሄድን፤ በማግስቱም ናጱሌ ደረስን፤12ከዚያም የመቄዶንያ ከተማ ወደ ሆነችው ወደ ፊልጵስዩስ ሄድን፤ ከተማዋ የወረዳው ዋና ከተማና የሮም ቅኝ ግዛት ነበረች፤ በዚችም ከተማ ብዙ ቀን ተቀመጥን።13በሰንበት ቀንም፣ በወንዝ አጠገብ በነበረው በር በኩል ወደ ውጭ ወጣን፤ ይህም ስፍራ የጸሎት ቦታ እንደ ሆነ ዐሰብን። በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩ ሴቶች ተናገርን።14ከትያጥሮን ከተማ የመጣችና የሐምራዊ ሐር ሻጭ የነበረች፣ ልድያ የምትባል፣ እግዚአብሔርን የምታመልክ አንድ ሴት ትሰማን ነበር። ጳውሎስ እየተናገረ የነበረውን በሚገባ እንድታደምጥ፣ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።15ከቤተ ሰብዋ ጋር በተጠመቀች ጊዜም፣ “በጌታ ማመኔን ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ ግቡና ተቀመጡ” ብላ ለመነችን፤ አስገደደችንም።16አንድ ቀን ጸሎት ቦታ ስንሄድ የጥንቈላ መንፈስ ያደረባት አንዲት ወጣት አገኘችን፤ በዚህ የጥንቈላ ሥራዋም ለአሳዳሪዎችዋ ከፍተኛ ገቢ ታስገኝ ነበር።17ይህችው ሴት ጳውሎስንና እኛን ከኋላ እየተከተለች፣ “እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፤ የመዳንን መንገድ ይነግሯችኋል” እያለች ትጮኽ ነበር።18ይህንም ብዙ ቀን ደጋገመች። ጳውሎስ ግን በዚህ እጅግ ተበሳጨ፤ ዘወር ብሎም መንፈሱን፣ “ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ” አለው፤ በዚያው ቅጽበትም መንፈሱ ወጣ።19አሳዳሪዎችዋም ተስፋ የሚያደርጉበት የገቢያቸው ምንጭ እንደ ጠፋ ባዩ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው በምድር ላይ እየጎተቱ በገበያ ስፍራ ባለ ሥልጣኖቹ ፊት አቀረቡአቸው።20ወደ ገዢዎችም አምጥተዋቸው፣ “እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ሳሉ በከተማችን ውስጥ ከፍተኛ ሁከት እየፈጠሩ ነው።21እኛ ሮማውያን ለመቀበል ያልተፈቀዱልንን ነገሮች ያስተምራሉ” አሉ።22በዚህ ጊዜ ሕዝቡ በጳውሎስና በሲላስ ላይ በአንድነት ተነሡ፤ ገዦቹም ልብሳቸውን አስወልቀው በዱላ እንዲደበድቡአቸው አዘዙ።23ብዙ ድብደባ ካደረሱባቸው በኋላ፣ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፤ የወኅኒ ጠባቂውም በጥንቃቄ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።24የወኅኒ ጠባቂውም ይህን ትእዛዝ ተቀብሎ፣ ወደ ውስጠኛው እስር ቤት ጣላቸው፤ እግራቸውንም ከግንድ ጋር አጣብቆ አሰራቸው።25እኩለ ሌሊት አካባቢም፣ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ በዝማሬ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎች እስረኞችም አደመጡአቸው።26ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስከሚናጋ ድረስ ታላቅ የምድር መናወጥ ተከሠተ፤ ወዲያውም የወኅኒው በሮች ሁሉ ተከፈቱ፤ የታሳሪዎችም ሁሉ ሰንሰለቶች ተፈቱ።27የወኅኒ ጠባቂውም ከእንቅልፉ ነቅቶ በሮቹ እንደ ተከፈቱ አየ፤ እስረኞቹ ያመለጡ ስለ መሰለውም፣ ሰይፉን መዞ ራሱን ሊገድል ቃጣ።28ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፣ “ራስህን አትጉዳ! እኛ ሁላችን እዚሁ አለን” ብሎ ጮኸ።29የወኅኒ ጠባቂውም መብራት ለምኖ ሮጦ ወደ ውስጥ ገባ፤ በፍርሀት እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ ፊት ተደፋ፤30ወደ ውጭም አስወጥቶአቸው፣ “ጌቶች ሆይ፣ ለመዳን ምን ማድረግ አለብኝ?” አላቸው።31እነርሱም፣ “በጌታ ኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት።32ጳውሎስና ሲላስ ለእርሱና አብረውት በቤት ለነበሩ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ተናገሩ።33የወኅኒ ጠባቂውም ሌሊት፣ በዚያው ሰዓት ወስዶአቸው ቍስላቸውን አጠበላቸው። እርሱና ቤተ ሰዎቹም ሁሉ ወዲያው ተጠመቁ።34ጳውሎስንና ሲላስንም ወደ ቤቱ ይዞአቸው ወጣ፤ ምግብም አቀረበላቸው። ሁሉም በእግዚአብሔርም በማመናችው ከቤተ ሰዎቹ ጋር እጅግ ደስ አለው።35ሲነጋም ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ልቀቋቸው” የሚል ትእዛዝ ለጠባቂዎቹ ላኩ።36የወኅኒ ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ ትእዛዝ ለእኔ ልከዋል፤ ስለዚህ ውጡና በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው።37ጳውሎስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ሮማውያን የሆንነውን እኛን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበውናል፤ ወደ ወኅኒም አስገብተውናል፤ ታዲያ፣ አሁን በድብቅ ያስወጡናል? በፍጹም አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን።”38ጠባቂዎቹም ይህንኑ አባባል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ ገዦቹም ጳውሎስና ሲላስ ሮማውያን እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ።39መጥተውም ተማጸኑአቸው፤ ከወኅኒም ካስወጡአቸው በኋላ፣ ከከተማው እንዲወጡ ጳውሎስንና ሲላስን ለመኑአቸው።40ጳውሎስና ሲላስም ከወኅኒው ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ። ወንድሞችንም ባዩአቸው ጊዜ፣ አበረታቱአቸው፤ ከዚያም ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ።
1አንፊጶልና አጶሎንያ በተባሉ ከተሞች በኩል ካለፉ በኋላም፣ ተሰሎንቄ ወደ ተባለች ከተማ መጡ፤ በዚያም ከተማ የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።2ጳውሎስም እንደ ልማዱ፣ ወደ አይሁድ ሄዶ፣ ለሦስት ሰንበታት ያህል ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር።3ቅዱሳት መጻሕፍትንም እየገለጠ፣ ክርስቶስ መከራን መቀበልና ከሙታን መነሣት እንደ ነበረበት እያስረዳም፣ «ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው» ይላቸው ነበር።4ከአይሁድም አንዳንዶቹ መልእክቱን ተቀብለው ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ፤ በተጨማሪም ለእግዚአብሔር ያደሩ ግሪኮች፣ የከበሩ ብዙ ሴቶችና ከፍተኛ ቍጥር ያላቸው ሰዎች ከእነርሱ ጋር ሆኑ።5ሌሎች ያላመኑ አይሁድ ግን፣ በቅንዓት በመነሣሣትና ክፉ ሰዎችን ከጎዳና ላይ በማሰባሰብ ሕዝብን አከማችተው ከተማዋን አወኩአት። የኢያሶንን ቤት በዐመፅ በመክበብም፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ለሕዝቡ ለማስረከብ ፈለጉ።6ሊያገኙአቸው ባልቻሉ ጊዜም፣ ኢያሶንንና ሌሎች ወንድሞችን ይዘው መሬት ለመሬት እየጎተቱ ወደ ከተማዋ ባለ ሥልጣናት ፊት አወጡአቸው፤ እንዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ «እነዚህ ዓለምን የገለባበጡ ሰዎች ወደዚህ ደግሞ መጥተዋል፤7ኢያሶን በቤቱ የተቀበላቸው እነዚህ ሰዎች የቄሣርን ሕግ የሚቃወሙ ናቸው፤ ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ ነው።»8ሕዝቡና የከተማው ሹሞች እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ፣ ታወኩ።9ከኢያሶንና ከሌሎቹም የዋስትና ገንዘብ ተቀብለው ለቀቁአቸው።10ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በዚያው ሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው። እነርሱም እዚያ በደረሱ ጊዜ፣ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ።11እዚህ የሚኖሩ ሰዎች በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ሰፊ አስተሳሰብ ስለ ነበራቸው፣ ነገሩ እንዲህ ይሆንን በማለት ቅዱሳት መጻሕፍትን በየዕለቱ እየመረመሩ፣ ልባቸው ቃሉን ለመቀበል ዝግጁ ነበር።12ስለዚህ ከእነርሱ ብዙዎች አመኑ፤ በተጨማሪ አንዳንድ ተደማጭነት ያላቸው የግሪክ ሴቶችና ሌሎች ወንዶችም አመኑ።13በተሰሎንቄ የነበሩ አይሁድም ጳውሎስ በቤርያም ደግሞ ቃሉን እንደ ሰበከ ባወቁ ጊዜ፣ ወደዚያ ሄደው ሕዝቡን በማነሣሣት አወኩ።14ወንድሞችም ወዲያው ጳውሎስን ወደ ባሕሩ አካባቢ እንዲሄድ አደረጉ ፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው ቆዩ።15ጳውሎስን ይሸኙ የነበሩት ሰዎችም እስከ አቴና ድረስ ወሰዱት። ከዚያም ሲነሡ፣ ሲላስና ጢሞቴዎስ በተቻለው ፍጥነት ወደ እነሱ እንዲመጡ የሚል መልእክት ከጳውሎስ ተቀብለው ሄዱ።16ጳውሎስ አቴና ተቀምጦ እየጠበቃቸው ሳለ፣ ከተማዋ በጣዖት የተሞላች መሆንዋን ሲያይ፣ መንፈሱ በውስጡ ተበሳጨበት።17ስለዚህም ነገር በምኵራብ ከሚያገኛቸው አይሁድ፣ እግዚዘብሔርንም ከሚያመልኩ ሌሎች ሰዎችና ዘወትር በገበያ ቦታ ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይነጋገር ነበር።18ከኤፌቆስና ከኢስጦኢኮች ወገን የሆኑ አንዳንድ ፈላስፎችም ደግሞ ጳውሎስን አገኙት። ከእነርሱም አንዳንዶች፣ «ይህ ለፍላፊ ምን እያለ ነው?» አሉ። ሌሎቹም፣ ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤው ሲሰብክ ስለ ሰሙት፣ «ስለ እንግዳ አማልክት የሚሰብክ ይመስላል» አሉ።19ከዚያም፣ «አንተ የምትናገረውን ይህን ዐዲስ ትምህርት ማወቅ እንችላለን ወይ?20ምክንያቱም እየሰማናቸው ያሉ ነገሮች እንግዳ ናቸው። ስለዚህ፣ የእነዚህን ነገሮች ትርጕም ማወቅ እንሻለን» አሉት።21አቴናውያንና ሌሎች በዚያ የሚኖሩ እንግዶች ሁሉ ጊዜአቸውን የሚያሳልፉት በሌላ ጉዳይ ሳይሆን፣ ስለ ዐዳዲስ ነገሮች በማውራት ወይም በመስማት ነበር።22ስለዚህ ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፤ «እናንተ የአቴና ሰዎች ሆይ፣ በየትኛውም መልክ እጅግ ሃይማኖተኞች እንደ ሆናችሁ እመለከታለሁ።23ምክንያቱም ወዲያ ወዲህ እየተመላለስሁ የምታመልኳቸውን ስመለከት፣ ላልታወቀ አምላክ የሚል ጽሑፍ የተጻፈበት አንድ መሠዊያ አይቻለሁ። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን አምላክ እኔ እነግራችኋለሁ።24ዓለምንና በውስጧ የሚገኙትን ሁሉ የፈጠረ አምላክ፣ የሰማይና የምድር ጌታ በመሆኑ፣ በእጅ በተሠራ መቅደስ ውስጥ አይኖርም።25ለሰዎች ሕይወት፣ እስትንፋስንና ሁሉንም ነገር የሚሰጠው እርሱ ራሱ ስለ ሆነ፣ እግዚአብሔር አንዳች እንደሚያስፈልገው በሰው እጅ አይገለገልም።26በምድር ገጽ ላይ የሚኖሩትንም ሕዝቦች ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ የሚኖሩባቸውንም ስፍራዎች ወሰን፣ ወቅቶችንም የወሰነላቸው እርሱ ነው።27ስለዚህ እግዚአብሔርን ቢፈልጉ ሊያገኙት ይችላሉ፤ እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እርሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።28ምክንያቱም የምንኖረው፣ የምንንቀሳቀሰውና በሕይወት የቆምነው በእርሱ ነው፤ ከእናንተ ባለ ቅኔዎች አንዱ እንዳለውም፣ 'እኛ ልጆቹ ነን።'29እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን፣ መለኮትን በሰው ጥበብና እንደ ተቀረጸ ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ አድርገን ማሰብ የለብንም።30ስለዚህ እግዚአብሔር የአለማወቅ ጊዜያትን አሳልፎ፣ አሁን ግን በየትኛውም ስፍራ ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ ያዛል።31ምክንያቱም በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ የሚፈርድበትን ቀን አዘጋጅቶአል። እግዚአብሔር ይህን ሰው ከሙታን በማስነሣቱ ለሁሉ ሰው ማረጋገጫ ሰጥቶአል።"32የአቴና ሰዎች ስለ ሙታን ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ፣ አንዳንዶቹ በጳውሎስ ላይ አፌዙ፤ሌሎች ግን፣ «ስለዚህ ጉዳይ ዳግመኛ እንሰማሃለን» አሉት።33ከዚህ በኋላ፣ ጳውሎስ ተለይቶአቸው ሄደ፤34አንዳንድ ወንዶች ግን ከእርሱ ጋር ተባብረው አመኑ፤ በእነዚህም ውስጥ የአርዮስፋጎስ አመራር አባል ዲዮናስዮስ፣ ደማሪስ የተባለች ሴትና ሌሎችም ይገኛሉ።
1ከዚህ በኋላ፣ ጳውሎስ ከአቴና ወደ ቆሮንቶስ ሄደ።2እዚያም ከጳንጦስ ወገን የሆነ አቂላ የሚባል አይሁዳዊ አገኘ። እርሱም አይሁድ ሁሉ ከሮም እንዲወጡ ቀላውዴዎብ ባዘዘው መሠረት፣ ከሚስቱ ከጵርቅላ ጋር በቅርብ ከኢጣሊያ የመጣ ሰው ነበር። ጳውሎስም ከእነርሱ ጋር ተቀራረበ።3ሥራቸው አንድ ዓይነት ስለ ሆነም፣ በእነርሱ ዘንድ እየኖረ ዐብሮአቸው ይሠራ ነበር። ሥራቸውም ድንኳን መስፋት ነበር።4በየሰንበቱም በምኵራብ ውስጥ በመገኘት እየተከራከረ፣ አይሁድንም ግሪኮችንም ያሳምን ነበር።5ሲላስና ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ እርሱ ወዳለበት በወረዱ ጊዜ ግን፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለአይሁድ እንዲመሰክር መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስን ገፋፋው።6አይሁድ በተቃወሙትና በተሳደቡ ጊዜ፣ ጳውሎስ ልብሱን እያራገፈባቸው፣ «ደማችሁ በራሳችሁ ላይ ይሁን፤ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ከአሁን ጀምሮ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ» አላቸው።7ከዚያም ወጥቶ ቲቶ ኢዮስጦስ ወደሚባል፣ እግዚአብሔርን ወደሚያመልክ ሰው ቤት ሄደ። ቤቱም በምኵራብ አጠገብ ነበር።8ቀርስጶስ የተባለም የምኵራብ አለቃ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር በጌታ አመነ። ጳውሎስ ሲናገር ከሰሙት ከቆሮንቶስ ሰዎች መካከልም ብዙዎቹ አምነው ተጠመቁ።9ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን እንዲህ አለው፤ "አትፍራ ተናገር፣ ዝምም አትበል።10ምክንያቱም እኔ ከአንተ ጋር አለሁ፤ ሊጎዳህ የሚነሣብህ ማንም የለም፤ እንዲያውም በዚህ ከተማ ብዙ ሰዎች አሉኝ።"11ጳውሎስም በመካከላቸው የእግዚአብሔርን ቃል እያስተማረ አንድ ዓመት ከስድስት ወር እዚያ ተቀመጠ።12ነገር ግን ጋልዮስ የአካይያ አገረ ገዢ በሆነ ጊዜ፣ አይሁድ በጳውሎስ ላይ በአንድነት ተነሡ፤ ይዘውም ፍርድ ፊት አቀረቡት።13ከዚያም፣ “ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዲያመልክ ይህ ሰው ከሕግ ውጪ እየቀሰቀሰ ነው” አሉ።14ጳውሎስ ሊናገር ሲልም፣ ጋልዮስ አይሁድን፣ “አይሁድ ሆይ፣ ጉዳዩ በርግጥ የበደል ወይም የወንጀል ቢሆን ኖሮ፣ ልታገሣችሁ በተገባኝ ነበር።15ነገር ግን ክርክሩ ስለ ቃላትና ስለ ስሞች፣ ደግሞም ስለ ገዛ ሕጋችሁ ስለ ሆነ፣ እናንተው ራሳችሁ ተነጋገሩበት። እኔ ስለ እንደዚህ ዐይነት ጉዳይ ፈራጅ መሆን አልፈልግም” አለ።16ከዚያም ጋልዮስም ከችሎቱ አስወጣቸው።17እነርሱ ሁሉ ግን የምኵራቡን አለቃ ሶስቴንስን በጉልበት ይዘው በፍርድ ወንበሩ ፊት ደበደቡት። ይሁን እንጂ፣ ይህ ድርጊታቸው ለጋልዮስ ደንታም አልሰጠውም።18ጳውሎስም ብዙ ቀናት ከተቀመጠ በኋላ፣ ወንድሞችን ተሰናብቶ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋር በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። ስእለት ስለ ነበረበትም፣ ከወደቡ ከክንክራኦስ ከመነሣቱ በፊት ራሱን ተላጨ።19ኤፌሶን በደረሱ ጊዜ፣ ጳውሎስ ጵርስቅላንና አቂላን ትቶአቸው ወደ ምኵራብ ሄዶ ከአይሁድ ጋር ይነጋገር ነበር።20እነርሱም ረዘም ላለ ጊዜ ዐብሮአቸው እንዲቆይ ሲለምኑት፣ ጳውሎስ እንቢ አለ።21ከዚያም፣ “እግዚአብሔር ቢፈቅድ እንደ ገና ተመልሼ እመጣለሁ” ብሎ ተሰናበታቸው። ከኤፌሶንም ተነሥቶ በመርከብ ሄደ።22ጳውሎስ ቂሣርያ በደረሰ ጊዜ፣ በኢየሩሳሌም ወደ ነበረችው ቤተ ክርስቲያን ወጥቶ ሰላምታ አቀረበላቸውና ወደ አንጾኪያ ወረደ።23በዚያም ጥቂት ጊዜ ከተቀመጠ በኋላ፣ ጳውሎስ ተለያቸው፤ በገላትያና በፍርግያ አካባቢ በማለፍም ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ አበረታታ።24ትውልዱ እስክንድርያዊ የሆነ፣ አጵሎስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እርሱም የንግግር ችሎታና በቂ የቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀት ያለው ሰው ነበር።25አጵሎስ የጌታን ትምህርት በሚገባ የተማረ በመሆኑ፣ በመንፈሱ ተነቃቅቶ ስለ ኢየሱስ በትክክል ይናገርና ያስተምር ነበር፤ የሚያውቀው ግን ስለ ዮሐንስ ጥምቀት ብቻ ነበር።26አጵሎስ ምኵራብ ውስጥ በድፍረት መናገር ጀመረ። ነገር ግን ጵርስቅላና አቂላ በሰሙት ጊዜ፣ ወደ እርሱ ቀርበው የእግዚአብሔር መንገድ ይበልጥ በትክክል አብራሩለት።27እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈለገ ጊዜ፣ ወንድሞች አበረታቱት፤ በአካይያ የነበሩ ደቀ መዛሙርት እንዲቀበሉትም ጻፉላቸው። እዚያ በደረሰ ጊዜም፣ በጸጋ ያመኑትን እጅግ ረዳቸው።28አጵሎስ ከቅዱሳት መጻሕፍት እያስደገፈ፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ በማሳየት በኀይሉና በችሎታው አይሁድን ተከራክሮ ረታቸው።
1አጵሎስ በቆሮንቶስ በነበረ ጊዜ፣ ጳውሎስ በላይኛው አገር አድርጎ ወደ ኤፌሶን ከተማ መጣ፤ በዚያም አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን አገኘ።2ጳውሎስም፣ “ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችኋል?” አላቸው። እነርሱም፣ “አልተቀበልንም፤ እንዲያውም መንፈስ ቅዱስ መኖሩን አልሰማንም” አሉት።3ጳውሎስም፣ “ታዲያ፣ በምን ተጠመቃችሁ?” አላቸው። እነርሱም፣ “የተጠመቅነው በዮሐንስ ጥምቀት ነው” አሉት።4ጳውሎስም መልሶ፣ “ዮሐንስ ያጠመቀው በንስሓ ጥምቀት ነው። ሰዎች ከእርሱ በኋላ በሚመጣው፣ በኢየሱስ ማመን እንደሚገባቸውም ነገራቸው” አለ።5ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ፣ በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ።6ጳውሎስም እጆቹን በሰዎቹ ላይ በጫነ ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤ እነርሱም በልዩ ቋንቋ መናገርና መተንበይ ጀመሩ።7ቍጥራቸውም ዐሥራ ሁለት ያህል ነበረ።8ጳውሎስ ከዚህ በኋላ ወደ ምኵራብ እየገባ ሦስት ወር ያህል በድፍረት ይናገር ነበር፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየገለጠ ሰዎችን ያስረዳ ነበር።9አንዳንድ አይሁድ ግን ልባቸውን አደንድነው በመቃወም፣ በሕዝቡ ፊት የክርስቶስን መንገድ ተሳደቡ፤ ስለዚህ ጳውሎስ ትቶአቸው ሄደ፤ ያመኑትንም ከእነርሱ አራቀ። ጢራኖስ በሚባል የትምህርት አዳራሽም በየዕለቱ ንግግር ያደርግ ጀመር።10ይህም፣ በእስያ የሚኖሩ አይሁድና ግሪኮችም ሁሉ የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ፣ ሁለት ዓመት ቀጠለ።11እግዚአብሔር በጳውሎስ እጅ ታላላቅ ተአምራትን ያደርግ ነበር፤12ስለዚህ የጳውሎስ አካል የነካው ጨርቅ ወይም መሐረብ ሲወሰድ፣ የታመሙት ይፈወሱ፣ አጋንንትም ከሰዎች ይወጡ ነበር።13አጋንንት እናስወጣለን እያሉ ከቦታ ቦታ የሚዞሩ አይሁድ ነበሩ፤ እነርሱም የኢየሱስን ስም ለገዛ ጥቅማቸው ለማዋል፣ በክፉ መናፍስት ላይ እየጠሩ፣ “እንድትወጡ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናዛችኋለን” ይሉ ነበር።14ይህን ያደረጉትም የአይሁድ የካህናት አለቃ የነበረው የአስቄዋ ሰባት ወንድ ልጆች ነበሩ።15ክፉው መንፈስም፣ “ኢየሱስን ዐውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም ዐውቃለሁ፤ ለመሆኑ እናንተ እነማን ናችሁ?” ብለው መለሱላቸው።16ክፉ መንፈስ ያለበትም ሰው ዘሎ ያዛቸው፤ አሸንፏቸውም ደበደባቸው። ከዚያም ቤት ቈስለው ዕራቁታቸውን ሸሹ።17ይህም በኤፌሶን ይኖሩ በነበሩ አይሁድና ግሪኮችም ዘንድ ሁሉ ታወቀ። እነርሱም ሁሉ በፍርሀት ተዋጡ፤ የጌታ ኢየሱስም ስም ተከበረ።18ደግሞም ካመኑት ብዙዎቹ መጥተው ቀደም ሲል ያደረጉትን ክፉ ነገር ሳይሸሽጉ ይናዘዙ ነበር።19አስማተኞችም የጥንቈላ መጻሕፍታቸውን ሰብስበው እያመጡ በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉ፤ ዋጋቸውም ሲተመን ሃምሳ ሺህ ብር ሆነ።20በዚህም መሠረት የጌታ ቃል በስፋትና በኀይል ተሠራጨ።21ጳውሎስ በኤፌሶን የነበረውን አገልግሎቱን ከፈጸመ በኋላ፣ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈስ ቅዱስ ሆኖ ወሰነ፤ ደግሞም፣ “እዚያ ከደረስሁ በኋላም፣ ሮሜን ማየት ይገባኛል” አለ።22ሲረዱት ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን፣ ጢሞቴዎስንና ኤርስጦንን ወደ መቄዶንያ ላካቸው። እርሱ ራሱ ግን ጥቂት ጊዜ በእስያ ቆየ።23በዚህ ጊዜ የጌታን መንገድ በተመለከተ በኤፌሶን ትልቅ ሁከት ተነሣ።24ድሜጥሮስ የሚባል አንድ ብር ሠሪም የዲያናን ምስል ከብር እያበጀ ለአንጥረኞች ትልቅ ገቢ ያስገኝላቸው ነበር።25ስለዚህ በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩትን ብዙ ሠራተኞች አንድ ላይ ሰብስቦ፣ “ሰዎች ሆይ፤ በዚህ ሙያችን ብዙ ገንዘብ እንደምናገኝ ታውቃላችሁ።26ይህ ጳውሎስ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን፣ ከብዙ በጥቂቱ በእስያ ሁሉ አብዛኛውን ሕዝብ በቃላት እያባበለ ከእኛ ማራቁን እያያችሁና እየሰማችሁ ነው። በእጅ የሚሠሩ አማልክት የሉም እያላቸው ነው።27የእኛ ሞያዊ ጥበብ አላስፈላጊ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ የታላቅዋ አምላክ የዲያና ቤተ መቅደስም እንደ ከንቱ ነገር የመቍጠር አደጋ ያሠጋል፤ እስያ ሁሉና ዓለሙ የሚያመልካት ይህች አምላክም ዝናዋን ታጣለች።”28ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ በቍጣ ተሞልተው፣ “የኤፌሶንዋ ዲያና ታላቅ ናት” እያሉ ጮኹ።29ከተማው ሁሉ ድብልቅልቁ ወጣ፤ ሕዝቡም በአንድ ላይ ገንፍለው ወደ ቲያትር ማሳያው ቦታ ገቡ። ከመቄዶንያ የመጡትንም የጳውሎስን የጕዞ ባልደረቦች፣ ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ያዙአቸው።30ጳውሎስ ወደ ሕዝቡ ሊደባለቅ ፈልጎ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ከለከሉት።31ደግሞም፣ የጳውሎስ ወዳጆች የነበሩ አንዳንድ የአካባቢ ሹሞች ጳውሎስ ወደ ቲያትር ማሳያ ቦታ እንዳይገባ መልእክት ላኩበት።32ሕዝቡ ሁሉ ግራ ተጋብቶ ነበርና፣ አንዳንዶቹ ስለ አንድ ነገር ሲጮኹ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ስለ ሌላ ነገር ይጮኹ ነበር። አብዛኛዎቹ ደግሞ ለምን ተሰብስበው እንደ ወጡ እንኳ አያውቁም ነበር።33አይሁድም እስክንድሮስን ገፋፍተው ወደ ሕዝቡ ፊት አወጡት። እስክንድሮስ ለሕዝቡ በእጅ ምልክት እያሳየ ሊያስረዳቸው ሞከረ።34ሕዝቡም አይሁዳዊ መሆኑን በተረዱ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ፣ “የኤፌሶንዋ ዲያና ታላቅ ናት” እያሉ ለሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ።35የከተማዋ ጸሓፊ ሕዝቡን ዝም ካሰኘ በኋላ፣ እንዲህ አለ፤ “እናንተ የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፣ የኤፌሶን ከተማ የታላቅዋ ዲያና ቤት መቅደስና ከሰማይ የወረደው ምስል ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ የትኛው ሰው ነው?36እንግዲህ ይህ የማይካድ ነገር መሆኑ ከታያችሁ፣ ጸጥ ልትሉ፣ አንዳች ነገርም በችኰላ ልታደርጉ አይገባም፤37ምክንያቱም አብያተ መቅደስን ያልሰረቁ፣ አማልክታችንንም ያልሰደቡ እነዚህን ሰዎች ወደዚህ ፍርድ ቤት አምጥታችኋል።38ስለዚህ ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉ አንጥረኞች የሚከሱት ሰው ካለ፣ ፍርድ ቤቱ ክፍት ነው፤ ዳኞችም አሉ፤ እዚያ እርስ በርስ ይካሰሱ።39ስለ ሌላ ጉዳይ የምትፈልጉት ነገር ካለ ግን፣ ችግሩ በመደበኛው ጉባኤ ይፈታል፤40ምክንያቱም በዛሬው ቀን የነበረው ዐመፅ ሳያስጠይቀን አይቀርም። የነበረው ግርግር መንሥኢ የለውም፤ እንዲህ ነው ብለን ልንገልጸውም አንችልም።”41ጸሓፊው ይህን ተናግሮ ጉባኤውን አሰናበተው።
1ሁከቱ ካበቃ በኋላ፣ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስጠርቶ አበረታታቸው። ከዚያም ተሰናበታቸውና ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣ።2በእነዚያም አካባቢዎች እያለፈ ያመኑትን እጅግ ካበረታታ በኋላ፣ ወደ ግሪክ ገባ።3በዚያም ሦስት ወር ከቈየ በኋላ፣ ወደ ሶርያ በመርከብ ለመሄድ እያሰበ ሳለ፣ አይሁድ አሤሩበት፤ ስለዚህ በመቄዶንያ አድርጎ ለመመለስ ወሰነ።4እስከ እስያ የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ፣ ከተሰሎንቄ የመጡት አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤኑ ጋይዮስ፣ ጢሞቴዎስ፣ እንዲሁም ከእስያ የመጡት ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ነበሩ።5እነዚህ ሰዎች ግን ቀድመውን በጢሮአዳ ጠበቁን።6እኛም ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ፣ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በዐምስት ቀን ውስጥ ጢሮአዳ ደረስንባቸው፤ እዚያም ሰባት ቀን ተቀመጥን።7በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቊረስ በተሰበሰብን ጊዜ፣ ጳውሎስ ለምእመናኑ ንግግር አደረገ። በሚቀጥሉት ቀናት ለመሄድ ዐቅዶ ስለ ነበረ፣ እስከ እኩለ ሌሊት መናገሩን ቀጠለ።8በተሰበሰብንበትም ሰገነት ላይ ብዙ መብራቶች ነበሩ።9አውጤኪስ የሚባል ወጣትም በመስኮት ተቀምጦ ሳለ፣ እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ወሰደው። ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ፣ ይህ ወጣት ገና ተኝቶ እንዳለ ከሦስተኛው ፎቅ ወደቀ፤ ሲያነሡትም ሞቶ ነበር።10ጳውሎስ ግን ወርዶ በላዩ ተዘረጋበት፣ ዐቀፈውም። ከዚያም፣ “በሕይወት ስላለ ከዚህ በኋላ አትታወኩ” አለ።11እንደ ገናም በደረጃ ወደ ላይ ወጣ፤ እንጀራ ቈርሶም በላ። እስኪነጋ ድረስም ለረዥም ጊዜ ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ፣ ተለይቶአቸው ሄደ።12ወጣቱንም በሕይወት እያለ አመጡት፤ በዚህም እጅግ ተጽናኑ።13እኛም ራሳችን ጳውሎስን በመርከብ ለማሳፈር ወዳሰብንበት ወደ አሶን ቀድመን በመርከብ ሄድን። እርሱም ያሰበው ይህንኑ ነበር፤ በመርከብ ለመሄድ ዐቅዶ ነበርና።14በአሶን ሲያገኘንም፣ ወዳለንበት መርከብ አስገብተነው ወደ ሚሊጢን ጕዞአችንን ቀጠልን።15ከዚያም በመርከብ ተነሣንና በማግስቱ ኪዩ በምትባለዋ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ደሴት ጎራ ብለን፣ በማግስቱ ወደ ሚሊጢን ከተማ ገባን፤16ጳውሎስም በእስያ ውስጥ ጊዜ ሳያባክን፣ ኤፌሶንን ዐልፎ በመርከብ ለመሄድ ወስኖ ነበርና፤ ምክንያቱም በተቻለው መጠን ሁሉ ለበዓለ ኀምሳ በኢየሩሳሌም ለመገኘት ቸኵሎ ነበር።17ሰዎችንም ከሚሊጢን ወደ ኤፌሶን ልኮ፣ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ወደ ራሱ አስጠራቸው።18ወደ እርሱ በመጡም ጊዜ፣ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ፣ ዘወትር እንዴት ከእናንተ ጋር እንደ ኖርሁ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።19ራሴን እጅግ ዝቅ በማድረግና በእንባ፣ ከአይሁድ ሤራ የተነሣ በገጠመኝ መከራም ውስጥ ጌታን ማገልገል አላቋረጥሁም።20ጠቃሚ የሆነውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽና በአደባባይም ሆነ ቤት ለቤት በመዞር እናንተን ከማስተማር ወደ ኋላ እንዳላልሁ ታውቃላችሁ።21በንስሓ ወደ እግዚአብሔር ስለ መመለስና በጌታችን በኢየሱስ ስለ ማመን አይሁድንና ግሪኮችን እንዴት ሳስጠነቅቃቸው እንደ ነበር ታውቃላችሁ።22እንግዲህ ተመልከቱ፤ እዚያ ምን እንደሚጠብቀኝ ሳላውቅ፣ በመንፈስ ቅዱስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፤23ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ እስራትና መከራ እንደሚቆየኝ በየከተማው ይመሰክርልኛል።24ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልሁትን የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎት እስከምጨርስ ድረስ፣ እንደ ውድ ነገር በመቍጠር፣ ለሕይወቴ አልሳሳላትም።25እንግዲህ ተመልከቱ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁትን የእኔን ፊት ሁላችሁ ዳግመኛ እንደማታዩ ዐውቃለሁ።26ስለዚህ ከማንም ሰው ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ ዛሬ እመሰክርላችኋለሁ፤27ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ ወደ ኋላ ብዬ አላውቅም።28ስለዚህ በገዛ ራሱ ደም የገዛትን የጌታን ጉባኤ ትጠብቁ ዘንድ፣ ስለ ራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ጠባቂ አድርጎ እናንተን ለሾመበት፣ ለመንጋው ሁሉ ተጠንቀቁ።29እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ለመንጋው ርኅራኄ የሌላቸው አጥፊ ተኵላዎች በመካከላችሁ እንደሚገቡ ዐውቃለሁ።30ከእናንተ መካከልም እንኳ ደቀ መዛሙርትን የራሳቸው ተከታዮች ለማድረግ አንዳንድ ሰዎች መጥተው ጠማማ ነገሮችን እንደሚናገሩ ዐውቃለሁ።31ስለዚህ ተጠንቀቁ። ሳላቋርጥ ቀንና ሌሊት፣ ሁላችሁንም ሦስት ዓመት በእንባ እንዳገለገልኋችሁም አስታውሱ።32አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያንጻችሁ፣ እንዲሁም በቅዱሳን ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ።33የማንንም ብር፣ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም።34እነዚህ እጆቼ የእኔንም፣ ከእኔ ጋር የነበሩትንም ሰዎች ፍላጎት ሲያሟሉ እንደ ነበር እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።35ደካሞችን በሥራ እንዴት እንደምትረዱ፣ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው” የሚለውንም የጌታ ኢየሱስን ቃል እንዴት እንደምታስታውሱ በሁሉም ረገድ አርኣያ ሆንኋችሁ።36ጳውሎስ ይህን ሁሉ ካለ በኋላ፣ ተንበርክኮ ከሁሉም ጋር ጸለየ።37ሁሉም እጅግ በማልቀስ ዐንገቱ ላይ ተጠምጥመው ሳሙት።38ፊቱን ዳግመኛ እንደማያዩ መናገሩም ከሁሉ በላይ አሳዘናቸው። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።
1ከእነርሱም ተለይተን የባሕር ላይ ጕዞአችንን በቀጠልን ጊዜ፣ ቀጥታ ወደ ቆስ ከተማ አመራን፤ በማግስቱም ወደ ሩድ ከተማ፣ ከዚያም ወደ ጳጥራ ከተማ ሄድን።2ወደ ፊንቄ የሚሻገር መርከብ ባገኘን ጊዜም ተሳፍረን መጓዝ ጀመርን።3የቆጵሮስን ደሴት ከሩቅ ባየን ጊዜ፣ ወደ ግራ ትተናት በባሕር ወደ ሶርያ ተጓዝን፤ መርከብዋ ጭነቷን የምታራግፈው በዚያ ስለ ነበር፣ ጢሮስ ወደብ ላይ ደረስን።4ደቀ መዛሙርቱን ካገኘን በኋላም፣ በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን። እነዚህም ደቀ መዛሙርት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይገባ በመንፈስ ቅዱስ ተናገሩት።5የምንቈይበት ጊዜ ሲገባደድ፣ ተነሥተን ጕዞአችንን ቀጠልን። ሁሉም፣ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ከከተማ እስክንወጣ ድረስ በመንገዳችን ሸኙን። ከዚያም እወደቡ ላይ ተንበርክከን ጸለይን፤ እርስ በርስም ተሰነባበትን።6እኛ በመርከቡ ተሳፈርን፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።7ከጢሮስ የተነሣንበትን ጕዞ በጨረስን ጊዜ፣ አካ ደረስን። በዚያም ወንድሞችን አገኘንና አንድ ቀን ከእነርሱ ጋር ቈየን።8በሚቀጥለው ቀን ከዚያ ተነሥተን ወደ ቂሣርያ ሄድን። ከዚያም ከሰባቱ አንዱ ወደ ሆነው፣ ወደ ወንጌል ሰባኪው ወደ ፊልጶስ ቤት ገብተን ከእርሱ ጋር ሰነበትን።9ይህም ሰው ትንቢት የሚናገሩ አራት ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት።10የተወሰኑ ቀናት እንደ ተቀመጥንም፣ አጋቦስ የሚሉት ነቢይ ከይሁዳ ወደ ነበርንበት ወረደ።11ወደ እኛም መጥቶ፣ የጳውሎስን መታጠቂያ ወሰደ፤ የገዛ ራሱን እጆችና እግሮችም አስሮ፣ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ ‘በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድ የዚህን መታጠቂያ ባለቤት እንደዚህ አድርገው ያስሩታል፤ አሳልፈውም ለአሕዛብ እጅ ይሰጡታል’” አለ።12እነዚህን ነገሮች በሰማን ጊዜ፣ እኛና በዚያ ስፍራ የሚኖሩ ሰዎችም ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ ለመንነው።13ጳውሎስም፣ “እያለቀሳችሁ ልቤን የምትሰብሩት ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔኮ መታሰር ብቻ ሳይሆን፣ ለጌታችን ለኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት ዝግጁ ነኝ” ብሎ መለሰ።14ጳውሎስ ምክር ለመቀበል እንዳልፈለገ በተረዳን ጊዜ፣ “የጌታ ፈቃድ ይሁን” ብለን መለመኑን አቆምን።15ከእነዚህ ቀናት በኋላ፣ እኛም የጕዞ ዕቃዎቻችንን ይዘን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣን።16ደግሞም ከቂሣርያ የነበሩ አንዳንድ ደቀ መዛሙርት ከእኛ ጋራ መጡ። ምናሶን የሚባለውንም ሰው ይዘውት መጡ፤ እርሱም የቆጵሮስ ሰው፣ ወደ ፊት ከእርሱ ጋር እንድንቀመጥ የታሰበ የቀድሞ ደቀ መዝሙር ነበረ።17ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ፣ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን።18በማግስቱም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ሄደ፤ ሽማግሌዎችም ሁሉ በዚያ ነበሩ።19ሰላምታ ካቀረበላቸው በኋላ፣ እግዚአብሔር በእርሱ አገልግሎት አማካይነት በአሕዛብ መካከል የሠራቸውን ነገሮች አንድ በአንድ ዘርዝሮ ነገራቸው።20እነርሱም ስለ ሰሙት ነገር እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉት፤ “ወንድም ሆይ፣ ከአይሁድ ያመኑት ስንትና ስንት ሺህ እንደ ሆኑ ታያለህ። ሁላቸውም ሕግን ለመጠበቅ የወሰኑ ናቸው።21በአሕዛብ መካከል የሚኖሩት አይሁድ ሁሉ ሙሴን እንዲተዉ እንደምታስተምራቸው፣ ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ እንደምትነግራቸውና በቀድሞው ልማድ እንዳይሄዱ እንደምታደርግ፣ ስለ አንተ ተነግሮአቸዋል።22እንግዲህ ምን እናድርግ? መምጣትህን እንደሚሰሙ ርግጠኞች ነን።23ስለዚህ አሁን እኛ የምንልህን አድርግ፤ ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች እዚህ አሉን።24እነዚህን ሰዎች ይዘህ ከእነርሱ ጋር ራስህን አንጻ፤ ጠጕራቸውን ለመላጨት የሚያስፈልጋቸውንም ገንዘብ ክፈልላቸው። በዚህም ስለ አንተ የተነገራቸው ሁሉ ውሸት እንደ ሆነ ያውቃሉ፤ አንተም ልማዱን ጠብቀህ እንደምትኖር ይረዳሉ።25ስላመኑ አሕዛብ ግን ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደም፣ ከታነቀ፣ እንዲሁም ከዝሙት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጽፈን ትእዛዝ ሰጥተናል።”26ጳውሎስም ሰዎቹን ይዞ በሚቀጥለው ቀን ራሱን ከእነርሱ ጋር እያነጻ ወደ መቅደሱ ገባ፤ ይኸውም መሥዋዕቱ ስለ እያንዳንዳቸው እስከሚቀርብ ድረስ መንጻቱ የሚወስደውን ጊዜ በመንገር ነው።27ሰባቱ ቀናት ወደ መገባደዱ ሲቃረቡ፣ ከእስያ የመጡ አንዳንድ አይሁድ ጳውሎስን በቤተ መቅደስ ውስጥ አዩት፤ ሕዝቡንም ሁሉ በእርሱ ላይ አነሣሡ፤ ያዙትም።28እንዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ርዱን። ሰዎችን ሁሉ ከሕዝቡ፣ ከሕጉና ከዚህ ስፍራ ጋር የማይስማሙ ነገሮችን የሚያስተምር ይህ ሰው ነው። ከዚህም በላይ የግሪክን ሰዎች ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት፣ ይህን ቅዱስ ስፍራ የሚያረክሰውም እርሱ ነው።”29ምክንያቱም ቀደም ሲል የኤፌሶኑን ሰው ጥሮፊሞስን ከእርሱ ጋር በከተማ ስላዩት፣ ጳውሎስ ወደ ቤተ መቅደስ ያስገባው መሰላቸው።30ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝቡም በአንድነት ተሰባስበው ጳውሎስን ያዙት፤ ጐትተውም ከቤተ መቅደስ አስወጡት፤ በሮቹም ወዲያው ተዘጉ።31ሊገድሉት ሲሞክሩም፣ መላዋ ኢየሩሳሌም እጅግ ታውካለች የሚል ወሬ ወደ ጭፍሮቹ አለቃ ደረሰ።32እርሱም ወዲያው ወታደሮችንና የመቶ አለቆችን ይዞ ሕዝቡ ወዳሉበት በሩጫ ወረደ። ሰዎቹም ሻለቃውንና ወታደሮችን ሲያዩ፣ ጳውሎስን መደብደብ አቆሙ።33ከዚያም ሻለቃው ወደ ጳውሎስ ሄዶ ያዘው፤ በሁለት ሰንሰለቶች እንዲታሰርም አዘዘ። ስለ ማንነቱና ስለ ፈጸመው ድርጊትም ጠየቀው።34ከሕዝቡም ግማሾቹ ስለ አንድ ነገር ሲጮኹ፣ የቀሩት ደግሞ ስለ ሌላ ነገር ይንጫጩ ነበር። ሻለቃውም ከጫጫታው ሁሉ የተነሣ፣ ስለ ምን እንደሚጮኹ እንኳ መለየት አልቻለም፤ ስለዚህ ጳውሎስን ወደ ወታደሮች ምሽግ እንዲያገቡት አዘዘ።35ጳውሎስ ወደ መወጣጫው ደረጃ በደረሰ ጊዜ፣ ከሕዝቡ ረብሻ የተነሣ፣ ወታደሮቹ ተሸክመውት ሄዱ።36ሕዝቡ “አስወግደው!” እያሉና እየጮኹ ከኋላ ይከተሉ ነበር።37ጳውሎስም ወደ ምሽጉ ሊገባ ጥቂት ሲቀረው፣ ሻለቃውን፣ “አንድ ነገር እንድናገርህ ትፈቅድልኛለህ?” አለው። ሻለቃውም፣ “የግሪክ ቋንቋ መናገር ትችላለህ ወይ?38አንተ ከዚህ በፊት ዐመፅ አስነሥተህ፣ አራት ሺህ ሰዎችን በማስሸፈት፣ ወደ ምድረ በዳ የገባህ ግብፃዊ አይደለህምን?” አለው።39ጳውሎስም፣ “እኔስ በኪልቅያ ከምትገኘው ከጠርሴስ ከተማ የመጣሁ አይሁዳዊ ነኝ፤ የታዋቂዋ ከተማ ዜጋ ነኝ። አንድ ነገር እለምንሃለሁ፤ ለሰዎቹ እንድናገር ፍቀድልኝ” አለው።40ሻለቃው በፈቀደለት ጊዜም፣ ጳውሎስ መወጣጫ ደረጃው ላይ ቆሞ፣ በእጁ ወደ ሕዝቡ አመለከተ። ሕዝቡ ጸጥ እረጭ ሲልም፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦
1“ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ አሁን ስለ ራሴ ለእናንተ የማቀርበውን መከላከያ አድምጡኝ።”2ሕዝቡም ጳውሎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲያናግራቸው በሰሙ ጊዜ፣ ጸጥ አሉ። ጳውሎስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤3“እኔ በኪልቅያዋ ጠርሴስ የተወለድሁ አይሁዳዊ ነኝ፤ የተማርሁትም በዚሁ ከተማ በገማልያል እግር ሥር ተቀምጬ ነው። የአባቶቻችንንም ጥብቅ የሕግ መንገድ በሚገባ ተምሬአለሁ። ዛሬ እናንተ ሁላችሁ እንደ ሆናችሁት፣ እኔም ለእግዚአብሔር ቀናተኛ ነኝ።4ይህን መንገድ እስከ ሞት አሳድጄዋለሁ፤ ሴቶችንና ወንዶችን አስሬ ለወኅኒ አሳልፌ ሰጠኋቸው።5ደግሞም ከእነርሱ ደብዳቤ ተቀብዬ፣ በደማስቆ ስለሚገኙ ወንድሞች ወደዚያ ለመጓዝ እንደ ተነሣሁ፣ ሊቀ ካህናቱና ሽማግሌዎች ሁሉ መመስከር ይችላሉ። ከዚያ መንገድ የሆኑትን አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣትና ለማስቀጣት ስንቀሳቀስም ነበር።6እየተጓዝሁ ወደ ደማስቆ ስቃረብ፣ ቀትር ላይ ድንገት ታላቅ ብርሃን ከሰማይ በዙሪያዬ በራ፤7እኔም መሬት ላይ ወደቅሁ፤ ከዚያም፣ 'ሳውል፣ ሳውል፣ ለምን ታሳድደኛለህ?' የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ።8እኔም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ?' ብዬ መለስሁለት። እርሱም፣ 'አንተ የምታሳድደኝ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ' አለኝ።9ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አዩ፤ ነገር ግን የተናገረኝን ድምፅ አልሰሙም።10እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ምን ላድረግ?’ አልሁ። ጌታም፣ ‘ተነሥና ወደ ደማስቆ ሂድ፤ ማድረግ የሚገባህን ሁሉ እዚያ ይነግሩሃል’ አለኝ።11ከዚያ ብርሃን ድምቀት የተነሣም አንዳች ማየት አልቻልሁም፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር በነበሩት ሰዎች እጅ እየተመራሁ ወደ ደማስቆ ገባሁ።12ለሕጉ በትጋት የሚታዘዝና በዚያ የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ መልካምነቱን የመሰከሩለት፣ ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው አገኘሁ።13እርሱም ወደ እኔ መጥቶ አጠገቤ በመቆም፣ ‘ወንድሜ ሳውል፣ ዐይንህን ገልጠህ እይ’ አለኝ። እኔም በዚያው ቅጽበት አየሁት።14እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘ቅዱሱን እንድታይና ከገዛ አፉ የሚወጣውን ድምፅ እንድትሰማ፣ የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን እንድታውቅ መርጦሃል፤15ምክንያቱም ስለ አየኸውና ስለ ሰማኸው ነገር ለሰዎች ሁሉ ምስክር ትሆንለታለህ።16ስለዚህ አሁን ለምን ታመነታለህ? ተነሥ፤ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅና ከኃጢአትህ ታጠብ።’17ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለስሁ በኋላም፣ በቤተ መቅደስ እየጸለይሁ ሳለሁ፣ ሸለብ አድርጎኝ ሰመመን ውስጥ ገባሁ።18እርሱም፣ ‘ከኢየሩሳሌም ቶሎ ብለህ ውጣ፤ ምክንያቱም ስለ እኔ የምትናገረውን ምስክርነትህን አይቀበሉህም’ ሲለኝ አየሁ።19እኔም እንዲህ አልሁ፤ ‘ጌታ ሆይ፣ በምኵራብ ሁሉ በአንተ ያመኑትን ሳስርና ስደበድብ እንደ ነበርሁ እነርሱ ራሳቸው ያውቃሉ።20የሰማዕትህን የእስጢፋኖስንም ደም በሚያፈሱበት ጊዜ፣ በመስማማት እዚያው ቆሜ ነበር፤ የገዳዮቹንም ልብሶች እጠብቅ ነበር።’21እርሱ ግን፣ ‘ተነሥተህ ሂድ፤ ምክንያቱም ወደ አሕዛብ እልክሃለሁ’ አለኝ።”22ሕዝቡም እስከዚህ ድረስ እንዲናገር ፈቀዱለት፤ ከዚህ በኋላ ግን፣ “እንደዚህ ያለ ሰው ከምድር ይወገድ፤ በሕይወትም ይኖር ዘንድ አይገባውም” እያሉ ይጮኹ ጀመር።23እየጮኹም ሳለ፣ ልብሳቸውን እያወለቁና አቧራም ወደ ላይ ይበትኑ ነበር፤24ሻለቃውም ጳውሎስን ወደ ወታደራዊው ምሽግ እንዲወስዱት አዘዘ። እርሱ ራሱ ሕዝቡ ለምን እንደዚያ እንደ ጮኹበት ለማወቅ ስለ ፈለገ፣ እየገረፉ ጳውሎስን እንዲመረምሩት ትእዛዝ ሰጠ።25ሰዎቹ በጠፍር ወጥረው ባሰሩት ጊዜ፣ ጳውሎስ በአጠገቡ የቆመውን መቶ አለቃ፣ “ሮማዊ የሆነን ሰው፣ ገና ሳይፈረድበት እንዲህ መግረፍህ ሕጋዊ ነው ወይ?” አለው።26መቶ አለቃውም ይህን ሲሰማ፣ ወደ ሻለቃው ሄዶ፣ “ምን ማድረግህ ነው? ሰውየውኮ የሮማ ዜጋ ነው” በማለት ነገረው።27ሻለቃውም መጥቶ፣ “አንተ የሮማ ዜጋ ነህን? እስቲ ንገረኝ” አለው። ጳውሎስም፣ “አዎ፣ ነኝ” አለ።28ሻለቃውም፣ “እኔኮ ይህን ዜግነት ያገኘሁት በብዙ ገንዘብ ነው” ብሎ መለሰለት። ጳውሎስም፣ “እኔ ግን ከመወለዴ ጀምሮ ሮማዊ ነኝ” አለ።29ሊመረምሩት የመጡ ሰዎችም ወዲያው ትተውት ሄዱ። ሻለቃውም ጳውሎስ የሮም ዜጋ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ፈራ፤ ምክንያቱም ጳውሎስን አሳስሮት ነበር።30በማግስቱም ሻለቃው፣ አይሁድ ጳውሎስን የከሰሱበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማወቅ ፈለገ። ስለዚህ ጳውሎስን ከእስራት አስፈታውና የካህናት አለቆችና ሸንጎው በሙሉ እንዲሰበሰቡ አዘዘ። ከዚያም ጳውሎስን አስመጥቶ በመካከላቸው አቆመው።
1ጳውሎስም ትኵር አድርጎ ወደ ሸንጎው በመመልከት፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እኔ እስካሁን ድረስ፣ በእግዚአብሔር ፊት በንጹሕ ኅሊና ሁሉ ኖሬአለሁ” አለ።2ሊቀ ካህናቱ ሐናንያም ጳውሎስ አጠገብ የነበሩትን ሰዎች አፉን እንዲመቱት አዘዛቸው።3በዚህ ጊዜ ጳውሎስ፣ “አንተ ነጭ ቀለም የተቀባህ ግድግዳ፣ እግዚአብሔር ይመታሃል። በሕጉ መሠረት ልትፈርድብኝ የተቀመጥህ፣ ሕጉን ጥሰህ እኔ እንድመታ ታዛለህን?” አለው።4በአጠገቡ ቆመው የነበሩትም፣ “የእግዚአብሔርን ሊቀ ካህናት እንዴት ትሰድባለህ?” አሉ።5ጳውሎስም፣ “ወንድሞች ሆይ፣ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላወቅሁም፤ ምክንያቱም፣ በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል ከአፍህ አይውጣ ተብሎ ተጽፎአል።”6ጳውሎስም ከሸንጎው አባላት ከፊሉ ሰዱቃውያን፣ ሌሎቹም ፈሪሳውያን መሆናቸውን ሲያይ፣ በሸንጎ መካከል ሆኖ በከፍተኛ ድምፅ፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እኔ የፈሪሳዊ ልጅ የሆንሁ፣ ፈሪሳዊ ነኝ። ፍርድ ፊት የቀረብሁትም የሙታን ትንሣኤ እንዳለ ስለማምን ነው” አላቸው።7ይህን በተናገረ ጊዜ፣ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ክርክር ተነሣ፤ ጉባኤውም ተከፋፈለ።8ምክንያቱም ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን የለም፤ መላእክትም የሉም፤ መናፍስትም የሉም ስለሚሉና፣ ፈሪሳውያን ግን እነዚህ ሁሉ አሉ ስለሚሉ ነው።9በዚህ ጊዜ፣ ታላቅ ውካታ ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ ጸሐፍትም ተነሥተው፣ “በዚህ ሰው ላይ አንድም ጥፋት አላገኘንም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት እንደ ሆነስ ማን ያውቃል?” በማለት ተከራከሩ።10ክርክሩም እየጋለ ሲሄድ፣ ጳውሎስን ይዘው እንዳይቦጫጭቁት ሻለቃው ፈራ፤ ስለዚህ ወታደሮቹ ወርደው ጳውሎስን በኀይል ይዘው ከሸንጎ አባላት መካከል እንዲወስዱትና ወደ ምሽጉ አምጥተው እንዲያስገቡት አዘዘ።11በሚቀጥለውም ሌሊት ጌታ በጳውሎስ አጠገብ ቆሞ፣ “አትፍራ፤ በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርኸው፣ በሮማም ደግሞ ልትመሰክር ይገባሃል” አለው።12በነጋም ጊዜ፣ አንዳንድ አይሁድ ጳውሎስን ሳንገድል እኽል ውሃ አንቀምስም በማለት በመሐላ ተስማሙ።13ይህን የዶለቱትም ሰዎች ቍጥር ከአርባ በላይ ነበር።14ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎችም ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ጳውሎስን እስከምንገድል ድረስ፣ እኽል እንዳንቀምስ በታላቅ ርግማን ተማምለናል።15ስለዚህ አሁን ሻለቃው ጳውሎስን ወደ እናንተ እንዲያወርደውና እናንተ የእርሱን ጉዳይ ይበልጥ በትክክል እንደምታዩለት አስመስላችሁ፣ ሸንጎው ለሻለቃው ያመልክት። በእኛ በኩል ግን እዚህ ከመምጣቱ በፊትም ቢሆን ልንገድለው ዝግጁ ነን።”16የጳውሎስ እኅት ወንድ ልጅም ጳውሎስን አድፍጠው እንደሚጠብቁት ዐወቀ፤ ሄዶም ወደ ምሽጉ ገብቶ ለጳውሎስ ነገረው።17ጳውሎስም አንዱን መቶ አለቃ ጠራና፣ “ይህን ወጣት ወደ ሻለቃው ውሰደው፤ የሚናገረው ነገር አለውና” አለ።18መቶ አለቃውም ወጣቱን ይዞ ወደ ሻለቃው አመጣውና እንዲህ አለ፤ “ጳውሎስ የተባለው እስረኛ ወደ ራሱ ጠርቶኝ፣ ይህን ወጣት ወደ አንተ እንዳቀርበው ለመነኝ፤ ወጣቱ ለአንተ የሚነግርህ ነገር አለው።”19ሻለቃውም እጁን ይዞ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ ወስዶት፣ “ልትነግረኝ የፈለግኸው ነገር ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው።20ወጣቱም እንዲህ አለ፤ “አይሁድ ስለ ጉዳዩ ትክክለኛነት ይበልጥ ለመረዳት የፈለጉ አስመስለው፣ ነገ ጳውሎስን ወደ ሸንጎው እንድታወርደው አንተን ለመለመን ተስማምተዋል።21ነገር ግን እሺ አትበላቸው፤ ምክንያቱም ከአርባ በላይ የሚሆኑ ሰዎች አድፍጠው እየጠበቁት ነው። ጳውሎስን ካልገደሉም እኽል ውሃ እንደማይቀምሱ ተማምለዋል። አሁንም እንኳ የአንተን መስማማት እየጠበቁ ነው እንጂ ዝግጁ ናቸው።”22ስለዚህ ሻለቃው ወጣቱን ልጅ፣ “ስለ እነዚህ ነገሮች ለእኔ መግለጥህን ለማንም እንዳትናገር” ብሎ ካስጠነቀቀው በኋላ፣ አሰናበተው።23ከመቶ አለቆቹም ሁለቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ “እስከ ቄሣርያ ለመሄድ የሚችሉ ሁለት መቶ ወታደሮችን፣ ሰባ ፈረሰኞችንና ሁለት መቶ ባለ ጦሮችን አዘጋጁ፤ ከሌሊቱም በሦስተኛው ሰዓት ትንቀሳቀሳላችሁ” አላቸው።24ጳውሎስ ወደ ሀገረ ገዡ፣ ወደ ፊልክስ የሚሄድበትንም ከብት እንዲያዘጋጁና በሰላም እንዲያደርሱት አዘዛቸው።25ከዚያም እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፈ፤26“ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ፣ ወደ ተከበረው ሀገረ ገዢ ፊልክስ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን።27ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ሲሉ፣ ከወታደሮች ጋር ደርሼባቸው አዳንሁት፤ ይህን ያደረግሁትም ሮማዊ ዜጋ መሆኑን ስለ ተረዳሁ ነው።28ለምን እንደ ከሰሱት ለማወቅ ስለ ፈለግሁም፣ ወደ ሸንጎአቸው ይዤው ወረድሁ።29የገዛ ራሳቸውን ሕግ በሚመለከት በተነሣ ጥያቄ ምክንያት ተከሶ እንጂ፣ ሞት ወይም እስራት የሚገባው ክስ እንደሌለበት ዐውቄአለሁ።30በዚህ ሰው ላይ ሤራ እንደ ተካሄደበትም ደርሼበታለሁ፤ ስለዚህም ፈጥኜ ወደ አንተ ላክሁት፤ ከሳሾቹም በእርሱ ላይ ያላቸውን ክስ አንተ ባለህበት እንዲያቀርቡ መመሪያ ሰጥቻቸዋለሁ። በደኅና ሰንብት።”31ስለዚህ ወታደሮቹ በታዘዙት መሠረት፣ ጳውሎስን ይዘው በሌሊት ወደ አንቲጳጥሪስ ወሰዱት።32በሚቀጥለውም ቀን፣ አብዛኞቹ ወታደሮች ፈረሰኞቹን ከእርሱ ጋር እንዲሄዱ ትተው፣ ወደ ምሽግ ተመለሱ።33ፈረሰኞቹም ቂሣርያ በደረሱና ደብዳቤውን ለሀገር ገዡ ሲሰጡ፣ ጳውሎስንም ለእርሱ አስረከቡት።34ሀገረ ገዡም ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ፣ ጳውሎስ ከየትኛው አውራጃ እንደ መጣ ጠየቀ፤ ከኪልቅያ እንደ መጣ ባወቀ ጊዜም፣35“ከሳሾችህ ወደዚህ ሲመጡ፣ በሚገባ እሰማሃለሁ” አለው። ከዚያም በኋላ፣ በሄሮድስ ቅጥር ግቢ እንዲጠብቁት አዘዘ።
1ከዐምስት ቀናት በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ፣ አንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ የተባለ አንድ የሕግ ባለ ሙያ ወደዚያ ሄዱ። እነዚህ ሰዎች ለገዡ አመልክተው ጳውሎስን ከሰሱት።2ጳውሎስ በገዡ ፊት በቆመ ጊዜ፣ ጠርጠሉስ ይከሰው ጀመር፤ ገዡንም እንዲህ አለው፤ «ክቡር ፊልክስ ሆይ፣ በአንተ ምክንያት ብዙ ሰላም አግኝተናል፤ የአንተ ማስተዋልም ለሕዝባችን ጥሩ መሻሻልን ያመጣለታል፤3ስለ ሆነም አንተ የምታደርገውን ሁሉ በፍጹም ምስጋና እንቀበለዋለን።4ብዙ እንዳላቈይህ፣ በቸርነትህ በዐጭሩ እንድትሰማኝ እለምንሃለሁ።5ይህ ሰው ቅንቅን ሆነና በመላው ዓለም ላይ ያሉትን አይሁዶች ሲያሳምፅ አግኝተነዋልና። የናዝራውያን ወገን መሪ ነው።6ቤተ መቅደሱንም እንኳ ሊያረክስ ሞክሯል፤ ስለዚህ ያዝነው።7ነገር ግን ወታደራዊው መኰንን ሉስዮስ መጥቶ፣ ጳውሎስን በኀይል ከእጃችን ወሰደው።8አንተም ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ጳውሎስን በምትጠይቀው ጊዜ ለምን እንደምንከሰው ልታውቅ ትችላለህ።»9አይሁድም አንድ ላይ ሆነው ጳውሎስን ከሰሱት፤ ነገሮቹም ሁሉ እውነት መሆናቸውን ተናገሩ።10ገዡ ግን እንዲናገር ሲጠይቀው፣ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ መልስ ሰጠ፤ «አንተ ለብዙ ዓመታት ለዚህ ሕዝብ ፈራጅ መሆንህን ዐውቃለሁ፤ ስለ ሆነም ደስ እያለኝ ስለ ራሴ እገልጽልሃለሁ።11ለማምለክ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከዐሥራ ሁለት ቀን እንደማይበልጥ አንተ መርምረህ ልትደርስበት ትችላለህ፤12እነርሱ በቤተ መቅደስ ባገኙኝ ጊዜም፣ ከማንም ጋር አልተከራከርሁም፤ በምኵራቦችም ሆነ በከተማው ሕዝብን አልቀሰቀስሁም፤13አሁን በእኔ ላይ የሚያቀርቡት ክስ እውነተኛ ለመሆኑ ማስረጃ የላቸውም።14ነገር ግን ለአንተ ይህን እነግርሃለሁ፤ እነርሱ የእምነት ክፍል ብለው እንደሚጠሩት እኔም በዚያ ተመሳሳይ መንገድ የአባቶቻችንን አምላክ አገለግላለሁ። በሕግና በነቢያት ለተጻፈው ሁሉ የታመንሁ ነኝ።15ልክ እነዚህ ሰዎች ደግሞ እንደሚጠብቁት፣ ስለሚመጣው የሙታን ማለትም የጻድቃንና የኀጥአን ትንሣኤ በእግዚአብሔር ላይ እምነት አለኝ።16በዚህም በሁሉም ነገር በእግዚአብሕርና በሰዎች ፊት ነቀፋ የሌለበት ኅሊና እንዲኖረኝ እሠራለሁ።17ከብዙ ዓመታትም በኋላ ለሕዝቤ ርዳታና የገንዘብ ስጦታ ለመስጠት መጣሁ።18ይህንም ባደረግሁ ጊዜ ከእስያ የሆኑ አንዳንድ አይሁድ፣ ሕዝብም ጩኸትም ሳይኖር በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዓት ላይ አገኙኝ።19እነዚህ ሰዎች በእኔ ላይ አንዳች ነገር ካላቸው፣ በፊትህ መጥተው ክሱን ሊያቀርቡብኝ ይገባቸዋል።20አለበለዚያም፣ እነዚሁ ሰዎች በአይሁድ ሸንጎ ፊት በቆምሁ ጊዜ፣ ምን እንዳጠፋሁ መናገር ነበረባቸው፤21«ዛሬ አንተ የምትፈርድብኝ ስለ ሙታን ትንሣኤ ነው» ብዬ በመካከላቸው ቆሜ ድምፄን ከፍ በማድረግ ከተናገርሁት ከዚህ አንድ ነገር በቀር፣ ምንም የተናገርሁት የለም።22ፊልክስ ግን ስለ መንገዱ በሚገባ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሆነም፣ «አዛዡ ሉስዮስ ከኢየሩሳሌም በሚወርድበት ጊዜ ለክሳችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ» ብሎ አይሁድን እንዲጠብቁ አደረጋቸው።23ከዚያም ጳውሎስን እንዲጠብቀው፣ ነገር ግን እንዲያደላለት፣ እርሱንም ከመርዳት ወይም ከመጎብኘት ማንም ወዳጆቹን እንዳይከለክል የመቶ አለቃውን አዘዘው።24ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ፊልክስ ድሩሲላ ከምትባል አይሁዳዊት ሚስቱ ጋር ተመልሶ መጣ፤ ጳውሎስንም በማስጠራት በክርስቶስ ኢየሱስ ስላለው እምነት ከእርሱ ሰማ።25ነገር ግን ጳውሎስ ስለ ጽድቅ፣ ራስን ስለ መግዛት፣ ስለሚመጣውም ፍርድ ከእርሱ ጋር በተነጋገረ ጊዜ፣ ፊልክስ ፈራ፤ «ለአሁኑ ሂድ፤ እንደ ገና ጊዜ ሲኖረኝ ግን፣ አስጠራሃለሁ» አለው።26በዚሁ ጊዜ፣ ጳውሎስ ገንዘብ ይሰጠኛል ብሎ ፊልክስ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ ስለዚህ ብዙ ጊዜ እያስጠራ ያነጋግረው ነበር።27ከሁለት ዓመት በኋላ ግን፣ ከፊልክስ ቀጥሎ ጶርቅዮስ ፊስጦስ ገዢ ሆነ፤ ፊልክስ ግን አይሁድን ለማስደሰት ፈልጎ ጳውሎስን በጥበቃ ሥር እንዲቆይ አደረገ።
1ፊስጦስም ወደ ክፍለ ሀገሩ ገባ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ከቂሣርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።2የካህናት አለቃውና ታዋቂ የሆኑት አይሁድ ጳውሎስን ፊስጦስ ላይ ከሰሱት፤ ለፊስጦስም በኀይል ተናገሩ።3በመንገድም ላይ ሊገድሉት ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስጠራው ፊስጦስን ለመኑት።4ፊስጦስ ግን መልሶ ጳውሎስ በቂሣርያ እስረኛ እንደ ሆነ፣ እርሱ ራሱም ወደዚያ እንደሚመለስ ተናገረ።5“ስለዚህ፣ የሚችሉ ከእኛ ጋር ወደዚያ መሄድ አለባቸው። ሰውየው ያጠፋው ነገር ካለ፣ ክሰሱት” አለ።6ፊስጦስም ስምንት ወይም ዐሥር ቀን ከቆየ በኋላ፣ ወደ ቂሣርያ ወረደ። በማግስቱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ።7ጳውሎስም በደረሰ ጊዜ፣ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁድ በአጠገቡ ቆሙ፤ በማስረጃ ማረጋገጥ ያልቻሉትን ብዙ ከባድ ክስም አቀረቡ።8ጳውሎስ፣ “በአይሁድ ስምም ላይ፣ በቤተ መቅደሱም ላይ፣ በቄሣርም ላይ በደል አልፈጸምሁም” ብሎ ራሱን ተከላከለ።9ፊስጦስ ግን አይሁድን ለማስደሰት ፈለገ፤ ስለሆነም፣ “እስከ ኢየሩሳሌም መውጣትና ስለ እነዚህ ነገሮች በዚያ ፍርድ እንድሰጥህ ትፈልጋለህን?” ብሎ ጳውሎስን ጠየቀው።10ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “ፍርድ ሊሰጠኝ በሚገባኝ በቄሣር የፍርድ ወንበር ፊት እቆማለሁ። አንተም ደግሞ በሚገባ እንደምታውቀው፣ አንድንም አይሁዳዊ አልበደልሁም።11ብበድልና ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ ቢሆን እንኳ፣ አልሞትም አልልም። እነርሱ በእኔ ላይ የሚያቀርቡት ክስ ከንቱ ከሆነ ግን፣ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም። ለቄሣር ይግባኝ ብያለሁ።”12ከዚያም ፊስጦስ ከሸንጎው ጋር ተነጋግሮ፣ “ለቄሣር ይግባኝ ብለሃልና ወደ ቄሣር ትሄዳለህ” ብሎ መለሰ።13ከጥቂት ቀናትም በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ፊስጦስን ለመጐብኘት ቂሣርያ ደረሱ።14ንጉሥ አግሪጳ በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፣ ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለንጉሡ አቀረበ፤ እንዲህም አለ፤ “ፊልክ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ።15እኔ በኢየሩሳሌም በነበርሁ ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች ክስ መሥርተውበት ለእኔ አመለከቱ፤ እንድፈርድበትም ለመኑኝ።16ለዚህም፣ የተከሰሰው ሰው በከሳሾቹ ፊት ቀርቦ ለተከሰሰበት ነገር እንዲከላከል ዕድል ሳይሰጠው አንድን ሰው አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ልማድ አይደለም ብዬ መልስ ሰጠሁ።”17ስለዚህ፣ እነርሱ በአንድ ላይ ወደዚህ በመጡ ጊዜ፣ አልዘገየሁም፤ ነገር ግን በማግስቱ በፍርድ ወንበር ተቀምጬ ሰውዬውን እንዲያመጡት አዘዝሁ።18ከሳሾቹ ቆመው በከሰሱት ጊዜ፣ ካቀረቡበት ክሶች ማንኛቸውም ከባድ አይደሉም ብዬ ዐሰብሁ።19ይልቁንም ስለ ገዛ ራሳቸው ሃይማኖትና ጳውሎስ ሕያው ነው ስለሚለው ሞቶ ስለ ነበረው ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ነበር።20ይህን ጉዳይ እንዴት እንደምመረምር ግራ ገብቶኝ ነበር፤ ስለ እነዚህ ነገሮችም በዚያ ለመፋረድ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ እንደ ሆነ ጳውሎስን ጠየቅሁት።21ጳውሎስ ግን የንጉሠ ነገሥቱን ውሳኔ እስኪያገኝ፣ በዘብ እንዲጠበቅ ይግባኝ ባለ ጊዜ፣ ወደ ቄሣር እስክሰደው ድረስ በጥበቃ ሥር እንዲሆን አዘዝሁት።”22አግሪጳ፣ “እኔ ደግሞ ይህን ሰው ልሰማው እፈልጋለሁ” ብሎ ፊስጦስን አነጋገረው። ፊስጦስም፣ “ነገ ትሰማዋለህ” አለው።23ስለ ሆነም፣ በማግስቱ፣ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ሥነ ሥርዓት ከወታደራዊ መኮንኖችና ከከተማዋ ታዋቂ ሰዎች ጋር ወደ አዳራሹ ገቡ። በፊስጦስ ትእዛዝም ጊዜ ጳውሎስን ወደ እነርሱ አመጡት።24ፊስጦስም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ እዚህ ከእኛ ጋር ያላችሁትም ሰዎች ሁሉ፣ ይህን ሰው ተመልከቱት፤ በኢየሩሳሌምና እዚህም ያሉት የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ከእኔ ጋር ተማከሩ፤ ይህ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ በሕይወት መኖር የለበትም ብለውም ጮኹብኝ።25እኔ ግን ለሞት የሚያበቃው ምንም በደል አለመፍጸሙን ዐወቅሁ፤ ነገር ግን ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ልሰደው ወሰንሁ።26ሆኖም ለንጉሠ ነገሥቱ ለመጻፍ አሳማኝ ነገር የለኝም። በዚህ ምክንያት ስለ ጉዳዩ የምጽፈው ነገር እንዲኖረኝ፣ በተለይ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ወደ አንተ አምጥቼዋለሁ።27አንድን እስረኛ መስደድና የቀረበበትን ክስም አለመግለጽ ለእኔ ምክንያታዊ ያልሆነ ይመስለኛልና።”
1አግሪጳም ጳውሎስን፣ «አንተ ለራስህ ተናገር» አለው። ከዚያም በኋላ፣ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ መከላከያውን አቀረበ።2«ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ዛሬ በፊትህ አይሁድ ስለ ከፈቱብኝ ክስ ሁሉ መከላከያዬን ሳቀርብ ራሴን ደስተኛ አድርጌ እቈጥረዋለሁ፤3ምክንያቱም በተለይ አንተ የአይሁድን ልማድና ጥያቄ ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ስለዚህ በትግዕሥት እንድታደምጠኝ እለምንሃለሁ።4በእውነት ከልጅነቴ ጀምሮ በሕዝቤ መካከልና በኢየሩሳሌም እንዴት እንደ ኖርሁ አይሁድ ሁሉ ያውቃሉ።5ከመጀመሪያው አንሥቶ እኔን ያውቁኛል፤ የሃይማኖታችን በጣም ወግ አጥባቂ ክፍል ፈሪሳዊ ሆኜ እንደ ኖርሁም ሊያምኑ ይገባል።6አሁን እዚህ ለፍርድ የቆምሁት እግዚአብሔር ለአባቶቻችን የሰጠውን ተስፋ የምፈልግ በመሆኔ ነው።7በዚህ ምክንያት ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን ቀንና ሌሊት በቅንነት እግዚአብሔርን ያገለግላሉ፤ እኛም ወደ እርሱ ለመድረስ ተስፋ እናደርጋለን። ንጉሥ ሆይ፣ አይሁድ እኔን የሚከሱኝ ስለዚህ ተስፋ ነው!8እግዚአብሔር ሙታንን እንደሚያስነሣ አይታመንም ብላችሁ ለምን ታስባላችሁ?9አንድ ጊዜ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስን ስም በመቃወም ብዙ ነገር ማድረግ አለብኝ ብዬ ዐሰብሁ።10በኢየሩሳሌምም ይህንኑ አደረግሁ፤ ከምእመናን ብዙዎችን ወኅኒ እንዲገቡ አደረግሁ፤ ለዚህም ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተቀብዬ ነበር፤ በሚገደሉበት ጊዜም፣ ተስማምቻለው።11ብዙ ጊዜም በምኵራቦች ሁሉ እንዲቀጡ አድርጌአለሁ፤ የስድብ ቃል እንዲናገሩም ጥረት አድርጌአለሁ። ምእመናኑን እጅግ እቈጣቸውና ሌሎች ከተሞች እንኳ አሳድዳቸው ነበር።12ይህን እያደረግሁ፣ ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ሄድሁ፤13ወደዚያ በመጓዝ ላይ እያለሁም ንጉሥ ሆይ፣ እኩለ ቀን ላይ ከፀሐይ ይልቅ የሚያበራ ብርሃን ከሰማይ አየሁ፤ በእኔና አብረውኝ ይጓዙ በነበሩት ሰዎች ዙሪያም አበራ።14ሁላችንም በመሬት ላይ በወደቅን ጊዜ፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ፣ «ሳውል፣ ሳውል፣ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይከፋብሃል» የሚል ድምፅ ሲናገረኝ ሰማሁ።15እኔም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ?' አልሁ። ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰልኝ፤ 'አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።16ተነሣና በእግርህ ቁም፤ እኔ የተገለጥሁልህ አሁን ስለ እኔ ስለምታውቃቸውና ኋላ ላይ ስለማሳይህ ነገሮች አገልጋዬና ምስክር እንድትሆን ልሾምህ ነው፤17ወደ እነርሱ ከምልክህ ሕዝብና ከአሕዛብም አድንሃለሁ ፤18ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣን ኃይልም ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ ይኸውም በእኔ በማመናቸው ለራሴ የለየኋቸው እነርሱ፣ ከእግዚአብሔር የኃጢአትን ይቅርታና ርስትን እንዲቀበሉ ነው።'19ስለዚህ፣ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ለሰማያዊው ራእይ አልታዘዝም አላልሁም፤20ነገር ግን መጀመሪያ በደማስቆ ላሉት፣ ከዚያም በኢየሩሳሌም፣ በመላው ይሁዳ፣ ደግሞም ለአሕዛብ ንስሓ እንዲገቡ፣ ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉና ለንስሓ የሚገባ ሥራ እንዲሠሩ ሰበክሁ።21በዚህ ምክንያት አይሁድ በቤተ መቅደስ ያዙኝና ሊገድሉኝ ሞከሩ።22እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶኛል፤ ስለዚህ ለታናናሾችና ለታላላቆች ለመመስከር እዚህ ቆሜአለሁ፤ ምስክርነቴም ሙሴና ነቢያት ይሆናል ብለው ከተናገሩት የሚያልፍ አይደለም፤23ይኸውም ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ ከሙታን ለመነሣትና ለአይሁድ ሕዝብ፣ ለአሕዛብም ብርሃንን ለመስበክ የመጀመሪያው ይሆናል የሚል ነው።24ጳውሎስም መከላከያውን እንደ ጨረሰ ፊስጦስ፣ «ጳውሎስ፣ አንተ ዕብድ ነህ፤ ብዙ መማርህ አሳብዶሃል» ሲል ጮኾ ተናገረ።25ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፤ «እጅግ የተከበርህ ፊስጦስ ሆይ፣ እኔ ዕብድ አይደለሁም፤ ነገር ግን እውነተኛውንና ትክክለኛውን ቃል በድፍረት እናገራለሁ።26ንጉሡ ስለ እነዚህ ነገሮች ያውቃልና እንደ ልብ እነግረዋለሁ፤ በመሆኑም ከእነዚህ ነገሮች አንዱም ከእርሱ የተሰወረ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ።27ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ በነቢያት ታምናለህን? እንደምታምን ዐውቃለሁ።»28አግሪጳም ጳውሎስን፣ «በአጭር ጊዜ ልታሳምነኝና ክርስቲያን ልታደርገኝ ትፈልጋለህን?» አለው።29ጳውሎስም፣ «በአጭር ይሁን ወይም በረዥም ጊዜ፣ አንተ ብቻ ሳትሆን፣ ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ፣ ከእነዚህ የወኅኒ ሰንሰለቶች በቀር እንደ እኔ እንድትሆኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ» አለ።30ከዚያም ንጉሡ፣ ገዥውም፣ በርኒቄም ደግሞ፣ ከእነርሱ ጋር ተቀምጠው የነበሩትም ተነሡ፤31ከአዳራሹም በወጡ ጊዜ፣ እርስ በርስ ተነጋግረው ፣«ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃ ምንም አላደረገም» አሉ።32አግሪጳ ፊስጦስን፣ «ይህ ሰው ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ኖሮ በነጻ ሊለቀቅ ይችል ነበር» አለው።
1ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሌሎችን እስረኞች የአውግስጦስ ክፍለ ጦር አባል ለሆነ ዩልዮስ ለተባለ የመቶ አለቃ አስረከቡአቸው።2እኛም ከአድራሚጥዮን ተነሥተን በእስያ ጠረፍ ሊሄድ በተዘጋጀ መርከብ ላይ ተሳፍረን ወደ ባሕር ተጓዝን። በመቄዶንያ ካለችው ተሰሎንቄ የሆነው አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋር ሄደ።3በማግስቱ ወደ ሲዶን ከተማ ደርሰን፣ ከመርከብ ወረድን፤ እዚያም ዩልዮስ ለጳውሎስ ቸርነት አደረገለት፤ ወደ ወዳጆቹ እንዲሄድና እንክብካቤ እንዲያደርጉለትም ፈቀደለት።4ከዚያም ተነሥተን ወደ ባሕር ሄድን፤ ነፋስ ይነፍስብን ስለ ነበር፣ በመርከብ ሆነን ነፋሱ በማያገኛት በቆጵሮስ ደሴት ዙሪያ ተጓዝን።5በኪልቅያና በጵንፍልያ አጠገብ ያለውን ባሕር ከተሻገርን በኋላም፣ የሉቅያ ከተማ ወደ ሆነው ወደ ሙራ ደረስን።6በዚያም፣ የመቶ አለቃው ከእስክንድርያ ወደ ኢጣሊያ የሚሄድ መርከብ አግኝቶ አሳፈረን።7ብዙ ቀንም በዝግታ ተጓዝንና በመጨረሻ በችግር ወደ ቀኒዶስ ደረስን፤ ነፋሱም በዚያ መንገድ እንዳንሄድ ስለከለከለን፣ በሰልሙና አንጻር ያለችውን ቀርጤስን ተገን አድርገን ተጓዝን።8በላሲያ ከተማ አጠገብ ወዳለው መልካም ወደብ ወደ ተባለው ስፍራ እስከምንደርስ ድረስ በችግር በጠረፉ በኩል ተጓዝን።9ብዙ ጊዜም አሳለፍን፤ የአይሁድ የጾም ወራት ደግሞ ዐልፎ ነበር፤ ጕዞውን መቀጠልም አደጋ የሚያስከትል ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ አስጠነቀቃቸው፤10እንዲህም አለ፤ “እናንተ ሰዎች፣ አሁን የምናደርገው ጕዞ አደጋና ብዙ ጉዳት እንደሚኖርበት ይታየኛል፤ አደጋውም በመርከቡና በጭነቱ ብቻ ሳይሆን፣ በእኛም ሕይወት ላይ የሚደርስ ነው።”11የመቶ አለቃው የሰማው ግን ጳውሎስ የተናገረውን ሳይሆን፣ በይበልጥ የመርከቡ አዛዥና ባለቤት ያሉትን ነው።12ክረምቱን ለማሳለፍ ወደቡ ተስማሚ ስላልነበረ፣ አብዛኛዎቹ ተጓዦች የሚቻል ከሆነ ከዚያ ተነሥተን ፊንቄ ወደ ተባለችው ከተማ እንድንሄድና ክረምቱን እዚያ እንድናሳልፍ ምክር ሰጡን። ፊንቄ በሰሜን ምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ አንጻር የምትገኝ የቀርጤስ ወደብ ነች።13የደቡቡ ነፋስ በቀስታ መንፈስ በጀመረ ጊዜ፣ መርከበኞቹ የፈለጉት እንደተከናወነላቸው ዐሰቡ። ስለዚህ ሸራውን አውርደው በባሕሩ ዳርቻ አቅራቢያ፣ በቀርጤስ በኩል አለፉ።14ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን፣ የሰሜን ምሥራቅ ዐውሎ ነፋስ የተባለ ኃይለኛ ነፋስ ደሴቲቱን አቋርጦ በመምጣት ይነፍስብን ጀመረ፤15መርከቡም ወደ ፊት በተገፋና ነፋሱን መቋቋም ባልቻለ ጊዜ፣ ዝም ብለነው በነፋሱ እየተነዳን ሄድን።16ቄዳ የተባለችውን ትንሽ ደሴት ተተግነን ተጓዝን፤ በትልቅ ችግርም ሕይወት አድን ጀልባው ላይ መውጣት ቻልን።17መርከበኞቹ ጀልባውን ወደ መርከቡ ጎትተው አወጡት፤ ገመዱንም የመርከቡን ዙሪያ ለማሰር ተጠቀሙበት። ስርቲስ በምትባል አሸዋማ ስፍራ እንዳንወድቅ ፈርተው ነበር፤ ስለዚህ የባሕር ሸራውን አውርደው እየተነዱ ሄዱ።18ዐውሎ ነፋሱ በጣም ስላየለብን፣ በማግስቱ መርከበኞቹ የመርከቡን ጭነት ወደ ባሕር መጣል ጀመሩ።19በሦስተኛው ቀን መርከበኞቹ በመርከቡ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን እያነሡ ጣሉ።20ለብዙ ቀንም ፀሐይና ከዋክብት ብርሃናቸውን ባልሰጡንና ትልቁ ማዕበልም በወረደብን ጊዜ፣ አንድንም ብለን ተስፋ ቈረጥን።21ተጓዦቹ ምግብ ሳይበሉ ብዙ ቀን ቈይተው ነበር፤ በዚያን ጊዜ ጳውሎስ በተጓዦቹ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፤ “እናንተ ሰዎች፣ ይህ አደጋና ጉዳት እንዳይደርስባችሁ፣ ከቀርጤስ አትነሡ ብዬ የነገርኋችሁን መስማት ነበረባችሁ፤22አሁንም መርከቡ ብቻ ይጎዳል እንጂ ከመካከላችሁ የሚሞት አይኖርምና አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ።23ምክንያቱም ባለፈው ሌሊት የእርሱ የሆንሁትና ደግሞም የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በአጠገቤ ቆሞ እንዲህ ብሏል፤24“ጳውሎስ ሆይ፣ አትፍራ። በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ ተመልከት፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ ዐብረውህ የሚጓዙትን ሁሉ ሰጥቶሃል።25ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ አይዞአችሁ፤ ልክ እንደ ተናገረኝ እንደሚሆን እግዚአብሔርን አምነዋለሁ።26ነገር ግን ወደ አንዲት ደሴት ደርሰን ልናርፍ ይገባል።”27በዐሥራ አራተኛውም ሌሊት፣ በአድርያቲክ ባሕር ወዲያና ወዲህ እየተንገላታን እያለን፣ እኩለ ሌሊት ገደማ፣ መርከበኞቹ ወደ መሬት የቀረቡ መሰላቸው።28የባሕር ጥልቀት መለኪያ ገመድ ጣሉና ጥልቀቱን አርባ ሜትር ሆኖ አገኙት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ መለኪያውን ሲጥሉም ሠላሳ ሜትር ሆኖ አገኙት።29ከዐለቶቹ ጋር እንጋጫለን ብለውም ፈሩ፤ ስለዚህ ከኋላ አራት መልሕቆችን አውርደው ቶሎ እንዲነጋ ጸለዩ።30መርከበኞቹ መርከቡን ትተው ለመሄድ መንገድ ይፈልጉና ሕይወት አድን ጀልባውን ወደ ባሕሩ ውስጥ ያወርዱ ነበር፤ መልሕቆቹንም ከቀስቱ የሚወረውሩ መሰሉ።31ጳውሎስ ግን መቶ አለቃውንና ወታደሮቹን፣ “እነዚህ ሰዎች በመርከቡ ካልቆዩ በቀር፣ እናንተ መዳን አትችሉም” አላቸው።32ከዚያም ወታደሮቹ የጀልባውን ገመዶች ቈረጡት፤ እንዲንሳፈፍም አደረጉት።33ቀኑ ሊነጋ ሲልም፣ ምግብ እንዲበሉ ጳውሎስ ሁሉንም መከራቸው። እንዲህም አላቸው፤ “ምንም ሳትበሉ ከቈያችሁ ይህ ዐሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው።34ስለዚህ በሕይወት እንድትኖሩ፣ ጥቂት ምግብ እንድትበሉ እለምናችኋለሁ፤ ከራሳችሁ ላይ አንዲቱም ጠጕር አትጠፋም።”35ይህን ተናግሮ፣ እንጀራ አነሣና በሁሉም ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ። ከዚያም እንጀራውን ቈርሶ መብላት ጀመረ።36በዚያን ጊዜ ሁሉም ተጽናንተው ምግብ በሉ።37በመርከቡ ውስጥ 276 ሰዎች ነበርን።38በልተው በጠገቡ ጊዜም፣ ስንዴውን ወደ ባሕሩ በመጣል የመርከቡን ጭነት አቃለሉ።39በነጋታውም፣ የነበሩበትን ምድር አላወቁትም፤ ነገር ግን በዳርቻ ያለውን የባሕር ሰርጥ አዩ፤ መርከቡን ወደ ሰርጡ መግፋት ይችሉ እንደሆነም ተነጋገሩ።40ስለዚህ መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕሩ ላይ ተዉአቸው። በዚሁ ጊዜም የመቅዘፊያዎቹን ገመዶች ፈትተው ሸራውን ወደ ነፋሱ ከፍ አደረጉና ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ።41ነገር ግን ሁለት ማዕበሎች ወደ ተገናኙበት ስፍራ መጡ፤ መርከቡም ወደ መሬት ገባ፤ የመርከቡ ቅስትም በዚያ ተተከለና የማይነቃነቅ ሆነ፤ የኋላ ክፍሉ ግን ከማዕበሉ ነውጥ የተነሣ ይሰባበር ጀመር።42የወታደሮቹ ዕቅድ ከመካከላቸው ማንም ዋኝቶ እንዳያመልጥ እስረኞቹን ለመግደል ነበር።43የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ለማዳን ፈለገ፤ ስለዚህ ዕቅዳቸውን አልተቀበለም፤ መዋኘት የሚችሉትም በመጀመሪያ ከመርከቡ ላይ እየዘለሉ ወደ የብስ እንዲወጡ አዘዘ።44ከዚያም የቀሩት ሰዎች በሳንቃዎችና ከመርከቡ በተገኙ ስብርባሪዎች ላይ ሆነው ተከትለው እንዲወጡ አደረገ። በዚህ ዐይነት ሁላችንም በደኅና ወደ የብስ ወጣን።
1ወደ መሬት በደኅና በደረስን ጊዜም፣ ደሴቲቱ ማልታ የምትባል መሆንዋን ዐወቅን።2የዚያች ደሴት ሰዎችም የተለመደውን ደግነት እንኳ አላሳዩንም፤ ሆኖም፣ በማያቋርጠው ዝናብና ብርድ ምክንያት እሳት አንድደው ሁላችንንም ተቀበሉን።3ነገር ግን ጳውሎስ ጭራሮ ሰብስቦ እሳቱ ላይ በጨመረው ጊዜ፣ ከሙቀቱ የተነሣ አንድ እፉኝት ወጣና በእጁ ላይ ተጣበቀ።4የደሴቲቱ ሰዎችም እፉኝቱ ከእጁ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ፣ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ሰው በእርግጥ ከባሕር ያመለጠ ነፍሰ ገዳይ ስለ ሆነ፣ ፍትሕ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ተባባሉ።5ጳውሎስ ግን እፉኝቱን በእሳቱ ላይ አራገፈው፤ አልተጐዳምም።6ሰዎቹም ሰውነቱ በትኵሳት ያብጣል ወይም በድንገት ይሞታል ብለው ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ተጠባብቀውት ምንም እንዳልደረሰበት ካዩ በኋላ፣ ዐሳባቸውን ለውጠው አምላክ ነው አሉ።7በአቅራቢያው ባለ አንድ ስፍራም ፑብልዮስ የተባለ የደሴቲቱ ገዢ መሬት ነበር፤ እርሱም ተቀብሎን ሦስት ቀን በደግነት አስተናገደን።8የፑብልዮስ አባት ትኵሳትና ተቅማጥ ይዞት ታሞ ነበር። ጳውሎስ ወደ እርሱ ሄዶ ጸለየ፤ እጆቹን ጫነበት፤ ፈወሰውም።9ይህ ከሆነ በኋላ፣ በደሴቲቱ የሚኖሩ ታመው የነበሩ ሌሎች ደግሞ መጡና ተፈወሱ።10ሰዎቹም እጅግ አከበሩን። ለመሄድ በምንዘጋጅበት ጊዜም፣ የሚያስፈልገንን ሰጡን።11ከሦስት ወር በኋላ፣ አፍንጫው ላይ የመንታ ወንድማማች ዓርማ በነበረበት፣ ክረምቱን በደሴቲቱ ባሳለፈ የእስክንድርያ መርከብ ላይ ተሳፍረን ጕዞ ጀመርን።12ወደ ሲራኩስ ከተማ ከደረስን በኋላም፣ እዚያ ሦስት ቀን ቈየን።13ከዚያም ተጕዘን ወደ ሬጊዩም ከተማ ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላ የደቡብ ነፋስ ተነሣ፤ በሁለት ቀንም ወደ ፑቲዮሉስ ከተማ መጣን።14እዚያም አንዳንድ ወንድሞችን አገኘንና ከእነርሱ ጋር ሰባት ቀን እንድንቈይ ተጋበዝን። በዚህ ዐይነት ወደ ሮም መጣን።15ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ከሰሙ በኋላ፣ ሊቀበሉን አፍዩስ ገበያና ሦስቱ ማደሪያዎች ድረስ መጡ። ጳውሎስ ወንድሞችን ባየ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ተጽናናም።16ወደ ሮም በገባን ጊዜ፣ ጳውሎስ ከሚጠብቀው ወታደር ጋር ብቻውን እንዲኖር ተፈቀደለት።17ቀን በኋላ፣ ጳውሎስ በአይሁድ መካከል መሪዎች የነበሩትን ሰዎች አንድ ላይ ጠራ። በተሰበሰቡ ጊዜም፣ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞች ሆይ፣ በሕዝቡ ወይም በአባቶች ሥርዓት ላይ የፈጸምሁት ስሕተት ባይኖርም እንኳ፣ ከኢየሩሳሌም በእስረኝነት ለሮማውያን እጅ ተላልፌ ተሰጠሁ።18እነርሱ ከመረመሩኝ በኋላ ለሞት የሚያበቃኝ ምክንያት ስላልነበረብኝ፣ በነጻ ሊለቁኝ ፈልገው ነበር።19ነገር ግን አይሁድ የሮማውያንን ፍላጎት ተቃውመው በተናገሩ ጊዜ፣ በሕዝቤ ላይ የማቀርበው ክስ ባይኖረኝም እንኳ፣ ወደ ቄሣር ይግባኝ ለማለት ተገደድሁ።20በዚህ ምክንያት፣ ላያችሁና ላነጋግራችሁ ልመና አቅርቤአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ በዚህ ሰንሰለት የታሰርሁት ለእስራኤል ስለ ተሰጠው እምነት ነው።”21ከዚያም እነርሱ እንዲህ አሉት፤ “ከይሁዳ ስለ አንተ ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ከወንድሞች መካከልም ስለ አንተ ያወራ ወይም ክፉ የተናገረ የለም።22ነገር ግን በሁሉም ስፍራ ተቃውሞ እየተወራበት መሆኑን እኛ ስለምናውቅ፣ ስለዚህ የሃይማኖት ወገን ምን እንደምታስብ ከአንተ መስማት እንፈልጋለን።”23ለጳውሎስ ቀን በቀጠሩለት ጊዜም፣ ብዙ ሰዎች ወደ መኖሪያ ቤቱ መጡ። እርሱም ጉዳዩን ገለጠላቸው፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም መሰከረላቸው። ከጠዋት እስከ ማታም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት እየጠቀሰ፣ ስለ ኢየሱስ ሊያሳምናቸው ጥረት አደረገ።24አንዳንዶች የተናገረውን ቃል ሲያምኑ፣ ሌሎች ግን አላመኑም።25እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ሲቀሩ፣ ጳውሎስ ይህን አንድ ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ ኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ በትክክል ተናገረ።26እንዲህም አለ፤ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና እንደዚህ በላቸው፤ ‘መስማትስ ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትስ ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አታደርጉም።27በዐይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ፣ በልባቸው እንዳያስተውሉ፣ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፣ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍኖአል።’28-29ስለዚህ፣ ይህ የእግዚአብሔር ድነት ወደ አሕዛብ እንደ ተላከ፣ እነርሱም እንደሚቀበሉት ዕወቁ።30ጳውሎስ በተከራየው በራሱ ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ኖረ፤ ወደ እርሱ የሚመጡትንም ሁሉ ይቀበል ነበር።31የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሰብክ፣ ያስተምርም ነበር። ይህንም ሲያደርግ ማንም አልከለከለውም።
1የእግዚአብሔርን ወንጌል በሐዋርያነት እንዲያገለግል ተለይቶ ከተጠራው ከኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከጳውሎስ።2ወንጌሉም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በነቢያቱ አስቀድሞ ተስፋ የሰጠው ነው።3ይህም ወንጌል በስጋ ከዳዊት ዘር ስለተወለደው ስለ ልጁ ነው።4እርሱም በቅድስና መንፈስ ኃይል ከሙታን በመነሳት የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ የተነገረለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር።5በስሙ ምክንያት ከእምነት የሚገኝ መታዘዝ በሕዝቦች ሁሉ መካከል እንዲሆን በእርሱ በኩል ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን።6እናንተም በእነዚህ ሕዝቦች መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን ተጠራችሁ።7ይህ መልዕክት የተጻፈው በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱስ ሕዝብ ለመሆን ለተጠራችሁ በሮም ላላችሁት ሁሉ ነው። ከእግዚአብሔር ከአባታችንና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።8ስለ እምነታችሁ በመላው ዓለም በመነገሩ ምክንያት አስቀድሜ ስለሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አምላኬን አመሰግናለሁ።9ባለማቋረጥ እንደማስባችሁ የልጁን ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።10አሁን በተቻለኝ መጠን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተሳክቶልኝ ወደ እናንተ እንድመጣ ሁልጊዜ በጸሎቴ እለምናለሁ።11የሚያበረታችሁን ጥቂት መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁ፥12ይኸውም የእኔና የእናንተ በሆነ የእርስ በርሳችን እምነት አማካይነት እንድንበረታታ ስለምጓጓ ነው።13ወንድሞች ሆይ፥ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ለመምጣት እንደ ሞከርኩኝና እስካሁን እንደተስተጓጎልኩኝ ሳታውቁ እንድትቀሩ አልፈልግም። ወደ እናንተ መምጣት የፈለግሁበት ምክንያት ከተቀሩት አሕዛብ እንዳገኘሁት ሁሉ ከእናንተ ደግሞ ጥቂት ፍሬ እንዳገኝ ነው።14ለግሪኮችና ግሪኮች ላልሆኑት፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉ ዕዳ አለብኝ።15ስለዚህ፥ በበኩሌ በሮም ለምትገኙት ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ለመስበክ ተዘጋጅቻለሁ።16በወንጌል አላፍርም! ምክንያቱም እርሱ አስቀድሞ ለአይሁድ ደግሞም ለግሪኮች የሚያምኑትን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ኃይል ስለሆነ ነው።17"ጻድቅ በእምነት ይኖራል" ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ በወንጌል ከእምነት ወደ እምነት ተገልጧልና።18በአመጻቸው እውነትን በሚያፍኑ አመጸኞችና ክፉዎች ሰዎች ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ከሰማይ ተገልጧል።19ይኽውም እግዚአብሔር ስላስታወቃቸው ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚገባው ነገር ለእነርሱ ግልጥ ነው።20የማይታዩት ገጽታዎቹ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ግልጥ ሆነው ይታያሉ። እነዚህም በተፈጠሩት ነገሮች አማካይነት ይታወቃሉ። ገጽታዎቹም የዘላለም ኃይሉና የመለኮት ባህርዩ ናቸው። በመሆኑም እነዚህ ሰዎች የሚያመካኙት አይኖራቸውም።21ምክንያቱም ስለ እግዚአብሔር ቢያውቁም እንደ እግዚአብሔርነቱ ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት ነው። ይልቁንም በሀሳባቸው ሞኞች ሆኑ፥ የማያስተውለው ልባቸውም ጨለመ።22ጥበበኞች ነን ቢሉም የማያስተውሉ ሆኑ።23የማይጠፋውን የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰው አምሳል፥በወፎች፥ አራት እግር ባላቸው አራዊትና በደረታቸው በሚሳቡ ፍጥረታት መልክ ለወጡ።24ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሰውነታቸውን እንዲያዋርዱ እግዚአብሔር ለልባቸው የክፋት ምኞት ለእርኩሰት አሳልፎ ሰጣቸው።25እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት የለወጡና በፈጣሪ ፈንታ ፍጥረትን ያመለኩና ያገለገሉ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም የተመሰገነ ነው።አሜን።26ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር ለአስነዋሪ ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፥ ሴቶቻቸውም ለተፈጥሮአቸው የሚገባውን ተግባር ተገቢ ባልሆነው ለወጡ።27እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለተፈጥሮአቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወተ-ሥጋ ምኞት ተቃጠሉ። እነዚህ ወንዶች የማይገባውን ነገር ከወንድ ጋር በማድረጋቸው ስለ ነውራቸው ቅጣትን የተቀበሉ ናቸው።28እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈቀዱ እነዚያን ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች እንዲያደርጉ ለማይረባ አዕምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።29እነርሱ በአመጻ ሁሉ፥ በጨካኝነት፥ በክፉ ምኞትና በምቀኝነት፥ በቅናት፥ በነፍስ መግደል፥ በጸብ፥ በማታለልና በክፉ ሃሳብ የተሞሉ ናቸው።30ሐሜተኞች፥ የሰው ስም አጥፊዎችና እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ቁጡዎች፥ ዕብሪተኞችና ትዕቢተኞች ናቸው። ክፉ ነገሮችን የሚያመነጩና ለወላጆቻችው የማይታዘዙ፥31ማስተዋል የሌላቸው፤ እምነት የማይጣልባቸው፥ ፍቅር የሌላቸውና የማይምሩ ናቸው።32እንደዚህ ያሉትን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት እንደሚገባቸው የሚናገረውን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ያውቃሉ፥እነርሱ ግን እነዚህኑ ነገሮች ራሳቸው የሚያደርጉ ብቻ ሳይሆኑ የሚያደርጉትን ሌሎችን የሚያበረታቱ ናቸው።
1ስለዚህ አንተ ሰው፥ አንተው ፈራጁ እነዚያኑ ነገሮች ስለምታደርግ በሌላው በምትፈርድበት ራስህን ትኮንናለህና የምታመካኘው የለህም።2ነገር ግን እነዚያን ነገሮች በሚያደርጉት ላይ ቁጣው በሚወርድባቸው ጊዜ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደሆነ እናውቃለን።3ነገር ግን አንተው ራስህ ያንኑ እያደረግህ እንደነዚያ ያሉትን በሚያደርጉት ላይ የምትፈርድ አንተ ሰው፥ይህንን አስተውል። ከእግዚአብሔር ፍርድ ታመልጣለህን?4ወይስ የቸርነቱን ባለጠግነት፥የቅጣቱን መዘግየትና ትዕግስቱን ታቃልላለህን? ቸርነቱ ወደ ንስሐ ሊመራህ እንደሆነ አታውቅምን?5ነገር ግን በፍርድ ቀን ያም የእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርድ በሚገለጥበት ጊዜ በድንዳኔህና ንስሐ በማይገባው ልብህ መጠን ለራስህ ቁጣን ታከማቻለህ።6እርሱ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል፤7በበጎ ተግባር በመጽናት ምስጋናን፥ክብርንና የማይጠፋውን ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል።8የራሳቸውን ጥቅም በሚፈልጉት፥ለአመጻ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙት ላይ ግን መቅሰፍትና ብርቱ ቁጣ ይመጣባቸዋል።9አስቀድሞ በአይሁዳዊ ቀጥሎም በግሪክ ሰው፥ክፋትን ባደረገ ነፍስ ሁሉ ላይ እግዚአብሔር መከራና ጭንቀትን ያመጣባቸዋል።10አስቀድሞ ለአይሁድ ቀጥሎም ለግሪክ መልካም ላደርጉ ሁሉ ግን ምስጋና፥ክብርና ሰላም ይሆንላቸዋል።11እግዚአብሔር ስለማያዳላ12ሕግ እያላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፥ሕግ ሳይኖራቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ደግሞ ያለ ሕግ ይጠፋሉ።13በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቁት ሕጉን የሚሰሙት ሳይሆኑ ሕጉን የሚያደርጉት ናቸው።14ሕግ የሌላቸው አሕዛብ በተፈጥሮአቸው የሕጉን ነገሮች በሚፈጽሙበት ጊዜ ሕግ ባይኖራቸውም እንኳ ለእነርሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸው።15በዚህም ሕጉ የሚጠይቃቸው ድርጊቶች በልቦናቸው መጻፋቸውን ያሳያሉ። ሃሳባቸው ሲከሳቸው ወይም ሲደግፋቸው ኅሊናቸው ደግሞ ለራሳቸውና16ለእግዚአብሔር ይመሰክራል። ይህም እኔ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደምሰብከው ወንጌል ሰዎች ሁሉ በስውር ስላደረጉት ነገር እግዚአብሔር በሚፈርድበት ቀን በዚያን ጊዜ ይሆናል።17በሕጉ በመመራትህ አይሁዳዊ ነኝ ትላለህ፥ በሕጉ ትደገፋለህ፥ በእግዚአብሔር በመመካት ደስ ትሰኛለህ፥18ፈቃዱን ታውቃለህ፥ ከእርሱ ውጪ የሆኑትን ነገሮች መርምረህ ትረዳ ይሆናል።19አንተ ራስህ የዕውሩ መሪ፥ በጨለማ ላሉት ብርሃን፥20የሰነፎች አስተማሪ፥ የሕጻናትም መምህር በመሆንህ በሕግ የእውቀትና የእውነት መልክ እንዳለህ ትታመን ይሆናል።21እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን?22አታመንዝር የምትል አንተ ታመነዝራለህን? ጣዖታትን የምትጸየፍ ቤተመቅደሶችን ትዘርፋለህን?23አንተ በሕጉ በመመካት የምትደሰተው ሰው ሕጉን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ትንቃለህን? ይህ ልክ "በእናንተ24ምክንያት በአሕዛብ መካከል የእግዚአብሔር ስም ይናቃል" ተብሎ እንደተጻፈው ነው።25ሕጉን ብትፈጽም በርግጥ መገረዝ ይጠቅማል፥ የሕጉ ተላላፊ ብትሆን ግን መገረዝህ እንደ አለመገረዝ ይሆናል።26እንግዲህ ያልተገረዘው ሰው የሕጉን ትዕዛዛት ቢጠብቅ አለመገረዙ እንደ መገረዝ አይቆጠርለትምን?27በፍጥረቱ ያልተገረዘው ሰው ሕጉን ቢፈጽም አይፈርድባችሁምን? ይህም እናንተ ቅዱሳት መጻሕፍትና መገረዝ እያላችሁ ሕጉን ተላለፊ ስለሆናችሁ ነው።28በውጫዊ ማንነቱ ብቻ አይሁዳዊ የሆነ እርሱ አይሁዳዊ አይደለም፥ የሥጋ ውጫዊ መገረዝ ብቻም መገረዝ አይደለም።29ነገር ግን በውስጣዊ ማንነቱ አይሁዳዊ የሆነ እርሱ አይሁዳዊ ነው፥ መገረዝም በፊደል ሳይሆን በመንፈስ በልብ የተደረገው ነው። እንዲህ ላለ ሰው ከሰዎች ሳይሆን ከእግዚአብሔር ምስጋና ይሆንለታል።
1እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድነው? የመገረዝስ ጥቅሙ ምንድነው?2በሁሉም አቅጣጫ ብልጫው ታላቅ ነው። አስቀድሞ ክእግዚአብሔር ዘንድ መገለጥ በአደራ የተሰጠው ለአይሁድ ነበር።3አንዳንድ አይሁድ ባያምኑስ? ያለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀረዋልን?4በምንም ዓይነት አያስቀረውም፤ ይልቁንም ሰው ሁሉ ውሸተኛ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔር እውነተኛ ነው። "በቃልህ ጸድቅ ሆነህ ትገኝ ዘንድ፥ ወደ ፍርድ በመጣህ ጊዜም ትረታ ዘንድ" ተብሎ ተጽፏልና።5የእኛ አመጻ የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያሳይ ከሆነ ግን ምን ማለት እንችላለን? እግዚአብሔር ቁጣውን በሚያመጣበት ጊዜ አመጸኛ አይደለም፥ ነወይ? ። ይህንን የምለው እንደ ሰው አስተሳሰብ ነው።6በፍጹም አይደለም። እንዲህ ከሆነማ እግዚአብሔር እንዴት በዓለም ላይ ይፈርዳል?7ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነት በእኔ ውሸት አማካይነት ለእርሱ ብዙ ምስጋና ካመጣ ለምን አሁንም እንደ ኃጢአተኛ ይፈረድብኛል?8"መልካም እንዲመጣ ክፉን እናድርግ" ስለማለታችን በሐሰት እንዳስወሩብንና አንዳንዶችም እንዳመኑት ታዲያ ለምን አንልም? የሚደርስባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው።9እንግዲህ ምን ይሁን? በዚህ ጉዳይ ራሳችንን ነጻ እያደረግን ነውን? በጭራሽ። አይሁድና ግሪኮች ሁሉም ከኃጢአት በታች ስለመሆናቸው አስቀድመን ወንጅለናቸዋልና።10እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ "አንድም እንኳን ጻድቅ የለም።11አንድ እንኳን የሚያስተውል የለም። እግዚአብሔርን የሚፈልግ አንድም የለም።12ሁሉም ተሳስተዋል። በአንድ ላይ የማይጠቅሙ ሆነዋል። መልካም የሚያደርግ የለም፥አንድም እንኳን የለም።13ጉሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው። ምላሳቸው አታሏል። የእባብ መርዝ በከንፈሮቻቸው ሥር አለ።14አፋቸው እርግማንና መራራነትን ተሞልቷል።15እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው።16በመንገዶቻቸው ላይ ጥፋትና መከራ አለ።17እነዚህ ሰዎች የሰላምን መንገድ አላወቁትም።18በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።"19ሕጉ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሆነ እናውቃለን። ይህም አፍ ሁሉ እንዲዘጋና መላው ዓለም ለእግዚአብሔር መልስ እንዲሰጥ ነው።20ይህ የሆነበት ምክንያት ሥጋን የለበሰ ሁሉ ሕግን በመፈጸም በእግዚአብሔር ዓይን ስለማይጸድቅ ነው። ኃጢአት የሚታወቀው በሕግ አማካይነት ነውና።21አሁን ግን የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጧል። ልዩነት ሳይደረግ22በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ ይሆንላቸው ዘንድ በሕግና በነቢያት የተመሰከረ ነው።23ሁሉም ኃጢአትን ሠርተዋል፥ከእግዚአብሔር ክብርም ጎድለዋል።24በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በተደረገው ቤዛነት በነጻ በጸጋው ይጸድቃሉ።25በደሙ በማመን የኃጢአት ማስተሰሪያ ይገኝ ዘንድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጥቷልና። በትዕግስቱ የቀደመውን ኃጢአት ስለመተዉ ለጽድቁ ማረጋገጫ እንዲሆን ክርስቶስን መስዋዕት አድርጎ26አቀረበው። በዚህ በአሁኑ ዘመን የእርሱ ጽድቅ እንዲታይ ይህ ሁሉ ሆነ። እንዲህም የሆነው እርሱ ጻድቅ መሆኑንና በኢየሱስ የሚያምነውን ሁሉ የሚያጸድቅ ራሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።27እንግዲህ ትምክህት ወዴት አለ? እርሱ ተወግዷል። ምን ላይ ተመሥርቶ? በሥራ ላይ ነውን? አይደለም፥በእምነት ላይ እንጂ።28ስለዚህ ማንኛውም ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት ይጸድቃል እንላለን።29ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ አምላክ ብቻ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? አዎን፥የአሕዛብም ደግሞ ነው።30እግዚአብሔር አንድ ከሆነ የተገረዙትንም ሆነ ያልተገረዙትን ስለ እምነታቸው ያጸድቃቸዋል።31እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? እንዲህስ አይሁን። ይልቁንም ሕግን እናጸናለን።
1እንግዲህ በስጋ አባታችን የሆነው አብርሃም ምን አገኘ እንበል?2አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን ኖሮ ለመመካት ምክንያት በኖረው ነበር፥ትምክህቱ ግን በእግዚአብሔር ፊት አይደለም።3ቅዱሱ መጽሐፍ ምን ይላል? "አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፥ይህም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት" ይላል።4ለሚሠራ ሰው ደሞዙ እንደ ተገቢ መብቱ እንጂ እንደ ነጻ ስጦታ አይቆጠርለትም።5ነገር ግን ለማይሠራ ይልቁንም ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ለእርሱ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።6ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን በሚቆጥርለት ሰው ላይ በረከትን ይናገራል።7እርሱም፤ "መተላለፋቸው የተተወላቸው፥ ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው እነርሱ የተባረኩ ናቸው።8ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ያ ሰው የተባረከ ነው።" ብሏል።9እንግዲህ ይህ በረከት የተነገረው በተገረዙት ላይ ብቻ ነው ወይስ ደግሞ ባልተገረዙትም ላይ? "ለአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት" እንላለን።10ታዲያ እንዴት ነበር የተቆጠረለት? አብርሃም ከመገረዙ በፊት ወይስ በኋላ? ከመገረዙ በፊት እንጂ ከተገረዘ በኋላ አልነበረም።11አብርሃም የመገረዝን ምልክት ተቀበለ። ይህም ከመገረዙ በፊት አስቀድሞ በእምነት ላገኘው ጽድቅ ማኅተም ነበር። የዚህ ምልክት ውጤት ምንም እንኳን ባይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት መሆኑ ነው። ይኸውም ጽድቅ ይቆጠርላቸዋል ማለት ነው።12በተጨማሪም ይህ ማለት አብርሃም አባት የሆነው በመገረዝ በኩል ለሚመጡት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የአባታችን የአብርሃምን ምሳሌነት ለሚከተሉትም ነው። ይህም ሳይገረዝ በፊት በነበረው እምነት ነው።13ዓለምን የሚወርሱበት ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው ይህ ተስፋ በሕግ በኩል የተሰጠ አልነበረም። ይልቅ ይህ በእምነት በኩል የተገኘ ጽድቅ ነበር።14በሕግ በኩል የሆኑት ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኗል፥ተስፋም ባዶ ሆኗል ማለት ነው።15ሕግ ቁጣን ያመጣልና ሕግ ከሌለ አለመታዘዝም የለም።16በዚህ ምክንያት በጸጋ ይሆን ዘንድ ይህ የሚደረገው በእምነት ነው። በመሆኑም ተስፋው ለዘሩ ሁሉ የተረጋገጠ ነው። ይህ ዘር ሕጉን የሚያውቁትን ብቻ ሳይሆን ደግሞም እንደ አብርሃም የሚያምኑትን ያካትታል።17"ለሕዝቦች ሁሉ አባት አድርጌሃለሁ" ተብሎ ስለተጻፈ እርሱ የሁላችንም አባት ነው። አብርሃም ለሙታን ሕይወትን በሚሰጥና የሌሉትን ነገሮች ወደ መኖር በሚጠራ በታመነበት በእግዚአብሔር ፊት ነበረ።18ውጫዊ ሁኔታዎች ሁሉ ተስፋ ሰጪዎች ባይሆኑም አብርሃም ስለ ወደፊቱ ሳይጠራጠር በእግዚአብሔር ታመነ። እንዲሁም "ዘርህ እንዲህ ይበዛል" ተብሎ እንደተነገረለት የብዙ ሕዝብ አባት ሆነ።19በእምነት ደካማ አልነበረም። አብርሃም በመቶ አመቱ ገደማ የራሱን ሰውነትና የሣራም ማህጸን ምውት መሆኑን ተገነዘበ።20ነገር ግን አብርሃም ከእግዚአብሔር ተስፋ የተነሣ በእምነት ዕጦት አላመነታም። ከዚህ ይልቅ በእምነት በረታ፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋናን ሰጠ።21እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ሊፈጽመው ደግሞ እንደሚችል በጥብቅ ተረዳ።22ስለዚህ ይህም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።23ተቆጠረለት የባለው ለእርሱ ጥቅም ብቻ የተጻፈ አይደለም።24ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛም ደግሞ ይቆጠርልን ዘንድ ተጽፏል።25እርሱም ስለ መተላለፋችን ተላልፎ የተሰጠውና እኛን ለማጽደቅ ከሙታን የተነሣው ነው።
1በእምነት ስለ ጸደቅን በጌታችን በኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን።2እኛም ደግሞ በእርሱ በኩል አሁን ወደቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መቅረብ አለን። በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ስለወደፊቱ በሰጠን ተስፋ በመተማመን ደስ ይለናል።3ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን በመከራዎቻችን ደግሞ ደስ ይለናል። መከራ መጽናትን እንደሚያደርግ እናውቃለን።4መጽናት ተቀባይነትን፥ ተቀባይነትም ስለ ወደፊቱ መተማመኛን ያስገኛል።5በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር ወደ ልባችን ውስጥ ስለፈሰሰ ይህ ተስፋ ሐዘን የለበትም።6ክርስቶስ በትክክለኛው ጊዜ ለኃጢአተኞች የሞተው እኛ ገና ደካሞች እያለን ነበር።7ስለ ጻድቅ ሰው የሚሞት ከስንት አንዱ ነው። ይህም ማለት ስለ ደግ ሰው ለመሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።8ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች እያለን ክርስቶስ ስለ እኛ መሞቱ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያረጋግጣል።9እንግዲህ አሁን በደሙ ስለ ጸደቅን ይበልጡኑ በእርሱ ከእግዚአብሔር ቁጣ እንድናለን።10ጠላቶች እያለን በልጁ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን።11ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን ይህንን ዕርቅ ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እኛ ደግሞ በእግዚአብሔር ደስ ይለናል።12ስለዚህ በአንድ ሰው አማካይነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፥እንደዚሁም ሞት በኃጢአት አማካይነት ገባ። ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ወደ ሰው ሁሉ ደረሰ።13ሕግ እስኪመጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረ፥ነገር ግን ሕግ በሌለበት ኃጢአት አይቆጠርም።14ይሁንና ሊመጣ ላለው ምሳሌ የሆነው የአዳምን አይነት ያለመታዘዝ ኃጢአት ባላደረጉት ላይ እንኳን ሳይቀር ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ።15ነጻ ስጦታው ግን እንደ መተላለፉ አይደለም። በአንዱ መተላለፍ ብዙዎች ከሞቱ የእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በኩል የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።16ስጦታው እንደተሰራው ኃጢአት ውጤት አይደለም። በአንድ ወገን በአንዱ ሰው መተላለፍ ምክንያት የኩነኔ ፍርድ መጣ። በሌላ ወገን ግን ጽድቅን የሚያስገኘው ነጻ ስጦታው ከብዙ መተላለፍ በኋላ መጣ።17በአንዱ ሰው መተላለፍ ሞት በእርሱ በኩል ከነገሠ የጸጋን ብዛትና በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት በኩል የጽድቅን ስጦታ የተቀበሉት አብልጠው ይነግሳሉ።18እንግዲህ በአንዱ መተላለፍ በኩል ሰዎች ሁሉ ወደ ኩነኔ እንደመጡ እንዲሁ በአንዱ የጽድቅ ሥራ ለሰዎች ሁሉ የሕይወት መጽደቅ መጣ።19በአንድ ሰው አለመታዘዝ በኩል ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደሆኑ እንዲሁ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።20ነገር ግን ሕግ ከጎን በመግባቱ መተላለፍ በዛ። ይሁን እንጂ ኃጢአት በበዛበት በዚያ ጸጋ ይበልጡኑ በዛ።21ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘላለም ሕይወት ጸጋው በጽድቅ አብልጦ እንዲነግሥ ይህ ሆነ።
1-3እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ውስጥ መኖራችንን እንቀጥልን? እንዲህ አይሁን። ለኃጢአት የሞትን እኛ እንዴት በእርሱ ውስጥ መኖር እንቀጥላለን? ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የተጠመቁ ሁሉ ወደ ከሞቱ ጋር ለመተባበር እንደተጠመቁ አታውቁምን?4እንግዲህ ከሞቱ ጋር ለመተባበር በጥምቀት አማካይነት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል። ይህም የሆነው ልክ ክርስቶስ በአብ ኃይል ከሙታን እንደ ተነሣ እኛ ደግሞ በታደሰ ሕይወት እንድንመላለስ ነው።5ሞቱን በሚመስለው ከእርሱ ጋር ከተባበርን ከትንሣኤው ጋር ደግሞ እንተባበራለን።6የኃጢአት ሰውነት ይጠፋ ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ ይህንን እናውቃለን። ይህም የሆነው ከዚህ በኋላ ለኃጢአት እንዳንገዛ ነው።7ከኃጢአት አኳያ ሲታይ የሞተ ሰው መጽደቁ ታውጆለታል።8ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር አብረን እንደምንኖር ደግሞ እናምናለን።9ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣና ሞቶ እንዳልቀረ እናውቃለን። ከዚህ በኋላ ሞት አይገዛውም።10ስለኃጢአት የሞተው ሞት ለዘላለም የሚሠራ የአንድ ጊዜ ሞት ነው። ይሁንና የሚኖረውን ሕይወት ለእግዚአብሔር ይኖራል።11ልክ እንደዚሁ እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደሞታችሁ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር እንደምትኖሩ መቁጠር ይገባችኋል።12ስለዚህ ለክፉ ምኞቱ እንድትታዘዙ በሚፈልግ የሚሞት ሥጋችሁ ላይ ኃጢአት እንዲነግሥ አትፍቀዱለት።13ከሙታን ሕያው እንደመሆናችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የሰውነት ክፍሎቻችሁን የአመጻ መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ። የሰውነት ክፍሎቻችሁን ለእግዚአብሔር የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ አቅርቡ።14ኃጢአት እንዲገዛችሁ አትፍቀዱለት። ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።15እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ባለመሆናችን ኃጢአት መሥራት አለብን? ከቶ እንዲህ አይሁን።16ትታዘዙት ዘንድ ራሳችሁን እንደ አገልጋይ ለምታቀርቡለት ለእርሱ አገልጋዮች እንደሆናችሁ አታውቁምን? ወደ ሞት የሚመራችሁ የኃጢአት አገልጋዮች ወይም ወደ ጽድቅ የሚመራችሁ የመታዘዝ አገልጋዮች ናችሁ።17ቀድሞ የኃጢአት አገልጋዮች ነበራችሁ፥ ነገር ግን ለተሰጣችሁ ትምህርት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!18ከኃጢአት ነጻ ተደርጋችኋል፥የጽድቅም አገልጋዮች ሆናችኋል።19በሥጋችሁ ድካም ምክንያት እንደ ሰው ልማድ እናገራለሁ። ልክ የሰውነታችሁን ክፍሎች ለእርኩሰትና ለክፋት እንደ ባሪያ አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ እንደዚያው አሁን የሰውነት ክፍሎቻችሁ ሊቀደሱ የጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ።20የኃጢአት ባሪያዎች በነበራችሁበት ጊዜ ከጽድቅ ውጪ ነበራችሁ።21አሁን በምታፍሩባቸው በእነዚያ ነገሮች ያን ጊዜ ምን ተጠቀማችሁባቸው? ምክንያቱም የእነዚያ ነገሮች ውጤት ሞት ነው።22አሁን ግን ከኃጢአት ነጻ ስለተደረጋችሁና ለእግዚአብሔር ባሪያዎች ስለሆናችሁ ለመቀደስ ፍሬ ታፈራላችሁ። ውጤቱም የዘላለም ሕይወት ነው።23የኃጢአት ደሞዝ ሞት ሲሆን የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የዘላለም ሕይወት ነው።
1ወንድሞች ሆይ፥ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ሕግ እንደሚገዛው አታውቁምን? ይህንን የምለው ስለ ሕግ ለሚያውቁት ነው።2ያገባች ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ ለእርሱ በሕግ የታሰረች ነች፥ባሏ ቢሞት ግን ከጋብቻ ሕግ ነጻ ትሆናለች።3እንግዲህ ባሏ በሕይወት እያለ ከሌላ ወንድ ጋር ብትኖር አመንዝራ ትባላለች። ባሏ ቢሞት ግን ከሕጉ ነጻ ስለሆነች ከሌላ ወንድ ጋር ብትኖርም አመንዝራ አትሆንም።4ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፥እናንተም በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ምውት ተደርጋችኋል። ይኸውም ለእግዚአብሔር ፍሬ እናፈራ ዘንድ ከሌላው ማለትም ከሙታን ከተነሣው ጋር እንድትተባበሩ ነው።5በሥጋ በነበርንበት ጊዜ ኃጢአታዊ ምኞት በሕግ በኩል ሞትን ሊያፈራ በሰውነታችን ክፍሎች ይሠራ ነበር።6አሁን ግን ከሕግ ነጻ ተደርገናል። ተይዘን ለነበርንበት ለዚያ ሞተናል።ይኸውም በአሮጌው ፊደል ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ እንድናገለግል ነው።7እንግዲህ ምን እንላለን? ሕጉ ራሱ ኃጢአት ነውን? አይደለም። ይሁንና በሕግ በኩል ባይሆን ኖሮ ኃጢአትን አላውቅም ነበር። ሕጉ "አትጎምጅ" ባይል ኖሮ መጎምጀትን አላውቅም ነበር።8ነገር ግን ኃጢአት በትዕዛዛት አማካይነት ዕድል አገኘና መጎምጀትን ሁሉ በውስጤ አመጣ። ምክንያቱም ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ስለሆነ ነው።9በአንድ ወቅት ያለ ሕግ ሕያው ነበርኩ፥ትዕዛዝ በመጣ ጊዜ ግን እኔ ሞትኩኝና ኃጢአት ህያው ሆነ።10ሕይወትን እንዲያመጣ የተሰጠው ትዕዛዝ ለእኔ ሞት ሆነ።11ምክንያቱም ኃጢአት በሕግ አማካይነት ዕድል አግኝቶ አታሎኛል። በትዕዛዝ አማካይነትም ገደለኝ።12በመሆኑም ሕጉ ቅዱስ ነው፥ትዕዛዙም ቅዱስ፥ጻድቅና በጎ ነው።13ስለዚህ በጎ የሆነው እርሱ ለእኔ ሞት ሆነብኝን? አይደለም። ነገር ግን ኃጢአት በጎ በሆነው በእርሱ አማካይነት ኃጢአትነቱ ይታወቅ ዘንድ በእኔ ሞትን አመጣብኝ። ይህ የሆነው በሕግ አማካይነት ኃጢአት ያለ ልክ ኃጢአታዊ ይሆን ዘንድ ነው።14ሕጉ መንፈሳዊ መሆኑን እናውቃለንና እኔ ግን ሥጋዊ ነኝ። ለኃጢአት ባርነት ተሽጫለሁ።15በርግጥ የማደርገውን አላውቅም። ለማድረግ የምፈልገውን አላደርግም፥ለማድረግ የምጠላውን ግን ያንኑ አደርጋለሁ።16ለማድረግ የማልፈልገውን የማደርግ ከሆንሁ ሕጉ መልካም ስለመሆኑ እስማማበታለሁ።17አሁን ግን ያንን የሚያደርገው በእኔ የሚኖረው ኃጢአት ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።18በእኔ ማለትም በሥጋዬ ውስጥ ምንም መልካም ነገር እንደሌለ አውቃለሁ። መልካም የማድረግ ፍላጎቱ አለኝ፥ነገር ግን ላደርገው አልችልም።19የምፈልገውን ያንን መልካሙን አላደርግም ክፉውን፥ያንን የማልፈልገውን ግን አደርጋለሁ።20ለማድረግ የማልፈልገውን የማደርግ ከሆነ እንግዲህ አሁን ያንን የሚያደርገው በእኔ ውስጥ የሚኖረው ኃጢአት እንጂ እኔ አይደለሁም።21እንግዲህ መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚፈልግ ሕግ በውስጤ እንዳለ አያለሁ፥ነገር ግን በተግባር በውስጤ ያለው ክፋት ሆኖ አገኘዋለሁ።22በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል።23ነገር ግን በሰውነቴ ክፍሎች ውስጥ ሌላ ሕግ አያለሁ። እርሱም በአዕምሮዬ ውስጥ ያለውን አዲሱን ሕግ በመቃወም ይዋጋል። በሰውነት ክፍሎቼ ውስጥ ባለ የኃጢአት ሕግ ይማርከኛል።24እኔ ምስኪን ሰው ነኝ! ለሞት ከሚዳርገኝ ከዚህ ሰውነት ማን ይታደገኛል?25እንግዲያውስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እኔ ራሴ በአእምሮዬ የእግዚአብሔርን ሕግ አገለግላለሁ። ሆኖም በሥጋ የማገለግለው የኃጢአትን ሕግ ነው።
1ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።2ምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶኛል።3በሥጋ ድካም ምክንያት ሕግ ሊፈጽመው ያልተቻለውን እግዚአብሔር ፈጽሞታል። እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአታዊ ሥጋ ምሳሌ ለኃጢአት መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ልኮ ኃጢአትን በሥጋው ኮነነ።4ይህንንም ያደረገው እንደ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕጉ ትዕዛዛት ይፈጸሙ ዘንድ ነው።5እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ ስለሥጋዊ ነገሮች ያስባሉ፥እንደ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን ስለመንፈስ ቅዱስ ነገሮች ያስባሉ።6የሥጋ አስተሳሰብ ሞት ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ አስተሳሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።7ይህ የሆነበት ምክንያት የሥጋ አስተሳሰብ ለእግዚአብሔር ሕግ ስለማይገዛ፥መገዛትም ስለማይችል የእግዚአብሔር ጠላት በመሆኑ ነው።8በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ለማስደሰት አይችሉም።9ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ውስጥ መኖሩ እውነት ከሆነ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። ነገር ግን የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ማንም ቢሆን ይህ የእርሱ ወገን አይደለም።10ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢኖር ሥጋ በኃጢአት ምክንያት ምውት ነው፥ መንፈስ ግን በጽድቅ ምክንያት ህያው ነው።11ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ ቢኖር ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በውስጣችሁ በሚኖረው በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።12ስለዚህ ወንድሞች ሆይ ዕዳ አለብን፥ነገር ግን እንደ ሥጋ ፈቃድ ልንኖር ለሥጋ አይደለም።13እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ መሞታችሁ አይቀርም፥የሥጋን ሥራ በመንፈስ ቅዱስ ብትገድሉ ግን በሕይወት ትኖራላችሁ።14በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።15ተመልሳችሁ እንድትፈሩ የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም። ይልቅ የተቀበላችሁት "አባ፥አባት" ብለን የምንጮህበትን የልጅነትን መንፈስ ነው።16የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ቅዱስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።17ልጆች ከሆንን ወራሾችም ነን፥ማለትም የእግዚአብሔር ወራሾች ነን። ከእርሱ ጋር እንድንከብር በርግጥ አብረነው ደግሞ መከራን ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን የምንወርስ ነን።18የአሁኑ ዘመን መከራ ሊገለጥልን ካለው ክብር ጋር ሊነጻጸር እንደማይገባው አስባለሁ።19ምክንያቱም ፍጥረት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት ስለሚጠባበቅ ነው።20ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቷልና ይህም ባስገዛው ፈቃድ እንጂ በራሱ ፈቃድ አይደለም። አስተማማኙ ተስፋም21ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ልጆች የክብር ነጻነት ይደርስ ዘንድ ነው።22አሁን እንኳን መላው ፍጥረት አብሮ በመቃተትና በምጥ ጣር ላይ መሆኑን እናውቃለን።23ይህም ብቻ አይደለም፥ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ የመጀመሪያው ፍሬ ያለን እኛ፥የሰውነታችን ቤዛ የሚሆነውን ልጅነታችንን እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን እንኳን በውስጣችን እንቃትታለን።24የዳንነው በዚህ ተስፋ ነው። ነገር ግን ተስፋ የምናደርገው የማይታየውን ነው፥የሚያየውንማ ማን በተስፋ ይጠባበቃል?25ገና ያላየነውን ተስፋ የምናደርግ ከሆነ ግን እንግዲያው በትዕግስት እንጠባበቀዋለን።26እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በድካማችን ውስጥ ያግዘናል። እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ስለማናውቅ መንፈስ ቅዱስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይቻል መቃተት ስለ እኛ ይማልድልናል።27መንፈስ ቅዱስ ስለ አማኞች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለሚማልድ ልብን የሚመረምረው እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን ሃሳብ ያውቃል።28እግዚአብሔርን ለሚወዱት፥ በዓላማው ለተጠሩት ለእነርሱ ሁሉን ነገር አጣጥሞ ለመልካም እንደሚሠራላቸው እናውቃለን።29ምክንያቱም አስቀድሞ ያወቃቸውን እነርሱን በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወሰነ።30አስቀድሞ የወሰናቸውን ደግሞ ጠራቸው። የጠራቸውን ደግሞ አጸደቃቸው። ያጸደቃቸውን ደግሞ አከበራቸው።31እንግዲህ ስለእነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?32ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ እንዴት ሁሉን ነገር ደግሞ ከልጁ ጋር በነጻ አይሰጠንም?33እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይኮንናቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው።34የሚኮንንስ ማነው? ስለ እኛ የሞተው፥ ይልቁንም ደግሞ ከሞት የተነሣው ክርስቶስ ነው። እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር በክብር ሥፍራ ይገዛል፥ስለ እኛም እየማለደልን ያለው እርሱ ነው።35ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ወይስ ጭንቀት ወይስ ስደት ወይስ ራብ ወይስ ራቁትነት ወይስ አደጋ ወይስ ሰይፍ ይለየናልን?36"ቀኑን ሙሉ ስለአንተ ብለን እንገደላለን። እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን" ተብሎ እንደተጻፈው ነው።37በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ውስጥ በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።38ሞት ቢሆን ሕይወት፥ መላእክት ቢሆኑ መንግሥታት፥አሁን ያሉት ነገሮች ወይም ሊመጡ ያሉት ቢሆኑ፥ ኃይላት ቢሆኑ፥39ከፍታም ቢሆን ዝቅታ፥ የትኛውም ሌላ ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየኝ እንደማይችል ተረድቻለሁ።
1በክርስቶስ እውነትን እናገራለሁ እንጂ አልዋሽም፣ ህሊናዬ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሆኖ ይመሰክርልኛል፣2ከፍተኛ ሀዘንና የማያቋርጥ ህመም በልቤ ውስጥ አለ።3በሥጋ ዘሮቼ ስለሆኑት ወንድሞቼ ሲባል እኔ እራሴ በተረገምኩና ከክርስቶስ በተለየሁ ብዬ እመኛለሁ።4እነርሱ እስራኤላውያን ናቸው። የልጅነት መብት ፥ክብሩ፥ቃል ኪዳኑ፥የህግ ስጦታው፥የአምልኮ ሥርዓቱ፥ የተስፋው ቃል አላቸው።5ከሁሉ በላይና ለዘላለም የእግዚአብሔር ብሩክ የሆነው ክርስቶስ በሥጋ የመጣው ከአባቶቻቸው ነው። ለእርሱ ለዘላለም ምስጋና ይሁን። አሜን!6ነገር ግን የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ተሻረ ማለት አይደለም። ምክንያቱም በእስራኤል የሚኖር ሁሉ እስራኤላዊ አይደለም።7ወይም የአብርሀም ዘር ሁሉ የአብርሀም ልጆች አይደሉም። ነገር ግን «ዘርህ በይስሀቅ ይጠራልሀል» ተባለ።8ይህም ማለት የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም። የተስፋው ቃል ልጆች ግን ዘሮቹ ሆነው ተቆጠሩ።9የተስፋው ቃል «በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ ለሳራም ልጅ ይሰጣታል» የሚል ነው።10ይህ ብቻ አይደለም፣ ርብቃ ከአባታችን ከይስሀቅ11ከጸነሰች በኋላ በምርጫ የሆነው የእግዚአብሔር ዓላማ ከሥራ የተነሳ ሳይሆን ከእርሱ ጥሪ የተነሳ ይጸና ዘንድ ልጆቹ ገና ሳይወለዱና ክፉም ሆነ ደግ ሳያደርጉ12«ታላቁ ለታናሹ ይገዛል» ተብሎ ተነግሯት ነበር።13ልክ «ያዕቆብን ወደድኩ ኤሳውን ጠላሁ» ተብሎ እንደተጻፈው ማለት ነው።14እንግዲህ ምን እንላለን? በእግዚአብሔር ዘንድ የጽድቅ መጓደል አለ ማለት ነው? በጭራሽ አይደለም።15ምክንያቱም ለሙሴ «የምምረውን እምራለሁ ለምራራለትም እራራለሁ» ብሎታል።16ስለዚህም ምህረት ለፈለገ ወይም ለሮጠ ሳይሆን ምህረትን ከሚያሳይ ከእግዚአብሔር ነው።17ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ስለፈርዖን ሲናገር «ኃይሌን በአንተ ላይ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይታወቅ ዘንድ ለዚህ ዋና ዓላማ አስነሳሁህ» ይላል።18ስለዚህም ከፈለገ ለአንዱ ምህረትን ይሰጠዋል ሌላውን ደግሞ ግትር ያደርገዋል።19«ታዲያ ሁልጊዜ ፈቃዱን የሚያደርግ ከሆነ ለምን ስህተትን ይፈልግብናል?» ትሉኝ ይሆናል።20በአንጻሩ ለእግዚአሔር መልስ የምትስጥ አንተ ማን ነህ? የሸክላ ጭቃ ቅርጽ ያወጣለትን ሰው ለምን እንደዚህ አድርገህ ሰራኽኝ ሊለው ይችላልን? ።21ሸክላ ሰሪው ከዚያው ጭቃ አንዱን ለየት ባለ ቀን አገልግሎት ላይ የሚውል ዕቃ ሌላውን ደግሞ በየቀኑ አገልግሎት የሚሰጥ ዕቃ አድርጎ ሊሰራው በሸክላ ጭቃው ላይ ሥልጣን የለውም እንዴ?22ቁጣውን ሊያሳይና ኃይሉ እንዲታወቅ የሚፈልገው እግዚአብሔር ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎችአብዝቶ ሊታገሳቸው ቢፈልገስ?23ይህን ያደረገው አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው የምህረት ዕቃዎቹ ላይ ክብሩን ሊያሳይ ቢሆንስ?24ይህንን ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ከአህዛብ ለተጠራን ለእኛም ቢያደርገውስ?25በትንቢት ሆሴዕም ላይ «ህዝቤ ያልሆነውን ህዝቤ ብዬ ያልተወደደችውንም የተወደደች ብዬ እጠራለሁ።26'ህዝቤ አይደላችሁም በተባሉበት በዚያው ቦታ 'የህያው እግዚአብሔር ልጆች' ይባላሉ» እንደሚለው ነው።27ኢሳያስ ስለእስራኤል «የእስራኤል ልጆች ብዛት እንደ ባህር አሸዋ ቢሆን እንኳ የሚድኑት ግን ትሩፋን ናቸው» ብሎ ይጮኸል።28ምክንያቱም እግዚአብሔር ቃሉን በምድር ላይ ሙሉ በሙሉ ፈጥኖ ይፈጽማል።29ይህም ኢሳያስ ቀደም ሲል «የሠራዊት ጌታ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ እንድ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በሆነብን ነበር» እንዳለው ነው።30እንግዲህ ምን እንላለን? ለጽድቅ ያልሮጡት አህዛብ በእምነት የሆነውን ጽድቅ አገኙ።31ለጽድቅ ህግ የተጉት እስራኤል ግን ወደዚያ ሊደርሱ አልቻሉም።32ለምን አልደረሱም? ምክንያቱም ጽድቅን የፈለጉት በእምነት ሳይሆን በሥራ ስለሆነ ነው። በማሰናከያው ድንጋይ ተሰናከሉበት።33«በጽዮን የማሰናከያ ድንጋይና የዕንቅፋት ዐለት አስቀምጣለሁ በእርሱ የሚያምን አያፍርም» ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
1ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ስለእነርሱ ለእግዚአብሔር የማቀርበው ልመና እንዲድኑ ነው።2በእውቀት የሆነ ባይሆንም ለእግዚአብሔር እንደሚቀኑ እኔ ራሴ ስለእነርሱ እመሰክራለሁ።3የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁምና የራሳቸውን ጽድቅ ሊመሰርቱ ይጥራሉ፤ለእግዚአብሔርም ጽድቅ ራሳቸውን አያስገዙም።4ምክንያቱም ክርስቶስ ለሚያምን ሁሉ ለጽድቅ የሚሆን የህግ ፍጻሜ ነው።5ሙሴ ከህግ ስለሚመጣ ጽድቅ ሲናገር «ከህጉ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርግ በዚያው ጽድቅ ይኖራል።» ይላልና።6በእምነት ስለሚሆን ጽድቅ ግን «በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል አትበል (ይህ ክርስቶስን ማውረድ ነውና)7ወይም ወደ ሲዖል ማን ይወርዳል አትበል (ይህ ክርስቶስን ከሙታን መካከል ማውጣት ነውና)።» ይላል።8ነገር ግን ቃሉ ምን ይላል? «ቃሉ ለአፍህና ለልብህ ቅርብ ነው።» ይላል። የምንሰብከው የእምነት ቃል ይህ ነው።9ስለዚህም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ።10ምክንያቱም ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል በአፉ መስክሮ ደግሞ ይድናል።11ምክንያቱም መጽሀፍ እንደሚል «በእርሱ የሚያምን አያፍርም» ።12በዚህ ጉዳይ በአይሁድና በግሪክ ልዩነት የለም። ያው አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና ለሚጠሩትም ሁሉ ባለጠጋ ነው።13የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።14ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት ይጠሩታል? ስለእርሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምኑበታል?15ያለ ሰባኪስ ከየት ይሰማሉ? «በመልካም ነገር የተሞላ ደስታን የሚሰብኩ እግሮች እንዴት ያማሩ ናቸው» ተብሎ እንድተጻፈ፣ ሳይላኩስ እንዴት ይሰብካሉ?16ነገር ግን ኢሳያስ «ጌታ ሆይ መልዕክታችንን ማን አምኗል» እንዳለው ሁሉም ወንጌልን አልተቀበሉም።17ስለዚህ እምነት የሚመጣው ከመስማት ሲሆን መሰማት ያለበትም የክርስቶስ ቃል ነው።18ነገር ግን «አልሰሙ ይሆንን?» እላለሁ። በሙሉ እርግጠኝነት ሰምተዋል።«ድምጻቸው በምድር ሁሉ ላይ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደርሷል።»19በተጨማሪም «እስራኤል አያውቁምን?» እላለሁ። ሙሴ አስቀድሞ «ህዝብ ባልሆነ በእሱ በቅናት አነሳሳችኋለሁ። በማያስተውልም ህዝብ በቁጣ አናውጣችኋለሁ» ይላል።20ደግሞም ኢሳያስ በድፍረት «ላልፈለጉኝ ተገኘሁ ላልጠየቁኝም ተገለጥኩ» ይላል።21ስለእስራኤል ግን «ለዚህ የማይታዘዝና ደንዳና ህዝብ ቀኑን ሙሉ እጄን ዘረጋሁ» ይላል።
1ታዲያ እግዚአብሄር ህዝቡን ጣላቸውን? ፥በጭራሽ። ምክንያቱም እኔ ራሴ ከቢንያም ወገን የሆንኩ የአብርሀም ዘር እስራኤላዊ ነኝ።2እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ህዝቡን አልጣላቸውም። ኤልያስ እስራኤልን በመቃወም ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት እንደተከራከረ መጽሀፍ የሚለውን አታውቁምን?3«ጌታ ሆይ ነቢያትህን ገድለዋል፣ መሰዊያዎችህንም አፍርሰዋል፣ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ሊገድሉኝም እየፈለጉኝ ነው።»4ነገር ግን እግዚአብሔር ምን ብሎ መለሰለት? «ለበዓል ያልሰገዱ ሰባት ሺ ሰዎችን ለራሴ ጠብቄ አቆይቻለሁ።»5በዚህም በአሁኑ ዘመንም ከጸጋ ምርጫ የተነሳ ትሩፋን አሉ።6ነገር ግን በጸጋ ከሆነ ከእንግዲህ በሥራ አይደለም።አለዚያ ጸጋ ከእንግዲህ ጸጋ መሆኑ ቀርቷል።7እንግዲህ ምን ይሁን፣ እስራኤል ይፈልገው የነበረውን ነገር አላገኘም ፥ የተመረጡት ግን አግኝተውታል፥ የቀሩት ግን ደንዳኖች ሆነዋል።8ይህም ልክ «እያዩ እንዳያዩ እየሰሙ እንዳይሰሙ እስከ አሁን እግዚአብሔር ያለማስተዋልን መንፈስ ሰጣቸው» ተብሎ እንደተጻፈው ነው።9ዳዊትም «ገበታቸው መረብ፥ወጥመድ፥የእንቅፋት ድንጋይና የበቀል ይሁንባቸው» ይላል።10እንዳያዩ አይናቸው ይጨልም፥ ሁልጊዜ ጀርባቸው እንደጎበጠ ይቅር።» ይላል።11«እስኪወድቁ ድረስ ተሰናከሉ» እላለሁን? ፈጽሞ አይሁን። በቅናት ሊያነሳሳቸው በእነርሱ ውድቀት ለአህዛብ ድነት ሆነ።12እንግዲህ ውድቀታቸው ለዓለም ሙላት ከሆነ ጉድለታችው ለአህዛብም ሙላት ከሆነ ሙላታቸው እንዴት ታላቅ ይሆን?13አሁን ለእናንተ ለአህዛብ እናገራለሁ። የአህዛብ ሀዋሪያ እንደመሆኔ በአገልግሎቴ እመካለሁ።14ምናልባት የገዛ ሥጋዬ የሆኑትን አስቀናና አንዳንዶቹን እናድን ይሆናል።15የእነኚያ መጣል ለዓለም የመታረቅ ምክንያት ከሆነ ተቀባይነት ማግኘታቸው ከሞት ወደ ህይወት ማምለጥ ካልሆን ምን ሊሆን ይችላል?16በኩሩ ቅዱስ ከሆነ ሊጡም ቅዱስ ነው። ሥሩ ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፉ ቅዱስ ነው።17ነገር ግን አንዳንዶቹ ቅርንጫፎች በመሰበራቸው ምክንያት አንተ የበረሀ ወይራ ዛፍ ቅርንጫፍ ባልወደቁት ቅርንጫፎች መካከል ብትጣበቅና የወይራ ዛፉን ሥር ብልጽግና ተካፋይ ብትሆን18በቅርንጫፎቹ ላይ አትኩራራ። ብትኩራራ ግን ሥሩ አንተን ተሸከምህ እንጂ አንተ ሥሩን አልተሸከመከውም።19«ቅርንጫፎቹ ስለተሰበሩ እኔ ተተካሁ» ትላለህ።20እውነት ነው ባለማመናቸው ምክንያት እነርሱ ተቆርጠው ወድቀዋል አንተ ደግሞ በእምነት ቆመሀል። ፍራ እንጂ ራስህ ከፍ አድርገህ አታስብ።21እግዚአብሔር ለመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች ካልራራ ለአንተም አይራራልህም።22እንግዲህ የእግዚአብሔርን የምህረት ሥራና ጭካኔ አስተውል። በአንድ በኩል ጭካኔው በወደቁት በአይሁድ ላይ መጣ፥በሌላ በኩል ደግሞ ጸንታችሁ ከቆያችሁ ምህረቱ ወደ እናንተ መጥቷል። አለበለዚያ ግን እናንተም ተቆርጣችሁ ትጣላላችሁ።23ደግሞም እነርሱ ባለማመናቸው ካልጸኑ እንደገና በዛፉ ላይ ሊተከሉ ይችላሉ። እግዚአብሔር እንደገና በዛፉ ላይ ሊተክላቸው ይችላልና።24እናንተ መነሻችሁ የበረሀ የወይራ ዛፍ የሆነና ተቆርጣችሁ የነበራችሁ ቅርንጫፎች ከተፈጥሮ ህግ ውጪ በመልካሙ የወይራ ዛፍ ላይ እንደገና ከተተከላችሁ የመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች እነኝህ አይሁድ ወደገዛ ዛፋቸው እንዴት እንደግና አይጣበቁም?25ወንድሞች ሆይ በራሳችሁ አስተሳሰብ ጥበበኞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ስለዚህ ምስጢር እንግዳ እንድትሆኑ አልፈልግም፡ የአህዛብ ሙላት እስኪፈጸም ድረስ ከፊል ድንዛዜ በእስራኤል ላይ ወድቋል።26ስለዚህም እስራኤል በሙሉ እንደተጻፈው ይድናሉ። «ከጽዮን ነጻ አውጪ ይነሳል ከያዕቆብም የማይገባ አካሄድን ያስወግዳል።27ኃጢአታቸውን በማስወግድላቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።»28በአንድ በኩል ወንጌልን በተመለከተ ስለእናንተ የተጠሉ ናቸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ በእግዚአብሔር ምርጫ ምክንያት ስለአባቶቻቸው የተወደዱ ናቸው።29ምክንያቱም የእግዚአብሔር ስጦታና ጥሪ አይለወጥም።30እናንተ ቀድሞ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙ የነበራችሁ አሁን ግን በእነርሱ አለመታዘዝ ምክንያት ምህረትን አግኝታችኋል።31ልክ እንደዚያው ዘንድ እነዚህ አይሁድ አሁን የማይታዘዙ ሆነዋል። በውጤቱም ለእናንት በተሰጠው ምህረት እነርሱ ደግሞ እንዲቀበሉ ነበር።32ምህረቱን ለሁሉ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ሁሉን ባለመታዘዝ ዘግቶታልና።33ኦ የእግዚአብሔር ጥበብና እውቀት ባለጠግነት ምን ያህል ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር መንገዱም እንዴት ከመታወቅ ያለፈ ነው!34«የጌታን ልብ የሚያውቅ ማነው? አማካሪውስ የሆነ ማነው?35ወይስ መልሶ ይከፍለው ዘንድ ለእግዚአብሔር ያበደረ ማነው?»36ሁሉም ነገር ከእርሱ በእርሱና ለእርሱ ነው። ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።
1ስለዚህም ወንድሞች ሆይ ሥጋችሁን ህያው መስዋዕት፥ቅዱስ፥ ለእግዚአብሔር የሚገባ አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ምህረት እለምናችኋለሁ፥ ያም ተገቢ የሆነ አገልግሎታችሁ ነው።2መልካም፥ተቀባይነት ያለውና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድታውቁ በታደስ አዕምሮ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትከትሉ።3ከእናንተ ማንም ስለራሱ ሊያስብ ከሚገባው በላይ እንዳያስብ በተሰጠኝ ጸጋ አሳስብለሁ። ይልቁኑም ለእያንዳንዱ ከእግዚአብሔር በተሰጠው እምነት ልክ በጥበብ ሊያስብ ይገባል።4ልክ እኛ በአንድ አካል ላይ ብዙ የአካል ክፍሎች ቢኖሩንም ተግባራቸው ግን ተመሳሳይ አይደለም።5እንዲሁ እኛም ብዙዎች ሳለን በክርስቶስ አንድ አካል ነን እያንዳንዳችንም አንዳችን የሌላችን የአካል ክፍል ነን።6በተሰጠን ጸጋ በኩል ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉን። የአንድ ሰው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ ባመነው መጠን ያድርገው።7የአንዱ ስጦታ ደግሞ ቸርነት ማድረግ ከሆነ ቸርነት ያድርግ። የማስተማር ስጦታ ያለው ያስተምር።8የማጽናናት ስጦታ ያለው ያጽናና፤ የመስጠት ስጦታ ያለው በልግስና ያድርገው፤ የመምራት ስጦታ ያለው በጥንቃቄ ይፈጽመው፤ምህረት የማድረግ ስጦታ ያለው በደስታ ያድርገው።9ፍቅራችሁ ያለግብዝነት ይሁን። ክፉ የሆነን ነገር ተጸየፉ፤መልካም የሆነውን ያዙ።10እውነተኛ የወንድማማች ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ።11ልግምተኞች አትሁኑ፤በመንፈሳችሁ ንቁ ሁኑ ፥ ጌታንም አገልግሉ።12ስላላችሁ የወደፊት ተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ትዕግስተኞች ሁኑ፥ጸሎታችሁ የማያቋርጥ ይሁን፤13ቅዱሳንን በችግራቸው እርዱ፤ መልካም ለማድረግ የሚያስችላቹሁን መንገዶች ፈልጉ።14የሚያሳድዷችሁን ባርኳቸው፥ባርኩ እንጂ አትርገሙ።15ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።16አንድ ልብ ይኑራችሁ፥ትሁት ሰዎችን ተቀበሉዋቸው እንጂ በትዕቢት አታስቡ። በራሳችሁ አመለካከት ጥበበኞች እንደሆናችሁ አታስቡ።17ክፉ ላደረገባችሁ ለማንም ክፉ አትመልሱ። በሰዎች ሁሉ ፊት መልካምን ነገር አድርጉ።18በተቻላችሁ መጠን በእናንተ በኩል ከሰዎች ሁሉ ጋር በሠላም ኑሩ።19የተወደዳችሁ ሆይ ስለራሳችሁ አትበቀሉ ይልቁኑ ለእግዚአብሔር ቁጣ ዕድል ስጡ።ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፦ «ጌታ 'በቀል የኔ ነው ብድራትን የምከፍለው እኔ ነኝ' ይላል»።20«ነገር ግን ጠላትህ ከተራበ መግበው። ከተጠማ ደግሞ የሚጠጣ ስጠው። ይህን ስታደርግ የእሳት ፍም በአናቱ ላይ ትከምራለህ።21ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።»
1ከእግዚአብሔር ካልተሰጠ በቀር ሥልጣን የለምና ሰው ሁሉ ለመንግስት ባለሥልጣናት ይገዛ። አሁን በሥልጣን ላይ ያለውም የተሾመው በእግዚአብሔር ነው።2ስለዚህም ይህን ሥልጣን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ይቃወማል፥ የሚቃወሙትም ሁሉ በራሳችው ላይ ፍርድን ያመጣሉ።3ምክንያቱም ገዢዎች ክፉ ለሚያደርጉ እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉም። ባለሥልጣንን አለመፍራት ትፈልጋለህ? መልካምን አድርግ ከእርሱ ሽልማትን ታገኛለህ።4ለመልካም ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። ክፉ የምታደርግ ከሆነ ግን ያለምክንያት ሠይፍ አልታጠቀምና ልትፈራ ይገባሀል። ምክንያቱም ክፉ የሚያደርገውን በቁጣ የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው።5ስለዚህ ስለ ቁጣው ብለህ ብቻ ሳይሆን ስለህሊናህ ብለህ ልትገዛ ይገባሀል።6በዚህ ምክንያት ግብርም ትከፍላላችሁ። ምክንያቱም ባለሥልጣናት ይህንን ጉዳይ ያለመታከት የሚቆጣጠሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው።7ለእያንዳንዱ የሚገባውን ስጡ፥ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ አክብሮት ለሚገባው አክብሮትን ስጡ።8እርስ በእርስ ከመዋደድ በቀር የማንም ዕዳ አይኑርባችሁ። ምክንያቱም ባልንጀራውን የሚወድ ህግን ፈጽሟል።9ምክንያቱም «አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ አትመኝ» የሚሉትና ሌሎቹም ትዕዛዛት «ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ» በሚለው ትዕዛዝ ተጠቃለዋል።10ፍቅር ያለው ባልንጀራውን አይጎዳም። ስለዚህ ፍቅር የህጉ ፍጻሜ ነው።11በዚህም ምክንያት ከእንቅልፍ የምትነቁበት እንደደረስ ታውቃላችሁ። መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ጊዜ ይልቅ ቅርብ ነው።12ሌሊቱ እያለፈ ቀኑም እየቀረበ ነው። ስለዚህ የጨለማን ሥራ ጥለን የብርሀንን የጦር ዕቃ እንልበስ።13ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያና በስካር ሳይሆን በቀን እንደሚመላለስ ሰው በተገቢው ሁኔታ እንመላለስ። በዝሙት ወይም በማይገታ ክፉ ምኞት፥ በጭቅጭቅና በቅናት አንመላለስ ።14ይልቁኑ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት ለሥጋችሁና ለክፉ ምኞቱም ዕድል አትስጡ።
1በእምነት ደካማ የሆነውን በጥያቄዎቹ ላይ በመፍረድ ሳይሆን በፍቅር ተቀበሉት።2አንዳንዱ ማንኛውንም ነገር በእምነት ይበላል፥በእምነቱ ደካማ የሆነው ደግሞ አትክልት ብቻ ይበላል።3ስለዚህ ማንኛውንም ዓይነት ምግብ የሚበላው የማይበላውን አይናቀው። የማይበላውም በሚበላው ላይ አይፍረድ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ተቀብሎታል።4በሌላው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? በገዛ ጌታው ፊት ወይ ይቆማል አሊያም ይወድቃል። ነገር ግን ጌታ ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።5አንደኛው አንዱን ቀን ከሌላው ቀን የሚበልጥ አድርጎ ይቆጥራል። ሌላው ደግሞ ሁሉም ቀናት አንድ ናቸው ብሎ ያምናል። እያንዳንዱ ሰው የራሱ መረዳት ይኑረው።6ቀንን የሚያከብር ለእግዚአብሔር ብሎ ያከብራል፥ የሚበላውም እግዚአብሔርን ያመሰግናልና ለእግዚአብሔር ብሎ ይበላል። የማይበላውም ራሱን ከመብላት ያቅባል። እርሱም እግዚእብሔርን ያመሰግናል።7ምክንያቱም ከእኛ ማንም ለራሱ የሚኖር ወይም የሚሞት የለም።8ብንኖር ለጌታ እንኖራልንና ብንሞትም ለጌታ እንሞታለንና። እንግዲያውስ ብንኖርም ብንሞትም የጌታ ነን።9ምክንያቱም በሙታንና በህያዋን ላይ ጌታ ይሆን ዘንድ ለዚህ ዓላማ ክርስቶስ ሞቷል ደግሞም ህያው ሆኗል።10ግን አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? አንተስ ወንድምህን ለምን ትንቃለህ? ሁላችንም በእግዚአብሔር የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።11ምክንያቱም «እኔ ህያው ነኝና ጉልበት ሁሉ በፊቴ ይንበረከካል ምላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል» ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፏል።12ስለዚህም እያንዳንዳችን ስለ ስራችን በእግዚአብሔር ፊት መልስ እንሰጣለን።13ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ አንዳችን በሌላችን ላይ አንፍረድ በዚያ ፋንታ ማንም በወንድሙ ፊት መሰናክል ወይም ወጥመድ እንዳያስቀምጥ እንወስን።14ምንም ነገር በራሱ ርኩስ እንዳልሆነ በጌታ በኢየሱስ አውቃለሁ ተረድቻለሁም። ማንኛውም ነገር ርኩስ ነው ብሎ ለሚያስብ ለእርሱ ብቻ ያ ነገር እርኩስ ነው።15በምግብ ጉዳይ ወንድምህን የምታሰናክል ከሆነ አንተ በፍቅር እየተመላለስክ አይደለም። ስለምግብህ ብለህ ክርስቶስ የሞተለትን ሰው አታጥፋ።16ስለዚህ መልካም ስራዎቻችሁን ለሰዎች መቀለጃ አታድርጉ።17ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ የሚሆን ጽድቅ፥ ሠላምና ደስታ እንጂ የመብልና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም።18ክርስቶስ እንዲህ ባል ሁኔታ የሚያገለግለውን እግዚአብሔር ይቀበለዋል በሰዎችም ይመሰገናል።19ስለዚህ ሠላም የሚገኝበትንና እርስበእርሳችን የምንተናነጽባቸውን ነገሮች እንፈልግ።20በምግብ ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አታበላሹ። በእርግጥም ሁሉ ነገር ንጹህ ነው፥ ነገር ግን እየተጠራጠረ ለሚበላ ለዚያ ሰው ክፉ ነው፣ እንዲሰናከልም ያደርገዋል።21ወንድምህን የሚጎዳ ከሆነ ሥጋ ባትበላም ወይን ባትጠጣም ወይም ምንም ባታደርግ መልካም ነው።22አንተ በግልህ ያለህ መረዳት ባንተና በእግዚአብሔር መሀል ይቅር። አምኖ የተቀበለውን ነገር በማድረጉ ራሱን የማይወቅስ የተባረከ ነው።23እየተጠራጠረ የሚበላ ግን በእምነት ስላልሆነ ይፈረድበታል። ምክንያቱም ያለ እምነት የሆነ ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው።
1እንግዲህ ብርቱዎች የሆንን እኛ የደካሞቹን ድካም ልንሸከም እንጂ ራሳችንን ብቻ ልናስደስት አይገባም።2መልካም ነውና እንድናንጸው እያንዳንዳችን ባልንጀራችንን ደስ እናሰኝ።3ምክንያቱም ክርስቶስ እንኳን እራሱን ደስ አላሰኘም። ይልቁንም «አንተን የሰደቡበት ስድብ በኔም ላይ ደረሰ» ተብሎ እንደተጻፈው ነው።4አስቀድሞ የተጸፈው ሁሉ በትዕግስትና በቅዱሳት መጽሀፍት እየተበረታታን ድፍረት እንድናገኝ ለትምህርታችን ተጽፎአል።5እንግዲህ የትዕግስትና የመጽናናት አምላክ ለእርስ በእርሳችሁ በክርስቶስ አንድ ልብ ይስጣችሁ።6በአንድ ልብና በአንድ አፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት እንድታመስግኑ ይህን ያድርግ።7ልክ ክርስቶስ እንደተቀበላችሁ ለእግዚአብሔር ክብር እርስ በእርሳችሁ ተቀባበሉ።8ስለ እግዚአብሔር እውነት ክርስቶስ የመገረዝ አገልጋይ ሆነ እላለሁ። ይህን ያደረገው ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ ሊያጸና9አህዛብ ደግሞ ስለምህረቱ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ነው። ይህም «በአህዛብ መካከል አመሰግንሀለሁ፣ለስምህም እዘምራለሁ» ተብሎ በተጻፈው መሰረት ነው።10እንደገናም ደግሞ «እናንተ አህዛብ ከህዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ» ይላል።11ደግሞም እንደገና «አህዛብ ሁላችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግኑት» ይላል።12ኢሳያስ ደግሞ «አህዛብን ሊገዛ የሚነሳ የእሴይ ሥር ይወጣል፥ አህዛብም በእርሱ ይመካሉ።» ይላል።13በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ ትሞሉ ዘንድ የተስፋ አምላክ በማመናችሁ ምክንያት በደስታና በሰላም ሁሉ ይሙላችሁ።14ወንድሞቼ ሆይ እናንተ ራሳችሁ በመልካምነትና በእውቀት እንደተሞላችሁ እርስ በእርሳችሁም ልትማማሩ እንደምትችሉ ስለእናንተ ተረድቻለሁ።15ነገር ግን ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ስጦታ ስለአንድ ጉዳይ ላሳስባችሁ በድፍረት ጽፌላችኋለሁ።16ይኸም ስጦታ የእግዚአብሔርን ወንጌልን እንደ ካህን እንዳቀርብላቸው ወደ አህዛብ የተላክሁ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ መሆኔ ነው። ይህን ማድረግ ያለብኝ የአህዛብ መስዋዕት ተቀባይነት እንዲያገኝና በመንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር እንዲቀርብ ነው።17እንግዲህ ደስታዬ በክርስቶስ ኢየሱስና ከእግዚአብሔር በሚሆኑ ነገሮች ነው።18አህዛብ ወደ መታዘዝ እንዲመጡ ክርስቶስ በእኔ ካከናወነው ነገር በቀር ስለምንም ነገር ለመናገር አልደፍርም። እነዚህም ነገሮች በቃልና በሥራ19በምልክትና በድንቆች ኃይል በመንፈስ ቅዱስም ኃይል የተከናወኑ ናቸው። ይህም በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እስከ አልዋሪቆን ድርስ የክርስቶስን ወንጌል በሙላት እንዳደርስ ነበር።20በዚህ መንገድ ፍላጎቴ ወንጌልን መስበክ ነው፥ ነግር ግን የምሰብከው በሌላው ሰው መሠረት ላይ እንዳልገነባ የክርስቶስ ስም በሚታወቅበት አካባቢ አይደለም።21ይህም «ስለእርሱ ያልተነገራቸው ያዩታል፥ ያልሰሙም ያስተውላሉ» ተብሎ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።22ስለዚህም ወደ እናንተ እንዳልመጣ ብዙ ጊዜ እንቅፋት ገጠመኝ።23አሁን ግን በዚህ ባሉ ክልሎች እንብዛም የምሰራው ነገር የለኝም ወደ እናንተም ለመምጣት ለበርካታ ዓመታት ስናፍቅ ነበር።24ስለሆነም ወደ እስፔን በምሄድበት ጊዜ ከእናንተ ጋር ደስ የሚያሰኝ ጥቂት ጊዜ አሳልፌ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ወደናንተ ጎራ ብዬ እንደማያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።25አሁን ግን በጌታ ያመኑትን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ።26ምክንያቱም በመቄዶኒያና በአካይያ ያሉ አማኞች በኢየሩሳሌም ባሉ አማኞች መካከል ለሚገኙ ድሆች የተወሰነ ድጋፍ ለማድረግ በደስታ ፈቅደዋል።27አዎ በደስታ ሊያደርጉት መልካም ፈቃዳቸው ነበር፥ ለነገሩ የእነርሱ ባለዕዳዎች ናችው። አህዛብ ከእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ከተካፈሉ እነርሱ ደግሞ በቁሳዊ ነገር ሊያገለግሏቸው ይገባል።28ስለዚህም ይህን ስጦታውን የማድረስ ተግባሬን ከፈጸምኩ በኋላ በእናንተ በኩል ወደ እስፔን አልፋለሁ።29ወደ እናንተ ስመጣ በክርስቶስ በረከት ተሞልቼ እንደምመጣ አውቃለሁ።30እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ ስለኔ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አብራችሁኝ እንድትጋደሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በመንፈስ ቅዱስም ፍቅር እለምናችኋለሁ።31በይሁዳ ካሉ የማይታዘዙ ሰዎች እንድጠበቅ አገልግሎቴም በኢየሩሳሌም ባሉ አማኞች ተቀባይነት እንዲያገኝ ጸልዩ።32በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እናንተ በደስታ መጥቼ አብሬያችሁ እንዳርፍ ጸልዩ።33የሠላም አምላክ ከሁላችሁም ጋር ይሁን። አሜን።
1በክንክራኦስ ያለችው ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነችውን እህታችንን ፌበንን2በጌታ እንድትቀበሏት አደራ ሰጥቻችኋለሁ። ይህንንም ከአማኞች በሚጠበቅ መልኩ አድርጉት፣ የእናንተን እርዳታ በምትፈልግበት በማንኛውም ነገር ከጎኗ ቁሙ። ምክንያቱም እርሷ እራሷ እኔን ጨምሮ ብዙዎችን የምትርዳ ነች።3በክርስቶስ የአግልግሎቴ አጋሮች ለሆኑት ለአቂላና ለጵርስቅላ ሠላምታ አቅርቡልኝ፥4እነርሱ ስለእኔ ህይወታቸውን ለአደጋ ያጋለጡ ናቸው። አመሰግናቸዋለሁ፥ እኔ ብቻ ሳልሆን የአህዛብ አብያተክርስቲያናትም ሁሉ ያመስግኗቸዋል።5በቤታቸው ላለች ቤተክርስቲያን ሠላምታ አቅርቡልኝ። በእስያ ለክርስቶስ የመጀምሪያው ፍሬዬ የሆነውን የምወደውን አጤኔጦንን ሠላም በሉልኝ።6ለእናንተ በሥራ ለደከመችው ለማሪያ ሠላምታ አቅርቡልኝ።7ዘመዶቼ ለሆኑትና አብረውኝ ታስረው ለነበሩት ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን ሠላምታ አቅርቡልኝ። እነርሱ በክርስቶስ በመሆን የቀደሙኝና ከሐዋሪያት መካከል በመልካም የተመሰከረላቸው ናቸው።8በጌታ ለምወደው ለጵልያጦን ሠላምታ አቅርቡልኝ።9በክርስቶስ አብሮን የሚሠራውን ኢሩባኖንና የተወደደውን ስንጣክን ሠላም በሉልኝ።10በክርስቶስ መሆኑ ለተመሰከረለት ለኤጤሌን ሠላምታ አቅርቡልኝ። የአርስጣባሉን ቤተሰቦች ሠላም በሉልኝ።11ለዘመዴ ለሄሮድዮና ሠላምታ አቅርቡልኝ። ከንርቀሱ ቤተሰቦች መካከል በጌታ ላመኑት ሠላምታ አቅርቡልኝ።12በጌታ ሥራ ለሚደክሙት ለፕሮፊሞንና ለጢሮፊሞስ ሠላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ ሥራ በብዙ የምትደክመውን የተወደደች ጠርሲዳን ሠላም በሉልኝ።13በጌታ ልተመረጠው ለሩፎን እና ለእርሱም ለእኔም እናት ለሆነችው ለእናቱ ሠላምታ አቅርቡልኝ።14አስቀራጦንን፥ አፍለሶንጳን፥ ሄሮሜንን፥ ጳጥሮባን፥ ሄርማንን እንዲሁም አብረዋቸው ያሉትን ወንድምች ሠላም በሉልኝ።15ለፍሌጎን፥ ለዩልያ፥ ለኔርያ ለእህቱም ለአልንጦን አብረዋቸውም ላሉት በጌታ ላመኑት ሁሉ ሠላምታ አቅርቡልኝ።16በተቀደሰ መሳሳም ሠላምታ ተለዋወጡ። የክርስቶስ አብያተክርስቲያናት ሁሉ ሠላምታ ያቀርቡላችኋል።17ወንድሞቼ ሆይ በመካከላችሁ የመለያየትንና የመሰናክል ምክንያት ስለሆኑት ሰዎች እንድታስቡ እለምናችኋለሁ። እነርሱ እናንተ ከተማራችሁት የወጣ ነገር ያስተምራሉና ከእነርሱ ተለዩ።18እንደነዚህ ያሉ ሰዎች የገዛ ሆዳቸውን እንጂ ክርስቶስን ጌታችንን አያገለግሉም። በለስላሳና በሚያባብል ቃላቸው የየዋሀንን ልብ ያታልላሉ።19የመታዘዛችሁ ምሳሌነታችሁ ለብዙዎች ደርሷል። ስለዚህም በእናንተ ደስ ይለኛል፥ ነገር ግን ለመልካም ነገር ጥበበኞች ለክፉ ነገር ደግሞ የዋሀን እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።20የሠላም አምላክ ሠይጣንን በፍጥነት ከእግራችሁ በታች ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሠላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን።21የሥራ አጋሬ ጢሞቴዎስና ዘመዶቼ ለቂዮስ፥ኢያሶንና ሱሲጴጥሮስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።22ይህን ደብዳቤ በእጄ የጻፍኩ እኔ ጤርጥዮስ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።23እኔና ቤተክርስቲያንን በሙሉ በቤቱ ያስተናገደን ጋይዮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። የከተማው ገንዘብ ያዥ ኤርስጦስ ወንድማችንም ቁአስጥሮስ ሰላም ብለዋችኋል።25እንግዲህ በወንጌሌ በኢየሱስ ክርስቶስም ስብከት ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ ተሰውሮ በነበረውና26አሁን ግን በዘላለማዊ አምላክ ትዕዛዝ በአህዛብ ሁሉ መካከል በተገለጠውና የእምነት መታዘዝ እንዲገኝ በትንቢታዊ መጽሀፍት አማካኝነት በታወቀው ሚስጥር መሠረት ሊያቆማችሁ ለሚችለው27ብቻውን ጥበበኛ አምላክ ለሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።
1በእግዚአብሔር ፈቃድ ሐዋርያ ሊሆን በክርስቶስ ኢየሱስ የተጠራ ጳውሎስና ወንድማችን ሶስቴንስ በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት።2የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት ደግሞ እንጽፍላቸዋለን።3ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።4ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰጣችሁ ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ሁልጊዜ ስለእናንተ አምላኬን አመሰግናለሁ።5በነገር ሁሉ፤በንግግርና በዕውቀት ሁሉ ባለጸጋ እንድትሆኑ አድርጎአችኋልና።6ስለክርስቶስ የተሰጠው ምስክርነት በመካከላችሁ እውነት ሆኖ እንደጸና ሁሉ ባለጸጎች አድርጎአችኋል።7ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ አንድም መንፈሳዊ ስጦታ አይጎድልባችሁም።8እርሱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።9ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።10ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ ሁላችሁም በአንድ አሳብ እንድትስማሙ እንጂ በመካከላችሁ መለያየት እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ድርስቶስ ስም አሳስባችኋለሁ። እንዲሁም በአንድ ልብና በአንድ ዓለማ የተባበራችሁ እንድትሆኑ አሳስባችኋለሁ።11በመካከላችሁ መከፋፈል እንደተፈጠረ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛል።12ይህን የምላችሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ "እኔ ከጳውሎስ ጋር ነኝ፥ ወይም ከአጵሎስ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከኬፋ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከክርቶስ ጋር ነኝ" ትላላችሁ።13ለመሆኑ ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? ወይም የተጠመቃችሁት በጳውሎስስ ስም ነውን?14ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ማናችሁንም ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።15ስለዚህ ማናችሁም በእኔ ስም እንደተጠመቃችሁ ለመናገር አትችሉም። (የእስጢፋኖስን ቤተ ሰብ ደግሞ አጥምቄአለሁ።16ከዚህ ውጪ ሌላ ማንን አጥምቄ እንደሆነ አላውቅም።)17ክርስቶስ ወንጌልን እንድሰብክ እንጂ እንዳጥምቅ አላከኝም። በሰው ጥበብ እንድሰብክ አልላከኝም፤ እንዲሁም የክርስቶስ መስቀል ኃይሉ ከንቱ መሆን ስለሌለበት በሰው የንግግር ጥበብ አልሰብክም ።18ስለመስቀሉ ያለው መልእክት ለሚጠፉት ሞኝነት፤ ነገር ግን ለምንድን ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው።19"የጥበበኖችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል ከንቱ አደርጋለሁ" ተብሎ ተጽፎአልና።20ጥበበኛ ሰው የት አለ? ፈላስፋስ የት አለ? የዚህ ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?21ዓለም በጥበብዋ እግዚአብሔርን ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል።22አይሁድ ታዓምራትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ።23እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን። ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለግሪክ ሰዎችም ሞኝነት ነው።24ነገር ግን እግዚአብሔር ለጠራቸው ለአይሁዶችም ሆነ ለግሪክ ሰዎች የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ የሆነውን ክርስቶስን እንሰብካለን።25ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሞኝነት የሚመስለው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድካም የሚመስለው ነገር ከሰዎች ብርታት ይበልጣል።26ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ በእናንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ተመልከቱ። ብዙዎቻችሁ በሰው መስፈርት ጥበበኞች አልነበራችሁም። ብዙዎቻችሁ ኃያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከመሳፍንት አልነበራችሁም።27ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ። ብርቱንም ነገር ለማሳፈር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ።28ዓለም እንደ ከበረ ነገር የምትቆጥረውን ከንቱ ለማድረግ እግዚአብሔ የዓለምን ምናምንቴ ነገር መረጠ። የተናቀውንና ያልሆነውን ነገር መረጠ።29ይህን ያደረገው ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመመካት ምክንያት እንዳይኖረው ነው።30በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና።31እንግዲህ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ፦"የሚመካ በጌታ ይመካ" ነው።
1ወንድሞችና እህቶች ሆይ፦ወደ እናንተ ስመጣ ስለ እግዚአብሔር የተሰወረውን የእውነት ምስጢር ሲሰብክላችሁ በሚያባብል የንግግር ችሎታ ወይም በላቅ ጥበብ አልመጣሁም።2በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀርና፥ እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና።3ወደ እናንተ የመጣሁት በድካምና በፍርሃት፤ እንዲሁም በብዙ መንቀጥቀጥ ነበር።4መልእክቴና ስብከቴም የመንፈስን ኃይል በመግለጥ እንጂ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤5ይህም እምነታችሁ በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ ላይ እንዳይመሠረት ነው።6በእምነታቸው በሰሉት ሰዎች መካከል በጥበብ እንናገራለን፤ ነገር ግን የምንናገረው የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም ከጊዜ በኋላ የሚሻሩትን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም።7ይልቁን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን ያዘጃውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን የጥበብ እውነት እንናገራለን።8የዚህም ዓልም ገዢዎች አንዳቸውም ይህን ጥበብ አላወቁትም፤ በዚያን ጊዜ ይህን አውቀውስ ቢሆን ኖሮ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር።9ነገር ግን፦ "ዓይን ያላየውን፤ ጆሮም ያልሰማውን፤ በሰውም ልብ ያልታሰበውን፤ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀውን ነገር" ተብሎ ተጽፎአልና።10እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካይነት የተሰወሩትን ነገሮች ገልጦናን ። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። በሰው ውስጥ ካለው ከእርሱ መንፈስ በቀር የሰውን አሳብ የሚያውቅ ማን ነው?11እንዲሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር የሚያውቅ ማንም የለም።12እኛ ግን ክእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠንን እንድናውቅ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበለንም።13የሰው ጥበብ ሊያስተምር የማይችለውን ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያስተምረውን ስለ እነዚህ ነገሮች በቃላት እንናገራለን። መንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊውን ቃላት በመንፈሳዊ ጥበብ ይገልጥልናል።14የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለው ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ስለሚሆንበት አይቀበለውም ። በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም።15የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው ሁሉን ይመረምራል፤ እርሱ ግን በማንም አይመረመርም።16"የጌታን አሳብ ማን አወቀው፤ ማንስ ሊያስተምረው ይችላል?" እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።
1ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ እንደ ሥጋውያን፤ በክርስቶስም እንደ ሕፃናት እንጂ መንፈሳውያን እንደ ሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።2ገና ጠንካራ ምግብ ለመብላት ስላልቻላችሁ ጠንካራ ምግብ ሳይሆን ወተት ጋትኋችሁ። እስከ አሁን ስንኳ ጠንካራ ምግብ ለመብላት ገና አልበቃችሁም።3ምክንያቱም ገና ሥጋውያን ናችሁና። ቅናትና ክርክር ስለ ሚገኝባችሁ በሥጋ ፈቃድ እየኖራችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰውስ ልማድ እየተመላለሳችሁ አይደለምን?4አንዱ፦ "እኔ ጳውሎስን እከተላለሁ" እንዲሁም ሌላውም፦ "እኔ የአጵሎስ ተከታይ ነኝ" ሲል እንደ ሰዎች ልማድ መመላለሳችሁ አይደለምን?5ታዲያ አጵሎስ ማን ነው? ጳውሎስስ ማን ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ እንደ ተሰጣቸው አገልጋዮች ናቸው።6እኔ ተክልሁ አጽሎስም አጠጣ፤ ግን ያሳደገው እግዚአብሔር ነው።7እንግዲህ የሚተክል ወይም የሚያጠጣ ምንም አይደለም። ነገር ግን የሚያሳድግ እግዚአብሔር ነው።8የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው። እንዲሁም እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መሠረት የራሱን ደመወዝ ይቀበላል።9ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነን። የእግዚአብሔር እርሻ፤ የእግዚአብሔርም ሕንፃ ናችሁ። ።10ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ጸጋ እንደ ዋና ሙያተኛ መሐንድስ መሠረትን ጠልሁ፤ ሌላውም ሰው በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ሰው ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ።11ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልም፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።12ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን፤ በብር፤ በከበረ ድንጋይ፤ በእንጨት፤ በሣር ወይም በአገዳ ቢያንጽ፤13የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ የቀን ብርሃንም ይገልጠዋልና። የእያንዳንዱም ሥራ ጥራት እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።14አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል። ነገር ግን የማንም ሥራ የተቃጠለበት ከሆነ ይከስራል።15ነገር ግን እርሱ ራሱ ከእሳት እንደሚያመልጥ ሆኖ ይድናል ።16እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደሚኖርባችሁ አታውቁምን?17ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም እናንተም ቅዱሳን ናችሁ።18ማንም ራሱን አያታልል። ከእናንተ መካከል ማንም በዚህ ዘመን ጥበበኛ እንደሆነው ቢያስብ፤ ጥበበኛ ይሆን ዘንድ እንደ ሞኝ ራሱን ይቁጠር።19የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። ምክንያቱም "እርሱ ጥበበኞችን በተንኮላቸው ይይዛል" ተብሎ ተጽፎአል።20ደግሞም፦ "ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆን ያውቃል" ተብሎ ተጽፎአል።21ስለዚህ ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤22ጳውሎስ ቢሆን፥ ወይም አጵሎስ ቢሆን፥ ወይም ኬፋ ቢሆን፥ ወይም ዓለምም ቢሆን፥ወይም ሕይወት ቢሆን፥ ወይም ሞት ቢሆን፥ ወይም ያለውም ቢሆን፥ ወይም የሚመጣውም ቢሆን23ሁሉ የእናንተ ነው፤ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።
1እንግዲህ ማንም ሰው እኛን የክርስቶስ አገልጋዮችና የእግዚአብሔር የተሰወረው ምሥጢር መጋቢዎች እንደሆነን ሊቆጥረን ይገባል።2በዚህ መሠረት መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይገባቸዋል።3ነገር ግን በእናንተ ወይም በየትኛውም ፍርድ ቤት መፈረድ ካለብኝ ለእኔ በጣም ትንሽ ነገር ነው።4እኔ በራሴ እንኳ አልፈርድም። እኔ ምንም ክስ የለብኝም ግን ፍጹም ነኝ ማለቴ አይደለም። በእኔ የሚፈርድ ጌታ ነው።5ስለዚህ ጊዜ ሳይደርስ፥ ጌታ ከመምጣቱ በፊት ስለምንም ነገር አትፍረዱ።እርሱም በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያወጣል፤ የልብንም አሳብ ይገልጣል። በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።6እንግዲህ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፦ "ከተጻፈው አትለፍ" የሚለውን ትርጉሙ ከእኛ መማር እንድትችሉ ስለ እናንተ ስል ለራሴና ለአጵሎስ እንደ ምሳሌ ተናገርሁ። ይህ ማናችሁም አንዳችሁ በሌላኛችሁ እንዳትታበዩ ነው።7በእናንተና በሌሎች መካከል ምን ልዩነት አለ? በነጻ ያልተቀበልከውስ ምን አለህ? በነጻ የተቀበልከው ከሆንህ እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድን ነው?8አሁን የምትፈልጉት ሁሉ አላችሁ! አሁንስ ባለ ጠጎች ሆናችኋል! ከእኛ ተለይታችሁ መንገሥ ጀምራችኋል! በርግጥ እኛ ከእናንተ ጋር መንገሥ እንድንችል እናንተ ብትነግሡ በተመኘሁ ነበር።9እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች ያደረገን ይመስለኛል። ለዓለም፥ ለመላእክትና ለሰዎች መታያ ሆነናልና።10እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ፤እኛ ግን የተዋረድን ነን።11እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጥማለን፤ እንራቆታለን፤ ያለርኅራኄ እንደበደባለን፤ ራሳችንን የምናስጠጋበት ስለሌለን እንክራተታለን።12በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን።13ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል።14እነዚህን ነገሮች የጻፍኩላችሁ ላሳፍራችሁ ሳይሆን እንደ ተወደዱ ልጆቼ አድርጌ እንድትታርሙ ልገስጻችሁ ነው።15በክርስቶስ ብዙ እልፍ አዕላፋት አሳዳጊዎች ቢኖሩአችሁ እንኳ ብዙ አባቶች የሉአችሁም። እኔ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ልጆቼ ናችሁ።16እንግዲህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ።17እንግዲህ የተወደደና ታማኝ የሆነውን በጌታ ልጄን ጢሞቲዎስን የላክሁላችሁ ለዚህ ነው ። እኔም በየስፍራውና በየአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንደማስተምር፤ በክርስቶስ ያሉትን መንገዶቼ እርሱ ያሳስባችኋል።18አንዳንዶቻችሁ ግን ወደ እናንተ የማልመጣ መስሎአችሁ በትዕቢት የምትመላለሱ አላችሁ።19ነገር ግን ጌታ ቢፈቅድ ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ። እነዚህ በትዕቢት የሚመላለሱት የሚናገሩትን ብቻ ሳይሆን ኃይላቸውንም ለማወቅ እሞክራለሁ።20ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል ብቻ አይደለምና። ምን ትፈልጋላችሁ?21በበትር ወይስ በፍቅርና በትህትና መንፈስ እንድመጣባችሁ ትፈልጋላችሁ?
1በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ሰምተናል፤የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብ መካከል እንኳ ተሰምቶ የማይታወቅ ነው። እንደሰማነው ከእናንተ አንዱ ከእንጀራ እናቱ ጋር የሚተኛ አለ።2ስለዚህ በትዕቢት የምትመላለሱ አይደላችሁምን? በዚህም ልታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ያደረገ ሰው ከመካከላችሁ ሊወገድ ይገባል።3እኔ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር አለሁ፤ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን ባደረገው ሰው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ።4እናንተ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምትሰበሰቡበት ጊዜ መንፈሴም ከጌታችን ኢየሱስ ኃይል ጋር እዚያው በመካከላችሁ አለ።5ይህ ሰው በጌታ በኢየሱስ ቀን ይድን ዘንድ፤ ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።6መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካ አታውቁምን?7እንግዲህ እርሾ የሌለ እንጀራ ሆናችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ ከአሮጌው እርሾ ራሳችሁን አንጹ። ምክንያቱም የፋሲካችን በግ የሆነው ክርስቶስ ታርዶአል።8ስለዚህ በአሮጌ እርሾ በመጥፎ አስተሳሰብና በክፋት ሳይሆን በቅንነትና በእውነት በዓልን እርሾ በሌለ ቂጣ እናድርግ።9ዝሙትን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ኅብረት እንዳታደርጉ በመልእክቴ ጽፌላችሁ ነበር።10በምንም ነገር የዚህን ዓለም ዝሙት ከሚያደርጉትን ወይም ገንዘብን ከሚመኙትን፥ ከነጣቂዎችንም፤ወይም ጣዖትን ከሚያመልኩትን ከማያምኑት አትተባበሩ። እንዲህ ቢሆን ኖሮ ከዓለም መውጣት በተገባችሁ ነበር።11አሁን ግን በክርስቶስ ወንድሞች ወይም እህቶች ተብለው ከሚጠሩት ከማናቸውም ዝሙትን ከሚያደርግ ወይም ገንዘብን ከሚመኝ ወይም ጣኦትን ከሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ነጣቂ ቢሆኑ ከእነርርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ። እንደነዚህ ካሉት ጋር አብራችሁ እንኳን አትብሉ።12ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉ ሰዎች ላይ ለመፍረድ እንዴት እደፍራለሁ? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን?13ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። "ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።"
1ከእናንተ አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ክርክር ቢኖረው፤ በቅዱሳን ፊት ስለጉዳዩ ከመነጋገር ይልቅ በማያምን ዳኛ ፊት ለመቆም ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ይደፍራልን?2ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፤ በትናንሽ ጉዳዮችን መፍረድ እንዴት ይሳናችኋል?3በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን? እንግዲህ በዚህ ዓለም ሕይወት ጉዳዮች ላይ የበለጠ ለመፍረድ እንዴት አንችልም?4ለዕለታዊ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ መፍረድ ካለባችሁ በቤተ ክርስቲያን መካከል ለሚነሱ ክርክሮች የማያምኑ ሰዎችን እንዲፈርዱ ታስቀምጣላችሁን?5አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። እንደዚህ ነውን? በወንድሞችና እህቶች መካከል ክርክሮችን ሊፈታ የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?6ነገር ግን አንዱ አማኝ ሌላውን አማኝ ለመክሰስ በማያምን ዳኛ ፊት ለመቆም ይሄዳልን?7እንግዲህ በክርስቲያኖች መካከል የእርስ በርስ ማንኛውም ክርክር ቢኖርባችሁ ለእናንተ ሽንፈት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ እይሻልምን?8ነገር ግን እናንተ ወድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ።9ዓመጸኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? በሐሰት አታምኑ። ዝሙት አድራጊዎች ቢሆኑ፣ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመዝሮች ወይም ግብረ ሶዶማውዎች ቢሆኑ፤ ወይም ሌቦች፥ ወይም ስግብግቦች፤ ወይም ሰካራሞች፣ ወይም ተዳዳቢዎች፥10ወይም ነጣቂዎች፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።11ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ። ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችሁማል።12ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ነገር ግን ሁሉም የሚጠቅም አይደለም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን በእኔ ላይ ምንም ነገር አይሠለጥንብኝም።13"መብል ለሆድ ነው፤ ሆድም ለመብል ነው።" እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም። ይልቁን ሥጋችንም ለጌታ ነው፤እንዲሁም ጌታ ለሥጋ ያዘጋጃል።14እግዚአብሔርም ደግሞ ጌታን አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል።ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን?15እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የሴተኛ አዳሪ ሴት ብልቶች ላድርጋቸውን? ሊሆን አይችልም።16ከሴተኛ አዳሪ ጋር የሚተባበር ከእርስዋ ጋር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? "ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ" በእግዚአብሔር ቃል ተጽፎአል።17ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን ከእርሱ ጋር አንድ መንፈስ ነው።18ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ሌላ ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚያደርግ ሰው ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ያድርጋል።19ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?20በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም። ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
1እንግዲህ ስለጻፋችሁኝ ነገር ሰው ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው።2ነገር ግን ስለ ዝሙት ፈተና ምክንያት እንዳይሆን እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ይኑረው፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሴት የራስዋ ባል ይኑራት።3ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ የሚገባትን ታድርግ።4ሚስት በገዛ ሰውነትዋ ላይ ሥልጣን ያላትም፤ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ባል በገዛ ሰውነቱ ላይ ሥልጣን የላውም ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።5በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ። ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ መሆን ትችላላችሁ።6ዳሩ ግን ይህን እንደ ፈቃድ እላለሁ እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም።7ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን እወዳለሁ። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ከእግዚአብሔር የተቀበለ አንዱ አንድ ዓይነት ሌላው ሌላ ዓይነት ስጦታ አለው።8ላላገቡትና ባሎቻቸው ለሞተባቸው ሴቶች ግን እላለሁ፦ እንደ እኔ ሳያገቡ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው።9ነገር ግን ራሳቸውን መግዛት የማይችሉ ከሆነ መጋባት ይሻላል። በምኞት ከመቃጠል ይልቅ መጋባት ይሻላቸዋልና።10ደግሞ የተጋቡትን እንዲ ብዬ አዛቸዋለሁ ይህንም እኔ ሳልሆን ጌታ ነው፦ "ሚስት ከባልዋ አትለይ፥11ብትለይ ግን ሳታገባ ትኑር" ወይም "ከባልዋ ጋር ትታረቅ፥እንዲሁም" ባልም ሚስቱን አይፍታት።"12ነገር ግን ሌሎችንም ጌታ ሳይሆን እኔ እላለሁ፦ ማንም ያላመነች ሚስት ያለው ወንድም፥ ከእርሱ ጋር ለመኖር ብትስማማ አይፍታት፤13እንዲሁም ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር፥ ከእርስዋ ጋር ለመኖር ቢስማማ አትፍታው። ያላመነች ሚስት በአማኙ ባልዋ ተቀድሳለችል፤14እንዲሁም ያላመነ ባል በአማኝ ሚስቱ ተቀድሶአል። አለዚያ ልጆቻቸውሁ ርኩሳን ይሆኑ ነበር፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው።15የማያምን የትዳር ጓደኛ ግን የሚለይ ከሆነ ይለይ። እንዲህ በሚመስል ነገር ወንድም ወይም እህት በቃል ኪዳን መታሰር የለባቸውም። እግዚአብሔር ግን በሰላም እንድንኖር ጠርቶናል።16አንቺ ሴት ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአሽ? ወይስ አንተ ሰው ሚስትህን ታድናት እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ?17እያንዳንዱ ሰው እንደተጠራው ዓለማና ጌታ በሰጠው ሕይወት ብቻ ይመላለስ። ይህ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የእኔ ድንጋጌ ነው።18ማንም ተገርዞ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? ወደ አለመገረዝ መመለስ የለበትም። እንዲሁም ማንም ሳይገርዝ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? መገረዝ የለበትም።19የእግአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ ነው እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ የሚያመጠው ችግር የለም።20እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ለእምነት በጠራበት ጊዜ እንደነበረ ይመላለስ።21እግዚአብሔር ሲጠራህ ባሪያ ነበርን? ይህ ሊገድህ አይገባም። ነፃ የምትወጣ ከሆንህ ተቀበለው።22አንድ ሰው በጌታ ባሪያ ሆኖ የተጠራ የጌታ ነፃ ሰው ነው፤ እንደዚሁም ነፃ ሆኖ ለእምነት የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው።23በዋጋ ተገዝታችልኋልና የሰው ባሪያ አትሁኑ።24ወድሞችና እህቶች ሆይ፤ እያንዳንዳችን በተጠራንበት እንደዚሁ ሆነን በእግዚአብሔር ዘንድ እንኑር።25ላላገቡት የጌታ ትእዛዝ የለኝም። ነገር ግን በጌታ ምሕረት እንደ ታመነ ሰው ሆኜ የራሴን ምክር እሰጣለሁ።26ስለዚህ ለችግር ጊዜ መፍትሔ እንዲሆን ሰው ሳያገባ መኖር ከቻለ መልካም ይመስለኛል።27በጋብቻ ቃል ኪዳን በሚስት ታስረሃልን? እንዲህ ከሆነ ከዚህ ነፃ ለመሆን አትሻ። በበጋብቻ በሚስት አልታሰርህ ወይም ያላገባህ ነህ? ሚስትን አትሻ።28ነገር ግን ካገባህ ኃጢአት አይሆንብህም። እንዲሁም ያላገባች ሴት ብታገባ ኃጢአት አይሆንባትም። ሆኖም ግን የሚያገቡ በኑሮአቸው ብዙ ችግር ይሆንባቸዋል፤ ከእንዲ ዓይነት ሕይወት እንድትርቁ እመኛለሁ።29ዳሩ ግን ወንድሞ ሆይ፤ ይህን እላለሁ፤ ዘመኑ አጭር ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸ እንደሌላቸው ይኑሩ።30የሚያላቅሱም እንደማያለቅሱ ይሁኑ፤ እንዲሁም የሚደሰቱ ደስታ እንደሌላቸው ይሁኑ፤31ደግሞ ማንኛውንም ነገር የሚገዙ ምንም እንደሌላቸ ይሁኑ፤ በዚህች ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደ ማይጠቀሙ ይሁኑ ምክንያቱም የዚች ዓለም አሠራር ሁሉ አላፊ ነውና።32ነገር ግን ያለ ጭንቀት እንድትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንደሚያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል።33ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአልና።34ያላገባች ሴት ወይም ድንግል በሥጋና በመንፈስ እንዴትምትቀደስ የጌታን ነገር ታስባለች። ያገባች ሴት ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።35ሌላ ሸክም ሊጭንባችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ጥቅም ይህን እላለሁ። ያለ ምንም ጉዳት በጌታ እንድትጸኑ ስለእውነት ይህን እላለሁ።36ዳሩ ግን ማንም ሰው ያጫትን ድንግል በአግባቡ ካልያዘ የእርስዋም ዕድሜ እየገፋ ከሄደ ሊያገባት ካሰበ ያግባት። ይህ ኃጢአት የለበትም።37ነገር ግን አንድ ሰው ላለማግባት ቢወስንና ስሜቱንም ለመቆጣጠር ከቻለ እርስዋን ባለማግባቱ መልካም ያደርጋል።38የእርሱንም እጮኛ የሚያገባት መልካም ያደርጋል፤እርስዋንም ለማግባት የማይመርጥ የበለጠ መልካም ያድርጋል።39አንዲት ሴት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ ከባልዋ ጋር የታሰረች ናት። ነገር ግን ባልዋ ቢሞት በጌታ የሆነውን ብቻ ለማግባት ነጻነት አላት።40እንደ እኔ ውሳኔ ግን ሳታገባ ብትኖር ደስተኛ ትሆናለች። እኔም የእግዚአብሔር መንፈስ ያለኝ ይመስለኛል።
1ለጣዖት ስለተሰዋ ሥጋ፦ "ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን" እናውቃለን።ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።2አንድ ሰው አንድ ነገር እንደሚያውቅ ቢያስብ፥ ያ ሰው ፥እንደሚገባ እንደሚያውቅ ገና አለወቀም።3ነገር ግን ማንም ሰው እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይታወቃል።4እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት በተመለከተ፦ "የዚህ ዓለም ጣዖት ከንቱ ነው፤" እና "ከአንዱም ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ የለም" ይህንን እናውቃለን።5ብዙ "አማልክትና ጌቶች" እንዳሉ ሁሉ፥ ምንም እንኳ በሰማይና በምድር አማልክት የተባሉ ቢኖሩ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ6እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ ብቻ አለን፤ እንዲሁም ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አለን።7ይሁን እንጂ ይህ ዕውቀት በሁሉም አይገኝም። በዚህ ፈንታ፥ አንዳንዶች ግን እስካሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ፦ ለጣዖት እንደ ተሠዋ አድርገው ይበላሉ። ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳሉ።8መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያደርሰንም። ስላልበላምንም አንረክስም፤ ወይም ስለበላንም የተሻለን አንሆንም።9ነገር ግን ይህ ነጻነታችሁ በእምነት ደካማ ለሆኑት ምክንያት ሆኖ መሰናከያ እንዳይሆን ተጠንቃቁ።10አንተ ዕውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ተቀምጠህ ስትበላ አንድ ሰው ቢያይህ፤ በእምነቱ ያልጠነከረ ሰው ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት አይደፋፈርምን?11ስለ ጣዖት ባሕርይ በአንተ ዕውቀት የተነሣ ክርስቶስ የሞተላቸው ደካማ ወንድም ወይም እህት ይጠፋሉ።12ስለዚህም ወንድሞችንና እህቶችን ስትበድሉና ደካማ ሕሊናቸውንም ስታቆሽሹ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።13ስለዚህም መብል ወንድሜንና እህቴን የሚያሰናክል ከሆን ወንድሜንና እህት እንዳላሰናክል ለዘላለ ከቶ ሥጋን አልበለም።
1እኔ ነፃ አይደለሁም? እኔ ሐዋርያስ አይደለሁም? ጌታችን ኢየሱስን አላየሁትም? እናንተስ በጌታ የሥዬ ፍሬዎች አይደላችሁም?2ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ቢያንስ ለእናንተ ሐዋርያ ነኝ። በጌታ ሐዋርያ ለመሆኔ እናንተ ማረጋገጫ ናችሁና።3ለሚጠይቁኝ መልሴ ይህ ነው።4እኛስ ለመብላትና ለመጠጣት መብት የለንም?5እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት፣ እንደ ጌታ ወንድሞች፣ እና እንደ ኬፋ፣ አማኝ የሆነች ሚስት ይዞ ለመሄድ መብት የለንም?6ወይስ የመሥራት ግዴታ ያለብን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?7በራሱ ወጪ በውትድርና የሚያገለግል ማን ነው? የወይን ተክል ተክሎ ከፍሬው የማይበላ ማን ነው? ወይስ ከሚጠብቀው መንጋ ወተት የማይጠጣ ማን ነው?8እነዚህን ነገሮች የምናገረው በሰው ሥልጣን መሠረት ነው? ሕጉስ ይህን አይልም?9በሙሴ ሕግ፦ "የሚያበራየውን በሬ፣አፉን አትሰር" ተብሎ ተጽፎአል። በእርግጥ እግዚአብሔር ስለ በሬዎች አስቦ ነው?10እየተናገረ ያለው ስለ እኛ አይደለም? የተጸፈው ስለ እኛ ነው፣ምክንያቱም የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ፣የሚያበራይም ከመከሩ ለመካፈል ተስፋ በማድረግ ሊያበራይ ይገባዋል።11በመካከላችሁ መንፈሳዊ ነገር ዘርተን ከሆነ፣ከእናንተ ቁሳዊ ነገሮችን ብናጭድ ይበዛብናል?12ሌሎች ይህን መብት ከእናንተ የሚያገኙ ከሆነ፣እኛስ የበለጠ መብት የለንም? ሆኖም ግን ይህን መብት ይገባናል አላልንም፣ይልቁንም ለክርስቶስ ወንጌል እንቅፋት እንዳንሆን ሁሉን ታገስን።13በመቅደስ የሚያገለግሉ ምግባቸውን ከመቅደስ እንደሚያገኙ አታውቁም፣በመሠዊያው ላይ የሚያገልግሉስ መሠዊያው ላይ ከሚሠዋው እንደሚካፈሉ አታውቁም?14እንዲሁም ደግሞ ወንጌልን የሚያውጁ ከወንጌል በሚገኝ እንዲኖሩ ጌታ አዟል።15እኔ ግን ከእነዚህ መብቶች አንዱንም ይገባኛል አላልሁም። ይህንንም የጻፍሁት አንዳች እንዲደረግልኝ አይደለም። ይህን ትምክህቴን ማንም ከሚወስድብኝ ሞትን እመርጣለሁ።16ይህ ግዴታዬ ስለሆነ ወንጌል ብሰብክ የምታበይበት ምክንያት የለኝም፣ ወንጌልን ባልሰብክ ግን ወዮልኝ!17ይህን በፈቃደኝነት ባደርገው ግን ሽልማት አለኝ። በፈቃደኝነት ባላደርገው ግን በአደራ የተሰጠኝ ኃላፊነት አለብኝ።18ታዲያ ሽልማቴ ምንድነው? በወንጌል ውስጥ ያለ ሙሉ መብቴን ትቼ ያለምንም ክፍያ ወንጌልን ስሰብክ ነው።19ምንም እንኳ ከሁሉም ነፃ ብሆንም፣ ብዙዎችን ለመማረክ እንድችል፣የሁሉ አገልጋይ ሆንሁ።20አይሁድን ለመማረክ እንድችል፣ እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ። ምንም እንኳ በሕግ ስር ባልሆንም፣ በሕግ ስር ያሉትን መማረክ እንድችል፣ ከሕግ ስር እንዳለ ሰው ሆንሁ።21ከሕግ ውጭ ያሉትን መማረክ እንድችል፣እኔ ራሴ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ ሳልሆን፣ ነገር ግን ከክርስቶስ ሕግ ስር እያለሁ፣ ከሕግ ውጭ እንዳለ ሰው ሆንሁ።22ደካማውን መማረክ እንድችል፣እንደ ደካማ ሆንሁ። አንዳንዶችን ማዳን እንድችል፣ ለሰዎች ሁሉ ብዬ ሁሉን ሆንሁ።23ይህን ሁሉ ያደረግሁት ከወንጌል በረከት መካፈል እንድችል፣ ስለ ወንጌል ብዬ ነው።24በሩጫ ውድድር የሚሳተፉ ሯጮች ሁሉ እንደሚሮጡ፣ ነገር ግን ሽልማት የሚቀበል አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? ስለዚህ ሽልማት ለማግኘት ሩጡ።25ለውድድር የሚዘጋጅ ሰው ሥልጠና ጊዜ ሁሉ ራሱን መቆጣጠር ይለማመዳል። እነርሱ የሚጠፋውን ሽልማት ለማግኘት ይሮጣሉ፣ እኛ ግን የማይጠፋውን ሽልማት ለማግኘት እንሮጣለን።26ስለዚህም ያለ ዓላማ አልሮጥም፣ወይም ንፋስ በቦክስ አልመታም።27ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ከውድድሩ ውጭ እንዳልሆን ሥጋዬን በመቆጣጠር አስገዛዋለሁ።
1ወንድሞች እና እህቶች፣ይህን እንድታውቁ እወዳለሁ፣አባቶቻችን ከዳመና በታች እና በባሕር ውስጥ አለፉ።2ሁሉም በዳመና እና በባሕር ውስጥ በሙሴ ተጠመቁ፣3መንፈሳዊ ምግብ ተመገቡ፣4ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ። እነርሱም ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዓለት ጠጡ፣ያም ዓለት ክርስቶስ ነበር።5ነገር ግን እግዚአብሔር በብዙዎች አልተደሰተምና ሬሳቸው ምድረ በዳ ውስጥ ወድቆ ቀረ።6እኛም እነርሱ እንዳደረጉት ክፉ ነገር እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ምሳሌ እንዲሆኑልን ተጽፈውልናል።7"ሕዝቡ ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፣በዝሙት ፍላጎት በመነሳሳት ሊጨፍሩ ተነሡ።" ተብሎ እንደተጻፈ፣ከእነርሱ አንዳንዶች እንዳደረጉት ጣዖት አምላኪዎች አትሁኑ።8ከእነርሱ ብዙዎች ዝሙት በመፈጸማቸው ምክንያት ሃያ ሦስት ሺ ሰዎች በአንድ ቀን እንደሞቱ፣እኛም ዝሙት አንፈጽም።9ከእነርሱም ብዙዎች ክርስቶስን እንደፈተኑት እና በእባብ እንደጠፉ፣እኛም ጌታን እንፈታተን።10በማጉረምረማቸው ምክንያት የሞት መልአክ እንዳጠፋቸው፣እኛም አናጉረምርም።11በእነርሱ ላይ የሆኑት እነኚህ ነገሮች ምሳሌ እንዲሆኑልን የተጻፈው፣ የዘመን ፍጻሜ ለደረሰብን ለእኛ ትምህርት እንዲሆንልን ነው።12ስለዚህ ማንም ቆሜአለሁ ብሎ የሚያስብ፣ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።13በሰው ሁሉ ላይ ከሚደርሰው በላይ የሆነ ፈተና አልደረሰባችሁም። ነገር ግን እግዚአብሔር ታማኝ ነውና ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አያደርግም። ይልቁን ፈተናውን መወጣት እንድትችሉ ከፈተናው ጋር ማምለጫ መንገዱንም ያዘጋጅላችኋል።14ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፣ከጣዖት አምልኮ ሽሹ።15ይህን የምናገራችሁ አስተዋዮች በመሆናችሁ ነው፤የምለውን አመዛዝኑ።16የምንባርከው የበረከት ጽዋ፣የክርስቶስን ደም መካፈል አይደለም? የምንቆርሰው እንጀራ የክርስቶስን ሥጋ መካፈል አይደለም?17እንጀራው አንድ እንደሆነ፣ብዙዎች ሆነን ሳለ አንዱን እንጀራ በመካፈል አንድ አካል ነን።18የእስራኤልን ሕዝብ ተመልከቱ፦ ከመሥዋዕቱ የሚበሉ ከመሠዊያው ተካፋዮች አይደሉም?19ስለዚህ ምን እያልሁ ነው? ጣዖት ምንም አይደለም እያልሁ ነው? ወይስ ለጣዖት የተሠዋ ምግብ ምንም አይደለም ማለቴ ነው?20እያልሁ ያለሁት፣አሕዛብ የሚሠዋቸው ነገሮች፣ለአጋንንት እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። ከአጋንንት ጋር ተካፋዮች እንድትሆኑ አልፈልግም! የጌታንም ጽዋ፣ የአጋንንትንም ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም።21በጌታም ማዕድ፣ በአጋንንትም ማዕድ ኅብረት ልታደርጉ አትችሉም።22ይህን ብማድረግ ጌታን ለቅናት እናነሳሳዋለን? ከእርሱ የምንበረታ ነን?23"ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፣" ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚጠቅም አይደልም። "ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፣" ነገር ግን ሁሉም ነገር ሰዎችን የሚያንጽ አይደለም።24ማንም ለራሱ መልካም የሆንውን ብቻ አያስብ። ይልቁን፣እያንዳንዱ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም የሆነውን ይፈልግ።25በገበያ ቦታ የሚሸጥ ማንኛውንም ነገር፣የኅሊና ጥያቄ ሳታነሱ መብላት ትችላላችሁ።26"ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የጌታ ነውና።"27አንድ አማኝ ያልሆነ ሰው ምግብ ቢጋብዛችሁና ግብዣውን ተቀብላችሁ መሄድ ብትፈልጉ፣ በፊታችሁ የቀረበላችሁን ማንኛውንም ነገር የኅሊና ጥያቄ ሳታነሱ ብሉ።28ነገር ግን እንድ ሰው፣"ይህ ምግብ ለጣዖት የተሠዋ ነው።" ብሎ ቢነግራችሁ አትብሉ። ይህን ማድረግ የሚገባችሁ፣ ለነገራችሁ ሰው እና ለኅሊና ስትሉ ነው።29ይህን ስል ስለ እናንተ ኅሊና ሳይሆን ስለ ሌላው ሰው ኅሊና ነው። ስለ ሌላው ኅሊና ሲባል ለምን በነፃነቴ ላይ ይፈረዳል?30ምግቡን በአክብሮት ከተቀበልሁ፣አመስግኜ ለበላሁት ነገር ለምን እሰደባልሁ?31ስለዚህ፣ስትበሉ እና ስትጠጡ፣ወይም በምታደርጉት ሁሉ፣ሁሉን ለጌታ ክብር አድርጉት።32ለአይሁዶች ወይም ለግሪኮች፣ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መሰናከያ አታድርጉ።33እኔ ሰዎችን ሁሉ በሁሉ ነገር ደስ ለማሰኘት እንደምፈልግ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ። የራሴን ጥቅም ሳይሆን፣ለብዙዎች ጥቅም የሚሆነውን እፈልጋለሁ። ይህን የማደርገው ወደ ድነት እንዲመጡ ብዬ ነው።
1እኔ ክርስቶስን እንደምመስል፣እናንተም እኔን ምሰሉ።2አሁን የማመሰግናችሁ በሁሉ ነገር ስለምታስቡኝ ነው። ለእናንተ ያስተላለፍኳቸውን ልምዶች ልክ እንደዚያው እንዳሉ አጥብቃችሁ በመያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።3ክርስቶስ የወንድ ሁሉ ራስ ፣ወንድ ደግሞ የሴት ራስ ፣ እግዚአብሔር የክርስቶስ ራስ እንደሆነ እንድትረዱ እፈልጋለሁ።4ራሱን ሸፍኖ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ የእርሱ ራስ የሆነውን ክብር ያሳጣል።5ነገር ግን ራሷን ሳትሸፍን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ራሷን ክብር ታሳጣለች። ይህን ማድረግ ልክ ጠጉሯን እንደመላጨት ነው።6ሴት ራሷን ካልሸፈነች፣ጠጕሯን አሳጥራ መቆረጥ ይኖርባታል። ሴት ጠጕሯን አሳጥራ መቆረጧ ወይም መላጭቷ አሳፋሪ ከሆነ፣ ራሷን ትሸፍን።7ወንድ ራሱን መሸፈን የለበትም፣ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔር መልክ እና ክብር ነውና።8ሴት ግን የወንድ ክብር ነች። ወንድ ከሴት አልተገኘምና። ይልቁንስ፣ሴት ከወንድ ተገኝታለች።9ወንድ ለሴት አልተፈጠረም፣ሴት ግን ለወንድ ተፈጥራለች።10ለዚህ ነው፣ ከመላእክቱ የተነሳ፣ ሴት በራሷ ላይ የሥልጣን ምልክት ሊኖራት የሚገባው።11የሆነ ሆኖ፣በጌታ ሴት ከወንድ፣ ወንድም ከሴት የተነጣጠሉ አይደሉም።12ሴት የተገኘችው ከወንድ እንደሆነ ሁሉ፣ወንድም የተገኘው ከሴት ነው። ሁሉም ነገር ደግሞ የተነኘው ከእግዚአብሔር ነው።13ራሳችሁ ፍረዱ፦ሴት ራሷን ሳትሸፈን ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ ተገቢ ነው?14ወንድስ ረጅም ጠጕር ቢኖረው አሳፋሪ እንደሆነ ተፈጥሮ ራሱ አያስተምራችሁም?15ሴት ግን ረጅም ጠጕር ቢኖራት ክብሯ እንደሆነ ተፈጥሮ ራሱ አያስተምራችሁም? ለእርሷ ጠጕር የተሰጣት እንደ መሸፈኛ ነውና።16ነገር ግን በዚህ ማንም ክርክር ሊያስነሳ ቢፈልግ፣እኛም ሆንን የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ከዚህ የተለየ ልምምድ የላቸውም።17በሚከተሉት መመሪያዎቼ ግን፣አላመሰግናችሁም። ምክንያቱም በምትሰበሰቡበት ጊዜ፣ ለተሻለ ነገር ሳይሆን እጅግ ለከፋ ነገር ትሰበሰባላችሁ።18በመጀመሪያ፣ በቤተክርስቲያን ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳለ ሰምቼአለሁ፣ ደግሞም ይህ እንደሚሆን በመጠኑም ቢሆን አምኜበታልሁ።19ምክንያቱም በእናንተ መካከል ተቀባይነትያላቸው እንዲለዩ የተለያዩ ቡድኖች መኖራቸው ግድ ነው።20በአንድነት በምትሰብሰቡበት ጊዜ፣የምትበሉት የጌታን ማዕድ አይደለምና።21በምትበሉበት ጊዜ፣ሌሎች ምግብ ከማግኘታቸው በፊት እያንዳንዱ ቀድሞ የየራሱን ምግብ ይበላል። አንዱ ተርቦ ሳለ ሌላው ይሰክራል።22የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁም? የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን በመናቅ ምንም የሌላቸውን ታዋርዳላችሁ? ምን ልበላችሁ? ታዲያ ላመስግናችሁ? ለዚህ አላምሰግናችሁም!23ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቼአለሁ፣ ጌታ ኢየሱስ ታልፎ በተሰጠበት ምሽት፣እንጀራ አንሳ።24ካመሰገነ በኋላ ቆረሰውና፣"ለእናንተ የሆነ ሥጋዬ ይህ ነው፣ይህን እኔን ለማስታወስ አድርጉት፣" አለ።25እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋን አንስቶ፣"ይህ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።ይህን በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ እኔን ለማስታወስ አድርጉት።"26ይህን እንጀራ በበላችሁ እና ይህን ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ፣ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ታውጃላችሁ።27ስለዚህ ማንም፣ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ የጌታን እንጀራ ቢበላ ወይም የጌታን ጽዋ ቢጠጣ፣ለጌታ ሥጋ እና ለጌታ ደም ተጠያቂ ይሆናል።28አንድ ሰው ራሱን ከመረመረ በኋላ እንጀራውን ይብላ ጽዋዉንም ይጠጣ።29የጌታ ሥጋ መሆኑን ሳይረዳ የሚበላ እና የሚጠጣ፣በራሱ ላይ ፍርድን ይበላል ይጠጣልም።30በመካከላችሁ ብዙዎች የታመሙ እና በሽተኞች የሆኑት ስለዚህ ነው፣ አንዳንዶችም ደግሞ ሞተዋል።31ነገር ግን ራሳችንን ብንመረምር አይፈረድብንም።32በጌታ ስንፈረድ ግን፣ከዓለም ጋር እንዳንኮነን እንገሠጻለን።33ስለዚህ፣ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ለመብላት ስትሰበሰቡ፣እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ።34ማንም የተራበ ቢኖር፣እቤቱ ይብላ፣እንዲያ ሲሆን ስትሰበሰቡ ለፍርድ አይሆንባችሁም። ስለ ጻፋችሁልኝ ሌሎች ነገሮች፣ስመጣ መመሪያዎችን እሰጣለሁ።
1ወንድሞች እና እህቶች መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተመለከተ፣የማታውቁት ነገር እንዲኖር አልፈልግም።2አረማውያን በነበራችሁበት ወቅት፣መናገር እንኳ በማይችሉ ጣዖታት ወደማታውቁት መንገድ ተመርታችሁ እንደነበር ታውቃላችሁ።3ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ፣"ኢየሱስ የተረገመ ነው፣" የሚል እንደሌለ ሁሉ፤ እንዲሁም በእግዚአብሔር መንፈስ ካልሆነ በቀር፣"ኢየሱስ ጌታ ነው፣" ሊል የሚችል እንደሌለ እወቁ።4ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ፣መንፈስ ቅዱስ ግን አንድ ነው።5አገልግሎቶች ልዩ ልዩ ናቸው፣ጌታ ግን አንድ ነው።6ልዩ ልዩ ሥራዎች አሉ፣ነገር ግን ለእያንዳንዱ ሰው ችሎታን የሚሰጥ አንዱ እግዚአብሔር ነው።7ደግሞም ለእያንዳንዱ መንፍስ ቅዱስን መግለጥ የተሰጠው ለሁሉም ጥቅም ሲባል ነው።8ለአንዱ የጥበብ ቃል በመንፈስ ቅዱስ ይሰጣል፣ለሌላው ደግሞ የእውቀት ቃል በዚያው መንፈስ ይሰጣል።9ለሌላው በዚያው መንፈስ እምነት ይሰጠዋል፣ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የፈውስ ስጦታ ይሰጠዋል።10ለሌላው ደግሞ የኃይል ሥራዎች፣ለሌላው ትንቢት መናገር። ለሌላው ደግሞ መናፍስትን መለየት፣ለሌላው በልዩ ልዩ ልሳኖች መናገር፣እና ለሌላው ልሳኖችን የመተርጎም ስጦታ ይሰጠዋል።11ነገር ግን፣ለእያንዳንዳቸው እንደወደደ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን በመስጠት በእነዚህ ሁሉ የሚሠራው ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው።12አካል አንድ ሆኖ ሳለ ብዙ ብልቶች እንዳሉት ሁሉ፣ ሁሉም ብልቶች የእንዱ አካል ክፍል እንደሆኑ፣በክርስቶስም እንዲሁ ነው።13በአንድ መንፈስ በአንድ አካል እንደተጠመቅን፣አይሁድ ይሁኑ ግሪኮች፣ባሪያ ይሁን ነጻ፣ሁሉ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተዋል።14አካል አንድ ብልት ብቻ ሳይሆን ብዙ ብልቶች አሉት።15እግር፣"እኔ እጅ አይደለሁም፣ስለዚህ የአካሉ ክፍል አይደለሁም፣" ቢል የአካሉ ክፍል መሆኑ አይቀርም።16ጆሮም ተነስቶ፣"ዓይን ስላይደለሁ፣የአካሉ ክፍል አይደለሁም፣" ቢል የአካሉ ክፍል ከመሆን አይቀነስም። አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን፣ መስማት ወዴት ይሆናል?17አካል ሁሉ ጆሮ ቢሆን፣ማሽተት ወዴት ይሆናል?18እግዚአብሔር ግን እያንዳንዱን የአካል ክፍል እንደወደደ ሠርቶታል።19ሁሉም አንድ ብልት ቢሆኑ ኑሮ፣አካል ወዴት በሆነ ነበር?20አሁን ግን ብዙ ብልቶች ያሉት፣ አንድ አካል ነው።21ዓይን እጅን፣"አንተ አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም። ራስም እግርን፣"አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም።22ነገር ግን ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣቸው ብልቶች አስፈላጊ ናቸው፣23ዝቅተኛ ግምት የምንሰጣቸውን የሰውነት ክፍሎች ትልቅ ክብር እንሰጣቸዋለን፣እምናፍርባቸውን ብልቶች ደግሞ በአክብሮት እንይዛለን።24የማናፍርባቸውን ብልቶች ደግሞ በአክብሮት መያዝ አያስፈልገንም ምክንያቱም ቀድሞዉኑ ክብር አግኝተዋል። እግዚአብሔር ግን ብልቶችን ሁሉ በአንድነት በማያያዝ ክብር ላልተሰጣቸው የበለጠ ክብርን ሰጥቷል።25እግዚአብሔር እንዲህ ያደረገው በአካል ውስጥ መከፋፈል እንዳይኖርና ይልቁን ብልቶች በበለጠ ፍቅር እርስ በርሳቸው አንዳቸው ሌላቸውን እንዲከባከቡ ነው።26እናም አንዱ ብልት ሲሰቃይ ሁሉም ብልቶች አብረው ይሰቃያሉ። አንዱ ብልት ሲከብር፣ሁሉም ብልቶች አብረው ሐሴት ያደርጋሉ።27እንግዲህ እናንተ የክርስቶስ አካል ስትሆኑ እያንዳንዳችሁ የአካሉ ብልቶች ናችሁ።28እግዚአብሔርም በቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ሐዋርያትን፣ሁለተኛ ነቢያትን፣ሦስተኛ አስተማሪዎችን፣ከዚያም ተአምራት ማድረግን፣በመቀጠል የፈውስ ስጦታዎችን፣እርዳታ የሚያደርጉትን፣ የአስተዳደር ሥራ የሚሠሩትን፣ እና ልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችን የሚናገሩትን ሰጥቷል።29ታዲያ ሁላችን ሐዋርያት ነን? ሁላችንስ ነቢያት ነን? ወይስ ሁላችን አስተማሪዎች ነን? ሁላችን ተአምራቶችን እናደርጋለን?30ሁላችን የፈውስ ስጦታዎች አሉን? ሁላችን በልሳኖች እንናገራለን? ሁላችን ልሳኖችን እንተረጉማለን?31የሚበልጡትን ስጦታዎች በከፍተኛ ጉጉት ፈልጉ። እጅግ የሚበልጠውንም መንገድ አሳያችኋልሁ።
1በሰዎች እና በመላእክት ልሳኖች ብናገር፣ግን ፍቅር ከሌለኝ፣የሚንጫጫ ቃጭል ወይም የሚጮህ ታንቡር ነኝ።2የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ የተሰወሩ እውነቶችን እና እውቀት ሁሉ ቢኖረኝ፣ተራሮችን ከስፍራቸው የሚያስወግድ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ፣ ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም የማይጠቅም ነኝ።3ድሆችን ለመመገብ ያለኝን ሁሉ ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ብሰጥ፣ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም አይጠቅመኝም።4ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይመቀኝም ደግሞም አይመካም። አይታበይም5ወይም ትህትና የጎደለው አይደለም። ራስ ወዳድ አይደለም። በቀላሉ አይበሳጭም፤ወይም በደልን አይቆጥርም።6ፍቅር በአመጽ ደስ አይሰኝም፣በእውነት ግን ደስ ይለዋል።7ፍቅር ሁሉን ይታገሳል፤ሁሉን ያምናል፤በሁሉም ድፍረት አለው በሁሉ ይጸናል።8ፍቅር ፍጻሜ የለውም። ትንቢቶች ያልፋሉ፤ልሳኖችም ቢሆኑ ያበቃሉ፤ዕውቀትም ቢሆን ጊዜ ያልፍበታል።9ከዕውቀት የተወሰነውን እናውቃልን፣ትንቢትም በከፊል እንተነቢያለን።10ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ፣ፍጹም ያልሆነው ወደ ፍጻሜ ይደርሳል።11ልጅ በነበርሁበት ጊዜ፣እንደ ልጅ እናገር ነበር፣እንደ ልጅም አስብ ነበር፣የመረዳት ችሎታዬም እንደ ልጅ ነበር። ጎልማሳ ስሆን ግን የልጅነት ነገሮችን አስወገድሁ።12አሁን በጨለማ ውስጥ ያለን ምስል በመስታዋት እንደሚያይ እንመለከታለን፣የዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን ዕውቀትን በከፊል አውቃለሁ፣የዚያን ጊዜ ግን ልክ እኔ ሙሉ በሙሉ እንደምታወቀው ሙሉ በሙሉ አውቃለሁ።13ነገር ግን እምነት፣ ተስፋ፣ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ግን ጸንተው ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጠው ፍቅር ነው።
1ፍቅርን ተከታተሉ ለመንፈሳዊ ስጦታዎችም ከፍተኛ ጉጉት ይኑራችሁ፣2በተለይም ደግሞ ትንቢት የመናገር ስጦታን በብርቱ ፈልጉ። በልሳን የሚናገር ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ይናገራል፣በመንፈስ የተሰወሩ ነገሮችን ይናገራልና ማንም አይረዳውም።3ትንቢት የሚናገር ግን ሰዎችን ለማነጽ፣ለማበረታታትና፣ ለማጽናናት፣ ይናገራል።4በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፣ትንቢት የሚናገር ግን ቤተክርስቲያንን ያንጻል።5እንግዲህ ሁላችሁም በልሳኖች ብትናገሩ ምኞቴ ነበር። ከዚያ ይበልጥ ትንቢት ብትናገሩ እወዳለሁ። በልሳን የተነገረውን የሚተረጉም ከሌለ፣ ቤተክርስቲያን እንድትታነጽ ልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር ይበልጣል።6ወንድሞች እና እህቶች፣ልሳን እየተናገርሁ ወደ እናንተ ብመጣ ምን እጠቅማችኋለሁ? በመገለጥ፣ወይም በእውቀት፣ወይም በትንቢት፣ወይም በማስተማር ካልሆነ ልጠቅማችሁ አልችልም።7ሕይወት የሌላቸው እንደ ዋሽንት ወይም ክራር ያሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች መለየት የሚቻሉ ድምፆችን ካላወጡ፣አንድ ሰው የትኛው የሙዚቃ መሣሪያ እንደተጫወተ እንዴት ማወቅ ይችላል?8መለከት ሊለይ በማይቻል ድምፅ ቢነፋ፣አንድ ሰው ለጦርነት ለመዘጋጀት ጊዜው እንደሆነ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?9እናንተንም በተመለከተ እንዲሁ ነው። ሊታወቅ የማይችል ንግግር ብትናገሩ አንድ ሰው ምን እንደተናገራችሁ እንዴት ሊያውቅ ይችላል? እናንተ ትናገራላችሁ ነገር ግን ማንም አይረዳችሁም።10በዓለም ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች እንዳሉ ጥርጥር የለውም፣11አንዳቸውም ግን ትርጉም የሌላቸው አይደሉም። የአንድን ቋንቋ ትርጉም የማላውቅ ከሆን ለሚናገረው ሰው እንግዳ እሆንበታለሁ፣ተናጋሪውም እንግዳ ይሆንብኛል።12ለእናንተም እንዲሁ ነው። ለመንፈስ ቅዱስ መገለጦች ከፍተኛ ፍላጎት ስላላችሁ፣ቤተክርስቲያንን ለማነጽ ጉጉት ይኑራችሁ።13ስለዚህ በልሳን የሚናገር መተርጎም እንዲችል ይጸልይ።14በልሳን በምጸልይበት ጊዜ መንፈሴ ይጸልያል፣አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።15ታዲያ ምን ላድርግ? በመንፈሴም እጸልያልሁ፣በአእምሮዬም እጸልያለሁ። በመንፈሴ እዘምራለሁ፣በአእምሮዬም እዘምራለሁ።16እንደዚያ ካልሆነ ግን እግዚአብሔርን በመንፈሳችሁ ብታመሰግኑና ሌላው ሰው በምታመሰግኑበት ሰዓት ምን እያላችሁ እንደሆነ ካላወቀ እንዴት "አሜን" ይላል?17በእርግጠኝነት በሚገባ እያመሰገናችሁ ነው፣ሌላው ሰው ግን እየታነጸበት አይደለም።18ከሁላችሁም የበለጠ በልሳን ስለምናገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።19በቤተክርስቲያን ውስጥ ግን ሰዎችን ማስተማር እንድችል፥ በልሳን አሥር ሺ ቃላትን ከምናገር፣ በአእምሮዬ አምስት ቃላትን መናገር እመርጣለሁ።20ወንድሞች እና እህቶች፣በአስተሳሰባችሁ ልጆች አትሁኑ። ይልቁን ክፋትን በተመለከተ እንደ ሕፃናት ሁኑ። ነገር ግን በአስተሳሰባችሁ ይበልጥ የበሰላችሁ ሁኑ።21በሕጉ እንደተጻፈው፣"የማያውቁት ቋንቋ ባላቸው ሰዎችና እንግዳ በሆነ ንግግር ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ። እንደዚያም ሆኖ አይሰሙኝም፣" ይላል እግዚአብሔር።22ስለዚህ ልሳኖች ለአማኞች ሳይሆን አማኝ ላልሆኑ ሰዎች ምልክት ናቸው። ትንቢት መናገር ግን ለማያምኑ ሰዎች ሳይሆን ለአማኞች ምልክት ነው።23ስለዚህ፣ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ሰው ሁሉ ቢሰበሰብ እና በልሳኖች በመናገር ላይ እያሉ ከውጭ ያሉና የማያምኑ ሰዎች ቢገቡ አብደዋል አይሉምን?24ነገር ግን ሁላችሁም ትንቢት እየተናገራችሁ ባለበት ሰዓት አማኝ ያልሆነ ወይም የውጭ ሰው ቢገባ በሚሰማው ነገር ሁሉ ኃጢአተኝነቱ ይሰማዋል። በሚነገረው ነገር ሁሉ ይፈረድበታል።25የልቡም ምስጢር ሁሉ ይገልጣል። ከዚህም የተነሳ፣ በግንባሩ ተደፍቶ እግዚአብሔርን ያመልካል። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው! ብሎ ያውጃል።26ታዲያ ምን ይሁን፣ወንድሞች እና እህቶች? በአንድነት በምትሰበሰቡበት ጊዜ፣እያንዳንዳችሁ መዝሙር፣ትምህርት፣መገለጥ፣ልሳን፣ወይም ልሳን መተርጎም አላችሁ። የምታደርጉትን ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማንጽ አድርጉት።27ማንም በልሳን ቢናገር ሁለትም ሦስትም ብትሆኑ ተራ በተራ አድርጉት። ሌላው ሰው ደግሞ በልሳን የተነገረውን ይተርጉም።28የሚተረጉም ከሌለ ግን፣ሁሉም ሰው ድምፁን ሳያሰማ ለራሱ እና ለእግዚአብሔር ብቻ ይናገር።29ሁለት ወይም ሦስት ነቢያቶች በሚናገሩበት ጊዜ ሌሎች የሚነገረውን በመመርመር ያዳምጡ።30ነገር ግን በስብሰባው ውስጥ አንድ ሰው መረዳት ከመጣለት በመናገር ላይ ያለው ዝም ይበል።31ትንቢት ስትናገሩ ሁሉም ሰው እንዲበረታታ እያንዳንዳችሁ ተራ በተራ መናገር ትችላላችሁ።32የነቢያቶች መንፈስ ለነቢያት ይገዛል።33እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ ግራ የመጋባት አምላክ አይደለም። በሁሉም የአማኞች አብያተክርስቲያናት ውስጥ፦34ሴቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ዝም ይበሉ። እንዲናገሩ አይፈቀድላቸውም። ሕጉ ይህን ይላልና ይልቁንስ ይገዙ ።35ሊያውቁ የሚፈልጉት ነገር ቢኖር፣ባሎቻቸውን በቤት ውስጥ ይጠይቁ። ሴት በቤተክርስቲያን ውስጥ መናገሯ አሳፋሪ ነውና።36የእግዚአብሔር ቃል የመጣው ከእናንተ ነውን? ወይስ ወደ እናንተ ብቻ ደርሷልን?37ማንም ሰው ራሱን ነቢይ እንደሆነ ወይም መንፈሳዊ እንደሆነ ቢያስብ፣የጻፍሁላችሁ ነገሮች የጌታ ትዕዛዛት እንደሆኑ ሊያውቅ ይገባዋል።38ነገር ግን ማንም ይህን ባያውቅ እርሱም ዕውቅና አያግኝ።39እንግዲህ ወንድሞች እና እህቶች፣ትንቢትን መናገር በቅንነት ፈልጉ፣ ማንንም ልሳኖችን እንዳይናገር አትከልክሉ።40ነገር ግን ማንኛውም ነገር በመልካም ምግባር እና በሥርዓት ይደረግ።
1ወንድሞች እና እህቶች፣ ስላወጅሁላችሁ እና እናንተም ጸንታችሁ ስለቆማችሁበት ወንጌል አሳስብባችኋለሁ።2የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣በዚህ ወንጌል መዳን ይሆንላችኋል፣አለዚያ ግን ማመናችሁ ምንም ጥቅም የለውም።3ለእናንተ ያስተላለፉሁት በቀዳሚነት አስፈላጊ የሆነውን እና እኔም የተቀበልሁትን ነው፤ መጽሐፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፣4ተቀበረ፣ በሦስተኛውም ቀን ተነሳ፣መጽሐፍትም ይህን ያረጋግጣሉ።5ለኬፋ ታየ፣ከዚያም ለእሥራ ሁለቱ።6እንደገና ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ወንድሞች እና እህቶች በእንድ ጊዜ ታየ። አብዛኛዎቹ እስካሁን ድረስ በሕይወት አሉ፣የተወሰኑት ደግሞ አንቀላፍተዋል።7ከዚያም ለያዕቆብ፣ደግሞም ለሐዋርያቱ ሁሉ ታየ።8ከሁሉም በኋላ፣ያለ ጊዜው እንደተወለደ ልጅ ለሆንሁት ለእኔ ታየ።9ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና። የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን አሳድጃለሁና ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም።10ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁትን ሆኜአለሁ፣በእኔ ውስጥ የነበረው ጸጋም በከንቱ አልነበረም። ይልቁን ከሁሉም በላይ ጠንክሬ ሠራሁ። ሆኖም ይህ የሆነው ከእኔ ሳይሆን ከእኔ ጋር ካለው የእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ነው።11ስለዚህ እኔም ሆንሁ እነርሱ ስንሰብክላችሁ አመናችሁ።12አሁን ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ ከተሰበከ፣ከእናንተ አንዳንዶች ታዲያ እንዴት የሙታን ትንሣኤ የለም ይላሉ?13ሙታን ትንሣኤ ከሌለ እንግዲያው ክርስቶስም ከሙታን አልተነሳማ።14ክርስቶስም ካልተነሳ ስብከታችንም፣የእናንተም እምነት ዋጋ የሌለው ሆኗላ።15እንግዲህ እኛም ስለ እግዚአብሔር የሐሰት ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፣ ምክንያቱም እርሱ ክርስቶስን ሳያስነሳ እኛ አስነስቶታል በማለታችን በእግዚአብሔር ላይ በሐሰት መስክረንበታል።16ሙታን ካልተነሱ፣ክርስቶስም አልተነሳም ማለት ነው።17ክርስቶስ ካልተነሳ ደግሞ፣ እምነታችሁ ምንም ዋጋ የለውምናም አሁንም በኃጢአታችሁ አላችሁ።18ስለዚህ በክርስቶስ ሆነው የሞቱ ደግሞ ጠፍተዋል ማለት ነው።19ክርስቶስ ተስፋ ያደረግነው ለዚህ ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ከሰዎች ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን።20አሁን ግን ክርስቶስ ከሙታን ሁሉ በኩር ሆኖ ተነስቷል።21ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደመጣ፣ የሙታን ትንሣኤም በአንድ ሰው በኩል መጥቷል።22በአዳም ሁሉም እንደሞቱ፣ሁሉም ደግሞ በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ።23ግን እያንዳንዱ በቅደም ተከተሉ መሠረት፦ ክርስቶስ በኩር፣ ቀጥሎ የክርስቶስ የሆኑት እርሱ ተመልሶ ሲመጣ ሕያዋን ይሆናሉ።24ከዚያም ክርስቶስ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር አብ ሲያስረክብ ፍጻሜ ይሆናል። ይህም የሚሆነው ግዛትን ሁሉ፣ ሥልጣንን ሁሉ፣ እና ኃይልን ሁሉ ሲደመስስ ነው።25ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሮቹ ስር እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋል።26ሊደመሰስ የሚገባው የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው።27"ሁሉን ከእግሮቹ በታች አደረገ።" ነገር ግን፣"ሁሉን አደረገ፣" ሲል፣ሁሉን እንዲገዛለት ያደረገውን እንደማይጨምር ግልጽ ነው።28ሁሉም ሲገዛለት፣ ልጁ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ ይገዛል። ይህ የሚሆነው እግዚአብሔር አብ ሁሉ በሁሉ እንዲሆን ነው።29አለበዚያ ግን ፤ ስለ ሙታን የሚጠመቁ ሰዎች ለምን ያደርጉታል? ሙታን ፈጽሞ የማይነሱ ከሆነ፣ስለምን ያጠምቁላቸዋል?30ስለምንስ በየሰዓቱ አደጋ ውስጥ እንወድቃለን?31ወንድሞች እና እህቶች፣ ስለ እናንተ በክርስቶስ ባለኝ ትምክህት ይህን እናገራለሁ፦ በየቀኑ እሞታለሁ ።32በሰው ዓይን ሲታይ፣ በኤፌሶን ከአውሬዎች ጋር መጋደሌ፣ ሙታን የማይነሱ ከሆነ ምን ይጠቅመኛል? "ነገ መሞታችን ስለማይቀር፣እንብላ፣ እንጠጣ።"33አትታለሁ፦ "መልካም ያልሆነ ግንኙነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።"34ራሳችሁን ተቆጣጠሩ! የጽድቅ ሕይወት ኑሩ! ኃጢአት ማድረግን አትቅጠጥሉ። አንዳንዶቻችሁ ስለ እግዚአብሔር ዕውቀት የላችሁም። ይህን የምላችሁ ላሳፍራችሁ ነው።35አንዳንዶች ግን እንዲህ ይላሉ፣"ሙታን የሚነሱት እንዴት ነው? በምን ዓይነት አካል ይመጣሉ?"36ዕውቀት የጎደላችሁ ናችሁ! የዘራችሁት ዘር ካልሞተ አይበቅልም።37የዘራችሁት አካል ተምልሶ አይበቅልም፣ይልቁን ዘር ነው እንጂ። ስንዴ ወይም የተዘራውን ሌላ ዓይነት ዘር ሆኖ ይበቅላል።38እግዚአብሔር እንደወደደ አካልን ይሰጠዋል፣ለእያንዳንዱም ዘር የራሱን አካል ይሰጠዋል።39ሥጋ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም። ይልቁን፣ የሰው ሥጋ አለ፣ እንዲሁም የእንሰሳት ሥጋ አለ፣ የአእዋፍት ሥጋም እንዲሁ፣ ዓሣም ደግሞ ሌላ ዓይነት ሥጋ አለው።40እንዲሁም ደግሞ ሰማያዊ አካልና ምድራዊ አካል አለ። ነገር ግን የሰማያዊ አካል ክብር አለ የምድራዊ አካል ክብር ደግሞ ሌላ ነው።41የፀሐይ ክብር አለ፣ የጨረቃ ክብር ደግሞ ሌላ ነው፣ ከዋክብት ደግሞ ሌላ ክብር አላቸው። የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ይለያል።42የሙታን ትንሣኤም ልክ እንደዚሁ ነው። የተዘራው የሚጠፋ ነው፣ የሚነሳው ደግሞ የማይጠፋ ነው።43ሲዘራ በውርደት ሲነሳ ግን በክብር ነው። ሲዘራ በድካም፣ሲነሳ ግን በኃይል ነው።44የተዘራው ፍጥረታዊ አካል፣የሚነሳው ግን መንፈሳዊ አካል ነው። ፍጥረታዊ አካል እንዳለ ሁሉ መንፈሳዊ አካልም አለ።45እንዲህም ተብሎ ተጽፎአል፣ "የመጀመሪያው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ።" የመጨረሻው አዳም ግን ሕይወት ሰጭ መንፈስ ሆነ።46መጀመሪያ የመጣው መንፈሳዊው ሳይሆን ፍጥረታዊው ነው፣ከዚያም መንፈሳዊው ተከተለ።47የመጀመሪያው ሰው ከምድር ሲሆን የተሠራውም ከአፈር ነው። ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው።48አንዱ ከአፈር እንደተሠራ፣ከአፈር የተሠሩ ሁሉ እንዲሁ ናችው። እንዲሁም ከሰማይ እንደሆነው ሰው፣ ከሰማይ የሆኑትም እንዲሁ ናቸው።49ልክ እኛ ከአፈር የተሠራውን ሰው እንደምንመስል፣ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩን ሰው መልክ እንይዛለን።50ወንድሞች እና እህቶች፣ አሁን እንዲህ እላለሁ፣ሥጋ እና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርስ አይችልም። እንዲሁም የሚጠፋው የማይጠፋውን ሊወርስ አይችልም።51ምስጢር የሆነ እውነት እነግራችኋለሁ፦ ሁላችን አንሞትም፣ግን ሁላችን እንለወጣለን።52የመጨረሻው መለከት ሲነፋ፣ዐይን ተጨፍኖ እስኪገለጥ ባለ ፍጥነት ድንገት እንለወጣለን። መለከቱ ሲነፋ፣ ሙታን የማይጠፋውን አካል ለብሰው ይነሳሉ፣ እኛም እንለወጣለን።53ይህ የሚጠፋው የማይጠፋውን ይለብሳል፣ ሟቹ ደግሞ የማይሞተውን ይለብሳል።54የሚጠፋው የማይጠፋውን ሲለብስ፣እና ይህ ሟች የሆነው የማይሞተውን ሲለብስ፣ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ይፈጸማል፣"ሞት በድል ተዋጠ።"55ሞት ሆይ ድል ማድረግህ የት አለ? ሞት ሆይ መንደፊያህ የት አለ?"56የሞት መንደፊያ ኃጢአት ነው፣ የኃጢአት ኃይል ደግሞ ሕጉ ነው።57ነገር ግን በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ ድል የሚሰጠን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!58ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የጸናችሁ እና የማትነቃነቁ ሁኑ። ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ሥራ ይብዛላችሁ፣ምክንያቱም በጌታ የምትደክሙት ድካም በከንቱ አይደለም።
1አሁን ደግሞ ለአማኞች የሚሰበሰበውን ገንዘብ በተመለከተ፣የገላትያ አብያተክርስቲያናትን እንዳዘዝሁት ሁሉ፣እናንተም እንደዚሁ አድርጉ።2እኔ ስመጣ ገንዘብ ከመሰብሰብ፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣እያንዳንዳችሁ እንደቻላችሁት መጠን የተወሰነ ገንዘብ አጠራቅሙ።3ወደ እናንተ በደረስሁ ጊዜ በመረጣችሁት ሰው በኩል ከደብዳቤ ጋር መባችሁን ወደ እየሩሳሌም እልከዋለሁ።4የእኔም መሄድ አስፈላጊ ከሆነ ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።5ነገር ግን ወደ መቄዶንያ መሄዴ ስለማይቀር፣ በመቄዶንያ በኩል ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ። በምሄድበት ሁሉ ለጉዞዬ እንድትረዱኝ፣6ምናልባትም ከእናንተ ጋር ልቆይና ክረምቱንም ከእናንተ ጋር ላሳልፍ እችላልሁ።7አሁን ግን ጊዜው ስለሚያጥር ላያችሁ አላስብም። ጌታ ቢፈቅድና ብመጣ ግን ከእናንተ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ለመቆየት ተስፋ አደርጋልሁ።8ግን በኤፌሶን እስከ በዓለ ኅምሳ ቀን ድረስ እቆያልሁ፣9ሰፊ በር የተከፈተልኝ ቢሆንም ብዙ ተቃዋሚዎች አሉብኝ።10ጢሞቴዎስ ልክ እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና ወደ እናንተ ሲመጣ፣ያለ አንዳች ስጋት ከእናንተ ጋር እንዲቀመጥ አድርጉ።11ማንም አይናቀው። ወደ አኔ ሲመጣ በሰላም እንዲሄድም እርዱት። ምክንያቱም ከሌሎች ወንድሞች ጋር እንዲመጣ እጠብቃለሁ።12አጵሎስን በተመለከተ፣ከወንድሞች ጋር በመሆን እንዲጎበኛችሁ አበረታትቼው ነበር። አሁን ለመምጣት አልወሰነም፣ይሁን እንጂ ዕድሉን ሲያገኝ ይመጣል።13ተጠንቀቁ፣በእምነትም ጸንታችሁ ቁሙ፣ቆራጦች ሁኑ፣በርቱ።14የምታደርጉት ሁሉ በፍቅር ይሁን።15የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች ታውቃላችሁ። እነርሱ በአካይያ የመጀመሪያ አማኞች እንደሆኑና አማኞችን ለማገልገል ራሳችውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ። ወንድሞች እና እህቶች16እንደዚህ ላሉ ሰዎች፣ በሥራ እየረዱንና አብረውን እየደከሙ ላሉ ሰዎች ሁሉ እንድትገዙ አሳስባችኋለሁ።17በእስጢፋኖስ፣በፈርዶናጥስ፣ እና በአካይቆስ መምጣት ተደስቼአልሁ። የእናንተን በዚህ ያለመኖር ጉድለት ሞልተውልኛል።18የእኔን እና የእናንተን መንፈስ አድሰዋል። እንዲህ ላሉ ሰዎችን እውቅና ስጧቸው።19በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ፣ እንዲሁም በቤታቸው ያለችው ቤተክርስቲያን በጌታ ስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።20ወንድሞች እና እህቶች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተለዋወጡ።21እኔ ጳውሎስ፣ ይህን በእጄ ጽፌአለሁ።22ማንም ጌታን የማይወድ ቢኖር፣ የተረገመ ይሁን። ጌታ ሆይ ና!23የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።24በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅሬ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
1በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ እና ወንድማችን ከሆነው ጢሞቲዎስ፥ በቆሮንቶስ ለምትገኝ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ላሉ አማኞች ሁሉ፡2ከእግዚአብሔር ከአባታችን እንዲሁም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ለናንተ ይሁን።3የምህረት አባት፥ የመፅናናት አምላክ እና በመከራችን ሁሉ የሚያፅናናን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።4እግዚአብሔር በመከራችን ሁሉ ያፅናናል፥እኛም ራሳችን በእርሱ በእግዚአብሔር በተፅናናንበት መፅናናት ልክ ሌሎችን ማፅናናት እንችላለን።5ምክንያቱም የክርስቶስ መከራ በእኛ ላይ እንደበዛ፥ መፅናናታችንም በክርስቶስ በኩል እንዲሁ ይበዛልናል።6ነገር ግን መከራን ብንቀበል፥ስለናንተ መፅናናት እና ድነት ነው። ወይንም ደግሞ የእኛ መፅናናት የእናንተም መፅናናት ማለት ነው፤ይህም እኛ በምንቀበለው መከራ እናንተም በተመሳሳይ መልኩ በትእግስት አብራችሁን ስለምትካፈሉ ነው።7በናንተም ያለን መታመን ፅኑ ነው፥በመከራችን እንደምትካፈሉ ሁሉ በመፅናናታችንን ደግሞ እንደምትካፈሉ እናውቃለን።8ወንድሞች ሆይ፥በእስያ ስለደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ በህይወት ለመኖር ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከአቅማችን በላይ ከብዶን ነበር።9በርግጥም ሞት ተፈርዶብን ነበር። ሆኖም ግን ያ የደረሰብን መከራ ሙታንን በሚያስነሳ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን አደረገን።10ከብርቱ ጥፋት አዳነን እንዲሁም ያድነናል። መታመናችንን በእርሱ ላይ አድርገናል፤እርሱም ይታደገናል።11በእናንተም የፀሎት ድጋፍ አምላካችን ስራውን ይሰራል። በመቀጠልም በብዙዎች ፀሎት አማካኝነት ለእኛ ስለተሰጠው ሞገስ በርካቶች ምስጋናን ያቀርባሉ።12የምንመካው በህሊናችን ምስክርነት ላይ ነው። ምክንያቱም በዚህ ዓለም ስንመላለስ የነበረው በንፁህ ህሊና እና ከእግዚአብሔር በሚሰጥ ቅንነት ነበር። በተለይም ከናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት የተመሰረተው በእግዚአብሔር ፀጋ ላይ እንጂ በምድራዊ ጥበብ ላይ አልነበረም።13ልታነቡትና ልትረዱት የማትችሉትን አንዳችም ነገር አንዳልፃፍንላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤14እናንተም በከፊል እንደተረዳችሁን በጌታችን በኢየሱስ ቀን እናንተ በእኛ እንደምትመኩ እኛም እንዲሁ በእናንተ እንመካለን።15ስለዚህ ርግጠኛ ስለነበርሁ፥ በመጀመሪያ ወደናንተ መምጣት ፈለግሁ፤ ይህ ደግሞ በሁለቱም ጉብኝቶቼ ተጠቃሚዎች እንድትሆኑ ነው።16ወደ መቄዶንያ ስሄድ ልጎበኛችሁ ፤ከዚያ ደግሞ ክመቄዶንያ ስመለስ ላያችሁ፤በኋላ ግን እናንተው ወደ ይሁዳ እንደምትልኩኝ አቅጄ ነበር።17ይህንን ሳስብ ታዲያ የወላወልኩ ይመስላችኋልን? ወይስ በአንድ ጊዜ እንደ ሰው መስፈርት "አዎን፥ አዎን" እና "አይደለም፥አይደለም" በማለት አቀድኩን?18ነገር ግን እግዚአብሔር የታመነ እንደሆነ፣ እኛም በሁለት ቃል "አዎን" እና "አይደለም" ብለን አንናገርም።19ምክንያቱም በእናንተ መካከል በእኔ፥ በስልዋኖስ እና በጢሞቲዎስ የተሰበከው የእግዚአብሔር ልጅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በአንድ ጊዜ "አዎን" እና "አይደለም" አልነበረም፥ይልቅስ ሁልጊዜም በእርሱ "አዎን" ነው።20በእርሱ የእግዚአብሔር ተስፋዎች ሁሉ "አዎን" ናቸው። ስለዚህ እኛም በእርሱ በኩል ለእግዚአብሔር ክብር "አሜን" እንላለን።21እንግዲህ እኛንም ከእናንተ ጋር በክርስቶስ የሚያፀናን እንዲሁም የሾመን እግዚአብሔር ነው።22ለዚህም ወደፊት ለሚሰጠን ዋስትና እንዲሆነን መንፈሱን በልባችን የሰጠን ማህተሙንም ያደረገብን እርሱ ነው።23ሆኖም ግን ወደ ቆሮንቶስ ያልመጣሁት እንዳላሳዝናችሁ አስቤ እንደሆነ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።24እኛም እምነታችሁ ምን መምሰል እንዳለበት በናንተ ላይ ልናዝዝ ሳይሆን በእምነታችሁ ፀንታችሁ እንድትቆሙ ለደስታችሁ የምንሰራ ነን።
1ስለዚህም በበኩሌ እንደገና ላስከፋችሁ ተመልሼ መምጣት አልፈለግሁም።2ባስከፋችሁ እንኳ ሊያስደስተኝ የሚችለው ያው ያስከፋሁት ሰው አይደለምን?3እንደፃፍኩላችሁ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ የሚገባችው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ ነው። ስለሁላችሁም እርግጠኛ የምሆንበት በእኔ ያለ ደስታ በተመሳሳይ መልኩ በእናንተም ዘንድ ያለ መሆኑ ነው።4የፃፍኩላችሁም በታላቅ ጭንቀት፥ በልብ መናወጥ እንዲሁም በብዙ እንባ ነበር፥ ምክንያቱ ደግሞ ለናንተ ያለኝን ጥልቅ ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳላሳዝናችሁ ነው።5ማንም ያሳዘነ ሰው ቢኖር እኔን ብቻ ያሳዘነ ሳይሆን በተወሰነ መልኩ ሁላችሁንም ነው።6ለዚያም ሰው በብዙዎች የደረሰበት ቅጣት ይበቃዋል።7ግን ይህን ሰው በብዙ ሐዘን እንዳይዋጥ ከመቅጣት ይልቅ ይቅር ልትሉትና ልታፅናኑት ይገባል።8ስለዚህም ለዚህ ሰው ፍቅራችሁን በይፋ እንድታረጋግጡለት አደፋፍራችኋለሁ።9የፃፍኩላችሁ በሁሉ ነገር ታዛዦች መሆናችሁን እንድፈትንና እንዳውቅ ነው።10አንድን ሰው ይቅር ብትሉት፣ እኔም ያንን ሰው ይቅር እለዋለሁ። እኔ ይቅር የምለው አንዳች ነገር ቢኖር ይቅርታ የማደርግለት በክርስቶስ ፊት ስለ እናንተ ስል ነው።11ይህን የማደርገውም ሰይጣን እንዳያታልለን ነው። ምክንያቱም የርሱን እቅድ አንስተውምና።12ምንም እንኳ ወደ ጥሮአዳ ስመጣ የክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ በጌታ በር ተከፍቶልኝ ነበር። ሆኖም ወንድሜን ቲቶን በዚያ ስላላገኘሁት በአዕምሮዬ አላረፍኩም ነበር።13ስለሆነም እነርሱን ትቼ ወደ መቄዶንያ ተመለስኩ።14ነገር ግን ሁልጊዜ በክርስቶስ በድል ለሚመራን፥ ጣፋጭ የእውቀት ሽታ በየስፍራውም ለሚናኘው ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።15ምክንያቱም በሚድኑትና በሚጠፉት መካከል ለእግዚአብሔር የክርስቶስ ጣፋጭ ሽታ ነን።16ለሚጠፉት ሰዎች፥ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ስንሆን ለሚድኑት ደግሞ ለህይወት የሚሆን የህይወት ሽታ ነን። ለነዚህ ነገሮች የበቃ ማነው?17የእግዚአብሔርን ቃል ለትርፋቸው እንድሚነግዱበት እንደ ብዙዎች አይደለንም። በዚያ ፈንታ በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት፥ ከእግዚአብሔር እንደተላክን በቅን ልቦና እንናገራለን።
1ራሳችንን እንደገና ልናወድስ እንጀምራለንን? አንዳንድ ሰዎች እንደሚያደርጉት ለናንተም ሆነ ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን? አያስፈልገንም።2እናንተ ራሳችሁ በልባችን ላይ የተፃፋችሁ፥በሁሉም ሰዎች የምትታውቁ እና የምትነበቡ የድጋፍ ደብዳቤያችን ናችሁ።3በእኛ የቀረባችሁ የክርስቶስ መልዕክት ከመሆናችሁም በላይ በህያው የእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም ያልተፃፋችሁ፤በሰዎች የልብ ፅላት ላይ እንጂ በድንጋይ ፅላት ላይ ያልተቀረፃችሁ ናችሁ።4እንግዲህ በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ላይ ይህ መታመን አለን።5ከእኛ የሆነ ብለን ልናስበው የምንችል አንዳች ችሎታ የለንም፤ነገር ግን ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው።6እርሱም የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች አደረገን። ይህ ኪዳን የፊደል ሳይሆን የመንፈስ ነው። ምክንያቱም ፊደል ይገድላል፣ መንፈስ ግን ህይወትን ይሰጣል።7የእስራኤል ህዝብ ከፊቱ ክብር የተነሳ እያደር የሚደበዝዘውን የሙሴን ፊት መመልከት እስኪያቅታቸው ድረስ በፊደላት በድንጋይ ላይ የተቀረፀው የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፤8የመንፈስ አገልግሎት እጅግ በክብር አይልቅምን?9የኩነኔ አገልግሎት ክብር ከነበረው፥የፅድቅ አገልግሎት እንደምን በክብር ይብዛ!10በርግጥም ቀድሞ በክብር የነበረው ከሱ በሚበልጥ ክብር ተሽሯል።11አላፊው በክብር ከሆነ ፀንቶ የሚኖረው በክብር እንዴት ይበልጥ!12እንግዲያውስ እንዲህ ያለ ትምክህት ስላለን እጅግ በድፍረት እንናገራለን።13እኛ የእስራኤል ህዝቦች የሚያልፈውን ክብር ትኩር ብለው መመልከት እንዳልቻሉት፤ ፊቱን በመሸፈኛ እንደ ከለለው እንደ ሙሴ አይደለንም።14ሆኖም ግን አእምሮዋቸው ተሸፈነባቸው። እስከዛሬም አሮጌው ኪዳን ሲነበብ ያው መሸፈኛ ይኖራል፤ሊገለጥም አይችልም፤ ምክንያቱም ሊወገድ የሚችለው በክርስቶስ ነው።15ሆኖም ግን እስከዛሬ ድረስ የሙሴ ህግ ሲነበብ በልባቸው ላይ መሸፈኛው ይኖራል።16ሰው ግን ወደ ጌታ መለስ ሲል ፥መሸፈኛው ይነሳል።17ጌታም መንፈስ ነው፤የጌታም መንፈስ ባለበት ነፃነት አለ።18እኛም ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት የጌታን ክብር እያየን እርሱን ወደሚመስል ከአንድ ክብር ደረጃ ወደ ሌላ ክብር ደረጃ እንለወጣለን፤ይህም የሚሆነው መንፈስ ከሆነው ጌታ ነው።
1እንግዲህ፥ይህ አገልግሎት ስላለን እንዲሁም ምህረት እንደተቀበልን መጠን፥ ተስፋ አንቆርጥም።2በዚያ ፈንታ ግን አሳፋሪ እና ድብቅ የሆኑ መንገዶችን ክደናል። የተንኮል ህይወት አንኖርም፥የእግዚአብሔርንም ቃል ያለ አግባብ አንጠቀምበትም። እውነትንም እየተናገርን ራሳችንን ለሰው ሁሉ ህሊና በእግዚአብሔር ፊት እናቀርባለን።3ሆኖም ግን ወንጌላችን የተሸፈነ ቢሆን፥የተሸፈነው ለሚጠፉት ሰዎች ብቻ ነው።4በእነርሱ ሁኔታ ታዲያ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምን አዕምሮዋቸውን አሳውሮታል። በዚህም የእግዚአብሔር መልክ የሆነውን የክርስቶስን የክብር ወንጌል ብርሃን እንዳያዩ አደረጋቸው።5ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክም፥እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ስንል የእናንተ አገልጋዮች ነን።6ውስጥ ብርሃን ይብራ" ያለው ራሱ እግዚአብሔር ነው፤እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔር ክብር የእውቀት ብርሃን እንዲሰጠን በልባችን ውስጥ አበራልን።7ነገር ግን እጅግ ታላቅ የሆነው ሃይሉ ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳልሆነ ለማሳየት ይህ ሃብት በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን።8በሁሉ መንገድ መከራን እንቀበላለን፥ሆኖም በዚያ አንዋጥም። እናመነታለን ነገር ግን ተስፋ በማጣት አንረበሽም።9ቢሆንም ግን ተረስተን አንቀርም።10የኢየሱስ ህይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ የእርሱን ሞት ሁልጊዜ በሰውነታችን እንሸከማለን።11ይህም የኢየሱስ ህይወት በሰብዓዊ ሰውነቶቻችን እንዲገለጥ እኛ ህያዋን የሆንን በየዕለቱ ስለ ኢየሱስ ምክንያት ለሞት ታልፈን እንሰጣለን።12በዚህም ምክንያት ሞቱ በእኛ፥ ህይወቱም በእናንተ ይሰራል።13ነገር ግን "አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ"ተብሎ እንደተፃፈ፡ ሁላችንም አንድ አይነት የእምነት መንፈስ አለን። ስለምናምንም እንናገራለን።14ጌታ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው እኛንም ከእርሱ ጋር ያስነሳናል። ከእናንተም ጋር ወደ ፊቱ እንዲያመጣን እናውቃለን።15የሚሆነው ለእናንተ ጥቅም ሲሆን ፀጋ ለብዙዎች ሲበዛ ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ምስጋናም ይጨምራል።16ስለዚህም ተስፋ አንቆርጥም። ምንም እንኳ ውጫዊው ማንነታችን እየደከም ቢመጣም ውስጣዊው ማንነታችን ዕለት በየዕለት ይታደሳል።17ይህ ጊዜያዊ፣ ቀላል መከራችን መለኪያ ለሌለው፥ ለላቀው ዘላለማዊ ክብር የሚያዘጋጀን ነው።18የሚታዩትን ነገሮች ሳይሆን የማይታዩትን ነገሮች እንመለከታለን። የምናያቸው ነገሮች ጊዜያዊ ሲሆኑ የማይታዩት ነገሮች ግን ዘላለማዊ ናቸው።
1ምድራዊው መኖሪያችን ቢፈርስ እንኳ በሰማይ በሰው እጅ ያልተሰራ ዘላለማዊ ቤት በእግዚአብሔር እንደተሰራልን እናውቃለን።2ድንኳን ውስጥ ሆነን እንቃትታለን፥ሰማያዊ መኖሪያችንንም ልንለብስ እንናፍቃለን።3ምክንያቱም ያን ለብሰን ስንገኝ ራቁታችንን ሆነን አንገኝም ።4በርግጥ በዚህ ድንኳን ውስጥ ሆነን ከብዶን እንቃትታለን፤ምክንያቱ ደግሞ ሟች የሆነው ሰውነት በህይወት መዋጥ ስላለበት እኛም ለብሰን እንጂ ራቁታችንን መሆን አንፈልግም።5ወደ ፊት ሊመጣ ላለው የመንፈሱን ዋስትና የሰጠን ለዚህም ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው።6እንግዲህ በሰውነታችን በዚህ ምድር በምንኖርበት ጊዜ በሰማይ ካለው ጌታ ርቀን እንዳለን ይህን እርግጠኛ ሁኑ7ምክንያቱም በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና።8ስለዚህ ይህ ድፍረት አለን፤ከሰውነታችን ተለይተን ከጌታ ጋር በሰማይ ቤት መሆንን እንመርጣለን።9ስለሆነም በምድርም ብንሆን ወይም ከምድር ብንለይ ግባችን እርሱን ማስደሰት ነው።10እያንዳንዳችን በሰውነታችን በዚህ ምድር ላይ የሰራነውን መልካምም ሆነ ክፉ እንቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረባችን ግድ ነው።11እንግዲህ ጌታን መፍራት ምን ማለት እንደሆን ስለምናውቅ ሰዎችን ግድ እንላለን። ማንነታችን በእግዚአብሔር ፊት የተገለጠ ስለሆነ ለናንተም ህሊና ግልፅ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ።12ራሳችንን ደግመን እንድታወድሱን አናቀርብላችሁም፥ ሆኖም በልብ ሳይሆን በውጫዊው መልክ ለሚመኩ መልስ መስጠት እንዲቻላችሁ እኛን ምክንያት አድርጋችሁ እንድትመኩ እናስታውቃችኋለን።13እንደ እብድ ቢያረገን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤እንደ ባለአዕምሮ ብንሆን ደግሞ ለእናንተ ስንል ነው።14የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፥ በዚህ ነገር እርግጠኞች ነን፡አንዱ ሰው ስለሁሉ ሞተ፥ ስለሆነም ሁሉም ሞቱ ማለት ነው።15በህይወት ያሉትም ስለእነርሱ ለሞተውና ለተነሳው እንጂ ለራሳቸው እንዳይኖሩ ክርስቶስ ስለሁሉ ሞተ።16ስለዚህም ምክንያት ክርስቶስን ከዚህ ቀደም በሰዋዊ መንገድ አይተነው ቢሆን፥ካሁን ጀምሮ ማንንም በሰዋዊ መስፈርት አንፈርድም። በማንም ላይ ከዚህ በኋል በዚህ መንገድ አንፈርድም።17ስለሆነም ማንም በክርስቶስ ውስጥ ቢሆን እርሱ አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌ ነገሮች አልፈዋል። ተመልከቱ፥ ሁሉ አዲስ ሆኗል።18እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሆኑት እኛን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ባስታረቀንና የዕርቅ አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው።19እግዚአብሔርም በደላቸውን ሳይቆጥርባቸው ዓለሙን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር። እኛንም ለዚህ የዕርቅ መልዕክት ታማኝ አድርጎ ሾመን።20ስለዚህም እግዚአብሔር በእኛ ሆኖ ልመናውን እንደሚያቀርብ፥ የክርስቶስ ተወካዮች ሆነን ተሹመናል። ከእናንተም ጋር በመሆን ስለ ክርስቶስ "ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!" ብለን ልመና እናቀርባለን።21እኛም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንሆን ሃጢያት ሰርቶ የማያውቀውን ክርስቶስን እግዚአብሔር የሃጢያት መስዋዕት አደረገው።
1እንደዚሁም፥ አብሮ እንደሚሰራ የእግዚአብሔርን ፀጋ እንዲሁ እንዳትቀበሉ እለምናችኋለሁ።2ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሏልና "በምቹ ጊዜ ሰማሁህ በድነትም ቀን ረዳሁህ።" ልብ በሉ፥ ምቹ ጊዜም ሆነ የድነት ቀን አሁን ነው።3አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ በማንም ፊት ማሰናከያ አናኖርም።4ከዚያ ይልቅ፥ በድርጊቶቻችን ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች መሆናችንን እናረጋግጣለን። ይህም በመፅናት፥በመከራ፥ በስቃይ፥በችግር5በመገረፍ፥ በእስራት፥ጥላቻ በተሞላ አመፅ፥ ፥በከባድ ስራ ፥እንቅልፍ በማጣት፥በርሃብ፥6በንፅህና፥በእውቀት፥በትዕግስት፥በርህራሄ፥በመንፈስ ቅዱስ፥በእውነተኛ ፍቅር፥7በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ሃይል ማለትም ለቀኝ እና ለግራ ለሚሆን ለፅድቅ የጦር ዕቃ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን።8በክብርም ሆነ በውርደት፥ በሃሜትም ሆነ በሙገሳ ውስጥ እንሰራለን። በሃሰት ብንከሰስም እውነተኞች ሆነን ተገኝተናል።9ያልታወቅን ሆነን ስንሰራ፥እንታወቃለን፤ የምንሞት ስንመስል ህያዋን ነን። በጥፋታችን እንደሚቅጣ ሰው ብንሆንም፥ሞት አልተፈረደብንም።10እንደ ሃዘንተኞች ስንሰራ ሁልጊዜም ግን ደስተኞች ነን፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለፀጎች እናደርጋለን፥ ምንም የሌለን ስንሆን፥ ሁሉም አለን።11የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ ሁሉን ነገር በግልፅ ነግረናችኋል፥ልባችንንም ለእናንተ ከፍተንላችኋል።12ልባችሁ በራሳችሁ መሻት እንጂ በእኛ ምክንያት አልተዘጋም።13ተገቢ በሆነ ሁኔታ እኔም እንደ ልጆች እናገራችኋለሁ፤ልባችሁን ክፈቱልን።14ከማያምኑ ጋር በማይሆን መንገድ በአንድ ላይ አትተሳሰሩ። ፅድቅ ከአመፀኝነት ጋር ምን መዛመድ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ህብረት አለው?15ክርስቶስስ ከቤልዖር ጋር ምን ስምምነት አለው? የሚያምንስ ከማያምን ጋር ምን ድርሻ አለው?16የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስስ ከጣዖታት ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔር "ከእነርሱም ጋር አድራለሁ፥በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸው እሆናለሁ፥ እነርሱም ህዝብ ይሆኑኛል" ብሎ ስለተናገረ እኛ የህያው እግዚአብሔር መቅደሶች ነን።17ስለዚህም "ከመካከላቸው ውጡ፤የተለያችሁም ሁኑ" ይላል ጌታ፥ "እርኩሱን አትንኩ፥እኔም እቀበላችኋለሁ።18አባት እሆናችኋለሁ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትሆኑኛላችሁ።" ብሏል ሁሉን የሚችል ጌታ።
1የተወደዳችሁ ሆይ፥ እነዚህ ተስፋዎች ስላሉን በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን እየተከተልን ስጋችንን እና መንፈሳችንን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንፃ።2ለእኛ በልባችሁ ስፍራ ስጡን! ማንንም አልበደልንም፥ማንንም አልጎዳንም፥ ማንንም ለራሳችን ጥቅም አልበዘብዝንም።3ይህንን የምላችሁ ልኮንናችሁ ብዬ አይደለም፤ምክንያቱም አብረን ለመሞትም ሆነ ለመኖር በልባችን ውስጥ አላችሁና ነው።4በእናንተም ታላቅ መታመን አለኝ፣ትምክህቴም ናችሁ። በመከራዎቻችን እንኳ መፅናናት እና የተትረፈርፈ ደስታ ሞልቶኛል።5ወደ መቄዶንያ በመጣን ጊዜ ሰውነታችን እረፍት አልነበረውም። ይልቁንስ በውጭ ግጭት እና በውስጥ ፍርሃት ስለነበረብን በሁሉ አቅጣጫ ተጨነቅን ።6ነገር ግን ተስፋ የቆረጡትን የሚያፅናና አምላክ በቲቶ መምጣት አፅናናን።7የእርሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን እናንተም እርሱን ያፅናናችሁት ማፅናናት እኛን አፅናናን። ለእኔም ያላችሁን ታላቅ ፍቅር፥ርህራሄ እና ጥልቅ ሃሳብ ሲነግረን በይበልጥ ተደሰትሁ።8ምንም እንኳ በመልዕክቴ ባሳዝናችሁም ለምን ፃፍኩ ብዬ አልፀፀትም። ነገር ግን፥የምፀፀተው መልዕክቴ ለጥቂት ጊዜም እንዳሳዘናችሁ ስለማውቅ ነው።9አሁን የምደሰትበት ምክንያት ስላዘናችሁ ሳይሆን ሃዘናችሁ ወደ ንስሃ ስለመራችሁ ነው። እግዚአብሔር የሚወደው አይነት ሃዘን እየተለማመዳችሁ ስለሆነ በእኛ ምክንያት ያጣችሁት ነገር የለም።10እግዚአብሔር የሚወደው ሃዘን ፀፀት የሌለበት፥ ወደ ድነት የሚመራ ንስሃን ያመጣል። ዓለማዊ ሃዘን ግን ሞትን ያመጣል።11እግዚአብሔር የሚወደው ሃዘን ምን አይነት ታላቅ ቁርጠኝነት እንዳመጣላችሁ እዩ። ይህም ታላቅ ቁርጠኝነት ምን ያህል ንፁህ መሆናችሁን፥ ምን ያህል በሃጢያት ላይ እንድትቆጡ እንዳደረጋችሁ፥ ምን አይነት ናፍቆት እንዳሳደረባችሁ፥ ምን አይነት በጎ ቅንዓት እንደፈጠረባችሁ ፥ፍትህ እንድታደርጉም ምን አይነት ጥልቅ መሻት እንዳደረገላችሁ ተመልከቱ! በዚህ በኩል በሁሉም ንፁህ መሆናችሁን አስመስክራችኋል።12ምንም እንኳ ብፅፍላችሁም የፃፍኩት ለክፉ አድራጊ ወይም በክፉ አድራጎቱ መከራ ለሚቀበል ሳይሆን ለእኛ ምን ያህል እንደምታስቡ በእግዚአብሔር ፊት እንዲታወቅ ነው።13በዚህ እንበረታታለን። እኛ ከመፅናናታችን በተጨማሪ በቲቶ ደስታ ሃሴት አድርገናል፤ መንፈሱ በሁላችሁ ምክንያት አርፏልና ነው።14ስለናንተ በመመካት ለእርሱ ተናግሬ ነበር፣እናንተም አላሳፈራችሁኝም። በሌላ አንፃር ስለናንተ የተናገርነው ሁሉ እውነት ነበር፥ለቲቶም ስለናንተ የተናገርነው ሁሉ ትክክል መሆኑ ተረጋግጧል።15እርሱም በፍርሃት እና በመንቀጥቀጥ ያደረጋችሁለትን አቀባበል እንዲሁም የሁላችሁንም መታዘዝ በሚያስብበት ጊዜ ለእናንተ ያለው ፍቅር ታላቅ ነው።16በናንተ ሙሉ መታመን ስላለኝ፥ሃሴት አደርጋለሁ።
1ወንድሞችና እህቶች ሆይ ለመቄዶንያ ለአብያተ ክርስቲያናት ስለ ተሰጠው የእግዚአብሔር ጸጋ እንድታውቁ እንፈልጋለን2እጅግ የሚፈትናቸው መከራ በደረሰባቸው ጊዜ የደስታቸው መብዛትና የደህንነታቸው አስከፊነት የልግስናቸውን መትረፍረፍ አብዝቷል።3የሚቻላቸውን ያህል ከሚቻላቸውም እንደ ሰጡ እኔ እመሰክርላቸዋለው። በፈቃዳቸውም ለቅዱሳን በሚሰጠው በዚህ አገልግሎት የመሳተፍ ዕድል ይኖራቸው ዘንድ4እኛን በብዙ ልመና ለመኑን።5ይህም የሆነው እኛ እንደጠበቅነው አይደለም ነገር ግን በመጀመሪያ ራሳቸውን በጌታ ከዚያም በእግዘአብሔር ፈቃድ ለእኛ ሰጡ።6ስለዚህ አስቀድሞ ከእናንተ ጋር የጀመረውን ተግባር በእናንተ ዘንድ ያለውን ይህን የልግስና ስራ ከፍጻሜ እንዲደርስ ቲቶን ግድ ብለነው ነበር።7ነገር ግን እናንተ በሁሉም ነገር በእምነት፥ በንግግር ፣በዕውቀት በትጋት ሁሉ እንዲሁም ለእኛ ባላችሁ ፍቅር እንደሚልቁ በዚህ በበጎ ስራ ደግሞ የምትልቁ ሁኑ።8ከሌሎች ሰዎች ትጋት ጋር በማወዳደር የፍቅራችሁን ቅንነት ለማረጋገጥ እንጂ ይህንን እንደ ትዕዛዝ አልልም እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና።9በእርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ ፥ እርሱ ባለ ጠጋ ቢሆንም እንኳ ስለ እናንተ ደኸየ።10በዚህ ጉዳይ እናንተን ስለሚጠቅማችሁ ነገር ምክር እለግሳችኋለው። ከአንድ ዓመት በፊት አንድን ነገር ለማድረግ መጀመር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ልታደርጉት መሻት በውስጣችሁ ነበር።11አሁን ያንኑ ማድረጋችሁን ፈጽሙ። እንግዲህ ልክ በዚያን ጊዜ ልታደርጉት ጉጉትና ጠንካራ ፍላጎት እንደ ነበራችሁ፣ወደ ፍጻሜ ልታመጡት ደግሞ ትችላላችሁ።12ይህን ስራ ለመስራት ጉጉት ካለ፣ አንድ ሰው በሌለው ሳይሆን ባለው ነገር ላይ ተመስርቶ ሲሰራ መልካምና ተቀባይነት ያለው ነው።13ይህ ተግባር ሚዛናዊነት እንዲኖር ነው እንጂ ሌሎች እንዲቀልላቸው እናንተም ሸክም እንዲበዛላችሁ አይደለም።14አሁን ያለው የእናንተ መትረፍ ለእነርሱ የሚያስፈልጋቸውን ይሞላል። ይህም ደግሞ ሚዛናዊነት ይኖር ዘንድ የእነርሱ መትረፍረፍ የእናንተ ፍላጎት ደግሞ እንዲሞላ ነው።15እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ «ብዙ ያለው ምንም አልተረፈውም ፣ጥቂት ያለው ግን ምንም አልጎደለውም።»16ነገር ግን እኔ ለእናንተ ያለኝን ቅን ሃሳብ በቲቶ ልብ ያኖረው እግዚአብሔር ይመስገን።17እርሱ ልመናችንን መቀበል ብቻ ሳይሆን ፣ ትጋትን በማሳየት በራሱ ፈቃድ ወደ እናንተ መጥቷልና።18ከእርሱ ጋርም ወንጌልን በማወጅ ስራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ልከናል።19ይህ ብቻ አይደለም ነገር ግን ለራሱ ለጌታ ክብርና እኛ ለመረዳት ያለንን ጉጉት ለመግለጥ ይህን የጸጋ ስራ እንዲያከናውን አብሮን ይጓዝ ዘንድ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ መርጠውት ነበር።20ስለምንሰበስበው ስለዚህ የልግስና ስጦታ ማንም ትችት ለማቅረብ ምክንያት እንዳያገኝ እንጠነቀቃለን።21በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በሰዎች ፊት ደግሞ የከበረውን ነገር ለማድረግ እንተጋለን።22ብዙ ጊዜ ፈትነን በበርካታ ተግባራት ተነሳሽነት ያለው ሆኖ ያገኘውን ፣አሁን ግን በእናንተ ላይ ትልቅ መታመን ምክንያት የበለጠ ትጋት የሚያሳየው ሌላ ወንድም ከእነርሱ ጋር እንልካለን።23ቲቶን በሚመለከት ግን ስለ እናንተ ከእኔ ጋር የሚሰራ አጋሬ ነው። ወንድሞቻችንን በሚመለከት አብያተ ክርስቲያናት የላኳቸው የክርስቶስ ክብር ናቸው።24ስለዚህ ፍቅራችንን ፣ በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ዘንድም ስለ እናንተ ለምን እንደ ተመካን ግለጡላቸው።
1ለቅዱሳን ስለ ሚሆነው አግልግሎት ለእናንተ ልጽፍላችሁ አያስፈልገኝም ።2ለመቄዶንያ ሰዎች ስለተመካሁት በውስጣችሁ ስላለው መሻት አውቃለው። በአካዶያ የሚነግሩት ካለፈው ዓመት ጀምሮ መዘጋጀትቱን ነገርኋቸው። የእናንተ ቅንዓት ብዙዎቻቸውን ለስራ አነሳስቷል።3እንግዲህ የተዘጋጃችሁ ትሆናላችሁ እንዳልኩት የተዘጋጃችሁ ትሆኑ ዘንድ፣ ስለ እናንተ መመካታችን ከንቱ እንዳይሆን ወድሞችን ልኬአለው።4ምናልባት አንዳቸው ከ እኔ ጋር ከሜቄዶንያ በመጡ፣ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ ሁላችንም ሀፍረት ይሰማናል ነገር ግን በእናንተ ስለምተማመን ፣ ስለ እናንተ የምለው ምንም የለኝም።5ስለዚህ ወደ እናንተ እንዲመጡና እናንተ ተስፋ ለሰጣችሁት ስጦታ በቅድሚያ ዝግጅት እንዲያደርጉ ወንድሞችን መለመን አስፈላጊ እንደሆነ አሰብሁ። ይህም እንድትሰጡ ስለ ተገደዳችሁ ሳይሆን በነጻ እንደተሰጠ ስጦታ ዝግጁ ይሆን ዘንድ ነው።6ፍሬ ነገሩ ይህ ነው ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂቱ ያጭዳል ፣ አትረፍርፎ የሚዘራ አትረፍርፎ ያጭዳል።7እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ ስትሰጡ በሐዘን ወይም በግድ አይደለም።8እግኢአብሔር ሁልጎዜ በነገር ሁሉ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝቷችሁ በብጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።9እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ «ሀብቱን በተነ ፣ለድሆችም አከፋፈለ።»10ለዘሪን ዘርን ለምግብ እንጀራን የሚሰጥ ፣የሚዘራ ዘርን ደግሞ ይሰጣል ያበዛውማል፣ ምርት ይጨምራል።11ለጋሶች እንድትሆኑ በሁሉም ረገድ መበልጸግ ትላላችሁ፣ ይህም በእኛ በኩል ለእግኢአብሔር ምስጋና ምክንያት ይሆናል።12ይህ የመስጠት አገልግሎት ለቅዱሳን ይሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚሰጥ ብቻ አይደለምና፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ብዙ ምስጋና ደግሞ ይበዛል።13በዚህ አገልግሎት ተፈትናችሁ አልፋችኋል ደግሞም በክርስቶስ ወንጌል ምስክርነት በመታዘዛችሁ ፣እንዲሁም ለእነርሱና ለሁሉ ባደረጋችሁት የስጦታችሁ ልግስና እግዚአብሔርን ታከብራላችሁ።14በእናንተ ላይ ካለው እጅግ ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ስለ እናንተ ሲጸልዩ ይናፍቁአችኋል።15ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
1እኔ ራሴ ጳውሎስ ፣ በፊታችሁ ትሁት የሆንሁ በክርስቶስ ገርነትና የዋህነት እለምናችኃለሁ።2እንደ ስጋ ፈቃድ እንደምንኖር የሚያስቡትን በምቃወምበት ጊዜ ፣ ከእናንተ ጋር ሳለሁ መሆን እንደሚገባኝ በራስ በመተማመን የምደፍር መሆን የለብኝም ብዬ እለምናችኃለው ።3ምንም እንኳ በስጋ የምንመላለስ ብንሆን፣ እንደ ስጋ አንዋጋም።4የምንዋጋባቸው የጦር መሳሪያዎች ሥጋዊ አይደሉምና ይልቁንም ምሽጎችን ለመስበር መለኮታዊ ኃይል አለቸው ፥ አሳሳች የሆኑ ክርክሮችንም ያፈርሳሉ።5ደግሞም በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ፥ እንዲሁም ለክርስቶስ ለመታዘዝ ሀሳብን ሁሉ እንማርካለን።6መታዘዛችሁም በተፈጸመ ጊዜ ፣ ይለመታዘዝን ተግባር ሁሉ ለመቅጣት እንዘጋጃለን።7በግልጽ ከፊታችን ያለውን ተመልከቱ ፥ ማንም የክርስቶስ እንደሆነ ቢያምን ልክ እርሱ የክርስቶስ እንደሆነ እኛ ደግሞ እንዲሁ መሆናችንን ራሱ ያሰበው።8ሊያንጻችሁ እንጂ ሊያጠፋችሁ የይደለ ጌት ኣስለ ሰለ ሰጠው ስልጣናችን ጥቂት አብዝቼ ብመካም እንኳ፥ አላፍርም።9በመልዕክቶቼም ላስደነግጣችሁ አልፈልግም።10አንዳንድ ሰዎች ፥«መልእቶቹ ጠንከር ያሉና ኃይለኛ ናቸው፥ ነገር ግን በአካል ደካማ ነው፥ ንግግሩም ሊሰማ የሚገባ አይደለም»ይሉናል።11እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን ስንርቅ በመልዕክት የምንለው፥እዚያ ስንሆን ከምናደርገው ጋር አንድ መሆኑን ይረዱ።12ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ጋር ራሳችንን እስከ ማስተያየት ወይም እስከ ማወዳደር ድረስ አንሔድም። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከሌላ ጋር ሲመዝኑና ራሳቸውን እርስ በእርስ ሲያወዳድሩ ፥ ማስተዋል ተላቸውም።13ይሁን እንጂ እኛ ከልክ በላይ አንመካም፥ ነገር ግን ወደ እናንተ እንኳ እስክንደርስ እግዚአብሔር በወሰነልን ስራ እንሆናለን።14ወድ እናንተ ስንደርስ ከመጠን አላለፍንምንና በክርስቶስ ወንጌል ወደእናንተ ለመድረስ የመጀመሪያዎች ነበርን።15በሌሎች ድካም ከልክ ያለፈ አንመካም ፥ ነገር ግን ከእናንተ አካባቢ አልፎ እንኳ16ወንጌልን እንሰብክ ዘንድ እምነታችሁ ሲያድግ ስራችን እጅግ እንደሚስፋፋ ተስፋ እናደርጋለን ። በሌላ ስፍራ እየተሰራ ስላለው ሥራ አንመካም።17«ነገር ግን የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ።»18ጌታ የሚያመሰግነው እንጂ፣ ራሱን የሚያመሰግን ተፈትኖ የሚወጣ አይደለምና።
1በጥቂት ሞኝነቴ ልትታገሱኝ ብትችሉ እመኝ ነበር፣ እናንተ ግን በእርግጥ ታግሳችሁኛል!2እኔ ስለ እናንተ እቀናለሁና እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል ለክርስቶስ ላቀችርባችሁ ለአንድ ባል ስላጨዋችሁ በእግዚአብሔር ቅንአት እቀናላችኃለው ።3ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳታለላት ፣ ሐሳባችሁ ለክርስቶስ ካልችሁ ቅንና ንጹህ ታማኝነት መረን እንዳትወጡ ብዬ እፈራለው።4አንድሰው መጥቶ እኛ ከሰበክበው የተለየ ሌላ ኢየሱስ ቢያውጅላችሁ፣ ወይም ቀድሞ ከተቀበላችሁት የተለየ መንፈስ ብትቀበሉ ወይም እናንተ ከተቀበላችሁት የተለየ ወንጌል ቢደርሳችሁ ደህና ትታገሱታላችሁና።5ከነዚያ «ገናና ሐዋርያት» በጥቂቱ እንኳ የማንስ አይደለሁም ብዬ አስባለውና።6ነገር ግን በአነጋገር ያልሰለጠንሁ አይደለሁም። በሁሉም መንገድና በሁሉም ነገር ይህን አሳውቀናችኋል።7የእግዚአብሔርን ወንጌል በነፃ ስለሰበኩለችሁ፥ እናንተ ከፍ እንድትሉ እኔ ራሴን በማዋረዴ ኋጢያት ሰራሁን?8እናንተን ማገልገል እችል ዘንድ ከእነርሱ እርዳታ በመቀበል ሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት«ጎዳሁ»።9አብሬአችሁ በሆንኩና በተቸገርሁ ጊዜም በማንም ላይ ሸክም አልሆንሁም። ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የሚያስፈልገኝን ሰጥተዋልና። በሁሉም ረገድ ለእናንተ ሸክም ከመሆን ተጠንቅቄአለሁ፣ይህን ማድረጌንም እቀጥላለው ።10የክርስቶስ እውነት በእኔ ውስጥ ያለ እንደ መሆኑ፣ ይህ የእኔ ትምህርት?11ለምንስ እንዲህ ይሆናል? ለማልወደችሁ ነውን? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል። እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን ራሳቸውን እንደ ክርስቶስ ሐዋርያት በማስመሰል ሐሰተኞች ሐዋርያት፣ አታላይ ሰራተኞች ናቸውና ።12እኔን የሚነቅፉትንና እኛ የምናደርገውን እነርሱም እያደረጉ እንደ ሆነ እየተናገሩ የሚመኩበትን ምክንያት ለማሳጣት አሁን የሚደረገውን ወደ ፊትም አደርጋለሁ።13እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ሐሰተኛ ሐዋርያትና አታላይ ሸራተኞች ናቸው።14ይህም የሚያስደንቅ አይደለም፣ ሰይጣን እንኳ ራሱን የብርሓን መልአክ በማስመሰሉ ርሱን ይለውጣልና።15የእርሱ አግልጋዮች ደግሞ የጽድቅ አገልጋዮች በማስመሰል ራሳቸውን ቢለውጡ እጅግ የሚያስደንቅ አይደለም። ዕጣ ፈንታቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።16ደግሜ እላለሁ፦ እኔ ሞኝ እንደሆንሁ ማንም አያስብ ። ሞኝ እንደሆንሁ ብታስቡ ግን በጥቂቱ እመካ ዘንድ እንደ ሞኝ ተቀበሉኝ።17እንደዚህ ታምኜ በመመካት የምናገረው፣ ጌታ የፈቀደው አይደለም፣ እኔ ግን እንደ ሞኝ እናገራለው።18ብዙ ሰዎች በሥጋ ሰለሚመኩ፣ እኔም ደግሞ እመካለው።19እናንተ ብልሆች ሆናችሁ ሞኞችን በደስታ ትታገሣላችሁና!20ማንም ባሪያዎች ቢያደርጋችሁ፣ ማንም በመካከላችሁ መለያየትን ቢፈጥር፣ ማንም መጠቀሚያ ቢያደርጋችሁ፣ ማንም ቢቀማችሁ ፣ወይም ፊታችሁን በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሱታላችሁና.21ይህንን ስናደርግ በጣም ደካሞች እንደ ነበርን እያፈርሁ እናገራለ። ሆኖም ማንም በሚመካበት ጊዜ ሁሉ እንደ ሞኝ እላለው፣ እኔ ደግሞ እመካለሁ።22እነርሱ ዕብራውያን ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ እስራኤላውያን ናቸውን እኔ ደግሞ ነኝ። የአብርሃም ዘር ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ።23የክርስቶስ አግልጋዮች ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ (እንደ እብድ እናገራለው) እኔ እበልጣለሁ፣ በከባድ ሥራ አብዝቼ በመታሰር አብዝቼ፣ በመደብደብ ከልክ በላይ፣ ብዙ የሞት አደጋዎችን በመጋፈጥ ብዙ ጊዜ ሆንሁ።24አይሁድ «አንድ ሲጎድል አርባ ጅራፍ»አምስት ግዜ ገረፉኝ።25ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ። አንድ ግዜ በድንጋይ ተወገርሁ። ሦስት ጊዜ የተሳፈርኩበት መርከብ ተሰበረ። አንድ ሌሊትና አንድ ቀን በባህር ላይ አሳለፍሁሁሁ፣26በተደጋጋሚ በመንገድ ተጓዝሁ። በወንዞች አደጋ፣ በወንበዴዎች አደጋ በወገኖቼ በኩል አደጋ፣ በአሕዛብ በኩል አደጋ፣ በከተማ አደጋ በምድረ በዳ አደጋ፣ በባሕር አደጋ፣ በሐሰተኞች በኩል አደጋ ነበረብኝ።27በከባድ ስራና በችግር፣ እንቅልፍ ባጣሁባቸው ብዙ ሌሊቶች፣ በረሃብና በጥም ፣ እንዲሁም የሚበላ በማጣት፣በብርድባ በራቁትነት ነበርሁ።28ከሌላውም ሁሉ በተለይ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያለኝ ጭንቀት ነው።29ደካማ ምን ነው እኔስ አልደክምምን? ኃጢአት እንዲሠራ ሌላውን ያሰናከለ ማን ነው፣ እኔስ በውስጤ አልናደድምን?።30መመካት ካለብኝ፣ ድካሜን ስለሚያሳየው ነገር እመካለው።31እንደማልዋሽ፣ ለዘላለም የተመሰገነው የጌታ ኢየሱስ አምላክና አባት ያውቃል።32በደማስቆ ከንጉስ አርስጦስዮስ በታች የሆነ ገዢ እኔን ይዞ ለማሰር ከተማዋን እየጠበቀ ነበር፣33ነገር ግን በቅጥሩ ባለ መስኮት በቅርጫት አወረዱኝ፣ ከእጆቹም አመለጥሁ።
1መመካት አለብኝ፤ ነገር ግን በመመካት ጥቅም አይገኝም። ከጌታ ወዳሉት ራዕዮችና መገለጦች ግን እሄዳለው።2በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ አላውቅም፤ እግዚአብሔር ግን ያውቃል። ከዐሥራ አራት ዓመታት በፊት በክርስቶስ የሆነ አንድ ሰው ወደ ሦስተኛ ሰማይ ተነጠቀ። እንደዚህ ያለውን ሰው ዐውቃለው።3በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ እኔ አላውቅም፣ እግዚአብሔ ግን ያውቃል፣4ይህ ሰው ወደ ገነት ተነጠቀ፤ ማንኛውም ሰው የማይናገራቸው እጅግ የተቀደሰ ነገሮችን ሰማ።5እንደዚህ ስላለው ሰው እመካለው ስለራሴ ግን ከድካሜ በቀር አልመካም።6ልመካ ከፈለግሁ፣ ሞኝ አይደለሁም፣ እውነትን እናገራለሁና፤ ነገር ግን ማንም በእኔ ከታየው ወይም ከእኔ ከተሰማው ፣7ወይም በመገልጦቹ ልዩ ባሕርይ ምክንያት የምበልጥ አድርጎ እንዳያስብ አልመካም።ስለዚህ እንዳልታበይ፣ እጅግ እንዳልኩራራ የሥጋ መውጊያ፣የሚነዘንዘኝ የሰይጣን መልዕክተኛ ተሰጠኝ።8መውጊያውን ከእኔ እንዲያነሣው ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።9እርሱም፣ «ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይል በድካም ይፈጸማልና» አለኝ። ስለሆነም የክርስቶስ ኃይል ያርፍብኝ ዘንድ አብዝቼ ስለ ድካሜ እመካለው።10ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም፣ በስድብ፣ በችግር፣ በስደት ፣ በጭንቀትም እርካታ ይሰማኛል በምደክምበት ጊዜ ሁሉ ብርቱ ነኝና።11ሞኝ ሆኜአለሁ! እንዲህ እንድሆን ያስገደዳችሁኝ እናንተ ናችሁ፣እናንተ እኔን ልታመሰግኑኝ ይገባችሁ ነበር፥ምክንያቱም እኔ ምንም ባልሆን እንኳ ከ«ገናና ሐዋርያት» የማንስ አልነበርሁም።12የአንድ ሐዋርያ እውነተኛ ምልክቶች በሁሉ ትዕግሥት፦ በምልክቶችና በድንቆች በብርቱ ተግባራትም በእናንተ መካከል ተደረጉ።13እኔ ሸክም ካልሆንሁባችሁ በቀር ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የምታንሱት እንዴት ነበር? ይህን ስሕትቴን ይቅር በሉኝ!14አስተውሉ! ለሦስተኛ ጊዜ ወደ እናንተ ለመምጣት ተዘጋጅቻለው፤ ሸክም አልሆንባችሁም፤ እናንተን እንጂ፣ የእናንተ የሆነውን አልፈልግም። ወላጆች ለልጆች እንጂ ልጆች ለወላጆች ገንዘብ አያስቀምጡምና።15እኔ እጅግ በጣምታልቅ በሆነ ደስታ ስለ ነፍሳችሁ እከፍላለው። እናንተን የበለጠ ብወዳችሁ፣ እኔ ከዚህ ያነሰ መወደድ አለብኝን?16ልክ እንደዚህ፣ እኔ አልከበድሁባችሁም፤ነገር ግን በጣም በተንኮልና በጥበብ ያታለልኃችሁ መሰላችሁ።17ወደ እናንተ በላክሁት በማንም ተጠቀምሁባችሁን?18ወደ እናንተ እንዲመጣ ቲቶን የግድ አልኩት ፤ ከእርሱ ጋርም ሌላውን ወንድም ላክሁት። ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? በአንድ መንገድ አልተጓዝንምን? በአንድ ፈለግስ አልተራመድንምን?19በዚህ ጊዜ ሁሉ ለእናንተ ራሳችንን የምንከላከል ይመስላችኃልን? በእግዚአብሔር ፊት ስለእናንተ ድፍረት በክርስቶስ ብዙ ነገር እየተናገርን ነበር።20ስመጣ እንደምፈልገው ሆናችሁ አላገኛችሁምብዬ እፈራለው። እናንተም እንደምትፈልጉት ሆኜ አታግኙኝም ብዬ እፈራለው ምናልባት ክርክር፣ ቅንዓት፣ የቁጣ መግንፈል፣ራስ ወዳድነት ያለበት ምⶉት፣ ሐሜት፣ ኩራትና ሁከት ይሆናሉ።21ተመልሼ ስመጣ፣ አምላኬ በፊታችሁ ዝቅ እንዳያደርገኝ ብዬ እፈራለው ፣ከዚህ በፊትም ኃጢያ ስለሠሩት፣ እንዲሁም ስለ ፈጸሙት ርኩሰትና ዝሙት መዳራትም ስለ ብዙዎቻቸው አዝናለው ብዬ እፈራለው።
1ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው። «ክስ ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች መጽናት አለበት።»2ሁለተኛ ስመጣ በፊት ኃጢያት ለሰሩትና ለሌሎች ሁሉ ተናግሬአለው፥ አሁንም ደግሞ እላለው ተመልሼ ስመጣ እንዲሁ አላልፋቸውም።3ክርስቶስ በእኔ በኩል እየተናገረ ስለ መሆኑ ማስረጃ ስለምትሹ ይህን እነግራችሏለው። ክርስቶስ ስለ እናንተ አይደክምም፥ ይልቁንም እርሱ በእናንተ ኃይለኛ ነው።4እርሱ በድካም ተሰቅሏልና፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል ሕያው ነው። እኛ ደግሞ በእርሱ ደካሞች ነንና፤ ነገር ግን በመካከላችሁ ብለው የእግዚአብሔር ኀይል ሕያዋን ነን።5በእምነት መሆናችሁን ለማየት ራሳችሁን መርምሩ። ራሳችሁን ፈትኑ። ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ እንደሚኖር አትገነዘቡምን? ተፈትናችሁ ካላለፋችሁ በቀር፣ እርሱ በእናንተ ይኖራል።6እኛ ግን ተፈትነን ያለፍን መሆናችንን እንደምታውቁ እተማመናለው።7እንግዲህ እናንተ ክፉ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፥ ይህንም የምናደርገው ፈተናውን ያለፍን መሰለን ለመታየት አይደለም፥ ነገር ግን ፈተናውን ያላለፍን ብንመስልም እንኳ፣ እናንተ ትክክል የሆነውን ታደርጉ ዘንድ እጸልያለው።8ስለ እውነት እንጂ የእውነት ተቃራኒ የሆነ ነገር መሥራት አንችልምና።9እኛ ደካሞች ሆነን እናንተ ብርቱዎች ስትሆኑ ደስ ይለናልና። እናንተ ፍጹማን እንድትሆኑ እንኛ ደግሞ እንጸልያለን።10ከእናንተ ርቄ እያለው እነዚህን ነገሮች ጻፍሁላችሁ፤ ከእናንተ ጋር ሳለው እናንተ ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ ያይደለ ጌታ የሰጠኝ ሥልጣንን በመጠቀም እንዳላመናጭቃችሁ ንችው።11በመጨረሻ፣ ወንድሞችና እኅቶች፣ ደስ ይበላችሁ! ለተሐድሶ ሥሩ፤ተበረታቱ፤እርስ በርሳችሁ ተስማሙ፤በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምልክም ከእናንተ ጋር ይሆናል።12በተቀደሰ አሳሳም ሰላም ተባባሉ።13ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።14የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ፍቅር፣የመንፈስ ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
1በሰው በኩል ወይም ከሰው ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ደግሞም እርሱን ከሞት ባስነሳው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆንኩት ጳውሎስ2አብረውኝ ካሉ ወንድሞች ጋር በገላትያ ለምትገኙ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ3ከአባታችን ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ4ይሁን፣እርሱ እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከአሁኑ ክፉ ዘመን ያድነን ዘንድ እራሱን ስለ ኃጢአታችን ሰጥቶአልና5ለእርሱ ከዘላለም እስከዘላለም ክብር ይሁን። አሜን!6ወደሌላ ወንጌል በዚህ ፍጥነት በመዞራችሁ እጅግ ተገርሜአለሁ። በክርስቶስ ጸጋ ከተጠራችሁ ከእርሱ ፊታችሁን ማዞራችሁ አስገርሞኛል።7ሌላ ወንጌል የለም፣ ነገር ግን የሚያውኩዋችሁና የክርስቶስን ወንጌል ሊያጣምሙ የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።8ነገር ግን እኛም ሆንን የሰማይ መልአክ አስቀድመን ከሰበክንላችሁ ሌላ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።9አስቀድመን እንዳልን እንደገና እላለሁ «ማንም ከተቀበላችሁት ወንጌል የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገም ይሁን»10ለመሆኑ እኔ የምጥረው ከሰው ወይስ ከእግዚአብሔር ይሁንታን ለማግኘት ነው? ጥረቴ ሰውን ለማስደሰት ነው? እስከአሁን ድረስ ሰውን ለማስደሰት እየጣርኩ ከሆነ እውነት እኔ የክርስቶስ አገልጋይ አይደለሁም።11ወንድሞች ሆይ የሰብኩላችሁ ወንጌል ከሰው እንዳልሆን እንድታውቁ እፈልጋለሁ።12ከጌታ ከኢየሱስ ከተሰጠኝ መገለጥ እንጂ ከሰው አልተቀበልኩትም ከሰውም አልተማርኩትም።13የይሁዲ እምነት ተከታይ በነበርኩበት በቀድሞው ህይወቴ ወቅት እንዴት ቤተክርስቲያንን በአመፅ አሳድድና አጠፋ እንደነበረ ስለእኔ ሰምታችኋል።14በይሁዲነት ከአብዛኛዎቹ አብረውኝ ከነበሩ አይሁዶች እየላቅሁ ነበር። ለአባቶቼም ወግ ከመጠን ያለፈ ቀናኢ ነበርኩ።15ነገር ግን እግዚአብሔር ገና በማህጸን ሳለሁ ሊመርጥኝ ወደደ፣16በአረማውያን መካከል አውጀው ዘንድ ልጁን በእኔ ለመግለፅ በጸጋው ጠራኝ። በጠራኝ ጊዜ ወዲያውኑ ከስጋና ከደም ጋር አልተማከርኩም17፣ከእኔ አስቀድመው ሃዋሪያት የሆኑት ወደሚገኙበት ወደ ኢየሩሳሌምም አልሄድኩም። ነገር ግን ወደ አረቢያ በኋላም ደግሞ ወደ መቄዶኒያ ተመለስኩ።18ከዚያም ከሶስት አመት በኋላ ኬፋን ለመጠየቅ ወደኢየሩሳሌም ሄጄ ከእርሱ ጋር አስራአምስት ቀናት ቆየሁ።19ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በስተቀር ሌሎች ሃዋሪያትን አላገኘሁም።20በምፅፍላችሁ በእነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት እንዳልዋሸሁ እወቁ።21ቀጥሎም ወደ ሶሪያና ኪልቂያ አውራጃዎች ሄድኩኝ።22እስከዚያን ጊዜ ድረስ በይሁዳ ላሉት አብያተክርስቲያናት በአካል አልታወቅም ነበር፣23ነገር ግን «ያ ቀድሞ ያሳድደን የነበረው ሰው አሁን ሊያጠፋው ሲጥር የነበረውን እምነት እየሰበከ ነው» የሚል ወሬ ብቻ ይሰሙ ነበር፣24ስለ እኔም እግዚአብሔርንም ያከብሩ ነበር።
1ከአስራ አራት ዓመት በኋላ ቲቶን ይዤ ከበርናባስ ጋር እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ሄድኩ።2የሄድኩበትም ምክንያት መሄድ እንዳለብኝ እግዚአብሔር ስላመለከተኝ ነበር። ሄጄም በአህዛብ መካከል እየሰበኩት ስላለው ወንጌል ነገርኳቸው፣ ነገር ግን በከንቱ እንዳልሮጥኩ ወይም እየሮጥኩ እንዳልሆን እርግጠኛ ለመሆን ይህን የተናገርኩት በሌሎቹ ዘንድ እንደ ዋና ለሚታሰቡት ብቻ ነበር።3ግሪካዊ የሆነው ሲላስ እንኳ እንዲገረዝ አልተገደደም።4ይህ ጉዳይ የተንሳው በክርስቶስ ያገኘነውን ነፃነት ለመሰለል ሾልከው በገቡ ውሸተኞች ወንድሞች ምክንያት ነበር።5የህግ ባሪያዎች ሊያደርጉን ይመኙ ነበር። ነገር ግን ለእናንተ ወንጌሉ ሳይለወጥ ይቆይላችሁ ዘንድ ለአንድ ሰዓት እንኳ ለሀሳባቸው አልተገዛንም።6ነገር ግን ሌሎች መሪዎች ናቸው ያልዋቸው ምንም አስተዋፅኦ አላደርጉልኝም። ማንም ይሁኑ ለእኔ ትርጉም አልነበረውም። ሆኖም ግን ልክ ጴጥሮስ ለተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተሰጠው ሁሉ7እኔም ላልተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተቀበልኩ አዩ፥8ምክንያቱም ለተገረዙት ሃዋሪያ ይሆን ዘንድ በጴጥሮስ የሰራ እግዚአብሔር ላልተገረዙት ሃዋሪያ እሆን ዘንድ በእኔም ስለሚስራ ነው።9እንደመሪዎች የሚታወቁት ያዕቆብ፥ኬፋና ዮሀንስ በእኔ ላይ ያለውን ፀጋ ባዩ ጊዜ እኛ ወደ አህዛብ እነርሱ ደግሞ ወደተገረዙት ይሄዱ ዘንድ የማህበራቸውም ተካፋዮች እንድንሆን ሙሉ መብት ሰጡን።10እኔ ለማድረግ የምናፍቀውን ድሆችን እንድናስብም አሳሰቡን።11ከዚያም ኬፋ ወደ አንፆኪያ በመጣ ጊዜ ሥራው ትክክል ስላልነበረ ፊት ለፊት ተቃወምኩት።12ምክንያቱም ከያዕቆብ ዘንድ ሰዎች ከመምጣታቸው በፊት ኬፋ ከአህዛብ ጋር ይበላ ነበር። ሰዎቹ በመጡ ጊዜ ግን እነኚህን የተገረዙ ሰዎች ፈርቶ ከአህዛብ ጋር መብላቱን አቆመ እንዲያውም ተለያቸው።13በርናባስ እንኳ በግብዝነታቸው እስኪሳብ ድረስ ሌሎቹም አይሁድ በኬፋ ግብዝነት ተካፋዮች ነበሩ።14ወንጌልን በሚፃረር መንገድ መሄዳቸውን ባየሁ ጊዜ ኬፋን በሁሉም ፊት «አንተ አይሁዳዊ ሆንህ በአህዛብ ስርአት የምትኖር ከሆነ አህዛብ በአይሁድ ስርአት እንዲኖሩ ለምን ታስገድዳቸዋልህ?» አልኩት።15እኛ«አህዛብ ኃጢአተኞች» ያልሆንን ነገር ግን በትውልድ አይሁዳዊ የሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ባለ እምነት እንጂ ማንም ህግን በመፈፀም እንደምይፀድቅ እናውቃለን።16በህግ ሥራ ማንም ሊፀድቅ ስለማይችል በህግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነት እንፀድቅ ዘንድ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ እምነት ተጠርተናል።17ነገር ግን እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲያፀድቀን እየፈለግን ሳለ ራሳችንን ኃጢአተኞች ሆነን እናገኛለን፥18ታዲያ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ሆነ ማለት ነው? በፍፁም አይደለም።19ምክንያቱም አውልቄ የጣልኩትን ህግን የመፈፀም ትምክህት እንደገና ብገነባ ራሴን ህግ ተላላፊ ሆኜ አገኘዋለሁ። በህግ በኩል ለህግ ሞቼአለሁ።20ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።21የእግዚአብሔርን ፀጋ አላቃልልም፥ ህግን በመጠበቅ ፅድቅ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ መሞቱ ከንቱ በሆነ ነበር።
1እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁ የገላቲያ ሰዎች ማነው በክፉ ዓይኑ ያያችሁ፥ ክርስቶስ እንደተሰቀል ሆኖ በፊታችሁ ተስሎ አልነበረምን?2ይህን ብቻ ከእናንተ ማወቅ እፈልጋለሁ። መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁት በህግ ሥራ ነው ወይስ የሰማችሁትን በማመናችሁ?3ይህን ያህል ሞኞች ናችሁ እንዴ፥ በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ ትጨርሳላችሁ?4በእርግጥ ይህ ከንቱ ከተባለ ያን ሁሉ መከራ የተቀብላችሁት በከንቱ ነውን?5መንፈስ ቅዱስን የሰጣችሁና በመካከላችሁ ኃይለኛ ነገርን ያደረገው እርሱ ይህን ያደረገው በህግ ሥራ ነው ወይስ ከእምነት በሆነ እምነታችሁ ነው?6ልክ አብርሀም «እንዳመነና እምነቱ እንደ ፅድቅ እንደተቆጠረለት»7የሚያምኑ ሁሉ የአብርሀም ልጆች እንደሆኑ አስተውሉ።8ቅዱሳት መፅሀፍት እግዚአብሔር አህዛብን እንደሚያፀድቅ አስቀድመው አመልክተዋል። ወንጌል «አህዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ» ተብሎ በመጀመሪያ ለአብርሀም ተሰብኳል።9ስለዚህም የሚያምኑ እምነት ከነበረው ከአብርሀም ጋር የተባረኩ ናቸው።10«ህግን ሁሉ ይፈፅም ዘንድ ለህግ የማይታዘዝ ሁሉ የተረገመ ነው» ተብሎ ተፅፎአልና በህግ ስራ የሚታመን ሁሉ በእርግማን ስር ነው።11«ጻድቅ በእምነት ይኖራልና» እግዚአብሔር ማንንም በህግ እንደማያጸድቅ ግልጽ ነው።12ህግ ከእምነት የመነጨ አይደለም፥ ይልቁኑም «በህግ ውስጥ ያሉትን እነዚያን ነገሮች የሚያደርግ በህግ ይኖራል»13«በእንጨት ላይ የሚሰቀል የተረገመ ነው» ተብሎ በተጻፈው መሰረት እርሱ ስለኛ እርግማን በመሆን ከህግ እርግማን ዋጀን።14የዚህ ተግባር ዓላማ የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ በእምነት እንቀበል ዘንድ በአብርሀም ላይ የነበረው በረከት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በአህዛብም ላይ እንዲሆን ነው።15የምናገረው በሰው ቋንቋ ነው። ልክ በሰዎች መካከል እንደተደረገ ውል ማንም ከዚህ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር አይችልም።16እንግዲህ ተስፋዎቹ የተነገሩት ለአብርሀምና ለዘሩ ነው። ብዙ ሰዎችን እንደሚያመለክት «ለዘሮቹ» አላለም። ነገር ግን አንድ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ«ለዘሩ» ብሎ ይናገራል። ያም ለዘሩ የተባለለት ክርስቶስ ነው።17እንግዲህ እንዲህ ልበል። አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠው ቃል ኪዳን ተስፋ ከ430 ዓመት በኋላ በተሰጠ ህግ አልተሻረም።18ምክንያቱም ውርሱ በህግ የመጣ ቢሆን ኖሮ በተስፋ በኩል ባልመጣ ነበር፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም በተስፋ አማካኝነት ርስትን እንዲያው ሰጠው።19ታዲያ ህግ ለምን አስፈለገ? የአብርሃም ዘር ተስፋ ወደተሰጣቸው እስኪመጣ ድረስ በመተላለፍ ምክንያት ህግ ተሰጠ፤ ህጉ በመካከለኛ አማካኝነት በመላዕክት አማካኝነት ተግባራዊ ሆኗል።20መካከለኛ ሲል ከአንድ ሰው በላይ እንደሆነ ያመለክታል፥ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።21ታዲያ ህግ የእግዚአብሔርን ተስፋ ይቃረናል ማለት ነው? በፍጹም አይደለም። ህይወትን ሊሰጥ የሚችል ህግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጠኝነት ጽድቅ በህግ በኩል ይመጣ ነበር።22ነገር ግን ይልቁኑ መጽሀፍ ሁሉን ነገር ከኃጢአት በታች እስርኛ አድርጓል። ስለዚህም እኛን በክርስቶስ ኢየሱስ ለማዳን እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ለሚያምኑ ተሰጠ።23ነገር ግን በክርስቶስ ማመን ከመምጣቱ በፊት እምነት እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በህግ ታስረንና ታግደን ነበር።24ስለዚህ በእምነት እንድንጸድቅ ህግ ወደ ክርስቶስ ዘመን የሚያደርሰን ሞግዚት ሆነ።25አሁን እምነት ስለመጣ ከዚህ በኋላ በሞግዚት ሥር አይደለንም።26ምክንያቱም ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ።27በክርስቶስ ስም የተጠምቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታል።28ሁላችሁ በክርስቶስ አንድ ስለሆናችሁ በዚህ ጉዳይ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች፥ በባሪያና ነጻ በሆነ፥በሴትና በወንድ መካከል ልዩነት የለም።29እንግዲህ የክርስቶስ ከሆናችሁ የአብርሀም ዘሮች እንደተስፋ ቃሉም ወራሾች ናችሁ።
1ያን የምለው ህጻን ሳለ ምንም እንኳ ሁሉም የእርሱ ቢሆንም ወራሹ ከባሪያ አይለይም።2ነገር ግን አባቱ የወሰነልት ቀን እስኪደርስለት ድረስ በተንከባካቢዎቹና በሞግዚቶቹ ስር ይቆያል።3እኛም ልጆች ሳለን በዚህ ዓለም ዋና ትምህርቶች እስራት ሥር ነበርን።4ነገር ግን በትክክለኛው ጊዜ እግዚአብሔር በህግ ሥር ያሉትን5ነጻ እንዲያወጣና የልጅነትን መብት እንዲኖረን ከሴት የተወለደውንና በህግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ።6ልጆች ስለሆናችሁ «አባ አባት» እያለ የሚጣራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ።7በዚህም ምክንያት ከእንግዲህ ልጆች እንጂ ባሮች አይደላችሁም፥ ልጆች ከሆናችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ።8ነገር ግን እግዘአብሔርን በማታውቁበት በቀድሞው ዘመን በባህሪያቸው ፈጽሞ አማልክት ላልሆኑት ተገዝታችሁ ኖራችሁ።9አሁን ግን እግዚአብሔርን አውቃችኋል ይልቁኑም በእግዚአብሔር ታውቃችኋል፥ ታዲያ እንዴት ወደ ደካማና ዋጋ ወደሌለው የዚህ ዓለም ዋና ትምህርት ተመለሳችሁ።እንደገና ባሮች መሆን ትፈልጋላችሁ?10ልዩ ቀናትን፥አዳዲስ ጨረቃዎችን፥ ወራትና ዓመታትን ታመልካላችሁ።11ስለ እናንተ የደከምኩት ድካም ከንቱ ሆኖብኝ እንዳይሆን ብዬ እፈራለሁ።12ወንድሞች ሆይ ልክ እኔ ለእናንተ እንደምሆነው እናንተም ለእኔ እንደዚያው እንድትሆኑ እለምናችኋለሁ።13ምንም ክፉ አላደርጋችሁብኝም ነገር ግን ወንጌልን በመጀመሪያ በሰብኩላችሁ ጊዜ የሥጋ ህመም አሞኝ እንደነበረ ታውቃላችሁ።14በሥጋዬ ላይ የነበረው ለእናንተ ከባድ ፈተና ቢሆንም አልተጸየፋችሁኝም አልጣላችሁኝምም፥ ይልቁኑ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ወይም ክርስቶስን በተቀበላችሁብት አቀባበል ተቀበላችሁኝ።15አሁን ደስታችሁ በምንድነው? ዓይናችሁን እንኳ አውጥታችሁ ልትሰጡኝ ፈቃደኛ እንደነበራችሁ እኔ ራሴ ምስክር ነኝ።16ታዲያ እውነትን ስለነገርኳችሁ የእናንተ ጠላት ሆንኩ ማለት ነው?17አጥበቀው ይፈልጓችኋል ነገር ግን ለመልካም አይደለም። እነርሱን እንድትከተሉ ከእኔ ሊለዩዋችሁ ይፈልጋሉ።18እኔ ከእናንተ ጋር ስሆን ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ ለመልካም ነገር መትጋት ተገቢ ነው።19ጨቅላ ልጆቼ ሆይ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ ስለእናንተ ምጥ ይዞኛል!20የእናንተ ነገር ግራ ስለገባኝ በመካከላችሁ ተገኝቼ በቁጣ ልናገራችሁ እመኛለሁ።21እስኪ እናንተ በህግ ሥር ለመሆን የምትፈልጉ ንገሩኝ ህጉ ምን እንደሚል አልሰማችሁምን?22አብርሃም አንድ ባሪያ ከነበረች ሴት አንድ ደግሞ ነጻ ከነበረች ሴት የተወለዱ ሁለት ልጆች እንደነበሩት ተጽፏል።23ነገር ግን ከባሪያይቱ የተወለደው በሥጋ ብቻ የተወለደ ነው፥ ከነጻይቱ የተወለደው ግን በተስፋ የተወለደ ነው።24እነዚህ ነገሮች እንደ ምሳሌ ሊገለጹ ይችላሉ።እነኚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ቃል ኪዳኖች ናቸው፥ አንደኛዋ በሲና ተራራ የተሰጠውንና ባርነትን የወለደውን ታመለክታለች፥ እርሷም አጋር ናት።25እንግዲህ አጋር በአረቢያ ምድር የሚገኘው የሲና ተራራ ስትሆን ከልጆቿ ጋር በባርነት የምትኖረውን የአሁኗን ኢየሩሳሌምን ትወክላለች።26ነገር ግን እናታችን የሆነችው ላይኛይቱ ጽዮን ነጻ ነች።27ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል «አንቺ ያልወለድሽና መካን የሆንሽ ሴት ሀሴት አድርጊ፥አንቺ መውለድን ያልተለማምድሽ ውጪና በደስታ ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የመካኗ ልጆች በዝተዋልና»።28እንግዲህ እናንተ ወንድሞቼ እንደ ይስሀቅ የተስፋ ልጆች ናችሁ።29ነገር ግን እንደ ሥጋ ፈቃድ የተወለደው እንደ መንፈስ ፈቃድ የተወለደውን እንዳሳደደው አሁንም እየሆነ ያለው እንደዚያው ነው።30መጽሀፍ ስለዚህ ነገር ምን ይላል«የባሪያይቱ ልጅ ከነጻይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱንና ልጇን አስወጣ»።31ስለዚህ ወንድሞች ሆይ እኛ የነጻይቱ እንጂ የባሪያይቱ ልጆች አይደለንም።
1ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው ። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፥ እንደገና በባርነት ቀንበር አትጠመዱ።2እኔ ጳውሎስ የምለውን ተመልከቱ ብትገረዙ ክርስቶስ በምንም ዓይነት መልኩ አይጠቅማችሁም።3የተገረዘ ሁሉ ህግን ሁሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት ብዬ እንደገና እመሰክራለሁ።4በህግ ልትጸድቁ የምትደክሙ ሁላችሁ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆናችኋል፤ከጸጋም ርቃችኋል።5ምክንያቱም እኛ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የጽድቅን ዋስትና ስለምንጠብቅ ነው።6በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍቅር የሆነ እምነት እንጂ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም ትርጉም የለውም።7በጥሩ ሁኔታ ትሮጡ ነበር። ታዲያ ለእውነት ከመታዘዝ ያስቆማችሁ ማነው?8ይህን እንድታደርጉ የሚያደርግ ጉትጎታ ከጠራችሁ የመጣ አይደለም።9ትንሽ እርሾ ሊጡን በሙሉ እንዲቦካ ያደርጋል።10በሌላ መልኩ እንደማታስቡ በጌታ እተማመንባችኋለሁ። ግራ የሚያጋባችሁ ማንም ይሁን ማን ፍርዱን ይቀበላል።11ወንድሞች ሆይ እስከአሁን ተገረዙ እያልኩ የምሰብክ ቢሆን ለምን እሰደድ ነበር? እንግዲያውስ የመስቀሉ እንቅፋት ይደመሰሳል።12የሚያስቷችሁ እራሳቸው ሄደው በተሰለቡ ብዬ እመኛለሁ።13ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለነጻነት ነው። ብቻ ነጻነታችሁን ለሥጋ ፈቃድ አትጠቀሙበት፥ በዚያ ፈንታ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ።14ምክንያቱም ህግ ሁሉ «ባልንጀራህን እንደራስህ ልትወድ ይገባል»15በሚለው ትዕዛዝ የተጠቀለለ ነው።16በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋን ክፉ ምኞት አትፈጽሙ እላችኋለሁ።17ምክንያቱም ሥጋ ከመንፈስ ተቃራኒ መንፈስም ከሥጋ ተቃራኒ ነገር ይመኛሉና ነው።18እነዚህ እርስ በእርሳቸው ስለሚቀዋወሙ በውጤቱ እናንተ የምትፈልጉትን ለማድረግ አትችሉም።19እንግዲህ የሥጋ ስራዎች የተገለጡ ናቸው። እነዚህም አስቀድሜ እንዳስጠነቀኩዋችሁ20ዝሙት፣እርኩሰት፣ክፉ ምኞት፣ጣዖትን ማምለክ፣ምዋርት፣ጥል፣ክርክር፣ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣አድመኛነት፣መለያየት፣21መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ስካር፥ ዘፋኝነትና የመሳሰሉት ናቸው፥ ፥አስቀድሜ እንደነገርኳችሁ እነዚህን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።22የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥23የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።24የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ስሜቱና መሻቱ ጋር ሰቅለውታል።25በመንፈስ የምንኖር ከሆነ በመንፈስ እንመላለስ።26አንታበይ፣ እርስ በእርሳችን ለክፉ አንነሳሳ፣ አንቀናና።
1ወንድሞች ሆይ አንድ ሰው ስቶ ቢገኝ መንፈሳዊያን የሆናችሁ እናንት በጨዋነት መንፈስ ልታቀኑት ይገባል።ወደ ፈተና እንዳትገቡ ለራሳችሁም ተጠንቀቁ።2የእርስ በእርሳችሁን ሸክም በመሸካከም የክርስቶስን ህግ ፈጽሙ።3ምክንያቱም ማንም ምንም ሳይሆን ምንም እንደሆነ ቢያስብ ራሱን ያታልላል።4እያንዳንዱ ከሌላው ጋር ሳያነጻጽር የራሱን ሥራ ሊመዝን ይገባል፥ያን ጊዜ የሚመካበት ሊያገኝ ይችላል።5እያንዳንዱ የየራሱን ሸክም ይሸከማልና።6ቃሉን የሚማር ከመምህሩ ጋር ሁሉን ነገር ይካፈል ዘንድ ይገባዋል።7አትታለሉ እግዚአብሔር አይቀለድበትም።ሰው ምንም ነገር ቢዘራ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል።8በሥጋው የሚዘራ ከሥጋው ውድቀትን ያጭዳል፤በመንፈስ የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ህይወት ያጭዳል።9በተገቢው ጊዜ ፍሬውን እናጭዳለንና መልካምን ከመስራት አንቦዝን።10ስለዚህም ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ሁሉ በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካምን እናድርግ።11በገዛ እጅ ጽህፈቴ ምን ዓይነት ትልልቅ ቃላት እንደጻፍኩላችሁ ተመልከቱ።12እነዚያ በሥጋ መልካም መስለው የሚታዩ ስለክርስቶስ መስቀል መከራ ላለመቀበል ብለው እንድትገረዙ ያስገድዱዋችኋል።የተገረዙት እራሳቸው ህጉን አይጠብቁ፣13ነገር ግን እናንተን እንድትገረዙ በማድረጋቸው ጉራ ለመንዛት እንድትገረዙ ይፈልጋሉ።14ዓለም ለእኔ ከተሰቀለበት እኔም ለዓለም ከተሰቀልኩበት ከክርስቶስ መስቀል በስተቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።15አዲስ ፍጥረት መሆን እንጂ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም።16በዚህ ሥርዓት ለሚሄዱ ሁሉ እንዲሁም የእግዚአብሔር ለሆነችው ለእስራኤል ሠላምና ምህረት ይሁን።17የክርስቶስን ምልክት በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ማንም አይረብሸኝ።18ወንድሞች ሆይ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁጋር ይሁን። አሜን!
1በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፥ ለእግዚአብሔር ለተለዩት በክርስቶስ ኢየሱስ ለሚያምኑ በኤፌሶን ለሚኖሩ ቅዱሳን፤2ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።3በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ።4እግዚአብሔር በክርስቶስ የምናምነውን እኛን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት መርጦናል። ይህም በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እንሆን ዘንድ ነው5እግዚአብሔር በፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ የራሱ ልጆች አድርጎ ሊቀበለን አስቀድሞ ወሰነን። ይህንንም የፈጸመው ሊያደርግ የፈለገውን ነገር ለማድረግ ደስ ስለተሰኘ ነበር።6ይህ ሁሉ የተፈጸመው በሚወደው ልጁ እንዲያው በነጻ ስለ ተሰጠን ክቡር ጸጋው እግዚአብሔር ይመሰገን ዘንድ ነው።7እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን በሚወደው ልጁ ደም ቤዛነትን ይኸውም የሐጢአት ይቅርታን አገኘን።8ይህም ጸጋ በጥበብና በማስተዋል ሁሉ ተትረፍርፎ ተሰጠን።9በክርስቶስ በተገለጠው ፈቃዱ መሠረት እግዚአብሔር በዕቅዱ ውስጥ ያለውን የተሰወረውን እውነት እንድናውቅ አድርጎናል፤10ዕቅዱን የሚፈጽምበት ጊዜ ሲድርስ በሰማይና በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ በአንድ ላይ በክርስቶስ ስር ይጠቀልላል።11ሁሉንም ነገር እንደ ገዛ ፈቃዱ በሚያደርገው ዕቅድ መሠረት በክርስቶስ ተመረጥን፤ አስቀድሞም ተወሰንን12ይህም የሆነው በክርስቶስ በማመን ቀዳሚ የሆንነው እኛ ለክብሩ ምስጋና ይሆን ዘንድ እንድንኖር ነው።13ባመናችሁበትና እንደ ተሰጠው ተስፋ በመንፈስ ቅዱስ በታተማችሁበት በክርስቶስ አማካይነት የመዳናችሁ ወንጌል የሆነውን የእውነት ቃል የሰማችሁት በክርስቶስ ነው14ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን ተስፋ የተደረገው ሀብት በእጅ እስገሚገባ ድረስ መንፈስ ቅዱስ የርስታችን ዋስትና የሚሆን መያዣ ነው።15ስለዚህ በጌታ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለእርሱም ቅዱሳን ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ16ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ማመስገንና እናንተንም በጸሎቴ ማስታወስ አላቋረጥሁም ።17የክብር አባት፥የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን ለማወቅ የሚያስችላችሁን የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤18የምጸልየውም የመጠራታችን አስተማማኝነት እና በእርሱ ቅዱሳን መካከል የርስቱ ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ19እንዲሁም እንደ ኀይሉ ብርታት አሠራር በእኛ በምናምነው ውስጥ የሚሠራው የኀይሉ ታላቅነት ምን እንደሆነ እንድትረዱ ነው።20ይህም እግዚአብሔር ከሙታን ባስነሳውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ እንዲቀመጥ ባደረገው ጊዜ በክርስቶስ ውስጥ የታየው ኀይል ነው።21ክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በአብ ቀኝ የተቀመጠውም ከማንኛውም ግዛት፥ ሥልጣን፥ኀይልና ጌትነት እንዲሁም በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚችለው ስም ሁሉ በላይ ነው።22እግዚአብሔር ሁሉም ነገር በክርስቶስ እግር ሥር እንዲገዛ አድርጓል፤ እርሱንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሁሉም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾሞታል23ቤተ ክርስቲያንም ሁሉንም ነገር በሁሉም መንገድ የሚሞላው የእርሱ ሙላት የሆነች አካሉ ናት።
1እንግዲህ እናንተ ከበደላችሁና ከሓጢአታችሁ የተነሳ የሞታችሁ ነበራችሁ።2በዚያን ጊዜ የዚህን ዓለም ክፉ መንገድ በመከተል፥ በአየር ላይ ባሉት ኀይላት ላይ ገዥ ለሆነው እንዲሁም በማይታዘዙት ልጆች ላይ ለሚሠራው መንፈስ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር።3በአንድ ወቅት እኛ ሁላችን ለሥጋችን ክፉ ምኞት እየታዘዝንና ፈቃዱን እየፈጸምን፥ የአእምሮአችንንም ሐሳብ እየተከተልን በእነዚህ በማያምኑት ሰዎች መካከል እንኖር ነበር፤ በተፈጥሮአችንም እንደሌሎቹ የቁጣ ልጆች ነበርን።4ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት በማድረግ ባለጠጋ ስለሆነ፥ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ5በበደላችን ሙታን በነበርንበት ጊዜ እንኳ ከክርስቶስ ጋር አዲስ ሕይወት ሰጠን፤የዳናችሁትም በጸጋ ነው፤6ከእርሱም ጋር አስነሳን፤በሰማያዊ ስፍራም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር እንድንቀመጥ አደረገን።7ይህንንም ያደረገው፥በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠውን የጸጋው ባለጠግነት ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ያሳይ ዘንድ ነው።8የዳናችሁት በእምነት አማካይነት በጸጋ ነውና ፤ ይህ ከእግዚአብሔር ያገኛችሁት ስጦታ እንጂ ከእናንተ የሆነ ነገር አይደለም።9ማንም ሰው እንዳይመካ በሥራ የተገኘ ነገር አይደለም10ምክንያቱም እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት እንድንፈጽመው ያዘጋጀውን መልካም ሥራ ለመሥራት በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።11ስለዚህ በአንድ ወቅት በአካል ላይ በሰው እጅ የሚከናወነውን መገረዝ ስላገኙ «የተገረዙ» በሚባሉት ዘንድ «ያልተገረዙ» ተብላችሁ የምትጠሩ በትውልድ አሕዛብ የነበራችሁ እንደሆነ አስታውሱ።12በዚያን ጊዜ ከክርስቶስ ተለይታችሁ፥ የእስራኤል ወገን ከመሆን ርቃችሁ፥ለተስፋውም ኪዳን ባዕድ ሆናችሁ ያለ ተስፋ እና ያለ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ትኖሩ እንደነበር ልብ በሉ።13ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁት በክርስቶስ ኢየሱስ በመሆን በክርስቶስ ደም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር እንድትቀርቡ ተደርጋችኋል።14አይሁድንና አሕዛብን ሁለቱን አንድ ሕዝብ ያደረገ እርሱ ሰላማችን ነውና ፤ በሥጋውም እርስ በርስ የለያየንን የጥል ግድግዳ አፈረሰ።15ይኸውም ከሁለቱ ሕዝቦች አንድ አዲስ ሕዝብ በመፍጠር ሰላምን ያደርግ ዘንድ የትእዛዛትንና የሕግ ደንቦችን በሥጋው ሻረ።16ይህንንም ያደረገው በመስቀሉ አማካይነት በመካከላቸው የነበረውን ጠላትነት ገድሎ ሁለቱን ሕዝቦች አንድ አካል በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ነው።17ኢየሱስ መጥቶ ርቀው ለነበሩት እና ቀርበው ለነበሩት ለእነዚያ የምሥራቹን ወንጌል ሰበከ፤ ሰላሙንም አወጀ።18በኢየሱስ አማካይነት እኛ ሁለታችንም በአንድ መንፈስ ወደ አብ መቅረብ እንችላለንና።19ስለዚህ እናንተ አሕዛብ ከቅዱሳንና ከእግዚአብሔር ቤተ ሰብ አባላት ጋር የአንድ አገር ዜጎች ናችሁ እንጂ ከእንግዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም።20እነዚህ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው።21ቤተ ሰቡ የሆነው ሕንጻ ሁሉ በኢየሱስ ኀይል አንድ ላይ ተገጣጥሞ ለጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ለመሆን ያድጋል።22እናንተም እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ሕንጻ እንድትሆኑ አብራችሁ በክርስቶስ እየታነጻችሁ ነው።
1በዚህ ምክንያት አሕዛብ ስለሆናችሁት ስለ እናንተ እኔ ጳውሎስ የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ሆኛለሁ።2ለእናንተ ጥቅም ሲባል ስለ ተሰጠኝ የእግዚእብሔር ጸጋ መጋቢነት ሰምታችኋል ብዬ አስባለሁ።3ቀደም ሲል እንደጻፍሁላችሁ እግዚአብሔር የተሰወረውን ምስጢር በመገለጥ እንዳውቅ አድርጓል።4ይህን በምታነቡበት ጊዜ ስለ ክርስቶስ ምስጢር እኔ ያለኝን መረዳት መገንዘብ ትችላላችሁ።5ምስጢሩም አሁን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለሓዋርያቱ እና ለነቢያቱ የተገለጠው ያህል ባለፉት ዘመናት ለነበሩ ሰዎች አልተገለጠም ነበር።6ይህም ምስጢር አሕዛብ በወንጌል አማካይነት አብረው ወራሾች፥ አብረው የካሉ ብልቶች እንዲሁም በክርስቶስ በተገኘው ተስፋ አብረው ተካፋዮች መሆናቸው ነው።7እንደ እርሱ ኀይል አሠራር በተሰጠኝ በእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ አገልጋይ ሆኛለሁ።8ምንም እንኳ ከቅዱሳን ሁሉ ያነስሁ ብሆንም፥ የማይመረመረውን የክርስቶስ የባለጠግነት ወንጌል ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ ይህ ጸጋ ለእኔ ተሰጠኝ።9እንዲሁም የሁሉን ነገር ፈጣሪ በሆነው በእግዚአብሔር ላለፉት ዘመናት ተሰውሮ ስለነበረው ምስጢር የእግዚአብሔር ዕቅድ ምን እንደሆነ ለሁሉም እገልጥ ዘንድ ተሰጠኝ።10በዚህም ምክንያት በቤተ ክርስቲያን አማካይነት ብዙ ገጽታ ያለው የእግዚአብሔር ጥበብ በሰማያዊ ስፍራ ላሉት አለቆችና ባለ ሥልጣናት እንዲታወቅ ነው።11ይህም የሆነው በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ በፈጸመው ዘላለማዊ ዕቅዱ መሠረት ነው።12በክርስቶስ በማመናችን በእርሱ ሆነን በድፍረትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለንና።13ስለዚህ ክብራችሁ በሆነው ለእናንተ ስል በምቀበለው መከራ ተስፋ እንዳትቆርጡ እለምናችኋለሁ።14በዚህም ምክንያት በአብ ፊት እንበረከካለሁ፤15እርሱም በሰማይና በምድር ላለ ቤተ ሰብ ሁሉ ስያሜ የሰጠ እና እነርሱንም የፈጠረ ነው።16የምጸልየውም ትጠነክሩ ዘንድ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን ኀይል እንዲሰጣችሁ ነው።17ይህም በእምነት ክርስቶስ በልባችሁ እንዲኖር፥ በፍቅሩ ሥር እንድትሰዱና እንድትታነጹ ነው፤18ደግሞም የክርስቶስ ፍቅር ስፋቱ፥ርዝመቱ፥ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር መረዳት ትችሉ ዘንድ ነው።19እንዲሁም በእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ሁሉ ትሞሉ ዘንድ ፥ ከሰው ዕውቀት ሁሉ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ታላቅ ፍቅር እንድታውቁ ነው።20እንግዲህ በእኛ ውስጥ እንደሚሠራው ሀይሉ መጠን ሁሉንም ነገር እኛ ከምንለምነው ወይም ከምናስበው በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው21በቤተ ክርስቲያንና በክርስቶስ ኢየሱስ በትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን፤አሜን።
1ስለዚህ የጌታ እስረኛ እንደመሆኔ በእግዚአብሔር ለተጠራችሁለት መጠራት የሚገባውን ሕይወት ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ።2ይኽውም እርስ በርስ በፍቅር ተቻችላችሁ በፍጹም ትሕትና፥በገርነትና በትዕግሥት እንድትኖሩ ነው።3በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ አድርጉ።4በተጠራችሁ ጊዜ በአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ ሁሉ፥ አንድ አካል እና አንድ መንፈስ አለ፤5አንድ ጌታ፥አንድ እምነት፥አንድ ጥምቀት አለ ፤6ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ፥በሁሉ የሚሠራ፥ በሁሉ የሚኖር ፥የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።7ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጥቶናል8ይህም የእግዚአብሔር ቃል «ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮኞችን ማረከ፤ለሰዎችም ስጦታ ሰጠ» በማለት እንደሚናገረው ነው።9«ወደ ላይ ወጣ» ሲል ደግሞም «ወደ ምድር ጥልቅ ወረደ» ማለት ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊያመለክት ይችላል?10ታች የወረደው ሁሉንም ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ያው እርሱ ራሱ ነው።11ወንጌል ሰባኪዎችን፥እረኞችን እና አስተማሪዎችን ስጦታ አድርጎ የሰጠ ክርስቶስ ራሱ ነው።12ያደረገው የክርስቶስን አካል ለማነጽና ለአገልግሎት ሥራ ቅዱሳንን ለማስታጠቅ ነው።13የሚሆነው ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደ ሚገኘው አንድነት እንዲሁም ወደ ክርስቶስ ሙላት ልክ እንዳደጉት ሰዎች ሙሉ ሰው ወደ መሆን ደረጃ እስከምንደርስ ድረስ ነው።14በሰዎች ረቂቅ ተንኮል እና ማታለል በተዘጋጀ የትምህርት ነፋስ ወዲያና ወዲህ የምንነዳ ሕጻናት መሆን አይገባንም15ይልቁንም እውነትን በፍቅር የምንናገር እና ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ በሁሉም መንገድ የምናድግ ሰዎች መሆን ይጠበቅብናል።16የአማኞችን አካል ሁሉ በሚያገናኘው ጅማት እየተያያዘና እየተጋጠመ፥እያንዳንዱም ክፍል የራሱን ተግባር እያከናወነ በፍቅር ያድጋል።17እየለመንኋችሁ ይህን የምናገረው፥ ከእንግዲህ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱት እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ነው።18እነርሱም አእምሮአቸው ጨልሞአል፤ካለማወቃቸውና ከልባቸው ደንዳናነት የተነሳ ከእግዚአብሔር ሕይወት ርቀዋል፤19ስግብግብነት ሁሉ ለሞላበት ቅጥ ላጣ ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።20ግን ስለ ክርስቶስ የተማራችሁት እንደዚህ አይደለም።21እርሱ የሰማችሁ እና የተማራችሁ ከሆነም በርግጥ የተማራችሁት ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን እውነት ነው።22ክፉ ምኞት የጎደፈውን አስቀድሞ ትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰው ልታስወግዱ ይገባል።23በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ24እውነተኛ በሆነው ጽድቅና ቅድስና በእግዚአብሔር የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።25ውሸትን አስወግዱ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ስለሆንን «እያንዳንዱ ከባልንጀራው ጋር እውነትን ይነጋገር»።26«ተቆጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ» በቁጣችሁ ጸሓይ እስከሚገባ ድረስ አትቆዩ፤27ዕድል አትስጡት።28የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ይልቁንም ለተቸገሩ ሰዎች ማካፈል ይችል ዘንድ በራሱ እጅ በተገቢው ሁኔታ እየሠራ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ይገባዋል።29ለማነጽ የሚያስፈልግ፥ ለሚሰሙትም ጸጋን የሚሰጥ ጠቃሚ ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።30ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ።31ሁሉ፥ቁጣንና ንዴትን፥ጭቅጭቅንና ስድብን ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ጋር ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ።32በርሳችሁ ቸሮች፥ ርኅሩሆች ሁኑ፤ ደግሞም እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲሁ ይቅር እንዳላችሁ እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።
1እንግዲህ እንደ ተወደዱ የእርሱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትመስሉ ሁኑ፤2እንደ ወደደን፥ ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንዳቀረበ ሁሉ እናንተም በፍቅር ኑሩ።3የሚገባ ባለመሆኑ ዝሙት፥ማንኛውም ርኩሰትና ስስት በእናንተ ዘንድ ሊኖር አይገባም፤4ጸያፍ ንግግር፥ዋዛ ወይም ውርደትን የሚያስከትል ቀልድ ለእናንተ ስለማይገባ ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ከዚህ ይልቅ የምታመሰግኑ ሁኑ።5አመንዝራ፥ርኩስ፥ ስግብግብ የሆነ ይኽውም ጣዖት አምላኪ ሰው በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማይኖረው ርግጠኛ ልትሆኑ ይገባል።6ከንቱ በሆነ ንግግር ማንም አያታላችሁ፤በእነዚህ ነገሮች ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ ይመጣል7ስለዚህ የእነርሱ ተባባሪዎች አትሁኑ።8ወቅት ጨለማ ነበራችሁና፤ አሁን ግን በክርስቶስ ብርሃን ናችሁ። ስለዚህ እንደ ብርሃን ልጆች ኑሩ።9ምክንያቱም ከብርሃኑ የሚገኘው ፍሬ መልካም ነገር ሁሉ፥ ጽድቅና እውነት ነው10እንዲሁም ጌታን ደስ የሚያሰኝ ነገር ለማድረግ አስቡ፤11ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፤ይልቁን ልትገልጡት ይገባል።12በስውር ያደረጉትን ነገር ለመግለጽ እንኳ አሳፋሪ ነውና።13በሚኖርበት ጊዜ ማንኛውም ነገር በግልጽ ይታያል።14ብርሃኑ በላዩ ላይ ስለሚያበራ ነው። ስለዚህ፥ «አንተ የምትተኛ ንቃ፤ከሙታን ተነሳ፤ክርስቶስም ያበራልሃል» ተብሎ ተነግሯል።15ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን፥እንደ ጥበብኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ።16ክፉዎች ስለሆኑ ዘመኑን ዋጁ።17ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።18ሕይወታችሁን ለጥፋት ስለሚዳርግ፥በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ይልቁንስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።19እርስ በርሳችሁ በመዝሙር፥በቅኔና በመንፈሳዊ ዝማሬ ተነጋገሩ፤ ጌታንም በልባችሁ አመስግኑ፤ለእርሱም ተቀኙ።20በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉም ነገር ሁልጊዜ እግዚአብሔር አብን አመስግኑ21ክርስቶስን ለማክበር ስትሉ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተገዙ።22ሚስቶች ሆይ! ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ።23ክርስቶስ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና።24ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ ሁሉ ሚስቶችም በማንኛውም ነገር ለባሎቻቸው ሊገዙ ይገባል።25ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ስለ እርስዋም ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ፥ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ።26ይህንንም ያደረገው በቃሉ አማካይነት በውሃ አጥቦ በማንጻት እንድትቀደስ፥27ጉድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ሳይታይባት ቅድስት የሆነችና ነውር የሌለባት ክብርት ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ለራሱ ሊያቀርባት ነው።28ባሎች የገዛ ሥጋቸውን እንደሚወዱ ሚስቶቻቸውን መውደድ ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል።29የራሱን ሥጋ የሚጠላ ማንም የለም፤ ይልቁን ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋልም። ይህም ክርስቶስ ልክ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚወድ ነው።30እኛ የእርሱ ብልቶች ነን።31ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ከሚስቱም ጋር አንድ ይሆናል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።32ታላቅ ምስጢር ነው፤ እኔም ይህን የምናገረው ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ነው።33ግን ከእናንተ እያንዳንዱ ደግሞ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ መውደድ ይገባዋል፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።
1ልጆች ሆይ፤ በጌታ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤ ይህ ተገቢ ነውና።2«አባትህንና እናትህን አክብር» በሚለው የመጀመሪያ ትእዛዝ ውስጥ ያለው ተስፋ3እንዲሆንልህ፥ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም» የሚል ነው።4እናንተም አባቶች ሆይ፤ ልጆቻችሁን አታስቆጡአቸው፤ ይልቁንስ በጌታ ሥርዓትና ምክር አሳድጓቸው።5ባሮች ሆይ፤ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙት ለምድራዊ ጌቶቻችሁም በታላቅ አክብሮት፥ በመንቀጥቀጥና በልባችሁ ቅንነት ታዘዙ፤6ለታይታ እነርሱን ደስ ለማሰኘት ብላችሁ ሳይሆን፥ እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከልብ በመፈጸም ታዘዙአቸው።7ሰውን ሳይሆን ጌታን እንደምታገለግሉ እያሰባችሁ በደስታ አገልግሉ።8ባሪያም ይሁን ነጻ ሰው እያንዳንዱ ሰው ለሚያደርገው መልካም ነገር ከጌታ ሽልማት እንደሚቀበል ልብ በሉ።9እናንተም ጌቶች ሆይ፤ ለባሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የእነርሱና የእናንተም ጌታ የሆነው እርሱ በሰማይ እንዳለና ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ተረድታችሁ አታስፈራሯቸው።10በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ የበረታችሁ ሁኑ።11የዲያብሎስን ተንኮል አዘል ዕቅድ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ።12ውጊያችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከአለቆች፥ ከሥልጣናት፥ ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦችና በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ርኩሳን መናፍስት ጋር ነው።13በክፉ ቀን ክፉውን በመቃወም ጸንታችሁ ትቆሙ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ፤ ጸንታችሁ ለመቆምም ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።14ወገባችሁን በእውነት ቀበቶ ታጥቃችሁ፥የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ ጸንታችሁ ቁሙ፤15የሰላምን ወንጌል ለማወጅ እግሮቻችሁ በዚያ ተጫምተው ዝግጁ ይሁኑ16የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ማጥፋት ትችሉ ዘንድ ሁል ጊዜ የእምነትን ጋሻ አንሱ።17የመዳንን ራስ ቁር አድርጉ፤የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ይህም የእግዚአብሔር ቃል ነው።18ዓይነት ጸሎትና ልመና ሁልጊዜ በመንፈስ በመጸለይና መልሱን ከእርሱ በመጠበቅ፥ ለቅዱሳንም ልመና በማቅረብ ትጉ።19ምስጢር በድፍረት ለመናገር አፌን በምከፍትበት ጊዜ ሁሉ ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ለእኔም ጸልዩልኝ።20መናገር እንደሚገባኝ በድፍረት እናገር ዘንድ በሰንሰለት የታሰረ መልእክተኛ የሆንሁት ለዚሁ ነውና።21ሁኔታ እንዳለሁና ምን እያደረግሁ እንደምገኝ፥ የተወደደ ወንድምና በጌታ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ቲኪቆስ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል።22ያለንበትን ሁኔታ እንድታውቁና እናንተንም እንዲያበረታታ በማለት ወደ እናንተ ልኬዋለሁ።23ከአብ፥ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር ከእምነት ጋር ለወንድሞች ይሁን።24ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ከሚወዱ ጋር ሁሉ ጸጋ ይሁን።
1የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቲዎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱሳን ለሆኑ በፊልጵስዩስ ከተማ ከእረኞችና ከዲያቆናት ጋር ለሚኖሩ ሁሉ።2ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ስላም ለአናንተ ይሁን።3ስለእናንተ በማስብበት ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።4ስለ ሁላችሁም በምጸልይበት ጊዜ ሁሉ በደስታ እጸልያለሁ።5ከመጀመሪያ ጀምሮ እስካሁን ወንጌል በሚሰበክበት ሥራ ስላሳያችሁት ትብብራችሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።6ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።7እናንተ በልቤ ስላላችሁ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰብ ይኖርብኛል። በእስራቴና ስለ ወንጌል በመቆሜ ስለእርሱም በመመስከሬ ሁላችሁም በጸጋ ተባባሪዎች ሆናችኋል።8በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ ጥልቅ ፍቅር ሁላችሁንም እንድምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።9ፍቅራችሁ በዕውቀትና በሙሉ መረዳት የበለጠ እንዲበዘላችሁ እጸልያለሁ።10ይህን የምጸልይበት ምክንያት የተሻለውን ነገሮችን መርምራችሁ እንድታውቁ እንዲሁም ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ቀን ንጹኃንና ነውር የሌለባችሁ ሆናችሁ እንድትገኙ ነው።11ይህ ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ ተሞልታችሁ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና እንዲሆን ነው።12ወንድሞች ሆይ፥በእኔ ላይ የደረሰው ሁሉ ወንጌል በጣም እንዲስፋፋ እንዳደረገ እንድታውቁ እወዳለሁ።13እኔም የታሰሁት በክርስቶስ ምክንያት መሆኑን የቤተ መንግሥት ጠበቂዎችና ሌሎችም እዚያ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ ሆኖአል።14በእኔ መታሰር ምክንያት በጌታ ወንድሞች ከሆኑት ብዙዎቹ የበለጠ ከቀድሞ ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሃት ለመናገር ድፍረት አግኝተዋል።15በርግጥ አንዳንዶቹ የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩት በቅናትና በፉክክር መንፈስ ነው፤ሌሎቹ ግን ክርስቶስን የሚሰብኩት በቅን ልቡና ነው።16እነዚህ የእግዚአብሔርን ቃል በቅን ልቡና የሚሰብኩት ከፍቅር የተነሳ ነው፤እነርሱም እኔ ስለወንጌል ቆሜ በመከራከርይ መታሰሬን ያውቃሉ።17እነዚያ ግን ስለ ክርስቶስ የሚሰብኩት በራስ ወዳድነትና ቅንነት በሌለበት አስተሳሰብ ነው። በእስራቴም ላይ ተጨማሪ መከራ ሊያመጡብኝ አስበው ነው።18ታዲያ ምን ይደረግ? በርግጥ በዚህ ደስ ይለኛል፤በማስመሰል ወይም በእውነት በሁሉም መንገድ ክርስቶስ ይሰበካል።19ምክንያቱም በእናንተ ጸሎትና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ርዳታ ነጻ እንደምወጣ አውቃለሁ።20እንደማላፍርበት በሙሉ መተማመ እጠባበቃለሁ። ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና በተለይም ዛሬም በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።21ስለዚህ ለእኔ ሕይወት ማለት በክርስቶስ መኖር ነው፤ ሞትም ማለት ማትፍረፍ ነው።22ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም።23ምክንያቱም በእነዚህ በሁለቱ አሳቦች መካከል ተወጥሬአለሁ። በአንድ በኩል ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለሆነ ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ።24ሆኖም በሥጋ መኖሬ ለእናንተ የበለጠ አስፈላጊ ነው።25እምነታችሁ እንዲያድግና ደስታን እንድታገኙ እንደምቆይና ከሁላችሁም ጋር እንደምቀጥል ስለዚህ ነገር እተማመናሉ።26በዚህ ምክንያት እኔም እንደገና ወደ እናንተ ስመጣት ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ በእኔ ትመካላችሁ።27እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁ ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ለወንጌልም እምነት በኅብረት መጋደላችሁን እሰማ ዘንድ ነው።28ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን፤ ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳናችሁ ምልክት ነው።29ምክንያቱም ከክርስቶስ የተነሳ ይህ የተሰጣችሁ አገልግሎት በእርሱ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን በእርሱ ምክንያት መከራ እንድትቅበሉም ጭምር ነው።30ስለዚህ አሁን ከእኔ ጋር የመከራ ተካፋዮች ሆናችኋል፤ ይህም መከራ ከዚህ በፊት ደርሶብኝ ያያችሁትና አሁንም እየደረሰብኝ መሆኑን የሰማችሁት ነው።
1በክርስቶስ መበረታታት ካላችሁ፤ከፍቅሩም መጽናናት ካላችሁ፤የመንፈስም ኅብረት ካላችሁ፤እርስ በእርሳችሁም ደግነትና ርኅራኄ ካላችሁ።2ስለዚህ በአንድ አሳብ፤ በፍቅር፤ በመንፈስ አንድነት፤በአንድ ዓላማ እየተስማማችሁ ደስታዬ እንዲፈጸም አድርጉት።3በራስ ወዳድነት ወይም በከንቱ ትምክህት ምንም አታድርጉ፤ነገር ግን በዚህ ፈንታ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትህትና ቁጠሩ።4እንዲሁም እያንዳንዳእሁ የራሳችሁን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም አስቡ።5በኢየሱስ ክርስቶስ የነበረ አሳብ በእናንተም ደግሞ ይኑር፤6እርሱም የመለኮት ባሕር ነበረው፥ ነገር ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርጋውን የመለኮት ባሕይ እንደ ያዘ አልቆጠረም። ክብሩን ትቶ ራሱን ባዶ አደረገ።7የባሪያንም መልክ ያዘ፤ በሰው አምሳል ተገለጠ፤ እንደ ሰውም ሆኖ በትህትና ራሱን ዝቅ አደረገ።8እንዲሁም እስከ ሞት፤ያውም እስከ መስቀል ሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።9ስለዚህም እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ሰጠው።10በዚህም ምክንያት ጉልበት ሁሉ በሰማይና በምድር፤ ከምድርም በታች ሁሉ በኢየሱስ እግሮች በታች እንዲንበረከኩ ነው።11አንደበትም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሆን፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው ብሎ እንዲመሰክር ነው።12ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፤ እኔ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ሁሉ እንደምትታዘዙ፥ይልቁንም አሁን ከእናንተ በራቅሁበት ጊዜ ይበልጥ ታዛዦች እንድትሆኑ ነው።13በፍርሃትና በመንቀጥቅቀጥም መዳናችሁን ሥሩ። ምክንያቱም ለመልካምነቱ መፍቃዱንና ማድረግን በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነው።14ማናቸውንም ነገር ሳታጉረምግሙና ሳትከራከሩ አድርጉ።15ይህን በማድረግ ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ታማኝ የአግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ። በዚህ በጠማናና በመጥፎ ትውልድ መካከል በዚህ ዓለም እንደ ደማቅ ብርሃን ታበራላችሁ።16ሕይወት የሚገኝበትን ቃል አጥብቃችሁ በምትይዙበት ጊዜ በከንቱ እንዳልሮጥሁና በከንቱም እንዳልደከምሁ ክርስቶስ በሚመለስበት ቀን ለማክበር ምክንያት ሊኖረኝ ይችላል።17ነገር ግን ለእግዚአብሔር በእምነት በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ የእኔም ሕይወት እንደ መሥዋዕት ሆኖ ቢቀርብ እንኳ ደስ ይለኛል። ከሁላችሁ ጋር ታላቅ ደስታ እደሰታለሁ።18እንዲሁም በተመሳሳይ ሁኔታ እናንተም ከእኔ ጋር ደስተኞች ትሆናላችሁ።19ነገር ግን እናንተ እንዴት እየሠራችሁ እንዳላችሁ ሰምቼ እንድጽናና ጢሞቲዎስን ወደ እናንተ ፈጥኜ እንደምልክ በጌታ በኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።20ስለ እናንተ ሁኔታ ከልብ የሚያስብ ከጢሞቲዎስ በስተቀር ሌላ ሰው የለኝም።21ሌሎቹ ግን የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ስለሚፈልጉ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ግድ የላቸውም።22ነገር ግን ጢሞቲዎስ ልጅ አባቱን እንደሚያገለግል ከእኔ ጋር ወንጌልን በማሠራጨት እንዳገለገለና ስለታማኝነቱም የተመሰከረለት መሆኑን እናንተም ታውቃላችሁ።23ስለዚህ የእኔን ሁኔታ እንዳወቅሁ በፍጥነት ጢሞቲዎስን ወደ እናንተ እንደምልክላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።24እንዲያውም እኔ ራሴ በቶሎ ወደ እናንተ እንደምመምጣት በጌታ እተማመናለሁ።25ነገር ግን ኤጳፍሮዲቱስን መልሼ ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እርሱ እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜና ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ባልደረባዬ ነው።26እርሱን ወደ እናንተ የምልከውም ሁላችሁንም ለማየት በመናፈቁና እናንተም መታመሙን በመስማታችሁ ስለ ተጨነቀ ነው። በእርግጥ በጠና ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት አደረገለት።27ከሕመሙ መዳኑ ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ሐዘን በሐዘን ላይ እንዳይደረርብኝ ለእኔም ጭምር ነው።28ስለዚህ እናንተ እርሱን በማየት እንድትደሰቱና የእኔም ሐዘን እንዲቃለል እርሱን ወደ እናንተ ለመላክ ከፍተኛ ፍላጎት አድሮብኛል።29እንግዲህ ኤጳፍሮዲቱስን በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት። እንደ እርሱ ያሉትን ሰዎች አክብሩአቸው ።30በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን በእናንተ ቦታ ሆኖ ሲያገለግለኝና የሚያስፈልገኝን ለማሟላት ስለ ክርስቶስ ሥራ በማለት ለሕይወቱ ሳይሳሳ በማድረግ ለሞት ተቃርቦ ነበር።
1በጨረሻም ወንድሞቼ ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ። ከዚህ በፊት የጻፍኩላችሁን ተመሳሳይ ነግሮች አሁንም ደግሜ ብጽፍላችሁ አይታክተኝም። እነዚህ ነገሮች እናንተን ከስሕተት ይጠብቃችኋል።2ከውሾች ተጠንቀቁ። ከክፉ ሠራተኞች ተጠንቀቁ፤ከሐሰተኞች መገረዝም ተጠንቀቁ።3እኛ በእግዚአብሔር መንፈስ የምናመልክ፤ በሥጋም የማንታመን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ የምንታመን የተገረዝን ነን።4በሥጋ ትምክሕት የሚያስፈልግ ቢሆን እኔ በብዙ ነገር ልመካ እችል ነበረ። ማንም በሥጋ የሚመካበት አለኝ ብሎ የሚያስብ ሰው ቢኖር እኔ ከእርሱ የበለጠ የምመካበት ብዙ አለኝ።5እኔ በተወለድኩ በስምንተኛው ቀን ተገርዤአለሁ፤ በትውልዴም ከብንያም ነገድ የሆንኩ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከዚህም የተነሳ ጥርት ያልኩ ዕብራዊ ነኝ። የአይሁድን ሕግ ስለ መጠበቅም ቢሆን ፈሪሳዊ ነበርኩ።6በቅንዓት ቤተ ክርስቲያን አሳድድ ነበር። ሕግን በመጠበቅ ስለ መጽደቅም ቢሆን ያለ ነቀፋ እኖር ነበር።7ነገር ግን ከዚህ በፊት ጠቃሚዎች ናቸው ብዬ አምንባቸው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ ስለ ክርስቶስ ብዬ ዋጋ እንደሌላቸው እንደ ከንቱ ነገሮች አድርጌ ቆጥሬአቸዋለሁ።8በርግጥ፥ ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ጌታዬ ዕውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ። ስለ እርሱም ሁሉን ነገር አጥቻለሁ። ክርስቶስንም ለማግኝትና በእርሱም ለመገኝት ስል ሁሉን ነገር እንደ ቤት ጥራጊ እቆጥራለሁ።9እንግዲህ በሕግ ላይ የተመሠረተው የራሴ ጽድቅ የለኝም። በዚህ ፈንታ በክርስቶስ በኩል በሚገኝ እምነት የእግዚአብሔር ጽድቅ አለኝ።10ይኸውም እርሱን የማወቅ ጽድቅ፤ የእርሱ የትንሣኤ ኃይልና የመከራው ተካፋይ የመሆንና በሞቱም ክርስቶስን ለመምሰል ነው።11ደግሞም ከሙታን ትንሣኤን አገኝ ዘንድ ነው።12እነዚህን ነገሮች ገና አልጨበጥኩአቸውም ፤ ፍጹም ሆኜአለሁ ማለትም አልችልም። ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘሁትን አገኝ ዘንድ ወደ ፊት ጥረቴን እቀጥላለሁ።13ወንድሞች ሆይ፤እኔ ራሴ ገና እንደጨበጥኩ አልቆጥርም። ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ይኸውም በስተኋላዬ የነበረውን እየረሰሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እተጋለሉ።14እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ጠርቶ ሽልማቴን ለማግኘት በፊት ወዳለው ግብ እሮጣለሁ።15ስለዚህ እኛ ብዙዎቻችን በመንፈሳዊ ሕይወት እንዳደጉ ሰዎች ነገሮችን ሁሉ ማሳብ ይኖርብናል። ደግሞ በማንኛውም ነገር የተለያየ አስተሳሰብ ቢኖራችሁ እግዚአብሔር ሁሉንም ግልጥ ያደርግላችኋል።16ይሁን እንጂ በደረሰንበት በዚያው ሁኔታ እንመላለስ።17ወንድሞች ሆይ፥ የእኔን ምሳሌነት ተከተሉ፤ በእኛም ምሳሌነት የሚመላለሱትን ሁሉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።18ከአሁን በፊት ብዙ ጊዜ እንደ ነገርኳችሁና አሁንም እንባዬን እያፈሰስኩ እንደምነግራችሁ ሁሉ ብዙዎቹ በአካሄዳቸው የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነዋል።19የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገርም ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ አሳባቸውም የሚያተኩረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው ስለዚህ የእነርሱም መጨረሻ ጥፋት ነው፤20ነገር ግን የሚመጣውን አዳኝ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንጠብቅ የሰማይ መንግሥት ዜጎች ነን።21እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል። ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኃይል ነው።
1ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ፤ ወዳጆቼም ሆይ፤ የምናፍቃችሁ፤ ደስታዬና አክሊሎቼ የሆናችሁ በዚህ መንገድ በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ።2ኤዎድያና ሲንጢኪ እርስ በርሳቸው በጌታ ተስማምተው እንዲኖሩ እለምናቸዋለሁ።3በርግጥ አንተም እዚያ ያለኸው የሥራ ባልደርባዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ። እነርሱም ወንጌልን በማሰራጨት ከእኔና ከቅሌምንጦስ ጋር እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቼ ጋር ብዙ ተጋድለዋል።4ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ።5ደግነታችሁ በሰዎች ሁሉ ዘንድ ይታወቅ።6ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፤ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ጌታ ቅርብ ነውና።7ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።8በመጨረሻም ወንድሞችሆይ፥ እውነት የሆነውን ሁሉ፤ ክቡር የሆነውን ሁሉ፤ ትክክል የሆነውን ሁሉ፤ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፤ ፍቅር የሆነውን ሁሉ፤ መልካም የሆነውን ሁሉ፤ በጎነት ቢሆን፤ ምስጋናም ቢሆን፤ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስቡ።9ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፤ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ማናቸውንም ነገር አድርጉ። የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።10እንደገና በመጨረሻ ጊዜ ለእኔ ማሰብ ስለ ጀመራችሁ በጌታ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። በርግጥ ከዚህ በፊት ስለ እኔ ያሰባችሁ ቢሆንም እኔን ለመርዳት ዕድሉን አላገኝችሁም ነበር።11ይህን የምለው ለራሴ ጥቅም አይደለም። ምክንያቱም በሁሉም ሁኔታ ባለኝ ነገር መርካትን ተምሬአለሁ።12በማጣትም ሆነ በማግኘት እንዴት መኖር እንዳለብኝ ዐውቃለሁ። በማንኛውም መንገድ የመጥገብንና የመራብን፤ የማግኝትንና የማጣትን ምሥጢር ተምሬአለሁ።13ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።14ይሁን እንጂ፤ እናንተ የችግሬ ተካፋዮች በመሆናችሁ መልካም አድርጋችኋል።15እናንተ የፊልጵስዩስ ሰዎች የወንጌልን ተልዕኮ በጀመርኩበት ጊዜ ከመቄዶንያ ስወጣ ከእናንተ በቀር በመስጠትም ሆን በመቀበል ከእኔ ጋር የተባበረ ሌላ ቤተ ክርስቲያን እንዳልነበረ ታውቃላችሁ።16በተሰሎንቄ በነበርኩበት ጊዜም ቢሆን ከአንድ ጊዜ በላይ ለሚያስፈልገኝ ርዳታ ልካችሁልኛል።17ይህንንም ስል የእናንተን ስጦታ ለማግኝት በመፈለግ ሳይሆን የልግሥናችሁ ፍሬ እንዲበዛላችሁ በመመኘት ነው።18ሁሉንም ነገር ተቀብያለሁ፤በዝቶልኛል፤ ሞልቶልኛልም። የላካችሁልኝን ስጦታ ከኤጳፍሮዲቱስ እጅ ተቀብዬአለሁ። ይህም ስጦታ በመልካም መዓዛ እንደ ተሞላ መሥዋዕት እግዚአንሔር የሚቀበለውና ደስ የሚሰኝበት ነው።19ደግሞም አምላኬ እንደ ክብሩ ባለጠግነቱ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል።20እንግዲህ ለአባታችንና ለአምላካችን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።21በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆኑት ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሰላምታ ያቀርቡላችሁኋል።22እዚህ ያሉት አማኞች ሁሉ በተለይም የሮማ ቤተ መንግሥት ያሉ ሠራተኞች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።23የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን።
1በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቲዎስ፤2በቆላስይስ ለሚኖሩ ለእግዚአብሔር ለተለዩና በክርስቶስ ታማኝ ለሆኑ አማኞች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ጸጋና ሰላም ይሁንላችሁ።3ለእናንተ በምንጸልይበት ጊዜ ሁሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን እናመሰግናለንን።4በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለእግዚአብሔር ለተለዩት ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተናል።5በሰማይ ከተጠበቀላችሁ ከመታመነ ተስፋ የተነሣ ይህ እምነትና ፍቅር አላችሁ። ስለዚህም ተስፋ በወንጌል የእውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ፤ ይህም ወደ እናንት ደርሶአል።6ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በእናንተም ዘንድ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በዓለም ዙሪያ ሁሉ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው።7በእኛ ምትክ ለእናንተ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ የሆነውና ከእኛም ጋር አብሮን ከሚያገለግል ከተወዳጁ ከኤጳፍራ ይህን ተምራችኋል።8ደግሞም በእግዚአብሔር መንፈስ ያላችሁን ፍቅር ነግሮናል።9ከዚህም ፍቅር የተነሣ ስለ እናንተ ከሰማንበት ቀን ጀምሮ ለእናንተ ከመጸለይ አላቋረጥንም። በፈቃዱ ዕውቀት፣ በጥበብ ሁሉና በመንፈሳዊ ማስተዋል እንድትሞሉ እንጸልይላችኋለን።10ጌታን ደስ በሚያሰኝ መንገድ በሁሉም እንደሚገባ እንድትመላለሱ፤ በማናቸውንም መልካም ሥራ ፍሬ እንድታፈሩና በእግዚአብሔርም ዕውቀት እንድታድጉ እንጸልያለን።11በሁሉም ነገር እንድትጽኑና ትእግሥት እንዲኖራችሁ ፣ከኅይሉ ክብር የተነሣም በሁሉ ብርታትና ጥንካሬ እንዲኖራችሁ እንጸልያለን።12በብርሃን ከሚኖሩት አማኞች ጋር የርስቱ ተካፋይ እንድንሆን ላበቃን ለእግዚአብሔር በደስታ ምስጋና ማቅረብ እንድትችሉ እንጸልያለን።13ከጨለማ ኅይል አዳነን፤ ወደ ተወደደውም ወደ ልጁ መንግሥት አሸጋገረን።14በልጁም የኅጢአታችንን ይቅርታ፣ ድነትን አገኘን።15ልጁ የማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው። እርሱ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው።16ምክንያቱም በሰማያትና በምድር፤ የሚታዩትና የማይታዩት ነገሮች ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል። ዙፋናትም ሆኑ ኅይላት ወይም ግዛቶችች ወይም ሥልጣናት፤ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥረዋል።17እርሱ ከሁሉ በፊት ነበረ፤ሁሉም ነገር የተያያዘው በእርሱ ነው።18እርሱ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱ የሁሉም መገኛና የሁሉም የመጀመሪያ፣ከሙታንም በኩር ነው።19በመሆኑም በሁሉም ነገሮች መካከል የመጀመሪያ ነው። በእርሱ የእግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ እንዲኖርና እግዚአብሔር በልጁ በኩል ሁሉን ነገር20ከራሱ ጋር ያስታርቅ ዘንድ ስለ ወደደ ነው። እግዚአብሔር ልጁ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በሰማያትም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስታረቀ።21እናንተም ቀድሞ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ነበር፤ በአሳባችሁና በክፉ ሥራችሁም ምክንያት ጠላቶች ነበራችሁ።22አሁን ግን ቅዱሳንና ንጹሓን፤ ነቀፋም የሌለባችሁ አድርጎ በፊቱ ሊያቀርባችሁ በልጁ ሞት እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቃችሁ። ይህም በእርሱ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ23በእምነት ጸንታችሁ እንድትኖሩ ነው። ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ ተሰብኮአል። እኔም ጳውሎስ አገልጋይ የሆንኩት ለዚህ ወንጌል ነው።24አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል። አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጎደለውን በሥጋዬ አሟላለሁ።25የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ለእናንተ እንድገልጥ ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ኅላፊነት ቃሉን ለመፈጸም የማገለግለው ይህችን ቤተ ክርስቲያን ነው።26ይህም ባለፉት ዘመናትና ትውልዶች ከሰው ልጆች ተሰውሮ የቆየውና አሁን ግን እግዚአብሔር ለሚያምኑት ሁሉ የገለጠው ምስጢር ነው።27እግዚአብሔርም በእናንተ መካከል ለአሕዛብ ሊገልጥላቸው የፈለገው የዚህ ምስጢር የክብር ብልጽግና ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።28የምንሰብከው እርሱን ነው። እያንዳንዱን ሰው በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ለማቅረብ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምክር ሰውን ሁሉ እንገስጻለን።29በውስጤ በኅይል በሚሠራው መሠረት በብርቱ እየታገልኩ እደክማለሁ።
1ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ሰዎች እንዲሁም ፊቴን በሥጋ አይተውት ስለማያውቁ ስለ ብዙዎች ምን ያህል ብርቱ ትግል እንዳደረግሁ እንድታውቁ እወዳለሁ።2ልባቸው ተጽናንቶና በፍቅር ተሳሰረው ፍጹም የሆነ የመረዳት ብልጽግና እንዲኖራቸውና የእግዚአብሔርን ምስጢር የሆነውን እውነት ክርስቶስን እንዲያውቁ እታገላለሁ።3የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የተሰወረው በእርሱ ነው።4ይህን የምላችሁ ማንም በሚያታልል ንግግር እንዳያስታችሁ ነው።5በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን እንኳ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ። የእናንተን መልካም ሥርዐትና በክርስቶስ ያላችሁን ጽኑ እምነት እያየሁ ደስ ይለኛል።6ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።7በእርሱም ተመሥርታችሁና ታንጻችሁ፤ እንደ ተማራችሁትም በእምነት ተደላድላችሁ ኑሩ፤ ምስጋናም ይብዛላችሁ።8በክርስቶስ ላይ ባልተመሠረተ በሰው ሠራሽ ልማድና በዓለማዊ ነገሮች፥ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።9የእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት በእርሱ ይኖራልና።10በእርሱም ተሞልታችኋል። እርሱ የአለቅነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ ነው።11በእርሱም ተገርዛችኋል፤ ይህም መገረዛችሁ የሥጋዊ አካል በማስወገድ በሰው እጅ የተደረገ ሳይሆን በክርስቶስ የተደረገ ነው።12በተጠመቃችሁ ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ተቀበራችሁ፤በእርሱም ክርስቶስን ከሞት ባስነሣው በእግዚአብሔር ኅይል በእምነት ተነሥታችኋል።13እናንተም በበደላችሁና በሥጋችሁ ባለመገረዝ ሙታን ሳላችሁ፤ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አድርጎ መተላለፋችንንም ሁሉ ይቅር ብሎአል።14እርሱ ይከሰን የነበረውን የዕዳ ጽሑፍ ደመሰሰው። ሁሉንም በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከእኛ አስወገደው።15ኅይላትንና ባለሥልጣናትን በመስቀሉ ድል አድርጎ በይፋ እንዲጋለጡ አደረጋቸው።16እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም የበዓላትን ቀናት ወይም የወር መባቻን፤ ወይም ሰንበትን በማክበር ምክንያት ማንም አይፍረድባችሁ።17እነዚሁ ሁሉ ወደ ፊት ሊመጡ ላሉት ነገሮች እንደ ጥላ ናቸው፤ እውነተኛው አካል ግን በክርስቶስ ነው።18አስመሳይ በሆነ ትሕትና የመላእክትን አምልኮ በመፈለግ ማንም ዋጋ እንዳያሳጣችሁ። እንዲህ ያለው ሰው ስለሚያየው ነገር በሥጋዊ አስተሳሰቡ ይታበያል።19እርሱም ራስ ከሆነ ከክርስቶስ ጋር አልተያያዘም። በእግዚአብሔር በተሰጠው እድገት በመገጣጠሚያና በጅማት አካልን በሙሉ አያይዞ የሚመግበውና ለአካል ሙሉ ዕድገት የሚሰጠው ራስ ነው።20ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፣ ለዓለማዊ ነገሮች እየታዘዛችሁ ስለ ምን ትኖራላችሁ? ትእዛዞቹም፦21«አትያዝ፤አትቅመስ፤ አትንካ!» የሚሉ ናቸው።22እነዚህ ሁሉ የሰው ትእዛዛትና ትምህርቶች ሥራ ላይ ከዋሉ በኋላ የሚጠፉ ናቸው።23እነዚህ ትእዛዞች ሰው ሰራሽ «ጥበብ» አምልኮና የሐሰት ትሕትና ሰውነትንም በማጎሳቆል ላይ የሚያተኩሩ፤ ነገር ግን ሥጋዊ ስሜትን በመቆጣጠር ረገድ ዋጋ ቢሶች ናቸው።
1እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ከሞት ካስነሣችሁ፤ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ።2በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ።3ምክንያቱም ሞታችኋል፤ ሕይወታችሁንም እግዚአብሔር በክርስቶስ ውስጥ ሰውሮታልና።4ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።5ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፦ እነርሱም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞት፣ ስግብግብነትና ጣዖትን ማምለክ ናቸው።6በእነዚህም ነገሮች ምክንያት በማይታዘዙ ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣባቸዋል።7እናንተም ራሳችሁ ከዚህ በፊት በማይታዘዙ ሰዎች መካከል ሳላችሁ እነዚህን ነገሮች እያደረጋችሁ ትመላለሱ ነበር።8አሁን ግን ቁጣን፤ ንዴትን፤ ተንኮልን፤ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።9አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁ፣ አንዳችሁ በሌላው ላይ አትዋሹ።10የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል ዕውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።11በዚህ ዕውቀት በግሪካዊና በአይሁዳዊ፣ በተገረዘና ባልተገረዘ፣ በሠለጠነና ባልሠለጠነ፣ በባሪያና በነጻ ሰው መካከል ልዩነት የለም፤ ክርስቶስ ግን ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።12ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ።13እርስ በርሳችሁ ታገሱ፤ እርስ በርሳችሁም ቸሮች ሆኑ። ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅርታ ቢኖረው፣ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።14በዚህ ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነው ፍቅር ይኑራችሁ።15የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።16የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤በመዝሙርና በውዳሴ፤ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።17በእርሱ እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።18ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ታዘዙ።19ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው።20ልጆች ሆይ፥ ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ ለወላጆቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ።21አባቶች ሆይ፥ልጆቻችሁ ተስፋ እንዳይቆርጡ አታስመርሩአቸው።22አገልጋዮች ሆይ፥ ሰውን ለማስደሰትና ለታይታ ሳይሆን በቅን ልብ ጌታን በመፍራት ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ።23የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው እንደምታደርጉ ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት።24ከጌታ ዘንድ እንደ ዋጋ የምትቀበሉት ርስት እንዳለ ታውቃላችሁና።25በዚህም የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ አድልዎ ስለሌለ ክፉ የሚሠራ ማንም ስለ ክፉ ሥራው ቅጣቱን ይቀበላል።
1ጌቶች ሆይ፥ እናንተም በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ዐውቃችሁ ለአገልጋዮቻችሁ በትክክልና የሚገባቸውን ስጡአቸው።2በንቃት እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ ሳታቋርጡ ጸልዩ።3የክርስቶስ ምሥጢር የሆነውን የቃሉን እውነት መናገር እንድንችል እግዚአብሔር በር እንዲከፍትልን ለእኛም ደግሞ በአንድ ልብ ጸልዩልን፤ ምክንያቱም እስር የሆንኩት ስለእርሱ ነውና።4እኔም እንደሚገባ ቃሉን መግለጥና መናገር እንድችል ጸልዩልኝ።5በውጪ ካሉት ጋር በጥበብ ተመላለሱ፤ ዘመኑንም ዋጁ።6ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መመለስ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን።7ቲኪቆስ መጥቶ እኔ ስላለሁበት ሁኔታ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል። እርሱም ተወዳጅ ወንድም፤ ታማኝ አገልጋይና በጌታ ሥራም የአገልግሎት ባልደረባዬ ነው።8እርሱንም ወደ እናንተ የላክሁበት ምክንያት ስለ እኛ ሁኔታ ትክክል የሆነውን እንዲነግራችሁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ነው።9ከእርሱም ጋር የእናንተ ወገን የሆነውን የታመነውንና የተወደደውን ወንድም አናሲሞስን ወደ እናንተ ልኬዋለሁ። እነርሱ በዚህ ስፍራ የተደረገውን ነገር ሁሉ ይነግሩአችኋል።10ከእኔም ጋር የታሰረው አርስጥሮኮስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ አንድ ጊዜ፥ «ወደ እናንተ በሚመጣበት ጊዜ ተቀበሉት» ብዬ አሳስቤአችሁ የነበረው የበርናባስ የአጎት ልጅ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል።11ኢዮስጦስ ተብሎ የሚጠራው ኢያሱም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ከተገረዙ ወገኖች መካከል ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት ሰዎች እነዚህ ብቻ ናቸው፤ ለእኔም መጽናናት ሆነውኛል።12የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። እርሱም ፍጹም ጠንክራችሁና ሙሉ በሙሉ ተማምናችሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ በሁሉ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ዘወትር ስለ እናንተ በጸሎት እየተጋ ነው።13ስለ እናንተ በሎዶቅያና በሂራፖሊስ ስላሉትም ሰዎች ተግቶ እንደሚሠራ እኔ ራሴ እመሰክርለታለሁ።14የተወደደው ሐኪም ሉቃስና ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።15በሎዶቅያ ላሉት ወንድሞች ለንምፉና በቤትዋም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ ።16ይህን መልእክት እናንተ ካነበባችሁ በኋላ በሎዶቅያ ሰዎች ዘንድ ባለችው ቤተ ክርስቲያን እንዲነበብ አድርጉ፤እናንተም ከሎዶቅያ የሚላክላችሁን መልእክት አንብቡ።17ለአርኪጳስም፥ «በጌታ አገልግሎት የተሰጠህን ሥራ በጥንቃቄ ፈጽም» ብላችሁ ንገሩልኝ።18ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍኩት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ በሰንሰለት ታስሬ እንዳለሁ አስታውሱና ጸልዩልኝ። የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
1ከጳውሎስ፣ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ በእግዚአብሔር አብና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ለተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን፤ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን!2በጸሎታቻን እያሳሰብን እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ስለ ሁላችሁም እናመሰግናለን።3በእምነት ስለምትሠሩት ሥራ፣ በፍቅር ስለምትደክሙት ድካምና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ በመታመን ስለመጽናታችሁ በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እናስታውሳችኋለን።4በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! መመረጣችሁን እናውቃለን፣5ወንጌላችን በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፥ ነገር ግን በኃይል፣ በመንፈስ ቅዱስና በብዙ መረዳትም እንጂ፥ ስለእናንተ ስንል በመካከላችሁ ደግሞ እንዴት እንደነበርን ታውቃላችሁ።6በብዙ መከራ ውስጥ ቃሉን ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ስትቀበሉት እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፣7በመቄዶንያ ሁሉና በአካይያ ላሉ ለሚያምኑት ምሳሌ ሆናችሁላቸዋል።8የጌታ ቃል ከእናንተ ተነሥቶ በመቄዶንያና አካይያ ብቻ ሳይሆን ምንም መናገር እስከማያስፈልገን ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ያላችሁ እምነት በሁሉ ሥፍራ ተወርቷል።9እኛን በሚመለከት እንዴት ያለ አቀባበል እንዳደረጋችሁልን፣ ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አምላክ ታገለግሉ ዘንድ ከጣዖታት እንዴት ወደ እግዚአብሔር ዘወር10እንዳላችሁ፣ደግሞም ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ያም ከሙታን ያስነሳውን፣ ሊመጣ ካለው ቁጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንደምትጠባበቁ እነርሱ ራሳቸው ይመሰክራሉ።
1ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ መምጣታችን ፍሬቢስ እንዳልነበረ እናንተው እራሳችሁ ታውቃላችሁ፣2ነገር ግን እንደምታውቁት ቀደም ሲል በፊልጵስዩስ መከራና እንግልት ደረሰብን። በብዙ ተቃውሞ መካከል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ለመንገር አምላካችን ድፍረት ሰጥቶናል።3የምንመክራችሁ ምክር ከስሕተት ወይም ከእርኩሰት ወይም ከማታለል የመነጨ አይደለም፣4ነገር ግን ወንጌልን በአደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር ታማኞች አድርጎ እንደቆጠረን እንዲሁ ሰውን ሳይሆን ልባችንን የሚመረምረውን እርሱን ደስ ለማሰኘት እንናገራለን።5እናንተው እንደምታውቁት መቼም ቢሆን የሽንገላን ቃል አልተጠቀምንም፣ ገንዘባችሁን በመመኘት እንዳልሆነም እግዚአብሔር ምስክር ነው፣6የክርስቶስ ሐዋርያት እንደመሆናችን ልንጠቀምባችሁ መብት ቢኖረንም እንኳን ከእናንተ ወይም ከሌሎች ክብርን ከማንም ሰው አልፈለግንም።7ይልቁንም እናት የራስዋን ልጆች እንደምትንከባከብ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን።8ለእናንተ ካለን ፍቅር የተነሳ የእግዚአብሔርን ወንጌል ብቻ ሳይሆን የራሳችንን ሕይወት እንኳን ጨምረን ብንካፈላችሁ ደስ ይለን ነበር፣ ምክንያቱም ለእኛ እጅግ የተወደዳችሁ ሆናችኋልና።9ወንድሞች ሆይ! የእግዚአብሔርን ወንጌል በሰበክንላችሁ ጊዜ በማናችሁም ላይ ሸክም ላለመሆን ቀንና ሌሊት እንደሠራን ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሳላችሁ።10በእናንተ በምታምኑት መካከል እንዴት በቅድስና፣ በጽድቅና ነቀፋ በሌለበት ኑሮ ራሳችንን እንዳቀረብንላችሁ እግዚአብሔርና እናንተም ጭምር ምስክሮች ናችሁ፣11እናንተው እንደምታውቁት አባት ለራሱ ልጆች እንደሚያደርገው እያንዳንዳችሁን መከርናችሁ፣ አበረታታናችሁና12መሰከርንላችሁ፣ይኸውም ወደ ራሱ መንግሥትና ክብር ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ ነው።13በዚህ ምክንያት እኛ ደግሞ ሳናቋርጥ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፣ የመልዕክቱን ቃል፣ የእግዚአብሔርን ቃል ከእኛ በሰማችሁ ጊዜ እንደ ሰው ቃል ሳይሆን፣ ነገር ግን እውነት እንደሆነ፣ በእናንተ በምታምኑት ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል ተቀበላችሁት።14እናንተም ወንድሞች ሆይ፣ በይሁዳ የሚኖሩ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑትን የእግዚአብሔር አብያተክርስቲያናት የምትመስሉ ሆናችኋል፣ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደደረሰባቸው እናንተ ደግሞ ከገዛ ራሳችሁ ሕዝብ ያንኑ መከራ ተቀብላችኋልና፣15አይሁድ ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ገደሉ፣ እኛንም አሳደዱን፣ እነርሱ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኙትም፥ ሰውን ሁሉ ይቃወማሉ።16ዘወትር ኀጢአታቸውን ለማብዛትም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ይከለክሉናል። ቁጣው በላያቸው ላይ መጥቶባቸዋል።17ወንድሞች ሆይ፣ እኛ ለጥቂት ጊዜ በልባችን ሳይሆን በአካል ተለይተናችሁ ነበር፣ በመሆኑም በነበረን ታላቅ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት የተቻለንን ያህል ጥረት አድርገናል፣18ወደ እናንተ ለመምጣት ፈልገን ነበር፣ እኔ ጳውሎስም ከአንድም ሁለት ጊዜ ሞከርኩኝ፣ ነገር ግን ሰይጣን አዘገየን።19ጌታችን ኢየሱስ በሚመጣበት ጊዜ በፊቱ ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም የመክበራችን አክሊል እንደሌሎቹ ሁሉ እናንተ አይደላችሁምን?20ምክንያቱም እናንተ ክብራችንና ደስታችን ናችሁ።
1ስለዚህ ከዚያ በላይ ልንታገስ ባልተቻለን ጊዜ በአቴና ለብቻችን መቅረታችን መልካም እንደሆነ አሰብን።2በእምነታችሁ ያጸናችሁና ያበረታችሁ ዘንድ ወንድማችንንና በክርስቶስ ወንጌል የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን ጢሞቴዎስን ላክንላችሁ፣3ይህንን ያደረግነውም በእነዚህ መከራዎቻችሁ ማንም እንዳይናወጥ ነው፣ ለዚህ እንደተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።4በእርግጥ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ወቅት መከራ ልንቀበል እንዳለን አስቀድመን ነግረናችሁ ነበር፣ እንደምታውቁት የሆነውም ይኸው ነው።5በዚህ ምክንያት ወደፊት ልታገስ ባቃተኝ ጊዜ ምናልባት ፈታኙ ፈትኗችሁ ልፋታችንም ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ስለ እምነታችሁ አውቅ ዘንድ ላክሁት።6ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ተመልሶ ስለ እምነታችሁና ፍቅራችሁ የምሥራች ባመጣልን ጊዜ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ ደግሞ ልናያችሁ እንደምንናፍቅ ሁሉ ልታዩን እንደምትናፍቁ ሲነግረን7በዚህ ምክንያት ወንድሞች ሆይ፣ በችግራችንና በመከራችን ሁሉ በእናንተ እምነት ተጽናንተናል።8በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ እኛ ደግሞ አሁን በሕይወት እንኖራለን።9በእናንተ ምክንያት በአምላካችን ፊት ስላገኘነው ደስታ ሁሉ ስለ እናንተ ለእግዚአብሔር እንዴት ያለ ምስጋና ማቅረብ እንችል ይሆን?10ፊታችሁን ለማየትና በእምነታችሁ የሚጎድላችሁን ለመሙላት ሌሊትና ቀን እጅግ አጥብቀን እንጸልያለን።11ራሱ አምላካችንና አባታችን፣ ጌታችንም ኢየሱስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅና፣12እኛ ደግሞ እንደምናፈቅራችሁ ጌታ ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ያትረፍርፍም።13ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁን ነቀፋ በሌለበት ቅድስና ያጸና ዘንድ ይህንን ያድርግላችሁ።
1በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፣ እንዴት መመላለስና እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንዳለባችሁ ከእኛ በተቀበላችሁት ትምህርት መሠረት አሁን እንደምትኖሩት ሁሉ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉ በጌታ በኢየሱስ እንመክራችኋለን እናደፋፍራችሁማለን።2በጌታ በኢየሱስ በኩል እንዴት ያለውን ትዕዛዝ እንደሰጠናችሁ ታውቃላችሁና፤3በቅድስና መኖራችሁ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣4ከእናንተ እያንዳንዱ ከዝሙት በመራቅ የራሱን አካል በቅድስናና በክብር ማግኘት እንዳለበት ታውቃላችሁ፣5እግዚአብሔርን እንደማያውቁ እንደ አሕዛብ የፍትወት ምኞት አይሁን፣6በዚህ ጉዳይ ማንም አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል፣ ምክንያቱም አስቀድመን እንደነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ ስለነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚበቀል ነውና።7እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለእርኩሰት አልጠራንም።8ስለዚህ ይህንን የማይቀበል ሰውን ሳይሆን የማይቀበለው ቅዱስ መንፈሱን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን ነው።9የወንድማማች መዋደድን በተመለከተ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፣ እርስ በርስ ስለመዋደድ እናንተው ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ተምራችኋልና።10በመቄዶንያ ላሉ ወንድሞች ሁሉ ይህንን ታደርጋላችሁ፣ ይሁን እንጂ ወንድሞች ሆይ፣ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉት ደግሞ እንመክራችኋለን።11ደግሞም ልክ እንዳዘዝናችሁ በጸጥታ እንድትኖሩ፣ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩና በገዛ እጆቻችሁ እንድትሠሩ እንመክራችኋለን።12በማያምኑት ዘንድ በአግባብ እንድትመላለሱና በኑሮአችሁ ምንም የሚጎድላችሁ እንዳይኖር ይህንን አድርጉ።13ወንድሞች ሆይ፣አንቀላፍተው ስላሉት ባለማወቃችሁ ስለወደፊቱ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሀዘናችሁ መሪር እንዲሆን አንፈልግም።14ኢየሱስ እንደሞተና እንደተነሳ ካመንን በእርሱ አምነው ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ያመጣቸዋል።15በጌታ ቃል የምንነግራችሁ ይህንን ነው፣ ጌታ በሚመጣበት ጊዜ እኛ ሕያዋን ሆነን የቀረነው አስቀድመው ያንቀላፉትን በርግጥ አንቀድምም።16ጌታ ራሱ በታላቅ ድምፅ፣ በመላዕክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳል፣ በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሳሉ።17ከዚያም እኛ ሕያዋን ሆነን የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፣ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር እንሆናለን።18ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በእነዚህ ቃላት ተጽናኑ።
1ወንድሞች ሆይ፣ አሁን ስለ ጊዜያትና ዘመናት ሊጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም።2ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ የጌታ ቀንም እንደዚያው እንደሆነ እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁና።3እርጉዝን ሴት የምጥ ህመም እንደሚሆንባት ሁሉ “ሁሉ ሰላምና ደህና ነው” በሚሉበት በዚያን ጊዜ ድንገተኛ ጥፋት ይመጣባቸዋል፣ እነርሱም በምንም መንገድ አያመልጡም።4ወንድሞች ሆይ፣ እናንተ ግን ያ ቀን እንደ ሌባ ይመጣባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም።5ሁላችሁም የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ልጆች አይደለንም።6እንግዲያውስ ሌሎች እንደሚያደርጉት አናንቀላፋ፣ ነገር ግን እንንቃ በመጠንም እንኑር።7የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉ፣ የሚሰክሩትም በሌሊት ይሰክራሉና።8የብርሃን ልጆች እንደመሆናችን በመጠን እንኑር፣ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር፣ የድነታችንን ተስፋ እርግጠኝነትም እንደ ራስ ቁር እንልበስ።9በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድነትን ልንቀበል እንጂ እግዚአብሔር ለቁጣ አልመደበንም፣10የነቃን ወይም ያንቀላፋን ብንሆን ከእርሱ ጋር እንድንኖር ስለ እኛ ሞቶአልና።11ስለዚህ አሁን እንደምታደርጉት ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ፣ አንዱም ሌላውን ያንጸው።12ወንድሞች ሆይ፣በመካከላችሁ በማገልገል የሚለፉትንና በጌታ የሚያስተዳድሯችሁን፣ የሚመክሯችሁንም እንድታከብሯቸው እንጠይቃችኋለን።13ደግሞም በሥራቸው ምክንያት ከፍ ያለ የፍቅር አክብሮት እንድታሳዩአቸው እንጠይቃችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ኑሩ።14ወንድሞች ሆይ እንመክራችኋለን፣ ያለ ሥርዓት የሚመላለሱትን ገስጹአቸው፣ ድፍረት ያጡትን አበረታቱአቸው፣ ደካሞችን ደግፉአቸው፣ሰውን ሁሉ ታገሱ።15ማንም ስለተደረገበት ክፉ ነገር ለሌላው በክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፣ ነገር ግን ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ መልካም የሆነውን ለማድረግ ሁልጊዜ ትጉ።16ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፣17ባለማቋረጥ ጸልዩ፣18ስለ ሁሉም ነገር አመስግኑ፣ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ነውና።19የመንፈስ ቅዱስን ሥራ አታዳፍኑ።20ትንቢትን አትናቁ።21ሁሉን መርምሩ፣ መልካም የሆነውን ያዙ፣22ማንኛውንም ዓይነት ክፋት አስወግዱ።23የሰላም አምላክ ራሱ ፈጽሞ ይቀድሳችሁ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ መላው መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና ሥጋችሁ ያለ ነቀፋ ይጠበቅ።24የጠራችሁ ታማኝ ነው፣ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።25ወንድሞች ሆይ፣ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ።26ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው።27ይህ መልዕክት ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አደራ እላችኋለሁ።28የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
1ከጳውሎስ፣ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ በእግዚአብሔር በአባታችን በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ለተሰሎንቄ ሰዎች ቤተክርስቲያን።2ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።3ወንድሞች ሆይ፣ ስለ እናንተ ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ አለብን፣ ይህ ተገቢ ነውና፣ ምክንያቱም እምነታችሁ እጅግ እያደገ ነውና፣ የእያንዳንዳችሁ ፍቅርም ለሌሎች የሚተርፍ ሆኗል።4በመሆኑም በስደቶቻችሁና በመከራዎቻችሁ ሁሉ ስለ መጽናታችሁ ስለ ትዕግስታችሁና እምነታችሁ እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር አብያተክርስቲያናት መካከል በልበ ሙሉነት እንመሰክራለን።5እናንተ ደግሞ መከራን ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት ብቁ ሆናችሁ ትቆጠሩ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ፍርድ ጻድቅ የመሆኑ ግልጽ ምልክት ነው።6መከራን ለሚያመጡባችሁ መከራን ይመልስላቸው ዘንድ ይህ በእግዚብሔር ፊት ቅን ፍርድ ነው፣7ጌታችን ኢየሱስ ከኀይሉ መላዕክት ጋር ከሰማይ በሚገለጥበት ጊዜ ከእኛ ጋር መከራን ለተቀበላችሁት ደግሞ እረፍትን ይሰጣችኋል።8እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ግን በሚነድ እሳት ይበቀላቸዋል።9ከጌታ ሀልዎትና ከኀይሉ ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት እየተቀጡ ይሰቃያሉ፣10እርሱ በቅዱሳኑ ሊከበር በሚመጣበት በዚያን ቀን፣ ምስክርነታችንን አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ይገረምባቸዋል።11በዚህ ምክንያት እኛ ደግሞ አምላካችን ለጥሪአችሁ የተገባችሁ አድርጎ ይቆጥራችሁና መልካሙን ምኞታችሁንና ማናቸውንም የእምነት ሥራ በኀይል ይፈጽምላችሁ ዘንድ ባለማቋረጥ እንጸልይላችኋለን።12ይህም በአምላካችንና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ምክንያት የጌታችን የኢየሱስ ስም በእናንተ እንዲከበርና እናንተም በእርሱ ትከብሩ ዘንድ ነው።
1ወንድሞች ሆይ፣ አሁን የምንለምናችሁ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለመሰብሰባችን ነው፣2ከእኛ የሆነ በሚመስል በመንፈስ፣ በቃል ወይም በደብዳቤ እነሆ የጌታ ቀን ሆኗል ብላችሁ በማመን በቀላሉ በአዕምሮአችሁ እንዳትናወጡ ወይም እንዳትደነግጡ እንለምናችኋለን።3በየትኛውም መንገድ ማንም አያስታችሁ። የመጨረሻው ክህደት ሳይመጣና የአመጽ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና።4የሚቃወመውና አምላክ ከተባለው ወይም ከሚመለከው ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ የሚያደርገው እርሱ ነው፣ በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እስኪቀመጥም ድረስ ራሱን እንደ አምላክ ያስተዋውቃል።5ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ስለእነዚህ ነገሮች እንደነገርኳችሁ ትዝ አይላችሁምን?6በትክክለኛው ጊዜ ብቻ ይገለጥ ዘንድ አሁን የሚከለክለው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ።7የአመጽ ምስጢር በሥራ ላይ ነው፣ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክለው አንድ ብቻ አለ።8ከዚያም ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚገድለውና በመምጣቱ መገለጥ የሚያጠፋው የአመጽ ሰው ይገለጣል።9የአመጽ ሰው አመጣጥ እንደ ሰይጣን አሰራር በኀይል ሁሉ፣ በምልክቶችና በሐሰተኛ ድንቆች፣10ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉት በአመጽ ማታለል ሁሉ ነው።11በዚህ ምክንያት ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል፣12ይኸውም እነዚያ እውነትን ያላመኑ ነገር ግን በአመጻ የተደሰቱ ሁሉ ይፈረድባቸው ዘንድ ነው።13ነገር ግን ስለ እናንተ በጌታ ስለተወደዳችሁት ወንድሞች ለእግዚአብሔር ሁልጊዜ ምስጋና ልናቀርብ ይገባናል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ መቀደስና እውነትን በማመን ለድነት እንደ በኩራት መርጧችኋልና፣14የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር እንድትካፈሉ በወንጌላችን ጠራችሁ።15እንግዲያውስ ወንድሞች ሆይ፣ ጸንታችሁ ቁሙ፣ በቃልም ሆነ ወይም በደብዳቤአችን የተማራችኋቸውን ልማዶች አጥብቃችሁ ያዙ።16አሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱና የወደደን፣ የዘላለምን መጽናናትና በጸጋው ተስፋ የምናደርግበትን መልካሙን መታመን የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን፣17በቃልና በመልካም ሥራ ሁሉ ልባችሁን ያጽናኑት፣ ያበርቷችሁም።
1በቀረውስ ወንድሞች ሆይ፣ በእናንተ ዘንድ ደግሞ እንደሚሆነው የጌታ ቃል በፍጥነት እንዲዳረስና እንዲከበር ስለ እኛ ጸልዩ፣2ሁሉ እምነት ያላቸው አይደሉምና ከአመጸኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ጸልዩልን።3ነገር ግን የሚያጸናችሁና ከክፉው የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።4ያዘዝናችሁን ነገሮች እንደጠበቃችሁና ወደፊትም እንደምትጠብቁ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል።5ጌታ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ወደ ክርስቶስ ጽናት ይምራው።6ወንድሞች ሆይ፣ ከእኛ እንደተቀበላችሁት ልማድ ሳይሆን ሥራ በመፍታት ከሚኖር ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።7እንዴት ምሳሌነታችንን መከተል እንደሚኖርባችሁ እናንተው ታውቃላችሁ። በመካከላችሁ በስንፍና አልተመላለስንም፣8ወይም ገንዘብ ሳንከፍል የማንንም ምግብ አልበላንም። ከዚያ ይልቅ ከእናንተ በማንም ላይ ሸክም ላለመሆን በድካምና በጥረት ሌሊትና ቀን ሠራን።9ይህንን ያደረግነው እኛን ትመስሉ ዘንድ ምሳሌ ልንሆንላችሁ ብለን እንጂ ሥልጣን ስላልነበረን አይደለም።10ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ሊሠራ የማይወድ ማንም ቢኖር እርሱ መብላት የለበትም” ብለን አዝዘናችሁ ነበር።11በመካከላችሁ ሥራ ፈት ሆነው የሚመላለሱ አንዳንዶች መኖራቸውን ሰምተናልና፤ ሥራ አይሠሩም ነገር ግን በሰው ጉዳይ ጣልቃ ይገባሉ።12እንደነዚህ ያሉትን በጸጥታ እንዲሠሩና የራሳቸውን ምግብ እንዲበሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸዋለንም።13እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፣ ትክክል የሆነውን ከማድረግ አትታክቱ፡፡14በዚህ ደብዳቤ ውስጥ ያለውን ቃላችንን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር ይህንን ሰው ልብ በሉት፣ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር ኅብረት አታድርጉ፡፡15እንደ ወንድም ገስጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቁጠሩት፡፡16የሰላም ጌታ ራሱ ሁልጊዜ በሁሉ መንገድ ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።17እኔ ጳውሎስ፣ ሰላምታዬ እንዲህ ነው፣ በራሴ እጅ በምጽፋቸው ደብዳቤዎች ሁሉ ላይ ምልክቴ ይህ ነው።18የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
1መታመኛችን በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ እና በአዳኛችን በእግዚአብሔር ትእዛዝ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ጳውሎስ፣2በእምነት እውነታኛ ልጄ ለሆነው፣ ለጢሞቴዎስ፡፡ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ለአንተ ይሁን፡፡3ወደ መቄዶንያን በሄደኩ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ልዩ ትምህርትን እናዳያስተምሩ፣4በእምነት የሆነውን የእግዚአብሔርን እቅድ ለማያግዙ ለታሪኮችና መጨረሻ የሌላቸውን የትውልዶችን ሐረግ ለመቁጠር ትኩረት ወደ መስጠት እንዳያዘነብሉ ታስጠነቅቃቸው ዘንድ በኤፌሶን እንድትቀመጥ አዘዝኩህ፡፡5ነገር ግን የትእዛዙ ግብ ከንጹህ ልብ፣ ከመልካም ኅሊና እና ከእውነተኛ እምነት የሚወጣ ፍቅር ነ|ው፡፡6አንዳንድ ሰዎች ከእነዚህ ነገሮች ርቀው ወደ ባዶ ወሬ ዞረዋል፡፡7የሕግ አስተማሪዎች ለመሆን ተመኝተዋል፤ ነገር ግን የሚናገሩትንና መሆን አለበት የሚሉትን ነገር አያውቁትም፡፡8ሆኖም ሕግ በትክክል ቢጠቀምበት መልካም እንደሆነ እናወቃለን፡፡9እንዲሁም ሕግ ለጻድቅ ሰው እንዳልተሠራ እናውቃለን፤ ነገር ግን ሕግ የተሰጠው፣ ሕገወጥ ለሆኑና ለአመጸኞች ሰዎች ፣ እግዚአብሔርን ለማይፈሩና ለኃጢአተኞች ፣10ለአመንዝሮችና ለግብረ ሰዶማውያን፣ ሰዎችን ባርያ አድርገው ለሚሸጡ፣ ለውሸተኞች፣ ለሐሰት ምስክሮች፣ ከእውነተኛው ትምህርት ርቀው ለሚገኙ ሰዎች ነው፡፡11ይህ እውነተኛ ትምህርት በተባረከው አምላካችን ለእኔ በአደራ የተሰጠው ወንጌል ነው፡፡12ለዚህ አገልገሎት ታማኝ እንድሆን ያበቃኝንና የሾመኝን፣ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግናለሁ፡፡13ምንም እንኳ አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ ብሆንም፣ ባለማወቅና ባለማመን ስላደረግሁት ከጌታ ዘንድ ምሕረትን አግኝቼአለሁ፡፡14ነገር ግን የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእምነትና ከፍቅር ጋር ይበልጥ በዛ፡፡15‹‹ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣ›› የሚለው መልዕክት ሁሉም ሊቀበሉት የተገባና አስተማማኝ ነው፡፡ እኔም ከእነዚህ ሁሉ የባስኩ ኃጢአተኛ ነኝ፡፡16በዚህም ምክንያት ከኃጢአተኞች ዋነኛ በምሆን በእኔ ክርስቶስ ኢየሱስ ትእግስቱን ሁሉ ሊያሳይ ምሕረትን አገኘሁ፤ ይህም የሆነው በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለም ሕይወት ለሚያገኙ ምሳሌ እሆን ዘንድ ነው፡፡17ስለዚህ ለዘላለም ንጉሥ ፣ ለማይሞተው እና ለማይታየው፣ ብቻውን አምላክ ለሆነው፣ ክብርና ግርማ ለዘላለም ይሁን፡፡ አሜን፡፡18ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ፣ ስለ አንተ አስቀድሞ በተነገረው ትንቢት ተስማምቼ ይህን አዝሃለሁ፤ መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤19ስለዚህም እምነትና መልካም ኅሊና ይኑርህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እነዚህን ክደው መርከብ አለመሪ እንደሚጠፋ በእምነት ነገር ጠፍተዋል፡፡20ከእነዚህም መካከል በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል እንዳይናገሩ፣ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው፣ ሄሜኔዎስ እና እስክንድሮስ ይገኙባቸዋል፡፡
1ስለዚህ ከሁሉ በፊት፣ ጸሎት፣ ምልጃና ምሥጋና ስለ ሰዎቸ ሁሉ እንዲደረግ እመክራለሁ፤ እግዚአብሔርን በመፍራትና በማክበር፣2በጸጥታ ሕይወት ሰላማዊ ኑሮ እንድንኖር፣ ለነገሥታትና በሥልጣን ላይ ላሉ ሁሉ ጸልዩ፡፡3ይህም በአዳኛችን በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ተቀባይነት ያለው ነገር ነው፡፡4እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ሁሉ ወደ ማውቅ እንዲደርሱ ይፈልጋልና፡፡5አንድ እግዚአብሔር አለና፣ እንዲሁም በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል፣ ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ አንድ መካከለኛ አለ፤6እርሱም ለሁሉ ራሱን ቤዛ አድርጎ የሰጠ፣ በትክክለኛው ጊዜ የተገለጠ ምስክር ነው፡፡7ለዚህም ዓላማ እኔ ራሴ፣ አወጅ ነጋሪና ሐዋርያ ሆኜአለሁ፡፡ እውነትን እናገራለሁ አልዋሽም፤ እኔ ለአሕዛብ የእምነትና የእውነት አስተማሪ ነኝ፡፡8ስለዚህ፣ ወንዶች ሁሉ በየሥፍራው ያለ ጥርጥርና ያለ ቁጣ የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሱ እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ፡፡9እንደዚሁም፣ ሴቶች አግባብ ያለው አለባበስ ይኑራቸው፣ ራሳቸውን በመግዛት ረጋ እንዲሉ እንጂ ጸጉራቸውን በወርቅ ወይም በዕንቁ በመሥራት ወይም ውድ የሆኑ ልብሶችን በመልበስ ሊያጌጡ አይገባም፡፡10ነገር ግን እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ሴቶች አግባብ እንደሆነው፣ በመልካም ሥራ ተውበው ይታዩ፡፡11ሴት በጸጥታና በመታዘዝ ትማር፡፡12ሴት በጸጥታ እንድትኖር እንጂ፣ እንድታስተምርና በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፡፡13አስቀድሞ አዳም ተፈጥሮአልና፣ ከዚያም ሔዋን፡፡14አዳም አልተታለለም፣ ነገር ግን ሴቲቱ ሙሉ ለሙሉ በመተላለፍ ተታልላለች፡፡15ሆኖም፣ በእምነትና በፍቅር፣ በቅድስናም በመልካም አዕምሮ ጸንታ ብትኖር፣ ልጆችን በመውለድ ትድናለች፡፡
1አንድ ሰው መሪነትን ቢፈልግ፣ መልካምን ሥራ ተመኝቶአል፣ የሚለው አባባል የታመነ ነው፡፡2ስለዚህ መሪው ነቀፋ የሌለበት፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ በመጠን የሚኖር፣ አስተዋይ፣ ሥርዓት ያለው፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ለማስተማር የሚበቃ፣3የማይሰክር፣ የማይጨቃጨቅ፣ ነገር ግን፣ ለሌሎች የሚጠነቀቅ፣ ሰላማዊ፣ ገንዘብን የማያፈቅር መሆን አለበት፡፡4ቤቱን በመልካም የሚያስተዳድርና ልጆቹም በሁሉም ረገድ የሚታዘዙለት ለሆን ይገባል፤5ሰው የራሱን ቤት በመልካም ማስተዳደር የማያውቅ ከሆነ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊጠነቀቅ ይችላል?6ዲያብሎስ በትእቢት እንደወደቀ እንዳይወድቅ አዲስ አማኝ የቤተ ክርስቲያን መሪ አይሁን፤7በውጭ ባሉት ዘንድ መልካም ምስክርነት ያለው ሊሆን ይገባል፣ በመሆኑም በነቀፋ እና በዲያብሎስ ወጥመድ አይወድቅም፡፡8ዲያቆናትም እንዲሁ፣ የተከበሩ፣ ቃላቸው አንድ የሆነ፣ ብዙ የወይን ጠጅ የማይጠጡ፣ የማይስገበገቡ መሆን አለባቸው፡፡9በንጹህ ኅሊና የተገለጠውን የእምነት እውነት ሊጠብቁ ይገባቸዋል፡፡10አስቀድመው ይገምገሙ፣ ከዚያም ያለነቀፋ ሆነው ከተገኙ በዲቁና አገልግሎት ይሾሙ፡፡11እንዲሁም ሴቶች የተከበሩ፣ የማያሙ፣ ልከኞችና በሁሉ ነገር የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡12ዲያቆናት እያንዳንዳቸው የአንዲት ሚስት ባል መሆን አለባቸው፤ ቤታቸውንና ልጆቻቸውንም በመልካም የሚያስተዳሩ ሊሆኑ ይገባል፡፡13መልካም አገልግሎት የሚያበረክቱ እነርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ ባላቸው እምነት ለራሳቸውእውነተኛ መሠረትና ድፍረትን ያገኛሉ፡፡14እነዚህን ነገሮች ስጽፍልህ ወደ አንተ በቅርቡ እንደምመጣ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡15ነገር ግን ብዘገይ፣ በእግዚአብሔር ቤት፣ ማለትም የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነው፣ በሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዴት መኖር እንደሚገባህ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፡፡16እኛ ሁላችን በዚህ እንስማማለን፡- ‹‹የተገለጠው እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር ታላቅ ነው፣›› ይህም በሥጋ የተገለጠው፣ በመንፈስ የጸደቀው፣ በመላእክት የታየው፣ በሕዝቦች መካከል የታወጀው፣ በዓለም የታመነው፣ በክብር ወደ ሰማይ ያረገ ነው፡፡
1አሁን ግን መንፈስ በመጨረሻ ዘመን አንዳንድ ሰዎች የራሳቸውን ኅሊና በውሸት በተሞላ ግብዝነት በማደንዘዝ፤2ለሚያስቱ መናፍስትና ለአጋንንት ትምህርት ትኩረት በመስጠት እምነትን ይክዳሉ በማለት በግልፅ ይናገራል፡፡3እውነትን ለማወቅ የመጡትን አማኞች ከምሥጋና ጋር ከሚቀበሉትና እርስበርሳቸው ከሚካፈሉት እግዚአብሔር ከፈጠረው ምግብ እንዲርቁ፣ ጋብቻንም እንዳያደርጉ ይከለክላሉ፡፡4በእግዚአብሔር የተፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፤ በምሥጋና የሚቀበሉት እንጂ የሚጣል የለውም፡፡5በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ነው።6እነዚህን ነገሮች ለወንድሞች ብታስረዳ፣ በእምነት ቃሎች እና በተከተልከውም መልካም ትምህርት የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ፡፡7ራስህን እግዚአብሔርን ለመምሰል አሰልጥን እንጂ፣ አሮጊቶች የሚወዱአቸውን አለማዊ ተረቶችን አትቀበል፡፡8የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጥቂት ነገር ይጠቅማል፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን መምሰል ለአሁኑና ለሚመጣውም ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁሉ ነገር ይጠቅማል፡፡9ይህ መልእክት የታመነና ሁሉም ሊቀበሉት የተገባው ነው፡፡10ለዚህም እንታገላለን ጠንክረንም እንሠራለን፣ ይህም የሚሆነው ሰዎችን ሁሉ በተለይም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው እግዚአብሔር ስለምንታመን ነው፡፡11እነዚህን ነገሮች አውጅ አስተምርም፡፡12ማንም ወጣትነትህን አይናቀው፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ፣ በቃልና በሥራ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና የእምነት ምሳሌ ሁን፡፡13እስክመጣ ድረስ፣ ማንበብህን፣ መምከርህን እና ማስተማርህን ቀጥል፡፡14በትንቢት ከሽማግሌዎች የእጅ መጫን ጋር ለአንተ የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል፡፡15ለእነዚሀ ነገሮች ተጠንቀቅ፣ በእነርሱም ጽና፣ ይህን በማድረግህ ማደግህ በሁሉም ዘንድ ይገለጻል፡፡16ለራስህ እና ለትምህርቱ ተጠንቀቅ፣ በእነዚህም ጽና ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህ፡፡
1ሽማግሌ የሆነውን አትገስጸው፣ ነገር ግን እንደ አባት ለምነው፣ ወጣቶችን እንደ ወንድሞች፣2አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ቆነጃጅቶችን እንደ እኅቶች በሙሉ ንጽሕና ለምናቸው፡፡3በትክክል መበለት የሆኑትን አክብር፤4ነገር ግን ባሏ የሞተባት ልጆችና የልጅ ልጆች ከሏት፣ እነርሱ ራሳቸው በቤታቸው አክብሮትን፣ ለወላጆቻቸው ብድራት መክፈልን ይማሩ፣ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡5ነገር ግን እውነተኛ መበለት ሁሉን ነገር ትታ በእግዚአብሔር ታምና ትኖራለች፣ ልመናዋን ሁል ጊዜ በእርሱ ፊት በማቅረብ ሌትና ቀን ትጠባበቃለች፡፡6የሆነ ሆኖ፣ መቀማጠልን የምትወድ ሴት በሕይወትም ብትኖር የሞተች ነች፡፡7ከወቀሳ የራቁ እንዲሆኑ እነዚህን ነገሮች ስበክ፡፡8ነገር ግን ማንም ለዘመዶቹ የሚያስፈልጋቸውን የማይሰጥ፣ ይልቁንም ለገዛ ቤተሰቡ የማያስብ እምነትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የከፋ ነው፡፡9ባሏ የሞተባት ሴት በመዝገብ ለመጻፍ እድሜዋ ከስድሳ ማነስ የለበትም፣ የአንድ ባል ሚስትም መሆን አለባት፡፡10ልጆቿን በሥርዓት የምታሳድግ፣ እንግዶችን የምትቀበል፣ ወይም የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ በመልካም ሥራ ሁሉ የተመሰከረላት መሆን አለባት፡፡11ወጣት መበለቶችን ግን እንደ መበለት አትመዝግባቸው፣ ምክንያቱም የክርስቶስ ተቃራኒ የሆነው ሥጋዊ ፍላጎታቸው ሲያይልባቸው ለማግባት ይፈልጋሉና፡፡12በዚህ ሁኔታ የቀድሞ እምነታቸውን ስለተዉ በደለኞች ናቸው፡፡13ለሥራ ፈትነትም ስለሚጋለጡ ከቤት ወደ በት የሚዞሩ ይሆናሉ፡፡ ሥራ ፈቶች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ሐሜተኞችና በሰው ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ የማይገባውን የሚናገሩ ይሆናሉ፡፡14ስለዚህ ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ እና ልጆችን እንዲወልዱ ቤታቸውንም በመልካም እንዲያስተዳድሩ፣ ተቃዋሚውም ክፉ እንደምናደርግ የሚከስበትን ምክንያት እንዲያሳጡት እመክራለሁ፡፡15አንዳንዶች ሰይጣንን ለመከተል ዞር ብለዋል፡፡16መበለቶች ያሏት አንዲት የምታምን ሴት ብትኖር፣ ትርዳቸው፣ ስለሆነም የቤተ ክርስቲያን ሸክም ይቀልላታል እውነተኞቹን መበለቶች ለመርዳት ትችላለች፡፡17በመልካም የሚያስተዳድሩ መሪዎች በተለይም በቃሉ ስብከትና በማስተማር የሚተጉ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል፡፡18የእግዚአብሔር ቃል ‹‹የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር›› እንዲሁም ‹‹ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል›› ይላል፡፡19ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ሳታገኝ በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል፡፡20ሁሉም ይማሩ ዘንድ አጥፊዎችን በሁሉ ፊት ገስጻሳቸው፡፡21በእግዚአብሔር ፊት፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፣ በተመረጡትም መላእክት ፊት አዝዝሃለሁ፣ አንዳች አድልኦ ሳታደርግ እነዚህን ደንቦች ጠብቅ፡፡22በማንም ላይ ቸኩለህ እጅህን አትጫን፣ ከማንም ኃጢአት ጋር አትተባበር፣ ርስህን በንጽሕና መጠበቅ አለብህ፡፡23በተደጋጋሚ ሆድህን ስለሚያምህ ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ ለወደፊቱ ውኃ ብቻ አትጠጣ፡፡24የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት በግልጽ የታወቀ ነው፣ ፍርድን ያስከትልባቸዋል፣ አንዳንዶች ግን ኋላ ይከተሉታል፡፡25ልክ እንደዚሁ አንዳንድ መልካም ሥራዎች የተገለጡ ናቸው፣ ነገር ግን ሌሎቹ በጊዜው የተገለጡ ባይሆንም እንኳ የተሰወሩ አይደሉም፡፡
1የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ እንዳይሰደብ ከቀንበር በታች ያሉ ባሪያዎች ለገዢዎቻቸው የሚገባቸውን ክብር ይስጡ፡፡2አማኞች የሆኑ ገዢዎች ያሉአቸው ባሪያዎች፣ በእምነት ወንድሞቻቸው ስለሆኑ ገዢዎቻቸውን መናቅ የለባቸውም፡፡ ይልቁንም በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የተወደዱ ወንድሞች በመሆናቸው አብልጠው ያገልግሉአቸው፡፡ እነዚህን ነገሮች አስተምር ግለጽም፡፡3ማንም ልዩ ትምህርትን ቢያስተምር፣ እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚረዳውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶሰን ቃል እና የእኛንም ጤናማ ቃል ባይቀበል፣4በትእቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፡፡ ነገር ግን በክርክርና በቃል በመዋጋት የተለከፈ ነው፣ ከዚህም ምቀኝነት፣ ክርክር፣ መሳደብ፣ ክፉ አሳብና፣ እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፡፡5እነርሱም አእምሮአቸው የተበላሸባቸው ከእውነትም የራቁ እግዚአብሔርን መምሰል ጥቅም ማግኛ የሚመስላቸው ናቸው፡፡6ባለው ለሚረካ ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፡፡7ወደ ዓለም ምንም አላመጣንምና፣ አንዳችም ይዘን መሄድ አይቻለንም፡፡8ምግብ እና ልብስ ካለን ያ ይበቃናል፡፡9ባለጠጋ ለመሆን የሚመኙ በፈተና ውስጥ ይወድቃሉ፣ በወጥመድ፣ ሞኝነት በመሰሉ አያሌ ጎጂ ምኞቶች፣ እንዲሁም ሰዎችን በሚያሰጥሙና በሚያጠፉ በሌሎች ነገሮች ላይ ይወድቃሉ፡፡10የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲመኙ ከእምነት ስተው ራሳቸውን በብዙ ሐዘን ጎዱ፡፡11አንተ ግን፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ ከእነዚሀ ነገሮች ሽሽ፡፡ ጽድቅን፣ እግዚአብሔርን መምሰል፣ ታማኝነትን፣ ፍቅርን፣ ጽናትን እና ለሰዎች መጠንቀቅን ተከታተል፡፡12መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፡፡ የተጠራህለትን በብዙ ምሥክሮች ፊት ስለመልካምነቱ የመሰከርክለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ፡፡13ሁሉን ነገር በፈጠረ፣ በእግዚአብሔር ፊት፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ፊት እውነትን በመሰከረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አዝዝሃለሁ፣14ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለነቀፋ ሆነህ ትእዛዛቱን በፍጹምነት ጠብቅ፡፡15እርሱም መገለጡን የተባረከውና፣ ብቻውን ኃያል የሆነው፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ በወሰነው በትክክለኛው ጊዜ ያሳያል፡፡16እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፡፡ ማንም ሰው አላየውም ሊያየውም አይችልም፡፡ ለእርሱ ክብር የዘላለምም ኃይል ይሁን፡፡ አሜን፡፡17በአሁኑ ዘመን ሀብታሞች ለሆኑት እንዳይታበዩ ንገራቸው፡፡ ደስ እንዲለን እግዚአብሔር በሚሰጠን እውነተኛ ብልጥግና እንጂ እርግጠኛ ባልሆነው በዚህ ምድራዊ ባለጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፡፡18በመልካም ሥራ ባለጠጎች እንዲሆኑ፣ መልካም የሆነውን እንዲያደርጉ ለማካፈልም ፈቃደኞች እንዲሆኑ ንገራቸው፡፡19በዚህ ሁኔታ በሚመጣው ዓለም ለራሳቸው መልካም መሠረትን ይጥላሉ፣ እውነተኛውንም ሕይወት ይይዛሉ፡፡20ጢሞቴዎስ ሆይ፣ ለአንተ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፡፡ የማይረባውን ወሬ አስወግድ፣ በሐሰት እውቀት ከተባለ እርስ በርሱ ከሚጋጭ ነገር ጋር ከመከራከር ራቅ፡፡21አንዳንድ ሰዎች ይህ እውቀት አለን በማለት ከእምነት ርቀዋል፡፡ ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡
1በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆነው የሕይወት ተስፋ፣ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ የሆነው፣ጳውሎስ2ለተወደደው ልጄ፣ ለጢሞቴዎስ፣ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእግዚአብሔር አባታችን፣ ቤታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ ይሁን፡፡3ሌትና ቀን በጸሎቴ ስለማስብህ፣ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹህ ኅሊና የማገለግለወን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፣4እምባህን እያሰብኩ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ፤5ያለህንም እውነተኛ እምነት አስባለሁ፣ ይህም እምነት አስቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፣ በአንተም እንዳለ ተረድቼአለሁ፡፡6እግዚአብሔር የሰጠህን በአንተ ያለውን ስጦታ እንድታነሣሣ ስእጆቼን በመጫኔ አሳስብሃለሁ፡፡7እግዚአብሔር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት እንጂ፣ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡8በጌታ እና የእርሱ እስረኛ በሆንኩት በእኔም ምሥክርነት አትፈር፣ እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል መከራን ተቀበል፡፡9ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ያዳነን፣ በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሆነው በራሱ እቅድና በጸጋወ ነው እጂ በእኛ ሥራ አይደለም፡፡10አሁን ግን የእግዚአብሔር ማዳን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ እና፣ ሞትን በማጥፋቱ እና የዘላለምን ሕይወት ወደ ብርሃን በማውጣቱ በወንጌሉ ተገልጦአል፣11ይህንንም ወንጌል ለማብሰር እኔ ሐዋርያ እና አስተማሪ ሆኜ ተሹሜአለሁ፡፡12ስለዚህ ምክንያት እኔ መከራ እቀበላለሁ፣ ነገር ግን አላፍርበትም፣ ያመንኩትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትን አደራ እስከዚያች ቀን ድረስ እንደሚጠብቅ ተረድቼአለሁ፡፡13ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር በምሳሌነት ጠብቅ፡፡14በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አድርገህ በእግዚአበሔር የተሰጠህንም አደራ ጠብቅ፡፡15በእስያ ያሉት ሁሉ ከእኔ ፈቀቅ እንዳሉ ታውቃለህ፣ ከእነዚህም ጊሊጎስ እና ሄርዋጌኔስ ይገኙባቸዋል፡፡16ጌታ ለሄኔሲፎሩ ቤተ ሰብ ምሕረትን ይስጣቸው፣ ብዙ ጊዜ አሳርፎኛልና፣ በሰንሰለቴም አላፈረበትም፡፡17ነገር ግን በሮም በነበረ ጊዜ፣ በብርቱ ፈልጎ አገኘኝ፣18ጌታ በዚያች ቀን ምሕረትን እንዲያገኝ ይስጠው፣ በኤፌሶን ምንያህል እንደረዳኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ፡፡
1እንግዲህ ልጄ ሆይ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጽጋ በርታ፡፡2ከብዙ ምስክሮች ጋር ከእኔ የሰማኸውን፣ ሌሎችን ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ፡፡3እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ወታደር ሆነህ አብረኸኝ መከራ ተቀበል፡፡4አለቃውን ማስደሰት የሚፈልግ ወታደር በምድራዊው ነገር ራሱን አያጠላልፍም፡፡5ማንም በስፖርታዊ ውድድር የሚሳተፍ፣ በደንቡ መሠረት ካልተወዳደረ የድሉን አክሊል ሊያገኝ አይችልም፡፡6በርትቶ የሚሠራው ገበሬ ምርቱን ከሚበሉት የመጀመሪያው ሊሆን ይገባል፡፡7የምለወን ተመልከት ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ፡፡8በወንጌል መልእክቴ የገለጽኩትን፣ ከሙታን የተነሣውንና ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፡፡9በዚህም ምክንያት እንደ ወንጀለኛ በመታሰር መከራ እቀበላለሁ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አይታሰርም፡፡10ስለዚህ ስለተመረጡት ስል በሁሉ እጸናለሁ፣ እነርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን መዳን ከዘላለማዊ ክብር ጋር ያገኙ ዘንድ፡፡11እንዲህ የሚለው ቃል የታመነ ነው ‹‹ከእርሱ ጋር ከሞትን፣ ከእርሱ ጋር እንኖራለን፡፡12ብንጸና ከእርሱ ጋር እንነግሣለን፡፡ ብንከዳው እርሱ ደግሞ ይክደናል፡፡13ባናምነው እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፣ ራሱን ሊክድ አይችልምና፡፡14እነዚህን ነገሮች አስታውሳቸው፡፡ በቃል እንዳይጣሉ በእግዚአብሔርም ዘንድ አስጠንቅቃቸው፣ይህ ምንም ጥቅም የሌለው የሚሰሙትንም የሚጎዳ ነው፡፡15የእውነትን ቃል በትክክል የሚይዝ፣ የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነሀ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ትጋ፡፡16እግዚአብሔርን ከመምሰል የሚያርቅህን አለማዊ ተረቶቸን አስወግድ፡፡17ቃላቸው እንደ ቆላ ቁስል ነው፣ ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ይገኙባቸዋል፣18እነዚህም ሰዎች ከእውነት ርቀው ትንሣኤ ሙታነ ካሁን ቀደም ሆናል ይላሉ፣ በዚህም የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ፡፡19ሆኖም፣ ‹‹ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል›› ደግሞም ‹‹የጌታን ስም የሚጠራ ከዓመፃ ይራቅ›› የሚለው ማኅተም ያለበት የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል፡፡20በሀብታም ቤት ውስጥ የሚገኙት የወርቅ እና የብር ዕቃዎች ብቻ አይደሉም ነገር ግን የእንጨት እና የሸክላ ዕቃዎችም ይገኛሉ፣ አንዳንዶቹ ለክብር ሌሎቹም ክብር ለማይሰጣቸው ሥራዎች ይውላሉ፡፡21ማንም ከማያስከብር ሥራ ራሱን ቢያነጻ፣ የተከበረ ዕቃ፣ የተቀደሰ፣ ለጌታውም የሚጠቅም፣ ለማንኛውም መልካም ሥራ የተዘጋጀ ይሆናል፡፡22ከወጣትነት ምኞት ራቅ፣ በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን ተከታተል፡፡23ነገር ግን ጠብን እንደሚያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፡፡24የጌታ አገልጋይ ሊጣላ አይገባውም፣ ከዚሀ ይልቅ ለሁሉ የሚጠነቀቅ፣ ለማስተማርም የሚበቃ በትእግስትም የሚጸና፣25በትህትናም ለሚቃወሙት ትምህርት የሚሰጥ ሊሆን ይገባዋል፡፡ እውነትን በማወቃቸው እግዚአብሔር ምናልባት ንስሐን ይሰጣቸው ይሆናልና፣26እንዲሁም ለዲያብሎስ እና ለፈቃዱ ከተያዙበት ወጥመድ ተላቀው ወደ ኅሊናቸው ሊመለሱ ይችሉ ይሆናል፡፡
1ነገር ግን ይህን እወቅ፣ በመጨረሻዎቹ ቀናት አደገኛ ዘመን ይመጣል፡፡2ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉ፣ ገንዘብን የሚወዱ፣ ትእቢተኞች፣ ትምክህተኞቸ፣ በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል የሚናገሩ፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣3ተፈጥሮአዊ ፍቅር የሌላቸው፣ ሰላምን የማይፈጥሩ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ አመጸኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣4ከዳተኞች፣ ምክርን የማይሰሙ፣ በትእቢት የተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፡፡5እግዚአብሔርን የመምሰል መልክ አላቸው ነገር ግን ኃይሉን ይክዳሉ፣ ከእነዚህ ሰዎች ራቅ፡፡6ከእነዚህም አንዳንዶች በቤተ ሰብ ውስጥ ሾልከው እየገቡ በኃጢአት የሚገረሙትንና በልዩ ልዩ ምኞትም የሚነዱትን ሞኞችን ሴቶች ይማርካሉ፡፡7እነዚህ ሴቶች ሁል ጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ይሞክራሉ፣ ነገር ግን ፈጽሞ ወደ እውነት እውቀት ሊደርሱ አይችሉም፡፡8ኢያኔስ እና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደተቃወሙት፣ እነዚህ የስህተት አስተማሪዎች እውነትን ይቃወማሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች አዕምሮአቸው የተበላሸባቸው፣ የእምነታቸውም እውነተኝነት ያልተረጋገጠ ነው፡፡9ዳሩ ግን የእነዚያ የሁለቱ ሰዎች ሞኝነት እንደተጋለጠ፣ እነዚህም ሞኝነታቸው ይገለጣልና አይሳካላቸውም፡፡10አንተ ግን ትምህርቴን፣ አካሄዴን፣ ዓላማዬን፣ እምነቴን፣ መጽናቴን፣ ፍቅሬን፣ ትእግስቴን፣11ስደቴን፣ መከራዬን፣ በአንጾኪያ፣ በኢቆንዮን እና በልስጥራን የደረሰብኝን ሁሉ ተከትለሃል፡፡ ይህን ሁሉ ስደት በጽናት አልፌዋለሁ፣ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ፡፡12በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደሚወደው ሊኖሩ የሚፈልጉ ሁሉ ይሰደዳሉ፡፡13ከፉ ሰዎች እና አታላዮች በክፋት እየባሱ ሌሎችንም እያሳቱና ራሳቸውም ችየሳቱ ይሄዳሉ፡፡14አንተ ግን በተማርህበትና በምታምንበት ነገር ጸንተህ ኑር፣ ከማን እንደተማርከው ታውቃለህና፡፡15ከሕፃንነትህ ጀምሮ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ስለሚገኘው መዳን ጥበብ ሊሰጡህ ስለሚችሉት ቅዱሳት መጻሕፍት አውቀሃል፡፡16በእግዚአብሔር የተገለጡ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ለመሠረተ እምነት፣ በእምነትም ለመጽናት፣ በጽድቅም ላለው ምክር ይጠቅማሉ፣17በመሆኑም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ የተዘጋጀ እና የታጠቀ እንዲሆን ያደርጉታል፡፡
1በእግዚአብሔር ፊት፣ በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ባለው በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፣ በመገለጡና በመንግስቱ፣ አዝዝሃለሁ፣2ቃሉን ስበክ ሲመችህም ሳይመችህም የተዘጋጀህ ሁን፡፡ እየታገስክና እያስተማርክ ዝለፍ፣ ገስጽ፣ ምከርም፡፡3ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት ዘመን ይመጣል፣ ይልቁን፣ ለፍላጎታቸው የሚስማማቸውን የሚሰብኩአቸውን አስተማሪዎችን በዙሪያቸው ይሰበስባሉ፡፡ ይህም ጆሮቻቸውን የሚያሳክክላቸው ይሆናል፡፡4ጆሮቻቸውን እውነትን ከመስማት ይመልሳሉ፣ ወደ ስህተትም ያዘነብላሉ፡፡5አንተ ግን፣ በነገር ሁሉ የነቃህ ሁን፣ መከራን ተቀበል፣ የወንጌላዊነትን ሥራ አድርግ፣ አገልግሎትህንም ፈጽም፡፡6እኔ እንደ መስዋዕት ልሰዋ ነው፡፡ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል፡፡7መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፣ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፣ እምነቱንም ጠብቄአለሁ፡፡8የጽድቅም አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፣ ይህንንም ጻድቅ ፈራጅ፣ የሆነው ጌታ፣ በዚያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፣ ለእኔ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ ነው፡፡9ወደ እኔ በቶሎ ልትመጣ ትጋ፣10ዴማስ ትቶኛልና፣ ይህንንም ዓለም ወድዶ ወደ ተሰሎንቄ ሄዶአል፡፡ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፣ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፡፡11ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ፡፡ ማርቆስን ይዘኸው ና እርሱ በሥራው እጅግ ይጠቅመኛል፡፡12ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ፡፡13ስትመጣ በጢሮአዳ የተውኩትን ልብሴን፣ ይልቁንም በብራና የተጻፉትን መጻሕፍት ይዘህልኝ ና፡፡14መዳብ አንጥረኛው አሌክሳንደር እጅግ ከፋብኝ፡፡ ጌታ ስለ ክፉ ሥራው ዋጋውን ይከፍለዋል፡፡15አንተም ደግሞ ከእርሱ ተጠበቅ፣ ቃላችንን እጅግ ተቃውሞአልና፡፡16በፊተኛው የፍርድ ቤት ክርክሬ ከአኔ ጋር ማንም አልቆመም፣ ነገር ግን ሁሉም ተዉኝ፡፡ ይህንንም አይቁጠርባቸው፡፡17ነገር ግን፣ አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት፣ የወንጌሉ ስብከት በእኔ እንዲፈጸም፣ ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፣ ከአንበሳም አፍ ዳንኩኝ፡፡18ጌታ ከክፉ ሥራዎች ሁሉ አውጥቶኛል፣ ለሰማያዊውም መንግሥቱ ይጠብቀኛል፡፡ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፡፡ አሜን፡፡19ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩ በተ ሰብ ሰላምታ አቅርብልኝ፡፡20ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፣ ነገር ግን ጥሮፊሞስ ስለታመመ በሚሊጢን ተውኩት፡፡21ከክረምት በፊት ልትመጣ ትጋ፡፡ ኤውግሎስና ጱዴስ፣ ሊኖስና ቅላውዲያም ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል፡፡22ጌታ ከመንፈስህ ጋር ይሁን፡፡ ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
1የእግዚአብሔር ባሪያና፣የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነው ጳውሎስ፣ በእግዚአብሔር የተመረጡት ሰዎች እምነት እንዲጸና፣ እግዚአብሔርን ከመምሰል ጋር የሚስማማውን የእውነት እውቀት ለማፅናት፣2የማይዋሽ እግዚአብሔር፣ በተረጋገጠ ዘላለማዊ ሕይወት ከዘመናት በፊት ተስፋን ሰጠ፣3እንደ መድሃኒታችን እግዚአብሔር ትዕዛዝ፣ በትክክለኛው ጊዜ፣ ቃሉን ለእኔ አደራ በሰጠኝ መልዕክት ገለጠ፡፡4የጋራችን በሆነ እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለቲቶ። ከእግዚአብሔር አብ፣ከመድሃኒታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ፀጋ፣ምህረትና ሰላም ለአንተ ይሁን።5አንተን በቀርጤስ የተውኩበት ምክንያት፣ ያልተጠናቀቁትን ነገሮች እንድታስተካክልና፣ በነገርኩህ መሠረት በየከተማው ሁሉ ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው፡፡6የቤተክርስቲያን ሽማግሌ፣ ነቀፋ የሌለበት፣የአንዲት ሚስት ባል፣ ከክፍዎችና ካልታረሙ ጋር ስማቸው የማይነሳ ታማኝ ልጆች ያሉት ሊሆኑ ይገባዋል።7የቤተክርስቲያን ሽማግሌ የእግዚአብሔርን ቤት የሚያስተዳድር መሪ ስለሆነ ነቀፋ የሌለበት፣ የማይጮህ፣ራሱን የሚገዛ ፣የማይቆጣ ፣ለወይን ጠጅ የማይገዛ፣ የማይጣላና ስስታም ያልሆነ ሊሆን ይገባል።8ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፣ መልካምን የሚወድ፣ ጠንቃቃ፣ ጻድቅ፣ መንፈሳዊና ራሱን የሚገዛ መሆን አለበት።9በጤናማ ትምህርት ሌሎችን ለማበረታታት፣ የሚቃወሙትን ለመገሠጽ እንዲችል እውነተኛውን ትምህር አጥብቆ መያዝ ይኖርበታል።10ሥርዓት የሌላቸው በተለይም ከተገረዙት ወገን የሆኑ ብዙዎች አሉ። ቃላቸው ከንቱ ነው። ሰዎችን ያስታሉ፣ በተሳሳተ መንገድም ይመራሉ።11እነዚህን ዝም ማሰኘት ይገባል። ለነውረኛ ትርፍ ብለው ማስተማር የማይገባቸውን እያስተማሩ፣ መላ ቤተሰብን ያፈርሳሉ።12ከነሱ ከራሳቸው ነብያት መካከል አንዱ፣ "የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፣ ክፉና አደገኛ አውሬዎች፣ ሰነፍ ሆዳሞች ናቸው" ብሏል፡፡13ይህም አባባል ትክክል ነው፣ ስለዚህ ጤነኛ እምነት እንዲኖራቸው አጥብቀህ ገሥጻቸው ።14ጊዜያቸውን በአይሁድ ተረትና፣ ከእውነት በራቁ ሰዎች ትዕዛዛት ላይ አያባክኑ።15ንጹሆች ለሆኑት፣ ሁሉም ንጹህ ነው፣ ለርኩሶችና ለማያምኑ ግን ንጹህ የሆነ ምንም የለም። ይልቁን፣ አዕምሯቸውና ሃሳባቸው እንኳ የረከሰ ነው፡፡16እግዚአብሔር እንደሚውያቁ ይናገራሉ፣ በሥራቸው ግን ይክዱታል። የሚያስጸይፉ የማይታዘዙና፣ ለመልካም ስራም የማይበቁ ናቸው፡፡
1አንተ ግን፣ ከጤናማው ትምህርት ጋር የሚስማማውን ተናገር።2በእድሜ የገፋ ሰዎች ልከኞች፣ ጨዋዎች፣ ጠንቃቆች ጤናማ እምነት፣ ፍቅርና ጽናት ያላቸው ሊሆኑ ይገባችዋል፡፡3በእድሜ የገፉ ሴቶችም እንዲሁ ጨዋዎችና፣ ከሃሜት የራቁ መሆን አለባቸው፡፡ ወይን ጠጅ ጠጪዎች መሆን አይገባቸውም። መልካም የሆነውን ማስተማር ይገባችዋል4ወጣት ሴቶችን በአስተሳሰባቸው ሚዛናዊ እንዲሆኑ እንዲያሳስቧቸው፣ የገዛ ባሎቻቸውና ልጆቻቸውን የሚወዱ፣ ጠንቃቃ እንዲሆኑ እንዲያበርቷቷቸው፣5የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ ንፁህ፣ መልካም የቤት አስተዳዳሪና፣ ለባሎቻቸውም የሚታዘዙ ይሁኑ።6በተመሳሳይ መንገድ፣ ወጣት ወንዶች ጠንቃቆች እንዲሆኑ አሳስባቸው።7በነገር ሁሉ ራስህን የመልካም ሥራ ምሳሌ አድርገህ ተገኝ፤ በትምህርትም ንጽህናን፣ ጨዋነት፣ የማይነቀፍ ጤናማ ቃላት ይኑርህ።8ስለ እኛ የሚናገረው ምንም ክፉ ነገር እንዳይኖር። የማይነቀፍ ስህተት የሌለበትን፣ ነገር ግን ሊቃወም የሚሞክረውን የሚያሳፍር ቃላትን ተናገር።9ባሪያዎች በሁሉም ነገር ለጌቶቻቸው ይታዘዙ። ጌቶቻቸውን ደስ ሊያሰኟቸው ይሞክሩ እንጂ፣ አይከራከሯቸው።10ስለ መድሃኒታችን እግዚአብሔር የምናስተምረው፣ በሁሉ መንገድ የሚማርክ እንዲሆን፣ ታማኝነትን ያሳዩ እንጂ አይስረቁ።11ሰዎችን ሁሉ ሊያድን የሚችለው የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧል፡፡12ይህም ፀጋ ሃጢዓተኝነትና ዓለማዊ ምኞትን እንድንክድና፣ በአሁኑ ዘመን በጥንቃቄ፣ በጽድቅና፣ እግዚአብሔርን በመምሰል እንድንኖር ያስለምደናል13ይህም የተባረከውን ተስፋችንን፣ የታላቁን አምላካችንና አዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ፣ ለመቀበል በደስታ እንድንጠባበቅ ነው።14ኢየሱስ ራሱን ለእኛ የሰጠው፣ ከዓመፅ ነፃ ሊያወጣንና ሊያነፃን፣ ገንዘቡና መልካምን ለማድረግ የሚናፍቅ ሕዝብ፣ ለራሱ ሊያደርገን፣ ዋጋ ለመክፈል ነው።15እነዚህን ነገሮች ተናገር፣ አበረታታ፣ በሙሉ ስልጣን ገስጽ፣ ማንም አይናቅህ።
1ለገዢዎችና ለባለሥልጣኖች እንዲገዙ፣ እንደታዘዟቸው፣ ለበጐ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ እንዲሆኑ፣2ማንንም እንዳይሳደቡ፣ የሌሎችንም ፈቃድ እንዲያከብሩ እንጂ እንዳይከራከሩ፣ ለሁሉም ሰው ትህትን እንዲያሳዩ አሳስባቸው።3እኛም ቀድሞ የማናስተውልና የማንታዘዝ ነበርን። የሳትንና የተለያዩ ምኞቶቻችንና ፍላጐቶቻችን ባሪያዎች ነበርን። በክፋትና በምቀኝነት እንኖር ነበር። የተጠላንና እርስበርስ የምንጠላላ ነበርን።4ነገር ግን፣ የመድሃኒታችን የእግዚአብሔር ርህራሔና ለሰው ልጅ ያለው ፍቅር በተገለጠ ጊዜ፣5ከምህረቱ የተነሳ፣ በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታድስ አዳነን እንጂ፣ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ምክንያት አይደለም።6እግዚአብሔር በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል፣ አብዝቶ መንፈስ ቅዱስን አፈሰሰልን።7ይህም በፀጋው ፀደቅን፣ የዘላለም ህይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን ነው።8እነዚህ ቃሎች የታመኑ ናቸው። በእግዚአብሔር የሚያምኑ እርሱ በፊታቸው ላኖረው መልካም ሥራ እንዲተጉ፣ እነዚህን ነገሮች በድፍረትት እንድትናገር እፈልጋለሁ። እነዚህ ነገሮች መልካምና ለሰዎች ሁሉ የሚጥቅሙ ናቸው።9ነገር ግን ከከንቱ ክርክር፣ ከዘር ቆጠራና በህግ ጉዳይ ከሚሆን ጸብና ግጭት ራቅ። እነዚህ ነገሮች፣ የማይገቡና የማይጠቅሙ ናቸው፡፡10አንዴ ወይም ሁለቴ ካስጠነቀቅከው በኋላ፥ በመካከሃላችሁ መከፋፈል የሚፈጥረውን ሰው አስወግደው፡፡11እንዲህ ዓይነቱ ሰው፣ ከእውነተኛው መንገድ የወጣ፣ ሃጢያት የሚያደርግና በራሱ የፈረደ እንደሆነ እወቅ።12አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፣ ክረምቱን ለማሳለፍ ወደ ወሰንኩበት ወደ ኒቆሊዎን ፈጥነህ ና።13የህግ ባለሞያውን፣ ዜማስንና አጵሎስን የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ሰጥተህ ቶሎ ላካቸው።14ወገኖቻችንም እለታዊ ፍላጎታቸውን ማግኛት እንዲችሉ ፍሬ ቢስም ሆነው እንዳይገኙ፣ መልካም ሥራ ማድረግን መማር አለባቸው።15ከኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል ። የሚወዱንን አማኞችን ሁሉ ሰላም በልልን። ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡አሜን።
1ስለክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ የሆነው ጳውሎስ ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ ጋር ለተወደደው ወንድማችንና የሥራ አጋራችን ለሆነው ለፊሊሞና፣2ለእህታችን ለአፒፊያ፣አብሮን ወታደር ለሆነው ለአክሪፋ እንዲሁም በቤትህ ላለችው ቤተክርስቲያን፡3ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሠላም ለእናንተ ይሁን።4በጸሎቴ ሁሉ ስላንተ እያነሳሁ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።5ምክንያቱም በጌታ በኢየሱስ ስላለህ እምነት ለቅዱሳንም ሁሉ ስላለህ ፍቅር ሰምቻለሁ።6በክርስቶስ በኩል የመልካም ነገር ሁሉ እውቀት በእኛ ውስጥ ስላለ በእምነት ያለህ ተካፋይነት ውጤታማ እንዲሆን እጸልያለሁ።7ወንድሜ ሆይ፣ ለዚህም ምክንያቱ የቅዱሳን ሁሉ ልብ በአንተ በማረፉ ምክንያት በፍቅርህ በጣም ደስ ስላለኝና ስለተጽናናሁ ነው።8ስለዚህም ምንም እንኳ ምን ማድረግ እንዳለብህ በክርስቶስ ለማዘዝ ድፍረት ቢኖረኝም9በዚህ ፈንታ እንደ ሽማግሌው አሁን ደግሞ ስለ ክርስቶስ እስረኛ እንደሆነው ጳውሎስ በፍቅር እለምንሀለሁ።10ልመናዬ በእስርቤት አባት ስለሆንኩት ስለ ልጄ ኦኖሲሞስ ነው።11ምክንያቱም ቀድሞ ለአንተ የማይጠቅም አሁን ግን ለአንተም ለእኔም ጠቃሚ በመሆኑ ነው።12የልቤ የሆነውን እርሱን ወደ አንተ ልኬዋለሁ።13በእኔ በኩልስ አንተን ወክሎ ስለ ወንጌል በእስር ቤት ያለሁትን ያገለግለኝ ዘንድ እኔ ጋ ቢቀር እወድ ነበር።14ነገር ግን መልካም ሥራህ በግድ ሳይሆን በፈቃድህ ይሆን ዘንድ ያለ አንተ ፈቃድ ምንም ማድረግ አልፈለግሁም።15ለጥቂት ጊዜ ከአንተ ተለይቶ የነበረው ምናልባት ለዘላለም የአንተ ይሆን ዘንድ ነው ።16ነገር ግን ከዚህ በኋላ ከባሪያ የተሻለ እንደተወደደ ወንድም እንጂ እንደባሪያ አይደለም፥ በተለይ ለእኔ የተወደደ ከሆነ ለአንተማ በሥጋም በጌታም የበለጠ ይሆናል።17እንግዲህ እንደ አጋርህ ከቆጠርከኝ እንደኔ አድርገህ ተቀበለው።18ነገር ግን በምንም መልኩ አሳዝኖህ ቢሆን ወይም ዕዳ ቢኖርበት በእኔ ላይ ቁጠረው።19እኔ ጳውሎስ እኔ እከፍላለሁ ብዬ በገዛ እጄ ጽፌአለሁ።የገዛ ህይወትህ እንኳ የኔ ነው ብዬህ አላውቅም።20አዎ ወንድሜ ሆይ እስኪ በጌታ ደስ ይበለኝ፥ ልቤም በክርስቶስ ይጽናና።21እንደምትታዘዘኝ በመተማመን ካልኩህም በላይ እንደምታደርግ ስለማውቅ ጽፌልሀለሁ።22በነገራችን ላይ ከጸሎታችሁ የተነሳ ወደ እናንተ እንደምመጣ ተስፋ ስለማደርግ አንድ የእንግዳ ክፍል አዘጋጅልኝ።23ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አብሮኝ የታሰረው ኤጳፍራ24እንዲሁም የሥራ አጋሮቼ ማርቆስ፣አርስጥሮኮስ፣ዴማስና ሉቃስ ሠላምታ ያቀርቡልሀል።25የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን። አሜን!
1ከረጅም ጊዜ በፊት በተለያዩ ዘመናትና በተለያዩ መንገዶች እግዚአብሔር በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ ነበር። 2አሁን ግን የሁሉም ነገር ወራሽ ባደረገው፣ ዓለምንም በፈጠረበት በልጁ ተናገረን። 3ልጁ የክብሩ ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አንድ ነው፤ በሥልጣን ቃል ሁሉን ደግፎ ይዞአል። የሰዎችንም ኃጢአት ካነዳ በኃላ በሰማይ በግርማው ቀኝ ተቀምጧል።4እርሱ የወረሰው ስም ከሰማቸው እጅግ የላቀ በመሆኑ፣ ከመላእክትም የበለጠ ሆኖአል። 5ለመሆኑ፣ ከመላክት መካከል፣ “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ደግሞስ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ለማን ነው?6የበኩር ልጁን ወደ ዓለም ሲያስገባ እግዚአብሔር፣ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ብሏል። 7ስለ መላእክቱ ግን፣"መላዕክቱን ነፋሳት፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል" ይላል።8ስለ ልጁ ግን፣ “አምላክ ሆይ፣ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ነው፤ የመንግሥትህም በትር የጽድቅ በትር ነው። 9ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፅንም ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ” ብሏል።10እንዲሁም፣ “ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ ምድርን ፈጠርህ፤ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። 11እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ። ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ። 12እንደ መጎናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ።13በየትኛውም ጊዜ ነበር እግዚአብሔር ከመላእክቱ ለአንዱ፣ “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው? 14ታድያ፣ መላእክት ሁሉ እኔን እንዲያመልኩና ድነት የሚወርሱትን ለመርዳት ተተላኩ መንፈሶች አይደሉምን?
1ስለዚህ ከሰማነው ነገር እንዳንወሰድ፣ ስለ ሰማነው ነገር ይበልጥ መጠንቀቅ አለብን።2በመላእክት አማካይነት የመጣው መልእክት ጽኑ ከሆነና፣ ማንኛውም መተላለፍና ዐመፅ ተገቢውን ቅጣት የሚቀበል ከሆነ። 3ታዲያ፣ይህንን ታላቅ መዳን ቸል ካልን እንዴት ማምለጥ እንችላለን? 4እግዚአብሔርም ምልክቶችን፣ ድንቆችንና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ፣እንደ ፈቃዱ በታደሉት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቱን አጽንቶአል።5ይህ እየተናገርንለት ያለውን ወደ ፊት የሚመጣውን ዓለም እግዚአብሔር ለመላእክት አላስገዛም። 6እንዲያውም በቅዱሳት መጻህፍት አንድ ሰው አንድ ስፍራ ሲናገር፣7ሰውን ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት። 18ማንኛውንም ነገር ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት” ብሏል። እግዚአብሔር ከእግሩ በታች ሲያስገዛለት ምንም ያላስገዛለት ነገር የለም። ነገር ግን በእሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት ገና አናይም።9ይሁን እንጂ፣ ከመከራውና ከሞቱ የተነሣ ከመላእክቱ በጥቂቱ አንሶ የነበረውን ኢየሱስ፣ የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናያለን። በእግዚአብሔር ጸጋ እርሱ ለሰው ሁሉ ሞትን ቀምሷል። 10ሁሉም በእርሱና ለእርሱ የሚኖር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት የድነታቸውን መሥራች በመከራው አማካይነት እግዚአብሔር ፍጹም ሊያደርገው ተገቢ ሆነ።11የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሁለቱም ከአንዱ ምንጭ፣ ከእግዚአብሔር ናቸው። በዚህም ምክንያት የሚቀድሳቸው እርሱን ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራቸው አላፈረም። 12እንዲያውም፣13እንዲሁም፣ “እኔ በእርሱ እታመናለሁ” ይላል። በተጨማሪ፣ “እነሆ እኔንና እግዚአብሔር የሰጠኝን ልጆች ተመልከቱ” ብሏል። 14ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በሥጋና ደም ስለሆኑ፣ በሞቱ አማካይነት ሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ማለትም ዲያብሎስን ለመሻር ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሥጋ ለብሶ። 15ይህም የሆነው ዕድሜ ልካቸውን በሞት ፍርሃት ምክንያት ዕድሜ ልካቸውን ባርነት ውስጥ የነበሩትን ሁሉ ነጻ ለማውጣት ነው።16እርግጥም እየረዳቸው ያለው መላእክትን ሳይሆን፣ የአብርሃም ዘሮችን ነው። 17ስለሆነም የእግዚአብሔር በሆነ ነገር ሁሉ መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህን ለመሆንና ለሰዎችም ሁሉ የኃጢአት ይቅርታን ለማስግገኘት በሁሉም ረገድ ወንድሞችን መምሰሉ አስፈላጊ ሆነ። 18ኢየሱስ ራሱ መከራ የተቀበለና የተፈተነ በመሆኑ፣ የሚፈተኑትን ሁሉ ሊረዳቸው ይችላል።
1ስለዚህ የሰማያዊ ጥሪ ተከፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች የእምነታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ። 2ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ ታማኝ እንደ ነበር ሁሉ፣ እርሱም ለሾመው ለእግዚአብሔር ታማኝ ነበር። 3ቤቱን የሚሠራው ከራሱ ከቤቱ የበለጠ ክብር እንዳለው ሁሉ፣ ኢየሱስም ከሙሴ ይልቅ የበለጠ ክብር እንደሚገባው ተቆጥሯል። 4ማንኛውም ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉም ነገር የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው።5ወደ ፊት መነገር ለሚገባው ነገር ምስክር እንዲሆን፣ ሙሴም በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ እንደ አገልጋይ ታማኝ ነበር። 6ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ሥልጣን ያለው ልጅ ነው። የምንተማመንበትንና የመተማመናችንን ድፍረት አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።7ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ፣ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ8በምድረበዳ በፈተና ቀን በአመጽ እንዳደረጋችሁት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።9ይህ የሆነው አባቶቻችሁ እኔን በመፈታተን ሲያምፁብኝና ዐርባ ዓመት ሙሉ ሥራዎቼን ባዩበት ጊዜ ነበር።10ስለዚህ በዚያ ትውልድ ደስ አልተሰኘሁም። እንዲህም አልኩ፤ ልባቸው ሁል ጊዜ ይስታል መንገዴንም አላወቁም።11ስለዚህ በቁጣዬ፥ "ወደ እረፍቴ አይገቡም" ብዬ ማልሁ።12ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ማንም የማያምን ክፉና ከሕያው እግዚአብሔር ዘወር የሚል ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።13ይልቁንስ ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልኸኛ እንዳይሆን ከዛሬ ጀምሮ በየዕለቱ እርስ በርሳችሁ ተበረታቱ።14ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ በእርሱ ያለንን ድፍረት አጥብቀን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ተባባሪዎች እንሆናለን። 15ስለዚህም፣ "ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ በአመጽ ጊዜ እንደሆነው ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ" ተብሏል።16ለመሆኑ፣እነዚያ ድምፁን ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ እየመራ ከግብፅ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን? 17ለአርባ ዓመት እግዚአብሔር የተቆጣባቸውስ እነማን ነበሩ? ኃጢአት ያደረጉና ሬሳቸው በበረሃ ወድቆ የቀረው አይደሉምን? 18ደግሞስ እነዚያ ያልታዘዙት ካልሆኑ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንደማይገቡ እግዚአብሔር የማለባቸው እነማን ሊሆኑ ነው? 19ባለማመናቸው ምክንያት ወደ ዕረፍቱ ሊገቡ እንዳልቻሉ እናያለን።
1ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ዕረፍት ከሆነው ዘላቂ ተስፋ የሚጎድል እንዳይመስለው በጣም መጠንቀቅ አለብን። 2ምክኒያቱም ለእስራኤላውያን እንደ ተነገረ ሁሉ ለእኛም ስለ እግዚአብሔር ዕረፍት መልካም ዜና ተነግሮናል፤ ሆኖም፣ የሰሙትን መልእክት ሰሞዎቹ በእምነት ስላልተቀበሉት አልጠቀማቸውም።3“ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፣ ብዬ በቁጣዬ ማልሁ” እንዳለው ሳይሆን እኛ ያመንን ግን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። የእርሱ ፍጥረት ሥራ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ 4ስለ ሰባተኛ ቀን በማመልከት አንድ ቦታ “በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ዐረፈ” ይላል። 5ደግሞም፣ “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ይላል።6ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ለመግባት ለአንዳንዶች አሁንም የተጠበቀባቸው በመሆኑና ፣ መልካሙን ዜና ከሰሙት እስራኤላውያን ብዙዎቹ ባለ መታዘዛቸው ምክንያት ወደ ዕረፍቱ ባለ መግባታቸው እግዚአብሔር በድጋሚ፣ 7“ዛሬ” የተባለ ቀን ወስኖአል።8ኢያሱ አሳርፎአቸው ቢሆን ኖሮ፣ እግዚአብሔር ስለ ሌላ ቀን አይናገርም ነበር። 9ስለዚህ ለእግዚአብሔር ሕዝብ አሁንም ቢሆን የሰንበት ዕረፍት ተጠብቆላቸዋል። 10ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት የገባ ሰው እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ ሁሉ፣ እርሱም ከሥራው ያርፋል። 11ስለዚህ ማንም የእነዚያን ሰዎች ዐመፅ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንናፍቅ።12የእግዚአብሔር ቃል ሕያው፣ የሚሠራና፣ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ፣ ስለታም ነው። ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ይወጋል። የልብን ሐሳብና ውስጥን ይመረምራል። 13ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም። እኛ ተጠያቂዎች በሆንንበት በእርሱ ዓይኖች ፊት ማንኛውም ነገር የተገለጠና የተራቆተ ነው።14እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ። 15ነገር ግን እርሱ ከኃጢአት በቀር በማንኛውም ነገር እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንምና። 16ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።
1እያንዳንዱ ሊቀ ካህን ከሰዎች መካከል ይመረጣል፤ ለኃጢአት መሥዋዕትንና መባን ለማቅረብ እግዚአብሔርን በሚመለከት ጉዳይ እነርሱን በመወከል ይሾማል። 2እርሱ ራሱም በድካም ውስጥ ያለ በመሆኑ ዐላዋቂዎችንና ከመንገድ የሳቱትን ሊራራላቸው ሊቀበላቸው ይችላል። 3ከዚህም የተነሣ ለሕዝቡ ኃጢአት እንደሚያድርገው ሁሉ እርሱም ለገዛ ራሱ ኃጥአት መሥዋዕት ማቅረብ ይኖርበታል።4እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም ይህን ክብር በራሱ አያገኘውም። 5ክርስቶስ ራሱም ቢሆን ሊቀ ካህናት የመሆንን መብት በገዛ ራሱ አልወሰደም። ይልቁንም እግዚአብሔር ለእርሱ፣6ይህም በሌላ ቦታ፣ እግዚአብሔር፣እንደመልከጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ" ይላል።7ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በነበረ ዘመን ፣ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ። እግዚአብሔርን በመፍራቱም ጸሎቱ ተሰማለት። 8ምንም እንኳ እርሱ ልጅ ቢሆንም፣ ከደረሰበት መከራ የተነሣ መታዘዝን ተማረ።9በዚህ ሁኔታ ሁሉ የዘላለም ድነት ምክንያት ሆነላቸው፤ 10እግዚአብሔርም እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት አድርጎ ሾመው። 11ስለ ኢየሱስ ብዙ የምንናገረው አለን፤ ሆኖም፣ ለመቀበል ዳተኞች ስለሆናችሁ፣ ለእናንተ ማስረዳት አዳጋች ነው።12እስከ አሁን ድረስ መምህራን መሆን ሲገባችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረታዊ መርሖዎች የሚያስተምራችሁ ሰው ገና ትፈልጋላችሁ። እናንተ የምትፈልጉት ወተት እንጂ፣ ጠንካራ ምግብ አይደለም። 13ወተት ብቻ ሊጋት ማንኛውም ሰው ገና ሕፃን ስለሆነ የጽድቅ ትምህርት ልምምድ የለውም። 14በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ ምግብ ግን መልካምንና ክፉውን መለየት ለተማሩና ትክክል የሆነውን ካልሆነው የመለየት ልምድ ላላቸው ትልልቅ ሰዎች ነው።
1ስለዚህ ስለ ክርስቶስ መልእክት በመጀመሪያ የተረዳነውን ተወት በማድረግ ወደ ብስለት ልንሻገር ይገባናል እንጂ ከሞተ ሥራ ንስሐ መግባትንና በእግዚአብሔር ማመንን፣2ወይም ጥምቀቶችን፣እጆች መጫንን፣ የሙታን ትንሳኤን እንዲሁም የዘላለም ፍርድን ወደ ሚመለከት መሠረትን የመጣል ትምህርት መመለስ አይገባንም።3እግዚአብሔር ከፈቀደ እነዚህንም እናደርጋለን4ይህንን የምናደርገው አንድ ጊዜ ብርሃን በርቶላቸው ሰማያዊውን ስጦታ የተቀበሉትን፣ከመንፈስ ቅዱስ ተሳታፊዎች የነበሩትን፣5መልካሙን የእግዚአብሔር ቃልና በመጪው ዘመን ሊመጣ ያለውን ኃይል ከቀመሱ በኃላ6የካዱትን በንስሐ እንዲታደሱ ማድረግ የማይቻል በመሆኑ ነው። እነዚህ ለሕዝብ መሳለቂያ ይሆን ዘንድ ራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ ራሳቸው እንደገና ይሰቅሉታል።7በእርሷ ላይ ብዙ ጊዜ የሚዘንበውን ዝናብ ተቀብላ ለደከሙባት የሚጠቅም ፍሬን የምታፈራ መሬት ከእግዚአብሔር በረከትን ትቀበላለች።8እሾህና አሜኬላ የምታበቅል ከሆነች ግን ዋጋ ቢስና እርግማን የሚጠብቃት ትሆናለች፣ ፍጻሜዋም መቃጠል ይሆናል።9እንደዚህ የምንናገር ብንሆንም፣ ወዳጆች ሆይ፣ እናንተንና ድነታችሁን በሚመለከት ግን የተሻለ ነገር ስለ መኖሩ እርግጠኞች ነን።10ምክንያቱም ቅዱሳንን በማገልገላችሁና አሁንም እያገለገላችኋቸው በመሆኑ ለስሙ ያላችሁን ፍቅር በማሳየት የሠራችሁትን ሥራ ይረሳ ዘንድ እግዚአብሔር ዓመፀኛ አይደለም።11በፍጹም የመተማመን ዋስትና እያንዳንዳችሁ ይህንኑ ትጋት እስከመጨረሻ እንድታሳዩ በእጅጉ እንናፍቃለን።12ከእምነትና ከትዕግሥት የተነሣ የተስፋ ቃሉን የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ቸልተኞች እንድትሆኑ አንፈልግም።13ምክንያቱም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተስፋ ቃል በገባለት ጊዜ ከራሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ14“በእርግጥ እባርክሃለሁ፣ ዝርያዎችህንም እጅጉን አበዛለሁ” በማለት በራሱ ምሎአልና።15በዚህ መንገድ በትዕግሥት ከጠበቀ በኃላ ተስፋ የተገባለትን ተቀበለ።16ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፣ በመካከላቸው ለሚፈጠርውም ለማንኛውም ሙግት መሐላ የመጨረሻው ማጽኛ ነው።17የዓለማውን የማይለወጥ ባሕርይ ለተስፋው ወራሾች ይበልጥ ግልጽ አድርጎ ለማሳየት እግዚአብሔር በወሰነ ጊዜ በመሃላ አጸናው።18ይህንን ያደረገው እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይችልባቸው ሁለት የማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን መተማመኛ አጥብቀን ይዘን አምባ ፍለጋ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ነው።19ከመጋረጃው በስተጀርባ ወዳለው ቅድስት የሚገባውና እኛ የያዝነው ይህ መተማመኛ፣ ሥጋት የሌለበትና አስተማማኝ የነፍሶቻችን መልሕቅ ነው።20በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት ለዘላለም ሊቀ ካህናት በመሆን ኢየሱስ ወደዚህ ስፍራ ለእኛ ቀዳሚ በመሆን ገብቷል።
1የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የነበረው ይህ መልኬ ጼዴቅ የባረከው አብርሃምን ነገሥታቱን ድል አድርጎ ሲመለስ ነበር።2አብርሃምም ከማረጀው ከማንኛውም ነገር አንድ አሥረኛውን ለእርሱ ሰጠው። ‘መልኬ ጼዴቅ’ የሚለውም የስሙ ትርጉም ‘የጽድቅ ንጉሥ’ ደግሞም ‘የሳሌም ንጉ’ ማለትም ‘የሰላም ንጉሥ’ ማለት ነው።3እርሱ አባትም ሆነ እናት፣ የትውልድ ሐረግም ሆነ የጅማሬ ወይም የፍጻሜ አመን የሌለው ነው። ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሁሉ እርሱም ካህን ሆኖ ለዘላለም ይኖራል።4ይህ ሰው እንግዲህ ምን ያህል ታላቅ እንደነበረ አስቡ። አባታችን አብርሃም በጦርነት ካገኛቸው ምርጥ ነገሮች አንድ አሥረኛ የሚሆነውን ሰጥቶታል።5በእርግጥ የክህነቱን አገልግሎት የተቀበሉትም የሌዊ ዝርያዎች ከአብርሃም ዝርያ የተገኙ ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከእስራኤላውያን ወገኖቻቸው አሥራትን ይሰበስቡ ዘንድ በሕጉ ታዘዋል።6ይሁን እንጂ የሌዊ ዝርያ ያልነበረው መልኬ ጼዴቅ የተስፋ ቃሎች ከነበሩት ከአብርሃም አሥራትን ተቀበለ፣ ባረከውም።7ታናሹ በታላቁ እንደሚባረክ የሚካድ ነገር አይደለም።8በአንድ በኩል ስናየው አሥራትን የሚቀበሉ ሰዎች አንድ ቀን ይሞታሉ በሌላ በኩል ስንመለከተው ግን ከአብርሃም አሥራትን የተቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር ተገልጿል።9በሌላ አነጋገር አሥራትን ይቀበል የነበረው ሌዊ እንኳን በአብርሃም በኩል አሥራትን ሰጥቷል።10ምክንያቱም መልኬ ጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ ሌዊ በቀደምት አባቱ በአብርሃም አብራክ ውስጥ ነበረና።11ሕዝቡ ሕጉን የተቀበሉት በዚህ ሥርዓት በነበሩ ጊዜ ነበርና ፍፁምና በሌዊ ክህነት ማግኘት የሚቻል ቢሆን ኖሮ በአሮን ሥርዓት ሳይሆን በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት የሚሾም ሌላ ካህን ወደፊት ይነሳ ዘንድ ምን ያስፈልግ ነበር?12ክህነቱ የሚለውጥ ከሆነ ደግሞ ሕጉም መለወጥ ይገባዋል።13እነዚህ ነገሮች እየተነገሩለት ያለው ከወገኖቹ ከቶ ማንም በመሠዊያው ላይ አገልግሎ የማያውቅ የሌላ ነገድ ወገን ነውና።14እንግዲያውስ ጌታችን ካህናትን በሚመለከት ሙሴ ከቶውንም ምንም ካልተናገረለት ከይሁዳ ነገድ የመጣ መሆኑ ግልጽ ነው።15መልከ ጼዴቅን የመሰለ ሌላ ካህን ቢነሳ የምንለው ይበልጥ ግልጽ ይሆናል።16ይሄኛው ካህን ደግሞ ሰብዓዊ ዝርያን መሠረት በሚያደርገው ሕግ ሳይሆን የማይጠፋ የሕይወት ያይልን መሠረት ባደረገ ሕግ ካህን የሆነ ነው።17ቅዱሳት መጻሕርትም ስለ እርሱ እንዲህ ሲሉ ይመሰክራሉ፦ “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ”18የቀደመው ትዕዛዝ ገለል የተደረገው ደካማና የማይጠቅም በመሆኑ ነውና።19ሕጉ ፍጹም ያደረገው ምንም ነገር አልነበረምና። ይሁን እንጂ ከዚህ በኃላ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የተሻለ መተማመኛ አለ።20ይሄኛው የተሻለው መተማመኛ ግን ያለ መሃላ እውን አልሆነም፣ ምክንያቱም እነዚህ ሌሎቹ ካህናት ምንም መሃላ አልፈጸሙም።21“ጌታ ምሎአል ሃሳቡንም አይቀይርም፤ ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ’” ተብሎ እንደተጻፈ።22በዚህም ደግሞ ኢየሱ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።23በእርግጥም ሞት ካህናቱን ለዘላለም ከማገልገል ያግዳቸዋል። እብንዱ ሌላውን እየተካ፣ ካህናት የሆኑት የበዙት ከዚህ የተነሣ ነው።24ኢየሱስ ግን ለዘላለም ስለሚኖር የእርሱ ክህነት የማይለወጥ ነው።25ስለዚይ ስለ እነርሱ ሊማልድ ምን ጊዜም በሕይወት ስለሚኖር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሙሉ በሙሉ ሊያድናቸው ይችላል።26እንደዚህ ያለው ማለትም ኃጢአትና ነቀፋ የሌለበት፣ ንጡሕ፣ ከኃጢአተኞች የተለየ ከሰማያትም በላይ ከፍ ያለ ሊቀ ካህን ሊኖረን ይገባል።27እርሱ ሊቀ ካህናቱ ሲያደርጉት እንደነበረው በመጀመሪያ ራሱ ለሠራቸው ኃጢአቶች ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ለፈፀሟቸው ኃጢአቶች በየቀኑ መሥዋዕቶችን ማቅረብ አያስፈልገውም። ራሱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ይህንን ለአብዴና ለመጨረሻ ጊዜ አድርጎታል።28ሕጉ ድካም ያለባቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፣ ከሕጉ በኃላ የመጣው የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የተደረገውን ልጁን ሾሟልና።
1እንግዲህ ልንናገር የፈለግነው ጉዳይ ዋና ነጥቡ ይሄ ነው፦ በሰማያት በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ ሊቀ ካህን አለን።2እርሱ እግዚአብሔር በተከላት እውነተኛይቱ የማደሪያ ድንኳን፣ በተቀደሰው መቅደስ አገልጋይ የሆነ ነው እንጂ ማንኛውም ሟች ሰው አይደለም።3ማንኛውም ሊቅቀ ካህናት የሚሾመው ስጦታዎችንና መሥዋዕቶችን ለማቅረብ በመሆኑ፣ የሚቀርብ ነገር ይዞ መገኘት አስፈላጊ ነው።4ታዲያ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ የሚኖር ቢሆን በሕጉ መሠረት ስጦታዎችን የሚያቀርቡ ስላሉ እርሱ በፍጹም ካህን መሆን ባልቻለም ነበር።5የማደሪያ ድንኳኑን ለመሥራት በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን”አስተውል፣ በተራራው ላይ ባየኸው ምሳሌ መሰረት ማንኛውንም ነገር እንድትሠራ” በማለት እንዳስጠነቀቀው ሁሉ እነርሱ የሰማያዊ ነገሮች ጥላና ግልባጭ የሆኑ ነገሮችን የሚያገለግሉ ናቸው።6ነገር ግን በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሠረተ የተሻለ ኪዳን መካከለኛው በመሆኑ ክርስቶስ አሁን የላቀ አገልግሎት ተቀብሏል።7ያ የመጀመሪያው ኪዳን ነቀፋ ካልነበረው ሁለተኛ ኪዳን የሚፈለግበት ምንም ምክንያት አይኖርም ነበር።8እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ነቀፋ ባገኘ ጊዜ እንደዚህ ብሎ ነበርና”አስተውሉ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ዘመን ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር።9“ከግብፅ ምድር በእጆቼ መርቼ ባወጣኋቸው በዚያን ዘመን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት እንደዚያ ቃል ኪዳን አይሆንም። በዚያ ኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ችላ አልኳቸው” ይላል እግዚአብሔር።10“ከእነዚያ ዘመናት በኃላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ይህንን ኪዳን ነው፥ ‘ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ፣ በልቦቻቸውም ላይ እጽፈዋለሁ። አምላካቸው እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።11እያንዳንዱ ጎረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን፥ ‘እግዚአብሔርን እወቅ እያለ አያስተምርም፣ እጅግ ታናሽ ከሆነው ጀምሮ እጅግ ታላቅ እስከሆነው ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና።12በዓመፅ ለፈጸሟቸው ድርጊቶች ሁሉ ምሕረት አደርጋለሁና ኃጢአቶቻቸውንም ከእንግዲህ አላስብምና”13‘አዲስ’ በማለቱም የመጀመሪያው ኪዳን አስረጅቷል። አሮጌ ነው ብሎ የገለጸውም ሊወገድ ተቃርቧል።
1የመጀመሪያው ኪዳን ቢሆን በዚህ ምድር ለሚከናወነው አምልኮም ሆነ ለአምልኮ ደንቦች ስፍራ ነበረው።2በመገናኛው ድንኳን የተዘጋጀ ቅድስት የተባለ ውጨኛ ክፍል ነበር። በዚህ ስፍራ መቅረዙ፣ ጠረጴዛውና የመንግስቱ መገለጫ ኅብስት ነበሩበት።3ከሁለተኛው መጋረጃም በስተጀርባ ቅድስተ ቅዱሳን የተባለ ሌላ ክፍል ነበረ።4ዕጣን ለማጠን የሚሆን የወርቅ መሠዊያ ነበረው። ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠ የኪዳን ታቦትም ነበረበት። በእርሱም ውስጥ መና ያለበት የወርቅ መሶብ፣ ያቆጠቆጠች የአሮን በትርና የኪዳኑ የድንጋይ ጽላቶች ነበሩት።5በኪዳኑም ታቦት ላይ በስርየት መክደኛው ላ ያሰፈፉ የከበሩ የኩሩቤል ምስሎች ነበሩ። ይሁን እንጂ ስለ እነዚህ ሁሉ አሁን በዝርዝር መግለጽ አንችልም።6እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከተዘጋጁ በኃላ፣ ካህናቱ አገልግሎቶቻቸውን ለመፈጸም በመደበኛነት በማደሪያው ድንኳን ውጫዊው ክፍል በኩል ይገባሉ።7ሊቀ ካህናቱ ግን በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ሁለተኛው ክፍል ይገባል፣ በሚገባበትም ጊዜ ለራሱና ሕዝቡም ባለማወቅ ለፈጸሟቸው በደሎች የደም መሥዋዕት ይዞ እንጂ እንደዚሁ አይደለም።8የመጀመሪያይቱ የመገናኛ ድንኳን በስፍራዋ ቆማ እስካለች ድረስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያመራው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ በምሳሌ እያሳየ ነው።9ይህም ለአሁኑ ጊዜ ተምሳሌት ነው። አሁን እየቀረአቡ ያሉት ስጦታዎችም ይሁኑ መሥዋዕቶች የአምላኪውን ሕሊና ፍጹም ማድረግ የሚችሉ አይደሉም።10ከተለያዩ የመንፃት ሥርዓቶች ጋር የተያያዙ ምግቦችና መጠጦች ብቻ ናቸው። እነዚህ ሁሉ አዲሱ ሥርዓት በሥራ ላይ እስኪውል ድረስ በሥጋዊ ደረጃ እንዲከበሩ የተሰጡ ሥርዓቶች ናቸው።11ክርስቶስ በሰው እጆች በተሠራችው ሳይሆን ላቅ ባለችውና ይበልጥ ፍጹምና ቅድስት በመሆነችው፣ ከዚህም ከፍጥረታዊው ዓለም ባልሆነችው ድንኳን በኩል ለመጡት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ መጥቷል።12ክርስቶስ እጅግ ቅድስት ወደሆነችው ስፍራ አንድ ጊዜ ለሰዎች ሁሉ የገባውና የዘላለም ቤዛችንን ያስገኘልን በፍየሎችና በጥጃዎች ደም ሳይሆን በራሱ ደም ነው።13የፍየሎችና የኮርማዎች ደም እንዲሁም የጊደሮች አመድ በሥርዓታዊ ደረጃ ንፁሕ ባልሆኑት ላይ መረጨቱ የሚያጠራቸውና ሰውነቶቻቸውንም ንፁሕ የሚያደርገው ከሆነ፣14ይልቁንም ነውር ሳይኖረው በዘላለማዊ መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናገለግል ዘንድ ሕሊናችንን ከሞተ ሥራ ምን ያህል ያነጻን ይሆን?15ከዚህም የተነሳ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በእግዚአብሔር የተጠሩት ስለ ዘላለም ርስት የተሰጣቸውን የስፋ ቃል ይቀበሉ አንድ በመጀመሪያው ኪዳን ሥር ከነበረባቸው የኃጢአት ቅጣት ነፃ እንዲወጡ የሞት ቅጣት ተፈጽሞ ስለነበረ ነው።16ይህም የሆነው አንድ ሰው ኑዛዜ እንደተወ ሲገለጽ ኑዛዜ የተወውን ሰው መሞት ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።17ምክንያቱም ኑዛዜ የሚጸናው ሞት ተከስቶ ከሆነ ብቻ ነው፣ ተናዛዡ በሕይወት እስካለ ሊጸና አይችልምና።18እንደዚህም በመሆኑ የመጀመሪያው ኪዳን እንኳን ያለ ደም አልጸናምና።19በሕጉ ውስጥ ያሉትን ማንኛቸውንም ትዕዛዛት ሙሴ ለሕዝቡ ሁሉ በሰጠ ጊዜ የጥጆችንና የፍየሎችን ደም ከውሃ፣ ከቀይ የበግ ፀጉርና ከሂሶጵ ጋር ቀላቅሎ በራሱ በሕጉ መጽሐፍና በሕዝብ ሁሉ ላይ ይረጭ ነበርና።20ይህንንም ካደረገ በኃላ “እግዚቸብሔር ለእናንተ ሕግጋቱን የሰጠበት የኪዳኑ ደም ይህ ነው” ይል ነበር።21በዚያው ዓይነት መንገድ ደሙን በመገናኛው ድንኳንና ለክህነት አገልግሎት በሚውሉት ዕቃዎች ሁሉ ላይ ይረጭ ነበር።22ሕጉ በሚለውም መሠረት ሁሉም ነገር የሚነጻው በደም ነበር ማለት ይቻላል። ደምም ካልፈሰሰ በስተቀር ይቅርታ የለም።23ስለሆነም በሰማይ ያሉት ነገሮች ግልባጮችም በእነዚህ የእንስሳት መሥዋዕቶች ይነጹ ዘንድ አስፈላጊ ነበር። ይሁን እንጂ ሰማያዊ የሆኑት ነገሮች ራሳቸው እጅግ በተሻሉ መሥዋዕት መንጻት ይገባቸዋል።24ክርስቶስ በእጅ ወደተሠራው የእውነተኛውም ግልባጭ ብቻ ወደነበረው ቅድስተ ቅዱሳን አልገባምና። ይልቁንም እርሱ የገባው እግዚአብሔር ባለበት ስለ እኛ አሁን እግዚአብሔር ፊት ወደሚቀርብበት ሰማይ በቀጥታ ገብቷል።25ወደዚያም የገባው የሌላውን ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንደሚገባው እንደ ሊቀ ካህናቱ በየጊዜው ራሱን ለማቅረብ አይደለም።26እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ከዓለም ጅማሬ አንስቶ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን ራሱን መሥዋዕት በማድረግ ኃጢአትን ለማስወገድ በዘመናት መጨረሻ የተገለጠው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።27እያንዳንዱ ሰው አንድ ጊዜ መሞት ከዚያ በኃላም ወደ ፍርድ መቅረብ እንደሚገባው ሁሉ28እንደዚሁም የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው ክርስቶስ ኃጢአትን ለማስወገድ ዓላማ ሳይሆን በትዕግሥት ለሚጠባበቁት ድነትን ያስገኝላቸው ዘንድ ዳግመኛ ይገለጣል
1ሕጉ ሊመጡ ላሉ መልካም ነገሮች ጥላ ብቻ እንጂ እውነተኛው አካል አይደለም። ሕጉ ካህናት ያለማቋረጥ በየዓመቱ በሚያቀርቧቸው በነዚያው መሥዋዕቶች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ከቶ ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም። 2ቢችል ኖሮ እነዚያ መሥዋዕቶች መቅረባቸው ይቀር አልነበረምን? እንደዚያ ቢሆን ኖሮ የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ከኃጢአታቸው ከነጹ በኋላ ስለ ኃጢአታቸው የሚያስታውሱት ነገር ምንም አይኖርም ነበር። 3-4ነገር ግን በእነዚያ መሥዋዕቶች ውስጥ በየዓመቱ የተፈጸሙትን ኃጢአቶች የሚያስታውስ ነገር አለ። ለዚህ ምክንያቱ የኮርማዎችና የበጎች ደም ኃጢአትን ማስወገድ ባለመቻሉ ነው።5ክርስቶስ ወደ ዓለም ሲመጣ፣ “አንተ መሥዋዕቶችን ወይም ስጦታዎችን አልፈለግህም። ይልቅ ለእኔ ሥጋን አዘጋጀህልኝ። 6አንተ በሚቃጠል መባ ወይም በኃጢአት መሥዋዕት ደስ አልተሰኘህም። 7ቀጥሎም፣ “እግዚአብሔር ሆይ በመጽሐፍ ስለ እኔ እንደተጻፈው እነሆ ፈቃድህን ለማድረግ እዚህ አለሁ” ብሏል።8ከላይ እንደተጠቀሰው፡“አንተ መሥዋዕቶችን፣ ስጦታዎችን ወይም ለኃጢአት የሚቃጠሉ ሙሉ መሥዋዕቶችን ማለትም በሕጉ መሠረት የሚቀርቡ መሥዋዕቶችን አልፈለግህ፣ በእነርሱም ደስ ስላልተሰኘህም” ብሏል። 9ደግሞም፣ “እነሆ ፈቃድህን ለማድረግ እዚህ አለሁ” አለ። ሁለተኛውን ሥርዓት ለመትከል የመጀመሪያውን ሥርዓት ወደ ጎን ያደርገዋል። 10በሁለተኛው ሥርዓት ለአንድ ጊዜና ለዘላለም በቀረበው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ አማካኝነት በእግዚአብሔር ፈቃድ ተቀድሰናል።11በእርግጥ እያንዳንዱ ካህን ኃጢአትን ፈጽሞ ሊያስወግድ የማይችሉትን መሥዋዕቶች ለማቅረብ በየዕለቱ ለማገልገል ይቆማል። 12ነገር ግን ክርስቶስ ለኃጢአት ሁሉ ለዘላለም የሚሆን አንድ መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ፣ 13ጠላቶቹ እስኪዋረዱና የእግሩ መረገጫ እስኪሆኑ ድረስ እየተጠባበቀ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል። 14ይህም በአንድ መሥዋዕት የተቀደሱትን ለዘላለም ፍጹማን ስላደረጋቸው ነው።15ደግሞም መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ይመሰክርልናል። ምክንያቱም በመጀመሪያ፣ 16“ ከእነዚያ ቀኖች በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃልኪዳን ይህ ነው፡ ሕጎቼን በልባቸው ውስጥ አደርጋለሁ፣ ደግሞም በአእምሮአቸው ውስጥ እጽፈዋለሁ” ስላለ ነው።17ቀጥሎም፣ “ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውን ከእንግዲህ አላስበውም” አለ። 18ለእነዚህ ነገሮች ይቅርታ በተረገበት በዚያ ለኃጢአት ከእንግዲህ ወዲያ መሥዋዕት አይቀርብም።19ስለዚህ ወንድሞች፣ በኢየሱስ ደም አማካኝነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ድፍረት አለን። 20ይህም በመጋረጃው ማለትም በሥጋው አማካኝነት ለእኛ የከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው። 21በእግዚአብሔር ቤት ታላቅ ካህን ስላለን፣ 22ልባችን በመረጨት ከክፉ ኅሊና ሁሉ ነጽቶ፣ ሥጋችንም በንጹሕ ውኃ ታጥቦ ባገኘነው የእምነት ሙሉ ዋስትና በእውነተኛ ልብ እንቅረብ።23ተስፋን የሰጠ እግዚአብሔር ታማኝ ስለሆነ፣ አምነን የምንመሰክረውን ተስፋ ያለ ማወላወል አጥብቀን እንያዝ። 24ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እርስ በርስ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ። 25አንዳንዶቹ ልማድ እንዳደረጉት በአንድነት መሰብሰባችንን አንተው። በዚህ ፈንታ ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችሁ ይበልጥ ተበረታቱ።26የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆን ብለን ኃጢአት ማድረጋችንን የምንቀጥል ከሆንን፣ ከእንግዲህ ለኃጢአት የሚሆን መሥዋዕት አይኖርም። 27ይልቅ የሚጠብቀን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች ሊበላ ያለ ብርቱ እሳት ብቻ ነው።28የሙሴን ሕግ የናቀ ማናቸውም ሰው በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ያለ ምንም ምሕረት ይሞታል። 29ታዲያ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፣ የተቀደሰበትን የቃልኪዳኑን ደም እንደ እርኩስ የቆጠረ፣ የጸጋን መንፈስ የሰደበ ሰው ምን ያህል የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?30“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ዋጋን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቃለንና። ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።” 31በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነገር ነው!32ነገር ግን ከበራላችሁ በኋላ በእንዴት ያለ ታላቅ ሥቃይ ውስጥ እንደታገሣችሁ እነዚያን የቀደሙ ወቅቶች አስታውሱ። 33በስድብና በስደት ለሕዝብ መሳለቂያ ተዳርጋችኋል፣ ደግሞም በዚህ ዓይነቱ ሥቃይ ውስጥ ካለፉ ሰዎችም ጋር አብራችሁ ነበራችሁ። 34ለእስረኞች ርኅራኄ አሳያችሁ፣ የተሻለና ዘላለማዊ ሀብት ለራሳችሁ እንዳላችሁ በመረዳትም የንብረታችሁን መነጠቅ በደስታ ተቀበላችሁ።35ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። 36ፈቃዱን ካደረጋችሁ በኋላ እግዚአብሔር ለእናንተ ተስፋ የገባውን ነገር ለመቀበል መታገሥ ያስፈልጋችኋል። 37“በጣም በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚመጣው በእርግጥ ይመጣል፣ አይዘገይምም።38የእኔ የሆነው ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል። ወደኋላ ቢመለስ በእርሱ ደስ አይለኝም።” 39እኛ ግን ለጥፋት ወደኋላ እንደሚያፈግፍጉት አይደለንም። ይልቅ እኛ ነፍሳቸውን ለማዳን ከሚያምኑት ነን።
1እንግዲህ እምነት ሰው በተስፋ ለሚጠበቀው ነገር ማረጋገጫ ያልታየውም ነገርም አስረጅ ነው። 2የቀድሞ አባቶቻችንም እምነታቸው የተረጋገጠው በዚሁ ነበር። 3ፍጥርተ-ዓለሙ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መፈጠሩን፣ የሚታየውም ከሚታዩት ነገሮች የተፈጠረ አለመሆኑን በእምነት እንረዳለን።4አቤል ከቃየል የበለጠ ተቀባይነት ያለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው በእምነት ነበር። ጻድቅ እንደሆነ የተመሰከረለትም በዚህ ምክንያት ነበር። ስላቀረባቸው መሥዋዕቶች እግዚአብሔር መስክሮለታል። ቢሞትም እንኳ አሁንም ይናገራል።5ሄኖክ ሞትን ሳያይ ወደ ላይ የተወሰደው በእምነት ነበር። “እግዚአብሔር ስለወሰደው አልተገኘም።” ከመወሰዱ በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተነግሮለታና። 6ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም፣ ወደ እግዚአብሔር የሚመጣ፣ እግዚአብሔር እንዳለና እርሱን ለሚሹትም ዋጋን እንደሚሰጥ ማመን ስለሚገባው ነው።7ኖኅ ገና ስላልታዩ ነገሮች ከእግዚአብሔር ሲያስጠነቅቀው እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን የሚያድንበትን መርከብ የሠራው በእምነት ነበር። ይህን በማድረግ ዓለምን ኮንኖ በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።8አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስትን ወደሚቀበልበት ቦታ ታዞ የሄደው በእምነት ነበር። የወጣው ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ ነበር። 9በተስፋው ምድር እንደ ባዕድ የኖረውም በእምነት ነበር። ያን ተስፋ ከእርሱ አብረው ከሚወርሱት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ውስጥ ኖረ። 10ይሄውም እግዚአብሔር መሠረት ያላትን፣ ያቀዳትንና ያነጻትን ከተማ ይጠባበቅ ስለነበር ነው።11አብርሃምና ሣራ እጅግ አርጅተው ሳሉ እንደሚወልዱ በተነገራቸው ጊዜ፣ ወንድ ልጅን እንደሚሰጣቸው ተስፋ የገባላቸውን እግዚአብሔር ታማኝ አድርገው ስለቆጠሩ ሣራ ለማርገዝ ኃይል ያገኘችው በእምነት ነበር። 12በመሆኑም፣ ሊሞት ከተቃረበ ከዚህ አንድ ሰው ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዝርያዎች ተገኙ። እነርሱም በሰማይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ጠረፍ እንዳለ አሸዋ በዙ።13እነዚህ ሁሉ የተሰጧቸውን ተስፋዎች ሳይጨብጡ እምነታቸውን እንደጠበቁ ሞቱ። ይልቁንም እነዚህን ተስፋዎች ከሩቅ አይተው ስለተቀበሏቸው በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውን ተገነዘቡ። 14እንደዚህ የሚሉ ሰዎች የራሳቸው የሆነ አገር እንዲሚሹ በግልጽ ያሳያሉ።15በእርግጥ ለቀው የመጡትን አገር ቢያሰቡ ኖሮ ለመመለስ ዕድሉ ነበራቸው። 16አሁን ግን የሚፈልጉት የተሻለውን ሰማያዊ አገር ነው። ስለዚህም፣ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ አያፍርም።17አብርሃም በተፈተነ ጊዜ ይስሐቅን ያቀረበው በእምነት ነበር። አዎን፣ 18“ዝሮችህ የሚጠሩት በይስሐቅ ነው” የተባሉለትን ተስፋዎቹን በደስታ ስለተቀበለ አንድ ልጁን ለመሥዋዕት አቀረበ። 19አብርሃም፣ እግዚአብሔር ይስሐቅን ከሞት ሊያስነሣ እንደሚችል አምኖ ነበር። ይስሐቅን ከሞት የመነሣት አምሳያ አድርጎ መልሶ ተቀበለው።20ይስሐቅ ገና ወደፊት የሚመጡትን ነገሮች አስቦ ያዕቆብንና ኤሳውን በእምነት ባረካቸው። 21ያዕቆብ ፍጻሜው በተቃረበ ጊዜ፣ የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን የባረካቸውና በምርኩዙ አናት ተደግፎ የሰገደው በእምነት ነበር። 22ዮሴፍ ሊሞት ሲቃረብ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ እንደሚወጡ የተናገረውና የእርሱን አጽሙን እንዲወስዱ ያዘዘው በእምነት ነበር።23ሙሴ ሲወለድ ወላጆቹ መልከ መልካም ሕፃን መሆኑን አይተው የንጉሡን ትእዛዝ ሳይፈሩ ለሦስት ወራት የደበቁት በእምነት ነበር። 24ሙሴም ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ፣ እንዳይባል እምቢ ያለው በእምነት ነበር። 25ለአጭር ጊዜ በኃጢአት ደስ ከመሰኘት ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን መካፈልን መረጠ። 26ዓይኖቹ ወደፊት የሚቀበለውን ዋጋ አተኩረው ስለተመለከቱ፣ በግብጽ ከሚገኝ ሀብት ይልቅ ክርስቶስን መከተል የሚያስከትልበትን ውርደት የላቀ ብልጽግና አድርጎ አሰበ።27ሙሴ ግብጽን ለቆ የወጣው በእምነት ነበር። የማይታየውን እርሱን ተመልክቶ በአቋሙ ስለጸና የንጉሡን ቁጣ አልፈራም። 28ቀሳፊው የእስራኤልን የበኩር ልጆች እንዳይነካ ሙሴ የፋሲካ በዓልንና የደም ርጭት ሥርዓትን ያካሄደው በእምነት ነበር።29እስራኤላውያን በደረቅ መሬት ላይ እንደሚሄዱ ቀይ ባሕርን የተሻገሩት በእምነት ነበር። ግብጻውያን ይህን ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ተዋጡ። 30የኢያሪኮ ግንብ በእምነት የወደቀው ለሰባት ቀናት ከተከበበ በኋላ ነበር። 31ሴተኛ አዳሪዋ ረዓብ ሰላዮቹን ለደህንነታቸው ተጠንቅቃ ስለተቀበለቻቸው ከማይታዘዙት ጋር ያልጠፋችው በእምነት ነበር።32-33እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ምን ልበል? በእምነት መንግሥታትን ድል ስላደረጉት፣ ፍትህን ስላስከበሩትና የተስፋ ቃሎችን ስለተቀበሉት ስለነጌደዎን፣ ባርቅ፣ ሳምሶን፣ ዮፍታሄ፣ ዳዊት፣ ሳሙኤልና ነቢያት እንዳልናገር ጊዜ ያጥረኛል። 34እነርሱ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፣ የእሳትን ኃይል አጠፉ፣ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፣ ከበሽታ ተፈወሱ፣ በጦርነት ኃያላን ሆኑ፥ የባዕድን ሠራዊት አባረሩ።35ሴቶች ሙታናቸው ከሞት ተነሡላቸው። ሌሎች የተሻለውን ትንሣኤ ያገኙ ዘንድ ከእስር መፈታታቸውን ለመቀበል እምቢ በማለት ተሠቃዩ። 36የተቀሩት ደግሞ በስድብና በግርፋት፣ እንዲያውም በሰንሰለት በመታሰር ተሠቃዩ። 37በድንጋይ ተወገሩ። በመጋዝ ለሁለት ተሰነጠቁ። በሰይፍ ተገደሉ። ይህ ዓለም ስላልተገባቸው 38በምድረበዳ፣ በተራሮች፣ በዋሻዎችና በየጉድጓዱ እየተጎሳቆሉ፣ መከራ እየተቀበሉና ግፍ እየተፈጸመባቸው የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው በመንከራተት ዞሩ።39እነዚህ ሰዎች ሁሉ ስለ እምነታቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው ቢሆኑም የተሰጣቸውን ተስፋ አልተቀበሉም። 40እነርሱ ያለ እኛ ፍጹም ስለማይሆኑ እግዚአብሔር ለእኛ የተሻለውን ነገር አስቀድሞ ሰጠን።
1እንደነዚህ ያሉ እጅግ ብዙ ምስክሮች ስላሉን፣ የሚከብደንን ነገር ሁሉና በቀላሉ የሚጠላልፈንን ኃጢአት አሽቀንጥረን እንጣል። ከፊታችን ያለውንም ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ። 2በእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይኖቻችን እንትከል። እርሱ ከፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉንና መስቀሉ የሚያስከትለውን ውርደት ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል። 3እንዳትደክሙ ወይም ልባችሁ እንዳይዝል፣ ከኃጢአተኞች የተሰነዘረበትን እንዲህ ያለውን የጥላቻ ንግግር የታገሠውን እርሱን አስቡ።4ደም እስከማፍሰስ ድረስ ኃጢአትን አልተቃወማችሁም፣ አልታገላችሁትምም። 5ደግሞም እንደ ልጆች፡ “ልጄ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቅልል፣ በሚቀጣህም ጊዜ ልብህ አይዛል። 6ጌታ የሚወደውን ይገሥጻል፣ የሚቀበለውን ማንኛውንም ልጅ ይቀጣል" በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ምክር ረስታችኋል።7አባት በልጆቹ እንደሚደረግ እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ስለሚያደርግ፣ መከራን እንደ ተግሣጽ በመቁጠር ታገሡ። ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? 8ነገር ግን እኛ ሁላችን ከምንካፈለው ተግሣጽ ውጭ ከሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።9ከዚህም በላይ የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እኛም እናከብራቸው ነበር። ይልቁንስ መንፈስ ለሆነው አባት እየታዘዝን መኖር የቱን ያህል ይገባናል? 10በእርግጥ አባቶቻችን ለእነርሱ መልካም መስሎ እንደታያቸው ለጥቂት ጊዜ ይቀጡን ነበር፣ እግዚአብሔር ግን የእርሱን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለጥቅማችን ያቀጣናል። 11ቅጣት በወቅቱ የሚያም እንጂ አስደሳች አይደለም። ይሁን እንጂ፣ ለለመዱት በመጨረሻ ሰላማዊ የጽድቅ ፍሬን ያፈራል።12ስለዚህ የዛሉ እጆቻችሁን ወደ ላይ አንሡ፣ የደከሙ ጉልበቶቻችሁንም እንደገና አበርቱ፤ 13የሚያነክስ ማንም ቢኖር እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ እግሮቻችሁ የሚራመዱባቸውን መንገዶች ቀና አድርጉ።14ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ፣ ቅድስናንም ተከታተሉ፣ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ሊያይ አይችልም። 15ማንም ከእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድል፣ መራራ ሥርም አድጎ እንዳያስጨንቅና ብዙዎችን እንዳይመርዝ ተጠንቀቁ። 16ለአንድ መብል ብሎ ብኩርናውን እንደሸጠ እንደ ኤሳው እግዚአብሔርን የማይፈራ፣ ወይም ሴሰኛ የሆነ ማንም እንዳይኖር ተጠንቀቁ። 17ከዚያ በኋላ በረከትን ለመውረስ እያለቀሰ በትጋት ቢፈልግም፣ ከአባቱ ዘንድ የይቅርታ እድል እንዳጣና እንደተጣለ ታውቃላችሁ።18የሚቃጠል እሳት፣ ጨለማ፣ ጭጋግና ማዕበል ወዳለበት በእጅ ሊነካ ወደሚችል ተራራ ገና አልመጣችሁም። 19የሰሙትም ሌላ ቃል እንዳይነገራቸው እስከሚለምኑ ወዳደረሳቸው ቃልን ወደሚያሰማ ድምጽ ወይም የመለከት ጩኹት ገና አልመጣችሁም። 20ይህም፣ “እንስሳም እንኳ ቢሆን ተራራውን ከነካ በድንጋይ ይወገር” ተብሎ የተሰጠውን ትእዛዝ ሊሸከሙት አልቻሉም። 21ሙሴ፣ “እጅግ ስለፈራሁ እየተንቀጠቀጥሁ ነኝ” እስከሚል ድረስ ይህ ስፍራ አስፈሪ ነበር።22አሁን ግን፣ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደሆነችው ወደ ጽዮን ተራራ፣ አእላፋት መላእክት በደስታ ወደሚያመልኩባት ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መጥታችኋል፤ 23በሰማይ ወደሚገኙት የበኩራን ሁሉ ጉባኤ፣ የሁሉም ፈራጅ ወደሆነው እግዚአብሔርና ፍጹም የተደረጉ የጻድቃን መንፈሶች ወዳሉበት መጥታችኋል፤ 24የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደሆነው ኢየሱስና ከአቤል ደም የተሻለውን ወደሚናገር ወደተረጨው ደም ደርሳችኋል።25የሚናገራችሁን እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ። እነርሱ በምድር ላይ ሆኖ ያስጠነቀቃቸውን እምቢ በማለታቸው ካላመለጡ፣ በሰማይ ሆኖ ከሚያስጠነቅቀን በእርግጥ አናመልጥም። 26በዚያን ጊዜ ድምጹ ምድርን አናወጠ። ነገር ግን፣ “አንድ ጊዜ ደግሜ ምድርን ብቻ ሳይሆን ሰማያትንም አናውጣለሁ” በማለት አሁን ተስፋ ሰጥቷል።27“አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚል ቃል፣ ያልተናወጡ ነገሮች መጽናታቸውን፣ የተናወጡት ማለትም የተፈጠሩት ነገሮች መወገዳቸውን ያመላክታል። 28ስለዚህ፣ ሊናወጥ የማይችል መንግሥት ስለተቀብልን አምላካችንን እናመስግነው፣ ደግሞም እግዚአብሔርን ተቀባይነት ባለው በአክብሮትና በፍርሃት እናምልከው፣ 29ምክንያቱም አምላካችን የሚባላ እሳት ነው።
1በወንድማማችነት ፍቅር መዋደዳችሁን ቀጥሉ። 2እንግዶችን መቀበል አትርሱ፣ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲያደርጉ ሳያውቁት መላእክትን አስተናግደዋል።3ከእነርሱ ጋር እንደታሰረ ሆናችሁ፣ በሰውነታችሁም እንደ እነርሱ መከራን እንደሚቀበል ሆናችሁ በእስራት ያሉትን አስቡ። 4ጋብቻ በሁሉም ዘንድ የተከበረ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በሴሰኞችና በአመንዝራዎች ላይ ይፈርድባቸዋል።5አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር የጸዳ ይሁን። እግዚአብሔር ራሱ፣ “እኔ ፈጽሞ አልተውህም፣ ደግሞም አልጥልህም” ስላለ፣ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ። 6ስለዚህ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰውስ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” ብለን በድፍረት እንናገራለን።7የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን አስቡ፣ የምግባራቸውንም ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሏቸው። 8ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬና ለዘላለምም ያው ነው።9በልዩ ልዩ እንግዳ ትምህርቶች አትወሰዱ፣ ለሚከተሏቸው ሰዎች ፋይዳ የሌላቸውን የአመጋገብ ሥርዓቶች በመጠበቅ ሳይሆን ልብ በጸጋ ሲጸና መልካም ነው። 10በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉት ከእርሱ እንዲበሉ ያልተፈቀደላቸው መሠዊያ አለን። 11ሊቀካህናቱ ለኃጢአት ስርየት የተሠዋውን የእንስሳት ደም ወደ ቅድስት ያመጣል፣ የእንስሳቱ ሥጋ ግን ከሰፈር ውጭ ይቃጠላል።12ደግሞም ኢየሱስ ሰዎችን በገዛ ደሙ ለመቀደስ ከከተማይቱ ቅጥር ውጭ መከራን ተቀበለ። 13ስለዚህ እኛም እርሱ የተሸከመውን ውርደት ተሸክመን ከሰፈር ውጭ ወደርሱ እንሂድ። 14በዚህ ምድር ምንም ዓይነት ዘላቂ ከተማ የለንም። ነገር ግን የምትመጣውን ከተማ እንጠብቃለን።15የስሙን ታላቅነት የሚናገሩ የከንፈሮቻችንን ፍሬ፣ ማለትም የምስጋና መሥዋዕቶችን ያለማቋረጥ በኢየሱስ በኩል ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይገባናል። 16ደግሞም መልካም ማድረግንና እርስ በርስ መረዳዳትን አትርሱ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚደሰተው እንደነዚህ ባሉ መሥዋዕቶች ነው። 17ተጠያቂነት ስላለባቸው ለነፍሳችሁ እንክብካቤ ለሚያደርጉ ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፣ ተገዙላቸውም። ለእናንተ ስለማይጠቅም በሐዘን ሳይሆን በደስታ እንዲንከባከቧችሁ ታዘዟቸው።18በሁሉም ነገር የከበረ ሕይወት ለመኖር የሚፈልግ ንጹሕ ኅሊና ስላለን ጸልዩልን። 19ወደ እናንተ ቶሎ መመለስ እንድችል ይበልጥ ይህን እንድታደርጉ አበረታታችኋለሁ።20-21እንግዲህ በዘላለም ኪዳን ደም የበጎች ታላቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን፣ ከሙታን ያስነሣው የሰላም አምላክ እግዚአብሔር፣በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በእኛ ውስጥ የሚሠራውን፣ በእርሱ ፊት ደስ የሚያሰኘውን ፈቃዱን እንድታደርጉ በማናቸውም መልካም ነገር ያስታጥቃችሁ። ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን። አሜን።22ወንድሞች ሆይ፤ አሁን በዐጭሩ የጻፍሁላችሁን ማበረታቻ እንድትቀበሉ አደፋፍራችኋለሁ። 23ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደተፈታ ዕወቁ፣ ቶሎ ከመጣም ከእርሱ ጋር አብሬ አያችኋለሁ።24ለመሪዎችና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በኢጣልያ ያሉት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። 25ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
1በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር እስረኛና አገልጋይ የሆነ ያዕቆብ በክርስቶስ ኢየሱስ ለሚያምኑና በመላው ዓለም ለተበተኑት ለአሥራ ሁለቱ ነገዶች ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡2ወንድሞቼ ሆይ፣ በልዩ ልዩ ፈተናዎች ውስጥ ማለፋችሁን እጅግ ደስ እንደሚያሰኝ ነገር ቊጠሩት፡፡3በፈተና ውስጥ ሳላችሁ በእግዚአብሔር ስታምኑ ይበልጥ ሌሎች ፈተናዎችን በትዕግሥት ለማሳለፍ የሚረዱዋችሁ መሆኑን ትረዳላችሁ፡፡4ክርስቶስን በሁሉም መንገድ ትከተሉ ዘንድ እስከ መጨረሻው በፈተና ጽኑ፤ ያንጊዜ መልካም ማድረግ አይከብዳችሁም፡፡5ከእናንተ አንዱ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ከፈለገ፣ በሚጠይቀው ላይ ሳይቈጣ በልግሥና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይጠይቅ፡፡6እግዚአብሔርን ስትለምኑ፣ የምትጠይቁትን እንደሚሰጣችሁ እመኑ፤ መልስ እንደሚሰጣችሁና ሁልጊዜም እንደሚረዳችሁ አትጠራጠሩ፤ የሚጠራጠሩ ሰዎች እግዚአብሔርን ሊከተሉት አይችሉም፤ መጠራጠር ልክ ተመልሶ እንደሚመጣ፣ ደግሞም በዚያው አቅጣጫ መጓዝን እንደማይቀጥል የባሕር ማዕበል ያለ ነገር ነው፡፡7በእርግጥ የሚጠራጠሩ ሰዎች የሚጠይቁትን ነገር ለመፈጸም እግዚአብሔር አንድ ነገር ሊያደርግ እንደሚችል አያምኑም፡፡8እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን ለመከተል ወይም ላለመከተል ያልወሰኑ ናቸው፤ እነዚህም የሚናገሩትን ነገር የማያደርጉ ሰዎች ናቸው፡፡9ድሀ የሆኑ አማኞች እግዚአብሔር ስላከበራቸው ደስ ሊሰኙ ይገባል፡፡10ባለጠጋ የሆኑ አማኞችም እግዚአብሔር ትሑታን ስላደረጋቸው ደስ ሊሰኙ ይገባል፤ ልክ የበረሃ አበቦች እንደሚደርቁ ሁሉ፣ እነርሱም ሆኑ ሀብታቸው የሚያልፉ ናቸውና፡፡11ፀሐይ በሚወጣ ጊዜ ሞቃታማ የሆነው ነፋስ ተክሎችን ያደርቃል፤ ደግሞም አበቦችን በምድር ላይ እንዲወድቁም ሆነ በውበታቸው እንዳይቀጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ባለ ጠጎች ልክ እንደሚሞቱ አበቦች ሁሉ ገንዘብን እየሰበሰቡ ሳሉ ይሞታሉ፡፡12በመከራ የሚጸኑትን ሰዎች እግዚአብሔር ያከብራቸዋል፤ ለሚወድዱት ሁሉ ተስፋ እንደ ሰጠው ለዘላለም እንዲኖሩ በማድረግ ብድራታቸውን ይከፍላቸዋል፡፡13በኃጢአት ስንፈተን እግዚአብሔር እየፈተነን ነው ብለን ልናስብ አይገባም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ክፉን እንድንሠራ አይፈልግምና፤ ክፉን እንዲያደርግ ማንንም አይፈትንምና፡፡14እያንዳንዱ ሰው የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲታለልና ሲሳብ ነው።15ክፉ ምኞት ከተፀነሰ በኋላ ኀጢአት ይወለዳል፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞት ይወለዳል።16የተወደዳችሁ ወንድሞቼ አትታለሉ።17ማንኛውም መልካምና ፍጹም ስጦታ እንደሚዘዋወር ጥላ ከማይለዋወጠው ከላይ ከሰማይ ከብርሃናት አባት ይወርዳል።18በፍጥረታቱ መካከል እንደ በኵራት እንድንሆን እግዚአብሔር በእውነት ቃል ሕይወት ሊሰጠን ወደደ።19የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን ዕወቁ። ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገዬ፣ ለመቆጣትም የዘገዬ ይሁን!20ምክንያቱም የሰው ቊጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣም።21ስለዚህ ርኵሰትንና በየቦታው ሞልቶ ያለውን ክፋት አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁ የተተከለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።22ለቃሉ ታዘዙ እንጂ፣ ሰሚዎች ብቻ በመሆን ራሳችሁን አታታልሉ።23ማንም ቃሉን እየሰማ ቃሉ የሚለውን ባያደርግ፣ ፊቱን በመስታወት እንደሚያይ ሰው ይሆናል።24ፊቱን አይቶ ይሄዳል፤ ምን እንደሚመስል ግን ወዲያው ይረሳዋል።25ፍጹሙንና ነጻ የሚያወጣውን ሕግ በጥንቃቄ የሚመለከትና የሚኖርበት እንጂ፣ ሰምቶ እንደሚረሳው ያልሆነ ሰው በሚያደርገው ሁሉ የተባረከ ይሆናል።26አንድ ሰው ሃይማኖተኛ ነኝ እያለ፣ አንደበቱን ግን ባይቆጣጠር፣ ልቡን ያስታል፤ ሃይማኖቱም ከንቱ ነው።27በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት ንጹሕና ርኵሰት የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው፤ አባት የሌላቸውንና መበለቶችን በችግራቸው መርዳት፤ በዓለም ካለ ርኵሰት ራስን መጠበቅ።
1ወንድሞች ሆይ፤ ለአንዳንዶች አድልዎ እያደረጋችሁ የክብር ጌታ የጌታችን አየሱስ ክርስቶስን እምነት እንከተላለን አትበሉ።2የወርቅ ቀለበት ያደረገና የሚያማምሩ ልብሶች የለበሰ ወደ ስብሰባችሁ ሲገባና እንዲሁም አዳፋ ልብሶች የለበሰ ድኻ ቢገባ3ትኵረታችሁ የሚያማምሩ ልብሶች የለበሰው ሰው ላይ ይሆንና፣ “እዚህ ደኅና ቦታ ላይ ተቀመጥ” ትሉታላችሁ፤ ድኻውን ግን፣ “እዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ በታች ተቀመጥ” ትሉታላችሁ4ታዲያ፣ በመካከላችሁ አድልዎ ማድረጋችሁ አይደለምን፤ ደግሞስ በክፉ ዐሳብ የተያዛችሁ ፈራጆች መሆናችሁ አይደለምን?5የተወደዳችሁ ወንድሞች ስሙ፤ በእምነት ባለ ጸጋ እንዲሆኑና፣ እርሱን ለሚወዱ ቃል የገባላቸውን መንግሥት እንዲወርሱ እግዚአብሔር የዚህ ዓለም ድኾችን አልመረጠምን?6እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ! የሚጨቁኗችሁ ባለ ጸጎች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጎትቱዋችሁስ እነርሱ አይደሉምን?7የተጠራችሁበትን መልካም ስም የሚሳደቡ ባለ ጸጎቹ አይደሉምን?8ይሁን እንጂ፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ተብሎ እንደ ተጻፈው የከበረውን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤9ለአንዳንዶች አድልዎ ብታደርጉ ግን፣ ኃጢአት ትሠራላችሁ፤ እንደ ሕግ ተላላፊዎችም ትቆጠራላችሁ።10ምክንያቱም ሕጉን የሚፈጽም፣ በአንዱ ግን የሚሰናከል፣ ሕጉን ሁሉ እንደ ተላለፈ ይቆጠራል!11“አታመንዝር” ያለው እግዚአብሔር፣ “አትግደልም” ብሎአልና። ባታመነዝር ሆኖም ግድያ ብትፈጽም፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ተላልፈሃል።12ስለዚህ ነጻ በሚያወጣው ሕግ እንደሚፈረድባቸው ሰዎች ተናገሩ፤ ደግሞም ታዘዙ።13ምክንያቱም ምሕረት በማያደርጉ፣ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይመጣባቸዋል። ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል!14ወንድሞቼ ሆይ፣ አንድ ሰው እምነት እንዳለው ቢናገር፣ ሥራ ግን ባይኖረው ምን ይጠቅማል? ያ እምነት ሊያድነው ይችላልን?15አንድ ወንድም ወይም እኅት ልብስና የዕለት ምግብ ባይኖራቸው16ከእናንተ አንዱ፣ “በሰላም ሂዱ፤ አይብረዳችሁ፤ በደንብ ጥገቡ” ቢላቸው፤ ለአካል የሚያስፈልጉ ነገሮችን ግን ባትሰጧቸው፣ ምን ይጠቅማል?17ሥራ የሌለው እምነትም እንዲሁ በራሱ የሞተ ነው።18ምናልባትም አንዱ፣ “አንተ እምነት አለህ እኔ ደግሞ ሥራ አለኝ” ሥራ የሌለው እምነትህን አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይል ይሆናል።19አንድ እግዚአብሔር መኖሩን ታምናለህ፤ ትክክል ነህ። አጋንንትም ይህን ያምናሉ፤ በፍርሃትም ይንቀጠቀጣሉ።20አንተ ሞኝ፣ እምነት ያለ ሥራ ከንቱ መሆኑን ማወቅ ትፈልጋለህ?21አባታችን አብርሃም፣ ልጁ ይስሐቅን መሠዊያው ላይ ባቀረበ ጊዜ በሥራ ጸድቆ አልነበረምን?22እምነት በሥራው ታየ፤ በዚያው ሥራ እምነት ዓላማውን ፈጸመ።23“አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ። ስለዚህም አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ።24ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን፣ በሥራ እንደሚጸድቅ ታያለህ።25በተመሳሳይ ሁኔታ ጋለሞታዪቱ ረዓብ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቅችምን?26ከመንፈስ የተለዬ አካል ሙት እንደ ሆነ ሁሉ፣ ከሥራ የተለዬ እምነትም የሞተ ነው።
1ወንድሞቼ፣ እኛ የባሰውን ፍርድ እንደምንቀበል በመገንዘብ፣ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አትሁኑ።2ሁላችንም በብዙ መንገድ እንሰናከላለን። በንግግሩ የማይሰናከል እርሱ ሰውነቱን ሁሉ መቆጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።3ፈረሶች አፍ ውስጥ ልጓም ብናደርግ ይታዘዙልናል፤ መላ አካላቸውንም መቆጣጠር እንችላለን።4ምንም እንኳ መርከቦች ግዙፍና በኃይለኛ ነፋስ የሚነዱ ቢሆኑም፣ የመርከቡ ነጂ በትንሽ መሪ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንደሚመራቸው አስተውሉ።5እንዲሁም አንደበት ትንሽ የሰውነት ክፍል ሆኖ፣ በታላላቅ ነገሮች ይኵራራል። ጫካ የቱንም ያህል ሰፊ ቢሆን፣ በትንሽ እሳት ፍንጣሪ እንደሚቃጠል ልብ አድርጉ!6አንደበትም እንዲሁ እሳት ነው፤ ሰውነትን ሁሉ የሚያረክስና የሕይወትንም መንገድ የሚያቃጥል፣ እርሱ ራሱም በገሃነም እሳት የሚቃጠል ሰውነታችን ብልቶች መካከል ያለ ኃጢአተኛ ዓለም ነው።7ማንኛውም እንስሳ፣ ወፎች፣ በምድር የሚሳቡና ባሕር ውስጥ ያሉ ፍጥረቶች በሰው ተገርተዋል፤8ነገር ግን ከሰው መካከል ማንም አንደበትን መግራት አልቻለም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ዕረፍት የለሽ ክፉ ነው።9በአንደበት ጌታና አባታችንን እንባርካለን፤ በዚያው አንደበት በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን።10ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣል። ወንድሞቼ፣ እንዲህ መሆን የለበትም።11ከአንድ ምንጭ ጣፋጭና መራራ ውሃ ይወጣልን?12ወንድሞቼ፣ የበለስ ዛፍ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ያበቅላልን? እንዲሁም ከጨው ውሃ ንጹሕ ውሃ ሊገኝ አይችልም።13ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? ያ ሰው ከጥበብ በሚገኝ ትሕትና በሥራው መልካም ሕይወትን ያሳይ።14በልባችሁ መራራ ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ካለ ግን አትኵራሩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።15ይህ ከላይ የሚመጣ ጥበብ አይደለም፤ ይልቁንም ምድራዊ፣ መንፈሳዊ ያልሆንና አጋንንታዊም ነው።16ምክንያቱም ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ባለበት ሁከትና ክፉ ሥራ ይኖራል።17ከላይ የሚመጣው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ከዚያም ሰላም ወዳድ፣ ጨዋ፣ ደግ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላበት፣ ለሰዎች አድልዎ የማያደርግ ቅን ነው።18ሰላምን ለሚያደርጉ የጽድቅ ፍሬ በሰላም ይዘራል።
1በእናንተ መከከል ያለው ፀብና ጭቅጭቅ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ ውጊያ ከገጠሙት ክፉ ምኞቶቻችሁ የመጣ አይደለምን?2የሌላችሁን ትመኛላችሁ። ትገድላላችሁ፤ ማግኘት ያልቻላችሁትን በብርቱ ታሳድዳላችሁ። ትጣላላችሁ፤ ትዋጋላችሁ፤ ይሁን እንጂ፣ ከእግዚአብሔር ስለማትለምኑ አታገኙም።3ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም፤ ምክንያቱም ክፉ ምኞቶቻችሁን ለማሳካት ክፉ ነገሮችን ስለምትለምኑ ነው።4እናንት አመንዝሮች! የዓለም ወዳጅ መሆን፣ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን እንደ ሆነ አታውቁም? ስለዚህ ማንም የዓለም ወዳጅ መሆን ቢፈልግ፣ የእግዚአብሔር ጠላት ይሆናል።5ወይስ እግዚአብሔር እኛ ውስጥ ያኖረው መንፈስ ለእርሱ ብቻ እንድንሆን አብዝቶ ይቀናል የሚለው የመጽሐፍ ቃል በከንቱ የተነገረ ይመስላችኋል?6እግዚአብሔር ግን አብዝቶ ጸጋውን ይሰጣል፤ መጽሐፍ፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” የሚለው በዚህ ምክንያት ነው።7ስለዚህ፣ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል።8ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፣ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች እጆቻችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።9እዘኑ፤ አልቅሱ፤ ጩኹ! ሳቃችሁን ወደ ሐዘን፣ ደስታችሁን ወደ ትካዜ ለውጡ።10በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ያደርጋችኋል።11ወንድሞች ሆይ፣ እርስ በርስ አትወነጃጀሉ። ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙ ላይ የሚፈርድ ሕጉ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በእግዚአብሔርም ሕግ ላይ ይፈርዳል። ሕጉ ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ ፈራጆች እንጂ፣ ሕጉን አድራጊዎች አይደላችሁም።12ሕጉን የሰጠና በሕጉም የሚፈርድ፣ ማዳንም መግደልም የሚቻለው አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ታዲያ፣ በባልንጀራህ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?13“ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ አገር እንሄዳለን፤ እዚያ አንድ ዓመት እንቆያለን፤ ነግደን እናተርፋለን” የምትሉ እናንተ ሰዎች ስሙ።14ነገ የሚሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? ሕይወታችሁስ ምንድን ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ ጭጋግ አይደላችሁምን?15ይልቁንም፣ “ጌታ ቢፈቅድ እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን” ማለት ይኖርባችኋል።16አሁን ግን በዕቅዶቻችሁ ትመካላችሁ። እንዲህ ያለው ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው።17ስለዚህ መልካም የሆነውን ማድረግ እንዳለበት እያወቀ ለማያደርግ ለዚያ ሰው ኃጢአት ይሆንበታል።
1እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስለሚመጡባችሁ ክፉ ነገሮች አልቅሱ ዋይ ዋይም በሉ።2ሀብታችሁ ሻግቶአል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል።3ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም እናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል። ለመጨረሻው ቀን ሀብታችሁን አከማችታችኋል።4ልብ በሉ፤ እርሻችሁን ላጨዱ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ ይጮኻል! የአጫጆቹም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ጆሮ ደርሶአል።5በምድር ላይ በምቾትና በመንደላቀቅ ኖራችኋል። ለዕርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል።6እናንተን ያልተቃወመውን ጻድቅ ሰው ኮንናችሁታል፤ ገድላችሁታል።7ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፣ የመጀመሪያውና የኋለኛው ዝናብ እስኪመጣ ድረስ የምድርን ፍሬ በትዕግሥት እንደሚጠብቅ ገበሬ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ።8እናንተም እንዲሁ ታገሡ፤ ልባችሁን አዘጋጁ፤ ምክንያቱም የጌታ መምጫ ቅርብ ነው።9ወንድሞች ሆይ፤ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ። ልብ በሉ፤ ፈራጁ በሩ ላይ ቆሞአል።10በጌታ ስም የተናገሩ ነቢያትን መከራና ትዕግሥት እንደ ምሳሌ ውሰዱት።11ልብ በሉ፤ በትዕግሥት የጸኑትን፣ “የተባረኩ” እንላቸዋለን። ስለ ኢዮብ ትዕግሥት ሰምታችኋል፤ ጌታ ለኢዮብ የነበረውንም ዓላማ ታውቃላችሁ፤ ጌታ እጅግ ሩኅሩኅና መሐሪ ነው።12ወንድሞቼ ሆይ፣ ከሁሉም በላይ አትማሉ፤ በሰማይም ሆነ በምድር ወይም በሌላ ነገር አትማሉ። ቃላችሁ “አዎን” ካላችሁ፣ “አዎን” ይሁን፤ “አይደለም” ካላችሁም፣ “አይደለም” ይሁን።13በእናንተ መካከል መከራ የደረሰበት አለ? እርሱ ይጸልይ። ደስ ያለው አለ? እርሱ ይዘምር።14በእናንተ መካከል የታመመ አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት እየቀቡ ይጸልዩለት፤15የእምነት ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሳል፤ ጌታም ያስነሣዋል። ኃጢአት አድርጎ ከሆነም እግዚአብሔር ይቅር ይለዋል።16እንዲሁ ጌታ ከበሽታ ሊፈውስና ኃጢአትን ይቅር ሊል ስለሚችል ያደረጋችሁትን ኃጢአት በተመለከተ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተናዘዙ፡፡ ጻድቃን ሰዎች ከጸለዩና አንድ ነገር እንዲያደርግላቸው ጌታን አጥብቀው ከጠየቁት፣ እግዚአብሔር ይገለጣል፤ ደግሞም በእርግጠኝነት ያን ነገር ያደርገዋል፡፡17ነቢዩ ኤልያስ እንደኛው ያለ ሰው ቢሆንም፣ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፡፡ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወራት ጊዜ ያህልም ዝናብ አልነበረም፡፡18ከዚያም ዝናብ እንዲዘንብ እግዚአብሔርን እየለመነ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ዝናብን ላከ፣ ተክሎችም ዐደጉና ሰብልን ሰጡ፡፡19ወንድቼና እኅቶቼ ሆይ፥ ከእናንተ አንዱ ዕውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል መልእክት መታዘዝ ቢያቆም፣ ከእናንተ አንዱ ያደርገው ዘንድ እግዚአብሔር ለዚያ ሰው የነገረውን ነገር በመንገር ሊያሳምነው ይገባል፡፡20የሚያሳምነው ሰውም ኃጢአት እየሠራ የነበረውን ሰው ተናግሮ ስሕተት ከመሥራት እንዲመለስ ስላስቻለው፣ እግዚአብሔር ያንን ሰው ከመንፈሳዊ ሞት ያድነዋል፤ ደግሞም ብዙ የሆኑት ኃጢአቶቹን ይቅር ይልለታል፡፡
1የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጴጥሮስ፤ በጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በእስያና በቢታንያ ተበትነው በመጻተኝነት ለሚኖሩ፤ ለተመረጡት፤2እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመታዘዝ በደሙ ለተረጩትና በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሱት፤ ጸጋ ለእናንተ ይሁን፤ ሰላማችሁም ይብዛ።3የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በመነሣቱ ምክንያት ላገኘነው ርስት ዋስትና እንዲሆነን በታላቅ ምሕረቱ አዲስ ልደትን ሰጠን፤4ይህም የማይጠፋ፣ የማይበላሽ እና የማያረጅ ርስት በመንግሥተ ሰማይ ተጠብቆላችኋል።5እናንተም በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኅይል ተጠብቃችኋል።6ምንም እንኳን አሁን በብዙ ልዩ ልዩ ዐይነት መከራ ማዘናችሁ ተገቢ ቢሆንም፣ በዚህ እጅግ ደስ ይላችኋል።7ይኸውም፣ በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም፣ ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እምነታችሁ እንዲፈተን ነው። ይህ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ አምነታችሁ ምስጋናን ክብርንና፣ ውዳሴን እንዲያስገኝላችሁ ነው።8ኢየሱስ ክርስቶስን ባታዩትም እንኳ ትወዱታላችሁ፤ አሁን ባታዩትም በእርሱ ታምናላችሁ፤ ሊነገር በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት በጣም ደስ ይላችኋል፤9አሁን የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ ነውና።10እናንተ ስለምትቀበሉት ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ይፈልጉና በጥልቅ ይመረምሩ ነበር፤11የሚመጣው መዳን ምን ዐይነት እንደ ሆነ ለማወቅ ይመረምሩ ነበር፤ እንዲሁም በእነርሱ ውስጥ የነበረው የክርስቶስ መንፈስ ስለ ክርስቶስ መከራና ከመከራው በኋላ ስለሚሆነው ክብር አስቀድሞ የተናገራቸው በምን ጊዜና እንዴት እንደሚፈጸም ይመረምሩ ነበር። ነቢያቱ ያገለግሉ የነበሩት እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳልነበረ ተገልጦላቸዋል፤12ይኸውም ከሰማይ በተላከው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወንጌልን ያበሠሩአችሁ ሰዎች የነገሩአችሁን በመግለጥ ነው፤ መላእክትም እንኳ ይህ ነገር ሲገለጥ ለማየት ይመኙ ነበር።13ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጠቁ፤ ጠንቃቆች ሁኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ በምታገኙት ጸጋ ላይ ፍጹም መተማመን ይኑራችሁ።14ታዛዦች ልጆች እንደ መሆናችሁ ባለማወቅ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።15ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ፣ እናንተም በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤16ምክንያቱም «እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ» ተብሎ ተጽፎአል።17ሳያዳላ በእያንዳንዱ ሰው ላይ እንደየሥራው የሚፈርደውን «አባት» ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፣ በእንግድነት ዘመናችሁ እርሱን በማክበር ኑሩ።18ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከማይረባ ሕይወት የተዋጃችሁት በሚጠፋ ነገር ማለትም በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፤19ይልቁንም የተዋጃችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም፣ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው።20ክርስቶስ የተመረጠው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ነው፤ አሁን ግን በመጨረሻው ዘመን ለእናንተ ተገለጠ።21በእርሱ አማካይነት፣ ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ታምናላችሁ። ይኸውም እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን ነው።22ለእውነት በመታዘዝ ለእውነተኛ የወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልብ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።23ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ ነገር ግን በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው።24ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፣ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤25የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። የተሰበከላችሁም ወንጌል መልእክቱ ይህ ነው።
1እንግዲህ ክፋትን ፣ ማታለልን ፣ ግብዝነትን፣ ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ።2በድነታችሁ በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹህ የሆነውን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤3ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ ከሆነ፣4በሰው ዘንድ ወደ ተናቀው፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠውና ክቡር ወደ ሆነው ወደዚህ ሕያው ድንጋይ ቅረቡ።5ደግሞም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ቅዱሳን ካህናት ትሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ትሠራላችሁ።6በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈው «እነሆ፤ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም» ።7እንግዲህ ለምታምኑት ለእናንተ እርሱ ክቡር ነው፤ ለማያምኑት ግን፣«ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ»8እንደዚሁም ደግሞ «ሰዎችን የሚያሰናክልና የሚጥላቸውም ዐለት ሆነ»። የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ የተመደቡት ለዚህ ነውና።9እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር የራሱ ያደረጋችሁ ሕዝብ ናችሁ።10ቀድሞ የእርሱ ሕዝብ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆናችኋል፤ ቀድሞ ምሕረትን አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።11ወዳጆች ሆይ፤ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍሳችሁን ከሚዋጉ ከኅጢኣት ምኞቶች እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።12ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል አኗኗራችሁ መልካም መሆን አለበት።13ስለ ጌታ ብላችሁ ለምድራዊ ባለ ሥልጣን ሁሉ ታዘዙ፤14የበላይ ባለ ሥልጣን ስለ ሆነ ለንጉሥ ቢሆን፣ ወይም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት፣ በጎ አድራጊዎችን ለማመስገን እርሱ ለሾማቸው ገዦች ታዘዙ፤15ምክንያቱም፣ መልካም በማድረግ የአላዋቂዎችን ከንቱ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።16እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ሆናችሁ በነጻነት ኑሩ እንጂ ነጻነታችሁን የክፋት መሸፈኛ አታድርጉት።17ለሰው ሁሉ ተገቢውን አክብሮት ስጡ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።18እናንተ አገልጋዮች ፤ ለመልካሞችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለክፉዎችም በፍጹም አክብሮት ታዘዙ።19ስለ እግዚአብሔር ሲል የግፍ መከራን የሚቀበል ሰው ምስጋናን ያገኛል።20ክፉ ሥራ ሠርታችሁ ስትቀጡ ብትታገሡ ምን ያስመሰግናችኋል? ነገር ግን መልካም ሥራ ሠርታችሁ መከራ ስትቀበሉ ብትታገሡ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስመሰግናችኋል።21የተጠራችሁት ለዚህ ነው፤ ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የእርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌ ሊተውላችሁ ነው።22እርሱ ኅጢአት አላደረገም፥ ተንኵልም በአፉ አልተገኘበትም፤23ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤24ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።25ቀድሞ ሁላችሁም እንደ ጠፉ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
1ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ እንኳ፣ ሚስቶቻቸው ቃል ሳይናገሩ በመልካም አኗኗራቸው ሊማርኳቸው ይችላሉ፤2ይህም የሚሆነው ለእነርሱ ያላችሁን አክብሮት በንጹሕ አኗኗራችሁ ሲመለከቱ ነው።3ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በመንቆጥቆጥ ወይም ጌጠኛ ልብስ በመልበስ አይሁን፤4ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን።5የቀድሞ ቅዱሳት ሴቶች የተዋቡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እነርሱ በእግዚአብሔር የሚደገፉና ለባሎቻቸ የሚታዘዙ ነበሩ።6ሣራም እንደዚሁ አብርሃምን «ጌታዬ» እያለች ትታዘዘው ነበር፣ እናንተም መከራን ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ፣ አሁን የእርሷ ልጆች ናችሁ።7እንዲሁም ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁ ደካማ አጋር መሆናቸውን ዐውቃችሁ፣ የሕይወትን ጸጋ ከእናንተ ጋር አብረው የሚካፈሉ መሆናቸውንም ተገንዝባችሁ አብራችኋቸው ኑሩ። ጸሎታችሁ እንዳይከለከል ይህን አድርጉ።8በመጨረሻም፣ ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ ተዛዘኑ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።9ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት በረከትን ለመውረስ ነው።10ስለዚህ «ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል።11ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም።12የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።»13መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው?14ነገር ግን በጽድቅ ምክንያት መከራ ቢደርስባችሁ ቡሩካን ናችሁ፤ ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።15ይልቁንም፣ ክርስቶስ የከበረ መሆኑን ተረድታችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ስላላችሁ መታመን ምክንያቱን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤16በክርስቶስ ያላችሁን መልካም አናናራችሁን የሚያክፋፉ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ።17እግዚአብሔር የሚፈልገው ይህን ከሆነ፣ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል፤18እንዲሁም ክርስቶስ አንድ ጊዜ ስለ ኀጢአታችን ሞቷል። ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ፣ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ እኛ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤19በመንፈስም ሄዶ በወህኒ ቤት ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤20በወህኒ የነበሩት እነዚህ ነፍሳት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ይጠብቃቸው የነበሩ እምቢተኞች ናቸው፤ እግዚአብሔር ከውሃ ያዳናቸው ጥቂት ሰዎችን፣ ይኸውም ስምንት ሰዎችን ብቻ ነበር።21ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድነው የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤22እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ አለ፤ መላእክት፣ ሥልጣናትና ኀይላትም ተገዝተውለታል።
1ክርስቶስ በሥጋው መከራን ስለ ተቀበለ፣ እናንተም በዚሁ ዐላማ ታጥቃችሁ ተነሡ፤ በሥጋው መከራን የሚቀበል ሰው ኀጢአትን ትቶአል።2እንዲህ ያለው ሰው ከእንግዲህ በሚቀረው ዕድሜ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ምኞት አይኖርም።3አሕዛብ ፈልገው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋ ምኞት፣ በስካር፣ ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ፣ በጭፈራና ርኵስ ከሆነ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።4እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ከአነርሱ ጋር አለመተባበራችሁ እንግዳ ሆኖባቸው ስለ እናንተ ክፉ ያወራሉ።5ነገር ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።6ወንጌል ለሙታን የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤ በሥጋቸው እንደ ሰው ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመንፈስ ይኖራሉ።7የሁሉም ነገር መጨረሻ ተቃርቦአል፤ ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በአስተሳሰባችሁም ጠንቃቆች ሁኑ።8ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ አስቀድሞ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤9ያለ ማጒረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነት ተቀባበሉ።10እንደ ታማኝ የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ መጋቢ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤11የሚናገር ቢኖር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢኖር እግዚአብሔር በሚሰጠው ብርታት ያገልግል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በሁሉም ነገር እንዲከብር ነው፤ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።12ወዳጆች ሆይ፤ እንደ እሳት የሚፈትን ብርቱ መከራ ስትቀበሉ፣ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ በመቍጠር አትደነቁ፤13ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ሐሴት አድርጉ።14ስለ ክርስቶስ ስም ብትሰደቡ፣ የክብር መንፈስ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ስለሚያርፍ ቡሩካን ናችሁ።15ከእናንተ ማንም እንደ ነፍሰ ገዳይ፣ እንደ ሌባ፣ እንደ ክፉ አድራጊ ወይም በሰው ነገር ጣልቃ እንደሚገባ ሰው ሆኖ መከራን አይቀበል፤16ማንም ክርስቲያን በመሆኑ መከራ ቢደርስበት፣ በዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፤17ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ ቀርቦአል። እንግዲህ ፍርድ የሚጀምረው በእኛ ከሆነ፣ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?18እንግዲህ፣ ጻድቅ ሰው የሚድነው በጭንቅ ከሆነ፣ ዐመፀኛውና ኀጢአተኛው እንዴት ይሆን ይሆን?”19ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ መልካም እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነው ፈጣሪ ዐደራ ይስጡ። ።
1እንግዲህ እኔም ከእነርሱ ጋር ሽማግሌና የክርስቶስ መከራ ምስክር የሆንሁ እንዲሁም ወደ ፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን በመካከላችሁ ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤2ስለዚህ፣ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቋቸውም ማድረግ ስላለባችሁ በግዴታ ሳይሆን፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ይሁን፤ ጥቅም ለማግኘት በመስገብገብ ሳይሆን፣ በበጎ ፈቃደኝነት ይሁን፤3እንዲሁም በእናንተ ኀላፊነት ሥር ላለው መንጋ መልካም ምሳሌ ሁኑ እንጂ እንደ ዐለቃ በላያቸው አትሠልጥኑ።4የእረኞች ዐለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።5ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ ምክንያቱም፣ «እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል» እንደ ተባለው፣6እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤7እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።8ጠንቃቆች ሁኑ፤ ንቁም፤ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሳ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል።9በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እንደሚቀበሉ ዐውቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።10ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ ፣ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለማዊ ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችኋል ፤ ያበረታችኋልም።11የገዥነት ሥልጣን ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ይሁን! አሜን።12እንደ ታማኝ ወንድም በምቈጥረው በስልዋኖስ አማካይነት ይህን ዐጭር መልእክት ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍሁላችሁም ልመክራችሁና ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልመሰክርላችሁ ነው። በዚህ ጸጋ ጸንታችሁ ቁሙ።13ከእናንተ ጋር የተመረጠችው፣ በባቢሎን የምትገኘው ሰላምታ ታቀርብላችኋለች፤ እንዲሁም ልጄ ማርቆስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል።14በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁም ሰላም ይሁን።
1ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ስምዖን ጴጥሮስ፤ በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ አማካይነት የተቀበልነውን ዐይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት፤2እግዚአብሔርንና ጌታችንን ኢየሱስን በማወቅ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።3በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እግዚአብሔርን በማወቅ እንድንኖር ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገን ሁሉ በመለኮቱ ኀይል ተሰጥቶናል።4በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ የከበረና ታላቅ ተስፋ ሰጠን፤ ይህንም ያደረገው በክፉ ምኞቶች ሰበብ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ ነው።5በዚህም ምክንያት፣ የሚከተሉትን ነገሮች ለመጨመር ትጉ፣ በእምነታችሁ ላይ ደግነትን፣ በደግነት ላይ ዕውቀትን፣6በዕውቀት ላይ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛት ላይ መጽናትን፣ በመጽናት ላይ እግዚአብሔርን መምሰልን፤7እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ ላይ ወንድማዊ መዋደድን፣ በወንድማዊ መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።8እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ ቢኖሩና በውስጣችሁ ቢያድጉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ዳተኞችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋል።9እነዚህ ነገሮች የሌሉት ግን ዕውር ነው፤ በቅርብ ያለውን ብቻ ያያል፤ ከቀድሞው ኀጢአቱ መንጻቱንም ረስቶአል።10ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ትጉ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም፤11በዚህም ወደ ጌታችንና አዳኛችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል።12ስለዚህ ምንም እንኳ እነዚህን ነገሮች ብታውቋቸውና በያዛችሁት እውነት ብትጸኑም፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዘወትር እናንተን ከማሳሰብ ቸል አልልም።13በዚህ ምድራዊ ድንኳን ውስጥ እስካለሁ ድረስ ስለ እነዚህ ነገሮች እናንተን ማሳሰብ ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ፤14ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገለጠልኝ ይህን ምድራዊ ድንኳን ቶሎ ለቅቄ እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤15ከተለየኋችሁም በኋላ እነዚህን ነገሮች ዘወትር እንድታስቡ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ።16ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ ዳግም መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ ግርማውን በዐይናችን አይተን መሰከርን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ተከትለን አይደለም።17«በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው» የሚል ድምፅ ከግርማዊው ክብር በመጣለት ጊዜ፣ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ሞገስን ተቀብሎአል።18ከእርሱ ጋር በተቀደሰው ተራራ ላይ በነበርንበት ጊዜ ይህን ከሰማይ የመጣውን ድምፅ ሰምተነዋል።19ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ በጨለማ ስፍራ ለሚያበራ መብራት እንደምትጠንቀቁ፣ የንጋቱ ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ።20ይህን በመጀመሪያ ዕወቁ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት የሚገኘውን የትንቢት ቃል ማንም ሰው በራሱ መንገድ የሚተረጒመው አይደለም፤21ምክንያቱም ትንቢት ከእግዚአብሔር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፈቃድ የመጣ አይደለም።
1ሐሰተኞች ነቢያት በእስራኤላውያን መካከል ነበሩ፤ በእናንተ መካከል ደግሞ ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ። ብዙዎች የእነርሱን መዳራት ይከተላሉ።2ከእነርሱም አድራጎት የተነሣ የእውነት መንገድ ይሰደባል።3እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ የሚያታልሉ ቃላትን በመጠቀም ይበዘብዙአችኋል። በእነርሱ ላይ ያለው ፍርድ አይዘገይም፤ መጥፊያቸውም የራቀ አይደለም።4እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሐነም ከጣላቸውና በሰንሰለት አስሮ እስከ ፍርድ ጊዜ ድረስ በጨለማ ውስጥ ካስቀመጣቸው፣5የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ ለጥንቱ ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣ፣6ደግሞም ኀጢአት በሚያደርጉ ሁሉ ላይ የሚመጣው ጥፋት ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ ከፈረደባቸው፣7በሕገ ወጦች ሴሰኝነት ነፍሱ እየተጨነቀ ይኖር የነበረውን ጻድቁን ሎጥን ግን አዳነው፤8ያ ጻድቅ ሰው በመካከላቸው ሲኖር በየቀኑ ያየውና ይሰማው በነበረው ሕገ ወጥ ድርጊታቸው ጻድቅ ነፍሱ ትጨነቅ ነበር።9ጌታ፣ እግዚአብሔርን የሚመስሉትን ሰዎች ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።10በተለይም ብልሹ የሥጋ ምኞታቸውን የሚከተሉትንና ሥልጣንን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደፋሮችና እብሪተኞች ስለ ሆኑ የከበሩትን ሲሳደቡ አይፈሩም፤11መላእክት ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ብርታትና ችሎታ ያላቸው ሆነው ሳሉ፣ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ ዘለፋ ያዘለ የፍርድ ቃል አይሰነዝሩም።12እነዚህ አእምሮ እንደ ጎደላቸው እንስሳት ለምርኮና ለጥፋት የተፈጠሩ ናቸው፤ የሚሳደቡትን ስለማያውቁ ይጠፋሉ።13እነርሱ የዐመፃቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ በቀን በመስከርና ያለ ልክ በመፈንጠዝ ይኖራሉ ፤ እነርሱ አሳፋሪዎችና ነውረኞች ናቸው። ከእናንተ ጋር ግብዣ ላይ ሲገኙ፣ በአታላይ ፈንጠዝያቸው ሐሴት ያደርጋሉ።14ዐይናቸው ቅንዝር የተሞላ በመሆኑ ኀጢአትን ከመሥራት ከቶ አይቈጠቡም፤ ጽኑ ያልሆኑትን ሰዎች ያስታሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ልጆች ናቸው።15ቀናውን መንገድ ትተው፣ በክፉ ሥራ የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ስተዋል፤16እርሱ ስለ መተላለፉ ተገሥጾአል፤ መናገር የማይችል አህያ በሰው ቋንቋ ተናግሮ የነቢዩን እብደት አስቍሟልና።17እነዚህ ሰዎች እንደ ደረቁ ምንጮችና በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዱ ደመናዎች ናቸው፤ የሚጠብቃቸውም ድቅድቅ ጨለማ ነው፤18ፍሬ ቢስ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወታቸው ሰዎችን ያጠምዳሉ፤ ከተሳሳተና ከብልሹ የሕይወት ዘይቤ ለማምለጥ የሚሞክሩትን ሰዎች ያጠምዳሉ።19እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው ሳሉ፣ ሌሎችን ነጻ ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለሚሸነፍለት ለማንኛውም ነገር ባሪያ ነውና።20ጌታችንንና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ፣ እንደ ገና ወደ ቀደሞው የርኵሰት ሕይወት ቢመለሱ፣ ከመጀመሪያው ይልቅ የኋለኛው የከፋ ይሆንባቸዋል።21የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ፣ ቀድሞውኑ የጽድቅን መንገድ ባያውቋት ይሻላቸው ነበር።22«ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል» እንዲሁም «ዐሣማ ቢታጠብም ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል» የሚለው ምሳሌ እውን ይሆንባቸዋል።
1ወዳጆች ሆይ! ይህን ሁለተኛ መልእክት የምጽፍላችሁ፣ ቅን ልቦናችሁን ለማነቃቃት ነው፤2ደግሞም አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያት የተነገረውን ቃል እንዲሁም በሐዋርያቶቻችሁ አማካይነት በጌታችንና በአዳኛችን የተሰጠውን ትእዛዝ እንድታስታውሱ ነው።3በቅድሚያ ይህን ዕወቁ፤ በመጨረሻዎቹ ቀኖች የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ዘባቾች እየዘበቱባችሁ ይመጣሉ።4እነርሱም፣ «የመምጣቱ ተስፋ ወዴት አለ? አባቶቻችን ሞተዋል፤ ከፍጥረት መጀመሪያም አንሥቶ እስካሁን ድረስ ሁሉም ነገር እንዳለ ይኖራል» ይላሉ።5እነዚህ ሰዎች ሰማያትና ምድር ከብዙ ዘመን በፊት በእግዚአብሔር ቃል ከውሃና በውሃ አማካይነት መፈጠራቸውን ፣ ሆን ብለው ይክዳሉ፤6በቃሉና በውሃ እማካይነት በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም በውሃ ተጥለቅልቆ ጠፋ።7ደግሞም በዚያው ቃል አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር ኀጢአተኞች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለእሳት ተጠብቀዋል።8ወዳጆች ሆይ፤ ፤በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፣ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን መሆኑን ይህን አትዘንጉ ።9አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዳችሁም እንድትጠፉ ስለማይፈልግና ሰው ሁሉ በቂ የንስሓ ጊዜ እንዲያገኝ ፈልጎ ስለ እናንተ ይታገሳል።10ይሁን እንጂ የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በእሳት ይቃጠላል፤ በምድርና በእርሷም ውስጥ በተሠራው ነገር ሁሉ ላይ ይፈረድበታል።11እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚጠፉ ከሆነ፣ ታዲያ እናንተ በቅድስናና እግዚአብሔርን በመምሰል ሕይወት ለመኖር እንዴት ዐይነት ሰዎች ልትሆኑ ይገባችኋል?12ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት በናፍቆት የምትጠባበቁና የምታፋጥኑ ሁኑ፤ በዚያን ቀን ሰማያት በእሳት ተቃጥለው ይጠፋሉ፤ ፍጥረታትም በእሳት ግለት ይቀልጣሉ፤13እኛ ግን እርሱ በሰጠን ተስፋ መሠረት፣ ጽድቅ የሰፈነበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንጠባበቃለን።14ስለዚህ ወዳጆች ሆይ፤ እነዚህን ነገሮች የምትጠባበቁ እንደ መሆናችሁ፣ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ ከእርሱም ጋር በሰላም እንድትገኙ ትጉ።15እንዲሁም ወንድማችን ጳውሎስ በተሰጠው ጥበብ መጠን እንደ ጻፈላችሁ፤ የጌታችን ትዕግሥት እናንተ እንድትድኑ እንደ ሆነ አስቡ፤ ምንም እንኳ በመልእክቶቹ ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ነገሮች ቢኖሩም፣16ጳውሎስ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፎአል፤ ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች እንደሚያጣምሙ ሁሉ እነዚህም ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።17እንግዲህ ወዳጆች ሆይ፤ ይህን አስቀድማችሁ ስላወቃችሁ፣ በዐመፀኞች ስሕተት ተስባችሁ ጽኑ መሠረታችሁን እንዳትለቅቁ ተጠንቀቁ።18ነገር ግን በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ፤ ለእርሱ አሁንም፣ ለዘላለምም ክብር ይሁን፤ አሜን!
1ከመጀመሪያው ስለ ነበረው፣ ስለ ሰማነው፣ በዓይኖቻች ስላየነው፣ ስለ ተመለከትነው ፣በእጆቻችንም ስለ ዳሰስነው ስለ ህይወት ቃል2ህይወትም ተገልጦ ነበር ፤እኛም አይተናል፣ምስክሮችም ነን፤ በአብ ዘንድ ስለ ነበረው ለእኛም ስለ ተገለጠው፣ የዘላለም ሕይወት እንናገራለን፤3ከእኛም ጋር ህብረት እንዲኖራቸሁ፣ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን፤ ህብረታችንም ከአብና፣ ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፡፡4ደስታችሁም ሙሉ እንዲሆን ፣እነዚህን ነገሮች እንጽፍላችኋለን።5ከእርሱ የሰማነው፣ለናንተም የምንነግራችሁ መልዕክት፣ እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ በእርሱም ምንም ጨለማ የለም፤ የሚል ነው፡፡6ከእርሱ ጋር ህብረት አለን እያልን፣ ነገር ግን በጨለማ ውስጥ ብንመላለስ፣እንዋሻለን ፣እውነትንም አናደርግም፡፡7እርሱ ብርሃን እንደሆነ ፣ በብርሃን ብንመለላለስ እርስ በርሳችን ህብረት ይኖረናል፡፡የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ከሃጢአት ሁሉ ያነጻናል።8ሃጢያት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፣ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።9ነገር ግን ሃጢያታችንን ብንናዘዝ፣ሃጢያታችንን ይቅር ሊለንና ከዓመጽ ሁሉ ሊያነጻን፣ የታመነና ፃድቅ ነው፡፡10ሃጢአት አላደረግንም ብንል፣ ሃሰተኛ እናደርገዋለን፣ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም፡፡
1የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣ሃጢያት እንዳታደርጉ ይህን እፅፍላችኋላሁ። ግን ማንም ሃጢያት ቢያደርግ ፣ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ፤እርሱም ፃድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡2እርሱ የእኛ ብቻ ሳይሆን፣ የዓለሙም ሁሉ ሃጢዓት ማስተስረያ ነው፣፡፡3ትዕእዛዙን የምንጠብቅ ከሆነ ፣በዚህ እርሱን እንዳወቅነው እናውቃለን።4"እግዚአብሔርን አውቀዋለሁ" የሚል ፣ግን ትዕዛዛቱን የማይጠብቅ፣ ውሸታም ነው ፣እውነትም በውስጡ የለም፡፡5ሆኖም ማንም ቃሉን ቢጠብቅ፣ በርግርጥ በዚያ ሰው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር ተገልጧል፤ በዚህም በእርሱ እንደሆንን እናውቃለን።6በእግዚአብሔር እኖራለሁ የሚል ፣ኢየሱስ ክርስቶስ እንደኖረ መኖር አለበት።7የተወደዳችሁ፣የምጽፍላችሁ በመጀመሪያ የነበረውን አሮጌ ትዕዛዝ እንጂ አዲስ ትዕዛዝ አይደለም።አሮጌውም ትእዛዝ የሰማችሁት ቃል ነው፡፡8ሆኖ በክርስቶስና በናንተ እውነት የሆነውን አዲሱን ትእዛዝ እጽፍላችኋለሁ።ምክንያቱም ጨለማው አልፎ እውነተኛው ብርሃን እያበራ ነው።9በብርሃን አለሁ እያለ ፣ወንድሙን ግን የሚጠላ ፣አሁንም እንኳ በጨለማ ውስጥ ነው፡፡10ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ይኖራል። የሚያሰናክል ሁኔታም የለም፡፡11ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ውስጥ ነው፣ በጨለማም ይኖራል፤ ወዴት እንደሚሄድም አያውቅም ፣ምክንያቱም ጨለማው ዓይኖች አሳውሮታል፡፡12ልጆች ሆይ! ኃጢያታችሁ በክርስቶስ ስም ይቅር ስለተባለ እፅፍላችኋለሁ፡፡13አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃኋልና እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ! ክፉውን ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡ ታናናሽ ልጆች ሆይ! አብን ስላወቃችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡14አባቶችሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ! ብርቱዎች ስለሆናቹ ፣የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር፣ ክፉውንም አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ፡፡15ዓለምን ወይም በዓለም ያሉት ነገሮች አትውደዱ። ማንም ዓለምን ቢወድ የአብ ፍቅር በርሱ ውስጥ የለም፡፡16በዓለም ያለው ሁሉ፣ የሥጋ ምኞት፣ የዓይን አምሮትና ትምክህት ከዓለም እንጂ ከአብ አይደሉም፡፡17ዓለሙና ምኞቱም ያልፋሉ፣የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል፡፡18ታናናሾች ልጆች ሆይ! የክርስቶስ ተቀዋሚ ስለመምጣቱ እንደሰማችሁት ፣ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፡፡ አሁንም እንኳ፣ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል፡፡19ከእኛው መካከል ወጥተዋል ፣ከእኛ ወገን ግን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑ ኖሮ፣ ከእኛ ጋር ፀንተው ይኖሩ ነበር። ሆኖም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ እንዲገለጥ ወጡ።20እናንት ግን፣ከቅዱሱ የተቀበላችሁት ቅባት ስላላችሁ፣ሁላችሁም እውነትን ታውቃላችሁ።21የምጽፍላችሁ እውነትን ስለማታውቁ አይደለም፤ነገር ግን ስለምታውቁትና፣ በእውነትም ምንም ሃሰት ስለሌለ ነው።22ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ከሚክድ በስተቀር ሃሰተኛ ማነው ነው? አብና ወልድን ስለሚክድ፣እንዲህ ዓይነት ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።23ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድንን የሚያውቅ አብም ደግሞ አለው።24እናንተ ግን ፣ከመጀመሪያው የሰማችሁት በውስጣችሁ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት፣በእናንተ ቢኖር፣እናንተም በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።25እርሱ የሰጠን ተስፋ ይህ ነው፤ እርሱም የዘላለም ሕይወት ነው።26የሚያስቷችሁን በተመለከተ ፣ ይህን ፅፌላችኋለሁ፡፡27እናንተ ግን የተቀበለች ቅባት በእናንተ ስለሚኖር ፣ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም። የርሱም ቅባት ስለ ሁሉም ነገሮች እውነት እንጂ ሃሰት ስለማያስተምራችሁ ፣ እንደተማራችሁት በርሱ ኑሩ፡፡28አሁንም የተወዳዳችሁ ልጆች፣ በሚገለጥበለት ጊዜ ድፍረት እንዲኖረንና ፣በመምጣቱም እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ፡፡29እርሱ ፃድቅ እንደሆነ ካወቃችሁ ፣ፅድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከርሱ እንደተወለደ ታውቃላችሁ፡፡
1የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።2የተወደዳችሁ፣አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፤ምክንያቱም ትክክለኛ ማንንነቱን እናየዋለን።3በእርሱም ላይ ይህ ጽኑ እምነት ያለው ሁሉ፣ እርሱ ንፁህ እንደሆነ ራሱን ያነፃል፡፡4ኃጢያትን የሚሠራ ሁሉ ዐመጽን ያደርጋል፣ ኃጢአትም ዐመጽ ነው፡፡5ኃጢያትን ለማስወገድ ክርስቶስ እንደተገለፀ ታውቃላችሁ፣ በእርሱም ኃጢያት የለም፡፡6በእርሱ የሚኖር ኃጢያት አያደርግም፡፡ ኃጢያት የሚያደርግ እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም፡፡7የተወደዳችሁ ልጆች፣ ማንም አያስታችሁ፡፡ ክርስቶስ ፃድቅ እንደሆነ ሁሉ፣ ፅድቅን የሚያደርግ ፃድቅ ነው።8ኃጢያት የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፤ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያው ኃጢያት አድርጓል፡፡ በዚህም ምንክያት የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ፣የእግዚአብሔር ልጅ ተገልጧል፡፡9የእግዚአብሔር ዘር በርሱ ስለሚኖር ፣ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢያትን አያደርግም፤ ከእግዚአብሔር ተወልዷልና ኃጢያትን ሊያደርግም አይችልም።10በዚህም የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ይታወቃሉ፡፡ ፅድቅን የማያደርግ ወይም ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፡፡11ከመጀመሪያው የሰማችኋት መልእክት፣ይህ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ የሚለው ነው።12ክፉ እንደሆነውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም። የገደለው ለምንድን ነው? ምክንያቱ የራሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ጽድቅ ስለነበረ ነው፡፡13ወንድሞች፣ ዓለም ቢጠላችሁ፣አትደነቁ።14ወንድሞችን ስለምንወድ ፣ከሞት ወደ ህይወት እንደተሻገርን እናውቃለን። ፍቅር የሌለው በሞት ውስጥ ይኖራል፡፡15ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ ነፍሰ ገዳይ የሆነ ሁሉ፣ በውስጡ የዘላለም ህይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ፡፡16ክርስቶስ ለእኛ ህይወቱን ሰጥቷልና፣በዚህ ፍቅርን እናውቃለን።እኛም ለወንድሞቻችን ህይወታችንን አሳልፈን መስጠት ይገባናል።17ነገር ግን ማንም የዚህ ዓለም ንብረት ያለውና፣ወንድሙም የሚያስፈልገውን አውቆ፣ባይራራለት፣ እንዴት የእግዚአብሔር ፍቅር በርሱ ይኖራል?18የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣በሥራና በእውነት እንጂ ፣በቃል ወይም በአንደበት አንዋደድ።19በዚህም ከእውነት እንደሆንንና፣ልባችንም በፊቱ ትክክል እንደሆነ እናረጋግጣለን።20ልባችን ግን የሚፈርድብን ከሆነ፣ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው፣ሁሉንም ያውቃል፡፡21ወዳጆች ሆይ! ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ፣በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን።22ትዕዛዙን የምንጠብቅና፣በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆነ፣ የምንለምነውንና ሁሉ እንቀበላለን፡፡23የርሱም ትዕዛዙ፣በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናምንና፣ ትእዛዙን እንደሰጠን እንደዚያው እርስ በርስ እንድንዋደድ ነው፡፡24የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ፣በርሱ ይኖራል እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡በዚህም በሰጠን በመንፈሱ፣ በእኛ ውስጥ እንደሚኖር እናውቃለን።
1ወዳጆች ሆይ! መንፈስን ሁሉ አትመኑ፣ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፣ ምክንያቱም ብዙ ሃሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ገብተዋል፡፡2የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ እናውቃለን፣- ጌታ ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው።3ኢየሱስን የማይቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። ይህ እንደሚመጣ የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፣ አሁን እንኳ በዓለም ውስጥ አለ፡፡4የተወደዳችሁ ልጆች! እናንተ ከእግዚአብሔር ስለሆናችሁ፣ እነዚህን መናፍስት አሸንፋችኋል፣ ምክንያቱም በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ይበልጣል፡፡5እነዚህ መናፍስት ከዓለም ናቸው፣ስለሆነም የሚናገሩት ሁሉ የዓለምን ነው፣ዓለምም ይሰማቸዋል፡፡6እኛ ከእግዚአብሔር ነን። እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል። ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም። በዚህም የእውነት መንፈስንና ፣የስህተትን መንፈስን እናውቃለን፡፡7ወዳጆች ሆይ! እርስ በርስ እንዋደድ፣ምክንያቱም ፍቅር ከእግዚአብሔር ነውና፣ ፍቅር ያለው ከእግዚአብሔር ተወልዷል፣ እግዚአብሔርንም ያውቃል፡፡8ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፣እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፡፡9በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በመካከላችን ተገልጧል፣ እግዚአብሔር በርሱ እንድንኖር ፣አንድ ልጁን ወደ ዓለም ላከው፡፡10ፍቅር እንደዚህ ነው፣እግዚአብሔርን ስለወደድነው ሳይሆን፣ እርሱ ስለወደደን ለኃጢያታችን ማስተሰረያ እንዲሆን ልጁን ላከ፡፡11ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን፣እኛም እርስ በርሳችን መዋደድ ይገባናል።12ማንም እግዚአብሔርን አላየውም። እርስ በርሳችን ብንዋደድ፣ እግዚአብሔር በኛ ይኖራል፣ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል፡፡13መንፈሱን ሰጥቶናልና፣ በዚህም እኛ በእርሱ እንደምንኖር፣ እርሱም በኛ እንደሚኖር እናውቃለን።14እኛም አይተናል፣እግዚአብሔር ልጁን የዓለም አዳኝ አድርጐ እንደላከውም እንመሰክራለን፡፡15ማንም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ቢቀበል፣ እግዚአብሔር በርሱ ይኖራል ፤እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል፡፡16እኛም እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል ደግሞም አምነናል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡17በፍርድ ቀን ድፍረት እንዲኖረን፣ይህም ፍቅር በመካከላችን ተፈጸሟል፣ እኛም በዚህ ዓለም እንደ እርሱ ነን ፡፡18በፍቅር ፍርሃት የለም። ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፣ ምክንያቱም ፍርሃት የሚያመለክተው ቅጣት መኖሩን ነው። የሚፈራ ግን ፍቅሩ ፍፁም አይደለም፡፡19አስቀድሞእግዚአብሔር ወዶናልና፣እኛም እንወደዋለን።20አንድ ሰው "እግዚአብሔርን እወዳለሁ" እያለ ወንድሙን ግን ቢጠላ ሃሰተኛ ነው፤የሚያየውን ወንድሙን የማይወድ፣ የማያየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልም።21እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙን መውደድ አለበት፣የሚል ትእዛዝ ከእግዚአብሔር ተቀብለናል።
1ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዷል።አባት የሆነውን የሚወድ ሁሉ፣ከርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።2እግዚአብሔርን ስንወድና ትዕዛዙን ስንፈጽም፣ የእግዚአብሔርን ልጆች እንደምንወድ በዚህ እናውቃለን።3እግዚአብሔርን የምንወደው የርሱን ትእዛዙን በመጠበቃችን ነው። የርሱም ትእዛዛት ከባዶች አይደሉም።4ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለምን የሚያሽንፈው እምነታችን ነው።5ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ከሚያምን በቀር፣ ዓለምን የሚየሸንፍ ማነው?6በውሃና በደም የመጣው እርሱም ነው፣እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በውሃ ብቻ ሳይሆን፣ነገር ግን በውሃና በደም የመጣ ነው። 7-8የጥንቶችቹ የተሻሉት ቅጅዎች ይተውታል። ሦሶት ምስክሮች አሉ፤እነርሱም መንፈሱ ፣ውሃውና ደሙ ናቸው፤ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።9የሰዎችን ምስክርነት የምንቀበል ከሆነ፣ የእግዚአብሔር ምስክርነት ደግሞ የበለጠ ነው። እግዚአብሔር ስለ ጁል የሰጠው ምስክር ይህ ነው።10በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በውስጡ ምስክር አለው። በእግዚአብሔር የማያምን ፣እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስለማያምን ሐሰተኛ አድርጎታል።11ምስክሩም ይህ ነው ፣እግዚአብሔር የዘላለምን ህይወት እንደሰጥንና፣ይህም ህይወት በልጁ መሆኑ ነው።12ልጁ ያለው ሕይወት አለው፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።13በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ፣የዘላለም ህይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ፣እነዚህን ነገሮች እጽፍላችኋለሁ።14በእርሱ ፊት ያለን ድፍረት ይህ ነው፣እንደ ፈቃዱ ማንኛውንም ነገር ብንጠይቀው፣ይሰማናል።15የምንጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ከርሱ የጠየቅነውን ሁሉ እንደተቀበልን እናውቃለን።16ማንም ወንድሙ ለሞት የማያበቃ ሃጢዓት ሲያደርግ ቢያይ፣ መጸለይ ይገባዋል፣ሞት የማይገባውን ሃጢዓት ለሚያደርጉት እግዚአብሔር ህይወትን ይሰጣል። ለሞት የሚያበቃ ኃጢዓት አለ። ያንን የተመለከተ ልመና እንዲያደርግ አላልኩም።17ዓመጽ ሁሉ ኃጢዓት ነው፣ ነገር ግን ለሞት የማያበቃ ኃጢዓት አለ።18ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢዓት እንደማያደርግ እናውቃለን፣ከእግዚአብሔር የተወለደውን፣እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቀዋል ፣ክፉውም አይነካውም።19እኛ ከእግዚአብሔር እንደሆንን፣ዓለም ሁሉ በክፉው ቁጥጥር ሥር እንደሆነ እናውቃለን።20እኛ ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣና እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋል እንደሰጠን እናውቃለን፤ እኛም እውነት በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለን እናውቃለን። እርሱም እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት ነው።21ልጆች ሆይ! ከጣዖታት ዓምልኮ ራሳችሁን ጠብቁ።
1ከሽማግሌው በእውነት ለምወዳችሁና እኔም ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወዱአችሁ ለተመረጥች እመቤትና ለልጆችዋ ።2ይህም ፍቅር በውስጣችን ካለውና ለዘላለም ከእኛ ጋር ከሚሆነው እውነት የተነሳ ነው።3በእውነትና በፍቅር ከእግዚአብሔር አብ ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ምህረትና ሠላም ከሁላችን ጋር ይሁን።4ከልጆችሽ መካከል ከአብ በተቀበልነው ትዕዛዝ መሠረት በእውነት ሲሄዱ በማግኘቴ እጅግ ሀሴት አደርጋለሁ።5እንግዲህ እመቤት አሁን አዲስ ትዕዛዝ እንደምሰጥ ሳይሆን እርስ በእርሳችን እንዋደድ ብዬ ከመጀመሪያው በነበረን ትዕዛዝ እለምንሻለሁ።6ይህም በትዕዛዛቱ መሰረት ልንጓዝበት የሚገባን ፍቅር ነው። ይህ ትዕዛዝ ከመጀመሪያው እንደሰማችሁት ልትራመዱበት የሚገባ ትዕዛዝ ነው።7ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምኑ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋል። ይህም አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።8ሙሉ ዋጋችሁን እንድትቀበሉ እንጂ እኛ ሁላችን የደክምንባቸውን ነገሮች እንዳታጡ ስለራሳችሁ ተጠንቀቁ።9በክርስቶስ ትምህርት ሳይጸና ዝም ብሎ ወደፊት የሚገሰግስ እግዚአብሄርን አያውቅም። በዚህ ትምህርት የሚጸና አብና ወልድ አሉት።10ማንም ወደ እናንተ መጥቶ ይህን ትምህርት ባያስተምር ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አትፍቀዱለት ሠላምም አትበሉት።11ምክንያቱም ሠላምታ የሚሰጠው ሁሉ በክፉ ሥራው ይካፈላል።12የምጽፍላችሁ ብዙ ነገር ነበረኝ ነገር ግን በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልፈለግሁም። ነገር ግን ደስታችን ሙሉ ይሆን ዘንድ ወደ እናንተ ልመጣና ፊት ለፊት ላወራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።13የተመረጠችው እህትሽ ልጆች ሠላምታ ያቀርቡልሻል።
1ሽማግሌው በእውነት ለምወደውና ለተወደደው ጋይዮስ።2የተወደድክ ሆይ በነፍስህ እንደበለጸግህ በሁሉ ነገር እንድትበለጽግና በመልካም ጤንነት እንድትሆን እጸልያለሁ።3ወንድሞች መጥተው በእውነት እንደምትሄድ ሲመሰክሩልኝ እጅግ ሀሴት አደረግሁኝ።4ልጆቼ በእውነት መንገድ እየሄዱ እንደሆነ ከመስማት የበለጠ ደስታ የለኝም።5የተወደድክ ሆይ ለወንድሞችም ሆነ ለእንግዶች በምታድርገው ነገር ስላለህ ታማኝነት6ሁሉም በጉባኤ ፊት ይመሰክሩልሀል።ለእግዚአብሔር እንደሚገባ በጉዞአቸው በመደገፍህ መልካም አድርገሀል።7ምክንያቱም ለተጠሩለት ስም አገልግሎት ሲወጡ ከአህዛብ ምንም አልወሰዱም።8ስለዚህም የእውነት ማህበርተኞች እንሆን ዘንድ እንደነዚህ ያሉትን መርዳት ይገባናል።9ስለአንድ ጉዳይ ለቤተክርስቲያን ጽፌ ነበር ነገር ግን በመካከላቸውአለቃ ሊሆን የሚወደው ዲዮትሪፈስ አይቀበለንም።10ስለዚህ በምመጣበት ጊዜ ያደረገውን ነገርና እንዴት ባሉ ክፉ ቃላት በእኛ ላይ እንደተናገረ አልረሳም።ይህም አልበቃ ብሎት ወንድሞችን አይቀበልም ሊቀበሉ የሚፈልጉትንም ይከለክላቸዋል ከቤተክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።11የተወደድክ ሆይ መልካሙን እንጂ ክፉን አትምሰል። መልካም የሚያደርግ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ እግዚአብሔርን አላየውም።12ለዲሜጥሮስ ሁሉም ይመሰክሩለታል እውነት እራሷም ትመሰክርለታልች። እኛም እንመሰክርለታለን የኛ ምስክርነት ደግሞ እውነት እንደሆነ ታውቃላችሁ።13የምጽፍልህ ብዙ ነገር ነበረኝ ነገር ግን በወረቀትና በቀለም ልጽፍልህ አልፈለግሁም።14ይልቁኑ ልጎበኝህ አስባለሁና በዚያን ጊዜ ፊት ለፊት እንነጋገራለን።15ሠላም ለአንተ ይሁን። ወገኖችሰላምታ ያቀርቡልሀል። በአንተ ዘንድ ላሉት ወገኖች በስማቸው እየጠራህ ሠላምታ አቅርብልኝ።
1የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ፥ የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ፤ ለተጠሩት፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዱትና በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቁት፤2ምሕረት ለእናንተ ይሁን፤ ሰላምና ፍቅርም ይብዛላችሁ።3ወዳጆች ሆይ፤ አብረን ስለምንካፈለው ድነት ልጽፍላችሁ ጥረት እያደረግሁ ሳለ፥ ለቅዱሳን አንዴና ለመጨረሻ ስለተሰጠው እምነት ጸንታችሁ ትጋደሉ ዘንድ ለመምከር እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።4ለፍርድ እንደሚዳረጉ ከብዙ ዘመን በፊት የተጻፈባቸው አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ወደ እናንተ ገብተዋልና። እነዚህ ሰዎች ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላቸው፥ የእግዚአብሔርን ጸጋ በሴሰኝነት የሚለውጡ፥ እርሱ ብቻ ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው።5ምንም እንኳ አስቀድማችሁ ሁሉን የምታውቁት ቢሆንም ጌታ አንድ ጊዜ ሕዝቡን ከግብጽ አውጥቶ እንደ አዳናቸው በኋላ ግን ያላመኑትን እንዳጠፋቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።6እንዲሁም የነበራቸውን የሥልጣን ደረጃ ባለመጠበቅ ተገቢ የመኖሪያ ስፍራቸውን የተውትን መላእክት እግዚአብሔር እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ በዘላለም እስራት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንዲቆዩ አድርጓል።7እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩት ከተሞች በተመሳሳይ ሁኔታ ራሳቸውን ለሴሰኝነትና ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ ለሆነ ግብረ ሥጋ ግንኙነት አሳልፈው ሰጡ፤ እነርሱም በዘላለም እሳት ተጥለው ለሚሰቃዩት ምሳሌ እንዲሆኑ ተደርገዋል።8በዚህ ሁኔታ እነዚህ ደግሞ በሚያልሙት ሕልማቸው የራሳቸውን ሥጋ ያረክሳሉ፤ሥልጣንን ይቃወማሉ፤በሰማይ ክብር ያላቸውንም ይሳደባሉ።9የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳ ዲያብሎስን በመቃወም ስለ ሙሴ ሥጋ በተከራከረው ጊዜ «ጌታ ይገሥጽህ» አለው እንጂ በእርሱ ላይ ሊፈርድ ወይም አንዳች የስድብ ቃል ሊናገር አልደፈረም።10እነዚህ ሰዎች ግን የማያውቋቸውን ነገሮች ሁሉ ይሳደባሉ። እነርሱም አእምሮ የሌላቸው እንስሳት እንደሚያደርጉት በደመ ነፍስ በሚያውቋቸው ነገሮች ይጠፋሉ።11ወዮላቸው፤ በቃየን መንገድ ሄደዋልና፤ለገንዘብ ሲሉ በበለዓም ስህተት ውስጥ ወድቀዋልና፤በቆሬም ዐመፅ ጠፍተዋልና።12እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ አብረዋችሁ ሲጋበዙ ችግር የሚፈጥሩባችሁ ድብቅ እንቅፋቶች ናቸው፤ ደግሞም ያለ ሃፍረት ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው። እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ውሃ አልባ ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው፥ ከሥራቸው የተነቀሉና ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው።13የራሳቸውን የነውር አረፋ የሚደፍቁ የተቆጣ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማም ለዘላለም የተጠበቀላቸው ተንከራታች ከዋክብት ናቸው።14ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖክ ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ በማለት ትንቢት ተናግሯል፤ «እነሆ፤ ጌታ ከብዙ ሺህ ቅዱሳኑ ጋር ይመጣል።15የሚመጣውም በሰው ሁሉ ላይ ለመፍረድ እንዲሁም ዐመፀኞችንና ኀጢአተኞችን ክፋት በተሞላበት ሁኔታ በፈጸሙት የዐመፅ ሥራቸውና በእግዚአብሔር ላይ በተናገሩት የስድብ ቃል ለመውቀስ ነው።»16እነዚህ የሚያጉረመርሙ፥ ሌላውን የሚከሱ፥ የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ፥ ጉራ የሚነዙና ጥቅም ለማግኘትም ሰዎችን የሚክቡ ናቸው።17እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፤የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት አስቀድመው የተናገሩትን ቃል አስታውሱ18ለእናንተም ሲናገሩ፥«በመጨረሻው ዘመን የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ዘባቾች ይመጣሉ» ብለዋል።19እነዚህ በሰዎች መካከል መለያየትን የሚፈጥሩ፥የሥጋን ምኞት የሚከተሉና መንፈስ ቅዱስ የሌላቸው ናቸው።20እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፤እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ ትጉ፤በመንፈስ ቅዱስም ጸልዩ።21በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ፤የዘላለም ሕይወትም ታገኙ ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ፈልጉ።22ለሚጠራጠሩ ሰዎች ርኅራኄ አድርጉላቸው፤23ከእሳት ነጥቃችሁ በማውጣት አንዳንዶችን አድኑ፤ ለሌሎች ድግሞ በእርኩስ ሥጋ የተበከለውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ምህረት አሳዩአቸው።24እንግዲህ ከመውደቅ ሊጠብቃችሁ፥ ነቀፋ ሳይኖርባችሁ በታላቅ ደስታ በክብሩ ፊት ሊያቀርባችሁ ለሚችለው25በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት አዳኛችን ለሆነው ብቸኛ አምላክ ከዘመናት ሁሉ በፊት፥ አሁንና እስከ ዘላለም ድረስ ክብር፥ ግርማ፥ ኀይልና ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
1ይህ ፈጥኖ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ራእይ ነው። እርሱም ይህን ራእይ መልአኩን ወደ አገልጋዩ ወደ ዮሐንስ በመላክ እንዲታወቅ አድርጓል።2ዮሐንስም የእግዚአብሔርን ቃል በሚመለከት ስላየው ማንኛውንም ነገር እና ክርስቶስን በሚመለከት ስለተሰጠው ምስክርነት ተናግሯል።3ዘመኑ ስለ ቀረበ ፥ የዚህን የትንቢት ቃል የሚያነብ የተባረከ ነው፤እንዲሁም የሚሰሙት ሁሉ በውስጡም የተጻፈው ን ነገር የሚፈጽሙ የተባረኩ ናቸው።4ከዮሐንስ፥በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ካለው፥ከነበረው፥ወደፊትም ከሚመጣውና በዙፋኑ ፊት ካሉት ከሰባቱ መንፈሶች5እንዲሁም ታማኝ ምስክር፥ከሙታን በኩርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለሚወደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፥6አባቱ ለሆነው እግዚአብሔር መንግሥትና ካህናት እንሆን ዘንድ ላደረገን ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤አሜን።7እነሆ፤እርሱ በደመና ይመጣል፤የወጉትን ጨምሮ ዐይን ሁሉ ያየዋል። የምድርም ነገዶች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤እንደዚያም ይሆናል፤አሜን።8ጌታ እግዚአብሔር፥«አልፋና ኦሜጋ፥ ያለሁና የነበርሁ፥ወደፊትም የምመጣው ሁሉን ቻይ እኔ ነኝ» ይላል።9እኔ ከእናንተ ጋር በመከራው፥በመንግሥቱና በኢየሱስ በሚገኘው ትዕግሥት ተካፋይ የሆንሁ ወንድማችሁ ዮሐንስ፥ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።10በጌታም ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤በኋላዬም የመለከትን ድምጽ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ።11ድምፁም እንዲህ የሚል ነበር፤«የምታየውን በመጽሓፍ ጻፈው፤ ከዚያም በኤፌሶን፥ በሰምርኔስ፥ በጴርጋሞን፥ በትያጥሮን፥ በሰርዴስ፥ በፊለደልፍያና በሎዶቅያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላከው።12ይናገረኝ የነበረው የማን ድምፅ እንደ ሆነ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወር በምልበትም ጊዜ ሰባት የወርቅ መቅረዞችን አየሁ።13በመቅረዞቹም መካከል እስከ እግሩ ድረስ የሚደርስ ረጅም ልብስ የለበሰና ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ የሰው ልጅ የሚመስለው ነበር።14ራሱና ጸጉሩ እንደ ነጭ የበግ ጸጉር ማለትም እንደ በረዶ ነጭ ነበሩ፤ዐይኖቹ የእሳት ነበልባል፥15እግሮቹም በእቶን እሳት እንደ ነጠረ የጋለ ናስ፥ ድምፁም እንደ ብዙ ወራጅ ውኃ ድምፅ ነበር።16በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤ከአፉም በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ፊቱም ጸሐይ በሙሉ ኀይልዋ ስታበራ የምታበራውን ያህል ያበራ ነበር።17ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅሁ፤ እርሱም ቀኝ እጁን በእኔ ላይ በመጫን እንዲህ አለኝ፤ «አትፍራ፤እኔ የመጀመሪያውና የመጨረሻው18ሕያውም ሆኜ የምኖር ነኝ። ሞቼ ነበር፤እነሆም ለዘላለም ሕያው ነኝ፤የሞትና የሲዖል መክፈቻም አለኝ።19ስለዚህ ያየኽውን፥አሁን ያለውን ሁኔታና ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ነገር ጻፍ።20በቀኝ እጄ ያሉት አንተም ያየሃቸውን የሰባቱን ከዋክብትና የሰባቱን የወርቅ መቅረዞች ምስጢር በተመለከተ ትርጉሙ ይህ ነው፤ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ሲሆኑ፥ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
1“በኤፌሶን ወዳለው መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ ‘ሰባቱን ከዋክብት በቀኝ እጁ የያዘውና በሰባቱ የወርቅመቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፤2‘ሥራህን፣ ትዕግሥትህንና ጽናትህን አውቃለሁ። ክፉ ሰዎችን መታገሥ አለመቻልህንም አውቃለሁ። ሐዋሪያት ሳይሆኑ “ሐዋሪያት ነን” የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸውም አውቃለሁ።”3በትዕግሥት እንደ ጸናህ፥ስለ ስሜ ብዙ መከራ ቢደርስብህም እንዳልደከመህ አውቃለሁ።4ነገር ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ይኽውም የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃል።5እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ ለይተህ እወቅ፤ንስሓ ግባ፤ቀደም ሲል ታደርገው የነበረውንም ነገር አድርግ። ንስሓ ካልገባህ እመጣብሃለሁ፤መቅረዝህንም ከስፍራው አስወግዳለሁ።6ነገር ግን ይህ መልካም ነገር አለህ፤ እኔ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃል።7ጆሮያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ይስማ። ድል ለሚነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው የሕይወት ዛፍ የመብላትን መብት እሰጠዋለሁ።”8«በሰምርኔስ ላለችው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "እነዚህ መጀመሪያም መጨረሻም የሆነው የእርሱ ቃሎች ናቸው፤ሞቶ የነበረው፥እንደ ገና ሕያው የሆነው እንዲህ ይላል፤9'"መከራህንና ድኽነትህንም አውቃለሁ፤ነገር ግን ባለጠጋ ነህ፤የሰይጣን ማኅበር ሆነው እያለ፥አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን ብለው የሚናገሩ ሰዎች የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።10ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ። ተመልከት ከእናንተ አንዳንዶቹን እንድትፈተኑ ዲያብሎስ እስር ቤት ያስገባችኋል፤ ለአሥር ቀን መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።11ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለው ይስማ። ድል የሚነሻ በሁለተኛው ሞት አይጎዳም።12«በጴርጋሞን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "እነዚህ በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ካለው የተነገሩ ቃሎች ናቸው፤እርሱም እንዲህ ይላል፤13'"የሰይጣን ዙፋን ባለበት በዚያ እንደምትኖር አውቃለሁ፤ነገር ግን ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል። ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ መካከል በተገደለው በታማኙ ምስክሬ በአንቲጳስ ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።14ነገር ግን የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉና እንዲሴስኑ በፊታቸው ማሰናከያ ያስቀምጥ ዘንድ ባላቅን የመከረው የበለዓምን ትምህርት አጥብቀው የሚከተሉ አንዳንድ ሰዎች በመካከልህ አሉ።15እንደዚሁም የኒቆላውያንን ትምህርት አጥብቀው የያዙ ሰዎች እንኳ በአንተ ዘንድ አሉ።16ስለዚህ ንስሓ ግባ፤አለበለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ከአፌም በሚወጣው ሰይፍ አዋጋቸዋለሁ።17ጆሮ ካለህ፥መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ስማ። ድል ለሚነሳ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤እንደዚሁም ከሚቀበለው ሰው በስተቀር ማንም የማያውቀውን አዲስ ስም የተጻፈብትን ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ።>18በቲያጥሮን ወዳለው መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “የእሰት ነበልባል የመሰሉ ዐይኖችና በእሳት ፍም የነጠረ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል።19ሥራህን፣ ፍቅርህንና እምነትህን፣ አገልግሎትህንና በትዕግሥት መጽናትህን አውቃለሁ። አሁን በቅርቡ ያደረግኸው ቀድሞ ካደረግኸው የበለጠ መሆኑን አውቃለሁ።”20ነገር ግን የምነቅፍብህ አንድ ነገር አለኝ፤ራሷን ነቢይት ብላ የምትጠራውን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለሃታል። ይህች ሴት በትምህርትዋ አገልጋዮቼ ሴሰኛ እንዲሆኑና ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉ ታስታቸዋለች።21ንስሓ እንድትገባ ጊዜ ሰጥቻት ነበር ፤ይሁን እንጂ ከርኩሰትዋ ንስሓ ለመግባት ፈቃደኛ አልሆነችም።22እነሆ በሥቃይ አልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩት እርስዋ ከፈጸመችው ነገር ንስሓ ካልገቡ በስተቀር በከባድ ሥቃይ እንዲወድቁ አደርጋለሁ።23በሞት እቀጣለሁ፤በመሆኑም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሰውን ሐሳብና ፍላጎትን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ። ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እከፍላለሁ።24ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትከተሉ ሁሉ እንዲሁም አንዳንዶች የሰይጣን ጥልቅ ምስጢር ነው የሚሉትን ነገር ለማታውቁ በትያጥሮን ለምትኖሩ ለቀራችሁት ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም።>25ሆኖም እስክመጣ ድርስ ያላችሁን ነገር አጸንታችሁ ጠብቁ።26ለሚነሣውና እስከ መጨረሻው እኔ የደረግሁትን ለሚያደርግ በሕዝቦች ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ።27በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላም ዕቃ የደቃቸዋል።28እኔ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ የንጋትን ኮከብ እሰጠዋለሁ።29ጆሮ ያለው መንፈስ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ይስማ።”
1«በሰርዴስ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "ሰባቱን የእግዚአብሔር መንፈሶችና ሰባቱን ከዋክብት የያዘው እንዲህ በማለት ይናገራል፤«ሥራህን ዐውቃለሁ፤ሕያው እንደሆንህ የሚገልጽ ዝነኛ ስም አለህ፤ነገር ግን ሞተሃል።2ሥራህን በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ሆኖ ስላላገኘሁት ንቃ፤ሊሞቱ የተቃረቡትን የቀሩትን ነገሮች አጽና።3እንግዲህ ምን እንደተቀበልህና ምን እንደሰማህ አስታውስ፤ጠብቀው፤ንስሓም ግባ። ነገር ግን ባትነቃ ፥እንደ ሌባ እመጣለሁ፤በምን ሰዓት እንደምመጣብህም አታውቅም።4ነገር ግን በሰርዴስ ልብሳቸውን ያላቆሸሹ ጥቂት ሰዎች አሉ። የተገባቸውም ስለ ሆነ፥ ነጭ ልብሳቸውን ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።5ድል የሚነሳ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ስሙን ከሕይወት መጽሐፍ ፈጽሞ አልደመስሰውም፤ይልቁን በአባቴና በመላእክቱ ፊት ለስሙ እመሰክራለሁ።6ጆሮ ካለህም መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት ይሚናገረውን ስማ።»7«በፊላደልፍያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥የሚከፍት እርሱ የከፈተውን ማንም የማይዘጋ፥የሚዘጋ እርሱ የዘጋውን ማንም ሊከፍት የማይችል ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፤8ሥራህን ዐውቃለሁ፤እነሆ፤ማንም ሊዘጋው የማይችል የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌአለሁ። ዐቅምህ ትንሽ እንደሆነ አውቃለሁ፤ይሁን እንጂ ቃሌን ጠብቀሃል፤ስሜንም አልካድህም።9እነሆ፤አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉት እነዚያ ከሰይጣን ማኅበር የሆኑት ውሸተኞች ናቸው። እነርሱንም እኔ እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ መጥተው በእግርህ እንዲወድቁ አደርጋለሁ።10በትዕግሥ እንድትጸና የሰጠሁህን ትእዛዜን ስለ ጠበቅህ ፥በምድር የሚኖሩትን ይፈትን ዘንድ በዓለም ላይ ሁሉ ሊመጣ ካለው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ።11በቶሎ እመጣለሁ፤አክሊልህን ማንም እዳይወስድብህ፥ያለህን አጥብቀህ ያዝ።12ድል የሚነሻውን በአባቴ ቤተ መቅደስ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያ በፍጹም አይወጣም። እርሱ ላይ የአምላኬን ከተማ ስም፣ ማለት ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የምትወጣውን የአዲሲቱ ኢዩሳሌምን ስም ደግሞ አዲሱ ስሜን እጽፋለሁ።13ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን የስማ።”14«በሎዶቅያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "ይህም በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ገዥ እንዲሁም እውነተኛና ታማኝ ምስክር ከሆነው ቃሉም አሜን ከሆነው የተነገረ ነው፤15ሥራህን አውቃለሁ፤በራድ ወይም ትኩስ አይደለህም። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆን ኖሮ መልካም ይሆን ነበር።16እንግዲህ ትኩስ ወይም በራድ ሳትሆን በመካከል ለብ ስላልህ ከአፌ ልተፋህ ነው።17«እኔ ሀብታም ነኝ፤ብዙ ገንዘብ አለኝ፤የጎደለኝ ምንም ነገር የለም» ትላለህ፤ነገር ግን እጅግ ጎስቋላ፥ምስኪን፥ድኻ፥ዕውርና የተራቆትህ እንደሆንህ አታውቅም።18ሀብታም ትሆን ዘንድ በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥የራቁትነትህን ሐፍረት ለመሽፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥አጥርተህ ለማየትም ዐይንህን እንድትኳል እመክርሃለሁ።19እኔ የምወዳቸውን እንዴት መኖር እንደሚገባቸው ያውቁ ዘንድ እቀጣቸዋለሁ፤ አስተምራቸዋለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ንስሓም ግባ።20እነሆ፤በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ። ማንም ድምጼን ሰምቶ ቢከፍትልኝ ወደ ቤቱ እገባለሁ፤ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።21እኔ ድል እንደነሳሁና በዙፋኑ ላይ ከአባቴ ጋር እንደተቀመጥሁ፥ድል ለሚነሳም በዙፋኔ ላይ ከእኔ ጋር የመቀመጥን መብት እሰጠዋለሁ።22መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።»
1ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እነሆ የተከፈተ በር በሰማይ አየሁ። እንደ መለከት ድምፅ ሆኖ ሲናገረኝ የነበረው የመጀመሪያው ድምፅ፥«ወደዚህ ና! ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ የሚሆነውን አሳይሃለሁ።» አለ።2ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤በሰማይ ዙፋን ተዘርግቶ አየሁ፤በዙፋኑም ላይ አንድ የተቀመጠ አካል ነበር።3በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ የነበረው መልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቁ ይመስል ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ የመረግድ ዕንቁ የመሰለ ቀስተ ደመና ነበር።4በዙፋኑም ዙሪያ ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤በእነዚህም ዙፋኖች ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።5ከዙፋኑም የመብረቅ ብልጭታና የነጎድጓድ ድምፅ ወጣ። በዙፋኑም ፊት ሰባት መብራቶች ይበሩ ነበር፤እነዚህም ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።6እንደዚሁም በዙፋኑ ፊት እንደ መስተዋት እጅግ የጠራ ባሕር ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ ሁሉ ከፊትና ከኋላ በዐይን የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።7የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ሲመስል፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ጥጃ ይመስል ነበር፤ሦስተኛው ሕያው ፍጡር የሰውን ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤አራተኛው ሕያው ፍጡር ደግሞ የሚበር ንስር ይመስል ነበር።8አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፍ ነበራቸው፤ከላይና ከሥርም በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ። እነርሱም ቀንና ሌሊት፥ «ቅዱስ፥ቅዱስ፥ቅዱስ፥ በሁሉም ላይ የሚገዛ፥የነበረና ያለ፥ወደፊትም የሚመጣው ጌታ አምላክ» ማለትን አያቋርጡም ነበር።9ሕያዋን ፍጡራኑም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ክብር፥ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፥10ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ሰገዱ፤አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው፥11«ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤አንተ ሁሉንም ነገር ስለፈጠርህ፥በፈቃድህ ስለፈጠርሃቸውና እንደዚያም ሆነው ስለተገኙ ክብር፥ሞገስ፥ኅይልም ልትቀበል ይገባሃል።» ይሉ ነበር።
1በዙፋኑም ላይ በተቀመጠው ቀኝ እጅ ከፊትና ከጀርባ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የታሸገ ጥቅልል መጽሓፍ አየሁ።2አንድ ብርቱ መልአክ፥«መጽሓፉን ሊከፍት፥ ማኅተሙን ሊፈታ የተገባው ማን ነው?» ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።3በሰማይ ቢሆን በምድር ወይም ከምድር በታች መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ ማንም አልቻለም።4መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ የተገባው ማንም ስላልተገኘ፥አምርሬ አለቀስሁ።5ነገር ግን ከሽማግሌዎች አንዱ፥«አታልቅስ፤እነሆ! ከዳዊት ሥር፥ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ መጽሓፉን ይከፍትና ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነስቷል» አለኝ።6በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን መካከል እንዲሁም በሽማግሌዎች መካከል አንድ ታርዶ የነበረ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ። እርሱም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤እነዚህም በምድር ሁሉ ላይ የተላኩ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።7ሄዶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ ጥቅልል መጽሓፉን ወሰደ።8ጥቅልል መጽሓፉንም በሚወስድበት ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን እና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም በገና እና የቅዱሳን ጸሎት የሆነው ዕጣን የሞላበት የወርቅ ዕቃ ይዘው ነበር።9እነርሱም እንዲህ የሚል አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤«መጽሓፉን ትወስድ እና ማኅተሞቹን ተፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፥ከቋንቋ ሁሉ፥ ከሕዝብና ከአገር ሁሉ ሰዎችን ዋጅተሃል።10አምላካችንን ያገለግሉ ዘንድ መንግሥትና ካህናት አደረግሃቸው፤እነርሱም በምድር ላይ ይገዛሉ።»11ከዚያም በኋላ ስመለከት፥በዙፋኑ፥በሕያዋኑ ፍጡራን እና በሽማግሌዎች ዙሪያ የብዙ መላእክት ድምፅ ሰማሁ፤ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር።12እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፥ጥበብና ብርታት፥ምስጋና እና ክብር ሊቀበል ይገባዋል።» አሉ።13በሰማይና በምድር፥ከምድር በታች እንዲሁም በባሕር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ ፥«ምስጋና፥ክብር፥ውዳሴ፥የመግዛትም ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን።» ሲሉ ሰማሁ፤14አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፥«አሜን» አሉ፤ሽምግሌዎችም በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
1ከዚህም በኋላ በጉ ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን ሲከፍት አየሁ፤ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን አንዱ እንደ ነጎድጓድ ባለ ድምፅ «ና!» ሲል ሰማሁ።2አየሁም ፤እነሆም አንድ ነጭ ፈረስ አየሁ፤ባላዩ ላይ የተቀመጠውም ቀስት ይዞ ነበር፤አክሊልም ተሰጠው። እንደ ድል አድራጊ ሆኖ ድል ይነሳ ዘንድ ወጣ።3በጉ ሁለተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር«ና!» ሲል ሰማሁ።4ከዚያም ደማቅ ቀይ ፈረስ ወጣ፤በፈረሱም ላይ ለተቀመጠው ሰዎች እርስ በርስ ይተራረዱ ዘንድ ሰላምን ከምድር እንዲያስወግድ ሥልጣን ተሰጠው፤ትልቅ ሰይፍም ተሰጠው።5በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር «ና!» ሲል ሰማሁ፤ ጥቁር ፈረስ አየሁ፤በፈረሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር።6ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን የመጣ የሚመስል ድምፅ፥«አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር፥ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፤ ነገር ግን ዘይቱንና ወይኑን አትጉዳ» ሲል ሰማሁ።7በጉ አራተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ የአራተኛው ሕያው ፍጡር ድምፅ «ና!» ሲል ሰማሁ።8ከዚያም በኋላ ግራጫ ፈረስ አየሁ፤በላዩም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ተብሎ ይጠራ ነበር፤ሲኦልም ይከተለው ነበር። ሞትና ሲኦልም የምድርን አንድ አራተኛ በሰይፍ፥በረሃብ፥ በበሽታ፥በዱር አራዊት እንዲገድሉ ሥልጣን ተሰጣቸው።9በጉ አምስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ቃልና በጽናት ስለ ጠበቁት ምስክርነት የተገደሉትን ሰዎች ነፍሶች ከመሠዊያው በታች አየሁ።10እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«በሁሉም ላይ የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ የሆንህ ጌታ አምላክ ሆይ፤በምድር በሚኖሩት ላይ የማትፈርደው፥ ደማችንስ የማትበቀለው እስከ መቼ ድረስ ነው?» በማለት ይጮኹ ነበር።11ከዚያም በኋላ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤እነርሱ እንደ ተገደሉ፥ ገና የሚገደሉ አገልጋይ ጓደኞቻቸው፥ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እንዲታገሱ ተነገራቸው።12በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ አየሁ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ። ፀሐይም እንደ ጥቁር ጨርቅ ጠቆረች፤ ጨረቃም ሙሉ በሙሉ እንደ ደም ቀላች።13የበለስ ዛፍ ኀይለኛ ነፋስ በሚወዘውዛት ጊዜ በላይዋ ያለ ያልበሰለ ፍሬ እንደሚረግፍ ሁሉ የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ረገፉ።14ሰማይም እንደ ብራና እየተጠቀለለ ተወገደ፤ እያንዳንዱ ተራራና ደሴት ከስፍራው ተነቀለ።15ከዚያም በኋላ የምድር ነገሥታት፥ታላላቅ ሰዎች፥ የጦር መኮንኖች፥ ሀብታሞች፥ብርቱዎች፥ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ።16ለተራሮችና ለዐለቶችም እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤«በላያችን ላይ ውደቁ፤ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት፥ከበጉም ቁጣ ሰውሩን17ታላቁ የቁጣቸው ቀን ስለ መጣ ማን መቆም ይችላል?»
1ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱም የምድር ማዕዘን ቆመው አየሁ፤ እነርሱም በምድር ቢሆን በባሕር ላይ ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ ፈጽሞ ነፋስ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳትን አጥብቀው ይከለክሉ ነበር።2የሕያው አምላክ ማኅተም የያዘ ሌላ መልአክ ከምስራቅ ሲመጣ አየሁ። እርሱም ምድርንና ባሕርን ይጎዱ ዘንድ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ወደ አራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኽ፥3«በአምላካችን አገልጋዮች ግምባር ላይ ማኅተም እስክናደርግ ድረስ ምድርንም ሆነ ባሕርን ወይም ዛፎችን እንዳትጎዱ» አለ።4ከእስራኤል ሕዝብ ነገድ ሁሉ የታተሙት ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ እንደ ሆነ ሰማሁ።5ከይሁዳ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከሮቤል ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከጋድ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥6ከአሴር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከንፍታሌም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከምናሴ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ7ከስምዖን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከሌዊ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከይሳኮር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥8ከዛብሎን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከዮሴፍ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከብንያም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ።9ከዚህ በኋላ ከሕዝብ፥ከነገድ፥ከወገንና ከቋንቋ ሁሉ የመጡ ቁጥራቸው ማንም ሊቆጥረው የማይችል አጅግ ብዙ ሕዝብ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ በእጃቸውም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው አየሁ።10በታላቅ ድምፅም «ማዳን፥ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!» እያሉ ይጮኹ ነበር።11መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑ እና በሽማግሌዎች ዙሪያ እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን ዙሪያ ቆመው ነበር፤እነርሱም በመሬት ላይ ወድቀው በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፥12«አሜን! ውዳሴ፥ ክብር፥ጥበብ፥ምስጋና፥ኀይልና ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአምላካችን ይሁን፤አሜን» ይሉ ነበር።13ከዚያም በኋላ ከሽማግሌዎች አንዱ፥«እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱ እነማናቸው ከየትስ የመጡ ናቸው?» በማለት ጠየቀኝ፤14እኔም «ጌታ ሆይ፥አንተ ታውቃለህ» አልሁት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤«እነዚህ በታላቁ መከራ ውስጥ አልፈው የመጡ ናቸው፤ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው በማንጻት ነጭ አድርገዋል።15ክዚህም የተነሳ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት መሆን ችለዋል፤ እርሱንም በመቅደሱ ውስጥ ቀንና ሌሊት ያመልኩታል። በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን በእነርሱ ላይ ይዘረጋል።16እነርሱም ከእንግዲህ አይራቡም፤አይጠሙምም። ፀሐይ አያቃጥላቸውም፤ ሙቀትም አያሰቃያቸውም።17ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናል፤ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ ይመራቸዋል፤እግዚአብሔር እንባንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል።»
1በጉ ሰባተኛውን ማህተም በፈታ ጊዜ በሰማይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ጸጥታ ሆነ፤2ከዚያም በእግዚአብሄር ፊት የቆሙ ስባት መላዕክትን አየሁ፡፤ሰባት መለከቶችም ተሰጣቸው።3ሌላም መልኣክ መጣ፤በእጁም ከወርቅ የተሰራ ጥና ይዞ ነበር።እርሱም በመሰዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር።በዙፋኑ ፊት ባለው በወርቅ በተሰራ መሰዊያ ላይ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር የሚያቀርበው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።4የእጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሄር ወጣ፤5መልአኩም ጥናውን ወስዶ ከመሰዊያው በወስድው እሳት ሞላው ከዚያም በኃላ ወደ ምድር ወረወረው፤የነጎድጛድ ድምጽ፤መብረቅ፤የምድር መናወጥም ሆነ።6ሰባት መለከቶችን የያዙ ስባት መላዕክት መለከቶቻቸውን ለመንፋት ተዘጋጁ።7የመጀመሪያውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ደም የተቀላቀለበት እሳትና በረዶ ሆነ። ይህም ወደ ምድር ተጣለ፤ ከዚህም የተነሣ የምድርም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የዛፎችም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የለመለመ ሣር ሁሉ ተቃጠለ።8ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገር ወደ ባህር ተጣለ፤ የባህር አንድ ሦስተኛ ወደ ደም ተለወጠ።9በባህር ውስጥ ካሉ ህያዋን ፍጥረታት አንድ ሦስተኛ ሞቱ፤ የመርከቦችም አንድ ሦስተኛ ተደመሰሱ።10ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ የወደቀውም በወንዞች አንድ ሦስተኛ በውሃ ምንጮች ላይ ነው።11የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል። የውኆችም አንድ ሦስተኛ መራራ ሆነ። ከውሃው መራራነት የተነሳ ብዙ ሰዎች ሞቱ።12አራተኛውም መልአክ መልከቱን ነፋ፤የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፣ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ። ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛ ጨለመ፤ በዚህም ምክንያት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛው ያለ ብርሃን ሆነ።13እነሆ በሰማይ መካከል ሲበርር የነበር አንድ ንስር በታላቅ ድምጽ፤ ሦስቱ መላእክት የቀሩትን መለከቶች ስለሚነፉ «በምድር ላይ ለሚኖሩ ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!» ሲል ሰማሁ።
1አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ አንድን ኮከብ ከሰማይ ወደ ምድር ሲወድቅ አየሁ። ኮከቡም የጥልቁ ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው፤2እርሱም ጥልቅ የሆነውን ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ፤ ከጕድጓዱ በሚወጣው ጢስ ምክንያት ፀሐይና አየር ወደ ጨለማነት ተለወጡ፤3ከጢሱም ውስጥ አንበጣዎች በምድር ላይ ወጡ፤የምድር ጊንጦችን ኅይል የመሰለ ኅይል ተሰጣቸው፤4የምድርንም ሣር ሆነ ማናቸውንም የለመለመ ተክል ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጎዱ ተነገራቸው። መጉዳት የነበረባቸው ግን በግንባራቸው ላይ የእግዚአብሔር ማህተም የሌለባቸውን ሰዎች ብቻ ነው።5እነርሱንም ቢሆን ለአምስት ወር ለማሰቃየት ብቻ እንጂ የመግደል ሥልጣን አልተሰጣቸውም። የእነርሱም ስቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሰማው ስቃይ ዐይነት ነበር።6በእነዚያ ቀናት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ነገር ግን አያገኙትም። ለመሞት በብርቱ ይሻሉ፤ ነገር ግን ሞት ከእነርሱ ይሸሻል።7አንበጦቹ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነበሩ። በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ነበር፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር።8የሴቶች ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው። ጥርሳቸው የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር።9የብረት ጥሩር የሚመስልጥሩር ነበራቸው፤ የክንፎቻቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት የሚጋልቡ ብዙ ፈረሶችና ሰረገሎች የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር።10እንደ ጊንጥ መንደፊያ ያለው ጅራት ነበራቸው። ሰዎችንም በጅራታቸው ባለ መንደፊያ ለአምስት ወር ለመጉዳት ስልጣን ነበራቸው።11በእነርሱም ላይ የጥልቁ ጕድጓድ መልአክ የሆነ ንጉሥ ነበራቸው። ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን ሲሆን በግሪክ ደግሞ አጶሊዮን ይባላል፥12የመጀመሪያው ወዮ አልፎአል፥ልብ በል! ከዚህ በኋላ ሌላ ሁለት ጥፋቶች ይመጣሉ።13ስድስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፥ በእግዚአብሔር ፊት ካለው በወርቅ ከተሰራው መሰዊያ ከቀንዶቹ ድምጽ ሲወጣ ሰማሁ።14ድምፁም መለከት የያዘውን ስድስተኛውን መልአክ፣ «በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው» አለው።15ለዚያ ሰዓትና ለዚያ ቀን ለዚያ ወርና ለዚያ ዓመት ተዘጋጅተው የነበሩት አራት መላእክት የሰዎችን አንድ ሦስተኛ እንዲገድሉ ተፈቱ።16የፈረሰኛው ሰራዊት ብዛት ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር።ቍጥራቸውንም ሰማሁ።17ፈረሶቹና በፈረሶቹ ላይ የሚጋልቡ በራእይ ያየኋቸው በዚህ ዐይነት ነበር፥ በደረታቸው ላይ የነበረው ጥሩር እንደ እሳት ቀይ፣ እንደ ያክንት (ጥቁር ሰማያዊ)፣ እንደ ዲንም ቢጫ ነበር፥ የፈረሶቹ ራስ የአንበሳ ራስ ይመስል ነበር። ከአፋቸው እሳትና ጢስ ዲንም ይወጣ ነበር።18በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች ማለትም ከአፋቸው በወጣው እሳት፤ ጢስና ዲን የሰዎች አንድ ሦስተኛ ተገደለ።19የፈረሶቹ ኃይል በአፋቸውና በጅራታቸው ነበር፥ ምክንያቱም ጅራታቸው እባብ ይመስላል፥ ራስ አላቸው፥ ሰውን የሚጎዱትም በእርሱ ነበር።20በእነዚያ መቅሰፍቶች ከመሞት የተረፉት ሰዎች ከክፉ ሥራቸው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወር፣ ከብር፣ ከናስ፣ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ፣ ማየት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖታት ማምለክንም አልተዉም።21እንዲሁም ከነፍሰ ገዳይነት ወይም ከሟርት፥ ከሴስኛነትና፥ ከሌብነት ንስሓ አልገቡም።
1ከዚህ በኋላ ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። እርሱም ደመናን የለበሰ ነበር። በራሱም ዙሪያ ቀስተ ደመና ነበር። ፊቱ እንደ ፀሐይ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምድ ነበሩ፤2የተከፈተ ትንሽ ጥቅል መጽሐፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባህር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አደረገ።3ከዚያም እንደሚያገሳ አንበሳ በመሰለ ታላቅ ድምጽ ጮኸ፤ በጮኸ ጊዜ፣ ሰባቱም ነጎድጓዶች ድምፃቸውን አሰሙ ፤4ሰባቱ ነድጓዶች በተናገሩ ድምፃቸውን ባሰሙ ጊዜ፣ እኔ ልጽፍ አሰብሁ። ነገር ግን «ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን በምስጢር ያዘው እንጂ አትጻፈው» የሚል ድምጽ ከሰማይ ሰማሁ።5ከዚያም በባህርና በምድር ላይ ቆሞ ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አነሣና6ዘላለም በሚኖረው ሰማይንና በእርሱ ያሉትን፣ ምድርንና በእርስዋ ያሉትን፣ ባህርንና በርስዋ ያሉትን በፈጠረው አምላክ ስም ማለ። እንዲህም አለ፤«ከእንግዲህ ወዲህ አይዘገይም7ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ መለከቱን በሚነፋበት ቀን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት በገለጠላቸው መሰረት የእግዚአብሔር ምስጢር ይፈጸማል።»8ከሰማይ የሰማሁት ድምጽ፣«በባህርና በምድር ላይ የቆመው መልአክ በእጁ የያዘውንና የተፈታውን ጥቅል መጽሐፍ ሂድና ውሰድ» ብሎ እንደገና ሲናገረኝ ሰማሁት»።9ወደ መልእኩም ሄጄ «ትንሹን ጥቅል መጽሐፍ ስጠኝ?» አልሁት። እርሱም «ውሰድና ብላ በሆድህም ውስጥ መራራ ይሆናል፤ በአፍህ ግን እንደ ማር ይጣፍጣል»አለኝ።10እኔም ትንሹን ጥቅል መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላሁት፤ በአፌ እንደ ማር ጣፈጠ፤ ከበላሁት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ።11ከዚህም በኋላ «ስለብዙ ሕዝቦች፤ አገራት፤ ልዩ ልዩ ቋንቋ ስለሚናገሩ ሰዎችና ሰለ ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት መናገር አለብህ» ተብሎ ተነገረኝ።
1ከዚያም ለመለኪያ የሚያገለግል አንድ ረዥም ዘንግ ተሰጠኝ፤እንዲህም ተባልሁ፣«ተነሥተህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፥ መሰዊያውንና በዚያ የሚያመለኩትንም ቍጠር።2ከቤተመቅደሱ ውጭ ያለውን አደባባይ ግን ተወው፤ እርሱ ለአሕዛብ የተሰጠ ስለ ሆነ አትለካው፥አሕዛብ ቅድስቲቱን ከተማ አርባ ሁለት ወራት ይረግጧታል።3ሁለቱ ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ለ1260 ቀን ትንቢት እንዲናገሩ ሥልጣን እሰጣቸዋለሁ።»4እነዚህም በምድር ጌታ ፊት የቆሙ ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው፤5ማንም እነርሱን ሊጎዳ ቢፈልግ እሳት ከአፋቸው ወጥቶ ጠላቶቻቸውን ይበላል፤ እነርሱን ሊጎዳ የሚፈልግ ሁሉ የሚሞተው በዚህ ዐይነት ነው፥6እነዚህ ምስክሮች ትንቢት በሚናገሩባቸው ቀናት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ለመዝጋት ሥልጣን አላቸው፥ እንዲሁም ውሆችን ወደ ደም ለመለወጥና በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት ምድርን ለመምታት ሥልጣን አላቸው፡7ምስክርነታቸውን በጨረሱ ጊዜ ከጥልቁ ጉድጛድ የሚወጣው አውሬ ከእነርሱ ጋር ይዋጋል፤ ያሸንፋቸዋል ይገድላቸውማል።8ሬሳቸውም በምሳሌያዊ አጠራር ሰዶም ወይም ግብጽ ተብላ በምትጠራው በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይጋደማል፤ ከተማይቱም የእነርሱ ጌታ የተሰቀለባት ናት፤9ከልዩ ልዩ ወገን፥ ነገድ፥ ከልዩ ልዩ ቋንቋና ሕዝብ የሆኑ ሰዎች ሶስት ቀን ተኩል ሬሳቸውን ይመለከታሉ፥ ሬሳቸውም እንዳይቀበር ይከለክላሉ።10ሁለቱ ነቢያት የምድርን ሰዎች ሁሉ አስጨንቀው ስለ ነበር፣ በእነርሱ ሞት በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም በዓል ያደርጋሉ፤ ስጦታም ይለዋወጣሉ።11ነገር ግን ሦስት ቀን ተኩል ካለፈ በኋላ፣ የሕይወት እስትንፋስ ከእግዚአብሔር መጥቶ ወደ ሬሳዎቹ ይገባል፤ በእግራቸውም ይቆማሉ፤ የሚመለከቷቸውም ሰዎች ታላቅ ፍርሃት ይወድቅባቸዋል።12ከዚህ በኋላ ሁለቱ ነቢያት፣ «ወደዚህ ውጡ» የሚል ታላቅ ድምጽ ከሰማይ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቷቸው በደመና ወደ ሰማይ ወጡ።13በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ወደመ። በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ለሰማይም አምላክ ክብርን ሰጡ።14ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ልብ በል! ሦስተኛው ወዮ ፈጥኖ ይመጣል።15ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤በሰማይም«የዓለም መንግሥት የጌታ አምላካችንና የእርሱ ክርስቶስ ሆናለች፤ እርሱም ለዘላለም ይነግሣል» የሚል ታላቅ ድምጽ ሰማሁ።16በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው ላይ የተቀመጡት ሃያ አራቱም ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤17እነርሱም እንዲህ አሉ፣«ያለህና የነበርህ፣ ሁሉን የምትችል፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ትልቁን ሥልጣንህን በእጅህ አድርገህ ስለ ነገሥህ እናመሰግንሃለን።18አሕዛብ ተቆጡ፤ ነገር ግን የአንተም ቁጣ መጣ ።በሙታን ላይ የምትፈርድበት ዘመንም መጣ፤ለአገልጋዮችህ፣ ለነቢያት፣ ለቅዱሳን፣ ስምህንም ለሚያከብሩት ለታናናሾችና ለታላላቆች ሽልማታቸውን የምትሰጥበት ጊዜ እንዲሁም ምድርን ያጠፏትን የምታጠፋበት ጊዜ ደረሰ።»19በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ፤የእርሱም የቃል ኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ የመብረቅ ድምጽ፣ነጎድጓድም፣የምድር መናወጥና ታላቅም ማዕበል ሆነ።
1በሰማይም ታላቅ ምልክት ታየ ፤ ፀሐይን የለበሰችና ጨረቃን ከእግሯ በታች ያደረገች፣ ዐሥራ ሁለት ከዋክብት ያሉት አክሊልም በራስዋ ላይ የደፋች አንዲት ሴት ታየች።2እርስዋም ነፍሰ ጡር ነበረች፤ ምጥ ይዟትም ተጨንቃ ትጮህ ነበር፥3እንዲሁም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ፤እነሆ፤ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች የነበሩት፤በራሶቹም ላይ ሰባት አክሊል የደፋ ትልቅ ቀይ ዘንዶ ታየ።4በጅራቱ የኮከቦችን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር ጣለ፤ዘንዶውም ሴቲቱ በምትወልድበት ጊዜ ልጅዋን ለመዋጥ አስቦ ልትወልድ ወደ ተቃረበችው ሴት ፊት ቆመ።5ሴቲቱም ሕዝቦችን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጅዋ ግን ወደ እግዚአብሔርና ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተወሰደ፤6ሴቲቱም ወደ ምድረበዳ ሸሽታ ሄደች፤ በዚያም እግዚአብሔር ለ1260 ቀን በክብካቤ ተይዛ እንድትጠበቅ አደረጋት።7በሰማይም ጦርነት ሆነ። ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ዘንዶውና መላእክቱ መልሰው ተዋጓቸው።8ነገር ግን ዘንዶው የማሸነፍ ዐቅም አልነበረውም፤ከዚያም ወዲያ እርሱና መላእክቱ በሰማይ የነበራቸውን ስፍራ አጡ።9ታላቁም ዘንዶ ወደ ምድር ተጣለ፤ እርሱም ሰዎችን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀደመው እባብ ነው።እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።10ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤«አሁን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የአምላካችን ሆኖአል፤ሥልጣንም የእርሱ ክርስቶስ ሆኖአል።ምክንያቱም ወንድሞቻችንን በአምላካችን ፊት ቀንና ለሊት ሲከሳቸው የነበረ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአል።11እነርሱም በበጉ ደምና በተናገሩት የምስክርነት ቃል ድል ነሡት፤ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋልና።12ስለዚህ ሰማይና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርና ባህር ግን ወዮላችሁ፤ ምክንያቱም ጥቂት ጊዜ እንደ ቀረው ዐውቆ ዲያቢሎስ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዷል።13ዘንዶው ወደ ምድር እንደተጣለ ባስተዋለ ጊዜ፤ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት፤14ሴቲቱ ከእባቡ ፊት ርቃ ለዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመንም እኩሌታ በክብካቤ ተጠብቃ ወደ ምትኖርበት በምድረ በዳ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ ሁለት የታላቅ ንስር ክንፎች ተሰጧት።15እባቡ የወንዝ ውሃ የሚያህል ውሃ ከአፉ ተፍቶ ሴቲቱ በጎርፍ እንድትወሰድ ብሎ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።16ነገር ግን ምድር አፍዋን ከፍታ ዘንዶው በአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ በመዋጥ ረዳቻት።17ከዚያም ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ ከትሩፋን ዝርያዎችዋ ጋር ሊዋጋ ሄደ። እነርሱም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና ስለ ኢየሱስ በታማኝነት የሚመሰክሩት ናቸው።18ዘንዶውም በባህር ዳር ባለው አሸዋ ላይ ቆመ።
1ከዚያም አንድ አውሬ ከባህር ሲወጣ አየሁ። እርሱም ዐስር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት። በቀንዶቹም ላይ አስር አክሊሎች ነበሩ፤ በራሶቹም ላይ እግዚአብሔርን የሚሰድብ ስሞች ነበሩት።2ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፤ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ይገዛም ዘንድ ዘንዶው የራሱን ኅይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ስልጣን ለአውሬው ሰጠው።3ከአውሬው ራሶቹ አንዱ ለሞት የሚያበቃ ቁስል እንደነበረው ሆኖ አየሁት፤ ነገር ግን ለሞት የሚያደርስው ቁስል ዳነ፤በዚህም ምክንያት ዓለም በሙሉ በመደነቅ አውሬውን ተከተለ።4አውሬውም ስልጣኑን በመስጠቱ ሁሉም ለዘንዶው ሰገዱለት «አውሬውን ማን ይመስለዋል? ከእርሱስ ጋር ማን ሊዋጋ ይችላል?» እያሉ ለአውሬው ሰገዱለት።5አውሬውም የትዕቢትና የስድብ ቃል የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፤ ለአርባ ሁለት ወራትም ስልጣኑን እንዲያሳይ ተፈቀደለት።6አውሬው አፉን ከፍቶ እግዚአብሔርን፤ የእግዚአብሔርን ስም፤ መኖሪያውንና በሰማይ የሚኖሩትን መሳደብ ጀምረ።7አውሬው ቅዱሳንን እንዲዋጋ ና፤ ድል እንዲነሳቸውም ስልጣን ተሰጠው። በነገድና በወገን በቃንቃና በህዝብ ሁሉ ላይ ስልጣን ተስጠው።8ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ ስሞቻቸው በታረደው በግ የህይወት መጽሀፍ ያልተጻፈ በዓለም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁ ሉ ለአውሬው ይሰግዳሉ።9የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።10«የሚማረክ ማንም ቢኖር ወደ ምርኮ ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገደል ማንም ቢኖር በሰይፍ ይገደላል» እንግዲህ የቅዱሳን ትዕግስትና እምነት የሚታየው በዚህ ጊዜ ነው።11ከዚህም በኃላ ሌላ አውሬ ደግሞ ከምድር ሲውጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶች የሚመስሉ ሁለት ቀንዶች ነበሩት አነጋግሩም እንደ ዘንዶው ነበር።12የመጀመሪያውን አውሬ ስልጣን ሁሉ በመጀመሪያው አውሬ ፊት ሆኖ ይሰራበት ነበር፤ ምድርና በእርስዋ ላይ የሚኖሩት ሁሉ ለአውሬው እንዲሰግዱለት ያደርጋል፤ ይህም አውሬ ያ ለሞት የሚያድርስ ቁስል የዳነለት የመጀመሪያው አውሬ ነው።13እርሱም በሰዎች ፊት እሳትን ከሰማይ እስከማውረድ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችን ያደርግ ነበር፤14እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተዓምራት በሰይፍ ቁስሎ የዳነውን የአውሬውን ምስል እንዲሰሩ በማዘዝ በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር።15እርሱም ምስሉ መናገር እንካ እስከሚችል ድረስ እስትንፋስ ለመስጠትና ለአውሬው የማይስግዱትን መግደል ይችል ዘንድ ለማድረግ ስልጣን ተሰጠው።16እርሱም ታናናሾችም ሆኑ ታላላቆች፤ ሀብታሞችም ሆኑ ድኾች ጌቶችም ሆኑ አገልጋዮች ሁሉም በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ላይ ምልክት እንዲያደርጉ አስገደዳቸው።17የአውሬው ስም የሆነው ምልክት ወይም የስሙ ቁጥር የሌለው ማንም ሰው መግዛትም ሆን መሸጥ አይችልም ነበር።18ይህ ጥበብን የሚጠይቅ ነው።የሚያስተውል የአውሬውን ቁጥር ያስላው፤ ቁጥሩም የሰው ቁጥር ነው፤ የውሬውም ቁጥር 666 ነው፤
1አየሁም እነሆ በጉ በጽዮን ተራራ በፊቴ ቆሞ ነበር። ከእርሱ ጋር የእርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።2በሰማይ እንደ ብዙ ውኃ ድምጽና ና እንደታላቅ ነጎድጋድ ድምጽ የመሰለ ድምጽ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምጽ በገና ደርዳሪዎች በገና እየደረደሩ የሚያሰሙትን ድምጽ ይመስል ነበር።3እነርሱም በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች በሽማግሌዎችም ፊት አዲስ መዝሙር ዘመሩ። ይህንም መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከአንድ መቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።4እነርሱም ራሳቸውን ከሴቶች ጋር ካላረከሱት ናቸው፤ ራሳቸውንም በግብረ ስጋ ግንኙነት ካለማርከስ ጠብቀዋል። እነርሱ ናቸው በጉ ወደሚሄድበት ሁሉ የሚከተሉት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኩራት ለመሆን ከሰዎች መካከል የተዋጁ ናቸው።5በአንደበታቸውም ሀሰት ተናግረው አያውቁም። ነቀፋም የሌለባቸው ናቸው።6በምድር ላይ ለሚኖሩ ለህዝብ፤ ለነገድ፤ ለቃንቃና ለወገን ሁሉ ለማብሰር ዘላለማዊውን የምስራች ቃል የያዘ ሌላ መልዓክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ7እርሱም በታላቅ ድምጽ «እግዚአብሄርን ፍሩ፤ አክብሩትም። ምክንያቱም የእርሱ የፍርድ ሰዓት ደርሳል፤ ሰማይን፤ ምድርን፤ ባህርንና የውሃ ምንጮችን የፈጠረን አምላክ አምልኩ» አለ8ሌላም ሁለተኛ መልአክ «የዝሙትዋ ፍትወት የሆነውን የሚያሰክር የወይን ጠጅ ለህዝቦች ሁሉ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፤ ወደቀች» እያለ የመጀመሪያውን መልዓክ ተከተለው9ሌላ ሶስተኛ መለዓክ በታላቅ ድምጽ እንዲህ እያለ ተከተላቸው «ለአውሬውና ለምስሉ ቢሰግዱ ምልክቱን በግምባሩ ወይም በእጁ ቢያደርግ፤10የእግዚአብሔርን የቁጣ የወይን ጠጅ ይጠጣል፤ ይህም የወይን ጠጅ ሳይበረዝ በቁጣው ጽዋ የተዘጋጀ ነው፤ ፅሚጠጣውም ሰው በቅዱሳን መላዕክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል፤11የስቃያቸውም ጢስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት ያደረጉ ሁሉ ቀንና ለሊት ዕረፍት የላቸውም።12የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቁና በኢየሱስ የሚያምኑማመኑ ቅዱሳን፤ ትዕግስታቸው የሚታየው እዚህ ላይ ነው።13ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማሁ «ይህን ጻፍ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ ሆነው የሚሞቱ የተባረኩ ናቸው» መንፈስም አዎ ስራቸው ስለሚከተላቸው ከድካማቸው ያርፋሉ» ይላል14አየሁም እነሆ ነጭ ደመና ነበር በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦ ነበር። በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል አድርጎአል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዞአል።15ከዚህም በኃላ ሌላ መልአክ ከመቅደሱ ወጣ በደመና ላይ የተቀመጠውን በታላቅ ድምጽ «የምድር መከር ደርሶአል የአጨዳ ሰዓትም ቀርቦአል፤ ስለዚህ ማጭድህን ስደድ» አለው።16በደመናው ላይ የተቀመጠውም ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደው ምድርም ታጨደች።17ሌላ መልዓክ ከሰማይ ባለው መቅደስ ወጣ፤ እርሱም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር።18በእሳትም ላይ ስልጣን ያለው ሌላ መልዓክ ከመሰዊያው አጠገብ ወጣና ስለታም ማጭድ የያዘውን መልዓክ በታላቅ ድምጽ «የዘለላዎቹ ፍሬዎች ስለበሰሉ የወይን ዘለላዎችን ሁሉ ከምድር ወይን ቁረጥ» አለው።19መልዓኩም ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደው፤ የምድርንም ወይን ዘለላ ቆረጠ፤ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር የቁጣ ወይን መጭመቂያ ውስጥ ጣለው።20ከከተማው ውጭ ባለው በወይን መጥመቂያም ተጨመቀ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረስ ልጋም ወደ ላይ ከፍ ያለና 300 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ደም ወጥቶ ፈሰሰ።
1ከዚህም በኃላ ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ የሚፈጽምባቸው የመጨረሻዎቹን ሰባት መቅሰፍት የያዙትን ሰባት መላዕክት አየሁ2እኔም እሳት የተቀላቀለበት የሚመስል የመስተዋት ባህር አየሁ፤ አውሬውንና የአውሬውን ምስል የስሙንም ቁጥር ድል የነሱትን በባህሩ አጥገብ ቆመው ነበር። እግዚአብሔር የሰጣቸውንም በገና ይዘው ነበር።3እነርሱም የእግዚአብሔር አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር «ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ ስራህ ታላቅና አስደናቂ ነው። የእዝቦች ንጉስ ሆይ መንገድህ ትክክልና እውነት ነው።4ጌታ ሆይ አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? ምክንያቱም አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ የጽድቅ ስራህ ስለተገለጠ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።»5ከዚህም በኃላ አየሁ እነሆ የምስክር ድንካን የሆንው ቅድስተ ቅዱሳን በሰማይ ተከፈተ።6ከቅድስተ ቅዱሳንም ሰባቱን መቅሰፍቶች የያዙት ሰባት መላዕክት ወጡ፤ የሚያንጸባርቅ ነጭ ልብስ ለብሰው ነበር። ደረታቸውንም በወርቅ መታጥቂያ ታጥቀው ነበር።7ከአራቱ ህያዋን ፍጡራን አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖረው አምላክ ቁጣ የተሞሉትን ሰባት የውርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላዕክት ሰጣቸው።8ቅድስተ ቅዱሳኑም ከእግዚአብሔር ክብርና ኃይል የተነሳ በጢስ ተሞላ፤ ሰባቱ መላዕክት የያዙእቸው ስባት መቅሰፍቶች እስኪፈጽሙ ድረስ ማንም ወደ ቅዱሰተ ቅዱሳኑ መገባት አልቻሉም።
1ሰባቱን መላእክት፣ “ሂዱና ሰባቱን የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች ምድር ላይ አፍስሱ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሲወጣ ሰማሁ።2የመጀመሪያው መልአክ ጽዋውን ምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬው ምልክት ባላቸውና ለምስሉ በሰገዱት አስከፊና የሚያሠቃይ ቁስል ወጣባቸው።3ሁለተኛው መልአክ ጽዋውን ባሕር ላይ አፈሰሰ፤ ባሕሩ እንደ ሞተ ሰው ደም ሆነ፤ ባሕር ውስጥ የነበረ ሕያው ፍጡር ሁሉ ሞተ።4ሦስተኛው መልአክ ጽዋውን ወንዞችና የውሃ ምንጮች ላይ አፈሰሰ እነርሱም ደም ሆኑ።5የውሃውም መልአክ፣ “ያለህና የነበርህ ቅዱስ ጌታ እንዲህ ስለ ፈረድህ ትክክል ነህ፣6ምክንያቱም የቅዱሳንህና የነበያትን ደም ስላፈሰሱ፣ ደም አጠጣሃቸው፤ ይህም የሚገባቸው ነው” ሲል ሰማሁ።7ከመሠዊያውም፣ “አዎን፣ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ፍርድህ እውነትና ትክክል ነው” የሚል ድምፅ ወጣ።8አራተኛው መልአክ ጽዋውን ፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ለእርሷም ሰዎችን በግለትዋ የማቃጠል ሥልጣን ተሰጣት።9ሰዎች በከባድ ሙቀቷ ተቃጠሉ፤ በእነዚህ መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔር ስም ሰደቡ። ንሰሐ አልገቡም፤ ክብርም አልሰጡትም።10አምስተኛው መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት በጨለማ ተዋጠ። ከሥቃያቸውም የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር።11ከሥቃያቸውና ከደረሰባቸው ቁስል የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ያም ሆኖ ግን ስላደረጉት ክፉ ሥራ ንስሐ ለመግባት ፈቃደኞች አልሆኑም።12ስድስተኛው መልአክ ጽዋውን ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለመጡ ነገሥታት መንገድ ለማዘጋጀት የወንዙ ውሃ ደረቀ።13ከዘንዶው አፍና ከአውሬው አፍ እንዲሁም ከሐስተኛው ነቢይ አፍ እንቁራሪት የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ስወጡ አየሁ።14እነዚህ ተአምራዊ ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው። ሁሉን በሚገዛ አምላክ ታላቅ ቀን ለሚደረገው ጦርነት የዓለም መንግሥታችን ሁሉ ለመሰብሰብ ወደ ወጥተው ሄዱ።15“ልብ በሉ! እኔ እንደ ሌባ እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይገኝና ሰዎችም ሐፍረቱን እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ የተባረከ ነው።”16መናፍስቱ ነገሥታቱን ሰብስበው በዕብራይስጥ አርማጌደን ወደሚባል ቦታ አመጧቸው።17ሰባተኛው መልአክ ጽዋውን አየር ላይ አፈሰሰ። በዚያን ጊዜ፣ “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱና ከዙፋኑ ወጣ።18ከዚያም የመብረቅ ብልጥታ፣ ሁካታ ነጎድጓድና ከባድ የመሬት መናወጥ ሆነ፤ የዚያ ዓይነት የምድር ነውጥ የሰው ልጅ ምድር ላይ መኖር ከጀመረ አንሥቶ ሆኖ የማያውቅ እጅግ ከባድ ነበር።19ታላቂቷ ከተማ ለሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ተደመሰሱ። እግዚአብሔር ታላቂቱ ባቢሎንን አስታወሰ፤ ለዚያች ከተማም የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንድትጠጣ ሰጣት።20ደሴቶች ሁሉ ጠፋ፤ ተራሮችም በቦታቸው አልተገኙም።21አንድ ታለንት የሚመዝን የበረዶ ድንጋይ ከሰማይ ወርዶ ሰዎች ላይ ወደቀ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሰቃቂ ከመሆኑ የተነሣ ሰዎች ስለ በረዶው ድንጋይ እግዚአብሔርን ተራገሙ።
1ሰባቱን ጽዋዎች ይዘው ከነበሩት ሰባት መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ አለን፤ “በብዙ ውሆች ላይ የተቀመጠችውን ታላቂቱ አመንዝራ የፍርድ ቅጣት አሳይሃለሁ፤2የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመንዝረሃል፤ ከዝሙቷ ወይን ጠጅ የምድር ነዋሪዎች ሰክረዋል።”3መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሐ ወስዶኝ፣ የስድብ ስሞች በሞሉበት ቀይ አውሬ ላይ የተቀመጠች ሴት አየሁ። አወሬው ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ነበሩት።4ሴትዬዋ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ፣ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች እንዲሁም በዕንቁዎች አጊጣ ነበር። በእዛም ጸያፍ ነገሮችና የዝሙቷ ርኩሰት የሞላበት የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር።5ግንባሯም ላይ፣ “ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር ጸያፍ ነገሮች እናት” የሚል ምስጢራዊ ትርጉም ያለው ስም ተጽፎ ነበር።6ሴትዬዋ በቅዱሳንና በኢየሱስ ሰማዕታት ደም ሰክራ አየሁ። ባየኋት ጊዜ በጣም ተደነቅሁ።7መልአኩ ግን፣ “ለምን ትደነቃለህ? የሴትዮዋንና የተሸከማትን አውሬ (ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉትን አውሬ) ምንነት እነግርሃለሁ።8ያየኸው አውሬ ቀድሞ ነበረ፤ አሁን የለም፤ ሆኖም በኃላ ከጥልቁ ጉድጓድ ይመጣል። ከዚያም ወደ ጥፋት ይሄዳል። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ሰማቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፈ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ቀድሞ የነበረውን፣ አሁን የሌለውን በኃላ ግን የሚመጣውን አውሬ ሲያዩ ይደነቃሉ።9ይህ አስተዋይ አእምሮን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴትዬዋ የተቀመጠችባቸው ሰባት ኮረብቶች ናቸው።10እነርሱም ሰባት ነገሥታት ናቸው። አምስቱ ወድቀዋል፤ አንድሱ አሁንም አለ፤ ሌለው ገና አልመጣም፤ በሚመጣበት ጊዜ ግን ለአጭር ጊዜ መቆየት ይገባዋል።11ቀድሞ የነበረው አሁን ግን የሌለው አውሬ ራሱ ስምንተኛው ንጉሥ ነው ሆኖም፣ ከሰባቱ አንዱም ነው ወደ ጥፋትም ይሄዳል።12ያዩኋቸው አሥር ቀንዶች ገና መንግሥት ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታት ናቸው፤ ነገር ግን ለአንድ ሰዓት ያህል ከአውሬው ጋር እንዲነግሡ ሥልጣን ይቀበላሉ።13እነዚህ ነገሥታት ተመሳሳይ ሐሳብ አላቸው፤ ኅይልና ሥልጣናቸውን ሁሉ ለአውሬው ያስረክባሉ።14በጉን ይዋጋሉ። ይሁን እንጂ፣ በጉ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ በመሆኑ እርሱ ያሸንፋቸዋል የተጠሩት፣ የተመረጡትና ታማኝ የሆኑት ከእርሱ ጋር ድል ይነሣሉ።”15መልአኩም፣ “አመንዝራዋ ተቀመጣባቸው የነበሩት ያየሃቸው ውሆች ሕዝቦችና ሰዎች፣ ወገኖችና ቋንቋዎች ናቸው” አለኝ።16ያየሃቸው አሥር ቀንዶች ከአውሬው ጋር አንድ ላይ ሆነው አመንዝራዋን ይጠላሉ። ያጠፏታል፤ ራቁትዋን ያስቀሯታል፤ ሥጋዋን ይበላሉ፤ ጨርሶ እስክትጠፋ በእሳት ያቃጥሏታል።17ምክንያቱም፣ የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም ድረስ ሥልጣናቸውን ለአውሬው ለመስጠት በመስማማት ዕቅዱን እንዲፈጽሙ እግዚአብሔር ይህን ሐሳብ በልባቸው ውስጥ አኑሮአል።18ያይየሃት ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትገባ ታላቂቱ ከተማ ናት።”
1ከዚህ በኋላ ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። ታላቅ ሥልጣንም ነበረው፤ ምድርም በክብሩ አበራች።2በታላቅ ድምፅም ጮኾ እንደኢህ አለ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩሳን መናፍስት ሁሉ ማደሪያ፣ የማንኛውም ርኩስና ጠያፍ ወፍ መጠጊያ ሆነች3ሕዝቦች ሁሉ ቁጣ በሚያመጣበት የዝሙቷ ወይን ጠጅ ሰክረዋል። የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመንዝረዋል። የምድር ነጋዴዎች በምቾት ኑሮዋ በልጽገዋል።”4ሌላ ድምጽም ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ፣ በኃጢአትዋ እንዳትካፈሉ የማመጣበትንም መቅሠፍት እንዳትቀበሉ ከእርሷ ውጡ።5ኃጢአቷ እስከ ሰማይ ተከምሯል እግዚአብሔር ክፉ ሥራዋን አስታውሷል።6በሰጠችው መጠን ስጧት፤ ባደረገችው መጠን ዕጥፍ አድርጉባት እርሷ በቀካቀከችው ጽዋ መጠን፣ ዕጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት።7እርሷ ራስዋን እንዳከበረችውና በምቾት በኖረችው መጠን፣ የዚያኑ ያህል ስቃይና ሐዘን ስጧት እርሷ በልቧ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጫለሁ መበለትም አይደለሁም ሀዘንም አይደርስብኝም’ ብላለች።8ስለዚህ፣ መቅሠፍቶችዋ በእብንድ ቀን ይደርሱባታል፣ ሞት፣ ሐዘንና ረሐብ ይመጡባታል። በእሳት ትቃጠላለች፤ እርሷ ላይ የሚፈርድ ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነው”9ከእርሷ ጋር ያመነዘሩና ቅጥ ያጣ ሕይወት የኖሩ፣ የቃጠሎዋ ጭስ ሲወጣ ሲያዩ ስለ እርሷ እየጮኹ ያለቅሳሉ።10ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው፣ “ታላቂቱ ከተማ፣ አንቺ ብርቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ውስጥ ቅጣትሽ መጥቷልና ወዮልሽ ወዮልሽ” ይላሉ።11ከእንግዲህ ሸቀጧን የሚገዛ ስለማይኖር የምድር ነጋዴዎች ለእርሷ ያለቅሳሉ፤ ያዝኑላታል፤12ሸቀጦችዋ ወርቅ፣ ብር፣ የከበረ ድንጋይ፣ ዕንቁ፣ ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊ ጨርቅ፣ ሐር ጨርቅ፣ ቀይ ጨርቅ፣ ማንኛውም ዓይነት ጣፋጭ ሽታ ያለው እንጨት፣ ማንኛውም ከዝሆን ጥርስ የተሠራ ዕቃ፣ ማንኛውም ከከበረ ድንጋይ የተሠራ ዕቃ፣ ነሐስ፣ ብረት፣ እብነ በረድ13ቀረፋ፣ ቅመም፣ የሚሸር እንጨት፣ ከርቤ፣ ዕጣን፣ ወይን ጠጅ፣ ዘይት፣ንጹሕ ዱቄት፣ ስንዴ፣ ከብቶች፣ በጎች፣ ፈረሶችና ሰረገሎች ባሪያዎችና የሰዎች ነፍሶች ናቸው።14አጥብቀሽ የተመኘሻቸው ነገሮች ከአንቺ አምልጠዋል። ምቾትና ውበትሽ ጠፍተዋል ከእንግዲህም አይገኙም።15በእርሷ የበለጸጉ እነዚህን ዕቃዎች የሚነግዱ ሰዎች ሥቃይዋን በመፍራት ከእርሷ ርቀው በመቆም በታላቅ ድምፅ ያለቅሳሉ16እንዲህም ይላሉ “ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ትለብስ ለነበች፤ በመርቅ፣ በከበረ ድንጋይና በዕንቁ ታጌጥ ለነበረች ታላቂቱ ከተማ ወዮ ወዮ!”17በእብንድ ሰዓት ያ ሀብት ሁሉ ጠፍቷል። የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ ሰዎች ሁሉ፣ መርከበኞችና በባሕር ላይ የሚሠሩ ሁሉ ርቀው ቆሙ።18ያቀጠሎዋን ጭስ ሲመለከቱ፣ “ ታላቂቱን ከተማ የሚመስላት ማነው?” እያሉ ጮኹ።19በራሳቸውም ላይ ዐመጽ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ፣ መርከቦች ያሏቸውና በእርሷ ሀብት የበለጸጉ ሁሉ ታላቂቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ስለ ወደመች ወዮላት ወዮላት” አሉ።20“ ሰማይ ሆይ ደስ ይበልህ፤ እግዚአብሔር ስለ እናንተ እርሷ ላይ ፈርዷልና እናንት ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያት ደስ ይበላችሁ!”21ከዚያም አንድ ብርቱ መልአክ ታላቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስልን ድንጋይ እንዲህ በማለት ወደ ባሕር ወረወሬ፣ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን በዚህ ሁኔታ በኅይል ተገፍታ ወደ ባሕር ትጣላለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጨርሶ አትታይም22የበገና ደርዳሪዎች፣ የሙዚቀኞች፣ የዋሽንትና መለኮት ነፊዎች ድምፅ ከእንዲህ በአንቺ አይሰማም። ማንኛውንም ዓይነት የጥበብ ሥራ የሚሠራ በአንቺ አይገኝም። የወፍጮ ድምፅም በአንቺ አይሰማም።23የመብራት ብርሃን፣ ከእንግዲህ በአንቺ አያበራም። የሙሽራውና የሙሽራይቱ ድምፅ ከእንግዲህ በአንቺ አይሰማም። ነጋዴዎችሽ የምድር ልዑላን ነበሩ ሕዝቦችን በመተትሽ አሳስተሻል።24የነቢያትና የቅዱሳን ደም፣ በዚህ ምድር የተገደሉ ሰዎች ሁሉ ደም በእርሷ ተገኝቷል።
1ከእነዚህ ነገሮች በኋላ የበዙ ሰዎች ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ “ሃሌ ሉያ ማዳን፣ ክብርና ኃይል የአምላካችን ነው።2በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን ታላቂቱን አመንዝራ ስለ ፈረደባት ፍርዱ እውነትና ትክክል ነው። እርሷ ያፈሰሰችውን የአገልጋዮቹን ደም ተበቅሎአል።3በድጋሚ “ሃሌ ሉያ፤ ጢስዋ ከዘላለም እስከ ዘላለም ከእርሷ ይወጣል” በማለት ተናገሩ።4ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “አሜን ሃሌ ሉያ!” በማለት ዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ሰገዱ።5ከዚያ በኋላ፣ “ታናናሾችም ታላላቆችም እርሱን የምትፈሩ አገልጋዮቹ ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ!” የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ።6ከዚያም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ብዙ ውሆች ድምፅና የብርቱ ነጎድጓድ የሚመስል ድምፅ እንዲህ አለ፤7ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ፤ የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሙሽራዋም ራስዋን ስላዘጋጀች፤ ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ ፤ ክብርንም እንስጠው።”8ደማቅና ቀጭን ንጹሕ ልብስ እንድትለብስ ገሰጣት። ቀጭኑ ልብስ የቅዱሳኑ የጽድቅ ሥራ ነው።9መልአኩም፣ “ወደ በጉ ሰርግ እንደመጡ የተጋበዙ ሰዎች የተባረኩ ናቸው ብለህ ጻፍ” አለኝ። በተጨማሪም፣ “እነዚህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃሎች ናቸው” አለኝ።10እኔም ልሰግድለት በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ እርሱ ግን፣ “እንዳታደርገው! እኔ ራሴ ከአንተና ስለ ኢየሱስ የተሰጠውን ምስክር ከያዙ ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ። ልችእግዚአብሔር ስገድ፤ ስለ ኢየሱስ የተሰጠው ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና” አልኝ።11ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አንድ ነጭ ፈረስ ተመለከትኩ ፈረሱ ላይ የተቀመጠው ታማኝና እውነተኛ ይባላል። በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋል።12ዐይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ ራሱም ላይ ብዙ አክሊሎች ነበሩ። ከእርሱ በቀር ማንም የማያውቀው ስም እርሱ ላይ ተጽፎ ነበር።13ደም የተነከረ ልብስ ለብሶ ነበር፤ ስሙ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ ይጠራል።14ቀጭን፣ ነጭና ንጹሕ ልብስ የለበሱ ሠራዊት በነጫጭ ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።15ከአፉም ሕዝቦችን የሚመታበት የተሳለ ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ በብረት በትር ይገዛቸዋል። ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን ቁጣ የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል።16ልብሱና ጭኑ ላይ፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ የሚል ስም ተጽፎበት ነበር።17አንድ መልአክ ፀሐይ ላይ ቆሞ አየሁ። እርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ኑ፣ ወደ ታላቁ የእግዚአብሔር ግብዣ ተሰብሰቡ።18መጥታችሁ የነገሥታትን፣ የጦር አዛዦችን፣ ሥጋ የኅያላንን ሥጋ፣ የፈረሰኞችንና በላያቸው የተቀመጡትን ሥጋ፣ የጌቶችን የባሮችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ፣ የሰዎችን ሁሉ ሥጋ ብሉ።”19አውሬውንና ከእርሱም ጋር የምድር ነገሥታትንና ሰራዊታቸውን አየሁ። ፈረሱ ላይ ተቀምጦ ከነበረውና ከሰራዊቱ ጋር ውጊያ ለመግጠም ተዘጋጅተው ነበር።20እነሆ አውሬው ተያዘ፤ ከእነርሱም ጋር በእርሱ ፊት ምልክቶችን የሚያደርገው ሐሰተኛ ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች አማካይነት የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳሳተ። ሁለቱም በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር በሕይወት እያሉ ተጣሉ።21የተቀሩትም ፈረስ ላይ ከተቀመጠው አፍ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ። ወፎችም ሁሉ ሥጋቸውን በልተው ጠገቡ።
1ከዚህ በኃላ የጥልቁ መክፈቻ ያለው አንድ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በእጁም ትልቅ ሰንሰለት ይዞ ነበር።2ዘንዶውን ይዞ ሺህ ዓመት አሰረው፤ ይህ ዘንዶ ዶያብሎስ ሰይጣን የተባለው የቀድሞው እባብ ነው።3ወደ ጥልቁ ጣለው፤ ዘግቶም በእርሱ ላይ ማኅተም አደረገበት። ይህን ያደረገው ሺህ ዓመቱ እስኮፈጸም ድረስ ከእንግዚህ ሕዝቦችን እንዳያሳስት ነው። ከዚያ በኋላ ለአጭር ጊዜ መፈታት ይኖርበታል።4ከዚያም ዙፋኖች አየሁ። ዙፋኖቹም ላይ የመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቀምጠው ነበር። ለኢየሱስና ለእግዚአብሔር ቃል ምስክር የተሰየፉ ሰዎችን ነፍሶችንም አየሁ። ለአውሬው ወይም ለምስሉ አልሰገዱም፤ ምልክቱም ግንባራቸው ወይም እጃቸው ላይ እንዲያረግ አልፈቀዱም። ከሞት ተነሥተው፣ ለሺህ ዓመት ከክርስቶስ ጋር ነገሡ።5የተቀሩት ሙታን ግን ሺሁ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ከሞት አልተነሡም። ይህ የመጀመሪያው ትንሣኤ ነው።6በመጀመሪያው ትንሣኤ ድርሻ የሚኖራቸው ሁሉ የተባረኩና የተቀደሱ ናቸው! እነዚህን በመሳሰሉት ላይ ሁለተኛው ሞት ኅይል አይኖረውም። የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።7ሽው ዓመት ካበቃ በኃላ ሰይጣን ከእስራት ይፈታል።8በአራቱ የምድር ማእዘን ያሉ ሕዝቦች ማለትም ጎግና ማጎግን ወደ ጦርነት ለማምጣት እያሳተ ወደ ጦርነት ለማምጣት ይወጣል ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ ያህል እጅግ ብዙ ነው።9እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ ሄደው የቅዱሳንን ሰፈር፣ እንዲሁም የተወደደችውን ከተማን ከበቡ። ሆኖም፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ በላቸው።10እነርሱን ያሳሳተው ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወደ ተጣለበት በዲን ወደሚነደው የእሳት ባሕር ተጣሉ። ቀንና ሌሊት ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሰቃያሉ።11ከዚያም አንድ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በላዩ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፣ ሆኖም፣ መሄጃ ቦታ አልነበራቸውም።12በዙፋኑ ፊት መታን፣ ታላላቆችና ታናናሾች ቆመው አየሁ፤ መጽሕፍትም ተከፈቱ። ከዚያም የሕይወት መጽሐፍ የተባለ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ። መታንም መጻሕፍቱም ውስጥ በተመዘገበው መሠረት እንደ ሥራቸው ተፈረደባቸው13ባሕር ውስጡ ያሉ ሙታንን ሰጡ። ሞትና ሲኦል ውስጣቸው ያሉትን ሙታን ስጡ፤ ሙታንም እንደ ሥራቸው ተፈረደባቸው።14ሞትና ሲኦል ወደ እሳቱ ባሕር ተጣሉ። የእሳቱም ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።15ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳቱ ባሕር ተጣለ።
1ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ ምክንያቱም የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያው ምድር አልፈው ነበር፤ ባሕርም ከእንግዲህ አልተገኘም።2ቅድስቲቱ ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባልዋ እንዳጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።3ከዙፋኑም እንዲህ የሚል ታላዝ ድምፅ ሰማሁ፣ “እነሆ የእግዚአብሔር መኖሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱ ጋር ይኖራል። እነርሱ ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ራሱም ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል።4እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ሞት፣ ወይም ሐዘን፣ ወይም ለቅሶ ወይም ሕመም አይኖርም። ምክንያቱም የቀድሞ ነገሮች አልፈዋል።5በዙፋኑ የተቀመጠው፣ “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” አለ። “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛ ስለሆኑ ጻፍ” አለ።6ለእኔም እንዲህ አለኝ፤”እነዚህ ሁሉ ተፈጽመዋል እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ነኝ። ለተጠማ ሰው ከሕይወት ውሃ ምንጭ እንዲጠጣ ያለ ዋጋ እሰጣለሁ።7ድል የነሣ እነዚህን ነገሮች ይወርሳል፤ አምላኩ እሆናለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል።8ነገር ግን የፈሪዎች፣ የእምነተ ቢሶች፣ የርኩሶች፣ የነፍስ ገዳዮች፣ የአመንዝራዎች፣ የሟርተኞች፣ የጦዖት አምላኪዎችና የሐሰተኞኦች ቦታቸው በዲን በሚቃጠለው እሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።9የመጨረሻዎቹ ሰባት መቅሠፍቶች የሞሉበትን ሰባት ድዋዎች ከያዙት ሰባት መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ፣ “ወደዚህ ና፣ የበጉን ሚስት ሙሽራዋን አሳይሃለሁ” አለኝ።10ከዚያም ወደ አንድ ታላቅና ከፍ ወዳለ ተራራ በመንፈስ ወሰደኝና ቅዱሳቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ።11ኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ክብር ነበራት፤ የብርሃንዋ ፀዳል እጅግ እንደከበረ ድንጋይ፣ እንደ አያሰጲድ ድንጋይ ጥርት ያለ ነበር።12አሥራ ሁለት በሮች ያሉት በጣም ታላቅ ረጅም ግምብ ነበራት በየበሮቹ አሥራ ሁለት መላእክት ነበሩ። በእነርሱም ላይ የአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ተጽፈው ነበር።13በምሥራቅ ሦስት በሮች፣ በሰሜን ሦስት በሮች፣ በደቡብ ሦስት በሮች፣ በምዕራብ ሦስት በሮች ነበሩ።14የከተማዋ ግምብ አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩት፤ በእነርሱም ላይ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።15ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ከተማዋን፣ በሮቹንና ቅጥሮቹን የሚለካበት የወርቅ ዘንግ ነበረው።16ከተማዋ አራት ማእዘን ነበረች፤ ርዝመትና ስፋቱ ዕኩል ነበር። በመለኪያ ዘንጉ ሲለካ ርዝመቱ 12,000 ምዕራፍ ሆነ (ርዝመቱ፣ ስፋቱና ከፍታዋ ዕኩል ነበር)።17ቅጥሯን ስለካ ስፋቱ በሰው መለኪያ (ይህም የመላእክት መለኪያም ነው) 144 ክንድ ሆነ18ቅጥሩ ከኢያሰጲድ፣ ከተማዋም እንደ መስተዋት በጠራ ንጹሕ ወርቅ የተሠራች ነበረች።19የቅጥሩ መሠረቶች በከበሩ ድንጋዮች ያጌጡ ነበር። የመጀመሪያው ኢያሰጲድ፣ ሁለተኛው ሶንፔር፣ ሦስተኛው ኬልቄዶን፣ አራተኛው መረግድ20አምስተኛው ሰርደንክስ፣ ስድስተኛው ሰርድዮን፣ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፣ ስምንተኛው ቢረሌ፣ ዘጠነኛው ወራውሬ፣ አሥረኛው ክርስጵራስስ፣ አሥራ አንደኛው ያክንት፣ አሥራ ሁለተኛው አሜቴስ ቲኖስ ነበረ።21አሥራ ሁለቱም በሮች፣ አሥራ ሁለት ዕንቁዎች ነበሩ፤ እያንዳንዱ በር ከአንድ ዕንቁ የተሠራ ነበር። የየከተማዋ መንገዶች ጥርት እንዳለ መስተዋት ንጽሕ ወርቅ ነበሩ።22በከተማዋ ምንም መቅደስ አላየሁም፤ ምክንያቱም ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደሷ ነበሩ።23የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራለት ከተማዋ የፀሐይ ወይም የጨረቃ ብርሃን አልነበራትም፤ ምክንያቱም በጉ ራሱ ብርሃንዋ ነው።24ሕዝቦችም በዚያች ከተማ ብርሃን ይመላለሳሉ። የምድር ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርሷ ያመጣሉ።25በሮቿ በቀን አይዘጉም፤ በዚያ ሌሊት የለም።26የመንግሥታትን ግርማና ክብር ወደ እርሷ ያመጣሉ27ርኩስ ነገር በፍጹም አይገባባትም። ጸያፍ ወይም አታላይ ወደዚያ አይገባም፤ ወደዚያ የሚገቡት ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፈ ብቻ ናቸው።
1ከዚያም መልአኩ፣ እንደ መስተዋት የጠራውን የሆነውን የሕይወት ውሃ ወንዝ አሳየኝ። ወንዙም የሚወጣው ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን ነበር2በከተማዋ ዋና መንገድ መካከል ያልፍ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ አሥራ ሁለት ወር ሙሉ አሥራ ሁለት ዓይነት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበር። የዛፉ ቅጠሎች ሕዝቦችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር።3ከእንግዲህ ምንም ዐይነት መርገም አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉ ዚፋን ከተማው ውስጥ ይሆናሉ፤ አገልጋዮቹም ያገለግሉታል።4ፊቱን ያያሉ፤ ስሙም ግንባሮቻቸው ላይ ይሆናል።5ከእንግዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም። ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።6መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛ ናቸው። ጌታ፣ የነቢያት መናፍቅ አምላክ ቶሎ መሆን ያለበትን ለአገልጋዮቹ እንዲያሳያቸው መልአኩን ላከ።”7“እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ! ለዚህ መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች የሚታአእ የተባረከ ነው።8እነዚህን ነገሮች የሰማሁና ያየሁ እኔ ዮሐንስ ነኝ። እነዚህን በሰማሁና ባይብሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ላሳየኝ መልአክ ለመስገድ በፊቱ ተደፋሁ።9እርሱ ግን፣ “እንዳታደርገው! እኔ ራሴ ከወንድሞችህ ከነቢያት ጋር፣ ለዚህ መጽሐፍ ቃል ከሚታዘዙት ጋር አብሬ አገልጋይ ነኝ። ይልቅ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ!”10እንዲህም አለኝ፤ ጊዜው በጣም ቅርብ ስለሆነ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች በማኅተም አትዝጋው።11ዐመፀኛው ማመፁን ይቀጥል። ርኩሱም ርኩሰት ማድረጉን ይቀጥል። ጻድቁም ጽድቅ የሆነውን ማድረጉን ይቀጥል። ቅዱስም ቅዱስ መሆን ይቀጥል።12“እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ። ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ዋጋ ከእኔ ዘንድ አለ።13እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ።14ከሕይወት ዛፍ ለመብላትና በበሮቿ ወደ ከተማዋ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ የተባረኩ ናቸው።15ውሾች፣ ጠንቋዮች፣ አመንዝራዎች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎችና ሐሰትን የሚወዱና የሚያደርጉ ግን በውጭ አሉ።16እኔ ኢየሱስ ለእናንተ እንዲመሰክር መልአኬን ወደ አብያተ ክርስቲያናት ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርጥ ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”17መንፈሱና ሙሽራይቱ፣ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማ ሁሉ፣ “ና!” ይበል። ማንም የተጠማ ቢኖር ይምጣ፣ የሚፈልግ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ።18የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ለሚሰሙ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፣ ማንም ትንቢቱ ላይ ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል።19ማንም ከዚህ መጽሐፍ ትንቢት ቢያጎድል እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ ከተጻፈው የሕይወት ዛፍና ቅድስት ከተማ ዕድሉን ያጎልበታል።20ለእነዚህ ነገሮች የሚመሰክር እርሱ፣”አዎን! ቶሎ እመጣለሁ” አሜን! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና! ይላል።21የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን