1 እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። 2 ምድርም ቅርፅ የሌላትና ባዶ ነበረች። ጥልቅ የሆነው ስፍራዋም በጨለማ ተውጦ ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ሰፍፎ ነበር። 3 እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ። 4 እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ ብርሃንኑም ከጨለማ ለየው። 5 እግዚአብሔርም ብርሃኑን ‘ቀን’ ጨለማውን ደግሞ ‘ሌሊት’ ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ ሌሊቱም ነጋ አንድ ቀን ሆነ። 6 እግዚአብሔርም፦ “በውሆች መካከል ጠፈር ይሁን፣ ውሆችንም ይለያዩ” አለ። 7 እግዚአብሔር ጠፈርን አደረገና ከጠፈር በላይና ከጠፈር በታች ያሉትን ውሆች ለየ። እንደዚያም ሆነ። 8 እግዚአብሔር ጠፈሩን ‘ሰማይ’ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ ሌሊቱም ነጋ ሁለተኛ ቀን። 9 እግዚአብሔር፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ወደ አንድ ስፍራ ይሰብሰብ፣ ምድሩም ይገለጥ” አለ። እንደዚያም ሆነ። 10 እግዚአብሔርም ምድሩን ‘የብስ’፣ ወደአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ ‘ባሕር’ ብሎ ጠራው። ይህም መልካም መሆኑን ተመለከተ። 11 እግዚአብሔር፦ እንደ ዓይነታቸው ዘርን የሚያፈሩ ተክሎችን፣ በውስጣቸው ዘርን ያዘሉ የፍራፍሬ ዛፎችን እንደዓይነታቸው የሚያፈሩ አዝርዕትን ታብቅል” አለ። እንደዚያም ሆነ። 12 ምድር እንደአይነታቸው የሚያፈሩ አዝርዕትን አበቀለች። ይህም መልካም እንደሆነ እግዚአብሔር ተመለከተ። 13 ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ ሶስተኛ ቀን ሆነ። 14 እግዚአብሔር፦ “ቀኑን ከሌሊቱ ይለዩ ዘንድ በሰማይ ብርሃናት ይሁኑ። እነዚህ ብርሃናት የዓመት ወቅቶችን፣ ቀናትንና ዓመታትን የሚለዩ ምልክቶች ይሁኑ። 15 ለምድርም ብርሃን ይሰጡ ዘንድ በሰማይ ላይ የሚገኙ ብርሃናት ይሁኑ” አለ። እንደዚያም ሆነ። 16 እግዚአብሔር ታላቁ ብርሃን በቀን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት ይሠለጥኑ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ። ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ። 17 ለምድርም ብርሃን ይሰጡ ዘንድና 18 በቀንና በሌሊት ላይ እንዲሠለጥኑ እንደዚሁም ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ በሰማይ አኖራቸው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደሆነ ተመለከተ። 19 ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ አራተኛ ቀን ሆነ። 20 እግዚአብሔር፦ “ውሆች በሕያዋን ፍጡራን የተሞሉ ይሁኑ፣ ወፎችም ከምድር በላይ ባለው በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ። 21 እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር ፍጥረታትን እንደዚሁም በምድር የሚንቀሳቀሱ፣ በውሆች ውስጥ የሚርመሰመሱና በክንፎቻቸው የሚበሩ ወፎችን እንደዓይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደሆነ ተመለከተ። 22 እግዚአብሔርም፦ “ብዙ ተባዙ የባሕርን ውሆች ሙሉአቸው፣ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው። 23 ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ አምስተኛ ቀን ሆነ። 24 እግዚአብሔርም፦ “ምድር እንደወገናቸው ሕያው ፍጥረታትን ማለትም ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡትንና የምድር አራዊትን ታስገኝ” አለ። እንደዚያም ሆነ። 25 እግዚአብሔር በየዓይነታቸው የምድር አራዊትን፣ በየዓይነታቸው ማናቸውንም በምድር የሚሳቡትን ፈጠረ። 26 እግዚአብሔርም፦ “ሰውን በመልካችን እንደ አምሳላችን እንፍጠር፣ ሰዎችም በባሕር ዓሣዎች፣ በሰማይ በሚበሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚሳቡ ማናቸውም ተሳቢ ፍጥረቶች ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ። 27 እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ፣ በራሱም አምሳል ፈጠረው። ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። 28 እግዚአብሔር ባረካቸው እንደዚህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሉአት ግዟትም። በባሕር ውስጥ ባሉት ዓሣዎች፣ በሰማይ ላይ በሚበሩት ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱት ማናቸውም ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ” 29 እግዚአብሔርም፦ “እነሆ፣ ምግብ ይሆኑላችሁ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ በውስጣቸው ዘርን ያዘሉ ማናቸውንም ተክሎችና በውስጣቸው ፍሬ ያላቸውን ማናቸውንም የፍራፍሬ ዛፎች ሰጥቻችኋለሁ። 30 በምድር ላይ ለሚገኙ እንስሳት ሁሉ፣ በሰማይ ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፣ እንዲሁም በምድር ላይ ለሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ማለትም የሕይወት እስትንፋስ ላለበት ማንኛውም ፍጡር ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ። እንደዚሁም ሆነ። 31 እግዚአብሔር የፈጠረውን ማንኛውንም ነገር ተመለከተ። እነሆ፣ እጅግ መልካም ነበረ። ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ ስድስተኛ ቀን ሆነ።
1 የምድር በውስጣቸው ያሉትም ሕያዋን ፍጡራን አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ። 2 እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጽሞ በዚሁ ቀን ከሥራው ሁሉ አረፈ። 3 እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ ያረፈው በዚህ ቀን ስለሆነ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም። 4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረበት ወቅት የሰማይና የምድር የአፈጣጠራቸው ታሪክ እንደዚህ ነበር። 5 እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ ዝናብ እንዲዘንብ ስላደረገና ምድርንም የሚያለማ ሰው ባለመኖሩ በምድር ላይ ምንም ቡቃያ አልነበረም፣ በምድር ላይ የሚበቅል ተክልም ገና አልበቀለም። 6 ነገር ግን ውሃ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር። 7 እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ። 8 እግዚአብሔር አምላክም በስተምሥራቅ በኩል በዔደን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፣ የአበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው። 9 ከምድር ውስጥም እግዚአብሔር አምላክ ለዓይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ። በአትክልት ስፍራው መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበር፣ መልካሙንና ክፉውን የሚያሳውቀውም ዛፍ በዚያ ነበር። 10 የአትክልት ስፍራውንም የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ይፈስ ነበር። ወንዙም ከኤደን ከወጣ በኋላ አራት ወንዞች ሆኖ ይከፋፈል ነበር። 11 የመጀመሪያው ፊሶን የተባለው ወንዝ ነበር፣ ይህም ወርቅ ይገኝበት የነበረውን መላውን የሐዊላ ምድር አቋርጦ የሚፈስው ወንዝ ነበር። 12 የዚያ አገር ወርቅ የጠራ ወርቅ ነበር፤ በተጨማሪም በዚያ አገር ሽቶና የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ። 13 የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ይባል ነበር፣ እርሱም መላውን የኢትዮጵያ ምድር አቋርጦ ይፈስ ነበር። 14 የሶስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ ይባል ነበር፣ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈሳል። አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ነበር። 15 እግዚአብሔር አምላክም የኤደንን የአትክልት ስፍራ ያለማና ይንከባከብ ዘንድ ሰውን ወስዶ በዚያ አኖረው። 16 እግዚአብሔር አምላክም እንዲህ በማለት አዘዘው፣ “በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም የፍሬ ዛፍ መብላት ትችላልህ። 17 ነገር ግን መልካሙንና ክፉውን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፣ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።” 18 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም። ስለዚህ የምትመቸውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” አለ። 19 እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር የምድር እንስሶችንና የሰማይ ወፎችን አበጀ። ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ይመለከት ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው። ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር አዳም ያወጣለት ስም ያ ስሙ ሆነ። 20 አዳም ለሁሉም ከብቶች፣ ለሁሉም የሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው። ነገር ግን ለአዳም ለራሱ የምትመች ረዳት አልተገኘለትም። 21 እግዚአብሔር አምላክ በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፣ ስለሆነም አዳም አንቀላፋ። እግዚአብሔር አምላክ አዳም አንቀላፍቶ ሳለ ከጎድን አጥንቶቹ አንዱን ወስዶ አጥንቱን የወሰደበትን ስፍራ በሥጋ ዘጋው። 22 እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም ከወሰደው የጎድን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት። ወደ አዳምም አመጣት። 23 አዳምም፦ “አሁን ይህቺ ከአጥንቴ የተገኘች አጥንት ከሥጋዬ የተገኘች ሥጋ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል” አለ። 24 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። 25 አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።
1 እግዚአብሔር በምድር ላይ ከፈጠራቸው ማናቸውም ሌሎች አራዊቶች ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኮለኛ ነበር። እርሱም ሴቲቱን፦ “በእርግጥ እግዚአብሔር ‘በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም ዛፍ አትብሉ’ ብሎአልን?” ብሎ ጠየቃት። 2 ሴቲቱም ለእባቡ፦ “በአትክልቱ ስፍራ ካሉት የዛፎች ፍሬዎች መብላት እንችላለን፤ 3 ነገር ግን በአትክልቱ ስፍራ መካከል ስለሚገኘው ዛፍ እግዚአብሔር “እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም” ብሎአል። 4 እባብም ለሴቲቱ፦ “በፍጹም አትሞቱም። 5 ከእርሱ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንደሚከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካሙንና ክፉውን የምታውቁ እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው አላት።” 6 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት መልካም፣ ሲያዩት ደስ የሚያሰኝና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደሆነ ተመልክታ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከእርሷ ጋር ለነበረውም ለባሏ ከፍሬው ሰጠችው፣ እርሱም በላ። 7 የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፣ ራቁታቸውን እንደነበሩም አወቁ። የበለስ ቅጠሎችንም በማጋጠም ከሰፉ በኋላ ለራሳቸው መሸፈኛ ግልድም ሠሩ። 8 ቀኑ ወደ ምሽት ሲቃረብ በአትክልት ስፍራው ሲመላለስ የእግዚአብሔር አምላክን ድምፅ ሰሙ፤ ስለዚህ አዳምና ሚስቱ ከእግዚአብሔር አምላክ ፊት በመሸሽ በአትክልቱ ስፍራ በነበሩት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። 9 እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ጠራውና፣ “የት ነህ?” አለው። 10 አዳምም፣ “በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ድምፅህን ሰማሁና ራቁቴን ስለነበርሁ ፈራሁ፤ በዚህም ምክንያት ተሸሸግሁ።” 11 እግዚአብሔርም፦ “ራቁትህን እንደሆንክ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ብዬ ካዘዝኩህ ከዛፉ ፍሬ በላህን?” አለው። 12 አዳምም፦ “አብራኝ እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝ፣ እኔም በላሁት” አለ። 13 እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ “ምንድነው ያደረግሽው?” አላት። ሴቲቱም፦ “እባቡ አታለለኝና በላሁ” አለች። 14 እግዚአብሔር አምላክም ለእባቡ፦ “ይህንን በማድረግህ ከእንስሳት ሁሉና ከምድር አራዊት ሁሉ ተለይተህ የተረገምህ ትሆናለህ። በደረትህ እየተሳብክ ትሄዳለህ፣ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ አፈር ትበላለህ። 15 በአንተና በሴቲቱ፣ በዘርህና በዘሯ መካካል ጠላትነትን አደርጋለሁ። የእርሷ ዘር ራስህን ይቀጠቅጣል፣ አንተም ተረከዙን ትነክሳለህ” አለው። 16 ለሴቲቱም እንዲህ አላት፦ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በስቃይም ትወልጃለሽ። ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፣ እርሱም ገዢሽ ይሆናል።” 17 ለአዳምም እንደዚህ አለው፦ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘ከእርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ከዛፉ ፍሬ ስለበላህ ከአንተ የተነሳ ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ በከባድ ድካም ምግብህን ከእርሷ ታገኛለህ። 18 ምድር እሾህና አሜኬላ ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። 19 ከተገኘህበት አፈር እስክትመለስ ድረስ በላብህ እንጀራን ትበላለህ። አፈር ነህና ወደ አፈር ተመልሰህ ትሄዳለህ”። 20 የሕያዋን ሁሉ እናት በመሆኗ አዳም ለሚስቱ ‘ሔዋን’ የሚል ስም አወጣላት። 21 እግዚአብሔር አምላክ ከቆዳ ልብስ አዘጋጅቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው። 22 እግዚአብሔር አምላክ፦ “መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማውቅ ረገድ አሁን ሰው ከእኛ እንደ አንዱ ሆኖአል። ስለዚህ አሁን እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ቀጥፎ እንዳይበላ ለዘላለምም እንዳይኖር ሊፈቀድለት አይገባም” አለ። 23 በዚህም ምክንያት የተገኘባትን ምድር እንዲያለማ እግዚአብሔር አዳምን ከኤደን የአትክልት ስፍራ አስወጣው። 24 ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ከአትክልት ስፍራው አባረረው፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ከኤደን የአትክልት ስፍራ በስተቀኝ በኩል ኪሩቤልን እንደዚሁም በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ አኖረ።
1 አዳምም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ። እርሷም ፀነሰች። ቃየንንም ወለደች። “በእግዚአብሔር ዕርዳታ ወንድ ልጅ ወለድሁ” አለች። 2 ከዚያ በኋላም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤል የበግ እረኛ ሲሆን ቃየን ግን ገበሬ ሆነ። 3 ከዕለታት አንድ ቀን ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መባ አቀረበ። 4 አቤል ደግሞ መጀመሪያ ከተወለዱ በጎች መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር በአቤልና በመሥዋዕቱ ደስ ተሰኘ፣ 5 በቃየንና በመሥዋዕቱ ግን ደስ አልተሰኘም። ስለዚህ ቃየን በጣም ተቆጣ፣ ፊቱም ተኮሳተረ። 6 እግዚአብሔር አምላክ ቃየንን፦ “ለምን ተቆጣህ፣ ፊትህስ ለምን ተኮሳተረ? 7 መልካም ብታደርግ ፊትህ ያበራ አልነበረምን? ያደረግኸው መልካም ካልሆን ግን ኃጢአት በደጅህ እያደባች ናት፣ ልትቆጣጠርህም ትፈልጋለች፣ አንተ ግን በቁጥጥርህ ሥር አድርጋት” አለው። 8 ቃየን ወንድሙን አቤልን፦ “ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው፣ በዚያም ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ በቁጣ ተነሳበት፣ ገደለውም። 9 ከዚያ በኋላም እግዚአብሔር ቃየንን፦ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” አለው። እርሱም፦ “አላውቅም፣ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” አለ። 10 እግዚአብሔርም፦ “ያደረግኸው ምንድን ነው? የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል” አለው። 11 “አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ። 12 ምድርንም በምታርስበት ጊዜ ፍሬዋን በሙላት አትሰጥህም። በምድር ላይ ኮብላይና ተንከራታች ትሆናለህ” አለው። 13 ቃየንም ለእግዚአብሔር፦ ቅጣቴ ከምችለው በላይ ነው። 14 በእርግጥም ዛሬ ከምድሪቱ አባርረኸኛል፣ እኔም ከፊትህ እሸሸጋለሁ። በምድር ላይ ኮብላይና ተንከራታች እሆናለሁ፣ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል” አለው። 15 እግዚአብሔርም፦ “ቃየንን የሚገድል ማንኛውም ሰው ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ ይወሰድበታል” አለ። ከዚያ በኋላም የሚያገኘው ማንኛውም ሰው እንዳይገድለው እግዚአብሔር በቃየን ላይ ምልክት አደረገበት። 16 ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፣ ከኤደን በስተምሥራቅ በነበረው ኖድ በተባለው ምድር ኖረ። 17 ቃየንም ከሚስቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ፣ እርሷም ፀነሰች፣ ሄኖክንም ወለደች። ቃየን ከተማን መሠረተ፣ የመሠረታትንም ከተማ በልጁ ስም ሄኖክ ብሎ ጠራት። 18 ሄኖክም አራድን ወለደ። አራድም መሑያኤልን ወለደ። መሑያኤልም መቱሳኤልን ወለደ። መቱሳኤልም ላሜክን ወለደ። 19 ላሜክም ዓዳና ጺላ የተባሉ ሁለት ሚስቶችን አገባ። 20 ዓዳ ያባልን ወለደች፣ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ለከብት አርቢዎች አባት ነበር። 21 የእርሱ ወንድም ዩባልም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበር። 22 ጺላም ከነሐስና ከብረት መሣሪያዎችን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች። የቱባልቃይንም እህት ናዕማ ትባል ነበር። 23 ላሜክ ለሚስቶቹ፦ “አዳና ጺላ ስሙኝ፣ እናንተ የላሜክ ሚስቶች የምላችሁን ስሙኝ ስለጎዳኝና ስላቆሰለኝ አንድ ሰው ገድያለሁ። 24 ቃየንን የሚገድል ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ የሚወሰድበት ከሆነ የላሜክ ገዳይማ ሰባ ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ ይወሰድበታል” አላቸው። 25 አዳም ከሚስቱ ጋር እንደገና የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ፣ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ምትክ ሰጠኝ” በማለት ስሙን ሤት ብላ ጠራችው። 26 ለሤትም ወንድ ልጅ ተወለደለት፣ ስሙንም ሄኖስ አለው። በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ጀመሩ።
1 የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረው ጊዜ በራሱ አምሳያ ፈጠራቸው፤ 2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፣ ባረካቸውም። በተፈጠሩም ጊዜ ‘ሰው’ ብሎ ጠራቸው። 3 አዳም ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፣ ስሙንም ‘ሤት’ ብሎ ጠራው። 4 አዳም ሤትን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ 5 930 ዓመት ሲሆነውም ሞተ። 6 ሤት ዕድሜው 105 ሲሆን ሄኖስን ወለደ። 7 ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሤት 807 ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 8 ሤት 912 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ። 9 ሄኖስ 90 ዓመት ሲሆነው ቃይናንን ወለደ። 10 ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 11 ሄኖስ 905 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ። 12 ቃይናን 70 ዓመት ሲሆነው መላልኤልን ወለደ። 13 ቃይናን መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 14 ቃይናን 910 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ። 15 መላልኤል 65 ዓመት ሲሆነው ያሬድን ወለደ። 16 መላልኤል ያሬድን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 17 መላልኤል 895 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ። 18 ያሬድ 162 ዓመት ሲሆነው ሄሮክን ወለደ። 19 ያሬድ ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 20 ያሬድ 962 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ። 21 ሄኖክ 65 ዓመት ሲሆነው ማቱሳላን ወለደ። 22 ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል 300 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 23 ሄኖክ 365 ዓመታት ኖረ። 24 ሄኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል ኖረ፣ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ስለወሰደው አልተገኘም። 25 ማቱሳላ 187 ዓመት ሲሆነው ላሜሕን ወለደ። 26 ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ 782 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 27 ማቱሳላ 969 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ። 28 ላሜሕ 182 ዓመት ሲሆነው አንድ ወንድ ልጅ ወለደ። 29 “ይህ ልጅ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከብርቱ ሥራችን ያሳርፈናል” ሲል ስሙን ‘ኖህ’ ብሎ ጠራው። 30 ላሜሕ ኖህን ከወለደ በኋላ 595 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 31 ላሜሕ 777 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ። 32 ኖህ 500 ዓመታት ሲሆነው ሴም፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።
1 የሰው ልጆች በምድር ላይ እየበዙ ሲሄዱ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው። 2 የእግዚአብሔር ልጆችም የሰዎች ሴቶች ልጆች የሚስብ ውበት እንዳላቸው ተመለከቱ። ከእነርሱ መካከልም የመረጧቸውን ሚስቶች አድርገው ወሰዱ። 3 እግዚአብሔርም፦ “እርሱ ሥጋ ስለሆነ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜውም 120 ዓመት ይሆናል” አለ። 4 የእግዚአብሔር ልጆች ከሰዎች ሴቶች ልጆች ጋብቻ በፈጸሙና ልጆችን በወለዱበት በዚያን ጊዜ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ግዙፍ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንት ዘመን ዝናን ያተረፉ ኅያላን ነበሩ። 5 እግዚአብሔር የሰው ልጆች ክፋት በምድር ላይ እየበዛ እንደሆነና የልቡም ሃሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ። 6 እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ ልቡም አዘነ። 7 በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር፦ “የፈጠርሁትን የሰው ልጅ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ፤ ስለፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና ከእነርሱም ጋር እንስሳትን፣ በደረታቸው የሚሳቡትን ፍጥረታትና የሰማይ ወፎችን ሁሉ አጠፋለሁ” አለ። 8 ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አገኘ። 9 የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው። ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፤ የእግዚአብሔርንም መንገድ የሚከተል ሰው ነበር። 10 ኖኅ ሴም፣ ካምና ያፌት የተባሉትን ሶስት ወንዶች ልጆች ወለደ። 11 በእግዚአብሔር ፊት በክፉ ሥራ ረከሰች በዓመፅም ተሞላች። 12 እግዚአብሔር ምድርን ተመለከተ፣ የተበላሸች እንደሆነችና በምድር የሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ በክፋት እንደሚኖሩ አየ። 13 እግዚአብሔርም ኖኅን፦ “ሥጋን የለበሰ ሁሉ ፍጻሜ ደርሶአል፣ ከእነርሱ የተነሳ ምድር በግፍ ተሞልታለችና። እኔም በእርግጥ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ። 14 አንተ ግን ከጥሩ እንጨት መርከብ ሥራ፤ መርከቧም ክፍሎች እንዲኖራት አድርግ፤ ውስጧንና ውጭዋንም በቅጥራን ለቅልቀው። 15 እንደዚህ አድርገህ ሥራት፦ ርዝመቷ 140 ሜትር፣ ወርዷ 23 ሜትር፣ ከፍታዋ 13. 5 ሜትር ይሁን። 16 ለመርከቧ ጣራ አብጅላት፣ ጣራና ግድግዳው በሚጋጠምበት ቦታ ግማሽ ሜትር ክፍተት ተው፤ ከጎኗ በር አውጣላት፤ ባለ ሦስት ፎቅ አድርገህ ሥራት። 17 እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባችውን ፍጡራን ሁሉ ለማጥፋት እነሆ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል። 18 ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋር ወደ መርከቧ ትገባላችሁ። 19 ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲቆዩ ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ወንድና ሴት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ። 20 ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቆዩ ዘንድ ወደ አንተ ይምጡ። 21 ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።” 22 ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።
1 እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ። 2 ከንፁህ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ወንድና ሴት፣ ንፁሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት ከአንተ ጋር አስገባ። 3 እንዲሁም ከሰማይ ወፎች ወገን ሰባት ወንዶችና ሰባት ሴቶች በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋር ታስገባለህ። 4 ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ላይ አጠፋለሁ።” 5 ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። 6 የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የ600 ዓመት ሰው ነበር። 7 ኖኅና ወንዶች ልጆቹ ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ። 8 ንፁሕ ከሆኑትና ንፁሕ ካልሆኑት እንስሳት ከወፎችና በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጡራን ሁሉ 9 ጥንድ ጥንድ ወንድና ሴት ሆነው ወደ ኖኅ መጡ፤ እግዚአብሄር ኖኅን ባዘዘው መሠረትም ወደ መርከቧ ገቡ። 10 ከሰባት ቀንም በኋላ የጠፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ። 11 ኖኅ በተወለደ በ600ኛው ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ። 12 ዝናቡም መዝነብ ጀመረ፣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ባለማቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ። 13 ዝናቡ መዝነብ በጀመረበት ቀን ኖኅና ሚስቱ ከልጆቻቸው ጋር ከሴም ከካም ከያፌትና ከሶስቱም ልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገቡ። 14 ከአራዊት ከእንስሳት በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዓይነት አብረዋቸው ገቡ። 15 የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸው ፍጡራን በሙሉ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ከኖኅ ጋር ወደ መርከቡ ገቡ። 16 ከሕያዋንም ፍጡራን ሁሉ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘው መሠረት ወንድና ሴት እየሆኑ ገቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር የመርከቡን በር ከውጭ ዘጋ። 17 የጥፋት ውሃም ለአርባ ቀናት ያለመቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ ውሃው እየጨመረ በሄድ መጠን መርከቧን ከምድር ወደ ላይ አነሳት። 18 ውሃው በምድር ላይ በጣም እየጨመረና ከፍ እያለ ሲሄድ፣ መርከቧ በውሃ ላይ ተንሳፈፈች። 19 ውሃው በጣም ከፍ በማለቱ፣ ከሰማይ በታች ያሉትን ታላላቅ ተራሮች ሁሉ ሸፈናቸው። 20 ውሃው ከተራሮች ጫፍ በላይ 7ሜትር ያህል ከፍ አለ። 21 በምድር ላይ የነበሩ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ፦ ወፎች፣ የቤት እንስሳት፣ አራዊት፣ በምድር የሚርመሰመሱ ፍጡራን ሰዎችም በሙሉ ጠፉ። 22 የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው በምድር የነበሩ ፍጡራን ሁሉ ሞቱ። 23 ሕይወት ያላቸው ፍጡራን ሁሉ ከሰዎች ጀምሮ እንስሳት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራንና የሰማይ ወፎች ሁሉም ከምድር ገጽ ጠፉ። ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቧ ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ። 24 ውሃውም ምድርን ሸፍኖ መቶ አምሳ ቀን ቆየ።
1 እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቧ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሳት ሁሉ አሰበ። በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ ውሃውም ጎደለ። 2 የጥልቁ ምንጮችና የሰማይ መስኮቶች ተዘጉ፣ ዝናቡም መዝነቡን አቆመ። 3 ውሃው ከምድር ላይ ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣ፤ ከመቶ ሃምሳ ቀን በኋላም የውሃው ከፍታ እጅግ ቀነሰ። 4 በሰባተኛው ወር፤ በአሥራ ሰባተኛው ቀን መርከቧ በአራራት ተራሮች ላይ አረፈች። 5 ውሃው እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ቀስ በቀስ እየጎደለ ሄደ። በአሥረኛው ወር መጀመሪያው ቀን የተራሮች ጫፎች ታዩ። 6 ከአርባ ቀን በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቧን መስኮት ከፍቶ፣ 7 ቁራን ወደ ውጭ ላከ፤ ቁራውም ውሃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር። 8 ከዚያም በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ ገጽ ጎድሎ እንደሆነ ለማወቅ ርግብን ላከ፤ 9 ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ መርከቡ ውስጥ አስገባት። 10 ሰባት ቀን ከቆየ በኋላ ኖኅ ርግቧን እንደገና ላካት። 11 እርሷም ወደ ማታ ተመለሰች፤ እነሆም የለመለመ የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጉደሉን አወቀ። 12 ደግሞም ሰባት ቀን ከቆየ በኋላ ኖኅ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ በዚህ ጊዜ ግን ርግቢቱ ወደ እርሱ አልተመለሰችም። 13 ኖኅ በተወለደ 601ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውሃው ከምድር ላይ ደረቀ። ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ዙሪያውን ተመለከተ፣ ምድሪቱም እንደደረቀች አየ። 14 በሁለተኛው ወር፣ በሃያ ሰባተኛው ቀን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ደረቀች። 15 ከዚያም እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው። 16 “አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከመርከቧ ውጡ። 17 እንዲዋለዱ፣ እንዲራቡና በምድር ላይ እንዲበዙ ከአንተ ጋር ያሉትን ወፎች፣ እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ይዘሃቸው ውጣ።” 18 ስለዚህ ኖኅ ከልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር ወጣ። 19 እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር የሚሳቡት፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ። 20 ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ። ንፁሕ ከሆኑት እንስሳትና ንፁሕ ከሆኑት ወፎች አንዳንዶቹን ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ። 21 እግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን መዓዛ አሸተተ፣ በልቡም እንዲህ አለ፦ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በእርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጡራንን ዳግመኛ አላጠፋም። 22 ምድር እስካለች ድረስ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ፣ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት አይቋረጡም።”
1 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን እንዲህ ሲል ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት፤ 2 አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በእንስሳት፣ በሰማይ ወፎች፣ በደረት በሚሳቡ ተንቀሳቃሽ ፍጡሮችና በባሕር ዓሦች፣ በምድር ላይ በሚገኙ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ላይ ይሁን። ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ። 3 ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፣ ለምለሙን ዕፅዋት እንደሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ። 4 ነገር ግን ሕይወቱ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ። 5 ሰውን የገደለ ሁሉ ስለሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፤ የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ። 6 የሰውን ደም የሚያፈስ ሁሉ ደሙ በሰው እጅ ይፈሳል፤ በእግዚአብሔር አምሳል እግዚአብሔር ሰውን ሠርቶታልና። 7 እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፣ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ ይንሠራፋም።” 8 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ አላቸው፦ 9 “እነሆ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጣው ዘራችሁ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ 10 እንዲሁም ከእናንተ ጋር ከነበሩት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ከወፎች፣ ከእንስሳት ከእናንተ ጋር ከመርከቧ ከወጡት በምድር ላይ ካሉት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር ኪዳን እገባለሁ። 11 ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋር ኪዳን እገባለሁ።” 12 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “በእኔና በእናንተ መካከል ከእናንተም ጋር ካሉ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ፣ ከሚመጣው ትውልድ ሁሉ ጋር፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤ 13 ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አድርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል። 14 ደመናን በምድር ላይ በጋረድሁና ቀስቴም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ 15 ከእናንተና ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር የገባሁትን ኪዳን አስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም። 16 ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ በእኔና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጡራን መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን አስባለሁ።” 17 ከዚያ በኋላም እግዚአብሔር ለኖኅ፦ “ይህ በእኔና በምድር ላይ በሚኖሩ ሕያዋን ሁሉ መካከል የገባሁት ኪዳን ምልክት ነው።” አለው። 18 ከመርከቧ የወጡትም የኖኅ ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ነበር፤ ካም የከነዓን አባት ነው። 19 እነዚህ ሶስቱ የኖኅ ልጆች ሲሆኑ፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከነዚሁ ነው። 20 ኖኅ ገበሬ መሆን ጀመረ፣ ወይንንም ተከለ። 21 ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ እርቃኑን ተኛ። 22 የከንዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። 23 ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በትከሻቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ። 24 ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ። 25 ከዚህም የተነሣ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም አገልጋይ ይሁን።” አለ። 26 ደግሞም፦ “የሴም አምላክ የሆነው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣ ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን። 27 እግዚአብሔር የያፌትን ግዛት ያስፋ፤ ያፌት በሴም ድንኳኖች ይኑር፤ ከነዓን የያፌት አገልጋይ ይሁን።” አለ። 28 ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ። 29 ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖሮ ሞተ።
1 የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ዝርያዎች የሚከተሉት ናቸው። ከጥፋት ውሃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው። 2 የያፌት ልጆች፦ ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕና ቴራስ ነበሩ። 3 የጋሜር ልጆች፦ አስከናዝ፣ ሪፋትና ቴርጋማ ነበሩ። 4 የያዋን ልጆች፦ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲምና ሮዳኢ ነበሩ። 5 ከእነዚህም በየነገዳቸው በየጎሳቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ። 6 የካም ልጆች፦ ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥና ከነዓን ነበሩ። 7 የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማና ሰበቀታ ነበሩ። የራዕማ ልጆች፦ ሳባና ድዳን ነበሩ። 8 ኩሽ በምድር ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ጦረኛ የነበረው የናምሩድ አባት ነበር። 9 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ አዳኝ ነበር። ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር። 10 የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች በሰናዖር ምድር የነበሩት፡- ባቢሎን፣ አሬክ፣ አርካድና ካልኔ ነበሩ። 11 ከዚያም ወደ አሦር ምድር ሄደና ነነዌን፣ ርሆቦትን፣ ካላሕን 12 እንዲሁም በነነዌና በካላሕ መካከል የነበረውን ታላቅ ከተማ ሬሴን የተባሉትን ከተሞች መሠረተ። 13 ምጽራይም የሎዳማውያን፣የዐናሚማውያን፣ የላህሚማውያን፣ የነፍታሌማውያን፣ 14 የፈተሩሲማውያንና ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የካስሎሂማውያንና የቀፍቶርማውያን አባት ነበር። 15 የከነዓንም የበኩር ልጅ ሲዶን ተከታዩም ሔት ይባሉ ነበር። 16 ሌሎቹም የከነዓን ዝርያዎች ኢያቡሳውያን፣ አሞራውያን፣ ጌርጌሳውያን፣ 17 ኤውያውያንን፣ ዓርቃውያን፣ ሲናውያን፣ 18 ኤርዋዳውያን፣ አርዋዳውያን፣ ደማራውያን፣ ሐማታውያን የሚባሉ ነበሩ። ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጎሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ። 19 የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል ገሞራን አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል። 20 እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ነበሩ። 21 ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅድመ አያት ነበር። 22 የሴም ልጆች ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ነበሩ። 23 የአራም ልጆች ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ ነበሩ። 24 አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ኤቦርን ወለደ። 25 ዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለነበር የአንደኛው ልጅ ስም ፍሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ። 26 ዮቅጣንም የአልሞዳድ፣ የሼሌፍ፥ የሐጸርማዌት፣ የዮራሕ፣ 27 የዐዶራም፣ የኢዛል፣ የዲቅላ፣ 28 የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣ 29 የኦፊር፣ የሐዊላና የዮባብ አባት ነበር። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዝርያዎች ነበሩ። 30 መኖርያ ስፍራቸውም በስተምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ስፋር ይደርስ ነበር። 31 እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ነበሩ። 32 የኖኅ ወንዶች ልጆች ጎሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነበር።
1 በዚያ ዘመን መላው ዓለም የሚናገረውና የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር። 2 ወደ ምሥራቅ ሲጓዙ፣ በሰናዖር አንድ ሜዳማ ቦታ አግኝተው በዚያ ሰፈሩ። 3 እርስ በርሳቸውም፣ “ኑ፣ ጡብ እንሥራና እስከበቃው ድረስ በእሳት እንተኩሰው” ተባባሉ። በድንጋይ ፈንታ ጡብ ተጠቀሙ፤ ጡቡን እርስ በርስ ለማያያዝም ቅጥራን ተጠቀሙ። 4 ከዚያም፣ “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆን ጫፉ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ። ያንን ካላደረግን በምድር ሁሉ ፊት መበታተናችን ነው” አሉ። 5 የአዳም ልጆች የሠሩትን ለማየት ያህዌ ወደ ከተማውና ወደ ግንቡ ወረደ። 6 ያህዌም፣ “አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ በመሆናቸው ይህን ማድረግ ችለዋል! ከእንግዲህ ማድረግ የፈለጉትን ለማድረግ ምንም የሚያቅታቸው አይኖርም። 7 ኑ እንውረድ፤ አርስ በርስ እንዳይግባቡም ቋንቋቸውን እንደበላልቀው” አለ። 8 ስለዚህ ያህዌ ከዚያ ቦታ ወደ መላው ዓለም በታተናቸው፣ እነርሱም ከተማዋን መሥራት አቋረጡ። 9 በዚያ የዓለምን ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዋ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም ያህዌ በመላው ዓለም በተናቸው። 10 የሴም ትውልድ ይህ ነው። የጥፋት ውሃ ከመጣ ሁለት ዓመት በኋላ ሴም መቶ ዓመት ሲሆነው አርፋድሰድን ወለደ። 11 አርፋድሰድን ከወለደ በኋላ ሴም አምስት መቶ ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 12 አርፋክሰድ በሰለሣ አምስት ዓመቱ ሰላን ወለደ፤ 13 ሰላን ከወለደ በኋላ አርፋክሰድ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ እርሱም ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 14 ሳላ ሰላሣ ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤ 15 ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። 16 ዔቦር አራት ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤ 17 ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር አራት መቶ ሰላሣ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 18 ፋሌቅ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ራግውን ወለደ፤ 19 ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 20 ራግው ሰለሣ ሁለት ዓመት ሲሆነው፣ ሴሮሕን ወለደ፤ 21 ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው ሁለት ሞት ሰባት ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 22 ሴሮሕ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ናኮርን ወለደ፤ 23 ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። 24 ናኮር ሃያ ዘጠኝ ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤ 25 ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር አንድ መቶ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ። 26 ታራ ሰባ ዓመት ሲሆነው አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ። 27 የታራ ትውልድ ይህ ነው። ታራ፣ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራን ወለደ። ሐራን ሎጥን ወለደ። 28 ሐራን አባቱ ታራ በሕይወት እያለ በተወለደበት ከተማ በከለዳውያን ዑር ሞተ። 29 አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ። የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካ የሐራን ልጅ ስትሆን፣ ሐራን የሚልካና የዮሳካ አባት ነበር። 30 ሦራ ምንም ልጅ ያልነበራት መካን ነበረች። 31 ታራ ልጁ አብራምን፣ የልጅ ልጁን ሎጥንና የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ዑር አብረው ወጡ። ሆኖም፣ ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ። 32 ታራ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖሮ በካራን ሞተ።
1 በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን፣ ወገንህንና የአባትህን ቤተ ሰብ ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ፤ 2 ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት አደርግሃለሁ። 3 የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግሙህንና የሚያዋርዱህን እረግማለሁ። በአንተ አማካይነት በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይባረካሉ።” 4 ስለዚህ አብራም ያህዌ እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ተነሥቶ ሲሄድ፣ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበር። 5 አብራም ሚስቱ ሦራን፣ የውንድሙ ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዞ በመጓዝ፣ ከነዓን ምድር ገቡ። 6 አብራም በሞሬ ያለው ግዙፍ የወርካ ዛፍ እስካለበት እስከ ሴኬም ዘልቆ ሄደ። በዚያ ዘመን ከነሻናውያን በዚህ ምድር ይኖሩ ነበር። 7 ያህዌ ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። ስለዚህ አብራም ለተገለጠለት ለያህዌ በዚያ መሠዊያ ሠራ። 8 ከዚያ በመነሣት ከቤቴል በስተ ምሥራቅ ወዳለው ተራራማ አገር ሄደ፤ ቤቴል በስተ ምዕራብ፣ ጋይ በስተ ምዕራብ ባለችበት ቦታ ድንኳኑን ተከለ። እዚያ ለያህዌ መሠዊያ ሠራ፤ የያህዌንም ስም ጠርቶ ጸለየ። 9 አብራም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ መጓዙን ቀጠለ። 10 በዚያ ምድር ጽኑ ራብ ስለ ነበር አብራም እዚያ ጥቂት ጊዜ ለመቆየት ወደ ግብፅ ሄደ። 11 ግብፅ በመግባት ላይ እያለ አብራም ሚስቱ ሦራን እንዲህ አላት፤ “መቼም አንቺ ቆንጆ ሴት መሆንሽን አውቃለሁ። 12 ግብፃውያን ሲያዩሽ ‘ይህች ሚስቱ ናት’ ይላሉ፤ እኔን ይገድሉኛል፤ አንቺን ግን ይተዉሻል። 13 ስለዚህ በአንቺ ምክንያት ለእኔ መልካም እንዲሆልኝ ሕይወቴም እንዲተርፍ እኅቱ ነኝ’ በዪ አላት። 14 አብራም ወደ ግብፅ ሲገባ፣ ሦራ ምን ያህል ቆንጆ እንደ ሆነች ግብፃውያኑ አዩ። 15 የፈርሾን ሹማምንት ባዩአት ጊዜ እርሷን እያደነቁ ለፈርዖን ነገሩት፤ ወደ ቤተ መንግሥትም ተወሰደች። 16 በእርሷ ምክንያት ፈርኦን አብራምን በክብር አስተናገደው፤ በጎች፣ በሬዎች፣ ወንድ አህዮች ወንድና ሴት ባሪያዎች፣ ሴት አህዮችና ግመሎች ሰጠው። 17 በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ያህዌ ፈርዖንና ቤተ ሰቡን በታላቅ መቅሠፍት መታ። 18 ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ለመሆኑ ምን እያደረግህብኝ ነው? ሚስትህ መሆንዋን ለምን አልነገርከኝም? 19 ለምን እኅቴ ናት አልከኝ? እኅቴ ናት ስላልከኝ ሚስቴ ላደርጋት ነበር። አሁንም ሚስትህ እቻት፤ ይዘሃት ሂድ” 20 ከዚያም ፈርዖን አብራምን በተመለከተ ለባለሟሎቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋር አሰናበቱት።
1 ስለዚህ አብራም ሚስቱንና ያለውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከግብፅ ወደ ኔጌብ ሄደ። ሎጥም ከእነርሱ ጋር ነበረ። 2 በዚህ ጊዜ አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ በልጽጎ ነበር። 3 ከኔጌብ ተነሥቶ እስከ ቤቴል ተጓዘ፤ ቀድሞ ድንኳን ተክሎበት ወደ ነበረው በቤቴልና በጋይ መካከል ወደ ነበረው ቦታ ደረሰ። 4 ይህ ቀድሞ መሠዊያ የሠራበት ቦታ ሲሆን በዚያ ያህዌን ጠራ። 5 ከአብራም ጋር ይጓዝ የነበረው ሎጥ የራሱ በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት። 6 ሁለቱ አንድ ላይ ይኖሩ ስለ ነበር ስፍራው አልበቃቸውም፤ በዚህ ላይ ንብረታቸውም በጣም ብዙ ስለ ነበር አብረው መኖር አልቻሉም። 7 ይህም በመሆኑ በአብራምና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተፈጠረ። በዚያ ዘመን ከነኣናውያንና ፌርዛውያን በዚያው አገር ይኖሩ ነበር። 8 አብራም ሎጥን እንዲህ አልው፤ “በእኔና በአንተ፣ በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ግጭት መኖር የለበትም፤ በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ ሰብ ነን። 9 ይኸው እንደምታየው ምድሩ ሰፊ ነው፤ ብንለያይ ይሻላል። አንተ ግራውን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ቀኙን ብትመርጥ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ። 10 ስለዚህ ሎጥ ዙሪያውን ሲመለከት እስከ ዞዓር ድረስ ያለው የዮርዳኖስ ረባዳ ሜዳ ሁሉ እንደ ያህዌ ገነት እንደ የግብፅ ምድር በጣም ለም ሆኖ አገኘው። እንዲህ የነበረው እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን ከማጥፋቱ በፊት ነበር። 11 ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ ሁሉ መርቶ ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ በዚህ ሁኔታ ዘመዳሞቹ ተለያዩ። 12 አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ባሉት ከተሞች መካከል ኖረ። እስከ ሰዶም ድረስ ባለው ቦታ ድንኳኖቹን ተከለ። 13 የሰዶም ሰዎች በጣም ዐመፀኞችና በያህዌም ፊት እጅግ ኀጢአተኞች ነበሩ። 14 ሎጥ ከእርሱ ከተለየው በኋላ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ቦታ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት። 15 ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁ። 16 ዘርህን እንደ ምድር ትቢያ አበዛዋለሁ፤ የምድር ትቢያ ሊቆጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር ሊቆጠር አይችልም። 17 እንግዲህ ምድሪቱን ስለምስጥህ ተነሣና በርዝመትና በስፋቱ ተመላለሰባት።” 18 ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቀለና በኬብሮን ወዳሉት የመምሬ ወርካ ዛፎች መጥቶ ኖረ፤ እዚያም ለያህዌ መሠዊያ ሠራ።
1 አምራፌል የሰናዖር ንጉሥ፣ አርዮክ የአላሳር ንጉሥ፣ ከሎደጎምር የኤላም ንጉሥ፣ ተድዓል የጎይም ንጉሥ፣ 2 በነበሩበት ዘመን፤ ከሰዶም ንጉሥ በላ፣ ከጎሞራ ንጉሥ ከብርሳ፣ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፣ ከሰቦይ ንጉሥ ከሰሜበር፣ እንዲሁም ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ወጡ። 3 እነዚህ የኋለኞቹ አምስት ነገሥታት የጨው ባሕር እየተባለች በምትጠራው በሲዶም ሸለቆ ተሰበሰቡ። 4 እነርሱም አሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ተገዙ፤ በአሥራ ሦስተኛው ዓመት ግን ዐመፁ። 5 በአሥራ አራተኛው ዓመት ከሎዶጎምርና ከእርሱም ጋር የነበሩት ነገሥታት መጥተው ራፋይምን፣ በአስታሮት ቃርናይምን፣ በካም ዙዚምን፣ በሴዊ ኑሚምን፣ በሸቮት ኢምንን፣ 6 የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይ በረሐማ አጠገብ እስካለው እስከ አልፋራን ድረስ ድል አደረጋቸው። 7 ከዚያም ተመልሰው ዓይንሚስፓጥ ወደሚባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌዋውያንና በሐሴስ ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ። 8 ከዚያም የሶዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የሰቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት ወደ ሲዶም ሸለቆ ሄደው ለጦርነት ተዘጋጁ። 9 እነዚህ አምስቱ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉስ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በአላሶር ንጉሥ በአርዮክ በእነዚህ ላይ ዘመቱባቸው። 10 በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጉድጓዶች ነበሩ፤ የሰዶምና የጎመራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጉድጓዶች ውስጥ ወደቁ። የተረፉትም ወደ ተራሮች ሸሹ። 11 አራቱ ነገሥታትም በሰዶምና በጎሞራ ያገኙትን ሀብትና ምግብ ሁሉ ዘርፈው ሄዱ። 12 በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብርሃምን ወንድም ልጅ ሎጥንና የነበረውን ንብረት ሁሉ ይዘው ሄዱ። 13 ከዚያ ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው። በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው የአስኮና የእውናን ወንድም በነበረው በአሞራዊው መምሬ ዋርካ ዛፎች አጠገብ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የአብራም አጋሮች ነበር። 14 ጠላት ዘመዶቹን ማርኮ መውሰዱን አብራም ሲሰማ በቤቱ ተወልደው ያደጉ ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ሰዎች ይዞ እስከ ዳን ድረስ ተከታተሏቸው። 15 አብራም ጠላቶቹን ለማጥቃት ሰራዊቱን ሌሊቱን በቡድን በቡድን ከፋፍሎ ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው። 16 ጠላት የማረከውን በሙሉ አስጣለ፤ ዘመዱ ሎጥንና ንብረቱን፣ እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎች ሰዎችን አስመለሰ። 17 አብራም የኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩ ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ ተብሎ በሚጠራው በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ። 18 የሰሌም ንጉሥ መልከጼዴቅ እንጀራና ወይን ጠጅ ይዞ መጣ። እርሱ የልዑል አምላክ ካህን ነበር። 19 አብራምም እንዲህ በማለት ባረከው፣ “ሰማይና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ። 20 ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠ ልዑል እግዚአብሔር ይባረክ።” አብራምም ይዞት ከነበረው ሁሉ አንድ አሥረኛውን ሰጠው። 21 የሰዶም ንጉሥ አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው። 22 አብራምም ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ቢሆን፣ 23 ደግሞም ‘አብራምን ባለጸጋ አደረግሁት’ እንዳትል የአንተ ከሆነ ምንም ነገር እንዳልወስድ ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ አምላክ ወደ ያህዌ እጄን አንሥቻለሁ። 24 አብረውኝ ያሉት ሰዎች ከበሉትና የእነርሱ ድርሻ ከሆነው በቀር ምንም ነገር አልወስድም። አውናን፣ ኤስኩልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”
1 ከዚህ በኋላ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፣ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ሽልማትህም እኔው ነን።” 2 አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ እኔ ልጅ የለኝም፤ የቤት ወራሽ የሚሆነው የደማስቆው ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ አንተ ለእኔ የምትሰጠኝ ምንድን ነው?” አለ። 3 በመቀጠልም አብራም “አንተ ልጅ እስካልሰጠኸኝ ድረስ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም” አለ። 4 በዚህ ጊዜ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ይልቁንም ወራሽህ የሚሆነው ከአብራክህ የሚከፈል የራስህ ልጅ ይሆናል።” 5 ከዚያም ወደ ውጭ አወጣውና እንዲህ አለው፤ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ መቍጠር ከቻልህ ከዋክብቱን ቍጠር። ዘርህም እንዲሁ ይበዛል።” 6 አብራም ያህዌን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት። 7 እንዲህም አለው፤ “ይህችን ምድር እንድትወርስ ልሰጥህ ከከለዳውያን ምድር ከዑር ያወጣሁህ እኔ ያህዌ ነኝ።” 8 አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ ይህችን ምድር እንደምወርስ እንዴት አውቃለሁ?” አለ። 9 በዚህ ጊዜ፣ “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንዲት ፍየልና አንድ በግ እንዲሁም ዋኖስና አንድ ርግብ አቅርብልኝ” አለው። 10 እርሱም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቆርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጣቸው፤ ወፎቹን ግን አልከፈላቸውም። 11 አሞሮች ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራምም አባረራቸው። 12 ፀሓይ ልትጠልቅ ስትል አብራም ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማም መጣበት። 13 በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ዘሮችህ የራሳቸው ባልሆነ ምድር ባዕድ እንደሚሆኑና እዚያ ለአራቶ መቶ ዓመት በባርነት እንደሚኖሩ በእርግጥ ዕወቅ። 14 እኔም ባሪያዎች ባደረጓቸው ሕዝብ እፈርዳለሁ፤ በኋላም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ። 15 አንተ ግን በሰላም ወደ አባቶችህ ትሄዳለህ፤ ዕድሜም ጠግበህ ትቀበራለህ። 16 በአራተኛውም ትውልድ እንደ ገና ወደዚህ ይመጣሉ፤ ምክንያቱም የአሞራውያን ኀጢአት ጽዋው ገና አልሞላም።” 17 ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና በተቆራረጡት ሥጋዎች መካከል አለፈ። 18 በዚያን ቀን ያህዌ እንዲህ በማለት ከአብራም ጋር ኪዳን አደረገ፤ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤ 19 የምሰጣቸውም የቄናውያንን፣ የቄንፌዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣ 20 የኬጢያውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የራፋይምን፣ 21 የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያን፣ የጌርሳውያንንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው።”
1 የአብራም ሚስት ሦራ ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ነገር ግን አጋር የምትባል ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት። 2 አብራምንም፣ "ያህዌ ልጅ እንዳልወደልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጅ አገኝ ይሆናልና ክአገልጋዬ ጋር ተኛ" አለችው። አብራም ሦራ በነገረችው ተስማማ። 3 የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋ ሚስት እንድትሆነው ለአብራም የሰጠችው አብራም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ነበር። 4 አብራም ክአጋር ግን'ኡንት አደረገ እርሷም ፀነሰች። አጋር መፅነሷን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን በንቀት ማየት ጀመረች። 5 በዚህ ጊዜ ሦራ አብራምን፣ "ይህ በደል የደረሰብኝ በአንተ ምክንያት ነው። ኅቅፍህ ውስጥ እንድትሆን አገልጋዬን ሰጠሁ፤ እርሷ ግን መፅነሷን ስታውቅ እኔን መናቅ ጀመረች። ያህዌ በእኔና በአንተ መካከ ይፍረድ" አለችው። 6 አብራምም መልሶ ሦራን፣ "አገልጋይሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ ናት እርሷ ላይ የፈለግሽውን ማድረግ ትችያልለሽ" አላት። ስለዚህ ሦራ ስላሠቃየቻት፣ አጋር ከቤት ጠፍታ ሄደች። 7 የያህዌ መልአክ አጋርን ምድረ በዳ ውስጥ በነበረ አንድ ምንጭ አጠገብ አገኛት፤ ያ ምንጭ ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ላይ ነበር። 8 መልአኩም፣ "የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፣ ከየት መጣሽ ወዴትስ እየሄድሽ ነው?" አላት። እርሷም፣ "ከእመቤቴ ከሦራ ኮብልዬ እየሄድሁ ነው" አለችው። 9 የያህዌ መልአክ፣ "ወደ እመቤትሽ ተመለዒ፤ ራስሽንም ለሥልጣንዋ አስገዢ" አላት። 10 ከዚያም የያህዌ መልአክ፣ "ዘርሽን እጅግ አበዛዋለሁ፤ ከበምዛቱም የተነሣ ሊቆጠር አይቻልም" አላት። 11 የያህዌም መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤ "እነሆ ፀንሰሻል ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ያህዌ ችግርሽን ሰምቷልና ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ። 12 እርሱ እንደ ዱር አህያ ይሆናል። ከሰው ሁሉ ጋር ይጣላል፤ ሰው ሁሉም ከእርሱ ጋር ይጣላል፤ ከወንድሞቹ ሁሉ ተነጥሎ ይኖራል።" 13 እርሷም ይሚያናግራትን ያህዌን፣ "አንተኮ እኔን የምታይ አምላክ ነህ"በማለት ጠራችው፤ ምክንያቱም፥ "እርሱ እኔን እንዳየ ሁሉ እኔም እርሱን አየው ይሆን?" ብላ ነበር። 14 ስለዚህ ያ ምንጭ ብኤርልያህሮኢ ተባለ፤ የሚገኘው በቃዴስና በባሬድ መካከ ልነው። 15 አጋር ለአብራም ወድን ልጅ ወለደችለው፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን ልጅ እስማኤል ብሎ ጠራው። 16 አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ አብራም ሰማንያ ስድስት ዓመት ሆኖት ነበር።
1 አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው እያለ ያህዌ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፤ "እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ ነቀፋም አይኑርብህ። 2 በእኔና በአንተ መካከል የተደረገውን ኪዳን አጸናለሁ፤ አንተንም እጅግ አበዛሃለሁ።" 3 አብራም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እግዚአበሔርም እንዲ አለው፤ 4 "እነሆ ኪዳኔ ክአንተ ጋር ነው። የብዙ ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ። 5 ከእንግዲህ ስምህ አብራም መባል የለበትም፤ ስምህ አብርሃም መባል እለበት፤ ምክንያቱም የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ። 6 እጅግ አበዛሃለሁ፣ ሕዝቦች ክአንተ ይገኛሉ፤ ነገሥታትም ክአንተ ይወጣሉ። 7 በእኔና በአንተ፣ ክአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በዘላለም ኪዳን አምላክ እሆናችኋለሁ። 8 ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ይህች አሁን የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣላለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።" 9 ከዚያም እግዚአብሔር አብርሃምን፣ "በአንተም በኩል፣ አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ። 10 በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ በእኔና በዘርህ መካከል መጠበቅ ያለባችሁ ኪዳኔ ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። 11 እናንተ ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእናንተ መካከል ያለው ኪዳን ምልክት ይሆናል። 12 በመካከላችሁ ያለው ማንኛውም ስምንት ዓመት የሞላው ወንድ የሚመጣው ትውልድ ሁሉ ይገረዝ። ይህ በቤትህ የተወለደውን በገንዘብህ የተገዛውን ሁሉ ይጨምራል። 13 ቤትህ ውስጥ የተወለደና በገንዘብህ የገዛኸው መገረዝ አለባቸው። ስለሆነም ኪዳኔ በዘላለም ኪዳን ሥጋችሁ ላይ ይሆናል። 14 ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን አፍርሷልና ከወገኖቹ ይወገድ።" 15 እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ሚስትህ ሦራን ክአንግዲህ ሥራ እንጂ ሦራ ብለህ አትጥራት። 16 እባርክሃለሁ፤ ከእርሷ ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ። እባርካታለሁ። እርሷም የብዙ ሕዝብ እናት ትሆናልች፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ክአርሷ ይወጣሉ። 17 በዚህ ጊዜ አብርሃም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ እየሳቀ በሉ እንዲህ አለ፤ "ለመሆኑ የመቶ ዓመት ሽማግሌ ልጅ መውልደድ ይችላል? የዘጠና ዓመቷ አሮጊት ሥራስ ብትሆን ልጅ መውለድ ይሆንላታል?" 18 አብርሃም እግዚአብሔርን፣ "ይልቅ፣ እስማኤልን ብቻ ባኖርህልኝ!" አለ። 19 እግዚአብሔርም፣ "እንደዚያ አይደለም፤ ሚስትህ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ። የዘላለም ኪዳኔን ከእርሱ ጋር፣ ከእርሱም በኋላ ከዘሩ ጋር እመጸርታለሁ። 20 እስማኤልን በተመለከተም ልምናህን ሰምቻለሁ። እነሆ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ። የአሥራ ሁለት ነገዶች አባት ይሆናል፤ ታላቅ ሕዝብ እንዲሆንም አደርጋለሁ። 21 ኪዳኔን ግን፣ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ሣራ ከምትወልድህል ከይስሐቅ ጋር እመሠርታለሁ።" 22 ከእርሱ ጋር መነጋገሩን ከጨረሰ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ላይ ወጣ። 23 በዚያኑ ዕለት አብርሃም ልጁ ይስሐቅን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትን በሙሉ፣ በገንዘቡ የገዛቸውን ሁሉ፣ ቤቱ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድ ሁሉ እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ገረዛቸው። 24 አብርሃም በተገረዘ ጊዜ እድሜው ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ነበር። 25 ልጁም እስማኤል በተገረዘ ጊዜ እድሜው አሥራ ሦስት ነበር። 26 በዚያው ቀን አብርሃምና ልጁ እስማኤልም ተገረዙ። 27 ቤቱ ውስጥ የተወለዱትን፣ ከውጭ በገንዘብ የተገዙትን ጨምሮ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ወንዶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ተገረዙ።
1 ቀኑ በጣም ሞቃት በሆነ ጊዜ አብርሃም በመምሬ ወርካ ዛፎች አቅራቢይ ኣድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ እያለ ያህዌ ተገለጥለት። 2 እርሱም ቀና ብሎ ሦስት ሰዎች ፊት ለፊቱ ቆመው አየ። ባያቸውም ጊዜ ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ፈጥኖ ወደ እነርሱ ሄዶ፣ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ። 3 አብርሃም እንዲህ አለ፤ "ጌታዬ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ባሪያህን አልፈህ አትሂድ። 4 ጥቂት ውሃ ትምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚያም ዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ። 5 ወደ እኔ ወዳገልጋያችሁ ከመጣችሁ የደከመ ሰውነታችሁ እንዲበረታ እስቲ ጥቂት እህል ላምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም. "እንዳልኸው አድርግ" አሉት። 6 ያኔውኑ አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወደ ነበረችበት ድንኳን ገብቶ፣ "ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ" አላት። 7 ከዚያም ወደ መንጋው በፍጥነት ሄዶ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ግን ገር የሆነ ጥጃ መረጠና ለአገልጋዩ ሰጠው፤ እርሱም በአስቸኳይ አደረሰው። 8 አብርሃምም እግሮ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀበላቸው፤ እነርሱ እየበሉ እያለ እርሱ ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር። 9 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "ሚስትህ ሥራ የታለች?" እርሱም፣ "ድንኳን ውስጥ ናት" አለ። 10 እነርሱም፣ "የዛሬ ዓመት በፀደይ ወቅት ልክ በዚሁ ጊዜ በእርግጥ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሥራ ልጅ ትወልዳለች" አለ። ሥራ ከጀርባ በነበረው ድንኳን ደጃፍ ሆና ታዳምጥ ነበር። 11 በዚህ ጊዜ አብርሃምና ሥራ በጣም አርጅተው ነበር፤ ሥራማ ልጅ የመውለጃ ጊዜ አልፎባት ነበር። 12 ስለዚህ ሣራ በልቧ፣ "ይህን ያህል ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛልን?" ብላ ሳቀች። 13 ያህዌ አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ካረጀሁ በኋላ እንዴት አድርጌ ልጅ እወልዳለሁ ስትል ሣራ የሳቀችው ለምንድን ነው? 14 ለመሆኑ ለያህዌ የሚሳነው ነገር አለ? እኔ በወሰንሁት የፀደይ ወቅት ወደ እናንተ እመለሳለህ፤ በሚመጣው ዓመት በዚህ ጊዜ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች።" 15 ሣራ ግን ፈርታ ስል ነበር፣ "ኧረ እልሳቅሁም" በማለት ካደች። እርሱም፣ "የለም፤ ስቀሻል እንጂ" አላት። 16 ሰዎቹ ለመሄድ ሲነሡ ቁልቁል ወደ ሰዶም ተመለከቱ። አብርሃምም ሊሸኛቸው ከእነርሱ ጋር ሄደ። 17 በዚህ ጊዜ ያህዌ እንዲህ አለ፤ "እኔ የማደርገውን ክአብርሃም መደበቅ አለብኝን? 18 አብርሃም በእርግጥ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይህሆናል፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ። 19 ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የያህዌን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቡን እንዲያስተምር እኔ አብርሃምን መርጬዋለሁ፤ ይኸውም ለአብርሃም የነገረውን ሁሉ ያህዌ እንዲፈጽምለት ነው።" 20 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ "በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ክስ በጣም ስለ በዛ፣ ኀጢአታቸውም በጣም ትልቅ ስል ሆነ፤ 21 ወደ እኔ የመጡ ክሶች ምን ያህል እውነት መሆናቸውን ለማየት ወደዚያ እወርዳለሁ፤ እንደዚይ ካልሆነም አውቃለሁ።" 22 ሰዎቹም ፊታቸውን ወደ ሰዶም አቅንተው ሄዱ፤ አብርሃም ግን ያህዌ ፊት እንደ ቆመ ነበር። 23 አብርሃም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ፣ "በእርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር ታጠፋለህን? 24 ምናልባት በከተማዋ ሃምሳ ጻድቃን ቢገኙስ? እዚያ ባሉ ጻድቃን ስትል ከተማዋን ሳታድን ታጠፋታለህን? 25 ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር በመግደል፣ ኀጢአተኛ ላይ የደረሰው በእርሱም እንዲደርስ ማድረግን የመሰለ ንገር ከአንተ ይራቅ! እንዲህ ያለው ከአንተ ይራቅ! የምድር ሁሉ ዳኛ እውነተኛ ጻድቅ የሆነውን አያደርግምን? 26 ያህዌም እንዲህ አለ፤ "በሰዶም ከተማ ውስጥ ሃምሳ ጻድቃን ካገኘሁ ፣ ለእነርሱ ስል ያንን ቦታ እምራለሁ።" 27 አብርሃምም መልሶ እንዲህ አለ፤ "እኔ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታዬ ጋር ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤ 28 ለመሆኑ ከአምሳዎቹ ጻድቃን አምስት ቢጎድሉ፣ በጎደሉት አምስቱ ምክንያት ከተማዋን በሙሉ ታጠፋለህን?" እርሱም፣ "እዚያ አርባ አምስ ጻድቃንካገኘሁ አላጠፋትም" አለ። 29 አብርሃምም እንደ ገና፣ "ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?" እለ፤ እርሱም፣ "ለአርባዎቹ ስል አላደርገውም" እለ። 30 አብርሃምም፣ "እባክህን ጌታዬ ይህን ያህል በመናገሬ አትቆጣኝ። እንደው ምናልባት ሰለሣ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፣ "ሰላሣ ጻድቃን ካገኘሁ አላደርገውም" በማለት መለሰ። 31 አብርሃምም፣ "መቼም አንዴ ከጌታዬ ጋር መናገር ጀምሬአለሁ! እንደው ምናልባት ሃያ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፥ "ለሃያዎቹ ስል አላደርገውም" አለ። 32 በመጨረሻም እንዲህ አለ፤ "እባክህ ጌታዬ አትቆጣኝ፤ አንዴ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት አሥር ቢገኙስ። እርሱም፣ "ለአሥሩ፣ ሲል አላጠፋትም" አለ። 33 ከአብርሃም ጋር መነጋገሩን እንደ ጨረሰ ያህዌ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።
1 ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ወደ ሰዶም መጡ፤ በሰዶም ከተማ መግቢያበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ሎጥ ሲያያቸው ሊቀበላቸው ተነሣ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ። 2 እርሱም፣ "እባካችሁ ጌቶቼ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ሌሊቱንም ከእኛ ጋር አሳልፉ፤ ከዚያ ጧት በማለዳ ተነሥታችሁ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም፣ "የለም፤ እዚሁ አደባባዩ ላይ እናድራለን" አሉት። 3 ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው እርሱ ቤት ለማደር አብረውት ገቡ። ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ። 4 ሆኖም፣ ገና ከመተኛታቸው በፊት የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት። 5 ሎጥን በመጣራት፣ "በዚህ ምሽት ወደ ቤትህ የመጡ ሰዎች የታሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን" አሉት። 6 ሎጥ ሊያነጋግራቸው ወደ ውጭ ወጣ መዝጊያውን ከበስተ ኋላው ዘጋ። 7 እንዲህም አለ፤ "ወንድሞቼ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ እለምናችሏለሁ። 8 ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁና የወደዳችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን ምንም ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ተብተዋልና።" 9 እነርሱ ግን፣ "ዞር በል!" ይኸ ሰውዬ ስደተኛ ሆኖ እዚህ ለመኖር መጣ፤ ደግሞ ዳኛ ሆነብን! ይልቁ በእነርሱ ላይ ካሰብነው የከፋ እንዳይደርስብህ ዘወር በልልን" አሉት ሎጥንም እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተቃርበው ነበር። 10 ሰዎቹ እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ ቤት አስገቡትና በሩን ዘጉ። 11 ከቤቱ ውጪ የነበሩትን ውጣቶችንም ሆን ሽማግሌዎችን ግን የሎጥ እንግዶች ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ እነርሱም በሩን ለማግኘት ይደነባበሩ ጀመር። 12 ከዚያም ሰዎቹ ሎጥን እንዲህ አሉት፤ "በከተማዋ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን፣ የወንዶች ልጆችህን ሚስቶች፣ የሴቶች ልጆችህን ባሎችና ሌሎች ዘመዶችህን ሁሉ ከዚህ አውጣ። 13 ምክንያቱም ይህን ቦታ ልናጠፋ ነው፤ በያህዌ ፊት ከተማዋ ላይ የሚቀርቡ ክሶች በጣም እየጮኹ በመሆናቸው እንድናጠፋት እርሱ ልኮናል።" 14 ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹን ባሎች፣ የሴት ልጆቹን እጮኞች፣ "ቶሎ ከዚህ ቦታ ውጡ፤ ያህዌ ከተማዋን ሊያጠፋ ነው" አላቸው። የሴት ልጆቹ ባሎች ግን የሚቀልድ መሰላቸው። 15 ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥኝ፣ "ከተተማዋ ላይ በሚመጣው ቅጣት አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱ ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ" እያሉ አቻኮሉት። 16 ሎጥ አመነታ፤ ያህዌ ምሕረት ስላደረገላቸው ሰዎቹ የእርሱ፣ የሚስቱንና የሁለት ሴት ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዋ አወጣቸው። 17 ከከተማው ካወጧቸው በኋላ ከሰዎቹ አንዱ፣ "ሕይወታችሁን ለማዳን ሩጡ! ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ወይም ረባዳው ስፍራ ላይ አትቆዩ። ወደ ተራሮች ሽሹ፤ አለበለዚያ ትጠፋላችሁ።" 18 ሎጥም እንዲህ አላቸው፤ "ጌቶቼ ሆይ፣ 19 እኔ ባሪያችሁ በፊታችሁ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርጋችሁልኛል፤ እኔ እንደ ሆንኩ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል። 20 ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ቦታ ያለች ትንሽ ከተማ አለች ሸሽቼ ወደዚያ ብሄድ ሕይወቴን ማዳን እችላለሁ።" 21 እርሱም፣ "ይሁን እሺ፤ ልመናህን ተቀብብያለሁ፤ ያክካትንም ከተማ አላጠፋትም። 22 አንተ እዚያ እስክትደርስ ምንም ማድረግ ስለማልችል በል ቶሎ ፍጠንና ወደዚያ ሽሽ" አለው። ስለዚህ ያቺ ከተማ ዞዓር ተባለች። 23 ሎጥ ዞዓር ሲደርስ ፀሓይ በምድሩ ወጥታ ነበር። 24 ከዚያ ያህዌ ሰዶምና ጎሞራ ላይ ድኝና እሳት አዘነበ። 25 እነዚያን ከተሞችና ረባዳ ቦታዎቹን፣ የከተሞቹ ነዋሪዎችንና እዚይ ኣያሉ ለምለም ነገሮችን ሁሉ አጠፋ። 26 ከኋላው የነበረችው የሎጥሚስት ግን ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች። 27 አብርሃም ጠዋት ማለዳ ተነሥቶ ያህዌ ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ። 28 ቁልቁል ሰዶምና ጎሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የነበረውን ምድር ተመለከተ። ከምድጃ የሚወጣ የመሰለ ጢስ ከምድሩ እየወጣ ነበር። 29 እግዚአብሔር በረባዳው ቦታ የነበሩ ከተሞችን ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው። ሎጥ የነበረበትን ከተሞች ቢያጠፋም፣ እርሱ ግን ከጥፋት መሐል አወጣው። 30 ሎጥ ግን በዞዓር መኖር ስለ ፈራ ከሁለት ሴቶች ልጆቹ ጋር ተራሮቹ ላይ ለመኖር ከዞዓር ወደ ላይ ወጣ። ስለዚህ እርሱና ሁለት ሴቶች ልጆቹ ዋሻ ውስጥኖሩ። 31 ታላቋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፣ "አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ከእኛ ጋር የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም። 32 ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር እናትርፍ።" 33 ስለዚህ በዚያ ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት። ታላቂቱ ልጅ ሄዳ ክአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቅም። 34 በሚቀጥለው ቀን ታላቂቱ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ "ትናንት ሌሊት እኔ ከእባቴ ጋር ተኛሁ። ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፣ ከዚያ አንቺ ሄደሽ ከእርሱ ጋር ትተኛለሽ፣ የአባታችንንም ዘር እናተርፋለን።" 35 ስለዚህ በዚያም ምሽት አባታቸውን ወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታናሺቱ ልጅ ሄዳ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም። 36 ሁለቱ የሎጥ ልጆች ክአባታቸው አረገዙ። 37 ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት ሞዓባውያን አባት ሆነ። 38 ታናሺቱም እንዲሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት አሞናውያን አባት ሆነ።
1 አብርሃም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ አካብቢ ሄደ፤ በቃዴስና በሱር መካከልም መኖር ጀመረ። ለጥቂት ጊዜ በጌራራ ተቀመጠ። 2 አብርሃም ሚስቱ ሥራራን፣ "እኅቴ ናት" ይል ነበር፤ ስለዚህ ይጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ሰዎች ልኮ ሣራን ወሰዳት። 3 እግዚአብሔር ግን በሕልም ወደ እቢሜሌክ መጥቶ፣ "እነሆ በወሰድካት ሴት ምክንያት አንተ ምውት ነህ፤ ምክንያቱም እርሷ ባለ ባል ናት" አለው። 4 አቢሜሌክ ገና አልሰረሰባትም ነበርና እንዲህ አለ፤ "ጌታ ሆይ፣ በደል ያልተገኘበትን ሕዝብ ልታጠፋ ነውን? 5 'እኅቴ ናት' ያለኝ እርሱ ራሱ አይደለምን? እርሷም ብትሆን 'ወንድሜ ነው' ብላኛለች። እኔ እንዲህ ያደረግሁት በቅን ልቦናና በንጹሕ እጅ ነው።" 6 በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም እንዲህ አለው፤ "አዎን፣ ይህን ያደረግኸው በልብ ቅንነት እንደ ነበር እኔም አውቃለሁ፤ እኔ ላይ ኀጢአት እንዳትፈጽም የጠበቅሁህና እንዳትነካትም ያደረግሁት በዚህ ምክንያት ነው፤ 7 ስለዚህ የሰውየውን ሚስት መልስለት፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ ይጸልይልሃል አንትም ትድናለህ። እርሷን ካልመለስህ፣ እንተና የአንተ የሆነው ሁሉ በእርግጥ እንደምትጠፉ ዐውቃለሁ።" 8 አቤሜሊክ ጧት በማለዳ ተነሥቶ ሹማምንቶቹን ሁሉ ጠራ። የሆነውን ሁሉ ሲነግራቸው በጣም ፈሩ። 9 ከዚያም አቤሜሌ አብርሃምን አስጠርቶ፣ "ለመሆኑ፣ ምን እያደረግህብን ነው? በእኔና በግዛቴ ላይ እንዲህ ያለውን ትልቅ መዘዝ ያመጣህብኝ ምን ብበድልህ ነው? መደረግ ያልነበረትን አድርገህብኛል" አለው። 10 በመቀጠልም፣ አብርሃምን፣ "እንዲህ እንድታደርግ ያነሣሣህ ምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው። 11 አብርሃምም፣ "በዚህ ቦታ እግዚአብሔርን መፍራት የለም፤ ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል በማለት ስላሰብሁ ነው። 12 በዚህ ላይ ደግሞ ከእናቴ ባትወለድም የአባቴ ልጅ እኅቴ ናት፤ በኋላም ሚስቴ ሆነች። 13 የአባቴን ቤት ትቼ በየአገሩ እንድዞር እግዚአብሔር ሲያዝዘኝ፣ "ለእኔ ለባልሽ ያለሽን ታማኝነት በዚህ አሳዪኝ፤ በምንሄድበት ቦታ ሁሉ 'ወንድሜ ነው' በዪ አልኳት።" 14 ከዚያ አቤሜሊክ በጎችና በሬዎች፣ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ለአብርሃም ሰጠው። ሚስቱ ሣራንም ለአብርሃም መለሰለት። 15 አቤሜሌክ እንዲህ አለ፤ "አገሬ አገርህ ነው፤ ደስ በሚያሰኝህ ቦታ ተቀመጥ።" 16 ሣራንም፣ "ለወንድምሽ አንድ ሺህ ጥሬ ብር እሰጠዋለሁ። ይህም፣ በአንቺ ላይ ለተፈጸመው በደል ካሣ እንዲሆንና አብረውሽ ያሉ ሁሉ አንቺ ንጹሕ ሴት መሆንሽን እንዲያውቁ ነው።" 17 ከዚያም አብርሃም ለአቤሜሌክ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ ልጅ ለመውለድም በቁ። 18 ከአብርሃም ሚስት ከሣራ የተነሣ በአቢሜሌክ ቤት የሚገኙ ሴቶችን ሁሉ ያህዌ ማኅፀናቸውን ዘግቶ ነበር።
1 ለአብርሃም በሰጠው የተስፋ ቃል መሰረት እግዚአብሔር ሳራን አሰባት፤ እንደገባላት የተስፋ ቃልም አደረገ ፤ 2 ስለዚህም ሳራ አርግዛ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው «በዚህ ጊዜ ይወለዳል» ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው። 3 አብርሃም ሚስቱ ሳራ የወለደችለትን ልጅ «ይስሐቅ» ብሎ ስም አወጣለት። 4 ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሰረት አብርሃም ገረዘው። 5 ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ አብርሃም መቶ ዓመት ሆኖት ነበር። 6 ሳራም «እግዚአብሔር ሳቅ አደረገልኝ ስለዚህ ይህንን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል»አለች። 7 ቀጥላም «ሳራ ለአብርሃም ልጆችን ወልዳ ታጠባለች» ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድሁለት» አለች። 8 ልጇም አድጎ ጡት መጥባት ተወ፤ ጡት ባስጣሉበትም ቀን አብርሃም ታላቅ ግብዣ አደረገ። 9 ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል ከዕለታት አንድ ቀን በሳራ ልጅ በይስሐቅ ላይ ሲያሾፍበት ሳራ አየች። 10 ስለዚህ ሳራ አብርሃምን«ይህችን አገልጋይ ከነ ልጅዋ ወዲያ አባርልኝ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም» አለችው። 11 እስማኤልም ልጁ ስለሆነ ይህ ጉዳይ አብርሃምን በብርቱ አስጨነቀው 12 እግዚአብሔር ግን አብርሃምን «ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ። ዘር የሚወጣልህ በይስሃቅ በኩል ስለሆን እርሳ የምትልህን ሁሉ አድርግ። 13 የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ዘርያ ስልሆን ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ» አለው 14 አብርሃም በማለዳ ተነሳ ጥቂት ምግብ ውሃም በአቁማዳ ለአጋር በትከሻዋ አደረገላት። ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም በቤርሳቤህ በረሃ ትንከራተት ጀመር። 15 በአቁማዳ የነበረው ውሃ ባለቀ ጊዜ ልጁን በቁጥቋጦ ስር አስቀምችጠችው። 16 እርስዋም «ልጄ ሲሞት ማየት አልፈልግም» በማለት ጥቂት ከልጅዋ ርቃ ተቀመጠች፤ እዚያም ሆና ድምጻን ከፍ አድርጋ ታለቅስ ጀመር። 17 እግዚአብሔሬም ልሉ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን «አጋር ሆይ የምትጨነቂበት ነገር ምንድር ነው? እግዚአብሔር የልጂን ለቅሶ ሰምቶአልና አትፍሪ። 18 ተነሺ ሂንና ልጁን አንስተስ አባብይው፤ የእርሱንም ዘር አበዛለሁ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ። 19 በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ዓይኖችዋን ከፈተላትና አንድ የውኃ ጉድጋድ አየች፤ ሄዳም በአቁማዳ ውሃ ሞላች ለልጅዋም አጠጣችው። 20 ልጁ እያደገ በሚሄድበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር። 21 በፋራንም በረሓ ኖረ፤ ቀስት በመወርወርም የታወቀ አዳኝ ሆነ። እናቱም ከአንዲት ግብጻዊት ጋር አጋባችው። 22 በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ከሰራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር ሄደና አብርሃምን «በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ 23 እኔንም ሆነ ልጆቼን ወይም ዝርያዎቼን እንዳትዋሸኝ አሁን በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ። እኔ ለአንተ ታማኝነትን አሳይቻለሁ፤ አንተም ለእኔና ለዚህች ለምትኖርባትአገር ታማኝንትን እንደምታሳይ ማልልኝ» አለው። 24 አብርሃምም «እሺ እምላለሁ» አለ። 25 አብርሃም የአቢሜሌክ አገልጋዮች ስለ ወሰዱበት የውሃ ጉድጋድ ለአቤሜሌክ አቤቱታ አቀረበ፤ 26 አቤሜሌክም «ይህን ያደረገ ማን እንደሆን አላውቅም። አንተም አልነገርኸኝም ይህንን ነገር ገና ዛሬ መስማቴ ነው» አለው። 27 ከዚህ በኋላ አብርሃም ብዙ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ በዚያን ቀን ሁለቱም የስምምነት መሀላ አደረጉ። 28 በዚያን ጊዜ አብርሃም ሰባት እንስት የበግ ጠቦቶችን ከመንጋው ለየ፤ 29 አቤሜሌክም «እንዚህን ሰባት ጠቦቶች ለይተህ ያቆምሃቸው ለምንድር ነው?» አለው። 30 አብርሃምም «እነዚህን ሰባት እንስት ጠቦቶች ተቀበለኝ እነርሱን ከተቀበልከኝ ይህን ጉድጋድ የቆፈርሁ እኔ መሆኔን ምስክር እንዲሆን ነው» አለው፤ 31 ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ የዚያ ቦታ ስም ቤርሳቤህ ተባል፤ 32 ይህን ስምምንት በቤርሳቤህ ተስማምተው ካደረጉ በኋላ አቤሜሌክና የሰራዊቱ አለቃ ፊኮል ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ 33 ከዚህ ብኃላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከልና የዘላለም አምላክ ለሆነው ሰገደ፤ 34 አብርሃም በፍልስጥኤም ምድር በእንግድነት ለረዥም ጊዜ ኖረ።
1 ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም «አብርሃም»ብሎ ጠራው፤ «እነሆ አለሁኝ» ብሎ መለሰ። 2 እግዚአብሔርም «የምትወደውን አንድ ልጅህን ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ። እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን የሚቃጠል መስዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ» አለው፤ 3 አብርሃም በማለዳ ተነስቶ ለመስዋዕት የሚሆን እንጨት ቆረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅን ና ሁለት ወጣት ሰዎችን ይዞ እግዚአብሔር ወደ ነገረው ቦታ ለመሄድ ጉዞ ጀመረ። 4 በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ። 5 ከዚህ በኃላ አብርሃም የርሱን ወጣቶች «እናንተ ከአህያው ጋር በዚህ ቆዩ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ከሰገድን በኃላ እንመለሳለን፤ 6 አብርሃምም የሚቃጠለውን መስዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንስቶ ለልጁ ለይስአቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢላዋውንና እሳቱን ያዘ ሁለቱም አብረው ሄዱ። 7 ይስሐቅ አብርሃምን «አባባ» አለው፤ እርሱም «እነሆ አለሁ ልጄ» አለው፤ ይስሐቅም «እነሆ እሳትና እንጨት ይዘናል ታዲያ ለመስዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?» በማለት አብርሃምን ጠየቀው። 8 አብርሃምም «ልጄ ሆይ ለመስዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር እራሱ ያዘጋጃል» አለው። ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ። 9 እግዚአብሔር ነገረው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሰዊያ ሰርቶ እንጨቱን ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሰዊያው ላይ አጋደመው። 10 ልጁን ለማረድ ቢላዋ አንስቶ እጁን ዘረጋ። 11 ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ «አብርሃም! አብርሃም!» ብሎ ጠራው። እርሱም «እነሆኝ አለሁኝ» አለ። 12 እርሱም «በልጁ ላይ እጅህን አትጫንበት፣ ምንም ዓይነት ጉዳትም አታድርስበት፣ እነሆ እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቻለሁ፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት አልተቆጠብህም» አለው። 13 አብርሃም ዙሪያውን በተመለከት ጊዜ ከበስተጀርባው ቀንዶቹ በቁጥቋጥ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ አቀረበው። 14 አብርሃምም ያን ቦታ «እግዚአብሔር ያዘጋጃል» ብሎ ጠራው። ዛሬም ቢሆን ሠዎች «እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል» ይላሉ። 15 የእግዚአብሔር መልአክ ለሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ከሰማይ ጠራውና፤ 16 እንዲህ አለው፤ «እግዚአብሔር ብዙ በረከት እንድምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ» ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቆጠብህ፤ 17 እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባህር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዝርያዎችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነስተው፤ ከተሞቻቸውን ይይዛሉ። 18 ትዕዛዜን ስለ ፈጸምህ የዓለም ህዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ»፤ 19 ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ ወጣቶችሁ ተመለሰና በአንድነት ሆነው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ። 20 ከዚህ ሁሉ በኋላ እንዲህ ተብሎ ለአብርሃም ተነገረው «ሚልካ ልጆችን ለወንድምህ ለናኮር ወልዳለች፤ 21 እነርሱም የመጀመሪያው ልጅ ዑፅ ወንድሙም ቡዝ የአራም አባት ቀሙኤል፤ 22 ኬሰድ፣ ሐዞ፣ ፊልዳሽ፤ ይድላፍና በቱኤል ናቸው። 23 በቱኤል ርብቃን ወለደ። ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለንኮር ወለደችለት፤ 24 ረኡማ የተባለች የናኮር ቁባት ደግሞ ጤባሕን፣ ገሐምን፣ ተሐሽና ማዕካን ወለደችለት።
1 ሣራ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ኖረች። እነዚህን ዓመታት ነበር ሳራ የኖረችው። 2 በከነዓን ምድር ባለችው ቂርያት አርባ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃም በሣራ ሞት ምክንያት እጅግ ሃዘነ አለቀሰም። 3 ከዚያም አብርሃም ከተቀመጠበት ከሚስቱ ሬሳ አጠገብ ተነሳ፣ ኬጢያውያንን እንዲህ አላቸው፤ 4 «እኔ በመካከላችሁ በእንግድነት የምኖር ነኝ። እባካችሁ የመቃብር ቦታ ስጡኝ፤ የሚስቴንም ሬሳ ልቅበርበት።» 5 የኬጢ ልጆችም ለአብርሃም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ 6 «ጌታ ሆይ ስማን፣ አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ። ከመቃብር ቦታችን በመረጥከው ስፍራ ሬሳህን መቅበር ትችላለህ፣ ማናችንም ብንሆን የሞተብህን ሰው እንዳትቀብርበት የምቃብር ቦታችንን አንከለክልህም።» 7 አብርሃም ተነሣ በኬጢያውያን ልጆች ፊት እጅ ነስቶ እንዲህ አለ። 8 የሚስቴን አስከሬን እዚህ እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ የጾሐር ልጅ ዔፍሮምን ስለ እኔ ሆናችሁ ልምኑልኝ፤ 9 በእርሻው ዳር ያለችውን መክፈል የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፣ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንት ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።» 10 ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ የኬጢም ሰው ኤፍሮንም የኪጥ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሲስሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ 11 «አይደለም ጌታዬ፣ ስማኝ። እርሻውን፣ በርሱም ዳር ያለውን ዋሻ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼአለሁ። ሬሳህን ቅበር።» 12 አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ። 13 የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፤ «እባክህ ፈቃደኛ ብትሆን አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ። አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፤ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ 14 ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ 15 «ጌታዬ ሆይ እኔን ስማኝ፤ የመሬቱ ዋጋ እራት መቶ ሰቅል ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይሄ በእኔና በአንተ መካከል ምንድር ነው? ሬሳህንም ቅበር» 16 አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ፤ አብርሃምም በኬት ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው፤ ብሩንም በወቅቱ የንግድ መለኪያ መሰረት መዘነለት። 17 በዚህም ሁኔታ በመምሬ አጠገብ በመክፈላ ያለውን የኤፍሮንን እርሻ ቦታ ከነዋሻው በከልሉ ካሉት ዛፎች ሁሉ ጭምር ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈ፤ 18 እርሻው በእርሱ ያለውን ዋሻው በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው እንጨት ሁሉ በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ ሆነ። 19 ከዚያም በኋላ ኬብሮን በምትባል በምምሬ ፊት በከነአን ፊት ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍሌ በሆነው ዋሻ ውስጥ ሚስቱን ሳራን ቀበረ። 20 እርሻውና በርሱ ያለው ዋሻው በኪጥ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።
1 በዚህ ጊዜ አብርሃም ሸመገለ፤ ዕድሜውም ገፋ፤ እግዚአብሔርም አብርሃምን በሁሉ ነገር ባረከው። 2 አብርሃምም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ የቤቱ ሁሉ አዛዥ የሆነውን አገልጋይ እንዲህ አለው፤ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ 3 እኔም በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናዊያን ለልጄ ሚስት እንዳታጭለት በሰማይና በምድር አምላክ እግዚአብሔር አስምልሃለሁ። 4 ነገር ግን ወደ ገዛ ሀገሬ እና ወደ ወገኖቼ ሄደህ ለልጄ ለይስሐቅ ሚስትን ታጭለታለህ። 5 አገልጋዩም «ምናልባት የምመርጥለት እጮኛ ከእንይ ጋሬ ወደዚህ አገር ለመምጣት እምቢ ብትልስ? ልጅህን ቀድሞ አንተ ወደ ነበርክበት አገር እንዲመለስ ላድርገው?» ብሎ ጠየቀ። 6 አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ «በምንም ዓይነት ምክንያት ቢሆን ልጄን ወደዚያ አገር መልሰህ እንዳትወስድ ተጠንቀቅ፤ 7 የሰማይ አምክክ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤትና ከትውልድ አገሬ አውጥቶ አምጥቶኛል፤ ይህንንም ምድር ለዝርያዎቼ እንደሚሰጥ በመሃላ ቃል ገብቶልኛል፤ ከዚያ ለልጄ ሚስት ማግኘት እንድትችል እግዚአብሔር መልአኩን በፊትህ ይልካል። 8 ልጅትዋ ከአንተ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንከዚህ መሓላ ነፃ ትሆናለህ፤ ልጄን ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደዚያ አትመልሰው።» 9 ከዚህ በኋላ አገልጋዩ እጁን በጌታው በአብርሃም ጉልበት ላይ አድርጎ አብርሃም ያዘዘውን ሁሉ እንደሚፈፅም በመሐላ ቃል ገባ። 10 የአብርሃም ንብረት ኀላፊ የነበረው መጋቢ ከጌታው ቤት ምርጥ የሆኑ የስጦታ ዕቃዎችን በዕሥር ግመሎች ጭኖ በሰሜን መስጴጦምያ ናኮር ወደሚኖርበት ከተማ ሄደ። 11 እዚያ በደረሰ ጊዜ ከከተማው ውጭ ባለ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ግመሎቹ ተንበርክከው እንዲያርፉ አደረገ፤ ሰዓቱም ሊመሽ ተቃርቦ፣ ሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚወጡበትን ጊዜ ነበር፤ 12 አገልጋዩ እንዲህ ብሎ ጸለየ፣ "የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ የእኔን አሳብ በመፈፀም ለጌታዬ ለአብርሃም ዘላለምዊ ፍቅርህን ግለጥ። 13 እነሆ፣ እኔ በዚህ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ የከተማይቱም ልጃገረዶች ውሃ ሊቀዱ ወደዚህ ይመጣሉ፤ 14 ከእነሱም አንድዋ ልጃገረድ 'እንስራሽን ዘንበል አድርገሽ ውሃ አጠጪኝ' እላታለሁ፤ 'አንተም ጠጣ፤ ግመሎችህም እንዲጠጡ ውጃ ቀድቼ አመጣለሁ' ካለችኝ ለአገልጋይህ ለይስሐቅ ፍቅርህን እንዳሳየኸው ዐውቃለሁ።" 15 ገና ጸሎቱን ሳፅቸርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት ባቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው። 16 ርብቃ ገና ወንድ ያልደረሰባት በጣም ቆንጆ ልጃገረድ ነበረች፤ እርስዋ ወደ ውሃው ጉድጓድ ወርዳ በእንስራዋ ውሃ ከቀዳች በኋላ ተመለሰች። 17 አገልጋዩም ወደ እርስዋ ሮጦ ሄዳና "እባክሽ ከእንስራሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ"አላት። 18 እርስዋም "እሺ ጌታዬ ጠጣ" አለችና እንስራዋን ከትከሻዋ አውርዳ ዘንበል አድርጋ ያዘችለት። 19 ጠጥቶም ከረካ በኋላ "ለግመሎችህም ውሃ እቀዳላቸዋለሁ፤ እስኪበቃቸውም ድረስ ይጠጡ" አለችው። 20 ወዲያውኑ፤ በእንስራዋ የያዘችውን ውሃ ግመሎቹ በሚጠጡበት ገዳን ላይ ገልብጣ ግመሎቹ ሁሉ ጠጥተው እስከሚረኩ ድረስ እየተጣደፈች ከጉድጓድ ውሃ መቅዳት ቀጠለች። 21 ሰውየውም እግዚአብሔር የሄደበትን ተልእኮ አቃንቶለት እንደሆን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ሁሉ ዝም ብሎ ይመለከት ነበር። 22 ግመሎቹ ጠጥተው በኋላ ሰውየው አምስት ግራም ያህል የሚመዝን የወርቅ ጎታቻ አውጥቶ በጆሮዋ ላይ አደረገላት፤ መቶ ዐሥር ግራም ያህል የሚመዝን ሁለት የወርቅ አምባሮችንም አውጥቶ በእጆችዋ ላይ አደረገላትና፤ 23 "የማን ልጅ ነሽ? እስቲ እባክሽ ንገሪኝ፤ ለእኔና አብረውኝ ቤት ይገኛልን?" ብሎ ጠየቃት። 24 እርስዋም "የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር፣ እናቱም ሚልካ ይባላሉ፤ 25 በቤታችን ብዙ ገለባና ድርቆሽ አለ፤ ለእናንተም ማደሪያ ቦታ ይገኛል" አለችው። 26 ሰውየምውም በመንበርከክ ለእግዚአብሔር ሰግዶ፣ 27 "ለጌታዬ የገባውን ቃል ኪዳንና ዘላለማዊ ፍቅሩን የጠበቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በቀጥታ መርቶ ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት ያመጣኝ እርሱ ነው" አለ። 28 ልጅትዋ ወደ ቤት ሮጣ ሄደችና የሆነውን ሁሉ ለእናትዋና ለእርስዋ ጋር ላሉት ሁሉ ነገረቻቸው። 29 ርብቃ ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፤ እርሱ የአብርሃም አገልጋይ ወዳለበት ውሃ ጉድጓድ እየሮጠ ሄደ። 30 ላባ ወደ ሰውየው የሄደው እኅቱ በጆሮዋ ላይ ያደረገችውን ጉትቻና በእጆችዋ ላይ ያደረገቻቸውን አንባሮች ስላየና ርብቃ ሰውየው ጉድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ አገኘው። 31 ስለዚህ ላባ "አንተ እግዚአብሔር የባረከህ ሰው! ና ወደ ቤት እንሂድ፤ በውጭ የቆምኸው ለምንድን ነው? በቤታችን ለአንተ ማደሪያ የተዘጋጀ ቦታ አለ" አለው። 32 ከዚህ በኋላ ሰውየው ወደ ቤት ሄደ፤ ላባም በግመሎቹ ላይ የነበረውን ጭነት አረግፎ ገለባና ድርቆሽ አቀረበላቸው፤ ቀጥሎም የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበትን አመጣላቸው። 33 ገበታ በቀረበው ጊዜ ጊዜ ሰውየው "የተላክሁበትን ጎዳይ ከመናገሬ በፊት እህል አልቀምስም" አለ። ላባም "ይሁን ተናገር" አለው። 34 እርሱም "እኔ የአብርሃም አገልጋይ ነን፤ 35 እግዚአብሔር ጌታዬ እጅግ ባርኮል፤ ባለጸጋም አድርጎታል፤ ብዙ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋ፣ ብርና ወርቅ፣ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ግመሎችና አህዮች ሰጥቶታል። 36 የጌታዬ ሚስት ሣራ በእርጅናዋ ዘምን ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤ ጌታዬም ያለውን ሀብት ሁሉ ለዚሁ ልጅ አውርሶታል። 37 ጌታዬ አብርሃም 'እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናዊያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳላጭለት፤ 38 ነገር ግን ወደ አባቴ ቤተሰብና ወደ ዘመዶቼ ሄደህ ለልጄ ሚስት እጭለት' ሲል በመሐላ ቃል ኪዳን አስገብቶኛል።' 39 እኔም ጌታዬን 'ልጅቷ ከእኔ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ ምን ላድርግ?' ብዬ ጠየኩት። 40 እርሱም እንዲህ አለኝ 'ዘውትር የማገለግለው እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፤ ጉዞህም የተቃና እንዲሆን ያደርጋል፤ በዚህ ሁኔታ አንተም ከአባትቴ ቤተሰብና ከዘመዶቼ መካከል ለልጄ ሚስት ልታጭለት ትችላለህ፤ 41 ከመሐላህ ነፃ የምትሆነው ወደ ዘመዶቼ ሄደህ እነርሱ ልጅትዋን አንሰጥም ብለው የከለከሉህ እንደሆነ ብቻ ነው።' 42 "ከዚያም በኋላ ዛሬ ወደ ውሃው ጉድጓድ ስመጣ እንዲህ ብዬ ጸለይሁ 'የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ የመጣሁበት ጉዳይ እንዲቃና አድርግልኝ፣ 43 እነሆ በዚህ ውሃ ጉድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ አንዲት ልጃገረድን ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ፣ 'እባክሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ' ብዬ እጠይቃታለሁ፤ 44 እርስዋም 'እሺ ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳቸዋለሁ'የምትለኝ ብትሆን፣ ለጌታዬ ልጅ ሚስት እንድትሆን አንተ የመረጥሃት እርስዋ ትሁን። 45 የኅሊና ጸሎትን ገና ሳልጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ ብቅ አለች፤ ወደ ጉድጓዱም ሄዳ ውሃ ቀዳች፤ እኔም 'እባክሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ አልኋት። 46 እርስዋም እንስራዋን በፍጥነት ከጀርባዋ አወረደችና ዘንበል አድርጋ 'እሺ ጠጣ፤ ግመሎችህንም አጠጣልሃለሁ' አለችኝ፤ ስለዚህ እኔም ጠጣሁ፤ ግመሎቼንም አጠጣችልኝ። 47 እኔም 'የማን ልጅ ነሽ?' ብዬ ጠየቅኋት። እርስዋም 'የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር እናቱም ሚልካ ይባላሉ' አለችኝ። ከዚህ በኋላ ጉትቻ በጆሮዋ ላይ፣ አንባሮቹንም በእጅዎችዋ ላይ አደረግሁላት፤ 48 ከዚህ በኋላ በጉልበቴ ተንበርክኬ ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ የጌታዬን የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር አመሰገንሁ፤ ምክንያቱም ለጌታዬ ልጅ ሚስት የምትሆነዋን ሴት ወዳገኘሁበት ወደ ጌታዬ ወንድም ቤት በቀና መንገድ የመራኝ እርሱ ነው። 49 እንግዲህ የጌታዬን ዐደራ በእውነት ተቀብላችሁ እርሱን ደስ ለማሰኘት የምትፈቅዱ እንደሆነ ንገሩኝ፤ የማትፈቅዱም እንደሆነ ቁርጡን ነገሩኝ፤ እኔም እግዚአብሔር ወደሚመራኝ እሄዳለሁ።" 50 ላባና ባቱኤልም "ይህ ነገር ከእግዚአብሔር የመጣ ስለሆነ፣ መከልከል አልችልም፤ 51 ርብቃ ይችውልህ፤ እነሆ ይዘሃት ሂድ፤ እግዚአብሔር ራሱ እንደተናገረው ለጌታዬ ልጅ ሚስት ትሁን" አሉት። 52 የአብርሃም አገልጋይ ይህን በሰማ ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ 53 ከውርቅና ከብር የተሠሩ ጌጣጌጦችን፣ እንዲሁም ልብስ አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ለወንድምዋና ለእናትዋም በጣም ውድ የሆኑ ስጦታዎችን አውጥቶ ሰጣቸው። 54 ከዚህ በኋላ የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩ ሰዎች በልተው ጠጥተው እዚያው አደሩ፤ ጠዋት በተነሡ ጊዜ የአብርሃም አገልጋይ "እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ ፍቀዱልኝ" አለ። 55 ነገር ግን የርብቃ ወንድምና እናትዋ "ልጅትዋ ዐሥር ቀን ያህል ከእኛ ጋር ትቆይ፤ ከዚህ በኋላ ከአንተ ጋር ልትሄድ ትችላለች" አሉት። 56 እርሱ ግን "እባካችሁ አታቆዩኝ፤ እግዚአብሔር የመጣሁበትን ጉዳይ ስላቃናልኝ ቶሎ ብፄ ወደ ጌታዬ ልመለስ" አላቸው። 57 እነርሱም "እስቲ ልጅቷን እንጥራትና እርስዋ የምትለውን እንስማ" አሉ። 58 ስለዚህ ርብቃን ጠሩና "ከዚህ ሰው ጋር መሄድ ትፈልጊያለሽ?" ብለው ጠየቅዋት። እርስዋም "አዎ እሄዳለሁ"አለች። 59 ስለዚህ ርብቃ ሞግዚትዋን አስከትላ፣ ከአብርሃም አገልጋይና ከእርሱ ሰዎች ጋር እንድትሄድ ፈቀዱላት። 60 "አንቺ እኅታችን የብዙ ሺ ሕዝብ እናት ሁኚ፤ ዝርያዎችሽም የጠላቶችሽን ከተሞች ይውረሱ" ብለው ርብቃን መረቁአት። 61 ከዚህ በኋላ ርብቃ ከተከታዮችዋ ጋር ለመሄድ ተነሣች፤ በግመሎቹ ላይ ተቀምጠው ከአብርሃም አገልጋይ ጋር ለመሄድ ተዘጋጁ። በዚህ ዐይነት የአብርሃም አገልጋይ ርብቃን ይዞ ሄደ። 62 በዚህ ጊዜ ይስሐቅ "ብኤር ላሐይ ሮኤ ወይም የሚያየኝን ሕያው አምላክ"የተባለው ኩሬ ወዳለበት በረሓ መጥቶ በኔጌብ ተቀምጦ ነበር። 63 ከለዕታት አንድ ቀን ወደ ማታ ጊዜ እያሰላሰለ በመስክ ውስጥ ሲዘዋወር ሳለ ግመሎች ሲመጡ በሩቅ አየ። 64 ርብቃ ይስሐቅ ባየች ጊዜ ከግመሏ ወረደችና፣ 65 "ያ በመስክ ውስጥ ወደ እኛ የሚመጣው ሰው ማን ነው?" ስትል የአብርሃምን አገልጋይ ጠየቀችው። አገልጋዩም "እርሱ ጌታዬ ነው!" አላት። ስለዚህ በጥፍነት በሻሽ ፊትዋን ሸፈነች። 66 አገልጋዩም ያደረገውም ነግር ሁሉ ለይስሐቅ ነገረው። 67 ከዚህ በኋላ ይስሐቅ እናቱ ሣራ ትኖርበት ወደነበረው ድንኳን ርብቃን ይዞአት ገባ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ይስሐቅ ርብቃን ወደዳት፤ በእናቱ ሞት ምክንያት ከደረሰበትም ሐዘን በዚህ ሁኔታ ተጽናና።
1 አብርሃም ቀጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ፤ 2 እርስዋም ዚምራንን፣ ዮቅሻንን፣ መዳንን፣ ምድያምን፣ ዩሽባቅንና ሹሐን ወለደችለት። 3 ዮቅሻንም ሳባንና ደዳንን ወለደ፤ የዳደንም ዝርያዎች አሹራውያን፣ ሌጡሻውያንና ሌአማውያን ናቸው። 4 የምድያም ልጆች ዔፋ፣ ዔፈር፣ ሐኖክ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚሁ ሁሉ የቁጠራ ዝርያዎች ናቸው። 5 አብርሃም ያለው ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤ 6 ከሌሎች ሴቶች ለተወለዱትም ልጆች ገና በሕይወት ሳለ ስጦታ ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ እነዚህ ሌሎች ልጆች ከይስሐቅ ርቀው ወደ ምሥራቅ አገር እንዲሄዱ አደረጋቸው። 7 የአብርሃም ዕድሜ በአጠቃላይ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤ 8 በዚህም ዐይነት አብርሃም በቂ ዕድሜ አግኝቶ ካረጀ በኋላ ሞተ፤ 9 ልጆቹ ይሰሐቅና እስማኤል ማክጴላ በተባለ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ ከመምሬ በስተምሥራቅ በሒታዊ በጶሐር ልጅ በዔፍሮን እርሻ ውስጥ የሚገኘው ነው። 10 እነሱም አብርሃም ከሒታዊያን ላይ የገዛው የመቃብር ቦታ ነው፤ በዚህ ዐይነት አብርሃም ሚስቱ ሣራ በተቀበረችበት ዋሻ ተቀበረ። 11 አብርሃም ከሞተ በኋላ ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር ባረከው፤ ይስሐቅ "ብኤርላሐይሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ" ተብሎ በመጠራት ኩሬ አጠገብ ይኖር ነበር። 12 የሣራ አገልጋይ ግብፃዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን እስማኤል፤ 13 ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፣ ቄዳር፣ አድብኤል፣ ሚብሣም፣ 14 ሚሽማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣ 15 ሐዳድ፣ ቴማ፣ ይጡር፣ ናፊሽና ቄድማ ናቸው። 16 እነዚህ የእስማኤል ልጆች ለአሥራ ሁለት ነገዶች ቅድመ አያቶች ነበሩ፤ ስማቸውም በኖሩባቸው ከተሞችና ስፍራዎች ሲጠራ ይኖራል። 17 እስማኤል መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ሲሆነው ሞተ። 18 የእስማኤል ዝርያዎች ከግብፅ በስተምጅራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር። የኖሩበትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዝርያዎች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር። 19 የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ታሪክ ይህ ነው። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ። 20 ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሞኖሩ ሶሪያውያን ነበሩ። 21 ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርስዋ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤ 22 የተፀነሱትም መንትያዎች ስለነበሩ እርስ በርሳቸው በማሕፀንዋ ውስጥ ይገፋ ነበር፤ እርስዋም "ይህን ዐይነት በገር ለምን ደረሰብኝ?" በማለት ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ተነሣሣች። 23 እግዚአብሔርም ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ታናሹ አገልጋይ ይሆናል" አላት። 24 የመውለጃዋም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ። 25 የመጀመሪያው ልጅ መልኩ ቀይ፣ ሰውነቱ ጠጉራም ነበር፤ ስለዚህ ዔሳው ተባለ። 26 ሁለተኛው ልጅ ሲወለድ የዔሳውን ተገረዝ ይዞ በመውጣቱ ያዕቆብ ተባለ፤ ልጆቹ በተወለዱ ጊዜ ይስሐቅ ስልሳ ዓመት ሆኖት ነበር። 27 ሁለቱም ልጆች አደጉ፤ ዔሳው በዱር መዋል የሚወደ ብልኅ አዳኝ ሆነ፤ ያዕቆብ ግን በቤት መዋል የሚወድ ጭምት ሰው ነበር። 28 ይስሐቅ ዔሳውን ይወድ ነበር። ምክንያቱም ዔሳው እያደነ ሥጋ ያበላው ነበር።ርብቃ ግን ያዕቆብን ትንን ነበር። 29 ለዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤ 30 ስለዚህም ያዕቆብ "ከዚህ ከቀይ ወጥ ሰጠኝ" አለው። ኤዶም የተባለውም ነዚሁ ምክንያት ነበር። 31 ያዕቆብም "በመጀመሪያ ብኩርናህን ሽጥልኝ" አለው። 32 ዔሳውም "እኔ በረሀብ መሞቴ ነው፤ ታዲያ ብኩርና ምን ያደርግልኛል?" አለው። 33 ያዕቆብም "እንግዲያውስ ብኩርናህን እንደምትሸጥልኝ መጀመሪያ ማልልኝ" አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኩርናውን ለያዕቆብ ሸጠ። 34 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኩርናውን በመናቅ አቃለላት።
1 በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ረሀብ ሌላ ዳግመኛ ረሀብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማዋን ንጉሥ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤ 2 በዚህም እግዚአብሔር ለይስሐቅ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፣ "ወደ ግብፅ አገር አትሂድ፤ እንድትኖርበትም በምነግርህ በዚህ ምድር ተቀመጥ፤ 3 እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ይህም ምድር ለአንተና ለዝርይዎችህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈፅማለሁ፤ 4 ዘርህን አንደ ሰማይ ክዋክብት አበዛዋልለሁ፤ ይህንንም ሁሉ ምድር አወርሳቸዋለሁ፤ ይህንንም ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ። 5 አንተን የምባርክበትንም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁት ሕግና ሥርዓት ሁሉ ስለ ጠበወ ነው። 6 ስለዚህ ይስሐቅ መኖሪያውን በገራር አደረገ፤ 7 በዚያ አገር ስሰዎችም ስለ ርብቃ "ምንህናት" ብለው በጠየቁት ጊዜ "እኅቴ ናት" አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቆንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው። 8 ይስሐቅ እዚያ አገር ብዙ ጊዜ ከቆያ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት ይስሐቅና ርብቃ እንደባልና ሚስት በመዳራት ሲጫወቱ አየ። 9 ስለዚህ አቢሜሌክ ይስሐቅን አስጠርቶ "ለካስ ርብቃ ሚስትህ ናት! ታዲያ "እኅቴ ናት' ያልከው ለምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው። እርሱም "ሚስቴ ነች ያልኩ እንደሆን ሰዎች ይገድሉኝል ብዬ አስፈራሁ ነው" ብሎ መለሰ። 10 አቢሜሌክ "ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? ከእኛ ሰዎች አንዱ በቀላሉ ሚስትህን ለመድፈር በቻለ ነበር፤" 11 ቀጥሎም አቢሜሌክ "ይህን ሰው ወይም ሚስቱን የሚነካ ሰው በሞቱ ይቀጣል"የሚል ማስጠንቀቂያ ለሕዝቡ ሰጠ። 12 ይስሐቅ በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፤ እግዚአብሔር ስለባረከውም በዚያኑ ዓመት መቶ እጥፍ አመረተ፤ 13 ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረበት ዘመን የእርሱ አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን የውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው። 14 ብዙ የበግና የከብት መንጋ፤ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት። 15 ስለዚህ የይስሐቅ አባት አብርሃም በሕይወት በነበረበት ዘመን የእሱን አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን ውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው። 16 በዚያን ጊዜ አቢሜሌክ ይስሐቅን "ኅይልህ ከእኛ ይልቅ እየበረታ ስለሄደ፤ አገራችንን ለቀህ ውጣ" አለው። 17 በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ያንን ቦታ ለቆ በገራር ሸለቆ ውስጥ ሰፈረ፤ እዚያም ተቀመጠ። 18 አብርሃም በሕይወት ሳለ አስቆፍሮአቸው የነበሩትን አብርሃም ከሞተ በኋላ ግን ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጉድጓዶች ይስሐቅ እንደገና እንዲቆፍሩ አደረገ፤ አባቱ ባወጣላቸ ስሞችም ጠራቸው። 19 የይስሐቅ አገልጋዮች በሸለቆው ውስጥ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሩና ጥሩ የምንጭ ውሃ አገኙ፤ 20 የገራር እረኞች ግን "ይህ ውሃ የእኛ ነው" በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ተጣሉ።በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ጉድጓዱን "ዔሤቅ" ብሎ ሰየመው። 21 የይስሐቅ አገልጋዮች ሌላ የውሃ ጉድጓድ ቁፈሩ፤ በዚህኛውም ጉድጓድ ምክንያት ሌላ ጠብ ተነሣ፤ ስለዚህ ይስሐቅ ይህን ጉድጓድ "ስጥና" ብሎ ሰየመው። 22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተናሳ "እነሆ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል ያንን ቦታ 'ረሖቦት" ብሎ ሰየመው። 23 ከዚያ በኋላ ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ፤ 24 በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና "እኔ የአባትህ አምላክ ነኝ፤እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ! ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ" አለው። 25 ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጉድጓድ ቆፈሩ። 26 አቢሜሌክ ከአማካሪው ከአሑዘትና ከሠራዊቱ ኣዥ ኮፊኮል ጋር ይስሐቅን ለመጎብኘት ከገራር ወት፤ 27 ስለዚህ ይስሐቅ "ከዚህ በፊት ጠልታችሁን አገራችሁ እንድወጣ አድርጋችሁኛል፤ ታዲያ አሁን ልትጎበኝ የመጣችሁት ለምንድን ነው?" አላቸው። 28 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፣ "እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈፀም አስበናል፤ በዚህም መጀረት ቃል ኮዳን እንድትገባልን የሚንፈለገው፣ 29 በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ምክንያቱም እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ አልሠራንም፤ ዘውትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።" 30 ከዚህ በኋላ፣ ይስሐቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡ። 31 በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ። 32 ከዚያኑ ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቁፈሩት ጉድጓድ ለይስሐቅ ነገሩት፤ "ውሃ አገኘን" ብለውም አበሠሩት። 33 እርሱም የውሃን ጉድጓድ "ሳቤህ"ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ "ቤርሳቤህ" እየተባለ ይጠራል። 34 ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆንው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ። 35 ይህም ጋብቻ ይስሐቅንና ርብቃን ሲያዝናቸው ይኖር ነበር።
1 ይስሐቅ አርጅቶ ዐይኖቹም ታውረው ነበር፤ ታላቁ ልጁን ዔሳውን፤ "ልጄ ሆይ!" ብሎ ጠራው፤ ልጁም "እነሆ አለሁ" አለ። 2 ይስሐቅም እንዲህ አለው፣ "እንደምታየኝ አርጅቻለሁ፤ የምሞትበትንም ቀን አላውቅም፤ 3 ስለዚህ የምታድንበትን ቀስትና ፍላጻ ያዝ፤ ወደ ዱር ሂድና አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤ 4 ልክ እንደምወደው አድርገህ ምግብ ሥራልኝ ከበላሁም በኋላ ከመሞቴ በፊት የመጨረሻ ምርቃቴን እሰጥሃለሁ።" 5 ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው ወደ አደን ከሄደ በኋላ፣ 6 ርብቃ ልጅዋን ያዕቆብን "አባትህ ዔሳውን እንዲህ ሲለው ሰማሁ፣ 7 አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤ ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሥራልኝ፤ ሳልሞትም በእግዚአብሔር ፊት እነርቅሃለሁ፤ 8 አሁንም ልጄ ሆይ! የምነግርህን አድምጥ፤ የማዝህንም አድርግ፤ 9 አባትህ እንደሚወደው አጣፋጩ ጥሩ ምግብ እንድሠራለት፣ ወደ መንጋዎች ሂድና ሁለት የሰቡ የፍየል ጥቦቶች አምጣልኝ፤ 10 አንተም ያዘጋጀሁትን ምግብ እንዲበላ ለአባትህ ወስደህ ታቀርብለታለህ፤ በዚህ ዐይነት አባትህ ከመሞቱ በፊት ይመርቅሃል።" 11 ያዕቆብ ግን እናቱን ርብቃን "የወንድሜ የዔሳው ገላ ጠጉራም ነው፤ የ እኔ ገላ ግን ምንም ጠጉር የሌለው ለስላሳ ነው፤ 12 ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝና እንዳታለልኩህ ቢያውቅ በምርቃት ፈንታ እርግማን እንደማተርፍ ታውቂ የለምን?" አላት። 13 እናቱም "ልጄ ሆይ! የአንተ እርግማን በእኔ ላይ ይሁን፤ አሁንም እንደነገርሁህ አድርግ፤ ሄድህ ጥቦቶቹን አምጣልኝ" አለችው። 14 ስለዚህ ሄዶ ጥቦቶቹን አመጣለት እርስዋም ልክ አባቱ እንደሚወደው እድርጋ ጥሩ ወጥ ሠራች፤ 15 የታላቁ ልጅዋን የዔሳውን የክት ልብስ ከተቀመጠበት ቦታ አውጥታ ለያዕቆብ አለበሰችው። 16 የፍየሎቹንም ቆዳ በክንዶቹ ላይና ጠጉር በሌለበት በአንገቱ ላይ አለበሰችው። 17 ያዘጋጀውንም ጥሩ ወጥ ከጋገረችው እንጀራ ጋር ልልጅዋ ለያዕቆብ ሰጠችው። 18 ያዕቆብ ወደ አባቱ ሄደና "አባባ!" አለው፤ እርሱም "እነሆ አለሁ! ለመሆኑ አንተ የትኛው ልጄ ነህ!" አለ። 19 ያዕቆብም "የበኩር ልጅህ ዔሳው ነኝ፤ እነሆ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ፤ እንድትመርቀኝ እስቲ ቀና በልና ያመጣሁልህን የአደን ሥጋ ተመገብ" አለው። 20 ይስሐቅም "ልጄ ሆይ! እንዴት ቶሎ ልታገኝ ቻልህ?" አለው። ያዕቆብም "አምላክህ እግዚአብሔር ስለረዳኝ በቶሎ ለማግኘት ቻልሁ" አለው። 21 ይስሕቅም "እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በልና ልዳብስህ፤ በእርግጥ አንተ ዔሳው ነህን?" አለው። 22 ያዕቆብም ወደ አባቱ ተጠጋ፤ አባቱም ዳሰሰውና "ድምፅህ የያዕቆብ ድምፅ ይመስላል፤ ክንድህ ግን የዔሳውን ክንድ ይመስላል" አለው። 23 ክንዶቹ እንደ ዔሳው ክንዶች ጠጉራም ስለ ነበሩ ይስሐቅ ያዕቆብን ለይቶ ማውቅ አልቻለም፤ ሊመርቀው ከዝዘጋጀ በኋላ፣ 24 "እርግጥ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?" ሲል እንደገና ጠየቀው፤ እርሱም "አዎ ነን" አለ። 25 ይስሐቅም "ልጄ! በል ከአደንከው ሥጋ አቅርብልኝ፤ ከበላሁም በኋላ እመርቅህለሁ" አለው። ያዕቆብም ምግቡን አቀረበለት፤ የወይን ጠጅም እንዲጠጣ አመጣለት። 26 ከዚህ በኋላ አባቱ ይስሐቅ "ልጄ ሆይ! ቀረብ በልና ሳመኝ" አለው፤ 27 ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብ ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፣ "እነሆ የልጄ መልካም ሽታ እግዚአብሔር እንደባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤ 28 እግዚአብሔር ከሰማይ የሚያረሰርሰው ተል ይስጥህ፤ ምድርህን ያለምልምልህ፤ እህልንና የወይን ጠጅህን ያብዛልህ፤ 29 መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችህም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህ የተመረቁ ይሁኑ።" 30 ይስሐቅ ያዕቆብን መርቆ እንዳበቃና ያዕቆብም አባቱን ፊት እንደወጣ ወዲያውኑ ዔሳው ከአደን ተመልሶ መጣ። 31 እርሱም በበኩሉ የጣፈጠ ወጥ ሠርቶ ለአባቱ አቀረበለትና "አባቴ ሆይ እንድትመርቀኝ፣ እስቲ ቀና ብለህ ካመጣሁልህ የአደን ሥጋ ብላ" አለው። 32 ይስሐቅም 'አንተ ማን ነህ?" አለው፤ እርሱም "እኔ የበኩር ልጅ ዔሳው ነኝ" አለ። 33 ይስሐቅም እጅግ ደንግጦ እየተነቀጠቀጠ "ታዲያ አውሬ አድኖ ያመጣልኝ ማን ነበረ? ልክ አንተ ከመምጣትህ በፊት ተመገብሁ የመጨረሻ ምርቃቴንም ሰጠሁት፤ ምርቃቱም ተእርሱ ሆኖ ይኖራል"አለው። 34 ዔሳው ይህን በሰማ ጊዜ ድምፁን ከፍ በማድረግ ምርር ብሎ እያለቀሰ "አባቴ ሆይ! እኔንም መርቀኝ!" አለ። 35 ይስሐቅም "ወንድምህ መጥቶ እኔን በማታለል የአንተን ምርቃት ወስዶብሃል"አለው። 36 ዔሳውም "እርሱ እኔን ሲያሰናክለኝ ይህ ሁለተኛው ነው፤ ያዕቆብ መባሉ ተገቢ ነው፤ ከዚህ በፊት ብኩርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ፤ ታዲያ ለእኔ ያስቀረከው ምንም ምርቃት የለምን? አለው። 37 ይስሐቅም "ቀድሞ ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?" አለው። 38 ዔሳውም "አባቴ ሆይ! ምርቃትህ እንዲት ብቻ ናትን? እባክህ እኔንም መርቀኝ" እያለ ለማልቀስ አባቱን ነዘነዘው። 39 ይስሐቅም አንዲህ አለው። "በረከት ከሞላበት ለምለም ምድር ርቀህ ትኖራለህ፤ የሰማይ ጠልም አታገኝም፤ 40 በሰይፍም ኅይል ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ፤ በተቃወምከውም ጊዜ ግን ከእርሱ ጭቁና ትላቀቃለህ።" 41 አባቱ ስለመረቀው ዔሳው ያዕቆብን አጥብቆ ጠላው፤ በልቡም "አባቴ በቅርብ ቀን ይሞታል፤ ከዚህ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ"ብሎ አሰበ። 42 ነገር ግን ርብቃ የዔሳውን ዕቅድ ስለ ሰማች፣ ያዕቆብን ጠርታ እንዲህ አለችው፣ "አድምጠኝ፤ ወንድምህ ዔሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ አስቦአል፤ 43 አሁንም ልጄ ሆይ! የምልህን አድርግ፤ ተነሥተህ በካራን ወደሚገኘው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ፤ 44 የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እዚያው ቆይ፤ 45 ቁጣውም ሲበርድ ያደረግህበትን ነገር ይረሳል፤ ከዚያ በኋላ ሰው ልኬ አስመጣሃለሁ፤ ሁለታችሁም በአንድ ቀን ማጣት አልፈልግም። 46 ርብቃ ይስሐቅን "ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሖታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱ ከገባ ለመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ"አለችው።
ይህ የሚናገረው ዓይኖች እንደ መብራት ብርሃን እየቀነሱ እንደሄዱ እና ማየት ወደ መሳን ደረጃ እንደደረሱ ነው:: አት: “ዓይኖቹ ማየት ተስኖአቸው” ወይም “ዓይኖቹ ወደ መታወር ደርሰው” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)::
“ዔሣው መለሰለት”“ዔሣው መለሰለት”
“እነሆ አለሁ” ወይም “እየሰማሁ ነኝ” በዘፍጥረት 22:1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
“ከዚያም ይሥሐቅም አለ”
“ይኼው ተመልከት” የሚለው ሀረግ ለሚቀጥለው ሃሳብ አጽንዖት የሚሰጥ ነው:: አት: “በጥንቃቄ ስማ ግምታዊ እውቀት” ወይም “ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ”
ይህ ይስሐቅ ቅርብ ጊዜ እንደሚሞት የሚያመለክት ነው:: አት: “ከማንኛውም ጊዜ ሊሞት ይሆናል”:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
አካላዊ ሞትን ይገልጻል
“ይስሐቅ ለታላቅ ልጁ ለዔሣው መመሪያልችን ይሰጣል”
“የአደን መሣሪያዎችህን”
የፍላጻ ኩሮጆ የቀስቶች መሸከሚያ ነው:: አት: “የቀስቶች መሸከሚያ ኩሮጆ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“የዱር እንስሳት አድነህ አምጣልኝ”
“ጣዕም ያለው” የሚለው ቃል እጅግ በጣም ጣፋጭ የሆነውን ነገር ያመለክታል:: አት: “የምወደው ዓይነት የሥጋ ምግብ አዘጋጅልኝ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን አባት መደበኛ የሆነ መንገድ ልጆችን ይመርቃል
በወቅቱ የሚለው ቃል ትኩረቱ ወደ ርብቃና ያዕቆብ መዞሩን ያሳያል:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“ይስሐቅ ለልጁ የተናገረውን ርብቃ ትሰማ ነበር”
ዔሣው ከወጣ በኋላ ርብቃ የሰማችውን ለያዕቆብ ተናገረች:: አት: “ዔሣው ለማምጣት በወጣ ጊዜ ርብቃም ለያዕቆብ ተናገረች” (አያየዥ ቃላት ይመልከቱ)
ዔሣውና ያዕቆብ ሁለቱም የይስሐቅና የርብቃ ልጆች ናቸው አንድ ወላጅ አንዱን ልጅ ከሌላኛው ልጅ አብልጦ እንደሚወድ ተደርገው የእርሱ ልጅ እና የእርስዋ ልጅ ተብለው ተጠርተዋል::
“ይኼው ተመልከት” የሚለው ሀረግ ለሚቀጥለው ሃሳብ አጽንዖት የሚሰጥ ነው:: አት: “በጥሞና ስማ ግምታዊ እውቀት” ወይም “ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ”
ይህ በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ ነው:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል አት: “ለዔሣውም ነገረው; ‘የዱር እንስሳ እንዲያድንና የሚወደውን ጣዕም የሥጋ ምግብ እንዲያዘጋጅለት’ ከዚያም ከመሞቱ በፊት በእግዚአብሔር ፊት የስሐቅ ዔሣውን እንዲባርከው” (በጥቅስ ውስጥ ጥቅሶችንና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)::
“የዱር እንስሳት አድነህ ገድለህ አምጣልኝ”
“የምወደው ዓይነት የሥጋ ምግብ አዘጋጅልኝ” ይህን በዘፍጥረት 27:4 እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
“በእግዚአብሔር ፊት እንዲመርቅህ”
ርብቃ ለሁለተኛ ልጅዋ ለያዕቆብ መናገርዋን ቀጠለች
ይህ በዚያ ወቅት የሚለውን የሚናገር አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ዋና ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው::
ርብቃ “ድምጼን” ያለችው የምትናገረውን ነገር ለማመልከት ነው:: አት: “ታዘዘኝ የምናገረውንም ነገር አድርግ” (ተዛማጅ ባሕሪይ የሚገልጽ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ጣፋጭ የሚለው ቃል በጣም ጥሩ ጣዕም ያለውን ነገር ያመለክታል:: በዘፍጥረት 27:4 ተመሳሳይ ቃል እንዴት እንደተተረጐመ ይመልከቱ::
“ከዚያም ወደ አባትህ ይዘህ ግባ”
ከበላ በኋላ ይመርቅሃል
ምርቃት የሚለው ቃል አባት ልጆቹን የሚናገረው መደበኛ ምርቃት ነው
ከመመቱ በፊት
“የእኔ ገላ ለስላሣ ነው” ወይም “እኔ ጸጉራም አይደለሁም”
መረገም ወይም መባረክ ምርቃት ወይም በረከት በአንድ ሰው ላይ እንደሚሆን ዕቃ ተደርገው ተነግረዋል አት ከዚያም ከዚህም የተነሣ ይረግመኛል ወይም አይባርከኝም (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“ልጄ ሆይ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን” መረገም ርግማን በአንድ ሰው ጫንቃ ላይ እንደሚሆን ዕቃ ተደርጐ ተገለጾአል:: አት “ልጄ ሆይ አባትህ አንተን ከመርገም እኔን ይርገመኝ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ርብቃ “ድምጼን” ያለችው የምትናገረውን ነገር ለማመልከት ነው:: አት: “የሚናገርህን ታዘዝ” ወይም “ታዘዘኝ” (ተዛማጅ ባሕሪይ የሚገልጽ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
“ጠቦቶቹን አምጣልኝ”
ጣፋጭ የሚለው ቃል በጣም ጥሩ ጣዕም ያለውን ነገር ያመለክታል:: በዘፍጥረት 27:4 ተመሳሳይ ቃል እንዴት እንደተተረጐመ ይመልከቱ::
የጠቦቶች ቆዳዎች ጸጉር ነበረባቸው
“የሠራችውን ጣፋጭ መብልና እንጀራውን ለልጅዋ ለይዕቆብ ሰጠችው”
“እናም አባቱ መለሰው” ወይም “ይስሐቅም መለሰው”
“አዎን እየሰማሁ ነኝ” ወይም “አዎን ምንድነው?” በዘፍጥረት 22 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
እንዳደርገው የነገርከኝን አድርጌአለሁ
“የታደነ” የምለው ቃል አንድ ሰው የዱር እንሰሳትን አድኖና ገድሎ የሚያቀርበውን ያመለክታል:: በዘፍጥረት 27:3 “የታደነ” የሚለው እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ያዕቆብም መለሰው
ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር እግዚአብሔር ለሁኔታው ምክንያን እንደሆነ ይገልጻል:: አት: “በማድንበት ጊዜ እንዲሳካልኝ ረድቶኛል” (ፈሊጣዊ አነጋገሮች ይመልከቱ)::
“በእርግጥ ልጄ ዔሣው መሆንህን”
“ያዕቆብ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ተጠጋ”
እዚህ ይስሐቅ የያዕቆብ ድምጽ ያዕቆብን እንደሚወክል ይናገራል፡፡ አት፡ “ድምጽህ የያዕቆብ ይመስላል” (ክፍልን እንደ ሙሉ ወይም ሙሉውን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ ይስሐቅ የዔሣው እጆች ዔሣውን እንደሚወከሉ ይናገራል፡፡ አት፡ እጆች ግን የኤሣው እጆች እንደሆኑ ይሰሙኛል፡፡ (ክፍልን እንደ ሙሉ ወይም ሙሉውን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይስሐቅ ልጁን ከመባረኩ በፊት ይህን ጥቃቄ ይጠይቀዋል:: አት፡ “ነገር ግን መጀመሪያ ይስሐቅ ጠየቀው” (የክስተቶች ቅደም ተከተል ይመልከቱ)
የታደነ የሚለው ቃል ሰዎች አድነውና ገድለው የሚያቀርቡትን የዱር እንሰሳ ያመለክታል:: በዘፍጥ 27:7 የታደነ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ::
“ይስሐቅ ጠጣ”
ልብሶች የኤሣው ልብሶች ሽታ እንዳሸቱ ግልጽ ነው:: አት: “እርሱም ልብሶቹን አሸተተ እናም ሽታው እንደ ዔሣው ልብሶች ሽታ ስለሆነ ባረከው” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይስሐቅ አሸተተ
ጠረን
“ከዚያም ባረከው” ይህ አባት ልጆቹን የሚባረከውን መደበኛ በረከት ያመለክታል::
“እነሆ” የሚለው ቃል ይህ እውነት ነው የሚለውን ለመግለጽ የተጠቀመ አበክሮአዊ ሥዕላዊ አገላለጽ ነው:: አት: “በእውነት የልጄ ጠረን”
እዚህ በረከት የሚለው ቃል እግዚአብሔር በእርሻው መልካም ነገሮች እንዲሆኑና ፍሬያማ እንዲሆን እንዲያደርግ ነው:: አት: “ያም እግዚአብሔር ፍሬያማ እንዲያደርግ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ የይስሐቅ ባረኮት ነው ለኤሳው የተናገረው መሰለሙ ነገር ግን የተናገረው ለያዕቆብ ነው
እዚህ “ይስጥህ” ነጠላና ያዕቆብን የሚያመለክት ነው በረከቱ ግን ለያዕቆብ ትውልድም የሚሆን ነው:: (ሁለተኛ ሰው አጠቃቀምንና ክፍልን እንደ ሙሉ እና ሙሉን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ጠል በሌሊት በተክሎች ላይ የሚሆን የውሃ ጠብታ ነው:: በትርጉም ይህን ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “ተክሎችዎን ለማጠጣት የሌሊት ጠል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ለም መሬት የመኖር መሬት ስብና ሀብታም እንደሆነች ተደርጐ ተገለጾአል:: አት: “እህልን የሚያመርት መልካም መሬት ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ”
“እህል”ና “ወይን” ያልተገለጹ እስከሆነ ድረስ ጠቅለል ባለ መልክ መግለጽ ይቻላል:: አት: “የተትረፈረፈ መብልና መጠጥ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እዚህ እነዚህ ተውላጤ ስሞች በነጠላ የተገለጹና የዕቆብን ያመለክታሉ በረከቱ ግን ለያዕቆብ ትውልድም ነው (ሁለተኛ ሰው አገላለጽንና ክፍልን እንደ ሙሉ እና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ ሕዝቦች ሰዎችን ያመለክታል አት የሁሉም ሕዝቦች ሰዎች ተደፍተው እጅ ይንሡህ:: (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ጐንበሥ በማለት አንድ ሰው አክብሮት መስጠትን ይገልጻል ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ
በወንድምችህ ላይ ጌታ ወይም ገዢ ሁን
ይስሐቅ ይህን በረከት በቀጥታ ለያዕቆብ ይናገራል ነገር ግን ይህ የያዕቆብ ትውልድ በኤሣው ትውልድና በሌሎች ማናቸውም የያዕቆብ ወንድሞች ትውልድ ላይ ገዢዎች እንደሚሆኑ ለእነርሱም ይሆናል፡፡ (ክፍል ለሙሉና ሙሉን ለክፍል የመጠቀም አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
የእናትህም ልጆች የሰግዱልሃል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር የሚረግሙህን ሁሉ ይርገማቸው“ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር የሚባርኩህን ሁሉ ይባርካቸው“ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“ከአባቱን ከይስሐቅን ድንኳን እንደወጣ”
የምወደው ጣፋጭ ሥጋ በዘፍጥረት 27፡3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
እዚህ “ልጅህ” ኤሣው ካደነው ያዘጋጀውን ምግብ በትህትና ያቀረበበት መንገድ ነው:: (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
የታደነ የሚለው ቃል ሰዎች አድነውና ገድለው የሚያቀርቡትን የዱር እንሰሳ ያመለክታል:: በዘፍጥ 27:7 የታደነ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ::
ይህ አንድ አባት ልጆቹን የሚባርክበት መደበኛ መንገድ ያመለክታል
ዔሣውን አለው
ይስሐቅም መንቀጥቀጥ ጀመረ
የታደነ የሚለው ቃል ሰዎች አድነውና ገድለው የሚያቀርቡትን የዱር እንሰሳ ያመለክታል:: በዘፍጥ 27:7 የታደነ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ::
የዔሣው ምሬት አንድ መራራ ጣዕም ካለው ነገር ጋር የሚመሳሰል ነበር:: አት: “በከፍተኛ ድምጽ አለቀሰ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ያዕቆብ የዔሣውን በረከት እንደወሰደ የሚገልጽ ምሳሌያዊ አገላለጽ ነው አት በአንተ ፈንታ እርሱን ባርከአለሁ (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ዔሣው በያዕቆብ ላይ ያለውን ቁጣ ለመጨመር ጥያቄ ይጠቀማል:: አት ያዕቆብ በእርግጥ ለወንድሜ ትክክለኛ ስም ነው:: (ቅኔያዊ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች እንዲህ የሚለውን የግርጌ ማስታወሻ ይጠቀማሉ ያዕቆብ የሚለው ስም ተረከዙን ያዘ የሚል ትርጉም አለው በመሠረታዊው ቋንቋ ቃሉ አታላይ የሚል አንድምታ አለው::
ይህ ብኩርና እንደ አንድ ዕቃ ከሰው እንደሚወሰድ አድርጐ ይናገራል:: አት: “የእኔ የሆነው ብኩርና በማታለሉ ምክንያት የእርሱ ሆኖአል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)::
ይህ ምርቃት እንደ አንድ ዕቃ ከሰው እንደሚቀማ አድርጐ ይናገራል:: አት : “አታልሎህ በእኔ ፈንታ እርሱን እንዲትመርቅ አድረጐሃል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)::
ያዕቆብን የባረከውን ዓይነት በረከት አባቱ እንደማይባርከው ዔሣው ያውቃል ይስሐቅ ያዕቆብን በሚባርክበት ጊዜ ሳይናገር የቀረው ካለ ዔሣው ይጠይቀዋል
ይስሐቅ ጥያቄ በመጠቀም ምንም ሊያደርገው የሚችለው ነገር እንደሌለ በአጽንዖት ይናገራል:: አት “ለአንተ የማደርገው የቀረ ነገር የለም” (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ይህ በአዎንታዊ መንገድ ሊነገር ይችላል:: አባቴ ሆይ አንድ የቀረ መረከት ለእኔ የሚሆን አለህን?
ዔሣውን አለው
ትኩረት አድርግ ስለቦታው የሚናገረው እውነትና ጠቃሚ ነው
ይህ ስለምድር ለምነት የሚናገር ምሳለያዊ አነጋገር ነው አት ለም ያልሆነ መሬት
በ27:39-4ዐ እነዚህ ተውላጤ ስሞች ነጠላና ዔሣውን ያመለክታሉ:: ነገር ግን ይስሐቅ የሚናገረው ለዔሣው ትውልድም የሚሆን ነው:: ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ::
ጠል በሌሊት በተክሎች ላይ የሚሆን የውሃ ጠብታ ነው:: በትርጉም ይህን ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “ተክሎችዎን ለማጠጣት የሌሊት ጠል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ሰይፍ ለአመጽ የሚቆም ነው:: አት: “ለመኖር የሚያስፈልግህን ለማግኘት ሰዎችን ትዘርፋለህ ትገድላለህ” (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃል ስለመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ አንድ ጌታ እንዳለውና የጌታውም የበላይ አገዛዝ አንደሚሸከምበት ቀንበር እንደተጫነበት ተደርጐ ተነግሮአል አት ከግዛቱ ራስህን ነጻ ታወጣለህ:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ልብ” ራሱ ዔሣውን ያመለክታል:: አት: “ዔሣው ለራሱ እንዲህ አለ” (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ) የአባቴ የለቅሶ ቀን ቀርቦአልና ይህ የቤተሰብ አባል ሲሞት አንድ ሰው የሚያዝንበት ቀናት ያመለክታል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “አንድ ሰው የዔሣውን ዕቅድ ለርብቃ ነገራት“ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“ተመልከት” “አዳምጥ” “ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጥ”
ራሱን ጥሩ ስሜት እንዲሰማው እያደረገ ነው
ይህ “አሁን ጊዜ” ማለት አይደለም:: ነገር ግን የሚቀጥለው አስፈላጊ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ተጠቅሞአል::
ቶሎ ከዚህ ሽሽ እናም ወደ ላባን ሂድ
ለተወሰነ ጊዜ
ወንድምህ እስኪበርድ
ያለ መቆጣት ቁጣ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ አቅጣጫ እንደሚዞር ተደርጐ ተነግሮአል:: አት: “በአንተ ላይ መቆጣቱን እስኪተው ድረስ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ርብቃ ሥጋትዋን ለመግለጽ ጥያቄ ትጠቀማለች አት ሁለታችሁን በአንድ ቀን ማጣት አልፈልግም! (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ይህ የሚገልጸው ኤሣው ያዕቆብን ከገደለ እርሱ ደግሞ ገዳይ በመሆኑ ስለሚገድሉት ነው:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ልጆቹዋ እንደሚሞቱባት የሚያመላክት ለዛ ያለ አገላለጽ ነው (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ አንድን ነገር የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ኤሣው የኬጢያውያን ሴት በማግባቱ ርብቃ መንኛ እንደተናደደች በማግነን ትኩረት መስጠትዋ ነው:: አት: “በማምረር ጠልቸዋለሁ” (hyperbole and Generalization/
“እነዚህ የኬጢያውያን ሴቶች” ወይም “የኬጢያውያን ትውልጆች”
“የአገሩ ሴቶች ልጆች” የአገሩ ሴቶች ማለት ነው:: አት: “በአገሩ የሚኖሩ እንደ እነዚህ ሴቶች” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይጠቀሙ)
ያዕቆብ ከኬጢያውያን ሴት ልጆች የሚያገባ ከሆነ ርብቃን ማነኛ እንደሚያስከፋት በማግነን ጥያቄ ትጠቀማለች:: አት: “ሕይወቴ የከፋ ይሆናል”
1 ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ መረቀው፤ እንዲህም ሲል አዘዘው፣ "ከነዓናዊት ሴት እንድታገባ፤ 2 ይልቅስ ተነሥተህ በመስጴጦምያ ወዳለው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጎትህ ከገባ ሴቶች ልጆች አንዷን አግባ፤ 3 ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ብዙ ልጆችም ይስጥህ፤ የብዙ ሕዝቦችም አባት ያድርግህ፤ 4 አብርሃምን እንደባረከ አንተንና ዘርህን ይባርክ፤ ይህንንም ለአብርሃም ሰጥቶት የነበረውንና አንተም ደስተኛ ሆነህ የኖርክበት ምድር ርስት አድርጎ ይስጥህ።" 5 በዚህ ሁኔታ ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ ያዕቆብም በመስጴጦምያ ወደሚያኖረው ወደ ላባ ሄደ፤ ላባ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ነበረ፤ አባቱም ሶርያዊው ባቱኤል 6 ይስሐቅ ያዕቆብን እንደመረቀና ሚስት እንደሚፈልግ ወደ መስጴጦምያ እንደላከው ዔሳው ተረዳ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ሲመርቀው "ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ" ብሎ ያዘዘው መሆኑንም ሰማ፤ 7 ያዕቆብ ለአባቱና ለእናቱ በመታዘዝ ወደ መስጴቶምያ መሄዱንም ተረዳ፤ 8 በዚህም አባቱ ይስሐቅ የከነዓንያውያንን ሴቶች እንደማይወድ ዔሳው ተገነዘበ፤ 9 ስለዚህ ከዚህ በፊት ከገባቸው ሌላ በተጨማሪ ወደ አብርሃም ልጅ ወደ እስማኤል ሄዶ ልጁን ማሕላትን አገባ፤ እርስዋም የነባዮት እኅት ናት። 10 ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤ 11 ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ ወደ አንድ ስፍራ መጥቶ ዐፈር፤ በዚያም አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ተኛ፤ 12 በሕልሙም ከመሬት እስከ ሰማይ የሚደርሰው መሰላል አየ፤ በመሰላሉም የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ላይ ይውጡና ወደ ታች ይውረዱ ነበር። 13 እግዚአብሔር በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፣ "እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለዝርያዎችህ እንዲሆን ይህን የተገኘበት ምድር እሰጥሃለሁ። 14 ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ እነርሱ በሁሉ አቅጣጫ ይዞታቸውን ያስፋፋሉ፤ በአንተና በዘርህ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ። 15 አይዞህ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚያም ምድር በደህና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈፅምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።" 16 ያዕቆብም ከእንቅልፉ ነቃና "በእርግጥ እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር"አለ። 17 በጣም ፈርቶም ስለነበር "ይህ እንዴት የሚያስፈራ ቦታ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ ወደ ሰማይ የሚያስገባው በር ይህ ነው"አለ። 18 ያዕቆብ በማግሥቱም ጠዋት በማለዳ ተነሣ፤ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ መታሰቢያ እንዲሆን እንደ ሐውልት አቆመው፤በላዩ ላይም የወይራ ዘይት አፈሰሰበት። 19 ይህንንም ስፍራ "ቤትኤል"ብሎ ሰየመው፤ ይህ ስፍራ ከዚያ በኋላ ሎዛ እየተባለ ይጠራ ነበር። 20 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ "ከእኔ ጋር ሆነህ በምትሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ፣ የሚያስፈልገኝን ምግብና ልብስ ብትሰጠኝ፣ 21 ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብትመልሰኝ፤ አንተ አምላኬ ትሆናለህ፤ 22 ይህ ለመታሰቢያነት ያቆምሁት ድንጋይ ወደ ፊት የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሁሉ ከዐሥር አንዱን እጅ ለአንተ እሰጣለሁ።"
አታግባ
ወዲያውኑ ሂድ
ይህ የመስጴጦምያ ግዛት ሌላ ስሙ ሲሆን የአሁኑ ራቅ የሚገኝበት ቦታ ነው:: በዘፍጥረት 25:2ዐ ይህ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
የሰውየው ትውልድ ወይም ሌሎች ዘመዶች: አት: “ቤተሰብ” (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ባቱኤል የርብቃ አባት ነው በዘፍጥረት 22፡22 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ወንድ አያትህ
ከሴት ልጆች
አጐትህ
ይስሐቅ ለያዕቆብ መናገሩን ቀጠለ
ያብዛው የሚለው ቃል እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዴት ፍሬያማ እንደሚያደርገው ይገልጻል:: አት: “ብዙ ልጆችንና ትውልድ ይሰጥሃል” (ድርብ ቃላት ይመልከቱ)
ይህ የሚናገረው አንድን ሰው ስለመባረክ ሲሆን በረከት አንድ ሰው ሊሰጥ እንደሚችል ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል ረቂቅ ስም “በረከት” “ይባርክ” በሚለው ሊገለጽ ይችላል:: አት: “አብርሃምን እንደባረከ አንተንና ዘርህን እግዚአብሔር ይባርክ” ወይም “ለአብርሃም የገባውን ተስፋ ለአንተና ለዘርህ እግዚአብሔር ይስጥ”:: (ዜይቤያዊ አነጋገርና ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
እግዚአብሔር የከነዓንን ምድር ለያዕቆብና ለዘሩ መስጠቱ ልጅ ከአባቱ ገንዘብ ወይም ሀብት እንደሚወርስ ተደርጐ ተገልጾአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“እስከአሁን ያለህበትን ምድር”
እግዚአብሔር ለአብርሃም ተሰፋ የሰጠውን
ይህ የመስጴጦምያ ግዛት ሌላ ስሙ ሲሆን የአሁኑ ራቅ የሚገኝበት ቦታ ነው:: በዘፍጥረት 25:2ዐ ይህ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ባቱኤል የርብቃ አባት ነው በዘፍጥረት 22፡22 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ታሪኩ ከያዕቆብ ወደ ዔሣው ይዞራል
ይህ ቃል እዚህ የተጠቀመው ከተነገረው ታሪክ ወደ ዔሣው የሕይወት መረጃ ፍሰቱ መቀየሩን ለማመልከት ነው (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ የመስጴጦምያ ግዛት ሌላ ስሙ ሲሆን የአሁኑ ራቅ የሚገኝበት ቦታ ነው:: በዘፍጥረት 25:2ዐ ይህ እንዴት አንደተተረጐመ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ሚስትን ያግባ
እንዲሁም ይስሐቅ ያዕቆብን እንደባረከው ኤሣው አየ
የከነዓን ሴት ልጆች ወይም የከነዓናዊያን ሴቶች
የዔሣውን ታሪካዊ ዳራ ይቀጥላል
ዔሣው ተገነዘበ
አባቱ ይስሐቅ የከነዓናውያንን ሴቶች አልተቀበለም
የከነዓን ሴት ልጆች ወይም የከነዓናዉያን ሴቶች
በዚህ ምክንያት ሄዴ
ከነበሩ ሚስቶች ተጨማሪ
የእስማኤል ሴት ልጆች አንዷ ነች (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ከእስማኤል ወንድ ልጆች አንዱ ነው (ስምችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ታሪኩ እንደገና ወደ ያዕቆብ ይመለሳል
ወደ አንድ ሥፍራ ደረሰ ጸሐይም ጠልታ ስለነበር አዳሩን ከዚያ ለማድረግ ወሰነ
ያዕቆብ ሕልም ዐለመ
ታችኛው አካል መሬትን በነካ መንገድ ቆሞ
ይህ እግዚአብሔር የሚኖርበትን ቦታ ያመለክታል
እነሆም የሚለው ቃል ለሚቀጥለው አስደናዊ መረጃ ትኩረት ለመስጠት ነው
ተገቢ ትርጉሞች 1 እግዚአብሔር በመሰላሉ ጫፍ ላይ ቆሞ 2 እግዚአብሔር በያዕቆብ ጐን ቆሞ
እዚህ “አባት” ቅድመ ዘር ማለት ነው:: አት: “አብርሃም ለዘርህ” ወይም “አብርሃም ለቅድመ አያትህ”
እግዚአብሔር ለያዕቆብ በሕልም መናገሩን ቀጠለ
በቁጥር መብዛትን አግንኖ ለማሳየት እግዚአብሔር የያዕቆብን ዘር ከምድር አሸዋ ጋር ያነጻጽራል:: አት: “መቁጠር ከምትችሉት በላይ ብዙ ዘር ይሆንላችኋል” ተመሣሣይ አባባል/simile ይመልከቱ
ትስፋፋለህ በነጠላ የተቀመጠና ያዕቆብን ያመለክታል እዚህ ያዕቆብ ዘሩን ይወክላል:: አት: “መቁጠር ከሚትችለው በላይ ብዙ ዘር ይሆንልሃል” (ተዛማጅ ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህም ሕዝቡ የምድራቸውን ድንበር የሰፋሉ እናም ብዙ ምድር ይወርሳሉ ማለት ነው
እንዚህ ሀረጐች በጣምራ “ወደ ሁሉም አቅጣጫዎች” የሚል ትርጉም ለመስጠት ተጠቅመዋል:: (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “በአንተና በዘርህ በምድር ያሉ ሕዝቦችን እባርካለሁ” (ተሻጋረ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተነገር ይመልከቱ)
ትኩረት ስጥ እኔ የሚናገረው እውነትና ጠቃሚ ነው፤ እኔ
ሁሉንም እስከሚፈጽምልህ ድረስ አልተውህም
“ደኀንነትህን እጠብቃለሁ” ወይም “እከላከልልሃለሁ”
ወደዚህች ምድር እመልስሃለሁ
ከእንቅልፉ ሲነቃ
የሰማይ ደጅ የሚለው ሀረግ የሚገልጸው የእግዚአብሔር ቤት እና የእግዚአብሔር መኖሪያ መግቢያ ቦታ እንደሆነ ነው (ድርብ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
ይህ ስለ እግዚአብሔር መኖሪያ ቦታ መግቢያ የሚናገረው በአካል እንደሚታይ አንድ ሰው በር ከፍቶ ሰዎችን እንደሚያስገባው የመንግሥት ቤት ተደረጐ ተገልጾአል:: (ዘይቤያዊ አባባል ይመልቱ)
ትልቅ ድንጋይ ወይም በጫፉ ቅርጽ ያለበት ለማስታወሻነት የቆመ ሐውልት ነው
ያዕቆብ ሐውልቱን ለእግዚአብሔር መቀደሱን የሚያመለክት ድርጊት ነው:: የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “ሐውልቱን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ዘይት በላዩ ላይ አፈሰሰበት” (ምልክታዊ ድርጊት ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ቤተል ማለት የእግዚአብሔር ቤት የሚለውን ተረጓሚዎች እንደ ግርጌ ማስታወሻ ያስቀምጣሉ
ይህ የከተማይቱ ስም ነው
“ስእለት አደረገ” ወይም “በተለይ ለእግዚአብሔር ቃል ገባ”
ያዕቆብ እግዚአብሔርን በሶስተኛ ሰው አገላለጽ ያናግረዋል ይህ በሁለተኛ ሰው አገላለጽ ሊገለጽ ይችላል:: አት: አንተ እንዲህ…የማመልከው አምላኬ ትሆናለህ” (ተዛማጅና ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ “እንጀራ” አጠቃላይ ምግብ ይገልጻል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
“ቤት” ለያዕቆብ ቤተሰብን ይገልጻል አት ወደ አባቴና ወደሌሎች የቤተሰብ አባላት (ተዛማጅና ተመሣሣይ ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ድንጋዩ እግዚአብሔር የተገለጠበትን ቦታ ያመለክታልና ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያመልኩበት ቦታ ይሆናል
1 ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በስተ ምሥራቅ ወዳለው አገር ደረሰ፤ 2 እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጉድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጉድጓድ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጉድጓድ ነበር፤ ጉድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤ 3 መንጋዎቹ ሁሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ ድንጋዩን አንከባለው ከጉድጓዱ ውሃ ያጠቱአቸው ነበር፤ መንጋዎቻቸውን ካጠጡ በኋላ ግን ድንጋዩንም መልሰው በጉድጓዱ አፍ ላይ ይከዱኑታል። 4 ያዕቆብም እረኞቹን "ወዳጆቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "እኛ የመጣነው ከካራን ነው" አሉት። 5 እርሱም "የናኮርን የልጅ ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?" ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም "አዎ እናውቀዋለን" አሉት። 6 እርሱም "ለመሆኑ እርሱ ደኅና ነውን?" አላቸው። እነርሱም "አዎ፣ ደኅና ነው፤ እንዲያውም ልጁ ራሔል ያችውልህ! በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ነች" አሉት። 7 ያዕቆብም "ጊዜው ገና ቀን ነው፤ መንጋዎቻቸውንም ወደ ቤት የምታስገቡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ታዲያ ለምን ውሃ አጠጥታችሁ አታሰማሩአቸውም? ፤ አለ። 8 እነርሱም "እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን" አሉት። 9 ያዕቆብም ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ወደዚያ መጣች፤ ምክንያቱም እርስዋ የበጎች እረኛ ነበረች። 10 ያዕቆብ ያጉቱን የላባን በጎች እየነዳች ስትመጣ ራሔልን አይቶ ወደ ጉድጓድ ሄደ፤ ጉድጓዱ የተከደነበትንም ድንጋይ አንከባሎ በጎቹን አጠጣቸው። 11 ከዚያ በኋላ ራሔልን ሳማት። ከደስታውም ብዛት የተነሣ አለቀሰ፤ 12 "እኔ የአባትሽ እኅት የሆነችው የርብቃ ልጅ ሄደች። 13 ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ አቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤ 14 ላባም "በእርግጥ አንተ ቅርብ የሥጋ ዘመዴ ነህ" አለው፤ ያዕቆብም አንድ ወር ያህል ከአጎቱ ጋር ተቀመጠ። 15 ላባ ያዕቆብን "ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነፃ ልታገለግለኝ አይገባህም፤ ስለዚህ ምን ያህል ደመወዝ ላስብልህ? አለው። 16 ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ታላቂቱ ልያ፤ ታናሽቱ ራሔል ይባሉ ነበር። 17 ልያ ዐይነ ልም ስትሆን፣ ራሔል ግን ቁመናዋ የሚያምር የደስ ደስ ያላት ነበረች። 18 ያዕቆብ ራሔልን እጅግ ስለወደዳት "ራሔልን ብትድርልኝ ሰባት ዓመት አገለግልሃለሁ" አለ። 19 ላባም "ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ እሺ ተስማምቼአለሁ፤ እዚሁ ከእኔ ጋር ኑር" አለው። 20 ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለነበር የቆየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው። 21 ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ላባን "እነሆ የአገልግሎት ዘመኔ ተፈፅሞአል፤ ሚስት እንድትሆነኝ ልጅህን ስጠኝ" አለው። 22 ላባም የሠርግ ድግስ አዘጋጅቶ በአቅራቢያው የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ጠራ። 23 ነገር ግን ላባ በራሔል ምትክ ልያን ለያዕቆብ ሰጠው፤ ያዕቆብም ከልያ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ። 24 ላባ ሴት አገልጋዩን ዚልፋን አገልጋያዋን እንድትሆን ለልጁ ለልያ ሰጣት። 25 በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ልያ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ ወደ ላባ ሄዶ "ይህ ያደረግህብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልሁህ ራሔልን ለማግኘት አልነበረም? ታዲያ ለምን አታለልከኝ"አለው። 26 ላባም "ታላቂቱ ሳትዳር፤ ታናሺቱን መዳር የአገራችን ልማድ አይደለም፤ 27 የልያ ሠርግ ሰባት ቀን እስኪሞላው ድረስ ጠብቅ፤ ከእንግዲህ ወዲይ ሰባት ዓመት የምታገለግለኝ ከሆነ ራሔልን እሰጥሃለሁ" አለው። 28 ያዕቆብም ነገሩ ተስማማ፤ ከልያ ጋር ሰባት ቀን ተሞሽሮ ከቆየ በኋላ፤ ላባ ልጁን ራሔልን ለያዕቆብ ሳረለት። 29 ላባ ሴት አገልጋዩን ባላን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለራሔል ሰጣት። 30 ያዕቆብ ከራሔልም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ከልያም አብልጦ ወደዳት፤ ከዚያ በኋላ ላባን ሰባት ዓመት አገለገለው። 31 ልያ የራሔልን ያህል እንዳልተወደደች እግዚአብሔር ባየ ጊዜ መውለድ እንድትችል ማሕፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መኻን ሆነች፤ 32 ልያ ርርግዛ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እግዚአብሔር መከራዬን ተመለከተ፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ባሌ ይወደኛል" ስትል ስሙን ሮቤል አለችው። 33 እንደገና አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወደች፤ "እግዚአብሔር እንዳልተወደድሁ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ' ስትል ስሙን ስምዖን አለችው። 34 እንደገና 'አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ "እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል" ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤ 35 እንደገና አረገዘችና ውንድ ልጅ ወለደች፤ "አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ" ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች።
ከከነዓን ምድር በስተምሥራቅ የሚገኙ የጳዳን አራም ሰዎች ማለት ነው::
እነሆ የሚለው ቃል በትልቁ ታሪክ ውስጥ አንድ ሌላ ክስተት መጀመሩን ያመለክታል:: በሚትተረጉሙበት ቋንቋ ይህን የመግለጽ መንገድ ሊኖሮት ይችላል::
ከዚሁ ጉድጓድ ይህ ሀረግ ታሪኩን ወደ ዳራው መረጃ ይመልስና እንዴት እረኞች በጐችን ውሃ እንደሚያጠጡ ይናገራል
“እረኞች ውሃ ያጠጣሉ” ወይም “በጐችን የሚጠብቁ ውሃ ያጠጣሉ”
አፍ ጉድጓዱ የተከፈተበትን ቦታ ያሳያል:: አት: “ጉድጓዱ የተከፈተበት ቦታ”
ያዕቆብም እረኞቹን አለ
ይህ ለእንግዶች በትህትና ሰላምታ የማቅረብ መንገድ ነው
አዚህ ወንድ ልጅ ወንድ ዘርን ያመለክታል ሌላ ተገቢ ትርጉም የናኮር የልጅ ልጅ ላባ
አሁን ተመልከት የእርሱ ሴት ልጅ ራሔል ከበጎች ጋር በመምጣት ላይ ነች
“ገና ጸሐይ በሰማይ ላይ ነች/ጊዜው ገና ነው” ወይም “ጸሐይ ገና በማብራት ላይ ነች”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “መንጐችን እስኪሰበስቡ” (ተሻጋረ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተነገር ይመልከቱ)
ይህም ሌሊቱን እንዲያሳልፉ በቅጥር ውስጥ መሰብሰብ ማለት ነው:: የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀት እና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በሜዳ ያለውን ሣር ይመገቡ
ውሃ ሊናጠጣቸው መጠበቅ አለብን ይህ ፈቃደኝነት ሳይሆን ጊዜን በሚመለከት ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ሌሎች እረኞች መንጐቻቸውን እስኪሰበስቡ” (ተሻጋረ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተነገር ይመልከቱ)
እዚህ አፍ ጉድጓዱ የተከፈተውን ቀዳዳ ያመለክታል አት ከጉድጓዱ ወይም ጉድጓዱ በተከፈተበት (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አጐቱ
እዚህ “አፍ” የተከፈተበትን ቦታ ያመለክታል:: አት: “ጉድጓዱ” ወይም “ጉድጓዱ የተከፈተበትን ቦታ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በጥንታዊቷ ቅርብ ምሥራቅ በመሳም ሰላምታ መለዋወጥ የተለመደ ነው:: ነገር ግን በወንዶች ዘንድ እምብዛም የታወቀ ነው:: በሚትተረጉሙበት ቋንቋ ባህል እንዲህ ዓይነቱ ስሜትን በመግለጽ ዘመዳሞች ሰላምታ የመለዋዋጥ ነገር ካለ ይህን ይጠቀሙ:: ከሌለ ግን ሌላ ተገቢ አባባል ይጠቀሙ::
ያዕቆብ የሚያለቅሰው ደስተኛ በመሆኑ ነው የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉሙ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ለአባትዋ የሚዛመድ
የእኀቱ ልጅ
አቀፈው
በጥንታዊቷ ቅርብ ምሥራቅ በመሳም ለዘመድ ሰላምታ ማቅረብ የተለመደ ነው:: ነገር ግን ይህ በወንዶች መካከል የታወቀ ነው:: በሚተረጉሙት ቋንቋ ለዘመድ የሚቀርብ ሰላምታ ስሜትን የሚገልጽ ከሆነ ይህን ይጠቀሙበት:: ካለሆነ ግን ሌላ ተገቢ አባባል ይጠቀሙ::
“ከዚያም ያዕቆብ ለራሔል የነገረውን ሁሉ ለላባ ነገረው”
እነዚህ ሀረጐች በቀጥታ የሚዛመዱ ናቸው:: አት: “የእኔ ዘመድ” ወይም “የቤተሰቤ አባል” (ተዛማጅ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ስለሚሠራለት ሥራ ለያዕቆብ መክፈል ስለአለበት ላባን ይህንን አግንኖ ለመናገር ጥያቄ ይጠቀማል:: ይህ በአዎንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ዘመዴ ቢትሆንም ለሚትሠራልኝ መክፈል በእርግጥ ትክክል ነው” See:RhetoricalQuestionandLitotes
ተገቢ ትርጉሞች 1 የልያ ዓይኖች ልም ነበሩ 2 የልያ ዐይኖች ታማሚ ነበሩ
እዚህ ወደደ የሚለው ቃል በአንድ ወንድና ሴት መካከል የሚሆን ስሜታዊ ወዋደድን ያመለክታል
ለሌላ ወንድ ከሚድራት ይልቅ
“ነገር ግን ጊዜው ጥቂት ቀናት ሆኖ ታየው”
“ለእርስዋ ያለውን ፍቅር ስመዝን” ወይም “ለእርስዋ ካለው ፍቅር የተነሣ”
ቀኔ ተፈጽሞአል የሚለው ሀረግ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: ይህ emphatic ዐረፍተ ነገር ነው:: አት: “ለአንተ መሥራት የሚገባኝን ጊዜ ስለፈጸምሁ እንዳገባት ሚስቴን ስጠኝ” ወይም “ለሰባት ዓመታት ስላገለገልሁ እንዳገባት ራሔልን ስጠኝ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የጋብቻ ሠርግ አዘጋጀ ምናልባት ላባን ሌሎች ሰዎች እንዲያዘጋጁ አደረገ:: አት: “ሌሎች የጋብቻ ሠርግ እንዲያዘጋጁ አደረገ”:: (ተዛማጅ ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልከቱ)::
ይህ የሚገልጸው ምሽት ስለነበረና ስላላያት ከልያ ጋር መሆኑን ያዕቆብ አላወቀም ነበር:: የዐረፍተ ነገሩ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እዚህ ጸሐፊው ላባን ዘለፋን ለልያ እንደሰጠ መረጃ ይሰጣል፡፡ ዘለፋን ለልያ ከሠርግ በፊት ሳይሰጣት አይቀርም:: (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ይመልከቱ)
ያዕቆብም ልያ በአልጋ አብሮአት በማየቱ ተገረመ:: “እነሆ” የሚለው ቃል ያዕቆብ ባየው ነገር እንዴት እንደተደነቀ የሚያሳይ ነው፡፡
ያዕቆብ ቁጣውንና መገረሙን ለመግለጽ ጥያቄ ይጠቀማል ይህ ቅኔ አዘልጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡ “ይህን ለእኔ ታደርጋለና ብዬ አላምንህም” (See: RhetoricalQuestion)
ያዕቆብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠቀመው ላባን ያታለለውን ጉዳቱን ለመግለጽ ነው ይህ ቅኔ አዘል ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገልግየሃለሁ (See: Rhetorical Question)
በቤተሰባችን አንሰጥም
የልያን ጫጉላ ሳምንት ፈጽም
የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ራሔልን እንሰጥሃለን (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ያዕቆብ ላባን የጠየቀውን አደረገ እናም የልያን ጫጉላ ሳምንት ማክበርን ፈጸመ
ይህ የራሔል ሴት አገልጋይ ስም ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ጋብቻዊ ግንኙነት እንደፈጸሙ የሚገልጽ አክብሮታዊ ወይም ለዛ አባባል ነው
በአንድ ወንድና በአንድ ሴት መካከል የሚሆን ስሜታዊ ፍቅር ያመለክታል
ይህ ተሻሪ ግሥ በያዘ መልክ ወይም በገቢር ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ያዕቆብ ልያን አልወደዳትም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ያዕቆብ ራሔልን ከልያ ይልቅ እንደወደዳት በማተኮር አግንኖ የሚናገር ነው አት ከራሔል አሳንሶ ወደዳት (አግንኖና በገሃድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ልያ እንዲትጸንስ ማድረጉ እግዚአብሔር ማሕጸንዋን እንደከፈተ ተደርጐ ተነግሮአል:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ሊትጸንስ አልቻለችም
ልያ ጸነሰች ወንድ ልጅም ወለደች
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: ሮበል የሚለው ስም ‘ወንድ ልጅ አየሁ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ልያ ያዕቆብ ስላልተቀበላት በስሜታዊ ሕመም ነበራት:: “መከራ” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር እንደተሰቃየሁ አየኝ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
እንደገናም ልያ ጸነሰች
ወንድ ልጅ ወለደች
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ስምዖን የሚለው ስም ‘ተሰማ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ባሌ ያቅፈኛል
ለእርሱ ሶስት ወንጆ ልጆች ወለድሁለት
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ሌዊ የሚለው ስም ‘የተጠጋ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ልያ እንደገና አረገዘች
ወንድ ልጅን ወለደች
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ይሁዳ የሚለው ስም ‘ምሥጋና’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
1 ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ እንዳልወለደችለት ባየች ጊዜ በእኅቷ ቀናች። ያዕቆብንም፣ “ልጅ ስጠኝ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው። 2 ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፤ “እኔ የሆድሽን ፍሬ በነሳሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን?” አላት። 3 እርሷም፣ “እነሆ፣ አገልጋዬ ባላ አለችልህ፣ ልጆች እንድትወልድልኝና እኔም ደግሞ በእርሷ አማካይነት ልጆች እንዳገኝ ከእርሷ ጋር ተኛ” አለችው። 4 ስለዚህ ባላን እንደሚስት አድርጋ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ከእርሷ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነት አደረገ። 5 ባላም አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደችለት። 6 ራሔልም፦ “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፣ ልመናዬንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጥቶኛል” አለች። ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። 7 የራሔል አገልጋይ ባላ ዳግመኛ አረገዘችና ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደች። 8 ከእኅቴ ጋር ብርቱ ትግል ታግዬ አሸነፍኋት” አለች። ስለዚህ ስሙን ንፍታሌም ብላ ጠራችው። 9 ልያም ልጅ መውለድ ማቆሟን እንደተረዳች፣ አገልጋይዋን ዘለፋን ሚስት እንድትሆነው ለያዕቆብ ሰጠችው። 10 የልያ አገልጋይ ዘለፋም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት፣ 11 ልያም፣ “እንዴት የታደልሁ ነኝ!” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው። 12 የልያም አገልጋይ ዘለፋ ለያዕቆብ ሁለተኛ ልጅ ወለደችለት፤ 13 ልያም፣ “እጅግ ደስ ብሎኛል፣ ከእንግዲህ ወዲያ ሴቶች ‘ደስተኛዋ’ ይሉኛል አለች፤ ስሙንም ‘አሴር’ ብላ ጠራችው። 14 በስንዴ መከር ወራት ሮቤል ወደ ዱር ሄዶ እንኮይ አገኘ፤ ለእናቱ ለልያም አመጣላት፤ ራሔልም ልያን፣ “እባክሽን ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት። 15 ልያም፦ “ባሌን የቀማሽኝ አነሰና የልጄን እንኮይ ደግሞ ልትወስጂ አማረሽ?” አለቻት። ራሔልም፣ “ስለልጅሽ እንኮይ ዛሬ ያዕቆብ ከአንቺ ጋር ይደር” አለቻት። 16 በዚያ ምሽት ያዕቆብ ከእርሻ ሲመለስ፣ ልያ ወጥታ ተቀበለችውና፣ “በልጄ እንኮይ ስለተከራየሁህ የዛሬው አዳርህ ከእኔ ጋር ነው” አለችው። ያዕቆብም በዚያች ሌሊት ከእርሷ ጋር አደረ። 17 እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፣ ስለዚህ አረገዘችና ለያዕቆብ አምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት። 18 ልያም፦ “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ደመወዜን ከፈለኝ” አለች። ስሙንም ይሳኮር አለችው። 19 ልያ አሁንም ደግማ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች። 20 እርሷም፣ “እግዚአብሔር በከበረ ስጦታ አድሎኛል፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለወለድሁለት ከእንግዲህ ባሌ አክብሮ ይይዘኛል” አለች፤ ስሙንም ዛብሎን አለችው። 21 ከዚያም በኋላ ሴት ልጅ ወለደች ስምዋንም ዲና አለቻት። 22 እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፤ ጸሎትዋንም ሰምቶ ልጅ እንድትወልድ አደረጋት፤ 23 አርግዛም ወንድ ልጅ ወለደችና፣ “እግዚአብሔር ዕፍረቴን አስወገደልኝ” አለች፤ 24 ደግሞም ሌላ ወንድ ልጅ ይጨምርልኝ ስትል ስሙን ዮሴፍ ብላ ጠራችው። 25 ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ተወለድሁበት አገር እንድመለስ አሰናብተኝ፤ 26 አንተን በማገልገል ያገኘኋቸውን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያህል አገልግሎት እንዳበረከትኩልህ ታውቃለህ።” 27 ላባም፣ “በአንተ ምክንያት እግዚአብሔር እንደባረከኝ በንግርት መረዳቴን ልነግርህ እወዳለሁ፤ 28 የምትፈልገውን ደመወዝ ንገረኝና እከፍልሃለሁ” አለው። 29 ያዕቆብም እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልሁህና የከብትህም መንጋ በእኔ ጠባቂነት እንዴት እንደረባልህ አንተ ታውቃለህ፤ 30 እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ በተሰማራሁበት ሁሉ እግዚአብሔር በረከቱን አብዝቶልሃል። ታዲያ፣ ለራሴ ቤት የሚያስፈልገኝን የማቀርበው መቼ ነው?” 31 ላባም፣ “ታዲያ ምን ያህል ልክፈልህ?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ የምልህን አንድ ነገር ብቻ ብታደርግልኝ መንጋህን ማሰማራቴንና መጠበቄን እቀጥላልሁ፤ 32 ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጉርጉርና ነቁጣ ጥቁርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቁጣና ዝንጉርጉር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤ 33 ወደፊት ደመወዜን ለመቆጣጠር በምትመጣበት ጊዜ ታማኝነቴ ይታወቃል፤ ደመወዜን ለመቆጣጠር ስትመጣ ዝንጉርጉር ያልሆነ ወይም ነቁጣ የሌለበት ፍየል ብታገኝ፣ እንዲሁም ጥቁር ያልሆነ በግ ብታገኝ የተሰረቀ መሆኑን መረዳት ትችላልህ” አለው። 34 ላባም፣ “እሺ አንተ ባልከው እስማማለሁ” አለ። 35 ነገር ግን በዚያኑ ዕለት ከተባት ፍየሎች ሽመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቁጣ ያለባቸውን ሁሉ እንዲሁም ከእንስት ፍየሎች ነቁጣ ያለባቸውን ዝንጉርጉር የሆኑትን ሁሉ መረጠ፤ ደግሞም ጥቋቁር የሆኑትንም በጎች ሁሉ ለየና ወንዶች ልጆቹን አስጠበቃቸው። 36 ከዚህ በኋላ ላባ መንጋውን ነድቶ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ከያዕቆብ ርቆ ሄደ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጋዎች መጠበቁን ቀጠለ። 37 ያዕቆብም ልብን፣ ለውዝና ኤርሞን ከሚባሉ ዛፎች እርጥብ በትሮችን ወሰደ፤ በበትሮቹ ያለው ነጭ እንዲታይ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው፤ 38 መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ ከፊት ለፊት እንዲያዩአቸው የተላጡትን በትሮች በውሃ ማጠጫዎቹ ውስጥ አደረጋቸው። መንጎቹም ስሜታቸው ሲነሣሣና ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ፣ 39 በትሮቹን ፊት ለፊት እያዩ ይሳረሩ ነበር፤ ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ የጣለባቸውንም ግልገሎች ወለዱ። 40 ያዕቆብ እነዚህን ግልገሎች ለብቻ ለየ፤ የቀሩትን ግን ዝንጉርጉርና ጥቁር በሆኑት በላባ መጋዎች ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በዚህ ዓይነት የራሱን መንጋ ከላባ መንጋ ጋር ሳይቀላቅል ለብቻ አቆማቸው። 41 ያዕቆብም ብርቱ እንስቶች አውራ ፈልገው በሚቅበጠበጡበት ጊዜ በትሮቹ አቅራቢያ እንዲጠቁ በትሮቹን በውሃ ገንዳዎች ውስጥ ፊት ለፊታቸው ያስቀምጥ ነበር፤ 42 ደካማ በሆኑት እንስቶች ፊት ግን በትሮቹን አያስቀምጥም ነበር፤ ስለዚህ ደካሞቹ ለላባ ሲሆኑ፣ ብርቱዎቹ ለያዕቆብ ሆኑ። 43 በዚህም ሁኔታ ያዕቆብ እጅግ ባለጸጋ ሆነ፤ ብዙ መንጋዎች፤ ሴቶችና ወንዶች አገልጋዮች፣ ብዙ ግመሎችና አህዮችም ነበሩት።
ራሔል ማርገዝ እንዳልቻለች ባወቀች ጊዜ
ራሔል ልጅ ባለመኖርዋ ምነኛ እንደተከፋች ማጋነንዋ ነው:: አት: ምንም እንደማልጠቅም ይሰማኛል:: (በማጋነንና በገሃድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እንዳረግዝ አድርገኝ
የያዕቆብ ቁጣ እንደ እሳት ተደርጐ ተገልጾአል፡፡ አት፡ “ያዕቆብ ራሔልን በጣም ተቆጣት” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ያዕቆብ ራሔልን ለመቆጣት የተጠቀመው ቅኔያዊ ጥያቄ ነው:: ይህም እንደ ዐረፍተ ነገር ልተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “እኔ እግዚአብሔር አይደለሁም! ልጅ እንዳትወልጂ የሚከለክለው እኔ አይደለሁም” (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ራሔል አለች
“ተመልከት” ወይም “ስማ” ወይም “ሊናገር ስላለሁ ነገር ትኩረት ስጥ”
በዚያን ጊዜ መካን ሴት በሕጋዊነት ልጅ የሚታገኝበት ተቀባይነት ያለው መንገድ ይህ ነው:: የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የራሔል ሴት ባሪያ ስም ነው፡፡ በዘፍጥረት 29፡29 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ይህ ባላ የሚትወልደው ልጅ ለራሔል እንደሚሆን የሚገልጽ አባባል ነው:: አት: “ለእኔ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በዚህ መንገድ ልጅ እንዲኖረኝ ታደርጋለች
የራሔል ሴት ባሪያ ስም ነው፡፡ በዘፍጥረት 29፡29 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ለያዕቆብ ወንድ ልጅም ወለደችለት
ራሔል ስም አወጣችለት
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ዳን የሚለው ስም ‘እርሱ ይፈርዳል’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ባላ እንደገና አረገዘች
ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅን ወለደችለት
ትግልን ታገልሁ የሚለው ሀረግ አጽንዖትን የሚሰጥ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው ራሔል እንደ እኀትዋ አንድን ልጅ ለማግኘት ያደረገችው ከልያጋር አካላዊ ትግል እንዳደረገች የሚገልጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው:: አት: “እንደ ታላቅ እኀቴ ልያ ልጅን ለማግኝት ትልቅ ተጋድሎ አድርጌያለሁ:: (ፈሊጣዊና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አሸነፍሁ ወይም ተሳክቶልኛል
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ንፍታለም የሚለው ስም ‘ትግሌ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ልያም በተረዳች ጊዜ
አገልጋይዋን ዘለፋን ሚስት እንዲትሆነው ለያዕቆብ ሰጠችው
የልያ ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ለያዕቆብ ወንድ ልጅን ወለደችለት
እንዴት ያለ መታደል ነው! ወይም ምን ዓይነት ዕድል ነው!
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ጋድ የሚለው ስም ‘እድለኛ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የልያ ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት
እንዴት የተባረኩ ነኝ! ወይም እንዴት ደስተኛ ነኝ !
ሴቶች ወይም ልጃገረዶች/ወጣት ሴቶች
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “አሴር የሚለው ስም ‘ደስታ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ሮቤልም ወጣ
ቀናት የሚለው አባባል በዓመት ውስጥ ያለ ወቅት ወይም ጊዜ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: አት “በዓመት ስንዴ በሚታጨድበት ጊዜ” ወይም “ስንዴ በሚታጨድበት ወቅት” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ከፍቅረኛ ጋር ለመተኛት ስሜት የሚያነሣሣና ፍሬን የሚጨምር የአትክልት ፍሬ ነው:: አት: “የፍቅር ፍሬ” (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ባሌን …. አይሰማሽምን? ይህ ራሔልን ለመቆጣት የተጠቀመችው ቅኔያዊ ጥያቄ ነው ይህ ጥያቄ በስድ ዐረፍት ነገር ሊገለጽ ይችላል:: ባሌን የማያስከፋ ነው:: (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ) …ደግሞ ሊትወስጂ አማረሽ? ይህንም ቅኔ አዘል ጥያቄ የተጠቀመችው ራሔልን ለመቆጣት ነው ይህ ጥያቄ በስድ ዐረፍት ነገር ሊገለጽ ይችላል:: አት: አሁን ደግሞ… አማረሽ! (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
“ከዚያም ያዕቆብ ይተኛ” ወይም “ያዕቆብ እንዲተኛ እፈቅዳለሁ”
ለልጄ “እንኮይ” ዋጋ በዘፍጥረት 3ዐ;14 እንኮይ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
አረገዘች
አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች
እግዚአብሔር ልያን መካሡ ለሚሠራው ሠራተኛ አንድ አለቃ ድርጐውን እንደሚከፍል እንደከፈለላት ተደርጐ ተገልጾአል “እግዚአብሔር የድርሻዬን ሰጠኝ” ወይም “እግዚአብሔር ካሠኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ይሳኮር የሚለው ስም ‘ካሣ አለ’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ልያ እንደገና አረገዘች
ስድስተኛ ወንድ ልጅም ለያዕቆብ ወለደች
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ዛብሎን የሚለው ስም ‘ክብር’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የልያ ሴት ልጅ ስምዋ ነው፡፡(ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
አሰባት የሚለው አባባል አስተዋላት ማለት ነው:: ይህ እግዚአብሔር ራሔልን ረስቶአታል ማለት አይደለም:: ጥያቄዋን አሰበ ማለት ነው:: አት: “እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ የፈለገችውንም ሰጣት” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ራሔል እንዳታፍር ያደረገው ሐፍረት አንድ ሰው ከአንድ ሰው ወስዶ እንደሚያስወግድ ዕቃ ተደርጐ ተነገሮአል:: ረቂቅ ስም ሐፍረት እንደ እፍረት ሊገለጽ ይችላል::
ተረጓሚዎች የሚከተለውን አንደ ግርጌ ማስታወሻ ተጨማሪ አድርገው ሊያቀርቡ ይችላሉ:: “ዮሴፍ” የሚለው ስም ‘እርሱ ይጨምር’ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የራሔል የመጀመሪያዎቹ ወንድ ልጆች ከሴት አገልጋይዋ ከባላ ነበር
ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ
እንዲመለስ
ያዕቆብ ላባንን የተስማሙበትን ኮንትራት ያስታውሳል (ዘፍጥረት 29 :27) ረቂቅ ስም “አገልግሎት” እንደ “አገለገለ” ሊገለጽ ይችላል:: አት: ለረጅም ጊዜያት እንዳገለገልሁህ ታውቃለህ:: (ረቂቅ ስሞች ይጠቀሙ)
ላባንም ያዕቆብን እንዲህ አለው
አይኖች ማየትን ይወክላሉ እናም ማየት ሃሳብን ወይም ውሳኔን ይወክላል:: አት: “በአንተ ፊት ሞገስ ካገኘሁ” ወይም “በእኔ የተደሰትህ ከሆንህ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው በሌላኛው ሰው ዘንድ ሞገስ ማግኘቱን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ተቀመጥ ምክንያቱም
በመንፈሳዊና ማጅካዊ ልምምዶቼ ተረድቸአለሁና
በአንተ ምክንያት
ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት እዚሁ ላቆይህ ምን ያህል መክፈል እንዳለብኝ ንገረኝ፡፡ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ያዕቆብ ላባንን አለው
ጥበቃ ከጀመርኩባቸው ጊዜ ከብቶች እንዴት እንደተመቻቸው
ለአንተ ሥራ ከመጀመረ በፊት መንጐችህ ጥቂት ነበሩ
ነገር ግን አሁን ሀብትህ በጣም ጨምሮአል
አሁንም እኔ ደግም ለቤተሰቤ የምሠራው መቼ ነው? ያዕቆብ ለቤተሰቡ የሚሆነውን ማቅረብ እንዳለበት ለማጽናት ጥያቄ ይጠቀማል ይህም ጥያቄ በዐረፍተነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “አሁን ለቤተሰበ የሚሆነውን ማሰብ አለብኝ” (ቅኔ አዘል ጥያቄችን ይመልከቱ)
“ታዲያ ምን መክፈል እችላለሁ?” ወይም “ታዲያ ምን መስጠት እችላለሁ?” ይህ የበለጠውኑ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት እንዲትቆይና እንዲትሠራልኝ ዘንድ ምን መክፈል እችላለሁ?(ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ)
ያዕቆብ ሊናገር ያለው እርሱ ከተናገረው ጋር እንደሚጻረር ለማሳየት አገናኝ ቃል “ነገር ግን” በመግቢያው ሊጠቀም ይቻላል:: አት: “ነገር ግን ይህንም ነገር ቢታደርግልኝ” (አገናኝ ቃላት ይመልከቱ)
“ይህ ነገር” የሚለው ሀረግ ያዕቆብ በቁጥር 32 የሚያቀርበውን ያመለክታል::
መንጎችህን እመግባለሁ እጠብቃለሁ
ማንኛውንም ዥንጉርጉርና ጥቁር የሆነውን በግና ዝንጉርጉር የሆነውን ፍዬል እለያለሁ
እንዚህ እዚሁ ለሚቆየው ዋጋዬ ይሁኑ
ታማኝነት የሚለው ቃል አማንነት ማለት ነው ይህም ታማኝነት አንድ ሰው ሰለሌላኛው ሰው በመደገፍ ወይም በመቃወም የሚሰጠው ምሥክርነት እንደሆነ ይናገራል:: አት: “ለአንተ ታማኝ መሆነንና አለመሆነን በኋላ ታውቀዋለህ”:: (ሰውኛ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ ገቢራዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል አት ማንኛውም ዥንጉርጉር ያለሆነ ፍዬልና ጥቁር ያልሆነ በግ ቢታገኘው እንደተሰረቀ መቁጠር ትችላለህ:: (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዙ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
“እንደተናገርከው ይሁን” ወይም “አንተ እደተናገርከው እናደርጋለን”
ሽመልመሌና ነቁጣ ያለባቸውን
ነቁጣ ያለባቸውን
ማንኛውም ነጭ ያለበት በግ
ጥቁር በጎችን ሁሉ
እዚህ “እጅ” “ቁጥጥር” ወይም “ጥበቃ” የሚተካ ነው:: አት: “ልጆቹ እንዲጠብቁ አደረጋቸው” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
እነዚህ ሁሉ ነጭ ዛፎች ናቸው:: (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የቅርፊታቸውን አንዳንድ ክፍሎችን በመላጥ የበትሮቹ ውስጠኛው ነጭ አካል እንዲታይ አደረገ
ከብቶችን ለማጠጣት ውሃን የሚይዙ ረጅምና ክፍት የሆኑ ገንዳዎች
“የመንዎች እንስሳት ይጸልሱ ነበር” ወይም “ይጠቃቁ ነበር”
ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸውን ግልገሎት ወለዱ
ይህ ለብዙ ዓመታት እንደተረገ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ለሚቀጥሉት ብዙ ዓመታት ያዕቆብ ለያቸው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ፊት ለፊት እያዩ
የራሱን መንጋ ለየ
እዚህ የመንጋዎች ዐይን በጎችን ወይም መንጋዎችን የሚያመለክትና የሚያዩትን እንደሚያተኩር ነው:: አት: (መንጋው እንዲያየው ዘንድ (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉውን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
በበትሮቹ ፊትለፊት
በደካማዎች እንስሳት
ይህን ይበልጥኑ ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “ደካማ ደካማዎቹ ዝንጉርጉርና ነቁጣ ስለሌላቸው ለላባን ሲሆኑ ብርቱ ብርቱዎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ ስላላቸው ለያዕቆብ ሆኑ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ያዕቆብ
“እጅግ በለጸገ” ወይም “ሀብታም ሆነ”
1 የላባ ወንዶች ልጆች፣ “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት እንዳለ ወስዶታል፤ ይህ ሁሉ እርሱ ያከማቸውም ሀብት ከአባታችን የተገኘ ነው” እያሉ ሲያወሩ ያዕቆብ ሰማ። 2 በላባም ዘንድ እንደቀድሞ ተወዳጅ አለመሆኑን ተረዳ። 3 እግዚአብሔርም ያዕቆብን፣ “ወደ አባቶችህ ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው። 4 ስለዚህ ያዕቆብ መንጋዎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤ 5 እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ ስለ እኔ ያለው አመለካከት እንደ ቀድሞ አለመሆኑን ተረድቻለሁ፤ ቢሆንም የአባቴ አምላክ አልተለየኝም፤ 6 መቼም ባለኝ አቅም አባታችሁን ማገልገሌን እናንተ ታውቃላችሁ። 7 አባታችሁ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ እየለዋወጠ አታልሎኛል፣ ሆኖም እንዲጎዳኝ እግዚአብሔር አልፈቀደለትም። 8 እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጉርጉሮቹ ይሆናሉ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጉርጉር ወለዱ’፤ ደግሞም፣ ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤ 9 ስለዚህ እግዚአብሔር የአባታችሁን ከብቶች ወስዶ ለእኔ ሰጠኝ። 10 እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ መሆናቸውን በሕልም አየሁ። 11 በዚያው ሕልም የእግዚአብሔር መልአክ፦ ‘ያዕቆብ’ ብሎ ጠራኝ፣ እኔም ‘እነሆ አለሁ’ አልሁ። 12 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘መንጋዎቹን የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸው መሆናቸውን ተመልከት፣ ላባ የፈጸመብህን በደል አይቻለሁ። 13 የድንጋይ ሐውልት በማቆም ዘይት ቀብተህ የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ይህን አገር ፈጥነህ ልቀቅ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመልሰህ ሂድ’ አለኝ።” 14 ራሔልና ልያም እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “ከአባታችን የምንወርሰው ድርሻ አለን? 15 እርሱ እኛን የሚያየን እንደ ባዕዳን አይደለምን? ደግሞም እኮ እኛን ሽጦናል፣ የተሸጥንበትንም ዋጋ ራሱ በልቶታል። 16 እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የነገረህን ሁሉ አድርግ።” 17 ከዚያም ያዕቆብ ተነሥቶ ልጆቹንና ሚስቶቹን በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤ 18 በመስጴጦምያ ካፈራው ሀብት ሁሉ ጋር ከብቶቹን በሙሉ ወደፊት አስቀደመ፣ ወደ አባቱም ወደ ይስሐቅ አገር፣ ወደ ከነዓን ምድር ጉዞውን ቀጠለ። 19 ላባ በጎቹን ሊሸልት ሄዶ ስለነበር፣ እርሱ በሌለበት ራሔል ከቤት የነበሩትን የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ ሄደች። 20 ያዕቆብ መሄዱን ለላባ ሳይገልጥለት አታሎት ሄደ፣ 21 የራሱ የሆነውን ሀብት ይዞ በፍጥነት ታጓዘ፤ የኤፍራጥስንም ወንዝ ተሻግሮ ወደ ኮረብታማው አገር ወደ ገለዓድ ሄደ። 22 ያዕቆብ መኮብለሉን ለላባ በሦስተኛው ቀን ተነገረው። 23 ከዘመዶቹ ጋር ሆኖ ያዕቆብን ተከታተለው፤ ሰባት ቀን ከተጓዙ በኋላ ገለዓድ በተባለው ተራራማ አገር ላይ ሊደርስበት ተቃረበ። 24 በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ለላባ በሕልም ተገለጠለትና “ያዕቆብን ክፉም ሆን ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ” አለው። 25 ያዕቆብ ገለዓድ በተባለው ኮረብታማ ስፍራ ድንኳኑን በመትከትል ሰፍሮ ሳለ ላባ ደረሰበት፤ ላባና ዘመዶቹም እዚያው ድንኳናቸውን ተክለው ሰፈሩ። 26 ከዚህ በኋላ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ስለምን እንዲህ አድርገህ አታለልኸኝ፤ ሴቶች ልጆቼንስ በጦርነት እንደተማረኩ ያህል ይዘሃቸው ለምን ሄድህ? 27 ሳትነግረኝ ተሰውረህ በመሄድ ለምን አታለልኽኝ? ነግረኸኝ ቢሆን በከበሮና በመስንቆ እየተዘፈነ በደስታ በሸኘሁህ ነበር። 28 ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን በመሳም እንድሰናበታቸው ባለማድረግህ የሞኝነት ተግባር ፈጽመሃል። 29 ጉዳት ሳደርስብህ እችል ነበር፣ ነገር ግን ባለፈው ሌሊት የአባትህ አምላክ፣ ‘ያዕቆብን ክፉም ሆነ ደግ አንድ ቃል እንዳትናገረው’ ብሎ አስጠነቀቀኝ፣ 30 ወደ ትውልድ አገርህ ለመመለስ ባለህ ብርቱ ፍላጎት እንደተለየኸኝ አውቃለሁ፣ ታዲያ የቤቴን ጣዖቶች የሰረቅኽብኝ ለምንድነው?” 31 ለላባ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ሴቶች ልጆችህን በኃይል ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ ብዬ ስለ ፈራሁ ነው በድብቅ የሄድኩት። 32 ነገር ግን ከእኛ መካከል የአንተን የጣዖት ምስል የሰረቀ ሰው ካለ ይሙት። የአንተ የሆነ አንዳች ነገር ከኔ ዘንድ ቢገኝ፣ አንተው ራስህ ዘመዶቻችን ባሉበት ፈልግና ውሰድ።” እንደዚህ ሲል ራሔል የጣዖታቱን ምስል መስረቋን ያዕቆብ አያውቅም ነበር። 33 ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን እንዲሁም ወደ ሁለቱ ደንገጡሮቹ ድንኳን ገባ፤ ነገር ግን ምንም አላገኘም። ከልያ ድንኳን ከወጣ በኋላ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ። 34 ራሔል ግን ጣዖቱቹን ወስዳ በግመሉ ኮርቻ ሥር በመሰወር በላያቸው ተቀምጣባቸው ነበር። ላባ በድንኳኑ ውስጥ ያለውን ጓዝ ሁሉ በርብሮ ምንም ነገር አላገኘም። 35 ራሔልም አባቷን፦ “በፊትህ ተነሥቼ መቆም ስላልቻልሁ፣ ጌታዬ አትቆጣ የወር አበባዬ መጥቶ ነው” አለችው፤ ስለዚህ በረበረ፤ የጣዖቱን ምስል ግን ማግኘት አልቻለም። 36 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ተቆጣ፤ ላባንም እንዲህ ሲል ወቀሰው፦ “እስቲ ወንጀሌ ምንድን ነው? ይህን ያህል የምታሳድደኝ ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው? 37 ዕቃዬን አንድ በአንድ በርብረሃል፤ ታዲያ የአንተ ሆኖ ያገኘኸው ዕቃ የትኛው ነው? ካለ፣ እስቲ በአንተም በእኔም ዘመዶች ፊት አቅርብና እነርሱ ያፋርዱን። 38 ሃያ ዓመት አብሬህ ኖሬአለሁ፤ በጎችህና ፍየሎችህ አልጨነገፉም፤ ከመንጋህም አንድ ጠቦት እንኳ አልበላሁም። 39 አውሬ የሰበረውንም ቢሆን እተካ ነበር፣ በቀንም ሆነ በሌሊት የተሰረቁትን ሁሉ ስታስከፍለኝ ኖረሃል። 40 ብዙ ጊዜ በቀን ሐሩርና በሌሊት ቁር እሠቃይ ነበር፤ በቂ እንቅልፍ ያገኘሁበት ጊዜ አልነበረም። 41 ሃያ ዓመት በቤትህ የኖርሁት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ዐሥራ አራት ዓመት ለሁለቱ ልጆችህ ብዬ አገለገልሁ፤ ስድስት ዓመት ስለመንጋዎችህ ስል አገለገልሁ፤ ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋውጠኽብኛል። 42 የአባቴ አምላክና እርሱም የሚፈራው የአብርሃም አምላክ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን ሰድደኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መከራዬን ዐይቶ፣ ልፋቴን ትመልክቶ ትናንት ሌሊት ገሠጸህ።” 43 ላባም ለያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እነዚህ ሴቶች የእኔው ልጆች ናቸው፤ ልጆቻቸውም የእኔ ናቸው፤ እነዚህም መንጋዎች የእኔ ናቸው፤ ይህ የምታየው ሁሉ የራሴ ነው፤ ታዲያ በእነዚህ ሴቶች ልጆቼና በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ዛሬ ምን ማድረግ እችላለሁ? 44 በል አሁን ቃል ኪዳን እንጋባ፤ ኪዳኑም በአንተና በእኔ መካከል ምስክር ይሁን።” 45 ያዕቆብም ድንጋይ ውስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፤ 46 ከዚያም ዘመዶቹን “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው። እነርሱም ድንጋይ እያመጡ ከመሩ፤ በክምሩም አጠገብ ምግብ በሉ። 47 ላባም ክምር ድንጋዩን ይጋርሠሀዱታ ብሎ ጠራው፤ ያዕቆብ ደግሞ ገለዓድ አለው። 48 ላባም “ይህ ክምር ድንጋይ በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለው። ገለዓድ ተብሎ የተጠራውም በዚሁ ምክንያት ነው፤ 49 ደግሞም ምጽጳ ተባለ ምክንያቱም ላባ እንዲህ ብሎአልና፤ “እንግዲህ ከዚህ በምንለያይበት ጊዜ እግዚአብሔር እኔንና አንተን ይጠብቀን፤ 50 ልጆቼን ብትበድላቸው ወይም ሌሎችን በላያቸው ብታገባ፣ ማንም ከእኛ ጋር ባይኖርም እንኳ እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ምስክር መሆኑን አትርሳ።” 51 ላባም ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ክምር ድንጋዩ እነሆ፤ በአንተና በእኔ መካካል ያቆምሁትም ሐውልት እነሆ፤ 52 ይህን ክምር ድንጋይ አልፌ አንተን ለማጥቃት ላልመጣ፣ አንተም ይህን ክምር ድንጋይና ይህን ሐውልት አልፈህ እኔን ለማጥቃት ላትመጣ፤ ይህ ክምር ድንጋይ ምስክር ነው፤ ይህም ሐውልት ምስክር ነው። 53 የአብርሃም አምላክ፣ የናኮር አምላክ፣ የአባታቸውም አምላክ በመካከላችን ይፍረድ።” ስለዚህ ያዕቆብ አባቱ ይስሐቅ በሚፈራው በእግዚአብሔር ማለ። 54 ያዕቆብ በኮረብታማው አገር ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው፤ እነርሱም ከበሉ በኋላ እዚያው አደሩ። 55 በማግስቱም ማለዳ ላባ የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆችን ስሞ መረቃቸው፤ ከዚያም ወደ አገሩ ተመለሰ።
ይህ ቃል የታሪኩን ትረካ መሥመር ለማቋረጥ ተጠቅሞአል በዚህ ጸሐፊው አዲስ ታሪክ ይጀምራል
ያዕቆብ የላባን ወንዳች ልጆች የሚሉትነ ሰማ
የላባን ወንዶች ልጆች ከመቆጣታቸው የተነሣ አጋንነው ይናገራሉ አት ያዕቆብ የወሰደው ነገር ሁሉ የአባታችን ነበር:: (ማጋነንና ገሃዳዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
አነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች በመሠረት አንድ ናቸው:: ሁለተኛው ያዕቆብ በላባን ፊት ያየውን ይገልጻል:: አት: “ያዕቆብም ላባን እንዳለተደሰተበት ተረዳ” (ተጓዳኝ ንጽጽር ይመልከቱ)
አባትህ ይስሐቅና አያትህ አብርሃም
ያዕቆብ መንጎቹ ወደተሠማሩበት መስክ እንዲመጡ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው
እነዚህ ሁለት አጫጭር ዐረፍተ ነገሮች ናቸው:: አት “ለመንጋው:: እንዲህም አላቸው” (የዐረፍተ ነገር ውቅር ይመልከቱ)
አባታችሁ በእኔ ደስተኛ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ
እናንተ የሚለው ቃል ራሔልንና ልያን ያመለክታል እንዲሁም ደግሞ ትኩረትን ይጨምራል፡፡ አት፡ “አባታችሁን ባለኝ ጉልበት ሁሉ እንዳገለገልሁ እናንተው ራሳችሁ ታውቃላችሁ” (ሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ዋሽቶኛል ወይም በፍትሃዊነት አላስተናገደኝም
ሊከፍለኝ የተናገረውን
ተገቢ ትርጉሞች 1 አካላዊ ጥቃት በማንኛውም መንገድ ለያዕቆብ መከራ መንስሄ በመሆን
ነጭ ምልክት ያላቸው እንስሳት
በጎቹ ወለዱ
ዝንጉርጉር ቀለም ያላቸው እንስሳት
ይህም እንዴት እግዚአብሔር የአባታችሁን እንስሳት ለእኔ እንደሰጠኝ ነው
ያዕቆብ ታሪኩን ለሚስቶቹ ለልያና ለራሔል መናገሩን ይቀጥላል
በሚጠቁበት ወራት
እዚህ “መንጋው” ሴት ፍዬሎችን ያመለክታል:: አት: “ሴት ፍዬሎች በሚጠቁበት” (ክፍልን ለሙሉና ሙሉውን ለክፍል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ዝንጉርጉር ትንሽ ነቁጣና ትልቅነቁጣ ያላቸው
ተገቢ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር በሰው መልክ ሲገለጥ 2) ከእግዚአብሔር መልእክተኞች አንዱሲገለጥ ሀረጉ በተክክል እስካልተገለጸ ለ”መልአክ” የሚንጠቀመውን መደበኛ ቃል በመጠቀም በቀላሉ እንደ “እግዚአብሔር መልእክተኛ” መተረጐም ተገቢ ነው::
እኔም መለስሁ
አዎን እየሰማሁ ነኝ ወይም አዎን ምንድነው? በዘፍጥረት 22: 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
የእግዚአብሔርም መልአክ ያዕቆብን መናገር ቀጠለ:: (ዘፍጥረት 31:1ዐ ይመልከቱ)
ይህ ቀና ብለህ ተመልከት ማለት ነው (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ “መንጋ” እንስት ፍዬሎች ብቻ ያመለክታል:: አት “የመንጋው እንስት ፍዬሎችን የሚያጠቋቸውን” (ክፍል ለሁሉና ሁሉን ለክፍል የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸው
ያዕቆብም ሐውልቱን ዘይፍ በመቀባት ለእግዚአብሔር የቀደሰው (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
የተወለድህበት ምድር
ይህ በተመሣሣይ ጊዜ ተናግረዋል ማለት አይደለም እንተስማሙ ያጸናል
ራሔልና ልያ በጥያቄ መልክ አባታቸው ሊሰጣቸው ምንም እንዳልቀረ አጥብቀው ይናገራሉ፡፡ አት፡ “ከአባታችን ልንወርሰው በፍጹም የቀረ ምንም ነገር የለም!” (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
አባታቸው እንዴት እንደሚያዩአቸው ያላቸውን ቁጣ በጥያቄ ይገልጸሉ:: አት: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ገቢራዊ ዓረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል አት አባታችን እንደ ሴት ልጆቹ ሳይሆን እንደባዕድ ሴቶች ያየናል:: (ቅኔ አዘል ጥያቄዎችና ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮች ይመልከቱ)
ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: ለራሱ ጥቅም ሽጦናል:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ላባን ለሴት ልጆቹ መስጠት የነበረበትን ገንዘብ በፍጹም ለራሱ መጠቀሙ የዱር አራዊት እንደ ምግብ ገንዘቡን እንደበሉት ተደርጐ ተነግሮአል:: አት: “በፍጹም ገንዘባችንን ተጠቅሞአል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይጠቀሙ)
ለእኛና ለልጆቻችን ይገባል
እዚህ አሁን የአሁን ጊዜ አይደለም ነገር ግን ለሚከተለውን አስፈላጊ ነጥብ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡
እግዚአብሔር የነገረህን ሁሉ አድርግ
ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ ወሰደ:: ወራሾች ስለሆኑ ወንዶች ልጆቹን ብቻ የጠቀሳል:: አት: “ልጆቹን” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ሁሉን ከብቶች ነዳ:: እዚህ “ከብቶች” ሁሉን የቤት እንስሳትን ይወክላል፡፡
በጳዳን አራም እያለ ያፈራቸውን ሌሎች ከብቶችንም
አባቱ ይስሐቅ ወደሚኖርበት አገር ወደ ከነዓን ሄዴ
ላባን የበጐቹን ጸጉር ሊያስቆርጥ በሄደበት ጊዜ
የኤፍራጥሰ ወንዝ ያመለክታል
ተጓዘ
ወደ ገለአድ ተራራዎች ወይም ወደ ገለአድ ተራራ
የወጡበትን ቀን እንደ አንድ ቀን መቁጠር የአይሁድ ለማድ ነው:: አት: “ከወጡበት ሁለት ቀናት በኋላ”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት አንድ ሰው ለላባን ነገረው ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮች ይመልከቱ
የቤተሰቡ መሪ ስለሆነ ያዕቆብ ብቻ ተጠቅሶአል ቤተሰቡ ከእርሱ ጋር እንደተጓዙ ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “ያዕቆብ ከሚስቶቹና የልጆቹ ጋር ኮበለለ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ላባን ይዞ ተነሣ
አሳደደው
ያዕቆብን ደርሶ ለመያዝ ላባን ሰባት ቀናት ተጓዘ
ያዘው
“ከዚያም” የሚለው ቃል የተጠቀመው ታሪኩን ወደ ላባን የሕይወት ዳራ መረጃ ለመቀየር ነው አት: “በዚያ ሌሊት እግዚአብሔር ለላባን ተገልጦ” (የዳራ መረጃዎች ይመልከቱ)
“ክፉ ሆነ ደግ” የሚለው ሀረግ የተጠቀመው “ምንም” ለማለት ነው፡፡ አት፡ ያዕቆብን ከመሄድ ለማቋረጥ ለመሞከር ምንም ነገር እንዳትናገር (See: Merism)
“ከዚያም” የሚለው ቃል የተጠቀመው ታሪኩን ወደ ያዕቆብናላባን የሕይወት ዳራ መረጃ ለመቀየር ነው:: አት: “ላባን ያዕቆብን በደረሰበት ጊዜ ያዕቆብ በኰረብታማው አገር ድንኳን ተክሎ ነበር: ከዚያም ላባንና ዘመዶቹ ደግሞ በኰረብታማው ገለዓድ አገር ድንኳን ተከሉ” (የዳራ መረጃዎች ይመልከቱ)
ያዕቆብ ቤተሰቡን ከራሱ ጋር ወደ ከነዓን ምድር መውሰዱ ልክ ያዕቆብ እንደ የጦር ምርኮኞችን እናም አሰገድዶአቸው እየወሰደ እንዳለ ላባን ይናገራል ላባን ስለተቆጣና ያዕቆብ ስላደረገው ነገር ጸጸት እንዲሰማው አግንኖ ይናገራል:: (ተመሣሣይ ንጽጽር የማጋነንና ገሃዳዊ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
በድብቅ ሸሸህ
በደስታ
እነዚህ መሣሪያዎች ሙዝቃን የሚገልጹ ናቸው፡፡ አት፡ “እናም በሙዝቃ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
የከበሮ ዓይነት ለምት የሚሆን አናት ያለው ዙሪያሙ ከብረት የተሠራና መሣሪያው በሚመታበት ጊዜ የሚርገበገብ የሙዝቃ መሣሪያ ነው ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ
እዚህ ወንዶች የልጅ ልጆች ወንድ ሆነ ሴት ሁሉን የልጅ ልጆችን ይወክላሉ:: አት: “የልጅ ልጆቼን እንዲስማቸው” (በወንዴ ጾታ የተጠቀሱ ሴት ጾታንም የመግለጽ አባባል ይመልከቱ)
በጅልነት አድርገሄዋል
ይህ የዚያን ጊዜ ማለተ አይደለም ነገር ግን ለሚከተለውን ጠቃሚ ነገር ትኩረት እንደሰጥበት ነው
እዚህ “እናንተ” ብዙና ከያዕቆብ ጋር ያሉትን ሁሉ ያመለክታል:: አት: “ሊጐዳችሁ የሚያስችለኝ ከእኔ ጋር ብዙ ሰዎች ነበሩ” (የሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
“ክፉ ሆነ ደግ” የሚለው ሀረግ የተጠቀመው “ምንም” ለማለት ነው፡፡ በዘፍጥረት 31:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት፡ “ያዕቆብን ከመሄድ ለማቋረጥ ለመሞከር ምንም ነገር እንዳትናገር” (See: Merism)
አንተ የሚለው ነጠላና ያዕቆብን ያመለክታል:: (የሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ ቤት ቤተሰብን ይወክላል:: አት: “ወደ አባትህና ሌሎች ቤተሰብህ ቤት ለመመለስ” (ክፍልን ሙሉና ሙሉውን ክፍል አድርጐ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ጣዖቶቼን
በድብቅ የወጣሁት ልጆችህን ከእኔ ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ ብዬ ስለፈራሁ ነው፡፡
ይህ በአዎንታዊ መንገድ መገለጽ ይችላል አት ጣዖቶችህን የሰረቀ ማንም ቢገኝ እንገድላለን (ምጸት ይመልከቱ)
የእኛ የሚለው ቃል የያዕቆብ ዘመዶችንና የላባን ዘመዶች ያመለክታል:: ሁሉም ዘመዶች ፍትሃዊና ግልጽ መሆኑን ለማረጋገጥ ያዩታል (ሁሉ አቀፍ አንደኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)
በእኛ ዘንድ ካለው ያንተ የሆነውን ፈልግና ውሰድ
ይህም ታሪኩን ወደ ያዕቆብ ሕይወት ዳራ መረጃ ይቀይራል (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)
ዘለፋንና ባላን ያመለክታል
ጣዖታቱን አላገኘም
ከዚያም የሚለው ቃል ታሪኩን ወደ ራሔል ሕይወት ዳራ መረጃ የቀይራል (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)
ሰው እንዲቀመጥበት በጋማ እንስሳት ጀርባ የሚደረግ መቀመጫ ነው
አንድን ሰው “ጌታዬ” ብሎ መጥራት የማክበር መንገድ ነው
ይህ ከማሕጸንዋ ወራዊ ደም የሚፈስበት ጊዜ ውስጥ እንዳለች ያለመክታል:: (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ በተዘዋዋሪ አንድን ነገር ስለመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ያዕቆብ ላባንን እንዲህ አለ
ወንጄሌ ምንድነው እና ኃጢአቴ ምን ሆን የሚሉ ሀረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ያዕቆብ ላባንን ምን ስህተት እንደሠራ ይጠይቀዋል አት ይህን ያህል በጽኑ የምታሳድደኝ ምን ስህተት ቢፈጽም ነው? (ተጓዳኝ ተነጻጻሪ አባባል ይመልከቱ)
እዚህ “ጽኑ” የሚለው ቃል ላባን በማጣደፍ ያዕቆብን ለመያዝ ባለው ተነሣሽነት እንዳሳደደው ይገልጻል (ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ)
ያንተ ሆኖ ያገኘሄው ዕቃ የትኛው ነው?
እዚህ እኛ የሚለውቃል የያዕቆብ ዘመዶችና የላባንን ዘመዶች ያመለክታል:: አት: ያገኘሄውን ማንኛውንም ነገር በዘመዶቻችን ፊተ አቅርብ (አካታች አንደኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ “ሁለታችን” ያዕቆብንና ላባን ያመለክታል:: “ይፍረዱን” የሚለው አባባል ከክርክሩ የትኛው ትክክል እንደሆነ ይወስኑ ማለት ነው፡፡
ያዕቆብ ለላባን መናገሩን ቀጠለ
2ዐ ዓመታት (ቁጥሮች ይመልከቱ)
እንስት የበግ ጠቦት
በእርግዝና ወቅት የተቀጨ ወይም ሞቶ የተወለደ ጠቦት አልነበረም ማለት ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊገለጽ ይችላል አት አውሬ ከእንሰሳትህ አንዱን በገደለ ጊዜ በድኑን ለአንተ አምጥቼ አላውቅም (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ያዕቆብ ከመንጋው የላባንን ሙት እንስሳት ምትክ መቁጠር በጫንቃው እንደተሸከመው ሽክም እንደነበር ተደርጐ ተገልጾአል:: አት: “ከመንጋህ እንደጠፋ ከመቁጠር ከመንጋዬ እንደጠፋ ቆጥረዋለሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በሞቃትና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ መሠቃየት የአየር ሁኔታዎች ያዕቆብ እንደ አውሬዎች እንደበሉ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት በቀን ሐሩርና በሌሊት ቁር ከመንጋዎችህ ጋር ነበርሁ (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ያዕቆብ ለላባን መናገሩን ቀጠለ
እነዚህ 2ዐ ዓመታት (ቁጥሮች ይመልከቱ)
14 ዓመታት (ቁጥሮች ይመልከቱ)
መክፈል ያለበትን አሥር ጊዜ ለዋውጦብኛል:: በዘፍጥረት 31:7 ደመወዜን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
የአብርሃምና የአባቴ የይስሐቅ አምላክ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ
እዚህ “አባቴ” የሚለው ቃል አባቱን ይሰሐቅን ያመለክታል::
እዚህ “ፍርሃት” ለእግዚአብሔር ያለውን ፍርሃት ያመለክታል፡፡
ይህ ምንም አለመኖር ማለት ነው:: አት: “ፍጹም ባዶ” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
መከራ የሚለው ረቂቅ ስም መከራ አየ በሚቶል ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር ልፋቴን አይቶ እንዴት መከራ እንዳሳየሄኝ ተመልክቶ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ላባን ምንም ማድረግ እንደማይችል አግንኖ ለመቅለጽ ጥያቄ ይጠቀማል ይህ አጋናኝ ጥያቄ በዐረፍተነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ነገር ግን ከእኔ ጋር ወደ ኋላ ለመመለስ በልጆቼና በልጅ ልጆቼ ምንም ላደርግ አልችልም” (አግናኝ ጥቃቄዎች ይመልከቱ)
እዚህ “ምስክር” የሚለው ቃል ሰውን አያመለክትም ነገር ግን ያዕቆብና ላባ የሚገቡትን ቃልኪዳን የሚያመለክትና በምሳለያዊነት የተጠቀመ ነው:: ምስክሩ ሁለቱ በሰላማዊ መንገድ ስስማሙ እንደተገኘ ሰው ተደርጐ ተነግሮአል (ሰውኛ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ በክስተቱ ማብቂያ ያቆመው ትልቅ ድንጋይ ሲሆን አስፈላጊ ክስተት እንደተከናወነ ለማመለከት ነው
ድንጋዩን አንዱን በአንዱ ላይ በማድረግ ከመሩ
አብሮ ምግብን መመገብ ቃል ኪዳን መፈጸሚያ አካል አንዱ ነው የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የማከተውን እንደግርጌ ማስናታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: “ይጋርሠሀዱታ” የሚለው ስም በላባን ቋንቋ “ክምር ምስክርነት” ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የማከተውን እንደግርጌ ማስናታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: “ገለዓድ” የሚለው ስም በላባን ቋንቋ “ክምር ምስክርነት” ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ድንጋዮች በእርግጥ እንደሰው ምስክር ሊሆኑ አይችሉም:: አት: “ይህ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ማስታወሻ ይሆናል” (በሰውኛ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የማከተውን እንደግርጌ ማስናታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: “ገለዓድ” የሚለው ስም በላባን ቋንቋ “ክምር ምስክርነት” ማለት ነው:: በዘፍጥረት 31:47 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የማከተውን እንደግርጌ ማስናታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: “ምጽጳ” የሚለው “የመጠበቂያ ማማ” ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እዚህ “አለመተያየት” በተለያየን ይወክላል:: አት “በተለያየን ጊዜ” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት ስለመጠቀም ይመልከቱ)
እዚህ “እኛ” ያዕቆብንና ላባን ያመለክታል:: አት: “ማንም የሚያየን ባይኖር”
“ተመልከት” “አስተውል” “ለሚናገረው ነገር ትኩረት ስጥ”
የሰላም ስምምነታቸውን በሚመለከት እነዚህ የድንጋይ ክምሮች ለላባና ለያዕቆብ የማስታወሻና ድንበር ምልክቶች ናቸው:: እነዚህ እንደሰው ምሰክሮች እንደሆኑ ተደርጐ ተነግሮአል (በሰውኛ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ “ፍርሃት” ይስሐቅ ለእግዚአብሔር ያለውን አክብሮትና ያንንም በመታዘዝ መግለጹን ያመለክታል፡፡
አብሮ ምግብ መብላት አብሮ ቃል ኪዳን የመግባት አካል ነው የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ቁጥር 55 በመጀመሪያው የዕብራይስጡ መጽሐፍ የምዕራፍ 32 የመጀመሪያ ቁጥር ነው ነገር ግን በአብዛኛዎቹ ዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሶች የምዕራፍ 31 የመጨረሻ ቁጥር ነው በዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሶች የተጠቀመውን የቁጥር አቀማመጥ በቋንቋዎ እንዲጠቀሙ ይመከራል
አዎንታዊና ጠቃሚ ነገሮች ለአንድ ሰው እንዲደረጉ መሻትን የሚገልጽ ማለት ነው
1 ያዕቆብ በጉዞ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መላእክት በመንገድ ተገናኙት። 2 ባያቸውም ጊዜ፤ “ይህ የእግዚአብሔር ሰፈር ነው” አለ፤ የዚያንም ቦት ስም መሃናይም አለው። 3 ያዕቆብም በኤዶም አገር ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤ 4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፤ “ጌታዬን ዔሳውን እንዲህ ትሉታላችሁ፤ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ብሎአል በሉት፤ ከላባ ዘንድ ተቀምጬ እስካሁን ድረስ እዚያው ኖርሁ፤ 5 ከብቶች፣ አህዮች፣ የበግና የፍየል መንጎች እንደዚሁም የወንድን የሴት አገልጋዮች አሉኝ፤ አሁንም ይህን መልእክት ለጌታዬ መላኬ በአንተ ዘንድ ሞግስ አገኛለሁ በሚል ተስፋ ነው።’” 6 የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንት ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት። 7 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እጅግ በመፍራት ተጨነቀ፤ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች በሁለት ክፍል መደባቸው፤ እንዲሁም በጎቹን፣ ፍየሎቹን፣ ከብቶቹንና ግመሎቹን በሁለት በሁለት መደባቸው። 8 ይህንንም ያደረገው፦ “ዔሳው የመጀመሪያውን ክፍል ቢያጠቃ፣ ሌላው ክፍል ሊያመልጥ ይችላል” ብሎ በማሰብ ነው። 9 ያዕቆብ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ፣ የአባቴ የይስሐቅ አምላክ ሆይ፣ ‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመልስ፣ እኔም በጎ ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፣ 10 እኔ ባሪይህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በስተቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሠራዊት ሆኛለሁ። 11 ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁኝ፤ 12 ነገር ግን አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።” 13 በዚያችም ሌሊት ያዕቆብ እዚያው አደረ፤ ካለው ሀብት ለወንድሙ ለኤሳው እጅ መንሻ እንዲሆኑ እነዚህን መረጠ፦ 14 ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችና ሃያ አውራ ፍየሎች፣ ሁለት መቶ እንስት በጎችና ሃያ አውራ በጎች፣ 15 ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፣ አርባ ላሞችና ዐሥር ኮርማዎች፣ ሃያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባት አህዮች። 16 እነዚህንም በየመንጋው ለይቶ፣ የሚነዱአቸውን ጠባቂዎች መደበላቸው፤ ጠባቂዎችንም እናንተ ቀድማችሁ ሂዱ፣ መንጋዎቹንም አራርቃችሁ ንዱአቸው” አላቸው። 17 ቀድሞ የሚሄደውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፤ ዔሳው አግኝቶህ ‘የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ 18 ‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ከበስተኋላችን እየመጣ ነው’ ብለህ ንገረው 19 እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎቹን የሚነዱትን ሌሎቹንም ሁሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ ‘ዔሳውን ስታገኙት ይህንኑ ትነግሩታላችሁ፤ 20 በተጨማሪም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ በሉት። ይህንንም ያዘዘው፣ ‘ዔሳው ከእኔ ጋር ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል’ ብሎ ስላሰበ ነበር። 21 ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከእርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩ ቦታ አደረ። 22 በዚያኑ ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ ሁለቱን ሚስቶቹን፣ ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና ዐሥራ አንዱን ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ። 23 ወንዙን አሻግሮ ከሸኛቸው በኋላ፣ ጓዙን ሁሉ ሰደደ። 24 ያዕቆብም ብቻውን እዚያ ቀረ፤ አንድ ሰውም እስኪነጋ ድረስ ሲታገለው አደረ። 25 ያም ሰው ያዕቆብን ታግሎ ማሸነፍ እንዳቃተው በተረዳ ጊዜ፣ የጭኑን ሹልዳ መታው፣ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤ 26 በዚያን ጊዜ ሰውዬው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለሆን ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው። 27 ሰውዬውም፣ “ስምህ ማን ነው?” አለው። እርሱም፣ “ያዕቆብ ነው” አለ። 28 ሰውዬውም፣ “ከእግዚአብሔርም ከሰዎችም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና ከእንግዲህ ስምህ እስራኤል እንጂ ያዕቆብ አይባልም” አለው። 29 ያዕቆብም፣ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። ሰውዬውም፣ “ስሜን ለማወቅ ለምን ፈለግህ?” አለው፤ በዚያም ስፍራ ባረከው። 30 ስለዚህ ያዕቆብ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ዐይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል አለው። 31 ጵኒኤልንም እንዳለፈ ፀሐይ ወጣችበት፣ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። 32 ከዚህም የተነሣ የእስራኤል ልጆች ሹልዳን ከጭኑ ጋር የሚያገናኘውን ሥጋ አይበሉም፤ ምክንያቱም ያዕቆብ ከሰውዬው ጋር ሲታገል ሰውዬው ሹልዳውን መትቶት ስለነበር ነው።
ተርጓሚዎች በግርጌ ማስታወሻዎች ሊጨምሩ ይችላሉ:: መሃናይም የሚለው ስም “ሁለት ሰፈሮች” ማለት ነው
ይህ በኤዶምያስ ግዛት ተራራማው ቦታ ነው:: ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ::
ይህ በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ አለው:: ቀጥታው ጥቅስ እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ ‘ይህ ለጌታዬ ለዔሣው ሊነግር የሚወደው ነው:: እስከዚህ እንዳለሁት ……በፊቱ’” (ጥቅስን በጥቅስ ውቅጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ያዕቆብ ወንድሙን ጌታው አድርጐ በማቅረብ የትህትና ቃል ይጠቀማል
ያዕቆብ ራሱን እንደአገልጋዩ በማድረግ የትህትና ቃል ይጠቀማል
ሞገስ ማግኘት የሚለው ሀረግ በሌሎች ሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ማትረፍን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው አት “መቀበልህን እንዲታረጋግጥልኝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ተመሣሣይ ምትክ ቃላትና ዘይቤያዊ አባባሎች ይመልከቱ)
4ዐዐ ሰዎች ቁጥሮች ይመልከቱ
አንድ ሰው በራሱ ወይም ከሌሎች ሥጋት የሚፈጥር ጉዳት ሲደረስበት የማሰማው ስሜት ነው
ተስፋ መቁረጥ ወይም መረበሽ
እዚህ ሠፈር ሰዎችን ይወክላል አት በአንዱ ሠፈር ባለው ሰው አደጋ ቢጣል በሌላው ሠፈር ያለው ሰው ያመልጣል፡፡ (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ለተላያዩ አማልክት ሳይሆን ሁሉም ያመለኩትን አንድ እግዚአብሔርን ያመለክታል አት የአያተ የአብርሃምና የአባተ የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር (ግምታዊ እውቀትና ጥብቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ በጥቅ ውስጥ የሚገኝ ጥቅሰ ነው:: በተዘዋዋሪ ጥቅስ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ወደ አገረና ወደ ሕዝቤ እንድመለስና በጐ ነገርንም አደርግልሃለሁ ያልከው እግዚአብሔር”
ወደ ቤተሰብህ
መልካም ነገር አደርግልሃለሁ ወይም በመልካምነት እንከባከብሃለሁ
ረቂቅ ስሞች ቸርነትና ታማኝነት እንደ ቸር እና ታዛዥ ሊገለጹ ይችላሉ አት እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረክልኝ የቃልኪዳን ታማኝ አይደለሁም ወይም ታዛዥ አይደለሁም (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተነገር ይመልከቱ)
“እኔ” የሚለው በትህትና ቃል ሲገለጽ ነው
ሆንሁ የሚለው ሐረግ ያለውን ሀብት የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው:: አት: “አሁን ግን ከእኔ ጋር በሁለት ክፍል ሠራዊት በቂ ሰዎች መንጋዎችና ሀብት አሉኝ” ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ
አትርፈኝ
እዚህ “እጅ” ጉልበትን ያመለክታል ሁለቱም ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ሁለተኛው የሚገልጸው ያዕቆብ የሚያስበው ወንድመ ዔሣው እንደሆነ ነው፡፡ አት፡ ከወንድሜ ከዔሣው ጉልበት ወይም ከወንድሜ ከዔሣው (ተመሣሣይ ምትክ ቃል ወይም ተጓዳኝ ንጽጽር ይመልከቱ)
እንደሚያጠፋ ፈርቼያለሁና
ይህ በጥቅስ ውስጥ ያለ ጥቅስ ነው እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ነገር ግን አንተ ራስህ አብለጽግሃለሁ እናም የዘረንም ቁጥር..” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና በዘዋዋሪ ጥቅችን ይመልከቱ)
መልካም ነገርን አደርግልሃለሁ ወይም በመልካምነቴ አሳይሃለሁ
የያዕቆብን ዘር ቁጥር እጅግ ብዙ ማድረጉ ቁጥሩ እንደ ባህር አሸዋ ቁጥር እንደሚሆን ተደርጐ ተነግሮአል (ተመሣሣይ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት: “ያም ከቁጥራቸው የተነሣ ማንም መቁጠር እስከማይችል” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
2ዐዐ (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
20 …. 30 …. 40 ….10 (ቁጥሮች ይመልከቱ)
እየጠቡ ያሉ ለጋ እንስሳት
እዚህ “በእነሱ እጅ” በእነሱ ቁጥጥር ሥር አደረገ ማለት ነው:: አት በየወገኑ ከፈላቸው እናም እያንዳንዱን መንጋ በእያንዳንዱ ባሪያ ቁጥጥር ሥር አደረገ (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንዱ መንጋ ከሌላው መንጋ በርቀት እንዲጓዝ አድረጉ
አዘዘው
ይህ በጥቅስ ውስጥ ያለ ጥቅስ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “የማን ነህ? ወዴትስ ተሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው? ብሎ ቢጠይቅህ” (ጥቅስ በጥቅስ ውስጥ እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶች ይመልከቱ)
ጌታህ ማን ነው?
በፊትህ ያለው የዚህ ሁለ ከብት ባለቤት ማን ነው?
ይህ በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ ነው በተዘዋዋሪ ጥቅስ መልክ ሊገለጽ ይችላል፤ አት፤ “በዚያን ጊዜ እነዚህ ሁሉ የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሣው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ሊገናኝህ ከበስተኋላችን እየመጣ ነው፤ ብለህ እንዲትነግረው እፈልጋለሁ::” (ጥቅስ በጥቅስ ውስጥ እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶች ይመልከቱ)
የዕቆብ ራሱን ትህትናን በተሞላ መንገድ የዔሣው ባሪያ አድርጐ ያቀርባል
ያዕቆብ በትህትና ዔሣውን እንደ ጌታው መቁጠሩን ያመለክታል
እኛ የሚናገረውን ባሪያ ያመለክታል እናም ሌሎች ባሪያዎችም ለዔሣው እጅ መንሻ ይዘው እየመጡ እንዳለ ይገለጻል (ብዙና ነጠላ “እኛ” ይመልከቱ)
ሁለተኛውን ቡድን አዘዘ
አማራጭ ተገቢ ትርጉሞች 1) “ደግሞም እንዲህ ትነግሩታላችሁ ባሪያህ ያዕቆብ” 2) “ደግሞም እንዲህ ትላላችሁ ባሪያህ ያዕቆብ”
አረጋጋው ይሆናል ወይም ቁጣው እንዲርቅ አደርግ ይሆናል
በርኀራኄ ይቀበለኛል
እዚህ እጅ መንሻ እጅ መንሻውን ይዘው የሄዱ ባሪያዎች ይወክላል (ምትክ አባባሎችን የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ “ራሱ” ያዕቆብ ከባሪያዎቹ ጋር እንዳለሄደ አበክሮ ይናገራል (ተጣቃሽ ተውላጤ ስም ይመልከቱ)
ሁለት ባሪያ/አገልጋይ ሚስቶቹ፤ ዘለፋና ባላ ማለት ነው
በወንዝ ጥልቅ ያልሆነ በቀላሉ የሚያሻግር ቦታ
ይህ የወንዝ ስም ነው ስሞችን እንዴት እንደሚተረጉሙ ይመልከቱ
ያለውን ነገር ሁሉ
ንጋት ድረስ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ልገለጽ ይችላል፤ አት: “በሚታገልበት ጊዜ የሚታገለው ሰው የያዕቆብን ሹልዳ ጐዳው” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ከዳሌ ጋር የተያያዘ ላይኛው የእግር አካል ነው
ጸሐይ ከመውጣትዋ በፊት
በአንድ ሰው ላይ በረከትን ማዘዝና ለዚያ ሰው መልካም ነገር እንዲሆኑለት ማድረግ ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ልገለጽ ይችላል፤ አት: “በእርግጥ አልለቅህም መጀመሪያ ባርከኝና ከዚያም እለቅሃለሁ” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ) (ድርብ አሉታዊ አባባሎች ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የግርጌ መስታወሻ እንደሚከተለው ሊጨምሩ ይችላሉ እስራኤል የሚለው ስም ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ማለት ነው ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ
ሰዎችን በገሃድ የሚገልጽ ነው
እርሱም ስለ ስሜ ለምን ተቀጠይቃለህ አለው ይህ አግናኝ ጥያቄ ያዕቆብን የሚያደነግጠው የሚገሥጸውና በእርሱና ከእርሱ ጋር ሲታገል በቆየው ሰው መካከል ምን እንደተከሰተ እንዲያስብ የሚያደርገው ነው:: አት: “ስሜን አትጠይቅ” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የግርጌ መስታወሻ እንደሚከተለው ሊጨምሩ ይችላሉ:: “ጵንኤል” የሚለው ስም “የእግዚአብሔር ፊት” ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)፡፡
“ፊት ለፊት” ሁለት ሰዎች በቅርበት በአካል የሚተያዩበት ማለት ነው::
ይህ በሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ሕይወቴን አትርፎአታል:: (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ታሪኩ ወደ እስራኤል ዘር ዳራ ትረካ እንተለወጠ አመላካች ነው (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)
ሹልዳን ከጭኑ ጋር የሚያገናኝ የጡንቻ ሥጋ ያመለክታል
ሲታገል ተነክቶ ነበር
1 ያዕቆብ አሻግሮ ተመለከተ፤ እነሆ፣ ዔሳው አራት መቶ ሰዎች አስከትሎ እየመጣ ነበር። ስለዚህ ያዕቆብ ልጆቹን ለልያ ለራሔልና ለሁለቱ አገልጋዮቹ አከፋፈላቸው። 2 ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ። 3 እርሱ ራሱም ቀድሞአቸው ሄደ፤ ወንድሙም ዘንድ እስኪደርስ ድረስ ሰባት ጊዜ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ። 4 ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጦ ሄዶ አቀፈው፤ በአንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። 5 ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን ዐየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ አብረውህ ያሉ እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። 6 በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሴት አገልጋዮችና ልጆቻቸው ቀርበው እጅ ነሡ፤ 7 ከዚያም ልያና ልጆቿ መጥተው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል መጡ፤ እነርሱም ቀርበው እጅ ነሡ። 8 ዔሳውም፣ “ወደ እኔ ተነድቶ የመጣው ይህ ሁሉ መንጋ ምንድነው?” አለው። ያዕቆብም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ በአንተ ዘንድ ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው። 9 ዔሳው ግን፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እኔ በቂ አለኝ፤ የራስህን ለራስህ አድርገው” አለው። 10 ያዕቆብም፣ “የለም፣ እንዲህ አይደለም፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፣ እጅ መንሻዬን ተቀበል፤ በመልካም ሁኔታ ተቀብለኸኝ ፊትህን ማየት መቻሌ ራሱ፣ የእግዚአብሔርን ፊት የማየት ያህል እቆጥረዋለሁ። 11 እግዚአብሔር በቸርነቱ አሟልቶ ስለ ሰጠኝ የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝና ያቀረብሁልህን እጅ መንሻ እባክህ ተቀበለኝ” አለው። ያዕቆብ አጥብቆ ስለለመነው፣ ዔሳው እጅ መንሻውን ተቀበለ። 12 ዔሳውም፣ “እንግዲህ እንሂድ፤ እኔም ከአንተ ቀድሜ እሄዳለሁ” አለው። 13 ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ እንደምታየው ልጆቹ ይህን ያህል የጠኑ አይደሉም፣ ለሚያጠቡት በጎችና ጥገቶች እንክብካቤ ማድረግ አለብኝ፤ እንስሳቱ ለአንዲት ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ በሙሉ ያልቃሉ። 14 ስለዚህ ጌታዬ፣ አንተ ቀድመኸኝ ሂድ፤ እኔም በምነዳቸው እንስሳትና በልጆቹ ጉዞ አቅም ልክ እያዘገምሁ ሴይር ላይ እንገናኛለን” 15 ዔሳው፣ “እንግዲያስ ከሰዎቼ ጥቂቶቹን ልተውልህ” አለው። ያዕቆብ ግን፣ “ለምን ብለህ? በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘቴ ይበቃኛል” አለው። 16 ስለዚህ ዔሳው በዚሁ ዕለት ወደ ሴይር ለመመለስ ተነሣ። 17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ። 18 ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም በሰላም ደረሰ፤ በከተማይቱም ፊት ለፊት ሰፈረ። 19 ድንኳኑን የተከለበትንም ቦታ የሴኬም አባት ከነበረው ከኤሞር በመቶ ጥሬ ብር ገዛው፤ 20 በዚያም መሠዊያ አቁሞ፤ ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው።
“እነሆ” የሚለው ቃል ለሚያስደንቀው ለታሪኩ አድስ ክፍል ትኩረት እንዲንስጥ ያደርጋል
400 ሰዎች (ቁጥሮች ይመልከቱ)
ይህ እያንዳንዷ ሴት ተመሣሣይ ቁጥር ልጆች እንዲኖራት ያዕቆብ ልጆቹን አከፈላቸው ማለት አይደለም እያንዳንዱ ልጅ ከእናቱ ወይም ከእናትዋ ጋር የሆን ዘንድ ያዕቆብ ለጆቹን አከፋፈላቸው (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“አገልጋይ ሚስቶች” ዘለፋንና ባላን ያመለክታል
እዚህ ራሱ የሚለው ያዕቆብ ራሱ በሌሎች ፊት ቀድሞ እንደሄደ ትኩረት ይሰጣል (ተጣቃሽ ተውላጤ ስም ይመልከቱ)
ጐንበስ ማለት አንድን ሰው በትህትና መቀበልንና ማክበርን ይገልጻል (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ያዕቆብን ሊገናኝ
ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ዔሣው በያዕቆብ ላይ እጆቹን ጠምጥሞ አቀፈው እናም ሳመው”
ይህ በግልጽ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ከዚያም እንደገና በመተያየታቸው ተደስተው ዔሣው ያዕቆብ አለቀሱ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ከያዕቆብ ጋር ያሉ ሴቶቹንና ልጆቹን አየ
የአንተ አገልጋይ የሚለው ሀረግ ያዕቆብ ራሱን በትህትና ያቀረበው መንገድ ነው:: አት: “እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ሴት አገልጋዮች፡፡ ባላንና ዘለፋን ያመለክታል፡፡
በሌላ ሰው ፊት ትህትናንና አክብሮትን የሚያሳይ ምልክት ነው:: (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
“ይህ ሁሉ” የሚለው ሀረግ ያዕቆብ በየቡድኑ በባሪያዎች ለዔሣው የላከውን ስጦታዎች ያመለክታል:: አት: “እነኛ የተለያዩ ቡድኖች ሁሉ እንዲገናኙኝ ለምን ላክሃቸው?”
ሞገስ ማግኘት የሚለው ሀረግ በአንድ ሰው ተቀባይነትን ማረጋገጥ የሚል ትረጉም የያዘ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው እንዲሁም ደግሞ ፊት ፍርድን ወይም ግማገማን ይወክላል አት አንተ ጌታዬ እንዲትደሰትብኝ ነው (ፈሊጣዊና ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ጌታዬ ዔሣው በትህት መንገድ ዔሣው የተገለጸበት ነው:: (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እንስሳት ወይም ንብረት የታወቁ ቃላት ናቸው:: አት: “በቂ እንስሳት አለኝ ወይም በቂ ንብረት አለኝ” (ድብቅ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሞገስ ማግኘት የሚለው ሀረግ በአንድ ሰው ተቀባይነትን ሰለማኘት የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው እዚህ ዓይን የማየት ምትክ ቃል ሲሆን ማየት ግምገማውን የሚገልጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው:: አት: “በእኔ የተደሰትህ እንደሆነ” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የሊጣዊና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“እጅ” ያዕቆብን ያመለክታል አት ይህ ለአንተ የሚሰጠው እጅ መንሻዬ ነው (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እንደ አድስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “በእርግጥም እጅ መንሻዬ”
ይህ ተመሣሣይ አባባል ግልጽ አይደለም ተገቢ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው 1 እግዚአብሔር ይቅር እንዳለለት ዔሣውም ይቅር እንዳለው ያዕቆብ ደስተኛ ነው ወይም 2 ያዕቆብ እግዚአብሔርን በመገናኘቱ እንደተደነቀው ሁሉ ዔሳውን በመገናኘቱ ተደንቆአል 3 ያዕቆብ በእግዚአብሔር መገኘት ራሱን እንዳዋረደው ሁሉ በዔሣው ፊት ራሱን ያዋርዳል (ተመሣሣይ አባባሎችን ይመልከቱ)
እዚህ ፊት ዔሣውን ያመለክታል ይህ ፊት በመባል ሊተረጐም ይችላል፤ ምክንያቱም “ፊት” የሚለው ቃል በዘፍጥረት 32:3ዐ “የእግዚአብሔር ፊት” እና “ፊት ለፊት” ለመግለጽ ተጠቅሞአል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ይህም አገልጋዮቼ ያመጡልህ” (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር በቸርነቱ ስለመለከተኝ ወይም እግዚአብሔር እጅግ በጣም ስለባረከኝ
አንድን ሥጦታ ላለመቀበል መገዳደር ነገር ግን ከዚያ በኋላ ሰጪው እንዳያዝን መቀበል የተለመደ ባህላዊ መንገድ ነው
ይህ በትህትናና በመደበኛ መንገድ ዔሣውን ማመልከት ነው:: አት: “አንተ ጌታዬ ታውቃለህ” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ትርጉሙም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አት፡ “በፍጥነት ለመጓዝ ልጆች ገና የጠኑ አይደሉም”:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ለአንድ ቀን እንኳ በፍጥነት እንዲጓዙ ቢናጣድፋቸው” (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ያዕቆብ ራሱን በመደበኛና በትህትና መንገድ የሚገልጸው ነው:: አት: “ጌታዬ እኔ ባሪያህ ነኝ” (ከፊቴ ቀድመህ ሂድ አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
“በሚነዱአቸው እንስባት እርምጃ ፍጥነት መጠን”
በኤዶም ግዛት የሚገኝ ተራራማ ሥፍራ ነው፡፡ በዘፍጥረት 32 3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ዔሣው ሰዎቹን መተው እንደሌለበት ለማጽናት ያዕቆብ ጥያቄን ይጠቀማል:: አት: “ይህን አታድርገው” ወይም “ይህን ማድረግ አይገባህም” (አግናኝ ጥያቄዎች ይመልከቱ)
ይህ በመደበኛና በትህትና ዔሣውን የሚግለጽ ነው:: አት: “አንተ ጌታዬ” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች እንደግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ ሱኮት የሚለው ስም መጠለያዎች ማለት ነው ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ
ይህ የተሠራው ቤት ለቤተሰቡም እንደሆነ ያመለክታል፡፡ አት፡ “ለራሱና ለቤተሰቡ ቤት ሠራ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ለሚጠብቁአቸው እንስሳት
ይህ አድስ የታሪኩን አካል ይጀምራል በሱኮት ካረፈ በኋላ ያዕቆብ ምን እንዳደረገ ጸሓፊው ይገልጻል
ያዕቆብ ….. ደረሰ ….. ሠፈረ
የእርሱም ቤተሰብ ከእርሱ ጋር እንደነበር ግልጽ ነው (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በቅርበት ሠፈረ
ከፊል ቦታ
የአንድ ሰው ስም ነው
ሴኬም የሰውዬውና የከተማይቱ ስም ነው
1ዐዐ (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የግርጌ ማስታወሻ እንደሚከተለው ሊጨምሩ ይችላሉ አት ኤል ኤሎሄ የሚለው ቃል እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
1 ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ሴት ልጅ ዲና፤ አንድ ቀን የዚያን አገር ሴቶች ለማየት ወጣች። 2 የአገሩ ገዥ የኤዊያዊ የኤሞር ልጅ ሴኬም ባያት ጊዜ ያዛት በማስገደድም ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ። 3 ልቡ በያዕቆብ ልጅ በዲና ተማረከ፤ ልጅቷንም በጣም ወደዳት፤ በጣፈጠም አንደበት አናገራት። 4 ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፣ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው። 5 ያዕቆብ የልጁን የዲናን ክብረ-ንጽሕና ሴኬም እንደደፈረ ሰማ፤ ነገር ግን ወንዶች ልጆቹ የከብት መንጋ ይዘው ተሰማርተው ስለነበር፣ እነርሱ እስኪመጡ ዝም ብሎ ቆየ፤ 6 ከዚያም የሴኬም አባት ኤሞር፣ ያዕቆብን ሊያነጋግረው ወጣ። 7 የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም የተፈጸመውን ድርጊት እንደሰሙ ወዲያውኑ ከመስክ መጡ፤ ሴኬም መደረግ የማይገባውን አስነዋሪ ነገር በእስራኤል ላይ በመፈጸም የያዕቆብን ልጅ ስለደፈረ አዘኑ እጅግም ተቆጡ። 8 ኤሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን በጣም ወዶአታል፤ ስለዚህ እንዲያገባት ፍቀዱለት፤ 9 በጋብቻ እንተሳሰር፣ ሴት ልጃችህን ስጡን፣ የእኛንም ሴቶች አግቡ። 10 አብራችሁንም መኖት ትችላላችሁ፤ አገራችን አገራችሁ ናት፣ ኑሩባት፤ ነግዱባት፣ ሀብት ንብረትም አፍሩባት። 11 ሴኬም ደግሞ የዲናን አባትን ወንድሞች እንዲህ አላቸው። “በእናንተ ዘንድ ሞገስ ላግኝ እንጂ የተጠየቅሁትን ሁሉ እሰጣለሁ፤ 12 ለሙሽራዋም ጥሎሽ የፈለጋችሁትን ያህል ጠይቁኝ፤ እርሷን እንዳገባ ፍቀዱልኝ እንጂ፣ የፈለጋችሁትን ሁሉ ለመጠት ዝግጁ ነኝ።” 13 ሴኬም እኅታቸውን ዲናን አስነውሮ ስለነበር የያዕቆብ ልጆች ለእርሱና ለአባቱ በተንኮል እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፣ 14 እንዲህ አሉአቸው፤ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ብንሰጥ ውርደት ስለሚሆንብን፣ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም። 15 ሆኖም የምንስማማበት አንድ መንገድ ብቻ አለ፤ ይኸውም አንተና በእናንተ ዘንድ ያሉት ወንዶች ሁሉ እንደኛ የተገረዛችሁ እንደሆነ ነው። 16 እንዲህ ከሆነ እናንተ የእኛን ሴቶች ልጆች ታገባላችሁ፣ እኛም የእናንተን ሴቶች ልጆች እናገባለን፣ አንድ ሕዝብ ሆነንም አብረን እንኖራለን። 17 ዐሳባችንን ባትቀበሉና ባትገረዙ ግን እኅታችንን ይዘን እንሄዳለን። 18 ያቀረቡትም ዐሳብ ለኤሞርና ለልጁ ለሴኬም መልካም መስሎ ታያቸው። 19 ከአባቱ ቤተሰብ ሁሉ እጅግ የተከበረው ይህ ወጣት የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወዶአት ስለነበር፣ ያሉትን ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም። 20 ስለዚህ ኤሞርና ልጁ ሴኬም ይህንኑ ለወገኖቻቸው ለመንገር ወደ ከተማቸው በር ሄዱ፤ 21 እንዲህም አሏቸው፤ “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር የሚኖሩት በሰላም ነው፣ በምድሪቱ ላይ አብረው ይቀመጡ፣ ተዘዋውረውም እንዲነግዱ እንፍቀድላቸው፤ ምድሪቱ እንደሆን ለእኛም ለእነርሱም ትበቃለች። ሴቶች ልጆቻቸውን እናገባለን፤ እነርሱም የእኛን ሴቶች ልጆች ያገባሉ፤ 22 ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋር እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው አብረውን ለምኖር ፈቃደኞች የሚሆኑት፣ የእኛ ወንዶች እንደ እነርሱ የተገረዙ እንደሆነ ብቻ ነው። 23 ታዲያ እንዲህ ብናደርግ ከብታቸው ንብረታቸው፣ እንስሶቻቸውም ሁሉ የእኛው ይሆኑ የለምን? ስለዚህ ባሉት እንስማማ፣ እነርሱም አብረውን ይኑሩ።” 24 የከተማይቱ ነዋሪዎች ሁሉ ኤሞርና ሴኬም ባቀረቡት ዐሳብ ተስማምተው ወንዶቹ ሁሉ ተገረዙ። 25 በሦስተኛውም ቀን የሁሉም ቁስል ገና ትኩስ ሳለ ከያዕቆብ ልጆች ሁለቱ፣ የዲና ወንድሞች ስምዓንና ሌዊ፣ ሰይፋቸውን መዘው ሳይታሰብ ወደ ከተማይቱ ገብተው ወንዶቹን በሙሉ ገደሏቸው። 26 ኤሞርንና ሴኬምንም በሰይፍ ገድለው፣ እኅታቸውን ዲናን ከሴኬም ቤት አውጥተው ይዘዋት ተመለሱ። 27 የቀሩትም የያዕቆብ ልጆች እኅታቸውን ስለደፈሩባቸው ወደ ሞቱት ሰዎች ቤት እየገቡ ከተማይቱን በሙሉ ዘረፉ። 28 የበግና የፍየል መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውንና አህዮቻቸውን እንዲሁም በከተማይቱና በአካባቢው የሚገኘውን ንብረታቸውን ሁሉ ወሰዱባቸው፤ 29 ሀብታቸውን ሁሉ ዘርፈው ሴቶቻቸውንና ሕፃናቶቻቸውን ሁሉ ማርከው በየቤቱ ያገኙትን ሁሉ ይዘው ሄዱ። 30 ያዕቆብ ስምዖንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በእኔ ላይ ከባድ ችግር አመጣችሁብኝ፤ እነሆ፣ በዚህ ድርጊት የተነሣ በዚህች ምድር የሚኖሩ ከነዓናውያንና ፌርዛውያን ይጠሉኛል፤ እኛ በቁጥር አነስተኞች ነን፣ እነርሱ ተባብረው ቢያጠቁን እኔና ቤተሰቤ እንጠፋለን።” 31 ስምዖንና ሌዊ ግን፣ “ታዲያ ሴኬም እኅታችንን እንደዝሙት አዳሪ ይድፈራትን?” አሉት።
በዚህ ይህ ቃል የታሪኩን አድስ ክፍል ለማመልከት ተጠቅሞአል፡፡
የልያ ሴት ልጅ ነች በዘፍጥረት 3ዐ:21 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የብሔር ስም ነው:: በዘፍጥረት 1ዐ፡17 ኤዊያዊያን የሚለውን ቃል እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ ሴኬምን ሳይሆን ኤምርን ያመለክታል በዚህ ቦታ ገዢ የንጉሥ ልጅ ማለት አይደለም ይህም ኤሞር በዚያ ለሚኖሩ ሰዎች መሪ እንደነበር ነው
ሴኬም ዲናን ደፈራት (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል ወይም በተዘዋዋሪ አንድን ነገር የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
“በዲና ተማረከ” ዲናን እንደወደዳትና ከእርስዋ ጋር ለመሆን አንድ ነገር ወደ ዲና እንዲመጣ እንዳስገደደው ስለ ሴኬም ይናገራል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ከዲና ጋር ለመሆን እጅግ በጣም ፈልጐአል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ወይም ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እንደሚወዳትና እንዲትወደው ለማድረግ ሊያሳምናት በሚስብ መንገድ አናገራት ማለት ነው
“አሁን” የተጠቀመው ከታሪኩ ወደ ያዕቆብ ዳራ መረጃ ለውጥ ማድረግን ለማመልከት ነው
“እርሱ” የሚለው ቃል ሴኬምን ያመለክታል
ሰኬም በጉልበት ከእርስዋ ጋር በመተኛት ዲናን እጅግ በጣም አዋረዳት ክብርዋን ነፈጋት ማለት ነው
ያዕቆብ ስለ ጉዳዩ ምንም አላደረገም ወይም አልተናገረም ማለት ነው:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ኤሞር ያዕቆብን ሊያነግረው ሄደ
ወንዶች ልጆች እጅግም ተቆጡ ወይም ደነገጡ
እዚህ እስራኤል የሚለው ቃል እያንዳንዱን የእስራኤል ቤተሰብ አባል ያመለክታል እስራኤል እንደብሔር ተደፍሮአል:: አት: “የእስራኤልን ቤት አዋርዶአል” ወይም “የእስራኤልን ስዎች አሳፍሮአል” (ክፍልን እንደሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘጥቤ ይመልከቱ)
የያዕቆብን ልጅ ስለደፈራት
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እንደዚህ አስነዋሪ ነገር ማድረግ አይገባውም ነበር” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ኤሞር ለያዕቆብና ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ነገራቸው
ፍቅር የሚለው ቃል በአንድ ወንድና ሴት መካከል የሚሆን ስሜታዊ ፍቅር ነው አት ወድዶአታልና ሊያገባት ይፈልጋል
በአንዳንድ ባህሎች ልጆች ማግባት ያለባቸውን ወላጆች ይወስናሉ
በጋብቻ መተሣሠር ከሌላ ዘር ብሔር ባህልና ጐሣ ሰዎች ጋር መጋባት ማለት ነው:: አት: “በአናንተና በእኛ ሰዎች መጋባትን እንፍቀድ”
ምድሪቱ የእናንም ናት
ሴኬም የዲናን አባት ያዕቆብን እንዲህ አለ
“ሞገስ ማግኘት” የሚለው ሀረግ በአንድ ሰው ተቀባይነትን ማረጋገጥ የሚናገር ዘይቤያዊ አነጋገር ነው ደግሞም ዓይኖች ማየትን ሲወክሉ ማየት ሀሳብን ወይም ፍረጃን ያመለክታሉ:: አት: “እንደተቀበላችሁን ካረጋገጥሁ የሚትጠይቁኝን ሁሉ እሰጣለሁ”:: (ፈሊጣዊና ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በአንዳንድ ባህሎች በጋብቻ ጊዜ ለሙሽሪቱ ቤተሰብ ሙሽራው በገንዘብ በንብረት በእንስሳትና በሌላም መልክ ስጦታ መስጠት የተለመደ ነው
ማታለል የሚለው ረቂቅ ስም መዋሽት እንደሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: ነገር ግን የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ለሴኬምና ለኤሞር በመለሱአቸው ጊዜ ዋሹአቸው (ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ)
ከእርሱ ጋር እንዲትተኛ በመድፈሩ ሴኬም ዲናን እጅግ በጣም አዋርዶአታል አስነውሮአታል ማለት ነው:: በዘፍጥረት 34:5 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
የያዕቆብ ወንድ ልጆች ለሴኬምና ለኤሞር እንዲህ አሉ
ዲናን በጋብቻ ሊንሰጥ አንስማማም
ይህም እኛን ያሳፍረናል:: እዚህ “እኛ” የያዕቆብን ወንዶች ልጆችንና የእስራኤልን ልጆች በአጠቃላይ ያመለክታል (የሚያካትትና የማያካትት እኛን ይመልከቱ)
ይህም ከያዕቆብ ቤተሰብ የሆነ ሰው በኤሞር ምድር የሚኖረውን ሰው ያገባል ማለት ነው
ኤሞርና ልጁ ሴኬም የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ባቀረቡት ሃሳብ ተስማሙ
ለመገረዝ
የያዕቆብ ሴት ልጅ ዲና
ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: እጅግ ስለሚያከብሩት ሌሎች ሰዎች ለመገረዝ እንደሚስማሙ ሴኬም እንደተረዳ ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት: “እርሱ በእነርሱ ዘንድ የተከበረ በመሆኑ የአባቱ ቤተሰብ ወንዶች ሰዎች ሁሉ ለመገረዝ እንደሚስማሙ ሴኬም ያውቅ ነበር” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)::
ሕጋዊ ውሳኔ ለመወሰን በከተሞች በር መሰባሰብ በመሪዎች የተለመደ ነው
ያዕቆብ ወንዶች ልጆቹና የእስራኤል ሰዎች
እዚህ “እኛ” ኤሞር ልጁንና የተናገሩአቸው በከተማው በር ያሉ ሰዎችን ሁሉ ያቀፈ ነው (ሁሉን ያቀፈ “እኛ” ይመልከቱ)
በምድሪቱ ይኑሩ ይነግዱበትም
ለዐረፍተ ነገሩ ትኩረት ለመስጠት ሴኬም “በእርግጥ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል:: “እነሆ ምድሪቱ በእርግጥ ለእነርሱም ሰፊ ናት” ወይም “እነሆ ለእነርሱ የሚበቃ በቂ መሬት አለ”
ይህ በአንዱ ቡድን ሴቶች በሌላው ቡድን ወንዶች መካከል የሚፈጸሙ ጋብቻዎችን ያመለክታል፡፡ በዘፍጥረት 34፡9 ተመሣሣይ ሀረጐችን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ኤሞርና ልጁ ሴኬም ለከተማዋ ሽማግሌዎች መናገራቸውን ቀጠሉ
ሰዎቹ ከእኛ ጋር እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው አብረውን ለመኖር ፈቃደኞች የሚሆኑት የእኛ ወንዶች እንደ እነርሱ የተገረዙ እንደሆነ ብቻ ነው
የያዕቆብ እንስሶችና ንብረቶች ለሴኬም ሰዎች እንደሚሆን ሴኬም ጥያቄ ምልክት በመጠቀም አበክሮ ይናገራል:: ይህ እንደዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት: “የእነርሱ እንስሳትና ንብረት ሁሉ ለእኛ ይሆናል” አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ስለዚህ ኤሞርና ሴኬም ወንዶችን ሁሉ የሚገርዙ ነበሩአቸው (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዘበት ዐረፍት ነገር ይመልከቱ)
ሶስት ተራ ቁጥር ሶስት ነው:: ያለ ተራ ቁጥር ሊነገር ይችላል:: አት: “ከሁለት ቀን በኋላ”
የከተማው ወንዶች ቆስለው ሳሉ
ሰይፋቸውን መዘው
ከተማ ሰዎችን ይወክላል አት እነርሱ የከተማይቱን ሰዎች ተዋጉ (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ እንደአዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ጥበቃ፡ ስምዖንና ሌዊ የከተማይቱን ወንዶች ሁሉ ገደሉ፡፡”
የኤሞር የሴኬምና ወንዶች ስዎቻቸው ሬሳ
በከተማይቱ ያለውን ጠቃሚ ነገር ሁሉ ወሰዱ
ሴኬም ብቻውን ዲናን አርክሶአት ነበር ነገር ግን የያዕቆብ ልጆች የሴኬም መላው ቤተሰብና በከተማው ያለው ሁሉ ሰው ለዚህ ድርጊት ተጠያቂ አድርገው ቆጥረዋል
ከእርሱ ጋር እንዲትተኛ በመድፈር ሴኬም ዲናን አዋረዳት ወይም ክብርዋን ነፈጋት/አሳፈራት ማለት ነው:: በዘፍጥረት 34: 5 አረከሳት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
የያዕቆብ ልጆች የሰዎችን መንጋ ወሰዱ
ንብረታቸውንና ገንዘባቸውን ሁሉ ሕጻናቶቻቸውንና ሴቶቻቸውን ሁሉ ማረኩ
ለአንድ ሰው የጭንቀት ምክንያት መሆን ጭንቀት በአንድ ሰው ላይ እንደሚመጣና እንደሚቀመጥ ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል አት: “ትልቅ ችግሮችን ፈጥራችሁብኛል” (ዜይቤያዊ አነጋገር ይጠቀሙ)
ያዕቆብ በዙሪያው በሚኖሩ ሰዎች ዘንድ እንዲጠላ ማድረግ የያዕቆብ ልጆች እርሱን እንደ መጥፎ ሽታ እንዳደረጉ ተገልጾአል ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት: “በምድሪቱ በሚኖሩ ዘንድ የተጠላሁ እንዲሆን አድርጋችሁኛል” (ዜይቤያዊ አነጋገር ይጠቀሙ)
እዚህ “እኔ” እና “እኔን” የሚሉ ቃላት ያዕቆብን ቤተሰብ በአጠቃላይ ይወክላሉ:: ያዕቆብ የቤተሰቡ መሪ ከመሆኑ የተነሳ “እኔ” ወይም “እኔን” ይጠቀማል:: አት: “ቤተሰብ አነስተኛ ነው … ተባብረው ቢነሡብኝና ቢያጠቁኝ ሁላችንንም ያጠፋሉ::” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ሠራዊት ይፈጥሩና ያጠቁኛል ወይም ሠራዊት ይፈጥሩና ያጠቁናል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ያጠፉኛል ወይም ያጠፉናል ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ”
ሴኬም ያደረገው ጥፋትና ሞት እንደሚገባው አበክረው ለመግለጽ ሌዊና ስምዖን ጥያቄ ይጠቀማሉ:: አት: “ሴኬም እህታችንን እንደ ሴተኛ አዳሪ/ጋለሞታ አድርጐ ባልቆጠረ ነበር!” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
1 እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሣና ወደ ቤቴል ሂድ፣ እዚያም ኑር። ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ አለው። 2 ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና አብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ። 3 ተነሥተን ወደ ቤቴል እንሂድ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ። 4 ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሰብስበው፣ የጆሮ ጉትቾቻቸውን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት። ያዕቆብም ወስዶ ሴኬም አጠገብ ካለው ዋርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። 5 ያንንም ቦታ ለቀው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው በነበሩት ከተሞች ሁሉ ላይ ፍርሃትና ድንጋጤ ስለለቀቀባቸው ያሳደዳቸው አልነበረም። 6 ያዕቆብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በከነዓን ወደምትገኘው፣ ቤቴል ወደተባለችው ወደ ሎዛ ደረሱ። 7 ያዕቆብም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ ስሙን ኤል ቤቴል አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ ሸሽቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነበር። 8 በዚህ ጊዜ የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ ሞተች፣ ከቤቴል ዝቅ ብሎ በሚገኘው የዋርካ ዛፍ ሥር ተቀበረች። ከዚህ የተነሣም ያ ቦታ አሉንባኩት ተባለ። 9 ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ዳግመኛ ተገለጠለትና ባረከው። 10 እግዚአብሔርም፣ “እስካሁን ስምህ ያዕቆብ ነበር፤ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ነገር ግን ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህም እስራኤል ብሎ ጠራው። 11 ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉም ማድረግ የሚችል አምላክ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑሩህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ። 12 ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ፤ ከአንተም በኋላ ይህችን ምድር ለዘርህ አሰጣለሁ።” 13 እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ከዚያ ስፍራ ወደ ላይ ወጣ። 14 ያዕቆብ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፣ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቁርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት። 15 ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው። 16 ከዚያም ከቤቴል ተነሥተው ሄዱ፤ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፣ ምጡም ጠናባት። 17 ምጧ እየበረታ በሄደ ጊዜ አዋላጅቱ፣ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ሌላ ወንድ ልጅ ልትወልጂ ነው” አለቻት። 18 እርስዋ ግን ልትሞት ታጣጥር ስለነበር ከመሞቷ በፊት ልጅዋን ‘ቤንኦኒ’ አለችው፤ አባቱ ግን ‘ብንያም’ አለው። 19 ራሔል ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ በቤተልሔም ተቀበረች። 20 ያዕቆብም በራሔል መቃብር ላይ ሐውልት አቆመ፤ እስከዛሬም የራሔል መቃብር ምልክት ይኸው ሐውልት ነው። 21 ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በዔዴር ግንብ ባሻገር ድንኳን ተክሎ ሰፈረ። 22 ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት፣ እነርሱም፦ 23 የልያ ልጆች፦ የያዕቆብ የበኩር ልጅ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤ 24 የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍ፣ ብንያም፤ 25 የራሔል አገልጋይ የባላ ልጆች፦ ዳን፣ ንፍታሌም፤ 26 የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦ ጋድ፣ አሴር፣ ናቸው። እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በመስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ናቸው። 27 ያዕቆብ በቂርያት አርባቅ (በኬብሮን) አጠገብ መምሬ በምትባል ስፍራ ወደሚኖረው አባቱ ወደ ይስሐቅ ሄደ፤ ይህም ስፍራ አብርሃምና ይስሐቅ የኖሩበት ነው። 28 ይስሐቅ መቶ ሰማንያ ዓመት ኖረ፤ 29 አርጅቶ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።
ውጣ የሚለው ቃል የተጠቀመው ቤቴል ከሴኬም በከፍታ ላይ ስለሚገኝ ነው
እግዚአብሔር ስለራሱ በሶስተኛ ሰው መንገድ ይናገራል:: አት: “ለእኔ ለአምላክህ መሠዊያ ሥራ” (እንደ አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው መግለጽን ይመልከቱ)
ለቤተሰቡ እንዲህ አላቸው
“ጣዖታትን አስወግዱ” ወይም “ሐሰተኞች አማልእክትን አስወግዱ”
ይህ እግዚአብሔርን ለማምለክ ከመቅረብ በፊት በአካላዊና ሥነምግባራዊ ሕይወት ራስን የማንጻት ልምድ ነበር
አድስ ልብሶችን መልበስ ወደ እግዚአብሔር ከመቀረባቸው በፊት ራሳቸውን ንጹህ የማድረጋቸው ምልክት ነበር (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
በመከራዬ ጊዜ ወይም በጭንቀተ ጊዜ
“ሁሉም የያዕቆብ ቤት ሰጠ” ወይም “የያዕቆብ ቤተሰብና አገልጋዮቻቸው ሰጡት”
እዚህ “በእጃቸው ያሉት” የእነርሱ የሆኑትን ይወክላል:: አት: “ሀብታቸው የሆኑትን ወይም ያላቸውን” (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ጉትቾቻቸውን ተገቢ ትርጉሞች እነሆ 1 የጆሮቻቸውን ወርቅ ብዙ ጣዖታትን ሊሠሩ ሊጠቀሙ ይችላሉ 2 እነዚህ ጉትቾች የሴኬም ከተማ ሰዎችን በተዋጉና ሁሉን ሰዎች በገደሉ ጊዜ የበዘበዙአቸው ናቸው:: ጉትቾች ስለኃጢአታቸው የሚያውሱ ይሆናሉና::
ያዕቆብንና ቤተሰቡን የከተሞች ሰዎች እንዲደነግጡ እግዚአብሔር ያደረገው ድንጋጤ እንደ አንድ ነገር በከተሞች እንደወደቀ ተደርጐ ተገልጾአል:: “ድንጋጤ” የተባለው ረቂቅ ስም እንደ “ፍርሃት” ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እግዚአብሔር በዙሪያው ያሉ የከተሞች ሰዎች ያዕቆብንና በቤተሰቡን እንዲፈሩ አደረገ” ዘይቤያዊ አነጋገርና ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ
“ከተሞች” በከተሞች የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላሉ::
ከያዕቆብ ቤተሰብ ማንም እንዳልተጠቃ ይገልጻል ነገር ግን የያዕቆብ ሴት ልጅ ከተደፈረች በኋላ ስምዖንና ሌዊ የሴኬምን ከነዓናዊያን ዘመዶችን አጠቁአቸው በዘፍረት 34:3ዐ ያዕቆብ ሊበቀሉ ይፈልጉ ይሆናል ብሎ ፈርቶአል አት የያዕቆብ ቤት ወይም የያዕቆብ ቤተሰብ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ የከተማ ስም ነው:: በዘፍጥረት 28 19 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የሚከተለውን የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ “ኤል ቤተል የሚለው ስም የቤተል አምላክ ማለት ነው” (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ራሱን ለያዕቆብ ያስታወቀበት በዚህ ቦታ ነበር
ይህ የአንዲት ሴት ስም ነው ስምችን ስለመተርጐም ይመልከቱ
ሞግዚት የሌላ ሴት ልጅን የሚትንከባከብ ሴት ማለት ነው ሞግዚት እጅግ የተከበረችና በቤተሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያላት ነች
“ዝቅ ብሎ” የሚለው ሀረግ የተጠቀመው እርስዋ የተቀበረችው ቦታ ከፍታ ከቤተል ዝቅ ብሎ ስለሚገኝ ነው::
ተርጓሚዎች የሚከተለውን የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ “አሎንባኩት የሚለው ስም ለቅሶ ያለበት ዋርካ ዛፍ ማለት ነው” (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
በቤተል እንደነበሩ ግልጽ ማድረግ ይቻላል አት ያዕቆብም ከጳዳን አራም ከተመለሰ በኋላ በቤተል በነበረበት ጊዜ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በረከት ለአንድ ሰው መልካም ነገር እንዲደረግለትና በዚያው ሰው ላይ የረከት ቃል መናገር ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ስምህ ያዕቆብ አይባልም” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው
ብዙ ልጆች እንዲኖሩት ያዕቆብ ብዙ ልጆችን እንዲወልድ እግዚአብሔር ተናገረው ብዛ የሚለው እንዴት መባዛት እዳለበት ይገልጻል በዘፍጥረት 1:22 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ድርብ ቃላትና ፈሊጣዊ ንግግር ይመልከቱ)
እዚህ ሕዝብ እና ሕዝቦች የያዕቆብ ዘሮች እነዚህን ሕዝቦች እንደሚመሠርቱ ነው:: (ተመሣሣይ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ወደ ላይ ወጣ የተጠቀመው ከምድር ከፍ ብሎ እግዚአብሔር እንደምኖር ለመግለጽ ነው:: አት: “እግዚአብሔር ተለየው”
ይህ በጫፉ መከሎ/ቅርጽ ያለው ትልቅ ድንጋይ ለመታሰቢያነት የቆመ ሐውልት ነው
ይህም ሐውልቱን ለእግዚአብሔር የመሰደስ ምልክት ነው (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የሚከተለውን የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ “በቴል የሚለው ስም የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው” (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የቤተልሔም ከተማ ሌላው ስም ነው
ምጡ አስጨንቆአት ሳለ
አንድ ሴት ልጅን በሚትወልድበት ጊዜ የሚታግዝ ሴት
“ነፍስ መውጣት” አንድ ሰው በሚሞትበት ጊዜ የመጨረሻ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ አት “ከመሞትዋ በፊት በመጨረሻዋ እስትንፋስ ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የሚከተለውን የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ “ቤንኦኒ የምለው ስም የጭንቀቴ ልጅ ማለት ነው” (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የሚከተለውን የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ “ብንያምን የምለው ስም የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው” የቀኝ እጅ የሚለው ሀረግ ልዩ የሚወደድ ቦታ ማለት ነው::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “እነርሱ ቀበሩአት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
በሚወስደው መንገድ
ይህ እስከዛሬም የራሔል መቃብር ምልክት ነው
እስካሁን ጊዜ ይህ ጸሐፊው፤ ይህ መልእክት የጻፈበትን ጊዜ ያመለክታል፡፡
የእስራኤል ቤተሰብና አገልጋዮቹ ከእርሱ ጋር እንደነበሩ ይገልጻል የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የራሔል ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:29 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ::
ይህ ዐረፍተ ነገር በሚከተሉት ቁጥሮች የሚቀጥለውን አድስ አንቀጽ ይጀምራል
12 ወንዶች ልጆች
የራሔል ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:29 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የልያ ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ በከነዓን ምድር በቤተልሔም አጠገብ የተወለደውን ብንያምን እንደማያካትት ይናገራል:: አብዛኛዎቹ የተወለዱት በጳዳን አራም ስለሆነ ይህንኑን ይጠቅሳል:: የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “በከነዓን ምድር ከተወለደው ከብንያምን በስተቀር በጳዳን አራም የተወለዱለት” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
መጣ የተባለው ሄዴ በሚለው ሊተካ ይችላል (ሄዴ እና መጣ ይመልከቱ)
የሔብሮን ከተማ ሌላ ስምዋ ነው የአብርሃም ወዳጆች በኖሩበት በመምሬ ስም ተጠርቶ ይሆናል በዘፍጥረት 13 18 ይህን እንዴት አንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የከተማ ስም ነው በዘፍጥረት 23 2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
18ዐ ዓመት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ይስሐቅም የመጨረሻውን እስትንፋስ ሰጠ ሞተም እንትንፋሱን ሰጠ/ነፍሱን ሰጠ ወይም ሞተ የሚሉ ሀረጐች በመሠረቱ አንድ ትርጉም አላቸው:: በዘፍጥረት 25:8 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት: “ይሥሐቅም ሞተ” (ድርብ ቃላት ይመልከቱ)
ይህ አንድ ሰው መሞቱን ትሁትና መንገድ የሚገልጽ ነው:: በዘፍጥረት 25:8 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ንኀብነት ለዛ ባለ ወይም በተዘዋዋሪ አንድን ነገር የመግለጽ ዘይቤያዊ አባባል ይመልከቱ)
ይስሐቅ ከሞተ በኋላ ከዚህ በፊት የሞቱ ወገኖች ነፍስ ወዳለበት ቦታ ነፍሱ ሄደች ማለት ነው ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል አት የሞቱትን የቤተሰብ አባላትን ተቀለቀለ ማለት ነው:: (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮችን ይመልከቱ)
አረጅቶ እና እድሜ ጠግቦ የሚሉ ሀረጐች በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: አበክረው የሚናገሩት ይስሐቅ ብዙ ዓመታትን እንደኖረ ነው:: አት: “ብዙ ዓመታትን ኖሮ ከአረጀ በኋላ” (ድርብ አባባል ይመልከቱ)
1 ኤዶም የተባለው የዔሳው የትውልድ ታሪክ የሚከተለው ነው፤ 2 ዔሳው ከነዓናውያን ሴቶችን አገባ፤ እነርሱም የኬጢያዊው የዔሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤውያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳት አህሊባማ፣ 3 እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችውን የእስማኤል ልጅ ቤስሞት ነበሩ። 4 ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት። 5 እንደዚሁም አህሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆቹ ናቸው። 6 ዔሳው ሚስቶቹንና ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ። 7 ብዙ ሀብት ስለነበራቸው አብረው መኖር አልቻሉም፣ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም። 8 ስለዚህ ዔዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ። 9 በተራራማው አገር በሴይር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤ 10 የዔሳው ልጆች ስም፦ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤ 11 የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤ 12 የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ትምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው። 13 የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህም ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው። 14 የፅብዖን የልጅ ልጅ፤ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት አህሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤ 15 ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኩር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ቄኔዝ 16 ቆሬ፣ ጎቶምና አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ። 17 የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሃማና፣ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ነበሩ። 18 የዔሳው ሚስት የአሕሊባማ ልጆች፦የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ ከዔሳው ሚስት አሕሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። 19 እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ። 20 በኤዶም ምድር ነዋሪዎች የነበሩት የሴይር ልጆች የነበሩ የሖራውያን አለቆች፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣ 21 ዲሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ በሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ። 22 የሎጣን ልጆች፦ ሖሪና ሔማም የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ትባል ነበር። 23 የሦባል ልጆች፦ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባልና ስፎና አውናንም፤ 24 የፅብዖን ልጆች፦ አያና፣ ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅባዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍልውሃ ምንጮችን በምድረበዳ ያገኘ ሰው ነው። 25 የዓና ልጆች፦ዲሶንና የዓና የሴት ልጅ አህሊባማ፤ 26 የዲሶን ልጆች፦ ሔምዳን፣ ሴስባን፣ ይትራንና ክራን፤ 27 የኤድር ልጆች፦ ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤ 28 የዲሳን ልጆች፦ዑፅና አራን። 29 የሖራውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ፅዖን፥ ዓና፣ 30 ዶሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ። 31 ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦ 32 የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነግሦ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። 33 ባላቅ ሲሞት፣ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ። 34 የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ሲሞት የቴማኒው ሑሳም ነገሠ። 35 ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር። 36 ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ። 37 ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ። 38 ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በልሐናን በምትኩ ነገሠ። 39 የዓክቦር ልጅ በልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብዔል ሲሆን፣ እርሷም መጥሬድ የወለደቻት የሜዛሃብ ልጅ ነበረች። 40 ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ፣ ዓለዋ፣ የቴት፣ 41 አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፌኖን፣ 42 ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣ 43 መግዲኤልና ዒራም፣ እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው ከኤዶም የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። ይህም ዔሳው የኤዶማውያን አባት ነበር።
ኤዶም የተባለው የዔሣው ትውልድ ይህ ነው ይህ በዘፍረት 36:1-8 የተጠቀሰውን የዔሣው ትውልድን ያስታውቃል:: አት “ይህ ኤዶም የተባለው የዔሣው ትውልድ ነው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እነዚህ የዔሣው ሚስቶች ስም ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
“ዔሎን የኬጥ ትውልድ” ወይም “ዔሎን የኬጥ ልጅ” ይህ የአንድ ሰው ስም ነው:: በዘፍጥረት 26:34 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የመንዶች ሰዎች ስም ናቸው
ይህ ትልቅ ሕዝብ ቡድንን ያመለክታል፡፡ በዘፍጥረት 1ዐ:17 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ከዔሣው ሚስቶች የአንዷ ስም ነው:: ዘፍጥረት 26:34 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ከእስማኤል ወንዶች ልጆች የአንዱ ስም ነው:: ዘፍጥረት 28:9 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የዔሣው ሚስቶች ስሞች ናቸው:: በዘፍጥረት 36:2-3 እነዚህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የዔሣው ወንድ ልጆት ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ በከነዓን ምድር በሚኖርበት ጊዜ የሰበሰበውን ወይም ያፈራውን ሁሉን ነገር ያመለክታል አት በከነዓን ምድር በሚኖርበት ጊዜ ያፈራውን ሀብት (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ወደ ሌላ ቦታ ሂዶ በዚው ኖረ ማለት ነው:: አት: “በሌላ ቦታ ለመኖር ሄደ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
የዔሣውና የያዕቆብ ሀብቶች
ያዕቆብና ዔሣው ያሉአቸውን ከብቶቻቸውን ለማሠማራት ምድሪቱ በቂ አልነበረችም:: አት “ከብቶቻቸውን ለማሠማራት አልበቃቸውም” ወይም “ለያዕቆብ ከብቶችና ለዔሣው ከብቶች በቂ አልነበረም” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የነበሩበት የሚለው ቃል ወደ አንድ ቦታ የመሄድና በዚያ መኖር ያመለክታል:: አት: “የሄዱበት ሥፍራ ወይም ቦታ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ዐረፍተ ነገር በዘፍጥረት 36: 9-43 ያለውን የዔሣው ትውልድ ዝርዝር ያስታውቃል (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በሴይር ተራራ ኖረዋል ማለት ነው:: የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “በተራራማው በሴይር አገር የኖሩ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እነዚህ የዔሣው ወንዶች ልጆች ስሞች ናቸው:: በዘፍጥረት 36:4 እነዚህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የዔሣው ሚስቶች ስሞች ናቸው:: በዘፍጥረት 36:2-3 እነዚህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የኤልፋዝ መንዶች ልጆች ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የኤልፋዝ ቁባት ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የዔሣው ወንዶች ልጆች ስሞች ናቸው:: በዘፍጥረት 36:4-5 እነዚህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የራጉኤል ወንዶች ልጆች ስሞች ናቸው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የወንድ ሰዎች ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የዔሣው ሚስቶች ስሞች ናቸው:: በዘፍጥረት 36 2 3 እነዚህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ ከዔሣው ወንዶች ልጆች የአንዱ ስም ነው በዘፍጥረት 36: 4 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የኤልፋዝ ወንዶች ልጆች ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ከዔሣው ሚስቶች የአንዷ ስም ነው በዘፍጥረት 36: 2-3 ስምዋን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የዔሣው ወንዶች ልጆች ስሞች ናቸው:: በዘፍጥረት 36:4-5 እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የራጉኤል ወንዶች ልጆች ስሞች ናቸው:: በዘፍጥረት 36:13 እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህም በኤዶም ምድር ኖረዋል ማለት ነው:: አት: “በኤዶም ምድር የኖሩ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እነዚህ የዔሣው ሚስቶች ስሞች ናቸው:: በዘፍጥረት 36 :2-3 እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የወንድ ሰው ስም ነው በዘፍጥረት 36፡2 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ሴይር የሚለው ቃል የአንድ ወንድ ሰውና የአንድ አገር ስም ነው
“ሖሪውያን” የሚለው ቃል የአንድ ሕዝብ ቡድን ስም ነው:: በዘፍረት 14:6 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ(ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ኤዶም በተባለው በሴይር የሚኖሩ
እነዚህ የወንዶች ሰዎች ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የሴት ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው:: በዘፍረት 36:2ዐ እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው:: በዘፍረት 36: 20-21 እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ይህ የአንዲት ሴት ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የአንድ ሕዝበ ወገን ስም ነው:: በዘፍጥረት 14:6 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ስዎች ስሞች ናቸው በዘፍረት 36:2ዐ-21 እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህም በሴይር ምድር ኖረዋል ማለት ነው:: አት “በሴይር ምድር የኖሩ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ እርሱ የኖረበት ከተማ ነበር ማለት ነው:: አት: “እርሱ የኖረበት ከተማ ስም” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የወንድ ሰው ስም ነው በዘፍጥረት 36 33 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህም ሐሳም በቴማኒ ምድር ኖሮአል ማለት ነው:: አት “በቴማኒ ምድር የኖረ ሐሳም” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ቴማኒ የተባለው ሰው ትውልድ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ እርሱ የኖረበት ከተማ ነበር ማለት ነው:: አት: “እርሱ የኖረበት ከተማ ስም” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ከመሥሬቃ የሆነው ሠምላ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የወንድ ሰው ስም ነው:: በዘፍጥረት 36:36 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ሳኦል በርሆቦት ይኖር ነበር:: ርሆቦት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ነው:: ይህ መረጃ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “ከዚያም ሳኦል በምትኩ ነገሠ:: እርሱም ከኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ከነበረችው ከርሆቦት ነው (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የቦታዎች ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ እርሱ የኖረበት ከተማ ነበር ማለት ነው:: አት: “እርሱ የኖረበት ከተማ ስም” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እርሷም የሜዛሃብ ልጅ መጥሬት የወለደቻት ነበረች
የሴት ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የነገድ መሪዎች
ነገዳቸውና አገራቸው በአለቆቻው ወይም በመሪዎቻቸው ስም ተሰይሞአል:: አት: “የነገዶቻቸውና የሚኖሩባቸው አገራቸው በመሪዎቻቸው ስም ተሠይሞአል” የእነርሱ ስሞች እነሆ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እነዚህ የህዝብ ወገኖች ወይም የነገዶች ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
“በሚኖሩባቸው ቦታዎች” ወይም “በኖሩባቸው ቦታዎች”
ይህ የስም ዝርዝር ዔሣው ነው የተባለው ይህ የትውልዱ አጠቃላይ ዝርዝር ነው ማለት ነው:: አት: “ይህ የዔሣው ትውልድ ዝርዝር ነው” (ተዛማጅ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
1 የዕቆብ አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ። 2 የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረ ጊዜ፣ ከአባቱ ሚስቶች ከባላቅና ከዘለፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር። እርሱም ስለወንድሞቹ ድርጊት ለአባቱ መጥፎ ወሬ ይዞለት መጣ። 3 እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወደው ነበር፣ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም ሰፋለት። 4 ወንድሞቹም አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው መሆኑን ሲያዩ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበት ሊያናግሩት አልቻሉም። 5 ዮሴፍ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት፤ 6 እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ” 7 ‘እኛ ሁላችን በእርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ ተነሣና ቀጥ ብሎ ቆመ፤ የእናንተ ነዶዎች ዙሪያውን ተሰብስበው ለእኔ ነዶ ሰገዱለት’” 8 ወንድሞቹም፣ “ታዲያ በእኛ ላይ ንጉሥ ሆነህ ልትገዛን ታስባለህን?” ብለው ጠየቁት። ስለ ሕልሙና ስለተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት። 9 እንደ ገናም ሌላ ሕልም አለመ፤ ለወንድሞቹም እነሆ፣ ሌላ ሕልም አለምሁ፣ ፀሐይና ጨረቃ፣ ዐሥራ አንድ ክዋክብትም ሲሰግዱልኝ ዐየሁ” ብሎ ነገራቸው። 10 ይህንኑ ለወንድሞቹ የነገራቸውን ሕልም ለአባቱም በነገረው ጊዜ፣ አባቱ፣ “ይህ ምን ዐይነት ሕልም ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም በፊትህ ወደ ምድር ተጎንብሰን በርግጥ ልንሰግድልህ ነው?” ሲል ገሠጸው። 11 ወንድሞቹ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው። 12 አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን መንጋዎች ይዘው ወደ ሴኬም ተሰማሩ፤ 13 እስራኤልም ዮሴፍን፣ “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ” አለው። ዮሴፍም፣ “እሺ እሄዳለሁ” አለ። 14 አባቱም፣ “በል እንግዲህ ሄድና የወንድሞችህንና የመንጋዎቹን ደኅንነት አይተህ ንገረኝ” አለው። በዚህ ዓይነት እስራኤል ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣ 15 ሜዳ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲባዝን አንድ ሰው አግኝቶት፣ “ምን እየፈለግህ ነው?” ሲል ጠየቀው። 16 ዮሴፍም፣ “ወንድሞቼን እየፈለግኋቸው ነው፤ መንጎቻቸውን የት እንዳሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህ?” አለው። 17 ሰውዬውም፣ “ከዚህ ሄደዋል፤ ደግሞም ‘ወደ ዶታይን እንሂድ’ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው። ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ሄደ፣ በዶታይን አቅራቢያም አገኛቸው። 18 ወንድሞቹም ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቅ ዐዩት፣ ወደ ነበሩበትም ስፍራ ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ። 19 እነርሱ እንዲህ ተባባሉ፦ “ያ ሕልም አላሚ መጣ፤ 20 ኑ እንግደለውና ከጉድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም፣ ‘ክፉ አውሬ ነጥቆ በላው’ እንላለን፤ እስቲ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን።” 21 ሮቤል ግን ይህን ምክር ሲሰማ ከእጃቸው ሊያድነው ፈለገ እንዲህም አለ፤ “አንግደለው፤ 22 የሰው ደም አታፍስሱ፣ ከምትገድሉት ይልቅ በዚህ በበረሃ ባለው ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት” አላቸው። ሮቤል ይህን ያለው ሕይወቱን ከእጃቸው አትርፎ ወደ አባቱ ሊመልሰው ዐስቦ ነበር። 23 ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደደረሰ፣ የለበሳትን በኅብረ ቀለማት የጌጠች እጀ ጠባቡን ገፈፉት፤ 24 ይዘውም ወደ ጉድጓድ ጣሉት፤ ጉድጓዱም ውሃ የሌለበት ደረቅ ነበር። 25 ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ፤ አሻግረው ሲመለከቱም ከገለዓድ የሚመጡ እስማኤላውያን ነጋዴዎች ጓዛቸውን በግመሎች ላይ ጭነው ተመለከቱ። ነጋዴዎቹ ሽቶ፣ በለሳን፣ ከርቤ በግመሎቻቸው ጭነው ወደ ግብፅ የሚወርዱ ነበሩ። 26 ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “ወንድማችንን መግደልና አሟሟቱን መደበቅ ምን ይጠቅመናል? 27 ከዚህ ይልቅ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች እንሽጠው፤ እጃችንን ግን በእርሱ ላይ አናንሳ። ምንም ቢሆን የሥጋ ወንድማችን ነው” ወንድሞቹም በሃሳቡ ተስማሙ። 28 የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማሴላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጉድጓድ ጎትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፣ እነርሱም ወደ ግብፅ ይዘውት ሄዱ። 29 ሮቤል ወደ ጉድጓዱ ተመልሶ ሲያይ፣ ዮሴፍን በማጣቱ ልብሱን በሐዘን ቀደደ። 30 ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ፣ “እነሆ፣ ልጁ እዚያ የለም! እንግዲህ እኔ ወዴት ብሄድ ይሻለኛል?” አለ። 31 ከዚህ በኋላ አንድ ፍየል አረዱና የዮሴፍን ልብስ በደም ነከሩት። 32 በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስቲ እየው” አሉት። 33 እርሱ የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ፣ “ይህማ የልጄ እጀ ጠባብ ነው! ፤ ክፉ አውሬ በልቶታል፣ በእርግጥም ዮሴፍ ተቦጫጭቆአል” አለ። 34 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለብሶ ስለ ልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፤ 35 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና አልቻለም፣ “በሐዘን እንደተኮራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ። 36 በዚህ ጊዜ የምድያም ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወስደው፣ ከፈርዖን ሹማምንት አንዱ ለነበረው ለዘበኞች አለቃ፣ ለጲጥፋራ ሸጡት።
አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ
ይህ ዐረፍተ ነገር በዘፍጥረት 37: 1-5ዐ:26 ያለውን የያዕቆብን ትውልድ ያስታውቃል፡፡ እዚህ ያዕቆብ መላው በተሰቡን ይወክላል፡፡ አት “ይህ የያዕቆብ ቤተሰብ ታሪክ ነው” (ክፍልን እንደሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
17 ዓመት ዕድሜ
ይህ የራሔል ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29: 29 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የልያ ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29: 24 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ ሴቶች ልጅ እንዲወልዱ ዘንድ ለያዕቆብ የተሰጡ የልያና የራሔል አገልጋዮች ናቸው
ስለወንድሞቹ መጥፎ ወሬ
ይህ ቃል ታሪኩ ስለ እስራኤልና ዮሴፍ ዳራ መረጃ መቀየሩን የሚያመለክት ነው (ዳራ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ወንድማማች ፍቅር ወይም ጓደኛ ፍቅር ወይም ቤተሰብ ፍቅር ያመለክታል ይህ በጓደኛሞችና በቤተሰብ መካከል የሚገለጽ ተፈጥሮአዊ የሰው ልጅ ፍቅር ነው
እስራኤል በአረጀ ጊዜ ዮሴፍን ወልዶአል ማለት ነው:: አት: “እስራኤል በአረጀ ጊዜ የተወለደው” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እስራኤል ለዮሴፍ ..አደረገለት
እጅግ የሚያምር እጄ ጠባብ
በሰላም ሊያናግሩት ዘንድ አልቻሉም
ይህ በዘፍጥረት 37:6-11 የተቀመጠው ታሪክ ማጠቃለያ ሀሳብ ነው::
የዮሴፍ ወንድሞች ከዚህ በፊት ከሚጠሉት በላይ ጠሉት
ሕልሜን ልንገራችሁ አድምጡኝ
ስለሕልሙ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ይናገራል
“እነሆ” የሚለው ቃል ለሚቀጥለው አስደናቂ ሃሳብ ትኩረት እንዲሰጠው ያነቃል
“እኛ” የሚለው ቃል ዮሴፍና ወንድሞቹን ሁሉ ያጠቃልላል (ሁሉን ያቀፈ እኛ ይመልከቱ)
እህል ከታጨደ በኋላ ፍሬው ከገለባው እስኪበጠር ድረስ በየነዶው ታሥሮና ተከምሮ ይጠበቃል
“እነሆ” የሚለው ቃል ዮሴፍ ባየው እንደተደነቀ ይገልጻል
እዚህ እንደሰው ነዶዎች ሲቆሙና ሲሰግዱ ይታያል እነዚህ ነዶዎች ዮሴፍንና ወንድምቹን ይወክላሉ (በሰውኛ መንገድ አገላለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለቱም ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው የዮሴፍ ወንድሞች ጥያቄዎችን በመጠቀም ዮሴፍን ማላገድ ጀመሩ እነዚህ በዐረፍተ ነገሮች መልክ ሊገለጹ ይችላሉ አት ንጉሣችን አትሆንም እኛም ለአንተ አንሠግድም (አግናኝ ጥያቄዎችንና ተዛማጅ ተመሣሣይ አባባል ይመልከቱ)
እኛ የሚለው ቃል ዮሴፍን ሳይሆን ወንድሞቹን ያመለክታል (ሁሉን አቀፍና ሁሉን የማያቅፍ “እኛ” ይመልከቱ)
ስለ ሕልሙና ልሰተናገረው ቃል
ዮሴፍ ሌላ ሕልም አለመ
11 ከዋክብት ቁጥሮች ይመልከቱ
እስራኤልም ገሠጸው አለውም
እስራኤል ዮሴፍን ለማረም ጥያቄዎችን ይጠቀማል:: ይህ እንደ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል:: አት: “ይህ ያየሄው ሕልም ትክክል አይደለም:: እኔ እናትህና ወንድሞችህ በፊትህ አንሰግድልህም!” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
አንድ ሰው ስኬታማና እጅግ ታዋቂ ከመሆኑ የተነሣ በቁጣ መሞላት ማለት ነው
ስለዮሴፍ ሕልም ትርጉም ማሰቡን ቀጠለ ማለት ነው:: አት: “የሕልሙ ትርጉም ምን እንደሆን ማሰቡን ቀጠለ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እስራኤል በንግግሩ ውስጥ ጥያቄ ይጠቀማል:: ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ወንድሞችህ በሰኬም በጎችን ይጠብቃሉ” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ለመሄድና ወንድሞቹን ለማየት ዮሴፍ እንዲዘጋጅ እስራኤል መጠየቁን የሚገልጽ ነው:: አት “ተዘጋጅ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ለመሄድ ተዘጅቸአለሁ(ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እስራኤል ዮሴፍን አለው
ወንድሞቹና በጎቹ እንዴት እንደሆኑ ዮሴፍ ተመልሶ እንዲነግረው እስራኤል ይፈልጋል አት ተመልሰው ያገኘሄውን ንገረኝ ወይም ርፖርት አቅርብልኝ (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ከሸለቆው
ዮሴፍ ወዲያና ወዲህ ሲባዝን አንድ ሰው ዮሴፍን አገኘው
በትልቁ ታሪክ ስለሌላ ክስተት መጀመሩን የሚያመለክት ነው በቀደሙ ክስተቶች ከነበሩ ሌሎች ሰዎች የሚያሳትፍ ነው በእርስዎ ቋንቋ ይህ የሚገለጽበት መንገድ ሊኖር ይችላል
ምን እየፈለግህ ነው?
ወዴት እንደሆነ እባክህ ንገረኝ
ከሰኬም 22 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ያለ ቦታ ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
በሩቅ እያለ የዮሴፍ ወንድሞች አዩት
እርሱን ለመግደል አቀዱ
ያ ባለ ሕልም ይሄው መጣ
ይህ አባባል ወንድሞቹ ዕቅዳቸውን መተግበር መጀመራቸውን ያሳያል:: አት: (ስለዚህ አሁን ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አደገኛ አውሬ ወይም ሰው ጨካኝ አውሬ
ንጥቆ በላው
ወንድሞቹ ሊገድሉት አቅደዋልና ስለዚህ እስከሞተ ድረስ ሕልሞቹ ይፈጸሙ እንደሆን መናገራቸው አሽሙራዊ/ሽሙጣዊ አባባል ነው:: አት “እስቲ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን” (በአሽሙር/ሽሙጥ መንገድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እነርሱ የመከሩትን ሰማ
ከእጃቸው የሚለው አባባል ሊገድሉት ያቀዱትን የወንድሞቹን እቅድ ያመለክታል:: አት “ከእነርሱ” ወይም “ከእቅዳቸው” (ተዛማጅ ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ሕይወት ማጥፋት የሚለው ሀረግ አንድን ሰው ስለመግደል በንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል በተዘዋዋሪ የሚገልጽ ነው፡፡ አት፡ “ዮሴፍን አንግደለው” (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል በተዘዋዋራ መንገድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
በግሡ አሉታዊነት ተጨምሮበታል ደግሞም ደምን ማፍሰስ አንድን ሰው ስለመግደል በንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል በተዘዋዋሪ የሚገልጽ ነው፡፡ አት የማንኛውንም ሰው ደም አታፍስሱ ወይም አትግደሉት (በአሉታዊነት አዎንታዊነትን የመግለጽ ዘይቤና ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ ቃል በተዘዋዋራ መንገድ የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
አታቆስሉት ወይም አትጉዱት ማለት ነው አት አትጉዱት (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል:: “ሮቤል ይህ ያለው ዮሴፍን ሊታርፈው ዘንድ ነው”
ከእጃቸው የሚለው አባባል ሊገድሉት ያቀዱትን የወንድሞቹን እቅድ ያመለክታል:: አት “ከእነርሱ” ወይም “ከእቅዳቸው” (ተዛማጅ ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
እናም ሊመልሰው
ይህ ሐረግ በታሪኩ ተፈላጊ ክስተት ለመጠቆም ተጠቅሞአል በቋንቋህ እንዲህ ዓይነት ካለ በዚህ ቦታ ሊጠቀሙ ይችላሉ
በኀብረ ቀለማት ያገጠች እጀ ጠባቡን ከላዩ ላይ ቀደዱት
ያገጠች እጀ ጠባብ፤ በዘፍጥረት 37:3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
እንጀራ በአጠቃላይ መግብን ያመለክታል አት ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ ወይም የያዕቆብ ወንድሞች ምግባቸውን ሊበሉ ተቀመጡ (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ አንስተው አዩ አንድሰው በውኑ አይኑን እንሰቶ እንደሚያይ ተደርጐ ተነግሮአል ደግሞም እነሆ የሚለው ቃል ሰዎች ላዩት ትኩረት ለመስጠት ተጠቅሞአል:: አት: “አይኖቻቸውን አነሡ እናም ወዲያውም የግመል ጓዝ አዩ” (ዘይቤያዊ አባባል ይመልከቱ)
ጭነው
ቅመማቅመም
የቆዳ ቁስለትን የሚፈውስና የሚከለክል ጣፋጭ ጣዕም ያለው ቅባታማ ነገር “መድኃኒት”
ወደ ግብጽ የሚያመጡ ይህ ግለጽ ሊደረግ ይችላል አት ለመሸጥ ወደ ግብጽ የሚወርዱ ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ
ይህ እንደዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል:: አት “ወንድማችንን በመግደልና አሟሟቱን በመደበቅ እንጠቀምም” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
የዮሴፍን ሞት በደበቅን የሚገልጽ ምሳሌዊ አነጋገር ነው:: አት “አሟሟቱን መደበቅ” (ዘይቤያዊ አባባል ይመልከቱ)
የእስማኤል ዘር ለሆኑ ለእነዚህ ሰዎች
ይህም “አናቆስለው” ወይም “አንጉዳው” ማለት ነው አት: “አንጉዳው” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ሥጋ የሚለው ዘመድ ለሚለው ቃለ የሚቆም ምትክ ቃል ነው:: አት: “እርሱ የሥጋ ዘመዳችን ነው” (ተዛማጅ ምትክ ቃላትን የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
የይሁዳ ወንድሞች ሰሙት ወይም የይሁዳ ወንድሞች በሐሳቡ ተስማሙ
ሁለቱም ስሞች የዮሴፍ ወንድሞች ያገኙአቸው ተመሣሣይ ነጋዴዎችን ያመለክታል
ለሃያ ጥሬ ብር ዋጋ (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት
ሮቤል ወደ ጉድጓዱ ተመልሶ ዮሴፍን በማጣቱ እነሆ ተገረመ:: “እነሆ” የሚለው ቃል ሮቤል ዮሴፍ በሄዱን ባወቀ ጊዜ መገረሙን ያሳያል::
ይህ የጥልቅ ጭንቀትና ሀዘን ምልክት ነው:: ይህ በግልጽ ሊገለጽ ይችላል:: አት: እጅግም ስላዘነ ልብሱን ቀደደ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የዮሴፍ መጥፋቱን ችግር ትኩረት ለመስጠት ሮቤል ጥያቄ ይጠቀማል:: አት: “ብላቴናው ሄዶአል እንግዲህ ወደ ቤት መመለስ አልችልም” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
አባቱ ያዘጋጀለት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ያመለክታል
የፍዬል ደም
እጀ በባቡን አምጥተው
በልቶታል
ያዕቆብ የዮሴፍን አካል ክፉ አውሬ እንደገነጣጠለ አሰበ:: አት: “በእርግጥም ዮሴፍን ቦጫጭቆታል” (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ ይመልከቱ)
ይህ ጥልቅ መጨነቅንና ሀዘንን የሚያመለክት ነው ይህ በግልጽ ሊገለጽ ይችላል አት ያዕቆብ እጅግ ስላዘነ ልብሱን ቀደደ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ወገብ የሰውነት መሀከለኛው አካል ነው አት ማቅ ለብሶ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እዚህ አባታቸውን ለማጽናናት የልጆች መጥጣት እንደ መነሣት ተደርጐ ተገልጾአል:: አት: “ወደ እርሱ መጡ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ነገር ግን እንዲያጽናኑት አልፈቀደም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ከዛሬ ጀምሮ እስከሚሞት ድረስ እንደሚያዝን ይገልጻል:: አት: “በሚሞትበትና ወደ ሙትን ሥፍራ በሚወርድበትም ጊዜም በእርግጥ እያዘንኩ ይሆናል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ምድያማዊያን ዮሴፍን ሸጡት
ንጉሡን ለሚጠብቁ ዘበኞች መሪ
1 በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ሒራ ወደተባለ ዐዱላማዊ ሰው ዘንድ ሄደ፣ መኖሪያውንም 2 እዚያም ሳለ፣ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ ዐየ፤ እርሷንም አግብቶ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ። 3 እርሷም አርግዛ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው። 4 እንደገናም አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም አውናን አለችው። 5 አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው፣ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር። 6 ይሁዳ የመጀመሪያ ልጁን ዔርን ትዕማር ከምትባል ልጃገረድ ጋር አጋባው። 7 የይሁዳ የበኩር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው። 8 ይሁዳ አውናንን፣ “ዋርሳዋ እንደመሆንህ ከወንድምህ ሚስት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በመፈጸም የወንድምህን ስም የሚያስጠራለት ዘር ተካለት አለው። 9 አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የእርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በፈጸመ ቁጥር የወንድሙን ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወለድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስ ነበር። 10 ይህም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሆኖ ስለተገኘ፣ እርሱንም እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው። 11 ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፤ ሴሎም እንደወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለፈራ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች። 12 ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፣ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደተምና ሄደ። 13 ሰዎቹም ለትዕማር፣ “አማትሽ የበጎቹን ጠጉር ወደሚሸልቱ ሰዎች ዘንድ ወደተምና እየሄዱ ነው” አሏት። ይህን እንድሰማች 14 የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፣ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ በር ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፣ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፣ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው። 15 ፊቷ በሻሽ ተሸፋፍኖ ሲያያት፣ ይሁዳ ዝሙት አዳሪ መሰለችው። 16 ምራቱ መሆኗን ባለማወቁ፣ እርሷ ወዳለችበት ወደ መንደሩ ዳር ጠጋ ብሎ፣ “እባክሽን አብሬሽ ልተኛ” አላት። እርሷም፣ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው። 17 “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርሷም “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ ምን መያዣ ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው። 18 “ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፣ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፣ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና አብሯት ተኛ፤ እርሷም አረገዘችለት። 19 ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሽዋን አውልቃ እንደወትሮዋ የመበለት ለብሷን ለበሰች። 20 ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶሎማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፣ እርሱ ግን ሊያገኛት አልቻለም። 21 “በኤናይም ከተማ መግቢያ ከመንገዱ ዳር የነበረች ያቺ ዝሙት አዳሪ የት ደረሰች?” ብሎ ዓዶሎማዊው ሰውዬ ጠየቀ። ሰዎቹም፣ “በዚህ አካባቢ እንደዚህ ያለች ዝሙት አዳሪ የለችም” አሉት። 22 ስለዚህ ወደ ይሁዳ ተመልሶ ሄደና፣ “ላገኛት አልቻልሁም፤ በዚያ የሚኖሩትም ሰዎች፥ ‘እንደዚህ ያለች ዝሙት አዳሪ እዚህ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው። 23 ይሁዳም፣ “እንግዲህ መያዣውን እንደያዘች ትቅር አለዚያ መሳቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፣ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ። 24 ከሦስት ወር ያህል በኋላ፣ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፣ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ። 25 እርሷም ተይዛ በምትወሰድበት ጊዜ ለአማትዋ፣ “እኔ ያረገዝሁት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” ስትል ላከችበት፤ ደግሞም፣ “የማኅተሙ ቀለበት ከነማንጠልጠያውና በትሩ የማን እንደሆነ እስቲ ተመልከት” አለችው። 26 ይሁዳም ዕቃዎቹን አውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም። 27 የመውለጃዋ ጊዜ እንደደረሰም ፅንሷ መንታ መሆኑ ታወቀ። 28 በምትወልድበትም ጊዜ አንደኛው እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም፣ “ይህኛው መጀመሪያ ወጣ” ስትል በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት፤ 29 ነገር ግን፣ እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም፣ “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፣ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ። 30 ከዚያ በኋላ እጁ ላይ ቀይ ክር የታሰረለት ወንድሙ ተወለደ፣ ስሙም ዛራ ተባለ።
ይህ ስለ ይሁዳ የሚናገረውን አድስ የታሪኩን ክፍል ያስታውቃል (አድስ ክስተት መጀመር ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
ኤራስ በዓዶሎም የሚኖር ወንድ ሰው ስም ነው (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ሴዋ ይሁዳን ያገባች ከነዓናዊ ሴት ነች (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
የይሁዳ ሚስት ጸንሣ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “አባቱ ዔር ብሎ ሰየመው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሰየመው
የቦታ ወይም የሀገር ስም ነው (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ይህ የይሁዳ ወንድ ልጅ ስም ነው:: በዘፍጥረት 38:3 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
በእግዚአብሔር ፊት የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር የዔርን ክፋት እንደአየው ያመለክታል:: አት: “ክፉ ነበርና እግዚአብሔር አየው” (ፊሊጣው አነጋገር ይመልከቱ)
ክፉ ከመሆኑ የተነሣ እግዚአብሔር ቀሠፈው:: ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “ስለዚህ እግዚአብሔር ቀሠፈው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ከይሁዳ ወንድ ልጆች የአንዱ ስም ነው በዘፍጥረት 38፡4 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ይህ ታላቅ ወንድም አግብቶ ሳለ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ተከታይ ወንድሙ ወደ መበለትዋ በመግባት ሩካቤ ሥጋ በመፈጸም ዘርን የማስቀጠል ባህል እንደሆነ ያመለክታል መበለትዋ የመጀመሪያ ወንድ ከወለደች ያ ወንድ ልጅ የሞተው ወንድም ልጅ እንደሆነ በመቆጠር የሟቹን ሀብት ይወርሳል::
በእግዚአብሔር ፊት የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር የአውናን ክፋት እንደአየው ያመለክታል:: አት: “ክፉ ነበርና እግዚአብሔር አየው” (ፊሊጣው አነጋገር ይመልከቱ)
ያደረገው ነገር ክፉ ከመሆኑ የተነሣ እግዚአብሔር ቀሠፈው:: ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “ስለዚህ እንዲሁ ደግሞ እግዚአብሔር ቀሠፈው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የታላቅ ወንድ ልጁ ሚስት
ይህም ማለት በዚህ በአባትዋ ቤት እንዲትኖር ነው:: አት “እናም በአባትሽ ቤት… ቢትኖሪ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይሁዳ ትዕማር ሴሎም ለአካለመጠን በደረሰ ጊዜ እንዲታገባው ያስባል፡፡ አት “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን በደረሰ ጊዜ ሊያገባሽ ይችላል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ከይሁዳ ወንድ ልጆች የአንዱ ስም ነው በዘፍጥረት 38፡5 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ሴሎም ትዕማርን ቢያገባ እንደ ወንድሞቹ ይሞትብኛል ብሎ ይሁዳ ሠግቶአል:: አት “እርሱ እርስዋን ካገባ እንደወንድሞቹ ይሞትብኛል ብሎ ስለሠጋ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ የወንድ ሰው ስም ነው በዘፍጥረት 38፡2 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ይሁዳም ሀዘኑን ባቆመ ጊዜ
ተምና የበጎቹንነ ጸጉም የሚሸልቱ ስዎች ወዳሉበት ሥፍራ
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ከዓዶላም ጓደኛው ሒራ አብሮት ሄደ
ሒራ የወንድ ሰው ስም ነው እናም ዓዶላም እርሱ የሚኖርበት ቀበሌ ስም ነው፡፡ በዘፍረት 38፡1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “አንድ ሰው ለትዕማር ነገራት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ስሚ ፤ እዚህ “እይው” የሚለው ቃል የትዕማርን ትኩረት ለመሳብ ተጠቅሞአል፡፡
የባልሽ አባት
መበለቶች የሚለብሱት ልብስ
ሴቶች ፊታቸውንና ጭንቅላታቸውን ለመሸፈን የሚጠቀሙት ከስስ ጨርስ የተሰራ ልብስ
ይህም ሰዎች እንዳያውቃት ራስዋን በልብስ በመከናነብ ሸፈነች ማለት ነው ሴቶች ራሳቸውን መከናነብ የሚያስችላቸው ሰፋፊ ልብሶች በባህሉ የተለመዱ ናቸው አት ሰዎች እንዳያውቃት በሰፋፊ ልብሶች ተከናነበች (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በመንገድ ዳር ወይም በመንገድ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ይሁዳ ለሴሎም ሚስት አድርጐ አልሰጣትም ነበር” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይሁዳ እንደ ጋለሞታ ያሰባት ፊትዋን ስለሸፈነች ብቻ ሳይሆን በከተማው መግቢያም ስለተቀመጠች ነው አት ጭንቅላትዋን ስለሸፈነችና ጋለሞቶች በሚቀመጡበት ቦታ ስለተቀመጠች ነበር (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ትዕማር በመንገዱ ዳር ነበረች አት እርስዋም ወደተቀመጠችበት ወደ መንገዱ ዳር ሄደ ወይም አዘነበለ(ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እባክሽ ወደ እኔ ነዪ ወይም እባክሽ አሁነ ነዪ
የልጁ ሚስት
ከፍዬሎች መንጋዬ
ማኀተም ብር መሣይ በላዩ ላይ ቅርጽ የተቀረጸበት የቀለጠ ሰም ለመቅረጽ የሚጠቀምበት ነው ቀለበት ማኀተም ያለበትና ባለቤቱ በአንገት የሚያደረገው ነው በትር ከረጅም እንጨት የተሠራና በአዳጋች በመንገድ የሚጠቀሙበት ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “እርሱም እርሷን አስረገዛት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሴቶች ፊታቸውንና ጭንቅላታቸውን ለመሸፈን የሚጠቀሙት ከስስ ጨርስ የተሰራ ልብስ ነበር:: በዘፍጥረት 38: 14 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
መበለቶች የሚለብሱትን ልብስ ለበሰች:: በዘፍጥረት 38: 14 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
በአዶሎም ቀበለ የሚኖር ሰው በዘፍጥረት 38፡ 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “መያዣውን ለማስመለስ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ እጅ የሚለው ቃል በእርስዋ ቁጥጥር ሥር እንደሆነ አበክሮት ይሰጣል:: የሴቲቱ እጅ ሴቲቱን ይወክላል:: አት “ከሴቲቱ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
በአዶሎም ቀበለ የሚኖር ሰው በዘፍጥረት 38 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በዚያ ከሚኖሩ ሰዎች እንዳንዶች
በቤተ ጣዖት የሚታገለግል ዝሙት አዳሪ
ይህ የቦታ ስም ነው በዘፍጥረት 38፡14 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የሆነውን ነገር ሰዎች ከሰሙ በይሁዳ ይስቁበታል ይሣለቁበታል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ወይም ደግሞ የሆነውን ሰዎች ካወቁ ይስቁብናል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ እና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ የታሪኩን አድስ አካል ጅማሬ ያመለክታል (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አንድ ሰው ለይሁዳ ነገረው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ትዕማር የታላቅ ልጅህ ሚስት
ከዚህ የሚለው ቃል ከዝሙት ከፈጸመችው ዝሙት ማለት ነው ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከዚህም አረገዘች” ወይም “አረገዘች” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አውጡአት
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እንዲትሞት እናቃጥላታለን” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እነርሱ ባወጡአት ጊዜ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የባልዋ አባት
ማኀተም ብር መሣይ በላዩ ላይ ቅርጽ የተቀረጸበት የቀለጠ ሰም ለመቅረጽ የሚጠቀምበት ነው:: ቀለበት ማኀተም ያለበትና ባለቤቱ በአንገት የሚያደረገው ነው በትር ከረጅም እንጨት የተሠራና በአዳጋች በመንገድ የሚጠቀሙበት ነው:: (በዘፍጥረት 38: 18 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ)
ይህ ከይሁዳ ወንድ ልጆች የአንዱ ስም ነው:: በዘፍጥረት 38፡5 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተረጐም ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ የታሪኩ አድስ ክፍል መጀመሩን ያመለክታል (አድስ ክስተት ስለማታወቅ ይመልከቱ)
እነሆ የሚለው ከዚህ በፊት ያልታወቀው ትዕማር መንታ ልጆችን እንደተሸከመች እንድንገረም ለማድረግ ተጠቅሞአል
እንዲህ ሆነ የሚለው ሀረግ በታሪኩ ዋና ክስተት ያመለክታል በቋንቋዎ ይህን የመሰለውን የመግለጽ አባባል ካለ ይጠቀሙ
ከሕጻኖች አንደኛው እጁን አወጣ
አንድ ሴት በሚትወልድበት ጊዜ የሚረዳት ሰው ነው በዘፍረት 35:17 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
ደማቅ ቀይ ክር
በአምባሩ ዙሪያ
እነሆ የሚለው ቃል ለሚከተለው የሚያስገርም መረጃ ትኩረት እንድንሰጠው ነው
ይህ ሁለተኛው ሕጻን ቀድም ሲወጣ አዋላጅዋ በማየት የተደነቀችውን የሚያሳይ ነው:: አት “እንዴት የራስህን መንገድ ጥሰህ ወጣህ!” ወይም “ሰንጥቀህ ቀድመህ ወጣህ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመለከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት “እርስዋ ስም ሰጠችው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የወንድ ልጅ ስም ነው ተርጓሚዎች እንደሚከተለው የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ:: ፋሬስ የሚለው ስም ጥሶ መውጣት ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የወንድ ልጅ ስም ነው ተርጓሚዎች እንደሚከተለው የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ:: ዛራ የሚለው ስም ቀይ ክር ወይም ደማቅ ቀይ ክር ማለት ነው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
1 ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖንም ሹማምንት አንዱ የነበረውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብፃዊው ጴጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው። 2 እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ስለነበረ ኑሮው ተቃናለት፤ እርሱም በግብፃዊው አሳዳሪው ቤት ኖረ። 3 አሳዳሪው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለና ሥራውንም ሁሉ እንዳከናወነለት ባየ ጊዜ፣ 4 ዮሴፍ በእርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፣ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፣ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኃፊነት ሰጠው። 5 ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር የግብፅዊውን ቤት ባረከ፣ የእግዚአብሔርም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ። 6 ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፣ የቀረበለትንም ከመመገብ በስተቀር፣ ማናቸውንም ጉዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ-መልካም ነበር፤ 7 ከጊዜ በኋላ የጌታው ሚስት ዮሴፍን ተመልክታ ስላፈቀረችው፣ “ና ከእኔ ጋር አብረን እንተኛ” አለችው። 8 እርሱ ግን ይህን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኃላፊነት ስለሰጠኝ፣ በቤቱ ውስጥ ስላልው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። 9 በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኃላፊነት ያለው ማንም የለም፣ ከአንቺ በቀር በእኔ ቁጥጥር ሥር ያላደረገው ምንም ነገር የለም፤ ይኸውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ፣ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እፈጽማለሁ?” 10 ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር፤ እርሱም ከእርሷ ጋር ይተኛ ዘንድ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም። 11 አንድ ቀን ዮሴፍ ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤት ሲገባ በቤት ውስጥ አንድም ሠራተኛ አልነበረም፤ 12 እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ፣ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጅዋ ላይ ትቶላት ከቤት ሸሽቶ ወጣ። 13 እርሷም ልብሱን በእጅዋ ላይ ትቶ ከቤት ሸሽቶ መውጣቱን በተመለከተች ጊዜ፣ 14 አገልጋዮችዋን ጠርታ እንዲህ አለቻቸው፣ “እነሆ፣ ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ ሊያዋርደኝ ነበር፤ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፤ እኔ ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ። 15 ዕርዳታ ለማግኘትም መጮኼን በሰማ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።” 16 የዮሴፍ አሳዳሪ እስኪመጣ ድረስ ልብሱን በእርስዋ ዘንድ አቆየችው። 17 በመጣም ጊዜ የሆነውን ታሪክ እንዲህ ስትል ዘርዝራ ነገረችው፤ “አንተ ወደዚህ የመጣኸው ዕብራዊ አገልጋይ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊያዋርደኝ ነበር። 18 ነገር ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ በጮኽሁ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።” 19 “የአንተ አገልጋይ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን ታሪክ በሰማ ጊዜ የዮሴፍ አሳዳሪ እጅግ ተቆጣ። 20 ዮሴፍንም ወስዶ፣ የንጉሥ እስረኞች ወደታሠሩበት እስር ቤት አስገባው። 21 እግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍቅሩን ዐሳየው፣ በእስር ቤት አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው። 22 ስለዚህ የእስር ቤቱ አዛዥ ዮሴፍን የእስረኞች ሁሉ አለቃ አደረገው፤ በእስር ቤት ላለውም ነገር ሁሉ ኃላፊ ሆነ። 23 እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እንዲቃናለት ስላደረገ የእስር ቤት አዛዥ በዮሴፍ ቁጥጥር ሥር በነበረው ነገር ምንም ዐሳብ አልነበረበትም።
ወደ ግብጽ መጓዝ ወደ ላይ ወደ ተስፋይቱ ምድር የመጓዝ ተጻራሪ ወደ ታች መውረድ ተደርጐ ይቆጠራል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እስማኤላዊያን ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት” (ፈሊጣዊ አነጋገርና ተሻጋሪ ግሥ እና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ እግዚአብሔር ዮሴፍን ረድቶታል ሁልጊዜም ከእርሱ ጋር ነበር ማለት ነው:: አት “እግዚአብሔር ዮሴፍን መራው አገዘውም” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ ጸሓፊው በአሳዳሪው ቤት መሥራቱን በአሳዳሪው ቤት እንደመኖር ይናገራል:: በአሳዳሪዎቻቸው ቤት መሥራት የሚችሉት በጣም ታማኝ የሆኑ ሎሌዎች ብቻ ናቸው፡፡ አት እርሱም በቤት ውስጥ ይሠራ ነበር (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አሳዳሪው እግዚአብሔር እርሱን እየረዳ እንደሆነ አየ ማለት ነው አት እግዚአብሔር እየረዳው እንደሆነ አሳዳሪው አየ (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ዮሴፍ የሚሠራው ሁሉ መከናወንለት አደረገ
ሞገስ ማግኘት በአንድ ሰው ተቀባይነትን ማስረገጥ ማለት ነው በእርሱ ዘንድ የሚለው ፈሊጣዊ አባባል በሰውዬው አመለካከት እንደሆነ ያመለክታል:: ተገቢ ትርጉሞች እነሆ 1) ጲጥፋራ በዮሴፍ ተደስቶአል 2) እግዚአብሔር በዮሴፍ ተደስቶአል (ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ)
የጲጥፋራ የግል ሎሌው ነበር ማለት ነው
ጲጥፋራ በቤቱና የጲጥፋራ በሆነው ሁሉ ላይ ለዮሴፍ በኃላፊነት ሰጠው
አንድ ነገር በአንድ ሰው ኃላፊነት ሥር ሲሆን ያ ሰው ያንን ነገር ለመንከባከብና ደኀንነቱን ለመጠበቅ ኃላፊነት አለው ማለት ነው:: አት “ዮሴፍ እንዲንከባከብ ሰጠው” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ተውላጤ ስሞችን ከመጠቀምዎ በፊት “ዮሴፍ” እና “ግብጻዊው” የሚሉ ቃላትን መጠቀም ይችላሉ:: ግብጻዊው ዮሴፍን በቤቱና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ኃላፊነት ሰጠው እናም ከጊዜ ወደ ጊዜ በዮሴፍ ምክንያት እግዚአብሔር የግብጻዊውን ቤት ባረከ::
እነዚህ ሁለቱ ጥቅሶች ለሚቀጥለው ክስተት ዳራ መረጃ እንደሆኑ ለአንባቢያን ለመናገር ይህ ሀረግ ተጠቅሞአል
ጲጥፋራ ዮሴፍን በቤቱና ባለው ተብት ሁሉ ላይ ሾመው
በሚባረከው ነገር ወይም ሰው መልካም ወይም ጠቃሚ ነገር እንዲደረግ ምክንያት መሆን ማለት ነው
እዚህ ጸሐፊው እግዚአብሔር የሰጠውን በረከት በአንድ ነገር ላይ እንደተቀመጠ መሸፈኛ አድርጐ ይናገራል:: አት: “እግዚአብሔር ባረከ” ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ
ይህ ቤት እረሻውንና ከብቶችን ያለመክታል የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “በጲጥፋራ ቤትና በከብቶችና እርሻው ሁሉ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቀ መረጃ ይመልከቱ)
አንድ ነገር በአንድ ሰው ቁጥጥር ሥር ሲሆን ያ ሰው ሊጠብቀውና ሊንከባከበው ኃላፊነት አለው ማለት ነው አት: “ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ለዮሴፍ ስልጣን ሰጠው”
ምን ምግብ መመገብ እንዳለበት ከመወሰን በቀር በቤቱ ስላለው ማንኛውም ነገር አይጨነቅም ነበር ይህ በአዎንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል አት ጲጥፋራ ምን መመገብ እንደሚፈልግ ብቻ ማሰብ ነበረበት በቤቱ ስላለው ማንኛውም ነገር መጨነቅ የለበትም (ግምታዊ እውቀትና ጥልቀ መረጃ ይመልከቱ)
“አሁንም” የሚለው ቃል ስለ ዮሴፍ ዳራ መረጃ ለመስጠት በታሪኩ መስመር ውስጥ ጣልቃ ማስገባቱን ያመለክታል (ዳራ መረጃ ይመልከቱ)
ሁለቱም ቃላት ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ዮሴፍ የሚያስደስት ቁመና እንዳለው ያመለክታሉ:: ጠንካራና ጥሩ ቁመና ነበረው:: አት: “ጠንካራና መልከመልካም ነበር”
እናም ደግሞ ይህ ሀረግ አድስ ክስተት መጀመሩን ሊያመለክት ተጠቅሞአል (አዲስ ክስተት ማታወቅ ይመልከቱ)
ስሚው ዮሴፍ የጲጥፋራን ሚስት መስብ/ትኩረት ለማግኘት ይህን ቃል ተጠቅሞአል
“ጌታዬ በኃላፊነቴ ሥር ስላለው ስለቤቱ ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም”:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ጌታዬ ስለቤቱ ያምነኛል” (ድርብ አሉታዊነት ይመልከቱ)
አንድ ነገር “በአንድ ሰው ኃላፊነት ሥር” ሲሆን ያ ሰው እንዲንከባከበውና እንዲጠብቀው ኃላፊነት አለው ማለት ነው:: አት፡ “ያለውን ሁሉ በኃላፊነት ስለሰጠኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ ጸሓፊው ኃላፊነትን እንደ ትልቅነት ይናገራል አት: “ከማንም ሰው የበለጠ ለዚህ ቤት ኃላፊነት አለኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ በአዎንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “እርሱ ያለሰጠኝ ነገር ቢኖር አንቺን ብቻ ነው” (አሉታዊነትን በአዎንታዊነት የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ዮሴፍ ትኩረት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማል ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ይህን ክፉ ድርጊት ፈጽሜ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት አልሠራም (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ከእርስዋ ጋር እንዲተኛ በተደጋጋሚ ትጠይቀው ነበር ማለት ነው:: የዚህ ጥቅስ ሙሉ ትርጉሙ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “ዮሴፍ ከእርስዋ ጋር እንዲተኛ ትጐተጉተው ነበር” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እንዲቀርባት
“እንዲሁም ደግሞ” የሚለው ሀረግ በታሪኩ አድስ ክስተት መጀመሩን ለማመልከት ነው (አዲስ ክስተት ስለማታወቅ ይመልከቱ)
በቤቱ ከሚያገለግሉ ሰዎች ማንም
“እናም ወዲያው ሮጦ ወደ ውጪ ወጣ” ወይም “እናም ወዲያው ሮጦ ከቤት ወጣ”
ከዚያም …. ጠራች እንዲህም ሆነ የሚለው ሀረግ በታሪኩ ሁለተኛውን ክስተት ለማመልከት ተጠቅሞአል (አዲስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
ወዲያው ሮጦ ከቤት ወጣ
በቤትዋ የሚሠሩ ሰዎች
“ተመልከቱ” ወይም “ሰማችሁ” ወይም “ስለሚናገረው ነገር ትኩረት አድርጉ”
እዚህ የጲጥፋራ ሚስት ዮሴፍ ሊይዛትና ከእርስዋ ጋር ሊተኛ እንደሞከረ ትከሳለች
ድምጼን ከፍ አድርጌ መጮሄን ሲሰማ እንዲህም ሆነ የሚለው ሀረግ የተጠቀመው በታሪኩ ሁለተኛውን ክስተት ለማመልከት ነው (አዲስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
የዮሴፍ ጌታ ይህ ጲጥፋራን ያመለክታል::
ይህን ነገር እንዲህ ብላ ነገረችው
“እኛ” የሚለው ቃል ጲጥፋራን ሚስቱንና ሌሎች በቤት ውስጥ ያሉትን ጠቃልላል (ሁሉ አቀፍ እኛን ይመልከቱ)
መሣቂያ ሊያደርገኝ ወደ እኔ ገባ መሣለቂያ የሚለው ቃል ሊይዘኝና ከእኔ ጋር ሊተኛ የሚለውን አባባል በንኀብነት ወይም አንድን ነገር ለዘብ ባለ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚገለጽ ነው:: አት “ወዳለሁበት ገባ አስገድዶ ከእኔ ጋር ሊተኛ ሞከረ” (ንኀብነት ወይም አንድን ነገር ለዘብ ባለ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚገለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
“ከዚያም” የጲጥፋራ ሚስት ይህን ሀረግ የተጠቀመችው ዮሴፍ ከእርስዋ ጋር ለመተኛት መሞከሩን ለእርሱ የሚትነግረውን የታሪኩን ሁለተኛውን ክስተት ለማመልከት ነው::(አዲስ ክስተት ስለማታወቅ ይመልከቱ)
ወዲያው ሮጦ ከቤት ወጣ
“እንዲህም ሆነ” የሚለው ሀረግ በታሪኩ አዲስ ክስተት መጀመሩን ለማመልከት ተጠቅሞአል (አዲስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
የዮሴፍ ጌታ ይህ ጲጥፋራን ያመለክታል ይህ መረጃ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት የዮሴፍ ጌታ ጲጥፋራ
ጲጥፋራ እጅግ ተቈጣ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አተ ንጉሡ እስረኞችን ያኖረበት ቦታ ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ
ዮሴፍ በዚያ ቆየ
እግዚአብሔር ለዮሴፍ ተጠነቀቀለት እናም ቸር ነበረ:: “ነገር ግን እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቸር ነበር” ወይም “እግዚአብሔር ዮሴፍን ተንከባከበ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ታማኝነት” የሚለው ረቂቅ ስም “ታማኝ” ወይም “በታማኝነት” ሊገለጽ ይችላል:: አት ከእርሱ ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ታማኝ ነበር ወይም በታማኝነት ወደደው (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ይህም እግዚአብሔር የወህኑ ቤት አዛዥ ዮሴፍን እንዲቀበለውና እንዲንከባከበው አደረገው አት እግዚአብሔር የእስር ቤቱ አዛዥ በዮሴፍ እንዲደሰት አደረገው (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“የእስረኞች አስተዳደር” ወይም “በእስር ቤቱ ኃላፊነት የተሰጠው”
እዚህ “እጅ” የሚለው የዮሴፍን ኃይል/አቅም ወይም ታማኝ ኃላፊነት ይወክላል”” አት “ዮሴፍን አለቃ አደረገው” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ዮሴፍ በዚያ ለሚደረገው ነገር ሁሉ ኃላፊ ነበር”
ይህ እግዚአብሔር እንዴት እንደረዳውና እንደመራው የሚያመለክት ነው፡፡ አት “እግዚአብሔር ዮሴፍን ስለመራው” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ዮሴፍ የሚያደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር ያሳካለት ነበር
1 ከዚህም በኋላ የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊውና የእንጀራ ቤት ኃላፊው ንጉሡን የሚያሳዝን በደል ፈጸሙ። 2 ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዡ፣ በሁለቱም ሹማምንቱ ላይ እጅግ ተቆጣ፤ 3 በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደታሠረበት እስር ቤት አስገባቸው። 4 የዘበኞቹም አለቃ እስረኞቹን ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ በእስር ቤትም ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። 5 ታስረው የነበሩት የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም ዐዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍቺ ነበረው። 6 በማግስቱ ጥዋት ዮሴፍ እነርሱ ወዳሉበት ክፍል በገባ ጊዜ ተክዘው አገኛቸውና፤ 7 “ዛሬ በፊታችሁ ላይ ሐዘን የሚታየው ለምንድን ነው?” አላቸው። 8 እነርሱም፣ “ሁለታችንም ሕልም ዐየን፤ ነገር ግን የሚተረጉምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፣ “ሕልም የመተርጎም ችሎታ የሚሰጥ እግዝአብሔር ነው፣ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው። 9 ስለዚህ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፤ “ከፊት ለፊቴ አንዲት የወይን ተክል ዐየሁ፤ 10 ተክሏም ሦስት ሐረጎች ነበሯት፤ ወዲያው እቆጥቁጣ አበበች፤ የወይን ዘለላውም ወዲያው በሰለ። 11 የፈርዖንንም ጽዋ ይዤ ነበር፣ የወይኑን ፍሬ ለቅሜ በጽዋው ውስጥ ጨምቄ ጽዋውን በእጁ ሰጠሁት።” 12 ዮሴፍም እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ የሕልሙ ትርጓሜ ይህ ነው፤ ሦስቱ ሐረግ ሦስት ቀን ነው፤ 13 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፣ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል፤ በፊት የመጠጥ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ኡሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ። 14 እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፣ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤ 15 ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በአፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።” 16 የእንጀራ ቤት አዛዡም፣ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም የተሰጠው ፍቺ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፣ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፣ ሦስት መሶቦች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 17 በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፣ ነገር ግን ወፎች ምግቡን ከመሶቡ እያነሱ የበሉት ነበር።” 18 ዮሴፍም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ 19 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ራስህን ካስቆረጠ በኋላ በእንጨት ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን የበሉታል።” 20 በሦስተኛው ቀን የፈርዖን ልደት በዓል ስለነበር ለመኳንንቱ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ በዚያኑ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምንቱ ካሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው። 21 የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር፤ 22 የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው ሰቀለው። 23 የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው።
ይህ ሀረግ የተጠቀመው በታሪኩ አዲስ ክስተት መጀመሩን ለማመልከት ነው፡፡ (አዲስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
ይህ ለንጉሡ መጠጥ የሚያቀርብ ሰው ነው
ይህ ለንጉሡ ምግብ የሚያዘጋጅ ሰው ነው
ጌታቸውን አስቆጡት
ዋና የመጠጥ አሳላፊና ዋና እንጀራ እቅራቢ
በዘበኞቹ አለቃ በሚተዳደረው የቤት ውስጥ እስር ቤት አስገባቸው
ንጉሡ ወደ እሥር ቤት አላስገባቸውም ነገር ግን እንዲታሠሩ አዘዛቸው፡፡ አት “እነርሱ እንዲያስገቡ አደረጋቸው” ወይም “ዘበኛው እንዲያስገባቸው አዘዘ” (ተዛማጅ ምትክ አባባሎችን የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ይህ ዮሴፍ የነበረበት ተመሣሣይ እስር ቤት ነው ወይም ይህ ጲጥፋራ ዮሴፍን ያስገባበት ተመሣሣይ እስር ቤት ነው (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
በእስር ቤት አያለ ጊዜያት ቀን ተቀመጡ
ዮሴፍ ወደ መጠጥ አሳላፊውና እንጀራ አቅራቢው ገባ
እነሆም የሚለው ቃል ባየው ነገር ዮሴፍ እንዴት እንደተገረመ የሚያሳይ ነው:: አት “እነርሱን አዝነው በማየቱ ተገረመ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ የጠጅ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ አቅራቢዎች አዛዥ ያመለክታል
በጌታው ግቢ በእስር ቤት፤ ጌታው የዮሴፍ ጌታ፤ የዘበኞች አለቃ የሚያመለክት ነው
አጽንዖት ለመስጠት ዮሴፍ ጥያቄ ይመለከታል:: ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ትርጓሜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው! ወይም ለሕልሞች ትርጉምን መስጠት የሚችል እግዚአብሔር ነው” (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ሕልማቸውን እንዲነግሩት ዮሴፍ ይጠይቃቸዋል:: አት “ሕልሞቻችሁን እባካችሁ ንገሩኝ”
ለንጉሡ መጠጦችን የሚያቀርብ ዋና ሰው ነው”” በዘፍጥረት 4ዐ: 2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
“በሕልሜ የወይን ጣፍ በፋቴ ሆና አየሁ!” የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ባየው ነገር እንደተደነቀና ዮሴፍ ትኩረት እንዲሰጠው ለማሳየት “እነሆ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል::
ዘለላዎችዋም ተንዠርግገው በሰሉ
ከእነዚያ የጁስ ጭማቂ አወጣሁ ማለት ነው አት ከእነዚያ ጁስ ጨምቄ አወጣሁ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የሕልሙ ትርጓሜ ይህ ነው
ሶስት ሐረጐች ሶስት ቀኖች ያመለክታሉ
እስከ ሶስት ቀኖች
እዚህ ፊርዖን ከእስር ቤት የመጠጥ አሳላፊዎችን አለቃ የሚያወጣው ፈርዖን ከፍ ከፍ እንደሚያደርገው ተደርጐ ተነግሮአል:: አት “ከእስር ቤት ያወጣሃል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ወደ ሥራህ ይመልስሃል
በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው
ቸር ሁንልኝ
ዮሴፍም የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ስለእርሱ ለፈርዖን እንዲነግረው ከዚህም የተነሣ ፈርዖን ከእስር ቤት እንዲያስወጣው ማለት ነው:: አት: “ስለእኔ ለፈርዖን በመንገር ከእስር ቤት እንዲወጣ እርዳኝ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “በእርግጥ ሰዎች አፍነው እምጥተውኛል” ወይም “በእርግጥ እስማኤላዊያን ይዘው አምጥተውኛል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ዕብራዊ ሰዎች ከሚኖሩበት ምድር
እናም ደግሞ እዚህ በግብጽ በሚርበት ጊዜ በእስር ቤት እንዲጣል የሚያደርገኝን ምንም ነገር አላደረግሁም
ይህ ለንጉሡ ምግብ የሚያቀርብ መሪ ሰው እንደሆነ ያመለክታል:: በዘፍጥረት 4ዐ:2 ይህ እንዴት እንደተተረጐመ ይመልከቱ::
እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ እናም በሕልሜ
ሶስተ መሶብ እንጀራ በራሴ ላይ ተሽክሜ ነበር! እዚህ የእንጀራ ቤቱ አዛዥ “እነሆ” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው ባየው ሕልም መገረሙንና ዮሴፍም ትኩረት እንዲሰጠው ለማሳየት ነው::
ለፈርዖን ከተዘጋጀው ምግብ
የሕልሙ ትርጉም ይህ ነው
ሶስት መሶቦች ሶስት ቀኖችን ይወክላሉ
ዮሴፍ በዘፍረት 4ዐ:13 ለመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ በሚናገርበት ጊዜ ደግሞ ራስህን ከፍ ያደርጋል የሚለውን ሀረግ ተጠቅሞአል እዚህ ግን የተለየ ትርጉም አለው አማራጭ ተገቢ ትርጉሞች: (1) በአንገትህ ገመድ በማሠር ራስህን ከፍ ያደርጋል ወይም (2) ራስህን በመቁረጥ ከፍ ያደርግሃል::
የ “ሥጋ” ቀጥታ ትርጉሙ የአንድ ሰው አካል ክፍል ማለት ነው
ከዚያም በኋላ በሶስተኛውም ቀን እዚህ እንዲህም ሆነ የሚለው ሀረግ የተጠቀመው አዲስ ክስተትን ለማመልከት ነው (አዲስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
ግብዣ ነበረው
ይህ ለንጉሡ መጠጥን የሚያዘጋጅና የሚያቀርብ መሪ ሰው ነበር፡፡ በዘፍጥረት 4ዐ፡2 እነዚህ ቃላት እንዴት እንደተተረጐሙ ይመልከቱ፡
ይህ ለንጉሡ ምግብን የሚያዘጋጅ መሪ ሰው እንደሆነ ያመለክታል:: በዘፍጥረት 4ዐ:2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ሹመት ወይም ኃላፊነት እንደመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ሥራው እንደሆነ ያመለክታል አት ለመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ሥራውን መልሶ ሰጠው (ተዛማጅ ምትክ ቃላትን ስለመጠቀም ይመልከቱ)
ፈርዖን ራሱ አልሰቀለውም ይሁን እንጂ እንዲሰቀል አዘዘ አት የእንጀራ ቤት አዛዥ እንዲሰቀል አዘዘ ወይም ዘበኞቹ ወይም ጥበቃዎቹ የእንጀራ ቤት አዛዡን እንዲሰቅሉ አዘዘ (ተዛማጅ ምትክ ቃላትን ስለመጠቀም ይመልከቱ)
ይህ ዮሴፍ ሕልማቸውን እንደተረጐመላቸው የሚለውን ያመለክታል አት የሁለቱን ሰዎች ሕልም ዮሴፍ እንደተረጐመላቸው እንዲሁ ሆነ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
1 ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለም፤ ሕልሙም በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤ 2 እነሆ፣ መልካቸው ያማረ፣ ሥጋቸው የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ይበሉ ጀመር። 3 ቀጥሎም መልካቸው የከፋ አጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወጡት ላሞች አጠገብ ቆሙ። 4 እነዚህ መልካቸው የከፋና አጥንታቸው የወጣ ላሞች፥ እነዚያን ያማሩና የወፈሩ ላሞች ሲውጡአቸው ዐየ፤ ከዚያም ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ። 5 ፈርዖንም እንደገና እንቅልፍ ወስዶት ሳለ ሌላ ሕልም ዐየ። በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዐየ፤ 6 ቀጥሎም የቀጨጩና ከበረሐ በተነሣ የምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎች ወጡ። 7 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፤ ሰባቱን የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጡአቸው፤ በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፣ ነገሩ ሕልም ነበር። 8 በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፣ ስለዚህ በግብፅ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፣ ይሁን እንጂ፣ ሕልሞቹን ሊተረጉምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም። 9 በዚያን ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ “የሠራሁት በደል ዛሬ ታወሰኝ። 10 ፈርዖን ሆይ! አንተ በእኔና በእንጀራ ቤት ኃላፊው ላይ ተቆጥተህ በዘበኞች አለቃ ቤት እንድንታሰር አድርገህ ነበር፤ 11 በዚያ ሳለን በአንድ ሌሊት ሁለታችንም የተለያየ ሕልም ዐየን፤ የእያንዳንዳችንም ሕልም የተለያየ ትርጉም ነበረው። 12 በዚያን ጊዜ የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የሆን አንድ ዕብራዊ ወጣት ከእኛ ጋር እስር ቤት ነበር። ሕልማችንን በነገርነው ጊዜ፣ ፍቺውን ነገረን፤ ለእያንዳንዳችንም እንደ ሕልማችን ተረጎመልን፤ 13 ነገሩም ልክ እርሱ እንደተረጎመልን፤ እኔ ወደ ቀድሞ ሹመቴ ተመለስሁ፤ የእንጀራ ቤት አዛዡም ተሰቀለ። 14 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ትዕዛዝ ሰጠ፤ ከእስር ቤትም በጥድፊያ ይዘውት መጡ፤ ጠጉሩንም ከተላጨና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ፈርዖን ፊት ቀረበ 15 ፈርዖንም ዮሴፍን፣ “ሕልም ዐይቼ ነበር፣ ሕልሜን ሊተረጉምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፣ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጎም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው። 16 ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “ይህ በእኔ አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በበጎነት ይመልስለታል” 17 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሕልሜ በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር። 18 ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው የማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ ዐየሁ። 19 ከእነርሱም በኋላ ዐቅመ ደካማ፣ መልካቸው እጅግ የከፋና አጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብፅ ምድር ከቶ ዐይቼ አላውቅም። 20 አጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፣ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። 21 ከዋጧቸውም በኋላ፣ ያው የበፊቱ መልካቸው ስላልተለወጠ እንደዋጧቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ ከዚያም ከእንቅልፌ ነቃሁ 22 ደግሞም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዐየሁ፤ 23 ቀጥሎም የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ። 24 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ያየኋቸውንም ሕልሞች ለአስማተኞች ነገርሁ፣ ነገር ግን ሕልሞቹን ማንም ሊተረጉምልኝ አልቻለም።” 25 ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዓይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል። 26 ሰባቱ የሚያምሩ ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው። 27 ከእነርሱም በኋላ አጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው። 28 አስቀድሜ ለፈርዖን እንደተናገርሁት እግዚአብሔር ወደፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል። 29 በመላው የግብፅ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ። 30 በዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጎዳት በግብፅ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም። 31 ከጥጋብ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል። 32 ሕልሙ ለፈርዖን በድጋሚ መታየቱ፣ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቆረጠ ስለሆነ ነው፤ ይህንንም እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ይፈጽመዋል፤ 33 እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፣ በመላው የግብፅ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም። 34 እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፣ አንድ አምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኃላፊዎችን ይሹም። 35 እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ። 36 የሚከማቸው እህል፣ ወደፊት በግብፅ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም። 37 ዕቅዱም ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት። 38 ፈርዖንም፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ልናገኝ እንችላለን?” ብሎ ጠየቃቸው። 39 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፣ “እግዚአብሔር ይህን ሁል ገለጠለህ እንዳንተ ያለ አስተዋይና ብልህ ሰው የለም። 40 አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።” 41 ከዚያም፣ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “በመላይቱ የግብፅ ምድር ላይ ኃላፊ አድርጌሃለሁ” አለው። 42 ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት። 43 በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፣ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው። 44 ከዝህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም በመላይቱ ግብፅ ያለ አንተ ፈቃድ ማንም ሰው እጁን ወይም እግሩን ማንቀሳቀስ አይችልም” አለው። 45 ፈርዖን ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም አስናት ተብላ የምትጠራውን ኦን ተብሎ የሚጠራው ከተማ ካህን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው። 46 ዮሴፍ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብፅን ምድር በሙሉ ዞረ። 47 በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። 48 በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፣ ዮሴፍ በግብፅ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፣ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ። 49 ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር። 50 ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣታቸው በፊት የኦን ከተማ ካህን የጶጢፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንድ ልጆች ወለደችለት። 51 ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው። 52 እንደዚሁም “መከራ በተቀበልሁበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው። 53 በግብፅ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን አለፈና 54 ዮሴፍ አስቀድሞ እንደተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፣ በመላው የግብፅ ምድር መስፋፋት ሲጀመር፣ 55 ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፍርዖንም ግብፃውያኑን፣ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው። 56 ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለሄደ፣ ዮሴፍ ጎተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላይቱ ግብፅ ጸንቶ ነበር። 57 ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለነበር፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ምድር መጡ።
ይህ ሀረግ የታሪኩ አድስ ክፍል መጀመሩን ያመለክታል በቋንቋዎ ይህን የሚገልጹበት መንገድ ካለ ያን ሊጠቀሙ ይችላሉ (አዲስ ክስተትን ማስታወቅ ይመልከቱ)
በእስር ቤት ከዮሴፍ አብረውት ስለነበሩት የፈርዖን መጠጥ አሳላፊዎች አለቃና እንጀራ ቤት አዛዥ ሕልሞችን ዮሴፍ ከተረጐመላቸው ሁለት ዓመታት ካለፊ በኋላ
እዚህ እነሆ የሚለው ቃል በሰፊው ታሪክ ሌላ ክስተት መጀመሩን ያመለክታል በቋንቋዎ ይህን የሚገልጹበት መንገድ ሊኖር ይችላል፡፡ አት “ቆሞ በመገኘቱ ገርሞት ነበር”
ፈርዖ ቆሞ ነበር
ጤናማና የወፈሩ
በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ይበሉ ነበር
በረግረጋማ ቦታ የሚበቅል ቀጭንና ረጅም ሣር ነው
እዚህ እነሆ የሚለው ቃል ፈረዖን እንደገና ባየው ነገር እንደተገረመ ያሳያል
ታማሚና የከሱ
“በወንዝ ዳር” ወይም “ወንዝ ዳረቻ ላይ” ይህ በአንድ ወንዝ ዳር ጠርዝ የሚገኝ ከፍታ ያለው መሬት ማለት ነው::
“ደካማና የከሱ” በዘፍጥረት 41:3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
“ጤናማና የደለቡ ወይም በደንብ የበሉ” በዘፍጥረት 41:2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ከእንቅልፉ ነቃ
“ሁለት” የሚለው ቃል ተራ ቁጥር ሁለት ነው:: አት “እንደገና” (ተራ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
እዚህ እነሆ የሚለው ቃል ፈርዖን ባየው ነገር እንደተገረመ የሚያሳይ ነው
ዛላዎች ፍሬዎች የሚንዠረግጉበት የበቆሎ ተክል አካል ነው
“በአንድ አገዳ ላይ ያፌራውን ወይም የተንዠረገገውን” አገዳ ወፍራምና ረጅም የተክል ክፍል ነው::
በአንድ አገዳ ጤናማና ያማረ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ያም ከምሥራቅ ደረቅ አየር የትነሳ የቀጨጩና በዋግ የተመቱ” (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የምሥራቅ ንፋስ ከረሃማ ተነሥቶ የሚነፍስ ነው፡፡ የምስራቅ ንፋስ ሙቀት እጅግ ጐጂ ነው፡፡
ዛላዎች አደጉ ወይም ተንዠረገጉ
እህል የተባለው ቃል የታወቀ ነው:: አት “የቀጨጩ የእህል ዛላዎች” (የተደበቁ ቃላትን የመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
በሉአቸው ሰው ምግብን እንደሚበላ የቀጨጩ የእሸት ዛላዎች ጤናማ የእሸት ዛላዎች ሲውጡ ፈርዖን በሕልሙ አየ
ጤናማና መልካም የእሸት ዛላዎች
ከእንቅልፉ ነቃ
እዚህ እነሆ የሚለው ቃል ፈርዖ ባየው ነገር እንደተገረመ ያሳያል
ሕልም ሲያልም ነበር
ይህ ሀረግ የተጠቀመው የታሪኩ አድስ ክፍል መጀመሩን ለማመልከት ነው:: በቋንቋዎ ይህን የሚገልጹበት መንገድ ካለ ይጠቀሙ:: (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይጠቀሙ)
እዚህ መንፈሱ የሚለው ቃለ የውስጥ ማንነቱን ወይም ስሜቱን ያመለክታል አት “በውስጥ ማንነቱ ታወከ” ወይም “ታወከ” (ተመሣሣይ ምትክ ቃል ስለመጠቀም ይመልከቱ)
አገልጋዮቹን እንደላካቸው መረዳት ይቻላል:: አት “እንዲጠሩ አገልጋዮቹን ላካቸው ወይም አገልጋዮቹ እንደጠሩ አዘዛቸው” (የተደበቁ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
የጥንት ነገሥታት አስማተኞችንና ጥበበኞችን እንደአማካሪዎች ይጠቀሙ ነበር
ይህ ለንጉሡ መጠጥን የሚያዘጋጅና የሚያቀርብ መሪ ሰው ነበር፡፡ በዘፍጥረት 4ዐ፡2 እነዚህ ቃላት እንዴት እንደተተረጐሙ ይመልከቱ፡
ዛሬ የሚለው ቃል የተጠቀመው አስንዎት ለመስጠት ነው በደሉ ቀደም ብሎ ለፈርዖን መናገር የነበረበት አንድ ነገር ነገር ግን ያልተናገረበት ነው:: አት “ለአንተ መናገር የረሳሁትን አሁን አስታወስኩ”
የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ፈርዖንን አንደ ሶሰተኛ ወገን ሰው ያመለክታል ይህም አነስተኛ ኃላፊነት ያለው ከፍተኛ ኃላፊነት ያለው የሚያስቀምጥበት የተለመደ መንገድ ነው እርስዎ ፈርዖን ተቆጥተው ነበር (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ እርሱ ፈርዖንን ያመለክታል አገልጋዮች የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዥ ያመለክታል:: አት “እኛ አገልጋዮችህ” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እኔንና የእንጀራ ቤት አዛዡን በዘበኞች አለቃ ኃላፊነት በተሰጠው እስር ቤት እስሮን ነበር:: እዚህ “ቤት” እስር ቤትን ያመለክታል::
ንጉሡ ጠባቂዎች ላይ ኃላፊነት የተሰጠው ወታደር ነው በዘፍጥረት 2ዐ:2-3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ለንጉሡ ምንብን የሚያዘጋጅ ዋና አስፈላጊ ሰው ነው፡፡ በዘፍጥረት 2ዐ:2-3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
“እኛ ሁለታችን በአንድ ሌሊት ሕልም አለምን” እዚህ እኛ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃንና እንጀራ ቤት አዛዡን ያመለክታል (ነጠላና ብዙ እኛ ይመልከቱ)
ሕልሞቻችን የተለያየ ትርጉም ነበራቸው
የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ለፈርዖ መናገሩን ቀጠለ
በእስር ቤት ከእንጀራ ቤት አዛዥና ከእኔ ጋር ነበር
ንጉሡ ጠባቂዎች ላይ ኃላፊነት የተሰጠው ወታደር ነው በዘፍጥረት 2ዐ:2-3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ሕልሞቻችንን ነገርነው እናም እርሱ ትርጉምቻቸውን ነገረን
እዚህ እርሱ ወይም እያንዳንዱ የሕልሙ ተርጓሚውን ሳይሆን የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃንና የእንጀራ ቤት አዛዥ በግል የሚያመለክት ነው አት ለእያንዳንዳችን ምን ሊሆን እንዳለ አስረዳን (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አጠቃቀም ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ የተጠቀመው በታሪኩ አስፈላጊ ክስተት ለማመልከት ነው በቋንቋዎ ይህን መግለጽ የሚችሉበት መንገድ ካለ ይጠቀሙ
ስለሕልሞቻችን እንደነገረን ሆነ
እዚህ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ማከበሩን ለመግለጽ የፈርዖን የማዕረግ ስም ይጠቀማል:: አት ወደ ሥራዬ እንዲመለስ ፈቀድክልኝ (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
የእንጀራ ቤት አዛዡን
እዚህ እርሱ ፈርዖንን ያመለክታል እና ይህም የእንጀራ ቤት አዛዡን እንዲሰቅሉት ፈርዖን ወታደሮቹን ማዘዙን ይወክላል አት እንዲሰቀል እርስዎ ወታደረችዎን አዝዘዋል:: (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽና ተዛማጅ ምትክ ቃላትን ስለመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ
ፈርዖን አገልጋዮቹን እንደላከ ይታወቃል አት ዮሴፍን እንዲያመጡት አገልጋዮችን ላከ (የተደበቁ ቃሎችን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
“ከእስር ቤት” ወይም “ከወህኒ”
በፈርዖን ፊት ለመቅረብ በመዘጋጀት ጊዜ የፊትና የራስ ጸጉርን መላጨት የተለመደ ተግባር ነበር
እዚህ መጣ የሚለው ገባ በሚለው ሊገለጽ ይችላል አት ፈርዖን ፊት ገባ (መጣ እና ገባ ይመልከቱ)
ሊተረጉምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም
አንተ ትርጉሙን ሊትነግረኝ ትችላለህ
እኔ የመተርጐም ችሎታ የለኝም
እግዚአብሔር ለፈርዖን የሚሻውን ትርጉም ይሰጠዋል
ስለሚያስገርመው መረጃ ዮሴፍ ትኩረት እንዲሰጠው ፈርዖን “እነሆ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል
በዐባይ ወንዝ ዳርቻ የለውን ከፍታ የለውን መሬት ያመለክታል:: በዘፍጥረት 41:3 የዚህ ተመሣሣይ ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት “በዐባይ ወንዝ ዳር”
ስለሚያስገርመው መረጃ ዮሴፍ ትኩረት እንዲሰጠው ፈርዖን “እነሆ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል
“የተቀለቡ/የደለቡና ጤናማ” በዘፍጥረት 41:2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
በወንዙም ዳር ያለውን ሣር ይመገቡ ነበር:: በዘፍጥረት 41:2 የዚህ ተመሣሣይ ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ስለሚያስገርመው መረጃ ዮሴፍ ትኩረት እንዲሰጠው ፈርዖን “እነሆ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል
አቅሜ ደካሞችና የከሱ ወይም የቀጨጩ በዘፍጥረት 41:3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
“አስከፊ” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ቅጽል ሊተረጐም ይችላል:: አት “የሚያስከፉ ላሞች” ወይም “የማይጠቅሙ የሚመስሉ ላሞች” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
“የደለቡ ወይም የተቀለቡ ላሞች” በዘፍጥረት 41:2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “የከሱ ላሞች የወፈሩትን መዋጣቸውን ማንም ሊነግረው እስከማይችል ነበር:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ፈርዖን ሕልሙን ለዮሴፍ መናገሩን ቀጠለ
ይህ ፈርዖን ከነቃና ተመልሶ ከተኛ በኋላ ያየውን ሕልም ይጀምራል፡፡ አት “እንደገናም ሕልም አለምሁ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ስለሚያስገርመው መረጃ ዮሴፍ ትኩረት እንዲሰጠው ፈርዖን “እነሆ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል::
የእሸት ወይም የእህል የሚለው አባባል የታወቀ ነው:: አት “ሰባት የእህል ዛላዎች” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
“በአንድ አገዳ ሲንዠረግጉ” አገዳ ወፍራምና ረጅም የተክል አካል ነው:: በዘፍጥረት 41:5 ይህን ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ስለሚያስገርመው መረጃ ዮሴፍ ትኩረት እንዲሰጠው ፈርዖን “እነሆ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል::
የደረቁና ፍሬ አልባ የሆኑ
“ከበረሃማ ቦታ የሚነፍሰው የምሥራቅ ንፋስ” የምሥራቁ ንፋስ ሙቄት አብዛኛውን ጊዜ ለእህሎች እጅግ አደገኛ ነበር::
አደገ ወይም ፍሬ ሰጠ
የእህል የሚለው ቃል የታወቀ ነው በዘፍጥረት 41:7 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ አት የቀጨጩ የእህል ዛላዎች (የተደበቁ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
“በሉ” ፈርዖን ያለመው ሕልም ሰው ምግብን እንደሚበላ ጤናማ ያልሆኑ የበቆሎ እህሎች ጤናማ ያልሆኑትን እንደበሉ ነው:: በዘፍጥረት 41:7 የዚህ ተመሣሣይ ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
የሚችል አንድም አልተገኘም ወይም ማንም አልቻለም
ትርጉሞችም ተመሣሣይ ናቸው የሚል አንድምታ አለው:: አት “ሁለቱም ሕልሞች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ዮሴፍ ፈርዖንን እንደሳስተኛ ወገን ሰው ያናግረዋል ይህ አክብሮትን መግለጫ መንገድ ነው:: እንደ ሁለተኛ ወገን ሰው መግለጽ ይቻላል:: አት “ቶሎ ሊያደርግ ያለውን እያሳየህ ነው” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ዮሴፍ የፈርዖንን ሕልም መተርጐም ይቀጥላል፡፡
የቀጨጩና ዐቅሜ ደካማ ላሞች በዘፍጥረት 41:3 የዚህ ተመሳሳይ ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከምሥራቁ ሙቀት አዘል ነፋስ የተነሣ የቀጨጩ ሰባት የእህል ዛላዎች” (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ዮሴፍ ፈርዖንን እንደ ሶስተኛ ወገን ሰው ያናግረዋል ይህም አክብሮች መግለጫ መንገድ ነው:: በሁለተኛ ወገን ሰው መልክ ልገለጽ ይችላል:: “እንደተናገርኩህ እነዚህ ይደረጋሉ…… ፈርዖን ለአንተ ገልጦልሃል” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
“እኔ የሚናገረው እውነትና ጠቃሚ ነውና ትኩረት ስጥ፤ ሰባት”
ጊዜ እንደሚመጣና በወቅቱ በአንድ ቦታ እንደሚሆን ይህ ስለጥጋብ ዓመታት ይናገራል:: አት “የተትረፈረፈ ምግብ በግብጽ በመላው የግብጽ ምድር የሚሆንበት ሰባት ዓመታት ይመጣሉ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ዮሴፍ የፈርዖንን ሕልምች መተርጐም ቀጠለ
ወደ አንድ ቦታው ተንቀሳቅሶ እንደሚመጣ ነገር ተደርጐ ስለ ሰባት ዓመታት ራስ ተነግሮአል አት ከዚም በኋላ እጅግ ጥቂት ምግብ የሚሆንበት ሰባት ዓመታት ይሆናሉ (ዘይቤይዊ አነጋገር ይመልከቱ)
….የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ የጥጋብ ዘመን ፈጽም ይረሳል:: ዮሴፍ ለጉዳዩ አጽንዖት ለመስጠት አንድን ሀሳብ በሁለት መንገድ ይገልጻል (ተመሣሣይ ተጓዳኝ አባባሎችን ይመልከቱ)
ምድር ሰዎችን ያመለክታል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “የግብጽ ሰዎች የተትረፈረፈ ምግብ የነበረበትን ዓመታት ሁሉ ይረሳሉ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤና ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አገር የሚለው የአገሪቷን መሬት ሰዎችና መላውን የአገሪቷን አካል ያመለክታል (ምትክ ቃላትን የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ተከትሎ እንደሚመጣ እንደ አንድ ነገር ስለሚመጣው ራብ ወይም ድርቅ ይናገራል፡፡ አት “ከዚያ በኋላ በሚሆነው ራብ ወይም ድርቅ የተነሣ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እግዚአብሔር ሁለት ሕልሞችን የሰጠህ ነገሮች በእርግጥ እንደሚከሰቱ ለማሣየት ነው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ዮሴፍ ለፈርዖን መናገሩን ቀጠለ
ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ስለሚቀጥለው ጠቃሚ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው
ዮሴፍ ለፈርዖን እንደ ሶስተኛ ወገን ሰው ይናገራል ይህ አክብሮትን የመግለጫ መንገድ ነው በሁለተኛ ወገን ሰው መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አንተ ፈርዖን ፈልግ” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ይሹመው ማለት ኃላፊነት ይስጠው ማለት ነው፡፡ አት “በግብጽ ግዛት ላይ ኃላፊነት ይስጠው ወይም በግብጽ ግዛት ላይ ይሹመው (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ ምድር በግብጽ ምድር ያሉ ሰዎችንና ሁሉን ነገር ይወክላል (ተመሣሣይ ተዛማጅ ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልቱ)
አምስተኛ የሚለው ቃል ክፍልፋይ ነው:: የግብጽን ምድር እህል ምርት በአምስት መደብ ይክፈሉ፤ ከዚያም አንዱን እጅ ወይም መደብ ይውሰዱ (ክፍልፋዮችን ይመልከቱ)
የተትረፈረፈ ምግብ ባለባቸው ሰባት ዓመታት
ፈርዖንን መምከሩን ቀጠለ
ሹማምንት ወይም ኃላፊዎች እንዲሰበስቡ ይደረግ
እነዚህ ዓመታት አንድ ነገር ተጉዞ ወደ አንድ ቦታ እንደማመጣ እንደሚመጡ ይናገራል:: አት “ቶሎ ሊመጡ ያሉ የጥጋብ ዓመታት” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በፈርዖን ሥልጣን ሥር የሚለው ሀረግ ፈርዖን ሥልጣን ይስጣቸው ማለት ነው አት እህሉን ለመሰብሰብ የፈርዖንን ሥልጣን ይጠቀም ፈሊጣዊ አነገጋር ይመልከቱ
እነርሱ የሚለው ቃል እህሉ እንዲጠበቅ የሚያዝዙ ሹማምንቶችንና ወታደሮች ያመለክታል አት ሹማምቶች እህሉ እንዲጠበቅ በዚያው ወታደሮችን ይመድቡ ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ
ምድሪቱ ሰዎችን ትወክላለች አት እህሉም ለሰዎች ምግብነት ይሆናል (ምትክ ቃላት ስለመጠቀም ይመልከቱ)
እዚህ “ምድር” ሰዎችን ይወክላል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት “በዚህ መንገድ በራብ ጊዜ ሰዎች አይራቡም” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ወይም ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ፊት ማየትን የሚያመለክት ሲሆን ማየት ማሰብን ወይም ብያኔን ያመለክታል አት ፈርዖንና ሎሌዎቹ ይህ መልካም እቅድ ሆኖ አገኙት
የፈርዖ ሹማምንት
ዮሴፍ የገለጸው ዓይነት ሰው
የእግዚአብሔር መንፈስ የሚኖርበት
እንዳንተ ያለ ውሳኔ አቅራቢ የለም:: በዘፍጥረት 41:33 ብልህ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
እዚህ “ቤት” የፈርዖን ቤተመንግሥትና በቤተመንግሥቱ ያሉ ሰዎችን ይወክላል:: የበላይ የሚለው ሀረግ ዮሴፍ የበላይ ኃላፊነት ይሰጠዋል ማለት ነው:: አት በቤተመንግሥቴ በሁሉም ላይ ሥልጣን ይሰጥሃል:: (ምትክ ቃላት ስለመጠቀም ዘይቤና ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል በሕዝቤ ላይ ገዥ ትሆናለህና አንተ የሚታዝዘውን ያደርጋሉ:: (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ ዙፋን ፈርዖን እንደንጉሥ ገዥ እንደሆነ ይገልጻል:: አት “በንጉሥነት ሚናዬ ብቻ”
“እየው” የሚለው ቃል ፈርዖን በሚቀጥለው ለሚናገረው አጽንዖት ይሰጣል:: አት “እየው አድርጌሃለሁ”
የበላይ አድርጌሃለሁ ማለት ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ ማለት ነው እዚህ ምድር ሰዎችን ያመለክታል አት በግብጽ ምድር ባለው በማንኛውም ላይ ኃላፊነት ሰጥቼሃለሁ (ምትክ ቃል የመጠቀም ዘይቤና ፈሊጣዊ አነጋገር ይጠቀሙ)
እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች የሚያመለክቱት ዮሴፍ ያቀደውን ሁሉ እንዲያደርግ ፈርዖን ለዮሴፍ ሥልጣን መስጠቱን ነው (ምልክታዊ ድርጊት የመልከቱ)
ይህ ቀለበት የፈርዖን ማኀተም የተቀረጸበት ነው:: ይህም ያቀደውን እንዲያከናውን ለዮሴፍ ገንዘብና ሥልጣንን ሰጠው::
የተልባ እግር የተሠራ ልብስ ሰማያዊ አበባ ካለው የተልባ እግር የተሠራ ለስላሳ ጠንካራ ልብስ ነው::
ይህ ድርጊት ለሰዎች ግልጽ የሚያደርገው የፈርዖን ሁለተኛ ሰው ዮሴፍ ብቻ መሆኑን ነው (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ስገዱና ዮሴፍን አክብሩ እጅ መንሣትና መስገድ ክብርንና አክብሮትን የመስጠት ምልክት ነው (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ማንኛውም ላይ ሾመው የሚለው ሀረግ ሁሉ ላይ ስልጣን ሰጠው ማለት ነው:: እዚህ ምድር ሰዎችን ያመለክታል በዘፍጥረት 41:41 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት “በግብጽ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገርና ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ፈርዖን የራሱን ሥልጣን አጽንቶ ይናገራል፡፡ አት “እንደ ፈርዖን እኔ የማዝዘው ያለአንተ”
እዚህ “እጅና እግር” የሰዎችን ድርጊቶች ይወክላሉ:: አት “ማንኛውም ሰው ምንም ነገር ያለፈቃድህ በግብጽ አያድርግ ወይም ማንኛውም ሰው ምንም ነገር በግብጽ ከማድረጉ በፊት ያንተን ፈቃድ ይጠይቅ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ “ሰው” ወንድም ሆነ ሴት በአጠቃላይ ማንንም ሰው ያመለክታል:: (በወንድ ጾታ የተገለጹ ቃላት ለሴት ጾታም መሆናቸውን ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የሚከተውን በግርጌ ማስታወሻ ሊጠቀሱ ይችላሉ:: “ጸፍናት ፐዕናህ” የሚለው ስም “ሚስጢሮችን ገላጭ” ማለት ነው፡፡
ጶጥፋራ የአስናት አባት ነው:: “ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ”
ዖን የጸሐይ አምላክ ራአ አምልዕኮ ማዕከል ያለባትና “የጸሐይ ከተማ” የነበረች እንዲሁም “ሄልዮቱ” ተብላ የሚትጠራ ከተማ ነች (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ሊመጣ ስላለው ያልታሰበ የድርቅ ጊዜ ዝግጅት ለማድረግ ዮሴፍ በመላይቱ የግሣብ ምድር ተዘዋወረ
3ዐ ዓመት ዕድሜ ቁጥሮችን ይመልከቱ
እዚህ በፊቱ መቆም ዮሴፍ ፈርዖንን ማገልገል መጀመሩን ያሳያል:: አት “ፈርዖንን ማገልገል በጀመረ ጊዜ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ዮሴፍ ዕቅዱን ለማከናወን ዝግጅት ሲያደርግ አገሪቱን በጥንቃቄ እንደመረመረ ነው
በሰባቱም መልካም ዓመታት
ምድራቱ ብዙ እህል አመረተች
እዚህ “እርሱ” የዮሴፍን አገልጋዮች ያመለክታል:: አት “ዮሴፍ አገልጋዮቹ እንዲሰበስቡ አዘዘ …. አከማቹ (ከፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
የእህሉን እጅግ መብዛት በአጽንዖት ለመናገር ከባሕር አሸዋ ጋር ያነጻጽራል፡፡ አት “ዮሴፍ ያከማቸው እህል ባህር ዳር እንዳለ አሸዋ እጅግ ብዙ ነበር” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ ዮሴፍ እና እርሱ የዮሴፍን አገልጋዮች ይወክላል:: አት “ዮሴፍ አገልጋዮቹ እንዲያከማቹ አደረገ … እነርሱም አቆሙ” (ከፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣቱ በፊት ይህም አንድ ነገር ተጉዞ ወደ አንድ ቦታ እንደሚመጣ ተደርጐ ስለሚመጡ ዓመታት ይናገራል:: አት “ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመጀመራቸው በፊት” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
የአንዲት ሴት ስም ነው:: በዘፍጥረት 41:45 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ዖን የጸሐይ አምላክ ራአ አምልዕኮ ማዕከል ያለባትና “የጸሐይ ከተማ” የሆነች እንዲሁም “ሄልዮቱ” ተብላ የሚትጠራ ከተማ ነች፡፡ በዘፍጥረት 41:45 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ተርጓሚዎች የሚከተለውን በግርጌ ማስታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ:: “ሚናሴ” የሚለው ስም ለመርሳት ምክንያት መሆን ማለት ነው::
ይህ የዮሴፍ አባት ያዕቆብንና ቤተሰቡን ያመለክታል
ተርጓሚዎች የሚከተለውን የግርጌ ማስታወሻ ሊጨምሩ ይችላሉ:: “ኤፍሬም” የሚለው ስም “ፍሬያማ መሆን” ወይም “ልጆችን መውለድ” ማለት ነው::
“ፍሬያማ” መበልጸግ ወይም ልጆችን መውለድ ማለት ነው:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ሥቃይ” የሚለው ረቂቅ ስም “መከራ ተከበልኩ” በሚለው ሊገለጽ ይችላል:: አት “መከራን በተቀበልሁት ምድር” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ከግብጽ ባለፈ የከነዓንንም ምድር ጨምሮ በዙሪያው ባሉ አገሮች ሁሉ
ይህም የሚያስረዳው በሰባት መልካም ዓመታት ሕዝቡ እህልን እንዲያጠራቅሙ ዮሴፍ ስላዘዛቸው ምግብ ነበራቸው (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እዚህ “ምድር” ሰዎችን ይወክላል:: አት “ግብጻዊያን ሁሉ በተራቡ ጊዜ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ ፊት የሚለው ቃል ምድር ላይ ማለትን ያመለክታል:: አት “ራቡ በየአገሩ ተስፋፋ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ “ዮሴፍ” የዮሴፍን አገልጋዮች ይወክላል:: አት “ዮሴፍ አገልጋዮቹ ጐተራዎችን ሁሉ እንዲከፍቱና ለግብጻዊያን እህል እንዲሸጥ አደረገ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ ምድር ከሁሉ አገራት የሆኑ ሰዎችን ይወክላል:: አት “በዙሪያው ካሉ አገሮች ሁሉ ሰዎች ወደ ግብጽ ይመጡ ነበር” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
በመላው ምድር በግብጻዊያንን የንግድ መሥመሮች የሚጠቀሙ በድርቅ የተጠቁ የተለያዩ የንግድ አጋሮችና አገሮች ሁሉ ወደ ግብጽ ይመጡ ነበር እንደማለት ነው
1 በግብፅ እህል መኖሩን ሲሰማ፣ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ለምን እርስ በርስ ትተያያላችሁ?” 2 በግብፅ አገር እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ በራብ ከመሞታችን በፊት ወደዚያ ሂድና እህል ግዙልን” አላቸው። 3 ስለዚህ ዐሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ሄዱ። 4 ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሃት ከወንድሞቹ ጋር አልላከውም። 5 ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፣ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ከሄዱት መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ። 6 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዢ ነበር፣ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደደረሱ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው ሰገዱለት። 7 ዮሴፍም ወንድሞቹን ባየ ጊዜ ዐወቃቸው፣ ነገር ግን የማያውቃቸው በመምሰል በቁጣ ቃል፣ “ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እህል ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን" ብለው መለሱለት። 8 ዮሴፍ ወንድሞቹን ቢያውቃቸውም እንኳ እነርሱ ግን አላወቁትም። 9 በዚህ ጊዜ ስለወንድሞቹ ያየው ሕልም ትዝ አለውና፣ “ሰላዮች ናችሁ፣ የመጣችሁት አገራችን በየትኛው በኩል ለጥቃት የተጋለጠች መሆኗን ለመሰለል ነው” አላቸው። 10 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን ሆይ፣ እንዲህስ አይደለም፤ እኛ አገልጋዮችህ የመጣነው እህል ለመሸመት ነው፤ 11 ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ነን፤ አገልጋዮችህም የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።” 12 እርሱም መልሶ፣ “አይደለም፣ ግብፅ በየት በኩል ለጥቃት የተጋለጠች መሆኗን ለመሰለል ነው” አላቸው። 13 እነርሱ ግን መልሰው፣ “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን አገር ከሚኖር ከአንድ ሰው የተወለድን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን። ትንሹ ወንድማችን አባታችን ዘንድ ሲሆን አንዱ ወንድማችን ሞቷል። 14 ዮሴፍም እንዲህ አላቸው፤ “ነገርኋችሁ እኮ፤ ሰላዮች ናችሁ 15 ታናሽ ወንድማችሁ እዚህ እስካልመጣ ድረስ ከዚህ ንቅንቅ እንደማትሉ በፈርዖን ስም እምላልሁ፤ ማንነታችሁ የሚረጋገጠውም በዚህ ነው። 16 ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁትም እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስት ቤት ትቆያላችሁ፤” 17 ሁሉንም ሦስት ቀን በእስር አቆያቸው። 18 በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ። 19 ታማኝ ሰዎች ከሆናችሁ፣ ከመካከላችሁ እንዱ እዚህ እስር ቤት ሲቆይ፣ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ትወስዱላቸዋላችሁ፤ 20 ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ። 21 እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፤ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፣ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ። 22 ሮቤልም መልሶ፣ “በዚህ ልጅ ላይ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው። 23 ዮሴፍ የሚያነጋግራቸው በአስተርጓሚ ስለሆነ የሚነጋገሩትን እንደሚሰማባቸው ዐላወቁም ነበር። 24 ከፊታቸውም ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ከዚያም ወደእነርሱ ትመልሶ እንደገና አነጋገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ዓይናቸው እያየ አሰረው፤ 25 ዮሴፍ ለአገልጋዮቹ በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፤ ብሩንም በያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ተደረገላቸው። 26 እነርሱም እህላቸውን በአህዮቻቸው ጭነው ጉዞአቸውን ቀጠሉ። 27 በመንገድም ለአዳር ሰፍረው ሳለ፣ ከእነርሱ አንዱ ከያዘው እህል ላይ ለአህያው ለመስጠት ስልቻውን ሲፈታ፣ በስልቻው አፍ ላይ ብሩን አገኘ። 28 እርሱም ወንድሞቹን፣ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፣ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ። 29 በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ከደረሱ በኋላ ያጋጠማቸውን ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩት፤ 30 “የግብፅ አገር አስተዳዳሪ ‘አገሬን ልትሰልሉ የመጣችሁ ናችሁ’ በማለት በቁጣ ቃል ተናገረን፤ 31 እኛ ግን እንዲህ አልነው፤ “እኛ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም። 32 እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆንን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፣ አንዱ የለም፣ ታናሽ ወንድማችን ግን ከአባታችን ጋር በከነዓን ይገኛል።’ 33 ከዚህ በኋላ የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው እንዲህ አለን፣ “ታማኝ ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው በዚህ ነው ከእናንተ መካከል አንዱን ወንድማችሁን እዚህ እኔ ዘንድ ትታችሁ የተቀራችሁት ለትራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁላቸው ሂዱ። 34 ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያን ጊዜም ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደፈለጋችሁ እየተዘዋወራችሁ መነገድ ትችላላችሁ። 35 እህሉንም ሲዘረግፉ በየስልቻቸው ውስጥ ብራቸው እንደተቋጠረ ተገኘ፤ የእያንዳንዳቸውን የተቋጠረ ብር ሲያዩም፣ እነርሱም ሆኑ አባታቸው ደነገጡ። 36 አባታቸው ያዕቆብም፣ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፣ ዮሴፍ የለም፣ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ” አለ። 37 በዚህን ጊዜ ሮቤል አባቱን፣ “ብንያምን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣው ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ወስደህ ግደላቸው፣ ስለዚህ በእኔ ኃላፊነት ላከው፤ እኔም መልሼ አመጣዋለሁ” እለው። 38 ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፣ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጉዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።
አሁንም የሚለው ቃል የታሪኩን አዲስ ክፍል ያመለክታል (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
ስለ እህል ምንም ባለማድረጋቸው ልጆቹን ለመቆጣት ያዕቆብ ጥያቄ ይጠቀማል:: አት “እዚሁ ዝም ብላችሁ አትቀመጡ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ከከነዓን ወደ ግብጽ መሄድ ወደ ታች እንደመውረድ መናገር የተለመደ ነበር
እዚህ “ግብጽ” ሰዎች እህልን የሚሸጡበት ያመለክታል:: አት “በግብጽ እህልን ከሚሸጡ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ብንያምና ዮሴፍ አንድ አባትና እናት ነበራቸው የዕቆብ የራሔል መጨረሻ ልጅዋ እንዲጐዳ ወይም ክፉ ነገር እንዲደርስበት አልፈለገም ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ
“መጡ” የሚለው ቃል “ሄዱ” በሚለው ሊተረጐም ይችላል:: እንዲሁም እህል እና ግብጽ የተባሉ ቃላት የታወቁ ናቸው:: አት “የእስራኤል ልጆች እህል ለመሸመት ከሌሎች ሰዎች ጋር ወደ ግብጽ ሄዱ” (ሄደ እና መጣ አጠቃቀምና ድብቅ ቃላት የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
“በዚህን ጊዜ” ታሪኩ ወደ ዮሴፍ ሕይወት መረጃ መቀየሩን ያመለክታል:: (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)
ምድር ግብጽን ያመለክታል:: አት “በግብጽ ላይ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እዚህ አገር ግብጽንና ዙሪያው ያሉ አገሮችን ያጠቃልላል አት እህል ለመሸመት ከተለያዩ አገሮች ለመጡ ሰዎች ሁሉ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“መጡ” እንደ “ሄዱ” ሊተረጐም ይችላል:: (መጣ እና ሄደ አጠቃቀም ይመልከቱ)
ይህ አክብሮትን የመስጠት ምልክት ነው:: (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ዮሴፍም ወንድዋቹን ባያቸው ጊዜ አወቃቸው
“የእነርሱ ወንድም እንዳልሆነ ታየ” ወይም “ወንድማቸው እንደሆነ እንዲያውቁት አልፈለገም”
ዮሴፍ መልሱን ቢያውቅም ይህ አግናኝ ጥያቄ አልነበረም የራሱን ማንነት ለወንድሞቹ ላለመግለጽ የመረጠው መንገድ ነበር
ሰላዮች ሌላ አገርን ለመጥቅ በስውር ስለአንድ አገር መረጃ ለማግኘት የሚጥሩ ሰዎች ናቸው::
የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት አገራችን በየትኛው በኩል እንደተጋለጠች ለማየትና ከዚያም ሊታጠቁን ለማየት መጥታችኋል (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
አንድን ሰው ለማክበር የሚጠቀሙበት አባባል ነው
ወንድሞቹ ራሳቸውን እንደ ባሪያዎች አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ይህም ከፍተኛ ሥልጣን ላለው ሰው የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው፡፡አት “እኛ ባሪያዎችህ” ወይም “እኛ” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ዮሴፍ ለወንድሞቹ አላቸው
የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “አይደለም በየት በኩል ምድራችን ለጥቃት የተጋለጠች መሆንዋን ለመሰለልና ከዚያም ሊታጠቁን ነው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
12ቱ ወንድሞች (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
“ስማን ትንሹ ወንድማችን” “እየው” የሚለው ቃል ቀጥለው ለምነግሩት ነገር ትኩረት እንዲሰጥ ተጠቅሞአል::
“በዚህን ጊዜ ትንሹ ወንድማችን ከአባታችን ጋር ነው”
“እንደነገርኋችሁ ሰላዮች ናችሁ” (በዘፍጥረት 42;9 “ሰላዮች” እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “የሚፈትናችሁ በዚህ ነው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ጠንከር ወይም ኮስተር ያለ መሃላ ነው አት በፈርዖን ሕይወት እምላለሁ
“ከእናንተ አንዱን ምረጡና ሂዶ ወንድማችሁን ይዞ ይመለስ”
የቀራችሁ በእሥር ቤት ትቆያላችሁ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት እውነት መናገራችሁን እንዳውቅ (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልክቱ)
በእስር ቤት
“ሶስት” የሚለው ተራ ቁጥር ነው:: አት “ከሁለተኛው ቀን በኋላ” (መቁጠሪያ ተራ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
የተቀመጠው መረጃ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “የሚለውን ካደረጋችሁ በሕይወት ትተርፉ አደርጋችኋለሁ” (የተደበቁ ቃላትን ስለመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ከልብ እግዚአብሔርን ማክበርንና ያንን ለእርሱ በመታዘዝ መግለጽን ያመለክታል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ልገለጽ ይችላል:: አት “እንዱን ወንድማችሁን እዚሁ እሥር ቤት ተውት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ ሂዱ ብዙ አመላካችና በእሥር ቤት የማይቆዩ ወንድሞች ሁሉን ያመለክታል (ብዙ አመላካች እናንተ ይመልከቱ)
እዚህ ቤቶች ቤተሰቦችን ይወክላል:: አት “በዚህ ራብ ወቅት ቤተሰቦቻችሁን ለመርዳት እህል ትወስዱላቸዋላችሁ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት የሚትነግሩ እውነት መሆኑን አውቃለሁ (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ ይመልከቱ)
ወንድሞቹ ሰላይ መሆናቸውን ካረጋገጠ ዮሴፍ በወታደሮቹ እንደሚያስገድላቸው የሚል ትርጉም ይኖረዋል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ነፍሱ ዮሴፍን ይወክላል አት ዮሴፍ እንደዚያ ሲጨነቅ አይተን ወይም ዮሴፍ እንደዚያ ሲሰቃይ አይተን (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
“ጭንቀት” የሚለው ረቂቅ ስም “መከራ” በሚለው ግሥ ሊተረጐም ይችላል:: አት “ይህ መከራ የደረሰብን በዚሁ ምክንያት ነው” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገልጽ ይችላል:: አት “በዚህ ልጅ ላይ ኃጢአት እንዳታደርጉ አልነገርኋችሁምን፤ነገር ግን” ወይም “ልጁ ላይ ክፉ እንዳታደርጉ ነግሬአችኋለሁ፤ ነገር ግን” (በጥቅሶች ውስጥ ጥቅሶችንና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
እዚህ አሁን በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም አሁን እና እዩ ሁለቱ የተጠቀሙት ለሚቀጥለው በጣም ጠቃሚ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው
እዚህ ደም የዮሴፍን ሞት ይወክላል ወንድምቹ ዮሴፍ እንደሞተ አስበዋል:: “ከእጃችን ይፈለጋል” የሚለው ሀረግ ስላደረጉት ነገር ይቀጣሉ ማለት ነው:: አት “ለሞቱ የሚገባውን ቅጣት እየተቀበልን ነን” ወይም “በመግደላችን መከራ እየተቀበልን ነን” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ወይም ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አስተርጓሚ አንድ ሰው የሚናገረውን ወደ ሌላ ቋንቋ የሚተረጉም ሰው ማለት ነው ዮሴፍ የእነርሱን ቋንቋ እንደማይናገር ለማስመሰል በራሱና በእነርሱ መካከል አስተርጓሚ አድርጐ ነበር
ዮሴፈ ወንድሞቹ የተናገሩትን በመስማቱ ስሜቱ ስለተነካ አለቀሰ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እስከዚህ ዮሴፍ ወንድሞቹን የሚያናግረው በተለየ ቋንቋ ስለሆነ አስተርጓሚ ይጠቀም ነበር (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እዚህ ለሚያዩት ነገር ትኩረት ለመስጠት ሰዎች በዐይኖች ተመስለዋል:: አት “በፊታቸው አሰረው” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲሰጡአቸው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ዮሴፍ ያዘዘውን ሁሉ አገልጋዮቹ አደረጉላቸው (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
በመንገድም አዳር ሰፍረው ሳሉ ከእነርሱ አንዱ ከያዘው እህል ላይ ለአህያው ለመስጠት ስልቻውን ሲፈታ በስልቻው አፍ ላይ ብሩን አየ
እዚህ እነሆ የሚለው ቃል ለሚቀጥለው አስገራሚ ሃሳብ ትኩረት እንድንሰጥ ለማድረግ ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልከ ሊገለጽ ይችላል አት አንድ ሰው ብሬን መልሳ አስቀመጠልኝ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልክቱ)
ይሄው በስልቻዬ እዩ
መፍራቻው ልባቸው በድንጋጤ እንደተዋጠ እንደተሞላ ተገልጾአል እዚህ ልብ በድፍረት ተመስሎአል አት እጅግ በጣም ፈሩ
የግብጽ ጌታ
በክፉ ንግግር ተናገረን
ሰላዮች ሌላን አገር ለመጥቀም ሰለአንድ አገር በሚስጢር መረጃ የሚሰበስቡ ሰዎች ናቸው:: በዘፍጥረት 42 9 ሰላዮች የሚለውን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::እኛም እንዲህ አልነው እኛ የታመንን ሰዎች ነን፡፡ ሰላዮች አይደለንም፡፡ እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆንን አሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፡፡ እንዱ በሕይወት የለም …..በከነዓን ይገኛል ይህ በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ ይዞአል:: ይህም እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል:: አት እኛ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም:: እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆንን አሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን:: አንዱ በሕይወት የለም … በከነዓን ይገኛል (በጥቅስ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
“ወንድም” የሚለው ቃል የታወቀ ነው አት “አንዱ ወንድማችን በሕይወት የለም” (የተደበቁ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይጠቀሙ)
“ወንድም” የሚለው ቃል የታወቀ ነው:: አት “ታናሽ ወንድማችን…. ዛሬ ከአባታችን ጋር አለ” (የተደበቁ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይጠቀሙ)
የግብጽ ጌታ
ቤቶች ቤተሰብን ይወክላሉ አት በራብ ወቅት ቤተሰባችሁን ለመርዳት እህል ይዛችሁላችሁ ሂዱ (ምትክ ቃላት ስለመጠቀም ይመልከቱ)
ወደ ቤታችሁ ሂዱ ወይም ሂዱ
በምድሪቱ እንዲትሸጡና እንዲትገዙ እፈቅድላችኋለሁ
ይህ ሀረግ እዚህ የተጠቀመው በታሪኩ ጠቃሚ ክሰተት ለማመልከት ነው በቋንቋዎ ይህን መግለጽ የማችሉበት መንገድ ካለ በዚህ ቦታ ሊጠቀሙ ይችላሉ
ተገረሙ ምክንያቱም እያንዳንዳቸው
ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ ወይም ሁለቱን ልጆች እንዳጣ አደረጋችሁኝ
እነዚህ ሁሉ ጐዱኝ
ይህ አብሮ እንዲሄድ ብንያምን እንዲሰጠውና በጉዞው እንደሚጠነቀቅለት ሮቤል የጠየቀው ጥያቄ ነው አት ለእርሱ ኃላፊነት ስጠኝ ወይም ለእርሱ እኔ ሊጠነቀቅለት ዘይቤያዊ አነጋገር ይጠቀሙ
ከከነዓን ወደ ግብጽ ጉዞ ስታሰብ እዚህ የተጠቀመው ወደታች መውረድ የሚለው አባባል የተለመደ ነው አት ልጄ ብንያምን አብሮአችሁ ወደ ግብጽ አይሄድም
እዚህ እናንተ ብዙን የሚያመለክትና የያዕቆብን ልጆች የሚገልጽ ነው( “እናንተ” አጠቃቀም ይመልከቱ)
የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “ባለቤቴ ራሔል ሁለትልጆች ነበራት ዮሴፍ ሞቶአልና ብንያም ብቻውን ቀርቶአል” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“ወደ ግብጽ ስትሄዱና ስትመለሱ” ወይም “ርቃችሁ ስትሄዱ” እዚህ “መንገድ” “ጉዞን” ያመለክታል
ወደ መቃብር ታወርዱታለችሁ እንዲሞትና ወደ መቃብር እንዲወርድ ታደርጉታላችሁ የሚል አባባል ነው:: መቃብር በተለምዶ እንደሚታመነው ከምድር በታች ስለሆነ ታወርዱታላችሁ የሚለውን ቃል ይጠቀማል:: አት “እኔን ሽማግሌውን በሐዘን እንድሞት ታደርጉታላችሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ያዕቆብን የሚያመለክትና ሽምግልና ዕድሜውን የሚገልጽ ነው አት “እኔ ሽማግሌ ሰው” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
1 አሁንም በምድሪቱ ላይ እንደጸና ነበር፤ 2 ከግብፅ ያመጡትንም እህል በልተው ከጨረሱ በኋላ፣ አባታቸው፣ “እስቲ እንደገና ወርዳችሁ፣ ጥቂት እህል ሸምቱልን” አላቸው። 3 ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ ያ ሰው ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤ 4 ወንድማችን ከእኛ ጋር እንዲወርድ ከፈቀድህ ወደዚያ ሄደን እህል እንሸምትልሃለን፤ 5 እርሱን የማትልከው ከሆነ ግን እኛም ወደዚያ አንወርድም፤ ያም ሰው፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም’ ብሎናል።” 6 እስራኤልም፣ “ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለዚያ ሰው በመንገር ለምን ይህን ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። 7 እነርሱም፣ “ሰውዬው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተ ሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ?’ ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታዲያ፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር?” ብለው መለሱለት። 8 ይሁዳም አባቱን እስራኤልን እንዲህ አለው፣ “ልጁን ከእኔ ጋር ስደደው፤ እኛም በቶሎ እንሂድ፣ ይህ ከሆነ አንተም፣ እኛም፣ ልጆቻችንም አንሞትም፣ እንተርፋለን። 9 ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኃላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘላለም በደለኛ እኔ ልሁን። 10 ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፣ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” 11 ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፣ ምድሪቱ ከምታፈራቸው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና ለውዝ በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው ስጦታ ውሰዱለት። 12 በየስልቾቻችሁ አፍ ላይ የተገኘውን ብር መመለስ ስላለባችሁ፣ ዕጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ ያ በየስልቾቻችሁ ውስጥ የተገኘው ብር ምናልባት በስሕተት የመጣ ሊሆን ይችላል። 13 ወንድማችሁንም ይዛችሁ ወደ ሰውዬው በቶሎ ሂዱ። 14 ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ይዛችሁ ለመመለስ እንድትችሉ ሁሉን የሚችል አምላክ በምሕረቱ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እኔ በበኩሌ ልጆቼን ካጣሁ፣ ባዶ እጄን መቅረቴ ነው።” 15 ስለዚህ ወንድማማቾቹ ገጸ በረከቱንና ዕጥፍ ገንዘብ ይዘው ከብንያም ጋር ወደ ግብፅ ለመሄድ ጉዞ ጀመሩ፤ እዚያም በደረሱ ጊዜ ዮሴፍ ፊት ቀረቡ። 16 ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፣ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፣ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ አንድ ከብት እረድና አዘጋጅ” አለው። 17 አዛዡም ዮሴፍ የነገረውን አደረገ፣ ሰዎቹንም ወደ ዮሴፍ ቤት ወሰዳቸው። 18 ሰዎቹም ወደ ዮሴፍ ቤት በመወሰዳቸው ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ወደዚህ የመጣነው ቀደም ሲል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው። ሰውዬው ሊያስረንና ባሪያዎች ሊያደርገን አህዮቻችንንም ሊወስድ ይችላል።” 19 ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፣ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤ 20 እንዲህም አሉት፤ “ለመጀመሪያ ጊዜ እህል ለመሸመት ወደዚህ መጥተን ነበር፤ 21 ነገር ግን ለአዳር በሰፈርንበት ቦታ የየስልቾቻችንን አፍ ስንከፍት እያንዳንዳችን በስልቾቻችን አፍ ላይ ብራችንን ሙሉውን አገኘነው። ገንዘቡንም ይኸው መልሰን ይዘን መጥተናል። 22 አሁንም እህል መሸመት የሚሆነን ተጨማሪ ብር ይዘን መጥተናል፤ በዚያን ጊዜ ገንዘቡን በየስልቾቻቸን ውስጥ ማን መልሶ እንዳስቀመጠው ግን አናውቅም” አሉት። 23 የቤቱ አዛዥም፣ “አይዞአችሁ አትፍሩ፣ በየስልቾቻችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ገንዘብ የሰጣችሁ የእናንተም የአባቶቻችሁም አምላክ ነው፤ እኔ እንደሆንሁ ብሩን ተቀብያለሁ” አላቸው። ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ አገናኛቸው። 24 የቤቱ አዛዥ ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገብቶ እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አቀረበላቸው፤ ለአህዮቻቸውም የሚበሉት ገፈራ ሰጣቸው። 25 ምሳ በዚያ እንደሚበሉ ተነገሯቸው ስለነበር፣ ዮሴፍ በቀትር ከመግባቱ በፊት እጅ መንሻዎቻቸውን ለማበርከት ተዘጋጁ። 26 ዮሴፍም ወደ ቤቱ ሲገባ የመጧቸውን ስጦታዎች አበረከቱለት፤ ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት። 27 ዮሴፍም ስለ ደኅንነታቸው ጠየቃቸው፣ ከዚያም፣ “ሽማግሌ አባት እንዳላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ደኅና ነው? አሁንም በሕይወት አለ?” አላቸው። 28 እነርሱም መልሰው፣ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው እጅ ነሡት። 29 ዮሴፍ በዓይኑ ሲቃኝ የእናቱን ልጅ ብንያምን ዐየና፣ “ያ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። ብንያምንም፣ “ልጄ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው። 30 ዮሴፍ ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ በጥልቅ ስለተነካ፣ ፈጥኖ ከፊታቸው ገለል አለ፤ ሰውር ያለ ቦታም ፈልጎ፣ ዕልፍኙ ውስጥ አለቀሰ። 31 ፊቱንም ከታጠበ በኋላ ወጣ፤ ስሜቱንም በመቆጣጠር ምሳ እንዲቀርብ አዘዘ። 32 ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደጸያፍ ይቆጥሩት ነበር። 33 ወንድማማቾቹ ከታላቁ አንስቶ እስከታናሹ እንደየዕድሜአቸው በዮሴፍ ፊት በተርታ ተቀምጠው ነበር፤ በመገረምም እርስ በርሳቸው ተያዩ። 34 ከዮሴፍ ገበታ ላይ እየተነሣ ለእያንዳንዳቸው ምግብ ሲቀርብ የብንያም ድርሻ ከሌሎቹ አምስት ዕጥፍ ነበር። እነርሱም እንዲህ ባለ ሁኔታ አብረውት ተደሰቱ እስኪረኩም ጠጡ።
ከነዓን የሚለው ቃል የታወቀ ነው ይህ ሃሳብ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት በከነዓን ምድር ራቡ የጸና ነበር (ድብቅ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ የተጠቀመው የታሪኩን አድስ ክፍል መጀመሩን ለማመልከት ነው በቋንቋዎ ይህን መግለጽ የሚችሉበት መንገድ ካለ ይጠቀሙ (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
ያዕቆብና ቤተሰቡ በልተው ከጨረሱ በኋላ
የያዕቆብ ታላቅ ልጆች ያመጡትን
እዚህ እኛ ያዕቆብን የያዕቆብን ልጆችና የቀሩ የቤተሰብ አባላትን ያመለክታል:: (ሁሉን አካታች “እኛ” ይመልከቱ)
ይሁዳ ለአባቱ ለያዕቆብ እንዲህ አለው
ይህ ዮሴፍን ነው የሚያመለክተው ነገር ግን ወንድምቹ ዮሴፍ መሆኑን አላወቁትም ነበር:: እነርሱም እርሱን ያመለከቱን እንደ “ያ ሰው” ወይም በዘፍጥረት 42:3ዐ እንደተነገረው “ያ ሰው የምድሪቱ ጌታ” ነው::
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል ይህም እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ታናሽ ወንድማችንን ይዘነው ካላመጣን ፊቱን ማየት እንደማንችል አስጠንቅቆናል” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
እንዲህም በማለት በጥብቅ አስጠንቀቆናል
ወደ ግብጽ አገር ያለ ብንያም መመለስ እንደማይችሉ ለአባቱ ለማጽናት በዘፍጥረት 43፡ 4-5 ይሁዳ ይህን ሀረግ ሁለት ጊዜ ይጠቀማል:: ፊቴን የሚለው የዚያ ሰው የዮሴፍ ፊት ያመለክታል:: አት “ፊቴን አታዩም” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዜይቤ ይጠቀሙ)
ይሁዳ ራሔል ከመሞትዋ በፊት የወለደችውን የመጨረሻ ልጅ ብንያምን ያመለክታል
ከከነዓን ወደ ግብጽ ጉዞ በሚነገርበት ጊዜ “ወደታች መውረድ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው
ለምን ይህ ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ?
ሰውየው ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቀን
እዚህ እኛ የሚለው በተለይ የሚያመለክተው ወደ ግብጽ የወረዱና ከሰውየው ጋር የተነጋገሩ ወንድሞችን ነው
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል አት አባታችን በሕይወት እንዳለና ሌላ ወንድም እንዳለን በቀጥታ ጠይቆናል:: (በጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
የጠየቀንን ጥያቄዎች መለስንለት
ሰውየው ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደሚነግር ልጆቹ አለማወቃቸውን አጽንተው ለመንገር ጥያቄ ይጠቀማሉ ይህ አግናኝ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል አት እንደዚህ … እንደሚለን አላወቅንም ነበር (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል አት ወንድማችንን የዘን ወደ ግብጽ እንድንወርድ እንደሚነግረን (በጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ከከነዓን ወደ ግብጽ ጉዞ በሚነገርበት ጊዜ “ወደታች መውረድ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው
እንድንድን እና እንዳንሞት የሚሉ ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: ይሁዳም በሕይወት ለመኖር ከግብጽ አህል መሸመት እንዳለባቸው በማጽናት ይናገራል:: አት “መላው ቤተሰባችን እንዲተርፍ ወደ ግብጽ ወርደን እህል መሸመት ይገባናል” (ተመሣሣይ ተጓዳኝ ንጽጽር ይመልከቱ)
እዚህ እኛ ወደ ግብጽ የሚጓዙ ወንድሞችን ያመለክታል:: (የሚያቅፍና የማያቅፍ እኛ ይመልከቱ)
እዚህ “እኛ” ወንድሞች እስራኤልና መላውን ቤተሰብ ያመለክታል (የሚያቅ “እኛ” ይመልከቱ)
እዚህ እኛ ወንድማማቾችን ያመለክታል (የሚያቅፍና የማያቅፍ “እኛ” ይመልከቱ)
እዚህ አንተ በነጠላ የተገለጸና እስራኤልን ያመለክታል (ሁለተኛ ወገን ሰው ወይም አንተ አጠቃቀም ይመልከቱ)
እኛ ወንድሞችን ያመለክታል በረሀቡ ጊዜ ሊሞቱ የሚችሉ ትናንሽ ልጆችን ያመለክታል
“ዋስ” የተባለው ረቂቅ ስም እንደ “ተስፋ” የተባለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል፡፡ (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ያዕቆብ ይሁዳን እንዴት ተጠያቂ እንደሚያደረገው በግልጽ መነገር አለበት አት በብንያም ላይ በሚደርሰው ነገር ሁሉ ምላሽ እንዲሰጥ ታደርገኛለህ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ)
ይህ አንድ ሰው እንደሚሸከመው ዕቃ ተደርጐ ኃላፊነትን መሸከም ይገልጻል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይሁዳ ቀድሞ መደረግ የነበረበት ነገር ግን ያልተደረገውን ነገር ይገጻል ተጨማሪ እህል ለመሸመት ልጆቹ ወደግብጽ ሳይሄዱ በመቆየታቸው አባቱን እንስራኤልን ይሁዳ በመውቀስ ይናገረዋል (የሚገመቱ ታሳቢ ሁኔታዎችን ይመልከቱ)
ሁለት ጊዜ መመላለስ በቻልን
ይህ ብቸኛ ምርጫችን ከሆነ ይህን አድረጉ
ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ መውረድ የሚለውን ቃል መጠቀም የተለመደ ነበር
ቆዳን ለማከምና ለመከላከል የሚጠቀሙበት ጣፊጨነት ያለው ቅባታማ ፍሬ ነው:: በዘፍጥረት 37:25 ይህን ቃል እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት “መድኃኒት”
የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች በዘፍጥረት 37:25 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
ትናንሽ አረንጓዴ ተክል ለውዞች (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ጣፋጭ ጣዕም ያለው የዛፍ ፍሬ (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰውን ይወክላል አት ዕጥፍ ገንዘብ ውሰዱ (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ እጅ ሙሉ ሰውን ይወክላል በስልቼቻችሁ አፍ የተመለሰው ብር የተባለው ሀረግ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አንድ ሰው በስልቾቻችሁ የጨመረውን ብር መልሳችሁ ወደ ግብጽ ውሰዱ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤና ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ብንያምንም ደግሞ ውሰዱ
ተመለሱ
ምሕረት የሚለው ረቂቅ ስም ርኀራኄ በሚለው ቅጽል ሊተረጐም ይችላል:: አት “ሁሉን የሚችል አምላክ ያ ሰው እንዲራራ ያድርግላችሁ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ስምዖንን
ልጆቼን ካጣሁ ያው አጣሁ ያዕቆብ ልጆቹን ቢያጣ እንዳጣ ሊቀበል አውቆታል ማለት ነው
እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰውን ይወክላል:: አት እነርሱም … ወሰዱ (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደዚያ ወረደ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር
ብንያም ከዮሴፍ ታላቅ ወንድሞች ጋር
የቤቱ አዛዥ የዮሴፍን ቤት ተግባራትን ለማሰተዳደር ኃላፊነት ነበረው
እዚህ “አመጣቸው” እንደ “ወሰዳቸው” ሊተረጐም ይችላል:: (“መጣ” እና “ሄደ” አጠቃቀም ይመልከቱ)
ወደ ዮሴፍ ቤት ውስጥ
የዮሴፍ ወንድሞች ፈሩ
ይህ ተሻጋሪ ግስ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፤ አት “ወደ ዮሴፍ ቤት ይሄዱ ነበር” ወይም “የቤቱ አዛዥ ወደ ዮሴፍ ቤት ይወስዳቸው ነበር” (ተሻጋሪና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)፡፡
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት የቤቱ አዛዥ እየወሰደን ያለው ያነ አንድ ሰው በስልቾቻችን በጨመረው ብር ሰበብ ነው (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ እንደ አድስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት “ሊከሰን እጋጣሚ እየጠበቀ ስላለ ሊያሰረን ይሆናል”
ወንድሞቹ ለቤቱ አዛዥ መናገር ቀጠሉ
ይህ ሀረገ በታሪኩ ዋና ክተት ለማመልከት ተጠቅሞአል በቋንቋዎ ይህን የሚገልጹበት መንገድ ካለ ይጠቀሙ::
ለአዳር በሠፈርንበት ቦታ በደረስን ጊዜ
እዚህ “እነሆ” የሚለው ቃል ወንድሞቹ ባዩት ነገር እንደተገረሙ ለማሳየት ተጠቅሞአል::
እያንዳንዳችን በየስልቾቻችን ሙሉውን ብሮቻችንን አገኘው
እዚህ እጆች ሙሉውን ሰው ይወክላሉ አት ብሮቻችንን መልሰን የዘነው መጣን (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ እጆች ሙሉ ሰው ይወክላሉ:: አት “ደግሞም እህል መሸመቻ የሚሆነንን ብር ይዘን መጥተናል” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደዚያ ወረደ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር
ረቂቅ ስም ሰላም እንደ ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ዘና በሉ ወይም ተረጋጉ” (ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ)
የቤቱ አዛዥ ሁለት የተለያዩ አምላኮችን እየተናገረ አይደለም አት “አምላካችሁ አባታችሁ የሚያመለከው”
ይህ ባህል ረጅም ጉዞ ተጉዘው ከመጡ በኋላ የደከሙ መንገደኞች ድካማቸው እንዲቀል የሚረዱበት ነው:: የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልክቱ)
ገፈራ ለከበቶች የሚሆን ድርቆሽ ነው
“እጅ” ሙሉን ሰው ይወክላል:: አት “ወንድሞች ያመጡአቸውን እጅ መንሻቸውን” (ክፍልን እንደሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ክብርና አክብሮት የሚገለጽበት መንገድ ነው:: (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
አባታቸውን እንደ “አገልጋይህ” ማመልከታቸው አክብሮታቸውን ለማሳየት ነው አት “አባታችን የሚያገለግልህ”
እነዚህ ቃላት በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው በሰውየው ፊት ጐንበስ በማለት አክብሮታቸውን ገለጹ:: አት “በፊቱ ሰገዱለት” (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ቀና ብሎ ሲመለከት ማለት ነው ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ
ይህ በአድስ ዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “የእናቱን ልጅ.. አየ:: ዮሴፍም አለ፤”
ተገቢ አማራጭ ትርጉሞች 1 ይህ ሰው ብንያምን እንደሆነ ለማረጋገጥ ዮሴፍ በውኑ ይጠይቃቸዋል ወይም 2) ይህ አግናኝ ጥያቄ ነው:: “ደግሞ ይህ ታናሽ ወንድማችሁ …. “ (አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
ይህ አንድ ሰው በዝቅተኛ ደረጃ ላለ ሌላ ሰው በጓደኝነት መንገድ የሚጠራው አጠራር ነው:: አት “ወጣቱ”
ተቻኩሎ ከክፍሉ ወጣ
ስሜቱ በጥልቀት የሚለው ሀረግ አንድ መልካም ነገር ሲከሰት የሚሰማ ታላቅ ስሜትን ያመለክታል:: አት “ለወንድሙ የመራራት ጠንካራ ስሜት ነበረው” ወይም “ለወንድሙ ጠንካራ የናፍቆት ስሜት ነበረው” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ዮሴፍ እንደሚናገር ግልጽ ማድረግ ይቻላል:: አት “እናም ለአገልጋዮቹ አላቸው” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ሰዎች እንዲመገቡ ምግብን ማቅረብ ማለት ነው፡፡
ይህም ዮሴፍ ወንድሞቹና ሌሎች በአንድ ክፍል በተለያየ ቦታ ተቀምጠው ይመገባሉ ማለት ነው አገልጋዮችም ለዮሴፍ ለብቻው ለመንድሞቹም ለብቻቸው እናም ከእርሱ ጋር ለሚበሉ ግብጻዊያን ደግሞ ለብቻቸው አቀረቡላቸው
እነዚህ ምናልባት ከእርሱ ጋር የሚበሉ የግብጽ ባለሥልጣናት ይሆናሉ ነገር ግን ከዮሴፍና ከዕብራዊያን ወንድሞቹ ተለይተው ተቀምጠዋል
ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል ይህንን ያደረጉበት ምክንያት ግብጻዊያን ከዕብራዊያን ጋር መመገብ ጸያፍ አድርገው ያስባሉ
እዚህ እንጀራ ጠቅላላ ምግብ ይወክላል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እያንዳንዱ ወንድም የት መቀመጥ እንዳለበት ዮሴፍ እንዳዘጋጀ ሊገመት ይገልጻል የተገለጸውን መረጃ ግልጽ ማድረግ ይቻላል አት የሚቀመጡበት ቦታ በተዘጋጀላቸው መሠረት በሰውየው/ዮሴፍ ፊት ወንድሞቹ ተቀመጡ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ)
“በኩር”ና “ታናሽ” የተጠቀሙት ሁሉም ወንድሞች በአንድነት እንደየዕድሜያቸው በተርታ እንደተቀመጡ ለመግለጽ ነው::( ነጠላ ነገር በብዙ የመግለጽ ዘይቤ/merism/ ይመልከቱ)
ይህን ባወቁ ጊዜ ሰዎቹ በጣም ተገረሙ
አምስት እጥፍ የሚለው ሀረግ በአጠቃላይ ብዙ በሚለው ሊገለጽ ይችላል:: አት “ብንያም የተቀበለው ድርሻ ወንድሞቹ ከተቀበሉት በጣም ብዙ ነበር”
1 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ያህል እህል በየስልቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዱንም ገንዘብ በየስልቻው አፍ አስቀምጠው። 2 ከዚያም የብር ዋንጫዬን በታናሹ ወንድማቸው ስልቻ አፍ ከእህሉ ዋጋ ጋር ጨምረው።” አዛዡም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ። 3 ጠዋት በማለዳ ወንድማማቾቹ አህዮቻቸውን ይዘው እንዲሄዱ ተደረገ። 4 ከከተማውም ምንም ያህል ርቀው ሳይሄዱ፣ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፤ “እነዚያን ሰዎች ቶሎ ድረስባቸውና፣ ‘በመልካም ፋንታ ክፉ የመለሳችሁት ስለ ምንድን ነው? 5 የጌታዬን የብር ዋንጫ የሰረቃችሁት ለምንድነው? ዋንጫው ጌታዬ የሚጠጣበትና ሁሉን ነገር መርምሮ የሚያውቅበት እንደሆነ አታውቁምን? ይህ ያደረሳችሁት በደል እጅግ ከባድ ነው’ ብለህ ነገራቸው።” 6 የቤቱ አዛዥም እንደደረሰባቸው፣ ልክ እንደተባለው ተናገራቸው። 7 እነርሱ ግን እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን እንዲህ ያለ ነገር ለምን ይናገራል? እኛ አገልጋዮችህ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም። 8 ከዚህ ቀደምም በየስልቾቻችን አፍ የተገኘውን ብር ከከነዓን እንኳ መልሰን አምጥተናል፤ ታዲያ አሁን ብር ወይም ወርቅ ከጌታህ ቤት እንዴት እንሰርቃለን? 9 የጠፋው ዕቃ ከአገልጋዮችህ የተገኘበት ይሙት፤ የቀረነው የጌታችን ባሮች እንሁን።” 10 አዛዡም መልካም ነው፤ እንዳላችሁት ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው ባሪያዬ ይሆናል፤ የቀራችሁት ግን ከበደል ነጻ ትሆናላችሁ” አላቸው። 11 ስለዚህ በፍጥነት ስልቻዎቻቸውን አወረዱ፤ እያንዳንዱም የራሱን ስልቻ ከፈተ። 12 ከዚያም አዛዡ ፍተሻውን ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ቀጠለ። በመጨረሻም ጽዋው በብንያም ስልቻ ውስጥ ተገኘ። 13 በዚህ ጊዜ ልብሶቻቸውን በሐዘን ቀደዱ፤ ሁሉም ስልቾቻቸውን በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማይቱ ተመለሱ። 14 ይሁዳና ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ሲገቡ፣ ዮሴፍ ገና ከቤቱ አልወጣም ነበር። እነርሱም በፊቱ ተደፍተው ሰገዱ። 15 ዮሴፍም፣ “ለምን እንዲህ ያለ ነገር አደረጋችሁ? እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን የሚያውቅበት ልዩ ጥበብ እንዳለው አታውቁምን?” ሲል ጠየቃቸው። 16 ይሁዳም፣ “ከእንግዲህ ለጌታችን ምን ማለት እንችላለን? ምንስ እንመልሳለን? እንዲህ ካለው በደል ንጹሕ መሆናችንን ማስረዳትስ እንዴት ይቻለናል? ምክንያቱም እግዚአብሔር የሠራነውን በደል ገልጦታል፤ እንግዲህ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሪያዎችህ እንሁን” አለ። 17 ዮሴፍም፣ “ይህንስ አላደርገውም፣ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ መሆን አለበት፤ ሌሎቻችሁ በሰላም ወደ አባታችሁ መመለስ ትችላላችሁ” አለ። 18 ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፣ ምንም እንኳ የፈርዖን ያህል የተከበርክ ብትሆንም እባክህ አትቆጣኝ። 19 ጌታዬ፣ ‘አባት ወይም ወንድም አላችሁ?’ ብሎ አገልጋዮቹን ጠይቆ ነበር። 20 እኛም፣ ‘አዎን ሽማግሌ አባት አለን፤ አባታችንም በስተርጅና የወለደው ትንሽ ልጅ አለው፣ ወንድምዬው ሞቶአል፣ ከአንድ እናት ከተወለዱት ልጆች መካከል የተረፈው እርሱ ብቻ ነው፤ አባቱም በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር። 21 ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፣ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን። 22 እኛም ለጌታዬ፣ ‘ልጁ ከአባቱ ሊለይ አይችልም፤ ከተለየው ደግሞ አባትዬው ይሞታል’ አልንህ። 23 አንተ ግን እኛን አገልጋዮችህን፣ ‘ታናሽ ወንድማችሁ አብሮአችሁ ወደዚህ ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም’ አልኸን። 24 እኛም ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ በተመለስን ጊዜ አንተ ጌታዬ ያልኸንን ነገርነው። 25 ከዚያም አባታችን፣ ‘እስቲ ተመልሳችሁ ጥቂት እህል ሸምቱልን’ ሲለን 26 ‘መሄድ አንችልም፤ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን አብሮን ሲሄድ ብቻ ነው። ታናሽ ወንድማችንን ይዘን ካልሄድን በስተቀር የሰውዬውን ፊት ማየት አንችልም’ አልነው። 27 አገልጋይህ አባቴም እንዲህ አለን፤ ‘ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆች እንደወለደችልኝ ታውቃላችሁ፤ 28 አንዱ በወጣበት በመቅረቱ በእርግጥ አውሬ በልቶት ይሆናል አልሁ፣ ከዚያ በኋላ ዐላየሁትም። 29 አሁን ደግሞ ይህን ልጅ ወስዳችሁ አንዳች ጉዳት ቢደርስበት ሽበቴን በመራር ሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።’ 30 እንግዲህ አሁን ልጁን ሳንይዝ ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ ብመለስ ሕይወቱ ከልጁ ሕይወት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ስለሆነ፣ 31 የልጁን ከእኛ ጋር አለመኖር ሲያይ አባቴ ይሞታል። ከዚህም የተነሣ እኛ አገልጋዮችህ የአባታችንን ሽበት በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እናወርደዋለን። 32 እኔ አገልጋይህ፣ “ልጅህን መልሼ ሳላመጣ ብቀር ለዘላለም በደለኛ አድርገህ ቁጠረኝ’ በማለት ስለ ልጁ ደህንነት በአባቴ ፊት ራሴን ዋስ አድርጌአለሁ። 33 ስለዚህ አሁን፣ አገልጋይህ በልጁ ፋንታ የአንተ የጌታዬ ባሪያ ሆኜ እዚሁ ልቅር ልጁ ግን ከወንድሞቹ ጋር ይመለስ። 34 ልጁን ሳልይዝ እንዴት ተመልሼ ወደ አባቴ እሄዳለሁ? እባክህ በአባቴ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዳይ አታድርገኝ።”
ይህ በታሪኩ አድስ ክስተት ይጀምራል ይህ በተለይ ከግብዣው ሁለተኛው ቀን ማግሥት የተከሰተውን ያመለክታል፡፡
የቤቱ አዛዥ የዮሴፍ ቤት ተግባራትን ለማስተዳደር ኃላፊነት ያለው ነበር
የእነርሱ ገንዘብ በትንሽ ቦርሳ ውስጥ የተቀመጡ የብር ሳንቲሞች ነበሩ
በስልቻው
የብሩን ዋንጫዬን ጨምረው
ወንድም የሚለው ቃል የታወቀ ነው አት በታናሽ ወንድማቸው ስልቻ (ድብቅ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
የማለዳ ብርሃን ሲወጣ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ሰዎችን ከነአህዮቻቸው ሸኙአቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ጥያቄ ወንድሞቹን ለመቆጣት ተጠቅሞአል:: አት እኛ “ለእናንተ መልካም ካደረግን በኋላ ክፉ መለሳችሁብን” (ሽንገላ አዘል/ rhetorical/ ጥያቄ ይመልከቱ)
ይህ ጥያቄ የተጠቀመው ወንድሞቹን ለመቆጣት ነው፡፡ አት “ይህ ጽዋ ጌታዬ የሚጠጣበትና የተሰወረ ነገርንም የሚያውቅበት እንደሆነ በእርግጥ ታውቃችሁ” (ሽንገላን የያዘ ጥያቄ ይመልከቱ) ይህ ያደረጋችሁት የፈጸማችሁት ድርጊት ክፉ ነው ያደረጋችሁት የሚለውን መደጋገሙ ትኩረት ለመስጠት ነው አት የፈጸማችሁት ነገር እጅግ ክፉ ነው ተመሣሣይ ተጓዳኝ ንጽጽር ነው::
ዮሴፍ የነገራቸው የነገረውን ነገራቸው
“ቃል” የተናገረውን ነገር:: ይወክላል ወንድሞቹ የቤቱን አዛዥ እንደ “ጌታዬ” ያመለክታሉ:: ይህ በከፍተኛ ኃላፊነት ላሌ ሰው የሚነገር መደበኛ አባባል ነው:: አት “ጌታዬ ለምን እንደዚህ ይናገራሉ?” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤና አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
አንድ ሰው አንድን ነገር የማያደርገው ያ ሰው አንድን ዕቃ ከራሱ አርቆ እንደማስቀመጥ ተደርጐ ተገልጾአል፣ (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“እኛ ስለምንናገረው ነገር ያድምጡ እናም የምንናገረው ነገር እውነት እንደሆነ ያያሉ፤ ብሩ”
“በየስልቾቻችን ያገኘነውን ብር ያውቃሉ”
ከከነዓን መልሰን ወደ አንተ አምጥተናል
ወንድምቹ ከግብጽ ጌታ እንዳልሠረቁ እትኩሮት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማሉ:: አት “ስለዚህ ከጌታህ ቤት የወሰድነው ምንም ነገር የለም!” (ሽንገላ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
እንዚህ በጣምራ ቃላት የተጠቀሙት ዋጋ ያለውን ምንም ነገር እንዳልሠረቁ ለመግለጽ ነው
ወንድምች ራሳቸውን እንደ “የአንተ አገልጋዮች” ይገልጻሉ:: ይህ ከፍተኛ ስልጣን ላለ ሰው የሚነገር መደበኛ መንገድ ነው:: እንዲሁም ይህ የተገኘበት ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክሊገለጽ ይችላል:: አት “ከእኛ አንዱ ጽዋውን/ዋንጫውን የሠረቀ ከተገኘ” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገለላለጽና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ ጌታችን የቤቱን አዛዥ ያመለክታል ይህ በሁለተኛ ሰው መልክ ሲገለጽ ይችላል አት እንደባሪዎች ሊትወስደን ትችላለህ (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ሰው አገለላለጽ ይመልከቱ)
መልካም ነው: እንዳላችሁት አደርጋለሁ:: እዚህ “አሁን” “በዚህ ጊዜ” ማለት አይደለም ነገር ግን የሚቀጥለው ዋና ነጥብ ትኩረትን ለመሳብ ተጠቅሞአል::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ከስልቾቻችን በአንዱ ጽዋውን ካገኘው ያ የተገኘበት ሰው ባሪያዬ ይሆናል (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የየራሱን ስልቻ አራገፌ
“ወንድም” የተባለው ቃል የታወቀ ነው:: “ከታላቅ ወንድም ….እስከ ታናሽ ወንድም” (የተደበቁ ቃላትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ እንደ አድስ ዐረፍተ ነገርና ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል በታናሹ ወንድም የቤቱ አዛዥ ጽዋውን በብንያምን ስልቻ አገኘ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ እነርሱ ወንድምቹን ያመለክታል ልብስን መቅደድ የታላቅ ሐዘን ወይም ተካዜ ምልክት ነው (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
በየአህዮቻቸው…. እናም ተመለሱ
ዮሴፍ እዚያው ነበረ
በፊቱም መሬት ላይ ወደቁ:: ይህ ወንድምቹ ጌታው ምሕረት እንዲያደርግላቸው የመፈለጋቸው ምልክት ነው:: (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ዮሴፍ ወንድሞቹን ለመቆጣት ጥያቄ ይጠቀማል:: አት “እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን በጥበብ እንደሚያውቅ ታውቃላችሁ” (ሽንገላን ያዘለ ጥያቄ ይመልከቱ)
ሶስቱም ጥያቄዎች ሁሉ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: የተደረገውን ለመግለጽ የሚናገሩት ምንም እንደሌለ ትኩረት ለመስጠት እነዚህን ጥያቄዎች ይጠቀማሉ፡፡ አት “ጌታዬ የምንናገረው የለንም የሚረባ ነገር መናገር አንችልም ራሳችንን ንጹህ ማድረግ አንችልም” (ተመሣሣይ ተጓዳኝ አገላለጽ እና ሽንገላ አዘል ጥያቄዎች ይመልከቱ)
እዚህ ጌታዬ ዮሴፍን ያመለክታል ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው በሁለተኛ ወገን ሰው መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ምን አንላለን … ባሪያዎችህ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ወንድሞቹ ራሳቸውን እንደ ባሪያዎች ያቀርባሉ :: እዚህ ገለጠ የሚለው እግዚአብሔር ወንድሞቹ ያደረጉትን ገለጠ ማለት አይደለም:: ነገር ግን እነርሱ ስላደረጉት ነገር እግዚአብሔር እየቀጣቸው ነው የሚል ትርጉም አለው:: አት “እግዚአብሔር ላለፈው ኃጢአት እየቀጣቸው ነው”
ወንድሞቹ ራሳቸውን እንደ ባሪያዎች ያቀርባሉ:; ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: በአንደኛ ወገን ሰው መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “በደላችንን” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰው ይወክላል:: እንዲሁም የተገኘበት የሚለው ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:; አት “ጽዋህን የወሰደው” (ምትክ ቃል አጠቃቀምና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የማያደርገው አንድ ነገር ያ ሰው ከራሱ አርቆ የሚያቀምጠው ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “ያን ነገር የሚያደርግ የእኔ ዓይነት አይደለም” (ዘይቤያዊ አነጋYገር ይመልከቱ)
እዚህ “እጅ” ሙሉ ሰው ይወክላል:: እንዲሁም የተገኘበት የሚለው ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:; አት “ጽዋዬን የወሰደው ሰው” (ምትክ ቃል አጠቃቀምና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ተጠግቶ
ይሁዳ ራሱን እንደ “አገልጋይህ ወይም ባሪያህ” ያመለክታል:: ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: ይህ በአንደኛ ወገን ሰው መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እኔ ባሪያህ ወይም አገልጋይህ”(አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
“ጆሮ” የሚለው ለሙሉ ሰው የሚሆን ምትክ ቃል ነው፡፡ አት “ጌታዬ ሊናገርህ” (ምትክ ቃል አጠቃቀም ይመልከቱ)
እዚህ ጌታዬ ዮሴፍን ያመለክታል፡፡ ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: ይህ በሁለተኛ ወገን ሰው መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ለአንተ”(አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
መቆጣት እንደሚያቃጥል እሳት ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “አባክህን እኔን አገልጋይህን አትቆጣኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ጌታው ትልቅ ሥልጣን እንዳለው ትኩረት ለመስጠት ከፈርዖን ጋር ያወዳድረዋል:: ይህም የሚገልጸው ሊቆጣውም ሊገድለውም እንደሚችል ነው አት “እንደ ፈርዖን ኃይለኛ ስለሆንህና ወታደሮችህም ሊገድሉኝ ስለሚችሉ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቀ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ጌታዬ አባት ወይም ወንድም እንዳለን ጠየቀን” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ይሁዳ ዮሴፍን “ጌታዬ” እና “እርሱ” በሚሉ ቃላት ያመለክተዋል:: አንዲሁም ደግሞ ወንድሞቹንና ራሱን እንደ “የእርሱ ባሪያዎች” ይገልጻል:: አት “አንተ ጌታዬ ባሪያዎችህን ጠየቅሄን ወይም አንተ ጠቀየቅሄን” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)
በዮሴፍ ፊት መናገሩን ይሁዳ ቀጠለ
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እናም እኛ እንዲህ አልን ‘አባት አለን አባቱም ይወድደዋል’” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ይሁዳ ዮሴፍን እንደ “ጌታዬ” ያመለክተዋል:: ይህ ለአንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: አት “ጌታዬ እኛም እንዲህ አልን”(አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ለጓደኛ ወዳጅ ወይም ለቤተሰብ አባል ያለውን ፍቅር ይገልጻል
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እናም አንተ ለባሪያዎችህን ታናሽ ወንድማችሁን አምጡት እኔም አየዋለሁ አልህ’” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ይሁዳ ወንድሞቹንና ራሱን እንደ እርሱ ባሪያዎች ያመለክታል:: አት “ከዚያም ለእኛ ለባሪያዎችህ እንዲህ አልህ”(አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)
ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ ሲነገር መውረድ የሚለው ቃል የተለመደ ነው:: አት “ወደ እኔ አምጡት” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “መልሰን እኛም ለጌታዬ ልጁ ….አይችልም፤ ….አባትየው ይሞታል” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ከማዘን የተነሣ አባታቸው እንደሚሞት ይገልጻል (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይሁዳ ታሪኩን ለዮሴፍ መናገር ቀጠለ
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከዚያም ለባሪያዎችህ ታናሽ ወንድማችን ከእኛ ጋር ካልመጣ ፊቴን አታዩም አልሄን ” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ይሁዳ ራሱንና ወንድሞቹን እንደ “እርሱ ባሪያዎች” ያመለክታል፡፡ ይህ ትልቅ ባለሥልጣን ለሆነ ለአንድ ሰው የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው፡፡ (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)
ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ ሲነገር መውረድ የሚለው ቃል የተለመደ ነው::
እዚህ “ፊት” ሙሉ ሰውን ይወክላል:: አት እንደገና አታዩኝም (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ የተጠቀመው የታሪኩ አድስ ክፍል መጀመሩን ለማመለከት ነው:: በቋንቋዎ ይህን የሚገልጹበት መንገድ ካለ ይጠቀሙ:: (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ ሲነገር “ወደ ላይ መውጣት” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው
ይሁዳ ዮሴፍን እንደ “ጌታዬ” ያመለክታል:: አት ጌታዬ የነገርከውን ቃል ነገርነው”(አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አባታችን አንደገና ወደ ግብጽ በመሄድ ለእኛና ለቤተሰቦቻችን እህል እንድንሸምት ተናገረን ” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ የያዘ ነው እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከዚያም ለእርሱ ወደ ግብጽ መውረድ አንችልም አልን ታናሽ ወንድማችን ከእኛ ጋር … ከእኛ ጋር ” (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
እዚህ ፊት ሙሉ ሰውን ይወክላል:: አት “ሰውየውን ለማየት” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
እንዲህ አለን ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆችን እንደወለደችልን እናንተ ታውቃላችሁ አንዱ ከእኔ ወጣ አውሬ በላው አላችሁኝ እስከ ዛሬም አላየሁትም ይህንም ከእኔ ለይታችሁ ደግሞ ብትወስዱ ክፉም ቢያገኘው ሽበቴን በሐዘን ወደ መቃበር ታወርዱታላችሁ ይህ ሁለት ደረጃና ሶስት ደረጃ ጥቅሶችን ይዞአል እነዚህም እንደተዘዋዋሪ ጥቅሶች ሊገለጹ ይችላሉ አት እንዲህ አለን ሚስቱ ራሔል ሁለት ወንዶች ልጆችን ብቻ እንደወለደችለት እናውቃለን ከእነርሱ አንዱ ወጣና አውሬ በላው እናም እስከ ዛሬ አላየሁትም ሌላውን ልጅ ብንወስደውና ክፉ ቢያገኘው በሐዘን እንዲሞት እናደርጋለን (ጥቅስን በጥቅስ ውሰጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)ከዚይ አለ
እዚህ “እኛ” ዮሴፍን አያካትትም (ነጠላና ብዙ ወይም አካታች “እኛ” ይመልከቱ)
እዚህ “እናንተ” ብዙና ወንድሞቹን ያመለክታል (“እናንተ” አጠቃቀም ዓይነት ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት አውሬ በላው ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ
ለአንድ ሰው አንድ ክፉ ነገር የሚደርሰበት ጉዳት ወደዚያ ሰው እንደሚመጣ ተደርጐ ተቆጥሮአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ወደ መቃብር ማውረድ” እንዲሞትና ወደ መቃብር እንዲወርድ ማድረግ ማለት ነው:: “ማውረድ” የሚለውን ቃል የተጠቀመው መቃብር በመሬት ውስጥ እንደሆነ በተለምዶ የታወቀ ስለሆነ ነው:: አት “ከዚያም እኔን ሽማግሌውን በሐዘን እንዲሞት ታደርጋላችሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ያዕቆብን የሚያመለክትና ሽምግልናውን አበክሮ የሚናገር ነው:: አት “እኔ ሽማግለው” (ምትክ ቃል አጠቃቀም ይመልከቱ)
ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ጠቃሚ ነገር ትኩረት እንዲሰጥበት ተጠቅሞአል
ይሁዳ ያለ ብንያምን ወደ አባቱ በሚመለስበት ጊዜ ምን ሊፈጠር እንደሚችል የሚገምተውን ነገር ግን እውነት የሆነውን ለዮሴፍ ይገልጻል (ግምታዊ ሁኔታዎችን ይመልከቱ)
እዚህ “መምጣት” “መሄድ” ወይም “መመለስ” በሚለው መተርጐም ይችላል::
ልጁ ከእኛ ጋር አለመኖር
አባታቸው ልጁ ከሞቴ እሞታለሁ ያለው አባባል የሁለቱ ሕይወት በአካል በጥብቅ የተሣሠረ እንደሆነ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “እርሱም ልጁ ካልተመለሰ እሞታለሁ ስላለ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይሁዳ ወደፊት ይሆናል ብሎ ስለሚገምተው ነገር በእርግጥ እደሚደረግ አድርጐ ይናገራል (ግምታዊ ሁኔታዎች ይመልከቱ)
ወደ መቃብር ማውረድ እንዲሞትና ወደ መቃብር እንዲወርድ ማድረግ ማለት ነው:: “ማውረድ” የሚለውን ቃል የተጠቀመው መቃብር በመሬት ውስጥ እንደሆነ በተለምዶ የታወቀ ስለሆነ ነው:: አት “እናም ሽማግሌውን አባታችንን በሐዘን እንዲሞት እናደርጋለን” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይሁዳ ራሱንና ወንድሞችን “ባሪያዎችህ” ብሎ ያመለክታል:: ይህ ለአንድ ትልቅ ባለሥልጣን መደበኛ መንገድ የሚነገርለት ነው:: አት “እኛ አገልጋዮችህ” ወይም “እናም እኛ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገንነ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ “ሽበት” ያዕቆብን የሚወክልና ሽምግልናውን የሚናገር ነው:: አት “ሽማግሌው አባታችን” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ) ስለ ልጁ ደኀንነት በአባቴ ፊት ራሴን ዋስ አድርጌአለሁ ረቂቅ ስም ዋስ ተስፋ በሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል አት ልጁን በሚመለከት ለአባቴ ተስፋ ስጥቼዋለሁ ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ
ይሁዳ ራሱን “ባሪያህ” ብሎ ያመለክታል፡፡ አት “ለእኔ ለባሪያህ” ወይም “ለእኔ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እንደበደለኛ መቆጠር በደል እንድሰው የሚሸከመው ነገር ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “አባቴ ይወቅሰኛል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ በአሁን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ዋና ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ተጠቅሞአል::
ይሁዳ ራሱን “ባሪያህ” ብሎ ያመለክታል፡፡ አት “እኔ ለባሪያህ” ወይም “እኔ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ መውጣት የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር
ብንያምን ወደ ቤት ካልተመለሰ አባቱ ሊኖረው የሚችለውን ሐዘን ለማተኮር ይሁዳ ጥያቄ ይጠቀማል:: አት “ልጁ ከእኔ ጋር ካልሆነ ወደ አባቴ መመለስ እልችልም“ (አግናኝ ወይም ሽንገላ አዘል ጥያቄዎች ይመልከቱ)
ከባድ መከራ የደረሰበት ሰው በዚያው ሰው ክፉ ነገር እንደመጣበት ተደርጐ ተነግሮአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
1 በዚያን ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩ ሰዎች ፊት ስሜቱን ሊገታ ባለመቻሉ፣ “እዚህ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፤ ስለዚህም ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት ጊዜ ከእርሱ ጋር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም። 2 ዮሴፍም ድምፁን ከፍ አድርጎ በማልቀሱ ግብፃውያን ሰሙት፣ ወሬውም ወደ ፈርዖን ቤተ ሰዎች ደረሰ። 3 ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ ለመሆኑ አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” ሲል ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ግን በፊቱ ተደናግጠው ስለነበር መልስ ሊሰጡት አልቻሉም። 4 ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በሉ” አላቸው፣ ወደ እርሱም በቀረቡ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ 5 አሁንም በመሸጣችሁ አትቆጩ፤ በራሳችሁም አትዘኑ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወት ለማዳን ሲል ከእናንተ አስቀድሞ እኔን ወደዚህ ልኮኛል። 6 በምድር ላይ ራብ ከገባ ይኸው ሁለት ዓመት ሆነ፣ ከዚህ በኋላም የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና አሉ። 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ሕይወታችሁን በታላቅ ማዳን ለመታደግና ዘራችሁ ከምድር ላይ እንዳይጠፋ በማሰብ ከእናንተ አስቀድሞ ወደዚህ ላከኝ። 8 ስለዚህ አሁን ወደዚህ የላከኝ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፣ እርሱም ለፈርዖን እንደ አባት፤ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታ፣ እንዲሁም በግብፅ ምድር ላይ ገዢ አደረገኝ። 9 አሁንም ‘በፍጥነት ወደ አባቴ ተመልሳችሁ እንዲህ በሉት፤ “ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔር የመላው ግብፅ ጌታ አድርጎኛል፤ ስለዚህ ሳትዘገይ ወደ እኔ ና። 10 ልጆችህን የልጅ ልጆችህን በጎችህን፣ ፍየሎችህን ከብቶችህንና ያለህን ሁሉ ይዘህ በአቅራቢያዬ በጌሤም ትኖራለህ። 11 ገና ወደ ፊት የሚመጣ የአምስት ዓመት ራብ ስላለ፣ በዚያ የሚያስፈልጋችሁን እኔ እሰጣችኋለሁ፤ ያለበልዚያ ግን አንተና ቤተ ስዎችህ ያንተም የሆነው ሁሉ፣ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።’ 12 ፊታችሁ ሆኜ የማናግራችሁ እኔ ዮሴፍ ራሴ መሆኔን እናንተም ሆናችሁ ወንድሜ ብንያም በዓይናችሁ የምታዩት ነው። 13 በግብፅ ስላሏኝ ክብርና ስላያችሁትም ሁሉ ለአባቴ ንገሩት፣ አባቴንም በፍጥነት ይዛችሁት ኑ። 14 ከዚያም በወንድሙ በብንያም አንገት ላይ ተጠምጥሞ አለቀሰ፤ ብንያምም እያለቀሰ ዮሴፍን አቀፈው። 15 የቀሩትምንም ወንድሞቹን አንድ በአንድ እየሳመ አለቀሰ። ከዚያም ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር መጨዋወት ጀመሩ። 16 የዮሴፍ ወንድሞች መምጣት በፈርዖን ቤተ መንግሥት በተሰማ ጊዜ፣ ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ ደስ አላቸው። 17 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ለወድሞችህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘እንዲህ አድርጉ እህዮቻችሁን ጭናችሁ ወደ ከነዓን ምድር ተመለሱ። 18 ከዚያም አባታችሁንና ቤተ ሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብፅ ምድር እሰጣችኋለሁ፤ በምድሪቱ በረከት ደስ ብሎአችሁ ትኖራላችሁ።’ 19 ደግሞም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ይህን አድርጉ፣ ከግብፅ ምድር ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን የምታጓጉዙባቸው ሠረገላዎች ወስዳችሁ፤ አባታችሁን ይዛችሁ ኑ። 20 ስለ ንብረታችሁ ምንም አታስቡ፣ ከግብፅ ምድር እጅግ ለም የሆነው የእናንተ ይሆናልና።’” 21 የእስራኤልም ልጆች ይህንኑ አደረጉ። ዮሴፍም ፈርዖን ባዘዘው መሠረት ሠረገላዎች አቀረበላቸው፤ የመንገድም ስንቅ አስያዛቸው። 22 ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የክት ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን ሶስት መቶ ጥሬ ብርና አምስት የክት ልብስ ሰጠው። 23 ለአባቱም በግብፅ ምድር ከሚገኘው የተመረጠ ነገር በዐሥር አህዮች፣ እንደዚሁም በዐሥር እንስት አህዮች ዳቦና ሌላ ምግብ አስጭኖ ሰደደለት። 24 ከዚህ በኋላ ወንድሞቹን አሰናበታቸው፤ ከእርሱም ሲሰናበቱ፣ መንገድ ላይ እንዳትጣሉ” አላቸው። 25 እነርሱም ከግብፅ ወጥረው በከነዓን ምድር ወደሚኖረው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ መጡ። 26 አባታቸውንም፣ እነሆ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በግብፅ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኖአል” ብለው ነገሩት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም። 27 ነገር ግን ዮሴፍ ያላቸውን ሁሉ በነገሩት ጊዜና እርሱን ወደ ግብፅ የሚወስዱበትን ዮሴፍ የላከለትን ሠረገላ ባየ ጊዜ የአባታቸው የያዕቆብ መንፈስ ታደሰ። 28 ከዚያም እስራኤል፣ “ልጄ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ ከመሞቴ በፊት ሄጄ ዐየዋለሁ” አለ።
ስሜቱን ሊገታ አልቻለም ማለት ነው ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ማልቀስ ጀምሮ ነበር”
አጠገቡ
እዚህ “ቤት” በፈርዖን ቤተመንሥት ያሉ ሰዎችን ይወክላል፡፡ አት “በፈርዖን በተመንግሥት ያለው ሁሉ” (ምትክ ቃላት የመጠቀም ዘይቤ ይመልከቱ)
እርሱን ፈርተው
ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አት “ወደ ግብጽ ላመጡኝ ነጋዴዎች እንደ ባሪያ የሸጣችሁኝ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“አትቈጩ” ወይመ “አትጨነቁ”
ትርጉሙም በግልጽ ሊነገር ይችላል፡፡ አት “እንደ ባሪያ ሸጣችሁኝ እናም ወደ ግብጽ ምድር ላካችሁን”
እዚህ “ሕይወት” ዮሴፍ በረሃቡ ጊዜ ያዳናቸውን ሰዎች ይወክላል:: አት “የብዙ ሰዎችን ሕይወት እንዳድን” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
የማይታረስባቸው ወይም ሰብል የማይሰበሰባቸው አምስት ዓመታት አሉ እዚህ የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበስብባቸው ሰብሎች ከድርቁ የተነሣ እንደማይመረቱ የሚገልጹ ናቸው:: አት “ረሃቡ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ይቀጥላል” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
“እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ከምድር ላይ ፈጽማችሁ እንዳትጠፉ” ወይም “ዘራች ከምድር ላይ እንዲኖር”
ማዳን የተባለው ረቂቅ ስም ማትረፍ በሚለው ሊገለጽ ይችላል:: አት “በታላቅ መንገድ በማትረፍ በሕይወት እንዲትኖሩ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ዮሴፍ ፍርዖንን ማማከሩና መርዳቱ ዮሴፍ እንደፈርዖን አባት ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “የፈርዖን መሪ ወይም አማካሪ አድርጐኛል” ወይም “የፈርዖን ዋና አማካሪ አድርጐኛል” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ “ቤት” በቤተመንግሥቱ የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላል:: አት “በቤተሰዎቹ ሁሉ ላይ” ወይም “በቤተመግሥቱ ላይ” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
እዚህ “ምድር” ሰዎችን ይወክላል:: አት “በግብጽ ምድር ሰዎች ሁሉ ላይ ገዥ” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ዮሴፍ ከግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሁለተኛ ደረጃ ገዥ ነው ማለት ነው:: ይህ የተነገረው መረጃ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ ሲነገር ወደ ላይ መውጣት የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር:: አት “ወደ አባቴ ሂዱ”
ይህ ሶስት ደረጃ ያለው ጥቅስ ነው በሁለት ደረጃዎች ቀለል ባለ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እኔ የምለውን ንገሩት እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ ሲነገር ወደ ታች መውረድ የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር:: አት “ወደዚህ ወደ እኔ ና”
ችግርን እንደ መድረሻ አድርጐ ይናገራል:: አት “ማጣት” ወይም “ረሀብ” (ዘይቤያዊ አነገር ይመልከቱ)
እዚህ “ዐይኖች” ሙሉ ሰው ይወክላሉ:: አት “እናንተ ሁላችሁና ብንያም ታያላችሁ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ አፍ ሙሉ ሰውን ይወክላል፡፡ አት “እኔ ዮሴፍ እነግራችኋለሁ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
የግብጽ ሰዎች በታላቅነት እንዴት እንደሚያከብሩኝ
ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ ሲነገር ወደ ታች መውረድ የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር:: አት “አባቴን ወደዚህ አምጡት”
ዮሴፍ ወንድሙን ብንያምን አቀፈውና ሁለቱም አለቀሱ
በጥንታዊቷ ቅርብ ምሥራቅ ዘመድን በመሳም ሰላምታ መስጠት የተለመደ ነበር:: በቋንቋዎ እንዲህ የመሰለ ስሜት ገላጭ ሰላምታ አሰጣጥ ካለ ያን ይጠቀሙ:: ከሌለ ግን ተገቢ የሆነውነ ቃል ይጠቀሙ::
ይህም ዮሴፍ በሳማቸው ጊዜ እያለቀሰ ነበር ማለት ነው
አስቀድመው ሊነጋገሩ ፈርተው ነበር:: አሁን ግን በነጻነት መነጋገር እንደሚችሉ ተሰማቸው:: የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉሙ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “ከዚያም በኋላ ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር በነጻነት መነጋገር ጀመሩ” (ግምታም እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል:: እንዲሁም ደግሞ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “የዮሴፍ ወንድሞች እንደመጡ በፈርዖን ቤተመንግሥት ያለው ማንኛውም ሰው ሰማ” (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅስ እናም ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የፈርዖንን ቤተመንሥት ይወክላል
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል:: አት “አህዮቻቸውን እንዲጭኑና ወደ አባታቸውና ቤተሰቦቻውው ወደ ከነዓን እንዲሄዱ ለወንድሞችህ ንገራቸው፤ ወደዚህ እንዲመጡና እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብጽ ምድር እንደሚጣቸወ፤ የምንሰጠውን በረከት እንደሚመገቡ ደግሞም ንገራቸው” (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅስ ይመልከቱ)
እኔም እጅግ ለም የሆነውን የግብጽ ምድር እሰጣችኋለሁ
ምድርቱ የሚትሰጠው መልካም እህል እንደ ምድሪቱ ስብ ተደርጐ ተቆጥሮአል:: አት “የምድሪቱንም እህል ትመገባላችሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ዮሴፍ ለወንድሞቹ ምን መናገር እንዳለበት ፈርዖን መናገሩን ቀጠለ
ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ጠቃሚ ነጥብ/ ቁም ነገር ትኩረት እንዲሰጥበት ተጠቅሞአል
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል:: እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊጠቀስ ይችላል:: አት “ደግሞም ከግብጽ ምድር ልጆቸችሁንና ሚስቶቻችሁን እናም አባታችሁንም ይዘው እንዲመጡ የሚያጓጉዙበትን ሠረገላዎች እንዲወስዱ ንገራቸው እኔም በግብጽ መልካም የሆነውን ስለሚሰጣቸው ንብረታችሁን ይዘው ለመምጣት ምንም አይጨነቁ (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅስ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት “ደግሞም እንትነግራቸው አዝሃለሁ ወይም ደግሞም ንገራቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሠረገላዎች ሁለት ወይም አራት ጐማ ያላቸው የጭነት ሠረገላዎች ናቸው እንስሳት ተሳቢውን ይገትቱታል
ለጉዞአቸው የሚያስፈልጋቸውን ሰጣቸው
አምስት መለወጫ ልብስ ከተሰጠው ከብንያምን በስተቀር ሌሎች አያንዳንዳቸው ሁለት መለወጫ ልብስ ተቀብለዋል (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
3ዐዐ ጥሬ ብር (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
አህዮቹ በሥጦታው ተካትተዋል (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ተገቢ ትርጉሞች የሚያጠቃልሉት 1) አትከራከሩ 2) አትኮራረፉ
ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደላይ” የሚለው ቃለ መጠቀም የተለመደ ነው
እዚህ “የግብጽ ምድር” የግብጽ ሰዎችን ይወክላል አት በግብጽ ሰዎች ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል:: (ምትከ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
እነርሱ የተናገሩትን እንደ እውነት መቀበል አቃተው
ለያዕቆብ ነገሩት
ዮሴፍ የነገራቸውን ማንኛውንም ነገር
እዚህ መንፈስ ሙሉ ሰው ይወክላል፡፡ አት “አባታቸው ያዕቆብ ከጭንቀቱ/ከሐዘኑ ተሻለው” ወይም “አባታቸው ያዕቆብ እጅግ ደስተኛ ሆነ” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም የመልከቱ)
1 እስራኤልም ጓዙን ሁሉ ጠቅልሎ ተነሣ፤ ቤርሳቤህም ሲደርስ፣ ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ መሥዋዕት ሠዋ። 2 እግዚአብሔርም ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ፣ “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፣ አለሁ” አለ። 3 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ በዚያ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና፤ 4 አብሬህ ወደ ግብፅ እወርዳለሁ፣ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፣ የዮሴፍ የራሱ እጆች በምትሞትበት ጊዜ ዓይኖችህን ይከድናል። 5 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን ለያዕቆብ በላከላቸው ሠረገላ ላይ አወጧቸው። 6 ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብፅ ወረዱ። 7 ወደ ግብፅም የወረደው፤ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን ማለት ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው። 8 ወድ ግብፅ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ የያዕቆብ ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦ የያዕቆብ የበኩል ልጆ ሮቤል። 9 የሮቤል ልጆች፦ ሄኖኅ፣ ፈሉሶ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው። 10 የስሞዖን ልጆች፦ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጸሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሳኡል ናቸው። 11 ልጆች፦ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው። 12 የይሁዳ ልጆች፦ ዔር አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። 13 የይሳኮር ልጆች፦ ቶላ፣ ፉዋ፣ ዮብና ሺምሮን ናቸው፤ 14 የዛብሎን ልጆች፦ ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤ 15 እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መሰጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቁጥር ሠላሳ ሦስት ነው። 16 የጋድ ልጆች፦ ጽፎን፣ ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤ 17 የአሴር ልጆች፦ ዩምና፣ የሱዋ፣ የሱዊና በሪዓ ናቸው፤ እኅታቸውም ሤራሕ ናት፤ የበሪዓ ልጆች፦ ሐቤርና መልኪኤል ናቸው፤ 18 እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው። 19 የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤ 20 በግብፅም የኦን ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት። 21 የብንያም ልጆች፦ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ንዕማን፥ አኪ፣ ሮስ፥ ማንፌን፣ ሑፊምና አርድ ናቸው። 22 እነዚህ ዐሥራ አራቱ፣ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። 23 የዳን ልጅ፦ ሑሺም ነው፤ 24 የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዮጽርና ሺሌም ናቸው፤ 25 እነዚህ ሰባቱ ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው። 26 ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የሄዱት የገዛ ዘሮቹ ብዛት ስድሳ ስድስት ሲሆን የልጆቹን ሚስቶች አይጨምርም። 27 ዮሴፍ በግብፅ የወለዳቸውን ሁለት ልጆች ጨምሮ ወደ ግብፅ የወረደው የያዕቆብ ቤተ ሰብ ቁጥር ሰባ ነበር። 28 ያዕቆብም ወደ ጌሤም ለመሄድ መመሪያ ይቀበል ዘንድ፣ ይሁዳን አስቀድሞ ወደ ዮሴፍ ላከው። እርሱም ጌሤም ሲደርሱ፣ 29 ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ። ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደደረሰ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ለረጅም ጊዜ አለቀሰ። 30 እስራኤልም ዮሴፍን፣ “በሕይወት መኖርህን ስላየሁ፣ ከእንግዲህ ብሞትም አይቆጨኝም” አለው። 31 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ እነግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል። 32 ሰዎቹ ከብት የሚጠብቁ ስለሆኑ እረኞች ናቸው፣ ሲመጡም በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውንና ከብቶቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል። 33 ፈርዖን አስጠርቶአችሁ፣ ‘ሥራችሁ ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ፤ 34 እናንተ፣ ‘እኛ አገልጋዮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከብት አርቢዎች በግብፃውያን ዘንድ እንደ ጸያፍ ስለሚቆጠሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”
ወደ ቤርባህ መጣ
“አዎን እየሰማሁ ነኝ”
ከከነዓን ወደ ግብጽ መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደ ታች መውረድ” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው::
እዚህ አንተን የሚለው ነጠላ አገላለጽና ያዕቆብን የሚያመለክት ነው እዚህ ያዕቆብ ታላቅ የሚሆነውን የእርሱን ዘር ይወክላል አት ብዙ ትውልድ እሰጥሃለሁና እነርሱም ታላቅ ሕዝብ ይሆናሉ (አንተ የሚለውን ቃል አጠቃቀምና ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
ወደ ግብጽ
ተሰፋ የተሰጠው ለያዕቆብ ነው ነገር ግን ተስፋው የሚፈጸመው ለእስራኤል ትውልድ ሁሉ ነው አት በእርግጥ ዘርህን ከግብጽ ምድር አወጣለሁ (አንተ የሚለውን ቃል አጠቃቀምና ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደላይ መውጣት” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው::
የራሱ እጆች ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል የሚለው ሀረግ እስራኤል በሚሞትበት ጊዜ ዮሴፍ እንደሚገኝና በሞቱ ጊዜ የዮሴፍ እጆች የያዕቆብን የዐይን ሽፋሽፍቶች እንደሚዘጉ የሚናገርበት መንገድ ነው:: አት “ዮሴፍም ቢሆን በሞትህ ዕለት ይገኛል” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው ዐይኑን ከፍቶ በሚሞበት ጊዜ የዐይኑን ሽፋሽፍቶች መበሳብ መዝጋት የተለመደ ባህል ነበር:: የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ከዚያ ወጣ
“ሠረገሎች” ሁለት ወይም አራት እግር ያላቸው የጭነት ሠረገሎች ናቸው እንስሳት ተሳቢውን ይጐትቱታል:: በዘፍትረት 45:19 ሠረገሎች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
“ያገኙትን” ወይም “ያፈሩትን”
ያዕቆብ ከራሱ ጋር ይዞአቸው መጣ
ወንድ የልጅ ልጆች
ሴት የልጅ ልጆች
ይህ ጸሐፊው የሚዘረዝራቸውን የሰዎች ስሞች ያመለክታል፡፡
የእስራኤል ቤተሰብ አባላት ሄኖኀ ፌሉሶ አስሮንና ከርሚ…ይሙኤል ያሚን ኦሃድ ያኪን ጾሐርና ሳኡል …ጌድሶን ቀዓትና ሜራሪ፤ እነዚህ ሁሉ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ ይሁዳ ከሚስቱ ከሰዋ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ነበሩ:: በዘፍጥረት 38:3-5 እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
እነዚህ ይሁዳ ከምራቱ ከታማር የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ነበሩ:: በዘፍጥረት 38:29-30 እነዚህን ስሞች እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
እነዚህ ሁሉ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የልያ ሴት ልጅ ስም ነው በዘፍጥረት 30:21 ይህን ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::(ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እዚህ ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆች የያዕቆብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እና የልያ የልጅ ልጆች ያመለክታል አት በአንድነት 33 ወንዶችና ሴቶች ልጆችና የልጅ ልጆች ነበረው (ቁጥሮች ይመልከቱ)
እነዚህ ሁሉ የወንድ ሰው ስሞች ናቸው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የሴት ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የልያ ሴት አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:24 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ ከዘለፋ የተወለዱ አሥራ ስድስት ልጆች የልጅ ልጆችና የልጁ ልጅ ልጆች ናቸው (ቁጥሮች ይመልከቱ)
የሴት ስም ነው:: በዘፍጥረት 41:45 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የወንድ ስው ስም ነው:: በዘፍጥረት 41:45 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ኦን የጸሐይ አምላክ ረሐ አምልዕኮ ማዕከል ያለባትና የጸሐይ ከተማ ደግሞም ሄልዮቱ የተባለች ከተማ ነች:: በዘፍጥረት 41:45 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ሰዎች ስሞች ናቸው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ራሔል የወለደቻቸው 14 ወንዶችና የልጅ ልጆች ናቸው
እነዚህ የወንድ ሰዎች ስሞች ናቸው:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የራሔል ሴት ባሪያ ወይም አገልጋይ ስም ነው:: በዘፍጥረት 29:29 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ ባላ የወለደቻቸው 7 ልጆችና የልጅ ልጆች እንደሆኑ ያመለክታል (ቁጥሮች ይመልከቱ)
66 (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
7ዐ (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
የጌሜምን መንገድ እንዲያሳያቸው
እዚህ “ዮሴፍ” አገልጋዮቹን ወይም ባሪያዎቹን ይወክላል:: አት “የዮሴፍ አገልጋዮች ሠረገላውን አዘጋጁለትና ዮሴፍም ….ወጣ” (ምትክ ቃላት ይጠቀሙ)
“ወደ ላይ ወጣ” የሚለው ሀረግ የተጠቀመው ዮሴፍ አባቱን ሊገናኘው ወደ ከፍታማ ሥፍራ ስለተጓዘ ነው:: አት “እስራኤልን ሊገናኘው ሄዴ”
እንገቱ ላይ ተጠመጠመና ረጅም ጊዜ አለቀሰ
“አሁን ለሞት ተዘጋጅቻለሁ” ወይም “አሁን እንግዲ የሚሞተው በደስታ ነው”
እዚህ “ፊት” ሙሉ ሰው ይወክላል”” ያዕቆብ ዮሴፍን በማየቱ የተሰማውን ደስታ ይገልጻል:: አት “አንተን እንደገና በሕይወት ስላየሁህ” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እዚህ ቤት ቤተሰቡን ይወክላል:: አት “የአባቱን ቤተሰብ” ወይም “የአባቱን ቤተሰዎች” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ወደ አንድ ትልቅ ባለሥልጣን ሄዶ መናገር ወደ ላይ ወጣ የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነበር አት ለፈርዖን ለመናገር እሄዳለሁ
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል ይህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ወንድሞቼ …ያላቸውን ሁሉ… ለፈርዖን እነግረዋለሁ” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ የተጠቀመው በታሪኩ ስለተከሰተው ዋና ክስተት ለማመልከት ነው፡፡ በቋንቋዎ ይህንን የሚገልጹበት መንገድ ካለ የጠቀሙ
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል:: ይህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ምን ሥራ ታከናውናላችሁ ብሎ ቢጠይቃችሁ” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል:: ይህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “እንዲህ በሉት….እኛና አባቶቻችን ሁላችን…” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
የዮሴፍ ቤተሰቦች ለፈርዖን ሲናገሩ ራሳቸውን ባሪያዎችህ ብለው ማቅረብ አለባቸው:: ይህ ለአንድ ታላቅ ባለሥልጣን የሚነገርለት መንገድ ነው:: ይህም እንደ አንደኛ ወገን ሰው ሊገለጽ ይችላል:: አት “እኛ አገልጋዮችህ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
“ጸያፍ” የሚለው ረቂቅ ስም “የሚያስጠላ” በሚለው ቅጽል ስም ሊተረጐም ይችላል:: አት “ግብጻዊያን የከብት ጠባቂዎችን እንደ ጸያፍ ይቆጥሩ ነበር” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
1 ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው። 2 ከወንድሞቹም መካከል አምስቱን መርጦ፣ ፈርዖን ፊት አቀረባቸው። 3 ፈርዖን የዮሴፍን ወንድሞች፣ “ሥራችሁን ምንድነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ፈርዖንን፣ “እኛ አገልጋዮችህ ልክ እንደአባቶቻችን ከብት አርቢዎች ነን” አሉት። 4 ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት። 5 ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “አባትንህና ወንድሞችህ ወደ አንተ መጥተዋል፤ 6 የግብፅ ምድር እንደሆነ በእጅህ ነው፤ አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው ምድር አስፍራቸው፤ በጌሤም ይኑሩ። ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ፣ የከብቶቼ ኅላፊዎች አድርጋቸው።” 7 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ቤተ መንግሥት አግብቶ በፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብ ፈርዖንን ከመረቀው በኋላ 8 ፈርዖን፣ “ለመሆኑ ዕድሜህ ምን ያህል ነው?” ሲል ያዕቆብን ጠየቀው። 9 ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋር ሲነጻጸር አጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት። 10 ከዚያም ያዕቆብ ፈርዖንን መርቆ፣ ተሰናብቶት ወጣ። 11 ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን በግብፅ እንዲኖሩ አደረገ፤ ፈርዖን በሰጠውም ትእዛዝ መሠረት ምርጥ ከሆነው ምድር ራምሴን በርስትነት ሰጣቸው። 12 ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተ ሰዎች በልጆቻቸው ቁጥር ልክ ቀለብ እንዲሰፈርላቸው አደረገ። 13 በመላው ምድር እህል ባለመኖሩ ራቡ እየጸና ሄደ፤ ከዚህ የተነሣም ግብፅና ከነዓን በራብ እጅግ ተጎዱ፤ 14 ዮሴፍ የግብፅና የከነዓን ሰዎች እህል በመሸመት የከፈሉትን ገንዘብ ሁሉ ሰብስቦ ወደ ፈርዖን ቤተ መንግሥት አስገባ። 15 የግብፅና የከነዓን ሕዝቦችም ገንዘባቸው ባለቀ ጊዜ፣ ግብፃውያን ሁሉ ወደ ዮሴፍ ቀርበው፣ “የምንበላው እህል ስጠን፣ ገንዘባችን አልቆብናል፤ ዓይንህ እያየ እንዴት በራብ እንለቅ?” አሉት። 16 ዮሴፍም ከብቶቻችሁን አምጡ፣ ገንዘባችሁ ካለቀ በከብቶቻችህ ለውጥ እህል እሰጣችኋለሁ አለ። 17 ስለዚህ ከብቶቻቸውን ወደ ዮሴፍ አምጡ፤ እርሱም በፈረሶቻቸው፣ በበጎቻቸው፣ በፍየሎቻቸው፣ በከብቶቻቸውና በአህዮቻቸው ለውጥ እህል ሰጣቸው። በከብቶቻቸው ልዋጭ ባገኙት ምግብ በዚያ ዓመት ሳይራቡ እንዲያልፉ አደረጋቸው። 18 ያም ዓመት ካለፈ በኋላ ሕዝቡ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዮሴፍ መጥተው እንዲህ አሉት፣ “እንግዲህ ከጌታችን የምንሰውረው ምንም ነገር የለም፤ ገንዘባችን አልቆአል፤ ከብቶቻችንንም አስረክበንሃል፤ እንግዲህ ለጌታችን የምንሰጠው፣ ከሰውነታችንና ከመሬታችን በቀር ሌላ ምንም ነገር የለንም። 19 ታዲያ እያየኸን እንዴት እንለቅ? መሬታችንም ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንና መሬታችንን ውሰድና በለውጡ እህል ስጠን፤ እኛ የፈርዓን አገልጋዮች እንሆናለን፤ መሬታችንም የእርሱ ይሁን፣ እኛም እንዳንሞት መሬታችንም ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው ዘር ስጠን። 20 ስለዚህ ዮሴፍ የግብፅን ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛለት፤ ራቡም እጅግ ስለጸናባቸው ግብፃውያን ሁሉ መሬታቸውን ሸጡ፣ ምድሪቱም የፈርዖን ርስት ሆነች። 21 ዮሴፍ በግብፅ አገር ዳር እስከ ዳር ያሉት ሰዎች ሁሉ የንጉሡ አገልጋዮች እንዲሆኑ አደረገ። 22 ሆኖም ዮሴፍ የካህናቱን መሬት አልገዛም፤ ምክንያቱም ካህናቱ ከፈርዖን ቋሚ አበል ስለሚያገኙ እርሱም ከሚሰጣቸው አበል ምግብ ያገኙ ስለነበረ መሬታቸውን አልሸጡም። 23 ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፣ “እነሆ፣ ዛሬ እናንተንም መሬታችሁንም ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁና ይህን ዘር ወስዳችሁ በመሬት ላይ ዝሩ። 24 መከሩ በሚሰበሰብበት ጊዜ ግን ከአምስት እጅ አንዱን ለፈርዖን ታስገባላችሁ፣ ከአምስት እጅ አራቱን ደግሞ ለመሬታችሁ ዘር፣ እንዲሁም ለራሳችሁ፣ ለቤተ ሰቦቻችሁና ለልጆቻችሁ ምግብ ታደርጉታላችሁ።” 25 እነርሱም፣ “እንግዲህ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤ በጌታችን ፊት ሞገስ ካገኘን ለፈርዖን ገባሮች እንሆናለን” አሉት። 26 ስለዚህ ዮሴፍ የምርቱ አንድ አምስተኛ ለፈርዖን እንዲገባ የሚያዝ የመሬት ሕግ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ይሠራበታል። በፈርዖን እጅ ያልገባው መሬት የካህናቱ ብቻ ነው። 27 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን በግብፅ አገር በጌሤም ይኖሩ ነበር፣ በዚያም ሀብት ንብረት አፈሩ፤ ቁጥራቸውም እጅግ እየበዛ ይሄድ ጀመር። 28 ያዕቆብ በግብፅ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ፣ ዕድሜውም አንድ መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነበር። 29 እስራኤልም የሚሞትበት ጊዜ መቃረቡን እንደተረዳ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ እጅህን በጭኔ ላይ አኑረህ፣ በጎነትንና ታማኝነትን ልታደርግልኝ ቃል ግባልኝ፤ በምሞትበት ጊዜ በግብፅ አትቅበረኝ፤ 30 እኔም ከአባቶቼ ጋር ሳንቀላፋ ከግብፅ አውጥተህ እነርሱ በተቀበሩበት ቦት ቅበረኝ” ዮሴፍም፣ “እሺ፣ እንዳልኸኝ አደርጋለሁ” አለ። 31 ያዕቆብ፤ “በል ማልልኝ” አለው። ዮሴፍም ማለለት፣ እስራኤልም በአልጋው ራስጌ ላይ ሆኖ ጎንበስ አለ።
UDB ክስተቶች በቅደም ተከተል ሲያስቀምጥ ULB ጸሐፊው እንዳስቀመጠ ይዘረዝራል (የክስተቶች ቅደም ተከተል ይመልከቱ)
ባሪያዎችህ በጎችን እናረባለን
የዮሴፍ ወንድምች ራሳቸውን እንደ “ባሪያዎችህ” ያቀርቡታል:: ይህ ብዙ ኃላፊነት ላለው ሰው የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: ይህም እንደ አንደኛ ወገን ሰው ሊገለጽ ይችላል:: አት “እኛ ባሪያዎችህ ወይም እኛ” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
“እኛና ቅድመ አባቶቻችን ሁላችን” ወይም “እኛና አባቶቻችን ሁሉ”
በግብጽ ለጊዜው ለመኖር መጥተናል
በጎች የሚሠሩበት ሣር የለምና
ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ዋና ነገር ትኩረት ለመስጠት ነው::
“የግብጽ ምድር ለአንተ ክፍት ነው” ወይም “መላው የግብጽ ምድር በአንተ እጅ ነው”
አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው በጌሤም ምድር አኑራቸው
ይህ የሚገለጸው ከብት የማርባት ችሎታ እንዳላቸው ነው:: አት “ከመካከላቸው ከብት በማርባት ትልቅ ችሎታ ያላቸውን የሚቃውቅ ከሆነ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እዚህ “ባረከው” የሚለው ለዚያ ሰው አዎንታዊና ጠቃሚ ነገሮች እንዲሆኑለት መሻቱን ገለጸ ማለት ነው
እድሜህ ስንት ዓመት ነው?
የእንግድነቴ ዘመን የሚለው ሀረግ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመዘዋወር በምድር ላይ ምን ያህል እንደኖረ ያመለክታል:: አት “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍኩት ዘመን 13ዐ ዓመት ነው” (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ከአብርሃምና ከይስሐቅ የሕይወት ዘመን ጋር ስነጻጸር ዮሴፍ የሕይወቱ ዘመን አጭር እንደሆነ ይናገራል
ያዕቆብ በሕይወቱ ብዙ ሥቃይና ችግር ተለማምዶአል
ከዚያም ዮሴፍ አባቱንና ወንድሙን ተንከባከባቸው በሚኖሩበት ሥፍራ እንዲመሠረቱ አደረገ
ይህ የጐሼም ምድር ሌላው ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እዚህ “ልጆች” በቤተሰብ ጥገኝነት ያሉ ትናንሽ ልጆች ማለት ነው:: አት “በየቤተሰቡ በሚገኙ ትናንሽ ልጆች ቁጥር”
ይህ ቃል ዋናው ታሪክ በመሃል የሚቋረጥበትን ለማመልከት ተጠቅሞአል:: በዚህ ጸሐፊው የታሪኩን አድስ ክፍለ መናገር ይጀምራል::
ይህ በእነዚህ አገሮች የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል አት የግብጽ ሰዎችና የከነዓን ሰዎች (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ተቀጨ ወይም ደከመ
ዮሴፍም የግብጽና የከነዓን ሰዎች ገንዘባቸውን ሁሉ ከዮሴፍ እህል ለመሸመት አውለዋል
ገንዘቡን እንዲሰበስቡና እንዲያመጡ ዮሴፍ አገልጋዮቹን እንዳዘዘ ይገመታል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
እዚህ ምድር በዚያ ምድር የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት “የግብጽና የከነዓን ሕዝቦችም ገንዘባቸው ባለቀ ጊዜ” (ምትከ ቃላት አጠቃቀምና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ከግብጽ ምድር እና ከከነዓን ምድር
ሰዎች እህል ለመሸመት እንዴት እንደጓጉ ትኩረት ለመሰጠት ጥቃቄ ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል፡ አት “ገንዘባችን ስላለቀብን እባካችሁ እንድንሞት አታድርጉ!” (ሽንገላ አዘል አግናኝ ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
እህል ምግብን በአጠቃላይ ይወክላል:: አት “እህልን ሰጣቸው” ወይም “እህልን አደላቸው” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ሰዎች ወደ ዮሴፍ መጡ
ሰዎችን ዮሴፍን እንደ” ጌታችን” ያመለክታሉ ይህ ትልቅ ሥልጣን ላሌው ሰው የሚነገርለት መደበኛ መንገድ ነው:: ይህ እንደ ሁለተኛ ወገን ሰው ሊገለጽ ይችላል:: አት” ከጌታችን የምንሰውረው የለም” ወይም “ከአንተ የምንሰውረው የለም” (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ ፊት ዮሴፍን ያመለክታል:: አት “ለጌታችን የምንሰጠው የቀረ የለንም” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
እዚህ ዐይኖች የዮሴፍን እይታ ያመለክታሉ ሰዎች እህልን ለመግዛት ምንኛ እንደጓጉ ለማተኮር ጥያቄ ይጠቀማሉ ይህ ጥያቄ እንደ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት “እኛ ስንሞት ምድራችም ስትጐዳ እባክህን እንዲሁ ዝም ብለህ አትመለከተን” (ምትክ ቃላት አጠቃቀምና ሽንገላ አዘል አግናኝ ጥያቄዎችን ይጠቀሙ)
የተዘራበት ዘር ስለሌለባት ምድሪቱ የተጐዳችና ጥቅም የሌላት መሆንዋ ምድሪቱ እንደሚትሞት ተደርጐ ተነግሮአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ስለዚህ ምድሪቱ የፈርዖን ሆነች
ነገር ግን የካህናቱን መሬት አልገዛም
ድርጐ በቋሚነት አንድ ሰው ለሌላ ሰው የሚሰጠው የገንዘብ ወይም የመግብ መጠን ነው:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ፈርዖን በየዕለቱ ለካህናት የተወሰነ ምግብ ይሰጥ ነበር” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ፈርዖን ከሰጣቸው ይመገቡ ነበር
ሊትዘሩ ትችላላችሁ
አምስት እጅ የሚለው ቃል ክፍልፋይ ነው፡፡ አት “በመከር ጊዜ እህላችሁን በአምስት መደብ ትከፍላላችሁ አንዱን መደብ እንደክፍያ ለፈርዖን ትሰጡታላችሁ እናም አራቱ መደቦች ለእናንተ ይሆናሉ” (ክፍልፋዮችን ይመልከቱ) ለቤተሰቦቻችሁና ለልጆቻችሁ ምግብ ታደርጉታላችሁ (የተደበቁትን ስለመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ሞገስ ማግኘት የሚለው ሀረግ በአንድ ሰው ተቀባይነትን ማግኘት የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: ደግሞም ዐይኖች ማየትንና ማየት ሃሳብንና በየናን ይወክላል:: አት “በእኛ ከተደሰትክ” (ፈሊጣዊና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“በግብጸ ምድር ላይ” ወይም “በመላው የግብጽ ምድር”
ጸሐፊው እስከጻፈበት ጊዜ ድረስ
በዘፍጥረት 47:24 አንድ እምስተኛ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
በዙ የሚለው ቃል እንዴት እንደአፈሩ ይገልጻል እነርሱም ብዙ ልጆች ነበሩአቸው (ድርብ ቃላት ይመልከቱ)
እዚህ ፍሬያማ መበልጸግ ወይም ብዙ ልጆች መኖር ማለት ነው
17 ዓመታት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ያዕቆብ የኖረው 147 ዓመት ነው (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ይህ ጊዜ እንደሚጓዝና አንድ ቦታ እንደሚመጣ ይናገራል:: አት “እስራኤል የሚሞትበት ጊዜ እንደደረሰ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ ዓይኖች የማየት ምትክ ቃል ነው እናም ማየት ሃሳብን ወይም አመለካከትን ይወክላል:: አት “በአንተ ፊት ሞገስ ካገኘሁ ወይም ካስደሰትኩህ” (ምትክ ቃላትና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ለሚቀጥለው ጠቃሚ ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው
አንድ ሰው በአንድ ሰው ተቀባይነቱን ማረጋገጥ ማለት ነው ፈሊጣሊ አነጋገር ይመልከቱ
ለጠንቃቃ ቃል መግባት የሚደረግ ምልክት ነው በዘፍጥረት 24:2 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
በጐነት እና ታማኝነት የተባሉ ረቂቅ ስሞች እንደ ቅጽል ስሞች ሊተረጐሙ ይችላሉ አት በበጐነትና በታማኝነት አድርግልኝ ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ
እባክህን የሚለው ለዚህ ጥያቄ እጽንዖት ይሰጣል
ማንቀላፋት መሞትን ለዘብ ባለ ቃል የሚገልጽ ነውፀፀ አት “በሚሞትበትና ከዚህ ቀደም የሞቱ ቤተሰቦቼን በሚገናኝበት ጊዜ” (ንኀብነት ወይም ለዘብ ባለና በተዘዋዋሪ መንገድ አንድን ነገር የመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
“ተስፋ ስጠኝ” ወይም “ማልልኝ”
“ተስፋ ሰጠው” ወይም “ቃል ገባለት”
1 ከጥቂት ጊዜ በኋላም፣ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ስለተነገረው ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ። 2 ለያዕቆብ፣ “ልጅህ ዮሴፍ ወደ አንተ መጥቶአል” ተብሎ በተነገረው ጊዜ፣ እስራኤል ተበረታትቶ አልጋው ላይ ተቀመጠ። 3 ያዕቆብም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር ሎዛ በምትባል ቦታ ተገለጠልኝ፤ ባረከኝም፤ 4 እንዲህም አለኝ፤ ‘ፍሬያማ አደርግሃለሁ፣ ዝርያዎችህም ብዙ ሕዝቦች ይሆናሉ፣ ይህችንም ምድር ለዝርያዎችህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ’ አለኝ።” 5 ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ የወለድሃቸው ሁለቱ ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ሆነው ይቆጠራሉ፤ ሮቤልና ስምዖን ልጆቼ እንደሆኑ ሁሉ፣ ኤፍሬምና ምናሴም ልጆቼ ይሆናሉ። 6 ከእነርሱ በኋላ የሚወለዱልህ ልጆች ግን፣ የአንተ ይሁኑ፤ በርስት ድልድላችው ግን በወንድሞቻቸው ስም ይቆጠራሉ። 7 ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ስመለስ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረኝ፤ እናትህ ራሔል በከነዓን ምድር ሞታብኝ አዘንሁ። እኔም ወደ ኤፍራታ ማለት ወደ ቤተ ልሔም በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።” 8 እስራኤልም የዮሴፍን ልጆች ባየ ጊዜ፣ “እነዚህ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤ 9 ዮሴፍም፣ “እነዚህ እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ብሎ መለሰለት፤ እስራኤልም “አቅርባቸውና ልመርቃቸው” አለ። 10 በዚህ ጊዜ እስራኤል ዓይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ አቀፋቸው። 11 እስራኤልም ዮሴፍን፣ “ዓይንህን እንደገና ዐያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ልጆችህን ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው። 12 ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጉልበት ፈቀቅ በማድረግ አጎንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ። 13 ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተቀኝ ከእስራኤል በስተግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተግራ ከእስራኤል በስተቀኝ በኩል አቀረባቸው። 14 እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፣ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኩሩ በምናሴ ላይ አኖረ። 15 ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ መንገዱን በመከተል ያገለገሉትና ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስ በዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ፣ 16 ከጉዳትም ሁሉ የታደገኝ ምልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይስሐቅ ስም ይጠሩ፣ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ። 17 ዮሴፍ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ቅር ተሰኘ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንስቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤ 18 ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፣ እንዲህ አይደለም በኩሩ ይህኛው ስለሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው። 19 አባቱ ግን፣ “ዐውቃለሁ፣ ልጄ ዐውቃለሁ፣ እርሱም እኮ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ፣ ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፤ ዘሮቹም ታላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” ብሎ እምቢ አለው። 20 በዚያን ዕለት ባረካቸው፣ እንዲህም አላቸው፤ “እስራኤላውያን በሚመርቁበት ጊዜ የእናንተን ስም በማስታወስ፤ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ’ ይላሉ” በዚህ ሁኔታም ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው። 21 ከዚህ በኋላ እስራኤል ዮሴፍን እንዲህ አለው፣ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ወደ አባቶቻችሁም ምድር መልሶ ያገባችኋል። 22 እነሆ በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራውያን እጅ የወሰድኋትን ምድር ከወንድሞችህ ድርሻ አብልጬ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።”
ይህ ሀረግ የታሪኩ አድስ ክፍል መጀመሩን ለማመልከቱ ተጠቅሞአል (አድስ ክስተት ስለማስታወቅ ይመልከቱ)
አደ ሰው ለዮሴፍ ነገረው
ስማ ፤አባትህ፤ እዚህ “እየው” የሚለው ቃል የዮሴፍን ትኩረት ለማግኘት ተጠቅሞአል::
ስለዚህ ዮሴፍ ይዞ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት “አንድ ሰው ለያዕቆብ በነገረው ጊዜ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ልጅህ ዮሴፍ መጥቶአል
እዚህ እስራኤል ተነሥቶ በአልጋው ሊቀመጥ የታገለውን አንድ ሰው አንድን ዕቃ እንደሚሰበስብ ብርታትን እንደሰበሰበ አድርጐ ጸሐፊው ይናገራል:: አት “በአልጋው ተነሥቶ ሊቀመጥ እስራኤል ከፍተኛ ጥረት አድርጐአል ወይም በአልጋው ተነሥቶ ሊቀመጥ እስራኤል ታግሎአል” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይጠቀሙ)
ይህ የከተማ ስም ነው:: በዘፍጥረት 28:19 የዚህን ከተማ ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ በሌላ ሀረግ እንደሚጀምር እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: “በከነዓን ምድር ባረከኝ እናም እንዲህ አለኝ”
እግዚአብሔር መደበኛ በረከትን በአንድ ሰው ላይ እንዳደረገ ያመለክታል
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል አት ፍሬያማ እንደሚያደርገኝና እንደሚያበዛች ተናግሮኛል:: እናም ለብዙ ሕዝብም ጉባዔ እንደሚያደርገኝና ይህችንም ምድር ከእኔ በኋላ ለዘላለም ርስት አድርጐ ለዘሬ እንደሚሰጠኝ ነግሮኛል (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
እዚህ ቦታ እነሆ የተጠቀመው እግዚአብሔር ሊናገር ስላለው ነገር ያዕቆብ ትኩረት እንዲሰጥ ለማንቃት ነው
አበዛሃለሁ የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር እንዴት ያዕቆብን ፍሬያማ እንደሚያደርገው ይገልጻል:: አት “ብዙ ዘር/ትውልድ እሰጥሃለሁ” (ድርብ ቃላትና ፈሊጣዊ አነጋገር ይጠቀሙ)
እዚህ አንተ ያዕቆብን ቢያመለክትም የያዕቆብን ትውልድ ይወክላል አት “ትውልድህን ብዙ ሕዝቦች አደርጋለሁ” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ቋሚ ርስት
ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ዋና ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ተጠቅሞአል
እንደ ዮሴፍ ወንድሞች ኤፍሬምና ሚናሴ ከምድሪቱ ክፍል የየራሳቸውን ርስት ይቀበላሉ
ተገቢ ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው 1 እንደ ሚናሴና ኤፍሬም ነገዶች ሌሎች የዮሴፍ ልጆች ምድሪቱን ይወርሳሉ 2 ዮሴፍ ከኤፍሬምና ሚናሴ የተለየ ምድር የሰጠዋል እናም የዮሴፍ ሌሎች ልጆች ያን ምድር ይወርሳሉ አት በርስት ድልደላቸው በወንድሞቻቸው ስም ይቆጠራሉ
ይህ የቤተልሔም ከተማ ስም ነው:: በዘፍጥረት 35:16 የዚህን ከተማ ስም እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ጸሐፊው የዳራ መረጃ ይሰጣል (የዳራ መረጃ ይመልከቱ)
እነዚህ የማን ወንዶች ልጆች ናቸው?
አባት ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን እብዛኛውን ጊዜ መደበኛ በረከት ይባርካል
በዚህን ጊዜ የሚለው ቃል የተጠቀመው ታሪኩ ወደ እስራኤል ዳራ መረጃ እንደተቀየረ ለማመልከት ነው (ዳራ መረጃ ይመልከቱ)
እስራኤል ሳማቸው
እዚህ “ፊት” ሙሉ ሰው ይወክላል:: አት እንደገና አይሃለሁ (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን አንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ዮሴፍ ልጆቹን በእስራኤል ጭን ወይም ጉልበት ላይ ማስቀመጡ እስራኤል እንደራሱ ልጆች እንደተቀበላው የሚገልጽ ምልክት ነው:: ይህም ለልጆች የወራሽነት መብት ከያዕቆብ ያስገኛል (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ዮሴፍ ለአባቱ ክብርን ለመስጠት ወደ ምድር አጐንበሶ ሰገደ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
እስራኤል ቀኝ እጁን በሚናሴ ላይ እንዲያደርግ ዮሴፍ ልጆቹን ያስቀምጣቸዋል ሚናሴ ታላቅ ወንድም ነው እናም ቀኝ እጅ ትልቅ በረከት የመቀበል ምልክት ነው (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማኖር እርሱ ትልቅ በረከት እንዲቀበል ምልክት ነበር (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ዮሴፍ ደግሞ ኤፍሬምንና ሚናሴን ይወክላል:: ዮሴፍ አባት ስለሆነ እርሱ ብቻውን ተጠቅሶአል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እግዚአብሔርን ማገልገል በእግዚአብሔር ፊት እንደመሄድ ተደርጐ ተነግሮአል አት አያቴ አብርሃምና አባቴ ይስሐቅ ያገለገሉት እግዚአብሔር (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እረኛ በጐቹን እንደምንከባከብ እግዚአብሔር እስራኤልን ተንከባክቦታል አት እረኛ እንስሳትን እንደሚንከባከብ የተንከባከበኝ (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ተገቢ ትርጉሞች አት እግዚአብሔር ያዕቆብን ለመጠበቅ የላከውን መልአክ ያመለክታል 2 ይህ እግዚአብሔር ያዕቆብን ለመጠበቅ በመልአክ መልክ የተገለጸውን ያመለክታል
አዳነኝ
እዚህ ስም ሰውን ይወክላል ስሜ በእነርሱ ይጠራ የሚለው ሀረግ አንድ ሰው ከሌላ ሰው የተነሣ እንዲታወስ የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ከኤፍሬምና ሚናሴ የተነሣ ሰዎች አብርሃም ይስሐቅንና እኔን ያስታውሱ” (ምትክ ቃል : ፈሊጣዊ አነጋገርና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ እነርሱ ኤፍሬምንና ሚናሴን ቢያመለክትም የእነርሱ ትውልድንም ይወክላል:: አት “በምድር ሁሉ ላይ የሚኖር ብዙ ትውልድ ይኑራቸው” (ምትክ ቃል እጠቃቀም ይመልከቱ)
ቀኝ እጅ በኩር ወንድ ልጅ የሚያገኘው ትልቅ በረከት ምልከት ነበር (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
እዚህ እርሱ ሚናሴን ቢያመለክትም የእርሱን ትውልድ ይወክላል አት ታላቅ ልጅህ ብዙ ትውልድ ይኖረዋል እናም ታላቅ ሕዝብ ይሆናል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
በዚያ ዕለት እንዲህ ብሎ
የእስራኤልም ሰዎች ሌሎችን በሚባርኩበት ጊዜ በስማችሁ ይባርካሉ
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስን ይዞአል ይህም እንደ ተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “በእናንተ ስም እግዚአብሔር ሌሎችን ሰዎች እንደ ኤፍሬምና እንደ ሚናሴ እንዲያደርግ ይጠይቁታል” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
እስራኤል ኤፍሬምን አስቀድሞ መጥራቱ ኤፍሬም ከሚናሴ ታላቅ እንደሚሆን የሚገልጽ ነው
ለኤፍሬም ትልቁን በረከት መስጠትና ኤፍሬም ከሚናሴ የተሻለ አድርጐ መውሰድ እስራኤል በአካል ኤፍሬምን ከሚናሴ በፊት እንዳስቀመጠው ተደርጐ ተገልጾአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ “እናንተ” “የእናንተ” ብዙና የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ ያመለክታል (“እናንተ” አጠቃቀም ይመልከቱ)
እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደሚረዳና እንደሚባረካቸው የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው አት እግዚአብሔር ይረዳችኋል ወይም እግዚአብሔር ይባርካችኋል (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ወደ ዘራችሁም ወይም ትውልዳችሁም ምድር
ተገቢ ትርጉሞች 1 ከወንድሞቹ ይበልጥ ብዙ ክብርና ሥልጣን ለዮሴፍ መሰጠቱ እርሱ በአካል ከሌሎች የበላይ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “ለአንተ ከሌሎች ለሚትበልጠው የተራራውን ዐምባ ሰጠሁህ” ወይም 2)ያዕቆብ ለዮሴፍ ወንድሞች ከሚሰጠው መሬት በላይ ለዮሴፍ እንደሚሰጠው ይገልጻል:: አት “ለአንተ ለወንድሞችህ ከሰጠሁት በላይ ridge ሰጠሁህ የተራራውን ዐምባ ሰጠሁህ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ አንተ በነጠላ የተገለጸና ዮሴፍን ያመለክታል (አንተ አጠቃቀም ይመልከቱ)
እዚህ ሰይፍ እና ቀስት በጦርነት መዋጋትን ያመለክታሉ፡፡ አት “የተዋጋሁትና ከአሞራዊያን እጅ የወሰድሁት ምድር” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
1 ያዕቆብ ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአንድነት ተሰብሰቡና ወደፊት የሚገጥማችሁን ነገር ልንገራችሁ፣ 2 እናንተ የያዕቆብ ልጆች፣ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፣ አባታችሁ እስራኤል የሚነግራችሁንም አድምጡ። 3 ሮቤል፣ ኃይልና የጎልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ የወለድሁህ የበኩር ልጄ ነህ። ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኃይል የምትበልጥ አንተ ነህ። 4 ይሁን እንጂ እንደ ውሃ የምትዋልል ስለሆንህ የበላይ አለቅነት ለአንተ አይገባም፣ ምክያንቱም የአባትህን መኝታ ደፍረሃል ምንጣፌንም አርክሰሃል። 5 “ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው፣ ዓመፅ ለመፈጸም የጦር መሣሪያዎቻቸውን ያነሳሉ። 6 ወደ ሸንጎአቸው አልግባ፣ ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፣ በቁጣ ተነሣስተው ወንዶችን ገድለዋል፣ የበሬዎችንም ቋንጃ እንደፈለጉ ቆራርጠዋል። 7 እጅግ አስፈሪ የሆነ ቁጣቸው፣ ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤ በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፣ በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ። 8 ይሁዳ ወንድሞችህ ያመሰግኑሃል፣ እጅህም የጠላቶችህን አንገት አንቆ ይይዛል፣ የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይስግዱልሃል። 9 ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፣ ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣ እንደ አንበሳ ያደፍጣል በምድርም ላይ ይተኛል፤ እንደ እንስት እንበሳም ያደባል፣ ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል? 10 በትረ መንግስሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤ የገዥነት ምርኩዝም ከእግሮቹ መካከል፣ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለት ‘ሴሎ’ እስኪመጣ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙለታል። 11 አህያውን በወይን ግንድ፣ ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፣ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጎናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል። 12 ዓይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣ ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ። 13 ዛብሎን በባሕር ዳርቻ ይኖራል፣ የመርከቦቹ መጠጊያም ይሆናል፣ ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል። 14 ይሳኮር፣ አጥንተ ብርቱ አህያ በጭነት መካከል የሚተኛ፣ ማረፊያ ቦታው መልካም፣ 15 ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ ትከሻውን ለሸክም ዝቅ ያደርጋል ከባድ የጉልበት ሥራም ይሠራል። 16 ዳን ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል። 17 ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣ የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤ ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣ የፈረሱን ሰኮና ይነክሳል። 18 እግዚአብሔር ሆይ፣ ማዳንህን እጠባበቃለሁ። 19 ጋድን ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፣ እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል። 20 አሴር ማዕደ ሰፊ ይሆናል፤ ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል። 21 ነጻ እንደተለቀቀች ሚዳቋ ነው፣ የሚያማምሩ ግልገሎች ይኖሩታል። 22 ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣ በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው። ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ። 23 ቀስተኞች በብርቱ ያጠቁታል፤ በቀስታቸውም እየነደፉ ያሳድዱታል፤ 24 ነገር ግን በያዕቆብ ኃያል አምላክ ክንድ፣ እረኛም በሆነው በእስራኤል አለት ቀስቱ ጸና ጠንካራ ክንዱም ቀልጣፋ ሆነ። 25 አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣ በሚባርክህ ሁሉን በሚችል አምላክ፣ ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣ ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣ ከማኅፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል። 26 ከጥንት ተራሮች በረከት፣ ከዘላለም ኮረብቶች ምርቃት ይልቅ፣ የአባትይ በረከት ይበልጣል፤ ይህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ። 27 ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው፤ ያደነውን ማለዳ ይበላል፤ የማረከውን ማታ ያከፋፍላል። 28 እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው። 29 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እኔ የምሞትበትና ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በኬጢያዊው በኤፍሮን እርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤ 30 ይህንን በከነዓን ምድር በመምሬ አጠገብ በማክፌል እርሻ ውስጥ ያለውን ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ የገዛው አብርሃም ነው። 31 በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤ እኔም ልያን የቀበርኋት እዚያው ነው፤ 32 እርሻውና ዋሻው የተገዙት ከኬጢያውያን ላይ ነው።” 33 ያዕቆብ እነዚህን ቃላት ለልጆቹ ተናግሮ እንዳበቃ እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ የመጨረሻ ትንፋሹን ተንፍሶ ሞተ፣ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።
ይህ ያዕቆብ ልጆቹን የሚባርከውን መጨረሻውን በረከት የጀምራል:: ይህም እስከ ዘፍጥረት 49:27 ይቀጥላል የያዕቆብ ምርቃቶች በግጥም መልክ ተጽፈዋል (ሥነ ግጥሞችን ይመልከቱ)
ሁለቱ ዐረፍተ ነገሮች ትኩረት ለመስጠት ተመሣሣይ ሃሳብ ይናገራሉ አት ወደ አባታችሁ ኑና በጥንቃቄ አድምጡ (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)
ያዕቆብ ራሱን እንደሶስተኛ ወገን ሰው ያቀርባል እንደአንደኛ ወገን ሰው ሊገለጽ ይችላል አት ልጆች ሆይ እኔን አባታችሁን ስሙ (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አጠቃቀም ይመልከቱ)
የበኩር ልጄ ኃይሌ የጉብዝናዬ መጀመሪያ የሚሉ ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ኃይል እና ጉብዝና የሚሉ ቃሎች የያዕቆብ ልጅ የመውለድ አቅሙን ያመለክታሉ በኩር እና መጀመሪያ የሚሉ ቃላት ሮቤል በኩር ልጁ እንደሆነ ይገልጻሉ (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)
ይህ እንደ አድስ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል አት በክብርና በኃይል የመጀመሪያ ትሆናለህ ወይም በክብርና በኃይል ማንኛውንም ሰው ትበልጣለህ
ያዕቆብ ሮቤል ቁጣውን እንደማይችል ለማተኮር በከባድ ማዕበል እንደሚዋልል ውሃ አድርጐ ያቀርበዋልና እርሱ የተረጋጋ አይደለም (ተመሣሣይ አባባል ይመልከቱ)
በወንድሞችህ መካከል የመጀመሪያ ወይም አለቃ አትሆንም
እዚህ መኝታና አልጋ የያዕቆብን ቁባት ባላን ያመለክታሉ ያዕቆብ ሮቤል ከባላ ጋር የተኛበትን ያመለክታል (ዘፍጥረት 35:22 ይመልከቱ) አት “ወደ አልጋዬ ስለወጣህና በቁባቴ ከባላ ጋር ስለተኛህ አዋርደህኛልና” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)
ይህ በትውልድ ወንድሞች መሆናቸውን አይገልጽም ያዕቆብ የሴኬም ሰዎችን ለመግደል አብረው መሥራታቸውን ለማተኮር ነው፡፡
ሰዎችን ለመጉዳትና ለመግደል ሰይፎቻቸውን ይጠቀማሉ
ያዕቆብ ራሱን ለመግለጽ ነፍሴ እና ልቤ የሚሉ ቃሎችን ይጠቀማልና ክፋን ለማድረግ ከሚያቅዱት ጋር ባለመተባበሩ ሌሎች ሰዎችና እግዚአብሔርም ደግሞ እጅግ እንዳከበሩት ይናገራል (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ጉባዔያቸው ውስጥ አልገኝ እነዚህ ሁለቱ ሀረጐች በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ያዕቆብ ሁለቱን በማገናኘት በክፉ እቅዳቸው እንደማይሳተፍ አበክሮ ይገልጻል አት ማንኛውንም እቅድ ለማዘጋጀት ከእነርሱ ጋር አልተባበርም (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)
ስምዖንና ለዊ ለዕይታ ብለው ቤሬዎችን አስነክሰዋል
ይህ የእንስሳትን ቋንጃ በመቁረጥ እንዳይራመዱ ማድረግ ነው
እግዚአብሔር ስምዖንና ሌዊን የሚረግመው እግዚአብሔር ቁጣቸውንና ንዴታቸውን እንደሚረግም ተደርጐ የገልጾአል:: (ዘይቤያዊ አነጋገርና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አብዛኛውን ጊዜ ነብይ ትንቢትን ሲናገር የሚናገረው ቃል እግዚአብሔር እንደሚናገር ይቆጠራል:: ይህም የሚናገረው ነበዩና እግዚአብሔር እንዴት እንደተቆራኙ ነው::
እረግማለሁ የሚለው ቃል የታወቀ ነው አት ንዴታቸው ጭከናን የተሞላ ስለሆነ እረግማለሁ (የተደበቁትን የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
“እኔ” እግዚአብሔርን ያመለክታል:: “እነርሱ” ስምዖንንና ለዊን ቢሆንም ምትክ ቃል ስለሆነ ለትውልዳቸውም ይሆናል:: “ያዕቆብ”ና “እስራኤል” ተወራራሽ ስሞችና የእስራእል ሕዝብ የሚተኩ ናቸው:: አት ትውልዳቸውን እበትናለሁ በእስራኤልም ሰዎች መካከል አሠራጫለሁ (ምትክ ቃላትና ተመሣሣይ ተነጻጻሪ አባባል ይመልከቱ)
ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ ይመልከቱ)
ሁለተኛው ዐረፍተ ነገር ለአንደኛው ምክንያት ነው ይህ “ስለ” ወይም “ምክንያቱም/የተነሣ” አገናኝ ቃላትን በመጠቀም ግልጽ ሊሆን ይችላል:: አት “ስለ እጅህ ያመሰግኑሃል” ወይም “ከእጅህ የተነሣ ያመሠግኑሃል” (አገናኝ ቃላት ይመልከቱ)
“ጠላቶችህን ታሸንፋለህ” የሚል አባባል ነው:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ለአንድ ሰው እጅ መንሣት ወይም አክብሮት በትህትና ለመግለጽ ጐንበስ ማለትን ይገልጻል (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
የአንበባ ደቦል እንደሆነ ስለ ይሁዳ ያዕቆብ ይናገራል:: ያዕቆብ የይሁዳን ጥንካሬ በአትኩሮት ይገልጻል:: አት “ይሁዳ እንደ አንበሳ ደቦል ነው” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“አንተ ልጄ ከአደንህ ተመለስህ”
ያዕቆብ ይሁዳን ከእንስት አንበሳ ጋር ያነጻጽራል አት እንስት አንበሳ በአደን ቀዳማይና ቡድንዋን የሚትከላከል ነች (ተመሣሣይ አባባል ይመልከቱ)
ያዕቆብ ይሁዳ ለሌሎች ሰዎች ምንኛ አስፈሪ እንደሆነ ትኩረት ለመሰጠቅ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት “ማንም ሊቀሰቅሰው አይችልም” (አግናኝ ጥያቄ ይመልከቱ)
በትርና ዘንግ ንጉሥ የሚይዛቸው ያገጡ ረጃጅም በትሮች ናቸው የሥልጣን አገዛዝ የሚተኩ ምልክቶች ናቸው እናም ይሁዳ የእርሱን ዘር ይወክላል:: አት “የአገዛዝ ሥልጣን ሁልጊዜም ለይሁዳ ዘር ይሆናል” (ምትክ ቃላትና ተመሣሣይ ተነጻጻሪ አባባል ይመልከቱ)
ተገቢ ትርጉሞች 1 ሰሎ ማለት ክብር ወይም አድናቆት ማለት ነው አት ሕዝቦች እስኪታዘዙለትና እስክያከብሩት ድረስ ወይም 2 ሰሎ የሴሎ ከተማን ይወክላል አት ገዥ ወደ ሰሎ እስኪመጣና ሕዝቦች እስኪታዘዙለት ድረስ ብዙ ሰዎች እንደሚናገሩት ይህ ትንቢት ከዳዊት ዘር ስለሚመጣው መስህ ነው ዳዊት ከይሁዳ ዘር ነውና
ሕዝቦች ሰዎችን ያመለክታሉ አት ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙለታል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ሁለቱም አረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው የወይኑ ፍሬ ብዙ ሰለሆነ አህያው ፍሬዎችን ቢበላ ጌታው እንደማይገደው ተደረጐ ተገልጾአል:: (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የእርሱ ወይም እርሱ በተጠቀሱባቸው ሁሉ ተገቢ ትርጉማቸው 1 የይሁዳን ዘር ያመለክታሉ:: “የእነርሱ” “እነርሱ” ወይም 2) እነርሱ በዘፍጥረት 49:1ዐ ምናልባት ሚናሴን የሚያመለክተውን ገዥ ያመለክታሉ::
ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው ይህም በጭማቂዎቻቸው ልብሶቻቸውን ማጠብ እንኳ የሚያስችል ብዙ ወይን ፍሬዎች ይኖራሉ ማለት ነው (ተመሣሣይ ተነጻጻሪ እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
አብዛኛውን ጊዜ ወደፊት የሚፈጸሙ ትንብቶች እንደተፈጸመ ተደርጐ ይገለጻል ይህ በአትኩሮት የሚናገረው ክስተቱ በእርግጥ እንደሚፈጸም ነው አት እነርሱ ያጥባሉ ወይም እርሱ ያጥባል (ወደፊት አመላካች ኃላፊ ክስተት ይመልከቱ)
የወይን ጭማቂን እንደ ወይን ደም ያቀርባል ይህም ጭማቂው ምንኛ ቀይ ቀለም እንዳለው ይገልጻል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ እንደ ቀይ ቀለም ወይን የሰውን ዐይን ቀለም ቅላት ያመለክታል:: ተገቡ አማራጭ ትርጉሞች እነሆ አት 1)ጥቁር ቀለም ያላቸው ዐይኖች ጤናማ ዐይኖች ናቸው ወይም 2) ብዙ የወይን ጠጅ ከመጠጣት የተነሣ የሰዎች ዐይኖች ይቀላሉ (ተመሣሣይ አባባል እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ የሰውን ነጭ ጥርስ ከወተት ንጣት ጋር ያነጻጽራል፡፡ ይህም ወተትን የሚጠጡበት ብዙ የሚታለቡ ላሞች እንደሚኖሩ ነው (ተመሣሣይ አባባል እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ የዛብሎንን ነገድ ያመለክታል:: የዛብሎት ነገድ ወይም ትውልድ በበሕር ዳር ይኖራል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
እዚህ እርሱ የዛብሎን ሰዎች የሚወርሱት ወይም የሚገነቡት የባሕር ዳር ከተሞችን ይወክላል እነዚህ የወደብ ከተሞች ለመረከበኞች መጠለያ ይሆናሉ (ምትክ ቃል አጠቃቀም ይመልከቱ)
በባህር ዳር ያለ መሬትና ለመርከቦች መቆሚያ ደኀንነት ያለው ቦታ ማለት ነው
ያዕቆብ ስለይሳኮርና ነገድ ወይም ትውልድ ሲናገር እንደ አህያ ይቆጥራቸዋል ይህም እጅግ የሚሠሩ እንደሚሆኑ በአትኩሮት ይገልጻል የይሳኮር ትውልድ አንደ አጥንተ ብርቱ አህያ ነው (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አብዛኛውን ጊዜ ወደፊት የሚፈጸሙ ትንቢቶች እንደተፈጸመ ተደርጐ ይገለጻል ይህ በአትኩሮት የሚናገረው ክስተቱ በእርግጥ እንደሚፈጸም ነው ይህም በወደፊት ጊዜ ሊገለጽ ይችላል አት “ይሳኮር… ይሆናል” ወይም “የይሳኮር ትውልድ… ይሆናል” (ወደፊት አመላካች ኃላፊ ክስተት ይመልከቱ)
እዚህ ይሳኮር ለነገዱ ምትክ ሆኖ የሚቆም ስም ነው አት “የይሳኮር ትውልዶች… ያያሉ …ይሆናሉ” (ምትክ ቃላት ይጠቀሙ)
ተገቢ ትርጉሞች 1 በጭነት መካከል ይተኛል ወይም 2 በሁለት በጐች አጥር መካከል ይተኛል ደግሞም በሌላ መንገድ ያዕቆብ ስለይሳኮር ልጆች እጅግ እንደሚሠሩና ከዚያም ለእረፍት እንደሚተኙ ይናገራል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
መልካም እረፍት የሚያገኙበት ቦታና የለማች ምድር
ትከሻውን ለሽክም ያመቻቻል ማለት ሸክምን በመሸከም እጅግ ይሠራል ማለት ነው (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ለሌሎች እንደባሪያ ያገለግላል
እዚህ ዳን ነገዱን ይወክላል የዳን ልጆች በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ
ተገቢ ትርጉሞች የራሱ ሕዝብ፤ 1) በዳን ሕዝብ 2) በእስራኤል ሕዝብ
ያዕቆብ ስለዳንና የእርሱ ትውልድ እንደ እባብ አድርጐ ይናገራቸዋል እባብ ምንም ትንሽ ቢሆን መንገደኛውን ከፈረስ ላይ ማውረድ ይችላል እንዲሁ ዳን ትንሽ ነገድ ሲሆን በጠላቶቹ ላይ አደገኛ ነው አት የዳን ልጆች በመንገድ ዳር እንዳለ እባብ ናቸው (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ረቂቅ ስም “ማዳን” እንደ “መዳን” ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት “እግዚአብሔር ሆይ እንዲታድነኝ እጠባብቃለሁ”
“እኔ” ያዕቆብን ያመለክታል
ጋድ ትውልዱን ይወክላል:: አት “የጋድ ልጆች ..ይጠቃሉ ነገር ግን እነርሱ” (ምትክ ቃል ይጠቀሙ)
አሴር የአሴር ልጆችን ይወክላል:: እት “የአሴር ልጆች ማእደ ሰፊ… እናም እነርሱ” ምትክ ቃል ይጠቀሙ
ንፍታሌም የንፍታሌምን ትውልድ ይወክላል:: አት “የንፍታሌም ልጆች.. እነርሱ… ይሆናሉ”
ከዳን ልጆች በመሸሽ በተራራማው የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል
እዚህ የበረከተ የሚለው ምግቡ ጣፋጭ ማለት ነው ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ
ያዕቆብ ስለንፍታሌም ልጆች ለመሮጥ እንደተለቀቀች እንደ እንስት ሚዳቋ እንደሆነ ይናገራል:: ይህም እነርሱ ፈጣን መልእክተኞች እንደሆኑ ነው:: አት “የንፍታሌም ዘሮች እንደተለቀቀች ሚዳቋ ይሆናሉ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ግልገሎች ትናንሽ የሚዳቋ ግልገሎች ናቸው የዕብራይስጡ ቃል ትርጉም ግልጽ አይደለም አንዳንድ ትርጉሞች መልካም ቃል ይሰጣል ወይም መልካም ነገር ይናገራል የሚለውን ተጠቅመዋል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ዮሴፍ ትውልዱን/ዘሩን ይወክላል ያዕቆብ እነርሱን ብዙ ፍሬ እንደሚያፈራ የዛፍ ቅርንጫፍ አድርጐ ይናገራል:: አት “የዮሴፍ ዘር ፍሬያማ የዛፍ ቅርንጫፍ ነው”
የዛፍ ዋና ቅርንጫፍ
ቅርንጫፎች አድገው ቅጥርን ማልበሳቸው እነዚያ በቅጥር ላይ እንደሚወጡ ተደርጐ ተገልጾአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ያዕቆብ ዮሴፍንና ዘሩን መባረክ ይቀጥላል
ቀስቱን የያዘው ሰው መጽናቱ ቀስቱ ራሱ እንደጸና ተደርጐ ተግልጾአል ወደ ጠላቱ በሚያልምበት ጊዜ ቀስቱ እንደሚጸና ይገልጻል አት ወደ ጠላቱ በሚያልምበት ጊዜ ቀስቱን አጽንቶ ይይዛል (ምትክ ቃላት አጠቃቀም እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እዚህ “እርሱ” ዘሩን የሚወክለውን ዮሴፍን ነው አት “ቀስቶቻቸውና እጆቻቸው” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ቀስትን መያዘ የለመዱ እጆች ስለሆኑ ሙሉ ሰው እንደ እጆች ተገልጾአል:: (ክፍልን እንደሙሉና ሙሉን እንደክፍል የመግልጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
እጆች የእግዚአብሔርን ኃይል ይገልጻሉ:: አት “የሁሉን ቻይ አምላክ ኃይል” (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
እዚህ ስም ሙሉ ሰው ይወክላል አት ከእረኛው የተነሣ (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ያዕቆብ እግዚአብሔር እረኛ እንደሆነ ይናገራል አት ይህም እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚመራና እንደሚጠብቅ ይናገራል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ያዕቆብ እግዚአብሔር ሰዎች የሚወጡበትና ከጠላቶቻቸው የምድኑበት አለት እንደሆነ ይናገራል ይህ የሚያጐላው እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚጠብቅ ነው (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ያዕቆብ ዮሴፍንና ዘሩን መባረክ ይቀጥላል (ዘፍጥረት 49:22-23 ይመልከቱ)
እዚህ “አንተ” ዘሩን የሚወክለውን ዮሴፍን ያመለክታል አት “የአንተን ዘር በሚረዳ ….በሚባርክህ” (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
ሰማይ ተክልን ወይም ሰብልን የሚያሳድገው ዝናብን ይወክላል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ጥልቅ ለወንዞችና ለኩሬዎች የሚሆን ውሃ የሚወጣበትን ይወክላል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
እዚህ ጡቶችና ማህጸን እናቶች የመውለድና ጡት የማጥባት አቅም ያመለክታል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ያዕቆብ ዮሴፍንና ልጆቹን መባረክ ይቀጥላል፡፡
የመሠረታዊው ቋንቋ ትርጉም ግልጽ አይደለም:: አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በጥንት ተራሮች ፈንታ ጥንት አባቶች ይጠቀማሉ::
እዚህ “እነርሱ” የአባቱ በረከቶች ናቸው::
ያዕቆብ እነዚህ በረከቶች ልጆቹ እጅግ በበለጡት ላይ እንዲሆን ይሻል:: አት “እጅግ በበለጡ በዮሴፍ ልጆች ራስ አናት ላይ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ከወንድሞቹ ዋና በሆነው
ብንያም ዘሩን የሚወክል ምትክ ስም ነው:: ያዕቆብ የብያም ልጆችን እንደ ተራበ ተኩላ ይናገራል:: ይህም አጉልቶ የሚናገረው አጥቂ ተዋጊዎች እንደሆኑ ነው:: የብንያም ነገድ ሰዎች እንደተራቡ ተኩላ ናቸው:: (ምትክ ቃልና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እነዚህም በዘፍጥረት 49: 1- 27 የተዘረዘሩትን ይመለከታል እያንዳንዱ ልጅ የነገድ አባት ሆኖአል፡፡
እዚህ “ባረካቸው” የሚለው መደበኛ በረከቶችን እንደተናገረ ነው
ለእያንዳንዱ የሚገባውን በረከት ባረከ
አዘዛቸው
ይህ ለመሞት መድረሱን በትህትና የሚገለጸበት መንገድ ነው፡፡ አት “ለመሞት ቀርበአለሁ ወይም ልሞት ነኝ” (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽንና ፈሊጣዊ አነጋገርን ይመልከቱ)
ያዕቆብ በሚሞትበት ጊዜ የራሱ ውስጠኛው ሰው/ ነፍሱ ወደየት እንደሚሄድ ያመለክታል:: ከሞት በኋላ አብርሃምንና ይስሐቅን አንደሚገናኝ ይጠብቃል (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽንና ፈሊጣዊ አነጋገርን ይመልከቱ)
ይህ ወንድ ሰው ስም ነው፡፡ “ኬጢያዊ” የኬጥ ዘር ነው:: በዘፍጥረት 23:8 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የአንድ ቦታ ወይም ግዛት ስም ነው፡፡ በዘፍጥረት 23፡9 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የሔብሮን ከተማ ሌላ ስምዋ ነው:: ምናልባት መምሬ የተባለው የአብርሃም ወዳጅ ስም የተሰየመ ሳይሆን አይቀርም:: በዘፍጥረት 13:18 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ(ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ያዕቆብ ለልጆቹ መናገሩን ይቀጥላል
ግዥው ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት “በዚያ አብርሃም የገዛውን” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ከኬጢያዊያን
“ለልጆቹ መመሪያ መሰጠቱን እንዳበቃ” ወይም “ልጆቹን አዝዞ እንዳበቃ”
ያዕቆብ በአልጋው ላይ ተቀምጦ ነበር አሁን ግን ሊሞት መልሶ እግሮቹን በአልጋ ላይ የሰበስባል
ይህ አንድ ሰው መሞቱን ለዛ ባለ ቋንቋ የሚገለጽበት መንገድ ነው (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽን ይመልከቱ)
ያዕቆብ በሞተ ጊዜ ውስጠኛው ሰው ወይም ነፍሱ ከእርሱ በፊት የሞቱ ወገኖች ወደሄዱበት ቦታ ተሰብስቦአል (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽንና ፈሊጣዊ አነጋገርን ይመልከቱ)
1 ዮሴፍ እጅግ ከማዘኑ የተነሣ በአባቱ ፊት ተደፍቶ አለቀሰ ሳመውም። 2 ከዚያም የአባቱ የእስራኤል አስከሬን እንዳይፈርስ ባለ መድኃኒት የሆኑ አገለጋዮች በመድኃኒት እንዲያሹት አዘዘ። ባለ መድኃኒቶቹም አስከሬኑ እንዳይፈርስ በመድኃኒት አሹት። 3 በአገሩ ልማድ መሠረት አስከሬኑ እንዳይፈርስ ማሸቱ አርባ ቀን ወሰደባቸው፤ ገብፃውያንም ሰባ ቀን አለቀሱለት። 4 የለቅሶው ወራት በተፈጸመ ጊዜ ዮሴፍ የፈርዖንን ባለሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፤ “መልካም ፈቃዳችሁ ቢሆን እባካችሁ ለፈርዖን፣ 5 ‘አባቴ ለመሞት ሲቃረብ በከነዓን ምድር ባዘጋጀው መቃብር እንድቀብረው በመሐላ ቃል አስገብቶኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ቀብሬ እንድመለስ ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቆአል’ ብላችሁ ንገሩልኝ” አላቸው። 6 ፈርዖንም፣ “ባስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው። 7 ስለዚህ ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ሄደ፣ የፈርዖን ሹማምንት በሙሉ፣ የቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንዲሁም የግብፅ ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖች ሁሉ ተከተሉት። 8 እንደዚሁም የዮሴፍ ቤተ ሰቦች ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተ ሰቦች ሁሉ ከዮሴር ጋር ሄዱ፣ በጌሤም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፣ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋዎቻቸው ብቻ ነበሩ። 9 እንዲሁም ሠረገሎች፣ ፈረሰኞች አብረውት ወጡ፤ አጀቡም እጅግ ብዙ ነበር። 10 እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ለቅሶ ተቀመጠ። 11 በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ ዐውድማ የተደረገውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ለግብፃውያን መራራ ልቅሶአቸው ነው” አሉ። በዮርዳኖስ አጠገብ ያለው የዚያ ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ተብሎ መጠራቱም ከዚሁ የተነሣ ነበር። 12 በዚህ ሁኔታ የያዕቆብ ልጆች አባታቸው እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ 13 አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦት እንዲሆን ከኬጢያዊው ከኤፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው። 14 ዮሴፍ አባቱን ከቀበረ በኋላ ከወንድሞቹና ለቀብር አጅበውት ከሄዱት ሰዎች ሁሉ ጋር ሆኖ ወደ ግብፅ ተመለሰ። 15 የዮሴፍ ወንድሞች ከአባታቸው ሞት በኋላ፣ “ከፈጸምንበት በደል የተነሣ ዮሴፍ ቂም ይዞ በበቀልን ምን እናደርጋለን ተባባሉ። 16 ስለዚህ እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ፣ አባትህ ከመሞቱ በፊት፣ 17 ‘ለዮሴፍ ወንድሞችህ በአንተ ላይ የፈጸሙትን ኃጢአትና ክፉ በደል ይቅር በላቸው’ ብላችሁ ንገሩት የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። አሁንም የአባትህን አምላክ አገልጋዮች ኃጢአት ይቅር በለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ። 18 ከዚያም ወንድሞቹ መጡና በፊቱ ተደፍተው፣ “እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን” አሉት። 19 ዮሴፍ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፣ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የተቀመጥሁ አይደለሁም፣ 20 እናንተ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ አድርጋችሁት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደሚታየው ሁሉ የብዙዎችን ሕይወት ለማዳን ለበጎ ነገር አዋለው። 21 አሁንም ቢሆን አትፍሩ፤ ለእናንተና ለልጆቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” በማለት በመልካም ንግግር አረጋጋቸው። 22 ዮሴፍ ከአባቱ ቤተ ሰቦች ጋር በግብፅ ተቀመጠ፤ አንድ መቶ ዐሥር ዓመትም ኖረ፤ 23 የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ ዐየ። ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች በጭኑ ላይ አድርጎ አቀፋቸው። 24 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጎበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል። 25 እግዚአብሔር በሚጎበኛችሁና ወደዚያች ምድር በሚመልሳችሁ ጊዜ ዐጽሜን ከዚህ ይዛችሁ የምትወጡ መሆናችሁን በማረጋገጥ ቃል ግቡልኝ” ብሎ አስማላቸው። 26 ዮሴፍም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሞላው ሞተ፣ አስከሬኑንም መድኃኒት ቀብተው በሬሳ ሳጥን ካስገቡት በኋላ በግብፅ ምድር አስቀመጡት።
እዚህ ተደፍቶ የሚለው ፈሊጣዊ አባባል ተመስጦ ማለት ነው፡፡ አት “በአባቱ ላይ ተደፍቶ በሀዘን” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አስከሬንን የሚያስተካክሉ አገልጋዮቹ
መቀባት ከቀብር በፊት አስከሬኑ እንዳይፈርስ የሚያቆዩበት ልዩ መንገድ ነው (ንኀብነት ወይም ለዛ ባለ መንገድ መግለጽን ይመልከቱ)
4ዐ ቀናት ወሰደባቸው (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
7ዐ ቀናት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
“የማዘኑ ቀናት” ወይም “ለእርሱ የማልቀስ ቀናት”
እዚህ የፈርዖን ቤት የፈርዖን ንጉሣዊ ፍርድ ቤት ወክል ባለሥልጣናት ያመለክታል ዮሴፍ ለፈርዖን ባለሥልጣናት ተናገረ (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
ሞገስ ማግኘት የሚለው ሐረግ በአንድ ሰው ፊት ተቀባይነትን ማትረፍ የሚናገር ፈሊጣዊ አባባል ነው:: አት “በእናንተ ፊት ሞገስ ካገኘሁ ወይም በእኔ ደስተኞች ከሆናችሁ” (ፈሊጣዊ አባባልና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ሁለት ደረጃና ሶስት ደረጃ ጥቅስ ይዞአል እነዚህ በተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጹ ይችላሉ:: አት “በከነዓን ምድር በቆፈረው መቃብር እንዲቀብረው አባቴ በሚሞትበት ጊዜ እንዳመለኝ ለፈርዖን ንገሩልኝ:: አባተን እንዲቀብረውና ከዚያም ተመልሸ እንዲመጣ ፈርዖንን ጠይቁልኝ” (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ሊሞት ነኝ
ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደ ላይ መውጣት” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው፡፡
የመንግሥት ምክር ቤት አባላት ለፈርዖን ነገሩትና ከዚያም ፈርዖን ለዮሴፍ መለሰ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ለእርሱ እንደማልህለት
ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደ ላይ መውጣት” የሚለውን ሀረግ መጠቀም የተለመደ ነው፡፡
የፈርዖን ከፍተኛ መሪዎች ሁሉ የቀብሩን ሥነሥርዓት ተካፈሉ (የሁኔቶች ሥርዓት ይመልከቱ)
የፈሪዖን ቤተምንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ያመለክታል
ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጐም ይችላል:: አት “የግብጽ ምድር ፤ እንዲሁም የዮሴፍ ቤተ ሰዎች ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰዎች ከእርሱ ጋር አብረውት ሄዱ” (የሁኔቶች ቅደም ተከተል ይመልከቱ)
እዚህ በሠረገላዎች የተቀመጡ ሰዎችን ያመለክታል (ምትክ ቃላት ይመልከቱ)
እጅግ ብዙ ሰዎች ጉባኤ ነበር
“እነርሱ” የሚለው ቃል በቀብር ሥነሥርዓቱን ይካፈሉ የነበሩ ሰዎችን ያመለክታል
ተገቢ ትርጉሞች 1) “አጣድ” የሚለው ቃል እሾህ ማለት ነው፤ አናም እጅግ ብዙ እሾሆች የሚበቅሉበት መሬት ሊባል ይችላል ወይም 2) “የአውድማው ባለቤት ስም ሊሆን ሊችላል:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እጅግ መራራና ከፍተኛ ልቅሶ አልቅሰው ነበር
7 ቀን (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ተገቢ ትርጉሞች 1) አጣድ የተባለው ሰው አውድማ ውስጥ ወይም 2) አጣድ በተባለው አውድማ ውስጥ:: (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የግብጻዊያን ልቅሶ መራራ ነበር
ተርጓሚዎች የሚከተለውን እንደ ግርጌ ማስታወሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ አቤል ምጽራይም የሚለው ስም የግብጻዊያን ሐዘን ማለት ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የያዕቆብ ልጆችም
ልክ መመሪያ እንደሰጣቸው
ልጆቹም አስከሬኑን ተሸክመውት
ማክፌላ የቦታ ወይም የግዛት ስም ነው በዘፍጥረት 23፡9 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የሔብሮን ከተማ ሌላ ስምዋ ነው በዚያ ይኖር በነበረው በአብርሃም ወዳጅ መምሬ ስም ሳትሰየም አትቀርም፡፡ በዘፍጥረት 13፡ 18 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ የወንድ ሰው ስም ነው ኬጢያዊ የኬጥ ዘር ነው በዘፍጥረት 23፡8 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ዮሴፍ ወደ ግብጽ ተመለሰ
አብረውት የሄዱት ሁሉ
እዚህ ቂም ዮሴፍ በእጁ እንደምይዝ ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል አት ምናልባት ዮሴፍ የጠላን ይሆናል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እርሱን የበደለውን ሰው መበቀል አንድ ሰው ከሌላ ሰው የተበደረውን እንደመመለስ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “ባደረግንበት ክፋት ምናልባት ልበቀለን ይችላል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ሁለት ደረጃና ሶስት ደረጃ ጥቅስ ይዞአል እንደተዘዋዋሪ ጥቅስም ሊገለጹ ይችላሉ:: አት “አባትህ ከመሞቱ በፊት እኛ የበደልንህን ይቅር እንዲትለን እንድንነግርህ አዝዞናል” (ጥቅስን በጥቅስ ውስጥ እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ያዕቆብ ለወንድማማቾች ሁሉ አባት ነው:: እዚህ ዮሴፍ አባቱ ለተናገረው ትኩረት እንዲሰጥ “አባትህ” ብለው ይናገራሉ:: አት “አባታችን ከመሞቱ በፊት”
በአንተ ላይ ስላደረጉት ክፉ ነገሮች
ይህ በዚህን ጊዜ ማለት አይደለም ነገር ግን ለሚቀጥለው ዋና ነጥብ ትኩረት እንዲሰጥበት ነው
ወንድሞቹ ራሳቸውን “የአባትህ አምላክ ባሪያዎች” ብለው ይገልጻሉ:: (አንደኛ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ወገን ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
የሴፍ ይህን መልእክት በሰማ ጊዜ አለቀሰ
በፊቱ ወደ መሬት ጐንበስ በማለት ሰግደው፤ ይህ የትህትና እና ለዮሴፍ ክብርን የመስጠት ምልክት ነው፡፡ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ዮሴፍ ወንድሞቹን ለማደፋፈር ጥያቄ ይጠቀማል:: አት “እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ አይደለሁም” ወይም “እኔ እግዚአብሔር አይደለሁም” (አግናኝ ወይም ሽንገላ አዘል ጥያቄዎችን ይመልከቱ)
እናንተ ክፉ ነገር አድርጋችሁብኝ
እግዚአብሔር ለመልካም አደረገው
ስለዚህ እኔን አተፍሩ
ሁል ጊዜ እናንተና ልጆቻችሁ በቂ ምግብ እንዲኖራችሁ አረጋግጣለሁ
እዚህ ልቦች ወንድሞቹን ያመለክታሉ:: አት “አጽናናቸውም ደስም አሰኛቸው” (ክፍልን እንደ ሙሉና ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
11ዐ ዓመት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
የኤፍሬም ልጆችና የልጅ ልጆች
ይህ የዮሴፍ ወንድ የልጅ ልጅ ስም ነው (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ አባበል ዮሴፍ እነዚህን የማኪርን ልጆች የራሱ የልጅ ልጆች አድርጐ ተቀበላቸው ማለት ነው:: ይህም ዮሴፍን ለመውረስ ልዩ መብት አላቸው ማለት ነው (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በዘፍጥረት 5ዐ: 24./26 “እናንተ” የሚለው ቃል የዮሴፍን ወንድሞች ነገር ግን ደግሞ የእነርሱን ልጆች ያመለክታል፡: (ምትክ ቃላት አጠቃቀም ይመልከቱ)
ከግብጽ ወደ ከነዓን መጓዝ በሚነገርበት ጊዜ “ወደ ላይ መውጣት” የሚለውን ቃለ መጠቀም የተለመደ ነው:: አት “ከዚህ ምድር ያወጣችኋል ወደ ምድራችሁ ይወስዳችኋል” (የክስተቶች ቅደም ተከተል ይመልከቱ)
መቶ አሥር ዓመታት
አንድን አስከሬን ከመቀበሩ በፊት እንዳይፈርስ ለማቆየት መድሃኒት መቀባት ልዩ የሆነ መንገድ ነበር በዘፍጥረት 5ዐ 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት “አኖሩት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“በሬሳ ሳጥን” ወይም “በሳጥን” ይህ ሳጥን የሞተ ሰው የሚቀመጥበት ነው::
1 እያንዳንዳቸው ቤተ ሰባቸውን በመያዝ፣ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦ 2 ሮሜል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ 3 ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ብንያም፣ 4 ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር። 5 ከያዕቆብ ዘር የተገኙት ሰዎች ሰባ ነበር። ዮሴፍ ቀድሞውኑ በግብፅ ውስጥ ነበረ። 6 ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ፣ ወንድሞቹ ሁሉና ያ ትውልድ በሙሉ ሞቱ። 7 ነገር ግን እስራኤላውያን እየተዋለዱ ሄዱ፤ ቊጥራቸውም እጅግ ጨምሮ በጣም ብርቱዎች ሆኑ፤ ምድሪቱንም ሞሏት። 8 በግብፅ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ ዐዲስ ንጉሥ ተነሣ። 9 ለሕዝቡም እንደዚህ አለ፤ “እስራኤላውያንን ተመልከቷቸው፤ ከእኛ ይልቅ በቍጥር በዝተዋል፤ እጅግም በርትተዋል። 10 በቍጥር እየበዙ እንዳይሄዱ፣ ጦርነት ቢነሣም ከጠላቶቻችን ጋር ዐብረው እንዳይወጉንና ምድሪቱ ጥለው እንዳይሄዱ ኑ በዘዴ እርምጃ እንውሰድባቸው።” 11 በከባድ ሥራ የሚያስጨንቋቸው አሠሪ አለቆችን በላያቸው ሾሙ። እስራኤላውያን ለፈርዖን ፊቶምና ራምሴ የተባሉ የንብረት ማከማቻ ከተሞችን ሠሩ። 12 ግን ግብፃውያን እስራኤላውያንን ባስጨነቋቸው ቊጥር፣ እስራኤላውያን በቊጥር እየበዙና በምድሪቱ እየተስፋፉ ሄዱ። ስለዚህ ግብፃውያን እስራኤላውያን መፍራት ጀመሩ። 13 ግብፃውያን እስራኤላውያንን በጥብቅ እንዲሠሩ አደረጓቸው። 14 በሸክላ ሥራና ጭቃ በማስቦካት፣ በዕርሻ ውስጥም ሁሉን ዐይነት ከባድ ሥራ በማሠራት አስመረሯቸው (ሕይወታቸውን መራራ አደረጉባቸው) ። የሚጠበቅባቸው ሥራ ሁሉ ከባድ ነበር። 15 ከዚያም በኋላ የግብፅ ንጉሥ ሲፓራና ፉሐ የሚባሉ ዕብራውያት አዋላጆችን እንዲህ አላቸው፤ 16 “ዕብራውያት ሴቶችን በማማጫው ላይ ስታዋልዱ፣ በሚወልዱበት ጊዜ ተመልከቱ። ወንድ ከተወለደ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።” 17 ነገር ግን አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ፈሩ፣ ንጉሡ ያዘዛቸውንም አልፈጸኩም፤ ትእዛዙን በመፈጸም ፈንታ ሕፃናት ወንዶችን በሕይወት እንዲኖሩ አደረጉ። 18 የግብፅ ንጉሥ አዋላጆቹን ጠርቶ፣ “ለምን ይህን አደረጋችሁ፣ ሕፃናት ወንዶችንስ ለምን አልገደላችኋቸውም?” አላቸው። 19 አዋላጆቹም ለፈርዖን፣ “ዕብራውያት ሴቶች እንደ ግብፃውያት ሴቶች አይደሉም። እነርሱ ብርቱዎች ናቸው፣ የሚወልዱትም አዋላጅ ወደ እነርሱ ከመምጣቱ በፊት ነው” በማለት መለሱለት፥ 20 እግዚአብሔር እነዚህን አዋላጆች ጠበቃቸው። ሕዝቡ በቍጥር በዙ፣ እጅግ ብርቱዎችም ሆኑ። 21 አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ፣ እግዚአብሔር ቤተ ሰቦችን ሰጣቸው። 22 ፈርዖን፣ “የተወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፣ ሴትን ልጅ ግን በሕይወት እንድትኖር ታደርጋላችሁ” በማለት ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
በአንድ ቤት አብረው የሚኖሩ ሰዎች ስብስብና ከቤተሰብ አባላት ውጭ ሌሎች አገልጋዮችም ጭምር ያሉበት ቤተሰብ ይባላል።
በቁጥር ሰባ የሚያህሉ ሰዎች ማለት ነው
የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ግብጽ ከመምጣታቸው በፊት ዮሴፍ በግብጽ ይኖር ነበር
ወንድሞቹ የተባሉት የዮሴፍ አስር ታላቅ ወንድሞቹና አንድ ታናሽ ወንድሙ ስብስብ ነው
ልጆችን አፈሩ የሚለው ሀረግ በተለዋጭ ዘይቤ የተጻፌ ነው። በእስራኤላውያን ዘንድ ልጅ መውልድ ከዛፍ ፍሬ ማፍራት ጋር ተነጻጽሮ ቀርቧል። የዚህ አማራጭ ትርጉም “ብዙ ልጆች ወለዱ” ወይም “ብዙ ልጆችን አገኙ” የሚል ነው።
ይህ በተደራጊ ግስ የተጻፈ ሲሆን በአድራጊ ግስ “እነርሱ ምድርቱን ሞሉ” ማለት ነው።
በሶስተኛ መደብ የተጠራው “እነርሱ” የሚለው ቃል “እስራኤላውያንን” ያመለክታል።
ግብጽ የሚለው ቃል የግብጽ ህዝብን የሚያመለክት ነው። የዚህ አማራጭ ትርጉም “የግብጽ ህዝብን የሚገዛ አዲስ ንጉስ ነገሰ” የሚል ነው።
የግብጽ ንጉስ ለህዝቡ እንዲህ ብሎ ተናገረ።
በግብጽ ምድር የሚኖሩ ህዝቦች ወይም ግብጻውያንን ማለት ነው።
ይህ አባባል ንጉሱንና እርሱ የሚመራውን ህዝብ ወይም ግብጻውያንን የሚያጠቃላል ነው። “እኛ” የሚለው መደብ መገለጫ ነው።
“ሰልፍ” የሚለው ጠላት በእኛ ጦርነት ባወጀ ጊዜ ወይም ጠላት ልወጋን በሚመጣበት ጊዜ የሚለውን ሀሳብ ይገልጻል። “ሰልፍ በተነሳብን” ጊዜ የሚለው በሰውኛ ዘይቤ የተገለጸ ነው፤ ምክንያቱም ሰልፍ እንደ ሰው ተነሳ የሚል አገላለጽ የያዘ ነው።
እስራኤላውያን ግብጽን ለቀው እንዳይሄዱ ማለት ነው።
ግብጻውያን እስራኤላውያንን ከባድ ወይም አስቸጋሪ ሥራ እንዲሰሩ ያስጨንቋቸው ነበር ማለት ነው።
እስራኤላውያን ከባድ ሥራ እንዲሰሩ የሚያስገድዱ የግብጽ “አሰሪ አለቆች” ማለት ነው።
ንጉሱና ሌሎች መሪዎች ወይም ሹማምንት ምግብና ሌሎች ተፈላጊ የሆኑ ንብረቶችን የሚያኖሩበት “ንብረት ማከማቻ ከተሞች” ማለት ነው።
ጭካኔ በተሞላበትና ርህራሄ በለሌው ስሜት ግፍ ይፈጽሙባቸው ነበር።
የአንድ ዛፍ ፍሬ መራራ ከሆነ እንደማይበላና ደስ እንደማይል ሁሉ የእስራኤላውያን ህይወት እለት ተዕለት በሚደርስባቸው ጭካነ መራራ በመሆኑ ደስተኞች አልነበሩም ማለት ነው። አባባሉ በተለዋጭ ዘይቤ የተገለጸ ነው።
ለቤት ሥራ የሚውል ከጭቃና ከሸክላ አፈር እንዲሁም በዘመናዊ መንገድ ከሲሚንቶ የሚሰራ ብሎኬት መሳይ ነገር ማለት ነው
ግብጻውያን እስራኤላውያንን የተለያዩና በጣም ከባድ የሆነ የጉልበት ሥራዎችን ያሰሩአቸው ነበር።
የግብጽ ንጉስ በወል ወይም በጋራ ስም “ፈርዖን” ተብሎ ይጠራል።
ሴቶች በሚወልዱበት ጊዜ የማዋለድ ሥራ የሚሰሩ ወይም አገልግሎት የሚሰጡ ሴቶች ማለት ነው
የዕብራውያን ሴቶች ስም ነው (ስሞችን የመተርጎም ዘዴ ተመልከት)
ሴቶች በሚወልዱበት ጊዜ የሚቀመጥቡት ድንጋይ ወይም መቀመጫ ማለት ነው። እስራኤላውያን ሴቶች ለመውለድ በዚህ ድንጋይ ላይ ሲቀመጡ ወይም ሴቶቹ በሚወልዱበት ጊዜ ማለት ነው።
ፈርዖን ይህንን ጥያቄ አዋላጆችን የጠየቀው ወንድ ህጻናትን ባለመግደላቸው ምክንያት ልገስጻቸው ፈልጎ ነው። ይህ ጥያቄ በመደበኛ ዓረፍተ ነገር ሲተረጎም “ወንድ ህጽናትን ባለመግደላችሁ ትዕዛዜን ተላልፋችሁኋል” የሚል ይሆናል። ጥያቄው በባህርዩ አጋናኝ ጥያቄ ነው።
አዋላጆች የንጉሱን ቁጣ ለማብረድ በጥበብና በምክንያታዊነት የተናገሩት ንግግር ዓይነት ነው።
ፈሪዖን እነዚህን ሴቶች እንዳይገድላቸው እግዚአብሔር ጠበቃቸው፥ ተከላከላቸው፥ ለክፉ አሳልፎ አልሰጣቸውም ማለት ነው።
እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ገዥ እንደሆነ አምነው ከፈሪዖን ይልቅ እግብቻ ሰሙ ማለት ነውዚአብሄርን ፈሩ፥ ለእርሱ ብቻ ታዘዙ፥ እርሱን
እግዚአብሔር ለእነዚህ አዋላጆች ቤተሰብ ወይም ልጅ ወይም ዘር ሰጣቸው ማለት ነው።
ወንዶች ልጆች ውሃው ውስጥ ሰጥመው እንድሞቱ ህዝቡ እያንዳንዱን ወንድ ልጅ ወደ አባይ ወንዝ እንድጥል ጥብቅ ትዕዛዝ ንጉሱ ሰጣቸው።
1 ከሌዊ ወገን የሆነ አንድ ሰው ሌዋዊት ሴት አገባ፡፡ 2 ሴትዮዋ ፀነሰች ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ ሕፃኑ መልከ መልካም መሆኑን ስታይ፣ ሦስት ወር ሸሸገችው፡፡ 3 ከዚያ በላይ ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፣ የደንገል ቅርጫት ወስዳ በዝፍትና በቅጥራን ለቀለቀችው፡፡ ከዚያም ልጁን በውስጡ አስተኝታ ውሃው ውስጥ በቄጠማው መካከል በወንዙ ዳርቻ አስቀመጠችው፡፡ 4 የሚያጋጥመውን ለማየት የሕፃኑ እኅት በርቀት ቆማ ነበር፡፡ 5 ጠባቂዎቿ በወንዙ ዳር እየሄዱ ሳለ፣ የፈርዖን ልጅ በወንዙ ለመታጠብ ወረደች፡፡ ልዕቲቱ ቅርጫቱን በቄጠማዎች መካከል አየችው፡፡ ቅርጫቱን እንዲያመጣላት ጠባቂዋን ላከች፡፡ 6 ቅርጫቱን ስትከፍተው፣ ሕፃኑን አየች፡፡ እነሆ፣ ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፡፡ ራራችለትና፣ «ይህ በእርግጥ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው» አለች፡፡ 7 ከዚያም በኋላ የሕፃኑን እኅት የፈርዖንን ልጅ፣ «ልሂድና ሕፃኑን የምታሳድግልሽ ዕብራዊት ሴት ልፈልግልሽ?» አለቻት፡፡ 8 የፈርዖንም ልጅ «ሂጂ» አለቻት፡፡ ወጣቷም ልጅ ሄዳ የሕፃኑን እናት አመጣች፡፡ 9 የፈርዖን ልጅ የሕፃኑን እናት፣ «ይህ ሕፃን ውሰጅና አሳድጊልኝ፤ ደሞዝ እከፍልሻለሁ» አለቻት፡፡ ሴትዮዋም ሕፃኑን ወስዳ አሳደገችው፡፡ 10 ሕፃኑ ባደገ ጊዜም ወደ ፈርዖን ልጅ አመጣችው፤ የልዕልቲቱም ልጅ ሆነ፡፡ «ከውሃ አውጥቼዋለሁና» ብላም ስሙን ሙሴ አለችው፡፡ 11 ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወገኖቹ ሄዶ የሚሠሩትን ከባድ ሥራ ተመለከተ፡፡ ከገዛ ወገኖቹ መካከል አንዱን ዕብራዊ አንድ ግብፃዊ ሲደበድበው አየ፡፡ 12 ግራና ቀኙን ተመልክቶ ማንም አለመኖሩን ሲያረጋግጥ፣ ግብፃዊውን ገድሎ በአሸዋ ውስጥ ደበቀው፡፡ 13 ቀን ሙሴ ወደ ውጭ ወጣ፤ እነሆም ሁለት ዕብራውያን ወንዶች እየተጣሉ ነበር፡፡በደለኛ የነበረውን ሰውየ፣ «ባልንጀራህ ለምን ትደበድበዋለህ?» አለው፡፡ 14 ሰውየው ግን፣ «አንተን በእኛ ላይ አለቃና ዳኛ ማን አደረገህ? ያን ግብፃዊ እንድ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ታስባለህ?» አለ፡፡ ሙሴም ፈራና፣ «ያደረግሁት በሌሎች ሰዎች ዘንድ በእርግጥ ታውቋል» አለ፡፡ 15 ስለ ጉዳዩ ሲሰማ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ፡፡ ነገር ግን ከፈርዖን ሸሽቶ በምድያም አገር ኖረ፡፡ እዚያም በአንድ የውሀ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፡፡ 16 ካህን ሰባት ሴት ልጆች ነበሩት፡፡ እነርሱም ወደ ጉድጓዱ መጥተው ውሀ ቀዱ፣ የአባታቸውን መንጋ ለማጠጣትም ገንዳውን ሞሉት፡፡ 17 መጥተው ሊያባርሯቸው ሞከሩ፣ ነገር ግን ሙሴ ሄዶ ዐገዛቸው፡፡ መንጋቸውንም አጠጣላቸው፤ 18 ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤል ሲሄዱም፣ አባታቸው፣ «ዛሬ እንዴት ቶሎ ወደ ቤት መጣችሁ?» አለ፡፡ 19 «አንድ ግብፃዊ ከእረኞች አዳነን፤ ውሀም ቀድቶ መንጋውን አጠጣልን» አሉ፡፡ 20 ልጆቹን፣ «ታዲያ የት አለ?» ሰውየውን ለምን ተዋችሁት? ምግብ ከእኛ ጋር እንዲበላ ጥሩት» አላቸው፡፡ 21 ሲፓራን እንዲያገባትም እንኳ ከሰጠው ሰውየ ጋር ለመኖር ሙሴ ተስማማ፡፡ 22 ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም፣ «የባዕድ ምድር ኗሪ ነኝ» ሲልም ስሙን ጌርሳም አለው፡፡ 23 ከረጅም ጊዜ በኋላ፣ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፡፡ እስራኤላውያን ከባርነት ሥራ የተነሣ አለቀሱ፣ ለርዳትም ጮኹ፤ ከባርነት ቀበራቸው የተነሣም ያሰሙት ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ወጣ፡፡ 24 እግዚአብሔር ልቅሶአቸውን ሲሰማ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳኑን ዐሰበ፡፡ 25 እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አየ፤ ሁኔታቸውንም ተረዳ፡፡
በዕብራይስጡና በቀድሞ አማርኛ ትርጉም (በ1954 ትርጉም) ይህ አገናኝ ሀረግ የለም። ነገር ግን በአንዳንድ እንግሊዘኛና በሌሎች አማርኛ ትርጉሞች እንደ አገናኝ ሀረግ የገባ ነው። ይህ አገናኝ ሀረግ አዲስ ሀሳብ ሲጀመር ወይም አንድ ታሪክ አልቆ ሌላ ታሪክ ሲጀመር የሚያሳይ ነው። ንጉሱ የዕብራውያን ወንድ ልጆች እንዲገደሉ ባዘዘበት ጊዜ ሌላ ታሪክ ሲከሰት ያሳየናል። ተርጓሚዎች በቋንቋቸው እንደዚህ ያሉ እገናኝ ሀረጎች ወይም ቃላት መኖሩን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።
በናይል ወንዝ ዳር የሚበቅልና የሚያድግ ከቀጤማ፥ ከመቃ፥ ወይም ከሸምበቆ የተሰራ ቅርጫት መሳይ ነገር ነው።
ለአስፋልት መንገድ ሥራ የሚጠቅም ቃጥራሜ ወይም ሬንጅ ዓይነት ነገር ነው። ውሃ ወደ ቅርጫቱ እንዳይገባ ወይም እንዳይሰርግ የሚያደርግ ነገር ነው። ጥቁር ወይም ቡናማ ቀለም ያለው ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት እና ከዛፍ ላይ የሚገኝ ሲሆን በተፈጥሮ የማጣበቅ ባህርይ ያለው ነው።
ውሃ ወደ ውስጥ እንዳይገባ ለጠፈችው ወይም አሸገችው ማለት ነው።
በወንዝ ዳር ወይም ደግሞ እርጥበት ባለበት አከባቢ የሚበቅል ረጅም ሳር መሳይ ነገር ነው፥ ምናልባት ሸምበቆ በሌለበት ወይም በማይታወቅበት ማህበረሰብ ውስጥ ሸምበቆ ወይም ቀርከሃ በምትክነት መጠቀም ይቻላል።
ሌሎች አይተዋት ማን እንደሆነች እንዳይጠቋትና እንዲሁም ህጻኑን ማየትና መከታተል በምትችልበት ርቀት ላይ ቆማ ሁኔታውን እየተከታተለች ነበር ማለት ነው።
አገልጋዮቹዋ እንደ ማለት ነው። በተለይ በንጉሱ ሴት ልጅ ላይ ምንም ጉዳት እንዳይደርስባትና ብቸኛ እንዳትሆን የሚጠብቋት አገልጋዮቿ ናቸው።
በታሪኩ መካከል ላይ ሌላ ጣልቃ ገብ ታሪክ ሲከሰት “በዚህን ጊዜ” በማለት የአንባቢን ትኩረት ይስባል። ይህ አገናኝ ሀረግ በቀድሞና በአዲሱ አማርኛ ትርጉም ላይ እንዲሁም በዕብራይስጡ ላይ አልተጠቀሰም።
ሕፃኑን እያጠባች የምታሳድግ ሴት ማለት ነው።
ይህን ሕፃን ወስደሽ እያጠባሽ አሳድጊልኝ
ልጁም የፈርዖን ሴት ልጅ የማደጎ ልጅ ሆነላት ማለት ነው
ሙሴ የሚለው የስሙ ትርጉም በዕብራይስጥ ቋንቋ “ማውጣት” የሚል ፍቺ ስላለው ተርጓሚዎች የግርጌ ማስታወሻ በመስጠት የስሙን ፍቺ ግልጽ ሊያደርጉ ይችላሉ።
አንድ ግብፃዊ ሰው ዕብራዊ ወገኑን ሲደበድበው ማየቱን የሚገልጽ ነው
ይህ ሁለት ተቃራኒ አቅጣጫዎች ጠቋሚ አገላለጽ አካባቢውን ቃኝቶ ሰው አለመኖሩን ለማጣራት ሁሉንም አቅጣጫ ተመለከተ የሚል አጠቃላይ ፍቺ ይዟል
ሙሴ በማግስቱ እየሆነ ያለውን ነገር ለማየትና ለማጣራት መውጣቱን ለመግለጽ ነው
ጥላቻውን የጀመረውን ወይም ጥፋተኛውን ወይም ጓደኛውን ቀድሞ መምታት የጀመረውን ዕብራዊ ወገኑን ማለት ነው። ይህ አባባል በዕብራውያን ዘንድ የታወቀና በባህሉ የተለመደ አባባል ነው።
ይህ ጥያቄ የሚያሳየው ሙሴ በሁለቱ ሰዎች መካከል ጣልቃ በመግባቱ ነገሩን ሳታጣራ ወይም በትክክል ሳትረዳ ለምን አለቃ ትሆናለህ ብሎ ለመገሰጽ የተጠቀመበት አባባል ነው። ይህ አጋናኝ ጥያቄ በመደበኛ ዐረፍተ ነገር ሲተረጎም “አንተ በእኛ ላይ ለመፍረድና መሪ ለመሆን አልተጠራህም” እንደ ማለት ነው።
ይህ አጋናኝ ጥያቄ የሚያመለክተው ውስጠ ወይራ ወይም አሽሙር ነው። አማራጭ ትርጉሙ፦ ትናንትና አንድ ግብጻዊ እንደገደልክ እናውቃለን፥ እኔን ግን አትገድለኝም” ሊሆን ይችላል።
በታሪኩ ውስጥ ፀሐፊው ሌላ ሀሳብ ሲያስገባ ወይም አዲስ የታሪክ ክፍል ሲጨምር እንመለከታለን። ሙሴ ያደርገውን ነገር ፈርዖን ሰምቶታል ማለት ነው ወይም ወሬው ወደ ፈርዖን ደረሰ ማለት ነው።
ጸሐፊው በታሪኩ ውስጥ አዳዲስ ሰዎችን ወይም ተዋንያንን ሲጨምር እናያለን፥
በጊዜው ዕብራውያን ውሃ የሚቀዱት ከጉድጓድ ነበርና ውሃ ለመቅዳት ወደ ጉድጓዱ እንደመጡ ያሳያል።
ከእንጨት ወይም ከድንጋይ ወይም ከሌሎች ነገሮች የሚሰራ ከብቶችን ውሃ ለማጠጣት ወይም መኖ ለመስጠት የሚያገለግል ነው።
እረኞችም መጥተው እነዚያን ሴቶች አባረሩአቸው፥ ከለከሉአቸው፥ አሳደዱአቸው እንደማለት ነው።
እረኞችም መጥተው ሴቶቹን ሲያባርሯቸው ሙሴ ከተቀመጠበት ተነሥቶ ተከላከለላቸው፥ ከእረኞችም እጅ አዳናቸው ወይም አስጣላቸው ማለት ነው።
ይህ ጥይቄ አነስተኛ የሆነ ቁጣ አዘል ንግግር ወይም ጥያቄ ነው። እንደ ዕብራውያን ባህል እነዚህ ሴቶች ልጆች ይህን ሰው በእንግድነት ወደ ቤታቸው መጋበዝ ነበረባቸው። በቀጥታ ዐረፍተ ነገር ሲነገር “ይህን ሰው በጉድጓድ ውሃው አጠገብ ትታችሁ መምጣት አልነበረባችሁም”
ሙሴም ከሰውየው ወይም ከራጉኤል ጋር ለመኖር ተስማማ ወይም ፈቃደኛ ሆነ ማለት ነው።
የራጉኤል ሴት ልጁ ነች
የሙሴ ታላቅ ልጁ ነው
በሰው አገር መጤ ወይም እንግዳ ነኝ ማለት ነው
ከመከራቸውና ከጭንቃቸው የተነሳ ማልቀሳቸውን የሚያሳይ ነው
የእስራኤላውያን ጩኸት እግር እንዳለው ሰው ወደ እግዚአብሔር እንደተጓዘ ወይም እንደሄደ በሰውኛ ዘይቤ የተነገረ ነው። በቀጥተኛ ዐረፍተ ነገር ሲነገር “እግዚአብሔር ጩኸታቸውን ሰማ” የሚል ነው።
ይህ አባባል በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ ነው። ሰው አንድን ነገር ረስቶ እንደገና እንደሚያስብ የተነገረ ዘይቤያዊ ንግግር ነው። በሌላ አገላለጽ፦ “እግዚአብሔር የገባውን ቃል ኪዳን አሰበ”።
1 ሙሴ የምድያምን ካህን፣ የዐማቱን የየቶርን በጎች ጠብቅ ነበር፡፡ በጎቹን ወደ ምድረ በዳው ዳርቻ ነድቶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ ደረሰ፡፡ 2 በዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቊጥቋጦ ውስጥ በእሳት ነበልባል ተገለጠለት፡፡ ሙሴ ተመለከተ፣ እነሆም ቊጥቋጦው እየተቀጣጠለ ነበር፤ ነገር ግን ቊጥቋጦው አልተቃጠለም፡፡ 3 ሙሴም፣ «ልቅረብና ቊጥቋጦው ለምን እንዳልተቃጠለ ይህን አስደናቂ ነገር ልይ» አለ፡፡ 4 ሊመለከት እንደ ቀረበ እግዚአብሔር ሲያየው፣ ከቊጥቋጦው ውስጥ ጠራው፤ «ሙሴ፣ ሙሴ» አለውመ፡፡ ሙሴም፣ «እነሆኝ» አለ፡፡ 5 እግዚአብሔር፣ «አትቅረብ! የቆምህበት ምድር ለእኔ ተቀድሶአልና ጫማህን አውልቅ» አለው፡፡ 6 ደግሞም፣ «እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ» አለው፡፡ ከዚያም በኋላ ሙሴ እግዚአብሔርን ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ፡፡ 7 እንዲህ አለ፤ «በግብፅ የሚኖሩትን የሕዝቤን ሥቃይ በእርግጥ አይቻለሁ፡፡ አሠሪ አለቆቻቸው ከሚያደርሱባቸው ጭቈና የተነሣ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ስለ ሥቃያቸው ዐውቃለሁና፡፡ 8 ከግብፃውያን አገዛዝ ነጻ ላወጣቸውና ከዚያም ጋር አውጥቼ ማርና ወተት ወደምታፈሰው መልካምና ለም ወደሆነችው፤ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያንን፣ ፌርዛውያን፣ ኤውያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ላሰገባቸው ወርጃለሁ አለ፡፡ 9 የእስራል ሕዝብ ጩኸት ወደ እኔ ደርሶአል፡፡ ይልቁንም ግብፃውያን ያደረሱባቸውን ጭቈና አይቻለሁ፡፡ 10 ስለዚህ ሕዝቤን፣ እስራኤላውያንን ከግብፅ እንድታወጣ ወደ ፈርዖን እልክልሃለሁ፡፡» 11 ግን፣ እግዚአብሔርን «ወደ ፈርዖን የምሄድና እስራኤላውያንን ከግብፅ የማወጣቸው እኔ ማን ነኝ?» አለው፡፡ 12 ሙሴን መልሶ፣ «እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፡፡ ይህ እኔ እንደ ላክሁህ ምልክት ይሆናል፡፡ ሕዝቡን ከግብፅ ስታወጣቸው፣ በዚህ ተራራ ላይ ታመልኩኛላችሁ» አለው፡፡ 13 ሙሴም እግዚአብሔርን፣ «ወደ እስራኤላውያን ስሄድና ‹የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል› ብዬ ስነግራቸው፣ እነርሱም፣ «ስሙ ማን ነው? ሲሉኝ ምን እነግራቸዋሉ? አለው፡፡ 14 እግዚአብሔርም ሙሴን፣ «እኔ ያለሁ የምኖርም ነኝ፡፡ ያለና የሚኖር ወደ እናንተ ልኮኛል ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው» አለው፡፡ 15 ደግሞም እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል፡፡ ስሜ ለዘለዓለም ይህ ነው፤ ለትውልዶች ሁሉ የታስበውም በዚህ ነው ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው፡፡» 16 ሂድና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ለእኔ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፣ «ጐብኝቻችኋለሁ፤ በግብፅ ውስጥ የደረሰባችሁንም አይቻለሁ፡፡ 17 በግብፅ ከደረሰባችሁ ጭቈና ነጻ ላወጣችሁና ማርና ወተት ወደምታፈሰው ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፌርዛውያን፣ ወደኤዊያውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ላገባችሁ ቃል ገብቻለሁ፡፡» 18 ሽማግሌዎቹም ይሰሙሃል፡፡ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ሂዱና፣ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገለጠልን፡፡ ስለዚህም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት እንድንችል በምድረ በዳው ውስጥ የሦስት ቀን ጕዞ እንሂድ በሉት፡፡ 19 ነገር ግን የግብፅ ንጉሥ እጁ ካልተገደደ በቀር ለመሄድ እንደማይፈቅድላችሁ ዐውቃለሁ፡፡ 20 በመካከላቸው በማድረጋቸው ተአምራት ሁሉ ግብፃውያንን እመታቸዋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ፣ እንድትሄዱ ይፈቅድላችኋል፡፡ 21 ሕዝብ ከግብፃውያን ዘንድ መወደድን እንዲያገኝ አደርጋለሁ፣ ስለዚህ ስትወጡ፣ ባዶ እጃችሁን አትወጡም፡፡ 22 ሴት ከግብፃውያት ጎረቤቶቿና በጎረቤቶቿ ቤቶች ውስጥ ከምትኖር ማንኛውም ሴት የብርና የወርቅ ጌጣጌጦች፣ ልብስም እንዲሰጣት ትጠይቃለች፡፡ እነርሱንም በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጓቸዋላችሁ፡፡ ግብፃውያንን በዚህ መንገድ ትበዘብዟቸዋላችሁ፡፡
አንድ የተለየ የእግዚአብሔር መልዓክ ወይም መልዕክተኛ ማለት ነው።
በዕብራይስጡ ያህዌ ተብሎ የሚጠራው ስም ነው። አንዳንድ የእንግሊዘኛ ትርጉሞች ይህን “YHWH” የሚለውን ስም “LORD” ይላሉ፤ ይህ ስም አዶናይ “ጌታ” ከሚለው ስም ይለያል። የእንግሊዘኛ ትርጉሞች ይህንን ስም ለመለየት “Lord” ብለዋል። በአማርኛችን “ያህዌ” እና “ኤሎሂም” የሚለው ስም “እግዚአብሔር” በሚለው ስም ተጠቅሶ እናገኛለን።
ይህ ገላጭ ቃል ለሰው ወይም ለግዑዝ ነገር ሊውል ይችላል። በዕብራይስጡ አዲስ ሀሳብ ለመግለጽ ወይም አዲስ ሀሳብ መኖሩን ለማሳየት ወይም ዕውቅና ለመስጠት የሚጠቀሙበት ነው።
“ራስህን ቀድስ” ወይም “ራስህን ለእግዚአብሔር ለይ” የሚል ነው
ይህ አባባል ሁለት ትርጉሞች ይኖሩታል፦ 1) የአባትህ 2) ቅድሜ አያትህ የሚል ሊሆን ይችላል። በዚህ ክፍል ትርጉሙ “ቅድሜ አያትህ” የሚል ከሆነ የአብርሃም፥ የይስሃቅ እና የያዕቆብ አምላክ የሚለው ትክክለኛ ትርጉም መሆኑ ነው። “አባትህ” የሚለው ከሆነ “የሙሴ አባት” መሆኑ ነው።
እስራኤላውያን ከባድ ሥራ እንዲሰሩ የሚያስገድዱ የግብጽ “አሰሪ አለቆች” ወይም “አሠሪዎቻቸው” ማለት ነው። ከምዕራፍ 1፡11 ጋር ተመሳሳይነት አለው።
ይህ ሐረግ በግነታዊ እና በተለዋጭ ዘይቤ የተገለጸ ነው። ይህ አገላለጽ ከምድሪቱ ወተትና ማር ይፈልቃል ማለት ሳይሆን ለከብት ርባታና ለእርሻ በጣም ምቹ የሆነ ምድር እንደሆነ ለማሳየት ነው። እንዲሁም “የምታፈስ” አገር የሚለው ቃልም ሁሉም ነገር የሞላባት ምድር የሚል ፍቺ ያለው ነው።
በእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ የዳበረች አገር መሆኑዋን ለማመልከት ነው
በእስራኤል ምድር ማር በሁለት መንገዶች ይመረታል። አንደኛው ከከብት እርባታ የሚገኘው ሲሆን ሁለተኛው ከተምር ዛፍና ከሌሎች ዕጽዋት የሚገኘው ነው።
እዚህ ጋር ጩኸታቸው ወደ እኔ ደርሷል ሲል ጩኸት እጅና እግር አውጥቶ እንደተራመደ አድርጎ ያቀርባል። ይህ በሰውኛ ዘይቤ የቀረበ ሲሆን “እግዚአብሔር የእስራኤል ሰዎች ጩኸት ሰምቷል” የሚል ነው።
ሙሴ ይህን ጥያቄ እግዚአብሔርን ሲጠይቅ እርሱ ደካማ ሰው መሆኑንና ማንም ሰው እርሱ የሚለውን አይሰማም ብሎ በማሰቡ ነበር። በመደበኛ ንግግር “እኔ ወደ ፈርዖን ለመሄድና የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ለማውጣት በቁ ሰው አይደለሁም” ማለቱ ነው።
ስሙ ማን እንደሆነ ሙሴ ለጠየቀው ጥያቄ እግዚአብሔር ሲመልስ እኔ “ያለሁና የምኖር ነኝ” ስለሆንኩ ስሙ “ ‘እኔ ነኝ’ የሆነ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል” ብለህ ንገራቸው አለው።
የዚህ ሀረግ አገላለጽ በሁለት መንገድ ልተረጎም ይችላል። 1) “ያለና የሚኖር ነኝ” የሚለው ሀረግ ስሙ ሊሆን ይችላል፤ 2) እግዚአብሔር ስሙን ሳይሆን ማንነቱን ለሙሴ እየነገረው ሊሆን ይችላል። ስለሆነም እግዚአብሔር ዘላለማዊ ስለሆነ ትናንት የነበረ፥ ዛሬም ያለና ነገም የሚኖር አምላክ ነው።
ይህ ስም ለትርጉም አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል “እኔ ሕያው ነኝ” በሚል ልተረጎም ይችላል።
እነዚህ ሶስቱ ሰዎች የሙሴ ቅድሜ አያቶች ናቸው፥ እንዲሁም የእስራኤላውያንም ቅድሜ አያቶች ናቸው።
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ቀድሞ እንዳያቸውና እንደተመለከታቸው እንዲሁም እንደጎበኝቸው ይሳያል።
“እነርሱ” የተባለው የእስራኤል ሽማግሌዎች ሲሆኑ “ቃልህን” የተባለው ደግሞ ሙሴ የሚናገረውን ቃል እንደሚሰሙ ለማመልከት ነው።
“በጽኑ እጅ” ምትካዊ ዘይቤ ሲሆን የሀይል ምንጭ የሆነውንና የእጁን ባለቤት አመልካች ነው። የዚህ ሀረግ ሁለቱ ፍቺዎች፦ 1) ፈርዖን ምንም ለማድረግ አቅም እንደለሌው 2) ፈርዖን እንዲለቅ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ብቻ መሆኑን ለማመልከት ነው።
እግዚአብሔር በታላቅ ሀይሉ ሲያጠቃው ወይም ሲያስገድደው እንደ ማለት ነው። እኔ እጄን እዘረጋለሁ ሲል “ሀይሌን እገልጣለሁ” ማለቱ ነው።
የዚህ ሀረግ ተቃራኒ ሀሳቡ ብዙ ነገሮችን ይዛችሁ፤ ውድና ያጌጡ ነገሮችን አግኝታችሁ በሙላት ትሄዳላችሁ ማለት ነው። የአገላለጹ ምክንያት ትኩረት ለመስጠት ነው።
ይህ አባባል 1) በእስራኤላዊት ጎረበት ከምትገኘው ከግብጻዊት ሴት፤ 2) በእስራኤላዊት ጎረበት የምትገኘው ቤት ከምትኖር ሴት ማለት ሊሆን ይችላል።
1 ሙሴም መልሶ፣ «ባያምኑኝስ ወይም ባይሰሙኝ ነገር ግን በምትኩ፣ እግዚአብሔር አልተገለጠልህም» ቢሉኝስ? 2 እግዚአብሔር ሙሴን፣ «በእጅህ ያለው ምንድን ነው?» አለው፡፡ ሙሴም «በትር» አለ፡፡ 3 እግዚአብሔር፣ «መሬት ላይ ጣለው» አለው፡፡ ሙሴም በትሩን መሬት ላይ ጣለው፤ በትሩም እባብ ሆነ፡፡ ሙሴ ከእባቡ ሸሸ፡፡ 4 እግዚአብሔር ሙሴን፣ «እጅህን ዘርግተህ የእባቡን ጅራት ያዝ» አለው፡፡ ሙሴም እጁን ዘረገና እባቡን ያዘው፡፡ እባቡ በእጁ ላይ እንደ ገና በትር ሆነ፡፡ 5 «ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር የተገለጠልህ መሆኑን እነዲያምኑ ነው፡፡» 6 ደግሞም እግዚአብሔር ሙሴን፣ «እጅህን በብትህ ውስጥ አግባ» አለው፡፡ እጁን ሲያወጣው እነሆ፣ እንደ በረዶ ነጽቶ ለምጽ ሆኖአል፡፡ 7 እግዚአብሔር፣ «እጅህን እንደ ገና በብብትህ ውስጥ አግባ» አለው፡፡ ሙሴም እጁን በብብቱ ውስጥ አገባ፣ ከብብቱ ሲወጣውም እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆኖ አየው፡፡ 8 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ «ባያምኑህ፣ የመጀመሪያውን የተአምር ምልክት ባይቀበሉ ወይም ባያምኑበት፣ ሁለተኛውን ያምናሉ፡፡ 9 እነዚህን ሁለት የተአምር ምልክቶች ባያምኑም እንኳ፣ ወይም ባይሰሙህ፣ ከወንዙ ጥቂት ውሀ ወስደህ በደረቁ መሬት ላይ አፍስሰው፡፡ ያፈሰስኸውም ውሀ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል፡፡» 10 እግዚአብሔርን፣ «ጌታ ሆይ፣ በፊትም፣ አንተ ለባሪያህ ከተናገርህ ወዲህም ርቱዕ አንደበት ያለኝ አይደለሁም፡፡ ኮልታፋና ንግግር የማልችል ሰው ነኝ» አለው፡፡ 11 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የሰውን አንደበት የፈጠረ ማን ነው? ሰውን ዲዳ ወይም ደንቈሮ ወይም እንዲያይ ወይም እንዲታወር የሚያደርግስ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለምን? 12 አሁን ሂድ፤ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፤ ምን እንደምትናገርም አስተምርሃለሁ፡፡» 13 ሙሴ ግን፣ «ጌታ ሆይ፣ እባክህ ልትልከው የምትፈልገውን ሌላ ሰው ላክ» አለ፡፡ 14 በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ተቈጣው፡፡ እንዲህም አለው፤ «ሌዋዊው ወንድምህ አሮንስ? እርሱ በሚገባ መናገር እንደሚችል ዐውቃለሁ፡፡ እንዲያውም ከአንተ ጋር ለመገናኘት እየመጣ ነውና ሲያይህ በልቡ ደስ ይሰኛል፡፡ 15 አንተ ለእርሱ ትናገራለህ፤ የሚናገራቸውንም ቃላት በአፉ ውስጥ ታስቀምጣለህ፡፡ እኔ በአፍህና በአፉ እሆናለሁ፣ ምን እነደምታደርጉም አሳያችኋለሁ፡፡ 16 ለሕዝቡ ይናገርልሃል፡፡ እርሱ የአንተ አፍ ይሆናል፤ አንተም ለእርሱ እንደ እኔ፣ አምላክ ትሆነዋህ፡፡ 17 ይህን በትር በእጅህ ትይዛለህ፣ በእርሱም ተአምራትን ታደርጋለህ፡፡» 18 ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የቶር ተመልሶ ሄደ፤ «ግብፅ ውስጥ ወዳሉት ዘመዶቼ ተመልሼ እንድሄድና አሁንም ድረስ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ» አለው፡፡ ዮቶርም ሙሴን፣ «በሰላም ሂድ» አለው፡፡ 19 ምድያም ውስጥ እያለ እግዚአብሔር «ሂድ፣ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ ሊገድሉህ የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ሞተዋል» አለው፡፡ 20 መሴም ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ፣ በአህያ ላይም አስቀምጦ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ የእግዚአብሔርን በትርም በእጁ ይዞ ነበር፡፡ 21 ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ወደ ግብፅ ተመልሰህ ስትሄድ፣ በእጅህ ያስቀመጥኋቸውን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት እንደምታደርግ ዐስብ፡፡ ነገር ግን እኔ ልቡን አደነድነዋለሁ፤ ሕዝቡ እንዲሄዱም አይፈቅድም፡፡ 22 እንዲህ ብለህ ንገረው፤ «እግዚአብሔር እየተናገረ ያለው ይህን ነው፤ እስራኤል ልጄ፣ በኵሬ ነው፤ 23 «እንዲያመልከኝ ልጄን ልቀቅ ብዬ እነግርሃለሁ፡፡» ነገር ግን ለመልቀቅ እምቢ ስላለህ፣ በኵር ልጅህን እገድላለሁ፡፡» 24 ላይ ለምሽቱ ዐርፈው ሳለ፣ እግዚአብሔር ሙሴን አግንኝቶ ሊገድለው ነበር፡፡ 25 ግን ስለታም ቢላዋ ይዛ የልጇን ሸለፈት ገረዘች፤ እግሩንም አስነካችው፡፡ ከዚያም በኋላ «አንተ ለእኔ በእውነት የደም ሙሽራዬ ነህ» አለች፡፡ 26 እግዚአብሔር ሙሴን ተወው፡፡ «አንተ የደም ሙሽራ ነህ» ብላ የተናገረችው በግርዘቱ ምክንያት ነው፡፡ 27 አሮንን፣ «ወደ ምድረ በዳ ሂድና ከሙሴ ጋር ተገናኝ» አለው፡፡ አሮን ሄደ፣ ሙሴንም በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አግኝቶ ሳመው፡፡ 28 እንዲናገር የላከለትን የእግዚአብሔር ቃሎች ሁሉና እንዲፈጽማቸው ያዘዘውን ተአምራት በሙሉ ለአሮን ነገረው፡፡ 29 በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ፡፡ 30 እግዚአብሔር ተአምራትም በሕዝቡ ፊት አሳየ፡፡ 31 አመኑ፡፡ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን የጐበኛቸውና የደረሰባቸውን ጭቈና የተመለከተ መሆኑን ሲሰሙም ሰገዱ፣ አመለኩትም፡፡
ምንም እንኳን ሙሴ በእግዚአብሔር (በያህዌ) ብያምንም በእርሱ አልታመነም። ይህ የሚያሳየው ሙሴ የእግዚአብሔርን ማንነት ያለመረዳቱን ያሳያል። ሙሴ የተረዳው እርሱ እንዲያደርግ የተጠየቃቸው ነገሮች በእርሱ ሀይል የሚሆኑ መስሎት ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር እየጠየቀ ያለው “በእርሱ እንዲታመንና ሀይሉን እንዲያስተውል ነው።
እጅህን ዘርጋና ጅራቷን ይዘህ አንሣት
ሙሴም እጁን ዘርግቶ ሲይዛት እባቧ ተለውጣ በእጁ ላይ እንደ ገና በትር ሆነች ማለት ነው
በዚህ ክፍል የዚህ ቃል ጥቅም ቃለ አጋኖ ለመፍጠር እና መደነቅን ለማሳየት ነው
እንደ በረዶ ነጭ ሆነ የሚል ሲሆን ተነጻጻሪ ዘይቤ ነው
ይህ ወንዝ የአባይ ወንዝ ወይም በእንግሊዘኛው ናይል ወንዝ የሚንለው ነው።
ደህና አድርጎ መናገር የማይችል ወይም አንደበቴ ርቱዕ ያልሆነ ሰው ማለት ነው
አንደበቱ የሚኮላተፍና አጥርቶ መናገር የማይችል ሰው ማለት ነው። ሙሴ ይህን የተናገረው አጥርቶ መናገር የማይችል ሰው መሆኑን ለመግለጽ ሲፈልግ ነው።
ኮልታፋና ተናግሮ ለማሳመን አቅም የሚያንሰው መሆኑን ያሳያል (ምትካዊ ዘይቤ)
እግዚአብሔር (ያህዌ) ይህን ጥያቄ ሲጠይቅ ሰዎች መናገር እንዲችሉ አድርጎ የፈጠረውና ለመናገርም አፍ የፈጠረው እርሱ ራሱ መሆኑን ለማጽናት ፈልጎ ነው (አጋናኝ ዘይቤ)
እግዚአብሔር (ያህዌ) ይህን ጥያቄ የጠየቀው ሰዎች መናገርና መስማት እንዲችሉ የሚያደርገው ራሱ እንደሆነ ለማሳየት ነው (አጋናኝ ጥያቄ)
እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ ሲጠይቅ ሁሉን ነገር የሚወስነው ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ለማጽናት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? (አጋናኝ ጥያቄ) ወይም ይህን ሁሉ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
“አፍ” የሚለው ቃል የሙሴ የመናገር ችሎታውን ለማሳየት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “የመናገር ችሎታ ለአንተ እሰጣለሁኝ” ወይም “መናገር እንድትችል አደርጋለሁ”
“ቁጣ” እንደ እሳት የመንደድ ባህርይ እንዳለው ተደርጎ የቀረበው ተለዋጭ ዘይቤ ነው። እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ ላይ እጅግ ተቆጣ።
ሌዋዊ የሆነው ወንድምህ አሮን/ከሌዊ ነገድ የሆነው ወንድምህ አሮን
“በልቡ” የሚለው ቃል የአንድ ሰው ውስጣዊ ሀሳቡንና ስሜቱን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፡ አንተን በሚያይበት ጊዜ በጣም ደስ ይለዋል (ምትካዊ ዘይቤ)
ቃሉን በአፉ ታደርገዋል የሚለው ሀረግ አንድን ነገር በአንድ ሰው አፍ ውስጥ እንደማኖር/እንደማስቀመጥ ይታይ ይሆናል። አማራጭ ትርጉም፦ “እርሱ መናገር ያለበትን መልዕክት ይሰጠዋል/ያቀርብለታል”
ከ “አፍህና ከአፉ” ጋር የሚሉ ቃላት የሚያሳዩት ሁለቱም የሚጠቀሙትን የቃላት ምርጫና አጠቃቀም ይመለከታል። ሙሴና አሮን መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ ተገቢ የሆነ ቃላት ይመርጣሉ ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ መልዕክታችሁን ለማስተላለፍ የሚያስችላችሁን ተገቢ ቃል እሰጣችኋለሁ (ምትካዊ ዘይቤ)
ይህ አባባል የሚያሳየን አሮን የሚናገረው ሙሴ የተናገረውን መልዕክት መሆኑን ነው።
እግዚአብሔር በሙሴ ላይ እንዳለው ዓይነት ሥልጣን ሙሴ በአሮን ላይ ይኖረዋል ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “እንተ ለአሮን ሲትናገር እኔ እግዚአብሔር ለአንተ (ለሙሴ) በተናገረው ስልጣን ለአሮን ትናገራለህ”
ሙሴ ወደ ሚስቱ አባት ወይም ወደ አማቹ ወደ ዮቶር ተመለሰ ማለት ነው
እኔ ልቡን አጸናዋለሁ ማለት አበረታታዋለሁ ወይም ድፍረት እሰጠዋለሁ ማለት ሳይሆን ልቡን አደነድነዋለሁ፥ አመጸኛ አደርገዋለሁ፥ እንዳይታዘዝና እንዳይሰማ አደርገዋለሁ ማለት ነው (ምትካዊና ንጽጽራዊ ዘይቤ)።
እስራኤል የሚለው ቃል መላውን የእስራኤል ህዝብ የሚወክል ቃል ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “የእስራኤል ህዝብ የእኔ ልጆች” ናቸው።
የእስራኤል ህዝብ የእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ሳይሆን ደስታና ኩራት የሆነ የእግዚአብሔር ልጅ ነው (ተለዋጭ ዘይቤ)።
የዚህ ትርጉም በትክክል ባይታወቅም ምናልባት ሙሴ ልጁን ባለመገረዙ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
የሙሴ ሚስት ስሟ ሲፖራ ወይም በዕብራይስጡ ጽፖራ ነው።
የተፈጥሮ ስለት ያለው ለመቁረጥ የሚያገለግል የባልጩት ድንጋይ
ይህ “ወደ እግሩም ጣለችው” የሚለው ሀረግ ሁለት ዋና ዋና የትርጉም አመለካከቶች አሉት። 1) ልጁ መገረዙን ለማመልከት በእግሩ ላይ የደም ምልክት እንድኖር ስትፈልግ እናቱ የቆረጠችውን ሸለፈት በልጁ እግር ላይ መጣሏን፤ 2) “እግር” የሚለው ቃል በእስራኤላውያን ዘንድ የአይነኬ ዘይቤ አገላለጽ በመሆኑ ወደ ሙሴ የመዋለጃ ብልት ላይ ጣለችው የሚል አመለካከትም አለው።
የዚህ ሀረግ ፍቺው ወይም መልዕክት ግልጽ አይደለም። እንደዚህ ዓይነት ንግግር በጊዜው በእስራኤል ታሪክ የሚታወቅ ልሆን ይችላል። አማራጭ ትርጉም፦ “በዚህ ደም ምክንያት አንተ ከእኔ ጋር ግንኙነት አለ” ወይም “በዚህ ደም ምክንያት አንተ ለእኔ ባሌ ነህ”
በዚህ ክፍል የታሪኩን አዲስ ጀማሮ ለማመልከት የሚረዳ አንድ አገናኝ ቃል መጠቀም ጥሩ ነው። ለምሳሌ፦ “በዚህን ጊዜ” ብሎ መቀጠል ይቻላል።
ይህ በሲና የሚገኘው ተራራ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በትክክል የትኛው ተራራ እንደሆነ አይናገርም።
በእርሱ ዘንድ የሚለው ቃል በሙሴ በኩል የሚለውን ፍቺ ይይዛል።
እግዚአብሔር እስርኤላውያንን አየ ወይም ለእነርሱ አሰበ የሚል ነው።
ተንበርክከው ሰገዱ የሚል ነው
1 እነዚህ ነገሮች ከሆኑ በኋላ፣ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ እንደዚህ አሉ፤ «የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹በምድረ በዳው ለእኔ በዓል እንዲያደርጉ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡»› 2 ፈርዖንም፣ «እግዚአብሔር ማን ነው? ቃሉን የምሰማው፣ እስራኤልንስ የምለቅ ለምንድን ነው? እግዚአብሔርን አላውቀውም፤ እስራኤልንም አልለቅም» አለ፡፡ 3 ሙሴና አሮንም፣ «የዕብራውያን አምላክ ከእኛ ጋር ተገናኝቶአል፡፡ በመቅሠፍትና በሰይፍ እንዳይመታን፣ ወደ ምድረ በዳው የሦስት ቀን ጕዞ እንድናደርግና ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ ፍቀድልን» አሉት፡፡ 4 የግብፅ ንጉሥ ግን፣ «አንተ ሙሴ አንተም አሮን! ሕዝቡን ሥራቸውን አስፈትታችሁ የምትወስዷቸው ለምንድን ነው? ወደ ሥራችሁ ሂዱ» አላቸው፡፡ 5 እንዲህ አላቸው፤ «በምድራችን አሁን ብዙ ዕብራውያን አሉ፤ እናንተም ሥራ ታስፈቷቸዋላችሁ፡፡» 6 በዚያው ቀን ፈርዖን ለሕዝቡ አሠሪዎችና ተቈጣጣሪዎች ትእዛዝ ሰጠ፡፡ እንዲህም አለ፤ 7 «እንደ ቀድሞው፣ ከእንግዲህ ወዲያ ለሸክላ ሥራ ጭድ አታቅርቡ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ይሂዱና ጭድ ይሰብስቡ፡፡ 8 ሆኖም በፊት የሚሠሩትን አንድ ዐይነት የሸክላ ቊጥር አሁንም ሠርተው እንዲያቀርቡ ማድረግ አለባችሁ፡፡ ከዚያ ያነሰ አትቀበሉ፤ ምክንያቱም ሰነፎች ናቸው፡፡ ‹እንሂድ ፍቀድልንና ለአምላካችን እንሠዋ› እያሉ የሚጮኹትም ለዚህ ነው፡፡ 9 እንዲተጉና ለማይረባ ንግግር ትኵረት እንዳይሰጡ ሥራውን ጨምራችሁ አክብዱባቸው፡፡» 10 ስለዚህ የሕዝቡ አሠሪ አለቆችና ተቈጣጣሪዎች ወጥተው ሄዱ፤ ለሕዝቡም ነገሯቸው፡፡ እንዲህም አሉ፤ «ፈርዖን የሚለው ይህ ነው፡- ‹ከእንግዲህ ወዲያ ምንም ጭድ አልሰጣችሁም፡፡ 11 ሂዱና ማግኘት ከምትችሉበት ፈልጋችሁ አምጡ፤ የሥራችሁ መጠንም አይቀላለም፡፡» 12 ሕዝቡ በጭድ ፈንታ ገለባ ለመሰብሰብ በግብፅ ምድር ሁሉ ተሠራጩ፡፡ 13 አለቆቹ፣ «ጭድ በሚቀርብላችሁ ጊዜ የምትሠሩትን ሥራችሁን ጨርሱ» ይሏቸውና ያስጠነቅቋቸው ነበር፡፡» 14 ፈርዖን የመደባቸው አሠሪ አለቆች የሠራተኞች ተቈጣጣሪ ያደረጓቸውን እስራኤላውያን ኀላፊዎች ገረፏቸው፡፡ አሠሪ አለቆቹ፣ «በፊት ታደርጉት እንደ ነበረው፣ ትናንትናም ዛሬም የሚጠበቅባችሁን ሸክላ በሙሉ ሠርታችሁ ያላቀረባችሁ ለምንድን ነው?» እያሉ ይጠይቋቸው ነበር፡፡ 15 እስራኤላውያን ተቈጣጣሪዎቹም ወደ ፈርዖን መጥተው አቤቱታ አቀረቡ፡፡ እንደዚህም አሉት፤ «ባሪያዎችህን በዚህ መንገድ ለምን እንድንኖር ታደርጋለህ? 16 ጭድ አይሰጡንም፤ ነገር ግን አሁንም ‹ሸክላ ሥሩ!› ይሉናል፡፡ እኛ ባሪያዎችህ ተገርፈናልም፤ ስሕተቱ ግን የገዛ ሕዝብህ ነው፡፡» 17 ግን እንዲህ አለ፤ «እናንተ ሰነፎች! እናንተ ሰነፎች! ‹ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ ፍቀድልን› ትላላችሁ፡፡ 18 ወደ ሥራ ተመለሱ፡፡ አንዳችም ጭድ አይሰጣችሁም፤ ነገር ግን አሁንም ያንኑ የሸክላ ቊጥር መሥራት አለባችሁ፡፡» 19 «የየቀኑን የሸክላ ቊጥር መቀነስ የለባችሁም» የሚለው ሲነገራቸው፣ እስራኤላውያን ተቈጣጣሪዎች ችግር ውስጥ እንደ ነበሩ አስተዋሉ፡፡ 20 ከፈርዖን ዘንድ ሲወጡ፣ ከቤተ መንግሥቱ ውጭ ቆመው ከነበሩት ከሙሴና ከአሮን ጋር ተገናኙ፡፡ 21 ለሙሴና ለአሮንም እንዲህ አሏቸው፣ «እግዚአብሔር ይይላችሁ፣ ይፍረድባችሁም፤ ምክንያቱም በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት አስጸያፊዎች እንድንሆን አድርጋችሁናል፡፡» 22 ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፣ «ጌታ ሆይ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ እንዲደርስበት ያደረግህ ለምንድን ነው? እኔንስ ቀድሞውኑ ለምን ላክኸኝ? 23 ስም ልነግረው ወደ ፈርዖን ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ አምጥቶአል፤ አንተም ሕዝብህን ከቶ ነጻ አላወጣኸውም» አለው፡፡
በትረካ ውስጥ “ከዚህ በኋላ” የሚለው አገናኝ ሀረግ አንድ ዋና ሀሳብ ከተነገረ በኋላ ቀጣይ የትረካው አካል መከተሉን ያመለክታል። ይሁን እንጂ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ተመልሰው ለመሄድ ምን ያህል ጊዜ እንደወሰደባቸው ግልጽ አይደለም።
እግዚአብሔርን በማምለክ የአግዚአብሔር በዓል እንዲያደርጉ ወይም እንዲያከብሩ ማለት ነው
ይህ አጋናኝ ጥያቄ የሚያሳየው ፈርዖን እግዚአብሔር እውነተኛ እና ልታወቅ የሚገባ አምላክ መሆኑን ለማወቅ አለመፈለጉን ወይም አለማወቁን አመልካች ነው። በመደበኛ ዐረፍተ ነገር ሲጻፍ፦ እግዚአብሔር (ያህዌ) ማን እንደሆነ አላውቅም ማለቱ ነው።
የእርሱን ድምጽ/ትዕዛዝ ሰምቼ የሚለው እግዚአብሔር የሚናገረውን ቃል ሰምቼ የሚል ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እርሱ/እግዚአብሔር የሚለውን ሰምቼ
ይህ ቃል “የእስራኤላውያን አምላክ ወይም ያህዌ” የሚለውን የሚገልጽ ነው
ይህ ሀረግ እግዚአብሔር በሽታ ሲልክብን ወይም ጦርነት ሲያስነሳብን ወይም ጠላት ሲልክብን ማለት ነው።
ፈርዖን ይህን አጋናኝ ጥያቄ ሙሴንና አሮንን ሲጠይቅ እስራኤላውያን ሥራ እንዳይሰሩ እያደረጉ ነው ብሎ ስላሰበና በእነርሱ ላይ መቆጣቱን ለመግለጽ ነው። እማራጭ ትርጉም፦ “ህዝቡ ሥራ እንዳይሰራ አታደርጉ ወይም ሥራ አትከለክሉ ወይም ሥራ አታስፈቱ”
ግብጻውያን አሠሪዎችና የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆችን የሚመለከት ነው
ይህን እንዳያደርጉ የተነገራቸው አስገባሪዎችና ሹማምቶችን ነው። “አትስጡ” የሚለው የወል ስም ስለሆነ አሰሪ አለቆችን ይመለከታል።
ግብጻውያን አሠሪዎችና የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆችን የሚመለከት ነው (ዘጸአት 1፡11 ተመለከት)
“አልሰጣችሁም” ሲል ለእናንተ የሚለውን የወል ስም የሚገልጽ ሲሆን እስራኤላውያንን የሚመለከት ነው።
ግብጻውያን ገለባ በመሰብሰብ ሥራ እስራኤላውያንን አያግዙአችሁም ማለት ነው። ራሳቸው ለገለባ ፍለጋ ይሄዳሉ ማለት ነው።
ይህን አገላለጽ በሌላ መልክ ሲገለጽ፦ ከዚህ በፊት በምትሰሩት ጡብ ልክ ሥራችሁን ሰርታችሁ ታቀርባላችሁ ማለት ነው።
የተሰጣቸውን ወይም የተጣለባቸውን ሥራ ለመስራት እስራኤላውያን በግብጽ ምድር መሰራጨታቸውን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፦ በግብጽ ምድር በሁሉም አከባቢዎች እስራኤላውያን ተበተኑ። (ግነታዊና ጥቅል ዘይቤያዊ አነጋገር ተመልከት)
የስንዴ፥ የገብስ፥ የጤፍ፥ እና የመሳሰሉት የሰብል ዓይነቶች ከአጨዳ ወይም ከውቂያ በኋላ የቀረው ክፍል ነው።
ግብጻውያን አሠሪዎችና የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆችን የሚመለከት ነው (ዘጸአት 1፡11 ተመለከት)
ግብጻውያን አሰሪዎቻቸው ይህን ጥያቄ እስራኤላውያንን የጠየቁት የምጠበቅባቸውን ጡብ ሰርተው ለማቅረብ ባለመቻላቸው ተቆጥተውባቸው ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ከዚህ ከደም እንደምታደርጉት ትናንትም ይሁን ዛሬ የሚጠበቅባችሁን ጡብ ሰርታችሁ ማቅረብ አልቻላችሁም (አጋናኝ ጥያቄ)።
ጥፋቱ ወይም ስህተቱ የገዛ ሰዎችህ ነው እንጂ የእኛ አይደለም ብለው አቤቱታ አቀረቡ
“ያዝዙናል” የሚለው ቃል ግብጻውያን አሰሪዎችን የሚመለከት ነው
ምክንያቱም እናንተ (ሙሴና አሮን) በንጉሡ በፈርዖንና በመኳንንቱ ዘንድ እጅግ እንድንጠላ አድርጋችሁናል (ተለዋጭ ዘይቤ)
ምክንያቱም እነርሱ እኛን እንዲገድሉ ምክንያት በመሆናችሁ ሰይፍን በእጃቸው ሰጥታችኋቸዋል። ሰይፍ የሚወከለው ያጠፉአቸው ዘንድ ምቹ አጋጣሚ መፈጠሩን ለማመልከት ነው።
ይህ አጋናኝ ጥያቄ የሚመለከተው ሙሴ በእስራሴላውያን መበደልና ርህራሄ የለሽ ተግባራቸው የተከፋ መሆኑን ያሳያል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር ሆይ በእስራኤላውያን ላይ በደረሰው ነገር በጣም አዝናለሁ
ሙሴ እስራኤላውያንን ነጻ እንዲያወጣ በመላኩ ማዘኑን የሚያመለክት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ወደዚህ ስፍራ ባትልከኝ እመርጥ ነበር።
“በስምህ” የሚለው የእግዚአብሔር መልዕክት ለማማመልከት ነው
1 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን፣ «በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ይለቃቸዋልና፣ ይህን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ከምድሩ ያስወጣቸዋል» አለው፡፡ 2 ለሙሴ እንዲህ አለው፤ «እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ 3 እኔ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን በስሜ፣ በእግዚአብሔር ለእነርሱ አልታወቅሁላቸውም ነበር፡፡ 4 የተሰደዱባትን፣ በእንግድነት የኖሩባትን የከነዓንን ምድር ልሰጣቸው፣ ከእነርሱ ጋር ኪዳን አጽንቻለሁ፡፡ 5 ደግሞም ግብፃውያን ባሪያ ያደረጓቸውን የአስራኤላውያንን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ፡፡ 6 ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ በግብፃውያን ሥር ከምትኖሩባት ባርነት እታደጋችኋለሁ፤ ከአገዛዛቸውም ነፃ አወጣችኋለሁ፡፡ በታላቅ ፍርድና ኀይሌን በማሳየት እታደጋችኋለሁ፡፡ 7 አድርጌ ወደ ራሴ እወስዳችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፡፡ ግብፃውያን ከጫኑባችሁ ባርነት ነፃ ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡ 8 ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ልሰጥ ቃል ወደገባሁባት ምድር አስገባችኋለሁ፡፡ ምድሪቱን ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡» 9 ይህን ለእስራኤላውያን በነገራቸው ጊዜ፣ በአስከፊው ባርነታቸው ተስፋ ከመቊረጣቸው የተነሣ አላደመጡትም፡፡ 10 ሙሴን እንዲህ አለው፤ 11 ሂድና ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን የእስራኤልን ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቅ ንገረው፡፡ 12 ሙሴም እግዚአብሔርን፣ «ተብታባ በመሆኔ እስራኤላውያን ካልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል? 13 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አናገራቸው፡፡ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር እንዲያስወጡ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖንና ስለ እስራኤላውያንም ትእዛዝ ሰጣቸው፡፡ 14 የአባቶቻቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል በኵር ልጅ የሮቤል ልጆች ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮንና ከርሚ ነበሩ፡፡ እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው፡፡ 15 የስምዖን ልጆች ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ዱሐርና የከነዓናዊቷ ሴት ልጅ ሳኡል ነበሩ፡፡ እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው፡፡ 16 የሌዊ ልጆች ስሞች ከትውልዶቻቸው ጋር እነዚህ ናቸው፤ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ነበሩ፡፡ ሌዊ መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፡፡ 17 የጌድሶን ልጆች ሉቤኒና ሰሜኢ ነበሩ፡፡ 18 የቀዓት ልጆች እንበረም፣ ይሰዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፡፡ ቀዓት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ኖረ፡፡ 19 የሜራሪ ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ፡፡ እነዚህ በትውልዶቻቸው መሠረት፣ የሌዋውያን የነገድ አባቶች ሆኑ፡፡ 20 የአባቱን እኅት ዮካብድን አገባ፤ እርሷምአሮንንና ሙሴን ወለደችለት፡፡ እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖሮ ሞተ፡፡ 21 የይስዓር ልጆች ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ፡፡ 22 ልጆች ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ፡፡ 23 የአሚካዳብን ልጅ፣ የነኦሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፡፡ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢተምርን ወለደችለት፡፡ 24 የቆሬ ልጆች አሴር፣ ሕልቃናና አብያሳፍ ነበሩ፡፡ እነዚህ የቆሬ ነገድ አባቶች ናቸው፡፡ 25 ልጅ አልዓር ከፏትኤል ልጆች አንዲቱን አገባ፡፡ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት፡፡ እነዚህ በየትውልዶቻቸው የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናቸው፡፡ 26 ሁለት ሰዎች፣ «እስራኤላውያንን በየተዋጊ ሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አውጡ» ብሎ እግዚአብሔር ያዘዛቸው አሮንና ሙሴ ነበሩ፡፡ 27 ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ለማውጣት እንዲፈቅድላቸው ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ተናገሩ፡፡ እነዚህ ሙሴና አሮን እነዚያው ራሳቸው ነበሩ፡፡ 28 እግዚአብሔር በግብፅ ውስጥ ሙሴን ባናገረው ጊዜ፣ 29 «እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው» አለው፡፡ 30 ግን እግዚአብሔርን፣ «እኔ ተብታባ ነኝ፤ ፈርዖን ታዲያ እንዴት ይሰማኛል? አለው፡፡
“የጸናች እጅ” የፈርዖን እጅ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሀይል ለማመልከት ነው። “እጅ” ምትካዊ ዘይቤ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ሀይል ይመለከታል። አማራጭ ትርጉም፦ “በእግዚአብሔር ሀይል ይለቃቸዋል፤ በሀይሌም ከምድርቱ አስወጥቶ ይሰዳቸዋል”
እኔ ራሴን ለአብርሃም፥ ለይስሃቅና ለያዕቆብ አሳየሁ
ነገር ግን ያህዌ በሚለው ስሜ አላወቁኝም
በአማርኛው ቅጅ “ለቅሶ” የሚለው ቃል በዕብራይስጡ ለቅሶ ሳይሆን “ጭንቀትን፥ ሰቆቃን፥ ማቃሰትን፥ መቃተትን” የሚመለከት ነው።
ትዕዛዛዊ ንግግር ነው፤ ሙሴ ለእስራኤላውያን እንድነግራቸው ያህዌ ሙሴን ሲያዘው ያሳየናል።
ግብጻውያንን በመቅጣት ወይም በመምታትና ለእስራኤላውያን እውነተኛ ፍርድ በማምጣት ነጻ አወጣችኋለሁ። “የተዘረጋች ክንድ” የሚለው ሀረግ ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ግብጻውያንን እቀጣለሁ ወይም እፈርድባቸዋለሁ” ማለት ነው።
ተስፋ ወደ ገባሁላቸው ምድር አስገባቸዋለሁ ወይም እሰጣችኋለሁ ብዬ ወደነገርኳቸው ምድር እወስዳችኋለሁ ማለት ነው።
ሙሴ ይህን ጥያቄ ሲጠይቅ ሁለት ነገሮችን ተስፋ ያደረገ ይመስላል። 1) ፈርዖን እንደማይሰማኝ ታውቃለህና አታስቸግረኝ ማለቱ ነው 2) እግዚአብሔር የቀድሞ ሀሳቡን ቀይሮ ሙሴን እንዲለቀውና በሙሴ በኩል ልፈጽም ያሰበውን ሀሳብ እንድተው መጠየቁ ነበር። ለዚህ ምክንያት አድርጎ ያቀረበው “እኔ አጥርቼ መናገር የማልችል ኮልታፋ ነኝ” በማለት ነበር። አማራጭ ትርጉም፦ “እስራኤላውያን እስካላመኑ ድረስ ፈርዖንም አያምነኝም”
የየቤተሰቡ ወይም የየነገድ አለቆች። አማራጭ ትርጉም፦ “የአያቶቻቸው አለቆች ወይም መሪዎች”
የወንዶች ስም ሲሆን የየነገድ ወይም ቅድመ አያቶቻቸው ስም ዝርዝር ነው። ከቁጥር 14-25 ድረስ ባለው ከፍል የተጠቀሱትን የዕብራይስጥ ስሞችንና ቁጥሮችን የመተርጎም ዘዴዎችን አስተውል።
“አንድን ነገድ” ወይም “አንድን ቤተሰብ” በሰልፍ ተራ በተራ መምራትን ያመለክታል። የእስራኤል ሰዎች “ሠራዊት” የተባሉት የጦር ሠራዊት ሆነው ሳይሆን “በየነገዳቸው እንደ ሠራዊት” በሰልፍ መውጣታቸውን ለማመልከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “የእስራኤልን ሕዝብ በየነገዳቸው ከግብጽ ምድር መርታችሁ አውጡ”
በዚህ አጋናኝ ጥያቄ ሙሴ የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለማስቀየር ያሰበ ይመስላል። እንዲሁም ወደ ፈርዖን ለመሄድ ካለመፈለጉም ሌላ በፈርዖን ድርጊትም ተስፋ የቆረጠ ይመስላል። አማራጭ ትርጉም፦ “እኔ የንግግር ችሎታ ስለሌለኝ ፈርዖን በርግጥ አይስማኝም”
1 ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ልብ በል፤ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አድርጌሃለሁ፡፡ ወንድምህ አሮን ነቢይህ ይሆናል፡፡ 2 እንድትናገር ያዘዝሁህን ሁሉ ትናራለህ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቀ፣ ወንድምህ አሮን ለፈርዖን ይናገራል፡፡ 3 ነገር ግን እኔ የፈርዖንን ለብ አደነድነዋሁ፤ የተአምራቴን ብዙ ምልክቶች፣ ብዙ ድንቆችም በግብፅ ምድር አሳያለሁ፡፡ 4 ነገር ግን ፈርዖን አይሰማችሁም፤ ስለዚህ እጄን በግብፅ ላይ አደርጋሁ፤ ሰራዊቱን፣ ሕዝቤን፣ የእስራኤልን ልጆች በታላቅ ፍርድ ከግብፅ ምድር አወጣለሁ፡፡ 5 በግብፅ ላይ ስዘረጋና እስራኤላውያንን ከመካከላቸው ሳወጣ፣ ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፡፡» 6 አሮን እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ፈጸሙ፡፡ 7 ባጋገሩት ጊዜ፣ የሙሴ ዕድሜ ሰማንያ፣ የአሮን ደግሞ ሰማንያ ሦስት ነበር፡፡ 8 ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ 9 ‹ተአምር አሳዩ› ሲላችሁ፣ አሮንን እንዲህ በለው፤ ‹በትርህን ውሰድና በፈርዖን ፊት ጣለው፤ እባብም ይሀናል፡፡»› 10 ሙሴ አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ እግዚአብሔር አዝዞአቸው የነበረውን አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት ጣለው፤ እባብም ሆነ፡፡ 11 ደግሞ ለጥበበኛ ሰዎቹና ለጠንቋዮቹ ጥሪ አደረገ፡፡ እነርሱም በምትሀታቸው ያንኑ አደረጉ፡፡ 12 እያንዳንዱ ሰው በትሩን ጣለ፤ በትሮቹም እባብ ሆኑ፣ ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን እባቦች ዋጣቸው፡፡ 13 አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ አልሰማምም፡፡ 14 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የፈርዖን ልብ ደንድኖአል፤ ሕዘቡም እንዲሄዱ አይፈቅድም፡፡ 15 ወደ ውሃው በሚሄድበት ጊዜ፣ በጠዋት ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እንዳገኘውም በወንዙ ዳር ቁም፤ ወደ እባብነት ተለውጦ የነበረውን በትርህን ውሰድ፡፡ 16 እንዲህ በለው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን እንድናገር ወደ አንተ ላከኝ፤ «በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፤ እስካሁን ድረስ አልሰማህም፡፡» 17 የሚናገረው ይህ ነው፤ «እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፡፡ የአባይን ወንዝ ውሀ በእጄ በያዝሁት በትር እመታዋለሁ፣ ወንዙም ወደ ደምነት ይለወጣል፡፡ 18 ውስጥ የሚገኙት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙ ይከረፋል፡፡ግብፃውያኑም ከወንዙ ውሀ መጠጣት አይችሉም፡፡» 19 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ አሮንን፣ ‹በትርህን ውሰድና ውሀቸው ደም እንዲሆን፣ በግብፅ ውሀዎች ላይ፣ በወንዞቻቸውም፣ በምንጮቻቸውም፣ በውሀ ማጠራቀሚያዎቻቸውና በኩሬዎቻቸው ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ ብለህ ንገረው፡፡ በመላው የግብፅ ምድር፣ ከዕንጨትና ከድንጋይ በተሠሩ ውሀ መያዣዎች ያለው ውሀም እንኳ ደም እንዲሆን ይህን አድርግ፡፡»› 20 ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን አንሥቶ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት የወንዙን ውሀ መታው፡፡ የወንዙ ውሀ በሙሉ ወደ ደምነት ተለወጠ፡፡ 21 ውስጥ ያለው ዓሣ ሞተ ወንዙም መከርፋት ጀመረ፡፡ ግብፃውያኑ ከወንዙ ውሀ መጠጣት አልቻም፤ ደሙም በግብፅ ምድር በየትኛውም ስፍራ ነበረ፡፡ 22 የግብፅ ጠንቋዮችም በምትሀታቸው ያንኑ ዐይነት ነገር አደረጉ፡፡ ስለዚህ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እግዚአብሔር ይሆናለ ብሎ ተናግሮት እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን ለመስማት እምቢ አለ፡፡ 23 ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ለዚህ ጉዳይ ትኵረትም እንኳ አልሰጠም፡፡ 24 ግብፃውያኑ ሁሉ በወንዙ ዙሪያ የሚጠጣ ውሀ ለማግኘት ቈፈሩ፤ ነገ ርግን የወንዙን ውሀ መጠጣት አልቻሉም፡፡ 25 እግዚአብሔር ወንዙን ከመታው በኋላ ሰባት ቀን ዐለፈ፡፡
አስተውል፤ ወይም ልብ በል፤ እኔ አንተን ለፈርኦን እንደ አምላክ አድርገሃለሁ።
“ልብ” ተብሎ በወካይ ዘይቤ የተገለጠው ራሱን ፈርዖንን ለመግለጽ ነው። የፈርዖንን ልብ ያደነደነው እግዚአብሔር ራሱ እንደሆነ ልብ ይሏል። ስለሆነም ልቡን እግዚአብሔር ስላደነደነው ፈርዖን ለመስማት አልፈለገም ወይም እምብተኛ ሆነ ማለት ነው። (ምዕራፍ 3፡21 ተመልከት)
“ድንቅና ታአምር” ሁለቱም ተመሳሳይ ወይም ቅርብ ፍቺ ያላችው ቃላት ናቸው። ታአምር ድርጊቱን ወይም ክስተቱን ሲገልጽ ድንቅ ምልክትን ወይም የክስተቱ ማረጋገጫ የሚመለከት ነው። ሁለቱም ከተፈጥሮ ክስተት ውጪ የሆኑ የእግዚአብሔር አሰራሮች ናቸው።
“እጄን” ሲል ለፍርድና ለቅጣት የተዘረጋውን የእግዚአብሔር እጅ እንጂ የማደፋፈር ወይም የማነቃቃት እጅ ማለት አይደለም። አማራጭ ትርጉም፦ ግብጻውያንን በመፍረድ ወይም በመቅጣት ታላቁን ሀይሌን አሳያቸዋለሁ”
ለሙሴ ዕድሜው ሰማንያ ዓመት ሲሆን የአሮን ዕድሜው ሰማንያ ሦስት ዓመት ነበር።
ፈርዖን እስቲ ተአምራት በማድረግ ማንነታችሁን ግለጡልኝ’ ቢላችሁ ለአሮን ንገረውና በትሩን ወስዶ በንጉሡ ፊት ይጣለው፤ በዚያን ጊዜ በትሩ ተለውጦ እባብ ይሆናል። (ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ንግግር ዕይነቶችን የመተርጎም ዘዴ ተመልከት)
ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን በትሮች ሁሉ ዋጠች።
ፈርዖን ድፍረት አገኘ ማለት ሳይሆን ፈርዖን እምቢ አለ ወይም እልከኛ ማለት ነው።
ፈርዖን ለመስማት አልፈለገም፥ እምቢተኛ ሆነ ማለት ነው
ወደ አባይ (ናይል) ወንዝ በሚወርድበት/በሚሄድበት ጊዜ
ለፈርዖን እንዲህ ብለህ ትነግረዋለህ
እነሆ፥ እኔ በዚህ በትር የአባይን ወንዝ ውሃ እመታለሁ
በግብፅ ምድር ደም በየቦታው ይሆናል
ፈርዖን ድፍረት አገኘ ማለት ሳይሆን ፈርዖን እምቢ አለ ማለት ነው።
ግልጽ ለማድረግ ከተፈለገ “በአባይ ወንዝ ውስጥ የነበሩ ዓሶች”
ብዙ ግብጻውያን ወይም የግብጽ ሰዎች ሁሉ
1 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ በለው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡ 2 ካልህ፣ አገርህን በሙሉ በጓጕንቸው መቅሠፍት እመታዋለሁ፡፡ 3 ጓጕንቸር ይርመሰመሳል፡፡ ጓጕንቸሮቹ ከወንዙ ይወጡና ወደ ቤትህ፣ ወደ መኝታ ክፍልህና ወደ ዐልጋህ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ አገልጋዮችህም ቤቶች ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ ሕዝብህ፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሃቆችም ይዛመታሉ፡፡ 4 ጓጕንቸሮቹ አንተን፣ ሕዝብህንና አገልጋዮችህን ሁሉ ይመታሉ፡፡» 5 ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «አሮንን፣ እጅህንና በትርህን በወንዞች፣ በምንጮችና በቦዮች ላይ ዘርጋና በግብፅ ምድር ላይ ጓጕንቸሮች እንዲወጡ አድርግ» በለው፡፡ 6 በግብፅ ውሆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕንቸዎቹም ወጥተው የግብፅን ምድር ሸፈኑት፡፡ 7 ጠንቋዮቹም በምትሃቸው ያንኑ አደረጉ፤ ጓጕንቸሮቹ በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አደረጉ፡፡ 8 ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ «ጓጕንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ላይ አንዲያስወግድ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፡፡ ከዚያም ለእግዚአብሔር እንዲሠዉ ሕዝቡን እለቃቸዋለሁ» አላቸው፡፡ 9 ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ «ጓጕንቸሮቹ ከአንተና ከቤቶችህ እንዲወገዱ፣ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን እንዲቈዩ፣ ለአንተ፣ ለአገልጋዮችህና ለሕዝብህ የምጸልይበትን ጊዜ ለእኔ መንገሩ የአንተ ድርሻ ነው፡፡» 10 «ነገ» አለው፡፡ ሙሴም ፈርዖንን መልሶ፣ «እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ እንድታውቅ አንተ እንደምትለው ይሁን፡፡ 11 ጓጕንቸሮቹ ከአንተ፣ ከቤቶችህ ከአገልጋዮችህና ከሕዝብህ ይወገዳሉ፡፡ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን ይቈያሉ» አለው፡፡ 12 አሮን ከፈርዖን ወጥተው ሄዱ፡፡ ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖን ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፡፡ 13 ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- ጓጕንቸሮቹ በየቤቱ፣ በየግቢውና በየሜዳው ሞቱ፡፡ 14 ሕዝቡ የሞቱትን ሰብስበው ከመሯቸው፤ ምድሩም ከረፋ፡፡ 15 ነገር ግን ፈርዖን ፋታ መገኘቱን ሲያይ፣ ልቡን አደነደነ፤ እንደዚህ ያደርጋል ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ እንድ ነበረ፣ ሙሴንና አሮንንም አልሰማቸውም፡፡ 16 ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «አሮንን እንዲህ በለው ‹በመላው የግብፅ ምድር ተባይ እንዲሆን የምድሩን ትቢያ በበትርህ ምታ፡፡» 17 እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፡- አሮን እጁን ዘርግቶ በበትሩ የምድሩን ትቢያ መታው፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባይ መጣ፡፡ የምድሩ ትቢያ ሁሉ በመላው የግብፅ ምድር ተባይ ሆነ፡፡ 18 በምትሃቸው ተባይ እንዲመጣ ሙከራ አደረጉ፤ ነገር ግን አልቻም፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባዮች ነበሩ፡፡ 19 ጠንቋዮቹ ታዲያ ፈርዖንን፣ «ይህ የእግዚአብሔር ጣት ነው» አሉት፡፡ ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እነርሱንም ለማድመጥ እምቢ አለ፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንዲህ እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ተናግሮት በነበረው መሠረት ነው፡፡ 20 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በማለዳ ተነሣና ፈርዖን ወደ ወንዙ ሲወጣ በፊት ለፊቱ ቁም፡፡ እንደዚህም ብለህ ንገረው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡ 21 የማትለቅ ከሆነ ግን፣ በአንተ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ፣ ወደ ቤቶችህም ውስጥ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፡፡ የግብፃውያን ቤቶች በዝንብ መንጋ ይሞላሉ፤ የሚቆሙበት ምድርም እንኳ ዝንብ ብቻ ይሆናል፡፡ 22 ግን በዚያ ቀን የዝንብ መንጋ እንዳይገኝባ፣ ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሤምን ምድር በተለየ ሁኔታ እይዛታለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር በዚህ ምድር እንዳለሁ እንድታውቅ ይህ ይሆናል፡፡ 23 በሕዝቤና በሕዝብህ መካከል ልዩነት እንዲኖር አደርጋለሁ፡፡ ይህ ተአምራዊ ምልክት ነገ ነው የሚሆነው፡፡» 24 እግዚአብሔር እንዲሁ አደረገ፤ ጥቅጥቅ ያለ የዝንብ መንጋም ወደ ፈርዖን ቤትና ወደ አገልጋዮቹ ቤቶች መጣ፡፡ በመላው የግብፅ ውስጥ ምድሩ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ተበላሽቶ ነበር፡፡ 25 ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ «ሂዱና በምድራችሁ ለአምላካችሁ ሠዉ» አላቸው፡፡ 26 እንዲህ ለማድረግ ለእኛ ትክክል አይደለም፤ ለአምላካችን በእግዚአብሔር የምንሠዋቸው መሥዋዕቶች ለግብፃውያን አስጸያፊዎች ናቸውና፡፡ ለግብፃውያን አስጸያፊ የሆኑትን መሥዋዕቶች እያን በፊታቸው ብንሠዋ፣ በድንጋይ አይወግሩንም? 27 ባዘዘን መሠረት፣ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት ያለብን ወደ ምድረ በዳወ የሦስት ቀን ጕዞ ሄደን ነው» አለ፡፡ 28 «እንድትሄዱና በምድረ በዳው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንድትሠዉ እፈቅድላችኋለሁ፡፡ ርቃችሁ መሄድ ግን የለባችሁም፡፡ ለእኔም ጸልዩልኝ» አለ፡፡ 29 «ከአንተ ወጥቼ እንደ ሄድሁ፣ የዝንቦቹ መንጋ አንተን ፈርዖንን፣ አገልጋዮችህንና ሕዝብህን ነገ ለቀው እንዲሄዱ ወደ እግዚአብሔር እጸልይልሃለሁ፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ሕዝባችን እንዲሄድ ባለመፍቀድ ከእንግዲህ ወዲያ ልታታልለን አይገባም» አለ፡፡ 30 ከፈርዖን ወጥቶ ሄደና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ 31 እግዚአብሔር ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- የዝንቡን መንጋ ከፈርዖን፣ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ላይ አስወገደ፡፡ አንድም አልቀረም፡፡ 32 ነገር ግን ፈርዖን በዚህም ጊዜ ልቡ አደነደነ፤ ሕዝቡም እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡
የአባይ ወንዝ በጓጉንቸሮች በእንቁራርቶች የተሞላ ይሆናል ወይም በአባይ ወንዝ እንቁራርቶች ይሞላሉ
የዚህ ሀረግ ትርጉም ሁለት ነው። 1) በኲሬዎች ሁሉ ላይ 2) የጓጉንቸሮች መራቢያ ሥፍራዎች ሁሉ
በወንዞች፥ በቦይ ውሃዎችና በኩሬ ውሃዎች ላይ በእጁ ያለውን በትር እንዲያነሳ ለአሮን ንገረው
እንቁራርቶች ወጥተው የግብጽን ምድር ሞሉ ወይም ምድሪቱን አለበሱአት
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ ወይም ሙሴና ፈርዖን እንዲመጡ አድርጎ
ለሹማምቶችህና ለሕዝብህ የምንፀልይበትን ጊዜ አንተው ወስን ወይም ለአንተና ለመኳንንትህና ለሕዝብህ የምጸልይበትን ሰዓት ብቻ ወስንልኝ ወይም ንገረን።
አንተም እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ሌላ አምላክ እንደሌለ እንዲታውቅ
እንዳልከው አደርጋለሁ ወይም እንደ ነገርከኝ እፈጽማለሁ
ሙሴ እያንዳንዱ ሰውና ሥፍራ በእንቁራርቶች እንደ ተወረረ እና ጭንቅ ውስጥ እንደገባ በመግለጽ መቅሰፍቱ እንደሚቆም አጽንኦት ሰጥቶ ይናገራል። በሌላ አገላለጽ፦ ከአንተ፥ ከቤትህ፥ ከሹማምንትህና ከሕዝብህ ሁሉ ዘንድ እንቁራርቶች ይወገዳሉ
ፈርዖን ችግሩ ካለፈና መረጋጋት ከሆን በኋላ እምቢ አለ።
እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳለው ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸው።
የምድሩን ትቢያ ወይም አቧራ ወይም አፈር
“ቅማል” የሚለው አንዳንደ ትንኝ ተብሎ ተተርጉሟል። በአማራጭነት ሁለቱንም ትርጉሞች መጠቀም ይቻላል። አማራጭ ትርጉም፦ በግብጽ አገር ያለውም ትቢያ ወይም አፈር ወይም አቧራ ሁሉ ወደ ተናካሽ ትንኝነት ወይም ወደ ቅማልነት ተለወጠ
“የእግዚአብሔር ጣት” የእግዚአብሔርን ሀይል ይወክላል። አማራጭ ትርጉም፦ “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው”
ፈርዖን ድፍረት አገኘ ማለት ሳይሆን ፈርዖን እምቢ አለ ማለት ነው።
ንጉሱን ፈርዖንን አግኘው/በፊቱ ቅረብ
ህዝቤ እንዲሄዱ ፈቃድ ስጣቸው
በተደራጊ ግስ የተጻፈው በአድራጊ ግስ ሲጻፍ፦ የዝንብ መንጋ የግብጽን ምድር ሁሉ ጎዳው።
በዕብራይስጡ “በዓይናቸው ፊት ብንሰዋ አይወግሩንም” ይላል። ይህ የተለመደ የዕብራውያንን አባባል ነው። ትርጉሙም አንድ ሰው በሚገኝበት ቦታ ወይም እርሱ ባለበት ሥፍራ እንደማለት ነው። አማርኛው በፊታቸው የሚለው የተፈጥሮ ፊታቸው ላይ ማለት ሳይሆን “እነርሱ ባሉበት ሥፍራ” ማለት ነው።
ይህን ዐረፍተ ነገር በአዎንታዊ ሲንተረጉም፤ “ከእንግዲህ በኋላ አንተ እውነት ልትነግረንና ህዝባችንንም እንዲሄዱ መፍቀድ አለብህ”
ፈርዖን አንተ እንዲህ መናገር የለብህም ወይም ፈርዖን አንተ አታታልለን
በዚህ ሀረግ አባባል ልቡን ያደነደነው እግዚአብሔር ሳይሆን ፈርዖን ራሱ አመጸኛ ሆነ፥ አልሰማም አለ። (ዘጸአት 7፡13 ተመልከት)
1 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ «ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ይናገራል፡፡ «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡» 2 ብትልና አሁንም ከልክለህ ብታስቀራቸው፣ 3 የእግዚአብሔር እጅ መስክ ላይ ባለው ከብትህ፣ በፈረሶችህ፣ በአህዮችህ፣ በግመሎችህ፣ በፍየሎችህና በበጎችህ ላይ ይሆናል፤ አስከፊ በሽታም ያመጣል፡፡ 4 እግዚአብሔር በእስራኤል ከብትና በግብፅ ከብት መካከል ልዩነት አድርጓል፡- የእስራኤል ከብት አይሞትም፡፡ 5 ጊዜ ወስኖአል፤ «በምድሪቱ ላይ ይህን የማደርገው ነገ ነው» ብሎአል፡፡ 6 ይህን በሚቀጥለው ቀን አደረገው፡- የግብፅ ከብት ሁሉ ሞተ፡፡ ከእስራኤል ከብት ግን አንድም አልሞተም፡፡ 7 ተከታትሎ አጣራ፣ ከእስራኤል ከብት አንድም እንኳ አለመሞቱን ተረዳ፡፡ ነገር ግን ልቡ ደንድኖ ነበር፤ ስለዚህ ሕዝቡ እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡ 8 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አላቸው፤ «ከምድጃ ላይ እፍኝ ዐመድ ውሰዱና አንተ ሙሴ ወደ ሰማይ ፈርዖን እያየ ዐመዱን በትነው፡፡ 9 በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ትቢያ ይሆናል፡፡ ይህም በመላው የግብፅ ምድር በሰውና በእንስሳት ላይ ዕባጭና ቊስል ያመጣል፡፡» 10 ስለዚህ ሙሴና አሮን ከምድጃ ዐመድ ወስደው ከፈርዖን ፊት ለፊት ቆሙ፡፡ ከዚያም ሙሴ ዐመዱን ወደ ሰማይ በተነው፡፡ ዐመዱ በሰውና በእንስሳ ላይ የሚወጣ ዕባጭና ቊስልን አመጣ፡፡ 11 በእነርሱና በሌች ግብፃውያን ሁሉ ላይ ወጥቶ በነበረው ዕባጭ ምክንያት ጠንቋዮቹ በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፡፡ 12 እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስለ አደነደነው፣ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንደዚህ እንደሚደርግ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት እንድ ነበረው ነው፡፡ 13 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በጠዋት ተነሣና ከፈርዖን ፊት ለፊት ቁም፤ እንደዚህ ብለህም ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናገሯል፡- «እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡ 14 ጊዜ በአንተ በራስህ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ እልካለሁ፡፡ ይህን የማየደርገውም በድምር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ እንድታውቅ ነው፡፡ 15 ጊዜ እጄን ዘርግቼ አንተንና ሕዝብህን በበሽታ በመምታት ከምድር ባጠፋኋችሁ ነበር፡፡ 16 ግን በሕይወት እንድትቈይ ያደረግሁህ፣ ኀይሌን እንድገልጥብህና ስሜም በምድር ሁሉ እንዲታወቅ ነው፡፡ 17 ሕዝቤን እንዳይሄድ በማድረግ በሕዝቤ ላይ ራስህን እያሳበይህ ነው፡፡ 18 ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሠረተችበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግብፅ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የበረዶ ማዕበል አመጣለሁ፡፡ 19 አሁን ሰው ላክና ከብትህን፣ በመስክ ላይ ያለህን ማንኛውንም ነገር ወደ ጠለያ ስፍራ ሰብስብ፡፡ መስክ ላይ የቀረና ወደ ቤት ያልመጣ ማንኛውም ከብትና ሰው ሁሉ በረዶው ይወርድባቸውና ይሞታሉ፡፡» 20 አገልጋዮች የእግዚአብሔር ቃል የተቀበሉት ባሮቻቸውንና ከብቶቻቸውን ወደ ቤት ለማምጣት ተጣደፉ፡፡ 21 የእግዚአብሔርን ቃል ከምር ያልተቀበሉት ግን ባሮቻቸውንና ከብታቸውን መስክ ላይ ተዉ፡፡ 22 ሙሴን እንዲህ አለው፤ «በሁሉም የግብፅ ምድር፣ በሕዝብ፣ በእንስሳትና በመላው የግብፅ ምድር መስክ ላይ ባሉ ተክሎች ሁሉ ላይ በረዶ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፡፡» 23 በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድ፣ በረዶና መብረቅ ወደ ምድር ላከ፡፡በግብፅም ምድር ላይ በረዶ አዘነበ፡፡ 24 ግብፅ አገር ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ በምድሪቱ ሁሉ ያልታየ እጅግ ከባድ የበረዶና የመብረቅ ቅልቅል ነበር የዘነበው፡፡ 25 የግብፅ ምድር፣ በረዶው መስክ ላይ ያለውን ማንኛውንም ነገር፣ ሰውንም እንስሳቱንም መታ፡፡ በመስክ ያለውን ተክል ሁሉ መታው፣ ዛፉንም ሁሉ ሰባበረው፡፡ 26 እስራኤላውያን በሚኖሩበት በጌሤም ምድር ብቻ በረዶ አልነበረም፡፡ 27 በኋላ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን እንዲጠሩ ሰዎችን ላከ፡፡ እንዲህም አላቸው፤ «በዚህ ጊዜ ኀጢአት ፈጽሜአለሁ፡፡ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢአተኞች ነን፡፡ 28 እግዚአብሔር ጸልዩ፤ ምክንያቱም ከባዱ ነጐድጓድና በረዶ እጅግ በዝቶብናል፡፡ እለቅቃችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ እዚህ አትቆዩም፡፡ 29 ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ «ከከተማዪቱ እንደ ወጣሁ፣ እጆቼን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፡፡ ነጐድጓዱ ያቆማል፣ በረዶም አይኖርም፡፡ በዚህ መንገድ አንተ ምድር የእግዚአብሔር መሆኗን ታውቃለህ፡፡ 30 ግን አንተንና አገልጋዮችህን በሚመለከት እግዚአብሔር አምላክን ገና በእውነት እንደማታከብሩ ዐውቃለሁ፡፡» 31 ጊዜ ተልባው አብቦ፣ ገብሱም ፍሬ በመያዝ ላይ ነበረ፣ ተልባውና ገብሱ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፡፡ 32 አጃው ግን ቈይተው የሚደርሱ ሰብሎች በመሆናቸው አልተጐዱም፡፡ 33 ሙሴ ከፈርዖንና ከከተማዪቱ ሲወጣ፣ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱና በረዶው ቆሙ፤ ዝናብም አልዘነበም፡፡ 34 ፈርዖን ዝናቡ፣ በረዶውና ነጐድጓዱ መቆሙን ሲያይ፣ እንደ ገና ኀጢአት አደረገ፤ ከአገልጋዮቹ ጋርም በአንድነት ልቡን አደነደነ፡፡ 35 የፈርዖን ልብ ስለ ደነደነ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንዲሄዱ አልፈቀደም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን ልቡን እንድሚያደነድን እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት የነበረው መንገድ ነው፡፡
“ልትለቅቃቸውም እንቢ ብትል ብትይዛቸውም” ሁለቱም አባባሎች ተመሳሳይ ናቸው። ፈርዖን ህዝቡን ለመልቀቅ እምቢ ብል ልደርስበት ያለውን ነገር ለማሳየትና ትኩረት ለመስጠት ሲፈለግ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እስራኤላውያንን ለመልቀቅ ባትፈልግና እምቢ ብትል
“የእግዚአብሔር እጅ” የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር ከብቶችን በበሽታ ለመጉዳት ሀይል እንዳለው የሚያመለክት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “የእግዚአብሔር (ያህዌ) ሀይል ከብቶችህን ይቀስፋል ወይም ይገድላል”
በፈርዖን ከብቶች ላይ የሚመጣ መቅሰፍት መሆኑን ያሳያል፤ ነገር ግን ፈርዖን የግብጽን ህዝብ ሁሉ በመወከል የቀረበ አነጋገር ነው።
“በእስራኤል ከብቶች” የተባለው የእስራኤላውያንን ከብቶች የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የእስራኤላውያን የሆኑ ከብቶች
“በግብጽ ከብቶች” የተባለው የግብጻውያንን ከብቶች የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የግብጻውያን የሆኑ ከብቶች
ጊዜ ቀጠረ ወይም ጊዜ ለየ ወይም ጊዜ ወሰነ
ይህ ግነታዊ ዘይቤ ዓይነት ነው። በርግጥ በዚህን ጊዜ የግብጻውያን ከብቶች ሁሉ አልሞቱም፤ ምክንያቱም በኋለኛው መቅሰፍት የሞቱ ሌሎች ከብቶች አሉ። በትርጉም ሥራ ወቅት “ሁሉ” የሚለው ቃል መቅረት የለበትም።
“ግብጽ” የሚለው ምድሪቱን ለማመልከት ሳይሆን የግብጽ ሰዎችንና ከብቶቻቸው ማለት ነው።
ንጉሡ የሆነውን ሁሉ ለማጣራት ሰዎችን በላከ ጊዜ ወይም ፈርዖን ያጣሩ ዘንድ ሰዎች ልኮ
ይህ ቃል የሚያመለክተው ፈርዖን በሆነው ነገር እጅግ መገረሙን የሚያሳይ ነው።
በዚህኛ ክፍል “ፈርዖን ልቡን አደነደነ” ወይም “እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና” ሳይሆን “የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ” የሚለው ትኩረቱ ልቡ እንደ ሰው ለመታዘዝ ፈቃደኛ አልሆነም ማለት ነው።
እሳት ከሚነድበት ቦታ እፍኝ ዐመድ ውሰዱ
መግል የሚቋጥር ቁስል ወይም ቡጉንጅ ወይም እባጭ ዓይነት ቁስል ሆነ ማለት ነው
የፈርዖን ልብ የተባለው ራሱ ፈርዖን ማለት ነው። ፈርዖን ለመስማት አልፈለገም ወይም እምብ አለ ማለት ነው። (ወካይ ወይም ተለዋጭ ዘይቤ ተመልከት)። በዚህኛ ክፍል የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ወይም ፈርዖን እንዳይሰማ ያደረገው እግዚአብሔር እንደሆነ ይገልጻል።
በአንተ ላይ ወይም አንተን ራስህን መቅሰፍቱ ይጎዳሃል ማለት ነው።
እግዚአብሔር በታላቅ ሀይሉ ለማጥቃት ወይም ለመጉዳት ሲነሳ ማለት ነው። “እኔ እጄን ዘርግቼ” ሲል ሀይሌን ለመግለጥ ሲነሳ ወይም ሀይሌን ሲገልጥ ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “አንተን ለመቅጣት ሀይሌን ሲጠቀም”
“ስሜ” የሚለው የእግዚአብሔር (ያህዌ) ዝና የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ ትልቅ እንደሆንኩ ሰዎች እስኪያውቁ ድረስ
ፈርዖን እስራኤላውያን እንዳይሄዱ ሲያደርግና እንቅፋት ሲሆንባቸው ምክንያቱ እግዚአብሔር ያንን እንዲያደርግ ስለፈቀደ ነው።
በሌላ አገላለጽ፦ ግብጽ እንደ አገር ከታወቀችበት ወይም ከተቋቋመች ጊዜ ጀምሮ ማለት ነው
በመስክ የተሰማሩ ከብቶችህና ከቤት ውጪ ያለ ማንኛውንም የአንተ ንብረት ሁሉ በፍጥነት ወደ መጠለያ እንዲያስገቡ ለአገልጋዮችህ አሁን ትእዛዝ ስጥ።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ስለተናገረው ነገር የፈሩት የፈርዖን ሹማምት ወይም እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር ሰምተው የታዘዙት የፈርዖን ሹማምት
እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ያልታዘዘ ወይም ችላ ያለ ወይም ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆነ
x
ሕዝቡንና ከብቶችን ጭምር ገደለ ወይም በህዝብና በከብቶች ላይ አደጋ አደረሰ
እስራኤላውያን ወይም የእስራኤል ህዝብ በሚኖሩባት
እጅን ወደ ላይ ማንሳት በሌላ መልኩ ለጸሎት መዘርጋት የሚያመለክት ተምሳሌት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “እጄን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ”
ለእግዚአብሔር ክብር እንደምትሰጡ፥ እግዚአብሔርን እንደማትታዘዙ
የእህል ዓይነት በተለይ የጥራጥሬ ዓይነት ነው።
የእህል ዓይነት ለሰዎችና ለከብቶች ምግብነት የሚውል
የስንዴና የገብስ ዘር የሆነ የእህል ዓይነት
እጁን ወደ ላይ አንስቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ
እንደገና ኃጢአት ሠራ
1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ «የፈርዖንና የአገልጋዮቹን ልብ አደነድናለሁና ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እነዚህን የተአምራቴን ምልክቶች ለማሳየት ይህን አድርጌአለሁ፡፡ 2 ይህን ያደረግሁት ግብፃውያንን እንዴት በከባድ አያያዝ እንደያዝኋቸውና በመካከላቸውም የተአምራትን ልዩ ልዩ ምልክቶች እንዳሳየሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትነግሯቸው ነው፡፡ በዚህ መንገድ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡ 3 አሮንም ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ አሉት፤ «የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹ራስህን በፊቴ ለማዋረድ እምቢ የምትለው እስከ መቼ ነው? እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡ 4 ግን ሕዝቤን አልለቅም ብትል፣ እነሆ፣ በነገው ቀን በአገርህ ላይ አንበጣዎችን አመጣለሁ፡፡ 5 ማንም ሰው መድሩን ማየት እስከማይችል ድረስ የምድሩን ገጽ ይሸፍኑታል፡፡ ከበረዶው አምልጦ የቀረውን ሁሉ ይበሉታል፡፡ መስክ ላይ የሚያድግላችሁንም ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፡፡ 6 አንበጣዎቹ የአንተን፣ የአገልጋዮችህን ቤቶች ሁሉ ይሞሏቸዋል፤ ይህም፣ አባትህም አያትህም በዚህ ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ቀን አነሥቶ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡» ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ሄደ፡፡ 7 ፈርዖንን፣ «ይህ ሰው ወጥመድ የሚሆንብን እስከ መቼ ነው? አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩት እስራኤላውያን ይሂዱ፡፡ ግብፅ መጥፋቷን ገና አልተገነዘብህምን?» አሉት፡፡ 8 ሙሴና አሮን፣ «ሂዱ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፡፡ ነገር ግን የሚሄዱት የትኞቹ ናቸው?» ወዳላቸው ወደ ፈርዖን እንደገና እንዲመጡ ተደረገ፡፡ 9 የምንሄደው ከወጣቶቻችንና ከሽማግሌዎቻችን፣ ከወንድና ከሴት ልጆችን ጋር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር በዓል ማክበር ስለሚገባን፣ የበግና የፍየል መንጎቻችንን፣ የቀንድ ከብቶቻችንንም ይዘን እንሄዳለን» አለ፡፡ 10 ፈርዖንም እንዲህ አላቸው፤ «እናንተንና ታናናሽ ልጆቻችሁን ስለችሁ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡ ነገር ግን ተመልከቱ፣ ክፉ ነገር ዐስባችኋል፡፡ 11 ከመካከላችሁ ወንዶች ብቻ ይሂዱና እግዚአብሔርን ያምልኩ፤ የምትፈልጉት ያንን ነውና፡፡» ከዚያም በኋላ ሙሴና አሮን ከፈርዖን ዘንድ እንዲወጡ ተደረገ፡፡ 12 እግዚአብሔርም ሙሴን፣ «አንበጣዎች የግብፅን ምድር እንዲወርሩትና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን፣ በምድሩ ያለውን ተክል ሁሉ እንዲበሉት እጅህን በግብፅ ምድር ላይ ዘርጋ» አለው፡፡ 13 ሙሴም በትሩን በግብፅ ምድር ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያ ቀንና ሌሊት ሁሉ የምሥራቅ ነፋስ በምድሩ ላይ እንዲነፍስ አደረገ። ማለዳ ላይ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አምጥቶ ነበር። 14 በግብፅ ምድር ሁሉ ተሠራጩ፤ አገሩንም ሁሉ ወረሩት። እንደዚህ እጅግ የበዙ አንበጣዎች በምድሩ ውስጥ ከዚህ በፊት አልነበሩም፤ ወደፊትም አይኖሩም። 15 ጨለማ እስኪሆን ድረስ የምድሩን ሁሉ ገጽ ሸፈኑት። በምድሩ ላይ ያለውን ማንኛውንም ተክልና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን የዛፍ ፍሬ ሁሉ በሉት። በግብፅ ምድር ሁሉ ለምለም ቅጠል ያለው ተክል አልቀረም፤ በመስክም ላይ ምንም ዛፍ አልነበረም። 16 ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔርና በእናንተ ላይ ኀጢአት ሠርቻለሁ። 17 እንግዲህ አሁን ኀጢአቴን ይቅር በሉኝና ይህን ሞት ከእኔ እንዲያስወግድልኝ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ።” 18 ስለዚህ ሙሴ ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። 19 አንበጣዎቹን ለቃቅሞ ወደ ቀይ ባሕር የሚከትታቸውን ብርቱ የምዕራብ ነፋስ አመጣ፤ በግብፅ ግዛት ሁሉ የቀረ አንድም አንበጣ አልነበረም። 20 ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ፈርዖን እስራኤላውያንን አልለቀቃቸውም። 21 ሙሴን፣ “በግብፅ ምድር ላይ የሚዳስስ ከባድ ጨለማ እንዲሆን እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው። 22 እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግብፅም ምድር ሁሉ ለሦስት ቀን ድቅድቅ ጨለማ ሆነ። 23 ቀኖች አንዱ ሌላውን ማየት አልቻለም፤ ከቤቱም የወጣ ማንም የለም። ለእስራኤላውያን ግን በሚኖሩበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው። 24 ፈርዖን ሙሴን አስጠርቶ፣ “ሂዱ እግዚአብሔርን አምልኩ። ቤተ ሰቦቻችሁም እንኳ ዐብረዋችሁ መሄድ ይችላሉ፤ በጎቻችሁና ከብቶቻችሁ ግን እዚህ መቅረት አለባቸው” አለው። 25 እንዲህ አለው፤ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንድንሠዋቸው ለመሥዋዕትና ለሚቃጠል መሥዋዕት እንስሳቱንም ልትሰጠን ይገባል። 26 ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር መሄድ አለባቸው፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማምለክ ልንወስዳቸው ይገባልና ከእነርሱ ሰኮናም እንኳ እዚህ አይቀርም። ምክንያቱም እግዚአብሔርን በምን እንደምናመልከው እዚያ እስክንደርስ ድረስ አናውቅም።” 27 ግን የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው ፈርዖን ሕዝቡን አልለቀቃቸውም። 28 ሙሴን፣ “ሂድ ከእኔ ዘንድ! ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና” አለው። 29 ሙሴም፣ “አንተ ራስህ ተናግረሃል። ፊትህን እንደ ገና አላየውም” አለው።
እግዚአብሔር ፈርዖንና ሹማምንቱን የማይሰሙና የማይታዘዙ መሆናቸውን ለመግለጽ ልባቸውን አደንድኛለሁ ይላል። (ዘጸአት 9፡12 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት)።
የዕብራይስጡ ቅጂ “እነዚህን ታአምራት” ይላል። አንድ ታአምር ሳይሆን ብዙ ታአምራትና ምልክቶችን አድርጓል ማለት ነው። አዲሱ መደበኛ አማርኛ ቅጂም እንደ ዕብራይስጡ “እነዚህን ታአምራት” ይላልና ተርጓሚዎች ትኩረት ሊሰጡት ይገባል።
ሙሴና አሮን የሚናገሩት ቃል የራሳቸው ሳይሆን የእግዚአብሔር መሆኑን ያሳያል። እነርሱም ተልከው የሄዱት በእግዚአብሔር ነውና።
ከዝናብ ጋር አብሮ የሚወርድ እህልና ቡቃያ የሚያጠፋ ነው
ዕንቅፋት መሆን ማለት ችግር ፈጣሪ፥ ፀብ ጫሪ ሰው እንደማለት ነው።
የፈርዖን ሹማምት ይህን ጥያቄ የጠየቁት በዚህ ሰው ምክንያት በግብጽ ምድር ጥፋት መምጣቱን ለማመልከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “ይህ ሰው በእኛ ላይ ጥፋት እንዲያመጣ አንፈቅድለትም”
የፈርዖን ሹማምት ንጉሱን ይህን ጥያቄ የጠየቁት ግብጽ በጥፋት ላይ መሆኗን ፈርዖን ማየት ወይም ማስተዋል ባለመቻሉ ነበር። አማራጭ ትርጉም፦ “ግብጽ በጥፋት ላይ መሆኗን አስተውል”። እነዚህ መቅሰፍቶች ግብጽን አጥፍተዋል ወይም “የሙሴና አሮን አምላክ ግብጽን አውድሟታል” እንደማለት ነው።
ፈርዖን ሙሴንና አሮንን ከፊቱ አባረራቸው ወይም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን እንዲያባርሩዋቸው እንዲያስወጧቸው አገልጋዮቹን አዘዘ ማለት ነው
ፈርዖን ይህን ያለው እስራኤላውያንና ልጆቻቸውን ለመልቀቅ እንደማይፈልግ ለማሳየት ነው።
ሙሴና አሮን ከፈርዖን ፊት እንዲወጡ ተደረገ ወይም ሙሴና አሮን የግድ ከፈርዖን ፊት እንዲወጡ አደረጓቸው
“የምስራቅ ነፋስ” ማለት ከምስራቅ በኩል የሚነፍስ ነፋስ ወይም ከምስራቅ በኩል የሚነሳ ነፋስ ማለት ነው።
አንበጦች በግብጽ ምድር ላይ እንዲመጡ ወይም አንበጦች የግብጽን ምድር እንዲወሩ እንደማለት ነው።
ከአንበጣው ብዛት የተነሳ አገሪቱ ጠቁራ ጨለማ እስክትመስል ድረስ የአንበጣ መንጋ ሸፈናት ማለት ነው።
በተጨማሪ ወይም አንድ ዕድል ስጡኝና እንደ ማለት ነው።
በዚህ ቦታ “ሞት” የተባለው በአንበጦች ምክንያት የመጣውን መቅሰፍት ወይም ጥፋት ለማመልከት ነው። ይህ ጥፋት እየከፋ ሲሄድ ሞት እንደሚያስከትል ለመግለጽም ጭምር ነው።
የዚህ ዐረፍተ ነገር ትክክለኛ ትርጉም እግዚአብሔርም አንበጦቹንም ጠራርጎ ወደ ቀይ ባሕር የሚነዳ ብርቱ ነፋስ ከምዕራብ በኩል አስነሣ ወይም ያህዌ ነፋሱን ወደ ብርቱ የምዕራብ ነፋስ ለወጠው ያም ነፋስ አንበጣዎቹን እየነዳ ወደ ቀይ ባህር ከተታቸው ማለት ነው።
የፈርዖን ልብ የተባለው ራሱ ፈርዖን ማለት ነው። ፈርዖን ለመስማት አልፈለገም ወይም እምቢ አለ ማለት ነው። (ዘጸአት 9፡12 ተመልከት)።
ድቅድቅ ጨለማ ወይም በእጅ እንደምዳሰስ ዓይነት ጨለማ
አንድ ሰኮናም የሚለው “ሙሉ ከብቱን” ለማመልከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ አንድ ከብት እንኳን አናስቀርም
የፈርዖን ልብ የተባለው ራሱ ፈርዖን ማለት ነው። ፈርዖን ለመስማት አልፈለገም ወይም እምብ አለ/እምብተኛ/ ሆነ ማለት ነው። ዘጸአት 9፡12 ተመልከት።
በሌላ አገላለጽ፦ ፈርዖንም ሕዝቡን መልቀቅ አልፈለገም
“ፊት” የሚለው “ሰውዬውን” ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔን እንዳታይ ተጠንቀቅ
በዚህ አባባል ሙሴ የፈርዖንን ንግግር ሲያጸናው እንመለከታለን። አንተ የተናገርከው እውነት ነው እንደማለት ነው። (ፈሊጣዊ ንግግር)
1 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ የማመጣው ገና አንድ መቅሠፍት አለ። ከዚያ በኋላ ከዚህ እንድትሄዱ ይፈቅድላችኋል። በመጨረሻ እንድሄድ ሲያደርግም፣ ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል። 2 ወንድና እያንዳንዱ ሴት ከጎረቤቱ ወይም ከጎረቤቱ የብርና የወርቅ ዕቃዎችን ስጡን ብለው እንዲጠይቁ ለሕዝቡ ተናገር።” 3 እስራኤላውያንን ደስ ለማሰኘት ግብፃውያን እንዲነሣሡ አደረገ። ሙሴም በፈርዖን አገልጋዮችና በግብፅ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የሚደነቅ ሰው ሆነ። 4 እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ይህን ተናግሯል፦ ‘እኩለ ሌሊት ላይ በመላው ግብፅ ዐልፋለሁ። 5 ላይ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ልጅ ጀምሮ፣ ወፍጮ ላይ እስከምትፈጨዋ እስከ ባሪያዪቱ በኵር ልጅና እስከ እንስሳቱ በኵር ሁሉ ድረስ በግብፅ ምድር ያሉ በኵር በሙሉ ይሞታል። 6 በቀድሞው ጊዜ ያልነበረ እንደገናም የማይደገም ታላቅ ዋይታ በግብፅ ምድር ሁሉ ይሆናል። 7 ሕዝብ ላይ ግን፣ በሰውም ሆነ በእንስሳ ላይ ውሻ እንኳ አይጮኽም። በዚህም ግብፃውያንንና እስራኤላውያንን የማስተናግድበት መንገድ የተለያየ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።’ 8 እነዚህ አገልጋዮችህ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ። ‘አንተና ተከታዮችህ ሁሉ ሂዱ!’ ብለውም ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ እወጣለሁ።” ከዚያም ሙሉ ከፈርዖን ዘንድ በትልቅ ቊጣ ወጥቶ ሄደ። 9 ሙሴን፣ “ፈርዖን እናንተን አይሰማችሁም። ይህም የሆነው ብዙ አስደናቂ ነገሮችን በግብፅ ምድር ላይ እንዳደርግ ነው” አለው። 10 አሮን እነዚህን ድንቆች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ። ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ፈርዖን የእስራኤል ሕዝብ ከምድሩ እንዲወጡ አልፈቀደም።
አንድ ሰው እንዳይቀር ሁላችሁንም በማባረር ያስወጣችኋል
ለህዝብ መናገርን በወካይ ዘይቤ ተጠቅሞ ለጆሮአቸው ተናገር ይላል። በሌላ አገላለጽ፦ ለህዝቡ ተናገር
የግብጽ ንጉስ ፈርዖን፤ ሹማምቱና ሕዝቡ ሁሉ ሙሴ ታላቅ ወይም የከበረ ሰው አድርገው ይቀበላሉ
በኩር የሚለው ቃል ሁል ጊዜ መጀመሪያ የተወለደን ወንድ (ሰውና እንስሳ) የሚመለከት ነው።
ይህ በንግስና ዙፋን ላይ የተቀመጠውን ፈርዖንን የመለከታል
የወፍጮ መጅ ገፊ እስከ ሆነችው ወይም በድንጋይ መፍጫ እህል በመፍጨት እስከምታገለግል
ሙሴ የእስራኤልን ህዝብ አስከትሎ ከግብጽ እንደሚሄድ መናገሩ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “ከዚያም በኋላ እሄዳለሁ” ወይም “እኔም ከዚያ በኋላ እሄዳለሁ”
በግብጽ ምድር ላይ ብዙ ተአምራት አደርግ ዘንድ ወይም በግብጽ ምድር ድንቅ ሥራዎቼ በብዛት እንዲታዩ
የፈርዖን ልብ የተባለው ራሱ ፈርዖን ማለት ነው። ፈርዖን ለመስማት አልፈለገም ወይም እምብ አለ ማለት ነው። (ወካይ ወይም ተለዋጭ ዘይቤ ተመልከት)። በዚህኛ ክፍል የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ወይም ፈርዖን እንዳይሰማ ያደረገው እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።
1 በግብፅ ምድር ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ነገራቸው፤ 2 ወር ለእናንተ የወሮች መጀመሪያ፣ የዓመቱም የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። 3 ጉባኤ ይህን ንገሩ፤ ‘በዚህ ወር ዐሥረኛ ቀን ላይ እያንዳንዳቸው ለራሳቸው አንድ ጠቦት የሚያንስ ከሆነ፣ 4 የቅርብ ጎረቤቱ ከቊጥራቸው ጋር የሚመጣጠን ጠቦት ያዘጋጁ። የሚመገቡትን በቂ ሥጋ መውሰድ እንዲችሉ፣ ጠቦቱ ለሁሉም የሚበቃ መሆን አለበት። 5 ወይም የፍየል ጠቦታችሁ እንከን የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ሊሆን ይገባል። ከበጎቹ ወይም ከፍየሎቹ አንዱን ልትወስዱ ትችላላችሁ። 6 እስከ ወሩ ዐሥራ አራተኛ ወር ድረስ አቆዩአቸው። ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ እነዚህን እንስሳት ፀሐይ ስትጠልቅ ይረዷቸው። 7 ከዚያም ከደሙ ጥቂት ውሰዱና ሥጋውን በምትበሉበት ቤት በር መቃንና ጉበን ላይ አድርጉት። 8 በእሳት ከጠበሳችሁት በኋላ፣ በዚያው ሌሊት ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ብሉት። 9 ወይም ቅቅሉን አትብሉት። ይልቁን ከጭንቅላቱ፣ ከእግሮቹና ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት ጠብሳችሁ ብሉት። 10 ድረስ ከሥጋው አንዳችም አታስቀሩ። የተራረፈ ነገር ቢኖር፣ በእሳት ይቃጠል። 11 ወገባችሁን ታጥቃችሁ፣ ጫማችሁን አጥልቃችሁና በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ ነው። ተጣድፋችሁ ልትበሉት ይገባል። የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። 12 በዚያ ሌሊት በግብፅ ምድር ሁሉ ዐልፋለሁ፤ በግብፅ ምድርም የሰውንና የእንስሳትን በኵር በሙሉ እመታለሁ። በግብፅ አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ። 13 ደሙ እኔ ወደ እናንተ በቤቶቻችሁ ላይ ምልክት ይሆናል። ደሙንም በማይበት ጊዜ የግብፅን ምድር ስመታ እናንተን ዐልፌአችሁ እሄዳለሁ። ይህ መቅሠፍት በእናንተ ላይ አይመጣም፤ አያጠፋችሁምም። 14 ቀን የእግዚአብሔር በዓል ቀን አድርጋችሁ የምታከብሩት የመታሰቢያ ቀን ይሆንላችኋል። ቀኑን እንድታከብሩት ለእናንተ፣ ለትውልዶቻችሁም ሁሉ ቋሚ ሥርዐት ይሆናችኋል። 15 ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ከቤታችሁ ታስወግዳላችሁ። ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የበላ ሰው ሁሉ ከእስራኤል ይወገድ። 16 በመጀመሪያው ቀን ለእኔ የተቀደሰ ጉባኤ ይደረጋል፤ በሰባተኛውም ቀን እንደዚሁ ያለ ሌላ ጉባኤ ይሆናል። ሁሉም የሚበላውን ከመቀቀል በቀር፣ በእነዚህ ቀኖች ሥራ አይሠራም። የምትሠሩት የምግብ ዝግጅቱን ሥራ ብቻ ነው። 17 በዓልን አክብሩት ምክንያቱም ሕዝባችሁን ሰራዊት በሰራዊት አድርጌ ከግብፅ ምድር ያወጣሁት በዚህ ቀን ነው። ስለዚህ ይህን ቀን በትውልዶቻችሁ ሁሉ አክብሩት፤ ለእናንተ ቋሚ ሥርዓት ይሆናችኋል። 18 የመጀመሪያ ወር ዐሥራ አራተኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ አንሥቶ፣ እስከ ወሩ ሃያ አንደኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ። 19 በሰባቱ ቀኖች በቤታችሁ ውስጥ እርሾ መገኘት የለበትም። እርሾ ያለበት እንጀራ የሚበላ እንግዳም ሆነ በምድራችሁ የተወለደ ሰው ከእስራኤል ማኅበረ ሰ ይወገዳል። 20 የተጋገረ አንዳችም መብላት የለባችሁም። የትም ብትኖሩ፣ መብላት የሚገባችሁ እርሾ የሌለበትን ነው።” 21 በኋላ ሙሴ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሂዱና ቤተ ሰቦቻችሁን ለመመገብ የሚበቁ ጠቦቶችን ወይም ግልገሎችን መርጣችሁ የፋሲካን በግ ዕረዱ። 22 ጭብጥ የሂሶጵ ቅጠል ያዙና በሳሕን ውስጥ በሚቀመጠው ደም ውስጥ በመንከር፣ የቤታችሁን ጉበን ዐናትና ሁለቱን መቃኖች እርጩ። እስኪነጋ ድረስ ከእናንተ አንድም ከቤቱ አይወጣ። 23 ለመቅሠፍት እግዚአብሔር ስለሚያልፍ፣ ደሙን በጉበኑ ዐናትና በሁለቱ መቃኖች ላይ ሲያይ፣ በበራፋችሁ ላይ ያልፋል፣ ቀሣፊውም ወደ ቤታችሁ እንዲገባና እናንተን እንዲቀሥፋችሁ አይፈቅድም። 24 ይህ ሥርዐት ለእናንተም ለልጆቻችሁም የሁልጊዜ ሥርዐት ስለ ሆነ ልታከብሩት ይገባል። 25 ቃል በገባላችሁ መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ ይህን የአምልኮ ሥርዐት ጠብቁት። 26 ‘ይህ የአምልኮ ሥርዐት ምን ትርጕም አለው?’ ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ፣ 27 እንደዚህ ብላችሁ ልትነግሯቸው ይገባል፤ ‘ይህ የእግዚአብሔር ፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ግብፃውያንን ሲቀሥፍ፣ በግብፅ ውስጥ በእስራኤላውያን ቤቶች ዐልፎ ሄዶአል። ቤተ ሰቦቻችንን ነጻ አውጥቷቸዋል።” ከዚያም ሕዝቡ ሰገዱ፣ እግዚአብሔርንም አመለኩት። 28 ሄደው እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዝዛቸው አደረጉ። 29 እኩለ ሌሊት ላይ በዙፋኑ ላይ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ልጅ ጀምሮ፣ በእስር ቤት ውስጥ እስካለው ሰው በኵር ልጅና እስከ እንስሳት በኵር ሁሉ ድረስ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር የሚገኝን በኵር በሙሉ ቀሠፈ። 30 አገልጋዮቹ ሁሉና ግብፃውያን በሙሉ ሌሊት ላይ ተነሡ። በግብፅ ውስጥ ጕልሕ የልቅሶ ጩኸት ነበረ፤ ሰው ያልሞተበት እንደም ቤት አልነበረምና። 31 ሙሴንና አሮንን በሌሊት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ተነሡ፤ እናንተና እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ። ማድረግ የምትፈልጉትን እንደ ተናገራችሁ ሂዱ፣ እግዚአብሔርን አምልኩ። 32 እንደ ተናገራችሁት፣ የበግና የፍየል መንጎቻችሁን፣ የቀንድና የጋማ ከብቶቻችሁንም ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።” 33 እስራኤላውያንን ከአገራቸው ለማባረር በትልቅ ጥድፊያ ላይ ነበሩ፤ “ሁላችንም ማለቃችን ነው” ብለው ነበርና። 34 ሕዝቡ እርሾ ያልተጨመረበትን ሊጣቸውን ያዙ። የቡሆ እቃዎቻቸውን ቀድሞውኑ በጨርቃቸው አስረው በትከሾቻቸው ተሸክመዋቸዋል። 35 ሕዝብ ሙሴ እንደ ነገራቸው አደረጉ። የወርቅና የብር ዕቃዎችን፣ ልብስም እንዲሰጧቸው ግብፃውያንን ጠየቁ። 36 ደስ ለማሰኘት እግዚአብሔር ግብፃውያንን አነሣሣ። ስለዚህ እስራኤላውያን የጠየቋቸውን ሁሉ ግብፃውያን ሰጧቸው። በዚህ መንገድ፣ እስራኤላውያን ግብፃውያንን በዘበዟቸው። 37 ከራምሴ በመነሣት ወደ ሱኮት ተጓዙ። ቊጥራቸው ከሕፃናቱና ከሴቶቹ ሌላ ስድስት መቶ ሺሕ ያህል እግረኛ ነበር። 38 እስራኤላዊ ያልሆነ ድብልቅ ሕዝቤም፣ ከበግና ከፍየል፣ እጅግ ብዙ ከሆነ የከብት መንጋ ጋር ዐብሯቸው ሄደ። 39 ከግብፅ ያመጡትን እርሾ ተባርረው ስለ ወጡና ምግብ ማዘጋጀት ስላልቻሉ ነው። 40 እስራኤላውያን በግብፅ ውስጥ የኖሩት አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር። 41 መቶ ሠላሳው ዓመት ፍጻሜ፣ በዚያው ቀን፣ ሁሉም የእግዚአብሔር ሰራዊት ከግብፅ ምድር ወጣ። 42 ሌሊት እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር እንዲያወጣቸው ለእስራኤላውያን ነቅቶ የመቆያ ሌሊት ነበር። ይህ ሌሊት እስራኤላውያን ሁሉ፣ መላ ትውልዶቻቸው ሊያከብሩት የሚገባ ሌሊት ነው። 43 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ ሕግ እነሆ፦ ባዕድ ሰው ፋሲካን አይበላውም። 44 የተገዛ እያንዳንዱ የእስራኤል ባሪያ ግን ከገረዛችሁት በኋላ መብላት ይችላል። 45 ቅጥር አገልጋዮች መብላት አይገባቸውም። 46 ምግቡ በአንድ ቤት ውስጥ መበላት አለበት። ሥጋ ከቤት ማውጣት፣ ዐጥንትም መስበር የለባችሁም። 47 የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በዓሉን ሊያከብር ይገባል። 48 ባዕድ ሰው ከእናንተ ጋር ቢኖርና ፋሲካን ለእግዚአብሔር ለማክበር ቢፈልግ፣ ወንድ ዘመዶቹ ሁሉ መገረዝ አለባቸው። ከዚያም በኋላ፣ ሰውየው መምጣትና በዓሉን ማክበር ይችላል። በምድሩ እንደ ተወለዱት ሰዎች ይሆናል። ይሁን እንጂ፣ ያልተገረዘ ሰው የፋሲካን ምግብ አይበላም። 49 አንድ ዐይነት ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው በሁለቱም ማለት በአገሬው ተወላጅና በመካከላችሁ በሚኖረው ባዕድ ሰውም ላይ ነው።” 50 እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ። 51 በዚያው ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አወጣቸው።
እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ አንድ ትርጉም ወይም ፍቺ ያላቸው ሲሆን አጽንዖት ለመስጠት የገባ በመሆኑ እስራኤላውያን ከግብጽ የወጡበትንና አዲስ ታሪክ የጀመረበት ስለሆነ ወሩ የአመቱ መጀመሪያ ወር እንዲሆንላቸው የተነገረ ወይም የተሰጠ ነው። ይህ ወር የሚጀምረው በአመዛኙ በሚያዚያ ወር አከባቢ ነው።
በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ቁጥር አንድን የበግ ጠቦት በልቶ ለመጨረስ የማይበቃ ከሆነ
“እርሱ” የተባለው የዚያ ቤተሰብ መሪ የሆነው ሰው ማለት ነው
“ምሽት” የሚለው ቃል ሙሉ በሙሉ ሲመሽ ሳይሆን ፀሐይ መጥለቂያ እና ማምሻ መካከል ያለው ሰዓት ሲሆን ከመጨለሙ በፊት ብርሃን ያለ መሆኑን አመልካቺ ነው።
የበሩን ወይም የደጃፉን ጎንና ጎን እንዲሁም የላኛውን ጉበን ማለት ነው።
በአማርኛ “ቂጣ እንጀራ” ወይም “እንጀራ ቂጣ” ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ላይሆን ይችላል። ቂጣውን እንጀራ ማለት እርሾ ያልገባበት ደረቅ ቂጣ ሲሆን እንደ ህብረተሰቡ አጠቃቀም “ቂጣ፥ ያልቦካ ቂጣ፥ ደረቅ ቂጣ” ሊሆን ይችላል።
መራራ ቅጠል የተባለው ምን ዓይነት ተክል እንደሆነ በስም አልተገለጸም። በአይሁዳውያን ባህል ሥጋ ለማድረቅ ወይም ለመቀመም የሚጠቀሙበት ተክል ዓይነት ነው።
የፍየሉን ወይም የበጉን ጥሬ ሥጋ ወይም በውሃ ተቀቅሎ የበሰለውን አትብሉ
ከሥጋው እስከ ጧት ድረስ ምንም አታስቀሩ
የወገብ መታጠቂያ ከቆዳ ወይም ከጥጥ የተሰራ የወገብ መታጠቂያ ወይም በእያንዳንዱ ባህል ማህበረሰቡ የሚጠቀመው የወገብ መታጠቂያ ሊሆን ይችላል።
በጥድፊያ ወይም በችኮላ ብሉት
“እርሱ” የሚለው በአስራ አራተኛው ቀን የበግ ወይም ፍዬል ጥቦት እረድና የመብላት ሥርዓቱን ማለት ነው።
የግብጽን አማልክት ወይም እግዚአብሔሮች ሁሉ እቀጣለሁ
እኔ ወደ እናንተ በሚመጣበት ጊዜ ደሙ የእስስራኤላውያን ቤት ስለመሆኑ ምልክት ይሆንልኛል።
እኔም ደሙን በማይበት ጊዜ አልፌአችሁ እሄዳለሁ ወይም ወደ ቤታችሁ ሳልገባ/ሳልጎበኛችሁ አልፌ እሄዳለሁ (ዘይቤያዊ ንግግር)
በሚቀጥሉት ትውልዶች ወይም ዘመናት ሁሉ ቋሚ ሥርዐት ሆኖ የእግዚአብሔር (ያህዌ) በዓል አድርጋችሁ ታከብሩታላችሁ።
“ይጥፋ” የሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ሶስት አማራጭ ፍቾች ይኖሩታል። 1) የእስራኤል ሰዎች ይህን ሰው ከመካከላቸው አውጥተው ማስወገድ አለባቸው 2) ይህ ሰው ከእስራኤላውያን እንደ አንዱ መታየት የለበትም 3) እስራኤላውያን ይህን ሰው መግደል ወይም ማጥፋት አለባቸው።
በመጀመሪያውና በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ
በእነዚያም ቀኖች ምግባችሁን ከማዘጋጀት በቀር ምንም ሥራ አትሠሩም
የምትሠሩት ሥራ ቢኖር ለእያንዳንዱ ምግብ ማዘጋጀት ብቻ ይሆናል።
ይህ አገላለጽ ለጦር ሠራዊት የተሰጠ ስም ሲሆን በዚህ ክፍል የተገለጸው “ክፍል ለክፍል ወይም ቡድን ለቡድን” በሰልፍ የሚወጣውን የእስራኤልን ህዝብ የሚመለከት ነው።
“ምሽት” የሚለው ቃል ሙሉ በሙሉ ሲመሽ ሳይሆን ፀሐይ መጥለቂያ እና ማምሻ መካከል ያለው ሰዓት ሲሆን ከመጨለሙ በፊት ብርሃን ያለ ማለት ነው።
ይህ ወር በእስራኤላውያን ዘመን አቆጣጠር የአመቱ የመጀመሪያ ወር ነው። በአውሮጳውያን አቆጣጠር የመጋቢት መጨረሻ ሳምንት እና የሚያዚያ የመጀመሪያ ሳምንት አከባቢ የሚጀምር ወር ነው።
የመጀመሪያ ወር በገባ በ21ኛው ቀን ማለት ነው
እስከ ሰባት ቀን ድረስ ምንም ዓይነት እርሾ በቤታችሁ መገኘት የለበትም
ዘጸአት 12፡15 ተመልከት
ዘጸአት 12፡5-8 ያለውን ማብራሪያ ተመልከት
ሸካራ የሆነ ትናንሽ ቅጠሎች ያሉት በተለይ ፈሳሽ ነገሮችን ለመርጨት የሚያገለግል የዛፍ ዓይነት ነው
የበሩን ወይም የደጃፉን ጎንና ጎን እንዲሁም የላኛውን ጉበን ማለት ነው።
“በደጁ” ላይ ያልፋል የሚለው ጠቅላላውን ቤተሰብ ወይም ቤት የሚመለከት ነው። ደም በመቃኖቻቸውና በጉበኖቻቸው ላይ የተገኘባቸው ቤቶችን እግዚአብሔር ሳይነካቸው ያልፋል ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር ቤታችሁን ትቶ ያልፋል
“ይህችን ነገር” የተባለው “የፋሲካ በዓል” ወይም “የቂጣ በዓል” ማለት ነው። የፋሲካ በዓል ማክበር እግዚአብሔኤርን (ያህዌን” ማክበር ነው።
በሌላ አገላለጽ፦ እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን መኖሪያ ቤቶች አልፎ በመሄድ ቤታቸውን ስላተረፈ ወይም በእስራኤላውያን ቤት የሚገኙትን በኩር ወንድ ልጆችን ባለመግደሉ”
ሄደውም በሙሴና በአሮን አማካይነት እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ
በኩር የሚለው ቃል ሁል ጊዜ መጀመሪያ የተወለደን ወንድ (ሰውና እንስሳ) የሚመለከት ነው። (ዘጸአት 11፡5 ተመልከት)
በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኵር ልጅ ጀምሮ
በጨለማ እስር ቤት ውስጥ እስካለው እስረኛ የበኵር ልጅ ድረስ ያለውን ማለት ነው። ምርኮኛ የተባለው አንድ እስረኛ ሳይሆን ሁሉንም እስረኛ ሲሆን አንደ አንድ ሰው የተጠቀሰው ለሁሉም ያገለግላል ማለት ነው።
በኩር የሆነ ወንድ ልጅ ያልሞተበት አንድ ቤት እንኳ አልነበረም
በግብጽ ምድር ሁሉ ታላቅ የለቅሶ ጩኸትና ዋይታ ሆነ
እስራኤላውያን ግብጽን ለቀው ካልወጡ ሁላችን እናልቃለን ብለው ግብጻውያን ስለፈሩ ---። አማራጭ ትርጉም፦ “እናንተ ለቃችሁ የማትሄዱ ከሆነ እኛም መሞታችን ነው”
በሌላ አገላለጽ፦ ሕዝቡ ያልቦካውን ሊጥ በየቡሆ ዕቃው አድርገው በጨርቅ ጠቅልለው በትከሻቸው ተሸከሙ
ራምሴ ግብጻውያን እህል ከሚያከማቹባቸው ከተሞች አንዱ ነው። (ዘጸአት 1፡11 ተመልከት)
“ህጻናት” የተባሉት ድጋፍ የሚፈልጉ ወንድና ሴት ልጆችን የሚመለከት ወይም ህጻናትና ሴቶችን የሚመለከት ሊሆን ይችላል። ጠቅላላ መዋጋት የሚችሉ ወንዶች ብዛት ስድስት መቶ ሺህ ያህል ነበር።
ከግብፅ ይዘው ከወጡት ሊጥ ያልቦካ ቂጣ ጋገሩ
ከግብፅ በጥድፊያ ወይም በችኮላ እንዲወጡ ስለተደረጉ ለራሳቸው ምግብ ለማዘጋጀት ጊዜ አልነበራቸውም
እስራኤላውያን በግብጽ ምድር የኖሩት አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር
እዚህ ጋር ሠራዊት የተባለው የእስራኤልን ህዝብ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ የግብጽን ምድር ለቆ ወጣ” (ዘጸአት 12፡17 ተመልከት)
ይህ ሌሊት እስራኤላውያን በመጠባበቅ ተግተው የሚያድሩበትና ለሚመጣው ትውልድ ወይም ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሌሊት ነው
“እርሱ” የተባለው የፋሲክን ምግብ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የባዕድ አገር ሰው የሆነ የፋሲካን ራት ወይም ምግብ አይብላ
በገንዘብ የገዛችሁት ማንኛውም ባሪያ ቢሆን
ምግቡ በሙሉ በዚያው በተዘጋጀበት ቤት ውስጥ መበላት አለበት ማለት ነው
የሚታረደው ጠቦት አጥንቶቹን አትስበሩ
አስቀድማችሁ በቤተሰቡ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ግረዙ
በሌላ አባባል የተገረዘ ሁሉ ከፋሲካው ምግብ መብላት ይችላል ማለት ነው
እግዚአብሔር በሙሴና በአሮን አማካይነት ያዘዘውን ሁሉ ፈጸሙ
አማራጭ ትርጉም፦ “እግዚአብሔር መላውን የእስራኤል ሕዝብ በክፍል በክፍል ከግብጽ ምድር መርቶ አወጣ”
1 ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 ‘በእስራኤላውያን ዘንድ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት በመጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ። በኵር የእኔ ነው።” 3 ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስታውሱት፤ በዚህ ቀን እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከዚህ ስፍራ አውጥቶአችኋልና። እርሾ ያለበት ምግብ አይበላም። 4 በዚህ ቀን፣ በአቢብ ወር ከግብፅ ወጥቷችኋል። 5 ለእናንተ ለመስጠት ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ኤውያውያን፣ ኢያቡሳውያን ምድር እግዚአብሔር ሲያስገባችሁ፣ ይህን አምልኮ በዚህ ወር ትፈጽማላችሁ። 6 ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት በዓል ይሆናል። 7 ቀን ሁሉ መበላት ያለበት ቂጣ ነው፤ እርሾ ያለበት እንጀራ በእናንተ ዘንድ መታየት የለበትም። በአዋሳኞቻችሁም ዘንድ እርሾ አይኑር። 8 ቀን፣ ‘ይህ እንዲህ የሚሆነው ከግብፅ ስወጣ እግዚአብሔር ለእኔ ካደረገው የተነሣ ነው’ ብላችሁ ለልጆቻችሁ ትነግሯቸዋላችሁ።’ 9 ይህም በእጃችሁና በግንባራችሁ ላይ መታሰቢያ ይሆናል። ይኸውም እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከግብፅ ስላወጣችሁ፣ የእግዚአብሔር ሕግ በአፋችሁ እንዲሆን ነው። 10 ይህን ሕግ በየዓመቱ በተወሰነለት ጊዜ ልትጠብቁት ይገባል። 11 ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በማለው መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደ ከነዓናውያን ምድር ሲያስገባችሁ፣ 12 በመጀመሪያ የተወሰደውን፣ የእንስሶቻችሁንም በኵር ሁሉ ለእግዚአብሔር ቀድሱ። ወንዶች የእግዚአብሔር ናቸው። 13 ከአህያ በመጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ በጠቦት ትዋጁታላችሁ። ካልዋጃችሁት፣ ዐንገቱን ስበሩት። ከወንድ ልጆቻችሁ መካከል በኵር የሆኑትን ሁሉ ዋጇቸው። 14 ልጅህ፣ ‘ይህ ምን ማለት ነው? ብሎ ወደፊት ቢጠይቅህ፣ እንደዚህ ትነግረዋለህ ‘ከባርነት ቤት፣ ከግብፅ እግዚአብሔር ያወጣን በብርቱ እጅ ነበር። 15 እኛን ለመልቀቅ በግትርነት እንቢ ባለ ጊዜ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ፣ የሰውንም ሆነ የእንስሳትን በኵር በሙሉ ገደለ። ከእንስሳት ሁሉ በመጀመሪያ የተወለደውን ለእግዚአብሔር የምሠዋውና ከወንድ ልጆችም በኵር የሆነውን የምዋጀውን በዚህ ምክንያት ነው።’ 16 ከግብፅ ያወጣን በብርቱ እጅ ነውና፣ ይህ በእጅህና በግንባር ላይ ማስታወሻ ይሆናል።” 17 ሕዝቡን ሲለቅቃቸው፣ እግዚአብሔር ምንም እንኳ ቅርብ ቢሆንም፣ በፍልስጥኤማውያን ምድር ባለው መንገድ አልመራቸውም። እግዚአብሔር፣ “ሕዝብ ጦርነት ቢያጋጥማቸው፥ ምናልባት ሐሳባቸውን ይለውጣሉ፣ ወደ ግብፅም ይመለሳሉ” ብሎ ነበርና። 18 እግዚአብሔር ሕዝቡን በምድረ በዳው ዙሪያ ውደ ቀይ ባሕር መራቸው። እስራኤላውያን ለውጊያ ተዘጋጅተው ከግብፅ ምድር ወጥተው ሄዱ፣ 19 ሙሴ የዮሴፍን ዐፅም ይዞ ሄደ፤ ምክንያቱም ዮሴፍ፣ “እግዚአብሔር በእርግጥ ይታደጋችኋልና ዐፅሜን ይዛችሁ እንድትሄዱ” በማለት እስራኤላውያንን አስምሎአቸው ነበር። 20 ከሱኮት በመጓዝ ምድረ በዳው ዳር ላይ በሚገኘው በአታም ሰፈሩ። 21 እግዚአብሔር ሕዝቡን በመንገድ ላይ ሊመራቸው ቀን ቀን በደመና ዐምድ በፊታቸው ሄደ። ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን ሊሰጣቸው በእሳት ዐምድ ሄደ። በዚህ ዐይነት ሕዝቡ በቀንም በሌሊትም መጓዝ ቻሉ። 22 እግዚአብሔር የቀኑን የደመና ዐምድ ወይም የሌሊቱን የብርሃን ዐምድ ከሕዝቡ ፊት አላነሣም።
በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን እግዚአብሔር ይፈልገዋል
“ይህን ቀን አስቡ” የሚለው አንድ ሰው ያለፈውን ነገር ወደ ኋላ እንዲያስታውስ መናገር የተለመደ አባባል ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ይህን ቀን አስታውሱ ወይም ይህን ቀን አትርሱ።
ህዝቡ በአንድ ቤት ታጉሮ እንደነበር ዓይነት አነጋገር የያዘ ዘይቤ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “በባርነት የነበራችሁበት ዘመን ወይም ሁኔታ”
ምክንያቱም እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ አውጥቷችኋል
እርሾ የገባበትን ዳቦ ወይም ምግብ አትብሉ
የአቢብ ወር ለእብራውያን የአመቱ መጀመሪያ ወር ነው። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር አቢብ ወር የሚጀምረው ከመጋቢት መጨረሻ ሳምንት እስከ ሚያዝያ መጀመሪያ ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።
ይህ ሐረግ በግነታዊ እና በተለዋጭ ዘይቤ የተገለጸ ነው። ይህ አገላለጽ ከምድሪቱ ወተትና ማር ይፈልቃል ማለት ሳይሆን ለከብት ርባታና ለእርሻ በጣም ምቹ የሆነ ምድር እንደሆነ ለማሳየት ነው። እንዲሁም “የምታፈስ” አገር የሚለው ቃልም ሁሉም ነገር የሞላባት ምድር የሚል ፍቺ ያለው ነው።
እስራኤላውያን በከነዓን ሲኖሩ በዓመቱ መጀመሪያ ወር ላይ ይህን በዓል (የፋሲካ በዓል) ማክበር አለባቸው (ዘጸአት 12፡25)
እስከ ሰባት ቀን ወይም ለሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልገባበትን ምግብ ትበላላችሁ
እርሾም ሆነ እርሾ የገባበት ምግብ በፍጹም በምድራችሁ አይገኝ
እርሾ በአገርህ ውስጥ በየትኛውም ሥፍራ/ቦታ/ አይገኝ
ይህ አነጋገር በቀጥታ አነጋገር ሲገለጽ፦ “በዓሉን በምታከብርበት ወቅት ይህን የምታደርገው ከግብጽ በወጣህበት ጊዜ እግዚአብሔር ያደረገልህን መልካም ነገር ለማስታወስ መሆኑን ለልጆችህ ንገራቸው”
ምክንያቱም እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ አውጥቷችኋል
እስራኤላውያን በዓሉን ወይም የፋሲካን በዓል ሲያከብሩ እነዚህን ሁለት የሚታዩ ምልክቶችን እንድያደርጉ ሙሴ ያሳስባቸዋል።
ሙሴ ሲናገር እስራኤላውያን በዓሉን ሲያከብሩ በእጃቸው የሆነ ነገር አስረው እንደምያከብሩ አድርጎ ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ ለምልከነት በእጅህ ላይ የሆነ ነገር እንደምታስረው ይሁን።
ሙሴ ሲናገር እስራኤላውያን በዓሉን ሲያከብሩ በግንባራቸው የሆነ ነገር አስረው እንደምያከብሩ አድርጎ ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ ለምልክትነት በግንባርህ ላይ የሆነ ነገር እንደምታስረው ይሁን።
ምክንያቱም እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ አውጥቷችኋል
እግዚአብሔር የከነዓናውያንን ምድር ለአንተ በሰጠህ ጊዜ
በኩር የተወለደ አህያ ለእግዚአብሔር አይለይም ወይም አይቀደስም። አማራጭ ትርጉም፦ በኩር የተወለደ አህያ የበግ ጠቦት በመተካት ከእግዚአብሔር ትዋጃለህ /መልሰህ ተገዛለህ/፤ ነገር ግን አህያውን መዋጀት ካልፈለግህ አንገቱን ስበረው።
በኩር ሆኖ የተወለደን ወንድ ልጅ ሁሉ መዋጀት /መልሰህ መግዛት/ ይገባሃል
በሌላ አገላለጽ፦ “በሚመጡት ዘመናት ልጆችህ የዚህ ሥርዓት ትርጉም ምንድን ነው” ብለው ቢጠይቁህ፥ እንዲህ ብለህ ታስረዳቸዋለህ
ምክንያቱም እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ
ህዝቡ በአንድ ቤት ታጉሮ እንደነበር ዓይነት አነጋገር የያዘ ዘይቤ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “በባርነት የነበራችሁበትን ሁኔታ ወይም ሕይወት”
እስራኤላውያን በዓሉን ወይም የፋሲካ በዓል ሲያከብሩ እነዚህን ሁለት የሚታዩ ምልክቶችን እንድያደርጉ ሙሴ ያሳስባቸዋል (ተነጻጻሪ ዘይቤ፤ ለተመሳሳይ አገላለጽ 13፡8-10 ተመልከት)
ቅርብ በሆነው መንገድ
እስራኤላውያን ረጅሙን ዕድሜያቸውን በባርነት ስላሳለፉ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን ስለሚፈልጉ ከመዋጋት ይልቅ ወደ ባርነት መመለስ ይፈልጋሉ
ኤታም ወደ ፍልስጥኤም በሚወስደው መንገድ ላይ በምድረ በዳው ዳር ላይ ወይም ድንበር ላይ ይገኛል
እግዚአብሔር ቀን በደመና ዐምድ /ምሶሶ መሳይ/፥ ሌሊት ብርሃን በሚሰጥ በእሳት ዐምድ /ምሶሶ መሳይ/ ይመራቸው ነበር
1 ለሙሴ እንዲህ ብሎ ተናገር፤ 2 በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በፊሀሒሮት ፊት፣ በበኣልዛፎንም አንጻር እንዲሰፍሩ ለእስራኤላውያን ንገር። በፊሀሒሮት ትይዩ በባሕሩ አጠገብ ትሰፍራላችሁ። 3 ፈርዖን ስለ እስራኤላውያን፣ ‘በምድሪቱ እየተንከራተቱ ነው፤ ምድረ በዳውም ዘግቶባቸዋል’ ይላል። 4 የፈርዖንን ልብ እኔ አደነድነዋለሁ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ይከታተላቸዋል። በፈርዖንና በመላው ሰራዊቱ ምክንያት እኔ እከብራለሁ። ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” ስለዚህ እስራኤላውያን በተነገራቸው መሠረት ሰፈሩ። 5 ንጉሥ እስራኤላውያን እንደ ሄዱ ሲነገረው፣ ፈርዖንና አገልጋዮቹ ሐሳባቸውን በመለወጥ፣ እስራኤላውያን ለእኛ ከመሥራት ነጻ ሆነው እንዲሄዱ መፍቀዳችን ምን ማድረጋችን ነው? አሉ። 6 ሠረገላዎቹ እንዲዘጋጁለት አደረገ፤ ሰራዊቱንም ከእርሱ ጋር ይዞ ሄደ። 7 መቶ ምርጥ ሠረገሎችንና የግብፅን ሌሎች ሠረገሎች በሙሉ፣ በያንዳንዳቸው ላይ መኮንኖች ያሉባቸውን ይዞ ተንቀሳቀሰ። 8 እግዚአብሔር የግብፅን ንጉሥ፣ የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ንጉሡ እስራኤላውያንን ተከታተላቸው። አሁን እስራኤላውያን በድል ወጥተው ሄደዋል። 9 ነገር ግን ግብፃውያን፣ ሁሉም የፈርዖን ፈረሶችና ሠረገሎች፣ የፈርዖን ፈረሰኞችና ሰራዊቱ እስራኤላውያንን አሳደዷቸው። በበኣልዛፎን አንጻር በባሕሩ አጠገብ ፊሀሒሮት ጥግ ሰፍረው እንዳሉ ደረሱባቸው። 10 ፈርዖን በቀረ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ወደ ላይ ተመለከቱ፣ ተደነቁም። ግብፃውያን ከኋላ እየተከተሏቸው ነበርና ፈሩ። እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። 11 እንዲህ አሉት፤ “እዚህ ያመጣኸንና በምድረ በዳ እንድንሞት ያደረግኸው በግብፅ መቃብር ታጥቶ ይህን ነግረንህ አልነበረምን? 12 ሠራተኞች እንድንሆን ተወን’ ብለንህ ነበር። በምድረ በዳ ከምንሞት፣ ለእነርሱ ሠራተኞች ሆነን ብንቀር ይሻል ነበር።’” 13 እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ። ጸንታችሁ ቁሙና ዛሬ እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርግላችሁን ትድግና ታያላችሁ። ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ዳግም አታዩአቸውም። 14 እግዚአብሔር ለእናንተ ይዋጋል፤ እናንተ መታገሥ ብቻ ነው ያለባችሁ።” 15 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሙሴ ለምን ትጮኽብኛለህ? እስራኤላውያን ወደ ፊት እንዲሄዱ ንገራቸው። 16 የእስራኤል ስዎች በባሕሩ ውስጥ በደረቅ መሬት እንዲሻገሩ በትርህን አንሣና እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርግተህ ለሁለት ክፈለው። 17 ተከትለዋቸው እንዲገቡ እኔ የግብፃውያንን ልብ የማደነድን መሆኔን ዕወቅ። ከፈርዖንና ከሰራዊቱ ሁሉ፣ ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ የተነሣ እኔ እከብራለሁ። 18 በፈርዖን፣ ሠረገሎቹና በፈረሰኞቹ ምክንያት ክብርን ሳገኝ፣ ግብፃውያኑ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።” 19 ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ በስተ ኋላቸው ሄደ። የደመናውም ዐምድ ከፊታቸው ተንቀሳቅሶ በስተኋላቸው ሄዶ ቆመ። 20 በግብፅ ሰራዊትና በእስራኤል መካከል መጣ። ለግብፃውያን የጨለማ ደመና ሲሆን፣ ለእስራኤላውያን ግን ሌሊቱን ብሩህ ያደረገ ደመና ነበር፤ ይህም ሌሊቱን ሙሉ አንደኛው ወገን ወደ ሌላው እንዳይጠጋ አደረገ። 21 እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ። እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት ባሕሩን በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ወደ ኋላ እንዲሄድ በማድረግ ባሕሩን ደረቅ መሬት አደረገው። በዚህ መንገድ ውሃው ተከፈለ። 22 እስራኤላውያን በባሕሩ መካከል ገብተው በደረቅ መሬት ዐለፉ። ውሃው በቀኛቸውና በግራቸውና በኩል ግድግዳ ሆነላቸው። 23 ተከታትለዋቸው መጡ። እነርሱ፣ የፈርዖን ፈረሶች ሠረገሎችና ፈረሰኞች ሁሉ እስራኤላውያኑ ተከትለው በባሕሩ መካከል ገቡ። 24 ላይ እግዚአብሔር በእሳቱና በደመናው ዐምድ ውስጥ የግብፃውያንን ሰራዊት ወደ ታች ተመለከተ። በግብፃውያን መካከልም ሽብር እንዲፈጠር አደረገ። 25 የሠረገሎቻቸው መንኯራኵሮች ተቆላለፉ፤ ፈረሰኞችም ለመንቀሳቀስ እጅግ ተቸገሩ። ስለዚህ ግብፃውያኑ፣ እግዚአብሔር እኛን እየወጋላቸው ነውና፣ ከእስራኤል እንሽሽ” አሉ። 26 ሙሴን፣ “ውሃው በግብፃውያኑ፣ በሠረገሎቻቸውና በፈረሰኞቻቸው ላይ ተመልሶ እንዲመጣባቸው እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ” አለው። 27 እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ንጋት ላይም ባሕሩ ወደ ተለመደ ስፍራው ተመለሰ። ግብፃውያኑ ከባሕሩ ሸሹ፤ እግዚአብሔር ግን ወደ ባሕሩ መካከል አስገባቸው። 28 ውሃው ተመስሎ በመምጣት የፈረዖንን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞችን ሠረገሎቹን ተከትለው ወደ ባሕሩ የገቡትን ጠቅላላ ሰራዊቱን ሸፈናቸው። አንድም ሳይሰምጥ የቀረ አልነበረም። 29 ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ላይ ተራምደው ሄዱ። ውሃው በቀኛቸውም በግራቸውም በኩል ለእነርሱ ግድግዳ ሆናላቸዋል። 30 እግዚአብሔር በዚያ ቀን እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ ታደጋቸው፤ እስራኤላውያኑም የግብፃውያኑን ሬሳ በባሕሩ ዳር አዩ። 31 እግዚአብሔር በግብፃውያኑ ላይ የገለጠውን ታላቅ ኀይል ሲያዩ፣ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አከበሩ፣ በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሙሴም ታመኑ።
እነዚህ በምስራቃዊው ግብጽ ላይ ያሉ ከተሞች ናቸው
ይህ ቀጥተኛ ንግግር ቀጥታ ባልሆነ ሲጻፍ፦ “ንጉሡ ፈርዖን የእስራኤል ህዝብ በበረሓ ተዘግተው ወይም መንገድ አጥተው በአገሪቱ ዙሪያ የሚንከራተቱ ይመስለኛ” ብሎ አሰበ።
ምድረ በዳው እስራኤላውያንን እንደጠለፋቸውና በአንድ ቤት ዘግቶ እንዳስቀመጣቸው አድርጎ ፈርዖን ይናገራል። ነገር ግን ሀሳቡ “እስራኤላውያን በምድረ በዳ መንገድ አጥተው” ማለት ነው።
የፈርዖን ልብ የተባለው ራሱ ፈርዖን ማለት ነው። ፈርዖን ለመስማት አልፈለገም ወይም እምብ አለ ማለት ነው። (ወካይ ወይም ተለዋጭ ዘይቤ ተመልከት)። በዚህኛ ክፍል የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ወይም ፈርዖን እንዳይሰማ ያደረገው እግዚአብሔር እንደሆነ ነው። (ዘጸአት 9፡12 ተመልከት)
በሌላ አገላለጽ፦ ፈርዖን እስራኤላውያንን ያብርራቸዋል ማለት ነው
ሰዎች እኔን ያከብሩኛል
በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ እንደ ሆንኩ ግብጻውያን ያውቃሉ
እስራኤላውያን እንደ ተነገራቸው አደረጉ ወይም እስራኤላውያን እግዚአብሔር እንደ ነገራቸው ፈጸሙ
ለግብጽ ንጉስ ፈርዖን
እስራኤላውያን እንዳመለጡ
ፈርዖንና አገልጋዮቹ/መኳንንቱ/ ሀሳባቸውን ቀይረው ወይም ለውጠው
ፈርዖንና መኳንንቱ ይህን ጥያቄ የጠየቁት የሞኝነት ተግባር እንደፈጸሙ ስላሰቡ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ይህ የሠራነው ነገር ምንድን ነው? እስራኤላውያንን እንዲሄዱ ፈቅደን አገልጋዮችን ማጣታችን አይደለምን? (አጋናኝ ጥያቄ የመተርግም ዘዴ ተመልከት)
ስድስት መቶ (600) ምርጥ ሠረገሎችን . . . አሰለፈ
የፈርዖን ልብ የተባለው ራሱ ፈርዖን ማለት ነው። ፈርዖን ለመስማት አልፈለገም ወይም እምብ አለ ማለት ነው። (ወካይ ወይም ተለዋጭ ዘይቤ ተመልከት)። በዚህኛ ክፍል የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ወይም ፈርዖን እንዳይሰማ ያደረገው እግዚአብሔር እንደሆነ ነው። (ዘጸአት 9፡12 ተመልከት)
በግብጽ ምስራቃዊው ክፍል የሚገኙ ከተሞች ነበሩ (ስሞችን የመተርጎም ዘዴ ተመልከት)
በዚህ ክፍል “ፈርዖን” የተባለው መላውን የፈርዖን ሠራዊት የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ንጉሡ “ፈርዖንና ሠራዊቱ እየቀረቡ መምጣታቸውን”
እስራኤላውያን ይህንን ጥያቄ የጠየቁት እንዳይሞቱ ከመፍራታቸው እና ከመደንገጣቸው የተነሳ ነው። ይህን አጋናኝ ጥያቄ በመደበኛ ዐረፍተ ነገር ሲንተረጉም፦ በግብጽ ምድር በቂ የመቃብር ቦታ አለ፤ ለመቀበር ወይም መቃብር ፍለጋ እዚህ ምድረ በዳ መምጣት አልነበረብንም።
እስራኤላውያን ይህን ጥያቄ ሙሴን የጠየቁት በምድረ በዳ እንድሞቱ በማምጣቱ ለመገሰጽ ወይም ለመተቸት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ እኛን ከግብጽ አውጥተኸን እንዲህ ሊታሰቃየን አይገባህም ነበር።
ይህ አጋናኝ ጥያቄ የሚያሳየው ከዚህ በፊት በግብጽ እያሉ ለእርሱ የነገሩትን ለማስታወስ ወይም አትኩሮት ለመስጠት ነበር። አማራጭ ትርጉም፦ ይህ ሁሉ እንደሚሆን ገና ከዚያ ሳንወጣ ወይም በግብጽ ሳለን ነግረንህ አልነበረምን?
በሌላ አገላለጽ፦ “እባክህ ተወን ወይም ይቅርብን ለግብጻውያን ባርያዎች ሆነን እናገልግል” ብለን ነግረንህ ነበር
ሙሴ ለህዝቡ/ለእስራኤላውያን/ እንዲህ ብሎ መልስ ሰጣቸው
እግዚአብሔር ዛሬ እናንተን እንዴት እንደምያድን/ለእናንተ እንዴት እንደሚሰራ/
ሙሴ እስራኤላውያንን በትህትና በማናገር እግዚአብሔር የግብጻውያንን ሰራዊት እንደሚደመስስ ይነግራቸዋል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር ዛሬ የግብጻውያንን ሰራዊት ይገድላል። (በአይነኬ ዘይቤ የተነገረ)
ሙሴ እርዳታ ፍለጋ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበረና እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ ሙሴን ለማስገደድ ሲጠቀምበት እናያለን። ይህን አጋናኝ ጥያቄ በሁለት መንገድ በአጋናኝ ጥያቄ ወይም በመደበኛ ዐረፍተ ነገር መተርጎም ይቻላል። 1) “ሙሴ አንተ ወደ እኔ የምትጮኸው ለምንድን ነው?” 2) ሙሴ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ እኔ አትጩህ ወይም ከእንግዲህ ወዲህ እኔን አትጥራ”
ውሃውን ለሁለት ክፈለው ወይም ውሃው ለሁለት ይከፈላል
“የግብጻውያንን ልብ” የተባለው ግብጻውያንን የሚመለከት ሲሆን “ገታራነታቸው ወይም እልከኝነታቸው” ልባቸው ጠንካራ እንደሆነ ተመስሎ ተነገረ። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ ግብጻውያን እንብተኞች ወይም እልከኞች አደርጋቸዋለሁ።
ግብጻውያን እስራኤላውያንን ተከትለው ባህሩ ውስጥ ይገባሉ
በግብጻውያን ሠራዊት መካከል እና በእስራኤላውያን ሠራዊት መካከል
የግብጽ ሠራዊት ሌሊቱን ሙሉ ወደ እስራኤላውያን ሠራዊት መጠጋት አልቻለም ወይም የግብጽ ሠራዊትና የእስራኤል ሠራዊት አንዱ ሌላው ጋር መጠጋት አልቻሉም
ይህ ነፋስ ከምስራቅ በኩል ይነሳና ወደ ምዕራብ ይነፍሳል
ፀሐይ የሚወጣበት አቅጣጫ
በሌላ አገላለጽ፦ “እግዚአብሔር ውሃውን ከፈለው”
አንድ ሰው ከፍርሃት የተነሳ ሲታወክ በትክክል ማሰብ አይችልምና ከልክ በላይ ደነገጡ ወይም ፈሩ ወይም የሚሆኑትን አጡ ማለት ነው።
የሠረገላዎቻቸውን ብረት ጎማ ወይም መንኩራኮር ከመሬት ወይም ከጭቃ ጋር አጣበቀባቸው
አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “ውሃው በግብጻውያን ላይ፥ በሰረገላዎቻቸው ላይና በፈረሰኞቻቸው ላይ እንዲመለስ እጅህን በባህሩ ላይ ዘርጋ”
የእብራይስጡ ትርጉም ከባህሩ ሸሹ ሳይሆን ወደ ባህሩ ሮጡ የሚል ፍቺ አለው። ይህ ማለት ግብጻውያን ከውሃው መሸሽ ሲገባቸው እየዋጣቸው ወዳለው ውሃ ይሮጡ ነበር።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ግብጻውያንን በባህሩ ውስጥ አሰጠማቸው
በተለያዩ ቦታዎች “እስራኤል” ተብሎ የተጠቀሰው “የእስራኤል ህዝብን” የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የእስራኤል ህዝብ ወይም እስራኤላውያን
“እጅ” የሚለው ቃል “ሀይልን” የሚመለከት ሲሆን እግዚአብሔር ከግብጻውያን ሀይል/ጥቃት/ጉልበት/ ማለት ይቻላል (ወካይ ዘይቤ ተመልከት)
በባህሩ አጠገብ አዩ
1 ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል። 2 ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆኖልኛል። እርሱ አምላኬ ነው፣ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፣ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። 3 ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው። 4 ሠረገሎችና ሠራዊት በባሕር ውስጥ ጥሎአል። የፈርዖን ምርጥ መኮንኖች በቀይ ባሕር ውስጥ ሰመጡ። 5 ማዕበሎቹ ሽፈናቸው፤ እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቆቹ ወረዱ። 6 እግዚአብሔር ሆይ፣ ቀኝ እጅህ ጠላትን ሰባበረ። 7 ላይ የተነሡትን በታላቅ ግርማ ገለበጥሃቸው። ቊጣህን ላክህ፤ እንደ ገለባም አርጎ በላቸው። 8 በአፍንጫህ እስትንፋስ ውሆች ተከመሩ፤ ፈሳሾች እንደ ክምር ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ በባሕሩ ውስጥ ረጋ። 9 ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፣ እይዛቸዋለሁ፣ ምርኮም እካፈላለሁ፤ ፍላጎቴ በእነርሱ ርዳታ ያገኛል፤ ሰይፌን እመዝዛለሁ፤ እጄም ታጠፋቸዋለች’ አለ። 10 ግን በነፋስህ እፍ አልህ፣ ባሕሩም ሸፈናቸው፤ በኀይለኛ ውሆች ውስጥ እንደ ብረት ሰመጡ። 11 ሆይ፣ ክአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና የከበረ፣ ተአምራትን በማድረግ በምስጋና ከፍ ያለ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? 12 እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው። 13 ፍቅርህ የታደግሃቸውን ሕዝብህን መራህ። በብርታትህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ መራሃቸው። 14 ይሰማሉ፣ ይንቀጠቀጣሉም፤ የፍልስጥኤምን ኗሪዎች ሽብር ይይዛቸዋል። 15 ጊዜ የኤዶም እለቆች ይደነግጣሉ፤ የሞዓብ መሪዎች ይርበደበዳሉ፤ የከነዓን ኗሪዎች ሁሉ ይቀልጣሉ። 16 ሆይ፣ ሕዝብህ እስከሚያልፉ፣ የታደግሃቸው ሕዝብህ ዐልፈው እስከሚሄዱ ድረስ፣ ሽብርና ድንጋቴ ይወድቅባቸዋል፤ ከክንድህ ብርታት የተነሣ፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ። 17 ሆይ፣ ማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፣ ጌታችን ሆይ፣ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣ በርስትህ ተራራ ላይ ሕዝብህን ታመጣቸዋለህ፣ ትተክላቸዋለህም። 18 ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል።” 19 ፈረሶች ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ ጋር ወደ ባሕሩ ውስጥ ሲገቡ፣ እግዚአብሔር የባሕሩን ውሀ መልሶ በላያቸው አመጣባቸው። እስራኤላውያን ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ሄዱ። 20 ይአሮን እኅት፣ ነቢይቱ ማርያም ከበሮ አነሣች፤ ሌሎቹ ሴቶችም በሙሉ ከበሮ ይዘው ከእርሷ ጋር እያሸበሸቡ ወጡ። 21 “ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል፤ በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና፣ ለእግዚአብሔር ዘመሩ” እያለች ዘመረችላቸው። 22 ሙሴ እስራኤላውያንን ከቀይ ባሕር እየመራቸው ወደ ሱር ምድረ በዳ ሄዱ። በምድረ በዳው ውስጥ ሦስት ቀን ሲጓዙ ውሀ አላገኙም። 23 ማራም ደረሱ፤ ነገር ግን እዚያ የሚገኘው ውሀ መራራ ስለ ነበረ ሊጠጡት አልቻሉም። ቦታውን ማራ ያሉት ከዚህ የተነሣ ነው። 24 ሕዝቡ፣ “ምን እንጠጣ?” ብለው በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። 25 ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፣ እግዚአብሔርም አንድ ዛፍ አሳየው። ሙሴም የዛፉን ዕንጨት ወደ ውሀው ውስጥ ጣለው፣ ውሀውም ጣፋጭ ሆነ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሕግና ሥርዐት የሰጣቸውና የፈተናቸው በዚያ ስፍራ ነበር። 26 እንዲህ አለ፤ “የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፥ ትክክለኛ የሆነውንም በፊቱ ብታደርጉ፣ ትእዛዛቱንም ብታስተውሉና ሕግጋቱን ሁሉ ብትጠብቁ፣ ግብፃውያን ላይ ካመጣኋቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤ እኔ ፈዋሻችሁ እግዚአብሔር ነኝና።” 27 በኋላ ሕዝቡ ዐሥራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ወደ ነበሩበት ወደ ኤሊም መጡ። በዚያም በውሀው አጠገብ ሰፈሩ።
ይህ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ለድል አድራጊነቱ የተዘመረ መዝሙር ነው። በሌላ አገላለጽ፦ “እርሱ በግብጻውያን ላይ በታላቅ አሸናፊነት ተገለጸ” ወይም “እርሱ በግብጻውያን ታላቅ ድል ተጎናጸፈ”
እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ ባህሩን መመለሱንና እነርሱን በባህር ማስጠሙን ሙሴ በሌላ አገላለጽ እግዚአብሔር በባህር ውስጥ እንደጣላቸው ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ “እርሱ በፈረሱና በፈረሰኛው ላይ ባህሩን መለሰባቸው” ወይም “እርሱ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባህር አሰጠማቸው”
እስራኤላውያንን የሚያሳድዱ ብዙ ፈረሶችንና ፈረስ ጋላቢዎችን የሚገልጽ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ፈረሶችንና ፈረስ ጋላቢዎችን
አማራጭ ትርጎሞች፦ 1) ሀይልን የሚሰጠኝ እግዚአብሔር ነው 2) እኔን የሚጠብቀኝ ወይም የሚከላከለኝ እግዚአብሔር ነው
ሙሴ እግዚአብሔርን የዝማሬዬ ምንጭ ነው ወይም እግዚአብሔር እኔ የሚዘምርለት እርሱ ነው
ሙሴ እግዚአብሔር መድሀኒቴ ብሎ ይጠራዋል ምክንያቱም እርሱ ከግብጻውያን እጅ አድኖአቸዋልና። አማራጭ ትርጉም፦ የሚያድነኝ እግዚአብሔር ነው
ሙሴ እግዚአብሔርን ተዋጊ ብሎ ይጠራል ምክንያቱም እርሱ በሀይሉ ግብጻውያንን ተዋግቶ አሸንፏል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር እንደ ብርቱ ተዋጊ ነው (ተለዋጭ ዘይቤ)
ሙሴ ስለእግዚአብሔር ሲዘምር እግዚአብሔር ባህሩን በፈርዖን፥ ሰረገሎችና በሠራዊቱ ላይ መመለሱን በባህር ውስጥ እንደመጣል ተነግሯል። አማራጭ ትርጉም፦ እርሱ በፈርዖን ሰረገላዎችንና በሠራዊቱ ላይ ባህሩን መልሷል ወይም እርሱ የፈርዖን ሰረገላዎችንና ሠራዊቱን በባህር አስጥሟል
ድንጋይ በባህር እስከ ውስጥ እንደሚሰጥም የጠላት ሠራዊት እስከ ባህሩ ጥልቅ ድረስ መስጠማቸውን ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ ድንጋይ በባህር ውስጥ እንደሚሰጥም እነርሱ በብሃር ውስጥ ሰጠሙ (ተነጻጻር ዘይቤ)
ሙሴ እግዚአብሔር እጅ እንዳለው አድርጎ ይናገራል፤ “ቀኝ እጅ” የእግዚአብሔርን ሀይል ወይም እግዚአብሔር በሀይሉ የሚሰራቸውን ነገሮች ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር ሀይልህ የከበረ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ አንተ በሀይልህ የምትሰራቸው ነገሮች ክቡር ናቸው (ወካይ ዘይቤ)።
ሙሴ እግዚአብሔር እጅ እንዳለው አድርጎ ይናገራል፤ “ቀኝ እጅ” የእግዚአብሔርን ሀይል ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር ሆይ ሀይልህ ጠላቶችን አደቀቀ ወይም እግዚአብሔር ሆይ በሀይልህ ጠላቶችን አደቀቅህ
በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ በእግዚአብሔር ላይ እንደመነሳት ተቆጥሯል፤ አማራጭ ትርጉም፦ በአንተ ላይ ያመጹ ወይም ጠላቶችህን
የእግዚአብሔርን ቁጣ ሙሴ ሲገልጽ አንድ ነገር ለመሥራት እንደ ተላከ አገልጋይ አድርጎ ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ ቁጣህን አሳየህ ወይም አንተ እንደ ቁጣ ሥራህን ፈጸምክ
x
በሌላ አገላለጽ፦ እኔ ፍላጎቴን አሟላለሁ ወይም እኔ የፈለግሁትን ከእነርሱ እወስዳለሁ
ጠላቶች እስራኤላውያንን በእጃቸው ሀይል እንደሚያጠፉ ሲናገሩ እጃቸው እያጠፋቸው እንደሆነ አስመስለው ይናገራሉ። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ በእጄ አጠፋቸዋለሁ
ሙሴ እግዚአብሔር በአፉ ወይም በአፍንጫው ነፋሱን እንደነፈሰባቸው አድርጎ ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ ነፈሱ እንዲነፍስ አድርገሃል
አረር ከባድ የብረት ዘር ሲሆን ነገሮች በውሃ ወይም በባህር ውስጥ እንድሰምጡ ሲፈለግ አረር ይጠቀማሉ። እዚህ ቦታ “አረር” የተጠቀሰበት ምክንያት ጠላቶች ምን ያህል ፈጥነው እንደ ጠፉ ለማሳየት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እንደ አረር ወይም ከባድ ብረት በሚናወጠው ውሃ ውስጥ ሰጥመው ቀሩ
ሙሴ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው የእግዚአብሔርን ትልቅነት ለመግለጽ ሲፈልግ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው?
ሙሴ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው የእግዚአብሔርን ትልቅነት ለመግለጽ ሲፈልግ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ታአምራትን የምታደርግ አንደ አንተ ያለ ማን ነው? ወይም ድንቅ ሥራዎችን የምትሰራ አንተን የሚመስል ማን ነው።
“ቀኝ እጅ” የእግዚአብሔርን ታላቅ ሀይል የሚገልጽ አባባል ሲሆን “በታላቅ ሀይልህ” የሚል ፍቺ አለው። “ዘረጋህ” የሚለው እግዚአብሔር እጅ እንዳለውና እጁን እንደዘረጋው አድርጎ ያሳያል። አማራጭ ትርጉም፦ በታላቅ ሀይልህ ይህን አደርግኸው
ሙሴ በሰውኛ ዘይቤ ምድር አፍ እንዳላትና ነገሮችን መዋጥ ወይም መብላት እንደምትችል አድርጎ ያቀርባል። አማራጭ ትርጉም፦ ምድር በላቻቸው ወይም አጠፋቻቸው
ይህ በፍርሃት ምክንያት መንቀጥቀጣቸውን የሚገልጽ ነው።
ፍልስጥኤማውያን ወይም በፍልስጥኤም የሚኖሩ ሰዎች ተሸበሩ/ታወኩ/
ሰዎች ከፍርሃት የተነሳ መድከማቸውን ሙሴ እንደ ቀለጡ አድርጎ ያሳያል። በሌላ አገላለጽ፦ የከነዓን ሕዝብ ወኔ ከዳቸው ወይም ድፍረት አጡ
አነዚህ ሁለቱ ቃላት የሚያሳዩት በእነርሱ ላይ ፍርሃት ሊመጣ እንደሆነ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “ፍርሃት በእነርሱ ላይ ይመጣል”
የእግዚአብሔር ክንድ የእርሱን ትልቅ ሀይል የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ከሀይልህ ትልቅነት የተነሳ”
አማራጭ ትርጉሞች፦ 1) እነርሱ እንደ ድንጋይ ዝም ይላሉ 2) እነርሱ እንደ ድንጋይ እንቅስቃሴ አልባ ይሆናሉ
“አንተ ታስገባቸዋለህ” የሚለው በሌላ አገላለጽ፦ አንተ ህዝብህን ወደ ከነዓን ታመጣቸዋለህ ወይም ትወስዳቸዋለህ የሚል ነው።
እግዚአብሔር የከነዓንን ምድር ለእስራኤላውያን ርስት አድርጎ መስጠቱን ሙሴ ተክል ከመትከል ጋር ሲያነጻጽር ይታያል። “የርስት ተራራ” የተባለው በከነዓን ምድር ያለው “የጽዮን ተራራ ነው”። እግዚአብሔር ምድርቱን እንደ ርስት አድርጎ ይሰጣቸዋል። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ እነርሱን በርስት ተራራቸው ታኖራቸዋለህ ወይም እነርሱ በርስት ተራራቸው ይኑሩ።
ማርያም የሙሴና የአሮን ታላቅ እህት ነበረች።
ከሙዚቃ መሳሪያዎች አንዱ ሲሆን ከተለያዩ ቁሳቁሶች ይሰራል፤ ለምሳሌ ከብረት፥ ከእንጨትና ከቆዳ ወዘተ።
ይህ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ለድል አድራጊነቱ የተዘመረ መዝሙር ነው። በሌላ አገላለጽ፦ “እርሱ በግብጻውያን ላይ በታላቅ አሸናፊነት ተገለጸ ወይም እርሱ በግብጻውያን ታላቅ ድል ተጎናጸፈ (15፡1 ተመልከት)
እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ ባህሩን መመለሱንና እነርሱን በባህር ማስጠሙን ሙሴ በሌላ አገላለጽ እግዚአብሔር በባህር ውስጥ እንደ አንድ ነገር እንደ ጣላቸው ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ እርሱ በፈረሱና በፈረሰኛው ላይ ባህሩን መለሰባቸው ወይም እርሱ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባህር አሰጠማቸው (15፡1 ተመልከት)
“እስራኤል” የሚለው የእስራኤልን ህዝብ የሚወክል ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ሙሴ የእስራኤልን ህዝብ መራቸው
እነዚህ ቦታዎች በትክክል የት ጋር እንደሆኑ በትክክል ማሳየት አይቻለም። ነገር ግን ቦታዎች ወይም መንደሮች ነበሩ፤ ምናልባት በከነዓን ምድር በደቡባዊ ምስራቅ የሚገኙ አከባቢዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
ህዝቡ በሙሴ ላይ ደስተኞች አለመሆናቸውን የሚገልጽ ነው፤ አማራጭ ትርጉም፦ በሙሴ ላይ አጉረመረሙ ወይም በሙሴ ላይ በቁጣ ተናገሩ
እግዚአብሔር ስለራሱ ድምጽ ይናገራል፤ ድምጹ እርሱን ይገልጻል ወይም ይወክላል። በሌላ አገላለጽ፦ ድምጼን ወይም እኔ የሚለውን (ወካይ ዘይቤ)
“በፊቱ” የሚለው በእግዚአብሔር ፊት ሲሆን አንድ ሰው በእግዚአብሔር በዓይኑ ፊት ቆሞ አንድ ነገር እንደምፈጽም የሚናገር ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር የሚቀበለውን መልካም ነገር አድርጉ ወይም እግዚአብሔር የሚፈልገውን ነገር አድርጉ
ውሃና መልካም አየር እንዲህም ትላልቅ ዛፎች ያሉበት ቦታ ነው።
“ዘንባባ” የተባለው በርግጥ ዘንባባ ሳይሆን ተምር ነው። ተምር በመልኩ ከዘንባባ ጋር ስለሚመሳሰል አማርኛው ትርጉም ዘንባባ ብሎታል። በሌላ አገላለጽ፦ ሰባ የተምር ዛፎች
1 የእስራኤል ማኅበር አባላት ከኤሊም ተንሥተው፣ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ዐሥራ አምስተኛ ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ። 2 በዳው ውስጥም ጠቅላላ የማኅበሩ አባላት በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ። 3 ሙሴንና አሮንንም፣ “በሥጋ ምንቸቶች ዙሪያ ተቀምጠን እስክንጠግብ ምግብ በምንበላበት በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን ኖሮ፤ ከዚያ አውጥታችሁ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁን መላውን ማኅበራችንን በረኃብ ልትጨርሱ ነውና” አሏቸው። 4 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንጀራ ከሰማይ አዘንብላችኋለሁ። በሕጌ የሚመሩ ወይም የማይመሩ መሆናቸውን እንድፈትናቸው፣ ሕዝቡ ይውጡና በየቀኑ ለአንድ ቀን የሚሆነውን ይሰብስቡ። 5 ቀን በየቀኑ ከሚሰበስቡት ዕጥፍ ይሰብስቡ፤ ያመጡትንም ያዘጋጁ።” 6 ከዚያም ሙሴና አሮን ለእስራኤል ሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “ከግብፅም ምድር ያወጣችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ማታ ታውቃላችሁ። 7 በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶአልና፣ የእግዚአብሔርንም ክብር ጠዋት ታያላችሁ። በእኛ ላይ ልታጕረመርሙ እኛ ለእናንተ ምንድን ነን?” 8 ደግሞ እንዲህ አለ፤ በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶታልና፣ እግዚአብሔር ማታ ሥጋ፣ ጠዋትም ምግብ እስክትጠግቡ ሲሰጣችሁ፣ ይህን ታውቁታላችሁ። አሮንና እኔ ምንድን ነን? የምታጕረመርሙት በእኛ ላይ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ ነው።” 9 ሙሴ አሮንን፣ “‘ጕርምርምታችሁን ሰምቶታልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በልህ ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ ተናገር’” አለው። 10 አሮን ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ እንደ ተናገረ፣ ወደ ምድረ በዳው ተመለከቱ፤ እነሆም፣ የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ውስጥ ታየ። 11 እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዲህ ብሎ ነገረው፤ 12 “የእስራኤልን ሕዝብ ጕርምርምታ ሰምቻለሁ። እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ማታ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ጠዋት ደግሞ እንጀራ ትበሉና ትጠግባላችሁ። ከዚያም በኋላ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ። 13 ላይ ድርጭቶች መጡና ሰፈሩን ሸፈኑት። በጠዋቱም የሰፈሩን ዙሪያ ጤዛ ተኝቶበታል። 14 ሲጠፋ፣ እንደ ዐመዳይ ያለ ስስ ቅርፊት በምድረ በዳው ላይ ታየ። 15 ሰዎች ሲያዩት፣ አንዳቸው ለአንዳቸው፣ “ምንድን ነው?” ተባባሉ። ምን እንደ ነበረ አላወቁም። ሙሴም እንዲህ አላቸው፤ “ይህ እንድትበሉት እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው። 16 እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶአል፦ ‘ለመብላት የምትፈልጉትን መጠን በሕዝባችሁ ቊጥር ለያንዳንዱ ሰው አንድ ጎሞር ሰብስቡ። የምትሰበስቡት እንደዚህ ነው፦ በድንኳናችሁ ውስጥ ለሚኖር ለእያንዳንዱ ሰው ለመብላት የሚበቃውን ሰብስቡ።” 17 የተነገራቸውን አደረጉ። አንዳንዶች የበለጠ፣ አንዳንዶችም ያነሰ ሰበሰቡ። 18 በጎሞር መጠን ሲለኩት፣ ብዙ የሰበሰቡት የተረፈ አላገኙም፤ ትንሽ የሰበሰቡትም ያጡትናየጎደለባቸው አልነበረም። እያንዳንዱ ሰው የሰበሰበው ለፍላጎቱ የሚበቃውን ያህል ነበር። 19 “ማንም ሰው ለነገ ከእርሱ ምንም ማስተረፍ የለበትም” አላቸው። 20 ግን ሕዝቡ ሙሴን አልሰሙትም። አንዳንዶቻቸው ከሰበሰቡት እስከሚቀጥለው ጠዋት የተወሰነ አስቀሩ፤ ያስቀሩት ምግብ ግን ተላ፣ ሸተተም። ሙሴ ተቆጣቸው። 21 የሰበሰቡት ጠዋት ጠዋት ነበር። እያንዳንዱ ሰው ለቀኑ የሚበቃውን ሰበሰበ። ፀሐይ ስትሞቅ ቀለጠ። 22 ቀን ለያንዳንዱ ሰው ሁለት ሁለት ጎሞር እንጀራ አድርገው ዕጥፍ ሰበሰቡ። የማኅበረ ሰቡ አለቆችም በሙሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት። 23 “እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘ነገ ፍጹም ዕረፍት፣ ለእግዚአብሔር ክብር የተቀደሰ ሰንበት ነው። መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤ መቀቀል የምትፈልጉትንም ቀቅሉ። ተርፎ የሚቀረውን ሁሉ እስከ ጠዋት ለራሳችሁ አስቀምጡት’” አላቸው። 24 የተረፈውን ሙሴ በነገራቸው መሠረት እስከ ጠዋት አቆዩት። አልሸተተም፤ ትልም አልነበረበትም። 25 እንዲህ አለ፤ “ዛሬ እግዚአብሔርን ለማክበር የተቀደሰ ሰንበት ነውና፣ ያስተረፋችሁትን ያን ምግብ ዛሬ ብሉት። ዛሬ ሜላ ላይ አታገኙትም። 26 ቀኖች ትሰበስቡታላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የሰንበት ቀን ነው። በሰንበት ቀን መና የለም።” 27 ቀን አንዳንዶች መና ሊሰበስቡ ወጡ፣ ነገር ግን ምንም አላገኙም። 28 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ትእዛዛቴንና ሕገጋቴን ለመጠበቅ እንቢ የምትሉት እስከ መቼ ነው? 29 በሉ፤ እግዚአብሔር ሰንበትን ሰጥቶአችኋል። ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሰጣችሁ ለሁለት ቀን የሚሆን እንጀራ ነው። ከእናንተ እያንዳንዱ በገዛ ስፍራው ይቆይ፤ በሰባተኛው ቀን ማንም ሰው ከስፍራው መውጣት የለበትም።” 30 በሰባተኛው ቀን ዐረፉ። 31 ምግቡን “መና” ብለው ጠሩት። ምግቡም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ፣ ጣዕሙም በማር በስሱ እንደ ተጋገረ ቂጣ ነበረ። 32 ሙሴም፣ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፦ ‘ከግብፅ ምድር ካወጣኋችሁ በኋላ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ልጆቻችሁ ማየት እንዲችሉ፣ አንድ ጎመር መና ለትውልዶቻችሁ ሁሉ ይቀመጥ” አለ። 33 አሮንን፣ “አንድ ማሰሮ ውሰድና አንድ ጎሞር መና አስቀምጥበት፤ ለትውልዶች ሁሉ ተጠብቆ እንዲቆይም በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው” አለው። 34 ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ አሮን መናውን በምስክሩ ፊት አስቀመጠው። 35 ወደሚኖሩበት ምድር እስከሚመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ። ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስከሚመጡ ድረስ የተመገቡት እርሱን ነው። 36 አንድ ጎመር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ነው።
“ሲን” የምድረ በዳው ስም ነው፤
በሁለተኛው ወር በአስራ አምስተኛ ቀን
ይህ ግነታዊ ዘይቤ አገላለጽ ሲሆን “እስራኤላውያን ሁሉ” (ጠቅላይ እና ግነታዊ ዘይቤ)
አጉረመረሙ ወይም ተቆጡ ወይም ተናደዱ
ይህ አገላለጽ አሁን ባለንበት ሁኔታ ውስጥ ከመጨናነቅ እዚያው ሞተን ቢሆን ይሻለን ነበር ብለው ተናገሩ። አማራጭ ትርጉም፦ ምነው በእግዚአብሔር (ያህዌ) እጅ ሞተን ባረፍነው ኖሮ ወይም ምነው በግብጽ ሳለን እግዚአብሔር በገደለን ኖሮ
“በእግዚአብሔር እጅ” የሚለው በአግዚአብሔር አሰራር ወይም እርምጃ የሚል ፍች አለው።
እግዚአብሔር ከሰማይ የሚልከውን ምግብ ከመዝነብ ጋር አነጻጽሯል። በሌላ አገላለጽ፦ ከሰማይ ምግብ እንደ ዝናብ እልክላችኋለህ /እሰጣችኋለህ/። “እንጀራ” የሚለው አንድ የተወሰነ የምግብ ዓይነት ይገልጻልና በአከባቢው የተለመደ ማንኛውንም የምግብ ዓይነት መጠቀም ይቻላል።
ህጌን ይታዘዙ ወይም አይታዘዙ እንደሆነ ማለት ነው
ትዕዛዜን ማለት ነው
ሙሴና አሮን ይህን አጋናኝ ጥያቄ የጠየቁት ህዝቡ በእነርሱ ላይ ማጉረምረማቸው ስንፍና ወይም ሞኝነት እንደሆነ ለማሳየት ነው። በአጋናኝ ጥያቄ ወይም በመደበኛ ዐረፍተ ነገር መተርጎም ይችላል። አማራጭ ትርጉም፦ በእኛ ላይ የምታጒረመርሙት እኛ ምን ስለሆንን ነው? ወይም በእኛ ለማጉረምረም እኛ ብቁ ሰዎች አይደለንም
ሙሴ “ምግብ” በማለት ፋንታ “እንጀራ ወይም ዳቦ” ይላል። ይህን ከሰማይ የሚሰጣቸውን ምግብ እንደ ሌሎቹ የምግብ ዓይነት ሁልጊዜ ይበሉታል።
ሙሴ ይህን አጋናኝ ጥያቄ የጠየቃቸው እርሱና አሮን ህዝቡ የፈለጉትን ነገር ለመስጠት እንደማይችሉ ለመግለጽ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔና አሮን እናንተ የምትፈልጉን ነገር መስጠት አንችልም
ህዝቡ ያጉረመረሙት የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሆኑት በሙሴና በአሮን ላይ ነበር። በሙሴና በአሮን ላይ ማጉረምረም በተዘዋዋሪ በእግዚአብሔር ላይ እንደማጉረምረም ነው። አማራጭ ትርጉም፦ በእኛ ላይ ስታጒረመርሙ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረማችሁ እንደሆነ እወቁ ወይም ማጉረምረማችሁ በእኛ ላይ ሳይሆን በርግጥ በእግዚአብሔር ላይ ነው
ይህ “እኔሆ” የሚለው ቃለ ህዝብ አንድ አስደናቂ ነገር እንዳየ ለማመልከት ወይም ትኩረት ለመሳብ ነው
ሙሴ “ምግብ” በማለት ፋንታ “እንጀራ ወይም ዳቦ” ይላል። ይህን ከሰማይ የሚሰጣቸውን ምግብ እንደ ሌሎቹ የምግብ ዓይነት ሁልጊዜ ይበሉታል። አማራጭ ትርጉም፦ በማለዳ/ጧት/ የምትፈልጉትን ያህል ምግብ ትጠግባላችሁ
ይህ አገናኝ ሀረግ በታሪኩ ውስጥ ያለውን በጣም አስፈላጊውን ክፍል ለይቶ ያሳያል። በአንተ ቋንቋ እንዲህ ባለሁ ጉዳይ ላይ አገልግሎት የሚሰጥ ቃል ካለ መጠቀም ይችላል።
ትናንሸ የሆኑ የወፍ ዝሪያዎች ናቸው፤
በጊዜው ለነበሩ ሰዎች “ውርጭ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። በአማርኛ ውርጭ የሚለው ቃል ወደ ከባድ ብርድ ያደላል። ነገር ግን “ውርጭ” እንደ በረዶ የመጋገር ባህርይ ያለው ስለሆነ አመዳይ ወይም እንደ ቅርፍት የተጋገረ ነገር ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ዐመዳይ ይመስል ነበር ወይም አመዳይ የሚመስል የተጋገረ ነገር
ሙሴ “ምግብ” በማለት ፋንታ “እንጀራ ወይም ዳቦ” ይላል። ይህ ከሰማይ የሚሰጣቸው ምግብ እንደ ሌሎቹ የምግብ ዓይነቶች ሁልጊዜ ይበሉታል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ወይም ዳቦ፥ ምግብ
አንድ ጎሞር ወደ ሁለት ሊትር ያህል ነው
ይህ ሀረግ በታሪኩ ውስጥ አዲስ ሀሳብ እየገባ ወይም እየጀመረ ስለመሆኑ ለማሳየት ነው። በቁጥር 22-23 ድረስ ባለው ክፍል በስድስተኛውና በሰባተኛ ቀን ህዝቡ መናውን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው ያሳያል። በአንተ ቋንቋ እንዲህ ያለ አገናኝ ሀረግ ካለ መጠቀም ጥሩ ነው።
ሥራ የማይሰራበትና እረፍት የሚደረግበት ቀን
በስብሶ መሽተት አልጀመረም
ዛሬ ሰንበት ስለሆነ እግዚአብሔርን ለማከበር ብቻ ይውላል
ነገር ግን በቀን ሰባት
እግዚአብሔር በየቀኑ ወይም በየማለደኣ ለሰጣቸው ምግብ እስራኤላውያን የሰጡት ስም ነው።
ምንም ምግብ አይኖርም ወይም ምንም ነገር አይኖርም
እግዚአብሔር ይህን አጋናኝ ጥያቄ የጠየቀ ህዝቡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዞች ስላልታዘዙ እነርሱን ለመተቸት ወይም ለመገሰጽ ነው። ይህን አጋናኝ ጥያቄ በመደበኛ ዐረፍተ ነገር ስንተረጉም፦ እናንተ እስራኤላውያን ትዕዛዞቼንና ህጎቼን ለመታዘዝ ፈቃደኛ አይደላችሁም
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሰንበትን የሰጣችሁ እንድታርፉ መሆኑን ልብ በሉ/አስተውል/
በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚበቃ ወይም የሚሆን ምግብ ስለምሰጣችሁ
የድንብላል ዘር ከቅመም ዘሮች አንዱ ሲሆን ምግብ ጣዕም እንዲኖረው የሚያደርግ ነው
በጣም ቀጭን ቂጣ ወይም እንደ እንጀራ በቀጭኑ የተጋገረ ነገር ነው
አንድ ጎሞር ወደ ሁለት ሊትር ያህል ነው
ጎሞርና ኢፍ ሁለቱም መለኪያዎች ናቸው። ኢፍ ወደ ሀያ ኪሎ ግራም ሲመዝን ጎሞር ሁለት ኪሎ ግራም ይመዝናል
1 የእስራኤል ማኅበር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመከተል ከሲን ምድረ በዳ ተነሡ፤ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሀ አልነበረም። 2 ሕዝቡ ሙሴን ወቀሡት፤ “የምንጠጣው ውሀ ስጠን” ብለውም ተናገሩት። ሙሴም፣ “ለምን እኔን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አላቸው። 3 ያ ሕዝቡ ውሀ በጣም ጠምቷቸው ስለ ነበር በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እንዲህም አሉት፤ “እኛንና ልጆቻችንን፣ ከብቶቻችንንም በውሀ ጥም ለመፍጀት ከግብፅ ለምን አወጣኸን?” 4 እነዚህን ሰዎች ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። 5 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች አንዳንዶችን፣ ወንዙን የመታህበትንም በትር ያዝና ከሕዝቡ ፊት ቀድመህ ሂድ። 6 ኮሬብ ባለው ዐለት ላይ እኔ ከፊትህ እቆማለሁ፤ ዐለቱንም ትመታዋለህ። ከእርሱም ሕዝቡ የሚጠቱት ውሀ ይወጣል።” ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት የታዘዘውን አደረገ። 7 ስላጕረመረሙና “እግዚአብሔር በመካከላችን አለ ወይስ የለም?” በማለት እግዚአብሔርን ስለ ተፈታተኑት ያን ስፍራ ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው። 8 መጥተው እስራኤልን ራፊዲም ላይ ወጉ። 9 ስለዚህም ሙሴ ኢያሱን፣ “ጥቂት ሰዎችን ምረጥና ውጣ፤ ከአማሌቃውያን ጋርም ተዋጋ። ነገ እኔ የእግዚአብሔን በትር ይዤ በኮረብታው ዐናት ላይ እቆማለሁ” አለው። 10 ሙሴ ባዘዘው መሠረት አማሌቃውያን ተዋጋቸው፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኮረብታው ዐናት ወጡ። 11 እጁን ወደ ላይ ሲያነሣ፣ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር፤ እጁን ሲያወርድ ግን አማሌቃውያን ለማሸነፍ ይጀምሩ ነበር። 12 የሙሴ እጆች እየደከሙ ሲሄዱ፣ አሮንና ሖር ድንጋይ ወስደው እንዲቀመጥበት ከእርሱ ሥር አስቀመጡለት። በዚያውም ጊዜ አሮንና ሖር አንዳቸው በአንድ ጎኑ፣ የቀረውም በሌላው ጎኑ በኩል በመሆን የሙሴን እጆች ወደ ላይ ደግፈው ያዙ። የሙሴ እጆችም ፀሐይ እስክትገባ ድረስ ጠንክረው ቆዩ። 13 ስለዚህም ኢያሱ አማሌቃውያንን በሰይፍ ድል አደረጋቸው። 14 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአማሌቃውያንን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ሙሉ በሙሉ ስለምደመስስ፣ ይህን በመጽሐፍ ጽፈህ ኢያሱ እየሰማ አንብበው” አለው። 15 ሙሴም መሠዊያ ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር አርማዬ ነው” ብሎ ሰየመው። 16 “እጅ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተነሥቶአልና፣ እግዚአብሔር በአማሌቃውያን ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጦርነት ያደርጋል” አለ።
“ሲን” የምድረ በዳው ስም ነው፤ (ዘጸአት 16፡1 ተመልከት)
በጉዞ ላይ ሰዎች የሚያርፉበት ወይም የሚቀመጡበት ሥፍራ ነው፤
ሙሴ እነዚህን ጥያቄዎች የጠየቃቸው ህዝቡን ለመገሰጽ ወይም ለመኮነን ነው። ይህ አጋናኝ ጥያቄ በመደበኛ ዐረፍተ ነገር ምተርጎምም ይቻላል፤ ከእኔ ጋር ልትጣሉ አይገባችሁም፤ እግዚአብሔርንም (ያህዌን) ልትፈታተኑ አያስፈልጋችሁም
እስራኤላውያን ይህንን እአጋናኝ ጥያቄ የጠየቁት በምድረ በዳ ልገድላቸው እንዳመጣቸው አድርገው ሙሴን ለመክሰስ ነው። ይህን አጋናኝ ጥያቄ በመደበኛ ዐረፍተ ነገር መተርጎምም ይቻላል፦ አንተ ከግብጽ ምድር ያወጣኸን እኛን፥ ልጆቻችንን እና ከብቶቻችንን በውሃ ጥም ለመፍጀት ወይም ለመግደል ነው
ከሕዝቡ ቀድም ብለህ ወደ ፊት ሂድ ወይም ከህዝቡ ፊት አልፈህ ሂድ
በምድረ በዳ ያለ ቦታ ሲሆን የስሙ ትርጉም “መፈታተን” ማለት ነው፤ “መሪባ” በምድረ በዳ ያለ ሥፍራ ሲሆን የስሙ ትርጉም “ማጉረምረም” ማለት ነው።
በምድረ በዳ ያለ ሥፍራ ሲሆን ሰዎች በጉዞ ላይ ሲሆኑ የሚያርፉበት ወይም የሚቀመጡበት ሥፍራ ነው፤
ኢያሱ ራሱንና ለውጊያ የመረጣቸውን እስራኤላውያንን ወክሎ ቀርቧል። አማራጭ ትርጉም፦ ኢያሱና እርሱ የመረጣቸው ሰዎች አማሌቃውያንን ወጉት
የሙሴና የአሮን ጓደኛ
እስራኤልና አማሌቅ ከሁለቱም ወገን ለውጊያ የተሰለፉ ሰዎችን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር . . . አማሌቃውያን ያሸንፉ ነበር
ፀሐፊው የሙሴ እጆች መድከማቸውን ለማሳየት ሲፈልግ እንደ ከበዱ አድርጎ ይገልጻል፤ በሌላ አገላለጽ፦ የሙሴ እጆች ደክመው ወይም ዝለው ነበር
በሰይፍ ተዋግቶ ድል አደረገ
እግዚአብሔር የአማሌቅን መደምሰስ ሲገልጽ የአንድን ሰው የማሰብ አቅምን ከማጥፋት ጋር ሲያነጻጽር ይታያል። አንድ ሰው ወይም ቡድን ወይም ማህበረሰብ ፈጽሞ ሲጠፋ የምያስታውሳቸው ወይም መታሰቢያ ይጠፋል። በሌላ አገላለጽ፦ እኔ አማሌቃውያንን ፈጽሞ አጠፋለሁ ወይም እደመስሳለሁ (ተለዋጭ ዘይቤ)
እጅ የማንሳት ልምምድ የሚታወቀው ሰዎች መሀላ ሲፈጽሙ ወይም ቃል ኪዳን ሲገቡ እጃቸውን ሲያነሱ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ምክንያቱም እጆች ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ዙፋን ተዘርግተዋል ወይም ምክንያቱም ሙሴ እጁን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ስላነሳ
በአማሌቃውያን ላይ ወይም በአማሌቅ ሰዎች ላይ
1 ካህን፣ የሙሴ ዐማት ዮቶር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ሰማ። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ያወጣቸው መሆኑን ዮቶር ሰምቶ ነበር። 2 ሙሴ ወደ ቤት ከመለሳት በኋላ፣ የሙሴ ዐማት ዮቶር የሙሴን ሚስት ሲፓራን፣ 3 ምድር ባዕድ ነበርሁ” ሲል ጌርሳም ብሎ የጠራውንና ሌላውንም ልጅ ተቀብሏቸው ነበር። 4 “የአባቶቼ አምላክ ረድቶኛል፤ ከፈርዖንም ሰይፍ አድኖኛል” ብሎ ነበርና፣ የሌላው ልጁ ስም አልዓዛር ነው። 5 ዐማት ዮቶር ከሙሴ ልጆችና ከሚስቱ ጋር በምድረ በዳው ውስጥ በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ ሰፍሮ ወደ ነበረው ወደ ሙሴ መጣ። 6 ሙሴን፣ “እኔ ዐማትህ፣ ዮቶር ከሚስትህና ከልጆችህ ጋር ወደ አንተ እየመጣሁ ነው” አለው። 7 ዐማቱን ሊቀበለው ወጣ፤ ሰገደ፤ ሳመውም። ስለ እያንዳንዳቸው ደኅንነት ተጠያይቀው ወደ ድንኳኑ ውስጥ ገቡ። 8 ሙሴም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሲል በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ያደረገውን በሙሉ፣ በመንገድም በእነርሱ ላይ የደረሰባቸውን ችግር ሁሉና እግዚአብሔር እንዴት እንደታደጋቸው ለዐማቱ ነገረው። 9 ዮቶር እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ በመታደግ እግዚአብሔር ባደረገው መልካም ነገር ሁሉ ተደሰተ። 10 እንዲህ አለ፤ “ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ አድኖአችኋል፤ ሕዝቡንም ከግብፃውያን እጅ ታድጎአቸዋልና እግዚአብሔር ይመስገን። 11 እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ ታላቅ እንደ ሆነ አሁን ዐውቃለሁ፤ ምክንያቱም ግብፃውያን እስራኤላውያንን በትዕቢት ይዘዋቸው በነበረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ታድጎአል።” 12 ዐማት ዮቶር የሚቃጠል መሥዋዕቶችን ለእግዚአብሔር አቀረበ። አሮንና የእስራኤል አለቆች ሁሉ ከሙሴ ዐማት ጋር በእግዚአብሔር ለመብላት መጡ። 13 በሚቀጥለው ቀን ሙሉ ሕዝቡን ሊዳኝ ተቀመጠ። ሕዝቡ ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ በእርሱ ዙሪያ ቆሙ። 14 የሙሴ ዐማት ሙሴ ለሕዝቡ ያደረገውን ሁሉ ተመልክቶ፣ “ምን እያደረግህ ነው? ብቻህን ለምን ትቀመጣለህ? ሰዎችስ ሁሉ ከጧት እስከ ማታ ድረስ ለምን በአንተ ዙሪያ ይቆማሉ?” አለው። 15 ዐማቱን እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ። 16 ሲኖራቸው፣ ወደ እኔ ይመጡና በመካከላቸው ላለው ችግር ውሳኔ እሰጣለሁ፤ የእግዚአብሔርን ሕገጋትና ሥርዐትም አስተምራቸዋለሁ።” 17 ዐማቱም ሙሴን መልሶ እንዲህ አለው፤ “የምታደርገው ተገቢ አይደለም። 18 ዐብረውህ ያሉ ሰዎች በእውነት ራሳችሁን ታደክማላችሁ። ይህ ለአንተ ከባድ ሸክም ነው። ይህን ተግባር ብቻህን ማከናወን አትችልም። 19 ስማኝ። ምክር እሰጥሃለሁ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ ምክንያቱም አንተ በእግዚአብሔር ፊት የሕዝቡ ወኪል ነህ፤ አቤቱታቸውንም ወደ እግዚአብሔር ታቀርባለህ። 20 ሥርዐታትና ሕገጋት ልታስተምራቸው፣ የሚሄዱበትን መንገድና የሚሠሩትን ሥራም ልታሳያቸው ይገባል። 21 እግዚአብሔርን የሚፈሩ ችሎታቸውን፣ ኢፍትሓዊ ጥቅምን የሚጠሉ የእውነት ሰዎችንከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ። ዕነርሱን መሪዎች እንዲሆኑ በሕዝቡ ላይ ሸለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች አድርገህ ሹማቸው። 22 ጉዳዮችን ሁሉ በሚመለከት ሕዝቡን የሚዳኙት እነርሱ ይሆናሉ፤ ከባድ ከባድ ጉዳዮችን ግን ወደ አንተ ያቀርባሉ። አነስተኛ ጉዳዮችን ሁሉ በሚመለከት፣ እነርሱ ራሳቸው ውሳኔ ሊሰጡባቸው ይችላሉ። በዚህ መንገድ ሥራው ለአንተ ይቀልልሃል፤ እነርሱም ሸክሙን ከአንተ ጋር ይሸከማሉ። 23 ይህን ብታደርግና እግዚአብሔርም እንደዚሁ እንድታደርግ ቢያዝዝህ፣ በርትተህ መሥራት ትችላለህ፤ መላው ሕዝብም ረክቶ ወደ ቤት መሄድ ይችላል።” 24 የዐማቱን ምክር በመስማት የነገረውን ሁሉ አደረገ። 25 ሙሴ ከእስራኤል ሁሉ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ ሸለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች አድርጎም የሕዝቡ መሪዎች እንዲሆኑ ሾማቸው። 26 በቀላላል ጉዳዮች ሕዝቡን ይዳኙ ነበር። ከበባድ ጉዳዮችን ለሙሴ አቀረቡ፤ ትንንሽ ጉዳዮችን ሁሉ ግን እነርሱ ለራሳቸው ብያኔ ሰጡባቸው። 27 በኋላ ሙሴ ዐማቱን አሰናበተው፤ ዮቶርም ወደ ገዛ ምድሩ ተመልሶ ሄደ።
የሙሴ የሚስቱ አባት
ይህ ሀረግ ሁለት ፍችዎችን ይዟል፦ 1) ዮቶር ሲፖራንና ሁለቱን ልጆቹን ወደ ሙሴ አመጣቸው 2) ዮቶር ሲፖራንና ሁለቱን ልጆች ወደ ቤት መልሶአቸው ነበር
ይህ አባባል ቀደም ብሎ ሙሴ የሰራውን ወይም ዮቶር ያደረገውን የሚያሳይ ነው። በሌላ አገላለጽ፦ ሙሴ ሚስቱን ወደ አማቾቹ ቤት ከላከ በኋላ
የሙሴና የሲፖራ ልጅ ሲሆን የስሙ ትርጉም እንግዳ ወይም መጻተኛ ማለት ነው
የሙሴና የሲፖራ ልጅ ሲሆን የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ረዳቴ ማለት ነው
በፈርዖን ወይም በፈርዖን ሠራዊት ከመገደል መትረፉን ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ በፈርዖን ወይም በፈርዖን ሠራዊት ከመገደል/ከመሞት/ አዳነኝ።
እርሱ ከእስራኤላውያን ጋር ወደ ሰፈረበት ወደ ምድረ በዳ
ሰዎች ታላቅ አክብሮትና ትህትናን እየሰጡ ስለመሆናቸው የሚያሳዩት እንደ ባህሉ በመሳምና እጅ በመንሳት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ራሱን ዝቅ አድርጎ እጅ በመንሣት ሳመው
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሲል ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ
በመንገድ ላይ ስላጋጠማቸው መከራ ሁሉ ወይም የደረሰባቸውን ፈተና ሁሉ
“እጅ” አንድ ሰው አንድን ነገር ለማድረግ የሚያስችል ሀይል እንዳለው የሚገልጽ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ከሀያላን ግብጻውያንና ከሀያሉ ፈርዖን ያተረፋችሁ/ያስመለጣችሁ/ያዳናችሁ/ (ወካይ ዘይቤ)
ዮቶር ይህንን አጋናኝ ጥያቄ የጠየቀው ሙሴ የሚያደርገው ነገር ጥሩ ወይም ትክክል እንዳለሆነ ለማሳየት ነው። በትርጉም ውስጥ አጋናኝ ጥያቄውን እንዳለ ማምጣጥ ይቻላል ወይም ወደ መደበኛ ዐርረፍተ ነገር መቀየር ይቻላል። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ በህዝቡ ላይ ይህን ሁሉ ነገር ማድረግ አልነበረብህም ወይም ለህዝቡ የምታደርገው ይህ ሁሉ ነገር ምንድን ነው?
“ተቀምጠሃል” የሚለው ቃል ወካይ ዘይቤ ሲሆን “ለፍርድ” ወይም “ለህዝቡ ፍርድ ለመስጠት” መቀመጡን ለማሳየት ነው። ዳኞች የሰዎችን ጉዳይ ለመስማት እና ለመዳኘት መቀመጣቸውን ሲገልጽ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ ብቻህን ትፈርዳለህ” ወይም “ህዝቡ ላይ እየፈረድክ ያለኸው አንተ ብቻ ነህ (ወካይ ዘይቤ)
ዮቶር ይህን አጋናኝ ጥያቄ የጠየቀው ሙሴ ብዙ ሥራ ብቻውን እየሰራ መሆኑን አጽንዖት ሰጥቶ ለመናገር ፈልጎ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ይህ ሁሉ ሰው ከጧት እስከ ማታ ድረስ በአንተ በዙሪያ ቆሞ ሳለ አንተ ብቻህን በፍርድ ወንበር ላይ ለምን ትቀመጣለህ? ወይም ይህ ሁሉ ሰው ከጧት እስከ ማታ ድረስ በአንተ ዙሪያ ቆሞ ሳለ አንተ ብቻህን ለፍርድ መቀመጥ አይገባህም
ሕዝቡ /ሰዎች/ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ወይም ለመፈለግ/ለመረዳት/
ዮቶር ሙሴ የሚሰራው ሥራ ከባድ መሆኑ ለማመልከት አንድን ነገር ከመሸከም ጋር ያነጻጽራል። አማራጭ ትርጉም፦ ሥራው ከአቅምህ በላይ ነው (ተለዋጭ ዘይቤ)
አንተ ራስህንም ሆነ ሕዝቡን በከንቱ ታደክማለህ
“ምክር እሰጥሃለሁ” ወይም “አቅጣጫ እጠቅምሃለሁ”
“ከአንተ ጋር ይሆናል” የሚለው የእግዚአብሔር እርዳታ ወይም እግዚአብሔር እንደምረዳው ለመግለጽ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር ይረዳሃል ወይም እግዚአብሔር ለሥራው ጥበብ ይሰጥሃል
ዮቶር ሲናገር ሙሴ የህዝቡን ጥያቄ ወይም አቤቱታ ወደ እግዚአብሔር ለማድረስ ይዞ እንደምመጣ አድርጎ ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ ጥያቄአችውን ለእግዚአብሔር ተናገር/አሳውቅ/
ህዝቡ እንዴት መኖር እንዳለባቸውና ምን ማድረግ እንደሚገባቸውም መናገር ወይም ማሳየት አለብህ እንደማለት ነው
በተጨማሪ/ነገር ግን/ አንተ . . . ሰዎችን ምረጥ
ይህ አባባል ሁለት ዓይነት ፍቺዎች ይኖሩታል፦ 1) እነዚህ ቁጥሮች በእያንዳንዱ ቡድን ውስጥ ያሉትን የሰዎች ቁጥር ወይም ብዛት አመልካች ናቸው፤ አማራጭ ትርጉም፦ “1000 ሰው ያለበት ቡድን፥ 100 ሰው ያለበት ቡድን፥ 50 ሰው ያለበት ቡድን እና 10 ሰው ያለበት ቡድን”፤ 2) እነዚህ ቁጥሮች በትክክል የሚታዩ ቁጥሮች ሳይሆኑ ምሳሌያዊ ናቸው፤ አማራጭ ትርጉም፦ “በጣም ትንሽ ሰው ቡድን መሪ፤ የትንሽ ሰው ቡድን መሪ፤ የብዙ ሰው ቡድን መሪ፤ በጣም ብዙ ሰው ቡድን መሪ”
በህዝቡ ላይ መፍረድ እንዲችሉ ሰይማቸው ወይም ሥልጣን ስጣቸው
ከባድ ያልሆኑ ወይም ቀላል በሆኑ ነገሮች ላይ እነርሱ ይፍረዱ/ይወስኑ/
አስቸጋሪ የሆነውን ጉዳይ ሁሉ ለአንተ እንዲያቀርቡ /ለአንተ እንድነግሩ/ አድርግ ወይም ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ከባድ ጉዳይ ወደ አንተ ያምጡት
ዮቶር ይህንን ሲናገር እነዚህ ሰዎች ከሙሴ ጋር አብረው አንድን ነገር ለመሸከምና እርሱን ለመርዳት የመጡ አስመሎ ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ ሥራውን በመሥራት ስለሚያግዙህ ሥራው ቀላል ይሆናል ወይም ከአንተ ጋር አብረው ስለሚሰሩ ሥራው ቀላል ይሆንልሃል
የሥራ ክብደቱ ለአንተ ቀላል ይሆናል ወይም የሥራ ጫና ይቀንስልሃል
ፀሐፊው የሚናገረው አንድን ነገር ለማድረግ የሚያስችል አቅም ወይም ችሎታ እንጂ ዕውቀት አይደለም። ከእስራኤላውያን መካከል ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ ወይም ከእስራኤላውያን መካከል ነገር የመለየት ችሎታ ያላቸውን መረጠ
ኡህ አባባል ሁለት ዓይነት ፍቺዎች ይኖሩታል፦ 1) እነዚህ ቁጥሮች በእያንዳንዱ ቡድን ውስጥ ያሉትን የሰዎች ቁጥር አመልካች ናቸው፤ አማራጭ ትርጉም፦ “1000 ሰው ያለበት ቡድን፥ 100 ሰው ይለበት ቡድን፥ 50 ሰው ያለበት ቡድን እና 10 ሰው ያለበት ቡድን”፤ 2) እነዚህ ቁጥሮች በትክክል የሚታዩ ቁጥሮች ሳይሆኑ ምሳሌያዊ ናቸው፤ አማራጭ ትርጉም፦ “በጣም ትንሽ ሰው ቡድን መሪ፤ የትንሽ ሰው ቡድን መሪ፤ የብዙ ሰው ቡድን መሪ፤ በጣም ብዙ ሰው ቡድን መሪ”
እነርሱ ሁልጊዜ የሕዝብ ዳኞች ሆነው አገለገሉ/ያገለግሉ ነበር/
አስቸጋሪ የሆኑትን ጉዳዮች ብቻ ወደ ሙሴ ያቀርቡ ነበር ወይም አስቸጋሪ በሆኑ ነገሮች ላይ ሙሴ እንዲፈርድ ወደ እርሱ ያመጡ ነበር
ቀላል በሆነው ነገር ላይ እነርሱ ራሳቸው ይወስኑ ነበር
በዚህ ምዕራፍ የተገለጹ ነገሮች የሙሴን ህግ እንዲቀበሉ ህዝቡን የሚያዘጋጅ ነበር። ህጉን ለመቀበል ህዝቡ ህጉ የሚጠይቀውን እያንዳንዱን ነገር ለመማርና ለማድረግ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው። የዚህ ምዕራፍ ክስተት ለእስራኤል አስፈላጊና ዋናው አካል ነበር።
1 ወር፣ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡበት በዚያው ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። 2 ከራፊዲም ከተነሡ በኋላ፣ ወደ ሲና ምድረ በዳ መጥተው በምድረ በዳው ውስጥ ከተራራው ፊት ለፊት ሰፈሩ። 3 ወደ እግዚአብሔር ወጣ። እግዚአብሔርም ከተራራው ጠርቶት እንዲህ አለው፤ 4 “ለያዕቆብ ቤት፣ ለእስራኤል ሕዝብ እንደዚህ ብለህ ተናገር፦ በግብፃውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ ፣ እናንተንም በርግም ክንፎች እንዴት እንደ ተከከምኋችሁና ወደ ራሴ እንዴት እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል። 5 ቃሌን በታዛዥነት ብትሰሙና ኪዳኔንም ብትጠብቁ፣ ከሕዝብ ሁሉ መካከል የእኔ ርስት ትሆናላችሁ፤ ምድር ሁሉ የእኔ ነውና። 6 እናንተ ለእኔ የካህናት መንግሕትና ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃሎች እነዚህ ናቸው። 7 መጣ፤ የሕዝቡንም ሽማግሌዎች ጠርቶ እግዚአብሔር ያዘዘውን እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፊታቸው ተናገረ። 8 ሁሉ በአንድነት፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ እናደርጋለን” በማለት መልስ ሰጡ። ሙሴ ሕዝቡ የተናገሩትን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ መጣ። 9 ሙሴን፤ “እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር፣ መስማት እንዲችሉና አንተንም ሁልጊዜ እንዲያምኑህ፣ ወደ አንተ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም ሕዝቡ የተናገሯቸውን ቃሎች ለእግዚአብሔር ነገረው። 10 ሙሴን፣ “ወደ ሕዝቡ ሂድ። ዛሬና ነገ ለእኔ ቀድሳቸው፤ ልብሳቸውንም እንዲያጥቡ አድርግ። 11 ቀንም ይዘጋጁ፤ በሦስተኛው ቀን እኔ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ እወርዳለሁና። 12 ዙሪያ ሁሉ ለሕዝቡ ወሰን አብጅና ለሕዝቡ እንዲህ በላቸው፤ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ወይም የተራራውን ግርጌ ጫፍ እንዳትነኩ ተጠንቀቁ። ተራራውን የነካ ይሞታል።’ 13 ዐይነቱን ሰው ማንም አይንካው። እንዲያውም የነካው በድንጋይ ይወገራል ወይም በቀስታ ይወጋል። ሰውም ሆነ እንስሳ ይሞታል። መለከቱ የማያቋርጥ ድምፅ ሲያሰማ፣ ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት ይችላሉ” አለው። 14 ሙሴም ከተራራው ወደ ሕዝቡ ወረደ። ሕዝቡን ለእግዚአብሔር ቀደሳቸው፤ ልብሳቸውንም አጠቡ። 15 “በሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ፤ ወደ ሚስቶቻችሁም አትጠጉ” አላቸው። 16 ቀን ጠዋት ላይ ነጏድጓድና የመብረቅ ብልጭታ፣ ከባድ ደመና እና ጉሉሕ የመለከት ድምፅ በተራራው ላይ ነበሩ። በሰፈሩ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንቀጠቀጡ። 17 ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኙ ሕዝቡን ከሰፈር አወጣቸው፤ በተራራው ግርጌም ቆሙ። 18 እግዚአብሔር በእሳትና በጢስ ወርዶበት ስለ ነበረ፣ የሲና ተራራ ሙሉ በሙሉ በጢስ ተሸፈነ። ጢሱ እንደ ምድጃ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ጠቅላላ ተራራውም በኀይል ተናወጠ። 19 ድምፅ እየጨመረና እየጎላ ሲሄድ፣ ሙሴ ተናገረ፤ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት። 20 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ወርዶ፣ ሙሴን ወደ ተራራው ጫፍ እንዲወጣ ጠራው። ሙሴም ወጣ። 21 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለማየት ዐልፈው ወደ እኔ እንድይመጡ፣ ሂድና ሕዝቡን አስጠንቅቃቸው፤ አለዚያ ብዙዎች ይሞታሉ። 22 ወደ እኔ የሚቀርቡ ካህናትም ራሳቸውን ይቀድሱ፤ እንዳላጠፋቸውም ለእኔ መምጣት ራሳቸውን ያዘጋጁ።” 23 እግዚአብሔርን፣ “ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት አይችሉም፤ ምክንያቱም ‘በተራራው ዙሪያ ወሰን አብጅና ለእግዚአብሔር ቀድሰው’ ብለህ አዝዘኸናል” አለው። 24 ሙሴን፣ “ከተራራው ወርደህ ሂድና አሮንን ክአንተ ጋር ይዘኸው ና፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን ወሰን ዐልፈው ወደ እኔ እንዲመጡ አትፍቀድላቸው፤ አለዚያ አጠፋቸዋለሁ” አለው። 25 ስለዚህ ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው።
እስራኤላውይ ወደ ሲና ምድረ በዳ የደረሱት በሶስተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ልክ ከግብጽ በወጡበት በዚያች ቀን ነበር። ይህ ማለት ከግብጽ የወጡበትና ወደ ምድረ በዳ የደረሱበት ቀን ተመሳሳይ ነበር ማለአት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ "በሶስተኛው ወር እስራኤላውያን ግብፅን ለቀው በወጡበት በዚያችው በተመሳሳይ ዕለት . . .
ይህ ሥፍራ የሚገኘው በሲና ምድረ በዳ ጫፍ አከባቢ እስራኤላውያን የሰፈሩበት ሥፍራ ነው (ዘጸአት 17፡1 ተመልከት)
“የያዕቆብ ቤት” የሚለው የያዕቆብን ቤተሰብ እና ትውልዱን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የያዕቆብ ተወላጆች ለሆኑት
“የእስራኤል ልጆች” የሚለው ሀረግ የሚገልጸው “የያዕቆብ ቤት” የሚለውን የሚያብራራ ነው።
እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ያደረገውን ጥበቃና ጥንቃቄ ሲገልጽ እርሱ ንስር እንደ ሆነና እነርሱን በክንፉ እንደ ተሸከማቸው አድርጎ ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ ንስር ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ እንደምትሸከም እኔም እናንተን እንዴት እንደተሸከምኳችሁ
“ቃሌን ብትሰሙ” የሚለው እንዲሁ መስማት ብቻ ሳይሆን መታዘዝንም ይጨምራል። በሌላ አገላለጽ፦ ቃሌን ብትሰሙና ለእኔም ብትታዘዙ
ቃል ኪዳኔ የምጠይቃችሁን ነገር ብትፈጽሙ
የእኔ ርስት ወይም ሀብት ትሆናላችሁ
እግዚአብሔር ህዝቡ ካህናት እንደሆኑ ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ የመንግስት ህዝብ የሆናችሁ ለእኔ እንደ ካህናት ናችሁ ወይም የመንግስት ህዝብ የሆናችሁ እናንተ ለእኔ ካህናት የሚሰሩትን የምትሰሩ ናችሁ
ይህ ሀረግ የሚያሳየን ሙሴ ለህዝቡ ሲናገር ቃሉን ለፊታቸው እንደተናገረ አድርጎ ያቀርባል። አማራጭ ትርጉም፦ እነዚህን ቃሎች ሁለ ለእነርሱ ተናገረ
እግዚአብሔር ለእርሱ የሰጠውን ትዕዛዝ
ሙሴ እነርሱ ያሉትን መልሶ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ወሰደ ወይም ለእግዚአብሔር ሪፖርት አደረገ
“የህዝቡ ቃል” ህዝቡ የተናገሩትን የሚገልጽ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ህዝቡ ያሉትን ወይም የተናገሩትን
የዚህ ሀረግ ትርጉም:- ራሳቸውን ቅዱስ እንዲያደርጉ ወይም እንዲለዩ ለህዝቡ ንገራቸው
ይህ ትዕዛዛዊ ሀረግ ሲሆን በሌላ አገላለጽ፦ ህዝቡ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ትዕዛዝ ተሰጣቸው
በህዝቡ ዙሪያ ደንበር ወይም ገደብ አድርግ ወይም ህዝቡ እንዳያልፉ ድንበር ወይም ገደብ አበጅላቸው
ማንም ሰው ተራራውን ቢነካ በርግጥ ይሞታል ወይም ተራራውን የሚነካ ማንም ቢሆን ግደሉት
ተራራውን የሚነካ በድንጋይ ተወግሮ ወይም በቀስት ተወግቶ ይሙት
ከፍ ባለ ድምፅ ወይም ለረጅም ጊዜ ጥሩንባ በተነፋ ጊዜ
ይህ በትህትና የተገለጸው ወደ ሌላ ሴት ሳይሆን ወደ ሚስቶቻቸው እንዳይቀርቡ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ከሚስቶቻችሁ ጋር አትተኙ ወይም ከሚስቶቻችሁ ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት አታድርጉ
እግዚኢአብሔር ከተራራው ስለመጣ ወይም ስለወረደ
ጪሱ ከትልቅ የእሳት ምድጃ ወይም ከትልቅ የእሳት ቃጠሎ እንደሚወጣ ጪስ ነበር
በጣም ትልቅና የሚያቃጥል የእሳት ምድጃ
የእምቢልታው ወይም የጥሩንባው ድምጽ እየበረታ ወይም እያየለ በመጣ ጊዜ
እዚህ ቦታ “ድምጽ” እግዚአብሔር የሚያሰማውን ድምጽ የሚመለከት ነው። የዚህ ሀረግ ፍቺው 1) እንደ መብረቅ እግዚአብሔር በትልቅ ድምጽ ተናግሯል 2) መብረቅ ድምጽ እንዲያወጣ በማድረግ 3) እግዚአብሔር ራሱ በከፍተኛ ድምጽ ተናገረ
ሙሴ ተራራው ላይ እንዲወጣ ጠየቀው/አዘዘው/
የተወሰነውን ክልል ወይም ድንበር አልፈው እንዳይመጡ
ከተራራው ላይ ውረድ/ሂድ/
የተወሰነውን ክልል ወይም ድንበር አልፈው እንዳይመጡ
1 እነዚህን ቃሎች እንዲህ በማለት ተናገረ፦ 2 ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። 3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። 4 በላይ በሰማይ ያለውን፣ ወይም በታች በምድር ያለውን፣ ከምድርም በታች በውሀ ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስልና ሥዕል ለራስህ ጣዖት አታብጅ። 5 አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። የሚጠሉኝን ሦስትና አራት ትውልድ በልጆች ላይ ቅጣት በማምጣት የአባቶችን ኀጢአት እቀጣለሁ። 6 በሚወዱኝና ትእዛዛቴን በሚጠብቁት በሺዎች ላይ ግን የኪዳን ታማኝነት አሳያለሁ። 7 የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ ስሜን በከንቱ የሚያነሣውን በደል ዐልባ አላደርገውምና። 8 እንድትቀድሰው፣ የሰንበትን ቀን ዐስብ። 9 ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን። 10 ቀን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በሰንበት ቀን አንተም ወንድ ልጅህም፣ ሴት ልጅህም፣ ወንድ አገልጋይህም፣ ሴት አገልጋይህም፣ እንስሳትህም፣ በግቢህ ያለ እንግዳም ሥራ አትሠሩም። 11 እግዚአብሔር ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በእነርሱ ውስጥ ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀን ፈጥሬ በሰባተኛው ቀን ዐርፌአለሁና። ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባረክሁት፤ ለራሴም ቀደስሁት። 12 እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር ብዙ ጊዜ እንድትቆይ፣ አባትህንና እናትህን አክብር። 13 አትግደል። 14 አታመንዝር። 15 አትስረቅ። 16 በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር። 17 የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፣ ወንድ አገልጋዩን፣ ሴት አገልጋዩን፣ በሬውን፣ አህያውን፣ ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።” 18 ሰዎች ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን አዩ፤ የመለከቱን ድምፅም ሰሙ፤ የሚጨሰውንም ተራራ ተመለከቱ። ሕዝቡ ይህን ሲያዩ፣ ተንቀጠቀጡ፤ ርቀውም ቆሙ። 19 ሙሴን፣ “አንተ ተናገረን፤ እኛም እንሰማሃለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲናገረን አታድርግ፤ አለዚያ እንሞታለን” አሉት። 20 ሙሴም ሕዝቡን፣ “አትፍሩ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር በእናንተ ዘንድ እንዲገኝና ኀጢአት እንዳትሠሩ ሊፈትናችሁ እግዚአብሔር መጥቶአልና” አላቸው። 21 ስለዚህ ሕዝቡ ርቀው ቆሙ፤ ሙሴም እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጨለማው ተጠጋ። 22 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ‘እኔ ከሰማይ ከእናንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል። 23 በቀር ሌሎች አማልክትን፣ የብር ወይም የወርቅ አማልክትን ለራሳችሁ አታብጁ። 24 የጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፣ በእርሱም ላይ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶችህን፣ የኅብረት መሥዋዕቶችህን፣ በጎችህንና በሬዎችህን ሠዋበት። ስሜ እንዲከበር በማደርግበት ስፍራ ሁሉ፣ ወዳንተ እመጣለሁ፤ እባርክሃለሁም። 25 መሠዊያ የምትሠራልኝ ከሆነ፣ በተጠረበ በድንጋይ አትሥራው፤ ለመጥረብ ስትል መሣሪያህን በላዩ ካሳረፍህበት ታረክሰዋለህና። 26 ሆነህ እንዳትጋለጥ፣ በመሠዊያዬ ላይ በደረጃ አትውጣ።”
በባርነት የነበራችሁበት ቦታ
ከእኔ በስተቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ
የማንኛውንም ዐይነት ምስል ተጠቅመህ ለራስህ ጣዖት አድርገህ አትሥራ
ማንኛውንም ጣዖት አታምልክ ለእርሱም እጅ ነስተህ አትስገድለት
እግዚአብሔር ህዝቡ እርሱን ብቻ እንዲያመልኩት ይፈልጋል
እግዚአብሔር ስለአባቶቻቸው ሀጢአት ልጆችን ወይም የሚቀጥለውን ትውልድ የሚቀጣ መሆኑን ይገልጻል
እስከ የልጅ ልጅ ድረስ
“ምህረት” የሚለው ቃል በዕብራይስጡ እግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታማኝ መሆኑን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔን ለሚወዱ ቃል ኪዳኔን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ ታማኝ አምላክ ነኝ
“ሺህ” የሚለው ቃል በወካይ ዘይቤ የተጠቀሰ ሲሆን የብዙ አመታትን ቁጥር የሚገልጽ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እስከ ዘላለም ድረስ
የአምላክህን ስም በከንቱ ወይም በግድየለሽነት ወይም በንቀት አታንሣ ወይም አትጠቀም
ይህ ድርብ አሉታዊ አገላለጽ እግዚአብሔር ሳይቀጣ እንደማያልፍ ለማመልከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ በደለኛውን በርግጥ እቀጣለሁ
በየቀኑ የምታደርጋቸውን ተግባራት በየዕለቱ ፈጽም
በአይሁዶች በቀድሞ ልምድ ከተሞች ዙሪያቸው የታጠረና ሰዎች እንድገቡና እንድወጡ በርም ነበራቸው። አማራጭ ትርጉም፦ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ወይም በአጥርህ ውስጥ የሚኖሩ የሌሎች አገሮች ሰዎች
ሁለት አማራጭ ትርጉሞች፦ 1) እግዚአብሔር የሰንበት ቀን መልካም ነገር እንዲያመጣ/እንዲያፈራ/ አድርጎታል 2) እግዚአብሔር የሰንበት ቀን መልካም ነው ብሏል
የሰንበትን ቀን ለራሱ ለይቶታል
ከሚስት ወይም ከባል ጋር ካልሆነ በቀር ከማንም ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት አታድርግ
በማንም ሰው ላይ በሐሰት አትመስክር ወይም ስለአንድ ሰው በውሸት አትናገር
አንድን ነገር ለማግኘት ከልክ በላይ አትፈልግ ወይም ለራሴ ይሁንልኝ ብለህ አትመኝ
ከቀንድ የተሰራ ድምጽ ማውጫ። ይህን ድምጽ ማውጫ መሳሪያ ለማያውቁ በስዕል ማሳየት ይቻላል።
ከተራራው ላይ ጭስ ሲወጣ ወይም በተራራው ቃጠሎ ምክንያት ጭስ ሲወጣ
በፍርሃት ተንቀጠቀጠቀጡ
“ራቅ ብለው ቆሙ” ወይም “በርቀትም ቆሙ”
እግዚአብሔርን በመፍራት ወይም በማክበር ኃጢአት ከመሥራት ተቆጥባችሁ እንድትኖሩ ነው”
ሙሴ . . . ጥቅጥቅ ወደ ሆነው ደመና ተጠጋ/ሄደ/
ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው
ከሰማይ ሆኜ እንደ ተናገርኋችሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል
እኔን ትታችሁ ሌሎችን አማልክት በጣኦት መልክ አትሥሩ
ከብርና ከወርቅ የተሰሩ ጣኦታት ወይም ከብርና ከወርቅ የተሰሩ አማልክት
ከአፈር፥ ከድንጋይ ወይም ከሸክላ የተሰራ መሰዊያ
“ስም” የእግዚአብሔርን ማንነት የሚገልጽ አባባል ነው (ወካይ ዘይቤ)። ስሜ እንዲታሰብበት እንዲከብርበት በወሰንኩት ስፍራ ወይም ስሜን እንዲታከብሩ በመረጥኩት ሥፍራ
ወደ ላይ ለመውጣት ደረጃ ያለውን መሰዊያ ለእኔ አትሥራ
ራቁትህን እንዳትሆን
1 የምትመሠርታቸው ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፦ 2 አገልጋይ ብትገዛ፣ ስድስት ዓመት ያገልግልህና በሰባተኛው ዓመት ያለ ክፍያ ነጻ ይውጣ። 3 ከመጣ፣ ብቻውን ነጻ ይውጣ፤ ሚስት ያገባ ከሆነ፣ ሚስቱም ዐብራው ነጻ ትውጣ። 4 ጌታው ሚስት አጋብቶት ከሆነና እርሷም ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆችን ከወለደችለት፣ ሚስቲቱና ልጆቿ የጌታዋ ይሆናሉ፤ ባልዮው ግን ብቻውን በነጻ ይሂድ። 5 ግን አገልጋይ፣ “ጌታዬን፣ ሚስቴንና ልጆቼን እወድዳለሁ፤ ነጻ ወጥቼ አልሄድም” ቢል፣ 6 ውደ ዳኞች ይውስደው፥ ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ ወስዶም ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም አገልጋይ ጌታውን ለዘለዓለም ያገለግለዋል። 7 ሰው ሴቶ ልጁን በአገልጋይነት ቢሸጣት፣ እንደ ወንዶቹ አገልጋዮች በነጻ መሄድ የለባትም። 8 ለራሱ የመረጣትን ጌታዋን ደስ ባታሰኝ፣ በዎጆ ይልቀቃት። ለባዕዳን እንዲሸጣት መብት የለውም፤ ምክንያቱም አታልሎአታል። 9 ለልጁ አያያዝ ያድርግለት። 10 ሌላ ሚስት ቢያጋባውም፣ የመጀመሪያዋን ሚስቱን ምግብ፥ ልብስ፣ ወይም ቊሳዊ መብት ማጕደል የለበትም። 11 ነገር ግን እነዚህን ሦስት ነገሮች የማይሰጣት ቢሆን፣ ያለ ምንም የገንዘብ ክፍያ በነጻ መሄድ ትችላለች። 12 ሰው ሰውን ቢደበድብና ቢገድል፣ ሊሞት ይገባዋል። 13 ሰውየው ዐስቦ ሳይሆን ድንገት አድርጎት ከሆነ፣ የሚሸሽበት ስፍራ አዘጋጃለሁ። 14 አንድ ሰው ባልንጀራውን ሆነ ብሎ በተንኮል ቢያጠቃውና ቢገድለው፣ ከእግዚአብሔር መሠዊያም እንኳ ተወስዶ ይገደል። 15 ወይም እናቱን የሚመጣ ይገደል። 16 የሚጠልፍና የሚሸጥ፣ ወይም የተጠለፈው ሰው በእጁየሚገኝበት ይገደል። 17 ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል። 18 ቢጣሉና እንደኛው ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታው፣ የተመታው ሰውም ባይሞትና ዐልጋው ላይ ቢቀር፤ 19 በኋላም ቢያገግምና በትሩን ተደግፎ በአካባቢው መንቀሳቀስ ቢችል፣ ለባከነበት ጊዜ የመታው ሰውን ይክፈል፤ ያገገመበትንም በሙሉ ይክፈል። ነገር ግን ያ ሰው የነፍስ ተጠያቂ አይደለም። 20 አንድ ሰው ወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን በበትር ሲመታና አገልጋዩም ከድብደባው የተነሣ ቢሞት፥ ያ ሰው መቀጣት አለበት። 21 ነገር ግን አገልጋዩ አንድ ወይም ሁለት ቀን በሕይወት ቢቆይ፣ ጌታው መቀጣት የለበትም፤ አገልጋዩ የግል ንብረቱ ነውና። 22 ሰዎች ቢጣሉና ነፍሰ ጡር ሴት ቢጎዱ፣ እርሷም ብትጨነግፍ፣ ሆኖም ሌላ ጉዳት ባይደርስባት፣ በደለኛው ሰውዬ የሴትዮዋ ባል የሚጠብቅበትንና ዳኞቹ የሚወስኑትን መክፈል አለበት። 23 ጉዳት ካደረሰ ግን፣ ሕይወትን ለሕይወት፣ 24 ዐይንን ለዐይን፣ ጥርስን ለጥርስ፣ እጅን ለእጅ፣ እግርን ለእግር፣ 25 ቃጠሎን ለቃተሎ፣ ቊስልን ለቊስል፣ ወይም ግርፋትን ለግርፋት በቅጣት ታስከፍላለህ። 26 አንድ ሰው የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ዐይን ቢመታና ቢያጠፋው፣ አገልጋዩን ስለ ዐይኑ ካሣ ነጻ ሊያደርገው ይገባል። 27 የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ጥርስ ቢያወልቅ፣ አገልጋዩን ለጥርሱ ካሣ ነጻ ሆኖ እንዲሄድ ማድረግ አለበት። 28 በሬ አንድን ሰው ወይም ሴት ቢወጋና የሞት አደጋ ቢያደርስ፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፣ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ከተጠያቂነት ነጻ ይሁን። 29 ግን በሬው የመዋጋት ልማድ ከቀድሞ ጀምሮ ካለበትና ባለቤቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በሬውን ሳይጠብቀው ቀርቶ፣ በሬው አንድ ወንድ ወይም ሴት ወግቶ ቢገድል፣ ያ በሬ በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም በሞት ይቀጣ። 30 ለሕይወቱ ካሣ እንዲከፍል ካስፈለገ፣ የተጠየቀውን ይክፈል። 31 በሬው የአንድን ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ይህ ሕግ የሚጠብቅበትን ያድርግ። 32 ወንድ ወይም ሴት አገልጋይን ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለአገልጋዩ ጌታ መክፈልና በሬውም በድንጋይ መወገር አለበት። 33 ሰው ጕድጓድ ቢከፍት ወይም ቢቆፍርና ሳይደፍነው ቀርቶ በሬ ወይም አህያ ቢገባበት፣ 34 ባለቤት ለጠፋው መክፈል ይኖርበታል። ለሞተው እንስሳ ባለቤት ገንዘብ መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል። 35 የአንድ ሰው በሬ የሌላ ሰውን በሬ ቢወጋና ቢሞት፣ የበሬዎቹ ባለቤቶች በሕይወት ያለውን በሬ ሽጠው የተሸጠበትንና የሞተውንም በሬ ይካፈሉ። 36 ነገር ግን በሬው ከቀድሞ ጀምሮ የመውጋት ልማድ ያለበት መሆኑ ከታወቀና ባለቤቱም ያልጠበቀው ከሆነ፣ በበሬው ፈንታ በሬውን መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል።
ለእስራኤላውያን የምትሰጣቸው ህግ ወይም ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ደንብ
ብቻውን የሚለው ሀረግ በአንዳንድ ቋንቋዎች ግልጽ ላይሆን ይችላል። ስለሆነም ገላጭ ሊያስፈልገው ይችላል። አማራጭ ትርጉም፦ ባሪያ እንዲሆንህ አንተ በገዛኸው ጊዜ ሚስት ያላገባ ከሆነ ወይም እርሱን ባርያ ስታደርገው ሚስት ያላገባ ከሆነ ወይም ሚስት ያገባው አንተ ባርያ አድርገህ ከገዛኸው በኋላ ከሆነ።
“ያለ ሚስት” ወይም “ሚስት ሳያገባ”
ባርያ ከመሆኑ በፊት አግብቶ ከሆነ ወይም በባርነት ከመገዛቱ በፊት ባለትዳር ከሆነ
ብሎ ነጻ መውጣት ባይፈልግ ወይም ብሎ አለመፈለጉን በግልጽ ብናገር
“ወስፌ” በጊዜው በእስራኤላውያን ባህል የተለመደው ጆር መብሻ መሳሪያ ነበር። ዛሬም እንደየህብረተሰቡ የመብሻ መሳሪያ መተካት ይቻላል። ስለሆነም በአማራጭ ጆሮውን በመብሻ ይብሳው ማለት ይቻላል።
እስከ ዕድሜ ልክ ወይም እስኪ ሞት ድረስ
ተመልሳ በሕዝብዋ ትዋጅ ወይም አባቷ መልሶ እርሷን እንዲገዛት መፍቀድ አለበት
ለባዕድ ሊሸጣት አይችልም ወይም ለባዕድ የመሸጥ ሥልጣን የለውም
የማይገባ ነገር ስላደረገባት ወይም ስላታለላት
ሚስት ትሆንለት ዘንድ ለልጁ ቢሰጣት ወይም ልጁ እንዲያገባት ቢፈልግ
ለመጀመሪያ ሚስቱ ምግብ፥ ልብስ እና ቀድሞ የነበራትንም የጋብቻ መብት አይከልክላት
የሚገባትን የምግብ አቅርቦት አያቋርጥባት
በባልና ሚስት መካከል ያለውን የተራክቦ ግንኙነት አያቋርጥ ወይም አይከልክላት
ሰው ሰውን ቢገድል ወይም ሰውን ደብድቦ የሚገድል
ይህንን ተደራጊ ግስ በአድራጊ ግስ መተርጎም ይቻላል፦ ይህን ሰው በርግጥ መግደል አለብህ ወይም ይህ ሰው መሞት አለበት
ሆን ብሎ ደፈጣ በማድረግ ሳይሆን ወይም ጉዳት ለማድረስ በልቡ ባያስብ ወይም ባያቅድ
ሸሽቶ በማምለጥ በሰላም የሚኖርበትን ስፍራ እኔ አዘጋጅለታለሁ
ሆን ብሎ ወይም አውቆ ሌላ ሰው ቢገድል
ሕይወቱን ለማዳን ወደ መሠዊያዬ ሸሽቶ ቢሄድ በሞት ይቀጣ
ይህን ዐረፍተ ነገር በአድራጊ ግስ ሲንተረጉም፦ ማንም አባቱን ወይም እናቱን ቢመታ አንተ እርሱን መግደል አለብህ
ፈጽሞ መሞት አለበት
“እጅ” በወካይ ዘይቤነት የቀረበ ስለሆነ የአንድን ሰው ሙሉ ማንነቱን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ በአንተ ቁጥጥር ሥር
በሞት ይቀጣ ወይም ፈጽሞ ይገደል
አባቱን ወይም እናቱን የሚራገም ወይም በአባቱና በእናቱ ላይ ክፉ ቃል የሚናገር
የተመታው ሰው ታሞ በአልጋ ላይ ቢውል ወይም አልጋ ላይ ተኝቶ ቢቀር
በኋላም ተነስቶ ወይም ህመሙ ሲሻለው ወይም በትር እየተመረኰዘ መራመድ ቢችል
ከእንጨት ወይም ከብረት የተሰራ የጉዞ መደገፊያ
ሰውዬው በመታመሙ ምክንያት የባከነውን የሥራ ጊዜ ወይም ሥራ ያልሰራበትን ቀናት የሚመለከት ነው።አማራጭ ትርጉም፦ ሥራ ሳይሰራ ከንቱ ያሳለፈው ጊዜ
“የመታው ሰው ካሣ ይክፈለው” ወይም “የመታው ሰው የህክምና ወጪ ሊከፍለው ይገባል”
አንድ ሰው በምቱ ምክንያት ቢሞትበት” ወይም “ጌታው ባርያውን ቢመታና ቢሞትበት”
ያ ሰው መቀጣት ይገባዋል ወይም ያንን ሰው መቅጣት አለብህ
በትርጉሙ ውስጥ ባርያው ለባለቤቱ ንብረቱ ወይም ሀብቱ እንደሆነ መገለጽ አለበት። አማራጭ ትርጉም፦ ምክንያቱም ጌታው ውድ የሆነውን ባርያውን በማጣቱ ተጎቷል
ህጻኑን ቢያስወርዳት ወይም ያለጊዜው ተወልዶ ቢሞትና በሴትዮዋ ላይ ሌላ ምንም ጒዳት ሳይደርስ ቢቀር
በሌላ አገላለጽ፦ አጥፊው ሰው መቀጣት አለበት ወይም ያጠፋው ሰው ተገቢውን ካሳ መክፈል አለበት
ዳኞች የፈረዱበትን ወይም የወሰኑበትን ካሳ መክፈል አለበት
ሴትዮዋ ብትጎዳ የጎዳትም ሰው በተመሳሳይ መልኩ መጎዳት አለበት። አማራጭ ትርጉም፦ ሰውዬው ለሕይወቷ ሕይወቱን፥ ለዓይኗ ዓይኑን መክፈል ወይም መጎዳት አለበት
የባርያ ጌታው ወይም አሳዳሪው
ለበደለው በደል ካሣ እንዲሆን ባሪያውን ነጻ ይልቀቅ
የአንድ ሰው በሬ አንድን ሰው በቀንዱ ወግቶ ቢገድል
በሬው በድንጋይ ተወግሮ ይሙት ወይም በሬውን በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉት
በሌላ አገላለጽ፦ የበሬውን ሥጋ አትብሉ ወይም የበሬው ሥጋ አይበላ
በሌላ አገላለጽ፦ የበሬው ባለቤት በነጻ ይለቀቅ ወይም የበሬውን ባለቤት በነጻ ልቀቁት አይጠየቅ
የበሬው ባለቤት ወይም ባለ ንብረቱ በሞት ይቀጣ ወይም የበሬውን ባለቤት ወይም ባለ ንብረቱን ግደሉት
ተጎጂዎች ካሳ ክፊያ ቢፈልጉ የበሬው ባለቤት ሕይወቱን ለማዳን ቢፈልግ ዳኞች የወሰኑበትን መክፈል አለበት። በትርጉሙ ውስጥ ይህ ግልጽ ሆኖ መታየት አለበት። አማራጭ ትርጉም፦ የበሬው ባለቤት ሕይወቱን ለመዋጀት ወይም ከሞት ለመትረፍ ካሣ እንዲከፍል ከተፈቀደለት ወይም ከተስማሙ ካሣውን በሙሉ መክፈል አለበት።
ያ በሬ ወይም የዚያ ሰው በሬ ወንድ ወይም ሴት ልጅ ወግቶ ቢገድል
330 ግራም ብር ይስጥ፤ አንድ ሰቅል 11 ግራም ብር ይመዝናል።
በሬውን በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉት ወይም በሬው በድንጋይ ተግሮ ይሙት
አንድ ሰው የጒድጓድ መክደኛ ቢያነሣ ወይም ጒድጓድ ቆፍሮ ሳይከድነው ቢተው
የበሬው ባለቤት ይጉዳቱን ካሳ ማግኘት አለበት። አማራጭ ትርጉም፦ ለበሬው ባለቤት ለሞተው እንስሳ ምትክ ካሳ ይከፈለው
ለሞተው እንስሳ ምትኩን የከፈለው ሰው የሞተውን እንሳሳ ለራሱ ወስዶ የፈለገውን ማድረግ ይችላል። የዚህ ክፍል የመልዕክቱ ዋና ሀሳብ ግልጽ ሆኖ መውጣት አለበት። አማራጭ ትርጉም፦ የሞተው እንስሳ ለጉድጓዱ ባለቤት ይሆናል ወይም የሞተውን እንስሳ ለራሱ ማስቀረት አለበት
የበሬውን ዋጋ በጋራ ይክፋፈሉ ወይም ገዘቡን አብረው ይካፈሉ”
በሌላ አገላለጽ፦ በሬው ተዋጊ መሆኑን ሰዎች የሚያውቁ ከሆነ ወይም የበሬው ባለቤት በሬው ተዋጊ መሆኑን የሚያውቅ ከሆነ
የበሬው ባለቤት በሬው በአግባቡ ባይጠብቀው ወይም ከአጥር ውስጥ እንዳይወጣ ባያደርግ
የገደለው በሬ ባለቤት በሬው ለሞተበት ሰው በሬ መካስ አለበት። ስለሆነም በትርጉም ውስጥ ይህ ሀሳብ በግልጽ መታየት አለበት። አማራጭ ትርጉም፦ በሬው ለሞተበት ሰው አንድ በሕይወት ያለ በሬ ካሣ መክፈል አለበት
1 ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅና ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፣ ለአንድ በሬ ዐምስት በሬ፣ ለአንድ በግም ዐምስት በግ መክፈል አለበት፥ 2 ሌባ በር ሰብሮ ሲገባ ቢገኝና ተደብድቦ ቢሞት፣ በማንም ሰው ላይ የደም ዕዳ አይኖርም። 3 ነገር ግን ሰብሮ ከመግባቱ በፊት ፀሐይ ከወጣ፣ በገደለው ሰው ላይ የደም ተጠያቂነት ይኖራል። ሌባ የሰረቀውን መመለስ አለበት። ምንም ነገር ከሌለው፣ የሰረቀውን እንዲከፍል እርሱ ራሱ መሸጥ ይኖርበታል። 4 ሆነ አህያ ወይም በግ ቢሆን የተሰረቀው እንስሳ በሕይወት እርሱ ዘንድ ከተገኘ፣ ዕጥፉን መልሶ መክፈል አለበት። 5 ሰው ከብቱን መስክ ላይ ወይም የወይን ዕርሻ ውስጥ አሰማርቶ ቢለቅቀውና በሌላ ሰው ዕርሻ ውስጥ ገብቶ ቢግጥ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክና የወይን ዕርሻ መካስ ይኖርበታል። 6 እሳት ቢነሣና በእሾኾችም ውስጥ ቢዛመት፣ ክምሩም፣ ያልታጨደውም እህል ወይም ዕርሻው ቢቃጠል፣ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይካሥ። 7 ሰው እንዲጠበቅለት ገንዘቡን ወይም ዕቃውን ለጎረቤቱ ቢሰጥ፣ በዐደራ ያስቀመጠውንም ከሰውዬው ቤት ሌባ ቢሰርቀውና ሌባውም ቢገኝ፣ ያ ሌባ ዕጥፍ መክፈል አለበት፤ 8 ባይገኝ ግን፣ የቤቱ ባለቤት እጁን በጎረቤቱ ንብረት ላይ መዘርጋቱንና አለመዘርጋቱን ለማየት፣ በዳኞች ፊት ሊቀርብ ይገባል። 9 ስለ በሬ፣ ስለ አህያ፣ ስለ በግ፣ ስለ ልብስ ወይም አንድ ሰው፣ “ይህ የእኔ ነው” ስለሚለው ስለ ማንኛውም የጠፋ ነገር የሚነሣ ክርክር ሁሉ፣ የሁለቱም ወገን አቤቱታ በዳኞች ፊት መቅረብ አለበት። ዳኞች በደለኛ ሆኖ ያገኙት ሰው ለጎረቤቱ ዕጥፍ መክፈል ይኖርበታል። 10 አንድ ሰው አህያ፣ በሬ፣ በግ፣ ወይም ማንኛውም እንስሳ እንዲጠበቅለት ለጎረቤቱ በዐደራ ቢሰጥና እንስሳው ቢሞት፣ ወይም ጕዳይ ቢደርስበት፣ ወይም ማንም ሳያይ ቢወሰድ፣ 11 ሰው በጎረቤቱ ንብረት ላይ እጁን መዘርጋቱን ወይም አለመዘርጋቱን ለመለየት፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት መማል አለባቸው። ባለቤቱ ይህን ሊቀበል ይገባል፤ ሌላውም ሰው ካሣ አይክሥም። 12 ነገር ግን እንስሳው ከእርፍሱ ተሰርቆ ከሆነ፣ ሌላው ሰው ለባለቤቱ ካሣ መካሥ አለበት። 13 አንድን እንስሳ አውሬ ቢዘነጥለው፣ ሌላው ሰውዬ እንስሳውን ማስረጃ አድርጎ ያቅርብ። ለተዘነጣጠለው እንስሳ ካሣ መክፈል የለበትም። 14 አንድ ሰው ከጎረቤቱ እንስሳ ቢዋስና እንስሳው ባለቤቱ በሌለበት ቢጎዳ ወይም ቢሞት፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መካሥ አለበት። 15 ባለቤቱ ካለበት ከሆነ ግን፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መክፈል የለበትም፤ እንስሳ ተከራይቶ የነበረ ከሆነ፣ በተከራየበት ዋጋ ይከፈላል። 16 አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድን ቢያታልልና ዐብሯት ቢተኛ፣ ለዚህ ተገቢ የሆነውን ማጫ ከፍሎ ሚስቱ ሊያደርጋት ይገባል። 17 አባቷ በሚስትነት አልሰጥህም ካለው፣ ልጃገረዶች ማጫ ከሚከፈለው ጋር እኩል የሆነ ገንዘብ መክፈል አለበት። 18 መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ። 19 ከእንስሳት ጋር የወሲብ ግንኙነት የሚያደርግ መምት አለበት። 20 ከእግዚአብሔር በቀር ለማንኛውም ባዕድ አምላክ መሥዋዕት የሚሠዋ ፈጽሞ መጥፋት ይኖርበታል። 21 መጻተኛውን አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና። 22 ማንኛዋንም መበለት ወይም አባትና እናት የሌለውን ልጁ ማስጨነቅ የለባችሁም። 23 የምታስጨንቋቸው ከሆነና እነርሱም ወደ እኔ ከጮኹ፤ እኔ እግዚአብሔር ጩኸታቸውን እሰማለሁ። 24 ቊጣዬ ይቀጣጠላል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለታት፣ ልጆቻችሁም አባት ዐልባዎች ይሆናሉ። 25 ከሕዝቤ መካከል ድኻ ከሆኑት ለአንዱ ገንዘብ ብታበድሩ፣ እንደ አራጣ አበዳሪ አትሁኑበት ወይም ወለድ አታስከፍሉት። 26 የጎረቤትህን ልብስ በመያዣነት ብትወስድ፣ ፀሐይ ከመግባቷ በፊት ልትመልስለት ይገባል። 27 ሰውነቱን የሚሸፍንበት ልብሱ እርሱ ብቻ ነውና። ምን ሌላ ልብስ ለብሶ መተኛት ይችላል? ወደ እኔ ሲጮኽ፣ ርኅሩኅ ነኝና እሰማዋለሁ። 28 ፈራጆችንም አትስደብ፤ የሕዝብህን አለቃም አትርገም። 29 ወይም ከወይን ጭማቂዎችህ የምታቀርባቸውን ስጦታዎች ማዘግየት የለብህም። የወንድ ልጆችህንም በኵር ለእኔ መስጠት አለብህ። 30 በበጎችህ ላይም ይህንኑ ማድረግ ይኖርብሃል። ልጆቹ ሰባት ቀን ክአእናቶቻቸው ጋር መቆየት ይችላሉ፤ በስምንተኛው ቀን ግን ለእኔ መስጠት አለብህ። 31 ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ስለዚህ መስክ ላይ አውሬ የዘነጣጠለውን ሥጋ ለውሾች ጣሉት፣ ልትበሉት አይገባም።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
በሌላ አገላለጽ፦ አንድ ሰው ሌባ ሆኖ ቢገኝ ወይም አንድ ሰው ሰርቆ ቢገኝ
በሌላ አገላለጽ፦ አንድ ሌባ የአንድ ሰው ቤት ሰብሮ ቢገባ
በሌላ አገላለጽ፦ አንድ ሰው ቢመታውና ሌባው ቢሞት
በሌላ አገላለጽ፦ ተከላካዩ ወይም ሌባውን መቶ የገደለው ሰው ለፈሰሰው ደም ወይም በመግደሉ ተጠያቂ አይሆንም
በሌላ አባባል፦ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወይም ብርሃን እያለ ሌባው ተመትቶ ቢገደል ግን ተከላካዩ በግድያው ተጠያቂ ይሆናል
ሌባው የሰረቀውን መክፈል አለበት ወይም ሌባው በሰረቀው ንብረት ምትክ ክፊያ መስጠት አለበት
ምንም ከሌለው ግን የሰረቀውን ይከፍል ዘንድ ራሱ በባርነት ይሸጥ
ሌባው የሰረቀው እንስሳ ሕያው ሆኖ ቢገኝ ወይም በሕይወት ቢገኝ
ለያንዳንዱ እንስሳ ዕጥፍ ዋጋ ወይም ሁለት እንስሳ ይክፈል
አንድ ሰው እንስሶቹ በእርሻው ወይም በመስክ ወይም በወይን ተክል ቦታ አሰማርቶ እያለ
እንስሶቹ ወደ ሌላ ሰው እርሻ ገብተው ሰብሉን ቢበሉት
ከራሱ እርሻ ሰብል ወይም የወይን ቦታ ምርጡን መክፈል አለበት
አንድ ሰው በእርሻው ውስጥ እሳት ቢያቀጣጥልና እሳቱ ወደ ቊጥቋጦ ተዛምቶ ቢሰራጭ
ወደ ሌላው ሰው እርሻ በመዛመት ያልታጨደውን ወይም ታጭዶ የተቀመጠውን ወይም የተከመረውን እህል ቢያቃጥል
እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይክፈል
እንዳይጠፋበት ወይም እንዳይሰረቅበት በአደራ ቢያስቀምጥ
በሌላ አገላለጽ፦ አንድ ሰው ወይም ሌባ ቢሰርቀው
በሌላ አገላለጽ፦ የሰረቀውን ሰው ብታገኘው ወይም ብታገኘው
ሌባው ካልተገኘ ግን ዕቃውን በዐደራ የተቀበለው ሰው ዳኞች ፊት ይቅረብ /ይምጣ/
“እጁን . . . እንዳልዘረጋ” የሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ነው። ይህን ዘይቤያዊ እነጋገር በተመሳሳይ ዘይቤያዊ ንግግር መትርጎም የሚቻል ከሆነ መተረጎም ጥሩ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የዚያን ሰው ንብረት ራሱ አለመስረቁን በመሐላ ያረጋግጥ
በሁለቱ መካከል ክርክር ቢነሣ ባለ ጉዳዮቹ ነገሩን ለዳኞች ያቅርቡት
እንስሳውን ሰርቀሃል ተብሎ የተከሰሰው ሰው አለመስረቁን በመሀላ ያረጋግጥ። የእንሳሳው ባለቤት ደግሞ የሰውየውን መሀላ መቀበል አለበት። በሌላ አገላልጽ፦ እንስሳውን በአደራ የተቀበለው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ይማል እንዲሁም የእንስሳው ባለቤት መሀላውን ይቀበል
በሌላ አገላለጽ፦ እንስሳው ከባለአደራው የተሰረቀ ከሆነ
በሌላ አገላለጽ፦ እንስሳው በአውሬ ተሰብሮን ተበልቶ ከሆነ
አውሬ ስለ ገደለውም ወይም ስለበላው ካሳ አይክፈል።
በውሰት ለሰጠው ሰው ካሳ መክፈል አለበት ወይም በውሰት ለሰጠው ሰው ሌላ እንስሳ በምትክ መስጠት አለበት
ባለቤቱ ከእንስሳው ጋር ከሆነ ግን ተበዳሪው መክፈል የለበትም
እንስሳውን የተከራየው ሰው ከክራይ ገንዘብ ይልቅ ምንም ዓይነት ካሳ መክፈል የለበትም። የክራዩ ገንዘብ ክሳርውን ይሸፍንለትታል ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ለኪራይ የተከፈለው ገንዘብ ጒዳቱን ወይም ኪሳራውን ያካክስለታል።
አንድ ሰው ያልታጨችን ልጃገረድ ከእርሱ ጋር እንድትተኛ ቢያታልላት
ለጋብቻ ያልታጨች ወይም ቃል ኪዳን ይላደረገች
ከእርሷ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ቢፈጽም
የሞራል ካሳ ከፍሎ ወይም የማጫ ዋጋ ከፍሎ
የሞራል ካሳ ከፍሎ ወይም የማጫ ዋጋ ከፍሎ
“ሚስት ያድርጋት” የተባለው አታሏት የደፈራት ወይም ክብረ ንጽህናዋን የወሰዳት”
እዚህ ጋር “የሚረክስ” የሚለው በአይነኬ ዘይቤ የተገለጸ ሲሆን አንድ ሰው ከእንስሳ የሚፈጽመውን የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚመለከት ነው። በሌላ አገላለጽ፦ “ከእንስሳ ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽምን ሰው ፈጽማችሁ ግደሉ”
ከእግዚአብሔር ሌላ ለማንኛውም አምላክ መሥዋዕት የሚያቀርብ በሞት ይቀጣ ወይም ግደሉት
መጻተኛውን ወይም እንግዳ ሰው አትበድል ወይም አታስጨንቅ
በሌላ አገላለጽ፦ ባል የሞተባትን ሴት እና አባትና እናት የሞቱበትን ድኻ ዐደግ አታጒላሉ” ወይም “ባል የሞተባትን ሴት እና ወላጅ አጥ ድኻ ዐደጉን እኩል አስተናግድ”
ባሏ የሞተባት ሴት
አባትና እናት የሞተበት
በጦርነት ወይም በተለየ አደጋ እንድትሞቱ አደርጋችኋለሁ
ለአንድ ሰው ገንዘብ ብታበድር
እንደ ገንዘብ አበዳሪ ወለድ ጨምሮ እንዲከፍልህ አትጠይቀው
የባልንጀራህን ወይም የጓደኛህን ልብስ መያዣ አድርገህ ብትይዝ
ምክንያቱም ለሰውነቱ መሸፈኛ ወይም ለብርድ መከላከያነት ያለው ልብስ ያ ብቻ ነው
ምክንያቱም ሌላ ለብሶ የሚተኛበት ወይም የሚያድረበት የለውም
በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ የስድብ ቃል አትናገር ወይም አታሰማ
የሕዝብንም አለቃ አትርገመው” ወይም “የህዝብህን መሪ እንድረግመው እግዚአብሔርን አትጠይቅ
በሌላ አገላለጽ፦ “የእህልህን ወይም የወይን ጠጅህን መስዋዕት ለእኔ ከማቅረብ ወደ ኋላ አትበል”
1 ማንም ሰው የሐሰት ወሬ እትናገር። ሐሰተኛ ምስክር ለመሆን ከክፉ ሰው ጋር አትተባበር። 2 ክፋት ለመፈጸም ሕዝብን አትከተል፤ ወይም ፍትሕን ለማጣመም ከሰዎች ጋር ተባብረህ ምስክርነት አትስጥ። 3 ድኻውን በሙግቱ አታድላለት። 4 በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኘው መልስለት። 5 የሚጠላህን ሰው አህያ እንደ ተጫነ ከጭነቱ ሥር ወድቆ ብታየው፣ ያን ሰው ትተኸው አትሂድ። አህያውን ለማንሣት ልታግዘው ይገባል። 6 ጊዜ ለድኻው ወገንህ የሚሰጠውን ፍትሕ አታጣምም። 7 በሐሰት ክስ ከሌሎች ጋር አትተ ባበር፤ ንጹሑንም ወይም ጻድቁንም አትግደል፤ እኔ ኀጢአተኛውን ንጹሕ አላደርግምና። 8 አትቀበል፤ ጕቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራል፤ የታማኝ ሰዎችን ቃልም ያጣምማልና። 9 የመጻተኛነትን ስለምታውቁት፣ መጻተኛን አታስጨንቁ፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና። 10 ስድስት ዓመት በመሬትህ ላይ ዘር ዝራ፤ መከሩንም ሰብስብ። 11 በሰባተኛው ዓመት ግን በሕዝብህ መካከል ያሉ ድኾች መብላት እንዲችሉ ሳታርሰው ዕዳሪውን ተወው። ከድኾች የሚተርፈውንም የዱር እንስሳት ይበሉታል። በወይን ቦታዎችህና በወይራ ዛፎችህም ይህንኑ ታደርጋለህ። 12 ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ። ይህን የምታደርገውም፦ በሬህ፣ አህያህ፣ የሴት አገልጋይህ ወንድ ልጅና መጻተኛው ሁሉ ዕረፍት እንዲያገኙና እንዲዝናኑ ነው። 13 የነገርኋችሁን ሁሉ ጠብቁ። የሌሎች አማልክትን ስም አትጥሩ፤ ወይም ስማቸው ከአፋችሁ አይሰማ። 14 በየዓመቱ ሦስት ጊዜ ልአእኔ በዓል ታከብራላችሁ። 15 በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት ሰባት ቀን ቂጣ ትበላለህ። በዚያ ጊዜ፣ ለዚህ በተወሰነው በአቢብ ወር በፊቴ ትቀርባለህ። ከግብፅ የወጣኸው በዚህ ወር ነበር። ነገር ግን በፊቴ ባዶ እጅህን መቅረብ የለብህም። 16 ላይ የዘራኸውን የእህልህን በኵራት፣ የመከርን በዓል አክብር። በዓመቱ መጨረሻ ምርትህን ከማሳ ስትሰበስብ፣ የመክተቻውን በዓል አክብር። 17 ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይቅረብ። 18 የመሥዋዕቱን ደም እርሾ ካለበት ዳቦ ጋር ለእኔ አታቅርብ። በበዓሎቼ የሚቀርበው የመሥዋዕቴ ሥብ እስከ ንጋት ድረስ መቆየት የለበትም። 19 የመሬትህን ምርጥ ፍሬ በኵራት ወደ እኔ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል። 20 በመንገድ የሚጠብቅህንና ወዳዘጋጀሁልህ ስፍራ መርቶ የሚያስገባህን መልአክ በፊትህ እልካለሁ። 21 ተከተለው፤ ታዘዝለትም። ኀጢአትህን ይቅር አይልህምና አታስቆጣው። ስሜ በእርሱ ላይ ነው። 22 ድምፁን በእውነት ብትሰማና የምነግርህን ሁሉ ብታደርግ፣ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ። 23 መልአክ በፊትህ ይሄዳል፤ አንተንም ወደ አሞራውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ያስገባሃል። እኔ እነርሱን አጠፋቸዋለሁ። 24 ለአማልክታቸው አትስገድ፤ አታምልካቸውም፤ ወይም ሕዝቡ እንደሚያደርጉት አታድርግ፤ ይልቁን ፈጽመህ ልታፈራርሳቸው፣ የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም ልትሰባብራቸው ይገባል። 25 እኔን አምላክህን እግዚአብሔርን አምልክ። ይህን ካደረግህ፣ የምትባውንና የምትጠጣውን እባርካለሁ። በሽታንም ከመካከልህ አጠፋለሁ። 26 የምትጨነግፍ ወይም የምትመክን ሴት አትምርም። ለአንተ ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ። 27 ምድር ሕዝብ ላይ ማስፈራቴን እልካለሁ። የሚያጋጥሙህን ሰዎች ሁሉ እገድላለሁ። ጠላቶችህን ሁሉ ከፍርሀት የተነሣ ጀርባቸውን ወደ አንተ እንዲያዞሩ አደርጋለሁ። 28 ከነዓናውያንና ኬጤያውያንን ከፊትህ እንዲያበሯቸው ተርቦችን በፊትህ እሰድዳለሁ። 29 ወና እንዳትሆንና የዱር አራዊትም እጅግ እንዳበዙብህ፣ የምድሪቱን ኗሪዎች በአንድ ዓመት ውስጥ ከፊትህ አላባርራቸውም። 30 ነገር ግን አንተ እስክትበዛና ምድሪቱን እስክትወርሳት ድረስ በትንሽ በትንሹ አስወጣቸዋለሁ። 31 ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድር በዳውም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አደርገዋለሁ። በምድሪቱ ኗሪዎች ላይ ድል እንድትጎናጸፍ አደርጋለሁ፤ ከፊትህም ታባርራቸዋለህ። 32 ወይም ከአማልክታቸው ጋር ኪዳን አታድርግ። 33 እነርሱ በምድርህ ውስጥ መኖር አይገባቸውም፤ አልዚያ በእኔ ላይ ኀጢአት እንድትሠራ ያደርጉሃል። አማልክታቸውን ብታመልክ፣ ይህ በእውነት ወጥመድ ይሆንብሃል።”
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
ተንኰል ያለበትን ምስክርነት በመስጠት ወይም በሀሰት በመመስከር
ይህ ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን አንድ ሰው ከብዙ ሰው ጋር በመስማማት ፍለጋቸውን መከተልን የሚያመለክት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ክፉ ለማድረግ የተሰባሰቡ ሰዎችን አትከተል ወይም ብዙ ሰዎች የሚፈልጉትን ለማድረግ ከእነርሱ ጋር አትተባበር
ፍትህን ወይም እውነተኛ ፍርድን ለማዛባት ወይም የህሊና ዳኝነት ለመካድ ወይም ላለመስማት
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
በፍርድ አደባባይ ወይም በዳኝነት አድልዎ በማድረግ የድኻውን ፍርድ አታጣምበትብ ወይም አታዛባ
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
ከእርሻ የምታገኘውን ምርት ሰብስብ
ሳትርሳት እንዲሁ ተዋት፤ ምድርቱን አሳርፋት
ድሆች በእርሻው ውስጥ ራሱ የበሰለውን ምርት ይበሉ ዘንድ ምድርቱን ሳታርስ ተው። አማራጭ ትርጉም፦ በሕዝብህ መካከል የሚገኙ ድኾች ምግብ ያገኙ ዘንድ ወይም በወገንህ መካከል ያሉት ድኾች ከእርሷ ምግብ ያገኛሉ
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
የነገርኳችሁን ሁሉ በጥንቃቄ አድምጡ
የሥራ እንስሳት እንዲያርፉ
በሌላ አገላለጽ፦ በቤትህ የተወለደው ባሪያና መጻተኛው ወይም የሌላ አገር ሰው ያርፉ ዘንድ
ሌሎችን አማልክት ስም መጥራት ፀሎትን የሚመለከት ነውና “ወደ ሌሎች አማልክት አትጸልዩ”
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
የአቢብ ወር ለእብራውያን የአመቱ መጀመሪያ ወር ነው። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር አቢብ ወር የሚጀምረው ከመጋቢት መጨረሻ ሳምንት እስከ ሚያዝያ መጀመሪያ ሳምንት ድረስ ነው። (ዘጸአት 13፡4 ተመልከት)
ይህ አነጋገር እግዚአብሔር ማንም ሰው ወደ ፊቱ ሲመጣ የሆነ ነገር ተሸክሞ እንድመጣ የሚጠይቅ ይመስላል። ነገር ግን ይህ ወካይ ዘይቤ የሚያሳየው “ወደ እኔ የሚመጣ ማንም ቢሆን መስዋዕት ሳይዝ አይምጣ” ወይም “ወደ እኔ የሚመጣ ማንም ቢሆን መስዋዕት ማምጣት አለበት” የሚል ነው።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
ይህ በዓል የዳስ በመባል ይታወቃል። ይህ ልምምድ የመጣው እርሻቸውን በዳስ ወይም በጊዜያዊ ጎጆ ውስጥ ሆነው ያረሱና እህሉ እስኪደርስ ድረስ በዚያ ዳስ ሆነው ከአውሬ ሲጠብቁ የነበሩ አርሶ አደሮች ልምምድ ነው። “መክተቻ” የተባለው የእህል ማከማቻ ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “በዓመቱ መጨረሻ የዳስ በዓል አክብሩ”
እዚህ ቦታ “ይታይ” የሚለው ለአምልኮ መሰብሰብን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ወንድ ሁሉ እግዚአብሔርን (ያህዌን) ለማምለክ በአንድ ላይ መሰብሰብ አለበት።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
ስቡ የሚበላ ሳይሆን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መስዋዕት ሆኖ መቅረብ አለበት። ስለሆነም “ለነገ እንዲያድር አይፈቀድም ወይም እስከ ነገ መቆየት የለበትም”
ከእርሻ ምርቱ የተሻለውን ወይም መጀመሪያ የደረሰውን”
ይህ ድርጊት የከነዓናውያን ልምምድ ሲሆን ምርታማነትን ይጭምራል ተብሎ ስለሚታሰብ የሚደረግ ነው። ስለሆነም እስራኤላውያን ይህንን ድርጊት እንዳያደርጉ ተከልክለዋል። አማራጭ ትርጉም፦ “የበግ ወይም የፍየል ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል”
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
በጥንቃቄ ተከተለው ወይም አዳምጠህ እግዚአብሔርን (ያህዌን) ታዘዝ
እርሱን የምታስመርር (ለቁጣ የምታነሳሳ) ከሆነ ይቅር አይልህም
በዚህ ቦታ “ስም” የእግዚአብሔርን ስልጣንን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ለእርሱ ስልጣን ስለሰጠሁ
እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚናገረውን በጥንቃቄ ብታደምጥ
እንዚህ ሁለት ነገሮች ተመሳሳይ ነገር የሚገልጹና አጽንኦት ለመስጠት የገቡ ናቸው።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
እስራኤላውያን ጣኦትን እንደምያመልኩ እንደ ሌሎች ህዝቦች መኖር የለባቸውም። አማራጭ ትርጉም፦ የሌሎችን ህዝቦች ሃይማኖታዊ ልማዶቻቸውን ወይም ሥርዓታቸውን አትከተል
ይህ አባባል አጠቃላይ የኑሮ ሁኔታ ለውጥ የሚመለከት ነው። ዘማራጭ ትርጉም፦ እርሱ የምትበላውን እህል እና የምትጠጣውን ውሃ ይባርክልሃል ወይም የምትበላውን እህልና የምትጠጣውን ውሃ ይባርክሃል
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
በሌላ አገላለጽ፦ በምድርህ ጽንስ የሚያስወርዳት ወይም መካን ሴት አትኖርም ወይም በምድርህ ያሉ ሴቶች ያረግዛሉ እንዲሁም ይወልዳሉ
ጊዜው ሳይደርስ የምትወልድ እና ልጇ የሚሞትባት ሴት
“ተርብ” ሰዎችን በመንደፍ ስቃይ የሚያስከትሉ በራሪ ነፍሳት
ምድርቱ ሰው የማይኖርባት ምድር እንዳትሆን
እግዚአብሔር (ያህዌ) ህጉን በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን መናገሩን ሲቀጥል እናያለን
“ወጥመድ” ሰዎች አውሬዎችን፥ ወፎችን፥ እና ሌሎች ነገሮችን ለማጥመድ ወይም ለመያዝ የሚጠቀሙት መሳሪያ ነው። በተመሳሳይ መልኩ እስራኤላውያን ሌሎች አማልክትን ብያመልኩ ወደ ጥፋት እንደምወስዳቸው ያመለክታል።
1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ እኔ ኑ፤ በርቀት ሆናችሁም ስገዱልኝ። 2 ሙሴ ብቻ ወደ እኔ መቅረብ ይችላል። ሌሎች መቅረብ የለባቸውም፤ ወይም ሕዝቡ ከሙሴ ጋር መምጣት አይችሉም።” 3 ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎችና ሕጎቹን ሁሉ ነገራቸው። ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፣ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ። 4 ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ ጻፈ። ማለዳ ላይም በተራራው ግርጌ መሠዊያ ሠራ፤ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ነገዶች እንዲወክሉም፣ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ። 5 የሚቃጠልና የኅብረት መሥዋዕቶችን ከበሬዎች ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡም፣ ጥቂት የእስራኤል ወጣት ወንዶችን ላከ። 6 ሙሴ የደሙን እኩሌታ በሣህን አደረገው፣ የቀረውንም እኩሌታ በመሠዊያው ላይ ረጨው። 7 መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ ጮኽ ብሎ አነበበላቸው። ሕዝቡም፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉእናደርጋለን፤ እንታዘዛለንም” ብለው ተናገር። 8 ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው። “ይህ፣ ይህን የተስፋ ቃል ከእነዚህ ቃሎች ጋር ለእናንተ በመስጠት፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባው የኪዳኑ ደም ነው” በማለትም ተናገረ። 9 ከዚያም በኋላ ሙሴ፣ አሮን፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ተራራው ወጡ። 10 የእስራኤልን አምላክ አዩት። ከእግሮቹ ሥርም እንደ ንጹሕ ሰማይ ከጠራ የሰንፒር ድንጋይ የተሠራ ወለል ነበረ። 11 በእስራኤላውያን ሽማግሌዎች ላይ ተቆጥሮ እጅ አላሳረፈባቸውም። እነርሱ እግዚአብሔርን አዩ፤ በሉ፣ ጠጡም። 12 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ተራራው ላይ ወደ እኔ ና፤ በዚያም ቆይ። የድንጋይ ጽላቱን ሕዝቡን እንድታስተምራቸውም የፋጽሏቸውን ሕጉንና ትእዛዛቱን እሰጥሃለሁ” አለው። 13 ስለዚህ ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋር ወደ እግዚአብሔር ተራራ ሄደ። 14 ሙሴ ሽማግሌዎቹን፣ “ተመልሰን ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ እዚህ ቆዩን። አሮንና ሖር ከእናንተ ጋር ናቸው። ክርክር የሚኖርበት ሰው ካለ፣ ወደ እነርሱ ይቅረብ” አላቸው። 15 ወደ ተራራው ወጣ፤ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው። 16 የእግዚአብሔር ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመናውም ተራራውን ስድስት ቀን ሸፈነው። በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው። 17 የእግዚአብሔርን ክብር እስራኤላውያን ሲያዩት እንደሚያጋይ እሳት ነበር። 18 ሙሴ ደመናው ውስጥ ገብቶ ወደ ተራራው ወጣ። በተራራውም ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየ።
እነዚህ የወንዶች ስም ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞችን የመተርግሞ ዘዴ የሚለውን ተመልከት፤ ከዘጸአት 6፡23 ጋር አነጻጽር።
ከእስራኤል ሰዎች ወይም መሪዎች ሰባ የሚሆኑ
ይህ ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ህዝቡ በፍጹም መስማማት መሆናቸውን ያሳያል። አማራጭ ትርጉም፦ በአንድነት ወይም በመስማማት
በተራራው ሥር ወይም ከተራራው ግርጌ ማለት ነው
ሙሴ ሰዎችን ለመርጨት ከደሙ ግማሹን ወስዶ በገበቴ ወይም በባዝ ውስጥ አኖረው። ይህ የሚያሳየው የእስራኤል ህዝብ ከእግዚአብሔር ጋር ለሚያደርገው ቃል ኪዳን ማጽኛ ይሆን ዘንድ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “ሙሴም ከእንስሶቹ ደም ግማሹን ወስዶ በገበቴ ውስጥ አኖረው”
“መሰዊያው” እግዚአብሔርን የሚወክል ነው። ይህ የሚያሳየው እግዚአብሔር በቃል ኪዳን ተሳታፊ መሆኑ የሚያረጋግጥ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “ከእንስሳው ደም ግማሹን በመሠዊያው ፊት ረጨው”
በሌላ አገላለጽ፦ ለእግዚአብሔር በሁሉ ነገር እንታዘዛለን
ይህ ደም ሙሴ በገበቴው ውስጥ የጨመረው ደም እንጂ ሌላ ደም አይደለም። አማራጭ ትርጉም፦ “ሙሴ በገበቴ ያለውን ደም ወስዶ
እነዚህ የወንዶች ስም ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ስሞችን የመተርግሞ ዘዴ የሚለውን ተመልከት፤ ከዘጸአት 6፡23 ጋር አነጻጽር።
ይህ አባባል እግዚአብሔር እግር እንዳለው አድርጎ የሚያቀርብ ሰውኛ ዘይቤ ነው።
ሰንፔር ከሚመባል ከሰማያዊ ድንጋይ የተሰራ የሚያንጸባርቅ ወለል
ጠንካራ የሆነ ለመራመድ ወይም ለመንዳት የሚያገልግል
ሰማያዊ ቀለም ያለው (የማይታወቁ ነገሮችን የመተርጎም ዘዴ የሚለውን ተመልከት)
የከበረ (ውድ) ድንጋይ ሲሆን ቀለሙ ሰማያዊ ነው
ይህ ተነጻጻሪ ዘይቤ ሲሆን “እንደ ጠራ ሰማይ የሚያበራ ወይም ደመና እንደሌለው ሰማይ የጠራ”
ይህ ማለት እግዚአብሔር የእስራኤል ሽማግሌዎችን አልጎዳቸውም ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር የእስራኤል መሪዎች የሆኑ ሰዎችን አልቀሠፈም”
በጠፍጣፋ ድንጋዮች ላይ እግዚአብሔር ህጉንና ትዕዛዛቱን ጻፌ። በሌላ አባባል፦ “እኔ በእነርሱ ላይ ትዕዛዛቱን የጻፍኩባቸውን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች”
ሙሴ ከረዳቱ ወይም ከአገልጋዩ ኢያሱ ጋር ተነሱ
እኔንና ኢያሱን ጠብቁ
ይህ ሰው የሙሴና የአሮን ቅርብ ጓደኛቸው ነው፤ ዘጸአት 17፡10 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት
የእግዚአብሔርን ህልዎት የሚወክለው አንጸባራቂ ብርሃን
የእግዚአብሔር (የያህዌ) ክብር ትልቅና እንደ እሳት የሚያቃጥል ሆኖ ቀርቧል። አማራጭ ትርጉም፦ እንደ ትልቅ እሳት የሚያቃጥል ነበር
ዓይኖቻቸው ማየትን፥ ማየታቸው ደግም ሀሳባቸውን ወይም የሚያዩትን ነገር እንዴት እንደሚፈርጁ አመልካቺ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ
1 ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “እያንዳንዱ ሰው ልቡ በፈቀደለት መሠረት ስጦታ ለእኔ እንዲያመጣ ለእስራኤላውያን ንገር። እነዚህን ስጦታዎች ተቀበልልኝ። 3 ከእነርሱ የምትቀበላቸውም ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ወርቅ፣ ብርና ነሐስ፤ 4 ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጕር፣ 5 ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቁርበት፣ የግራር ዕንጨት፤ 6 ለመቅደሱ መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያው ዘይት ቅመሞችና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፤ 7 ለኤፉድና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቆች። 8 እንዳድር ሕዝቡ መቅደስ ይሥሩልኝ። 9 ለመገናኛው ድንኳንና ለዕቃዎቹ ሁሉ እኔ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ሥሩት። 10 ሁለት ክንድ ተኩል፣ ስፋቱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት ይሠሩ። 11 ውስጡንም ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት። 12 የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህለት በታቦቱ አራት እግሮች ላይ፣ ሁለቱን በአንድ ጎኑ፣ ሁለቱን ደግሞ በሌላው ጎኑ አስቀምጣቸው። 13 መሎጎያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና አወርቅ ለብጣቸው። 14 ታቦቱን ለመሸከም መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎን ባሉ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ። 15 መሎጊያዎቹ ምንጊዜም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ይቀመጣሉ እንጂ ከዚያ አይወጡም። 16 የኪዳኑን ምስክሮች በታቦቱ ውስጥ ታስቀምጣለህ። 17 ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሥራ። 18 ለሁለቱ የስርየት መክደኛ ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ ትሠራለህ። 19 ኪሩብ ለስርየት መክደኛው አንድ ጫፍ፣ ሌላውን ኪሩብ ደግሞ ለሌላው ጫፍ በማድረግ ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው መሠራት አለባቸው። 20 ክንፎቻቸውን ወደ ላይ መዘርጋትና የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው መጋረድ ይኖርባቸዋል። እርስ በርሳቸው መተያየትና ወደ ስርየት መክደኛውም መመልከት አለባቸው። 21 መክደኛውን በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ በታቦቱ ውስጥም የምሰጥህን የኪዳኑን ምስክሮች ታስቀምጣለህ። 22 እኔ ከአንተ ጋር የምገናኘው በታቦቱ ነው። በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ ከአንተ በተናገርሁበት በምስክሩ ታቦት ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ነው። 23 እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሥራ። 24 ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት። 25 አንድ ስንዝር ስፋት ያለው ጠርዝ ለጠርዙ በዙሪያው ከሚኖረው የወርቅ ክፈፍ ጋር አብጅለት። 26 አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራለትና ቀለበቶችን አራቱ እግሮቹ ባሉበት ከሚገኙት አራት ማዕዘኖች ጋር አያይዛቸው። 27 ለማስቀመጥና ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል፣ ቀለበቶቹ ከክፈፉ ጋር መያያዝ አለባቸው። 28 የጠረጴዛው መሸከሚያ እንዲሆኑም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና በወርቅ ለብጣቸው። 29 ቊርባኑን ለማፍሰስ ጥቅም እንዲሰጡ ወጭቶችን፣ ጭልፋዎችን፣ ማንቆርቆሪያዎችንና ጎድጓዳ ሣህኖችን ከንጹህ ወርቅ ሥራ። 30 በጠረጴዛውም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ። 31 መቆሚያና ዘንግ አበጅተህበት ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ መቅረዝ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ ሁሉ ወጥ ሆነው ከመቅረዙ ጋር ይሠራሉ። 32 ሦስት ቅርንጫፎች በአንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፍ ደግሞ በሌላው ጎን፣ ስድስት ቅርንጫፎች ለመቅረዙ ይውጡለት። 33 የመጀመሪያው ቅርንጫፍ የለውዝ አበቦችን መስለው የተሠሩ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ክአበባ ጋር፣ በሌላው ቅርንጫፍም እንደዚሁ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች የተቀረጹበት ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ሊኖሩት ይገባል። ከመቅረዙ በሚወጡት በስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ ላይ የሚሆነውም እንደዚሁ አንድ ዐይነት ነው። 34 ላይ የለውዝ አበባ መስለው የተቀረጹ አራት ጽዋዎች ከቀንበጦቹና ከአበባዎቹ ጋር ሊኖሩበት ይገባል። 35 በመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ፣ በሁለተኛው የቅርንጫፎች ጥንድ ሥርም እንደዚሁ ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይኖረዋል። በሦስተኛው የቅርንጫፎቹ ጥንድ ሥርም ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይበጅለታል። ከመቅረዙ በሚወጡ በስድስቱ ቅርንጫፎች ሁሉ የሚሆነውም ይኸው አንድ ዐይነት ነው። 36 ቀንበጦቻቸውና ቅርንጫፎቻቸው ሁሉ አንድ ወጥና ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መሆን አለባቸው። 37 መቅረዙንና ሰባት መብራቶችን ሠርተህ ፊት ለፊት ላለው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጥ አድርግ። 38 የኵስታሪ መሰብሰቢያ ሣህኖቻቸው ከንጹሕ ወርቅ መሠራት አለባቸው። 39 መቅረዙንና የመቅረዙን ዕቃ ሁሉ ለመሥራት አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ተጠቀም። 40 ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት የሠራሃቸው ስለ መሆንህ እርግጠኛ ሁን።
ይህ ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ስጦታ ለመስጠት የተነሳሳን አንድ ሰው ፍልጎት ወይም በጎ ፈቃድ ያሳያል አማራጭ ትርጉም፦ ስጦታ ለመስጠት የሚፈልግ ሰው
“ተቀበሉ” ተብሎ የተነገራቸው ሙሴንና የእስራኤል መሪዎችን/ሽማግሌዎችን/ ነው። የሚቀበሉትም ህዝቡ የሚያመጣውን ስጦታ ወይም መስዋዕት ወይም ቁርባን ነው።
እስራኤላውያን ማድረግ ያለባቸውን ነገር እግዚአብሔር(ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
አማራጭ ትርጉሞች፦ 1) በሰማያዊ፥ ሀምራዊና ቀይ ቀለም የተቀቡ ልብሶች/ሶፎች/ ወይም 2) ላይነኖችን ለመቀባት የሚረዱ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ሰማያዊ ቀለም
ነጣ ያለ ቀይ ቀለም ወይም በቀይ ቀለም የተቀለመ ጨርቅ
ግዙፍና ሳር በል የሆነ የባህር እንስሳ
የደረቁ የእጽዋት ተዋጽኦ ሲሆን ሰዎች ፈጭተው ጥሩ ሽታ እንድኖረው ዘይት ወይም ምግብ በዚያ ላይ ጨምረው የሚሰሩት ነው።
በላዩ ላይ ሁለት ቅርፍት ያለው ማለትም ነጭ ወይም ጥቁር፥ ቀይ ያለው የድንጋይ ዓይነት
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
“ቤተ መቅደስ” የሚለው “ቅዱስ ስፍራ” የሚገልጽ ሲሆን “ድንኳን” ደግሞ “ቅዱስ ድንኳን” ወይም ጊዜያዊ ቤት/መቆያ/ዳስ/ የሚል ፍቺ አለው። ሁለቱም ተመሳሳይ ፍቺ የሚሰጡ ተወራራሽ ቃላት ናቸው።
“እኔ በማሳይህ” የሚለው ሀረግ ሙሴን የሚመለከት ሲሆን “ሥሩት” ሙሴንና የእስራኤልን ህዝብ የሚመለከት ነው።
ሁሉንም እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ርዝመቱ አንድ ሜትር ከአስራ አምስት ሴንቲ ሜትር ስፋቱና ከፍታው ሥልሳ ዘጠኝ ሳንቲ ሜትር። አንድ ክንድ 46 ሴንቲ ሜትር ያክል ነው።
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
“የወርቅ ቀለበቶችን አድርግለት” የሚለው ወርቆችን በማቅለጥ በቀለበት መልክ ማውጣቱን ወይም ማድረቁን የሚመለከት ነው። በሌላ አገላለጽ፦ አራት የወርቅ ዋልታዎችንም ወይም ቀለበቶችን ሠርተህ
ታቦቱን ለመሸከም እንዲያገለግል
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በምስክሩ ታቦት ላይ የሚቀመጥና የስርየት መስዋዕቱን የሚሸፍን መክደኛ ነው
ርዝመቱ አንድ ሜትር ከአስራ አምስት ሴንቲ ሜትር ስፋቱና ከፍታው ሥልሳ ዘጠኝ ሳንቲ ሜትር። አንድ ክንድ 46 ሴንቲ ሜትር ያክል ነው።
ተቀጥቅጦ የተሰራ ወርቅ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በምስክሩ ታቦት ላይ የሚቀመጥና የስርየት መስዋዕቱን የሚሸፍን መክደኛ ነው
እነርሱም ከክዳኑ ጋር አብረው/ተያይዘው/ የተሠሩ ይሁኑ
እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ቀጥሏል
እኔ በታቦቱ መክደኛ ላይ ባሉ በሁለቱ ክሩቤሎች ውስጥ ሆኜ ለአንተ እገለጥልሃለሁ
በምስክሩ ታቦት ላይ የሚቀመጥና የስርየት መስዋዕቱን የሚሸፍን መክደኛ ነው
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ርዝመቱ አንድ ሜትር ከአስራ አምስት ሴንቲ ሜትር ስፋቱና ከፍታው ሥልሳ ዘጠኝ ሳንቲ ሜትር። አንድ ክንድ 46 ሴንቲ ሜትር ያክል ነው።
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በባህላዊው ልከት አንድ ጋት የአራት ጣቶች ጥምር ማለት ሲሆን ከ8-10 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው።
ጠርዝ ሥራለት/አብጅለት/
የወርቅ ቀለበቶችን በጠርዙ ላይ አያይዝ
ጠረጴዛውን ለመሸከም እንዲያገለግል
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በሌላ አገላለጽ፦ አንተ እነርሱን አስገብተህ ጠረጴዛውን መሸከም እንድትችል
በሌላ አገላለጽ፦ አንተ እነርሱን ለወይን ጠጅ መቅጃ እንድትጠቀም
በጠረጴዛው ላይ ሆኖ ለእኔ የሚቀርበው የተቀደሰ ኅብስት/ዳቦ/
መብራት ማስቀመጫ ባላ መሳይ ነገር
ለጌጥ ወይም የውበት አበባዎች፥ እንቡጦችና ቀንበጦች ከእርሱ ጋር አንድ ሆነው ይሠሩ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል። በሚቀጥሉት ክፍሎች እግዚአብሔር (ያህዌ) የመብራት ማስቀመጫውን (የመቅረዙን) አሰራር ዝርዝር ይናገራል (ዘጸአት 25፡31-32 ተመልከት)
ነጭ ወይም ሮዝ ቀለም/ቀላ ያለ አምራዊ/ መልክ ያለው አበባ የሚያወጣና አምስት ቀነበጦች ያሉት
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል። በሚቀጥሉት ክፍሎች እግዚአብሔር (ያህዌ) የመብራት ማስቀመጫውን (የመቅረዙን) አሰራር ዝርዝር ይናገራል (ዘጸአት 25፡31-32 ተመልከት)
እንቡጦቹ፥ ቅርንጫፎቹና መቅረዙ ሁሉም አንድ ወጥ ሆነው ይሰሩ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
ከፊት ለፊት በኩል ወይም ወደ ፊት እንዲያበሩ
መለኮሻዎችንና የአመድ ማስቀመጫ ሳሕኖችን ከንጹሕ ወርቅ ሥራ
አንድ መክሊት ወደ ከ33-35 ኪሎ ግራም ያህል ነው። በሌላ አገላለጽ፦ መብራት ማስቀመጫውን (መቅረዙን) እና እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም ከሆነ ንጹሕ ወርቅ ሥራ።
አማራጭ ትርጉም፦ “እኔ አንተን በተራራው ላይ ያሳየሁትን ምሳሌ ተከትለህ በጥንቃቄ ሥራ”
1 ከተፈተለ በፍታ ድር፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከተሠሩና ኪሩቤል ከተጠለፉባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ጋር ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ። ይህም ብልኅ ሠራተኛ የሚሠራው ሥራ ነው። 2 የያንዳንዱ መጋረሣ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። መጋረጃዎቹ ሁሉ እኩል መጠን ይኑራቸው። 3 ዐምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርስ መያያዝ አለባቸው፤ ሌሎቹ ዐምስት መጋረጃዎችም እንደዚሁ እርስ በርሳቸው መገጣጠም ይኖርባቸዋል። 4 በአንደኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ ግምጃ ቀለበቶችን አድርግ። ለሁለተኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝም ይህንኑ አበጅለት። 5 ዐምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው የመጋረጃ ወገን፣ ዐምሳ ቀለበቶችን በሌላው የመጨረሻ መጋረጃ ላይ አድርግ። ይህን የምትሠራውም ቀለበቶቹ እርስ በርስ እንዲተያዩ በማድረግ ነው። 6 ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዊችብ ሠርተህ ማደሪያ ድንኳኑ አንድ እንዲሆን፣ መጋረጃዎቹን በእነርሱ አያይዛቸው። 7 ከማደሪያው በላይ ለድንኳን የሚሆኑ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሥራ። 8 መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። ዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች እኩል መጠን ይኑራቸው። 9 ዐምስት መጋረጃዎችን በአንድነት፣ ስድስት መጋረጃውችንም እንዲሁ እርስ በርስ አያይዛቸው። ስድስተኛውን መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ዕጠፈው። 10 በመጀመሪያ ተገጣጣሚ የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ ሁለተኛውን የመጋረጃ አካል በሚያገጣጥመው የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አድርግ። 11 ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሥራና በቀለበቶቹ ውስጥ አስገ ባቸው። ከዚያም አንድ ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን አገጣጥመው። 12 መጋረጃዎች ተንጠልጥሎ ያለው ቀሪ ግማሽ መጋረጃ ከማደሪያ ድንኳኑ ጀርባ ይንጠልጠል። 13 ከመጋረጃዎቹ እርዝመት የተረፈው በአንድ በኩል አንድ ክንድ ምጋረጃ፣ 14 በሌላው ጎንም አንድ ክንድ መጋረጃ ማደሪያው ድንኳን መሸፈኛ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና ከዚያም በላይ የሚሆን የአስቆጣ ቁርበት አዘጋጅ። 15 ለማደሪያው ድንኳን የሚሆኑ ወጋግራዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅ። 16 ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን። 17 በርስ የሚያገናኗቸው ሁለት ጕጣጕጦች በያንዳንዱ ወጋግራ ላይ ይኑር። የመገናኛ ድንኳኑን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሥራ። 18 ድንኳን ወጋግራዎችን ስታበጅ፣ በደቡብ መኩል ላለው ሃያ ወጋግራዎችን አብጅ። 19 ወጋግራዎች የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ። ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መጋጠሚያዎች እንዲሆኑ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ። በሌሎች ወጋግራዎች በያንዳንዳቸው ሥርም ለሁለት መጋጠሚያዎቻቸው ሁለት መቆሚያዎች ይዘጋጁ። 20 በሰሜን በኩል ላለው ለሁለተኛው የመገናኛው ድንኳን ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና አርባ የብር መቆሚያዎቻቸውን ሥራ። 21 በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች. በእያንዳንዱ ሥር ይሁኑ። 22 በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳኑ የኋላ ጎን ስድስት ወጋግራዎችን አብጅ። 23 ለኋላ ማእዘኖቹም ሁለት ወጋግራዎችን አብጅ። 24 እነዚህ ወጋግራዎች ከታች ጥንድ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የተያያዙ መሆን አለባቸው። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የሚሆነው በዚህ መንገድ ነው። 25 ወጋግራዎች ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ሊኖሩ ይገባል። በሁሉም ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ናቸው ያሉት፤ በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋራ ሥርም ሁለት መቆሚያዎችና በእያንዳንዱም ሥር እንዲሁ። 26 ድንኳኑ አንደኛ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን ከግራር ዕንጨት አዘጋጅ፤ 27 ለማደሪያ ድንኳኑ ሌላ ጎንም ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛ ድንኳኑ የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን እንዲሁ አብጅ። 28 በወጋግራዎቹ መካከል ላይ ያለው አግዳሚ ከዳር እስከ ዳር መድረስ አለበት። 29 ወጋግራዎቹን በወርቅ ለብጣቸው። አግዳምዎችን ደግፍ በመያዝ እንዲያገለግሉም የወርቅ ቀለበቶቻቸውን ሥራላቸው፤ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለብጣቸው። 30 ድንኳኑን መትከል ያለብህ በተራራው ላይ ያየኸውን ምሳሌ በመተከትል ነው። 31 ብልኅ ሠራተኛ ኪሩቤልን የጠለፈበት፣ የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ግምጃና አምሮ የተፈተለ በፍታ መጋረጃ አብጅ። 32 በወርቅ በተለበጡ የግራር ዕንጨት አራት ዐምዶች ላይ ልትሰቅለው ይገባል። እነዚህ ዐምዶች በአራት የብር መቆሚያዎች ላይ የተቀመጡ የወርቅ ኵላቦች ይኖሯቸዋል። 33 መጋረጃውን በማያያዣዎቹ አንጠልጥለው፤ የምስክሩንም ታቦት አግባው። መጋረጃው ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳን ይለየዋል። 34 በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ባለ ውበምስክሩ ታቦት ላይ የስርየት መክደኛውን አስቀምጥ። 35 ከመጋረጃው ውጭ፣ መቅረዙንም ከመገናኛው ድንኳን ደቡባዊ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ አስቀምጥ። ጠረጴዛው በሰሜናዊ ጎኑ በኩል መቀመጥ ይኖርበታል። 36 መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ በጥልፍ ብሚያስጌጥ ሠራተኛ የተሠራ መጋረጃ አብጅለት። 37 ዐምስት ምሰሶዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅና በወርቅ ለብጣቸው። ኵላቦቻቸውም የውርቅ መሆን እላቸው፤ ዐምስት የነሐስ መቆሚያዎችንም ሥራላቸው።
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
በዚህ ክፍል “ሥራ” ተብሎ የታዘዘው ሙሴ ነው። ሙሴ ሥራውን ለሚሰራው ሰው የሥራውን ዝርዝር እንዲያሳየውና በሀላፊነት እንዲቆጣጠረው መታዘዙን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፦ “ለሠራተኛው ንገረው”
ክብደት ያለው እና ትልቅ የተሰፋ ጨርቅ ሲሆን መገናኛውን ድንኳን ለመሸፈንና የድንኳኑን ውስጠኛውን ክፍል ለመከፋፈል የሚያገለግል ነው።
በቀይ ቀለም የተቀባ ወይም የተነከረ ሱፍ ጨርቅ
የተውቡና ያገጡ ነገሮችን በእጅ የሚሰራ “እደ ጥበብ” ሰራተኛ
ርዝመቱ 12 ሜትር ከ88 ሳ.ሜት እንዲሁም ወርዱ 1.ሜትር ከ82 ሳንት ሜትር
በአድራጊ ግስ ሲጻፍ፦ አምስቱን መጋረጃዎችን በአንድ ላይ ስፏቸው እንዲሁም ሌሎችን አምስት መጋረጃዎችን በአንድ ሰፏቸው
መጋረጃዎችን ለማያያዝ የሚጠቅሙ/የሚያገለግሉ/ ከሰማያዊ ጨርቅ የተሰሩ ቀለበቶች ናቸው።
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
የመጋረጃዎችን ርዝመት፥ ስፋትና ከፍታ የሚያሳዩ ቁጥሮች ናቸው።
አንድ ክንድ 46 ሴንት ሜትር ያህል ነው
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
መጋረጃዎችን ለማያያዝ የሚጠቅሙ/የሚያገለግሉ/ ከሰማያዊ ጨርቅ የተሰሩ ቀለበቶች ናቸው
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
አንድ ክንድ 46 ሴንት ሜትር ያህል ነው
በቀይ ቀለም የተነከረ የበግ ቁርበት
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ድንኳኑን የሚደግፉ ቋሚዎችን ወይም ለማደሪያው ድንኳን ወጋግራዎችን አብጅ”
ወደ ሰባ (70) ሴንት ሜትር ያህል ነው
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
የብር መቆሚያዎችን አብጅ
በእያንዳንዱ ወጋግራ/ተራዳ ሥር ሁለት ሁለት መቆሚያ አድርግ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ከታች በኩል ተጣምረው እስከ ላይ አንደኛው ዋልታ መያያዝ አለባቸው
የብር መቆሚያዎች ይኑሩ/ይሰሩ/
የመገናኛውን ድንኳን እንዴት መገንባት እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ቀጥሏል
አግዳሚዎች/ አግዳሚ ብረቶች/አግዳሚ እንጨቶች/
የመገናኛው ድንኳን ፊቱ ወደ ምስራቅ የተመለሰ ነው
የመገናኛውን ድንኳን እንዴት መገንባት እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ቀጥሏል
በዚህ ክፍል “አድርግ” ተብሎ የታዘዘው ሙሴ ነው። ሙሴ ሥራውን ለሚሰራው ሰው የሥራውን ዝርዝር እንዲያሳየውና በሀላፊነት እንዲቆጣጠረው መታዘዙን ያመለክታል። አማራጭ ትርጉም፦ “እንዲሠራ ለሠራተኛው ንገረው”
የቃል ኪዳን ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ በኩል አኑረው/አስቀምጠው
መጋረጃው ቅድስት የተባለውን ስፍራ ቅድስተ ቅዱሳኑ ከተባለው ሥፍራ የሚለይ ይሁን
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በታቦቱ ላይ የሚቀመጠው የማስተሰሪያ መስዋዕት የተሰራበት መክደኛ ወይም መሸፈኛ (ዘጸአት 25፡17 ተመልከት)
የቃል ኪዳን ታቦት እንደማለት ነው። በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፉት ቃላት እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ምስክር እንዲሆን ነው።
ይህ ገበታ የህሊዎተ እግዚአብሔር መገኛ ምሳሌ የሆነው ዳቦ ያለበት ነው። በሌላ አገላለጽ፦ ጠረጴዛውን/የዳቦ ማስቀመጫውን/ ከቅድስተ ቅዱሳኑ ክፍል ውጪ ከማደሪያ ድንኳን በስተ ሰሜን በኩል አኑር/አስቀምጥ/
የመገናኛውን ድንኳን እንዴት መገንባት እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ቀጥሏል
ይህ አገላለጽ ሁለት ፍቺዎች አሉት፤ 1) በቀይ ቀለም የተቀባ ወይም የተነከረ ክር ወይም የሱፍ ጨርቅ 2) ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ የሆነ ክር ወይም የሱፍ ጨርቅ።
በእጅ የተፈተለ ወይም የተሰራ የሱፍ ክርም ማግም ሊሆን ይችላል
በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ ወይም በጥልፍ ዐዋቂ የተጠለፈ መጋረጃ
1 ዐምስት ክንድ ወርዱም ዐምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ። መሠዊያው አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ከፍታ ይኑረው። 2 ማእዘኖች የበሬ ቀንድ ቅርጽ እንዲኖራቸው ታደርጋለህ። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር አንድ ወጥና በነሐስ የተለበጡ ይሆናሉ። 3 የመሠዊያውን ዕቃዎች፦ የዐምድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ የሥጋ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ሁሉ ከነሐስ አብጃቸው። 4 ለመሠዊያው ከነሐስ እንደ መረብ የተሠራ ፍርግርግ አብጅለት። በፍርግርጉ አራት ማእዘኖች በያንዳንዳቸው ላይም የነሐስ ቀለበት አድርግ። 5 አጋማሽ ወገብ እስከ ታች እንዲደርስ ፍርግርጉን ከመሠዊያው እርከን ሥር አድርገው። 6 ለመሠዊያው መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት አበጅተህ በነሐስ ለብጣቸው። 7 በቀለበቶቹ ውስጥ መግባትና መሠዊያውን ለመሸከም በሁለቱ ጎኖቹ ላይ መቀመጥ አለባቸው። 8 ባዶ እንዲሆን ከሳንቃዎች አብጀው። በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ልትሠራው ይገባል። 9 ድንኳን አደባባይ ሥራለት። በአደባባዩ ደቡብ ጎንም አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው የአማረ በፍታ መጋረጃዎች ይደረጉ። 10 መጋረጃዎቹ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች ጋር ሃያ ምሰሶዎች ይኑሯቸው። ከምስሶዎቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎችም መኖር አለባቸው። 11 በሰሜን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎች፣ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎችም ጋር ከምሰሶውቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎች ሊኖሩ ይገባል። 12 በአደባባዩ ምዕራብ ጎንም ዐምሳ ክንድ ርዝመት ያለው መጋረጃ ይደረግ። ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎችም ይኑሩት። 13 በምሥራቅም በኩል አደባባዩ ዐምሳ ክንድ እርዝመት ይኑረው። 14 የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ሊኖራቸው ይገባል። ሦስት ምሰዎችም ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ይኖሯቸዋል። 15 ሌላው ጎንም ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖሩታል። የራሳቸው ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ይኖሯቸዋል። 16 መግቢያ መጋረጃ ሃያ ክንድ እርዝመት ያለው፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ጠላፊ ጠልፎበት የተሠራ ይሁን። አራት ምሰሶዎች ከአራት መቆሚያዎች ጋር ሊኖሩት ይገባል። 17 የአደባዩ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎችና ኵላቦች፣ የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሯቸው። 18 የአደባባዩ እርዝመት አንድ መቶ ክንድ፣ ወርዱ ዐምሳ ክንድ፣ ቁመቱ ዐምስት ክንድ ይሁን፤ የበፍታ መጋረጃዎችና የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሩት። 19 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ ዕቃ ሁሉ፣ የድንኳኑ ካስማዎችም በሙሉ፣ አደባባዩም ከነሐስ መሠራት አለባቸው። 20 ሁልጊዜ እንዲበሩ ለመብራቶቹ የወይራ ጭማቂ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡ እስራኤላውያንን እዘዛቸው። 21 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣ ከመጋረጃው ውጭ በምስክሩ ታቦት ፊት፣ አሮንና ልጆቹ መብራቶቹን ከማታ እስከ ንጋት ድረስ በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ። ይህም ለእስራኤል ትውልድ ሁሉ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
ዝርመቱ 2.3 ሜትር፥ የጉኑ ስፋት 2.3 ሜትር ያህል ነው
አንድ ክንድ ወደ 46 ሴንት ሜትር ያህል ነው
በመሰዊያው አራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ቀንድ መሳይ ጒጦች /ነገር/ አውጣ
ቀንዶቹም ከመሠዊያው ጋር አብሮ የተሠሩ ይሁን
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
ለዐመድ ማጠራቀሚያነት የሚያገለግሉ ድስቶች /ድስት መሳይ ነገሮች/
የእሳት መጫሪያዎች ወይም የእሳት መለኮሻዎች
በመሰዊያው ላይ ለመጠቀም የሚያገለግሉ ማንኛውንም ቁሳቁስ
እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የነሐስ መከላከያ አብጅለት/ሥራለት/
እንጨት በእሳት ሲቃጠል ለመያዝ የሚያገለግል ከነሐስ ብረት የተሰራ መያዣ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
መከላከያው እስከ መሠዊያው እኩሌታ/ግማሽ/ ድረስ እንዲዘልቅ ከመሠዊያው ክፈፍ/ጫፍ በታች አድርገው/አስቀምጠው
እንጨት በእሳት ሲቃጠል ለመያዝ የሚያገለግል ከነሐስ ብረት የተሰራ መያዣ (ዘጸአት 27፡4 ተመልከት)
መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉ አግዳሚ እንጨቶች/ብረቶች/
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
በሌላ አገላለጽ፦ መሠዊያውን ለመሸከም አግዳሚ እንጨቶችን/ብረቶችን/ ከመሠዊያው በእያንዳንዱ ጐን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አግባ።
ሳንቃ ከእንጨት ወይም ከብረት የተሰራ ጠፍጣፋ ነገር ነው። አማራጭ ትርጉም፦ መሠዊያው ውስጡ ባዶ ሆኖ ከሳንቃዎች መስራት አለብህ
ይህ ሀረግ ወይም ዓረፍተ ነገር በቀድሞ አማርኛ ትርጉም (በ1954/62) ላይ የተዘለለ/የተተወ ሀሳብ ነው። በዕብራይስጡና በሌሎች አማርኛና እንግሊዘኛ ትርጉሞች ይገኛል።
ለድንኳኑ አደባባይ ክልል የሚሆን ከቀጭን የሐር ክር (የጨርቅ ዓይነት) መጋረጃዎችን ሥራ
ቀጭን የሐር ክር ወይም ጨርቅ
ይህ ወደ 46 ሜትር የምያህል ርዝመት ያለው ነው።
በምሶሶዎች ላይ ከብር ዘንጎችንና/ቋሚዎችንና/ መስቀያዎችን አድርግላቸው/ሥራላቸው/
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
ቁጥር 10 ለመተርጎም ቁጥር 9-10 ያለውን እንዴት እንደተረጎምክ ማየቱ የተሻለ ነው። ምክንያቱም ብዙ ተመሳሳይ ነገሮች ተጠቅሰዋል።
ከብር የተሰሩ መስቀያዎችና ቋሚዎች አድርግ ወይም ከብር መስቀያዎችንና ቋሚዎችን ሥራ
ሃያ ሶስት (23) ሜትር የሆነ መጋረጃዎችን ሥራ
አስር ምሶሶዎችን ሥራ
የአደባባዩ ስፋት 23 ሜትር አድርግ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
አማራጭ ትርጉሞች፦ 1) በሰማያዊ፥ ሀምራዊና ቀይ ቀለም የተቀቡ ልብሶች/የሱፍ ጨርቆች/ ወይም 2) ላይነኖችን ለመቀባት የሚረዱ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ሰማያዊ ቀለም
ለአደባባዩ በር ወይም መግቢያ 9 ሜትር የሆነ መጋረጃ ሥራ
ከጥሩ የሐር ክር የተሠራና የተፈተለ በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ
በጥልፍ ያጌጠና ያማረ መጋረጃ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
የድንኳኑ አደባባይ ርዝመቱ አርባ ስድስት ሜትር የጐኑ ስፋት ሃያ ሶስት ሜትር ሆኖ ይሰራ
መጋረጃው ከጥሩ /ከቀጭን/ የሐር ጨርቅ/ክር/ የተሰራ ይሁን ወይም መጋረጃውን ከጥሩ/ከቀጭን/ የሐር ጨርቅ/ክር/ ሥራ
በድንኳኑ ውስጥ የሚገኙት ለማናቸውም አገልግሎት የሚውሉ የመገልገያ ዕቃዎችን ሁሉ፥ የድንኳኑንና የአደባባዩ ካስማዎችን ሁሉ ከነሐስ ብረት ሥራቸው።
ከብረት ወይም ከእንጨት የተሰሩ በአንድ በኩል ሹል የሆኑ ድንኳን ለመወጠር የሚያገለግሉ ናቸው
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በሌላ ስሙ የማደሪያ ድንኳን ተብሎ ይታወቃል
የቃል ኪዳን ታቦት ሲሆን በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፉት ቃላት እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ምስክር እንዲሆን ነው።
ይህ በእስራኤል ሕዝብና ወደፊት በሚነሣው ወይም በሚመጣው ትውልድ ዘንድ ቋሚ/የፀና/ ሥርዓት ሆኖ ይኑር/ይቀጥል/
1 ሆነው እንዲያገለግሉኝ ወንድምህን ዘሮንንና ልጆቹን ናዳብን፣ አብድዩን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ከእስራኤል መካከል ወደ አንተ ጥራ። 2 ለወንድምህ ለአሮን ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን አዘጋጅ። እነዚህ ልብሶች ለአሮን ክብርና ማዕርግ የሚሆኑ ናቸው። 3 ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግለኝ የአሮንን ልብሶች የሚሠሩለትን፣ በልባቸው ጥበበኛ የሆኑትን፣ የጥበብን መንፈስም የሞላሁባቸውን ሰዎች ሁሉ አነጋግር። 4 የሚሠሯቸው ልብሶችም የደረት ኪስ፣ ኤፉድ፣ ቀሚስ፣ ጥልፍ የተጠለፈበት ሸሚዝ፣ መጠምጠሚያና መታጠቂያ ናቸው። ለእኔ የተቀደሱትን እነዚህን ልብሶች መሥራት አለባቸው። ልብሶቹ ካህናት ሆነው እንዲያግለግሉኝ ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናሉ። 5 ወርቅ፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የአማረ በፍታ ይጠቀሙ። 6 ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግን ኣአምሮ ከተፈተለ በፍታ ይሥሩት። ሥራው የብልኀተኛ ሙያተኝ ሥራ ሊሆን ይገባል። 7 ኤፉዱ ከሁለቱ ጠርዞቹ ጋር የሚያያዙ ሁለት የትከሻ ንጣዮች ይኑሩት። 8 በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉድ መሆን አለበት፦ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን። 9 ሁለት የመረግድ ድንጋዮችን ወስደህ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅረጽባቸው። 10 ስድስቱ ስሞቻቸው በአንድ ድንጋይ፣ ስድስቱ ሌሎች ደግሞ በሌላው ድንጋይ ላይ እንደየልጁ ልደት ቀደም ተከተል ይቀረጹ። 11 ሠራተኛ ማኅተም እንደሚቀርጽ የእስራኤልን ዐሥራ ሁለት ልጆች ስሞች በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ቅረጽ። ድንጋዮቹንም በወርቅ ክፈፋቸው። 12 ሁለቱን ድንጋዮች የእስራኤልን ልጆች አምላክ የሚያስታውሱ ድንጋዮች እንዲሆኑ በኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ አስቀምጥ። መታሰቢያ እንዲሆኑ አሮን ስሞቻቸውን በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ይሸከማል። 13 ፈርጦችንና 14 እንደ ገመድ የተጎነጎኑ የንጹሕ ወርቅ ድሪዎችን አበጅተህ ከፈርጦቹ ጋር አያይዛቸው። 15 ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ ኤፉዱ በተሠራበት መንገድ ፍርድ የሚሰጥበትን የደረት ኪስ አብጅ። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሥራው። 16 አራት ማእዘን ያለ ውይሁን። የደረት ኪሱን ዐጥፈህ ድርብ አድርገው። አንድ ስንዝር እርዝመት፣ አንድ ስንዝር ስፋትም ይኑረው። 17 ዕንቆችን በአራት ረድፍ አስቀምጥ። የመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶነዝዮንና አብረቅራቂ ዕንቊ ሊኖሩት ይገባል። 18 ሁለተኛው ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና አልማዝ ይኑሩት። 19 ሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶንና አማቴስጢኖስ ይገኙበታል። 20 አራተኛው ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ይኑሩት። በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ ሊደረግላቸው ይገባል። 21 ድንጋዮቹ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት መቀመጥ፣ ከእስራኤል ነገዶች አንዱን በመወከልም በቀለበት ማተሚያ እንደሚቀረጽ እያንዳንዱ ስም የተቀረጸባቸው መሆን አለባቸው። 22 ኪሱ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አብጅለት። 23 ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከደረት ኪሱ ሁለት ጎኖች ጋር አያይዛቸው። 24 የወርቅ ድሪዎች ከደረት ኪሱ ሁለት ማእዘኖች ጋር አያይዛቸው። 25 ጕንጕን ድሪዎች ሌሎች ጎኖች ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋር አገናኛቸው። ከኤፉፉ የትከሻ ንጣዮች ጋርም በፊቱ በኩል አያይዛቸው። 26 የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከውስጠኛው የኤፉዱ ጎን ቀጥሎ ባለው ጠርዝ ላይ፣ በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጎኖች ላይ አድርጋቸው። 27 ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን አብጅና በብልኀት ከተጠለፈው ከሴፉዱ መታጠቂያ በላይ፣ መጋጠሚያው አጠገብ ከኤፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያይዛቸው። 28 ከኤፉዱ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችሉ፣ የደረት ኪሱን ቀለበቶቹ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ ማሰር አለባቸው። ይህም የሚሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋር ሳይያያዝ እንዳይቀር ነው። 29 አሮን ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ፣ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች በደረት ኪሱ ላይ ለፍርድ በልቡ ላይ ይሸከም። ይህም በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም መታሰቢያ ሆኖ ያገለግላል። 30 በፍርድ መስጫው የደረት ኪስ ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አስቀምጥ። አሮን ወደ እግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ፣ ኡሪምና ቱሚም በደረቱ ላይ መኖር አለባቸው፤ አሮንም ለእስራኤል ፍርድ መስጫውን በእግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ ሁልጊዜ መሸከም ይኖርበታል። 31 ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ሰማያዊ ይሁን። 32 ለራስ ማስገቢያ ክፍተት ይኑረው፤ ክፍተቱም እንዳይቀደድ ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ይኑረው። ይህ ሥራ የሸማኔ ሥራ መሆን አለበት። 33 የግርጌ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ፣ የሐምራዊና የቀይ ማግ ሮማኖችን በዙሪያው አድርግ። በመካከላቸውም ዙሪያውን የወርቅ ሻኵራዎችን አብጅ። 34 የወርቅ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ እየተፈራረቁ መቀመጥ አለባቸው። 35 ወደ መቅደሱ ሲገባና በእግዚአብሔር ፊት ሲሆን፣ ከመቅደስ ሲወጣም፣ ድምፁ እንዲሰማ ቀሚሱን አሮን ሲያገለግል ይልበሰው። ይህም የሚደረገው አሮን እንዳይሞት ነው። 36 ከንጹሕ ወርቅ ሳሕን አብጅና በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ፣ “ቅዱስ ለእግዚአብሔር” ብለህ በላዩ ቅርጽበት። 37 ሳሕን ከመጠምጠሚያው ፊት ጋር በሰማያዊ ገመድ አያይዘው። 38 ሁልጊዜም በአሮን ግንባር ላይ ይሁን፤ አሮን እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ለይተው ከሚያቀርቧቸው የተቀደሱ ስጦታዎች ጋር የሚያያዝ ማንኛውንም በደል ይሸከማል። እግዚአብሔር ስጦታዎቻቸውን እንዲቀበል፣ መጠምጠሚያ ሁልጊዜ በአሮን ግንባር ላይ መሆን አለበት። 39 ሸሚዙንም፣ መጠምጠሚያውንም ከአማረ በፍታ ትሠራለህ። መታጠቂያውም በጥልፍ ጠላፊ እንዲሠራ ታደርጋለህ። 40 ለአሮን ልጆችም ሸሚዞቹን፣ መታጠቂያዎችንና የራስ ማሰሪያዎችን ለክብራቸውና ለማዕረጋቸው ታደርጋለህ። 41 ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው። ቅባቸው፣ ሹማቸውም፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም ለእኔ ቀድሳቸው። 42 እስከ ጭን የውስጥ ሰውነታቸውን የሚሸፍን የውስጥ ልብሶችን ከበፍታ ሥራ። 43 ልጆቹ ውደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ፣ ወይም መቅደሱ ውስጥ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ እነዚህን የውስጥ ልብሶች መልበስ አልባቸው። በደል እንዳይገኝባቸውና እንዳይሞቱ ይህን ማድረግ ይገባቸዋል። ይህ ለአሮንና ከእርሱም በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
“ወደ አንተ” የተባለው ሙሴ ነው። በሌላ አገላለጽ፦ ወደ አንተ ጥራቸው
የወንዶች ስም ዝርዝር ነው (ስሞችን የመተርጎም ዘዴ ተመልከት)
ይህ በወል ስም የተጠቀሰው “የእስራኤላውያንን” የሚመለከት ነው
ለእኔ የተለየ እንዲሆን
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ባጌጠ ጥልፍ የተሰራና በእፉዱ ላይ በውጭ በኩል የሚለበስ ልብስ ወይም ኮት። ነገር ግን እንደ ዛሬው የሸሚዝ ዓይነት ከጃኬት ወይም ከኮት ሥር የሚለበስ አይደለም
ረዘም ያለ ከልብስ/ከጨርቅ/ የተሰራ በራስ ላይ የሚጠመጠም ነው
ከልብስ/ከጨርቅ/ የተሰራ በወገብ ላይ ወይም በደረት ላይ የሚለበስ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በቀጭኑ ከተፈተለ ከተጠመዘዘ ሐር ጨርቅ/ክር/ ወይም ከላይነን ጨርቅ ሥሩ
የጥልፍ ዐዋቂዎች በጥልፍ አስጊጠው ይሥሩ
መተሳሰር ወይም መያያዝ እንዲችል ሆኖ
ይህ የተመረጠ ወይም የከበረ ድንጋይ የሚባለው ድንጋይ ዘር ሲሆን የተለያየ ቀለም ያለው የድንጋይ ዓይነት ለምሳሌ ነጭ፥ ጥቁር፥ ቀይ ወይም ሰማያዊ ቀለም አለው።
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
የቅርጽ ሠራተኛ ማኅተም እንደሚቀርጽ አደርገህ
የቅርጽ ሠራተኛ በጠንካራ ነገር ላይ ለምሳሌ በድንጋይ፥ በብረት ወይም በእንጨት ላይ በመቅረጽ የሚሰራ ማለት ነው።
በኤፉዱ ትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ጋር አያይዛቸው
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በኤፉዱ ትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ጋር አያይዛቸው (28፡11 ተመልከት)
ሁለት የወርቅ ፈርጦች ሥራ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
የፍርድ መስጫውን ወይም የእግዚአብሔር ፈቃድ መጠየቂያውን የደረት ኪስ ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው አድርገህ ሥርው
አንድ ስንዝር ወደ ሃያ ሁለት ሴንት ሜትር ያህል ነው።
ዕይታ፦ በዚህ ሥፍራ አስራ ሁለት የድንጋይ ዓይነቶች ተዘርዝረዋል። በዕብራይስጥ የትኛው ቃል የትኛውን የድንጋይ ዓይነት እንደሚገልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን እርግጠኛ አይደሉም። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጅዎች የተለያየ የድንጋይ ዓይነት ዝርዝር ያቀርባሉ።
በአማርኛ ቅጅዎች የከበሩ ድንጋዮች ወይም ዕንቁዎች ተብለው ይታወቃሉ።
ይህ የተመረጠ ወይም የከበረ ድንጋይ የሚባለው ድንጋይ ዘር ሲሆን የተለያየ ቀለም ያለው የድንጋይ ዓይነት ለምሳሌ ነጭ፥ ጥቁር፥ ቀይ ወይም ሰማያዊ ቀለም አለው።
እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች ወይም ዕንቁዎች ናቸው
የከበረ ድንጋይ ወይም ዕንቁ ሲሆን ቀለሙ ሰማያዊ ነው።
በወርቅ ፈርጥ ላይ ይቀመጣሉ
ምልከታ፦ እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ለእያንዳንዱ የእስራኤል ልጆች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ይሁኑ/ይሰሩ/
የዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስሞች እንደ ማኅተም የተቀረጸባቸው (ዘጸአት 28፡11 ተመልከት)
እንደ ገመድ የተጐነጐነ ወይም እንደ ገመድ ሆኖ የተጌጠ የወርቅ ድሪ ከንጹሕ ወርቅ ሥራ (ዘጸአት 28፡14 ተመልከት)
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
እንደ ገመድ የተገመዱ የወርቅ ፈርጦች
እነዚህ ሁለት የወርቅ ከበቶች ኤፉዱን በሁለት በኩል የሚያቅፉ ናቸው (ዘጸአት 28፡14)። አማራጭ ትርጉም፦ ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ በውስጥ በኩል ከኤፉዱ ቀጥሎ ባለው የደረት ኪስ ከታችኛዎቹ ማእዘኖች ጋር እንዲያያዙ አድርገህ ሥራ።
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በብልኀት ከተጠለፈው ወይም በጥልፍ ያጌጠው የኤፉድ መታጠቂያ
ከኤፉዱ ጋር እንዳይላቀቅ፣ ከኤፉድ መታጠቂያ ጋር በማገናኘት በሰማያዊ ገመድ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር መያያዝ አለበት
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለዘላለም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርድ መስጫው ደረት ኪስ በልቡ ላይ ይሸከም (ዘጸአት 28፡17-21 ተመልከት)
አሮን በልቡ ላይ ወይም በደረቱ ላይ ይሸከም
ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በሚገባበት ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆኑ ዘንድ ኡሪሙንና ቱሚሙን በደረት ኪሱ አድርግ
እነዚህ ነገሮች ምን እንደሆኑ አይታወቅም ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ የሚረዱ ድንጋዮች ሳይሆኑ አይቀሩም።
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በኤፉዱ መደረቢያ ቀሚስ ወይም ረጅም ልብስ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
የፍራፍሬ ዛፍ ሲሆን ክብ የሆነ የፍሬው ውጫዊ ክፍሉ ቀይ ነው።
ሮማን የሚመስለው የወርቅ መርገፍ ወይም ጸናጽል
አሮን በክህነት በሚያገለግልበት ጊዜ ይህን ቀሚስ መልበስ አለበት
በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወደ መቅደሱ ሲገባና ከመቅደሱ ሲወጣ የጸናጸሎች ድምፅ ይሰማል
ይህ የሚያሳየን አሮን በትክክል እግዚአብሔርን ካልታዘዘ እንደሚሞት ነው። በሌላ አገላለጽ፦ ምክንያቱም አሮን እንዳይሞት
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በማኅተም ላይ እንደሚቀረጽ ቅረጸው (ዘጸአት 28፡11 ተመልከት)
ረዘም ያለ ከልብስ/አጨርቅ/ የተሰራ በራስ ላይ የሚጠመጠም
አሮንም በግንባሩ ላይ ያድርገው ወይም ይልበሰው
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ረዘም ያለ ከልብስ/አጨርቅ/ የተሰራ በራስ ላይ የሚጠመጠም
ከልብስ/ከጨርቅ/ የተሰራ በወገብ ላይ ወይም በደረት ላይ የሚለበስ (ዘጸአት 28፡4)
በጥልፍ ጥበብ ወይም በጥልፍ ጠላፊ ያጌጠ ይሁን
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ከልብስ/ከጨርቅ/ የተሰራ በወገብ ላይ ወይም በደረት ላይ የሚለበስ (ዘጸአት 28፡4 ተመልከት)
ከጨርቅ የተሰሩ ጠበብ ያሉ የራስ ማሰሪያዎችን
በሌላ አገላለጽ፦ እነዚህን ልብሶች አሮንና ወንድ ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ከጥሩ በፍታ (ሐር ጨርቅ/ክር/ የተሰራ ከወገባቸው እስከ ጭናቸው የሚደርስ ቊምጣ ሱሪ ወይም የውስጥ ሱሪ ሥራላቸው
ማደሪያው ድንኳን ሌላ ስሙ ነው (27፡1 ተመልከት)
ይህ እንግዲህ ለአሮንና ለትውልዱ ሁሉ ጸንቶ የሚኖር (የማይለወጥ) ሥርዓት ይሆናል
1 ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነርሱን ለእኔ ለመቀደስ አሁን የምታደርገው ይህ ነው። ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች፣ 2 የሌለበትን እንጀራና ዘይት የተቀላቀለበትን እንጎቻ ውሰድ፤ ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣም አድርግ። 3 በአንድ ሌማት አድርጋቸውና ከወይፈኑና ከአውራ በጎቹ ጋር አቅርባቸው። 4 አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ አቅርባቸው። በውሀም እጠባቸው። 5 ውሰድና፦ ሸሚዙን፣ የኤፉዱን ቀሚስ፣ ኤፉዱን፣ የደረት ኪሱን፣ በብልኀት የተጠለፈውን የኤፉዱን መታጠቂያ በወገቡ ዙሪያ በማስታጠቅ አሮን አልብሰው። 6 ቅዱሱን አክሊል በላዩ አስቀምጠህ መጠምጠሚያውን በአሮን ራስ አድርግ። 7 ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ቅባው። 8 አምጥተህ ሸሚዞችን አልብሳቸው። 9 መታጠቂያዎችን ለአሮንና ለልጆቹ ታስታጥቃቸዋለህ፤ የራስ ማሰሪያዎችንም ታደርግላቸዋለህ። የክህነቱ ሥራ በዘለዓለማዊ ሕግ የእነርሱ ይሆናል። እኔን እንዲያገለግሉኝ አሮንና ልጆቹን ትክናቸዋለህ። 10 በመገናኛው ድንኳን ፊት አቅርብ፤ አሮንና ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ። 11 በእኔ በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ዕረደው። 12 ከወይፈኑ ደም ጥቂት በጣትህ ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ታደርጋለህ፤ 13 የሆድ እቃዎችን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ ጉበቱን የሚሸፍነውንና ሁለቱን ኩላሊቶች በላያቸው ካለው ስብ ጋር ወስደህ ሁሉንም በመሰዊያው ላይ ታቃጥላቸዋለህ። 14 ነገር ግን የወይፈኑን ሥጋ ግን ቁርበቱንና ፈርሱን ጭምር ከሰፈር ውጭ አውጥተህ ታቃጥላለህ። ያ የኀጢአት መሥዋዕት ይሆናል። 15 የአውራ በግም ውሰድና አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን ይጫኑበት። 16 በጉን ዕረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው። 17 በጉን ለሁለት ክፈልና የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን እጠብ፤ የሆድ ዕቃውንም ከተቆራተጡ ብልቶችና ከራሱ ጋር 18 ላይ አስቀምጥ። ከዚያም እውራ በጉን ሙሉ በሙሉ አቃጥለው። ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል። ይህም ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል። 19 ሌላውንም አውራ በግ ወስደህ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት። 20 በኋላ አውራ በጉን ዕረደው፤ ከደሙም ጥቂት ውሰድና በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍና በልጆቹ ቀኝ ጆሮዎች ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጆቻቸውና በቀኝ እግሮቻቸው አውራ ጣቶች ላይ አድርግ። ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው። 21 ካለው ደም፣ ከመቅቢያው ዘይትም ጥቂት ውሰድና በአሮንና በልብሶቹ፣ በልጆቹና በልብሶቻቸውም ላይ እርጨው። አሮንና ልብሶቹ፣ ልጆቹና ልብሶቻቸው ከእርሱ ጋር ይቀደሱልኛል። 22 በጉን ሥብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በላያቸው የሚገኘውን ሥብ፣ የቀኙን ወርችም ውሰድ፤ ይህ አውራ በግ ካህኑ ለእኔ የሚቀደስበት ነውና። 23 እንጀራ፣ አንድ በዘይት የተጋገረ እንጎቻና አንድ ስስ ቂጣ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ከሚሆነው ያለ እርሾ ከተጋገረው ኅብስት ሌማት ትወስዳለህ። 24 እነዚህን በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታስቀምጣለህ። እነርሱ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዟቸው፤ መሥዋዕት አድርገውም ለእኔ ያቅርቧቸው። 25 ከእጆቻቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ አቃጥለው። ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል። 26 የአሮንን የክህነት አውራ በግ ፍርምባ ወስደህ ወዝውዘውና መሥዋዕት አድርገህ ለእኔ ለእግዚአብሔር አቅርበው። ይህም አንተ የምትበላው የአንተ ድርሻ ይሆናል። 27 የመሥዋዕቱን ፍርምባና የቀረበውን የመሥዋዕቱን ወርች ለእኔ ቀድስልኝ፤ ሁለቱም አሮንና ልጆቹ ለእኔ ካህናት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከአውራ በጉ የሚገኙ ናቸው። 28 የሚሰጧቸው እነዚህ የሥጋ ክፍሎች ምንጊዜም የአሮንና የልጆቹ ናቸው። በኅብረቱ መሥዋዕቶች ሥርዐት፣ ከእስራኤላውያን ለካህናቱ፣ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ይሆናሉ። 29 የአሮን የተቀደሱ ልብሶች ከእርሱ በኋላ ለልጆቹም ይሆናሉ። በልብሶቹ የአሮን ልጆች ለእኔ መቀባትና መካን አለባቸው። 30 በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እኔን ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባ፣ አሮንን ከልጆቹ መካከል የሚተካ እነዚያን ልብሶች ሰባት ቀን ይልበስ። 31 የክህነቱን አውራ በግ ውሰድና ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ቀቅለው። 32 ልጆቹ የአውራ በጉን ሥጋና በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር ባለው ሌማት የተቀመጠውን ኅብስት ይብሉት። 33 ለማስተስረይና ለእኔ እንዲቀደሱ የቀረቡትን ሥጋውንና ኅብስቱን መብላት አለባቸው። ሌላ ሰው መብላት አይችልም፤ ምክንያቱም ምግቡን ለእኔ የተቀደሰ አድርገው ሊይዙት ይገባል። 34 መሥዋዕቱ ሥጋ፣ ወይም ከኅብስቱ እስከሚቀጥለው ጠዋት ድረስ አንዳች የሚተርፍ ከሆነ፣ አቃጥለው። ለእኔ የተቀደሰ ስለ ሆነ መበላት የለበትም። 35 በዚህ መንገድ እንድታደርገው ያዘዝሁህን ሁሉ በመከተል ለአሮንና ለልጆቹ ትፈጽምላቸዋለህ። እነርሱን ሰባት ፍቀን ቀድስልኝ። 36 ለስርየት የሚሆን የኀጢአት መሥዋዕት በየቀኑ አንድ ወይፈን አቅርብ። ማስተሰረያውን በማድረግም መሠዊያውን አንጻ፤ ለእኔ ለመቀደስም ቅባው። 37 ሰባት ቀን ማስተሰረያ አድርግለትና ለእግዚአብሔር ቀድሰው። ከዚያ በኋላ መሠዊያው ሙሉ በሙሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ መሠዊያውን የሚነካውም ሁሉ ይቀደሳል። 38 የአንድ ዓመት ጠቦቶችን ዘወትር በየቀኑ በመሠዊያው ላይ አቅርብ። 39 ጠቦት ማለዳ፣ ሌላውን ደግሞ ምሽት ላይ ታቀርበዋህ። 40 ከመጀመሪያው ጠቦታ ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛን ያማረ ዱቄት ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋር በመለወስ፣ ሩብ ወይንንም የመጠጥ ቍርባን በማድረግ አቅርብ። 41 ሁለተኛውን ጠቦት በምሽት ሠዋው። በማለዳ እንደ ተሠዋው ጠቦት ተመሳሳይ የእህልና የመጠት ቍርባን ማቅረብ አለብህ። እነዚህ መሥዋዕቶች ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያላቸው በእሳት የቀረቡልኝ መሥዋዕቶች ናቸው። 42 ትውልዶች ሁሉ ዘወትር የሚቀርቡ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ናቸው። ላናግራችሁ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በእኔ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕቶቹን አቅርቧቸው። 43 ከእስራኤላውያን ጋር የምገናኝበት ቦታ ያ ነው፤ ድንኳኑ በክብሬ ይቀደስልኛል። 44 የመገናኛውን ድንኳንና መሠዊያውን የእኔ ብቻ እንዲሆኑ እቀድሳቸዋለሁ። ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን እለያቸዋለሁ። 45 በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤ አምላካችውም እሆናለሁ። 46 በመካከላቸው እንድኖር፣ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካችው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
እግዚአብሔር የካህናት ልብስ ዝግጅትና አሰራር ላይ የሰጠውን መመሪያ ጨርሶ ወደ ካህናትን ወደ መቀደስ ሥርዓት ሲሻገር እናያለን።
ይህን የሚሰራው ሙሴ እንደ ሆነ ማመልከቱ ነው።
አሮንና ልጆቹ ካህናት ሆነው በፊቴ ወይም እኔን እንዲያገለግሉኝ የምትለያቸው
በአንደኛ መደብ የተገለጸው እግዚአብሔር /ያህዌ/ ነው። በሌላ አገላለጽ፦ “እኔን እንዲያገለግሉ”
ቀንበር ያልተቀመጠበት ወጣት በሬ ማለት ነው
እርሾ ያልነካው በወይራ ዘይት የታሸ ወይም ወይራ ዘይት የመጨመረበት ቂጣ
ምርጥ የሆነ የስንዴ ዱቄት ወስደህ ስስ/ቀጭን/ ቂጣ ጋግረህ ዘይት ቀባው
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
“ሌማት” የተባለው የዳቦ/የቂጣ/የእንጀራ/ ወይም ሌላ ምግብ ማስቀመጫ የሚያመለክት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ሁሉንም በመሶብ ወይም በቅርጫት መሳይ ነገር ታስቀምጣቸዋለህ/ ታኖራቸዋለህ/
በዚህ ክፍል “ታቀርባቸዋለህ” የሚለው መስዋዕት ማቅረብን የሚመለከት ነው። በሌላ አገላለጽ፦ አንድ ኰርማ/ወይፈን/ እና ሁለቱን አውራ በጎች በምትሠዋበት ጊዜ ለእኔ መባ/መስዋዕት/ አድርገህ አቅርብልኝ/ሰዋልኝ/
በሌላ ስሙ የማደሪያ ድንኳን ተብሎ ይታወቃል (ዘጸአት 27፡21 ተመልከት)
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
ባጌጠ ጥልፍ የተሰራና በእፉዱ ላይ በውጭ በኩል የሚለበስ ልብስ ወይም ኮት። ነገር ግን እንደ ዛሬው የሸሚዝ ዓይነት ከጃኬት ወይም ከኮት ሥር የሚለበስ አይደለም (ዘጸአት 28፡4 ተመልከት)
ይህ ከቀጭን የሐር ልብስ/ጨርቅ/ክር/ ተገምዶ የተሰራ የወገብ ወይም በደረት አከባቢ የሚያደርጉት መታጠቂያ ነው (ዘጸአት 28፡8 ተመልከት)
አንድ ሰው ወይም ካህኑ በራሱ ላይ ዙሪያውን የሚጠመጥመው ራስ መሸፈኛ ነው (ዘጸአት 28፡4 ተመልከት)
በዚህ ክፍል የተጠቀሰው “አክሊል” በጠፍጣፋ/ዝርግ/ ወርቅ ላይ “ቅድስና ለእግዚአብሔር” ወይም “ለእግዚአብሔር የተለየ” ተብሎ የተቀረጸውን የሚመለከት ነው። ይህ ጠፍጣፋ/ዝርግ/ ወርቅ ከራስ መጠምጠሚያው ላይ የተሰፋ ወይም የተያያዘ ነበር።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
የአሮን ልጆች ወደ አንተ ታመጣቸዋል/ታቀርባቸዋለህ/
ባጌጠ ጥልፍ የተሰራና በእፉዱ ላይ በውጭ በኩል የሚለበስ ልብስ ወይም ኮት። ነገር ግን እንደ ዛሬው የሸሚዝ ዓይነት ከጃኬት ወይም ከኮት ሥር የሚለበስ አይደለም። በሌላ አገላለጽ፦ ሸሚዝ/ኮት/ አልብሳቸው (ዘጸአት 28፡4)
ይህ ከቀጭን የሐር ልብስ/ጨርቅ/ክር/ ተገምዶ የተሰራ የወገብ ወይም በደረት አከባቢ የሚያደርጉት መታጠቂያ ነው (ዘጸአት 28፡4 ተመልከት)
በራስ/በጭንቅላት/ ላይ የሚደረግ/የሚለበስ/ ውበት ያለው ከልብስ/ከጨርቅ/ የተሰራ ጥብቅ ጥምጥም
የክህነት አገልግሎታቸው/ሥራቸው/ተግባራቸው/
ለዘለዓለም ቋሚ ሥርዓት ይሆናል (ዘጸአት 28፡43 ተመልከት)
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
በሌላ ስሙ የማደሪያ ድንኳን ተብሎ ይታወቃል (ዘጸአት 27፡21 ተመልከት)
ወይፈኑን/ወጣት በሬውን/ የሚያርደው ሙሴ እንጂ አሮን ወይም ካህናቱ አይደሉም። ወይፈኑ የሚታረደው በድንኳኑ በራፍ/ደጃፍ/ ላይ እንጂ ውስጥ አይደለም።
ከታረደው ወይፈን ደም ወስደህ
እግዚአብሔር(ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
በመሰዊያው አራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ቀንድ መሳይ ጒጦች ላይ (ዘጸአት 27፡2)
የቀረውን /የተረፈውን/ ደም በመሠዊያው ሥር አፍስሰው
የሆድ ዕቃውን /ውስጠኛውን ሆድ ዕቃ/ የሚሸፍነውን ሞራ/ስብ/
ነገር ግን የተረፈውን የኰርማውን ሥጋ፥ ቆዳውን፥ አንጀቱን ሁሉ ወስደህ ከሰፈር ውጪ አቃጥለው፤ ይህ የኃጢአት መሥዋዕት ነው
ይህ አውራ በግ የሚታረደው ካህናትን ለማንጻት ነው፤ በጉን የሚያርደው አሮን ወይም የእርሱ ልጆች ሳይሆኑ ሙሴ ነው።
የወይፈኑ መስዋዕት ከሰፈር ውጪ ወይም ከመገናኛው ድንኳን ደጅ ላይ ታርዷል ነገር ግን አውራ በጉ በሰፈር ውስጥ ወይም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይታረዳል።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
በዚህ ዐይነት እርሱ፥ ልጆቹ እና ልብሶቻቸው ጭምር ለእኔ የተለዩ ይሆናሉ
እነዚህ የበግ፥ የፍየል፥ የከብት፥ ወዘተ ውስጠኛው የሰውነት ክፍል አካላት ናቸው
በመሶብ/በቅርጫት/ ካለው ለእኔ ለእግዚአብሔር ከቀረበው ቂጣ ከየአንዳንዱ ዐይነት አንድ ሙልሙል/ክብ/ ዳቦ ውሰድ (ዘጸአት 29፡2)
አንተ በእግዚአብሔር ፊት ካስቀምጥከው
ዕይታ፦ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
“ሁሉንም” የተባለው ቀደም ባሉት ቁጥሮች የተዘረዘሩትን የመስዋዕት ዓይነቶችን ማለቱ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “ይህን ሁሉ ምግብ በአሮንና በልጆቹ እጅ ላይ አኑር/አስቀምጥ/
ይህም በእሳት የሚቃጠል መስዋዕት ሆኖ ለእግዚአብሔር ይቀርባል/ይሰዋል/
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
አሮንን ለክህነት አገልግሎት ለመሾም ከታረደው የበግ ጠቦት
አሮንና ልጆቹ ከሚካኑበት /ለእግዚአብሔር ከሚለዩበት/ የበግ ጠቦት
ለአሮንና ለልጆቹ ቋሚ ሥርዓት ይሁን
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
እነርሱም (ልጆቹ) ተቀብተው የክህነት ሹመት/ሥልጣን/ በሚቀበሉበት ጊዜ ይልበሱት
እነዚህ ልብሶች ተራ ልብሶች ወይም ደግሞ የአሮን የግሉ ልብሶች ሳይሆኑ የክህነት ልብሶች ናቸው። አማራጭ ትርጉም፦ አሮን በሚሞትበት ጊዜ የክህነት ልብሶቹ ለልጆቹ መተላለፍ አለባቸው፤
በሌላ ስሙ የማደሪያ ድንኳን ተብሎ ይታወቃል (ዘጸአት 27፡21 ተመልከት)
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
ለካህናት የአገልግሎት ሹመት/ሥልጣን/ በምትሰጥበት ጊዜ የታረደው የበግ ጠቦት
ይህ ቦታ ከቅድስተ ቅዱሳን ወጭ ያለው ቅዱስ ስፍራ የሚመለከት አይደለም። ነገር ግን በመገናኛው ደንኳን አደባባይ ላይ ያለውን ሥፍራ የሚመለከት ነው።
በሌላ ስሙ የማደሪያ ድንኳን ተብሎ ይታወቃል (ዘጸአት 27፡21 ተመልከት)
በሌላ አገላለጽ፦ ከካህናት ሌላ ማንም ሰው አይብላው
በሌላ አገላለጽ፦ ምክንያቱም የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ነው
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
አሮንና ልጆቹ ለክህነት አገልግሎት ስትሾም ወይም ሥልጣን ስትሰጥ ልክ እኔ ባዘዝኩህ ሥርዓት መሠረት ፈጽም
በዚህም ዐይነት መሠዊያው ፍጹም የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
በየዕለቱ አንድ ዓመት የሆናቸውን ሁለት ጠቦቶች መሥዋዕት አድርገህ በመሠዊያው ላይ አቅርብ፤
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
አንድ አራተኛ (¼) ማለት ነው
አንድ አስረኛ (1/10) ማለት ነው
አንድ ኢን ወደ 3.7 ሊትር ያህል ነው
አንድ ኢፍ ወደ 22 ሊትር ያህል የሚመዝን ነው
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
ይህ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መዓዛው ደስ የሚያሰኝ የምግብ መባ/መስዋዕት/ ነው፤
ይህ ዘወትር ለልጅ ልጃችሁ ወይም በየዓመቱ የሚፈጸም
በሌላ ስሙ የማደሪያ ድንኳን ተብሎ ይታወቃል
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
በሌላ አገላለጽ፦ ክብሬ ወይም ሕሊዎቴ ይህን ስፍራ የተቀደሰ ወይም የተለየ ያደርገዋል
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
1 ዕጣን የሚጤስበት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ። 2 እርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ይሁን። አራት ማእዘንና ሁለት ክንድ ከፍታ ይኑረው። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር ወጥ ይሁኑ። 3 የዕጣን መሠዊያውን ላይኛ ክፍል፣ ጎኖቹንና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለብጣቸው። የመሠዊያውን ዙሪያ በወርቅ ክፈፈው። 4 ከክፈፉ በታች በሁለቱ ትይዩ ጎኖቹ ላይ እንዲያያዙ ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አብጅ። ቀለበቶቹ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎችን ደግፈው የሚይዙ ናቸው። 5 ከግራር ዕንጨት ሥራና በወርቅ ለብጣቸው። 6 የዕጣን መሠዊያውን ከመጋረጃው ፊት በምስክሩ ታቦታ አጠገብ አስቀምጠው። ይህም እኔ ከአንተ ጋር በምገናኝበት፣ በምስክሩ ታቦታ ላይ ካለው ከስርየት መክደኛው ፊት ይሆናል። 7 ደስ የሚያሰኝ መዐዛ ያለውን ዕጣን ሁልጊዜ ጧት ቷት ያጢስ። ማጤስ ያለበትም መብራቶቹን በሚያዘጋጅበት ጊዜ ነው። 8 መብራቶቹን በምሽት ሲያበራም፣ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ማጤስ አለበት። ይህ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር በትውልዶች ሁሉ የሚጤስ ዕጣን ይሆናል። 9 ነገር ግን ሌላ ዕጣን፣ አንዳችም የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የእህል ቍርባን በዕጣን መሠዊያው ላይ አታቅርብ፤ ምንም ዐይነት የመጠጥ ቍርባንም አታፍስስበት። 10 መሠዊያው ቀንዶች ላይ አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ማስተስረያ ያድርግ ይህንም የሚያደርገው የኀጢአት ስርየት ደሙን በመጠቀም ነው። ሊቀ ካህናቱ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህን ያድርገው። ይህ መሥዋዕት ሙሉ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።” 11 ሙሴን እንዲህ አለው፤ 12 ስትቆጥራቸው፣ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ሕይወት ቤዛ ለእግዚአብሔር መክፈል አለበት። ስትቆጥራቸውና ከቆጠርሃቸውም በኋላ በመካከላቸው መቅሠፍት እንዳይኖር ይህን አድርግ። 13 የተመዘገበ እያንዳንዱ ሰው በመቅደሱ ሰቅል ክብደት መሠረት የብር ግማሽ ሰቅል ይክፈል። ይህ ግማሽ ሰቅልም ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ይሆናል። 14 ከሃያ እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው የተቆጠረ ሁሉ ይህን መሥዋዕት ለእኔ ማቅረብ አለበት። 15 ለሕይወታቸው ማስተስረያ ለማድረግ ይህን መሥዋዕት ለእኔ ሲያቀርቡ፣ ባለጠጋው ከግማሽ ሰቅል የበለጠ፣ ድኻውም ከዚያ ያነሰ መስጠት የለባቸውም። 16 የማስተስረያ ገንዘብ ከእስራኤላውያን ተቀበልና ለመገናኛ ድንኳኑ ሥራ አውለው። ለሕይወታችሁ ማስተስረያ ማድረግ በፊቴ ለእስራኤላውያን መታሰቢያ ይሁን።” 17 ሙሴን እንዲህ አለው፤ 18 ትልቅ የናስ ሳሕን ከናስ መቆሚያ ጋር አብጅ። በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠውና ውሀ አድርግበት። 19 ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ውስጡ ባለው ውሀ ይታጠቡ። 20 መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ እኔን ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ እንዳይሞቱ በውሀ መታጠብ አለባቸው። 21 እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ሊታጠቡ ይገባል። ይህ ለአሮንና ለዘሮቹ በትውልዶቻቸው ሁሉ የሁልጊዜ ሕግ ይሁን።” 22 ሙሴን እንዲህ አለው፤ 23 ምርጥ ቅመሞች፦ ዐምስት መቶ ሰቅል ፈሳሽ ከርቤ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጣፋጭ ሽታ ያለው ቀረፋ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጠጅ ሣር፣ 24 ዐምስት መቶ ሰቅል ብርጕድ በመቅደሱ ሰቅል ክብደት ተለክቶ፣ አንድ የኢን መስፈሪያ ወይራ ዘይትም ውሰድ። 25 ቅመሞች በሽቶ ቀማሚ ሥራ የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት አዘጋጅ። ይህ ለእኔ የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት ይሆናል። 26 ዘይት የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦትም፣ 27 ጠረጴዛውንና ዕቃውንም ሁሉ፣ መቅረዙንና ዕቃውን፣ የዕጣን መሠዊያውንም፣ 28 የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረቢያ መሠዊያውን ከዕቃው ሁሉ ጋር፣ መታጠቢያ ሳሕኑንም ከመቆፕሚያው ጋር ቅባ። 29 ለእኔ የተቀደሱ እንዲሆኑ እነርሱን ለይልኝ። እነርሱን የሚነካ ማንኛውም ነገርም የተቀደሰ ይሆናል። 30 ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፣ ለእኔም ለያቸው። 31 እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት መሆን አለበት። 32 የሰው ቆዳ ሊቀባበት አይገባም፤ እንደዚህ ያለ አንዳችም ዘይት በአንድ ዐይነት ቀመር መሥራት የለባችሁም ምክንያቱም ይህ ዘይት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዘይት ነው። እናንተም ቅዱስ መሆኑን ዐስቡ። 33 እንደዚህ የሚሠራ ሁሉ፣ ወይም ከዚህ ዘይት ጥቂት በሰው ላይ የሚያፈስስ ሁሉ፣ ከወገኑ ይወገድ።’” 34 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “የጣፋጭ ሽቶ ቅመሞችን፦ የሚንጠባጠብ ሙጫ፣ በዛጎል ውስጥ ያለ ሽቶ፣ የሚሸት ሙጫ ከንጹሕ ዕጣን ጋር፣ እያንዳንዱን በእኩል መጠን ውሰድ፥ 35 በሽቶ ቀማሚ እንደ ተሠራ፣ በጨው የተቀመመ፣ ንጹሕና ለእኔ የተቀደሰ ዕጣን አድርገው። 36 አድቅቀህ ትወቅጠዋለህ። ከፊሉን ከአንተ ጋር በምገናኝበት፣ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ባለው በምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት አስቀምጥ። ለእኔ የተቄደሰ መሆኑንም ዐስብ። 37 እንደምትዘጋጀው ዕጣን በአንድ ዐይነት ቀመር ለራስህ ምንም አታድርግ። ለአንተ እጅግ ቅዱስ ይሁን። 38 እንደ ሽቶ ለመጠቀም እንደዚህ አድርጎ የሚሠራ ሁሉ ከገዛ ወገኑ ይወገድ።”
የአምልኮ ዕቃዎችን እንዴት መሥራት እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይነግረዋል።
በመሰዊያው አራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ቀንድ መሳይ ጒጦች ከመሰዊያው ጋር አንድ ወጥ ሆነው ይሰሩ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች እንዲገቡበት ከክፈፉ ሥር አያይዛቸው
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
የቃል ኪዳን ታቦት ሲሆን በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፉት ቃላት እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ምስክር እንዲሆን ነው (ዘጸአት 26፡33 ተመልከት)።
በምስክሩ ታቦት ላይ የሚቀመጥና የስርየት መስዋዕቱን የሚሸፍን መክደኛ ነው
እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ ወይም እኔም ከአንተ ጋር እዚያ እገናኛለሁ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
በእግዚአብሔር ፊት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ወይም በህሊዎተ እግዚአብሔር ፊት በሚመጡት ዘመናት
ይህ ትዕዛዝ በሙሴ በኩል ለአሮን የተሰጠ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ አሮን በየምሽቱ መብራቶቹን ሲያበራ እንዲሁ ያድርገዋል።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ቀጥሏል።
በመሰዊያው አራቱም ማእዘን ጫፍ ላይ ቀንድ መሳይ ጒጦች ላይ
በሚመጡት ዘመናት ወይም ጊዜያት ሁሉ
አንተ የእስራኤልን ሕዝብ በምትቈጥርበት ጊዜና በቆጠራው ወቅት
እያንዳንዱ ሰው በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ ስድስት ግራም ብር ይክፈል፤ ግማሽ ሰቅል (½) ከ5.5 – 6 ግራም ይመዝናል።
በጊዜው ወይም በዚያን ጊዜ ሁለት ዓይነት ሚዛን እንዳለ ይታወቃል፤ አንደኛ መደበኛ የሆነ መገበያያ ሰቅል ሲሆን ሌላኛው በቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሰጥ ሰቅል ነው።
አንድ ሰቅል ሃያ ኦቦሊ ያህል ሲሆን በዘመናዊ ሚዛን ወደ 0.6 ግራም የሚመዝን ነው፤ ኦቦሊ ከሁሉም ትንሹ የክብደት መለኪያ ነው።
ሃያ ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል።
ከወንድ እስራኤላውያን ብቻ
ተርጓሚዎች የክብደት፥ የርዝመት፥ የፈሳሽና ሌሎችን መለኪያችን ስተረጉሙ ህብረተሰቡ በሚረዳው መለኪያ ብጠቀሙ መልካም ነው። ግማሽ ሰቅል ወደ 6 ግራም የሚመዝን ነው።
ይህ አባባል የተለያየ ትርጉም ሊኖረው ይችላል፦ 1) እስራኤላውያን ለነፍሳቸው ወይም ለሕይወታቸው ቤዛ እንዲያቀርቡ ይህ ያሳስባቸዋል 2) እስራኤላውያን ለነፍሳቸው ወይም ለሕይወታቸው ቤዛ እንዳቀረቡ ያስገነዝባቸዋል። አማራጭ ትርጉም፦ ይህም መባ ለሕይወታቸው ቤዛ ስለሚሆን እኔ እነርሱን እያስታወስኩ እጠብቃቸዋለሁ”
የመታጠቢያ ገንዳ ወይም ገበቴ። ይህ የመታጠቢያ ገንዳ ካህናት የሚታጠቡበትን ውሃ የሚያኖሩበት ነው
የመታጠቢያ ገንዳው መቀመጫ ወይም ማስቀመጫ
የእንስሳት መስዋዕት ማቅረቢያ ቦታ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በዚህ ውሃ አሮንና ልጆቹ እጃቸውንና እግራቸውን ለመታጠብ ይገለገሉበታል
ይህም ለእነርሱና ከእነርሱ በኋላ ለሚመጡ ዘሮቻቸው/ትውልዶቻቸው/ የዘለዓለም ሥርዓት ሆኖ ይኖራል
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ጥሩ ሽታና ጣዕም እንዲኖረው ከደረቀ ዕጽዋትና ዘር ተፈጭቶ የተሰራና ዘይት ወይም ምግብ የገባበት ዱቀት ነክ ነገር ነው (ዘጸአት 25፡6 ተመልከት)
አንድ ሰቅል 11 ግራም ሲሆን ተርጓሚዎች ማህበረሰቡ በየዕለቱ አገልግሎቱ የምጠቀምበትን መለኪያ መጠቀም የተሻለ ነው። 500 ሰቅል ----- 5.5 ኪሎ ግራም፤ 250 ሰቅል ---- 2.75 ኪሎ ግራም፤ 250 ሰቅል ---- 2.75 ኪሎ ግራም ሲሆን በጠቅላላው 11 ኪሎ ግራም ያህል ነው።
ጣፋጭ ሽታ ያለው ቀረፋ (የቅመም ዓይነት)
በጊዜው ወይም በዚያን ጊዜ ሁለት ዓይነት ሚዛን እንዳለ ይታወቃል፤ አንደኛው መደበኛ የሆነ መገበያያ ሰቅል ሲሆን ሌላኛው ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሰጥ ሰቅል ነው።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ቀጥሏል
የቃል ኪዳን ታቦት ሲሆን በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፉት ቃላት እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ምስክር እንዲሆን ነው።
ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚያገለግለውን መሠዊያ ወይም የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበት መሰዊያ
እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ መናገሩን ቀጥሏል
ሁሉንም ለእግዚአብሔር የተለየ አድርገህ ታስቀምጣቸዋለህ
ይህ የተቀደሰ ወይም ለእግዚአብሔር የተለየው የቅባት ዘይት ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ለእኔ አገልግሎት ይሁን፤
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
ለእግዚአብሔር የተለየው ዘይት በማንኛውም ተራ ሰው ላይ አይፍሰስ ወይም የማንኛውንም ተራ ሰው ቆዳ/ሥጋ/ አይንካ፤
ይህን የመሰለ ቅባት የሚሠራ ወይም ከዚህ ቅባት ወስዶ ካህን ያልሆነውን ሰው የሚቀባ
ይህ ሀረግ ወደ ሶስት የተለያዩ ፍቺዎች አሉት፤ 1) እኔ ይህን ሰው ከእስራኤላውያን እንደ አንዱ አድርጌ እቀበላቸዋለሁ 2) እስራኤላውያን ይህ ሰው ከመካከላቸው ያውጡ/ይለዩ/ 3) እስራኤላውያን ይህን ሰው መግደል አለበት
ጣፋጭ ቅመሞች፥ የሚንጠባጠብ ፈሳሽነት ያለው ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ
ይህ አባባል ሁለት ፍቺዎች አሉት፦ 1) ሙሴ ጣፋጭ ሽቶ ለመስራት ሌላ ሰው እንደቀጠረ 2) ጣፋጭ ሽቶ እንደሚሰራ ሰው ሙሴ ራሱ ሽቶዎችን እንደሰራ፤ አማራጭ ትርጉም፦ “የሚሸት ሙጫና ጣፋጭ ሽታ ያለው ዕጣን ወስደህ”
ከእርሱም ጥቂቱን ወስደህ በመውቀጥ
እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ በኩል መናገሩን ቀጥሏል
በዚህ ዐይነት የምታደባልቁትን ዕጣን ለራሳችሁ መጠቀሚያ አታድርጉት
በዚህ ዐይነት የምታደባልቁትን ዕጣን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ወይም የተለየ አድርገህ አቅርብ
ይህ ሀረግ ወደ ሶስት የተለያዩ ፍቺዎች አሉት፤ 1) እኔ ይህን ሰው ከእስራኤላውያን እንደ አንዱ አድርጌ እቀበላቸዋለሁ 2) እስራኤላውያን ይህ ሰው ከመካከላቸው ያውጡ/ይለዩ/ 3) እስራኤላውያን ይህንን ሰው መግደል አለበት
1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስሙ ጠርቼዋለሁ። 3 ለሁሉም ዐይነት የእጅ ሞያ ጥበብን፣ ማስተዋልንንና ዕውቀትን እንዲሰጠው፣ ባስልኤልን በመንፈስ ሞልቼዋለሁ፤ 4 ይኸውም ጥበባዊ ሥራዎችን በወርቅ፣ በብርና በነሐስ እንዲሠራ፣ 5 ዐይነት የእጅ ሞያ ለማከናወንም ድንጋይ እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው። 6 ከእርሱም በተጨማሪ የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ከዳን ነገድ መርጬዋለሁ። ያዘዝሁህንም ሁሉ እንዲሠሩ የእጅ ሞያ ዐዋቂዎች በሆኑት ልብ ውስጥ ብልኀትን አስቀምጫለሁ። 7 የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦት፣ በታቦቱ ላይ ያለውን የስርየት መክደኛና የድንኳኑን ዕቃ ሁሉ፦ 8 ጠረጴዛውንና ዕቃውን፣ ንጹሑን መቅረዝ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር፣ የዕጣኑን መሠዊያ: 9 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋርና ትልቁን ሰን ከነመቆሚያው የሚያካትት ይሆናል። 10 የተሠሩትን ልብሶች፦ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ ለእኔ የተለዩትን የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም ይጨምራል። 11 ዘይቱንና የመቅደሱን ጣፋጭ ዕጣንም ያካትታል። እነዚህ የእሥ ሞያ ዐዋቂዎች እነዚህን ሁሉ እኔ ባዘዝሁህ መሠረት ይሥሯችው።” 12 ሙሴን እንዲህ አለው፤ 13 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የእግዚአብሔርን የሰንበት ቀኖች ጠብቁ፤ እናንተን ለራሱ የለያችሁ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ፣ ይህ በእርሱና በእናንተ መካከል በትውልዶቻችሁ ሁሉ ምልክት ነውና። 14 ስለዚህ ለእናንተ የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰንበት ነውና አክብሩት። ሰንበትን የሚያረክስ ሁሉ ይሞታል። በሰንበት የሚሠራም ከወገኑ ተነጥሎ ይጥፋ። 15 ስድስት ቀን ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ክብር የተጠበቀና የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት ሰንበትን ያክብሩ። 16 በትውልዶቻቸው ሁሉ ቋሚ ሕግ አድረገው ሰንበትን ሊያከብሩት ይገባል። 17 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፣ ሰንበት በእግዚአብሔርና በእስራኤላውያን መካከል ሁልጊዜ ምልክት ይሆናል።” 18 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ከሙሴ ጋር የሚያደርገውን ንግግር ከጨረሰ በኋላ፣ በገዛ እጁ የጻፈባቸውን የምስክሩን ሁለት የድጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።
ይህ “በስሙ ጠርቼዋለሁ” የሚለው ስሙን መጥራት ሳይሆን “ለሥራው ለይቼዋለው ወይም መርጬዋለሁ” ማለት ነው። የእብራይስጥ ስሙ “ብጻልኤል” ሲሆን አማርኛ ትርጉሞች “ባስልኤል” ብለውታል። አማራጭ ትርጉም፦ “እኔ ባስልኤን መርጬዋለሁ”
የወንዶች ስም ሲሆን የባስልኤል አባትና አያት የሚመለክቱ ናቸው
እግዚአብሔር (ያህዌ) በአንድ ፈሳሽ መያዣ ውስጥ መንፈሱን እንደሚሞላ ባስልኤልን እሞላዋለሁ እያለ ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ መንፈሴን ለባስልኤል ሰጥቼዋለሁ
ማንኛውም ዓይነት ሥራ የመሥራት ችሎታና ጥበብ
የእጅ ጥበብ ሥራዎችን ሁሉ መስራት እንዲችሉ ታላቅ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጌአለሁ
እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ከህዝቡ ጋር የሚገናኝበት ድንኳን ማለት ነው
የቃል ኪዳኑ ታቦት
በምስክሩ ታቦት ላይ የሚቀመጥና የስርየት መስዋዕቱን የሚሸፍን መክደኛ ነው
ዕጣን የሚሰዋበት ቦታ ወይም የሚቀርብበት ቦታ
የሚቃጠል መስዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቀርብበት ቦታ ወይም የሚሰዋበት ቦታ
ከንጹህ ወርቅ የተሰራውን የወርቅ መቅረዝ ወይም የብርሃን ማስቀመጫ
በጥብቅ የተሰራ የሊኖ ልብስ ሲሆን ካህናት በክህነት አገልግሎት ወቅት የሚለብሱት ልብስ ነው
እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን የሚነግራቸው የሰንበት ቀን በማክበር እርሱን እንድታዘዙ ነው።አማራጭ ትርጉም፦ “የሰንበት ቀን በማክበር እኔን መታዘዝ አለባችሁ”
ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ወይም እስከ ልጅ ልጃችሁ ድረስ ምልክት ይሆናል
እግዚአብሔር ለራሱ የለያችሁ ወይም የመረጣችሁ ሰዎች ናችሁ
የሰንበት ቀን ማክበር ቅዱስ ተግባር ስለሆነ ሰንበቴን አክብሩ
ሰንበትን ማክበር የማይፈልግ ወይም የሰንበት ቀን አክብሮት የሚሽር ሰው ወይም ትኩረት የማይሰጥና የሚንቅ ሰው
በአድራጊ ግስ፦ ይህን ሰው ግደሉ ወይም ከመካከላችሁ አስወግዱ ወይም ይህ ሰው በሞት ይቀጣ
ይህ አባባል በተለያዩ መንገዶች ልተረጎም ይችላል
ቀን 7 ወይም የሳምንቱ 7ኛ ቀን
እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን የሚነግራቸው የሰንበት ቀን በማክበር እርሱን እንድታዘዙ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የሰንበት ቀን በማክበር እኔን መታዘዝ አለባችሁ
እግዚአብሔር ራሱ የጻፋቸው ወይም እግዚአብሔር ራሱ በራሱ እጅ የጻፋቸው
1 ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ሕዝቡ ሲመለከቱ፣ በአሮን ዙሪያ ተሰብስበው እንዲህ አሉት፤ “በፊታችን የሚሄድ ጣዖት ሥራልን። ከግብፅ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳጋጠምው አናውቅም።” 2 እንዲህ አላቸው፤ “በሚስቶቻችሁ ጆሮዎች፣ በወንድና በሴት ልጆቻችሁ ጆሮዎችም ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቁና ወደ እኔ እምጧቸው።” 3 ሁሉም በጆሮዎቻቸው ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቀው ወደ አሮን አመጧቸው። 4 ወርቁን ከእነርሱ ተቀብሎ በማቅለጥ ቅርጽ ሰጠው፤ የጥጃ ምስልም አደረገው። ሕዝቡም፣ “እስራኤል፣ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ነው” አሉ። 5 ይህን ባየው ጊዜ፣ በጥጃው ምስል ፊት መሠዊያ ሠራ፤ “ነገ ለእግዚአብሔር ክብር በዐል ይሆናል” ብሎም ዐወጀ። 6 ሕዝቡ በማግስቱ ማልደው በመነሣት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረቡ። ሊበሉና ሊጠጡም ተቀመጡ፤ ለመዝፈንም ተነሡ። 7 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ራሳቸውን በክለዋልና ቶሎ ሂድ። 8 መንገድ ፈጥነው ወጥተዋል። ለራሳቸው የጥጃ ምስል ሠርተው ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለታል። ‘እስራኤል፣ ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው ብለውም ተናግረዋል።’” 9 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ። ተመልከት፣ ዐንገተ ደንዳናዎች ናቸው። 10 በእነርሱ ላይ እንዲቀጣጠልና እንዳጠፋቸው ተወኝ። ከአንተም ታላቅ ሕዝብ አደርጋለሁ (አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ) ።” 11 ግን አምላኩ እግዚአብሔር ዝም እንዲልለት ፈለገ፤ እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፣ በታላቁ ኀይልና በኀያል እጅ ከግብፅ ባወጣሃው ሕዝብህ ላይ ቊጣህ ለምን ይቀጣጠላል? 12 ‘እግዚአብሔር በተራሮች ላይ ሊገድላቸውና ከገጸ ምድር ሊያጠፋቸው ዐስቦ ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከሚነድደው ቊጣህ ተመለስ፤ በሕዝብህ ላይ ይህን ቊጣ ከማምጣትም ታገሥ። 13 ‘ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፣ የተናገርሁትን ይህንም ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጠዋለሁ፤ የዘለዓለም ርስታቸው ይሆናል’ ያልሃቸውንና በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህ አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን ዐስብ።” 14 ከዚያም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ አመጣባቸዋለሁ ካለው ቊጣ ታገሠ። 15 ተመለሰ፤ የምስክሩን ሁለት ጽላት በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ። ጽላቱ በሁለቱም ጎኖቻቸው፣ በፊትም በኋላም ተጽፎባቸው ነበር። 16 የእግዚአብሔር ሥራ ነበር፤ በጽላቱ ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር። 17 ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር። 17 ኢያሱ የሕዝቡን ጫጫታ ሲሰማ፣ ሙሴን፣ “በሰፈር ውስጥ የጦርነት ድምፅ አለ” አለው። 18 ሙሴም “የድል አድራጊ ድምፅ አይደለም፤ ድል የተደረገ ሕዝብ ድምፅም አይደለም፤ የምሰማው የዘፈን ድምፅ ነው” ብሎ መለሰለት። 19 ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ፣ ጥጃውንና የሚጨፍረውን ሕዝብ አይቶ በጣም ተናደደ። ጽላቱን ከእጁ ወርውሮ በተራራው ግርጌ ሰበራቸው። 20 ሠርተውት የነበረውን ጥጃም ወስዶ አቃጠለው፤ ዱቄት እስከሚሆን ድረስ በመፍጨትም በውሀ ውስጥ በተነው። ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ እንዲጠጣው አደረገ። 21 “እንደዚህ ያለ ታላቅ ኀጢአት ያመጣህበት ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው?” አለው። 22 እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ “ጌታዬ ሆይ ቊጣህ አይንደድ። እነዚህ ሰዎች ለክፋት የተዘጋጁ እንደ ሆኑ ታውቃለህ። 23 እንደዚህ ብለውኛል፤ ‘በፊታችን የሚሄድ አምላክ አብጅልን። ከግብፅ ያወጣን ሰውየ ይህ ሙሴ ምን እንዳጋጠመው አናውቅም።’ 24 እኔም፣ ‘ወርቅ ያለው ሰው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው። እነርሱም ወርቁን ሰጡኝ። በእሳት ውስጥም ጣልሁትና ይህ ጥጃ ወጣ።” 25 መዘባበቻ እንዲሆኑ አሮን መረን ስለ ለቀቃቸው፣ ሕዝቡ ከቊጥጥር ውጭ መሆናቸውን ሙሴ አስተዋለ። 26 በሰፈሩ መግቢያ ቆሞ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ” አለ። ሌዋውያን ሁሉ በሙሴ ዙሪያ ተሰበሰቡ። 27 ሌዋውያኑን እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ይታጠቅና በሰፈሩ ሁሉ ከበር እስከ በር ወደ ኋላና ወደ ፊት እየተመላለሰ ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል።’” 28 ሌዋውያኑ ሙሴ ያዘዘውን ፈጸሙ። በዚያ ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺሕ ያህል ሰዎች ሞቱ። 29 ሌዋውያኑን፣ “ዛሬ ከእናንተ እያንዳንዱ በልጁና በወንድሙ ላይ እርምጃ ስለ ወሰደ፣ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀድሳችኋል። ስለዚህም እግዚአብሔር ዛሬ ባርኳችኋል” አላቸው። 30 በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን፣ “ታላቅ ኀጢአት ሠርታችኋል። አሁን ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ። ምናልባት ለኀጢአታችሁ ማስተሰረያ ማድረግ እችል ይህናል” አላቸው። 31 ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ ሄደ፤ እንዲህም አለ፤ “ወዮ! እነዚህ ስዎች ታላቅ ኀጢአት ሠርተዋል፤ ለራሳቸውም ከወርቅ ጣዖት አበጅተዋል። 32 ግን እባክህ ኀጢአታቸውን ይቅር በል፤ ይቅር የማትላቸው ከሆነ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍ እኔን ደምስስልኝ።” 33 ሙሴን እንዲህ አለው፤ እኔን የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ። 34 ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ነገርኋችሁ ስፍራ ምራው። እነሆ፣ የእኔ መልአክ በፊትህ ይሄዳል። ሕዝቡን በምቀጣበት ቀን ግን ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።” 35 አሮን በሠራው ጥጃ ስላደረጉት፣ እግዚአብሔር በሕቡ ላይ መቅሠፍት ላከባቸው።
ይህ በዘይቤያዊ አነጋገር የተገለጸ ሲሆን አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር እንደተገለጠ ወይም እንደታዬ አድርጎ ተገልጿል። አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ ዘገየ በተረዱ ወይም ባስተዋሉ ጊዜ”
አሮንን አንድ ጥያቄ ለመጠየቅና ለማስገደድ እንደ መጡ ያሳያል። አማራጭ ትርጉም፦ ወደ አሮን መጥተው ወይም ቀርበው
እኛን የሚመሩን ወይም መሪ ልሆኑን የሚችሉ
ሙሴንና የሙሴን እግዚአብሔር የተቃወሙ ሰዎች ሁሉና እግዚአብሔር አምላካቸው እንዳይሆን ሙሴ መሪያቸው እንዳይሆን ያልፈለጉ ሰዎች ሁሉ ማለት ነው
“ሰብራችሁ” የሚለውን ቃል አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አውልቃችሁ” ብሎ ተርጉሟል። ነገር ግን ይህ ትርጉም ልል ነው። በዕብራይስጡ ለማለት የተፈለገው “የወርቅ ጉትቻዎቻችሁን ከጆሮአችሁ ሰብራችሁ አውጥታችሁ” የሚል ጠንካራ ቃል ወይም ግስ ይጠቀማል።
አሮን ወርቆችን በማቅለጫ አቅልጦ፥ በጥጃም መልክ ቀርጾ ጣኦት ሰራላቸው።
ይህ ግልጽ ያልሆነ አባባል ነውና ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ነው። አሮን የእስራኤል ህዝብ ያደረገውን ባየ ጊዜ ወይም አሮን የሰራውን የወርቅ ጥጃ ባየ ጊዜ በሚል መተርጎም ይቻላል።
በአማርኛችን የዚህ ሀረግ ትርጉም በጣም ተደብቋል። “ሊዘፍኑም ተነሡ” የሚለው ተራ ዘፈን ሳይሆን ከሰው ባህርይ የወጣ ተግባር ሲፈጽሙ ነበር። ከበሉና ከጠጡ በኋላ ራሳቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው በሜዳ ላይ ይሰስኑ፥ ይዳሩና ይዘሙቱ ነበር። የእንስሳነት ባህርይ ተላብሰው ልቅ ወሲብ ይፈጽሙ ነበር ማለት ነው።
እግዚአብሔር ሙሴን ሲናገር እስራላውያን ካሳየኋቸው መንገድ ፈቀቅ ብለዋል ሲል አንድ መንገድ እግዚአብሔር አሳይቷቸው እነርሱ ግን ያንን መንገድ ትተው በሌላ መንገድ እንደሄዱ አድርጎ ያቀርባል። አማራጭ ትርጉም፦ እንድያደርጉ ያዘዝኳቸውን ትዕዛዛት አላደረጉም ወይም ትዕዛዜን ለምድረግ ፈቃደኛ አይደሉም
ለራሳቸውም በጥጃ ምስል የተቀረጸ ጣዖትን ሠርተው ለእርሱ ሰገዱለት
እግዚአብሔር (ያህዌ) ይህን ህዝብ አውቃለሁ በማለት ፋንታ ይህን ህዝብ አየሁ ይላል። አማራጭ ትርጉም፦ ይህን ህዝብ አውቃለሁ
“አንገተ ደንዳና” የሚለው ሀረግ “ልቤ ደነዳና ወይም የማይታዘዝ ልብ” የሚለውን ትርጉም ይይዛል። ነገር ግን አማርኛው የልብን እልከኝነት በአንገተ ደንዳናነት ሲተካው እናያለን።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ከሙሴ ጋር ሲያደርግ የነበረው ንግግር ላይ ሌላ አዲስ የንግግር ምዕራፍ ሲከፍት እናያለን፥ ስለሆነም ያህዌ ሊያደርግ ያለውን ነገር ለሙሴ ሲናገር እናያለን።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ቁጣው እንደ እሳት ትኩስና የሚያቃጥል እንደሆነ ይናገራል። አማራጭ ትርጉም፦ በእነርሱ ላይ እጅግ ተቈጥቼ ላጠፋቸው ስለ ተዘጋጀሁ ተወኝ
“አንተን” የተባለው ሙሴ ሲሆን በተውላጠ ስም ተጠቅሷል።
ሙሴ ይህን ጥያቄ እግዚአብሔርን (ያህዌን) የጠየቀው እግዚአብሔር በህዝቡ ላይ እንዳይቆጣ ለመለመን ወይም ለማሳመን ነው። ይህ አጋናኝ ጥያቄ በመደበኛ ዐረፍተ ነገር ሲተረጎም፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ በሥልጣንህና በታላቅ ኀይልህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸውን ሕዝብህን አትቆጣ
ሁለቱ ሀረጎች ተመሳሳይ ፍቺ የሚጋሩ ሲሆን ለንግግሩ አጽንኦት ለመስጠት የገቡ ናቸው።
“ጽኑ እጅ” የሚያመለክተው ከዚህ በፊት እስራኤላውያንን ከግብጽ ለማውጣት እግዚአብሔር የሰራቸውን ሥራዎች የሚያመለክት ነው።
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንዳያጠፋቸው እግዚአብሔር ምክንያት እየሰጠ ንግግሩን ይቀጥላል።
ይህ አጋናኝ ጥያቄ የሚያመለክተው እስራኤላውያንን እንዳያጠፋቸው ሙሴ እግዚአብሔርን ሲለምን የሚያሳይ ነው። አማራጭ ትርጉም ግብጻውያን ‘እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣቸው በተራራዎች ላይ ሊገድላቸውና ፈጽሞ ሊያጠፋቸውና ለክፉ ነግር ነው’
ከምድር ላይ
ከክፉ ቍጣህ ተመለስ ወይም ሀይለኛ ቁጣህን ተው
አብርሃምን፥ ይስሃቅንና ያዕቆብን (እስራኤልን) አስታውስ
ቃል ኪዳን የገባህላቸውን
ለዘላለምም ይወርሱአታል ወይም የራሳቸው አድርገው ይይዟታል
በሁለት ጠፍጣፋ ድንጋዮች ላይ የተጻፉ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት /ትዕዛዞች/
ሙሴም
እግዚአብሔር የጻፈባቸውን ሁለቱን ጠፍጣፋ ድንጋዮች
“ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ወይም በድሎህ ነው ይህን የመሰለ ክፉ ኃጢአት እንዲሠራ ያደረግኸው?”
ሀጢአት እንደ አንድ ግዑዝ ነገር ሆኖ አሮን በህዝቡ ላይ እንዳመጣበት በዘይቤያዊ አነጋገር ሙሴ ይገልጸዋል። አማራጭ ትርጉም፦ ይህን ክፉ ሀጢአት እንዲሰሩ ምክንያት የሆንከው አሮን አንተ ነህ
ጌታዬ በእኔ ላይ እንዲህ በሀይል አትቈጣ
ይህ ሕዝብ ምን ያህል የክፋት ዝንባሌ እንዳለው ወይም ክፉ የማድረግ ፍላጎት እንዳለው አንተ ታውቃለህ
“ይህ ሙሴ” የሚለው ሀረግ ህዝቡ ለሙሴ ያለው አክብሮት እንደ ወረደባቸው የሚገልጽ ነው። ከዚህ በፊት ሙሴን እንደማያውቁና እርሱም የማይታመን ሰው እንደሆነ “ይህ ሙሴ” በሚለው ሀረግ አርቀው ይናገራሉ።
እኔ የወርቅ ጉትቻዎቻቸውን ወይም ጌጣጌጦቻቸውን አውልቀው ወይም ሰብረው እንዲያመጡልኝ ነገርኳቸው
አሮን ሀላፊነት የወርቅ ጥጃውን ስለመስራቱ ላለመውሰድ ሲፈልግ እኔ ወርቆቹን ወደ እሳት ጣልኩኝ ነገር ግን ይህ ጥጃ ወጣ ብሎ ሲያስተባብል እናያለን።
ህዝቡ ነውረኛ ነገር በማድረግና ራሳቸውም ነውረኛ በመሆን ልቅ ተግባር ፈጽመዋል።
ሙሴ ወደ ሰፈሩ መግቢያ በር/ደጅ/ ቆሞ የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እርሱ እንድመጣ ለእስራኤላውያን ተናገረ።
ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆነ ሰው የእግዚአብሔር ወገን እንደሆነ በዘይቤያዊ ንግግር ቀርቧል። በሰፈሩም ውስጥ በዚህና በዚያ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፤ የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም ይግደል በሰፈር ውስጥ ከአንዱ በር/ደጅ/ ወደ ሌላው በር/ደጅ/ እያለፈ ወይም እየዞረ እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል።
“3000 ሰው ሞተ”
እግዚአብሔርን የምታገለግሉ ካህናት ሆናችሁ ራሳችሁን ቀድሳችኋል
እግዚአብሔርን (ያህዌ) በመታዘዝ እያንዳንዳችሁ ልጆቻችሁንና ወንድሞቻችሁን ገድላችኋል
እናንተ ጣዖት በማምለክ እጅግ የከፋ ሀጢአት ሰርታችኋል
ሙሴ ወደ እግዚአብሔር በመለመን እግዚአብሔር ይቅር እንዲላቸው ልመና ለማቅረብ ሲዘጋጅ ይታያል። አማራጭ ትርጉም፦ ምናልባት ስለ ኃጢአታችሁ ይቅርታ አስገኝላችሁ ይሆናል
“እባክህ ደምስሰኝ” የሚለው ሙሴ ስለራሱ ሲናገር ያሳያል። አማራጭ ትርጉም፦ ይህ የማይሆን ከሆነ ወይም ይቅር የማትላቸው ከሆነ የእኔን ስም ሰርዝ
የሕዝብህ ስሞች ከተጻፉበት መዝገብ
“እርሱን” የሚለው ያንን ሀጢአት የሰራውን ሰው ስም ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔን የበደለኝን ሰው ስም ከመጽሐፌ እሰርዛለሁ
ይህ መጽሐፍ ሙሴ የሚናገረው የእግዚአብሔር (ያህዌ) መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ ባለበት እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።
ነገር ግን እኔ እነርሱን የምቀጣበት ጊዜ ሲደርስ ስለ ኀጢአታቸው የምቀጣው እኔ እግዚአብሔር ነኝ
በምን ዓይነት ሁኔታ ህዝቡን እንደቀሰፈ አልተገለጸም ነገር ግን በበሽታ ሊሆን ይችላል። አማራጭ ትርጉም፦ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ከባድ በሽታ ላከ
የጥጃ ምስል ጣኦት የሰራው አሮን ቢሆንም ያንን የጥጃ ምስል ጣኦት አሮን እንዲሰራው ያስገደዱት ህዝቡ ነበሩ። አማራጭ ትርጉም፦ አሮን የጥጃ ምስል ጣኦት እንዲሰራ ህዝቡ በማስገደዳቸው
1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተና ከግብፅ ያወጣሃው ሕዝብ ከዚህ ሂድ። ‘ለዘርህ እሰጠዋለሁ’ ባልሁ ጊዜ፣ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማልሁበት ምድር ሂድ። 2 በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ፤ ከነዓናውያንን፣ አሞራውያንን፣ ኬጤያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያንንም አስወጣቸዋለሁ። 3 ማርና ወተት ወደምታፈስሰዋ ምድር ሂዱ፤ ነግር ግን እናንተ ግትሮች ስለ ሆናችሁ፣ እኔ ከእናንተ ጋር አልወጣም። በመንገድ ላይ ላጠፋችሁ እችላለሁ።” 4 እነዚህን አስጨናቂ ቃሎች ሲሰሙ፣ አለቀሱ፤ ምንም ዐይነት ጌጥ ያደረገ ሰውም አልነበረም። 5 ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበር፤ “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እናንተ ግትር ሰዎች ናችሁ። ለአፍታ እንኳ ዐብሬአችሁ ብሄድ፣ አጠፋችኋለሁ። ስለዚህ ምን እንደማደርግባችሁ ለመወሰን ጌጣጌጦቻችሁን አውልቁ።” 6 እስራኤላውያንም ከኮሬብ ተራራ ጀምረው ጌጦቻቸውን አወለቁ። 7 አንድ ድንኳን ወሰደና በተወሰነ ርቀት ላይ ከሰፈር ውጭ ተከለው። የመገናኛ ድንኳን ብሎ ጠራው። ስለ ማንኛውም ጕዳይ እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ሰው ሁሉ ከሰፈሩ ውጭ ወደሚገኘው የመገናኛ ድንኳን ይሄድ ነበር። 8 ወደ ድንኳኑ ሲሄድ፣ ሕዝቡ ሁሉ በየድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሞ ወደ ድንኳኑ ሲገባ ሙሴን ይመለከት ነበር። 9 ወደ ድንኳኑ በሚገባበት ጊዜ ሁሉ፣ የደመና ዐምድ ይወርድና በድንኳኑ መግቢያ ላይ ይቆማል። እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር ይነጋገራል። 10 ሕዝቡ በድንኳኑ መግቢያ ላይ የደመናውን ዐምድ ቆሞ ሲያዩት፣ እያንዳንዱ ሰው በራሱ ድንኳን መግቢያ ላይ ይነሣና ይሰግዳል። 11 እግዚአብሔር አንድ ሰው ጓደኛውን እንደሚያነጋግር፣ ሙሴን ፊት ለፊት ያነጋግረዋል። ከዚያም በኋላ ሙሴ ወደ ሰፈሩ ይመለሳል፤ አገልጋዩና ወጣት የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ ግን ከድንኳኑ አይለይም ነበር። 12 ሙሴ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሕዝብ ምራው ብለኸኝ ነበር፤ ከእኔ ጋር ማንን እንደምትልክ ግን አላሳወቅኸኝም። ‘በስም ዐውቅሃለሁ፤ በፊቴም ሞገስ አግኝተሃል’ ብለሃል። 13 በፊትህ ሞገስ ካገኘሁ፣ እንዳውቅህና በፊትህ ሞገስን በማግኘት እንድቀጥል መንገዶችህን አሳየኝ። ይህ ሕዝብ የአንተ ሕዝብ እንደ ሆነም አስታውስ።” 14 እግዚአብሔርም መልሶ፣ “የእኔ ሀልዎት ከአንተ ጋር ዐብቶ ይሄዳል፤ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው። 15 እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “የአንተ ሀልዎት ዐብሮን የማይሄድ ከሆነ፣ ከዚህ አታውጣን። 16 ከእኛ ጋር ካልሄድህ፣ እኔና ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ ያገኘን መሆናችን እንዴት ሊታወቅ ይችላል? እኔና ሕዝብህ በምድር ገጽ ካለው ሕዝብ ሁሉ የተለየን የምንሆነው አንተ ከእኛ ጋር ብትሄድ ብቻ አይደለምን?” 17 ሙሴን፣ “በፊቴ ሞገስን ስላገኘህና በስምም ስለማውቅህ፣ የጠየቅኸውን አድረጋለሁ” አለው። 18 “እባክህ ክብርህን አሳየኝ” አለ። 19 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ ስሜን እግዚአብሔርንም በፊትህ ዐውጃለሁ። የምምረውን እምረዋለሁ፤ የምራራለትንም እራራለታለሁ።” 20 ነገር ግን እግዚአብሔር፣ ፊቴን ማየትና በሕይወት መኖር የሚችል ሰው ስለሌለ፣ አንተ የእኔን ፊት ማየት አትችልም” ብሎ መለሰለት። 21 እንዲህ አለ፤ “እነሆ፣ በእኔ ዘንድ ስፍራ አለ፤ አንተ በዚህ ዐለት ላይ ትቆማለህ። 22 ክብሬ በዚያ ሲያልፍ፣ እኔ እስከማልፍ ድረስ አንተን በዐለቱ ስንጥቅ ውስጥ በእጄ እሸፍንያለሁ። 23 ከዚያም እጁን አነሣውና ጀርባዬን ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም።”
ምልከታ፦ እግዚአብሔር (ያህዌ) በህዝቡ ላይ መቆጣቱን ቀጥሎ ይናገራል።
ይህ ሐረግ በግነታዊ እና በተለዋጭ ዘይቤ የተገለጸ ነው። ይህ አገላለጽ ከምድሪቱ ወተትና ማር ይፈልቃል ማለት ሳይሆን ለከብት እርባታና ለእርሻ በጣም ምቹ የሆነ ምድር እንደሆነ ለማሳየት ነው። እንዲሁም “የምታፈስ” አገር የሚለው ቃልም ሁሉም ነገር የሞላባት ምድር የሚል ፍቺ ያለው ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ለከብት እርባታና ለእርሻ ምቹ የሆነ ምድር
በእንስሳት ምርትና ተዋጽኦ የዳበረች አገር መሆኑዋን ለማመልከት ነው
በእስራኤል ምድር ማር በሁለት መንገዶች ይመረታል። አንደኛው ከንብ እርባታ የሚገኘው ሲሆን ሁለተኛው ከተምር ዛፍና ከሌሎች ዕጽዋት የሚገኘው ነው።
ጸሐፊው የማይታዛዝ ህዝብ መሆኑን ለማሳየት በዘይቤያዊ አነጋገር ይገልጻል። የልባቸው እልከኝነት ከአንገት ደንዳናነት ጋር ተነጻጽሯል። አንገተ ዳንዳና ማለት ገታራና የማይመለስ ወይም መታጠፍ የማይችል ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ የማይሰማና የማይታዘዝ ህዝብ፤ ለለውጥ ያልተዘጋጀ ህዝብ ወይም ከገታራ አቋሙ የማይመለስ ማለት ነው።
ምንም ዐይነት ጌጣጌጥ (የጆሮ ጌጥ፥ የአንገት ሀብል፤ እና ሌሎች ጌጣጌጦች) ማድረግ አልፈለጉም
እናንተ የማትታዘዙና የማትሰሙ ለለውጥም ያልተዘጋጃጅችሁ ሰዎች ናችሁ
ደመናው እንደ አምድ ይታይ ነበር ወይም የአምድ ቅርጽ ነበረው ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “ደመናው በአምድ ቅርጽ ይወርድ ነበር”
የጋራ መረዳት ከለሌው ከየት እንደሚወርድ አይገልጽም። አማራጭ ትርጉም፦ “ከሰማይ ይመጣ ነበር”
በራዕይና በህልም ሳይሆን እግዚአብሔር በቀጥታ አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ፊት ለፊት ወይም አንዱ ሌላውን እያየ እንደምነጋገር ከሙሴ ጋር ይነጋገር። አማራጭ ትርጉም፦ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ከሙሴ ጋር በቀጥታ ይነጋገር ነበር”
ኢያሱ ከሙሴ ይልቅ ወጥት ሲሆን “ብላቴና” የተባለው ወጣት መሆኑን ያሳያል፥ ሎሌው የተባለው “ረዳት” መሆኑን ይገልጻል። አማራጭ ትርጉም፦ “ረዳቱ ወጣት”
“እይ” ወይም “ስማ” ወይም “አድምጠኝ” እንደማለት ነው። ቃሉ በዕብራይስጥ ትኩረት ለመሳብ ወይም የሀሳብ አንድነት መኖሩን ለማመልከት የገባ ነው።
አንድን ሰው በስም ማወቅ ያንን ሰው በሚገባ ወይም በትክክል እናውቄዋለን ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “እኔ አንተን በደንብ አውቅሃለሁ”
በዚህ ሀረግ “ሞገስ አገኘህ” የሚለው የሚያመለክተው ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ዕውቅና ያገኘ ወይም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ ደስ ተሰኘ ማለት ነው። “እኔ ፊት” የተባለው በእግዚአብሔር እይታ ወይም የእግዚአብሔርን ግምገማ የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ አንተን ገምግሜ ዕውቅና ሰጥቼሃለሁ ወይም በአንተ ተደስቻለሁ/በአንተ ደስ ይለኛል/
ይህን ሀረግ በሁለት መልኩ መተርጎም ይቻላል፦ ወደፊት ማድረግ የምትፈልገውን ነገር እባክህ ንገረኝ ወይም ወደፊት ህዝቡ ማድረግ የሚገባቸውን ነገር እባክህ አሳያቸው
ዕረፍት እሰጥሃለሁ
ሰዎች ሁሉ እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ?
እግዚአብሔር “አንተ’ እያለ በነጠላ ቁጥር የሚናገረው “ሙሴን” የሚመለከት ነው።
በዚህ ሀረግ “ሞገስ ስላገኘህ” የሚለው የሚያመለክተው ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ዕውቅና ያገኘ ወይም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ ደስ ተሰኘ ማለት ነው። “በፊቴ” የተባለው በእግዚአብሔር እይታ ወይም የእግዚአብሔርን ግምገማ የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ አንተን ገምግሜ ዕውቅና ሰጥቼሃለሁ ወይም በአንተ ተደስቻለሁ/በአንተ ደስ ይለኛል/
አንድን ሰው በስም ማወቅ ያንን ሰው በሚገባ ወይም በትክክል እንደማወቅ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ አንተን በደንብ ወይም በሚገባ አውቅሃለሁ
እግዚአብሔር (ያህዌ) ከሙሴ ፊት መልካምንቱን አሳልፎ የእግዚአብሔር መልካምነት በፊቱ እንደሚሄድ ዓይነት አቀራረብ አለው። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ የእኔን መልካምነት እንዲታይ መልካምነቴን በፊት አሳልፋለሁ
“እይ” ወይም “ስማ” ወይም “አድምጠኝ” እንደማለት ነው። ቃሉ በዕብራይስጥ ትኩረት ለመሳብ ወይም የሀሳብ አንድነት መኖሩን ለማመልከት የገባ ነው።
እግዚአብሔር ከሙሴ ፊት ለፊት ስለሚሄድ ሙሴ ማየት የሚችለው የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ጀርባ ነው
እግዚአብሔር በሙሴ ፊት ስለሚሄድ ጀርባውን እንጂ ፊቱን ማየት አይሆንለትም። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ ፊቴን ማየት አትችልም
1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንደ መጀመሪያዎቹ ጽላት አድርገህ ጥረብ። በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላት ላይ ተጽፈው የነበሩ ቃሎችን በእነዚህ ጽላት ላይ እጽፍባቸዋለሁ። 2 ማለዳ ላይ ተዘጋጅተህ ወደ ሲና ተራራ ውጣና በዚያ በተራራው ዐናት ላይ በፊቴ ቁም። 3 ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይምጣ። በተራራው ላይ በየትኛውም ስፍራ ማንም እንዲታይ አታድርግ። የበግና የፍየል መንጋዎች፣ የቀንድ ከብቶችም እንኳ በተራራው ፊት ለፊት ሣር መጋጥ የለባቸውም።” 4 ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንድ መጀመሪያዎቹ አድርጎ ጠረበ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ሲና ተራራ ወጣ። ሙሴ ሁለቱን የድንጋይ ጽላት በእጁ ይዞ ነበር። 5 እግዚአብሔር በደመና ወርዶ ከሙሴ ጋር በእዚያ ቆመ፤ ስሙን እግዚአብሔርንም ዐወጀ። 6 በሙሴ ፊትም እንዲህ እያለ በማወጅ ዐለፈ፤ “እግዚአብሔር፣ ርኅሩኅም ቸርም አምላክ እግዚአብሔር፣ ለቊጣ የዘገየ፣ በጽኑዕ ፍቅርና በታማኝነት ባለ ጸጋ፣ 7 ጽኑዕ ፍቅሩን ለሺሕ ትውልድ የሚጠብቅ፣ ክፋትን፣ ዐመፅንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፤ በደለኛውን ግን ከቶ ንጹሕ አያደርገውም። ለአባቶች ኀጢአት ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ይቀጣል።” 8 ሙሴ ወዲያውኑ ወደ መሬት ዝቅ ብሎ ሰገደ። 9 አለ፤ “ጌታዬ ሆይ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ እባክህ ዐብረኸን ሂድ፤ ይህ ሕዝብ ግትር ሕዝብ ቢሆንም፣ ክፋታችንና ኀጢአታችንን ይቅር በለን፤ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።” 10 እንዲህ አለ፤ “እነሆ፣ ኪዳን እገባለሁ። በምድር ሁሉ አየትኛውም ሕዝብ ዘንድ ተደርገው የማያውቁ ድንቆችን በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ። በአንተ ዘንድ የማደርገው የሚያስፈራ ነውና፣ ዐብሮህ ያለው ሕዝብ ሁሉ ሥራዬን ያያል። 11 የማዝዝህን ፈጽም። አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጤያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኢዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን በፊትህ አስወጣቸዋለሁ። 12 አገር ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ አለዚያ በመካከልህ ወጥመድ ይሆኑብሃል። 13 ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን አድቅቋቸው፤ የአሼራ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ። 14 ስሜ ‘ቀናተኛ’ የሆነ እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና ሌላ አምላክ አታምልክ። 15 ስለዚህም ከምድሪቱ ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን በመከተልያመነዝራሉና፣ መሥዋዕትም ያቀርቡላቸዋልና አንተንም አንዱ ስለሚጋብዝህና ከመሥዋዕቱም ጥቂት ስለምትበላ፣ 16 ከዚያም ከሴቶች ልጆቹ የተወሰኑትን ለወንዶች ልጆችህ ትወስዳለህ፤ ሴት ልጆቹም አማልክታቸውን በመከተል ያመነዝራሉ፤ ወንዶች ልጆችህንም ለአማልክታቸው እንዲያመነዝሩ ያደርጓቸዋል። 17 የተሠሩ አማልክትን ለራስህ አታብጅ። 18 የቂጣ በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት እርሾ ያልገባበትን ዳቦ በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር ሰባት ቀን ብላ፤ ከግብፅ የወጣሃው በአቢብ ወር ነበርና። 19 በኵር ሁሉ፣ የከብትህም እንኳ ተባዕት በኵር በሙሉ፣ የበሬዎችህም የበጎችም በኵር የእኔ ነው። 20 የአህያውን በኵር በጠቦት ዋጀው፤ ካልዋጀኸው ግን ዐንገቱን ስበረው። በኵር ወንድ ልጆችህን ሁሉ ዋጃቸው። ባዶ እጁን በፊቴ የሚቀርብ ማንም እይኑር። 21 ቀን ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍ። በዕርሻና በመከር ጊዜም እንኳ ዕረፍ። 22 ሱባዔ በዓል ከስንዴው በኵራት ጋር፣ የመክተቻውንም በዓል በዓመቱ መጨረሻ አክብር። 23 በአንተ ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእስራኤል አምላክ ፊት ይቅረብ። 24 በፊትህ አስወጣቸዋለሁ፤ ወሰንህንም አሰፋዋለሁ። በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ለመውረርና ለመቆጣጠር ማንም አይመኝም። 25 ደም ከእርሾ ጋር አታቅርብ፤ ወይም በፋሲካ በዓል የቀረበው መሥዋዕት ሥጋ እስከ ማለዳ ተርፎ አይቆይ። 26 የዕርሻህ ምርጥ በኵራት ወደ ቤቴ አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።” 27 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እነዚህን ቃሎች ጻፋቸው፤ በተናገርሏቸው በእነዚህ ቃሎች ክአንተና ከእስራኤል ጋር ኪዳን አድርጌአለሁና አለው። 28 አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር እዚያው ነበረ። ምግብም አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም። 29 ሁለቱን የምስክሩን ጽላት በእጁ ይዞ ከሲና ተራራ ወረደ። ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገረ ሳለ፣ ፊቱ የሚያበራ ምሆኑን አላወቀም። 30 እስራኤላውያን ሙሴን ሲያዩት፣ ፊቱ ይበራ ነበር፤ ስለዚህም ወደ እርሱ ለመጠጋት ፈሩ። 31 ግን ጠራቸው፤ አሮንና የሕዝቡ መሪዎችም ወደ እርሱ መቱ፣ ሙሴም ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ። 32 ከዚያ በኋላም፣ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ሙሴ መጡ፤ እርሱም በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሔር ሰጥቶት የነበረውን ትእዛዝ ሁሉ ነገራቸው። 33 ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ፣ በፊቱ ላይ መሸፈኛ አደረገ። 34 ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር በፊቱ በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያወልቀው ነበር። ሲወጣ ምን እንዲል እንደታዘዘ ለእስራኤላይዋን ይነግራቸዋል። 35 እስራኤላውያን የሚያበራውን ፊቱን ሲያዩ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ መሸፈኛውን እንደ ገና በፊቱ ላይ ያደርገዋል።
ጠፍጣፋ ድንጋዮች (ዘጸአት 31፡18 ተመልከት)
በተራራው ላይ መታየት በተራራው ላይ አንድ ሥራ እንደ መሥራት ይቆጠራል። አማራጭ ትርጉም፦ ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይምጣ፤ በተራራው በማንኛውም በኩል ወይም ቦታ ማንም ሰው አይታይ
በግ ወይም ከብት ማንኛውም እንስሳ በተራራው ግርጌ ወይም አጠገብ አይሰማራ
“እግዚአብሔር በተራራው ላይ ከሙሴ ጋር ቆመ”
የዚህ ዐረፍተ ነገር ፍቺ 1) እርሱ ስሙን እግዚአብሔር (ያህዌ) ብሎ ተናገረ 2) እርሱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ማን እንደሆነ ተናገረ። ስሙ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ አመልካች ነውና።
እግዚአብሔር ስለራሱ ይናገራል፤ አማራጭ ትርጉም፦ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ርህሩህና መሐሪ አምላክ ነኝ
ይህ አባባል በተለያዩ ቅጂዎች በሁለት መንገድ ይታያል። አንዳንድ ቅጂዎች በአንደኛ መደብ ሲንገሩ ሌሎች በ3ኛ መደብ ይናገራል። ስለዚህ በሁለቱም ትክክል ናቸው፤ 1) እኔ ለቊጣ የዘገየሁ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅሬና ታማኝነቴ የበዛ ነው 2) እግዚአብሔር (ያህዌ) ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ ነው
ቃል ኪዳኔን እስከ ሽህ ትውልድ ድረስ እጠብቃለሁ ወይም ዘለዓለማዊ ፍቅሬንም እስከ ብዙ ሺህ ትውልድ እጠብቃለሁ
በሶስተኛ መደብ የተነገረው እግዚአብሔር ራሱን በሶስተኛ መደብ ሲናገር ይታያል። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ እግዚአብሔር ሀጢአተኛውን/በደለኛውን ሳልቀጣ አልተውም
በአባቶች ሀጢአት ምክንያት ልጆቻችሁንና ልጅ ልጆቻችሁን እስከ ሶስትና አራት ትውልድ ድረስ እቀጣለሁ
በዚህ ሀረግ “ሞገስ አግኝቼ” የሚለው የሚያመለክተው ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ዕውቅና ያገኘ ወይም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ ደስ ተሰኘ ማለት ነው። “በፊትህ” የተባለው በእግዚአብሔር እይታ ወይም የእግዚአብሔርን ግምገማ የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ አንተን ገምግሜ ዕውቅና ሰጥቼሃለሁ፤ ወይም በአንተ ተደስቻለሁ/በአንተ ደስ ይለኛል/
ሁለቱ ቃላት የፍች ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም ልዩነት በመካከላቸው እንዳለ እሙን ነው። እዚህ ጋር በአንድ ላይ የመጡበት ምክንያት አጽንኦት ለመስጠት ነው። ሁለቱን ቃላት ለየብቻ ለመተርጎም የማይቻል ከሆነ ሀጢአታችንን ሁሉ ይቅር በለን ማለት ይቻላል።
ይህ አነጋገር አንድ ሰው አንድን ንብረት ካለበት ቦታ እንደሚወስድ ዓይነት አነጋገር ርስትህ አድርገህ ውሰደን ይላል። አማራጭ ትርጉም፦ የራስህ ሕዝብ አድርገህ ተቀበለን ወይም እኛን ህዝብህን እንደ ርስትህ የራስህ አድርገህ ተቀበለን
“በህዝብህ” የተባለው አንተ በምትመራው ህዝብ ፊት ወይም አንተ የምትመራው ህዝብ ሁሉ እያየ
ይህ የሚያስፈራው ነገር ህዝቡ እንዲፈራ የሚያደርግ ነገር ይሆናል። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ነገር አይቶ ህዝቡ ይፈራል ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ ለአንተ የማደርገው ነገር ህዝቡ እኔን እንዲፈራ የሚያደርግ ነው
“በአንተ ዘንድ” የተባለው ሙሴንና የእስራኤልን ህዝብ የሚመለከት ነው
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴና እስራኤላውያን ማድረግ ያለባቸውን ነገር እየቀጠለ ይናገራል።
ሌሎችን ሀጢአት እንዲሰሩ የሚያደርጉ እንደ ወጥመድ ተቆጥረዋል። አማራጭ ትርጉም፦ እነርሱ ሀጢአት እንድትሰሩ ያደርጓችኋል
“ቀናተኛ” የተባለው እግዚአብሔር ክብሩን ለማንም እንደማያጋራና የራሱን ክብር እንደሚጠብቅ የሚያሳይ ነው። የእግዚአብሔር ህዝብ ሌሎች አማልክት ቢያመልኩ እግዚአብሔር ክብሩ ይነካል፤ ምክንያቱም የእርሱ የሆኑት እርሱን የማያመልኩ ከሆነ ሌሎችም አያመልኩትም ማለት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ክብሬን እጠብቃለሁ
ይህ የእግዚአብሔርን ባህርይ የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ
ቀጥሎ እግዚአብሔር የሚናገረው እስራኤላውያን ከሌሎች ህዝቦች ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት ያሳያቸዋል።
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከሌላ ወንድ ጋር እንደማመንዘር እንደሆነ ይነግራቸዋል። አማራጭ ትርጉም፦ “እነርሱ ሌሎች አማልክት አመለኩ” ወይም “ምክንያቱም እነርሱ ወደ ሌላ ወንድ እንደሚሄዱ አመንዝራዎች ሌሎች አማልክትን አምልከዋል”
ለሌሎች አማልክት የተሰዋን ምግብ መብላት ምን ያህል ክፉ እንደሆነ በግልጽ ያትታል። አማራጭ ትርጉም፦ አንተ (እናንተ) እነርሱ ለአማልክታቸው የሚያቀርቡትን (የሚሰውትን) ምግብ በመብላት አማልክቶቻቸውን ለማምለክ ትፈተናላችሁ ወይም እነርሱ ለአማልክቶቻቸው የሰውትን ምግብ በመብላት ራሳችሁን አመንዝራ ታደርጋላችሁ
እግዚአብሔር (ያህዌ) እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው በሙሴ በኩል ያሳስባቸዋል።
ለሰባት ቀን ወይም እስከ ሰባት ቀን
እስራኤላውያን ከግብጽ የወጡት በአቢብ ወር ስለሆነ ለእነርሱ የአመቱ መጀመሪያ ወር ነው። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር አቢብ ወር የሚጀምረው ከመጋቢት መጨረሻ ሳምንት እስከ ሚያዝያ መጀመሪያ ሳምንት ድረስ ነው። (ዘጸአት 13፡4 ተመልከት)።
እግዚአብሔር (ያህዌ) እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው በሙሴ በኩል ያሳስባቸዋል።
በኩር ሆኖ የሚወለድ ወይም የሚወጣ
በኩር ሆኖ የሚወለድ ወንድ እና አህያ የእግዚአብሔር (የያህዌ) ነው፤ ነገር ግን መስዋእት ሆነው እንዲቀርቡለት ያህዌ አይፈልግም። በእነርሱ ፋንታ እስራኤላውያን በጎችን እንዲሰዉለት ተጠይቀዋል። ስለሆነም እስራኤላውያን በኩር ሆኖ የተወለደን አህያ ወይም ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር መልሰው እንዲገዙ ተፈቅዶላቸዋል። የምይዋጁ ከሆነ አንገቱን ቆልምመው ለመስዋዕት እንዳይቀርብ እንድያደርጉ ተጠይቀዋል።
ይህ አነጋገር እግዚአብሔር ማንም ሰው ወደ ፊቱ ሲመጣ የሆነ ነገር ተሸክሞ እንድመጣ የሚጠይቅ ይመስላል። ነገር ግን ይህ ወካይ ዘይቤ የሚያሳየው ወደ እኔ የሚመጣ ማንም ቢሆን መስዋዕት ሳይዝ አይምጣ ወይም ወደ እኔ የሚመጣ ማንም ቢሆን መስዋዕት ማምጣት አለበት
እግዚአብሔር (ያህዌ) እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው በሙሴ በኩል ያሳስባቸዋል።
“በእርሻም ወቅትም ሆነ በመከር ወቅት በሰባተኛው ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ” ወይም “በእርሻና በመከር ጊዜ እንኳ ቢሆን ማረፍ አለብህ”
ይህ በዓል የዳስ በመባል ይታወቃል። ይህ ልምምድ የመጣው እርሻቸውን በዳስ ወይም በጊዜያዊ ጎጆ ውስጥ ሆነው ያረሱና እህሉ እስኪደርስ ድረስ በዚያ ዳስ ሆነው ከአውሬ ሲጠብቁ የነበሩ አርሶ አደሮች ልምምድ ነው። “መክተቻ” የተባለው የእህል ማከማቻ ማለት ነው።
እግዚአብሔር (ያህዌ) እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው በሙሴ በኩል ያሳስባቸዋል
እግዚአብሔር (ያህዌ) እስራኤላውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው በሙሴ በኩል ያሳስባቸዋል
ደሙ መስዋዕት ከሚቀርበው እንስሳ የተገኘ ሲሆን የተሰዋው ለእግዚአብሔር ነበር። አማራጭ ትርጉም፦ የእንስሳ ደም ለእኔ በምታቀርብበት ጊዜ
እርሾ ካለው ወይም ከገባበት ከማንኛውም ነገር ጋር
በተራራው ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት
በጽላቶቹ ላይ የቃል ኪዳን ቃላት የሆኑትን ዐሥሩን ትእዛዞች የጻፈው ሙሴ ይሁን ወይስ እግዚአብሔር ግልጽ አይደለም። እንደዚህኛው አባባል የጻፈው ሙሴ እንደሆነ ያሳይል ነገር ግን ከሌሎች አውድ ስንመለከት የጻፈው እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው። “እርሱ” የሚለው ተውላጠ ስም ስለማን እንደሆነ አጠያያቂ ነው
በሌላ አገላለጽ፦ “የግንባሩ ቆዳ” ማለት ሲሆን ጠቅላላ “ፊቱን” የሚመለከት ነው። ፊቱ እንደሚያበራ ወይም እንደሚያንጸባርቅ ሆነ ወይም ፊቱ አበራ ወይም አንጻባረቀ
ወደ ሙሴ ለመቅረብ ፈሩ ወይም ፈርተው ነበር
ወደ ሙሴ ተመልሰው መጡ
ሙሴም እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ የገለጠለትን ሕግ ሁሉ ለእስራኤላውያን ሰጣቸው ወይም እንዲያደርጉ አዘዛቸው
መሸፈኛውን ወይም ሻሹን ከፊቱ ላይ ያነሳ ነበር
እግዚአብሔር (ያህዌ) እርሱን (ሙሴን) ያዘዘውን ነገር እርሱ ለእስራኤላውያን ነገራቸው ማለት ነው
1 የእስራኤልን ማኅበረ ሰብ ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፤ “እንድትፈጽሟቸው እግዚአብሔር የሰጣችሁ ትእዛዝት እነዚህ ናቸው። 2 ስድስት ቀን ሥራ ትሠራላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት የሰንበት ቀን ይሁንላችሁ። በዚያ ቀን ሥራ የሚሥዐራ ሁሉ ይሞታል። 3 በሰንበት ቀን በማንኛችሁም ቤት ውስጥ እሳት አይንደድ።” 4 ሁሉን የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው። 5 ከልብ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቅርቡ። ሁሉም ለእግዚአብሔር የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ መባያምጣ፤ 6 ሐምራዊና ቀይ ማግ፣ ቀጭን በፍታ፣ የፍየል ጠጒር፣ 7 በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር ዕንጨት፣ 8 መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያ ዘይቱ ቅመምና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፣ 9 መረግዶችና ለኤፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ ሌሎች ዕንጨቶችንም መባ አድርጎ ያቅርብ። 10 በመካከላችሁ ያሉ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ይምጡና እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ይሥሩ፦ 11 ከድንኳኑ ጋር፣ መደሪያውን፣ ማያያዣዎቹን፣ ክፈፎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ቋሚዎቹንና መሠረቶቹን፤ 12 ታቦቱንም ከነመሎጊያዎቹ፣ የስርየት መክደኛውንና የሚሸፍነውን መጋረጃ፤ 13 ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ ዕቃዎቹንም ሁሉን ኣየገጽ ኅብስቱን፤ 14 የመብራቶቹን መቅረዝ ከዐባሪ ዕቃዎቹ ጋር፣ መብራቶቹንና የመብራቶቹን ዘይት፤ 15 የዕጣኑን መሠዊያ ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣ የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መጋረጃ፣ 16 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ ከነሐስ መጫሪያው፣ ከመሎጊያዎቹና ከዕቃዎቹ ጋር፤ ትልቁን የመታጠቢያ ሰን እስከ ማስቀመጫው፤ 17 የአድደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመሠረቶቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢይ ኣመጋረጃ፤ 18 የማደሪያውን ድንኳን ካስማዎች ከነገመዶቻቸው፤ 19 ውስጥ ለማገልገል በብልኀት የተሠሩ ልብሶችን፣ ካህናት ሆነው ለማገልገል ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ የሚሆኑ የተቀደሱ ልብሶችን ያምጡ።” 20 ከዚያም ሁሉም የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጥተው ሄዱ። 21 ልቡ የተነሣሣና ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለውስጡም ለሚደረገው አገልግሎትና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ስጦታን ሰጡ። 22 ፈቃደኛ የነበሩ ወንዶችም ሴቶችም መጥተው የአፍንጫ ጌጦችን፣ የጆሮ ጌጦችን፣ ቀለበቶችን፣ ድሪዎችንና ሁሉንም ዓይነት የወርቅ ጌጣጌጦች አመጡ። 23 ሐምራዊ፣ ቀይም ቀይ ማግ፣ ያማረ በፍታ፣ የፍየል ጠጕር፣ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ወይም የአስቆጣ ቆዳ የነበራቸውም አመጡ። 24 ለማንኛውም ተግባር የሚጠቅም የግራር ዕንጨት የነራቸው፣ የብርና የነሐስ ስጦታ ማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ በስጦታነት ለእግዚአብሔር አቀረቡ። 25 ብልኀተኛ ሴቶችም ሁሉ ማግ ፈትለው፣ የፈተሉትን ሰማያዊ፣ ሕዐምራዊ፣ ወይም ቀይ ማግ አመጡ። 26 ያነሣሣቸውና ብልኀተኛ የሆኑ ሴቶች ሁሉ የፍየል ጠጕር ፈተሉ። 27 ለአፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችንና ሌሎች ዕንቆችን አመጡ፤ 28 ለመቅቢያው ዘይትና ጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን ዘይትና ቅመምም አመጡ። 29 የነጻ ፈቃድ ስጦታ ለእግዚአብሔር በሙሴ በኩል እንዲፈጸም አዝዞት ለነበረው ሥራ ሁሉ ቍሳቍሶችን አመጡ። 30 እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እግዚአብሔር የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስም ጠርቶታል። 31 ለሁሉም ዐይነት የጥበብ ሥራ ጥበብን፣ ማስተዋልንና ዕውቀትን ሊሰጠው ባስልኤልን በመንፈሱ ሞልቶታል፤ 32 የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ጥበባዊ ሥራዎችን ለመሥራት፣ 33 የጥበባዊ ሥራ ዐይነቶችን ሁሉ ለመሥራት ድንጋዮችን እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው። 34 እግዚአብሔር በባስልኤልና ከዳን ነገድ በሆነው በአሂሳሚክ ልጅ በኤልያብ ልብ ይህን ችሎታ አስቀመጠ። 35 ጥበበኛ ሰዎች፣ እንደ ቀራጺዎች፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ፣ ባማረ በፍታም እንደ ጥልፍ ጠላፊዎችና እንደ ሸመና ሠራተኞች እንዲሠሩም ብልኀትን ሞላባቸው። እነርሱ በሥራ ዐይነቶች ሁሉ ጥበበኞች የሆኑ የጥበብ ባለሙያዎች ናቸው።
የሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ወይም በአይሁዶች አቆጣጠር ቅዳሜ ማለት ነው
ይህ በተደራጊ ግስ የተጻፈው በአድራጊ ግስ ሲጻፍ፦ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራበት ማንኛውም ሰው ግደሉት
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ያዘዛቸው ነገሮች እርሱ እስራኤላውያን እንዲያደርጉ ይነግራቸዋል።
ለእግዚአብሔር መባ ወይም መስዋዕት አቅርቡ
“ልብ” መባውን የሚያቀርበውን ሰው ማመልከቱ ነው። አማራጭ ትርጉም፦ እያንዳንዱ ሰው ልቡ የፈቀደውን ወይም ፈቃደኛ የሆነ ማንም ሰው”
እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ያዘዛቸው ነገሮች እርሱ እስራኤላውያን እንዲያደርጉ ቀጥሎ ይነግራቸዋል።
የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ወይም ጥበብ ያለው እያንዳንዱ ሰው
መጋረጃዎችን ለማገናኘት የሚያገለግሉ ቀለበቶች ናቸው (ዘጸአት 26፡4-6 ተመልከት)
በመሬት ላይ የተሰኩና ሌሎችን ከመሬት ጋር ለማገናኘትና እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ የሚያገልግሉ እንደመሰረት የሚያገለግሉ ናቸው (ዘጸአት 26፡31)
በታቦቱ ላይ የሚቀመጠው የማስተሰሪያ መስዋዕት የተሰራበት መክደኛ ወይም መሸፈኛ
ይህ ዳቦ ወይም ህብስት የእግዚአብሔርን ህልዎት የሚወክል ነው። (ዘጸአት 25፡30 ተመልከት)
እንጨት ሲቃጠል ለመያዣነት የሚያገለግል የነሐስ መከላከያ ብረት
ቀጥ ብለው የቆሙና ድጋፍ የሚሰጡ እንጨቶች ናቸው።
በመሬት ላይ የተሰኩና ሌሎችን ከመሬት ጋር ለማገናኘትና እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ የሚያገልግሉ እንደመሰረት የሚያገለግሉ ናቸው (ዘጸአት 26፡19)
ከእንጨት ወይም ከብረት የተሰሩ የድንኳን ጠርዞችን ወይም ማዕዘኖችን ለመወጠር የሚያገለግሉ ናቸው (ዘጸአት 27፡19 ተመልከት)
በጥበብ ያጌጡ ወይም የተቀደሱ ልብሶች
እያንዳንዱን ነገር የሚመለከት ነው። ከእያንዳንዱ ነገድ የሆኑ የእስራኤል ህዝቦች
“ልብ” የሰውየው ማንነት የሚመለከት ሲሆን ልቡ ለእግዚአብሔር ነገር ክፍት የሆነ ለመስጠት ልቡ የፈቀደው ወይም ያነሳሳው
“መንፈስ” የሰው ማንነት መግለጫ ሲሆን የሰው መንፈስ ወይም ፈቃድ አመልካች ነው። መንፈሱ የፈቀደው ወይም ፈቃደኛ የሆነ ማለት ነው።
ፈቃደኛ የነበሩ ወይም የሆኑ
ለቁጥር 23 ዘጸአት 25፡4-5 ትርጉም ተመልከት
በእጃቸው የሠሩትን ጥሩ በፍታ ወይም ማግ በሰማያዊ፥ በሐምራዊና በቀይ ቀለም ቀለሙት
“ልብ” ሴቶችን የሚመለከት ሲሆን ፈቃደኛ የነበሩና ጥበብ ያላቸው ሴቶች ማለት ነው
ከቁጥር 27-29 ያለውን ክፍል ከምዕራፍ 25፡1-2 እና ቁጥር 3-7 በማነጻጸር ተርጉም።
የመንፈስ መሞላት አንድ ባዶ ነገር ውስጥ እንድን ነገር እንደመሙላት ይቆጠራል። የእግዚአብሔር መንፈስ ችሎታ ሰጠው።
ማናቸውንም የጥበብ ሥራ መሥራት እንዲችል (ዘጸአት 31፡1-2 እና 31፡3-5)
ሙሴ ለህዝቡ ንግግሩን ይቀጥላል
“በልባቸው” የሚለው ባስልኤልና የእርሱን የሥራ ጓደኞችን የሚመለከት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ ዕውቀታቸውን ለሌሎች የማስተማርን ችሎታ ሰጥቶአቸዋል
ማናቸውንም የጥበብ ሥራ ለመሥራት እንዲችሉ
ማንኛውንም ዐይነት ሥራ ያከናውኑ ዘንድ ጥበብን ሰጣቸው
1 ስለዚህ ባስልኤልና ኤልያብ፣ የልብ ጥበበኞች የነበሩና እንዲፈጽሙት እግዚአብሔር ያዘዘውን በመከተል መቅደሱ እንዴት እንደሚሠራ ለማወቅ ብልኀትንና ማስተዋልን ያስቀመጠባቸውም ሁሉ ይሠራሉ። 2 ባስልኤልንና ኤልያብን፣ እግዚአብሔር በልቡ ብልኀትን አስቀምጦበት የነበረ ጥበበኛ ስውን ሁሉ፣ መጥቶ ሥራውን ለመሥራት ልቡ ያነሣሣውንም ጠራ። 3 የጠራቸውም ለመቅደሱ ሥራ እስራኤላውያን አምጥተውት የነበረውን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ተቀበሉ። ሕዝቡ የነጻ ፈቃድ ስጦታዎችን ጠዋት ጠዋት ወደ ሙሴ ማምጣት አላቋረጡም ነበር። 4 ስለዚህ በመቅደሱ ሥራ ላይ የተሰማሩ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ከሚሠሩት ሥራ ተነሥተው መጡ። 5 ሙሴን፣ “እግዚአብሔር እንድንሠራው ላዘዘን ሥራ ከሚበቃው በጣም የሚበልጥ ሕዝቡ እያመጡ ነው” አሉት። 6 ሙሴም በሰፈሩ ውስጥ ያለ ማንም ሰው ለመቅደሱ ሥራ ሌላ ስጦታ እንዳያመጣ ትእዛዝ ሰጠ። ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ስጦታ ማምጣቱን አቆሙ። 7 ለሥራው ሁሉ ከሚበቃው በላይ ቍሳቍሶች ነበሯቸው። 8 ያሉ ጥበበኞችም ሁሉ ከአማረ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግም ከተሠሩትና ኪሩቤልም ከተጠለፉባቸው ዕሥር መጋረጃዎች ጋር የመገናኛውን ድንኳን ሠሩት። ይህም እጅግ ጥበበኛ የነበረው የባስልኤል ሥራ ነው። 9 መጋረጃ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ሁሉም መጋረጃዎች እኩል መጠን ነበራቸው። 10 ባስልኤል ዐምስት ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርጎ እርስ በርስ አገጣጠማቸው። 11 መጋረጃዎች የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይና በሁለተኛውም ተገጣጣሚ መጋረጃ የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይ ሰማያዊ ቀለበቶችን አደረገ። 12 በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዞች ዐምሳ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ። ስለሆነም ቀለበቶቹ እርስ በርስ ትይዩ ሆነው የተደረጉ ነበር። 13 ባስልኤል ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርቶ የመገናኛው ድንኳን ወጥ እንዲሆን መጋረጃዎቹን አያያዛቸው። 14 ባስልኤል በማደሪያው ላይ ላለው ድንኳን ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሠራ። 15 የእያንዳንዱ መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ዐሥራ አንድ መጋረጃዎች እያንዳንዳቸው እኩል መጠን ነበራቸው። 16 መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው፣ ስድስቱንም መጋረጃዎች እንደዚሁ እርስ በርሳቸው አያያዛቸው። 17 ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን በሁለተኛዎቹ ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ። 18 ባስልኤል ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን ለማገጣጠም ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሠራ። 19 ለድንኳኑ መሸፈኛ በቀይ ቅለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ከበላዩም የሚህን የአቆስጣ ቆዳ ሠራ። 20 ባስልኤል ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ። 21 ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 22 እርስ በርስ ለማያያዝ በያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ማያያዣዎች ነበር። የመገናኛውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሠራ። 23 ባስልኤል በዚህ መንገድ ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ። ለደቡቡ ጎንም ሃያ ወጋግራዎችን አበጀ። 24 ባስልኤል ከሃያዎቹ ወጋግራዎች ሥር የሚሆኑ አራ የብር መቆሚያዎችን አበጀ። ማያያዣዎች ለመሆን ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ከያንዳንዱ ሌላ ወጋግራ በታችም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች ነበሩ። 25 ጎን ላለው ለመገናኛው ድንኳን ሁለተኛ ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና 26 የብር መቆሚያዎቻቸውን አበጀ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንዲሁ ሁለት ሁለት መቆሚያ አበጅቶአል። 27 በስተ ምዕራብ ላለው ለመገናኛው ድንኳን ጀርባ ባስልኤል ስድስት ወጋግራዎችን ሠራ። 28 ድንኳን የኋላ ማእዘኖች ሁለት ወጋግራዎችን አበጀ። 29 እነዚህ ወጋግራዎች ከታች የተነጣጠሉ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የየያያዙ ነበር። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የተደረገው በዚህ መንገድ ነበር። 30 ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ስምንት ወጋግራዎች ነበሩ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለውም ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ለያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ሁለት በመሆን ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ነበሩ። 31 ባስልኤል የግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን አበጀ፦ ለመገናኛው ድንኳን አንድ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት፣ አግዳሚዎችን፣ 32 የመገናኛው ድንኳን ጎን ወጋግራዎች አምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳን የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን ሠራ። 33 አግዳሚዎቹን የሥራቸውም በወጋግራዎች መካከል ላይ ከዳር እስከ ዳር እንዲደርሱ አድርጎ ነው። 34 ወጋግራዎቹን በወርቅ ለበጣቸው። አግዳሚዎችን ለማያያዝ የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ፣ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለበጣቸው። 35 በብልኀተኛ ሠራተኛ ሥራ ኪሩቤል የተጠለፉበትን መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም ሠራው። 36 አራት የግራር ዕንጨት ምሰሶዎችን አበጅቶ በውርቅ ለበጣቸው። ለምሰሶዎችም የወርቅ ኵላቦችን ሠርቶ አራት የብር መቆሚያዎችን አደረገላቸው። 37 ለድንኳኑ መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም በጥልፍ ጠላፊ ሥራ የተዘጋጀ መጋረጃ አበጀለት። 38 የመጋረጃውን ዐምስት ምሰሶዎች ከኵላቦች ጋር ሠራ። የምሰሶዎችን ዐናትና ዘንግ በወርቅ ለበጣቸው። ዐምስት መቆሚያዎቻቸውም ከነሐስ የተሰሩ ነበሩ።
ሁለቱም ወንዶች ሲሆኑ እግዚአብሔር ለመገናኛው ድንኳን ሥራ የጠራቸው ናቸው (ዘጸአት 31፡1-2፤ 31፡6)
እግዚአብሔር ጥበብን በውስጡ እንዳስቀመጠለት የሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን እግዚአብሔር ጥበብ የሰጠው ማለት ነው።
እንዲያደርጉ /እንዲሰሩ/ እግዚአብሔር ባዘዘው መንገድ ወይም ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው
ሁለቱም ወንዶች ሲሆኑ እግዚአብሔር ለመገናኛው ድንኳን ሥራ የጠራቸው ናቸው (ዘጸአት 31፡1-2፤ 31፡6)
እግዚአብሔር ችሎታ የሰጣቸውንና ሥራውን ለመሥራት ፈቃደኛ የሆኑትን ሰዎች ሁሉ
“ልብ” የሰውዬውን ማንነት የሚመለከት ሲሆን ለእግዚአብሔር ሥራ ውስጡ/ልቡ/ፈቃደኛ የሆነ ወይም ለእግዚአብሔር ሥራ ራሱን ያዘጋጀ ወይም ምላሽ የሰጠ ማለት ነው
የመቅደሱን ሥራ የሚሰሩ ጥበበኞች የሆኑ ባለሙያዎች ሥራ ትተው ወደ ሙሴ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘን ሥራ ለመሥራት የሚያስችል በቂና ከበቂ በላይ ስጦታ ህዝቡ እያመጡ ነው ብለው ተናገሩ።
ምዕራፍ 38፡8-10 ካለው ክፍል ጋር አነጻጽር እንዲሁም ምዕራፍ 26፡1-3 ተመልከት።
የማደሪያው ድንኳን መጋረጃዎች በቁጥር አስር ሲሆኑ የተሰሩት ከልብስ ሆኖ አንዱ ከሌላው ጋር በስፌት ተያይዘው በግድግዳው ላይ ይሰቀላሉ።
ከሰማያዊ ጨርቅ የተሰሩ ቀለበቶች
እነዚህ መጋረጃዎች የመገናኛውን ድንኳን ለመከፋፈልና ለመሸፈን የሚረዱ ሰፊና ከባድ የጨርቅ መጋረጃዎች ናቸው
በወል ስም የተጠቀሰው “አደረጉ” የሚለው የሚያመለክተው ባስልኤልና ከእርሱ ጋር የመገናኛውን ድንኳን ሥራ የሚሰሩ ሰዎች ሁሉ የሚዳስስ ነው።
ሀምሳ የወርቅ ቀለበቶችን (ክብ ነገሮችን)
የመጋረጃው ቁጥር 11 መሆኑን ያመለክታል
ይህ የልከት ዘዴ ባህላዊ ሲሆን የአንድ ሰው ከክንድ መጋጠሚያ እስከ መካከለኛው ጣት ደረስ ያለው ክፍል ነው።
ተመሳሳይ ክፍሎችን ምዕራፍ 26፡11 እና 26፡14 ተመልከት።
ምዕራፍ 26፡15-18 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከትና ከዚህኛ ክፍል ትርጉም ጋር አነጻጽር።
በደቡብ በኩል ላለው የማደሪያ ድንኳን ሃያ ወጋግራ (ቋሚዎችን) አደረጉ ወም ሰሩ
ከዚህ ክፍል ጋር ተመሳሳይ የሆነውን ዘጸአት 26፡19-21 ተመልከት።
ለሁለተኛው ክፍል በሰሜን በኩል ወጋግራዎች ነበሩ
ምዕራፍ 26፡22-23 ያለውን ክፍል እንዴት እንደተረጎምክ እይ
በምዕራብ በኩል ባለው
ከኋላ በኩል ባለው ለሁለቱ ማዕዘናት
ምዕራፍ 26፡24-25 ተመልከትና ማስተካከያ አድርግ
ዘጸአት 26፡26-28 እና 26፡29 ተመልከት
ለመገናኛው ድንኳን ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ መውሰድ ወይም ማሳለፍ
መቆሚያዎች ከነሐስ ብረት የተሰሩ ስለመሆናቸው የሚናገር ነው። ምዕራፍ 26፡36-37 አነጻጽር።
1 ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱ አንድ ተኩል ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦታ ከግራር ዕንጨት ሠራ። 2 ውስጡንና ውጩንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት። 3 ለአራት እግሮቹም አራት የወርቅ ቀለበቶችን፣ በአንዱ ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን፣ በሌላውም ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን ጨምሮ ሠራ። 4 ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 5 ታቦቱን ለመሸከም በታቦቱ ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አስገባቸው። 6 ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። 7 ባስልኤል ለስርየት መክደኛው ሁለት ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ አበጀ። 8 አንዱ ኪሩብ ለአንዱ የስርየት መክደኛ፣ ሌላውም ለሌላው የስርየት መክደኛ ጫፍ ነበረ። ኪሩቤል ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው ተበጅተው ነበር። 9 ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት የስርየት መክደኛውን በድንፎቻቸው ጋረዱት። እርስ በርስ ትይዩ ሆነውም ወደ ስርየት መክደኛው መካከል ይመለከቱ ነበር። 10 ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሠራ። 11 ወርቅ ለበጠው፤ ዙሪያውንም በንጹሕ ወርቅ ከፈፈው። 12 አንድ ስንዝር ጠርዝ ከወርቅ ክፈፍ ጋር አበጀለት። 13 የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርቶ የጠረጴዛው እግሮች ካሉበት ማእዘኖች ጋር አያያዛቸው። 14 ለመሸከም መሎጊያዎችን ማስገባት እንዲቻል ቀለበቶቹ ከጠርዙ ጋር ተያይዘው ነበር። 15 ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 16 በጠረጴዛው ላይ የሚቀመጡ ዕቃዎችን፦ ድስቶችን፣ ዝርግና ጎድጓዳ ሳሕኖችን ጭልፋዎችን፣ ወጭቶችንና የመጠጥ መሥዋዕቱን ማፍሰሻ ማንቆርቆሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። 17 ከነማቆሚያውና ከነዘንጉ ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ ሠራ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ በሙሉ ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ነበር የተሠሩት። 18 ቅርንጫፎች በመቅረዙ አንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፎች ደግሞ በሌላው የመቅረዙ ጎን ተሠርተው ስድስት ቅርንጫፎች ነበር። 19 ቅርንጫፍ ከቀንበጥና ክአበባ ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ነበሩት፤ በሌላውም ቅርንጫፍ እንደዚሁ የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ነበር። ከመቅረዙ ለሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር። 20 በመቅረዙ መካከል ላይ ባለው ዘንግ ላይ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ እራት ጽዋዎች ከቀንበጦቻቸውና ከአበቦቻቸው ጋር ተሠርተዋል። 21 በመጀመሪያ የቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮት የተሠሩ ቀንበጦች ነበር። ከመቅረዙ በሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር። 22 ቅርንጫፎቻቸው ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበር። 23 መቅረዙንና ሰባቱን መብራቶች፣ መኮስተሪያዎቹንና የኵስታሪ ማስቀመጫዎቻቸውን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። 24 መቅረዙንና ዐባሪ ዕቃዎቹን ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠራቸው። 25 እርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ የሆነውን የዕጣኑን መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። አራት ማእዘንና ቁመቱም ሁለት ክንድ ነበር። ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበር። 26 የዕጣኑን መሠዊያ፦ ዐናቱን፣ ጎኖቹንና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጣቸው። ለዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት። 27 በሁለቱ ተነጻጻሪ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ ሥር እንዲያያይዙት ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ። ቀለበቶቹ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎችን ለመያዝ የሚያገለግሉ ናቸው። 28 ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 29 የተቀሰውን የመቅቢያ ዘይትና የሽቶ ቀማሚ ሥራ የሆነውን፣ ንጹሕና ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን ሠራ።
ርዝመቱ 1.1 ሜትር፤ ስፋቱና ከፍታው 0.7 ሜትር ያህል ነው
እነዚህ እግሮች እንደሰው ወይም እንስሳ እግር የተቆጠሩ ሲሆን ታቦቱን የሚሸከሙ ወይም የሚደግፉ ናቸው።
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶችንና ሌሎችን በሚመለከት ዘጸአት 25፡13-14፥ 17 ተመልከት።
የሠራው መሪ ባስልኤል በመሆኑ ሥራውን ብቻውን እንደሠራ አድርጎ ያቀርባል ነገር ግን ሥራው የተከናወነው ከሥራ ባልደረቦቹ ጭምር ነብር።
አንድ ክንድ በሜትር ሲለካ ከ46-50 ሳንቲ ሜትር ሲሆን ወደ ሜትር ሲቀየር 115 ሴ.ሜትር እና 70 ሳ.ሜ ያህል ነው።
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው የሥርየት መክደኛው አሠራር በሚመለከት (37፡7-9) ዘጸአት 25፡18-20 ያለውን ክፍል እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት።
እርሱ እነዚህን አንድ አድርጎ ሠራቸው
የክሩቤል ምስሎችን እውነተኛ ክሩቤል በማስመሰል ክንፎቻቸውን ዘርግተው አንዱ ከሌላው ጋር ተገናኝተውና የስርየት መደኛውን ሸፍነው እንዲቀመጡ አደረጋቸው። አማራጭ ትርጉም፦ ባስልኤል እነዚህን ክንፍ ያላቸውን ፍጥረታት የአንዱ ክንፍ ከሌላው ጋር እንድገናኙ አድርጎና ክንፎቻቸውን የዘረጉ እንዲሆኑ አድርጎ ሠራቸው።
የክሩቤል ዓይኖች አንዱ ሌላውን እንዲመለከቱ ተደርገው የተሰሩ ናቸው
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው ምዕራፍ 37፡10-13 ያለውን ክፍል ከምዕራፍ 25፡23-26 ካለው ክፍል ጋር በማነጻጸር በተገቢው መንገድ ለመተርጎም ሞክር።
ርዝመቱ 92 ሴ.ሜትር፤ ወርዱ 46 ሴ.ሜትር እና ቁመቱ 69 ሴ.ሜትር ያህል ነበር
በባህላዊው ልከት አንድ ጋት የአራት ጣቶች ጥምር ማለት ሲሆን ከ8-10 ሳ.ሜትር ነው።
እነዚህ እግሮች እንደሰው ወይም እንስሳ እግር የተቆጠሩ ሲሆን ታቦቱን የሚሸከሙ ወይም የሚደግፉ ናቸው።
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው ምዕራፍ 37፡14-16 ያለውን ክፍል ከምዕራፍ 25፡27-29 ካለው ጋር በማነጻጸር ተገቢውን የትርጉም ሂደት በመከተል መልዕክቱን ተርጉም።
“ቀለበቶች ከክፈፉ ጋር ተያይዘው ተሰሩ ወይም ቀለበቶችን ከክፈፉ ጋር አያይዘው ሰሩ”
ዝርግ ሳህኖችን፥ ድስቶችን፥ ጎድጓዳ ሳህኖችን (ውሃ መያዣዎችን) እና ማንቆርቆሪያዎችን . . .
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው ምዕራፍ 37፡17-19 ያለውን ክፍል ከምዕራፍ 25፡31-33 ካለው ጋር በማነጻጸር ተገቢውን የትርጉም ሂደት በመከተል መልዕክቱን ለመተርጉም ሞክር።
የአበባ ቅርጽ ያላቸው ጽዋዎችን፥ እንቡጦችንና የፈኩ አበቦችን አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው
ከእንቡጦችና ከፈኩ አበቦች ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሶስት ጽዋዎች
ነጭ ወይም ሮዝ መልክ ያለው የለውዝ አበባ በለውዝ ዘፍ ላይ ያደገ የሚመስል ነበር
በዚህ ክፍል ያሉ ቃላትና ዕቃዎችን እንዴት እንደተርጎምክ በምዕራፍ 25፡34-36 ተመልከት።
በመቅረዙ ላይ እንቡጦችና አበቦች አደረገ
የለውዝ አበባ የሚመስሉ አራት ጽዋዎች ወይም ስኒዎች አደርገ ወይም ሰራ
ከመቅረዙ ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሰሩ እንቡጦች
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው በዚህ ክፍል የተጠቀሱ ቃላትና ቁሶችን እንዴት እንደተረጎምክ በ25፡37-39 ላይ ተመልከት
እነዚህ መኮስተሪያዎች ሁለት ሆነው ከብረት ወይም ከእንጨት የተሰሩ ሲሆን በአንድ በኩል የተያያዙ ናቸው፥ ዕቃዎችን ቆንጥጦ ለመያዝና ለማውጣት የሚያገለግሉ እንደ መቆንጠጫ ያሉ ናቸው።
x
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው የዚህን ክፍል (37፡25-26) ትርጉም ከምዕራፍ 30፡1-3 ካለው ጋር አነጻጽር
ቀንዶቹ ከመሰዊያው ጋር በአንድ ላይ ተያይዘው የተሰሩ ናቸው
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የማደሪያውን ድንኳንና በውስጡ የሚገኙ ሥራዎችን ስለመሥራታቸው የዚህን ክፍል (37፡27-28) ትርጉም ከምዕራፍ 30፡4-5 ካለው ጋር አነጻጽር
የሽቱ ቀማሚ ሥራ የሆነውን ንጹህና መልካም መዓዛያለውን ዕጣን
1 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። ዐምስት ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ስፋት፣ አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ቁመት ነበረው። 2 ማእዘኖችም የበሬ ቀንዶችን የሚመስሉ ቅርጾችን በመሥራት አስረዘማቸው። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ መሠዊያውንም በነሐስ ለበጠው። 3 ለመሠዊያው የሚያስፈልገውን ዕቃ ሁሉ፦ ለዐመድ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን በሙሉ ከነሐስ ሠራ። 4 ከደረጃው ሥር ከመሠዊያው እኩሌታ እስከ ታች የሚደርስ እንደ መረብ የተሠራ የነሐስ ፍርግርግ ለመሠዊያው አበጀ። 5 ፍርግርግ አራት ማእዘኖች ለመሎጊያዎቹ መያዣ አራት ቀለበቶችን ሠራላቸው። 6 ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በነሐስ ለበጣቸው። 7 መሎጊያዎቹን መሠዊያውን ለመሸከም በመሠዊያው ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። መሠዊያውን ክፍት አድርጎ በሳንቃዎች ሠራው። 8 ባስልኤል ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን ከነሐስ መቆሚያ ጋር ሠራ። ሳሕኑን የሠራውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ የሚያገለግሉት ሴቶች ይጠቀሙባቸው ከነበሩ መስተዋቶች ነው። 9 ሠራው። በአደባባዩ ደቡብ ጎን ላይ የነበሩት መጋረጃዎች ከአማረ በፍታ የተሠሩና አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው ነበሩ። 10 መጋረጃዎቹ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ መቆሚያዎች ነበሯቸው። ከምሰሶዎቹና ከብር ዘንጎቹ ጋር የተያያዙ ኵላቦችም ነበሩ። 11 ጎን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎችና ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች፣ ከምሰሶዎቹ ጋር ከተያያዙ ኲላቦችና ከብር ዘንጎች ጋር ነበር። 12 የምዕራቡ ጎን መጋረጃዎች ዐምሳ ክንድ የሚረዝሙ፣ ዐሥር ምሰስዎችና መቆሚያዎች ያሏቸው ነበሩ። የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎች ብር ነበሩ። 13 አደባባዩም በምሥራቁ ጎን ላይ ዐምሳ ክንድ ይረዝም ነበር። 14 የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች እርዝመት ዐሥራ ዐምስት ክንድ ነበረ። ሦስት ምሰሶዎች ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ነበሯቸው። 15 በአደባባዩ መግቢያ ሌላ ጎን ላይም ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሚረዝሙና ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው መጋረጃዎች ነበሩ። 16 በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች ሁሉ አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ ነበሩ። 17 የምሰሶዎቹ መቆሚያዎች ከነሐስ፣ የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎቻቸው፣ የዐናታቸውም መሸፈኛ ከብር የተሠሩ ነበሩ። የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ በብር የተለበጡ ነበር። 18 የአደባባዩ በር መጋረጃቅ እርዝመት ሃያ ክንድ ነበረ። ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠራ ነበረ። እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች ሃያ ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ቁመት ነበረው። 19 የነሐስ መቆሚያዎችና የብር ኵላቦች ነበሩት። የዐናታቸው መሸፈኛና ዘንጎቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ። 20 የመገናኛው ድንኳን ካስማዎች ሁሉ የተሠሩት ከነሐስ ነበር። 21 የሙሴን ትእዛዝ በመከተል በተመዘገበው መሠረት የመገናኛው ድንኳን፣ ይኸውም የምስክሩ ድንኳኝ ቆጠራ ይህ ነው። በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር መሪነት ይህ የሌዋውያኑ ሥራ ነበረ። 22 ከይሁዳ ነገድ የሆነው፣ የሖር የልጅ ልጅ፣ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ ፈጸመ። 23 ከባስልኤልም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ቅርጽ አውጪ ሠራተኛ፣ የእጅ ጥበብ ሙያተኛ፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ግምጃና በአማረ በፍታ ጥልፍ ጠላፊም ሆኖ ዐብሮት ሠራ። 24 ከመቅደሱ ሥራ ጋር ለተያያዘው ተግባር ሁሉ ጥቅም ላይ የዋለው ወርቅ ማለትም፣ ከስጦታው የተገኘው ወርቅ ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል መጠን መሠረት ሃያ ዘጠኝ መክሊትና ሰባት መቶ ሠላሳ ሰቅል ነበረ። 25 ማኅበረ ሰቡ የሰጠው ብር በመቅደሱ ሰቅል መጠን ተመዝኖ አንድ መቶ መክሊትና አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰባ ዐምስት ሰቅል፣ 26 በአንድ ሰው አንድ ቤካ ይኸውም በመቅደሱ ሰቅል መጠን ግማሽ ሰቅል ነበረ። ይህ ቍጥር የተደረሰበት በሕዝብ ቆጠራው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆናቸው ተቆጥረው በተገኘው ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ወንዶች ቍጥር በያንዳንዱ ሰው ተሰልቶ ነው። 27 የመቅደሱንና የመጋረጃዎችን መቆሚያዎች ለመሥራት አንድ መቶ የብር መክሊት ወጪ ሆኖአል፦ መቆሚያዎቹ በጠቅላላ አንድ መቶ ሆነው፣ ለያንዳንዱ መቆሚያ አንድ መክሊት ተከፍሎአል ማለት ነው። 28 በቀሩት አንድ ሺሕ ሰባቶ መቶ ሰባ ዐምስት የብር ሰቅሎች ባስልኤል የምሰሶዎቹን ኵላቦች ሠርቶ ዐናታቸውን ሸፈነባቸው፤ ዘንጎችንም ለምሰሶዎቹ ሠራባቸው። 29 ከስጦታ የተገኘው ነሐስ ተመዝኖ ሰባ ታለንትና ሁለት ሺሕ አራት መቶ ሰቅል ሆነ። 30 በዚህም የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የነሐስ መሠዊያውን፣ የእርሱንም የነሐስ ፍርግርግ፣ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ፣ 31 የአደባባዩን መቆሚያዎች፣ የአደባባዩን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የመገናኛውን ድንኳንና የአደባባዩን ድንኳን ካስሞች ሁሉ ሠራበት።
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የመገናኛውን ድንኳንና የውስጡን ቁሳቁስ ሥራ ይቀጥላሉ።
የእነዚህ ዕቃዎች ዝርዝርና ፍቺያቸውን እንዴት እንደተረጎምክ ዘጸአት 27፡1-3 ካለው ክፍል ጋር አነጻጽር።
ርዝመቱ 2.30 ሜትር፥ ስፋቱ 2̄.30 ሜትር እና ቁመቱ 1.38 ሜትር ነበር
ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የመገናኛውን ድንኳንና የውስጡን ቁሳቁስ ሥራ ይቀጥላሉ። ምዕራፍ 38፡4-5 ያለውን ክፍል ለመተርጎም ምዕራፍ 27፡4-5 ያለውን ክፍል እንዴት እንደተረጎምክ አነጻጽር።
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የመገናኛውን ድንኳንና የውስጡን ቁሳቁስ ሥራ ይቀጥላሉ
መሠዊያው ከሳንቃ (ጠፍጣፋ የሆነ) የተሠራ ሆኖ ውስጡ ክፍት ነበር (ዘጸአት 27፡7-8 ተመልከት)
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የመገናኛውን ድንኳንና የውስጡን ቁሳቁስ ሥራ ይቀጥላሉ
“መቀመጭው” የመታጠቢያው ሳህን የሚቀመጥበት ነው። አማራጭ ትርጉም፦ “የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን ጭምር ከነሐስ ሠራ” ዘጸአት 30፡18 ተመልከት።
የነሐስ ብረቱ ከመስተዋት የተገኘ (የመጣ) ነበር። የመታጠቢያ ሳህኑ የተሰራው ከመስተዋት ነበር። ይህ መስተዋት ሴቶች ካመጡት የነሐስ መስተዋቶች የተሰራ ነበር።
አንጻባራቂና ሰዎች ፊታቸውን ወይም ሌሎችን ነገሮች ለማየት የሚጠቀሙት የብረት ቁራጭ ነው
ባስልኤልና የሥራ ጓደኞቹ የመገናኛውን ድንኳንና የውስጡን ቁሳቁስ ሥራ ይቀጥላሉ
ይህን ክፍል ለመተርጎም ይረዳህ ዘንድ ዘጸአት ምዕራፍ 27፡9-10 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት
ርዝመቱ 46 ሜትር ወይም 4600 ሴ. ሜትር የሆነ
ይህን ክፍል ለመተርጎም ይረዳህ ዘንድ ዘጸአት ምዕራፍ 27፡11-12 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት
46 ሜትር ርዝመት . . . 23 ሜትር ርዝመት
ይህን ክፍል ለመተርጎም ይረዳህ ዘንድ ዘጸአት ምዕራፍ 27፡13-16 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት። የመግቢያው ደጅ ባለበት በምሥራቅ በኩልና በድንኳኑ መግቢያ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች።
ባስልኤልና ሌሎች የሥራ ባልደረቦቹ መጋረጃዎችን ከጥሩ በፍታ (ሐር) ሰርተውት ነበር።
ይህን ክፍል ለመተርጎም ይረዳህ ዘንድ ዘጸአት ምዕራፍ 27፡16-19 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት።
ባስልኤልና የሥራ ባልደረቦቹ የምሰሶዎቹ እግሮች የሠረኡትከነሐስ ብረት ነበር።
ባስልኤልና የሥራ ባልደረቦቹ /ጓደኞቹ/ ጫፎቻቸውንና ዘንጎቻቸውን ከብር ሠርተውት ነበሩ
ባስልኤልና የሥራ ባልደረቦቹ የማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉ ቁሶችን ቀጥለው ሠሩ
በኢታማር መሪነት በሌዋውያን ሀላፊነት የተቆጠረሩ የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች ዝርዝር ቈጠራ ይህ ነው
እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ያዘዛቸውን ነገሮች ሁሉ ሠሩ።
እነዚህ የወንዶች ስም ዝርዝር ነው
እነዚህ የወንዶች ስም ዝርዝር ነው
አንጥረኛ (የእጅ ጥበብ ባለሙያ) እና ፕላን (ዕቅድ) አውጪ ባለሞያ
ሰዎች ለሥራው የሠጡት ወርቅ በሙሉ
አንድ መክሊት 33 ኪሎ ግራም ሲሆን 29 መክሊት 960 ኪሎ ግራም ወርቅ እና አንድ ሰቅል 3.3 ክሎ ግራም ሲሆን 100 ሰቅል 330 ኪሎ ግራም ይሆናል። በጠቅላላው የወርቁ ቁጥር 1290 ኪሎ ግራም ወርቅ ነበር።
በጠቅልላው 1775 ሰቅል ወይም 5858 ኪሎ ግራም ብር ነበር
አንድ ሰቅል 11 ግራም ሲሆን የሰቅል ግማሽ 5.5 ግራም ይሆናል።
ይህ የሰቅል ግማሽ የተሰበሰበው ዕድሜያቸው 20 አመት የሆናቸው፥ በቆጠራው የተካተቱና ግማሽ ሰቅል (አንድ ቤካ) መስጠት የሚገባቸው ሰዎች ቁጥር ማለት ነው።
የቤተመቅደስ የሰቅል ሚዛን ደረጃውን የጠበቀ ስለሆነ “በተቀደሰ ሚዛን፤ በታወቀው ሚዛን” ይባላል።
3300 ኪሎ ግራም የሚመዝን ብር
ወደ 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን
በጠቅላላው 2300 ክሎ ግራም የሚመዝን የነሐስ ብረት ነበር
ከነሐስ ብረት የተሰራ ሲሆን እንጨት በእሳት ሲቃጠል ለመያዝ የሚያገለግል (ዘጸአት 27፡4 ተመልከት)
ከእንጨት ወይም ከብረት የተሰሩ የድንኳን ጠርዞችን ወይም ማዕዘኖችን ለመወጠር የሚያገለግሉ ናቸው (ዘጸአት 27፡19 ተመልከት)
1 በመቅደሱ ውስጥ ለሚከናወነው አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተሠሩ ልብሶችን አበጁ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለቤተ መቅደሱ የሚሆኑ የአሮንን ልብሶች ሠሩ። 2 ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሠራ። 3 ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በአማረ በፍታ ለመ|ሥራት ወርቁን ቀጥቅጠው ወደ ሽቦነት ቆራረጡት። 4 የትከሻ ንጣዮችን ሠርተው ከላይኛዎቹ ጠርዞቹ ጋር አያያዙት። 5 በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉዱ ሲሆን፣ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፣ አምሮ ከተፈተለ በፍታ ይኸውም ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከኤፉድ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ። 6 የመረግድ ድንጋዮችን በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ አበጁላቸው፤ እንደ ማኅተምም የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቀረጹባቸው። 7 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ ባስልኤል በሴፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች አድርጎ አስቀመጣቸው። 8 ኪሱንም ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ እንደ ኤፉዱ አበጀው። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከአማረ በፍታ ሠራው። 9 ኪሱ አራት ማእዘን ነበረ። ርዝመቱም ወርዱም አንድ ስንዝር ሆኖ የተደረበ ዕጥፍ ነበረ። 10 በውስጡም አራት የዕንቍ ድንጋዮች ፈድፎች አበጅተዋል። በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮንና አብራቅራቂ ዕንቍ ነበሩት። 11 ረድፍ በሉር፣ ሰንፔር፣ አልማዝ፤ 12 በሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶን፣ አሜቴስጢኖስ፤ 13 በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ነበሩ። ድንጋዮቹ በወርቅ ፈርጥ ዙሪያቸውን የተከፈፉ ነበር። 14 እያንዳንዳቸው በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት የተቀመጡ ነበር። እያንዳንዱ ስም ከዐሥራ ሁለቱ ነገዶች አንዱን በመወከል በማተሚያ ቀለበት ላይ እንደሚቀረጽ የተቀረጸባቸው ነበሩ። 15 ኪሱ ላይ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አበጁ። 16 ሁለት የወርቅ ፈርጦችንና ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ሁለቱን ቀለበቶች ከደረት ኪሱ ሁለት ጠርዞች ጋር አያያዟቸው። 17 ሁለቱን የተጎነጎኑ የወርቅ ድሪዎች በደረት ኪሱ ጠርዞች ሁለት ቀለበቶች ውስጥ አስቀመጧቸው። 18 ሌሎች ሁለት ጫፎች ከሁለት ፈርጦች ጋር አያያዟቸው። ከኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ጋር በኤፉዱ ፊት አገናኗቸው። 19 የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከውስጠኛው ጠርዝ ቀጥሎ በሚገኘው ጎን በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጠርዞች ላይ አስቀመጧቸው። 20 ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው፣ በመያዣው አጠገብ በብልኀት ከተሠራው የወገብ መታጠቂያ በላይ፣ ከአፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያያዟቸው። 21 በብልኀት ከተሠራው ከኤፉዱ የወገብ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችል፣ የደረት ኪሱን በራሱ ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ፈትል አሰሩት። ይህ የሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ የተነጠለ እንዳይሆን ነው። የተደረገውም እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው። 22 የኤፉዱን ቀሚስ ሙሉ በሙሉ የሸማኔ ሥራ ከሆነው ከሐምራዊ ጨርቅ ሠራው። 23 መካከሉ ላይ ዐንገት ማስገቢያ ነበረው። እንዳይቀደድም ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ነበረው። 24 በታችኛው የቀሚሱ ዘርፍ ላይም የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ማግና የአማረ በፍታ ሮማኖችን አበጁ። 25 ሻኵራዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በታችኛው የቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ላይ በሮማኖቹም መካከል፣ 26 አገልግሎት በቀሚሱ ጠርዝ ላይ ሻኵራን ሮማን፣ ሻኵራና ሮማን እያደረጉ አስቀመጧቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው። 27 ለአሮንና ለልጆቹ ሸሚዞችን ከአማረ በፍታ ሠሩ። 28 የራስ መጠምጠሚያዎችን፣ ቆቦችንና ሱሪዎችን ከአማረ በፍታ፣ 29 መታጠቂያዎችንም ከአማረ በፍታ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ጥልፍ ጠላፊ እንደሚሠራው አድርገው አበጇቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው። 30 አክሊል ሠሌዳ ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ በላዩ ቅዱስ ለእግዚአብሔርን ቀረጹበት። 31 እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ በመጠምጠሚያው ዐናት ላይ ለማንጠልጠል ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት። 32 ድንኳን፣ የማደሪያው ሥራ ተጠናቀቀ። የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጣቸውን መመሪያዎች በመከተል ሁሉንም አደረጉ። 33 ድንኳኑንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ ካስማዎቹን፣ ወጋግራዎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ምሰሶዎቹንና መቆሚያዎቹን፣ 34 በቀይ ቀለም የተነከረውን የአውራ በግ ቆዳ መሸፈኛ፣ የአስቆጣ ቆዳዊን መሸፈኛና የሚሸፍነውን መጋረጃ፣ 35 የምስክሩን ታቦት፣ መሎጊያዎቹንና የስርየት መክደኛውን ወደ ሙሴ አመጡ። 36 ጠረጴዛውን፣ የጠረጴዛውን ዕቃዎች ሁሉና የገጽ ኅብስቱን፤ 37 የንጹሑን ወርቅ መቅረዝና የረድፍ መብራቶችን ከዐባሪ ዕቃዎቹና ከመብራቶቹ ዘይት ጋር፤ 38 መሥዐዊያውን፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዐዛ ያለን ዕጣን፣ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃ፤ 39 የነሐስ መሠዊያውን ከነሐስ ፍርግርጉና ከመሎጊያዎቹ፣ ከዕቃዎቹ፣ ከትልቁ የመታጠቢያ ሳሕንና ከመቆሚያው ጋር አመጡ። 40 የአደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመቆሚያዎቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃም፣ ገመዶቹንና የድንኳን ካስማዎችን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውለውን ዕቃ ሁሉ አመጡ። 41 አገልግሎት በጥበብ የተሠሩትን ልብሶች፣ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም አመጡ። 42 ስለዚህም የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሥራውን በሙሉ አከናወኑ። 43 ሙሴ ሥራውን ሁሉ ሲፈትሽ፣ እነሆ ሁሉን አከናውነውታል። ያከናወኑትም እግዚአብሔር አዝዞት በነበረው በዚያው መንገድ ነው። ሙሴም ሕዝቡን ባረካቸው።
“አደረጉ” የሚለው ቃል ባስልኤል፥ ኤልያብና ማናቸውንም ሥራ ለመሥራት ችሎታንና ዕውቀትን የሰጣቸው ሌሎች ሰዎች ማለት ነው
እነዚህ ሰዎች ሥራውን የሰሩት እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነው ማለት ነው።
በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
ይህ የሰው ስም ነው፤ ልንጽጽር ዘጸአት 31፡1-2 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት
በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
ለኤፉዱም ማንገቻ በትከሻ ላይ የሚወርዱ ሁለት ማንጠልጠያ ሠርተው ጐንና ጐኑ እንዲያያዙ አደረጉ
እነዚህ ሰዎች ሥራውን የሰሩት እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነው ማለት ነው። ቁጥር 1 ተመልከት።
በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
የመረግድ ድንጋዮችን ወስደው የወርቅ ፈርጥ ቅርጽ በድንጋዩ ላይ ቀርጸው እንደ ማለት ነው
በ12ቱ (በእስራ ሁለቱ) የእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ከድንጋይ የተቀረጸ
በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
አዲሱ አማርኛ እና መደበኛው አማርኛው ትርጉም “ሠሩት” ብሎ በወል ስም ይጠቅሳሉ። የዕብራይስጡ ቅጅ፥ የቀድሞ አማርኛ ቅጅና ለሎች ተአማኒነት ያላቸው ቅጅዎች “አደረገው” ይላሉ። “ሠሩት” በሚል የተረጎሙት ትኩረታቸው ባስልኤል፥ ኤልያብና ሌሎች ሰዎችን ታሳቢ በማድረግ ነው። “አደረገው” በሚል የተረጎሙት ትኩረታቸው የሥራው ዋና መሪ ባስልኤል ስለሆነ ትኩረታቸው በእርሱ ላይ ነው። የዕብራይስጡ ቅጅ ትኩረቱ በባስልኤል ላይ ስለሆነ “እርሱ አደረገው” የሚል ነው። ስለሆነም አደረገው የሚለው ትክክለኛ ትርጉም ነው።
በዘመናዊ የርቀት መለኪያ ከ20-22 ሴንቲ ሜትር ያህል ነው።
በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
ሠራተኞች የከበሩ ድንጋዮችን በተነገራቸው መሰረት በአራት ረድፍ አደርገው ሰሩት
የአነዚህን ድንጋዮች ስም ዝርዝር በየቋንቋው ለማግኘት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ዕንቁ የተባሉት “የከበሩ ወይም ውድ” የድንጋይ ዓይነቶች መሆናቸውና አንዱ ከሌላው የተለየ መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ስለሆነም በትርጉም ወቅት ተውሶ ወይም ባዕድ ቃላትን በመጠቀም ትርጉሙን ግልጽ ማድረግ ይቻላል።
እነዚህን የከበሩ ወይም ውድ ድንጋዮችን በወርቅ ፈርጥ ወይም በተቀረጸው ወርቅ ላይ አስቀመጡ
በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
ከንጹህ ወረቅ የተሰሩ የወርቅ ሰንሰለት ወይም ገመድ መሳይ
በምዕራፍ 28፡26-27 በተጠቀሰው መሰረት በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
ለማያያዣነት የሚያገለግሉ የወርቅ ቀለበቶች ወይም ክብ ነገር
ከጨርቅ ወይም ከጨርቅ ክር የተሰራ የወገብ መታጠቂያ ወይም ቀበቶ ሲሆን የእጄ ጥበብ ባለሙያ የሰራው ዓይነት ማለት ነው
በምዕራፍ 28፡28 በተጠቀሰው መሰረት በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
ከኤፉዱ እንዳይላቀቅ የሚያደርግ ወይም በጥብቅ እንዲተሳሰር የሚያደርግ
በምዕራፍ 28፡31-33 በተጠቀሰው መሰረት በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
ይህ የሰው ስም ነው፤ ልንጽጽር ዘጸአት 31፡1-2 ላይ ስሞችን እንዴት እንደምትተረጉም አስተውል
በምዕራፍ 28፡34-35 ላይ በተሰጠው መመሪያ መሰረት በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
ከጥሩ ወርቅ ጸናጽሎችን ወይም ትናንሽ ድምጽ የሚሰጡ ቁርጥራጭ ነገሮችን ማለት ነው።
በአገልግሎት ወቅት እንዲለብሱ ጸናጽሎችንና ሮማን ፍሬ መሳይ ስዕሎችን በቀሚሱ ጠርዝ ወይም ጫፍ ዙሪያ አደረጉ
በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
እንደነዚህ ያሉትን ክፍሎች በ28፡39-40 እና 42 ላይ ያለውን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት።
ወንዶች ራሳቸውን የሚሸፍኑበት ከጨርቅ የተሰራ ራስ ጥምጥም
ከሌሎች ልብሶች ቀደም ተብሎ የሚለበስ የውስጥ ሱሪ ማለት ነው፥ (የጋራ መረዳትና ያልተገለጹ ሀሳቦች እንዴት እንተረጉማለን የሚለውን ተመልከት)
በትከሻ ወይም አንገትጌ ላይ የሚለበስና እንዲሁም በወገብ ላይ የሚለበስ የወገብ መታጠቂያ ነው።
በምዕራፍ 28፡36-37 ላይ በተሰጠው መመሪያ መሰረት በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ካህናት ልብሶች ዝግጅት ይቀጥላል
ከንጹህ ወርቅ በራስ ላይ የሚደረግ ቆብ መሳይ ነገር
በምዕራፍ 35፡4-9 እና 35፡10-12 ላይ በተሰጠው መመሪያ መሰረት እስራኤላውያን የተሰጣቸውን ሥራ ሲጨርሱ ያሳየናል።
ይህ በተደራጊ ግስ የተገለጸው ዐረፍተ ነገር “የእስራኤል ልጆች የመገናኛውን ድንኳን ሥራውን ሁሉ ጨረሱ” በሚለው ልተረጎም ይችላል። “የመገናኛው ድንኳን የማደሪያውም” የሚሉ ቃላት ሁለቱም ስለአንድ ነገር የሚያወሩ ናቸው።
የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሰረት የተሰራውን የመገናኛውን ድንኳን ወደ ሙሴ አመጡ ማለት ነው።
መጋረጃዎችን በአንድ ለማያያዝ የሚጠቅሙ ነገሮች ወይም አቃፊዎች ናቸው። ዘጸአት 26፡4-6 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት።
ምሶሶዎች የሚቆሙባቸው እግሮች ማለት ነው።
ከታቦቱ ላይ የሚቀመጥ መሸፈፍኛ ወይም መክደኛ ሲሆን የስርየት መስዋዕት የሚቀርብበትም ጭምር ነው።
በባስልኤልና በሥሩ ያሉ የሥራ ቡድኖች ማደሪያውንና መገናኛ ድንኳኑን ለሙሴ ሲያቀርቡ እናያለን።
ህልዎተ እግዚአብሔር መገለጫ የሆነው ዳቦ ነው። በመገናኛው ድንኳን ወይም በማደሪያው ውስጥ የእግዚአብሔር መኖር ምልክት የሆነው ዳቦ ነው። ከተራ ዳቦ የተለየ መሆኑን ለማመልከት በአማርኛ ኅብስት ተብሏል። ዘጸአት 25፡30 ተመልከት
እንጨት በእሳት ሲነድ በአንድ በኩል እንጨቱን ለመያዝ የሚያገለግል ከነሐስ ብረት የተሰራ ዘንግ ማለት ነው።
በባስልኤልና በሥሩ ያሉ የሥራ ቡድኖች ማደሪያውንና መገናኛ ድንኳኑን ለሙሴ ሲያቀርቡ እናያለን።
ሥራውን በሀላፊነት የሚመራው ባስልኤልና የእርሱ ቡድን ይሁን እንጂ እስራኤላውያንም በሥራው ላይ ተሳታፊ ነበሩ።
በትክክልና በታዘዙት መሰረት ሰርተውት ነበር።
1 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2 “በዐዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ወር የመጀመሪያ ቀን ማደረያውን፣ የመገናኛውን ድንኳን ትከለው። 3 ታቦት በውስጡ አስቀምጠው፤ ታቦቱንም በመጋረጃ ከልለው። 4 ጠረጴዛውንም ወደ ውስጥ አምጣና በላዩ የሚቀመጡትን ዕቃዎች በሥርዐት አስቀምጥ። ከዚያም መቅረዙን አስገብተህ መብራቶቹን አስተካክል። 5 የወርቅ የዕጣን መሠዊያውን በምስክሩ ታቦት ፊት አስቀምጥ፤ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃም አድርግ። 6 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት አስቀምጥ። 7 ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠው፤ ውሀም አድርግበት። 8 በዙሪያውም አደባባይ ሥራለትን በአደባባዩ መግቢያ ላይ መጋረጃውን ስቀል። 9 መቅቢያ ዘይቱን ውሰድና መገናኛውን ድንኳንና አውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ቅባ። እርሱንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም የተቀደሰ ይሆናል። 10 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያና የመሠዊያውን ዕቃዎች ሁሉ ቅባቸው። 11 መሠዊያውን ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም ለእኔ እጅግ የተቀደሰ ይሆንልኛል። 12 ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ አምጣና በውሀ እጠባቸው። 13 ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን ለአሮን አልብሰው፤ ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግልም ቅባው፤ ቀድሰውም። 14 ልጆቹንም አምጣና ሸሚዞችን አልብሳቸው። 15 ካህናቴ ሆነው እንዲያገለግሉኝ፣ አባታቸውን እንደ ቀባኸው እነርሱንም ቅጣቸው። የእነርሱ መቀባት በትውልዶች ሁሉ የዘለቄታ ካህንነትን ለእነርሱ ያስገኛል።” 16 ሙሴ ያደረገው ይህ ነው፦ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ተከተለ። እነዚህንም ሁሉ አደረገ። 17 በሁለተኛው ዓመት የመጀመሪያ ወር አንደኛ ቀን ላይ የመገናኛው ድንኳን ተተከለ። 18 ሙሴ መገናኛውን ድንኳን ተከለ፤ መቆሚያዎቹንም በስፍራቸው አስቀመጠ፤ ወጋግራዎቹን አቁሞ አግዳሚዎቹን አያያዘ፤ ምሰሶዎቹንም አቆመ። 19 በማደሪያው ላይ መሸፈኛውን ዘረጋ፤ ድንኳኑንም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ከበላዩ አስቀመጠው። 20 ምስክሩን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጠው። 21 ወደ መገናኛው ድንኳን አመጣው። እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ የምስክሩን ታቦት ለመከለል መጋረጃውን አደረገ። 22 ሰሜን ጎን ከመጋረጃው ውጭ ጠረጴዛውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ። 23 እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው፣ ኅብስቱን በጠረጴዛው ላይ በሥርዐት በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጠው። 24 መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ደቡብ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ በማደሪያው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠው። 25 መብራቶቹን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእግዚአብሔር ፊት አበራቸው። 26 የተሠራውን የዕጣን መሠዊያም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ፊት ለፊት አደረገው። 27 ላይም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን አቀጣጠለ። 28 መጋረጃውን በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሰቀለ። 29 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ አስቀመጠ። በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን እግዚአብሔር እንዳዘዘው አቀረበ። 30 የመታጠቢያ ሳሕኑን በመገናኛው ድንኳንና በመሠውያው መካከል አኖረው፤ የመታጠቢያ ውሀም በውስጡ አደረገ። 31 ሙሴ፣ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በመታጠቢያው ውሀ ይታጠቡ ነበር፤ 32 መገናኛው ድንኳን ውስጥ በሚገቡትና መሠዊያው ወዳለበት ወደ ላይ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ታጥበውታል። 33 ሙሴ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን አቆመ። መጋረጃውንም በአደባባዩ መግቢያ ዘረጋ። ሙሴ በዚህ መንገድ ሥራውን ፈጸመ። 34 ደመናውም የመገናኛውን ድንኳን ሸፈነ፤ የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ሞላው። 35 ደመናው በላዩ ስላረፈና የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ስለ ሞላው፣ ሙሴ መገናኛው ድንኳን ውስጥ መግባት አልቻለም ነበር። 36 ከማደሪያው ድንኳን በተነሣ ጊዜ ሁሉ፣ የእስራኤል ሰዎች ይጓዛሉ። 37 ግን ደመናው ከማደሪያው ላይ ካልተነሣ፣ ሕዝቡ አይጓዙም። ደመናው እስከሚነሣበት ቀን ድረስ ይቆያሉ። 38 በሁሉም የእስራኤል ሕዝብ ፊት በጕዟቸው ሁሉ ቀን የእግዚአብሔር ደመና፣ ማታ ደግሞ እሳቱ በማደሪያው ላይ ነበረ።
እስራኤላውያን ከግብጽ የወጡበት ቀን የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ሆኖ ተቆጠረላቸው። ይህ ወር ለእስራኤላውያን ሚያዚያ ወር ነው። የመጽሐፍ ቅዱሱ የወር አቆጠጠር የሚጀምረው በዚሁ ወር ነው።
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የምስክሩን ወይም የቃል ኪዳኑን ታቦት ታኖራለህ
ታቦቱን ከመጋረጃው በስተጀርባ ወይም ታቦቱን በመጋረጃ ትጋርዳለህ ማለት ነው
በሌላ ስሙ የሚታወቀው የቃል ኪዳን ታቦት ተብሎ ነው። በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፉት ቃላት እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ምስክር እንዲሆን ነው።
ይህ የወይራ ዘይት ሲሆን ማደሪያ ድንኳኑንና ሌሎችንም ዕቃዎች ለእግዚአብሔር የተለየ ለማድረግ ወይም ቅዱስ ለማድረግ የሚቀቡት ነው።
ሙሴ አሮንና ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን እንዲያመጣቸው ትእዛዝ ተሰጠው።
አሮንን ለእኔ የተለየ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ አድርገው
በሚመጡት ዘመናት ወይም ትውልዶች ሁሉ ካህናት ሆነው ያገለግሉኛል
ሙሴ መገናኛውን ደንኳን ወይም ማደሪያውን ድንኳን ተከለ በሚል በአድራጊ ግስ መተርጎም ይቻላል።
ይህ የነገናኛው ድንኳን ተከላና አሰራር የተፈጸመው ልክ እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር በወሩም በመጀመሪያው ቀን ላይ ነበር።
ሙሴ የድንኳኑን ተከላ የሚመራ መሪ ይሁን እንጂ ህዝቡ ያግዙትና በሥራው ይተባበሩት ነበር።
እግሮቹንም አኖረ ወይም ምሰሶዎቹን አቆመ የሚል ነው።
ታቦቱን ወደ መገናኛው ድንኳን ውስጥ አስገባው ወይም አስገብቶ አስቀመጠ የሚል ይሆናል
በእግዚአብሔር ፊት መብራቶቹን አበራ
ይህ መጋረጃ ቅድስተ ቅዱሳንን ከቅዱስ ስፍራው የሚለየው ነው። ስለሆነም የወርቁን መሰዋያዊ ከመጋረጃው ፊት ለፊት ሲያስቀምጥ ቅድስተ ቅዱሳኑ ከበስተሁዋላው ነው ማለት ነው።
በመታጠቢያው ሳህን ባለው ውሃ ውስጥ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውንና እግራቸውን ታጠበ።
በመታጠቢያው ሳህን ባለው ውሃ ውስጥ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውንና እግራቸውን ታጠበ።
የእግዚአብሔርም መገኘት የመገናኛ በድንኳኑ ውስጥ ይታይ ነበር።
በጉዞአቸው ሁሉ እስራኤላውያን የሰፈሩበትን ቦታ ለቀው የሚንቀሳቀሱት ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሣበት ጊዜ ብቻ ነበር።
1 ያህዌ ከመገናኛው ድንኳን ሆኖ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ አለው፣ 2 “ለእስራኤላዊያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ከእናንተ መሃል ማንም ሰው ለያህዌ መባ በሚያቀርብበት ጊዜ ከከብቶቻችሁ ወይም ከመንጋው እንስሳት መሃል አንዱን ያቅርብ፡፡ 3 መባው ከመንጋው መሃል የሚቃጠል መስዋዕት ከሆነ፣ ነውር የሌለበት ወንድ መስዋዕት ያቅርብ፡፡ መስዋዕቱ በያህዌ ፊት ተቀባይነት ያለው ይሆን ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያቅርበው፡፡ 4 በሚቃጠለው መስዋዕት ራስ ላይ እጁን ይጭናል፣ ይህም በእርሱ ምነትክ ያስተሰርይለት ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ 5 ከዚያ በያህዌ ፊት ወይፈኑን ይረድ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ካህናቱ የአሮን ልጆች ደሙን ያቀርቡና በመሰዊያው ላይ ይረጩታል፡፡ 6 ከዚያም ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ቆዳ መግፈፍና ብልቶችንም ማውጣት ይኖርበታል፡፡ 7 ከዚያም ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ላይ ዕሳት ይለኩሱና እንጨት ይጨምሩበታል፡፡ 8 ካህናቱ የአሮን ልጆች የስጋውን ብልቶች፣ የከብቱን ጭንቅላትና ስቡን በመስዋዕቱ ምድጃ ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ በስርዓት ይደረድሩታል፡፡ 9 ነገር ግን ካህኑ የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ማጠብ ይኖርበታል፡፡ በመስዋዕቱ ላይ የሚገኘውን ሁሉ የሚቃጠል መስዋዕት አብርጎ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለእኔ ጣፋጭ ሽታ ይሆናል፤ ይህም ለእኔ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡ 10 ለመስዋዕት የሚያቀርበው የሚቃጠል መስዋዕት ከመንጋው ከሆነ፣ ከበጎች ወይም ከፍየሎች መሃል ነውር የሌለበት ተባዕት መስዋዕት ማቅረብ አለበት፡፡ 11 በያህዌ ፊት መስዋዕቱን ከመሰዊያው በስተቀኝ በኩል ይረደው፡፡ ካህናቱ የአሮን ልጆች የመስዋዕቱን ከብት ደም በመሰዊያው ዙሪያ ሁሉ ይርጩት፡፡ 12 ከዚያ ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ጭንቅላቱንና ስቡን እንዲሁም ብልቶቹን ይቆራርጥ፡፡ ከዚያም በመሰዊያው በሚገኘው የሚነድ እንጨት ላይ በስርዓት ይደርድረው፡፡ 13 ነገር ግን የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፡፡ ከዚያ ካህኑ መባውን በሙሉ ያቅርብና በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህም የሚቃጠል መስዋዕት ነው፣ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፤ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡ 14 “ካህኑ ለያህዌ የሚያቀርበው የሚቃጠል የወፎች መስዋዕት ከሆነ፣አንድ ወፍ ወይም ዕርግብ ማቅረብ አለበት፡፡ 15 ካህኑ መስዋዕቱን ወደ መሰዊያው ያመጣና አንገቱን ይቆለምመዋል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ደሙም በመሰዊያው ጎን ተንጠፍጥፎ ይፈሳል፡፡ 16 የወፉን ማንቁርትና በውስጡ ያሉትን ያስወግድ፣ ከዚያም አመድ በሚደፉበት ከመሰዊያው በስተ ምስራቅ ይወርውረው፡፡ 17 ክንፎቹን ይዞ ይሰንጥቀው፣ ነገር ግን ለሁለት አይክፈለው፡፡ ከዚያ ካህኑ በዕሳቱ ላይ ባለው እንጨት መሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡”
1 ማንኛውም ሰው ለያህዌ የእህል ቁርባን ሲያቀርብ፣ መባው መልካም ዱቄት ይሁን፣ ዘይት ያፈስበታል ደግሞም ዕጣን ያድርግበት፡፡ 2 ቁርባኑን ወደ ካህናቱ ወደ አሮን ልጆች ይወስደዋል፣ ካህኑ ከዘይቱና በላዩ ካለው ዕጣን ጋር ከመልካሙ ዱቄት እፍኝ ይወስዳል፡፡ ከዚየም ካህኑ የያህዌን በጎነት ለማሰብ መስዋዕቱን በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ነው፣ ለእርሱ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡ 3 ከእህል መስዋዕቱ የተረፈው ሁሉ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ በዕሳት ከተዘጋጀው መስዋዕት ለእርሱ የተለየ ነው፡፡ 4 በምድጃ የተጋገረ እርሾ የሌለበት የእህል ቁርባን ስታቀርብ፣ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ለስላሳ ዳቦ መሆን አለበት፣ ወይም እርሾ የሌለበት በዘይት የተቀባ ቂጣ መሆን አለበት፡፡ 5 የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ ላይ የተጋገረ ከሆነ፣ እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን፡፡ 6 ቆራርሰህ በላዩ ዘይት ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡ 7 የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ የሚዘጋጅ ከሆነ ከመለካም ዱቄትና ዘይት ይዘጋጅ፡፡ 8 ከእነዚህ ነገሮች የተዘጋጀውን የእህል ቁርባን ወደ ያህዌ ማቅረብ አለብህ፣ እናም ይህ ወደ መሰዊያው ወደሚያመጣው ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡ 9 ከዚያም የያህዌን በጎነት ለማሰብ ካህኑ ከእህል ቁርባኑ ጥቂት ይወስዳል፣ ቀጥሎም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፡፡ 10 ከእህል ቁርባኑ የሚተርፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ለያህዌ በዕሳት ከሚዘጋጀው ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየ ነው፡፡ 11 ለያህዌ በምታቀርቡት የእህል ቁርባን ውስጥ እርሾ አይግባበት፣ ለያህዌ በዕሳት በምታዘጋጁት ቁርባን ውስጥ ምንም እርሾ፣ ወይም ማር አታቃጥሉ፡፡ 12 እነዚህን እንደ በኩራት ፍሬዎች ለያህዌ ታቀርባላችሁ፣ ነገር ግን በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ ለመስጠት አታቀርቧቸውም፡፡ 13 የእህል ቁርባንህን ሁሉ በጨው አጣፍጠው፡፡ ከእህል ቁርባንህ በፍጽም የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨው አይታጣ፡፡ በመስዋዕቶችህ ሁሉ ጨው ማቅረብ አለብህ፡፡ 14 ለያህዌ ከፍሬህ በኩራት የእህል ቁርባን ስታቀርብ ከእሸቱ በእሳት የተጠበሰውንና የተፈተገውን አቅርብ፡፡ 15 ከዚያ በላዩ ላይ ዘይትና እጣን ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡ 16 ከዚያ ካህኑ የተፈተገውን እህል እና ዘይት እንዲሁም ዕጣን የያህዌን በጎነት በአንክሮ ለማሰብ ከፊሉን ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ የሚቀርብ የዕሳት መስዋዕት ነው፡፡
1 ማንኛውም ሰው ከመንጋው መሃል ወንድም ሆነ ሴት እንስሳ የህብረት መስዋዕት እንስሳ ቢያቀርብ፣በያህዌ ፊት ነውር የሌለበት እንስሳ ያቅርብ፡፡ 2 እጁን በመስዋዕቱ እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፣ ከዚያም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያርደዋል፡፡ ከዚያ ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ይረጩታል፡፡ 3 የህብረት መስዋዕቱን ለያህዌ በዕሳት ያቀርባል፡፡ ሆድቃውን የሸፈነውን ወይም ከዚያ ጋር የተያያዘውን ስብ፣ 4 እና ሁለቱን ኩላሊቶች እንዲሁም በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን ስብ፣ እና የጉበቱን መረብ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡ 5 የአሮን ልጆች ከሚቃጠለው መስዋዕት ጋር እነዚህን በዕሳቱ ላይ በሚገኘው እንጨት በመሰዊያው ላይ ያቃጥሉታል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ይሆናል፡፡ 6 ለያህዌ የሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት ወንድም ይሁን ሴት እንስሳ ነውር የሌለበት ይሁን፡፡ 7 መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነ፣ በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡ 8 እጁን በመስዋዕቱ ራስ ላይ ይጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡ 9 የህብረት መስዋዕቱን በእሳት እንደሚቀርብ መስዋዕት አድርጎ ለያህዌ ያቀርባል፡፡ ስቡን፣ላቱን እስከ ጀርባ አጥንቱ ድረስ፣እንዲሁም የሆድ እቃውን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ፣ 10 እና ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር ያለውን ስብ፣ በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን እና የጉበቱን መሸፈኛ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡ 11 ከዚያም ካህኑ ሁሉንም ለያህዌ በመሰዊያው ላይ በእሳት የመበል ቁርባን አድርጎ ያቃጥላል፡፡ 12 የሚያቀርበው መስዋዕት ፍየል ከሆነ፣በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡ 13 እጁን በፍየሉ ራስ ላይ መጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ማረድ ይኖርበታል፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡ 14 በእሳት የተዘጋጀውን መስዋእቱን ለያህዌ ያቀርባል፡፡ የሆድ እቃውን የሸፈነውንና በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡ 15 እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር የሚገኘውን ስብ፣ በጎድኖች እና ከኩላሊቶቹ ጋር በጉበቱን መሸፈኛው ላይ የሚገኘውን ስብ እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡ 16 ካህኑ እነዚህን ሁሉ በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ እንዲሆን እንደ መብል መስዋዕት አድርጎ ሁሉንም ያቃጥለዋል፡፡ ስቡ ሁሉ የያህዌ ነው፡፡ 17 “‘ይህ ለእናንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቀዋሚ መታሰቢያ ነው፣ እናንተ ስብ ወይም ደም አትብሉ፡፡’”
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2 “ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ማንም ሰው ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር በማድረግ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ደግሞም የተከለከለ አንዳች ነገር ቢያደርግ፣ እንዲህ ይደረግ፡፡ 3 ኃጢአት የሰራው ሊቀ ካህኑ ቢሆንና በህዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኃጢአት ቢሰራ ስለ ሰራው ኃጢአት ለያህዌ ነውር የሌለበት ወይፈን የኃጢአት መስዋእት አድርጎ ያቅርብ፡፡ 4 ወይፈኑን በያህዌ ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣ፤ ካህኑ እጆቹን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫንና በያህዌ ፊት ይረደው፡፡ 5 የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውድና ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣው፡፡ 6 ካህኑ ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ ሰባት ጊዜ በቅድስተ ቅዱሳኑ መጋረጃ ላይ ከደሙ ጥቂት በያህዌ ፊት ይረጫል፡፡ 7 ደግሞም ካህኑ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በያህዌ ፊት ከደሙ ጥቂት ወስዶ መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን በመሰዊያው ቀንዶች ይጨምራል፤ የቀረውን ወይፈኑን ደም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡ 8 የሆድ ዕቃውን የሸፈነውንና ከሆድ ዕቃው ጋር የተያያዘውን የበደል መስዋዕቱን የሆነውን ወይፈን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡ 9 (ቁጥር 9?) 10 ለህብረት መስዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን አውጥቶ እንዳቀረበ ሁሉ ይንንም አውጥቶ ያቀርባል፡፡ ከዚያም ካህኑ እነዚህን ክፍሎች ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡ 11 የወይፈኑን ቆዳና ማንኛውንም ስጋ ከጭንቅላቱና ከእግሮቹ እንዲሁም ከሆድዕቃው ክፍሎችና ከፈርሱ ጋር፣ 12 የቀረውን የወይፈኑን ክፍሎች ሁሉ ከእነዚህ ክፍሎች ሁሉ ከመንደር ተሸክሞ አመዱን ወደ ደፉበት ለእኔ ወደሚነጹበት ስፍራ ወስዶ እነዚያን ክፍሎች በእንጨት ላይ ያቃጥላቸው፡፡ እነዚያን የከብቱን ክፍሎች አመዱን በደፉበት ስፍራ ያቃጥለው፡፡ 13 መላው የእስራኤል ጉባኤ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ጉባኤውም ኃጢአት መስራቱን ባያውቅና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ፈጽሞ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣ 14 ከዚያም፣ የፈጸሙት በደል በታወቀ ጊዜ፣ ጉባኤው ለኃጢአት መስዋዕት ወይፈን ይሰዋና ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ያምጣው፡፡ 15 የጉባኤው ሽማግሌዎች በያህዌ ፊት በወይፈኑ ላይ እጃቸውን ይጫኑና በያህዌ ፊት ይረዱት፡፡ 16 የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣል፣ 17 ከዚያ ካህኑ ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በመጋረጃው ላይ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡ 18 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣በያህዌ ፊት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ከደሙ ጥቂት ይጨምርበታል፤ ደግሞም ለሚቃጠል መስዋዕት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በመሰዊያው ታች ደሙን በሙሉ ያፈሳል፡፡ 19 ስቡን ሁሉ ከእንስሳው ቆርጦ ያወጣና በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡ 20 ወይፈኑን በዚህ መልክ ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለኃጢአት መስዋዕት እንዳቀረበው ወይፈን ሁሉ፣ በዚህኛውም ወይፈን ይህንኑ ያደርጋል፣ እናም ካህኑ ለህዝቡ ማስተስረያ ያደርጋል፣ እናም ጉባኤው ይቅር ይባላል፡፡ 21 ካህኑ ወይፈኑን ከመንደር ያወጣና የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለ ይህኛውንም ያቃጥለዋል፡፡ ይህ ለጉባኤው የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡ 22 የህዝቡ መሪ ኃጢአት ለመስራት ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ አምላኩ ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ማናቸውም ነገሮች አንዱን አድርጎ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣ 23 ከዚያም የሰራው ኃጢአት ቢታወቀው፣ ነውር የሌለበት ተባዕት ፍየል ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡ 24 እጁን በፍየሉ ራስ ላይ ይጭንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ በያህዌ ፊት ይረደው፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡ 25 ካህኑ ያኃጢአት መስዋዕቱን ደም በጣቱ ይውሰድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረው፣ ደግሞም ደሙን ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፍስሰው፡፡ 26 ልክ እንደ ሰላም መስዋዕት ሁሉ ስቡን በሙሉ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ካህኑ የህዝቡ መሪ ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያድርግለታል፣ መሪውም ይቅር ይባላል፡፡ 27 ከተራው ህዝብ መሃል አንድ ሰው ኃጢአት ለማድረግ ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ከእነዚህ ነገሮች መሃል አንዱን ቢፈጽም፣ እናም በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ 28 ከዚያም የፈጸመው በደል ቢታወቀው፣ ለበደሉ መስዋዕት ነውር የሌለበት ሴት ፍየል ያቅርብ፡፡ 29 በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጭናል ከዚያም በሚቃጠል መስዋዕቱ ስፍራ የኃጢአት መስዋዕቱን ያርዳል፡፡ 30 ካህኑ በጣቱ ጥቂት ደም ወስዶ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ የተቀረውን ደም ሁሉ በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡ 31 መስዋዕቱ በተወሰደበት ሁኔታ ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፡፡ ካህኑ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፣የሰውየውንም ኃጢአት ያስተሰርያል፡፡ 32 ለኃጢአት መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ቢያቀርብ ነውር የሌለባት ሴት ጠቦት ያምጣ፡፡ 33 በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርድበት ስፍራ ለኃጢአት መስዋዕት ያርዳል፡፡ 34 ካህኑ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን ሁሉ ያፈሰዋል፡፡ 35 ከሰላም መስዋዕቱ የጠቦቱ ስብ በወጣበት ሁኔታ፣ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፣ከዚያ ካህኑ በያህዌ መስዋዕቶች ላይ በእሳት በሚቀርበው መሰዊያ ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ካህኑ መስዋእት አቅራቢው የሰራውን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፣ እናም ሰውየው ይቅር ይባላል፡፡
1 ማንም ሰው ያየውንም ሆነ የሰማውን አንዳች ነገር መምስከር ሲገባው ባለመመስከር ኃጢአት ቢሰራ፣ ይጠየቅበታል፡፡ 2 ወይም ማንም ሰው እግዚአብሔር ንጹህ አይደለም ያለውን ማናቸውንም ነገር ቢነካ፣ ይህ ንጹህ ያልሆነ ነገር የዱር እንስሳ ስጋ ወይም የሞተ የቤት እንስሳ ቢሆን፣ ወይም ማናቸውንም ያልነጻ ሰው ቢነካ፣ ደግሞም ይህን ማድረጉን ባያውቅ፣ ስለ ነገሩ ባወቀ ጊዜ ኃጢአጠኛ ይሆናል፡፡ 3 ቁጥር 3 (?) 4 ወይም ማንም ሰው በችኮላ ክፉ ወይም በጎ ለማድረግ በከንፈሮቹ ቢምል፣በችኮላ የማለው መሀላ ምንም አይነት ይሁን፣ ስለ ነገሩ ባያውቅ እንኳን፣ ነገሩን ባወቀ ጊዜ ከእነዚህ በማናቸውም ነገር ኃጢአተኛ ይሆናል፡፡ 5 አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በማንኛውም በደለኛ ሆኖ ሲገኝ፣የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት መናዘዝ አለበት፡፡ 6 ከዚያም ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕቱን ወደ ያህዌ ማምጣት አለበት፣ ለኃጢአት መስዋዕት ሴት ጠቦት በግ ወይም ሴት ፍየል ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፡፡ 7 ጠቦት መግዛት ካልቻለ፣ ለኃጢአቱ የበደል መስዋዕት ለያህዌ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች ማምጣት ይችላል፤ አንዱ ለኃጢአት መስዋዕት እና ሌላኛው ለሚቃጠል መስዋዕት ያመጣል፡፡ 8 እነዚህን ወደ ካህኑ ያመጣል፣ እርሱም በመጀመሪያ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ያቀርባል - እርሱም የመስዋዕቱን ራስ ከአንገቱ ይቆለምማል ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ አይለያየውም፡፡ 9 ከዚያ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በመሰዊያው ጎን ይረጫል፣ ከዚያ የቀረውን ደም በመሰዊያው ስር ደሙን ያንጠፈጥፈዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡ 10 ከዚያ ሁለተኛውን ወፍ በህጉ መሰረት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል፣ እናም ካህኑ ሰውየው ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያደርገዋል፤ ይቅር ይባላል፡፡ 11 “ነገር ግን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች መግዛት ሳይችል ቢቀር፣ ለሰራው ኃጢአት የኢፍ መስፈሪያ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ያኃጢአት መስዋዕት ስለሆነ ዘይት ወይም ዕጣን አይጨምርበት፡፡ 12 መስዋዕቱን ወደ ካህኑ ያቅርበው፣ካህኑም ለያህዌ በጎነት ምስጋና ለማቅረብ ከዱቄቱ እፍኝ ይወስዳል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ለያህዌ በመስዋዕቱ ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡ 13 ካህኑ ሰውየው የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ይቅር ይባላል፡፡ ከመስዋዕት የተረፈው እንደ እህል ቁርባኑ ሁሉ የካህኑ ይሆናል፡፡’” 14 ከዚያም ያህዌ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣ 15 “ማንም ሰው የያህዌን ትዕዛዝ በመጣስ እርሱ ካለው ውጭ ሆኖ ኃጢአት ቢሰራ፣ ነገር ግን ይህንን ሁን ብሎ ባያደርግ ለያህዌ የበደል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ይህ መስዋዕት ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ዋጋውም ለኃጢአት መስዋዕት በቤተ መቅድስ ገንዘብ በጥሬ ብር መገመት አለበት፡፡ 16 ቅዱስ ከሆነው በማጉደል ለሰራው በደል ዕዳውን በመክፈል ያህዌን ደስ ማሰኘት አለበት፣ እናም አንድ አምስተኛውን በዚህ ላይ ጨምሮ ለካህኑ ይስጥ፡፡ ከዚያ ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጠቦት ጋር ያስተሰርይለታል፤ እናም ይቅር ይባላል፡፡ 17 ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ቢያደርግ፣ ምንም እንኳን ነገሩን ሳያውቅ ቢያደርገውም በደለኛ ነው፤ ስለዚህም በበደሉ ጥፋተኛ ነው፡፡ 18 ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ጠቦት ያቅርብ ለካህኑ ለበደል መስዋዕት ተመጣጣኝ ዋጋ ያምጣ፡፡ ከዚያም ካህኑ ሳያውቅ ከሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ይቅር ይባላል፡፡ 19 ይህ የበደል መስዋዕት ነው፣ በያህዌ ፊት በእርግጥ ኃጢአተኛ ነው፡፡”
1 ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2 “ ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና የያህዌን ትዕዛዝ ቢተላለፍ፣ ታማኝነቱን አፍርሶ ሃሰተኛ ቢሆን፣ ወይም ጎረቤቱ በአደራ የሰጠውን ቢክድ፣ ወይም ቢያታልል ወይም ቢሰርቀው፣ወይም ጎረቤቱን ቢበድል 3 ወይም ከጎረቤቱ የጠፋ ነገር አግኝቶ ቢዋሽ፣ እናም በሃሰት ቢምል፣ ወይም እነዚህን በመሰሉ ሰዎች በሚበድሉባቸው ጉዳዮች ኃጢአት ቢሰራና፣ 4 በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ በስርቆት የወሰደውን ይመልስ ወይም የበደለውን ይካስ፣ ወይም ታማኝነቱን አጉድሎ የወሰደውን ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፡፡ 5 ወይም በማንኛውም ጉዳይ ላይ ቢዋሽ፣ ሙሉ ለሙሉ ይመልስ፤ እንዲሁም ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ለባለንብረቱ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይክፈል፡፡ 6 ከዚያም የበደል መስዋዕቱን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ነውር የሌለበት ጠቦት ከመንጋው የኃጢአት መስዋእት ለያህዌ ወደ ካህኑ ያምጣ፡፡ 7 ካህኑ የኃጢአት ማስተስረያ በያህዌ ፊት ያቀርባል፣ እናም በዳዩ ለሰራው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል፡፡” 8 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 9 “አሮንን እና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘የሚቃጠል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የሚቃጠለው መስዋዕት በመሰዊያው ምድጃ ላይ ሌሊቱን ሁሉ እስከ ማለዳ ይገኝ፣ ደግሞም የመሰዊያው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡ 10 ካህኑ የበፍታ ልብሱን ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ ቀሚን ይልበስ፡፡ እሳቱ በመሰዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠለውን መስዋዕት ከበላ በኋላ አመዱን ይፈስ፣ ከዚያም አመዱን ከመሰዊያው ጎን ይድፋው፡፡ 11 አመዱን ከሰፈር ውጭ ንጹህ ወደ ሆነ ስፍራ ለመውሰድ የለበሰውን አውልቆ ሌላ ልብስ ይልበስ፡፡ 12 በመሰዊው ላይ ያለው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡ መጥፋት የለበትም፣ እናም ካህኑ በየማለዳው እንጨት ይጨምርበት፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ በላዩ የሚቃጠል መስዋዕት ያድርግበታል፣ ደግሞም የሰላም መስዋዕት ስብ በላዩ ያቃጥልበታል፡፡ 13 እሳቱ ሳያቋርጥ በመሰዊያው ላይ ይንደድ፤መጥፋት የለበትም፡፡ 14 የእህል ቁርባን ህግ ይህ ነው፡፡ የአሮን ልጆች ከያህዌ ፊት በመሰዊያው ላይ ያቀርቡታል፡፡ 15 ካህኑ የእህል ቁርባን አድርጎ እፍኝ መልካም የእህል ዱቄትና ዘይት እንዲሁም ዕጣን ለመስዋዕት ይውሰድና የያህዌን በጎነት ምስጋና ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ 16 አሮንና ልጆቹ ከመስዋዕቱ የቀረውን ይመገቡት፡፡ ይህም እርሾ ሳይገባበት በተቀደሰው ስፍራ ይብላ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረ ግቢ ይመገቡት፡፡ 17 በእርሾ መጋገር የለበትም፡፡ እኔ በእሳት የተዘጋጀ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ የኃጢአት መስዋዕትና የበደል መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው፡፡ 18 ለሚመጣው ተውልድ ሁሉ ለዘመናት ሁሉ ወንድ የሆነ የአሮን ትውልድ ድርሻው አድርጎ ከያህዌ ከሚቀርበው የእሳት ቁርባን ሊበላው ይችላል፡፡ ማናቸውም እርሱን የሚነካ ቅዱስ ይሆናል፡፡” 19 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 20 “ይህ አሮንና ልጆቹ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፣ እያንዳንዳቸው የአሮን ልጆች በሚቀቡበት ቀን ለያህዌ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፡፡ እንደ ተለመደው የእህል ቁርባን የኢፍ አንድ አስረኛ ክፍል መልካም ዱቄት፤ በጠዋት ግማሹን የተቀረውን ግማሽ ደግሞ ምሽት ያቀርቡታል፡፡ 21 በመጥበሻ ላይ በዘይት ይጋገራል፡፡ በእርጥቡ ሳለ፣ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ታቀርበዋለህ፡፡ የእህል ቁርባኑን ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ቆራርሰህ ታቀርበዋለህ፡፡ 22 ከሊቀ ካህኑ ልጆች መሃል ተተኪ ካህን የሚሆነው ወንድ ልጅ መስዋዕቱን ያቀርባል፡፡ ለዘለዓለም እንደታዘዘው፣ መስዋዕቱ በሙሉ ለያህዌ ይቃጠላል፡፡ 23 ካህኑ የሚያቀርበው እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ይቃጠላል፤አይበላም፡፡” 24 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 25 “አሮንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፣ ‘የኃጢአት መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የኃጢአት መስዋዕት የሚታረደው የሚቃጠል መስዋዕት በሚታረድበት ስፍራ ያህዌ ፊት ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡ 26 የኃጢአት መስዋዕት የሚያቀርበው ካህን ይመገበዋል፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረግቢ በተቀደሰው ስፍራ ይበላ፡፡ 27 የመስዋዕቱን ስጋ የሚነካ ሁሉ ይቀደሳል፣ደሙ በየትኛውም ልብስ ላይ ቢረጭ ደሙ የነካውን የጨርቁን ስፍራ በተቀደሰ ቦታ እጠበው፡፡ 28 የተቀቀለበት የሸክላ ማሰሮ ግን ይሰበር፡፡ 29 ከካህናቱ መሀል ማናቸውም ወንድ ከዚህ መብላት ይችላል ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡ 30 በተቀደሰው ስፍራ ወደ መገናኛው ድንኳን ለማስተስረይ ደሙ ከቀረበው የኃጢአት መስዋዕት ምንም አይበላ፡፡
1 የበደል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡ 2 የበደል መስዋዕቱን በሚታረድበት ስፍራ የበደሉንም መስዋዕ ይረዱት፣ ደሙን በመሰዊያው እያንዳንዱ ጎን ይርጩት፡፡ 3 በመስዋዕቱ ከብት ውስጥ ያለው ስብ ሁሉ ይቃጠል፤ ላቱ፣የሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነው ስብ በመሁሉ፣ 4 በጎድኑ አጠገብ ያለው ስብ፣ ሁለቱ ኩላሊቶችና በላያቸው ያለው ስብ፣ ጉበቱን የሸፈነው ስብ፣ ከኩላሊቶቹ ጋር - እነዚህ ሁሉ ይቅረቡ፡፡ 5 ካህኑ እነዚህን ክፍሎች በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት አድርጎ በመሰዊያው ላይ ለያህዌ ያቃጥል፡፡ ይህ የበደል መስዋዕት ነው፡፡ 6 እያንዳንዱ ካህን ከዚህ መስዋዕት መብላት ይችላል፡፡ በተቀደሰ ስፍራ ይበላ ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡ 7 የኃጢአት መስዋዕት ልክ እንደ በደል መስዋዕት ነው፡፡ የሁለቱም ህግ ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህ ህጎች የማስተስረይ አገልግሎት ለሚሰጡ ካህናት ያገለግላሉ፡፡ 8 የየትኛውንም ሰው የሚቃጠል መስዋዕት የሚያቀርብ ካህን የመስዋዕቱን ቆዳ መውሰድ ይችላል፡፡ 9 በምድጃ የሚዘጋጅ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን፣ እና በመጥበሻ የሚዘጋጅ እንዲህ ያለው እያንዳንዱ መስዋዕት ወይም በመጋገሪያ መጥበሻ ላይ የሚዘጋጅን መስዋዕት፣ መስዋዕቱን የሚያሳርገው ካህን ይወስደዋል፡፡ 10 ደረቅም ሆነ በዘይት የተለወሰ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ለአሮን ትውልዶች እኩል የእነርሱ ነው፡፡ 11 ይህ ሰዎች ለያህዌ የሚያቀርቡት የሰላም መስዋዕት ህግ ነው፡፡ 12 ማንም ሰው ምስጋና ለማቅረብ ይህን ቢያደርግ፣ እርሾ የሌለበት መስዋዕት አድርጎ ያቅርበው፣ ነገር ግን ቂጣውን በዘይት ይለውሰው፣ ቂጣው በመልካም ዱቄት የተዘጋጀ በዘይት የተለወሰ ይሁን፡፡ 13 ደግሞም ምስጋና ለማቅረብ፣ ከሰላም መስዋዕቱ ጋር በእርሾ የተዘጋጀ ህብስት ያቅርብ፡፡ 14 ከእነዚህ መስዋዕቶች ከእያንዳንዳቸው አንድ አይነት መስዋዕት ለያህዌ ያቅርብ፡፡ ይህ የሰላም መስዋዕቱን ደም በመሰዊያው ላይ ለሚረጩት ካህናት ይሰጥ፡፤ 15 ምስጋና ለማቅረብ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርበው ሰው መስዋዕቱ በሚቀርብበት ዕለት የመስዋዕቱን ስጋ ይብላ፡፡ ከስጋው እስከ ማግስቱ አይደር፡፡ 16 ነገር ግን መስዋዕቱ የሚያቀርበው ለስዕለት ከሆነ፣ ወይም በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ መስዋዕት ከሆነ ስጋው መስዋዕቱን ባቀረበበት ዕለት ባያልቅ በማግስቱ ሊበላ ይችላል፡፡ 17 ሆኖም፣ ከመስዋዕቱ የተረው ስጋ በሶስተኛው ቀን ይቃጠል፡፡ 18 አንድ ሰው ካቀረበው የበጎ ፈቃድ መስዋዕት አንዳች ስጋ በሶስተኛው ቀን ቢበላ ይህ ተቀባይነት የለውም፤ መስዋዕቱን ላቀረበውም ዋጋ የለውም፡፡ ደስ የማያሰኝ ነገር ይሆናል፣ ስጋውን ለሚበላውም ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል፡፡ 19 ንጹህ ያልሆነ ነገር የነካ ከዚህ ስጋ አይበላም፡፡ ስጋው መቃጠል ይኖርበታል፡፡ የተረውን ስጋ፣ ማንኛውም ንጹህ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል፡፡ 20 ሆኖም፣ ለያህዌ የሚቀርበውን የሰላም መስዋዕት ስጋ የበላ ንጹህ ያልሆነ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡ 21 ማንኛውም ሰው ንጹህ ያልሆነ ነገር ቢነካ - ንጹህ ያልሆነን ሰው፣ ወይም ንጹህ ያልሆነን አውሬ፣ ወይም ንጹህ ያልሆነ እና ደስ የማያሰኝ ነገር ቢነካ፣ እና ከዚያም ለያህዌ ከቀረበው የሰላም መስዋዕት ስጋ ቢበላ ያሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡ 22 ቀጥሎም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 23 “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ አትብሉ፡፡ 24 ሳይታረድ ሞቶ የተገኘ እንስሳ ስብ፣ ወይም በዱር አውሬ የተገደለ እንስሳ ስብ ለሌላ ተግባር ሊውል ይችላል፣ ነገር ግን የዚያን እንስሳ ስብ በፍጹም አትብሉ፡፡ 25 ሰዎች በእሳት ለያህዌ መስዋዕት አድርገው ሊያቀርቡ የሚችሉትን እንስሳ ስብ የሚላ ማንኛውም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡ 26 በቤቶቻችሁ የወፍም ሆነ የእንስሳ ማናቸውም ዐይነት ደም አትብሉ፡፡ 27 ማናቸውንም ደም የበላ ማንም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡’” 28 ደግሞም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 29 “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ለያህዌ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርብ ከመስዋዕቱ ላይ ወስዶ ለያህዌ ያቅርብ፡፡ 30 ለያህዌ በእሳት የሚዘጋጀውን መስዋዕት፣ በእርሱ በራሱ እጅ ያቅረበው፡፡ ስቡን ከፍርምባው ጋር ያቅርበው፣ ስለዚህ ፍርምባውን በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ያቅርበው፡፡ 31 ካህኑ ስቡን በመሰዊያ ላይ ያቃጥለው፣ ነገር ግን ፍርምባው የአሮንና የትውልዱ ነው፡፡ 32 የቀኙን ወርች ከሳለም መስዋዕታችሁ የቀረበ ስጦታ አድርጋችሁ ለካህኑ ስጡት፡፡ 33 የሰላም መስዋዕቱንና ስቡን ደም የሚያቀርበው ከአሮን ትውልድ ውስጥ የሆነው ካህን ከመስዋዕቱ ውስጥ የቀኝ ወርቹ የእርሱ ድርሻ ነው፡፡ 34 ለእኔ የተወዘወዘውንና የቀረበውን የፍርምባውንና የወርቹን መስዋዕት እኔ ስለ ወሰድኩ፣ እነዚህን ሊቀካህን ለሆነው ለአሮንና ለዘሩ ሰጥቻለሁ፣ ይህ ሁልጊዜም በእስራኤል ህዝብ ከሚዘጋጀው የሰላም መስዋዕት ድርሻቸው ይሆናል፡፡ 35 ሙሴ በካህናት አገልግሎት ያህዌን እንዲያገለግሉ እነርሱን ባቀረበ ቀን ይህ ለአሮንና ለዘሮቹ በእሳት ለያህዌ ከሚቀርበው መስዋዕት ድርሻቸው ነው፡፡ 36 እርሱ ካህናትን በቀባ ቀን ያህዌ ከእስራኤል ህዝብ ድርሻቸው ሆኖ ለእነርሱ እንዲሰጥ ያዘዘው ይህ ነው፡፡ ይህ ሁልጊዜም በትውልዶች ሁሉ ድርሻቸው ይሆናል፡፡ 37 ይህ የሚቃጠል መስዋዕት፣ የእህል ቁርባን፣ የኃጢአት መስዋዕት፣ በደል መስዋዕት፣ የክህነት ሹመት መስዋዕት እና የሰላም መስዋዕት ስርዓት ነው፤ 38 ይህ ያህዌ ለሙሴ በሲና ተራራ ላይ የእስራኤል ህዝብ መስዋዕታቸውን በሲና ምድረበዳ የሚያቀርቡበትን ህግጋት ለሙሴ በሰጠበት ቀን የተሰጠ ስርዓት ነው፡፡
ይህ በጥቅስ ውስጥ የተጠቀሰ ጥቅስ ነው፡፡ ቀጥተኛው ጥቅስ እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊወሰድ ይችላል፡፡ አት፤ ከዚያም እግዚአብሔር ለሙሴ ተናገረ እናም ለእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲናገር እንዲህ አለው፤ “…ሥብ አትብሉ”:: (ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶች ይመልከቱ)
“የሞተ ነገር ግን መሥዋዕት ያልሆነውን”
ይህ በተሻጋሪ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አውሬዎች የገደሉት ከብት ሥብ”:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ይህ በተሻጋሪ ግሥ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት “ለሌላ ተግባር ያውሉት”:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ::)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል አት “የሚቃጠል መሥዋዕት”
ያ ሰው ከሕዝቡ ዘንድ መወገድ ብጣሽ ጨርቅ ወይም የዛፍ ቅርንጫፍ እንደሚቆረጥ ከሕዝቡ ዘንድ እንደተቆረጠ ተደርጐ ተገልጾአል:: ይህ በተሻጋሪ ግሥ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: በዘሌዋዊያን 7:2ዐ ይህን እንዴት እንደተረጐመ ይመልከቱ:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
በማንኛውም ቤቶቻችሁ “በየትኛውም ቤቶቻችሁ” ወይም “በማንኛውም በሚትኖሩበት ቦታ”
ይህ በጥቅስ ውስጥ የተጠቀሰ ጥቅስ ነው፡፡ ቀጥተኛው ጥቅስ እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊወሰድ ይችላል፡፡ አት “ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን ተናገረ፤ እናም ለእስራኤል ሕዝብ እንዲናገር እንዲህ አለው፤ መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው፤”(ጥቅሶችን በጥቅስ ውስጥና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶች ይመልከቱ)
በራሱ እጅ ያቅርበው የሚለው አባባል በዐረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ሊቀመጥ ይችላል በእሳት ያቅርበው የሚለው ሀረግ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል አት ፤ እርሱ ራሱ መሥዋዕት አድርጐ ለማቃጠል ያቀደውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቅርበው፤ (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ::)
እዚህ “እጅ” መላውን ሰው ያመለክታል:: አት “እርሱ ራሱ ያቅርበው” (see synecdoche/ክፍልን እንደ ሙሉ እናም ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዜይቤያዊ አነጋገር ወይም ሥዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ)::
የአንድ እንስሳ ከአንገት በታች ፊተኛ የአካል ክፍል ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ ካህኑ ይህን ለእግዚአብሔር የሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርጐ ሊያቀርብ ይችላል:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)፡፡
መሥዋዕቱን ከፍ አድርጐ መያዝ ሰውየው መሥዋዕቱን ለእግዚአብሔር ማቅረቡ የሚያመለክት ምልክት ነው፡፡ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)::
ከጉልበት በላይ ያለው የእንስሳ አካል ክፍል ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እና ይህ መሣዋዕት ተደርጐ ይቅረብ”፤ (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)፡፡
እዚህ “እኔ” እግዚአብሔርን ያመለክታል::
“ያም እንደመሥዋዕት የሚሰጥ”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)፡፡
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ ያም ለእነርሱ እንዲሰጡ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ አዘዘ:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)፡፡
“ሙሴ ካህናቱን በቀባበት”
በዘሌዋዊያን 3:17 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ይህ በዘሌዋዊያን 7:29 የተጀመረው ንግግር ማብቂያ ነው::
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “አሮንንና ልጆቹን፣ የክህነት ልብሶቹን፣ የቅባት ዘይቱን፣የኃጢአት መስዋዕቱን ወይፈኖች፣ ሁለቱን ጠቦቶች፣ እርሾ የሌለበትን ህብስት መሶብ ከእርሱ ጋር ውሰድ፡፡ 3 በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሁሉንም ጉባኤ ሰብስብ፡፡” 4 ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፣ ጉባኤውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ተሰበሰበ፡፡ 5 ከዚያም ሙሴ ለጉባኤው እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ይህ ነው፡፡” 6 ሙሴ አሮንንና ልጆቹን አቀረበና በውሃ አጠባቸው፡፡ 7 አሮንን እጀ ጠባብ አለበሰውና በወገቡ ዙሪያ መቀነት አስታጠቀው፣ ቀሚ አጠለቀለትና ኤፉድ ደረበለት፣ ከዚያም ኤፉዱን በጥበብ በተጠለፈ መቀነት አስታጠቀው፡፡ 8 በቀሚሱ ላይ ደረት ኪስ አደረገለት፣ በደረት ኪሱ ውስጥ ኡሪምና ቱሚም አደረገበት፡፡ 9 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው በራሱ ላይ ጥምጥሙን ጠመጠመለት፣ በጥምጥሙ ላይ ከፊት በኩል ወርቃማ ቅብና ቅዱስ አክሊል አደረገለት፡፡ 10 ሙሴ የቅባቱን ዘይት ወሰደ፣ ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀባው፤ እናም ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡ 11 በመሰዊያው ላይ ዘይቱን ሰባት ጊዜ ረጨው፣ እናም መሰዊያውንና መገልገያዎቹን ሁሉ ቀባቸው፣ እንዲሁም የመታጠቢያ ሳህኑንና ማስቀመጫውን፣ ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡ 12 አሮንን ያህዌ ለመለየት ከቅባቱ ዘይት ጥቂቱን በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰው፡፡ 13 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው የአሮንን ወንድ ልጆች አቅርቦ እጀጠባብ አለበሳቸው፣ በወገባቸው ዙሪያ መታጠቂያ አሰረላቸው፣ በራሳቸው ላይ በፍታ ጨርቅ ጠቀለለላቸው፡፡ 14 ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት በሬ አመጣ፣ አሮንና ልጆቹ ለኃጢአት መስዋዕት ባመጡት በሬ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ፡፡ 15 በሬውን አርዶ ደሙን በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ በጣቱ ጨመረ፣ በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፣ ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር ለየው፡፡ 16 በመስዋዕቱ ሆድ ዕቃ ውስጥ ያለውን ስብ ሁሉ አወጣ፣ በጉበቱ መሸፈኛና በሁለቱ ኩላሊቶች ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሰዊያው ላይ ሁሉንም አቃጠለው፤ 17 ነገር ግን በሬውን፣ ቆዳውን፣ ስጋውን እና ፈርሱን ያህዌ እንዳዘዘው ከሰፈር አውጥቶ አቃጠለው፡፡ 18 ሙሴ ለሚቃጠል መስዋዕት ጠቦቱን አቀረበ፣ አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፡፡ 19 ሙሴም ጠቦቱን አርዶ በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ረጨ፡፡ 20 ጠቦቱን ቆራርጦ ራሱንና ቁርጥራጩን እንዲሁም ስቡን አቃጠለ፡፡ 21 የሆድ ዕቃውን ክፍሎችና እግሮቹን በውሃ አጠበ፣ ከዚያም ጠቦቱን በሙሉ በመሰዊያው ላይ አቃጠለ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፤ ደግሞም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ ጣፋጭ መዓዛ ነው፡፡ 22 ከዚያም ሙሴ ሌላውን ጠቦት ያቀርባል፣ ይህም የክህነት ሹመት መስዋዕት ነው፣ እናም አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ይጭናሉ፡፡ 23 አሮን ጠቦቱን ያርዳል፣ ሙሴም ከደሙ ጥቂት ወስዶ በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ያደርጋል፡፡ 24 የአሮንን ልጆች አቅርቦ፣ በቀኝ ጆሯቸው ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጃቸው አውራ ጣት ላይ እና በቀኛ እግራቸው አውራ ጣት ላይ ከደሙ ጥቂት ወስዶ ያደርጋል፡፡ ከዚያ ሙሴ የበጉን ደም በመሰዊያው ጎኖች ሁሉ ይረጫል፡፡ 25 ስቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃ ክፍሎች ውስጥ ሁሉ የሚገኘውን ስብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኩላሊቶች እና በላያቸው የሚገነውን ስብ እንዲሁም ቀኝ ወርቹን ወሰደ፡፡ 26 በያህዌ ፊት ከነበረው መሶብ እርሾ የሌለበት አንድ ህብስት ይወስዳል፣ደግሞም በዘይት ተለውሶ ከተሰራው ዳቦ አንዱን እና አንድ ስስ ቂጣ ይውሰድና በስቡና በቀኝ ወርች ላይ ያኖረዋል፡፡ 27 ሁሉንም በአሮን እጆችና በአሮን ወንድ ልጆች እጆች ላይ ያስቀምጠዋል፣ ይህንንም ለሚወዘወዝ መስዋዕት በያህዌ ት ያቀርባሉ፡፡ 28 ከዚያም ሙሴ ከእጃቸው ይወስድና የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበው፡፡ እነዚህ የክህነት ሹመት መስዋዕት ናቸው፤ ጣፋጭ መዓዛ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ነው፡፡ 29 ሙሴ ፍርምባውን ወስዶ ለያህዌ መስዋዕት አድርጎ ይወዝውዘው፡፡ ያህዌ እንዳዘዘው ይህ ከጠቦቱ የክህነት ሹመት የሙሴ ድርሻ ነው፡፡ 30 ሙሴ በመሰዊያው ላይ ካለው ከቅባት ዘይቱና ከደሙ ጥቂት ወስዶ እነዚህን በአሮን ላይ፣ በልብሶ ላይ፣ በወንድ ልጆቹ ላይ እና ከእርሱ ጋር በልጆቹ ልብሶች ላይ ይረጫል፡፡ በዚህ መንገድ አሮንና የክህነት ልብሱን እንዲሁም ልጆቹንና ልብሳቸውን ለያህዌ ይቀድሳል፡፡ 31 ደግሞም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ አለ፣ “በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ስጋውን ቀቅሉት፣ በዚያም ስፍራ በሹመት መስጫው መሶብ ውስጥ ያለውን ህብስትም ‘አሮንና ልጆቹ ይብሉት’ ብዬ እንዳዘዝኩት ብሉት፡፡ 32 ከስጋውና ከህብስቱ የተረፈውን በሙሉ አቃጥሉት፡፡ 33 የሹመት ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሰባት ቀናት ከመገናኛው ከመገናኛው ድንኳን መግቢያ አትለፉ፡፡ ያህዌ በሰባት ቀናት ውስጥ ይሾማችኋል፡፡ 34 በዚህ ቀን የሚሆነው እናንተን ለማስተረይ ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ነው፡፡ 35 ለሰባት ቀናት ቀንም ሆነ ሌሊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ትቆያላችሁ፣ ደግሞም የያህዌን ትዕዛዝ ትጠብቃላችሁ፣ ይህን ካደረጋችሁ አትሞቱም፣ ምክንያቱም የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡” 36 ስለዚህም አሮንና ልጆቹ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን ሁሉንም ነገር አደረጉ፡፡
በዘጸአት መጽሐፍ በሙሴ በዘገበው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሠረት በምዕራፍ 8 ሙሴ አሮንና ልጆቹን ካህናት አድርጐ ይሾማቸዋል፡፡
“የካህናት ልብሶች” ወይም “ካህናት የሚለብሱት ልብሶች”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፤ አት፤ እግዚአብሔር እንድናደርገው ያዘዘን (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)፡፡
ይህ ምልክታዊ ድርጊት ነው:: ይህም ካህናት እንዲሆኑ የሚያዘጋጃቸው የመንጻት ሥርዓት ነው፤ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)::
እነዚህ ልዩ አልባሳት ሕዝቡ ለካህናት እንዲያዘጋጁ እግዚአብሔር ያዘዛቸው ናቸው:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃዎች ይመልከቱ)::
በወገብ ወይም በደረት የሚታሠር ቀጭን ረጅም ልብስ ነው፡፡
“በላዩም አሰረው”
“ሙሴ ለአሮን የደረት ኪስ በላዩ አደረገለት”
እነዚህ ልዩ አልባሳት ሕዝቡ ለካህናት እንዲያዘጋጁ እግኢብሔር ያዘዛቸው ናቸው:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃዎች ይመልከቱ)::
እነዚህ ነገሮች ምን እንደሆኑ ግልጽ አይደሉምና መገለጽ አለባቸው ካህኑ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ የሚጠቀማቸው ዕቃዎች ናቸው፡፡ (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
የሰው ራስ የሚሸፍንና በዙሪያውን የሚጠመጠም በረጅም የተቆረጠ ጨርቅ ነው፡፡
ሁለቱ ሀረጐች አንድን ነገር የሚገልጹ ናቸው ንጹህ የወርቅ ቆብ ከጥምጥሙ ጋር ተያይዞ ይገኛል::
እነዚህም ማሠሮዎች ምጣዶች ወይም ሳህኖች መቆስቆሻዎችና ሹካዎች ሁሉ፤
ይህ በመሠዊያውና በታቦቱ መካከል የሚገኝ የመዳብ ሳህን ነው፡፡
ይህ የመታጠቢያው ሳህን የሚቀመጥበት የመዳፍ መቆሚያ ነው፡፡
ሙሴ አፈሰሰው::
ይህ መታጠቂያ በብዙነት ሲገለጽ ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 8፡7 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
አሮንና ልጆቹን መሥዋዕት ከሚያቀርቡት እንስሳ ጋር የሚያስመስል ምልክታዊ ድርጊት ነው:: በዚህ መንገድ በእንስሳው በኩል ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ:: በዘሌዋዊያን 1:4 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ምልክታዊ ድርጊቶችን ይመልከቱ)
ይህ የመሠዊያው ማዕዘኖችን ያመለክታል:: በበሬ ቀንድ መልክ የተቀረጹ ናቸው:: በዘሌዋዊያን 4:7 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመለከቱ::
“መሠዊያውን ለእግዚአብሔር ይለየው”
እዚህ ማስተሠርየት ማለት ወሠዊያውን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ጥቅም ብቁ ማድረግ ነው:: አት ለኃጠአት መሥዋዕቶች መቃጠል ቦታውን ምቹ ለማድረግ ነው::
ሆድንና ጨጓራዎችን ነው:: በዘሌዋዊያን 1:9 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
በዘሌዋዊያን 3፡4 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ቁርበት ወይም የቤት እንስሳት ቆዳ፤
ይህም አሮንና ልጆቹ መስዋዕት የሚያቀርቡት እንስሳ መመሰላቸውን የሚገልጽ ምልክታዊ ድርጊት ነው፡፡ በዚህ መንገድ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ያቀርባሉ:: በዘለዋዊያን 1;4 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ሙሴ በጉን ቆራረጠ
እግዚአብሔር መሥዋዕትን በማቅረብ በቅንነት በሚያመልከው ሰው እንደሚደሰት በሚቃጠል መሥዋዕት ሽታ እንደተደሰተ ተደርጐ ተገልጾአል:: በዘሌዋዊያን 1:9 የዚህ ተመሳሳይ ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊገለጽ ይችላል:: አት፤ እርሱ ለእግዚአብሔር ያቃጠለው መሥዋዕት: ተሻጋሪ ግሥ የያዘ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ::
“ቅድስና” የሚለው ቃል ረቂቅ ስም ነው አት “አሮንና ለጆቹን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለይቶ የሚያቀርብ አውራ በግ” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ይህም አሮንና ልጆቹ መስዋዕት በሚያቀርቡት እንስሳ መመሰላቸውን የሚገልጽ ምልክታዊ ድርጊት ነው፡፡ በዚህ መንገድ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ያቀርባሉ:: በዘሌዋዊያን 1;4 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ደሙ ከእንስሳው እንደወጣ ሙሴ በሳህን እንደያዘው የሚያመለክት ነው የዚህ ዐረፍት ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ
ሆድና ጨጓራዎችን ነው፡፡ ይህን በዘሌዋዊያን 1:9 እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
በዘሌዋዊያን 3:4 እንዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ከጉልበት በላይ የሚገኝ የእግር አካል ክፍል፤ በዘሌዋዊያን 7፡32 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ይህ በመሶብ ያለው ዳቦ ያለበትን ቦታ የሚያመለክት አይደለም፡፡ ይህ የሚናገረው ሙሴ ለእግዚአብሔር ያቀረበውን ዳቦ ነው፡፡
እዚህ” እጆች” መላውን ሰው ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም (አት)፤ “ሁሉንም ለአሮንና ለልጆቹ ሰጠው” (See Synecdoche/ክፍልን እንደ ሙሉ እናም ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዜይቤያዊ አነጋገር ወይም ሥዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ)::
አሮንና ልጆቹ መሥዋዕት እንዳቀረቡ የሚናገር ነው፡፡ የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉሙ ግልጽ ሊሆን ይችላል:: አት ፤ “እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት እንደመወዘወዝ መሥዋዕት ወዘወዙት”:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር የሚቀርብበት ምልክታዊ ድርጊት ነው፡፡ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
እዚህ “እነዚህ” ሥቡን ወርቹንና ዳቦዎች በአጠቃላይ ያመለክታል::
እዚህ “እጆች” መላውን ሰው ያመለክታሉ:: አት፤ “ከአሮንና ልጆቹ” (See Synecdoche/ክፍልን እንደ ሙሉ እናም ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዜይቤያዊ አነጋገር ወይም ሥዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ):: የቅድስና ወይም የመለየት መሥዋዕት ናቸው:: አሮንና ልጆቹን ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚለዩ መሥዋዕቶች ናቸው::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት (ተሻጋሪ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመለከቱ)::
እግዚአብሔር መሥዋዕትን በማቅረብ በቅንነት በሚያመልከው ሰው እንደሚደሰት በሚቃጠል መሥዋዕት ሽታ እንደተደሰተ ተደርጐ ተገልጾአል:: በዘሌዋዊያን 1:9 የዚህ ተመሳሳይ ሀረግ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::(ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ከአንገት በታች ያለ የእንስሳ የፊት አካል ነው::
አንድን ሰው ካህን የማድረግ ሥርዓታዊ በዓል ነው::
አሮንና ልጆቹ በሚቀደሱበት ጊዜ መሥዋዕቶችን የያዘው መሶብ ማለት ነው፡፡ አት፤ “መሶቡ”
ይችላል:: አት: “እንዲታደርጉ እንዳዘዝሁት” (ጥቅሶችን በጥቅሶች ውስጥ እና ቀጥታና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ የክህነት ቀናት እስኪፈጽሙ፤ (ድረስ ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮች ይመልከቱ) ክህነት ይህ አንድን ሰው ካህን የማድረግ ሥርዓታዊ በዓል ነው በዘሌዋዊያን 8:29 ይህን እንዴት እንደተረጐው ይመልከቱ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ እኛ ማድረግ ያለብን (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“ሥርየት” የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት፤ “ኃጢአታችሁን ለማስተሠርየት” (ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እርሱ ያዘዘኝ ይህ ነው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
1 በስምንተኛው ቀን ሙሴ አሮንንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራ፡፡ 2 አሮንን እንዲህ አለው፣ “ለኃጢአት መስዋዕት ከመንጋው እምቦሳ እና ነውር የሌለበትን አውራ በግ ወስደህ በያህዌ ፊት ሰዋቸው፡፡ 3 እስራኤል ሰዎች እንዲህ ባላቸው፣ ‘ለኃጢአት መስዋዕት ወንድ ፍየል ውሰድ እንደዚሁም ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት እምቦሳና ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዓት ውሰድ፤ 4 እንዲሁም በያህዌ ፊት የሰላም መስዋት ለመስዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ውሰድ፣ በዘይት የተለወሰ የእህል ቁርባንም አቅርብ፣ ምክንያቱም ዛሬ ያህዌ ይገለጥላችኋል፡፡” 5 ስለዚህም ሙሴ ያዘዘውን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን አመጡ፣ የእስራኤል ጉባኤም ሁሉ ቀርበው በያህዌ ፊት ቆሙ፡፡ 6 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንድታደርጉት ያዘዘው ይህንን ነው፣ስለዚህም ክብሩ ይገለጥላችኋል፡፡” 7 ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ወደ መዊያው ቀርበህ የኃጢአት መስዋዕትህንና የሚቃጠል መስዋዕትህን አቅርብ፣ ደግሞም ያህዌ እንዳዘዘው ለራስህና ለህዝቡ አስተስርይ፣ ለህዝቡ ማስተስረያ ለማቅረብ መስዋዕቱን ሰዋ፡፡” 8ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡ 8 ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡ 9 የአሮን ልጆቸ ደሙን አቀረቡለት፣ እርሱም ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ጨመረ፤ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፡፡ 10 ሆኖም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ስቡን፣ ኩላሊቶቹን እና በመሰዊያው ላይ የጉበቱን ሽፋን የኃጢአት መስዋዕት አድርጎ አቃጠላቸው፡፡ 11 ስጋውንና ቆዳውን ከሰፈር ውጭ አቃጠለው፡፡ 12 አሮን የሚቃጠለውን መስዋዕት አረደ፣ ልጆቹ በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደም ሰጡት፡፡ 13 ከዚያ የሚቃጠለውን መስዋዕት ከከብቱ ራስ ጋር እየቆራረጡ ሰጡት፣ እርሱም በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡ 14 የሆድ ዕቃዎቹንና እግሮቹን አጥቦ በመሰዊያው ላይ በሚቃጠል መስዋዕቱ ላይ አቃጠላቸው፡፡ 15 አሮን አንድ ፍየል የህዝቡን መስዋዕት አቀረበ፣ ከዚያ ለኃጢአታቸው መስዋዕት አድርጎ አረደው፤ በመጀመሪያው ፍየል ላይ እንዳደረገው ሁሉ ለኃጢአት መስዋዕትነት ሰዋው፡፡ 16 ያህዌ እንዳዘዘው የሚቃጠል መስዋዕቱን አቅርቦ ሰዋው፡፡ 17 የእህል ቁርባኑን፣ ከእህል ቁርባኑ እፍኝ ሙሉ ወስዶ ከማለዳው የሚቃጠል መስዋዕት ጋር በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡ 18 እንዲሁም ለህዝቡ የሰላም መስዋዕት የሆነውን መስዋዕት በሬውንና አውራ በጉን አረደ፡፡ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደሙን ሰጡት፡፡ 19 ሆኖም፣ የበሬውንና የአውራ በጉን ስብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነውን ስብ፣ ኩላሊቶቹን፣ የጉበቱን ሽፋን 20 እነዚህን በፍርምባው ላይ አደረጉ፣ ከዚያም አሮን ሙሴ ባዘዘው መሰረት ስቡን በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡ 21 አሮን ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ይወዝስዘውና እነዚህን ለያህዌ ያቅርብ፡፡ 22 ከዚያ አሮን አጆቹን ወደ ህዝቡ አንስቶ ይባርካቸው፤ ቀጥሎ የኃጢአት መስዋዕቱን፣ የሚቃጠል መስዋዕቱንና የሰላም መስዋዕቱን አቅርቦ ይወርዳል፡፡ 23 ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ይሂዱ፣ ከዚያ ተመልሰው ይውጡና ህዝቡን ይባርኩ፣ እናም የያህዌ ክብር ለህዝቡ ሁሉ ይገለጣል፡፡ 24 ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥቶ የሚቃጠል መስዋዕቱንና በመሰዊያው ላይ ያለውን ስብ ሁሉ በላ፡፡ ህዝቡ ሁሉ ይህንን ባዩ ጊዜ ጮኸው በፊታቸው ተደፉ፡፡
ስምንተኛ የሚለው ቃል ተራ ቁጥር ስምንት ነው:: (ተራ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
“በእግዚአብሔር መገኘት”
ሙሴ ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል::
ሙሴ ለአሮን መናገር ቀጠለ:: ይህም በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ ነው:: ቀጥተኛ ጥቅስ እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል:: አት “አንድ አውራ ፍየል ይዘው….ለሕዝቡ ሁሉ እንዲያቀርቡ እስራኤላዊያንን ንገራቸው:: (ጥቅሶችን በጥቅሶች እና ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
“የአሥራ ሁለት ወር ዕድሜ”
“ለእግዚአብሔር ለመሠዋት”
እዚህ እናንተ የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል (See forms of you/ሁለተኛ ሰው አገላለጽ አይነቶችን ይመልከቱ)
እዚህ “ክብር” የእግዚአብሔርን መገለጥ ያመለክታል:: አት “እርሱ የክብሩ መገኘት ይገልጥለችሁ/ያሳያችሁ ዘንድ” (See Mentonymy/ተመሣሣይ ትርጉም የያዙ አባባሎች ዜይቤያዊ ንግግር ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት የተለያዩ መሥዋዕቶች ናቸው:: የመጀመሪያው የልቀ ካህኑን ኃጢአቶች ለማስተሠርየት ነው:: ሊቀ ካህኑ ኃጢአቶችን ሲፈጽም ሕዝቡን በደለኛ ያደርጋል:: ዘሌዋዊያን 4:3 ይመልከቱ:: ሁለተኛው ሕዝቡ የሠራቸውን ኃጢአት ለማስተሠርየት ነው::
ይህ ከእንስሳው እንደወጣ ደሙን የአሮን ልጆች በሳህን እንደያዙት ይገልጻል፡፡ የዐረፍተ ነገሩ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል (ግምታዊ እውቀት እና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ የመሠዊያውን ማዕዘናት ያመለክታል እንደ በሬ ቀንዶች መልክ የተቀረጹ ናቸው፡፡ በዘሌዋዊያን 4፡7 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
“ከመሠዊያው በታች”
“አሮን በእሳት አቃጠለው”
በዘሌዋዊያን 3፡4 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
ይህ የቤት እንስሳ ቆዳ ወይም ሽፋን ነው:: በዘሌዋዊያን 7: 8 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ከእንስሳው እንደወጣ ልጆቹ ደሙን እንደያዙት የሚያመለክት ነው:: የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀት እና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የውስጥ ክፍሎች ሆድንና አንጀቶችን ነው፡፡ በዘሌዋዊያ 1፡9 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
“መጀመሪያ” የሚለው ቃል ለተራ ቁጥር አንድ ነው:: አት “ለራሱ መሥዋዕት የሚያቀርበው ፍየል” (ተራ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ይህ የየዕለቱን የመጀመሪያ መሥዋዕት ያመለክታል፡፡ ካህኑ ከማንኛውም መሥዋዕት በፊት በማለዳ ይህን የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ አለበት፡፡ የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“አሮን ዐረደ”
ይህም ደሙ በሳህኑ እንደነገበር ያመለክታል፤ የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ::
ይህ ሆድና አንጀቶችን ነው፡፡ ይህን በዘሌዋዊያን 1፡9 እንዴት እንደረጐሙ ይመልከቱ፡፡
በዘሌዋዊያ 3፡4 እነዚህን ቃላት አንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
የአሮን ልጆች ክፍሎችን ወሰዱ
“እነዚህ” የሚለው ቃል ቀድም ተብለው የተገለጹ ሥብንና የሆድ ዕቃዎችን ያመለክታል::
ከአንገት በታች የሚገኝ የእንስሳ ፊተኛ አካል ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 7፡3ዐ ይህን እንዴት አንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ከጉልበት በላይ የሚገኝ የእግር አካል ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 7፡32 ይህን እንዴት እንደተዘጐሙ ይመልከቱ፡፡
“ለእግዚአብሔር”
“ካቀረበ በኋላ ወረደ” የሚለው ሀረግ የተጠቀመበት መሠዊያው ሕዝቡ ከቆመበት ቦታ ከፍ ብሎ ስለሚገኝ ነው::
እዚህ “ክብር” የእግዚአብሔርን መገኘት ይወክላል:: አት፤ እግዚአብሔርም የመገኘቱን ክብር ለሁሉም ሕዝብ አሳየ:: (See Metonymy/ /ተመሣሣይ ትርጉም የያዙ አባባሎች ዜይቤያዊ ንግግር ይመልከቱ)
“የሚበላውን እሳት እግዚአብሔር ላከ”
እሳቱ መሥዋዕቱን ሙሉ በሙሉ ያቃጠለው እሳቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እንደበላ ወይም እንዳቃጠለ ተነግሮአል፡፡ (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“በግምባራቸው ወደ መሬት አጐነበሡ” ይህ የማክበርና ክብር መስጠት ምልክት ነው:: (ምልክታዊ ድርጊቶችን ይመልከቱ)
1 የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናዎቻቸውን ወስደው እሳት አደረጉበት ከዚያም ዕጣን ጨመሩበት፡፡ ከዚያ በያህዌ ፊት እርሱ እንዲያቀርቡ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ ዕሳት አቀረቡ፡፡ 2 ስለዚህም ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥታ በላቻቸው፣ እነርሱም በያህዌ ፊት ሞቱ፡፡ 3 ከዚያም ሙሴ አሮንን፣ “ያህዌ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ ላይ ቅድስናዬን እገልጻለሁ፡፡ በሰዎች ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ሲል ይህን ማለቱ ነው” አለው፡፡ አሮንም ምንም አልመለሰም፡፡ 4 ሙሴ የአሮን አጎት የሆነውን የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ “ወደዚህ ኑና ከመቅደሱ ደጃፍ ወንድሞቻችሁን ተሸክማችሁ ከሰፈር አውጣቸው፡፡” 5 ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው ቀርበው የክህነት ቀሚሳቸውን እንደለበሱ ተሸክመው ከሰፈር አወጧቸው፡፡ 6 ከዚያም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምር እንዲህ አላቸው፣ “እንዳትቀሰፉ ፀጉራችሁን አትንጩ፣ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፣ ያህዌ በህዝቡ ላይ ሁሉ እንዳይቆጣ ተጠንቀቁ፡፡ ነገር ግን ቤተዘመዶቻችሁና መላው የእስራኤል ቤት የያህዌ እሳት ለበላቻቸው ያልቅሱ፡፡ 7 እናንተ ግን ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትለፉ፣ የያህዌ የቅባት ዘይት በእናንተ ላይ ነውና ትሞታላችሁ፡፡ ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው አደረጉ፡፡ 8 ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ 9 “አንተ፣ ወይም ከአንተ ጋር የሚሆኑ ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ እንዳትሞቱ ወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፣ 10 ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው መሃል ለመለየት፣ ንጹህ በሆነውና ንጹህ ባልሆነው መሃል ለመለየት፣ 11 ለእስራኤል ህዝብ ሁሉ በሙሴ በኩል ያህዌ ያዘዘውን ስርዓት ሁሉ አስተምሩ፡፡” 12 ሙሴ ለአሮንና ለተረፉት ልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምርን እንዲህ አላቸው፣ “በእሳት ለያህዌ ከቀረበው የእህል ቁርባን የተረፈውን መስዋዕት ውሰድ፣ እጅግ ቅዱስ ነውና እርሾ ሳይገባበት ከመሰዊያው አጠገብ ብሉት፡፡ 13 በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፣ ምክንያቱም በእሳት ለያህዌ ከቀረበው መስዋዕት ይህ የአንተና የልጆችህ ድርሻ ነው፣ እንድነግርህ የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡ 14 ለመስዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና ለያህዌ የቀረበውን ወርች እግዚአብሔር ደስ በሚሰኝበት በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፡፡ እነዚህን ድርዎቻችሁን አንተ፣ እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ብሉት፣ እነዚህ የእስራኤል ህዝብ ከሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት የአንተና የልጆችህ ድርሻ ሆነው ተሰጥተዋል፡፡ 15 ለያህዌ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን ወርች እና መስዋዕት ሆኖ የተወዘወዘውን ፍርምባ በእሳት ከተዘጋጀው የስብ መስዋዕቶች ጋር ከፍ አድርገው ለመወዘወዝና ለያህዌ መስዋዕት ለማድረግ በአንድነት ያቅርቧቸው፡፡ ይህም ያህዌ እንዳዘዘው ለዘለዓለም የአንተና የልጆችህ ድርሻ ይሆናል፡፡” 16 ከዚያ ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት ስለሚሆነው ፍየል ጠየቀ፣እናም በእሳት እንደተቃጠለ አወቀ፡፡ ስለዚህም በአልአዛርና በኢታምር በተቀሩትም የአሮን ልጆች ላይ ተቆጣ፤ እንዲህም አላቸው፣ 17 “ይህ የኃጢአት መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ሆኖ ሳለና የጉባኤውን በደል በእረሱ ፊት እንድታስወግዱበትና ኃጢአታቸውንም እንድታስተረዩላቸው ሰጥቷችሁ ሳለ ስለምን በቤተ አምልኮው ስፍራ አልበላችሁትም? 18 ተመልከቱ፣ ደሙ ወደ ቤተመቅደስ ውስጥ አልመጣም፤ እንዳዘዝኳችሁ በቤተ መቅደሱ አካባቢ ለትበሉት ይገባ ነበር፡፡” 19 ከዚያም አሮን ለሙሴ እንደህ ሲል መለሰለት፣ “እነሆ፣ ዛሬ የኃጢአት መስዋዕታቸውን እና የሚቃጠል መስዋዕታቸውን በያህዌ ፊት አቀርቡ፣ እናም ይህ ነገር በእኔ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ እኔ የኃጢአት መስዋዕቱን ብበላ ኖሮ ይህ በያህዌ ፊት ደስ ያሰኝ ነበርን?” 20 ሙሴ ያንን ሲሰማ መልሱ አረካው፡፡
እንዚህ የአሮን ልጆች ስሞች ናቸው
ካህናት ፍምን ወይም እጣንን የሚሸከሙበት ጐድጓዳ የብረት መያዣ ነው
“የሚያቃጥል ፍም ጨመሩ”
“እርሱ እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው መንገድ ስላልሆነ እግዚአብሔር መሥዋዕታቸውን አላጸናም/አለፈቀደም”
“ያልተፈቀደ እሳት ለእግዝአብሔር”
“ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር እሳት ላከ”
“ከእግዚአብሔር ወጥቶ”
ሙሉ በሙሉ እሳቱ ሰዎችን ያቃጠለው እሳቱ እንደበላቸው ወይም ሙሉ በሙሉ እንዳቃጠላቸው ተገልጾአል፡፡ (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“በእግዚአብሔር መገኘት ሞቱ”
ይህ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ ይዞአል ቀጥተኛ ጥቅስ እንደተዘዋዋሪ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፤ “ወደ እኔ በሚቀርቡት …ቅድስናዬን አግልጣለሁ እናም በሕዝቡ.. እከብራለሁ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ይናገር የነበረው ይህ ነው” (ጥቅሶችን በጥቅሶች ውስጥ እናም ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጥቅሶችን ይመልከቱ)
ወደ እኔ በሚቀርቡት የሚለው ሀረግ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናትን ያመለክታል፡፡ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ቅዱስ እንደሆንሁ እገልጣለሁ ወይም ሊያገለግሉት ወደ እኔ የሚቀርቡ ቅዱስ እንደሆንሁ ይወቁኝ
እግዚአብሔር ከተናገረው ሁለተኛው ክፍል እግዚአብሔርን ለማገልገል ስለሚቀርቡ ካህናት ይመለከታል፡ ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “በሕዝብ ሁሉ ፊት ሊያከብሩኝ ይገባል” ወይም “በሕዝብ ሁሉ ፊት ከፍ ሊያደርጉኝ የገባል”፡፡
እንዚህ የሰው ስሞች ናቸው:: (የሰው ስሞች ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህ በሥጋ ወንድሞች ናቸው ማለት አይደለም፡፡ እዚህ “ወንድሞች” ዘመዳሞች; የአጐት ወይም የአክስት ልጆች
ሚሳኤልና ኤልጻፋን መጥተው
የናዳብና አብዩድ ሙት አካል በክህነት ልብሶቻቸው እንዳለ ተሸክመው
እነዚህ የአሮን ልጆች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
አሮንና ልጆቹ ምንም ዓይነት ውጫዊ ሃዘን ወይም ትካዜ እንዳያሳዩ እግዚአብሔር ይናገራቸዋል፡፡ (ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ)
ከዚህ የተነሣ እንዳትሞቱ
እዚህ “ጉባኤ” መላውን የእስራኤል ጉባዔ እንጂ የቡድን መሪዎችን አይደለም (See Synecdoche/ክፍልን እንደ ሙሉ እናም ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዜይቤያዊ አነጋገር ወይም ሥዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ)::
እዚህ “ቤት” ሰዎችን ይወክላል:: አት : “መላው የእስራኤል ሕዝብ”
“እግዚአብሔር በእሳት ስላጠፋቸው ሰዎች”
እዚህ “ይህ” ወደ ኋላ መለስ ብሎ ካህናት ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይን ወይም ጠንካራ መጠጥ እንዳይጠጡ የታዘዙትን የሚያመለክት ነው::
በዚህ አድስ ዐረፍተ ነገር መጀመር ይቻላል:: “መለየት ይችሉ ዘንድ ይህን ያድርጉ”
“የተቀደሰ” እና “ያልተቀደሰ” ቅጽል ሥሞች እንደ ቅጽል ግሥ ሊገለጹ ይችላሉ:: አት: “ቅዱስ በሆነውና ቅዱስ ባልሆነው ወይም ለእግዚአብሔር በተለየውና በተራው” (ቅጽል ሥሞችን ይመልከቱ)
“ርኩሱ” እና “ንጹሑ” ቅጽል ሥሞች እንደ ቅጽል ግሥ ሊገለጹ ይችላሉ:: አት: “ርኩሰ በሆነውና ንጹህ በሆነው በካከል ወይም እግዚአብሔር በማይቀበለውና በሚቀበው መካከል” (ቅጽል ሥሞችን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እንዲነካ ያልፈለገው ሰው ወይም አንድ ነገር በአካል ርኩስ ተደርጐ ተገልጾአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እንዲነካ የፈለገው ሰው ወይም አንድ ነገር በአካል ንጹህ ተደርጐ ተገልጾአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት”(ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮች ይመልከቱ)
የእህል ቁርባኑ እጅግ ቅዱስ ስለሆነ ይህን እንዲትናገር ያዘዝሁት ነው:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ይህም እንዲናገር እግዚአብሔር ያዘዘኝ ነው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮችን ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “ለእግዚአብሔር የተወዘወዘውና የቀረበው ፍርምባና ወርች” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮችን ይመልከቱ)
ከአንገት በታች የሚገኝ የእንስሳ ፊት አካል ክፍል ነው፡፡
ከጉልበት በላይ የሚገኝ ላይኛ የእግር አካል ክፍል ነው፡፡
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ጥቅም ተገቢ ሥፍራ በአካል ንጹህ ተብሎ ተገልጾአል፡፡ (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “እግዚአብሔር እነዚህን ለእናንተ ድርሻ አድርጐ ስጥቶአችኋል” (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮች ይመልከቱ)
እዚህ “አንተ” አሮንን ያመለክታል:: (ሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
ድርሻው ለአሮንና ለልጆቹ ተደርጐ እንደተገለጸ ይተርጉሙ፡፡ አት፡ “ይህ ድርሻ ሁልጊዜ ለአንተና ለልጆችህ ይሆናል” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “ካህናት ሁሉንም አቃጥለዋል”
እነዚህን ስሞች በዘሌዋዊያን 1ዐ:6 እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ሙሴም በጥያቄ መልክ አልዓዛርንና ኢታምርን ይቆጣቸዋል፡፡ ይህ ጥያቄያዊ አገላለጽ በስድ ዐረፍተ ነገር ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አት፡ በፊቱ መብላት የገባችሁ ነበር፡፡
የኃጢአት መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው፡፡
እግዚአብሔር የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር ማለቱ ኃጢአት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ላይ የሚያስወግደው ነገር እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በመገኘቱ
ይህ በተሻጋሪ ግሥ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “እነርሱ ደሙን አላመጡም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዙ ዐረፍተ ነገሮችን ይመልከቱ)
አሮን ስለሞቱ ሁለት ልጆቹ ያውሳል
እነዚህ መሥዋዕቶች በእግዚአብሔር ፊት በፍስሃና በደስታ መበላት አለባቸው፡፡ በልጆቹ ሞት ምክንያት ሀዘንተኛ ስለሆነ መሥዋዕቶችን ቢበላ እግዚአብሔር ደስተኛ እንደማይሆን ለማተኮር አሮን በጥያቄ መልክ ያስቀምጣል:: ይህም ጥያቄ በስድ ዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጐም ይችላል:: “በእርግጥ እግዚአብሔር አልተደሰተም ኖሮአል::” (See Rehtorical Question/ንግግራዊ ጥያቄ ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በሏቸው፣ ‘በምድር ላይ ከሚገኙ እንስሳት ሁሉ የምትመገቧቸው ህያዋን ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡ 3 የተሰነጠቀ ሰኮና ያላቸውንና የሚያመሰኩትን ትመገባላችሁ፡፡ 4 ሆኖም፣ የሚያመሰኩ ቢሆኑም ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የሌላቸውን እንደ ግመል ያሉትን አትብሉ፤ምክንያቱም ያመሰኳሉ ነገር ግን ሰኮናው አልተሰነጠቀም፡፡ ስለዚህ ግመል ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡ 5 እንዲሁም ሽኮኮ ያመሰኳል ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የለውም፣ ይህም ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡ 6 ጥንቸል ቢያመሰኳም የተሰነጠቀ ሰኮና ስለሌለው ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡ 7 አሳማ የተሰነጠቀ ሰኮና ቢኖረውም፣ አያመሰኳም ስለዚህ ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡ 8 የእነዚህን ስጋ ፈጽሞ አትብሉ፣ ጥንባቸውንም አትንኩ፡፡ እነርሱ ለእናንተ ንጹህ አይደሉም፡፡ 9 በውቂያኖስም ሆነ በባህር በውሃ ውስጥ ከሚኖሩ እንስሳት የምትበሏቸው ክንፍና ቅርፊት ያላቸው ናቸው፡፡ 10 ነገር ግን በውቂያኖስ ወይም በባህር የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ህያዋን ፍጥረታት ሁሉ፣በውሃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን ጨምሮ እንዲሁም በውሃ ውስጥ ያሉት እንዲህ ያሉ ህያዋን ፍጥረታት በሙሉ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡ 11 ጸያፍ ሊሆኑ ስለሚገባቸውም፣ ስጋቸውን ልትበሉ አይገባም፣ እንደዚሁም በድናቸውም ጸያፍ ነው፡፡ 12 በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ቅርፊት የሌላቸው እንስሳት ሁሉ፣በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡ 13 ልትጸየፏቸው የሚገቡና የማትበሏቸው ወፎች እነዚህ ናቸው፤ ንስር፣ ጥንብ አንሳ፣ 14 ጭላት፣ ማንኛውም አይነት የሎስ 15 ማንኛውም አይነት ቁራ፣ 16 የተለያ አይነት ጉጉት፣ የባህር ወፍ እና ማንኛውም ዐይነት ጭልፊት፡፡ 17 ትናንሽና ትላልቅ ጉጉቶችን ትጸየፋላችሁ፣ርኩምና ጋጋኖ፣ 18 የተለያዩ ጉጉቶች፣ ይብራ፣ 19 ሽመላ፣ ማናቸውም ዐይነት የውሃ ወፍ፣ ሳቢሳ፣ ጅንጁላቲ ወፍና የለሊት ወፍ፡፡ 20 በእግራቸው የሚራዱ ክንፍ ያላቸው በራሪ ነፍሳት በሙሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው፡፡ 21 ሆኖም ግን ከእግራቸው በላይ በምድር ላይ የሚፈናጠሩበት አንጓ ያላቸውን ማናቸውንም የሚበሩ ነፍሳት መብላት ትችላላችሁ፡፡ 22 እንደዚሁም ደግሞ ማናቸውንም ዐይነት አንበጣ፣ ትልቅ የአንበጣ ዝርያ፣ ፌንጣና ዝንቢት መብላት ትችላላችሁ፡፡ 23 ነገር ግን አራት እግር ያላቸው የሚበሩ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጠሉ ናቸው፡፡ 24 ከእነዚህ እንስሳት ውስጥ የአንዱን በድን ብትነኩ እስከ ማታ ድረስ የረደሳችሁ ናችሁ፡፡ 25 ከእነዚህ የአንዱን በድን ያነሳ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ነው፡፡ 26 ማንኛውም ሙሉ ለሙሉ ያልተሰነጠቀ ሰኮና ያለው እንስሳ ወይም የማያመሰኳ እንስሳ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ነው፡፡ እነዚህን የነካ ሁሉ ይረክሳል፡፡ 27 በአራት እግሩ ከሚራመድ እንስሳ መሃል በመዳፋቸው የሚሄዱ ሁሉ በእናንተ ዘንድ እርሱስ ናቸው፡፡ እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን የነካ እስከ ማታ እርኩስ ነው፡፡ 28 እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን ያነሳ ልብሱን ይጠብ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡ እነዚህ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ ናቸው፡፡ 29 በምድር ላይ ከሚሳቡ እንስሳት መሃል፣ በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡ አቁስጣ፣ አይጥ፣ ማናቸውም አይነት እንሽላሊት 30 ትንሽ የቤት ላይ እንሽላሊት እና እስስት 31 ከሚሳቡ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡፡ ከእነዚህ የሞቱትን አንዳቸውን የነካ ሰው እስከ ምሽት እርሱስ ይሆናል፡፡ 32 ከእነዚህ መሃል አንዱ ሞቶ በማናቸውም ከእንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቆዳ ወይም ከበርኖስ በተሰራ ነገር ላይ ቢወድቀቅ ያዕቃ እርኩስ ይሆናል፡፡ ዕቃው ምንም ይሁን ለምንም አይነት ተግባር ይዋል ውሃ ውስጥ ይነከር እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡ 33 ንጹህ ያልሆነ እንስሳ የገባበት ወይም የነካው የሸክላ ማሰሮ እንዲሁም በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ እርኩስ ይሆናል፤ ያንን ማሰሮ ሰባብረው፡፡ 34 ማናቸውም ለመበላት የተፈቀደ ምግብ፣ ንጹህ ካልሆነ ማሰሮ ውሃ ቢገባበት እርኩስ ይሆኖል፡፡ እንዲህ ካለው ማሰሮ ማንኛውም ነገር ቢጠጣ ያረክሳል፡፡ 35 እርኩስ ከሆነ እንስሳ በድን ማናቸውም አካሉ የወደቀበት ምድጃም ሆነ የማብሰያ ሸክላ እንዲሁም ማንኛውም ነገር ይረክሳል፡፡ ይሰባበር፡፡ እርኩስ ነው፣ በእናንተም ዘንድ የተጠላ ይሁን፡፡ 36 የመጠጥ ውሃ የሚገኝበት ምንጭ ወይም የውሃ ጉድጓድ እንዲህ ያሉ እንስሳት ቢገኙበትም ንጹህ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው በውሃው ውስጥ የሚገኘውን እርኩስ የሆነውን በድን ቢነካ እርኩስ ይሆናል፡፡ 37 ንጹህ ያልሆነ እንስሳ በድን በዘር ላይ ቢወድቅ፣ እነዚያ ዘሮች የረከሱ ይሆናሉ፡፡ 38 ነገር ግን በዘሮቹ ላይ ውሃ ቢፈስ ንጹህ ያልሆነው እንስሳ በድን ማንኛውም አካል የተክል ዘሩ ላይ ቢወድቅ ዘሩ በእናንተ ዘንድ እርኩስ ይሆናል፡፡ 39 ለመበላት ከተፈቀደው እንስሳ አንዱ ቢሞት፣ በድኑን የነካው ሰው እስከ ምሽት እርኩስ ይሆናል፡፡ 40 ደግሞም እንዲህ ያለውን በድን ያነሳ ሰው ልብሱን ያጥባል፣ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡ 41 ማንኛውም በምድር ላይ የሚሳብ እንስሳ ጸያፍ ነው፤ አይበላም፡፡ 42 በሆዱ የሚሳብ እንስሳ ሁሉ፣ እና በአራቱም እግሮቹ የሚራመድ፣ወይም ማንኛውም ብዙ እግሮች ያሉት - በምድር የሚሳብ እንስሳን ሁሉ፣ አትብሉ፤ እነዚህ ጸያፍ ናቸው፡፡ 43 በደረቱ በሚሳብ ማናቸውም ህያው ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፤ እነዚህ እናንተን ያረክሳሉ፡፡ 44 እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ በምድር በሚንቀሳቀስ በማናቸውም አይነት እንስሳ ራሳችሁን አታርክሱ፡፡ 45 እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ ስለዚህ እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱስ መሆን አለባችሁ፡፡ 46 ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በውሃ ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ማናቸውም ህያዋን ፍጥረታት፣ እንዲሁም በምድር ላይ ስለሚሳቡ ፍጥረታት ህጉ ይህ ነው፤ 47 ንጹህ ባልሆኑና ንጹህ በሆኑት መካከል ልዩነት ለመፍጠር፣ እና በሚበሉ ህያዋን ነገሮችና በማይበሉ ህያዋን ነገሮች መሃል ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡’”
በየብስ ሚኖሩ እንስሳት ሁሉ
ሕዝቡ እንዲበሏቸው የተፈቀደላቸውንና ያልተፈቀደላቸውን እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን ይናገራል::
ይህም ሰኮናው አንድ ከመሆን ይልቅ ለሁለት የተሰነጠቀውን ማለት ነው::
ሕዝቡ እንዲበሏቸው የተፈቀደላቸውንና ያልተፈቀደላቸውን እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገርን ቀጠለ::
በድንጋማ ቦታዎች የሚኖር ትንሽ እንስሳ ነው፡፡ (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እነዚህን እንስሳት ሕዝቡ እንዲበላ ተገቢ እንዳይደለ እግዚአብሔር ስለተናገረ በአካል ርኩስ ተብለው ተገልጸዋል፡፡
ሁልጊዜ በጉዳጓድ በመሬት ውስጥ የሚኖር ጆሮው ረጅም የሆነ እንስሳ ነው፡፡
ሙት አካላቸውን/በድናቸውንም አትንኩ
ሕዝቡ እንዲበሏቸው የተፈቀደላቸውንና ያልተፈቀደላቸውን እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገርን ቀጠለ::
በዉሃ ውስጥ እንዲንሣፈፍ የሚያደርጉ የዓሣ ስስና ጠፍጣፋ የአካል ክፍሎች ናቸው፡፡
የዓሣን አካል ቆዳ የሚሸፍኑ ትናንሽ ቅርፊቶች ናቸው፡፡
በባሕሮችና በወንዞች ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ፍጡሮች ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው፡፡
እግዚአብሔር ሕዝቡ እነዚህን ፍጡሮች መብት እንዳይቀበሉና እንዲንቁ ያዝዛቸዋል፡፡ ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “እነዚህን ተጸየፉአቸው ወይም ሙሉ በሙሉ አትቀበሉአቸው:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ እንዲበሏቸው የተፈቀደላቸውንና ያልተፈቀደላቸውን እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገርን ቀጠለ::
አስጸያፊ የተናቀ ወይም ያልተቀበለ ነገር ነው፡፡ ይህም ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “በእናንተ ዘንድ ስለሚትጸየፉ” ወይም “እናንተ ሙሉ በሙሉ ስላተቀበላችሁ”:: (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “የእነርሱን ሙት አካል ትጸየፋላችሁ” ወይም “የእነርሱን ሙት አካል አትንኩ” (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ ይመልከቱ)
ክንፍና ቅርፊት የሌለው ማንኛውም በውሃ ውስጥ የሚኖር
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት: “ተጸየፉት” ወይም “ሙሉ በሙሉ አትቀበሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ እንዲበሏቸው የተፈቀደላቸውንና ያልተፈቀደላቸውን እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገርን ቀጠለ::
እነዚህ አእፋት በሌሊት የሚንቀሳቀሱ ወይም የሞቱ እንስሳትንና ጥንብ የሚመገቡ ናቸው፡፡ (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ሕዝቡ እንዲበሏቸው የተፈቀደላቸውንና ያልተፈቀደላቸውን እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገርን ቀጠለ::
እነዚህ አእዋፋት በተለይ በሌሊት የማይተኙና ጥንብና ትላትሎችን የሚመገቡ ናቸው የማይታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ::
ትልቅ ወፍ
እነዚህ እንሽላሊቶችንና ጥንብ ነገር የሚመገቡ ወፎች ናቸው፡፡
የሌሊት ወፍ ወፍ ባትሆንም ክንፍ ስላለውና ስለሚበርር በዝርዝሩ ውስጥ ተካትቶአል፡፡ ጸጉራማ አካል ያለውና በሌሊት የማይተኛ ነው፡፡ ጥምብንና ትላትሎችን የሚመገብ ነው::
ሕዝቡ እንዲበሏቸው የተፈቀደላቸውንና ያልተፈቀደላቸውን እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገርን ቀጠለ::
“አስጸያፊ” የሚለው ቃል በግሥ ሃረግ ሊተረጐም ይችላል አት ክንፍ ኖሮአቸው አራት እግር ያሉአቸውን ነፍሳት ይጸየፉ፡፡ (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
እዚህ “አራት እግር” የሚለው ሀረግ በምድር የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውንና እንደ አእዋፋት ከመሠሉ ሁለት እግር ካላቸው ከሚበርሩ ነፍሳት እንደሚለዩ የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው:: አት፡ “በምድር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እነዚህ ዕጽዋት ተመጋቢና የሚፈናጠሩ ትናንሽ እንስሳት ናቸው፡፡ (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
“አራት እግር ያሉአቸው የሚበርሩ ፍጥረታት”
ሕዝቡ ርኩስ አድርጐ መቁጠር ስላለባቸው እንስት እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን ይናገራል::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “የእነዚህን እንስሳት በድን አንዳቸውን ከነካችሁ ርኩስ ያደርጋችኋል” (ተሻጋሪ ግሥና የማይሻገር ግሥ የያዘውን ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ከእነዚህ በድን እንስሳት አንዱን በመንካቱ ምክንያት ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ተቀባይነት ያጣው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎ ተገልጾአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በሚቀጥሉት ጥቅሶች የተዘረዘሩ እንስሳትን ያመለክታል::
ሕዝቡ ርኩስ አድርጐ መቁጠር ስላለባቸው እንስሳት እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገር ይቀጥላል::
ሕዝቡ አንዲመገቡ ያልተገቡ እግዚአብሔር የተናገራቸው እነዚህ እንስሳት በአካል ርኩስ ተብለው ተገልጸዋል፡፡ (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ድፍን በመሆን ፈንታ ሰኰናው ለሁለት የተሰነጠቀ ማለት ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 11፡3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ይህ ምግብን ከሆድ እንደገና ወደ አፍ በማምጣት የሚያኝኩ እንስሳት ማለት ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 11፡3 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
እነዚህን እንስሳት በመንካቱ ምክንያት ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ያልተገባ ሰው በአካል ርኩስ ተደርጐ ተገልጾአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሾህና ያላቸው እንስሳት መረገጫ አካል
ጸሐይ እስክትጠልቅ
ሕዝቡ ርኩስ አድርጐ መቁጠር ስላለባቸው እንስሳት እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገር ይቀጥላል::
ሕዝቡ አንዲመገቡ ያልተገቡ እግዚአብሔር የተናገራቸው እነዚህ እንስሳት በአካል ርኩስ ተብለው ተገልጸዋል፡፡
ወፎችንና ትናንሽ እንስሳትን የሚመገብ ቡኒ ጸጉር ያለው ትንሽ እንስሳ ነው
እነዚህ አራት እግር ያላቸው የተለያዩ ተሳቢ እንስሳት ናቸው:: ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ::
በአሽዋ የማኖር እንሽላሊት ነው::
ሕዝቡ ርኩስ አድርጐ መቁጠር ስላለባቸው እንስሳት እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገር ይቀጥላል::
ሕዝቡ አንዲመገቡ ወይም እንዲነኩ ያልተገቡ እግዚአብሔር የተናገራቸው እነዚህ እንስሳት በአካል ርኩስ ተብለው ተገልጸዋል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ከነዚህ እንስሳት በድን አንዱን በመንካቱ ምክንያት ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ያልተገባ ሰው በአካሉ ርኩስ ተደርጐ ተገልጾአል:: (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ጸሐይ እስክትጠልቅ
ከነዚህ በድን እንስሳት አንዳቸው በመጣላቸው ምክንያት ሕዝቡ እንዲነኩአቸው ያልተገባ እግዚአብሔር የተናገረው ነገር በአካል ርኩስ ተደርጐ ተገልጾአል በውሃ ከታጠበ በኋላ ንጹህ ተደርጐ ተገልጾአል (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ከታጠበ በኋላ ሕዝቡ አንድነካ የተገባ እግዚአብሔር የተናገረው ነገር በአካል ንጹህ ተደርጐ ተገልጾአል፡፡
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ “የተጠቀሙ ቢሆን በውሃ ይደረግ ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ”
ርኩስ የሆነ ውሃ በላዩ ላይ በመፍሰሱ ምክንያት ሕዝቡ መብላት ያልተገባው ምግብ ርኩስ ተደርጐ ተነግሮአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሙት አካላት
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ ይህን ይሰባብሩት ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ፡፡
ሕዝቡ ርኩስ አድርጐ መቁጠር ስላለባቸው እንስሳት እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገር ይቀጥላል::
ከምንጭ ወይም ከውሃ ማጠራቀሚያ ሕዝቡ እንዲጠጣ የተፈቀደለት በአካል ንጹህ ተብሎ ተነግሮአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
እግዝአብሔር የተናገረው ሕዝቡ እንዲበላ ወይም እንዲነካ ያልተገባው የእንስሳ በድን በአካል ርኩስ ተብሎ ተገልጾአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
የእነዚህን እንስሳት በድን በመንካቱ ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ያልተገባ ሰው በአካል ርኩስ ተደርጐ ተነግሮአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ለመዝራት የሚያስቡት ዘር
ሕዝቡ እንዲዘራ የተገባው እግዚአብሔር የተናገረው ዘር ንጹህ ተደርጐ ሲገለጽ ያልተገባው ዘር ግን ርኩስ እንደሆነ ተነግሮአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል አት ነገር ግን በዘሩ ላይ ውሃ ከጨበሩበት ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ
የእንስሳ በድን በመንካቱ ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ያልተገባ ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያል አነጋገር ይመልከቱ)
ጸሐይ እስኪጠልቅ
ሕዝቡ ርኩስ አድርጐ መቁጠር ስላለባቸው እንስሳት እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገር ይቀጥላል::
ተሻጋሪ ግሥ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: “ተጸየፉት” ወይም “አትቀበሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ ይመልከቱ)
ተሻጋሪ ግሥ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: “ይህን አይብሉ”:: (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: “እነዚህን ተጸየፉአቸው” ወይም “ እነዚህን አትቀበሉአቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ ርኩስ አድርጐ መቁጠር ስላለባቸው እንስሳት እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገር ይቀጥላል::
ርኩስ እንስሳ እንዳይበሉ ያዘዛቸውን ትዕዛዝ ለማጠንከር እግዚአብሔር ሁለት ጊዜ ተመሣሣይ ሃሳብ ይደግማል:: (ተጓዳኝ ንጽጽር ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔር ዓላማ ያልተገባ ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል አት እንግዲህ ከእነርሱ የተነሣ ንጹሃን አትሆኑም (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሕዝቡ ምን እንዲበላ እንደፈቀደና ምን እንዳይበላ እንደከለከለ ለሙሴና ለአሮን በመናገር ያበቃል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል አት እናንተ መለየት ስለአለባችሁ ነገሮች (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ እንዲነካና እንዲበላ የተገባቸው እግዚአብሔር የተናገራቸው እንስሳት በአካል ርኩስ ተብለዋል እና ሕዝቡ እንዲነካና እንዲበላ የተነገራቸው በአካል ንጹህ ተብለዋል ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ
ይህ በተሻጋሪ ግሥ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፡ የሚትበሉትንና የማትበሉትን፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንደህ በላቸው፣ ‘አንዲት ሴት ብታረግዝና ወንድ ልጅ ብትወልድ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ወቅት ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለችም፡፡ 3 በስምንተኛው ቀን ህጻኑ ልጅ መገረዝ አለበት፡፡ 4 ከዚያ የእናቲቱ ከደሟ መንጻት ለሰላሳ ሶስት ቀናት ይቆያል፡፡ ምንም አይነት የተቀደሰ ነገር መንካት የለባትም ወይም የመንጻቷ ቀናት እስኪፈጸም ድረስ ወደ ቤተመቅደስ አትምጣ፡፡ 5 ሴት ልጅ ከወለደች፣ በወር አበባዋ ወቅት እንደነበረችው ለሁለት ሳምንታት ንጹህ አትሆንም፡፡ ከዚያ የእናትየው የመንጻት ስርዓት ለስድስት ቀናት ይቀጥላል፡፡ 6 ወንድ ልጅም ሆነ ሴት ልጅ ከወለደች በኋላ የመንጻቷ ቀናት ሲያበቃ ለካህኑ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ የአንድ አመት ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዕት እንዲሁም ለኃጢአት መስዋዕት ዋኖስ ወይም ዕርግብ ታቅርብ፡፡ 7 ከዚያ ካህኑ መስዋዕቱን በያህዌ ፊት ይሰዋና ያስተሰርይላታል፣ እናም ከደሟ መፍሰስ ንጹህ ትሆናለች፡፡ ወንድም ይሁን ሴት ልጅ ለወለደች ሴት ህጉ ይህ ነው፡፡ 8 ጠቦት ማቅረብ ባትችል፣ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት ርግቦች ትውሰድ፣ አንዱን ለሚቀጠል መስዋዕት ሌላውን ለኃጢአት መስዋዕት ታቅርብ እናም ካህኑ ያስተሰርይላታል፣ ከዚያም ንጹህ ትሆናለች፡፡’”
ከማዕጸንዋ ደም ስለሚፈስስ ሰዎች የማይነኩአት ሴት በአካል ርኩስ ተብላለች ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ
ይህ በወር ከማዕጸንዋ ደም የሚፈስስበት ጊዜ ያመለክታል (See Euphemism/ንኣብነት ወይም ጸያፍ አባበሎችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ካህኑ ብቻ ይህንን ድርጊት ይፈጽም ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል አት ካህኑ ወንድ ህጻን ልጅን ይገርዘው፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህች እናት ለሠላሣ ሶስት ቀናት ርኩስ ትሆናለች ማለት ነው፡፡
33 ቀናት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ከማዕጸንዋ ደም ስለሚፈስሳት ሌሎች ሰዎች የማይነኳት ሴት በአካል ርኩስ ትብላለች፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
14 ቀናት
ከማዕጸንዋ ደም የሚፈስስበት ወራዊ ጊዜ ያመለክታል በዘሌዋዊያን 12:2 እንዴት አንደተረጐሙ ይመልከቱ (See: Euphemism/ንኣብነት ወይም ጸያፍ/አሳፋሪ አባበሎችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
66 ቀናት
የአንድ እናት የመንጻት ቀኖችዋ ሲፈጸም
ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ ወልዳ ከሆነ የአንዱ እናት የመንጻት ቀኖችዋ የተለያየ እንደሆነ ያመለክታል፡፡
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ይህ በወሊድ ጊዜ ከሚፈስሳት ደም ያነጻታል”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የመስዋዕት እንስሳ የመግዛት አቅም ማነስ በሚገልጽ መንገድ ይተርጉሙ፡፡ አት፡ “ጠቦት ለመግዛት በቂ ገንዘብ ከሌላት”
ሌሎች ሰዎች መንካት የማችሏት ሴት በአካል ንጹህ ተብላለች፡፡
1 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ 2 “ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ችፍታ ወይም ቋቁቻ ቢወጣና ቢቆስል በሰውነቱ ላይ የቆዳ በሽታ ይሆናል፣ በዚህ ጊዜ ወደ ሊቀካህኑ አሮን ይምጣ፣ አሊያም ካህናት ከሆኑት ልጆቹ ወደ አንዱ ይምጣ፡፡ 3 ከዚያ በሰውነቱ ቆዳ ላይ ያለውን በሽታ ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ በበሽታው ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠ፣ እና በሽታው በቆዳው ላይ ከሚታየው ይልቅ የከፋ ሆኖ ከተገኘ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ካህኑ ከመረመረው በኋላ፣ ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ 4 በቆዳው ላይ የታየው ቋቁቻ ነጭ ከሆነ፣ እና ወደ ቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ እንዲሁም በህመሙ አካባቢ የሚገኘው ጸጉር ወደ ነጭነት ካልተለወጠ፣ ካህኑ በሽታው ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያገልግለው፡፡ 5 በሰባተኛው ቀን፣ ካህኑ በእርሱ እይታ በሽታው አየከፋ በቆዳው ላይ እየሰፋ አለመሄዱን ለማየት ይመርምረው፡፡ በሽታው ለውጥ ካላሳየ፣ ካህኑ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት ሰውየውን አግልሎ ያቆየው፡፡ 6 በሰባተኛው ቀን በሽታው እየተሻለው እንደሆነና በቆዳው ላይ እየሰፋ እንደላሆነ ለማየት ካህኑ ሰውየውን ደግሞ ይመረምረዋል፡፡ በሽታው ለውጥ ካለው፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆነኑን ይገልጻል፡፡ ይህ ሽፍታ ነው፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚህ በኋላ ንጹህ ነው፡፡ 7 ነገር ግን ሰውየው ራሱን ለካህን ካሳየ በኋላ ሽፍታው በቆዳው ላይ ከተስፋፋ፣ እንደገና ራሱን ለካህን ያሳይ፡፡ 8 ሽፍታው ይበልጥ በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ መሆኑን ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ከተስፋፋ፣ ከዚያ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አይደለም ይላል፡፡ ይህ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ነው፡፡ 9 ተላላፊ የቆዳ በሽታ በአንድ ሰው ላይ ሲገኝ፣ ይህ ሰው ወደ ካህን ይምጣ፡፡ 10 ካህኑ በሰውየው ቆዳ ላይ ነጭ ዕብጠት መኖሩን ለማየት ይመረምረዋል፣ ጸጉሩ ወደ ነጭነት መቀየሩን፣ ወይም በዕብጠቱ ላይ የስጋ መላጥ መኖሩን ይመልከት፡፡ 11 እንዲህ ያለ ነገር ካለ፣ ይህ ጽኑ የቆዳ ህመም ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፡፡ ሰውየውን አያገለውም፣ ምክንያቱም ቀድሞውኑም ንጹህ አይደለም፡፡ 12 በሽታው በቆዳው ላይ በሰፊው ጎልቶ ከታየና የሰውየውን ቆዳ ከአናቱ እስከ እግሩ ከሸፈና፣ ካህኑ ይህ እስከ ታየው ድረስ፣ በሽታው የሰውየውን አካል ሸፍኖት እንደሆነ ለማየት ይመርምረው፡፡ 13 እንዲህ ሆኖ ከተገኘ፣ በሽታው ያለበት ሰው ንጹህ አለመሆኑን ካህኑ ይግለጽ፡፡ ሁሉም ወደ ንጣት ተለውጦ ከሆነ ንጹህ ነው፡፡ 14 ነገር ግን የስጋ መላጥ ከታየበት፣ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡ 15 ካህኑ የስጋውን መላጥ ማየትና ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፣ ምክንያቱም የተላጠ ስጋ ንጹህ አይደለም፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ 16 ነገር ግን የተላጠው ስጋ መለልሶ ነጭ ቢሆን፣ ሰውየው ወደ ካህኑ ይሂድ፡፡ 17 ካህኑ ስጋው ወደ ነጭነት ተመልሶ እንደሆነ ይመረምረዋል፡፡ እንዲህ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ይገልጻል፡፡ 18 አንድ ሰው በቆዳው ላይ እባጭ ወጥቶ ሲድን፣ 19 እና በዕባጩ ስፍራ እብጠት ወይም ቋቁቻ፣ ቀላ ያለ ንጣት፣ ሲኖር ይህን ካህኑ ሊያየው ይገባል፡፡ 20 ካህኑ ይህ ወደ ታማሚው ቆዳ ዘልቆ የገባ መሆኑን እና በዚያ ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት መለወጡን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቃል፡፡ እብጠቱ በነበረበት ስፍራ እየሰፋ ከሄደ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ 21 ነገር ግን ካህኑ ይህንን መርምሮ በውስጡ ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ከተመለከተ፣ እና ይህም ከቆዳው ስር ካልሆነ ሆኖም ከደበዘዘ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡ 22 በቆዳው ላይ በሰፊው ከተስፋፋ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አይደለም ይበል፡፡ ይህ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡ 23 ነገር ግን ቋቁቻው በቦታው ከሆነና ካልተስፋፋ፣ ይህ የእባጩ ጠባሳ ነው፣ እናም ካህኑ ንጹህ ነው ብሎ ያስታውቅ፡፡ 24 አንድ ሰው ቆዳው ቃጠሎ ሲኖርበትና የስጋው መላጥ ቀላ ያለ ንጣት ወይም ነጭ ጠባሳ ሲሆን፣ 25 ካህኑ ያጠባሳ ስፍራ ወደ ንጣት መለወጡን እና ወደ ቆዳው ዘልቆ መግባቱን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንደዚህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ከቃጠሎው አልፎ ከውስጥ የመጣ ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ 26 ነገር ግን ካህኑ በሚመረምርበት ጊዜ በስፍራው ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ቢደርስበትና ቁስሉ ከቆዳው ስር ሳይሆን ቢቀር እየከሰመ ቢመጣ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡ 27 ከዚያም ካህኑ በሰባተኛው ቀን ይመርምረው፡፡ ምልክቱ በሰፊው በቆዳው ላይ ቢስፋፋ፣ ካህኑ ንጹህ አይደለም ብሎ ያሳውቅ፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ 28 ምልክቱ በስፍራው ከቆየና በቆዳው ላይ እየሰፋ ካልሄደ ነገር ግን ከከሰመ ይህ በቃጠሎው የመጣ እብጠት ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፣ ይህ ከቃጠሎው የመጣ ጠባሳ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፡፡ 29 በአንድ ወንድ ወይም ሴት ራስ ወይም አገጭ ላይ ተላላፊ በሽታ ቢኖር፣ 30 ችግሩ ከቆዳው ስር የዘለቀ መሆኑና በላዩ ቢጫ ስስ ጸጉር እንዳለ ለማየት ካህኑ ካህኑ የተላላፊ በሽታ ምርመራ ያድርግለት፡፡ ይህ ከተገኘ፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ይህ የሚያሳክክ በሽታ ነው፣ በራስ ወይም አገጭ ላይ የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ 31 የሚያሳክከውን በሽታ መርምሮ ከቆዳ ስር ያልዘለቀ መሆኑን ቢያይ፣ ደግሞም በውስጡ ጥቁር ጸጉር ባይኖር፣ ካህኑ ሰውየውን በሚያሳክክ በሽታው ምክንያት ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡ 32 በሰባተኛው ቀን በሽታው ተስፋፍቶ እንደሆነ ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ቢጫ ጸጉር ከሌለና፣ በሽታው ላይ ላዩን ብቻ ከታየ፣ 33 ሰውየው ይላጭ፣ ነገር ግን በሽታው የሚገኝበት ዙሪያ መላጨት የለበትም፣ እናም ካህኑ የሚያሳክክ በሽታ ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡ 34 በሰባተኛው ቀን በሽታው በቆዳው ላይ መስፋፋቱን ማቆሙን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያደርጋል፡፡ በሽታው ቆዳውን ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ ካህኑ የሰውየውን ንጹህ መሆን ያሳውቅ፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡ 35 ነገር ግን ካህኑ ንጹህ መሆኑን ካሳወቀ በኋላ የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ ከሄደ ፣ 36 ካህኑ ዳግም ይመርምረው፡፡ በሽታው በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ ከሄደ፣ካህኑ ቢጫ ጸጉር መኖሩን መፈለግ አይኖርበትም፡፡ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡ 37 ነገር ግን ካህኑ ሰውየውን የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ መሄዱን እንዳቆመ ከተመለከተ ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፡፡ 38 አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በቆዳቸው ላይ ነጭ ምልክቶች ቢወጣ 39 ምልክቱ ዳለቻ መልክ ያለው በቆዳ ላይ የወጣ ሽፍታ ብቻ መሆኑን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግ፡፡ ሰውየው ንጹህ ነው፡፡ 40 የሰውየው ጸጉር ከራሱ ላይ ካለቀ፣መላጣ ነው፣ ነገር ግን ንጹህ ነው፡፡ 41 ደግሞም ከፊት ለፊት ጸጉሩ ተመልጦ ራሰ በራ ቢሆንም ንጹህ ነው፡፡ 42 ነገር ግን በህመም ምክንያት ፈዘዝ ያለ ቅላት በተመለጠው ራሱ ላይ ወይም በግምባሩ ላይ ቢኖር፣ ይህ በተላላፊ በሽታ ምክንያት የመጣ ነው፡፡ 43 በቆዳ ላይ ተላላፊ በሽታ ሲኖር እንደሚታየው በመላጣው ወይም በበራው ላይ በህመሙ ዙሪያ ፈዘዝ ያለ ቅላት መኖሩን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግለት፡፡ 44 ይህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ አለበት እናም ንጹህ አይደለም፡፡ በእርግጥ ካህኑ ሰውየው በራሱ ላይ ካለበት በሽታ የተነሳ ንጹህ እንደልሆነ ያስታውቅ፡፡ 45 ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው የተቀደደ ልብስ ይልበስ፣ ጸጉሩን በከፊል ይሸፍን፣ እስከ አፍንጫው ይከናነብና ‘እርኩስ ነኝ፣ እርኩስ ነኝ’ እያለ ይጩህ፡፡ 46 ተላላፊው በሽታ ባለበት ቀናት ሁሉ እርኩስ ነው፡፡ እየሰፋ ሊሄድ በሚችል በሽታ ምክንያት ንጹህ ስላልሆነ፣ ለብቻው ይኑር፡፡ ከሰፈር ውጭ ይኑር፡፡ 47 በማናቸውም ነገር የተበከለ የሱፍም ሆነ የተልባ ዕግር ጨርቅ፣ 48 ወይም ከሱፍም ሆነ ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ፣ ወይም ቆዳም ሆነ ከቆዳ በተሰራ ልብስ - 49 በልብሱ ላይ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ ብክለት ቢገኝበት፤ በቆዳው፣ በተጠለፈው ወይም በተሰፋው ነገር፣ ወይም ማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ለይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ካህኑ ይህን ይመልከት፡፡ 50 ካህኑ የሚበከለውን ዕቃ ይመርምር፣ የተበከለውን ማናቸውንም ነገር ለሰባት ቀናት ይለየው፡፡ 51 በሰባተኛው ቀን እንደገና ብክለቱን ይመርምር፡፡ በልብሱ ወይም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ በተሸመነው ወይም በተጠለፈው ማናቸውም ልብስ ላይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ወይም በቆዳ ወይም ከቆዳ በተሰራ ማናቸውም ነገር ላይ ብክለቱ ቢሰፋ ጎጁ ነው፣ እናም ዕቃው ንጹህ አይደለም፡፡ 52 ካህኑ ያንን ልብስ ያቃጥል፣ ወይም ማናቸውም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ነገር፣ ማናቸውም ጎጂ ብክለት የተገኘበት ነገር በሽታ ያመጣልና ያቃጥለው፡፡ ዕቃው ሙሉ ለሙሉ ይቃጠል፡፡ 53 ካህኑ ዕቃውን መርምሮ ብክለቱ በልብ ወይም በተሸመነው ወይም በተለጠፈው ልብስ ወይም በቆዳ ዕቃዎቹ ላይ እየሰፋ የሚሄድ አለመሆኑን ካወቀ፣ 54 ብክለቱ የተገኘባቸውን ዕቃዎች እንዲያጥቡ ያዛቸዋል፤ ደግሞም ዕቃውን ለሰባት ቀናት ያግልል፡፡ 55 ከዚያ ካህኑ የተበከለውን ዕቃ ከታጠበ ከሰባት ቀናት በኋላ ይመረምረዋል፡፡ ብክለቱ ቀለሙን ካልቀየረውና እየሰፋ ባይሄድ እንኳን ንጹህ አይደለም፡፡ ብክለቱ የትም ላይ ይሁን ዕቃዎቹን አቃጥሏቸው፡፡ 56 ካህኑ ዕቃውን ከመረመረና ልብሱ ከታጠበ በኋላ ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ከተበከለው የልብሱ ወይም የቆዳው ክፍል ወይም ከተሸመነው ወይም ከተጠለፈው ዕቃ ቀድዶ ያውጣው፡፡ 57 እንዲህም ሆኖ ብክለቱ አሁንም በተሸመነው ወይም በተጠለፈው፣ ወይም በማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ላይ ከተገኘ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው፡፡ ብክለት ያለበትን ማናቸውንም ነገር አቃጥለው፡፡ 58 ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተሰራ ወይም የተለጠፈ ልብስ ወይም ማናቸውም ነገር፣ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ማናቸውም ነገር - ስታጥበው ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ዕቃው ዳግመኛ ይታጠብ እናም ንጹህ ይሆናል፡፡ 59 ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ለተሸመነ ወይም ለተጠለፈ፣ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ ለተሰራ ማናቸውም ነገር ብክለት ህጉ ይህ ነው፣ ስለዚህ ንጹህ ነው ወይም እርኩስ ነው ብለህ ማሳወቅ ትችላለህ፡፡”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ከዚያም አንድ ሰው ያምጣው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ከአሮን ልጆች ወደ አንዱ
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና ለአሮን መናገር ቀጠለ
እዚህ እርሱ የቆዳ በሽታ ያለበትን ሰው ያመለክታል
ከአንድ ሰው በቀላሉ ወደ ሌላው መተላለፍ የሚችል በሽታ
ካህኑም ሰውየው ርኩስ መሆኑን ይግለጽ፡፡ ሌሎች ሰዎች የማይነኩት ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ለ 7 ቀናት ቁጥሮችን ይመልከቱ”
እዚህ እርሱ የቆዳ በሽታ ያለበትን ሰው ያመለክታል
ይህም የቆዳው በሽታ መጠኑን ካልጨመረ ወይም ወደ ሌላው የሰውነት አካል ካልተላለፈ ማለት ነው
“ቀን 7” (ተራ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
“7 ቀናት” (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች መንካት የሚችሉት ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ
ይህ የሚያስከፋ የቆዳ አካል ነው ፤ነገር ግን ወደ ሌላ ሰው የማይተላለፍ ነው፡፡
በሽታው ያለበትን ሰው ያመለክታል
ሌሎች ሰዎች የማይነኩት ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
በዘሌዋዊያን 13፡3 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
በሽታው ተሠራጭቶ እንደሆነ ካህናት ይወስናሉ:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “አንድ ሰው ወደ ካህኑ ያምጣው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ ቀይ ሥጋ በእባጩ ላይ የተከፈቱ ቁስሎችን ወይም አዲስ ቆዳ ያደገውን ነገር ግን ዙሪያው እንደቆሰለ እንዳለ የሚያመለክት ነው፡፡
ይህ የተደገመ ወይም ለረጅ ጊዜ በተደጋጋሚ የሚከሰት ነው፡፡
ሌሎች ሰዎች ሊነኩት የማይችሉት ሰው በአካል ርኩስ ይባላል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል
ሌሎች ሰዎች ሊነኩት የሚችሉት ሰው በአካል ንጹህ ይባላል፤ እናም ሌሎች ሰዎች ሊነኩት የማይችሉት ሰው በአካል ርኩስ ይባላል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች የማይነኩት ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ ርኩስ የቆዳ በሽታ ያለበትን ሰው ያመለክታል
በዘሌዋዊያን 13፡1ዐ ይህን እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
በዘሌዋዊያን 13፡3 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ሌሎች ሰዎች የሚነኩት ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል
የሚያምም እብጠት የያዘ የቆዳ አካል ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱም ካህኑን ያሳየው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች የማይነካው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል
እዚህ “ይህ” በቆዳው ላይ የሚታይ ነጭ እብጠት ቀላ ያለ ነገር ማለት ነው
ሌሎች ሰዎች የማይነካው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች የማነካው ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
በዘሌዋዊያን 13፡3 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ሌሎች ሰዎች የማይነካው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
እዚህ “ይህ” በቆዳው ላይ የሚታይ ነጭ ጠባሳ ነገር ማለት ነው
ሌሎች ሰዎች የማይነካው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በዘሌዋዊያን 13፡3 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ሌሎች ሰዎች የሚነካው ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ሌሎች ሰዎች መንካት የማይገባው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ሰውየው በቁስሉ ላይ ያለውን ጸጉር ሳይሆን በቁስሉ ዙሪያ ያለውን ጸጉር ይላጭ”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
እዚህ የሚያሳክክ ቁስል በሰውየው ራስ ወይም ጉንጭ ላይ የሚታይ የሚያሳክክ ቁስል ያመለክታል ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ
ሌሎች ሰዎች የሚነካው ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ሌሎች ሰዎች መንካት የሚገባው ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች መንካት የማይገባው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ደለቻ/ደብዛዛ ነጭ ነገር
በዘሌዋዊያን 13:6 ይህን ቃል እንዴት አንደተረጐሙ ይመልከቱ::
እዚህ “እርሱ” በአጠቃላይ ለወንዶችና ለሴቶች እንዴሚውል ያመለክታል: አት: “ያ ሰው ንጹህ ነው” (የወንድ ጾታ ቃላት ሴት ጾታን ስለማካተት ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች መንካት የሚገባው ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ሌሎች ሰዎች መንካት የሚገባው ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
በዘሌዋዊያን 13:3 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ሌሎች ሰዎች መንካት የማይገባው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው የቆዳ በሽታ ሲኖረው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ሠፈር አብዛኛው እስራኤላዊያን የሚኖሩበት ቦታ ነው በሽታው ወደሌላ ሰው ስለሚዛመት ወይም ስለሚተላለፍ ንጹህ ያለሆነው ሰው በመካከላቸው እንደኖር አልተፈቀደም
ሌሎች ሰዎች መንካት የማይገባው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አረንጓደ ወይም ቀይ መሣይ ደዌ በላይ ላዩ ያለው ልብስ ወይም በለምጽ ደዌ የተበከለ ልብስ
በላዩ ላይ ጐጂ ነገር ስለታየበት ርኩስ ነው
በርጥብና በተጣሉ ነገሮች ላይ የሚበቅል በአብዛኛው ነጭ ሻገታ ፋንገስ ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “አንድ ሰው በሸማኔ ዕቃ ወይም በእጅ የሠራውን ማንኛው ነገር”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“አረንጓዴ ወይም ቀይ መሣይ ዴዌ በልብስ ላይ ቢገኝ”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “አንድ ሰው ከቆዳ የሠራው ማንኛው ነገር”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “የዕቃው ባለቤት ለካህኑ ያሣየው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“7 ቀናት” (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
“ሰባተኛ ለተራ ቁጥር 7 ነው”፡፡ (ተራ ቁጥሮች ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “አንድ ሰው ቆዳን የተጠቀመበቅ ማንኛውም ነገር”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ማንኛውንም ጐጂ ደወው ያለበትን ነገር ቢያገኝ”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ እንዲነካ ያልተገባው ማንኛውም ነገር በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ክፉ ደወው ዕቃውን የሚነካውን ሰው በሽታ ሊያስይዝ ይችላል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ዕቃውን ፈጽሞ ያቃጥለው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
የዕቃው ባለቤቶችን ካህኑ ይዘዝ እዚህ ሕዝቡ የተበከሉ የቤት ዕቃዎችን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ካህኑ ይናገራቸዋል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ክፉ ደዌውን ያገኙበት ነገር”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ዴዌው ያለበትን ነገር ካጠቡ በኋላ”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ሕዝቡ እንዲነካ ያልተገባው ማንኛውም ነገር በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ እርሱ ካህኑን አያመለክትም አንድ ሰው ዕቃውን ያቃጥል ማለት ነው፡፡
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ባለቤቱ ካጠበው በኋላ”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
እዚህ እርሱ በተለይ ካህኑን የሚያመለክት አይደለም አንድ ሰው ዕቃውን ማቃጠል አለበት ማለት ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ባለቤቱ የሚያጥብ በኋላ”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ሕዝቡ እንዲነካ የተገባው ማንኛውም ነገር በአካል ንጹህ ተብሎአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
በዘሌዋዊያን 13፡47-48 እንነዚህን ቃላት እንዴት አንደተረጐሙ ይመልከቱ፡፡
ስለሆነም ካህኑ ያስታውቀው
ሕዝቡ እንዲነካ የተገባው ማንኛውም ነገር በአካል ንጹህ ተብሎአል:: እናም ሕዝቡ እንዲነካ ያልተገባው ማንኛውም ነገር በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “የታመመ ሰው በሚነጻበት ቀን ህጉ ይህ ነው፡፡ ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡ 3 ካህኑ የሰውየው ተላላፊ የቆዳ በሽታ መዳኑን ለመመርመር ከሰፈር ይወጣል፡፡ 4 ከዚያም ካህኑ የሚነጻው ሰው ህይወት ያላቸው ሁለት ንጹህ ወፎችን፣ የጥድ ዕንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድርና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል፡፡ 5 ካህኑ የታመመው ሰው ከወፎቹ አንዱን አርዶ በሸክላ ማሰሮ ውስጥ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ 6 ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ፣የጥዱን እንጨትና፣ ደማቁን ቀይ ድርና ሂሶጵ ይቀበለውና ህይወት ያለውን ወፍ ጨምሮ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ቀደም ሲል በታረደው ወፍ ደምና ንጹህ ውሃ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ 7 ከዚያ ካህኑ ይህንን ውሃ ከበሽታው በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጫል፣ ከዚያ በኋላ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡ 8 የነጻው ሰው ልብሱን ያጥባል፣ ፀጉሩን በሙሉ ይላጫል፣ገላውንም ይታጠባል፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር ይመለስ፣ ነገር ግን ከድንኳኑ ውጭ ለሰባት ቀናት ይቆያል፡፡ 9 በሰባተኛው ቀን የራሱን ፀጉር በሙሉ ይላጭ፣ ልብሶቹን ይጠብ፣ ገላውን በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡ 10 በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸው ሁለት ወንድ የበግ ጠቦቶች፣አንድ ነውር የሌለበት የአንድ አመት የበግ ጠቦት ያምጣ፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ የላመ ዱቄት እና አንድ ሊትር ዘይት ለእህል ቁርባን ያቅርብ፡፡ 11 የመንጻት ስርዓቱን የሚያስፈጽመው ካህን የሚነጻውን ሰው ከእነዚህ ነገሮች ጋር ይዞ፣ በያህዌ ፊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይቆማል፡፡ 12 ካህኑ ወንዱን ጠቦት ወስዶ ለኃጢአት መስዋዕት ከአንዱ ሊትር ዘይት ጋር ያቀርባል፤ እነዚህንም በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ይወዘውዘዋል፤ ለእርሱም ያቀርበዋል፡፡ 13 ወንዱን ጠቦት የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ባቀረቡበት ስፍራ በቤተ መቅደስ ያርደዋል፤ እንደ በደል መስዋዕቱ ሁሉ የኃጢአት መስዋዕቱም ለካህኑ ይሰጥ፣ ምክንያቱም ይህ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡ 14 ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባ፡፡ 15 ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ወስዶ በእርሱ በራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣ 16 ከዚያም በግራ እጁ መዳፍ ላይ በፈሰሰው ዘይት ውስጥ የቀኝ እጁን ጣት ያጠልቃል፣ በጣቱ ላይ ካለው ዘይት በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡ 17 ካህኑ በእጁ ላይ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት፣ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡ ይህንን ዘይት በበደል መስዋዕቱ ደም ላይ ያድርገው፡፡ 18 ካህኑ በእጁ የቀረውን ዘይት፣ በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፍስስ፣ እናም ካህኑ በያህዌ ፊት የሚነጻውን ሰው ያሰርይለታል፡፡ 19 ከዚያ ካህኑ የኃጢአት መስዋዕቱን ይሰዋል፤ ደግሞም ንጹህ ባለመሆኑ ምክንያት መንጻት ላለበት ሰው ያሰርይለታል፣ እናም ከዚህ በኋላ የሚቃጠል መስዋዕቱን ይሰዋል፡፡ 20 ካህኑ የሚቃጠለውን መስዋዕትና የእህል ቁርባኑን በመሰዊያ ላይ ያቀርባል፡፡ ካሁኑ ለሰውየው ማስተስረያ ያቀርብለታል፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡ 21 ሆኖም ሰውየው ደሃ ከሆነና እነዚህን መስዋዕቶች ማቅረብ ካልቻለ ለኃጢአቱ ማስተስረያ የበደል መስዋዕት አንድ ወንድ ጠቦት፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄትና አንድ ሊትር ዘይት ያቅርብ፣ 22 ሰውየው በአቅሙ ከሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ጋር፣ አንደኛውን ወፍ የኃጢአት መስዋዕት ሌላኛው ደግሞ የሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል፡፡ 23 በስምንተኛው ቀን ስለ መንጻቱ ወደ መገናኛው ድንኳን በያህዌ ፊት ያምጣቸው፡፡ 24 ከዚያ ካህኑ ጠቦቱን ለበደል መስዋዕት ደግሞም አንዱን ሊትር ዘይት፣ይወስድና ለያህዌ የበደል መስዋዕት ይወዘውዛል፣ እናም ለእርሱ እነዚህን ያቀርባቸዋል፡፡ 25 ለበደል መስዋዕት ጠቦቱን ያርዳል፣ እናም ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡ 26 ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ጥቂቱን በገዛ ራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣ 27 በቀኝ ጣቱ ከዘይቱ በግራ እጁ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡ 28 ከዚያ ካህኑ በእጁ ካለው ዘይት ጥቂቱን በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ የበደል መስዋዕቱን ደም ባደረገበት ተመሳሳይ ስፍራዎች ይቀባል፡፡ 29 የተረፈውን በእጁ ያለውን ዘይት ያስተሰርይለት ዘንድ በያህዌ ፊት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሳል፡፡ 30 ሰውየው በአቅሙ ካቀረበው ከእርግቦቹ ወይም ከዋኖሶቹ አንዱን ይሰዋ - 31 ከእህል ቁርባኑ ጋር፣ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ከዚያም ካህኑ ለሚነጻው ሰው በያህዌ ፊት ያስተሰርይለታል፡፡ 32 ለመንጻት ዋናውን መስዋዕት ማቅረብ ለማይችል ተላላፊ የቆዳ በሽታ ላለበት ሰው የመንጻት ህጉ ይህ ነው፡፡” 33 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣ 34 “ርስት አድርጌ ወደሰጠኋችሁ ወደ ከነዓን ምድር ስትመጡ፣ ርስት በሆናችሁ ምድር በቤታችሁ እየሰፋ የሚሄድ ብክለት ባደርግባችሁ፣ 35 የቤቱ ባለቤት ወደ ካህኑ መጥቶ ይናገር፡፡ እንዲህም ይበል፣ “በቤቴ ብክለት ያለ ይመስለኛል፡፡’ 36 ከዚያ ካህኑ በቤቱ ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም ነገር እርኩስ እንዳይሆን ብክለት መኖሩን ለማየት ወደዚያ ቤት ከመግባቱ አስቀድሞ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉ ያዛል፣ ከዚህ አስቀድሞ ካህኑ ያንን ቤት ለማየት ይገባል፡፡ 37 ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መኖሩን፣ ደግሞም አረንጓዴ ሆኖ ወይም ቀላ ብሎ በግርግዳዎቹ ላይ መታየቱን ይመርምር፡፡ 38 ቤቱ ሻጋታ ካለው፣ ካህኑ ከዚያ ቤት ይወጣና ለሰባት ቀናት በሩን ይዘጋዋል፡፡ 39 በሰባተኛው ቀን ካህኑ ተመልሶ ይመጣና ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መስፋፋቱን ለማየት ይመረምራል፡፡ 40 እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ሻጋታ የተገኘባቸውን ድንጋዮች ከግድግዳው ላይ እየፈነቀሉ እንዲያወጡና ከከተማ ውጭ ቆሻሻ ስፍራ መጣያ እንዲጥሏቸው ያዛል፡፡ 41 የቤቱ የውስጥ ግድግዳዎች ሁሉ እንደዲፋቁ ይጠይቃል፣ እነርሱም እየተፋቁ የተነሱትን የተበከሉትን ቁሶች ከከተማ አውጥተው በቆሻሻ መጣያ ስፍራ ይጥላሉ፡፡ 42 ባስወገዷቸው ድንጋዮች ስፍራ ሌሎች ድንጋዮች ወስደው ያስቀምጡ፣ ቤቱን ለመምረግ አዲስ ጭቃ ይጠቀሙ፡፡ 43 ድንጋዮቹ ተነስተውና ግርግዳው ተፍቆ እንዲሁም ተለስኖ ዳግም ብክለቱ ከወጣና ከታየ፣ 44 ካህኑ ብክለቱ መስፋፋቱን ለመመልከት ቤቱን ይመርምር፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ይህ ጎጂ ብክለት ነው፤ ቤቱ ንጹህ አይደለም፡፡ 45 ቤቱ ይፍረስ፡፡ የቤቱ ድንጋዮች፣ በሮች፣ እና ፍርስራሾች ከከተማ ውስጥ በቆሻሻ መጣያ ይጣል፡፡ 46 በተጨማሪም፣ ቤቱ በተዘጋባቸው ጊዜያት ወደዚያ ቤት የሄደ ሁሉ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡ 47 ማንም በዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እንዲሁም በዚህ ቤት ውስጥ የተመገበ ሰው ልብሱን ይጠብ፡፡ 48 ቤቱ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ ወዴት እንደተስፋፋ ለመመርመር ካህኑ ወደዚያ ቤት ቢገባ፣ እናም ብክለቱ ተወግዶ ቢሆን ቤቱ ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ 49 ከዚያ ካህኑ ቤቱን ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የጥድ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድር እና ሂሶጵ ይውሰድ፡፡ 50 ከወፎቹ አንዱ ንጹህ ውሃ በያዘ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ያርደዋል፡፡ 51 የጥድ እንጨት፣ሂሶጵደማቅ ቀይ ድር እና በህይወት ያለ ወፍ ይውድና በታረደው ወፍ ደም ውስጥ እና በንጹህ ውሃ ውስት ይነክራቸዋል፣ከዚያም ቤቱን ሰባት ጊዜ ይርጨው፡፡ 52 ቤቱን በወፉ ደምና በንጹህ ውሃ፣ በህይወት በሚገኘው ወፍ፣ በጥድ እንጨት፣በሂሶጵና በደማቅ ቀይ ድር ያነጻዋል፡፡ 53 በህይወት የሚገኘውን ወፍ ግን ከከተማ ውጭ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡ በዚህ መንገድ ቤቱን ያስተሰርያል፣ ቤቱም ንጹህ ይሆናል፡፡ 54 ለሁሉም አይነት ተላላፊ የቆዳ በሽታና እንዲህ ያለውን በሽታ ለሚያመጡ ነገሮች፣ እንዲሁም ለሚያሳክክ ህመም፣ 55 እንዲሁም ለልብስና ለቤት ብክለት፣ 56 ለእብጠት፣ ለሚያሳክክ ህመም፣ እና ለቋቁቻ፣ 57 በእነዚህ ሁኔታዎች እርኩስና ንጹህ የሚሆነውን ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡”
አንድ ሰው ከቆዳ በሽታ ሲነጻ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ሰውየው በሥርዓቱ መሠረት ንጹህ እንደሆነ ካህኑ የሚያሳውቅበት ቀን ያመለክታል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “አንድ ሰው ወደ ካህኑ እንዲወስደው ይገባል”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
አንድ ሰው ከቆዳ በሽታ ሲነጻ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
በዘሌዋዊያን 13:3 እነዚህን ቃላት እንዴት አንደተረጐሙ ይመልከቱ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ሕዝቡ እንዲበላቸውና ለመሥዋዕትነት እንዲያቀርቡ የተፈቀዱ ወፎች በአካል ንጹህ ተብለዋል (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“ቀይ ድር”
ለመድኃኒትነት የሚጠቀሙት መልካም በዓዛ ያለው ዕጽ ነው (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
አንድ ሰው ከቆዳ በሽታ ሲነጻ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ሰውየው ያረደው ወፍ”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ተቀባይነት ያለውና ሌሎች ሰዎች ሊነኩት የሚችሉት ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል፡፡ ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ
አንድ ሰው ከቆዳ በሽታ ሲነጻ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ካህኑ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ሌሎች ሰዎች ሊነኩት የሚችሉት ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
እዚህ “እርሱ” የሚነጻውን ሰው ያመለክታል::
አንድ እፍ 22 ሊትር ነው:: መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎች ይመልከቱ
አንድ ሎግ ዐ.31 ሊትር ነው::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
አንድ ሎግ ዐ.31 ሊትር ነው:: መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎችን ይመልከቱ
ይህ ሀረግ የቀደመውን ሀረግ የሚገልጽና ካህኑ ጠባቱን የሚያርድበት ቦታ የሚናገር ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
አንድ ሎግ ዐ.31 ሊትር ነው:: መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎችን ይመልከቱ
በእግዚአብሔር መገኘት ጥቂት ዘይት ይርጭ
በመዳፉ ውስጥ ከቀረው ዘይት
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
በእግዚአብሔር መገኘት
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ):: ሰውየውም ንጹህ ይሆናል
ሌሎች ሰዎች ሊነኩት የሚችሉት ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
አንድ ሰው ከቆዳ በሽታ ሲነጻ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ለመግዛት ገንዘብ ከሌለው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ካህኑ ለእርሱ… ይወዘውዘው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
የእፍ አንድ አሥረኛ 22 ሊትር ነው
አንድ ሎግ ዐ.31 ሊትር ነው:: (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎችን ይመልከቱ)
አንድ ሎግ ዐ.31 ሊትር ነው:: (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎችን ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
አንድ ሰው ከቆዳ በሽታ ሲነጻ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን ይናገራል፡፡
ጥቂት ዘይት በእግዚአብሔር መገኘት ይርጭ:: በምን ላይ ካህኑ ዘይቱን እንደሚረጭ አልተገለጸም::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
“ካህኑ ይሠዋል”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እርሱ የሚያነጻው ሰው”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
በዘሌዋዊያን 13፡3 እንዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
መደበኛ መሥዋዕት ለመግዛት በቂ ገንዘብ የሌለው ሰው እንዳሆነ ግልጽ በማድረግ ይተረጉሙ:: አት “በቂ ገንዘብ የሌለው ሰው” (ግምታዊ ዕውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
እዚህ እናንተ የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል (ሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
በዘሌዋዊያን 13:47 ይህን ቃል እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
“ርስት አድርጌ የሚሰጣቸው” በግሥ መልክ ሊተረጐም ይችላል አት “የሚትወርሱት ምድር” (ረቂቅ ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
አንደ ካህኑ ቤቱ ርኩስ መሆኑን ካስታወቅ በቤቱ ውስጥ ያለው ሁሉም ነገር ርኩስ ይሆናል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “በቤት ውስጥ የቀረው ምንም ነገር ርኩስ መሆኑን ማስታወቅ አይገባውም”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ሕዝቡ እንዲኖሩት ወይም እንዲነኩት ያለተገባ እንደሆነ እግዚአብሔር የተናገረው ቤት በአካል ርኩስ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ክፉ ደዌው ከግድግዳዎች ላይኛው አካል ከፍል ባለፍ ሠርጾ የገባ እንደሆነ ካህኑ መርምሮ የሚወስንበት ማለት ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ክፉ ደዌውን ካገኙ”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ሕዝቡ እንዳይሠፍር ወይም ለእግዚአብሔር ዓላማዎች የማይጠቅም እግዚአብሔር የተናገረው ሥፍራ በአካል ርኩስ ተብሎአል ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ
እዚህ እርሱ ካህኑን ያመለክታል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ባለቤቱ የቤቱን ውስጠኛ ግድግዳዎችን ይፍቃል”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ይህም ክፉ ደዌ የነካው ዕቃ ማለት ነው ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እነርሱ የሚፍቁት የተበከለው ዕቃ”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ሕዝቡ እንዳይሠፍር ወይም ለእግዚአብሔር ዓላማዎች የማይጠቅም እግዚአብሔር የተናገረው ሥፍራ በአካል ርኩስ ተብሎአል ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ
ይህም ክፉ ደዌ የነካው ዕቃ ማለት ነው ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “እነርሱ ያስወገዱአቸው ድንጋዮች”፡፡ (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ድንጋዮችን በአድስ ጭቃ ይሸፍኑ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ባለቤቱ ቤቱ ውስጥ ድንጋዮችንና የግድግዳዎችን ፍቅፋቂ ካስወገደ በኋላ አድስ ድንጋዮችን በጭቃ ይመርጋል፡፡” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ሰዎችን ለማኖር ያልተገባ ቤት በአካል ርኩስ ተብሎአል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ቤቱን ይፍርሱት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ድንጋዩን እንጨቱንና ምርጊቱን ያስወጡት/ያስወግዱት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ቤቱን በመግባቱ ምክንያት ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ያልተገባውና ሰዎች የማይነኩት ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል፡፡ ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ፡፡
ጸሐይ እስኪጠልቅ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ባለቤቱ በአዲስ ጭቃ ድንጋዮችን ከመረገ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ሰዎችን ለማኖር የተገባ ቤት በአካል ንጹህ ተብሎአል
በዘሌዋዊያን 14:4 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ያረደው ወፍ ደም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
“ካህኑ በሥርዓቱ መሠረት ቤቱን ያንጻ”
ሰዎችን ለማኖር የተገባ ቤት በአካል ንጹህ ተብሎአል:: (ዜይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በዘሌዋዊያን 13፡3 እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
በዘሌዋዊያን 13፡47 ይህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
በዘሌዋዊያን 13:6 ይህን ቃላት እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
ሌሎች ሰዎች የማይነኩት ሰውና ዕቃዎች በአካል ርኩስ ተብለዋል እናም ሰዎች መንካት የሚችሉአቸው በአካል ንጹህ ተብለዋል:: (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣ 2 ‹ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብላችሁ ንገረቸው፣ ‹ማንም ሰው ከሰውነቱ የሚወጣ የሚመረቅዝ ፈሳሽ ሲኖርበት፣ ንጹኅ አይደለም፡፡ 3 ንጹኅ የማይሆነ ከሚመረቅዝ ፈሳሽ የተነሳ ነው፡፡ ከሰውነቱ የሚወጣ ፈሳሽ ቢቀጥል ወይም ቢቆም ንጹህ አይደለም፡፡ 4 የሚተኛበት አልጋ ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፣ የሚቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፡፡ 5 አልጋን የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ ሰውየውም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹኅ አይደለም፡፡ 6 የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበት ሰው በተቀመጠበት ማናቸውም ነገር ላይ የተቀመጠ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 7 የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበትን ሰው አካል የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፡፡ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 8 እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ሰው ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ፣ ያ ሰው ልብሱን ማጠብና እርሱም በውሃ መታጠብ አለበት፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡ 9 ፈሳሽ ያለበት ሰው የተቀመጠበት ማንኛውም ኮርቻ ንጹኅ አይደለም፡፡ 10 ከዚያ ሰው በታች ያለን ማንኛውንም ነገር የነካ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፣ እነዚያን ነገሮች የተሸከመ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡ 11 እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ማንም ቢሆን አስቀድሞ እጆቹን በውሃ ሳያጠራ ቢነካ፣ የተነካው ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡ 12 እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበትን ሰው የነካ ማናቸውም አይነት የሸክላ ዕቃ ይሰበር፣ የእንጨት የተሰራ ማጠራቀሚያ ሁሉ በውሃ ይንጻ፡፡ 13 ፈሳሽ ያለበት ሰው ከፈሳሹ ሲነጻ ለመንጻቱ ለእራሱ ሰባት ቀናትን ይቁጠር፤ ከዚያ ልብሶቹን ይጠብ ሰውነቱን በምንጭ ውሃ ይታጠብ፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡ 14 በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ኖሶች ይውሰድና ወደ መገናኛ ድንኳን ያህዌ ፊት ይቅረብ፣ በዚያ ወፎቹን ለካህኑ ይስጥ፡፡ 15 ካህኑ አንዱን ለሀጢአት መስዋዕት እና ሌላውን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርባቸው፣ እናም ካህኑ ለሰውዬው ስለ ፈሳሹ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡ 16 የማንንም ሰው የዘር ፈሳሽ ሳይታሰብ በድንገት ከእርሱ ቢወጣ፣ መላ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡ 17 ማናቸውም የዘር ፈሳሽ የነካ ልብስ ወይም ሌጦ በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡ 18 አንዲት ሴትና አንድ ወንድ አብረ ቢተኙና ወደ እርሷ የዘር ፈሳሽ ቢተላለፍ ሁለቱም በውሃ ይታጠቡ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደሉም፡፡ 19 አንዲት ሴት የወር አበባ ሲፈሳት፣ ያለመንጻቷ ለሰባት ቀናት ይቀጥላል፣ እርሷን የነካ ሁሉ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 20 በወር አበባ ወቅት የምትተኛበት ማንኛውም ነገር ንጹህ አይደለም፤ እንደዚሁም የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይደለም፡፡ 21 አልጋውን የነካ ማንኛም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ ያሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 22 የተቀመጠችበትን ማናቸውንም ነገር የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ ያ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 23 በአልጋም ይሁን በማንኛም ነገር ላይ ብትቀመጥ የተቀመጠችበትን ነገር የነካ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 24 ከእርሷ ጋር የተኛ ንጹህ ያልሆነ ፈሳሽ ቢነካ፣ ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለም፡፡ የሚተኛበትም አልጋ ንጹህ አይደለም፡፡ 25 አንዲት ሴት ከወር አበባ ቀናት በኋላ ለብዙ ቀናት ደም መፍሰሱን ቢቀጥል፣ ይህም ከወር አበባ ጊዜያት በኋላ ፈሳሽ ቢኖርባት፣ ንጹኅ ባልሆነችባቸው ፈሳሽ ባለባት ጊዜያት ሁሉ፣ በወር አበባ ወቅት ላይ እንዳለች ሁሉ እርኩስ ይሆናል ንጹህ አይደለችም፡፡ 26 ደሟ በሚፈስባቸው ጊዜያት የምትተኛበት አልጋ ሁሉ በወር አበባ ወቅት እንደምትተኛበት እርኩስ ይሆናል፣ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ልክ በወር አበባ ወቅት እንደሚሆነ ንጹህ አይደለም፡፡ 27 ደግሞም ከእነዚህ ነገሮች ማናቸንም የነካ ሁሉ ንጹህ አይደለም፤ ልብሶቹን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡ 28 ነገር ግን ከደም መፍሰሳ ብትነጻ፣ ለራስዋ ሰባት ቀናትን ትቆጥራለች፣ እናም ከዚያ በኋላ ንጹኅ ናት፡፡ 29 በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ትወሰድና ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለካህኑ ትስጥ፡፡ 30 ካህኑ አንዱን ወፍ ለሀጢአት መስዋእት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፣ ስለ ፈሳሽም እርኩሰት በያህዌ ፊት ያስተሰርይላታል፡፡ 31 የእስራኤል ሰዎች ከእርኩሰታቸው የምትይች እንደዚህ ነ፣ ይህ ከሆነ በመካከላቸ የምኖርበትን ቤተ መቅደሴን በማርከስ በእርኩሰታቸ አይሞቱም፡፡ 32 ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚጣ፣ የዘረ ፈሳሹ ከእርሱ ለሚጣና ለሚያረክሰ ማንኛም ሰ ህግጋቱ እነዚህ ናቸ፡፡ 33 ለማንኛም በር አበባ ላይ ላለች ሴት፣ ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚፈሰ ሰ ሁሉ፣ ንድም ይሁን ሴት፣ እንዲሁም ንጹህ ካልሆነች ሴት ጋር ለሚተኛ ንድ ህጉ ይህ ነ፡፡”
የሰው አካል ክፍሎች የሚወጣ (See Euphemism/ንኣብነት ወይም ጸያፍ/አሳፋሪ አባበሎችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች የማይነኩት ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል(ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“አካሉ ርኩስ ነው”
ሰውየው የተኛበት አልጋ ወይም የተቀመጠበት ማንኛውም ነገር ሌሎች ሰዎች የማይነኩት በአካል ርኩስ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች የማይነካው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“ጸሐይ እስኪጠልቅ”
ሌሎች ሰዎች የማይነካው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“ጸሐይ እስኪጠልቅ”
ማንኛውንም የአካል ክፍል የሚነካ
ሌሎች ሰዎች መንካት የሚችሉት ሰው በአካል ንጹህ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች የማይነካው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ኮረቻ በፈረስ ላይ ለመቀመጥ በጀርባው የሚቀመጥ ከቆዳ የተሥራ መቀመጫ ነው
መንካት ያልተገባ እግዚአብሔር የተናገረው ማንኛውም ነገር በአካል ርኩስ ተብሎአል ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ
ቁስልን ለማስወገድ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴና አሮን መናገር ይቀጥላል
የቁስል ፈሳሽ ያለውን ሰው ያመለክታል
ሌሎች ሰዎች የማይነካው ሰው በአካል ርኩስ ተብሎአል፡፡ (ዜይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“ጸሐይ እስኪጠልቅ”
ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው የነካው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል፡፡ አት፤ “ፈሳሽ ነገር በሚወጣው ሰው የተነካው ሰው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የሚነካውን ማንኛውንም የሸክላ ዕቃ ይስበሩት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “የእንጨቱንም ዕቃ ሁሉ አንድ ሰው በውሃ ይጠበው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ከበሽታው እየገገመ ያለው ሰው በአካል ንጹህ እንደሆነ ተገልጾአል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ከፈሳሽ ነገር ይፈወሳል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር እና ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች መንካት የሚችለው ሰው በአካል ንጹህ እንደሆነ ተነገሮአል:: (ዘይቤያዊ አጋገር ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች መንካት የሌለባቸው ሰዎችና ዕቃዎች በአካል ርኩስ ተብለዋል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ጸሐይ እስኪትጠልቅ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አንድ ሰው ዘር የነካውን ልብስ ወይም ቁርበት ሁሉ በውሃ ማጠብ አለበት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሁለቱም ከሴት ማዕጸን ደም የሚፈስስበትን ጊዜ ያመለክታሉ
“ንጹህ እንዳልሆነች ይቀጥላል”
ሌሎች ሰዎች መንካት የሌለባቸው ሰዎችና ዕቃዎች በአካል ርኩስ ተብለዋል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ የወር አበባ የሚፍስሳትን ሴት ያመለክታል
ሌሎች ሰዎች የማይነኩት ሰው በአካል ርኩስ ይባላል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ንጹህ ያልሆነው ፈሳሽዋ ወይም ከማዕጸንዋ የሚወጣው ፈሳሽ
ሌሎች ሰዎች መንካት የሌለባቸው ሰዎችና ዕቃዎች በአካል ርኩስ ተብለዋል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ከመደበኛ የወር አበባዋ ጊዜ ውጪ ከማዕጸንዋ ደም የሚፈስሳት ከሆነ እንደወር አበባዋ ጊዜ ርኩስ ነች ማለት ነው::
ሌሎች ሰዎች መንካት የሌለባቸው ሰዎች በአካል ርኩስ ተብለዋል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች የማይነኩት ዕቃዎች በአካል ርኩስ ተብለዋል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)::
እዚህ “እርስዋ” የሚለው የወር አበባ ያላትን ሴት ነው::
ከፍሳሽዋ እየተሻላት ያለች ሴት በአካል ንጹህ ተብላለች ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ከደምዋ ፍሳሽ እየተሻላት ያለች” (ዘይቤያዊ አገላለጽ እና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች መንካት የሚችሉአት ሴት በአካል ንጹህ ተብላለች (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)::
ስለራስዋ ታቀርባለች
ርኩስ የሚያደርጋት የደም ፍሳሽዋ
ሕዝቡን ከሚያረክሰው ነገር ስለመከላከል እግዚአብሔር የሚናገረው ሕዝቡን ከርኩሰት በርቀት እንደመጠበቅ ተገልጾአል:: “ርኩሰት” የተባለው ረቂቅ ስም እንደ “ርኩስ” ሊገለጽ ይችላል:: አት ይህ የእስራኤልን ሕዝብ ከርኩሰት ለመከላከሉበት ነው (ዘይቤያዊ አገላለጽ እና ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ሌሎች ሰዎች የማይነኩአቸውና ለእግዚአብሔር ዓላማ ተቀባይነት የሌላቸው ሰዎች በአካል ርኩስ ተብሎአል ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ
እነዚህ መደረግ የሚገባቸው ነገሮች ናቸው::
ሌሎች ሰዎች የማይነኩአቸው ሰዎች በአካል ርኩስ ተብለው ተገልጸዋል::
የወር አበባ የሚፈስሳት ወይም ከማዕጸንዋ ደም የሚፈስሳት
1 ያህ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረ፡ - ይህ የሆነ የአሮን ሁለቱ ልጆች ¨ደ ያህ«ከቀረቡና ከሞቱ በሀላ ነበር፡፡ 2 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለ፣ “ለ¨ንድምህ ለአሮን እንዲህ ብለህ ተናገረ፣ በፈለገ¬ ጊዜ ሁሉ በመጋረጃ ¬ስጠኛ ¨ዳለ ¨ደ ቅድስተ ቅዱሳኑ፣ በታቦቱ ላይ ወዳለ ወደ ማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ላይ እገለጣለሁ፡፡ 3 ስለዚህም አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መቅረብ ያለበት እንደዚህ ነው፡፡ ለሀጢአት መስዋዕት ወይፈን፣ ለሚቃጠል መስዋዕት አ¬ራ በግ ይዞ መግባት አለበት፡፡ 4 ቅዱሱን በፍታ ቀሚስ ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ የስጥ ሱሪ ይልበስ፣ ደግሞም የበፍታ መጠምጠሚያ የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፡፡ ቅዱሳኑ አልባሳት እነዚህ ናቸው፡፡ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብና እነዚህን ልብሶች ይልበስ፡፡ 5 ከእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁለት ወንድ ፍየሎችን ለሀጢአት መስዋዕት እንዲሁም አንድ አ¬ራ በግ ለሚቃጠል መስዋዕት ይውሰድ፡፡ 6 ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማ¬ን ለኃጢአት መስዋዕት ያቅርብ፣ ይህም ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ነው፡፡ 7 ቀጥሎም ሁለቱም ፍየሎች ወስዶ በመገናኛ¬ ድንኳን መግቢያ ላይ በያህዌ ፊት ያቁማቸው፡፡ 8 ከዚያ አሮን በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጣል፣ አንዱን ዕጣ ለያህዌ ሌላ¬ን ዕጣ ለሚለቀቀው ፍየል ይጣል፡፡ 9 ከዚያም አሮን ዕጣ ለያህ«የ¨ጣለትን ፍየል ያቀርባል፣ ያንን ፍየልም ለኃጢአት መስªዕት ያቀርበªል፡፡ 10 ለመለቀቅ ዕጣ የጣትን ፍየል ግን ወደ ምድረበዳ በመልቀቅ ለስርየት ከነህይ¨ት ለያህዌ መቅረብ አለበት፡፡ 11 ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማን ለሀጢአት መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ማድረግ አለበት፣ ስለዚህ ኮርማን ለራሱ የሀጢአት መስዋዕት አድርጎ ይረዳ፡፡ 12 አሮን በያህዌ ፊት ከመሰዊያ የከሰል እሳት የሞላውን ማጠንት ይውሰድ፣ በእጆቹ ሙሉ የላመ ጣፋጭ ዕጣን ይያዝና እዚህንም ነገሮች ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡ 13 በዚያም በያህ«ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ይጨምር፣ ከእጣኑ የሚ¨ጣ ጢስ በምስክሩ ላይ ያለ የማስተሰርያን ክዳን ይሸፍናል፡፡ እንዳይሞት ይህንን ያድርግ፡፡ 14 ከዚያም ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውሰድና በጣቱ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ ከደሙ ጥቂት ¨ስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡ 15 ከዚያም ለህዝቡ ኃጢአት የኃጢአት መስªዕት ፍየሉን ይረድና ደሙን ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡ በዚያም በኮርማ ደም እንዳደረገ ሁሉ ያድርግ በማስተሰርያ¬ ክዳን ላይ ደሙን ይርጭ ከዚያም በማስተሰርያ¬ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡ 16 በእስራኤል ህዝብ ያልተቀደሱ ተግባራት፣ በአመጻቸ¬ና በኃጢአቶቻቸ¬ ሁሉ ምክንያት ለተቀደሰ ስፍራ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡ ንጹህ ያልሆኑ ተግባሮቻቸ¬ በታዩ ጊዜያት፣ ያህ በመካከላቸ¬ ለሚያድርበት ለመገናኛ¬ ድንኳንም ይህን ያድርግ፡፡ 17 አሮን ለማስተሰርይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚገባበት ሰዓትና እንዲሁም ለእርሱ፣ ለቤተሰቡና ለእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ማስተሰርዩን እስከሚጨርስ ድረስ ማንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አይገኝም፡፡ 18 በያህ«ፊት ወዳለ መሰዊያ ይሂድና መሰዊያን ያስተሰርይ፣ ከኮርማ ደም ጥቂት እንዲሁም ከፍየሉ ደም ጥቂት ይ¬ስድና በመሰዊያ ዙሪያ ባሉ ቀንዶች ሁሉ ¬ስጥ ያስነካ፡፡ 19 መሰዊያዉን ንጹህ ካልሆነ የእስራኤል ሰዎች ድርጊቶች ለማንጻትና ለያህዌ ለመለየት በላዩ ካለ ጥቂት ደም ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭ፡፡ 20 ቅድስተ ቅዱሳኑን፣ የመገናኛን ድንኳንና መሰዊያን ማስተሰርያ¬ን ሲጨርስ በህይወት የሚገኘ¬ን ፍየል ያቅርብ፡፡ 21 አሮን ህይወት ባለው ፍየል ላይ ሁለቱንም እጆቹን ይጫንና የእስራኤልን ህዝብ በደልን ሁሉ፣ አመጻቸውን ሁሉ፣ እና ሀጢአታቸውን ሁሉ በላዩ ላይ ይናዘዝበት፡፡ ከዚያም ያንን ሃጢአተኛነት በፍየሉ ራስ ላይ አድርጎ ፍየሉን ወደ በረሃ ለመስደድ ኃላፊነት ባለበት ሰው አማካይነት ወደ በረሃ ያባው፡፡ 22 ፍየሉ የሰቹን በደል ሁሉ ይሸከምና ገለልተኛ ¨ደ ሆነ ስፍራ ይሄዳል፡፡ በበረሃ ስፍራም፣ ሰ¬ዬ¬ ፍየሉን ይለቀªል፡፡ 23 ከዚያም አሮን ወደ መገናኛ ድንኳን ይመለስና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ከመሄዱ አስቀድሞ የለበሰን የበፍታ ልብሶች ያወልቃል፣ እነዚያን ልብሶችም በዚያ ስፍራ ያስቀምጣቸዋል፡፡ 24 በተቀደሰ ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያም የዘወትር ልብሱን ይልበስ፣ ከዚያም ወጥቶ የራሱን የሚቃጠል መስዋዕቱን የህዝቡን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መንገድ ለራሱና ለህዝቡ ማስተሰርያ ያቀርባል፡፡ 25 በመሰዊያ ላይ የኃጢአት መስዋዕቱን ስብ ያቃጥል፡፡ 26 የሚሰደደውን ፍየል የለቀቀው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡ 27 በተቀደሰው ስፍራ ለማስተሰርያው ደማቸው የቀረበው የኃጢአት መስªዕቱ ኮርማ እና የኃጢአት መስªዕቱ ፍየል ከሰፈር ውጭ ይውስዳቸው። በዚያም ቆዳቸውን፣ ስጋቸውንና ፈርሳቸውን ያቃጥላFቸው፡፡ 28 እነዚህን የእንስሳውን ክፍሎች የሚያቃጥለው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ፣ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡ 29 በሰባተኛው ወር፣ በወሩ በአስረኛው ቀን ራሳችሁን ትሁት ታደርጋላችሁ ስራም አትሰሩበትም ለእናንተም ሆነ ለመጻተኛው ይህ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፡፡ 30 ይህ የሚሆነው በዚህ ዕለት በያህዌ ፊት ቅዱስ ትሆኑ ዘንድ ከኃጢአቶቻችሁ ሁሉ እንድትነጹ ማስተሰርያ ስለሚደረግላችሁ ነው፡፡ 31 ይህ ለእናንተ ክቡር ሰንበት ዕረፍት ነው፣ ራሳችሁን ትሁት ማድረግ አለባችሁ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡ይህ በእናንተ መሀል ሁልጊዜም መታሰቢያ ነው 32 ሊቀ ካህኑ፣ በአባቱ ስፍራ ሊቀካህን ሊሆን የሚቀባውና የሚሾመው፣ ይህን ማስተሰርያ ማስፈጸምና ቅዱስ የሆነውን የበፍታ ልብሶች መልበስ አለበት፡፡ 33 ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመስዋዕቱ፣ ማስተሰርያ ያደርጋል፤ እንደዚሁም ለካህናቱና ለጉባኤው ሰዎች በሙሉ ማስተሰርያ ያደርጋል፡፡ 34 "ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፣ ለእስራኤል ሰዎች ለኃጢአቶቻቸው ሁሉ ማስተሰርያ ለማቅረብ ይህ በየአመት አንድ ጊዜ ይደረግ፡፡” ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ተደረገ፡፡
ናዳብና እብዩድ ይመለከታል እግዚአብሔር ያልተቀበለውን እሳት በማቅረባቸው ምክንያት ሞተዋል ዘሌዋዊያን 1ዐ: 1-2 ይመልከቱ::
“ይህም እንዲህ”
“ከውጨኛው ልብስ ውስጥ በሰውነት ላይ የሚያርፍ ከበፍታ የተሠራ ልብስ”
“በወገብ ወይም በደረት ዙሪያ የሚታጠቅ ከቀጭን ረጅም ጨርቅ የተሠራ”
“ከጨርቅ ክፍልፋዮች የተሠራ ጭንቅላት መሸፈኛ ሻሽ”
“ከእስራኤል ጉባዔ”
ስለራሱ የኃጢአት መስዋዕት
የሚለቀቀው ፍዬል አሮንም አንድ ሰው ፍዬሉን ወደ ምድረ በዳ እንዲለቅቀው ያደርጋል
ዕጣው የመደበው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ነገር ግን አሮን ፍዬሉን በሕይወት በእግዚአብሔር ፊት ማቅረብ አለበት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
በማስተሠረያ ቀን አሮን ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
በኋላ በመሠዊያው መክደኛ ላይ ለመርጨት አሮን የወይፈኑን ደም በሳኀን ይያዝ የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ካህናት የሚጠቀሙት የእሳትና የዕጣን መያዣ
መልካም በዓዛ የሚያሸት ዕጣን ይህ የዕጣኑን ሽታ ያመለክታል እንጂ ጣፋጭነት አይደለም
ይህ በዘሌዋዊያን 16:11 እንደተገለጸው አሮን በሳህን የያዘው ደም ነው::
ደሙን ለመርጨት ጣቱን ይጠቀም
በመክደኛው ላይ ደም ያድርግ ወይም ይርጭ እንዲሁ ደግሞ ወደ ቅዱሳነ ቅዱስ እንደገባ ከፊት ለፊቱ በመክደኛው ጐን ይርጨው
ሁኔኛ ትርጉሞች: 1) ከሥርየቱ መክደኛ በታች በደረት አካባቢ 2) በሥርየቱ መክደኛ ፊት በመሬት
በማስተሠረያ ቀን አሮን ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
አሮን በወይፈኑ ደም እንዳደረገው ሁሉ ደሙን ይርጨው የቀደሙ ሕጐችን በዘሌዋዊያን 16:14 እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
የእስራኤል ኃጢአት ቅድስተ ቅዱሳኑን አርክሶአል
እነዚህ ቃላት በመሠረቱ አንድ ናቸው ሰዎች ሁሉ ዓይነት ኃጢአቶች እንደሠሩ አበክረው ያሳያሉ
ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዳይኖር የሚያደርጉ ኃጢአታዊ ድርጊቶች ርኩስ ድርጊቶች ተብለዋል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“ርኩሰት ድርጊቶቻቸው” የሚለው ሀረግ ኃጢአታዊ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ሰዎችን ያመላክታል (See Metonymy/ምትክ ተመሳሳይ አባባሎች ይመልከቱ)
ይህ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኝ የመሥዋዕት መሠዊያ ነው
እንደ ቅዱስ ቦታና መገናኛ ድንኳን መሠዊያው ከሰዎች ኃጢአት የተነሣ ርኩስ ይሆናል
በመሠዊያው ማዕዘናት ያሉ ቅርጾች ይህም የመሠዊያው ማዕዘናት ያመለክታል:: እንደ በሬ ቀንዶች የተቀረጹ ናቸው:: በዘሌዋዊያን 4:7 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች መጠቀሚያ የሚገባው መሠዊያ ንጹህ እንደሆነ ተገልጾአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔር የተለየው መሠዊያ ከሕዝቡም ኃጢአት አንደተለየ ተደርጐ ተነግሮአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
በእግዚአብሔር ፊት ሰዎች ተቀባይነት እንዳይኖራቸው የሚያደርጉ ኃጢአታዊ ድርጊቶች ርኩስ ድርጊቶች ተብለው ተነግረዋል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ፍዬል በዘለዋዊያን 16:1ዐ ላይ የሚለቀቅ ፍዬል ተብሎአል::
በፍዬሉ ላይ ይናዘዝበት
እዚህ የአሮን ድርጊቶች ያ ፍዬል የበደላቸውን ቅጣት እንደሚሸከም ዓይነት የሕዝቡን ኃጢአት ወደ ፍዬሉ የማስተላለፍ ምልክት ናቸው:: (ምልክታዊ ድርጊቶችን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁሉ በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: ሕዝቡ የፈጸመውን ማንኛውንም ኃጢአት አሮን ይናዘዛል::
እነዚህ አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሰኑ በሚገባበት ጊዜ የሚለብሱአቸው ልዩ ልብሶች ናቸው::
እዚህ “ቅዱስ ሥፍራ” የመገናኛ ድንኳን አያመለክትም:: ይህ ሰውነቱን እንዲታጠብ የተለየ ልዩ ሥፍራ ነው::
እነዚህ ለመደበኛ ተግባራት አሮን የሚለብሱአቸው ልብሶች ናቸው፡፡
“አሮን ያቅጥል”
የሕዝቡን ኃጢአት የተሸከመውን የሚለቀቀውን ፍዬል ስለነካ ሰውየው ርኩስ ነው
“ተለቅቆ የሚሄድ ፍዬል” በዘሌዋዊያን 16:8 ይህን እንዴት አንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መልክ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አሮን ያገባቸው ደማቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አንድ ሰው ተሸክሞ ይውሰድ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ቈዳቸው ወይም የእነርሱ ቈዳ፤ እዚህ “እነርሱ” ወይፈኑንና ፍዬሉን ያመለክታል::
እናንተ የሚለው ቃል ብዙና የእስራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ነው:: (የሁለተኛ ሰው አገላለጾች ይመልከቱ)
ይህ በዕብራይጥ የቀን መቁጠሪያ ሰባተኛ ወር ነው አሥረኛው ቀን በምዕራባዊያን አቆጣጠር መስከረም ማገባደጃ ወይም መጨረሻ አካባቢ ነው:: (የዕብራይጥ ወራትንና መደበኛ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አሮን ሥርየት ያደርግላችኋል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ተቀባይነት ያሉአቸው ሰዎች ንጹህ ተብለዋል::
ይህ በየሳምንቱ የሚያከብሩት የሰንበት ቀን አይደለም:: በሥርየት ቀን የሚደረግ ልዩ ሰንበት ነው::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እነርሱ የሚቀቡትና የሚሾሙት ሰው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሊቀ ካህን ሲሞት ከልጆቹ አንዱ ይተካዋል::
ቅድስተ ቅዱሳን በሚገባበት ጊዜ ሊቀ ካህኑ የሚለብሱአቸው ልዩ ልብሶች ናቸው
“ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ”
በማስተሠረያ ቀን ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይፈጽማል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እናም ሙሴ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ” ወይም “እናም አሮን እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረገ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
1 እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣ 2 አሮንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤል ህዝብ ሁሉ እንዲህ በላቸው፡፡ ያህዌ ያዘዘውን ንገራቸው፡፡ 3 “ከእስራኤል ሰዎች መሀል ማንም ለመስዋዕት በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈር ውጭ በሬ፣ በግ፣ ወይም ፍየል ያረደ ሰው፣ 4 ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ በመቅደሱ ፊት ለያህዌ መስዋዕት ለማድረግ ባመጣው ውሃ ያ ሰው ስላፈሰሰው ደም በደለኛ ነው” ደም አፍስሷልና ያ ሰው ከህዝቡ መሃል ተለይቶ ይጥፋ፡፡ 5 የዚህ ትእዛዝ ዓላማ የእስራኤል ሰዎች ለያህዌ በሜዳ ላይ የሚያቀርቧቸውን መስዋዕቶች ወደ ካህናት ለያህዌ የህብረት መስዋዕት አድርገው በመገናኛው ድንኳን መግቢያ እንዲያቀርቡ ነው፡፡ 6 ካህኑ የመስዋዕቱን ደም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በያህዌ መሰዊያ ላይ ይረጫል፤ ስቡን ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ አድርጎ ያቃጥለዋል፡፡ 7 ሕዝቡ ከእንግዲህ መስዋዕቱን ለጣኦት አይሰዋ፣ እንዲህ ያለው ተግባር ምንዝርና ነው፡፡ ይህ በትወልዶቻቸው ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ 8 እንዲህ በላቸው፣ “ማንኛውም እስራኤላዊ፣ ወይም ማንኛውም በእነርሱ መሀል የሚኖር መጻተኛ፣ የሚቃጠል መስዋዕት የሚሰዋ ወይም መስዋዕት የሚያቀርብ 9 እና ለያህዌ ለመሰዋት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ የማያመጣው ያ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡ 10 ደግሞም ከእስራኤል አንዱ፣ ወይም በእነርሱ መሀል ከሚኖር መጻተኛ አንዱ፣ ደም ቢበላ፣ ፊቴን ከዚያ ሰው አስቆጣለሁ፣ ማንንም ደም የሚበላን ሰው ከህዝቡ መሃል አጠፋዋለሁ፡፡ 11 የእንስሳ ህይወቱ በደሙ ውስጥ ነው፡፡ በመሰዊያ ላይ ማስተሰርያ ይሁናችሁ ዘንድ ደሙን ለሕይወታችሁ ሰትቻችኋለሁ፣ ምክንያቱም ማስተሰርያ የሚሆነው ደም ነው፣ ለሕይወት ስርየት የሚያስገኘው ደም ነው፡፡ 12 ስለዚህም ለእስራኤላውያን ከመሀላችሁ ማንም ደም አይብላ እላለሁ፣ በመሀላችሁ የሚኖር ማንም ሙያተኛም ቢሆን ደም አይብላ፡፡ 13 ከእስራኤል ሰዎች መሀል ማንም ቢሆን፣ ወይም በእነርሱ መሃል የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣ የሚበላ እንስሳ ቢያርድ ወይም ወፍ ቢያጠምድ ደሙን ያፍስና በአፈር ይሸፍነው፡፡ 14 የእያንዳንዱ ፍጥረት ነፍስ ደሙ ነውና፡፡ ስለዚህም ነው ለእስራኤላውያን፣ የማንኛውም ፍጥረት ደም አትብሉ፣ የእያንዳንዱ ሕያው ፍጥረት ሕይወት ደሙ ነው፡፡ ማንም ይህን የሚበላ ተቆርጦ ይጥፋ” ብዬ የተናገርኩት፡፡ 15 እያንዳንዱ የሞተ፣ ወይም በዱር አውሬ የተዘነጠለ እንስሳ የበላ ሰው የአገር ተወላጅ ይሁን በመሀላችሁ የሚኖ መጻተኛ ልብሶቹን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስ ምሽት ድረስ ንጹህ አይሆንም፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡ 16 ነገር ግን ልብሱን ባያጥብ ወይም ሰውነቱን ባይታጠብ፣ በበደሉ ተጠያቂ ነው፡፡
በታቦቱ ፊት
ከኀብረተሰቡ የሚገለል ሰው የልብስ ጨርቅ ወይም የዛፍ ቅርንጫፍ እንደሚቆረጥ ከሕዝቡ እንደሚቆረጥ ተደርጐ ተነግሮአል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: በዘሌዋዊያን 7:2ዐ ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልኩቱ:: አት፤ “በሕዝቡ ዘንድ ያ ሰው እንዲኖር አይገባም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ካህኑም መሥዋዕት አድርጐ እንዲያቀርባቸው ወደ ካህኑ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ስህተት አማልዕክትን በማምለክ ለእግዚአብሔር ታማኝ ያልሆነው ሕዝብ በማመንዘር ባለቤቱን እንደካደ ሰው እንደሆነ ተገልአል አት፡ ለእግዚአብሔር ታማኝ ላልሆኑበት፤ (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
በዘሌዋዊያን 3: 17 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
የሰውየው ከማኀበረሰቡ መገለሉ አንድ ቢጣሽ ጨርቅ ከልብስ ወይም ቅርንጫፍ ከዛፍ እንደሚቆረጥ ከሕዝቡ እንደተቆረጠ ተደርጐ ተነግሮአል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ያ ሰው በሕዝቡ መካከል መኖር የለበትም” ወይም “ያ ሰው ከሕዝቡ መለየት አለበት” ( ዘይቤያዊ አገላለጽና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር “በጥብቅ እንደወሰነ” ይገልጻል:: አት: “ያን ሰው ለመቃወም በአእምሮዬ ወስኛለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“በቁጣ ሊገናኘው”
የሰውየው ከማኀበረሰቡ መገለሉ አንድ ቢጣሽ ጨርቅ ከልብስ ወይም ቅርንጫፍ ከዛፍ እንደሚቆረጥ ከሕዝቡ እንደተቆረጠ ተደርጐ ተነግሮአል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ያ ሰው በሕዝቡ መካከል መኖር የለበትም” ወይም “ያ ሰው ከሕዝቡ መለየት አለበት” ( ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህም ማለት ደም ሕይወት ስለሆነ እግዚአብሔር ደምን ተጠቅሞ የሰዎችን ኃጢአት ያስተሠርያል:: ይህ የተለየ ዓላማ ስላለው ሰዎች ደምን መብላት አይገባቸውም
እዚህ “እኔ” ያህዌን ያመለክታል
“ከእናንተ ማንም ደም ያለበትን ሥጋ አይብላ”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ያ እንዲበሉ እኔ የተናገርሁት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“ደሙን የአፈር ብናኝ ያልብሰው”
ይህም ማለት ደም ፍጡር በሕይወት እንዲኖር ያደርጋል የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት: “ከደሙ የተነሣ እያንዳንዱ ፍጡር በሕይወት ሊኖር ይችላሉ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የሰውየው ከማኀበረሰቡ መገለሉ አንድ ቢጣሽ ጨርቅ ከልብስ ወይም ቅርንጫፍ ከዛፍ እንደሚቆረጥ ከሕዝቡ እንደተቆረጠ ተደርጐ ተነግሮአል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ደምን የሚበላ ማንኛውም ሰው በሕዝቡ ዘንድ መኖር የሌበትም” ወይም “ደም የሚበላውን ሰው ከሕዝቡ መለየት አለባችሁ” (ዘይቤያዊ አገላለጽና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር መናገሩን ይቀጥላል
በአውሬ የተገደለው እንስሳ አውሬዎች አንሰሳውን ዘነጣጥለው እንደከፋፈሉት ተነግሮአል፡፡ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አውሬዎች የገደሉት” (ዘይቤያዊ አገላለጽና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“እስራኤላዊ”
ሌሎች ሰዎች ሊነኩት የማይችሉአቸው ሰው ርኩስ ተብሎአል እናም ሌሎች ሰዎች መንካት የሚችሉአቸው ሰው ንጹህ ተብሎአል::(ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“ጸሐይ እስኪጠልቅ”
የሰውየው በደል አንድን ግዑዝ ዕቃ ሰው እንደተሸከመ ተደርጐ ተነግሮአል:: እዚህ “በደል” የሚለው ቃል ለበደሉ የሚሰጠውን ቅጣት ያመለክታል:: አት: ያም እርሱ ለበደሉ ተጠያቂ ነው ወይም ስለ ኃጢአቱ እቀጣዋለሁ:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ወይም ምትክ ተመሳሳይ አባባሎችን ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 3 እኔ በማስገባችሁ ምድር፤ ቀድሞ ትኖሩበት በነበረው በግብጽ የነበሩ ሰዎች ያደርጓቸው የነበሩ ነገሮችን አታድርጉ፣ ደግሞም በከነአን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ያደርጓቸው የነበሩ ነገሮችን አታድርጉ፡፡ የእነርሱን ልምዶች አትከተሉ፡፡ 4 እናንተ መፈጸም ያለባችሁ የእኔን ህጎች ነው መጠበቅ ያለባችሁ የእኔን ትዕዛዛት ነው፣ ስለዚህም በእነርሱ ትኖራላችሁ፣ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ 5 ስለዚህም እኔን ትዕዛዛትና ህጎች ትጠብቀላችሁ፡፡ አንድ ሰው እነዚህን ቢጠብቅ፣ በእነርሱ ምክንያት በህይወት ይኖራል፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 6 ማንም ሰው ከቅርብ ዘመዱ ጋር አይተኛ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 7 ከእናትህ ጋር በመተኛት አባትህን አታዋርድ፡፡ እርሷ እናትህ ናት! እርሷን ማዋረድ የለብህም፡፡ 8 ከአባትህ ሚስት ከየትኛዋም ጋር አትተኛ፤ አባትህን በዚያን አይነት ማዋረድ የለብህም፡፡ 9 የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ ብትሆን በቤት ውስጥ አብራህ ብታድግ ወይም ርቃ ብታድግም ከየትኛዋም እህትህ ጋር አትተኛ፡፡ 10 ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ጋር ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ ይህ እፍረት ይሆንብሃል፡፡ 11 ከአባትህ ከተወለደች ከእንጀራ እናትህ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ እህትህ ናት፣ እናም ከእርሷ ጋር መተኛት የለብህም፡፡ 12 ከአባትህ እህት ጋር አትተኛ፡፡ ለአባትህ የቅርብ ዘመድ ናት፡፡ 13 ከእናትህ እህት ጋር አትተኛ፡፡ ለእናትህ የቅርብ ዘመድ ናት፡፡ 14 ወንድም ከሚስቱ ጋር በመተኛት አታዋርደው” ለዚያ ተግባር ወደ እርሷ አትቅረብ፣ አክስትህ ናት፡፡ 15 ከምራትህ ጋር አትተኛ፡፡ የወንድ ልጅህ ሚስት ናት፣ ከእርሷ ጋር አትተኛ፡፡ 16 ከወንድምህ ሚስት ጋር አትተኛ፣ በዚህ መንገድ አታዋርደው፡፡ 17 ከአንዲት ሴትና ከልጇ ጋር ወይም ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ጋር ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ እነርሱ ለእርሷ የቅርብ ዘመዶች ናቸው፣ እናም ከእነርሱ ጋር መተኛት ጸያፍ ነው፡፡ 18 የሚስትህን እህት ሁለተኛ ሚስት አድርገህ አታግባ፤ ሚስትህ በህይወት ሳለች ከእህቷ ጋር አትተኛ፡፡ 19 አንዲት ሴት በወር አበባዋ ወቅት ላይ ሳለች አብረሃት አትተኛ፡፡ በዚያን ጊዜ ንጹኅ አይደለም፡፡ 20 ከጎረቤትህ ሚስት ጋር አትተኛ፣ በዚህ መንገድ ራስህን አታርክስ፡፡ 21 ከልጆችህ አንዳቸውንም በእሳት ውስጥ እንዲያልፉ አትስጥ፣ በዚህ ድርጊት ለሞሎክ መስዋዕት አድርህ ትሰጣቸዋለህ፣ የአምላክህን ስም ማቃለል የለብህም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 22 ከወንዶች ጋር ከሴት ጋር እንደምትተኛው አትተኛ፡፡ ይህ ጻያፍ ነው፡፡ 23 ከማናቸውም እንስሳ ጋር አትተኛ ራስህን አታርክስ፡፡ ማንም ሴት ከማናቸውም እንስሳ ጋር መተኛት የለባትም፡፡ ይህ አስጸያፊ ወሲብ ነው፡፡ 24 ከእነዚህ መንገዶች በየትኛውም ራስህን አታርክስ፣ ከአንተ አስቀድሞ ያባረርኳቸው ህዝቦች በእነዚህ ሁሉ መንገዶች ረክሰዋል፡፡ 25 ምድሪቱ ረከሰች፣ ስለዚህም በኃጢአታቸው ቀጣኋቸው፣ ምድሪቱም በላይዋ የሚኖሩትን ተፋቻቸው፡፡ 26 ስለዚህ እናንተ የእኔን ትዕዛዛትና ህግጋቴን መጠበቅ አለባችሁ፣ እናንተ ተወላጅ እስራኤላዊያንም ሆናችሁ በእንተ መሀል የሚኖሩ እንግዶች ከእነዚህ ያልተገቡ ነገሮች የትኞቹንም ማድረግ የለባችሁም፡፡ 27 ከእናንተ አስቀድሞ በዚህ ምድር የኖሩ ሰዎች የሰሩት ጸያፍነት ይህ ነው፣ እናም አሁን ምድሪቱ ረከሰች፡፡ 28 ስለዚህም ምድሪቱ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ሰዎች እንደተፋች እናንተንም ካረከሳችኋት በኋላ እንዳትተፋችሁ ተጠንቀቁ፡፡ 29 ከእነዚህ አስነዋሪ ነገሮች መሀል የትኛውንም ነገር ያደረገ፣ እንዲህ ያለ ነገሮችን ያደረገው ሰው ከህዝቡ መሀል ተለይቶ ይጠፋል፡፡ 30 ስለዚህ በእነዚህ ነገሮች እንዳታረክሱ ከእናንተ አስቀድሞ በዚህ ስፍራ ይፈፀሙ የነበሩትን ጸያፍ ልምዶች ባለማድረግ ትዕዛዛቴን መጠበቅ አለባችሁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ።
እነዚህ ሁለቱ ሐረጐች በመሠረቱ አንድ ትርጉም ያላቸውና ሕዝቡ እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበቸው የሚያተኩሩ ናቸው:: ይህን ተጓዳኝ ንጽጽር የእግዚአብሔርን ሕጐች ሁሉ መጠበቅ እንደሚገባቸው እንደ አንድ ዐረፍተ ነገር መተርጐም ይችላሉ አት ሕጐቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ ታዘዙ:: (ተጓዳኝ ንጽጽር ይመልከቱ)
የእግዚአብሔርን ሕጐች መታዘዝ አንድ ሰው የሚራመድበት ጐዳና ተደርገው ተነግረዋል:: አት: “ስለዚህ ባሕሪያችሁን በእነርሱ መሠረት ተለማመዱ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
አንዳንዴ አንድ ወንድ ከአንድ በላይ ሚስቶች ይኖሩታል:: አባቱን ካገባች ከማንኛዋም ሴት ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙት ማድረግን እግዚአብሔር አልፈቀደም::
ይህም አንድ ሰው ከተመሳሳይ ወላጅ ወይም የተለየ አባት ወይም እናት ቢኖራትም ከእህቱ ጋር በግብረ ሥጋ አይገናኝ ማለት ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “በቤት ውስጥ ያደገች ወይም ከቤት ውጭ ያለች ቢትሆን” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አማራጭ ትርጉሞች እነሆ ፤ (1)ከግማሽ እህትህ ጋር ግብረ ሥጋ አትፈጽም ፤(2)የእንጀራ እህት ጋር እዚህ ያ ሰው ተመሣሣይ አባት ወይ እናት ከሌላት እኀቱ ጋር ማለት ነው፤ወላጆቻቸው በተጋቡ ጊዜ ወንድምና እኀት ሆነዋልና፤
“የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለመፈጸም ወደ እርስዋ አትሂድ”
እግዚአብሔር ደጋግሞ የሚናገረው ለትዕዛዙ አጽንዖት ለመስጠት ነው::
ይህ ከሴት ማዕጸን በወራዊ ጊዜ ደም የሚፈስስበት ነው
የማንኛውንም ሰው ሚስት
እዚህ “አስጸያፊ” እግዚአብሔር እንዲሆኑ ያደረገውን የተፈጥሮአዊ ነገሮች ሥርዓት መተላለፍን ያመለክታል::
ይህ በከነዓን የሚኖሩ ሰዎች ያመለክታል:: “ሕዝብ” ወይም “አሕዛብ” የተባለው ሀሳብ “ሰዎች” በሚለው ግልጽ እንደሚሆን አድርገው ይተርጉሙ:: አት የአሕዛብ ሰዎች በእነዚህ ረክሰዋል:: (Metonymy/ምትክ አቻ ትርጉም ያላቸውን ተመሳሳይ አባባሎችን ይመልከቱ)
“ሰዎች ምድሪቱን አርክሶአታል”
እግዚአብሔር ሕዝቡን ከምድሪቱ በጉልበት ማስወጣቱ ምድሪቱ እንደሰው ሰዎችን እንደተፋች ተደርጐ ተነግሮእል (ዘይቤያዊ አነጋገርና በሰውኛ አገላለጽ ይመልኩቱ)
“ከእነኚህ አስጸያፊ ድርጊቶች”
ይህ “እነዚህን ጸያፍ ድርጊቶች” ያመለክታል
“ስለዚህ እኔን ለመታዘዝ ተጠንቀቁ”
እግዚአብሔር ሕዝቡን ከምድሪቱ በጉልበት ማስወጣቱ ምድሪቱ እንደሰው ሰዎችን እንደተፋች ተደርጐ ተነግሮእል:: በዘሌዋዊያን 18:25 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት: “ከዚህም የተነሣ እነርሱን ከምድሪቱ በጉልበት እንዳወጣሁት እናንተንም ከምድሪቱ አወጣለሁ”(ዘይቤያዊ አነጋገርና በሰውኛ አገላለጽ ይመልኩቱ)
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩ ያበቃል
ከማኀበረሰቡ መገለሉ ሰዎች አንድ ቢጣሽ ጨርቅ ከልብስ ወይም ቅርንጫፍ ከዛፍ እንደሚቆረጥ ከሕዝቡ እንደተቆረጠ ተደርጐ ተነግሮአል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እነዚህ ሰዎች በሕዝቡ ዘንድ እንዳይኖሩ ወይም እነዚህን ሰዎች ከሕዝቡ እንዲትለዩአቸው” (ዘይቤያዊ አገላለጽና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ከአናንተ በፊት የነበሩ ሰዎች ያደረጉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ “እነዚህ” ጸያፍ ልምዶችን ያመለክታል::
1 ሙሴን እንዲህ አለው 2 “ለእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ቅዱስ እንደሆንኩ እናተም ቅዱሳን ሁኑ፡፡ 3 እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፣ እናንተም ሰንበቴን ጠብቁ፡፡ እኔ አምላካች ያህዌ ነኝ፡፡ 4 ጥቅም ወደሌላቸው ጣኦታት ዘወር አትበሉ፣ ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልዕክትን አታብጁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 5 ለያህዌ የህብረት መስዋእቶችን ስታቀርቡ፣ ተቀባይነት ልታገኙ በምትችሉበት መንገድ አቅርቡ፡፡ 6 መስዋዕቱ ባቀረባችሁበት ቀን አሊያም በማግስቱ ይበላ፡፡ አንዳች ነገር እስ ሶተኛው ቀን ቢተርፍመ ይቃጠል፡፡ 7 በሶስተኛው ቀን ቢበላ የረከሰ ነው፡፡ ተቀባይነት አያገኝም፣ 8 ነገር ግን የበላው ሁሉ በበደለኛነቱ ይጠየቅበታል ምክንያቱም ለያህዌ የተለየውን አርክሷል፡፡ ያ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡ 9 የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ፤ የእርሻችሁን ቀርጢያ ሁሉ አትልቀሙ፣ አሊያም የአዝመራችን ምርት ሁሉ አትሰብስቡ፡፡ 10 ከወይን ተክልህ እያንዳንዱን ወይን ፍሬ አትሰብስብ፣ አሊያም በወይን ስፍራ የወዳደቁትን የወይን ፍሬዎች አትልቀም፡፡ ለድሆችና ለመጻተኞች እነዚህን ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 11 አትስረቁ፡፡ አትዋሹ፡፡ አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ፡፡ 12 በሃሰት በስሜ አትማሉ የአምላካችን ስም አታርክሱ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 13 ጎረቤትህን አትበድል ወይም አትዝረፈው፡፡ የቀን ሰራተኛውን ክፍያ በአንተ ዘንድ አታሳድር፡፡ 14 መስማት የተሳነውን ሰው አትርገመው ወይም ከእውሩ ፊት ማሰናከያ ድንጋይ አታስቀምጥ ይልቁንም አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 15 ፍትህን አታጣም፡፡ አንድ ሰው ድሃ ስለሆነ ልታደላለት አይገባም፣ እንደዚሁም አንድ ሰው ባለጸጋ ስለሆነ አታዳላለት፡፡ ይልቁንም ለጎረቤትህ በጽድቅ ፍረድ 16በሰዎች መሃል በሀሳት ሃሜትን አታሰራጭ 16 በሰዎች መሃል ሀሜትን እያሰራጨህ አትዙር፣ ይልቁንም የጎረቤትህን ሕይወት አቅና፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 17 በልብህ ወንድምህን አትጥላ፡፡ በእርሱ ምክንያት የኃጢአቱ ተካፋይ እንዳትሆን ጎረቤትህን በቅንነት ገስጸው፡፡ 18 ከህዝብህ ማንንም አትቀበል ወይም በማንም ላይ ቂም አይኑርህ፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ ጎረቤትህን እንደራስህ ውደድ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 19 ትዕዛዛቴን መጠበቅ አለብህ፡፡ እንስሳትህን ከሌሎች ልዩ ዝርያ ካላቸው እንስሳት ጋር አታዳቅል፡፡ በእርሻህ ላይ ስትዘራ የተለያየ የዘር ዐይነቶችን አትደባልቅ፡፡ ከሁለት የተለያዩ አይነት ነገሮች ተደባልቆ የተሰራ ልብስ አትልበስ፡፡ 20 ቤዛ ካልተከፈለላት ወይም ነጻ ካልወጣች ለባል ከታጨት ባሪያ ከሆነች ልጃገረድ የተኛ ሁሉ ይቀጡ፡፡ ሊገደሉ ግን አይገባም ምክንያቱም ነጻ አልወጣችም፡፡ 21 ሰውዬው ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለበደል መስዋዕት ለያህዌ አውራ በግ ያምጣ፡፡ 22 ከዚያ ካህኑ በያህዌ ፊት ሰውዬው ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕት አውራ በግ በማቅረብ ያስተሰርይለታል፡፡ ከዚያ የሠራው ኃጢአት ይቅር ይባልለታል፡፡ 23 ወደምድሪቱ ስትገቡና ለምግብ የሚሆን ሁሉንም ዐይነት ዛፎች ስትተክሉ፣ ዛፎቹ ያፈሩትን ፍሬ ለመብላት እንደተከለከለ ቁጠሩት፡፡ ፍሬው ለእናንተ ለሶስት ዓመታት የተከለከለ ነው፡፡ አይበላም፡፡ 24 ነገር ግን በአራተኛው አመት ፍሬው ሁሉ ለያህዌ ለምስጋና የሚሰዋ ቅዱስ ይሆናል፡፡ 25 አመት ፍሬውን መብላት ትችላላችሁ፡፡ በመጠበቃችሁ ዛፎቹ ብዙ ያፈራሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 26 ደሙ በውስጡ ያለበትን ስጋ አትብሉ፡፡ ስለ ወደፊቱ መናፍስትን አታማክሩ፣ ደግም ከተፈጥሮ በላይ በሆኑ ኃይላት ሌሎችን ለመቆጣጠር አትፈልጉ፤፡፡ 27 እንደ ጣኦት አምላኪዎች የጸጉራችሁን ዙሪያ አትላጩ ወይም የጺማችሁን ዙሪያ አትቆረጡ፡፡ 28 ለሙታን ሰውነታችሁን በስለት አትቁረጡ ወይም በሰውነታችሁ ላይ ንቅሳት አታድርጉ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 29 ሴት ልጅህን ሴተኛ አዳሪ በማድረግ አታወርዳት፣ በዚህ ነገር አገረ ወደ ግልሙትና ትገባለች ምድሪቱም በእርኩሰት ትሞላለች፡፡ 30 ጠብቁ የቤተመቅደሴን ቅድስና አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 31 ወደ ሙታን ጠሪዎችና መናፍስትን ወደሚያነጋግሩ ዘወር አትበሉ፡፡ እነዚህን አትፈልጉ፣ ካልሆነ ያረክሷችኋል፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 32 ፀጉሩ ለሸበተ ሰው ተነስለት ደግሞም በዕድሜ የገፋውን ሰው አክብር፡፡ አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 33 በምድርህ በመካከልህ መጻተኛ ቢኖር፣ አትግፋው፡፡ 34 በመካከላችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደ ተወላጅ እስራኤላዊ ወገናችሁ ቁጠሩት ደግሞም እንደ ራሳችሁ ውደዱት፣ ምክንያቱም እናንተም በግብጽ ምድር መጻተኞች ነበራችሁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 35 ርዝመትን፣ ክብደትን፣ ወይም ብዛትን ስትለኩ፡፡ ሀሰተኛ መለኪያ አትጠቀሙ፡፡ 36 ትክክለኛ መስፈሪያን፣ ትክክለኛ ሚዛኖችን፣ ትክክለኛ የኢፍ እና የኢን መለኪያዎችን ተጠቀሙ፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 37 ትዕዛዛቴንና ህግጋቴን ሁሉ ጠብቁ፣ አድርጓቸውም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
“ሰንበታቴን አክብሩ” ወይም “ለአረፍኩት ቀን ክብር ስጡ”
ጣዖታትን ማምለክ ወደ እነሱ ዘወር እንደማለት ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “የማይረቡ ጣዖታትን ማምለክ አትጀምሩ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገር ይቀጥላል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: ሁኔኛ ትርጉሞች እነሆ 1)እግዚአብሔር መስዋዕቱን የሚያቀርበውን ሰው ይቀበላል አት፤ “ እንዲቀበልህ በሥርዓት መሥዋዕትህን አቅርብ” ወይም 2) እግዚአብሔር የሚያቀርበውን ሰው መሥዋዕት ይቀበላል አት፤ “ መስዋዕትህን እንዲቀበል በሥርዓት አቅርብ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ እናም ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ይብሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ያቃጥሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ቢበሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የተመደበውን ጊዜ አሳልፎ የቀረበውን መሥዋዕት መብላት መስዋዕቱ የማሸፍነውን በደል መጨመርና እግዚአብሔርን መበደል ነው ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ለመብላት አይቀበሉ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የሰውየው በደል አንድን ግዑዝ ዕቃ ሰው እንደተሸከመ ተደርጐ ተነግሮአል:: እዚህ “በደል” የሚለው ቃል ለዚያ በደሉ የሚሰጠውን ቅጣት ያመለክታል:: አት: ማንኛውም ለራሱ በደል ተጠያቂ ነው ወይም እግዚአብሔር ማንንም ስለኃጢአቱ ይቀጣል:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ወይም ተመሳሳይ ትርጉም ያለቸው ምትክ አባባሎች ይመልከቱ)
ሰውየው ከማኀበረሰቡ ዘንድ መገለሉ አንድ ቢጣሽ ጨርቅ ከልብስ ወይም ቅርንጫፍ ከዛፍ እንደሚቆረጥ ከሕዝቡ እንደተቆረጠ ተደርጐ ተነግሮአል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: በዘሌዋዊያን 7:2ዐ ይህን አንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት፤ “ሰውየው በሕዝቡ ዘንድ አይኑር ወይም ይህንን ሰው ከሕዝቡ ይለዩት” (ዘይቤያዊ አገላለጽና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“እህሎቻችሁን በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ዳርና ዳር ያለውን ሙሉውን አትጨዱ”
ይህ ሁለተኛ ጊዜ ወደኋላ በመመለስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሰበሰብ የቀረውን እንደገና መስብሰብን ያመለክታል:: የዚህ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት:: ወደኋላ ተመልሰው የቀረውን ሁሉ አይልቀሙ:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“እውነት ላልሆነው ነገር ስሜን በመጠቀም አትማሉ”
እዚህ “ባልጀራ” “ማንኛውም ሰው” ማለት ነው ይህ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት “ባልጀራህን አትጉዳ ወይም አትቀማውም” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ሥራው በቀኑ በተፈጸመ ጊዜ አስሠሪው ለሠራተኛው ወዲያው መክፈል እንዳለበት እግዚአብሔር ያዝዛል የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉሙ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ድርብ አሉታዊ ቃላት ለአትኩሮት ተጠቅመዋል:: ይህ በአዎንታዊ መንገድ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ሁልጊዜ ትክክለኛውን ፍርድ ይስጡ” (See Litotes/ በአሉታዊነት አዎንታዊነትን የመግለጽ አነጋገር ዘይቤ ይመልከቱ)
“ድሃ” እና “ባለጠጋ” የተባሉ ቃላት ሁለት ጫፍ የረገጡ አባባሎች ናቸውና ሲጣመሩ “ማንኛውም ሰው” የሚል ትርጉም ይሰጣሉ አነዚህን ጽንሰ ሀሳቦች ግልጽ ለማድረግ ይተርጉሙ:: አት: “ያለውን ገንዘብ ተመልክተህ ለማንኛውም ሰው አታድላ”:: (See Merism/ብዙውን በነጠላ መልቅ የመግለጽ አነጋገር ዘይቤ ይመልከቱ)
“ለማንኛውም ሰው በትክክለኛነት ፍረድ”
“ስለሌሎች ሰዎች የሚጐዳውን እውነት ያልሆነውን መልእክቶች አታውራ”
አንድን ሰው በቀጣይነት መጥላት ይህን ሰው ከልብ እንደመጥላት ተደርጐ ተነግሮአል:: አት: “ወንድምህን በቀጣይነት አትጥላው” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“ኃጢአትን የሚሠራውን ሰው አርመው”
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አንድ ሰው ከሁለት ዓይነት ነገሮች የሠራው ልብስ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሌላ ሰው ለማግባት ከተስማማች ሴት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ነገር ግን የወደፊት ባልዋ ያልዋጃትና ነጻነት ያልሰጣት ብትሆን” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሴት ባሪያዋንና ከእርስዋ ጋር ያመነዘረውን ትቀጣላቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አትግደሉአቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“ሰውየውም ለበደል መሥዋዕት የሚሆን አንድ አውራ በግ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለእግዚአብሔር ያምጣ”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “የሠራውን ኃጢአት እግዚአብሔር ይቅር ይልለታል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
እግዚአብሔር መከልከሉን ለማተኮር ደግሞ ይናገራል እናም ለመጀመሪያ ሶስት ዓመታት ፍሬ የሚሰጠውን ዛፍ ይገልጻል አት: “ከዚያም ለመጀመሪያ ሶስት ዓመታት የዛፎች ፍሬ አትብሉ” (ተዛማጅ ንጽጽር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እነርሱ የሚያፈሩትን ፍሬ እንዳትበሉ እኔ ከልክያችኋለሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ፍሬውን ከልክያችኋለሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አትብሉ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ “ሕዝብ” እና “ምድር” የተባሉ ቃላት በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታሉ:: አት፤ “ግልሙትናን ወይም ሌሎች ርኩሰቶችን የሚለማመዱ ሰዎች በዚያ ነገር እንደወደቁ ወይም እንደተሞሉ ተደርገው ተገልጸዋል” አት ሰዎች ግልሙትናንና ርኩስ ተግባራትን መለማመድ ጀመሩ( ተመሳሳይ ምትክ አባባሎችንና ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ሁነኛ ትርጉሞች 1) ሙታንና መናፍስ የተለያዩ ናቸው 2) ይህ ድርብ ቃል ነው የሙታን መናፍስት (See Doublet/ ድርብ ቃላትንና አባባሎችን ይመልከቱ
እንዚያን ሰዎች አትፈልጉአቸው፤ እንደዚያ ካደረጋችሁ ያረክሱአችኋል፡፡
በአንድ ሰውፊት መነሣት የማክበር ምልክት ነው ምልክታዊ ድርጊት ይመልከቱ::
ከዕድሜ የተነሣ ጸጉሩ የሸበተውን ሰው ወይም ሽማግሌ ሰው ያመለክታል
ይህ ነገሮች በሚትመዝኑበት ጊዜ በማወቅ ትክክለኛ ልከት የማይሰጡ መሣሪያዎችን የመጠቀም ልምምድን ይከለክላል::
የእህል መለኪያ ነው (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎች ይመልከቱ)
የፈሳሽ መለኪያ ነው (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎች ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእስራኤል ሰዎች መሃል ማንም ሰው፣ ወይም ማንኛውም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ከልጆቹ መሃል አንዱን ለሞሎክ ቢሰጥ በዕርግጥ ይገደል፡፡ በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች በድንጋይ ይውገሩት፡፡ 3 እኔም በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አዞርበታለሁ፣ ከህዝቡም መሃል እቆርጠዋለሁ ምክንያቱም የተቀደሰውን ስፍራዬን ለማርከስና ቅዱሱን ስሜን ለማቃለል ልጁን ለሞሎክ ሰጥቷል፡፡ 4 ያ ሰው ከልጆቹ አንዱን ለሞሎክ ሲሰጥ ዚያች ምድር ሰዎች እንዳላዩ ቢሆን፣ ባይገድሉት፣ 5 እኔ ራሴ በዚያ ሰውና በቤቱ ላይ ፊቴን አዞራለሁ፣ እኔ ቆርጬ እጥለዋለሁ እንደዚሁም ከሞሎክ ጋር በሚያመነዝረው በማንኛውም ላይ ይህን አደርጋለሁ፡፡ 6 ወደ ሙታን ጠሪዎች ዘወር የሚል፣ ወይም ከመናፍስት ጋር ከሚነጋገሩ ጋር የሚመነዝርን ሰው ፊቴን አዞርበታለሁ፤ ከህዝቡም መሃል አጠፋዋለሁ፡፡ 7 ስለዚህ ራሳችሁን ለያህዌ ስጡ ተቀደሱም፣ ምክንያቱም እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 8 ትዕዛዛቴን ጠብቁ አድርጓቸውም፡፡ ለራሴ የመረጥኳችሁ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 9 ወይም እናቱን የሚረግም ሁሉ ይገደል፡፡ አባቱን ወይም እናቱን ረግሟልና በደለኛ ነው ሞት ይገባዋል፡፡ 10 ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ዝሙት የፈጸመ ሰው፣ ከጎረቤቱ ሚስት፣ ጋር ያመነዘረ ይገደል አመንዝራውና አመንዝራይቱም ሁለቱም ይገደሉ፡፡ 11 ከአባቱ ሚስት ጋር ሊተኛት የወደቀ የገባ አባቱን ያዋርዳል፡፡ ልጅየውም የአባቱ ሚስትም ሁለቱም ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡ 12 አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ሊገደሉ ይገባል ያልገባ ፍትወት ፈጽመዋል በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡ 13 አንድ ወንድ ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከሌላ ወንድ ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ጸያፍ ነገር አድርገዋል፡፡ በእርግጥ ሞት ይገባቸዋል፡፡ ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡ 14 አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቲቱንም ቢያገባ፣ ይህ አሳፋሪ ነው፡፡ እርሱና ሴቲቱ ሁለቱም በእሳት ይቃጠሉ፣ ይህ ሲደረግ በመሀላችሁ ክፋት አይኖርም፡፡ 15 አንድ ሰው ከእንስሳ ጋር ቢተኛ፣ በእርግጥ ይገደል፣ እንስሳይቱንም ግደሏት፡፡ 16 አንዲት ሴት ለመገናኘት ወደ ማንኛውም አይነት እንስሳ ብተቀርብ ሴትየዋንም እንስሳውንም ግደሏቸው፡፡ በእርግጥ ሊገደሉ ይገባል፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡ 17 አንድ ሰው የአባቱ ልጅ ከሆነችውም ሆነ የእናቱ ልጅ ከሆነች እህቱ ጋር ቢተገኛ እህትም ከእርሱ ጋር ብትተኛ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፤ ምክንያቱም ከእህቱ ጋር ተኝቷል፡፡ በደሉን ይሸከማል፡፡ 18 አንድ ሰው አንዲትን ሴት በወር አበባዋ ወቅት አብሯት ቢተኛና ቢገናኛት፣ የደሟ ምንጭ የሆነውን የደም መፍሰሷን ገልጧል፡፡ ወንዱም ሴቷም ሁለቱም ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፡፡ 19 ከእናትህ ወይም ከአባትህ እህት ጋር አትተኛ፣ ምከንያቱም የቅርብ ቤተ ዘመድህን ታዋርዳለህ፡፡ በደልህን ልትሸከም ይገባሃል፡፡ 20 አንድ ሰው ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ አጎቱን አዋርዷል፡፡ በደላቸውን ሊሸከሙ ይገባል ያለ ልጅ ይቀራሉ፡፡ 21 አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ቢያገባ ይህ እርኩስ ነው ምክንያቱም ዘመዱ ሆኖ ሳለ የወንድሙን ትዳር አፍርሷል፣ ልጅ አልባ ይሆናሉ፡፡ 22 ስለዚህም ስርአቶቼንና ህግጋቶቼን ሁሉ መጠበቅ አለባችሁ፤ እንድትኖርባት ያመጣኋቸው ምድር እንዳትተፋችሁ ህግጋቴንና ሥርዓቶቼን ጠብቁ፡፡ 23 ከፊታችሁ በማባርራቸው ህዝቦች ልምዶች አትመላለሱ፣ እነርሱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርገዋል፣ እኔም እነርሱን ጠላሁ፡፡ 24 እኔ እንዲህ እላችኋለሁ፣ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፣ ምድሪቱን እንድትወርሷት ለእናንተ እሰጣችኋለሁ፣ ወተትና ማር የምታፈስ ምድር ናት፡፡ ከሌላው ህዝብ የለየኋችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ” 25 ስለዚህ እናንተ ንጹህ በሆኑና ንጹኅ በሆኑ እንስሳት መሃል፣ ንጹኅ በሆኑና ንጹህ ባልሆኑ ወፎች መሃል ልዩነት አድርጉ፡፡ ለእናንተ ርኩስ ናቸው ብዬ በለየኋቸው ንጹኅ ባልሆኑ እንስሳት ወይም ወፎች ወይም በማንኛውም በምድር ላይ በሚሳብ ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፡፡ 26 እኔ ያህዌ ቅዱስ እንደሆንኩ፣ ደግሞም ለእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ህዝቦች እንደለየኋችሁ ቅዱሳን ሁኑ፡፡ 27 ከሙታን ጋር የሚነጋገር አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ወይም ከመናፍስት ጋር የሚነጋገር በእርግጥ ይገደል፡፡ ህዝቡ በድንጋይ ወግፎ ይግደላቸው በደለኞች ናቸውና ሞት ይገባቸዋል፡፡
ሞሎክን የሚያመልኩ ልጆቻቸውን በእሳት መሥዋዕት አድርገው ያቀርባሉ የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት: “ለሞሎክ እንደመስዋዕት ከልጆቹ ማንኛውን የሚገድል” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “የአገረው ሕዝብ በድንጋይ ወግረው ይግደሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር የሚገልጸው “በጥብቅ መወሰኑን” ነው:: አት: “ይህን ሰው ሊጠላው በአእምሮዬ ወስኛለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በቁጣ ተሞልቻለሁ
ልጁን መስዋዕት አደረገ
“እናም ይህን በማድረጉ መቅደሴን አርክሶአል ቅዱስ ስሜንም አቃልሎአል”
የእግዚአብሔር ስም እግዚአብሔርንና ምሥክርነቱን ይገልጻል:: አት: “ምሥክርነቴን አላከበራችሁም” ወይም “አላከበራችሁኝም” (ተመሣሣይ ምትክ አባባሎችና ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
አይተው ቸል ቢሉ" የሚለው ሀረግ ማየት እንደተሳናቸው ይገልጻል ይህ የሚናገረው አንድን ነገር እንዳላዩ ቸል ማለትን ነው:: (ተመሳሳይ ምትክ አባባሎች ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ ለእግዚአብሔር ታማኝ ያለሆኑትን ከአመንዝራዎች ጋር ያነጻጽራል:: አት: “ለእግዚአብሔር ታማኝ ያልሆኑት” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ ታማኝ ያለሆኑ ሰዎችን ከአመንዝራዎች ጋር ያነጻጽራል:: አት: “ይህን በማድረጋቸው ከእኔ ሳይሆን ከመናፍስት ምክርን ይሻሉ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር “በጥብቅ መወሰኑን” ይገልጻል:: አት: ያን ሰው ሊጠላው በአእምሮዬ/በሀሳቤ ወስኛለሁ:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ )
በቁጣ ተሞልቻለሁ
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል
“ጠብቁ” “አድርጉ” የሚሉ ቃላት በመሠረቱ አንድ ናቸው:: እነዚህ ቃላት በአንድነት የተቀመጡት ሰዎች እግዚአብሔርን መታዘዝ እንዳለባቸው ትኩረት ለመስጠት ነው:: (Parallelism/ተመሣሣይ ተጓዳኝ ቃላት ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ በእርግጥ ግደሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: “ከማንም ሰው ሚስት ጋር የሚያመነዝር ሰው” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ በእርግጥ ሁለቱንም ግደሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ አንድ ሰው ከአባቱ ሚስት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙት ማድረጉን ለዛ ባለ አባባል ይገልጻል:: አንዳንድ አባባሎች እንደ “አባቱ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ” የሚሉ በጣም ቀጥተኛ ሀረጐችን ይጠቀማሉ:: (See Euphmism/ንኣብነት ወይም ለዛ ያለ ወይም በተዘዋዋሪነት አንድን ነገር ስለሚገልጹ ቃላት ይመልከቱ)
እዚህ አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙት መፈጸም እግዚአብሔር ነውር የከፋ ኃጢአት ይለዋል:: በዘሌዋዊያን 18:23 ነውር እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ይህ ከሌላ ወንድ ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸሙን ለዛ ባለ አባባል ይገልጻል አንዳንድ አባባሎች እንደ “አንድ ወንድ ሰው ግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ” የሚሉ በጣም ቀጥተኛ ሀረጐችን ይጠቀማሉ:: (See Euphmism/ንኣብነት ወይም ለዛ ያለ ወይም በተዘዋዋሪነት አንድን ነገር ስለሚገልጹ ቃላት ይመልከቱ)
ከወንድ ጋር እንደፈጸመው ከሴት ጋር ቢፈጽም፤ አት: “እንዲሁ ከሴት ጋር ቢፈጽም” (See Simile/ተመሣሣይ አባባሎችን/ድርጊቶችን ይመልከቱ
“አሳፋሪ ነገር” ወይም “የሚዘገንን ነገር”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ በእርግጥ ግደሉአቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሰውየውንና ሴቶቹን ሁለቱንም በእሳት ይቃጥላችሁ ግደሉ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “በእርግጥ ግደሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሁለቱም ሀረጐች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: እንስሳውና ሴቲቱ እንዲሞቱ አጽንዖት የሰጣሉ:: (Parallelism/ተመሣሣይ ተጓዳኝ አባባሎች ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “በእርግጥ ግደሉአቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ አንድ ሰው ከእህቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙት መፈጸሙን ለዛ ባለ አባባል ይገልጻል:: አንዳንድ አባባሎች እንደ “አንድ ሰው ግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ” የሚሉ በጣም ቀጥተኛ ሀረጐችን ይጠቀማሉ:: (See Euphmism/ንኣብነት ወይም ለዛ ያለ ወይም በተዘዋዋሪነት አንድን ነገር ስለሚገልጹ ቃላት ይመልከቱ)
ከተለየ አባት ወይም እናት ቢትሆንም ከእህቱ ጋር ግብረሥጋ ግንኙነት መፈጸም አይችልም የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “ሙሉ እህት ወይም ግማሽ እህት ብትሆንም” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ከማኀበረሰቡ የተገለለው ሰው ብጣሽ ጨርቅ ከልብስ ወይም ቅርንጫፍ ከዛፍ እንደሚቆረጥ ከሕዝቡ ተቆርጦ እንደተወገደ ተደረጐ ተገልጾአል ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: ይህን ሃሳብ በዘልዋዊያን 7:2ዐ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ አት፤ “ያ ሰው በሕዝቡ ዘንድ አይኑር” ወይም “ያን ሰው ከሕዝቡ ለዩት” (ዘይቤይዊ አነጋገር ወይም ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ ሰውየው በኃጢአቱ ይጠየቅበታል ማለት ነው:: አት: “በኃጢአቱ ተጠያቂ ነው” ወይም “ቅጡት” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ለአንድ ሴት በየወሩ ከማዕጸንዋ ደም የሚፈስስባት ጊዜ”
በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋር ግንኙነት ማድረግን አንድ የተደበቀ ነገር ሽፋን መግለጥ ጋር ያነጻጽራል ይህ አሳፋሪ አድራጐት መሆኑ መገለጽ አለበት አት የደምዋን ፍሳሽ በመግለጡ አሳፋሪ ነገር አድርጐአል:: (ዘይቤያዊ አገላለጽ ግምታዊ አውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ለምን መደረግ እንዳበት በግልጽ ይነገር:: ይህን አሳፋሪ ተግባር ስለፈጸሙ ሰውየው ሴቲቱም ሁለቱ ተለይተው ይጥፉ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ አንድ ሰው ከአባቱ እኀት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙት መፈጸሙን ለዛ ባለ አባባል ይገልጻል:: አንዳንድ አባባሎች እንደ “አንድ ሰው ግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ” የሚሉ በጣም ቀጥተኛ ሀረጐችን ይጠቀማሉ:: (See Euphmism/ንኣብነት ወይም ለዛ ያለ ወይም በተዘዋዋሪነት አንድን ነገር ስለሚገልጹ ቃላት ይመልከቱ)
“በደላችሁን ትሸከማላችሁ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር “በኃጢአታችሁ ትጠየቃላችሁ” ማለት ነው:: አት: “በኃጢአታችሁ ትጠየቁታላችሁ” ወይም “እቀጣችኋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)::
በብዙዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ሕተመቶች ይህ “ያለ ልጅ ይቀራሉ” ተብሎ ተተርጉሞአል::
ይህ ሀረግ መጥፎ ምግብን ባለመቀበል እንደሚተፋ ሰው ምድሪቱ እንደምትተፋቸው ይገልጻል ምግብን ካለመቀበል ፈንታ ምድሪቱ ሰዎችን አትቀበልም ታስወጣችኋለች:: በዘለዋዊያን 18 25 ይህን ፈሊጣዊ አባባል እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት “የማስገባባት ምድር እንዳትተፋችሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ሰውኛ አገላለጽ ይመልከቱ)
የጣዖት አድራጊዎች ተግባራት መለማመድ የእነርሱን መንገድ እንደመከተል ተደርጐ ተገልጾአል:: አት: “አትከተሉአቸው ዘይቤይዊ አነጋገር’ ይመልከቱ::
አስወግዱ
ማርና ወተት መፍሰስ የሚለው ሀረግ ለሁሉ ሰው በቂ ምግብ የያዘ ባለጸጋና ፍሬያማ ማለት ነው:: አት: “ለእንስሳትና ለእርሻ እጅግ አመቺ አገር” ወይም “ፍሬያማ ምድር “ (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ለይቻችኋለሁ ወይም የራሴ አድጌአችኋለሁ
መነጋገር የሚሞክር
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “በእርግጥ ግደሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው “ለካህናቱ፣ ለአሮን ልጆች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእናንተ መሃል ማንም በመካከላችሁ በሞተ ሰው አይርከስ፣ 2 ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በስተቀር ማንም አይርከስ ለእናቱ እና አባቱ፣ ለወንድ ልጁና ለሴት ልጁ፣ ወይም ለወንድሙ 3 ወይም በቤቱ ከምትኖር ባል ካላገባች ልጃገረድ እህቱ በስተቀር አይርከስ፡፡ ለእርሷ ግን ራሱን ንጹህ ላያርግ ይችላል፡፡ 4 ለሌሎች ዘመዶቹ ግን እስኪረክስ ድረስ ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡ 5 ካህናት ራሳቸውን አይላጩ ወይም የጺማቸውን ዳርቻ አይላጩ፣ አሊያም ሰውነታቸውን በስለት አይቁረጡ፡፡ 6 እነርሱ ለአምላካቸው የተለዩ ይሆኑ፣ የአምላካቸውን ስም አያቃሉ፣ ምክንያቱም ካህናቱ የአምላካቸውን “ምግብ” መስዋዕቱን ለያህዌ በእሳት ያቀርባሉ፡፡ ስለዚህም እነርሱ የተለዩ ይሁኑ፡፡ 7 ለአምላካቸው የተለዩ ስለሆኑ ማናቸውንም ጋለሞታ እና የረከሰች ሴት እንደዚሁም ከባሏ የተፋታችን ሴት ማግባት የለባቸውም፡፡ 8 የአምላክህን “ምግብ” የሚያቀርብ ነውና እርሱን መለየት አለብህ፡፡ በፊትህ ቅዱስ መሆን አለበት፣ ምክንያቱም ለራሴ የለየሁህ እኔ፣ ያህዌ ቅዱስ ነኝ፡፡ 9 ማንኛዋም የማንኛውም ካህን ሴት ልጅ ጋለሞታ ብትሆን አባቷን ታሳፍራለች፡፡ በእሳት ትቃጠል፡፡ 10 ከወንድሞቹ መሃል ሊቀ ካህን የሆነው፣ የሹመቱ ዘይት በራሱ ላይ የፈሰሰበት፣ ደግሞም የሊቀ ካህኑን ልዩ ልብሶች ለመልበስ የተጾመ ጸጉሩን ይሸፍን ልብሱን አይቅደድ፡፡ 11 ለአባቱ ወይም ለእናቱም ቢሆን እንኳን የሞተ ሰው በሚገኝበትና ራሱን በሚያረክስበት ማናቸውም ስፍራ አይሂድ፡፡ 12 ሊቀካህኑ የቤተ መቅደሱን የተቀደሰ ስፍራ ትቶ አይሂድ ወይም የአምላኩን ቅድስና አያቃል፣ ምክንያቱም በአምላኩ የቅባት ዘይት ሊቀ ካህን ሆኖ ተሾሞ ነበርና፡፡እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 13 ካህኑ ድንግሊቱን ሚስቱ አድርጎ ያግባት፡፡ 14 ባሏ የሞተባትን ሴት፣ የተፋታችን ሴት፣ ወይም ጋለሞታን ሴት አያግባ፡፤ እንዲያ ካሉት ሴቶች መሃል አያግባ፡፡ ከራሱ ህዝብ መሃል ድንግሊቱን ብቻ ማግባት ይችላል፡፡ 15 እነዚህን ህጎች ይጠብቅ፣ በህዝቡ መሃል ልጆቹን እንዳያረክስ ህግጋቱን ይጠብቅ፣ እርሱን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 16 ያህዌ እንደህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣ 17 “አሮንን እንዲህ ብለህ ንገረው፣ ማናቸውም ከወገንህ መሀል በትወልዳቸው ውስጥ አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ የአምላኩን ‹ምግብ› ለመሰዋት መቅረብ የለበትም፡፡ 18 ማናቸውም አካላዊ እንከን ያለበት ሰው ወደ ያህዌ መቅረብ የለበትም፣ እንደ ዐይነ ስውር፣ ሽባ የሆነ ሰው፣ አካሉ የጎደለ ወይም አካሉ የተወላገደ፣ 19 እጆቹ ወይም እግሮቹ ሽባ የሆነ፣ 20 መጻጉ ወይም ድንክ ሰው፣ ወይም በዐይኖቹ ላይ እንከን ያለበት ሰው፣ ወይም በሽታ የያዘው፣ ሞጭሟጫ፣ እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ ወደ ያህዌ አይቅረብ፡፡ 21 ከካህኑ ከአሮን መሃል ምንም አካላዊ ጉድለት ያለበት ሰው ለያህዌ የእሳት መስዋዕቶች ለመሰዋት አይቅረብ፡፡ አካላዊ ጉድለት ያለበት እንዲህ ያለው ሰው የአምላኩን ‹ምግብ ለማቅረብ መቅረብ የለበትም፡፡ 22 ከቅድስተ ቅዱሳኑም ሆነ ከቅዱሱ የአምላኩ ምግብ ሊበላ ግን ይችል፣ 23 ሆኖም፣ ወደ መጋረጃው መግባት የለበትም ወይም ወደ መሰዊያው አይቅረብ፣ ምክንያቱም አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ ስለዚህም ቅዱሱን ስፍራዬን አያርክስ፣ ለራሴ የለየኋቸው እኔ ያህዌ ነኝ፡፡” 24 ሙሴ እነዚህን ቃላት ለአሮን፣ ለልጆቹ፣ እና ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ ተናገረ፡፡
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ያልተገባ ሰው ርኩስ ተብሎአል (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
በእራኤላዊያን መካከል
ያላገባች ወጣት ሴት
ካህናቶች የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ:: እዚህ ጸሐፊው ምን ለማለት እንደፈለገ ግልጽ ላይሆን ይችላል:: ሁኔኛ ትርጉሞች እነሆ 1) የጢማቸውን ከፊሉን ክፍል ይላጩ:: 2) ማንኛውንም የጢም ክፍል አይላጩ::
የተለዩ ይሁኑ
“ስም” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ባህሪይ ያመለክታል:: አት: “የእግዚአብሔርን ምሥክርነት እታቃልሉ ወይም እግዚአብሔርን አያቃልሉ” (ተመሣሣይ ምትክ አባባሎችን ይመልከቱ)
እዚህ ምግብ አጠቃላይ ምግብን ያመለክታል እግዚአብሔር እነዚህ የሚቀርቡ መሥዋዕቶችን አይመገብም:: እግዚአብሔርን የሚያስደስተውን የምግብ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ሰዎች ቅንነትን ነው: (See Synecdoche/ክፍልን እንደ ሙሉ ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ካህናት አያግቡ
ለተለዩ ናቸው
ካህኑን እንደቅዱስ ቁጠሩት
እዚህ ምግብ አጠቃላይ ምግብን ያመለክታል እግዚአብሔር እነዚህ የሚቀርቡ መሥዋዕቶችን አይመገብም:: እግዚአብሔር ምግብን እንደማይመገብ ግልጽ በማድረግ ይህን ይተርጉሙ (See Synecdoche/ክፍልን እንደ ሙሉ ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እንደ ቅዱስ ቁጠሩት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “በእሳት አቃጥሉአት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ካህናት ማድረግ ያለባቸው ምን እንደሆነ እግዚአብሔር ለሙሴ በናገሩ ይቀጥላል
አዲስ ልቀካህን ለይቶ በመቀባት ሥርዓተ በዓል የሚጠቀሙበት የመቀብያ ዘይት ነው:: የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይጠቀሙ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “በራሱ ላይ የመቀብያ ዘይት ያፈሰሱበትና የለዩት ሰው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ራስ መንጨትና ልብስ መቀደድ የሀዘን ምልክቶች ናቸው:: የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ከራሱ ጐሣ ከሌዊ ጐሣ
የረከሰችውን ወይም ያልተገባችውን ሴት በማግባት ካህኑ የሚወልዱአቸው ልጆች ለእርሱ ያልተገቡ ይሆናሉ:: አት: “ያልተገባችውን ሴት በማግባት ያልተገቡ ልጆች አይኑሩት” (ፈሊጣዊ አነጋር ይመልከቱ)::
የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን የእህል መሥዋዕት ለማቃጠል አይቅረብ” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
አንድ ካህን ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ዝርዝር አካላዊ መሥፈርቶችን ማሟላት አለበት:: ይህም የአካል ጐዶሎነት የኃጢአት ወጤት ወይም ማንኛውም የአካል ጐዶሎነት ያለው ሰው ወደ እግዚብሔር መቅረብ አይችልም ማለት አይደለም::
“ፊቱና አካሉ የተበላሸ”
“ምግብ” አጠቃላይ ምግብ ያመለክታል:: አት “በእግዚአብሔር መሠዊያ የሚቃጠል የእህል መሥዋዕት ለማቅረብ” (See Synecdoche/ክፍልን እንደ ሙሉ ሙሉን እንደክፍል የመግለጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ “እርሱ” የአካል ጐዶሎነት ያለውን ካህን ያመለክታል
የአምላኩን ምግብ መሥዋዕቶች ይብላ ከመሥዋዕቶቹ ከፊሎች የካህናት ናቸውና ሊበሉ ይችላሉ
ይህ ደግሞ መሥዋዕት ሆኖ ስለቀረበው ምግብ ነው የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት ከእነዚህ አንዳንድ መሥዋዕቶች በቅዱስ ሥፍራ ቀርበዋል ወይም ከእነዚህ አንዳንዶች በቅዱሳነ ቅዱሳን ቀርበዋል:: (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“ለአሮን ልጆች”
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2 “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፣ የእስራኤል ሕዝብ ለእኔ ከለይዋቸው የተቀደሱ ነገሮች እንዲጠበቁ ንገራቸው፡፡ የተቀደሰው ስሜን አያርክሱ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 3 እንዲህ በላቸው፣ በዘመን ሁሉ ከትውልዳችሁ መሀል ማንም ንጹህ ያልሆነ ሰው የእስራኤል ህዝብ ለያህዌ ወደ ለየው ቅዱስ ነገሮች ቢቀርብ፣ ያ ሰው እኔ ፊት ከመቅረብ የተከለከለ ነወ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 4 ከአሮን ትውልድ ውስጥ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ያለበት፣ ወይም ከሰውቱ ፈሳሽ የሚወጣ ንጹኅ እስኪሆን ድረስ ለያህዌ ከሚቀርብ መስዋዕት አይብላ፡፡ማንም ከሞተ ጋር በመነካካት ንጹህ ያልሆነውን ማንኛውንም ነገር የነካ፣ ወይም የዘር ፈሳሽ ካለበት ሰው ጋር በመነካካት፣ 5 ወይም የሚያረክሰውን ማናቸውንም በሆዱ የሚሳብ እንስሳ የነካ፣ ወይም ማናቸውንም የሚያረክሰውን ሰው የነካ፣ ማንኛውም አይነት እርኩሰት የሚያስከትል ነገር የነካ 6 ማናቸውንም እርኩስ ነገር የነካ ካህን እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ ሰውነቱን በውሃ ካልታጠበ በቀር ከተቀደሱት ነገሮች አንዳች አይብላ፡፡ 7 ፀሐይ ስትጠልቅ፣ በዚያን ሰዓት ንጹህ ይሆናል፡፡ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ከተቀደሱት ነገሮች መብላት ይችላል፣ ምክንያቱም ለእርሱ የተፈቀዱ ምግብ ናቸው፡፡ 8 ሞቶ የተገኘን ማናቸውም ነገር አይብላ ወይም እርሱን የሚያረክሰውን በዱር እንስሳ የተገደለውን አይብላ፡፡ 9 ካህናት ትእዛዛቴን ይጠብቁ፣ ይህን ካላደረጉ በኃጢአት በደለኛ ይሆናሉ ደግም ስሜን በማቃለል ይሞታሉ፡፡ ለራሴ የለየኋቸው እኔ ያህዌ ነኝ፣ 10 ማንም የካህኑ ቤተሰብ ያልሆነ ሰው፣ የካህኑን እንግዶች ጨምሮ፣ ወይም ቅጥር አገልጋዮቹ ጭምር ቅዱስ ከሆነው አንዳች አይብሉ፡፡ 11 ነገር ግን ካህኑ በገንዘቡ ባሪያ ቢገዛ ያ ባሪያ ለያህዌ ከተለዩ ነገሮች መብላት ይችላል፡፡ የካህኑ ቤተሰብ አባላት እና በቤቱ የተወለዱ ባሪያዎች ከእርሱ ጋር ከእነዚህ የተቀደሱ ነገሮች መብላት ይችላሉ፡፡ 12 የካህኑ ሴት ልጅ ካህን ያልሆነ ሰው ብታገባ ለመስዋዕት ከመጣው ውስጥ አንዳች አትበላም፡፡ 13 ነገር ግን የካህኑ ሴት ልጅ ባሏ የሞተባት ከሆነች፣ ወይም ከባሏ ከተፋታች፣ እና ልጅ ያልወለደች ከሆነች እንደ ልጅነቷ ዘመን ለመኖር ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ ከአባቷ ምግብ መብላት ትችላለች፡፡ ነገር ግን ማንም የካህን ቤተሰብ ያልሆነ ከካህናት ምግብ መብላት አይችልም፡፡ 14 አንድ ሰው ሳያውቅ ቅዱሱን ምግብ ቢበላ፣ ከወሰደው አንድ አምስተኛ ጨምሮ ለካህኑ ይመልስ፡፡ 15 የእስራኤል ህዝብ ለያህዌ የወዘወዙትንና ያቀረቡትን ቅዱስ ነገሮች ማቃለል የለባቸውም፣ 16 ያልተፈቀደላቸውን ቅዱሱን ምግብ በመብላት ራሳቸውን በደለኛ የሚያደርጋቸውን ኃጢአት እንዲሸከሙ ማድረግ የለባቸውም እነርሱን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ” 17 ያህዌ እንዲህ አለው፣ 18 “ለአሮንና ልጆቹ እንዲሁም ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንዲህ በላቸው፣ ‹ማንኛውም እስራኤላዊ፣ ወይም በእስራኤል የሚኖር ባይተዋር፣ ለስዕለትም ይሁን፣ ወይም ለበጎ ፈቃድ መስዋዕት ሲያቀርቡ፣ ወይም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ሲያቀርቡ፣ 19 ተቀባይነትን እንዲያገኝ ከቀንድ ከብታቸው፣ ከበግ ወይም ፍየሎች ውስጥ ነውር የሌለበትን ተባዕት እንስሳ ያቅርቡ፡፡ 20 ነውር ያለበትን ግን አታቅርቡ፡፡ ይህን እኔ አልቀበልም፡፡ 21 ከከብቱ ወይም ከመንጋው ለስዕለት የህብረት መስዋዕት ለያህዌ የሚሰዋ ሁሉ፣ ወይም የበጎ ፍቃድ መስዋዕት የሚያቀርብ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ነውር የሌለበትን መስዋዕት ያቅርብ፡፡ በእንስሳው ላይ እንከን አይኑርበት፡፡ 22 ዕውር፣ አንካሳ ወይም ሰንካላ፣ ወይም ኪንታሮት፣ ህመም፣ ወይም ቁስል ያለበትን እንስሳ አትሰዉ፡፡ እዚህን በእሳት መስዋዕት አድርጋችሁ በመሰዊያ ላይ ለያህዌ አታቅርቡ፡፡ 23 የበጎ ፈቃድ መስዋዕት አድርጋችሁ ጎደሎ ወይም ትንሽ በሬ ወይም በግ ማቅረብ ትችላላችሁ፣ እንዲህ ያለው መስዋዕት ግን ለስዕለት ተቀባይነት የለውም፣ 24 ለያህዌ ሰንበር ያለበት፣ የተሰበረ፣ የተዘነጠለ፣ ወይም የዘር ፍሬው የተቀጠቀጠ እንስሳ አታቅርቡ፡፡ እነዚህን በምድራችሁ አታቅርቡ፣ 25 ለእግዚአብሔር ለምግብ የሚቀርብ አድርጋችሁ ከመጻተኛው እጅ አትቀበሉ፣ ምክንያቱም በእነዚህ ላይ ጉድለቶች ወይም ነውሮች አሉባቸው እነዚህን ከእናንተ አልቀበለም፡፡›” 26 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 27 “አንድ ጥጃ ወይም አንድ የበግ ወይም የፍየል ግልገል ሲወለድ፣ ከእናቱ ጋር ሰባት ቀናት ይቆይ፡፡ ከዚያም ከስምንተኛው ቀን አንስቶ፣ ለያህዌ በእሳት መስዋዕት ሆኖ መቅረብ ይችላል፡፡ 28 አንዲትን ላም ወይም ሴት በግ ከጥጃዋ ወይም ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ፡፡ 29 ለያህዌ የምስጋና መስዋዕት ስታቀርቡ፣ ተቀባይነት ባለው መንገድ አቅርቡ፡፡ 30 መስዋዕቱ በቀረበበት ቀን ይበላ፡፡ እስከ ማለዳው አንዳች አታስቀሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 31 ትዕዛዛቴን ጠብቁ አድርጓቸውም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 32 ቅዱስ ስሜን አታቃሉ፡፡ በቅድስናዬ በእስራኤል ህዝብ መታወቅ አለብኝ፡፡ እናንተን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ፣ 33 አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
“ቅዱስ ከሆኑ ነገሮች ምን ጊዜ መራቅ እንዳለባቸው ንገራቸው” አንድ ካህን ርኩስ በሆነና ቅዱስ የሆኑ ነገሮች መንካት የሌለበት ሁኔታዎችን እግዚአብሔር ይገልጻል፡፡
እዚህ “ማርከስ” የሚለው ቃል አለማክበርን ይገልጻል፡፡ “ስም” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ባህሪይ ያመለክታል:: አት “ምሥክርነቴን አላከበሩም” ወይም “አላከበሩኝም” ( See Metonymy/ተዛማጅ ባህሪይ የሚቀልጽ ምትክ ቃላት የመጠቀም አነጋገር ዘይቤ ይመልከቱ)
“ከዛሬ/ከአሁን ጀምሮ”
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ያልተገባው ሰው ንጹህ ያልሆነ ወይም ርኩስ ተበሎአል:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔርን ማገልገል የማይችል ካህን ብጣሽ ጨርቅ ከልብሰ ወይም ቅርንጫፍ ከዛፍ ተቆርጦ እንደሚወገድ ከእግዚአብሔር መገኘት ተቆርጦ እንደተወገደ ተደርጐ ተገልጾአል፡፡ አት: “ያ ሰው ካህን ሆኖ ማገልገል አይችልም” (ዘይቤይዊ አገላለጽና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ከአንድ ሰው ወደ ሌላው በቀላሉ ሊተላለፍ የሚችል የቆዳ በሽታ ነው
“የሰውነት ፈሳሽ ነገር”
ይህ የሰውን ሀፍረተ አካላት ለዛነት በተሞላ አባባል ይገልጻል፡፡ በዘሌዋዊያን 15 1 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ አት ከሀፍረተ አካላቶች (see Euphemism/ንኣብነት ወይም ለዛ ያለ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ አንድን ነገር የመግለጽ ዘይቤያዊ አባባል ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች የተገባ ሰው ንጹህ ተበሎአል:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለመንካ ወይም ለመብላት ያልተገባ ያለው አንድ ነገር በአካል ርኩስ ነው:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ሙት አካል በመንካት”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ያቀረባቸው መሥዋዕቶች” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት ወይም በደረት የሚሳብ እንስሳ በመንካት ወይም ርኩስ የሆነውን ሰው በመንካት የረከሰ ማንኛውም ሰው (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ያልተገባው ሰው ርኩስ ተብሎአል (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ጸሐይ እስከሚትጠልቅ
ከዚያም ካህኑ ንጹህ ይሆናል ለእግዚአብሔር ዓላማዎች የተገባው ሰው ንጹህ ተብሎአል (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የገደለውን” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አሮንና ልጆቹ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
“ተዋጽኦ” የሚለው ቃል እንደ ግሥ ሐረግ ሊተረጐም ይችላል:: አት: “ሰዎች ያዋጡት የተቀደሰው መሥዋዕት” (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
ሁኔኛ ትርጉሞች 1)ምግቡን የበላ ሰው ተመሣሣይ ዓይነት ምግብ ይተካ 2) ስለበላው ምግብ ለካህኑ ገንዘብ ይክፈል አንድ አምስተኛ ከአምስት ተመሣሣይ ክፍሎች አንዱን ማለት ነው:: (ክፍልፋዮችን ይመልከቱ)
እዚህ “ከፍ አድርገው” የሚለው ሀረግ ለእግዚአብሔር አንድን ነገር በአክብሮት የማቅረብ ድርጊታዊ ምልክት ነው:: “ማቅረብ” ከሚለው ጋር በመሠረቱ አንድ ነው :: አት: “አቅርበዋል” (ምልክታዊ ድርጊቶችንና ድርብ ቃላትን/doublet ይመልከቱ)
ኃጢአት ሰው እንደሚሸከመው ዕቃ ተደርጐ ተገልጾአል ሁኔኛ ትርጉሞች 1) ስለ ኃጢአታቸው ተጠያቂና በደለኛ ይሆናሉ አት ስለሠሩት ኃጢአት በደለኛ ይሆናሉ ወይም 2) ኃጢአት የሚለው ቃል ለሠሩት ኃጢአት ስለሚሰጥ ቅጣት ምትክ ቃል ነው አት በደለኞች ስለሆኑ ቅጣትን ይቀበላሉ:: (ዘይቤያዊ አነጋገርና ምትክ ተመሣሣይ ቃላት ይመልከቱ)
እንግዳ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እግዚአብሔር እንዲቀበለው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር እንዲቀበለው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እኔ እንዲቀበለው” ወይም “እግዚአብሔር እንዲቀበለው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እነዚህ ቃላት በአደጋ ምክንያት የተከሰቱ የአካል ጐደሎነት ያመለክታሉ
እነዚህ የቆዳ በሽታዎችን ያመለክታሉ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “አልቀበለውም” ወይም “እግዚአብሔር አይቀበለውም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እነዚህ ቃላት በተፈጥሮ ችግር ያለባቸውን እንስሳት ያመለክታሉ
እዚህ ምግብ አጠቃላይ ምግብ ይወክላል መሥዋዕት ሆነው የቀረቡትን እግዚአብሔር አይበላም:: ካህናት በእግዚአብሔር መሠዊያ መሥዋዕት ያቀርባሉ እናም ከሥጋው ይበላሉ:: አት: “ለእግዚአብሔር እንስሳን እንደምግብ መሥዋዕት አታቅርቡ” (See Synecdoche/ክፍልን እንደ ሙሉ ሙሉን እንደ ክፍል የመግለጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እጅ የሚለው ቃል መላውን ሰው ይወክላል ባእዳን እንስሳትን በማኮላሸት ለእግዚአብሔር ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ስለሚያደርጉ እነርሱ መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡትን እንስሳት እስራኤላዊያን እንዳይጠቀሙ ይገልጻል (see Synecdoche, ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እግዚአብሔር እነዚህን ከእናንት አይቀበልም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሊትቀበሉት ትችላላችሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ለሚቃጠል መሥዋዕት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ብሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርባችኋል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“ጠብቁ” እና “አድርጉ” የሚሉ ቃላት ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ሕጐች እንዲታዘዙ ትኩረት የሚሰጡ ናቸው:: አት: “ሕጐቼን ታዘዙ” (See Doublet/ ተመሣሣይ ትርጉም ያላቸውን ድርብ ቃላትን ይመልከቱ)
እዚህ “ስም” የሚለው ቃል እግዚአብሔርንና ምሥክርነቱን ይወክላል፤ እናም “ማርከስ” ማለት እግዚአብሔር ፈጣሪና የዓለም ሁለ አምላክ በመሆኑ የሚገባውን ክብር አለመስጠት ነው:: (ተዛማጅ ባህርይ የሚገልጹ ምትክ ቃላት አጠቃቀም ዘይቤ ይመልከቱ/See Metonymy)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እስራኤላዊያን ቅዱስ መሆነን ማወቅ አለባቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ በላቸው፣ ‹ለያህዌ የተለዩ የተቀደሱ ባዕሎቻችሁ፣ እንደ ቅዱስ ጉባኤዎቻችሁ የምታውጇቸው፣ የእኔ መደበኛ በዓላት ናቸው፡፡ 3 ስድስት ቀናት ትሰራላችሁ፣ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ እረፍት የሚደረግበት ሰንበት ነው፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለያህዌ ሰንበት ስለሆነ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡ 4 እነዚህ ለያህዌ የተመረጡ በዓላት ብላችሁ በተወሰነላቸው ጊዜ የምታውጇቸው የተቀደሱ ስብሰባዎች ናቸው፡፡ 5 በመጀመሪያው ወር በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን ጸሀይ ስትጠልቅ የያህዌ ፋሲካ ነው፡፡ 6 በዚያው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን የያህዌ የቂጣ በዓል ነው፡፡ ለሰባት ቀናት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ትበላላችሁ፡፡ 7 በመጀመሪያው ቀን ለያህዌ የተለየ ጉባኤ ይኖራችኋል፣ የተለመደ ተግባራችሁን አትሰሩበትም፡፡ 8 ለሰባት ቀናት በእሳት የሚቀርብ መስዋዕት ለያህዌ ታቀርባላችሁ ሰባተኛው ቀን የተለመደ ተግባራችሁን የማታከናውኑበት ለያህዌ የተለየ ጉባኤ የሚደረግበት ነው›” 9 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 10 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው ‹ወደምሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ እና የመጀመሪያውን አዝመራ ስትሰበስቡ፣ ከበኩራቱ ፍሬዎች ለካህኑ አንድ ነዶ ታመጣላችሁ፡፡ 11 ነዶው ተቀባይነትን እንዲያገኝ ካህኑ በያህዌ ፊት ይወዘውዘውና ለእርሱ ያቀርበዋል፡፡ ካህኑ ነዶውን የሚወዘውዘውና ለእኔ የሚያቀርበው በሰንበት ቀን ማግስት ነው፡፡ 12 ነዶውን በምትወዘውዙበትና ለእኔ በምታቀርቡበት ቀን ለያህዌ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ 13 የእህል ቁርባን ለያህዌ መልካም መዓዛ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት፣ እና ከነዚህም ጋር የኢን አንድ አራተኛ ወይን የመጠጥ ቁርባን መቅረብ አለበት፡፡ 14 ለአምላካችሁ ይህን መስዋዕት እስከምታቀርቡበት ቀን ድረስ ምንም ዓይነት ዳቦ፣ አሊያም የተጠበሰ እሸት ወይም ለምለሙን እሸት አትብሉ፡፡ ይህ ለትወልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ 15 ከዚያ ሰንበት ቀን ማግስት አንስቶ ነዶውን ለመወዝወዝና ለያህዌ ለማቅረብ ካመጣችሁት ቀን ጀምራችሁ ሰባት ሙሉ ሳምንታት፣ ሰባት ሰንበት ትቆጥራላችሁ፣ 16 እስከ ሰባተኛው ሰንበት ማግስት ድረስ ትቆጥራላሁ፡፡ ያም ማለት ሀምሳ ቀናት ትቆጥራላችሁ፡፡ ከዚያ ለያህዌ የአዲስ አዝመራ መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ 17 ከየቤቶቻችሁ ከኢፍ ሁለት አስረኛ የተጋገሩ ሁለት ዳቦዎች ታመጣላችሁ፡፡ ከመልካም ዱቄት የሚዘጋጅና በእርሾ የተጋገሩ ይሁኑ፤ ከበኩራት ፍሬዎች የሚቀርቡ የሚወዘወዙና ለያህዌ የሚቀርቡ መስዋዕቶች ይሆናሉ፡፡ 18 ከዳቦው ጋር ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እድሜ ያላቸው ሰባት ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈን በሬ፣ እና ሁለት አውራ በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ እነርሱም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናሉ፣ ከእህል ቁርባን ከመጠጥ ቁርባን ጋር፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት እና ለያህዌ መልካም መዓዛ ያለው መስዋዕት ይሆናሉ፡፡ 19 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ታቀርባላሁ፣ እንዲሁም ለህብረት መስዋዕት የአንድ አመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ወንድ ጠቦቶች ለመስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ 20 ካህኑ ከበኩራት ፍሬዎች ዳቦ ጋር በያህዌ ፊት ይወዘወዛቸው፣ እነርሱንም መስዋዕት አድርጎ ለእርሱ ከሁለት ጠቦቶች ጋር ያቅርብ፡፡ ለያህዌ ቅዱስ መስዋዕቶች ሲሆኑ የካህኑ ድርሻ ናቸው፡፡ 21 በዚያው ቀን ማወጅ አለባችሁ፡፡ የተቀደሰ ጉባኤ ይኖራል፣ እናም የተለመደ ስራችሁን አትሰሩም፡፤ ይህ የህዝባችሁ በትውልዶች ሁሉ በምትኖሩበት ሥፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ 22 የምድራችሁን ፍሬ ስትሰበስቡ፣ የእርሻችሁን ጥግጋት ሁሉ ሙሉ ለሙሉ አትሰብስቡ፣ የሰብላችን ቃርሚያ ሁሉ አትሰብስቡ፡፡ እነዚህን ለድሆችና ለመጻተኛው ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡” 23 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 24 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር፣ የወሩ የመጀመሪያው ቀን ለእናንተ ታላቅ እረፍት ይሆናል፣ በመለኮት ድምጽ መታሰቢያ የሚደረግበት፣ እና የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል፡፡ 25 የተለመደ ሥራ አትሰሩበትም፣ ለያህዌ የእሳት መስዋዕት አቅርቡበት፡፡›” 26 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 27 “አሁን የዚህ የሰባተኛው ወር አስረኛ ቀን የስርየት ቀን ይሆናል፡፡ ለያህዌ የተለየ ጉባኤ መሆን አለበት፣ ራሳችሁን ማዋረድና ለያህዌ በእሳት መስዋዕት መሰዋት አለባችሁ፡፡ 28 በዚያን ቀን ምንም ሥራ አትስሩ ምክንያቱም በአምላካችሁ በያዌ ፊት ለራሳች ማስታሰርያ የምታቀርቡበት የስርየት ቀን ነው፡፡ 29 በዚያን ቀን ራሱን የማያዋርድ ማንም ቢሆን ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡ 30 በዚያን ቀን ማናቸውንም ሥራ የሚሰራውን ማንንም ቢሆን፣ እኔ ያህዌ ከህዝቡ መሀል አጠፋዋለሁ፡፡ 31 በዚያ ቀን ማናቸውንም ዐይነት ሥራ አትሰሩም፡፡ ይህ በህዝባችሁና ትውልዶቻችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ 32 ይህ ቀን ለእናንተ የከበረ የሰንበት ዕረፍት ይሁንላችሁ፣ እናንተም በወሩ በዘጠነኛው ቀን ራሳችን አዋርዱ፡፡ ከምሽት እስከ ምሽት ሰንበትን ጠብቁ፡፡” 33 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 34 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር አስራ አምስተኛው ቀን ለያህዌ የዳስ በዓል ይሆናል፡፡ ይህም ሰባት ቀናት ይወስዳል፡፡ 35 በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይኖራል፡፡ የተለመደውን ሥራ አትስሩበት፡፡ 36 ለሰባት ቀናት ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡበት፡፡ በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሁን፣ እናንተም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ይህ ክቡር ጉባኤ ነው፣ እናም አንዳች የተለመደ ሥራ አትስሩበት፡፡ 37 እነዚህ ለያህዌ የተለዩ በአላት ናቸው፣ ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ለማቅረብ ቅዱስ ጉባኤ የምታውጁበት፣ የሚቃጠል መስዋዕትና የእህል ቁርባን፣ የመስዋዕቶችና የመጠጥ ቁርባች እያንዳንዱን በየራሱ ቀን ለይታችሁ ለእግዚአብሔር የምታውጁባቸው በዓላት ናቸው፡፡ 38 እነዚህ በአላት ከያህዌ ሰንበታትና ከእናንተ ስጦታዎች ተጨማሪ ናቸው፣ ስጦቻችሁ ሁሉ፣ እና ለያህዌ የምትሰጧቸው የበጎ ፈቃድ መስዋዕቶቻችሁ ሁሉ ናቸው፡፡ 39 የዳስ በዓልን በሚመለከት፣ በሰባተኛው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን፣ እናንተ የምድሪቱን ፍሬዎች ስትሰበስቡ ይህን የያህዌ በዓል ለሰባት ቀናት ማክበር አለባችሁ፡፡ የመጀመሪያው ቀን የፍፁም ዕረፍት ቀን ይሆናል፣ ስምንተኛው ቀንም እንደዚሁ የፍጹም ዕረፍት ቀን ይሆናል፡፡ 40 በመጀመሪያው ቀን ከዛፎቹ መልካሞቹን ፍሬዎች ውሰዱ፣ የዘንባባ ዛፎች ዝንጣፊዎች፣ እና የለምለሙ ዛፎች ቅርንጫፎች፣ ከወንዝ ዳርቻ ለምለም ዛፎች ቅርንጫፎች ወስዳችሁ በአምላካችሁ በያህዌ ፊት ለሰባት ቀናት ሃሴት ታደርጋላችሁ፡፡ 41 በየአመቱ ለሰባት ቀናት፣ ይህን በዓል ለያህዌ ታከብራላችሁ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ ይህን በዓል በሰባተኛው ወር አክብሩ፡፡ 42 ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ትኖራላችሁ፡፡ እስራኤላዊ የሆነ ሁሉ ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ይቀመጥ፣ 43 ከእናንተ በኋላ የሚመጣው ትውልድ፣ የልጅ ልጆቻችሁ፣ እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ሳወጣ በእንደዚህ ዐይነት ዳሶች ውስጥ እንዴት እንዲኖሩ እንዳደረግኩ ያውቃሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡›” 44 በዚህ መንገድ፣ ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ ለያህዌ የተለዩትን በዓላት አስታወቁ፡፡
እነዚህ እግዚአብሔር ቀን የመደበላቸው በዓላት ናቸው፡፡ በእነዚህ በዓላትሕዝቡ እርሱን ያመልካል፡፡ አት፡ “ለእግዚአብሔር የሆኑ በዓላት” ወይም “የእግዚአብሔር በዓላት”
በተለዩ ቀናትና ጊዜያት ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
ይህ ሕዝቡ መለማመድ ያለበት ነው ስድስት የሥራ ቀናት በኋላ በሰባተኛው ቀን ማረፍ አለባቸው
በዚያ ቀን እግዚአብሔርን ለማምለክ ሕዝቡ እንዲሰበሰብ የተፈለገው ያ ቀን የስብሰባ እንደሆነ ተደርጐ ተገልጾአል:: አት “የተቀደሰ ቀን፤ በአንድነት እኔን ለማምለክ የሚትሰባሰቡበት ጊዜ”
“በመደበኛው ጊዜ”
በዕብራዊያን የቀን አቆጣጠር የመጀመሪያ ወር እግዚአብሔር እስራኤላዊያንን ከግብጽ ያመለክታል አሥራ አራተኛው ቀንና አሥራ አምስተኛው ቀን በምዕራባዊያን አቆጣጠር በሚያዝያ ወር መግቢያ ናቸው:: (የእብራይጥ ወራትና ተራ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ጸሐይ ስጠልቅ
“መጀመሪያውን ቀን ጉባዔ ለማድረግ ለዩ” ወይም “የመጀመሪያውን ቀን እንደ ልዩና የጉባዔ ቀን ቁጠሩት”
በመሠዊያው በማቃጠል ለእግዚአብሔር ያቀርቡታል
በዚያ ቀን እግዚአብሔርን ለማምለክ ሕዝቡ እንዲሰበሰብ የተፈለገው ያ ቀን የስብሰባ እንደሆነ ተደርጐ ተገልጾአል:: ለእግዚአብሔር የተቀደሰ/የተለየ ማለት በሚሰባሰቡበት ጊዜ እግዚአብሔርን ያመልኩታል ማለት ነው:: አት: “ሰባተኛው ቀን በአንድነት ተሰባስባችሁ እግዚአብሔርን የሚታመልኩበት ቀን ነው”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እግዚአብሔር እንዲቀበልላችሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
አንድ ኢፍ 22 ሊትር ነው:: አት: አራት ከግማሽ ሊትር (መጽሐይ ቅዱሳዊ መለኪያዎችን ይመልከቱ)፡፡
አንድ ኢን 3.7 ሊትር ነው:: አት: አንድ ሊትር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎችን ይመልከቱ::
የተቀቀለ ወይም ያልተቀቀለ ጥራጥሬ አይሁን ይህም ለሚመጡት ትውልዶች የዘላለም ሥርዓት ነው:: ይህም እነርሱ ሆነ ቀጣይ ትውልዳቸው ይህን ሥርዓት ለዘላለም መጠበቅ አለባቸው ማለት ነው በዘሌዋዊያን 3:17 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
“5ዐ ቀናት” ተራ ቁጥሮችን ይመልከቱ
ይህ ቁጥር 7 መደበኛ ስያሜ ነው (መደበኛ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ያም ሁለት አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ የላመ ዱቄት ወስዳችሁ በእርሾ የጋገራችሁት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
በግምት 4.5 ሊትር ያህላል:: አት: አራት ከግማሽ ሊትር (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎች ይመልከቱ)
በመልካም በዓዛው የእግዚአብሔር መደሰት መሥዋዕቱን በሚያቃጥለው ሰው መደሰትን ይወክላል:: አት: “እግዚአብሔር ይደሰትባችኋል” ወይም “እግዚአብሔርን ያስደስተዋል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
አት: “መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ዳርና ዳር ድረስ ያለውን ሁሉ አትሰብስቡ”
ይህ በዕብራዊያን ቀን አቆጣጠር ሰባተኛ ወር ነው:: መጀመሪያው ቀን በምዕራባዊያን አቆጣጠር መስከረም ወር አጋማሽ አካባቢ ነው:: (የዕብራይስጥ ወራትንና መደበኛ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ለሥራ ሳይሆን ለአምልዕኮ ብቻ የተመደበ ጊዜ ማለት ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን በእሳት አቅርቡ” ወይም “ለእግዚአብሔር በመሠዊያው መሥዋዕትን አቃጥሉ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ በዕብራዊያን ቀን አቆጣጠር ሰባተኛ ወር ነው:: በምዕራባዊያን አቆጣጠር አሥረኛው ቀን መስከረም ወር መጨረሻ አካባቢ ነው:: (የዕብራይስጥ ወራትንና መደበኛ ቁጥሮችን ይመልከቱ)
የእስራኤልን ሕዝብ ኃጢአት ሁሉ እግዚአብሔር ይቅር እንዲል በየዓመቱ በዚህ ቀን ሊቀ ካህኑ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርባል:: አት፡ “ለይቅርታ ወይም ለሥርየት መሥዋዕት የሚቀርብበት ቀን” (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
በየዓመቱ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
መገለል እንደ መቆረጥ ተነግሮአል በዘሌዋዊያ 7:2ዐ ይህን ሀሳብ እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ:: አት: “ከሕዝቡ ዘንድ መወገዝ አለበት” ወይም “ ሰውየውን ከሕዝቡ መለየት አለባችሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገርና ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
በየዓመቱ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
“በሥርየት ቀን”
ይህም እነርሱ ሆነ ቀጣይ ትውልዳቸው ይህን ሥርዓት ለዘላለም መጠበቅ አለባቸው ማለት ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 3:17 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ይህ በየሳምንቱ በሰባተኛው ቀን እንደሚከበረው ሰንበት አይደለም፡፡ ይህ በሥርየት ቀን የሚከበር ልዩ ሰንበት ነው፡፡
በዚህ ዐውድ ራሳቸውን ዝቅ ማድረግ ማንኛውን ምግብ አለመብላታቸውን ያመለክታል ይህ ግልጽ ሆኖ ሊነገር ይችላል:: አት: “ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ ምግብንም አትብሉ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ በዕብራይስጥ ቀን መቁጠሪያ ሰባተኛ ወር ነው በምዕራባዊያነ ቀን መቁጠሪያ ዘጠነኛው ቀን መስከረም ወር መጨረሻ አካባቢ ነው ይህም ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት የሰባተኛው ወር ዘጠነኛ ቀን (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ከጸሐይ መግቢያ እስከሚቀጥለው ቀን ጸሐይ መግቢያ
x
እግዚአብሔር ስለ ዳስ በዓል መመሪያዎችን ያስተላልፋል
ሕዝቡ በየዓመቱ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
በ23: 1-36 የተጠቀሱ በዓላትን ነው::
እግዚአብሔር የዳስ በዓል መመሪያዎችን ያስተላልፋል
እነዚህ ቅርጫፎች የሚጠቅሙት 1) ጊዜያዊ ዳስ ለመሥራት 2) የበዓላቸውን ደስታ በማውለብለብ አንዳንድ ትርጉሞች እነዚህን ጥቅሞች ግለጽ አድርገው ሲገልጹ ሌሎች ግን ግልጽ ሳያደርጉ ይተዋሉ:: (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በውሃ አጠገብ የሚበቅሉ ረጅ ቀጭን ቅጠሎች ያሉአቸው ተክሎች ወይም ዛፎች ናቸው (ያልታወቁትን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
እግዚአብሔር የዳስ በዓል መመሪያዎችን ያስተላልፋል
“የልጅ ልጆቻችሁ” ከአንድ ትውልድ ቀጥሎ የሚኖር እያንዳንዱን ትውልድ የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው: አት: “ትውልዳችሁ የሚመጣው ትውልድ ሁሉ ያውቃሉ ወይም ትውልዳችሁ ሁሉ ለዘላለም ያውቃል” (ፈሊጣዊ አባባሎች ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “የእስራኤል ሰዎች መቅረዞች ሁልጊዜም እንዲነዱና ብርሃን እንዲሰጡ ከወይራ ፍሬ የተጠመቀ ንጹኅ ዘይት ለመቅረዞችህ ወደ አንተ እንዲያመጡ እዘዛቸው፡፡ 3 አሮን ያለማቋረጥ ከምሽት እስከ ማለዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ውጭ በቃልኪዳኔ ድንጋጌ ፊት መቅረዙን በያህዌ ፊት ያለማቋረጥ ያብራ፡፡ ይህ በትወልዳች ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፡፡ 4 ሊቀ ካህኑ በንጹኅ ወርቅ በተሰራው የመቅረዝ መያዣ ላይ መቅረዞቹ ሁልጊዜም በያህዌ ፊት እንዲበሩ ያደርጋል፡፡ 5 መልካም ዱቄት ወስደህ አስራ ሁለት ዳቦዎች ጋግር፡፡ ለእያንዳንዱ ዳቦ የኢፍ ሁለት እስረኛ መጠን ተጠቀም፡፡ 6 ከዚያ በሁለት ረድፍ ደርድራቸው፣ በአንዱ መስመር ስድስቱን በንጹኅ ወርቅ በተሰራ ጠረጴዛ ላይ በያህዌ ፊት ደርድር፡፡ 7 በእያንዳንዱ የዳቦዎቹ ረድፍ እንደ ዳቦዎቹ ምልክት ንጹኅ ዕጣን አድርግበት፡፡ ይህ ዕጣን ለያህዌ በእሳት የሚቀርብ መስዋእት ይሆናል፡፡ 8 በእያንዳንዱ የሰንበት ዕለት ሊቀ ካህኑ የእስራኤልን ህዝብ ወክሎ የዘላለም ቃልኪዳን ምልክት አድርጎ ህብስቱን በመደበኛነት ለያህዌ ያቀርባል፡፡ 9 ይህ መስዋዕት የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሆናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየና ለያህዌ በእሳት ከሚቀርበው መስዋዕት የተወሰደ ስለሆነ ቅዱስ በሆነው ስፍራ ይብሉት፡፡” 10 እናቱ እስራኤላዊ የሆነች እና አባቱ ግብፃዊ የሆነ ልጅ በእስራኤል ህዝብ መሀል ወጣ፡፡ ይህ እስራኤላዊት ሴት ልጅ በሰፈር ውስጥ ከእስራኤላዊ ሰው ጋር ተጣላ፡፡ 11 የእስራኤላዊቷ ሴት ልጅ የያህዌን ስም ሰደበ እግዚአበሔርንም ረገመ፣ ስለዚህም ህዝቡ ወደ ሙሴ አመጡት፡፡ የእናቱ ስም ሰሎሚት ነበር፣ የደብራይ ልጅ ስትሆን ከዳን ወገን ነበረች፡፡ 12 ያህዌ ራሱ ፈቃዱን እስኪገልጽላቸው ድረስ በጥበቃ ስር አቆዩት፡፡ 13 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 14 “እግዚአብሔርን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር አውጡት የሰሙት ሁሉ እጆቻቸውን በላዩ ይጫኑ፣ ከዚያም መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገረው፡፡ 15 ለእስራኤል ሰዎች ብለህ ግለጽላቸው፣ ‹አምላኩን የተሳደበ ማንኛውም ሰው በደሉን ይሸከም፡፡ 16 ተወላጅ የሆነ እስራኤላዊም ቢሆን ወይም መጻተኛ የያህዌን ስም በስድብ ያቃለለ መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገሩትና ይገደል፡፡ ማንም ሰው የያህዌን ስም ቢሳደብ፣ ይገደል፡፡ 17 ሌላ ሰው የገደለ ይገደል፡፡ 18 የሌላውን ሰው እንስሳ የገደለ በገደለው ፈንታ ይክፈል፣ ህይወት ስለ ህይወት ነው፡፡ 19 አንድ ሰው ጎረቤቱን ቢጎዳ፣ እርሱ በጎረቤቱ ላይ ያደረገው ነገር ይደረግበት፡፡ 20 ስብራት ስለ ስብራት፣ አይን ስለ አይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፡፡ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት እንዳደረሰ፣ በእርሱም ላይ እንደዚያው ይደረግበት፡፡ 21 ማንም እንስሳ የገደለ ሰው መልሶ ይክፈል ማንም ሰው የገደለ ይገደል፡፡ 22 ለመጻተኛውም ይሁን ለተወላጅ እስራኤላዊው አንድ አይነት ህግ ይኑራችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝና፡፡” 23 ሙሴ ለእስራኤል ሰዎች ይህን ነገራቸው፣ ሰዎቹም ያህዌን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር ውጭ አመጡት፡፡ በድንጋይ ወገሩት፡፡ የእስራኤል ሰዎች የያህዌን ትዕዛዝ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ፈጸሙ፡፡
በመገናኛ ድንኳን ስላሉ ነገሮች እግዚአብሔር ለሙሴ መመሪያ ይሰጣል
“ንጹህ የወይራ ዘይት”
ለእግዚአብሔር በተቀደሰው መገናኛ ድንኳን ያለውን መብራት ያመለክታል:: ይህም ግልጽ መደረግ አለበት:: አት: “በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያለው መብራት” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በመገናኛ ድንኳን ስላሉ ነገሮች እግዚአብሔር ለሙሴ መመሪያ መስጠቱን ይቀጥላል
“የኪዳን ምሥክር” የሚለው ሀረግ ሕግጋት የተጻፉባቸው ጽላቶች ወይም ጽላቶች የተቀመጡበት ሣጥን ያመለክታል:: እነዚህም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተጀርባ ባለው እጅግ የተቀደሰ ቦታ በሆነው ክፍል ይቀመጣሉ፡፡ አት: “ከመጋጃው ውጭ በምስክሩ ጽላቶች ፊት” ወይም “ከመጋረጃው ውጭ በኪዳኑ ሣጥን ፊት” (See Synecdoche/ ክፍል ሙሉን እንደሚወክል እናም ሙሉ ክፍልን እንደሚወክል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
በግድግዳ ላይ የሚንጠልጠል ወፍራም ጨርቅ ነው:: እንደመስኮት መጋረጃዎች ስስ አይደለም::
“ከጸሐይ ጥልቀት እስከ ጸሐይ መውጣት” ወይም “ሌሊቱን ሙሉ”
ይህም እነርሱ ሆነ ቀጣይ ትውልዳቸው ይህን ሥርዓት ለዘላለም መጠበቅ አለባቸው ማለት ነው፡፡ በዘሌዋዊያን 3:17 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
በመገናኛ ድንኳን ስላሉ ነገሮች እግዚአብሔር ለሙሴ መመሪያ መስጠቱን ይቀጥላል
4.5 ሊትር ያህላል:: አት አራት ከግማሽ ሊትር (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎች ይመልከቱ)
ይህ ጠረጴዛ በቅዱስ ቦታ ነው ማለትም ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ነው
በመገናኛ ድንኳን ስላሉ ነገሮች እግዚአብሔር ለሙሴ መመሪያ መስጠቱን ይቀጥላል
ዕጣኑ በኀብስቱ ላይ ሳይሆን በየረድፉ በተቆራረሱ ጐን ሊሆን ይችላል አት ንጹህ ዕጣን በየረድፉ በተቆራረሱ አጠገብ አኑር (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ዕጣኑ ምን እንደሚወክል መገለጽ አለበት አት: “እያንዳንዱ የተቆራረሰው የኀብስቱ አካለ መስዋዕት እንደሆነ ይወክላል” ወይም “የተቆራረሱ አካላት መሥዋዕት መሆናቸውን ይወክላል”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ለእግዚአብሔር ዕጣኑን አጢሱ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው ይህ ኀብስት”
“ከሚቀርበው መሥዋዕት ሊወስዱት የማችሉት”
“ለእግዚአብሔር የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች” ወይም “ለእግዚአብሔር የሚታቃጥሉአቸው መሥዋዕቶች”
ይህ ሀረግ በመጽሐፉ አድስ ክፍል መጀመሩን ያመለክታል
ሁለቱ ሀረጐች በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: አት: “እግዚአብሔርን በመስደብ አቃለለ” ወይም “ስለእግዚአብሔር ክፉ ነገር ተናገረ” ተመሣሣይ ንጽጽር ይመልከቱ::
የሴትየዋ ስም ነው:: ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ::
የሰውየው ስም ነው:: ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ::
ሰውየው በደለኛ ሰለመሆኑ ለማሣወቅ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት:: (ምልክታዊ ድርጊቶችን ይመልከቱ)
እግዚአብሔርን በረገመው ሰው ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገር ቀጠለ
ስለኃጢአቱ የሚሠቃየው በደሉን እንደተሸከመ ተደርጐ ተነግሮአል:: አት: “ስለኃጢአቱ ይሠቀይ” ወይም “ይቀጣ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሕዝቡ ይግደለው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አንድ ሰው አንድን መጥፎ ነገር ቢያደርግ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሰውን የገደለ ሰው ግደሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እንዴት ካሣውን መክፈል እንዳለበት ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “ሕይወት ያለውን ያንኑ ዓይነት እንስሳ በመስጠት ይተካ” (ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የአንዱ ሕይወት የሌላኛውን እንደሚተካ የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው አት የአንድ ሕይወት የሌላኛውን ይተካ (ፈሊጣዊ አገላለጽ ይጠቀሙ)
አንድ ሰው አንድን መጥፎ ነገር ቢያደርግ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “የዚያው ዓይነት ጉዳት ፈጽሙበት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አነዚህ ሀረጐች አጽንዖት የሚሰጡት አንድ ሰው በሌላው ሰው ያደረሰበትን ጉዳት ተመሣሣይ ዓይነት ጉዳት በቅጣት እንዲቀበል ነው
ይህ የተሠበሩ አጥንቶችን ያመለክታል:: አት: “በተሠበረው አጥንት ፈንታ የአጥንት ስብራት” ወይም “የአንድን ሰው አጥንት ሰብሮ እንደሆነ አጥንቱ ይሰበር” ወይም “የአንድን ሰው አጥንት ሠብሮ እንደሆን ከእርሱ አጥንቶች አንዱን ይስበሩ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ዓይን እንዲጐዳ ወይም እንዲወገድ ያመለክታል:: “የአንድን ሰው አይን አጥፍቶ እንደሆነ ከአይኖቹ አንዱ ይወገድ” ወይም “የአንድን ሰው አይን አጥፍቶ እንደሆነ ከእርሱ ዓይኖች አንዱን ያጥፉ” (ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው ጥርስን ከአገጭ መትቶ ማስወጣት ማለት ነው:: አት: “የአንድን ጥርስ አውልቆ ከሆነ ከጥርሶቹ አንድ ይውለቅ” ወይም “የአንድን ሰው ጥርስ አውልቆ ከሆነ ከጥርሶቹ አንዱን ያውልቁት” (ፈሊጣዊ አባባል ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሰውን የሚገድለውን ሰው ይግደሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“ሕጉን ታዘዙ”
1 ያህዌ በሲና ተራራ ላይ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‹እኔ ወደሰጠኋችሁ ምድር ስትገቡ፣ ምድሪቱ ለያህዌ የሰንበት ዕረፍት ታክብር፡፡ 3 እርሻህን ለስድስት አመታት ታርሳለህ፣ ለስድስት አመታት የወይን ተክልህን እየገረዝህ ምርቱን ትሰበስባህ፡፡ 4 በሰባተኛው አመት ግን፣ ለምድሪቱ የከበረ የሰንበት ረፍት ይሁንላት፣ ለያህዌ ሰንበት ነው፡፡ እርሻህን አታርስም፡፡ ወይም የወይን ተክልህን አትገርዝም፡፡ 5 ሳትዘራው የበቀለውን አትጨደው፣ ያልገረዝከውን የወይን ተክል ፍሬ አትለቅመውም፡፡ ይህ ለምድሪቱ የከበረ የእረፍት አመት ነው፡፡ 6 ያልሰራህበት ምድር በሰባተኛው ዓመት ያፈራችው ሁሉ ለአንተ ምግብ ይሆናል፡፡ አንተ፣ ወንድና ሴት ባሮችህ፣ ለቅጥረኛ አገልጋዮችህ እና ከአንተ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞች ምግብ ይሁን፡፡ 7 ምድሪቱ ያፈራችውን ሁሉ የቤት እንስሳትህና የዱር እንስሳት ይመገቡት፡፡ 8 ሰባት የሰንበት አመታትን ቁጠር፣ ይህም ማለት፣ ሰባት ጊዜ ሰባት አመታት ነው፣ ስለዚሀ ሰባት የሰንበት አመታት ይሆናሉ፣ ድምሩ አርባ ዘጠኝ አመታት ነው፡፡ 9 በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን ከፍ ያለ የመለከት ድምጽ በሁሉም ስፍራ ንፉ፡፡ በማስተሰርያ ቀን በምድራችሁ ላይ ሁሉ መለከት ንፉ፡፡ 10 አምሳኛውን አመት ለያህዌ ለዩና በምድሪቱ ላይ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ሁሉ ነጻነትን አውጁ፡፡ ይህ ለእናንተ ንብረትና ባሮች ወደየቤተሰቦቻቸው የሚመለሱበት ኢዩቤልዩ ይሆንላችኋል፡፡ 11 አምሳኛው አመት ለእናንተ ኢዮቤልዮ ይሆናል፡፡ አትተክሉም ወይም አዝመራ አትሰበስቡም፡፡ ሳትዘሩ የበቀለውን ብሉ፣ ሳትገርዙት ወይናችሁ ያፈራውን ፍሬ ሰብስቡ፡፡ 12 ኢዮቤልዩ ነውና፣ ለእናንተ ቅዱስ ይሆናል፡፡ በሜዳ ሳትዘሩት የበቀለውን ምርት ብሉ፡፡ 13 በዚህ የኢዮቤልዩ አመት የእያንዳንዱን ሰው ንብረት መልሱለት፡፡ 14 ለጎረቤትህ ማናቸውንም መሬት ሸጠህለት ቢሆን ወይም ከጎረቤትህ ማንኛውንም መሬት ገዝተህ ቢሆን አንዱ ሌላውን አያታል ወይም እርስ በእርሱ ያልተገባ ነገር አታድርጉ። 15 ከጎረቤትህ መሬት ብትገዛ፣ እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ድረስ ያሉትን አመታት እና ሊሰበሰብ የሚችለውን ሰብል ከግምት አስገባ፡፡ መሬቱን የሚሸጠው ጎረቤትህም እነዚህን ነገሮች ከግምት ያስገባል፡፡ 16 እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ብዙ አመታት የሚቀር ከሆነ ይህ የመሬቱን ዋጋ ከፍ ያደርገዋል፣ እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ጥቂት አመታት የሚቀር ከሆነ ይህ የመሬቱን ዋጋ ዝቅ ያደርገዋል፣ ምክንያቱም ለአዲሱ የመሬቱ ባለቤት መሬቱ የሚሰጠው አዝመራ መጠን ለሚቀጥለው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ከቀረው አመታት ቁጥር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ 17 አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ ወይም አንዳች ሌላችሁን አታሳስቱ፤ ይልቁንም አምላካችን አክብሩ፣ እኔ አምላካች ያህዌ ነኝ፡፡ 18 ስለዚህ ትዕዛዛቴን ጠብቁ፣ ህግጋቴን ፈጽሙ እናም አድርጓቸው፡፡ ይህን ካደረጋችሁ በምድሪቱ ላይ በሰላም ትቀመጣላችሁ፡፡ 19 ምድሪቱ ምርቷን ትሰጣለች፣ እናንተም ትጠግባላችሁ በዚያም በሰላም ትኖራላችሁ፡፡ 20 እንዲህ ልትሉ ትችላላችሁ “በሰባተኛው አመት ምን እንበላለን አንዘራም፣ ምርታችንንም አንሰበስብምና፡፡” 21 በስድስተኛው አመት በረከቴ እንዲሆንላችሁ በእናንተ ላይ አዛለሁ፣ ምድሪቱ ለሶስት አመታት የሚሆን ምርት ትሰጣለች፡፡ 22 በስምንተኛው አመት ትተክላላችሁ፣ በቀደሙት አመታት ካመረታችሁትና ከሰበሰባችሁት ምግብ መብላት ትቀጥላላችሁ፡፡ 23 መሬት ለአዲስ ጊዜያዊ ባለቤቶች አይሸጥ፣ ምክንያቱም መሬቷ የእኔ ናት፡፡ እናንተ ሁላችሁም በምድሬ ላይ እንግዶችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች ናችሁ፡፡ 24 የያዛችሁትን ምድር ሁሉ የመቤዠት መብት እንዳላችሁ ማስተዋል አለባችሁ፤ በገዛችሁት ቤተሰብ መሬቱ ተመልሶ እንዲገዛ መፍቀድ አለባችሁ፡፡ 25 እስራኤላዊ ወገናችሁ ደሃ ቢሆንና በዚህም ምክንያት ከንብረቱ ቢሸጥ፣ የቅርብ ዘመዱ ለአንተ የሸጠልህን ንብረት መልሶ ይግዛ፡፡ 26 ሰውዬው ንብረቱን የሚቤዥለት ምንም ዘመድ ባይኖረው፣ ነገር ግን ሀብት ቢያፈራና ንብረቱን መልሶ መቤዠት ቢችል፣ 27 መሬቱ ከተሸጠበት ጊዜ አንስቶ ያሉትን አመታት ያሰላና ለሸጠለት ሰው ቀሪ ሂሳቡን ይክፈል፡፡ ከዚያ ወደ ራሱ ንብረት ይመለስ፡፡ 28 ነገር ግን መሬቱን ለራሱ ማስመለስ ባይችል፣ የሸጠው መሬት እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ በገዛው ሰው ባለቤትነት ስር ይቆያል፡፡ በኢዮቤልዩ አመት፣ መሬቱ ለሸጠው ሰው ይመለስለታል፣ ከመሰረቱ ባለቤት የነበረው ወደ ንብረቱ ይመለሳል፡፡ 29 አንድ ሰው በተቀጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ቤቱን ቢሸጥ፣ በተሸጠበት በአመት ጊዜ ውስጥ መልሶ ሊገዛው ይችላል፡፡ 30 ለአንድ ሙሉ አመት ውስጥ ካልተቤዠ፣ በተቀጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቤት፣ የገዛው ሰው ትውልድ የልጅ ልጅ ቋሚ ንብረት ይሆናል፡፡ ያ ቤት በኢዮቤልዩ ተመላሽ አይሆንም፡፡ 31 ነገር ግን በዙሪያቸው ቅጥር የሌላቸው መንደሮች ቤቶች ከአገሩ የእርሻ መሬት ጋር የሚታዩ ንብረቶች ይሆናሉ፡፡ ተመልሰው ሊዋጁ ይችላሉ፣ በኢዮቤልዩ ተመላሽ ይሆናሉ፡፡ 32 ሆኖም፣ የሌዋውያን ንብረት የሆኑ ቤቶች በማንኛውም ጊዜ ሊዋጁ ይችላሉ፡፡ 33 ከሌዋዊያን አንዱ የሸጠውን ቤት መልሶ ባይቤዥ፣ በከተማ ውስጥ የሚኘው የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ተመላሽ ይሆናል፣ በከተማ የሚገኝ የሌዋዊ ቤቶች በእስራኤል ሰዎች መሀል የእነርሱ ንብረት ነው፡፡ 34 በከተማዎቻቸው ዙሪያ የሚገኙ እርሻዎች ግን አይሸጡም ምክንያቱም እነዚህ የሌዋዊያን ቋሚ ንብረት ናቸው፡፡ 35 የአገራቸው ሰው ወገናችሁ ደሃ ቢሆን፣ ስለዚህም ራሱን መቻል ቢያቅተው፣ መጻተኛውን እንደምትረዱ እርዱት ወይም በመሀከላችሁ የሚኖርን ባዕድ እንደምትረዱ ዕርዱት፡፡ 36 ወለድ አታስከፍሉት ወይም በማናቸውም መንገድ ከእርሱ ትርፍ ለማግኘት አትሞክሩ፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን አክብሩ በመሆኑም ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር አብሮ መኖር ይችላል፡፡ 37 በወለድ ገንዘብ አታበድሩት፣ ወለድም አታስከፍሉት፣ ትርፍ ለማግኘት ምግባችሁን አትሽጡለት፡፡ 38 የከነዓንን ምድር እሰጣችሁና አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ 39 የአገርህ ሰው ወገንህ ደሃ ቢሆንና ራሱን ለአንተ ቢሸጥ፣ እንደ ባሪያ አታሰራው፡፡ 40 እንደ ተቀጣሪ አገልጋይ አስተናግደው፡፡ ከአንተ ጋር በጊዜያዊነት እንደሚኖር ሰው ይሁን፡፡ እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ በአንተ ዘንድ ያገለግል፡፡ 41 ከዚያ ከአንተ ዘንድ ይሄዳል፣ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉ ልጆቹ፣ ወደ ራሱ ቤተሰቦችና ወደ አባቱ ይዞታ ይመለሳሉ፡፡ 42 እነርሱ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ናቸውና፡፤ እንደ ባሪያዎች አይሸጡም፡፡ 43 በጭካኔ ልትገዛቸው አይገባም፣ ነገር ግን አምላክህን አክብር፡፡ 44 በዙሪያህ ከሚኖሩ ህዝቦች ወንድና ሴት ባሪያዎችን ከእነርሱ መሀል መግዛት ትችላለህ፡፡ 45 በመሀልህ ከሚኖሩ መጻተኞችም ባሪያዎችን መግዛት ትችላለህ፣ ይህም ማለት፣ ከአንተ ጋር ካሉ ቤተሰቦቻቸው፣ በምድርህ ከተወለዱ ልጆች ባሪያዎችን መግዛት ትችላለህ፡፡ እነርሱ የአንተ ሀብት ይሆናሉ፡፡ 46 እንዲህ ያሉትን ባሪያዎች ንብረት አድርገው እንዳይዟቸው ከአንተ በኋላ ለልጆችህ ውርስ አድርገህ መስጠት ትችላለህ፡፡ ከእነርሱ ሁልጊዜም ባሪያዎችህን መግዛት ትችላለህ ነገር ግን ከእስራኤላዊያን መሀል በወንድሞችህ ላይ በጭካኔ መግዛት የለብህም፡፡ 47 መጻተኛው ወይም ከአንተ ጋር በጊዜያዊነት ከሚኖረው እንግዳ መሃል አንዱ ባለጸጋ ቢሆንና ከእስራኤላዊ ወገንህ መሃል አንዱ ደሃ ቢሆን፣ ለራሱም ለዚያ ባዕድ ቢሸጥ፣ ወይም ከባዕዳን ቤተሰብ መሃል ለአንዱ ቢሸት፣ 48 እስራኤላዊ ወገንህ ከተገዛ በኋላ ተመልሶ ይገዛ፡፡ ከቤተሰቡ መሃል አንዱ ይቤዠው፡፡ 49 የሚቤዠው አጎቱ፣ የአጎቱ ልጅ፣ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ከቤተሰቡ ውስጥ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ ሊቤዠው ይችላል፡፡ ወይም፣ እርሱ ራሱ ባለፀጋ ቢሆን፣ ራሱን መቤዠት ይችላል፡፡ 50 ከገዛው ሰው ጋር ይደራደር፣ ለገዛው ሰው ራሱን ከሸጠበት አመት ጀምረው እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ ይቁጠሩ፡፡ የመቤዣው ዋጋ ለገዛው ሰው መስራቱን መቀጠል በሚኖርበት አመታት ቁጥር ለተቀጣሪ አገልጋይ በሚከፍለው ክፍያ ይሰላል፡፡ 51 እስከ ኢዮቤልዩ ለመድረስ ብዙ አመታት የሚኖር ከሆነ፣ ለቤዣው መልሶ የሚከፍለው የገንዘብ መጠን ከእነዚያ ቀሪ አመታት ጋር የተመጣጠነ ይሁን፡፡ 52 ለኢዮቤልዩ አመት የቀሩት አመታት ጥቂት ከሆኑ፣ ከገዛው ሰው ጋር ለኢዮቤልዩ በቀሩት አመታት ልክ ይደራደር፣ ለመቤዣው በቀሩት አመታት ውስጥ ይክፈለው፡፡ 53 በየዓመቱ እንደ ቅጥር ሰው ይኑር፡፡ በግፍ አለመስተናገዱን ማረጋገጥ ይገባሃል፡፡ 54 በእነዚህ መንገዶች ካልተዋጀ፣ እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ እርሱና ከእርሱ ጋር ልጆቹም አብረው ያገልግሉ፡፡ 55 እስራኤላውያን የእኔ አገልጋዮቼ ናቸው፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
ምድር በሰንበት ማረፍን እንደሚታዘዝ ሰው ተደርጋ ተገልጻለች ሰዎች በየስንበቱ እንደሚያርፉ ሁሉ በሰባተኛው ዓመት ምድሪቱ ን ባለማረስ ሰዎች እግዚአብሔርን ያከብራሉ:: አት: “ምድሪቱ በሰባተኛው ቀን ለእግዚአብሔር እንዲትርፍ የሰንበትን ሕግ ጠብቁ” ወይም “በሰባተኛው ዓመት ምድሪቱን ባለማረስ የእግዚአብሔርን ሰንበት ጠበቁ” (ሰውኛ አገላለጽና ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ወይንን መገረዝ ጥሩ ፍሬ እንዲያፈራ የወይኑን ተክልና ቅርንጫፎቹን መቁረጥ ማለት ነው ፡፡
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “የምድሪቱን የዕረፍት ሰንበት አክብሩ” ወይም “ምድሪቱን በሰባተኛው ዓመት ባለማረስ የሰንበትን ሕግ ጠብቁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
25: 5-6 እንደሚናገረው የእርሻው ባለቤት እንደመጀመሪያዎቹ ስድስት ዓመታት ሠራተኞችንና ምርቱን መቆጣጠር እግዚአብሔር አይፈቅድም ነገር ግን ግለሰቦች ወደ እርሻዎች በመውጣት ያገኙትን ፍሬ እንዲለቅሙና እንዲበሉ ይፈቅዳል፡፡
ለስድስት ዓመታት እንደሚየደርጉት ማንም ያልተንከባከውን ወይም ያልገረዘውን ወይን ማለት ነው ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ያልገረዙአቸው ወይኖቻችሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ባልተሠራ መሬት የሚበቅለው ማንኛውም
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ያላረሳችሁት ማሣዎቻችሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
በምድሪቱ የሚበቅለው ማንኛውም
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ መናገር ይቀጥላል
“ሰባት ምድብ ሰባት ዓመታት”
“49 ዓመታት” (ቁጥሮች ይመልከቱ)
በዕብራይስጥ የቀን መቁጠሪያ ሰባተኛ ወር ነው:: በምዕራባዊያን አቆጣጠር አሥሪኛው ቀን መስከረም ወር መጨረሻ አካባቢ ነው:: (የዕብራዊያን ወራትና መደበኛ ቁጥሮች ይመልከቱ)
የእስራኤልን ሕዝብ ኃጢአት ሁሉ እግዚአብሔር ይቅር እንዲል በየዓመቱ በዚህ ቀን ሊቀካህኑ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርባል በዘሌዋዊያን 23:27 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ይህ መደበኛ ቁጥር ነው፡፡ አት፡ 5ዐ ዓመት (ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ኢዩቤልዩ መሬትን ለርስቱ ባለቤት የሚመልሱበትና ለባሪያዎች ነጻነትን የሚያወጁበት ዓመት ነው አት: “ምርኮ የመመለስ ዓመት” ወይም “መሬት የመመለስና ለባሪያዎች የነጻነት ዓመት”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ንብረትንና ባሪያዎችን መልሱ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“የምርኮ ዓመት” ወይም “መሬትን የመመለስ ዓመት” ለማን መሬትን እንደሚመልሱ ግልጽ ተደረግ አለበት:: አት: “ለእኔ መሬትን የሚትመልሱበት ዓመት” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የእርሻው ባለቤት እንደመጀመሪያዎቹ ስድስት ዓመታት ሠራተኞችንና ምርቱን መቆጣጠር እግዚአብሔር አልፈቀደም:: ነገር ግን ግለሰቦች ወደ እርሻዎች በመውጣት ያገኙትን ፍሬ እንዲለቅሙና እንዲበሉ ፈቅዶአል፡፡
“በዚህ የመመለስ ዓመት” ወይም “በዚህ የመሬት መመለስና የባሪያ ነጻ መውጣት ዓመት”
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ በናገሩን ቀጠለ
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሊትሰበሰቡ ትችላላችሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
x
እነዚህ ሀረጐች ሁሉ በመሠረቱ ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው:: እግዚአብሔር የተናገረውን ማንኛውንም ነገር ሕዝብ እንዲታዘዝ ትኩረት ይሰጣሉ (ተመሣሣይ ተጓዳኝ ንጽጽር ይመለከቱ)
ሆዳችሁ እስኪጠግብ በቂ ምግብ ትበላላችሁ:: አት: “እስኪትጠግቡ ትበላላችሁ” ወይም “ብዙ ምግብ ትበላላችሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ እናንተ የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል (ሁለተኛ ሰው አገላለጽ ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እንደሚታዘዝለት ሰው አድርጐ ስለ በረከቱ ይናገራል፡፡ አት፡ “በረከተን እልክላችኋለሁ ወይም እባርካችኋለሁ” (ሰውኛ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ከሰበሰባችሁት ምግብ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር መናገሩን ይቀጥላል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “መሬትን ለዘለቄታው ለአንድ ሰው አትሽጡ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
መዋጀት የሚለው ስም “ሊዋጅ” ወይም “እንደገና ሊገዛ” በሚሉ ግሶች ሊገለጽ ይችላል:: አት: “የመሬቱ ባለቤት መሬቱን በፈለገበት ጊዜ መዋጀት እንደሚችል ይታወቅ” (ረቂቅ ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “የቅርብ ዘመዱ ወገኑ የሸጠውን እንዲዋጅለት አድርጉ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “መሬቱን ከሸጠ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት: “ገዢው የገዛውን ገንዘብ መጠን ይመልስልት” (ግምታም እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
የመመለስ ዓመት መሬት የሚመለስበት ዓመት በዘሌዋዊያን 25: 1ዐ ይህን እንዴት እንተረጐሙ ይመልከቱ::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “የገዛ ሰው መሬቱን ይመልሳል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ወደ ራሱ መሬት ይመለሳል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እርሱ ከሸጠ በኋላ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“መዋጀት” የሚለው ስም “ሊዋጅ” ወይም “እንደገና ሊገዛ” በሚሉ ግሶች ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ሊዋጅ መብት አለው” (ረቂቅ ስሞችን ስለመተርጐም ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እርሱ ወይም ቤተሰቡ/ወገኑ ቤቱን ካልዋጀው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “የገዛው ሰው ቤቱን አይመልስለትም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“የመመለስ ዓመት” ወይም “መሬት የሚመለስበትና ባሪያዎች ነጻ የሚወጡበት ዓመት”
አንዳንድ መንደሮች በዙሪያቸው ቅጥር የላቸውም
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እነዚያን ቤቶች መዋጀት ይችላሉ እናም የገዙአቸውም ይመልሱ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“የመመለስ ዓመት” ወይም “መሬት የሚመለስበትና ባሪያዎች ነጻ የሚወጡበት ዓመት”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሌዋዊያን በከተሞቻቸው ያሉ ቤቶቻቸውን” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ሌዋዊያን እነዚያን ምን ጊዜም ሊዋጁ ይችላሉ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “በከተማው ውስጥ ያለውን ቤት የገዛ ይመልሳል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ ምን ማድረግ አንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
ካበደርከው ተጨማሪ እንዲከፍል አታድርግ
ባለቤቱ እስራኤላዊውን ባሪያ ሳይሆን እንደ ተከበረ ሰው ይቁጠረው ማለት ነው::
“የመመለስ ዓመት” ወይም “መሬት የሚመለስበትና ባሪያዎች ነጻ የሚወጡበት ዓመት”
ለሕዝቡ ምን መናገር እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
የአገረው ሰዎች አገልጋዮቼ ናቸው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እንደ ባሪያዎች አትሽጡአቸው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“ከአሕዛብ መካከል ባሪያዎችን ግዙ”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “መጻተኛ የእስራኤላዊውን ወገን ከገዛ በኋላ ከእስራኤላዊ ቤተሰብ አንድ ሰው ይህን ሰው ይዋጀው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እስራኤላዊ ባሪያ ሊሆን የሚችለው እስከ ኢዩቤልዩ ዓመት ብቻ ነው እነዚህ መመሪያዎች ቢሆኑም ከኢዩቤልዩ ዓመት በፊት ነጻነቱን ሊዋጅ ቢፈልግ ይችላል::
“የመመለስ ዓመት” ወይም “መሬት የሚመለስበትና ባሪያዎች ነጻ የሚወጡበት ዓመት”
ይተመናል የሚለው ግሥ በተሻጋሪ ግሥ ሊገለጽ ይችላል አት፤ “የመዋጀቱን ወጋ ይተምናሉ ” ወይም እስራኤላዊውን ነጻ ለማውጣት ለመጻተኛው ምን ያህል መከፈል እንዳለበት ይተምናሉ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እስራኤላዊው ነጻነቱን ከተዋጀ እስራኤላዊው መሥራት የሚገባው ነገርግን ያልሠራውን ለማሥሠራት መጻተኛው አገልጋይ መቅጠር ይኖርበታል:: “ተከፈለ” እናም “ተቀጠረ” የሚሉ ግሶች በተሻጋሪ ግሥ መልክ ሊገለጹ ይችላሉ:: አት፤ “ለአንድ ቅጥር ሠራተኛ በሚከፈለው ተመን መሠረት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“እስራኤላዊው መሥራት የሚገባቸው ነገርግን ያማይሠራባቸው እስከ ቀጣይ ኢዩቤልዩ ያሉ ዓመታት ቁጥር”
እስራኤላዊው በሪያ ይክፈል
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “እንደባሪያ አድርጐ የገዛው መጻተኛ ይንከባከበው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: አት፤ “ማንም አይጨክንበት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: እናም የሚዋጀው ሰው ግልጽ ሊደረግ ይችላል:: አት፤ “ባሪያ አድርጐ ከገዛው ማንም በእነዚህ መንገዶች የማይዋጀው ከሆነ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር እና ግምታዊ እውቀትና ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
በዚህ መንገድ
እስራኤላዊው ባሪያና ልጆቹ እስከ ኢዩቤልዩ ዓመት መጻተኛውን ያገልግሉ እናም ከዚያ በኋላ መጻተኛው እስራኤላዊውንና ልጀቹን ነጻ ይልቀቅ
እስራኤላዊያን አገልጋዮቼ ናቸው
1 “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፤ ጣኦታትን አታብጁ፣ የተቀረጸ ምስልንም አታቁሙ፣ ወይም ለአምልኮ የድንጋይ አምዶችን አታቁሙ፣ እንደዚሁም ልትሰግዱላቸው ማናቸውንም የቀረፀ የድንጋይ ምስል በምድራችሁ አታድርጉ፡፡ 2 ሰንበቴን ጠብቁ የተቀደሰውን ስፍራዬን አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 3 በህጌ ብትኖሩና ትዕዛዛቴን ብትጠብቁ ብትታዘዟቸውም፣ 4 ዝናብን በወቅቱ እሰጣችኋለሁ፤ ምድር ምርቷን ትሰጣችኋለች፣ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጧችኋል፡፡ 5 የወቃችሁት እስከ ወይን አዝመራችሁ ድረስ ይቆያል፣ የወይን ፍሬ አዝመራችሁም እስከምትዘሩበት ወቅት ድረስ ይቆያል፡፡ እንጀራችሁን በምድሪቱ ቤታችን በሰራችሁበት ጠግባችሁ ትበላላችሁ በእረፍት ትኖራላችሁ፡፡ 6 በምድሪቱ ሰላምን እሰጣለሁ፣ ምንም ነገር ሳያስፈራችሁ ተዘልላችሁ ትቀመጣላችሁ፡፡ ከምድሪቱ አደገኛ እንስሳትን አስወጣለሁ፣ በምድራች ሰይፍ አያልፍም፡፡ 7 ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፣ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡ 8 ከእናንተ አምስታችሁ መቶውን ታሳድዳላችሁ፣ ከእናንተ መቶው አስር ሺኅ ያሳድዳል፤ ጠላቶቻች በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡ 9 ወደ እናንተ በሞገስ እመለከታለሁ፣ ፍሬያማም አደርጋችኋለሁ፣ አበዛችሁማለሁ፤ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ፡፡ 10 ለረጅም ጊዜ የተከማቸ እህል ትበላላችሁ፡፡ ለአዲሱ ምርታችሁ ስፍራ ስለሚያስፈልጋችሁ የተከማቸውን እህል ታወጣላችሁ፡፡ 11 ማደሪያዬን በመካከላችሁ አደርጋለሁ፣ እኔም እናንተን አልጣላችሁም፡፡ 12 በመካከላችሁ እሆናለሁ አምላካችሁም እሆናለሁ፣ እናንተም የእኔ ህዝብ ትሆናላችሁ፡፡ 13 ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፣ ስለዚህም የእነርሱ ባሮች አትሆኑም፡፡ የቀንበራችሁን ብረት ሰብሬያሁ፣ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌያለሁ፡፡ 14 ነገር ግን እኔን ባትሰሙኝ፣ እነዚህን ትዕዛዛቴን ሁሉ ባትጠብቁ፣ 15 ትዕዛዛቴን ብትተዉና ህግጋቴን ብትጠሉ፣ እናም ትዕዛዞቼን ሁሉ ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ነገር ግን ቃልኪዳኔን ብታፈርሱ 16 እነዚህን ነገሮች ብታደርጉ፣ እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፡ ፍርሃትን እሰድባችኋለሁ፣ ዐይኖችንና ሕይወታችሁን የሚያጠፋ በሽታና ትሳት አደርስባችኋለሁ፡፡ በከንቱ ትዘራላችሁ፣ ምክንያቱም ፍሬያቸውን ጠላቶቻችሁ ይበሉታል፡፡ 17 ፊቴን በጠላትነት ወደ እናንተ እመልሳለሁ፣ ከጠላቶቻችሁ ሀይል በታች ትወድቃላችሁ፡፡ የሚጠሏችሁ ሰዎች ይገዙዋችኋል፣ ማንም ሳያሳድዳችሁ እንኳን ትሸሻላችሁ፡፡ 18 ትዕዛዛቴን ባትሰሙ፣ ከዚህ በኋላ ስለ ሀጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡ 19 የትእቢታችሁን ኃይል እሰብራለሁ፡፡ ሰማይን በላያችሁ እንደ ብረት ምድራችሁንም እንደ ናስ አደርጋለሁ፡፡ 20 ብርታታችሁ ለአንዳች ነገር አይጠቅምም፣ ምክንያቱም ምድራችሁ አዝመራዋን አትሰጥም፣ በምድራችሁ ዛፎቻችሁ ፍሬያቸውን አይሰጡም፡፡ 21 በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ ብትመላለሱና ከኃጢአታችሁ በላይ እኔን ባትሰሙኝ፣ በእናንተ ላይ ሰባት ዕጥፍ ድንጋጤ አመጣለሁ፡፡ 22 ልጆቻችን የሚነጥቁ፣ ከብቶቻችሁን የሚያጠፉ፣ እናንተን በቁጥር ጥቂት የሚያደርጉ አደገኛ አውሬዎችን እሰድባችኋሉሁ፡፡ ስለዚህም ጎዳናዎቻችሁ በረሃ ይሆናሉ፡፡ 23 በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ትምህርቶቼን ባትሰሙ ነገር ግን በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ መመላለሳችሁን ብትቀጥሉ፣ 24 እኔም በእናንተ ላይ ጠላት እሆናለሁ፡፡ እኔ ራሴ በሀጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡ 25 ቃልኪዳን በማፍረሳችሁ በእናንተ ላይ የበቀል ሰይፍ አመጣለሁ፡፡ በከተሞቻችሁ ውስጥ በአንድነት ትሰበሰባላችሁ፣ በዚያም በማህላችሁ በሽታን እልካለሁ፣ እናንተም በጠላቶቻችሁ ሀይል ትሸነፋላችሁ፡፡ 26 የምግብ አቅርቦታችሁን ስቆርጥ፣ አስር ሴቶች በአንድ ምድጃ እንጀራችሁን ይጋግራሉ፣ እንጀራችሁንም በሚዛን ያካፍሏችኋል፡፡ ትበላላችሁ ነገር ግን አትጠግቡም፡፡ 27 እነዚህ ነገሮች ሁሉ ሆነው ባትሰሙት፣ ነገር ግን በእኔ ላይ በጠላትነት መመላሳችሁን ብትቀጥሉ፣ 28 እኔ በቁጣ እመጣባችኋለሁ፣ በኃጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡ 29 ወንድ ልጆቻችሁን ስጋና የሴት ልጆቻችሁን ስጋ ትበላላችሁ፡፡ 30 የአምልኮ ሥፍራችሁን አጠፋለሁ፣ የእጣን መሰዊያዎቻችሁን እቆርጣለሁ፣ በድኖቻችሁን በድን በሆኑ በጣኦቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፣ ደግሞም እኔ ራሴ እጸየፋችኋለሁ፡፡ 31 ከተሞቻችሁን ፍርስራሽ አደርጋለሁ የተቀደሱ ቦታዎቻችሁን አጠፋለሁ፡፡ በመስዋዕቶቻችሁ መዓዛ ደስ አልሰንም፡፡ 32 ምድሪቱን አጠፋለሁ፡፡ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁ በጥፋቱ ይደነግጣሉ፡፡ 33 በአገራት መሃል እበትናችኋለሁ፣ ሰይፌን መዝዤ አሳድዳችኋለሁ፡፡ ምድራችሁ ባድማ ትሆናለች፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ፡፡ 34 ከዚያም ምድሪቱ ባድማ ሆኖ እስከቆየች ድረስና እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር እስከቆያችሁ ድረስ የሰንበት ዕረፍቷን ታገኛለች፡፡ በነዚያ ጊዜያት፣ ምድሪቱ ታርፋለች ሰንበቶቿንም ታገኛለች፡፡ 35 ፍርስራሽ ሆና እስከቆየች ድረስስ እረፍት ይሆንላታል፣ እናንተ በውስጧ ስትኖሩ በሰንበቶቻችሁ ያላገኘችውን ዕረፍት ታገኛች፡፡ 36 እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር በቀራችሁት ላይ በልቦቻችሁ ውስጥ ፍርሃት እሰዳለሁ፣ ስለዚህም የቅጠል ኮሰሽታ እንኳን ያስደነግጣችኋል፣ ከሰይፍ እንደሚሸሽ ትሆናላች፡፡ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትወድቃላች፡፡ 37 ማንም ባያሳድዳችሁም እንኳን ከሰይፍ እንደሚሸሽ ሰው አንዳችሁ በሌላችሁ ላይ ትደነቃቀፋላችሁ፡፡ በጠላቶቻችሁ ፊት ለመቆም ምንም ሀይል አይኖራችሁም፡፡ 38 ከአገራት መሀል ተለይታችሁ ትጠፋላችሁ፣ የጠላቶቻችሁ ምድር ራሱ በፍርሃት ይሞላችኋል፡፡ 39 ከእናንተ መሃል የቀሩት በዚያ በጠላቶቻችሁ ምድር በሀጢአቶቻቸው ይጠፋሉ፣ እንዲሁም በአባቶቻቸው ሀጢአቶች ምክንያት ይጠፋሉ፡፡ 40 ሆኖም የእነርሱንና የአባቶቻቸውን ሀጢአቶች ቢናዘዙ፣ ለእኔ ታማኝ ካልሆኑበት ክህደታቸው ቢመለሱ፣ ከእኔ ጋር ተላት ከሆኑበት አካሄዳቸው ቢመለሱ 41 እኔ በእነርሱ ላይ እንድነሳ ካደረገንና ለጠላቶቸው ምድር አሳልፌ እንድሰጣቸው ካደረገ አካሄዳቸው ቢመለሱ ያልተገረዙ ልቦቻቸው ዝቅ ቢሉ፣ እናም በሀጢአቶቻቸው የደረሰባቸውን ቅጣታቸውን ቢቀበሉ፣ 42 ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባለሁ፤ እንዲሁም፣ ምድሪቱን አስባለሁ፡፡ 43 ምድሪቱ ለቀዋት ስለሄዱ ባዶ ትቀራለች፣ ስለዚህ ካለእነርሱ በተተወችበት ጊዜ በሰንበቶቿ ታርፋለች፡፡ እነርሱ በሀጢአታቸው ቅጣታቸውን ይቀበላሉ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው ስርአቴን ትተዋል ህግጋቴንም ጠልተዋል፡፡ 44 ሆኖም ከዚህ ሁሉ ባሻገር፣ በጠላቶቸው ምድር ውስጥ ሲሆኑ፣ እኔ አልተዋቸውም ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ አልጠላቸውም፣ ደግሞም ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አልረሳም፣ እኔ አምላካቸው ነኝ፡፡ 45 ነገር ግን ስለ እነርሱ ስል አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባሁ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡” 46 በሙሴ በኩል ያህዌ በሲና ተራራ ላይ በራሱና በእስራኤል ህዝብ መሃል ያደረጋቸው ትዕዛዛት፣ ደንቦችና ህጎች እነዚህ ናቸው፡፡
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
የሰንቤታቴን ሕጐች ታዘዙ
ይህም አንድ አባባል በሶስት መንገዶች መግለጽ ነው እግዚአብሔር እንዲያደርጉ ያዘዙአቸውን ማንኛውም ነገር ሕዝቡ እንዲታዘዝ ትኩረት የሚሰጡ ናቸው:: አት ትዕዛዜንና ሥርዓተን በጥንቃቄ ብትጠብቁ (ተመሣሣይ ተጓዳኝ ንጽጽር ይመልከቱ)
እንደሥርዓቱ መኖር በሥርዓቱ እንደመሄድ ተደርጐ ተነግሮአል አት በሥርዓቴ መሠረት ቢትመላለሱ ወይም በሥርዓቴ መሠረት ቢትኖሩ (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ምግብ የተባለው ሁሉን ምግብ ዓይነት ነው እስክትጠግቡ ሆዳችሁ እስክጠግብ ማለት ነው:: አት: እስክትጠግቡ ትበላላችሁ ወይም ብዙ ምግብ ትበላላችሁ (ፈሊጣዊ አነጋገርና Synecdoche/ ክፍል ሙሉውን ሙሉው ክፍልን እንደሚወክል የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
በምድሪቱ ላይ ሰላም እንዲሆን ምክንያት አደርጋለሁ
እዚህ “ሰይፍ” የሚለው ቃል “የጠላት ሠራዊት” ወይም “የጠላት ጥቃት” ይወክላል:: አት “ምንም ሠራዊት አያጠቃህም” (See Metonymy/ ተዛማጅ ባሕሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላት ወይም አባባሎች ይመልከቱ)
“መልካምነቴን አሳያለሁ” ወይም “እባርክሃለሁ”
እነዚህ ሁለቱ ሀረጐች በትውልድ እንድበዙና ትልቅ ሕዝብ እንድሆኑ እግዚአብሔር እንደሚያደርጋቸው ያመለክታሉ (see doublet/ተመሣሣይ ትርጉም ያላቸውን ድርብ ቃላት ይመልከቱ)
ዛፎች ብዙ ፍሬ እንደሚያፈሩ ብዙ ልጆች እንደሚኖራቸው እግዚአብሔር ይናገራል:: አት: ብዙ ልጆች እንድኖሩአችሁ አደርጋለሁ (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ለረጅም ጊዜ የምትመገቡት የተሰበሰበ ብዙ እህል ይኖራችኋል” ወይም “ለመሰብሰብና ለረጅም ጊዜ ለመብላት ብዙ እህል ይኖራችኋል”
መኖሪያዬን በአናንተ መካከል አደርጋለሁ
እቀበላችኋለሁ
በእነርሱ መካከል መመላለስ ከእነርሱ ጋር መኖርን ይወክላል አት ከእናንተ ጋር እኖራለሁ:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ባርነታቸውን ከባድ ሥራን ለመሥራት በእንስሳት እንደሚደረግባቸው ቀንበር አድርጐ ይገልጻል:: ቀንበርን መስበር እነርሱን ነጻ ማውጣቱን ያመለክታል:: አት: ከባድ ሥራ እንድትሠሩ ከተደረጋችሁበት ምድር ነጻ አውጥቸአችኋለሁ:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ ሕጉን ባይጠብቅ ምን እንደሚደርስበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
እነዚህ ነገሮች የሚለው ሀረግ በዘሌዋዊያን 26: 14-15 የተዘረዘሩ ነገሮችን ያመለክታል
እዚህ ድንጋጤ እነርሱን ሊያስደነግጣቸው የሚችሉ ነገሮችን ያመለክታል:: አት: “የሚያስደነግጥ በሽታ አመጣባችኋለሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ቀስ በቀስ ሕይወታችሁን እወስዳለሁ ወይም ቀሰ በቀስ እንዲትሞቱ አደርጋለሁ:: ይህንን የሚያደርጉት ትኩሳትና በሽታዎች ናቸው፡፡
በከንቱ ነው የሚለው ሀረግ ከሥራቸው ምንም አያገኙም ማለት ነው፡፡ አት፡ “ዘርን በከንቱ ትዘራላችሁ” ወይም “ዘርን ትዘራላችሁ ነገርግን ከዚያ ምንም አታገኙም” (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር እግዚአብሔር ለመጨከን እንደወሰነ ይናገራል:: አት: እናንተን ለመጥላት በሀሳቤ ወስኛለሁ:: (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ጠላቶቻችሁ ድል ያደርጓችኋል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ ሰባት እጥፍ በእርግጥ በቁጥሩ ልክ ማለት አይደለም እግዚአብሔር የቅጣቱን መጠን በፍጹም እንደሚጨምር ያመለክታል (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እንዳይታበዩ ኃይልን መጠቀም ትዕቢታቸውን እንደመሥበር ተደርጐ ተነግሮአል:: አት: “ባላችሁ ጉልበት የማሰማችሁን ትዕቢት ለማቆም እቀጣችኋለሁ” ወይም “በጉልበታችሁ እንዳትታበዩ እቀጣችኋለሁ”:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህም እግዚአብሔር ዝናብ እንዳይዘንብ ያደርጋል ማለት ነው:: ይህም ሰዎች ዘርን እንዳይዘሩ ወይም እህልን እንዳያመርቱ ምድሪቱን ያደርቃል ማለት ነው:: (see Simile)
እጅግ ብዙ መሥራት ኃይል እስኪያልቅ ድረስ ሙሉ ጉልበትን ተጠቅሞ መሥራት ተደርጐ ተገልጾአል:: “በከንቱ ያልቃል” የሚለው ሀረግ እጅግ ብዙ ቢሠሩም ምንም አያገኙም ማለት ነው አት በከንቱ እጅግ ብዙ ትሠራላችሁ ወይም እጅግ ብዙ ትሠራላችሁ ነገርግን ብዙ በሠራችሁት ምንም አታገኙም ዘይቤያዊ አገላለጽ ወይም ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ
“መቀጠል” ባሕሪይን ይገልጻል:: በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ እግዚአብሔርን መቃወምን ወይም እርሱን አለመቀበልን ይወክላል አት: “በእኔ ላይ አታምጹ”
መበተን የሚለው ረቂቅ ስም መምታት በሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት: ሳባት ጊዜ እመታችኋለሁ:: (ረቂቅ ስሞች ይመልከቱ)
እግዚአብሔር በእስራኤላዊያን ላይ መቅሰፍትን ማምጣቱ በመቅሠፍት እንደሚመታቸው ወይም እንደሚጐዳቸው ተደርጐ ተገልጾአል አት: “በእናንተ ላይ ሰባት እጥፍ በላይ መቅሠፍት አመጣለሁ” ወይም “ሰባት ጊዜ በላይ በአሠቃቂነት እቀጣችኋለሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ ሰባት እጥፍ መደበኛ ሰባት ጊዜ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የቅጣቱን አሠቃቂነት ይጨምራል ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር ይመልከቱ)
“ኃጢአቶች” የሚለው ረቂቅ ስም “ኃጢአት” በሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “ምን ያህል ኃጢአት እንደሠራችሁ በዚያ መጠን” (ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ)
“መንጠቅ” ማለት ማጥቃት ወይም አስገድዶ ማውጣት ነው ::አት: “ልጆቻችሁን የነጥቁአችኋል” ወይም “ልጆቻችሁን አስገድደው ይወስዱባችኋል” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
“ማንም በመንገዶቻችሁ ላይ አይራመድም” አልባ ይሆናሉ ማለት ማንም በዚያ አይኖርም ማለት ነው
“እንደዚህ በሚቀጣበት ጊዜ” ወይም “እንደዚህ ቢቀጣችሁ”
ቅጣቱን መቀበል ለዚያ ተገቢ ምላሽ መስጠት ነው:: እዚህ ተገቢ ምላሽ እግዚአብሔርን መታዘዝ ነው:: አት: “አሁንም ቅጣቴን አልተቀበላችሁም” ወይም “አሁንም አልታዘዛችሁኝም” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
መሄድ ባሕሪይን ይወክላል:: እርሱን በማመጽ መሄድ ማለት እርሱን ማመጽ ወይም እርሱን መቃወም ማለት ነው አት፡ “አምጸውብኛል” ወይም “ተቃውመውኛል” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
መሄድ ባሕሪይን ይወክላል:: እነርሱን በማመጽ መሄድ ማለት እነርሱን ማመጽ ወይም እርሱን መቃወም ማለት ነው አት፡ “ እኔም አምጽባችኋለሁ” ወይም “እቃወማቸዋለሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ቁጥር 7 ፍጹምነትን ይወክላል:: አት: “እኔ ራሴ ብዙ ጊዜ እቀጣችኋለሁ” ወይም “እኔው ራሴ እጅግ አሠቃቂ በሆነ መንገድ እቀጣችኋለሁ”
“ኃጢአቶች” የሚለው ረቂቅ ስም “ኃጢአት” በሚለው ግሥ ሊገለጽ ይችላል:: አት: “በእኔ ላይ ኃጢአት መሥራታችሁን ስለቀጠላችሁ” (ረቂቅ ስሞችን ይመልከቱ)
እዚህ “ሰይፍ” ሠራዊትን ወይም ከሠራዊት የሚደርስ ውጊያን ይወክላል:: አት: “የጠላት ሠራዊት አመጣበሃለሁ” ወይም “ጠላት እንዲዋጋህ አደርጋለሁ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
እቀጣችኋለሁ
“ቃልኪዳኔን ስላልታዘዛችሁ” ወይም “ቃል ኪዳኔን ስለማትታዘዙ”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ትሰበሰባላችሁ” ወይም “ትሸሻላችሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ “እጅ” “ቁጥጥር ሥር” ማለት ሲሆን እናም በጠላት መሸነፍን ያመለክታል:: ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ለጠላቶቻችሁ እጅ አሳልፊ እሠጣችኋለሁ” ወይም “ጠላቶቻችሁ እንዲቆጣጠራችሁ አደርጋለሁ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሰዎች የሰበሰቡትን እህል ማጥፋት ወይም ሰዎች ይህን እንዳያገኙ ማድረግ የምግብ አቅርቦታቸውን ማቋረጥ ተደርጐ በተነግሮአል፡፡ አት፡ “የሰበሰባችሁትን እህል ባጠፋሁ ጊዜ” ወይም “ምግብን እንዳታገኙ ባደረግሁ ጊዜ” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህም ጥቂት ዱቄት ከመኖር የተነሣ ብዙ ሴቶች የሚያመጡአቸው ለአንድ ምጣድ ብቻ እንደሚሆን ያመለክትል
መስማት እርሱ ያለውን መታዘዝ ይወክላል አት ካለታዘዛችሁ ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
መሄድ ባህሪይን ያመለክታል አንድን ሰው በማመጽ መሄድ እርሱን ማመጽ ወይም እርሱን መቃወም ነው፡፡ አት፡ ‘አመጻችሁብኝ” ወይም “ተቃወማችሁኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
መሄድ ባህሪይን ያመለክታል አንድን ሰው በማመጽ መሄድ እርሱን ማመጽ ወይም እርሱን መቃወም ነው፡፡ አት፡ “እኔ አምጽባችኋለሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ ሰባት እጥፍ መደበኛ ሰባት ጊዜን አያመለክትም እግዚአብሔር የቅጣቱን አሠቃነት መጠን ይጨምራል ማለት ነው (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እነዚህን ለማድረግ ሠራዊትን ስለሚልክ ይህን ራሱ እንደሚያደርግ ተደርጐ ተናግሮአል አት “ለማፍረስ … ለመቁረጥ… በድኖቻችሁን ለመጣል ሠራዊትን እልካለሁ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
ሙት አካሎቻችሁ
በሕይወት ኖረው እንደሞቱ አስመስሎ እግዚአብሔር ጣዖቶቻቸው በድን እንደሆኑ ይናገራል:: አት: “ሕይወት የሌላቸው ጣዖቶቻችሁ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ፈንታ ጣዖቶቻቸውን ያመለኩባቸው ቦታዎች ናቸው
የእግዚአብሔር በመልካም መዓዛ ሽታ መደሰቱ መሥዋዕቱን በሚያቃጥሉ መደሰቱን ነው:: በዚህ ቦታ ግን ሰዎች መሥዋዕታቸውን ያቀጥላሉ ነገር ግን እግዚአብሔር በእነርሱ አልተደሰተም:: አት: “መሥዋዕቶችን ታቀርባላችሁ ወይም ታቃጥላላችሁ ነገር ግን እኔ አልደሰትባችሁም::” (ዘይቤያዊ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ ጠላቶችን ሊኮ እንደሚዋጋቸው ያመለክታል አት ሊዋጋችሁ የጠላት ሠራዊት እልክባችኋለሁ ወይም በሠይፎቻቸው ለመዋጋት የጠላት ሠራዊት እልክባችኋለሁ ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ምድራችሁን ትተዋላችሁ እናም ጠላቶቻችሁ ከተሞቻችሁን ያፈርሳሉ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ በየሰባት ዓመቱ ምድሪቱን ባለማረስ የሰንበትን ሕግ መታዘዝ አለባቸው:: እግዚአብሔር ምድሪቱን የሰንበትን ሕግና እረፍት እንደታዘዘ ሰው አድረጐ ይናገራል:: አት: “ከዚያም በሰንበት ሕግ መሠረት ምድሪቱ ታርፋለች” ወይም “ከዚያም የሰንበት ሕግ እንደሚያዝዘው ምድሪቱ አትታረስም” (ሰውኛ አገላለጽ ይመልከቱ)
ያልተታረሰውን መሬት እረፍት እንዳገኘ ሰው አድርጐ እግዚአብሔር ይናገራል:: ምድሪቱ መታረስ የለባትም::
በእነርሱ ልብ ድንጋጤን መስደድ እነርሱን ማሳፈርን ይወክላል:: አት: “እጅግ እንዲታፍሩ አደርጋችኋለሁ”:: (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ሰይፍ የሚወክለው ሰይፍን በመያዝ ሊገድል የተዘጋጀ ሰው ወይም ከጠላት ሠራዊት የሚሆን ውጊያን ነው:: አት: “በሰይፍ ከሚያሳድዳችሁ እንደሚትሸሹ” ወይም “ከጠላት ሠራዊት እንደሚትሸሹ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
እስራኤላዊያን በጉልበት ወደ ጠላቶቻቸው አገር በሚሄዱበት ጊዜ ምን እንደሚሆን እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
ሰይፍ የሚወክለው ሰይፍን በመያዝ ሊገድል የተዘጋጀ ሰው ወይም ከጠላት ሠራዊት የሚሆን ውጊያን ነው:: አት: “በሰይፍ ከሚያሳድዳችሁ እንደሚትሸሹ” ወይም “ከጠላት ሠራዊት እንደሚትሸሹ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
በጠላቶች ፊት መቆምበጠላቶች ጥቃትና ውጊያ አለመውደቅን ያመለክታል:: አት: “በሚዋጉአችሁ ጊዜ ጠላቶቻችሁን ለመቋቋም” ወይም “ጠላቶቻችሁን መልሳችሁ ለመዋጋት” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
እግዚአብሔር የጠላቶቻቸውን ምድር እስራኤላዊያንን እንደሚበላ እንደ አውሬ አድርጐ ይናገራል መቦጫጨቅ የሚለው ቃል አብዛኛዎቹ እስራኤላዊያን በዚያ እንደሚሞቱ ትኩረትን ይሰጣል አት በጠላቶቻችሁ ሀገር ትሞታላችሁ (See Personification/ አንድ ነገር አካል እንዳለው የመግለጽ ዘይቤ ይመልከቱ)
ሳይሞቱ የቀሩት
በኃጢአታቸው መንመነው ማለቅ በኃጢአታቸው ምክንያት መንምነው ማለቅን ያመለክታል
እዚህ አባቶች የቀደሙ አባቶቻቸውን ያመለክታል (See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
እዚህ አባቶች የቀደሙ አባቶቻቸውን ያመለክታል ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
“ለእኔ ታማኝ ባልሆኑበት መንገድ እናም ለእነርሱ መልካም ሆኜ ሳለሁ በእኔ ላይ ያመጹበትን”
መሄድ ባህሪይን ያመለክታል አንድን ሰው በማመጽ መሄድ እርሱን ማመጽ ወይም እርሱን መቃወም ነው፡፡ አት፡ ‘አመጹብኝ” ወይም “ተቃወሙኝ” (ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ እቃወማችኋለሁ የሚለውን ይወክላል አት እቃወማቸዋሁ(ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ)
እዚህ “ያልተገረዘ ልብ” ሙሉውን ሰው ያመለክታል:: አት: “በልቤ ደንዳናነት ካለመዘዝ ፈንታ ራሳቸውን ቢያዋርዱ” (See Synecdoche)
እዚህ “አስባለሁ” ሆን ብሎ ማሰብን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው:: እዚህ ቦታ ቃል ኪዳኑን እንደሚፈጽም ያመለክታል:: አት: በዚያን ጊዜ ከያዕቆብ ከይስሐቅና ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን እፈጽማለሁ::
እዚህ “አስባለሁ” ሆን ብሎ ማሰብን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው:: እዚህ ስለምድሪቱ ያለውን ተስፋ ቃል እንደሚፈጽም ያመለክታል:: አት: “ስለምድሪቱ ያለውን ተስፋ ቃል እፈጽማለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገርና Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “የእስራኤል ሕዝብ ምድራቸውን ይተዋሉ/ይለቅቃሉ ወይም ባዶ ያደርጋሉ” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ስለምድሪቷ አንድ ሰው በእረፍቱ እንደሚደሰት አድረጐ ይናገራል ምክንያቱም በእርስዋ ላይ ዘርን የሚዘራ ወይም ሰብልን የሚያሳድግ አይኖርም ይህም ምድሪቱ ለም እንዲትሆን ያደርጋታል:: አት: “ምድሪቱ በሰንበታት ትጠቀማለች” (ሰውኛ አገላለጽ ይመልከቱ)
ይህ የመታዘዝ በረከቶችና ያለታዘዝ ቅጣቶችን እግዚአብሔር በሲና ተራራ ለሙሴ የተናገረውን መልእክት ያጠቃልላል
እዚህ “አስባለሁ” ሆን ብሎ ማሰብን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አባባል ነው:: እዚህ ቦታ ቃል ኪዳኑን እንደሚፈጽም ያመለክታል:: አት: በዚያን ጊዜ ከአባቶቻችሁ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን እፈጽማለሁ:: (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
ይህ የአሕዛብ ማወቅ ነው:: አት: “አሕዛብ እያወቁ” ወይም “አሕዛብ ይህን ያውቃሉ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
የአዛብ ሕዝብን ይወክላል:: አት:” የአሕዛብ ሕዝብ” ( See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለ፣ 2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‹አንድ ሰው ለያህዌ ሰውን ለመስጠት የተለየ ስዕለት ቢሳል ተመጣጣን ዋጋ ለመክፈል ተከታዮን ዋጋዎች ተጠቀም፡፡ 3 ከዚያ እስከ ስልሳ አመት ዕድሜ ላለው ወንድ መደበኛው ዋጋ በቤ መቅደሱ ሰቅል መለኪያ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ይሁን፡፡ 4 ለተመሳሳይ ዕድሜ ክልል ለሴቷ መደበኛው ዋጋ ሰላሳ ሰቅሎች ይሁን፡፡ 5 ከአምስት አመት እስከ ሀያ አመት ዕድሜ ለወንድ መደበኛው ዋጋ ሀያ ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴቷ አስር ሰቅሎች ነው፡፡ 6 ከአንድ ወር ዕድሜ እስከ አምስት አመት ለወንድ መደበኛው ዋጋ አምስት የብር ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴት ሶስት የብር ሰቅሎች ነው፡፡ 7 ከስልሳ አመት በላይ ለወንድ መደበኛው ዋጋ አስራ አምስት ሰቅሎች፣ ለሴት አስር ሰቅሎች ይሁን፡፡ 8 ነገር ግን ስዕለቱን የገባው ሰው መደበኛውን ዋጋ መክፈል ባይችል፣ በስለት የተሰጠው ሰው ወደ ካህኑ ይቅረብ፣ ካህኑም ያንን ሰው የተሳለው ሰው ሊከፍል በሚችል ዋጋ ይተምነዋል። 9 አንድ ሰው ለያህዌ እንስሳ መሰዋት ቢፈልግ፣ ያህዌ ያንን ቢቀበል፣ ከዚያ ያ እንስሳ ለእርሱ ይለያል፡፡ 10 ሰውዬው እንዲህ ያለውን እንስሳ መለወጥ ወይም መቀየር የለበትም፣ መልካሙን በመጥፎው ወይም መጥፎውን በመልካሙ አይቀይርም፡፡ አንዱን እንስሳ በሌላው ቢለውጥ፣ ያ እንስሳና የተለወጠው ሁለቱም ንጹህ ይሆናሉ፡፡ 11 ሆኖም፣ ሰውዬው ለያህዌ ሊሰጥ የተሳለው ንጹህ ካልሆነ ስለዚህ ምክንያት ያህዌ ያንን አይቀበልም፣ ከዚያ ሰውዬው እንስሳውን ወደ ካህኑ ማምጣት አለበት፡፡ 12 ካህኑ በገበያው የእንስሳ ዋጋ ይተምነዋል፡፡ ማናቸውም ካህኑ ለእንስሳው የሰጠው ዋጋ፣ ያ የእንስሳው ዋጋ ይሆናል፡፡ 13 እናም ባለቤቱ እንስሳውን ሊዋጅ ቢፈልግ፣ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይዋጀው፡፡ 14 አንድ ሰው ቤቱን ለያህዌ መቀደስ ሲፈልግ፣ ካህኑ የቤቱን ዋጋ ይተምናል፡፡ ማናቸውም ካህኑ የተመነው ዋጋ ያ የዚያ ቤት ዋጋ ነው፡፡ 15 ነገር ግን ባለቤቱ ቤቱን ቢለይና በኋላ ሊዋጀው ቢፈልግግ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አመስተና ይጨመር፣ እናም ከዚያ እንደገና የእርሱ ይሆናል፡፡ 16 አንድ ሰው ከመሬቱ ለያህዌ ለመለየት ቢፈልግ፣ የመሬቱ ዋጋ ግምት ለመዝራት በሚያስፈልገው ፍሬ መጠን ይተመናል፡፡ አንድ ሆሜር መስፈሪያ ገብስ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ያወጣል፡፡ 17 እርሻውን በኢዮቤልዩ አመት ቢለይ፣ የተገመተው ዋጋ ይፀናል፡፡ 18 እርሻውን ከኢዮቤልዩ በኋላ ቢለይ ግን፣ ካህኑ የእርሻ መሬቱን ዋጋ እስከ ቀጣዩ የኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባሉ አመታት ቁጥር ያሰላና የተገመተው ዋጋ ይቀነሳል፡፡ 19 እርሻውን የለየው ሰው ሊዋጀው ቢፈልግ፣ በተገመተው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛ ይጨምራ፣ እናም መሬቱ ተመልሶ የእርሱ ይሆናል፡፡ 20 እርሻውን ካልዋጀ ወይም ለሌላ ሰው ሸጦት ከሆነ፣ ከዚያ በኋላ ተመልሶ ሊዋጅ አይችልም፡፡ 21 ይልቁንም፣ እርሾው፣ በኢዮቤልዩ ተመልሶ ሲለቀቅ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ እንደተሰተ እርሻ ሁሉ ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ ይሆናል፡፡ የካህናቱ ንብረት ይሆናል፡፡ 22 አንድ ሰው የገዛውን መሬት ለያዌ ቢለይ፣ ነገር ግን መሬቱ ከሰውዬው ቤተሰቦች መሬት ውስጥ ባይሆን፣ 23 ካህኑ የእርሻውን ዋጋ እስ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባለው ጊዜ መተን ይተምናል፣ ሰውዬውም ዋጋውን በዚያ ቀን ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ አድርጎ ይከፍላል፡፡ 24 በኢዮቤልዮ አመት፣ እርሻው ከገዛው ሰው ተወስዶ ወደ መሬቱ የቀድሞ ባለቤት ይመለሳል፡፡ 25 የሚተመኑ ዋጋዎች ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል ዋጋ ሊተመኑ ይገባል፡፤ ሃያ ጌራ ከአንድ ሰቅል ጋር እኩል ነው፡፡ 26 ከእንስሳት በመጀመሪያ የሚወለደው ግን አስቀድሞም ቢሆነ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው 27 ንጹህ ያልሆነ እንስሳ ከሆነ፣ ባለቤቱ በተመገተው ዋጋ መልሶ ይግዛውው ደግሞም ከዋጋው በላይ አንድ አምስተኛ ይጨምርበት፡፡ እንስሳው ካልተዋጀ፣ በተተመነው ዋጋ ይሸጥ፡፡ 28 ሆኖም፣ አንድ ሰው ለያህዌ ከለየው ሰውም ሆነ ወይም እንስሳ፣ ወይም የቤተሰቡ ርዕስት ምንም ነገር አይሽጥ ወይም አይዋጅ ማናቸውም የተለየ ነገር ለያህዌ ቅዱስ ነው፡፡ 29 እንዲጠፋ ለተለየ ሰው ምንም መዋጃ አይከፈልለትም፡፡ ያ ሰው መገደል አለበት፡፡ 30 አስራት ሁሉ፣ በምድሪቱ ላይ የበቀለ ሰብልም ሆነ ወይም የዛፍ ፍሬ የያህዌ ነው፡፡ ለያህዌ የተቀደሰ ነው፡፡ 31 አንድ ሰው ከአስራቱ አንዳች ቢዋጅ፣ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛ ይቸምር፡፡ 32 ከመንጋ ወይም ከከብት አስራት ሁሉ፣ ከእረኛው በትር ስር የሚያልፍ ሁሉ፣ ከአስር አንዱ ለያህዌ ይለይ፡፡ 33 እረኛው የተሸለውን ወይም የከፋውን እንስሳ አይፈልግም፣ ደግሞም አንዱን በሌላው አይተካ፡፡ ቢለውጠው እኗን፣ የተለወጠውና የሚለወጠው ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ፡፡ ሊዋጅ አይችልም፡፡” 34 ያህዌ በሲና ተራራ ለሙሴ የሰጣቸው ለእስራኤላውያን የተሰጡ ትእዛዛት እነዚህ ናቸው፡፡
በዚህ ዐውድ ስእለቱ ራሱን ወይም ሌላን ሰው ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ይሆናል፡፡ ይህ ግልጽ ተደርጐ ሊነገር ይችላል፡፡ አት: “ማንም አንድን ሰው ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቢሳል” (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔር ሰውን በመስጠት ፈንታ የተወሰነ ብር ይክፈል አት በሰው ፈንታ እንደሚከተሉት ተመጣጣኝ ዋጋ መሠረት ለእግዚአብሔር ስጦታ ያቅርብ ወይም በሰው ፈንታ እንደሚከተሉት የነሐስ መጠን ይክፈል (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“የሚከፈል የዋጋ መጠን” ወይም “መከፈል ያለበት”
2ዐ 6ዐ 5ዐ 3ዐ ቁጥሮችን ይመልከቱ
የዘመናዊ ሚዛኖች መለኪያ መጠቀም ካስፈለገ ሁለቱ መንገዶች እነሆ:: አት: “ሃምሳ ሰቅል ብር እያንዳንዳቸው አሥር ግራም የመዘናሉ” ወይም “5ዐዐ ግራም ብር” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
የተለያየ ሚዛን ያላቸው ሰቅሎች አሉ:: በተቀደሰው የመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሰዎች በመጠቀም ያለባቸው ይህን ሚዛን ነው:: ይህም 11 ግራም ይመዝናል:: አት: “በመቅደሱ የሚጠቀሙበትን ዓይነት ሰቅል ይጠቀሙ” ወይም “ብርን ሲመዝኑ በመቅደሱ የሚጠቀሙበትን ሚዛን ይጠቀሙ” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
የዘመናዊ ሚዛኖች መለኪያ መጠቀም ካስፈለገ ሁለቱ መንገዶች እነሆ:: አት: “ሠላሣ ሰቅል ብር እያንዳንዳቸው አሥር ግራም የመዘናሉ” ወይም “3ዐዐ ግራም ብር” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
5 20 10 3 ቁጥሮችን ይመልከቱ
“የሚከፈል የዋጋ መጠን” ወይም “መከፈል ያለበት”
የዘመናዊ ሚዛኖች መለኪያ መጠቀም ካስፈለገ ሁለቱ መንገዶች እነሆ:: አት: “ሃያ ሰቅል ብር እያንዳንዳቸው አሥር ግራም የመዘናሉ” ወይም “ሁለት መቶ ግራም ብር” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
እድሜ እና ግምቱ የሚሉ አዚህ ተዘለዋል:: ነገርግን ታሳቢ እንደሆኑ መረዳት ተገቢ ነው:: አት “ይህን እድሜ ለሆነ ሴት ግምቱ አሥር ሰቅል ነው”(መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
የዘመናዊ ሚዛኖች መለኪያ መጠቀም ካስፈለገ ሁለቱ መንገዶች እነሆ:: አት: “አሥር ሰቅል ብር እያንዳንዳቸው አሥር ግራም የመዘናሉ” ወይም “አንድ መቶ ግራም ብር” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
የዘመናዊ ሚዛኖች መለኪያ መጠቀም ካስፈለገ ሁለቱ መንገዶች እነሆ:: አት: “አምስት ሰቅል ብር እያንዳንዳቸው አሥር ግራም የመዘናሉ” ወይም “ሃምሳ ግራም ብር” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
የዘመናዊ ሚዛኖች መለኪያ መጠቀም ካስፈለገ ሁለቱ መንገዶች እነሆ:: አት: “ሶስት ሰቅል ብር እያንዳንዳቸው አሥር ግራም የመዘናሉ” ወይም “ሠላሣ ግራም ብር” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
ስድሳ ዓመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ
6ዐ 15 1ዐ ቁጥሮችን ይመልከቱ
የዘመናዊ ሚዛኖች መለኪያ መጠቀም ካስፈለገ ሁለቱ መንገዶች እነሆ:: አት: “አሥራ አምስት ሰቅል ብር እያንዳንዳቸው አሥር ግራም የመዘናሉ” ወይም “ አንድ መቶ ሃምሳ ግራም ብር” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
እድሜ እና ግምቱ የሚሉ አዚህ ተዘለዋል:: ነገርግን ታሳቢ እንደሆኑ መረዳት ተገቢ ነው:: አት “ይህን እድሜ ለሆነ ሴት ግምቱ አሥር ሰቅል ነው”(መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ): Ellipsis/ ዐውዱ ሊገልጽ የሚችሉ ቃላትን ወይም አባባሎችን የመደበቅ ወይም የመዝለል ዘይቤ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “የሚሰጠውን ሰው ለካህኑ ማቅረብ አለበት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ለሙሴ ይናገራል
ለያህዌ ለያቸው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “እርሱንና በእርሱ ምትክ የሚቀርበውን” ወይም “ሁለቱ እንስሶች” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እንስሳውን መሥዋዕት አድርጐ ካልተቀበለ ያ እንስሳ በአካል የረከሰ ወይም የቆሸሸ ተብሎ ተገልጾአል :: የተለየ ዓይነት ወይም እንከን ያለበት እንስሳ ስለሆነ ርኩሰ ተብሎአል አት በእርግጥ እግዚአብሔር የማይቀበለው ነው
ይህ አንድ ሰው ሲሸጥ ወይም ሲገዛ እንስሳው የሚያወጣው መደበኛ ዋጋ ነው
እንደገና ሊገዛው ቢፈልግ
አምስተኛ ከአምስት እኩል ክፍሎች አንዱን ነው አት የቤቱን ዋጋ በአምስት ይክፈለው ከእነዚህ እኩል ክፍሎች የአንዱን ክፍል በላዩ ላይ ይጨምር እናም ሁሉን ይክፈል፡፡ (ክፍልፋዮችን ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ሰውየው ሊዘራ የሚያስፈልገው ዘር መሠን” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እዚህ አንድ ሆሜር ገብስ ዘር የሚወክለው አንድ ሆሜር ገብስ ሊዘራበት የሚችልበትን መሬት ነው:: አት: “አንድ ሆሜር ገብስ ዘር በሙሉ ሊዘራበት የሚጠይቅ መሬት ዋጋ” ወይም “አንድ ሆሜር የገብስ ዘር የሚወስድ መሬት” ዋጋ (See Metonymy/ ተዛማጅ ባህሪይ የሚገልጹ ምትክ ቃላትና አባባሎች ይመልከቱ)See Metonmy)
አንድ ሆሜር 22 ሊትር ነው (መጽሐፍ ቅዱሳዊ መለኪያዎችን ይመልከቱ)
ዘመናዊ የክብደት መለኪያዎችን መጠቀም ካስፈለገ ሁለት መንገዶች አሉ:: አት: “የሃምሳ ሰቅል ብር የእያንዳንዱ ሰቅል ዋጋ አሥር ግራም ነው” ወይም “አምስት መቶ ግራም ብር” (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችንና ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ይህ በየ5ዐ ዓመት ይደረጋል:: በዘሌዋዊያን 25: 1ዐ “ኢዩቤልዩ” እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ
“የተተመነው ዋጋ ይጸናል” ወይም “የተተመነው ዋጋ ተመሣሣይ ሆኖ ይጸናል” አት: “ዋጋው ተመሣሣይ ይሆናል” ወይም “የዋጋው መጠን ሙሉ ይሆናል” (ዘይቤይዊ አነጋገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ከተተመነው ዋጋ ይቀንሳል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ሊዋጀው አይችልም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እርሻውን የሚዋጅበት ጊዜ ግልጽ ሊደረግ ይችላል አት ከኢዩቤልዩ ዓመት በፊት እርሻውን ባይዋጅ (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
“በመመለስ ዓመት” ወይም “መሬት የሚመለስበትና ባሪያዎች ነጻ የሚወጡበት ዓመት” ይህ አይሁዳዊያን መሬትን ለባለመሬቱ የሚመልቱበትና ለባሪያዎች ነጻነትን የሚያውጁበት ዓመት ነው:: በዘሌዋዊያን 25:13 ይህን እንዴት እንደተረጐሙ ይመልከቱ::
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “አንድ ሰው ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ይሰጠዋል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለቱ ሀረጐች ተመሣሣይ ሰው ያመለክታሉ:: የታወቀው መንገድ መሬቱ የተገዛው ከባለርስቱ ነው
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “የሸጠው ሰው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ካህኑ ዋጋውን ይተምናል” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
የተለያዩ የሰቀል ዓይነቶች አሉ ይህ በቅዱስ ድንኳን መቅደስ ሰዎች ከሚጠቀሙት አንዱ ነው መጽሐፍ ቀዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ
የዚህ ዐረፍተ ነገር ዋና ዓላማ የመቅደሱ ሰቅል ምን ያህል እንደሚመዝን ለመናገር ነው፡፡ ጌራ እስራኤላዊያን ከሚጠቀሙት ሚዛኖች ወይም መለኪያዎች አነስተኛው ነው አት አንድ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፡፡ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማዛኖችን ይመልከቱ)
ዘመናዊ ሚዛኖችን መጠቀም ካስፈለገ ሁለት መንገዶች አሉ፡፡ አንድ ሰቅል አሥር ግራም ይመዝናል፡፡ (ቁጥሮችንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛኖችን ይመልከቱ)
“ማንም ለእግዚአብሔር መቀደስ አይችልም”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “በዋጋው ላይ አንድ አምሰተኛ ይጨምር” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ሰውየው እንስሳውን ካልዋጀው” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ካለው ለእግዚአብሔር የሰጠውን ማንኛውም ነገር ሰውም ሆነ እንስሳ ወይም በውርስ የተገኘ መሬት አይሸጥም አየዋጅምም” ወይም “አንድ ሰው ካለው ለእግዚአብሔር የሰጠውን ማንኛውም ነገር ሰውም ሆነ እንስሳ ወይም በውርስ የተገኘ መሬት አይሸጥም አይዋጅምም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር የሰጠው ማንኛውም ነገር ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው”
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ማንም የመዋጀት ካሣ አይከፍልም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ለምን ሰውየው እንዲጠፋ እንደተወሰነ ግልጽ መደረግ አለበት፡፡ አት ከኃጢአቱ የተነሣ እንዲጠፋ እግዚአብሔር የወሰነው ማንኛውም ሰው (ግምታዊ እውቀት ወይም ጥልቅ መረጃ ይመልከቱ)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ያን ሰው እንዲገደል አድርጉ” ወይም “ያን ሰው ግደሉት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
“አንድ ሰው ከአሥራቱማንኛውንም መዋጀት ቢፈልግ”
ይህ እንስሳትን የማቆጥሩበትም መንገድ ያመለክታል:: አት: “የእረኛን በትር ከፍ በማድረግ በሥሩ ወደ ሌላኛው ጐን እንስሳት እንዲያልፉ በማድረግ በምትቆጥሩበት ጊዜ” ወይም “እንስሳትን በምትቆጥሩበት ጊዜ” (See Metonymy)
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “አንድ አሥረኛውን ለእግዚአብሔር ቀድሱት” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
አያንዳንዱ አሥረኛው
ሁለቱም እንስሳት
ይህ ተሻጋሪ ግሥ በያዘ መንገድ ሊተረጐም ይችላል:: “ሊዋጀው አይችልም” ወይም “መልሶ ሊገዛው አይችልም” (ተሻጋሪ ግሥ ወይም የማይሻገር ግሥ የያዘ ዐረፍተ ነገር ይመልከቱ)
ይህ ማጠቃለያ ዐረፍተ ነገር ነው:: በቀደሙት ምዕራፎች የተሰጡ ወይም የተነገሩ ትእዛዛትን ያመለክታል::
1 ያህዌ በሲና ምድረ በዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ተናገረው፡፡ ይህ የሆነው የእስራኤል ህዝብ ከግብጽ ምድር በወጣበት በሁለተኛው አመት በሁለኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ነበር፡፡ ያህዌ እንዲህ አለ፣ 2 “በየነገዱ፣ በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የእስራኤል ወንዶች ቆጠራ ይደረግ፡፡ በስም ቁጠራቸው፡ እያንዳንዱ ወንድ፣ በሰው ቁጠር፣ 3 ሀያ አመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ወንድ ሁሉ ይቆጠር፡፡ ለእስራኤል ወታደር ሆኖ ሊዋጋ የሚችለውን ሁሉ ቁጠር፡፡ አንተና አሮን በታጣቂ ቡድኖቻቸው የወንዶችን ቁጥር መዝግቡ፡፡ 4 ከእያንዳንዱ ጎሳ አንድ ሰው፣ የነገድ አለቃ ከአንተ ጋር የጎሳው መሪ ሆኖ ያገልግል፡፡ እያንዳንዱ መሪ ለጎሳው የሚዋጉትን ወንዶች ይምራ፡፡ 5 ከአንተ ጋር ሆነው መዋጋት ያለባቸው መሪዎች ስሞቻቸው እነዚህ ናቸው፡ ከሮቤል ጎሳ፣ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር፣ 6 ከስምዖን ጎሳ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፤ 7 ከይሁዳ ጎሳ፣ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፤ 8 ከይሳኮር ጎሳ የሶገር ልጅ ናትናኤል፤ 9 ከዛብን ጎሳ፣ የኬሎን ልጅ ኤልያብ፤ 10 ከኤፍሬም ጎሳ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ፤ ከምናሴ ጎሳ፣ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል፤ 11 ከብንያም ጎሳ የዮሴፍ ልጅ፣ የጌዲዮን ልጅ አቢዳን፤ 12 ከዳን ጎሳ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር፣ 13 ከአሴር ጎሳ፣ የኤክራን ልጅ ፉግኤል፣ 14 ከጋድ ጎሳ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ፤ 15 እና ከንፍታሌም ጎሳ፣ የዔናን ልጅ አኪሬ” ናቸው፡፡ 16 ከሕዝቡ የተመረጡት ወንዶች እነዚህ ነበሩ እነርሱ የአባቶቻቸውን ጎሳዎች ይመራሉ፡፡ በእስራኤል የነገዶች መሪዎች ነበሩ፡፡ 17 ሙሴና አሮን በስም የተመዘገቡትን እነዚህን ወንዶች ወሰዱ፣ 18 ከእዚህ ወንዶች ጋር በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የእስራኤል ወንዱን ሁሉ ሰበሰቡ፡፡ ከዚያም ሃያ አመት የሞላውና ከዚያ በላይ የሆነ እያንዳንዱ ወንድ የትውልድ ሐረጉን ተናገረ፡፡ እያንዳንዱ የነገዱን ስም እና የትውልድ ሐረጉን መጥራት ነበረበት፡፡ 19 ከዚያም ሙሴ በሲና ምድረ በዳ ያህዌ እንዲያደርገው ባዘዘው መሠረት ቁጥራቸውን መዘገበ፡፡ 20 የእስራኤል በኩር ከሆነው ከሮቤል ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉት ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 21 ከሮቤል ጎሳ 46500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 22 ከስምኦን ትውልዶች ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉት ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 23 ከስምዖን ጎሳ 59300 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 24 ከጋድ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 25 ከጋድ ጎሳ 45650 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 26 ከይሁዳ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስም ተቆጠሩ፡፡ 27 ከይሁዳ ጎሳ 7460 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 28 ከይሳኮር ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 29 ከይሳኮር ጎሳ 54400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 30 ከዛብሎን ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 31 ከዛብን ጎሳ 57400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 32 ከዮሴፍ ልጅ ከኤፍሬም ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 33 ከኤፍሬም ጎሳ 40500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 34 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፤ 35 ከምናሴ ጎሳ 32200 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 36 ከብንያም ትውልዶች ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፤ 37 ከብንያም ጎሳ 35400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 38 ከዳን ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 39 ከዳን ጎሳ 62700 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 40 ከአሴር ትውልዶች፣ ወደ ጦርት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 41 ከአሴር ጎሳ 41500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 42 ከንፍታሌም ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡ 43 ከንፍታሌም ጎሳ 53400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 44 ሙሴና አሮን እነዚህን ወንዶች ሁሉ አስራ ሁለቱን የእስራኤል ጎሳዎች ከሚመሩ አስራ ሁለት ሰዎች ጋር ሆነው ቆጠሩ፡፡ 45 ስለዚህም ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው ለጦርነት መውጣት የሚችሉ የእስራኤል ወንዶች ሁሉ በየቤተሰባቸው ተቆጠሩ፡፡ 46 የቆጠሯቸው ወንዶች 603550 ናቸው፡፡ 47 ከሌዊ ትውልድ የሆኑት ግን አልተቆጠሩም፣ 48 ምክንያቱም ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበር፣ 49 “የሌዊን ጎሳ አትቆጥርም ወይም እነርሱን በእስራኤል ህዝብ ቆጠራ ውስጥ አታስገባቸው፡፡ 50 ይልቁንም፣ ሌዋውያንን የቃልኪዳኑን ስርዓቶች በቤተመቅደስ እንዲፈጽሙ መድባቸው፣ እንደዚሁም በቤተመቅደስ ውስጥ የሚገኙ መገልገያዎችንና ማናቸውንም ነገሮች እንዲንከባከቡ ሹማቸው፡፡ ሌዋውያን ጽላቱን ይሸከሙ፣ እንዲሁም የቤተመቅደሱን ዕቃዎች ይሸከሙ፡፡ 51 ቤተመቅደሱ ወደ ሌላ ስፍራ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ፣ ሌዋውያኑ ይንቀሉት፡፡ ቤተመቅደሱ ሲተከል፣ ሌዋውያን ይትከሉት፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚጠጋ ማናቸውም እንግዳ ይገደል፡፡ 52 እስራኤላውያን ድንኳኖቸውን ሲተክሉ፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ራሱ የጦር ቡድን ዐርማ አጅግ ቀርቦ ይስራ፡፡ 53 ሆኖም፣ ሌዋውያኑ ቁጣዬ በእስራኤላውያን ላይ እንዳይሆን ድንኳናቸውን በቃል ኪዳኑ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፡፡ ሌዋውያኑ የቃልኪዳኑን ማደሪያ ሀላፊዎች ናቸው፡፡” 54 እስራኤላውያን እነዚህን ሁሉ ነገሮች አደረጉ፡፡ ያህዌ በሙሴ በኩል ያዘዛቸውን ነገሮች ሁሉ አደረጉ፡፡
ይህ ስም በብሉይ ኪዳን ዘመን ለሕዝቡ የገለጠው የራሱ ሥም ነው፡፡እግዚአብሔር የሚለውን ቃል በሚመለከት ትርጉሙን ለማወቅ የትርጉም ቃላቱን ገፅ ይመልከቱ፡፡
በዕብራውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት ይሄ ሁለተኛ ወር ነው፡፡በምዕራባውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት የመጀመሪያው ቀን የካቲት አጋማሽ አካባቢ ላይ የሚውል ነው፡፡(የዕብራውያን የቀን ወራትንና ተከታታይ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ሁለተኛው ዓመት” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት የወንዶቹን ስም በመመዝገብ ቁጥራቸውን ማወቅ ማለት ነው፡፡“የእያንዳንዱን ሰው ሥም በመፃፍ ቁጠሯቸው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“የሃያ ዓመት ዕድሜ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ወንዶች በየጦር ክፍሉ መመደባቸውን ያመለክታል፡፡
“ የአንድ ነገድ መሪ”
“ይርዳችሁ” ኤሊሱር፤ሰለሚኤል፤ነአሶን፤ናትናኤል እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ) ፡
እግዚአብሔር የነገድ መሪዎችን ስም መዘርዘር ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር የነገድ መሪዎችን ስም መዘርዘር ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር የነገድ መሪዎችን ስም መዘርዘር ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ) ፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር የመረጣቸው ሰዎች” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እነዚህ ሰዎች አንድ ላይ እንዲሳበሰቡ አድርጓቸው”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”ስማቸውን የመዘገቧቸው ሰዎች” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በዕብራውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት ሁለተኛው ወር ነው፡፡በምዕራባውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት የመጀመሪያው ቀን የሚውለው መጋቢት ወር መካከል አካባቢ ይሆናል፡፡ይህንን በዘኁልቁ 1፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(የዕብራውያን ወርንና የቅደም ተከተል ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ ሁለተኛው ዓረፍተ ነገር ከመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር ጋር ተመሣሣይነት ያለው ሲሆን እንዲጨመር የተደረገውም ጉዳዩን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ ተበሎ ነው፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“በየስማቸው መጥራት” የሚለው የሚያመለክተው “መናገርን.” ነው፡፡ ”እያንዳንዱ ሰው መናገር ነበረበት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”ስሞቹን ሁሉ ቆጠሩ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ወደ ጦርነት ለመሄድ አቅም ያለው”
“አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር ….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ) 59,300
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡ 20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር ….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“አርባ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡ 20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር ….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ወንዶች” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡ 20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር ….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሃምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ወንዶች” (ኦሪት ዘኁልቁን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር ….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሃምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ወንዶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“አርባ ሺህ አምስት መቶ ወንዶች” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“አርባ ሺህ አምስት መቶ ወንዶች” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ወንዶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር…. በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ስድሣ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ቆጠሩ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ቆጠሩ”
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር ….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሃምሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ ቆጠሩ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ተቆጠሩ”የሚለው ቃል በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይሄ ሐረግ በሕዝብ ቆጠራው ወቅት ለብዙ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ወንድ ሁሉ ከስሙ አንፃር ….በየወገናቸው፤በየአባቶቻቸው ቤቶች ተቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ስድስት መቶ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ሃምሣ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴና አሮን ከሌዊ ወገን የሆኑትን ሰዎች አልቆጠሩም” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
በአንዳንድ ቋንቋዎች ይሄ ፍዝ ግሥ ነው፡፡አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በተለየ መንገድ ሊፃፍ ይችላል፡፡”ከሌዊ ወገን የሆኑቱ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “የሌዊ ወገን” የሚያመለክተው በሌዊ ነገድ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ነው፡፡“የሌዊን ወገን አትቁጠረው” (ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
የማደሪያው ድንኳን በዚህ ረዥም ሥም የሚጠራበት ምከኒያት እግዚአብሔር የምሥክሩን ሕግ ያስቀመጠው እዚያ ውስጥ በመሆኑ ነው፡፡
“በእርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የመገናኛ ድንኳኑን ነው፡፡
ጉዞ በሚጀምሩበት ወቅት ማደሪውን የመሸከም ኃላፊነት የእነርሱ ነበር፡፡ “በምትጓዙበት ወቅት ሌዋውያን ማደሪያውን መሸከም ይኖርባቸዋል” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት ድንኳኖቻቸውን በማደሪያው ዙሪያ ይተክላሉ ማለት ነው፡፡“ድንኳኖቻቸውን በዙሪያው መትከል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ማደሪያው በሚያርፍበት ወቅት” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እንግዳ የሆነ ሰው መገደል ይኖርበታል” ወይም “ወደ ማደሪያው አካባቢ የሚመጣን እንግዳ ሰው መግደል ይኖርባችኋል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ትልቅ ባንዲራ
“የጦር ክፍሎቹ”
ማደሪያው በዚህ ረዥም ሥም የተጠራበት ምክኒያት የእግዚአብሔር ሕግ ያለበት ምሥክሩ በውስጡ በመቀመጡ ነው፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡50 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
እዚህ ላይ ቁጣው በእነርሱ ላይ ስለማይወርድ እሥራኤላውያንን እንደማይቀጣቸው ነው የሚናገረው፡፡“መውረድ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቁጣው በእነርሱ ላይ ተግባራዊ የመሆኑን ጉዳይ ነው፡፡ “በቁጣዬ የእሥራኤልን ሕዝብ እንዳልቀጣ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እሥራኤላውያን ሊያደርጉት ስለሚገባቸው ነገር ለሙሴ የተናገረ ሲሆን ሙሴ ደግሞ ለእሥራኤላውያን ትዕዛዙን አስተላለፈ፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንደገና እንዲህ አለ፣ 2 “እያንዳንዱ እስራኤላዊ በየአባቶቻቸው ቤቶች በአርማው ስር በቦታው ይሰፈር፡፡ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ በሁሉም አቅጣጫ ይሰፍራሉ፡፡ 3 ፀሐይ በምትወጣበት፣ በመገናኛው ድንኳን በስተምስራቅ ይሁዳ በቦታው ይሰፍራል፡፡ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን የይሁዳ ህዝብ መሪ ነው፡፡ 4 የይሁዳ ህዝብ ቁጥር 74600 ነው፡፡ 5 የይሳኮር ጎሳ ከይሁዳ ቀጥሎ ይስፈር፡፡ የሶገር ልጅ ናትናኤል የይሳኮርን ሰራዊት ይምራ፡፡ 6 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 54400 ነው፡፡ 7 የዛብሎን ጎሳ ከይሳኮር ቀጥሎ ይስፈር፡፡ የኬሎን ልጅ ኤልያብ የኤሎንን ሰራዊት ይምራ፡፡ 8 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 57400 ነው፡፡ 9 ጠቅላላው የይሁዳ ሠራዊት ቁጥር 186400 ነው፡፡ እነርሱ በቅድሚያ ይወጣሉ፡፡ 10 በስተደቡብ አቅጣጫ የሮቤል ምድብ በስፍራው ይሆናል፡፡ የሮቤል ምድብ መሪ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነው፡፡ 11 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 46500 ነው፡፡ 12 ስምዖን ከሮቤል ቀጥሎ ይሰፍራል፡፡ የስምዖን ህዝብ መሪ የሱሪሰዳይ ልጅ ስለሚኤል ነው፡፡ 13 በእርሱ ምድብ የሚገኘው የሰራዊት ቁጥር 59, 300 ነው፡፡ 14 የጋድ ጎሳ ይቀጥላል፡፡ የጋድ ህዝብ መሪ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነው፡፡ 15 በእርሱ ምድብ የሚገኘው የሰራዊት ቁጥር 45650 ነው፡፡ 16 በሮቤል ምድብ የሚገኙት በክፍላቸው መሠረት 151450 ናቸው፡፡ እነርሱ ቀጥለው ይወጣሉ፡፡ 17 ቀጥሎ፣ የመገናኛው ድንኳን ሌዋውያንን ከሁሉም ምድብተኞች መሃል አድርጎ ከሰፈር ይወጣል፡፡ ወደ ሰፈር በገቡበት ስርዓት ከሰፈር ይውጡ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በዐርማው ስር በስፍራው ይሁን፡፡ 18 የኤፍሬም ሰፈር ክፍሎች በስፍራቸው ይሁኑ፡፡ የኤፍሬም ህዝብ መሪ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነው፡፡ 19 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 40500 ነው፡፡ 20 ከእነርሱ የሚቀጥለው የምናሴ ጎሳ ነው፡፡ የምናሴ መሪ የፍርዱሱር ልጅ ገማልኤል ነው፡፡ 21 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 32200 ነው፡፡ 22 ቀጣይ የሚሆነው የብንያም ጎሳ ነው፡፡ የብንያም መሪ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነው፡፡ 23 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 35400 ነው፡፡ 24 በኤፍሬም ምድብ የሚኙት በክፍላቸው መሰረት 108100 ናቸው፡፡ እነርሱ ሶስተኛ ሆነው ይወጣሉ፡፡ 25 በሰሜን የዳን ሰፈር ምድብተኞች ይሰፍራሉ፡፡ የዳን ህዝብ መሪ የአሚሳዓይ ልጅ አብዔዘር ነው፡፡ 26 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 62700 ነው፡፡ 27 የአሴር ጎሳ ህዝብ ሰፈር ከዳን ቀጥሎ ነው፡፡ የአሴር መሪ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነው፡፡ 28 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 41500 ነው፡፡ 29 ቀጣዩ የንፍታሌም ጎሳ ነው፡፡ የንፍታሌም መሪ የዔናን ልጅ አኪሬ ነው፡፡ 30 በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 53400 ነው፡፡ 31 ከዳን ጋር በሰፈር የሚገኙት ቁጥራቸው 157600 ነው፡፡ እነርሱ በዐርማቸው ስር ከሰፈር በመጨረሻ ይወጣሉ፡፡” 32 በየቤተሰባቸው የተቆጠሩት እስራኤላውያን እነዚህ ናቸው፡፡ በየክፍሎቻቸው በሰፈሮቻቸው የተቆጠሩት በጠቅላላ 603550 ናቸው፡፡ 33 ነገር ግን ሙሴና አሮን በእስራኤል ሕዝብ መሀል ሌዋውያንን አልቆጠሩም፡፡ ይህም ያህዌ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነበር፡፡ 34 የእስራኤል ሕዝብ ያህዌ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ በየአርማቸው ስር ሰፈሩ፡፡ በአባቶቻቸው ቤቶች መሠረት በየነገዳቸው ከሰፈር ወጡ፡፡
“የአባቶች ቤቶች ምልክቶች” የሚባሉት ነገዶች በአራት ትላልቅ ቡድኖች የሚከፋፈሉበት ሁኔታ ነው፡፡እያንዳንዳቸው የተከፈሉት የአባቶች ቤቶች በአንድ ላይ መስፈር ነበረባቸው፡፡የአባቶች ቤቶች ወይም ነገዶች የሚለዩት በሚይዙት ዓርማ ነው፡፡
እያንዳንዱ ዘመድ አዝማድ ከዓርማቸው አንፃር ለእነርሱ መቀመጫ እንዲሆን የተመደበላቸው የመሥፈሪያ ቦታ ነበራቸው፡፡
ምልክት ትልቅ ባንዲራ ነው፡፡
“የአባቶች ቤቶች ምልክቶች” ማለት ነገዶች በትላልቅ ቡድኖች የሚከፋፈሉበት ነው፡፡እያንዳንዱ ነገድ በአንድነት ላይ እንዲሰፍር የሚታዘዝ ሲሆን እነርሱን የሚወክል ዓርማ ነበራቸው፡፡በኦሪት ዘኀልቁ 2፡2 ላይ የአባቶች ቤቶች ምልክቶች የሚለውን እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
በዘኁልቁ 1፡7 ላይ ይሄንን እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ስም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሃምሣ ሰባት ሺህ አራት መቶ” ይሄ የሚያመለክተው የሰዎቹን ቁጥር ነው፡፡“57,400” (ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ስም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሃምሣ ሰባት ሺህ አራት መቶ” ይሄ የሚያመለክተው የሰዎቹን ቁጥር ነው፡፡“57,400” (ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
“ቁጥሩ በአጠቃላይ አንድ መቶ ሰማንያ ስድሰት ሺህ አራት መቶ ነው፡፡”ይሄ ቁጥር በየአባቶቻቸው በቶች ምልክት ሥር የሰፈሩትን የይሁዳ ነገድ ሰዎች የሚያካትት ነው፡፡ “በይሁዳ ዓርማ ሥር የሰፈሩት ሰዎች ቁጥር 186,400 ነው፡፡”
ይሄ የሚያመለክተው ከመገናኛ ድንኳኑ በስተ ምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩትን የይሁዳ፤የይሳኮርና የዛብሎንን ነገዶች ነው፡፡
ይሄ ማለት እሥራኤላውያን ከሠፈራቸው መንቀሳቀስ በሚጀምሩበት ወቅት ሌሎች ነገዶች ከመንቀሳቀሳቸው በፊት የይሁዳ ነገድ ከፊታቸው በመቅደም መጓዝ ይጀምራል ማለት ነው፡፡“በጉዞ ወቅት የይሁዳ ነገድ ቀዳሚ ይሆናል፡፡” ወይም “እሥራኤላውያን የሰፈሩበትን ቦታ በሚለቁበት ወቅት እነዚያ ነገዶች የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ” (ቁጥሮች የሚለውንና በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“በየአባቶቻቸው በቶች ምልክት”ማለት አራት ነገዶች በትላልቅ ቡድኖች የሚከፋፈሉበት ሁኔታ ነው፡፡እያእንዳንዱ ነገድ በአንድ ላይ እንዲሰፍር የሚታዘዝ ሲሆን እነርሱን የሚወክል ዓርማ ነበራቸው፡፡በኦሪት ዘኀልቁ 2፡2 ላይ በየአባቶቻቸው በቶች ምልክት የሚለውን እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የዚህን ሰው ሥም በዘኁልቁ 1፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ” ይሄ የሚያመለክተው የሰዎችን ቁጥር ነው፡፡“46,500”(ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በዘኁልቁ 1፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሃምሳ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ”ይሄ የሚያመለክተው የሰዎችን ቁጥር ነው፡፡ “59,300” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሣ” ይሄ የሚያመለክተው የሰዎችን ቁጥር ነው፡፡ “45,650” (ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
“የተቆጠሩት ሰዎች በአጠቃላይ … አንድ መቶ ሃምሣ አንድ ሺህ አራት መቶ ሃምሣ ናቸው” ይሄ ቁጥር በሮቤል የአባቶቻቸው በቶች ዓርማ ሥር የሰፈሩትን ወንዶች ሁሉ የሚያካትት ቁጥር ነው፡፡“በተከፋፈሉበት ክፍል መሠረት በሮቤል የአባቶቻቸው በቶች ምልክት ሥር የሰፈሩት ወንዶች ሁሉ ቁጥር 151,450 ነው፡፡” (ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት እሥራኤላውያን ሠፈራቸውን ለቀው መጓዝ በሚጀምሩበት ወቅት የሮቤል ሠፈር ከይሁዳ በመቀጠል ጉዞውን ይቀጥላል ማለት ነው፡፡“በጉዞ ወቅት የሮቤል ሠፈር ሁለተኛ በመሆን ጉዞውን ይጀምራል”ወይም “እሥራኤላውያን ሠፈሩን ለቅቀው በሚሄዱበት ወቅት እነዚያ ነገዶች በሁለተኛ ረድፍነት መጓዝ ይቀጥላሉ”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት በሚጓዙበት ወቅት የመገናኛው ድንኳን ሌዋውያን ተሸክመውት በነገዶቹ መካከል መጓዝ ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሥራ ሁለቱን ነገዶች ነው፡፡
እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱ የሆነ ምልክት ወይም ዓርማ ሊኖረው አይችልም፡፡ይሄ የሚያመለክተው የነገዱን ምልክት ነው፡፡ “በነገዱ ዓርማ” (ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“በየአባቶቻቸው በቶች ዓርማ ሥር” ማለት ነገዶቹ የተከፋፈሉባቸው አራት ትላልቅ ቡድኖች ናቸው”እያንዳንዱ ነገድ ከዓርማው አንፃር አንድ ላይ እንዲሰፍር ይታዘዝ ነበር“የአባቶች ቤቶች የሚወከሉት በዓርማ ነው፡፡በኦሪት ዘኁልቁ 2፡2 ላይ “ዓርማ” የሚለውን እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“አርባ ሺህ አምስት መቶ”ይሄ የሚያመለክተው የሰዎቹን ቁጥር ነው፡፡ “40,500” (ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ማለት ከኤፍሬም ነገድ በመቀጠል የምናሴ ነገድ ይከተላል ማለት ነው፡፡
“ሰላሣ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ” ይሄ የሚያመለክተው የሰዎቹን ቁጥር ነው፡፡“32,200 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሰላሣ አምስት ሺህ አራት መቶ” ይሄ የሚያመለክተው የሰዎቹን ቁጥር ነው፡፡“35,400 ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“የተቆጠሩት አንድ መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ” ”ይሄ ቁጥር በኤፍሬም የአባቶች ቤቶች ዓርማ ሥር የሰፈሩትን የነገድ ሰዎች የሚያካትት ነው፡፡ “በኤፍሬም ዓርማ ሥር የሰፈሩት ሰዎች ቁጥር 108,100 ነበር፡፡” (ቁጥሮች የሚለውንና በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት እሥራኤላውያን ከሰፈራቸው ሲንቀሳቀሱ የኤፍሬም ነገድ ከይሁዳና ከሮቤል በመቀጠል ጉዞውን ይጀምራል ማለት ነው፡፡“ጉዞ በሚጀመርበት ወቅት የኤፍሬም ሠፈር ሶስተኛ ሆኖ ጉዞውን ይቀጥላል” ወይም “እሥራኤላውያን የሰፈሩበትን ሥፍራ በሚለቅቁበት ወቅት እነዚያ ነገዶች ቀጥለው ይለቅቃሉ” (ተከታታይ ቁጥሮችንና በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው በዳን ነገድ ምልክት ሥር የሚገኙትን የዳን፤የአሴርና የንፍታሌምን ሠራዊቶች ነው፡፡ “በዳን ምልክት ሥር የሚሰፍሩ ሠራዊቶች” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በዘኁልቁ 1፡12 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ስድሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ” ይሄ የሚያመለክተው የሰዎቹን ቁጥር ነው፡፡“62,700 ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ” ይሄ የሚያመለክተው የሰዎቹን ቁጥር ነው፡፡“41,500” (ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡ (ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሃምሣ ሶስት ሺህ አራት መቶ”ይሄ የሚያመለክተው የሰዎችን ቁጥር ነው፡፡“53,400” (ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እያንዳንዱ ነገድና ሠራዊቱ የት ሥፍራ ላይ እንደሚሰፍሩ ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“የተቆጠሩት ሁሉ …አንድ መቶ ሃምሣ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ” ”ይሄ ቁጥር በዳን የአባቶች ቤቶች ምልክት ሥር የሰፈሩትን የነገድ ሰዎች የሚያካትት ነው፡፡“በዳን ምልክት ሥር የሰፈሩት የሰዎቸ ቁጥር 157,600” (ቁጥሮች የሚለውንና በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴና አሮን ሁሉንም ቆጠሯቸው”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡
“ስድስት መቶ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ሃምሣ ናቸው፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ወደሌላ ሥፍራ መቼ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ነው፡፡“መጓዝ ሲጀምሩ ከሠፈራቸው ይወጡ ነበር” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ያህዌ በሲና ተራራ ከሙሴ ጋር በተነጋገረበት ጊዜ የአሮንና የሙሴ ትውልዶች ታሪክ ይህ ነበር፡፡ 2 የአሮን ልጆች ስሞቻቸው የበኩር ልጁ ናዳብ፣ እንዲሁም አብዩድ፣ አልዓዛር እና ኢታምር ነበሩ፡፡ 3 የአሮን ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፣ እነዚህ የተቀቡ ካህናትና እንደ ካህናት ሊያገለግሉ የተሾሙ ነበሩ፡፡ 4 ነገር ግን ናዳብ እና አብዩድ በሲና ምድረበዳ ተቀባይነት የሌለው እሳት ለእርሱ ሲሰዉ በያህዌ ፊት ወድቀው ሞቱ፡፡ ናዳብና አብዩድ ልጅ አልነበራቸውም፣ ስለዚህም አልዓዛርና ኢታምር ብቻ ከአባታቸው ከአሮን ጋር ካህናት ሆነው አገለገሉ፡፡ 5 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 6 “የሌዊን ጎሳ ይረዱት ዘንድ ወደ ካህኑ ወደ አሮን አምጣቸው፡፡ 7 በአሮንና በመላው ማህበሩ ስም በመገናኛው ድንኳን ፊት አገልግሎት ይስጡ፡፡ በቤተመቅደሱ ውስጥ ያገልግሉ፡፡ 8 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ላሉ ነገሮች ሁሉ ጥንቃቄ ያድርጉ፣ እንዲሁም የእስራኤል ጎሳዎች የቤተ መቅደሱን አገልግሎት እንድፈጽም ይርዱ፡፡ 9 ሌዋውያኑን ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፡፡ እነርሱ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲያገለግል ሙሉ ለሙሉ የተሰጡ ናቸው፡፡ 10 አሮንንና ልጆቹን ካህን አድርገህ ሹማቸው፣ ነገር ግን ማናቸውም ባዕድ ወደ ቤተ መቅደሱ ቢቀርብ ይገደል፡፡” 11 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 12 “እነሆ፣ እኔ ከእስራኤል ህዝብ መሃል ሌዋውያንን መረጥኩ፡፡ ከእስራኤል ሕዝብ መሃል በኩር የሆነውን ወንድ ሁሉ ከመውሰድ ፈንታ ይህን አድርጌያለሁ፡፡ ሌዋዊያን የእኔ ናቸው፡፡ 13 ማናቸውም በኩር የእኔ ነው፡፡ በግብጽ ምድር በኩሩን ሁሉ በመታሁ ዕለት፣ በእስራኤል በኩር ሆኖ የተወለደውን የሰውንም ሆነ የእንስሳትን በኩር ሁሉ ለራሴ ለየሁ፡፡ እነርሱ የእኔ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡” 14 በሲና ምድረበዳ ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 15 “በእያንዳንዱ ቤተሰብ፣ በአባቶቻቸው ቤቶች የሌዊን ትውልዶች ቁጠር፡፡ አንድ ወር እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለውን ወንድ ሁሉ ቁጠር፡፡” 16 ሙሴ እንዲያደርግ በታዘዘው መሠረት የያህዌን ቃል ሰምቶ ቆጠራቸው፡፡ 17 የሌዊ ልጆች ስም፣ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው፡፡ 18 ከጌድሶን ልጆች የመጡ ነገዶች ሎቢኒ እና ሰሜኢ ናቸው፡፡ 19 ከቀዓት ልጆች የመጡ ነገዶች፣ አንበረም፣ ይስዓር፣ኬብሮን እና ዑዝኤል ናቸው፡፡ 20 ከሜራሪ ልጆች የመጡ ነገዶች፣ ሞሖሊና ሙሴ ናቸው፡፡ በነገድ የተዘረዘሩ የሌዋውያን ነገዶች እነዚህ ናቸው፡፡ 21 የሊቤናና የሰሜአ ነገዶች የመጡት ከጌርሶን ነው፡፡ እነዚህ የጌርሶን ነገዶች ናቸው፡፡ 22 አንድ ወር ከሞላው አንስቶ ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው ወንድ ሁሉ ተቆጥሮ ነበር፣ በጠቅላላው 7500 ነበሩ፡፡ 23 የጌርሶን ነገዶች ከቤተመቅደሱ ምዕራብ አቅጣጫ ይስፈሩ፡፡ 24 የጌርሶንን ትውልዶች የላኤለ ልጅ ኤሊሳፍ ይምራ፡፡ 25 የጌርሶን ቤተሰብ የመገናኛው ድንኳን ጨምሮ የማደሪያውን ድንኳን ኃላፊነት ይውሰድ፡፡ እነርሱ ለድንኳኑ፣ ለመደረቢያዎቹና ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ ሆኖ ለሚያገለግለው መጋረጃ ጥንቃቄ ያደርጉ፡፡ 26 ለአደባባዩ ጌጦች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፣ በአደባባይ መግቢያ ላይ ለሚገኘው መጋረጃ፣ ቅዱሱን ስፍራና መሰዊያውን የሚከበውን አደባባይ ይጠብቁ፡፡ የመገናኛው ድንኳን ገመዶች እና በውስጡ የሚገኘውን ነገር ሁሉ ይጠብቁ፡፡ 27 ከቀዓት የመጡት ነገዶች እነዚህ ናቸው የአንበረማውያን ነገድ የይሰዓራውያን ነገድ፣ የኬብሮናውያን ነገድ፣ እና የዑዝኤላውያን ነገድ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገዶች የቀዓት ወገኖች ናቸው፡፡ 28 አንድ ወር እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው 8600 ወንዶች የያህዌ የሆኑ ነገሮችን ለመጠበቅ ተቆጠሩ፡፡ 29 የቀዓት ቤተሰብ ትውልዶች ከቤተ መቅደሱ በስተደቡብ አቅጣጫ ይስፈሩ፡፡ 30 የዑዝኤል ልጅ ኤሊሳፈን የቀዓታዊያንን ነገድ ይምራ፡፡ 31 እነርሱ ታቦቱን፣ ጠረጴዛውን፣ የመቅረዝ ማስቀመጫውን፣ መሰዊያዎቹን፣ ለአገልግሎታቸው የሚጠቀሙባቸውን ቅዱሳን ዕቃዎች፣ መጋረጃውን፣ እና በዚያ ዙሪያ ያለውን ስራ ሁሉ ይንከባከቡ፡፡ 32 የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ሌዋውያንን የሚመሩትን ሰዎች ይምሩ፡፡ እርሱ ቅዱሱን ስፍራ የሚንከባከቡትን ሰዎች ይቆጣጠር፡፡ 33 ሁለቱ ነገዶች ኮሜራሪ ነገድ የመጡ ናቸው፡ እነዚህም የሞሖላውያን ነገድ እና የሙሳያውያን ነገድ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገዶች የመጡት ከሜራሪ ነው፡፡ 34 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው 6200 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡ 35 የሜራሪን ነገድ የአቢካኤል ልጅ ሲሪኤል ይምራ፡፡ 36 እነርሱ የቤተመቅደሱን ጣውላዎች፣ መቀርቀሪያዎች፣ ምሰሶዎች፣ መሰረቶች፣ ሁሉንም መገልገያዎች፣ እና ከእነርሱ ጋር የተያያዙ ነገሮች ሁሉ፣ 37 መቅደሱ ዙሪያ የሚገኙ ምሰሶዎችና ቋሚዎችን ጨምሮ፣ ከማስገቢያዎቻቸው፣ ችካሎችና ገመዶች ጋር ይጠብቁ፡፡ 38 ሙሴ፣ አሮን እና ልጆቹ ከመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት፣ በፀሀይ ማውጫ ከቤተ መቅደሱ በስተ ምስራቅ ይስፈሩ፡፡ እነርሱ በቅድስተ ቅዱሳን ለሚከናወኑ ተግባራት እና ለእስራኤል ህዝብ ግዴታዎች ሀላፊነት አለባቸው፡፡ ማንኛውም ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ የሚቀርብ ባዕድ ይገደል፡፡ 39 ሙሴና አሮን ያህዌ እንዳዘዘው በሌዊ ነገዶች ውስጥ የሚገኙትን አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን ወንዶች ሁሉ ቆጠሩ፡፡ ሃያ ሁለት ሺህ ወንዶችን ቆጠሩ፡፡ 40 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አንድ ወር ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን በኩር የሆኑ የእስራኤል ወንዶች ቁጠር፡፡ ስሞቻቸውን ጻፍ፡፡ 41 በእስራኤል ህዝብ በኩር ምትክ ሌዋውያንን ለእኔ ውሰድ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ እንደዚሁም የሌዋውያንን ቀንድ ከብቶች፣ በመጀመሪያ በሚወለዱ የእስራኤላውያን የቀንድ ከብቶች ምትክ ውሰድ፡፡” 42 ያህዌ እንዳዘዘው ሙሴ የእስራኤልን ሰዎች በኩር በሙሉ ቆጠረ፡፡ 43 ዕድሜያቸው አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆኑትን በኩር ወንዶች ሁሉ በስም ቆጠረ፡፡ 22273 ወንዶችን ቆጠረ፡፡ 44 እንደገና፣ ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 45 “በእስራኤል ህዝብ በኩር ሁሉ ምትክ ሌዋውያንን ውሰድ፡፡ በህዝቡ የቀንድ ከብት ምትክ የሌዋውያንን ቀንድ ከብት ውሰድ፡፡ ሌዋውያን የእኔ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡ 46 ከሌዋውያን ቁጥር በላይ የሆኑትን 273 የእስራኤል በኩሮች ለመዋጀት ለእያንዳንዳቸው አምስት ሰቅሎች ተቀበል፡፡ 47 የቅድስተ ቅዱሳኑን ሰቅል እንደ መደበኛ ክብደት ተጠቀም፡፡ (አንድ ሰቅል አምሳ አምስት ግራም ነው) 48 ያገኘኸውን የመዋጆ ዋጋ ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፡፡” 49 ስለዚህም ሙሴ በሌዋውያን ከተዋጁት በላይ ቁጥራቸው ያለፈውን መዋጃ ክፍያ ሰበሰበ፡፡ 50 ሙሴ ከእስራኤል ሕዝብ በኩሮች ገንዘብ ሰበሰበ፡፡ በቤተ መቅደሱ ሚዛን መዝኖ 1365 ሰቅሎች ሰበሰበ፡፡ 51 ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ የመዋጃውን ገንዘብ ሰጣቸው፡፡ ሙሴ ያህዌ እንዲያደርግ የተናገረውን ሁሉ አደረገ፣ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡
እዚሀ ላይ ፀሐፊው “አሁን” የሚለውን ቃል የተጠቀመው አዲስ የታሪክ ዘገባን መናገር ሲጀምር ነው፡፡
“ናዳብ በኩር ነበር፡፡
እነዚህ የሰው ሥሞች ናቸው፡፡(ስሞችን እንዴት መተርጎም እንደሚገባ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴ የቀባቸውና የቀደሳቸው” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የእዚህን ሰዎች ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 3፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሞቱ”የሚለው ቃል በድንገት ሞቱ ለማለት ነው፡፡ “በእግዚአብሔር ፊት ድንገት ሞቱ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን መገኘት ነው፡፡ማለትም የሚከናወነውን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይመለከት ነበር ለማለት ነው፡፡“በእግዚአብሔር ህልውና ፊት” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እሣት”የሚለው ቃል “የሚቃጠል መሥዋዕት”የሚለውን ሃሣብ ለመግለፅ የዋለ ቃል ነው፡፡“እግዚአብሔር ያልተቀበለውን የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ነገድ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የነገዱን ሰዎች ነው፡፡“የሌዊን ነገድ ሰዎች አቅርብ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት በእነርሱ ምትክ ነገሮችን ተግባራዊ ማድረግ ማለት ነው፡፡
እዚህ ላይ “የእሥራኤል ነገዶች”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡“የእሥራኤልን ሕዝብ እርዱ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“ማካሄድ”የሚለው ቃል ትርጉም “ማገልገል” ማለት ነው፡፡“በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ አገልግሎትን በመሥጠት የእሥራኤልን ነገዶች ሊያግዟቸው ይገባል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“የመገናኛ ድንኳን ሥራ”
“አንተ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴን ነው፡፡
ይሄ በድጊጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሉ በሙሉ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እዚያ አጠገብ የሚደርስ ማንኛውንም እንግዳ ሰው መግደል አለባችሁ” ወይም “እዚያ አካባቢ የሚደርስ ሌላ ሰው ሞት ይጠብቀዋል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ፍቺ ግልፅ ሊደረግ ይችላል፡፡“ማንኛውም ወደ መገናኛ ድንኳኑ የሚቀርብ እንግዳ ሰው” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“አዳምጥ”ወይም “ለምነግርህ ነገር ትኩረት ስጥ”
“ሌዋውያንን መርጫለሁ”
እግዚአብሔር ወንድ የሆኑ ትውልዶችን እንዲቆጥር ሙሴን እያዘዘው ነው፡፡“ወንድ የሆኑትን ቁጠር” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን አንድ ላይ በመቀናጀት የቀረቡት እግዚአብሔርን ስለመታዘዙ አፅንዖት ለመስጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሌዊ ትውልዶች የሥም ዝርዝር ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ፀሐፊው “ሲወርድ ሲዋረድ”ሲል አገላለለፁ ልክ “እየመጡ” እንደሆነ ዓይነት ይመስላል፡፡“ሲወርድ ሲዋረድ የሚመጡ ነገዶች” “የጌድሶን ትውልድ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ፀሐፊው በእንቅስቃሴ ላይ ያሉ ይመስል የሚወርዱ ብሎ ይናገራል፡፡“እየተንቀሳቀሰ የሚመጣ ይመስል” ወይም “ከጌድሶን ወገን ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጡ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ሎቤናውያን” እና “ሰሜአውያን”በየትውልዳቸው ከአባቶቻቸው ቤቶች ሥም አንፃር የሚጠሩበት ሥም ነው፡፡ “ጌድሶናውያን” ከጌድሶን ትውልድ የመጡ ሰዎች ሥም ነው፡፡((ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ))
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴ ዕድሜያቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ቆጠረ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰባ አምስት መቶ”ወይም “ሰባት ሺህ አምስት መቶ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የሰው ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“በመገናኛ ድንኳኑ ደጃፍ ያለው መጋረጃ”
“ማለትም ማደሪያውንና መሠዊያውን የሚከብበው አደባባይ”
እነዚህ ከቀአት ወገን የሆኑ የነገዶች ሥም ዝርዝር ነው፡፡ (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴ 86,000 ሺህ ወንዶችን ቆጠረ”
“ሰማንያ ስድስት ሺህ”(ኦሪት ዘኁልቁን ይመልከቱ)
“አንድ ወር ከሞላው ጀምሮ ከዚያ በላይ”
እነዚህ ቁጥሮች ከቀአት ዝርያ ስለመጡት ነገዶች መረጃን ይሰጠናል፡፡“(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ካህናት ለአገልግሎታቸው የሚጠቀሙባቸው የተቀደሱ ዕቃዎች”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ከሜራሪ ዝርያ የመጡ የነገዶች ሥም ዝርዝር ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይቸላል፡፡“ሙሴ 6,200 ወንዶችን ቆጠረ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ወንዶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ትናንሽ እንጨቶችን አንድ ላይ በማድረግ የግድግዳዎች ወይም የበሮች የተወሰኑ ክፍሎች የሚሰሩበት ነው፡፡
እነዚህ ለሕንፃው ጥንካሬን የሚሰጡ ደጋፊ ርብራቦች ናቸው፡፡
ምሰሶ ከእንጨት የተሰራ ሆኖ ወደላይ ቀጥ ብሎ የሚቆምና ቤትን ለመደገፍ ጥቅም ላይ የሚውል ነገር ነው፡፡
መሰረቶች ምሰሶዎች በቦታቸው ላይ ፀንተው እንዲቆሙ የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው፡፡
ይሄ ማለት ርብራቦቹን፤ማቆሚያዎቹንና መሠረቶቹን ለማገናኘት የሚጠቅሙ ቁሣቁሶች ሁሉ ናቸው፡፡
እዚህ ላይ “ካስማዎቹ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ምሰሶዎቹንና አውታሮቹን ነው፡፡
እዚህ ላይ “የእርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሮንን ነው፡፡
ይሄ የመገናኛው ድንኳን የምሥራቅ አቅጣጫ ነው፡፡“ፀሐይ በሚወጣበት ምሥራቅ አቅጣጫ” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“መፈፀም”የሚለው አሕፅሮተ ሥም ሲሆን እንደ ሥም ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሥራዎችን ማከናወን” (አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ወደ መቅደሱ የሚጠጋውን እንግዳ ሰው ግደሉ”ወይም “ወደ መቅደሱ የሚጠጋ ማንኛውም ልዩ ሰው መገደል ይኖርበታል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“22,000 ሰዎች” ወይም ”22,000 ወንዶች“ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የሌዋውያንን እንስሳት ነው፡፡“የሌዋውያንን ከብቶች ሁሉ መውሰድ ይኖርብሃል፡፡”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“በኩር የሆኑትን ወንዶች ሁሉ”
“ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሶስት” ወንዶች“(ቀጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“መዋጀት”የሚለው ስም(ሰዋሰው) “መዋጀት”በሚለው ግሥ ሊተረጎም ይችላል፡፡“መዋጀት”(አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
“ሁለት መቶ ሰባ ሶስት የበኩር ልጆች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“የእሥራኤል ወንድ የበኩር ልጆች”
አንድ ሰቅል በግምት ከ11 ግራም ጋር የሚሰተካከል ነው፡፡“55 ግራም አካባቢ”(የመፅሐፍ ቅዱስ ሚዛንና የመፅሐፍ ቅዱስ ገንዘብ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት ከአጠቃላይ የሌዋውያን ቁጥር ይልቅ በእሥራኤል ውስጥ በሚገኙ ለሎች ነገዶች ውስጥ 273 ወንዶች አሉ ማለት ነው፡፡
ይሄ ማለት የሰቅሉ ሚዛን ቤተመቅደስ ውስጥ ከሚገኙት ጋር ተመሳሳይነት ሊኖረው ይገባል ማለት ነው፡፡“ለሰቅሉ ሚዛን መለኪያ የምታደርገው ቤተመቅደሱ ውስጥ ካለው ጋር በማስተያየት ነው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሃያ አቦሊ”አንድ አቦሊ ከ .57 ኪሎ ግራም ጋር ተመጣጣኝነት ያለው ነው፡፡(ቁጥሮች የሚለውንና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ገንዘብ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴ የሰበሰባቸውን ሰቅሎች ነው፡፡“ለመቤዣቸው የሰበሰብከው ገንዘብ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ “መቤዠት”የሚለው ስም(ሰዋሰው) “ተቤዠ”በሚል ሥም ሊተረጎም ይችላል፡፡“መቤዠት”(አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ ሺህ ሶስት መቶ ስድሣ አምስት ሰቅሎች”አንድ ሰቅል 11 ግራም አካባቢ ነው፡፡“ከላይ የተጠቀሱት የሰቅሎች ሚዛን 15 ኪሎ ግራም ብር አካባቢ ይሆናል”(ቁጥሮች የሚለውንና መፅሐፍ ቅዱሳዊ ገንዘብ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ሙሴ የሰበሰበውን ገንዘብ ነው፡፡
እዚህ ላይ “የእርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሮንን ነው፡፡
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ተቀናጅተው የተነገሩትም ለጉዳዩ አፅንኦት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “የእግዚአብሔር ቃል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለሙሴ የተናገረውን እግዚአብሔርን ነው፡፡(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንዲህ አላቸው፡፡ 2 “ከሌዋውያን መሃል የቀዓት ትውልዶችን ወንዶችን፣ በነገድ እና በየአባቶቸው ቤተሰቦች ቁጠሩ፡፡ 3 ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ወንዶች ሁሉ ቁጠሩ፡፡ እነዚህ ወንዶች በመገናኛው ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይምጡ፡፡ 4 የቀዓት ትውልድ በመገናኛው ድንኳን ለእኔ የተለዩትን እጅግ ቅዱስ የሆኑ ነገሮች ይጠብቁ፡፡ 5 ህዝቡ ጉዞውን ለመቀጠል ሲነሳ፣ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳን ውስጥ ይግቡ፣ ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳን የሚለየውን መጋረጃ ያውርዱት፣ ከዚያም የቃልኪዳኑን ታቦት ምስክር በእርሱ ይሸፍኑት፡፡ 6 ታቦቱን በአስቆጣ ቁርበት ይሸፍኑት፡፡ በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑት፡፡ ለመሸከም ምሰሶ ያስገቡበት፡፡ 7 በህብስት ማቅረቢያው ጠረጴዛ ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ያንጥፉበት፡፡ በላዩ ድስቶቹን፣ ማንኪያዎችን እና ለመቅጃ ገንቦ ያስቀምጡበት፡፡ 8 በጠረጴዛው ላይ ህብስት አይታጣ፡፤ በደማቅ ቀይ ጨርቅ እና እንደገና በአቆስጣ ቁርበት ይሸፍኗቸው፡፡ ጠረጴዛውን ለመሸከም ምሰሰዎች ያስገቡ፡፤ 9 ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው የመቅረዝ መያዣውን ይሸፍኑ፣ ከመብራቶቹ ጋር፣ መቆንጠጫ፣ ዝርግ ሰሃኖች፣ እና ለመብራቶቹ የዘይት ገንቦዎችን ይውሰዱ፡፡ 10 መቅረዞቹንና መገልገያዎቹን በአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ ውስጥ ያድርጉ፣ ከዚያም በመሸከሚያ መያዣ ላይ ያስቀምጡቱ፡፡ 11 በወርቅ መሰዊያው ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ያንጥፉ፡፤ እርሱንም በአቆስጣ ቁርበት ይሸፍኑት፣ ከዚያ መሸከሚያ ምሰሶ ያስገቡበት፡፡ 12 ዕቃዎቹን ሁሉ ለሥራ ወደተቀደሰው ስፍራ ይውሰዱና በሰማያዊ ጨርቅ ይጠቅልሉ፡፡ በአስቆጣ ቁርበት ሸፍነው ዕቃዎቹን በመሸከሚያ መያዣ ላይ ያስቀምጡ፡፡ 13 ከመሰዊያው አመዱን ያራግፉና ሐምራዊ ጨርቅ በመሰዊያው ላይ ያንጥፉ፡፡ 14 በመሰዊያው ላይ የሚጠቀሙባቸውን መሳሪያዎች ሁሉ በመሸከሚያው መሎጊያ ላይ ያስቀምጡ፡፡ እነዚህ ዕቃዎች፣ የእሳት ማንደጃዎች፣ ሜንጦዎች የእሳት መጫሪያዎች፣ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ እና ለመሰዊያው የሚያገለግሉ ሌሎች መሳሪያዎች ናቸው፡፡ መሰዊያውን የአስቆጣ ቁርበት ይሸፍኑትና ከዚያ መሸከሚያ ምሰሶ ያስገቡበት፡፡ 15 አሮንና ልጆቹ ቅዱሱን ስፍራና መገልገያዎቹን ሙሉ ለሙሉ ሸፍው ሲጨርሱ፣ እና ህዝቡ ወደፊት ሲንቀሳቀስ በዚያን ጊዜ የቀዓት ትውልዶች ቅዱሱን ስፍራ ለመሸከም ይቅረቡ፡፡ የተቀደሱ ዕቃዎችን ከነኩ ይገደሉ፡፡ የቀዓት ትውልዶች የሥራ ድርሻ በመገናኛው ድንኳን የሚገኙ መገልገያዎችን መሸከም ነው፡፡ 16 የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ለመብራት የሚሆነውን ዘይት ያዘጋጃል፡፡ የጣፋጩን እጣን ዝግጅት ይቆጣጠራል፣ መደበኛውን የእህል ቁርባን፣ የቅባት ዘይቱን፣ ጠቅላላውን ቤተ መቅደስ እና በውስቱ ያሉትን ሁሉ፣ እንዲሁም በቅዱስ መገልገያዎችና ቁሳቁሶች ላይ ሀላፊነት ይኖረዋል፡፡” 17 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ 18 “የቀዓት የጎሳ ነገዶች ከሌዋዊያን መሃል እንዲወገዱ አትፍቀዱ፡፡ 19 በህይወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እንዳይሞቱ ይህን በማድረግ ጠብቋቸው፡፡ እጅግ ወደ ተቀደሱ ነገሮች ሲቀርቡ 20ለአፍታ እንኳን የተቀደሰውን ስፍራ ለማየት ወደ ውስጥ አይግቡ፣ አሊያ ይሞታሉ፡፡ 20 አሮንና ልጆቹ ወደ ውስጥ ይግቡ፣ ከዚያ አሮንና ልጆቹ ለእያንዳንዱ ቀዓታዊ የሚሰራውን ሥራ ይስጡት፣ ለእያንዳንዳቸው የየራሳቸውን ተግባራት ይስጧቸው፡፡ 21 ያህዌ እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፣ 22 “ጌድሶናውያንንም በአባቶቻቸው ቤተሰቦች፣ በየነገዳቸው ቁጠራቸው፡፡ 23 ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠራቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ማገልገል የሚችሉትን ሁሉ ቁጠራቸው፡፡ 24 የጌድሶናውያን ነገዶች ሲያገለግሉና ሲሸከሙ ተግባራቸው ይህ ነው፡፡ 25 የመቅደሱን መጋረጃዎች ይሸከሙ፣ የመገናኛውን ድንኳን፣ መሸፈኛውን፣ በላዩ ላይ የሚገኘውን የአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ እና ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ የሚሆኑትን መገረጃዎች ይሸከሙ፡፡ 26 የአደባባዩን መጋረጃ ይሸከሙ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃ፣ በቤተ መቅደሱና በመሰዊያው አጠገብ ያሉትን፣ ገመዶቻቸውን፣ ለአገልግሎታቸው የሚጠቀሙባቸውን መሳሪያዎች ሁሉ ይሸከሙ፡፡ በእነዚህ ነገሮች መደረግ ያለበትን ሁሉ፣ እነርሱ ያድርግ፡፡ 27 አሮንና ልጆቹ የጌድሶናውያን ትውልዶች ማገልገል ያለባቸውን አገልግሎት ይምሯቸው፡፡ በሚያጓጉዟቸው ነገሮች ሁሉ፣ በሁሉም አገልግሎቶቻቸው ይምሯቸው፡፡ ያለባቸውን ሀላፊነቶች ሁሉ ትሰጧቸዋላችሁ፡፡ 28 ለመገናኛው ድንኳን የጌድሶናዊያን ነገድ ትውልዶች አገልግሎት ይህ ነው፡፡ የካህኑ የአሮን ልጅ ኢታምር በአገልግሎታቸው ይምራቸው፡፡ 29 የሜራሪ ትውልዶችን በነገዳቸው ቁጠራቸው፣ በአባቶቻቸው ቤተሰቦችም እዘዛቸው፣ 30 ከሰላሳ አመት እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠራቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የሚመጡትን ሁሉ ቁጠር፡፡ 31 በመገናኛው ድንኳን የሚሰጧቸው አገልግሎቶችና የሥራ ድርሻቸው ይህ ነው፡፡ ቤተ መቅደሱን ለማስጌጥ እንክብካቤ ያድርጉ፣ የድንኳኑን ወርዶችና ቋሚዎች እና ካስማዎች ይሸከማሉ፣ 32 በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ከሚገኙ ቋሚዎች ጋር፣ ችካሎቻቸውን፣ ካስማዎችን እና ገመዶቻቸውን ከተለያዩ መገልገያዎች ጋር ይሸከማሉ፡፡ መሸከም ያለባቸውን ቁሶች በስም ዘርዝር፡፡ 33 የሜራሪ ነገድ ትውልዶች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር መሪነት በመገናኛው ድንኳን የሚሰጡት አገልግሎት ይህ ነው፡፡” 34 የማህበሩ መሪ የሆኑት ሙሴና አሮን የቀዓታውያንን ትውልዶች በአባቶቻቸው ቤተሰቦች ነገዶች ቁጠሯቸው፡፡ 35 ሰላሳ አመት ዕድሜ የሞላቸውንና ከዚያ በላይ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቁጠሯቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የሚመጡትን ሁሉ ቁጠሯቸው፡፡ 36 በየነገዳቸው 2750 ወንዶች ቁጠሩ፡፡ 37 ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ቀዓታዊያንን ወንዶች ሁሉ በየነገዳቸውና በየቤተሰባቸው ቁጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡ 38 የጌድሶናውያን ትውልዶች በየነገዳቸው፣ በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ተቆጠሩ፣ 39 ዕድሜያቸው ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት የሆኑ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የመጡ እያንዳንዳቸው ተቆጠሩ፡፡ 40 በየነገዳቸው እና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የተቆጠሩት ወንዶች ቁጥር 2630 ነበሩ፡፡ 41 ሙሴና አሮን በመገናኛው ድኗን የሚያገለግሉትን የጌድሶናውያንን ነገዶች ትውልዶች ቆጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ፣ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡ 42 የሜራሪያውያን ትውልዶች፣ በየነገዳቸውና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ተቆጠሩ፣ 43 ዕድሜያቸው ከሰላሳ እስከ አምሳ የሆኑ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል የመጡ እያንዳንዳቸው ተቆጠሩ፡፡ 44 በየነገዳቸው እና በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የተቆጠሩት ወንዶች ቁጥር 3200 ነበሩ፡፡ 45 ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉትን የሜራሪ ትወልዶች የሆኑትን እነዚህን ወንዶች ሁሉ ቆጠሩ፡፡ ይህን በማድረግ፣ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲሰሩት ያዘዛቸውን አደረጉ፡፡ 46 ስለዚህም ሙሴ፣ አሮን፣ እና የእስራኤል መሪዎች ሁሉንም ሌዋውያን በየነገዳቸው በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች ቆጠሯቸው 47 ከሰላሳ እስከ አምሳ አመት ዕድሜ ያላቸውን ቆጠሯቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ ማገልገል የሚችሉትን፣ እና በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙ ዕቃዎችን መንከባከብና መሸከም የሚችሉትን እያንዳንዳቸውን ቆጠሯቸው፡፡ 48 በጠቅላላው 8580 ወንዶች ቆጠሩ፡፡ 49 በያህዌ ትዕዛዝ፣ ሙሴ እያንዳንዱን ወንድ ቆጠረ፣ እያንዳንዱን በተሰጠው የሥራ አይነት መሰረት ቆጠረ፡፡ እያንዳዱን ሰው በሚሸከመው ሀላፊነት አይነት ቆጠረ፡፡ ይህን በማድረግ ያህዌ በሙሴ በኩል ያዘዛቸውን በመስራት ያህዌ ያዘዘውን አደረጉ፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ከ30 እስከ 50 ዓመት ድረስ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ጉባዔ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እየሰሩ ያሉትን ሰዎች ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በተለየ ሁኔታ ለእኔ የመረጥኩትን”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ሠፈር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሠፈሩ ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ነው፡፡“ሰዎቹ ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ሰዎች ወደ ሌላ ሥፍራ መጓዛቸውን ነው፡፡“ወደ ሌላ ሥፍራ መጓዝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቅድስተ ቅዱሳኑን ከቅዱስ ቦታ የሚለየውን ነው፡፡
የመገናኛ ድንኳኑን እንዲሸከሙ ለማስቻል መሎጊያዎቹ ከመገናኛው ድንኳኑ ጎን በቀለበት ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡ይሄ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“መሎጊያዎቹን ከመገናኛ ድንኳኑ ጎን በሚገኙት ቀለበት ውስጥ አስገባቸው” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ሕብስቱ የእግዚአብሔርን ሕልውና የሚወክል ነው፡፡“የእግዚአብሔር የመገኘት ሕብስት” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“በእርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰማያዊውን መጎናፀፊያ ነው፡፡
የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ፍቺ የበለጠ ግልፅ ሊሆን ይችላል፡፡“ወጪቶችና” እና“ፅዋዎች”የመጠጥ ቁርባንን ለማቅረብ አገልግሎት ይሰጡ ነበር፡፡” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እነርሱን የሚለው ቃል ወጭቶቹን፤ጭልፋዎቹን፤ፅዋዎቹንና መቅጃዎቹን የሚያመለክት ነው፡፡
እንጀራ ዘወትር ሊኖር ይገባል፡፡
“ቀይ ልብስ”
ጠረጴዛውን መሸከም ይችሉ ዘንድ መሎጊያዎቹ በጠረጴዛው ጠርዞች ላይ በቀለበት ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋሉ፡፡ይሄ የበለጠ እንዲብራራ ማድረግ ይቻላል፡፡“መሎጊያዎቹን በጠረጴዛው ጠርዞች ላይ በቀለበት ውስጥ አስገቡት” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“በአስቆጣ ቁርበት..መሸፈን ይኖርባቸዋል”
“መሸከም ይችሉ ዘንድ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በመሸከሚያ ላይ ማድረግ ይኖርባቸዋል”
ጠረጴዛውን መሸከም ይችሉ ዘንድ መሎጊያዎቹ በመሠዊያው አጠገብ ባለው ሥፍራ ላይ በቀለበት ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋሉ፡፡“የመሸከሚያ መሎጊያዎቹን በመሠዊያው ጎን ባሉት ቀለበቶች ላይ አስገቧቸው፡፡” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ዕቃዎችን ለመሸከም እንዲቻል ከመሎጊያዎች የተሰራ አራት ማዕዘን እንጨት፡፡
“ሥራ”የሚለው ቃል አሕፅሮተ ሥም ሲሆን “ማገልገል” በሚለው ሥም ሊገለፅ የሚችል ነው፡፡“እግዚአብሔርን በመቅደስ ውስጥ በሚያገለግሉበት ወቅት ጥቅም ላይ የሚውል” (አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
“ሥራ”የሚለው ቃል (አሕፅሮተ ሥም ሲሆን “ማገልገል” በሚለው ሥም(ሰዋሰው) ሊገለፅ የሚችል ነው፡፡“ “በመሠዊያው ላይ አገልግሎት በሚካሄድበት ወቅት” (አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ))
መሠዊያውን መሸከም ይችሉ ዘንድ መሎጊያዎቹ በመሠዊያው አጠገብ በሚገኙት ቀለበቶች ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋሉ፡፡ይሄንን የበለጠ ማብራራት ይቻላል፡፡“የመሸከሚያ መሎጊያዎቹን በመሠዊያዎቹ ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገቧቸው” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ቤተመቅደሱ የሚያመለክተው አሮንና ልጆቹ በልብሶችና በቆዳዎች የሸፈኗቸውን ዕቃዎች ሁሉ ነው፡፡“የቤተመቅደሱን ዕቃዎች ሁሉ መሸከም” (ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሠፈር የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሠፈሩ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ነው፡፡“ሰዎች ወደፊት በሚጓዙበት ወቅት” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“የተቀደሰውን ዕቃ”
እዚህ ላይ “ብርሃን”የሚለው ቃል የሚያመለከተው “መብራትን”ነው፡፡“ለመብራቶቹ የሚያስፈልግ ዘይት” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“መጠበቅ” የሚለው አሕፅሮተ ሥም እንደ ሥም(ሰዋሰው) ሊገለፅ ይችላል፡፡“የሚጠብቁት ሰዎች” (አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የቀአትን የዘር ሐረግ ነው፡፡በኦሪት ዘኁልቁ 3፡27 ላይ ይሄንን እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ ሐረግ የሚያመለክተው የቀአታውያንን ሞት ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “ከሌዋውያን ወገን ፈፅሜ እንዳጠፋቸው ምክኒያት የሚሆኑትን ነገሮች የሚያደርጉትን ሁሉ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሐረግ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ቀጥሎ ስለሚናገረው ነገር ነው፡፡ሙሴ ቀአታውያን እንዳይጎዱ ለመከላከል ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ እንዳይገቡ ያግዳቸዋል፡፡
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ተቀናጅተው የቀረቡትም ለጉዳዩ አፅንኦት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡
ይሄ የሚያመለክተው ወንዶችን ብቻ ነው፡፡“የጌድሶን የወንድ ትውልዶች” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ከ30 ዓመት እስከ 50 ዓመት”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“የተሰባሰቡት“የሚለው ቃል የሚያመለክተው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለሥራ የቀሩትን ሰዎች ነው፡፡ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 4፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ ዓረፍተ ነገር የሚቀጥሉት ቁጥሮች ስለ ምን እንደሚናገሩ መግለጫ የሚሰጥ ነው፡፡
ይሄ የሚያመለክተው የጌድሶናውያንን ትውልድ ነው፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 3፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ በመገናኛው ድንኳኑ ላይ የሚደረግ የውጪ ሽፋን ነው፡፡“በዚያ ላይ የሚደረግ የአስቆጣ ቁርበት”ወይም “በአስቆጣ ቁርበት የሚሰራ የላይኛው መሸፈኛ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለእነዚህ ሥራዎች የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የጌድሶናውያን ትውልዶችን በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ እግዚአብሔርን እንዴት ማገልገል እንዳለባቸው ልትነግሯቸው ይገባል፡፡
እዚህ ላይ “አገልግሎት”በሥም ሊገለፅ የሚችል አሕፅሮተ ሥም ነው፡፡“ይሄ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር አሁንም እየተናገረ ስላለው ነገር ነው፡፡“የጌድሶናውያን ትውልዶች በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ የሚያገለግሉት እንደዚህ ነው”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ የሚያመለክተው ወንዶችን ብቻ ነው፡፡“የሜራሪ የወንድ ትውልዶች” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ስማቸውን ዘርዝር”
“የ30 ዓመት ዕድሜ…የ50 ዓመት ዕድሜ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“የተሰባሰቡት“የሚለው ቃል የሚያመለክተው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለሥራ የቀሩትን ሰዎች ነው፡፡ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 4፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ይሄ ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር ቀጥሎ ሊናገር ስላለው ነገር ነው፡፡
እዚህ ላይ “እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የአዳራሹን ምሰሶዎች ነው፡፡
እነዚህ ሁሉ የመገናኛ ድንኳኑ ክፈፎች ናቸው፡፡እነዚህን ክፍሎች ሁሉ እንዴት እንደተረጎማችኋቸው ተመልከቱ፡፡(ኦሪት ዘኁልቁ 4፡31-32 ይመልከቱ)
“መሸከም የሚገባውን ዕቃ በእያንዳንዱ ወንድ ስም መዝግቡት”
“እጅ በታች”የሚለው ቃል በሥም(ሰዋሰው) የሚገለፅ አሕፅሮተ ሥም ነው፡፡“በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ትዕዛዝ መሠረት” (አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ የሚያመለክተው ወንዶቹን ብቻ ነው፡፡“የቀአት የወንድ ትውልዶች”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የቀአትን ትውልዶች ነው፡፡ይሄንን በኦሪት ዘኁልቁ 43፡27 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“30 ዓመት…50 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “የሚገቡ”የሚለው ቃል ወንዶቹ “በራሳቸው ምርጫ” ያደረጉት ነገር ነው ማለቱ ሣይሆን እዚያ ስብስብ ውስጥ እንዲገቡ “መመደባቸውን”ነው የሚያሣየው፡፡“ማህበሩን እንዲቀላቀሉ የተመደቡት ሰዎች ሁሉ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ማህበር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለመሥራት የቀሩትን ሰዎች ነው፡፡ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 4፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ወንዶቹን ነው፡፡“የጌድሶን የወንድ ትውልዶች” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡“የጌድሶንን ትውልድ የቆጠሩት ሙሴና አሮን ናቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ከ30 እስከ 50 ዓመት ድረስ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “የሚገቡ”የሚለው ቃል ወንዶቹ “በራሳቸው ምርጫ” ያደረጉት ነገር ነው ማለቱ ሣይሆን እዚያ ስብስብ ውስጥ እንዲገቡ “መመደባቸውን”ነው የሚያሣየው፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ማህበሩን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለመሥራት የቀሩትን ሰዎች ነው፡፡ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 4፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴና አሮን በየወገናቸው የቆጠሯቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ”ይሄ የሚያመለክተው 2,630 ሰዎች መሆናቸውን ነው፡፡(ቁጥሮች የሚለውንና ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴንና አሮንን ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴና አሮን የሜራሪን ትውልዶች ቆጠሩ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ከ30 ዓመት ጀምሮ እስከ 50 ዓመት ድረስ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “የሚገቡ”የሚለው ቃል ወንዶቹ “በራሳቸው ምርጫ” ያደረጉት ነገር ነው ማለቱ ሣይሆን እዚያ ስብስብ ውስጥ እንዲገቡ “መመደባቸውን”ነው የሚያሣየው፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ስብስብ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ለመሥራት የቀሩትን ሰዎች ነው፡፡ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 4፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴና አሮን ከየነገዳቸው አንፃር የቆጠሯቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ተቆጠሩ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴንና አሮንን ነው፡፡
ይሄ የሚመለክተው ወንዶቹን ነው፡፡“ከሠላሳ እስከ ሃምሣ ዓመት ዕድሜ ላይ ያሉ ወንዶች”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሰማንያ ወንዶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔር እንዳዘዘው”
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ዓይነት ትርጉም ያላቸው ሲሆን ሙሴ ወንዶቹን እንዴት እንደቆጠራቸው አፅንኦት ለመስጠት ሲባል የተደረገ ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ከተመደበበት የሥራ ዓይነት አንፃር”ወይም “እያንዳንዱን ሰው ከመደበበት ሥራ አንፃር”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ያደርጋል”
እዚህ ላይ “እነርሱ” እና “የሰጣቸው”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴንና አሮንን ነው፡፡
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2 “የእስራኤል ሰዎች ተላላፊ የቆዳ በሽታ ያለበትን ሁሉ፣ በስቃይ የሚመግለውን ሁሉ፣ እና ማንኛውንም በድን በመንካት ረከሰውን ሁሉ ከሰፈር እንዲያስወጡ እዘዛቸው፡፡ 3 ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች እነዚህን ከሰፈር አስወጣቸው፡፡ እኔ በውስጡ እኖራለሁና ሰፈሩን አያርክሱ፡፡” 4 የእስራኤለ ሰዎችም ይህንኑ አደረጉ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከሰፈር አስወጧቸው፡፡ የእስራኤል ሰዎች ያህዌን ታዘዙ፡፡ 5 ያህዌ ሙሴን እንደገና እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 6 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፡፡ አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት አንዱ በሌላው ላይ በደል ሲፈጽም፣ እና ለእኔ ታማኝ ሳይሆን ሲቀር ያ ሰው በደለኛ ነው፡፡ 7 በዚህን ጊዜ በዳዩ ኃጢአቱን ይናዘዝ፡፡ በዳዩ የበደሉን ዋጋ ሙሉ ለሙሉ ይክፈል፣ ደግሞም አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይክፈል፡፡ ይህንን ለበደለው ይስጥ፡፡ 8 ነገር ግን ተበዳዩ ክፍያውን ለመቀበል የቅርብ ዘመድ ባይኖረው፣ በዳዩ የበደሉን ዋጋ ከአውራ በግ ጋር ለራሱ ማስተስረያ በካህኑ በኩል ለእኔ ይክፈል፡፡ 9 ከተቀደሱ ነገሮች ሁሉ የሚቀርቡ መስዋዕቶች ሁሉ፣ በእስራኤል ሰዎች ለእኔ የሚለዩ ነገሮች፣ የዚያ ካህን ይሆናሉ፡፡ 10 የእያንዳንዱ ሰው የተቀደሱ ነገሮች የካህኑ ይሆናሉ፡፡ አንድ ሰው ለካህኑ የሚሰጣቸው ማናቸውም ነገሮች የዚያ ካህን ይሆናሉ፡፡” 11 ያህዌ እንደገና ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 12 “ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ እንዲህ በላቸው፣ “ምናልባት የአንድ ሰው ሚስት ወደ ሌላ ሰው ሄዳ በባሏ ላይ ኃጢአት ሰርታ ይሆናል፡፡ 13 ከባሏ ሌላ ሰው ከእርሷ ጋር ተኝቶ ይሆናል፡፡ በዚያ ሁኔታ፣ እርሷ ረክሳለች፡፡ ምንም እንኳን ባሏ ነገሩን ባያይም ወይም ስለነገሩ ባያውቅም፣ ደግሞም ድርጊቱን ስትፈጽም ማንም ባይዛትም፣ በእርሷ ላይ የሚያረጋግጥ ማንም ባይኖርም፣ 14 የሆነ ሆኖ፣ የቅናት መንፈስ ሚስቱ እንደ ረከሰች ለባልየው ይነግረው ይሆናል፡፡ ሆኖም፣ ሚስቱ ሳትረክስ የቅናት መንፈስ በሀሰት በሰውየው ላይ መጥቶ ይሆናል፡፡ 15 በዚህ ሁኔታ፣ ሰውየው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፡፡ ባልየው የመጠጥ ቁርባን ለእርሷ ያምጣ፡፡ የኢፍ አንድ አስረኛ የገብስ ዱቄት ያምጣ፡፡ ስለ ቅናት የሚቀርብ የእህል ቁርባን ነውና፣ምንም ዘይት ወይም እጣን አይጨምርበት፤ ምናልባት ተፈጽሞ ሊሆን ለሚችል ኃጢአት ጠቋሚ የእህል ቁርባን ነው፡፡ 16 ካህኑ ያምጣትና በያህዌ ፊት ያቁማት፡፡ 17 ካህኑ አንድ ገንቦ ቅዱስ ውሃና ከማደሪያ ድንኳኑ ወለል አፈር ይውሰድ፡፡ አፈሩን ውሃው ውስጥ ይጨምረው፡፡ 18 ካህኑ ሴትየዋን በያህዌ ፊት ያቁማት የሴትየዋን ጸጉርም ይግለጥ፡፡ ካህኑ የቅናት መስዋእት የሆነውን የእህል ቁርባን በእጇ ያስይዛታል፡፡ ካህኑ በሴትየዋ ላይ እርግማን ሊያስከትል የሚችለውን በውስጡ አቧራ ያለበትን መራራ ውሃ በእጆቹ ይያዝ፡፡ 19 ካህኑ ሴትየዋን ያስሞላት፤ እንደህም ይበላት፣ “ማንም ሰው ከአንቺ ጋር ተኝቶ ካልሆነ፣ እና ተሳስተሸ ካልሆነ እናም እርኩሰት ካልፈጸምሽ፣ እርግማን ከሚያጣው ከዚህ መራራ ውሃ በእርግጥ ነፃ ትሆኛለሽ፡፡ 20 ነገር ግን፣ አንቺ በባልሽ ስር ያለሽ ሴት፣ ተሳስተሸ ቢሆን፣ ረክሰሽ ቢሆን፣ እና ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር ተኝቶ ቢሆን፣ 21 ከዚያ፣ (ካህኑ በእርሷ ላይ ዕርግማን የሚያስከትል መሃላ ያስምላታል፣ ከዚያ በኋላ ሴትየዋን እንዲህ ማለቱን ይቀጥል) ‘ያህዌ ህን ማድረግሽን ለህዝብሽ በመርገምሽ ያሳያል፡፡ ያህዌ ጭንሽን ካሰለለና ሆድሽን ካሳበጠ ይህ ይታወቅ፡፡ 22 ዕርግማኑን የሚያጣው ይህ ውሃ ወደ ሆድሽ ይገባል፣ ሆድሽን ያሳብጣል፣ እንዲሁም ጭኖችሽን ያሰልላል፡፡” ሴትየዋ እንዲህ ብላ ትመልስ፣ “አሜን፣ በደለኛ ከሆንኩ ይህ በእኔ ላይ ይሁን፡፡” 23 ካህኑ እነዚህን ዕርግማኖች በጥቅል ብራና ላይ ይጻፍ፣ ከዚያ የተጻፉትን እርግማኖች በመራራው ውሃ አጥቦ ያስለቅቅ፡፡ 24 ካህኑ ዕርግማን የሚያመጣውን መራራ ውሃ እንድትጠጣ ያድርግ፡፡ ዕርግማኑን የሚያመጣው ውሃ ወደ ውስጧ ገብቶ መራራ ይሆናል፡፡ 25 የቅናት መስዋዕቱን የእህል ቁርባን ከሴትየዋ እጅ ይቀበል፡፡ የእህል ቁርባኑን በያህዌ ፊት ወደ መሰዊያው ያምጣው፡፡ 26 ካህኑ ከእህል ቁርባኑ እፍኝ ሙሉ ዘግኖ ይውሰድና በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ከዚያ ለሴትየዋ መራራውን ውሃ እንድትጠጣው ይስጣት፡፡ 27 ውሃውን እንድትጠጣው ሲሰጣት በባሏ ላይ በደል በመፈፀም ረክሳ ከሆነ፣ ዕርግማን የሚያስከትለው ውሃ ወደ ውስጧ ይገባና መራራ ይሆናል፡፡ ሆዷ ያብጣል ጭኗ ይመነምናል፡፡ ሴትየዋ ከህዝቧ መሃል የተረገመች ትሆናለች፡፡ 28 ሴትየዋ የረከሰች ካልሆነችና ንጹህ ከሆነች፣ ነጻ ትሆናለች፡፡ ልጆችን መጸነስ ትችላለች፡፡ 29 የቅናት ህግ ይህ ነው፡፡ ከባሏ ውጭ ለሄደች እና ለረከሰች ሴት ህጉ ይህ ነው፡፡ 30 የቅናት መንፈስ ለያዘውና በሚስቱ ለቀና ሰው ህጉ ይህ ነው፡፡ ሴትየዋን በያህዌ ፊት ያምጣ፣ ካህኑም ይህ የቅናት ህግ የሚገልጸውን ሁሉ በእርሷ ላይ ያድርግ፡፡ 31 ሰውየው ሚስቱን ወደ ካህን በማቅረቡ ከበደል ነጻ ይሆናለ፡፡ ሴትየዋ በድላ ከሆነ ማናቸውንም በደል ትሸከማለች፡፡”
ይሄ የሚያመለክተው ቆዳን ለበሽታ የሚዳርገውንና ወደ ሌሎች ሰዎች በፍጥነት የሚዛመተውን የቆዳ በሽታ ነው፡፡
ይሄ የሚያመለከተው ከተከፈተ ነገር ውስጥ የሚወጣን ፈሳሽ ነው፡፡
አንድ ሰው ሬሣ የሚነካ ከሆነ እንደረከሰ ነበር የሚቆጠረው፡፡የእግዚአብሔርን ዓላማ ለማስፈፀም ተቀባይነት የሌለው ሰው አካሉ ንፁህ እንዳልሆነ ተደርጎ ነው የሚገለፀው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር በመሆኑ የእሥራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ነው፡፡
ይሄ ማለት የረከሱትን ሰዎች አስወጧቸው ማለት ነው፡፡የዚህ ሙሉ ሃሣቡ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የእሥራኤል ሰዎች የረከሱትን ሰዎች ከሠፈራቸው ውጪ እንዲወጡ አደረጓቸው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰዎች እርስ በእርስ የሚያደርጓቸው ማንኛውም ዓይነት ኃጢአቶች”
አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ ኃጢአትን ቢሰራ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፀ ስለሚቆጠር እግዚአብሔር ይሄንን ሰው ታማኝ እንዳልሆነ ሰው ይቆጥረዋል ማለት ነው፡፡“እኔንም በድለዋል”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
አብዛኛውን ጊዜ የተበደለው ሰው ገንዘቡን የሚወስድ ቢሆንም ሰውዬው በሕይወት ከሌለ ግን የገንዘቡ ክፍያ ለቅርብ ዘመዱ እንዲተላለፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብረራ ይችላል፡፡“የተበደለው ሰው በሕይወት ከሌለና ገንዘቡን የሚቀበልለት የቅርብ ዘመድ የማይኖረው ከሆነ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀት ወይም የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ጥፋተኛ የተባለው ሰው የበደለ ከሆነ”
አንድ ሰው በበደለው በደል ምክኒያት ገንዘቡን ለካህኑ የሚሰጥ ከሆነ ለእግዚአብሔር እንደሰጠ ነው የሚቆጠረው፡፡
ማስተሰረያ የሚደረገው ለሰውዬው ኃጢአት ነው፡፡እዚህ ላይ እግዚአብሔር እያመለከተ ያለው ኃጢአቱን የፈፀመውን ሰው ነው፡፡“ለኃጢአቱ ማስተሰረያ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእሥራኤል ሰዎች የተቀደሰውን ነገር ለይተው ወደ ካህኑ የሚያመጧቸው”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን አንድ ላይ ሆነው እንዲቀርቡ የተፈለገበት ምክኒያት አንድ ሰው የሚሰጠው የተቀደሰ ነገር ለተሰጠው ለዚያ ካህን እንደሆነ አፅንኦት ለመሥጠት ተፈልጎ ነው፡፡(ተመሣሣይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በመሠረቱ ሊሆን የሚችል ነገር ነው፡፡
ካህኑ “በእግዚአብሔር ፊት” መሠዊያው አጠገብ ያመጣታል፡፡“በመሠዊያው አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ያስቀምጣታል” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“በእግዚአብሔር ሕልውና ፊት”
ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 5፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“የራስን መንገድ መከተል” ምሣሌያዊ አነጋገር ሲሆን “ታማኝ አለመሆን”ማለት ነው፡፡ “ለባለቤትሽ ታማኝ ካልሆንሽ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ኃጢአትን በመፈፀም” ይሄ ሐረግ የሚያመለክተው “ዝሙትን ስለመፈፀም ነው”
ከሆነ ነገር “ነፃ ትሆናላችሁ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በእርሱ አለመጎዳትን ነው፡፡“ሊጎዳችሁ የሚችል ውኃ ለጉዳት አይሰጣችሁም”(ምሣሌያዊ አነጋገርን የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ መራራው ውኃ መርገምን ሊያመጣ እንደሚችል ተደርጎ ተገልጿል፡፡ይሄ ማለት አንዲት ሴት ኃጢአተኛ ከሆነች ውኃውን በምትጠጣበት ወቅት ልጅ እንዳትወልድ ምክኒያት ይሆንባታል ማለት ነው፡፡“ይሄ መራራ ውኃ መርገም ሊሆንብህ ይችላል”(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሐረግ የሚያመለክተው በባሏ ሥልጣን ሥር መሆኗን ነው፡፡“በባሏ ሥልጣን ሥር” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“የራስን መንገድ መከተል”የሚለው ሐረግ ምሣሌያዊ አነጋገር ሲሆን “ታማኝ አለመሆን”ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሣችሁን አርክሳችኋል” (ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“መርገምን ሊያወርድ”የሚለው ቃል ምሣሌያዊ አነጋገር ሲሆን በላይዋ ላይ መርገም ይመጣል የሚል ፍቺ ያለው ነው፡፡“በላይዋ ላይ መርገም እንዲመጣ ሊያደርግ የሚችል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ፀሐፊው የሚናገረው ሌሎች ሰዎች እንዲረግሟት መንስኤ የሚሆነውን እግዚአብሔር ለሴትዬዋ የሚሰጣትን መርገም በተመለከተ ልክ ሴትዬዋ ራስዋ መርገም እንደሆነች አድርጎ ነው የሚገልፀው፡፡“እግዚአብሔር የረገመሽ በመሆኑ ሌሎች ሰዎችም ይረግሙሻል፡፡እግዚአብሔርም በእውነት ስለመረገምሽ ሰዎች እንዲመለከቱ ያደርጋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”ይህንን ለሕዝብሽ እንደ እርግማን ያሣየዋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡1)ሴትዬዋ ልጅ ለመውለድ አትችልም 2)እርግዝናው የሚጨናገፍ በመሆኑ ሕፃኑ ልጅ በሕይወት አይኖርም፡፡
እዚህ ላይ “ጭን” የሚለው ቃል የሴትን ማሕፀን ወይም ሌላ የሰውነት አካሏን ለመጥራት የተጠቀሙበት ጨዋ የሆነ አገላለፅ ነው፡፡“ማሕፀንሽ ጥቅም የማይሰጥ ይሆናል”(ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት ቀለሙን ከብራናው ላይ ያጥበዋል ማለት ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልከ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የፃፋቸው መርገሞች”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ቁጥር 24 በአጠቃላይ የሚገልፀው ካህኑ ምን ማድረግ እንዳለበትና ሴትዬዋ ውኃውን በምትጠጣበት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን ነገር አስመልክቶ ነው፡፡ቁጥር 25 እና 26 ካህኑ ይህንን ሥራ እንዴት ማከናወን እንደሚኖርበት በዝርዝር ያብራራል፡፡ካህኑ ውኃውን ለሴትዬዋ ከሰጣት በኋላ የምትጠጣው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
አንድ እፍኝ እህል አጠቃላዩን የእህል ቁርባን ይወክላል፡፡ይሄ ማለት በጠቃላይ ቁርባኑ ለእግዚአብሔር ይሆናል ማለት ነው፡፡
“የቅንአት የእህል ቁርባን”ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 5፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “ድርጊቱን ከመፈፀሟ የተነሣ የረከሰች ከሆነ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ኃጢአት”የሚያመለክተው በተለይ ዝሙት መፈፀምን ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ዝሙትን ሠርታለች” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1)ሴትዬዋ ልጅ ለመውለድ አትችልም 2)የሴትዋ ፅንስ ስለሚጨናገፍ ሕፃኑ ልጅ በሕይወት አይኖርም፡፡እዚህ ላይ “ጭን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሴትን ማሕፀን ወይም የአካሏን ክፍል ነው፡፡(ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ) ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 5፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሕዝቧ ይረግማታል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አላረከሳትም”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ጥፋተኛ አለመሆን” “ንፁህ መሆን” በሚል ቃል ይገለፃል፡፡ (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1)“ከዚያ በኋላ የተረገመች አትሆንም”2)“ከዚያ በኋላ ከመርገም ነፃ ትሆናለች”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ታረግዛለች”
“ቅንአትን የሚዳኝ ሕግ”
“መሸሽ”የሚለው ቃል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙም “ታማኝ አለመሆን”ማለት ነው፡፡“ለባልዋ ታማኝ ያልሆነች”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራስዋን ታረክሳለች”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የሰውን የቅንአት አስተሳሰብና ስሜቶችን ነው፡ይህንን በዘኁልቁ 5፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡“ቅንአት ያለበት ሰው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ሚስቱ ከሌላ ሰው ጋር በመተኛት ታማኝ አለመሆኗን መጠርጠር ማለት ነው፡፡“ሚስቱ ለእርሱ ታማኝ እንዳልሆነች ይጠረጥራል” ወይም “ከሌላ ሰው ጋር እንደተኛች ይጠረጥራል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“በእግዚአብሔር ህልውና ፊት”
“ሚስቱን ወደ ካህኑ በማምጣቱ የተሳሳተ ነገር እንደፈፀመ ሰው በደለኛ አይባልም ”
“መከራውን መቋቋም ያስፈልጋል”
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ እንዲህ በላቸው፣ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ናዝራዊ ሆኖ ራሱን ለያህዌ በተለየ ስዕለት ሲለይ፣ 3 ከወይንና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፡፡ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የተሰራ ኮምጣጤ አይጠጣ፡፡ ማናቸውንም የወይን ጭማቂ አይጠጣ ወይም የወይን ፍሬ ወይም ዘቢብ አይብላ፡፡ 4 ለእኔ በተለየባቸው ቀናት ሁሉ፣ ከፍሬያቸው ግልፋፊ የተሰራ ማናቸውንም ነገር ጨምሮ ከወይን የተሰራ ምንም ነገር አይብላ፡፡ 5 ለያህዌ ራሱን የለየባቸው ቀናት እስኪያበቁ ድረስ በስለቱ ጊዜያት ሁሉ ራሱን ምላጭ አይንካው፡፡ ለያህዌ የተለየ ይሁን፡፡ ፀጉሩ በራሱ ላይ እንዲያድግ ይተወው፡፡ 6 ራሱን ለያህዌ በለየባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ ወደ ሞተ ሰው አይቅረብ፡፡ 7 አባቱ፣ እናቱ፣ ወንድሙ ወይም እህቱ ቢሞቱ እንኳን ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡ ይህም የሚሆነው ማንም ሰው በረጅም ጠጉሩ እንደሚመለከተው፣ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው፡፡ 8 በተለየበት ጊዜ ሁሉ ለያህዌ የተለየ ቅዱስ ነው፡፡ 9 አንድ ሰው ድንገት አጠገቡ ቢሞት እና ማንነቱን የለየበትን ፀጉሩን ቢያረክስበት፣ መንጻት ባለበት ከሰባተኛው ቀን በኋላ ራሱን ይላጭ፡፡ ራሱን መላጨት ያለበት በዚያን ጊዜ ነው፡፡ 10 በስምተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ያቅርብ፡፡ 11 ካህኑ አንዱን ወፍ ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን የሚቃተል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ሬሳ አጠገብ በመሆን ኃጢአት ሰርቷልና እነዚህ ለእርሱ ስርየት ይቀርባሉ፡፡ በዚያው ዕለት ራሱን መልሶ ለያህዌ ይስጥ፡፡ 12 ለተለየበት ጊዜ ራሱን ለያህዌ መልሶ ይስጥ፡፡ ለበደል መስዋዕት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት ያምጣ፡፡ ራሱን ከማርከሱ በፊት የነበሩ ቀናት አይቆጠሩም፣ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ተለይቶ ባለበት ጊዜ ረክሷል፡፡ 13 ናዝራዊ መለየቱ ስለሚያበቃበት ጊዜ የተሰጠው ህግ ይህ ነው፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያምጡት፡፡ 14 መስዋዕቱን ለያህዌ ያቅርቡ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ለህብረት መስዋዕት ነውር የሌለበት አውራ በግ ያምጣ፡፡ 15 እንደዚሁም እርሾ ያልገባበት አንድ መሶብ ዳቦ፣ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ዳቦዎች፣ በዘይት የተቀባ እርሾ የሌለበት የገብስ ቂጣ፣ ከእህል ቁርባንና ከመጠጥ መስዋዕቶች ጋር ያምጣ፡፡ 16 ካህኑ እነዚህን በያህዌ ፊት ያቅርባቸው፡፡ እርሱ የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ያቅርብ፡፡ 17 ለያህዌ የህብረት መስዋዕቱን፣ እርሾ ካልገባበት ከመሶቡ ዳቦ ጋር፣ አውራ በጉን መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ እንዲሁም ካህኑ የእህል ቁርባኑን እና የመጠጥ መስዋዕቱን ጭምር ያቅርብ፡፡ 18 ናዝራዊው ለእግዚአብሔር መለየቱን የሚያሳየውን ፀጉሩን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጭ፡፡ ፀጉሩን ከራሱ ወስዶ የህብረት መስዋዕቶቹ በሚቀርቡበት በሚነደው እሳት ውስጥ ይጨምረው፡፡ 19 ካህኑ የተቀቀለውን አውራ በግ ወርች፣ ከመሶቡ ውስጥ እርሾ ያልገባበትን አንድ ዳቦ፣ እና አንድ እርሾ ያልገባበት የገብስ ቂጣ ይውሰድ፡፡ ናዝራዊው መለየቱን የሚያሳየውን ጸጉሩን ከተላጨ በኋላ ካህኑ እነዚህን በእጆቹ ያስይዘው፡፡ 20 ካህኑ እነዚህን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ከፍ አድርጎ ያንሳቸውና ለእርሱ ያቅርባቸው፡፡ ይህ ከፍ ተደርጎ ከተነሳው ፍርምባና ከቀረበው ወርች ጋር ለካህኑ ተለየ ቅዱስ ምግብ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል፡፡ 21 ለያህዌ ለመለየት ስዕለቱን ያቀረበ ናዝራዊ ህጉ ይህ ነው፡፡ ማናቸውንም ሌሎች ነገሮች ቢሰጥ በናዝራዊነት ህግ መሠረት እንዲጠብቃቸው የተሰጡትን ቃል ኪዳኖች ለመጠበቅ የገባውን የስዕለት ግዴታዎች መጠበቅ አለበት፡፡” 22 ያህዌ እንደገና ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 23 “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፣ ‘የእስራኤልን ሰዎች በዚህ መንገድ ባርኳቸው፡፡ እንደዚህ በሏቸው፣ 24 “ያህዌ ይባርችሁ ይጠብቃችሁ፡፡ 25 ያህዌ ብርሃኑን በእናንተ ላይ ያብራራ ፊቱን ይመልስላችሁ፣ ይራራላች፡፡ 26 ያህዌ በሞገስ ያጥግባችሁ፣ ሰላምንም ይስጣችሁ፡፡’” 27 ለእስራኤል ሕዝብ ስሜን የሚያስተዋውቁት በዚህ መንገድ ነው፡፡ እኔም እባርካቸዋለሁ፡፡”
“ራስን ለሆነ ሰው መለየት”ማለት ለዚያ ሰው “ራስን መስጠት”ማለት ነው፡፡“ይሰጣል…ራሱን ይሰጣል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህ ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉም ሊጠጣቸው ወይም ሊበላቸው አይገባም ማለት ነው፡፡“መውሰድ አይገባውም”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ከወይን የሚሰሩት ሆምጣጤ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት ወይንና ሌላ ጠንካራ መጠጦች ለብዙ ጊዜ እንዲፈሉ ከተደረገ በኋላ መራራ የሚሆነው መጠጥ ነው፡፡
ግልፅ የተደረገውን መረጃ የበለጠ ልታብራሩት ትችላላችሁ፡፡ “ወይም ሰዎች ከጠንካራ መጠጥ የሚሰሩት ሆምጣጤ”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
የደረቁ ወይኖች
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን ለእኔ የተለየ ያደርጋል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ከወይን የማይሰሯቸው ነገሮች”(ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡)
እነዚህ ሁለት ፅንፍ የያዙ ነገሮች የቀረቡት በአጠቃላይ የወይን ፍሬ መበላት እንደሌለበት አፅንዖት ለመስጠት ነው፡፡“ከየትኛውም የወይን ክፍል” (ሆን ብሎ አጋኖ መናገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“መለየት”ማለት“ራስን መስጠት”ማለት ነው፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ማንም ሰው ቢሆን በራሱ ላይ ምላጭ መጠቀም የለበትም”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“መለየት” የሚለው ቃል አሕፅሮተ ሥም ሲሆን በግሥ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡እዚህ ላይ “መለየት”ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን “ለአንድ ነገር ራስን መስጠት ማለት ነው”“ራሱን ለእግዚአብሔር የለየበት ወራት”ወይም “ራሱን ለእግዚአብሔር የሰጠበት ወራት”(አሕፅሮተ ሥምንና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለእግዚአብሔር የሚለይበት ወራት የመጠናቀቂያ ጊዜ አለው ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን ለእግዚአብሔር መለየት አለበት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “መለየት”ማለት“ራስን መሥጠት”ማለት ነው፡፡“ራሱን ይሰጣል..ራሱን ሰጥቷል…ራስን መሥጠት”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔር ዓላማዎች ተቀባይነት የሌለው ሰው ልክ አካሉ ንፁህ እንዳልሆነ ዓይነት ተደርጎ ነው የሚገለፀው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን ለይቷል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“መለየት” የሚለው አሕፅሮተ ሥም በግሥ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን የለየ በመሆኑ”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን ለእግዚአብሔር አውሏል” ወይም “ራሱን ለእግዚአብሔር ለይቷል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ራስ”የሚለው ቃል የሚወክለው መሐላውን በተምሣሌትነት የሚገልፀውን የናዝራዊ ሰውን ፀጉር ነው፡፡“ለእግዚአብሔር የተለየ መሆኑን ለሰዎች ሁሉ የሚያሳየውን ረዥሙን ፀጉር ይላጨዋል”ወይም “ራሱን ተላጨ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“መንፃት”የሚለው አሕፅሮተ ሥም እንደ ግሥ ሐረግ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን ለእግዚአብሔር በለየበት ወቅት”(አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
“ቀን 7”(ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“ቀን 8” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“ራሱን እንደገና ሊለይ ባለበት ቀናት”
ሰውዬው ለመሥዋዕት ይቀርብ ዘንድ ጠቦቱን ወደ ካህኑ ማምጣት ይኖርበታል፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ትርጉም የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ለበደል መሥዋዕት ይሆን ዘንድ የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ወደ ካህኑ ማምጣት ይኖርበታል፡፡”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን ከመላጨቱ በፊት የነበሩት ቀናት የማይቆጠሩ ይሆናሉ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን አረከሰ”ወይም “ራሱን ተቀባይነት እንዳይኖረው አደረገ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “መለየት”ማለት “መሰጠት”ማለት ነው፡፡ይሄ አሕፅሮተ ሥም በግሥ መልክም ሊገለፅ ይችላል፡፡ “መሠጠቱ”ወይም “ራሱን መሥጠቱ”ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንና አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንድ ሰው ሊያቀርበው ይገባል”ወይም “መቅረብ ይኖርበታል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ቁርባኑን ወደ ካህኑ ማምጣት ይኖርበታል፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ፍቺ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“በካህኑ አማካይነት መሥዋዕት ይሆን ዘንድ መሥዋዕቱን ለካህኑ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡”ወይም “ቁርባኑን ለእግዚአብሔር ካቀረበ በኋላ ካህኑ ይሰዋዋል፡፡”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ያለ እርሾ ያዘጋጀው ቂጣ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዘይት የለወሰው መልካም ዱቄት” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እርሾ የሌለው ቂጣ ሆኖ በዘይት የተለወሰ“(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የተቆራረጡ ጠፍጣፋ ቂጣዎች
“የእነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ናዝራዊ ሰው እንዲያመጣ የተጠየቀውን ቁርባን ነው፡፡አብዛኛውን ጊዜ የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ከሌሎች የመሥዋዕት ዓይነቶች ጋር እንዲቀርቡ ይጠየቁ ነበር፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ፍቺ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ከሌሎች የመሥዋዕት ዓይነቶች ጋር እንዲቀርቡ እግዚአብሔር የሚጠይቀው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ካህኑን ሲሆን “የእርሱ”የሚለው ቃል ደግሞ መሐላውን ያደረገውን ሰው ነው፡፡
“እንደ ሕብረት መፍጠሪያ መሥዋዕት”
ግንዛቤ የተገኘበትን መረጃ የበለጠ ልታብራራሩት ትችላላችሁ፡፡“ካህኑ የመጠጥ ቁርባኑን ….ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይኖርበታል”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “መለየት”ማለት “መሠጠት”ማለት ነው፡፡አሕፅሮተ ሥሙ በግሥ መልክ ሊፃፍ ይችላል፡፡“መሠጠቱን የማሣወቅ”ወይም “ራሱን እንዴት እንደሰጠ ለማሣወቅ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንና አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ እንግዲህ አውራውን በግ ቀቅሎታል ማለት ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የቀቀለው የአውራ በጉ ወርች”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “መለየት”ማለት “ራስን መሥጠት” ማለት ነው፡፡ይሄ አሕፅሮተ ሥም “ተለየ” በሚል ግሥ መገለፅ ይችላል፡፡“ራሱን መሥጠቱን ማመልከት”ወይም “ራሱን ለእግዚአብሔር መሥጠቱን ማሣወቅ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንና አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
ዕቃዎቹን ለናዝራዊው ከሰጠው በኋላ ካህኑ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ እንደገና ከእርሱ ይቀበላቸዋል፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ከዚያ በኋላ ካህኑ እንደገና ወስዶ ሊወዘውዛቸው ይገባል”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“እርሱንም ጭምር”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ካህኑ የወዘወዘው”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እርሱ ያቀረበውን”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “መለየት”ማለት “መሠጠት”ማለት ነው፡፡አሕፅሮት ስሙ በግሥ መልክ ሊፃፍ ይችላል፡፡“የእርሱ መሠጠት”ወይም “ራሱን ለእግዚአብሔር መለየቱ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንና አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው አንድ ናዝራዊ የሆነ ሰው እንዲሰጥ ከታዘዘው በላይ ለመሥጠት መወሰኑን ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ተጨማሪ የሚያቀርበው ቁርባን የሚኖር ከሆነ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“የተሳላቸውን የስእለት መሥፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል”
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሣሣይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን አንድ ላይ እንዲቀናጁ የተደረገው መታዘዝ እንደሚኖርበት አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የናዝራዊ ሕግ የሚያመለክተው”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እናንተ”የሚለው የብዙ ቁጥር ነው፡፡(እናንተ በሚል በተለያዩ መልኮች የተገለፁትን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“መጠበቅ”ማለት“መከላከል”ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ለሆነ ሰው በጎ አስተሳሰብ አለው ማለት ነው፡፡በፈገግታም ሊገለፅ ይችላል፡፡አሕፅሮት ስሙ በግሥ መልክ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ፈገግ ሲልልህ”ወይም“ወደ አንተ በቅንነት ሲመለከት”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ይመልከትህ”የሚለው ቃል በዚያ ሰው ላይ በጎ የሆነ አስተያያት እንዳለው የሚገልፅ ነው፡፡“አደላልህ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “አንተ”የሚለው ቃል ነጠላ ነው፡፡(አንተ በሚል በተለያዩ መልኮች የተገለፁትን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ እግዚአብሔር “ስሜን”ሰጥቻለሁ ብሎ በመናገሩ እሥራኤላውያን የራሱ እንደሆኑ ያውጃል፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ የእኔ መሆናቸውን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
1 ማደሪያ ድንኳኑን በጨረሰ ቀን፣ ከመገልገያ ዕቃዎቹ ጋር ቀብቶ ለያህዌ ለየው፡፡ በመሰዊያውና በዕቃዎቹ ላይ እንዲሁ አደረገ፡፡ ቀብቶ ለያህዌ ለያቸው፡፡ 2 በዚያ ቀን፣ የእስራኤል መሪዎች፣ የአባቶቻቸው ቤተሰቦች አባቶች መስዋዕቶችን አቀረቡ፡፡ ጎሳዎቹን የሚመሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የህዝብ ቀጠራውን ተቆጣጠሩ፡፡ 3 መስዋዕቶቻቸውን ያህዌ ፊት አመጡ፡፡ ስድስት የተሸፈኑ ሰረገሎችና አስራ ሁለት በሬዎች አመጡ፡፡ ለየሁለቱ መሪዎች አንድ ሰረገላ አመጡ፣ እያንዳንዱ መሪ አንድ በሬ አመጣ፡፡ እነርሱ እነዚህን ነገሮች በማደሪያው ድንኳን ፊት አቀረቡ፡፡ 4 ከዚያም ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ 5 “መስዋዕታቸውን ከእነርሱ ተቀበልና ለመገናኛው ድንኳን ሥራ አውላቸው፡፡ ለሥራው እንደሚያስፈልጋቸው ለእያንዳንዱ፣ መስዋዕቶቹን ለሌዋውያን ስጥ፡፡” 6 ሙሴ ሰረገሎቹንና በሬዎቹን ወስዶ ለሌዋውያኑ ሰጣቸው፡፡ 7 ለጌድሶናውያን ተውልዶች ለስራቸው እንደሚያስፈልግ ሁለት ሰረገላዎችና አራት በሬዎች ሰጠ፡፡ 8 ለሜራሪ ትውልዶች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር በኩል አራት ሰረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጠ፡፡ ይህን ያደረገው ሥራቸው ይህን ስለሚጠይቅ ነው፡፡ 9 ለቀዓት ትውዶች ከእነዚህ ነገሮች ምንም አልሰጠም፣ ምክንያቱም የእነርሱ የሥራ ድርሻ የያህዌ የሆኑትን ነገሮች በገዛ ትከሻቸው ከመሸከም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ 10 መሪዎቹ ሙሴ መሰዊያውን በቀባ ዕለት ስጦታዎቻቸውን ለመሰዊያው መቀደስ ሰጡ፡፡ መሪዎቹ መስዋዕቶቻቸውን በመሰዊያው ፊት አቀረቡ፡፡ 11 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እያንዳንዱ መሪ ለመሰዊያው መቀደስ በራሱ ቀን መስዋዕቱን ማቅረብ አለበት፡፡” 12 በመጀመሪያው ቀን፣ ከይሁዳ ጎሳ የሆነው፣ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፣ መስዋዕቱነ አቀረበ፡፡ 13 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የብር ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሳህን ነበሩ፡፡ እነዚህ ሁለትም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 14 በተጨማሪም በእጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሃን ሰጠ፡፡ 15 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ፣ እና የአንድ አመት ወንድ ጠቦት በግ ሰጠ፡፡ 16 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 17 ሁለት በሬዎች፣ አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ የበግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የአሚናዳብ ልጅ የነአሶን መስዋዕት ነበር፡፡ 18 በሁለተኛው ቀን፣ የይሳኮር መሪ፣ የሶገር ልጅ ናትናኤል፣ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 19 አንድ መቶ ሰላሳ ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 20 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 21 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 22 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 23 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሶገር ልጅ የናትናኤል መስዋዕት ነበር፡፡ 24 በሶስተኛው ቀን የዛብሎን መሪ፣ የኬሎን ልጅ ኤልያብ፣ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 25 አንድ መቶ ሰላሳ ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 26 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 27 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 28 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 29 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኬሎን ልጅ የኤልያብ መስዋዕት ነበር፡፡ 30 በአራተኛው ቀን፣ የሮቤል ትውልድ መሪ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 31 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 32 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 33 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 34 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 35 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሰዲዮር ልጅ የአሌሊሱር መስዋዕት ነበር፡፡ 36 በአምስተኛው ቀን፣ የስምዖን ትውልድ መሪ፣ የሱሪሰዳይ ልጅ ስልሚኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 37 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 38 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ። 39 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 40 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 41 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የሱሪሰዳይ ልጅ የስልሚኤል መስዋዕት ነበር፡፡ 42 በስድስተኛው ቀን፣ የጋድ ትውልድ መሪ፣ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 43 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 44 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 45 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 46 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 47 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የራጉኤል ልጅ የኤሊሳፍ መስዋዕት ነበር፡፡ 48 በሰባተኛው ቀን፣ የኤፍሬም ትውልድ መሪ፣ የዓመሁድ ልጅ ኤሊሳማ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 49 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 50 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 51 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 52 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 53 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የራጉኤል ልጅ የኤሊሳፍ መስዋዕት ነበር፡፡ 54 በስምንተኛው ቀን፣ የምናሴ ትውልድ መሪ፣ የፍደሱር ልጅ ገሚልኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 55 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 56 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 57 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 58 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 59 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የፍደሱር ልጅ የገማልኤል መስዋዕት ነበር፡፡ 60 በዘጠነኛው ቀን፣ የብንያም ትውልድ መሪ፣ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 61 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 62 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 63 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 64 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 65 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የጋዲዮን ልጅ የአቢዳን. መስዋዕት ነበር፡፡ 66 በአስረኛው ቀን፣ የዳን ትውልድ መሪ፣ የአሚሳይ ልጅ አኪዔዘር መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 67 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 68 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 69 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 70 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 71 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የፍደሱር ልጅ የገማልኤል መስዋዕት ነበር፡፡ 72 በአስራ አንደኛው ቀን፣ የአሴር ትውልድ መሪ፣ የኤክራን ልጅ ፋግኤል መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 73 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 74 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 75 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 76 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 77 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኤክራን ልጅ የፋግኤል መስዋእት ነበር፡፡ 78 በአስራ ሁለተኛው ቀን፣ የንፍታሌም ትውልድ መሪ፣ የዔናን ልጅ ኢኬሬ መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ 79 መስዋዕቱ ይህ ነበር፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 130 ሰቅሎችን የሚመዝን አንድ ሳህን እና ሰባ ሰቅሎች የሚመዝን አንድ ጎድጓዳ የብር ሰሀን በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መስዋዕቱን አቀረበ፡፡ እነዚህ ሁለቱም ዕቃዎች ለእህል ቁርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ ነበሩ፡፡ 80 በተጨማሪም በዕጣን የተሞላ አስር ሰቅሎች የሚመዝን አንድ የወርቅ ሰሀን ሰጠ፡፡ 81 ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ኮርማ፣ አንድ አውራ በግ እና የአንድ አመት ወንድ በግ ጠቦት ሰጠ፡፡ 82 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ሰጠ፡፡ 83 ሁለት በሬዎች አምስት አውራ በጎች፣ አምስት ወንድ ፍየሎች፣ እና አንድ አመት የሆናቸው አምስት ወንድ በግ ጠቦቶች፣ ለህብረት መስዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ ሰጠ፡፡ ይህ የኤናን ልጅ የኤኪሬ መስዋዕት ነበር፡፡ 84 የእስራኤል መሪዎች ሙሴ መሰዊያውን በቀባበት ቀን እነዚህን ሁሉ ነገሮች አቀረቡ፡፡ አስራ ሁለት የብር ሳህኖች፣ አስራ ሁለት የብር ጎድጓዳ ሳህኖች እና አስራ ሁለት የወርቅ ሰሃኖች አቀረቡ፡፡ 85 እያንዳንዱ የብር ሳህን 130 ስቅሎች ሲመዝን እያንዳንዱ ጎድጓዳ ሰሀን ሰባ ሰቅሎች ይመዝናል፡፡ ሁሉም የውሃ መያዣዎች በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን 2400 ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡ 86 አስራ ሁለቱ ዕጣን የተሞሉ የወርቅ ሰሃኖች እያንዳንዳቸው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አስር ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡ ሁሉም የወርቅ ሳህኖች 120 ሰቅሎች ይመዝናሉ፡፡ 87 ለሚቃጠል መስዋዕት አስራ ሁለት በሬዎች፣ አስራ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ ሁለት የአንድ አመት ጠቦቶች አቀረቡ፡፡ የእህል ቁርባናቸውን ሰጡ፡፡ ለኃጢአት መስዋዕት አስራ ሁለት ወንድ ፍየሎች ሰጡ፡፡ 88 ከብቶቻቸው ሁሉ፣ ሀያ አራት በሬዎች፣ ስልሳ አውራ በጎች፣ ስልሳ ወንድ ፍየሎች እና አንድ አመት የሆናቸው ስልሳ ወንድ ጠቦት በጎች የህብረት መስዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡ እነዚህ ሁሉ መሰዊያውን ለመቀደስ በሚቀባበት ጊዜ የቀረቡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ 89 ሙሴ ከያህዌ ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ሲነጋገር ድምጹን ሰማ፡፡ ያህዌ ከማስተሰርያ መክደኛ በላይ ሆኖ በቃል ኪዳን ታቦቱ ላይ፣ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ለእርሱ ተናገረ፡፡
“ሙሴ ማደሪያውን መሥራቱን አጠናቀቀ”
እነዚህ ሁለት ሐረጎች በተለያዩ መንገዶች ሁለት ተመሳሳይ የሆኑ ቡድኖችን ነው የሚገልፁት፡፡“የእሥራኤል አለቆች የሆኑትና በተመሳሳይ ሁኔታ አባቶች ቤቶች አለቆች የሆኑ” (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ የአባቶች ቤቶች መሪዎች “አለቆች”ተብለው ተጠርተዋል፡፡ “የአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“ቆጠራ”የሚለው አሕፅሮተ ስም እንደ ግሥ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አሮንንና ሙሴን በቆጠራ አግዘዋቸዋል”(አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት መባቸውን ከሰጡ በኋላ ወደ መገናኛ ድንኳኑ አመጡት ማለት ነው፡፡ምናልባትም እነዚህ ሐረጎች ነገሩን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ ሊቀናጁ ይችላሉ፡፡“መባቸውን ለእግዚአብሔር ካመጡ በኋላ በመገናኛ ድንኳኑ ፊት አቀረቡት፡፡”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
6 የተከደኑ ሠረገሎችና 12 በሬዎች
“ለእንዳንዱ ለሥራው እንደሚያስፈልገው መጠን”
ይሀንን በኦሪት ዘኁልቁ 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ምክኒያቱም ለሥራ የሚያስፈልጋቸውን ያህል ነበር”
“በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ተቆጣጣሪነት”ወይም “የካህኑ የአሮን ልጅ የሆነው ኢታምር ሥራቸውን ተመለከተ”
ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ምክኒያቱም ሥራውን ለማከናወን የሚያስፈልጋቸው ይሄ ስለነበር”
ይሄ የሚያመለክተው ሠረገሎቹንና በሬዎቹን ነው፡፡
ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሥራቸው የሚሆነው”
ለእግዚአብሔር የሆኑት ነገሮች የሚለውንና በአግባቡ ያልተገለፀውን ነገር በሚገባ ልትገልፁት ትችላላችሁ፡፡“ እግዚአብሔር ለመገናኛ ድንኳኑ እንዲሆን የመደበው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሥጦታዎችን አቀረቡ”
“አንድ መሪ በእያንዳንዱ ዕለት መሥዋዕቱን ማቅረብ ይኖርበታል”
“ቀን 1”ወይም “ቀን ቁጥር 1” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“አንድ መቶ ሠላሣ ሰቅል የሚመዝን” “አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ክብደቶች በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፉ ይችላሉ፡፡” “አንድ ኪሎ ግራም አካባቢ የሚመዝን”ወይም “አንድ ኪሎ ግራምና 430 ግራሞች” (ቁጥሮችንና የመፅሐፍ ቀዱስ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰባ ሰቅል የሚመዝን አንድ የብረት ድስት”አስፈላጊ የሚሆን ከሆነ እነዚህን መመዘኛዎች በዘመናዊ መለኪያ መለካት ይችላል፡፡“አንድ አስረኛ ኪሎግራም አካባቢ የሚመዝን”ወይም “770 ግራም የሚመዝን አንድ የብረት ድስት”
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን የሚጠቀሙበት ነው፡፡ሚዛኖቹን ወደ ዘመናዊ መለኪያ እየለወጣችሁ ከሆነ ይሄንን ሐረግ የመተርጎሚያ ሌላ መንገድ እነሆ፡፡“በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የሚዛን ደረጃ የተለካ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ) “እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ቀን 2”ወይም “ቀን ቁጥር 2” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ430 ግራሞች ይመዝናሉል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን ሰዎች የሚጠቀሙበት ነው፡፡ሚዛኖቹን ወደ ዘመናዊ መለኪያ እየለወጣችሁ ከሆነ ይሄንን ሐረግ የመተርጎሚያ ሌላ መንገድ እነሆ፡፡“በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው ደረጃ ሚዛን የተለካ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡” በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የወርቅ ሳህን አንድ አሥረኛ ኪሎ ግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሳህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“ይሄ የሶገር ልጀ ናትናኤል ያቀረበው ነው”
የዚህን ሰው ስም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ቀን 3”ወይም “ቀን ቁጥር 3” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ430 ግራሞች ይመዝናሉ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የጥራት ደረጃ መሠረት የተመዘነ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡” በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ ወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የኬሎን ልጅ ኤልያብ ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡”
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡19 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ቀን 4”ወይም “ቀን ቁጥር 4” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የጥራት ደረጃ መሠረት የተመዘነ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡” በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን እንዴት በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ ወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎ ግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡”
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ቀን 5”ወይም “ቀን ቁጥር 5” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን ሰዎች የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው ደረጃ ሚዛን የተለካ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡” በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን እንዴት በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ ወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የሱዲዮር ልጅ ሰለሚኤል ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡”
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ቀን 6”ወይም “ቀን ቁጥር 6” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው ደረጃ ሚዛን የተለካ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን እንዴት በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ ወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡”
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ቀን 7”ወይም “ቀን ቁጥር 7” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡10 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የጥራት ደረጃ መሠረት የተመዘነ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ ወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የአሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡”
“ቀን 8”ወይም “ቀን ቁጥር 8” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡10 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው ደረጃ ሚዛን የተለካ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ ወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የፍሳዱል ልጅ ገማልኤል ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡”
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ቀን 9”ወይም “ቀን ቁጥር 9” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን ሰዎች የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የጥራት ደረጃ መሠረት የተመዘነ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ ወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎ ግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የአቢዳን ልጅ ጋዴዮን ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡”
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ቀን 10”ወይም “ቀን ቁጥር 10” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡12 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው ደረጃ ሚዛን የተለካ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን እንዴት በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ የወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዜር ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡”
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡12 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ቀን 11”ወይም “ቀን ቁጥር 11” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ 430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን ሰዎች የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የጥራት ደረጃ መሠረት የተመዘነ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ ወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የኤክራን ልጅ ፋግኤል ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡” ኤክራንና ፋግኤል የሰዎች ሥም ነው፡፡ስማቸውን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“ቀን 12”ወይም “ቀን ቁጥር 12” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ 430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”አንድ የብር ሣህን አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ሣህን 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን ሰዎች የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የጥራት ደረጃ መሠረት የተመዘነ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡”በዘይት የተለወሰው መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ይሄ በዘመናዊ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡እነዚህን ተመሳሳይ የሆኑ ሚዛኖችን እንዴት በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመለከቱ፡፡”አንድ ወርቅ ሣህን አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝናል”ወይም “አንድ የወርቅ ሣህን 110 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው”
“የዔናን ልጅ አኪሬ ያቀረበው መሥዋዕት ይሄ ነበር፡፡”
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“መለየት”የሚለው ሐረግ ለአንድ ለተወሰነ ዓላማ ራስን መሥጠት ማለት ነው፡፡በዚህ መሠረት ሥጦታዎቹ የሚሰጡት ለእግዚአብሔር ነበር፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ቀን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በአጠቃላይ ዘመኑን ነው፡፡የእሥራኤል አለቆች እነዚህን ነገሮች በአሥራ ሁለት ቀናት ነበር የሚሰውት፡፡ “ሙሴ መሠውያውን በቀባበት ወቅት”
አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“አንድ የብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ተኩል ገደማ ይመዝናል”ወይም “አንድ ብር ወጭት አንድ ኪሎ ግራም ከ 430 ግራሞች ይመዝናል”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዱ የብር ድስት 70 ሰቅል ይመዝን ነበርይመዝናል”አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላል፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”እያንዳንዱ የብር ድስት አንድ አሥራ ስምንተኛ ኪሎግራም ገደማ የሚመዝን ነው”ወይም “አንድ የብር ድስት 770 ግራም ይመዝናል፡፡”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል”ወይም “ሃያ አራት መቶ ሰቅል”
የተለያዩ ዓይነት የሰቅል ሚዛኖች ነበሩ፡፡ይሄኛው ሰዎች በመቅደሱ ውስጥ ለሚገኘው የተቀደሰው ድንኳን የሚጠቀሙበት ነው፡፡“ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡በመቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የጥራት ደረጃ መሠረት የተመዘነ”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለከያ የሚለውን ይመልከቱ)
“የብር ዕቃዎቹ ሁሉ በአንድ ላይ ተመዘኑ…የወርቅ ዕቃዎቹ ሁሉ በአንድ ላይ ተመዘኑ”
እነዚህ የሚያመለክቱት ከብር የተሰሩትን በሳህንና በወጭት መልክ የመጡትን ሥጦታዎች ነው፡፡
“እንዳንዳቸው አሥራ ሁለቱ የወርቅ ሣህኖች …10 ሰቅል ይመዝኑ ነበር፡፡አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚህ ሚዛኖች በዘመናዊ መለኪያዎች ሊፃፉ ይችላሉ፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 7፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡”እያንዳንዳቸው 12 የወርቅ ሣህኖች…. አንድ አሥረኛ ኪሎግራም ይመዝኑ ነበር”ወይም “እንዳንዳቸው 12ቱ የወርቅ ሣህኖች 110 ግራም ይመዝኑ ነበር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ መቶ ሃያ ሰቅል” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“12..24…60”እነዚህ ቁጥሮች ከፊደል ይልቅ በቁጥር ሊፃፉ ይችሉ ይሆናል፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ ዓመት የሆነው”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴ ከቀባው በኋላ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የእርሱ”የሚለው የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ድምፅ ነው፡፡“እግዚአብሔር ሲናገረው ሰማ” (ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚያመለክቱት ተመሳሳይ የሆነን ሥፍራ ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 4፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“እግዚአብሔር ለሙሴ ተናገረው”
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “አሮንን እንዲህ በለው፣ ‘ሰባቱ መብራቶች በምትለኩሳቸው ጊዜ በመቅረዙ ፊት ለፊት ብርሃን ይስጡ፡፡’” 3 አሮን ይህን አደረገ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ብርሃን እንዲሰጡ መብራቶቹን በመቅረዙ ላይ ለኮሳቸው፡፡ 4 መቅረዙ የተሰራው በዚህ መንገድ ነበር፡፡ ያህዌ አሰራሩን ለሙሴ አሳይቶት ነበር፡፡ ከመሰረቱ እስከ ጫፍ በአበባ መልክ የዋንጫ መልክ ቅርጽ አስይዘህ ወርቁን ቀጥቅጠህ አብጀው፡፡ 5 እንደገና፣ ያህዌ ሙሴን እንዲሀ ሲል ተናገረው፣ 6 “ከእስራኤል ሰዎች መሃል ሌዋውያንን ወስደህ አንጻቸው፡፡ 7 እነርሱን ለማንጻት ይህን አድርግ፣ የማንጻት ውሃ እርጫቸው፡፡ ፀጉራቸው በሙሉ እንዲላጩ፣ ልብሶቻቸውን እንዲያጥቡ፣ እና በዚህ መንገድ ራሳቸውን እንዲያነጹ አድርግ፡፡ 8 ከዚያ ጥጃና በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት የእህል ቁርባን ይውሰዱ፡፡ ሌላ ጥጃ ለኃጢአት መስዋዕት ያዘጋጁ፡፡ 9 ሌዋውያኑን ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት አቅርባቸውና መላውን የእስራኤል ማህበረሰብ ሰብስብ፡፡ 10 በእኔ በያህዌ ፊት ሌዋውያንን አቅርብ፡፡ የእስራኤል ሰዎች እጃቸውን በሌዋውያን ላይ ይጫኑ፡፡ 11 አሮን ሌዋውያኑን በእኔ ፊት ያቅርባቸው፣ የእስራኤልን ህዝብ ወክለው በእርሱ ፊት ከፍ አድርገው እንደሚያቀርቡ አቅርባቸው፡፡ ሌዋውያን እኔን እንደሚያገለግሉ እርሱ ይህን ያድርግ፡፡ 12 ሌዋውያኑ በበሬዎቹ ላይ እጃቸውን ይጫኑ፡፡ ሌዋውያኑን ለማስተሰርይ፣ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ኮርማ አቅርቡ፣ ደግሞም ሌላውን ኮርማ የሚቃጠል መስዋዕት አድርገህ ለእኔ አቅርብ፡፡ 13 ሌዋውያኑን በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፣ እናም እንደ ሚወዘወዝ መሥዋዕት ለእኔ ከፍ አድርገህ አቅርባቸው፡፡ 14 በዚህ መንገድ ሌዋውያኑን ከእስራኤል ሰዎች መሃል ለያቸው፡፡ ሌዋውያን ለእኔ ይለዩ፡፡ 15 ከዚያ በኋላ ሌዋውያኑ ወደ መገናኛው ድንኳን ለአገልግሎት ይግቡ፡፡ እነርሱን አንጻቸው፡፡ እንደ ስጦታ ለእኔ ከፍ አድርገህ አንሳቸው፡፡ 16 ከእስራኤል ህዝብ መሀል እነርሱ ሙሉ ለሙሉ የእኔ ናቸውና ይህን አድርግ፡፡ ከእስራኤል ወገን በኩር ሁሉ፣ ማህጸን ከከፈተው ከእያንዳንዱ ወንድ ልጅ ቦታውን ይወስዳሉ፡፡ እኔ ሌዋውያንን ለራሴ ለይቻለሁ፡፡ 17 ከሰውም ሆነ ከእንስሳው የእስራኤል ህዝብ በኩሩ ሁሉ የእኔ ነው፡፡ በግብፅ ምድር የበኩሩን ህይወት ሁሉ በወሰድኩ ቀን፣ እኔ እናንተን ለራሴ ለየኋችሁ፡፡ 18 በበኩሩ ሁሉ ምትክ፣ ከእስራኤል ሰዎች መሀል ሌዋውያንን ወሰድኩ፡፡ 19 ሌዋውያንን ለአሮንና ለልጆቹ እንደ ስጦታ ሰጠኋቸው፡፡ በመገናኛው ድንኳን የእስራኤልን ሰዎች ሥራ ይስሩ ዘንድ ከእስራኤል ሰዎች መሃል ወሰድኳቸው፡፡ ወደተቀደሰው ስፍራ ሲቀርብ ምንም ጥፋት እንዳይደርስባቸው ለእስራኤል ሰዎች እንዲያስተሰርዩ እነርሱን ሰጠኋቸው፡፡” 20 ሙሴ፣ አሮንና መላው የእስራኤል ህዝብ ይህንን ከሌዋውያን ጋር አደረጉ፡፡ ሌዋውያንን በሚመለከት ያህዌ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ የእስራኤል ሰዎች ከእነርሱ ጋር ይህን አደረጉ፡፡ 21 ሌዋውያን ልብሶቻቸውን በማጠብ ራሳቸውን ከኃጢአት አነጹ፡፡ አሮን ለያህዌ ስጦታ አድርጎ አቀረባቸው፤ ደግም ይነጹ ዘንድ የንስሃ ማስተስረያ አደረገላቸው፡፡ 22 ከዚያ በኋላ፣ ሌዋውያኑ በአሮንና በአሮን ልጆች ፊት አገልግሎታቸውን ይሰጡ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፡፡ ይህም ያህዌ ስለ ሌዋውያን ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነበር፡፡ ሌዋውያንን በሙሉ በዚህ መንገድ ተቀበሉ፡፡ 23 ያህዌ እንደገና ለሙሴ ተናገረ፡፡ እንዲህም አለ፣ 24 “ይህ ሁሉ፤ ሃያ አምስት አመት እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ላላቸው ሌዋውያን ነው፡፡ በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል መምጣት አለባቸው፡፡ 25 አምሳ አመት ሲሞላቸው በዚህ መንገድ ማገልገላቸውን ያቁሙ፡፡ በዚያ ዕድሜ መደበኛ አገልግሎታቸውን ያቁሙ፡፡ 26 በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉ ወንድሞቻቸውን ሊያግዙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዕድሜያቸው አምሳ ከሆነ በኋላ በዚህ መንገድ አያገለግሉ፡፡ ለሌዋውያን በእነዚህ ጉዳዮች ሁሉ መመሪያ ልትሰጣቸው ይገባል፡፡
“በመቅረዙ ፊት ያበራሉ”
“ማብራት”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የመቅረዙን ማስቀመጫ ሰሩት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ከአፈራው አበባ ጋር እንዲመሳሰሉ የተቀጠቀጡ ፅዋዎችን እንዲቀርፁ ይታዘዙ ነበር፡፡“ከአበቡት አበባዎች ጋር እንዲመሳሰሉ የተቀጠቀጡ ፅዋዎች”(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እነርሱን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሌዋውያንን ነው፡፡
ሙሴ በእነርሱ ላይ ውኃ መርጨቱ የድነታቸው ተምሣሌት ነው፡፡“የደህንነት ተምሣሌት የሆነውን ውኃ በእነርሱ ላይ መርጨት”(ተምሳሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ሌዋውያን የራሣቸውን ልብስ ማጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ግንዛቤ የተገኘበትን ይህንን ሃሣብ የበለጠ ልታብራሩት ትችላላችሁ፡፡“ልብሣቸውን እንዲያጥቡ አድርግ”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
ሌዋውያን የራሣቸውን ልብስ ማጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ግንዛቤ የተገኘበትን ይህንን ሃሣብ የበለጠ ልታብራሩት ትችላላችሁ፡፡“ልብሣቸውን እንዲያጥቡ አድርግ”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
የወይፈን ሥጦታ በሚቀርብበት ወቅት አብዛኛውን ጊዜ የእህል ሥጦታም አብሮ ይሰጥ ነበር፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዘይት የለወሱት መልካም ዱቄት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ማህበሩን ሁሉ አንድ ላይ አድርጋቸው”
እዚህ ላይ እግዚአብሔር የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር ራሱን የሚገልፅበት ሥሙን ነው፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ሰው ላይ“ እጅ የመጫን” ድርጊት የሚከናወነው አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ቤት ሥራ ወይም አገልግሎት በሚለይበት ወቅት ነው፡፡ለእኔ ይለዩ ዘንድ የእሥራኤል ሕዝብ በሌዋውያን ላይ እጃቸውን መጫን ይኖርባቸዋል፡፡(ተምሳሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
አሮን ሌዋውያንን ለእግዚአብሔር የሚያቀርባቸው መሥዋዕቶችን በሚያቀርብበበት ስሜት ውስጥ ሆኖ ነው፡፡“የሚወዝወዝ ሥጦታ እንደሆኑ”(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ተምሣሌታዊ አነጋገር ሲሆን ለሌዋውያን የከብቶች ሥጦታ እንደሚሰጣቸው ለመግለፅ ነው፡፡በዚህ መንገድ ሰውዬው በእንስሳው አማካይነት ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀርባል፡፡(ተምሳሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
አሮን ቁርባንን እንደሚያነሳ እንዲሁ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ፊት ማቅረብ ነበረበት፡፡ “የሚወዘወዝ ቁርባንን እንደምታቀርብልኝ እንዲሁ እነርሱን ለእኔ ለይልኝ”
እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች የሚደጋግመው ለጉዳዩ አፅንዖትን ለመስጠት ነው፡፡ይሄ መከናወን የሚኖርበት ሌዋውያኑ በመገናኛ ድንኳን ውስጥ አገልግሎትን ከመጀመራቸው አስቀድሞ ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ነገር ግን በመጀመሪያ ልታነጿቸው ይገባል፡፡እንደ ሥጦታ ልታቀርቧቸው ይገባችኋል (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የሚወዘወዙ ቁርባን ይመስል አሮን እነርሱን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ነበረበት፡፡“የሚወዘወዝ ቁርባን ለእኔ እንደሚቀርብ እንዲሁ እነርሱን ለእኔ ማቅረብ ይኖርብሃል፡፡”(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በጋራ እንዲነገሩ የተደረገው በኩር ልጆችን በተመለከተ የበለጠ አፅንዖት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“ማሕፀንን የሚከፍት” ማለት ለመጀመሪያ ጊዜ ልጅን የሚወልድ ማለት ነው፡፡ይሄ የሚያመለክተው እናት ለመጀመሪያ ጊዜ የምትወልደውን ወንድ ልጅን ነው፡፡“ለእናቱ የመጀመሪያ ሆኖ የተወለደ ወንድ ልጅ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ አንድ ሰው ሌላ ሰውን በሚገድልበት ወቅት የሚገለፅበት የትህትና አነጋገር ነው፡፡“ገደልኩ”(ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እነርሱን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው “በእሥራኤል መካከል የተወለዱትን በኩሮች ነው”
“ወስጃለሁ” የሚለው ቃል በመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር ግልፅ ሲሆን በሁለተኛውም እንዲሁ ሊደገም ይችላል፡፡“በኩሮቹን ከመውሰድ ይልቅ…ሌዋውያንን በሙሉ ወስጃለሁ”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሌዋውያን አሮንና ልጆቹን እንዲያግዟቸው የመደበበትን ሁኔታ ልክ እግዚአብሔር ለአሮንና ለልጆቹ እንደ ሥጦታ እንደሰጣቸው ተደርጎ ሲነገር እናያለን፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እነርሱን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሌዋውያንን ነው፡፡
እዚህ ላይ “እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡
እዚህ ላይ ተመሳሳይ መረጃ የሚሰጡ ሶስት ተመሳሳይ ዓረፍተ ነገሮች አሉ፡፡እንዲደጋገም የተፈለገበት ምክኒያት ሰዎቹ በሌዋውያን ላይ ያደረጉት ነገር በእግዚአብሔር ትዕዛዝ እንደሆነ አፅንዖት ለመሥጠት ነው፡፡ሙሴና አሮን የእሥራኤልም ማህበር ሁሉ ሌዋውያንን በሚመለከት እግዚአብሔር የሰጠውን ትዕዛዝ ሁሉ ፈፀሙ፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“አገልግሎት”የሚለው አሕፅሮተ ሥም በግሥ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ማገልገል”(አሕፅሮተ ሥምን የሚለውን ይመልከቱ)
x
“በሃምሳ ዓመት ዕድሜ” ወይም “ሃምሳ ዓመት ሲሞላቸው”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
1 ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው አመት በመጀመሪያው ወር፣ በሲና ምድረ በዳ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2 “የእስራኤል ሰዎች በተወሰነው የአመቱ ወቅት ፋሲካን ያድርጉ፡፡ 3 በዚህ ወር በእስራ አራተኛው ቀን፣ ምሽት ላይ፣ በተወሰነው በአመቱ ወቅት ፋሲካን አድርጉ፡፡ ፋሲካን አድርጉ፣ ደንቦቹን ጠብቁ፣ ከዚህ ጋር የተያያዙ ደንቦችን ሁሉ ታዘዙ፡፡” 4 ስለዚህ፣ ሙሴ የፋሲካን በዓል እንዲያከብሩ ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ ነገራቸው፡፡ 5 ስለዚህ በመጀመሪያው ወር በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን፣ ምሽት ላይ፣ በሲና ምድረ በዳ ፋሲካን አከበሩ፡፡ የእስራኤል ሰዎች ያህዌ ለሙሴ እንዲያደርግ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፡፡ 6 በሞተ ሰው በድን የረከሱ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ፡፡ እነርሱ በዕለቱ ፋሲካን አላከበሩም፡፡ በዚያ ቀን እነዚህ ሰዎች ሙሴና አሮን ፊት ቀረቡ፡፡ 7 እነዚያ ሰዎች ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “እኛ በሰው በድን አካል ምክንያት ንጹህ አይደለንም፡፡ ሆኖም በእስራኤል ሰዎች መሃል በተወሰነው የአመቱ ወቅት ለያህዌ መስዋዕት ከማቅረብ ለምን ትከለክለናለህ” 8 ሙሴ እንዲህ አላቸው፣ “ያህዌ ስለ እናንተ ምን ትዕዛዝ እንደሚሰጥ እስከምሰማ ጠብቁኝ፡፡” 9 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 10 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ከእናንተ ማናችሁም ወይም ከትውልዳችሁ ማንም በበድን አካል ምክንያት እርኩስ ቢሆን፣ ወይም ሩቅ መንገድ ሄዶ ቢሆን፣ ለያህዌ ፋሲካን ማክበር ይችላል፡፡’ 11 እነርሱ በሁለተኛው ወር በአስራ አራተኛው ቀን ፋሲካን ያክብሩ፡፡ እነርሱ ፋሲካን እርሾ ባስገባበት እንጀራ ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉ፡፡ 12 እስከ ማለዳ አንዳች አያስተርፉለት፣ አሊያም ከእንስሳቱ አጥንት አይስበሩ፡፡ የፋሲካን ህግጋት ሁሉ ይጠብቁ፡፡ 13 ነገር ግን ማናቸውም ንጹህ የሆነና ሩቅ መንገድ ያልሄደ ሰው፣ ነገር ግን ፋሲካን ሳያከብር የቀረ ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፤ ምክንያቱም እርሱ በተወሰነው የአመቱ ወቅት የሚቀርበውን ያህዌ የሚጠይቀውን መስዋዕት አላቀረበም፡፡ ያሰው ኃጢአቱን ይሸከም፡፡ 14 እንግዳ በመሀላችሁ ቢኖርና ፋሲካን ለያህዌ ክብር ቢያብር፣ ፋሲካን መጠበቅና እርሱ ያዘዘውን ሁሉ ማድረግ አለበት፣ የፋሲካን ህግጋት ሁሉ መጠበቅ እንዲሁም የፋሲካን ህግነት መጠበቅ አለበት፡፡ ለመጻተኞች እና በምድሪቱ ለተወለዱ ሁሉ ተመሳሳይ ህግ ይኑርህ፡፡” 15 የማደሪያው ድንኳን በተተከለበት ቀን፣ ደመና የማደሪያውን ድንኳን ፣ የቃል ኪዳኑን ምስክር ድንኳን ሸፈነው፡፡ በምሽት ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ነበር፡፡ እስከ ንጋት እሳት ይመስል ነበር፡፡ 16 በዚያ መልክ ቀጠለ፡፡ ደመናው የማደሪያ ድንኳኑን ሸፍኖ በምሽት እሳት ይመስል ነበር፡፡ 17 ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተወሰደ ጊዜ ሁሉ፣ የእስራኤል ሰዎች ከመጓዝ ያቋርጡ ነበር፡፡ ደመናው በቆመ ጊዜ ሁሉ፣ ህዝቡ አንድ ቦታ ይሰፍራል፡፡ 18 የእስራኤል ሰዎች በያህዌ ትዕዛዝ ይጓዛሉ፣ በእርሱም ትእዛዝ በሰፈራቸው ይቆያሉ፡፡ ደመናው በማደሪያው ድንኳን ላይ ሲቆም፣ በሰፈራቸው ይቆያሉ፡፡ 19 ደመናው በማደሪያው ድንኳን ለብዙ ቀናት ሲቆይ፣ የእስራኤል ሰዎች የያህዌን ትዕዛዝ ተከትለው መጓዝ ያቆማሉ፡፡ 20 አንዳንድ ጊዜ ደመናው በማደሪያው ድንኳን ላይ ለጥቂት ቀናት ይቆያል፡፡ በዚህ ሁኔታ የያዌን ትእዛዝ ተከትለው በአንድ ቦታ ይሰፍራሉ፣ ከዚያ በእርሱ ትእዛዝ እንደገና ይጓዛሉ፡፡ 21 አንዳንድ ጊዜ ደመናው ከምሽት እስከ ማለዳ በሰፈር ይገኛል፡፡ ማለዳ ደመናው ሲነሳ፣ እነርሱ ይጓዛሉ፡፡ ቀንም ይሁን ሌሊት ጉዟቸውን የሚቀጥሉት ደመናው ከተነሳ ብቻ ነው፡፡ 22 ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ለሁለት ቀናት፣ ለወር ወይም ለአመት ቢቆይ በዚያ ስፍራ እስከ ቆየ ድረስ የእስራኤል ሰዎች በሰፈሮቻቸው ይቆያሉ አይጓዙም፡፡ ነገር ግን ደመናው ሲንቀሳቀስ እነርሱም ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡ 23 በያህዌ ትዕዛዝ ይሰፍራሉ፣ በእርሱ ትዕዛዝ ይጓዛሉ በሙሴ በኩል የተሰጣቸውን የያህዌን ትዕዛዝ ይፈጽማሉ፡፡
ይሄ ማለት ከግብፅ ምድር የወጡት ከአንድ ዓመት ቀደም ብሎ ነው ማለት ነው፡፡ሁለተኛ ዓመታቸውን እየጀመሩ የነበሩት በበረሃ ውስጥ ሆነው ሳሉ ነው፡፡(ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
በዕብራውያን የዘመን አቆጣጠር መሠረት ይሄ የመጀመሪያው ወር ነው፡፡እግዚአብሔር የእሥራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ያወጣበትን ጊዜ የሚያመለክት ነው፡፡(የዕብራውያን ወራትንና ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡“ወጡ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው መልቀቅን ነው፡፡“የግብፅ ምድርን ከለቀቁ በኋላ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“የተመደበው”የሚለው ቃል ቀደም ሲል መርሐ ግብር በተያዘለት መሠረት ማለት ነው፡፡ይሄ ማለት በየዓመቱ ይህን ያደርጋሉ ማለት ነው፡፡“ሕዝቡ…በዓመቱ በሚያከብሩት መሠረት” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፋሲካን የሚያከብሩበት ዓመት ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ ሊብራራ የበለጠ ይችላል፡፡ “በአሥራ አራተኛው ቀን …አክብሩት፡፡በየዓመቱ ማክበር የሚኖርባችሁ በዚህ ወቅት ነው ነው” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ቀን 14” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ሁለቱ እንዲቀናጁ የተደረጉት ትዕዛዙን መፈፀም የሚኖርባቸው ስለመሆኑ አፅንዖት ለመስጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“ልትጠብቁት”የሚለው ቃል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን አክብሩት ማለት ነው፡፡ “ልታከብሩት ይገባል”ወይም “ትኩረት ልትሰጡት ይገባል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ጠብቁት” የሚለው ቃል ትርጉሙ አክብሩት ማለት ነው፡፡“ለፋሲካ በዓል ትኩረት ስጡ”ወይም “የፋሲካን በዓል አክብሩ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“በመጀመሪያው ወር በ14ኛው ቀን” ይሄ የዕበራውያንን የዘመን አቆጣጠር ያሣያል፡፡(የዕብራውያን ወራትንና ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያሣየው የሞተ ሰው ሬሣን ከመንካታቸው የተነሣ የረከሱ መሆናቸውን ነው፡፡የዚህን ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ልታብራሩት ትችላላችሁ፡፡“የሞተ ሰው ሬሣ ከመንካታቸው የተነሣ ረከሱ” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር አንድን ሰው በመንፈሣዊ ሕይወቱ ተቀባይነት እንደሌለውና ወይም የረከሰ እንደሆነ የሚቆጥረውን ሰው እዚህ ሥፍራ ላይ ልክ ሰውነቱ ንፁህ እንዳልሆነ ተደርጎ ይገለፃል፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ጠብቁ”የሚለው ቃል ትኩረት ስጡት ማለት ነው፡፡ “ፋሲካን በአግባቡ ትኩረት ስጡት”ወይም “ፋሲካን አክብሩት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት የሞተ ሰው ሬሣ ነክተዋል ማለት ነው፡፡የዚህን ዓረፍተ ነገር ሙሉ ፍቺ ማብራራት ትችላላችሁ፡፡“የሞተ ሰው ሬሣ ከመንካታችን የተነሣ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎቹ ይሄንን ጥያቄ የሚጠይቁት በፋሲካ በዓል ላይ እንዳይሳተፉ የተደረጉበትን ሁኔታ ቅሬታ ለማቅረብ ነወ፡፡ይሄ ምላሽ የማያሻው ጥያቄ በዓረፍተ ነገር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በእሥራኤል ሕዝብ መካከል ….ከመሥዋዕቱ ሥጦታ እኛን ማግለላችሁ ተገቢ አይደለም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
አቋም መያዝ ወይም አስቀድሞ መወሰን፡፡
እዚህ ሥፍራ ላይ እግዚአብሔር አንድን ሰው በመንፈሣዊ ሕይወቱ ተቀባይነት እንደሌለውና ወይም የረከሰ እንደሆነ የሚቆጥረውን ሰው ልክ ሰውነቱ ንፁህ እንዳልሆነ ተደርጎ ይገለፃል፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት የሞተ ሰው ሬሣ ነክተዋል ማለት ነው፡፡የዚህን ዓረፍተ ነገር ሙሉ ፍቺ የበለጠ ማብራራት ትችላላችሁ፡፡“የሞተ ሰው ሬሣ ከመንካታችን የተነሣ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ጠብቁ”የሚለው ቃል በአግባቡ አስቡት ማለት ነው፡፡ “ፋሲካን በአግባቡ አስቡት”ወይም “ፋሲካን አክብሩት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “መብላት”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ማክበርን ነው፡፡“ለፋሲካ ትኩረት ሥጡ”ወይም “ፋሲካን አክብሩ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“14ኛ ቀን 2ተኛ ወር” ይሄ የአይሁዳውያንን የቀን አቆጣጠር የሚያመለክት ነው፡፡(የዕብራውያን ወራትንና ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“ፀሐይ ስትገባ”
“እርሾ የሌለው ቂጣ”
እነዚህ ቅጠሎች ትናንሾች ሲሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ጠንካራና መራራ ጣዕም ያላቸው ናቸው፡፡
“እና ከእርሱ ማንኛውንም እንት መስበር አይኖርባቸውም”
እዚህ ሥፍራ ላይ እግዚአብሔር አንድን ሰው በመንፈሣዊ ሕይወቱ ተቀባይነት እንዳለው የሚቆጥረውን ሰው ልክ ሰውነቱ ንፁህ እንደሆነ ተደርጎ ይገለፃል፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ጠብቁ”የሚለው ቃል ትኩረት ስጡት ማለት ነው፡፡ “ፋሲካን በአግባቡ ትኩረት ስጡት”ወይም “ፋሲካን አክብሩት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “መቆረጥ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ንብረቱን መንጠቅና ማባረርን ነው፡፡ “ያ ሰው መባረር ይኖርበታል”ወይም “ያንን ሰው ማባረር ይኖርባችኋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አቋም መያዝ ወይም አስቀድሞ መወሰን፡፡
እዚህ ላይ አንድ ሰው የኃጢአትን ውጤቶች መሸከም እንዳለበት የሚገልፀውን ሃሣብ ኃጢአቱን እንደ ዕቃ እንደሚሸከመው ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ያ ሰው የኃጢአቱን ቅጣት መሸከም ይኖርበታል”
እዚህ ላይ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡(እናንተ የሚለውን የተለያዩ አገላለፆች የሚለውንይመልከቱ)
“ያ መፃተኛ ሰው እግዚአብሔር የሚያዝዘውን ትዕዛዛት መጠበቅና ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል”
በመሠረቱ እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ሁለቱ ሐረጎች እንዲቀናጁ የተደረጉበት ምክኒያት መፃተኛው የፋሲካን ሕጎች በሙሉ መታዘዝ እንደሚኖርበት አፅንዖት ለመሥጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“በእሥራኤል ምድር ውስጥ”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሌዋውያን ማደሪያውን ተከሉ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የመገናኛ ድንኳኑ ሌላ ሥም ነው፡፡“የምሥክሩ ድንኳን ሥርዓቶች የሚለውን ሐረግ ”በኦሪት ዘኁልቁ 1፡50 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ ደመናው በሌሊት የሚኖረውን ገፅታ የሚገልፅ ነው፡፡እዚህ ላይ ደመናው ከእሣት ጋር ሲመሳሰል እንመለከታለን፡፡“ሌሊት በሚሆንበት ወቅት ማለዳ እስኪነጋ ድረስ ደመናው ግዙፍ እሣት ይመስል ነበር” (ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
ደመናው ከመገኛና ድንኳኑ በላይ ይውል እንደነበረ መግለፁ ተገቢ ሊሆን ይችላል፡፡“ደመናው በዚህ መልኩ በመገናኛ ድንኳኑ ላይ ይቆይ ነበር” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የደመናው አምሳል ከግዙፍ እሣት ጋር ተነፃፅሯል፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ተንቀሳቀሰ” ወይም “እግዚአብሔር ደመናውን አነሳው”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ደመናው መጓዙን አቋረጠ” “
“ትዕዛዝ”የሚለው ቃል እንደ ሥም (ሰዋሰው)ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በሚያዝበት ወቅት” (አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
“ከማደሪያው በላይ”
እዚህ ላይ “መሥራት” የሚለው ቃል ማቋቋም ማለት ነው፡፡“ሠፈራቸውን ማቋቋም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት ደመናው በማደሪያው ላይ የሚቆየው ለአንድ ሊሊት ብቻ ነው ማለት ነው፡፡የዚህን ዓረፍተ ነገር ትርጉም የበለጠ ልታብራሩት ትችላላችሁ፡፡ “ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ብቻ”ወይም “በማደሪያው ላይ ለአንድ ሌሊት ብቻ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ደመናው በማደሪያው ላይ የሚቆይ ከሆነ” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ደመናው ሲንቀሳቀስ ጉዞ ይጀምራሉ”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ደመናው ብድግ አለ”ወይም “እግዚአብሔር ደመናውን አነሳው”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ትዕዛዝ”የሚለው ቃል እንደ ግሥ ሊገለፅ ይችላል፡፡ (አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በሙሴ በኩል የሰጠው ትዕዛዝ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 ”ሁለት የብር መለከቶች አብጁ፡፡ በብር ቀጥቅጠህ አብጃቸው፡፡ መለከቶቹን ማህበረሰቡን በጋራ ለመጥራትና ከመንደሮቸው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ለማሰማት ተጠቀምባቸው፡፡ 3 ካህናቱ ማህበረሰቡን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በፊትህ ለመሰብሰብ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡ 4 ካህናቱ አንድ መለከት ብቻ ከነፉ፣ የእስራኤል ነገድ መሪዎች ይሰበስቡ፡፡ 5 ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፉ፣ በስተምስራቅ የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡ 6 ለሁለተኛ ጊዜ ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፋ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡ ለጉዟቸው ከፍ ያለ የመለከት ድምጽ ያሰሙ፡፡ 7 ማህበረሰቡ በአንድነት ሲበሰበሰብ፣ መለከቶች ይነፉ ነገር ግን ድምጹ ከፍ አይበል፡፡ 8 የካህኑ የአዘሮን ልጆች፣ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘንድ ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም ስርዓት ይሆናል፡፡ 9 በሚወሯችሁ ተቃዋሚዎቻች ላይ በምድራች ለጦርነት ስትወጡ፣ ለማንቂያ የመለከት ድምጽ ታሰማላችሁ፡፡ እኔ፣ አምላካችሁ ያህዌ፣ አስባችኋለሁ ደግሞም ከጠላቶቻችሁ አድናችኋለሁ፡፡ 10 እንደዚሁም፣ በመደበኛ ባዕላቶቻችሁም ሆነ በወራቶች መጀመሪያ ላይ በክብረ በዓል ወቅት ለሚቃጠል መስዋዕቶቻችሁ ክብርና በህብረት መስዋዕቶቻችሁ መስዋዕቶች ላይ መለኮቶችን መንፋት አለባች፡፡ እነዚህ እናንተ የእኔ የአምላካችሁ ለመሆናችሁ መታሰቢያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡” 11 በሁለተኛው አመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በወሩ ሀያኛ ቀን ደመናው ከቃል ኪዳኑ ምስክር ማደሪያ ላይ ተነሳ፡፡ 12 የእስራኤል ሰዎች ከሲና ምድረበዳ ተነስተው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ደመናው በፋራን ምድረ በዳ ውስጥ ቆመ፡፡ 13 የመጀመሪያ ጉዟቸው፣ በሙሴ በኩል የተሰጣቸውን የያህዌን ትዕዛዝ ተከትለው አደረጉ፡፡ 14 በይሁዳ ትውልዶች ዓርማ ስር ያለው ሰፋሪዎች በመጀመሪያ ተንቀሳቀሱ፡፡ የይሁዳን ሠራዊት የሚመራው የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር፡፡ 15 የይሳኮርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበር፡፡ 16 የዛብሎንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበር፡፡ 17 የማደሪያ ድንኳኑን የተሸከሙት የጌድሶን እና የሜራሪ ትውልዶች፣ ማደሪያ ድንኳኑን ነቅለው ጉዟቸውን ጀመሩ፡፡ 18 ቀጥሎ፣ በሮቤል ሰፈር ሰራዊት ዓርማ ስር የነበሩት ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ የሮቤልን ሰራዊት የሚመራው የሶዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበር፡፡ 19 የስምዖንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራዊ የሱሪስዓይ ልጅ ስለሚኤል ነበር፡፡ 20 የጋድን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነበር፡፡ 21 ቀዓታውያን ተነሱ፡፡ እነርሱ የቅድስተ ቅዱሳኑን ቅዱስ ዕቃዎች ተሸከሙ፡፡ ቀዓታውያን ቀጣዩ ሰፈር ከመድረሳቸው አስቀድሞ ሌሎች ማደሪያ ድንኳን ይተክላሉ፡፡ 22 የኤፍሬምን ሰራዊት የሚመራው የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበር፡፡ 23 የምናሴን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበር፡፡ 24 የብንያምን ትውልዶች ሠራዊት የሚመራው የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበር፡፡ 25 በዳን ትውልዶች ዓርማ ስር የሰፈሩት ሠራዊቶች በመጨረሻ ይወጣሉ፡፡ የዳንን ሰራዊት የሚመራው የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር፡፡ 26 የአቤርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነበር፡፡ 27 የንፍታሌምን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የዔናን ልጅ አኪሬ ነበር፡፡ 28 የእስራኤል ሰዎች ሰራዊቶች ጉዟቸውን ያደረጉት በዚህ መልክ ነው፡፡ 29 ሙሴ ከምድያማዊው የራጉኤል ልጅ ከአባብ ጋር ተነጋገረ፡፡ ራጉኤል የሙሴ ሚስት አባት ነበር፡፡ ሙሴ ከአባብ ጋር ተነጋገረ እንዲህም አለ፣ “ያህዌ እሰጣችኋለሁ ወዳለን ስፍራ እየተጓዝን ነው፡፡ ያህዌ እንዲህ ብሎን ነበር፣ ‘እኔ ለእናንተ የተናገርኩትን እርሷኑ ስፍራ እሰጣችኋለሁ፡፡’ አንተ ከእኛ ጋር አብረኸን ና እኛም መልካም እናደርግልሃለን፡፡ ያህዌ ለእስራኤል መልካም ለማድረግ ቃል ገብቷል፡፡” 30 አባብ ግን ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እኔ ከአንተ ጋር አልሄድም፡፡ እኔ ወደ ገዛ ምድሬና ወደ ራሴ ህዝብ እሄዳለሁ፡፡” 31 ከዚያም ሙሴ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “እባክህን ከእኛ አትለይ፡፡ በበረሃ እንዴት መስፈር እንደሚቻል ታውቃለህ፡፡ ስንሰፍር ልትመለከተን ይገባል፡፡ 32 ከእኛ ጋር ብትሄድ፣ ያህዌ ለእኛ የሚያደርግልንን በጎነት ያንኑ እኛም ለአንተ እናደርግልሃለን፡፡” 33 ከያህዌ ተራራ ተነስተው ለሶስት ቀናት ተጓዙ፡፡ የያህዌ የቃልዳኑ ታቦት የሚያርፍበትን ስፍራ እንዲያገኙ ለመፈለግ ለሶስት ቀናት በፊታቸው ተጓዘ፡፡ 34 ሲጓዙ የያህዌ ደመና በቀን ብርሃን በላያቸው ነበር፡፡ 35 ታቦቱ በተነሳበት ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ እንዲህ ይላል፣ “ያህዌ ሆይ፣ ተነስ፡፡ ጠላቶችህን በትን፡፡ የሚጠሉህ ከአንተ እንዲሸሹ አድርግ፡፡” 36 ታቦቱ በቆመ ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ “ያህዌ ሆይ፣ ብዙ አስር ሺህ ወደሚሆኑት እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር፡፡
ይሄ ማለት እግዚአብሔር የሆነ ሰው መለከት እንዲሰራ ለሙሴ ትዕዛዝን ሰጥተታል ማለት ነው፡፡ራሱ አይደለም የሰራቸወ፡፡“ለአንድ ሰው ሁለት መለከቶቸን እንዲሰራ ንገረው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ መለከቶቹን የሚነፋው ራሱ ሳይሆን መለከቶቹን እንዲነፉ ካህናቱን ያዝዛቸዋል፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“አንተ እዚያው እያለህ” ይሄ ማለት ካህኑ መለከቱን በሚነፋበት ወቅት ሙሴ እዚያው መገኘት አለበት ማለት ነው፡፡
እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆኑ የነገድ ክፍሎችን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡እዚህ ላይ ሁለተኛው ሐረግ ጥቅም ላይ የዋለው የመጀመሪያውን ሐረግ ለማብራራት ሲባል ነው፡፡“የእሥራኤል ነገድ አለቆች የሆኑ መሪዎች”(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ነው፡፡እግዚአብሔር ለሙሴ እየተናገረ ቢሆንም የሚያመለክተው ግን ካህናቱን ነው፡፡ካህናቱ እንጂ ሙሴ መለከቱን አይነፋም፡፡“ከፍ ባለ ድምፅ በሚነፉበት ወቅት”(እናንተ የሚለውን በተለያየ መልክ የሚገልፀውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ነው፡፡እግዚአብሔር ለሙሴ እየተናገረ ቢሆንም የሚያመለክተው ግን ካህናቱን ነው፡፡ካህናቱ እንጂ ሙሴ መለከቱን አይነፋም፡፡“ከፍ ባለ ድምፅ በሚነፉበት ወቅት”(እናንተ የሚለውን በተለያየ መልክ የሚገልፀውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“ቁጥር 2 ጊዜ”ወይም “እንደገና”(ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“ማሕበሩን በአንድነት መሰብሰብ”
“እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ካህናቱን ሲሆን “የእነርሱ”የሚለው ቃል ደግሞ የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡
“ለእናንተ ሕግ ይሁን” እዚህ ላይ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡(እናንተ ለሚለው ቃል የተለያዩ አገላለፆች የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር አንተ የሚለውን ቃል እየተጠቀመ ለሙሴ እየተናገረ ቢሆንም በመሠረቱ የሚናገረው ወደ ጦርነት ለሚወጣው ለእሥራኤል ሕዝብ ነው፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ ወደ ጦርነት በሚወጣበት ወቅት…እሥራኤል በምትገፋበት ወቅት”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚሀ ላይ እግዚአብሔር ሙሴን አንተ እያለ እየተናገረው ቢሆንም በመሠረቱ ግን ሙሴ ካህናቱን መለከት እንዲያስነፋቸው ነበር ይናገረው የነበረው፡፡ (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“ትታሰባላችሁ”የሚለው ሐረግ “ትታወሳላችሁ ማለት ነው፡፡“አስባችኋለሁ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“መከበር”የሚለው ስም “ማክበር”በሚለው ግሥ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በምታከብሩበት ወቅት”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ እግዚአብሔር ለሙሴ ቢናገርም በመሠረቱ ካህናቱ መለከቱን እንዲነፉ ነው የፈለገው፡፡“ካህናቱ መለከቱን እንዲነፉ ትዕዛዝ መሥጠት ይኖርብሃል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
በዕብራውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት አሥራ ሁለት ወራት አሉ፡፡በብርማ ቀለም የሚደምቀው የጨረቃ በርሃን የመጀመሪያው ምዕራፍ በቀን አቆጣጠሩ ላይ የመጀመሪያው ወር መሆኑን ያመለክታል፡፡(የዕብራውያን ወራት የሚለውን ይመልከቱ)
በእነዚህ ሐረጎች ውስጥ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር በመሆኑ የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝበ ነው፡፡(እናንተ ለሚለው ቃል የተለያዩ አገላለፆች የሚለውን መልከቱ)
“ለመሥዋዕቱ ከብር”
“ለእኔ መታሰቢያ ይሆናችኋል” “መታሰቢያ”የሚለው ቃል “መታሰብ”በሚለው ግሥ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እኔን እንድታሰቡ ያደርጋችኋል”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው መለከቶቹንና መሥዋዕቶቹን ነው፡፡
“2ተኛ ዓመት”ይሄ የሚያመለክተው እግዚአብሔር እሥራኤላውያንን ከግብፅ ያወጣበትን ሁለተኛውን ወር ነው፡፡ (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“በ2ተኛውም ወር ከወሩም በ20ኛው ቀን”በዕብራውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት ይሄ ሁለተኛው ወር ነው፡፡”(የዕብራውያን ወራትንና ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ደመናው ብድግ አለ”ወይም “እግዚአብሔር ደመናውን አነሳው”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይ መልከቱ)
መገናኛ ድንኳኑ በዚህ ረዥም በሆነ ሥምም ጭምር የሚጠራበት ምክኒያት የእግዚአብሔር ሕግ ያለበት የቃል ኪዳኑ ሰነድ በውስጡ የሚቀመጥ በመሆኑ ነው፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 1፡50 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸው ትዕዛዛት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሠፈር በይሁዳ ሥር የሚገኙ የተለያዩ ነገዶችን የሚያካትት ነው፡፡ይሁዳን፤ይሳኮርንና ዛብሎንን፡፡
ሌሎቹ ሁሉ ከሠፈራቸው ከመነሣታቸው በፊት እነርሱ ሠፈራቸውን በመጀመሪያ ለቀው ይሄዱ ነበር፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የእነዚህን ሰዎች ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
x
ይሄ የሚያመለክተው የቀአትን የትውልድ ሐረግ ነው፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 3፡27 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ የሚያመለክተው በኤፍሬም ክፍል ውስጥ ያሉትን የነገድ ሠራዊቶችን ነው፡፡ሮቤል፤ስምዖንና ጋድ፡፡ኤፍሬም፤ምናሴና ብንያም፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡10 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡10 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ የሚያመለክተው በዳን ክፍል ውስጥ ያሉትን የነገድ ሠራዊቶችን ነው፡፡ሮቤል፤ስምዖንና ጋድ፡፡ኤፍሬም፤ምናሴና ብንያም፡፡ዳን፤አሴርና ንፍታሌም፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡12 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 1፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ የሰው ሥም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔር ለእኛ የነገረንን”
“ከመልካም አያያዝ ጋር እንንከባከብሃለን”
“ዓይን ትሆንልናለህ”ማለት ምሪት መሥጠትና መንከባከብ ማለት ነው፡፡“በበረሃ ውስጥ ምሪት ልትሰጠንና እንዴት መኖር እንደሚገባን ልታሣየን ትችላለህ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡
ይሄ የሚያመለክተው የሲናን ተራራ ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ፍቺ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የሲና ተራራ፤የእግዚአብሔር ተራራ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የተወሰኑ ሌዋውያን የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው በእሥራኤል ሕዝብ ፊት ይሄዱ ነበር፡፡“እየተጓዙ እያሉ የተወሰኑ ሰዎች የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ፊት ለፊት ይሄዱ ነበር”(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)
“በየዕለቱ”ወይም “ቀን ሣለ”
እዚህ ላይ ታቦቱ ልክ ሰው ይመስል ጉዞ እንደሚጓዝ ዓይነት ነው የሚገለፀው፡፡ታቦቱን የሚሸከሙ ሰዎች ነበሩ፡፡“ታቦቱ በተጓዘ ቁጥር ሰዎች ይሸከሙት ነበር፡፡”(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ተነሳ”የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር ሥራውን እንዲጀምር የሚጠየቅበት ሲሆን በዚህ አውድ ግን ሙሴ ጠላቶቻቸውን እንዲበትንላቸው እየለመነ ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ ጠላቶቹ ከራሱ ከእግዚአብሔር የሚሸሹ ይመስል እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ከእሥራኤል ሕዝብ እንዲሸሹ ምክኒያት እንዲሆንላቸው ነው የሚለምነው፡፡“አንተን የሚጠሉህን ከታቦትህና ከሕዝብህ እንዲሸሹ አድርጋቸው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ታቦቱ ሰው ይመስል እንደሚጓዝ ዓይነት ተደርጎ ነው የሚገለፀው፡፡ታቦቱን የሚሸከሙት ሰዎች ነበሩ፡፡“ሰዎች እንደተሸከሙት ታቦቱ ያርፍ ነበር”(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የሰዎቹን ቁጥር ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ትርጉም የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“እልፍ አእላፋት ሕዝብ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ህዝቡ ያህዌ እየሰማ ስለ ችግሮቻቸው አጉረመረሙ፡፡ ያህዌ ህዝቡን ሰምቶ ተቆጣ፡፡ ከያህዌ ዘንድ እሳት መጥታ በሰፈሩ ዙሪየ ከነበሩ ሰዎች አንዳንዶችን በላች፡፡ 2 ከዚያም ህዝቡ ወደ ሙሴ ጮኸ፣ ስለዚህም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እሳቱም ቆመ፡፡ 3 ስፍራው ተቤራ ተብሎ ተጠራ፣ ምክንያቱም የያህዌ እሳት ከመሀላቸው ሰዎችን አቃጥላለች፡፡ 4 አንዳንድ ባዕዳን ከእስራኤላውያን ትውልዶች ጋር መስፈር ጀመሩ፡፡ እነርሱ የተሻለ ምግብ መብላት ፈለጉ፡፡ ከዚያ የእስራኤል ሰዎች ማልቀስና “እንድንበላ ማን ስጋ ሊሰጠን ይችላል” ማለት ጀመሩ፡፡ 5 በግብጽ በነጻ እንበላ የነበረውን አሳውን፣ ዱባውን፣ በጢኹን፣ ባሮ ሽንኩርቱን፣ ቀይ ሽንኩርቱንና ነጭ ሽንኩርቱን እናስታውሳለን፡፡ 6 አሁን ደካሞች ነን፡፡ ከመና በስተቀር ምንም የምንበላው የለም፡፡” 7 መና እንደ ድንብላል ፍሬ ያለ መልክ ነበረው፡፡ ሙጫ ይመስላል፡፡ 8 ሰዎቹ እየተዘዋወሩ ይሰበስቡታል፡፡ በወፍጮ ይፈጩታል፣ በሙጫ ያደቁታል፣ በገንቦዎቹ ይቀቅሉታል፣ ቂጣ አድርገውም ይጋግሩታል፡፡ እንደ ንጹህ የወይራ ዘይት ይጣፍጣል፡፡ 9 ምሽት በሰፈር ውስጥ ጤዛ ሲወርድ፣ መናውም ይወርዳል፡፡ 10 ሙሴ ህዝቡ በየቤቱ ሲያለቅስ አዳመጠ፣ ደግሞም እያንዳንዱ ሰው በእርሱ ድንኳን ደጃፍ ነበር፡፡ ያህዌ በጣም ተቆጥቶ ነበር፣ ደግም የእነርሱ ማጉረምረም በሙሴ እይታ ስህተት ነበር፡፡ 11 ሙሴ ወደ ያህዌ እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “ለምን ባሪያህን እንዲህ አስጨነከው? ስለምን በእኔ ደስ አልተሰኘህም? የዚህን ህዝብ ሁሉ ሸክም እንድሸከም አደረግከኝ፡፡ 12 እኔ ይህን ህዝብ ሁሉ ፀንሼዋለሁን? ‘አባት ልጁን እነደሚያቅፍ ይህን ህዝብ ወደ ደረትህ አስጠግተህ ተሸከመው’ ትለኝ ዘንድ እኔ ወልጃቸዋለሁን?’ ትሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው ወደ ማልክላቸው ምድር እንዲገቡ እኔ ልሸከማቸውን? 13 ለእነዚህ ሁሉ ሰዎች የምሰጣቸውን ስጋ ከየት አገኛለሁ? በእኔ ፊት እያለቀሱ እንዲህ ይላሉ ‘የምንበላው ስጋ ስጠን፡፡’ 14 እኔ ብቻዬን ይህን ሁሉ ህዝብ ልሸከም አልችልም፡፡ እጅግ በዝተውብኛል፡፡ 15 እንዲህ እስካደረግኸኝ ድረስ፣ አሁኑኑ ግደለኝ፣ ለእኔ መልካም ከሆንክ፣ መከራዬን ከእኔ አርቅ፡፡” 16 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ከእስራኤል መሪዎች ሰባዎቹን ወደ እኔ አምጣ፡፡ የህዝቡ መሪዎችና አለቃዎች መሆናቸውን እርግጠኛ ሁን፡፡ ከአንተ ጋር እንዲቆሙ ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣው፡፡ 17 እኔ ወርጄ በዚያ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፡፡ ከአንተ ላይ ካለው መንፈስ ጥቂት ወስጄ በእነርሱ ላይ አደርገዋለሁ፡፡ እነርሱ ከአንተ ጋር የህዝቡን ሸክም ይሸከማሉ፡፡ አንተ ብቻህን ሸክሙን አትሸከምም፡፡ 18 ለህዝቡ እንዲህ በል፣ ‘ነገ ራሳችሁን ለያህዌ ለዩ፡፡ ያህዌ እየሰማ አልቅሳችኋልና፣ በእርግጥ ስጋ ትበላላች፡፡ እንዲህ ብላችኋል፣ “እንበላ ዘንድ ማን ስጋ ይሰጠናል? ለእኛስ በግብጽ መሆን መልካም ነበር፡፡” ስለዚህ ያህዌ ስጋ ይሰጣችኋል፣ እናም ስጋ ትበላላችሁ፡፡ 19 ስጋ የመትበሉት ለአንድ ቀን፣ ለሁለት ቀናት፣ ለአምስት ቀናት፣ ለአስር ቀናት ወይም ለሃያ ቀናት አይደለም፣ 20 ነገር ግን በአፍንጫችሁ እስኪወጣ ድረስ ወር ሙሉ ስጋ ትበላላችሁ፡፡ ነገሩ ያስጸይፋችኋል፣ ምንያቱም በመሀላችሁ ያለውን ያህዌ እምቢ ብላችኋል፡፡ በፊቱ አልቅሳችኋል፡፡ እንዲህ ብላችኋል፣ “ለምን ከግብጽ ወጣን?” 21 ከዚያ ሙሴ እንዲህ አለ፣ “እኔ ከ600000 ሰዎች ጋር ነኝ፣ አንተ ግን እንዲህ አልክ፣ ‘ወር ሙሉ እንዲበሉ ስጋ አበላቸዋለሁ፡፡’ 22 እነርሱን ለማጥገብ እኛ እንስሳትንና የከብት መንጋ ሁሉ እናርዳለን? እነርሱን ለማርካት የባህር አሶችን ሁሉ እናጠምዳን?” 23 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እጄ አጭር ናትን? አሁን ቃሌ እውነት መሆን አለመሆኑን ታያለህ፡፡” 24 ሙሴ ወጥቶ ለህዝቡ የያህዌን ቃላት ነገራቸው፡፡ ሰባዎቹን የህዝብ መሪዎች ሰበሰበና በድንኳኑ ዙሪያ አቆማቸው፡፡ 25 ያህዌ በደመና ውስጥ ወረዳና ሙሴን ተናገረው፡፡ ያህዌ በሙሴ ላይ ከነበረው መንፈስ ጥቂት ወሰደና በሰባዎቹ ሽማግሌዎች ላይ አደረገው፡፡ መንፈሱ ሲያርፍባቸው፣ ትንቢት ተናገሩ፣ ነገር ግን በዚያ ወቅት እንጂ በሌላ ጊዜ ደግመው አልተነበዩም፡፡ 26 አልዳድና ሞድ የተባሉ ሁለት ሰዎች በሰፈር ቀርተው ነበር፡፡ መንፈሱ በእነርሱ ላይም አረፈ፡፡ ስሞቻቸው በመዝገብ ተጽፎ ነበር፣ ነገር ግን ወደ ድንኳኑ አልሄዱም ነበር፡፡ ሆኖም ግን፣ እነርሱም በሰፈር እያሉ ተነበዩ፡፡ 27 በሰፈር የነበረ አንድ ወጣት ሰው ወደ ሙሴ ሮጦ መጥቶ እንዲህ አለው፣ “ኤልዳድና ሞዳድ በሰፈር ውስጥ እየተነበዩ ነው፡፡” 28 ከእርሱ የተመረጡ ሰዎች አንዱ የሆነው የሙሴ ረዳት የነዌ ልጅ ኢያሱ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አለቃዬ ሙሴ ሆይ፣ ከልክላቸው፡፡” 29 ሙሴ እያሱን እንዲህ አለው፣ “አንተ ለእኔ ተቆርቁረህ ነውን? እኔ መላው የያህዌ ህዝቦች ነቢያት ቢሆኑ እርሱ በሁሉም ላይ መንፈሱን ቢያደርግ እመኛለሁ!” 30 ከዚያ ሙሴና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ሰፈር ተመለሱ፡፡ 31 ከዚያ ከያህዌ ዘንድ ነፋስ ወጥቶ ከባህር ድርጭቶችን አመጣ፡፡ ከሰፈሩ በአንድ በኩል የአንድ ቀን የእግር መንገድ ርቀት ላይ፣ ደግሞም በሌላኛው በኩል በአንድ ቀን የእግር መንገድ ርቀት ድረስ ድርጭቶቹ ወደቁ፡፡ ድርጭቶቹ ሰፈሩን ከመሬት ሁለት ኪዩብ ከፍታ በሚሆን መጠን ሞሉት፡፡ 32 ሰዎቹ ያን ዕለት ምሽቱን ጨምሮ እንዲሁም በማግስቱም ድርጭቶችን በመሰብሰብ ሥራ ተጠምደው ነበር፡፡ ማንም ከአስር የቆሮስ መስፈሪያ ያነሰ ድርጭት አልሰበሰበም፡፡ በሰፈሩ ሁሉ ድርጭቶቹን ተከፋፈሉ፡፡ 33 ስጋው ገና በጥርሳቸው ውስጥ እያላመጡት ሳለ፣ ያህዌ በእነርሱ ላይ ተቆጣ፡፡ ህዝቡን በታላቅ በሽታ መታው፡፡ 34 በዚያ ሥፍራ ስጋ ለማግኘት የጎመጁትን ሰዎች ስለቀበሯቸው የስፍራው ስም ቂብሮት ሃታአባ ተባለ፡፡ 35 ሰዎቹ ከቂብሮት ሃታአባ ወደ ሰፈሩበት ወደ ሐጽሮት ተጓዙ፡፡
“እግዚአብሔር የሚያነድን እሣት ላከ”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለዚያ ሥፍራ ሥም ሰጡት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እሥራኤላውያን ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ከመና ሌላ ተጨማሪ የሚበሉት ነገር እንደሚፈልጉ ለመጠየቅ ነበር፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሥጋ የመብላት መሻት አለን”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“መብላት አንፈልግም” ወይም“” “መብላት አንችልም”
የዚህ ዕፅዋት ዘር በሚደርቅበት ጊዜ በቅመምነት ያገለግላል፡፡
ይሄ የሚያጣብቅ ነገር ያለው ሲሆን የገረጣ ቢጫ ቀለም አለው፡፡
ዓይኑ መመልከቱን የሚያመለክት ሲሆን መመልከቱ ደግሞ አስተሳሰቡን ወይም የፍርድ አሰጣጡን ይወክላል፡፡“በሙሴ አስተሳሰብ”ወይም “በሙሴ ዳኝነት”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ምላሽ የማያሻቸውን ብዙ ጥያቄዎች ለእግዚአብሔር ያቀርባል፡፡(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እነዚህን ጥያቄዎች የጠየቀው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ባለው ግንኙነት ላይ የተቃውሞ ጥያቄ ለማቅረብ ነበር፡፡በድርጊት መልክ ሊገለፁ ይችላሉ፡፡ሙሴ ስለራሱ በሶስተኛ አካልነት ነው የሚናገረው፡፡“እኔ ባሪያህን በእንደዚህ ዓይነት መጥፎ ሁኔታ መያዝ አልነበረብህም፡፡በእኔ ልትናደድ አይገባም”ወይም “እኔ ባሪያህ ያጠፋሁት ጥፋት ስለሌለ ጥሩ ባልሆነ ሁኔታ እኔን መያዝ አልነበረብህም!”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄንና የመጀመሪያ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ አካል የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ሕዝቡን የመምራቱንና የሚያስፈልጋቸውን ነገር የመሥጠቱን ነገር ልክ ከባድ የሆነ ሸክምን ከመሸከም ጋር ያነፃፅረዋል፡፡“ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ኃላፊነትን ሰጠኸኝ፤እኔ ግን ከብዶኛል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ይህን ጥያቄ የሚጠይቀው አባታቸው እንዳልሆነ እግዚአብሔርን ለማሳሰብ ነው፡፡“የእነዚህ ሰዎች ሁሉ አባት አይደለሁም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እግዚአብሔር እንዲያስታውስለት የፈለገው ምንም እንኳን አባታቸው ባይሆንም እሥራኤላውያንን መንከባከብ እንደሚገባው መናገሩን ነበር፡፡“እኔ ስላልወለድኳቸው እንደ ሕፃን ልጅ ተሸከማቸው ልትለኝ አትችልም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
እሥራኤላውያንን መንከባከብ ልክ ዕርዳታ የሚያሻውን ሕፃን ልጅ ከመሸከም ጋር ተነፃፅሯል፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህ ዓረፍተ ነገር ትርጉም የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“እንድሸከማቸው እንድሰጣቸው መጠበቅ የለብህም!”ወይም “ልሸከማቸው አልችልም...ልሰጣቸው”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ይሄንን ጥያቄ የሚያነሳው ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ሥጋ መሥጠት የማይቻል መሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡“ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚበቃ ሥጋ ለማግኘት የምችልበት ሁኔታ የለም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ የመምራቱንና ለሕዝቡ የሚያስፈልጋቸውን ነገር የማቅረቡን ጉዳይ ልክ እነርሱን እንደሚሸከም ዓይነት አድርጎ ይገልፀዋል፡፡“ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለብቻዬ ለማቅረብ አልችልም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“ይሄ ኃላፊነት ለእኔ አስቸግሮኛል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“መንፈስ”የሚለው ቃል እግዚአብሔር ለሙሴ የተናገረውን ነገር እንዲያደርግ ኃይል የሚሰጠውን የእግዚአብሔርን መንፈስ ነው የሚያመለክተው፡፡“እግዚአብሔር የሰጠህ በአንተ ያለው መንፈስ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር የመምራቱንና አስፈላጊ ነገሮችን የማቅረቡን ጉዳይ ልክ ሙሴና ሌሎች መሪዎቹ እንደሚሸከሙት ነገር አድርጎ ነው የሚገልፀው፡፡“የሕዝቡን ሸክም ከአንተ ጋር ይሸከማሉ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር የመምራቱንና ለሕዝቡ አስፈላጊ ነገሮችን የማቅረቡን ጉዳይ ልክ ሙሴና ሌሎች መሪዎቹ እንደሚሸከሙት ነገር አድርጎ ነው የሚገልፀው፡፡“ብቻህን አትሸከማቸውም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እሥራኤላውያን ይህንን ጥያቄ ያቀረቡት ከመና ሌላ ተጨማሪ የሚበሉት ነገር እንደሚፈልጉ ለመጠየቅ ነበር፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሥጋ የመብላት ፍላጎት አለን”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/እግዚአብሔር ምግቡ በትውከት መልክ በአፍንጫቸው እንደሚወጣ ነው የሚናገረው፡፡“ታምማችሁ እስክታስታውኩ ድረስ”ወይም “በአፍንጫው በሚወጣበት ሁኔታ እጅግ ብዙ ሥጋን ይበላሉ” “በአፍንጫቸው የሚወጣ እስኪመስል ድረስ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሕዝቡ ይሄንን ጥያቄ የጠየቀው ቅሬታውን ለመግለፅና አቤቱታን ለማቅረብ ነበር፡፡“ከግብፅ ምድር መውጣት አልነበረብንም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“ስድስት መቶ ሺህ ሕዝብ” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያቀርበው ሕዝቡ እንዲጠግብ ለማድረግ በቂ ሥጋ ስለመኖሩ ጥርጣሬ ስለገባው ነው፡፡ “እነርሱን ለማጥገብ የበሬና የበግ መንጋ እንዲሁም የባህርን ዓሣ ሁሉ መግደል ይኖርብናል”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ቃላት ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡በአንድነት የሚያመለክቱት ነገር ቢኖር ብዙ ከብቶች የመኖራቸውን ጉዳይ ነው፡፡(ሁለት ተመሳሳይ ገፅታ ያላቸው የሚለውን ይመልክቱ)
“ሁሉ” የሚለው ቃል የተጋነነ ሲሆን ለእሥራኤል ሕዝብ ሁሉ ምግብ ለማቅረብ የማይቻል መሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡(የተጋነነ ንፅፅር እና አጠቃላይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“ረሃባቸውን ለማስታገስ”
እዚህ ላይ “እጅ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ኃይል ነው፡፡እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው እግዚአብሔር ለሕዝቡ በቂ ሥጋ ሊሰጥ አይችልም ብሎ በማሰቡ ሊገስፀው ነው፡፡“ይህንን የማድረግ በቂ ኃይል የለኝም ብለህ ታስባለህ?”ወይም “ይህንን ለማድረግ ከበቂ በላይ ኃይል እንዳለኝ ማወቅ ይኖርብሃል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውንና ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔር የተናገረው ነገር”
“መንፈስ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለሙሴ የተሰጠውን የእግዚአብሔርን መንፈስ ነው፡፡ተመሳሳይ ሐረጎችን በኦሪት ዘኁልቁ 11፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ለሙሴ የሰጠው የተወሰነ ኃይል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ለሽማግሌዎቹ ኃይልን መሥጠት መንፈስን በእነርሱ ላይ ማድረግ በሚል መልኩ ነው የተገለፀው፡፡ተመሣሣዩን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 11፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ለሰባ ሽማግሌዎች ሰጠ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ከመንፈሱ ኃይል ማግኘትን መንፈሱ እንደወረደባቸው ተደርጎ ተነግሯል፡፡“ከመንፈሱ ኃይልን ባገኙበት ወቅት”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ከመንፈሱ ኃይል ማግኘትን መንፈሱ እንደወረደባቸው ተደርጎ ተነግሯል፡፡“መንፈሱ ኃይልን ሰጣቸው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴ ሥማቸውን በዝርዝሩ ውስጥ ፃፈው”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“መተንበዩን እንዲያቆሙ ንገራቸው”
ሙሴ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው እግዚአብሔርን ለመውቀስ ነበር፡፡አስፈላፊ ሆኖ ከተገኘ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለእኔ ስትል ልትቀና አይገባህም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
አስፈላጊ ከሆነ እግዚአብሔር የሚቀናበት ነገር ምን እንደሆነ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ለእኔ የሆነውን ነገር ሊወስዱ ይችላሉ ብለህ ሰጋህን?”ወይም “ሰዎች ሥልጣኑን አያከብሩለትም ብለህ ተጨነቅክን?”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሰዎች ኃይል የሚሰጠውን የእግዘአብሔርን መንፈስ ልክ እግዚአብሔር መንፈሱን በእነርሱ ላይ እንደሚያስቀምጥ አድርጎ ይገልፀዋል፡፡“የእግዚአብሔር መንፈስ ኃይልን ሁሉ ይሰጣቸው ዘንድ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ትንሽ ወፍ”(ያልታወቁትን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)
“በእያንዳንዱ አቅጣጫ አንድ ሰው ቀኑን ሙሉ የሚጓዝበትን መንገድ ያህል”
ክንድ የመለኪያ ዓይነት ሲሆን 46 ሴንቲ ሜትር አካባቢ ይሆናል፡፡“92 ሴንቲ ሜትር ያህል” ወይም “አንድ ሜትር ያህል” (መፅሐፍ ቅዱሣዊ ርቀትንና ቁጥሮችን ይመልከቱ)
ይሄ ድርብ አሉታዊ ሲሆን በአዎንታዊ ዓረፍተ ነገር ሊገለፅም ይችላል፡፡
የቆሮስ መሥፈሪያ የመለኪያ ዓይነት ሲሆን 220 ሊትር ያህል ይሆናል፡፡“220 ሊትር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ የመጠን መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡አንድ ላይ በመሆን አፅንዖት የሚሰጡት ሥጋውን ገና እየበሉ እያሉ ያኔውኑ እግዚአብሔር ቅጣቱን የላከባቸው መሆኑን ነው፡፡“ገና ሥጋውን እየበሉ እያሉ”(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሥፍራውን የምኞት መቃብር ብለው ጠሩት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውንና ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በበረሃ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ስፍራ ስም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
1 “ከዚያ ማርያም እና አሮን ሙሴ ባገባት ኩሻዊ ሴት ምክንያት በሙሴ ላይ በተቃውሞ ተናገሩ፡፡ 2 እንዲህም አሉ፣ “ያህዌ የተናገረው ከሙሴ ጋር ብቻ ነውን? ከእኛስ ጋር አልተናገረምን?” ያህዌ እነርሱ የተናገሩትን ሰማ፡፡ 3 ሙሴ ፣ በምድር ላይ ከሚገኝ ከማንኛውም ሰው ይልቅ በጣም ትሁት ሰው ነበር፡፡ 4 ወዲያውኑ ያህዌ ከሙሴ፣ ከአሮንና ማርያም ጋር ተናገረ “እናንተ ሶስታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን ውጡና ኑ፡፡” ስለዚህም ሶስቱም ወጥተው መጡ፡፡ 5 ከዚያም ያህዌ በደመና አምድ ወረደ፡፡ በድንኳኑ መግቢያ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራቸው፡፡ ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ፡፡ 6 ያህዌ እንዲህ አለ፣ “አሁን ቃሎቼን ስሙ፡፡ አንድ የእኔ ነብይ በመካከላችሁ ሲሆን፣ ራሴን፣ በራዕይ እገልጥለታለሁ፣ በህልምም እናገረዋለሁ፡፡ 7 አገልጋዬ ሙሴ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ እርሱ በቤቴ ላይ ሁሉ የታመነ ነው፡፡ 8 እኔ ከመሴ ጋር በቀጥታ እናገራሁ፣ በራዕይ ወይም በዘይቤ አይደለም፡፡ እርሱ የእኔን መልክ ያያል፡፡ ስለዚህ በአገልጋዬ በሙሴ ላይ ስትናገሩ ለምን አልፈራችሁም?” 9 የያህዌ ቁጣ በእነርሱ ላይ ነደደ፣ ከዚያም ትቷቸው ሄደ፡፡ 10 ደመናው ከድንኳኑ ላይ ተነሳ፣ እናም ማርያም በድንገት በለምጽ ተመታች እንደ በረዶ ነጭ ሆነች፡፡ አሮን ወደ ማርያም ዞር ብሎ ሲመለከታት በልምጽ መመታቷን አየ፡፡ 11 አሮን ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እባክህን በአንተ ላይ የፈጸምነውን ይህን በደል አትቁጠርብን፡፡ በስንፍና ተናግረናል፣ ደግሞም በድለናል፡፡ 12 እባክህን ከእናቱ ማህጸን ሲወጣ ጭንጋፍ ሆኖ እንደ ተወለደ ከፊል አካሉ እንደተበላ ሆና አትተዋት፡፡” 13 ስለዚህም ሙሴ ወደ ያህዌ ጮኸ፡፡ እንዲህም አለ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህ፣ እባክህ ፈውሳት፡፡” 14 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አባቷ በፊቷ ላይ ቢተፋባት፣ ለሰባት ቀናት በሀፍረት ትቆያለች፡፡ ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት ዝጋባት፡፡ ከዚያ በኋላ መልሰህ አምጣት፡፡” 15 ስለዚህም ማርያም ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት ተዘጋባት፡፡ እርሷ ወደ ሰፈር እስክትመለስ ድረስ ህዝቡ ጉዞ አላደረገም፡፡ 16 ከዚያ በኋላ፣ ህዝቡ ከሐዴሮት ተነስቶ ተጓዘና በፋራን ምድረበዳ ሰፈረ፡፡
ማርያምና ሙሴ ይሄንን ጥያቄ የጠየቁት ሙሴ ብዙ ሥልጣን ሲኖረው እኛ ግን የሚገባንን ያህል ሥልጣን የለንም በሚል ምክኒያት ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር የተናገረው ለሙሴ ብቻ አይደለም፡፡ከእኛም ጋር ተነጋግሯል፡፡”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “አሁን”የሚለው ቃል ከዚህ ቀጥሎ ላለው አስፈላጊ ነጥብ ሰው የበለትኩረት እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
“አሁን”የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በዋናው ታሪክ ላይ እረፍት ለመሥጠት ነው፡፡ተራኪው የሙሴን ባህርይ በሚመለከት የጀርባ ታሪኩን ይናገራል፡፡(የጀርባ ታሪክ የሚለውን ይመልከቱ)
የደመናው ቅርፅ አምድ እንደሆነ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“የአምድ ቅርፅ ያለው ደመና”ወይም “ረዥም ደመና” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ለሙሴ እንደዚያ አልናገርም”
እዚህ ላይ ቤቴ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን አገር ነው፡፡በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ መሆን እሥራኤልን ለመምራት ታማኝ መሆንን ያመለክታል፡፡“ሙሴ ሕዝቤን በታማኝነት ይመራል”ወይም“ሕዝቤን እሥራኤልን እንዲመራ እምነት የምጥልበት ሙሴን ነው” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ የጠየቀው ማርያምንና አሮንን ለመገሰፅ ነው፡፡በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይቸላል፡፡“ባሪያዬን ሙሴን በመቃወም ለመናገር መፍራት ነበረባችሁ፡፡”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“በሙሴ ላይ”የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር የሚናገረው ባሪያው እርሱ ስለመሆኑ ግልፅ ይሆናል፡፡“በባሪያዬ በሙሴ ላይ”(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
የእግዚአብሔር ቁጣ እሣት እንደሆነ ዓይነት ተደርጎ ነው የተነገረው፡፡“እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ በጣም ተቆጣ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ለምፅ የማርያምን ሥጋ ወደ ነጭነት ቀየረው፡፡“በጣም ነጭ ሆነ”(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
የሰዎችን ኃጢአት መያዝ ማለት ለፈፀሙት ኃጢአት ተጠያቂ ናቸው ማለት ነው፡፡ይሄ የሚያመለክተው በኃጢአታቸው የመቀጣታቸውን ጉዳይ ነው፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
በማርያም ላይ የተጣበቀባት ለምፅ ሕይወቷ እስኪያልፍ ድረስ ሥጋዋ እየበሰበሰ እንዲሄድ የሚያደርግ ነበር፡፡እየበሰበሰ የሚሄደው ሥጋ ልክ እንደሚባላ ነገር ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ከእናቱ ሆድ በወጣ ጊዜ ግማሽ ሥጋው ተበልቶ እንደሞተ አትሁን”(ተነፃፃሪ የሚለውንና ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“እባክህ”የሚለው ቃል የተደገመው ለጉዳዩ አፅንዖት ለመሥጠት ነው፡፡
ይሄ የሚያመለክተው ሊሆን ይችል የነበረ ነገር ተግባራዊ አለመደረጉን ነው፡፡በአንድ ሰው ፊት ላይ ምራቅ መትፋት ትልቅ ስድብ ነበር፡፡(በግምት ላይ የተመሠረቱ ሁኔታዎችንና ተምሣሌታዊ ድርጊቶች የሚለውን ይመልከቱ)
ከሠፈር ውስጥ ከወጣች በኋላ ተመልሣ ለመምጣት ያለመቻሏን ሁኔታ ልክ ከጀርባዋ በር እንደተቆለፈባት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ማርያም ከሠፈር ውጪ እንደትሄድ ተደረገ”ወይም “ማርያም ከሠፈር ውጪ እንድትሆን ተደረገ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልከ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴ ማርያምን ከሠፈር ውጪ ዘጋባት”ወይም “ሙሴ ማርያምን ከሠፈር ውጪ ላካት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በበረሃ ውስጥ ያለ የአንድ ሥፍራ ሥም ነው፡፡ይህንን በኦሪት ዘኁልቁ 11፡35 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
1 ዚያም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 ”ለእስራኤላውያን የሰጠኋቸውን የከነዐንን ምድር እንዲያዩ ጥቂት ሰዎችን ላክ፡፡ ከአባቶቻቸው ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሰው ላክ፡፡ ከመሀላቸው የሚላከው እያንዳንዱ ሰው መሪ መሆን አለበት፡፡” 3 ሙሴ የያህዌን ትእዛዝ እንዲያደርጉ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፡፡ ሁሉም ከእስራኤል ሰዎች መሃል የተመረጡ መሪዎች ነበሩ፡፡ 4 ስሞቻቸው እነዚህ ነበሩ፡ ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፡፡ 5 ከስምዖን ነገድ፣ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፡፡ 6 ከይሁዳ ነገድ፣ የዩፎኒ ልጅ ካልብ፡፡ 7 ከይሳኮር ነገድድ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፡፡ 8 ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፡፡ 9 ከብንያም ነገድ፣ የራፋ ልጅ ፈልጢ፡፡ 10 ከዛብን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፡፡ 11 ከዮፍ ትውልዶች፣ ይህም፣ ከምናሴ ነገድ ነው፣ የሱሲን ልጅ ጋዲ፡፡ 12 ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፡፡ 13 ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፡፡ 14 ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፡፡ 15 ከጋድ ነገድ፣ የማኪ ልጅ ጉዲኤል ነበሩ፡፡ 16 ምድሪቱን እንዲያዩ ሙሴ የላቸው ሰዎች ስሞች እነዚህ ነበሩ፡፡ ሙሴ የነዌ ልጅ አውሴን፣ ኢያሱ ብሎ ጠራው፡፡ 17 ሙሴ እነርሱ የከነዓንን ምድር እንዲያዩ ላካቸው፡፡ እንዲህ አላቸው፣ “ከነጌብ ጀምራችሁ እስከ ተራራማው አገር ድረስ ሂዱ፡፡ 18 ምድሪቱ ምን እንደምትመስል ተመልከቱ፡፡ በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን እዩ፣ ጠንካሮች ወይም ደካሞች መሆናቸውን፣ እና ጥቂት ወይም ብዙ መሆናቸውን ተመልከቱ፡፡ 19 የሚኖሩባት ምድር ምን እንደምትመስል እዩ፡፡ መልካም ናት ወይስ መጥፎ? በዚያ ምን አይነት ከተሞች አሉ? ሰፈር አይነት ናቸው? የተቀጠሩ ከተሞችስ ናቸውን? 20 ምድሪቱ ምን እንደምትመስል እዩ፣ ለእርሻ የተመቸች ናት ወይስ አይደለችም፣ በዚያ ዛፎች አሉ ወይስ የሉም፡፡ ብርቱ ሁኑና ከምድሪቱ ምርት ከየአይነቱ ይዛችሁ ኑ፡፡” ወቅቱ የወይን ፍሬ ማፍራት የጀመረበት ነበር፡፡ 21 ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው በሌለቦ ሐማት አጠገብ፣ ከጺን ምድረበዳ እስከ ሌቦ ድረስ ምድሪቱን ተመለከቱ፡፡ 22 ከኔጌብ ወጥተው እስከ ኬብሮን ደረሱ፡፡ ከዔናቅ ነገድ ዝርያ የሆኑ የአኪመን፣ የሴሲና፣ እና የተላሚ ነገዶች በዚያ ነበሩ፡፡ ኬብሮን ግብጽ ውስጥ የተመሰተረችው ከከጣኔዎስ ሰባት አመት ቀደም ብላ ነበር፡፡ 23 ኤሽኮል ሸለቆ ሲደርሱ፣ የወይን ዘለላ የያዘ ቅርንጫፍ ቆረጡ፡፡ ከቡድናቸው በሁለቱ መሃል በበትር አድርገው የወይኑን ዘለላ ተሸከሙት፡፡ እንደዚሁም ሮማንና በለስም አመጡ፡፡ 24 የእስራኤል ሰዎች በዚየ ከቆረጡት የወይን ዘለላ የተነሳ፣ ያቺ ስፍራ የኤሽኮል ሸለቆ ተብላ ተጠራች፡፡ 25 ምድሪቱን መርምረው ከአርባ ቀናት በኋላ ተመለሱ፡፡ 26 የተላኩት ሰዎች፣ ሙሴና አሮን እንዲሁም መላው የእስራኤል ማህበረሰብ ወዳሉበት በፋራን ምድረበዳ ወደምትገኘው ወደ ቃዴስ መጡ፡፡ ወደ እነርሱና ወደ መላው ማህበረሰብ ተመልሰው መጥተው፣ የምድሪቱን ፍሬ አሳይዋቸው፡፡ 27 ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “ወደ ላከን ምድር ደረስን፡፡ በእርግጥም ወተትና ማር ታፈሳለች፡፡ ከምድሪቱ ምርት እነሆ፡፡ 28 ሆኖም፣ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ናቸው፤¨ከተሞቹም የተመሸጉና ትላልቅ ናቸው፡፡ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዝርያዎችም አይተናል፡፡ 29 አማሌቃውያን በነጌብ ይኖራሉ፡፡ ኬጢያውያን፣ ኢያቡሳዊያን፣ እና አሞራዊያን በተራራማው አገር ይኖራሉ፡፡ ከነዓናዊያን በባህሩ አቅራቢያ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ይኖራሉ፡፡” 30 ከዚያ ካሌብ በሙሴ ዙሪያ የተሰበሰቡበትን ሰዎች ሊያበረታታቸው ተነሳ፣ እንዲህም አለ፣ “በአንድ ጊዜ ተነስተን እንውጣና ምድራቸውን እንውረስ፣ ምክንያቱም በሚገባ ልናሸንፍ እንችላለን፡፡” 31 ግን ከእርሱ ጋር የሄዱት ሌሎች ሰዎች እንዲህ አሉ፣ “እኛ ሰዎቹን ማጥቃት አንችልም ምክንያቱም እነርሱ ከእኛ ይልቅ ጠንካሮች ናቸው፡፡” 32 ስለዚህም ስለተመለከቷት ምድር በእስራኤለ ሰዎች መሀል ተስፋ አስቆራጭ ወሬ አሰራጩ፡፡ እንዲህም አሉ፣ “የተመለከትናት ምድር በላይዋ የሚኖሩትን የምትበላ ናት፡፡ በዚያ ያየናቸው ሰዎ ሁሉ ቁመተ ረጃጅም ሰዎች ናቸው፡፡ 33 በዚያ የኤናቅ ዝርያዎችን አይተናል፣ ከግዙፋኑ ሰዎች የመጡትን ግዙፎቹን ሰዎች አይተናል፡፡ ከእነርሱ ጋር ስንተያይ፣ በእኛ በራሳችን ዐይን እንደ አንበጣ ነበርን፣ ደግሞም በእነርሱም ዐይን እንደዚሁ ነበርን፡፡”
እግዚአብሔር የከነዓንን ምድር ለእሥራኤል ሕዝብ ለመስጠት የወሰነ ቢሆንም ወደዚያ ግን አልገቡም ነበር፡፡“ልሰጥ የወሰንኩትን”ወይም “በቅርቡ የምሰጠውን”(የቆየ ትንቢት የሚለውን ይመልከቱ)
“አንተ የላክኸው እያንዳንዱ ሰው በነራሱ ነገድ መካከል አለቃ መሆን ይኖርበታል፡፡”
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁሉ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁሉ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
በዮሴፍና በምናሴ መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ነገድ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁሉ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
የእነዚህን ሰዎች ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 13፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ሙሴ ይህን ጥያቄ የሚጠይቀው የተላኩት ሰዎች በሚመለሱበት ወቅት ሊያቀርቡ የሚገባቸውን መረጃ በሚመለከት ግልፅ ለማድረግ በመፈለግ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “ምድሪቱ መልካም ወይም ክፉ፤ምን ዓይነት ከተሞች እንዳሉ፤ከተሞቹ ሰዎች የሚኖሩባቸው ሠፈሮች ብቻ እንደሆኑ ወይም የጦር ምሽግ መኖር አለመኖሩን አጣሩ” (ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
የተመሸጉ ከተሞች ራሣቸውን ከጠላት ጦር ለመከላከል ሲሉ ጠንካራ ቅጥሮች ይኖሯቸዋል፡፡ሠፈሮች ግን እንደዚህ ዓይነት ቅጥሮች የሏቸውም፡፡
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ጺን” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ቋንቋ ምድረ በዳ ማለት ነው፡፡(ቃላትን መዋስና መቅዳት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ግብፃውያን ጺንን ከመገንባታቸው ሰባት ዓመታት በፊት ከነዓናውን ኬብሮንን ገንብተዋት ነበር” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ በየአባቶቻቸው ቤቶች የነገድ ስሞች አንፃር የተሰየሙ ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሰው ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የቦታ ስም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“በየወገኖቻቸው ባሉ ሁለት ሰዎች መካከል”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለዚያ ሥፍራ ሥም ሰጡት” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ከ40 ቀናት በኋላ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ቃል”የሚለው የሚያመለክተው መረጃን ነው፡፡“መረጃቸውን ይዘው ተመለሱ” ወይም “የተመለከቱትን ነገር ዘገቡ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“በእርግጥም ወተትና ማር እዚያ ይፈስሳሉ”ምድሪቱ ለእንስሳትና ለዕፅዋት ተስማሚ መሆኗን ለመግለፅ ከእነዚያ እንስሳት የሚገኘው ወተትና ማር በምድሪቱ ላይ እንደሚፈስስ ነገር አድርገው ይገልፁታል፡፡“ከብቶችን ለማሳደግና አህልን ለማግኘት ድንቅ የሆነ ሥፍራ ነው”ወይም “በእርግጥም ለምለም የሆነ አገር ነው”ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ወተት ከላምና ከፍየል የሚገኝ ነገር በመሆኑ ከብቶችንና ከከብቶች የሚገኘውን ምገብ ያመለክታል፡፡“ከከብቶች የሚገኝ ምግብ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ማር ከአበቦች የሚገኝ ነገር በመሆኑ ዕፅዋትንና ከዕፅዋት የሚገኘውን ምገብ ያመለክታል፡፡“ከዕፅዋት የሚገኝ ምግብ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከካሌብና ከኢያሱ በስተቀር በጊዜው ለስለላ የሄዱትን ሰዎች ሁሉ ነው፡፡
ሰዎቹ ምድሪቱ ወይም በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች እጅግ አደገኞች መሆናቸውን ለመግለፅ ምድሪቱ ሰዎችን የምትበላ እንደሆነች አድርገው ያቀርቡታል፡፡“እጅግ አደገኛ ምድር”ወይም “ሰዎቹ ነፍሳችንን የሚያጠፉበት ምድር” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሰው ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ማየት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ግምገማንና የፍርድ ውሳኔ መሥጠትን ነው፡፡“በእኛ አስተሳሰብ…በእነርሱ አስተሳሰብ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎቹ ስለ አንበጣ የተናገሩት በዚያ ምድር ካሉት ሰዎች ጋር ራሣቸውን ሲያነፃፅሩ ምን ያሀል ትንሽ መሆናቸው እንደተሰማቸው ለመግለፅ ብለው ነው፡፡“እኛን ከእነርሱ ጋር ስናነፃፅረው የአንበጣ ያህል ትናንሾች ነን›፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
1 “በዚያን ምሽት ማህበረሰቡ በሙሉ ድምጹን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፡፡ 2 እስራኤል ሰዎች ሁሉ ሙሴንና አሮንን ነቀፉ፡፡ መላው ማህበረሰብ እንዲህ አሏቸው፣ “በግብጽ ምድር ብንሞት ይሻለን ነበር፡፡ ውይም ምነው በዚህ በረሃ በሞትን ኖሮ! 3 ያህዌ ለምን በዚህ ምድረበዳ በሰይፍ እንድንሞት ወደዚህ ምድር አመጣን? ሚስቶቻችንና ትናንሽ ልጆቻችን የተጠቁ ይሆናሉ፡፡ ወደ ግብጽ መመለስ አይሻለንምን?” 4 እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “ሌላ መሪ እንምረጥ፣ እናም ወደ ግብጽ እንመለስ፡፡” 5 ከዚያ ሙሴና አሮን በእስራኤል ህዝብ በማህበረሰቡ ጉባኤ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፡፡ 6 ምድሪቱን ለማየት ከወጡት ውስጥ ከነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዩፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፡፡ 7 እስራኤል ሰዎች መላው ማህበረሰብ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፣ “በውስጧ ያለፍነውና የተመለከትናት ምድር በጣም መልካም መድር ናት፡፡ 8 ያህዌ በእኛ ደስ ከተሰኘ፣ ወደዚህች ምድር ያስገባናል ደግሞም እርሷን ለእኛ ይሰጠናል፡፡ ምድሪቱ ወተትና ማር የምታፈስ ናት፡፡ 9 ነገር ግን በያህዌ ላይ አታምጹ፣ ደግሞም በምድሪቱ የሚኖሩትን ህዝቦች አትፍሩ፡፡ በቀላሉ እንደ ምግብ እንበላቸዋለን፡፡ ጥላቸው ከእነርሱ ተገፏል፣ ምንያቱም ያህዌ ከእኛ ጋር ነው፡፡ እነርሱን አትፍሯቸው”፡፡ 10 ነገር ግን መላው ማህበረሰብ እስከ ሞት ሊወግሯቸው ተነሰቡቸው፡፡ ከዚያ የያህዌ ክብር በመገናኛው ድንኳን ለመላው የእስራኤል ሰዎች ታየ፡፡ 11 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ይህ ህዝብ እስከ መቼ እኔን ይንቀኛል በመካከላቸው በሃይሌ ያደረኳቸውን ምልክቶች እያዩ እንኳን እስከ መቼ በእኔ አያምኑም 12 በበሽታ እመታቸዋለሁ፣ ወደ ርስታቸው አላስገባቸውም፣ ሆኖም ከአንተ ከራስህ ነገድ ከእነርሱ ይልቅ ታላቅና ሃያል ህዝብ አበጃለሁ፡፡” 13 ሙሴ ያህዌን እንዲህ አለው፣ “ይህን ብታደርግ፣ ግብጻዊያን ስለዚህ ነገር ይሰማሉ፣ ምክንያቱም አንተ ይህን ህዝብ በኃይልህ ከእነርሱ አድነሃቸዋል፡፡ 14 ለዚህች ምድር ነዋሪዎች ይህንን ይናገራሉ፡፡ አንተ ያህዌ፣ ከዚህ ህዝብ ጋር እንደሆንክ እነርሱ ሰምተዋል፣ ምክንያቱም አንተ ፊት ለፊት ታይተሃል፡፡ የአንተ ደመና በእኛ ህዝብ ላይ ሆኗል፡፡ አንተ በእነርሱ ፊት በቀን በደመና አምድ በምሽት በእሳት አምድ ሄደሃል፡፡ 15 አሁን ይህንን ህዝብ እንደ አንድ ሰው ብትገድል፣ ዝናህን የሰሙ ህዝቦች እንዲህ ይላሉ፣ 16 ‘ያህዌ ይህንን ህዝብ ሊሰጣቸው ወደ ማለላቸው ምድር ሊያስገባቸው ባለመቻሉ ምክንያት፣ በምድረበዳ ገደላቸው፡፡ 17 አሁን፣ እኔ እለምንሃለሁ፣ ታላቁን ሀይልህን ተጠቀም፡፡ አንተ እንዲህ ብለሃልና፣ 18 ‘ያህዌ ለቁጣ የዘገየ ነው፣ በቃል ኪዳን ታማኝነቱ የተትረፈረፈ ነው፡፡ እርሱ በደልና መተላለፍን ይቅር ይላል፡፡ የአባቶችን ኃጢአት ቅጣት እስከ ሁለትና ሶስት ትውልድ በልጆቻቸው ላይ ሲያመጣ በደላቸውን በምንም አይነት ሳይቀጣ አይቀርም፡፡’ 19 የቃል ኪዳን ታማኝነነትህን ታላቅነት ስላልተረዳ ይህ ህዝብ ይበድላል፣ በግብጽ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ሁልጊዜም ይቅር እንዳልካቸው ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፡፡” 20 ያህዌ እንዲህ አለው፣ “ልመናህን ሰምቼ ይቅር ብያቸዋለሁ፣ 21 ነገር ግን፣ እኔ ሕያው ስለሆንኩና መላው ምድርም በእኔ ክብር የተሞላች ስለሆነች፣ 22 ክብሬን፣ በግብጽና በምድረበዳው ጉዟቸው ያደረኳቸውን የሀይሌን ምልክቶች አይተው እነዚያ ህዝቦች ሁሉ - እስከ አሁን ድረስ በእነዚህ አስር ጊዜ ተፈታተኑኝ እንጂ ድምጼን አልሰሙም፡፡ 23 ስለዚህ ለአባቶቻቸው የማልኩላቸውን ምድር በፍጹም አያዩም፡፡ እኔን ከናቁት ውስጥ አንዳቸውም ምድሪቱን አያዩም፣ 24 ከባሪያዬ ከካሌብ በስተቀር፣ ምክንያቱም እርሱ የተለየ መንፈስ አለው፡፡ እርሱ እኔን በሙሉ ልቡ ተከትሎኛል፣ ሊያያት ወደሄደበት ምድር እኔ እመጣዋለሁ፡፡ የእርሱ ትውልዶች ይወርሷታል፡፡ 25 (አሁን አማሌቃዊያንና ከነዓናውያን በሸለለቆው ይኖራሉ፡፡) ነገ ተመልሳችሁ በሸምበቆው ባህር በኩል ወደ ምድረ በዳው ሂዱ፡፡” 26 ህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ 27 ”እኔን የሚነቅፈውን ይህን ክፉ ማህበረሰብ እስከ መቼ እታገሳለሁ የእስራኤል ሰዎች በእኔ ላይ ሲያጉረመርሙ ሰምቻለሁ፡፡ 28 እንዲህ በላቸው ‘እኔ ሕያው ነኝ’ ይላል ያህዌ፣ ‘እኔ እየሰማሁ፣ የተናገራችሁትን፣ ያንኑ አደርግባችኋለሁ፡፡ 29 በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፣ እናንተ በእኔ ላይ ያጉረመርማችሁ ሁላችሁም፣ በህዝብ ቆጠራው የተቆጠራችሁ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ ትሞታላችሁ፡፡ 30 መኖሪያችሁ ትሆን ዘንድ እንደምሰጣችሁ ቃል ወደገባሁላችሁ ምድር ከዮፍኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከእናንተ አንዳችሁም አትገቡም፡፡ 31 ነገር ግን ተጠቂ ይሆናሉ ያላችኋቸው ትንንሽ ልጆቻችሁን፣ እኔ ወደ ምድሪቱ አስገባቸዋለሁ፡፡ እናንተ የናቃችኋትን ምድር እነርሱ ይገቡባታል! 32 እናንተ ግን፣ በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፡፡ 33 ልጆቻችሁ ለአርባ አመታት በምድረዳ ይንከራተታሉ፡፡ በረሃው ሁላችሁንም እስኪገድላችሁ ድረስ፣ እነርሱ እናንተን የአመጽ ድርጊቶች ዋጋ ይከፍላሉ፡፡ 34 ምድሪቱን በተመለከታችሁባቸው አርባ ቀናት ልክ፣ ለአርባ አመታት ስኃጢአታችሁ መከራ ትቀበላላችሁ - ለእያንዳንዱ ቀን አንድ አመት፣ እናም የእኔ ጠላት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡ 35 እኔ ያህዌ፣ ይህንን ተናግሬያለሁ፡፡ በእኔ ላይ በተነሱ በዚህ ክፉ ማህበረሰብ ላይ በእርግጥ ይህን አደርጋሁ፡፡ በዚህ ምድረ በዳ ይጠፋሉ፡፡ በዚህ ስፍራ ይሞታሉ፡፡” 36-37 ስለዚህ ሙሴ ምድሪቱን እንዲያዩ የላካቸው ሰዎች ሁሉ በያህዌ ፊት በወረርሽኝ አለቁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው የተመለሱ ነበሩ፡፡ ይህም መላው ማህበረሰብ በሙሴ ላይ እንዲያጉረመርም አደረገ፡፡ 38 ምድሪቱን ለማየት ከሄዱት ሰዎች መሀል፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የዩፎኒ ልጅ ካሌብ ብቻ በህይወት ቀሩ፡፡ 39 ሙሴ እነዚህን ቃላት ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች ሲናገር፣ በጥልቅ አዘኑ፡፡ 40 ማልደው ተነስተው ወደ ተራራው ጫፍ ወጥተው እንዲህ አሉ፣ “እነሆ፣ አሁን በዚህ አለን፣ ደግሞም ያህዌ ቃል ወደገባልን ስፍራ እንሄለን፣ እኛ በድለናል፡፡” 41 ነገር ግን ሙሴ እንዲህ አለ፣ “ለምን አሁን የያህዌን ትእዛዝ ትሽራላችሁ ድል አይቀናችሁም፡፡ 42 አትውጡ፣ ምክንያቱም በጠላቶቻችሁ እንዳትሸነፉ ሊጠብቃችሁ ያህዌ ከእናንተ ጋር አይደለም፡፡ 43 በዚያ አማሌቃዊያንና ከነዓናዊያን አሉ፣ እናንተም በሰይፍ ታልቃላችሁ ምክንቱም ያህዌን ከመከተል ፊታችሁን መልሳችኋል፡፡ ስለዚህ እርሱ ከእናንተ ጋር አይሆንም፡፡” 44 እነርሱ ግን ወደ ተራራማው አገር ለመሄድ በድፍረት ተነሱ፣ ሆኖም፣ ሙሴም ሆነ የያህዌ የቃል ኪዳኑ ታቦት ከሰፈር አብሯቸው አልወጣም፡፡ 45 ከዚያ አማሌቃዊያን ወርደው መጡ፣ እንደዚሁም በተራሮቹ የሚኖሩ ከነዓናዊያን መጡባቸው፡፡ እነርሱም እስራኤላውያንን አጠቋቸው እስከ ሔርማ መንገድ ድረስ አሳደዷቸው፡፡
እዚህ ላይ ሰዎቹ ጥያቄ የሚያነሱት እግዚአብሔር በአግባቡ እንዳልያዛቸው ለመግለፅ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በሠይፍ እንድንገደል ለማድረግ ሲል ብቻ እግዚአብሔር ወደዚህ ሥፍራ ሊያመጣን አይገባም ነበር” (ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ሠይፍ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሠይፍ መሞትን ወይም በጦርነት ውስጥ መሞትን ነው፡፡ “ሰዎች በሠይፍ ሲያጠቁን መሞት”ወይም “በጦርነት ውስጥ መሞት”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎቹ ይሄንን ጥያቄ የሚጠይቁት ሌሎች ሰዎችም ወደ ግብፅ ብንመለስ ይሻለናል ብለው በሃሣባቸው እንዲስማሙላቸው ለማድረግ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ከነዓንን ለማሸነፍ ከምንጥር ይልቅ ወደ ግብፅ ብንመለስ ይሻለናል”
ይሄ የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡
“ፊታቸው መሬቱን ነክቶ ሰገዱ”ሙሴና አሮን ይህንን ያደረጉት ራሣቸውን በእግዚአብሔር ፊት ማዋረዳቸውን ለማሣየት ነበር፡፡ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ስላመፀ ሊቀጣቸው ይችል ይሆናል ብለው በመስጋታቸው ነበር፡፡“በእግዚአብሔር ፊት ትህትናን ለማሣየት ፊትን ወደ መሬት መድፋት”ወይም “ወደ እግዚአብሔር ለመፀለይ ፊትን ወደ መሬት መድፋት”(ተምሣሌታዊ ደርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የሰው ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴ ከላካቸው መካከል አንዳንድ ሰዎች” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ልብስን መቅደድ የሚመለክተው አንድ ሰው ችግር ላይ እንዳለና በርቱ ለቅሶ እያለቀሰ የሚገኝ መሆኑን ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት)
ምድሪቱ ለእንስሳትና ለዕፅዋት ተስማሚ መሆኗን ለመግለፅ ከእነዚያ እንስሳት የሚገኘው ወተትና ማር ልክ በምድሪቱ ላይ እንደሚፈስስ ዓይነት ነገር አድርገው ይገልፁታል፡፡ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 1፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ከብቶችን ለማርባትና ለእህል ዕድገት እጅግ የሚያመች ሥፍራ ነው”ወይም “እጅግ ለም የሆነ መሬት ነው” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱና ካሌብ ለሕዝቡ መናገራቸውን ይቀጥላሉ፡፡
ኢያሱና ካሌብ ጠላቶቻቸውን ማጥፋት እንጀራን እንደመብላት ያህል ቀላል እንደሆነ ይናገራሉ፡፡“ምግብን የመብላት ያህል በቀላሉ እናጠፋቸዋለን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ጥላቸውን ከላያቸው ላይ ይገፍፋል” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“መከላከያቸው” የሚለው አሕፅሮተ ሥም “መከላከል”በሚለው ሥም(ሰዋሰው)ሊገለፅ ይችላል፡፡ (አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ የጠየቀው መቆጣቱን ለመግለፅና ሕዝቡን በሚመለከት ትዕግሥቱ ማለቁን ለማሣየት ነው፡፡እነዚህ በድርጊቶች ሊገለፁ ይችላሉ፡፡“ይሄ ሕዝብ ለብዙ ጊዜ ጠልቶኛል፡፡በፊቱ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ አላመነብኝም....እነርሱ፡፡(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“የእኔ ሕዝበ እንዳልሆኑ እቆጥራቸዋለሁ”በአንዳንድ ቅጂዎች ትርጓሜ መሠረት ደግሞ ሊያጠፋቸው እንደፈለገ የሚያመለክት ሊሆንም ይችላል፡፡
እዚህ ላይ “የራስህን የሚለው ቃል ነጠላ ስለሆነ የሚያመለክተው ሙሴን ነው፡፡(አንተ የሚለው ቃል በተለያየ መንገድ የሚገለፅበት የሚለውን ይመልከቱ)
ለዚህ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1/ሙሴ እግዚአብሔር ራሱን ለሕዝቡ የሚገልፅበትን ሁኔታ ልክ ፊቱን እንዲያዩ እንደፈቀደላቸው አድርጎ ያቀርበዋል 2/ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ለመግለፅ ልክ እግዚአብሔር ለሙሴ በሚናገርበት ወቅት ፊቱን እንደተመለከተ ዓይነት አድርጎ ተነግሯል፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንተ ለእኔ የምትናገረው በቀጥታ ነው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ሁሉንም በአንድ ጊዘ መግደልን ልክ አንድን ሰው እንደመግደል ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ሁሉንም በአንድ ጊዜ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ታማኝነት”የሚለው አሕፅሮተ ቃል “ታማኝ”ወይም “በታማኝነት”ተብሎ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ዘወትር ለቃል ኪዳኑ ታማኝ የሆነ”ወይም “ሕዝቡን ዘወትር በታማኝነት ያፈቅራል” (አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
“እውነትም ኃጢአተኛ የሆኑ ሰዎችን ይቅር አይልም” የሰዎችን ኃጢአት ማስወገድ የሚለው ቃል ለመቀጣት ፈቃደኛ ላለመሆናቸው ምሣሌያዊ አነጋገር ነው፡፡እግዚአብሔር የበደለኞችን ኃጢአት ይቅር አይልም፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ መቅጣት የሚለው ሃሣብ የተገለፀው ልክ አንድ ቁሣቁስ መጥቶ በሕዝብ ላይ እንደሚቀመጥ ዓይነት ተደርጎ ነው፡፡“በበደሉ ሰዎች ኃጢአት ምክኒያት የበደሉትን ሰዎች ትውልድ ሲቀጣ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ክብሬ ምድርን ሁሉ ይሞላል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“መፈታተኑን አላቋረጡም”
እዚህ ላይ አሥር ጊዜ ሲባል ለብዙ ጊዜያት ለማለት ነው፡፡“ለብዙ ጊዜ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “መስማት”የሚለው ቃል የሚመለክተው መታዘዝን ሲሆን የእግዚብሔር ድምፅ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ደግሞ የእርሱን ንግግር ነው፡፡“የተናገርኩትን ነገር አልታዘዛችሁም” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እዚሀ ላይ “መንፈስ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አስተሳሰቡን ነው፡፡ካሌብ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ነበር፡፡አስተሳሰቡ ምን እንደነበረ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የተለየ አስተሳሰብ የነበረው በመሆኑ”ወይም “እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ስለነበረ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውንና ግልፅ የሆነ ትግበራ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው በሕዝቡ ላይ ያለው ትዕግሥት በመሟጠጡ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለብዙ ጊዜ ሲያጉረመርምብኝ የኖረውን ይህንን ማህበረሰብ ታግሼዋለሁ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“ማጉረምረም”የሚለው አሕፅሮተ ሥም በሥም(ሰዋሰው) መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ ሲያጉረመርም ሰምቻለሁ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“ስትናገሩ እንደሰማኋችሁ”
የበድኖቻቸው መውደቅ የሚያመለክተው የሚሞቱ መሆኑን ነው፡፡“ትሞታላችሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ቆጠራ በተካሄደበት ወቅት ሙሴ የቆጠራችሁ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ”
የበድኖቻቸው መውደቅ የሚያመለክተው የሚሞቱ መሆኑን ነው፡፡“ትሞታላችሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
አንዳንድ የትርጉም ቅጂዎች “ልጆቻችሁ በምድረ በዳ ይቅበዘበዛሉ”የሚለውን ሃሣብ ይመርጡታል፡፡ይሄ የሆነበት ምክኒያት ከብቶቹ የሚግጡት ሣር እስከሚያገኙ ድረስ እረኞቹ ከቦታ ቦታ ይዘዋወሩ ስለነበረ ነው፡፡
“ከድርጊታችሁ ፍሬ የተነሣ ሊሰቃዩ ይገባል”ወይም “ከእናንተ ድርጊት የተነሣ እነርሱ ሊሰቃዩ ይገባል”
በድን ሬሣ ነው፡፡በድኖቻችሀ እስኪጠፉ ድረስ የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድ ሰው ሣይቀር የሚሞት መሆኑን ነው፡፡“ከእናንተ የመጨረሻው ሰው እስከሚሞት ድረስ”ወይም “ሁላችሁም እስክትሞቱ ድረስ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“በኃጢአታችሁ ፍሬ ተሰቃዩ”ወይም “ከኃጠአታችሁ የተነሣ ተሰቃዩ”
ይሄ ምናልባት በሕይወት አይኖሩም ለማለት ሊሆን ይችላል፡፡“ፍፃሜያቸው ይሆናል”ወይም “ይጠፋሉ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውንና ግልፅ የሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“በእግዚአብሔር ፊት በመቅሠፍት”የሚለው ቃል የሚያመለከተው በእግዚአብሔር የተመቱ መሆኑን ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ስለምድሪቱ ከፉ ወሬ ያመጡትን ሰዎች በእግዚአብሔር ተቀስፈው ሞቱ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውንና ግልፅ የሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ነገር የተናገሩት ሃሣባቸውን መለወጣቸውንና ከአንድ ቀን በፊት ማድረግ የነበረባቸውን ነገር ለማድረግ መፈለጋቸውን አፅንኦት ለመሥጠት ነው፡፡የእናንተ ቋንቋ ይህንን የማብራራት የራሱ መንገድ ሊኖረው ይችላል፡፡
ሙሴ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው የእሥራኤልን ሕዝብ ለመገሰፅ ነው፡፡ይሄ አሕፅሮተ ሥም በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንደገና መተላለፍ የለባችሁም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
እነርሱን ማገዝ ከእነርሱ ጋር እንደመኖር ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እግዚአብሔር አይረዳችሁም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ጠላቶቻችሁ ድል እንዳይነሷችሁ ለመከላከል” ወይም “በጠላቶቻችሁ ላይ ድልን እንድታገኙ ለማድረግ” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚሀ ላይ “ሠይፍ”የሚያመለክተው ጦርነትን ነው፡፡“በጦርነት ውስጥ ትሞታላችሁ”ወይም “ከእነርሱ ጋራ ስትዋጉ ይገድሏችኋል” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔርን መታዘዝ እርሱን እንደ መከተል ተደርጎ የተገለፀ ሲሆን የሚናገረውን ቃል አለመፈፀም ደግሞ ከእርሱ እንደመመለስ ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እግዚአብሔርን መታዘዝ አቁማችኋል”ወይም “እግዚአብሔርን ላለመታዘዝ ወስናችኋል” “(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)”
እነርሱን ማገዝ ከእነርሱ ጋር እንደመኖር ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡“አይረዳችሁም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነርሱ ግን ወደ ተራራው ራስ ሊወጡ ደፈሩ፡፡“እግዚአብሔር ያልፈቀደው ነገር ቢሆንም እነርሱ ግን ወደ ተራራው ራስ ሊወጡ ደፈሩ፡፡”
አብዛኛው የእሥራኤል ምድር ከፍታ ያለው ሥፍራ ነው፡፡የእሥራኤል ልጆች ከነዓናውያንን ለመውጋት የዮርዳኖስን ወንዝ በተሻገሩበት ወቅት ወደ ከነዓን ምድር ውስጥ ዘልቀው ለመግባት መውጣት የሚኖርባቸው ተራራዎች ነበሩ፡፡
1 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ያህዌ ለእናንተ ወደሚሰጣችሁ ወደ ምትኖሩባት ምድር ስትገቡ 3 ለእርሱ በእሳት መስዋዕት ስታቀርቡ፣ የሚቃጠል መስዋዕት ወይም ስዕለት ስታመጡ ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ፣ ወይም በባዕላቶቻችሁ ለያህዌ ስጦታዎችን ከከብቶች ወይም ከመንጋችሁ ስታቀርቡ 4 ለያህዌ መስዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው፣ በአንድ አራተኛ ኢን ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ 5 እንዲሁም የኢን አንድ አራተኛ ወይን ለመጠጥ መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ይህን ከሚቃጠል መስዋዕት ጋር ወይም እያንዳንዱ ጠቦት ሲቀርብ አድርጉት 6 አውራ በግ የምታቀርቡ ከሆነ፣ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት በአንድ ሶስተኛ ኢን ዘይት የተለወሰ የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ 7 ለመጠጥ መስዕት፣ የኢን አንድ ሶስተኛ ወይን አቅርቡ፡፡ ይህ ለያዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፡፡ 8 ለሚቃተል መስዋዕት በሬ፣ ወይም ስዕለት ለማድረስ መስዋዕት ወይም ለያህዌ የህብረት መስዋዕት ስታዘጋጁ 9 ከበሬው ጋር በግማሽ ኢን ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ 10 ለያዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ለመጠጥ ቁርባን የኢን ግማሽ ወይን፣ በእሳት የሚረብ መስዋዕት አቅርቡ፡፡ 11 እያንዳንዱ በሬ፣ እያንዳንዱ አውራ በግ፣ እና እያንዳንዱ ወንድ ጠቦት በግ ወይም ጠቦት ፍየል ሲቀርበ በዚህ አይት ይሁን፡፡ 12 እያንዳንዱ የምታዘጋጁት መስዋዕት እና ስጦታ እዚህ እንደተገለፀው ይቅረብ፡፡ 13 ማንም ሰው ለያህዌ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ለማቅረብ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ሲያመጣ፣ የአገር ተወላጅ የሆነ እስራኤላዊ ሁሉ እነዚህን ነገሮች በዚህ መንገድ ያድርግ፡፡ 14 መጻተኛው ከእናንተ ጋር ቢኖር፣ ወይም በእናንተ ትውልድ መሀል የሚኖር ማናቸውም ሰው፣ ለያህዌ መልካም መዓዛ ለማቅረብ በእሳት የተዘጋጀ መስወዕት ያድርግ፡፡ እርሱ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ፡፡ 15 ለማህበረሰቡ እና ከእናንተ ጋር ለሚኖር መጻተኛ ተመሳሳይ ህግ ይሁን፣ ይህ በትውልዳች ሁሉ የፀና ህግ ይሁን፡፡ እናንተ እንደ ታያችሁት፣ ከእናንተ ጋር የሚኖሩ እንግዶች በአንድ አይነት ይታያሉ፡፡ 16 ለእናንተም ሆነ ከእናንተ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞች ተመሳሳይ ህግና ደንቦች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡” 17 ያህዌ ዳግም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 18 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ወደ ማስገባችሁ ምድር በመጣች ጊዜ፣ 19 በምድሪቱ የተመረተውን ምግብ በበላችሁ ጊዜ፣ መስዋዕት መሰዋትና ለእኔ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 20 ከመጀመሪያው ቡኬታችሁ ከአውድማው የማንሳት መስዋዕት ህብስት አቅርቡ፡፡ በዚህ መንገድ መስዋዕታችሁን አቅርቡ፡፡ 21 በትውልዶች ሁሉ ከመጀመሪያው ቡኬታችሁ የማንሳት መስዋዕት ለእኔ ትሰጣላችሁ፡፡ 22 አንዳንድ ጊዜ ለማድረግ ሳታስቡ ለሙሴ የነገርኩትን እነዚህን ህጎች ሁሉ በተመላለፍና 23 ትዕዛዛትን ለእናንተ መስጠት ከጀመርኩበት ቀን አንስቶ በትውልዳችሁ ቀጣይ ዘመናት በሙሴ በኩል ያዘዝኳችሁን ነገሮች በሙሉ ባታደርጉ ኃጢአት ትሰራላችሁ፡፡ 24 ማህበረሰቡ ሳያውቅ በደል ፈጽሞ ሲገኝ፣ መላው ህብረተሰብ ለያህዌ መልካም መዓዛ እንዲሆን አንድ ወይፈን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ከዚሁ ጋር የእህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን እንዲሁም ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል በደንቡ መሠረት ያቅርብ፡፡ 25 ካህኑ ለመላው የእስራኤል ማህበረሰብ ማስተስረያ ያቀርባል፡፡ ኃጢአቱ የተፈፀመው፣ ባለማወቅ ስለሆነ ይቅር ይባላሉ፡፡ ለእኔ በእሳት የተዘጋጀውን መስዋዕታቸውን አቅርበዋልና ይቅር ይባለሉ፡፡ በእኔ ፊት ሳያውቁ ለፈጸሙት ስህተት የኃጢአት መስዋዕታቸውን አቅርበዋልና፡፡ 26 ከዚያ መላው የእስራኤል ማህበረሰብና ከእነርሱ ጋር የሚኖሩ መጻተኞች ይቅር ይባላሉ፣ ምክንያቱም ሁሉም ኃጢአቱን የፈፀሙት ሆን ብለው አይደለም፡፡ 27 አንድ ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሰራ ለኃጢአት መስዋዕት የአንድ አመት ሴት ፍየል ያቅርብ፡፡ 28 ካህኑ ሳያውቅ ኃጢአት ለሰራው ሰው በያህዌ ፊት ያስተሰርይለታል፡፡ ያ ሰው ማስተሰርያ ሲደረግ ይቅር ይባላል፡፡ 29 ማናቸውንም ነገር ሁን ብሎ ላላደረገ ተመሳሳይ ህግ ይኑራችሁ፣ በእስራኤል ሰዎች መሀል ለሚኖረው ተወላጅም ሆነ መጻተኛ ተመሳሳይ ህግ ይኑራቸው፡፡ 30 ነገር ግን ራሱን ለመከላከል አንዳች ነገር ያደረገ ሰው፣ የአገር ተወላጅም ይሁን መጻተኛ እኔን ያቃልላል፡፡ ስለዚህ ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ፡፡ 31 ምክንቱም እርሱ ቃሌን ንቋል ደግሞም ትዕዛዛቴን ተላልፏል፣ ያ ሰው ሙሉ ለሙሉ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡ ኃጢአቱ በራሱ ላይ ይሆናል፡፡” 32 የእስራኤል ህዝቦች በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ፣ አንድ ሰው በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም አገኙት፡፡ 33 ያገኙት ሰዎች ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው ማህበረሰብ አቀረቡት፡፡ 34 በእርሱ ላይ ምን መደረግ እንዳለበት የታወቀ ህግ ስላልበረ በጥበቃ ሥር አቆዩት፡፡ 35 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “በእርግጥ ሰውየው መገደል አለበት፡፡ መላው ማህበረሰብ ከሰፈር ውጭ በድንጋይ ይውገረው፡፡” 36 ስለዚህም መላው ማህበረሰብ ሰውየውን ከሰፈር ውጭ አውጥተው ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው እስኪሞት ድረስ ወገሩት፡፡ 37 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 38 “ለእስራኤል ትውልዶች በየለብሳቸው ጠርዝ ዘርፍ እንዲያስሩ ንገራቸው፣ ዘርፎቹን በእያንዳንዱ ጠርዝ በሰማያዊ ገመድ እንዲያንጠለጥሉ እዘዛቸው፡፡ በሚቀጥሉት ትውልዶቻቸው ሁሉ ይህን ያድርጉ፡፡ 39 ይህንን ስትመለከቱ፣ በትዕዛዛት ሁሉ፣ እንድትሄዱ፣ የራሳችሁን ልቦናና እይታ ሳትከተሉ ቀድሞ ታደርጉት ከነበረው መንፈሳዊ አመንዝራነት ለመመለስ ይህ ለእናንተ ልዩ ማስታወሻ ይሆናችኋል፡፡ 40 ትዕዛዛቶቼን ሁሉ እንድትጠብቁና አስተዋዮች እንድትሆኑ ይህን አድርጉ፣ ደግሞም ቅዱሳንና ለእኔ ለአምላካችሁ የተለያችሁ ትሆናላች፡፡ 41 አምላካችሁ እሆን ዘንድ፣ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
ዘኁልቁ 15፤1-32 ድረስ ያለው ክፍል ሙሴ ለእሥራኤላውያን እንዲናገራቸው እግዚአብሔር የተናገረውን የሚገልፅ ነው፡፡
“ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታን ማቅረብ”እግዚአብሔር በጣፋጩ ሽታ ደስ መሰኘቱ የሚያመለክተው መሥዋዕቱን በሚያቀርበው ሰው መደሰቱን ነው፡፡“ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ ጣፋጭ ሽታን በማቅረብ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው በኦሪት ዘኁልቁ 15፡3 የተጠቀሱትን መሥዋዕቶች ነው፡፡
መስፈሪያ የመለኪያ ዓይነት ሲሆን ከ22 ሊትር ጋር እኩል ነው፡፡“2 ሊትር ያህል”ወይም “ሁለት ሊትር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
ኢን የመለኪያ ዓይነት ሲሆን ከ3.7 ሊትር ጋር እኩል ነው፡፡“1 ሊትር ያህል”ወይም “አንድ ሊትር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
መስፈሪያ የመለኪያ ዓይነት ሲሆን ከ22 ሊትር ጋር እኩል ነው፡፡“4 ሊትር ያህል”ወይም “አራት ተኩል ሊትር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
ኢን የመለኪያ ዓይነት ሲሆን ከ3.7 ሊትር ጋር እኩል ነው፡፡“አንድ ሊትር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔርን የሚያስደስት ሽታ ይወጣዋል” እግዚአብሔር በጣፋጩ ሽታ ደስ መሰኘቱ የሚያመለክተው መሥዋዕቱን ባቀረበው ሰው ሐሴት ማድረጉን ነው፡፡“እርሱን መሥዋዕት በማድረግ እግዚአብሔርን ታስደስታላችሁ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ወደ ዘመናዊ መለኪያ ልትለውጡት ትችላላችሁ፡፡“ስድስትና አንድ ከግማሽ ሊትር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ወደ ዘመናዊ መለኪያ ልትለውጡት ትችላላችሁ፡፡“ሁለት ሊትር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
“በመሠዊያው ላይ የምታቃጥሉት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔርን የሚያስደስት ሽታ ማቅረብ” በቅን ልብ መሥዋዕትን በሚያቀርብ ሰው እግዚአብሔር መደሰቱን ለመግለፅ ልክ እግዚአብሔር በመልካም ሽቱ መሥዋዕት እንደሚደሰት ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እርሱን በማቅረብ እግዚአብሔርን ማስደሰት፡፡”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እናንተ ልታደርጉት ይገባል” (ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡በተናገርኩት መሠረት መፈፀም ይኖርባችኋል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በእሣት ላይ የሚያቀጥሉትን”
“ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ ሽታ ለማቅረብ” የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር በቅን ልብ መሥዋዕትን በሚያቀርብ ሰው መደሰቱን ለመግለፅ ልክ እግዚአብሔር በመልካም ሽቱ መሥዋዕት እንደሚደሰት ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እርሱን በማቅረብ እግዚአብሔርን ማስደሰት፡፡”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በመሠዊያው ላይ ቁርባንን ማቃጠል ይኖርበታል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ ለማቅረብ”የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር በቅን ልብ መሥዋዕትን በሚያቀርብ ሰው መደሰቱን ለመግለፅ ልክ እግዚአብሔር በመልካም ሽቱ መሥዋዕት እንደሚደሰት ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እርሱን በማቅረብ እግዚአብሔርን ማስደሰት፡፡”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ለዚህ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት1/ “እናንተና በመካከላችሁ ያሉት መፃተኞች በእግዚአብሔር ፊት እኩል ናችሁ”ወይም “እናንተንም ሆነ መፃተኛውን የሚገዛው ሕግ ተመሳሳይ ነው”
እናንተ እንደምታደርጉት እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት የሚያደርጉበት ምክኒያት በእግዚአብሔር ፊት እንደ እሥራኤላውያን መሆን ያለባቸው በመሆኑ ነው፡፡ይሄ የሚያመለክተው ሕጎቹን ሁሉ እንደ እሥራኤላውያን መጠበቅ አለባቸው ማለት ነው፡፡እናንተ እንደምታደርጉት ማድረግና ሕጎቹንም ሁሉ መጠበቅ ይኖርባቸዋል”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ምድሪቱ የምታበቅለው እንጀራ”ወይም “እናንተ በምድሪቱ ውስጥ የምታመርቱት እንጀራ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ለዚሀ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1/በመከር ወቅት የሚሰበስቡት የመጀመሪያው ሰብል ወይም 2/በመጀመሪያ ከሚያገኙት ሰብላቸው የሚሰሩት ሊጥ (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እንጎቻ ተብሎ መጠራቱ የሚያመለክተው ሊጡን በመጀመሪያ መጋገር ያለባቸው መሆኑን ነው፡፡
“ማንሣት”የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው እንደ ሥጦታ መቅረቡን ነው፡፡“እንደ ሥጦታ ማቅረብ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሥጦታው ከአውድማ ነው ተብሎ የተገለፀው የእህል ሥጦታቸውን ከሌላው ሰብል ለይተው የሚያስቀምጡበት ሥፍራ አውድማ በመሆኑ ነው፡፡
እግዚአብሔር ሙሴ ለእሥራኤል ሕዝብ መናገር ስላለበት ነገር መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እዚህ ላይ “እናንተ” የሚለው ቃል የሚመለክተው እሥራኤላውያንን ነው፡፡
“እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ ለማቅረብ” የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር በቅን ልብ መሥዋዕትን በሚያቀርብ ሰው መደሰቱን ለመግለፅ ልክ እግዚአብሔር በመልካም የሽቱ መሥዋዕት እንደሚደሰት ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ እርሱን በማቅረብ እግዚአብሔርን ማስደሰት፡፡”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ማድረግ ይኖርባችኋል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሕጉ እንደሚያዘው”ወይም “ሕጉን ሳወጣ ባዘዝኩት መሠረት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ይቅር እላቸዋለሁ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በእሣት የሰሩት”ወይም “በመሠዊያው ላይ ያቃጠሉት”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእሥራኤልን ልጆች ማህበር ሁሉ ይቅር እላቸዋለሁ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ ዓመት የሞላው ፍየል”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ካህኑ መሥዋዕትን በሚያቀርብበት ወቅት የዚያን ሰው ኃጢአት ይቅር እላለሁ”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ተለይቶ ይጥፋ” የሚለው ምሣሌያዊ አነጋገር ቢያንስ ሶስት ሃሣቦችን በውስጡ አዝሏል፡፡1/“የራሱ ሕዝብ ሊያባርረው ይገባል”2/“ከእሥራኤል ሕዝብ እንደ አንዱ አልቆጥረውም” “የራሱ ሕዝብ ሊገድለው ይገባል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ትዕዛዝን አለመፈፀም አንድን ነገር እንደመስበር ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ትዕዛዜን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም” ወይም “ያዘዝኩትን ነገር አልፈፀመም”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ኃጢአት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው 1/ለተሰራው ኃጢአት የሚፈረድበትን ቅጣት2/በዚያ ኃጢአት ምክኒያት የደረሰ በደል፡፡ኃጢአት 1/ለመቀጣትና 2/ለበደል ምሣሌያዊ አነጋገር ነው፡፡ “1/በሰራው ኃጢአቱ ምክኒያት እቀጣዋለሁ” ወይም 2/ “እንደ በደለኛ እቆጥረዋለሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውንና (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ))
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ አልተናገረም ነበር”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰውዬውን በእርግጥም መግደል ይኖርባችኋል”ወይም “ሰውዬው በእርግጥ መሞት ይኖርበታል”(ገቢራዊና ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የእሥራኤል ሕዝብ”
“እነርሱን ለመታዘዝ”
እዚህ ላይ “መመልከት”የሚለው ቃል ማሰብ ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ልብ አንድ ሰው የሚሻውን ነገር የሚያመለክት ሲሆን ዓይን ደግሞ አንድ ሰው የሚያየውንና የሚፈልገውን ነገር ያመለክታል፡፡“የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እንዳታስቡ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ልባቸው ያሻውን ነገር እያደረጉ እግዚአብሔርን ያለመታዘዛቸውን ሁኔታ አንዲት ሴት ለባልዋ ታማኝ ካለመሆኗ የተነሣ ከሌላ ሰው ጋር ዝሙት እንደምትፈፅም ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡ይሄ አሣፋሪ ድርጊት ስለመሆኑ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“በሚያሣፍር ሁኔታ ለእኔ ታማኝ አልሆናችሁም”ወይም “ከመታዘዝ ይልቅ እነዚሀን ነገሮች ታደርጋላችሁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን፤በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሙሴ ለእሥራኤል ሕዝብ መናገር የሚኖርበትን ነገር መንገሩን ቀጥሏል፡፡ “እናንተ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“ማስታወስ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሐረግ የተደጋገመው አፅንኦት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡
1 የይስዓር ልጅ ቆሬ የቀዓት ልጅ የሌዊ ልጅ፣ ከኤሊያብ ልጆች ከዳታንና አቤሮን ጋር፣ እንዲሁም የፍሬት ልጅ ኦን፣ የሮቤል ትውልዶች ሆነው ተሰበሰቡ፡፡ 2 እነርሱም ከእስራኤል ሌሎች ሰዎች ጋር ሆነው በሙሴ ላይ ተቃውመው ተነሱ፣ የማህበረሰቡ መሪዎች የሆኑ የታወቁ ሁለት መቶ ሀምሳ ሰዎች ተነሱበት፡፡ 3 ሙሴንና አሮንን ለመቃወም በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ሙሴንና አሮንን እንደዚህ አሏቸው፣ “እናንተ ያለ ልክ አብዝታችሁታል፡፡ መላው ማህበረሰብ ቅዱስ ነው፣ ለያህዌ የተለየ ነው፣ እያንዳንዳቸው ንጹሃን ናቸው፣ ያህዌም በመሀከላቸው ነው፡፡ ለምን ራሳችሁን ከተቀረው የያህዌ ማህበረሰብ ከፍ ታደረጋላችሁ?” 4 ሙሴ ይህንን ሲሰማ፣ በግምባሩ ተደፋ፡፡ 5 ለቆሬና ለእርሱ ወገኖች እንዲህ አላቸው፤ “ማለዳ ያህዌ የእርሱ የሆኑት እነማን እንደሆኑ ይለያል፣ ማን ለእርሱ እንደ ተለየ ይታወቃል፡፡ የመረጠውን ሰው ወደ ራሱ ይለያል፡፡ የመረጠውን ወደ ራሱ ያመጣዋል፡፡ 6 ቆሬና የአንተ ቡድን ሁላች ይህን አድርጉ፡፡ ማጠንት ያዙ 7 ነገ በያህዌ ፊት እሳትና እጣን በላያቸው ጨምሩ፡፡ ያህዌ የሚመርጠው ሰው እርሱ፣ ለያህዌ የተለየ ይሆናል፡፡ እናንተ የሌዊ ትውልዶች ከልክ አልፋችኋል፡፡” 8 እንደገና፣ ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፣ “አሁን ስማ፣ እናንተ የሌዊ ትውልዶች 9 የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማህበረሰብ እናተን ለይቶ ወደራሱ ማቅረቡ፣ በያህዌ የማደሪያ ድንኳን እንድታገለግሉ ማድረጉ፣ እነርሱን እንድታገለግሉ በማህበረሰቡ ፊት እናንተን ማቆሙ ለእናንተ ትንሽ ነገር ነውን? 10 እርሱ አንተን፣ የቅርብ ዘመዶችህንና የሌዊ ትውልዶችን ከአንተ ጋር አቅርቧችኋል፣ እናንተ ግን ክህነቱንም እየፈለጋችሁ ነው! 11 አንተና የአንተ ተከታዮች ሁሉ በያህዌ ላይ በአንድ ላይ ተነሳችሁ፡፡ ስለዚህ ለምን እግዚአብሔርን በሚታዘዘው በአሮን ላይ ታጉረመርማላችሁ?” 12 ከዚያ ሙሴ የኤልያብን ልጆች ዳታንንና አብሮንን ጠራቸው፣ እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፣ “እኛ ወደዚያ አንመጣም፡፡ 13 እኛን በምድረበዳ ልትገድለን ወተትና ማር ከሚፈስባት ምድር ያወጣኸን ትንሽ ነገር ሆኖ ነውን? አሁን ራስህን በእኛ ላይ ገዢ ማድረግ ትፈልጋለህ! 14 በተጨማሪም፣ እኛን ወተትና ማር ወደምታፈስ ምድር አላመጣኸንም፣ ወይም እርሻዎችንና የወይን ተክሎችን ውርስ አድርገህ አልሰጠኸንም፡፡ አሁን በባዶ ተስፋ ልታታልለን ትፈልጋህ? ወደ አንተ አንመጣም፡፡” 15 ሙሴ እጅግ ተቆጥቶ ነበር፣ ወደ ያህዌ እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “መስዋዕታቸውን አትቀበል፡፡ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳን አልወሰድኩም፣ ከእነርሱ አንዳቸውንም አልበደልኩም፡፡” 16 ከዚያ ሙሴ ቆሬን እዲህ አለው፣ “ነገ አንተና የአንተ የሆኑ በያህዌ ፊት ይቅረቡ፤ አንተ፣ እነርሱና አሮን በያህዌ ፊት ቁሙ፡፡ 17 እያንዳንዱ የራሱን ማጠኛ ይያዝና በውስጡ እጣን ይጨምርበት፡፡ ከዚያ እያንዳንዱ ሰው ማጠኛውን በያዌ ፊት ያምጣ፣ ሁለት መቶ አምሳዎቹ ሰዎችህ ማጠኛዎቻቸውን ይዘው ይቅረቡ፡፡ አንተና አሮንም ደግሞ የየራሳቸችሁን ማጠኛ አምጡ፡፡” 18 ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ማጠኛውን ወሰደ፣ በውስጡ እሳት አደረገ፣ እጣንም ጨመረበት ከሙሴና ከአሮን ጋር በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ቆሙ፡፡ 19 ቆሬ መላውን ማህበረሰብ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በሙሴና በአሮን ላይ በተቃውሞ ሰበሰበ፣ የያህዌ ክብር ደግሞ ለማህበረሰቡ ሁሉ ታየ፡፡ 20 ከዚያ ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፣ 21 ”በቶሎ ከማጠፋው ከዚህ ማህበረሰብ መሀል ራሳችሁን ለዩ፡፡” 22 ሙሴና አሮን በግንባራቸው ተደፍተው እንዲህ አሉ፣ “ የሰው ልጆች ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሰራ ማህበረሰቡን በሙሉ ልትቆጣ ይገባልን?” 23 ያህዌ ለሙሴ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ 24 ”ለማህበረሰቡ እንዲህ በል፣ ‘ከቆሬ፣ ከዳታንና ከኤብሮን ድንኳኖች ውጡ፡፡’” 25 ከዚያ ሙሴ ተነስቶ ወደ ወደ ዳታንና አብሮን ሄደ፤ የእስራኤል መሪዎች እርሱን ተከተሉት፡፡ 26 ለማህበረሰቡ እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ “አሁን የእነዚህን ክፉ ሰዎች ድንኳኖች ልቀቁ፣ የእነርሱ የሆነውን አንዳች ነገር አትንኩ፣ አለበለዚያ በእነርሱ ኃጢአቶች ሁሉ እናንተም ትጠፋላችሁ፡፡” 27 ስለዚህ በቆሬ፣ በዳታንና በኤብሮን ድንኳኖች በእያንዳንዱ አቅጣጫ የሚገኝ ማህበረሰብ ከእነርሱ ራቁ፡፡ ዳታንና አብሮን ወደ ውጭ ወጥተው ከሚስቶቻቸው፣ ከወንዶች ልጆቻቸውና ከህፃናቶቻቸው ጋር በድንኳኖቸው ደጃፍ ላይ ቆሙ፡፡ 28 ከዚያ ሙሴ እንዲህ አለ፣ “በዚህም ያህዌ እነዚህን ስራዎች ሁሉ እንድሰራ እንደላከኝ ታውቃላችሁ፣ እኔ በራሴ ፈቃድ እነዚህን ነገሮች አልሰራኋቸውም፡፡ 29 እነዚህ ሰዎች በተለመደው ሁኔታ ተፈጥሯዊ ሞት ቢሞቱ፣ ያህዌ እኔን አላኝም ማለት ነው፡፡ 30 ነገር ግን ያህዌ ምድሪቷን ቢከፍትና እርሷ እንደ ተከፈተ አፍ ሆና፣ ከነቤተሰቦቻቸው ብትውጣቸው፣ ደግሞም በህይወታቸው ሳሉ ወደ ሲኦል ቢወርዱ፣ ያን ጊዜ እነዚህ ሰዎች ያህዌን እንደናቁ ታውቃላችሁ፡፡” 31 ሙሴ እነዚህን ቃላቶች ተናግሮ እንደጨረሰ፣ ምድሪቱ ከነዚህ ሰዎች በታች ተከፈተች፡፡ 32 መሬት አፏን ከፈተችና ዋጠቻቸው፣ ቤተሰቦቻቸው፣ እና የቆሬ ሰዎች ሁሉ እንዲሁም ያላቸው ሀብት ሁሉ ተዋጠ፡፡ 33 እነርሱና በየቤተሰባቸው እያንዳንዱ በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ወረዱ፡፡ መሬት በላያቸው ተከደነች፣ እናም በዚህ መንገድ ከማህበረሰቡ መሀል ጠፉ፡፡ 34 በዙሪያቸው የነበሩ እስራኤላዊያን ሁሉ ከጩኸታቸው የተነሳ ሸሹ፡፡ እንዲህ እያሉም ጮኹ፣ “መሬት እኛንም ደግሞ ልትውጠን ነው!” 35 እሳት ከያህዌ ዘንድ ወጥታ የሚያጥኑትን 250 ሰዎች በላቻቸው፡፡ 36 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 37 ”ጥናዎቹ ለእኔ የተለዩ ናቸውና ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአላዓዛር ከሚጤሱት የተረፉትን ጥናዎች እንዲወስድ ንገረው፡፡ ከዚያ ረመጡን ይበትኑት፡፡ 38 በኃጠአታቸው ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡትን ሰዎች ጥናዎች ውሰድ፡፡ ጥናዎቹ የተቀጠቀጡ ሰሀኖች ተደርገው ለመሰዊያው መሸፈኛነት ይዋሉ፡፡ ለእኔ የተለዩ ናቸውና፣ እነዚያ ሰዎች በእኔ ፊት ያቅርቧቸው፡፡ እነዚህም ለእስራኤል ሰዎች ለእኔ መገኘት ምልክት ይሆናሉ፡፡” 39 ካህኑ አልዓዛር የተቃጠሉት ሰዎች ይጠቀሙባቸው የነበሩትን የናስ ጥናዎች ይውሰድና ለመሰዊያው መሸፈኛነት ይቀጥቅጣቸው፣ 40 ይህም፤ ለእስራኤል ሰዎች ማስታወሻ እንዲሆን፣ ማንም የአሮን ትውልድ ያልሆነ መጻተኛ በያህዌ ፊት ለማጠን እንዳያቀርብና እንደ ቆሬና እንደ እርሱ ተከታዮች እንዳይሆኑ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዳዘዘው ልክ እንደዚያ እንዳይሆንባቸው ነው፡፡ 41 ነገር ግን በማግስቱ የእስራኤል ማህበረሰብ በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ በማጉረምረም ተነሱባቸው፡፡ እነዲህም አሉ፣ “እናንተ የያህዌን ሰዎች ገድላችኋል፡፡” 42 ከዚያም እንዲህ ሆነ፣ ማህበረሰቡ በሙሴና በአሮን ላይ በተቃውሞ ሲሰበሰብ፣ ወደ መገናኛው ድንኳን አሻግሮ ሲመለከቱ፣ እነሆ ደመናው ድንኳኑን ሸፍኖት ነበር፡፡ የያህዌ ክብር ታየ፣ 43 እናም ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ወደፊት መጡ፡፡ 44 ከዚያ ያህዌ ሙሴን ተናገረው፡፡ እንደህም አለው፣ 45 “ከዚህ ማህበረሰብ ፊት ራቅ፣ እኔ በቶሎ አጠፋቸዋለሁ፡፡” ከዚያ ሙሴና አሮን በግምባራቸው ተደፉ፡፡ 46 ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ማጥንቱን ውሰድ፣ ከመሰዊያው እሳት ወስደህ አድርግበት፣ በውስጡ እጣን ጨምርበት፣ በቶሎ ወደ ማህበረሰቡ ውሰደው፣ እናም ለእነርሱ አስተሰርይ፣ ምክንያቱም ከያህዌ ዘንድ ቁጣ እየመጣ ነው፡፡ መቅሰፍቱ ጀምሯል፡፡” 47 ስለዚህም አሮን ሙሴ እንደመራው አደረገ፡፡ ወደ ማህበረሰቡ መሃል ሮጠ፡፡ መቅሰፍቱ በህዝቡ መካከል በፍጥነት መስፋፋት ጀመሮ ነበር፣ ስለዚህም እርሱ እጣኑን ጨምሮ ለህዝቡ ማስተሰርያ አደረገ፡፡ 48 አሮን በሙታኑና በህያዋኑ መሀል ቆመ፣ በዚህ መንገድ መቅሰፍቱ ቆመ፡፡ 49 በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 14700 ነበር፣ ይህም በቆሬ ምክንያት የሞቱትን ሳይጨምር ነው፡፡ 50 አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ወደ ሙሴ ተመለሰ፣ መቅሰፍቱም አበቃ፡፡
የዚህን ሰው ሥም በኦሪት ዘኁልቁ 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
በአንድ በኃላፊነት በሚገኝ ሰው ላይ ማመፅና መተቸት ልክ ለመጣላት እንደተነሱ ዓይነት ነገር ተደርጎ ተገልጿል፡፡“በሙሴ ላይ አመፁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“250”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ዝነኛ የሆኑ የማህበረሰቡ አባላት” ወይም“በማህበረሰቡ ውስጥ ዋና የሆኑ ሰዎች”
ይሄ የሚያመለከተው አንድ ሰው ማድረግ ከሚገባው በላይ ማድረጉን ነው፡፡“ማድረግ ከሚገባችሁ በላይ አድርጋችኋል”ወይም “ሊኖራችሁ ከሚገባው በላይ የሆነ ሥልጣን ያላችሁ ይመሰላችኋል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎቹ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቁት ሙሴንና አሮንን ለመገሰፅ ብለው ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “በተቀረው የእግዚአብሔር ጉባዔ ላይ ራሣችሁን ከፍ ማድረጋችሁ ትክክል አይደለም” (ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
አንድ ሰው አስፈላጊ ነኝ ብሎ የማመኑን ነገር ራስን ከፍ ከማድረግ ጋር ተነፃፅሯል፡፡“ራሣችሁን ከሌሎች የበለጠ አስፈላጊ ነን ብላችሁ ትገምታላችሁ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያሣየው ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ራሱን ማዋረዱን ነው፡፡በእግዚአብሔርና በመረጣቸው ሰዎች ላይ በማመፃቸው እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊቀጣ ይችላል ብሎ ፈራ፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ለራሱ የለየውን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለቀአትና ከቀአት ጋር ለነበሩት ሰዎች መናገሩን ይቀጥላል፡፡
ዕጣንን ለማጤስ የሚያገለግል ዕቃ፡፡
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“በእግዚአብሔር ሕልውና ፊት”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ያንን ሰው ለራሱ የተለየ ያደርገዋል” (ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለከተው አንድ ሰው ማድረግ ከሚገባው በላይ አልፎ ማድረጉን ነው፡፡“ማድረግ ከሚገባችሁ በላይ አድርጋችኋል”ወይም “ሊኖራችሁ ከሚገባው በላይ የሆነ ሥልጣን ያላችሁ ይመሰላችኋል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ይህንን ጥያቄ የሚያነሣው ቀአትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመገሰፅ ብሎ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እነርሱን ማገልገል ትንሽ ነገር መስሎ ይታያቸኋል”ወይም “እነርሱን ማገልገል እንደ ትንሽ ነገር መስሎ ሊታያችሁ አይገባም፡፡”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“ለእናንተ የማይበቃችሁ” ወይም “ለእናንተ ጠቃሚ ያልሆነ”
ክህነት መፈለግን ልክ በዓይናቸው እንደሚፈልጉት ዓይነት በሚመስል መልኩ ተገልጿል፡፡“ክሀነትን ትፈልጋላችሁ” ወይም “እናንተም ካህናት መሆን ትፈልጋላችሁ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ይህንን ጥያቄ የሚያነሳበት ምክኒያት የአሮንን መልካም የሆነ ድርጊት በመጥቀስ ለመሞገት ነበር፡፡ምክኒያቱ ደግሞ አሮን እግዚአብሔር አድርግ የሚለውን ነገር የሚያደረግ ሰው ሰለነበረ ነው፡፡“የምታጉመርሙት በአሮን ላይ ሣይሆን አሮንን በሚያዝዘው በእግዚአብሔር ላይ ነው”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ዳታንና አቤሮን ይህንን ጥያቄ የሚጠይቁት ሙሴን ለመገሰፅ ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እኛን እዚህ ምድረ በዳ አምጥተህ በምድረ በዳ ልትገድለን ማሰብህን ምንም እንዳልሆነ ነገር ቆጥረኸዋል”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“በቂ ያልሆነ”ወይም “ጠቃሚ ያልሆነ”
ምድሪቱ ለከብቶችና ለዕፅዋት ተስማሚ መሆኗን ለመግለፅ ከእነዚያ እንስሳት የሚገኘው ወተትና ማር ልክ በምድሪቱ ላይ እንደሚፈስስ ነገር አድርገው ይገልፁታል፡፡ይህንን ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 14፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ከብቶችን ለማርባትና እህልን ለማብቀል እጅግ የያመች ሥፍራ ነው”ወይም “እጅግ ለም የሆነ መሬት ነው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎቹ ነገሩን አጋንነው የሚናገሩት ከአነርሱ ውስጥ አንድ ሰው ቢሞት ሙሴን ተጠያቂ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡(የተጋነነ ንፅፅር እና አጠቃላይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለዘላለም የሚሰጣቸውን ነገር በውርስ እንደሚያገኙት ነገር አድርገው ነው የሚናገሩት፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎቹ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቁት ሙሴን ለመቃወም ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በባዶ ተስፋ ልታሳውረን ትፈልጋለህ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎችን ማታለል ሰዎችን እንደ ማሳወር ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ልታታልለን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ተስፋ የተሰጣቸው ነገሮች ያለመከናወናቸውን ለመግለፅ ባዶ ከሆነ ዕቃ ማስቀመጫ ጋር ያነፃፅሩታል፡፡“የማትፈፅማቸው የተስፋ ቃሎችህ”ወይም “እነዚህ ነገሮች ይደረጋሉ እያልክ የማታከናውናቸው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ አንድ “አህያ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሊወስድ የሚችለውን ነገር ነው፡፡“ከእነርሱ አንዲት ነገር አልወሰድኩም፡፡አንድ አህያ እንኳን”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
ዕጣንን ለማጤስ የሚያገለግል ዕቃ፡፡
እነርሱን ማጥፋት ልክ እግዚአብሔር እንደሚበላቸው ዓይነት ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡“አጠፋቸው ዘንድ”ወይም “አጠፋቸዋለሁ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያሣየው ሙሴና አሮን በእግዚአብሔር ፊት ራሣቸውን ማዋረዳቸውን ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ነፍስ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለመኖር ብቁ መሆንን ነው፡፡“ለሰው ሁሉ ሕይወትን የሚሰጠው እግዚአብሔር” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴና አሮን ይህን ጥያቄ የሚጠይቁት ስለ ሕዝቡ ልመናን ለማቅረብ ብለው ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንድ ሰው ኃጢአትን በመሥራቱ እባክህን በማህበሩ ሁሉ ላይ አትቆጣ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
መጥፋታቸው ልክ አንደ ምግብ እንደሚበሉ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ትጠፋላችሁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ከኃጢአታቸው የተነሣ መጥፋታቸው ልክ ኃጢአት እንደሚያጠፋቸው ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“በኃጢአታቸውም ትጠፋላችሁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የሰራችኋቸው ኃጢአቶቻችሁ ሁሉ ያጠፏችኋል”ወይም “ከኃጢአቶቸቻው ሁሉ የተነሣ እግዚአብሔር ያጠፋችኋል” (ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “በዚህ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴ ቀጥሎ የሚናገረውን ነገር በሚመለከት ነው፡፡
ሙሴ እዚህ ላይ የሚናገረው ልክ ምድር ሕይወት እንዳለው ነገር ሆኖ እነዚህ ሰዎች የሚወድቁበት የተከፈተ ጉድጓድ ደግሞ ሊበላቸው እንደተዘጋጀ ሠፊ አፍ አስመስሎ ነው፡፡“ከበታቻቸው ያለው መሬት ተሰነጠቀ፤ምድርም አፍዋን ከፍታ ዋጠቻቸው”(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እዚህ ላይ የሚናገረው ልክ ምድር ሕይወት እንዳለው ነገር ሆኖ እነዚህ ሰዎች የሚወድቁበት የተከፈተው ጉድጓድ ደግሞ የምድርን አፍ አስመስሎ ነው፡፡“ከበታቻቸው ያለው መሬት እንደ ሠፊ አፍ ተከፍቶ በዚያ ወደቁና በእርሱ ውስጥ ተቀበሩ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በኦሪት ዘኁልቁ 16፡30 ላይ ተመሳሳይ የሆነ ሐረግ ይገኛል፡፡እዚያ ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው “እሥራኤላውያንን ሁሉ”ነው፡፡
ሰዎቹ የሚናገሩት ልክ ምድር ሕይወት እንዳላት ነገር አድርገው ነው፡፡“ምናልባት መሬት ተከፍታ እኛንም ልትውጠን ትችላለች”ወይም “ምድር እንደገና የምትከፈት ከሆነ እኛም እዚያ ውስጥ ወድቀን ልንቀበር እንችላለን” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በእሣት መጥፋታቸው ልክ በእሣት እንደተበሉ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡ “እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ 250 ሰዎች አጠፋ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ሁለት መቶ ሃምሳ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ 250 ሰዎች ያቃጠለውን እሳት የሚያመለክት ነው፡፡
ሕይወት ማጣት የሚያመለክተው መሞታቸውን ነው፡፡“የሞቱት ሰዎች”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጥናዎቹን ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “ካህኑ አልዓዛር ይጠፍጥፋቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እነርሱ”እና“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጥናዎቹን ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የተቀቃጠሉት ሰዎች የተጠቀሙባቸውን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እንደ እነርሱ እንዴት ሊሆኑ እንደሚችሉ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ቆሬና ወገኑ እንደሞቱ መሞት”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሐረግ ጥቅም ላይ እንዲውል የተደረገው በታሪኩ ውስጥ ጠቃሚ ክስተት መኖሩን ለማመልከት ነው፡፡
“በሙሴና በአሮን ላይ ለማጉረምረም ተሰባሰቡ”
“በድንገት ደመናው” እዚህ ላይ“እነሆም”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በተመለከቱት ነገር ሰዎቹ መደነቃቸውን ነው፡፡
እግዚአብሔር እነርሱን የማጥፋቱን ነገር እንደሚበላቸው ዓይነት ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡“አጠፋቸው ዘንድ”ወይም “አጠፋቸዋለሁ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ሙሴና አሮን በእግዚአብሔር ፊት ራሣቸውን ማዋረዳቸውን ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ቁጣ ከእግዚአብሔር ዘንደ ወጥቶአል የሚለው ቃል የሚያሣየው እግዚአብሔር መቆጣቱን ነው፡፡“እግዚአብሔር መቆጣቱን እያሳየ ነው” ወይም “እግዚአብሔር በጣም ከመቆጣቱ የተነሣ ቁጣውን ወደ ተግባር እየለወጠው ነው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ዕጣኑን በጥናው ላይ ማድረጉ የሚያመለክተው ማቃጠሉን ነው፡፡“ዕጣኑን አቃጠለው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“መቅሠፍቱ መስፋፋቱን አቆመ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“በቁጥር አሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 ”ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ ከእነርሱ በትሮችን ውሰድ፣ ከየነገዱ አባቶች አንድ በትር ውሰድ፡፡ ከእያንዱ መሪ አንድ በአጠቃላይ ከየነገድ የተመረጡ አስራ ሁለት በትሮችን ውሰድ፡፡ የእያንዳንዱን ሰው ስም በበትሩ ላይ ጻፍ፡፡ 3 የአሮንን ስም በሌዊ በትር ላይ ጻፍ፡፡ ለእያንዳንዱ መሪ ከየአባቶቹ ነገድ አንድ በትር ሊኖር ያስፈልጋል፡፡ 4 በትሮቹን ከአንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ከምስክሩ ኪዳን ፊት አስቀምጣቸው፡፡ 5 እንዲህ ይሆናል፣ እኔ የምመርጠው ሰው በትር ታቆጠቁጣለች፡፡ የእስራኤለ ሰዎች በአንተ ላይ የሚያደርጉትን ማጉረምረማቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ፡፡” 6 ሙሴ ለእስራኤል ሰዎች ተናገረ፡፡ ሁሉም የነገዱ መሪዎች በትሮቻቸውን ሰጡት፣ ከእያንዳንዱ መሪ አንድ በትር፣ ከየነገዱ አባቶች ተመረጠ፣ በአጠቃላይ አስራ ሁለት በትሮች ተመረጡ፡፡ የአሮን በትር ከእነዚህ መሀል ነበር፡፡ 7 ከዚያ ሙሴ እነዚህን በትሮች ወስዶ በያህዌ ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡ 8 በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሄደ፣ እናም የሌዊ ነገድ የሆነችው የአሮን በትር አቆጥቁጣ አየ፡፡ እምቡጥ አብቅላ፣ አበባና ለውዝም አፍርታ ነበር! 9 ሙሴ በትሮቹን ሁሉ ከያህዌ ፊት ወደ እስራኤል ሰዎች ሁሉ አመጣቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱን በትር አግኝቶ ወሰደ፡፡ 10 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አስቀምጣት፡፡ ባመፁት ሰዎች ላይ ለበደላቸው ምልክት ይሆን ዘንድ አስቀምጣት፣ ስለዚህም በእኔ ላይ የሚያሰሙትን ማጉረምረም ፍጻሜ ታደርግለታለህ፤ ይህ ካልሆነ ይሞታሉ፡፡” 11 ሙሴ ልክ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡ 12 የእስራኤል ሰዎች ሙሴን፣ “እኛ ሁላችንም እዚህ መሞታችን ነው፣ ሁላችንም መጥፋታችን ነው! 13 ወደ ያህዌ ማደሪያ ድንኳን የቀረቡ፣ እያንዳንዳቸው ወደዚህ የመጡ ይሞታሉ፡፡ ሁላችንም መጥፋት ይኖርብናልን?” አሉት፡፡
“12” (ቁጥሮች የሚለውን ይመለክቱ)
እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እዚህ ላይ ሌዊ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሌዊን ነገድ ነው፡፡
እዚህ ላይ “አለቃ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው “እያንዳንዱን”መሪ ነው፡፡
“የምሥክሩ ድንኳን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ምሥክሩየተፃፉበት ሠሌዳ የሚቀመጥበትን ሣጥን ነው፡፡“የምሥክሩ ድንኳን”ወይም “ምሥክሩን የሚይዘው ሣጥን”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
“በመረጥኩት ሰው በትር ላይ የለመለመ ነገር ይወጣል”
እዚህ ላይ “ማጉረምረም”የሚለው አሕፅሮተ ሥም ሲሆን በግሥ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “የእሥራኤል ሕዝብ በአንተ ላይ ከማጉረምረም እንዲታቀቡ አድርጋቸው”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ከእያንዳንዱ ነገድ ሙሴ የመረጠው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የምሥክሩ ድንኳን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ምሥክሩ የተፃፉበት ሠሌዳ የሚቀመጥበትን ሣጥን ነው፡፡“የምሥክሩ ድንኳን”ወይም “ምሥክሩን የሚይዘው ሣጥን”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
“እንዲህም ሆነ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድ ልዩ የሆነ ነገር መከናወኑን ነው፡፡በእናንተ ቋንቋ ተመሳሳይ የሆነ አገላለፅሊኖራችሁ ይችል ይሆናል፡፡
“የምሥክሩ ድንኳን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ምሥክሩ የተፃፉበት ሠሌዳ የሚቀመጥበትን ሣጥን ነው፡፡“የምሥክሩ ድንኳን”ወይም “ምሥክሩን የሚይዘው ሣጥን”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ማጉረምረም”የሚለው አሕፅሮተ ሥም ሲሆን በግሥ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ “የእሥራኤል ሕዝብ በአንተ ላይ ከማጉረምረም እንዲታቀቡ አድርጋቸው”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
በማጉረምረማቸው የሚቀጥሉ ከሆነ የሚከሰተው ነገር ይሄ ነው፡፡እግዚአብሔር ይሄ እንዳይሆን ነበር የሚሻው፡፡“እንዳይሞቱ”(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ተቀናጅተው የቀረቡበት ምክኒያት ለጉዳዩ አፅንኦት ለመስጠት ተፈልጎ ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
1 “ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “አንተ፣ ወንዶች ልጆችህና የአባትህ ቤቶች በቤተ መቅደሱ ላይ ለሚሰራው በደል ተጠያቂ ትሆናላች፡፡ በክህነቱ ላይ ለሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ግን አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ወንዶች ልጆች ብቻ ተጠያቂ ትሆናላችሁ፡፡ 2 ከአባትህ ነገድ የሆኑት ሌዋዊያንን በሚመለከት ከአንተ ጋር ይሆኑና አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ስታገለግሉ እንዲረዷችሁ አምጣቸው፡፡ 3 እነርሱ አንተንና መላውን ድንኳን ያገልግሉ፡፡ ሆኖም፣ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ማናቸውም ነገሮች አይቅረቡ ወይም ከመሰዊያው ጋር አይነካኩ፣ አለበለዚያ እነርሱና አንተም ጭምር ትሞታላችሁ፡፡ 4 እነርሱ ከአንተ ጋር ሆነው ለመገናኛው ድንኳንና ከድንኳኑ ጋር ለተያያዙ ስራዎች ሁሉ እንክብካቤ ማድረግ አለባቸው፡፡ መጻተኛው ወደ አንተ አይጠጋ፡፡ 5 አንተ ለተቀደሰው ስፍራና ለመሰዊያው ሀላፊነት መውሰድ አለብህ፣ እንደገና ቁጣዬ በእስራኤል ሰዎች ላይ እንዳይመጣ ይህን አድርግ፡፡ 6 ከእስራኤል ትውልዶች መሀል ሌዋውያንን የመረጥኩት እኔ ራሴ ነኝ፡፡ እነርሱ ከመገናኛው ድንኳን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመስራት ለእኔ የተሰጡ ለእናንተ ስጦታዎች ናቸው፡፡ 7 ከመሰዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ያሉትን አገልግሎቶች ሁሉ በሚመለከት ግን የክህነቱን ስራ የምትሰሩት አንተና ወንዶች ልጆችህ ብቻ ናችሁ፡፡ አንተ ራስህ እነዚያን ሀላፊነቶች መወጣት አለብህ፡፡ እኔ ክህነቱን ስጦታ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፡፡ ማናቸውም መጻተኛ ወደዚህ ቢጠጋ ይገደል፡፡” 8 ከዚያ ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ለእኔ የሚወዘወዙትን መስዋዕቶችና የእስራኤል ሰዎች ለእኔ የሰጧቸውን ቅዱስ መስዋዕቶች አያያዝ ሀላፊነቶች ሰጥቼሃለሁ፡፡ እነዚህን ስጦታዎች ቀጣይ ድርሻህ አድርጌ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ሰጥቻለሁ፡፡ 9 ለያህዌ ሙሉ ለሙሉ ከተለዩ ከእነዚህ ስጦታዎች ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የማይቃጠሉት የአንተ ናቸው፡፡ ህዝቡ የሚያመጣው ማናቸውም መስዋዕት፣ የእህል ቁርባኑን፣ የኃጢአት መስዋዕቱን፣ እና የበደል መስዋዕቱን ሁሉ ጨምሮ፣ እነዚህ እጅግ ቅዱስ የሆኑ ለእኔ የሚለይዋቸውና የሚያመጧቸው ስጦታዎች የአንተና የወንዶች ልጆችህ ይሆናሉ፡፡ 10 አንተ የምትመገባቸው እነዚህ ስጦታዎች፣ ሙሉ ለሙሉ ለእኔ የተለዩ ናቸው፡፡ በመሀል የሚገኝ ማናቸውም ወንድ እነዚህን ስጦዎች ይብላ፡፡ እነርሱ በእናንተ ዘንድ ለእኔ የተለዩ ተደርገው ይቆጠሩ፡፡ 11 እነዚህ የእናንተ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ከእስራኤል ሰዎች ከሚሰበሰቡ መስዋዕቶች ውስጥ የተለዩት ስጦታዎቻቸው ሁሉ፣ በእኔ ፊት የተወዘወዙና ለእኔ የቀረቡ ስጦዎች ሁሉ የእናንተ ናቸው፡፡ እነዚህን ለእናንተ፣ ለወንዶች ልጆቻችሁ፣ እና ለሴቶች ልጆቻችሁ፣ ቀጣይ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻለሁ፡፡ እያንዳንዱ በቤተሰብህ ውስጥ የመንጻት ሥርዓት የፈፀመ ሁሉ ከእነዚህ ስጦታዎች መመገብ ይቻላል፡፡ 12 ከዘይቱ ምርጥ የሆነውን፣ ከአዲሱ ወይንና ሰብል ምርጡን፣ ህዝቡ ለእኔ ካቀረበው በኩራቱን፣ እነዚህን ሁሉ ለእናንተ ሰጥቻለሁ፡፡ 13 ለእኔ የሚያመጡት፣ በምድራቸው ካለው በመጀመሪያ የደረሰው ፍሬ ሁሉ የአንተ ነው፡፡ በቤተሰብህ ውስጥ ያለ ንጹህ የሆነ ሁሉ እነዚህን ነገሮች መብላት ይችላል፡፡ 14 በእስራኤል ማናቸው ፈጽሞ የተሰጠ ነገር የአንተ ይሆናል፡፡ 15 እያንዳንዱ ማህጸን የሚከፍት ሁሉ፣ ሰዎች ለያህዌ የሰጡት በኩር ሁሉ፣ የሰውም ይሁን የእንስሳ በኩር የአንተ ይሆናል፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ሰዎቹ መጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ መልሰው ይግዙ፣ ንጹህ ያልሆኑ እንስሳትን በኩራት መልሰው ይግዙ፡፡ 16 በሰዎች ተመልሰው የሚገዙ አንድ ወር ከሞላቸው በኋላ መልሰው ይገዙ፡፡ ከዚያ ሰዎቹ በመቅደሱ ሰቅል ዋጋ መልሰው ከሀያ ጌራ ጋር እኩል ዋጋ ባለው በአምስት ሰቅሎች ዋጋ ሊገዟቸው ይችላሉ፡፡ 17 ነገር ግን የላም በኩር፣ ወይም የበግ በኩር፣ ወይም የፍየል በኩር ከሆነ እነዚህን እንስሳት መልሰህ አትግዛ፤ እነዚህ ለእኔ የተሰዉ ናቸው፡፡ ለእኔ ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ፣ ደማቸውን በመሰዊያ ላይ እርጨው፣ ስባቸውን በእሳት የቀረበ መስዋዕት አድርገህ ኣቃጥለው፡፡ 18 ስጋቸው ለአንተ ይሁን፡፡ ልክ እንደ ሚወዘወዘው ፍርምባና እንደ ቀኙ ወርች ስጋቸው የአንተ ይሆናል፡፡ 19 የእስራኤል ሰዎች ለእኔ ያቀረቧቸውን ቅዱስ የሆኑ መስዋዕቶች ሁሉ እኔ፤ ለአንተ፣ ለወንድ ልጆችህ እና ለሴት ልጆችህ ቀጣይ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፡፡ ለጨው ኪዳንና ለዘለዓም የአንድነት መስዋዕት ሆነው በፊቴ ከአንተና ከትውልድህ ጋር ይኖራሉ፡፡” 20 ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “አንተ በህዝቡ ምድር ርስት አይኖርህም፣ ወይንም ደግሞ በህዝቡ መሀል የሀብት ድርሻ አይኖርህም፡፡ በእስራኤል ህዝብ መሀል እኔ ድርሻህና ርስትህ ነኝ፡፡ 21 እስራኤላዊያን የሚያመጡትን አስራት ሁሉ፣ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚሰጡት አገልግሎት ድርሻቸው አድርጌ ለሌዊ ትውልድ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ 22 ከአሁን አንስቶ ከእስራኤል ህዝቡ ወደ መገናኛው ድንኳን አይቅረብ፣ ከቀረቡ በኃጢአታቸው ሀላፊነትን ይወስዳሉ፤ እናም ይሞታሉ፡፡ 23 ከመገናኛው ድንኳን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ሌዋውያን ይስሩ፡፡ ይህን በሚመለከት ለማናቸውም ኃጢአት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ይህ በእናተ ህዝብ ትውልዶች ሁሉ ቀዋሚ ህግ ይሆናል፡፡ በእስራኤል ህዝብ መሀል ሌዋውያን ርስት ሊኖቸው አይገባም፡፡ 24 እስራኤላዊያን መባ አድርገው ለእኔ ያቀረቡትን አስራት እኔ ለሌዋውያን ርስታቸው አድርጌ የሰጠሁት እነዚህን ነው፡፡ ለዚህም ነው እንዲህ የምላቸው፣ ‘እነርሱ በእስራኤል ህዝብ መሀል ርስት አይኖራቸውም፡፡’” 25 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 26 ”ለሌዋውያን እንዲህ በላቸው፣ ‘ከእነርሱ የአንተ ርስት አድርጎ ያህዌ ለእናንተ የሰጣችሁን አስራት ከእስራኤል ሰዎች ስትቀበሉ፣ ከዚያ አስራት ለእርሱ አንድ አስረኛውን መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፡፡ 27 እናንተ የምታቀርቡት መስዋዕት በእናንተ ዘንድ ከአውድማ እንደ ቀረበ የእህል አስራት ወይም ከወይን መጥመቂያ እንደ ቀረበ አስራት ሊቆጠር ይገባዋል፡፡ 28 እንደዚሁም ከእስራኤል ሰዎች ከተቀበላችሁት አስራት ሁሉ ለያህዌ መባ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ከእነዚህም ለካህኑ ለአሮን ለእግዚአብሔር ከቀረበው ስጦታ መስጠት አለባች፡፡ 29 ከተቀበላችሁት ስጦታ ሁሉ፣ ከእያንዳንዱ ለያህዌ መባ መስጠት አለባችሁ፡፡ ይህንን ምርጥ ከሆነው ሁሉና ለእናንተ ከሰጠኋችሁ እጅግ ከተቀደሱት ነገሮች ማድረግ አለባችሁ፡፡’ 30 ስለዚህም እንደዚህ በላቸው፣ ‘ከተቀበላችሁት ምርጡን ስታቀርቡ፣ ይህ በሌዋውያን ዘንድ ከአውድማ እንደቀረበ ምርትና ከወይን መጥመቂያ እንደቀረበ ሊቆጠር ይገባል፡፡ 31 የተቀረውን ስጦታዎቻችሁን በማንኛውም ስፍራ ልትበሉ ትችላላችሁ፣ እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ብሉት፣ ምክንያቱም በመገናኛው ድንኳን ለምትሰጡት አገልግሎት ክፍያችሁ ነው፡፡ 32 ከተቀበላችሁት ምርጥ የሆነውን ለያህዌ ካቀረባችሁ፣ ያን በመብላታችሁና በመጠጣታችሁ ምንም አይት በደል በራሳችሁ ላይ አታመጡም፡፡ ነገር ግን የተቀደሱ የእስራኤል ህዝቦች ስጦታዎች አታቃሉ፣ አሊያ ትሞታላች፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ማንኛውም ሰው በመቅደሱ ላይ የሚሰራው ኃጢአት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ማንኛውም ሰው በክህነት አገልግሎቱ ላይ የሚሰራው ኃጢአት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ማንኛውም ካህን”
እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል፡፡
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሌዊ ነገድ አባላትን የሚያመለክት ሲሆን “አንተ”የሚለው ቃል ደግሞ የሚያመለክተው አሮንን ነው፡፡(አንተ/እናንተ የሚለው ቃል በተለያየ መንገድ የሚገለፅበት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚሀ ላይ “እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው“በቤተመቅደሱ ውስጥ ባሉት ሥፍራዎች ሁሉ”የመግባት መብት ያላቸውን ማንኛውንም የሌዊ ነገድ አባላትን ነው፡፡“እነርሱ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም አሮንንና በተፈቀደላቸው አገልግሎት ውስጥ የሚገኙትን ሌዋውያንን ነው፡፡“(ተውላጠ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር በመሆኑ የሚያመለክተው አሮንንና የተቀሩትን ሌዋውያን ነው፡፡(አንተ/እናንተ የሚለው ቃል በተለያየ መንገድ የሚገለፅበት የሚለውን ይመልከቱ)
ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ እጅግ እንደተቆጣ ያመለክታል፡፡2/“በእሥራኤል ሕዝብ ላይ ዳግም በእጅጉ እንዳልቆጣ”2/ይሄ የሚያሣየው ከመቆጣቱ የተነሣ መቅጣቱን ያመለክታል፡፡“የእሥራኤልን ሕዝብ ደግሜ እንዳልቀጣ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እግዚአብሔር ሌዋውያን አሮንን እንዲያግዙት የመደበበትን ሁኔታ እግዚአብሔር ለአሮን እንደተሰጠ ሥጦታ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ለአንተ እንደ ሥጦታ ናቸው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ለእግዚአብሔር “የተሰጡ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ለማገልገል መለየታቸውን ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለራሴ የለየኋቸውን”ወይም“ለራሴ ለይቼያቸዋለሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውንና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“አንተ”እና “የአንተ”የሚሉት ቃላት የነጠላ ቁጥር በመሆናቸው የሚያመለክቱት አሮንን ነው፡፡በሌሎች ሥፍራዎች ላይ “እናንተ”እና“የእናንተ”የሚሉት የብዙ ቁጥር በመሆናቸው የሚያመለክቱት አሮንንና ልጆቹን ነው፡፡(አንተ/እናንተ የሚለው ቃል በተለያየ መንገድ የሚገለፅበት የሚለውን ይመልከቱ)
“የካህናትን ተግባር አከናውኑ”
በመጋረጃው ውስጥ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከመጋረጃው ጀርባ የሚገኘውን የውስጥ ክፍል ነው፡፡“ከመጋረጃው ጀርባ ባለው ከፍል ውስጥ የሚገኘውን ነገር ሁሉ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሌላ ሰው ቢቀርብ መገደል ይኖርበታል”ወይም “ሌላ ሰው ከቀረበ መግደል ይኖርባችኋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ሊቀርቡት የማይገባቸው ነገር ምን እንደሆነ በግልፅ ሊብራራ ይችላል፡፡“ቅዱሱን ሥፍራ የሚቀርብ ሰው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ማንሳት”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አንድን ነገር ለእግዚአብሔር መሥጠትን ወይም ማቅረብን ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ለእኔ የሚያቀርቧቸውመሥዋዕቶች”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ይህንን ውሳኔ ቀድሞ የወሰነ በመሆኑ ጉዳዩን እንደፈፀመው ዓይነት አድርጎ ይናገራል፡፡“እነዚህን የማንሣት ቁርባኖች ለአንተ ሰጥቼሃለሁ”
ድርሻ ማለት አንድ ሰው የተወሰነውን የአንድ ነገር ክፍል ሲወስድ ማለት ነው፡፡“በማይቋረጥ መልኩ የምትወስዱት ድርሻችሁ”
“በመሠዊያው ላይ ሙሉ በሙሉ የማታቃጥሉት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል
እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል
ይሄ የሚያመለክተው ጥራት ያላቸውንና የሚያመርቷቸውን ዘይት፤ወይንና እህልን ነው፡፡
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘትን ንፁሕ እንደመሆን አድርጎ አቅርቦታል፡፡“በቤትህ ውስጥ በእኔ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሰው ሁሉ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡“ማሕፀንን የሚከፍት ወንድ ሁሉ”(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“ማሕፀን መክፈት”የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገርእናት የምትወለደው የመጀመሪያ ወንድ ልጇ ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
መጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ልጃቸውን መሥዋዕት ከማድረግ ይልቅ ለልጆቻቸው ሲሉ ለካህኑ ገንዘብ መክፈል ነበረባቸው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንድ ወር ከሞላቸው በኋላ ሰዎች መልሰው ሊቤዧቸው ይገባል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ምናልባት የሚያመለከተው ሰዎችን እንጂ ንፁሕ ያልሆኑ እንስሳትን ለማመልከት አይመስልም፡፡
በዘመናዊ የመለኪያ መንገድ መተቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እነዚሀን ተግባራዊ የማድረጊያ መንገዶች እነሆ፡፡“አምስት ብር ቁርጥራጮች….እያንዳንዱ አምስት ግራም ያህል የሚመዝን”ወይም“በቤተመቅደሱ ውስጥ ጥቅም ላይ ባሉት የጥራት ደረጃዎች መሠረት የሚመዝን አምሳ ግራም ብር”(መፅሐፍ ቅዱሣዊመለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
ሰቅል የክብደት መለኪያ ነው፡፡የሚመዘነው ነገር ምን እንደሆነ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያየ ዓይነት የሰቅል ዓይነቶች ነበሩ፡፡ይሄኛው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በሚገኘው የተቀደሰው ሥፍራ ላይ ሰዎች የሚጠቀሙበት ዓይነት ነበር፡፡ሃያ አቦሊ ይመዝን ነበር፡፡ይሄ 11 ግራም ገደማ ይሆናል፡፡(መፅሐፍ ቅዱሣዊ መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል፡፡
በመጀመሪያ እንስሣቱን መግደል በተመለከተየበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“እንስሳቱን ገድለህ ደማቸውን ልትረጭ ይገባሃል” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በእሣት የምትሰራውን”ወይም“በመሠዊያው ላይ በእሣት የምታቃጥለውን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር በጣፋጭ ሽታ መደሰቱ የሚያመለክተው ቁርባኑን በሚሰዋው ሰው ደስ መሰኘቱን ነው፡፡“እና እግዚአብሔር በአንተ ደስ ይለዋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የመወዝወዝ ፍርምባውንና ቀኙን ወርች እንደ መሥዋዕት የምታቀርቡልኝ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እግዚአብሔር ይህንን ውሳኔ ቀድሞ የወሰነ በመሆኑ ጉዳዩን እንደፈፀመው ዓይነት አድርጎ ይናገራል፡፡“ለአንተ ሰጠሁህ”
ድርሻ ማለት አንድ ሰው የተወሰነውን የአንድ ነገር ክፍል ሲወስድ ማለት ነው፡፡“በማይቋረጥ መልኩ እንደምትወስዱት ድርሻችሁ”
ሁለቱ ሐረጎች የሚያመለክቱት ተመሳሳይ የሆነ ነገርን ነው፡፡“እነዚህ ሐረጎች በጋራ በመሆን አፅንዖት የሚሰጡት ኪዳኑ ለዘላለም የሚፀና መሆኑን ነው፡፡”“ዘላለማዊ የሆነ ሥምምነት”(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
“በጨው የተደረገ ቃል ኪዳን”ጨው ዘለቂነትን የሚያመለክት ሲሆን በመሥዋዕትና በቃል ኪዳን ወቅት በሚደረጉ ምግቦች ላይ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረግ ነበር፡፡”ዘላቂነት ያለው ኪዳን”ወይም “ዘላለማዊ ኪዳን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሌሎች ሰዎች የሚይዙትን ምድር እንደሚወርሱት ዓይነት አድርጎ ይናገራል፡፡“ከሕዝቡ ምድር አንዱንም አትወርሱም” ወይም “እሥራኤላውያን ከሚይዟቸው መሬቶች ውስጥ አንዱንም አትወስዱም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር አሮንና ዘሩ እርሱን በክህነት በማገልገላቸው የሚጠብቃቸውን ታላቅ ክብር ሲገልፅላቸው ልክ እግዚአብሔር ራሱን እንደሚወርሱት አድርጎ ነው የሚናገረው፡፡“በዚያ ምትክ የምኖራችሁ እኔ ነኝ”ወይም“በዚያ ምትክ እንድታገለግሉኝ እፈቅድላችኋለሁ፤በአገልግሎታችሁም ወቅት የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሁሉ አዘጋጅላችኋለሁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እዚህ ላይ“ተመልከት”የሚለው ቃል የሚቀጥለው ነገር ላይ የበለጠ አፅንኦት እንዲደረግ ያነሳሳል፡፡“በእርግጥ እኔ ሰጥቼያለሁ”
እግዚአብሔር አሮንና ዘሩ የሚቀበሉትን ነገር እንደሚወርሱት ዓይነት አድርጎ ነው የሚናገረው፡፡“ለእሥራኤል ሁሉ የምሰጠውን እንደ ድርሻቸው መጠን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለአሮን መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እግዚአብሔር ሌሎች የእስራኤል ሰዎች የሚይዙትን ምድር እንደሚወርሱት ዓይነት አድርጎ ይናገራል፡፡ሌዋውያን የትኛውንም ምድር አይቀበሉም”“ሌላው የእሥራኤል ሕዝብ የሚቀበለውን መሬት መቀበል አይኖርባቸውም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር አሮንና ዘሩ የሚቀበሉትን ነገር እንደሚወርሱት ዓይነት አድርጎ ነው የሚናገረው፡፡“ለእሥራኤል ሁሉ የምሰጠውን እንደ ድርሻቸው መጠን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል ሕዝብ ከሰብሎቻቸውንና ከእንስሳቶቻቸው አንድ አሥረኛውን በሥጦታ መልክ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን እግዚአብሔር ደግሞ ይሄንን ለሌዋውያን ይሰጣቸዋል፡፡
የሚወርሱት ነገር ይመስል እግዚአብሔር አሮንና ትውልዱ ስለሚቀበለው ነገር እግዚአብሔር ይናገራል፡፡”ለእሥራኤል ሁሉ ከምሰጠው የእናንተ ድርሻ የሆነው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አሥራታችሁን ለመሥጠት ማሰብ ይገባችኋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሙሴ ለሌዋውያን መናገር የሚኖርበትን ነገር መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እዚህ ላይ“የእርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው፡፡በመሠረቱ የእግዚአብሔርን የማንሣት ቁርባንድርሻ መሥጠት የነበረባቸው ለእግዚአብሔር ነው፡፡“ለእግዚአብሔር መሥጠት የሚገባችሁን ቁርባንለአሮን መሥጠት ይኖርባችኋል”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ የሰጠህን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
“ከእሥራኤል ሕዝብ ምርጥ የሆነውን ነገር የተቀበልከውን”
“ሥጦታዎቹ”እሥራኤላውያን የሚያቀርቧቸው መሥዋዕቶች ሆነው ሌዋውያን የሚቀበሏቸው ነገሮች ናቸው፡፡
“እርሱን በምትበሉበትና በምትጠጡበት ወቅት በደለኞች አትሆኑም”
1 ያህዌ ለሙሴና ለአሮን ተናገረ፤ እንዲህም አለ፣ 2 ”ይህ እናንተን የማዛችሁ ትዕዛዝ መታሰቢየ ነው፡፡ የእስራኤል ሰዎች ወደ አንተ ቀንበር ተጭኟት የማታውቅ፣ እንከን ወይም ነውር የሌለባት ቀይ ጊደር እንዲያመጡ ንገራቸው፡፡ 3 ጊደሯን ለካህኑ ለአልዓዛረ ስጠው፡፡ ከሰፈር ውጭ ያውጣት አንድ ሰው በፊቱ ይረዳት፡፡ 4 ካህኑ አልአዛር ከጊደሯ ደም በጣቱ ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ፊት ባለው አቅጣጫ ሰባት ጊዜ ይርጨው፡፡ 5 ሌላ ካህን እርሱ እያየ ጊደሯን ያቃጥላት፡፡ ቆዳዋን፣ ስጋ እና ደሟን ከፈርሷ ጋር ያቃጥል፡፡ 6 ካህኑ የዝግባ እንጨት፣ ሂሶጵ፣ እና ደማቅ ሱፍ ይውሰድና ጊደሯ በምትቃጠልበት እሳት ውስጥ ይጨምር፡፡ 7 ከዚየ ልብሱን ይጠብ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፡፡ ከዚያ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ከቆየበት ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡ 8 ጊደሯን ያቃጠለው ሰው ልብሱን በውሃ ይጠብ ገላውንም ይታጠብ፡፡ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡ 9 ንጹህ የሆነ አንድ ሰው የጊደሯን አመድ አፍሶ ከሰፈር ውጭ ንጹህ በሆነ ስፍራ ይድፋው፡፡ ይህ አመድ ለእስራኤል ሰዎች ለማህበረሰቡ ይጠበቅ፡፡ አመዱ ከኃጢአት መስዋዕት የተገኘ እንደመሆኑ፣ ከኃጢአት ለመንጻት በውሃ ይበጠብጡታል፡፡ 10 የጊደሯን አመድ ያፈሰው ሰው ልብሱን ይጠብ፡፡ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡ ይህ ለእስራኤላዊያንና ከእነርሱ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞችም ቋሚ ህግ ይሆናል፡፡ 11 ማንም የሞተን ሰው አካል የነካ ሁሉ ለሰባት ቀናት እርኩስ ነው፡፡ 12 እንዲህ ያለው ሰው በሶስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፡፡ ከዚያ ንጹህ ይናል፡፡ ነገር ግን በሶስተኛው ቀን ራሱን ካላነጻ፣ በሰባተኛው ቀን ንጹህ አይሆንም፡፡ 13 የሞተን ሰው የነካ ማንም ቢሆን፣ የሞተን ሰው የነካ ሁሉ፣ እናም ራሱን ያላነጻ ይህ ሰው የያህዌን ማደሪያ ያረክሳል፡፡ ያ ሰው ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ፤ ምክንያቱም ከእርኩሰት የሚያነጻው ውሃ አልተረጨበትም፡፡ እርኩስ ሆኖ ይቆያል፣ ያለመንጻቱ በእርሱ ላይ ይቆያል፡፡ 14 አንድ ሰው በድንኳን ውስጥ በሚሞትበት ጊዜ ህጉ ይህ ነው፡፡ ወደ ድንኳኑ የገባ እያንዳንዱ ሰውና ቀድሞውኑም በድንኳኑ ውስጥ የነበረ ሰው ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለም፡፡ 15 ያልተከደነና ያልተሸፈነ ማናቸውም ዕቃ ይረክሳል፡፡ 16 በተመሳሳይ፣ በሰይፍ የተገደለንም ሰው ሆነ ማናቸውንም በሌላ ሁኔታ የሞተን ሰው፣ ወይም የሞተን ሰው አጽም፣ ወይም መቃብር የነካ ማናቸውም ከድንኳን ውጭ ያለ ሰው ለሰባት ቀናት ንጹህ አደለም፡፡ 17 ለረከሰ ሰው ይህን አድርግ፡ ከተቃጠለው የኃጢአት መስዋዕት ጥቂት አመድ ውሰድና በንጹህ ውሃ በዕቃ ውስጥ በጥብጠው፡፡ 18 ንጹህ የሆነ ሰው ሂሶጵ ይውሰድና ውሃው ውስጥ ይንከረው፤ ከዚያም በድንኳኑ ላይ፣ በድንኳኑ ውስጥ ባሉ ዕቃዎች ሁሉ ላይ፣ በዚያ በሚገኙ ሰዎች ላይ፣ እንዲሁም የሞተ ሰውን አጽም፣ የተገደለን ሰው፣ የሞተን ሰው ወይም መቃብር በነካ ሰው ላይ ይርጨው፡፡ 19 በሶስተኛው ቀንና በሰባተኛው ቀን፣ ንጹህ የሆነው ሰው ንጹህ ያልሆነውን ሰው ይርጨው፡፡ ያልነጻው ሰው በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፡፡ ልብሱን ይጠብ ገላውንም በውሃ ይታጠብ፡፡ ምሽት ላይ ንጹህ ይሆናል፡፡ 20 ነገር ግን ሳይነጻ የሚቆይ ማናቸው ሰው፣ ራሱን ለማንጻት ያልፈቀደ ሰው ያ ሰው ከማህበረሰቡ ተለይቶ ይጥፋ፣ ምክንቱም የያህዌን መቅደስ አርክሷል፡፡ ከእርኩሰት የሚያነጻው ውሃ በእርሱ ላይ አልተረጨምና እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡ 21 ለእነዚህ ሁኔታዎች ይህ ቀጣይ ህግ ይሆናል፡፡ ለመንጻት የሚሆንን ውሃ የሚረጨው ሰው ልብሶቹን ይጠብ፡፡ የሚያነጻውን ውሃ የሚነካ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ 22 ማናቸውም ንጹህ ያልሆነ ሰው የነካው ነገር እርኩስ ይሆናል፡፡ ያንን የነካ ሰው እስከ ምሽት እርኩስ ይሆናል፡፡”
በመሠረቱ እነዚህ ቃላት ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡“የሕግ ትዕዛዝ”ወይም “ሕጋዊነት ያለው ደንብ” (ሁለት ተመሳሳይ ገፅታ ያላቸው ነገሮች የሚለውን ይመልክቱ)
እዚህ ላይ“ለአንተ”የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር በመሆኑ የሚያመለክተው ሙሴን ነው፡፡
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሣሣይ ዓይነት ትርጓሜ ያላቸው ሲሆኑ የሚያሳስበውም እንስሳው ምንም ዓይነት እንከን የማይገኝበት መሆን እንዳለበት አፅንኦት ለመሥጠት ነው፡፡(ሁለት ተመሳሳይ ገፅታ ያላቸው የሚለውን ይመልክቱ)
“በእርሱ እይታ ሥር”ወይም“ይመለከተው ዘንድ”
“ካህኑ የሚለው ቃል የሚያመለክተው አልዓዛርን ነው፡፡
“ደማቅ ቀይ ልብስ”
እዚህ ላይ“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አልዓዛርን ነው፡፡
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አለማግኘት ወይም የተቀደሱ አገልግሎቶችን ለማከናወን ብቁ ያለመሆን ጉዳይ ሰውዬው ንፁሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ነው የሚነገረው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘትናወይም የተቀደሱ አገልግሎቶችን ለማከናወን ብቁ የመሆን ጉዳይ ሰውዬው ንፁሕ እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚነገረው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አመዶቹ መከማቸት ይኖርባቸዋል፡፡”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘት ንፁሕ እንደመሆን ተደርጎ ነው የሚነገረው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አለማግኘት ወይም የተቀደሱ አገልግሎቶችን ለማከናወን ብቁ ያለመሆን ጉዳይ ሰውዬው ንፁሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ነው የሚነገረው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ንፁሕ መሆን”እና “መቀደስ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘትን ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ንፁሕ ያልሆነ”“መርከስ”“ቅድሰና ማጣት” እና “በኃጢአት መበከል”የሚሉት ሃሣቦች የሚያመለክቱት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለማግኘትን ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“የማንኛውም ሰው ሬሣ”
ይሄ ሰው አንድ ንፁሕ የሆነ ሰው ይጠራና ከውኃ ጋር የተደባለቀ የጊደር አመድ በመርጨት እንዲያጠራው ይጋብዘዋል፡፡አንድን ሰው እንዲያጠራው በመጥራቱ ልክ ያ ሰው ራሱ እንደሚያጠራው ዓይነት ተደርጎ ነው የሚገለፀው፡፡“አንድን ሰው እንዲያጠራው መጋበዝ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በአዎንታዊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በሰባተኛው ቀን ንፁሕ የሚሆነው በሶስተኛው ቀን ራሱን ያጠራ እንደሆነ ብቻ ነው”(ድርብ አሉታዎች)
“መጥፋት”የሚል ቃል የሚያመለክተው ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ማንኛውም ግንኙነት ተቋርጦ መባረሩን ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 9፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ያ ሰው መባረር አለበት”ወይም “ያንን ሰው ማባረር አለባችሁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ማንም ሰው በርኩሰቱ ላይ ውኃን አልረጨም”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የረከሱ ነገሮች እንዲነፁ ለማድረግ የሚረጭ ውኃ”ወይም“ነገሮችን ለማንፃት የሚረጭ ውኃ”
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በአንድ ላይ እንዲነገሩ የተደረገው ለጉዳዩ አፅንኦት ለመስጠት ሲባል ነው፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“ንፁሕ ያልሆነ”የሚለው ሃሣብ የሚያመለክተው በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለማግኘትን ወይም ለአገልግሎት ብቁ አለመሆንን ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በአዎንታዊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የተከፈቱ ዕቃዎች ንፁሕ የሚሆኑት መሸፈኛ የሚደረግላቸው ከሆነ ብቻ ነው፡፡“ድርብ አሉታዊነት”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሌላ ሰው በሠይፍ የገደለው ሰው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ንፁሕ ያልሆነ”የሚለው ሃሣብ የሚያመለክተው በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለማግኘትን ወይም ለአገልግሎት ብቁ አለመሆንን ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ንፁሕ መሆን”እና “መቀደስ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘትን ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ንፁሕ መሆን”እና “መቀደስ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት መኖሩን ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ንፁሕ ያልሆነ”የሚለው ሃሣብ የሚያመለክተው በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለማግኘትን ወይም ለአገልግሎት ብቁ አለመሆንን ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
1 የእስራኤል ሰዎች፣ መላው ማህበረሰብ በመጀመሪያው ወር ወደ ሲና ምድረ በዳ ሄደው በቃዴስ ሰፈሩ፡፡ማርያም በዚያ ሞታ ተቀበረች፡፡ 2 ማህበረሰቡ ውሃ ተጠማ፣ ስለዚህ በሙሴና በአሮን ላይ አምጸው ተሰበሰቡ፡፡ 3 ህዝቡ በሙሴ ላይ አጉረመረሙ፡፡ እንዲህም አሉ፣ “ወገኖቻችን እስራኤላውያን በያህዌ ፊት በሞቱበት ጊዜ እኛም ብንሞት ኖሮ ይሻል ነበር! 4 እዚህ እንሞት ዘንድ የያህዌን ማህበረሰብ፣ እኛንና ከብቶቻችንን ለምን ወደዚህ ምድረበዳ አመጣችሁን? 5 ወደዚህ አስፈሪ ስፍራ ልታመጡን ለምን ከግብጽ እንድንወጣ አደረጋችሁን? እዚህ፤ እህል፣ በለስ፣ ወይም ወይም ሮማን የለም፡፡ የሚጠጣም ውሃ የለም፡፡” 6 ስለዚህ ሙሴና አሮን ከጉባኤው ፊት ወጥተው ሄዱ፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ሄደው በግምባራቸው ተደፉ፡፡ ከዚያ የያህዌ አንጸባራቂ ክብር ታያቸው፡፡ 7 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 8 “በትርህን ውሰድና አንተና ወንድምህ አሮን ማህበረሰቡን ሰብስቡ፡፡ በፊታቸው ለዓለቱ ተናገር፣ ውሃ እንዲያፈስም አለቱን እዘዘው፡፡ ከዚያ ዓለት ውሃ አውጥተህ ትሰጣቸዋለህ፣ ማህበረሰቡና ከብቶቻቸው ይጠጡ ዘንድ ውሃ ስጣቸው፡፡” 9 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው ከያህዌ ፊት በትሩን ወሰደ፡፡ 10 ከዚያ ሙሴና አሮን ጉባኤውን በአለቱ ፊት ሰበሰቡ፡፡ ሙሴ ጉባኤውን እንዲህ አለ፣ “እናንተ አመጸኞች፣ አሁን ስሙ፡፡ ከዚህ ዓለት ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን?” 11 ከዚያ ሙሴ እጁን አንስቶ በበትሩ አለቱን ሁለት ጊዜ መታው፣ እናም ብዙ ውሃ ወጣ፡፡ ማህበረሰቡ ጠጣ፣ እንዲሁም ከብቶቻቸው ጠጡ፡፡ 12 ከዚያ ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ “እኔን ስላላመናችሁ ወይም በእስራኤል ሰዎች ዐይኖች ፊት ቅዱስ አድርጋች ስላለያችሁኝ፣ ይህን ጉባኤ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር አታስገቧቸውም፡፡” 13 ይህ ቦታ የመሪባ ውሃ ተብሎ ተጠራ፣ ምክንያቱም በዚያ የእስራኤል ሰዎች ከያህዌ ጋር ተጣልተው ነበር፣ እርሱም ራሱን በቅድስናው ገለፀላቸው፡፡ 14 ሙሴ ከቃዴስ መልዕክተኞችን ወደ ኤዶም ንጉስ ላከ፡ ወንድምህ እስራኤል ይህን ይላል፡ “በእኛ ላይ የደረሱትን አስቸጋሪ ነገሮች ታውቃለህ፡፡ 15 አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወርደው ለዘመናት በግብጽ መኖራቸውን ታውቃለህ፡፡ ግብጻውያን በእኛና በአባቶቻችን ላይ እጅግ ከፉብን፡፡ 16 እኛ ወደ ያህዌ ስንጮህ፣ እርሱ ድምጻችንን ሰምቶ መልዓክ ልኮ ከግብጽ አወጣን፡፡ እነሆ፣ በምድርህ ዳርቻ በምትገኘው በቃዴስ እንገኛለን፡፡ 17 በምድርህ እንድናልፍ እንድትፈቅድልን እጠይቅሃለሁ፡፡ በእርሻዎች ወይም በወይን ሥፍራዎች ውስጥ አናልፍም፣ አሊያም ከጉድጓዶቻችሁ ውሃ አንጠጣም፡፡ የንዱን አውራ ጎዳና ይዘን እንሄዳለን፡፡ ድንበርህን እስክናልፍ ድረስ ወደ ግራም ወደ ቀኝም አንልም፡፡” 18 የኤዶም ንጉስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “በዚህ በኩል ማለፍ አትችሉም፡፡ ይህን ብታደርጉ፣ ሰይፍ ይዤ እወጣባችኋለሁ፡፡” 19 ከዚያ የእስራኤል ሰዎች እንዲህ አሉት፣ “እኛ በአውራ ጎዳናው እንሄዳለን፡፡ እኛም ሆን ከብቶቻችን ውሃህን ብንጠጣ፣ ለዚያም እንከፍላለን፡፡ ሌላ ምንም ነገር ሳናደርግ በእግራችን እንለፍ፡፡” 20 የኤዶም ንጉስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፣ “በዚህ በኩል አታልፉም፡፡” ስለዚህም የኤዶም ንጉስ በብርቱ ክንድ አያሌ ወታደሮች ይዞ በእስራኤላዊያን ላይ መጣባቸው፡፡ 21 የኤዶም ንጉስ እስራኤላውያን በድንበሩ አቋርጠው እንዳያልፉ ተቃወመ፡፡ በዚህ ምክንያትና እስራኤል ከኤዶም ምድር ተመለሱ፡፡ 22 ስለዚህ ህዝቡ ከቃዴስ ተነስቶ ተጓዘ፡፡ የእስራኤል ህዝብ፣ መላው ማህበረሰብ ወደ ሖር ተራራ መጣ፡፡ 23 ያህዌ በሖር ተራራ ለሙሴና አሮን ተናገራቸው፡፡ እንዲህም አለ፣ 24 ”አሮን ለእስራኤል ህዝብ ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባምና ወደ አባቶቹ ይሰበሰባል፡፡ ይህም የሚሆነው እናንተ ሁለታችሁም በመሪባ ውሃ በእኔ ቃሎች ላይ ስላመፃችሁ ነው፡፡ 25 አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ አምጣቸው፡፡ 26 የአሮንን የክህነት ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቀህ ልጁን አልዓዛርን አልብሰው፡፡ አሮን በዚያ ይሞትና ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል፡፡” 27 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡ መላው ማህበረሰብ እያየ ወደ ሖር ተራራ ወጡ፡፡ 28 ሙሴ የአሮንን የክህነት ልብሶች ከእርሱ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው፡፡ አልዓዛር በተራራው አናት ላይ በዚያ ሞተ፡፡ ከዚያ ሙሴና አልዓዛር ከተራራው ወደ ታች ወረዱ፡፡ 29 መላው ማህበረሰብ አሮን እንደ ሞተ ባየ ጊዜ፣ ጠቅላላው አገሩ ለሰላሳ ቀናት ለአሮን አለቀሰ፡፡
እዚህ ላይ “ፂን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በዕብራይስጥምድረ በዳ የሚለውን ሥያሜ ነው፡፡(ቃላትን መቅዳት ወይም መዋስ የሚለውን ይመልከቱ)
በዕብራውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት ይሄየመጀመሪያ ወራቸው ነው፡፡እግዚአብሔር ከግብፃውያን ነፃ ያወጣቸውን ጊዜ የሚያመለክት ነው፡፡በምዕራባውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት የመጀመሪያ ወር የሚሆነው በመጋቢት የመጀመሪያዎቹ ቀናትና በየካቲት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ወቅት ነው፡፡(የዕብራውያን ወራት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ቀበሯት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ማህበረሰቡን ነው፡፡
“ለአመፅ ተሰባሰቡ”
ይሄ የሚያመለክተው በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት መሆናቸውን ነው፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል ሕዝብ በሙሴና በአሮን ላይ ማጉረምረማቸውን ይቀጥላሉ፡፡
ሕዝቡ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው በሙሴና በአሮን ላይ ለማጉረምርም ነው፡፡እንደ መግለጫ ሊታይ ይችላል፡፡“የእግዚአብሔርን ሕዝብ ከከብቶቹ ጋር እንዲሞት ለማድረግ እዚህ በረሃ ውስጥ ማምጣት አልነበረብህም” (ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ሕዝቡ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው በሙሴና በአሮን ላይ ለማጉረምርም ነው::እንደ መግለጫ ሊታይ ይችላል፡፡“እኛን ወደዚህ አስከፊ ሥፍራ ለማምጣት ከግብፅ ምድር ልታወጣን አይገባህም ነበር”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ሙሴና አሮን በእግዚአብሔር ፊት ራሣቸውን ማዋረዳቸውን ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሰዎቹ የሚያዩትን ነገር በሚመለከት“ዓይናቸው”እንደ ወኪል ሆኖ ቀርቧል፡፡“አንተን በሚመለከቱበት ወቅት”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ድንኳን ነው፡፡“ከእግዚአብሔር ድንኳን”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ከብስጭት የተነሣ ሲሆን ሕዝቡ በማጉረምረማቸው ሊገስፃቸው ነበር፡፡ይሄ እንደ መግለጫ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ውኃ የለም ብላችሁ አጉረምርማችኋል፡፡እንደዚህ ከሆነ ከዚህ ዓለት ውኃ እናወጣላችኋለን”ወይም“ከዚህ ዓለት ውኃ ብናወጣላችሁ እንኳን ደስተኞች አትሆኑም፡፡ቢሆንም ግን አደርገዋለሁ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“እኛ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴንና አሮንን ሲሆን እግዚአብሔርንም የሚያካትት ሊሆን ይችላል፡፡ሆኖም ግን ሕዝቡን አያካትትም፡፡(“እኛ”የሚለውንና አካታችና አካታች ያልሆነውን የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ በእግዚአብሔር ላይ አለመታመኑና እግዚአብሔርን ያለማክበሩ ነገር በእርሱ ላይ መታየቱ በግልፅ ሊብራራ ይችላል፡፡“በእሥራኤል ልጆች ዓይኖች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ ባለማመናችሁምክንያት እኔ በተናገርኩት መንገድ ልታደርግ ሲገባህ በራስህ ሃሣብ ተመስርተህ ዓለቱን መታህ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሰዎቹ የሚያዩትን ነገር በሚመለከት “ዓይናቸው”እንደ ወኪል ሆኖ ቀርቧል፡፡“አንተን በሚመለከቱበት ወቅት”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ይሄንን ሥፍራ የሚጠሩት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ይሄንን ሐረግ የተጠቀመበት ምክኒያት ዘሮቻቸው የሆኑት ያዕቆበና ኤሳው ወንድማማቾች ስለሆኑ እሥራኤላውንና ኤዶማውያን ዘመዳሞች እንደሆኑ አፅንዖት ለመስጠት ፈልጎ ነው፡፡
“ዕርዳታ ያደርግልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በፀለይን ጊዜ”
እዚህ ላይ“ድምፅ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው መጮሃቸውንና ለእርሱ የተናገሩትን ነገር ነው፡፡“ጩኸታችንን አዳመጠ”ወይም “የጠየቅነውን ነገር ሰማን”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“እነሆ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ስላለፈው ነገር ማውራት ማቆማቸውንና አሁን ስላሉበት ሁኔታ እየተናገሩ መሆኑን ይገልፃል፡፡
መልዕክተኞቹ ስለ ኤዶም ንጉሥ መናገራቸውን ይቀጥላሉ፡፡
“አንልም”የሚለው ቃል የሚያመለክተው መንገድ መልቀቅን ነው፡፡“በየትኛውም አቅጣጫ ቢሆን መንገዱን አንለቅም”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሰሜናዊውን የደማስቆ የሰሜኑን ክፍል ክፍል በደቡብ ከሚገኘው የአካባ ባህረ ሰላጤ ጋርየሚያገናኝ ዋና መንገድ ነው፡፡
“አንተ”የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር በመሆኑ የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ የሚወክለውን ሙሴን ነው፡፡“ሕዝብህን በሠይፍ እንዳልገጥም አንተ በምድሬ ላይ አታልፍም”(አንተ/እናንተ የሚለው ቃል በተለያየ መንገድ የሚገለፅበት የሚለውንና ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ሠይፍ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የንጉሡን ሠራዊት ነው፡፡“ሠራዊቴን እልካለሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሐረግ የሚያመለክተው የእሥራኤልን መልዕክተኞች ነው፡፡
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው በዚያ በኩል በእግራቸው ለማለፍ እንደፈለጉ ብቻ ነው፡፡የኤዶምን ህዝብ ለማጥቃት በሠረገሎች አይመጡም ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ እጅ የሚለው ቃል የሚያመለከተው የንጉሡን ጠንካራ ሠራዊት ነው፡፡“የኤዶም ንጉሥ እሥራኤልን ይዋጉ ዘንድ ብዙ ተዋጊዎች ያሉበትን ጠንካራ ሠራዊት ላከ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አዶማውያንን ነው፡፡
“ማህበር ሁሉ”የሚለው ቃል የሚሰጠው ያለምንም ልዩነት እዚያ የተገኘና “የእሥራኤል ሕዝብ”አካል የሆነ እያንዳንዱ ግለሰብ እዚያ ስለመገኘቱ አፅንኦት ይሰጣል፡፡ (ሁለት ተመሳሳይ ገፅታ ያላቸው የሚለውን ይመልክቱ)
ይሄ ጨዋ በሆነ አነጋገር አሮን መሞት አለበት ማለት ነው፡፡ይሄ የሚያመለክተው አሮን መሞት ያለበት መሆኑንና መንፈሱም አባቶቹ ወዳሉበት ሥፍራ መሄድ ያለበት መሆኑን ነው ፡፡“አሮን መሞተ አለበት”(ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
“እኔ የተናገርኩትን ተግባራዊለማድረግ እምቢ አላችሁ”
እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
በመሠረቱ እነዚሀ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡ይሄ የሚያመለክተው አሮን መሞት ያለበት መሆኑንና መንፈሱም አባቶቹ ወዳሉበት ሥፍራ መሄድ ያለበት መሆኑን ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውንና ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
“30 ቀናት”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
1 በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓረድ ንጉስ እስራኤል ወደ አታሪም እየመጣ በመንገድ ላይ መሆኑን ሲሰማ፣ ከእስራኤል ጋር ተዋግቶ አንዳንዶቹን በምርኮ ወሰደ፡፡ 2 እስራኤል ለያህዌ እንዲህ ብሎ ማለ፣ “በእነዚህ ህዝቦች ላይ ድል ብትሰጠን፣ ከዚያም ከተማቸውን ሙሉ ለሙሉ እናጠፋለን፡፡” 3 ያህዌ የእስራኤልን ድምጽ ሰምቶ በከነዓናዊያን ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ ሙሉ ለሙሉ እነርሱንና ከተማቸውን አጠፉ፡፡ ያ ስፍራ ሖርማ ተብሎ ተጠራ፡፡ 4 ከሖር ተራራ ተነስተው ኤዶም ምድር ዙሪያ ለመድረስ በቀይ ባህር መንገድ ተጓዙ፤ ህዝቡ በመንገድ ሳለ እጅግ ተስፋ ቆረጡ፡፡ 5 በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ እንዲህ ሲሉ አጉረመረሙ፡፡ “በበረሃ እንሞት ዘንድ ለምን ከግብጽ አወጣችሁን በዚህ ዳቦ የለም፣ አንዳች ውሃ የለም፣ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል፡፡” 6 ከዚያ ያህዌ በሰዎቹ መካከል መርዛም እባቦችን ሰደደ፡፡ እባቦቹ ሰዎችን ነደፉ፤ ብዙ ሰዎችም ሞቱ፡፡ 7 ሰዎች ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉ፣ “እኛ በድለናል ምክንያቱም በያህዌና በአንተ ላይ በተቃውሞ ተናግረናል፡፡ እባቦቹን ከእኛ እንዲያርቅ ወደ ያህዌ ጸልይልን፡፡” ስለዚህም ሙሴ ለህዝቡ ጸለየ፡፡ 8 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እባብ አብጅና በምሰሶ ላይ አንጠለጠለው፡፡ እንዲህ ይሆናል፣ የተነደፈ ሁሉ ያንን ከተመለከተ ይድናል፡፡” 9 ስለዚህም ሙሴ የናስ እባብ አበጅቶ በምሰሶ ላይ አንጠለጠለው፡፡ እባብ ማናቸውንም ሰው በነከሰ ጊዜ፣ ሰውየው ወደ ናሱ እባብ ከተመለከተ ይድናል፡፡ 10 ከዚያ የእስራኤል ሰዎች ተጉዘው በአቦት ሰፈሩ፡፡ 11 ከአቦት ተጉዘው በስተምስራቅ በሞአብ አንጻር በዒዮዓባሪም በምድረ በዳ ሰፈሩ፡፡ 12 ከዚያ ተጉዘው በዘሬድ ሸለቆ ሰፈሩ፡፡ 13 ከዚያ ተጉዘው እስከ አሞራዊያን ድንበር በሚዘልቀው በምድረበዳ ባለው በአሮን ወንዝ ሌላኛው ዳርቻ ሰፈሩ፡፡ የአርኖን ወንዝ በሞዐብና አሞራዊያን መሀል የሞአብን ወሰን ያበጃል፡፡ 14 በያህዌ የጦርነት መጽሐፍ ጥቅልል፣ በሱፋ ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ እና የአርኖን ሸለቆዎች፣ 15 ወደ ዔር ከተማና ወደ ሞአብ ዳርቻ የሚወስዱ የሸለቆዎች ቁልቁለት” ተብሎ የተፃፈው ስለዚህ ነው፡፡ 16 ከዚያ ተነስተው ወደ ብኤር ተጓዙ፣ ይህም ስፍራ የውሃ ጉድጓድ የሚገኝበትና ያህዌ ሙሴን፡ - “ውሃ እሰጣቸው ዘንድ ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸው” ብሎ የተናገረበት ነው፡፡ 17 ከዚያ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፡፡ “አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ፡፡ ስለዚህ እናንተም ዘምሩ፡፡ 18 መሪዎቻችን የቆፈሩት ጉድጓድ፣ የተከበሩ የህዝብ አለቆች በበትረ መንግስታቸውና በበትሮቻቸው የማሱት ጉድጓድ፡፡” ከዚያ ከምድረበዳው ተነስተው ወደ መቴና ተጓዙ፡፡ 19 ከመቴና ተነስተው ወደ ነሃሊኤል፣ ከነሃሊኤል ወደ ባሞት እና ከባሞት በሞአብ ምድር ወደሚገኘው ሸለቆ ተጓዙ፡፡ 20 በፈስጋ ተራራ ጫፍ ሆኖ ምድረበዳው ቁልቁል የሚታይበት ይህ ስፍራ ነው፡፡ 21 ከዚያ እስራኤል ወደ አሞራዊያን ንጉስ ወደ ሴዎን እንዲህ ብለው መልእክተኞችን ላኩ፣ 22 ”በምድርህ እንለፍ፡፡ ወደ እርሻዎች ወይም ወደ ወይን አትክልቶች አንገባም፡፡ ከጉድጓዶችህ ውሃ አንጠጣም፡፡ ድንበርህን እስክናልፍ ድረስ በንጉሱ አውራ መንገድ እንጓዛለን፡፡” 23 ንጉስ ሴዎን ግን እስራኤልን በድንበሩ እንዲያልፉ አልፈቀደም፡፡ ይልቁንም፣ ሴዎን ወታደሮቹን አሰባስቦ በምድረ በዳ እስራኤልን ለመውጋት ወጣ፡፡ 24 እስራኤል የሴዎንን ጦር በሰይፍ ወግቶ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ወንዝና እስከ አሞን ሰዎች ወሰን ድረስ ምድሩን ወሰደ፡፡ የአሞን ሰዎች ድንበር ግን የተመሸገ ነበር፡፡ 25 እስራኤል የአሞራዊያንን ከተሞች ሁሉ፣ ሐስቦንንና መንደሮቹን ጭምር ይዞ በእነዚያ ውስጥ ተቀመጠ፡፡ 26 ሐስቦን ከሞአብ የቀድሞ ንጉስ ጋር የተዋጋው የአሞራዊያን ንጉስ የሴዎን ከተማ ነበረች፡፡ ሴዎን እስከ አርኖን ወንዝ ድረስ ያለውን ምድሩን ሁሉ ወሰደበት፡ 27 በምሳሌያዊ ንግግር የተናገሩ፣ “ወደ ሐሴቦን ኑ፡፡ የሴዎን ከተማ እንደ ገና ትገንባና ዳግም ትታነጽ፡፡ 28 እሳት ከሐሴቦን ተንቦገቦገ፣ ነበልባል ከሴዎን ከተማ የሞአብን ዔር አጠፉ፣ ደግሞም የአርን ተራሮች ባለቤቶችን በላ፡፡ 29 ሞአብ ዋይታ ሆነብህ! የከሞስ ህዝብ እናንተ ጠፋችሁ፡፡ ለአሞራውያን ንጉስ ለሴዎን ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት ሴቶች ልጆቹን ለምርኮ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ 30 እኛ ግን ሴዎንን አሸንፈናል፡፡ ሐስቦን እስከ ዴናን ድረስ ወድማለች፡፡ ወደ ሜድባ እስከምታደርሰው ኖፋ ድረስ ሁሉንም አሸንፈናቸዋል፡፡” 31 ስለዚህ እስራኤል በአሞራዊያን ምድር መኖር ጀመረ፡፡ 32 ከዚያ ሙሴ ሰዎችን ምድሪቱን እንደያዙ ወደ ኢያዜር ላከ፡፡ እነርሱ መንደሮቿን ማረኩ በዚያ የነበሩትንም አሞራዊያን አባረሩ፡፡ 33 ከዚያ ወደ ባሳን በሚስደው መንገድ ዞረው ሄዱ፡፡ የባሳን ንጉስ ዐግ በእነርሱ ላይ ዘመተ፣ እርሱና ሰራዊቱ ሁሉ በኤድራይ ሊዋጓቸው ወጡ፡፡ 34 በዚያን ጊዜ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እርሱን አትፈራው፣ ምክንያቱም እኔ በእርሱ፣ በሰራዊቱና በምድሩ ላይ ሁሉ ላይ ድል ሰጥቼሃለሁ፡፡ በሔስቦን እንደነበረው በአሞራዊያን ንጉስ በሴዎን ላይ እንዳደረከው በእርሱ ላይ አድርግበት፡፡” 35 ስለዚህም እርሱን፣ ወንዶች ልጆቹን እና መላውን ሰራዊቱን አንድም ሰው በህይወት እስከ ማይተርፍለት ድረስ ፈጇቸው፡፡ ከዚያም ምድሩን ወረሱ፡፡
“ሠልፍ አደረገ”ማለት ሠራዊቱ ተዋጋ ማለት ነው፡፡“የእርሱ ሠራዊት ከእሥራኤል ሕዝብ ጋር ተዋጋ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ ስእለትን ተሳለ”ወይም “እሥራኤላውያን ስእለትን ተሳሉ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰማ”ማለት የጠየቁትን ነገር አደረገላቸው ማለት ነው፡፡“እሥራኤል ጥያቄ ባቀረበለት መሠረት ተግባራዊ አደረገው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ድምፅ”የሚለው ቃልከጥያቄያቸው ጋር የተያያዘ አባባል ነው፡፡“እሥራኤል የጠየቀውን”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“የእሥራኤል ሕዝብ የከነዓናውያንን ሠራዊትና ከተሞቻቸውን ፈፅሞ አጠፉ”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ያንን ሥፍራ ሔርማ ብለው ጠሩት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ሕዝቡ ይሄንን ጥያቄ የጠየቀው ሙሴን ለመገሰፅ ነበር፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እኛን በምድረ በዳ ለመግደል ከግብፅ ልታወጣን አይገባህም ነበር”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ክፉ ነገርን ተናግረናል”
“እኛ”እና “ከእኛ”የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ሙሴን ሣይሆን ሕዝቡን ነው፡፡(“እኛ”የሚለውንና አካታች ሆነውንና ያልሆነውን የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እውነተኛ የሆነ እባብን መሥራት የማይችል በመሆኑ የእባብ ናሙና እንዲሰራ ነበር የተፈለገው፡፡ይሄ ተግባራዊ መሆን ያለበት መረጃ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የእባብ ምሳሌን ሥራ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እባብ የሚነድፈው ሰው በሙሉ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ከነሐስ የሰራ እባብ”
እዚህ ላይ “እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በእባብ የተነደፈውን “ማንኛውንም ሰው”ነው፡፡
እዚህ ላይ “ፊት ለፊት”የሚለው ቃል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን “ከእነርሱ ማዶ”ወይም “ከእነርሱ አጠገብ”ማለት ነው፡፡“ከሞአብ በመቀጠል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት እነዚህ ሁለት ሕዝቦች እንደ ድንበር በሚያገለግላቸው በወንዙ አጠገብ ባሉ ክፍሎች ላይ ይኖሩ ነበር ማለት ነው፡፡አሞራውን በወንዙ ደቡብ ክፍል ሲኖሩ አሞራውያን ደግሞ በወንዙ የሰሜኑ ክፍል ነበር የሚኖሩት፡፡
እነዚህ ሁለቱም የቦታ ሥሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“ወደ አርኖን ከተማ የሚያመራውና በሞአብ ድንበር ላይ ተንጣሎ የሚገኘው ሸለቆ“
እነዚህ እንደ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ሊገለፁ ይችላሉ፡፡“ወደ ብኤር፤በዚያ ጉድጓድ ነበረ”
ይሄ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ጥቅስ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ይኸውም እግዚአብሔር ሙሴን “ሕዝቡን ወደ እርሱ እንዲሰበስብ አድርጎ ውኃን ለመሥጠት የተናገረበት ነው”(ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ አባባሎች የሚለውን ይመልከቱ)
“ምንጭ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በጉድጓድ ውስጥ ያለውን ውኃ ነው፡፡እሥራኤላውያን የሚያዳምጣቸው ሰው ይመስል ለውኃው የሚናገሩ ሲሆን ጉድጓዱን እንዲሞላላቸው ይጠይቁታል፡፡“አንተ ውኃ ጉድጓዱን ሙላ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውንና ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ውኃውን በመቆፈር ረገድ መሪዎች ያላቸውን ሚና አፅንኦት በመሥጠት ይናገራል፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
በትረመንግሥትየያዝየነበረውሥልጣንበነበራቸውሰዎችሲሆንበትርደግሞይያዝየነበረውበሁሉምሰውነበር፡፡እነዚህሁለቱለቁፋሮአገልግሎትየሚውሉመሣሪያዎችአይደሉም፡፡እነዚህሁለትቁሣቁሶች የሚያሣዩት በአካባቢያቸውየሚገኙትን ነገሮች ለመጠቀም ኩራት የሚባል ነገር የሌለባቸው ስለመሆኑ አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡“በትረ መንግሥታቸውንና በትራቸውን እንኳን ሳይቀር ይጠቀማሉ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ሥሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የተራራ ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ይሄ አነጋገር ተራራው ከፍ ያለ እንደሆነ ለመግለፅ ሲሆን ተራራው ከሥሩ የሚገኘውን ምድረ በዳ እንደሚመለከት ሕይወት እንዳለው ሰው አድርጎ ያቀርበዋል፡፡“ከምድረ በዳው ይልቅ ከፍ ያለ ነው”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንና ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እሥራኤል”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እሥራኤልን ሕዝብና በተለይም መሪዎቿን ነው፡፡“ከዚያ በኋላ እሥራኤላውያን”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“በየትኛውም እርሻና የወይን ቦታችሁ አንገባም”
ይሄ ደማስቆን በስተ ሰሜንንና የአካብን ባህረ ሠላጤ በደቡብ በኩል የሚያስተሳስር አውራ ጎዳና ነው፡፡ይሄንን በዘኁልቁ 20፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“በእነርሱ ድንበር በኩል ለማለፍ” እዚህ ላይ “እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሞራውያንን ነው፡፡
ይሄ የቦታ ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እርሱም”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራሱንና ሠራዊቱን የሚወክለው ንጉሥ ሴዎን ነው፡፡“ከእሥራኤላውያን ጋር ተዋጉ”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እሥራኤል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡“እሥራኤላውን ጥቃት አደረሱ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“ስለታም በሆነው የሠይፉ ክፍል” “የሠይፍ ሥለት”የሚለው ቃል የሚያያዘው ከሞትና ፍፁም ከሆነ ጥፋት ጋር ነው፡፡“ሙሉ በሙሉ ድል ነሷቸው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“የአሞራውያንን ምድር ድል አደረጉ” እዚህ ላይ “የእነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሞራውያንን ነው፡፡
“አሞናውያን..አሞራውያን”ወይም “አሞን ሕዝብ ወይም የአሞር ሕዝብ” እነዚህ ስሞች ተመሳሳይ ቢሆኑም የሚያመለክቱት ግን ሁለት የተለያዩ ሕዝቦችን ነው፡፡
“ጠንካራ የሆነ መከላከያ ነበረው” እሥራአላውያን አሞናውያንን አላጠቁም፡፡
እዚህ ላይ“ሁሉ”የሚለው ቃል አካታች ሲሆን የሐሴቦን ከተማ በቅርብ ካሉት መንደሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ይገልፃል፡፡“ሐሴቦንና የሚቆጣጠራቸው በቅርብ የሚገኙ ከተሞች”
እዚህ ላይ“የእርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሞአብን ንጉሥ ነው፡፡
እነዚሀ የሚያመለክቱትለአንድ ከተማ የተሰጡ ሁለት ስሞችን ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንድ ሰው የሴዎንን ከተማ ይገንባና ይመሥርት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሣሣይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ከተማዋ ሙሉ በመሉ የምትገነባ ስለመሆኗ አስረግጦ ለመናገር ነው፡“ሙሉ በሙሉ ዳግም ይገነባል”(ሁለት ተመሳሳይ የሆነ ገፅታ ያላቸው የሚለውን ይመልክቱ)
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሣሣይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆንውድመቱ ከሐሴቦን እንደሚጀምር አስረግጦ ይናገራል፡፡እሣቱ የሚያመለክተው አጥፊ የሆነ ሠራዊትን ነው፡፡“ንጉሥ ሴዎን ከሐሴቦን ከተማ ጠንካራ የሆነ ጦርን እየመራ መጣ” (ተመሳሳይነት የሚለውንናምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የሴዎን ሠራዊት የዔርን ከተማ እንደሚበላ አውሬ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“በሞአብ ምድር ያለውን የኤርን ከተማ አጠፋ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚያመለክቱት አንድ ዓይነት ሕዝብን ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ኮሞስ ሞአባውያን ያመለኩት የነበረ ጣዖት ነው፡፡“ኮሞስን የሚያመልክ ሕዝብ”
“እርሱ”እና “የራሱ”የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ኮሞስን ነው፡፡
እዚህ ላይ “እኛ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ዲቦን ድል የነሱትን እሥራኤላውያንን ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሐሴቦንን ደምስሰናታል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁሉ በሴዎን መንግሥት ውስጥ የነበሩ ቦታዎች ናቸው፡፡ይሄ የሚያሳየው እሥራኤላውያን የሴዎንን አገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ አጥፍተውታል ማለት ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ሆን ብሎ አጋኖ መናገር የሚለውን ይመልከቱ)
“አሳደዷቸው”
“አጠቋቸው”
እሥራኤላውያን ሴዎንን ፈፅመው አጥፍተዋት ነበር፡፡“የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን እንዳጠፋህ እንዲሁ አጥፋው”
“ስለዚህ የእሥራኤል ሠራዊት ዓግን ገደለው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእርሱ የሆኑት ሰዎች ሁሉ ሞቱ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የእርሱን ምድር በቁጥጥራቸው ሥር አደረጉት”
1 የእስራአል ህዝብ ከከተማዋ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሌላ ዳርቻ ኢያሪኮ አጠገብ ወደሚገኘው የሞአብ ሜዳ ደርሰው እስኪሰፍሩ ደረስ ተጓዙ፡፡ 2 የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞራዊያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ፡፡ 3 ሞአብ የእስራኤልን ህዝብ በጣም ፈርቶ ነበር ምክንያቱም ብዙ ነበሩ፣ እናም ሞአብ በእስራኤል ህዝብ ተሸብሮ ነበር፡፡ 4 የሞብ ንጉስ ለምድያም ሽማግሌዎች፣ “ይህ ብዙ ህዝብ፣ በሬ በሜዳ ላይ ያለን ሳር በልቶ እንደሚጨርስ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ በልቶ ይጨርሳል፡፡” አለ፡፡ በዚያን ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉስ ነበር፡፡ 5 እርሱም በአገሩና በወገኖቹ መሀል በኤፍራጦስ ወንዝ አጠገብ በፋቱራ ወደተቀመጠው የቢያር ልጅ በልዓም መልዕክተኞችን ላከ፡፡ አስጠርቶትም እንዲህ አለው፣ “እነሆ፣ ከግብጽ አንድ ህዝብ ወደዚህ መጥቷል፡፡ የምድርን ፊት ሸፍነዋል፣ ደግሞም እዚሁ አጠገቤ ናቸው፡፡ 6 ስለዚህ አሁን መጥተህ ይህን ህዝብ ርገምልኝ፣ ምክንያቱም ከእኔ አቅም በላይ ናቸው፡፡ ምናልባት ከረገምክልኝ በኋላ እነርሱን ለማጥቃትና ከምድሪቱ ለማባረር እችል ይሆናል፡፡ የባረከው ሁሉ እንደሚባረክ አውቃለሁ፣ የረገምከው ሁሉ እንደሚረገም አውቃለሁ፡፡” 7 ስለዚህ የሞአብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎች የምዋርቱን ዋጋ ይዘው ሄዱ፡፡ ወደ በለዓም መጥተው የባላቅን ቃል ነገሩት፡፡ 8 በለዓምም እንዲህ አላቸው፣ “ዛሬ ምሽት እዚህ እደሩ፡፡ ያህዌ የሚለኝን አሳውቃችኋለሁ፡፡” ስለዚህም የሞብ መሪዎች ያን ምሽት ከበለዓም ዘንድ ተቀመጡ፡፡ 9 እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፣ “ወደ አንተ የመጡት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው” 10 በለዓም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “የሞአብ ንጉስ የሴፎር ልጅ ባላቅ፣ እነርሱን ወደ እኔ ልኳቸዋል፡፡ እንዲህም አለ፣ 11 ‘እነሆ፣ ከግብጽ የመጡ ሰዎች የምድሬን ገጽ ሸፍነዋል፡፡ አሁን መጥተህ እነርሱን ርገምልኝ፡፡ ይህ ከሆነ ምናልባት እነርሱን መዋጋትና ማባረር እችል ይሆናል፡፡” 12 እግዚአብሔር ለበለዓም እንዲህ መለሰለት፣ “ከእነዚህ ሰዎች ጋር መሄድ የለብህም፡፡ የእስራአልን ህዝብ መርገም የለብህም ምክንያቱም እነርሱ የተባረኩ ናቸው፡፡” 13 በለዓም በጠዋት ተነስቶ ለባላቅ መሪዎች እንዲህ አላቸው፣ “ወደ ምድራችሁ ተመልሳችሁ ሂዱ ምክንያቱም ያህዌ ከእናንተ ጋር እሄድ ዘንድ አልፈቀደልኝም፡፡ 14 ስለዚህም የሞብ መሪዎች ተመልሰው ወደ ባላቅ ሂዱ፡፡ እንደህም አሉት፣ “በለዓም ከእኛ ጋር ለመምጣት አልፈቀደም፡፡” 15 ባላቅ እንደገና ከመጀመሪያዎቹ መልዕክተኞች የከበሩ ብዙ መሪዎችን ላከ፡፡ 16 እነርሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፣ “የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ብሏል፣ ‘እባክህ ወደ እኔ ለመምጣት አንዳች ነገር አያግድህ፣ 17 ምክንያቱም እጅግ ከፍ ያለ ክፍያ እከፍልሃለሁ፣ ታላቅ ክብርም እሰጥሃለሁ፣ ደግሞም እንዳደርገው የምትነግረኝን ሁሉ አደርጋሁ፡፡ ስለዚህ እባክህ መጥተህ ይህን ህዝብ ርገምልኝ” 18 በለዓለም ለባላቅ ሰዎች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “ባላቅ ብርና ወርቅ የሞላበትን ቤተ መንግስቱን ቢሰጠኝ እንኳን ከአምላኬ፣ ከያህዌ ቃል አልፌ መሄድ አልችልም፣ ደግሞም እርሱ ከነገረኝ አሳንሼ ወይም ጨምሬ አላደርግም፡፡ 19 ስለዚህ አሁን፣ እባካችሁ ያህዌ የሚለኝን ተጨማሪ ነገር አውቅ ዘንድ ዛሬ ምሽትም ደግሞ በዚህ እደሩ፡፡” 20 እግዚአብሔር በምሽት ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፣ “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ እስከ መጡ ድረስ ተነስተህ ከእነርሱ ጋር ሂድ፡፡ ነገር ግን እንድታደርገው የምነግርህን ብቻ አድርግ፡፡” 21 በለዓም በጠዋት ተነስቶ አህያውን ጫንና ከሞአብ መሪዎች ጋር ሄደ፡፡ 22 ነገር ግን በመሄዱ፣ የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደ፡፡ የያህዌ መልአክ፣ በአህያው ላይ ተቀምጦ የሚሄደውን በለዓምን ሊቃወመው በመንገድ ላይ ቆመ፡፡ የበለዓም ሁለቱ አገልጋዮቹም አብረውት ነበሩ፡፡ 23 አህያዋ የያህዌን መልአክ የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በመንገድ ላይ ቆሞ አየችው፡፡ አህያዋ ከመንገድ ዘወር ብላ ወደ ሜዳው ሄደች፡፡ በለዓለም አህያይቱን ወደ መንገድ እንድትለስ መታት፡፡ 24 የያህዌ መልአክ በመንገዱ ጠባብ መተላፊያ ላይ በወይን እርሻው መሀል፣ በስተቀኙና በስተግራው ግድግዳ ባለበት ስፍራ ቆመ፡፡ 25 አህያይቶ የያህዌን መልአክ አየች፡፡ ወደ ግድግዳው ተጠግታ የበለዓምን እግር አጣበቀችው፡፡ በለዓም እንደገና አህያይቱን መታት፡፡ 26 የያህዌ መልአክ እንደ ገና ራቅ ብሎ ሄዶ ወደ የትኛውም አቅጣጫ መዞሪያ በሌለበት ሌላ ጠባብ መተላፊያ ስፍራ ቆመ፡፡ 27 አህያይቱ የያህዌን መልአክ አይታ ከበለዓም በታች ተኛች፡፡ የበለዓም ቁጣ ነደደ፣ በበትሩም አህያይቱን መታት፡፡ 28 ያህዌ የአህያይቱን አፍ ስለከፈተ መናገር ቻለች፡፡ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “እነዚህን ሶስት ጊዜያት እንድትመታኝ የሚያደርግ ምን ነገር አደረግሁብህ” 29 በለዓም አህያይቱን፣ “በእኔ ላይ የማይረባ ድርጊት ስለፈጸምሽ ነው፡፡ በእጄ ላይ ሰይፍ ቢኖር እወድ ነበር፡፡ በእጄ ላይ ሰይፍ ቢኖር ኖሮ፣ ይህን ጊዜ ገድዬሽ ነበር” አላት፡፡ 30 አህያይቱ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ስትቀመጥብኝ የኖርክብኝ አህያህ አይደለሁምን? ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ነገር በአንተ ላይ የማድረግ ልማድ ነበረኝን?” በለዓም “እይ” አለ፡፡ 31 ከዚያ ያህዌ የበለዓምን ዐይኖች ከፈተ፣ እናም የያህዌ መልአክ በእጁ ሰይፉን ይዞ በመንገዱ ላይ ቆሞ አየ፡፡ በለዓም ዝቅ ብሎ በግምባሩ ተደፋ፡፡ 32 የእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “አህያህን ለምን በእዚህ ሶስት ጊዜያት መታሀት የምቃወምህ ሆኜ መጥቻለሁ ምክንያቱም ድርጊቶችህ በፊቴ መጥፎዎች ነበሩ፡፡ 33 አህያይቱ አይታኝ በእነዚህ ሶስት ጊዜያት ከእኔ ዞር አለች፡፡ እርሷ ዞር ባትልልኝ ኖሮ፣ በእርግጥ አንተን እገድልህና የእርሷን ነፍስ እተው ነበር፡፡” 34 በለዓም ለያህዌ መልአክ እንዲህ አለ፣ “እኔ በድያለሁ፡፡ እኔን ተቃውመህ በፊቴ ቆመህ እንደነበር አላወቅሁም፡፡ አሁን እንግዲህ፣ ይህ ጉዞ አንተን ደስ ካላሰኘ፣ ወደመጣሁበት እመለሳለሁ፡፡” 35 የያህዌ መልአክ ግን በለዓምን እንዲህ አለው፣ “ከሰዎቹ ጋር ጉዞህን ቀጥል፡፡ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ መናገር አለብህ፡፡” ስለዚህም በለዓም ከባላቅ መሪዎች ጋር ሄደ፡፡ 36 ባላቅ የበለዓምን መምጣት ሲሰማ፣ ሞአብ ውስጥ ወዳለችው በድንበር ላይ ወደምትገኘው አርኖን ከተማ ሊቀበለው ወጣ፡፡ 37 ባላቅ በለዓምን እዲህ አለው፣ “እንዲጠሩህ ሰዎችን ወደ አንተ አልላኩም ነበርን? ለምን ወደ እኔ አልመጣህም? እኔ ላከብርህ አልችልምን?” 38 ከዚያም በለዓም ለባላቅ መለሰለት፣ “በእርግጥ ወደ አንተ መጥቻለሁ፡፤ አሁን አንዳች ነገር ለመናገር እኔ አንዳች ሀይል አለኝን? መናገር የምችለው እግዚአብሔር በአፌ ላይ ያስቀመጠውን ቃል ብቻ ነው፡፡” 39 በለዓም ከባላቅ ጋር ሄደ፣ እነርሱም ወደ ቂርያት ሐጾት ደረሱ፡፡ 40 ከዚያ ባላቅ በሬዎችንና በጎችን ሰዋ፣ ለበለዓምና ከእርሱ ጋር ለነበሩ መሪዎችም ሰጣቸው፡፡ 41 ማለዳ፣ ባላቅ በለዓምን ወደ ካሞት በኣል ይዞት ሄደ፡፡ በለዓም ከዚያ ሆኖ ማየት የሚችለው በሰፈሮቻቸው ካሉት እስኤላዊያን ጥቂቶቹን ብቻ ነበር፡፡
እሥራኤላውያን የሰፈሩት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ በኩል ነበር፡፡ኢያሪኮ ደግሞ ከወንዙ በስተ ምዕራብ በኩል ነበር፡፡
ባላቅ የሞአብ ንጉሥ ነበር፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ሴፎር የባላቅ አባት ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ዓይነት ትርጉም ያላቸው ሲሆን ሞአብ ምን ያህል እንደፈራ አፅንዖት የሚሰጡ ናቸው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ሞአብ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሞአብን ሕዝብ ነው፡፡“ሞአባውያን በሙሉ ከፍተኛ የሆነ ፍርሃት ይዟቸው ነበረ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“ምከኒያቱም በቁጥር ብዙዎች ነበሩ”
ሞአባውያንና ምድያማውያን የተለያዩ ሕዝቦች ቢሆኑም በዚያን ወቅት ምድያማውያን ይኖሩ የነበሩት በሞአብ ምድር ውስጥ ነበር፡፡
እሥራኤላውያን ጠላቶቻቸውን የሚያጠፉበትን መንገድ በመስክ ላይ ሣርን እንደሚበሉ በሬዎች ተደርገው ተገልፀዋል፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ዋናውን ታሪክ ስለ ባላቅ የኋላ ታሪክ መረጃ ወደ መስጠት ያዞረዋል፡፡(የጀርባ ታሪከ የሚለውን ይመልከቱ)
“ባላቅ መልዕክተኞችን ላከ”
ይሄ የበለዓም አባት ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የአንድ ከተማ ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“የበለዓም አገርና ሕዝብ”
“ባላቅ በለዓምን ጠራው”ባላቅ በቀጥታ ከበለዓም ጋር አልተነጋገረም፡፡ሆኖም ሃሣቡን ያስተላለፈው በላካቸው መልዕክተኞች አማካይነት ነው፡፡
ይሄ ብዛታቸውን ለመገለፅ ተጋንኖ የቀረበ አነጋገር ነው፡፡“እጅግ ብዙዎች ናቸው”(የተጋነነ ንፅፅር እና አጠቃላይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የምድርን ገፅ ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ላባርራቸው”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎችን የመባረክም ሆነ የመርገም ኃይል እንዳለህ እኔ አውቃለሁ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የምዋርቱን ዋጋ”የሚለው አሕፅሮተ ሥምበድርጊት መልከ ሊገለፅ ይችለላል፡፡“እሥራኤልን እንዲረግም ለበለዓም የሚከፈል ገንዘብ”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
“ወደ በለዓምም ሄዱ”የሚለውን አባባል ልትመርጡ ትችሉ ይሆናል፡፡(መሄድና መምጣት የሚለውን ይመልከቱ)
“ከባላቅ የተላከውን መልዕከት ነገሩት”
ይሄ የሰው ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የበለዓም መልዕክት ልክ አንድን ዕቃ ተሸክሞ እንደሚመጣ ዓይነት ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡“እነግራችኋለሁ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔር ለበለዓም ተገለጠለት
እግዚአብሔር ጥያቄውን ያነሳው በአዲስ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይት ለመጀመር ነው፡፡ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ በመግለጫ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ወደ አንተ ስለመጡት ሰዎች ማንነት ንገረኝ” (አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህየሰው ሥሞችናቸው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
በለዓም ባላቅ ለእርሱ የላከውን መልዕክት መልሶ ይናገረዋል፡፡እነዚህን ሐረጎች በዘኁልቁ 22፡5-6 ያለውን ክፍል እንዴት እንደተረጎማችኋቸው ተመልከቱ፡፡
“አባርራቸው”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የባረክኋቸው በመሆኑ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሰው ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ወደ በለዓምም ሄዱ”የሚለውን ልትመርጡ ትችሉ ይሆናል፡፡(መሄድና መምጣት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሰው ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ ነጠላ ሥም እሥራኤላውያንንየሚያየውልክ እንደ አንድ የህዝብ ስብስብ ነው፡፡
ይሄ ሰው ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
በለዓም ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ነገርን እየገለፀ ነው፡፡እግዚአብሔርን እንዳይታዘዝ ሊያደርገው የሚችል ነገር ሊኖር እንደማይችል አስረግጦ እየተናገረ ነው፡፡(ተግባራዊ ሊሆኑ የማይችሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያሣየው በምንም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን በለዓም እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ወደ ኋላ የማይል መሆኑን ነው፡፡
ኮርቻ እንስሳት ጀርባ ላይ ለግልቢያ ሲባል የሚደረግ መቀመጫ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቁጣ የመጨመሩ ነገር ልክ እሣት መንደድ እንደሚጀምር ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በኃይል ተቆጣ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እንደ በለዓም ጠላት” ወይም “በለዓምን ለማስቆም”
ሠይፍ ጥቅም ላይ ሊውል ከሰገባው ወጥቷል፡፡“ጥቃት ለማድረስ ሠይፉን ዝግጁ አደረገ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
አህያይቱ ይህንን ያደረገችው ከእግዚአብሔር መልአክ ለመሸሽ ብላ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ እንስሳት“የእርሷ”ወይም “እርሷ”በመባል ይጠቀሳሉ፡፡“ሊመልሰው”
ይሄ ሙከራ በመንገድ ላይ ቆሞ ከነበረው መልአክ ለማምለጥ የተደረገ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ እንስሳት“የእርሷ”ወይም “እርሷ”በመባል ይጠቀሳሉ፡፡“ሄደ”
“የበለዓምን እግር ከቅጥሩ ጋር አጋጨችው”ወይም “የበለዓምን እግር ከቅጥሩ ጋር ስታጣብቀው እግሩ ተጎዳ”
የበለዓም ቁጣ የመጨመሩ ነገር ልክ እሣት መንደድ እንደሚጀምር ዓይነት ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡በዘኁልቁ 22፡22 ላይ ያለውን ተመሳሳይ ሐረግ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“በለዓም በኃይል ተናደደ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የመናገር ችሎታ አፍ ከመክፈት ጋር ተነፃፅሯል፡፡“ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ልክ እንደ ሰው እንደሚናገር ለአህያይቱ የመናገር ችሎታን ሰጣት”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“አህያይቱ በለዓምን ተናገረችው”
ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የተጠየቀበት ምክኒያት በለዓም በአህያዋ ላይ የሰራው ጥፋት ተገቢነት የሌለው መሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ከብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ ነኝ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የተጠየቀበት ምክኒያት በለዓም በአህያዋ ላይ የሰራው ጥፋት ተገቢነት የሌለው መሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለአንተ እንደዚህ ዓይነት ባህርይ የማሳየት ልማድ አልነበረኝም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
የአንድ ሰው“ዓይን መክፈት” “ከማየት ችሎታ”ጋር ተነፃፅሮ ቀርቧል፡፡“ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ለበለዓም የማየት ችሎታን ሰጠው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ሠይፍ ጥቅም ላይ ሊውል ከሰገባው ወጥቷል፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡23 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ለማጥቃት ከተዘጋጀ ሠይፉ ጋር”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያሣየው በዓለም ራሱን በመልአኩ ፊት ማዋረዱን ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የተነሳበት ምክኒያት በለዓም የሰራው ሥራ ጥፋት መሆኑን ለማሳሰብ ነው፡፡ይሄ በመገለጫ መልክ ሊተረጎም ይችለል፡፡“አህያህን ሦስት ጊዜ መምታት አልነበረብህም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“ጠላትህ እንደሆነ ሰው” ወይም “ተቃዋሚምህ እንደሆነ ሰው”
ይሄ ግምታዊ አባባል የሚያሣየው ሊከሰት ይችል የነበረን ነገርና ከአህያይቱ ድርጊት የተነሣ የበለዓም ሕይወት መትረፉን ነው፡፡(በግምት ላይ የተመሰረቱ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)
“ጉዞዬን እንድቀጥል የማትፈልግ ከሆነ”
“ባላቅ ከላካቸው አለቆች ጋር” “ባላቅን” በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ የወንዝ ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 21፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የተጠየቀው በለዓም በመዘግየቱ ምክኒያት ለመገሰፅ ነበር፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊረጎም ይችላል፡፡“በእርግጥ ሰዎች እንዲጠሩህ ልኬብህ ነበር” (ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የተጠየቀው በለዓም በመዘግየቱ ምክኒያት ለመገሰፅ ነበር፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊረጎም ይችላል፡፡“ወደ እኔ መምጣት ነበረብህ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የተጠየቀው በለዓም በመዘግየቱ ምክኒያት ለመገሰፅ ነበር፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊረጎም ይችላል፡፡“በእርግጥም ወደ እኔ ዘንድ በመምጣትህ ገንዘብ ልከፍልህ እንደምችል አንተ ታውቃለህ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም ይሄንን ጥያቄ የሚጠይቅበት አቢይ ምክኒያት ባላቅ እንዲያደርግ የሚፈልገውን ነገርሁሉ ለማድረግ የማይችል መሆኑን ለመናገር ነው፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊረጎም ይችላል፡፡“ነገር ግን የምፈልገውን ነገር ሁሉ የመናገር ሥልጣን የለኝም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ መልዕክት የሚነገረው ልክ አንድን ነገር እግዚአብሔር በአፉ ውስጥ እንደሚያስቀምጥ ዓይነት ተደርጎ ነው፡፡“እግዚአብሔር እንድናገረው የሚፈልገው መልዕክት”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የከተማ ሥም ነው፡፡
“ከመሥዋዕቱ ጥቂት ሥጋ”
ይህንን ሃሣብ ሊገልፁ የሚችሉት 1/ይሄ በዘኁልቁ 29፡11 ላይ ካለው የማሞዝሥፍራን ያመለክታል፡፡ማሞዝ የሚለው ቃል ከፍታ የሆነ ሥፍራ ማለት ነው፡፡ወይም 2/ሰዎች ለበአል መሥዋዕት የሚያቀርቡበት ሌላ ሥፍራ ነው፡፡
1 በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “በዚህ ሰባት መሰዊያዎችንና ሰባት በሬዎችን እንዲሁም ሰባት አውራ በጎችን አዘጋጅልኝ፡፡” 2 ስለዚህም ባላቅ በለዓም እንደጠየቀው አደረገ፡፡ ከዚያም ባላቅና በለዓም በእያንዳንዱ መሰዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቀረቡ፡፡ 3 ከዚያ በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “አንተ በሚቃጠል መስዋዕትህ አጠገብ ቁም እኔ እሄዳለሁ፡፡ ምናልባት ያህዌ ሊገናኘኝ ይመጣ ይሆናል፡፡ እርሱ የሚያሳየኝን ሁሉ እነግርሀለሁ፡፡” ስለዚህም በለዓም ዛፎች ወደ ሌሉበት የተራራ ጫፍ ሄደ፡፡ 4 እግዚአብሔር እርሱን ተገናኘው፣ በለዓምም ለእግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ “እኔ ሰባት መሰዊያዎችን አበጅቻለሁ፣ ደግሞም በእያንዳንዱ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ አቅርቤያለሁ፡፡” 5 ያህዌ በበለዓም አፍ ላይ መልዕክት አኑሮ እንዲህ አለ፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና እንዲህ በለው፡፡” 6 ስለዚህ በለዓም በሚቃጠል መስዋዕቱ አጠገብ ወደቆመው ወደ ባላቅ ከእነርሱ ጋር ወደ ነበሩት የሞአብ መሪዎች ሁሉ ተመለሰ፡፡ 7 ከዚያ በለዓም ትንቢቱን መናገር ጀመረ እንዲህም አለ፣ “ባላቅ እኔን ከአራም አመጣኝ፣ የሞአብ ንጉስ ከምስራቅ ተራሮች አመጣኝ፡፡ ‘ና፣ ያዕቆብን ዕርገምልኝ’ አለኝ፡፡ ‘ና፣ እስራኤልን ተፈታተንልኝ’ አለኝ፡፡ 8 እግዚአብሔር ያልረገመውን እኔ እንዴት መርገም እችላለሁ? ያህዌ ያልተቃወማቸውን እኔ እንዴት መቃወም እችላለሁ? 9 ከአለቶች በላይ ሆኜ አየዋለሁ፣ ከተራሮች ላይ ሆኜ ወደ እርሱ አያለሁ፡፡ ተመልከት፣ ብቻውን የሚኖር ራሱን እንደ ተራ ህዝብ አድርጎ የማይቆጥር ህዝብ አለ፡፡ 10 የያዕቆብን ትቢያ ማን መቁጠር ይችላል ወይም ከእስራኤል ሩቡን እንኳን ማን ይቆጥራል? የጻድቁነ ሞት እኔ ልሙት፣ ደግሞም የህይወቴ መጨረሻ እንደ እርሱ ይሁን!” 11 ባላቅ በለዓምን እንዲህ አለው፣ “ምን እያደረግክብኝ ነው ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፣ ነገር ግን እነሆ አንተ እነርሱን ባረካቸው፡፡” 12 በለዓም መለሰለት እንዲህም አለ፣ “ያህዌ በአፌ ላይ ያደረገውን ብቻ ለመናገር መጠንቀቅ የለብኝምን?” 13 ስለዚህም ባላቅ እንዲህ አለው፣ “እባክህ ከእኔ ጋር ልታያቸው ወደ ምትችልበት ሌላ ቦታ ና፡፡ ከእነርሱ ሁሉንም ሳይሆን፣ በቅርብ ያሉትን ብቻ ታያለህ፡፡ በዚያ እነርሱን ትረግምልኛለህ፡፡” 14 ስለዚህ በለዓምን ወደ ጾፊም ሜዳ፣ ወደ ፊስጋ ተራራ ጫፍ ይዞት ሄደና ተጨማሪ ሰባት መሰዊያዎችን አበጀ፡፡ በእያንዳንዱ መሰዊያ አንድ በሬና አንድ አውራ ጠቦት ሰዋ፡፡ 15 ከዚያ በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “እኔ በዚያ ያህዌን ለመገናኘት ስሄድ፣ አንተ እዚህ በሚቃጠል መስዋዕትህ አጠገብ ቁም፡፡” 16 ያህዌ በለዓምን ተገናኝቶ በአፉ ምልክት አኖረ፡፡ እንዲህም አለው፣ “ወደ ባላቅ ተመለስና መልዕክቴን ንገረው፡፡” 17 በለዓም ወደ ባላቅ ተመልሶ በሚቃጠል መስዋዕቱ አጠገብ አገኘው፣ የሞአብ መሪዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ ባላቅ እንዲህ ሲል ጠየቅ፣ “ያህዌ ምን ነገረህ?” 18 በለዓም ትንቢቱን መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “ባላቅ፣ ተነስና አድምጥ፡፡ አንተ የሴፎር ልጅ እኔን አድምጠኝ፡፡ 19 እግዚአብሔር ይዋሽ ዘንድ ሰው አይደለም፣ ወይም ሀሳቡን ይቀየር ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፡፡ ላያደርግ አንዳች ነገር ቃል ይገባልን? ላይፈጽመውስ አንዳች ነገር አደርጋለሁ ይላልን? 20 እነሆ፣ ለመባረክ ታዝዣለሁ፡፡ እግዚአብሔር በረከትን ለቋል፣ እኔ ልከለክል አልችልም፡፡ 21 እርሱ በያዕቆብ ላይ አንዳች ችግር ወይም በእስራኤል ላይ ድካም አላየም፡፡ ያህዌ አምላካቸው ከእነርሱ ጋር ነው፣ የንጉሳቸውም እልልታ ከእነርሱ ጋር ነው፡፡ 22 እግዚአብሔር እንደ ጎሽ በሆነ ሀይል ከግብጽ አወጣቸው፡፡ 23 በያዕቆብ ላይ የሚሰራ ምንም አስማት የለም፣ የትኛውም ሟርት እስራኤልን አይጎዳም፡፡ ይልቁንም ስለያዕቆብና ስለ እስራኤል እንዲህ ይባልላቸዋል፣ ‘እግዚአብሔር ያደረገውን እዩ!’ 24 እዩ፣ ህዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሳል፣ እንደ አንበሳ ተነስቶ ያጠቃል፡፡ ያደነውን እስኪበላ የገደለውን ደም እስኪጠጣ አያርፍም፡፡” 25 ከዚያ ባላቅ በለዓምን እንዲህ አለው፣ “እነርሱን ባትረግማቸው እንኳን ጨርሰህ አትባርካቸው፡፡” 26 በልዓም ግን ባላቅን መልሶ እንዲህ አለው፣ “እንድናገር ያህዌ የነገረኝን ሁሉ መናገር እንዳለብኝ አልነገርኩህምን?” 27 ስለዚህም ባላቅ ለበለዓም እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “አሁን ና፣ እኔ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፡፡ ምናልባት በዚያ እነርሱን እንድትረግምልኝ እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል፡፡” 28 ስለዚህም ባላቅ በለዓምን ምድረበዳውን ቁልቁል ወደሚያይበት ወደ ፌጎር ተራራ ጫፍ ወሰደው፡፡ 29 በለዓም ባላቅን እንዲህ አለው፣ “በዚህ ስፍራ ሰባት መሰዊያዎችን አብጅና ሰባት በሬዎች እንዲሁም ሰባት አውራ በጎች አዘጋጅ፡፡” 30 ስለዚህ ባላቅ ባለዓም እንደነገረው አደረገ፤ በእያንዳንዱ መሰዊያ ላይ አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ሰዋ፡፡
ይሄ የሞአብ ንጉሥ ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ሰባትም ወይፈን ሰባትም አውራ በግ ለመሥዋዕት እረድልኝ”
“በዚህ በመሥዋትህ ዘንድ ቆይ እኔም ራቅ ወዳለ ሥፍራ እሄዳለሁ”
እነዚህን አንስሳት እንደሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ስለማቅረቡ ቀደም ብሎ ተገልጿል፡፡“አንድ ወይፈንና አንድ በግ አዘጋጅቼ በመሥዋዕት መልክ አቃጥያቸዋለሁ” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር በለዓም እንዲናገር የሚሰጠውን መልዕክት ልክ በአፉ እንደሚያስቀምጠው ዓይነት ተደርጎ ተነግሯል፡፡“እግዚአብሔር ለባላቅ መነገር የሚገባውን ነገር እንዲነግረው ለበለዓም ነገረው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮችተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡በለዓም የእሥራኤልን ሕዝብ እንዲረግም ጫና የሚያደርጉ ናቸው፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ በለዓም እግዚአብሔርን አልታዘዝም ለማለት ፈቃደኛ አለመሆኑን ያሣያል፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡“ነገር ግን እግዚአብሔር ያልረገመውን ልረግም አልችልም፡፡እግዚአብሔር ያልተጣላውን ልጣላ አልችልም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሐረጎችተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡በለዓምከኮረብታ አናት ላይ ሆኖ እሥራኤልን ተመለከተ፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እሥራኤልን ነው፡፡
“የተወሰነ የሕዝብ ክፍል አለ”
ይሄ አሉታዊ አነጋገር ጥቅም ላይ የዋለው ተቃራኒው ነገር እውነት መሆኑን አስረግጦ ለመናገር ነው፡፡“ራሣቸውን የተለየ ሕዝብ አድርገው ይቆጥራሉ”(በተዘዋዋሪ መንገድ ሃሣብን መግለፅ የሚለውን ይመልከቱ)
“የያዕቆብ ትቢያ”ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን የእሥራኤል ሕዝብ ቁጥር የትቢያን ያህል ብዛት እንዳለው አድርጎ ይናገራል፡፡ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ በዓረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡“ለቁጥር የሚያዳግቱ እሥራኤላውያን አሉ፡፡ብዙ ከመሆናቸው የተነሣ አንድ አራተኛውን እንኳን መቁጠር የሚችል ሰው አይኖርም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውንና ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሰላማዊ የሆነ ሞት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ይሄ በዚህ መልክም ሊነገርም ይችላል፡፡“ሠላም የሞላበት የፃድቅ ሰው ሞት”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የእሥራኤልን ሕዝብ እንደ አንድ ሰው አድርጎ የሚያመለክት ገላጭ ነው፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሞአብ ንጉሥ ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ባላቅ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው በለዓምን ለመውቀስ ነበር፡፡ይሄንን ጥያቄ በዓረፍተ ነገር መልክም መተርጎም ይቻላል፡፡“ይህንን በእኔ ላይ አድረገሃል ብዬ አላምንም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የሚመጣውን አስደንጋጭ ድርጊት ነው፡፡
በለዓም ይሄንን አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የሚጠይቀው ለድርጊቶቹ ምክኒያት ለመሥጠት ነው፡፡ይሄ በመግለጫ መልክ ሊተረጎም ይችላል፡“እግዚአብሔር የተናገረኝን ነገር ብቻ ለመናገር መጠንቀቅ አለብኝ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
መልዕክቱ እገዚአብሔር በአፍ ውሰጥ እንደሚያስቀምጠው ዓይነት ነገር ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡ይህንንተመሳሳይ ሐረግ በዘኁልቁ 22፡38 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“እግዚአብሔር የሚናገረኝን ብቻ ለመናገር”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“እዚያ ሆነህ እሥራኤላውያንን ትረግምልኛለህ”
“ፆፊም”የሚለው ቃል “አጥብቆ በዓይን መከታተል”ወይም “መሰለል” የሚገልፅ የግርጌ ማሰታወሻ ላይ ተርጓሚዎቹ ማስቀመጥ ሊኖርባቸው ይችል ይሆናል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የተራራ ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 21፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ መልዕክት ልክ እግዚአብሔር በአፉ ውስጥ እንዳደረገለት ዓይነት ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡ተመሰሳዩን ሐረግ በዘኁልቁ 22፡38 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“መናገር ያለበትን ነገር ነገረው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ከዚያ እግዚአብሔር ተናገረ”
እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን የተደጋገሙበት ምክኒያት ባላቅ ለጉዳዩ ትኩረት መሥጠት እንደሚኖርበት አፅንዖት ለመሥጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ባላቅን ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ተመሳሳይ ሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር የሚፈፅም ስለመሆኑ አፅንዖት ይሰጣሉ፡፡እነዚህ ሁለት አስፈላጊ የሆኑ ጥያቄዎቸ በዓረፍተ ነገር መልከ ሊገለፁ ይችላሉ፡፡“ቃል የገባውን ነገር ተግባራዊ ሳያደርግ የቀረበት ጊዜ የለም፡፡ምን ጊዜም ቢሆን አደርገዋለሁ ያለውን ነገር በትክክል ተግባራዊ ያደርገዋል”(ተመሳሳይነት የሚለውንና ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር እሥራኤላውያንን እንድባርክ አዝዞኛል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት1/እግዚአብሔር ለእሥራኤል የሰጠው መልካም የሆኑ ነገሮችን ብቻ ነው፡፡ወይም2/በእነርሱ ላይ ፍርድን ያመጣ ዘንድ በእሥራኤል ላይ ምንም ዓይነት ኃጢአት አላየም፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔር ንጉሣቸው በመሆኑ በደስታ እልል ይላሉ”
ይሄ ንፅፅር የእግዚአብሔር ኃያል ጉልበት ከበሬ ጋር የሚነፃፀር መሆኑን ነው የሚያመለክተው፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሣሣይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ማንም ሰው በእሥራኤል ላይ መርገምን ቢደርገ ሊሰራለት አይችልም ለማለት ነው፡፡“እዚህ ላይ ያዕቆብ የሚል ቃል የሚያመለክተው እሥራኤልን ነው” (ተመሳሳይነት የሚለውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ሊናገሩ ይችሉ ይሆናል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለእነርሱ ያደረገላቸው ነገር መልካም መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡“እግዚአብሔር ለእነርሱ ያደረገላቸውን መልካም ነገር ተመልክቱ!”
ይህ ጥቅስ ረዥም የሆነ ምሣሌያዊ አነጋገር ሲሆን እሥራኤል ጠላቷን ድል የማድረጓን ጉዳይ ልክ አንበሣ ያደነውን ነገር እንደሚበላ ዓይነት አድርጎ ያቀርበዋል፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሞአብ ንጉሥ ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
በለዓም ይህንን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ የሚጠይቀው ወደ ባላቅ ከመምጣቱ በፊትም ቢሆን እግዚአብሔርን ላለመታዘዝ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ለባላቅ ማሳሰቢያን ለመሥጠት ነው፡፡ይሄ በዓረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡“ከዚያ በፊት እግዚአብሔር የሚናገረኝን ነገር ብቻ እንደምናገር ነግሬሃለሁ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ምድረ በዳ እሥራኤል ሰፍሮበት የነበረው ሥፍራ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡“እሥራኤል በነበረበት ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
1 በለዓምም ያህዌ እስራኤልን መባረክ እንደፈቀደ ባየ ጊዜ፣ በሌላ ጊዜ እንደሚያደርገው አስማት ለማድረግ አልወጣም፡፡ ይልቁንም፣ ወደ ምድረበዳው ቁልቁል ተመለከተ፡፡ 2 ዐይኖቹን አቅንቶ እስራኤልን በየነገዱ ሰፍሮ አየ፣ የእግዚአብሔር መንፈስም በእርሱ ላይ መጣ፡፡ 3 ይህን ትንቢት ተቀብሎ እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “ዐይኖቹ እጅግ የተከፈቱለት የቢዖር ልጅ በለዓም እዲህ ይላል፡፡ 4 እርሱ የእግዚአብሔርን ቃላት ይናገራል ይሰማልም፡፡ እርሱ ሁሉን ቻይ ከሆነው ዘንድ ዐይኖቹ ተከፍተውለት በፊቱ ከሚሰግድለት ዘንድ የሆነውን ራእይን ይመለከታል፡፡ 5 ያዕቆብ ሆይ ድንኳኖችህ ምንኛ ያማሩ ናቸው፣ እስራኤል ሆይ መኖሪያዎችህ እንዴት ያምራሉ! 6 እንደ ሸለቆዎች ተዘርግተዋል፣ በወንዝ ዳር እንዳሉ መናፈሻ ስፍራዎች፣ በያህዌ እንደተተከሉ ሬቶች፣ በውሃ ዳርቻ እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው፡፡ 7 ማድጋዎቻቸው በውሃ የተትረፈረፉ ናቸው፣ ሰብላቸው ውሃ አይታጣውም፡፡ ንጉሳቸው ከአጋግ ይበልጣል፣ መንግስታቸው የከበረ ነው፡፡ 8 እግዚአብሔር እርሱን ከግብጽ አውጥቶታል፡፡ እንደ ጎሽ ብርታት አለው፡፡ የሚዋጉትን መንግስታት ይፈጃቸዋል፡፡ አጥንቶቻቸውን ይሰባብራል፡፡ በቀስቶቹ ይወጋቸዋል፡፡ 9 እንደ አንበሳ ይሰባብራቸዋል፣ እንደ ሴት አንበሳ ያደቃቸዋል፡፡ ማን ሊቋቋመው ይችላል? የሚባርኩት ሁሉ ይባረኩ፤ የሚረግሙት ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፡፡” 10 የባላቅ ቁጣ በበለዓም ላይ ነደደ፣ እጆቹን አጣፍቶ በለዓምን እንዲህ አለው፣ “እኔ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፣ ነገር ግን አንተ ሶስት ጊዜም ባረካቸው፡፡ 11 ስለዚህ አሁኑኑ ከእኔ ተለይተህ ወደ ቤትህ ሂድልኝ፡፡ እጅግ አድርጌ አከብርሃለሁ ብዬ ነበር፣ ነገር ግን አንዳች ሽልማት እንዳታገኝ ያህዌ ከለከለህ፡፡” 12 ከዚያ በለዓም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “ወደ እኔ ለላካቸው መልዕክተኞች እንዲህ ብያቸው ነበር፣ 13 ‘ባላቅ በብርና ወርቅ የተሞላውን ቤተ መንግስቱን ቢሰጠኝ እንኳን፣ ያህዌ ከተናገረው ውጭ አንዳች መጥፎ ወይም መልካም፣ ወይም አንዳች እኔ ላደርግ የምፈልገውን አልናገርም፡፡ መናገር የምችለው ያህዌ ተናገር ያለንን ብቻ ነው፡፡’ ይህን ለእነርሱ አልተናገርኩምን? 14 ስለዚህ እነሆ አሁን ወደ ህዝቤ እመለሳለሁ፡፡ ነገር ግን አሁን በቅድሚያ ይህ ህዝብ በሚመጡት ቀናት በአንተ ህዝብ ላይ ሊያደርግ ያለውን ላስጠንቅህ፡፡” 15 በለዓም ይህን ትንቢት መናገር ጀመረ፣ “ዐይኖቹ እጅግ የተከፈቱለት የቢዖር ልጅ በልዓም ይህን ናገራል፡፡ 16 ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቃል የሚሰማ ሰው ትንቢት ነው፣ ከልዑል ዘንድ ዕውቀት ከተሰጠው፣ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ራዕይ ከተቀበለው፣ በተከፈተ ዐይን በፊቱ ከሚሰግደው፣ ሰው የተነገረ ትንቢት ነው፡፡ 17 እኔ እርሱን አያለሁ፣ ነገር ግን እርሱ አሁን እዚህ አይደለም፡፡ እኔ እርሱን እመለከታለሁ፣ ነገር ግን እርሱ በቅርብ አይደለም፡፡ ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፣ በትረ መንግስት ከእስራኤል ይነሳል፡፡ እርሱ የሞአብን መሪዎችን ይበታትናል፣ የሴትንም ትውልዶች ያጠፋል፡፡ 18 ከዚያ እስራኤል በሃይል ድል የሚነሳው ኤዶም፤ የእስራኤል ርስት ይሆናል፣ ደግሞም የእስራኤል ጠላት የሆነው ሴይር፣ የእነርሱ ርስት ይሆናል፣ 19 ከያዕቆብ ግዛት ያለው ንጉስ ይወጣል፣ እርሱም ከከተማቸው የተረፉትን ቅሬታዎች ያጠፋል፡፡” 20 ከዚያ በለዓም አማሌቅን ተመልክቶ ትንቢት መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “አማሌቅ ታላቅ ህዝብ ነበር፣ነገር ግን መጨረሻው ጥፋት ይሆናል፡፡” 21 ከዚያ በለዓም ወደ ቄናውያን ተመልክቶ ትንቢቱን ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “የምትኖርበት ስፍራ አስተማማኝ ነው፣ ጎጆችህም በአለቶች መሀል ነው፡፡ 22 ሆኖም ግን እናንተ ቄናውያን አሶር ምርኮ አድርጎ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ፡፡” 23 ከዚያ በለዓም የመጨረሻውን ትንቢቱን መናገር ጀመረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “አወይ! እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ ማን ይተርፋል? 24 መርከቦች ከኪቲም ዳርቻዎች ይመጣሉ፤ አሶርን ያጠቃሉ ዔቦርን ይይዛሉ፣ ነገር ግን እነርሱም ደግሞ መጨረሻቸው መደምሰስ ነው፡፡ 25 ከዚያ በለዓም ተነስቶ ሄደ፡፡ ወደ ቤቱ ተመለሰ፣ ባላቅም ተነስቶ ሄደ፡፡
“ዓይኖቹን አነሳ”የሚለው ቃል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ወደ ላይ መመልከት ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት ትንቢትን መናገር ይችል ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረው ማለት ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ይህንን ትንቢት ሰጠው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ቢዖር የበለዓም አባት ነበር፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያሣየው በሚገባ ማየቱንና መገንዘቡን ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ሆኖ ትንቢት መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እዚህ ላይ በለዓም ራሱን የሚጠራው“እርሱ” እያለ ነው፡፡
ይሄ የትህትና ድርጊት ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
“ዓይኖቹ የተከፈቱለት”የሚለው ቃል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን በለዓም እግዚአብሔር መናገር የፈለገውን ነገር የማወቅ ችሎታ ተሰጥቶታል ለማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡ለበለዓም የእሥራኤል ሰፈር ውብ እንደሆነበት አስረግጠው የሚናገሩ ናቸው፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ሆኖ ትንቢት መናገሩን ይቀጥላል፡፡
በለዓም እሥራኤልን በሚመለከት ሸለቆዎቸን እንኳን መሸፈን እስኪችሉ ድረስ ዘንድ በቁጥር እጅግ ብዙ እንደሆኑ አድርጎ ነው የሚናገረው፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም እሥራኤላውያንን በቂ ውኃ እንደሚጠጡና የተትረፈረፈ ምርትን እንደሚያስገኙ አትክልቶች አድርጎ ያቀርባቸዋል፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
የእሬት አትከልቶች መልካም የሆነ ሽታ ያላቸው በደረቅ የአየር ሁኔታ ውስጥ እንኳን በሚገባ ማደግ የሚችሉ ናቸው፡፡በለዓም እሥራኤላውያን እንደ እሬት አትክልቶች እንደሚያድጉና መልካም እንደሚሆኑይናገራል፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር የተከለው እሬት”(ያልታወቁ ነገሮችን መተርጎም፤ተነፃፃሪ የሚለውንና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ዝግባ በእሥራኤል ውስጥ ከነበሩት ዛፎች ትልቁ ነው፡፡በለዓም እሥራኤላውያን ልክ ውኃ እንደሚጠጣ ዝግባ ዛፍ ግዙፍ ሆነው እንዳደጉ ዓይነት አድርጎ ይናገራል፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ሆኖ ትንቢት መናገሩን ይቀጥላል፡፡
ብዛት ያለው ውኃ በምድር ላይ እንዳሉና እግዚአብሔር እንደባረካቸው ሰብሎች ተቆጥሯል፡፡“እግዚአብሔር ለሰበሎቻቸው ይሆን ዘንድ ብዙ ውኃ በመሥጠት ይባርካቸዋል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
በሚገባ ውኃ የጠጣ ዘር የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተትረፈረፈ ሰብል ይኖራቸው ዘንድ የእግዚአብሔር በረከት በእነርሱ ላይ የሚመጣ መሆኑን ነው፡፡“ጤናማ የሆኑ ሰብሎችን ያበቅሉ ዘንድ ለሚዘሩት ዘር ከበቂ በላይ የሆነ ውኃን ያገኛሉ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ከሌሎች አገራት ይልቅ እጅግ እንደሚባርካቸው አፅንዖት የሚሰጥ ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“ከፍ ከፍ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ታላቅ የሆነ ክብርና ሥልጣንን ነው፡፡ይሄ የሚያመለክተው ወደፊት የሚነሣው የእሥራኤል ንጉሥ ከአጋግ ይልቅ የበለጠ ክብርና ሥልጣን የሚኖረው መሆኑን ነው፡፡አጋግ የአማሌቃውያን ንጉሥ ነበር፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ))
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሌሎች ሰዎች ለመንግሥታቸው ክብርን ይሰጣሉ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ሆኖ ትንቢት መናገሩን ይቀጥላል፡፡
“እግዚአብሔር እሥራኤላውያንን አውጥቷቸዋል”
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር አፅንዖት የሚሰጠው እሥራኤላውያን ታላቅ የሆነ ጉልበት ያላቸው መሆኑን ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም እሥራኤላውያንን ልክ ዱር አውሬዎች ጠላቶቻቸውን ከሚበሉት አበላል ጋር አነፃፅሯቸዋል፡፡ይሄ ማለት ጠላቶቻቸውን ያጠፏቸዋል ማለት ነው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር ሆኖ ትንቢት መናገሩን ይቀጥላል፡፡
በዚህ ፈሊጣዊ አነጋገር ውስጥ በለዓም እሥራኤላውያንን ከሴትና ከወንድ አንበሳ ጋር መሳስላቸዋል፡፡ይሄ ማለት አደገኞችና ሁልጊዜ ለማጥቃት ዝግጁ ናቸው ማለት ነው፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም ይህንን ጥያቄ የሚያነሳው ማንም ሰው ቢሆን እሥራኤልን እንዳያስቆጣ ለማስጠንቀቅ ነው፡፡ይሄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡“ማንም ቢሆን እርሱን ለመረበሽ ድፍረቱ አይኖረውም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር እሥራኤላውያንን የሚባርኩትን ይባርክ፤የሚረግሙትንም ይርገም”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የባላቅ ቁጣ የመንደዱ ጉዳይ ልክ ሊነድድ እነደጀመረ ዓይነት እሣትተደርጎ ተገልጿል፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ባላቅ በኃይል ተናደደ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የታላቅ ብስጭትና ንዴት ምልክት ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ባላቅ እየገለፀ ያለው ፈፅሞ ሊሆን የማይችልን ነገር ነው፡፡ይሄ ዓረፍተ ነገር አስረግጦ የሚናገረው በምንም ዓይነት መንገድ በለዓም ለእግዚአብሔር እንዳይታዝ የሚያደርገው ነገር የማይኖር መሆኑን ነው፡፡(ምናባዊ ሁኔታዎች)
በለዓም ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ቀደም ሲል የተናገረውን ለባላቅ ለማሳሰብ ነው፡፡ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ በዓረፍተ ነገር መልክም ሊተረጎም ይችላል፡፡“ይህንን ነግሬያቸዋለሁ”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
“እሥራኤላውያን”
ቢዖር በለዓም አባት ነበረ፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው በሚገባ የሚያይና የሚረዳ መሆኑን ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 24፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ዕውቀት”የሚለው ረቂቅ ሥም በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ታላቁ እግዚአብሔር የገለጠለትን ነገር የሚያውቅ ሰው”(አሕፅሮተ ሥሞች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ለእግዚአብሔር የመገዛት ምልክት ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
በለዓም ከአራቱ ትንቢቶች መካከል አንዱን መናገር ይጀምራል፡፡
እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡በለዓም ወደፊት ስለሚከሰተው ነገር ራዕይ አየተመለከተ ነው፡፡“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የወደፊቱን የእሥራኤል መሪ ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ኮከብ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በእሥራኤል ላይ ሥልጣን የሚይዘውን ንጉሥ ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ቋንቋ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ያዕቆብ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የያዕቆብን ትውልድ ነው፡፡“ከያዕቆብ ትውልድ መካከል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ከመጀመሪው ዓረፍተ ነገር ጋር ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያለው፡፡እዚህ ላይ “በትር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ብርቱ የሆነ ንጉሥን ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“እሥራኤል”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የወደፊት እሥራኤላውያንን ነው፡፡“ወደፊት ከሚወለዱት እሥራኤላውያን መካከል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/ሞዓብ መሪዎችን አናት ይመታል2/የሞዓብን መሪዎች ያጠፋል፡፡
ይሄ የሤት ዝርያዎች የሆኑ ሞአባውያንን የሚመለከት ነው፡፡
በለዓም የመጀመሪዎቹን አራት ትንቢቶች መናገር ያበቃል፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እሥራኤላውያን ኤዶምን በቁጥጥራቸው ሥር ያደርጓታል፡፡”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“አማሌቅ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የአማሌቅን ሕዝብ ነው፡፡ራዕዩ የቀጠለው ወደ አሜሌቃውያን አቅጣጫ ከተመለከተ በኋላ ሲሆን ከዚያ በኋላ ስለ አማሌቃውያን መተንበዩን ይቀጥላል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ነጠላ ሥም ጥቅም ላይ የዋለበት ምክኒያት አማሌቃውያን እንደ አንድ ግለሰብ በመታየታቸው ነው፡፡(የመጀመሪያ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ አካል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ሥም የቃየን ትውልድ ሆነ ሕዝብ ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“የምትኖርበት ሥፍራ ከባድ መከላከያ ያለው ነው”
ይሄ ምሣሌያዊ አነጋገር ሲሆን ደህንነቱ በተጠበቀ ሥፍራ ላይ መኖር ማለት ነው፡፡“የምትኖርበት ሥፍራ ዓለታማ በሆኑ ከፍታ ሥፍራዎች ላይ እንዳለ ወፍ ጎጆ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚሀ ላይ የቄናውያን መጥፋት በእሣት እንደሚቃጠሉ ዓይነት ሆኖ ተገልጿል፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ነገር ግን እናንተ ቄናዊያን አሦራውያን አንድ ነገር በእሣት እንደሚጠፋ ያጠፏችኋል፤በምርኮኝነትም ይወስዷኋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ በዓረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ይህንን በሚያደርግበት ወቅት ማንም በሕይወት አይኖርም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በሜዲተራንያን ባህር ውስጥ የሚገኝ የአንድ ደሴት ከተማ ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“ጥፋት”የሚለው ረቂቅ ሥም በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር እነርሱንም ያጠፋቸዋል”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሞአብ ንጉሥ ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
1 እስራኤል በሰጢም ተቀመጠ፣ ወንዶቹም ከሞዓብ ሴቶች ጋር ተኙ፣ 2 ይህም ሞአባዊያኑ ህዝቡን ለእነርሱ አማልዕክት የተሰዋውን ስለጋበዟቸው ነው፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ለጣኦት የተሰዋውን በሉ ደግሞም ለሞአባውያን አማልዕክት ሰገዱ፡፡ 3 የእስራኤል ወንዶች የፌጎርን በኣል በማምለክ ተባበሩ፣ እናም የያህዌ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፡፡ 4 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ብርቱ ቁጣዬ ከእስራኤል ይርቅ ዘንድ የህዝቡን መሪዎች ሁሉ ግደልና እነርሱን በቀን ብርሃን ለማጋለጥ ስቀላቸው፡፡” 5 ስለዚህም ሙሴ ለእስራኤል መሪዎች እንዲህ አለ፣ “እያንዳንዳችሁ የፌጎርን በኣል በማመልክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ፡፡” 6 ከዚያ ከእስራኤል ወንዶች አንዱ ቀርቦ ከቤተሰቡ አባላት ጋር አንዲት ምድያማዊት ሴት አመጣ፡፡ ሙሴና መላው የእስራኤል ህዝብ እያዩ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ሆነው እያለቀሱ ሳለ ይህ ሆነ፡፡ 7 የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ካህኑ ፊንሀስ ይህን ሲመለከት፣ ከማህበሩ መሀል ጦሩን በእጁ ይዞ ተነሳ፡፡ 8 እርሱም ወደ ድንኳኑ እስራኤላዊውን ሰው ተከትሎ ገብቶ የእስራኤላዊውን ወንድና የምድያማዊቷን ሴት የሁለቱንም አካላት በአንድነት በጦሩ ወጋ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ህዝብ ላይ የላከው መቅሰፍት አቆመ፡፡ 9 በመቅሰፍቱ የሞቱት በቁጥር ሃያ አራት ሺ ነበሩ፡፡ 10 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 11 “ካህኑ፣ የአሮን ልጅ የአልአዛር ልጅ ፊንሀስ፣ ቁጣዬን ከእስራኤል ህዝብ አርቋል ምክንያቱም በእነርሱ መሃል የእኔን ቅንአት ቀንቷል፡፡ ስለዚህ የእስራኤልን ህዝብ በቁጣዬ ፈጽሞ አላጠፋኋቸውም፡፡ 12 ስለዚህ እንዲህ በል፣ ‘ያህዌ እንዲህ ይላል፣ “እነሆ፣ ለፊንሐስ የሰላሜን ኪዳን እሰጠዋለሁ፡፡ 13 ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለትውልዱ፣ ዘለዓለማዊ የክህነት ኪዳን ይሆናል፤ ምክንያቱም እርሱ ለእኔ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ቀንቷል፡፡ ለእስራኤል ህዝብ አስተሰርይዋል፡፡” 14 ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው የእስራኤላዊ ሰው የሰሉ ልጅ ስም ዘንበሪ ሲባል፣ የስምኦናውያን አባቶች ቤተሰብ መሪ ነበር፡፡ 15 የተገደለችው የምድያም ሴት ስም ከስቢ ነበር፣ እርሷም ከምድያም ቤተሰብ የጎሳው መሪ የሱር ሴት ልጅ ነበረች፡፡ 16 ስለዚህም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 17 ”ምድያማዊያንን እንደ ጠላት ቆጥራችሁ አጥፏቸው፣ 18 እነርሱ በአታላይነታቸው እንደ ጠላት አስተናግደዋችኋልና፡፡ በፌጎር በሆነውና በእናታቸው በከስቢ ጉዳይ በፌጎር ምክንያት በመቅሰፍቱ ቀን በተገደለችው በምድያም አለቃ ልጅ ወደ ክፉ መርተዋችኋል፡፡”
ይሄ በሞአብ ውስጥ የሚገኝ የቦታ ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የአምልኮ ሥርዓት ድርጊት ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ብኤልፌጎር የተራራ ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 23፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
የእግዚአብሔር ቁጣ መንደድ ከሚጀምር እሣት ጋር ተመሳስሎ ተነግሯል፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ይህንንሐረግ በዘኁልቁ 22፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“እግዚአብሔር በጣም ተናደደ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውንና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ጣዖትን በማምለክ ጥፋተኛ የሆኑ መሪዎችን ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ጣዖትን በማምለክ ጥፋተኛ የሆኑ የሕዝብ መሪዎች ሁሉ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት የሕዝቡ መሪዎች እነዚህን ሰዎች ከገደሉ በኋላ ሬሣቸውን ሰዎች ሁሉ ሊያዩ በሚችሉበት ሥፍራ ላይ ይተውታል ማለት ነው፡፡
“በጣዖት አምልኮ ውስጥ ያልተሳተፉ የእሥራኤል መሪዎች”
ፌጎር የተራራ ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 23፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ የሚያመለክተው ወደ ሠፈሩ ከአርሷ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ለማድረግ ወደ ሠፈሩ ይዟት መምጣቱን ነው፡፡የዚህ ሙሉ ትርጉም የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ከምድያማዊቷ ሴት ጋር አብሮ ለመተኛት ወደ እሥራኤላውያን ሠፈር አመጣት”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ዓይን ፊት” የሚለው ቃል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ስለ ጉዳዩ ሰምተዋል ወይም ጉዳዩን አውቃውታል ማለት ነው፡፡
ይሄ የአሮን ልጅ ሥም ነው፡፡ይህንን በዘኁልቁ 3፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“ፊንሐስ ተከትሎ ገባ”
የእግዚአበሔር ቁጣ ለመቆም እንዲችል ወደ አንድ ሥፍራ በአካል መገፋት እንዳለበት ዓይነት ነገር ተደርጎ ነው የሚነገረው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር እዚሀ ላይ የተገለፀው ልክ የእሥራኤልን ሕዝብ እንደሚበላ ጨካኝ አውሬ ተደርጎ ነው፡፡“በእጅጉ የተናደድኩ ቢሆንም የእሥራኤልን ሕዝብ ግን አላጠፋሁም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የእግዚአብሔርን ንግገር ካለፈው ጥቅስ እንዲቀጥል ያደርገዋል፡፡ይሄ በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ አለው፡፡ቀጥተኛ የሆኑት ጥቅሶች ቀጥተኛ እንዳልሆኑ ጥቅሶች ሊገለፁ ይችላሉ፡፡(በጥቅሶች ውስጥ ጥቅሶችና ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ጥቅሶች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ዋናውን ታሪክ ወደ ጀርባ ታሪክ በመቀየር ስለ ዘንበሪና ስለ ከስቢ ያወሳል፡፡(የጀርባ ታሪክ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ፊንሐስ የገደለው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የሰው ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የአንዲት ሴት ሥም ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“መሽንገል”የሚለው ረቂቅ ሥም እንደ ሥም ሊገለፅ ይችላል፡፡“እናንተን በማታለል”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
“ይህንን ክፉ ሥራ እንድትሰሩ አግቧቧችሁ”
እነዚህ ሁለቱም ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ሃሣብ ያላቸው ሲሆን እነዚህ ነገሮች የተከናወኑት በፌጎር ተራራ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡
ፌጎር የተራራ ሥም ነበር፡፡ይህንን በዘኁልቁ 23፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ፊንሐስ የገደለው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ከመቅሰፍቱ በኋላ እንዲህ ሆነ፣ ያህዌ ለሙሴና ለካህኑ ለአሮን ልጅ ለአልዓዛር እንዲህ አላቸው፡፡ 2 “የእስራኤልን ማህበረሰብ ሁሉ ቁጠሩ፣ ሀያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን፣ ለእስራኤል ለመዋጋት ወደ ጦርነት መውጣት የሚችሉትን ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤቶች ቁጠሯቸው፡፡” 3 ስለዚህም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በሞአብ ሜዳ በዮርዳኖስ አጠገብ ኢያሪኮ ሳለ ለህዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፣ 4 “ከሃያ አመት ጀምሮ ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸውን ከግብጽ ምድር የወጡትን ያህዌ ሙሴንና የእስራኤል ሰዎችን እንዳዘዘው ሁሉ ቁጠሯቸው፡፡” 5 ሮቤል የእስራኤል በኩር ነበር፡፡ ከወንድ ልጁ ከሄኖክ የሄኖካውያን ጎሳዎች መጡ፡፡ ከፈለስ የፈለሳውያን ጎሳ መጡ፡፡ 6 ከአስሮን የአስሮናውያን ጎሳ መጡ፡፡ ከከርሚ የከርማውያን ጎሳ መጡ፡፡ 7 እነዚህ የሮቤል ጎሳ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 43730 ወንዶች ነበሩ፡፡ 8 ኤልያብ የፈሉስ ልጅ ነበር፡፡ 9 የኤልያብ ወንዶች ልጆች ነሙኤል፣ ዳታን፣ እና አቤሮን ነበሩ፡፡ እነዚህ ቆሬን ተከትለው ሙሴንና አሮንን በመቃወም በያህዌ ላይ ያመጹት እነዚያው ዳታንና ኤብሮን ነበሩ፡፡ 10 ሁሉም የእርሱ ተከታዮች ሲሞቱ፣ ምድር አፏን ከፍታ ከቆሬ ጋር ሁሉንም በአንድነት ዋጠቻቸው፡፡ በዚያ ጊዜ፣ በእሳት መቀጣጫ የሆኑትን 250 ወንዶችን በላች፡፡ 11 ነገር ግን የቆሬ የዘር ሀረግ አልጠፋም፡፡ 12 የስምዖን ትውልዶች እዚህ ነበሩ፡ በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጎሳ፣ በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጎሳ፣ በያኪን በኩል የያኪናውያን ጎሳ፣ 13 በዛራ በኩል የዛራውያን ጎሳ፣ በሳኡል በኩል የሳኡላውያን ጎሳ ነበሩ፡፡ 14 እነዚህ የስምዖን ጎሳ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 22200 ወንዶች ነበሩ፡፡ 15 የጋድ ጎሳ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በጽፎን በኩል የጽፎናውያን ጎሳ፣ በሐጊ በኩል የሐጋውያን ጎሳ፣ በሺኒ በኩል፣ የሺናውያን ጎሳ፣ 16 በኤስና በኩል፣ የኤሶናውያን ጎሳ፣ በዔሪ በኩል የዔራውያን ጎሣ፣ 17 በአሮዲ በኩል የሮዳውያን ጎሳ፣ በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጎሳ፡፡ 18 እነዚህ የጋድ ጎሳ ትውልድ ነበሩ፣ ቁጥራቸው 40500 ወንዶች ነበሩ፡፡ 19 የይሁዳ ልጆች ዔር እና አውናን ነበሩ፣ እነዚህ ወንዶች ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል፡፡ 20 የይሁዳ ጎሳ ሌሎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፣ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጎሳ፣ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጎሳ፣ እና በዛራ በኩል የዛራውያን ጎሳ ነበሩ፡፡ 21 የፋሬስ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ በኤስሮም በኩል የኤስሮማውያን ጎሳ፣ በሐሙል በኩል፣ የሐሙላውያን ጎሳ፡፡ 22 እነዚህ የይሁዳ ጎሳ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 76500 ነበሩ፡፡ 23 የይሳኮር ጎሳዎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡፡ በቶላ በኩል የቶላውያን ጎሳ፣ በፋዋ በኩል ቦፋውያን ጎሳ፣ 24 በያሱብ በኩል፣ የያሱባውዩን ጎሳ፣ በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጎሳ፡፡ 25 እነዚህ የይሳኮር ጎሳዎች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 64300 ወንዶች ነበሩ፡፡ 26 የዛብሎን ጎሳዎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡፡ በሴሬድ በኩል የሴሬዳውያን ጎሳ፣ በኤሎን በኩል የኤሎናውያን ጎሳ፣ በያህልኤል በኩል የያህልኤላውያን ጎሳ፡፡ 27 እነዚህ የዛብሎን ጎሳዎች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 60500 ወንዶች ነበሩ፡፡ 28 የዮሴፍ ጎሳ ትውልዶች ምናሴና ኤፍሬም ነበሩ፡፡ 29 የምናሴ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጎሳ (ማኪር የገለዓድ አባት ነበር) ፣ በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጎሳ ነበሩ፡፡ 30 ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በኢዔዝር በኩል የኢዔዝራውያን ጎሳ፣ በኬሌግ በኩል የኬሌጋውያን ጎሳ፣ 31 በእስራኤል በኩል የእስራኤላውያን ጎሳ፣ በሴኬም በኩል፣ የሴካማውያን ጎሳ፣ 32 በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጎሣ፣ በኦፌር በኩል የኦፌራውያን ጎሣ፣ 33 ልጅ ሰለጳዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፣ ነገር ግን ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት፡፡ የሴት ልጆቹ ስሞች እነዚህ ነበሩ፡ ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግሳ፣ ሚልካና ቲርዳ፡፡ 34 እነዚህ የምናሴ ጎሳዎች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 52700 ወንዶች ነበሩ፡፡ 35 የኤፍሬም ጎሳዎች ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በሲቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጎሣ፣ በቤኬር በኩል የቤኬራውያን ጎሣ፣ በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 36 የሱቱላ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በዔዴን በኩል፣ የዔዴናውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 37 እነዚህ የኤፍሬም ጎሣ ትውልዶች ነበሩ፡ ቁጥራቸው 32500 ወንዶች ነበሩ፡፡ እነዚህ የዮሴፍ ትውልዶች፣ በየጎሣቸው ተቆጠሩ፡፡ 38 የብንያም ጎሣ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጎሣ፣ በአስቤል በኩል የአስቤላውያን ጎሣ፣ በኢኪራን በኩል፣ የኢኪራናውያን ጎሣ፣ 39 በሶፋን በኩል፣ የሶፋናውያን ጎሣ፣ በሑፋም በኩል፣ የሑፋፋማውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 40 የቤላ ወንዶች ልጆች አርድ እና ናዕመን ነበሩ፡፡ ከአርድ የአርዳውያን ጎሣ መጣ፣ ከናዕማን የናዕመናውያን ጎሣ መጣ፡፡ 41 የብንያም ጎሣ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡፡ ቁጥቸው 45600 ወንዶች ነበሩ፡፡ 42 የዳን ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በስምዔ በኩል፣ የስምዔያናውያን ጎሣዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የዳን ትውልድ ጎሣዎች ነበሩ፡፡ 43 የስምዔያውያን ጎሣዎች በጠቅላላ 64400 ወንዶች ነበሩ፡፡ 44 የአሴር ትውልድ ጎሣዎች እነዚህ ነበሩ፡ በዩምና በኩል የዩምናውያን ጎሣ፣ በዩሱዋ በኩል፣ የየሱዋውያን ጎሣ፣ በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 45 የብንያም ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጎሣ፣ በመልኪኤል በኩል የመልኪኤላውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 46 የአሴር ሴት ልጅ ስም ሤራህ ነበር፡፡ 47 እነዚህ የአሴር ጎሣ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 53400 ወንዶች ነበር፡፡ 48 የንፍታም ጎሣ ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ በያሕድኤል በኩል፣ የያህጽኤላውያን ጎሣ፣ በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጎሣ፣ 49 በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ 50 እነዚህ የንፍታሌም ጎሣ ትውልዶች ነበሩ፣ ቁጥራቸው 45400 ወንዶች ነበር፡፡ 51 ይህ በእስራኤል ህዝብ መሃል ጠቅላላው የወንዶች ቁጥር ነበር፡፡በጠቅላላው 601730 ነበሩ፡፡ 52 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣ 53 “ምድሪቱ በእነዚህ ሰዎች መሃል ርስት ሆኖ እንደ ስሞቻቸው ቁጥር መሰረት ትከፋፈል፡፡ 54 ብዙ ቁጥር ላለው ጎሳ ሰፋ ያለውን ርስት ስጥ፣ አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ጎሣዎች አነስ ያለውን ርስት ስጣቸው ለእያንዳንዱ ቤተሰብ እንደ ተቆጠረው ወንድ ብዛት ርስት ስጣቸው፡፡ 55 ሆኖም ምድሪቱ በዕጣ ትከፋፈል፡፡ ምድሪቱን በየአባቶቸው ጎሳዎች መሀል እንደምትከፋፈል ይወርሷት፡፡ 56 ርስታቸው በየጎሳው ብዛትና አነስተኛት መጠን ይከፋፈል፣ ክፍፍሉ በዕጣ ይሁን፡፡” 57 በየነገዳቸው የተቆጠሩት የሌዋውያን ነገዶች እነዚህ ነበሩ፡ በጌድሶን በኩል፣ የጌድሶናውያን ጎሣ፣ በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጎሣ፣ በሜራሪ በኩል፣ የሜራርያውን ጎሣ ነበሩ፡፡ 58 የሌዊ ጎሳዎች እነዚህ ነበሩ፡ የሊብናውያን ጎሣ፣ የኬብሮናውያን ጎሣ፣ የሞሐላውያን ጎሣ፣ የሙሳውያን ጎሣ፣ እና የቆሬያውያን ጎሣ ነበሩ፡፡ ቀዓት የእንበረም የዘር ሀረግ ነበር፡፡ 59 የእንበረም ሚስት ስሟ ዮካብድ ነበር፣ ከሌዋውያን ወገን ግብጽ ውስጥ የተወለደች ነበረች፡፡ ከእንበረም ልጆቻቸውን አሮንን፣ ሙሴን እና እህታቸውን ማርያምን ወለደች፡፡ 60 ለአሮን የተወለዱለት ናዳብ እና አብዩድ፣ ኤልዓዛር እና ኢታምር ነበሩ፡፡ 61 ናዳብና አብዩድ ያህዌ በፊቱ ተቀባይነት የሌለውን የእሳት መስዋዕት ሲያቀርቡ ሞቱ፡፡ 62 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያቸው ሌዋውያን ወንዶች ቁጥር ሃያ ሶስት ሺ ነበር፡፡ ነገር ግን ከእስራኤል ትውልዶች ጋር አብረው አልተቆጠሩም፡፡ ምክንያቱም ለእነርሱ በእስራኤል ሕዝብ መሃል ምንም ርስት አልተሰጣቸውም ነበር፡፡ 63 በሙሴና በካህኑ አልዓዛር የተቆጠሩት እነዚህ ናቸው፡፡ በሞአብ ሜዳ በዮርዳኖስ ኢያሪኮ ውስጥ የእስራኤልን ህዝበ ቆጠሩ፡፡ 64 የእስራአል ትውልዶች በሲና ምድረ በዳ በተቆጠሩ ጊዜ በእነዚህ መሀል በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር የተቆጠረ ሌላ ሰው ግን አልነበረም፡፡ 65 ያህዌ እነዚያ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ በምድረበዳ እንደሚሞቱ ተናግሮ ነበር፡፡ ከዩፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከመሀላቸው በህይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
የሚቆጥሩት ሴቶችን ሣይሆን ወንዶችን ብቻ ነበር፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“በማህበሩ ውሰጥ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ቁጠሩ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“20 ዓመትና ከዚያ በላይ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ለእሥራኤል መሪዎች ተናገሩ፡፡
ሜዳ ሠፊና ለጥ ያለ መሬት ነው፡፡
“20 ዓመትና ከዚያም በላይ”
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ እሥራኤል የሚለው ቃል የሚያመለክተው ያዕቆብ በመባል የሚታወቀውን ሰው ነው፡፡
እዚህ ላይ“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሮቤልን ነው፡፡
“አርባ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሣ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
የእነዚህን ሰዎች ሥም በዘኁልቁ 16፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
እዚህ ላይ ምድሪቱ የተቆጠረችው ልክ አንድ ሰው አፉን ከፍቶ አንድን ነገር እንደሚበላ ዓይነት ነው፡፡“እግዚአብሔር ምድሪቱ እንድትከፈት ካደረገ በኋላ ሰዎቹ በዚያ ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ”(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ እሣቱ የተገለፀው ልክ አንድ ትልቅ እንስሳ አንድን ነገር እንደሚውጥ ተደርጎ ነው፡፡ “እግዚአብሔር 250 ሰዎችን ለመግደል እሣትን ተጠቀመ”(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሁለት መቶ ሃምሣ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“የቆሬ ቤተሰቦች በሙሉ”
“መጨረሻቸው ሆነ”
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሃያ ሁለት ሰሺህ ሁለት መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አርባ ሺህ አምስተ መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ስድሳ አራት ሺህ ሶስት መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ስድሳ ሺህ አምስት መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“እነዚህ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የዮሴፍ ልጆች ከሆኑት ከኤፈሬምና ከምናሴ ልጆች የተወለዱትን ትውልድ ሁሉ ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊበራራ ይችላል፡፡“እነዚህ የያዕቆብ ልጆች ከሆኑት ከኤፍሬምና ከምናሴ ዘር የተገኙ ናቸው፡፡እነርሱም ተቆጠሩ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በየወገናቸው ቆጠሯቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ስድሳ አራት ሺህ አራት መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእሥራኤል መሪዎች ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎችን ከትውልዳቸውና ከነገዳቸው አንፃር እየቆጠሩ ነው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውንና ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ሰዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አጠቃላይ ቁጥሩ”
“ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰላሣ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“መሬቱን ማከፋፈል አለባችሁ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ከኦሪት ዘኁልቁ 26፡5 ጀምሮ በየወገናቸው የተቆጠሩትን ሁሉ ነው፡፡
“በእያንዳንዱ ወገን ውስጥ ባለው የሕዝብ ቁጥር መሠረት”
እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
በዚህ ምንባብ ወስጥ “ርስት”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተወረሰውን መሬት ነው፡፡የዓረፍተ ነገሩ ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“እንደ ርስት አድርገህ የበለጠ ትሰጣቸዋለህ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእሥራኤል መሪዎች የቆጠሯቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ምድሪቱን ማከፋፈል አለባችሁ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ዕጣ በመጣል”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ታከፋፍሉታላችሁ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“መሬቱን ለእነርሱ ማከፋፈል ይኖርባችኋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሌዋውያን ነገድ የሥም ዝርዝር ነው፡፡ምንም መሬት ባለመቀበላቸው ምክኒያት ሙሴ ሌዋውያንን ለብቻቸው ቆጠራቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“መሪዎቹ በየነገዳቸው ቆጠሯቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የእነዚህን ሰዎች ሥም በዘኁልቁ 3፡17-19 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“እርሷና እንበረም ልጆች ነበሯቸው”
የእነዚህን ሰዎች ሥም በዘኁልቁ 3፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
እዚህ ላይ“እሣት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው “የሚቃጠል መሥዋዕትን”ነው፡፡ተመሳሳይ የሆነውን ሐረግ በዘኁልቁ 3፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“እርሱ ባልተቀበለው ሁኔታ የሚቃጠል መሥዋዕትን አቀረቡ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“መሪዎቹ የቆጠሯቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“23,000”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ ወርና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡እዚህ ላይ “ርስት”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተወረሰውን መሬት ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ምንም ዓይነት መሬት በርስትነት እአይሰጣቸውም አለ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴና ካህኑ አልዓዛር የቆጠሯቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰዎች አልነበሩም”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሙሴና ካህኑ አሮን የቆጠሯቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእሥራኤልን ትውልድ በቆጠሩበት ወቅት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሲና ምድረ በዳ ተቆጥረው የነበሩትን ሰዎች ሁሉ ነው፡፡ይሄ በአዎንታዊ መለኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እስከ አሁን ድረስ በሕይወት ያሉት ሰዎች”(ድርብ አሉታውያን)
ዮፎኒየካሌብ አባት ነበር፡፡ይህንን በዘኁልቁ 13፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ነዌ የኢያሱ አባት ነበር፡፡ይህንን በዘኁልቁ 11፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
1 ከዚያ ከዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ የአፌር ወንድ ልጅ የገለአድ ወንድ ልጅ የማኪር ወንድ ልጅ የምናሴ ወንድ ልጅ የሰለጵዓድ ሴት ልጆች ወደ ሙሴ መጡ የሰለዓድ ሴት ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፡፡ ማህላህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጳ፡፡ 2 እነርሱም በሙሴ፣ በካህኑ አልዓዛር፣ በመሪዋች፣ እና በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በመላው ማህበረሰቡ ፊት ቆሙ፡፡ እንዲህም አሉ፣ 3 “አባታችን በምድረበዳው ሞተ፡፡ እርሱ በቆሬ አመጽ በያህዌ ፊት አምጸው በአንድነት ከተነሱት መሀል አልነበረም፡፡ የሞተው በራሱ ኃጢአት ነበር፣ አባታችን የሞተው በራሱ ኃጢአት ምክንያት ነበር፡፡ 4 ስለምን ወንድ ልጅ ስለሌለው የአባታችን ስም ከጎሳው አባላት ተለይቶ ይጠፋል? በአባታችን ቤተዘመዶች መሀል መሬት ስጠን፡፡” 5 ሙሴ ጉዳያቸውን ያህዌ ፊት አቀረበ፡፡ 6 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣ 7 ”የሰለጰዓድ ሴት ልጆች የተናገሩት ትክክል ነው፡፡ በአባታቸው ዘመዶች መሃል በእርግጥ ርስት አድርገህ መሬት ስጣቸው፣ ደግሞም የአባታቸው ርስት ወደ እነርሱ መተላፉን አረጋግጥ፡፡ 8 ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይኖው ቢሞት፣ ርስቱ ወደ ሴት ልጁ እንዲተላፍ አድርጉ፡፡ 9 ሴት ልጅ ባይኖረው፣ ርስቱን ለወንድሞቹ ስጡ፡፡ 10 ወንድሞች ባይኖት፣ ርስቱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ፡፡ 11 አባቱ ወንድሞች ባይኖሩት ርስቱን በጎሳው ውስጥ ለቅርብ ዘመዱ ስጡ፣ ያም ሰው ይውሰደው፡፡ ይህም ያህዌ እንዳዘዘኝ፣ ለእስራኤል ህዝብ በአዋጅ የፀና ህግ ይሆናል፡፡’” 12 “ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ወደ ዓባሪም ተራሮች ወጥተህ ለእስራኤል ህዝብ የሰጠሁትን ምድር ተመልከት፡፡ 13 ከተመለከትካት በኋላ፣ አንተም ደግሞ ወደ ሰዎችህ እንደ ወንድምህ አሮን ሁሉ ትሰበስባለህ፡፡ 14 ይህ ይሆናል፤ ምክንያቱም በጺን ምድረበዳ እናንተ ሁለታችሁ በትእዛዛቶቼ ላይ አምጻችኋል፡፡ በዚያ፣ ውሃው ከአለቱ ሲፈስስ በቁጣህ ምክንያት በመላው ማህበረሰብ ዐይኖች ፊት እኔን በቅድስና ማክበር አልቻልክም፡፡” ይህ በጺን ምድረበዳ በቃዴስ የሚገኝ የመሪባ ውሃ ነው፡፡ 15 ከዚያ ሙሴ ለያህዌ እንዲህ አለ፣ 16 “የሰዎች ሁሉ መንፈስ አምላክ ያህዌ ሆይ፣ በዚህ ማህበረሰብ ላይ መሪ የሚሆን ሰው ሹም፣ 17 በፊታቸው የሚወጣና የሚገባ ሰው፣ እየመራ የሚያስወጣቸውና የሚያስገባቸው፣ ህዝብህ እረኛ እንደሌላቸው በጎች እንዳይሆን ሰው ሹምለት፡፡” 18 ያህዌ ሙሴን፣ “የእኔ መንፈስ የሚኖርበትን፣ የነዌን ልጅ ኢያሱን ውሰድና እጆችህን በእርሱ ላይ ጫን፡፡ 19 በካህኑ አልዓዛር ፊትና በመላው ማህበረሰብ ፊት አቁመህ እንዲመራቸው በፊታቸው ሹመው፡፡ 20 ከአንተ ስልጣን በእርሱ ላይ አድርግ፣ ስለዚህም መላው የእስራኤል ማህበረሰብ እርሱን ይታዘዙታል፡፡ 21 እርሱም በኡሪም በመጠየቅ ፍቃዴን ለማወቅ በካህኑ አልዓዛር ፊት ይሄዳል፡፡ ህዝቡ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር መላው የእስራኤል ሰዎች፣ መላውም ማህበረሰብ የሚወጣውና የሚገባው በእርሱ ትዕዛዝ ይሆናል፡፡ 22 ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እርሱን እንዳዘዘው አደረገ፡፡ ኢያሱን ወስዶ በካህኑ አልዓዛርና በመላው ማህበር ፊት አቆመው፡፡ 23 ያህዌ እንዲያደርግ እንዳዘዘው ሁሉ እጆቹን በላዩ ጫነና እንዲመራ ሾመው፡፡
ከዚያም ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገኖች፤የምናሴ ልጅ፤የማኪር ልጅ፤የገለዓድ ልጅ፤የኦፌር ልጅ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ወደ ሙሴ ቀረቡ፡፡ይሄ የትውልድን ሐረግ ይናገራል፡፡
ይህንን በዘኁልቁ26፡33 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይህንን በዘኁልቁ 26፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ቀረቡ”
በቆሬ ማህበር ውስጥ የነበሩት ሰዎች ተሰባሰበው በእግዚአብሔር ላይ አመፁ፡፡እግዚአብሔር ከኃጢአታቸው የተነሣ እንዲሞቱ አደረገ፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“በእግዚአብሔር ላይ ያመፁ የቆሬ ማህበር ተከታዮች በመሆናቸው የሞቱ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ከራሱ ኃጢአት የተነሣ”
በዚያን ዘመን መሬት የመውረስ ሥልጣን የነበረው ወንድ ልጅ ብቻ ነበር፡፡ሴቶቹ ይህንን ጥያቄ የጠየቁት ውርሱን በመውረስ የዘር ሐረጉ እንዲቀጥል ለማስቻል ነበር፡፡ይሄ እንደ መግለጫ ሊፃፍ ይችላል፡፡“አባታችን ወንድ ልጅ ስለሌለው ብቻ የአባታችንን ሥም ከነገድ አባልነቱ ልትፍቁት አይገባም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የአባታቸው ዘመዶች በወረሱት ርሰት አካባቢ የሚወርሱት ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ያቀረቡት ጥያቄ ነው፡፡የዚህ ፍቺ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የአባታችን ዘመዶች ባሉበት ሥፍራ ላይ ርስትን ሥጠን”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት የአባታቸው ዘመዶች በወረሱት ርሰት አካባቢ የሚወርሱት ርስት ይሰጣቸዋልማለት ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የአባታቸው ወንድሞች ወደሚኖሩበት”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ክስተት አንድ ሰው ወንድ ልጅ የማይኖረው ከሆነ መሬቱን ማን ሊወርስ እንደሚችል ለመወሰን የእግዚአብሔር ሕግ እንዲወጣ ምክኒያት ሆኗል፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ ሁሉ የሚታዘዘው ሕግ ይሁን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“እኔን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴን ነው፡፡
እነዚህ በሞአብ ውስጥ የሚገኙ የተያያዙ ተራራዎች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ እግዚአብሔር ለእሥራኤላውያን እየሰጠ ያለውን ምድር ልክ ሰጥቶ እንደጨረሰ ዓይነት አድርጎ ይናገራል፡፡በዚህ መልኩ የሚናገርበት ምክኒያት የሚሰጣቸው ስለመሆኑ አስረግጦ ለማሳሰብ ነው፡፡“ለእሥራኤል ሕዝብ የምሰጠውን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ጨዋ የሆነ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙም ሙሴ እንደሚሞትና መንፈሱም አባቶቹ ወዳሉበት የሚሄድ መሆኑን ነው፡፡“መሞት አለብህ”(የጨዋ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
አሮን መሞቱ የታወቀ ነገር ቢሆንም የበለጠ ግን ልታብራሩት ትችላላችሁ፡፡“ታላቅ ወንድምህ አሮን እንደሞተ”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ሙሴና አሮንን ነው፡፡
ይህንንዓረፍተ ነገርበዘኁልቁ 13፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ተአምራታዊ በሆነ መልኩ ውኃን ባወጣበት ወቅት ነበር፡፡እግዚአብሔር ድንጋዩን እንዲናገረው ሙሴን አዘዘው፡፡በዚህ ምትክ ግን በሕዝቡ ከመናደዱ የተነሣ ዓለቱን በበትሩ መታው፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“ቅዱስ እንደሆንኩ አላሰባችሁም”
እዚህ ላይ ያዩትን ነገር አፅንዖት ለመስጠት ሰዎች የሚወከሉት “በዓይኖቻቸው”ነው፡፡“ማህበሩ ሁሉ ባለበት ፊት”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 20፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/እዚህ ላይ “መንፈስ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሕዝብን ሁሉ ነው፡፡“የሰው ዘር ሁሉ የበላይ የሆነው እግዚአብሔር”ወይም 2/“መንፈስ”የሚለው ቃልየሚያመለክተው እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ሕይወትንና ትንፋሽን መሥጠቱን ነው፡፡ “ለሰው ሁሉ ትንፋሽን የሚሰጠው እግዚአብሔር”ወይም“ለሰው ሁሉ ሕይወትን የሚሰጠው እግዚአብሔር”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
በተወሰኑ ሰዎች “ላይ”መሆን ማለት እነርሱን ለመምራት ሥልጣን መያዝ ማለት ነው፡፡“ማህበሩን የሚመራ ሰው”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ሕዝቡን የሚመራና በጦርነትም ወቅት ሠራዊቱን የሚመራ ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ንፅፅር ሲሆን የዚህ ሃሣብ ትርጉም ሕዝቡ መሪ የማይኖረው ከሆነ የተቅበዘበዘና ደካማ ይሆናል ማለት ነው፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሲል ኢያሱ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚከተልና የሚታዘዝ ነው ማለቱ ነው፡፡
ይሄ አንድን ሰው ለእግዚአብሔር ለመለየት የሚካሄድ ሥርዓት ነው፡፡“እርሱን ለመቀባት እጅህን በላዩ ላይ ጫንበት”(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ያዩትን ነገር አፅንዖት ለመስጠት ሰዎች የሚወከሉት “በዓይኖቻቸው”ነው፡፡“የእሥራኤልን ሕዝብ ይመራ ዘንድ በሁሉ ፊት ኢያሱን እዘዘው”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለሙሴና ለኢያሱ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እዚሀ ላይ እግዚአብሔር ልክ በላዩ እንደሚደረግ ነገር ወይም አልባሳት ለኢያሱ ክብሩን እንዲያኖርበት ይናገረዋል፡፡“ከሥልጣንህ የተወሰነውን ክፍል መሥጠት ይኖርብሃል”ወይም “ሰዎች ማድረግ የሚኖርባቸውን ነገር እርሱ ይወስን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የተቀደሰ ድንጋይ ሲሆን ሊቀ ካህኑ በደረቱ ላይ የሚያደርገው ነገር ነው፡በእግዚአብሔር ነገር ላይ ውሳኔ ለመሥጠት የሚጠቀምበት ነገር ነበር፡፡(የማይታወቁትን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት ኢያሱ የእሥራኤልን ማህበር እንቅስቃሴዎች የማዘዝ ሥልጣን ይኖረዋል ማለት ነው፡፡“መውታጣ”እና “መግባት”የሚሉት ቃላት በእንቅስቃሴያቸው ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው አፅንዖት የሚሰጡ ሁለት ተቃራኒ የሆኑ ትዕዛዛቶች ናቸው፡፡“የማህበሩን እንቅስቃሴ ይመራል” (ሆን ብሎ አጋኖ መናገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በጥምረት የቀረቡበት ምክኒያት ለጉዳዩ አፅንኦት ለመሥጠት ሲባል ነው፡፡“እርሱና የእሥራኤል ሕዝብ ሁሉ”(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“በማህበሩ ፊት እንዲቆም አዘዘው”
“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴን ሲሁን “እርሱ”የሚለው ቃል ደግሞ የሚያመለክተው ኢያሱን ነው፡፡
እጅ መጫን አንድን ሰው ለተለየ የእግዚአብሔር አገልግሎት ለመለየት የሚደረግ ሥርዓት ነው፡፡(ተምሣሌታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ግልፅ የሆነውንና ሰዎችን የመምራትን ጉዳይ የበለጠ ልታብራሩት ትችላላችሁ፡፡“ሰዎችን መምራት”ወይም“የእሥራኤላውያን መሪ መሆን”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሴን ነው፡፡
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 ”የእስራኤል ሰዎችን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘በወቅቱ ለእኔ መስዋዕቶችን አቅርቡ፣ ለእኔ ጣፋጭ መዓዛ ያለው በእሳት የተበጀ መስዋዕት ለእኔ አቅርቡልኝ፡፡’ 3 ደግሞም እንዲህ በላቸው፣ ‘ይህ ለያህዌ የምታቀርቡት የእሳት መስዋዕት ነው፡፡ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ጠቦት፣ እንደ መደበኛ መስዋዕት በእያንዳንዱ ቀን ሁለት ጠቦቶች አቅርቡ፡፡ 4 አንዱን ጠቦት በማለዳ ታቀርባላችሁ፣ ሌላውን ጠቦት በምሽት ታቀርባላችሁ፡፡ 5 በተጠለለ የኢን አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የአፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አድርጋችሁ አቅርቡ፡፡ 6 ይህ በሲና ተራራ የተደነገገ ለያህዌ የሚቀርብ በእሳት የተዘጋጀ መልካም መዓዛ ያለው መደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፡፡ 7 ከዚህ ጋር የሚቀርበው የመጠጥ መስዋዕት ለአንዱ ጠቦት የኢን አንድ አራተኛ ይሁን፡፡ በተቀደሰው ስፍራ ለያህዌ የመጠጥ ስጦታ አፍስሱ፡፡ 8 ሌላውን ጠቦት ከሌላ የእህል ቁርባን ጋር በማለዳ ባቀረባችሁት መስዋዕት አይነት በምሽት አቅርቡ፡፡ ከዚህ ጋር ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን በእሳት የተዘጋጀ ሌላ የመጠጥ መስዋዕትም አቅርቡ፡፡ 9 በሰንበት ቀን ነውር የሌላቸው ሁለት የአንድ አመት ጠቦቶች፣ እና በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አድርጋችሁ ከመጠጥ መስዋዕት ጋር አቅርቡ፡፡ 10 ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ በየሰንበቱ የሚቃጠል መስዋዕት እንዲሆን ነው፡፡ 11 በየወሩ መጀመሪያ፣ ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ እና ነውር የሌለባቸው ሰባት ወንድ የበግ ጠቦት መስዋዕት አድርጋችሁ አቅረቡ፡፡ 12 ለእያንዳዱ ወይፈን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፣ ደግሞም ከአውራ በጉ ጋር በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ 13 እንደዚሁም ለእያንዳንዱ ጠቦት የኢፍ አንድ አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ ይህ ለያህዌ የሚቀርብ በእሳት የተዘጋጀ መልካም መዓዛ የሚሰጥ የሚቃጠል መስዋዕት የሚሆን ነው፡፡ 14 የሰዎች የመጠጥ ቁርባን ላንድ ኮርማ በሬ የኢን ግማሽ ወይን ጠጅ ይሁን፣ ከአውራ በጉ ጋር የኢን አንድ ሶስተኛ፣ ለአንድ ጠቦት በግ የኢን አንድ አራተኛ ወይን ጠጅ ይሁን፡፡ ይህ አመቱን በሙሉ በእያንዳንዱ ወር የሚቃጠል መስዋዕት ነው፡፡ 15 ለያህዌ አንድ ወንድ ፍየል የኃጢአት መስዋዕት መቅረብ አለበት፡፡ ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርብ የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ነው፡፡ 16 በመጀመሪያው ወር፣ በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን የያህዌ ፋሲካ ይውላል፡፡ 17 በዚህ ወር የአስራ አምስተኛው ቀን ክብረ በዓል ይሆናል፡፡ ለሰባት ቀናት እርሾ የሌለበት ቂጣ ይበላል፡፡ 18 በመጀመሪያው ቀን ያህዌን ለማክበር ቅዱስ ጉባኤ ይደረጋል፡፡ በዚያ ቀን የዘወትር ሥራችሁን አትሰሩም፡፡ 19 ሆኖም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ የሚቃጠል መስዋዕት ስጦታ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ሰባት ወንድ የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፡፡ 20 ከወይፈኑ ጋር በዘይት የተለወሰ የኢን ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን፣ ከአውራ በግ ጋር የኢን ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡ 21 ከእያንዳንዳቸው ከሰባቱ ጠቦቶች ጋር፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት አቅርቡ፣ 22 እንዲሁም አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአት መስዋዕት ለማስተሰርያ አቅርቡ፡፡ 23 እነዚህን በየጠዋቱ ከሚያስፈልገው መደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት በተጨማሪ አቅርቡ፡፡ 24 እዚህ እንደ ተገለፀው፣ እነዚህን መስዋዕቶች በየቀኑ ማቅረብ አለባችሁ፣ በፈሲካ ሳምንት፣ በእሳት የተዘጋጀው የምግብ መስዋዕት ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይቅረብ፡፡ ይህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ መቅረብ አለበት፡፡ 25 በሰባተኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፣ ደግሞም በዚያ ቀን የየዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑ፡፡ 26 እንደዚሁም በበኩራት ፍሬ ቀን፣ በክብረ በዓላችሁ ሳምንታት የአዲስ እህል ስጦታ ለያህዌ ስታቀርቡ፣ ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ ደግሞም በዚያ ቀን የተለመደ የየዕለት ተግባራችሁን አትስሩ፡፡ 27 ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ሁለት ወይፈኖች፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ሰባት የአንድ አመት ጠቦት በጎች አቅርቡ፡፡ 28 ከእነዚህ ጋር እነዚህን የእህል ቁርባን አቅርቡ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ ለእያንዳንዱ ወይፈን የኢፍ ሶስት አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ እና ለአውራ በጉ ሁለት አስረኛ የእህለ ቁርባን አቅርቡ 29 የኢፍ አንድ አስረኛ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ለእያንዳንዳቸው ሰባት ጠቦቶች አቅርቡ፣ 30 ደግሞም አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአታችሁ ማስተሰርያ አቅርቡ፡፡ 31 ነውር የሌለባቸውን እነዚያን እንስሳት ከመጠጥ ቁርባናቸው ጋር ስታቀርቡ ይህ ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕትና ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የእህል ቁርባን በተጨማሪ መሆን አለበት፡፡’”
“እኔ በመረጥኩኩት ቀን”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በመሠዊያው ላይ የምታቀርቡት መብል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የምወደውን ሽታ”
እግዚአብሔር ህዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት ለሙሴ መንገሩን ይቀጥላል፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በእሳት የሚቃጠል ቁርባን”ወይም “በመሥዋዕቱ ላይ በእሣት ያቃጠላችሁት ቁርባን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ከ..ጋር የለወሳችሁት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“አሥረኛ እጅ”ማለት አሥር አኩል ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ ክፍል ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ሁለት ሊትሮች”ወይም “የኢፍ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ”(ይሄ ሁለት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“አራተኛ እጅ”ማለት አራት አኩል ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ ክፍል ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“አንድ ሊትር”ወይም “የኢን መስፈሪያ አንድ አራተኛ”(ይሄ አንድ ሊትር ያህል ይሆናል) (ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“የተወቀጠ ዘይት”ወይም “ንፁህ ወይራ ዘይት”ይሄ የሚያመለክተው ከወይራ ተወቅጦ የወጣን ዘይት ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ያዘዘው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በእሣት ላይ ያቃጠላችሁት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“አራተኛ እጅ”ማለት አራት አኩል ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ ክፍል ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“አንድ ሊትር”ወይም “የኢን መስፈሪያ አንድ አራተኛ”(ይሄ አንድ ሊትር ያህል ይሆናል) (ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ዓረፍተ ነገር የሚያሣየው ከበግ ጠቦቱ ጋር አብሮ የሚቀርበውን የመጠጥ ቁርባን ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ጠንካራ የሆነ የመጠጥ ቁርባን ሊሆን የሚገባው ሲሆን በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ ልታፈስሱት ይገባል”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንተ ያቀረብከው ዓይነት”
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
“ከአሥር እጅ ሁለት እጅ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች ሁለቱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“አራት ሊትር ተኩል”ወይም “ከመሥፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ”(አራት ሊትር ተኩል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዘይት የለወሳችሁት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ብዙ ቁርባኖች አብሮ የመጠጥ ቁርባን እንዲቀርብ የሚጠይቁ ናቸው፡፡የዚህ ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“የመጠጥ ቁርባንም አብሮ ይቀርባል”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
“ከአሥር እጅ ሶስት እጅ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች ሶስቱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ስድስት ሊትር”ወይም “ከመሥፈሪያው ከአሥር እጅ ሶስት እጅ”(ስድስት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዘይት የለወሳችሁት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ኢፍ”የሚለው ቃል ግልፅ ቢሆንም የበለጠ ሊብራራ ግን ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ ሁለት እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ ሁለቱ ማለት ነው፡፡“አራት ተኩል ሊትር መልካም ዱቄት”ወይም “ሁለት አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን፤ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ አሥረኛ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች አንዱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ሁለት ሊትር”ወይም “ከመሥፈሪያው አሥረኛ እጅ”(ሁለት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በእሣት ላይ ያቃጠላችሁት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ግማሽ”ማለት ሁለት እኩል ከሆኑ ክፍሎች ውስጥ አንደኛው ክፍል ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ሁለት ሊትር”ወይም “የኢን ግማሽ”(ሁለት ሊትር)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢን አንድ ሶስተኛ”አንድ ሶስተኛ ማለት ሶስት እኩል ከሆኑ ክፍሎች ውስጥ አንደኛው ክፍል ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“1.2 ሊትር”ወይም “አንድ ሊትርና አንድ አምስተኛ ሊትር”(ሁለት ሊትር ማለት ነው)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“አራተኛ እጅ”ማለት አራት እኩል ከሆኑ ክፍሎች ውስጥ አንደኛው ክፍል ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“አንድ ሊትር”ወይም “የኢን አራተኛ እጅ”(አንድ ሊትር ያህል የሆነ)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ለኃጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፡፡(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
“በመጀሪያው ወር በወሩ በ14ኛው ቀን…በዚሁ ወር በ15ኛው ቀን” “ይሄ የሚያመለክተው የመጀመሪያውን የዕብራውያንን ወር ነው” (የዕብራውያን ወራትናተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“የእግዚአብሔርን ፋሲካ ልታከብሩት ይገባል”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዓል ልታደርጉ ይገባል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እርሾ የሌለው ቂጣ ልትበሉ ይገባል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የበዓሉን የመጀመሪያ ዕለት ነው፡፡ይሄ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“በበዓሉ በ1ኛው ቀን” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማክበር መሰብሰብ ይኖርባችኋል፡፡” “የተቀደሰ ጉባዔ”የሚለው ሐረግ ሰዎች ተሰብስበው እግዚአብሔርን ሲያመልኩ ማለት ነው፡፡እግዚአብሔርን ማምለክ የተቀደሰ ክስተት ነው፡፡
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
“የሚቃጠል”የሚለው ቃል በፍዝ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ይኖርባችኋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ከአሥር እጅ ሶስት እጅ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች ሶስቱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ስድስት ሊትር”ወይም “ከመሥፈሪያው ከአሥር እጅ ሶስት እጅ”(ስድስት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዘይት የለወሳችሁት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢፍ መሥፈሪያ መልካም ዱቄት”የሚለው ቃል በበፊቱ ሐረግ ግልፅ ተደርጓል፡፡ይሄ ሊደገምም ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ ሁለት እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ ሁለቱ ማለት ነው፡፡“አራት ተኩል ሊትር የሆነ መልካም ዱቄት”ወይም “ሁለት አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን፤ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“አንድ አሥረኛ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች አንዱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ሁለት ሊትር”ወይም “ከመሥፈሪያውአንድ አሥረኛ እጅ”(ሁለት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
x
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በየማለዳው እንዲቀርብለት ከሚፈልገው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እኔ እግዚአብሔር እዚህ በገለፅኩት መሠረት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የመብሉን ቁርባን በመሠዊያው ላይ ማቃጠል ይኖርባችኋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ለእግዚአብሔር እንደ ጣፋጭ ሽታ”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ልትሰውት ይገባል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማክበር መሰብሰብ ይኖርባችኋል፡፡” “የተቀደሰ ጉባዔ”የሚለው ሐረግ ሰዎች ተሰብስበው እግዚአብሔርን ሲያመልኩ ማለት ነው፡፡እግዚአብሔርን ማምለክ የተቀደሰ ክስተት ነው፡፡
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
በበኩራት ቀንሲባልዕለቱን ነው፡፡“ይሄ የሚያመለክተው በዓሉ በሚከበርበት ሣምንታት ውስጥ ለእግዚአብሔር የእህል ቁርባን የሚያቀርቡበትን ዕለት ነው፡፡
“እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማክበር መሰብሰብ ይኖርባችኋል፡፡” “የተቀደሰ ጉባዔ”የሚለው ሐረግ ሰዎች ተሰብስበው እግዚአብሔርን ሲያመልኩ ማለት ነው፡፡እግዚአብሔርን ማምለክ የተቀደሰ ሁኔታ ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዘይት የለወሳችሁት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢፍ መሥፈሪያ መልካም ዱቄት”የሚለው ቃል በበፊቱ ሐረግ ግልፅ ተደርጓል፡፡ይሄ ሊደገምም ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ ሁለት እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ ሁለቱ ማለት ነው፡፡“አራት ተኩል ሊትር የሆነ መልካም ዱቄት”ወይም “ሁለት አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን፤ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“ሶስት አሥረኛ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች ሶስቱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ስድስት ሊትር”ወይም “የኢፍ መሥፈሪያሶስት አሥረኛ”(ስድስት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢፍ መሥፈሪያ መልካም ዱቄት”የሚለው ቃል በበፊቱ ሐረግ ግልፅ ተደርጓል፡፡ይሄ ሊደገምም ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ ሁለት እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ ሁለቱ ማለት ነው፡፡“አራት ተኩል ሊትር የሆነ መልካም ዱቄት”ወይም “ሁለት አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን፤ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
“አንድ አሥረኛ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች አንዱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ሁለት ሊትር”ወይም “ከመሥፈሪያው አንድ አሥረኛ እጅ”(ሁለት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እናንተ በዘይት የምትለውሱት መልካም ዱቄት” (ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“መሥዋዕት ማቅረብ”የሚለው ሐረግ “መሰዋት”በሚለው ሥም ሊገለፅ ይችላል፡፡(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
“የእነርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እያንዳንዱ እንስሳ በሚሰዋበት ወቅት አብረው መቅረብ የሚገባቸውን የመጠጥ ቁርባኖችን ነው፡፡“ከአነርሱ ጋር አብረው የሚቀርቡት የመጠጥ ቁርባኖች”ወይም “የሚያጅቧቸው የመጠጥ ቁርባኖች”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
1 ”በሰባተኛው ወር፣ በወሩ በመጀመሪያው ቀን፣ ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፡፡ በዚያ ቀን የተለመደውን የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑ፡፡ ይህ ቀን መለከቶችን የምትነፉበት ቀን ይሆናል፡፡ 2 ለያህዌ መልካም መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና እያንዳንዳቸው ነውር የሌለባቸው ሰባት የአንድ አመት ጠቦቶች አቅርቡ፡፡ 3 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባናቸውን፣ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት አቅርቡ፤ ለወይፈኑ የኢፍ ሶስት አራተኛ፣ ለአውራ በጉ የኢፍ ሁለት አስረኛ 4 እና ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት አቅርቡ፡፡ 5 ለኃጢአት ማስተስረያ አንድ ወንድ ፍየል አቅርቡ፡፡ 6 በየወሩ መጀመሪያ ከምታደርጉት የተለየ የሚቃጠል መስዋዕትና አብሮ ከሚቀርበው የእህል ቁርባን በተጨማሪ፣ እነዚህን መስዋዕቶች በሰባተኛው ወር አድርጉ፡፡ እነዚህ ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት ከእህል ቁርባኑና የመጠጥ ቁርባኖች በተጨማሪ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ እነዚህን መስዋዕቶች ስታደርጉ፣ ለያህዌ በእሳት የሚዘጋጀውን መስዋዕት ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ የተደነገገውን ትፈጽማላችሁ፡፡ 7 በሰባተኛ ወር በአስረኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት ታዋርዳላችሁ በዕለቱ ሥራ አትሰሩም፡፡ 8 ለያህዌ ጣፋጭ ማዐዛ ያለው የሚቃጠል መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና የአንድ አመት ሰባት ወንድ ጠቦት በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ እያንዳንዳቸው ነውር የሌለባቸው ይሁኑ፡፡ 9 ከዚህ ጋር የእህል ቁርባን፤ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፣ ለወይፈኑ የኢፍ ሶስት አስረኛ፣ ለአውራ በጉ የኢፍ ሁለት አስረኛ፣ 10 እና ለሰባቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ አንድ አስረኛ ታቀርባላችሁ፡፡ 11 አንድ ወንድ ፍየል ለኃጢአት መስዋዕት ማቅረበ አለባችሁ፡፡ ይህ ለኃጢአት ማስተስረያ፣ ለመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና ከእነዚህ ጋር በሚቀርበው የመጠጥ መስዋእቶች በተጨማሪ የሚቀርብ ነው፡፡ 12 በሰባተኛው ወር አስራ አምስተኛው ቀን ያህዌን ለማክበር የተቀደሰ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ በዚያ ቀን የተለመደውን የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑም፣ ደግሞም ለሰባት ቀናት ክብረ በዓሉን ለእርሱ ታደርጋላችሁ፡፡ 13 በእሳት የተዘጋጀ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ የሚሆን የሚቃጠል መስዋዕት ማቅረብ አለባችሁ፡፡ አስራ ሶስት ወይፈኖች፣ እና የአንድ አመት ዕድሜ ያላቸው አስራ አራት ወንድ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ እያንዳንችው ነውር የሌለባቸው መሆን አለባቸው፡፡ 14 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባን፣ ለአስራ ሶስቱም ወይፈኖች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ ሶስት አስረኛ፣ ለሁለቱ አውራ በጎች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ ሁለት አስረኛ 15 እና ለአስራ አራቱ ጠቦቶች ለእያንዳንዳቸው የኢፍ አንድ አስረኛ፤ በዘይትየተለወሰ መልካም ዱቄት አቅርቡ፡፡ 16 ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕት፤ ከዚህ ጋር ከሚቀርበው የእህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 17 በስብሰባው ሁለተኛ ቀን፣ አስራ ሁለት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 18 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባን የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 19 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 20 በስብሰባው ሶስተኛ ቀን፣ አስራ አንድ ወይፈኖች ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 21 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሰረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 22 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮ ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 23 በስብሰባው አራተኛ ቀን፣ አስር ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 24 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች፣ ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 25 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 26 በስብሰባው አምስተኛ ቀን፣ ዘጠኝ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 27 ከእነዚህም ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ፣ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 28 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 29 በስበሰባው ስድስተኛ ቀን ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች፣ እና አስራ አራት ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 30 ከእነዚህ ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ለኮርማዎቹ፣ ለአውራ በጎቹ፣ እና ለጠቦቶቹ በተወሰነው ቁጥር መሠረት እንደ ትዕዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 31 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው እህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረበ አለባችሁ፡፡ 32 በስብሰባው ሰባተኛ ቀን፣ነውር የሌለባቸው፣ ሰባት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎች እና አስራ አራት የአንድ አመት ወንድ የበግ ጠቦቶች ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 33 ከወይፈኖች፣ከአውራ በጎች እና ጠቦቶች ጋር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባኖች ታቀርባላችሁ፡፡ 34 ከመደበኛው የሚቃጠል መስዋዕትና አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እንዲሁም ከመጠጥ ቁርባኑ በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 35 በስብሰባው ስምንተኛ ቀን፣ ሌላ የከበረ ጉባኤ ታደርጋላችሁ፡፡ በዚያን ቀን የተለመደ የዕለት ተግባራችሁን አታከናውኑም፡፡ 36 የሚቃጠል መስዋዕት ታደርጋላችሁ፣ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ያለው መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ እና ነውር ሌለባቸው ሰባት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ 37 ለወይፈኑ፣ ለአውራ በጉ፣ እና ለጠቦቶቹ የእህል ቁርባናቸውንና የመጠጥ ቀርባናቸውን በተወሰነው ቁጥር መሰረት እንደ ትእዛዙ ታቀርባላችሁ፡፡ 38 ከመደበኛ የሚቃጠል መስዋዕት፣ አብሮት ከሚቀርበው የእህል ቁርባን፣ እና የመጠጥ ቁርባን በተጨማሪ ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ማቅረብ አለባችሁ፡፡ 39 በተወሰነ ክብረ በዓላቶቻችሁ ለያህዌ የምታቀርቧቸው እነዚህ ናቸው፡፡ እነዚህም ከስለቶቻችሁና የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ናቸው፡፡ እነዚህን የሚቃጠሉ መስዋዕቶቻችሁ፣ የእህል ቁርባኖች፣ የመጠጥ ቁርባኖች፣ እና የህብረት መስዋዕቶች አድርጋችሁ አቅርቧቸው፡፡” 40 ሙሴ ያህዌ ለእስራኤል ሰዎች እንዲናገር ያዘዘውን ሁሉ ተናገረ፡፡
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
ይሄ የሚያመለክተው የዕብራውያንን ሰባተኛ ወር ነው፡፡“በ1ኛው ወር በ7ኛው ወር”(የዕብራውያን ወራትንናተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማክበር በአንድነት ተሰብሰቡ” “የተቀደሰ ጉባዔ”የሚለው ቃል ሰዎች እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚሰበሰቡበት ሁኔታ ማለት ነው፡፡እግዚአብሔርን ማምለክ የተቀደሰ ክስተት ነው፡፡
“እናንተ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እዚህ ላይ የእሥራኤልን ሕዝብ የሚወክሉትን ካህናትን ነው፡፡ካህናት አምልኮው እንዲጀመር መለከትን ይነፋሉ ወይም ማህረሰቡ በአንድነት እንዲሰባሰብ ለማድረግ፡፡“ካህናት መለከቶችን የሚነፉበት ቀን ይሆናል”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
ይሄ የሚያመለክተው እያንዳንዱ እንስሳ በሚሰዋበት ወቅት አብረው መቅረብ የሚገባቸውን የእህል ቁርባኖችን ነው፡፡“ከአነርሱ ጋር አብረው የሚቀርቡት የእህል ቁርባኖች”ወይም “የሚያጅቧቸው የእህል ቁርባኖች”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዘይት የለወሳችሁት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢፍ መሥፈሪያ መልካም ዱቄት”የሚለው ቃል በበፊቱ ሐረግ ግልፅ ተደርጓል፡፡ይሄ ሊደገምም ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ ሁለት እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ ሁለቱ ማለት ነው፡፡“አራት ተኩል ሊትር የሆነ መልካም ዱቄት”ወይም “ሁለት አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን፤ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“ሶስት አሥረኛ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች ሶስቱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ስድስት ሊትር”ወይም “የኢፍ መሥፈሪያ ሶስት አሥረኛ”(ስድስት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢፍ መሥፈሪያ መልካም ዱቄት”የሚለው ቃል በበፊቱ ሐረግ ግልፅ ተደርጓል፡፡ይሄ ሊደገምም ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ አንድ እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ማለት ነው፡፡“ሁለት ሊትር መልካም የሆነ ዱቄት”ወይም “አንድ አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“መሥዋዕት ማቅረብ”የሚለው ሐረግ “መሰዋት”በሚለው ሥም ሊገለፅ ይችላል፡፡(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
“በ7ኛ ወር…በእያንዳንዱ ወር በ1ኛው ቀን”“ወር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የዕብራውያንን የወር አቆጠጠር ነው፡፡(የዕብራውያን ወራትንናተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“በየወሩ፤የተለየ የሚቃጠል መሥዋዕት …ከእርሱ ጋር” ይሄ በየወሩ መጀመሪያ ላይ የሚደረግ መሥዋዕት ነው፡
ይሄ የሚያመለክተው ካህናቱ በየዕለቱ መሥጠት የሚገባቸውን መሥዋዕት ነው፡፡የእህል ቁርባኑና የመጠጡቁርባን ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡“ዘወትር የሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት አብረው ከሚቀርቡት ከእህል ቁርባንና ከመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእግዚብሔርን ትዕዛዝ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ”ወይም “እግዚአብሔር ያዘዘውን ትዕዛዝ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር ያቃጠላችሁት ቁርባን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
“በ7ኛ ወር…በእያንዳንዱ ወር በ1ኛው ቀን” “ወር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የዕብራውያንን የወር አቆጠጠር ነው፡፡(የዕብራውያን ወራትንናተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማክበር በአንድነት ተሰብሰቡ” “የተቀደሰ ጉባዔ”የሚለው ቃል ሰዎች እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚሰበሰቡበት ሁኔታ ማለት ነው፡፡እግዚአብሔርን ማምለክ የተቀደሰ ክስተት ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዘይት የለወሳችሁት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሶስት አሥረኛ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች ሶስቱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ስድስት ሊትር”ወይም “የኢፍ መሥፈሪያ ሶስት አሥረኛ”(ስድስት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢፍ መሥፈሪያ መልካም ዱቄት”የሚለው ቃል በበፊቱ ሐረግ ግልፅ ተደርጓል፡፡ይሄ ሊደገምም ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ ሁለት እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ ሁለቱ ማለት ነው፡፡“አራት ተኩል ሊትር የሆነ መልካም ዱቄት”ወይም “ሁለት አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን፤ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢፍ መሥፈሪያ መልካም ዱቄት”የሚለው ቃል በበፊቱ ሐረግ ግልፅ ተደርጓል፡፡ይሄ ሊደገምም ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ አንድ እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ማለት ነው፡፡“ሁለት ሊትር መልካም የሆነ ዱቄት”ወይም “አንድ አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“መሥዋዕት ማቅረብ”የሚለው ሐረግ “መሰዋት”በሚለው ሥም ሊገለፅ ይችላል፡፡(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
የእህሉ ቁርባን ከሚቃጠለው ቁርባን ጋር መቅረብ ነበረበት፡፡የመጠጥ ቁርባኑ ከኃጢአት መሥዋዕቱና ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት፡፡“አብረው ከሚቀርቡት የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
“በ7ኛ ወር…በ15ኛው ቀን” “ወር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የዕብራውያንን የወር አቆጠጠር ነው፡፡(የዕብራውያን ወራትንናተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማክበር በአንድነት ተሰብሰቡ” “የተቀደሰ ጉባዔ”የሚለው ቃል ሰዎች እግዚአብሔርን ለማምለክ የሚሰበሰቡበት ሥርዓት ማለት ነው፡፡እግዚአብሔርን ማምለክ የተቀደሰ ሁኔታ ነው፡፡
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“መጠበቅ”የሚለው ቃል መከታተል ወይም ማክበር ማለት ነው፡፡“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው፡፡“በዓሉን ለእግዚአብሔር መጠበቅ ይኖርባችኋል”ወይም “በዐሉን ለእግዚአብሔር ልታከብሩት ይገባል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በመሠዊያ ላይ ልታቃጥሉት ይገባል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“14 ወይፈኖች፤2 አውራ በጎች፤14 የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዘይት የለወሳችሁት መልካም ዱቄት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሶስት አሥረኛ”ማለት አሥር እኩል ከሆኑ ክፍሎች ሶስቱ ማለት ነው፡፡ይሄ ዘመናዊ በሆነ መለኪያ ሊፃፍ ይችላል፡፡“ስድስት ሊትር”ወይም “የኢፍ መሥፈሪያ ሶስት አሥረኛ”(ስድስት ሊትር ያህል ይሆናል)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢፍ መሥፈሪያ መልካም ዱቄት”የሚለው ቃል በበፊቱ ሐረግ ግልፅ ተደርጓል፡፡ይሄ ሊደገምም ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ ሁለት እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ ሁለቱ ማለት ነው፡፡“አራት ተኩል ሊትር የሆነ መልካም ዱቄት”ወይም “ሁለት አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን፤ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“የኢፍ መሥፈሪያ መልካም ዱቄት”የሚለው ቃል በበፊቱ ሐረግ ግልፅ ተደርጓል፡፡ይሄ ሊደገምም ይችላል፡፡“ከአሥር እጅ አንድ እጅ”ማለት እኩል ከሆኑ አሥር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ማለት ነው፡፡“ሁለት ሊትር መልካም የሆነ ዱቄት”ወይም “አንድ አሥረኛ የኢፍ መሥፈሪያ”(4.5 ያህል የሚሆን)(ክፍልፋዮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ሚዛን የሚለውን ይመልከቱ)
“መሥዋዕት ማቅረብ”የሚለው ሐረግ “መሰዋት”በሚለው ሥም ሊገለፅ ይችላል፡፡(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
የእህሉ ቁርባኑና የመጠጥ ቁርባኑ ዘወትር ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት፡፡
“በበዓሉ 2ተኛ ቀን” እዚህ ላይ “ጉባዔ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በበዓሉ ወቅት ያሉትን ሣምንታት ነው፡፡(ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“14 ወይፈኖች፤2 አውራ በጎች፤14 የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የእህሉ ቁርባን ከሚቃጠለው ቁርባን ጋር መቅረብ ነበረበት፡፡የመጠጥ ቁርባኑ ከኃጢአት መሥዋዕቱና ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት፡፡“አብረው ከሚቀርቡት የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
“በበዓሉ 3ተኛ ቀን” እዚህ ላይ “ጉባዔ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በበዓሉ ወቅት ያሉትን ሣምንታት ነው፡፡(ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“11 ወይፈኖች፤2 አውራ በጎች፤14 የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የእህሉ ቁርባን ከሚቃጠለው ቁርባን ጋር መቅረብ ነበረበት፡፡የመጠጥ ቁርባኑ ከኃጢአት መሥዋዕቱና ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት፡፡“አብረው ከሚቀርቡት የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
“በበዓሉ 4ተኛ ቀን” እዚህ ላይ “ጉባዔ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በበዓሉ ወቅት ያሉትን ሣምንታት ነው፡፡(ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“14 ተባት ጠቦቶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የእህሉ ቁርባን ከሚቃጠለው ቁርባን ጋር መቅረብ ነበረበት፡፡የመጠጥ ቁርባኑ ከኃጢአት መሥዋዕቱና ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት፡፡“አብረው ከሚቀርቡት የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
“በበዓሉ 5ተኛ ቀን” እዚህ ላይ “ጉባዔ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በበዓሉ ወቅት ያሉትን ሣምንታት ነው፡፡(ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“14 ተባት ጠቦቶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የእህሉ ቁርባን ከሚቃጠለው ቁርባን ጋር መቅረብ ነበረበት፡፡የመጠጥ ቁርባኑ ከኃጢአት መሥዋዕቱና ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት፡፡“አብረው ከሚቀርቡት የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
“በበዓሉ 6ተኛ ቀን” እዚህ ላይ “ጉባዔ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በበዓሉ ወቅት ያሉትን ሣምንታት ነው፡፡(ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“14 ተባት ጠቦቶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የእህሉ ቁርባን ከሚቃጠለው ቁርባን ጋር መቅረብ ነበረበት፡፡የመጠጥ ቁርባኑ ከኃጢአት መሥዋዕቱና ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት፡፡“አብረው ከሚቀርቡት የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
“በበዓሉ 7ተኛ ቀን” እዚህ ላይ “ጉባዔ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በበዓሉ ወቅት ያሉትን ሣምንታት ነው፡፡(ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“14 ተባት ጠቦቶች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት”
የእህሉ ቁርባን ከሚቃጠለው ቁርባን ጋር መቅረብ ነበረበት፡፡የመጠጥ ቁርባኑ ከኃጢአት መሥዋዕቱና ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት፡፡“አብረው ከሚቀርቡት የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሕዝቡ ማድረግ ያለበትን ነገር እግዚአብሔር መንገሩን እንደቀጠለ ነው፡፡
“ስምንተኛው”የሚለው ቃል ስምንት ለሚለው ተከታታይ ቁጥር ነው፡፡ (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔርን ለማምለክ እንደገና ተሰብሰቡ”ይሄ ከመጀመሪው ቀን በዓል ጋር የሚመሳሰል ሌላ ጉባዔ ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በመሠዊያው ላይ ማቃጠል ይኖርባችኋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ መሥዋዕቶች መቅረብ የሚኖርባቸው ከወይፈን፤ከበግ ጠቦትና ከአውራ በግ ጋር ነበር፡፡”የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የእህሉ ቁርባን ከሚቃጠለው ቁርባን ጋር መቅረብ ነበረበት፡፡የመጠጥ ቁርባኑ ከኃጢአት መሥዋዕቱና ከሚቃጠለው መሥዋዕቱ ጋር አብሮ መቅረብ ነበረበት፡፡“አብረው ከሚቀርቡት የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን ጋር”(ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)
“የምታቀርቧቸው መሥዋዕቶች እነዚህ ናቸው”
“በዕቅድ የተያዙ በዓላት”እነዚህ በዓላት በተያዘላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት በቋሚነት የሚከናወኑ ናቸው፡፡“በተቆረጠላቸው”ማለት“በተመደበላቸው”ወይም“አስቀድሞ በተወሰነላቸው”ጊዜ ማለት ነው፡፡
1 ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ የጎሳ መሪዎች እንዲህ አላቸው፣ “ያህዌ ያዘዘው ይህን ነው፡፡ 2 ማንም ሰው ለያህዌ ስዕለት ሲሳል፣ ወይም በቃል ኪዳን ራሱን በመሀላ ሲያስር፣ ቃሉን ማፍረስ የለበትም፡፡ ከአፉ የወጣውን ማናቸውንም ነገር ለማድረግ ቃልኪዳኑን መጠበቅ አለበት፡፡ 3 አንዲት ወጣት ሴት በአባቷ ቤት እያለች ለያህዌ ብትሳልና በመሀላ ራሷን ብታስር፣ 4 አባቷም ስዕለቷንና ራሷን ያሰረችበትን መሀላ ቢሰማ፣ እርሱም እርሷን ለመመለስ አንዳች ነገር ባይናገር መሀላዎቿ ሁሉ መፈፀም አለባቸው፡፡ ራሷን ያሰረችባቸው ቃልኪዳኖች ሁሉ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡ 5 ነገር ግን አባቷ ስለ ስዕለቷና ስለገባችው ቃል ኪዳን ሰምቶ ምንም ነገር ባይነግራት በራሷ ላይ የወሰደቻቸው የገባቻቸው መሀላዎችና ቃል ኪዳኖች መፈጸም አለባቸው፡፡ 6 ሆኖም ግን፣ አባቷ የገባቻቸውን መሀላዎች ሁሉና የከበሩ ቃል ኪዳኖቿን ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ነገር ቢሰማ፣ ደግሞም በዚያው ቀን ማድረግ ያለበትን ቢነግራት መሀላዋን ለመፈጸም አትገደድም፡፡ ያህዌ ይቅር ይላታል ምክንያቱም አባቷ ማድረግ ያለባትን ነግሯታል፡፡ 7 እነዚያ መሀላዎች እያሉባት ባል ብታገባ ወይም በችኮላ መሀላ ብታደርግና ራሷን ግዴታ ውስጥ ብታስገባ እነዚያ ግዴታዎች መፈጸም አለባቸው፡፡ 8 ነገር ግን ባሏ በዚያው ቀን ሰምቶ ቢከለክላት የገባቸውን መሀላና በችኮላ ራሷን ያሰረችበትን መሀላዋን ያስቀራል፡፡ ያህዌ ከዚህ ነጻ ያደርጋታል፡፡ 9 ባሏ የሞተባት ወይም ከባሏ የተፋታች ሴት ግን ራሷን የሰራችባቸው ነገሮች ሁሉ ተፈፃሚ ይሆኑባታል፡፡ 10 ከባሏ ቤተሰቦች ጋር ያለች ሴት ብትሳል ራሷን በቃል ኪዳን መሀላ ብታስር፣ 11 እና ባልዋ ሰምቶ ምንም ነገር ባይነግራት ስእለቷን ባያስቀር፣ ስዕለቶቿ ሁሉ መፈጸም አለባቸው፡፡ ራሷን ያሰረችባቸው ቃልኪዳኖች ሁሉ መፈጸም አለባቸው፡፡ 12 ነገር ግን ባሏ ስለ ስዕለቶቿ በሰማ ቀን እንዲቀሩ ካደረገ፣ ስለ ስዕለቶቿ ወይም ቃልኪዳኖቿ ከከንፈሯ የወጡ ነገሮች ሁሉ የግዴታ መፈጸም አይኖርባቸውም፡፡ ባልዋ አስቀርቷቸዋል፡፡ ያህዌ ነጻ ያደርጋታል፡፤ 13 አንዲት ሴት የገባችውን እያንዳንዱን መሀላ ወይም ስእለት እንድታጥፍ የሚያደርጋትን አንዳች ነገር በባሏ ሊጸና ወይም ሊሻር ይችላል፡፡ 14 ነገር ግን ቀናት ሲያልፉ ባሏ አንዳች ካልነገራት፣ ስዕቶቿን ሁሉ እና ቃል የገባቻቸውን ነገሮች ያፀናባታል፡፡ ስዕቶቿንና መሀላዎቿን የሚያፀናባት ስለእነዚህ በሰማበት ጊዜ ምንም ስላልነገራት ነው፡፡ 15 ባሏ የሚስቱን ስዕለት ከሰማ ከረጅም ጊዜ በኋላ ሊሽር ቢሞክር፣ ስለእርሷ ኃጢአት ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡” 16 ያህዌ ሙሴ እንዲያውጃቸው የሰጠው ቋሚ መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፡፡ በአንድ ወንድና በሚስቱ መሀል፣ እንዲሁም በአባትና በወጣትነቷ በአባቷ ቤት ስለምትኖር ሴት ልጁ ያህዌ የሰጠው ቋሚ መመሪያ ይህ ነው፡፡
እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በጋራ እንዲቀርቡ የተደረጉት ስለ ስእለትና ስለ መሐላ አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እዚህ ላይ የሚናገረው አንድ ሰው አንድ ነገር ለማድረግ ቃል የመግባቱን ጉዳይ አስመልክቶ ቢሆንም የሚገባው ቃል ቁሣቁስ ይመስል ራሱ ላይ እንደሚያስረው ዓይነት አድርጎ ያቀርበዋል፡፡“አንድ ነገር ለመፈፀም ራስን መሥጠት”ወይም “አንድን ነገር ለመፈፀም ቃል መግባት” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን በጋራ እንዲቀርቡ የተደረጉት የገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረግ እንደሚኖርበት አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“ቃሉን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰውዬውን መሐላና ቃል ኪዳን መግባት ነው፡፡ሙሴ እነዚሀን ነገሮች ተግባራዊ አለማድረግን ልክ አንድን ዕቃ ከመስበር ጋር አመሳስሎ ነው የሚናገረው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“አፍ”የሚለው ቃል ሰውዬው የሚናገረውን ነገር ለመግለፅ የዋለ ነው፡፡“አደርገዋለሁ የሚለውን ነገር ሁሉ ማድረግ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ አንዲት ሴት ቃል የመግባቷን ጉዳይ ልክ ራሷን በአንድነገር እንደምታስረው ዓይነት አድርጎ ነው ያቀረበው፡፡“የገባቸውን ቃል ለመፈፀም ራሷን ሰጠች”ወይም “አንድ ነገር ለመፈፀም ቃል ገባች”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡አፅንኦት የሚሰጠው የገባችውን ቃል በሚመለከት ነው፡፡“መሐላው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ አንዲት ሴት ቃል የገባቸውን ነገር ለመፈፀም ስትል የምታደርገውን መሠጠት ልክ ከሰውነቷጋር እንዳሰረችው ቁሣቁስ አድርጎ ነው የሚያቀርበው፡፡“የገባቸውን ቃል ለመፈፀም ራሷን ሰጠች”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ያለችውን ነገር ብትሰረዘው”
እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን መሐላዋን ሁሉ መጠበቅ እንዳለባት አፅነዖት የሚሰጥ ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን መሐላዋ የፀና እንደሆነና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባት የሚያስረዳ ነው፡፡“ተግባራዊ እንድታደርገው ትገደዳለች”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሐረጎች በጣም የተመሳሰለ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡ቃል የገባቸውን ነገር አጥብቀው የሚያሳስቡ ናቸው፡፡“መሐላዋን”(ሁለት ተመሳሳይ የሆነ ገፅታ ያላቸው የሚለውን ይመልክቱ)
እዚህ ላይ ሴትዬዋ መሐላዋን ለመፈፀም ራሷን መሥጠቷን ልክ መሐላውን ሰውነቷ ላይ እንደምታደርገው ልብስ ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ራሷን የሰጠችበት”ወይም “ቃል የገባችው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን መሐላዋ የፀና እንደሆነና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባት የሚያስረዳ ነው፡፡ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 30፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ተግባራዊ እንድታደርገው ትገደዳለች”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ አንዲት ሴት ቃል የገባቸውን ነገር ለመፈፀም ስትል የምታደርገውን መሠጠት ልክ ከሰውነቷጋር እንዳሰረችው ቁሣቁስ አድርጎ ነው የሚያቀርበው፡፡“ ረጋ ባለ መንፈስ ቃል የገባችውን ነገር ለመፈፀም የምታደርገው መሠጠት”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ የሴትዋን ቃል ዝም ማለቱን ልክ አንድ ባለሥልጣን በሥልጣኑ እንደሚከለክላት ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን መሐላዋ የፀና እንደማይሆንና ተግባራዊ ማድረግ እንደማይጠበቅባት የሚያስረዳ ነው፡፡ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 30፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ተግባራዊ እንድታደርገው አትገደድ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው መሐላዋን ባትፈፀምም እንኳን እግዚአብሔር ይቅር ያላት መሆኑን ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“መሐላዋን ባትፈፅምም እግዚአብሔር ይቅር ይላታል”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡መሐላዋ የፀና እንደማይሆንና ተግባራዊ ማድረግ እንደማይጠበቅባት የሚያስረዳ ነው፡፡ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 30፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ተግባራዊ እንድታደርገው አትገደድ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በአግባቡ ሳይታሰብ የሚደረግ ነገር፡፡
“ግዴታዎች”የሚለው ቃል “ማስገደድ”በሚለው ሥም ሊገለፅ ይችላል፡፡“ራስዋን ግዴታዎች ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች”(አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)
“ያደረገችው መሐላ…ማለትም በችኮላ የተናገረችው ንግግር” እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች የሚያመለክቱት አንድን ነገር ነው፡፡ሁለተኛው ሐረግ ሴትዬዋ ያደረገችውን መሐላ የሚገልፅ ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
“ችኩል አነጋገር”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በችኮላ የገባችውን የተስፋ ቃል ነው፡፡እዚህ ላይ “አንደበቷ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራሷን ሴትዬዋን ነው፡፡አንደበቷ ከምትናገረው ነገር ጋር የተያያዘ በመሆኑ “አንደበቷ”በሚለው ቃል ተወክላለች፡፡“በችኮላ የተናገረቻቸው ነገሮች” ወይም“በችኮላ ቃል መግባቷ”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ አንዲት ሴት ቃል የገባቸውን ነገር ለመፈፀም ስትል የምታደርገውን መሠጠት ልክ ከሰውነቷ ጋር እንዳሰረችው ቁሣቁስ አድርጎ ነው የሚያቀርበው፡፡“ ረጋ ባለ መንፈስ ቃል የገባችውን ነገር ለመፈፀም የምታደርገው መሠጠት”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ አንዲት ሴት ቃል የገባችውን ነገር ባትፈፅምም እግዚአብሔር ይቅር እንደሚላት ለመግለፅ ከታሰረችበት ነገር እንደምትለቀቅ ዓይነት አድርጎ አቅርቦታል፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ይቅር ይላታል” “የገባችውን ቃል ባትፈፅምም እግዚአብሔር ይቅር ይላታል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ))
ሙሴ እግዚአብሔር ያዘዘውን ነገር ለነገድ መሪዎች መናገሩን ይቀጥላል፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንድ ሰው የፈታት ሴት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ አንዲት ሴት ቃል የገባቸውን ነገር ለመፈፀም ስትል የምታደርገውን መሠጠት ልክ ከሰውነቷ ጋር እንዳሰረችው ቁሣቁስ አድርጎ ነው የሚያቀርበው፡፡“ቃል የገባችውን ነገር ለመፈፀም የምታደርገው መሠጠት”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን መሐላዋ የፀና እንደሆነና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባት የሚያስረዳ ነው፡፡ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 30፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ተግባራዊ እንድታደርገው ትገደዳለች”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚመለከተው ያገቡ ሴቶችን ነው፡፡የዚሀን ሃሣብ የበለጠ ልታብራሩት ትችላላችሁ፡፡“ያገባች ሴት ስእለት ብትሳል”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“መተግበሩ ግዴታ ይሆናል”የሚለው ቃል የሚፀናና እርሱን ለመፈፀም ትገደዳለች ማለት ነውየዚህን ተመሳሳይ ሐረግ በኦሪት ዘኁልቁ 30፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ከዚያም መሐላዋን ሁሉ ተግበራዊ ማድረግ ይኖርባታል….መፈፀም ይኖርባታል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በመሠረቱ እነዚሀ ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ተደጋገመው የቀረቡት ለጉዳዩ አፅንዖት ለመሥጠት ሲሆን ተቀናጀተውም ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡“ስእለቷና መሐላዋ ሁሉ የፀና መሆን ይኖርበታል” (ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሴትዬዋ የተናገረችው ንግግር ከከንፈሯ እንደወጣ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ከዚያ በኋላ የተናገረችው ነገር ሁሉ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን መሐላዋ የፀና እንደማይሆንና ተግባራዊ ማድረግ እንደማይጠበቅባት የሚያስረዳ ነው፡፡ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 30፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ተግባራዊ እንድታደርገው አትገደድ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ አንዲት ሴት ቃል የገባችውን ነገር ባትፈፅምም እግዚአብሔር ይቅር እንደሚላት ለመግለፅ ከታሰረችበት ነገር እንደምትለቀቅ ዓይነት አድርጎ አቅርቦታል፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ይቅር ይላታል” “የገባችውን ቃል ባትፈፅምም እግዚአብሔር ይቅር ይላታል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውንና (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ))
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የአንዲት ሴት ባል ራሰዋን ያሰረችበትን ማንኛውንም ነገር ማለትም ስእለት ወይም መሐላ ማጽናት ወይም ማፍረስ የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ ሙሴ አንዲት ሴት ቃል የገባችውን ነገር ለመፈፀም ስትል የምታደርገውን መሠጠት ልክ ከሰውነቷ ጋር እንዳሰረችው ቁሣቁስ አድርጎ ነው የሚያቀርበው፡፡“ቃል የገባችውን ነገር ለመፈፀም የምታደርገው መሠጠት”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ አንዲት ሴት የምትገባቸው ቃል ኪዳኖች አካሏን እንደሚያስሩ ነገሮች አድርጎ አቅርቧቸዋል፡፡“ግዴታዎች” “ቃል ኪዳኖች”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ግልፅ የሆነውን ይህንን መረጃ የበለጠ ልታብራሩት ትችላላችሁ፡፡“ጉዳዮቹን አስመልክቶ ምንም ነገር ስላልተናገረ”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውን ይመልከቱ)
ስእለቷን የማትፈፀም ከሆነ በእርሷ ምትክ ኃጢአቷን ይሸከማል ማለት ነው፡፡የዚህ ዓረፍተ ነገር ሙሉ ሃሣብ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡“ስእለቷን ባትፈፀም በኃጢአቷ ጥፋተኛ አትባልም፡፡እርሱ ግን በእርሷ ምትክ ጥፋተኛ የሚሆን ይሆናል፡፡”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “የእስራኤል ህዝብ ምድያማውያንን ይበቀሉ፡፡ ያን ካደረግህ በኋላ፣ ወደ ወገኖችህ ትከማቻለህ፡፡” 3 ስለዚህም ሙሴ ለህዝቡ እንዲህ አለ፣ “በምድያማውያን ላይ የያህዌን በቀል ይፈጽሙ ዘንድ ከወንዶቻችሁ አንዳንዶቹን ወደ ጦርነት እንዲወጡ አስታጥቋቸው፡፡ 4 እያንዳንዱ በእስራኤል ውስጥ ያለ ጎሳ ለጦርነት አንድ ሺህ ወታደሮችን መላክ አለበት፡፡” 5 ስለዚህ ከእስራኤል ብዙ ሺህ ወንዶች መሀል ከእያንዳንዱ ጎሳ አንድ ሺህ ሰው ለጦርነት ቀረበ፣ በጠቅላላው አስራ ሁለት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡ 6 ከዚያ ሙሴ ከየጎሳው አንድ ሺህ ሰዎችን ከካህኑ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሃስ ጋር እና ከተቀደሰው ስፍራ ከጥቂት ቁሳቁሶችና እንዲሁም ምልክቶችን ለማሰማት በእጁ ያሉትን መለከቶች አስይዞ ወደ ጦርነት ላካቸው፡፡ 7 እነርሱም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ከምድያማውያን ጋር ተዋጉ፡፡ ሰዎቹን ሁሉ ፈጇቸው፡፡ 8 የምድያምን ነገስታት ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር ሑርን እና እና ሪባን ከተቀሩት ጋር በሰይፍ ገደሏቸው፡፡ 9 የእስራኤል ጦር፤ የምድያምን ሴቶች፣ ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውን ሁሉ፣ መንጋዎቻቸውን እና ንብረቶቻቸውን ሁሉ ምርኮ አደረጉ፡፡ እዚህን ሁሉ ዘርፈው ወሰዱ፡፡ 10 የሚኖሩባቸውን ከተሞችና ሰፈሮች ሁሉ አቃጠሉ፡፡ 11 የሰውና እንስሳት ምርኮዎቻቸውንና እስረኞችን ወሰዱ፡፡ 12 እስረኞችን፣ የዘረፉትን፣ እና የያዙትን ነገሮች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛር፣ እና ወደ እስራኤል ማህበረሰብ አመጡ፡፡ እነርሱም እነዚህን ኢያሪኮ አጠገብ ዮርዳስ፣ በሞአብ ሜዳ ላይ ወደ ሚገኘው ሰፈር አመጡ፡፡ 13 ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛር፣ እና የማህበረሰቡ መሪዎች በሙሉ ሊቀበሏቸው ከሰፈር ወጡ፡፡ 14 ሙሴ ግን ከጦርነት በተመለሱት በጦሩ መኮንኖች፣ በሻለቃዎችና በመቶ አለቆች ላይ ተቆጥቶ ነበር፡፡ 15 ሙሴ መኮንኖቹን እንዲህ አላቸው፣ “ሴቶቹ ሁሉ በህይወት እንዲኖሩ ተዋችኋቸውን?” 16 እነዚህ ሴቶች በበለዓም ምክር፣ የእስራኤል ህዝብ በያህዌ ላይ በፌጎር ኃጢአት እንዲሰራና መቅሰፍት እንዲወርድበት ያደረጉ ናቸው፡፡ 17 ስለዚህ አሁን፣ ትናንሾቹን ወንዶች ሁሉ ግደሉ፣ ከወንድ ጋር የተኙ ሴቶችን ሁሉ ግደሉ፡፡ 18 ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁትን ወጣት ልጃገረዶች ግን ለራሳችሁ ውሰዱ፡፡ 19 ከእስራኤል ሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት መቆየት አለባችሁ፡፡ ማንንም ሰው የገደላችሁ ሁሉና ወይም የሞተ ሰው የነካችሁ ሁሉ በሶስተኛው ቀንና በሰባተናው ቀን ራሳችሁን ማንጻት አለባችሁ፡፡ እናንተና ምርኮኞቻችሁ መንጻት አለባችሁ፡፡ 20 ልብሶቻችሁን አንጹ፣ ከእንስሳት ቆዳ እና ከፍየል ፀጉር የተሰሩ ማናቸውንም ነገሮች፣ እንዲሁም ከእንጨት የተሰሩ ነገሮችን ሁሉ አንጹ፡፡” 21 ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነት የሄዱትን ወታደሮች እንዲህ አላቸው፣ “ይህ ያህዌ ለሙሴ የሰጠው የተደገነገገ ህግ ነው፡ 22 ወርቁ፣ ብሩ፣ ነሀሱ፣ ብረቱ፣ ቆርቆሮውና እርሳሱ 23 እና ማናቸውም እሳት የሚቋቋምን ነገር በእሳት ውስጥ አሳልፉት እናም የተቀደሰ ይሆናል፡፡ እነዚያን ነገሮች በማንጻት ውሃ አንጹዋቸው፡፡ በእሳት ውስጥ ማለፍ የማይችለውን ማናቸውንም ነገር በውሃ አንጹ፡፡ 24 እናም ልብሶችሁን በሰባተኛው ቀን እጠቡ፣ ከዚያም የተቀደሳችሁ ትሆናላች፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ እስራኤል ሰፈር መግባት ትችላላችሁ፡፡” 25 ከዚያም ያህዌ ሙሴን እንደዚህ አለው፣ 26 ”ሰዎችም ይሁኑ እንስሳት፣ የተማረኩትንና የተወሰዱትን ነገሮች ሁሉ ቁጠሩ፡፡ አንተ፣ ካህኑ አልዓዛር፣ እና የማህበረሰቡ መሪዎች እንዲሁም የጎሳ አባቶች 27 ምርኮዎቹን ለሁለት ክፍል ክፈሏቸው፡፡ ለጦርነት በወጡ ወታደሮችና በተቀረው ማህበረሰብ መሃል ምርኮውን አከፋፍሉ፡፡ 28 ከዚያ ወደ ጦርነት ከወጡ ወታደሮች ለእኔ የሚሰጥ ግብር ጣል፡፡ ይህ ግብር ከሰዎችም ይሁን፣ ከቀንድ ከብት፣ ከአህዮች፣ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ከየአምስት መቶው አንዱ ይሁን፡፡ 29 ይህን ግብር የእነርሱ ከሆነው ከከፊሉ ድርሻቸው ወስደህ ለእኔ የሚቀርብ ስጦታ እንዲሆን ለካህኑ አልዓዛር ስጠው፡፡ 30 ደግሞም ከከፊሉ የእስራኤል ህዝብ ድርሻ ከሆነው ሰዎች፣ ከቀንድ ከብቶች፣ ከአህዮች፣ ከበጎች ከፍየሎች፣ ከየሀምሳው መሀል አንዱን ወሰድ፡፡ እነዚህን ማደሪያዬን ለሚያገለግሉት ለሌዋውያን ስጣቸው፡፡” 31 ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ፡፡ 32 ወታደሮቹ በዝብዘው የወሰዱት ምርኮ 675000 በጎች፣ 33 ሰባሁለት ሺህ በሬዎች፣ 34 ስልሳ አንድ ሺህ አህዮች፣ 35 እና ሰላሳ ሁለት ሺህ ከወንድ ጋር ያልተኙ ሴቶች ነበሩ፡፡ 36 ለወታደሮች የተጠበቀላቸው ግማሹ 337000 በጎች ነበሩ፡፡ 37 ከዚህ ውስጥ የያህዌ ድርሻ 675 በጎች ነበር፡፡ 38 በሬዎቹ ሰላሳ ስድስት ሺህ ሲሆኑ የያህዌ ግብር 72 ነበር፡፡ 39 አህዮች 30500 ነበሩ፣ ከዚህ ውስጥ የያህዌ ድርሻ 61 ነበር፡፡ 40 ሰዎቹ አስራ ስድስት ሺ ሴቶች ነበሩ፣ ከዚህ ውስጥ ለያህዌ የተሰጠው ግብር 32 ነበር፡፡ 41 ሙሴ ለያህዌ የሚቀርቡትን ስጦታዎች ግብር ወሰደ፡፡ እርሱም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ለካህኑ አልዓዛር ይህንን ሰጠ፡፡ 42 ሙሴ ወደ ጦርት ከሄዱ ወታደሮች የወሰደውን የእስራኤል የሆነውን ግማሽ ምርኮ በተመለከተ፤ 43 የማህበረሰቡ ከምርኮ ግማሹ 337500 በጎች፣ 44 ሰላሳ ስድስት ሺህ በሬዎች፣ 45 ሰላሳ ሺ አምስት መቶ አህዮች፣ 46 እና አስራ ስድስት ሺ ሴቶች ነበሩ፡፡ 47 ከእስራኤል ህዝብ ግማሽ ከሆነ ድርሻው፣ ሙሴ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት ከየአምሳው መሀል አንድ ወሰደ፡፡ እርሱም ያህዌ እንዲያደርገው ባዘዘው መሠረት የያህዌን ማደሪያ ለሚያገለግሉ ለሌዋውያን እነዚህን ሰጠ፡፡ 48 ከዚያ የሰራዊቱ መኮንኖች፣ የሻለቃ አዛዦች እና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ መጡ፡፡ 49 እንዲህም አሉ፣ “ባሮችህ በእኛ ስር ያሉትን ወታደሮች ቆጠርን፣ አንድ ሰው እንኳን አልጎደለም፡፡ 50 እኛ የያህዌን ስጦታ አምጥተናል፣ እያንዳንዱ ሰው ያገኘውን፣ የወርቅ ዕቃዎች፣ አልቦዎችና አንባሮች፣ የጣት ቀለበቶች፣ የጆሮ ጉትቻዎች፣ እና የአንገት ሀብሎች ማስተስረያ እንደሆነን በያህዌ ፊት አምጥተናል፡፡” 51 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ወርቁንና የእጁ ጥበብ ውጤት የሆኑትን የጌጥ ዕቃዎች ሁሉ ከእነርሱ ተቀበሉ፡፡ 52 ለያህዌ ያቀረቧቸው የወርቅ ስጦታዎች ሁሉ ከሻለቃዎችና ከመቶ አለቃዎች የተቀበሏቸው ስጦታዎች ክብደታቸው 16750 ሰቅሎቸ ነበር፡፡ 53 እያንዳንዱ ወታደርና እያንዳንዱ ሰው ከምርኮው ለራሱ ወስዷል፡፡ 54 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ወርቁን ወሰዱ፡፡ ለያህዌ የእስራኤል ህዝብ ማስታወሻ አድርገው ወርቁን ወደ መገናኛው ድንኳን አስገቡት፡፡
ምድያማውያን እሥራኤላውያን ጣኦት እንዲያመልኩ በመገፋፋታቸው ምክኒያት እግዚአብሔር ሊቀጣቸው ነው፡፡
በመሠረቱ እነዚህ ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡ይሄ ጨዋ በሆነ አነገገር ቡሴ የመሞቻው ጊዜ መሆኑንና መንፈሱ አባቶቹ ወዳሉበት የሚሄድ መሆኑን የሚገልፅ ነው፡፡ (ተመሳሳይነት የሚለውንና ሥርዓት የሌለውን አነጋገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
“ከሰዎችህ መካከል ለተወሰኑት ሰዎች መሣሪያ አስታጥቃቸው”
“ሄደህ ከምድያማውያን ጋር በመዋጋት ላደረጉት ነገር ቅጣትን ሥጣቸው”
“1000…2000”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ከእሥራኤል አንድ ሺህ ወንዶች”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ከእያንዳንዱ ነገድ 1000 ሰዎች ለጦርነት ተላኩ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የሌዊን ነገድ ጨምሮ 12ቱም ነገዶች ሰዎችን ላኩ፡፡እያንዳንዱ ነገድ 1000 ለጦርነት የሚሰለፉ ሰዎችን ላከ፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የምድያማውያን ነገሥታት ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ቢኦር የበለዓም አባት ነበር፡፡ይህንን በዘኁልቁ 22፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
“የምድያማውያንን ንብረቶች የራሳችው አደረጉት”
“እሥራኤላውያን ሠራዊቶች ምድያማውያን የሚኖሩባቸውን የምድያማውያንን ከተሞችና የምድያማውያንን ሠፈሮች ሁሉ አጠፉ”
“የእሥራኤል ሠራዊት ወሰደው”
ይሄ የሚያመለክተው ቁሳቁሶቹን ሁሉ በመውሰዳቸው ምክኒያት ምድያማውያንን ከሞት መታደጋቸውን ነው፡፡
ሠፊ ሆኖ ለጥ ያለ መሬት፡፡
ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ሻለቆቹ ወይም የመቶ አለቆዎቹ የሚመሯቸው በሥራቸው የሚገኙ ሠራዊቶች ትክክለኛ ቁጥር ነው፡፡“1000 ሰራዊት የሚመሩ ሻለቃዎችና 100 ሠራዊት የሚመሩ መቶ አለቃዎች”ወይም 2/“ሺዎችና መቶዎች የሚሉት ቃላት የታላላቅና የአነስተኛ የጦር ክፍሎች ስያሜዎች ናቸው እንጂ የሠራዊቱን ትክክለኛ ቁጥር የሚያመለክቱ አይደሉም” “ሠፊ የጦር ክፍል ያላቸው ሻለቃዎችና አነስተኛ የጦር ክፍል ያላቸው መቶ አለቃዎች””(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ማን ሊድን እንደሚገባና እንደፈሚቀድለት ሕጉ በግልፅ አስቀምጦታል፡፡ሠራዊቱ ግን ሕጉን በመፃረር ሰቶችንና ልጆችን በሕይወት እንዲኖሩ አድርገዋቸዋል፡፡ይሄ የሠራዊት መሪዎቹን ለመገሰፅ የቀረበ ጥያቄ ነው፡፡(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ቃል እዚህ ሥፍራ ላይ ጥቅም ላይ እንዲውል የተደረገው ከዚህ በመቀጠል የሚነገረውን ነገር ሕዝቡ በጥሞና እንዲያዳምጥ ታስቦ ነው፡፡“አዳምጡ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ከወንድ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያደረገ”(ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለእሥራኤል የጦር መሪዎች በእግዚአብሔር ፊት ንፁሕ መሆንን በተመለከተ ይነግራቸዋል፡፡
ይሄ የሚያመለክተው ድንግል ሴቶችን ነው፡፡(ሥርዓት የሌለውን ነገር በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እዚሀ ላይ የሚናገረው የጦር አዛዦችን ብቻ ሣይሆን ማንኛውንም በጦርነቱ ላይ ተሣትፎ ያደረጉ ሰዎችን ሁሉ ነው፡፡
ወደ ሠፈሩ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት በመንፈሣዊ ሕይወታቸው ዳግም ንፁሕ ሊሆኑ ይገባል፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንድ ሰው ከቁርበትከፍየልም ጠጉር፤ከእንጨትም የሠራውን ሁሉ” (ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
አልዓዛር ከሠልፍ የመጡትን ሰዎች ከጦርነት መልስ በኋላ በሕጉ ሥርዓት መሠረት እንዴት ንፁህ መሆን እንደሚገባቸው ያስተምራቸዋል፡
በዚያን ወቅት ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ ብረቶች፡፡
“የማይቃጠለውን”
“እሣት ውስጥ አሰቀምጡት”
ይሄ የሚያመለክተው አንድ ሰው ከኃጢአት ቁርባን የወሰደውን ውኃ ከአመድ ጋር የመደባለቁን ሁኔታ ነው፡፡(ኦሪት ዘኁልቁ 19፡17-19)
እነዚህ በሚከናወኑ ሥርዓቶች በእግዚአብሔር ፊት ንፁህ ሆኖ የመገኘት ልማዶች ናቸው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ወታደሮቹ የወሰዱትን ንብረት በሙሉ ቁጠሩ” (ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው እስራኤላውያን በጦርነት ውስጥ ከገደሏቸው ወይም ከማረኳቸው ሰዎች የወሰዷቸውን ንብረቶችን ነው፡፡
“የየነገዶቹ መሪዎች”
እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
“እኔ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡“ወታደሮቹ ከማረኳቸው ነገሮች ላይ ቀረጥ በመጣል ለእኔ አምጣው፡፡(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“በየአምስት መቶው”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ከወታደሮቹ ድርሻ”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እርሱ ለእኔ የሚሰጠውን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
“የእሥራኤል ሕዝብ ከበዘበዘው ከግማሹ”
“ከየ50”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የመገናኛ ድንኳኑንና ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን መሥዋዕቶች በበላይነት የሚቆጣጠሩና የሚጠብቁ፡፡
ይሄ ቃል ጥቅም ላይ እንዲውል የተደረገውበዋናነት በሚሰጠው ትምህርት ላይ የተወሰነ እረፍት እንዳለ ለማሣየት ነው፡፡እዚህ ላይ ሙሴ ከተበዘበዙት ነገሮች ውስጥ ለወታደሮቹ፤ለሕዝቡና ለእግዚአብሔር ምን ያህል እንደተሰጠ ዝርዝራቸውን ያወጣል፡፡
“ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በጎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“72,000 በሬዎች፤60 ሺህ አህዮችና 32,000 ሴቶች” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ድንግል የሆኑ ሴቶችን ነው፡፡(ሥርዓት የሌለውን ቃል በመልካም ነገር መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ከተበዘበዙት ነገሮች ውስጥ ለወታደሮቹ የሚሰጠውንና ተቀርጦ ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ዝርዝር ማውጣት ይጀምራል፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለወታደሮቹ ከበጎቹ የሚደርሳቸው ድርሻ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ሶስት መቶ ሰላሣ ሰባት ሺህ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ስድስት መቶ ሰባ አምስት”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“36,000”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
72(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ከተበዘበዙት ነገሮች ውስጥ ለወታደሮቹ የሚሰጠውንና ተቀርጦ ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ዝርዝር ማውጣት ይጀምራል፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰላሣ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
61(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
16,000(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
32 (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ለእግዚአብሔር ቁርባን የሚሆነውን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ከተበዘበዙት ነገሮች ውስጥ ለወታደሮቹ የሚሰጠውንና ተቀርጦ ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ዝርዝር ማውጣት ይጀምራል፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ሶስት መቶ ሰላሣ ሰባት ሺህ አምስት መቶ በጎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“ሰላሣ ስድስት ሺህ በሬዎች”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“16,000 ሴቶች”ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው የተማረኩ ወንዶቹና ያገቡ ሴቶች በሙሉ በሕይወት እንዳይኖሩ ተደርጓል፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ከተበዘበዙት ነገሮች ውስጥ ለወታደሮቹ የሚሰጠውንና ተቀርጦ ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ዝርዝር ማውጣት ይጀምራል፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
በሕዝቡ ላይ የተጣለው ግብር በወታደሮቹ ላይ ከተጣለው ግብር ይልቅ ከፍ ያለ ነበር፡፡
ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ሻለቆቹ ወይም የመቶ አለቆዎቹ የሚመሯቸው በሥራቸው የሚገኙ ሠራዊቶች ትክክለኛ ቁጥር ነው፡፡“1000 ሰራዊት የሚመሩ ሻለቃዎችና 100 ሠራዊት የሚመሩ መቶ አለቃዎች”ወይም 2/ “ሺዎችና መቶዎች የሚሉት ቃላት የታላላቅና የአነስተኛ የጦር ክፍሎች ስያሜዎች ናቸው እንጂ የሠራዊቱን ትክክለኛ ቁጥር የሚያመለክቱ አይደሉም” “ሠፊ የጦር ክፍል ያላቸው ሻለቃዎችና አነስተኛ የጦር ክፍል ያላቸውመቶ አለቃዎች” ይህንንተመሳሳይ ሐረግ በዘኁልቁ 31፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የሠራዊት አዛዦቹ ራሣቸውን “ባሪያዎችህ” እያሉ የጠሩት ከፍተኛ ሥልጣን ካለው ሰው ጋር ንግግር በሚደረግበት ወቅት ጥቅም ላይ የሚውል ትህትና ያለበት አቀራረብ ስለሆነ ነው፡፡
ይሄ በአዎንታዊ በሆነ አገላለፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሁሉም ሰው እዚህ እንደሚገኝ እርግጠኞች ነን”(በተዘዋዋሪ መንገድ ሃሣብን መግለፅ የሚለውን ይመልከቱ)
የሠራዊቱ አዛዦች ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላሉ፡፡
እነዚህ ሰዎች የሚያደርጓቸው ጌጣጌጦች ናቸው፡፡
“ሕይወታችንን ስላዳነን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ”
“የወርቅ ዕቃዎችን ሁሉ”ወይም “የወርቅ ጌጣጌጦችን ሁሉ”
“የሻለቆችቹና የመቶ አለቆቹ ለእግዚአብሔር የሰጡት የወርቅ ሥጦታ ሁሉ የመዘነው…”
ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/እነዚህ ቁጥሮች የሚያመለክቱት ሻለቆቹ ወይም የመቶ አለቆዎቹ የሚመሯቸው በሥራቸው የሚገኙ ሠራዊቶች ትክክለኛ ቁጥር ነው፡፡“1000 ሰራዊት የሚመሩ ሻለቃዎችና 100 ሠራዊት የሚመሩ መቶ አለቃዎች”ወይም 2/ “ሺዎችና መቶዎች የሚሉት ቃላት የታላላቅና የአነስተኛ የጦር ክፍሎች ስያሜዎች ናቸው እንጂ የሠራዊቱን ትክክለኛ ቁጥር የሚያመለክቱ አይደሉም” “ሠፊ የጦር ክፍል ያላቸው ሻለቃዎችና አነስተኛ የጦር ክፍል ያላቸው መቶ አለቃዎች” ይህንንተመሳሳይ ሐረግ በዘኁልቁ 31፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“አሥራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
አንድ ሰቅል 11 ግራም ነው፡፡(መፅሐፍ ቅዱሣዊ ገንዘብ የሚለውን ይመልከቱ)
ወርቆቹ መታሰቢያ የሚሆኑት እግዚአብሔር ድል የሰጣቸው መሆኑን ለማሳሰብ ነው፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በምድያማውያን ላይ ሕዝቡ የበቀል እርምጃ የወሰደ መሆኑን እግዚአብሔር ያስበው ዘንድ ነው፡፡
1 በዚህ ጊዜ የሮቤልና የጋድ ትውልዶች ብዙ የቀንድ ከብቶች ነበራቸው፡፡ የኢያዜርንና የገለዓድን ምድር ሲመለከቱ፣ ምድሪቱ ለከብቶቻቸው መልካም መሆኗን አዩ፡፡ 2 ስለዚህ የጋድና ሮቤል ትውልዶች ወደ ሙሴ፣ ወደ ካህኑ አልዓዛርና ወደማህበሩ መሪዎች መጥተው እንዲህ አሉ፣ 3 “ያህዌ በእስራኤል ህዝብ ፊት የመታው አጣሮት፣ ዲቦን ኢያዜር፣ ኒምራ፣ ሐሴናን፣ ኤልያሊ፣ ሴባማ፣ ናባውና ባያን 4 ምድሩ ለከብቶች መልካም ነው፡፡ እኛ፣ የአንተ አገልጋዮች ብዙ ከበቶች አሉን፡፡” 5 ደግሞም እንዲህ አሉ፣ “በፊትህ ሞገስ አግኝተን ከሆነ፣ ይህች ምድር ለእኛ ለአገልጋዮችህ ርስት ሆና ትሰጠን፡፡ ዮርዳኖስን አቋርጠን እንድንሄድ አታድርግ፡፡” 6 ሙሴ ለጋድና ሮቤል ትውልዶች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እናንተ በዚህ ተቀምጣችሁ ወንድሞቻችሁ ወደ ጦርነት ሊሄዱ ይገባልን? 7 የእስራኤል ህዝብ ያህዌ ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ ለምን ልባቸውን ታደክማላችሁ? 8 አባቶቻችሁ ከቀዴስ በርኔ ምድሪቱን እንዲያዩ በላክኋቸው ጊዜ ያደረጉት ተመሳሳይ ነገር ነበር፡፡ 9 እነርሱ ወደ ኤሽኮል ሸለቆ ሄዱ፡፡ ምድሪቱን ካዩ በኋላ የእስራኤልን ልብ አደከሙ፤ ስለዚህም ያህዌ ወደ ሰጣቸው ምድር ለመግባት ተቃወሙ፡፡ 10 በዚያ ቀን የያህዌ ቁጣ ነደደ፡፡ በመሀላ እንዲህ አለ፣ 11 ‘ከግብጽ ምድር ከወጡ ሰዎች ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ከሆናቸው፣ መሃል አንዳቸውም ለአብርሃም፣ ለይስሃቅ፣ እና ለያዕቆብ ልሰጣቸው በመሀላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩም፣ ምክንያቱም እነርሱ በሙሉ ልባቸው አልተከተሉኝም፤ 12 ከቂኔዛዊው ከዩፎኒ ልጅ ከካሌብ፣ እና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር፡፡ ካሌብና ኢያሱ ብቻ በሙሉ ልባቸው ተከትለውኛል፡፡’ 13 ስለዚህም የያህዌ ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፡፡ በፊቱ ክፉ ያደረገው ትውልድ ሁሉ እስኪጠፋ ድረስ ለአርባ አመታት በምድረበዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው፡፡ 14 እናንተ እንደ ሌሎች ኃጢአተኛ ሰዎች የያህዌን ቁጣ በእስራኤል ላይ ለመጨመር በአባቶቻችሁ እግር ተተካችሁ፡፡ 15 እርሱን ከመከተል ፊታችሁን ብታዞሩ፣ እርሱ እስራኤልን ዳግም በበረሃ ይተዋል እናንተም ይህን ሁሉ ህዝብ ታጠፋላችሁ፡፡” 16 ስለዚህም ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉ፣ “በዚህ ለከብቶቻችን አጥር እና ለቤተሰቦቻችን ከተማ እንድንገነባ ፍቀድል፡፡ 17 ሆኖም፣ እኛ እራሳችን ወደ ስፍራቸው እስክናባርራቸው ድረስ ከእስራኤል ጦር ጋር ለመውጣት እንነሳለን እንታጠቃንም፡፡ ቤተሰቦችን ግን እስከ አሁን በዚህ ምድር ከሚኖሩ ሌሎች ሰዎች የተነሳ በተቀጠሩ ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ፡፡ 18 የእስራኤል ህዝብ እያንዱ ሰው ርስቱን እስኪያገኝ ድረስ ወደ ቤቶቻችን አንመለስም፡፡ 19 እኛ ከእነርሱ ጋር ከዮርዳኖስ ማዶ ያለውን ምድር አንወርስም፣ ምክንያቱም የእኛ ርስት እዚህ በዮርዳኖስ ምስራቅ በኩል ያለው ነው፡፡” 20 ስለዚህም ሙሴ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “የተናገራችሁትን ካደረጋችሁ፣ ወደ ጦርነት በያህዌ ፊት ለመውጣት ራሳችሁን ካስታጠቃችሁ፣ 21 ከዚያ በኋላ እያንዳንዳቸው የእናንተ የታጠቁ ወንዶች ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያባርራቸው ድረስ በያህዌ ፊት ዮርዳኖስን ማቋረጥ አለባቸው፡፡ 22 ደግሞም ምድሪቱ በእርሱ ፊት ጸጥ ብላ ትገዛለች፡፡ ከዚያ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፡፡ እናንተም በያህዌና በእስራኤል ፊት ጥፋተኛ አትሆኑም፡፡ ይህ ምድር በያህዌ ፊት ርስታችሁ ይሆናል፡፡ 23 እንዲህ ካላደረጋችሁ ግን፣ በያህዌ ፊት በደለኞች ትሆናላችሁ ኃጢአታችሁ እንደሚከተላችሁ እርግጠኞች ሁኑ፡፡ 24 ለቤተሰቦቻችሁ ከተሞችን ገንቡ ለበጎቻችሁም ጉረነዎች ስሩላቸው፤ ከዚያ ያላችሁትን አድርጉ፡፡” 25 የጋድና ሮቤል ትውልዶች ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “እኛ አገልጋዮችህ አንተ ጌታችን ያዘዝከንን እናደርጋለን፡፡ 26 ልጆቻችን፣ ሚስቶቻችን፣ መንጎችንና የቀን ከብቶቻችን በገለዓድ ከተሞች ይቆያሉ፡፡ 27 ሆኖም፣ እኛ፣ የአንተ አገልጋዮች ለጦርነት በያህዌ ፊት እንወጣን፤ ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ሰው አንተ ጌታችን እንዳልከው ያደርጋል፡፡” 28 ስለዚህም ሙሴ ለካህኑ አልዓዛር፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና በእስራኤል ህዝብ መሃል የጎሳዎች አባቶች ለሆኑ መሪዎች እነርሱን በሚመለከት መመሪያዎቻችን ሰጠ፡፡ 29 ሙሴ እንዲህ አላቸው፣ “የጋድና የሮቤል ትውልዶች ከእናንተ ጋር ዮርዳስን ቢሻገሩና በያህዌ ፊት ለጦርነት የታጠቀ እያንዳንዱ ወንድ እና ምድሪቱ በፊታችሁ ቢገዙ፣ የገለዓድን ምድር ለእነርሱ ርስት አድርገህ ትሰጣቸዋለህ፡፡ 30 ነገር ግን ታጥቀው ከአንተ ጋር ዮርዳኖስን ባይሻገሩ፣ ርስታቸውን በከነአን ምድር ከአንተ ጋር ያገኛሉ፡፡” 31 ስለዚህም የጋድና ሮቤል ትውልዶች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ያህዌ ለእኛ ለባሮችህ እንደተናገረው፣ የምናደርገው ነገር ይህ ነው፡፡ እንሻገራለን፡፡ 32 እኛ ታጥቀን በያህዌ ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፣ ነገር ግን የተወረሰው ርስታችን በዚህኛው የዮርዳስ ክፍል ከእኛ ጋር ይቀራል፡፡” 33 ስለዚህ ሙሴ ለጋድና ለሮቤል ትውልዶች፣ እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ከፊል ነገድ፤ የአሞውያንን ንጉስ የሴዎንን ግዛት እና የባሳንን ንጉስ የዓግን ግዛቶች ሰጣቸው፡፡ ለእነርሱ ምድሪቱን ሰጣቸው፣ እንዲሁም ከተማዎቿን ከዳርቻዎቻቸው ጋር እና በዙሪያቸው ያሉ ከተሞችን አደላቸው፡፡ 34 የጋድ ትውልዶች ዲቦንን፣ አጣሮትን፣ አሮዔርን፣ 35 ዓጥሮት ሾፋንን፣ አያዜርን፣ ዮግብሃን፣ 36 ቤት ነምራንን እና ቤት ሃራንን የተቀጠሩ ከተሞችና ለበጎች ጉረኖዎች ያላቸው አድርገው እንደገና ገነቧቸው፡፡ 37 የሮቤል ትውልዶች ሐሴቦንንና፣ ኤልያሊንና ቂርያትይምን፣ 38 ናባውን፣ በአልሜዎንን (ስማቸው በኋላ ተቀይሯል) እና ሴባማንን እንደገና ገነቧቸው፡፡ እነርሱም ዳግም ለገነቧቸው ከተሞች ሌላ ስሞችን ሰጡ፡፡ 39 የምናሴ ልጅ የማኪር ትውልዶች ወደ ገለዓድ ሄደው በውስጧ ይኖሩ ከነበሩት ከአሞራውያን ከለአድን ወሰዱ፡፡ 40 ከዚያ ሙሴ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ገለዓድን ሰጠው፣ የእርሱም ሰዎች መኖሪያችን በዚያ አደረጉ፡፡ 41 የምናሴ ልጅ ኢያዕር ሄዶ ከተማቸውን ይዞ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ሰየማቸው፡፡ 42 ኖባህ ሄዶ ቄናትንና መንደሮቿን ይዞ፣ በራሱ ስም ኖባህ ብሎ ሰየማት፡፡
ይሄ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በዋናው የታሪክ ሂደት ላይ የተወሰነ እረፍት እንዳለ ለማሣየት ነው፡፡እዚህ ላይ ሙሴ ስለ ሮቤልና ስለ ጋድ ነገዶች ስለጀርባ ታሪካቸው መረጃን ይሰጣል፡፡(የኋላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተማዎቹ ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ከሮቤልና ከጋድ የመጡ ሰዎች ለሙሴ፤ለአልዓዛርና ለሌሎቹ መሪዎች መናገራቸውን ይቀጥላሉ፡፡
በዚያ ምድር የነበሩትን ሰዎች ድል እንዲያደርጓቸው እግዚአብሔር ችሎታውን የሰጣቸው ቢሆንም ልክ እግዚአብሔር ራሱ በእሥራኤላውያን ፊት ወጥቶ ጥቃት እንዳደረሰ ዓይነት ተድርጎ ተገልጿል፡፡“በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ድል እንደንነሳቻው እግዚአብሔር ችሎታውን ሰጠን” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የሮቤልና የጋድ ሰዎች በዚህ መልክ ራሣቸውን የሚጠሩት ከፍ ያለ ሥልጣን ላለው ሰው አክበሮትን ለመሥጠት ነው፡፡
እዚህ ላይ“ሞገስ” የሚለው ቃል ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ተቀባይነትን ማግኘት ወይም መሪዎቹ በእነርሱ ደስ መሰኘታቸውን የሚያሣይ ነው፡፡እዚህ ላይ “ዓይኖች”የሚለው ቃል እይታ ለሚለው ቃል ገላጭ ሲሆን እይታ ደግሞ የማመዛዘን ችሎታውን የሚያመለክት ምሣሌያዊ አነጋገር ነው፡፡“በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝተን ከሆነ”ወይም “በእኛ ደስ የተሰኘህ ከሆነ”(ፈሊጣዊ አነጋገር፤ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃልንና ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ይህንን ምድር ለእኛ ስጠን”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
የፈለጉት ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ተሻግረው መሬት መጠየቅ ሣይሆን ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ በኩል የሚገኘውን ሥፍራ ነበር የፈለጉት፡፡“በዚያኛ በኩል ለእኛ መሬትን ለመሥጠት ብለህ የዮርዳኖስ ወንዝን እንድሻገር አታድርገን”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ሮቤልንና ጋድን ለመገሰፅ ብሎ ነው፡፡“ወንድሞቸችሁ ጦርነት ላይ እያሉ እናንተ በዚህ ምድር መቀመጣችሁ ተገቢ አይደለም”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ከሮቤልና ከጋድ ሃሣብ ሕዝቡን ለመከላከል ነው፡፡“እግዚአብሔር የሰጣቸውን ….. የሰውን ልብ አታድክሙ”ወይም “ድርጊታችሁ የሰዎችን ልብ ሊያደክሙ ይችላሉ….እግዚአብሔር የሰጣቸውን”(ምላሽ የማያሻው ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ልብ”የሚለው ቃል የሚወክለው ራሣቸው ሰዎቹን ሲሆን የሚያመለክተውም የስሜታቸው መሠረት የሆነውን ነገርነው፡፡“የእሥራኤል ሕዝብ እንዳይሄድ ተስፋ ታስቆርጡታላችሁ”ወይም “የእሥራኤል ሕዝብ እንዳይሄድ ምክኒያት ትሆናላችሁ”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለሮቤልና ለጋድ ሰዎች መናገሩን ይቀጥላል፡፡
ይሄ የቦታ ሥም ነው፡፡ይህንንበዘኁልቁ 13፡23 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው በምድሪቱ ውስጥ ያለውን ነገር መመልከታቸውን ነው፡፡“በምድሪቱ ውስጥ የሚገኙትን ጠንካራ ሰዎችና ከተማዎቹን ተመለከቱ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ልብ”የሚለው ቃል የሚወክለው ራሣቸው ሰዎቹን ሲሆን የሚያመለክተው የስሜታቸው መሠረት የሆነውን ነው፡፡ይህንንበዘኁልቁ 32፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“የእሥራኤልን ሕዝብ ተስፋ አስቆረጡ”(ነገርን በተለየ መንገድ መረዳት የሚለውን ይመልከቱ)
x
እግዚአብሔር መናደዱን ለመግለፅ ልክ እሣት መቀጣጠል ከመጀመር ጋር ተመሳስሎ ነው የተነገረው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር በእሥራኤል ላይ በጣም ተናደደ”(ምሣሌያዊ አነጋገርና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“40 ዓመት”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ትውልዱን ሁሉ አጠፋ…ፊት”ወይም “ትውልዱ ሁሉ…በእግዚአብሔር ፊት ጠፋ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
በአንድ ሰው ፊት ማለት ሰውዬው ሊያየው በሚችልበት ሁኔታ ውስጥ መሆን ማለት ነው፡፡“በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ያደረገ”ወይም “የእግዚአብሔር ሕልውና ባለበት ክፉ ነገርን ያደረገ”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የሮቤልና የጋድ ሰዎች ልክ የአባቶቻቸውን ሥራ ማድረጋቸው አባቶቻቸው ባደረጉት ሥፍራ ላይ እንደቆሙ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እንደ አባቶቻችሁ ማድረግ ጀምራችኋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎች እግዚአብሔር የበለጠ እየተናደደ እንዲሄድ የሚያደርጉት ድርጊት ልክ ሰዎች በእሣቱ ላይ ነዳጅ እንደሚጨምሩ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እግዚአብሔር በእሥራኤል ላይ የበለጠ እንዲናደድ ምክኒያት መሆን”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“ይሄ ሁሉ ሕዝብ”ወይም“ይሄ ሁሉ ትውልድ”
“መሣሪያችንን ታጥቀን ዝግጁዎች እንሆናለን”ወይም “በጦርነት ለመሣተፍ ዝግጁ እንሆናለን”
“ደህንነታቸው በተጠበቁ ከተማዎች ውስጥ”
ሮቤልና ጋድ መናገራቸውን እንቀጠሉ ነው፡፡
ሰዎች እንደ ቋሚ ንብረት የሚቀበሉት ንብረት ልክ እንደሚወስዱት ንብረት ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“የሚደርሰውን የመሬት ድርሻ በንብረትነት ወስዷል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“የጦር መሣሪያችሁን ብትወስዱ”
የዚህ ትርጉም እግዚአብሔር በጦርነቱ ወቅት በፊታቸው በመሄድ ጠላቶቻቸውን ድል እንዲያደርጉ ጉልበትን በመሥጠት ምድራቸውን እንዲወርሱ ያደርጋል ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያሳድድ ድረስ፡፡እዚህ ላይ የሚገኙት ተውላጠ ስሞች ሁሉ የሚያመለክቱት እግዚአብሔርን ነው፡፡እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ድል እንዲያደርጉ ያገዛቸውን ሁኔታ ልክ እግዚአበሔርየእነርሱን ጦርነት እየተዋጋ እንዳለ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“እግዚአብሔር ሠራዊቶቻችን ድል እንዲደርጓቸውና ከእርሱ ፊት እስኪዲያሳድዷቸው ድረስ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ “ምድሪቱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኑሯቸውን በዚያ ያደረጉትን ሰዎች ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እሥራኤላውያን በዚያ ምድር የሚኖሩትን ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ድል አደረጓቸው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃልና ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በኩል ወደሚገኘው ሥፍራ የሚመለሱ መሆናቸውን ነው፡፡“ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በኩል ወደሚገኘው ሥፍራ ልትመለሱ ትችሉ ይሆናል”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ለዚህ ተስማሚ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/“የሚጠበቅባችሁን ግዴታ በእግዚአብሔርና በእራኤል ፊት ፈፅማችኋል”ወይም 2/“እግዚአብሔርም ሆነ የእሥራኤል ሕዝብ እናንተን የሚወቅሱበት ነገር የላቸውም”
ሙሴ በዚህ ሥፍራ ላይ ስለ ኃጢአት የሚናገረው ልክ አንድ ግለሰብ ጥፋተኛ የሆነን ሰው እንደሚኮንንዓይነት ነው፡፡ይሄ ማለት ሰዎች በሰሩት ኃጢአት ልክ ከመቀጣት አይድኑም ማለት ነው፡፡“እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችሁ እንደሚቀጣችሁ እርግጠኛ ሁኑ”(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)
የጋድና የሮቤል ሰዎች ራሣቸውን “ባሪያዎችህ”እያሉ ነው የሚጠሩት፡፡ይሄ ከፍ ያለ ሥልጣን ላለው ሰው አክበሮት ለመሥጠት የሚውል ቃል ነው፡፡
ዮርዳኖስን እንደሚሻገሩ ግልፅ ልታደርጉት ተችላላችሁ፡፡“የዮርዳኖስን ወንዝ ይሻገራሉ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“በጦርነት ውስጥ ለመሣተፍ የተዘጋጀ ሰው ሁሉ”
“የጦር መሣሪያውን ዝግጁ ያደረገ ሰው ሁሉ”
እዚህ ላይ “ምድሪቱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ነው፡፡ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በዚያ ምድር የሚኖሩትን ሰዎች እግዚአብሔርድል እንድትነሱ የሚያደርጋችሁ ከሆነ” ወይም “በምድሪቱ ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎች ድል እንድታደርጓቸው እነርሱ የሚያግዟችሁ ከሆነ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“የጋድና የሮቤል ትውልዶች በከነዓን ምድር ርታቸውን ይወርሳሉ”
ዮርዳኖስን እንደሚሻገሩ የበለጠ ግልፅ ልታደርጉት ትችላላችሁ፡፡“ዮርዳኖስን የምንሻገረው ለጦርነት ዝግጁ ሆነን ነው”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ሕዝቡ እንደ ቋሚ ንብረትነት የሚወስደውን መሬት በውርስ እንደሚወስዱት ዓይነት ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡“የራሣችን የምናደርገው የመሬት ድርሻችን” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ፈሊጣዊ አጋገር የሚያመለክተው የራስ ንብረት ማድረግን ነው፡፡“የራሣችን ይሆናል”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት የተለያዩ ግዛቶችን የገዙ ነገሥታት ሥሞች ናቸው፡፡“የሴዎን ግዛትና…የዐግ ግዛት”(ምልክቶች እንጂ ቃላት ጥቅም ላይ የማይውሉበት የሚለውንና ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ሰሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ሰሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በኋላ ላይ ሰዎች የእነዚሀን ከተሞች ስሞች ለወጧቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሰው ሥም ነው፡፡ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 26፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
እነዚህ የሰዎች ሰሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)አ
እነዚህ የከተሞች ሰሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
1 የእስራኤል ህዝብ በሙሴና አሮን መሪነት በየታጣቂ በድኖቻቸው ሆነው ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ ያደረጓቸው ጉዞዎች እነዚህ ነበሩ፡፡ 2 ሙሴ በያህዌ እንደታዘዘው፣ ከተነሰቡት አንስቶ እስሚሄዱበት ድረስ ያሉትን ስፍራዎች ጻፈ፡፡ ከስፍራ ስፍራ ያደረጓቸው እንቅስቃሴዎች እነዚህ ነበሩ፡፡ 3 በመጀመሪያው ወር፣ በወሩ በአስራ አምስተኛ ቀን ከራምሴ ተነስተው ተጓዙ፡፡ ከፋሲካው በኋላ በማለዳ፣ የእስራኤል ሕዝብ በግልጽ ግፃዊያን ሁሉ እያይዋቸው ወጡ፡፡ 4 ግብፃዊያን ያህዌ በመካከላቸው የገደላቸውን በኩሮቻቸውን እየቀበሩ ሳለና በአማልክቶቻቸው ላይ ጥፋት እያደረሰ ሳለ ይህ ሆነ፡፡ 5 የእስራኤል ሕዝብ ከራምሴ ወጥቶ በሱኮት ሰፈረ፡፡ 6 ከሱኮት ወጥተው በኤታሞ፣ በምድረ በዳው 7 ከኤታም ወጥተው ከበአልዛፎን በተቃራኒ ወደ ፊሀሔርት ተመልሰው በሚግዶል በተቃራኒ ሰፈሩ፡፡ 8 ከዚያም ከፈሀሔርት በተቃራኒ ተነስተው በባህሩ መሃል ወደ ምድረበዳው ሄዱ፡፡ ለሶስት ቀናት በኤታም ምድረ በዳ ተጉዞው በማራ ሰፈሩ፡፡ 9 ከማራ ተነስተው ኤሊም ደረሱ፡፡ በኤሊም አስራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የቴምር ዛፎች ነበሩ፡፡ የሰፈሩት በዚያ ስፍራ ነው፡፡ 10 ከኤሊም ተነስተው ቀይ ባህር አጠገብ ሰፈሩ፡፡ 11 ከቀይ ባህር ተነስተው በሲን ምድረበዳ ሰፈሩ፡፡ 12 ከሲን ምድረበዳ ተነስተው በራፍቃ ሰፈሩ፡፡ 13 ከራፍቃ ተነስተው በኤሉስ ሰፈሩ፡፡ 14 ከኤሉስ ተነስተው የሚጠጣ ውሃ በሌለበት ሰራፊዲም ሰፈሩ፡፡ 15 ከራፊዲም ተነስተው በሲና ምድረበዳ ሰፈሩ፡፡ 16 ከሲና ምድረበዳ ተነስተው በቂብሮት ሃታቫ ሰፈሩ፡፡ 17 ከቂብሮት ሃታቫ ተነስተው በሐዴሮት ሰፈሩ፡፡ 18 ከሐዴሮት ተነስተው በሪትማ ሰፈሩ፡፡ 19 ከሪትማ ተነስተው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ፡፡ 20 ከሬምን ዘፋሬስ ተነስተው በልብና ሰፈሩ፡፡ 21 ከልብና ተነስተው በሪሳ ሰፈሩ፡፡ 22 ከሪሳ ተነስተው በቀሄላታ ሰፈሩ፡፡ 23 ከቀሄላታ ተነስተው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ፡፡ 24 ከሻፍር ተራራ ተነስተው በሐራዳ ሰፈሩ፡፡ 25 ከሐራዳ ተነስተው በመቅሄሎት ሰፈሩ፡፡ 26 ከመቅሄሎት ተነስተው በታሐት ሰፈሩ፡፡ 27 ከታሐት ተነስተው በታራ ሰፈሩ፡፡ 28 ከታራ ተነስተው በሚትቃ ሰፈሩ፡፡ 29 ከሚትቃ ተነስተው በሐሹምና ሰፈሩ፡፡ 30 ከሐሽምና ተነስተው በምሴሮት ሰፈሩ፡፡ 31 ከሞሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ፡፡ 32 ከብኔያዕቃን ተነስተው በሖር ሃጊድጋድ ሰፈሩ፡፡ 33 ከሖር ሃጊድጋ ተነስተው በዮጥባታ ሰፈሩ፡፡ 34 ከዮጥባታ ተነስተው በዔብሮና ሰፈሩ፡፡ 35 ከዔብሮና ተነስተው በዔድዮን ጋብር ሰፈሩ፡፡ 36 ከዔድዮን ጋብር ተነስተው በቃዴስ በምትገኘው ጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፡፡ 37 ከቃዴስ ተነስተው በሖር ተራራ፣ በኤዶም ምድር ዳርቻ ሰፈሩ፡፡ 38 ካህኑ አሮን፤ በያህዌ ትዕዛዝ ወደ ሖር ተራራ ወጣ፣ የእስራኤል ህዝብ ከግብጽ ምድር በወጣበት በአርባኛው ዓመት፣ በአምስተኛው ወር፣ በወሩ በመጀመሪያው ቀን ካህኑ አሮን በዚያ ሞተ፡፡ 39 አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት ዕድሜው 123 ነበር፡፡ 40 በከነዓን ምድር በደቡባዊ በረሃ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉስ የእስራኤልን ህዝብ መምጣት ሰማ፡፡ 41 እነርሱ ከሖር ተራራ ተነስተው በሴልምና ሰፈሩ፡፡ 42 ከሴልምና ተነስተው በፋኖን ሰፈሩ፡፡ 43 ከፋኖን ተነስተው በአቦት ሰፈሩ፡፡ 44 ከአቦት ተነስተው በሞአብ ዳርቻ በኢየ አባሪም ሰፈሩ፡፡ 45 ከኢየ አባሪም ተነስተው በዲቦን ጋድ ሰፈሩ፡፡ 46 ከዲቦን ጋድ ተነስተው በዓልምን ዲብላታይም ሰፈሩ፡፡ 46ከዲቦን ጋድ ተነስተው በዓልምን ዲብላታይም ሰፈሩ፡፡ 47 ከዓልምን ዲብላታይም ተነስተው ከናባው ተራራ በተቃራኒ በዓብሪም ተራራ ሰፈሩ፡፡ 48 ከዓብሪም ተራራ ተነስተው በሞብ ሜዳዎች በዮርዳኖስ ኢያሪኮ ላይ ሰፈሩ፡፡ 49 በሞብ ሞአብ ዮርዳስ ላይ ከቤት የሺሞት እስከ አቤልስጢም ድረስ ሰፈሩ፡፡ 50 ያህዌ ሙሴን በሞአብ ሜዳዎች ዮርዳስ ውስጥ በኢያሪኮ ሳለ እንዲህ አለው፣ 51 “ለእስራኤላዊያን እንዲህ በላቸው፣ ‘ዮርዳኖስን አቋርጣችሁ ወደ ከነዓን ስትገቡ፣ 52 የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አስወጡ፡፡ የተቀረጹ ምስሎቻቸውን በሙሉ አጥፉ፡፡ የማምለኪያ ስፍራዎቻቸውንና የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ሁሉ ደምስሱ፡፡ 53 የምድሪቱን ሀብት ውሰዱ በዚያም መኖር ጀምሩ፣ ምክንያቱም እኔ ምድሪቱን ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቻቸኋለሁ፡፡ 54 ምድሪቱን በእጣ እንደየ ጎሳው ብዛት ውረሱ፡፡ ብዙ ህዝብ ላለው ጎሳ ሰፊ መሬት ስጥ፣ አነስተኛ ቁጥር ላለው ጎሳ አነስ ያለ መሬት ስጥ፡፡ እያንዳንዱ ጎሳ እጣው በወደቀለት ስፍራ ያ መሬት ርስቱ ይናል፡፡ ምድሪቱን በአባቶችሁ ጎሳ መሰረት ትወርሳላችሁ፡፡ 55 የምድሪቱን ነዋሪዎች ከፊታችሁ ጨርሳችሁ ባታስወጡ ግን፣ እንዲቀሩ ያደረጋችኋቸው ሰዎች በዐይናችሁ ውስጥ እንደገባ ባዕድ አካል እና በጎናችሁ እንደገባ እሾህ ይሆኑባችኋል፡፡ በመትኖሩበት ምድር ሕይወታችሁን ከባድ ያደርጉባችኋል፡፡ 56 እኔ በእነዚህ ህዝቦች ላይ ላደርስባቸው ያቀድኩትን በእናንተም ላይ ደግሞ አደርገዋለሁ፡፡’”
“በየጦር ክፍሎቻቸው” “ይሄ የሚያሣየው እያንዳንዱ ነገድ የታጠቁና ከጠላት የሚከላከሉላቸው የራሣቸው ሰዎች ነበሯቸው ማለት ነው”“የታጠቀ ሠራዊት”የሚለውን ሐረግ በዘኁልቁ 1፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ከአንድ ሥፍራ ወደ ሌላ ሥፍራ”
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“በመጀመሪያ”የሚለው ተከታታይ ቄጥር የሆነው አንድ ሲሆን “በአሥራ አምስተኛው”የሚለው ደግሞ ተከታታይ ቁጥር የሆነው አሥራ አምስት ነው፡፡ይሄ ለዕብራውያን የመጀመሪያው ወራቸው ነው፡፡በምዕራባውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት አሥራ አምስተኛው ቀን የሚውለው በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ነው፡፡(የዕብራውያን ቀን አቆጣጠርናተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“እሥራኤላውያን ከግብፃውያን ሳይደበቁ ፊት ለፊት እያይዋቸው ወጡ”
ይሄ የሚያመለክተው በኩር የሆኑ ወንድ ልጆችን ነው፡፡“በኩር ወንድ ልጆቻቸውን”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር በግብፅ ከሚመለኩት ጣዖታት ይልቅ እጅግ ኃያል እንደሆነ የሚያረጋግጠውን ነገር ልክ እግዚአብሔር ጣዖቶቻቸውን እንደቀጣ ዓይነት ተደርጎ ተገልጿል፡፡“ከጣዖቶቻቸው ይልቅ ኃያል እንደሆነ አረጋገጠ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“ከሆነ ቦታ ለቀቁ”
“በምድረው በዳ ድንበር”
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው እሥራኤላውያን ከግብፃውያን ሠራዊት ያመልጡ ዘንድ እግዚአብሔር ቀይ ባህርን የከፈለበትን ሁኔታ ነው፡፡
“12 የውኃ ምንጮች…70 ዘንባቦች”(ቁጥሮች የሚለውን ተመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ውኃ ለማግኘት የተቸገሩበት ሁኔታ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“ከአርባኛው”የሚለው ቃል አርባ ለሚለው ቁጥር ተከታታይነትን የሚያመለክት ነው፡፡“ከ40 ዓመት በኋላ” (ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“አምስተኛው”የሚለው ቃል አምስት ለሚለው ቁጥር ተከታታይነትን የሚያመለክት ነው፡፡“በዕብራውያን አቆጣጠር መሠረት ይሄ አምስተኛው ወር ነው”በምዕራባውያን የቀን አቆጣጠር መሠረት የመጀመሪያው ቀን የሚውለው ሐምሌ መሐል አካባቢ ነው፡፡(የዕብራውያን ቀን አቆጣጠርንና ተከታታይነት ያለው ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
“መቶ ሃያ ሶስት ዓመት”(ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
“የዓራድ ከነናዊ ንጉሥ”(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የከነዓናውያን ከተማ ሥም ነበር፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
“የእሥራኤል ልጆች እየመጡ እንደሆነ ወሬ ሰማ”
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ እሥራኤላውያን ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ የተጓዙባቸውን የቦታዎች የሥም ዝርዝር መፃፍ ይጀምራል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ሠፊ የሆነና ለጥ ያለ መሬት
“ከፍ ያሉ ሥፈራዎቻቸውን ሁሉ ታፈርሳላችሁ”
እግዚአብሔር ሕዝቡ ምን ማድረግ እንደሚኖርበት ለሙሴ እየተናገረ ነው፡፡
ሕዝቡ እንደ ቋሚ ንብረትነት የሚወስደውን መሬት በውርስ እንደሚወስዱት ዓይነት ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“እያንዳንዱ ነገድ በሚወጣለት ዕጣ መሠረት መሬቱን ይረከባል”
እግዚአብሔር ሕዝቡ ምን ማድረግ እንደሚኖርበት ለሙሴ እየተናገረ ነው፡፡
በአንድ ሰው ወስጥ ትንሽ ነገር ዓይኑ ውስጥ ቢገባ ወይም ትንሽ እሾህ በሰው ቆዳ ውስጥ ቢገባ እንደሚያበሳጭ ሁሉ ከከነዓናውያን መካከል የተወሰኑ ሰዎች በምድሪቱ ላይ ቢቀሩ ለእሥራኤላውያን ትልቅ ችግርን ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 2 “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘የእናንተ ወደምትሆን የከነዓን ምድርና ወደ ድንበሮቿ ስትገቡ፣ 3 ደቡባዊ ድንበራችሁ ከሲና ምድረ በዳ እስከ ኤዶም ይደርሳል፡፡ የደቡባዊ ድንበር ምስራቃዊ ጫፍ በጨው ባህር ደቡባዊ ጫፍ ድረስ ይሆናል፡፡ 4 ከአቅራቢም ኮረብታ ድንበራችሁ ወደ ደቡብ ይዞርና በሲና ምድረበዳ በኩል ያልፋል፡፡ ከዚያ ተነስቶ፣ በቃዴስ በርኔ ደቡብ ያልፍና ወደ ሐጸር አዳር እና ርቆ ዓጽምን ይደርሳል፡፡ 5 ከዚያ ተነስቶ፣ ድንበሩ ከጽሞን ወደ ግብጽ ጅረት ዞሮ እስከ ባህሩ ይከተለዋል፡፡ 6 ምዕራባዊው ድንበር የታላቁ ባህር ዳርቻ ይሆናል፡፡ ይህ ምዕራባዊ ድንበራችሁ ይሆናል፡፡ 7 ሰሜናዊ ድንበራችሁ ከታላቁ ባህር እስከ ሆር ተራራ እስከ ምትይዙት ስፍራ ድረስ ይሰፋል፣ 8 ከዚያ ከሖር ተራራ እስከ ሌና ሐማት፣ ከዚያ እስከ ጽዳድ ይደርሳል፡፡ 9 ከዚያ ድንበሩ እስከ ዚፍሮን ይቀጥልና ሐጻር ዔርን ሲደርስ ይጨርሳል፡፡ ይህ ሰሜናዊ ድንበራችሁ ይሆናል፡፡ 10 ምስራቃዊ ድንበራችሁን ከሐጸር ዔናን በደቡብ እስከ ሴፋም ታደርጋላችሁ፡፡ 11 ምስራቃዊ ድንበራችሁ ታች እስከ ሴፋም ወርዶ በዓይን ምስራቅ በኩል ራብላ ይደርሳል፡፡ ድንበሩ እስከ ከኔሬት ባህር ምስራቅ ይዘልቃል፡፡ 12 ከዚያ ድንበሩ በደቡብ በዮርዳኖስ ወንዝ በኩል እስከ ጨው ባህር እና ታች የጨው ባህር ምስራቅ ዳርቻ ድረስ ይቀጥላል፡፡ ይህች ድንበሩን ተከትሎ ዙሪያውን በሙሉ የእናንተ ምድራችሁ ናት፡፡ 13 ሙሴ የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ ሲል አዘዘ፣ “ያህዌ ለዘጠኙ ጎሳዎችና ለአንዱ ጎሳ እኩሌታ እንዲሰጣችሁ ያዘዘው፣ በዕጣ የምትካፈሏት ምድር ይህች ናት፡፡ 14 የሮቤል ጎሣ ትውልዶች እና የጋድ ጎሣ ትውልዶች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ በየአባቶቻቸው ጎሣዎች የንብረት አከፋፈልን ስርዓት ተከትለው ርስታቸውን ተቀብለዋል፡፡ 15 ሁለቱ ጎሣዎችና የአንዱ ጎሣ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ወዲያ በኢያሪኮ በስተ ምስራቅ በጸሀይ መውጫ የርስታቸውን ድርሻ ተቀብለዋል፡፡” 16 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣ 17 “ምድሪቱን ርስታችሁ አድርገው የሚያፋፍሏችሁ ሰዎች ስማቸው እነዚህ ናቸው፡ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፡፡ 18 ለየጎሣቸው ምድሪቱን እንዲያካፍሉ ከየነገዱ አንድ መሪ ምረጡ፡፡ 19 የሰዎቹም ስሞች እነዚህ ናቸው፡ ከይሁዳ ነገድ የዩፎኒ ልጅ ካሌብ፡፡ 20 ከስምኦን ጎሣ ትውልዶች የዓሁድ ልጅ ሰላሚኤል፡፡ 21 ከቢኒያም ጎሣ፣ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፡፡ 22 መሪ ከሆነው ከዳን ጎሣ ትውልዶች፣ የዩግሊ ልጅ ቡቂ፡፡ 23 ከዮሴፍ ትውልዶች፣ መሪ ከሆነው ከምናሴ ትውልዶች የሱፊድ ልጅ አኒኤል፡፡ 24 መሪ ከሆነው ከኤፍሬም ጎሣ ትውልዶች፣ የሺፍጣን ልጅ ቱሙኤል፡፡ 25 መሪ ከሆነው ከዛብሎን ጎሣ ትውልዶች የፈርናክ ልጅ ኤሊሳፈን፡፡ 26 መሪ ከሆነው ከይሳኮር ጎሣ ትውልዶች፣ የሖዛ ልጅ ፈልጢኤል፡፡ 27 መሪ ከሆነው ከኤሴር ጎሣ፣ የሴሌሚ ልጅ አሒሁድ፡፡ 28 መሪ ከሆነው ከንፍታሌም ጎሳ ትውልዶች፣ የዓሚሁድ ልጅ ፈዳሄል” ናቸው፡፡ 29 ያህዌ እነዚህን ሰዎች የከነዓንን ምድር እንዲያካፍሉና ለእያንዳንዱ የእስራኤል ጎሣዎች ድርሻቸውን እንዲሰጡ አዘዘ፡፡
ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 33፡12 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
እግዚአብሔር ሙሴ ለእሥራኤላውያን የሚሰጠው መሬት ድንበሩ የት እንደሆነ ይነግረዋል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሙሴ ለእሥራኤላውያን የሚሰጠው መሬት ድንበሩ የት እንደሆነ ይነግረዋል፡፡
እግዚአብሔር ሙሴ ለእሥራኤላውያን የሚሰጠው መሬት ድንበሩ የት እንደሆነ ይነግረዋል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 20፡22 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡
እግዚአብሔር ሙሴ ለእሥራኤላውያን የሚሰጠው መሬት ድንበሩ የት እንደሆነ ይነግረዋል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት በከነዓን ምድር ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ በኩል ወደፊት የሚኖሩት የእሥራኤል የቀሩት ነገዶች ናቸው፡፡የሮቤል፤የጋድና ግማሹ የምናሴ ነገድ መሬታቸውን ከዮርዳኖሰ በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀብለዋል፡፡
“እግዚአብሔር ንብረቱን ለአባቶቻቸው ቤት በመደበው መሠረት”
“የሮቤልና የጋድ ነገዶችና ግማሹ የምናሴ ነገድ”
እዚህ ላይ “እናንተ”የሚለው ቃል የብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡እነዚህ ሰዎች መሬቱን ለመከፋፈል ዕጣ ይጥላሉ፡፡ከዚያ በኋላ በየነገዶቹ ያከፋፍሉታል፡፡(እናንተ የሚለውን የተለያየ አገላለፆች ይመልከቱ)
ለየነገዶቹ መሬቱን ለማከፋፈል እገዛ የሚያደርጉት ሰዎች የሥም ዝርዝር እነዚህ ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ለየነገዶቹ መሬቱን ለማከፋፈል እገዛ የሚያደርጉት ሰዎች የሥም ዝርዝር እነዚህ ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ለየነገዶቹ መሬቱን ለማከፋፈል እገዛ የሚያደርጉት ሰዎች የሥም ዝርዝር እነዚህ ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ለየነገዶቹ መሬቱን ለማከፋፈል እገዛ የሚያደርጉት ሰዎች የሥም ዝርዝር እዚህ ላይ ይጠናቀቃል፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ያህዌ ሙሴን በሞአብ ሜዳ ዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ እንዲህ አለው፣ 2 ”የእስረኤል ሰዎችን ለሌዋውያን ርስታቸው ከሆነው ከድርሻቸው እንዲሰጧቸው እዘዝ፡፡ የሚኖሩባቸውን ከተሞችና በዙሪያቸውም የግጦሽ መሬት ይስጧቸው፡፡ 3 ሌዋውያን እነዚህን ከተሞች መኖሪያቸው ያድርጓቸው፡፡ የግጦሽ መሬቱ ለከብቶቻቸው ለመንጎቻቸው እና ለእንስሳቻቸው ይሁኑ፡፡ 4 ለሌዋውያኑ የምትሰጣቸው በከተሞቹ ዙሪያ የሚገኘው የግጦሽ መሬት ከከተማ ቅጥር በየአቅጣጫው ስፋቱ አንድ ሺህ ክንድ ይሆናል፡፡ 5 ከከተማዋ በምስራቅ አቅጣጫ ሁለት ሺህ ክንድ ለካ፣ በስተደቡብ በኩልም ሁለት ሺህ ክንድ ለካ፣ በምዕራብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፣ እና በሰሜን በኩል ሁለት ሺህ ክንድ ለካ፡፡ ይህ በከተማቸው ዙሪያ የግጦሽ መሬት ይሆናል፡፡ ከተማይቱ በመሃል ትሆናለች፡፡ 6 ለሌዋውያን የምትሰጧቸው ስድስቱ ከተሞች የስደተኞች ከተሞች ሆነው ያገለግሉ፡፡ እነዚህን ከተሞች በነፍስ መግደል ለተከሰሱ መሸሻ ስፍራ እንዲሆኑ ስጣቸው፡፡ እንዲሁም ሌሎች አርባ ሁለት ከተሞችን ስጣቸው፡፡ 7 ለሌዋውያን የምትሰጣቸው ከተሞች በጠቅላላው አርባ ስምንት ይሆናሉ፡፡ ከከተሞቹ ጋር የግጦሽ መሬትም ትሰጣቸዋለህ፡፡ 8 ብዙ የሆኑ የእስራኤል ህዝብ ጎሳዎችና ብዙ መሬት ያላቸው ጎሣዎች ብዙ ከተሞች ይሰጣቸዋል፡፡ አነስተኛዎቹ ጎሣዎች ጥቂት ከተሞች ይሰጣቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ነገድ እንደ ተቀበለው እንደ ድርሻው መጠን ለሌዋውያኑ መስጠት አለበት፡፡” 9 ከዚያም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ 10 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ዮርዳኖስን አቋርጣችሁ ወደ ከነዓን ስትገቡ፣ 11 ይሁነኝ ብሎ ሰው ያልገደለ ሰው ወደ እነዚያ ከተሞች መግባት እንዲችል የመሸሸጊየ ከተማ ሆነው የሚያገለግሉ ከተሞችን ምረጡ፡፡ 12 እነዚህ ከተሞች ከደመኞቻችሁ የምትሸሸጉባቸው ይሁኑ፣ ስለዚህም የተከሰሰው ሰው በቅድሚያ በማህበሩ ፊት ለፍርድ ሳይቀርብ አይገደልም፡፡ 13 የመሸሸጊያ ከተማ አድርጋችሁ ስድስት ከተሞችን ምረጡ፡፡ 14 ከዮርዳኖስ ወዲያ ሶስት ከተሞችን፣ በከነዓን ምድር ደግሞ ሶስት ከተሞችን ስጡ፡፡ እነዚህ የመሸሸጊያ ከተሞች ይሆናሉ፡፡ 15 እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ሰዎች፣ ለመጻተኞች፣ እና ለማናቸውም በመሀላቸው ለሚኖር ሳያውቅ ሰውን ለገደለ መሸሸጊያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ 16 ነገር ግን የተከሰሰው ሰው ተበዳዩን በብረት መሳሪያ ቢመታውና ተጠቂው ቢሞት፣ ተከሰሹ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ እርሱ በእርግጥ ይገደል፡፡ 17 የተከሰሰው ሰው በእጁ በያዘው ድንጋይ ተበዳዩን ቢመታና ተበዳዩ ቢሞት ተከሳሹ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ በእርግጥ ይገደል፡፡ 18 የተከሰሰው ሰው ተበዳዩን ሊገድል በሚችል የእንጨት መሳሪያ ቢመታውና ተበዳዩ ቢሞት ተከሳሹ በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ ሊገደል ይገባዋል፡፡ 19 ደም ተበቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው፡፡ ሲያገኘው፣ ሊገድለው ይችላል፡፡ 20 ተከሳሹ አንድን እየተደበቀ ወይም እየተሸሸገ ያለ ሰው በጥላቻ ቢገፈትረው ወይም አንዳች ነገር ቢወረውርበትና ከዚህም የተነሳ ተበዳዩ ቢሞት፣ 21 ወይም በጥላቻ መትቶ ቢጥለውና ከዚህም የተነሳ ተበዳዩ ቢሞት መትቶ የገደለው በእርግጥ ይገደል፡፡ ነብስ ገዳይ ነው፡፡ ደም ተበቃዩ ነብሰ ገዳዩን ሲያገኘው ይግደለው፡፡ 22 ነገር ግን ተከሳሹ ሰው ቀድሞ ባልታሰበበት ጥላቻ ተበዳዩን ቢመታው ወይም ሳያስበው አንዳች ነገር ወርውሮ ቢመታው፣ 23 ተበዳዩን ሳይመለከት ሊገድለው የሚችል ድንጋይ ቢወረውርበት፣ ተከሳሹ የተበዳዩ ጠላት አይደለም፤ ተበዳዩን ለመጉዳት እየሞከረ አልነበረም፡፡ የሆነ ሆኖ ተበዳዩ ቢሞት፣ 24 በዚህ ሁኔታ፣ ማህበረሰቡ በተከሳሹና በደም ተበቃዩ መሀል በእነዚህ ህጎች መሠረት ይዳኝ 25 ማህበረሰቡ ተከሳሹን ከደም ተበቃዩ እጅ ያድነው፡፡ ማህበረሰቡ ተከሳሹን በመጀመሪያ ወዳሸሸበት መሸሸጊያ ከተማ ይመልሰው፡፡ ተከሳሹ፣ በቅዱሱ ዘይት የተቀባው በወቅቱ ያለው ሊቀካህን እስኪሞት ድረስ በዚያ ይኑር፡፡ 26 ነገር ግን የተከሰሰው ሰው በማንኛውም ጊዜ ከሸሸበት ከተማ ድንበር አልፎ ቢሄድ፣ 27 እና ደም ተበቃዩ ከመሸሸጊያ ከተማው ድንበር ውጭ ቢያገኘውና ቢገድለው፣ ደም ተበቃዩ በነብሰ ገዳይነት ጥፋተኛ አይሆንም፡፡ 28 ለዚህም ምክንያቱ ተከሳሹ ሰው እስከ ሊቀ ካህኑ ሞት ድረስ በመሸሸጊያ ከተማው መቆየት ስለነበረበት ነው፡፡ 29 እነዚህ ህጎች፤ በምትኖባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ በትውልዳቸው ሁሉ ለእናንተ የጸኑ ናቸው፡፡ 30 ሰውን የገደለ ማንኛውም ሰው፣ በምስክሮች ቃል እየረጋገጠ መገደል አለበት፡፡ ነገር ግን የአንድ ምስክር ቃል ብቻውን ማንንም ሰው ለመግደል በቂ አይደለም፡፡ 31 ደግሞም፣ በነብስ ገዳይነት ጥፋተኛ ለሆነ ሰው ሕይወት የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፡፡ ያ ሰው በእርግጥ ይገደል፡፡ 32 ወደ መሸሸጊያ ከተማ ለሄደ የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፡፡ ሊቀ ካህኑ እስኪሞት ድረስ የነፍስ ዋጋ በመቀበል ወደ ራሱ ርስት ተመልሶ እንዲገባ አትፍቀዱለት፡፡ 33 በዚህ መንገድ የምትኖሩባትን ምድር አታርክሱ፣ ምክንቱም በነፍስ ግድያ የሚፈስ ደም ምድሪቱን ያረክሳል፡፡ ምድር በላይዋ ደም ሲፈስ፣ ደም ካፈሰሰው ሰው ደም በስተቀር ሌላ ምንም ማስተስረያ ማድረግ አይቻልም፡፡ 34 ስለዚህ የምትኖሩባትን ምድር አታርክሱ ምክንያቱም እኔ በውስጧ እኖራለሁ፡፡ እኔ፣ ያህዌ፣ በእስራኤል ሰዎች መሃል እኖራለሁ፡፡”
ሠፊ ሆኖ ለጥ ያለ ሜዳ
እግዚአብሔር የራሣቸው የሆነ መሬትለሌዋውያንያልሰጣቸው በመሆኑ በሌሎች ነገዶች ከተማዎች ውስጥ መቀመጥ ነበረባቸው፡፡
እንስሳት ሣር የሚግጡባቸው የመሬት ክፍል
“1000 ክንድ”ዘመናዊ የርቀት መለኪያን መጠቀም ከፈለጋችሁ ከዚህ በሚከተለው መልኩ ለማድረግ ትችላላችሁ፡፡“457 ሜትር”(ቁጥሮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ርቀት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
“2000 ክንድ”አንድ ክንድ 46 ሴንቲ ሜትር ነው፡፡(ቁጥሮችና መፅሐፍ ቅዱሣዊ ርቀት የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የሰው ነፍስ ያጠፉ ሰዎችን ሲሆን ነገር ግን ሰውዬውን የገደሉት ሆን ብለው ነው ወይስ ሳያስቡት ነው? የሚለውጥያቄ ግን ገና ውሳኔ ያላገኘ መሆኑን ነው፡፡
“42...48” (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
በድንገት ወይም ሳያደፍጡ ወይም ሆን ብለው ሳይጠብቁ
ጥፋተኛ የሆነውነ ሰው ለመበቀል የሚያደባ የቅርብ ዘመድን ነው፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ጥፋተኛው ሰው ወደ ማህበሩ ፈርዶ ፍርዱን ለማግኘቱ በፊት አንድ ሰው እንዳይገድለው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
እግዚአብሔር ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በእርግጥም ልትገድሉት ይገባል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውንና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ደም”የሚለው ቃል መግደል ለሚለው ሃሣብ ሌላ ገላጭ ቃል ነው፡፡“የገደለውን ሰው የሚበቀል” ወይም “ለመበቀል የሚፈልግ የቅርብ ዘመድ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የቅርብ ዘመድ የሆነ ሰው ጥፋተኛውን ሰው መግደል አለበት“ ወይም “ጥፋተኛው ሰው መሞት አለበት”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“ከጥላቻ የተነሣ ቀደም ሲል ጉዳዩን በተመለከተ ላይ ዕቅድ ሳይነድፍ”
አንድ ሰው ሌላን ሰው ሆነ ብሎ ለመጉዳት የሚያደርገው ክትትል አንድ ሰው ለማጥቃት ደፈጣ የሚያደርግ አስመስሎ ነው የተገለፀው፡፡“የሚጠቃውን ሰው ለመጉዳትት ሆነ ተብሎ ያልተደረገ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ደም”የሚለው ቃል መግደል ለሚለው ሃሣብ ሌላ ገላጭ ቃል ነው፡፡ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 35፡19 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ ማለት ማህበሩ ግድያው የተፈፀመው በአጋጣሚ ነው ብሎ የሚያስብ ከሆነ የተገደለው ሰው የቅርብ ዘመድ የሆነ ሰው እንዳይገድለው ያድኑታል፡፡ነገር ግን ማህበሩ ግድያው የተፈፀመው ታስቦበት እንደሆነ ካመነ የሟች የቅርብ ዘመድ የሆነ ሰው ጥፋተኛውን ሰው መግደል ይኖርበታል፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በቅዱስ ዘይት የቀባኸው ሰው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ላይ“ደም”የሚለው ቃል መግደል ለሚለው ሃሣብ ሌላ ገላጭ ቃል ነው፡፡ይህንን ሐረግ በዘኁልቁ 35፡19 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ለሙሴ መናገሩን ይቀጥላል፡፡
“ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ትውልዶቹ በሙሉ”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እርሱን ልትገድሉት ይገባቸኋል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውንና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው የመማፀኛ ከተማውን ለቅቆ ወደ ቤቱ ለመመለስ የፈለገን ሰው ነው፡፡“የመማፀኛ ከተማውን ለቅቆ እንዲሄድ መደፍቀድ የለባችሁም፡፡ወደ ቤቱ በመሄድ በራሱ ንብረት ላይ እንዲቀመጥ መፍቀድም የለባችሁም፡፡”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
“የነፍስ ዋጋን በመቀበል”
በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ምድር አካሉ እንደተመረዘ ነገር ተገልጿል፡፡ከሰው መግደል ጋር በተያያዘ የፈሰሰው ደም ምድሪቱ በእኔ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖራት የሚያደርግ በመሆኑ በዚህ ዓይነትሁኔታ ምድራችሁ በፊቴ ተቀባይነት እንዳይኖራት አታድርጉ፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
“የነፍስ ዋጋን በመቀበል”
ይሄ የሚያመለክተው አንድ ሰው ሆነ ብሎ ሌላ ሰው የገደለ ሲሆን ነው፡፡“አንድ ሰው በምድሪቱ ላይ ደም የሚያፈስስ ከሆነ ምድሪቱ የምትነፃው ያ ደም ያፈሰሰው ሰው ሲገደል ብቻ ነው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ከዚያ ከዮሴፍ ትውልዶች ጎሣ የሆኑት፣ የአባቶቻቸው ቤተሰቦች መሪዎች፣ የምናሴ ልጅ በሆነው በሚኪር ልጅ ገለዓድ የተመሠረተው ጎሳ በሙሴና በእስራኤላዊያን አባቶች ቤተሰቦች አለቆች ፊት መጥተው ተናገሩ፡፡ 2 እንዲህም አሉ፣ “ጌታችን ሆይ፣ ያህዌ ለእስራኤል ህዝብ ርስታቸውን በዕጣ እንድታካፍላቸው አዞሃል፡፡ የወንድማችንን የሰለጰዓድን ድርሻ ለሴት ልጆቹ እንድትሰጥ ያህዌ አዝዞህ ነበር፡፡ 3 ነገር ግን ሴት ልጆቹ ከእስራኤል ሰዎች ከሌላ ጎሣ ወንዶችን ቢያገቡ፣ ድርሻቸው የሆነው መሬት ከአባቶቻችን ድርሻ ተነቅሎ ወደ ሌላ ጎሣ ይተላለፋል፡፡ መሬቱ የገቡበት የሌላ ጎሳ ድርሻ ይሆናል፡፡ በዚያ ሁኔታ፣ ከእኛ ርስትነት ይነቀላል፡፡ 4 ይህ ሲሆን፣ የእስራኤል ኢዮቤልዩ ሲመጣ፣ የእነርሱ ድርሻ የተጋቧቸው ጎሣዎች ርስት ይሆናል፡፡ በዚህ መንገድ የእነርሱ ድርሻ ከእኛ አባቶች ጎሣ ይወሰዳል፡፡ 5 ስለዚህም ሙሴ በያህዌ ቃል ለእስራኤል ሰዎች ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ እንዲህም አለ፣ “የዮሴፍ ትውልዶች ጎሣ የተናገሩት ትክክል ነው፡፡ 6 ያህዌ ስለ ሰለጰዓድ፣ ሴት ልጆች ያዘዘው ይህ ነው፡፡ እንዲህም አለ፣ ‘የመረጡትን ያግቡ፣ ነገር ግን ማግባት ያለባቸው ከአባታቸው ጎሣ ብቻ ነው፡፡’ 7 የእስራኤል ሰዎች ድርሻ ከአንድ ጎሣ ወደ ሌላው መሄድ የለበትም፡፡ እያንዳንዱ እስራኤላዊ የራሱን ጎሣ ድርሻ ይዞ መቀጠል አለበት፡፡ 8 ከጎሣዋ ርስት የወረሰች እያንዳንዷ የእስራኤል ሴት፣ ማግባት ያለባት ከአባቷ ጎሣ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው እያንዳንዱ እስራኤላዊ የአባቶቹን ርስት ይዞ እንዲኖር ነው፡፡ 9 ከአንዱ ጎሣ ወደ ሌላው ምንም ርስት መተላለፍ የለበትም፡፡ የእስራኤል ህዝብ እያንዳንዱ ጎሣ የራሱን ርስት ይዞ መቀጠል አለበት፡፡” 10 ስለዚሀ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ፡፡ 11 የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ማህለህ፣ ቲርጳ፣ ጌግላ፣ ሚልካ፣ ኑዔ 12 ልጅ የምናሴትን ትውልዶች አገቡ፡፡ በዚህ መንገድ፣ ርስታቸው የአባታቸው ጎሣ ርስት ሆኖ ቀረ፡፡ 13 ያህዌ በሙሴ በኩል በሞአብ ሜዳዎች በዮርዳኖስ ኢያሪካ ላይ ለእስራኤል ሰዎች የሰጣቸው ትዕዛዛትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፡፡
ይሄ የሰው ሥም ነው፡፡የዚህን ሰው ሥም በዘኁልቁ 26፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር አዝዞሃል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሰው ሥም ነው፡፡የዚህን ሰው ሥም በዘኁልቁ 26፡33 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በአባቶቻችን ርስት ውስጥ ድርሻ አይኖረውም”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ድርሻው የሚሆነው…”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የርስታችን አካል አይሆንም”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ የሚያመለክተው በየሃምሣ ዓመቱ የሚደረገውን በዓል ነው፡፡በዚህ የበዓል ወቅት አንድ ሰው የሸጠው መሬትም ሆነ ንግድ ወደ መጀመሪያ ባለቤቱ መመለስ ይኖርበታል፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና የተሟላ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ድርሻቸው ….”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የእኛን ነገድ የመሬት ድርሻ ይወስዱታል”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት”
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ደስ ያላቸውን ሰው ያግቡ”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
ይሄ በድርጊት መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“የሚያገቡትን ሰው ግን ከአባታቸው ቤት ብቻ ነው ማግባት የሚኖርባቸው”(ገቢራዊ ወይም ፍዝ የሚለውን ይመልከቱ)
“ድርሻ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እንዳንዱ ነገድ በርስት መልክ የሚቀበለውን መሬት ነው፡፡“ምንም ዓይነት የመሬት ድርሻ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)
“በነገዷ ውስጥ የመሬት ርስት ያላት”
እያንዳንዱ ነገድ ንብረቱ የሚያደርገውን መሬት እንደሚቀበሉት ዓይነት ውርስ ተደርጎ ነው የሚነገረው፡፡ (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ባለቤትነትን ከአንድ ነገድ ወደ ሌላ ማስተላለፍን በተመለከተ ልክ አንድ ንብረት ከአንድ ሰው እጅ ወደ ሌላ ሰው እጅ እንደተላለፈ ዓይነት ተደርጎ ነው የሚገለፀው፡፡“ማንም ሰው ቢሆን የመሬት ድርሻ ባለቤትነትን ከአንድ ነገድ ወደ ሌላ ነገድ ማስተላለፍ አይኖርበትም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህን ስሞችበዘኁልቁ 26፡33 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ይመልከቱ)
የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች በንብረትነት የወሰዱት መሬት ልክ እንደወረሱት ውርስ ተደርጎ ተገልጿል፡፡“በውርስ መልክ የተቀበሉት መሬት”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሰፊና ለጥ ያለ መሬት
1 ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በምድር በዳ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ሜዳ በዓረባ፥ በፋራን፥ በጦፌል፥ በላባን፥ በሐጼሮት፥ በዲዛሃብ መካከል ሳሉ፥ ለአስራኤል ሁሉ የተናገራቸው እነዚህ ቃላት ናቸው። 2 በሴይር ተራራ መንገድ ከኮሬብ እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ የአሥራ አንድ ቀን ጉዞ ነው። 3 በአርባኛው ዓመት በአሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሙሴ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ያዘዘውውን ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ነገራቸው። 4 ይህም እግዚአብሔር በሐሴቦን ይኖር የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስታዎትና በኤድራይ ይኖር የነበረውንም የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመታ በኋላ ነበር። 5 በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ምድር ሙሴ እንዲህ ብሎ እነዚህን መመሪያዎች ይናገር ጀመር፦ 6 እግዚአብሔር አምላካችን በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን፦ በዚህ ተራራ የኖራችሁበት ይብቃችሁ። 7 ጉዞኣችሁን ወደ ኮረብታማው ወደ አሞራውያን አገር ወደ ድንበሮቹም፥ ሁሉ በዓረባም በደጋውና በቆላው፥ በደቡብና በባሕር ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስ ወንዝ ሸለቆ እስከ ታላቁ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ሄዱ። 8 እነሆ ምድሪቱን በፊታችሁ አድርጌአለሁ፤ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሂዱና ውረሱ። 9 በዚያን ጊዜ እንዲህ ብዬ ተናግሬአችሁ ነበር፦ እኔ በራሴ ብቻዬን ልሸከማችሁ አልችልም። 10 እግዚአብሔር አምላካችሁ አብዝቶአችኋል፥ እነሆም እናንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዙ ናችሁ። 11 የአባቶቻችሁ እግዚአብሔር አምላክ ሺህ ጊዜ ሺህ ያድርጋችሁ፤ ተስፋ እንደሰጣችሁም ይባርካችሁ። 12 ነገር ግን እኔ በራሴ ድካማችሁን፥ ሸክማችሁንና ክርክራችሁን እሸከም ዘንድ ብቻዬን እንዴት እችላለሁ? 13 ከእናንተ መካከል ከየነገዶቻችሁ ጥበበኞች፥ አስተዋዮችና አዋቂዎች የሆኑትን ሰዎች ምረጡ፤ እኔም እነርሱን የእናንተ አለቆች አደርጋቸዋለሁ ብዬኣችሁ ነበረ። 14 እናንተም እንዲህ ብላችሁ መለሳችሁ፦ የተናገርከንን ነገር ለማድረግ ለእኛ መልካም ነው። 15 ስለዚህም ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን ወሰድሁ፥ በእናንተም ላይ አለቆች እንዲሆኑ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳ አለቆች፥ የአሥር አለቆችና ሹማምንት በየገዶቻችሁ አደረግኋቸው። 16 በዚያን ጊዜም ፈራጆቻችሁን እንዲህ ብዬ አዘዝኳቸው፦ በወንድሞቻችሁ መካከል፤ በሰውና በወንድሙ መካከልና በመጻተኛ ላይ በጽድቅ ፍረዱ። 17 በክርክርም ጊዜ ለማንም ፊት አድልዎ አታድርጉ፥ ታላቁን እንደምትሰሙ፥ ታናሹንም ስሙ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለሆነ የሰው ፊት መፍራት አይገባችሁም። ከክርክርም አንድ ስንኳ ቢከብዳችሁ ወደ እኔ አምጡት እኔም እሰማዋለሁ። 18 በዚያን ጊዜም ልታደርጉት የሚገባችሁን ነገር ሁሉ አዘዝኋችሁ። 19 ከኮሬብም ተነስተን፥እግዚአብሔር አምላካችን እንዳዘዘን እንዳያችሁትም በታላቁና እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ምድረ በዳ ሁሉ ተጉዘን በተራራማው በአሞራውን አገር ሄድን፥ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን። 20 እኔም እንዲህ አልኋችሁ፦ እግዚአብሔር አምላካችን ወደ ሚሰጠን ወደ ተራራማው አሞራውያን አገር መጣችኋል። 21 እነሆ እግዚአብሔር አምላካችሁ ምድሪቱን በፊታችሁ አድርጎአል፤ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንዳላችሁ ውጡ፥ ውረሱአት፥ አትፍሩ አትደንግጡም። 22 ከእናንተም ሁላችሁ ወደ እኔ መጥታችሁ እንዲህ አላችሁ፦ ምድሪቱን እንዲሰልሉልንና እናጠቃቸው ዘንድ የሚገባንን የመንገዱንና የምንገባባቸውን ከተሞች ሁኔታ ተመልሰው እንዲነግሩን ከፊታችን ሰዎችን እንድስደድ። 23 ነገሩም ደስ አሰኘኝ፤ ከእናንተም ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎችን መረጥሁ። 24 እነርሱም ወደ ተራራማው አገር ሄዱ፥ ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጥተው ሰለሉአት። 25 እነርሱም ከምድሪቱ ፍሬ በእጃቸው ወሰዱ፥ ወደ እኛም ይዘውት መጡ። እነርሱም ደግሞ፦ እግዚአብሔር አምላካችን የሚሰጠን ምድር መልካም ናት ብለውም አወሩልን። 26 ምድሪቷንም ማጥቃት እንቢ ብላችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፥ ። 27 በድንኳናችሁም ውስጥ እንዲህ እያላችሁ አጉረመረማችሁ፦ እግዚአብሔር ስለ ጠላን እንዲያጠፋን በአሞራውያን እጅ አሳልፎ ይሰጠን ዘንድ ከግብፅ ምድር አወጣን። 28 አሁን ወዴት መሄድ እንችላለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሽጉና እስከ ሰማይም የደረሱ ናችው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፤ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን እንዲቀልጥ አደረጉ። 29 እኔም አልኋችሁ፦ አትደንግጡ፥ እነርሱንም አትፍሩአቸው። 30 በፊታችሁ የሚሄደው እግዚአብሔር አምላካችሁ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ በፊታችሁም በግብፅና በምድረ በዳ እንዳደረገላችሁ ሁሉ፤ 31 ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄድዳችሁበት መንገድ ሁሉ ሰው ልጁን እንደሚሸከም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተሸከማችሁ እናንተ አይታችኋል። 32 ዳሩ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁን በዚህ ነገር አላመናችሁትም፤ 33 በፊታችሁም ሆኖ በምትሄዱበት መንገድ ድንኳናችሁን እንድታቆሙ ቦታ እንድታገኙና በሌሊት በእሳት፥ በቀንም በደመና እንድትሄዱ መንገዱን ያሳታችሁ እርሱ ነው። 34 እግዚአብሔርም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቆጣ፥ ምሎም፥ እንዲህ አለ፦ 35 በርግጥ ለአባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ የማልሁላቸውን መልካሚቱን ምድር ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር ከእነዚህ ሰዎች ከዚህ ክፉ ትውልድ ማንም አያይም። 36 እርሱም እግዚአብህሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱና ለልጆቹ እሰጣለሁ ብሎ ማለ። 37 እግዚአብሔርም ደግሞ በእናንተ ምክንያት እኔን ተቆጣኝ እንዲህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደዚያ አትገባም 38 በፊትህ የሚሄድ አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደዚያ ይገባል፥ እርሱም እስራኤላውያን ምድሪቱን እንዲወርሱ ይመራቸዋልና፤ አደፋፍረው። 39 ከዚህም በተጨማሪ፦ ለጉዳት ይዳረጋሉ፥ ዛሬም መልካሙንና ክፉውን መለየት የማይችሉ ናቸው ያላችኋችሁ ታናናሽ ሕፃናታችሁ ልጆቻችሁ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ። ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ ይወርሱታልም። 40 እናንተ ግን ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ። 41 እናንተም፦ እግዚአብሔርን በድለናል፥ እግዚአብሔር አምላክችሁ እንዳዘዘን ሁሉ እንወጣለን፥ እንዋጋማለን ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር ለመውጣትና ለማጥቃት ተዘጋጀ። 42 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ እኔ በእናንተ መካከል ስለማልገኝ፥ በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትሸነፉ አትውጡ፥ አትዋጉም በላቸው አለኝ። 43 እኔም ተናገርኋችሁ እናንተም አልሰማችሁም። በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፥ አልሰማችሁም በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ለማጥቃት ወጣችሁ። 44 ነገር ግን በተራራማው አገር ይኖሩ የነበሩ አሞራውያን በእናንተ ላይ ወጥተው እንደ ንብ አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር መቱአችሁ። 45 ተመልሳችሁም በእግዚአብሔር ፊት አለቀሳችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ድምፃችሁን አልሰማም፥ ወደ እናንተም አላዳመጠም። 46 ሁሉም ቀናት በቆያችሁባችሁ ለብዙ ቀን በቃዴስ ተቀመጣችሁ።
ይህ የሚያመለክተው ከእስራኤል በስተምስራቅ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሮ ያለውን ምድር ነው። ሙሴ ለእስራኤላውያን በሚናገርበት ጊዜ ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ ነበር። አ.ት፡ ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ከኮሬብ ወደ ቃዴስ በርኔ ለመጓዝ አሥራ አንድ ቀን ይፈጃል”
ይህ ከሙት ባህር በስተደቡብ ያለ ተራራማ አካባቢ ነው። አካባቢው “ኤዶም” በመባልም ይታወቃል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“11” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
መቁጠሪያ ቁጥሮች ወደ ተራ ቁጥሮች ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “ሙሴ በተናገራቸው ጊዜ በምድረ በዳ የኖሩት ለ40 ዓመታት፣ ለ11 ወራትና ለ1 ቀን ነበር። (መቁጠሪያ ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
40ኛ (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በዕብራውያኑ የቀን አቆጣጠር አሥራ አንደኛው ወር ነው። የመጀመሪያው ቀን በምዕራባውያን አቆጣጠር ወደ ጥር ወር አጋማሽ ይቃረባል።(የዕብራውያን ወራት እና መቁጠሪያ ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
11ኛ (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ራሱን ለሕዝቡ የገለጠበት ስሙ ነው። ያህዌ እንዴት እንደሚተረጎም ለመረዳት የትርጉም ቃል ገጽን ተመልከት።
“እስራኤላውያን እንዲያሸንፉ እግዚአብሔር አስችሏቸው ነበር”
እነዚህ የነገሥታት ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው ከእስራኤል በስተምስራቅ ከዮርዳኖስ ወንዝ ባሻገር ያለውን ምድር ነው። ሙሴ ይህንን በሚናገርበት ጊዜ ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ ነበር። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 1፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ”።
“እኛ” የሚለው ቃል ሙሴንና ሌላውን የእስራኤል ሕዝብ ያመለክታል።
ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ከዚህ በኋላ በዚህ ተራራ አጠገብ መቆየት አይኖርባችሁም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ተመልሳችሁ” የሚለው ቃል አንድን ተግባር ለመጀመር ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “እንደገና ጉዞአችሁን ቀጥሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔ ለእስራኤላውያን ለመስጠት ቃል በገባላቸው ምድር አካባቢዎቹን እያብራራላቸው ነው።
ይህ አሞራውያን ይኖሩ ከነበሩበት አቅራቢያ የሚገኝ ኮረብታማ አካባቢ ነው።
ዝቅና ለጥ ያለ የምድር አካባቢ
“ለምናገረው ነገር ትኩረት ስጡ”
“አሁን ይህችን ምድር ሰጥቻችኋለሁ”
እግዚአብሔር ራሱን እንደ ሌላ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እኔ እግዚአብሔር ምያለሁ” (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)
“አባቶች” የሚለው ቃል አያት፣ ቅድም አያቶችን ሁሉ የሚወክል ነው። አ.ት፡ “አያት፣ ቅድም አያቶች” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው ሙሴን ነው። “በዚያን ጊዜ” የሚለው ሐረግ እስራኤላውያን በኮሬብ፣ ይኸውም የሲና ተራራ ራሱ ነው፣ በዚያ የነበሩበትን ጊዜ ነው። አ.ት፡ “በኮሬብ በነበርንበት ጊዜ ነገርኳችሁ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እዚህ ጋ “ልሸከማችሁ” ማለት “ልመራችሁ” ወይም “ላስተዳድራችሁ” ማለት ነው። አ.ት፡ “በራሴ ልመራችሁ ይከብደኛል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ግነት ሲሆን ትርጉሙም እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን ቁጥር እጅግ አብዝቶታል ማለት ነው። አ.ት፡ “እጅግ ብዙ ሕዝብ”(ግነት፣ ጥቅል አስተያየት እና Simile)
“አንድ ሺህ” የሚለው ሐረግ “በጣም ብዙ” የሚል ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በጣም ብዙ ጊዜ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1000 (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ችግሮቻቸውን በሙሉ ለብቻው መፍታት እንደማይችል አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ችግራችሁን፣ ሸክማችሁንና ክርክሮቻችሁን ለብቻዬ መሸከም አልችልም”። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ የተሸከመውና ሊፈታቸው ያስፈልጉ የነበሩት የሕዝቡ ችግሮችና ቅሬታዎች ለእርሱ ልክ ቁስ አካል የመሸከም ያህል እንደከበዱት ይናገራል። አ.ት፡ “ችግሮቻችሁን፣ ቅሬታዎቻችሁን መፍታት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሙግታችሁን” ወይም “አለመግባባቶቻችሁን”
“ከእያንዳንዱ ነገድ እስራኤላውያን የሚያከብሯቸው ሰዎች”
“ወገኖቻችሁ የሚያከብሯችሁን ሰዎች”። ይህ በዘዳግም 1፡13 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት።
የ1000 ቡድን _ የ100 ቡድን _ የ50 ቡድን _ እና የ10 ቡድን (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በእስራኤል መንግሥት የተለያዩ መሪዎች የሚጠሩባቸው መጠሪያዎች ናቸው።
“ከእያንዳንዳችሁ ነገድ”
“እስራኤላውያን እርስ በእርሳቸው በሚኖራቸው ክርክር ላይ ትክክለኛና ፍትሐዊ ውሳኔ ስጡ”
“አድልዎ አታድርጉ”
“ታናሽ” እና “ታላቅ” የተባሉት እነዚህ ሁለት ጽንፎች ሕዝቡን ሁሉ ይወክላሉ። አ.ት፡ “ሕዝቡን ሁሉ በእኩል ትዳኙታላችሁ” (See: Merism)
“ፊት” የሚለው ቃል የሰውን ሁለንተና የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። “አትፈሩም” ትዕዛዝ ነው። “ማንንም አትፍሩ” (See: Synecdoche)
ይህ ማለት በኮሬብ፣ በሲና ተራራ በነበሩበት ጊዜ ማለት ነው። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ያቋረጣችሁት ያ ሰፊና አደገኛ ምድረ በዳ
ሙሴ ለአንድ ሰው የሚናገር ይመስል የሚናገረው ለእስራኤላውያን ነው፤ በመሆኑም እነዚህ ቅርጾች ብዙ ሳይሆኑ ነጠላ ቁጥር ናቸው። (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)
“አሁን ይህቺን ምድር ሊሰጣችሁ ነው”። ይህ በዘዳግም 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ተመልከት
“12 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
መመለስ መመሪያውን ለመታዘዝ መጀመራቸውን የሚገልጽ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ያንን ስፍራ ትተው ሄዱ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከኢየሩሳሌም በስተደቡብ የሚገን በኬብሮን አውራጃ የሚገኝ ሸለቆ ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“መውጋት የሚችሉባቸውን አካባቢዎች ተመለከቱ”
“12ቱ ሰዎች ወሰዱ”
“ከምድሪቱ ፍሬ ጥቂቱን አነሡ”
ተናጋሪው “ቃል” አንድ ሰው ሊያመጣው የሚችለው ቁስ አካላዊ ነገር ይመስል ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ቀጥተኛው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አምላካችን የሚሰጠን ምድር ጥሩ እንደሆነ ተነግሯል”
እስራኤላውያን አሞራውያንን እንዲወጉና እንዲያጠፏቸው እግዚአብሔር አዘዛቸው፣ ነገር ግን እስራኤላውያን ፈሩ፣ ከእነርሱ ጋር ለመዋጋትም እምቢ አሉ”። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እዚህ ጋ “በ እጅ” ማለት ለአሞራውያን በእነርሱ ላይ የበላይ እንዲሆኑ መስጠት ማለት ነው። አ.ት፡ “ለአሞራውያን ኃይል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ይህ ጥያቄ ምን ያህል እንደ ፈሩ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ምንም መሄጃ የለንም”። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ፈርተዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “በጣም እንድንፈራ አደረጉን” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከተሞቹ ሰፊና ጠንካራ በመሆናቸው ምክንያት ሰዎቹ ምን ያህል እንደ ፈሩ አጽንዖት የሚሰጥ ግነት ነው። አ.ት፡ “ሰማይ የሚደርሱ የሚመስሉ ግንቦች አሏቸው” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የኤናቅ ሕዝብ ተወላጆች ሲሆኑ በጣም ረጃጅምና ኃይለኞች ነበሩ። (See: Assumed Knowl- edge and Implicit Information and ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ለአባቶቻችሁ ነገርኳቸው”
እዚህ ጋ ሰዎቹ ስላዩት ነገር አጽንዖት ለመስጠት በ”ዐይኖቻቸው” ተወክለዋል። አ.ት፡ “እናንተ ራሳችሁ ያያችሁት” (See: Synecdoche)
ሙሴ፣ እስራኤላውያን አንድ ሰው የሆኑ ይመስል “አንተ” እና “የአንተ” እያለ ይናገራል፤ እነዚህ አገባቦች ሁሉ ነጠላ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
እዚህ ጋ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚያደርግላቸው ክብካቤ ከአባት ጋር ተነጻጽሯል። አ.ት፡ “አባት ልጁን እንደሚንከባከብ አምላካችሁ እግዚአብሔር ተንከባክቧችኃል” (See: Simile)
“እግዚአብሔር ሊሰጣችሁ ቃል ወደገባላችሁ ወደዚህ ምድር እስክትመጡ ድረስ”
ባለፈው ዘመን በጉዞአቸው ሁሉ እግዚአብሔር በእስራኤል ፊት የሄደባቸውን መንገዶች በሙሉ ሙሴ ያስታውሳቸዋል።
“ድንኳኖቻችሁን ትከሉ”
“ስትናገሩ የነበረውን ሰማ”
በእርሱ ላይ ያመጹት እግዚአብሔር ሊሰጣቸው ቃል ወደ ገባላቸው ምድር እንዳይገቡ ማለ።
“ይገባሉ”
“ከካሌብ በቀር”
ይህ የካሌብ አባት ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ራሱን እንደ ሌላ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እርሱ ሙሉ በሙሉ ታዞኛል” (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው ሙሴ በእስራኤል ሕዝብ ላይ በመቆጣቱ ምክንያት እግዚአብሔር እንዲያደርግ የነገረውን ያልታዘዘበትን ጊዜ ነው። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ የኢያሱ አባት ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ኢያሱ በሙሴ ፊት ለምን ይቆም እንደነበረ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እንደ አገልጋይህ በፊትህ የሚቆመው” ወይም “የሚረዳህ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
የትኛው ክፉ እና የትኛው ደግ እንደሆነ ገና የማያውቁ
“ወደ ኋላችሁ ተመለሱና በመጣችሁበት መንገድ ተመልሳችሁ ሂዱ”
“እርሱን ባለመታዘዝ በእግዚአብሔር ላይ አምጸናል”
“እንታዘዛለን”
እዚህ ጋ “ኮረብታማው አገር” የተባለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚወክለው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “በኮረብታማው አገር የሚኖሩትን ሰዎች ለመውጋት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከእናንተ ጋር ስለማልሆን ጠላቶቻችሁ ያሸንፏችኋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ኮረብታማው አገር” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የቆመው በዚያ ለሚኖሩ ሰዎች ነው። አ.ት፡ “በኮረብታማው አገር የሚኖሩትን ሰዎች ወጉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ንብ” ትንሽ፣ በራሪ ነፍስ ሲሆን በመንጋ ሆኖ የሚበርና ስጋት የሚሆኑባቸውን ሰዎች የሚነድፍ ነው። ይህ ማለት በጣም ብዙ አሞራውያን የእስራኤል ወታደሮችን ከጦርነቱ እስኪሸሹ ድረስ ወግተዋቸዋል። (See: Simile and የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ አነስተኛ ምድር ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ከወታደሮቻችሁ ብዙዎቹን ገደሉ”
“ወደ ቃዴስ ተመለሳችሁና አለቀሳችሁ”
1 ከዚያም እግዚአብሔርም እንደተናገረኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ጉዞአችንን በምድረ በዳ ውስጥ ተመለስን፤ 2 በሴይርም ተራራ ዙሪያ ለብዙ ቀናት ተጓዝን። 3 እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ይህን ተራራ የዞራችሁበት ይበቃችኋል፤ ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሄዱ። 4 ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር በሚኖሩ በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ድንበር ታልፋላችሁ፤ እነርሱም ይፈሩአችኋል። 5 ስለዚህ የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ያህል እንኳ አልሰጣችሁም፥ ከእነርሱም ጋር እንዳትዋጉ እጅግ ተጠንቀቁ።። 6 የምትበሉትንም ምግብ ከእነርሱም በገንዘብ ትገዛላችሁ፤ የምትጠጡትንም ውኃ ደግሞ በገንዘብ ትገዛላችሁ። 7 አምላካችሁ እግዚአብሔር ፤ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መጓዛችሁን ስላወቀ የእጃችሁን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና። በእነዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አልጎደለባችሁም። 8 በሴይርም ከሚኖሩት ከወንድሞቻችሁ ከዔሳው ልጆች በዓረባ መንገድ ከኤላትና ከዔጽዮን ጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን። 9 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ሞዓብን አታስጨንቁአቸው፤ አትውጋቸውም። ምክንያቱም የእነርሱን ምድር ርስት እንዲሆንላችሁ አልሰጣችሁም፤ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ሰጠኋችሁ። 10 አስቀድሞ ታላቅና ብዙ ሕዝብ ሆነው እንደ ዔናቅምልጆች በቁመት የረዘሙ ኤሚማውያን በዚያ ይኖሩ ነበር፤ 11 እነርሱም ደግሞ እንደ ዔናቅ ልጆች ራፋይም ይባሉ ነበር፤ ሞዓባውያን ግን ኤሚም ይሉአቸዋል። 12 ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ይኖሩ ነበር፥ የዔሳው ልጆች ግን አሳደዱአቸው። እግዚአብሔርም በሰጠው በርስቱ ምድር እስራኤል እንዳደረገ፥ ከፊታቸው አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም መኖር ጀመሩ። 13 እግዚአብሔርም፦ ተነሡ የዘሬድንም ወንዝ ተሻገሩ አለ። የዘሬድንም ወንዝ ተሻገርን። 14 ከቃዴስ በርኔ ከመጠንበት ዘሬድን ወንዝን እስከ ተሻገርንበት ቀኖች ድረስ ሠላሳ ስምንት ዓመታት ነበሩ። እግዚአብሔር እንደ ማለላቸው ለመዋጋት ብቁ የሆኑ ሰዎች ትውልድ ሁሉ ከሕዝብ መካከል የጌድይት በዚያን ጊዜ ነበር። 15 ከዚህ በተጨማሪ፥ ከመሄዳቸው በፊት ከሕዝቡ መካከል ለማጥፋት የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ከብዶ ነበረ። 16 ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ሁሉ ከሕዝቡ መካከል በሞቱና በጠፉ ጊዜ 17 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ 18 አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ። 19 ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ በአሞን ልጆች አቅረቢያ ስትደርስ አታስጨንቁአቸው አትውጋቸውም፤ ምክንያቱም ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና ። 20 ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቆጠረ። ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ይኖሩ ነበር፤ 21 አሞናውያን ግን ዛምዙማውያን ብለው የሚጠሩአቸው እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው ረጅም ነበር። 22 እግዚአብሔር ከአሞራውያን ፊት አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ይኖሩ ነበር። ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍተው በሴይር ለሚኖሩት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፤እነርሱም አሳድደው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ። 23 እስከ ጋዛ ድረስ ባሉ መንደሮች ይኖሩ የነበሩትን ኤዋውያንን ከከፍቶር የወጡ ከፍቶራውያን አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ኖሩ። 24 ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንንና ምድሪቱን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻለሁ። እርስዋን ለመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ። 25 ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ወሬህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፥ ድንጋጤም ይይዛቸዋል። 26 ከቅዴሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦ 27 ወደ ቀኝና ግራ ሳልል በአገርህ ላይ በአውራ ጎዳና ልለፍ። 28 የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፥ የምጠጣውንም ውኃ በገንዘብ እንድገዛ ስጠኝ፤ 29 በሴይር የሚኖሩ የዔሳው ልጆች፥ በዔርም የሚኖሩ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ ብቻ በእግሬ ልለፍ። 30 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችሁ ዘንድ ልቡን ስላደነደነና ስላጸና የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም ። 31 እግዚአብሔርም፦ እነሆ ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት ጀመርሁ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር አለኝ። 32 ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊጋጠሙን ወደ ያሀጽ ወጡ። 33 እግዚአብሔር አምላካችንም አሳልፎ ስለሰጠን አሸነፈነው፥እርሱንና ልጆቹን፥ ሕዝቡንም ሁሉ እስኪሞቱ ድረስ አሸነፍን፤መታንም። 34 በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን የተቀመጡባቸውንም ሰዎች ሁሉ ሴቶችንና ሕፃናትን አንዳችም ሳናስቀር አጠፋን። 35 ከብቶቻቸውንና በከተሞቻቸው ያሉትን ብቻ ብዝበዛ ለራሳችን ወሰድን። 36 በአርኖን ቆላ ጫፍ ካለው ከአሮዔር ከሸለቆውም ውስጥ ካለው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ ማናቸውም ከተማ ከእኛ በላይ አልሆነም። እግዚአብሔር አምላካችን በፊታችን ባሉት ጠላቶቻችን ላይ ድልን ሰጠን። 37 ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ወደ ከለከለን ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማው አገር ወዳሉት ከተሞች አልደረስንም።
“ከዚያም ተመለስንና ሄድን”
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እስራኤላውያን ሴይር ተብሎ በሚጠራው ተራራ አቅራቢያ ለረጅም ጊዜ ተጉዘዋል ወይም 2) እስራኤላውያን ሴይር ተብሎ በሚጠራው ተራራ አካባቢ ለረጅም ጊዜ ተቅበዝብዘዋል።
ይህ ከሙት ባህር በስተደቡብ የሚገኝ ተራራማ አካባቢ ነው። አካባቢው “ኤዶም” በመባልም ይጠራል። ይህንን በዘዳግም 1፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህንን አንዳንድ ቋንቋዎች “ብዙ ሌሊቶች” ብለው ይተረጉሙታል።
“ዘመዶቻችሁ የኤሳው ተወላጆች”
እግዚአብሔር ለኤሳው ተወላጆች ይህንን ክልል እንደ ሰጣቸው እስራኤላውያንን ያስታውሳቸዋል።
እግዚአብሔር የሚሰጣቸው ትዕዛዝ ሳይሆን ፈቃድ ወይም መመሪያ ነው፣ እንዳይሰርቁም ይነግራቸዋል። “ከእነርሱ ምግብ እንድትገዙ እፈቅድላችኋለሁ” ወይም “ምግብ ከፈለጋችሁ ከእነርሱ መግዛት ይኖርባችኋል”
“ከኤሳው ተወላጆች”
ይህ ቃል የማያስፈልግ ወይም ትርጉሙን ግልጽ የማያደርግ ከሆነ መተው ይኖርብህ ይሆናል።
ሙሴ እስራኤላውያንን አንድ ሰው እንደሆኑ ዓይነት አድርጎ ይናገራል፣ በመሆኑም “አንተ” እና “የአንተ” ተብለው የተነገሩት ሁሉ ነጠላ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
የ “እጅህ ሥራ” የሚያመለክተው ያደረጉትን ሥራ ሁሉ ነው። አ.ት፡ “ሥራህን ሁሉ” (See: Synec- doche)
እዚህ ጋ ሕዝቡ ሲጓዙ የደረሰባቸው እንደ “መንገድ” ተነግሯል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“40 ዓመታት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ “የምትፈልጉት ሁሉ ነበራችሁ” የተጋነነ አባባል ነው። (የተጋነነ አባባል የሚለውን ተመልከት)
“በዘመዶቻችን”
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “መጓዛችንን ቀጠልን” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ሞዓብ” የሚለው ቃል የሚወክለው የሞዓብን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “የሞዓብን ሕዝብ አታስቸግሯቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በሞዓብ የሚገኝ የአንድ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የእስራኤል ሕዝብ ከሞዓብ ተወላጆች ጋር ዝምድና ነበራቸው። ሞዓብ የሎጥ ልጅ ነበር። ሎጥ ደግሞ የአብርሃም የወንድም ልጅ ነበር። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እነዚህ ቃላት ከሞዓባውያን በፊት በምድሪቱ ላይ ስለነበሩት ስለ ኤሚም ሕዝብ ዳራዊ መረጃ ይሰጣሉ። ቋንቋህ ዳራዊ መረጃን ለማመልከት የተለየ መንገድ ይኖረው ይሆናል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ግዙፍ እንደሆኑ የሚታሰቡ የሕዝብ ወገን ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በጣም ረጃጅምና ኃይለኞች የነበሩ የዔናቅ ሕዝቦች ተወላጆች ናቸው። ይህንን በዘዳግም 1፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የአንድ የሕዝብ ወገን ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ከእነርሱ ጋር አንዱም በሕይወት እንዳይኖር ሁሉንም ገደሏቸው” ወይም “ሁሉንም በመግደል ከአጠገባቸው አስወገዷቸው”
“ከዚያም እግዚአብሔር፣ “አሁን ተነሡ _ ዜሬድ’ ስለዚህ”። ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከዚያም እግዚአብሔር ተነሥተን _ ዜሬድ ተናገረን። ስለዚህ” (ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
አንድ ነገር ለማድረግ ጀምሩ (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ምንጭ ከደቡብ ምስራቅ ወደ ሙት ባህር በመፍሰስ በኤዶምና በሞዓብ መካከል ድንበር ያበጃል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“አሁን” የሚለው ቃል ከትረካው የእስራኤል ሕዝብ ለምን ያህል ጊዜ እንደተጓዙና በዚያ ትውልድ ላይ እግዚአብሔር ወደተቆጣበት ዳራዊ መረጃ መቀየሩን ያመለክታል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
“38 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ “ሞተው ነበር” የሚል የትህትና አነጋገር ነው። (See: Euphemism)
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር እጅ” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ኃይል ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ኃይሉን በእነርሱ ላይ ተጠቅሟል” ወይም “እግዚአብሔር ቀጣቸው” (See: Synecdoche)
ሙሴ ለእስራኤላውያን አንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ በመሆኑም “አንተ” እና “አታስቸግሯቸው” የሚልበት ትዕዛዝ አገባብ ሁሉ ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
ይህ በሞዓብ የሚገኝ የአንድ ከተማ ስም ነው። “ዔር”ን በዘዳግም 2፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የእስራኤል ሕዝብ ከአሞን ተወላጆች ጋር ዝምድና ነበራቸው። አሞን የሎጥ ልጅ ነበር። ሎጥ ደግሞ የአብርሃም የወንድሙ ልጅ ነበር። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች ያንን ደግሞ ይቆጥሩ ነበር”። (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ሕዝብ ወገን ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 2፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የረፋይም ሕዝብ ወገን ሌላው ስማቸው ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ሕዝብ ወገን ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 2፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“አሞናውያን እንዲያሸንፏቸው ፈቀደላቸው” ወይም “አሞናውያን ሁሉንም እንዲገድሏቸው ፈቀደላቸው”
“አሞናውያኑ ረፋይማውያን የነበራቸውን ሁሉ ወሰዱባቸው፣ ረፋይማውያን ይኖሩ በነበሩበትም ስፍራ ኖሩ”
ይህ የአንድ ሕዝብ ወገን ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 2፡12 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ሖራውያን የነበራቸውን ሁሉ ወሰዱባቸው፣ ሖራውያን ይኖሩ በነበሩበትም ስፍራ ኖሩ”
እነዚህ የሕዝብ ወገን ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
x
ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔር ለሙሴ እየነገረው ነው። “አሁን ተነሡ” ወይም “አሁን ሂዱ”
“ጉዞአችሁን ቀጥሉ”
ይህ የአርኖን ወንዝ ሸለቆ ስም ነው። እርሱ በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ድንበር ያበጃል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“በእጃችሁ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉም “በቁጥጥራችሁ ወይም በኃይላችሁ ሥር” ማለት ነው። አ.ት፡ “እንድታሸንፉ ኃይልን ሰጥቻችኋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለእስራኤላውያን አንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ በመሆኑም “አንተ” እና “የእናንተ” እንዲሁም ትዕዛዝ የሆኑት “ለመውረስ ጀምሩ” እና “ተዋጉ” ሁሉም አገባቦች ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
ይህ የአንድ ንጉሥ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ከእርሱና ከሰራዊቱ ጋር ተዋጋ”
“ፍርሐት” እና “ድንጋጤ” የሚሉት ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ቢሆንም ፍርሐቱ ታላቅ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “ከባድ ፍርሐት ጣሉባቸው” (See: Doublet)
ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በየአገሩ ያሉ ሕዝቦች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሕዝቡ በጭንቀት እንደሚንቀጠቀጡ አጽንዖት ይሰጣል። (See: Hendiadys)
እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው ሙሴን ነው።
ይህ በአርኖን ሸለቆ አቅራቢያ የሚገኝ ቦታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሰውና የቦታ ስም ነው። እነዚህን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ሰላምን ባቀርብላቸው” ወይም “ስለ ሰላም ከሚጠይቅ መልዕክቴ ጋር”
ይህ ሐረግ ሁሌም በአንድ አቅጣጫ እንደሚሄዱ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። “አቅጣጫዬን አልቀይርም” ወይም “ሁሌም መስመሬን ጠብቄ እጓዛላሁ” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እስራኤላውያን ከአሞራውያን እንደማይሰርቁና ሴዎንና ሕዝቡ ምግብና ውሃ እንዲሸጡላቸው ሴዎንን ይጠይቀዋል እንጂ ትዕዛዝ አይሰጠውም። አ.ት፡ “ለምበላው ምግብና ለምጠጣው ውሃ መክፈል እንዳለብኝ አስባለሁ”
ሙሴ ስለራሱ አድርጎ የሚናገረው እስራኤላውያንን ሲያመለክት ነው። አ.ት፡ “እንበላው ዘንድ - ለእኔና ለሕዝቤ ሽጥልኝ - እንጠጣው ዘንድ - ስጠን” (See: Synecdoche)
“በምድርህ ተራምደን ብቻ እንለፍ”
ይህ የቦታ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 2፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሰውና የቦታ ስም ነው። እነዚህን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራል፣ ስለዚህ በሁሉም አገባብ “ያንተ” የሚለው ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
ሁለቱም ሐረጎች ትርጉማቸው ተመሳሳይ ሲሆን አጽንዖት የሚሰጠው እግዚአብሔር “በጣም ግትር እንዲሆን አደረገው” ለማለት ነው። (See: Parallelism)
“ሴዎንን እና ምድሩን ለአንተ ልሰጥህ”
“ትወርሰው ዘንድ የእርሱን ምድር ለራስህ ውሰድ”
ይህ የአንድ ንጉሥ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሞዓብ ውስጥ የነበረ የአንድ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“የንጉሥ ሴዎንን ከተሞች በሙሉ ያዝን”
“በየከተማው ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች ሁሉ ገደልን”
ይህ በአርኖን ወንዝ ሰሜናዊ ዳርቻ የሚገኝ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“አርኖን” የወንዝ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 2፡24 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ አሉታዊ አገላለጽ በጦርነት የነበራቸው ስኬት ላይ አጽንዖት ለመስጠት ጥቅም ላይ ውሏል። ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ምንም እንኳን ከተማው ዙሪያው በረጃጅም ቅጥር የታጠረ ቢሆንም በየከተማው ያሉትን ሕዝቦች ማሸነፍ ችለናል። (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እስራኤላውያኑን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራል፣ ስለዚህ “አንተ” ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
ይህ በሴዎን እና በአሞናውያን ምድር መካከል ድንበር ያበጀ ወንዝ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
1 ተመልሰን በባሳን መንገድ ሄድን፥ የባሳን ንጉሥ ዐግና ሕዝቡ ሁሉ በኤድራይ ሊዋጉን መጡ። 2 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴሶን ላይ እንዳደረግህ በእርሱም ታደርግበታለህ አለኝ። 3 እግዚአብሔር አምላካችንም በባሳን ንጉሥ በዐግ ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን ድልን ሰጠን። እኛም አንድ እንዳይቀር እስኪሞቱ ድረስ መታነው። 4 በዚያን ጊዜም አንድም ያልወሰድነው ሳይቀር ሁሉንም ስድሳ ከተሞችን፦ በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት፥ የአርጎብን አገር ሁሉ ከተሞችን ወሰድን። 5 እነዚህም ከተሞች ሁሉ ዙሪያቸው በረጅም ቅጥር፥ በበሮቻቸውና በመወርወሪያዎች የተመሸጉ ነበር፤ በአጠገባቸውም ብዙ ያልተመሸጉት ከተሞች ነበሩ። 6 በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ከወንዶችና ሴቶች ከሕፃናትም ጋር ፈጽሞ አጠፋናቸው። 7 ነገር ግን ከአጠፋናቸው ከተሞች ሁሉ ከብቶቹን ሁሉ ምርኮም ለራሳችን ወሰድን። 8 በዚያም ጊዜ ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ ምድሪቱን ከዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩ ከሁለቱ ከአሞራውያን ነገሥታት እጅ ወሰድን፤ 9 (ሲዶናውያን አርሞንዔምን ሢርዮን ብለው ይጠሩታል፥ አሞራውያንም ሳኔር ብለው ይጠሩታል) ፤ 10 በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ በባሳንም ያሉትን የዐግን መንግሥት ከተሞች እስከ ስልካና፤እስከ ኤድራይ ድረስ ባሳንን ሁሉ ወሰድን። 11 ከራፋይም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ተርፎ ነበር፤ እነሆም አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች አገር በረባት አልኖረምን? ይህም በሰው ክንድ ልክ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። 12 በዚያን ጊዜ በአርሞን ሸለቆ ከአሮዔር ርስት አድርገን የወሰደነውን ይህን የገለዓድን ተራራማ ምድር እኩልታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገድ ሰጠኋቸው። 13 ከገለዓድም የቀረውን የዐግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ የአጎብንም ምድር ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ። (ይህም ተመሳሳይ አገር የራፋይም ምድር ተብሎ ይቆጠራል።) 14 የምናሴ ነገድ አንዱ ኢያዕር እስከ ሄሸራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አካባቢ ሁሉ ወሰደ። ይህንም የባሳንን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ የሚጠራውን በስሙ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ጠራ። 15 ለማኪርም ገለዓድን ሰጠሁት። 16 ለሮቤል ነገድና ለጋድም ነገድ ከገለዓድ ጀምሮ እስከ አርግኖን ሸለቆ ድረስ የሸለቆውን እኩሌታ ዳርቻውንም እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ሰጠኋቸው። 17 ከኪኔሬት እስከ ዓርባ ባሕር (እርሱም የጨው ባሕር) ድረስ ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ ያለውን የዮርዳኖስን ሸለቆ ዳቻውንም ሰጠኋቸው። 18 በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ እናንተ የጦር ሰዎች መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ ከእስራኤል ልጆች ፊት ታልፋላችሁ። 19 ነገር ግን ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ (ብዙ ከብቶች እንዳሉአችሁ አውቃለሁ) በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀመጣሉ፤ 20 ይኸውም እግዚአብሔር እናንተን እንዳሳረፈም ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁላችሁ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ። 21 በዚያም ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ብዬ አዘዝሁት፦አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ያደረገውን ሁሉ ዓይኖችህ አይተዋል፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታትም ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል። 22 አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ ስለ እናንት ስለሚዋጋ አትፈራቸውም ብዬ አዘዝሁት። 23 በዚያም ጊዜ እኔ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ለመንሁ፦ 24 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህንና ብርቱ እጅህን ለእኔ ለባሪያህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይ ወይም በምድር እንደ አንተ፥ እንደ ኃይልህ፥ ያደርግ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው? 25 እኔም ወደዚያ ልሂድና በዮርዳኖስም ማዶ ያለውን መልካሙን ምድርና መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ለመየት እለምንሃለሁ። 26 እግዚአብሔር ግን እናንተ ባለመስማታችሁ ምክንያት ተቆጣኝ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ስለዚህም ነገር ደግመህ እንዳትናገረኝ ይበቃሃል። 27 ይህን ዮርዳኖስን ስለማትሻገር ወደ ፈስጋ ራስ ውጣና ዓይንህንም ወደ ምዕራብ፥ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብምና ወደ ምሥራቅ ዓይንህን አንሥተህ ተመልከት። 28 በዚህ ፈንታ ኢያሱን አስተምራው፥ አደፋፍረው እንዲሁም አጽናው፤ ምክንያቱም እርሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሄዳል፥ አንተም የምታየውን ምድር ያወርሳቸዋል። 29 ስለዚህም በቤተ ፌጎርም በሸለቆው ውስጥ ቆየን።
እነዚህ የነገሥታት ስሞች ናቸው። እነዚህን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። እነዚህ በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ሙሴ እስራኤላውያንን እንደሆነ ያህል ይናገረዋል፣ ስለዚህ “አትፍራ” የሚለው ትዕዛዝና “አንተ” እና “የአንተ” የሚለው አገባብ ሁሉ ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
እዚህ ጋ “እርሱን” እና “የእርሱ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ዐግን ነው።
እግዚአብሔር ሊያደርግ ያለውን አስቀድሞ እንዳደረገው ቆጥሮ ይናገራል። (See: Predictive Past)
“በእርሱ” የሚለው ቃል”በእርሱ ሕዝብ ላይ” ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ሴዎንን እንዳደረግኸው ዐግንና ሕዝቡን ታጠፋቸዋለህ” (See: Synecdoche)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የዐግን ሕዝብ በሙሉ በቁጥጥራችን ሥር አደረገ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
አስራኤላውያን ማንንም በሕይወት እንዳላስቀሩ አጽንዖት ለመስጠት ይህ ምጸት ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “የእርሱ የሆነው ሕዝብ ሁሉ ሞተ” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
ይህ 60ዎቹን ከተሞች በሙሉ ስለመውሰዳቸው አጽንዖት የተሰጠበት ድርብ አሉታ ነው። አ.ት፡ “እያንዳንዱን ስልሳ ከተማ ወሰድን” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)
“60 ከተሞች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በባሳን ውስጥ ያለ የአንድ አካባቢ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“እነዚህ ከተሞች በሙሉ በ -- የተጠበቁ ነበሩ”
“በጣም ብዙ ከሆኑት በተጨማሪ” ወይም “በጣም ብዙ የሆኑትን ሳይጨምር”
ይህ የአንድ ንጉሥ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“በየከተማው የሚኖሩትን ሰዎች በሙሉ በመግደል”
እዚህ ጋ “ከእጃቸው” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር “ከቁጥጥራቸው” ማለት ነው። አ.ት፡ “ከሁለት ነገሥታት ቁጥጥር” ወይም “ከሁለቱ ነገሥታት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“የአሞራዊ ሕዝቦች -- የባሳን ምድር -- የኤድራይ ከተማ -- ንጉሥ ዐግ”። እነዚህን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ይህ ከእስራኤል በስተምስራቅ ከዮርዳኖስ ወንዝ ባሻገር ያለውን ምድር ያመለክታል። ሙሴ ይህንን በሚናገርበት ጊዜ ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ ነበር። ይህንን በዘዳግም 1፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ”
እነዚህን ቃላት በዘዳግም 2፡24 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
እነዚህ በሙሉ ከባሳን በስተሰሜን ዳርቻ ላይ ያለው የአንድ ተራራ ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአርኖን ወንዝና በገለዓድ ተራራ መካከል ያለ ረጅምና ሰፊ ስፍራ ነው።
ይህ በኤድሪ አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የንጉሥ ዐግ ዳራዊ መረጃ ነው። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
ይህንን በዘዳግም 2፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ለምነግርህ ጠቃሚ ነገር ትኩረት ስጥ”።
ጸሐፊው የእስራኤል ሕዝብ ወደ ረባት እንዲሄዱና ዐግ ምን ያህል ታላቅ እንደነበረ ያዩ ዘንድ ለማስታወስ ጥያቄ ያቀርባል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) “የሚኖረው -- በረባት ነበር” ወይም “በረባት -- ይኖራል” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
አንድ ክንድ 46 ሴንቲ ሜትር ይረዝማል። (መጽሐፍ ቅዱሳዊ የርቀት መለኪያ የሚለውን ተመልከት)
“አብዛኛው ሰው በሚጠቀምበት የክንድ መለኪያ”
የዚህን ከተማ ስም በዘዳግም 2፡36 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እነዚህን ቃላት በዘዳግም 2፡24 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
እነዚህን ቃላት በዘዳግም 3፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ጸሐፊው የእስራኤል ሕዝብ ስለ ያዙት ምድር ዳራዊ መረጃ ማቅረብ ይጀምራል። የአንተ ቋንቋ ቀጥሎ የሚመጣው ዳራዊ መረጃ መሆኑን የሚያሳይበት መንገድ ካለ እርሱን እዚህ ጋ መጠቀም አለብህ። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
የዚህን ምድር ስም በዘዳግም 2፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ከባሳን በስተምዕራብ የሚኖሩ የሕዝብ ወገን ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ተርጓሚዎች የሚከተለውን የግርጌ ማስታወሻ ያደርጉ ይሆናል፡ “ ‘ሓቦት ኢያዕር’ ማለት ‘የኢያዕር የድንኳን መንደሮች’ ወይም ‘የኢያዕር ግዛት’ ማለት ነው”።
እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው ሙሴን ነው።
ማኪር የምናሴ ልጅ ነበር። እርሱ ሙሴ ይህንን ምድር ከመስጠቱ በፊት ሞቶ ነበር። ስሙ ለሰውየው ተወላጆች ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ለማኪር ተወላጆች” (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአርኖን የወንዝ ሸለቆ ስም ነው። እርሱ በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ድንበር ያበጃል። ይህንን በዘዳግም 2፡24 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በሴዎን ምድር እና በአሞናውያን ምድር መካከል ድንበር ያበጀ ወንዝ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 2፡37 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“የሮቤላውያን እና የጋዳውያን ድንበር ምዕራባዊ ወሰናቸው ነው”
የኪኔሬት ባህር “የገሊላ ባህር” ወይም “የጌንሳሬጥ ሐይቅ” ተብሎም ይጠራል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከአባሪም ሰንሰለታማ ተራራ በስተሰሜን የሚገን የተራራ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ሌሎች እስራኤላውያን እግዚአብሔር ተስፋ የሰጣቸውን የቀረውን ምድር ድል ያደርጉ ዘንድ የሮቤል ነገድ፣ የጋድ ነገድና ከፊሉ የምናሴ ነገድ እንዲያግዟቸው ሙሴ ያስታውሳቸዋል (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“የጦር መሣሪያዎቻችሁን ትይዙና ቀድማችሁ የዮርዳኖስን ወንዝ ትሻገራላችሁ”
“እስራኤላውያን ባልንጀሮቻችሁ”
ጸሐፊው የማረፍን ችሎታ በስጦታ እንደሚሰጥ ቁሳዊ አካል አድርጎ ይናገራል። በተጨማሪም፣ “ማረፍ” የሚለው ቃል ጦርነት የሌለበትን ሰላማዊ ኑሮ የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ወድሞቻችሁ እንዲያርፉ እግዚአብሔር ይፈቅዳል” ወይም “በጦርነት መዋጋትን አቁመው በሰላም እንዲኖሩ እግዚአብሔር ለወንድሞቻችሁ ይፈቅዳል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከእስራኤል በስተምስራቅ ከዮርዳኖስ ወንዝ ባሻገር ያለውን ምድር ያመለክታል። ሙሴ ይህንን በሚናገርበት ጊዜ ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ ነበር። በዘዳግም 1፡1 ላይ እነዚህን ቃላት እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ”
እግዚአብሔር ለእነዚህ ሦስት ነገዶች ምድራቸውን እንዲወርሱ ከመፍቀዱ በፊት ሌሎቹ ነገዶች መሬታቸውን መውረስ እንዳለባቸው ሙሴ አጽንዖት ይሰጣል። “የምትመለሱት ከዚያ በኋላ ብቻ ነው”።
እዚህ ጋ “ዐይኖችህ” የሚያመለክተው ኢያሱን ነው። አ.ት፡ “አንተ ዐይተሃል” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው ሙሴን ነው። ይህ ማለት በጣም ቅንና ስሜታዊ በሆነ መንገድ እግዚአብሔርን ጠይቆታል።
እዚህ ጋ “አገልጋይህ” የሚለው ቃል ለአንድ ታላቅ ሥልጣን ላለው በትህትና የመናገር መንገድ ነው። አ.ት፡ “ለአገልጋይህ ልታሳየኝ”
እዚህ ጋ ፈሊጣዊ የሆነው “እጅ” መቆጣጠር ወይም ኃይል ማለት ነው። አ.ት፡ “ኃይልህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ሥራዎች ለማድረግ ኃይል ያለው ብቸኛው አምላክ እርሱ መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት በጥያቄ መልክ ያቀርባል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “. . . የሚያደርግ ሌላ አምላክ የለም”። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
የእነዚህ ሁለት ጽንፎች ትርጉም በአንድነት “የትም ቦታ” ማለት ንው። (See: Merism)
“ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ”። ሙሴ ይህንን ቃል ለእግዚአብሔር በሚናገርበት ጊዜ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ ሞዓብ ውስጥ ነበረ።
ይህ የሚያመለክተው ሙሴ በእስራኤል ሕዝብ ላይ በመቆጣቱ ምክንያት እግዚአብሔር እንዲያደርግ ያዘዘውን ያልታዘዘበትን ጊዜ ነው። ይህንን በዘዳግም 1፡37 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህንን በዘዳግም 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ዐይኖችህን አንሣ” የሚሉት ቃላት ዘይቤአዊ አነጋገር ሲሆን ተመልከት ማለት ነው። አ.ት፡ “ተመልከት” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በፈስጋ ተራራ አጠገብ በሞዓብ ውስጥ የሚገኝ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
1 አሁንም እስራኤል ሆይ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወት እንድትኖሩና የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ሄዳችሁ እንድትወርሱ የማስተምራችሁን ሥርዓትንና ድንጋጌን ስሙ። 2 እኔ የማዛችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዛትን ሁሉ ሳትጨምሩና ሳታጎሉ ትጠብቃላችሁ። 3 ከብዔልፌጎርም የተነሣ፥ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከመካከላችሁ እንዳጠፋ ዓይኖቻችሁ አይተወል። 4 እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁን የተከተላችሁ እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወት አላችሁ። 5 እነሆ እናንተ ለመውረስ በምትሄዱባቸው ምድር ሰዎች መካከል ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር አምላኬ እንዳዘዘኝ ሥርዓትንና ድጋጌን አስተማርኋችሁ። 6 ስለዚህ ጠብቁአቸው፥ አድርጉአቸውም፤ ምክንያቱም ስለእነዚህ ሥርዓት ሰምተው፦ 'በእውነት ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው' በሚሉ ሰዎች ሁሉ ፊት ይህ ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ነው። 7 በምንጠራው ጊዜ ሁሉ እንደምቀርበን እንደ እግዚአሔር አምላካችን፥ ወደ እነርሱ የቀረበ አምላክ ያለው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነው? 8 ዛሬ በፊታችሁ እንደማኖራው ሥርዓት ሁሉ ጽድቅ የሆነው ሥርዓትና ድንጋጌ ያለው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነው? 9 ዓይኖቻችሁ ያዩትን ነገር እንዳትረሱ በሕይወታችሁም ዘመን ሁሉ ከልባችሁ እንዳይጠፋ ብቻ አስታውሉ፤በጥንቃቄም ራሳችሁን ጠብቁ። እግዚአብሔር፦ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ እንደተናገረኝ፥ 10 በእግዚአብሔር አምላካችሁ ፊት በኮሬብ በቆማችሁ ቀን እንደሰማችሁ፥ይህን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ዘንድ እንዲታውቅ አድርጉ። 11 እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር። እስከ ሰማይም መካከል ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፤ ጨለማና ደመና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ። 12 እግዚአብሔርም በእሳት ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ ድምፅን በቃል ሰማችሁ መልክን ግን አላያችሁም፤ ድምፅን ብቻ ሰማችሁ። 13 ታደርጉትም ዘንድ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን አሥሪቱን ቃላት አስታወቃችሁ። በሁለቱም በድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው። 14 በዚያን ጊዜ ትወርሱአት ዘንድ በምትሄዱባት ምድር የምታዳርጉትን ሥርዓትና ድንጋጌ አስተምራችሁ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዝኝ። 15 እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት መካከል ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክን ከቶ እንዳላያችሁ፤ለራሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ። 16 የማናቸውንም ፍጥረት ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል በወንድ ወይም በሴት፥ 17 ወይም በማናቸውም በምድር ባለው በዱር እንስሳ መልክ፥ ወይም ከሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ምሳሌ፥ 18 ወይም በምድር ላይ የሚሳበውን ሁሉ ምሳሌ፥ ወይም ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ በማድረግ እንዳትረክሱ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። 19 ዓይኖቻችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት ሕዝብ ሁሉ የመደባቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊት ሁሉ ባያችሁ ጊዜ አምልኮና ስግደት በማቅረብ እንዳትስቱ ተጠንቀቁ። 20 እናንተን ግን እግዚአብሔር እንደ ዛሬው ሁሉ የርስቱ ሕዝብ ትሆኑለት ዘንድ ወስዶ ከብረት እሳት ከግብፅ አወጣችሁ። 21 ከዚህም በተጨማሪ እግአብሔር በእናንተ ምክንያት ተቆጣኝ፣ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር ፥እግዚአብሔር አምላካችሁም ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደመልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ። 22 እኔ ግን በዚህች ምድር እሞታለሁ፥ ዮርዳኖስንም አልሻገርም፥ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፥ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ። 23 እግዚአብሔር አምላካችሁም ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እግዚአብሔር አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ። 24 እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና። 25 ልጆችን የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ብዙ ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ በማናቸውም ምስል የተቀረጸውን ምስል አድርጋችሁ በረከሳችሁም ጊዜ፥ ታስቆጡትም ዘንድ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በሠራችሁ ጊዜ ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ፤ 26 ከምትገቡባት ምድር እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆኑ እጠራለሁ፤ ዘመናችሁም አይረዝምም፥ ፈጽሞም ትጠፋላችሁም። 27 እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ በአሕዛብም መካከል ጥቂት ትሆናላችሁ፥እግዚአብሔርም ያስወጣችሁኋል። 28 በዚያም የማያዩትን፥ የማይሰሙትን፥ የማይበሉትን፥ የማያሸቱትንም በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት ታመልካላችሁ። 29 ነገር ግን ከዚያ እግዚአብሔር አምላካችሁን ትሻላችሁ፤ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም የፈለጋችሁት እንደ ሆነ ታገኛላችሁ። 30 በተጨነቃችሁና ይህም ሁሉ በደርሰባችሁ ጊዜ በዘመኑ ፍጻሜ ወደ እግዚአብሔር አምላካችሁ ትመለሳላችሁ፥ ድምፁንም ትሰማላችሁ። 31 እግዚአብሔር አምላካችሁ መሓሪ አምላክ ነውና፥ አይተዋችሁም፥ አያጠፋችሁምም፤ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን ቃል ኪዳኑን አይረሳም። 32 እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ከሰማይ እስከ ዳርቻዋ ድረስ ከቶ እንዲህ ያለ ታላቅ ነገር ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰምቶ እንደ ሆነ ከእናንተ በፊት የነበረውምን የቀደመውን ዘመን ጠይቁ። 33 እናንተ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደሰማችሁት ሌላ ሕዝብ ሰምቶአልን? 34 ወይም እግዚአብሔር አምላካችሁ በዓይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንዳደረገው ሁሉ በፈተናና በተአምራት በድንቅና በጦርነት በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ በታላቅም ማስፈራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ለራሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ በዐይናችሁ ፊት አድርጎ ያውቃልን? 35 እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ የተገለጡ ናቸው፤ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም። 36 ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳት አሳያችሁ፤ ድምፁንም ከእሳት መካከል ሰማችሁ። 37 አባቶቻችሁን ስለወደደ ከእነሱም በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ከግብፅም በታላቁ ኃይል በመገኘቱ አወጣችሁ፤ 38 ዛሬ እንደ ሆነ ከእናንተ የጸኑትን ታላላቆችን አሕዛብ ከፊታችሁ ሊስያወጣቸውና ለእናንተም ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ሊሰጣችሁ ነው። 39 እንግዲህ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቁ፤ በልባችሁም ያዙት። 40 ለእናንተ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችሁም ለዘላለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ። 41 በዚያን ጊዜ ሙሴ አስቀድሞ ጠላት ያልነበረውን ሰው ሳያውቅ የገደለው ሰው 42 ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖር ዘንድ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞች መረጠ። 43 ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቦሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ። 44 ሙሴ በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት። 45 ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ እግዚአብሔር የተናገራቸው የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች፥ ሥርዓቶች፥ ሌሎችም ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤ 46 በቤተ ፌጎር አንጻር ባለው ሸለቆ፥ በሴዎን ምድር፣ ከዮርዳኖስ በስትምሥራቅ፥ በነበሩበት ጊዜ፥ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ በወጡበት ጊዜ ድል ያደረጉአቸው በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአራውያን ንጉሥ ነበር። 47 የእርሱንና የባሳንን ንጉሥ የዐግን ምድር ወሰዱ፤ 48 በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩትን የሁለቱ የአሞራያን ነገሥታት እነዚህ ናቸው። ይህም ምድር ከአርኖን በአሮዔር ዳርቻ እስከ ሴዎን ተራራ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ፥ 49 በምሥራቅ በኩል የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ሜዳ በሙሉ ጨምሮ በዮርዳኖስ ማዶ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለውን ዓረባ ሁሉ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ያለው ነው።
እግዚአብሔር እንዲያደርጉት የሚፈልግባቸውን ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ እየነገራቸው ነው።
“እና ታዘዟቸው”
እግዚአብሔር ሕዝቡ አዲስ ሕግ እንዲያዘጋጁ ወይም አስቀድሞ የሰጣቸውን ቸል እንዲሉ አይፈልግም።
እዚህ ጋ “ዐይኖት” የሚያመለክቱት የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “ዐይታችኋል” (See: Synecdoche)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በብዔልፌጎር በሠራችሁት ኃጢአት ምክንያት” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህንን በዘዳግም 3፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “የአንተ” እና “አንተ” ነጠላ ቁጥር ናቸው። (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)
ጸሐፊው በእግዚአብሔር መታመንና እርሱን መታዘዝን በአካላዊ ሁኔታ አንድን ሰው ከመያዝ ጋር አመሳስሎ ይናገራል። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ጠንቃቆች የነበራችሁ እናንተ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ልብ በሉ”
“በምድሪቱ በምትኖሩበት ጊዜ ልትታዘዟቸው ይገባችኋል”
በመሠረቱ ሁለቱም ሐረጎች የሚሉት ተመሳሳይ ነገር ሲሆን እንዲታዘዟቸው አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “በጥንቃቄ ታዘዟቸው” (See: Doublet)
የነገር ስም የሆኑት “ጥበብ” እና “ማስተዋል” እንደ ቅጽል ሐረግ ሊተርጎሙ ይችላሉ፣ የነገር ስም የሆነው “ፊት” ሰዎች የአንድን ነገር ዕሴት እንዴት እንደሚፈርዱ ወይም እንደሚወስኑ ያመለክታል። አ.ት፡ “ጥበበኞችና አስፈላጊ የሆነውን የምትረዱ መሆናችሁን ለሕዝቦች የሚያሳየው ይህ ነው” (See: የነገር ስም እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“መንግሥት” የሚለው ቃል ለዚያ መንግሥት ሕዝብ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የዚህ ታላቅ መንግስት ሕዝብ ጥበበኞችና አስተዋዮች ናቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ምላሽ የማይፈልጉ ጥያቄዎች እንደ መግለጫ ሆነው መተርጎም ይችላሉ። አ.ት፡ “እንደ እርሱ ያለ ታላቅ ሕዝብ የለም። ዛሬ ሌላ ታላቅ ሕዝብ የለም”። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለእስራኤላውያን ይናገራል፣ ስለዚህ “አንተ”፣ “የአንተ” እና “ራሳችሁ” እንዲሁም “አስተውሉ”፣ “ጠብቁ” እና “አስታውቁ” የሚሉት ትዕዛዛት በሙሉ ነጠላ ቁጥር ናቸው። (ተውላጠ ስም እና Forms of You የሚለውን ተመልከት)
“በጥንቃቄ አስተውሉ፣ እነዚህን ነገሮች ሁል ጊዜ ለማስታወስም እርግጠኞች ሁኑ”
እነዚህ ሐረጎች የሚሉት ተመሳሳይ ነገር ሲሆን የእስራኤል ሕዝብ ያዩትን ማስታወስ እንዳለባቸው አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Parallelism)
እዚህ ጋ “ዐይኖች” ሰውን ይወክላሉ። አ.ት፡ “ዐይታችኋል” (See: Synecdoche)
“ሕዝቡን በአንድ ላይ ሰብስበህ ወደ እኔ አምጣልኝ”
ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። “ልብ” የአንድ ነገር “መካከል” ወይም “ውስጠኛው ክፍል” ማለት ሲሆን “ሰማይ” ደግሞ የሚያመለክተው ጠፈርን ነው። አ.ት፡ “ወደ ጠፈር በሚደርስ እሳት” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ድቅድቅ ጨለማ” የሚገልጸው ደመናን ነው። አ.ት፡ “ጥቅጥቅ ባለ ጥቁር ደመና” (See: Hendiadys)
ሌላው አማራጭ ትርጉም “ከባድ ደመና” የሚለው ነው።
“እግዚአብሔር ዐወጀ”
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ስለዚህ በምታደርጉት ነገር በጣም መጠንቀቅ ይኖርባችኋል” ወይም 2) “ነፍሳችሁን በጥንቃቄ ጠብቁ”
“ትክክል ያልሆነውን ነገር አታድርጉ”
“በመሬት ላይ የሚጎተት”
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት አገባቦችና “ማንሣት”፣ “መመልከት” እና “መቅረብ” ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማንም ለማምለክ እንድትፈልግ እንዲያደርግህ አትፍቀድ” ወይም “ታመልክ ዘንድ ለራስህ ፈቃድን አትስጥ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በጠፈር ላይ ለማየት የምትችላቸውን ነገሮች ሁሉ”። ይህ በሌላ አባባል ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ያመለክታል።
ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። ሙሴ፣ ምግብን እንደመሳሰሉ ትናንሽ ነገሮች እግዚአብሔር ለሕዝብ ወገኖች አከፋፍሎ እንደሚሰጣቸው የሚናገረው ስለ ከዋክብት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የማብሰያው ብረት እንደሚግል ሙሴ የሚናገረው ስለ ግብፅና እስራኤላውያን እንደ ብረት ሆነው በዚያ ይሠሩ ስለነበረው ከባድ ሥራ ነው። አ.ት፡ “ሰዎች ከባድ ሥራ እንድትሠሩ ከሚያደርጉበት ምድር አውጥቶ አመጣችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ “የእርሱ ብቻ የሚሆንለት ሕዝብ” ተብሎ ሊተረጎም የሚችል ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ በእስራኤል ሕዝብ ላይ በመቆጣቱ ምክያንት እግዚአብሔርን ሳይታዘዝ የቀረበትን ጊዜ ያመለክታል። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። ይህንን በዘዳግም 1፡37 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ሙሴ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለእስራኤላውያን ይናገራል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
“በጥንቃቄ አስተውሉ”
ሙሴ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለእስራኤላውያን ይናገራል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
ሙሴ፣ እግዚአብሔር ሲቆጣ የሚያደርጋቸውን ነገሮችን እሳት ከሚያቃጥልበት መንገድ ጋር ያነጻጽራል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሌሎች አማልክትን እንድታመልክ ስለማይፈልግ እሳት እንደሚያደርገው አምላክህ እግዚአብሔር በብርቱ ይቀጣሃል፣ ያጠፋሃልም”።(ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት ነጠላ ቁጥሮች ናቸው።
የአንዱ አባት ወይም አያት መሆን
“ትክክል ያልሆነውን ብታደርጉ”። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “እርሱ ክፉ ያለውን በማድረግ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ታስቆጡታላችሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) ሙሴ ለሚናገረው በሰማይ የሚኖሩትን ሁሉና ምድርን ምስክር አድርጎ ይጠራል ወይም 2) ሙሴ፣ ሰዎችን የሆኑ ይመስል ሰማይና ምድር እርሱ ለሚናገረው ምስክር እንዲሆኑ ይጠራቸዋል። (See: (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት and Personification)
ረጅም ቀናት የረጅም ዕድሜ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ረጅም ዘመን መኖር አትችሉም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በ4፡27 ላይ እንደተመለከተው እያንዳንዱ እስራኤላዊ አይገደልም። እዚህ ጋ “ፈጽሞ መጥፋት” በጥቅሉ ብዙ እስራኤላውያን እንደሚሞቱ አጽንዖት መስጫ ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ነገር ግን እግዚአብሔር ብዙዎቻችሁን ያጠፋችኋል” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሕዝቡ ዘር የሆነ ይመስል እግዚአብሔር እርሻ ላይ እንደሚበትናቸው ሙሴ ይናገራል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ወደተለያዩ አገሮች ይላካችኋል፣ በዚያ እንድትኖሩም ያስገድዳችኋል”።(ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ይልካችኋል” ወይም “ጠላቶቻችሁ እንዲወስዷችሁ ያደርጋል”
እዚህ ጋ “የሰው እጅ” የሚያመለክተው ሰውን ራሱን ሲሆን “ሥራ -- እንጨትና ድንጋይ” ደግሞ የቀረጿቸውን ጣዖታት ያመለክታሉ። አ.ት፡ “ሰዎች የሠሯቸው የእንጨትና የድንጋይ ጣዖታት” (See: Synecdoche)
“ነገር ግን በሌሎች አገሮች በምትኖሩበት ጊዜ”
እዚህ ጋ “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“በእርግጥ እርሱን ለመፈለግ በምትሞክሩበት ጊዜ” ወይም “እርሱን በእርግጥ ለማወቅ በምትሞክሩበት ጊዜ”
እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የሰውን ውስጠኛ ማንነት የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። እነዚህ ሁለት ሐረጎች በአንድነት የተነገሩት “ሙሉ በሙሉ” ወይም “በቅንነት” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)
“ይደርስብሃል”
“ከዚያ በኋላ” ወይም “ከዚያም”
እዚህ ጋ “መስማት” ዘይቤአዊ አነጋገር ሲሆን ትሩሙ ማድመጥና መታዘዝ ነው። በተጨማሪም፣ “ድምፁን” የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ሆኖ እርሱ በሚናገረው ላይ አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “እርሱ የሚላችሁን ታዘዙት” (የአነጋገር ዘይቤ እና Synecdoche የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ፣ ባለፈው ጊዜ እግዚአብሔር እንዴት አስገራሚ በሆነ መንገድ እንደተናገራቸው የእስራኤል ሕዝብ እንዲያስታውሱ ተደርገዋል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከእናንተ በስተቀር እግዚአብሔር ከእሳት መካከል ተናግሮት በሕይወት የኖረ ሌላ ሕዝብ የለም”።(ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ እግዚአብሔር በድምፁ ተወክሏል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሲናገር ድምፁን ሰምታችኋል” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “ጽኑ እጅ” እና “የተዘረጋች ክንድ” የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ጽኑ ኃይሉን በማሳየት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዐይኖች” የሚያመለክቱት የሰውን ሁለንተናውን ነው። አ.ት፡ “በፊት ለፊታችሁ” (See: Synecdoche)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች አሳይቶአችኋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“እንደሰማችሁ አረጋግጧል . . . እንዳያችሁ አረጋግጧል”
ሙሴ ከብዙ ዓመታት በፊት በሲና ተራራ የተናገራቸውን እነዚያኑ ሕዝቦች ይናገር ይመስል ለሕዝቡ ይናገራል። በመሠረቱ በሲና ተራራ የነበሩት ሰዎች እነዚህን ቃላት ለሚናገራቸው ሰዎች አባቶቻቸው ነበሩ። አ.ት፡ “አባቶቻችሁን … አድርጓል፣ አባቶቻችሁ ሰምተዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብንና የያዕቆብን ወንዶች ልጆች ነው።
“ከሀልዎቱ በሚመጣ በታላቅ ኃይሉ” ወይም “በታላቅ ኃይሉ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አስታውሰው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“በሰማይ” እና “በምድር” የሚሉት ሁለት ሐረጎች ሁለት ጽንፎችን የሚያሳዩ ሲሆኑ ትርጉማቸው “በሁሉ ስፍራ” ማለት ነው። አ.ት፡ “በሁሉ ነገር ላይ” (See: Merism)
ረጅም ቀናት ለረጅም ሕይወት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ረጅም ዕድሜ ለመኖር እንድትችል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በቀጣዮቹ ምዕራፎች ሙሴ የሚሰጣቸውን ሕግጋት ያመለክታል።
ይህ በሞዓብ ውስጥ ፈስጋ ተራራ አጠገብ የሚገኝ ከተማ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 3፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ንጉሥ ሴዎን … አሞራውያን ሕዝቦች … የሐሴቦን ከተማ”። እነዚህን ስሞች በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
የንጉሥ ሴዎንን ምድር
ይህንን በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ከእስራኤል በስተምስራቅ፣ ከዮርዳኖስ ወንዝ ባሻገር ያለውን ምድር ያመለክታል። ሙሴ ይህንን በሚናገርበት ጊዜ ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ ነበር። አ.ት፡ “ከዮርዳኖስ ወንዝ አቅጣጫ በስተምስራቅ … ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ በኩል”
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 2፡36 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የአንድ ቦታ ስም ነው። ይህንን በዘዳግም 2፡24 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እነዚህ የተራራ ስሞች ናቸው። እነዚህን ስሞች በዘዳግም 3፡8-9 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
እነዚህን ስሞች በዘዳግም 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
1 ሙሴም የእስራኤል ልጆችን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአቸውና እንድትጠብቁአቸው ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራውን ሥርዓቶችንና ድንጋጌዎችን ስሙ። 2 እግዚአብሔር አምላካችን ከእኛ ጋር በኮሬብ ቃል ኪዳን አድርጎአል። 3 እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ቃል ኪዳን አላደረገም ዛሬ በሕይወት ካለነው ከእኛ ጋር ነው። 4 እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ፊት ለፊት በተራራው ላይ በእሳት መካከል ተናገረ፥ 5 (በዚያን ጊዜ ከእሳቱም የተነሣ ፈርታችሁ ወደ ተራራው ባልቀረባችሁ ጊዜ ቃሉን ልገልጥላችሁ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር) ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ 6 ከባርነት ቤት፥ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። 7 ከእኔ በቀር በፊቴ ሌሎች አማልክት አይኑራችሁ። 8 በላይ በሰማይ፥ወይም በታች በምድር፣ወይም ከምድርም በታች በውኃ፥ ማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል ለራሳችሁ አታድርጉ። 9 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ ስለሆንኩ ለአማልክት አትስገዱላቸው፥ ወይም እነርሱን አታገልግሉአችሁ። በሚጠሉኝ ላይ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የእባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ ቅጣትን ያመጣል፥ 10 ለቃል ኪዳኔም ታማኝነት ለሚያሳዩኝና ለሚወዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ አምላክ ነኝ። 11 የአምላካችሁን ስም በከንቱ አትጠቀሙ፥ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠቀመውን ከበደል አያነጻውምና። 12 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ የሰንበትን ቀን ትቀድሱት ዘንድ ጠብቁ። 13 ስድስት ቀን ሥሩ ተግባራችሁንም ሁሉ አድርጉ፤ 14 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ሰንበት ነው። እናንተ እንደምታርፉ ሁሉ አገልጋያችሁና የቤት ሠራተኛችሁ ያርፉ ዘንድ እናንተ ወንድ ልጆቻችሁ፥ ሴት ልጆቻችሁም ፥ አገልጋዮቻችሁ፥ የቤት ሠራተኞቻችሁም በፊታችሁ፥ አህዮቻችሁም፥ ከብቶቻችሁም፥ ሁሉ በደጆቻችሁ ውስጥ ያለው እንግዳም ጭምር በሰንበት ምንም ሥራ አትሥሩ። 15 እናንተም በግብፅ በሪያ እንደ ነበራችሁ አስቡ፥ እብዚአብሔር አምላካችሁ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ከዚያ አውጣችሁ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሰንበትን ቀን ትጠብቁ ዘንድ አዘዛችሁ። 16 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ ምድር ላይ ዕድሜአችሁ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንላችሁ አባታቸውንና እናታቸውን አክብሩ። 17 አትግደሉ። 18 አታመንዝሩ። 19 አትስረቁ። 20 በባልንጀራችሁ ላይ በሐሰት አትመስክሩ። 21 የባልንጀራችሁን ሚስት አትመኙ፤ የባልጀራችሁን ቤት፥ እርሻውንም፥ አገልጋዩንም፥ የባልጀራችሁንም በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከባልጀራችሁ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኙ። 22 እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳትና በደመና በጨለማም ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምፅ፥ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤአችሁ ሁሉ ከተናገረው ምንም አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላችቶች ላይ ጻፋቸው ለእኔም ሰጠኝ። 23 ተራራው በእሳት ሲነድድ ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ እናንተ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም ወደ እኔ ቀረባችሁ። 24 አላችሁም፦ እነሆ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳትም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰዎችም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል። 25 አሁን እንግዲህ ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን እንሞታለን? እኛ የእግዚአብሔርን የአምላካችንን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን። 26 ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወቱ የኖረ ማን ንው? 27 አንተ ቅረብ፤ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ ስማ፤ እግዚአብሔር አምላካችንም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እናደርገዋለን አላችሁ። 28 በተናገራችሁኝም ጊዜ እግዚአብሔር የእናንተን ቃል ሰማ። እግዚአብሔርም አለኝ፦ይህ ሕዝብ የተናገሩህን ቃል ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩትም ሁሉ መልካም ነው። 29 ለእነርሱ ለዘላለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዘዜን ሁሉ እንዲጠብቁ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው በነበራቸው! 30 ሄደህ እንዲህ በላቸው፦ ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ። 31 አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁሙ፥ ርስት አድርጌ በምሰጣቸውም ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዓቴን፥ ድንጋጌንም ሁሉ እነግርሃለሁ። 32 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ። 33 በሕይወት እንድትኖሩ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሄዱ።
እዚህ ጋ “ሁሉ” የሚለው ቃል ግነት ነው። ሙሴ በእስራኤል ያሉ ሁሉ ቃሉን እንዲሰሙና እንዲታዘዙ ፈልጓል፣ ይሁን እንጂ ሁሉ ይሰማው ዘንድ ምናልባት ድምፁ በጣም ከፍ ያለ አልነበረም። (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ጆሮ” የሚያመለክተው የሰውን ሁለንተናውን ነው። ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር አጽንዖት የሚሰጠው ሰዎቹ ኃጢአትን እንዳያደርጉ ሙሴ የነገራቸውን እንደሚያውቁና ኃጢአት መሥራታቸውን አለማወቃቸውን እንዳይናገሩ ነው። አ.ት፡ “ዛሬ የምነግራችሁን” (Synecdoche እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያደረገው ከኋለኛው የእስራኤል ትውልድ ጋር ደግሞ እንጂ በኮሬብ ከነበሩት ጋር ብቻ አይደለም ወይም 2) እግዚአብሔር በሩቅ ከነበሩት አባቶቻቸው አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን ከመሳሰሉት ጋር ይህንን ቃል ኪዳን አላደረገም፤ ይልቁንም ይህ ቃል ኪዳን የጀመረው በኮሬብ ከነበሩት እስራኤላውያን ጋር ነው።
ለእርስ በርሳቸው ቅርበት ያላቸው ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ እርስ በርስ እንደሚተያዩ ለመግለጽ የቋንቋህን የአነጋገር ዘይቤ ተጠቀም። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“እኔን እንጂ ሌሎች አማልክትን ማምለክ የለብህም”
ይህ በይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከእግሮቻችሁ በታች ባለው ምድር ላይ ያለ ወይም ከምድር በታች በውሃ ውስጥ ያለ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“የተቀረጹትን ምስሎች አታምልኩ ወይም እነርሱ የሚያዟችሁን አታድርጉ”
“መቼም ቢሆን”
“እኔን ብቻ እንድታመልኩኝ እፈልጋለሁ”
“ታማኝነት” የሚለው የነገር ስም “በታማኝነት” ወይም “ታማኝ” ተብሎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሚወዱኝን ሺዎችን በታማኝነት እወዳቸዋለሁ” ወይም “ከሚወዱኝ ከሺዎች ጋር ለቃል ኪዳን ታማኝ እሆናለሁ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
አንዳንድ ትርጓሜዎች “ለሚወዱኝ ለአንድ ሺህ ትውልዶች” በሚል ይነበባሉ። “ሺዎች” የሚለው ቃል ለመቁጠር የሚበዛውን ቁጥር ለማመልከት የሚውል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ለሚወዱኝ ለእነርሱ እስከ ዘላለም” (Assumed Knowledge and Implicit Information፣ ፈሊጣዊ አነጋገር እና ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“በእግዚአብሔር ስም አትጠቀም”
ይህንን በዘዳግም 5፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“በግድየለሽነት” ወይም “ተገቢውን አክብሮት ባለመስጠት” ወይም “ለተሳሳቱ ዓላማዎች”
ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በደለኛ አድርጎ ይቆጥረዋል” ወይም “እግዚአብሔር ይቀጣዋል” (ድርብ አሉታዎች የሚለውን ተመልከት)
“ለእግዚአብሔር እንድትለየው”
“የተለመደውን ሥራህን ሁሉ ሥራ”
“ቀን 7”። እዚህ ጋ “ሰባተኛው” ለሰባት ተራ ቁጥር ነው። (See: Ordinal Numbers)
“በዚያን ቀን ምንም አትሥራ”
እዚህ ጋ “ደጆች” ከተማን ራሱን የሚያመላክት ነው። አ.ት፡ “በማኅበረሰብህ መካከል” ወይም “በከተማህ ውስጥ” ወይም “ከአንተ ጋር የሚኖሩ” (See: Synecdoche)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ማስታወስ አለብህ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ጽኑ እጅ” እና “የተዘረጋች ክንድ” የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያሳይ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡34 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ጽኑ ኃይሉን በማሳየት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህንን በዘዳግም 5፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ከሚስትህ በቀር ከሌላ ከማንም ጋር አትተኛ”
“ስለ ሌላው ሰው ውሸትን አትናገር”
ይህንን በዘዳግም 5፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ድምፅ” የሚለው ቃል የቃልን ድምፅ ወይም ተናጋሪውን ሰው የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የቃሉን ድምፅ ሰምታችኋል” ወይም “እግዚአብሔር ሲናገር ሰምታችኋል” (See: Synecdoche)
እግዚአብሔር ከተናገራቸው እንደሚሞቱ በማሰብ ፈርተው ነበር። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እንሞታለን ብለን ፈርተናል” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “… ያደረገ ከእኛ በቀር ሌላ አንድም ሕዝብ የለም”። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሰዎችን ሁሉ ወይም ሕያዋን ፍጥረታትን ይወክላል። አ.ት፡ “ሰዎች ሁሉ” ወይም “ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “እኔን” የሚያመለክተው ሙሴን ነው።
የአንተ ቋንቋ ለአንድ ነገር የሞኖርን ብርቱ ፍላጎት የሚገልጽ የአነጋገር ዘይቤ ካለው እዚህ ጋ ልትጠቀምበት ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “ቢኖሩ በጣም ደስ ይለኝ ነበር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“የእስራኤልን ሕዝብ ታስተምራለህ”
ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ ትዕዛዝ እየሰጠ ነው።
ይህ እግዚአብሔርን የማይታዘዘውን ሰው ከትክክለኛው መንገድ ከሚወጣው ሰው ጋር ያነጻጽረዋል። አ.ት፡ “በየትኛውም መንገድ ለእርሱ የማትታዘዝ መሆን የለብህም” ወይም “የሚላችሁን ሁሉ ማድረግ አለባችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ረጅም ቀናት የረጅም ዕድሜ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። ይህንን በዘዳግም 4፡40 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ረጅም ዕድሜ መኖር እንድትችሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 ከዮርዳኖስ ማዶ በምትውርሱአት ምድር የምትጠብቃችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳስተምራችሁ ያዘዘኝ እነዚህ ትእዛዘት፥ ሥርዓትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤ 2 እኔ የማዛችሁን ሥርዓትንና ትእዛዘትን በመጠበቅ እናንተ፥ ልጆቻችሁ፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዘመናችሁ ዕድሜአችሁ እንዲረዝም እግዚአብሔር አምላካችሁን አክብሩ። 3 እንግዲህ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ መልካምም እንዲሆንላችሁ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ተስፋ እንደሰጣችሁ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር እጅግ እንድትበዙ ነው። 4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፥ እግዚአብሔር አምላካችን አንድ እግዚአብሔር ነው። 5 እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ፥ በፍጹም ኃይላችሁ ውደዱ። 6 እኔም ዛሬ እናንተን የማዝዘው ቃል በልባችሁ ይሁን፤ 7 በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድም ስትሄዱ፥ ስትተኙም፥ ስትነሡም፥ ልጆቻችሁን አስተምሩአቸው። 8 በእጃችሁም ምልክት አድርጋችሁ እሰሩት፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁንላችሁ። 9 በቤታችሁም መቃኖች በደጃፋችሁም በሮች ላይ ጻፉት። 10 እግዚአብሔር አምላካችሁ ለእናንተ ሊሰጣችሁ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባገባችሁ ጊዜ፥ ያልሠራሃችኋቸውን ታላላቅና መልካም ከተሞች፥ 11 በመልካም ነገሮች ሁሉ የተሞሉ ቤቶች ያልማስሃችኋቸውን የተማሱ ጉድጓዶች፥ ያልተከልሃችኋቸውን ወይንና ወይራ በሰጣችሁ ጊዜ፥ 12 በበላችሁና በጠገባችሁ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ። 13 አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ፤ እርሱንም አምልኩት በስሙም ማሉ። 14 በዙሪያችሁ ያሉትን አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት ፍለጋ እንዳትሄዱ፥ እንዳከተከተሉ፤ 15 ምክንያቱም በመካከላችሁ ያለው እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ አምላክ ስለሆነ፥ ቁጣው እንዳይነድባችሁና ከምድር ገጽ እንዳያጠፋችሁ ተጠንቀቁ። 16 በማሳህ እንደተፈታተናችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁን አትፈታተኑት። 17 ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዘትንና ሥርዓቱን አጥብቃችሁ ጠይቁ። 18 መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን ነገር አድርጉ፤ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ 19 እግዚአብሔርም እንደተናገረ ጠላቶቻችሁን ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣላችሁ ዘንድ። 20 በኋለኛው ዘመንም ልጆቻችሁ እንዲህ ብለው በጠየቃችሁ ጊዜ፦ እግዚአብሔር አምላካችን ያዘዛችሁ የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች፥ ሥርዓትና ሌሎችስ ድንጋጌዎች እነዚህ ምንድን ናቸው? 21 እናንተም ለልጆቻችሁ እንዲህ በሉአችው፦ በግብፅ አገር የንጉሥ ፈርዖን አገልጋዮች ነበርን፥ እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ ከግብፅ አወጣን፥ 22 እግዚብብሔርም በግብፅና በፈርዖን፥ በቤቱም ሁሉ ላይ በዓይናችን ፊት ታላቅና ክፉ፥ ምልክትና ተአምራትን አደረገ። 23 ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር አምጥቶን እርስዋን ይሰጠን ዘንድ ከዚያ አወጣን። 24 እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን እግዚአብሔር አምላካችንን እንፈራ ዘንድ ይህችንም ሥርዓት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን። 25 እርሱም እንዳዘዘን በእግዚአብሔር በአምላካችን ፊት እንፈጽመው ዘንድ ይህን ትእዛዝ ሁሉ ብንጠብቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።
“ትታዘዙ ዘንድ … ለመታዘዝ”
“ከዮርዳኖስ ወንዝ ወዲያ ማዶ ሄዳችሁ”
ረጅም ቀናት የረጅም ዕድሜ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህ በዘዳግም 4፡26 እንዳለው በተመሳሳይ “ረጅም ዘመን እንድትኖሩ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ዕድሜአችሁን እንዳረዝመው” ወይም “ረጅም ዕድሜ እንድትኖሩ አደርጋችሁ ዘንድ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ስማ” ማለት ታዘዝ ሲሆን “እነርሱን” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት፣ ሕግጋትና ሥርዓት ስማ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information
“ታዘዛቸው”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “የተትረፈረፈ ወተትና ማር የሚፈስባት ምድር” ወይም “ከብት ለማርባትና ለእርሻ ምርጥ የሆነ ምድር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“አምላካችን እግዚአብሔር አንድና ብቸኛ አምላክ ነው”
እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። እነዚህ ሦስቱ ሐረጎች በአንድነት ጥቅም ላይ የዋሉት “በፍጹም” ወይም “በቅንነት” ለማለት ነው። በዘዳግም 4፡29 ላይ “በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ” የሚለውን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ የሚናገረው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ነው።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ሁል ጊዜ ማስታወስ አለብህ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“በትጋት እንድታስተምረው አዝሃለሁ … እንድትናገረው አዝሃለሁ”። አንባቢው እነዚህን እንደ ትዕዛዝ ሊረዳቸው ይገባዋል።
ይህ “እነዚህን ቃላት በብራና ላይ ጻፋቸው፣ ብራናውን በትንሽ ኪስ ውስጥ አድርገውና ኪሱን እሰረው” ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር በተራው “በአካል እዚያ ያሉ ያህል እነዚህን ቃሎች ታዘዛቸው” ለሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል። አ.ት፡ “እነዚህን ቃላት እሰራቸው”። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሕጌን እንድታስታውስ እንደሚያደርግህ አንዳች ነገር”
ይህ “እነዚህን ቃላት በብራና ላይ ጻፋቸው፣ ብራናውን በትንሽ ኪስ ውስጥ አድርገውና በዚያ እንዲቀመጥ ትንሹን ኪስ በግምባርህ ላይ እሰረው” ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር በተራው “በአካል እዚያ ያሉ ያህል እነዚህን ቃሎች ታዘዛቸው” ለሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል። አ.ት፡ “ቃሎቼ እንደ ግምባር ጌጥ ያገለግላሉ”። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
አንድ ሰው በግምባሩ ላይ የሚያደርጋቸው ጌጣ ጌጦች
ይህ ትዕዛዝ ነው።
የከነዓንን ሕዝቦች በሚያሸንፉበት ጊዜ እነዚህ ከተሞች በሙሉ የእስራኤል ሕዝብ ይሆናሉ።
እዚህ ጋ “የባርነት ቤት” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው እስራኤላውያን ባሪያዎች የነበሩበትን ስፍራ፣ ግብፅን ነው። አ.ት፡ “ባሪያ ሆነህ ከኖርክበት ስፍራ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ማክበር የሚኖርብህ አምላክህን እግዚአብሔርን እንጂ ሌላውን አይደለም፤ ማምለክ ያለብህ እርሱን ብቻ ነው፣ መማል የሚኖርብህም በእርሱ ስምና በእርሱ ስም ብቻ ነው”። እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሌሎች አማልክቶችን እንዳያመልኩ ወይም እንዳያገለግሉ ስለመናገሩ ምናልባት የአንተ ቋንቋ አጽንዖት የሚሰጥበት ሌላ መንገድ ይኖር ይሆናል።
በእግዚአብሔር ስም መማል ማለት እግዚአብሔርን የመሓላው መሠረት ወይም ኃይል ማድረግ ማለት ነው። “በስሙ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ራሱን ነው። አ.ት፡ “ትምላለህ፣ እግዚአብሔር እንዲያጸናውም ትጠይቃለህ” ወይም “በምትምልበት ጊዜ ስሙን ትጠራለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በመካከልህ የሚኖር”
ሙሴ የእግዚአብሔርን ቁጣ አንድን ነገር ለማቃጠል እሳት ከሚለኩስ ሰው ጋር ያነጻጽረዋል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ቁጣን መለኮስ በጣም የመቆጣት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ቁጣውን ያነዳል” ወይም “አምላክህ እግዚአብሔር በጣም ይቆጣል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ምንህም እስከማይተርፍ ድረስ ያጠፋሃል”
እዚህ ጋ “መፈተን” ማለት እግዚአብሔርን መገዳደርና ትክክለኛ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ማስገደድ ማለት ነው።
ይህ በምድረ በዳው ውስጥ ያለ የቦታ ስም ነው። ተርጓሚው ምናልባት፣ “’ማሳህ’ የሚለው ስም ትርጉም ‘መፈተን’ ማለት ነው” የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ይኖርበት ይሆናል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ትዕዛዝና በረከት ነው። እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ከታዘዙት ከእርሱ በረከትን ይቀበላሉ። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ትክክልና መልካም የሚለውን አድርግ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
በዚህ ጥያቄ “የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች” ትርጉማቸውንና ዓላማቸውን ይወክላሉ። አ.ት፡ “የታዘዙት የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች ለአንተ ምን ትርጉም አላቸው” ወይም “የታዘዝከውን የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች መታዘዝ የሚኖርብህ ለምንድነው”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው ሙሴ የእግዚአብሔርን ቃል የሚነግራቸው የትልልቆቹ እስራኤላውያንን ልጆች ነው።
እዚህ ጋ “ጽኑ እጅ” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ኃይል ነው። ይህንን በዘዳግም 4፡34 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡ አ.ት፡ “በጽኑ ኃይሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ቤቱ” የሚለው ፈሊጣቂ አነጋገር የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “በሕዝቡ ሁሉ ላይ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዐይኖቻችን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰውን ሁለንተናውን ነው። አ.ት፡ “ልናያቸው በምንችልበት” (See: Synecdoche)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም መብራራት ይችላል። አ.ት፡ “ወደ ከነዓን ሊያስገባን” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“በእግዚአብሔር ሀልዎች” ወይም “እግዚአብሔር ሊያየን በሚችልበት”
ሁል ጊዜ፣ በየትኛውም ሁኔታ ታዘዝ
“ይህ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጠበቅን ያመለክታል። ይህ እግዚአብሔር ጻድቅ አድርጎ እንደሚቆጥራቸው የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ጻድቅ አድርጎ ይቆጥረናል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወሱአት ወደምትገቡባት ምድር ባመጣችሁ ጊዜ፤ ከፊታችሁም ብዙ አሕዛብ ከእናንተ የበለጡትንና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ ኬጢያዊውን፥ ጌርጌሳውያንን፥ አሞራውያንብ፥ ከነዓናውያንን፥ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አወጣቸው። 2 እንዲሁም ጦርነት በገጠማችሁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁ ድል በሰጣችሁ ጊዜ፥ እነርሱን ማጥቃት አለባችሁ፥ ከዚያም ፈጽሞ ማጥፋት ይኖርባችኋል። 3 ከእርሱም ጋር ቃል ኪዳን ማድረግ ወይም ምሕረት አለማድረግ፥ ከእነርሱም ጋር አትጋቡም፤ ሴት ልጆቻችሁን ለወንድ ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴት ልጃቸውንም ለወንድ ልጃችሁ አትውሰዱ። 4 ሌሎች አማልክትን እንዳያመልኩ፥ ልጆቻችሁን እኔን እንዳይከተሉ ይመልሳሉ፥ የእግዚአብሔርም ቁጣ ይነድድባችኋል ፈጥኖም ያጠፋችኋል። 5 በእነርሱ ላይ የምታደርጉባቸው እንደዚህ ነው፥ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቁረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ። 6 እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የተለያችሁ ሕዝብ ናችሁ። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምድርም ገጽ ከሚኖሩ ሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ መረጣችሁ። 7 እግዚአብሔርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቁጥር ስለ ባዛችሁ አይደለም፤ እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቁጥር ጥቂቶች ነበራችሁና፤ 8 ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን ቃል ኪዳን ስለ ጠበቀ ነው። እግዚአብሕር በጽኑ እጅ ያወጣችሁ፥ ከባሪነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ ለዚህ ነው። 9 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ እርሱ አምላክ እንደ ሆነ ለሚወድዱትና ትእዛዘትንም ለሚጠብቁት፥ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆን እወቁ፥ 10 ነገር ግን የሚጠሉትን በፊታቸው ሊያጠፋቸው ብድራትን ይመልሳል፤እንዲሁም ብድራትን ለመመለስ አይዘገይም። 11 እንግዲህ ታደርጉት ዘንድ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘት፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎችን ጠብቁ። 12 እነዚህን ድንጋጌዎችን ሰምታችሁ ብትጠብቁና ብታደርጉ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ለአባቶቻችሁ የማለላችውን ቃል ኪዳን በታማኝነት ለእናንተ ይጠብቅላችኋል። 13 እርሱም ይወድዳችኋል፥ ይባርካችኋል፥ ያበዛላችኋል፤ እንዲሁም የሆዳችሁንና የምድራችሁን ፍሬ፥ እህላችሁን፥ ወይናችሁን፥ ዘይታችሁን፥ የከብቶቻችሁንና የበጎቻችሁን መንጋ ይባርካል። 14 ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረካችሁ ትሆናላችሁ፥ በሰዎቻችሁና በከብቶቻችሁ ዘንድ ወንድ ወይም ሴት ቢሆኑ መካን አይሆንባችሁም። 15 እግዚአብሔርም ሕመምን ሁሉ ከእናንተ ያርቃል፥ የምታውቁአችሁን ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በእናንተ ላይ አያደርስባችሁም በሚጠሉባችሁም ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል። 16 እግዚአብሔር አምላካችሁም በእጃችሁ አሳልፎ የሚሰጣችሁን አሕዛብ ሁሉ ታጠፋቸዋላችሁ፥ ዓይናችሁም አያዝኑላቸውም። ወጥመድ እንዳይሆኑባችሁአማልክታቸውንም አታምልኩአችሁም። 17 በልብህም እንዲህ ብትሉ፦ እነዚህ አሕዛብ ከእኔ ይልቅ ይበዛሉና አወጣቸው ዘንድ እንዴት እችላለሁ? 18 እግዚአብሔር አምላካችሁ በፈዖንና በግብፅ ሁሉ ያደረገውን ትዝ ስለሚላችሁ እነሱን አትፍራቸው፤ 19 አምላካችሁ እግዚአብሔር ዓይናችሁ ፊት ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንና ተአምራትን በማድረግ በጸናችው እጅ፥ በተዘረጋውም ክንድ አወጣችሁ። እንዲሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተ በምትፈሩአችሁ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል። 20 በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላካችሁ ራሳቸውን የተሸሸጉትን ከፊታችሁ እስኪጠፉ ድረስ በመካከላችው ተርብ ይሰድድባቸዋል። 21 እግዚአብሔር አምላካችሁ ታላቅና የተፈራ አምላክ በመካከላችሁ ስላለ፤ ከእነርሱ የተነሣ አትደንግጡ። 22 እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን አሕዛብ ጥቂት በጥቂት ከፊታችሁ ያወጣቸዋል። ሁሉንም አንድ ጊዜ አታጠፋቸውም፤ ወይም የዱር አራዊት በዙሪያችሁ በጣም ብዙ ይሆናሉ። 23 እግዚአብሔር አምላካችሁ እነርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ እስኪጠፉም ድረስ በታላቅ ድንጋጤ ያስደነግጣቸዋል። 24 ነገሥታታቸውንም በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋቸዋላችሁ። እስክታጠፏቸውም ድረስ ማንም በፊታችሁ ይቆም ዘንድ አይችልም። 25 የተቀረጸውንም የአማልክታቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላላችሁ፤ ከብር ወይም ከወርቅ የተሠሩትንም ለራሳችሁ ለመውሰድ አትመኙ፥ በእግዚአብሔር በአምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመዱበት ከእርሱ ምንም አትውሰዱ። 26 እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆኑ ርኩስን ነገር ወደ ቤታችሁ አታግቡ ለማምለክም አትቃጡ፥ ለጥፋት የተለየ ስለ ሆነ ፈጽሞ ተጸየፉት፥ ጥሉትም።
አንድ ሰው ለሌላው እንደሚሰጠው ቁሳዊ ነገር ሙሴ የሚናገረው ስለ ድል ነው። አ.ት፡ “እንድታሸንፋቸው ያስችልሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እነርሱን” የሚያመለክተው በዘዳግም 7፡1 የተጠቀሱትን ሰባት አገሮች ነው።
“ልጆችህ ከሌሎች አገሮች ሕዝቦች ጋር እንዲጋቡ ብትፈቅድ፣ የሌሎች አገሮች ሰዎች”
ሙሴ የእግዚአብሕርን ቁጣ እሳትን ከሚለኩስ ሰው ጋር ያነጻጽረዋል። ይህ የሚያስቆጣውን ስለሚያጠፋበት ስለ እግዚአብሔር ኃይል አጽንዖት ይሰጣል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በአንተ ላይ እግዚአብሔር ቁጣውን ያነዳል” ወይም “ከዚያም እግዚአብሔር በአንተ ላይ በጣም ይቆጣል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“አንተ” የሚለው ቃል እስራኤላውያንን ሁሉ ስለሚመለከት ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
እዚህ ጋ ሙሴ የሚናገረው ለእስራኤላውያን ሁሉ ነው፣ ስለዚህ እነዚህ ቃላት ብቁ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን የእርሱ እንዲሆኑ በተለየ ሁኔታ መምረጡ ከሌሎች ሕዝቦች እንደለያቸው ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት “በምድር ላይ ከሚኖሩት” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ሌሎችን ከወደደበት በላይ እናንተን አልወደዳችሁም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ጽኑ እጅ” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ኃይል ነው። እነዚህ ቃላት በዘዳግም 4፡34 ላይ ደግሞ ይታያሉ። አ.ት፡ “በጽኑ ኃይሉ”(ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ለ1,000 ትውልድ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
የዚህ የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም “እግዚአብሔር እንደቀጣቸው ያውቁ ዘንድ በግልጽና በፍጥነት ይበቀላቸዋል” የሚል ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“አይዘገይም” የሚለው ቃል እግዚአብሔር በብርቱ ይቀጣል የሚለውን አጽንዖት ዝቅ አድርጎ የሚያሳይ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የሚጠሉትን ሁሉ በብርቱ ይቀጣቸዋል” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
“የሕዝብህ ቁጥር እንዲበዛ ያደርጋል”
ይህ “ልጆችህን” የሚል የአነጋገር ዘይቤ ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ “ምርትህን” የሚል የአነጋገር ዘይቤ ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ከብትህ እንዲበዛ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሌሎች ሕዝቦችን ከምባርክበት በበለጠ እባርክሃለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ሁሉም ልጆች ሊኖሯቸው እንደሚችሉ አጽንዖት ለመስጠት አሉታዊ መግለጫዎችን ይጠቀማል። ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እናንተ ሁላችሁም ልጆች ይኖሯችኋል፣ ከብቶቻችሁም ይበዛሉ” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
“አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት ብዙ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
“እንደማትታመም እርግጠኛ ሁን” ወይም “ፍጹም ጤና እንድትሆን እጠብቅሃለሁ”
ሙሴ በሽታን እግዚአብሔር በሰዎች ጫንቃ ላይ እንደሚጭነው ከባድ ቁስ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እርሱ በየትኛውም ክፉ በሽታ እንድትታመም አያደርግህም … ነገር ግን ጠላቶችህ በእነርሱ እንዲታመሙ ያደርጋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሁሉንም የሕዝብ ወገኖች ፈጽመህ እንድታጠፋቸው አዝሃለሁ”
ይህ ትዕዛዝ ነው። ሙሴ ዐይን የሚያየው ራሱን ዐይንን እንደሆነ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “የምታየው እንድትራራላቸው እንዲያደርግህ አትፍቀድ” ወይም “የምታደርገው እንደሚጎዳቸው በማየትህ ምክንያት አትራራላቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በፍጹም አታምልክ”
ሕዝቡ ሌሎች አማልክትን ካመለኩ በወጥመድ እንደሚያዝ እንስሳ ይሆናሉ፣ ከዚያም ማምለጥ አይችሉም። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሀገራቱ ከእነርሱ ይልቅ ብርቱዎች እንደሆኑ ቢያስተውሉም እንኳን ሕዝቡ መፍራት የለባቸውም። አ.ት፡ “ምንም እንኳን በልብህ -- ብትናገር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ብታስብ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሕዝቡ ሌሎች አገራትን ስለ ፈሩበት ስሜት አጽንዖት ለመስጠት ሙሴ በጥያቄ መልክ ይጠቀማል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል።አ.ት፡ “ላሸንፋቸው አልችልም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ማስታወስ አለብህ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዕይኖችህ” የሚወክለው የሰውን ሁለንተና ነው። አ.ት፡ “ያየኸው” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “ጽኑ እጅ” እና “የተዘረጋች ክንድ” የእግዚአብሔርን ኃይል የሚገልጹ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። ይህንን በዘዳግም 4፡34 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እና በጽኑ ኃይሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በተጨማሪም፣ እግዚአብሔር”
ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) ሰዎችን እንዲነድፉና እንዲያሳምሙ እግዚአብሔር ትክክለኛ በራሪ ነፍሳትን ይልክባቸዋል፣ ወይም 2) እግዚአብሔር ሕዝቡ እንዲፈሩና እንዲሸሹ ያደርጋቸዋል።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ከዚህ በኋላ እንዳታያቸው ይሞታሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ከቶ”
“ታላቅና ድንቅ አምላክ” ወይም “ሰዎቹን እንዲፈሩ የሚያደርግ ታላቅ አምላክ”
“በዝግታ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንድታሸንፍ ያስችልሃል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ከሌሎች ሕዝቦች በሆኑት ሰራዊቶች ላይ ድልን”
“በአግባቡ ማሰብ እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እስክታጠፋቸው ድረስ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እስራኤላውያን የእነዚያን አገራት ሕዝቦች በሙሉ ፈጽመው ስለሚያጠፏቸው ወደፊት ማንም አያስታውሳቸውም። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“አንተን በመቃወም የሚቆም” ወይም “አንተን በመቃወም ራሳቸውን መከላከል”
ይህ ትዕዛዝ ነው።
“የሌሎች ሕዝቦችን አማልክት”
እነዚህ ቃላት አማልክቶቹን እንዲያቃጥሉ በተሰጣቸው መመሪያ ላይ ተጨማሪዎች ናቸው
በጣዖታቱ ላይ ያለውን ወርቅ ወይም ብር መውሰድ እንኳን ሕዝቡ እንዲያመልኳቸው ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህንን በማድረጋቸው በወጥመድ እንደተያዘ እንስሳ ይሆናሉ። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወጥመድ ይሆንባችኋል” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት))
እነዚህ ቃላት ሕዝቡ ጣዖታቱን እንዲያቃጥሉ እግዚአብሔር ለምን እንደፈለገ ይነግሩናል። “አምላካችሁ እግዚአብሔር በጣም ስለሚጠላው ይህንን አድርጉ”
“መጥላት” እና “መጸየፍ” የሚሉት ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ሆኖ ሳለ ለጥላቻው ጥልቅነት አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ፈጽመህ ትጠላዋለህ” (See: Doublet)
እግዚአብሔር አንድን ነገር መርገሙና ሊያጠፋው መማሉ ነገሩን ከየትኛውም ነገር ለይቶ እንደሚያስቀምጠው ሆኖ ተነግሯል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እርሱን እግዚአብሔር ለጥፋት ለይቶ አስቀምጦታል” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊድምፅ የሚለውን ተመልከት))
1 በሕይወት እንድትኖሩና እንድትበዙ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱአት ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘትን ሁሉ ጠብቁ። 2 እግዚአብሔር አምላካችሁ በልባችሁ ያለውን፥ ትእዛዘቱን መጠበቃችሁን ወይም አለመጠበቃችሁን ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁና ትሁት እንድትሆኑ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራችሁን መንገድ ሁሉ አስቡ። 3 አስጨነቃችሁ፥ እንድትራቡም አደረጋችሁ፥ እንዲሁም እናንተና ልጆቻችሁ፥ አባቶቻችምሁ የማያውቁአቸውን መና መገባችሁ። ይህም ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል እንጂ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ያስታውቃችሁ ዘንድ ነው። 4 በእነዚህ አርባ ዓመታት ውስጥ የለበሳችሁት ልብስ አላረጀም፥ እግራችሁም አላበጠም። 5 ሰውም ልጁን እንደሚገሥጽ እንዲሁም እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን እንደሚገሥጽ በልባችሁ አስቡ። 6 በመንገዱም እንድትሄዱ እርሱንም እንድትፈሩ የእግዚአብሔ የአምላካችሁን ትእዛዝ ጠብቁ። 7 እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደ መልካምና፥ ከሸለቆና ከኮረብታ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾች የሚመነጩ ምንጮች ወዳሉባት ምድር፤ ስንዴና ገብስ፤ 8 በለስና ሮማን፥ ወይራና ማር ወደ ሞሉባት፥ 9 ሳይጎድላችሁ እንጀራ ወደምትበሉባት ምድር፥ አንዳችም ወደማታጡባት፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር አመጣችሁ። 10 እናንተም ትበላላችሁ፥ ትጠግባላችሁ፥ ስለ ሰጣችሁም ስለ መልካሚቱ ምድር እግዚአብሔር አምላካችሁን ትባርካላችሁ። 11 ዛሬ እኔ እናንተን የማዝዛውን ትእዛዘትን፥ ድንጋጌዎችንና ሥርዓቶችን ባለመጠበቅ እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ። 12 ከበላችሁና ከጠገባችሁ ሙሉም ከሆናችሁ በኋላ መልካምም ቤት ሠርታችሁ በዚያ መኖር ከጀመራችሁ በኋላ እንዳትረሱ ተጠንቀቁ። 13 የላምና የበግ መንጋ ከበዛላችሁ በኋላ፥ ብራችሁና ወርቃችሁም፥ ያላችሁም ሁሉ ከበዛላችሁ በኋላ፥ 14 ልባችሁ እንዳይኮራ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ። 15 መርዛማ እባብና ጊንጥ፥ውኃ በሌለባትና ጥማትም ባለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራችሁን፥ ከዐለት ድንጋይም ውኃን ያወጣላችሁን፥ 16 በመጨረሻም ዘመን መልካም ያደርግላችሁ ዘንድ ሊፈትናችሁ ሊያዋርዳችሁም አባቶቻችሁ ያላውቁትን መና በምድረ በዳ ያበላችሁን እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዳትረሱ፥ 17 በልባችሁም፦ ጉልባታችን የእጃችን ብርታት ይህን ሀብት አመጣልን እንዳትሉ። 18 ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶቻችሁ የማለላችሁን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ሀብት ለማከማቸት ጉልበት ሰጥቶአችኋል፥ እግዚአብሔር አምላካችሁን አስቡ። 19 አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ብትረሳ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል፥ ብታመልካቸውም፥ ብትሰግድላቸውም ፈጽሞ እንደምትጥፉ እኔ ዛሬውኑ እመሰክርባችኋልለሁ። 20 የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ቃል ስላልሰማችሁ እግዚአብሔር ከፍታችሁ እንደሚያጠፋቸው እንደ አሕዛብ እንዲሁ እናንተ ትጠፋላችሁ።
“አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት አገባቦች በሙሉ እንዲሁም ግሦቹ ብዙ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ማስታወስ አለብህ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“40 ዓመታት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ምን ያህል ደካማና ኃጢአተኛ እንደሆንክ ሊያሳይህ”
“ለመግለጥ” ወይም “ለማሳየት”
ልብ የሰው ባህርይ ምሳሌ ነው። አ.ት፡ “ምን ዓይነት ሕዝብ እንደሆንክ” ወይም “ባህሪህን እንዴት መግለጥ እንዳለብህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እግዚአብሔር ምን ያህል ደካማና ኃጢአተኛ መሆንህን አሳየህ”። በዘዳግም 8፡2 ላይ “ትሁት ሊያደርግህ” የሚለው ቃል እንዴት እንደተተረጎመ ተመልከት።
“እንድትበላው መናን ሰጠህ”
እዚህ ጋ “እንጀራ” የሚወክለው ሁሉንም የምግብ ዓይነት ነው። አ.ት፡ “ሰዎች በሕይወት ለመኖር እንዲችሉ የሚፈልጉት ምግብ ብቻ አይደለም” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር አፍ” በፈሊጣዊ አነጋገር እግዚአብሔር የሚናገረው ቃል ማለት ነው። አ.ት፡ “ሰዎች በሕይወት መኖር እንዲችሉ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መታዘዝ አለባቸው” ወይም “ሰዎች በሕይወት መኖር እንዲችሉ እግዚአብሔር የሚነግራቸውን መፈጸም አለባቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ “ማስታወስ” የሚገባቸው የመጨረሻው ንብረታቸው ነው (ዘዳግም 8፡2)
“40 ዓመታት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በዘዳግም 8፡1-2 የሚጀምረውን የትዕዛዛቱን ዝርዝር የሚቀጥል ነው።
እዚህ ጋ ፈሊጣዊ አነጋገር የሆነው “ልብ” የሚወክለው የአንድን ሰው አሳብና ማስተዋል ነው። አ.ት፡ “አስተውል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ከ -- ምድር” ወይም “ -- ያላትን ምድር”
ይህ ምጸታዊ አነጋገር በአዎንታዊነት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የተትረፈረፈ ምግብ የምታገኝበትን ምድር” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የምትፈልገውን ሁሉ የምታገኝበት” (ድርብ አሉታዊ የሚለውን ተመልከት)
ድንጋዮቹ በብረት ማዕድን የተሞሉ ናቸው። የብረት ማዕድን ሰይፍና ማረሻ ለመሥራት የሚያገለግል ጠንካራ ብረት ነው።
“የመዳብ ማዕድን ታወጣለህ”። መዳብ የቤት ውስጥ መገልገያዎችን ለመሥራት የሚያገለግል ለስለስ ያለ ብረት ነው።
“እስክትጠግብ ድረስ የምትበላው በቂ ምግብ ይኖርሃል”
“ታመሰግናለህ” ወይም “ምስጋናን ታቀርባለህ”
“ትዕዛዞቹን መጠበቅህን አታቁም” ወይም “ትዕዛዛቱን መጠበቅህን ቀጥል”
“የምትበላው በቂ ምግብ በሚኖርህ ጊዜ”
እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው ውስጠኛውን ሰው ነው። መታበይና ከእንግዲህ እግዚአብሔርን ያለመታዘዝ እንደ ሰው ልብ መነሣሣት ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ትታበያለህ፣ ከእንግዲህም እግዚአብሔርን አትታዘዝም” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“የከብትህ፣ የበግና የፍየል መንጋህ”
በቁጥር እጅግ መጨመር
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በጣም ብዙ ነገሮች አሉህ” ወይም “በጣም ብዙ ንብረት አለህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው ውስጠኛውን ሰው ነው። መታበይና ከእንግዲህ እግዚአብሔርን ያለመታዘዝ እንደ ሰው ልብ መነሣሣት ሆኖ ተነግሯል። በዘዳግም 8፡12 ላይ ተመሳሳዩን ሐረግ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ትታበያለህ፣ ከእንግዲህም እግዚአብሔርን አትታዘዝም” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለእስራኤላውያን ስለ እግዚአብሔር የሚያውቁትን ማስታወስ ጀምሯል (ለይቶ ማሳወቅ ማሳወቅን ወይም ማስታወስን ሲቃረን የሚለውን ተመልከት)
ይህ በግብፅ በባርነት የነበሩበትን ጊዜ የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ባሪያዎች ከነበራችሁበት ስፍራ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለእስራኤላውያን ስለ እግዚአብሔር የሚያውቁትን ማስታወስ ቀጥሏል (ዘዳግም 8፡14)። (ለይቶ ማሳወቅ ማሳወቅን ወይም ማስታወስን ሲቃረን የሚለውን ተመልከት)
“የመራህ እግዚአብሔር … ያመጣህ እግዚአብሔር … እግዚአብሔር መገበህ”
“መርዘኛ እባብ”
ይህ ሐረግ ልክ ሰው ውሃ በሚፈልግበት ጊዜ እንደሚጠማ ምድሪቱ መጠማቷን ይገልጻል። አ.ት፡ “ደረቅ ምድር” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
“ሊረዳህ” ወይም “ለአንተ መልካም ስለነበረ”
ይህ ምናልባት ሰዎች ልባቸው “በሚታበይበት” እና “እግዚአብሔርን በሚረሱበት” ጊዜ የሚያደርጉት ሦስተኛው ነገር ነው። (ዘዳግም 8፡14)። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው የአንድን ሰው ኃይል ወይም ችሎታ ነው። አ.ት፡ “እኔ በጣም ብርቱና ኃይለኛ ስለሆንኩኝ ይህንን ሀብት አግኝቻለሁ” ወይም “እነዚህን ነገሮች ሁሉ በራሴ ኃይልና ችሎታ አግኝቻለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ትዕዛዝ ነው። አ.ት፡ “ነገር ግን አስታውስ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “እርሱ በዚህ መንገድ ያጸናል” ወይም 2) “በዚህ መንገድ እርሱ ሊያጸና የታመነ ነው”
“ስለዚህ ይችላል”
እንዲቆም ወይም እንዲኖር ማድረግ
“አሁን እንደሚያደርገው ሁሉ” ወይም “ቃል ኪዳኑን አሁን እንዳጸናው ሁሉ”
መከተል የመታዘዝ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክቶችን ማገልገል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አንተ” የሚሉት እነዚህ አገባቦች ሁሉ ብዙ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
“አስጠነቅቃችኋለሁ” ወይም “በምስክሮች ፊት እነግራችኋለሁ”
“ያለምንም ጥርጥር ትሞታላችሁ”
“በፊት ለፊታችሁ”
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” ማለት እግዚአብሔር ያደርጉት ዘንድ ለሕዝቡ የሚነግራቸው ማለት ነው። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ስላልታዘዛችሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 እስራኤል ሆይ፥ ስሙ፥ ከእናንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ እስከ ሰማይም ድረስ የተመሸጉትን ታላላቅ ከተሞች ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው፤ 2 የኤናቅ ልጆች ፥ ታላቅና ረጅም ሕዝብ፥ እናንተም የምታውቃቸው ስለ እነርሱም እንዲህ ያላችኋቸው፦ በዔናቅ ልጆች ፊት ማን መቆም ይችላል? 3 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁም እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊታችሁ ስለሚያልፍ፥ ዛሬ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊታችሁም ያዋርዳቸዋል፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገራችሁ እናንተ ታሳድዳቸዋላችሁ ፈጥናችሁም ታጠፋቸዋላችሁ። 4 እግዚአብሔር አምላካችሁ ከፊታችሁ ካወጣቸው በኋላ ፦ እንወርሳት ዘንድ ወደዚህች ምድር እግዚአሔር ያመጠን፥ ስለ ጽድቄ ነው፥ እነዚህንም አሕዛብ እግዚአብሔር ከፊታችን ያወጣቸው ኃጢአተኞች ስለ ሆኑ ነው፥ ብላችሁ በልባችሁ እንዳትናገሩ። 5 ምድራቸውን ትወርሱአት ዘንድ የምትገቡት ስለ ጽድቃችሁ ወይም ስለ ልባችሁ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ከፊታችሁ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኃጢአት ምክንያትና ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ይፈጽም ዘንድ ነው። 6 እንግዲህ እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆናችሁና እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጣችሁ ስለጽድቃችሁ እንዳይደለ እወቁ። 7 እግዚአብሔር አምላካችሁን በምድረ በዳ እንዳስቁጣችሁት ከግብፅ አገር ከወጣችሁበት ቀን ጀምሮ ወደዚህ ስፍራ እስከ መጣችሁ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ አስቡ። 8 በኮሬብ ደግሞ እግዚአብሔርን አስቆጣችሁ፤ እግዚእብሔርም ሊያጠፋችሁ ተቆጣባችሁ። 9 እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባውን የቃል ኪዳን፥ የድንጋዩን ጽላቶችን ከእግዚአብሔር ለመቀበል ወደ ተራራ ወጥቼ በተራራው ላይ ለአርባ ቀናትና አርባ ሌሊት በቆየሁበት ጊዜ እንጀራም አልበለሁም፥ ውኃም አልጠጠሁም። 10 እግዚአብሔርም በእርሱ ጣት የተጻፉትን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶችን ሰጠኝ፤ በጽላቶቹም ላይ በተራራው ሥር በነበረው ጉበዔ እግዚአብሔር በእሳት መካከል ሆኖ የተናገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። 11 ከአርባ ቀንና ከእርባ ሌሊትም በኋላ እግዚአብሔር ሁለቱን የድግንጋይ ጽላቶች፥ ያቃል ኪዳኑን ጽላቶች ሰጠኝ። 12 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥተህ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ረክሰዋል። ፈጥነው ካዘዝኋቸውም መንገድ ፈቀቅ ብለዋል። ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሰቸው አድርገዋል። 13 ከዚህም በተጨማሪ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና መሆኑን አይቼአለሁ። 14 ስለዚህ አጠፋቸው፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስሳለሁ፥ አንተንም ከእነርሱ ለሚበረታና ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ። 15 እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድሁ፥ ተራራውም በእሳት ይነድድ ነበር። ሁለቱም የቃል ኪንን ጽላቶች በእጆቼ ነበሩ። 16 እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁን እንደበደላችሁ አየሁ። ለእናንተም ለራሳችሁ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር። እግዚአብሔርም ካዘዛችሁ መንገድ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር። 17 ሁሉቱንም ጽላቶች ወስጄ፥ ከእጆቼ ጣልኋቸው። በዓይናችሁም ፊት ሰበርኋቸው። 18 ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ከማድረጋችሁ የተነሣ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ወደቅሁ፥ እንጀራም አልበላሁም፥ ውኃም አጠጣሁም ነበር። 19 ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ ከተቆጣባችሁ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ስለ ፈራሁ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያን ጊዜም ሰማኝ። 20 እግዚአብሔርም አሮንን ሊያጠፋው እጅግ ተቆጣው፤ ስለ አሮንም ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ጸለይሁ። 21 ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወስድሁ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቅዝቅሁትም፤ ዱቄትም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት። ዱቄቱንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት። 22 እግዚአብሔርንም በቀቤራ፥ በማሳህ፥ በምኞት መቃብርም አስቆጥታችሁት ነበር። 23 እግዚአብሔርም ውጡ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ትእዛዝ ላይ አመፃችሁ፥ በእርሱም አላመናችሁም፤ወይም ድምፁንም አልሰማችሁም። 24 እናንተን ካወቅሁበት ቀን ጀምሮ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀኞች ነበራችሁ። 25 እግዚአብሔር ያጠፋችሁ ዘንድ ስለ ተናገረ በእነዚያ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ወደቅሁ። 26 ጌታ በእግዚአብሔርም ፊት እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ በታላቅነትህና በኃያልነትህ ከግብፅ ያወጣቸውን፥ የተበዠሃቸውን ሕዝብህንና ርስትህን አታጥፋ ። 27 አገልጋዮችህን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ደንዳናነት፥ ክፋቱንና ኃጢአቱን አትመልከት፤ 28 እኛንም ያወጣህባት ምድር ሰዎች እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ ስላልቻለ፤ ስለጠላቸውም በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው ይላሉ። 29 እነርሱም በታላቅ ኃይልህ በጸነችውም ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዛብህና ርስትህ ናቸው።
“እስራኤል” የሚለው ቃል የእስራኤልን ሕዝብ የሚመለከት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ስማ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“መሬታቸውን ለመውሰድ”
ይህ ከተሞቹ በጣም ሰፊና ጠንካራ በመሆናቸው ምክንያት ሕዝቡ መፍራታቸውን አጽንዖት ለመስጠት የተደረገ ግነት ነው። በዘዳግም 1፡28 ላይ ተመሳሳዩን ቃላት እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ሰማይ የሚደርሱ የሚመስሉ ግንቦች ነበሯቸው” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
በጣም ረጃጅምና ኃያላን የነበሩ የዔናቅ ሕዝብ ተወላጆች ናቸው። ተመሳሳዮቹን ቃላት በዘዳግም 1፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።(See: Assumed Knowledge and Implicit Information እና ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት የዔናቅ ልጆች ኃያላን በመሆናቸው ሰዎች ይፈሯቸው ነበር። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በዔናቅ ልጆች ፊት ራሱን መከላከል የሚችል አልነበረም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ፀሐይ ከጠለቀችበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ቀናትና ሳምንታት ስለጀመሩባት ስለዚያች ቀን ማለቱ ነው።
እግዚአብሔር የሌሎች ሕዝቦችን ሰራዊት ለማጥፋት የሚችል ኃያል ነው። (See: Simile)
“ልትቆጣጠራቸው እንድትችል ደካማ ያደርጋቸዋል”
እዚህ ጋ “በልብህ” ማለቱ “በአሳብህ” ለማለት ነው። አ.ት፡ “በራስህ አታስብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሌሎች ሕዝቦችን አሳዶ ሲያስወጣቸው”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። “ዘወትር የምታስበውና የምትመኘው ትክክለኛውን ነገር ስለሆነ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ቃሉ” የሚለው ፈሊጣዊ በሆነ አነጋገር የሚያመለክተው እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ነው። አ.ት፡ “ተስፋውን ይፈጽም ዘንድ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
አብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ ሙሴ ለሚናገራቸው ሰዎች “አባቶቻቸው” ናቸው።
ሙሴ በማስታወስ አስፈላጊነት ላይ አጽንዖት ለመስጠት ተመሳሳዩን ትዕዛዝ በአዎንታዊና በአሉታዊ ቃላት ይደግማቸዋል። አ.ት፡ “ለማስታወስ ተጠንቀቅ” (See: Doublet)
እዚህ ጋ “አንተ” የሚያመለክተው ከሙሴ ጋር ያሉትንና በተጨማሪም በቀደመው ትውልድ የነበሩትን እስራኤላውያንን ነው። (See: Forms of You)
“አንተ” የሚሉት ሁሉም አገባቦች ብዙ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
ይህ የሚያመለክተው የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆን ነው።
እዚህ ጋ “የድንጋይ ጽላቶች” ይኸውም እግዚአብሔር አሥሩን ትዕዛዛት የጻፈባቸውን መሆኑን ሁለተኛው ሐረግ ግልጽ ያደርጋል። (See: Parallelism)
“40 days and 40 nights” “40 ቀንና 40 ሌሊት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ለእናንተ የነገራችሁን እነዚያኑ ቃላት በእነርሱ ላይ ጻፋቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር እንደ ሰው በእሳት መካከል ቆሞ በታላቅ ድምፅ የተናገረ ይመስል ነበር።
የነገር ስም የሆነው “ጉባዔ” እንደ ግሥ “በአንድነት መሰብሰብ” ተብሎ ሊገለጽ ይችላል። አ.ት፡ “እናንተ እስራኤላውያን ሁላችሁ መጥታችሁ በአንድ ስፍራ በተገናኛችሁበት ቀን” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
“40 ቀንና 40 ሌሊት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች” የተባሉት እግዚአብሔር አሥሩን ትዕዛዛት የጻፈባቸውን መሆኑን ሁለተኛው ሐረግ ግልጽ ያደርጋል። (See: Parallelism)
“ሕዝብህ … የተሳሳተ ነገር እያደረጉ ነው” እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ሙሴ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጠበቅን በመንገድ ላይ ከመሄድ ጋር አመሳስሎ ይናገራል። አ.ት፡ “ትዕዛዞቼን እምቢ ማለት ጀምረዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ስማቸው ፈጽሞ እንዲጠፋ አደርጋለሁ” ወይም “ማንም እንዳያስታውሳቸው ሁሉንም እገድላቸዋለሁ”። ተመሳሳዩን ሐረግ በዘዳግም 7፡24 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
እዚህ ጋ “ተመለከትሁ” የሚለው ቃል ሙሴ ባየው ነገር መደነቁን ያሳያል።
የእስራኤል የቀደመው ትውልድ ያመልኩት ዘንድ የብረት ጥጃ እንዲሠራላቸው አሮንን ጠየቁት። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ሙሴ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጠበቅ በመንገድ ላይ ከመሄድ ጋር አመሳስሎ ይናገራል። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 9፡12 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
እዚህ ጋ “ዐይኖቻችሁ” የእስራኤልን ሕዝብ የሚወክል ምሳሌ ነው። አ.ት፡ “እዚያው በፊት ለፊታችሁ ሰባበርኳቸው” ወይም “ልታዩአቸው በምትችሉበት ስፍራ ሰባበርኳቸው” (See: Synecdoche)
“በመሬት ላይ በግምባሬ ወደቅሁ”። ይህ እግዚአብሔር ታላቅ እንደሆነና ሙሴ ምንም እንዳይደለ ማሳያ መንገድ ነው።
“40 ቀንና 40 ሌሊት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ቁጣና ጽኑ ቅሬታ” የሚሉት ቃላት እግዚአብሔር ስለ ተቆጣና ቅር ስለተሰኘ ሊያደርግ ያለውን የሚያመለክቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በእናንተ ተቆጥቶ ነበር -- በእናንተ ላይ እጅግ አዝኖ ነበር -- እስኪያጠፋችሁ ድረስ ተቆጥቶ ነበር፣ እኔም ስለሚያደርገው ነገር ፈርቼ ነበር”
ሙሴ ምናልባት ሌሎች ሰዎች ሥራውን በቀጥታ እንዲሠሩት አዝዟቸው ይሆናል። አ.ት፡ “የሚወስዱ … የሚያቃጥሉ … የሚሰብሩ … የሚፈጩ … የሚበትኑ ሰዎች ነበሩኝ”
እዚህ ጋ የሠሩት የወርቅ ጥጃ ራሱ የእነርሱ “ኃጢአት” መሆኑ ተመልክቷል። አ.ት፡ “በኃጥአተኝነት የሠራችሁት ጥጃ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ የሄዱባቸው የተለያዩ ቦታዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ሊሰጣቸው የነገራቸው ምድር በኮረብታዎቹ ላይ ያለ ሲሆን እነርሱ የነበሩት ቆላው ላይ ነው፣ ስለዚህ ያገኙት ዘንድ ወደ ኮረብታዎቹ መውጣት ነበረባቸው።
“ትዕዛዝ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ራሱን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ላይ አመፃችሁ፤ ትዕዛዙንም አልጠበቃችሁም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ድምፁን” ማለት እግዚአብሔር ተናግሮችት የነበረውን ነው። አ.ት፡ “የተናገረውን ታዘዙት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ልመራችሁ ከጀመርኩበት ጊዜ አንሥቶ”። አንዳንድ ትርጉሞች “ካወቃችሁ ጊዜ ጀምሮ”፣ ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔር እነርሱን ያወቀበት ቀን በሚል ይነበባሉ
“በመሬት ላይ በግምባሬ ተደፋሁ”። ይህንን በዘዳግም 9፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“40 ቀንና 40 ሌሊት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ገንዘብ በመክፈል ከባርነት ነጻ እንዳደረጋቸው በሚመስል መልኩ ሙሴ ይናገራል። አ.ት፡ “አድነሃቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ታላቅነት” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ታላቅ ኃይል የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በታላቅ ኃይልህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ብርቱ እጅ” የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ኃይል ነው። ተመሳሳዮቹን ቃላት በዘዳግም 4፡34 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “በብርቱ ኃይልህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አስታውስ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ያ ምድር” የሚሉት ቃላት የግብፅን ሕዝብ የሚያመለክቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። “ስለዚህ የግብፅ ሰዎች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሊሉ ይችላሉ”
እነዚህ ሐረጎች መሠረታዊ አሳባቸው አንድ ሆኖ ሕዝቡን ለማዳን እግዚአብሔር በተጠቀመበት ታላቅ ኃይሉ ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Doublet)
1 በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ እንደ መጀመሪያ ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራ ውጣ፤ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ። 2 በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት በእነዚህ ጽላቶች ላይ እጽፋለሁ፤ አንተም በታቦቱ ውስጥ ታደርጋቸዋለህ። 3 ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደፊተኞቹም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ፥ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። 4 በተራራው ሥር የጉባዔው ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት መካከል ሆኖ የተናገራችሁን አሥርቱን ቃላት በመጀመሪያ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፤ ከዚያም እግዚአብሔር እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ። 5 ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፤ ጽላችቶችንም በሠረሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው፤እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ሆኑ። 6 የእስራኤልም ልጆች ከብኤሮት ብኔ ያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ። በዚያ አሮን ሞተ፥ በዚያም ተቀበረ፥ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆኖ አገለገለ። 7 ከዚያም ወደ ጉድጎዳ ተጓዙ፤ከጉድጎዳም ወደ ውኃ ምንጮች ምድር ወደ ዮጥባታ ተጓዙ። 8 በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር የሌዊን ነገድ እግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከሙና እርሱንም እንዲያገለግሉ፥ በፊቱም ይቆሙ ዘንድ በስሙም እንዲባርኩ መረጠ። 9 ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው እግዚአብሔር ርስቱ ነው። 10 በተራራውም ላይ እንደ መጀመሪያውም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየሁ። እግዚአብሔርም እንደገናም ሰማኝ፤ እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ አልፈለገም። 11 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥተህ በሕዝቡ ፊት ሆነህ ሕዝቡን በጉዞው ምራው፤ ለአባቶቻቸው የማለሁላቸውን ምድር ሄደው ይገባሉ። 12 እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትውድድ ዘንድ፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ መልካምም እንዲሆንልህ 13 ዛሬ ለአንተ የማዘዘውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ከሆነ በቀር እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? 14 እነሆ፥ ሰማይና ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ነው። 15 ብቻ እግዚአብሔር ስለ አባቶቻችሁ ደስ ተሰኝቶአል፥ እነርሱንም ወድዶቸዋል፤ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራችሁን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዝብ ሁሉ መካከል መረጣችሁ። 16 ስለዚህ እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ አንገተ ደንዳኖች አትሁኑ። 17 እግዚአብሔር አምላካችሁ የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል። 18 እግዚአብሔር ለድሃ አደጉና ባል ለሞተባት ይፈርዳል፥ ምግብና ልብስም የሚሰጥ ነው። 19 ስለዚህ እናንተም በግብፅ አገር ስደተኞች ስለ ነበራችሁ ስደተኛውን ውደዱ። 20 እግዚአብሔር አምላካችሁን ፍሩ፥ እርሱንም አምልኩት። በእርሱም ተጣበቁ፤ በስሙም ማሉ። 21 እርሱ ዓይኖቻችሁ ያዩትን እነዚህን ታላላቆችንና የሚያስፈሩትን ነገሮች ያደረገላችሁ ክብራችሁ ነው፤ አምላካችሁም ነው፤ ። 22 አባቶቻችሁ ሰባ ሰዎች ሆነው ወደ ግብፅ ሄዱ፤ አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁ ብዛታችሁን እንደ ሰማይ ክዋክብት አደረገ።
“ጸሎቴን ከጨረስኩ በኋላ”
ይህ የሚያመለክተው ሙሴ የሰበራቸውን የመጀመሪያዎቹን ጽላቶች ስብስብ ነው። አ.ት፡ “ቀድሞ በነበሩህ ጽላቶች” (See: Ellipsis እና ደረጃን አመልካች ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሲና ተራራን ያመለክታል።
ይህ የሚያመለክተው ሙሴ የሰበራቸውን የመጀመሪያዎቹን ጽላቶች ስብስብ ነው። አ.ት፡ “ቀድሞ በነበሩኝ ጽላቶች” (Ellipsis እና ደረጃን አመልካች ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ወደ ሲና ተራራ ወጣ”
እግዚአብሔር እንደ ሰው በእሳት መካከል ቆሞ በታላቅ ድምፅ የሚናገር ይመስል ነበር። ይህንን በዘዳግም 9፡10 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የነገር ስም የሆነው “ጉባዔ” “በአንድነት መሰብሰብ” በሚል ግሥ መነገር ይችላል። ይህንን በዘዳግም 9፡10 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው ሙሴን ነው።
x
ይህ የእስራኤል ሕዝብ ወዴት እንደተጓዙ ዳራዊ መረጃ ይሰጣል። አሮንን በሞሴራ ተፈጥሮአዊ ሞት መሞቱን ደግሞ ያስታውቃል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የእስራኤል ሕዝብ በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ የሄዱባቸው የተለያዩ ቦታዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ተርጎሚው፣ “’ብኤሮት ብኔያዕቃን’ የሚለው ስም ‘የያዕቃን ሰዎች የውሃ ጉድጓድ’ ማለት ነው” የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ይኖርባቸው ይሆናል።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እርሱን የቀበሩት በዚያ ነው” ወይም “እስራኤላውያን በዚያ ቀበሩት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአሮን ልጅ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። “እግዚአብሔር የሚያዘውን መስዋዕት እንዲያቀርብ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ስም” ሥልጣንን ያመለክታል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር ተወካዮች ሆነው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ዛሬ እንደሚያደርጉት”
የሌዊ ነገድ ወደዚያ በደረሱ ጊዜ ከተስፋይቱ ምድር ድርሻቸውን አልተቀበሉም። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ መደረግ ይችል ይሆናል።(See: Assumed Knowledge and Implicit Informa- tion)
እግዚአብሔር ሌዊና ተወላጆቹ ከእርሱ ጋር ስለሚኖራቸው የተለየ ዝምድና ሲናገር ራሱን ሊወርሱት እንደሚችሉ አንዳች ነገር አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እነርሱ የሚኖራቸው እግዚአብሔር ነው” ወይም “እግዚአብሔር እርሱን እንዲያገለግሉት ይፈቅድላቸዋል፣ በዚያም አገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን ያቀርብላቸዋል”
እዚህ ጋ፣ ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “የአንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“ለሌዊ ነገድ ተናገራቸው”
“አንደኛ” የአንድ መደበኛ ቁጥር ነው። እዚህ ጋ፣ ሙሴ ለመጀመሪያ ጊዜ የድንጋይ ጽላቶችን ከእግዚአብሔር ለመቀበል ወደ ሲና ተራራ የወጣበትን ያመለክታል” (መደበኛ ቁጥር የሚለውን ተመልከት)
“40 ቀንና 40 ሌሊት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“ምድሪቱን ውሰድ” ወይም “ምድሪቱን ተረከብ”
ይህ የሚያመለክተው አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን ነው።
“የምሰጥህን፣ ለአባቶቻቸው”
እዚህ ጋ “እስራኤል” የሚለው በፈሊጣዊ አነጋገር የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል። አ.ት፡ “አሁንም፣ የእስራኤል ሕዝብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ ለማስተማር በጥያቄ ይጠቀማል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር እንድታደርገው የሚፈልገው ይህንን ነው፤ መልካም እንዲሆንልህ ትፈራው ዘንድ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔርን መታዘዝ በመንገድ ላይ እንደመሄድ መሆኑን ሙሴ ይናገራል። አ.ት፡ “ትዕዛዙን ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ፣ “ልብ” እና “ነፍስ” የሰውን ውስጣዊ ማንነት የሚመለከት ፈሊጣዊ ንግግር ነው። እነዚህ ሁለት ሐረጎች “በፍጹም” ወይም “በቅንነት” ለማለት በአንድነት ጥቅም ላይ ውለዋል። እነዚህን ሐረጎች በዘዳግም 4፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)
“ልነግርህ ያለሁት እውነትና ጠቃሚ ስለሆነ ለ -- አስተውል”
እነዚህ ቃላት ሁለት ጽንፎች ተጣምረው በሁሉም ቦታ ያሉ ሁሉም ነገሮች የእግዚአብሔር መሆናቸውን ያሳያሉ። (See: Merism)
ይህ በሰማያት ያሉትን ከፍ ያሉ ስፍራዎች ያመለክታሉ። በሰማያት ያሉ ነገሮች በሙሉ የእግዚአብሔር ናቸው።
እዚህ ጋ፣ “አንተ” የሚለው ቃል እስራኤላውያንን በሙሉ የሚመለከት በመሆኑ ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“በዚህ ምክንያት”
“ሸለፈት” የሚለው ቃል በመገረዝ ጊዜ የሚወገደውን የወንድ አካል ሽፋን ያመለክታል። እዚህ ጋ፣ ሙሴ የሚያመለክተው መንፈሳዊ መገረዝን ነው። ይኸውም፣ ሕዝቡ ከሕይወታቸው ኃጢአትን ማስወገድ አለባቸው ማለት ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ገናናው እግዚአብሔር” ወይም “ብቸኛው እውነተኛ አምላክ”
“ገናናው ጌታ” ወይም “ታላቁ ጌታ”
“ሰዎች እንዲፈሩ የሚያደርጋቸው”
“ሰዎች አባት የሌላቸውን በፍትሐዊነት እንዲይዙ እግዚአብሔር ያረጋግጣል”
እነዚህ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውና የሚንከባከባቸው ዘመድ የሌላቸው ልጆች ናቸው።
እውነተኛ መበለት ባሏ የሞተባትና በእርጅና ዕድሜዋ የሚረዳት ልጅ የሌላት ሴት ናት።
“በዚህ ምክንያት”
“ልታመልከው የሚገባህ እርሱን ነው”
ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ግንኙነት መኖርና በእርሱ ላይ ሙሉ በሙሉ መታመን ከእግዚአብሔር ጋር መጣበቅ በሚል መልኩ ተነግሯል። አ.ት፡ “በእርሱ ላይ መታመን አለብህ” ወይም “ልትታመንበት የሚገባህ በእርሱ ላይ ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በእግዚአብሔር ስም መማል ማለት እግዚአብሔርን የተደረገው መሐላ መሠረት ወይም ኃይል ማድረግ ማለት ነው። እዚህ ጋ፣ “ስም” የሚወክለው እግዚአብሔርን ራሱን ነው። በዘዳግም 6፡13 ላይ ተመሳሳዩን ሐረግ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ትምላለህ፣ እግዚአብሔር እንዲያጸናውም ትጠይቀዋለህ” ወይም “በምትምልበት ጊዜ ስሙን ትጠራለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ፣ “ዐይኖች” የሚያመለክተው የሰውን ሁለንተና ነው። አ.ት፡ “አንተ ራስህ ያየኸውን” (See: Synecdoche)
ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) “ልታመሰግን የሚገባህ እርሱን ነው” ወይም 2) “አንተ ስለምታመሰግነው ሌሎች ሕዝቦች ያመሰግኑሃል”
“በስተደቡብ ወደ ግብፅ ወረዱ” ወይም “ወደ ግብፅ ሄዱ”
“70 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከሙሴ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን ቁጥራቸው እጅግ ብዙ እንደነበር አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “መቁጠር ከምትችለው በላይ” (See: Simile)
1 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውዳዱት፥ ሁልጊዜም መመሪያዎቹን፥ ሥርዓቶቹን፥ ድንጋጌዎችንና ትእዛዛትን ጠብቁ። 2 የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ቅጣት፥ታላቅነቱን፥ ኃያልነቱን፥ የተዘረጋውንም ክንዱን፥ ላላወቁት ወይም ላላዩት ልጆቻችሁ እየተናገርሁ እንዳልሆነ አስታውሉ፤ 3 በግብፅም መካከል በንጉሡ በፈርዖንና በአገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋውን ተአምራቱንና ሥራውን፥ 4 በተከተሉአችሁም ጊዜ በግብፅ ጭፍራ፥ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ያደረገውን፥በኤርትራ ባሕር ውኃ እንዳሰጠማቸው፥ እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው፥ 5 ወደዚህ ስፍራ እስከትመጡ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን፥አይተዋል። 6 በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተ ሰቦቻቸውን ድንኳኖቻቸውንም ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ፥ በኤልያብ ልጆች፥ በዳታንና በአቤሮን እግዚአብሔር ያደረገውን አላዩም። 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ያደረገውን ታላቁ ሥራ ሁሉ ዓይኖቻቸው አይተዋል። 8 እንግዲህ እንድትጠነክሩ ትወርሱአትም ዘንድ ወደምትሄዱባት ምድር እንድትሄዱ ዛሬ ለእናንተ የማዘዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤ 9 እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁና ለዘራቸው ይሰጣቸው ዘንድ በማለላቸው ወተትና ማርም በምታፈስሰው ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዘም ትእዛዘትን ጠብቁ። 10 ትወሱአት ዘንድ የምትሄዱባት ምድር በመጣችሁበት በግብፅ አገር ዘር እንደዘራችሁና ውኃ በእግራችሁ ታጠጡ እንደነበረ፥ እንደ አትክልት ቦታ አይደለችም፤ 11 ነገር ግን ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ የምትገቡባት ምድር ኮረብታና ሸለቆ ያለባት በሰማይ ዝናብ ውኃ የምትጠጣ አገር ናት፤ 12 አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ የሆነ አገር ናት። 13 እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ እግዚአብሔር አምላካችሁን ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ፥ ትወድዱና ታገለግሉት ዘንድ ዛሬ የማዝዛችሁን ትእዛዘትን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥ 14 እህላችሁን፥ ወይናችሁን፥ ዘይታችሁን ትሰበስቡ ዘንድ በየዚዜው ለምድራችሁ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን የወቅቱን ዝናብ ይሰጣችኋል። 15 በሜዳ ለእንስሶቻችሁም ሣርን እሰጣለሁ፤ትበላላችሁ፣ ትጠግባላችሁም። 16 ልባችሁ እንዳይስት ፈቀቅ እንዳትሉ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም፥ 17 የእግዚአብሔርም ቁጣ እንዳይነድድባችሁ ዝናብ እንዳይዘንብ ምድሪቱም ፍሬዋን እንዳትሰጥ ሰማይን እንዳይዘጋባችሁ፤ እግዚአብሔርም ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ እንዳትጠፉ ተጠንቀቁ። 18 ስለዚህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደ ክታብ ይሁኑላችሁ። ፥ 19 በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድ ላይም ስትሄዱ፥ ስትተኙ፥ ስትነሡም ልጆቻችሁንም አስተምሩአቸው። 20 በቤታችሁ መቃኖችና በከተሞቻችሁ በሮች ላይ ጻፈው፥ 21 እግዚአብሔርም እንዲሰጣቸው ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር፥ እንደ ሰማይ ቀኖች በላይ በምድር ከፍ ያሉና የልጆቻችሁም ዘመን የረዘመ ይሁን ። 22 እግዚአብሔር አምላካችሁን ትወድዱ ዘንድ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘት ሁሉ ብትጠብቁ፥ ብታደርጉአቸውም፥ 23 እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣል፤ ከእናንተም የሚበልጡትን፥ የሚበረቱትንም አሕዛብ ትወርሳላችሁ። 24 የእግራችሁ ጫማ የሚረግጥበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም ከሊባኖስ ወንዝ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል። 25 በእናንተም ፊት ማንም መቆም አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ እንደ ተናገራችሁ ማስፈራታችሁና ማስደንገጣችሁ በምትረግጡበት ምድር ሁሉ ላይ ያኖራል። 26 እነሆ፥ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤ 27 በረከትም የሚሆነው፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ትእዛዝ ብትሰሙ 28 እንዲሁም መርገም የሚሆነው የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ትአዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አምልክት ብትከተሉ ነው። 29 እግዚአብሔር አምላካችሁ ትወሱአት ዘንድ እናንተም ወደምትሄዱባት ምድር ባገባሃችሁ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙንም በጌባል ተራራ ይሆናል። 30 እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ከምዕራብ ካለው መንገድ በኋላ በዓረባ በሚኖሩት በከነዓናውያን ምድር በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ አይደለምን? 31 እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፥ ትወርሱአታላችሁ፥ ትቀመጡባታላችሁም። 32 እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራውን ሥርዓትና ድንጋጌዎች ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።
“ሁልጊዜ ታዘዝ”
“ያልተለማመዱት”
እዚህ ጋ፣ “ጽኑ እጅ” እና “የተዘረጋች ክንድ” የተባሉት የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያመለክቱ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡34 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ወይም ጽኑ ኃይሉን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በግብፅ ውስጥ”
እዚህ ጋ፣ “ሀገር” የሚወክለው ሕዝቡን ነው። አ.ት፡ “በሕዝቡ ሁሉ ላይ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እግዚአብሔር ያደረገውን ልጆቻችሁም ቢሆኑ አላዩም”
“በግብፅ ወታደሮች”
እዚህ ጋ “እናንተ” ማለት ከ40 ዓመታት በፊት የነበሩትን እስራኤላውያን ማለት ነው።
ይህ ማለት ሙሴ ወደ ከነዓን ከመሻገራቸው በፊት ሲናገራቸው የነበረበት ከዮርዳኖስ ሸለቆ አጠገብ ያለ ሜዳ ነው።
ሙሴ የሚያመለክተው ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁበትን ያለፈውን ጊዜ ሁነት ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ መደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“የሮቤል ተወላጆች”
እግዚአብሔር ምድሪቱ ተሰንጥቃ ሰዎች እንዲወድቁበት ማድረጉ ምድር አፍ እንዳላትና ሰዎችን የመዋጥ ችሎታ እንዳላት ተደርጎ ተነግሯል። (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው አገልጋዮቻቸውንና እንስሶቻቸውን ነው።
ይህ ማለት በዳታን፣ በአቤሮን፣ በእንስሶቻቸውና በንብረታቸው ላይ ስለሆነው ነገር የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ምስክሮች ናችው።
እዚህ ጋ “ዐይኖች” የሚወክሉት የሰውን ሁለንተና ነው። አ.ት፡ “ነገር ግን እናንተ አይታችኋል” (See: Synecdoche)
“ምድሪቱን መውሰድ
የእስራኤል ሕዝብ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ከነዓን መግባት ስለነበረባቸው “የምትገቡባት” የሚለው ሐረግ ጥቅም ላይ ውሏል።
ረጅም ቀናት ረጅም ዕድሜን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ረጅም ዘመን መኖር እንድትችል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በዘዳግም 6፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የተትረፈረፈ ወተትና ማር የሚፈስባት ምድር” ወይም “ለከብት ዕርባታና ለእርሻ ምርጥ የሆነ ምድር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) “እግር” ወደ እርሻዎቹ ውሃ የመሸከምን ከባድ ሥራ የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ውሃ ለማጠጣት ምድከሙን” ወይም 2) ውሃ የጠጣውን እርሻ በእግሮቻቸው መገልበጥ ነበረባቸው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“የአትክልት ስፍራ” ወይም “የልዩ ልዩ አትክልት ስፍራ”
ምድሪቱ ብዙ ዝናብ መቀበሏና መምጠጧ ልክ ምድሪቱ ውሃውን እንደምትጠጣው ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ከሰማይ የሚወርደው ዝናብ የተትረፈረፈ ውሃ ይሰጣታል” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዐይኖች” የሚወክሉት ትኩረትንና ክብካቤን ነው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ዘወትር ይመለከታታል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “መጀመሪያ” እና “መጨረሻ” የሚሉት ሁለት ጽንፎች በአንድነት ጥቅም ላይ የዋሉት ዓመቱን በሙሉ ለማለት ነው። አ.ት፡ “ሙሉውን ዓመት ባለማቋረጥ” (See: Merism)
ይህ ማለት እስራኤላውያን እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ከታዘዙ እርሱ የሰጣቸውን ተስፋ ይፈጽምላቸዋል።
እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው ሙሴን ነው።
“በሙሉ ልብህ” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ “በፍጹም” ማለት ሲሆን “በ . . . ነፍስህ” ማለት “በሁለንተናህ” ማለት ነው። እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው። ይህንን በዘዳግም 4፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “በሁለንተናህ” ወይም “በሙሉ ኃይልህ” (የአነጋገር ዘይቤ እና Doublet የሚለውን ተመልከት)
“በተገቢው ወቅት በምድርህ ላይ ዝናብ እንዲዘንብ አደርጋለሁ”
እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው። ይህ በሦስተኛ መደብ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይሰጣችኋል” ወይም “እርሱ ይሰጣችኋል”
ይህ የሚያመለክተው በመጀመሪያ በዘር ወቅት የሚዘንበውን ዝናብና ሰብሉን ለምርትነት የሚያበቃውን ዝናብ ነው። አ.ት፡ “የመከርንና የፀደይን ዝናብ” ወይም “ዝናብን በወቅቱ”
“ተጠንቀቁ” ወይም “ልብ በሉ”
እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው የአንድን ሰው ምኞት ወይም አሳብ ነው። ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ምኞታችሁ እንዳያታልላችሁ” ወይም “ራሳችሁን እንዳታታልሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔርን መተውና ሌሎች አማልክትን ማምለክ ሰው በአካሉ ከእግዚአብሔር ተለይቶ በሌላ አቅጣጫ እንደሚሄድ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን ማምለክ ትጀምራላችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የእግዚአብሔር መቆጣት መንደድ እንደ ጀመረ እሳት ተደርጎ ተነግሯል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስለዚህ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ እንዳይቆጣ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ዝናብ ከሰማይ እንዳይወርድ ማድረጉ እርሱ ሰማይን እንደሚዘጋ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “በምድሪቱ ላይ ሰብል እንዳይበቅል ዝናብ ከሰማይ እንዳይዘንብ እንዳያደርግ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ የሚያዝዘውን ዘወትር የሚያስብና የሚያመዛዝን ሰው ልቡና ነፍሱ መያዣ ዕቃ እንደሆኑና የሙሴ ቃላት መያዣውን እንደሚሞላ አንዳች ይዘት ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ አ.ት፡ “የምነግራችሁን እነዚህን ቃላት ለማስታወስ በጣም ተጠንቀቁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“የሰጠኋችሁን እነዚህን ትዕዛዛት”
እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የሚወክሉት የአንድን ሰው አዕምሮ ወይም አሳብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እነዚህን ቃላት እሰሯቸው”። ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር በብራና ላይ የሚጽፍን፣ ብራናውን በትንሽ ኪስ መሰል ማስቀመጫ የሚከተውንና የሚያስረውን ሰው ይወክላል። ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር በሌላ መልኩ ሕዝቡ የሙሴን ትዕዛዛት ለመታዘዝ መጠንቀቅ አለበት የሚል ትርጉም ያለው ዘይቤአዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል። ተመሳሳዮቹን ሐረጎች በዘዳግም 6፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሕጌን እንድታስታውስ እንደሚያደርግህ አንዳች ነገር”
“ቃሎቼ በዐይኖችህ መካከል እንደ ክታብ ይሆኑልህ”። ይህ የሙሴን ቃላት በብራና ላይ የሚጽፍ፣ ብራናውን በትንሽ ኪስ መሰል ማስቀመጫ የሚከትና በዐይኖቹ መካከል የሚያስርን ሰው የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር በሌላ መልኩ ያ ሰው ሙሴ የሚያዘውን ትዕዛዝ ሁሉ ለመታዘዝ መጠንቀቅ አለበት የሚል ትርጉም ያለው ዘይቤአዊ አነጋገር ሊሆን ይችላል። በዘዳግም 6፡8 ላይ ተመሳሳዮቹን ሐረጎች እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
አንድ ሰው በግምባሩ ላይ የሚያስራቸው ጌጣ ጌጦች
“በቤትህ” እና “በመንገድ” የሚሉትን የተለያዩ ቦታዎች መጠቀምና ተቃራኒዎቹ “ስትተኛ” እና “ስትነሣ” ሁልጊዜ በሁሉ ቦታ ማለትን ይወክላሉ። የእስራኤል ሕዝቦች በየትኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ማጥናትና ለልጆቻቸው ማስተማር ነበረባቸው። (See: Merism)
እነዚህን ቃላት በዘዳግም 6፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አንተንና ልጆችህን ረጅም ዕድሜ እንድትኖሩ እንዲያደርጋችሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን ያመለክታል።
ሕዝቡ በምድሪቱ የሚኖሩበት ዘመን ሰማይ ከምድር በላይ ለምን ያህል ጊዜ ከመቆየቱ ጋር ተነጻጽሯል። ይህ “ለዘላለም” ብሎ የመናገር መንገድ ነው። አ.ት፡ “ለዘላለም የእነርሱ እንዲሆን ሊሰጣቸው” ወይም “በዚያ ለዘላለም እንዲኖሩ ለመፍቀድ” (See: Simile)
“ያዘዝኳችሁን ሁሉ ለመፈጸም ብትጠነቀቁ”
አንድ ሰው እንዴት መኖርና ማድረግ እንዳለበት እግዚአብሔር መፈለጉ እንደ እግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና ተደርጎ ተነግሯል። አንድ ሰው እግዚአብሔርን ሲታዘዝ በእግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና እንደሄደ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ከእግዚአብሔር ጋር የመልካም ግንኙነት መኖርና ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መታመን አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚጣበቅ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “በእርሱ ለመታመን” ወይም “ከእርሱ ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖር”። ተመሳሳዮቹ ቃላት በዘዳግም 10፡20 ላይ እንዴት እንደተተረጎሙ ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ሀገሮች” የሚወክሉት ቀድሞ በከነዓን ይኖሩ የነበሩትን የሕዝብ ወገኖች ነው። አ.ት፡ “ከእናንተ በፊት የነበሩትን እነዚህን የሕዝብ ወገኖች ሁሉ፣ ከሕዝብ ወገኖች ምድሪቱን ትወስዳላችሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የእስራኤል ሰራዊት በከነዓን ከሚኖሩት የሕዝብ ወገኖች ይልቅ ጥቂትና ደካማ ቢሆኑም እንኳን የእስራኤል ሕዝብ ድል እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ያስችላቸዋል።
እዚህ ጋ “የእግራችሁ ጫማ” የሚወክለው የሰውን ሁለንተና ነው። አ.ት፡ “የምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ” (See: Synec- doche)
“ከኤፍራጥስ ወንዝ”
“በፊታችሁ መቆም” የሚለው ሐረግ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ማንም ሊያስቆማችሁ አይችልም” ወይም “ማንም ሊቃወማችሁ አይችልም”
እግዚአብሔር ሕዝቡ በጣም እንዲፈሩ ማድረጉ ፍርሐትና ድንጋጤን እርሱ እንደ ዕቃ በሕዝቡ ላይ እንደሚያኖራቸው በመሰለ መልኩ ተነግሯል። አ.ት፡ “አምላካችሁ እግዚአብሔር በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ ሕዝቡ እንዲፈሯችሁ ያደርጋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ፍርሐት” እና “ድንጋጤ” የሚሉት ቃላት ትርጉማቸው ተመሳሳይ ሲሆን የፍርሐቱ መጠን ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ከእናንተ የተነሣ ከባድ ፍርሐት” (See: Doublet)
እዚህ ጋ “ምድሪቱ” የሚለው በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች በሙሉ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ልብ በሉ”
እግዚአብሔር እንዲባርካቸው ወይም እንዲረግማቸው ይፈልጉ እንደሆነ ሕዝቡ እንዲመርጡ መፍቀዱ በረከትና መርገም ሙሴ በፊታቸው እንደሚያስቀምጣቸው ቁሶች ተደርገው ተነግሮላቸዋል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንዲባርካችሁ ወይም እንዲረግማችሁ ዛሬ መምረጥ አለባችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “በረከት” እና “መርገም” በግሥነት ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “… ካደረጋችሁ እግዚአብሔር ይባርካችኋል፣ … እግዚአብሔር ይረግማችኋል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለሕዝቡ የሚነግራቸው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ እንደ እግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና ሆነው ተነግረዋል። ለእግዚአብሔር ትዕዛዝ ያለመታዘዝ ሌሎች አማልክቶችን ለመከተል በሌላ አቅጣጫ ለመመለስ ከእግዚአብሔር በአካል እንደተለዩ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን ለማምለክ ዛሬ እኔ የማዛችሁን ትዕዛዝ እምቢ ብትሉ ግን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው ሌሎች የሕዝብ ወገኖች የሚያመልኳቸውን አማልክት ነው። እስራኤላውያን ራሱን ስለገለጠላቸውና ኃይሉን ስለተለማመዱ እግዚአብሔርን ያውቁታል።
በረከቱ እና መርገሙ አንድ ሰው በተራሮች ላይ እንደሚያስቀምጣቸው ቁሶች ተደርገው ተነግሮላቸዋል። አ.ት፡ “ከእናንተ ጥቂቱ በገሪዛን ተራራ አናት ላይ ቆማችሁ እግዚአብሔር እንዲባርካችሁ የሚያስደርገውን ቃል ታውጃላችሁ፣ ሌሎቹ በጌባል ተራራ አናት ላይ በመቆም እግዚአብሔር እንዲረግማችሁ የሚያስደርገውን ቃል ያውጃሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኙ ተራሮች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እስራኤላውያን የሚገኙት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ ነው። ሙሴ እነዚህ ተራሮች የሚገኙባቸውን ስፍራዎች ለማስታወስ በጥያቄ መልክ ያቀርባል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እንደምታውቁት ሞሬ የሚገኘው ከዮርዳኖስ ማዶ ነው” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ”
“በምስራቅ”
“ጌልገላ አጠገብ” ይህ ምናልባት ኢያሪኮ ከተማ አጠገብ ያለው ስፍራ ላይሆን ይችላል። ምናልባት ሙሴ ሴኬም አቅራቢያ ያለውን ስፍራ እያመለከተ ይሆናል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በጌልገላ አቅራቢያ የሚገኙ የተቀደሱ ዛፎች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሙሴ በዘዳግም 12፡26 የሚሰጣቸው ሥርዓቶችና ሕግጋት ናቸው።
እነዚህ አዲስ ናቸው ማለት አይደለም። ሙሴ ከ40 ዓመታት በፊት የሰጣቸውን ሥርዓቶችና ሕግጋት እየከለሰላቸው ነው።
ሙሴ ለሕዝቡ የሚነግራቸው ሥርዓቶችና ሕግጋት በሕዝቡ ፊት እንደሚያስቀምጣችው ቁሶች ተደርጎ ተነግሮላቸዋል። አ.ት፡ “እኔ የምሰጣችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንድትወርሱ በሚሰጣችሁ ምድር፥ ሁልጊዜ በምድር እያላችሁ የምትጠብቁአችሁ ሥርዓትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው። 2 እናንተ የምትወርሱአቸው አሕዛብ አማልክታቸውን ያመለኩባቸውን በረጅም ተራሮች በኮረብቶችም ከለምለምም ዛፍ በታች ያለውን ስፍራ ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉአቸው። 3 መሠዊያቸውንም አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥የማልመኪያ ዐፀዶቻችቸውንም በእሳት አቃጥሉ፥የአማልክታቸውንም የተቀረጹ ምስሎች ቆራርጡአቸው፥ ከዚያም ስፍራ ስማቸውን አጥፉ። 4 እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዲህ ባለ ሁኔታ አታምልኩ። 5 ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ከነገዶቻችሁ ሁሉ ስሙን በዚያ ያኖር ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ ትመጣላችሁ፥ ማደሪያውንም ትሻላችሁ። 6 ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላም መሥዋዕታችሁንም፥ አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቁርባን፥ ስእለታችሁንም በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት ውሰዱ። 7 በዚያም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ብሉ፥ እጃችሁንም በምትዘረጉበት እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ ነገር ሁሉ እናንተና ቤተ ሰባችሁ ደስ ይበላችሁ። 8 ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን፥ እኛ በዚህ ዛሬ የምናደርገውን ሁሉ አታደርጉም፥ 9 እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ዕረፍትና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና። 10 ነገር ግን ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁም በሚያወርሳችሁ ምድር በተቀመጣችሁ ጊዜ ያለ ፍርሃትም እንድትኖሩ፥ ከከበቡአችሁ ጠላቶች ሁሉ ዕረፍት በሰጣችሁ ጊዜ በዚያ ጊዜ 11 እግዚአብሔር አምላካችሁ ፥ ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላም መሥዋዕታችሁን አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁ ያነሣችሁትንም ቁርባን፥ ለእግዚአብሔርም ተስላችሁ የመረጣችሁትን ስእልታችሁን ሁሉ ውሰዱ። 12 እናንተም፥ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ አገልጋዮቻችሁና የቤት አገልጋዮቻችሁ፥ ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ የተቀመጠው ሌዋዊም፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ። 13 የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን በሚታያችሁ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርቡ ተጠንቀቁ። 14 ነገር ግን እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አቅርቡ፥ በዚያም የማዝዛችሁን ሁሉ አድርጉ። 15 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሰጣችሁ በረከት ሰውነታችሁ እንደ ፈቀደ በደጆቻችሁ ሁሉ ውስጥ አርዳችሁ ብሉ፤ንጹሕም ያልሆነ ሰው እንደ ሚቋና እንደ ዋላ ያለውን ይብላው። 16 ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ ያፍስሰው፤ ደሙን አትብሉ። 17 የእህላችሁን፥ የወይናችሁን፥ የጠጃችሁን የዘይታችሁንም፥ አሥራት፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት የተሳላችሁትንም ስእለት ሁሉ በፈቃዳችሁም ያቀረባችሁትን፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቁርባን በደጆቻችሁ መብላት አትችሉም። 18 በዚህ ፈንታ እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም አገልጋዮቻችሁና የቤት አገልጋዮቻችሁ፥በአገራችሁ ደጅ ያለው ሌዋዊ እግዚአብሔር አምላካችሁ በመረጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ብሉት፥ እጃችሁንም በምትዘረጉባችሁ ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ። 19 በምድራችሁ ላይ በምትኖሩባት ዘመን ሁሉ ሌዋዊውን ቸል እንዳትሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። 20 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ነገራችሁ አገራችሁን ባሰፋ ጊዜ፥ ሰውነታችሁም ሥጋ መብላት ስለ ወደደ፦ ሥጋ እንብላ፥ ስትሉ እንደ ሰውነታችሁ ፈቃድ ሥጋን ብሉ። 21 እግዚአብሔር አምላካችሁ በዚያ ስሙን ያኖር ዘንድ የመረጠው ስፍራ ከእናንተ ሩቅ ቢሆንም እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከላምና ከበግ መንጋችሁ እንዳዛዝኋችሁ እረዱ፥ እንደ ሰውነታችሁም ፈቃድ ሁሉ በአገራችሁ ደጅ ብሉ። 22 ሚዳቋና ዋላ እንደሚበሉ እንዲሁ ብሉ፥ ንጹሕ ሰው ንጹሕ ያልሆነም ይብለው። 23 ደሙ ሕይወት ነውና፥ ነፍሱንም ከሥጋው ጋር መብላት አይገባችሁምና፥ ደሙን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ። 24 በምድር ላይ እንደ ውኃ አፍስሱት እንጂ አትብሉ። 25 በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ስታደርጉ ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላችሁ አትብሉ። 26 ነገር ግን የተቀደሰውን ነገራችሁን ስእለታችሁንም ይዛችሁ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ሂዱ። 27 የሚቃጠለውንም መሥዋዕታችሁን ሥጋውንና ደሙን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርቡ፤ የመሥዋዕታችሁም ደም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፥ ሥጋውንም ብሉ። 28 በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርጉ ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዛችሁን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምታችሁ ጠብቁ። 29 እግዚአብሔር አምላካችሁ ትወርሱአቸው ዘንድ የምትሄዱባቸውን አሕዛብን ፊታችሁ ባጠፋ ጊዜ፥ እናንተም በወረሳችሁ ጊዜ፥ በምድራቸውም በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ 30 ከፊታችሁ ከጠፉ በኋላ እነርሱን ለመከተል እንዳትጠመዱ፦ እነዚህ አሕዛብ አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እንዲሁ ደግሞ እኔም አደርጋለሁ ብላችሁ ስለ አማልክታቸው እንዳትጠይቁ ተጠንቀቁ። 31 እግዚአብሔር የሚጠላውን ርኩሰት ሁሉ እነዚህን ለአማልክታቸው አድርገዋል፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ለአማልክታቸው በእሳት አቃጥሎአቸዋል፥ እናንተም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ እንዲሁ አታድርጉ። 32 እኔ የማዝዛችሁን ነገር ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምሩ ከእርሱም ምንም አታጉድሉ።
“መታዘዝ አለባችሁ”
“በምድር ላይ በምትኖሩበት” የሚለው ሐረግ አንድ ሰው በሕይወት እስካለ ደረስ የሚል የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በሕይወት እስካላችሁ ድረስ” (የአነጋገርዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ማጥፋት አለባችሁ”
እዚህ ጋ “ሕዝቦች” የሚወክሉት በከነዓን የሚኖሩትን የሕዝብ ወገኖች ነው። አ.ት፡ “መሬታቸውን የምትወስዱባቸው የሕዝብ ወገኖች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“የእነዚያን ሕዝቦች መሠዊያ ማፈራረስ አለባችሁ” ወይም “የእነዚያን ሕዝቦች መሠዊያዎች ማጥፋት አለባችሁ”
“ሰባብራችሁ ጣሉ” ወይም “ብትንትናቸውን አውጡ”
እዚህ ጋ “ስማቸውን” የሚወክለው “መታሰቢያቸውን” ነው። አ.ት፡ “ማንም እንዳያስታውሳቸው ፈጽማችሁ አጥፏቸው” ወይም “እነዚህን ሐሰተና አማልክት የሚወክል የትኛውንም ነገር አጥፉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሕዝቦች አማልክቶታቸውን የሚያመልኩባቸውን እያንዳንዱን ስፍራ ያመለክታል።
“እነዚያ ሕዝቦች አማልክቶቻቸውን እንዳመለኩ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ማምለክ የለባችሁም”
እዚህ ጋ “ስሙን” የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ራሱን ነው። እግዚአብሔር የሚኖርበትን አንድ ቦታ ይመርጣል፣ ሰዎች እርሱን ለማምለክ ወደዚያ ይመጣሉ። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ወደሚወስነው ስፍራ ለማምለክ ይሄዳሉ
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ሙሉ ሰውነትን ነው። አ.ት፡ “የምታቀርቡት ስጦታ” (See: Synecdoche)
“ስእለታችሁን የምትፈጽሙበትን ስጦታዎቻችሁን፣ የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁን”። እነዚህ የስጦታ ዓይነቶች ናቸው።
ሕዝቡ ከእያንዳንዱ የቤት እንስሳው በመጀመሪያ የሚወለደውን ወንድ እንዲሰጡት እግዚአብሔር ይፈልጋል
ይህ የሚያመለክተው የእስራኤል ልጆች እንዲያመልኩበት እግዚአብሔር የሚመርጥላቸውን ስፍራ ነው።
እዚህ ጋ “እጃችሁ በነካው” የሚወክለው ሙሉውን ሰውና እርሱ የሠራውን ነው። አ.ት፡ “በሠራችሁት ሥራ ሁሉ ደስ ይበላችሁ” (See: Synecdoche)
“ዛሬ እዚህ እንደምናደርገው ማድረግ የለባችሁም”። ይህ ማለት በዚያ ወቅት ከሚያመልኩበት በተለየ ሁኔታ በተስፋይቱ ምድር ማምለክ ይኖርባቸዋል።
ዐይን ማየትን፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላል። አ.ት፡ “እያንዳንዱ የሚያደርገው ልክ ነው ብሎ የሚያስበውን ነው” ወይም “አሁን እያንዳንዱ የሚያደርገው ልክ ነው ብሎ የሚወስነውን ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ማረፊያ” የሚለው የነገር ስም እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወደምታርፉበት ምድር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ የሚሰጣቸው ምድር አባት ለልጆቹ እንደሚተውላቸው ርስት ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ቋሚ ንብረት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ምድር” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው የከነዓንን ምድር ነው።
እግዚአብሔር የከነዓንን ምድር ለእስራኤል ሕዝብ መስጠቱ እርሱ ለልጆቹ ርስት እንደሚሰጣቸው አባት ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በዙሪያችሁ ካሉ ከጠላቶቻችሁ ሁሉ ሰላምን ይሰጣችኋል”
እዚህ ጋ “ስም” የሚወክለው እግዚአብሔርን ራሱን ነው። አ.ት፡ “አምላካችሁ እግዚአብሔር ለመኖር በሚመርጠው ስፍራ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ሙሉውን ሰው። አ.ት፡ “የምታቀርቡት ስጦታ” (See: Synecdoche)
“ስእለታችሁን ለመፈጸም የምታቀርቧቸውን የበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁን በሙሉ”
“በእግዚአብሔር ሀልዎት ደስ ይበላችሁ”
እዚህ ጋ “በሮች” የሚያመለክተው ከተማውን ራሱን ነው። አ.ት፡ “በከተማችሁ ውስጥ የሚኖረው ሌዋዊ” ወይም “ከእናንተ ጋር የሚኖረው ሌዋዊ” (See: Synecdoche)
እግዚአብሔር ለሌዋውያን ምንም መሬት ያለመስጠቱ እውነታ ለልጆቹ ርስት እንዳልሰጣቸው አባት ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እርሱ” የሚያመለክተው ሌዊን ነው። ሌዊ ተወላጆቹን በሙሉ ይወክላል። አ.ት፡ “ምንም ድርሻ የላቸውም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ተጠንቀቁ”
“ደስ በሚያሰኛችሁ ስፍራ ሁሉ” ወይም “በምትፈልጉት ስፍራ ሁሉ”
የሚቃጠል ስጦታ መቅረብ ያለበት በመገናኛው ድንኳን ነው። የመገናኛው ድንኳን የት መደረግ እንዳለበት እግዚአብሔር ራሱ ይመርጣል።
ሕዝቡ ለመሥዋዕት እንስሶችን ማረድ የሚችለው እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ ብቻ ነው። ለምግብ የሚሆኑ እንስሶችን በፈለጉበት ሁሉ ማረድ ይችላሉ። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ መደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information
እዚህ ጋ “በሮች” ከተማውን በሙሉ ይወክላሉ። አ.ት፡ “በከተማችሁ ውስጥ” ወይም “በቤታችሁ” (See: Synecdoche)
ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀባይነት የሌለው ሰው በአካሉ ንጹሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀባይነት ያለው ሰው በአካሉ ንጹሕ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በፍጥነት መሮጥ የሚያስችል ቀጭንና ረጅም እግሮች ያሏቸው የዱር እንስሶች ናቸው። አ.ት፡ “አጋዘንና ድኩላ” (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
ደም ሕይወትን ስለሚወክል ሕዝቡ ደሙን ከምግባቸው ጋር እንዲበሉት እግዚአብሔር አልፈቀደላቸውም። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እዚህ ጋ “በሮች” የሚወክሉት መላውን ከተማ ይወክላሉ። አ.ት፡ “በከተማህ ውስጥ” ወይም “በቤትህ ውስጥ” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ሙሉውን ሰው። አ.ት፡ “ለእግዚአብሔር የምታቀርበውን የትኛውንም ስጦታ” (See: Synecdoche)
“ስጦታዎቻችሁን ትበላላችሁ”
“በእግዚአብሔር ሀልዎት”
እዚህ ጋ “በር” የሚወክለውን መላውን ከተማ ነው። አ.ት፡ “በከተማችሁ ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ ሁሉ” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “እጅህን የምታኖርበት” የሚወክለው ሙሉውን ሰውና እርሱ የሚሠራውን ነው። አ.ት፡ “ስላሠራኸው ሥራ ሁሉ ደስ ይበልህ” (See: Synecdoche)
“ተጠንቀቅ”
ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በሚገባ ጠብቀው” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ስም” የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ራሱን ነው። እርሱ የሚኖርበትንና ሕዝቡ እርሱን ለማምለክ የሚመጣበትን ስፍራ እግዚአብሔር ይመርጣል። አ.ት፡ “መኖሪያውን ይመርጣል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “በሮች” የሚወክሉት መላውን ከተማውን ነው። አ.ት፡ “በከተማህ ውስጥ” ወይም “በማኅበረሰብህ መካከል” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “ነፍስ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “እንደምትመኘው” (See: Synecdoche)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ልክ ሚዳቋውን እና ድኩላውን እንደምትበላ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በፍጥነት መሮጥ የሚችሉ ቀጭንና ረጅም እግሮች ያሏቸው የዱር እንስሶች ናቸው። እነዚህን በዘዳግም 12፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀባይነት የሌለው ሰው በአካሉ ንጹሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀባይነት ያለው ሰው በአካሉ ንጹሕ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ደም ሕይወትን የሚያቆይበት መንገድ ደም ራሱ ሕይወት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ደሙ ሕይወትን ያቆያል” ወይም “ሰዎችና እንስሳት በሕይወት እንዲኖሩ የሚያደርጋቸው ደም ነው።” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ፣ “ሕይወት” የሚለው ቃል የሚወክለው ሕይወትን የሚያቆየውን ደሙን ነው። አ.ት፡ “ሕይወትን የሚያቆየውን ከሥጋ ጋር አትብላው” ወይም “ሕይወትን የሚያቆየውን ደም ከሥጋ ጋር አትብላ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ዐይን ማየትን ይወክላል፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ውሳኔ ትክክል የሆነው” ወይም “እግዚአብሔር ትክክል ነው የሚለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ስእለቶችህን ለመፈጸም ስጦታዎችን” ወይም “የስእለት ስጦታዎች”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ካህኑ የመሥዋዕቱን ደም ያፈሰዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የእግዚአብሔር ሕግ የእንስሳው የትኛው ክፍል የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የትኛው ክፍል ለካህኑ እንደሚሆንና የትኛውን ክፍል አቅራቢው መብላት እንዳለበት ግልጽ ያደርጋል። የዚህ መግለቻ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከሥጋው ጥቂቱን ትበላለህ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“የማዝህን ሁሉ በጥንቃቄ ስማና ታዘዘው”
እዚህ ጋ “ልጆች” ማለት ተወላጆቻቸው ሁሉ ማለት ነው። አ.ት፡ “አንተና ተወላጆችህ እንድትበለጽጉ” (See: Synecdoche)
“መልካም” እና “ትክክለኛ” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ትክክለኛ ባህርይ አስፈላጊ በመሆኑ ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ትክክል የሆነውን በምታደርግበት ጊዜ” (See: Doublet)
ዐይን ማየትን ይወክላል፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ውሳኔ መልካምና ትክክል የሆነው” ወይም “እግዚአብሔር መልካምና ትክክል ነው የሚለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር በከነዓን የሚኖሩትን የሕዝብ ወገኖች ማጥፋቱ አንድ ሰው ቁራጭ ጨርቅ ወይም ከዛፍ ላይ ቅርንጫፍን እንደሚቆርጥ እንደሚቆርጣቸው ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ሕዝቦች” የሚወክሉት በከነዓን የሚኖሩትን ሰዎች ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሁሉንም ነገር በምትወስዱባቸው ጊዜ”
“ተጠንቀቁ”
ስለ ሌሎች አማልክት የሚማርና የሚያመልክ ሰው በአዳኝ ወጥመድ እንደሚያዝ ሆኖ ተነግሮለታል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እንደ እነርሱ አታድርጉ … አማልክታቸውን የመጠየቅ ሙከራ ለማድረግ እንዳትማሩ” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት))
የከነዓን የሕዝብ ወገኖች ጣዖታትን እንደሚያመልኩ እስራኤላውያን ጣዖታትን ማምለካቸው ከሌሎች የሕዝብ ወገኖች በስተኋላ እንደ ተከተሉ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በፊታችሁ ካጠፋቸው በኋላ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛ የሆነው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንተም እንደዚያው ልታደርግ እነዚያ የሕዝብ ወገኖች አማልክታቸውን እንዴት እንዳመለኩ ብትጠይቅ” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
ተጨማሪ ሕጎችን መፍጠርም ሆነ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ሕጎች ቸል ማለት አይኖርባቸውም።
1 በመካከላችሁም፦ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክት ወይም ተአምራት ቢሰጣችሁ፥ እንደ ነገራችሁም 2 ምልክቱ ወይም ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም፦ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት ሄደን እንከተል እናምልካቸውም ቢላችሁ፥ 3 እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ እግዚአብሔር አማላካችሁ ሊፈትናችሁ ነውና፥ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስሙ። 4 እግዚአብሔር አምላካችሁን ተከተሉ፥ እርሱንም አክብሩ፥ ትእዛዘትንም ጠብቁ፥ ድምፁንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩት፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ። 5 ከግብፅ ምድር ካወጣችሁና ከባርነት ቤት ካዳናችሁ ከእግዚአብሔር ከአምላካችሁ ሊያስታችሁ ስለተናገረ ያ ነቢይ ወይም ያ ሕልም አላሚ ይገደል። ያም ነቢይ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ ሊያወጣችሁ ነው። ስለዚህ ክፉውን ነገር ከመካከላችሁ አርቁ። 6 የእናታችሁ ልጅ፥ ወንድማችሁ ወይም ወንድ ልጃችሁ ወይም ሴት ልጃችሁ ወይም በብብታችሁ ያለች ሚስታሁ ወይም እንደ ነፍሳችሁ የምትቆጥሩት ወዳጃችሁ በስውርም ሊፈትናችሁ፦ ኑ፥ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ የማታውቁአችሁን አማልክት ሄደን እናምልክ ብሉአችሁ፥ 7 ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ሌላኛው ምድር ዳር ድረስ ወደ እናንተ የቀረቡት ከእናንተም የራቁት በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት ቢያስታችሁ እሺ አትበሉ። 8 አትስማሙአቸው፤አትስማቸውም። ዓይናችሁም አይራራላቸው፥ አትምራቸውም፥ አትሸሽጋቸውም። 9 በዚህ ፈንታ ፈጽማችሁ ግደሉአቸው፤ እርሱን ለመግደል የእናንተ እጅ በእርሱ ላይ ይሁን፤ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ይሁን። 10 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣችሁ ከእግዚአብሔር ከአምላካችሁ ሊያርቃችሁ ወድዶአልና፥ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገሩት። 11 እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ፥ በመካከላችሁም እንዲህም ያለ ክፉ ሥራ ለማድረግ አይቀጥሉም። 12 እግዚአብሔር አምልካችሁ ልትኖሩባችሁ በሚሰጣችሁ በአንዲቱ ከተማችሁ እንዲህ ሲባል ብትሰሙ፡- 13 አንዳንድ ክፉ ሰዎች ከእናንተ መካከል ወጥተው፦ የማታውቋቸውን ሌሎችን አማልክት ሄደን እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ፥ ሲሉ ብትሰሙ፤ 14 ታጣራላችሁ፥ ትመረምራላችሁ፥ በሚገባም ትጠይቃላችሁ። እነሆም፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከላችሁ እንደ ተደረገ እውነት ሆኖ ቢገኝ። 15 የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋላችሁ፤ ከተማይቱን በእርስዋም ያለውን ሁሉ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፉአቸዋላችሁ። 16 ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባላችሁ፥ ከተማይቱንም ዕቃዋንም ሁሉ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በእሳት ፈጽማችሁ ታቃጥላላችሁ፤ እንደ ገና የማትሠራ ሆና ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቀራለች። 17 ለጥፋት ከተለዩ ነገሮች ምንም እርም ነገር በእጃችሁ አይገኙ። እግዚአብሔር ከቁጣ ትኩሳት ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶቻችሁም እንደማለላቸው ይምራችሁና ይራራላችሁ ዘንድ፥ ያበዛላችሁም ዘንድ ነው። 18 ዛሬ እኔ የማዝዛችሁን ትእዛዘት ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኘውን ታደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ቃል ስሙ።
“በመካከላችሁ ቢመጣ” ወይም “በመካከላችሁ ነኝ ቢል”
ይህ ከእግዚአብሔር በሕልም መልዕክት የሚቀበል ሰው ነው።
እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ የተለያዩ ተአምራቶችን ያመለክታል። (See: Doublet)
“ቢከናወን” ወይም “ቢመጣ”
ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እንድታመልክና እንድታገለግል ቢነግርህ አትስማው” (ቀጥተና እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከሌሎች አማልክት ኋላ መሄድ ወይም መከተል ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን እንከተል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ከማታውቃቸው አማልክት” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ሌሎች የሕዝብ ወገኖች የሚያመልኳቸውን አማልክት ነው። ራሱን ስለገለጠላቸውና ኃይሉን ስለተለማመዱት እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ያውቁታል።
“ያ ነቢይ የሚለውንም ሆነ ሕልም አላሚው የሚናገረውን አትስማው”
እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። እነዚህ ሁለት ሐረጎች “በፍጹም” ወይም “በቅንነት” የሚል ትርጉም እንዲሰጡ በአንድነት ጥቅም ላይ ውለዋል። ይህንን በዘዳግም 4፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔርን መታዘዝና ማምለክ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ኋላ እንደ ሄዱ ወይም እንደተከተሉት ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን ታዘዙ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚወክለው እግዚአብሔር የሚናገረውን ነው። አ.ት፡ “እርሱ የሚለውን ታዘዙ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት መኖሩና ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መታመን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር እንደሚጣበቅ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “በእርሱ ተማመን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “መግደል አለብህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “አመፅ” እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እንድታምፅ ሊያደርግህ ሞክሯል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ባሪያ ከነበሩበት ከግብፅ ማዳኑ ሕዝቡን ከባርነት ለመቤዠት ገንዘብ እንደከፈለ በሚመስል መልኩ ተነግሯል። አ.ት፡ “ ባሪያዎች ከነበራችሁበት ስፍራ ያዳናችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የባርነት ቤት” የእግዚአብሔር ሕዝብ ባሪያዎች የነበሩበትን ግብፅን ይወክላል። አ.ት፡ “ባሪያዎች የነበራችሁበት ግብፅ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር አንድ ሰው እንዴት መኖር ወይም ማድረግ እንዳለበት የሚፈልግበት ሁኔታ ሕዝቡ እንዲሄዱበት እንደሚፈልገው መንገድ ወይም ጎዳና ሆኖ ተነግሯል። አንድን ሰው እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ለማስቆም የሚሞክር በእግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና ላይ እንዳይሄድ እንደተከላከል ሆኖ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘውን እንዳትፈጽም የሚያደርግህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ክፋትን” የሚያመለክተው ክፉ ሰውን ወይም ክፉ ባህርይን ነው። ይህ ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስለዚህ ይህንን ክፉ ነገር የሚያደርገውን ሰው ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ማስወገድ አለብህ” ወይም “ስለዚህ ይህንን ክፉ ሰው መግደል አለብህ” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
እቅፍ የሰው ድረት ነው። ይህ የአነጋገር ዘይቤ ወደ ደረቱ አስጠግቶ ይይዛታል፣ ይኸውም ይወዳታል፣ ይንከባከባታል ማለት ነው። አ.ት፡ “የምትወዳት ሚስትህ” ወይም “በፍቅር የምታቅፋት ሚስትህ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ነፍስ” የሚወክለው የሰውን ሕይወት ነው። ይህ ማለት ሰውየው ለራሱ ሕይወት የሚገደውን ያህል ስለ ጓደኛው ይገደዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “ውድ ጓደኛህ” ወይም “ራስህን የምትወደውን ያህል የምትወደው ጓደኛህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ወደ ሌላው የምድር ጫፍ ሄደህ እንድታመልክ ሊያሳምንህ በምስጢር ይሞክራል” (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
“በዙሪያህ ያሉ”
እዚህ ጋ ሁለቱ የምድር ጽንፍ ማጣቀሻዎች “በምድር ላይ በሁሉ ስፍራ” ማለት ነው። አ.ት፡ “በመላው ምድር ላይ” (See: Merism)
“እርሱ በሚፈልገው አትስማማ”
እዚህ ጋ “ዐይንህ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “በርኅራኄ አትመልከተው” ወይም “አትማረው” (See: Synecdoche)
“ምህረት ልታሳየው ወይም እርሱ ያደረገውን ከሌሎች ልትደብቅ አይገባም”
ይህ ማለት በበደለኛው ሰው ላይ የመጀመሪያውን ድንጋይ እርሱ መወርወር ነበረበት። “እጅ” የሚለው ቃል የሚወክለው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “በመጀመሪያ እስኪሞት ድረስ የምትመታው አንተ መሆን አለብህ” (See: Synecdoche)
“ከእግዚአብሔር ሊመልስህ”። አንድ ሰው ሌላውን እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊገታው መሞከሩ ያንን ሰው በአካሉ እግዚአብሔርን ትቶ እንዲመለስ ለማድረግ እንደሞከረ ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን እንዳትታዘዝ ሊያደርግህ ሞክሯል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ፣ “የባርነት ቤት” የሚወክለው የእግዚአብሔር ሕዝብ ባሪያዎች የነበሩበትን ግብፅን ነው። አ.ት፡ “ባሪያዎች ከነበራችሁበት ስፍራ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሕዝቡ ስለተገደለው ሰው በሚሰሙበት ጊዜ እርሱ እንዳደረገው ለማድረግ እንደሚፈሩ ያመለክታል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ከመካከልህ” የሚለው ሐረግ እነዚህ ክፉ ሰዎች በማኅበረሰቡ መካከል የሚኖሩ እስራኤላውያን ነበሩ ማለት ነው።
ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የማያውቋቸውን አማልክት ሄደው እንዲያመልኩ በከተማቸው የሚኖሩትን አስገድደዋል”። (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
አንድ ሰው ሌላውን እግዚአብሔርን እንዳይታዘዝ ቢያደርገው ያ ሰው በአካሉ ከእግዚአብሔር ተለይቶ እንዲመለስ እንዳደረገው ተቆጥሮ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሐረጎች ሁሉ በመሠረቱ የሚሉት አንድ ነገር ነው። ሙሴ በከተማይቱ ስለሆነው ነገር እውነቱን በጥንቃቄ እንዲያጣሩ አጽንዖት እየሰጠ ነው። (See: Doublet)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የከተማይቱ ሰዎች እንዲህ ያለ አስከፊ ነገር አድርገው እንደሆን (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ስለት” የሚወክለው ሙሉውን ሰይፉን ነው። አ.ት፡ በሰይፎቻችሁ” (See: Synecdoche)
“ብዝበዛውን ሁሉ”። ይህ ሰራዊት በጦርነት ድል ካደረገ በኋላ የሚሰበስበውን ሀብትና ንብረት ያመለክታል።
“የፍርስራሽ ቁልል”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከተማይቱን ማንም ደግሞ አይሥራት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር አንድን ነገር መርገሙና ሊያጠፋው መማሉ እርሱ ቁሱን ከሌሎች ነገሮች ለይቶ እንደሚያስቀምጠው ሆኖ ተነግሯል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አጥፋው ብሎ ካዘዘህ ነገር ውስጥ የትኛውንም ማቆየት የለብህም” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ አንድ ሰው የሆነ ነገርን ለራሱ የሚያቆይበት መንገድ ነው። አ.ት፡ “አታቆይ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ከእንግዲህ ያለመቆጣቱ ቁጣው እንደ አንድ ቁስ ተቆጥሮ እግዚአብሔር በአካል ከእርሱ እንደሚመለስ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር መቆጣቱን ይተዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አባቶችህ” ማለት አያቶችህ ወይም ቅድም አያቶችህ ማለት ነው።
እዚህ ጋ “ድምፅ” እግዚአብሔር የሚናገረውን ይወክላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የሚናገረውን ታዘሃል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ዐይን ማየትን ይወክላል፣ ማየትም ማሰብን ወይም መወሰንን ይወክላል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ውሳኔ ትክክል የሆነውን” ወይም “አምላክህ እግዚአብሔር ትክክል እንደሆነ የሚቆጥረውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 እናንተ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ሕዝብ ናችሁ። ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አታቆስሉ፥ የትኛውንም የፊታችሁን ክፍል አትላጩ። 2 ምክንያቱም እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ፤ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለራሱ ሕዝብ ትሆኑ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን መርጦአልና። 3 ርኩስን ነገር ሁሉ አትብሉ። 4 የምትበሉአቸው እንስሶች እነዚህ ናቸው፦ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፥ 5 ዋላ፥ ሚዳቋ፥ የበረሃ አጋዘን፥ አጭ፥ በራይሌ፥ የተራራ በግ (ድኩላ)። 6 ከእንስሶች ሰኮናው የተሰነጠቀውን ጥፍሩም ከሁለት የተከፈለውን የሚያመነዥከውንም እንስሳ ሁሉ ትበላላችሁ። 7 ነገር ግን ከማያመሰኩ ወይም ሰኮናቸው ካልተሰነጠቀ፥ እነዚህን አትበሉም፤ ግመል፥ ጥንቸል፥ ሽኮኮን፥ አትበሉም። የሚያመነዥኩና ነገር ግን ሰኮናቸው ያልተሰነጠቀም እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው። 8 እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስለማያመነዥክ፥ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋውን አትብሉ በድኑንም አትንኩ። 9 በውኃ ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው፤ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ። 10 ነገር ግን ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸውን አትበሉም፥ ለእናንተ ርኩስ ናቸው። 11 ንጹሕ የሆኑትን ወፎችን ሁሉ ትበላላችሁ። 12 ነገር ግን ከወፎች ሊበሉ የማይገባቸው እነዚህ ናቸው። ንስር፥ ገዴ፥ ዓሣ አውጭ፥ 13 ጭልፊት፥ ጭላት፥ በየወገኑ፥ 14 ቁራም ሁሉ በየወገኑ፥ 15 ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቃል፥ በየወገኑ፥ 16 ጉጉት፥ ጋጋኖ፥ 17 የውኃ ዶሮ ይብራ፥ 18 ጥምብ አንሣ፥ አሞራ፥ እርኩም ሽመላ ሳቢሳ፥ በየወገኑ፥ ጅንጅላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ፥። 19 የሚበርርም ተንቀሳቃሽ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ አይበሉም። 20 ንጹሕ የሆኑትን ወፎች ሁሉ ብሉ። 21 የበከተውን ሁሉ አትብሉ፥ ይበላው ዘንድ በአገራችሁ ደጅ ለተቀመጠ፥ መጻተኛ ትሰጠዋላችሁ፥ ወይም ለእንግዳ ትሸጣላችሁ። ምክንያቱም እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የተቀደሰ ሕዝብ ናችሁ። የፍየሉን፥ ጠቦት፥ በእናቱ ወተት አትቀቅሉ። 22 ከእርሻችሁ በየዓመቱ ከምታገኙት ከዘራችሁ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣላችሁ። 23 ሁልጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁን መፍራት ትማሩ ዘንድ ስሙ፤ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት የእህላችሁን የወይን ጠጃችሁንም የዘይታችሁንም አሥራት የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት ብሉ። 24 እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ ጊዜ መንገዱ ሩቅ ቢሆን፥ እግዚአብሔር አምላካችሁም ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ ቢርቅባችሁ ግን ወደዚያ ለመሸከም ባትችሉ ትሸጣላችሁ፥ 25 የዋጋውንም ገንዘቡ በእጃችሁ ይዛችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደ መረጠው ስፍራ ትሄዳላችሁ። 26 በዚያም በገንዘቡ የፈለጋችሁትን በሬ ወይም፥ በግ ወይም፥ የወይን ጠጅ፥ ወይም ብርቱ መጠጥ፥ ወይም የፈለጋችሁትን ሁሉ ትገዛላችሁ፤ በዚያም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፥ እናንተና ቤተ ሰባችሁም ደስ ይላችኋል። 27 ድርሻና ርስት ከእናንተ ጋር ስለሌለው በአገራችሁ ደጅ ውስጥ ያለውን ሌዋዊውን ቸል አትበሉ። 28 በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት ሌዋዊው ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለ የፍሬአችሁን አሥራት ሁሉ አምጥታችሁ በአገራችሁ ደጅ ታኖራላችሁ፤ 29 በአገራችሁም ደጅ ያለ መጻተኛ፥ ድሀ አደግ፥ ባል የሞተባት መጥተው ይበላሉ፤ ይጠግባሉም። ይኸውም እግዚአብሔር አምላካችሁ በምታደርጉት በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ይባርካችሁ ዘንድ ነው።
“እናንተ” የሚለው አገባብ በሙሉ የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። ሙሴ የሕዝቡ አካል ሆኖ ተካቶአል። አ.ት፡ “እኛ… ሕዝብ ነን … እኛ የተለየን ሕዝብ ነን … መርጦናል”
እነዚህ በከነዓን ይኖሩ የነበሩት የሕዝብ ወገኖች ለሞቱ ሰዎች ሐዘናቸውን የሚገልጹበት መንገድ ነበር። ሙሴ እንደዚያ እንዳያደርጉ ለእስራኤል ሕዝብ ይነግራቸዋል። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። (See: Symbolic Action and Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ከራሳችሁ ጸጉር ላይ ከፊት ያለውን አትላጩት”
እነዚህን ቃላት በዘዳግም 7፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
እግዚአብሔር በልዩ ሁኔታ የእርሱ እንዲሆኑ የእስራኤልን ሕዝብ መምረጡ እነርሱን ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ እንደለያቸው ተደርጎ ተነግሯል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን ከሌሎች ሕዝቦች ለይቶአችኋል” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት))
ይህ ማለት በመሠረቱ ከዐረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ጋር ተመሳሳይ ነገር ነው። ሁለቱም የሚሉት የእስራኤል ሕዝብ በልዩ ሁኔታ የእግዚአብሔር መሆኑን ነው። (See: Parallelism)
“የግል ንብረቱ የሆነ ሕዝብ” ወይም “የእርሱ ሕዝብ”
“በዐለም ላይ ካሉ የሕዝብ ወገኖች ሁሉ”
የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር መበላት የለባቸውም ያላቸውን የትኛውንም ነገር መብላት አይጠበቅባቸውም።
እነዚህ የተለያዩ ዓይነት አጋዘኖች ናቸው። የአንተ ቋንቋ እያንዳንዱን እንስሳ የሚወክል ቃል ከሌለው “ልዩ ልዩ ዓይነት አጋዘን” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
ይህ በፍጥነት መሮጥ የሚችል ቀጭንና ረጅም እግር ያለው የዱር እንስሳ ነው። ይህንን በዘዳግም 12፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የአጋዘን ዓይነት (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁለቱም የድኩላ ዓይነቶች ናቸው። የአንተ ቋንቋ እያንዳንዱን እንስሳ የሚወክል ቃል ከሌለው “የተለያዩ የድኩላ ዓይነቶች” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
የድኩላ ዓይነት (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
“የተሰነጠቀ ሰኮና ያለው”። ይህ ሰኮናው አንድ ሙሉ ከመሆን ይልቅ ሁለት ቦታ የተሰነጠቀ ነው።
ይህ ማለት እንስሳው ምግቡን ከሆዱ ውስጥ እያመጣ እንደገና ያኝከዋል።
ይህ ረጃጅም ጆሮዎች ያሉት ትንሽ እንስሳ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የሚኖረው ምድር ላይ በጉድጓዶች ውስጥ ነው። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
ይህ ትንሽ እንስሳ ሲሆን የሚኖረው በዐለታማ አካባቢ ነው። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ሕዝቡ ሊበላው አይገባውም የሚለው አንዳች ነገር በአካላዊነቱም ንጹሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ሕዝቡ ሊበላው አይገባውም የሚለው አንዳች ነገር በአካላዊነቱም ንጹሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት እነዚህን የመሳሰሉትን እንስሳት መብላት ትችላላችሁ”
ዓሳ በውሃ ውስጥ ለመንቀሳቀስ የሚጠቀምበት ቀጭንና ሰፋ የሚል የአካል ክፍሉ
የዓሳውን አካል የሚሸፍኑ ትናንሽ ንብርብሮች
እግዚአብሔር ሕዝቡ ሊበላው አይገባውም የሚለው አንዳች ነገር በአካላዊነቱም ንጹሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ሕዝቡ ሊበላው ይችላል የሚለው እንስሳ፣ ያ እንስሳ በአካላዊነቱም ንጹሕ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በሌሊት የሚንቀሳቀሱ ወይም ትናንሽ እንስሳትንና የሞቱ እንስሳትን የሚመገቡ የወፍ ዝርያዎች ናቸው። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በሌሊት የሚንቀሳቀሱ ወይም ትናንሽ እንስሳትንና የሞቱ እንስሳትን የሚመገቡ ሁሉም ዓይነት ወፎች ናቸው። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ትናንሽ እንስሶችንና እንሽላሊቶችን የሚመገቡ የወፍ ዓይነቶች ናቸው። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
በተለይ በምሽት የሚበር፣ ነፍሳትንና ዐይጦችን የሚመገብ፣ ክንፍና ጸጉራማ አካል ያለው እንስሳ
ይህ ማለት በመንጋ ሆነው የሚንቀሳቀሱ በራሪ ነፍሳት ሁሉ ማለት ነው።
እግዚአብሔር ሕዝቡ ሊበላው አይገባውም የሚለው እንስሳ በአካላዊነቱም ንጹሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ልትበሏቸው አይገባም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ሕዝቡ ሊበላው ይችላል የሚለው እንስሳ፣ ያ እንስሳ በአካላዊነቱም ንጹሕ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በተፈጥሮአዊ ሞት የሚሞተውን እንስሳ ማለት ነው።
እግዚአብሔር በልዩ ሁኔታ የእርሱ እንዲሆኑ የእስራኤልን ሕዝብ መምረጡ እነርሱን ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ እንደለያቸው ተደርጎ ተነግሯል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን ከሌሎች ሕዝቦች ለይቶአችኋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከምርታቸው ከየአሥሩ እጅ አንድ እጁን እንዲሰጡ ማለት ነው።
“በየዓመቱ”
“በእግዚአብሔር ሀልዎት ፊት”
እዚህ ጋ “እርሱ” የሚያመለክተው የምርቱንና የቀንድ ከብቱን አስራት ነው።
“መባህን በገንዘብ ትሸጠዋለህ”
“ገንዘቡን በቦርሳ አድርገህ ይዘኸው ሂድ”
“የምትፈልገውን ሁሉ”
“በእግዚአብሔር ሀልዎት ፊት”
እዚህ ጋ “በር” የሚወክለው ከተማውን ወይም መንደሩን በሙሉ ነው። አ.ት፡ “በከተማህ ውስጥ የሚኖረውን ሌዋዊ ሁሉ” (See: Synecdoche)
ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከአስራትህ ጥቂቱን ለሌዋዊው ስለመስጠትህ እርግጠኛ” (See: Double Negatives)
የሌዊ ነገድ ርስት የሚሆናቸውን የመሬት ድርሻ አልወሰዱም። የእግዚአብሔር ካህናት ሆነው እርሱ ማገልገላቸው የእነርሱ የርስት ድርሻ ነው። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እግዚአብሔር ለሌዋውያን መሬት አለመስጠቱ ርስት እንዳልሰጣቸው ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ለሌዋውያን፣ ወላጆቻቸውን ላጡ ልጆች፣ ለመበለቶችና መጻተኞች እንዲሰጣቸው እስራኤላውያን በ3 ዓመት አንድ ጊዜ አስራታቸውን በየከተማቸው ማከማቸት ነበረባቸው። (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “በሮች” የሚወክሉት ከተማውን ወይም መንደሩን በሙሉ ነው። አ.ት፡ “በከተማህ ውስጥ” (See: Synecdoche)
እግዚአብሔር ለሌዋውያን ምንም መሬት አለመስጠቱ ርስት እንዳልሰጣቸው ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁለቱም ወላጆቻቸው የሞቱባቸውና የሚንከባከባቸው ዘመድ የሌላቸው ልጆች ናቸው።
ይህቺ ባል የሞተባትና በእርጅናዋ የሚረዳት ልጅ የሌላት ሴት ናት።
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው የሰውን ሁለንተናውን ነው። ይህ የሚያመለክተው አንድ ሰው የሚሠራውን ሥራ ነው። አ.ት፡ “በምትሠራው ሥራ ሁሉ” (See: Synecdoche)
1 በየሰባት ዓመት የዕዳ ምሕረት ታደጋላችሁ። 2 ይህ ዕዳ ምሕረት አፈጻጸም እንከሚከተለው ነው፤ አበዳሪ ሁሉ ለባልንጀራው ላበደረው እንዲተውዋውና ከባልጀራው ወይም ወንድሙ መልሶ እንዳይጠይቅ እግዚአብሔር ያወጀው ይህ ነው። 3 ለእንግዳ ያበደራችሁትን መጠየቅ የምትችሉ ሲሆን፥ ለእስራኤላዊ ወንድማችሁ ያበደራችሁትን ግን ምሕረት አድርጉለት። 4 ይሁን እንጂ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ትወርሱአት ዘንድ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ውስጥ አብዝቶ ስለሚባርካችሁ በመካከላችሁድኻ አይኖርም። 5 ይህ የሚሆነው የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ድምፅ ፈጽማችሁ ስትሰሙና ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዘትን ሁሉ ስትታዘዙ ብቻ ነው። 6 እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ተሰፋ መሠረት ስለሚባርካችሁ እናንተ ለብዙ አሕዛብ ታበድራላችሁ እንጂ እናንተ አትበደሩም፤ብዙ አሕዛብን ትገዛላችሁ እንጂ ማንም እናንተን አይገዛችሁም። 7 እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ደኻ ቢኖር፥ በደኻ ወንድማችሁ ላይ ልባችሁ አይጨክን፥ለደኻ ወንድማችሁ ላይም እጃችሁን ከመዘርጋት አትቆጥቡ፤ 8 ነገር ግን እጃችሁን በትክክል ፍቱለት ለማያስፈልገውም ቅር ሳትሉ አበድሩት። 9 ዕዳ የሚሠርዝበት ሰባተኛ ዓመት ቀርቦአል፥ በማለት ክፉ አሳብ አድሮባችሁ በችግረኛ ወንድማችሁ ላይ እንዳትጨክኑና ምንም ሳትሰጡት እንዳይቀር እርሱ በእናንተ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኾ በደለኞች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። 10 በቅን ልቦና ስጡት፥ ስትሰጡትም ልባችሁ አይጸጸት፥ከዚያም የተነሣ ግዚአብሔር አምላካችሁ ሥራችሁንና እጃችሁን ያረፈበትን ሁሉ ይባርክላችኋል። 11 በምድሪቱ ላይ ሁልጊዜ ድኾች አይጠፉም፥ስለዚህ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞቻችሁ ለድኾችና ለችግራኞች እጃችሁን እንድትዘረጉ አዛችኋለሁ። 12 እናንተም ወንድማችሁን ዕብራዊውን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዙ ስድስት ዓመት ያገልግላችሁ በሰባተኛውም ዓመት ከእናንተ ዘንድ አርነት አውጡት። 13 ከእናንተም ዘንድ አርነት በሚታወጣበት ጊዜ ባዶውን አትስደዱት። 14 ነገር ግን ከመንጋህ፥ ከአውድማችሁም፥ ከወይራችሁም መጥመቂያም ትለግሱታላችሁ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን ትሰጡት ዘንድ ይገባል። 15 እናንተም በግብፅ አገር ባሮች እንደ ነበራችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁም እንደ ነበራችሁ አስቡ፤ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን እንድታደርጉ አዛችሁኋለሁ። 16 ነገር ግን አገልጋያችሁ እናንተንና ቤተ ሰቦቻችሁን በመውደዱና ከእናንተ ጋር ደስተኛ ሆኖ ከመኖሩ የተነሣ፦ ከእናንተ መለየት አልፈልግም ቢላችሁ፦ 17 ጆሮውን ከቤታችሁ መዝጊያ ላይ በማስደግፍ በወስፌ ትበሳላችሁ፤ከዚያም ዕድሜ ልኩን አገልጋያችሁ ይሆናል። በቤት አገልጋዮችሁም ላይ እንዲሁ አድርግ። 18 አገልጋያችሁን አርነት ማውጣት ከባድ መስሎ አይታያችሁ፤ ምክንያቱም የስድስት ዓመት አገልግሎቱ አንድ የቅጥር ሠራተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምታደጉት ነገር ሁሉ ይባርካችኋልና። 19 የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን ተባዕት በኩር ሁሉ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቀድሱ። የበሬአችሁን በኩር አትሥሩባቸው፥ የበጋችሁንም በኩር አትሸልቱ፥ 20 እርሱ በሚመርጠው ስፍራ እናንተና ቤተ ሰባችሁ በየዓመቱ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ትበሉታላችሁ። 21 አንድ እንስሳ እንከን ካለበት፤ አንካሳ ወይም ዕውር ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ፤ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር አትሠዉ። 22 የከተሞቻችሁ ትበላላችሁ፤ በሥርዓቱ መሠረት ንጹሕ የሆነውም ሆነ ያልሆነው ሰው፥ እንደ ድኩላ እንደ ዋላ ያሉትን ይበላዋል። 23 ደሙን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሱት እንጂ አትብሉት።
“7 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ሰዎች የተበደሩህን ሁሉ ተውላቸው”
“ዕዳውን የምትሰርዘው እንደዚህ ነው”
ለሌሎች ሰዎች ገንዘብ የሚያበድር ሰው
“ጓደኛ” እና “ወንድም” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም የሚጋሩ ሲሆኑ ከሌላው እስራኤላዊ ወዳጃቸው ጋር ባላቸው የቅርብ ግንኙነት ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “እስራኤላዊ ጓደኛው” (See: Doublet)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ዕዳን እንድትምር እግዚአብሔር አዞሃልና” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንዲመለስልህ መጠየቅ የለብህም” ወይም “ተመልሶ እንዲከፈልህ መጠየቅ የለብህም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ድኻ” የሚለው ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ድኻ ሕዝብ” ውይም “ድኻ የሚሆን አንድም ሰው” (See: Nominal Adjectives)
ይህ የከነዓንን ምድር ያመለክታል።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚሰጣቸው ምድር ርስታቸው እንደሚሆን ተቆጥሮ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው ራሱን እግዚአብሔርን ነው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር የሚናገረውን ለመታዘዝ ከተጠነቀቅህ ብቻ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ገንዘብ” የሚለው ቃል የሚታወቅ ነው። የዚህን መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “ገንዘብ ታበድራለህ … ገንዘብ አትበደርም” (See: Ellipsis)
እዚህ ጋ “ሕዝቦች” የሚወክሉት ሰዎችን ነው። አ.ት፡ “ለብዙ ሀገር ሰዎች … በብዙ ሀገር ሰዎች ላይ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “መግዛት” በገንዘብ ዐቅም መብለጥ ማለት ነው። ይህ ትርጉሙ በዐረፍተ ነገሩ የመጀመሪያ ክፍል ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው። (See: Parallelism)
እዚህ ጋ “ሰው” ማለት በጥቅሉ ሰው ነው። አ.ት፡ “ድኻ የሆነ ሰው ቢኖር”
“ከእስራኤላዊ ጓደኞችህ አንዱ”
እዚህ ጋ “በሮች” የሚወክሉት ከተማን ወይም መንደርን በሙሉ ነው። አ.ት፡ “በየትኛውም ከተማህ” (See: Synecdoche)
ግትር መሆን ሰዎቹ ልባቸውን እንዳደነደኑ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ግትር አትሁን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ለድኻው ሰው ለመስጠት የማይፈቅድ ሰው ድኻው ሰው ከእርሱ ምንም እንዳያገኝ እጁን እንደሚከድን ተደርጎ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “ድኻ የሆነውን እስራኤላዊ ጓደኛህን ለመርዳት እምቢ አትበል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ድኻውን ሰው የሚረዳ እጁን እንደ ከፈተለት ተደርጎ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “ነገር ግን ልትረዳው በእርግጥ ይገባሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው የሰውን አዕምሮ ነው። አ.ት፡ “ክፍ አሳብ አታስብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የምሕረት ዓመት ስለቀረበ ይህንን የሚያስበው ሰው ድኻው ሰው ሊመልስለት እንደማይችል በማሰብ ድኻውን ለመርዳት እንደሚያመነታ ያመለክታል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ሰባተኛው” የሚለው ቃል የሰባት ደረጃ አመልካች ቁጥር ነው። (ደረጃን አመልካች ቁጥር የሚለውን ተመልከት)
“ዕዳን የመሰረዝ ዓመት”
በቅርብ የሚሆን አንድ ነገር በአካል የቀረበ በሚመስል መልኩ ተነግሯል። አ.ት፡ “በቅርቡ ይሆናል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አትጨክን፣ ለእስራኤላዊ ጓደኛህ የትኛውንም ነገር ከመስጠት አትንፈገው”
“ዕርዳታ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል”
“አንተ ያደረግኸውን እግዚአብሔር ኃጢአት ይለዋል”
እዚህ ጋ “ልብ” ሙሉውን ሰው ይወክላል። አ.ት፡ “ቅር አይበልህ” ወይም “ደስ ይበልህ” (Synecdoche እና ምጸት የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅህን በምታኖርበት” የሚወክለው ሙሉውን ሰውና እርሱ የሚሠራውን ሥራ ነው። አ.ት፡ “በምትሠራው ሁሉ” (See: Synecdoche)
ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በምድር ላይ ድኾች ሁሌም ይኖራሉና” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)
“ድኾች” የሚለው ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሆኖ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ድኾች ሰዎች” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በምድርህ ላይ -- እጅህን እንድትከፍት አዝሃለሁ” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ)
አንድን ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ የሚሆን ሰው እጁን እንደሚከፍት ተደርጎ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “እስራኤላዊ ጓደኛህን፣ የተቸገሩትንና ድኾችን እርዳቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ችግረኛ” እና “ድኻ” የሚሉት ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ሆኖ እነዚህ ራሳቸውን መርዳት የማችሉ ሰዎች መሆናቸው ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ራሳቸውን መርዳት የማይችሉ እስራኤላውያን ጓደኞችህን እርዳቸው” (See: Doublet)
እዚህ ጋ “ወንድም” ማለት ወንድ ይሁን ሴት በአጠቃላይ እስራኤላዊ የሆነ ማለት ነው። አ.ት፡ “አንድ እስራኤላዊ ጓደኛህ” ወይም “አንድ ዕብራዊ ጓደኛህ” (ተባዕታዊ ቃል ሴቶችን ሲጨምር የሚለውን ቃል ተመልከት)
አንድ ሰው ዕዳውን መክፈል ባይችል አንዳንድ ጊዜ የተበደረውን ለመክፈል ራሱን ለባርነት ይሸጥ ነበር። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ራሳቸውን ለአንተ የሸጡ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“6 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“7 ዓመት”። ይህ “ሰባተኛ” የሰባት ደረጃን አመልካች ቁጥር ነው። (ደረጃን አመልካች ቁጥር የሚለውን ተመልከት)
ለራሱ ወይም ለቤተሰቡ የሚያቀርበው አስፈላጊ ነገር የሌለው ሰው እጆቹ ባዶ እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ለእርሱና ለቤተሰቡ የሚያቀርበው እንዲኖረው ሳትሰጠው እንዲሄድ አታድርገው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በደግነት ስጠው”
እዚህ ጋ “አንተ” የሚለው ቃል ለብዙ ዓመታትባሪያዎች የነበሩትን ቅድም አያቶቹን ይጨምራል። አ.ት፡ “በአንድ ወቅት የአንተም ሕዝብ ባሪያዎች እንደነበሩ አስብ” (See: Forms of You)
እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ በግብፅ ባሪያ ከነበረበት ማዳኑ ሕዝቡን ከባርነት ለመቤዠት ገንዘብ የከፈለ በሚመስል መልኩ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛ የሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከአንተ አልለይም ቢልህ” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ
እዚህ ጋ “ቤት” የሚወክለው የሰውየውን ቤተሰብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ከዚያም ራሱን በቤትህ የበር መቃን ላይ ታስደግፍና በጆሮው የጉትቻ ማንጠልጠያ ቦታ ላይ የወስፌው ጫፍ እንጨቱ ጋ እስኪደርስ ትበሳዋለህ”
ቀዳዳ ለማበጀት የሚጠቅም ጫፉ የሾለና ቀጥ ያለ መሣሪያ (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
“እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ድረስ” ወይም “እስኪሞት ድረስ”
ይህ ማለት አንድን ሰው በነጻ በሚያሰናብቱበት ጊዜ ቅር መሰኘት የለባቸውም። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በነጻ በምታሰናብተው ጊዜ ደስ ይበልህ” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ባለቤቱ ሥራ ለማሠራት ከሚቀጥረው ሰው ባነሰ ዋጋ ብቻ ይህንን ባሪያ አሠርቶታል ማለት ነው።
ይህ ተከፍሎት የሚሠራ ሰው ማለት ነው።
ሱፍ ወይም ጸጉር መቁረጥ
“በእግዚአብሔር ሀልዎት ፊት”
“በእያንዳንዱ ዓመት” ወይም “በየዓመቱ”
ሽባ ወይም አካሉ የተጎዳ
እዚህ ጋ “በሮች” የሚወክሉት ከተማውን ወይም መንደሩን ነው። አ.ት፡ “በማኅበረሰብህ ውስጥ” ወይም “በከተማህ ውስጥ” (See: Synecdoche)
ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀባይነት የሌለው ሰው በአካሉም ንጹሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀባይነት ያለው ሰው በአካሉም ንጹሕ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በፍጥነት መሮጥ የሚያስችል ረጅምና ቀጭን እግሮች ያሏቸው የዱር እንስሳት ናቸው። እነዚህን በዘዳግም 12፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
“ደሙን አትመገበው”። ደም ሕይወትን ስለወከለ እስራኤላውያን ደም እንዲመገቡ እግዚአብሔር አልፈቀደላቸውም። (ዘዳግም 12:23ን ተመልከት)
1 እግዚአብሔር አምላካችሁ በአቢብ ወር ከግብፅ በሌሊት ስላወጣችሁ የአቢብ ወር ጠብቁ፥ የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ፋሲካ አክብሩበት። 2 እግዚአብሔር ለሰሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋችሁ አንዱን እንስሳ እግዚአብሔር በአምላካችሁ ፋሲካ አድርጋችሁ ሠዉ። 3 ከቦካ ቂጣ ጋር አትብሉ፤ ከግብፅ የወጣችሁ በችኮላ ነውና፥ ከግብፅ የወጣችሁበትን ጊዜ በሕይወታችሁ ዘመን ሁሉ ታስቡ ዘንድ ያልቦካ ቂጣ ሰባት ቀን ብሉ። 4 ከምድራችሁ ሁሉ ላይ በእናንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዉም ላይ ማናቸውም ሥጋ እስከ ጧት ድረስ እንዲቆዩ አታድርጉ። 5 እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ በማናቸውም ከተማ በሮች ላይ ፋሲካን መሠዋት አይገባችሁም። 6 በዚህ ፈንታ፥ ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችን በመረጠው ስፍራ ፀሐይ ስትጠልቅ በምሽት ላይ ከግብፅ ከወጣችሁበት ሰዓት ላይ በዚያ ፋሲካ ሰዉ። 7 ሥጋውንም ጠብሳችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚመርጠው ስፍራ ብሉ፥ ሲነጋም ወደ ድንኳናችሁ ተመልሳችሁ ሂዱ። 8 ለስድስት ቀንም ያልቦካ ቂጣ ብሉ፤ በሰባተኛው ቀን በእግዚአብሔር በአምላካችሁ የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ ሥራም አትሥሩበት። 9 እህላችሁን ማጨድ ከምትጀምሩበት ዕለት አንሥቶ ለራሰችሁም ሰባት ሳምንታትን ቁጠሩ። 10 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን በፈቃዳችሁ የምታመጡትን ስጦታ በማቅረብ በመከሩ በዓል እግዚአብሔር አምላካችሁን አክብሩ። 11 እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ወንዶችና ሴቶች አጋልጋዮቻችሁ በከተሞቻችሁ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ በመካከላችሁ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና ባል የሞተባቸው እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ። 12 እናንተም በግብፅ ባሪያዎች እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፥ እነዚህንም ሥርዓቶች በጥንቃቄ ጠብቁ አድርጉም። 13 የእህላችሁን ምርት ከዐውድማችሁ ፤ ወይናችሁንም ከመጭመቂያችሁ ከሰበሰባችሁ በኋላ የዳስን በዓል ሰባት ቀን አክብሩ። 14 በበዓላችሁ እናንተና ወንድና ሴት ልጆቻችሁ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮቻችሁ፥ በከተማው ያለ ሌዋዊ መጻተኛ፥ አባት አልባውና ባል የሞተባት ደስ ይበላችሁ። 15 እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በዓሉን ሰባት ቀን አክብሩ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በእህል ምርታችሁና በእጆቻችሁ ሥራ ሁሉ ይበርካችኋል፤ ደስታችሁም ፍጹም ይሆናል። 16 ወንዶቻችሁ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በመከር በዓልና በዳስ በዓል ላይ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ይቅረቡ፥ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ባዶ እጁን አይቅረብ፥ 17 በዚህ ፈንታ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን እያንዳንዱ እንደ ችሎታው ይስጥ። 18 እግዝዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ከተማ ሁሉ ለየነገዶቻችሁ ዳኞችንና አለቆችን ሹሙ፥ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ፥ 19 ፍርድ አታዛቡ፥ አድልዎ አታደርጉ፥ ጉቦም አትቀበሉ፥ ጉቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና። 20 በሕይወት እንድትኖሩና እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣችሁን ምድር እንድትወርሱ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተሉ። 21 ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በምታደርጉት መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የእንጨት ዐምድ አታቁሙ። 22 እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለእናንተ አታቁሙ።
ይህ በዕብራውያን የቀን አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ነው። እርሱ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ አውጥቶ ያመጣበትን ጊዜ ያስታውሳል። በምዕራባውያኑ አቆጣጠር በመጋቢት መጨረሻና በሚያዝያ መጀመሪያ አካባቢ ነው። (የዕብራውያን ወራት እና ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ፋሲካን ጠብቀው” በዓሉን ማክበርና የፋሲካን ምግብ መብላት እንዳለባቸው ያመለክታል። አ.ት፡ “የፋሲካን ምግብ አክብር” ወይም “የፋሲካን ምግብ ብላ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Infor- mation)
እዚህ ጋ “ፋሲካ” የሚወክለው ለፋሲካ በዓል የሚሠዋውን እንስሳ ነው። አ.ት፡ “ለፋሲካ መሥዋዕት ታቀርባለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እርሱ” የሚያመለክተው የሚሠዉትንና የሚበሉትን እንስሳ ነው።
“7 ቀን” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ እርሾ የሌለበት እንጀራ ስም ነበር። ሙሉ ትርጉሙ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ይህ እንጀራ በግብፅ በነበራችሁበት ጊዜ ምን ያህል እንደተሰቃያችሁ ያስታውሳችኋል” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ሕዝቡ በፍጥነት ግብፅን ለቀው መውጣት ስለነበረባቸው እርሾ ጨምረውበት እንጀራ ለመጋገር በቂ ጊዜ አልነበራቸውም። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግለጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በችኮላ ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ እርሾ የገባበት እንጀራ ለማዘጋጀት ጊዜ አልነበራችሁም” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“በሕይወት እስካላችሁ ድረስ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አስታውሱ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በመካከላችሁ ምንም እርሾ አይኑራችሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በክልሎቻችሁ ሁሉ ውስጥ” ወይም “በምድራችሁ ሁሉ ላይ”
ይህ “የመጀመሪያ” አንድን የሚያመለክት የደረጃ አመልካች ቁጥር ነው። (ደረጃን አመልካች ቁጥር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ፋሲካ” የሚወክለው የሚሠዋውን እንስሳ ነው። አ.ት፡ “ለፋሲካ እንስሳውን መሠዋት አይኖርባችሁም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “በሮች” የሚወክሉት ከተሞቹን ወይም መንደሮችን ነው። አ.ት፡ “በየትኛውም መንደሮችህ ውስጥ” (See: Synecdoche)
“ፀሐይ ስትጠልቅ”
“ማብስል ይኖርብሃል”
“6 ቀን” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ሰባተኛ” የሰባት ደረጃን አመልካች ቁጥር ነው (ደረጃን አመልካች ቁጥር የሚለውን ተመልከት)
“ልዩ ስብሰባ”
“7 ሳምንት ቁጠር” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ማጨድ ከምትጀምርበት” የሚለው ሐረግ መከር መሰብሰብ የሚጀመርበትን ጊዜ ማመላከቻ መንገድ ነው። አ.ት፡ “እህል መሰብሰብ ከምትጀምርበት ጊዜ ጀምሮ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሣር፣ ሰብል፣ እና ወይን ለመቁረጥ የሚያገለግል ቆልማማ ምላጭ ያለው መሣሪያ ነው። (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “የበጎ ፈቃድ ስጦታህን ትሰጣለህ” (See: Synecdoche)
“አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ሰጠህ ምርት መጠን”። ይህ ማለት ሰዎቹ ምን ያህል መስጠት እንደሚኖርባቸው የሚወስኑት በዚያ ዓመት ባመረቱት ምርት መጠን ይሆናል።
እነዚህ አንድን ተለይቶ የታወቀን ሰው አያመለክቱም። የሚያመለክተው እንዲህ ያሉትን ሰዎች በአጠቃላይ ነው። አ.ት፡ “ወንዶች ልጆቻችሁን፣ ሴቶች ልጆቻችሁን፣ ወንዶች ባሪያዎቻችሁን፣ ሴቶች ባሪያዎቻችሁን፣ የትኛውንም ሌዋዊ” (See: Generic Noun Phrases)
እዚህ ጋ “በሮች” የሚወክሉት ከተሞችን ወይም መንደሮችን ነው። አ.ት፡ “በመንደሮችህ ውስጥ” (See: Synecdoche)
ይህ የሚያመለክተው እንዲህ ያሉትን የመሰሉ ሰዎችን በአጠቃላይ ነው። አ.ት፡ “መጻተኞችን ሁሉ፣ ወላጆቻቸውን ያጡትን፣ መበለቶችን” (See: Generic Noun Phrases)
እነዚህ አባትና እናት የሞቱባቸውና የሚንከባከባቸው ዘመድ የሌላቸው ልጆች ናቸው።
ይህ ማለት ባል የሞተባትና በእርጅናዋ የሚረዳት ልጅ የሌላት ሴት ማለት ነው።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አስታውስ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የዚህ በዓል ሌሎች ስሞች፣ “የመገናኛው ድንኳን በዓል”፣ “የዳስ በዓል”፣ እና “የመሰብሰብ በዓል”። በመከር ጊዜ ገበሬዎች በመስኩ ላይ ጊዜያዊ መጠለያ ይሠሩ ነበር። ይህ በዓል የሚደረገው የዓመቱ መከር ከተሰበሰበ በኋላ ነበር።
“7 ቀን” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “በሮችህ” የሚለው ቃል የሚወክለው ከተሞችንና መንደሮችን ነው። “በመንደሮችህ ውስጥ” (See: Synecdoche)
“የመጠለያ በዓሉን”
እዚህ ጋ “እጆች” የሚወክሉት ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “የምትሠራውን ሥራ ሁሉ” (See: Synecdoche)
እግዚአብሔር ሴቶቹ እንዲመጡ ባይጠይቅም ለእነርሱም ተፈቅዶላቸዋል። ወንዶቹ መላውን ቤተሰባቸውን መወከል ይችሉ ነበር።
“ይምጡና በእግዚአብሔር ሀልዎት ፊት ይቁሙ”
“በእግዚአብሔር ፊት ስጦታ ሳይዙ አይምጡ”። እነዚህ ሁለት አሉታዊ ሐረጎች በአንድ ላይ አዎንታዊ ትርጉም አላቸው። አ.ት፡ “ወደ እግዚአብሔር ፊት የሚመጣ ሁሉ ስጦታ ያምጣ” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
“ዳኞችን ሹም” ወይም “ዳኞችን ምረጥ”
እዚህ ጋ “በሮች” የሚወክለው ከተማን ወይም መንደርን ነው። አ.ት፡ “በመንደሮችህ ሁሉ ውስጥ” (See: Synecdoche)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ትመርጣቸዋለህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ሕዝቡን በፍትሐዊነት ዳኙ”
ሙሴ ስለ ፍትሕ ሲናገር ብርቱው ሰው ከደካማው ሰው በጉልበት እንደሚቀማው አንዳች ቁሳዊ አካል አድርጎ ይናገራል። ይህ በአዎንታዊ መልኩ ሊነገር ይችላል። የአንተ ቋንቋ “ለመውሰድ ኃይል ተጠቀም” ለማለት አንድ ቃል ይኖረው ይሆናል። አ.ት፡ “በምትዳኝበት ጊዜ ኢፍትሐዊ አትሁን” ወይም “ትክክለኛ ውሳኔዎችን ስጥ” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት and Double Negatives))
እዚህ ጋ “አንተ” የሚያመለክተው እነዚያን ዳኞችና አለቆች ተደርገው የተሾሙትን ነው። (See: Forms of You)
ጉቦ መቀበል ሰዎችን እንደሚያበላቸው ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ጉቦን የሚቀበል ጥበበኛ ሰው እንኳን ይታወራል፣ ጉቦን የሚቀበል ጻድቅ ሰውም እንኳን ሐሰትን ይናገራል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ክፉ በሆነው ነገር ላይ እንዳይናገር ጉቦን የሚቀበል ጠቢብ ሰው የሚታወር ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ጠቢቡ” የሚለው ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ጠቢብ ሰው” ወይም “ጥበበኛ ሰዎች” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
“ጻድቅ” የሚለው ስማዊ ቅጽል እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ጻድቁን ሰው እንዲዋሽ ያደርገዋል” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
ፍትሕ በሚራመድ ሰው ተመስሎ ተነግሮለታል። ትክክለኛና ቅን የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው ፍትሕን በቅርበት እንደተከተለ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “አግባብነት ያለውን ብቻ አድርግ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚሰጣቸውን ምድር መቀበል ሕዝቡ ምድሪቱን ከእግዚአብሔር እንደሚወርስ ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አንተ” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ በሙሉ ነው። (See: Forms of You)
“አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠላውን” የሚለው ሐረግ ስለ ማምለኪያ የድንጋይ ዐምድ የበለጠ መረጃ ይሰጣል። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ስለሚጠላቸው የትኛውንም የማምለኪያ የድንጋይ ዐምድ” (See: Distinguishing versus Informing or Reminding)
ይህ የሚያመለክተው ሐሰተኞችን አማልክት ለማምለክ የሚጠቀሙባቸውን ጣዖታት የሆኑ ዐምዶችን ነው።
1 እንከን ወይም ጉድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ እግዚአብሔር ለአምላክችሁ አትሠዉ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነውና። 2 እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ከተሞች በሮች አብሮአችሁ የሚኖር ወንድ ወይም ሴት ኪዳኑን በማፍረስ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ሲፈጽም ቢገኝ፥ 3 ትእዛዜንም በመተላለፍ ባዕዳን አማልክትን ያመለከ፥ ለእርሱም ማለትም ለፀሐይ ወይምለጨረቃ ወይም ለሰማይ ከዋክብት የሰገደ፥ 4 እናንተ ይህ መደረጉን ብትሰሙ ነገሩን በጥንቃቄ መርምሩ፥ የተባለውም እውነት ከሆንና እንዲህ ያለ አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ዘንድ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፥ 5 ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስዳችሁ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገሩት። 6 ሞት የሚገባው ሰው በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፥ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል። 7 ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት ክፉን ከመካከላችሁ አስወግዱ። 8 በአንድ የነፍስ ግድያ ዓይነትና በሌላ በአንድ ዓይነት ሕጋዊ ክርክርን በሌላ ወይም በአንድ የክስ ዓይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጉዳይ ቢነሣ፥ ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ጉዳይ በከተሞቻችሁ ውስጥ ቢያጋጥማችሁ፥ ተነሥታችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚመርጠው ስፍራ ውጡ። 9 ካህናት ወደ ሆኑት ሌዋውያንና በዚያን ጊዜ ዳኛ ወደ ሆነው ሰው ሄዳችሁ ስለ ጉዳዩ ጠይቁአቸው፥ እነርሱም ውሳኔውን ይነግሩአችኋል። 10 እናንተም እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ እነርሱ በሚሰጡአችሁ ውሳኔ መሠረት ፈጽሙ። እንድፈጽሙ የሚሰጡአችሁን መመሪያ ሁሉ በጥንቃቄ አድርጉ፥ 11 በሚያስተምሩአችሁ ሕግና በሚሰጡአችሁ መመሪያዎች መሠረት ፈጽሙ፥ እነርሱ ከሚነግሩአችሁ ቀኝም ግራም አትበሉ። 12 እግዚአብሔር አምላካችሁን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህን ወይም ዳኛ የሚንቅ ይገደል፥ ከእስራኤልም መካከል ክፉውን አስወግዱ። 13 ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲሰማ ይፈራል፤ ከዚያ ወዲያም እንዲህ ያለውን የንቀት ድርጊት አይደግመውም። 14 እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፥ በምትወርሱአትና በምትቀመጡባት ምድር በዙርያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፥ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ ብትሉ፥ 15 ከዚያ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚመርጠውን ንጉሥ በላይህ ታነግሣለህ፥ ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንጂ እስራኤላዊ ወንድምህ ያልሆነውን ባዕድ በላይህ አታንግሥ። 16 ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ ወይም ደግሞ የፈረሰኞችን ቁጥር ለመጨመር ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስ፤ 17 እግዚአብሔር በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ፥ ብሎአችኋልና፤ ልቡ እንዳይስትም ብዙ ሚስቶችን አያግባ፥ ብዙ ብር ወይም ወርቅ ለራሱ አያብዛ። 18 በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ የዚህን ሕግ ቅጅ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ በጥቅልል መጽሐፍ ለራሱ ይጻፍ። 19 እግዚአሔር አምላኩን ማክበር ይማር ዘንድ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዓት በጥንቅቄ ይጠብቅ ዘንድ ከእርሱ ጋር ይሁን፤በሁሉም ቀኖች ያንብበው። 20 ይህን የሚያደርገው ከወንድሞቹ ላይ ልቡ እንዳይኮራ፥ ከትእዛዘትም ወደ ኋላ እንዳይመለስ፥ እርሱና ልጆቹም ረጅም ዘመን ይገዙ ዘንድ፥ ከሕጉ ቀኝ ወይም ግራም አበል።
“እንከን ያለበት” ወይም “አንዳች ጉድለት ያለበትን”። እንስሳው ሲታይ ጤነኛና እንከን የሌለበት
“ያ ለእግዚአብሔር አስቀያሚ ይሆናል
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ብታገኝ” ወይም “አንድ ሰው ቢኖር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የከተማ በሮች” ከተሞችን ወይም መንደሮችን ይወክላሉ። አ.ት፡ “ከከተሞችህ በአንዱ ቢኖር” (See: Synecdoche)
የእግዚአብሔር ፊት የእግዚአብሔርን ውሳኔ ወይም ምዘና ይወክላል። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ክፉ ነው ብሎ የሚያስበው ነገር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ቃል ኪዳኑን አይታዘዝም”
“የትኛውንም ኮከብ”
“እንዲያደርገው ለማንም ያላዘዝኩትን”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ስለዚህ የእምቢተኝነት ተግባር ቢነግርህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “ምርመራ” እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሆነውን ነገር በጥንቃቄ መርምር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው እንዲህ ያለውን አስከፊ ነገር በእስራኤል አድርጎ እንደሆነ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አፍ” የሚወክለው የመስካሪዎችን ምስክርነት ነው። ይህ ወደ አድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በሰውየው ላይ ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ከመሰከሩበት ከዚያ በኋላ ታስወግደዋለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር፣ አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አፍ” የሚወክለው የመስካሪውን ምስክርነት ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ነገር ግን በእርሱ ላይ የሚመሰክረው አንድ ሰው ብቻ ከሆነ ያንን ሰው ማስወገድ አይኖርብህም” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ምስክሮችን በሙሉ ነው። አ.ት፡ “ድንጋዮቹን ለመወርወር ምስክሮቹ ራሳቸው የመጀመሪያ ይሁኑ፣ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ በእርሱ ላይ ድንጋይ በመወርወር ይግደሉት” (See: Synecdoche)
“ጉዳይ ቢኖር” ወይም “ሁኔታ ቢኖር”
“መብት” አንድ ሰው አንድን ነገር የሚያደርግበት ወይም አንድ ነገር እንዲኖረው የሚያስችለው ሕጋዊ ስልጣን ነው።
እዚህ ጋ “የከተማ በሮች” ከተሞችን ወይም መንደሮችን ይወክላል። አ.ት፡ “በመንደርህ ውስጥ” (See: Synecdoche)
የነገር ስም የሆነው “ምክር” እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እንዲመክሩህ ጠይቃቸው” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “ውሳኔ” እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ይሰጣሉ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
ካህናትና ዳኛው የሚወስኑትን የሚታዘዝ ሰው በአካሉ ከሕግ ኋላ እንደተከተለ ተደርጎ ተነግሯል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስለ ጉዳዩ ዳኛውና ካህናት የሚወስኑትን ታዘዝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ካህኑን የማይታዘዝ … ወይም ዳኛውን የማይታዘዝ
ስማዊ ቅጽል የሆነው “ክፉን” እንደ ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይህንን ክፉ ነገር ያደረገውን ሰው ከእስራኤል መካክል ታስወግደዋለህ” ወይም “ይህንን ክፉ ሰው ግደለው” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
ሕዝቡ የዕብሪት ተግባር የፈጸመው ሰው ስለመገደሉ በሚሰሙበት ጊዜ ይፈራሉ እነርሱ ራሳቸው የዕብሪትን ተግባር አይፈጽሙም እንደ ማለት ነው። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“በምትመጡበት” የሚለው ቃል “በምትሄዱበት” ወይም “ስትገቡ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። (ሂድ እና ና የሚለውን ተመልከት)
ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛ የሆነው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከዚያም በዙሪያህ ያሉ ሀገራት ሕዝቦች ንጉሥ እንዳላቸው አንተም እንዲኖርህ ትወስናለህ፣ ከዚያም” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እንደ አንድ ሰው ቆጥሮ የሚናገራቸው ሰዎች አሉት። ወደ ብዙ ቁጥር ተውላጠ ስም መተርጎም በይበልጥ የተለመደ ይሆናል። አ.ት፡ “በዙሪያችን … ለራሳችን እናነግሣለን” (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)
በእስራኤል ለአንድ ሰው እንደ ንጉሥ እንዲገዛቸው ሥልጣን መስጠታቸው ሕዝቡ ያንን ሰው ከእነርሱ በላይ ባለ ቦታ ላይ እንዳስቀመጡት ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በዙሪያዬ ያሉ ሕዝቦች”
እዚህ ጋ “ሀገራት” የሚወክሉት በሀገራቱ ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎች ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እንደ አንተው እስራኤላዊ ከሆኑት አንዱን”
የእነዚህ ሁለት ሐረጎች ትርጉም ተመሳሳይ ነው። ሁለቱም የሚያመለክቱት እስራኤላዊ ያልሆነውን ሰው ነው። የእስራኤል ሕዝብ መጻተኛው እንዲገዛቸው እንዳይፈቅዱ እግዚአብሔር አጽንዖት ሰጥቷል። አ.ት፡ “በራስህ ላይ መጻተኛውን” ወይም “እስራኤላዊ ያልሆነውን በራስህ ላይ” (See: Doublet)
ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ሌላ ትዕምርተ ጥቅስ አለው። ቀጥተኛው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ዳግመኛ ወደ ግብፅ እንዳትመለሱ ብሏልና” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ልብ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። ባዕዳን ሴቶችን የሚያገባና የእነርሱን ሐሰተኛ አማልክት ለማምለክ የሚጀምር እስራኤላዊ ንጉሥ ልቡ ከእግዚአብሔር እንደሚመለስ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን ማክበሩን በማቆም ሐሰተኞች አማልክትን ማምለክ እንዲጀምር እንዳያደርጉት” (Synecdoche and ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዙፋን” የሚወክለው ሰውየው እንደ ንጉሥ የሚኖረውን ኃይልና ሥልጣን ነው። በዙፋን መቀመጥ ንጉሥ መሆን ማለት ነው። አ.ት፡ “ንጉሥ በሚሆንበት ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “በግሉ የዚህን ሕግ ቅጅ በጥቅልል ላይ ለራሱ ይጻፍ” ወይም 2) “የዚህን ሕግ ቅጅ የሚጽፍለትን ሰው ይሹም”
“ሌዋውያን ካህናት ከሚጠብቁት ከሕጉ ቅጅ”
እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ የሚሉት ተመሳሳይ ነገር ሲሆን ንጉሡ የእግዚአብሔርን ሕግ በሙሉ መታዘዝ እንዳለበት አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Parallelism)
እዚህ ጋ “ልቡ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። የአንድ ንጉሥ ዕብሪተኛ መሆን ልቡ እንደ ታበየ ሆኖ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “ዕብሪተኛ እንዳይሆን” ወይም “እንደ እርሱ ካለው እስራኤላዊ ይልቅ የተሻለ እንደሆነ እንዳያስብ” (Synecdoche እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
አንድ ንጉሥ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት አለመታዘዙ አንድ ሰው ከትክክለኛው መንገድ እንደሚወጣ በሚመስል መልኩ ተነግሯል። ይህ በአዎንታዊ መልኩ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከትዕዛዛቱ የትኛውንም ሳይታዘዝ እንዳይቀር” ወይም “ትዕዛዛቱን ሁሉ እንዲጠብቅ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ምጸት የሚለውን ተመልከት)
1 ሌዋውን ካህናት፥ የሌዊ ነገድ ሁሉ ከእስራኤል ጋር የመሬት ድርሻ ወይም ርስት ስለማይኖራቸው ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርበው ድርሻቸው ነውና ይብሉ። 2 እግዚአብሔር በሰጣቸው ተስፋ መሠረት እርሱ ራሱ ርስታቸው ስለሆነ በወንድሞቻቸው መካከል ርስት አይኖራቸውም። 3 ኮርማ ወይም በግ የሚሠዋው ሕዝብ ለካህኑ የሚሰጠው ድርሻ ወርቹን፥ ሁለት ጉንጮችንና የሆድ ዕቃውን ነው። 4 የእህላችሁን፥ የአዲሱን ወይናችሁንና የዘይታችሁን በኩራት እንዲሁም ከበጎቻችሁ በመጀመሪያ የተሸለተውን ጠጉር ትሰጣላችሁ። 5 በእግዚአብሔር ስም ቆሞ ለዘላለም ያገለግል ዘንድ እግዚአብሔር አምላክህ ከነገዶቻችሁ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጦአል። 6 አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በእስራኤል ካሉት ከተሞቻችሁ መካከል በፍጹም ፈቃድ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ቢመጣ፥ 7 በእግዚአብሔር ፊት ቆመው እንደሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ፥ እርሱም በእዚግአብሔር በአምላኩ ስም ያገልግል። 8 ከቤተ ሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳ ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል። 9 እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ምድር በምትገቡበትጊዜ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተሉ። 10 በመካከላችሁ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሥዋ ሟርተኛ፥ ወይም መተተኛ፥ ሞራ ገለጭ፥ ጠንቋይ፥ ወይም በድግምት የሚጠነቁል፥ 11 መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከላችሁ ከቶ አይገኝ። 12 እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ከእነዚህ አጸያፊ ልምዶች የተነሣ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚያን አሕዛብ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል። 13 በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ነውር የሌላው ይሁን። 14 ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፥ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያዳምጣሉ፤ እናንተ ግን ይህን እንድታደርጉ እግዚአብሔር አምላካችሁ አልፈቀደላችሁም። 15 እግዚአብሔር አምላካችሁ ከገዛ ወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል። እርሱን አድምጡ። 16 በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት እንዳልሞት የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ድምፅ አንስማ፤እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግመን አንይ ብላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን የጠየቃችሁት ይህ ነውና። 17 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ የተናገሩት መልካም ነው። 18 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ። ቃሌን በአፉ አደርጋለሁ፤ የማዘውንም ሁሉ ይነግራቸዋል። 19 ማንም ሰው ነቢዩ በስሜ የሚናገረውን ቃሌን ባይሰማ፤ እኔ ራሴ ተጠያቂነት አደርገዋለሁ። 20 ነገር ግን እንዲናገር እኔ ያላዘዝሁትን ቃል በድፍረት በስሜና በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ይገደል። 21 እናንተም በልባችሁ እግዚአብሔር ያልተነገረውን መልእክት እንዴት ማወቅ እንችላለን? ብትሉ፥ 22 ነቢዩም በእግዚአብሔር ስም የተናገርው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገኘ፤ መልእክቱ እግዚአብሔር የተናገርው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።
ሌዋውያን የትኛውንም መሬት ከእግዚአብሔር አለመቀበላቸው ርስት እንዳልተቀበሉ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ከሕዝቡ መሬት የትኛውንም አይወስዱም” ወይም “እስራኤላውያን ከሚወስዱት መሬት የትኛውንም አይቀበሉም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ምንም ክፍል” ወይም “ምንም ድርሻ”
“በሌሎች የእስራኤል ነገዶች መካከል” ወይም “በሌሎች እስራኤላውያን መካከል”
አሮንና የእርሱ ተወላጆች እንደ ካህናት እግዚአብሔርን በማገልገላቸው ታላቅ ክብር እንደሚኖራቸው ሙሴ ሲናገር እግዚአብሔርን እንደሚወርሱት አንዳች ነገር አድርጎ ይናገራል። ተመሳሳዩን ሐረግ በዘዳግም 10፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ከዚያ ይልቅ እግዚአብሔር ይኖራቸዋል” ወይም “ከዚያ ይልቅ፣ እግዚአብሔር እርሱን እንዲያገለግሉት ይፈቅድላቸዋል፣ በዚያም አገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን ያቀርብላቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ጨጓራና አንጀት ነው።
“ለካህኑ ትሰጠዋለህ”
እዚህ ጋ “እርሱን” ሌዋውያንን ሁሉ ይወክላል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ስም” የቆመው ለራሱ ለእግዚአብሔርና ለሥልጣኑ ነው። አ.ት፡ “የእርሱ ልዩ አገልጋዮች እንዲሆኑ” ወይም “እንደ እግዚአብሔር ተወካዮች እንዲያገለግሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እርሱን” የሚወክለው ሌዋውያንን ሁሉ ነው። አ.ት፡ “ሌዋውያንና ተወላጆቻቸው ለዘላለም” (See: Synec- doche)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በብርቱ ቢፈልግ” ወይም “በእርግጠኝነት ቢፈልግ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ስም” የሚወክለው እግዚአብሔርን እና የእርሱን ሥልጣን ነው። አ.ት፡ “ከዚያም አምላኩን እግዚአብሔርን በካህንነት ያገልግል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በእግዚአብሔር ሀልዎት ፊት በመቅደሱ የሚያገለግሉት”
ካህኑ ከአባቱ የሚወርሰው ይህ ነው
(ሂድ እና ና የሚለውን ተመልከት)
በዙሪያቸው ያሉትን ሀገራት ሰዎች ሃይማኖታዊ ተግባራት እግዚአብሔር ይጠላል። እርሱ እጅግ ክፉዎች እንደሆኑ አድርጎ ይመለክታቸዋል። እዚህ ጋ “ሀገሮች” ሰዎቹን ይወክላሉ። አ.ት፡ “የሌሎች ሀገራት ሰዎች የሚያደርጓቸውን አስከፊ ነገሮች አታድርጉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በመካከልህ ማንም አይኑር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ አስማትን የሚለማመዱ የተለዩ ሰዎች ናቸው። የትኛውንም ዓይነት አስማት እግዚአብሔር ከልክሏል። ለእንደዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች ሁሉ የሚሆን ቃል ከሌለህ በይበልጥ ጥቅል በሆነ መልኩ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወደፊት የሚሆነውን ለማወቅ በመሞከር፣ ዕጣ ለመጣል ወይም የሙታንን መናፍስት ለማነጋገር አስማት የሚጠቀም ማንም ቢሆን”
በሲኒ ውስጥ ያሉ ቅርጾችንና ስዕሎችን የሚያነብና ከሚያየው ተነሥቶ ወደፊት የሚሆኑትን ሁነቶች የሚተነብይ
እዚህ ጋ “እነርሱን” የሚያመለክተው አስቀድሞ በከነዓን የሚኖሩትን ሰዎች ነው።
እዚህ ጋ “ሕዝቦች” የሚለው ቃል የቆመው በከነዓን ለሚኖሩ የሕዝብ ወገኖች ነው። አ.ት፡ “ለእነዚህ የሕዝብ ወገኖች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“መሬታቸውን የምትወስድባቸው እነዚህ ሕዝቦች”
ነቢይ እንዲሆን እግዚአብሔር አንድን ሰው መሾሙ እግዚአብሔር ሰውየውን እንደሚያነሣው ወይም ብድግ እንደሚያደርገው ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እንዳንተው እስራኤላዊ ከሆኑት አንዱ”
እዚህ ጋ “አንተ” የሚያመለክተው ከ40 ዓመታት በፊት በኮሬብ ተራራ የነበሩትን እስራኤላውያንን ነው።
“በኮሬብ በአንድ ላይ በተሰበሰባችሁበት ቀን”
ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛ የሆነው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተደርጎ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ጉባዔ በተደረገበት ቀን እንዳትሞት ፈርተህ ስለነበር የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማትም ሆነ ከእንግዲህ የእርሱን ታላቅ እሳት ማየት እንደማትፈልግ በተናገርክ ጊዜ” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ እግዚአብሔር ለተናገረው አጽንዖት ለመስጠት የእርሱ በሆነ ”ድምፅ” ተወክሏል። አ.ት፡ “አምላካችን እግዚአብሔር እንደገና ሲናገር አንስማ” (See: Synecdoche)
እግዚአብሔር፣ አንድን ሰው ነቢይ እንዲሆን መሾሙ፣ እግዚአብሔር ሰውየውን እንደሚያነሣው ወይም ብድግ እንደሚያደርገው ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እንደ እነርሱ እስራኤላዊ ከሆኑት መካከል”
ነቢዩ ምን ማለት እንዳለበት እግዚአብሔር ለእርሱ መንገሩ እግዚአብሔር በነቢዩ አፍ ውስጥ ቃልን እንደሚጨምርበት ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ለእስራኤል ሕዝብ ይነግራቸዋል”
እዚህ ጋ “ስሜ” የሚወክለው እግዚአብሔርን እና ሥልጣኑን ነው። አ.ት፡ “መልዕክቴን በሚናገርበት ጊዜ የማይሰማው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በኃላፊነት እጠይቀዋለሁ” ወይም “እቀጣዋለሁ”። እዚህ ጋ “እርሱን” የሚያመለክተው ነቢዩን የማይሰማውን ሰው ነው።
“መልዕክት ለመናገር የሚደፍር” ወይም “በዕብሪተኝነት መልዕክት የሚናገር”
እዚህ ጋ “ስሜ” የሚያመለክተው ራሱን እግዚአብሔርንና ሥልጣኑን ነው። አ.ት፡ “ለእኔ” ወይም “በእኔ ሥልጣን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“መልዕክትን”
እዚህ ጋ “ስም” የሚወክለው አማልክቱን ራሳቸውን ወይም ሥልጣናቸውን ነው። ይህ ማለት ሐሰተኞቹ አማልክት አንድን መልዕክት እንዲናገር እንደ ነገሩት ነቢዩ ያስታውቃል ማለት ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው የሰውን አሳብ ነው። አ.ት፡ “ራስህን ትጠይቃለህ” ወይም “ለራስህ ትናገራለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ነቢዩ የሚናገረው መልዕክት ከእግዚአብሔር መሆኑን እንዴት እናውቃለን? እዚህ ጋ “እኛ” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው።
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ስም” የሚያመለክተው ራሱን እግዚአብሔርን እና ሥልጣኑን ነው። አ.ት፡ “ነቢይ እኔን ወክሎ እንደሚናገር ያስታውቃል” ወይም “ነቢይ በእኔ ሥልጣን እንደሚናገር ያስታውቃል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ነቢዩ ይህንን መልዕክት የተናገረው ያለ እኔ ሥልጣን ነው”
1 እግዚአብሔር አምላካችሁ ምድራቸውን ለእናንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ በሚደመስሳቸው ጊዜና እናንተም እነርሱን አስለቅቃችሁ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጡበት ጊዜ፥ 2 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር አማካይ ስፍራ ሦስት ከተሞችን ለራሳችሁ ምረጡ፥ 3 ሰው የገደለ ሁሉ እንዲሸሽባቸው እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር መንገዶችን ሠርታችሁ በሦስት ክፈሉአቸው። 4 በተንኮል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ገድሎ ሕይወቱን ለማትረፍ ለሚሸሽ ሰው መመሪያው የሚከተለው ነው። 5 እነሆ፥ አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ለመቁረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፥ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፥ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል። 6 አለበለዚያ በተንኮል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፥ መንገዱ ረጅም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል። ይህ ከመሆኑ በፊት ባልንጀራውን ያልጠላ ከሆነ መሞት አይገባውም። 7 ሦስት ከተሞችን ለራሳችሁ እንድትመርጡ ያዘዙአችሁ በዚሁ ምክንያት ነው። 8 ለአባቶቻችሁ በመሐላ በገባላቸው ቃል መሠረት አምላካችሁ እግዚአብሔር ወሰናችሁን ሲያሰፋውና ለእነርሱ በሰጣቸው መሠረት ምድሪቷን ሁሉ ሲሰጣችሁ፤ 9 እግዝክአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱና ምን ጊዜም በመንገዱ እንድትሄዱ ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ሕግጋት ሁሉ በጥንቃቄ የምትጠብቁ ከሆነ በእነዚህ ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራላችሁ። 10 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር የንጹሕ ሰው ደም እንዳይፈስና በሚፈሰውም ደም በደለኛ እንዳትሆኑ ይህን አድርጉ። 11 ነገር ግን አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው አድፍጦ ጥቃት ቢያደርስበት፥ ቢገድለውና ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥ 12 የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፥ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት። 13 አትራራለት፥ ነገር ግን መልካም እንዲሆንላችሁ የንጹሑን ደም በደል ከእስራኤል አስወግዱ። 14 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወርሱአት በሚሰጣችሁ ምድር ውስጥ ለእናንተ በሚተላለፍላችሁ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልጀራችሁን የድንበር ምልክት አታንሡ። 15 በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍ ሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ አንድ ምስክር አይበቃም፥ጉዳዩ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት መረጋገጥ አለበት። 16 ተንኮለኛ የሆነ ምስክር አንድን ሰው በሐሰት ለመመስከር ቢነሣ፤ 17 ክርክሩ የሚመለከታቸው ሁለቱ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ። 18 ፈፋጆችም ጉዳዩን በጥልቅ ይመርምሩት፥ 19 ያም ምስክሩ በወንድሙ ላይ በሐሰት የመሰከረ መሆኑ ከተረጋገጠ በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያሰበውን በእርሱ ላይ አድርጉበት ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ። 20 የቀሩትም ሰዎች ይህን ሰምተው ይፈራሉ፤ እንዲህ ያለው ክፉ ነገርም ለወደፊቱ በመካከላችሁ ከቶ አይደገምም። 21 ርኅራኄ አታድርጉ ሕይወት ለሕይወት፥ ዐይን ለዐይን፥ ጥርስ ለጥርስ፥ እጅ ለእጅ፥ እግር እግር ይመለስ።
እግዚአብሔር በከነዓን የሚኖሩትን ሰዎች ማጥፋቱ አንድ ሰው የጨርቅ ቁራጭ ወይም የዛፍ ቅርንጫፍ እንደሚቆርጥ እርሱም እንደሚቆርጣቸው ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በከነዓን የሚኖሩትን የሕዝብ ወገኖች ይወክላል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ይኖሩ የነበሩት እነዚያ ሕዝቦች”
“ከነዚያ ሕዝቦች ምድሪቱን ስትወስድ” ወይም “እነዚያ ሕዝቦች ከለቀቁ በኋላ ምድሪቱን የራስህ ስታደርግ”
“3 ከተሞችን ምረጥ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ሰዎች ወደ እነዚህ ከተሞች ለመጓዝ እንዲቀላቸው መንገዶችን መሥራት ይኖርባቸዋል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ከሚመርጧቸው ከተሞች አንዱ በእያንዳንዱ የምድሪቱ ክፍል ውስጥ ይሁን። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ምድሪቱን መስጠቱ ሕዝቡ ምድሪቱን እንደወረሱ ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“መመሪያዎቹ እነዚህ ናቸው” ወይም “አቅጣጫዎቹ እነዚህ ናቸው”
“ሰው” የሚለው ቃል እንዳለበት ይታወቃል። አ.ት፡ “ሌላውን ሰው የገደለ ሰው” (See: Ellipsis)
“ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ የሚያመልጥ” ወይም “ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ የሚሮጥ”
“ሕይወቱን ለማዳን”። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የሟች ቤተሰብ ተበቅለው እንዳይገድሉት” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እዚህ ጋ “ባልንጀራ” ማለት በአጠቃላይ የትኛውም ሰው ማለት ነው። አ.ት፡ “በድንገት ሌላውን ሰው የሚገድል የትኛውም ሰው”
“ነገር ግን ባልንጀራውን ከመግደሉ በፊት አልጠላው እንደሆነ”። ባልንጀራውን አስቦበት የሚገድልበት ምክንያት እንዳልነበረው ያመለክታል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ደራሲው አንድ ሰው ሌላውን በድንገት የሚገድልበትን መላ ምታዊ ሁኔታ ይሰጣል። (See: Hypothetical Situations)
የመጥረቢያው የብረት ክፍል ከእንጨቱ እጀታ ወልቆ
ይህ ማለት የመጥረቢያው ራስ ባልንጀራውን መትቶ ገድሎታል ማለት ነው።
የሟቹ ሰው ቤተሰብ ምናልባት ሊበቀሉት እንደሚሞክሩ ያመለክታል። በዚያ ያሉት ሰዎች ጥበቃ እንዲያደርጉለት እርሱን የገደለው ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ መሸሽ ይችላል (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እዚህ ጋ “ደም” የሚወክለው የተገደለውን ሰው ነው። “ደም ተበቃዩ” ሰው የሟቹ የቅርብ ዘመድ ነው። ገዳዩን ለመቅጣት ኃላፊነቱ የዚህ ዘመድ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ሌላውን ሰው የገደለ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የአንድ ሰው በጣም መቆጣት ልክ ቁጣ እንደሚግል አንዳች ነገር ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “በጣም ተቆጥቶ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
"ደም ተበቃዩ ሟችን የገደለውን ሰው ይመታና ይገድለዋል”
“ሌላውን ሰው የገደለው በድንገት ስለሆነና ጠላቱ ስላልነበረ፣ ሰውየውን ለመጉዳትም ስላላቀደ ያ ሰው መሞት የሚገባው ባይሆንም”
“የምትወርሰውን ተጨማሪ መሬት ይሰጥሃል”
“እርሱ እንደሚያደርገው ለቅድም አያቶችህ ተስፋ የሰጠውን”
“እነዚህን ትዕዛዛት በሙሉ ብትታዘዝ”
እግዚአብሔር፣ አንድ ሰው እንዲኖረውና እንዲያደርገው የሚፈልግበት አግባብ እንደ እግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና ተቆጥሮ ተነግሯል። እግዚአብሔርን የሚታዘዝ ሰው በእግዚአብሔር መንገድ ወይም ጎዳና እንደ ሄደ ተቆጥሮ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “ዘወትር እንድትታዘዘው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከዚያም አንድ ሰው በድንገት ሌላውን ሰው ከገደለ እንዲያመልጥበት ተጨማሪ ሦስት ከተሞችን ትመርጣለህ” (ቁጥሮች እና Assumed Knowl- edge and Implicit Information የሚለውን ተመልከት)
“አስቀድሞ ካዘጋጀኻቸው ከሦስቱ ከተሞች በተጨማሪ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የቤተሰቡ አባላት ንጹሕ የሆነውን ሰው እንዳይገድሉ ይህንን አድርግ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ደም” የሚወክለው የሰውን ሕይወት ነው። ደም ማፍሰስ ማለት ሰው መግደል ማለት ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማንም ንጹሕ የሆነውን ሰው አይግደል” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በምድሪቱ” ወይም “በግዛቱ”
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ የሚሰጣቸው ምድር ርስት እንደሆነ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የእስራኤል ሕዝብ “ከደም ተበቃዩ” የሚያመልጥበትን ከተማ ባለመሥራታቸው በሚሞተው ሰው ምክንያት በደለኛ መሆናቸው የሟቹ በደል በእነርሱ ላይ እንደሚሆን ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ደም” የሚወክለው ሕይወትን ሲሆን “የደም በደለኛ” የሚያመለክተው አንድ ሰው ንጹሕ የሆነን ሰው ስለ መግደሉ የሚኖርበትን በደል ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት አንድ የቤተሰብ አባል ንጽሕ የሆነን ሰው ቢገድል፣ ከዚያም ይህ እንዲሆን ዝም በማለታቸው የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ በደለኛ ይሆናሉ።
እዚህ ጋ “ባልንጀራ” ማለት በአጠቃላይ ማንኛውም ሰው ማለት ነው።
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “እርሱን ለመግደል ተደብቆ ይጠብቀዋል” ወይም “ሊገድለው ያቅዳል” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ያጠቃዋል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“እስኪሞት ድረስ ቢጎዳው” ወይም “ቢገድለው”
“እንዲያመጡት ሰው ይላኩ፣ እርሱንም ከተከለለበት ከተማ መልሰው ያምጡት”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አሳልፈው ይስጡት” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው የአንድን ሰው ሥልጣን ነው። አ.ት፡ “ኃላፊነት ላለበት ዘመዱ ሥልጣን” ወይም “ኃላፊነት ላለበት ዘመዱ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የተገደለው ሰው ዘመድ ነው። ይህ ዘመድ ገዳዩን ለመቅጣት ኃላፊ ነው።
“ገዳዩ እንዲሞት” ወይም “ኃላፊነት ያለበት ዘመድ ገዳዩን እንዲገድለው”
እዚህ ጋ “ዐይንህ” የሚወክለው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “ምሕረት አታድርግለት” ወይም “አትዘንለት” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “የደም በደል” የሚወክለው ንጹሕ የሆነውን ሰው የመግደልን በደል ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ በንጹሕ ሰው ሞት ምክንያት በደለኛ እንዳይሆን ነፍሰ ገዳዩን ግደለው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እስራኤል” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በመሬቱ ድንበር ላይ ያለውን ምልክት በማንሣት ከባልንጀራህ መሬት አትውሰድበት” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“የቀደሙት አባቶችህ ያስቀመጡትን”
ሙሴ ይህንን የሚለው ሕዝቡ ለረጅም ዓመታት በምድሪቱ በተቀመጡ ጊዜ የቀደሙት አባቶቻቸው በመጀመሪያ ምድሪቱን በወሰዱ ጊዜ ያበጁትን ድንበር እንዳያነሡ ነው።
እግዚአብሕር ለእስራኤል ሕዝብ መሬት መስጠቱ ምድሪቱን እንደወረሱ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር እንድትወርሰው በሚሰጥህ ምድር” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ አንድ ምስክር” ወይም “አንድ ምስክር ብቻ”
እዚህ ጋ “መነሣት” ማለት በፍርድ ቤት መቆምና አንድን ሰው በመቃወም ለዳኛው መናገር ማለት ነው። አ.ት፡ “አንድ ሰው ስላደረገው ክፉ ነገር ለዳኞች እንዳይናገር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
አንድ ሰው በየትኛውም ጊዜ ክፉ ነገር ሲያደርግ”
እዚህ ጋ “አፍ” የሚወክለው ምስክሮች የሚናገሩትን ነው። ቢያንስ ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች መኖር እንዳለባቸው ያመለክታል። አ.ት፡ “በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት” ወይም “ቢያንስ ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ተፈጽሟል ያሉትን መሠረት በማድረግ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Assumed Knowledge and Implicit Information የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰውየው በደለኛ መሆኑን ታረጋግጣለህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“መቼ” ወይም “ከሆነ”
“አንድን ሰው ለመጉዳት የሚሞክር ምስክር”
እዚህ ጋ “መነሣት” ማለት ፍርድ ቤት ውስጥ መቆምና አንድን ሰው በመቃወም ለዳኛው መናገር ማለት ነው። አ.ት፡ “ሰውየውን ችግር ላይ ለመጣል ኃጢአት ሠርቷል ብሎ ለዳኛው የሚናገር” ወይም “ዳኛው እንዲቀጣው አንድን ሰው ኃጢአት ሠርቷል ብሎ ለዳኛው የሚናገር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“እርስ በእርስ ያልተስማሙ”
ይህ ማለት ሁለቱ ሰዎች የእግዚአብሔር ሀልዎት ወደሚያድርበት ቅዱስ ስፍራ መሄድ አለባቸው ማለት ነው። ስለ እግዚአብሔር ሕጋዊ ውሳኔዎችን የመስጠት ሥልጣን ያላቸው ካህናትና ዳኞች በተቀደሰው ስፍራ አሉ። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ፊት ይቁሙ” የሚለው ሐረግ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህ ማለት ሥልጣን ወዳለው አካል መሄድና እርሱ ስለ ጉዳዩ ሕጋዊ ውሳኔ እንዲሰጥ ማድረግ ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ዳኞቹ የሆነውን ነገር ለማወቅ ጠንክረው መሥራት አለባቸው”
“ከዚያም ሐሰተኛውን ምስክር ሌላውን ሰው እንድትቀጣ በፈለገበት መንገድ ትቀጣዋለህ”
ስማዊ ቅጽል የሆነው “ክፉን” እንደ ቅጽል ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ክፉውን ልምምድ ከመካከልህ ታርቃለህ” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
“ሐሰተኛውን ምስክር በምትቀጣበት ጊዜ የቀረው ሕዝብ”
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ስለ ቅጣቱ ይሰሙና እነርሱም እንዳይቀጡ ይፈራሉ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ደግመው አያደርጉም”
እዚህ ጋ “ዐይኖች” የሚያመለክቱት ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “አትራራለት” ወይም “ምሕረት አታድርግለት” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ ትርጉሙ ግልጽ ስለሆነ ሐረጎቹ አጥረዋል። ይኸውም አንድ ሰው ሌላውን ሰው በጎዳበት በዚያው መልኩ ሕዝቡ ይቀጣዋል ማለት ነው። (See: Ellipsis)
1 ጠላቶቻችሁን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄዱ ሠርገሎችንና ፈረሶችን ከእናንተ የሚበልጥ ሰራዊትንም በምታዩበት ጊዜ፥ አትፍሩአቸው፥ ከግብፅ ያወጣችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንተ ጋር ነውና። 2 ወደ ውጊያው ቦታ ስትቃረቡ፥ 3 ካህኑ ወደ ፊት ወጣ ብሎ ለሠራዊቱ ይናገር፥ እንዲህም ይበል እስራኤል ሆይ ስማ በዛሬው ቀን ጠላቶቻችሁን ለመግጠም ወደ ጦርነት ልትገቡ ነው። ልባችሁ አይባባ፤ አትፍሩ፤ አትደግጡ፤ በጠላቶቻችሁ ፊት አትሸበሩ። 4 ድልን ያቀዳጃችሁ ዘንድ ስለ እናንተ ጠላቶቻችሁን ሊወጋ አብሮአችሁ የሚወጣው አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና። 5 አለቆቹም ለሠራዊት እንዲህ ይበሉ፥ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፥ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ሲሞት፥ ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል። 6 ወይን ተክሎ ገና ያልበላለት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፣ ያለበለዚያ በጦርነቱ ሲሞት፥ ሌላ ሰው ይበለዋል። 7 ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፥ ያለበለዚይ በጦርነቱ ሲሞት ሌላ ሰው ያገባታል። 8 በዚያም አለቆቹ፦ የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞችም ልብ እንዳይባባ፥ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ በማለት ጨምረው ይናገሩ። 9 አለቆቹ ለሰራዊቱ ተናግረው ሲያበቁ አዛዦችን በሰራዊቱ ላይ ይሹሙ። 10 አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምቱበት ጊዜ አስቀድማችሁ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፉ፥ 11 ከተቀበሉአችሁና ደጃቸውን ከከፊቱላችሁ በከተማዋ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ የጉልበት ሥራ ይሥሩ፥ ያገልግላችሁም። 12 ዕርቀ ሰላምን ባለመቀበል ውጊያ ከመረጡ፥ ከተማዪቱን ክበቡአት። 13 እግዚአብሔር አምላካችሁ አሳልፎ በእጃችሁ በሰጣችሁ ጊዜ በውስጧ ያሉትን ወዶች በሙሉ በሰይፍ ግደሉአቸው። 14 ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን እንስሳትንና በከተምዩቱ ውስጥ የሚገኘውን ማናቸውንም ነገር በምርኮ ለራሳችሁ አድርጉ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከጠላቶቻችሁ የሚሰጣችሁን ምርኮ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ። 15 እንግዲህ የአካባቢያችሁ አሕዛብ ከተሞች ባልሆኑትና ከእናንተ እጅግ ርቀው በሚገኙት ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርጉት ይኸው ነው። 16 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ በአሕዛብ ከተሞች ውስጥ እስትንፋስ ያለውን ነገር አታስተርፉ። 17 በዚህ ፈንታ፥ ኬጢያዊውን፥ አሞራዊውን፥ ከነዓናዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውን፥ ኢያቡሳዊውን እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መሠረት ፈጽማችሁ ደምስሱአቸው። 18 አለበለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጻያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩአችኋል፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ላይ ኃጢአት ትሠራላችሁ። 19 አንድን ከተማ ተዋገታችሁ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ በምታድርጉበት ጊዜ፥ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፋችሁ ማጥፋት የለባችሁም። የዛፎችን ፍሬ መብላት ስለምትችሉ አትቁረጡአቸው። ከባችሁ የምታጠፉአችሁ የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን? 20 የሚበላ ፍሬ እንደማያፈራ የምታውቁትን ዛፍ ግን ልትቆርጡና ጦርነት የምታካሄዱባትን ከተማ በድል እስክትቆጣጠሩአት ድረስ ለከበባው ምሽግ መሥሪያ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
“ከጠላቶችህ ጋር ለመዋጋት ወደ ጦርነት በምትወጣበት ጊዜ”
ሰዎች ብዙ ፈረሶችና ሠረገላዎች ያሉትን ሰራዊት በጣም ጠንካራ እንደሆነ ይቆጥሩ ነበር። የዚህ መግለዓ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ ወደ ከነዓን አምጥቷቸዋል። ከግብፅ ወደ ከነዓን የሚደረገውን ጉዞ ለማመልከት “ወደ ላይ” የሚለውን ቃል የተለመደ ነበር። አ.ት፡ “ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣችሁ እግዚአብሔር”
“ለእስራኤል ወታደሮች ተናገር”
እነዚህ አራቱም አገላለጾች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ እንዳይፈሩ ጠንከር ያለ አጽንዖት ይሰጣሉ። የአንተ ቋንቋ ይህንን አሳብ የሚገልጹ አራት መንገዶች ከሌሉት ከአራት በሚያንሱ ቃላት መጠቀም ትችላለህ። (See: Parallelism)
እዚህ ጋ “ልባችሁ” የሕዝቡን የሕዝቡን ድፍረት ይወክላል። የልብ መሸበር የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን “አትፍሩ” ማለት ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች ድል ማድረጉ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ሆኖ እንደሚዋጋ ጦረኛ ተደርጎ ተነግሮለታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ድል ሊሰጣችሁ”
ከአለቆቹ ሥራ አንዱ ከሰራዊቱ ማን መሰናበት እንዳለበት መወሰን ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ወታደር በዚህ ካለ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ”
አለቃው አንድን ወታደር ሊያጋጥመው የሚችለውን ሁኔታ ይዘረዝራል። አ.ት፡ “እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት በእርሱ ፈንታ ሌላ ሰው ቤቱን እንዳያስመርቅ” (See: Hypothetical Situations)
“እዚህ አዲስ ወይን ተክሎ ፍሬውን ያልሰበሰበ ወታደር ካለ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ”
አለቃው አንድን ወታደር ሊያጋጥመው የሚችለውን ሁኔታ ይዘረዝራል። አ.ት፡ “እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት በእርሱ ፈንታ ሌላ ሰው ፍሬውን እንዳይሰበስብ” (See: Hypothetical Situations)
“ሚስት ለማግባት ቃል ኪዳን ያደረገ፣ ነገር ግን ያላገባት የትኛውም ወታደር እዚህ ቢኖር ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ”
አለቃው አንድን ወታደር ሊያጋጥመው የሚችለውን ሁኔታ ይዘረዝራል። አ.ት፡ “እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት በእርሱ ፈንታ ሌላ ሰው እንዳያገባት” (See: Hypothetical Situations)
“እዚህ ያለ የትኛውም ወታደር ቢፈራና ልቡ ቢሸበር ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ”
ሁለቱም ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ነው። አ.ት፡ “በጦርነት ለመዋጋት የሚፈራ” (See: Doublet)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እርሱ እንደፈራ ሌላውም እስራኤላዊ እንዳይፈራ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ልብ” የሚወክለው የአንድን ሰው ድፍረት ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“የእስራኤልን ሕዝብ እንዲመሩ አለቆቹ አዛዦችን መሾም አለባቸው”
እዚህ ጋ “ከተማ” ሕዝቡን ይወክላል። አ.ት፡ “የአንድን ከተማ ሕዝብ ለመውጋት በምትሄድበት ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በከተማው ለሚኖሩ ሰዎች እጅ እንዲሰጡ ዕድል ስጣቸው”
እዚህ ጋ “በሮች” የሚያመለክቱት የከተማይቱን በሮች ነው። “በሮቻቸውን ከከፈቱልህ” የሚለው ሐረግ የሚወክለው የሚማረኩትንና እስራኤላውያን ወደ ከተማቸው እንዲገቡ የሚፈቅዱትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “በሰላም ወደ ከተማቸው እንድትገባ ከፈቀዱልህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እርሱ” የሚያመለክተው ሕዝቡን የሚወክለውን ከተማውን ነው። አ.ት፡ “ነገር ግን የከተማይቱ ሰዎች እጃቸውን ባይሰጡ” ወይም “ነገር ግን የከተማይቱ ሰዎች ያቀረብክላቸውን የሰላም ጥሪህን ባይቀበሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ልጆቹን”
“የሚጠቅሙትን ነገሮች በሙሉ”
እነዚህ በጦርነት ድል ያደረጉ ሰዎች ከወጓቸው ሰዎች ላይ የሚወስዷቸው ጠቃሚ ነገሮች ናቸው።
እዚህ ጋ “ከተሞች” የሚወክሉት ሕዝቡን ነው። አ.ት፡ “በከተሞች የሚኖሩት ሰዎች በሙሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ለሕዝቡ በከነዓን የሚሰጣቸው ከተሞች እነርሱ የሕዝቡ ርስት እንደሆኑ ተቆጥረው ተነግሮላቸዋል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሕይወት ያለበትን ሁሉ በሕይወት አታስቀር”። ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሕይወት ያለውን ሁሉ ግደል” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
x
“በጦርነት ተዋጋ”
“ዛፎቹን በመጥረቢያ ቁረጣቸው”
ይህ ሰዎቹ አስቀድመው የሚያውቁትን ለማስታወስ የቀረበ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የፍሬ ዛፎች ሰዎች ስላልሆኑ ጠላቶችህ አይደሉም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“የሚበላ ፍሬ የማይሰጡ ዛፎች መሆናቸውን ስታውቅ”
እነዚህ አንድን ከተማ ለመክበብ የሚያስፈልጉ መሰላሎችና ማማዎችን የመሳሰሉ መሣሪያዎችና መዋቅሮች ናቸው።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “የከተማይቱ ሰዎች በጦርነቱ እስኪሸነፉ ድረስ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እርሱ” የሚወክለው የከተማይቱን ሕዝብ የሚወክለውን ከተማ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወርሱአት በሚሰጣችሁ ምድር ላይ አንድ ሰው ተገድሎ ሜዳ ላይ ቢገኝና ገዳዩም ማን እንደ ሆነ ባይታወቁ፥ 2 ሽማግሌዎቻችሁና ዳኞቻችሁ ወጥተው የተገደለ ሰው ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት አንሥቶ በአቅራቢያው እስካሉት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ። 3 ከዚያም የተገደለ ሰው ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ በጣም ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችና ቀንበር ያልተጫነባትን ጊደር ይዘው፥ 4 ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን አንገት ይስበሩ፥ 5 እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ፥ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጉዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ። 6 ከዚያም ሬሳው በተገኘበት አቅራቢያ ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎች ሁሉ፥ በሸለቆው ውስጥ፥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤ 7 እንዲህም ብለው ይናገሩ፥ እጆቻችን ደም አላፈሰሱም፤ ድርጊቱ ሲፈጸምም ዐይኖቻችን አላዩም። 8 እግዚአብሔር ሆይ፥ ስለ ተቤዥኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፥ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ። ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል። 9 በዚህም መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ቀና የሆነውን ስታደርጉ የንጹሑን ደም የማፍሰስ በደልን ከመካከላችሁ ታስወግዳላችሁ። 10 ከጠላቶቻችሁ ጋር ጦርነት ልትገጥሙ ወጥታችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር እነርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአችሁ በማረካችሁ ጊዜ፥ 11 ከምርኮኞቹ መካከል ቆንጆ ሴት አይታችሁ ብትማርኩ፥ ሚስታችሁ ልታደርጉአት ትችላላችሁ፤ 12 ወደ ቤታችሁ ውሰዱአት፥ ጠጉሯን ትላጭ፥ ጥፍሯንም ትቁረጥ። 13 ስትማርኩአት የለበሰችውንም ልብስ ታውልቅ፥ እቤታችሁ ተቀምጣ ለአባትና ለናቷ ወር ሙሉ ካለቀሰችላቸው በኋላ፥ ከእርሷ ጋር ለመተኛና ባል ልትሆለት፥ እርሷም ሚስት ልትሆናችሁ ትችላለች። 14 ነገር ግን በእርሷ ደስተኛ ባትሆን፥ ወደምትፈልገው እንድትሄድ ነጻነት ስጡአት፥ ውርደት ላይ ስለ ጠላችኋት በገንዘብ ልትሸጡአት ወይም እንደ ባሪያ ልትቆጥሩአት አይገባችሁም። 15 አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት አንደኛዋን የሚወዳት፥ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፥ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት፥ በኩር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥ 16 ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፥ የብኩርናን መብት ከማይወዳት ሚስቱ ከወለደው በኩር ልጅ ገፎ ከሚወዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤ 17 በዚህ ፈንታ፥ ከተጠላችው ሚስቱ ለተወለደው ልጅ ካለው ሁብት ሁሉ ሁለት እጥፍ ድርሻውን በመስጠት ብኩርናውን ያስታውቅ ያ ልጅ የአባቱ ኃይል መጀመሪያ ነውና የብኩርና መብት የራሱ ነው። 18 አንድ ሰው የአባቱን ወይም የእናቱን ትእዛዝ የማይሰማ፥ ቢቀጡትም የማይታረም እልከኛና ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥ 19 አባትና እናቱ ይዘው በሚኖሩበት ከተማ በር ወዳሉት አለቆች ያምጡት፥ 20 ይህ ልጃችን እልከኛና ዐመፀኛ ነው፥ አይታዘዘንም አባካኝና ሰካራም ነው ብለው ለአለቆች ይንገሯቸው። 21 ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይወገሩት፥ ክፉውንም ከመካከላችሁ ታስወግዳላችሁ፥ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል። 22 አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ፈጽሞ ቢገደልና ሬሳው በእንጨት ላይ ቢሰቀል፥ 23 ሬሳውን በእንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድሩት ምክንያቱም በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሚሰጣችሁን ምድር እንዳታረክሱ በዚያኑ ዕለት ቅበሩት።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ማንነቱ ባልታወቀ ሰው የተገደለን ሰው ቢያገኝ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የሞተው ሰው ሜዳ ላይ ወድቋል።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማን እንደ ገደለው ማንም አያውቅም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ለከተሞቹ ያለውን ርቅት ይለኩ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማንነቱ ያልታወቀ ሰው የገደለውን እርሱን” ወይም “ሬሳውን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
x
“ወደ ሸለቆው ይምጡ”
“ካህናቱ እርሱን እንዲያገለግሉት አምላክህ እግዚአብሔር ስለመረጣቸው”
ሙሴ ለአንድ ሰው እንደሚናገር አድርጎ ለእስራኤል ሕዝብ ስለሚናገር “የአንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“የእስራኤልን ሕዝብ እንዲባርኩ”
እዚህ ጋ “በ -- ስም” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ራሱንና የእርሱን ሥልጣን ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ራሱ የሚለውንና የሚያደርገውን የሚልና የሚያደርግ እርሱ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አለመግባባቶችንና የጸብ ምክንያቶችን ሁሉ የሚፈቱት እግዚአብሔር እና እነርሱ ይሆናሉ”
x
እግዚአብሔር በግብፅ ባሪያ የነበረውን የእስራኤልን ሕዝብ ማዳኑ ሕዝቡን ከባርነት ለመቤዠት ገንዘብ እንደከፈለላቸው በሚመስል መልኩ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ንጹሕን ሰው እንደ ገደሉ በደለኞች አድርገህ አትቁጠራቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከዚያም ስለ ንጹሑ ሰው ሞት እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ይቅር ይላቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ንጹሕን ሰው ስለ መግደልህ ከእንግዲህ በደለኛ አትሆንም”
x
“እናንተ ወታደሮች የሆንችሁ ውጡ”
“ከእርሷ ጋር ለመተኛት ብትፈልግ” ለሚለው የትህትናን ሐረግ ተጠቀም።
“ለታገባት ብትፈልግ”
“ጸጉሯን ከራሷ ላይ ትመለጠው”
“የጣቶቿን ጥፍር ትቁረጥ”
ይህንን የምታደርገው በዘዳግም 21፡12 እንደተጠቀሰው ሰውየው ወደ ቤቱ ካመጣትና ጸጉሯን ተቆርጣ፣ የእጅና የእግር ጣት ጥፍሮቿን ከተቆረጠች በኋላ ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የሕዝቧን ልብስ ታወልቅና የእስራኤላውያንን ልብስ ትለብሳለች” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እርሷን በማረክህ ጊዜ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ወሩን በሙሉ” ወይም “አንድ ወር ሙሉ”
ሰውየው ከሴቲቱ ጋር ስለ መተኛቱ ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል። አአ.ት፡ “ነገር ግን አብረሃት ከተኛህ በኋላ ሚስትህ እንዳትሆን ከወሰንክ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“መሄድ ወደምትፈልግበት ትሂድ”
“ከእርሷ ጋር ከተኛህ በኋላ ስለ ሰደድካት አሳፍረሃታልና”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፣ 1) “ሰውየው ከሚስቶቹ አንደኛዋን ይወዳል፣ ሌላይቱን ሚስቱን ይተላታል” ወይም 2) “ሰውየው ሌላይቱን ሚስቱን ከሚወድበት በበለጠ አንደኛውን ሚስቱን ይወዳታል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ሁለቱም ሚስቶቹ ልጆችን ወልደውለታል”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በኩሩ ሰውየው ከሚጠላት ሚስቱ የተወለደ ከሆነ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ሰውየው በ-- ጊዜ”
“ሰውየው ንብረቱን ለልጆቹ ርስት አድርጎ ይሰጣቸዋል”
“ከተጠላችው ሚስቱ በተወለደው ልጅ ምትክ ከተወዳጅ ሚስቱ የተወለደውን ልጅ በኩር አያድርገው”
“ሁለት ዕጥፍ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ያ ልጅ ሰውየው የወንዶች ልጆች አባት መሆኑን የሚያሳይ ነው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ድምፅ” አንድ ሰው የሚናገረውን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አባቱ ወይም እናቱ የሚሉትን የማይታዘዝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ስለ መጥፎ ተግባሩ ይቅጡት” ወይም “ያሰልጥኑትና ያስተምሩት”
“እንዲመጣ ያስገድዱት”
“ልጃችን”
እዚህ ጋ “ድምፅ” አንድ ሰው የሚናገረውን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ወይም የሙሉው ሰው ተምሳሌት ነው። አ.ት፡ “እንዲያደርግ የምንነግረውን አያደርግም” ወይም “አይታዘዘንም” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Synecdoche የሚለውን ተመልከት)
ብዙ የሚበላና የሚጠጣ ሰው
አስካሪ መጠጥ አብዝቶ የሚጠጣና ብዙ ጊዜ የሚሰክር ሰው
“እስኪሞት ድረስ ድንጋይ ወርውሩበት”
ቅጽሉ “ክፉ” ስማዊ ሐረግ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይህንን ክፉ ነገር የሚያደርገውን ሰው ከእስራኤላውያን መካከል ታርቃለህ” ወይም “ይህንን ክፉ ሰው ግደለው” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
“እስራኤል” የሚለው ቃል የእስራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በልጁ ላይ ስለሆነው ነገር ይሰማሉ፣ እነርሱንም ሕዝቡ እንዳይቀጣቸው ይፈራሉ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“አንድ ሰው በሞት ልትቀጣው እስከሚያስፈልግህ ድረስ እጅግ የከፋ ነገር ካደረገ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አስወግደው” ወይም “ግደለው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) “ከሞተ በኋላ ዛፍ ላይ ስቀለው” ወይም 2) “ግደለውና በቋሚ እንጨት ላይ ስቀለው”
“በምታስወግደው ጊዜ በዚያው ቀን ቅበረው”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) “ሰዎች የሚሰቅሉትን ሁሉ እግዚአብሔር ይረግማቸዋል” እና 2) “ሰዎች እግዚአብሔር የረገማቸውን በዛፍ ላይ ይስቀሏቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር የረገመውን በዛፍ ላይ ሰቅለህ በመተው
1 የእስራኤላዊ ወንድማችሁ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታዩ ወደ እርሱ መልሳችሁ አምጡለት እንጂ ዝም ብላችሁ አትለፉት፥ 2 ወንድማችሁ በአቅራቢያ ባይኖር፥ ወይም የማን መሆኑን የማታውቁ ከሆነ ባለቤቱ ፈልጎ እስኪ መጣ ድረስ ወደ ቤታችሁና ወስዳችሁ ከእናንተ ዘንድ አቆዩት፤ ከዚያም መልሳችሁ ስጡት። 3 የእስራኤላዊ ወንድማችሁን አህያ ወይም ልብስ ወይም የጠፋበትን ማናቸውንም ነገር ስታገኙ እንደዚህ አድርጉ፥ በቸልታ አትለፉት። 4 የወንድማሁ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታዩት በእግሩ እንዲቆም ርዳው እንጂ አልፋችሁ አትሂዱ። 5 ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ እንዲህ የሚያደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ይጸየፈዋልና። 6 በመንገድ ስታልፉ አንዲት ወፍ ጫጩቶቿን ወይም ዕንቁላሎቿን የታቀፈችበትን ጎጆ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ብታገኙም እናቲቱን ከነጫጩቶቿ አትውሰፉ፤ 7 ጫጩቶቿን መውሰድ ትችላላችሁ እናቲቱን ግን መልካም እንዲህንላችሁና ዕድሜአችሁም እንዲርዝም ልቀቁት፤ 8 አዲስ ቤት በምትሠሩበት ጊዜ፥ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ ቤታችሁ ላይ የደም በደል እንዳታመጡ፥ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጁለት። 9 በወይን ተክል ቦታችሁ ውስጥ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝሩ ይህን ካደረጋችሁም የዘራችሁት ሰብል ብቻ ሳይሆን የወይን ፍሬአችሁ ይጠፋል። 10 በሬና አህያ በአንድ ላይ ጠምዳችሁ አትረሱ። 11 ሱፍና ሐር አንድ ላይ ተፈትሎ የተሠራ ልብስ አትልበሱ። 12 በምትለብሱት ልብስ ላይ በአራቱ ማእዘኖች ዘርፍ አድርጉ። 13 አንድ ወንድ ሚስት አግብቶ አብሮአት ከተኛ በኋላ ቢጠላት፥ 14 ስሟንም በማጥፋት፥ ይህችን ሴት አገባኋት፥ዳሩ ግን በደረስሁባት ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁም ቢል፥ 15 የልጂቱ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዪቱ በር ወዳሉት አለቆች ይምጡ። 16 የልጂቱም አባት ለአለቆቹ እንዲህ ይበል፥ ልጄን ለዚህ ሰው ዳርሁለት፥ እርሱ ግን ጠላት፤ 17 ስሟንም በማጥፋት ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም ብሎኛል፤ ነገር ግን የልጄ ድንግልና ማረጋገጫ ይኸውላችሁ። ከዚያም ወላጆቿ የደሙን ሸማ በከተማዪቱ አለቆች ፊት ይዘርጉት። 18 ከዚያም በኋላ አለቆቹ ሰውየውን ይዘው ይቅጡት፥ 19 ይህ ሰው የአንዲት እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቶአልና አንድ መቶ ሰቅል ብር ያስከፍሉት፥ ገንዘቡንም ለልጂቱ አባት ይስጡት፥ ሴቲቱም ሚስቱ ሆና ትኖራለች፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም። 20 ሆኖም ክሱ እውነት ሆኖ ሴቲቱ ድንግል ለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ ማቅረብ ካልተቻለ፥ 21 በአባቷ ቤት ሳለች በማመንዘር በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪ ተግባር ፈጽማለችና ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያምጣት፥ እዚያም የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት። 22 አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አብሮአት የተኛው ሰውና ሴቲቱ ሁለቱም ይገደሉ። ክፉውን ከእስራኤል ማስወገድ አለባችሁ። 23 አንድ ሰው የታጨች ድንግል በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርሷ ጋር ቢተኛ፥ ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፥ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስግድዶ ስለ ደፈረ፥ 24 ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከላችሁ ማስወገድ አለባችሁ። 25 ነገር ግን አንድ ሰው የታጨችውን ልጃገረድ ከከተማ ውጭ አግኝቶ በማስገደድ ቢደፍራት፥ ይህን ድርጊት የፈጸመው ሰው ብቻ ይገደል። 26 በልጃገረዲቱ ላይ ግን ምንም አታድርጉባት፥ ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ምንም አልሠራችም፥ ይህ ዓይነቱ ጉዳይ አደጋ ጥሎ ባልንጀራውን ከሚገድል ሰው አድራጎት ጋር የሚመሳሰል ነው። 27 ምክንያቱም ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ከተማ ውጭ ስላገኛትና ብትጮኽም እንኳ ለርዳታ የደረሰላት ምንም ሰው ስላልነበር ነው። 28 አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድ አግኝቶ በማስገደድ ቢደርስባትና ቢጋለጡ 29 ሰውየው ለልጅቷ አባት አምሳ ስቅል ብር ይክፈል፥ ልጃገረዲቱን አስገድዶ ደፍሮአታልና እርሷን ማግባት አለበት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም። 30 አንድ ሰው አባቱን ሚስት ማግባት የለበትም፥ የአባቱንም መኝታ አያርክስ።
“ከባለቤቱ ርቆ ሲሄድ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንዳላየኻቸው አትሁን” ወይም “ምንም ነገር ሳታደርግ አትሂድ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“እስራኤላዊ ወንድምህ ከአንተ ርቆ የሚኖር ከሆነ”
“ወይም የእንስሳው ባለቤት ማን እንደሆነ ካላወቅህ”
“ባለቤቱ ፈልጎት እስኪመጣ ድረስ እንስሳው በአንተ ዘንድ ይቆይ”
“አህያውንም በተመሳሳይ መንገድ መልስለት”
“በተመሳሳይ መንገድ ልብሱን መልስለት”
“የወንድ ልብስ”
ወፎች ከጭራሮ፣ ሣር፣ እጽዋትና ጭቃ ለራሳቸው የሚሠሩት ቤት
“ከትናንሽ ወፎች ወይም በጎጆው ውስጥ ካሉ ዕንቁላሎች ጋር”
“እናቲቱ ወፍ በጫጩት ወፎች ላይ ተቀምጣለት”
ረጅም ቀናት የረጅም ዕድሜ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ረጅም ዓመት መኖር እንድትችል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ቅዱስ ስፍራ” የሚለው ቃል በተቀደው ስፍራ የሚሠሩትን ካህናት የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ቅዱስ ስፍራ ያሉ ካህናት ምርቱን ሁሉ እንዳይወስዱት” ወይም “ምርቱን ሁሉ እንዳታረክሰውና ካህናቱ ከመጠቀም እንዳይከለክሉህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በወይን ተክል ቦታ የሚበቅለውን ፍሬ”
በበጎች ላይ የሚበቅል ለስላሳና የሚጠቀለል ጸጉር
ከቃጫ ተክል የሚሠራ ክር (የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
በአንድ ላይ ታስረው በእያንዳንዱ የካባው ማዕዘን ላይ የሚንጠለጠሉ ክሮች
አንድ ሰው በሌሎች ልብሶቹ ላይ ደርቦ የሚለብሰው ረዘም ያለ ልብስ
“ከዚያም ከጋብቻዋ በፊት ከሌላ ሰው ጋር ስለመተኛቷ ቢከሳት”
የነገር ስም የሆነው “ምስክርነት” እንደ ግሥ ሐረግ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች መጥፎ ሰው እንደሆነች እንዲያስቡ ያደርጋል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆኑት “ማረጋገጥ” እና “ድንግልና” እንደ ግሣዊ ሐረጎች ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “ቀደም ሲል የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንዳልነበራት የሚያረጋግጥ አንዳች ነገር ውሰድ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ሳያገባት በፊት ከሌላ ሰው ጋር ስለመተኛቷ ከሷታል” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
የነገር ስም የሆኑት “ማረጋገጥ” እና “ድንግልና” እንደ ግሣዊ ሐረጎች ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “ልጅህ ቀደም ሲል የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላለመፈጸሟ ማረጋገጫ ማቅረብ አልቻለችም” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆኑት “ማረጋገጥ” እና “ድንግልና” እንደ ግሣዊ ሐረጎች ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “ይሁን እንጂ ልጄ ቀደም ሲል የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንዳልፈጸመች ይህ ያረጋግጣል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከዚያም ድንግል እንደነበረች ማስረጃ እንዲሆን እናትና አባቷ በደም የተነከረውን ጨርቅ ለሽማግሌዎቹ ያሳያሉ።(See: Assumed Knowledge and Implicit Information
“ቅጣት እንዲከፍል ያድርጉት”
“100 ሰቅል” (ገንዘብ በመጽሐፍ ቅዱስ እና ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ገንዘቡን ለልጅቱ አባት ስጡት”
የነገር ስም የሆነው “ምስክርነት” እንደ ግሣዊ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች የእስራኤልን ድንግል መጥፎ ሰው አድርገው እንዲያስቧት አድርጓል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
“እንዲፈታት በፍጹም አትፍቀድለት”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ሕይወቱን ሙሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ሆኖም እውነት ቢሆን” ወይም “ሆኖም ሰውየው የተናገረው እውነት ቢሆን”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰውየው ልጅቱ ድንግል ስለመሆኗ ማረጋገጫ አላገኘም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆኑት “ማረጋገጫ” እና “ድንግልና” እንደ ግሣዊ ሐረጎች ሊተረጎሙ ይችላሉ። አ.ት፡ “ልጅቱ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጽማ እንደማታውቅ የሚያስረዳ አንዳች ነገር” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
“ከዚያም ሽማግሌዎቹ ልጅቱን ያውጧት”
“እስክትሞት ድረስ ድንጋይ ወርውሩባት”
“በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪ ነገር አድርጋለችና”
“በአባቷ ቤት ውስጥ እየኖረች እንደ ሴተኛ አዳሪ ማድረግ”
ቅጽል የሆነው “ክፉ” እንደ ስማዊ ሐረግ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይህንን ክፉ ነገር ያደረገውን ከእስራኤላውያን መካከል አስወግድ” ወይም “ይህንን ክፉ ሰው አስወግደው” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ሌላውን ሰው ቢያገኝ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በዚህ መንገድ ታስወግዳለህ”
“አንድን ሰው እንድታገባ ቃል የተገባላት”
እነዚህ ትዕዛዛት ለእስራኤል እንደ ቡድን የተነገሩ ናቸው፣ በመሆኑም ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“ከዚያም ልጅቱንና ከእርሷ ጋር የተኛውን ሰው አምጧቸው”
“ምክንያቱም ለእርዳታ አልተጣራችም”
በዚያን ዘመን እስራኤላውያን ለጋብቻ የተጫጩ ወንድና ሴትን እንደ ባልና ሚስት ይቆጥሯቸው ነበር። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ምክንያቱም የእስራኤላዊ ወንድሙ ከምትሆን ልጅ ጋር ተኝቷል” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ቅጽሉ “ክፉ” እንደ ስማዊ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይህንን ክፉ ነገር ያደረገውን ሰው ከእስራኤላውያን መካከል አስወግደው” ወይም “ይህንን ክፉ ሰው አስወግደው” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ወላጆቿ አንድን ሰው እንድታገባ የተስማሙባት፣ ሆኖም ገና ያላገባችው ልጅ ማለት ነው።
“ከዚያም ከእርሷ ጋር የተኛውን ሰው ብቻ ግደሉ”
“ስላደረገችው ነገር በሞት አትቅጧት”
“ምክንያቱም ይህ ሁኔታ አንድ ሰው ሌላውን ሰው አጥቅቶ ከሚገድልበት ሁኔታ ጋር ስለሚመሳሰል ነው”
“ምክንያቱም ሰውየው ልጅቱን ከሰፈር ውጪ ሥራ ላይ ሆና አግቷታል”
“ሆኖም ወላጆቿ ለሚያገባት ሰው እንደሚድሩለት ቃል ያልገቡለት”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ስለሆነው ነገር ቢያውቅ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
አንድ ሰቅል አሥራ አንድ ግራም ይመዝናል። አ.ት፡ “አምሳ የጥሬ ብር ዝርዝር” ወይም “550 ግራም ጥሬ ብር” (See: Biblical Money and Numbers)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ዕድሜውን ሙሉ አይፍታት” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ምንም እንኳን እናቱ ባትሆንም የቀድሞ የአባቱን ሚስት ማግባት የለበትም” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
1 ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቆረጠ ማናቸውም ሰው ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። 2 ዲቃላም ይሁን፥ የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። 3 አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ አሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። 4 ምክንያቱም ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህልና ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም። በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም እናንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት። 5 ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ በብዓምን አልሰማውም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለሚወዳችሁ ርግማኑን ወደ በረከት አደረገላችሁ። 6 በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ሰላምን ለእነርሱ አትመኙ። 7 ወንድማችሁ ስለ ሆነ ኤዶማዊውን አትጸየፈው፤ መጻተኛ ሆናችሁ በአገሩ ኖራችኋልና ግብፃዊውን አትጥሉት። 8 ለእነርሱ የተወለዳቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ መግባት ይችላሉ። 9 ጠላታችሁን ለመውጋት ወጥታችሁ በሰፈራችሁ ጊዜ ከማናቸውም ርኩሰት ራሳችሁን ጠብቁ። 10 ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከስሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቆይ። 11 እየመሸ ሲመጣ ግን ገላውን ይታጠብ ፀሐይ ስትጠልቅም ወደ ሰፈሩ ይመለስ። 12 ለመጸዳጃ የሚሆንህን ቦታ ከሰፈር ውጭ አዘጋጅ። ከትጥቅህም ጋር መቆፍሪያ ያዝ፥ 13 በምትጸዳዳበት ጊዜ አፈር ቆፍረህ በዐይነ ምድርህ ላይ መልስበት። 14 እግዚአብሔር አምላክህ ሊጠብቅህ ጠላቶህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈር ውስጥ ስለሚዘዋወር በመካከልህ አንዳች ነውር አይቶ ከአንተ እንዳይመለስ፥ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን። 15 አንድ ባሪያ ከአሳዳሪው ኮብልሎ ወደ እናንተ ቢመጣ፥ 16 ለአሳዳሪው አሳልፋችሁ አትስጡት፥ ደስ በሚያሰኘው ቦታን ራሱ በመረጠው ከተማ በመካከላችሁ ይኑር፤ እናንተም አታስጨንቁት። 17 ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይኑራችሁ። 18 ለዝሙት አዳሪ ሴት ወይም ለወንድ ዝሙተኛ የተከፈለውን ዋጋ ለማናቸውም ስእለት አድርጋችሁ ለመስጠት ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካችሁ ቤት አታምጡ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና። 19 የገንዘብ፥ የእህል ወይም የማንኛውንም ነገር ወለድ ለማግኘት ለወንድማችሁ በወለድ አታበድሩ። ባዕድ ለሆነ ሰው በወለድ ማበደር ትችላላችሁ። 20 ነገር ግን ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር እጃችሁ በሚነካው በማናቸውም ነገር እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲባርካችሁ ለእስራኤልዊ ወንድማችሁ በወለድ አታበድሩት። 21 ለእግዚአብሔር ለአምልካችሁ ስእለት ከተሳላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ አጥብቆ ከእናንተ ይሻዋልና፤ ኃጢአት እንዳይሆንባችሁ ለመክፈል አትዘግዩ። 22 ሳትሳሉ ብትቀሩ ግን በደለኛ አትሆኑም። በአንደበታችሁ የተናገራችሁትን ሁሉ ለመፈጸም ጠንቃቃ ሁኑ፥ 23 ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር በገዛ አንደበታችሁ ፈቅዳችሁ ስእለት ተስላችኋልና። 24 ወደ ባልንጀራችሁ የወይን ተክል ቦታ በምትገቡበት ጊዜ ያሰኛችሁን ያህል መብላት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን አንዳችም በዕቃችሁ አትያዙ። 25 ወደ ባልንጀራችሁ እርሻ በምትገቡበት ጊዜ እሸት መቅጠፍ ትችላላችሁ፤ በሰብሉ ላይ ግን ማጭድ አታሳርፉበት።
“የወንድ አካሉ የተቀጠቀጠ ወይም የተቆረጠበት ሰው”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ማኅበረሰብ ሙሉ አባል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ወላጆቹ ዘመዳሞች ሆነው ወይም በዝሙት የወለዱት ልጅ ወይም 2) ከሴተኛ አዳሪ የተወለደ ልጅ።
ይህ “አሥረኛ” የአሥር ደረጃን አመልካች ቁጥር ነው። አ.ት፡ “ከዲቃላው ልጅ ተወላጆች አሥረኛ ትውልድ በኋላ እንኳን” (ደረጃን አመልካች ቁጥር የሚለውን ተመልከት)
“ከእነዚህ ተወላጆች ማናቸውም”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ማኅበረሰብ ሙሉ አባል አይሁኑ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ “አሥረኛ” የአሥር ደረጃን አመልካች ቁጥር ነው። አ.ት፡ “ከተወላጆቹ ከአሥር ትውልድ በኋላ እንኳን” (ደረጃን አመልካች ቁጥር የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ምግብና መጠጥ በማቅረብ አልተቀበሏችሁም” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” የሚለው ቃል እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ትኩረት አልሰጠውም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“እንዲረግምህ ሳይሆን እንዲባርክህ አደረገው”
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “ከአሞናውያንና ከሞዓባውያን ጋር የሰላም ስምምነት ከቶ ማድረግ የለብህም” ወይም 2) “ለእነዚያ 2 የሕዝብ ወገኖች መልካም እንዲሆንላቸውና ለመበልጸግ የሚያስችላቸውን ምንም ነገር አታድርግ”
x
“ኤዶማዊውን አትጥላው”
“ዘመድህ ነውና”
“ግብፃዊውን አትጥላው”
ይህ “ሦስተኛ” የሦስት ደረጃን አመልካች ቁጥር ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ኤዶማዊ ወይም ግብፃዊ በእስራኤላውያን ማኅበረሰብ ውስጥ ለመኖር ቢመጣ፣ የልጅ ልጆቹ የዚያ ማኅበረሰብ ሙሉ አባል ሊሆኑ ይችላሉ” (See: (ደረጃን አመልካች ቁጥር እና Assumed Knowledge and Implicit Information የሚለውን ተመልከት))
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
“ጠላቶችህን ለመውጋት”
“መጥፎ ከሆኑ ነገሮች ሁሉ ራስህን አርቅ”
ይህ ዘር ማፍሰሱ የተነገረበት የትህትና አባባል ነው። አ.ት፡ “በእንቅልፍ ላይ እያለ ዘር ስለፈሰሰው ንጹሕ ያልሆነ ማንኛውም ሰው” (See: Euphemism)
“ለመቆፈር የምትጠቀምበት መሣሪያ ይኑርህ”
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከሌላ ሀገር ከጌታው አምልጦ ወደ እስራኤል የመጣ ባሪያ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ባሪያው በሕዝብህ መካከል ይኑር”
እግዚአብሔር በማንኛውም ሰው በየትኛውም ምክንያት በወንድና በሴት የሚደረጉ የአመንዝራነት ዓይነቶችን የሚከለክል ዝርዝር ይሰጣቸዋል። (See: Merism)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፤ ሙሴ፣ 1) ሴቶችና ወንዶች ወሲባዊ ተግባርን የመቅደስ አገልግሎት አካል እንዳያደርጉ ይከለክላቸዋል ወይም 2) ሴቶችና ወንዶች ገንዘብ ለማግኘት ወሲባዊ ተግባር እንዳይፈጽሙ ለመከልከል ሻል ባለ ቃል ይጠቀማል። (See: Euphemism)
“በዝሙት ሥራ ገንዘብ የምታገኝ ሴት ያንን ገንዘብ ወደ -- ቤት አታምጣ”
ገንዘብ ለማግኘት ከእርሱ ጋር ወንዶች ወሲብ እንዲፈጽሙ የሚፈቅድ ወንድ
“ወደ መቅደስ”
“ስእለት ለመፈጸም”
የሴትና የወንድ ዝሙት አዳሪዎችን ዋጋ
“ለእስራኤላዊ ወንድምህ አንዳች ነገር ብታበድረው ካበደርከው በላይ እንዲመልስልህ አታድርገው”
ለአንድ ሰው ማበደርና ያ ሰው ከተበደረው በላይ እንዲመልስ ማስገደድ
“ለአንድ ሰው ገንዘብ፣ ምግብ ወይም የትኛውንም ነገር በምታበድርበት ጊዜ ወለድ አታስከፍለው”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በምትሠራሁ ሁሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ስእለትህን ለመፈጸም ረጅም ጊዜ አትውሰድ”
“ምክንያቱም ስእለትህን ካልፈጸምክ አምላክህ እግዚአብሔር ይነቅፍሃል፣ ይቀጣሃልም”
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ካልተሳልክ ግን የምትፈጽመው ስእለት የለህምና ኃጢአት አትሠራም” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “የተናገርከው ቃል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ታደርገው ዘንድ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተሳልከውን ማንኛውንም ነገር”
“ልታደርገው ስለፈለግህ ቃል ስትገባ ሰዎችህ የሰሙህን ነገር ሁሉ”
“ስትናገር ሰዎች የሰሙህን”
“ከዚያም እስክትጠግብ ድረስ ወይን በመብላት መደሰት ትችላለህ”
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ሆኖም ይዘህ ለመሄድ በከረጢትህ ውስጥ ምንም ወይን አትጨምር” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ሰብሉ ባፈራበት የባልንጀራህ እርሻ መካከል በምታልፍበት ጊዜ”
“ከዚያም ከሰብሉ ፍሬ በእጅህ ወስደህ መብላት ትችላለህ”
“ነገር ግን የባልንጀራህን የደረሰ ሰብል አጭደህ አትውሰድ”
ገበሬዎች ስንዴ ለመሰብሰብ የሚጠቀሙበት ስለታም መሣሪያ
1 አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት የፍቺ ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት። 2 ከቤቱ ከወጣች በኋላ ሌላ ባል ሊታገባ ትችላለች። 3 ሁለተኛ ባሏም እንደዚሁ ጠልቷት የፍቺ ወረቀት በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ቢሰዳት፥ ወይም ቢሞት፥ 4 ከዚያ በኋላ ፈቶአት የነበረው የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደ ገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጡ። 5 አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፥ ለጦርነት አይሂድ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሥራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ እቤቱ ይቆይ፥ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት። 6 ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም እንኳ ቢሆን፥ የብድር መያዣ አድርጋችሁ አትውሰዱ፤ የሰውን ነፍስ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆናልና። 7 አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባሪያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግድ። 8 የለምጽ ደዌን በተመለከተ ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡአችሁን መመሪያ በትክክል ለመፈጸም ጥንቃቄ አድርጉ። እኔ ለእነርሱ የሰጠሁትን ትእዛዝ በጥንቃቄ ተከተሉ። 9 ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በመንገድ ላይ ሳላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሙሴ እህት በምርያም ላይ ያደረገባትን አስታውሱ። 10 ማናቸውንም ነገር ለባልንጀራችሁ ስታበድሩ መያዣ አድርጎ የሚሰጣችሁን ለመቀበል ወደ ቤቱ አትግቡ። 11 እንንተ ከውጭ ሆናችሁ ጠብቅ፥ ያበደራችሁም ሰው መያዣውን ከቤት ያምጣላችሁ። 12 ሰውየው ድኻ ከሆነ መያዣውን ከእናንተ ዘንድ አታሳድሩበት። 13 መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሐይ ሳትጠልቅ መልሱለት። ከዚያም ያመሰግናችኋል፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቆጠርላችኋል። 14 ድኻና ችግረኛ የሆነውን የምንዳ ሠራተኛ እስራኤላዊ ወንድማችሁም ሆነ፥ከከተሞቻችሁ ባንዲቱ የሚኖረውን መጻተኛ አትበዝብዙት፤ 15 የሠራበትን ሒሳብ በዕለቱ ፀሐይ ሳትጠልቅ ክፈሉት፤ ድኻ በመሆኑ በጉጉት ይጠባበቀዋልና። ያለበለዚያ ወደ እግዚአብሔር ይጮኸና ኃጢአት ይሆንባችኋል። 16 አባቶች ስለ ልጆቻቸው፥ ልጆችም ስለ አባቶቻቸው አይገደሉ፤ እያንዳንዱ በራሱ ኃጢአት ይገደል። 17 መጻተኛው ወይም አባት ለሌለው ልጅ ፍትሕ አትንፈጉት፤ ባል የሞትባትንም መደረቢያ መያዣ አታድርጉ። 18 እናንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበራችሁና እግዚአብሔር አምላካችሁ ከዚያ እንደ ተቤዣችሁ አስታውሱ፤ ይህን እንድታደርጉ ያዘዙአችሁ ለዚህ ነው። 19 የእርሻችሁን ሰብል በምታጭዱበት ጊዜ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሳችሁ አትሂዱ፤እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ ሥራ ሁሉ እንዲባርካችሁ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ። 20 የወይራ ዛፋችሁን ፍሬ በምታራግፉበት ጊዜ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሳችሁ አትሂዱ ለመጻተኛ፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ። 21 የወይን ተክላችሁን ፍሬ ስትሰበስቡ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለሱበት የቀረውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ። 22 በግብፅ ባሮች እንደነበራችሁ አስታውሱ፤ ይህን እንድታደርጉ ያዘዙአሁን ለዚህ ነው።
“ሚስት ወስዶ” እና “በሚያገባት” የሚሉት ሐረጎች ትርጉማቸው አንድ ነው። አ.ት፡ “አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በሚያገባበት ጊዜ” (See: Doublet)
እዚህ ጋ “ዐይኖች” የሚወክሉት ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “እንደማይወዳት ከወሰነ” (See: Synecdoche)
“በሆነ ምክንያት ከእርሱ ጋር ሊያቆያት ያለመፈለግ ውሳኔ አድርጓል”
“ከዚህ በኋላ በጋብቻ ውስጥ እንደሌሉ የሚገልጽ ሕጋዊ ወረቀት ለሚስቱ ይስጣት”
“ሄዳ ሌላ ሰው እንድታገባ”
“ሁለተኛው ባሏ እንደሚጠላት ቢወስን”
ይህ ሰውየውና ሴቲቱ ከእንግዲህ በጋብቻ ውስጥ እንዳልሆኑ የሚናገር ሕጋዊ ወረቀት ነው። ይህንን በዘዳግም 24፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ለሴቲቱ ይስጣት”
“ሴቲቱን ያገባት ሁለተኛው ሰው”
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በፍቺውና እንደገና ሌላ ሰው በማግባቷ ከረከሰች በኋላ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ምድር ኃጢአት ልትሠራ እንደምትችል ተደርጋ ተነግሮላታል። አ.ት፡ “በምድሪቱ ዙሪያ በደል እንዳታስፋፋ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
“አንድ ሰው በቅርቡ አንዲትን ሴት በሚያገባበት ጊዜ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከቤቱ እንዲርቅና የትኛውንም ዓይነት ሥራ እንዲሠራ ማንም አያስገድደው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በቤቱ ለመኖር ነጻ ይሁን”
ክብደት ባላቸው ሁለት ክብ ድንጋዮች እህል በመፍጨት ዱቄት ለመሥራት የሚያስችል መሣሪያ
ከወፍጮ ጋር ያለ የላይኛው ክብ ድንጋይ
“ሕይወት” የሚለው ቃል አንድ ሰው ራሱን በሕይወት ለማቆየት የሚያስፈልገው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ሰውየው ለቤተሰቡ ምግብ ለማዘጋጀት የሚጠቀምበትን መውሰዱ ነውና” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ “አንድ ሰው ቢጠለፍ” እንደማለት ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ሲጠልፍ ብታገኘው” (የአነጋገር ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
አንድን ንጹሕ ሰው ኃይልን በመጠቀም ከቤቱ ወስዶ ማሰር ነው
“የትኛውንም እስራኤላዊ ወንድሙን”
“ከዚያም ሌሎች እስራኤላውያን ያንን ሌባ ስለድርጊቱ በመግደል ይቅጡት”
“ክፉ” የሚለው ቅጽል እንደ ስማዊ ሐረግ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይህንን ክፉ ነገር ያደረገውን ሰው ከእስራኤላውያን መካከል አስወግደው” ወይም “ይህንን ክፉ ሰው አስወግደው” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ሙሴ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለእስራኤላውያን ይናገራል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላትና “ጥንቃቄ አድርግ” እና “ትዝ ይበልህ” የሚሉት ትዕዛዛት ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
“የምትሠቃየው በለምጽ እንደሆነ ልብ በል” ወይም “ለምጽ ይኖርብህ እንደሆነ ልብ በል”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሰጠሁህን መመሪያዎች በሙሉና ሌዋውያን የሆኑት ካህናቱ እንድታደርገው የሚያስተምሩህን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ሙሴ ለእስራኤላውያን የሚናገረው እንደ ቡድን ነው፣ ስለዚህ “አንተ” የሚሉት እነዚህ አገባቦች ብዙ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
“እኔ እንዳዘዝኳቸው በትክክል ስለማድረግህ እርግጠኛ ሁን”
“እነርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሌዋውያን የሆኑትን ካህናት ነው።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “(የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ግብፅን ስትለቅ በነበረበት ጊዜ”
“ኮቱን አታሳድርበት”
ይህ የሚያመለክተው ብድሩን ባይመልስ በምትኩ ሊሰጥህ ቃል የገባውን ነገር ነው። ይህንን በዘዳግም 24፡10 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ብድሩን እንደሚመልስልህ ለማሳየት የሰጠህን መልስለት”
“የተቀጠረን አገልጋይ አትበድለው”
በየቀኑ ለሥራው የሚከፈለው ሰው
እነዚህ ሁለት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ይህ ሰው ራሱን መርዳት የማይችል በመሆኑ ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Doublet)
እዚህ ጋ “የከተማ በሮች” ማለት መንደሮች ወይም ከተሞች ማለት ነው። አ.ት፡ “ከከተሞችህ በአንዱ” (See: Synecdoche)
“ሰውየው በየቀኑ ማግኘት የሚገባውን ገንዘብ ልትሰጠው ይገባል”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እስራኤላውያኑ ፀሐይ ስትጠልቅ የአዲሱ ቀን ጅማሬ እንደሆነ ያስባሉ። አ.ት፡ “ሥራውን በሠራበት በዚያው ቀን ለሰውየው ልትከፍለው ይገባል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ድኻ ስለሆነና ለቀጣይ ቀኑ ምግቡን ለመግዛት በደሞዙ ስለሚተማመን” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“እግዚአብሔርን እንዳይጠራና እንዲቀጣህ እንዳይጠይቀው”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከልጆቻቸው አንዱ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት ወላጆችን አትግደል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወላጆቻቸው ባደረጉት ክፉ ነገር ምክንያት ልጆቻቸው አይገደሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድን ሰው መግደል የሚኖርብህ እርሱ ራሱ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት ብቻ ነው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ስለፍትሕ አንድ ጉልበተኛ የሆነ ሰው ከደካማው ላይ በኃይል እንደሚቀማው አካላዊ ቁስ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “የመጻተኛውን ወይም አባቱን ያጣውን ልጅ ፍትሕ አታጓድል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
x
“በእርሻህ ውስጥ ሰብል በምታጭድበት ጊዜ”
አንዳንድ ትርጉሞች ይህንን እንደ “እስር” ይተረጉሙታል። ትርጉሞቹ ሁሉ የሚያመለክቱት በቀላሉ ለመሸከም የሚቻል፣ በይበልጥም በአንድ ላይ የታሰሩ የአገዳ እህሎችን ነው።
የሚታወቀውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ነዶውን መጻተኛው፣ ወላጆቹን ያጣው ወይም መበለቲቱ እንዲወስዱት ተወው” (See: Ellipsis)
እዚህ ጋ “እጆች” የሚያመለክቱት ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “በምትሠራው ሥራ ሁሉ” (See: Synecdoche)
የሚታወቀውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ፍሬው ሲረግፍ ለማንሣት የወይራ ዛፍህን ቅርንጫፎች በምትነቀንቅበት ጊዜ” (See: Ellipsis)
“ከወይራ ዛፉ ላይ እያንዳንዱን ፍሬ አትልቀም”
የሚታወቀውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “በቅርንጫፎቹ ላይ የሚቀሩት የወይራ ፍሬዎች መጻተኞች፣ ወላጆቻቸውን ያጡና መበለቶች ለቅመው የሚወስዷቸው ናቸው” (See: Ellipsis)
“የማትለቅመው የወይን ፍሬ ለመጻተኛው፣ አባቱን ላጣውና ለመበለቲቱ ይሆናል”
እነዚህ የሚያመለክቱት የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ነው። አ.ት፡ “ለመጻተኞች፣ ወላጆቻቸውን ላጡና ለመበለቶች” (See: Generic Noun Phrases)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አስታውስ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
1 በሰዎች መካከል ጠብ ቢነሣ ወደ ፍርድ አደባባይ ቢሄዱ፥ ዳኞች ተበዳይን ነጻ፥ በዳይን ግን ጥፋተኛ፥ በማድረግ የፍርድ ውሳኔ ይስጡ። 2 በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፥ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፥ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ። 3 ሆኖም ግርፋቱ ከአርባ የሚበልጥ አይሁን፥ ከዚህ ካለፈ ግን እስራኤላዊ ወንድማችሁ በፊታችሁ የተዋረደ ይሆናል። 4 እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰሩ። 5 ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና፥ ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥የሟቹ ሚስት ከቤተ ሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት። 6 በመጀመሪያ የምትወልደውም ልጅ ስሙ ከእስራኤል ፈጽሞ እንዳይጠፋ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራ። 7 ሆኖም ግን አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ለማግባት ባይፈልግ ሴትዮዋ በከተማዋ በር ወዳሉት ሽማግሌዎች ሄዳ የባለቤቴ ወንድም የወንድሙን ስም በእስራኤል ለማስጠራት አልፈለገም፥ የዋርሳነት ግዴታውንም አልፈጸመልኝም ትበላቸው። 8 ከዚያም የከተማው ሽማግሌዎች ያን ሰው ጠርተው ያነጋግሩት እርሱም እርሷን ላገባት አልፈልግም ብሎ በሐሳቡ ቢጸና፥ 9 የወንድሙንም ሚስት በሽማግሌዎች ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፥ የአንድ እግሩን ጫማ በማውለቅ በፊቱ ላይ ትትፋበትና የወንድሙን ቤት ማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ያለው ድርጊት ይፈጸምበታል ትበል። 10 የዚያም ሰው የዘር ሐረግ በእስራኤል ዘንድ ጫማው የወለቀበት ቤት ተብሎ ይታወቃል። 11 ሁለት ሰዎች ቢደባደቡ፥ የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል መጥታ እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዘው 12 ፥እጇን ቁረጡ አትራሩላት። 13 በከረጢታችሁ ውስጥ ከባድና ቀላል የሆኑ ሁለት የተለያዩ ሚዛኖች አይኑሩአችሁ። 14 በቤታችሁም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት የተለያዩ መስፈሪያዎች አይኑሩአችሁ። 15 እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም ትክክለኛና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑራችሁ። 16 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲህ ያሉትን ጽድቅ ያልሆን ነገሮች የሚፈጽመውንና የሚያምታታውን ሁሉ ይጸየፈዋልና። 17 ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ በእናንተ ላይ ያደረጉባችሁን አስታውሱ፤ 18 ደክማችሁና ዝላችሁ በነበራችሁበት ጊዜ በጉዞ ላይ አግኝቶአሁ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአቤርንም አልፈሩም። 19 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ ባሳረፋችሁ ጊዜ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስሱ፤ ከቶ እንዳትረሱ!
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ዳኛው በደለኛውን ሰው እንዲገርፉት ካዘዛቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሲገርፉት ያያቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ስላደረገው ክፉ ሥራ ባዘዘው ቁጥር ልክ”
“ዳኛው በደለኛውን ሰው 40 ጊዜ እንዲገርፉት ሊነግራቸው ይችላል” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ሆኖም ዳኛው ከ40 ጊዜ በላይ እንዲገረፍ ማዘዝ አይኖርበትም”
“ዳኛው ከ40 ጊዜ በላይ እንዲገርፉት የሚያዛቸው ከሆነ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ያን ጊዜ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት እስራኤላዊውን ወንድምህን ያዋርደዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ስለሚያዩት ነገር አጽንዖት ለመስጠት ሕዝቡ በ “ዐይኖቻቸው” ተወክለዋል። አ.ት፡ “ተዋርዷል፣ እናንተ ሁላችሁም አይታችሁታል” (See: Synecdoche)
ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፣ 1) “ወንድማማቾች በአንድ ንብረት ላይ የሚኖሩ ከሆነ” ወይም 2) “ወንድማማቾች ተቀራርበው የሚኖሩ ከሆነ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ያን ጊዜ የሟች ቤተሰቦች መበለቲቱ ሌላ ሰው እንድታገባ መፍቀድ የለባቸውም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“የሟች ወንድም እንዲያደርግ የሚጠበቅበትን ያድርግ”
“ስም” የሚለው ቃል የሰውየውን የቤተሰብ ሐረግ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የሟች ወንድሙ የቤተሰብ ሐረግ ይቀጥላል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ስም” የሚለው ቃል የሰውየውን የቤተሰብ ሐረግ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የቤተሰቡ ሐረግ ከእስራኤል እንዳይጠፋ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ሽማግሌዎች በጉዳዮች ላይ ወደሚዳኙበት ወደ ከተማው በር ትሂድ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እዚህ ጋ “ስም” የሚያመለክተው በተወላጆቹ አማካይነት የአንድን ሰው መታሰቢያ ነው። አ.ት፡ “ለወንድሙ ወንድ ልጅ ለመስጠት እምቢ ቢል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እኔን በማግባት ከዋርሳ የሚጠበቅበትን ተግባር አልፈጸመም”
“ላገባት አልፈልግም”
“በዚያ ያሉ ሽማግሌዎች እያዩአት ተራምዳ ትቅረበው”
እዚህ ጋ “ቤት” የቤተሰብ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ለወንድሙ ወንድ ልጅ የማይሰጥና የወንድሙን የቤተሰብ ሐረግ የማያስቀጥል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በእስራኤል ያሉ ሰዎች ቤተሰቡን እንደ -- ያውቃሉ”
እዚህ ጋ ጫማ የማውለቁ ምሳሌ ወንድምየው ከሟች ወንድሙ ሀብት ምንም እንደማይወስድ ማሳያ ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። ደግሞም ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል. አ.ት፡ “የወንድሙ ሚስት ጫማውን ከእግሩ ያወለቀችበት ሰው ቤት” ወይም “የወንድሙን ሚስት ያላገባው ሰው ቤተሰብ” ወይም “ሁሉም ሰው የሚንቀው ቤተሰብ” ወይም “አሳፋሪው ቤተሰብ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” ኃይልን ወይም ቁጥጥርን ያመለክታል። አ.ት፡ “ደብዳቢው እንደ ገና እንዳይደበድበው” ወይም “እርሱን ከሚመታው ሰው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዐይን” ማለት ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “አትዘንላት” ወይም “ምሕረት አታድርግላት” (See: Synecdoche)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። በተጨማሪም የሚታወቀውን መረጃ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “ነገሮችን በምትገዛበት ጊዜ ከምትናገረው የሚበልጥን ሚዛን በመጠቀም፣ በምትሸጥበት ጊዜ ደግሞ ከምትናገረው ያነሰ ሚዛን በመጠቀም ሰዎችን አታጭበርብር” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information and Ellipsis)
ሚዛኖች አንድ ነገር ምን ያህል እንደሚከብድ ለማወቅ መለኪያው ላይ የሚቀመጡ ድንጋዮች ነበሩ
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ በተጨማሪም፣ የሚታወቀውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ነገሮችን በምትገዛበት ጊዜ ከምትናገረው የሚበልጥ መለኪያ በመጠቀም፣ እንዲሁም በምትሸጥበት ጊዜ ከምትናገረው የሚያንስ መለኪያ በመጠቀም ሰዎችን ማጭበርበር የለብህም። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information and Ellipsis)
መለኪያ አንድ ነገር ምን ያህል እንደሆነ የሚለካበት ቅርጫት ወይም ሌላ መያዣ ነበር።
“ትክክል እና አግባብነት ያለው”
እነዚህን ቃላት በዘዳግም 25፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ረጅም ዘመን እንድትኖር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“የተለያየ መጠን ያላቸውን ሚዛኖችና መለኪያዎችን በመጠቀም ሰዎችን የሚያጭበረብሩ ሁሉ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን “አማሌቅ” አማሌቃውያን ሰዎችን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አማሌቃውያን ያደረጉብህን አስታውስ” (የአነጋገር ዘይቤ፣ ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“በጉዞ ላይ እያለህ እንዴት እንደተገናኙህ”
“የኋላ መስመር ላይ የነበሩትን ሰዎችህን አጠቃ”
“በኋለኛው መስመር ላይ ደካሞች የነበሩትን ሰዎች በሙሉ”
እነዚህ ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ሕዝቡ ምን ያህል ደክመው እንደነበሩ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ደክመውና ዝለው” (See: Doublet)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን ቅጣት አልፈራም” ወይም “እግዚአብሔርን አላከበረም” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ከእንግዲህ ማንም እንዳያስታውሳቸው አማሌቃውያንን በሙሉ ግደላቸው”
1 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ ወደ ሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፥ ስትወርሱአትና ስትኖሩባት፤ 2 እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሚሰጣችሁ ምድር ከሁሉም የመጀመሪያ ፍሬ ውሰዱት። ከዚያም በቅርጫት ውስጥ አድርጉትና እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ሂዱ። 3 በዚያን ወቅት ወደ ሚያገለግለው ካህን ሄዳችሁ ፦ እግዚአብሔር ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ እግዚአብሔር አምላካችሁን ለማምስገን እቀባለለሁ በለው። 4 ካህኑም ቅርጫቱን ከእጃችሁ ተቀብሎ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ መሠዊያ ፊት ለፊት ያኖረዋል። 5 እናንተም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት እንዲህ ብላችሁ ትናገራላችሁ፦ አባቴ ዘላን ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ፥ ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ። 6 ግብፃውያንም በመጥፎ ሁኔታ እንገላቱን፥ አሠቃዩንም። እንደ ባሪያ ከባድ ሥራ እንድንሠራ አደረጉን። 7 ከዚያ በኋላ ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኸን፥ እርሱም ጩኸታችንን ሰማ፤ መከራችንን፣ ድካማችንንና የተፈጸመብንን ግፍ ተመለከተ። 8 ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር በብርቱ እጅና በተዘረጋው ክንዱ፥ በታላቅ ድንጋጤና ታምራት በምልክትና በድንቅ ከግብፅ አወጣን፤ 9 ወደዚህም ስፍራ አመጣን፥ ማርና ወተት የምታፈሰውን ይህችን ምድር ሰጠን። 10 እግዚአብሔር ሆይ እነሆ፥ አንተ ከሰጠኸኝ ከምድሪቱ የመጀመሪያ ፍሬ አምጥቻለሁ፤ ቅርጫቱንም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አኑራሃው አምልከው፤ 11 ለአንተና ለቤትህ ባደረገው መልካም ነገር አንተ፥ ሌዋውያንና መጻተኞች በእግአብሔር በአምላክህ ፊት ደስ ይበላችሁ። 12 የአሥራት ዓመት የሆነውን የሦስተኛውን ዓመት ፍሬ አንድ አሥረኛ ለይታችሁ ካወጣችሁ በኃላ በየከተሞቻችሁ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፥ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥አባት ለሌለውና ባል ለሞተባቸው ስጡአቸው። 13 ከዚያ በኋላ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንዲህ በል፦ በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ከቤቴ አምጥቼ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም። 14 በሐዘን ላይ ሳለሁ፥ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም ባልነጻሁበትም ጊዜ ከዚህ ላይ ያነሣሁትምና ለሙታን ያቀረብሁት ምንም ነገር የለም። አምላኬን እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፥ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። 15 ከቅዱስ ማደሪያ ሆነህ ከሰማይ ተመልከት፥ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በማለህላቸው መሠረት፥ ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ባርክ። 16 እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን ሥርዓትንና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ዛሬ ያዝዛችኋል፤ እናንተም በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትፈጽሙት ዘንድ ተጠንቀቁ። 17 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆነ በመንገዱም እንደምትሄዱ፥ ሥርዓቱን፥ ትእዛዙንና ሕጉን እንደምትጠብቁ እንደምትታዘዙለት በዛሬው ዕለት ተናግራችኋል። 18 እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት እንንተ ሕዝቡና ርስቱ መሆናችሁን ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቁ በዛሬው ዕለት ተናግሮአል፤ 19 ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ ለማመስገን፥ ለማክበረና ከፍ ለማድረግና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቅዱስ ሕዝብ እንደምትሆኑ ማረጋገጫ ሰጥቶአል።
“ከምርትህ በኩራት ጥቂቱን” ወይም “ከመጀመሪያው የሰብል ምርትህ ጥቂቱን”። ይህ “መጀመሪያ” የአንድ ደረጃን ማሳያ ቁጥር ነው። (ደረጃን ማሳያ ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ እስራኤላዊ ወንድ ቅርጫቱን በሚያቀርብበት ጊዜ መናገር የሚኖርበት የዐረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ነው።
ይህ የእስራኤላውያኑ ሁሉ ቅድመ ቅድም አያት የነበረውን ያዕቆብን ያመለክታል። እርሱ ለብዙ ዓመታት በሶሪያ በሚገኝ በአራም ናሃሪም ይኖር ነበር።
“ቀሪ ሕይወቱን በዚያ ኖሯል”
“እርሱ” የሚለው ቃል “የያዕቆብን ተወላጆች” የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በመሠረቱ እነዚህ ቃላት የሚሉት አንድ ነገር ነው። እስራኤል ብዙና ኃይለኛ ሕዝብ መሆኑ ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “በጣም ታላቅ” (See: Doublet)
በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚሉት አንድ ነገር ነው። ግብፃውያን የጭካኔ ተግባር እንደ ፈጸሙባቸው አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Doublet)
እዚህ ጋ “እኛ” የሚያመለክተው በግብፅ ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤል ሕዝብ ነው። ተናጋሪው በግብፅ ቢኖርም ባይኖርም ራሱን ከሕዝቡ አንዱ አድርጎ ይጨምራል። (See: Inclusive “We”)
እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው እና ጩኸቱን ወይም ጸሎቱን ነው። አ.ት፡ “ጩኸታችንን ሰማ” ወይም “ጸሎታችንን ሰማ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ግብፃውያን ያሰቃዩን የነበረውን፣ ስንሠራው የነበረውን በጣም ከባድ የሆነውን ሥራ እና ግብፃውያኑ ይጨቁኑን የነበረውን”
እዚህ ጋ “እኛ” የሚያመለክተው በግብፅ ይኖሩ የነበሩትን የእስራኤል ሕዝብ ነው። ተናጋሪው በግብፅ ቢኖርም ባይኖርም ራሱን ከሕዝቡ አንዱ አድርጎ ይጨምራል። (See: Inclusive “We”)
እዚህ ጋ “ብርቱ እጅ” እና “የተዘረጋች ክንድ” የእግዚአብሔርን ኃይል የሚያመለክቱ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡34 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ብርቱ ኃይሉን በማሳየት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ያዩአቸውን ሰዎች በሚያስፈሩ ድርጊቶች”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በዘዳግም 6፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡ አ.ት፡ “ብዙ ወተትና ማር የሚፈስባት ምድር” ወይም “ከብት ለማርባትና ለእርሻ ምርጥ የሆነች ምድር”
“ከአዝመራው የመጀመሪያውን ፍሬ” ወይም “ከአዝመራው የመጀመሪያውን ሰብል”
“ቅርጫቱን አስቀምጠው”
“አምላክህ እግዚአብሔር ስላደረገልህ መልካም ነገሮች ሁሉ ደስ ይበልህ፣ አመስግንም”
ይህ “ሦስተኛ” የሦስት ደረጃን አመልካች ቁጥር ነው። የእስራኤል ሕዝብ በየሦስት ዓመቱ ከአዝመራው አንድ አሥረኛውን ለድኾች ይሰጡ ነበር። (ደረጃን አመልካች ቁጥር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁለቱም ወላጆቻቸው የሞቱባቸውና የሚንከባከባቸው ዘመድ የሌላቸው ልጆች ናቸው።
ይህ ማለት ባል የሞተባትና በእርጅናዋ ጊዜ የሚንከባከብ ልጅ የሌላት ሴት ማለት ነው።
እዚህ ጋ “በሮች” ማለት መንደሮች ወይም ከተሞች ማለት ነው። አ.ት፡ “እነዚያ በመንደርህ ውስጥ የሚኖሩት የሚበሉት በቂ ምግብ እንዲኖራችው” (See: Synecdoche)
እነዚህ እስራኤላዊው እንዲለው የሚጠበቅበት የሌላው አነጋገር የመጀመሪያ ቃላት ናቸው።
ይህ ማለት የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በሙሉ ታዟል።
“ባለቀስኩበት ወቅት የትኛውንም አስራት አልበላሁም”
እዚህ ጋ “ያልነጻ” ማለት በሕጉ መሠረት ንጹሕ ያልሆነ ሰው ማለት ነው። ንጹሕ ያልሆነ ሰው ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን አስራት እንዲነካ እግዚአብሔር አይፈቅድለትም”። የዚህ አነጋገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በሕጉ መሠረት ንጹሕ ባልነበርኩበት ጊዜ” ወይም “ልነካው እንደማልችል ሕጉ በሚናገርበት ጊዜ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” እግዚአብሔር ለተናገረው የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። ሁለቱም አነጋገሮች ተመሳሳይ ትርጉም ይጋራሉ። ሰውየው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በሙሉ ስለመታዘዙ አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Parallelism የሚለውን ተመልከት))
እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚሉት ተመሳሳይ ነገር ነው። አ.ት፡ “ከቅዱስ ማደሪያህ፣ ከሰማይ” (See: Dou- blet)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በዘዳግም 6፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ብዙ ወተትና ማር የሚፈስባት ምድር” ወይም “ከብት ለማርባትና ለእርሻ ምርጥ የሆነች ምድር”
እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት የሚመለከቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። እነዚህ ሁለት ሐረጎች በአንድ ላይ “ሙሉ በሙሉ” ወይም “በቅንነት” ለማለት ጥቅም ላይ ውለዋል። ይህንን በዘዳግም 4፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “መሄድ”፣ “መጠበቅ” እና “መስማት” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው። እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚያመለክተው እግዚአብሔር የተናገረውን ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ያዘዘው ሁሉ ሙሉ በሙሉ እንድትጠብቅ” (See: Parallelism and Metonymy)
“የእርሱ የሚሆንን ሕዝብ”
1 ሙሴና የእስራኤል አለቆች ሕዝቡን እንዲህ ብለው አዘዙ፦ ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ። 2 አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁሙና በኖራ ለስኑአቸው። 3 የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማርና ወተት ወደምታፈሰው፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገሩ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፉባቸው። 4 ዮርዳኖስን እንደ ተሻገራችሁም ዛሬ ባዘዙአችሁ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከሉአቸው በኖራም ለስኑአቸው። 5 እዚያም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የድንጋይ መሠዊያ ሥራ፥ በድንጋዮቹም ላይ ማናቸውንም የብረት መሣሪያ አታሳርፉባቸው። 6 የእግዚአብሔር የአምላካችሁን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥሩ፥ በላዩም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡበት። 7 በላዩም የኅብረት መሥዋዕት ሠዉ፤ ብሉም፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ። 8 በድንጋዮቹም ላይ የዚህ ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርጋችሁ ጻፉባቸው። 9 ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም፥ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ እስራኤል ሆይ፥ ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! እናንተ ዛሬ የእግዚአብሔር የአላካችሁ ሕዝብ ሆናችኋል። 10 ስለዚይም እግዚአብሔር አምላካችሁን ታዘዙ፥ ዛሬ የሚሰጣችሁን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ጠብቁ። 11 ሙሴ በዚያኑ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ 12 ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ስምዖን ፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዮሴፍና ብንያም ወገኖች ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ። 13 ሮቤል፥ ጋድ፥ አሴር፥ ዛብሎን፥ ዳንና ንፍታሌምወገኖች በጌባል ተራራ ላይ ለመርገም ይቁሙ። 14 ሌዋውያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦ 15 ጥበበኛ የሠራውን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ የሆነውን ምስል የሚቀርጽ ወይም ጣዖትን የሚያበጅ በስውርም የሚያቆም ሰው የተረገመ ይሁን። ሕዝብም ሁሉ፥ አሜን ይበል። 16 አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገም ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። 17 የባልንጀራውን የድንበር ድንጋይ ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። 18 ዐይነ ስዉርን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። 19 በመጻተኛው፥ አባት በሌለውና ባል በሞተባት ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። 20 ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን፤ የአባቱን መኝታ ያረክሳልና። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። 21 ከማናቸውም እንስሳ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። 22 የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው ከእኅቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን። 23 ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። ከሚስቱ እናት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። 24 በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። 25 ንጹሕውን ሰው ለመግደል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። 26 የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
ሙሴ እንደ አንድ ቡድን አድርጎ የሚናገረው ለእስራኤላውያን ነው፣ ስለዚህ በሁለቱም አገባብ “አንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
እዚህ ጋ “እኔ” የሚያመለክተው ሙሴን ነው። ሽማግሌዎቹ ከሙሴ ጋር ተስማምተው በዚያ አሉ፣ ሆኖም ብቸኛው ተናጋሪ እርሱ ነው።
ይህ ዓይነቱ በአብዛኛው የኖራ፣ አሸዋና ውሃ ድብልቅ ሲሆን በአንድ ነገር ላይ የሚቀባ ነው። ሲደርቅ አንድ ሰው በላዩ ላይ መጻፍ እንዲችል ጠንካራና ለስላሳ ገጽታ ይኖረዋል። አ.ት፡ “ቅባቸው” ወይም “ልትጽፍባቸው እንዲያስችሉህ አድርግ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በዘዳግም 6፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ብዙ ወተትና ማር የሚፈስባት ምድር” ወይም “ለከብት እርባታና ለእርሻ ምርጥ የሆነች ምድር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለእስራኤላውያን የሚናገረው እንደ ቡድን አድርጎ ነው፣ ስለዚህ “አንተ” የሚልበት አገባብና “አስቀምጥ” የሚለው ትዕዛዝ ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“ቅባቸው” ወይም “ልትጽፍባቸው እንዲያስችሉህ አድርግ”። ይህንን በዘዳግም 27፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ በሴኬም አቅራቢያ የሚገኝ ተራራ ነው። እርሱን በዘዳግም 11፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ድንጋዮቹን በማለስለስ በተሻለ ሁኔታ በአንድ ላይ እንዲገጣጠሙ ለማድረግ የሚያገለግሉ መሮዎችን ያመለክታል። የዚህ አነጋገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የመሠዊያውን ድንጋዮች በብረት መሣሪያ አትጥረባቸው” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ማንም በብረት መሣሪያ ያልጠረባቸው በተፈጥሮ ቅርጻቸው ያሉ ድንጋዮች
ይህ በኖራ ተቀብተው በጌባል ተራራ ላይ የሚቆሙትን ድንጋዮች ያመለክታል። ይህንን በዘዳግም 27፡12 እና 27፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር እርሱ የሚናገረውን ያመለክታል። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር የሚናገረውን ታዘዝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እያዘዘ ነው። ሌዋውያኑ ከሙሴ ጋር በመስማማት በዚያ ይገኛሉ፣ ሆኖም የሚናገረው እርሱ ብቻ ነው።
እዚህ ጋ “ነገዶች” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው የስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍ፣ እና ብንያም ነገድ ሕዝቦችን ነው። አ.ት፡ “የእነዚህ ነገዶች ሕዝቦች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
x
ይህንን በዘዳግም 11፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“እግዚአብሔር እስራኤልን እንዴት እንደሚረግማቸው በታላቅ ድምፅ ተናገር”
ይህ ሌዋዊው ለእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ጮክ ብሎ የሚያደርገው ንግግር ነው። ይህ ንግግር በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በድብቅ የሚያቆመውን ሰው እግዚአብሔር ይርገመው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ሰው የሠራው አንድ ነገር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ነገሮችን ጥሩ አድርጎ መሥራት የሚያውቅ ሰው
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሰውየውን ይርገመው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የዚህ አነጋገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በመሬቱ ድንበር ላይ ያሉትን ምልክቶች በማንሣት ከባልንጀራው መሬት የሚወስድ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በዘዳግም 27፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሰውየውን ይርገመው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ስለ ፍትሕ የሚናገረው አንድ ጉልበተኛ የሆነ ሰው ደካማ ከሆነው ሰው ላይ በኃይል እንደሚቀማው አካላዊ ቁስ አድርጎ ነው። የአንተ ቋንቋ ምናልባት “ጉልበቱን ተጠቅሞ የሚነጥቅ” ለማለት የሚያስችል አንድ ቃል ይኖረው ይሆናል። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 24፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “መጻተኛውን -- መበለቲቱን የሚበድል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁለቱም ወላጆቻቸው የሞቱባቸውና የሚንከባከባቸው ዘመድ የሌላቸው ልጆች ናቸው።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በዘዳግም 27፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሰውየውን ይርገመው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአባቱን ሌላኛዋን ሚስት እንጂ የሰውየውን እናት አያመለክትም።
አንድ ሰው ሚስት በሚያገባበት ጊዜ እርሱ ብቻ ከእርሷ ጋር የመተኛት ሕጋዊ መብት ይኖረዋል። የዚህ አነጋገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የአባቱን ሕጋዊ መብት ወስዶበታል” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
የዚህ አነጋገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከየትኛውም ዓይነት እንስሳ ጋር የሚተኛ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በዘዳግም 27፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሰውየውን ይርገመው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት አንድ ሰው ከሌላ እናት ወይም አባት ብትወለድም እንኳን ከእህቱ ጋር ሊተኛ አይችልም።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በዘዳግም 27፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሰውየውን ይርገመው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በዘዳግም 27፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሰውየውን ይርገመው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
1 ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በፍጹም ብትታዘዙና እኔ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዘትን ሁሉ በጥንቃቄ ብትከተሉ አምላካችሁ እግዝአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ አሕዝብ ሁሉ በላይ ከፍ ያደርጋችኋል። 2 እግዚአብሔር አምላካችሁን ብትታዘዙ እነዚህ በረከቶች ሁሉ የእናንተ ይሆናሉ፤ አይለዩአችሁምም። 3 በከተማና በእርሻ ትባረካላችሁ። 4 የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ የምድራችሁ አዝመራ፥ የእንስሳታችሁ ግልገሎች፥ የክብታችሁ ጥጃ፥ የበግና የፍየል ግልገሎቻችሁም ይባረካሉ። 5 እንቅባችሁና ቡሓቃያችሁም ይባረካሉ። 6 ስትጓዙ ትበረካላችሁ፤ ስትወጡም ትባረካላችሁ። 7 እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶቻችሁን በፊታችሁ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤በአንድ አቅጣጫ ቢመጡባችሁ በሰባት አቅጣጫም ከእናንተ ይሸሻሉ። 8 እግዚአብሔር በጎተራችሁና እጃችሁ በነካው ሁሉ በረከቱን ይልካል። አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ይባርካችኋል። 9 የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ትእዛዞች የምትጠብቁና በመንገዱ የምትሄዱ ከሆነ በማለላቸው ተስፋ መሠረት የተቀደሰ ሕዝቡ አድርጎ ያቆማችኋል። 10 ከዚያ የምድር አሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም መጠራታችሁን ያያሉ፤ ይፈርሁማል። 11 እግዚአብሔርም ሊሰጣችሁ ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ በእንስሳታችሁ፥ ግልገል፥ በምድራችሁም ሰብል፥ የተትረፈረፈ ብልጽግና ይሰጣችኋል። 12 እግአብሔር ለምድራችሁ በወቅቱ ዝናብን ለመስጠትና የእጃችሁን ሥራ ሁሉ ለመባረክ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትላችኋል፤ እናንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራላችሁ እንጂ ከአንዳቸውም አትበደሩም። 13 እግዚአብሔም ራስ እንጂ ድራት አያደርጋችሁም፤ ዛሬ የምሰጣችሁን የአምላካችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ብትጠብቁ መቼውንም ቢሆን በላይ እንጂ ፈጽሞ በታች አትሆኑም። 14 ሌሎች አማልክት በመከተል እነርሱን በማገልገል ዛሬ ከምሰጣችሁ ትእዛዞች ቀኝም ግራም አትበሉ። 15 ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ባትታዘዙ በዛሬዋ ዕለት የምሰጣችሁን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ሁል በጥንቃቄ ባትከተሉአቸው እነዚህ ርግማኖች ሁሉ ይደርሱባችኋል፤ ያጥለቀልቁአችኋልም። 16 በከተማ ትረገማላችሁ፤ በእርሻም ትረገማላችሁ። 17 እንቅባችሁና ቡሓቃያችሁ የተረገሙ ይሆናሉ። 18 የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ የእርሻህ ሰብል፥ የመንጋችሁ ጥጆች፥ የበግና የፍየል ግልገሎቻችሁ ይረገማሉ። 19 ስትገቡ ትረገማላችሁ፤ ስትወጡም ትረገማላችሁ። 20 እርሱን በመተው ክፉ ድርጊት ከመፈለጋችሁ የተነሣ እስክትደመስሱ ፈጥናችሁም እስክትጠፉ ድረስ እጃችሁ በነካው ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ርግማንን መደናገርንና ተግሣጽን ይሰድባችኋል። 21 እግዚአብሔር ልትወርሱአት ከምትገቡባት ምድር ላይ እስኪያጠፋችሁ ድረስም በደዌ ይቀሥፋችኋል። 22 እግዚአብሔር እስክትጠፉ ድረስ በሚቀሥፍ ደዌ ትኩሳትና ዕባጭ ኃይለኛ ሙቀትና ድርቅ ዋግና አረማሞ ይመታችኋል። 23 ከራሳችሁ በላይ ያለው ሰማይ ናስ ከእግራችሁ በታች ያለው ምድርም ብረት ይሆናል። 24 እግዚአብሔር የምድራችሁን ዝናብ ወደ አቧራነትና ወደ ትቢያነት ይለወጠዋል፤ ይህም እስክትጠፉ ድረስ ከሰማይ ይወርድባችኋል። 25 እግዚአብሔር በጠላቶቻችሁ ፊት እንድትሸነፉ ያደርጋችኋል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣበቸዋላችሁ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሽሻላችሁ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀያ ትሆናላችሁ። 26 ሬሳችሁ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ በማስፈራራትም የሚያባርሩአቸው አይኖርም። 27 እግዚአብሔር በማትድኑበት በግብፅ ብጉጅ፥ በእባጭ በሚመግል ቁስልና በእከክ ያሠቃያችኋል። 28 እግዚአብሔር በእብደት፥ በዕውርነትና ግራ በማጋባት ያስጨንኣቃችል። 29 በእኩለ ቀን በጨለማ እንዳለ ዕውር በዳበሳ ትሄዳላችሁ። የምታደርጉት ሁሉ አይሳካላችሁም። በየዕለቱ ትጨቆናላችሁ፤ ትመዘበራላችሁም፤ የሚታደጋችሁም አይኖርም። 30 ሚስት ለማግባት ልጃገረድ ታጫላችሁ ሌላው ግን ወስዶ በኃይል ይደፍራታል። ቤት ትሠራላችሁ፤ ግን እናንተ አትኖሩበትም። ወይን ትተክላላችሁ ፍሬውን ግን አትበሉም። 31 በሬህ ዐይናችሁ እያየ ይታረዳል፤ ከሥጋውም አንዳች አትቀምሱም። አህያችሁም በግድ ይወሰድባችኋል፤ አትበሉም። በጎቻችሁ ለጠላቶቻችሁ ይሰጣሉ፤ የሚያሰጥላቸውም አይኖርም። 32 ወዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ለባዕድ ሕብብ ይሰጣሉ፤ እጃችሁንም ለማንሣት እቅም ታጣላችሁ፤ ይመጣሉ፤ በማለትም ዐይኖቻችሁ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ። 33 የምድራችሁንና የድካማሁን ፍሬ ሁሉ የማታውቁት ሕዝብ ይበላዋል፤ 34 ሁልጊዜ በጭቆናና በጫን ትኖራላችሁ፤ በምታዩት ሁሉ ትጃጀላላችሁ። 35 እግዚአብሔር ከእግራችሁ ጥፍር እስከ ራስህ ጠጉር በሚወርር ሊድን በማይችልና በሚያሠቃይ ቁስል ጉልበታችሁንና እግራችሁን ይመታችኋል። 36 እግዚአብሔር እናንተንና በላያችሁ ያነገሣችሁትን ንጉሥ፥ እናንተና አባቶቻችሁ ወደ ማታውቁት ሕዝብ ይወሰዳችኋል፤ ከዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማክልትን ታመልካላችሁ። 37 እግእብብሔር እንድትገቡ በሚመራችሁ ምድር ለአሕዛብ ሁሉ መሸማቀቂያ ማላገጫና መዘባበቻ ትሆናላችሁ። 38 በእርሻ ላይ ብዙ ዘር ትዘራላችሁ አንበጣ ስለሚበላው የምትሰበስቡ ጥቂት ይሆናል። ወይን ትተክላላችሁ ትንከባከበዋላችሁ፤ 39 ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጡም ዘለላውንም አትሰበስቡም። 40 በአገራችሁ ምድር ሁሉ የወይራ ዛፍ ይኖራችኋል፤ ፍሬው ስለሚረግፍባችሁ ግን ዘይቱን አትቀቡም። 41 ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻችሁን ትወልዳላችሁ ነገር ግን በምርኮ ስለሚወሰዱ፤ አብረዋችሁ አይኖሩም። 42 ዛፋችሁንና የምድራችሁን ሰብል ሁሉ አንበጣ መንጋ ይወረዋል። 43 በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ከእናንተ በላይ ከፍ ከፍ ሲል እናንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላላችሁ። 44 እርሱ ያበድራችኋል እንጂ እናንተ አታበድሩም። እርሱ ራስ ይሆናል፤ እናንተ ግን ጅራት ትሆናላችሁ። 45 እነዚህ ርግማኖች እስክትጠፉ ድረስ ይከተሉአችኋል፤ ሁሉ በእናንተ ላይ ይመጣሉ፤ ይህም የሚሆነው አምላካችሁን እግዚአብሔርን ስላልታዘዛችሁና የሰጣኋችሁን ትእዛዝና ሥርዓት ስላልጠበቃችሁ ይወርዱባችኋልም። 46 እነዚህ ርግማኖች እንደ ምልክትና ድንቅ ነገሮች ሆነው በእንንተና በዘራችሁ ለዘላለም ይሆናል። 47 በብልጽግና ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁን በደስታና በሐሤት ስላላገለገችሁ በራብና በጥም በእርዛትና በከፋ ድኽነት 48 እግዚአብሔር የሚያስነሣባችሁን ጠላቶቻችሁን ታገለግላላችሁ፤ እስኪያጠፉአችም ድረስ በአንገታችሁ ላይ የብረት ቀንበር ይጭንባችኃል። 49 እግዚአብሔር እንደ ንስር በፈጣን የሚበሩና ቋንቋውን የማታውቁአችሁን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፥ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣነሰባችኋል፤ 50 ሽማግሌ የማያከብር፥ ለወጣትም መልካም ያልሆኑና የሚያስፈራና ጨካኝ ሕዝብ ነው። 51 እስክትጠፉም ድረስ የእንስሳታችሁን ግልገልና የምድራችሁን ሰብል ይበላል፤ እስኪያጠፋችሁም ድረስ እህል፤አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት የመንጋችሁን ጥጃና የበግና ፍየል መንጋችሁን ግልገል አያስቀሩላችሁም። 52 የምትታመኑባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገራችሁ ያሉትን ከተሞቻችሁን ሁሉ ይከባል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጥጣችሁምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል። 53 ጠላቶቻችሁ ከበው በሚያስጨንቁአችሁ ጊዜ ከሥቃይ የተነሣ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችህን የአብራካችሁ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆቻችሁን ሥጋ ትበላላችሁ። 54 ሌላው ይቅርና በመካከላችሁ በጣም ደግና ርኅሩኅ የሆነው ሰው እንኳ ለገዛ ወንድሙ ወይም ለሚወዳት ሚስቱ ወይም ለተረፉት ልጆቹ አይራራላቸውም። 55 ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ያህል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ከተሞቻችሁ ሁሉ በመከበባቸው ጠላቶቻችሁ ከሚያደርሱባችሁ ሥቃይ የተነሣ ለእርሱ የቀረለት ይህ ብቻ ነውና። 56 በመካከላችሁ ተመቻችታና ተቀማጥላ የምትኖር ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ እግሯን አፈር ነክቶት የማያውቅ ሴት የምትወደውን ባሏን፥ የገዛ ወንድና ሴት ልጆቿን ትንቃለች። 57 ከማሕፀኗ የወጣውን የምትወልዳቸውን ሕፃናት ትጠየፋለች፤ በመከራው ወቅት ጠላቶቻችሁ ከተሞቻችሁን ከበው በሚያስጨንቁአችሁ ጊዜ ሌላ የሚበላ ስለማይኖር እነርሱን ደብቃ ትበላለች። 58 በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን የዚህን ሕግ ቃሎች ባትከተሉና የተከበረውና አስፈሪ የሆነውን የአምላካችሁን 59 የእግዚአብሔርን ስም ባታከብሩ እግዚአብሔር አስፈሪ መቅሠፍት፥ አስጨናቂና ለብዙ ጊዜ የሚቋይ መዓት አሠቃቂና በቀላሉ የማይወገድ ደዌ በእናንተና በዘሮቻችሁ ላይ ይልክባችኋል። 60 የምትፈሩአችሁንም የግብፅ በሽታዎች ሁሉ ያመጣባችኋል፤ በእናንተም ላይ ይጣበቃሉ። 61 ደግሞም እግዚአብሔር በዚህ የሕግ መጽሐፍ ያልተጸፈውን ማንኛውንም ዓይነት ደዌና መከራ እስክትጠፉ ድረስ ያመጣባችኋል። 62 ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስላልታዛዝችሁ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝታችሁ ቢሆን እንኳ እናንተ ጥቂት ብቻ ትቀራላችሁ። 63 እግዚአብሔር ለእናንተ መልካም በማድረግና ቁጥራችሁን በማብዛት ደስ እንዳተሰኘ ሁሉ ፤ እናንተን በመደምሰስና በማጥፋት ደስ ይለዋል። ከምትወርሱዋት ምድር ትነቀላላችሁ። 64 ከዚያም እግዚአብሔር ከአንዱ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ዳርቻ በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይበትናችኋል። በዚያም አባቶአኣችሁ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ። 65 በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኙም፤ ለእግራችሁም ጫማ ማረገጫ አይኖርም፤ እዚያም እግዚአብሔር የሚጨነቅ አእምሮ፥ የሚደክም ዐይንና ተስፋ የሚቋርጥ ልብ ይሰጣችኋል። 66 ዘመናችሁን በሙሉ ቀንና ሌሊት በፍርሃት እንደ ተዋጣችሁ ሕይወትታችሁ ዘወትር በሥጋት ትኖራላችሁ። 67 ልባችሁ በፍርሃት ከመሞላቱና ዐይናችሁ ከሚያየው ነገር የተነሣ ሲነጋ ምነው አሁን ሲመሽ ፥ደግሞ ምነው አሁን በነጋ ትላላችሁ። 68 ዳግመኛ አትመለሱባትም ባልሁ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብፅ ይመልሳችኋል። እዚያም እንደ ወንድና ሴት ባሪያ ለጠላቶቻችሁ ለመሸጥ ራሳችሁን ታቀርባላችሁ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው እርሱ የሚናገረውን ነው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ለሚናገረው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ትታዘዘው ዘንድ”
ሙሴ ከፍ ባለ ኮረብታ ላይ በአካል ከፍ እንደ ማለት አስፈላጊ ስለ መሆን ወይም ታላቅ ስለ መሆን ይናገራል። አ.ት፡ “ከ -- ይልቅ በጣም አስፈላጊ ያደርግሃል” ወይም “ከ-- ይልቅ ታላቅ ያደርግሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ በረከቶችን የሚገልጻቸው በድንገት እንደሚያጠቃቸው ወይም አሳዶ እንደሚይዛቸው ሰው አድርጎ ነው። አ.ት፡ “ፈጽሞ በምትገረምበት እንዲህ ባለ መንገድ እግዚአብሔር ይባርክሃል፣ ይኸውም ልታመልጥ በማትችልበት መልኩ ይባርክሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይባርክሃል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ቁንጽል፣ እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ይባርካቸዋል የሚል ትርጉም አለው። (See: Merism)
“ልጆችህ፣ ሰብልህ፣ እና እንስሶችህ” እነዚህ የአነጋገር ዘይቤዎች እስራኤላውያን ዋጋ ለሚሰጧቸው ነገሮች በሙሉ በቁንጽል አመልካቾች ናቸው። (የአነጋገር ዘይቤ እና Merism የሚለውን ተመልከት)
ይህ ጥምረት እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን እንስሶች እንደሚያበዛቸውና እንደሚያበረታቸው በሦስት መንገድ መናገሪያ ነው። አ.ት፡ “የከብቶቻችሁ ጥጃዎች እና የበግና የፍየል መንጋ ጠቦቶቻችሁ ከእንስሶቻችሁ ሁሉ ጋር” (See: Doublet)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይባርካል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እስራኤላውያን ቅርጫትን ጥራጥሬ ለመሸከም ይጠቀሙበት ነበር። “ቡሓቃ” እንጀራ ለመጋገር ዱቄቱን የሚያዋህዱበት ጎድጎድ ያለ ዕቃ ነው። አ.ት፡ “የምታበቅለው እህል እና የምትበላው ምግብ ሁሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ጥምረት በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚኖራቸውን የሕይወት ተግባራት በሙሉ ያመለክታል። (See: Merism)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሚዋጉህን ጠላቶችህን እንድታሸንፋቸው ያደርግሃል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ሆኖም በሰባት አቅጣጫ ከአንተ በሩጫ ይሸሻሉ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ትክክለኛው ቁጥር ከሰባት ሊበልጥ ወይም ሊያንስ ይችላል። አ.ት፡ “በብዙ የተለያዩ አቅጣጫዎች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር አንድ ሰው በድንገት እስራኤላውያንን እንዲያጠቃቸው የሚያዝ በሚመስል መልኩ እግዚአብሔር እንደሚባርካቸው ሙሴ ያብራራል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በሚባርክህ ጊዜ በጎተራህ ባለው ጥራጥሬ ብዛት ትገረማለህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በምትሠራው ነገር ሁሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ የራሱ እንዲሆን በተለየ ሁኔታ መምረጡ ሌሎች ሕዝቦች በሙሉ ከሚኖሩበት ስፍራ ልዩ በሆነ ቦታ እግዚአብሔር እንዳስቀመጣቸው ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ለእርሱ የሚሆን ቅዱስ ሕዝብ ያደርግሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “በእግዚአብሔር ስም ተጠርተሃል” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉም የእርሱ መሆን ማለት ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የራሱ አድርጎ ጠርቶሃል” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 28፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “በልጆች፣ እንስሳትና ሰብል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ዝናቡን የሚያስቀምጥባቸው ሕንጻዎች በሚመስሉበት መልኩ ዝናብ ስለሚያዘንቡ ደመናት ይናገራል። አ.ት፡ “ደመናት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሰብሎች በሚፈልጉት ጊዜ”
“እጅ” የሚለው ቃል የሙሉው ሰው ተምሳሌት ነው። አ.ት፡ “የምትሠራው ሥራ ሁሉ” (See: Synec- doche)
ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር የእስራኤልን ሕዝብ እንደ እንስሳ ይገልጸዋል፣ ይኸውም እስራኤላውያን ሁልጊዜ የሌሎች ሕዝቦች መሪዎች ይሆናሉ እንጂ ከቶም አገልጋዮቻቸው ለመሆን ከኋላ አይከተሉም ማለት ነው። እስራኤላውያን በኃይል፣ በገንዘብና በክብር ብልጫ ያላቸው ይሆናሉ። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እስራኤላውያን በሌሎች ላይ ገዢዎች ይሆናሉ እንጂ ሌሎች አይገዟቸውም።
ሙሴ የሚናገረው ለእስራኤላውያን በሙሉ ነው፣ ስለዚህ “አንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
እግዚአብሔርን አለመታዘዝና ሌሎች አማልክትን ማምለክ ልክ አንድ ሰው በአካሉ ከእግዚአብሔር ቃል ተመልሶ በሌላ አቅጣጫ እንደ ሄደ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን በማገልገል ዛሬ እኔ የማዝህን ባትታዘዝ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ሙሴ ሕዝቡ ባይታዘዙ የሚደርስባቸውን እርግማን መዘርዘር ይጀምራል።
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉሙ እግዚአብሔር የሚናገረው ማለት ነው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር የሚናገረው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እርግማኖቹን የሚገልጻቸው በድንገት እንደሚያጠቃቸው ወይም አሳዶ እንደሚይዛቸው ሰው አድርጎ ነው። አ.ት፡ “ፈጽሞ በምትደነቅበት ሁኔታ እግዚአብሔር ይረግምሃል፣ ይህም አንተን ከሚረግምበት ከእርግማኑ ማምለጥ በማትችሉበት ሁኔታ ነ፞ው” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ይህንን በዘዳግም 28፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይረግምሃል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የዚህ ጥምረት ትርጉም እግዚአብሔር በሁሉም ስፍራ ይባርካቸዋል የሚል ነው። ይህንን በዘዳግም 28፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (See: Merism)
እስራኤላውያን ቅርጫትን ጥራጥሬ ለመሸከም ይጠቀሙበት ነበር። “ቡሓቃ” እንጀራ ለመጋገር ዱቄቱን የሚያዋህዱበት ጎድጎድ ያለ ዕቃ ነው። ይህንን በዘዳግም 28፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የምታበቅለው እህል እና የምትበላው ምግብ ሁሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ይረግማል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ “ልጆችህ፣ ሰብልህ” ለሚለው የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህንን በዘዳግም 28፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ጥምረት እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን እንስሳ ብዙና ብርቱ እንደሚያደርጋቸው በሁለት መንገድ የተነገረበት ነው። አ.ት፡ “የከብቶቹ ጥጃዎች፣ የበግና የፍየል መንጋው ጠቦቶች” (See: Doublet)
ይህ ጥምረት የሚያመለክተው በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚሆነውን የሕይወት ተግባራት በሙሉ ነው። ይህንን በዘዳግም 28፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (See: Merism)
“እልቂት፣ ፍርሀት እና መሳቀቅ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በምትሠራው ነገር ሁሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ጠላቶችህ እስኪያጠፉህ ድረስ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በአንተ ላይ ይኖራል”
እዚህ ጋ “እኔን” የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው።
“በአንተ ላይ ይኖራል”
“በሽታና የሚያቃጥል ትኩሳት ያደክምሃል”። እነዚህ ሁሉ የሚያመለክቱት ሰዎች እንዲዳከሙና እንዲሞቱ የሚያደርጋቸውን በሽታ ነው።
“በዝናብ እጥረት”
በሰብል ላይ የሚበቅል ሻጋታ ሲሆን እንዲበሰብሱ ያደርጋቸዋል
ሙሴ በእስራኤላውያን ላይ ስለሚደርስባቸው ክፉ ነገሮች ሲናገር ከእስራኤላውያን በስተኋላ ሆነው በሚያሳድዱ ሰዎች ወይም እንስሶች አስመስሎ ይናገራል። አ.ት፡ “በእነርሱ ምክንያት ትሰቃያለህ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ዝናብ ስለማይኖር ሰማዩ እንደ ናስ እንደሚሆን ይናገራል። አ.ት፡ “ሰማይ -- ዝናብን አይሰጥም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ምድር ምንም ሰብል ስለማይበቅልባት እንደ ብረት እንደምትሆን ይናገራል። አ.ት፡ “መሬቱ ላይ ምንም ነገር አይበቅልም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እግዚአብሔር በዝናብ ምትክ አሸዋ አዘል ውሽንፍር ይልካል”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እስኪያጠፋህ ድረስ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ጠላቶችህን መትተው እንዲጥሉህ ያደርጋቸዋል”
ይህንን በዘዳግም 28፡7 ላይ እንዴት እንደተረግምከው ተመልከት።
ይህ ማለት እስራኤላውያን ፈርተውና ደንግጠው ከጠላቶቻቸው ይሸሻሉ። የቃላቶቹን ተመሳሳይነት በዘዳግም 28፡7 ውስጥ ተመልከት። (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በብዙ የተለያዩ አቅጣጫዎች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሌሎች ሀገራት ሰዎች ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ያባርሯችኋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ግብፃውያንን በረገምኩበት በዚያው የቆዳ በሽታ”
እነዚህ ልዩ ልዩ ዓይነት የቆዳ በሽታዎች ናቸው።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማንም ሊፈውስህ የማይችለውን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በእኩለ ቀን እንኳን በዳበሳ እንደሚሄዱ እንደ ዐይነ ሥውራን ትሆናለህ”። እያንዳንዱ በሕይወቱ በሚደሰትበት ጊዜ እንኳን እስራኤላውያን አስቸጋሪ ሕይወት ይኖራቸዋል። (See: Simile)
“የበረቱ ሕዝቦች ሁልጊዜ ይጨቁኑሃል፣ ይዘርፉሃልም”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው በሬህን ሲያርደው ታያለህ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው አህያህን በጉልበት ይወስድብሃል፣ አይመልስልህምም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በጎችህን ለጠላቶችህ እሰጣቸዋለሁ” ወይም “ጠላቶችህ በጎችህን እንዲወስዱ እፈቅድላቸዋለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ለሌሎች ሕዝቦች እሰጣቸዋለሁ” ወይም “ጠላቶችህ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይወስዷቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዐይኖችህ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “እነርሱን በመጠባበቅና ዳግመኛ ልታያቸው በመናፈቅ ትደክማለህ” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “ብርታት በእጅህ ላይ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው ኃይልን ነው። አ.ት፡ “ስለጉዳዩ አንዳች ለማድረግ ኃይል አይኖርህም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ሀገር” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሀገሩ ሕዝብ ማለት ነው። አ.ት፡ “የሀገሩ ሕዝብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“የተጨቆንክ” እና “የተረገጥክ” የሚሉት ቃላት መሠረታዊ ትርጉማቸው አንድ ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሁልጊዜ ይጨቁኗችኋል፣ ይረግጧችኋልም” ወይም “ባለማቋረጥ ይጨቁኗችኋል” (Doublet እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“የምታየው እንድታብድ ያደርግሃል”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማንም መፈወስ በማይችልበት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምስሌ” እና “መሳለቂያ” የሚሉት ቃላት በመሠረቱ ትርጉማቸው አንድ ነው። ይህ እንደ አዲስ ዐረፍተ ነገር ተደርጎ መተርጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በሚልክህ ስፍራ ሕዝቡ የጥላቻ፣ ስለ አንተም ምሳሌና መሳለቂያን ያደርጋል” ወይም “እግዚአብሔር ከጥላቻ የተነሣ ወደሚስቁብህና ወደሚቀልዱብህ ሕዝቦች ይልክሃል” (See: Doublet)
ሰዎች ሌሎችን ለማሳፈር የሚጠቀሙበት ቃል ወይም ሐረግ
“ነገር ግን በጣም ጥቂት ምግብ ታከማቻለህ”
ሰዎች የቆዳቸውን ጤና ለመጠበቅ የወይራ ዘይት ይቀቡ ነበር።
ፍሬው ከመብሰሉ በፊት እንደሚረግፍ ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “ፍሬው ከመብሰሉ በፊት የወይራ ዛፎችህ ፍሬአቸውን ያረግፋሉ” ወይም “የወይራው ፍሬዎች ከመብሰላቸው በፊት ከወይራ ዛፎችህ ላይ ይወድቃሉ” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ ማንነቱ የታወቀ መጻተኛ አይደለም፣ ነገር ግን በጥቅሉ መጻተኞችን ያመለክታል። አ.ት፡ “መጻተኞች የሆኑ -- እነርሱ -- ለእነርሱ” (See: Generic Noun Phrases)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ የሚለው ከእስራኤላውያን የበለጠ ኃይል፣ ገንዘብና ክብር መጻተኞች ይኖራቸዋል ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት መጻተኞች ከእስራኤላውያን የበለጠ ኃይልና ሥልጣን ይኖራቸዋል። በዘዳግም 28፡13 ተመሳሳዩን ሐረግ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እርግማኖችን በድንገት እንደሚያጠቃቸው ወይም አሳዶ እንደሚይዛቸው ሰው አድርጎ ይገልጻቸዋል። ተመሳሳዩን በዘዳግም 28፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንደዚህ በሚያስገርምህ መንገድ ይረግምሃል፣ ይህም እንደሚያሳድድህና ሳይረግምህ በማታመልጠው ሁኔታ ይሆናል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” የሚሉት ቃላት እግዚአብሔር ለሚናገረው ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። አ.ት፡ “አምላክህ እግዚአብሔር ለተናገረው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ትዕዛዝ” እና “ሥርዓት” የሚሉት ቃላት “እግዚአብሔር እንድታደርገው ያዘዘህን ሁሉ” ለሚለው ጥምረት ናቸው። (See: Doublet)
እዚህ ጋ “በደስታ” እና “በልብ ሐሴት” ማለት ትርጉማቸው አንድ ነው። ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለማምለክ እጅግ ደስ ይላቸው እንደነበረ አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Doublet)
x
ሁለቱም ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ጠላት ከእስራኤል እጅግ ሩቅ ከሆነ ሀገር እንደሚመጡ አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Doublet)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ስለ እርሱ ከማታውቀው ስፍራ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ጠላት በድንገት ስለሚመጣ እስራኤላውያን ሊያስቆሟቸው አይችሉም። (See: Simile)
“ሀገር” የሚለው ቃል የዚያን ሀገር ሕዝብ የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ቁጡ ፊት ያለው፣ አዛውንቶችን የማያከብርና ርኅራኄ የሌለው ሕዝብ ሀገር”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እስኪያጠፉህ ድረስ” ወይም “ምንም ነገር እስከማያስቀሩልህ ድረስ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የከተማ በሮች” የሚወክሉት ከተማን ነው። አ.ት፡ “ከተሞችህን” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “የወንድና የሴት ልጆችህን ሥጋ” የሚለው “የገዛ ሰውነትህን ፍሬ” የሚለውን ዘይቤአዊ አነጋገር ያብራራል። የጠላት ሰራዊት ከተማቸውን ከከበበ በኋላ ሕዝቡ የገዛ ልጆቻቸውን እስኪበሉ ድረስ ይራባሉ። (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Parallelism የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚናገረው በወላጆቻቸው ሰውነት የተመረቱ ፍሬዎች በሚመስሉበት ሁኔታ ስለ ልጆች ነው። አ.ት፡ “የገዛ ራሳችሁ ልጆች” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በመካከላችሁ ደግና በጣም ርኅሩኅ የሆነ ማነው? እርሱም እንኳን--”። ሙሴ የሚለው፣ አንድ ሰው ልጆቻቸውን ይበላሉ ብሎ የሚገምታቸው ብቻ ሳይሆኑ የመጨረሻዎቹ ይሆናሉ ብሎ የሚገምታቸውም እንኳን እነርሱ ልጆቻቸውን ይበላሉ።
እዚህ ጋ “የከተማ በሮች” የሚወክሉት ከተሞቹን ራሳቸውን ነው። አ.ት፡ “ከተሞችህ በሙሉ” (See: Synecdoche)
x
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኔ የጻፍኩትን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ስም” የተባለው ፈሊጣዊ አነጋገር ራሱን እግዚአብሔርን ያመለክታል። አ.ት፡ “ታላቅና አስፈሪ የሆነው አምላክህ እግዚአብሔር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እግዚአብሔር በአንተና በዘርህ ላይ አስከፊ መቅሰፍት ይልካል” ወይም “እግዚአብሔር አንተንና ዘሮችህን በአስከፊ መቅሰፍቶች እንድትሰቃዩ ያደርጋል”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንደገና በግብፅ በሽታዎች እንድትሰቃይ ያደርግሃል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በሽታዎቹ አያቆሙም፣ ደግሞም ማንም ከእነርሱ ሊያድንህ አይችልም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እያንዳንዱ” በአጠቃላይ ሲሆን “ብዙ” ማለት ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኔ ያልጻፍኳቸው ሌሎች ህመሞችና መቅሰፍቶች እንኳን” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት፣ አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እስኪያጠፋህ ድረስ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ ቡድን አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” የሚልበት አገባብ ሁሉ ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
ይህ ማለት ባለፈው ጊዜ ብዙ እስራኤላውያን ነበሩ። (See: Simile)
እዚህ ጋ “የእግዚአብሔር ድምፅ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚያመለክተው እግዚአብሔር የሚናገረውን ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ለሚናገረው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ ቡድን አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” የሚልበት አገባብ ሁሉ ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“እግዚአብሔር ለእናንተ መልካም በማድረግና እንድትበዙ በማድረግ ተደስቶ ነበር"
“እንድትሞቱ በማድረግ ደስ ይለዋል”
ሕዝቡ ፍራፍሬ የሆኑ ይመስል እግዚአብሔር እንደ ቁጥቋጦ እንደሚነቅላቸው ለመናገር ሙሴ ዘይቤአዊ አነጋገርን ይጠቀማል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ልትወርሱ ከምትገቡባት ምድር ያስወግዳችኋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ ቡድን አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ እዚህ ጋ “አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት ብዙ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
እነዚህ ሁለት ጽንፎች በአንድነት በምድር ላይ በሁሉም ስፍራ ማለት ነው። አ.ት፡ “በምድር ሁሉ” ወይም “በምድር ሁሉ ላይ” (See: Merism)
እዚህ ጋ “ለእግርህ መርገጫ” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “የምታርፍበት ቋሚ ቤት ስለማይኖርህ ባለማቋረጥ ትቅበዘበዛለህ” (See: Synecdoche)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንድትፈራ፣ ተስፋ እንዳይኖርህና እንድታዝን ያደርግሃል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ትኖር ወይም ትሞት እንደሆነ አታውቅም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ከሚሰማህ ፍርሀት የተነሣ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዐይኖች” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “እንድታያቸው የማስገድድህን አስፈሪ ነገሮች” (See: Synecdoche and Assumed Knowledge and Implicit Information)
x
1 እግዚአብሔር በኮሬብ ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞዓብ ምድር ከእስራኤላውያን ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው የኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው። 2 ሙሴ እስራኤላውያንን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እግዚአብሔር በግብፅ በፈርዖን፥ በሹማምንቱ ሁሉና በመላ አገሩ ያደረተውን ሁሉ ዐይኖቻችሁ አይተዋል። 3 እነዚያን ከባድ ፈተናዎች ታምራዊ ምልክቶችና ታላቅ ድንቆች በገዛ ዐኖቻችሁ አይታችኋል። 4 ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር የሚያስተውል አእምሮ ወይም የሚያይ ዐይን ወይም የሚሰማ ጆሮ አልሰጣችሁም። 5 በምድረ በዳ በመራኋችሁ በእነዚያ አርባ ዓመታት ውስጥ ልብሳችሁ አላረጀም፥ የእግራችሁም ጫማ አላለቀም፥ 6 ቂጣ አልበላችሁም፥ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንህ ታውቁ ዘንድ ነው። 7 ወደዚህ ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ የሐሴንቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው። 8 ምድራቸውንም ወስደን ለሮቤላውያን ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠን። 9 እንግዲህ የምታደርጉት ሁሉ እንዲከናወንላችሁ፤ የዚህ ኪዳን ቃሎች በጥንቃቄ ተከተሉ። 10 እናንተ ሁላችሁ መሪዎቻችሁና አለቆቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁና ሹሞቻችሁ እንዲሁም ሌሎች የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል፤ 11 ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ እንጨታችሁን እየፈለጡ ውሃዎቻችሁንም እየቀዱ በሰፈራችሁ የሚኖሩ መጻተኞችም አብረአችሁ ቆመዋል። 12 እዚህ የቆማችሁ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ከእናንተ ጋር ወደ ሚያደርገውና በመሐላ ወደሚያጸናው ኪዳን፥ከእግዚአብሔር ከአምላካችሁ ጋር ትገቡ ዘንድ ለእናንተ በሰጣችሁ ተስፋና፥ 13 ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት እርሱ አምላካችሁ ይሆን ዘንድ እናንተም ሕዝቡ መሆናችሁን በዛሬው ዕለት ለማረጋገጥ ነው። 14 እኔም ይህ የቃል ኪዳን የማደርገው ከእናንተ ጋር ብቻ አይደለም፤ 15 አብራችሁን በእግዚአብሔር በአምላካችን ፊት እዚህ ከቆማችሁት ጋር ብቻ ሳይሆን ዛሬ እዚህ ከሌሉትም ጋር ነው። 16 በግብፅ ምድር እንዴት እንደኖርንና ወደዚህ ስንመጣም በየአገሮቹ ውስጥ እንዴት እንዳለፍን ራሳችሁ ታውቃላችሁ። 17 በመካከላቸውም አስጸያፊ ነገሮቻቸውን፦ የእንጨትና የድንጋይ፥ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል፤ 18 የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከእግዚአብሔር ከአምላካችን የሚመልስ ወንድ፥ ሴት፥ቤተ ሰብ፥ ወይም ጎሣና ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ አይገኙ፤ ከመካከላችሁ እንዲህ ያለውን መራራ መርዝ የሚያወጣ ሥር እንዳይኖር ተጠንቀቁ። 19 እንዲህ ያለው ሰው የዚህን ቃል ኪዳን በሚሰማበት ጊዜ በልቡ ራሱን በመባረክ፦ እንደ ልቤ ግትርነት ብመላለስም እንኳ ሰላም አለኝ ብሎ ያስባል። ይህም እርጥቡን ከደረቁ ጋር ያጠፋል። 20 እግዚአብሔር ለዚህ ሰው ፈጽሞ ምሕረት አያደርግለትም፥ ቁጣውና ቅናቱ በእርሱ ላይ ይነድበታል፤ በዚህ መጽሐፍ የተጸፉት ርግማን ሁሉ ይወርድበታል፤ እግዚአብሔርም ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል። 21 በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የኪዳኑ ርግማን መሠረት እግዚአብሔር እርሱን ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ለጥፋት ይለየዋል። 22 የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሩቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና እግዚአብሔር ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ፤ 23 ምድሩቱ በሙሉ የተቃጠለ ጨውና ዲን ዐመድ ትሆናለች፤ አንዳች ነገር አይተከልባት፤ ምንም ነገር አያቆጠቁጥባትም። የሚያድግ ተክል አይገኝባትም። የምደርስባት ውድመት እግዝክአብሔር በታላቅ ቁጣ እንደ ገለባበጣቸው እንደሰዶምና ገሞራ እንደ አዳማና ሊባዮ ጥፋት ይሆናል። 24 አሕዛብም ሁሉ፤ እግዚአብሔር በዚች ምድር ላይ ይህን ለምን አደረገባት? ይህ አስፈሪና የሚነድ ቁጣስ ለምን መጣባት? ብለው ይጠይቃሉ። 25 ሕዝቡም እንዲህ ይላሉ፦ የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር ያወጣቸውንና ከእነርሱም ጋር ያደረጉትን ቃል ኪዳን ሕዝቡ ስለ ተዉ ነው፤ 26 ወጥተውም የማያውቋቸውን እርሱም ያላዘዛቸውን ሌሎችን አማልክት ስለአመለኩአቸውና ስለሰገዱላቸውም ነው። 27 ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ የተጸፈውን ርግማን ሁሉ እስኪያመጣባት ድረስ የእግዚአብሔር ቁጣው በዚህች ምድር ላይ ነደደ። 28 እግዚአብሔር በታላቅ አስፈሪነት፥በቁጣና በንዴት ከምድራቸው ነቀላቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው የሚል ይሆናል። 29 ምስጢር የሆነው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ ለዘላለም እንድንተገብረው ዘንድ የኛና የልጆቻችን ነው።
ይህ ሙሴ የሚናገረውን ቃል ያመለክታል።
ይህ እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር ከመግባታቸው በፊት ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ የቆዩበት ስፍራ ነው። “በሞዓብ ምድር እያሉ”
እነዚህ ተጨማሪ ትዕዛዛት በአዲሱ ምድራቸው በሚቀመጡበት ጊዜ ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ኪዳን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲያደርጉት የተሰጣቸው ነበር። እነዚህ አዲስ ትዕዛዛት የሌላ ቃል ኪዳን ሳይሆኑ በመጀመሪያው ኪዳን ላይ ተጨማሪዎች ነበሩ።
እግዚአብሔር ያደረገውንና እነርሱም ያዩትን እንዲያስታውሱ እግዚአብሔር ይጠብቅባቸዋል። እዚህ ጋ “ዐይኖች” ሙሉውን ሰው የሚወክሉ ሲሆኑ ሰውየው ባየው ነገር ላይ አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ያደረገውን እንድታዩና እንድታስታውሱ እርሱ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል። (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “ዐይኖች” ያዩትን እንዲያስታውሱ እግዚአብሔር እንደሚጠብቅባቸው አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “ሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ መሰቃየቱን እራሳችሁ አይታችኋል” (See: Synecdoche)
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “የአንተ” የሚለው ቃል እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“ምልክቶች” እና “ድንቆች” የሚሉት ቃላት ሁለቱም የሚያመለክቱት እግዚአብሔር በግብፅ ላይ የላካቸውን መቅሰፍቶች ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ኃይለኛ ነገሮች ሁሉ” (See: Doublet)
ሕዝቡ ልብ፣ ዐይንና ጆሮ አላቸው። ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ካዩትና ከሰሙት እግዚአብሔር ማን እንደሆነ፣ እንዴት እና ለምን እርሱን መታዘዝ እንደሚኖርባቸው እንዲያስተውሉ አላደረጋቸውም ይላል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ማስተዋል እንድትችሉ አድርጓችኋል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህን ስሞች በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
እዚህ ጋ “በእኛ ላይ” የሚያመለክተው ሙሴንና የእስራኤልን ሕዝብ ነው። (See: Inclusive “We”)
እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚሉት ተመሳሳይ ነገር ሲሆን ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መታዘዝ እንዳለባቸው አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “የዚህን ቃል ኪዳን ቃሎች ሁሉ ታዘዙ” (See: Parallelism)
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ’ እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥር ናቸው። (See: Forms of You)
በእስራኤላውያን መካከል ብዙ መጻተኞች ነበሩ። አ.ት፡ “በሰፈርህ ውስጥ በመካከልህ የሚኖሩ መጻተኞች፣ ከእነርሱ እንጨት የሚቆርጡልህ ውሃ የሚቀዱልህ” (See: Generic Noun Phrases)
“በቃል ኪዳኑ ልትስማማ እና አምላክህ እግዚአብሔር የሚያዝህን ሁሉ ለመታዘዝ እንድትምል”
“ለእርሱ ብቻ የሚሆን የሕዝብ ወገን”
x
እዚህ ጋ “ልብ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ሲሆን “መመለስ” ማለት መታዘዝን ማቆም ነው። አ.ት፡ “ከእንግዲህ አምላካችንን እግዚአብሔርን የማይታዘዝ” (See: Synecdoche)
ሙሴ በድብቅ ሌላ አምላክ ስለሚያመልክ ሰው ሲናገር እርሱን እንደ ሥር እና ያንን አምላክ ለማገልገል የሚሠራውን ክፉ ሥራና ሌሎችም እንዲያደርጉት የሚያበረታታውን ሰዎችን እንደሚመርዝ መራራ እጽዋት ቆጥሮ ይናገራል።(ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በቁጥር 18 የተገለጸው ሰው ነው።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ራሱን እንኳን ደስ ያለህ የሚል” ወይም “ራሱን የሚያበረታታ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን ለመታዘዝ እምቢ እያልኩኝም እንኳን” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እርጥብ” እና “ደረቅ” የሚሉት ቃላት ጻድቅና ክፉ የሆኑትን ሰዎች የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። ይህ “እያንዳንዱን” የሚል ጥምረት ይፈጥራል። አ.ት፡ “ይህ እግዚአብሔር በምድሪቱ የሚኖሩትን ጻድቅና ክፉ የሆኑትን ሁለቱንም ዓይነት ሰዎች እንዲያጠፋቸው ያደርገዋል” (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Merism የሚለውን ተመልከት))
እነዚህ ስማዊ ቅጽሎች እንደ ስም ሊተረጎሙ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ ምድሪቱ ደረቅ ስለምትሆንና ሰዎች ሰብላቸው እንዲበቅል ዝናብ ስለሚፈልጉ እነዚህ ቃላት “ሕያው - ምውት” ወይም “ጥሩ -- መጥፎ” ለሚሉት ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው። አ.ት፡ “እርጥብ ነገሮች -- ደረቅ ነገሮች” ወይም “ጥሩ ሰዎች -- መጥፎ ሰዎች” (ስማዊ ቅጽል እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ልክ እሳት በኃይል እንደሚነድ የእግዚአብሔር ቁጣና ቅንዓትም በኃይል ሊነድ ይችላል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር የቅንዓቱ ቁጣ እንደ እሳት ይግላል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ቅንዓት” የሚለው ቃል “የእግዚአብሔርን ቁጣ” ያብራራል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር የቅንዓቱ ቁጣ” (See: Hen- diadys)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኔ የጻፍኩትን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እርግማኖቹን በድንገት በሚያጠቃቸው ሰው መስሎ ይገልጻቸዋል። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 28፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት እግዚአብሔር ሰውየውንና ቤተሰቡን ፈጽሞ ያጠፋቸዋል። ወደፊት ሰዎች አያስታውሱትም። በዘዳግም 7፡24 ላይ ተመሳሳይ ሐረግ ይታያል።
“ከእናንተ በኋላ -- ልጆቻችሁ” የሚሉት ቃላት “የሚመጣው ትውልድ” ማን መሆኑን ይናገራሉ።
“እግዚአብሔር የከነዓንን ምድር በመቅሰፍትና በበሽታ እንዴት እንደረገማት”
ሰዎች መሬቱ ምንም ነገር እንዳያበቅል ዲንና ጨው ያደርጉበታል። “እግዚአብሔር ምድሪቱን በዲንና በጨው እንዳቃጠላት በሚያዩበት ጊዜ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማንም ዘር ሊዘራበት የማይችልበትና ሰብሉ ፍሬ የማያፈራበት ስፍራ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ተገለበጡ” የሚለው የነገር ስም እንደ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ፈጽሞ እንዳጠፋቸው ጊዜ”
እነዚህ እግዚአብሔር ከሰዶምና ገሞራ ጋር ያጠፋቸው ከተሞች ስሞቻቸው ናቸው።(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆኑት “ንዴት” እና “ቁጣ” በመሠረቱ ትርጉማቸው አንድ ነው፣ በመሆኑም እንደ ቅጽላዊ ሐረግ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በጣም በተቆጣ ጊዜ” (See: Doublet)
ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከሌሎች ሀገራት ሁሉ ጋር በመሆን እግዚአብሕር በምድሪቱ ላይ ይህንን ለምን እንዳደረገና ይህ የቁጣው ግለትስ ትርጉሙ ምንድነው በማለት ይጠይቃሉ” (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
“ዘሮቻችሁና የሌሎች ሀገራ ሰዎች ሁሉ -- ይላሉ”
ጸሐፊው በሁለት ቃላት አማካይነት የሚያስተላልፈው አንድ አሳብ ነው። አ.ት፡ “የዚህ አስፈሪ ቁጣ ትርጉሙ ምንድነው?” (See: Hendiadys)
ይህ “እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህንን ያደረገው ለምንድነው?” ለሚለው መልስ ነው (ዘዳግም 29፡24)። “እስራኤላውያን የቃል ኪዳኑን ተስፋና ሕግ ስላልተከተሉ እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ ይህንን አድርጓል”
“ሌሎች አማልክትን ታዘዙ፣ አመለኳቸውም”
ሙሴ የእግዚአብሔርን መቆጣት ከአንድ እሳት ከሚለኩስ ሰው ጋር ያነጻጽራል። ይህ እግዚአብሔር እርሱን የሚያስቆጣውን የትኛውንም ነገር ስለሚያጠፋበት ኃይሉ አጽንዖት ይሰጣል፤ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር አይችልም። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ በጣም ተቆጥቷል” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድር” ሕዝቡን የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ያመጣባቸው ዘንድ የዚህ ምድር ሰዎች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኔ የጻፍኩትን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እስራኤል እግዚአብሔር ከአትክልት ስፍራ ነቅሎ ከጣለው መጥፎ ተክል ጋር ተነጻጽሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ከምድራቸው አስወግዷቸዋል -- እንዲሄዱም አስገድዷቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በመሠረቱ “ንዴት”፣ “ቁጣ” እና “መዓት” የሚሉት ቃላት ትርጉማቸው ተመሳሳይ ሲሆን በእግዚአብሔር ቁጣ ታላቅነት ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “እጅግ ታላቅ በሆነ ቁጣው” ወይም “እጅግ ስለተቆጣ” (See: Doublet)
“አምላካችን እግዚአብሔር ያልገለጣቸውና እርሱ ብቻ የሚያውቃቸው አንዳንድ ነገሮች”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እርሱ የገለጣቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
x
1 በፊታችሁ ያስቀመጥሁት ይህ በረከትና መርገም ሁሉ በእናንተ ላይ ሲመጣና አምላካችሁ እግዚአብሔር በትኖአችሁ ከምትኖሩበት አሕዛብ መካከል ሆናችሁ፤ 2 ወደ ልባችሁ ተመልሳችሁ ነገሮቹን በምታስተውሉበት ጊዜ፥ እንዲሁም ዛሬ እኔ በማዝዛችሁ ሁሉ መሠረት እናንተና ልጆቻችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመልሳችሁ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እርሱን ስትታዘዙ፤ 3 እግዚአብሔር አምላካችሁ ምርኮአችሁን ይመልስላችኋል፤ ይራራላችሁማል፤ እናንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከል እንደ ገና ይሰበስባችኋል። 4 ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ብትጋዙ እንኳ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከዚያ ይሰበስባችኋል፤ መልሶም ያመጣችኋል። 5 የአባቶቻችሁ ወደ ሆነችው ምድር ያመጣችኋል፤ እናንተም ትወርሱታላችሁ፤ ከአባቶቻችሁ ይበልጥ ያበለጽጋችኋል፤ያበዛችሁማል። 6 እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እንድትወዱት፤በሕይወትም እንድትኖሩ እግዚአብሔር አምላካችሁ የእናንተንና የዘራችሁን ልብ ይገርዛል። 7 አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህን ርግማን ሁሉ በሚጠሉአችሁና በሚያሳድዱአችሁ ጠላቶቻችሁ ላይ ያደርገዋል። 8 እናንተም ተመልሳችሁ ለእግዚአብሔር ትታዘዛላችሁ፥ ዛሬ እኔ የማዛችሁን ትእዛዛ ሁሉ ትጠብቃላችሁ። 9 በዚያም እግዚአብሔር በእጃችሁ ሥራ ሁሉን በወገባችሁ ፍሬ በእንስሳታችሁ፥ ግልገሎችና በምድራችሁ ሰብል እጅግ ያበለጽጋችኋል። በአባቶቻችሁ ደስ እንደ ተሰኘ ሁሉ እግዚአብሔር እናንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋልና። 10 ይህም የሚሆነው አምላካችሁን እግዚአብሔርን ከታዘዛችሁና በዚህ የሕግ መሕሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን በመጠበቅ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ስትመለሱ ነው። 11 ዛሬ የምሰጣችሁ ትእዛዝ ይህን ያህል አስቸጋሪ ወይም ከእናንተ የራቀ አይደለም። 12 እንድንፈጽሙት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? እንዳትሉ በሰማይ አይደለም። 13 ደግሞም እንድናደርገው አምጥቶ ይነግረን ዘንድ ማን ባሕሩን ይሻገራል? እንዳትሉም ከባሕር ማዶ አይደለም። 14 ነገር ግን ቃሉ ለእናንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ታደርጉትም ዘንድ በአፋችሁና በልባችሁ ውስጥ ነው። 15 እነሆ ዛሬ ሕይወትንና በረከትን፥ ሞትንና ጥፋትን በፊታችሁ አኑሬአለሁ። 16 እግዚአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱ በመንገዱም እንድትሄና ትእዛዙን፥ ሥርዓቱንና ሕጉን እንድትጠብቁ አዝዛችኋል፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ ትበዛላችሁም፤ አምላካችሁም ትወርሱአት ዘንድ በምትገቡበት ምድር ይባርካችህኋል። 17 ዳሩ ግን ልባችሁን ወደ ኋላ በመለሰና ባትታዘዙ ለሌሎች አማልክት ለመስገድ ብትታለሉና ብታመልኩአችሁ፤ 18 በርግጥ እንደምትጠፉ እኔ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ትወርሱአት ዘንድ በምትገቡባት ምድር ብዙ አትኖሩባትም። 19 ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና ርግማንን በፊታችሁ እንዳስቀመጣችሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራችኋለሁ። እንግዲህ እናንተና ልጆቻችሁ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጡ፤ 20 ይኸውም እግዚአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱ ቃሉን እንድታደምጥና ከእርሱ ጋር እንድትጣበቁ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወታችሁ ነው፤ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለሕስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ ይሰጣችኋል።
እዚህ ጋ “እነዚህ ነገሮች” የሚያመለክቱት በምዕራፍ 28 – 29 የተዘረዘሩትን በረከቶችና እርግማኖች ነው። “በመጡብህ” የሚለው ቃል የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙ ሲደርስብህ ማለት ነው። አ.ት፡ “እነዚህ ነገሮች ሁሉ በሚደርሱብህ ጊዜ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በፊት ለፊታቸው ያስቀመጠው ዕቃ ይመስል መልኩ ሙሴ ለሕዝቡ ስለ ነገራቸው በረከቶችና እርግማኖች ይናገራል። አ.ት፡ “አሁን ስለነገርኳችሁ ጉዳይ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አስታውሳቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“በሌሎች ሕዝቦች ውስጥ በምትኖርበት ጊዜ”
“እንድትሄድ አስገድዶሃል”
እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚያመለክተው እግዚአብሔር የሚናገረውን ነው። አ.ት፡ “እርሱ የሚለውን ታዘዝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት የሚያመለክቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች በአንድ ላይ “ፍጹም” ወይም “በቅንነት” ለማለት ጥቅም ላይ ውለዋል። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)
“ከምርኮኝነት ነጻ ያወጣሃል”። የነገር ስም የሆነው “ምርኮኝነት” እንደ ግሳዊ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከማረኩህ ከእነርሱ ነጻ ያወጣሃል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
“እነዚያ የተማረኩት ሰዎችህ እጅግ ሩቅ በሆነ ስፍራ የሚኖሩ ቢሆኑም እንኳን”
“ከጠፈር በታች” ወይም “በምድር ላይ”
ይህ በቀጥታ ሥጋን ማስወገድ አይደለም። ይህ ማለት እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ያስወግዳል፣ እርሱን እንዲወዱትና እንዲታዘዙትም ያስችላቸዋል ማለት ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ልብ” እና “ነፍስ” የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት የሚያመለክቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። እነዚህ ሁለቱ ሐረጎች በአንድ ላይ “ፍጹም” ወይም “በቅንነት” ለማለት ጥቅም ላይ ውለዋል። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Doublet የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ድምፅ” ማለት እግዚአብሔር የሚናገረውን ማለት ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የሚናገረውን ታዘዝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እርግማኖቹን አንድ ሰው በሌላው አናት ላይ ሊያደርግ እንደሚችለው ሸክም ወይም መሸፈኛ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ጠላቶችህ በእነዚህ እርግማኖች ምክንያት እንዲሰቃዩ ያደርጋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “በምትሠራው ሥራ ሁሉ” (See: Synecdoche)
እነዚህ ሦስት ሐረጎች “በልጆች -- በጥጆች -- በሰብሎች” ለሚለው የአነጋገር ዘይቤ ናቸው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 28፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
አንድ ሰው ቁሳዊ አካል ላይ ሊደርስ እንደሚችል ሁሉ ትዕዛዛቱ አንድ ሰው እንዲያደርግ የሚፈልገውን ከትዕዛዛቱ መረዳት እንደሚቻል ሙሴ ይናገራል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚፈልግብህን ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ አይሆንብህም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ሙሴ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄን በመጠቀም የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለማወቅ በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው ማሰባቸው ላይ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ ጥያቄ እንደ ንግግር ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለመማር ወደ ሰማይ መጓዝ አለበት፣ ከዚያም ልንታዘዛቸው እንችል ዘንድ ምን እንደ ሆኑ ሊነግረን መመለስ አለበት” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ማወቅ በጣም አስቸጋሪ ነው ብለው የሚያስቡበትን አሳብ ይቀጥላል። ይህ ጥያቄ እንደ ንግግር ሆኖ ሊተርጎም ይችላል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ለመማር አንድ ሰው ባህሩን አቋርጦ መጓዝ ከዚያም ተመልሶ ምን እንደሆኑ ሊነግረን ያስፈልጋል” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ሕዝቡ ቀደሞውኑ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ያውቃሉ፣ ለሌሎችም ሊነግሯቸው ይችላሉ። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
አንድን ነገር ሌላው ሰው ሊያይ በሚችልበት ማስቀመጥ ስለ አንድ ነገር ለአንድ ሰው የመንገር ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ስለ ጉዳዩ ነግሬሃለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ግልጽ ያልሆነውን መረጃ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “መልካም የሆነውንና በሕይወት እንድትኖር የሚያደርግህን፣ ክፉ የሆነውንና እንድትሞት የሚያደርግህን” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
በቁጥር እጅግ መጨመር
እዚህ ጋ “ልብ” የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ለእግዚአብሔር ያለህን ታማኝነት ብታቆም -- እና በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች እንድትሰግድና ሌሎች አማልክትን እንድታመልክ ቢያባብሉህ” (Synecdoche እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
x
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሙሴ ለሚናገረው ምስክሮች እንዲሆኑ በሰማይና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ይጠራል ወይም 2) ሙሴ እንደ ሰዎች ቆጥሯቸው ለሰማይና ለምድር ይናገራል፣ እርሱ ለሚናገረው ምስክሮች እንዲሆኑም ይጠራቸዋል። (See: (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት and Personification and Apostrophe)
“ክፉ ነገሮችን ስለማድረግህ ለመናገር ፈቃደኛ እንዲሆን”
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ ቡድን አድርጎ ይናገራል። (See: Forms of You)
እዚህ ጋ “ድምፅ” እግዚአብሔር የሚናገረውን ያመለክታል። አ.ት፡ “እርሱ የሚለውን ታዘዝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በእርሱ ላይ እንድትተማመን”
እነዚህ ሐረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸውና እግዚአብሔርን የሚገልጹ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ሲሆኑ ሕይወትን የሚሰጥና የሰዎችን የሕይወት ዘመን የሚወስን እርሱ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ረጅም ሕይወት እንድትኖር የሚያስችልህ እግዚአብሔር ብቻ ነው” (Doublet እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሞላላው ሊሞላ ይችላል። አ.ት፡ “ለአባቶቻችሁ ሊሰጣችሁ ምሏል” (See: Ellipsis)
1 ሙሴም ወጥቶ እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል በሙሉ ነገራቸው። 2 እንዲህም አላቸው፦ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል ከእንግዲህ መወጣትና መግባት አልችልም፤ እግዚአብሔርም ዮርዳኖስን አትሻገርም ብሎኛል፥ 3 እግዚአብሔር አምላካችሁ ራሱ በፊታችሁ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊታችሁ ያጠፋቸዋል፤ እናንተም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው፤ ኢያሱም እናንተን ቀድሞ ይሻገራል። 4 እግዚአብሔር የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው እነዚህንም ያጠፋቸዋል። 5 እግዚአብሔር እነርሱን በፊታችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ያዘዝኋችሁን ሁሉ በእነርሱ ላይ ታደርጋላችሁ። 6 ብርቱና ደፋር ሁኑ፥ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡል አላቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንት ጋር ይሄዳልና አይተዋችሁም አይጥላችሁምም። 7 ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ሊሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ከዚህ ሕዝብ ጋር አብረህ ስለምትገባ፤ ምድሪቱን ርስታችው አድርገህ ስለምታከፋፍል በርታ፤ ደፋርም ሁን። 8 እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ይሄዳል፤ ከአንተም ጋር ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አተውህምም አትፍራ ተስፋም አትቁረጥ። 9 ሙሴም ይህን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት ለሚሸከሙ፥ ለሌዊ ልጆች፤ ለካህቱና ለእስራኤል አለቆች ሁሉ ሰጠ። 10 ከዚያም በኋላ ሙሴ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ዕዳ በሚተውበት የዳስ በዓልም በሚከበርበት በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ 11 እስራኤል ሁሉ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ሲታይ ይህ ሕግ በእነርሱ ፊት በጆሮአቸው ታነባቸዋላችሁ። 12 እነርሱም ይስሙና አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት ይማሩ ዘንድ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ በጥንቃቄ እንዲከተሉ ሕዝቡን ይኸውም ወንዶችን፥ ሴቶችንና ልጆቻቸሁንና በከተሞቻችሁን የሚኖረውንም መጻተኛ ሰብስቡ። 13 ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸሁም መስማትና አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት ሊማሩ ይገባቸዋል። 14 እግዚአብሔር ሙሴን እነሆ የምትሞትበት ቀን ቀርቦአል፥ ትእዛዝ እንድሰጠው ኢያሱን ጥራውና ወደ መገናኛው ድንኳንም ቅረቡ። 15 እግዚአብሔር በድንኳኑ ላይ በደመና ዐምድ ተገለጠ፤ የደመናውም ዐምድ ከድንኳኑ ደጃፍ ላይ ቆመ። 16 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ እነሆ ከአባቶቻችሁ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል፤ እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ። 17 በዚያም ቀን ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ይነዳል፤ እተዋቸዋለሁም። ፊቴንም ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያም ቀን ይህ ጥፋት የደረሰሰብን አምላካችን ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን? ይላሉ። 18 ወደ ባዕዳን አማልክት በመዞር በፈጸሙት ክፋታቸው የተነሣ በዚያን ቀን ፊቴን ከእነርሱ ፈጽሞ እሰውራለሁ። 19 እንግዲህ ይህን መዝሙር ለራሳችሁ ጻፉና ለእስራኤል ልጆች አስተምሩ። ስለ እኔ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ እንዲዘምሩ አድርጉ። 20 ወተትና ማር ወደምታፈሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር ባመጣሃቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፥ ከበለጸጉም በኋላ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ። 21 ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዛሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸውም አፍ የሚረሳ አይሆንም፤ ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ አውቃለሁ። 22 ስለዚህም ሙሴ ይህን መዝሙር በዚያን ቀን ጻፈና እስራኤላውያንን አስተማራቸው። 23 እግዚአብሔርም ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በር ደፋር ሁን፤ የእስራኤልን ልጆች በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ታስገባቸዋለህና እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ በማለት ትእዛዝ ሰጠው። 24 ሙሴ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የዚህን ሕግ ቃል በመጽሐፍ ጽፎ እንዳበቃ፤ 25 የእስራኤልን የኪዳን ታቦት የሚሸከሙ ሌዋውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ 26 ይህን የሕግ መጽሐፍ ውሰዱ፤ በዚያም በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት። 27 ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆናችሁ አውቃለሁ፥ተመልከቱ እኔ ዛሬ በሕይወት ከእናንተ ጋር እያለሁ እንኳን በእግዚአሔር ላይ እንደህ ካመፃችሁ ከሞትሁ በኋላማ እንዴት አታደርጉም? 28 ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ ጠርቼባቸው ይህን ቃል ይሰሙ ዘንድ ብጆሮኣቸው እንድናገር ፤ የነገድ አለቆቻችሁን በሙሉና ሹሞቻችሁን ሁሉ በፊቴ ሰብስቡ። 29 እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ አውቃለሁና። በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፤ ይህ የሚሆነው እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ለቁጣ ስለምታነሣሡት በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል። 30 ሙሴ የዚህን መዝሙር ቃል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ለተሰበሰበው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በጆሮአቸው አሰማ።
“120 ዓመት ዕድሜ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “መውጣት” እና “መግባት” የተሰኙ ሁለት ጽንፎች በአንድ ላይ አንድ ጤነኛ ሰው ሊያደርግ የሚችለውን ሙሴ ከእንግዲህ ማድረግ አይችልም ማለት ነው። (See: Merism)
ሙሴ እስራኤላውያኑን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
“ምድራቸውን ትወስዳለህ”
“እግዚአብሔር ቃል እንደገባው ኢያሱ መርቶ ወንዙን ያሻግራችኋል”
እዚህ ጋ “ሴዎን” እና “ዐግ” ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታትና ሰራዊታቸውን ያመለክታል። እነዚህን ስሞች በዘዳግም 1፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “በአሞራውያን ነገሥታት በሴዎን፣ በዐግና በሰራዊቶቻቸው ላይ -- አደረገ” (See: Synecdoche)
ይህ ማለት የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ በዚያ ነበሩ ማለት ነው። አ.ት፡ “በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ብርቱና ደፋር ሁን”። ይህንን በዘዳግም 31፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ምድሪቱን እንዲወስዱ ትረዳቸዋለህ”
“ካህናት ለሆኑት ለሌዋውያኑ ሰጣቸው”
“7 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ዕዳን ለመሰረዝ”
የዚህ በዓል ሌሎች ስሞች፣ “የመገናኛው ድንኳን በዓል”፣ “የዳስ በዓል”፣ እና “የመሰብሰብ በዓል”። በመከር ጊዜ ገበሬዎች በመስኩ ላይ ጊዜያዊ መጠለያ ይሠሩ ነበር። ይህ በዓል የሚደረገው የዓመቱ መከር ከተሰበሰበ በኋላ ነበር። ይህንን በዘዳግም 16፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ሙሴ እስራኤላውያኑን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚለው ቃል እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
“መስማት ይችሉ ዘንድ”
“እኔ ለምነግርህ ትኩረት ስጥ”
ይህ በላይኛው ክፍል ቅርጽ የያዘ ጥቅጥቅ ያለ የጢስ ደመና ነበር
“እኔ ለምነግርህ ትኩረት ስጥ”
ይህ “ትሞታለህ” የማለት የትህትና አገላለጽ ነው። አ.ት፡ “ትሞትና ከአንተ በፊት ከሞቱት ቅድመ ቅድም አያቶችህ ጋር አብረህ ትሆናለህ” (See: Euphemism)
አመንዝራ መሆን ከእግዚአብሔር ሌላ ሌሎች አማልክትን ለማምለካቸው ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ለእኔ አለመታመን ይጀምራሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ቁጣውን እሳት ከሚለኩስ ሰው ጋር ያነጻጽራል። ይህ እርሱን የሚያስቆጣውን የትኛውንም ነገር በሚያጠፋ በእግዚአብሔር ኃይል ላይ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ቁጣዬን በእነርሱ ላይ አነድዳለሁ” ወይም “በእነርሱ ላይ እቆጣለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አልረዳቸውም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እውጣቸዋለሁ” ወይም “ጠላቶቻቸው እንዲውጡአቸው እፈቅድላቸዋለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ “ፈጽመው ጠፉ” ለሚለው ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ጥፋቱንና መከራውን እንደ ሰው መስሎ ይገልጻቸዋል። አ.ት፡ “ብዙ ጥፋትና መከራ ይደርስባቸዋል” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ጥፋቱንና መከራውን እንደ ሰው መስሎ ይገልጻቸዋል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “-- መካከል እነዚህ ጥፋቶች እያጠፉኝ ነው” (ሰውኛ እና ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“ከእንግዲህ እግዚአብሔር እየጠበቀን አይደለም” ወይም “እግዚአብሔር ለብቻችን ትቶናል”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንዲያሰላስሉትና እንዲዘምሩት አድርጋቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ብዙ ወተትና ማር የሚፈስባት ምድር” ወይም “ከብት ለማርባትና ለእርሻ ምርጥ የሆነች ምድር” ይህንን በዘዳግም 6፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እዚህ ጋ ክፋትና መከራ ሰብዓዊ ፍጥረት ሆነው ሰዎችን ሊያገኙ የሚችሉ መስለው ተገልጸዋል። አ.ት፡ “ይህ ሕዝብ ብዙ ክፋትና መከራ በሚገጥመው ጊዜ” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
መዝሙሩ እንደ ሰብዓዊ ፍጥረት ሆኖ በፍርድ ቤት ውስጥ በእስራኤል ላይ እንደሚመሰክር ይናገራል። (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ዘሮቻቸው በአፋቸው ውስጥ መጠበቃቸውን አይረሱም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ዘሮቻቸው በአፋቸው ውስጥ መጠበቅ እንዳለባቸው ያስታውሳሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በአፋቸው መርሳት” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ስለ እርሱ መናገርን ማቆም ማለት ነው። አ.ት፡ “ዘሮቻቸው ለእርስ በእርሳቸው ስለ እርሱ ከመናገር አያቆሙም”
ሰዎች ለማድረግ የሚያቅዱት እርሱ እንደ አካላዊ ቁስ ተደርጎ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “ለማድረግ የሚያቅዱት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ስለምድሪቱ የሰጠው ተስፋ ለእስራኤል ሕዝብ እንደሚሰጣቸው ነበር። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እሰጣቸዋለሁ ብዬ ተስፋ የሰጠዃቸው ምድር” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ብርቱና ደፋር ሁን” ይህንን በዘዳግም 31፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ሙሴ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለሌዋውያን ይናገራል፣ ስለዚህ “አንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
ሙሴ እንደ አንድ ሰው አድርጎ ለሌዋውያን ይናገራል፣ ስለዚህ “አንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
በዘዳግም 9፡6 ላይ “እልኸኛ” የሚለውን እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ ሕዝቡ እንዴት ያሉ አመጸኞች እንደነበሩ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እኔ ከሞትኩኝ በኋላ እንኳን በይበልጥ አመጸኛ ትሆናላችሁ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “በጆሮአቸው” ማለት ሕዝቡን ራሳችውን ማለት ነው። አ.ት፡ “የዚህ መዝሙር ቃሎች እነግራችው ዘንድ” (See: Synecdoche)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሙሴ ለሚናገረው ምስክሮች እንዲሆኑ በሰማይና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ይጠራል ወይም 2) ሙሴ እንደ ሰዎች ቆጥሯቸው ለሰማይና ለምድር ይናገራል፣ እርሱ ለሚናገረው ምስክሮች እንዲሆኑም ይጠራቸዋል። ተመሳሳይ ሐረግ በዘዳግም 30፡19 ላይ ይታያል።
“ሙሉ በሙሉ ስሕተት የሆነውን ታደርጋላችሁ”። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት፡
“የሰጠዃችሁን መመሪያ መከተል ታቆማላችሁ”። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 9፡12 እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው የእግዚአብሔርን ውሳኔ ወይም ምዘና ነው። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ውሳኔ ክፉ የሆነ” ወይም “እግዚአብሔር ክፉ ነው ብሎ የሚቆጥረውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጆቻችሁ” ማለት ሕዝቡን ራሳቸውን ማለት ነው። አ.ት፡ “በሠራችሁት ሥራ ምክንያት” (See: Synec- doche)
እዚህ ጋ “ጆሮዎች” የሚያመለክቱት ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ አሰማቸው” (See: Synec- doche)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ዘመረ” ወይም 2) “ተናገረ”
በውስጠ ታዋቂነት ያለውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እርሱን ያስተማረበትን የመዝሙሩን ቃላት” (See: Ellipsis)
1 ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ እኔም እናገራለሁ፤ ምድር ሆይ፥ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ። 2 ትምህርቴም እንደ ዝናብ ይውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፥ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ። 3 እኔ የእግዚአብሔርን ስም አውጃለሁ፤ የአምላካችንን ታላቅነት አወድሱ። 4 እርሱ ዐለትና ሥራውም ፍጹም፥ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው። የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፤ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው። 5 በእርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል። ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም። ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው። 6 እናንተ ተላላና ጥበብ የጎደላችሁ ሕዝብ፤ለእግዚአብሔር የምትመልሱለት በዚህ መንገድ ነውን? አባታችሁና ፈጣሪያችሁ የሠራችሁና ያበጃችሁእርሱ አይደለምን? 7 የጥንቱን ዘመን፥ የብዙ ዓመቶችን አስታውሱ፤ አባቶቻችሁን ጠይቁ ይነግሩማልም፥ ሽማግሌዎቻችንም ጠይቁ ያስረዱአችኋል። 8 ታላቁ አምላክ ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፤ በእስራኤል ልጆች ቁጥር ልክ፤ የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ። 9 የእግዚአብሔር ድርሻ የገዛ ሕዝቡ ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና። 10 እርሱን በምድረ በዳ፤ ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አግኘው፤እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው። 11 ንስር ጎጆዋን እንደትጠብቅ፤ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፥ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፥ እግዚአብሔር ክንፎቹን ዘርግቶ፥ ተሸከሞ ወሰዳቸው። 12 እግዚአብሔር ብቻ መራው ምንም ባዕድ አምላክ ከእርሱ ጋር አልነበረም። 13 በምድር ከፍታ ላይ አስኬደው፤ የእርሻንም ፍሬ መገበው፤ ከዐለት ድንጋይ ማር አበላው፤ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው። በወንድና በሴት ልጆቹ ተቆጥቶአልና። 14 የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወትት የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፤ የባሳንን ሙኩት በግ፤ መልካም የሆነውንም ስንዴ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ ጠጠህ። 15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ስብ ጠገበ፥ ሰውነቱ ደነደነ፥ ለሰለሰም። የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ የመጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀው። 16 በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፤ በአስፈያፊ ጣዖቶቻቸውም አስቆጡት። 17 አምላክ ላልሆኑ አጋንንት፥ ላላወቋቸው አማልክት፥ ከጊዜ በኋላ ለተነሡ አማልክት፥ አባቶቻችውም ላልፈሯቸው አማልክት ሠዉ። 18 አባት የሆናችሁን ዐለት ከዳችሁት፤ የወለዳችሁን አምላክ ረሳችሁ። 19 እግዚአብሔር ይህን አይቶ ተዋቸው፤ በወንድና በሴት ልጆቹ አስጥተውታልና። 20 እርሱም እንዲህ ብሎአል፦ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆንም አያለሁ፤ ጠማማ ትውልድ፤ የማይታሙንም ልጆች ናቸውና። 21 አምላክ ላልሆነው አስቀኑኝ፤ በከንቱ ጣዖቶቻቸውም አስቆጡኝ። እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋል፤ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣቸዋለሁ። 22 በቁጣዬ እሳት ተቀጣጥሎአልና፤እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነዳል፤ ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል። 23 በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ። ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እተኩሳለሁ። የሚያጠፋ ራብ፤በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድባቸዋለሁ፤ 24 የአራዊትን ሹል ጥርስ፥ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድባቸዋለሁ። 25 ሰይፍ መንገድ ላይ ያስቀራቸዋል፤ በመኝታቸውም ድንጋጤ ይነግሣል፤ጎልማሳውና ልጃገረዷ፤ ሕፃኑና ሽማግሌው ይጠፋሉ። 26 ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ፥ እበትናቸዋለሁም፤አልሁ፤ 27 ድል ያደረገው እጃችን ነው ብለው፥ ጠላቶቻቸው በስሕተት እንዳይታበዩ፥ የጠላት ማስቆጣት እንዳይሆን እሠጋለሁ። 28 እስራኤላውንም አእምሮ የጎደላቸው፤ ማስተዋልም የሌላቸው ናቸው። 29 አስተዋዮች ቢሆኑ ኖሮ ይህን በተገነዘቡና መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን ባስተዋሉ ነብር። 30 መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው እግዚአብሔር ካልተዋቸው በቀር፥ አንድ ሰው እንዴት ሺሁን ያሳድዳል፥ ሁለቱስ እንዴት አሥር ሺሁን እንዲሸሹ ያደጋሉ? 31 የእነርሱ መጠጊያ ዐለታቸው እንደ እኛ መጠጊያ ዐለት አለመሆኑን፤ ጠላቶቻችንም እንኳ አይክዱም። 32 ወይናቸው ከሰዶም ወይን ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤ የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፥ ዘለላቸውም መራራ ነው። 33 ወይናቸው የእባብ መርዝ፤ መርዙም የጨካኝ እባብ ነው። 34 ይህስ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፤ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? 35 በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፥ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቦአል፤ የሚመጣባቸውም ነገሮች ይፈጥንባቸዋል። 36 ኃይላቸው መድከሙን ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል። 37 እንዲህም ይላል፦ መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፤ አማልክታቸው ወዴት አሉ? 38 የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፤ የመጠጥ ቁርባናችውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው? እስቲ ይነሡና ይርዷችሁ! እስቲ መጠለያ ይስጧችሁ! 39 እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤እገድላለሁ፤ አድናለሁ፤አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም። 40 እጄን ወደ ሰማይ አነሣለሁ፤ ለዘላለምም ሕያው እንደ ሆንሁ እናገራለሁ።። 41 የሚያብራቀርቅ ሰይፌን ስዬ እጄ ለፍርድ ስይዘው፤ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ ለሚጠሉኝም እንደሥራቸው እከፍላቸዋለሁ። 42 ሰይፌ ሥጋ በሚበላበት ጊዜ፥ ፍላጾቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ደሙ የታረዱትና የምርኮኞች የጠላት አለቆችም ራስ ደም ነው። 43 አሕዛብ ሆይ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ይቤዣቸዋል። 44 ሙሴም ከነዌ ልጅ ከኢያሱ ጋር መጥቶ የመዝሙር ቃሎችን በሕዝቡ ጆሮ ተናገረ። 45 ሙሴም እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለመላው እስራኤል ተናገሮ ጨረሰ። 46 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዟቸው እኔ ዛሬ በግልጥ የምነግራችሁን ቃሎች ሁሉ በልባችሁ አኑሩ። 47 ቃሎቹ ለእናንተ ሕይወታችሁ ናቸው፥ ባዶ ቃሎች አይደሉም፥ በእነርሱ ዮርዳንስን ተሻገራችሁ በምትወርሷትም ምድር ረጅም ዘመን ትኖራላችሁ። 48 በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ 49 ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር ከዓብሪም ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ናባው ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓን ምድር አሻግረህ ተመልከት። 50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተስበስበ ሁሉ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ። 51 ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሁለታችሁም በሲን ምድረ በዳ በቃዴስ በምሪባ ውሃ አጠገብ በእስራኤላውያን መካከል በእኔ ላይ ባለመታመናችሁ፤ እንዲሁም በእስራኤላውያን መካከል የሚገባውን አክብሮት ባለመስጠታችሁ ነው። 52 ስለዚህ ምድሪቱን ከሩቅ ሆነህ ታያታለህ እንጂ ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።
እዚያ ሆነው ይሰሙ ይመስል እግዚአብሔር ለሰማያትና ለምድር ይናገራል። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር የሚናገረው በሰማይና በምድር ለሚኖሩት ነው፤ ወይም 2) እግዚአብሔር እንደ ሰው ቆጥሯቸው ለሰማይና ለምድር ይናገራል። (See: Apostrophe)
ይህ ማለት የእርሱን ጠቃሚ ትምህርት ሕዝቡ በትጋት እንዲቀበሉ እግዚአብሔር ይፈልጋል። (See: Simile)
ጤዛ የሚታይበትን ሂደት የሚገልጽ ቃል በራስህ ቋንቋ ተጠቀም።
ቅዝቃዜ ባለበት ጠዋት በቅጠሎችና በሣር ላይ የሚገኝ ውሃ
“አዲስ ተክሎች”
ከባድ ዝናብ
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር መልካም መሆኑን ተናገር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“አምላካችን ታላቅ መሆኑን ሰዎች ማወቃቸውን አረጋግጡ”
ይህ እንደ ዐለት ብርቱ እና ሕዝቡን መጠበቅ ለሚችለው ለእግዚአብሔር ሙሴ የሰጠው የተፀውዖ ስም ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እርሱ የሚያደርገው ሁሉ”
መንገድ ላይ መራመድ አንድ ሰው ሕይወቱን እንዴት እንደሚኖረው የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ሁሉንም ነገር በትክክለኛ መንገድ አድርጓል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁለት ቃላት በመሠረቱ የሚሉት አንድ ነገር ሆኖ እግዚአብሔር ፍትሐዊና ትክክለኛውን ነገር እንዳደረገ አጽንዖት ይሰጣሉ። (See: Doublet)
“ትክክል ያልሆነን ነገር በማድረግ ተቃወሙት”። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
“ወልጋዳ” እና “ጠማማ” የሚሉት ቃላት በመሠረቱ ትርጉማቸው አንድ ነው። ሙሴ ትውልዱ ምን ያህል ክፉ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ይጠቀምባቸዋል። አ.ት፡ “ፈጽሞ ክፉ የሆነ ትውልድ” (See: Doublet)
ሙሴ ሕዝቡን ለመገሰጽ ይህንን ጥያቄ ይጠቀማል። አ.ት፡ “-ሕዝብ፣ ለእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ማቅረብ አለባችሁ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“ሞኝ” እና “የማትረባ” የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆኑ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ባለመታዘዛቸው ምን ያህል ሞኞች እንደሆኑ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “እጅግ ሞኞች የሆናችሁ ሰዎች” (See: Doublet)
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥሮች ናቸው።
ሙሴ ሕዝቡን ለመገሰጽ በጥያቄ መልክ ይጠቀማል። ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የፈጠረህ አባትህ ነው” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚሉት ቃላት እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አስታውስ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ከረጅም ዓመታት በፊት”። ሙሴ፣ የእስራኤል ቅድመ ቅድም አያቶች ይኖሩ የነበሩበትን ጊዜ ያመለክታል።
ይህ ቀደም ሲል በነበረው ክፍል ሙሴ ተናግሮት የነበረው ድጋሚ ነው። ሙሴ የእስራኤል ሕዝብ እንደ ሕዝብ በታሪካቸው ላይ እንዲያተኩሩ ይፈልጋል። (See: Parallelism)
“ግልጽ ያደርግልሃል” ወይም “እንድታስተውለው ያስችልሃል”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ሕዝቡ ሊኖሩ በሚገባቸው ስፍራ ላይ አስቀመጣቸው”። “ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ” የሚሉ ተመሳሳይ ቃላት በዘዳግም 4፡21 ላይ ይታያሉ። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር እያንዳንዱን የሕዝብ ወገን ከአማልክቱ ጋር በራሱ ግዛት እንዲኖር ወስኗል። በዚህ መንገድ የሕዝብ ወገኖችን ጣዖታት ተጽዕኖ ገድቧል።
እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚናገሩት በመሠረቱ አንድ ነገር ነው፣ ስለሆነም ሊጣመሩ ይችላሉ። አ.ት፡ “የያዕቆብ ዘሮች የእግዚአብሕር ርስት ናቸው” (See: Parallelism)
“ያዕቆብን አገኘው -- ጋረደውና ተጠነቀቀለት -- ጠበቀው”። ይህንን ምናልባት ሙሴ እንደ ብዙ ሕዝብ አድርጎ የሚናገረው ስለ እስራኤላውያን እንደሆነ መተርጎም ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “ቅድመ ቅድም አያቶቻችንን አገኛቸው -- ጋረዳቸውና ተጠነቀቀላቸው -- ጠበቃቸው”
እዚህ ጋ “ጭው ያለ” የሚያመለክተው ባዶ መሬት ላይ ነፋሱ ሲነፍስ የሚያሰማውን ድምፅ ነው።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። የዐይን ብሌን የሚያመለክተው አንድ ሰው ለማየት የሚያስችለውን በዐይኑ ኳስ ውስጥ ያለውን ጥቁሩን ክፍል ነው። ይህ በጣም አስፈላጊና ጥንቃቄ የሚፈልግ የሰውነት ክፍል ነው። ይህ ማለት የእስራኤል ሕዝብ ለእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊና እርሱ ጥበቃ የሚያደርግለትም ነው። አ.ት፡ “በጣም ዋጋ እንዳለውና ውድ ነገር ጠብቆታል”(የአነጋገር ዘይቤ እና Simile የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት እስራኤላውያን በበረሃ እያሉ እግዚአብሔር ጠብቋቸዋል፣ ተከላክሎላቸዋልም። (See: Simile)
የወፍ የክንፉ ውጫዊ ጫፍ
ሙሴ እንደገና እስራኤላውያንን “ያዕቆብ” በማለት ይናገራል (ዘዳግም 32፡9-10)። ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ ብዙ ሕዝብ አድርጎ እንደተናገራቸው መተርጎም ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “መራቸው -- ከእነርሱ ጋር”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። “እርሱን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በምድሪቱ የከፍታ ስፍራዎች ላይ አስኪዷቸዋል” ወይም “ምድሪቱን እንዲወስዱና እንዲሰፍሩባት እግዚአብሔር ረድቶአቸዋል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ “ያዕቆብ” በመቁጠር መናገሩን ይቀጥላል (ዘዳግም 32፡9-10)። ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ ብዙ ሕዝብ አድርጎ እንደተናገራቸው መተርጎም ያስፈልግህ ይሆናል። “አባቶቻችንን እንዲሄዱ አደረጋቸው -- መገባቸው -- አጠገባቸው” (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)
“የሚበላው ብዙ ሰብል ወዳለበት ምድር አመጣው”
ምድሪቱ በዐለት ቀዳዳዎች ውስጥ ማር የሚሠሩ ብዙ የጫካ ንቦች ነበሯት። በተጨማሪም፣ በዐለቶች፣ በኮረብቶችና በተራራዎች ላይ የሚበቅሉ ዘይት የሚሰጡ ብዙ የወይራ ዛፎች ነበሩ።
ይህ ልክ እናት ለሕፃን ልጇ ጡቷን እንደምትሰጠው ዓይነት ነው። “ማር እንዲጠባ ፈቀደለት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ በሚገባ እንደ ተቀለበና ባለቤቱ ይሹሩን ብሎ እንደሰየመው እንስሳ ስለ እስራኤላውያን ይናገራል። “ ’ይሹሩን’ ማለት ‘ቀጥተኛ የሆነ’ ማለት ነው” የሚል የግርጌ ማስታወሻ ልትጨምርበት ትችላለህ። የአንተ ቋንቋ እስራኤላውያንን እንደ ይሹሩን የማይገልጻቸው ከሆነ የተከፈተው ተለዋዋጭ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንደሚያደርገው እስራኤላውያንን እንደ ብዙ ሕዝብ ማመልከት ትችላለህ። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
በሚገባ የተቀለበው እንስሳ፣ ገር ከመሆን ይልቅ የሚራገጠው ይሹሩን እግዚአብሔር ቢንከባከባቸውም እንኳን ያመጹትን እስራኤላውያንን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ለይሹሩን በሚዘምረው መዝሙር እስራኤላውያንን ይገስጻቸዋል። “ሰባችሁ፣ በጣምም ሰባችሁ፣ የሚቻላችሁን ያህልም ሰባችሁ”
ይህ ማለት እግዚአብሔር እንደ ዐለት ብርቱ ነው፣ ሕዝቡን ለመጠበቅም ይችላል ማለት ነው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሙሴ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው የተጸውዖ ስም እንደ ዐለት ብርቱና ሕዝቡን ለመጠበቅ የሚችል ነው። ይህንን በዘዳግም 32፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አስቀኑት።
“የእስራኤል ሕዝብ ሠዉ”
ይህ ማለት እስራኤላውያን ስለ እነዚህ አማልክት የተማሩት በቅርቡ ነው።
ሙሴ ለእስራኤላውያን እንደ ብዙ ሰው ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “የአንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” እና “የአንተ” የሚልበት አገባብ ሁሉ ብዙ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
እዚህ ጋ እግዚአብሔር ብርቱና መከላከያ ስለሆነ ዐለት ተብሎ ተጠርቷል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን የመከላከል ክብካቤ ትተሃል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሙሴ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው የተጸውዖ ስም እንደ ዐለት ብርቱና ሕዝቡን ለመጠበቅ የሚችል ነው። ይህንን በዘዳግም 32፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ እግዚአብሔርን ከአባትና ከእናት ጋር ያነጻጽራል። ይኸውም፣ እግዚአብሔር በሕይወት እንዲኖሩና ሕዝብ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “አባት ያደረጋችሁ … ሕይወትን የሰጣችሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ እግዚአብሔር ሕይወትን የሰጣቸውንና ሕዝብ ያደረጋቸውን የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ከእነርሱ እርቃለሁ” ወይም “እነርሱን መርዳቴን አቆማለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“የሚደርስባቸውን አያለሁ”
እዚህ ጋ “እኔን” የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው።
“ሐሰተኞች አማልክትን”
“ነገሮች” ምን እንደሆኑ ግልጽ ማድረግ ይኖርብህ ይሆናል። አ.ት፡ “የማይጠቅሙ ጣዖታት” (See: Assumed Knowl- edge and Implicit Information)
“የአንድ ሕዝብ ወገን ያልሆኑ ሰዎች”
“ሞኝ” የሚለውን በዘዳግም 32፡6 እንዳለው አድርገህ ተርጉመው።
እግዚአብሔር ቁጣውን ከእሳት ጋር ያነጻጽረዋል። ይህ የሚያስቆጣውን በሚያጠፋበት ኃይሉ ላይ አጽንዖት ያደርጋል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስለ ተቆጣሁ እሳት መለኮስ ጀምሬአለሁ፣ ይውጣል . . . የሚያጠፋ ነው . . . ተቀምጧል” ወይም “በምቆጣበት ጊዜ ጠላቶቼን እንደ እሳት አጠፋለሁ፣ በምድርና በ . . . ያለውን ሁሉ አጠፋለሁ . . . እውጣለሁ . . . አስቀምጣለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“እስከ ሙታን ዓለም ድረስ”
በእስራኤላውያን አናት ላይ የሚቆልላቸው ቆሻሻዎች የሆኑ በሚመስል መልኩ በእስራኤላውያን ላይ ስለሚደርስባቸው መጥፎ ነገሮች እግዚአብሔር ይናገራል። አ.ት፡ “ብዙ መጥፎ ነገሮች እንደሚደርሱባቸው አረጋግጣለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ በእርግጠኝነት እንዲደርስባቸው የሚያደርጋቸውን መጥፎ ነገሮች አንድ ሰው በቀስቱ ፍላጻዎችን ከማስወንጨፉ ጋር ያነጻጽራል። አ.ት፡ “እነርሱን ለመግደል ማድረግ የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። የነገር ስም የሆነው “ረሀብ” “ይራባሉ” ወደሚል ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይዝላሉ፣ በመራባቸው ምክንያትም ይሞታሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
“የሚያቃጥል እሳት” ለሚለው ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እስራኤላውያን በንዳድ ይሰቃያሉ ወይም 2) በድርቅ ወይም በረሀብ ወቅት የአየሩ ሁኔታ ባለተለመደ መልኩ ሞቃት ይሆናል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እነርሱ . . . ረሀብ፣ የሚያቃጥል ሙቀትና አሰቃቂ ጥፋት ይውጣቸዋል” ወይም “እነርሱ . . . ረሀብ፣ በሚያቃጥል ሙቀትና በአሰቃቂ ጥፋት ይሞታሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ጥርስና መርዝ እንስሳው እነዚህን ነገሮች በመጠቀም የሚገድልባቸው ናቸው። አ.ት፡ “እንዲነክሷቸው የዱር አራዊትን፣ ነክሰው እንዲመርዟቸው በአፈር ላይ የሚሳቡትን ነገሮች እልካለሁ” (See: Synecdoche)
እዚህ ጋ “ሰይፍ” የሚወክለው የጠላትን ሰራዊት ነው። አ.ት፡ “እስራኤላውያን ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ የጠላት ሰራዊት ይገድላቸዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
x
“የጠላትን ትንኮሳ ሰግቼ ነበር”
ይህ የነገር ስም እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ጠላት እንዳይተነኩሰኝ” ወይም “ጠላት እንድቆጣ እንዳያደርገኝ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር የእርሱን ጠላቶች እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ጠላቴን” ወይም “ጠላቶቼን” (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)
“አሳስቶ መረዳት”
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው የሰውን ጉልበት ወይም ኃይል ነው። ከፍ ከፍ ማለት ጠላትን የማሸነፍ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እኛ ይበልጥ ኃይለኞች በመሆናችን አሸንፈናቸዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እውነት እንዲሆኑ የሚመኛቸውን አንዳንድ ነገሮች ይናገራል፤ ይሁን እንጂ ጥበበኞች እንዳልሆኑና አለመታዘዛቸው እግዚአብሔር ይህንን ጥፋት እንዲያመጣባቸው እንደሚያደርገው እንዳልተገነዘቡ ያውቃል። (See: Hypothetical Situations)
የነገር ስም የሆነው “ፍርድ” እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በእነርሱ ላይ ሊደርስባቸው ያለ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ ጠላቶቻቸው ለምን እንዳሸነፏቸው ለማስተዋል ጥበበኞች ስላለመሆናቸው ጥያቄን በመጠቀም ሕዝቡን ይገስጻቸዋል። ይህ ጥያቄ ክፍት በሆነው ተለዋዋጭ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ውስጥ እንዳለው መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
በውስጠ ታዋቂነት ያለውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “1 የጠላት ወታደር የእናንተን 1000 ሰዎች እንዴት ሊያሳድድ ቻለ፣ 2 የጠላት ወታደሮችስ የእናንተን 10000 ሰዎች እንዲሸሹ ለማድረግ እንዴት ቻሉ” (See: Numbers and Ellipsis)
ሙሴ ሐሰተኛ አማልክት የሚያመልኩ ጠላቶችን በሰዶም ገሞራ ከኖሩት ክፉ ሕዝቦች እና መርዛማ ፍሬ ከሚያፈሩ የወይን ሐረጎች ጋር ያነጻጽራቸዋል። ይህ ማለት እስራኤላውያን በዙሪያቸው እንዳሉት ሕዝቦች ለማድረግ ከጀመሩ ጠላቶቻቸው ክፉዎች ስለሆኑ እስራኤላውያንን ለሞት ያበቋቸዋል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ወይን ለሕዝብ ወገን ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። “ወይናቸው በሰዶምና ገሞራ ይበቅል የነበረው ወይን ቅርንጫፉ ነው” ወይም አ.ት፡ “በሰዶምና ገሞራ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች እንዳደረጉት በተመሳሳይ መንገድ ክፉ ያደርጋሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“የወይን ዘለላዎቻቸው
ሙሴ የእስራኤል ሕዝብን ጠላቶች መርዘኛ ፍሬና ወይን ከሚያበቅል የወይን ሐረግ ጋር ማነጻጸሩን ይቀጥላል። ይህ ማለት ጠላቶቻቸው ክፉዎች ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
መርዘኛ እባቦች
ይህ ጥያቄ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ያለው ዕቅድ ዋጋ እንዳለው ሀብት በምስጢር እንደተጠበቀ አጽንዖት ይሰጣል። ምላሽ የማይፈልገው ጥያቄ እንደ ንግግር ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል። ደግሞም፣ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ለእስራኤል ሕዝብና ለጠላቶቻቸው ለማድረግ ያቀድኩትን እኔ አውቃለሁ፣ አንድ ሰው ዋጋ ባላቸው ንብረቶቹ ላይ እንደሚቆልፍባቸው በእነዚያ ዕቅዶች ላይ ቆልፌባቸዋለሁ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በቀል” እና “ብድራትንም” የሚሉት ቃላት በመሠረቱ ትርጉማቸው ተመሳሳይ ነው። አ.ት፡ “እኔ እበቀላለሁ፣ የእስራኤልንም ጠላቶች እቀጣለሁ” (See: Doublet)
አንድ ሰው ስላደረገው ነገር ቅጣት ወይም ሽልማት
መጥፎ የሆነ ነገር ደርሶባቸዋል። አ.ት፡ “ተስፋ የላቸውም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“እነርሱን የማጠፋበት ጊዜ”
ሊቀጡአቸው በትጋት የሚሮጡ ሰዎችን በሚመስሉበት መልኩ እግዚአብሔር በጠላቶቹ ላይ ሊመጡ ስላሉት መጥፎ ነገሮች ይናገራል። አ.ት፡ “ፈጥኜ እቀጣቸዋለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “ፍትሕ” እንደ ቅጽል ወይም ተውሳከ ግሥ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ለሕዝቡ ፍትሐዊ የሆነውን ነገር ያደርግላቸዋል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
“አገልጋዮቹን መርዳት እንዳለበት ይሰማዋል”
ከሌሎች አማልክት ከለላ ስለመፈለጋቸው የእስራኤልን ሕዝብ እግዚአብሔር ይገስጻቸዋል። ይህ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ተመልከቱ፣ እስራኤላውያን እንደሚጠብቋቸው ያሰቧቸው አማልክት ሊረዷቸው አልመጡም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረባቸው የእስራኤልን ሕዝብ እግዚአብሔር ይገስጻቸዋል። ይህ ጥያቄ እንደ ንግግር ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እስራኤላውያን ሥጋና ወይን ያቀረቡላቸው አማልክት ሊረዷቸው አልመጡም” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
በእስራኤላውያን ላይ ለማፌዝ እግዚአብሔር ይህንን ይናገራል። እነዚህ አማልክት ሊረዷቸው እንደማይችሉ ያውቃል። አ.ት፡ “እነዚህ ጣዖታት ሊነሡና ሊረዱ ወይም ሊጠብቋችሁ አይችሉም” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
“እኔ፣ እኔ ራሴ” ወይም “እኔ፣ እኔ ብቻዬን”። እግዚአብሔር እርሱ ብቻ አምላክ መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት “እኔ”ን ይደጋግማል።
“እጄን ወደ ሰማይ አንሥቼ እምላለሁ” ወይም “ምያለሁ”። እጅን ማንሣት የመማል ምልክት ነው።
“ለዘላለም መኖሬ እርግጥ የመሆኑን ያህል” ወይም “ማለቂያ በሌለው ሕይወቴ እምላለሁ”። በዘዳግም 32፡41-42 የተናገረው እንደሚፈጸም ይህ አነጋገር እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያረጋግጣል።
“አንጸባራቂውን ሰይፌን በምስልበት ጊዜ”። ይህ ማለት እግዚአብሔር በጠላቶቹ ላይ ለመፍረድና ለመቅጣት ተዘጋጅቷል ማለት ነው። አ.ት፡ “በጠላቶቼ ላይ ለመፍረድ በምዘጋጅበት ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ሙሉውን ሰው ነው (See: Synec- doche)
ፍላጻዎች ሰው የሆኑና የሚያሰክር መጠጥ ይሰጣቸው ይመስል እግዚአብሔር ስለ ፍላጻዎቹ ይናገራል፣ ሰይፉም ስለ ራበው ደሙ ተንጠፍጥፎ ያልወጣለትን እንስሳ እንደሚበላ ሰው መስሎ ይናገራል። እነዚህ ዘይቤአዊ አነጋገሮች ብዙ ጠላቶችን ለመግደል ፍላጻዎችንና ሰይፍን የሚጠቀምን ወታደር የሚያመለክቱ ፈሊጣዊ አነጋገሮች ናቸው። ይህ በተራው እግዚአብሔር በጦርነት ውስጥ ጠላቶቹን ስለመግደሉ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው።(ዘይቤአዊ አነጋገር፣ ፈሊጣዊ አነጋገር እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ሊሆን የሚችለው ትርጉም “በራሳቸው ላይ ረጅም ጸጉር ካላቸው ጠላቶች” የሚለው ነው።
ሙሴ በዚያ ኖረው ይሰሙት ይመስል በየሀገራቱ ሁሉ ለሚኖሩ ሰዎች ይናገራል። (See: (ፈሊጣዊ አነጋገር እና Apostrophe የሚለውን ተመልከት))
እዚህ ጋ “የአገልጋዮቹን ደም” የሚወክለው የተገደሉትን የእርሱን ንጹሕ አገልጋዮች ሕይወት ነው። አ.ት፡ “አገልጋዮቹን የገደሉትን ጠላቶቹን ይበቀላቸዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “ተናገረ . . . መናገር” ወይም 2) “ዘመረ . . . መዘመር” ናቸው።
x
“ሙሴ ለእስራኤል ሕዝብ ተናገራቸው”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ለ -- ትኩረት ስጡ” ወይም “ስለ -- አስቡ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ባይታዘዙ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ምን እንደሚያደርግባቸው የተናገረውን ለማመልከት “መስክሬላችኋለሁ” ማለቱን ያመለክታል ወይም 2) እንዲያደርጉት እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ለማመልከት “አዝዥችኋለሁ” የሚሉት ናቸው
“ልጆቻችሁና ተወላጆቻችሁ”
“ይህ ሕግ ነው”
ይህ ምጸት በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በጣም ጠቃሚ የሆነ ነገር” (ምጸት የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “ሕይወት” “መኖር” ወደሚል ግሥ ሊተረጎም ይችላል። ሕግን ራሱን የሚወክለውን የመታዘዝን ፈሊጣዊ አነጋገር ግልጽ ማድረግ ይኖርብህ ይሆናል። አ.ት፡ “ብትታዘዝው በሕይወት ትኖራለህና” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ረጅም ቀናት የረጅም ሕይወት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። እነዚህን ቃላት በዘዳግም 4፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። አ.ት፡ “ረጅም ጊዜ መኖር እንድትችል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሞዓብ ውስጥ የሚገን የተራራ ሰንሰለት ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“አባሪም እና ናባው ተራራ ላይ ውጣ”
ይህ ከአባሪም ተራሮች ከፍተኛው ስፍራ ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ከኢያሪኮ ከወንዙ በወዲያ ማዶ”
ይህ በሙታኑ ዓለም የሙሴ መንፈስ ከዘመዶቹ መንፈስ ጋር እንደሚገናኝ በትህትና የተነገረበት መንገድ ነው። አ.ት፡ “ከአንተ በፊት ከሞቱት አባቶችህ ጋር ተገናኝ” (See: Euphemism)
ይህ በኤዶም ዳርቻ የሚገኝ ተራራ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በበረሃው ውስጥ ሙሴ እግዚአብሔርን ያልታዘዘበት ስፍራ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በይሁዳ በስተደቡብ ዳርቻ የሚገኝ ምድረበዳ ስም ነው(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
1 የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት ለእስራኤላውያን የሰው ቃለ ቡራኬ ይህ ነው። 2 እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሐይ ወጣ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጣ፤ በስተቀኙ የሚነድ እሳት ነበር። 3 በእርግጥ ሕዝቡን የምትወድ አንተ ነህ፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው። ከእግርህ ሥር ሁሉ ይስገዳሉ፤ ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤ 4 ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው። 5 የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፤ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፤ እግዚአብሔር በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር። ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት። 6 የወገኖቹ ቁጥርም ጥቂት ይሁን። 7 ስለይሁዳ የተነገረው ባትኮት ይህ ነው። ሙሴም እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ የይዳን ጩኸት ስማ፤ ወደ ወገኖቹም እንደገና አምጣው። ስለእርሱ ተዋጋለት፤ አቤቱ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋ ረዳቱ ሁን! 8 ስለ ሌዊም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ቱሚምህና ኡሪምህ ለምትወደው ሰው ይሁን፤ ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤ በመሪባም ውሃ ከእርሱ ጋር ተከራከርህ። 9 ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፤ ስለ እነርሱ ግድ የለኝም አለ። ወንድሞቹን አልለያቸውም፤ ልጆቹንም አላወቃቸውም። ስለቃልህ ከለላ አደረገ፤ ኪዳንህንም ጠበቀ። 10 ሥርዓትህን ለያዕቆብ፤ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራል። ዕጣን በፊትህ፤ ያሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በምሠዊያህ ላይ ያቀርባል። 11 እግዚአብሔር ሆይ፥ ኃይሉን ሁሉ ባርክለት፤ በእጁ ሥራ ደስ ይበልህ፤ በእርሱ ላይ የሚነሡበትን ሽንጣቸውን ቁረጠው፤ ጠላቶቹንም እንደገና እንዳይነሡ አድርገህ ምታቸው። 12 ሙሴ ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ በእርሱ ተጠብቆ በሰላም ይረፍ፤ ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር የሚወደውን ሰው በትክሻዎቹ መካከል ያርፋል። 13 መሴ ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦ እግአብሔር ምድሩን ይባርክ፤ ውድ በሆኑ ሰማያዊ ነገሮች፥ ጠል ከላይ በማውረድ፤ ከታች በጥልቅ በተንጣለለው ነገሮች ይባርክ። 14 ከፀሐይ በተሠሩ ምርጥ ፍሬ፤ ጨረቃም በምትሰጠው እጅግ መልካም ነገር፤ 15 ከጥንት ተራሮች በተገኘ ምርጥ ስጦታ፤ በዘላለማዊ ኮረብቶች ፍሬያማነት ይባርክ። 16 ምድር በምታስገኘው ውድ ስጦታና በብዛት በቁጥቋጦም ውስጥ በነበረው በእርሱ መልካም ሞገስ። እነዚህ ሁሉ በረከቶች በወንድሞቹ መካከል ገዥ በሆነው፤ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ። 17 በግርማው እንደ በኩር ኮርማ ነው፤ ዘንዶቹም የጎሽ ቀንዶች ናቸው። በእነርሱም ሕዝቦችን በምድር ዳርቻ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ይወጋል፤ እነርሱም የኤፍሬም አሥር ሺዎቹ ናቸው። 18 ስለ ዛብሎንም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ዛብሎን ሆይ፥ ወደ ውጭ በመውጣትህ፤ አንተም ይሳኮር በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ። 19 እነርሱም አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ። እነርሱም ከባሕሮች በአሸዋ ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ያወጡበታል። 20 ስለ ጋድም ሙሴ እንዲህ አለ፦ የጋድን ግዛት የሚያሰፋ የተባረከ ይሁን! ክንድንና ራስን በመገነጣጠል፤ ጋድ እንደ አንበሳ በዚያ ይኖራል። 21 ለአለቃን ድርሻ ሆኖ የተጠበቀለትን ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ። ከሕዝብ አለቆች ጋር መጣ። በእስራኤል ላይ የወሰነውን የእግዚአብሔርን ሥርዓትንና ፍርዱን ፈጸመ። 22 ስለ ዳንም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ዳን ከባሳን ዘሎ የሚወጣ፤ የአንበሳ ደቦል ነው። 23 ስለ ንፍታሌምም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም በእግዚአብሔር ሞገስ ረክቶአል፤ በበረከቱም ተሞልቶአል፤ ባሕሩንና የደቡብን ምድር ይወርሳል። 24 ስለ አሴርም ሙሴ እንዲህ አለ፦ አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ይሁን፤ በወንሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ። 25 በዘመንህና ደህንነትህ ሁሉ የደጃፍህ መቀርቀሪያ ብረትና ናስ ይሁን፤ ኃይልህም በዘመንህ ሁሉ ይኖራል። 26 አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ በግርማው በደመናትም የሚገሠግሥ፤ እንደ ይሽሩን አምላክ ያለ ማንም የለም። 27 ዘላለማዊ አምላክ መኖርያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከበታችህ ናቸው፤ እርሱን አጥፋው! በማለት፤ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል። 28 ስለዚህ እስራኤል በሰላም ይሆራል።። የሰማያት ጠል በሚወርድበት፤ እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር የያዕቆብን ምንጭ የሚነካው የለም። 29 እስራኤል ሆይ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፤ እንዳንተ ያለ ማን ነው? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፤ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ ተሸብራው በፍርሃት፤ ወደ አንተ ይመጣሉ። አንተም ከፍታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።
ሙሴ እግዚአብሔርን ከንጋት ፀሐይ ጋር ያነጻጽራል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ከሲና በመጣ ጊዜ ከሴይር ወጥታ ከፋራን ተራራ የምታበራዋን ፀሐይ መስሎ ታይቷቸው ነበር” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በእስራኤል ሕዝብ ላይ”
“10000 መላእክት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች ትርጉሞች 1) “በቀኝ እጁ የእሳት ነበልባል ነበር” ወይም 2) “የእሳትን ሕግ ሰጣቸው” ወይም 3) “ተራሮቹን ቁልቁል በመውረድ ከደቡብ መጣ”
“የእስራኤል ሕዝብ”
የተጸውዖ ስሞች የሆኑት “የእርሱ” እና “የአንተ” የሚያመለክቱት እግዚአብሔርን ነው። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር ቅዱሳን ሁሉ በእጁ ውስጥ ናቸው . . . እግሩ . . . ቃሎቹ” (ተውላጠ ስም የሚለውን ተመልከት)
እጅ የኃይል እና የጥበቃ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ቅዱስ ሕዝቡን ሁሉ አንተ ትጠብቃለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ንብረት” ወይም “ዋጋው ውድ የሆነ ንብረት”
“እግዚአብሔር ነገሠ”
ይህ የእስራኤል ሌላው ስሙ ነው። ይህንን በዘዳግም 32፡15 እንዳለው አድርገህ ተርጉመው።
ሙሴ እያንዳንዱን የእስራኤል ነገዶች መባረኩን በዚህ ይጀምራል።
ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎች ትርጉሞች 1) “የእርሱ ሰዎች ጥቂቶች አይሁኑ” ወይም 2) “የእርሱ ሰዎች ጥቂቶች ቢሆኑም እንኳን”
እዚህ ጋ “የይሁዳ ድምፅ” የይሁዳን ሕዝብ ጩኸትና ጸሎት ያመለክታል። አ.ት፡ “የይሁዳ ሕዝብ ወደ አንተ በጸለየ ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “ረዳት” እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እንዲዋጋ እርዳው” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሊቀ ካህናቱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ በሚፈልግበት ጊዜ በደረቱ ላይ የሚሸከማቸው ቅዱስ ድንጋዮች ነበሩ። እዚህ ጋ “የአንተ” የሚያመለክቱት እግዚአብሔርን ነው። (See: Forms of You እና የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)
“ለአንተ ቅዱስ የሆነ” ወይም “አንተን ደስ ለማሰኘት የሚፈልገው”። ይህ የሌዊን ነገድ ያመለክታል።
ይህንን በዘዳግም 6፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። ተርጓሚው፣ “ ‘ማሳህ’ ማለት ‘መፈተን’ ማለት ነው” የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ይችላል።
ይህንን በዘዳግም 32፡51 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። ተርጓሚው፣ “ ‘መሪባ’ ማለት ‘መከራከር’ ወይም ‘መጣላት’ ማለት ነው” የሚል የግርጌ ማስታወሻ መጨመር ይችላል።
ሙሴ ለእግዚአብሔር እየተናገረ ነው፣ ስለዚህ እነዚህ ቃላት ሁሉ ነጠላ ቁጥሮች ናቸው።
በእርሱ ደስ ይበልህ
እዚህ ጋ “እጆች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሙሉውን ሰው ነው። አ.ት፡ “እርሱ የሠራውን ሥራ ሁሉ” (See: Synecdoche)
ወገብ የጉልበት ማዕከል እንደሆነ ይታሰባል፣ እዚህ ጋ የሚወክለውም ጉልበትን ነው። አ.ት፡ “ጉልበታቸውን ውሰድ” ወይም “ፈጽመህ አጥፋ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሐረግ ዘይቤአዊ አነጋገር ሆኖ ሁለት ጊዜ ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “ለመዋጋት ተነሥ . . . እንዳያንሠራሩ አድርጋቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ከ -- ጋር ተዋጋ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ሙሴ የሚያመለክተው የብንያም ነገድ አባላትን ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በሕይወት እንዲኖሩ የሚወድላቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “ደኅንነት” ግሣዊ ሐረግ በመጠቀም ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ማንም ሊጎዳው በማይችልበት ስፍራ ይኖራል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር የብንያምን ነገድ በኃይሉ ይከላከልላቸዋል ወይም 2) እግዚአብሔር በብንያም ነገድ ኮረብታማ አካባቢ ይኖራል። በሁለቱም ትርጉሞች፣ እግዚአብሔር ይንከባከባቸዋል የሚል አንድምታ አለው።
ይህ የሚያመለክተው የኤፍሬምንና የምናሴን ነገዶች ነው። ሁለቱም ነገዶች የተገኙት ከዮሴፍ ነው።
“የእርሱ” የሚለው ቃል የኤፍሬምንና የምናሴን ነገዶች የሚወክለውን ዮሴፍን ያመለክታል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ምድራቸውን ይባርክ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ከሰማይ በሆነ የከበረ ጠል” ወይም “ከሰማይ በሆነ የከበረ ዝናብ”
ቅዝቃዜ ባለው ማለዳ ላይ በቅጠልና ሣር ላይ ውሃ የሚፈጥር። ይህንን በዘዳግም 32፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ በከርሠ ምድር ውስጥ የሚገኘውን ውሃ ያመለክታል።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በዘዳግም 33፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ምድሩን ይባርክ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ፀሐይ እንዲበቅሉ በሚያደርጋቸው ምርጥ ሰብሎች”
“ከወር እስከ ወር በሚበቅሉ ምርጥ ሰብሎች”
ሙሴ ምናልባት የምግብ ሰብሎችን ሳያመለክት አይቀርም። የዚህ አነጋገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “እጅግ ምርጥ የሆኑ ፍሬዎች . . . የከበሩ ፍሬዎች” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“ከረጅም ዘመን ጀምሮ የኖሩ ተራሮች”
“ለዘላለም የሚኖሩ ኮረብቶች”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። ይህንን በዘዳግም 33፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “የእርሱን ምድር እግዚአብሔር ይባርክ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
x
በሬ በዘይቤአዊ አነጋገር ትልቅና ጉልበታም የሆነን ነገር ያመለክታል። “በኩር” የሚለው ቃል በዘይቤአዊ አነጋገር ክብር ማለት ነው። አ.ት፡ “ሰዎች ብዙና ኃያላን የሆኑትን የዮሴፍን ተወላጆች ያከብሯቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ቀንድ የብርታት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “እርሱ እንደ -- ብርቱ ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በቀንዶቹ መግፋቱ ስለ ብርታቱ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “እርሱ በጣም ብርቱ ስለሆነ ይገፋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት የኤፍሬም ነገድ ከምናሴ ነገድ ይልቅ ይበረታል። አ.ት፡ “የኤፍሬም ሕዝብ ከ10000 ብዙ ዕጥፍ . . . (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
የዛብሎን ሕዝብ የሚገኙት በሜዴትራንያን ባህር አጠገብ ነበር። በባህር ላይ እየተጓዙ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ይገበያዩ ነበር። የይሳኮር ሕዝቦች በእርሻና ከብት በማርባት ሰላማዊ ኑሮን የሚመርጡ ነበሩ። በውስጠ ታዋቂነት ያሉ መረጃዎችን ግልጽ ልታደርጋቸው ትችላለህ። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
“እነርሱ የሚያቀርቡት በዚያ ነው”
“ተቀባይነት ያላቸውን መሥዋዕቶች” ወይም “ተገቢነት ያላቸውን መሥዋዕቶች”
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) በባህሩ ማዶ ካሉ ሕዝቦች ጋር ይገበያያሉ ወይም 2) አሸዋን በመጠቀም የሸክላ ሥራ መሥራት ጀምረው ነበር።
እዚህ ጋ “መጥባት” የሚለውን ቃል የዕብራይስጡ ትርጉም አንድ ሕፃን ልጅ የእናቱን ጡት እንዴት እንደሚመገብ ያመለክታል። ይህ ማለት አንድ ሕፃን ከእናቱ ወተት እንደሚያገኝ ሕዝቡ ከባህር ሀብት ያገኛሉ። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “እግዚአብሔር ጋድን ይባርከው፣ የሚኖርበትንም ብዙ መሬት ይስጠው” ወይም 2) ለጋድ የሚኖርበትን ብዙ ምድር ሰጥቶታልና ሰዎች እግዚአብሔር መልካም ነው ይበሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት የጋድ ሕዝብ ብርቱና ደህንነቱ የተጠበቀ ስለሆነ በጦርነት ጠላቶቻቸውን ያሸንፋሉ። (See: Simile)
የዳን ሕዝብ እንደ አንበሳ ደቦል ብርቱዎች ናቸው፣ በባሳን የሚኖሩትን ጠላቶቻቸውን ወጉ። በውስጠ ታዋቂነት ያሉትን መረጃዎች ግልጽ ልታደርጋቸው ትችላለህ። (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Ellipsis የሚለውን ተመልከት))
የዳን ሕዝብ እንደ አንበሳ ደቦል ብርቱዎች ናቸው፣ በባሳን የሚኖሩትን ጠላቶቻቸውን ወጉ። በውስጠ ታዋቂነት ያሉትን መረጃዎች ግልጽ ልታደርጋቸው ትችላለህ። (See: (ዘይቤአዊ አነጋገር እና Ellipsis የሚለውን ተመልከት))
እግዚአብሔር በንፍታሌም መደሰቱ “ሞገስ” ምግብ ሆኖ ንፍታሌም ዳግመኛ እስከማይራብ ድረስ የበላው በሚመስል መልኩ ተነግሮለታል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በእርሱ ስለ ተደሰተበት የሚፈልገው መልካም ነገሮች ሁሉ አሉት” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በረከቶች ምግብ ሆነው ንፍታሌም ተጨማሪ መያዝ እስከማይችል ድረስ የበላው በሚመስል መልኩ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ስለ ባረከው የሚፈልገው ሁሉ አለው”
ሙሴ የንፍታሌምን ነገድ አንድ ሰው እንደ ሆኑ አድርጎ ይናገራል፣ ስለዚህ እነዚህ ቃላት ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
ይህ በገሊላ ሐይቅ ዙሪያ ያለውን ምድር ያመለክታል። የዚህ ንግግር ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
የወይራ ዘይት ለምግብነትና ለፊትና ለክንድ ቆዳ ጥቅም ላይ ይውል ነበር። እግር ይቆሽሻል፣ ስለዚህ እግርን በወይራ ዘይት ውስጥ መጨመር ዋጋ ያለውን ዘይት ማበላሸት ይሆናል። የዚህ ንግግር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ማባከን እንዲቻለው ብዙ የወይራ ዘይት ይኑረው” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
አንድ ሰው የሆኑ ይመስል ሙሴ የሚናገረው ለአሴር ነገድ ነው፣ ስለዚህ “የአንተ” የሚሉት አገባቦች ሁሉ ነጠላ ቁጥሮች ናቸው። (See: Forms of You)
ከተሞች ጠላት እንዳይገባባቸው በበሮቻቸው አግድመት ላይ ረጃጅም መቀርቀሪያዎች ይኖራቸው ነበር። የዚህ ንግግር ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በጠላቶችህ ከመጠቃት እንድትድን” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ የእስራኤል ሕዝብ ሌላው ስሙ ነው። ትርጉሙም “ቀጥተኛ የሆነ” የሚል ነው። ይህንን በዘዳግም 32፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።(ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
በጦር ሜዳ ላይ በሠረገላው እንደሚሄድ ንጉሥ በጠፈር መካከል በደመና ላይ የሚሄድ ይህ የእግዚአብሔር ምስል ነው። አ.ት፡ “ንጉሥ በጦር ሜዳ መካከል እንደሚሄድ በሰማያት መካከል ይሄዳል. . . በሠረገላው እንዳለ ንጉሥ በደመናት ላይ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አንተን ለመርዳት” ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” የሚለው ቃል እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
የነገር ስም የሆነው “መጠጊያ” መጠለያ ወይም ከአደጋ ማምለጫ ስፍራ ማለት ሲሆን እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የዘላለም አምላክ ሕዝቡን ይጠብቃል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
“የዘላለም ክንዶች” የሚሉት ቃላት እግዚአብሔር ሕዝቡን ለዘላለም እንደሚጠብቃቸው ለሰጠው ተስፋ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ሕዝቡን ለዘላለም ይረዳቸዋል፣ ይንከባከባቸዋልም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴ እርሱ የሚናገረው የሚፈጸም ስለመሆኑ አጽንዖት ለመስጠት ወደፊት ሊሆን ያለውን ባለፈ ጊዜ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እርሱ ወግቶ ያስወጣቸዋል. . . ይላል” (See: Predictive Past)
ሙሴ እስራኤላውያንን እንደ አንድ ሰው አድርጎ ይናገራቸዋል፣ ስለዚህ “አንተ” የሚለው ቃልና “አጥፋው” የሚለው ትዕዛዝ እዚህ ጋ ነጠላ ቁጥር ነው። (See: Forms of You)
በአንተ ቋንቋ ይህ ቀጥተኛ ትዕምርተ ጥቅስ በሚገባ የማያገለግል ከሆነ ቀጥተኛ ወዳልሆነው ትዕምርተ ጥቅስ ልትለውጠው ትችላለህ። አ.ት፡ “እንድታጠፋቸው ይነግርሃል” (See: Direct and Indirect Quotations)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሙሴ እርሱ የሚናገረው የሚፈጸም ስለመሆኑ አጽንዖት ለመስጠት ወደፊት ሊሆን ያለውን ባለፈ ጊዜ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል። “እስራኤል ይኖራል . . . የያዕቆብ ምንጭ የተጠበቀ ይሆናል” ወይም 2) ሙሴ፣ “እስራኤል ይኑር . . . የያዕቆብ ምንጭም የተጠበቀ ይሁን” በማለት እስራኤልን እየባረከ ነው የሚሉት ናቸው። (See: Predictive Past)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የያዕቆብ ቤት ወይም 2) የያዕቆብ ተወላጆች (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ጠል የዝናብን ያህል አስፈላጊ ስለመሆኑ ተነግሯል። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሙሴ “እንደ ዝናብ ብዙ ጠል ምድሪቱን ይሸፍናት” በማለት እስራኤልን እየባረከ ነው ወይም 2) ሙሴ “ብዙ ጠል እንደ ዝናብ ምድሪቱን ይሸፍናታል” በማለት ወደ ፊት ምን ሊሆን እንዳለ ይነግራቸዋል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ቅዝቃዜ ባለበት ጠዋት በቅጠሎችና በሣር ላይ የሚገኝ ውሃ። ይህንን በዘዳግም 32፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እንደ ንግግር ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። ድግሞም በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እንደ አንተ ያለ እግዚአብሔር ያዳነው የሕዝብ ወገን የለም . . . በግርማ”። (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ አገላለጽ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው እንደሚከላከልላቸውና ጠላቶቻቸውን እንዲወጉ እንደሚያስችላቸው ይናገራል። (See: Merism)
“ጋሻ” የሚለው ቃል እግዚአብሔር እስራኤላውያንን የመጠበቁና የመከላከሉ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። የነገር ስም የሆነው “ረዳት” እንደ ግሥ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አንተን የሚጠብቅህና የሚረዳህ” (ዘይቤአዊ አነጋገር እና የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
“ሰይፍ” የሚለው ቃል ጦርነቶችን ለማሸነፍ በሰይፍ ለመግደል ኃይል ማግኘትን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ግርማ እንዲኖርህና ጦርነቶችን እንድታሸንፍ የሚያስችልህ እርሱን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሌሎች ሕዝቦች ሐሰተኞች አማልክትን ያመለኩባቸውን ስፍራዎች እስራኤላውያን ይደመስሱታል ወይም 2) እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ድል በሚያደርጉበት ጊዜ በጀርባቸው ላይ ይረማመዱባቸዋል።
1 ሙሴ ከሞዓብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ ወደ ናባው ተራራ ሄደ። በዚያም እግዚአብሔር ከገለዓድ እስከ ዳን ያለውን ምድሪቱን ሁሉ፤ 2 ንፍታሌምን ሁሉ፥የኤፍሬምንና የምናሴን ግዛት እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ አሳየው፤ 3 ኔጌብንና የዘንባባ ከተማ ከሆነችው ከኢያሪኮ ሸለቆ እስከ ዞዓር ያለውን ምድር ሁሉ አሳየው። 4 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለአብርሃም፥ ለይስሐንና ለያዕቆብ ለአባቶቻችሁ እሰጣለሁ ብዬ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው ምድር፥ በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም አለው። 5 እግዚአብሔር እንደተናገረው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞዓብ ምድር ሞተ። 6 በሞዓብ ምድር በቤተ ፌጎር ፊት ለፊት ባለው ሸለቆ እግዚአብሔር ቀበረው፤ ይሁን እንጂ መቃብሩ የት እንደ ሆን እስከ ዛሬ ማንም አያውቅም። 7 ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሃያ ዓመት ነበር፤ ሆኖም ዐይኑ አልፈዘዘም፤ ጉልበቱም አልደከመም። 8 የልቅሶውና የሐዘኑ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ እስራኤላውያን በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን አለቀሱለት። 9 ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ አደመጡት፤ እግዚአብሔር ሙሴን አዞት የነበረውንም ሁሉ አደረገ። 10 እግዚብብሔር ፊት ለፊት ያወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል አልተነሣም። 11 እግዚአብሔር ልኮት እነዚያን ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆች ሁሉ በግብፅ በፈርዖን በሹማምንቱና በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንዲያደርግ የላከውን ያደረገ ማንም ሰው አልነበረም። 12 ሙሴ በእስራኤል ሁሉ ፊት ያሳየውን ታላቅ ኃይል ያሳየ ወይም ያደረገውን አስደናቂ ተግባር የፈጸመ ማንም ነቢይ የለም።
ይህ ከአባሪም የተራራ ሰንሰለት በስተሰሜን የሚገኝ የፈስጋ ተራራ ጫፉ ነው። ይህንን በዘዳግም 32፡49 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህንን በዘዳግም 3፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
x
ይህ በሞዓብ የነበረ መንደር ነው። ይህንን በዘዳግም 3፡29 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ለራስህ ተመልከተው”
ይህ የሚያመለክተው ይህ የተጻፈበትን ወይም የታረመበትን ጊዜ እንጂ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ያለውን የአሁኑን ጊዜ አይደለም።
“የ120 ዓመት ዕድሜ . . . 30 ቀን” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ዐይኖቹና አካሉ ገና ብርቱና ጤናማ ነበሩ ማለት ነው።
ይህንን በዘዳግም 1፡38 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ጸሐፊው ኢያሱን አንድን ነገር እንደሚይዝ ዕቃ፣ መንፈስን ደግሞ በመያዣው ውስጥ እንደሚጨመር ቁሳዊ አካል አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ . . . በጣም ጥበበኛ እንዲሆን እግዚአብሔር ኢያሱን አስቻለው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የዚህ ንግግር ሙሉ ትርጉም ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ኢያሱ እግዚአብሔርን እንዲያገለግል ለመለየት ሙሴ እጆቹን በእርሱ ላይ ጭኖበት ነበር” (See: Assumed Knowledge and Implicit Information)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህ ማለት እግዚአብሔርና ሙሴ በጣም የቀረበ ግንኙነት ነበራችው ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ታላላቆቹን ሁሉ ያደረገ”
1 እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴ ዋና ረዳት የሆነውን የነዌ ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2 አገልጋዬ ሙሴ ሞቶአል። ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ። 3 የእግራችሁ ጫማ የሚረግጥውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ።ለሙሴም ተስፋ እንደ ሰጠሁት ሰጥቻችኋለሁ። 4 ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ፤ የኪጢያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻእሁ ይሆናል። 5 በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ማንም ሊቋቋምህ አይችልም። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ። አልጥልህም አልትውህም። 6 ለአባቶቻቸው፦እሰጣችኋለሁ ብዬ ተስፋ የሰጠ'ኋችሁውን ምድር ይህ ሕዝብ እንዲወርስ ታደርጋለህና ጽና አይዞህ። 7 ስለዚህም ጽና እጅግ በርታ። አገልጋዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግን ሁሉ ትጠብቀው ዘንድ ተጠንቀቅ። በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አትበል። 8 ስለዚህ ሕግ መጽሐፍ ሁልጊዜ ተናገር። የተጻፈበትንም ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ በቀንና በሌሊትም አሰላስለው። የዚያን ጊዜም የተከናወነልህና የተሳከልህ ትሆናለህ። 9 በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና፦ "ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ ተስፋ አትቁረጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?" 10 ኢያሱም የሕዝቡን አለቆች እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ 11 "በሰፈሩ መካከል እለፉ፤ ሕዝቡንም፦ ለራሳችሁ ስንቃችሁን አዘጋጁ ብላችሁ እዘዙአቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲትወርሱ ወደሚሰጣችሁ ምድር በሦስት ቀናት ውስጥ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ትወርሳላችሁ። 12 ኢያሱም የሮቤልን ልጆች የጋድንም ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ 13 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዲህ ብሎ ያዘዛቸውን ቃል አስቡ፦አምላካችሁ እግዚአብሔር እረፍት ይሰጣችኋል፤ይህንንም ምድር ይሰጣችኋል። 14 ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በሰጣችሁ ምድር ይቀመጣሉ። ነገር ግን ተዋጊ የሆኑ ሰዎቻችሁ እግዚአብሔር ለእናንተ እንደሰጣችሁ 15 ወንድሞቻችሁን እረፍት እስኪሰጥ ድረስ ከወንድሞቻችሁ ፊት በመሆን እነርሱንም ለመርዳት ይሄዳሉ ። እነርሱም ደግሞ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ምድር ይወርሳሉ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ብዮርዳኖሴ ማዶ በፀሐይ መውጫ ወደሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ትመለሳላችሁ፤ ትወርሳላችሁም። 16 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሰለት፦ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን። 17 ለሙሴ እንደ ታዘዝን ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን። ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ እግዚአብሔር አምላክህ ብቻ ከአንተጋር ይሁን። 18 በትእዛዝህ ላይ የሚያምፅና ቃልህን የማይታዘዝ ማንም ቢሆን ይገደል። ብቻ ጽና፥ በርታ።
ይህ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ለህዝቡ ራሱን የገለጸበት ስም ነው፡፡ ይህንን እንዴት እንደሚተረጉሙት ስለ ያህዌ የቃል ትርጉም ገጽ/ጽሁፍን ይመልከቱ፡፡
የኢያሱ አባት (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"ማቋረጥ" ማለት "ከወንዙ ማዶ መሄድ/ወንዙን ማቋረጥ" ማለት ነው፡፡ "ከዚህ ዳርቻ ወደ ዮርዳኖስ ወዲያኛው ዳርቻ መሄድ/ማቋረጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"አንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢያሱን ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መገለጫ መልኮች ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ምድሪቱን በመጭው ጊዜ ለእስራኤል መስጠቱ የተገለጸው አስቀድሞ እንደሰጣቸው ተደርጎ ነው፡፡ ይህ ምድሪቱን በእርግጥ እንደሚሰጣቸው አጉልቶ ያሳያል፡፡ "ለእናንተ ሁሉንም ስፍራ እሰጣችኋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የወደፊት ሃላፊ ጊዜ የሚለውን ይመልከቱ)
"እናንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢያሱን እና የእስራኤል ህዝብን ሁለቱንም ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መገለጫ መልኮችን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው የዮርዳኖስን ወንዝ ሲያቋርጡ ኢያሱ እና እስራኤላውያን የሚጎዙበትን ስፍራ ሁሉ ነው፡፡ "በዚህ ምድር በምትሄዱበት ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌ ከኢያሱ ጋር ንግግሩን ቀጠለ
"የአንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢያሱን ብቻ ሳይሆን የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መገለጫ መልኮችን ይመልከቱ)
በቁጥር 5 "አንተ" እና "የአንተ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ኢያሱን ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መገለጫ መልኮችን ይመልከቱ)
"መተው" እና "መጣል" የሚሉት ቃላት በመሰረታዊነት አንድ አይነት ነገሮች ናቸው፡፡ ያህዌ እነዚህን አንድ ላይ ያጣመራቸው እዘኒህን ነገሮች እንደማያደርግ ለማጉላት ነው፡፡ "በእርግጥ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር እሆናለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ጥንድ አሉታዎች የሚሉትን ይመልከቱ)
ያህዌ ለኢያሱ ጥብቅ ትዕዛዛትን ሰጠው (ሃላፊነቶች -ሌሎች ጥቅሞች የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌ ኢያሱን በጽናት ፍርሃቶቹን እንዲያሸንፍ ያዘዋል፡፡ (ሃላፊነቶች -ሌሎች ጥቅሞች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአዎንታዊ ትዕዛዝ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ይህንን በትክክል ተከተል" ወይም "በትክክል ተከተላቸው" (ሃላፊነቶች -ሌሎች ጥቅሞች የሚለውን ይመልከቱ)
"ግብህን ጨብጥ" ወይም "ግብህ ላይ ድረስ"
ያህዌ ከኢያሱ ጋር ንግግሩን ቀጠለ
"ሁልጊዜ" የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ መናገር ተጋኖ የተገለጸበት ነው፡፡ (ኩሸት እና ማጠቃለል የሚሉትን ይመልከቱ)
አነዚህ ሁለት ቃላት በመሰረቱ አንድ ትረጉም ይዘዋል እናም ታላቅ ብልጽግናን ያጎላሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ያህዌ ኢያሱን ማዘዙን ያመለክታል፡፡ "እኔ አዝዤሃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌ ኢያሱን እያዘዘው ነው፡፡ (ሃላፊነቶች -ሌሎች ጥቅሞች የሚለውን ይመልከቱ)
በጥቅስ ውስጥ ቀረበው ቀጥተኛ ባለሆነ ጥቅስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ወደ ሰፈር ግቡ ህዝቡ ለራሱ የሚሆነውን እንዲያዘጋጅ እዘዙ፡፡ በሶስት ቀናት ውስጥ ይህንን ዮርዳኖስን አቋርጠው ያህዌ አምላካቸው እንዲወርሷት የሰጣቸውን ምድር ይወርሳሉ፡፡" (በጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ጥቅስ የሚለውን ይጠቀሙ)
ይህ የእስራኤልን ህዝብ ያመለክታል፡፡ "የእስራኤል ህዝብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ ያህዌ የሚገኝበትን ቀን እንደ መጀመሪያ ቀን እየቆጠረ ነበር፡፡ "ከአሁን በኋላ ሁለት ቀናት" ወይም "ከነገ በኋላ ባለው ቀን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡
"አቋርጡ" የሚለው የሚያመለክተው ከወንዙ ወዲያ ማዶ መሻገርን ነው፡፡ "ከዮርዳኖስ ወንዝ ወዲያ ማዶ ተጓዙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የሮቤል፣ የጋድ እና የምናሴ ነገድ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምስራቅ መቀመጥ መረጡ፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የሮቤል ትውልዶች ነበሩ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የጋድ ትውልዶች ነበሩ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌ ለሮቤላዊያን፣ ለጋድአዊያን እና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ መናገሩን ቀጠለ
"የእናንተ ትናንሽ ልጆች"
ይህ የሚያመለክተው ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ መስራቅ ያለውን ስፍራ ነው፡፡ ቆይቶ ብዙዎቹ እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ በስተ ምስራቅ ይኖራሉ፣ ስለዚህም ምስራቁን "ከዮርዳኖስ ማዶ" ብለው ይጠሩታል፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ሁሉም ገና በስተ ምስራቅ ናቸው፡፡ "ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ እስራኤላውያን የሚይዟቸውን በከነዓን የሚኖሩ ጠላቶቻቸውን ሁሉ እንደሚያሸንፉ ያመለክተል፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በዚያ በምድሪቱ በሰላም እንደሚኖሩ ያመለክታል፡፡
ይህ የዮርዳኖስን ምስራቃዊ ጎን ያመለክታል፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ለኢያሱ የመለሱለት እነዚህ እስረኤላውያን፤ በተለይ ሮቤላዊያን፣ ጋድአዊያን እና ከምናሴ ነገድ እኩሌታዎቹ ነበሩ፡፡
እነዚህ ሁለት ሀረጋት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ደግሞም ማናቸውንም አይነት መልክ የያዘ አለመታዘዝ እንደሚያስቀጣ አጉልተው ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሞት እንፈርድበታለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
እስራኤል እና እግዚአብሔር፤ ኢያሱ ለእስራኤል ህዝብ መሪ ሆኖ እንዲቀጥል ሁለቱም ባህርያት አስፈላጊው እንደሆኑ ይቆጥራሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
1 የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ "ሄዳችሁ ምድሪቱን፥ በተለይም ኢያሪኮን ሰልሉ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰዎች በስውር ላከ። እነርሱም ሄደው ረዓብ ወደምትባል ሴተኛ አዳሪ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። 2 ለኢያሪኮም ንጉሥ፦ እነሆ የእስራኤል ሰዎች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ ገብተዋል ብለው ነገሩት። 3 የኢያሪኮም ንጉሥ፡-አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ ወደ አንቺ የመጡትንና ወደ ቤትሽ የገቡትን ሰዎች አውጪ ብሎ ወደ ረዓብ መልእክት ላከ። 4 ነገር ግን ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሽሸገቻቸው። እርስዋም፦አዎን ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ ሆኑ አላወቅሁም፤ 5 የከተማውም በር የሚዘጋበት ጊዜ ላይ ሰዎቹ ወጡ፤ ወዴት እንደ ሄዱ አላውቅም፤ፈጥናችሁ ከተከተላችሁ ምናልባት ልትይዙአቸው ትችላላችሁ አለች። 6 እርስዋ ግን ወደ ሰገንቱ አውጥታቸው፤ በዚያም በጣሪያ ውስጥ ባዘጋጀችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሸጋቸው። 7 ሰዎቹ ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው። አሳዳጆችም እንደወጡ በሮቹ ተቆለፉ። 8 ሰዎቹም ሳይተኙ ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች። 9 ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦እግዚአብሔር ምድሪቱን አሳልፎ እንደሰጣችሁ እናንተንም መፍራት በላያችን እንደ ወደቀ፤ በምድሪቱም በሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደ ቀለጡ አውቃለሁ። 10 ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፤ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል። 11 ይህን በሰማን ጊዜ ልባችን ቀለጠ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተንሣ ከዚያ ወዲያ ለማንም ነፍስ አልቀርለትም። 12 እሁንም እባካችሁ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንዳደረግሁ እናንተ 13 ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድታደርጉ፥ አባቴንና እናቴን፥ ወንድሞቼንና እኅቶቼንና ቤተ ሰቦቻቸውን ሁሉ እንድታድኑ፤ እንዲሁም ከሞት እንድታድኑን በእግዚአብሔር ማሉልኝ እውነተኛ ምልክትም ስጡኝ። 14 ሰዎቹ፦ "ይህን ነገራችንን ባትገልጪ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ እስከሞት እንኳ ይሆናል፤ እግዚአብሔርም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ምሕረትን እናደርጋለን እንዲሁም ታማኝ ሆነን እንገኛለን፤" አሉአት። 15 ቤትዋም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ስለነበረ በመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው። 16 እርስዋም፦አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ ኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለቻቸው። 17 ሰዎቹም አሉአት፦ይህን የምንልሽን ካላደረግሽ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን። 18 እነሆ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ክር እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው ፤አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የእባትሽንም ቤተ ሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ቤት ሰብስቢ። 19 ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ሁሉ ደሙ በራሱ ላይ ይሆንበታል፤ እኛም ንጹሐን እንሆናለን። ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን አንድ ሰው ቢነካው ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል። 20 ነገር ግን ይህንን ጉዳያችንን ብትገልጪ እኛም ከዚህ ካማልሽን መሐላ የተነሣ የሰጠንሽን ተስፋ ከመጠበቅ ነፃ እንሆናለን። 21 እርስዋም፦ እንደቃላችሁ ይሁን አለች። ሰደደቻቸውም እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ክር በመስኮቱ በኩል አንጠለጠልችው። 22 እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ እዚያ ለሦስት ቀናት ቆዩ። በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም። 23 ሁለቱም ሰዎች ተመለሱ፤ ከተራራውም ወርደው ተሻገሩ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደረሰባቸውንም ሁሉ ነገሩት። 24 ለኢያሱም እንዲህ አሉት፦ በእውነት እግዚአብሔር ይህን አገር ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤ በአገሩም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከእኛ የተነሣ እየቀለጡ አሉት።
ይህ የኢያሱ አባት ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በዮርዳኖስ ወንዝ ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ስፍራ ስም ነው፡፡ ትርጉሙ "የግራር ዛፎች" ማለት ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሰዎች እስራኤላውያን ምድሪቱን እንዴት እንደሚወሯት መረጃ ለማግኘት የሄዱ ነበሩ፡፡
ጋለሞታይቱ ረዓብ ሁለቱን እስራኤላውያን ሰላዮች ከጉዳት ጠበቀች፡፡
ይህ የሆነው የንጉሡ መልዕክተኛ ከእርሷ ጋር ከመነጋገሩ አስቀድሞ ነው፡፡
ይህ ጋለሞታይቱን ረዓብን ያመለክታል
ቀኑ ወደ ምሽቱ ጨለማ መግባት የሚጀምርበት ጊዜ ነው
ይህ ሰዎቹን እንዴት እንደ ደበቀቻቸው በኢያሱ 2፡4 ላይ ሚገኝ የመረጃ ዳራ እና ማብራሪያ ነው፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)
ጣራው ጠፍጣፋ ጠንካራ ነበር፣ በመሆኑም ሰዎች በዙሪያው ሊረማመዱ ይችሉ ነበር
ልብስ ለመስራት የሚውል፣ ክር/ቃጫ ለማግኘት የሚተከል ተክል፡፡
ሰዎቹ ሰላዮቹን የተከተሏቸው ረዓብ በኢያሱ 2፡5 ላይ ከነገረቻቸው የተነሳ ነው፡፡
የወንዝ ወይም ሌላ የውሃ አካል፣ በእርምጃ ወደ ሌላኛው ዳርቻ በእርምጃ ለመሻገር የሚቻልበት ጥልቀት የሌለው ስፍራ
ይህ የሚያመለክተው በምሽቱ ወደ መኝታ መሄድን ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"እናንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክው መላውን የእስራኤል ሰዎች ነው፡፡ (እናንተ የሚለውን ቃል መገለጫ መልኮችን ይመልከቱ)
ፈርተናል የሚለው የተገለጸው ፍርሃት ራሱ መጥቶ እንዳጠቃቸው ተደርጎ ነው፡፡ "እናንተን ፈራን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የፈራውን ህዝብ ከሚቀልጥና ከሚወርድ በረዶ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉሞች ሊሆኑ የሚችሉት 1) በእስራኤላውያን ፊት ደካማ እንደሚሆኑ ወይም 2) እንደሚበታተኑ ነው፡፡ "እናንተን መቋቋም እስከማይችሉ ድረስ እጅግ ይፈራሉ" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ረዓብ ከእስራኤላውያን ሰላዮች ጋር መነጋገሯን ቀጠለቸ
ይህ የቀይባህር ሌላው ስም ነው
እነዚህ የአሞራውያን ነገሥታት ስሞች ናቸው፡፡(ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ በአንድ ላይ የቀረቡት ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ልባችን ቀለጠ" የሚለው ሃረግ የፈሩትን የኢያሪኮ ሰዎች ልብ እየቀለጠ ከሚወርድ በረዶ ጋር ነው ያነጻጽራል፡፡ (ጥንድ ትረጉም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)
ረዓብ ከእስራኤላውያን ሰላዮች ጋር መነጋገሯን ቀጠለቸ
እነዚህ ረዓብ ከሰለዮቹ እርግጠኛ የሆነ ምልክት መፈለጓን የሚገልጹ ተመሳሳይ ሃሳቦች ናቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
"እናንተ" የሚለው ቃል ሁለቱን ሰላዮች ያመለክታል፡፡ (እናንተ የሚለውን ቃል መገለጫ መልኮችን ይመልከቱ)
"አትግደሉን" የሚለውን ትሁት በሆነ መንገድ መግለጽ፡፡ (ዩፊሚዝም/የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
እስራኤላውያን ሰላዮች ረዓብ የጠየቀችውን በኢያሱ 2፡12 ቃል የገቡላትን ፈጸሙ
እስከ ሞት ድረስ እንኳን ቢሆን፣ ህይወታችንን ለእናንተ ህይወት ይህ ፈሊጥ ቃልኪዳናቸውን ካልጠበቁ እግዚአብሔር እርግማኑን በእነርሱ ላይ እንዲያመጣባቸው የሚምሉበት እና የሚጠይቁበት መንገድ ነው፡፡ "ቃል የገባነውን ሳናደርግ ብንቀር፣ ያህዌ እኛን ያጥፋን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እስራኤላውያኑ ሰላዮች ከረዓብ ጋር መነጋገራቸውን ቀጠሉ፡፡
ይህ ሰላዮቹ ለረዓብ የገቡትን ቃል ኪዳን የሚፈጽሙበትን ሁኔታ ይገልጻል፡፡ "ይህ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው " ይህንን ደማቅ ቀይ ገመድ በመስኮቱ በኩል እሰሪው " የሚለውን በኢያሱ 2፡18 የሚገኘውን ነው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታ የሚለውን ይመልከቱ)
እስራኤላውያኑ ሰላዮች በኢያሱ 2፡15 የገለጹትን ሁኔታ ያብራራሉ፡፡
እስራኤላውያኑ ሰላዮች ከረዓብ ጋር መነጋገራቸውን ቀጠሉ፡፡
ይህ ሃረግ መላምታዊ በመፍጠር አንድን ሁኔታ ይገልጻል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "ደም" የሚለው የሚገልጸው የአንድ ሰውን መሞት ነው፡፡ ለራሳቸው ሞት ተጠያቂነቱ የተገለጸው ደም በራሳቸው ላይ እንደሚሆን ተደርጎ ነው፡፡ "ሞታቸው የገዛ ራሳቸው ጥፋት ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)
"ንጹሃን እንሆናለን"
እዚህ ስፍራ "እጅ ቢጫን" የሚለው አንድ ሰው እንዲጎዳ ምክንያት መሆን በጨዋ አገላለጽ የተገለጸበት ነው፡፡ "በማንም ላይ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት ብንሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
ሁለቱ እስራኤላውያን ሰላዮች ከረዓብ ጋር መነጋገራቸውን ቀጠሉ፡፡
ሰላዮቹ ረዓብ ወደ እርሷ መምጣታቸውን እንዳትናገር ጠየቋት፣ ወይም ይህ ካልሆነ ቤተሰቧቿን ለማዳን ከገቡት መሃላ ነጻ ይሆናሉ፡፡
"አንቺ" የሚለው ረዓብን ያመለክታል፡፡ (አንቺ የሚለውን ቃል መገለጫ መልኮችን ይመልከቱ)
ረዓብ ቤተሰቧችዋ እንዲጠበቁ ከእነርሱ የመሃላ ቃል ጋር ተስማማች
ሁለቱ እስራኤላውያን ኢያሪኮን ለቀው ወጡ፡፡
ወደ ኢያሪኮ ተመለሱ ማለቱ ሊረዳ ይችላል፡፡ "የእነርሱ አሳዳዶች ወደ ኢያሪኮ ከተማ ተመለሱ" በሚለው ውሰጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው ሰላዮቹን ያላገኟቸውን ሰዎች ነው
ሁለቱ ሰዎች ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ተመለሱ፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ እስራኤላውያን ወዳረፉበት ስፍራ መመለሳቸውን የሚገልጹ ተመሳሳይ አባባሎች ናቸው
"አቋርጠው" ማለት ከወንዙ ተቃራኒ ዳርቻ መሄድ ማለት ነው፡፡ "ከዚህኛው ዳርቻ ወደ ተቃራኒው የዮርዳኖስ ዳርቻ መሄድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የወንድ ስም ነው፤ የኢያሱ አባት፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እኛ" የሚለው ቃል እስራኤልን ያመለክታል
የምድሪቱ ነዋሪዎች ለእስራኤላዊያን ያላቸው አቋም ሲታይ በሙቀት እንደሚቀልጥ ነገር ይመስላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
1 ኢያሱም በጠዋት ተነሣ፥ እነርሱም ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፤ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ሳይሻገሩም በዚም ሰፈሩ። 2 ከሦስት ቀንም በኋላ አለቆች በሰፈሩ መካከል ሄዱ። 3 ሕዝቡንም እንዲህ ብለው አዘዙ፦የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ መከትል አለባችሁ። 4 በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን። በዚህ መንገድ በከዚሄ በፊት አልሄዳችሁበትምና የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ። 5 ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ እግዚእአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ነገ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱ። 6 ከዚያም ኢያሱ ካህናቱን እንዲህ አለ፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ። ስለዚህ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት አለፉ። 7 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በዚህ ቀን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደርጋለሁ። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከእንተ ጋር መሆኔን ያውቃሉ። 8 አንተም የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት፦ በዮርዳኖስ ውኃ ዳር ስትደርሱ በዮርዳኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ ታዛቸዋለህ። 9 ከዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አለ፦ ወደዚህ ቀርባችሁ የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ቃል ስሙ አለ። 10 ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነና እርሱም ኤዊያዊውንም ፈርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ከፊታችሁ ፈጽሞ እንደሚያወጣ በዚህ ታውቃላችሁ። 11 እነሆ የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ በዮርዳኖስ ውስጥ ያልፋል። 12 አሁምን ከእስራኤል ነገዶች አሥራ ሁለት ሰዎችን ምረጡ፤ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን። 13 እንዲህም ይሆናል የምድርም ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት የእግራቸው ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ሲቆም የዮርዳኖስም ውኃ ይቆማል፤ ከላይ የሚፈሰው ውኃ ሳይቀር መፍሰሱን ያቆማል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል። 14 ሕዝቡም ዮርዳኖስን ለመሻገር ከድንኳናቸው በወጡ ጊዜ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ቀድመው ሄዱ። 15 የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ወደ ዮርዳኖስ እንደመጡ፤ እግራቸውም የውኃውን ጫፍ በጠለቁ ጊዜ (በመከር ወራት ሁሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ እንደሚፈስ) 16 ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ እንደ ክምርም ሆነ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ አጠገብ ተሻገሩ። 17 የእስራኤልም ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው አስኪሻሩ ድረስ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካክል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር።
"ተነሱ" የሚለው ሃረግ "መንቃት" ማለት ነው፡፡
እስራኤላውያን ወደ ተስፋ ምድራቸው ወደ ከነዓን ከመግባታቸው አስቀድሞ ከሰፈሩበት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምዕራብ በሞአብ ምድር የሚገኝ ስፍራ
እነዚህ የማዘዝ ወይም ስልጣን ደረጃን የያዙ ሰዎች ናቸው
ይህ የእስራኤል ህዝብ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
"2,000 ክንድ" ክንድ የሚለው ቃል ከክርን እስከ ጣት ጫፍ ድረስ ያለው እርቀት መለኪያ ነው፡፡ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ርቀት እና ቁጥሮች የሚሉትን ይመልከቱ)
ይህ በያህዌ ፊት ንጹህ ለመሆን የሚደረግን ልዩ ዝግጅት ያመለክታል፡፡
ያህዌ ሁሉም የሚያየው እና የሚዳስሰው ተአምራት ያደርጋል
ይህ ሌዋውያን ታቦቱን ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ይዘው መሄዳቸውን ያመለክታል
ካህናቱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያህዌ ለኢያሱ ነገረው፡፡
ዐይኖች የሚለው ማየትን ሲወክል ፣ ማየት የሚለው ማሰብን ወይም ፍርድን ይገልጻል፡፡ "ህዝቡ የማደርገውን ያያል፣ ደግሞም አንተን ታላቅ ሰው እንዳደረግኩህ ያስተውላሉ" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ወደ ዳርቻ ወይም ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ደረሰ
ያህዌ ምን ሊያደርግ እንደሆነ ኢያሱ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፡፡ከፊታችሁ ሊያጠፋቸው ያህዌ በምድሪቱ የሚኖሩ ሌሎች ህዝቦችን ከምድሪቱ ይወጡ ዘንድ ወይም እንዲገደሉ ያደርጋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"አቋርጠው" ማለት ከወንዙ ተቃራኒ ዳርቻ መሄድ ማለት ነው፡፡ "ከዚህኛው ዳርቻ ወደ ተቃራኒው የዮርዳኖስ ዳርቻ መሄድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌ ምን ሊያደርግ እንደሆነ ኢያሱ ለእስራኤላውያን መናገሩን ቀጠለ፡፡
የእስራኤል አባቶች ቀይ ባህርን እንዳቋረጡ፣ እነዚህ ሰዎች ዮርዳኖስን በደረቅ ምድር ያቋርጣሉ
ይህ የሚያመለክተው የእግራቸውን ስር ነው
ይህ ቃል የሚያመለክተው የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ ወደ እስራኤል የሚወርድበትን አቅጣጫ ነው
ውሃው በአንድ ነጥብ ወይም ስፍራ ላይ ይቆማል፡፡ ካህናቱ ዙሪያ አይፈስም
ይህ የውሃውን ገጽ እንዲሁም ውሃው ወደ ደረቅ ምድር የሚፈስበትን ዳርቻ ያመለክታል፡፡ (ስኔክቲኪ/ ዘይቤያዊ አነጋጋር- የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ፤ የሚለውን ይመልከቱ)አሁን ዮርዳኖስ ውሃ ሞልቶ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ይፈስ ነበር ይህ የመረጃ ዳራ ያህዌ ሊያደርግ ያለውን አጉልቶ ያሳያል፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)
ተአምራዊው የዮርዳኖስ ባህር መውረዱ ቀጠለ
ይህ የዮርዳኖስ ወንዝ የሚፈስበትን ያመለክታል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ሃረግ ከወንዙ ተቃራኒ ዳርቻ መሄድ ማለት ነው፡፡ "ከዚህኛው ዳርቻ ወደ ተቃራኒው ዳርቻ መሄድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
1 ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ 2 "ከሕዝቡ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎች ምረጥ። 3 እንዲህ ብለህ ትእዛዝ ስጣቸው፦"በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ አሥራ ሁለት ድንጋዮችን አንሡ፤ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው።" 4 ከዚያም ኢያሱ ከእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንድ አንድ ሰው የመረጣቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ጠራቸው። 5 ኢያሱም አላቸው፦"በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በዮርዳኖስ መካከል፤ እያንዳንዱም ሰው በጫንቃው ከአንዳንድ ድንጋይ ጋር በእስራኤል ልጆች ሁሉ ነገድ ቁጥር አሥራ ሁለት ድንጋዮችን ተሸክመው ይለፉ። 6 ፤ልጆቻችሁም በሚመጣው ዘመን፦ እነዚህ ድንጋዮች ለእናንተ ምን ትርጉም አላቸው? ብለው በሚጠይቁበት ጊዜ ይህ በመካከላችሁ ምልክት ይሆናል። 7 በዚያን ጊዜ እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትመልሳላችሁ፦ "በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት የዮርዳኖስ ውኃ ስለተቋረጠ ነው። በተሻገሩም ጊዜ የዮርዳኖስ ውኃ ቆመ፤ እነዚህም ድንጋዮች ለእስራኤል ልጆች ለዘላለም መታሰቢያ ይሆናሉ።" 8 የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቁጥር ከዮርዳኖስ መካከል እንደ እስራኤል ነገድ ቁጥር አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ። በዚያም በሚያድሩበት ስፍራ አኖሩአቸው። 9 ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎችን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ተከለ። እስከ ዛሬም ድረስ መታሰቢያ ሆነው በዚያ አሉ። 10 ሙሴም ኢያሱን እንዳዘዘው ሁሉ እግዚአብሔር ኢያሱን ለሕዝቡ እንዲነገር ያዘዘው ነገር ሁሉ እስክፈጸም ድረስ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ነበር። ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ። 11 ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው መሻገራቸውን በጨረሱ ጊዜ የእግዚአብሔር ታቦትና ካህናቱ በሕዝቡ ፊት ተሻገሩ። 12 ሙሴም እንዳዘዘቸው የሮቤል ልጆች፥ የጋድም ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእስራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ። 13 አርባ ሺህ ያህል ሰዎች ጋሻና ጦራቸውን ይዘው ለጦርነት በእግዚእብሔር ፊት ወደ ኢያሪኮ ሜዳ ተሻገሩ። 14 በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው። ሕዝቡም ሙሴን እንዳከበሩት በዕድሜው ሁሉ አከበሩት። 15 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 16 "የምስክርን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት ከዮርዳኖስ እንዲወጡ እዘዝ።" 17 ኢያሱም ካህናቱን፦ ከዮርዳኖስ ውጡ ብሎ አዘዛቸው። 18 የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ከዮርዳኖስ መካከል በወጡ ጊዜና የካህናቱም እግር ጫማ ደረቅ መሬት መርገጥ በጀመረ ጊዜ የዮርዳኖስ ውኃ ወደ ስፍራው ተመለሰ፤ ቀድሞም ከአራት ቀናት በፊት እንደ ነበረ በዳሩርቻው ሁሉ መፍሰስ ጀመረ። 19 ሕዝቡም በመጀመሪያው ወር በአሥረኛው ቀን ከዮርዳኖስ ወጡ። ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ በኩል በጌልገላ ሰፈሩ። 20 ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን አሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አቆማቸው። 21 ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ "በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ አባቶቻቸውን፦ እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው? ብለው ሲጠይቁ፥ 22 ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ። 23 እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ እግዚአብሔር የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ። 24 የእግዚአብሔርም እጅ ጠንካራ እንደ ሆነች የምድር አሕዛብ ሁሉ እንዲያውቁ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ለዘላለሙ እንድታከብሩ ነው።
ምንም እንኳን ያህዌ በቀጥታ ለኢያሱ ቢናገርም፣ አንተ የሚለው በተጠቀሰ ጊዜ ሁሉ እስራኤልን ያጠቃልላል፡፡ (ተውላጠ ስም/የስም ምትክ የሚለውን ይመልከቱ)
"አቋረጠ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከወንዙ ተቃራኒ ዳርቻ መሄድን ነው፡፡ "አቋርጦ ሄደ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የዮርዳኖስ ወንዝ ፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
በጥቅስ ውስጥ የተቀመጠው ቀጥተኛ እንዳልሆነ ጥቅስ ሊቀርብ ይችላል፡፡ "ካህናቱ በደረቅ ምድር ቀመውበት ከነበረበት ስፍራ ከዮርዳኖስ መሃል አስራ ሁለት ድንጋዮችን እንዲያነሱ ይህንን ትዕዛዝ ስጣቸው፣ እነዚያንም ድንጋዮች ይዘህ መጥተህ ዛሬ ምሽት በምታድርበት ስፍራ አኑራቸው" (በጥቅስ ውስጥ ጥቅስ እና ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅሶች የሚሉትን ይመልከቱ)
ኢያሱ ለአስራ ሁለቱ ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ነገራቸው፡፡ወደ ዮርዳኖስ መሃል እያንዳንዳችሁ በትከሻችሁ ድንጋይ ትሸከማላችሁ እያንዳንዳቸው አስራ ሁለቱ ሰዎች ከዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ትልልቅ ድንጋይ አንስተው መተሰቢያ ለማኖር ወደ ሌላው ዳር ተሸክመው ወሰዱ፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ለእስራኤላውያን የአስራ ሁለቱ ድንጋዮች ክምር ትርጉሙ ምን እንደሆነ ነገራቸው
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ያህዌ የዮርዳኖስን ውሃ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት አቋረጠው" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
"የዮርዳኖስ ወንዝ ነበር"
የዮርዳኖስ ወንዝ ካህናቱ ተሸክመውት እስከ ነበረው ታቦት ድረስ እንዳይፈስ እግዚአብሔር አግዶት ነበር
ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ቁልቁል ይፈስ የነበረው ውሃ በታቦቱ ፊት ቆመ፣ ስለዚህም ታቦቱን ጨምሮ ሁሉም በደረቀ የወንዝ መፋሰሻ ተጓዙ
ኢያሱ እና መላው እስራኤል ያህዌ እንዳዘዘው መስራታቸውን ቀጠሉ
ይህ የሚያመለክተው አስራ ሁለቱ ወንዶች ከዮርዳኖስ ወንዝ መፍሰሻ ድናጋዮችን መሸከማቸውን ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ አስራ ሁለቱ ሰዎች ከወንዙ መፋሰሻ የተሸከሟቸው ድንጋዮች ሳይሆኑ አስራ ሁለት ተጨማሪ ድንጋዮች ነበሩ፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ማለት ጸሐፊው ይህንን መጽሐፍ እስከሚጽፍበት ቀን ድረስ መታሰቢያው በዚያ ነበር
ይህ የዮርዳኖስን ወንዝ ያመለክታል፡፡
ይህ የእስራኤልን ህዝብ ያመለክታል፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ማለት ከወንዙ ተቃራኒ ዳርቻ መሄድ ነው፡፡ "ከዚህኛው ዳርቻ ወደ ተቃራኒው ዳርቻ መሄድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው በህዝቡ ፊት መሆንን ወይም በሁሉም ህዝብ እይታ ውስጥ መሆንን ነው፡፡ እያንዳንዱ ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው አይቷል፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ እስራኤላውያንን በዮርዳኖስ ወንዝ ምስራቅ ለማስፈር እና ጦርነቱን በመምራት ግዴታቸውን የሚወጡ የሶስቱ ነገዶች ወታደሮች ነበሩ፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ህዝብ ነው
ይህ ማክበርን ብቻ የሚያመለክት አይደለም፣ ነገር ግን ሙሴን ሲከተሉ ያደርጉት እንደነበረው ለእርሱ ትዕዛዛት መገዛትን እና እርሱን እንደ ሰራዊቱ አዛዥ መቀበልን ጭምር ያመለክታል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ለቀደመው ትውልድ የዮርዳኖስን ወንዝ መክፈል ቀይ ባህርን ከመክፈል ልዩነት እንደሌለው ግልጽ እያደረገ ነበር የዮርዳኖስ ውሃ ወደ ቦታው ተመልሶ በዳርቻዎቹ ሞልቶ ፈሰሰ የዮርዳኖስ ወንዝ እስራኤላውያን በደረቅ ምድር ከማለፋቸው በፊት እና በኋላም በዳርቻዎቹ ሞልቶ ይፈስና አካባቢውን ያጥለቀልቅ ነበር አራት ቀናት "4 ቀናት" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ እስራኤል የዮርዳኖስ ወንዝን በደረቅ ምድር ማቋረጣቸውን ያመለክታል፡፡በአራተኛው ወር በአስረኛው ቀን ይህ በዕብራውያን ቀን አቋጣጠር የመጀመሪያው ወር ነው፡፡ አስረኛው ቀን በምዕራባውያን ቀን አቋጣጣር በመጋት መጨረሻ አቅራቢያ ነው፡፡ (የዕብራውያን ወራት እና ተከታታይ ቁጥሮች የሚሉትን ይመልከቱ)
ከዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥ ያወጧቸው አስራ ሁለቱ ድንጋዮች ኢያሱ በደረቅ ምድር የመሻገራቸውን መታሰቢያ መገንባት ይችል ዘንድ እያንዳንዱ ነገድ ከዮርዳኖስ ወንዝ አንድ ድንጋይ መውሰድ ነበረበት፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ለህዝቡ ስለ ድንጋይ ክምሩ ማስታወሱን ቀጠለ፡፡ ለልጆቻችሁ ንገሩ እስራኤላውያን ልጆቻቸው ያህዌን ለዘለዓለም ያከብሩ ዘንድ የእግዚአብሔርን ተአምራቶች ለእነርሱ ማስተማር ነበረባቸው፡፡ የያህዌ እጅ ታላቅ ነው ይህ የያህዌ ሃይል ታላቅ መሆኑን ያመለክታል፡፡ "ያህዌ ታላቅ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
1 በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል የነበሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፥ በታላቁም ባሕር አጠገብ የነበሩ የከነዓናውያን ነገሥታት ሁሉ፥ የእስራኤል ሕዝብ እስኪሻገሩ ድረስ የዮርዳኖስን ውኃ እግዚአብሔር እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ ልባቸው ቀለጠ፤ ከእስራኤልም ሕዝብ የተነሣ የአንድም ሕዝብ ነፍስ አልቀረላቸውም። 2 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፦"የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርተህ የእስራኤልን ሕዝብ እንደገና ግርዛቸው።" 3 ኢያሱም የባልጩት ድንጋይ ስለት ሠርቶ ግብት ሃራሎት (ትርጉሙም የግርዛት ኮረብታ) በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ወንዶች ሁሉ ገረዛቸው። 4 ኢያሱም የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ከግብፅ የወጡት ወንዶች ሁሉ ጦረኞችን ሁሉ ጭምር ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ። 5 የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ነገር ግን ከግብፅ በወጡበት መንገድ በምድረ በዳ የተወለዱት ሕዝብ ሁሉ አልተገረዙም ነበር። 6 ከግብፅ የወጡ የእስራኤል ሕዝብና ጦረኞች ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው እስኪሞቱ ድረስ አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይጓዙ ነበር ። እግዚአብሔርም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንደማያሳያቸው ማለላቸው። 7 እግዚአብሔር በእነርሱ ፋንታ ያስነሳቸው በመንገድ ሳሉ ሳይገረዙ የነበሩ ኢያሱም ገረዛቸው እነዚህን ልጆቻቸው ነበሩ። 8 ሕዝቡም ሁሉ በተገዙ ጊዜ እስኪድኑ ድረስ በሰፈር ውስጥ በየስፍራቸው ነበሩ። 9 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ይጠራል። 10 የእስራኤልም ሕዝብ በጌልገላ ሰፈሩ። ከወሩም በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በኢያሪኮ ሜዳ ፋሲካ አደረጉ። 11 ከፋሲካውም በዓል ቀን በኋላ በዚያው ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ቂጣና ቆሎ በሉ።. 12 ከምድሪቱም ፍሬ ከበሉበት ቀን በኋላ መና ተቋረጠ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ለእስራኤል ልጆች መና አልነበራቸውም፤ ነገር ግን በዚያ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ። 13 ኢያሱ ወደ ኢያሪኮ አጠገብ በነበረ ጊዜ ዓይኖቹን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው። 14 እርሱም፦ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ እዚህ መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ ጌታዬ ለአገልጋዩ የሚነግረው ምንድን ነው? አለው። 15 የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፦ አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።
እነዚህ ሁለት ሃረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው የፍርሃታቸውን ጥልቀት ያጎላሉ፡፡ (ትይዩ ተነጻጻሪ ዘይቤ/ፓራራሊዝም የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "ልቦች" የሚለው ድፍረትን ያመለክታል፡፡ ሰም በእሳት እንደሚቀልጥ ድፍረታቸው ቀልጦ ጠፍቶ እጅግ ፈርተው ነበር፡፡ "ድፍረታቸውን ሁሉ አጡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)በውስጣቸው ነፍስ አልቀረም ነበር እዚህ ስፍራ "ነፍስ" የሚለው የሚያመለክተው ለመዋጋት ያላቸውን ፈቃድ ነው፡፡ "ለመዋጋት አንዳች ፈቃድ አልነበራቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ከ600,000 በላይ ወንዶች ነበሩ፣ ስለዚህም ኢያሱ በዚህ ተግባር ላይ በነበረበት ጊዜ ሌሎች ብዙ ሰዎች እንደረዱት ግልጽ ነው፡፡ ይህ አንባቢውን ግራ የሚያጋባው ከሆነ፣ ተርጓሚው ይህንን ግልጽ ማድረግ ሊያስፈልገው ይችላል፡፡ "ኢያሱ እና እስራኤላውያኑ ራሳቸው የባልጩት ምላጭ አዘጋጅተው… ወንዶችን ሁሉ ገረዙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ እስራኤል ራሳቸውን ለያህዌ ዳግም መስጠታቸውን የሚታወስበት ስፍራ ስም ነው፡፡ ትርጉሙ "የሸለፈት ኮረብታ" ማለት ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የእስራኤል ወንዶች ሁሉ የሚገረዙበት ምክንያት ተገልጽዋል፡፡
ወታደር ለመሆን እድሜያቸው የደረሰ ወንዶች
እዚህ ስፍራ "ድምጽ" የሚለው የሚያመለክተው ያህዌ የተናገራቸውን ነገሮች ነው፡፡ "ያህዌ ያዘዛቸውን ነገሮች ታዘዙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)ወተት እና ማር የምታፈስ ምድር ምድሪቱ ወተት እና ማር ከእነዚያ እንስሳት እና ተክሎች በምድሪቱ እንደሚፈስ፣ ለእንስሳት እና ተክሎች መልካም እንደሆነች እግዘአብሔር ተናገረ፡፡"ከብቶችን ለማርባት እና እህል ለማብቀል እጅግ መልካም ሆነች ምድር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)
ውርደታቸው የተገለጸው መንገዳቸውን እንደዘጋ ትልቅ ድናጋይ/ቆጥኝ ተደርጎ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "አንከባልላለሁ" የሚለው "ማስወገድ" የሚል ትርጉም አለው፡፡ "በዚህ ዕለት የግብጽን ውርደት ከእናንተ ላይ አስወግጃለሁ" ወይም "በግብጽ ባሮች በነበራችሁ ጊዜ ተዋርዳችሁ ነበር፡፡ ዛሬ ግን፣ ከእንግዲህ የተዋረዳችሁ እንዳትሆኑ አድርጌያችኋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በምዕራባውያን ቀን አቆጣጠር ወደ መጋቢት መጨረሻ ነው፡፡ "የመጀመሪያው ወር አስራ አራተኛ ቀን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የዕብራውያን ቀን አቆጣጠር እና ተከታታይ ቁጥር እንዲሁም ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ ወደላይ አነሳ የሚለው የተነገረው ኢያሱ በቀጥታ ዐይኖቹን በእጆቹ እንዳነሳ ተደርጎ ነው፡፡ "አቅንቶ ሲመለከት አንድ ሰው ቆሞ አየ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር
"እነሆ" የሚለው ቃል ለአዲስ መረጃ ልዩ ትኩረት እንድንሰጥ ያነቃናል፡፡ እርስዎ የሚተረጉሙበት ቋንቋ ይህን የሚተረጉምበት የራሱ መንገድ ሊኖረው ይችላል፡፡
እዚህ ስፍራ "እርሱ" እና "የእርሱ" የሚሉት ቃላት ሚያመለክቱት ከኢያሱ ፊት የቆመውን ሰው ነው፡፡
"እርሱ" የሚለው ቃል ኢያሱ ያየውን ሰው ያመለክታል፡፡
ይህ ሰውየው ለኢያሱ ጥያቄ መልስ መስጠት የጀመረበት ነው፣ "አንተ ከእኛ ወይስ ከጠላቶቻችን ጋር ነህ?" ይሀ አጭር መልስ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "እኔ ከእናንተም ሆነ ከጠላቶቻችሁ ከየትኛውም ወገን አይደለሁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ኢያሱ በአምልኮ ወደ ምድር ተደፋ ይህ የአምልኮ ድርት ነበር፡፡ (ትምዕርታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ) ጫማህን ከእግርህ አውልቅ ይህ የውዳሴ/አምልኮ ድርጊት ነበር፡፡ (ትምዕርታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
1 ከእስራኤልም ሠራዊት የተነሣ የኢያሪኮ በሮች መጽሞ ተዘግተው ነበር። ወደ እርስዋም የሚገባና የሚወጣ ማንም አልነበረም። 2 እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን የሠለጠኑ ወታደሮችዋንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁ። 3 ሠራዊቶኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ መዞር አለባቸው። ይህንንም ለስድስት ቀናት አድርጉት። 4 ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ይዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ። 5 ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ የመለከቱንም ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኽ፥ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል። እያንዳንዱ ወታደር ወደፊት በመሄድ ማጥቃት አለባቸው። 6 ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አላቸው። 7 ሕዝቡንም፦ ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ሠራዊቱም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አለ። 8 ኢያሱም ለሕዝቡ እንደተናገረው ሰባቱ ካህናት ሰባቱን ቀንደ መለከት በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይዘው ወደፊት እያለፉ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ከኋቸው ይከተላቸው ነበር። 9 ሠራዊቱም በካህናቱ ፊት ቀንደ መለከታቸውን እየነፉ ይሄዱ ነበር፤ ከዚያም ከቃል ኪዳን ታቦት ኋላ ደጀን ጦር ይሄድ ነበር፤እንዲሁም ካህናቱ ቀንደ መለከታቸውን ያለማቋረጥ ይነፉ ነበር። 10 ኢያሱ ግን ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ እኔ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ፥ ከአፋችሁም ድምፅ አይውጣ፤ በዚያን ጊዜ ብቻ ትጮኻላችሁ። 11 ስለዚህ እግዚአብሔር የዚያን ቀን የቃል ኪዳን ታቦት አንድ ጊዜ ከተማይቱን እንዲዞር አደረገው፤ ከዚያም ወደ ማደሪያቸው ገቡ፤ ሌሊቱንም እዚያው አደሩ። 12 ከዚያም ኢያሱ ማለዳ ተነሣ ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ተሸከሙ። 13 ሰባቱም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በቀስታ እየሄዱ ቀንደ መለከቱንም ይነፉ ነበር። ሠራዊቱም በፊታቸው ይሄዱ ነበር። የደጀን ጦር ከእግዚአብሔር ታቦት ኋላ በሚድበት ጊዜ የቀንደ መለከት ድምፅ ያልማቋረጥ ይሰማ ነበር። 14 በሁለተኛውም ቀን ከተማይቱን አንድ ጊዜ ዞረው ወደ ሰፈር ተመለሱ፤ ስድስት ቀንም እንዲሁ አደረጉ። 15 በሰባተኛውም ቀን ሲነጋ ማልደው ተነሡ፥ ከዚህ በፊት በተለመደው ሁኔታ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ፤ ከተማይቱን ሰባት ጊዜ የዞሩት በዚያ ቀን ነው። 16 በሰባተኛውም ቀን ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ሲነፉ ኢያሱ ሕዝቡን አዘዘ፦ እግዚአብሔር ከተማይቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ። 17 ከተማይቱና በእርስዋም ያለው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየና ለጥፋት ይሆናሉ። የላክናቸውን መልክተኞች ስለ ሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋ ረዓብ ብቻና ከእርስዋም ጋር በቤትዋ ውስጥ ያሉት ሁሉ በሕይወት ይኖራሉ። 18 እናንተ ግን ለጥፋት የተለዩ ነገሮችን ከለያችሁት በኋላ አንዳች እንዳትወስዱ ራሳችሁን ጠብቁ። ለጥፋትም ከሆነው ነገር አንዳች የወሰዳችሁ እንደ ሆነ የእስራኤልን ሰፈር እንዲጠፋ ታደርጉታላችሁ፥ ችግርም ታመጣላችህ። 19 ብር፥ ወርቅ፥ ናስና ከብረት የተሠሩ ዕቃዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን። ወደ እግዚአብሔርም ግምጃ ቤት ይግባ። 20 ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ። ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታልቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ሲወድቅ፤ ሕዝቡም እያንዳንዱ አቅንቶ ወደ ፊቱ ወደ ከተማይቱ ወጣ፤ ከተማይቱንም ያዙ። 21 በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም ፥በጉንና አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ። 22 ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉትን ሁለቱን ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ ወደ ሴተኛ አዳሪዋ ቤት ግቡ ከዚያም ሴቲቱንና ከእርስዋ ጋር ያሉትን ሁሉ እንደ ማላችሁላት አውጡ። 23 ሰላዮቹም ወጣቶች ሄደው ረዓብን አውጧአት፤ አባትዋንና እናትዋን፥ ወንድሞችዋንም፥ አብሯት የነበሩ ቤተ ዘምዶችዋንም ሁሉ አወጡ። ከእስራኤልም ሰፈር ውጭ ወዳለው ስፍራ አመጦአቸው። 24 ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። ብሩ፥ ወርቅ፥የናሱና የብረት ዕቃዎች ብቻ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አስቀመጡአቸው። 25 ነገር ግን ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የሰደዳቸውን መልክተኞች የሸሸገች ሴተኛ አዳሪዋን ረዓብን፥ የአባትዋንም ቤተ ሰብ፥አብሯት የነበሩትንም ሁሉ ኢያሱ በሕይወት እንዲሆሩ ፈቀደላቸው። እርስዋም ኢያሱ ኢያሪኮን እንዲሰልሉ የላካቸውን ሰዎች ስለሸሸገች በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ትኖራለች። 26 በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ ይህችን ኢያሪኮ ከተማን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን። መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይሙት፥ እርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይሙት፥ ብሎ ማለ። 27 እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበር፤ ዝናውም በምድር ሁሉ ላይ ወጣ።
ይህ ቃል እዚህ ስፍራ ያገለገለው ዋናው የታሪክ መስመር ሌላ መስመር እንዲከተል ነው፡፡እዚህ ላይ ተራኪው የኢያሪኮ በሮች ለምን እንደተዘጉ እና እንደተቆለፉ ይነግረናል፡፡
ያህዌ ለኢያሱ ይህንን በእርግጥ እንደሚያደርግ የሚነግረው አስቀድሞ ነገሩ ያደረገው መሆኑን በመግለጽ ነው፡፡ (ሃላፊ የትንቢት ጊዜ የሚለውን ይመልከቱ)
"እጅ" የሚለው ቃል እጅ የሚፈጽመውን ለመቆጣጠር የሚውል ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ስለዚህ አንተ ይህንን መፈጸም ትችላለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ለኢያሱ ህዝቡ ማድረግ ያለበትን መናገሩን ቀጠለ
"ይህንን ለስድስት ቀናት በየዕለቱ በቀን አንዴ ማድረግ አለባችሁ"
ሰባቱ ካህናት ታቦቱን ከያዙና በከተማይቱ ዙሪያ ከሚጓዙ ሌሎች ካህናት ፊት ይሂዱ
እግዚአብሔር ለኢያሱ ህዝቡ ማድረግ ያለበትን መናገሩን ቀጠለ
"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰባቱን ካህናት ነው "ቀንደ መለከት" እና "መለከት" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት በኢያሱ 6፡4 የተጠቀሰውን ካህናቱ የሚነፉትን ቀንደ መለከት ነው
"የከተማይቱ ውጫዊ ቅጥር" ወይም "ከተማይቱ የታጠረችበት ገንብ"
የኢያሱ አባት ነው፡፡(ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዛችሁ ተጓዙ)
አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ያህዌን በመታዘዝ" ወይም 2) በያህዌ ታቦት ፊት ለፊት" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
x
ከአንድ ሰው አፍ የሚወጣ ድምጽ የሚያመለክተው የዚያን ሰው ንግግር ወይም ጩኸት ነው፡፡ "አትጩሁ ወይም አትናገሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ህዝቡን ከተማዋን መዞር ከመጀመራቸው አስቀድሞ አዘዛቸው፡፡ "ኢያሱ ህዝቡን አዝዞ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የድርጊቶች ቅደም ተከተል የሚለውን ይመልከቱ)
"7 ካህናት… 7 ድምጸ መለከቶች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ማለት ድምጸመለከቶቻቸውን ከፍ ያለ ድምጽ እንዲያሰሙ አድርገው ደጋግመው ነፉ ማለት ነው፡፡ "ያለማቋረጥ ድምጸ መለከቶቹ ከፍ ያለ ድምጽ እንዲያሰሙ አደረጉ" ወይም "ያለ ማቋረጥ ድምጸ መለከቶቹን ነፉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡
በሚቀጥለው ዕለት (ተከታታይ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ) እነርሱ ይህንን አደረጉ እስራኤል በኢያሪኮ ዙሪያ በእየለቱ አንድ ጊዜ ዞሩ
"6 ቀናት" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የእስራኤልን ህዝብ ያመለክታል
"ድምጸ መለከቶቹን ከፍ አድርገው ነፉ" ወይም "ድምጸ መለከቶቹን ነፉ"
ኢያሱ ያህዌ ከተማዋን በእርግጥ ለእነርሱ እንደሚሰጥ ነገሩ ከመሆኑ አስቀድሞ እንደተፈጸመ እየተናገረ ነው፡፡ (ኃላፊ የትንቢት ጊዜ የሚለውን ይመልከቱ)
"እናንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው መላውን የእስራኤል ህዝብ ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መገለጫ መልኮች ይመልከቱ)
ኢያሱ ለእስራኤል ህዝብ መናገሩን ቀጠለ
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከተማይቱን እና በውስጣ የሚኖሩትን ሁሉ ይጠፉ ዘንድ ለያህዌ መለየት አለባችሁ" ወይም " ከተማቱን እና በውስጧ ሚኖሩትን ሁሉ በማጥፋት ለያህዌ መለየት አለባችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
መጠንቀቅ የሚለው የተገለጸው ራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ነገሮቹን አለመውሰዳችሁን ጥንቃቄ አድርጉ" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በከተማይቱ ላይመጥፎ ነገር እንዲፈጠር አንዳች ነገር ማድረግ የተገለጸው በላይዋ ላይ ችግር ማምጣት በሚል ነው፡፡ "በእርሷ ላይ መጥፎ ነገር እንዲደርስ ምክንያት ትሆናላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌን ለማምለክ የተለዩ ነገሮች ስብስብ
"የእስራኤል ሰዎች ጮኹ"
"መለከቶቹን ከፍ አድረገው ነፉ" ወይም "ቀንደ መለከቶቹን ነፉ"
"የሰይፍ ስለት" የሚለው የሚገልጸው ወታደሮች በጦርነት ውስጥ የሚጠቀሙባቸውን ሰይፎች እና ሌሎች መሳሪያዎች ነው፡፡ "በሰይፎቻቸው በከተማይቱ ውስጥ የሚገኙትን ሁሉ ሙሉ ለሙሉ አጠፉ" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ ሚለውን ይመልከቱ)
"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው እስራኤላውያን ወታደሮችን ነው፡፡ ረዓብን እና ቤተሰቧቿን ከከተማይቱ ያወጡትን ሁለት ወጣት ወንዶች ብቻ የሚያመለክት አይደለም፡፡
"እርሷ" የሚለው ቃል ረዓብን እና ትውልዷቿን ያመለክታል፡፡ "የእርሷ ትውልድ በእስራኤል ይኖራል" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
"አሁን" ወይም "ዛሬ ድረስ፡፡" የመጀመሪያው ጸሐፊ ይህንን ታሪክ እንደጻፈው የረዓብ ትውልዶች አሁንም በእስራኤል ይኖራሉ
በያህዌ አይኖች ፊት የተረገመ የሚለው የሚገልጸው በያህዌ የተረገመ ማለትን ነው፡፡ "ዳግም የሚገነባት ሰው ያህዌ የረገመው ይሁን" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ለኢያሪኮ አዲስ መሰረትን የሚጀምር ሰው የሚከፍለው ዋጋ የመጀመሪያ ልጁ መሞት ነው፡፡ ይህ የተነገረው ሰውየው ለስራው እንደሚከፍለው ተመን/ዋጋ ተደርጎ ነው፡፡ "መሰረቱን ከጣለ፣ የመጀመሪያ ወንድ ልጁን ያጣል" ወይም "መሰረቱን ከጣለ፣ የመጀመሪያ ልጁ ይሞታል" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የኢያሪኮን አዲስ በሮች የሚያቆም ሰው የሚከፍለው ዋጋ የታኛሹ ልጁ መሞት ነው፡፡ ይህ የተነገረው ሰውየው ለስራው እንደሚከፍለው ተመን/ዋጋ ተደርጎ ነው፡፡ "በሮቿን ካቆመ፣ የመጨረሻ ልጁን ያጣል" ወይም " "በሮቿን ካቆመ፣ የመጨረሻ ልጁ ይሞታል" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የያህዌን ሳይሆን፣ የኢያሱን ዝና ያመለክታል፡፡ በምድሪቱ በሚኖሩ መሃል ታዋቂ ሆነ የሚለው የተገለጸው ዝናው እንደተስፋፋ ተደርጎ ነው፡፡ "ኢያሱ በምድሪቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ" ወይም "በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ስለ ኢያሱ አወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
1 የእስራኤል ሕዝብ ግን እንዲጠፉ ከተለዩ ነገሮች በመውሰድ ታማኝነትን አጎደሉ። ከይሁዳ ነገድ የሆነ አካን፥ እርሱም የከርሚ ልጅ፥ የዘንበሪ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ እንዲጠፉ ከተለዩት ነገሮች ወስደ፤ የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ። 2 ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤት አዌን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ከኢያሪኮ ሰዎችን ላከ። እርሱም፦ ውጡ ምድሪቱንም ሰልሉ ብሎ ተናገራቸው። ሰዎቹም ወጡ፥ ጋይንም ሰለሉ። 3 እነርሱም ወደ ኢያሱ ተመልሰው፡- ሕዝብን ሁሉ ወደ ጋይ አትላክ። ጋይን እንዲመቱ ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ይላክ። የጋይ ሰዎች በቁጥር ጥቂቶች ስለሆኑ ሕዝብ ሁሉ በውጊያ እንዲደክም አታድርግ። 4 ከሠራዊቱ ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ብቻ ወደዚያ ወጡ፤ እነርሱም ከጋይ ሰዎች ፊት ሸሹ። 5 የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያህል ሰዎችን መቱ፥ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው፤ በቁልቁለቱም መቱአቸው። የሕዝቡም ልብ ፈራ፤ ድፍረትንም አጡ። 6 ኢያሱም ልብሱን ቀደደ። እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድርስ በግምባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ። 7 ኢያሱም አለ፦ ወዮ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ ይህን ሕዝብ ቀድሞኑ ዮርዳኖስን ለምን አሻገርኸው? እንዲያጠፉን በአሞራውያን እጅ ለምን አሳልፈህ ሰጠሃን? ከዚህ የተለየ ምርጫ ማድረግ በቻልንና በዮርዳኖስም ማዶ በተመቀመጥን ይሻለን ነበር። 8 ጌታ ሆይ የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት ከሸሹ በኋላ ምን ማለት እችላለሁ? 9 ይህንን ከነዓናውያንና በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ይሰማሉ። እነርሱም ይከብቡናል፥ በምድር ያሉትም ሕዝብ ስማችን እንዲረሳ ያደርጋሉ። ለታላቁ ስምህስ የምታደርገው ምንድን ነው? 10 እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ተነስተህ ቁም! ለምን በግምባርህ ተደፍተሃል? 11 እስራኤል ኃጢአትን አድርጎአል። ያዘዝኋቸውንም ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል። ለጥፋት ከተለዩት ነገሮችን ሰርቀዋል፤ ሰርቀው የወሰዱትንም ኃጢአት በዕቃቸውም ውስጥ ሸሸጉት። 12 በዚህም ምክንያት የእስራኤል ሕዝብ በጠላቶቻቸው ፊት መቆም አይችሉም። ራሳቸው ለጥፋት የተለዩ ሆነው በጠላቶቻቸው ፊት ሸሹ። በመካከላችሁ እስካሁን ያለውን መወገድ ያለበትን እርም ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ ከዚህ በኃላ ከእናንተ ጋር አልሆንም። 13 ተነሣና ሕዝቡን ቀድስልኝ፤ እንዲህም በላቸው፦ራሳችሁን ለነገ ለእግዚአብሔር ቀድሱ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፤ እስራኤል ሆይ ፥ሊጠፉ የሚገቡ ነገሮች እስካሁን በመካከላችሁ አለ። መጥፋት ያልባቸው ነገሮች ከመካከላችሁ እስክታጠፉ ድረስ በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም። 14 ነገም ራሳችሁን በየነገዳችሁ ታቀርባላችሁ፤ እግዚአብሔርም በዕጣ የሚለየው ነገድ በየወገኖቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ወገን በየቤተ ሰቦቹ ይቀርባል። እግዚአብሔርም የሚለየው ቤተ ሰብ አንድ በአንድ ይቀርባል። 15 ለጥፋትም የተለየ ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን በማፍረሱና በእስራኤልም ላይ ክፉ ነገር እንዲመጣ በማድረጉ እርሱና ለእርሱም ያለው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠላል። 16 ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እስራኤልንም በየነገዶቻቸው አቀረበ፤ የይሁዳም ነገድ ተለየ። 17 የይሁዳንም ወገን አቀረበ፥የዛራም ወገን ለየ። የዛራንም ወገን እያንዳንዱን አቀረበ፤ ዘንበሪም ተለየ። 18 የቤተ ሰቡንም እያንዳንዱን አቀረበ፤ ከይሁዳም ነገድ የሆነ የከርሚ ልጅ የዘንበሪ ልጅ የዛራ ልጅ አካን ተለየ። 19 ከዚያ ኢያሱ አካንን አለው፦ ልጄ ሆይ፥ በእስራኤልም አምላክ ፊት እውነቱን ተናገር፥ ለእርሱም ተናዘዝ። ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ ከእኔም አትሸሽግ። 20 አካንም መልሶ ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእውነት የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በድያለሁ። ያደረግሁትም ይህንን ነው፦ 21 በዘረፋ መካከል አንድ የሚያምር የባቢሎን ኮት፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም። እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው አለው። 22 ኢያሱም መልእክተኞችን ሰደደ፥ ወደ ድንኳኑም ሮጡ፤ ዕቃዎቹም ነበሩ። በድንኳኑም ውስጥ ተሸሽጎ አገኙት ብሩም ከበታች ነበረ። 23 ከድንኳኑም መካከል ዕቃዎቹን ወስደው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ አመጡት። በእግዚአብሔርም ፊት አኖሩት። 24 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ኮቱንም፥ ወርቁንም፥ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያውዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው። 25 ኢያሱም እንዲህ አለው፦ ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔርም ዛሬ ያስጨንቅሃል። እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ሁሉንም በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው። 26 በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ሆነ። እግዚአብሔርም ከቁጣው ትኩሳት ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ነው።
"ያህዌ ፈጽማችሁ በማጥፋት/በመደምሰስ ለእኔ ለዩልኝ ያላቸው ነገሮች"
እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"ቁጣ" እና "ነደደ" የሚሉት የሚገልጹት በአካል እሳት እንዳለ ሳይሆን የቁጣውን ከፍተኛነት ደረጃ ነው፡፡ "የያህዌ ቁጣ እንድ እሳት ነደደ" ወይም "ያህዌ እጅግ ተቆጥቶ ነበር" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን ሰራዊት ነው፡፡
"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የጋይን ሰዎች ነው፡፡
እነዚህ ወንዶች የሰራዊቱ ክፍል ነበሩ፡፡ "የሰራዊቱ ክፍል የሆኑ ሶስት ሺህ ወንዶች ወጡ"
"3,000 ወንዶች… 36 ወንዶች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
"ቀለጠ" እና "እንደ ውሃ ሆነ" የሚሉት ሃረጋት ተመሳሳይ ትርጉምን ይጋራሉ፤ በአንድነት ተቀናጅተው የቀረቡት ሰዎቹ እጅግ ፈርተው እንደነበር አጉልቶ ለማሳየት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ ላይ ህዝቡ የተገለጸው በእነርሱ "ልቦች" ነው ይህም ስሜቶቻቸውን በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ "ህዝቡ እጅግ ፈርቶ ነበር" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ ሚለውን ይመልከቱ
"ህዝቡ" የሚለው ሃረግ የሚያመለክተው እስራኤላውያን ወታደሮችን ነው፡፡
እነዚህን ነገሮች ያደረጉት በእግዚአብሔር ፊት ምን ያህል እንዳዘኑ እና እንደተጨነቁ ለማሳየት ነው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ እግዚአብሔር ዮርዳኖስን አሻግሮ ያመጣቸው ምክንያቱ ይህ እንደሆነ እየጠየቀ ነበር፡፡ "ይህን የደረግከው አሞራውያን ያጠፉን ዘንድ ለእነርሱ እጆች አሳልፈህ ልትሰጠን ነውን?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኢሊፕሰስ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)
የአሞራውያን እጆች የሚለው የሚገልጸው አቅማቸውን እና ሃይላቸውን ነው፡፡ እነርሱን ለመደምሰስ እስራኤላውያንን ለእጆቻቸው መስጠት የሚለው የሚገልጸው አሞራውያን እስራኤላውያንን እንዲቆጣጠሩ እና እንዲያጠፏቸው መፍቀድን ነው፡፡ "አሞራውያን እንዲያጠፉን ትፈቅዳለህን?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
"ባደረግን ኖሮ" የሚለው ቃል የሚያሳየው አንድ ነገር ምነው ባልሆነ ኖሮ የሚል ፍላጎትን መግለጫ ነው፡፡ "ምነው የተለየ ውሳኔ አድርገን ቢሆን ኖሮ"
ኢያሱ መጨነቁን ለያህዌ ይገልጻል
ኢያሱ ይህን የሚናገረው ምን መናገር እንዳለበት እንኳን እስከሚረበሽ ድረስ ተስፋ መቁረጡን ለመግለጽ ነው፡፡ "ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም፡፡ እስራኤል ጀርባውን ለጠላት ሰጥቷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ማድረግ የሚገልጸው ከጠላቶቻቸው ፊት መሸሻቸውን ነው፡፡ "እስራኤል ከጠላቶቻቸው ሸሽተዋል/ እስራኤላውያንን ጠላቶቻቸው አሳደዋቸል" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ሰዎች የእስራኤልን ስም እንዲረሱ ማድረግ የሚገልጸው፤ እስራኤላውያንን እንዲረሱ ማድረግን ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህንን የሚያደርጉት እስራኤላውያንን በመግደል ነው፡፡ "ይከቡናል፣ ይገድሉንማል፤ ደግሞም የምድር ህዝብ ሁሉ ይረሳናል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)
"ታላቁ ስምህ" የሚለው ሃረግ እዚህ ስፍራ የሚገልጸው የእግዚአብሔርን ዝና እና ሃይል ነው፡፡ "እናም ስለዚህ አንተ ታላቅ መሆንህን ህዝቦች ያውቁ ዘንድ ምን ታደርጋለህ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ይህንን ጥያቄ ያነሳው እስራኤላውያን ከተደመሰሱ፣ ሌሎች ህዝቦች እግዚአብሔር ታላቅ አይደለም ብለው ያስባሉ የሚለውን ለእግዚአብሔር ለማሳሰብ/ እግዚአብሔርን ለማስጠንቀቅ ነው፡፡ "ከዚያ ለስምህ ታላቅነት ልታደርገው የምትችለው ምንም ነገር አይኖርም" ወይም "ከዚያ ሰዎች አንተ ታላቅ መሆንህን አያውቁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)
ያህዌ እስራኤል ለምን እንደተረገመ ለኢያሱ መለሰለት፡፡
እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት ኢያሱ በዚያ በፊቱ መደፋቱን ለመገሰጽ ነው፡፡ "በአፍር ላይ በዚያ መደፋትህን አቁም!" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ)
እነዚህ በኢያሱ 6፡18-19 "እንዲጠፉ የተለዩ" ነገሮች ናቸው፡፡ "የተረገሙት ነገሮች" ወይም "እግዚአብሔር የረገማቸው ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡
ኃጢአታቸውን መደበቅ የሚለው የሚገልጸው ኃጢአት መስራታቸውን ሌሎች እንዳያውቁ ለማድረግ መሞከራቸውን ይገልጻል፡፡ "እነዚያን ነገሮች ሰርቀዋል፣ ከዚያም ቀጥሎ ኃጢአት መስራታቸውን ሰዎች እንዳያውቁ ለማድረግ ሞክረዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
በጠላቶቻቸው ፊት መቆም የሚለው የሚወክለው ጠላቶቻቸውን ውጤታማ ሆነው መውጋት አይችሉም የሚለውን ነው፡፡ "ጠላቶቻቸውን ውጤታማ ሆነው መውጋት አይችሉም" ወይም "ጠላቶቻቸውን ማሸነፍ አይችሉም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ማድረግ የሚወክለው ከጠላቶቻቸው መሸሻቸውን ነው፡፡ "ከጠላቶቻቸው ሸሹ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ከእስራኤል ጋር መሆን የሚወክለው እስራኤልን መርዳትን ነው፡፡ "ከእንግደህ በኋላ አልረዳችሁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌ ከኢያሱ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ፤ ደግሞም ለህዝቡ መናገር ያለበትን ነገረው፡፡(ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የእስራኤልን ህዝብ ያመለክታል
ከጠላቶቻቸው ፊት መቆም የሚገልጸው ከጠላቶቻቸው ጋር ተዋግተው በስኬት ማሸነፍን ነው፡፡ "ከጠላቶቻችሁ ጋር በስኬት መዋጋት አትችሉም" ወይም "ጠላቶቻችሁን ማሸነፍ አትችሉም"
ያህዌ ከኢያሱ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ፤ ደግሞም ለህዝቡ መናገር ያለበትን ነገረው፡፡
የእስራኤልን ህዝብ የሚመሰርቱ አስራ ሁለት ነገዶች ነበሩ፡፡ "በየነገዶቻችሁ" የሚለው ሃረግ ትርጉሙ "በእያንዳንዱ ነገድ" ማለት ነው፡፡ "እያንዳንዳቸው ነገዶቻችሁ ራሳቸውን ለያህዌ ማቅረብ ይኖርባቸዋል " በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ነገድ ከበርካታ ጎሳ የሚመሰረት ነው፡፡ "ያህዌ ከለየው ነገድ፣ እያንዳንዱ ጎሳ ወደፊት ይቀርባል" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የእስራኤል መሪዎች እጣ ያወጣሉ፣ እናም ይህንን በማድረግ፣ ያህዌ የለየውን ነገድ ያውቃሉ፡፡ ይህ ይበልጥ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ያህዌ በእጣ የሚለየው ነገድ" ወይም "እጣ ስናወጣ ያህዌ የሚለየው ነገድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡
ጎሳ በብዙ ቤተሰቦች የሚመሰረት ነበር፡፡ "ያህዌ ከሚለየው ጎሳ፣ እያንዳንዱ ቤተሰብ ወደፊት መቅረብ ይኖርበታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ቤተሰብ በርካታ ሰዎች በውስጡ ነበሩት፡፡ "ያህዌ ከለየው ቤተሰብ፣ እያንዳንዱ ሰው ወደፊት መቅረብ ይኖርበታል" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ያህዌ የለየው ሰው" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ቃልኪዳንን ማፍረስ የሚለው ያለመታዘዝን ያመለክታል፡፡ "እርሱ የያህዌን ቃል ኪዳን አፍርሷል" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ እስራኤልን በያህዌ ፊት ለማቅረብ የያህዌን ትዕዛዝ ተከተለ
"በየነገዱ/ነገድ በነገድ" የሚለው ሃረግ እያንዳንዱ ነገድ ማለት ነው፡፡ "እያንዳንዱን የእስራኤል ነገድ ወደፊት አቀረበ" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በዐድራጊ አረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ያህዌ የይሁዳን ነገድ ለየ" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ፡፡
"በነፍስ ወከፍ/ በግለሰብ" የሚለው ሃረግ እያንዳንዱ ሰው የሚል ትርጉም የሚሰጥ ፈሊጥ ነው፡፡ በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ ግለሰቦች የተባሉት የቤተሰባቸው መሪዎች/አባወራ ነበሩ፡፡ "እርሱም የዛራውያንን ጎሳዎች እያንዳንዱን ሰው ወደፊት አቀረበ" ወይም "ከዛራውያን ጎሳ የቤተሰቡ መሪ የሆን እያንዳንዱን ሰው ወደፊት አቀረበ" (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)
ጎሳው ስሙን ያገኘው ዛራ ከተባለው ሰው ስም በመነሳት ነው
እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው፡፡ እነዚህን በኢያሱ 7፡1 ላይ በተረጎሙበት መሰረት ይተርጉሙ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"ንስሃ/ኑዛዜ" የሚለው ረቂቅ ስም "ተናዘዘ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ለእርሱ ተናዘዝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)
መረጃን መደበቅ የሚወክለው አንድ ሰው ነገሩን እንዳያውቅ ጠብቆ ለመያዝ መሞከርን ነው፡፡ "ያደረግከውን እንዳላውቅ ልትሸሽገኝ አትሞክር" (ዘይቤያዊ አነጋገርየሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ከሁለት ኪሎ ግራም በላይ ነው፡፡(መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክብደት መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ከ500 ግራም በላይ ነው፡፡ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ የክብደት መለኪያ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኔ በመሬት ውስጥ ደብቄያቸዋለሁ" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
"ኢያሱ የላካቸው ሰዎች አዩ/አገኙ"
በእርስዎ ቋንቋ ውስጥ የሚገኝን በርካታ ትንንሽ እቃዎችን ከትልቅ ቦርሳ/ሻንጣ መሬት ላይ መድፋትን የሚገልጽ ቃል ይጠቀሙ
የስሙ ትርጉም "የችግር ሸለቆ" ማለት ነው፣ ነገር ግን አኮርን በተጻፈበት አጠራሩ እንዳለ አኮር ብሎ መተርጎሙ ይመረጣል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት አካንን ለመገሰጽ ነው፡፡ "አንተ አኛን አስጨነቅከን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሰሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ሊሰጡ የሚችሉ አማራጭ ትርጉሞች 1)እስራኤላውያን የአካንን ቤተሰብ አቃጥለው ገደሉ፤ከዚያም ድንጋይ ከመሩባቸው ወይም 2) እስራኤላውያን የአካንን ቤተሰብ በድንጋይ ወግረው ገደሉ ከዚያም በድናቸውን አቃጠሉ ወይም 3) አካን እና ያለው ሁሉ በድንጋይ ተወገረ ከዚያም ተቃጠለ
ቁጣውን አራቀ የሚለው የሚገልጸው ቁጣውን አቆመ ማለት ነው፡፡ የሚነድ ቁጣ የሚለው የሚወክለው ጠንካራ ቁጣን ነው፡፡ "ያህዌ ከቁጣው ተመለሰ/መቆጣቱን አቆመ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይህንን እስከጻፈበት ጊዜ ድረስ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ይጠራ ነበር
1 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራ አትደንግጥ። ጦረኞችንም ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ። ተመልከት፥ የጋይን ንጉሥ፥ ሕዝቡን፥ ከተማውንና ምድሩን በእጅህ ሰጥቼሃለሁ። 2 በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ ምርኮውንና ከብቱን ግን ለራሳችሁ ትወስዳላችሁ። ከከተማይቱም በስተ ኋላ ድብቅ ጦር አዘጋዝጅ አለው። 3 ኢያሱም ተነሣና ጦረኞቹንም ሁሉ ወደ ጋይ ወሰዳቸው። ኢያሱም ጽኑዓን ኃያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መርጦ በሌሊትም ሰደዳቸው። 4 እንዲህም ብሎ አዘዘቸው፦ እነሆ፥ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ። ከከተማይቱ በጣም ርቃችሁ አትሂዱ፤ነገር ግን ሁላችሁም ተዘጋጁ። 5 እኔና ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማይቱ እንቀርባለን። እንደ በፊቱ ሊያጠቁን በሚመጡበት ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን። 6 አስቀድመን እንደ ሸሸን፥ የምንሸሸ ይመስላቸዋል፥ ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል። እንዲህም ይላሉ፦ባለፈው እንዳደረጉት ከፊታችን እየሸሹ ነው። እኛም ከእነርሱ እንሸሻለን። 7 እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ መጥታችሁ ከተማዋን ትይዛላችሁ። እግዚአብሔር አምላካችሁም እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል። 8 ከተማይቱንም በያዛችኋት ጊዜ በእሳት አቃጥሉአት። በእግዚአብሔርም ቃል እንደታዘዛሁ ታደርጋላችሁ። እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ። 9 ኢያሱም ሰደዳቸው፤ እነርሱም ወደሚደበቁበት ስፍራ ሄደው፥ በጋይና በቤቴል መካከልም ከጋይ በስተምዕራብ ተደበቁ። ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ። 10 ኢያሱም ማልዶ ተነሣና ሕዝቡን አሰለፈ፤እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች የጋይን ሕዝብ አጠቁ ። 11 ከእርሱም ጋር የነበሩ ጦረኞች ሁሉ ሄደው፥ ወደ ከተማይቱ ደረሱ። ወደ ከተማይቱ አጠገብ መጡና በሰሜን በኩል በጋይ ሰፈሩ። በእነርሱና በጋይ መካከል ሸለቆ ነበረ። 12 አምስት ሺህ ያህል ሰዎችንም ወስዶ በቤቴልና በጋይ መካከል በከተማይቱም በምዕራብ በኩል በድብቅ አስቀመጣቸው። 13 በከተማይቱ የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ፤ በከተማይቱ ሰሜን በኩል ዋና ጦርና በከተማይቱ ምዕራብ በኩል ደጀን ጦር ጠባቂዎችን አኖሩ። ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው አደረ። 14 የጋይም ንጉሥ ባየ ጊዜ ይህ ስለታወቀ፥እርሱና ሠራዊቱ በማለዳ ተነስተው እስራኤልን ለማጥቃት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ወዳለው ሰፍራ ቸኮሉ። ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር ለማጥቃት እንዳለ አያውቅም ነበር። 15 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ራሳቸው በፊታቸው ድል የተነሡ መስለው ወደ ምድረ በዳው መንገድ ሸሹ። 16 በከተማይቱም የነበሩ ሰዎች ሁሉ በአንድነት ከኋላቸው እንዲሄዱ ተጠሩ፤ ኢያሱንም አሳደዱት፥ ከከተማይቱም ርቀው ወጡ። 17 በጋይና በቤቴልም ውስጥ እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም። ከተማይቱንም ክፍት አድርገው፥ እስራኤልን አሳደዱ። 18 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ በእጅህ ያለውን ጦር በጋይ አነጣጥር፤ ጋይንም በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ። ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ። 19 የተደበቁትም ሠራዊት ፈጥነው ከስፍራቸው ወጥተው ኢያሱም እጁን እንደ ዘረጋ ሮጡ። ወደ ከተማይቱም ሮጡ፤ ገብተውም ያዙአት። ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት። 20 የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ተመለከቱ። ከከተማይቱ ወደ ሰማይ የሚወጣውን ጢስ አዩ፤ ወዲህ ወይም ወዲያም መንገድ ማምለጥ አልቻሉም። ወደ ምድረ በዳ ሸሽተው የነበሩ የእስራኤላውያን ጦር ሠራዊት ያሳድዱአቸው የነበሩትን ለመግጠም ተመለሱ። 21 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ ድብቅ ጦር ከተማይቱን እንደ ያዙ ወደ ላይ ከሚወጣ ጢስ ጋር ባዩ ጊዜ፥ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉ። 22 ሌሎቹም ወደ ከተማይቱ ሄደው የነበሩ የእስራኤል ሠራዊት ለማጥቃት ወጡ። ስለዚህም የጋይ ሰዎች በእስራኤል ሠራዊት መካከል ሌሎቹ በዚህ በኩልና ሌሎቹ በዚያ በኩል ተያዙ። እስራኤልም የጋይን ሰዎች አጠቁአቸው፤ አንዳቸውም አልተረፉም፤ አላመለጡምም። 23 በሕይወት የያዙትን የጋይንም ንጉሥ ማርከው ወደ ኢያሱ አመጡት። 24 እንዲህም ሆነ፤ የጋይን ሰዎች ሁሉ በሜዳና በምድረ በዳ አጠገብ እስራኤልን ሲያሳድዱ በነበሩበት ቦታ ሁሉም የመጨረሻ በሰይፍ ስለት እስኪ ወድቁ ድረስ ጨርሰው ከገደሉአቸው በኋላ፥ እስራኤል ሁሉ ወደ ጋይ ተመለሱ። በሰይፍም ስለት መቱአቸው። 25 በዚያም ቀን በሰይፍ ስለት የወደቁት ወንዶችና ሴቶች የጋይ ሰዎች ሁሉ አሥራ ሁለት ሺህ ነበሩ። 26 ኢያሱም የጋይን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ ጦር የዘረጋባትን እጁን አላጠፈም። 27 እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዳዘዘው የዚያችን ከተማ ከብትና ምርኮ ለራሳቸው ወሰዱ። 28 ኢያሱም ጋይን አቃጠላት፥ ለዘላለም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆን አደረጋት። እስከ ዛሬም ድረስ ባዶ ስፍራ ሆነች። 29 የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው። ኢያሱም ፀሐይ በገባች ጊዜ የንጉሡን አስክሬን ከዛፍ አወርደው፥ በከተማይቱ በር አደባባይ እንዲጥሉት አዘዘ። በላዩም ታላቅ የድንጋይ ክምር አደረጉት። እስከ ዛሬ ድረስም ይህ የድንጋይ ክምር አለ። 30 ከዚያም ኢያሱ በጌበል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ። 31 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ እንዳዘዘ፦ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደተጻፈው፥ መሠዊያው ካልተወቀረ ድንጋይና ብረት ካልነካው ነበረ። በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዉ። 32 የእስራኤልም ሰዎች ፊት በድንጋዮቹ ላይ የሙሴን ሕግ ቅጂ ጻፈባቸው። 33 እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ በመጻተኞችና በአገሩ ልጆች ፥እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ሆነው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በካህናትና በሌዋውያን ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘ፥የእስራኤልን ሕዝብ አስቀድሞ ባረኩ። 34 ከዚህም በኋላ ኢያሱ በሕጉ መጽሐፍ እንደ ተጻፉ የሕጉን ቃሎች ሁሉ በረከቱንና እርግማኑን አነበብ። 35 ኢያሱም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ፊት በሴቶቹም፥ በሕፃናቱም፥ በመካከላቸውም በሚኖሩት መጻተኞች ፊት ሙሴ ካዘዘው አንዲት ቃል ሳያስቀር ሁሉን አነበበ ።
እነዚህ ሁለት ሃረጋት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ያህዌ ያቀናጃቸው ለፍርሃት አንዳች ምክንያት ስለሌለ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
እነርሱን ለእስራኤላውያን እጆች አሳልፎ መስጠት የሚወክለው ለእስራኤል ድልን እና የበላይነትን መስጠትን ነው፡፡ "በጋይ ንጉሥ እና በህዝቡ ላይ ደግሞም በእርሱ ከተማ እና በምድሩ ላይ ድልን ሰጥቼሃለሁ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
እግዚአብሔር ሊያደርግ ቃል የገባውን ልክ እንዳደረገው ያህል ይናገራል፣ ምክንያቱ እርሱ በእርግጥ ስለሚያደርገው ነው፡፡ "እኔ በእርግጥ ሰጥቼሃለሁ" ወይም "እኔ እሰጣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትንቢታዊ ኃላፊ ጊዜ የሚለውን ይመልከቱ)
"እርሷ" የሚለው ቃል የጋይን ከተማ ያመለክታል፡፡ ከተማዎች ብዙውን ጊዜ ሴት እንደሆኑ ተደርጎ ይነገሩ/ይገለጹ ነበር፡፡ "ንጉሥዋ" ወይም "የእነርሱ ንጉሥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
"የእስራኤል ሰራዊት"
"30,000 ወንዶች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ለወታደሮቹ የጦር ሜዳውን እቅድ መግለጹን ቀጠለ
እዚህ ስፍራ "እጅ" ምሳሌነቱ እስራኤላውያን በጠላቶቻቸው ላይ ያላቸውን የበላይነት እና ሃይል የሚገልጽ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ለወታደሮቹ የጦር ሜዳውን እቅድ መግለጹን አጠናቀቀ፡፡
ይህ ሃረግ የሚያመለክተው ኢያሱ በጋይ እንዲያደፍጡ የተመረጡ ሰላሳ ሺህ ወንዶችን መላኩን ነው
"ጥቃት የማድረሻው ጊዜ እስኪደርስ ድረስ እነርሱ የሚደበቁበት ስፍራ ነው"
ይህ ቡድን ከ"ሰላሳ ሺህ ወንዶች" ውስጥ የተወሰደ ይመስላል (ኢያሱ 8፡9)፡፡ 25,000 የሚያህሉት ወንዶች ከተማዋን ሲያጠቁ ይህ አነስ ያለው ቡድን አድፍጦ ቆየ፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እስራኤላውያን ጋይን ለመውጋት ተዘጋጁ
ይህ በደፈጣ ላይ ከሆኑት ውጭ ያለውን ትልቁን የተዋጊ ቡድን ያመለክታል
እነዚህ "በከተማይቱ ምዕራብ አቅጣጫ አድፍጠው የተቀመጡ" ናቸው (ኢያሱ 8፡12 ይመልከቱ)
"ከጋይ ሰዎች አስቀድሞ ራሳቸው ይሸነፉ" "ከእነርሱ አስቀድሞ" የሚለው ሃረግ የሚወክለው የጋይ ሶች የሚያዩትን እና የሚያስቡትን ነው፡፡ "የጋይ ሰዎች እስራኤላውያን እንደተሸነፉ ያስቡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
"ይሸነፉ" የሚለው ሃረግ በአድርጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የጋይ ሰዎች እስራኤላውያንን ያሸነፉ ይምሰላቸው" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "ከእነርሱ" እና "እነርሱ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት የጋይን ሰራዊት ነው፡፡
እዚህ ስፍራ "ከእነርሱ" እና "እነርሱ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት የእስራኤልን ሰራዊት ነው
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የከተማይቱ መሪዎች የከተማይቱን ህዝብ በአንድነት ጠሩ" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ስለ ሁሉም ሰዎች አጠቃላይ በሆነ መንገድ ይጽፋል፣ ነገር ግን፣ "ሰዎች ሁሉ" የሚለው የሚያመለክተው መዋጋት የሚችሉትን ሰዎች ብቻ ነው፡፡ "በከተማይቱ የነበሩ የእስራኤልን ሰራዊት ማባረር የሚችሉ ሰዎች ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና ማጠቃለያ የሚሉትን ይመልከቱ፡፡
"ከተማይቱን ክፍት ትተው"
እዚህ ስፍራ "ወደቁ" የሚለው ሞቱ/ተገደሉ ለሚለው ኢፊሚዝም/የማያስደስትን ቃለ ሻል ባለ ቃል መጠቀም ነው፡፡ እንደዚሁም "የሰይፍ ስለት" የሚለው የሚወክለው ሰይፎችን በሙሉ ሲሆን ሰይፎች የሚለው የሚወክለው አንድም ጦርነትን ወይም የእስራኤልን ሰራዊት ነው፡፡ "በጦርነቱ ውስጥ ሞቱ" ወይም "የእስራኤል ወታደሮች በወጓቸው ጊዜ ሞቱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኢፊሚዝም/የማያስደስትን ቃለ ሻል ባለ ቃል መጠቀም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"12,000" ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ
ይህ በአንድ ወቅት ሰዎች የሚኖሩበት፣ አሁን ግን ማንም የማይኖርበት ስፍራ ነው
"ዛሬ" ወይም "አሁን ድረስ"
በከነዓን የሚገኝ ተራራ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአዎንታዊ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ኢያሱ ሙሴ ያዘዘውን ቃል ሁሉ አነበበ" ወይም "ኢያሱ የሙሴን ህግጋት ሁሉ አነበበ" (ድርብ አሉታዎች)
ይህ የእስራኤልን መንግስት ያመለክታል
1 ከዚያም በዮርዳኖስ ማዶ በተራራማውና በቆላማው በታላቁ ባሕር ዳርቻ በሊባኖስም ፊት ለፊት የነበሩ ነገሥታት ሁሉ፥ ኬጢያዊ አሞራዊም ከነዓናዊም ፌርዛዊም ኤዊያዊም ኢያቡሳዊም 2 ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። 3 የገባዖን ሰዎችም ኢያሱ በኢያሪኮና በጋይ ያደረገውን በሰሙ ጊዜ፥ 4 እነርሱ ደግሞ የማታለል ዕቅድ አደረጉ። ራሳችውን እንደ መልእክተኛ አድርገው ቀረቡ። ያረጀና የተቀደደ ጆኒያ ወስደው በአህዮቻቸውም ላይ ጫኑ። ደግሞም ያረጀ፥የተቀደደና የተሰፋ አሮጌ ወይን ጠጅ አቁማዳ ጫኑ። 5 ያረጀ የተሰፋም ጫማ በእግራቸው አደረጉ፤ አሮጌምና የተቀደድ ልብስም ለበሱ። ለስንቅም የያዙት እንጀራ ሁሉ የደረቀና የሻገተ ነበረ። 6 ኢያሱም ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ሄደው ለእርሱና ለእስራኤል ሕዝብ፦በጣም ሩቅ አገር ከሆነ ተጉዘን የመጠን ነን፥ ከእኛ ጋር ኪዳን አድርጉ አሉ። 7 የእስራኤልም ሰዎች ኤዊያውያንን፦ ምናልባት በመካከላችን የምትቀመጡ ትሆናላችሁ። እንዴትስ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን እናደርጋለን? አሉአቸው። 8 እነርሱም እንዲህ አሉት፦ እኛ የእናንተ አገልጋዮች ነን። ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ? 9 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ አሉት፦ እኛ አገልጋዮችህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ስም የተነሣ እጅግ ከራቀ አገር እዚህ መጥተናል። ዝናውንም በግብፅም ያደረገውን ሁሉ፥ 10 በዮርዳኖስ ማዶም በነበሩት በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሐሴቦን በንጉሥ በሴዎን በአስታሮትም በነበረው በባሳን ንጉሥ በዐግ ያደረገውን ሁሉ ሰምተናል። 11 ሽማግሌዎቻችንና በአገራችን የሚኖሩት ሁሉ፦ ለጉዞአችሁም ስንቅ በእጃችሁ ያዙ። ልትገናኙአቸውም ሂዱና እንዲህ በሉአቸው፦ እኛ አገልጋዮቻችሁ ነን፤ ከእኛም ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ። 12 ወደ እናንተ ለመምጣት በተነሣንበት ቀን ይህን እንጀራ ትኩስን ለስንቅ ከቤታችን የወሰደነው ነው። ነገር ግን ተመልከቱ፥ አሁንም ደረቅና የሻግብተ ነው። 13 እነዚህም የጠጅ አቁማዳዎች ስንሞላቸው አዲስ ነበሩ፤ እነሆም፥ ተቀድደዋል። ጉዞአችንም እጅግ ሩቅ ስለ ነበረ ልብሶቻችንና ጫማዎቻችን አርጅተዋል። 14 እስራኤላውያንም ከስንቃቸው ወሰዱ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔርም ምክርን አልጠይቁም ነበር። 15 ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ስምምነት አደረገ፥ በሕይወት እንዲተዋቸውም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። የማኅበሩም አለቆች ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ። 16 የእስራኤላውያንም ከገባዖን ሰዎች ጋር ቃል ኪዳኑን ካደረጉ ከሦስት ቀን በኋላ፥ ሰዎቹ እዚያው አጠገባቸው የሚኖሩ ጎረቤቶቻቸው መሆናቸውን ዐወቁ። 17 ከዚያም እስራኤላውያን ተዘጋጅተው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው መጡ። የከተሞቻቸውም ስም ገባዖን፥ ክፈራ፥ ብኤሮትና ቂርያትይዓይሪም ናቸው። 18 የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን አድርገው ስለነበረ እስራኤላውያንም ጥቃት አልደረሱባቸውም። የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ በመሪዎቹ ላይ አጉረመረሙ፥ 19 ነገር ግን መሪዎቹ ሁሉ ለማኅበሩ እንዲህ አሉ፦ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ቃል ኪዳን ስለገባንላቸው አሁን ጉዳት ልናደርስባቸው አንችልም፥ 20 የምናደርግላቸው ነገር ቢኖር ይህ ነው፦ የገባንላቸውን የቃል ኪዳን ማሐላ ብናፈርስ ቁጣ እንዳይደርስብን በሕይወት እንዲኖሩ ማድረግ ነው። የሕዝቡም አለቆች ለሕዝባቸው እንዲህ አሉ፦ በሕይወት ይኑሩ። 21 ስለዚህም የእስራኤል አለቆች ስለእነርሱ እንደ ተናገሩት ገባዖናውያን ለእስራኤላውያን ሁሉ እንጨት ሰባሪና ውኃ ቀጂ ሆኑ። 22 ከዚያም ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ እዚሁ በመካከላችን እየኖራችሁ፥ ከእናንተ ሩቅ ስፍራ ነው የመጠነው፥ ብላችሁ ያታለላችሁን ለምንድን ነው? 23 ስለዚህ በዚህ ምክንያት እናንተ የተረገማችሁ ናችሁ፥ አንዳንዶቻችሁም ለአምላኬ ቤት ሁል ጊዜ እንጨት ሰባሪና ውኋ ቀጂ አገልጋዮች ትሆናላችሁ። 24 እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፥ እግዚአብሔር አምላክህ አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው፥ ምድሪቱን በሙሉ ለእናንተ እንደሚሰጣችሁና ነዋሪዎቿንም ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው በእርግጥ ለእኛ አገልጋዮችህ ተነግሮናል፥ ስለዚህ ከእናንተ የተነሣ ለሕይውታችን በመሥጋት ይህን አድርገናል። 25 እነሆ አሁን በእጅህ ነን፥ መልካምና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን። 26 ስለዚህ ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ከእስራኤል ሰዎች እጅ አዳናቸ እስራኤላውያንም አልገደሏቸውም። 27 በዚያም ዕለት ኢያሱ የገባዖንን ሰዎች ለማኅበረ ሰቡና እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለሚቆመው የእግዚአብሔር መሠዊያ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ሰባሪችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው።
ለዮርዳኖስ ወንዝ አጭር ስያሜ ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)በአንድ እዝ ስር እዚህ ስፍራ "እዝ/አዛዥ" የሚለው የሚወክለው የሚያዛቸውን አዛዥ ነው፡፡ በእርሱ ስር መሆን የሚወክለው የእርሱን ትዕዛዞች መቀበልን ነው፡፡ "የአንድን መሪ ትዕዛዞች መቀበል" በሚለው ውሰጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱን እና እስራኤላውያንን ለማታለል የተደረገ ማጭበርበር
"ደረቅ እና በሻጋታ የተሞላ" ወይም "የሻገተ እና ያረጀ
ይህ መላውን የእስራኤል መንግስት ያመለክታል፡፡ (ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መወከል)
ይህ የገባዖናውያን ሌላ ስማቸው ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ የእስራኤል ህዝብ ከማናቸውም ነገር በላይ ለያህዌ ትእዛዝ ትኩረት ሰጥተው መከተል እንዳለባቸው ትኩረት ይሰጣል፡፡ "በእኛ አቅራቢያ የምትኖሩ ከሆናችሁ፣ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን መግባት አንችልም" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ለዮርዳኖስ ወንዝ አጭር ስያሜ ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የተሸነፈው የአሞራውያን ንጉሥ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
x
የዚህ ሃረግ ትረጉም "ይዛችሁ ሂዱ" የሚል ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል የሚወክለው ከአቅርቦት ውስጥ ገባዖናውያን ያላቸውን ነው፡፡ (ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር ወከል)አግኟቸውና እንዲህ በሏቸው "እነሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ሰዎች ነው
እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ነገር መደረጉን ይናገራሉ፡፡ የእስራኤል ህዝብ መሪ ኢያሱ፣ ገባዖናውያንን እንደማይገድል ቃል ገባ፡፡ የእስራኤል ህዝብ መሪዎችም በተመሳሳዩ ይህንኑ ቃል ኪዳን ገቡ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ ይህ ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ህዝብ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በቅደም ተከተል ቁጥር ሶስትን ያመለክታል (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ከገባዖን ከተሞች አንዱ ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ ይህ ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ህዝብ ነው፡፡
"ገባዖናውያን እንጨት ቆራጮች እና ውሃ ቀጂዎች ሆኑ"
እዚህ ይህ ሃረግ የሚያመለክተው የማደሪያውን ድነኳን፣ የያህዌን ማደሪያ ስፍራ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
"መልካም" እና "ትክክል" የሚሉት ቃላት በመሰረቱ አንድ አይነት ነገር ማለት ናቸው፡፡ "ተገቢ እና ትክክል የሚመስልህን ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ገባዖናውያንን ነው፡፡እስከዚህ ቀን ድረስ "እስከ አሁን ድረስ እንኳን፡፡" ይህ ማለት ህዝቡ እነዚህን ነገሮች ጸሐፊው ይኖር እስከ ነበረበት ጊዜ ድረስ ጭምር ማድረጋቸውን ቀጥለው ነበር ማለት ነው
1 የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶነጼዴቅ ኢያሱ ጋይን ይዞ ፈጽሞ እንደ ደመሰሳት፤ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ ያደረገውን ሁሉ ሰማ። እንዲሁም የገባዖን ሰዎች ከእስራኤል ጋር እንዴት የሰላም ውል አድርገው በመካከላቸው መኖራቸውን ሰማ። 2 የኢየሩሳሌም ሕዝብ ፈሩ፥ ምክንያቱም ገባዖን እንደ ነገሥታቱ ከተማ ሁሉ ታላቅ ከተማ ነች። ገባዖንም ከጋይ ይልቅ ትልቅና ሰዎቿም ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ። 3 ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፥ ወደ የኬብሮን ንገሥ ሆነም፥ ወደ የያርሙት ንጉሥ ጲርአም ፥ ወደ የለኪሶ ንጉሥ ያፈዓና ወደ የዔግሎን ንጉሥ ዳቤር ላከ። 4 ወደዚህ መጥታችሁ አግዙኝ። ገባዖን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ስላደረጉ ገባዖንን እንምታ። 5 ከዚያም አምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለት የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥና የዔግሎን ንጉሥ ያላቸውን ሠራዊታቸውን ሁሉ አስተባብረው፥ ገባዖንን ወጓት። 6 የገባዖንም ሰዎች ወደ ኢያሱና ወደ ጌልገላ ሠራዊት መልእክት ላኩ። እንዲህም አሉ፦ ከአገልጋዮቻችሁ እጃችሁን አታውጡ ፍጠኑ። በፍጥነት መጥታችሁ አድኑን። በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ኃይላቸውን አስተባብረው እኛን ለማጥቃት ተሰልፈውብናልና እርዱን። እኛን ባሮችህን አትተወን ርዳን ፈጥነህ በመድረስም አድነን ብለው ላኩበት። 7 ስለዚህ ኢያሱ እርሱና ተዋጊዎች ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ጨምሮ ከጌልገላ ወጣ። 8 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለ፦ አትፍራቸው። በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ ማንም ሊቋቋሙህ አይችልም። 9 ኢያሱም ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሥ አድሮ ድንገት ደረሰባቸው። 10 እግዚአብሔም የጠላትን ሠራዊት በእስራኤል ፊት ግራ አጋባቸው። እጅግ መታቸው። በገባዖንም ወደ ቤት ሖሮን በሚያስወጣው መንገድ እስከ ዓዜቅ መንገድ እስከ መቄዳም ድረስ ተከትሎአቸው አሳድዶ መታቸው። 11 ከቤት ሖሮን ወደ ዓዜቃ ቁልቁል በሚወስደው መንገድ ላይ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሽሹበት ጊዜ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ ድንጋዮች ወረወረባቸው ሞቱም። በእስራኤል ሰዎች ሰይፍ ከሞቱት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋዮች የሞቱት የበለጡ ነበሩ። 12 ከዚያም እግዚአብሔር ለእስራኤል በአሞራውያን ላይ ድል በሰጠበት ዕለት ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ። ኢያሱም በእስራኤል ፊት እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፦ "ፀሐይ፥ በኤሎን ሸለቆ በገባዖን ላይ ይቁም።" 13 ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪ በቀል ድረስ፤ ፀሐይ ባለችበት ቆመች፥ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህም በያሻር መጽሐፍ ላይ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይ በሰማዩ መካከል ቆመች፥ ለሙሉ ቀን ያህል አልተንቀሳቀሰችም ነበር። 14 እግዚአብሔር የሰውን ቃል እንደዚያ የሰማበት ዕለት ከዚያ በፊት ወይም ከዚያ በኋላ አልነበረም። እግዚእአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበር። 15 ኢያሱና መላው እስራኤል ወደ ጌልገላ ሰፈር ተመለሱ። 16 በዚህ ጊዜ አምስቱ የአሞራውያን ገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ራሳቸውን ደብቀው ነበር። 17 ኢያሱም አምስቱ ነገሥታት በመቄዳ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ሰማ፤ 18 ኢያሱም እንዲህ አለ፦ ትልልቅ ድንጋዮች ወደ ዋሻው አፍ አንከባልሉ፤ወታደሮችንም እንዲጠብቁአቸው በዚያ አቁሙ። ቸልም አትበሉ። 19 ጠላቶቻችሁን አሳዱአቸው፤ ከበስተ ኋላ ሆናችሁም ጥቃት አድርሱባቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ አድርጉአቸው። 20 ኢያሱና እስራኤል ልጆች ፈጽሞ እስኪያጠፉ ድረስ ከታላቅ ጭፍጨፋ ጋር ጨረሱ። የተረፉት ጥቂቶቹ ብቻ ወደ ተመሸጉት ከተሞቻቸው ደረሱ። 21 ከዚያም ሠራዊቱ በሙሉ በደኅና ተመልሶ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ ተመለሰ። በእስራኤላውያንም ላይ አንድት ቃል ለመናገር ማንም ሰው የደፈረ አልነበረም። 22 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ የዋሻውንም አፍ ክፈቱና ከዋሻው እነዚህን አምስቱን ነገሥታት አምጡልኝ። 23 እነርሱም እንዳለው አደረጉ። እነዚህንም አምስቱን ነገሥታት፦ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፥ የኬብሮንን ንጉሥ፥ የያርሙትን ንጉሥ የለኪሶን ንጉሥና የዔግሎንን ንጉሥ አውጥተው አመጡለት። 24 እነዚህን ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባማጡበት ጊዜ፥ እርሱም እያንዳንዱን የእስራኤል ሰዎች ጠራቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት ሄደው የነበሩትን የጦር አዛዦችን እንዲህ አላቸው፦ እግሮቻችሁን በእነዚህ ነገሥታት አንገት ላይ አድርጉ። እነርሱም ወደ ፊት ቀርበው እግሮቻቸውን በነገሥታቱ አንገት ላይ አሳረፉ። 25 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ አትፍሩ፥ አትደንግጡም። በርቱ፥ ጽኑም። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምትዋጉበት ጊዜ በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲህ ያደርጋል። 26 ከዚያም ኢያሱ ነገሥታቱን መትቶ ገደላቸው። በአምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው። አስክሬናቸውም እስኪመሽ ድረስ ተሰቅለው ነበር። 27 የፀሐይ መጥለቂያ በሆነ ጊዜ ኢያሱ ትእዛዝ ሰጠ፦ ከዚያም የነገሥታቱን አስክሬኖች ከዛፎቹ ላይ እንዲያወርዱ ቀድሞ ራሳቸውን ደብቀው ወደነበሩበት ዋሻ ውስጥ እንዲጥሉአቸው አዘዛቸው። በዋሻውም አፍ ላይ ትልልቅ ድንጋዮች አኖሩ። እነዚያ ድንጋዮች እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ። 28 በዚህ መንገድ በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከንጉሥዋም ጭምር ሁሉንም በሰይፍ ገደለ። በሕይወት ያሉትንም ፍጥረት ሁሉ ምንም ሳያስቀር ፈጽሞ አጠፋቸው። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፥ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ። 29 ኢያሱና እስራኤላውያን ከመቄዳ ወደ ልብና አለፉ። ወጓትም። 30 እንደገናም ከልብና ጋር ጦርነት ገጠሙ። እግዚአብሔርም ከተማይቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱም በተከማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ። ሕይወት ያለውን ምንም አላስቀረም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ አደረገ። 31 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከእርሱ ጋር ከልብና ወደ ለኪሶ አለፉ። በእርስዋም ሰፈሩ፤ ጦርነትም አደረጉ። 32 እግዚአብሔርም ለኪሶን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠው። ኢያሱም በሁለተኛው ቀን ያዛት። በልብና እንዳደርገው በሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ። 33 ከዚያ የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት መጣ። ኢያሱ ግን አንድ እንኳ ሳያስተርፍ እርሱንና ሕዝቡን መታቸው። 34 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን በሙሉ ከለኪሶን ወደ ዔግሎን አለፉ። እዚያም ሰፈሩ፤ ወጓትም፤ 35 በዚያኑ ዕለት ከተማዋንም ያዟት። ኢያሱም በለኪሶ እንዳደረገ ከተማይቱንና በውስጧ የሚገኙትን ፈጽመው በሰይፍ ስለት አጠፏት። 36 ከዚያም ኢያሱና እስራኤላውያን ከዔግሎን ወደ ኬብሮን አለፉ። በከተማይቱም ጦርነት አደረጉ። 37 ከተማዪቱንም ከንጉሥዋ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጭምር ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። በዔግሎን እንዳደርጉት ሁሉ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ። ማንኛውንም ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ አጠፋ። 38 ከዚያ ኢያሱና እስራኤል ሠራዊት ከእርሱ ጋር ወደ ኋላ ተመልሰው በደቤርን አለፉ፤ ጦርነቱንም አደረጉ። 39 ከተማዪቱን ንጉሥዋንና በአካባቢ ያሉ መንደሮቿን ሁሉ ያዙ። ከተማይቱንና በውስጧ ያለውንም ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ፥ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። ኢያሱ በኬብሮን ያደረጉትን ሁሉ በዳቤርና በንጉሥዋ ላይ አደረጉት። 40 ኢያሱ ተራራማውን አገር ኔጌቭን ቆላና የተራራውን ሸንተረሮች ጨምሮ ምድሪቱን በሙሉ ከነገሥታቷ ጋር አሸነፈ። ከነገሥታቱንም ያስቀረው ማንም የለም። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረትሕይወት ያላቸውን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋቸው። 41 ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ፥ የጎሶምን ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ በሙሉ አጠፋ። 42 ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን የያዘው በአንድ ጊዜ፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ስለተዋጋ ነው። 43 ኢያሱ ከመላው እስራኤላውያን ጋር ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የንጉሦች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"እኔ ወዳለሁበት ተጓዝ፡፡" ኢየሩሳሌም በከነአን ለሚገኙ ከተሞች ሁሉ ከፍ ባለ ስፍራ ላይ የምትገኝ ከተማ ነበረች፡፡
"5 ንጉሦች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ማለት ሰፈራቸውን በከተማቸው ዙሪያ አደረጉ፡፡ ይህ በከተማይቱ የሚኖሩትን ማዳከሚያ መንገድ ነበር፡፡ ድርጊቱ ሰዎች ከከተማይቱ እንዳያመልጡ ያግዳል፣ እንደዚሁም ሌሎች ምግብ እና ውሃ ወደ ከተማይቱ እንዳያመጡላቸው ያግዳል፡፡
"እነርሱ" የሚለው ቃል እዚህ ስፍራ የሚያመለክተው ገባዖናውያንን ነው፡፡
ይህ ትሁት ልመና በሁለት አሉታዎች ተገልጾዋል፣ ይህም አዎንታዊ ድርጊት/እርዳታ ማስፈለጉን በአጽንኦት ለመግለጽ ነው፡፡ "እባክህ መጥተህ በብርቱ እጆችህ ታደገን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እጆች" የሚለው ቃል የእስራኤልን ህዝብ ጥንካሬ ያመለክታል፡፡ "የአንተ ጥንካሬ" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው የሚወክለው የእስራኤልን ህዝብ ጥንካሬ እና ጠላቶቻቸውን የማሸነፍ አቅማቸውን ነው፡፡ "እነርሱ" የሚለው ቃል አጥቂ የሆነውን ሰራዊት ያመለክታል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው ቃል ጥቃት የሚጥለውን ሰራዊት ያመለክታል፡፡
እዚህ ስፍራ መላው የእስራኤል ሰራዊት የተጠቀሱት በመሪያቸው በኢያሱ ነው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)ያህዌ በእስራኤል ፊት ጠላቶቻቸውን ግራ አጋባቸው እዚህ ስፍራ "እስራኤል" የሚለው መላውን የእስራኤል ሰራዊት ያመለክታል፡፡ ቤትሖሮን… ዓዜቅ… መቄዳም እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"ከሰማይ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው"
ኢያሱ በዚህ ቀን ጊዜ ያህዌ ጊዜ መንቀሳቀሱን እንዲያቆም ጸለየ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን መልከቱ) ፀሐይ… ጨረቃ ኢያሱ ፀሐይን እና ጨረቃን እንደ ሰው አዘዛቸው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ) የኤሎን ሸለቆ ይህ የቦታ ስም ነው (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የእስራኤልን ህዝብ ያመለክታል (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይህንን ጥያቄ ትዕይንቱ በሚገባ መመዝገቡን ለአንባቢው ለማስታወስ እንደ መረጃ ዳራ ተጠቅሞበታል፡፡ "ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፏል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና የመረጃ ዳራ የሚሉትን ይመልከቱ)
ይህ የከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
መልዕክተኞች መጥተው ለኢያሱ ነገሩት፡፡ "አንድ ሰው ለኢያሱ ነገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ተመልከቱ)
"በእጃችሁ" የሚለው ሀረግ ትርጉሙ "ማድረግ የምትችሉት" ማለት ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
በኢያሱ 10፡10 ውስጥ በተረጎሙት መሰረት ይተርጉሙ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"ማንም አንዳች ነገር በመቃወም መናገር አልደፈረም" ወይም "ማንም ለማማረር ወይም ለመቃወም አልደፈረም"
እዚህ ስፍራ "አፍ" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙ "መግቢያ" ማለት ነው፡፡ "የዋሻውን መግቢያ ክፈቱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው (ስሞች እንዴት ይተጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
በዚህ ስፍራ የእስራኤል ሰዎች የሚለው የሚወክለው ወታደር የሆኑትን ብቻ ነው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ ማለውን ነገር መወከል የሚለውን ይመልከቱ)
"ጸሐፊው ይህንን ታሪክ እስከጻፈ ድረስ"
ይህ የከተማ ስወም ነው፡፡ ይህንን በኢያሱ 10፡10 ውስጥ እንዴት እንደ ተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)በውስጧ የሚገኙትን ሙሉ በሙሉ ደመሰሰ፡፡ አንድም ነገር በህይወት አላስቀረም፡፡ ኢያሱ አንድም ሰው ወይም እንስሳ በህይወት አለማስቀረቱን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ፣ ሁለተኛው ዐረፍተ ነገር የመጀመሪያውን አረፍተ ነገር አጠቃሎ ያቀርባል፡፡
ይህ የከተማ ስወም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው "መቆጣጠር" ማለት ነው፡፡ "ለእስራኤል አሳልፎ ሰጣት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ የእነርሱ "እጅ" የሚለው የሚወክለው የእነርሱን የበላይነት/መቆጣጠር ነው፡፡ "ያህዌ ለኪሶን ለእስራኤል መንግሥት አሳልፎ ሰጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ታላቅ የሆነ ንጉሥ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በአንድነት የዔግሎን ከተማ ሙሉ ለሙሉ መጥፋትን ይገልጻሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የከተማ ስወም ነው፡፡ ይህንን በኢያሱ 10፡3 ውስጥ እንዴት እንደ ተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ሰይፉ የሚወክለው የእስራኤልን ሰራዊት ነው፣ መምታት የሚለው የሚገልጸው የማረድ እና የመደምሰስ ሃሳብን ነው፡፡ "ያዙ፣ገደሉ፣ ደመሰሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ሰይፉ የሚወክለው የእስራኤልን ሰራዊት ነው፣ መምታት የሚለው የሚገልጸው የማረድ እና የመደምሰስ ሃሳብን ነው፡፡ "ገደሉ ደግሞም ደመሰሷቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሃረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ሃረጎቹ የእስራኤል ህዝብ በያህዌ ትዕዛዝ የፈጸመውን ሙሉ ለሙሉ የመደምሰስ ተግባር ያጎላሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በኢያሱ 10፡28 ጀምሮ የተዘረዘሩትን ነገሥታት እና ምድራቸውን ያመለክታል
እዚህ ስፍራ ኢያሱ የሚወክለው ጠቅላላውን ሰራዊቱን ነው፡፡ "ኢያሱ እና ወታደሮቹ ማረኩ/ያዙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ)
ይህ በአንድ ቀን ማለት አይደለም፡፡ በርካታ ቀናት ወይም ሳምንታት ሊወስድ በሚችል በአንድ ወታደራዊ ዘመቻ ወቅት ማለት ነው፡፡
1 የአሦርም ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ፥ ወደ ዮባብ ንጉሥ፥ ወደ ማዶን ንጉሥ፥ ወደ ሺምሮን ንጉሥና ወደ አዚፍ ንጉሥ መልእክት ላከ። 2 ደግሞም በሰሜናዊ በተራራማው አገር፥ በየርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ከኪኔሬት በስተ ደቡብ ፥ በምዕራቡ ቆላማ አገሮችና ከኮር ኮረብታማ በስተ ምዕራብ ወዳሉት ነገሥታት ላከ። 3 በምሥራቅና በምዕራብ ወደሚገኙት ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያንና በኮረብታማው አገር ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሳውያን እንዲሁም በምጽጳ ምድር በአርሞንዔም ተራራ ወዳሉት ወደ ኤዊያውያን ነገሥታት መልእክት ላከ። 4 እንዚህም ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በቁጥርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ እጅግ ከብዙ ወታደሮች ጋር መጡ። ታላቅም ቁጥር ፈረሶችና ሠረገሎች ነበሩአቸው። 5 እነዚህ ሁሉ ነገሥታት እስራኤልን ለመውጋት ኃይላቸውን አስተባብረው በማሮን ውሃ አጠገብ በተቀጠረው ጊዜ ሰፈሩ። 6 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቆርጣለህ፥ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ። 7 ኢያሱና ሠራዊቱ ሁሉ መጡ። በድንገትም ወደ ማሮን ውሃ መጥተው ጠላቶቻቸውን አጠቁኣቸው። 8 እግዚአብሔርም ጠላትን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። በሰይፍም ስለት አጠቁአቸው፥ ወደ ሲዶና፥ወደ ማስሮን፥ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ በስተምሥራቅ አሳደዷቸው። ከእነርሱም በሕይወት አንድንም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት አጠፉአቸው። 9 ኢያሱም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእነርሱ ላይ አደረጉ። የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቆረጠ፥ ሠረገሎቻቸውንም አቃጠለ። 10 በዚያን ጊዜም ኢያሱ ወደ ኋላ ተመልሶ አጾርን ያዘ። ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለው። (አጾርም የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ የበላይነት ነበራች።) 11 በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ በሕይወት ካለው ፍጡር አንድ እንኳ ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ። አሦርንም በእሳት አቃጠሏት። 12 ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውን ሁሉ ማረካቸው፥ በሰይፍም ስለት አጠፋቸው። የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው በሰይፍ ስለት አጠፋቸው። 13 እስራኤልም በተራራው ላይ ከተሠሩ ከተሞች ከአጾር በስተቀር ሌሎችን አላቃጠሉም። ኢያሱ ይህችን ለብቻዋ አቃጠላት። 14 እስራኤላውያንም ምርኮውን በሙሉ ከእነዚህም ከተሞች የተገኙትን እንስሳት ለራሳቸው ወሰዱ። ሕዝቡን በሙሉ ሁሉም ሙት እስኪሆኑ ድረስ በሰይፍ ስለት ገደሉአቸው። በሕይወት ካለው ፍጡር አንድም አልቀሩም። 15 እግዚአብሔር አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ሙሴም ኢያሱን አዘዘው። ኢያሱም እግዚአብሔር ሙሴን ካዘዘው ሁሉ እርሱ ያልፈጸመው አንዳች ነገር አልነበረም። 16 ኢያሱም ማለት ተራራማውን አገር፥ ኔጌቭን ሁሉ፥ የጎሶምን ምድር በሙሉ፥ የኮረብታ ግርጌ። የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ፥ የእስራኤልም ኮረብታማ አገርና ቆላማውን የምዕራቡን ቆላዎችን ሁሉ፥ያንን ምድር በሙሉ ወሰደ። 17 እንዲሁም እስከ ሴይር በሚደርሰው ከሐላቅ ተራራ አንሥቶ ከአርሞንዔም ተራራ በታች በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ እስካለው እስከ በዓል ጋድ ድረስ ያለውን ምድር በሙሉ ያዘ። ነገሥታታቸውንም ሁሉ ያዘ፥ መትቶም ገደላቸው። 18 ኢያሱ ከእነዚህ ነገሥታት ጋር ረጅም ጊዜ ጦርነት አደረገ። 19 በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በስተቀር ከእስራኤላውያን ጋር የሰላም ስምምነት ያደረገ አንድም ከተማ አልነበረም። እስራኤል ሁሉንም ከተሞች የያዙት በጦርነት ነበር። 20 እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ያለ አንዳች ርኅራኄ ፈጽሞ ይደመስሳቸው ዘንድ እስራኤልን እንዲወጉ ልባቸውን ያደነደናቸው ራሱ እግዚአብሔር ነበር። 21 በዚያንም ጊዜ ኢያሱ መጥቶ ዔናቅን አጠፋ። ይህንንም በተራራማው አገር በኬብሮን፥ በዳቤርና በአናብ እንዲሁም በመላው ይሁዳና የእስራኤል ተራራማ አገሮች ያሉትን ላይ አደረገ። እርሱም እነርሱንና ከተሞቻቸውን በሙሉ አጠፋቸው። 22 ከእነዚህም ጥቂቶቹ ብቻ በጋዛ፥ በጌትና በአሽዶድ ከቀሩት በስተቀር በእስራኤል አገር ከዓናቅ የቀሩት አልነበሩም። 23 ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ምድሪቱን በሙሉ ያዘ። ኢያሱም እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራእላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
እነዚህ የንጉሦች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የስፍራ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ሁሉም የከነዓን ንጉሦች በኢያሱና በእስራኤል ላይ ዘመቱ
ማንም የባህር ዳርቻ አሸዋን መቁጠር አይችልም፡፡ ይህ ግነት የሚያገላው እነዚህ ነገሥታት የሰበሰቧቸውን ወታዶች ብዛት ነው፡፡ "በወንዝ ዳርቻ እንደሚገኝ አሸዋ እንዲህ ያለ ታላቅ ቁጥር ያለው ወታደር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና ማጠቃለያ የሚሉትን ይመልከቱ)
ይህ የስፍራ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እስራኤ ጠላቶቹን ለመማረክ እና ሁሉንም ለመደምሰስ ያስቻለው ያህዌ የእስራኤል ጠላት የሆኑትን ወታደሮች በሙሉ ከገደለ በኋላ አሳልፎ እንደሰጣቸው ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ " እስራኤል ጠላቶቹን ሁሉ እንዲያጠፋ አሳልፌ እሰጠዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"እግሮቻቸውን በመቁረጥ ፈረሶቻቸውን ስንኩል ማድረግ" ይህ ከፈረሶቹ እግር በስተኋላ ያልን ጅማት በመቁረጥ ፈረሶቹ መራመድ እንዳይችሉ የማድረግ ልምምድ ነው፡፡
ይህ የስፍራ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል የሚወክለው ሃይልን ነው፡፡ ያህዌ የእስራኤል ሰራዊት ጠላቶቻቸውን እንዲማርኩ ማድረጉ የተገለጸው ልክ ጠላቶቻቸውን በእጃቸው ላይ እንዳስቀመጠ ተደርጎ ነው፡፡ "ያህዌ እስራኤል ጠላቶቹን እንዲማርክ አሳልፎ ሰጠው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡
"አጥቋቸው… አጥቋቸው"
ይህ የስፍራ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ፈረሶቹ መሮጥ እንዳይችሉ ያኋላ እግራቸው ጅማት የተቆረጠበት ልምምድ ነው፡፡ ይህንን ቃል በኢያሱ 11፡6 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡
"ኢያሱ የሐጾርን ንጉሥ በሰይፍ ገደለ"
የሐጾር ከተማ ታላቅነት የተገለጸው ሐጾር የእነዚህ መንግሥታት ሁሉ ራስ ነበር በሚል ነው፡፡ "ሐጾር ከእነዚህ መንግሥታት ሁሉ ታላቅ ነበረች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር እና ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚሉትን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ሙሉ ለሙሉ ጥፋት መፈጸሙን ያጎላሉ፡፡(ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
"እርሱ" የሚለው ቃል ኢያሱን ያመለክታል፤ ደግሞም እርሱን ራሱን እና ሰራቱን ይወክላል፡፡ በከተማይቱ ውስጥ የሚገኙ ህይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ ሙሉ ለሙሉ መደምሰስ የሚለው የተነገረው እነዚያ ህይወት ያላቸው ነገሮች ሀሉ ለመጥፋት የተሰጡ እንደሆኑ ተደርጎ ነው፡፡ "ሰራዊቱ ሙሉ ለሙሉ ደመሰሳቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ዘይቤያው አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)
"እነርሱን ገደለ"
"በትንንሽ ኮረብቶች ላይ የተመሰረቱ ከተሞች"
ይህ ሃረግ የሚያመለክተው የእስራኤልን ሰራዊት ነው፡፡ (ደጋጋሚ ተውላጠ ስም/የስም ምትክ)
እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ሙሉ ለሙሉ ጥፋት መፈጸሙን ያጎላሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ አሉታዊ ሃረግ ኢያሱ ያህዌ ያዘዘውን ሁሉ እንዳደረገ አጉልቶ ይገልጻል፡፡ "ኢያሱ ያህዌ ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረገ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የስፍራ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌ የከተሞቹ ናሪዎች ልባቸው እንዲደነድን ያደረገበት ምክንያት የተገለጸው ልክ ያህዌ ልባቸው ጠንካራ እንዲሆን እንዳደረገ ሆኖ ነው፡፡ "በልበ ደንዳናነት ምላሽ እንዲሰጡ ያደረገው ያህዌ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የዔናቅ ትውልዶች ነበሩ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የስፍራ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ምድሪቱን ለእስራኤላውያን የሰጠበት መንገድ የተገለጸው ለአስራኤላውያን ርስትን በቆሚነት እንደሰጣቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ኢያሱ ለእስራኤላውያን ምድሪቱን ቋሚ ርስት አድርጎ ሰጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ቃል እዚህ ስፍራ ያገለገለው በዋናው ታሪክ ፍሰት ቆም ለማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ጸሐፊው የመረጃ ዳራ መስጠት ይጀምራል፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ እስከ ቁጥር 24 የሚገኙትን የንጉሦች ስም ዝርዝር ያመለክታል፡፡
እነዚህ የስፍራ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህን ቃላት በኢያሱ 9፡10 እንዴት እንተረጎሟቸው ይመልከቱ፡፡
1 የእስራኤልም ሰዎች ድል ያደረጉአቸው ነገሥታት እነዚህ ነበሩ። እስራኤላውያንም ከአዮርዳኖንም ሸለቆ በስተ ምሥራቅ ጀምሮ እስከ ፀሐይ መውጫ ድረስ፥ ከአርሞን ወንዝ ሸለቆ ወደ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ። የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን በሐሴቦን ተቀመጠ። 2 በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ፥ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ገዛ። 3 ሴዎንም በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓርባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥በቤት የሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር (እስከ ጨው ባሕር) ወደ ምሥራቅ ድረስ በደቡብም በኩል ከፍስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር ገዛ። 4 የባሳን ንጉሥ ዐግ ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ ተቀመጠ። 5 እርሱም የአርሞንዔምንም ተራራ፥ ስልካንና ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ፥ እስከ ንጉሥ ሀሴቦን ድረስ ገዛው ። 6 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፤ ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው። 7 ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ያሸነፉአቸ ነገሥታትና አገሮች እነዚህ ናቸው፡- በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል፥ በሊባኖስ ሸለቆ አጠገብ ወደ ኤዶን አጠገብ ሃላክ ተራራ ድረስ ነው። ኢያሱም ለእስራኤል ነገዶች ሁሉ ምድሪቱን ርስት አድርጎ ሰጣቸው። 8 ተራራማውን አገር፥ በቆላውንም፥ በዓረባንም፥ የተራሮችን ቁልቁለት፥ ምድረ በዳውንም፥ የደቡቡም ያሉትን ኬጢያውያን፥ አሞራውያንም፥ ከነዓናውያንም፥ ፌርዛውያንም፥ ኤዊያውያንም፥ ኢያቡሳውያንም ሰጣቸው። 9 የኢያሪኮ ንጉሥ ጨምሮ፦ በቤቴል አጠገብ ያለው የጋይ ንጉሥ፥ 10 የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ 11 የያርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ 12 የአግሎን ንጉሥ፥ የጌዝር ንጉሥ፥ 13 የዳቤር ንጉሥ፥ የጌድር ንጉሥ፥ 14 የሔርማ ንጉሥ፥ የዓራድ ንጉሥ፥ 15 የልብና ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ 16 የመቄዳ ንጉሥ፥ የቤቴል ንጉሥ፥ 17 የታጱዋ ንጉሥ፥ ይአፌር ንጉሥ፥ 18 የአፌቅ ንጉሥ፥ የሽሮን ንጉሥ፥ 19 የማዶ ንንጉሥ፥የአሶር ንጉሥ፥ 20 የሺምሮን፥ ሚሮን ንጉሥ፥ የአዚፍ ንጉሥ፥ 21 የታዕናክ ንጉሥ፥የመጊዶ ንጉሥ፥ 22 የቃዴስ ንጉሥ፥ በቀርሜሎስ የነበረ የዮቅንዕም ንጉሥ፥ 23 በዶር ኮረብታ የነበረ የዶር ንጉሥ፥ የጌልገላ አሕዛብ ንጉሥ፥ 24 የቲርሳ ንጉሥ፥ ነገሥታቱ ሁሉ ሠላሳ አንድ ናቸው።
ይህ ቃል እዚህ ስፍራ ያገለገለው በዋናው ታሪክ ፍሰት ቆም ለማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ጸሐፊው የመረጃ ዳራ መስጠት ይጀምራል፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ እስከ ቁጥር 24 የሚገኙትን የንጉሦች ስም ዝርዝር ያመለክታል፡፡
እነዚህ የስፍራ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህን ቃላት በኢያሱ 9፡10 እንዴት እንተረጎሟቸው ይመልከቱ፡፡
እነዚህ የሮቤል ትውልዶች ናቸው፡፡
እነዚህ የጋድ ትውልዶች ናቸው፡፡
እኩሌታ ነገድ የሚባሉበት ምክንያት ሌላኛው የነገዱ እኩሌታ በከነዓን ምድር ርስታቸውን ስለተቀበሉ ነው፡፡
እነዚህ የስፍራ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ "የርሙት፣" "ለኪሶ፣" እና "ዔግሎን" የሚሉትን ስሞች በኢያሱ 10፡3 በተረጎሙበት ተመሳሳይ መንገድ ይተርጉሙ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"በድምሩ 31" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
1 ኢያሱም ሸመገለ በዕድሜም አረጀ፤ እግዚአብሔርም አለው፦ አንተ ሸመገልህ፥ በዕድሜህም አረጀህ ያልተወረሰ እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርቶአል። 2 የቀረውም ምድር ይህ ነው፤ የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ፥ 3 (በግብፅ ፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል አስካለው የከነዓናውያን ንብረት ሆኖ ተቆጠረው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን የአስቀሎና፥የጌትና የአቃሮን አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት።) 4 በደቡብም በኩል የከነዓናውያንም ምድር ሁሉ፥ ለሲዶናውያንም የምትሆን መዓራ እስከ አሞራውያን ዳርቻ እስከ አፌቅ ድረስ፥ 5 የጌባላውያንም ምድር፥ በፀሐይ መውጫ በኩል ሊባኖስ ሁሉ፥ ከኣል ጋድ ከአርሞንዔም ተራራ በታች እስከ ሐማት ድረስ ያለው ። 6 በተራራማውም አገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሮን ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ። እነዚህን ከእስራኤል ፊት አባርራቸዋለሁ። እንዳዘዝሁም፤ምድራቸውን ለእስራኤል ርስት አድርገህ ለመመደብ እርግጠኛ ሁን። 7 አሁንም ይህን ምድር ለዘጠኙ ነገድ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገህ አከፋፍል። 8 የእግዚእብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ ሰጣቸው ከሌላ እኩሌታ የምናሴ ነገድ ጋር የሮብልና የጋድ ሰዎች በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ አዞአቸው የነበረውን ርስታቸውን ተቀበሉ። 9 በአርኖን ወንዝ ሸለቆ ዳር ካለው ከአሮዔር፥ (በሸለቆውም መካከል ካለው ከተማ ጀምሮ) የሜድባን ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥ 10 በሐሴቦንም የአሞርውያን ንጉሥ የሴዎን ከተሞች ሁሉ እስከ አሞራውያን ዳርቻ ድረስ፥ 11 ገለዓድንም፥ የጌሹራውያንና የማዕካታውያንን አካባቢ ሁሉ፥ የአርሞንዔምንም ተራራ ሁሉ፥ባሳንንም ሁሉ እስከ ሰልካ ድረስ፥ 12 በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፥ እነርሱም ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ መታቸው አወጣቸውም። 13 ነገር ግን የእስራኤል ሰዎች ጌሹራውያንን ወይም ማዕካታውያንን አላወጡም ነበር። በዚህ ፈንታ ጌሹርና ማዕካት እስከ ዛሬም ድረስ በእስራኤል መካከል ይኖራሉ። 14 ሙሴም ለሌዊ ነገድ ለብቻ ርስት አልሰጠም። እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ ተናገረው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የሚቀረበው፥ በእሳት የተደረገ መሥዋዕት ርስታቸው ነው። 15 ሙሴም ለሮቤል ልጆች ነገድ በየወገናቸው ርስትን ሰጥጣቸው። 16 ድንበራቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳር ካለችው ከአሮዔር ጀሞሮ በሸለቆው መካከል ያለችው ከተማ፥ 17 ሐሴቦንና በሜዳውም ያሉት ከተሞችዋ ሁሉ፥ዲቦን፥ ባሞት በኣል፥ ቤት በኣልምዖን፥ 18 ያሀጽና ቅዴሞት፥ ሜፍዓት፥ 19 ቂርያታይም፥ ሴባማ፥ ጼሬትሻሐና በሸለቆውም ተራራ ያለውና ሁሉ ሮቢን ተቀበለ። 20 ሮቤም ቤተ ፌጎርን፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድርን፥ ቤት የሺሞትን፥ 21 የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት፥ በሐሴቦንም የነገሠው፥ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የምድያምን አለቆች፥ ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርንና ሪባን፥ የሴዎን መሳፍንት፥ መታቸው። 22 የእስራኤል ሰዎች ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉ። የሮቤልም ልጆች ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝና ዳርቻው ነበረ። 23 የሮቤል ነገድ ድንበር የዮርዳኖስ ወንዝ ነው፥ ይህም ድንበራቸው ነው። ይህም ከከተሞቻቸውና መንደሮቻቸው በየወገኖቻቸው ለሮቤል ነገድ የተሰጣቸው ርስት ነበረ። 24 ይህም መሴ ለጋድ ነገድ በየውገኖቻቸው ርስት አድርጎ የሰጣቸው ነው። 25 ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞራውያንም ምድር እኩሌታ፥ 26 ከረባት በስተምሥራቅ፥ አስካለው እስከ አሮዔር ድረስ፥ ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ ነበር። 27 ሙሴም ቤትሀራምን፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮትና ጻፎን፥ የቀሩትንም የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ከዮርዳኖስን እንደ ድንበር በምሥራቅ በኩል ባለው በዩርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ሰጣቸው። 28 ይህም የጋድ ነገድ ከከተሞቻቸውና ከመንደሮቻቸው ጋር በየወገኖቻቸው ርስት ነበረ። 29 ሙሴም ለምናሴ እኩሌታ ነገድ ርስትን ሰጣቸው። ለምናሴም ነገድ እኩሌታ በየወገኖቻቸው መሠረት የተመመደበ ነበረ። 30 ድንበራቸውም ባሳን ሁሉ፥ ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ በባሳንም ያሉት የኢያፅር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፤ 31 የገለዓድም እኩሌታ፥ አስታሮትና ኤድራይ ነበር፤ (የ'ዐግ በባሳን ያሉ የመንግሥት ከተሞች) ። እነዚህም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ልጆች ሆኑ፤ ለማኪር ሰዎች እኩሌታ በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። 32 ይህም ሙሴ በምሥራቅ በኩል በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ሜዳ ሳለ፥ የከፈለው ርስት ነው። 33 ሙሴም ለሌዊ ነገድ ርስት አልሰጣም ነበር። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው ርስታቸው ነው።
እስራኤል ገና ሊይዘው የሚገባው ምድር ይህ ነው በማለት ማብራራት ይቻላል፡፡ "አስራኤላያን ገና ወዲፊት የሚይዙት ምድር ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አሁን ከነዓናውያን ንብረታቸው አድርው የሚቆጥሩት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የአንድ ቡድን ሰዎች የወል ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በገባኦን የሚኖሩ ሰዎች የወል ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እስራኤላውያን የእኔ ነው የሚሉት ምድር ቋሚ ሃብቸው አድርገው እንደሚቀበሉት ርስታቸው ተድረጎ ተገልጽዋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ወንዙ ከጎንና ጎኑ ከሚገኘው ስፍራ እጅግ ዝቅ ብሎ የሚገኝበት ነው
ከወንዝ በላይ ከፍ ብሎ የሚገኝ ሜዳማ መሬት
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
" የጌሹራውያን እና ማዕካታውያን የሚኖሩበት ምድር"
እነዚህ የህዝብ የወል ስም ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "ሙሴ" የሚወክለው ራሱን እና እርሱ የሚመራቸውን እስራኤላውያን ሰራዊት ነው፡፡ "ሙሴ አና እስራኤላውያን መቷቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልቱ)
ይህ የአንድ ቡድን ሰዎች የወል ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"ጌሹራውያን" እና "ማዕካታውያን" አንድም "የጌሹራውያን" እና "የማዕካታውያን" አባቶች ናቸው ወይም የሚኖሩባቸው ከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ "እነዚያ ህዝቦች በእስራኤላውያን መሃል ይኖራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ጸሐፊው ይህንን መጽሐፍ እሰከ ጻፈበት ጊዜ ድረስ ያለውን ጊዜ ያመለክታል
ሙሴ ለእስራኤል ነገድ የሰጠው ምድር ቋሚ ሃብት እንደተቀበሉ ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ሌዋውያን በክህነት ያህዌን በማገልገል ያላቸውን ታላቅ ክብር መስዋዕቶቹን እነርሱ እንደሚወርሷቸው ነገሮች አድርጎ ይገልጻል፡፡ "ለያህዌ የሚቀርቡ መሥዋዕቶቸ … ለእነርሱ የሚሰጣቸው ይሆናል" (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
x
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"የምድያም መሪዎችን እንዳሸነፈ"
የዮርዳኖስ ወንዝ የሮቤል ነገድ የተቀበለው ምዕራባዊ ዳርቻ ነው
ሙሴ ለሮቤል ነገድ የሰጠው ምድር የሮቤል ነገድ በቋሚነት እንደ ተቀበለው ርስት ተደርጎ ይገለጻል፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሙሴ ለእያንዳንዱ ጎሳቸው የሰጠው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለጋድ ነገድ የሰጠው ምድር የጋድ ነገድ በቋሚነት እንደ ተቀበለው ርስት ተደርጎ ይገለጻል፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ የሰጠው ርስት ለእነርሱ እንደ ሰጠው ቋሚ ርስት ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
የነገዱ እኩሌታ ብቻ ይህንን ምድር ተቀብሏል፣ ምክንያቱ የነገዱ ቀሪው እኩሌታ ከዮርዳኖስ ማዶ ባለው ምድር ርስቱን ተቀብሏል፡፡
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሙሴ ርስታቸውን ሰጥቷቸው ነበር" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሙሴ እነዚህን ሰጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ሙሴ ለእስራኤል ነገዶች የሰጣቸው ከዮርዳኖስ በስተምስራቅ የሚገኘው ምድር በቋሚነት እንደሰጣቸው ርስት ተደረጎ ተገልጽዋል፡፡ "ይህ ሙሴ ለእነርሱ ርስት አድርጎ የሰጣቸው ምድር ነው፡፡" (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ሌዋውያን በክህነት አገልግሎታቸው ያህዌን በማገልገል ያላቸውን ታላቅ ክብር የገለጸው የሚወርሱት ያህዌን እንደሆነ በመናገር ነው፡፡ "የእነርሱ ርስት የእስራኤል አምላክ ያህዌ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
1 የእስራኤልም ሕዝብ በካነዓን ምድር የወረሱት ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ በእስራኤልም ነገድ መካከል የአባቶቻቸው አለቆች ያካፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፤ 2 እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገዶችና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አካፈሉአቸው፤ 3 ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም። 4 የዮሴፍ ነገድ፥ ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ። ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተወሰኑ ከተሞች፥ ለእንስሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን መሰምርያቸው በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም። 5 እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው የእስራኤል ሕዝብ አደረጉ፥ ምድሩንም ተካፈሉ። 6 የይሁዳም ነገድ በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ። ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ ለእግዚአብሔር ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ነገር ታውቃለህ። 7 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ፤ እኔም በልቤ እንደ ነበረ መረጃ አመጠሁለት። 8 ነገር ግን ከእኔ ጋር የሄዱ ወንድሞቼ የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ። እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ። 9 ሙሴም በዚያ ቀን፦ አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም በእርግጥ ርስት ይሆናል ብሎ ማለ። 10 አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገር በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲጓዙ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመት በሕይወት አኖረኝ። እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ። 11 ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጉልበታም ነኝ፥ ጉልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበር፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት፥ ለመውጣትና ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው። 12 እንግዲህ በዚያን ቀን እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ተራራማ አገር ስጠኝ። አንተም በዚያ ቀን ታላላቅና በተመሸጉ ከተሞቻቸው ጋር ዔናቃውያን በዚያ እንደ ነበሩ ሰምተህ ነበር። እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ እግዚአብሔርም ከእኔ ጋር ይሆናል፥ አሳድዳቸዋለሁ። 13 ኢያሱም ባረከው፤ ለዮፎኒም ልጅ ለካሌብ ኬብሮንን ርስት አድርጎ ሰጠው። 14 ስለዚህም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆንች። 15 የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር። (አርባቅም በዔናቅ ሰዎች መካከል ከፍ ያለ ነበረ።) ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።
የእስራኤል ህዝብ ያገኘው ምድር የተገለጸው በቋሚነት እንደተቀበለው ሃብቱ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
"የነገዶቹ አለቆች"
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አልዓዛር፣ ኢያሱ፣ እና የጎሳ አለቆች ርስታቸውን ለማከፋፈል እጣ ጣሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ"እጅ" የሚለው ሙሴን ራሱን እና ያህዌ ሙሴን የእርሱን ትዕዛዝ ማስፈጸሚያ አድርጎ እንደ ተገለገለበት የሚገልተጽ ቃል ነው፡፡ "በሙሴ አማካይነት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልቱ)
ሙሴ ለነገዶቹ የሰጣቸው መሬት የተገለጸው በቋሚነት እንደ ተቀበሉት ርስት ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሙሴ ለሌዋውያን ምንም ድርሻ ርስት አድርጎ አልሰጣቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
"ክፍል"
ግሱ የተወሰደው ከቀደመው ሀረግ ነው፡፡ "ነገር ግን እርሱ ለመኖሪያነት አንዳንድ ከተሞችን ብቻ ሰጣቸው" (ኢሊፕሲስ/የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)
ለብቶች ግጦሽ የሚውል መስክ
ለቤተሰቦቻቸው ያቀርቧቸው ዘንድ የሚያስፈልጋቸው ቁሳዊ/አካላዊ ነገሮች
ይህ የወንድ ስም ነው (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የአንድ ቡድን ሰዎች የወል ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚለው ቃል የሚወክለው ሃሳብን ነው፡፡ ሀረጉ ፈሊጣው ሲሆን የሚያመለክተው በእውነተኛነት የቀረበን መረጃ ነው፡፡ "ለእርሱ ዳግም እውነተኛ መረጃ ይዤ መጣሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ህዝቡ በጣም እንዲፈራ ማድረግ የተገለጸው የህዝቡ ልብ እንዲቀልጥ እንደተረገ ተደርጎ ነው፡፡ "ህዝቡ በጣም እንዲፈራ አደረጉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ለያህዌ ታማኝ መሆን የተገለጸው ያህዌን ሙሉ ለሙሉ እንደ መከተል ተደርጎ ነው፡፡ "ሁሌም ለያህዌ ታማኝ ነበርኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ካሌብ እና የእርሱ ትውልድ የሚኖራቸው ምድር የተገለጸው በቋሚነት እንደ ተቀበሉት ርስት ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እግርህ" የሚለው የሚወክለው ካሌብን ነው፡፡ "የረገጥከው ምድር" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልቱ)
ህዝቡ በጣም እንዲፈራ ማድረግ የተገለጸው የህዝቡ ልብ እንዲቀልጥ እንደተረገ ተደርጎ ነው፡፡ "ህዝቡ በጣም እንዲፈራ አደረጉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ለያህዌ ታማኝ መሆን የተገለጸው ያህዌን ሙሉ ለሙሉ እንደ መከተል ተደርጎ ነው፡፡ "ሁሌም ለያህዌ ታማኝ ነበርኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ካሌብ እና የእርሱ ትውልድ የሚኖራቸው ምድር የተገለጸው በቋሚነት እንደ ተቀበሉት ርስት ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እግርህ" የሚለው የሚወክለው ካሌብን ነው፡፡ "የረገጥከው ምድር" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልቱ)
"ትኩረት ስጥ፣ ምክንያቱም የምናገረው እውነትም ዋጋ ያለውም ነገር ነው"
"የእስራኤል ህዝብ በምድረ በዳ ሲጓዝ"
"በዚያን ጊዜ ጠንካራ የነበርኩትን ያህል አሁንም ጠንካራ ነኝ"
ይህ የየዕለት ክንዋኔን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "በየዕለቱ ለማደርጋቸው ነገሮች" (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ብዙ ትላልቅ ኮረብቶች ወይም ትናንሽ ተራሮች 2) አንድ ተራራ
ይህ የአንድ ቡድን ሰዎች የወል ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ኬብሮን ካሌብ በቋሚነት እንደተቀባለት ርስት ተደርጋ ተገልጻለች፡፡ (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ጸሐፊው ይህንን መጽሐፍ እሰከ ጻፈበት ጊዜ ድረስ ያለውን ጊዜ ያመለክታል፡፡
ለያህዌ ታማኝ መሆን የተገለጸው ሙሉ ለሙሉ ያህዌን መከተል ተደርጎ ነው፡፡ "ሁሌም ለያህዌ ታማኝ ነበር" (ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የስፍራ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ህዝቡ ከዚያ በኋላ ጦርነት ውስጥ አለመግባቱ የተገለጸው ምድሪቱ ራሷ ሰው እንደሆነች እና ከጦርነት እንዳረፈች ተደርጎ ነው፡፡ ይህንን ሀረግ በኢያሱ 11፡23 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ "ከዚህ በኋላ ህዝቡ በምድሪቱ ጦርነት አላደረገም" (ሰውኛ ዘይቤ እና ዘይቤያው አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)
1 ለይሁዳም ልጆች ነገድ በየወገናቸው መሬትን ማከፋፈል እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብም መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ዕጣ ሆነላቸው። 2 በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ እስከሚያይ እስከ ባሕረ ልሳን ነበረ። 3 ከዚያም ቀጥሎ ከኮረብታ በስተደቡብ በኩል ወደ ጺንም አለፈ፤በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይዘልቃል፤ በሐጽሮንም በኩል አልፎ ወደ አዳርም ደረሰ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥ 4 ወደ አጽሞንም አለፈ፥ በግብፅም ወንዝ በኩል ወጣ፥ የድንባሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበር፤ በደቡብ በኩል ያለው ድንበራቸው ይህ ነው። 5 በምሥራቅም በኩል ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር እስከ ዮርዳኖስም መጨረሻ ነበረ። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር በዩርዳኖስ መጨረሻ እስካለው እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበር። 6 ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሖግላ ወጣ፥ በቤት ዓርባ በሰሜን በኩል አለፈ። (ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን) ድንጋይ ወጣ። 7 ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ወጣ፥ በሰሜን በኩል በአዱሚም ኮረብታ ፊት ለፊት፥በወንዙም በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ዞረ። ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤት ሳሚስ ውኃ አለፈ፥ መውጫውም በዓይን ሮጌል አጠገብ ነበረ። 8 ከዚያ ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ (ኢየሩሳሌም) ወደምትባለው ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ደቡብ ወገን ወጣ፤ ድንበሩም በራፋይም ሸለቆ ዳር በሰሜን በኩል ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በምዕራብ ወገን ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ወጣ። 9 ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ። ቂርያትይዓሪም ወደምትበል ወደ በኣላ ደረሰ። (ከዚያም ድንበሩ በባኣላ ዙሪያ እንደ ቂርያት በተመሳሳይ ታጠፈ) ። 10 ድንበሩም ከባአላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓሪም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረድ፥ በተምና በኩልም አለፈ። 11 ድንበሩም ወደ አቃሮን ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፤ወደ ሽክሮን ደረሰ ወደ በኣላ ተራራ አለፈ፥ በየብኒኤል በኩልም ወጣ፤ የድንበሩም መውጫ በባሕሩ አጠገብ ነበረ። 12 በምዕራቡም በኩል ያለው ድንበር እስከ ታላቁ ባሕርና እስከ ዳርቻው ድረስ ነበረ።ለይሁዳ ልጆች በየወገናቸው በዙሪያው ያለ ድንበራቸው ይህ ነው። 13 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት አርበቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም ዘርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። 14 ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴስን፥ አኪመንንና ተላሚን ከዚያ አሳደደ። 15 ከዚምም በዳቤር ሰዎች ላይ ወጣ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ ቂርያት ሤፍር ትባል ነበር። 16 ካሌብም እንዲህ አለ፦ ቂርያት ሤፍርን ለሚመታ ለሚይዛትም ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ አለ። 17 የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት። ስለዚህም ካሌብ ልጁን ዓክሳን አጋባው። 18 ዓክሳም ወደ እርሱ በመጣች ጊዜ ከአባትዋ እርሻ ለመለምን ገፋፈችው፤ እርስዋም ከአህያዋ ወረደች፤ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት። 19 እርስዋም፦ ስጦታ ስጠኝ፤ የኔጌቭ ምድር ሰጥተኸኛል፥ አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት። 20 በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ የተሰጠ ርስት ይህ ነው። 21 በድቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ አጠገብ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉትን የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ ቀብስኤል፥ ዓዴር፥ ያጉር፥ 22 ቂና፥ ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥ 23 ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ዪትናን 24 ዚፍ፥ጠሌም፥በዓሎት። 25 ሐጾርሐ ዳታ፥ ሐጾር የምትባለውም ቂርታይሐጾር፥ 26 አማም ሽማዕ፥ ሞላዳ፥ 27 ሐጸርጋዳ፥ሐሽሞን፥ ቤትጳሌጥ፥ 28 ሐጸርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ፥ 29 በኣላ፥ ዒዮም፥ ዓጼም፥ 30 ኤልቶላድ፥ ኪሲል፥ ሔርማ፥ 31 ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥ 32 ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን፥ ሪሞም፤ ሀያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። 33 በቆላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥ 34 ዛኖዋ፥ ጫይንገኒም፥ ያጱዋ፥ ዓይናም፥ 35 የሩት፥ ዓዶላም፥ ሰኮት፥ ዓዜቃ፥ 36 ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግርራ፥ ግርሮታይም፤ አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 37 ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥ 38 ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅትኤል፥ 39 ለኪሶ፥ በጽቃት፥ አግሎን 40 አዶላም፥ ከቦን፥ ለሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ 41 ግዴሮት፥ ቤት ዳጎን፥ ናዕማ፥ መቄዳ፤አሥራ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው። 42 ልብና፥ ዔቴር፥ ዓሻን፥ 43 ይፍታሕ፥ አሽና፥ንጺብ፥ 44 ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው። 45 አቃሮን፥ ከተመሸጉና ካልተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ ጋር፤ 46 ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕር ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር። 47 በአዛጦን የተመሸጉና መንደሮችዋም፥ ጋዛና የተመሸጉ ከተሞችና መንደሮችዋ፥ እስከ ግብፅ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ካርቻ ክረስ። 48 በተራራማውም አገር ሳምር፥ የቲር፥ ሶኮ፥ 49 ደና፥ ዳቤር የምትባለው ቂርያትሰና፥ 50 ዓባብ፥ኤሽትሞዓ፥ ዓኒም፥ 51 ጎሶም፥ ሖሎን፥ ጊሎ፤ አሥራ አንድ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው። 52 አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥ 53 ያንም፥ ቤትታጱዋ፥ አፌቃ፥ 54 ሑምጣ፥ ኬብሮን የምትባል ቂርያትአርባቅ፥ ጺዖር ፤ ዘጠኝ ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው። 55 ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣም 56 ኢይዝራሴል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥ 57 ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፤ አሥር ከተሞና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው። 58 ሐልሑል፥ ቤት ጹር፥ ጌዶር፥ 59 ማዕራት፥ ቤትዓኖት፥ ኤልትቆን፤ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው። 60 ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያት በኣል፥ ረባት፤ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 61 በምድረ በዳ ቤትዓረባ፥ ሚዲን፥ ስካካ፥ 62 ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ፤ ስድስት ከተሞችና ቁጥር ስፍር የሌላቸው መንደሮቻቸው። 63 በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
ይህ በረሃማ ስፍራ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
" ወደ ደቡብ ፊቱን ከመለሰው ባህረ ሰላጤ፣ በጨው ባህር መጨረሻ" እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ አቅጣጫን ያመለክታሉ፡፡ ሁለተኛው ሀረግ ደቡባዊው ዳርቻ የሚጀምርበትን ነጥብ ያብራራል
"እስከ ደቡብ ከሚደርሰው ባህረ ሰላጤ" ወይም "ከደቡባዊ ባህረ ሰላጤ"
ወደ መሬት ክፍል ገባ የሚል አነስተኛ የባህር ክፍል
"የይሁዳ ነገድ ድንበር የሆነ ምድር"
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
በግብጽ አጠገብ፣ በምድሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ ዳርቻ የሚገኝ ትንሽ የወንዝ ውሃ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ወንዙ ወደ ባህሩ ገብቶ የሚያበቃበት ነጥብ የወንዙ መግቢያ ተብሎ ይገለጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"ዳርቻ… ነበር"
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ምናልባት አንድ ሰው ለድንበር ምልክትነት ያስቀመጠው፣ በዚያ ቦሃን በተባለ ሰው ስም የተሰየመ ትልቅ ድንጋይ ሊሆን ይችላል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ስሞች የሴሲን፣ አኪመን እና ተላሚን ጎሳ የነበሩ ትውልዶችን ይወክላሉ፡፡ በዚህ ዐውድ "ልጆች" እና "ትውልዶች" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ይሰጣሉ፡፡ "የኤናቅ ትውልድ የሆኑት ሶስቱ ጎሳዎች፣ ሴሲን፣ አኪመን እና ተላሚን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
"ከዚያ ተነስቶ ሊወጋቸው ወጣ"
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሴት ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ዓክሳ የጎቶንያ ሚስት እንደምትሆን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ዓክሳ የጎቶንያ ሚስት በሆነች ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ቀጥተኛ ንግግር ሆኖ ሊተረጎም ይችላል፡፡ " ‘የእርሻ መሬት እንዲሰጠኝ አባቴን ለምነው' በማለት ገፋፋችው" (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ ትምህርተ ጥቅሶች
"የላይኛው" እና "የታችኛው" የሚሉት ቃላት በአመዛኙ የውሃ ምንጮቹን መልከዓ ምድራዊ ከፍታ የሚያመለክቱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
የይሁዳ ነገድ የተቀበለው ርስት የተገለጸው ቋሚ ሃብታቸው አድርገው እንደተቀበሉት ርስት ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሰውን ደቡባዊ ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ ይህ ዝርዝር እስከ ኢያሱ 15፡32 ድረስ ይቀጥላል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የከተሞቹ ስም ዝርዝር ይቀጥላል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የከተሞቹ ስም ዝርዝር ይቀጥላል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሰውን ሰሜናዊ ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሳቸውን ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሳቸውን ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሳቸውን ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሳቸውን ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
መንደሮች
በግብጽ አጠገብ፣ በምድሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ ዳርቻ የሚገኝ ትንሽ የወንዝ ውሃ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሳቸውን ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሳቸውን ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሳቸውን ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሳቸውን ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው ይሁዳ የወረሳቸውን ከተሞች ይዘረዝራል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው ጸሐፊው ይህንን መጽሐፍ እስከ ጻፈበት ጊዜ ድረስ ያለውን ወቅት ነው
1 የዮሴፍም ልጆች የመሬት ድልድል በኢያሪኮ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳውና በተራራማው በኩል ከኢያሪኮ ወደ ቤቴል ወጣ። 2 ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አለፈ። 3 ወደ ምዕራብም እስከ የፍርሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤት ሖሮን ዳርቻ እስከ ጌዝር ድረስ ዘልቆ፥ መጨራሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበር። 4 የዮሴፍም ነገድ ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን የተቀበሉት በዚህ መንገድ ነበር። 5 የኤፍሬምም ነገድ ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፦ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮት አዳር እስከ ላይኛው ቤት ሖሮን ድረስ ነበረ፤ 6 ከዚያ ወደ ባሕሩ ቀጠለ። ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ ሚክምታት በሰሜን በኩል ወደ ምሥራቅ ወደ ተአናት ሴሎ ዞረ፥ ከዚያም ወደ ኢያኖክ በምሥራቅ በኩል አለፈ። 7 ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ። 8 ድንበሩም ካታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መውጫውም በባሕሩ መጨራሻ ነበረ። የኤፍሬም ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ፤ 9 ይኸውም፥ በምናሴ ነገድ ርስት መካከል ለኤፍሬምም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ነው። 10 በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም ነበር፤እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ሆኖም እነዚህ ሰዎች የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ ተደርገው ነበር።
"የዮሴፍ ነገድ" በውስጡ፣ የዮሴፍን ሁለት ልጆች ነገዶች ማለት የምናሴ እና ኤፍሬም ነገዶችን ይይዛል፡፡ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስቀድሞ በዮርዳኖስ ምስራቅ የሰፈረ በመሆኑ፣ ይህ ሀረግ የሚያመለክተው የኤፍሬምን ነገድ እና የምናሴን ነገድ እኩሌታ ነው፡፡ "የኤፍሬም ነገድ እና የቀረው ሌላው ግማሽ የምናሴ ነገድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የአንድ ቡድን ሰዎች የወል ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የአንድ ቡድን ሰዎች የወል ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"የዮሴፍ ልጆች፣ የምናሴ እና ኤፍሬም ነገዶች"
የምናሴ እና ኤፍሬም ነገዶች የያዙት ምድር የተገለጸው እንደ ቋሚ ሀብታቸው አድርገው እንደተቀበሉት ተደርጎ ነው፡፡ "ይህንን ምድር ርስታቸው አድርገው ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ ለጎሳቸው የሰጠው ድንበር" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ኤፍሬም የያዘው ምድር የተገለጸው ቋሚ ሀብታቸው አድርገው እንደተቀበሉት ተደርጎ ነበር፡፡ "የኤፍሬም ነገድ ርስቱ አድርጎ የተቀበለው ምድር ይህ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ ለጎሳቸው የሰጠው" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ የመረጣቸው ከተሞች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ )
የምናሴ ነገድ የያዙት ምድር የተገለጸው እንደ ቋሚ ሀብታቸው አድርገው እንደተቀበሉት ተደርጎ ነው፡፡ "የምናሴ ነገድ ርስቱ አድርጎ በተቀበለው ምድር ውስጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው ጸሐፊው ይህንን መጽሐፍ እስከ ጻፈበት ጊዜ ድረስ ያለውን ወቅት ነው
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እስራኤላውያን እነዚህን ሰዎች ባሪያ ሆነው እንዲያገለግሉ ያስገድዷቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ )
1 ለምናሴ ነገድ የተመደበው ይህ ነበር፤ እርሱም የዮሴፍ በኩር ነበር። የምናሴም በኩር የገለዓድ አባት ማኪር ራሱም የገለዓድ አባት ነበር። የማኪርም ወገኖች የገለዓድና የባሳን ምድር ተሰጣቸው ምክንያቱም ማኪር የጦር ሰው ነበርና። 2 ለቀሩት ለምናሴ ልጆች በየወገኖቻቸው ለአቢዔዝር ልጆች፥ለኬሴግ ልጆች ለአሥሪኤል ልጆች፥ ለሴኬም ልጆች፥ ለአፌር ልጆች፥ልሸሚዳ ልጆች ተሰጣቸው። የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ወንዶች ልጆች በየወገኖቻቸው የተሰጣቸው እነዚህ ናቸው። 3 ለምናሴ ልጅ፥ ለማኪር ልጅ፥ ለገለዓድ ልጅ፤ ለኦፌር ልጅ፥ ለሰለጰዓድግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩአቸውም የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። 4 እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ አለቆች ቀርበው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርም ሙሴን ከወንድሞቻችን ጋር ርስት እንዲሰጠን አዝዞ ነበር። ስለዚህ ትእዛዙን በመከተል በአባታቸው ወንድሞች መካከል ለእነዚያ ሴቶች ርስት ሰጣቸው። 5 በዮርዳኖስ ማዶ ካለው በገለዓድና በባሳን ምድር ለምናሴ አሥር የመሬት መደቦች ተመድቦ ነበር፤ 6 ምክንያቱም የምናሴ ሴቶች ልጆች ከወንዶቹ ጋር ርስት ተቀብለዋል። የገለዓድም ምድር ለቀሩት ለምናሴ ነገድ ተመደበ። 7 የምናሴም የድንበር ክልል ከአሴር ጀምሮ በሴኬም ፊት ለፊት እስካለው እስከ ሚክምታት ድረስ ደረሰ። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ታጱዋ ምንጭ አጠገብ ወደሚኖሩ ሰዎች አለፈ። 8 (የታጱዋ ምድር ለምናሴ ነበረ፤ በምናሴ ዳርቻ ያለው ታጱዋ ከተማ ግን ለኤፍሬም ነገድ ሆነ።) 9 ድንበሩም ወደ ቃና በኩል ወደ ታች ወረደ። እነዚህ ከወንዙ በስተደቡብ ያሉ ከተሞች በምናሴም ከተሞች መካከል ለኤፍሬም ሆኑ። የምናሴም ድንበር በወንዙ በስተሰሜን በኩል ሆኖ በባሕሩ መጨራሻ ነበረ። 10 በደቡብ በኩል ያለው ለኤፍሬም ነበረ፥ በሰሜንም በኩል ያለው ለምናሴ የነበረው ድንበሩ ባሕር ነበረ። በሰሜን በኩል ወደ አሴር፥ በምሥራቅ ም በኩል ወደ ይሳኮር ደረሰ። 11 በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤት ሳንና መንደሮችዋን፥ ይብልዓምንና መንደሮችዋን፥ ዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የዓይንዶር ሰዎችንና መንደሮችዋን፥ የታዕናክ ሰዎችንና መንደሮችዋን ፥ የመጊዶ ሰዎችንና መደሮችዋን ፥ ሦስቱ ኮረብቶች ምናሴ ወረሳቸው። 12 ሆኖም የምናሴ ነገድ ግን እነዚህን ከተሞች ርስት አድርጎ ሊወስዳቸው አልቻሉም፤ ምክንያቱም ከነዓናውያን በዚያ ምድር መኖራቸውን ቀጥለው ነበር። 13 የእስራኤልም ሕዝብ እየጠነከሩ በመጡ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከምካከላቸው እንዲወጡ አላደረጉም ነበር። 14 ከዚያም የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ እኛ ብዙ ሕዝብ ሆነን ሳለን፥ እግዚአብሔርም ባርኮን እያለ ለምን አንድ ክፍል፥ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸን? አሉት። 15 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ በቁጥር ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ወደ ዱር ወጥታችሁ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለራሳችሁ መንጥሩ። ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦአችሁ እንደ ሆነ ይህንን አድርጉ። 16 የዮሴፍም ልጆች እንዲህ አሉ፦ '"ተራራማውም አገር አይበቃንም። ነገር ግን በሸለቆውም ውስጥ ለሚኖሩት፥ በቤት ሳንና በመንደሮችዋ በኢይዝራኤልም ሸለቆ ለሚኖሩት ከነዓናውያን የብረት ሰርገሎች አላቸው።" 17 ከዚያም ኢያሱ ለዮሴፍ ልጆች መለሰላቸው፦ ለመሆኑ ለኤፍሬምና ለምናሴ እናንተ ብዙ ሕዝብ ናችሁ፥ ጽኑም ኃይልም አላችሁ። አንድ ክፍል መሬት ብቻ ሊኖራችሁ አይገባም። 18 ተራራማውም አገር ለእናንተ ይሆናል። ዱር እንኳ ቢሆንም ትመነጥሩአቸዋላችሁ፥ ለእናንተም እንዲሆኑ ታደርጋላችሁ። ከነዓናውያንም የብረት ሰረገሎች ያሉአቸውና ኃይለኞች ቢሆኑም ልታስለቅቁአቸው ትችላላችሁ። ታሳድዳቸዋላችሁ አላቸው።
እዚህ ስፍራ "ራሱ" የሚለው የሚያጎላው ይንኑ ሰው ነው - ማኪር የምናሴ በኩር ነበር፣ እርሱ ራሱ የገለዓድም አባት ነበር፡፡ "እርሱ በኩርም ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ደጋጋሚ/ሪፍሌክቲቭ ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ የገለዓድን እና የባሳን ምድር ለማኪር ተውልዶች ሰጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ )
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ ምድሪቱን አወረሰ… እናም ለጎሳቸው ሰጠ" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ )
እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የሴት ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ምድሪቱ የተገለጸችው ሰዎቹ በቋሚነት እንደሚወርሷት ተደርጎ ነው፡፡ "ለእኛ ጥቂት መሬት ርስት አድርጎ ለመስጠት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ኢያሱ ለእነዚያ ሴቶች ርስት ሰጣቸው" ወይም 2) "አልዓዛር ለእነዚያ ሴቶች ርስት ሰጣቸው" የሚሉ ናቸው፡፡
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ አስር ቁራሽ መሬት ሰጠ" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ )
"አስር ክፍሎች/ድርሻ"
ምድሪቱ የተገለጸችው እንደ ቋሚ ሀብት እንደተቀበሏት ተደርጎ ነው፡፡ "ምድሪቱን ርስት አድርገው ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ የገለዓድን ምድር ሰጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
በስተ ደቡብ በኩል
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"የምናሴ ምድር ድንበር"
በጣም ትንሽ ወንዝ
የጅረት ስም (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) በስተ ሰሜን የምናሴ ምድር ዳርቻ እስከ አሴር ነገድ ምድር ሊደርስ ይችላል ወይም 2) አሴር ለመድረስ ወደ ሰሜን መጓዝ ይኖርበታል፡፡ "አሴር በስተ ሰሜን ይገኛል" ወይም "አሴር ለመድረስ ወደ ሰሜን መጓዝ ያስፈልጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ግሱ በፊተኛው ሀረግ ይገኛል፡፡ "በስተ ምስራቅ፣ ወደ ይሳኮር ሊደረስ ይቻላል" (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የኤፍሬም እና ምናሴን ነገዶች ያመለክታል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
የኤፍሬም እና የምናሴ ነገድ ሰዎች ይህንን ጥያቄ የጠየቁት ኢያሱ ለእነርሱ ተጨማሪ መሬት መስጠት እንደሚገባው አጽንኦት ለመስጠት ነው፡፡ "ያህዌ ባርኮናልና…ከአንድ በላይ ልትሰጠን ይገባ ነበር፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በሁለተኛው ሀረግ፣ ምድሩ የተገለጸው ህዝቡ ቋሚ ሀብት አድርጎ እንደተቀበለው ነው፡፡ " አንድ እጅ መሬት የእኛ ርስት ተደርጎ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ዘይቤያዊ አነጋጋር የሚሉትን ይመልከቱ)
ክፍል
"ብዙ ህዝብ"
"በቁጥር ብዙ ህዝብ እስከ ሆናችሁ ድረስ"
የአንድ ቡድን ሰዎች የወል ስም፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ትውልዶችን ነው፡፡ "የዮሴፍ ትውልዶች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት)
"የዱሩን ዛፎች ትመነጥራላችሁ" ወይም "ዛፎቹን ትቆርጣላችሁ/ትመነጥራላችሁ"
1 የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ። በዚያም የመገናኛውን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው። 2 ከእስራኤልም ልጆች መካከል ያልተካፈሉ ሰባት ነገዶች ቀርተው ነበር። 3 ኢያሱም ለእስራኤል ሰዎች አላቸው፦ የአባቶቻቸሁ እግዚአብሔር አምላክ የሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ እስከ መቼ ድረስ ቸል ትላላችሁ? 4 ከየነገዱም ሦስት ሦስት ሰዎች ምረጡ፥ እኔም እልካቸዋለሁ። ተነሥተውም የምድሪቱን ላይና ታች ይለካሉ። እንደ ርስታቸውም መጠን ይጽፉታል፤ ወደ እኔም ይመለሳሉ። 5 በሰባትም ክፍል ይከፍሉታል። ይሁዳም በደቡብ ድንበር ባሉበት ይጸናሉ፤ የዮሴፍ ወገኖች በሰሜን በኩል በዳርቻው ውስጥ ይቀጥላሉ። 6 እናንተም ምድሪቱን በሰባት ክፍል ትጽፋላችሁ፥ የጻፋችሁትንም ወደ እኔ ታመጣላችሁ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ። 7 ለሌዋውያንም ርስት የላቸውም፤ የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና። የጋድም፥ የሮቤልም፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀበሉ።ይህም የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸው ርስታቸው ይህ ነው። 8 ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ ሂዱ፥ በምድሩም ላይና ታች ዞራችሁ ጻፉት፥ ከዚያም ወደ እኔ ተመለሱ። በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ። 9 ሰዎቹም ሄደው ምድሩን ላይና ታች ዞሩ። እንደ ከተሞችም በሰባት ክፍል ከፈሉት፥ ዝርዝራቸውንም ጻፉት። ከዚያም ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ሴሎ ተመለሱ። 10 ኢያሱም በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣጠላቸው። በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደ ክፍሎቻቸው ምድሩን አካፈላቸው። 11 የምድሩም ዕጣ ለብንያምም ነገድ በየወገኖቻቸው ተሰጠ። የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ነበረ። 12 በሰሜን በኩል ድንብራቸው ከዮርዳኖስ ይጀራል። ድንበሩም ወደ ኢያሪኮ ወደ ሰሜን በኩል፥በተራራማው አገር ወደ ምዕራብ ደረሰ። መውጫውም በቤት አዌን ምድረ በዳ ነብረ። 13 ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ። ድንበሩም በታችኛው ቤት ሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮት አዳር ወረደ። 14 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ዘለቀ፥ በቤⶆሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ይዞራል፤ መውጫውም ቂርታትይዓሪም በትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያት በኣል ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ። 15 የደቡብም ዳርቻ ከቂርያት ይዓሪም ውጪ ይጀምራል። ድንበሩም በምዕራብ በኩል ወደ ነፍቶ ውኃ ምንጭ ሄደ። 16 ድንበሩም በበን ሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰንን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይን ሮጌልም ወረደ። 17 ወደ ሰሜንም ዞረ፤ በኢን ሳሚስ አቅጣጫ በአዱሚም ዐቀበት ፊት ለፊት ወዳለው ወደ ጌሊሎትወጣ፤ ከዚያሜ ወደ ሮቤ ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወረደ፤ 18 በሰሜንም ወገን ወደ ዓረባ አጠገብ አለፈ፥ ወደ ዓረባም ወረደ። 19 ድንበሩም ወደ ቤት ሖግላ ወደ ሰሜን በኩል አለፈ። መውጫውም በዮርዳንስ መጨረሻ በደቡብ በኩል ባለው በጨው ባሕር ልሳን አጠገብ ነበር፥ ይህም የደቡቡ ዳርቻ ነበረ። 20 በምሥራቅም በኩል ድንበሩ ዮርዳኖስ ነበረ። ይህ በዙሪያቸው ዳርቻ በየወገኖቻቸው የብንያም ልጆች ርስት ነበረ። 21 የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻችቸው እነዚህ ነበሩ፦ ኢያሪኮ፥ ቤት ሖግላ፥ ዓመቀጺጽ፥ 22 ቤት ዓረባ፥ ዘማራይም፥ ቤቴል፥ 23 ዓዊም፥ ፋራ፥ ኤፍራታ፥ 24 ክፊርዓሞናይ፥ ዖፍኒ፣ ጋባ፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 25 ገባዖን፥ ራማ፥ ብኤሮት፥ 26 ምጽጳ፥ ከፊራ፥አሞቂ፥ 27 ፍርቄም፥ይርጵኤል፥ ተርአላ፥ 28 ዼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባልየኢያቡስ ከተማ፥ ቂርያትጊብዓት፤ አሥራ ሦስት ከትሞችና መንደሮቸችው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
የመገናኛ ድንኳኑን ከመትከላቸው አስቀድሞ በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎችን ማረኩ፡፡ "ምድሪቱን ከማረኩ በኋላ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የትዕይንቶች ቅደም ተከተል የሚለውን ይመልከቱ)
ነገዶቹ የሚቀበሉት መሬት የተገለጸው በቋሚነት እንደተቀበሉት ሀብት ተደርጎ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ ርስት አድርጎ መሬት ላልሰጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)
ኢያሱ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው እስራኤላውያን ምድሪቱን ለመውረስ እንዲነሳሱ ለማበረታታት ነው፡፡ "የሰጣችሁን … ለረጅም ጊዜ፣ ቸል ብላችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
"ላይኛው እና ታችኛው" የሚሉት ቃላት በየአቅጣጫው የሚል ትርጉም አላቸው፡፡ይህንን በኢያሱ 18፡4 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡"በምድሪቱ በሁሉም አቅጣጫ" ወይም "በምድሪቱ በሙሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ማለት እያንዳንዱ ነገድ የሚቀበለውን የርስት ድርሻ ይገልጻል ማለት ነው
ሄደው የሚመለከቱት ምድር የተገለጸው እያንዳንዱ ነገድ እንደ ቋሚ ሀብት የሚወርሰው ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች የሚያደርገውን ንግግር ቀጠለ
"እነርሱ ምድሩን ይከፋፈላሉ"
"የይሁዳ ነገድ ይቀራል"
እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የዮሴፍን ትውልዶችን ነው፡፡ ይህ ሀረግ የኤፍሬምን እና ምናሴን ነገዶች ያመለክታል፡፡ "የኤፍሬም እና የምናሴ ትውልዶች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)
ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች የሚያደርገውን ንግግር ቀጠለ
"አንዳች የመሬት ድርሻ"
ኢያሱ ሌዋውያን ያህዌን በክህነት በማገልገል ያላቸውን ታላቅ ክብር ርስት አድርገው እንደሚወርሱት ነገር አድርጎ ይናገራል፡፡ "እነርሱ ያላቸው ድርሻ የያህዌ ካህን መሆን ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"የምናሴ ነገድ ግማሹ"
ነገዱ የተቀበለው መሬት የተገለጸው ቋሚ ሀብታቸው አድርገው እንደተቀበሉት ነው፡፡ "ምድሪቱን ርስታቸው አድርገው ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ወደ ምድሪቱ ለሚሄዱ ለሃያ አንዱ ሰዎች ተናገረ
"ላይኛው እና ታችኛው" የሚሉት ቃላት በየአቅጣጫው የሚል ትርጉም አላቸው፡፡ይህንን በኢያሱ 18፡4 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡"በምድሪቱ በሁሉም አቅጣጫ" ወይም "በምድሪቱ በሙሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ ለእያንዳንዱ ነገድ ከምድሪቱ ድርሻ ድርሻውን ሰጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
"የይሁዳ ትውልዶች ርስት በሆነው ምድር እና የዮሴፍ ትውልዶች ርስት በሆነው ምድር መሃል"
ይህ የሚያመለክተው የኤፍሬምንና የምናሴን ትውልዶች ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ አንድ አይነት ነገርን ያመለክታል፡፡
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ምናልባት አንድ ሰው ለድንበር ምልክትነት ያስቀመጠው፣ በዚያ ቦሃን በተባለ ሰው ስም የተሰየመ ትልቅ ድንጋይ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን በኢያሱ 15፡6 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የመሬቱ አቀማመጥ በስላች መልክ ወይም በጉብታ በመሆኑ ትከሻ እንደሆነ ተደርጎ ተገጽዋል፡፡ "የቤተ ዓረባ ስላች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የመሬቱ አቀማመጥ በስላች መልክ ወይም በጉብታ በመሆኑ ትከሻ እንደሆነ ተደርጎ ተገጽዋል፡፡ "የቤተ ሓግላን ስላች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የብንያም ነገድ የተቀበለው ምድር የተገለጸው ቋሚ ሀብታቸው አድርገው እንደተቀበሉት ተደርጎ ነው፡፡ "የብንያም ነገድ እንደ ርስት አድርጎ የተቀበለው ምድር ይህ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ ለእያንዳንዱ ጎሳ ይህን ሰጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው በምድሪቱ የነበሩትን የብንያም ነገዶች ርስት አድርገው የተቀበሏቸውን ከተሞች መዘርዘሩን ቀጠለ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የብንያም ነገድ የተቀበለው ምድር የተገለጸው ቋሚ ሀብታቸው አድርገው እንደተቀበሉት ተደርጎ ነው፡፡ "የብንያም ነገድ እንደ ርስት አድርጎ የተቀበለው ምድር ይህ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
1 ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መካከል ነበረ። 2 እነርዚህም ርስታቸው ሆኑላቸው፤ ቤርሳቤህም ሤባ፥ሞላዳ፥ 3 ሐጸርሹዕል፥ ባለ፥ዔጼም፥ 4 ኤልቶላድ፥ በቱል፥ ሔርማ፥ ጺቅላግ፥ 5 ቤትማርካቦት፥ ሐጸርሱሳ፥ 6 ቤተ ለባኦት፥ ሻሩሔን፤ አሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 7 ዓይን፥ ሪሞን፥ ዔቴር፥ ዓሻን፤ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው፤ 8 እስከ ባዕላት ብኤርና እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞችና ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ። 9 ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ። የይሁዳም ልጆች ዕድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸ መካከል ወረሱ። 10 ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። የርስታቸውም ድንበር ወደ ሣሪድ ደረሰ። 11 ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼትም ደረሰ፤ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ። 12 ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎት ታቦር ዳርቻ ዞረ። ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ። 13 ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋትሔፍርና ወደ ዒታቃጺን አለፈ፥ ወደ ሪምንና ወደ ኒዓ ወጣ። 14 ድንበሩም በሰሜን በኩል ወደ ሐናቶን ዞረ፥ መውጫውም በይፍታሕኤል ሸለቆ ነበረ። 15 ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም፤ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 16 የዛብሎን ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። 17 አራተኛውም ዕጣ ለይሳኮር ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። 18 ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥ወደ ከስሎት፥ወደ ሱነም፥ 19 ወደ ሐፍራይም፥ ወደ ሺአን፥ ወደ አናሐራት፥ 20 ወደ ረቢት፥ ወደ ቂሶን፥ ወደ አቤጽ፥ 21 ሬሜት፥ ወደ ዓይንጋቢም፥ ወደ ዓይንሐዳ፥ ወደ ቤት ጳጼጽ ደረሰ፤ ድንበሩም ወደ ብቦርና ወደ ሻሕጽይማ፥ ወደ ቤት ሳሚስ ደረሰ። 22 የድንበራቸውም መውጫ ዮርዳኖስ ነበረ፤ አሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 23 የይሳኮር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። 24 አምስተኛውም ዕጣ ለአሴር ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። 25 ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥ ቤጤን፥ አዚፍ፥ አላሜሌክ፥ ዓምዓድ፥ ሚሽአል ነበረ፤ 26 በምዕራብ በኩል ወደ ቀርሜሎስና ወደ ሺሖርሊብናት ደረሰ። 27 ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤት ዳጎን ዞረ፥ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤት ዓሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፤ በስተ ግራ ቡልም ወደ ካቡል ወጣ። 28 ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረአብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲኖናም ደረሰ። 29 ድንበርም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፤ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፤ መውጫውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤ 30 ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ። እነዚህም ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። 31 የአሴር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። 32 ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። 33 ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ ከጸዕነኒም ዛፍ፥ ከአዳሚኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ። 34 ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ከዚያም በደቡም በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳስም ወንዝ በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ። 35 የተመሸጉትም ከትሞች እነዚህ፦ ነበሩ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥ 36 አዳማ፥ ራማ፥ አሶር፥ 37 ቃዴስ፥ኤድራይ፥ ዓይንሐጽር፥ ይርአን፥ 38 ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤት ዓናት፥ ቤት ሳሚስ፤ አሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው ያልተቆጠሩ። 39 የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። 40 ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። 41 የርስታቸውም ዳርቻ ይህ ነበረ፤ ጾርዓ፥ ኤሽታኦል፥ ዒርሼሜሽ፥ 42 ሸዕለቢን፥ ኤሎን፥ ይትላ፥ ኤሎን፥ 43 ተምና፥አቃሮን፥ 44 ኢልተቄ። ገባቶን።ባዕላት፥ ይሁድ፥ 45 ብኔንርቅ፥ ጋትሪሞ፥ 46 ሜያርቆን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆን። 47 የዳንም ልጆች ዳርቻ አልበቃቸውም፥ የዳንም ልጆች ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለመቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። ስምዋንም በአባቶታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠርአት። 48 የዳን ነገድ ርስት በየወገኖቻቸ እነዚህ ከትሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። 49 ምድሩንም ሁሉ በየድንበሩ ርስት እንዲሆን ከፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት። 50 በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት። ከተማውንም እንደ ገና ሠርቶ ተቀመጠበት። 51 ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ነገዶችና የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። የምርሪቱንም ማከፋፈል ሥራ ጨረሱ።
"ኢያሱ ለሁለተኛ ጊዜ ዕጣ ሲጥል፣ ዕጣው የስምዖንን ነገድ አመለከተ"
በዝርዝር ውስጥ ሁለተኛው ቁጥር (ተከታታይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
"ኢያሱ ምድሪቱን ለእያንዳንዱ ጎሳ ሰጠ"
ምድሪቱ የተገለጸችው ነገዶቹ በቋሚነት የተቀበሏት ሃብት ተደርጋ ነው፡፡ "ርስት አድርገው የተቀበሉት ምድር የይሁዳ ነገድ ርስት አድርገው በተቀበሉት ምድር መሃል ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ጸሐፊው በምድሪቱ የነበሩትን የስምዖን ነገዶች ርስት አድርገው የተቀበሏቸውን ከተሞች መዘርዘሩን ቀጠለ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህችን ከተማ ስም በኢያሱ 15፡31 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ
የስምዖን ነገድ የተቀበሏቸው ምድር እና ከተሞች የተገለጹት ቋሚ ርስታቸው አድርገው እንደ ተቀበሉት ሀብት ተደርጎ ነው፡፡ "የስምዖን ነገድ ርስታቸው አድርገው የተቀበሏቸው ምድር እና ከተሞች እነዚህ ነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ ለጎሳቸው የሰጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኢያሱ ለይሁዳ ነገድ ድርሻ አድርጎ የሰጠው ምድር " በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
"የይሁዳ ምድር ድርሻ መሃል"
ይህንን ሀረግ በኢያሱ 19፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ
በዝርዝር ውስጥ ሦስተኛው ቁጥር (ተከታታይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
"ቅንዓምን አቋርጦ"
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ሀረግ በኢያሱ 19፡1 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ
በዝርዝር ውስጥ አራተኛው ቁጥር (ተከታታይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የተራራ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የይሳኮር ነገድ የተቀበለው ምድር እና ከተማ የተገለጹት ቋሚ ርስት አድረገው እንደተቀበሏቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ይህ የይሳኮር ነገድ ወርስ አድርጎ የተቀበለው ምድር እና ከተማዎች ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ሀረግ በኢያሱ 19፡1 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ
በዝርዝር ውስጥ አምስተኛው ቁጥር (ተከታታይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ሀረግ በኢያሱ 19፡1 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ
በዝርዝር ውስጥ ስድስተኛው ቁጥር (ተከታታይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚገኘው በተመሳሳይ "ሐማት" ባለበት ሳይሆን፣ በገሊላ ባህር ምዕራብ የባህር ዳርቻ ነው፡፡
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የንፍታሌም ነገድ የተቀበለው ምድር እና ከተማ የተገለጹት ቋሚ ርስት አድረገው እንደተቀበሏቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ይህ ንፍታሌም ነገድ ወርስ አድርጎ የተቀበለው ምድር እና ከተማዎች ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ሀረግ በኢያሱ 19፡1 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ
በዝርዝር ውስጥ ሰባተኛው ቁጥር (ተከታታይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዳን ነገድ የተቀበለው ምድር የተገለጸው ቋሚ ርስት አድርገው እንደተቀበሉት ተደርጎ ነው፡፡ "የዳን ነገድ ወርስ አድርጎ የተቀበለው ርስት ግዛት/ክልል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)ጾርዓ፣ ኤሽታኦል፣ ዒር ሼሜሽ፣ ሸዕለቢን፣ ኤሎን፣ እና ይትላ እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህንን ሀረግ በኢያሱ 19፡1 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ
በዝርዝር ውስጥ ሰባተኛው ቁጥር (ተከታታይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)
የዳን ነገድ የተቀበለው ምድር የተገለጸው ቋሚ ርስት አድርገው እንደተቀበሉት ተደርጎ ነው፡፡ "የዳን ነገድ ወርስ አድርጎ የተቀበለው ርስት ግዛት/ክልል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)ጾርዓ፣ ኤሽታኦል፣ ዒር ሼሜሽ፣ ሸዕለቢን፣ ኤሎን፣ እና ይትላ እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"ከኢዮጴ በተቃራኒ" ወይም "ከኢዮጴ አጠገብ
ይህ የከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የዳን ነገድ የተቀበለው ምድር እና ከተማ የተገለጹት ቋሚ ርስት አድረገው እንደተቀበሏቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ይህ የዳን ነገድ ወርስ አድርጎ የተቀበለው ምድር እና ከተማዎች ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ የተቀበላት ከተማ የተገለጸችው ቋሚ ርስቱ አድርጎ እንደተቀበላት ርስቱ ተደርጎ ነው፡፡ "በምድራቸው ርስት አድርገው ለነዌ ልጅ ለኢያሱ ከተማ ሰጡት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የተለያዩ ነገዶች የተቀበሏቸው መሬት እና ከተሞች የተገለጹት ቋሚ ሀብት አድርገው እንደተቀበሏቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ውርስ ተደርጎ የተሰጣቸው… ምድርና ከተሞች ድርሻቸው እነዚህ ናቸው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
1 ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2 ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፡ 3 ሳያውቅም ሰውን የገደለ እንዲሸሽባቸው በሙሴ እጅ የነገርኋችሁን የመማፀኛ ከተሞችን ለዩ። እነዚህም ከተሞች ከተገደለበት ከማንኛውም ከደም ተበቃይ የሚሸሹበት ቦታ ይሆኑላችኋል። 4 ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ ለከተማይቱ ሽማግሌዎች ጉዳዩን ያስረዳል። እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡታል። 5 ሰው የሞተበትም ደም ተበቃዩ መጥቶ ለመበቀል ቢሞክር፥ የከተማውም ሰዎች ሰውየውን ለከተማው ባለሥልጣናት አሳልፈው መስጠት አይኖርባቸውም። ይህን ማድረግ የማይገባቸው እርሱ የገደለው ከዚህ በፊት ጥላቻ ሳይኖርና ሆነ ብሎ ባለመሆኑ ነው። 6 በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያን ጊዜ ያለው በሊቀ ካህንነት የሚያገለግለው እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ። ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ፥ ሸሽቶ ከነበረበት ከተማ ወደ ከተማውና ወደ ቤቱ ይመለሳል። 7 በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያትአርባቅን ለዩ። 8 ከዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፣ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ቶላንን ለዩ። 9 ማንም ሰው ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽና በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ናቸው። ይህም ሰው በማኅብሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ነው።
እዚህ ስፍራ "የሙሴ እጅ" የሚለው የሚያመለክተው ሙሴ የጻፋቸውን መጽሐፍት ነው፡፡ "ሙሴ በጻፋቸው ነገሮች አማካይነት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
x
እዚህ ስፍራ "እርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሳያውቅ እንድን ሰው የገደለን ሰው ነው፡፡
"ሰውየውን ሳያወቅ በድንገት እንደገደለው የከተማይቱን ሽማግሌዎች ያሳምናል/ያስረዳል"
"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሽማግሌዎችን ሲሆን "እርሱን" የሚለው የሚያመለክተው ሳያውቅ አንድን ሰው የገደለን ሰው ነው፡፡
ይህ ሽማግሌዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ከተማይቱን በጭምር ያመለክታል፡፡
እዚህ ስፍራ የአንድ ሰው የፈሰሰ ደም የሚለው የሚገልጸው መሞትን ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ ይህንን በኢያሱ 20፡3 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ "የሞተውን ሰው መበቀል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)
እነዚህ ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው
ይህ ሀረግ የሚገልጸው ፍትህን በመፈለግ አብረውት በሚኖሩ ወገኖቹ ችሎት ፊት መቆምን ነው
በዚህ ክፍል ውስጥ በርካታ ስሞች አሉ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የዮርዳኖስ ወንዝ አጭር ስም ነው
እዚህ ስፍራ "በእጅ" የሚለው ለአንድ ነገር ልዩ ምክንያት መሆን የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "መገደል የለበትም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ ይህንን ሀረግ በኢያሱ 20፡3 እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ "የአንድን ሰው ሞት መበቀል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)
1 ከዚያም የሌዋውያን ወገኖች አለቆች ወደ ካህኑ አልዓዘር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ እስራኤል ነገዶች አለቆች ቀርቡ። 2 እነርሱም በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ እንዲህ አሉአቸው፡- እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውንና ለከብቶቻችንም መሰማሪያ የሚሆኑ ከተሞች እንድትሰጡን አዞአችኋል። 3 ስለዚህም የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሚከተሉትን ከተሞች ለከብቶቻቸውም መሰማሪያ ጭምር እንዲሆኑ ርስታቸውን ለሌዋውያን ሰጡአቸው። 4 ለቀዓትም ወገኖች የዕጣው ውጤት እንዲህ ሆነ፦ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች፥ ከይሁዳ ነገድ ከስምዖንም ነገድ ከብንያምም ነገድ አሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጣቸው። 5 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድና ከምናሴ ነገድ እክኩሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ተቀበሉ። 6 ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴር ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳን ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጣቸው። 7 ለሜራሪም ልጅች በየወገኖቻቸው ከሮቤል ነገድ፥ከጋድ ነገድና ከዛብሎን ነገድአሥራ ሁለት ከተሞ ተቀበሉ። 8 እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዛቸው የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ። 9 ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው እነዚህን ከተሞች ሰጡ። 10 እነዚህ ከተሞች ከሌዊ ልጆች ነገድ የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ተሰጥቶአቸው ነበር። የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ወጥቶላቸው ነበር። 11 እንደ ኬብሮን ተመሳሳይ ቦታ በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት አርባቅ (ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ) የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን የከብቶች መሰማሪያዋን ሰጡአቸው። 12 የከተማይቱንም እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት። 13 ለካህኑም ለአሮን ልጆች ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና መሰማሪያዋን፥ ልብናን ከመሰማሪያዋን ጋር ሰጡ፤ 14 የቲርንና መሰማሪያዋን፥ ኤሽት ሞዓንና መሰማሪያዋን፥ 15 ሖሎንንና መሰማሪያዋን፥ ዳቤርንና መሰማሪያዋን፥ 16 ዓይንንና መሰማሪያዋን፥ ዮጣንና መሰማሪያዋን፥ ቤት ሳሚስንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ነበሩ። 17 ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰማሪያዋን፥ ናሲብንና መሰማሪያዋን፥ 18 ዓናቶትንና መሰማሪያዋን፥ አልሞንንና መሰማሪያዋን፤አራት ከተሞችን ሰጡ። 19 ለአሮን ልጆች ለካህናት የተሰጡ ከተሞች ከመሰማሪያቸው ባጠቃላይ አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው። 20 ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ወገኖች ሌዋውያን የተሰጣቸ ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ዕጣ ወጥቶላቸው ነበር። 21 ለእነርሱም በኤፍሬም ተራራማ አገር ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥ 22 ቂብጻይምንና መስማሪያዋን፥ ቤት ሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 23 ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና መሰማሪያዋን፥ ገባቶንንና መሰማሪያዋን፥ 24 ኤሎንንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 25 ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 26 ለቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች የተሰጡ ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸውን ጋር አሥር ከተሞችናቸው። 27 ለሌሎች ሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነችውን ጎላንንና መሰማሪያዋን፥ በኤሽትራንና መሰማይያዋን ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 28 ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰማሪያዋን፥ ዳብራትንና መሰማሪያዋን፥ 29 የያርሙትንና መሰማሪያዋን፥ ዓይንጋኒምንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ለጋሪሶን ነገድ ሰጡአቸው። 30 ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰማሪያዋን፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋን፥ 31 ሔልቃትንና መሰማሪያዋን፥ ረአብንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 32 ከንፍታሌምም ነገድ ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞትዶርንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ለጌድሶን ነገድ ሰጡአቸው። 33 የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ከመሰማሪያቸው ጋር አሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው። 34 ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንና መሰማሪያዋን፥ 35 ዲሞናንና መሰማሪያዋን፥ ነህላልንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 36 ለሜራሪ ነገድ ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰማሪያዋን፥ ያሀጽንና መሰምሪያዋን፥ 37 ቅዴሞትንና መሰማሪያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 38 ሳያውቁ ነፍሰ ገዳይ ለሆኑት መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ከጋድም ነገድ በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንማ መሰማሪያዋን ሰጡ። 39 ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን ሜራሪ ነገድ ደግሞ የተሰጡ ባጠቃላይ አራት ከተሞች ናቸው። 40 ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ባጠቃላይ አሥራ ሁለት ከተሞች ነበሩ። 41 በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማሪያቸው ነበሩ። 42 እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰማሪያቸው ጋር ነበሩ፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ በዚህ ዓይነት መንገድ ነበሩ። 43 እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ። ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። 44 እግዚአብሔርም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው። ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ይቋቋማቸው ዘንድ ማንም ሰው አልቻለም፤ እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። 45 እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።
እነዚህ ስሞች የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"ሌዋውያን ለእነርሱ አሏቸው"
"በእጅ" የሚለው ሀረግ ያህዌ ትዕዛዙን ለመስጠት/ማቅረብ ሙሴን እንደተጠቀመበት የሚገልጽ ፈሊጣ አነጋገር ነው፡፡ "ያህዌ ያዛችሁ ዘንድ ሙሴን ተናገረው/ አዘዘው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው በተከታዮቹ ቁጥሮች የሚዘረዘሩትን/የሚጻፉትን ከተሞች ነው፡፡
ከመሪዎች ፍላጎት ውጭ በዕጣ ምርጫ የማድረግ ዘዴ ብዙውን ጊዜ የሚካሄደው እግዚአብሔር ውጤቱን ይወስን በሚል ሃሳብ ነው፡፡ ይህንን እንዴት በኢያሱ 19፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡
በዚህ ቡድን ውስጥ እነዚህ ካህናት የሌዊ ትውልድ የሆኑ የቀዓት ልጆች ነበሩ፡፡ ከእነርሱ ከፊሎቹም የአሮን ትውልድ፣ የቀዓት የልጅ ልጆች ነበሩ፡፡
የከተሞች ቁጥር (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የነገዱ ግማሽ የተባለበት ምክንያት ቀሪው ግማሽ ርስታቸውን ዮርዳኖስን ወንዝ ከማቋረጣቸው አስቀድሞ ስተቀበሉ ነው፡፡
ጌርሶን ከሌዊ ልጆች አንዱ ነበር፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ከመሪዎች ፍላጎት ውጭ በዕጣ ምርጫ የማድረግ ዘዴ ብዙውን ጊዜ የሚካሄደው እግዚአብሔር ውጤቱን ይወስን በሚል ሃሳብ ነው፡፡ ይህንን እንዴት በኢያሱ 19፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡
ሜራሪ ከሌዊ ልጆች አንዱ ነበር፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"በእጅ" የሚለው ሀረግ ትርጉሙ ያህዌ ሙሴን ትዕዛዙን ለማቅረብ ተጠቀመበት ማለት ነው፡፡ "ያህዌ ሙሴ እንዲያዝ ነገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
በዚህ ቡድን ውስጥ እነዚህ ካህናት የሌዊ ትውልድ የሆኑ የቀዓት ልጆች ነበሩ፡፡ ከእነርሱ ከፊሎቹም የአሮን ትውልድ፣ የቀዓት የልጅ ልጆች ነበሩ፡፡ ይህንን እንዴት በኢያሱ 19፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡
ይህ መረጃ የቂርያት አርባቅን ከተማ ስለ መሰረታት ሰው ስም የቀረበ የመረጃ ዳራ ነው፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ከተራሮች አነስ ያለ ተፈጥሯዊ ከፍታ ያለው ምድር
በሳር ወይም ለከብቶች ግጦሽ ተስማሚ በሆነ ተክል የተሸፈነ አካባቢ
ብዙውን ጊዜ ተክሎች የሚገኙበት በከተማ ዙሪያ ሚገኝና የከተማይቱ ይዞታ የሆነ መሬት
ብዙውን ጊዜ ከከተማ የሚያንስ፣ አነስተኛ ማህበረሰብ፡፡
እነዚህ ሁሉ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
በክፍሉ/ምንባቡ ውስጥ የከተሞች እና የነገዶች ቁጥር
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የብንያም ነገድ ገባዖንን ሰጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"13 ከተሞች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
በዚህ ቡድን ውስጥ እነዚህ ካህናት የሌዊ ትውልድ የሆኑ የቀዓት ልጆች ነበሩ፡፡ ከእነርሱ ከፊሎቹም የአሮን ትውልድ፣ የቀዓት የልጅ ልጆች ነበሩ፡፡ ይህንን እንዴት በኢያሱ 19፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከተሞችን ተቀበሉ/ተሰጧቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ከመሪዎች ፍላጎት ውጭ በዕጣ ምርጫ የማድረግ ዘዴ ብዙውን ጊዜ የሚካሄደው እግዚአብሔር ውጤቱን ይወስን በሚል ሃሳብ ነው፡፡ ይህንን እንዴት በኢያሱ 19፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡
የከተሞች ስሞች (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው የከተሞቹን ቁጥር ዝርዝር በአጠቃላይ ነው (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የዳን ነገድ ለቀዓት ኤልተቄን ሰጧቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
በዚህ ቡድን ውስጥ እነዚህ ካህናት የሌዊ ትውልድ የሆኑ የቀዓት ልጆች ነበሩ፡፡ ከእነርሱ ከፊሎቹም የአሮን ትውልድ፣ የቀዓት የልጅ ልጆች ነበሩ፡፡ ይህንን ተመሳሳይ ሀረግ በኢያሱ 21፡20 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የከተሞቹን ቁጥር ያመለክታል፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የምናሴ ነገድ እኩሌታ ለቀዓት ነገድ ታዕናክን ሰጧቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የተመዘገቡ ከተሞች ቁጥር (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
በዚህ ቡድን ውስጥ እነዚህ ካህናት የሌዊ ትውልድ የሆኑ የቀዓት ልጆች ነበሩ፡፡ ከእነርሱ ከፊሎቹም የአሮን ትውልድ፣ የቀዓት የልጅ ልጆች ነበሩ፡፡ ይህንን በኢያሱ 21፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ ሌሎች የሌዊ ነገዶች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ጎላንን ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
የከተሞች ስሞች (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው ሰውን ለመግደል ታስቦ ያልተደረገን ግድያ ነው
የከተሞች ቁጥር (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የጌርሶን ነገድ ደግሞ ቂሶንን ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
የከተሞች ስሞች (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ከአሴር ነገዶች፣ ሚሽአልን ሰጡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከአሴር ነገድ ሚሽአልን ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው የተመዘገቡ/የተዘረዘሩ ከተሞችን ዝርዝር ነው (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የጌርሶን ከንፍታሌም ነገድ ቃዴስን ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሰው ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"በጠቅላላው 13 ከተሞች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የተቀሩት ሌዋውያን- የሜራሪ ነገድ- ከዛብሎን ነገድ ዮቅናምን ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሰው ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የከተሞች ስሞች (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ከተሞቹ በጠቅላላው የተጠቀሱት እንደ ቁጥር ነው፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የሜራሪ ነገዶች ከሮቤል ነገዶች ቦሶርን ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የከተሞቹን ቁጥር ያመለክታል፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የከተሞች ስሞች (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከጋድ ነገድ ራሞትን ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የሜራሪ ነገድ ደግሞ ሐሴቦንን ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"በአጠቃላይ 12 ከተሞች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እነዚህን አስራ ሁለት ከተሞች በዕጣ መጣል ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
ከመሪዎች ፍላጎት ውጭ በዕጣ ምርጫ የማድረግ ዘዴ ብዙውን ጊዜ የሚካሄደው እግዚአብሔር ውጤቱን ይወስን በሚል ሃሳብ ነው፡፡ ይህንን እንዴት በኢያሱ 19፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሌዋውያኑ ከተሞቻቸውን ከምድሪቱ መሃል ተቀበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
"48 ከተሞች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
"መሃላ ሰጠ"
ሃሳቡን ለማጉላት ይህ የተገለጸው በአሉታ ነው፡፡ "እነርሱ ጠላቶቻቸውን ሁሉ አሸነፉ" (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "በእጆቻቸው" የሚለው "ከጉልበታቸው ስር አደረጋቸው/አንበረከከላቸው" ማለት ነው፡፡ "ጠላቶቻቸውን ሁሉ እንዲያሸንፉ ሃይል ሰጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት)
ሃሳቡን ለማጉላት ይህ የተገለጸው በአሉታ ነው፡፡ "ያህዌ ለእስራኤል ቤት የተናገረው እያንዳንዱ መልካም ቃል ኪዳን ተፈጸመ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)
1 በዚያን ጊዜም ኢያሱ የሮቤል ልጆችንና የጋድ ልጆችን የምናሴንም ነገድ እኩሌታ ጠራቸው። 2 እንዲህም አላቸው፦ የእግዚእአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ሁሉ ጠብቃችኋል፥ እኔም ላዘዝኋችሁ ነገር ሁሉ ታዝዛችኋል። 3 ይህንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወንድሞቻችሁን አልተዋችሁም፥ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቃችኋል። 4 አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራቸው ወድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል። አሁን እንግዲህ ተመለሱ፥ ወደ ቤታችሁና የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ። 5 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችሁን ትወድዱ ዘንድ መንገዱንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ ወደ እርሱም ትጠጉ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩ ዘንድ ብቻ እጅግ ተጠንቀቁ። 6 ኢያሱም መረቃቸው፥ ሰደዳቸውም፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ። 7 ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ሙሴ በባሳን ውስጥ ርስት ሰጥቶአቸው ነበር፤ ለቀረው እኩሌታው ግን ኢያሱ በዮርዳኖስ ማዶ በምዕብብ ወንን በወንድሞቻቸው መካከል ርስት ሰጣቸው። ኢያሱም ወደ ቤታቸው በሰደዳቸው ጊዜ 8 እንዲህ ብሎ መረቃቸው፦ በብዙ ብልጥግና በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ። 9 የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ የእስራኤል ሕዝብ በከነዓን በሴሎ ትተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ። በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉአት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ ሄዱ። 10 በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያም በመጡ ጊዜ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዚያ በዩርዳኖስ አጠገብ ታላቅ መሠዊያ ሠሩ። 11 ለእስራኤልም ልጆች፦ እነሆ፥ በከነዓን ምድር ዳርቻ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው ግዛት፥ የእስራኤል ልጆች ባሉበት ወገን፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ መሠዊያ ሠርውዋል፤ የሚል ወሬ ደረሰላቸው። 12 የእስራኤል ሕዝብ ይህን በሰሙ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወጥተው እነርሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰበስቡ። 13 የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መልእክት ላኩ። የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ደግሞ ላኩ፥ 14 ከእርሱም ጋር አሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ እያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቃ ነበሩ። 15 በገለዓድም ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ግድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ መጡ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩአቸው፦ 16 የእግዚአብሔር ማኅበር ሁሉ የሚለው ይህ ነው፦ ይህ በእስራኤል አምላክ ላይ ያደረጋችሁት ኃጢአት ምንድን ነው? ዛሬ እግዚእአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋል ዛሬም በራሳችሁ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል። 17 በፌጎር ያደረገነው ኃጢአታችን አይበቃምን? እስከ ዛሬም ድረስ ከዚያ ኃጢአት ራሳችንን አላነጸንበትም። ከዚያም ኃጢአት የተነሣ በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ወረደ። 18 እናንተ ዛሬ እግዚአብሔርን ከመከተል መመለስ ይገባችኋልን? ዛሬ በእግዚአሔር ላይ ብታምፁ ነገ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ይቆጣል። 19 የርስታችሁም ምድር የረከሰ ቢመስላችሁ የእግዚአብሔር ማደሪያ ወደ ሚቀመጥበት ወደ እግዚአብሔር ርስት ምድር አልፋችሁ በመካከላችን ውረሱ። ከአምላካችንም ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለእናንተ መሠዊያ በመሥራታችሁ በእግዚአብሔርና በእኛ ላይ አታምፁ። 20 የዛራ ልጅ አካን እርም ነገር በመውሰድ ኃጢአትን ስለ ሠራ በእስራኤል ማኅበር ሁሉ ላይ ቁጣ አልወረደምን? እርሱም በኃጢአት ብቻውን አልሞተም። 21 ከዚያም የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ለእስራኤል አለቆች እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ 22 ሁሉን የሚችል አምላክ እግዚአብሔር ታላቁ አምላክ እግዚአብሔር እርሱ ያውቃል፥ እስራኤልም እንዲያውቅ ያደርጋል! በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደ ሆነ ዛሬ አታድነን እግዚአሔርን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን 23 መሥዋዕትና የእህልን ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅነትትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይበቀለን። 24 ይልቁንም ከልባችን ፍርሃት የተነሣ፦ በሚመጣው ዘመን ልጆቻችንን፦ እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች፥ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ምን አላችሁ? 25 እግዚአብሔር በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአል። እናንተ የሮቤልና የጋድ ልጆች በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታ የላችሁም ይሉአቸዋል ብለን ይህን አደረግን። በዚህም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እግዚአብሔርን ከመፍራት ያስተዋቸዋል። 26 ስለዚህ፦ መሠዊያ እንሥራ አልን፤ ነገር ግን ለሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት አይደለም፤ 27 ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንት የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል። 28 ስለዚህም አልን፦ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ወይም ለትውልዳችን፥ ይህን እንላለን እኛ፦ እነሆም አባቶቻችን ያደረጉትን የእግዚአብሔርን መሠዊያ ምሳሌ እዪ በእኛና በእናንተ መካከል ምስክር ነው እንጂ ስለሚቃጠል መሥዋዕታችን ስለሌላ መሥዋዕት አይደለም። በማደሪያው ፊት ካለው ከአምላካችን 29 ከእግዚአብሔር መሠዊያ ሌላ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእህል ቁርባን ለሌላ መሥዋዕትም የሚሆን መሠዊያን የሠራነው በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ እግዚአብሔርንም ዛሬ መከተልን ለመተው በማለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ። 30 ካህኑ ፊንሐና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር ከነበሩት የእስራኤል አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው። 31 የካህኑም በአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ለሮቤል ልጆችና ለጋድ ልጆች ለምናሴም ልጆች፦ ይህን መተላለፍ በእግዚአብሔር ላይ አላደረጋችሁምና እግዚአብሔር በመካከላችን እንዳለ ዛሬ እናውቃለን፤ አሁን የእስራኤልን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ አድናችኋል አላቸው። 32 የካህኑም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና አለቆቹ ከሮቤል ልጆችና ከጋድ ልጆች ዘንድ ከገለዓድ አገር ወደ ከነዓን አገር ወደ እስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ ወሬም አመጡላቸው። 33 ነገሩም የእስራኤል ልጆችን ደስ አሰኘ፤ የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ ከዚያም ወዲያ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የተቀመጡባትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ወጥተው አንዲወጉአቸው አልተናገሩም። 34 የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፦ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት።
የሮቤል ነገድ ሰዎች (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የጋድ ነገድ ሰዎች (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "ድምጼ" የሚለው የሚያመለክተው ኢያሱ የተናገራቸውን ነገሮች ነው፡፡ "የተናገርኩትን ሁሉ ታዛችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት)
ይህ በአዎንታዊ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከወንድሞቻችሁ ጋር ቆይታችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌን የሚታዘዝ ሰው በያህዌ መንገዶች ወይም ጎዳናዎች እንደሄደ ተደርጎ ይነገራል፡፡ "እርሱ ያለውን ነገር ሁሉ መታዘዝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"ልብ" እና "ነፍስ" የሚሉት ቃላት እዚህ ስፍራ ላይ ያገለገሉት የሰውን ሁለንተና ለመግለጽ ነው፡፡ "በሙሉ ሃሳባችሁ እና ስሜታችሁ" ወይም "በሁለንተናችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የዮርዳኖስ ወንዝ አጭር ስያሜ ነው
ጠንካራ፣ ከባድ፣ ማግኔት የሚስበው ነገር
ያሸነፈው ሰራዊት ካሸነፈው ህዝብ ዋጋ ያለውን ማናቸውንም ነገር ይወስዳል
"በእጅ" የሚለው ሀረግ ያህዌ ትዕዛዙን ለመስጠት/ለማቅረብ ሙሴን እንደተጠቀመበት የሚገልጽ ፈሊጣ አነጋገር ነው፡፡ "ያህዌ ያዛችሁ ዘንድ ሙሴን ተናገረው/ አዘዘው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የዮርዳኖስ ወንዝ አጭር ስያሜ ነው
ከዮርዳኖስ ወንዝ ባሻገር የሚኖሩ እስራኤላውያን ነገዶች መሰዊያውን ወደ ገነቡበት ከነዓን ይገባሉ፡፡ ይህ ስፍራ የተገለጸው ሌሎች ነገዶች የሚኖሩበት የከነዓን "ፊት " ወይም "መግቢያ" እንደነበረ ተደርጎ ነው፡፡ "ወደ ከነዓን ምድር መግቢያ ላይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
የከተማ ስም (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
በሁለት አገራት ወይም ህዝቦች መሃል በጦር ትጥቅ የሚደረግ ግጭት
የወንድ ስም (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
መላው የእስራኤል ህዝብ በአንድነት የተገለጸው በነጠላ ቁጥር አንድ ሰው እንደሆኑ ተደርጎ ነው፡፡ "ሌሎቹ እስራኤላውያን ሁሉ ይጠይቃሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡
ይህ ጥያቄ የቀድሞ ኃጢአታቸው ምን ያህል የከፋ እንደሆነ አጉልቶ ያሳያል፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አስቀድመን በፌጎር እጅግ ክፉ ኃጢአት ሰርተናል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ በኢያሱ 13፡20 ላይ በተረጎሙት መንገድ ይተርጉሙት፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ በአዎንታዊ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እስከ አሁን ድረስ በዚያ ኃጢአት ውስጥ እንገኛለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ጥያቄ ህዝቡን በኃጢአቱ ለመገሰጽ ውሏል፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ዛሬ ያህዌን ከመከተል መራቅ የለባችሁም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
የወንዶች ስሞች ናቸው (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ጥያቄዎች ህዝቡ ባለፊት ኃጢአቶች ስለደረሰበት ቅጣት ለማስታወስ ውለዋል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በዐፍተ ነገር ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "የዛራ ልጅ አካን ለእግዚአብሔር የተለዩ ነገሮችን በመንካት ኃጢአት ሰርቷል፡፡ ደግሞም በዚያ ምክንያት እግዚአብሔር መላውን የእስራኤል ህዝብ ቀጥቷል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ሶስቱ ነገዶች የቀረበባቸው እውነት ላለመሆኑ ሁለት መላምታዊ ሃሳቦችን አቅርበዋል፡፡ ሌሎች አማልክትን ለማምለክ መሰዊያ አላበጁም፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)
የሮቤል ነገድ፣ የጋድ እና የምናሴ ነገድ እኩሌታ መልሳቸውን ሰጡ፡፡
ይህ ሶስቱ ነገዶች የሌሎች ነገዶች ልጆች ወደ ፊት ሊያደርጉት ይችላሉ ብለው ያሰቡት መላምታዊ ክስ ነው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)
ሶስቱ ነገዶች ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀሙት ሊያስወግዱት የሚፈልጉትን ሁኔታ አጉልተው ለማሳየት ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከእስራኤል አምላክ ከያህዌ ጋር አንዳች የላችሁም!" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
የሮቤል ነገድ፣ የጋድ እና የምናሴ ነገድ እኩሌታ መልሳቸውን መስጠት ቀጠሉ፡፡
ይህ ሶስቱ ነገዶች የሌሎቹ ነገዶች ልጆች ወደ ፊት ሊያደርጉት ይችላሉ ብለው ያሰቡት የመላምታዊ ክሱ ቀጣይ ነው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የዮርዳኖስ ወንዝ አጭር ስያሜ ነው ስለዚህ የእናንተ ልጆች የእኛን ልጆች ያህዌን ከማምለክ እንዲያቆሙ ሊያደርጉ ይችላሉና ሶስቱ ነገዶች መሰዊያ የገነቡት ለወደፊት ይህ መላምታዊ ሁኔታ እንዳይፈጠር ለማስወገድ ነው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)
የሮቤል ነገድ፣ የጋድ እና የምናሴ ነገድ እኩሌታ አሁን መልሳቸውን ሰጡ፡፡
መሰዊያው የተገለጸው ለሶስቱ ነገዶች መብቶች ማስረጃ መስጠት የሚችል ምስክር እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ሶስቱ ነገዶች እንዲሆን የማይሹት መላምታዊ ሁኔታ ነው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)
"ምንም ክፍል" ወይም "ምንም ርስት"
የሮቤል ነገድ፣ የጋድ እና የምናሴ ነገድ እኩሌታ አሁን መልሳቸውን ሰጥተው አበቁ፡፡
ሶስቱ ነገዶች በቀረበባቸው ክስ በመጪው ዘመን ሊሆንም ላይሆንም ስለሚችለው ያላቸውን መልስ እየሰጡ ነው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)
የማመጽ ሃሳብ እንደሌላቸው ይህ ሃሳብ የተገለጸው፣ ከእነርሱ በጣም በሩቅ ስፍራ ላይ እንደሚገኝ ነገር ተደርጎ ነው፡፡ "እኛ በእርግጥ አናምጽም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ያህዌን መከተልን ማቆም የተገለጸው እነርሱ ከእርሱ እንደዞሩ ተደርጎ ነው፡፡ "እርሱን መከተል አቆሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"መልዕክቱን ሰሙ" በዐይኖቻቸው ፊት መልካም ነበር እዚህ ስፍራ "በዐይኖቻቸው ፊት" የሚለው "በእነርሱ አስተያየት" ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"ለእርሱ የገባችሁትን ቃል ኪዳን ማፍረስ"
እዚህ ስፍራ "የያህዌ እጅ" የሚለው የሚያመለክተው ቅጣትን ነው፡፡ ህዝቡን መጠበቅ የተገለጸው ከእርሱ እጅ እንደ ማዳን ተደርጎ ነው፡፡ "ያህዌ እኛን እንዳይቀጣን ጠብቃችሁናል" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት)
እዚህ ስፍራ "በዐይኖች ፊት ደስ የሚያሰኝ" የሚለው "ተቀባይነት አገኘ" ማለት ነው፡፡ "ህዝቡ የሽማግሌዎቹን ንግግር ተቀበለ"በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"በምድሪቱ የሚገኘውን ማናቸውንም ነገር ማጥፋት"
ይህ የሚያመለክተው ሮቤላውያንን እና ጋዳውያንን ነው
መሰዊያው የተነገረው የሶስቱ ነገዶች ማረጋገጫ ምስክር እንደሆነ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
1 ከብዙ ቀናት በኋላ፥እግዚአብሔርም እስራኤልን በዙሪያቸው ካሉት ጠላቶቻቸው ሁሉ ካሳረፈ፥ ኢያሱ ሸምግሎ ነበር። 2 ኢያሱም እስራኤልን ሁሉ ሽማግሌዎቻቸውን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እኔ በጣም ሸምግያለሁ። 3 እናንተም አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው። 4 ተመልከቱ! እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ መድቤላችኋለሁ። 5 እግዚአሔር አምላካችሁም እርሱ ከፊታችሁ በብርቱ ይበትናቸዋል፥ ከፊታችሁም ያሳድዳቸዋል። እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ። 6 ስለዚህም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለመጠበቅና ለማድረግ በጣም በርቱ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ። 7 በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፥ አትማሉባቸውም፥ አታምልኩአቸውም፥ አትስገዱላቸውም። 8 እስከ ዛሬ ድረስ እንዳደረጋችሁት በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ተጣበቁ። 9 እግዚአብሔርም ታላላቆችንና ኃይለኞችን መንግሥታት ከፊታችሁ አስወጣላችሁ። እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም። 10 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተጋገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና፥ ከእናንተ አንድ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል። 11 እግዚእብሔር አምላካችሁን ትወድዱት ዘንድ ትኩረት አድርጉ። 12 እናንተ ግን ተመልሳችሁ በመካከላችሁ ከቀሩት ከእነዚህ አሕዛብ ጋር ብትጣበቁ፥ወይም ከእነርሱም ጋር ብትጋቡ፥ ወይም እናንተ ወደ እነርሱም ወደ እናንተ ኅብረት ብታደርጉ፥ 13 ከዚያም እግዚአብሔር አምላካችሁ ከመካከላችሁ እነዚህን ሰዎች እንደማያስወጣችሁ በርግጥ እወቁ። በዚህ ፈንታ ከዚህች እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ ለእናንተም መውደቂያና ወጥመድ፥ በጎናችሁም መግረፊያ፥ በዓይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል። 14 እነሆም ዛሬ የምድርን መንገድ ሁሉ እሄዳለሁ፤ እናንተም እግዚአብሔር ስለ እናንተ ከተናገረው ከመልካም ነገር ሁሉ አንድ ነገር እንዳልቀረ በልባችሁ ሁሉ በነፍሳችሁም ሁሉ እወቁ፥ ሁሉ ደርሶላችኋል፤ ከእርሱም አንድ ነገር አልቀረም። 15 እግዚአብሔ አምላካችሁ የተናገረው መልካም ነገር ሁሉ እንደ ደረሰላችሁ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እናንተን እስኪያጠፋችሁ ድረስ እግዚአብሔር እንዲሁ ክፉን ነገር ሁሉ ያመጣባችኋል። 16 የእግዚአብሔር አምላካችሁን ቃል ኪዳን ብታፈርሱ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ከሰጣትችሁም ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።
ለብዙ አመታት የኖረ
ይህ የዮርዳኖስ ወንዝ አጭር ስያሜ ነው
ይህ የሚያመለክተው ፀሐይ የምትጠልቅበትን አቅጣጫ ነው
የሙሴን ትዕዛዛት አለመጠበቅ የተገለጸው ከዚህ መንገድ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ዞር ማለት ተብሎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ከእነርሱ ጋር የቀረበ ወዳጅነት መመስረት 2) ከእነርሱ ጋር በጋብቻ መተሳሰር
መናገር
ይህ የሚያመለክተው የሌሎችን ህዝቦች አማልዕክት ነው
"ያህዌን አጥብቆ መያዝ፡፡" በያህዌ ማመን የተገለጸው እርሱን አጥብቆ እንደመያዝ ተደርጎ ነው፡፡ "በያህዌ ማመንን መቀጠል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"እስከ ዛሬ ዘመን ድረስ"
እዚህ ስፍራ "መቆም" የሚለው የሚወክለው በጦርነት ውስጥ ስፍራ/ምድር መያዝን ነው፡፡ "አንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን መላ ህዝብ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት እና አንተ የሚለው ቃል ልዩ ልዩ መልኮች የሚሉትን ይመልከቱ)
አንድ ብቻ
"1,000" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የእነዚህን ህዝቦች እምነቶች መቀበል የተገለጸው እነርሱን ጋር አጥብቆ መያዝ ተደርጎ ነው፡፡ "የእነዚህን ህዝቦች እምነቶች መቀበል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"መሰናክል" እና "ወጥመድ" የሚሉት ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ቃላቱ በአንድነት የሚናገሩት ሌሎች ህዝቦች ለእስራኤል ከፍተኛ ችግር እንደሚሆኑ ነው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)
እነዚህ ሀረጋት የሚናገሩት እነዚህ ህዝቦች በእስራኤል ላይ የሚፈጥሩት ችግር የጅራፍ እና የእሾህ ያህል የሚያሰቃያቸው መሆኑን ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ሞቱን ለመናገር ትሁት አገላለጽ ይጠቀማል፡፡ "መሞቴ ነው/ልሞት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ጸያፍ ወይም አስነዋሪ ቃልን ሻል ባለ ቃል መጠቀም)
እዚህ ስፍራ "ልቦች" እና "ነፍሶች" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ቃላቱ በአንድነት ሆነው ጠለቅ ያለ ግላዊ እውቀትን ያጎላሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ቃላት የያህዌ ቃል ኪዳኖች ሁሉ መፈጸማቸውን ትኩረት ሰጥተው ይገልጻሉ፡፡ ይህ በአዎንታዊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እያንዳንዱ ቃል ተፈጸመ/እውን ሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ድርብ አሉታ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)
ይህ በቀደመው ቁጥር ውስጥ የተጠቀሰውን ቅጣት አስፈሪነት ያመለክታል
እነዚህ ሁለት ሀረጋት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሁለተኛው ህዝቡ እንዴት "ሌሎችን አማልክት እንደሚያመልክ" ይገልጻል፡፡" (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
በዚህ ስፍራ "ይነዳል" የሚለው ቃል፣ ልክ እሳት "እንደሚቀጣጠል" ወይም "በመቀጣጠል" እንደሚጀምር፣ ወይም ደረቅ ሳርን/ጭድን ወይም ጭራሮን ማቃጠል መጀመር ቀላል የሆነውን ያህል የያህዌ ቁጣ ለመጀመሩ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "ያህዌ በእናንተ መቆጣት ይጀምራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
1 ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበስበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎችን፥ አለቆቻቸውን፥ ፈራጆቻቸውንና ሹማምቶቻቸውን ጠራቸው፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። 2 ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ፥ የአብርሃምና የናኮር አባት ታራ፥ አስቀድመው በወንዝ ማዶ ተቀመጡ፤ ሌሎችንም አማልክት አመለኩ። 3 አባታችሁንም አብርሃምን ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ወስጄ በከነዓን ምድር ሁሉ መራሁት፤ ዘሩንም በልጁ በይስሐቅ በኩል እንዲበዛ ሰጠሁት። 4 ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት። ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፥ ነገር ግን ያዕቆብና ልጂቹ ወደ ግብፅ ወረዱ። 5 ሙሴንና አሮንንም ላክሁ፥ ግብፃውያንን በመቅሠፍት መታሁ። ከዚያም በኋላ አወጣኋችሁ። 6 አባቶቻችሁንም ከግብፅ አወጣኋችው፤ ወደ ባሕሩም መጣችሁ። ግብፃውያንም አባቶቻችሁን በሰረገሎችና በፈረሰኞች እስከ ኤርትራ ባሕር ድረስ አሳደዱአቸው። 7 አባቶቻችሁም ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ። ባሕሩንም በእነርሱ ላይ መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም። ዓናኖቻችሁም በግብፃውያን ላይ ያደረግሁትን አይታችኋል። ለረጅም ጊዜም በምድረ በዳ ተቀመጣችሁ። 8 እኔም በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ተቀመጡበት ወደ አሞራውያን ምድር አመጣኋችሁ። ከእናንም ጋር ተዋጉ፥ በእጃችሁ አሳልፌ ሰጠኋችሁ። ምድራቸውንም ወረሳችሁ፤ ከፊታችሁም አጠፋኋቸው። 9-10 የሞዓብም ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ ተንሥቶ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ እንዲረግማችሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን ልኮ አስጠራው።እኔ ግን በለዓምን አልሰማሁትም። እርሱም በዚህ ፈንታ ባረካችሁ፥ እኔም ከእጁ አዳንኋችሁ። 11 ዮርዳኖስንም ተሻግራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ። የኢያሪኮም ሰዎች፥ ከአሞራዊውያን፥ ከፌርዛዊውያን፥ ከከነዓናዊውያን፥ ከኬጢያዊውያን፥ ከጌርጌሳዊውያን፥ ከኤዊያዊውያንና ከኢያቡሳዊውያን፥ ጋር ተዋጉአችሁ። በእነርሱም ላይ ድልን ሰጠኋችሁ፤አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋችሁ። 12 በፊታችሁ ያሉትን ሁለቱን የአሞራውያንን ነገሥታት እንዲያስወጡአቸው በፊታችሁም ተርብን ሰደድሁባቸው። ይህም በእናንተ ሰይፍና ቀሥት አይደለም። 13 ያልደከማችሁበትንም ምድር፥ ያልሠራችኋቸውንም ዛሬ የተቀመጣችሁባቸውን ከተሞች ሰጠኋችሁ። ያልተከላችኋቸውን ወይንና ወይራ በላችሁ። 14 አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት አምልኩት፤ አባቶቻችሁም በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በግብፅም ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፤ እግዚአብሔርንም አምልኩ። 15 እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ እባቶቻችሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤተ ሰቦቼ ግን እግዚአብሔርን እናመካለን። 16 ሕዝቡም መልሰው እንዲህ አሉ፦ እግዚአብሔርን ትተን ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከእኛ ይራቅ፥ 17 እኛንና አባቶቻችንን ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በዓይናችንም ፊት እነዚያን ታላላቅ ተአምራት ያደረገ፥ በሄድንባትም መንገድ ሁሉ ባለፍንባችውም አሕዛብ ሁሉ መካከል የጠበቀን፥ እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ነው። 18 እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ በምድሪቱም የተቀመጡትን አሞራውያን ከፊታችን አስወጣ። ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና፤ እግዚአብሔርን እናመልካለን። 19 ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ እርሱ ቅዱስና፥ ቀናተኛ አምላክ ነውና፥ እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም። 20 እግዚአብሔርን ትታችሁ እንግዶችን አማልክት ብታመልኩ፥ ተመልሶ ክፉ ነገር ያደርግባችኋል፥ መልካም ካደረገላችሁ በኋላ ያጠፋችኋል። 21 ሕዝቡም ኢያሱን፦ እንዲህ አይሁን እግዚአብሔርን እናመልካለን አሉት። 22 ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን፦ እግዚአብሔርን እንድታመኩት እንደመረጣችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ አላቸው። እነርሱም፦ ምስክሮች ነን አሉ። 23 እርሱም፦ አሁን እንግዲህ በመካከላችሁ ያሉትን እንግዶችን አማልክት አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አዘንብሉ አላቸው። 24 ሕዝቡም ኢያሱን፦ አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፥ ድምፁንም እንሰማለን፥ አሉ። 25 በዚያን ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። በሴምም አዋጅንና ሕግን አደረገላቸው። 26 ኢያሱም እነዚህን ቃላት ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ጻፈ። ታላቁንም ድንጋይ ወስዶ በእግዚአብሔር መቅደስ አጠገብ ከነበረችው ከአድባሩ ዛፍ በታች አቆመው። 27 ኢያሱም ለሕዝቡ፦ ተመልከቱ፥ የተናገረነውን ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል። እግዚአብሔር የተናገርነውን ሁሉ ሰምቶአል። እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል አላቸው። 28 ስለዚህም ኢያሱ ሕዝቡን ወደ እያንዳንዱ ርስት እንዲሄዱ አደረገ። 29 ከዚህ ነገር በኋላ የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድሜው መቶ አሥር ዓመት ሞልቶት ሞተ። 30 በተራራማውም በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በራሱ ርስት በተምና ሴራ ቀበሩት። 31 ኢያሱ በነረበት ዘመን ሁሉ፤ከኢያሱም በኋላ በነበሩት ለእስራኤልም ያደረገውን የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ባወቁት በሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን አመለኩ። 32 የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ የወጡት የዮሴፍን አጥንት ያዕቆብ ከሴም አባት ከኤሞር ልጆች በገዛው እርሻ በሴኬም ቀበሩት። እርሱም በአንድ መቶ ብር ገዛው፤እርሻውም ለዮሴፍ ልጆች ርስት ሆነ። 33 የአሮንም ልጅ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራውም በኤፍሬም አገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓ መሬት ቀበሩት።
ኢያሱ ለነገዶቹ ያደረገው ስብሰባ የተገለጸው ሁሉንም በአንድ ቋት ውስጥ እንዳከማቻቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ኢያሱ መላው የእስራኤል ነገድ ከእርሱ ጋር እንዲገኛኝ ጠየቀ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"መጥተው ከፊት ለፊት ቆሙ" ወይም "ከፊት መጡ"
"ከብዙ አመታት በፊት"
ኢያሱ ያህዌ አስቀድሞ የተናገረውን መናገር ጀመረ፡፡ ጥቅሱ እስከ ቁጥር 13 መጭሻ ድረስ ይቀጥላል፡፡
እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ያህዌ እርሱ ከህዝቡ ጋር ስላለው ስምምነት የተናገረውን መጥቀሱን ቀጠለ
የቦት ወይም የስፍራ ስም (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ግብጽ ከከነዓን ምድር በአቀማመጥ ዝቅ ያለ ነው፡፡ "ተጓዙ"
ኢያሱ ያህዌ እርሱ ከህዝቡ ጋር ስላለው ስምምነት የተናገረውን መጥቀሱን ቀጠለ፡፡
ያህዌ በቀጣይነት ስለ ቀደሙትና ስለ አሁኖቹ መላ እስራኤላውያን የሚናገሩትን እነዚህን ሁለት ሀረጎች በመለዋወጥ ይናገራል፡፡ "እናንተ" የሚለው ቃል በዚህ ንግግር ውስጥ ሁሉ ብዙ ቁጥር ሲሆን መላውን የእስራኤል ህዝብ ያመለክታል፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መልኮች/ቅርጾች ይመልከቱ)
ኢያሱ ያህዌ እርሱ ከህዝቡ ጋር ስላለው ስምምነት የተናገረውን መጥቀሱን ቀጠለ፡፡
ያህዌ በቀጣይነት ስለ ቀደሙትና ስለ አሁኖቹ መላ እስራኤላውያን የሚናገሩትን እነዚህን ሁለት ሀረጎች በመለዋወጥ ይናገራል፡፡ "እናንተ" የሚለው ቃል በዚህ ንግግር ውስጥ ሁሉ ብዙ ቁጥር ሲሆን መላውን የእስራኤል ህዝብ ያመለክታል፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መልኮች/ቅርጾች ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው ቀይ ባህርን ነው
ሰው የማይኖርበት አካባቢ፣ በረሃ
ኢያሱ ያህዌ እርሱ ከህዝቡ ጋር ስላለው ስምምነት የተናገረውን መጥቀሱን/መናገሩን ቀጠለ፡፡
"እናንተ" የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን በእዚህ ንግግር ውስጥ ሁሉ መላውን የእስራኤል ህዝብ ይገልጻል፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መልኮች/ቅርጾች ይመልከቱ)
ይህ የዮርዳኖስ ወንዝ አጭር ስያሜ ነው
እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው የሚያመለክተው ሃይልን ነው፡፡ "እንድትማርኳቸው አቅም ሆናችሁ" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ያህዌ እርሱ ከህዝቡ ጋር ስላለው ስምምነት የተናገረውን መጥቀሱን/መናገሩን ቀጠለ፡፡
የወንዶች ስም (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"እናንተ" የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን በእዚህ ንግግር ውስጥ ሁሉ መላውን የእስራኤል ህዝብ ይገልጻል፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መልኮች/ቅርጾች ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው የሚያመለክተው ሃይልን ነው፡፡ "እንድትማርኳቸው አቅም ሆናችሁ" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ኢያሱ ያህዌ እርሱ ከህዝቡ ጋር ስላለው ስምምነት የተናገረውን መጥቀሱን/መናገሩን ቀጠለ፡፡
"እናንተ" የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን በእዚህ ንግግር ውስጥ ሁሉ መላውን የእስራኤል ህዝብ ይገልጻል፡፡ (አንተ የሚለውን ቃል መልኮች/ቅርጾች ይመልከቱ)
ይህ የዮርዳኖስ ወንዝ አጭር ስያሜ ነው
በአንድነት የምትኖርና በፍጥነት የምትበር ተናዳፊ ትንሽ ነፍሳት፡፡ እዚህ ስፍራ ብዙ "ተርቦች" እንደ አንድ ብቻ ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡
ኢያሱ ያህዌ እርሱ ከህዝቡ ጋር ስላለው ስምምነት የሚናገረውን/የሚጠቅሰውን አጠናቀቀ፡፡
ዐይኖች የሚለው የሚወክለው ማየትን፣ ሲሆን ማየት ደግሞ ሃሳብን ወይም መሻትን ይገልጻል፡፡ "የማትፈልጉ ከሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚገልጸው በቤቱ የሚኖሩ ቤተሰቦቹን ነው፡፡ "ቤቴ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪ በመነሳት ለአንድ ነገር ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ህዝቡ ከአባቶቻቸው ጋር እንደነበሩ አድርገው ይናገራሉ፣ ደግሞም "እኛን" እና "እኛ" የሚሉት ቃላት "የእኛ አባቶች" ከሚለው ጋር ለዋውጠው ይጠቀማሉ፡፡ (ተውላጠ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው የባርነታቸውን ስፍራ የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ባሮች በነበርንበት አገር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"እኛ በውስጣቸው ባለፍንባቸው አገሮች"
ይህ የሚያመለክው እስራኤላውያንን ነው፡፡
እግዚአብሔር ህዝቡ እርሱን ብቻ እንዲያመልከው ይፈልጋል
የያህዌ ቁጣ የተገለጸው እነርሱን እንደሚያጠፋ እስት ሆኖ ነው፡፡ "በእሳት እንደሚያጠፋ እርሱ እናንተን ያጠፋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክው እስራኤላውያንን ነው፡፡
ያህዌን ብቻ ለመታዘዝ መወሰን የሚለው የተነገረው ልባቸውን ወደ እርሱ እንደ ማዞር ተደርጎ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚለው የሚገልጸው መላ ማንነትን ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ፣ "ልብ" ብዙ ቁጥር ነው፤ ምክንያቱም መላውን እስራኤል እንደ አንድ ቡድን ይገልጻል፡፡ የሆነ ሆኖ፣ "የእናንተ" የሚለው ብዙ ቁጥር እንደመሆኑ ይህንን በብዙ ቁጥር መተርጎሙ እጅግ የተሻለ ይሆናል፡፡ "ራሳችሁን ወደ ያህዌ መልሱ" ወይም "ያህዌን ለመታዘዝ ወስኑ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር፣ ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና አንተ የሚለው ቃል መልኮች/ቅርጾች የሚሉትን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክው እስራኤላውያንን ነው፡፡
እዚህ ስፍራ "መስማት" የሚለው መታዘዝ ማለት ነው፡፡ "እርሱ እንድናደርገው የነገረንን ነገር ሁሉ እንታዘዛለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሙሴ መጽሐፍት ቀጣይ ሊሆን ይችላል፡፡
"በዚያ አኖረው/አደረገው"
ይህ የሚያመለክው እስራኤላውያንን ነው፡፡
ኢያሱ ያስቀመጠው ድንጋይ የተገለጸው የተባለውን ሁሉ እንደሰማ እና የተነገረውን ለመመስከር እንደሚችል ሰው ተደርጎ ነው፡፡ (ሰውኛ የሚለውን ዘይቤ ይመልከቱ)
"ሆናችሁ ባትገኙ"
"የአንድ መቶ አስር አመት ሽማግሌ" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የቦታ ስሞች (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የኢያሱን መላ ህይወት የሚያመለክት ፈሊጥ ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"ከኢያሱ በኋላ የኖሩ"
የዚህን ዐረፍተ ነገር አጀማመር ስርአት መለወጥ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ "የእስራኤል ህዝብ የዮሴፍን አጽም ከግብጽ አውጥተው በሴኬም ቀበሯቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡
"100 ሰቅል/ገንዘብ" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
የወንድ ስም (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
የቦታ ስም (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
1 ከኢያሱ ሞት በኋላ፣ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው ጠየቁ፡- “ከነዓናውያንን ለመዋጋት ወደላይ ስንሄድ ማን ይመራናል?” 2 እግዚአብሔርም አላቸው፡- “ይሁዳ ይመራችኋል፡፡ ተመልከቱ፣ ምድሪቱን ለእነርሱ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፡፡” 3 የይሁዳም ሰዎች ለወንድሞቻቸው ለስምዖን ሰዎች እንዲህ አሏቸው፡- “ከነዓናውያንን አብረን እንወጋቸው ዘንድ ከእኛ ጋር ለእኛ ወደተሰጠው ክልል ኑ፡፡ እኛም እንዲሁ ለእናንተ ወደተሰጠው ክልል እንመጣለን፡፡” ስለዚህም የስምዖን ነገድ ከእነርሱ ጋር ሄዱ፡፡ 4 የይሁዳ ሰዎችም ወደ ላይ ወጡ፣ እግዚአብሔርም በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ በቤዜቅም ከእነርሱ አስር ሺህ ሰዎችን ገደሉ፡፡ 5 አዶኒ ቤዜቅን በቤዜቅ አገኙት፣ ከእርሱም ጋር ተዋግተው ከነዓናውያንና ፌርዛውያንን አሸነፉ፡፡ 6 አዶኒ ቤዜቅ ግን ሸሸ፣ ተከታትለውም አገኙትና ያዙት፣ የእጁንና የእግሩን አውራጣቶች ቆረጡ፡፡ 7 አዶኒ ቤዜቅም እንዲህ አለ፡- “የእግርና የእጅ አውራ ጣቶቻቸው የተቆረጠባቸው ሰባ ነገስታት ከእኔ ማዕድ ስር መብላቸውን ሰበሰቡ፡፡ እኔ እንዳደረግሁት፣ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አደረገብኝ፡፡” እርሱንም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፣ በዚያም ሞተ፡፡ 8 የይሁዳ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ከተማ ጋር ተዋግተው ተቆጣጠሯት፡፡ በሰይፍ ስለት ወጓት፣ ከተማዋንም አቃጠሏት፡፡ 9 ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሰዎች በኮረብታማው አገር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ለመዋጋት፣ወደ ኔጌብና ወደ ምዕራቡ ኮረብታ ግርጌ ወረዱ፡፡ 10 ይሁዳም በኬብሮን (የኬብሮን ስም ቀድሞ ቂርያት አርባቅ ትባል ነበር) የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ለመውጋት ሄደ፣ ሴሲን፣ አክመንና ቴላሚንም ድል አደረጉ፡፡ 11 ከዚያም የይሁዳ ሰዎች ወደ ዴብር (የዴብር ስም ቀድሞ ቅርያት ሤፍር ተብላ ትጠራ ነበር) ሄዱ፡፡ 12 ካሌብም አለ፣ “ቅርያት ሤፍርን የሚዋጋና የሚቆጣጠራትን ሰው፣ ሴት ልጄን ዓክሳን ሚስት ትሆነው ዘንድ እሰጠዋለሁ፡፡” 13 የካሌብ ታናሽ ወንድም የቄናዝ ልጅ ጎቶንያልም ዴብርን ተቆጣጠረ፣ ስለዚህ ካሌብ ሴት ልጁን ዓክሳን ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው፡፡ 14 ዓክሳም ወዲያውኑ ወደ ጎቶንያል መጣች፣ ለእርሱም አባቷ እርሻ እንዲሰጣት እንዲለምነው ጠየቀችው፡፡ ከአሕያዋም በወረደች ጊዜ፣ ካሌብ እንዲህ ብሎ ጠየቃት፣ “ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ?” 15 እርሷም እንዲህ አለችው፣ “በረከትን ስጠኝ፡፡ በኔጌብ ምድር ያለውን መሬት ሰጥተኸኛልና፣ የውሃ ምንጭንም ስጠኝ፡፡” ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት፡፡ 16 የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮችም ከባለ ዘንባባዋ ከተማ ለቀው ከይሁዳ ሰዎች ጋር በኔጌብ ወዳለችው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ከይሁዳ ሰዎች ጋር በዓራድ አጠገብ ለመኖር ሄዱ፡፡ 17 የይሁዳ ሰዎችም ከወንድሞቻቸው ከስምዖን ሰዎች ጋር ሄዱና በጽፋት ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን ወጓቸው፣ፈጽሞም አጠፏት፡፡ የከተማይቱም ስም ሔርማ ይባል ነበር፡፡ 18 በተጨማሪ የይሁዳ ሰዎች ጋዛንና በዙርያዋ ያለውን አገር፣ አስቀሎናንና በዙርያዋ ያለውን አገር እንደዚሁም አቃሮንንና በዙርያዋ ያለውን አገር ሁሉ ተቆጣጠሩ፡፡ 19 እግዚአብሔርም ከይሁዳ ሰዎች ጋር ነበር፣ የኮረብታማውንም አገር ተቆጣጠሩ፣ ነገር ግን በረባዳው ምድር የሚኖሩትን ሰዎች ማስወጣት አልቻሉም ነበር ምክንያቱም ነዋሪዎቹ የብረት ሰረገሎች ነበሯቸው፡፡ 20 ሙሴም እንደተናገረ ኬብሮንን ለካሌብ ሰጡት፣ እርሱም የዔናቅን ሶስት ልጆች ከዚያ አስወጣቸው፡፡ 21 ነገር ግን የቢንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ኢያቡሳውያንን አላስወጧቸውም፡፡ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከዛሬ ድረስ ከቢንያም ሰዎች ጋር በኢየሩሳሌም ይኖራሉ፡፡ 22 የዮሴፍ ወገንም ቤቴልን ለመውጋት ተዘጋጁ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነበር፡፡ 23 ቀድሞ ሎዛ ተብላ ትጠራ የነበረችውን ቤቴልን ለመሰለል ሰዎችን ላኩ፡፡ 24 ሰላዮቹም ከከተማው አንድ ሰው ሲወጣ አዩ፣ እንዲህም አሉት፣ “ወደ ከተማው እንዴት መግባት እንደምንችል እባክህ አሳየን፣ ለአንተም ቸርነት እናደርግልሃለን፡፡” 25 እርሱም ወደ ከተማው መግቢያውን መንገድ አሳያቸው፡፡ እነርሱም በሰይፍ ስለት ከተማውን ወጉ፣ ያንን ሰውና ቤተሰቦቹንም እንዲያመልጡ አደረጓቻው፡፡ 26 ሰውየውም ወደ ኬጢያውያን ሐገር ሄደና ከተማ ገነባ ስሙንም ሎዛ አለው፣ የዚያ ቦታ ስምም እስከዛሬ ሎዛ ነው፡፡ 27 የምናሴ ሰዎች በቤትሳንና በመንደሮቿ፣ በታዕናክና በመንደሮቿ፣ በዶርና በመንደሮቿ፣ በይብለዓምና በመንደሮቿ፣ በመጊዶና በመንደሮቿ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አላስወጡአቸውም፣ ምክንቱም ከነዓናውያን በዚያ ለመቀመጥ ወስነው ስለነበር ነው፡፡ 28 እስራኤልም በበረታ ጊዜ፣ ከነዓናውያንን የጉልበት ስራ እየሰሩ እንዲያገለግሉአቸው አስገደዷቸው፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አላስወጧቸውም፡፡ 29 ኤፍሬም በጌዝር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያን አላስወጣቸውም፣ ስለዚህ ከነዓናውያን በእነርሱ መካከል በጌዝር መኖር ቀጠሉ፡፡ 30 ዛብሎንም በቂድሮን የሚኖሩትን ሰዎች ወይም በነህሎል ይኖሩ የነበሩትንም ሰዎች አላስወጣቸውም፣ ስለዚህ ከነዓናውያን በእነርሱ መካከል መኖር ቀጠሉ፣ ነገር ግን ዛብሎን ከነዓናውያን የጉልበት ስራ እየሰሩ እንዲያገለግሉአቸው ያስገድዳቸው ነበር፡፡ 31 አሴር በዓኮ፣ በሲዶን፣ በአሕላብ፣ በአክዚብ፣ በሒልባን፣ በአፌቅ፣ በረአብም የሚኖሩትን ሰዎች አላስወጣቸውም፡፡ 32 ስለዚህ የአሴር ነገድ በምድሪቱ በሚኖሩት በከነዓናውያን መካከል ኖሩ፣ ምክንያቱም አላስወጧቸውም ነበር፡፡ 33 የንፍታሌም ነገድ በቤት ሳሚስና በቤት ዓናት ይኖሩ የነበሩትን ሰዎችን አላስወጧቸውም፡፡ ስለዚህ የንፍታሌም ነገድ በምድራቸው ይኖሩ በነበሩ በነዓናውያን ሰዎች መካከል አብረው ኖሩ፡፡ ይሁን እንጂ የቤት ሳሚስና የቤት ዓናት ነዋሪዎች ለንፍታሌም ሰዎች የጉልበት ስራ እንዲሰሩ ይገደዱ ነበር፡፡ 34 አሞራውያንም የዳን ነገድ በኮረብታማው አገር እንዲኖሩ አስገደዷቸው፣ ወደ ሜዳማ ስፍራ ወርደው እንዲኖሩ አልፈቀዱላቸውም ነበር፡፡ 35 ስለዚህ አሞራውያን በሔሬስ ተራራ፣ በኤሎን፣ በሸዓልቢምም ኖሩ፣ ነገር ግን የዮሴፍ ቤት ወታደራዊ ኃይል በእነርሱ ላይ በረቱባቸው፣ ከዚህ የተነሳ ከባድ የጉልበት ስራ እየሰሩ 36 የአሞራውያንም ድንበር በሴላ ካለው ከአቅረቢም ኮረብታ ጀምሮ እስከ ኮረብታማው አገር ድረስ ነው፡፡
መጽሐፈ መሳፍንት የኢያሱን ታሪክ የሚቀጥል ሲሆን በተጨማሪም የአዲሱ ታሪክ ክፍል ጅማሬም ነው።
ይህ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ለሕዝቡ የገለጠው ስሙ ነው። ያህዌን እንዴት መተርጎም እንደሚኖርብህ ለመገንዘብ የትርጉም ቃል ገጽን ተመልከት።
“እኛ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ሳይሆን የእስራኤልን ሕዝብ ነው።
እዚህ ጋ “ይሁዳ” የሚወክለው የይሁዳ ነገድ የሆነውን ሕዝብ ነው። በመጀመሪያ እንዲወጉ እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች ያዛቸዋል። አ.ት፡ “የይሁዳ ሰዎች በመጀመሪያ መውጋት አለባቸው”
“እዩ” ወይም “ስሙ” ወይም “የምነግራችሁን ልብ በሉ”
ይህ ከነዓናውያን ይኖሩበት የነበረውን ምድር ያመለክታል። አ.ት፡ “የከነዓናውያን ምድር”
“እስራኤላውያን ባልንጀሮቻቸውን” ወይም “ዘመዶቻቸውን”
የይሁዳና የስምዖን ነገድ ሰዎች ከተቀሩት እስራኤላውያን ሕዝቦች ጋር በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ሰፍረው ነበር። ለይሁዳ ተሰጥቶት የነበረው ምድር ከሸለቆው በላይ በኩል፣ በኮረብታው ላይ ነበር። አንዳንድ ቋንቋዎች፣ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎቹ ወደ ላይ መውጣታቸውን ወይም መውረዳቸውን አያመለክቱም። አ.ት፡ “ከእኛ ጋር ኑ” ወይም “ከእኛ ጋር ሂዱ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ወደ መደበልን … እግዚአብሔር ወደ መደበላችሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“እኛም ደግሞ ከእናንተ ጋር እንሄዳለን” ወይም “በተመሳሳይ እኛም ከእናንተ ጋር እንሄዳለን”
በውስጠ ታዋቂ የስምዖን ሰዎችም ከይሁዳ ሰዎች ጋር ሆነው መዋጋታቸውን ያመለክታል።
“10,000 ያህሉን ገደሉ” ወይም “ብዙ ሕዝብ ገደሉ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“የከነዓናውያንና የፌርዛውያን ወታደሮች” ወይም “ጠላቶች”
በከነዓን ተራራዎች ላይ ያለ አካባቢ። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሰው የከነዓናውያንና የፌርዛውያን ሰራዊት አለቃ ነበር። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እርሱን” የሚያመለክተው በመሠረቱ አዶኒቤዜቅንና ሰራዊቱን ነው። አ.ት፡ “እርሱንና ሰራዊቱን ተዋጓቸው”
“አባረሩት”
“70 ነገሥታት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የእኔ ሰዎች የእጆቻቸውንና የእግሮቻቸውን አውራ ጣቶች እንዲቆርጡ ያዘዝኳቸው” ወይም “የእጅና የእግሮቻቸውን አውራ ጣት የቆረጥናቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ነገሥታት ፍርፋሪ እንዲለቅሙ መገደዳቸው አዶኒቤዜቅ እነዚህን ነገሥታት ምን ያህል እንዳዋረዳቸው ያሳያል። እዚህ ጋ ምግብ “መልቀም” ማለት እንደሚመገቡት ያመለክታል። አ.ት፡ “ከጠረጴዛዬ ስር ፍርፋሪ ይበሉ ነበር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ከተማ” የሚወክለው ሕዝብን ነው። አ.ት፡ “በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች እና … አሸነፏቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እርሷ” የሚያመለክተው ከተማን፣ ይኸውም የሚኖሩባትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “የከተማይቱን ሰዎች ወጓቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በሰይፋቸው ጫፍ”። እዚህ ጋ “ሰይፍ” የሚወክለው ወታደሮች በጦርነት ውስጥ የሚጠቀሙበትን ሰይፍና ሌሎች የጦር መሣሪያዎች ነው። አ.ት፡ “በሰይፎቻቸው” ወይም “በጦር መሣሪያዎቻቸው”
ከኢየሩሳሌም በሚጓዙበት ጊዜ “ወረዱ” የሚለውን ቃል መጠቀም የተለመደ ነበር። አ.ት፡ “የይሁዳ ሰዎች ለመዋጋት ሄዱ”
“በደቡባዊው የይሁዳ ምድረ በዳ”
ከተራራ በታች ያሉ ኮረብታዎች ወይም የተራራ ወገብ
ይህ ዳራዊ መረጃ ነው። ይህንን መጽሐፍ በመጀመሪያ ያነበቡ አንዳንድ ሰዎች ምናልባት ቂርያት አርባቅ የሚለውን ሰምተው ይሆናል፣ ነገር ግን እርሱኑ የኬብሮን ከተማ ብለው እንደሚጠሩት አያውቁም ነበር። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በኬብሮን የሚኖሩ የሦስቱ ከነዓናውያን አለቆች ስም ነው። እያንዳንዱ አለቃ ሰራዊቱን ይወክላል። አ.ት፡ “ሴሲን፣ አኪመን፣ ተላሚና ሰራዊታቸው” (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ደራሲው ምናልባት ይህንን የጻፈው አንባቢዎቹ ከተማይቱን በዳቤር ስም ስለሚያውቋት ይሆናል። እስራኤላውያን በወጓት ጊዜ ግን ቅርያት ሤፍር በመባል ትታወቅ ነበር። አ.ት፡ “ቂርያትሤፍር ተብላ የምትጠራውን” (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
“ባለፈው ዘመን” ወይም “በድሮ ጊዜ”
እዚህ ጋ “ቂርያት ሤፍር” የሚወክለው ሕዝቡን ነው። አ.ት፡ “የቂርያት ሤፍርን ሕዝብ የሚወጋና የሚያሸንፍ ከተማቸውንም የሚወስድ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የካሌብ ሴት ልጅ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ዓክሳ ለጎቶንያል አጥብቃ ነገረችው”
ይህ የሚያሳየው በቁጥር 14 ላይ በጠየቀችው ጊዜ እርሻውን እንደሰጣት ነው። በቁጥር 15 ደግሞ ከእርሻው በተጨማሪ የምንጩን ውሃ ትጠይቀዋለች።
“ውለታ ዋልልኝ” ወይም “ይህንን አድርግልኝ”
ካሌብ ዓክሳን ለጎቶንያል ስለዳረለት ጎቶንያል በማረካት በኔጌብ ከተማ ከእርሱ ጋር ኖረች። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉሙ መብራራት መቻል አለበት። አ.ት፡ “በኔጌብ እንድኖር እስከዳርከኝ ድረስ”
“የሙሴ የሚስቱ አባት”
“ከቄናውያን ሰዎች አንዱ የሆነው አማቱ ወጣ”
“የዘንባባዎቹን ከተማ ትቶ … ወደ ምድረበዳ ወጣ”
ይህ የኢያሪኮ ሌላኛው ስም ነው።
ይህ በከነዓን የሚገኝ የአንድ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ወንድሞች” ማለት በሌላው የእስራኤል ነገድ ውስጥ የሚኖሩ ዘመዶች ማለት ነው።
ይህ በከነዓን የሚገኝ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እስራኤላውያን ጻፋትን ከደመሰሷት በኋላ ስሟን ሔርማ ብለው ቀየሩት። “ሔርማ” ማለት “ፈጽሞ መጥፋት” ማለት ነው። (እና ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ላይ “ከ. . . ጋር” ማለት እግዚአሔር የይሁዳን ሕዝብ ረድቶታል ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ዛፍ የሌለበት፣ በጣም ሰፊ ለጥ ያለ መሬት
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሙሴ ኬብሮንን ለካሌብ ሰጥቶት ነበር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የሕዝብ ወገን መሪዎች የሆኑት መላውን ማኅበር ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “የዔናቅ ሦስቱ ወንዶች ልጆቹና ሰዎቻቸው”
ይህ የአንድ ሰው ስም ነው። ዔናቅና ተወላጆቹ በረጅም ቁመታቸው የታወቁ ነበሩ። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“እስካሁን ድረስ”። ይህ የሚያመለክተው መጽሐፈ መሳፍንት የተጻፈበትን ጊዜ ነው።
እዚህ ጋ “ቤት” የሚወክለው ተወላጆችን ነው። ምናሴና ኤፍሬም የዮሴፍ ልጆች ሲሆኑ የ “ዮሴፍ ቤት” የምናሴንና የኤፍሬምን ተወላጆች ሊያመለክት ይችላል። አ.ት፡ “የምናሴና የኤፍሬም ተወላጆች” ወይም “የምናሴና የኤፍሬም ነገድ ሰዎች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ቤቴል” የሚያመለክተው በቤቴል የሚኖሩትን ሰዎች ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በምስጢር መረጃ ለማግኘት
ይህ የዳራው መረጃ ነው። በመጀመሪያ ይህንን መጽሐፍ ያነበቡት ሰዎች ምናልባት ቤቴል ብለው የሚጠሯት ከተማ ሎዛ እንደነበረች አያውቁም ይሆናል። (ዳራዊ መረጃ እና ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
በምስጢር መረጃ የሚያገኙ ሰዎች
እዚህ ጋ “ከተማ” የሚወክለው ሕዝቡን ነው። አ.ት፡ “የከተማይቱን ሰዎች ወጉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በሰይፍ ጫፍ”። “ሰይፍ” እዚህ ጋ የሚወክለው ሰዎች በጦርነት ጊዜ የሚጠቀሙባቸውን ሰይፍና ሌሎች የጦር መሣሪያዎችን ነው። አ.ት፡ “በሰይፎቻቸው” ወይም “በጦር መሣሪያዎቻቸው”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አምልጥ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
በቤቴል አቅራቢያ፣ በኬጢያውያን ምድር የምትገኘው፣ እንደ አዲስ የተቆረቆረችውና ሰውየው የተዋት ይህች ከተማ በሎዛ ስም ትጠራ ነበር።
“እስካሁን ስሟ ነው”። እዚህ ጋ “እስከ ዛሬ ድረስ” የሚያመለክተው መጽሐፈ መሳፍንት የተጻፈበትን ጊዜ ነው።
እነዚህ የከተሞች ስም ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“መወሰን” በአንድ ነገር ቁርጠኛ አቋም መያዝ ነው። አ.ት፡ “ከነዓናውያን ያችን ምድር ላለመተው ቁርጠኛ አቋም ይዘው ስለነበር”
እዚህ ጋ “እስራኤል” የሚወክለው ሕዝቡን ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ በበረታ ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ከነዓናውያን ከባድ ሥራ እንዲሠሩላቸው አስገደዷቸው”
እዚህ ጋ “ኤፍሬም” ማለት የኤፍሬም ነገድ ሰዎች ወይም ወታደር ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በኤፍሬም አካባቢ ከሚገኙ ከተሞች የአንዱ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዛብሎን” የሚወክለው የዛብሎንን ነገድ ሰዎች ወይም ወታደሮችን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በከነዓን ምድር የሚገኙ ከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዛብሎን” የሚወክለው የዛብሎንን ነገድ ሰዎች ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አስቸጋሪ ሥራ”
እዚህ ጋ “አሴር” የሚወክለው የአሴርን ነገድ ሰዎች ወይም ወታደሮች ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ በከነዓን ምድር የሚገኙ ከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የንፍታሌም ሰዎች የቤት ሳሚስንና የቤት ዓናትን ሰዎች እንደ ባሪያ እንዲሠሩላቸው አስገደዷቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ከመውረድ አስቆሟቸው”
ዛፍ የሌለበት በጣም ለጥ ያለ ሰፊ መሬት
ይህ የኤሎን ከተማ የተሠራበት ረጅም ኮረብታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“የዮሴፍ ተወላጅ የሆነው ነገድ ሕዝብ ብርቱ ሠራዊት ስለነበራቸው ድል ሊያደርጓቸው ችለዋል”
እዚህ ጋ “ቤት” የሚወክለው ተወላጆችን ነው። ምናሴና ኤፍሬም የዮሴፍ ልጆች ሲሆኑ የ“ዮሴፍ ቤት” የምናሴንና የኤፍሬምን ተወላጆች ሊያመለክት ይችላል። አ.ት፡ “የምናሴና የኤፍሬም ተወላጆች” ወይም “የምናሴና የኤፍሬም ነገድ ሰዎች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከሙት ባህር በደቡብ ምዕራብ በኩል የሚገኝ መተላለፊያ ነበር። “የጊንጥ መተላለፊያ” በመባልም ይጠራል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
1 የእግዚአብሔር መልዓክም ከጌልጌላ ወደ ቦኪም ወጣ፣ እንዲህም አለ፣ “ከግብጽ አወጣኋችሁ፣ ለአባቶቻችሁ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፡፡ እንዲህም አልሁ፣ ‘ከእናንተ ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን አላፈርስም፡፡ 2 በዚህ ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ፡፡ መሰዊያቸውን ማፍረስ አለባችሁ፡፡’ እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም፡፡ ይህ ያደረጋችሁት ምንድን ነው? 3 አሁንም እላለሁ፣ ‘ከነዓናውያንን ከእናንተ ፊት አላወጣም፣ ነገር ግን እነርሱ የጎን እሾህ ይሆኑባችኋል፣ ጣዖቶቻቸውም ለእናንተ ወጥመድ ይሆናሉ፡፡’” 4 የእግዚአብሔር መልዓክም እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ጮሁ አለቀሱም፡፡ 5 ያንንም ቦታ ቦኪም ብለው ጠሩት፡፡ በዚያም ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረቡ፡፡ 6 ኢያሱም ሰዎችን ወደ መንገዳቸው በላካቸው ጊዜ፣ የእስራኤል ሕዝብ ምድሩን ለመውሰድና የራሳቸው ለማድረግ ለእንዳንዳቸው ወደተመደበላቸው ቦታ ሄዱ፡፡ 7 ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራንና ለእስራኤል ምን እንዳደረገም ያዩ ከእርሱ በኋላም በኖሩ ሽማግሌዎች ዘመን ሁሉ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አገለገለ፡፡ 8 የእግዚአብሔር አገልጋይ፣ የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ በመቶ አስር ዓመቱ ሞተ፡፡ 9 እነርሱም በኤፍሬም ኮረብታማው አገር በሰሜናዊው ገአስ ተራራ በምድሪቱ ድንበር በተዘጋጀለት ቦታ በተምናሔሬስ ቀበሩት፡፡ 10 ያ ሁሉ ትውልድም ወደ አባቶቻቸው ተሰበሰቡ፡፡ ከእነርሱም በኃላ እግዚአብሔርንና እርሱ ለእስራኤል ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሳ፡፡ 11 የእስራኤል ሕዝብም በእግዚአብሔር ዓይን ክፉ የሆነውን ነገር አደረጉ፣ የበኣል አማልክትንም አመለኩ፡፡ 12 ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፡፡ ሌሎች አማልክትን፣ በዙርያቸው የነበሩ ሕዝቦች አማልክትን ተከተሉ፣ ለእነርሱም ሰገዱ፡፡ እግዚአብሔርንም አስቆጡት ምከንያቱም 13 እግዚአብሔርን ትተዋልና፣ በኣልንና አስታሮትንም አምልከዋልና፡፡ 14 የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ ንብረታቸውን ለሰረቋቸው ወራሪዎች አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ራሳቸውን ከጠላታቸው መከላከል እንዳይችሉ፣ በዙርያቸው በጠላቶቻቸው ብርታት ተይዘው እንደ ነበሩት ባርያዎች አሳልፎ ሸጣቸው፡፡ 15 እስራኤል ለውጊያ በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ፣ ለእነርሱ እንደማለላቸው ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ይከፋ ነበር፡፡ ከዚህ የተነሳ እነርሱም በጣም ተጨነቁ፡፡ 16 ያን ጊዜ ንብረታቸውን ከሚሰርቋቸው ሰዎች ኃይል ያድናቸው ዘንድ እግዚአብሔር መሳፍንትን አስነሳላቸው፡፡ 17 ይሁን እንጂ እነርሱ መሳፍንቶቻቸውን ሊሰሟቸው አልቻሉም፡፡ ለእግዚአብሔር አልታመኑም፣ ራሳቸውንም እንደ አመንዝራዎች ለሌሎች አማልክት ሰጡ፣ አመለኳቸውም፡፡ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይከተሉ ከነበሩት ከአባቶቻቸው መንገድ ወዲያውኑ ዘወር አሉ፣ እነርሱ ራሳቸው እንደ አባቶቻቸው አላደረጉም፡፡ 18 እግዚአብሔር ለእነርሱ መሳፍንትን ባስነሳላቸው ጊዜ፣ መሳፍንቱ በኖሩበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር መሳፍንቱን ረዳቸው፣ ከጠላቶቻቸውም ጉልበት ሁሉ አዳናቸው፡፡ በጨቆኗቸውና መከራ ባሳዩአቸው ሰዎች ምክንያት ወደ እርሱ በጮኹ ጊዜ እግዚአብሔር ለእነርሱ አዘነላቸው፡፡ 19 ነገር ግን መስፍኑ በሞተ ጊዜ፣ ተመልሰው አባቶቻው ያደርጉ ከነበረውም እጅግ የከፋ ነገር አደረጉ፡፡ ሌሎች አማልክትን በመከተል እነርሱን ያገለግሉና ያመልኩ ነበር፡፡ ክፉ ድርጊታቸውንና እልኸኛ መንገዳቸውንም ለመተው ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ 20 የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ እንዲህም አለ፣ “ይህ ሕዝብ ለአባቶቻቸው የገባሁትን ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱ፣ ድምጼንም ስላልሰሙ 21 ከአሁን በኋላ ኢያሱ ሲሞት ሳያወጣቸው የተዋቸውን አሕዛብ ከፊታቸው አላወጣቸውም፡፡ 22 ይህን የማደርገው እስራኤል አባቶቻቸው እንዳደረጉት የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁና በዚያም ይሄዱ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እፈትናቸው ዘንድ ነው፡፡” 23 እግዚአብሔርም እነዚያን አሕዛብ የተዋቸው፣ በፍጥነትም ያላስወጣቸው፣ ኢያሱም እንዲያሸንፋቸው ያልፈቀደለት ለዚህ ነው፡፡
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “እግዚአብሔርን የሚወክል መልአክ” ወይም 2) “እግዚአብሔርን የሚያገለግል መልዕከተኛ” ወይም 3) መልአክ መስሎ ከሰው ጋር የተነጋገረውን እግዚአብሔርን ራሱን ያመለክት ይሆናል የሚሉት ናቸው።
“ጌልገላን ትቶ ወደ ቦኪም ሄደ”
መልአኩ ሕዝቡን ከገሰጻቸው በኋላ እስራኤላውያን ለዚህ ስፍራ በ2፡5 ላይ የሰጡት ስም ይህ ነው። “ቦኪም” ማለት “ማልቀስ” ማለት ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የእግዚአብሔር መልአክ ለእስራኤል ሕዝብ መናገሩ ግልጽ ነው።
“ከግብፅ መራችሁ”
“ቅድም አያቶቻችሁ” ወይም “የቀድሞ አባቶቻችሁ”
ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “አደርግላችኋለሁ ያልሁትን እንዳላደርግ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ድምፅ” እዚህ ጋ የሚወክለው እግዚአብሔር የተናገረውን ነው። አ.ት፡ “ትዕዛዞቼን አልጠበቃችሁም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዳልታዘዙና በዚህም ምክንያት መከራ እንደሚደርስባቸው እንዲገነዘቡ ነው። አ.ት፡ “የከፋ ነገር አድርጋችኋል” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ይህ ቀጥታ የሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “…ወጥመድ እንደማልሆንባችሁ አሁን እነግራችኋለሁ”
ከነዓናውያን እስራኤላውያንን ማስቸገራቸው ለእስራኤላውያን የጎን ውጋት እንደሚሆኑባቸው ተነግሯል። አ.ት፡ “መከራ ያመጡባችኋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እስከ 7 ሴንቲ ሜትር የሚረዝምና ከአንዳንድ እጽዋት ጋር አብሮ የሚበቅል ትናንሽ የሚወጉ ነገሮች ያሉበት እንጨት
እስራኤላውያኑ የከነዓናውያንን አማልክት ማምለካቸው ልክ አደን የሚያድን ሰው ያጠመደው ወጥመድ እንስሳውን ይዞ ለሞት እንደሚዳርገው ሁሉ ሐሰተኞቹ አማልክት አጥፊዎቻቸው እንደሚሆኑ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በብዙ ዕንባ አለቀሱ”
እዚህ ጋ “አሁን” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ዋነኛው ታሪክ የተገታበትን ለመለየት ነው። እዚህ ላይ ከኢያሱ በኋላ የነበረው ትውልድ እንዴት ኃጢአትን እንደ ሠሩና ሐሰተኞች አማልክትን እንዳመለኩ፣ እግዚአብሔር እንደቀጣቸው ሆኖም እንዲታደጓቸው መሳፍንትን እንደላከላቸው ተራኪው ጠቅለል ያለ ማብራሪያ መስጠት ይጀምራል። ይህ ማጠቃለያ የሚያበቃው በ2፡23 ላይ ነው።
በ1፡1-2፡5 ላይ ያለው ሁነት የተፈጸመው ከኢያሱ ሞት በኋላ ነው። ይህ በኢያሱ መጽሐፍ መጨረሻ የተፈጸሙት ሁነቶች በድጋሚ የታሰቡበት ነው።
ይህ አገላለጽ በይበልጥ ግልጽ መሆን ይችላል። አ.ት፡ “ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ስፍራ”
ይህ ማለት አንድ ሰው የኖረበት ጊዜ ማለት ነው። አ.ት፡ “ዕድሜውን ሙሉ”
ይህ ማለት የሙሴን ሕግ ከማስጠበቅ አንጻር በማኅበራዊ ፍትሕና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ እስራኤላውያንን ሲረዱ የነበሩ ሰዎች ናቸው።
ይህ ማለት ከሌላው የበለጠ ዓመት መኖር ነው። አ.ት፡ “እርሱ ከኖረው የበለጠ ኖረዋል”
ይህ የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“አንድ መቶ አሥር ዓመት ዕድሜው ላይ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ወደ ሰጠው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በምድሪቱ ላይ የአንድ አካባቢ ስም ነው።
ይህ የአንድ ተራራ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ደግሞም ወደ አባቶቻቸው ተሰብስበው ነበር” የሚለው ሐረግ የዚያ ትውልድ ሰዎች ሲሞቱ ከእነርሱ በፊት የሞቱት አባቶቻቸው ወዳሉበት ወደዚያው ስፍራ ነፍሶቻቸው ሄዷል ማለት ነው። መሞታቸውን በትህትና የመግለጽ መንገድ ነው።
ይህ ማለት የአንድ ሰው ወይም የአንድ ሕዝብ ወገን የሆኑ አያቶች ማለት ነው።
“ዕድሜው ገፋ” ወይም “ሸመገለ”
እዚህ ጋ “የማያውቅ” ማለት የቀደመው ትውልድ ያውቅ እንደ ነበረ እግዚአብሔር ወይም የእርሱ ኃይል በሕይወታቸው የሚሠራውን ያልተለማመዱ ማለት ነው።
የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው ፍርዱን ወይም ምዘናውን ነው። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ፍርድ ክፉ የሆነውን” ወይም “እግዚአብሔር ክፉ ነው ያለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የበኣል ብዙ ቁጥር ነው። “በኣል” የአንድ ሐሰተኛ አምላክ ስም ሆኖ ሳለ ቃሉ አብዛኛውን ጊዜ ከበኣል ጋር ለሚመለኩ ለሌሎች የተለያየዩ አማልክትም ጥቅም ላይ ውሏል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ከእንግዲህ እግዚአብሔርን የማይታዘዙ እስራኤላውያን፣ በአካል ከእርሱ እንደተነጠሉና እንደተዉት ተቆጥሮ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አያቶቻቸው” ወይም “የቀደሙት አባቶቻቸው”
የእስራኤላውያኑ ሐሰተኞች አማልክትን ማምለክ መጀመር እስራኤላውያን ሐሰተኞች አማልክትን ተከትለው እንደሄዱ ተቆጥሮ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአምልኮትና ለአንድ ሰው አክብሮትን የመስጠት ተግባር ነው።
“እግዚአብሔር እንዲቆጣ አስደረጉት”
ይህ የአስታሮት ብዙ ቁጥር ሲሆን በተለያዩ ቅርጾች የምትመለክ እንስት አምላክ ናት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እሳት እንደሚቃጠል ተገልጿል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ በጣም ተቆጣ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ወራሪዎች ሀብታቸውን እንዲቀሟቸው ተዋቸው”
ጠላቶች እስራኤላውያኑን እንደ ባሪያ አድርገው እንዲወስዷቸው እግዚአብሔር መፍቀዱ ለባርነት ሸጣቸው ተብሎ ተነግሯል። “ለተገዙላቸው” የሚለው ቃል በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እርሱ፣ ጠላቶቻቸው ድል እንዲያደርጓቸውና ባሪያ አድርገው እንዲወስዷቸው፣ ከእንግዲህም ብርቱዎቹን ጠላቶቻቸውን መቋቋም እንዳይችሉ ፈቀደ”። (ዘይቤአዊ አነጋገር፣ አድራጊና ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው የእግዚአብሔርን እጅ ነው። አ.ት፡ “ያሸንፏቸው ዘንድ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ረዳቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እጅግ ተሠቃይተው ነበር”
እግዚአብሔር እንዲፈርዱ ሰዎችን መሾሙ ሰዎችን እንዳነሣቸው ወይም ብድግ እንዳደረጋቸው ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው ኃይልን ነው። አ.ት፡ “ከጠላቶቻቸው ኃይል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“መሳፍንታቸውን አልታዘዙም”
የሕዝቡ እግዚአብሔርን ከድቶ ሌሎች አማልክትን ማምለክ እንደ ሴተኛ አዳሪ እንዲቆጠሩ ማስደረጉ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሐሰተኛ አማልክትን በማምለክ ከዱት”
ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዳመለኩ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው ያለማድረጋቸው፣ ከአባቶቻቸው መንገድ ተመልሰው በሌላ አቅጣጫ እንደሄዱ እንዲነገርላቸው ሆኗል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ቅድመ አያቶቻቸው” ወይም “የቀድሞ አባቶቻቸው”
እግዚአብሔር እንዲፈርዱ ሰዎችን መሾሙ ሰዎችን እንዳነሣቸው ወይም ብድግ እንዳደረጋቸው ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እነርሱ” የሚለው ቃል እስራኤላውያንን ያመለክታል።
እዚህ ጋ “እጅ” እስራኤልን የሚጎዱበትን የጠላትን ኃይል ያመለክታል። አ.ት፡ “የጠላቶቻቸውን ኃይል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“መስፍኑ በሕይወት እስከ ኖረ ድረስ”
ለአንድ ሰው ወይም ለአንድ ነገር የርኅራኄ መኖር
አንድ ሰው ከመከራው የተነሣ የሚጮኸው ጩኸት፣ እስራኤላውያኑ በመከራቸው ጊዜ ስቃያቸውን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “በተሠቃዩ ጊዜ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ከቶ ያለመታዘዛቸው በአካል ከእግዚአብሔር እንደ ተለዩ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ቅድመ አያቶቻቸው” ወይም “የቀድሞ አባቶቻቸው”
የእስራኤላውያን ሌሎች አማልክትን ማምለክ ከሌሎች አማልክት ኋላ እየተራመዱ እንደሄዱ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሌሎች አማልክትን አገለገሉ፣ ሰገዱላቸውም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ክፉ ነገር ማድረጋቸውንና እልኸኛ መሆናቸውን ለማቆም እምቢ አሉ”። ይህ በአዎንታዊ አገላለጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ክፉ ነገር ማድረጋቸውንና እልኸኝነታቸውን ቀጠሉ”
የእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እሳት እንደ ነደደ ተገልጿል። ይህንን በመሳፍንት 2፡14 ላይ እንዴት እንደ ተረጎምከው ተመልከት።
እዚህ ጋ “ሕዝብ” የሚወክለው ሰዎቹን ነው። አ.ት፡ “እነዚህ ሰዎች ተላልፈዋል” ወይም “እስራኤላውያኑ ተላልፈዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ፣ ይህ የሚያመለክተው የአንድ ሰው ወይም የአንድ ሕዝብ ወገን የሆኑ አያቶችን ነው።
እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚወክለው እግዚአብሔር የተናገረውን ነው። አ.ት፡ “እኔ ያዘዝኳቸውን አልታዘዙም” ወይም “አልታዘዙኝም”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ሕዝቦች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከእስራኤል በፊት በከነዓን ይኖሩ የነበሩትን የሕዝብ ወገን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሰዎች እንዲኖሩት ወይም እንዲያደርጉት እግዚአብሔር የሚፈልገው ሕይወት እንደ መንገድ ወይም ጎዳና ተደርጎ ተነግሯል። እግዚአብሔርን የሚታዘዝ ሰው በመንገዱ ላይ እየሄደ እንዳለ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁለት ሐረጎች የሚሉት አንድ ነገር ስለሆነ መጣመር ይችላሉ። አ.ት፡ “ኢያሱ ፈጥኖ እንዲያሸንፋቸውና እንዲያስወጣቸው አላደረገም”
እዚህ ጋ “እጅ” ኃይልን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን “ኢያሱ” ራሱንና ሰራዊቱን ይወክላል። አ.ት፡ “በኢያሱና በሰራዊቱ ኃይል ሥር” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የሚለውን ተመልከት)
1 እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ሳያስወጣ ያስቀራቸው እስራኤልን ይልቁንም ደግሞ በከነዓን በተደረጉት ጦርነቶች ያልተዋጉትን በእስራኤል የሚገኙትን እያንዳንዱ ሰው ይፈትን ዘንድ ነው፡፡ 2 (ይህንን ያደረገው ውጊያ የማያውቁትን አዲሱ የእስራኤል ትውልድ ውጊያን ለማስተማር ነው) ፡- 3 አምስቱ የፍልስጤማውያን ነገስታት፣ ከነዓናውያንም ሁሉ፣ ሲዶናውያን እና ከበዓልኤርሞንየም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች ይኖሩ የነበሩትም ኤውያውያን ነበሩ፡፡ 4 እነዚህ ሕዝቦች ሳይወጡ እንዲቀሩ የተደረጉት እግዚአብሔር እስራኤልን መፈተኛ እንዲሆኑ ነው፣ እነርሱ ለአባቶቻቸው በሙሴ በኩል የሰጣቸውን ሕግ ይታዘዙና አይታዘዙ እንደሆነ ለማረጋገጥ ነው፡፡ 5 ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፌርዛውያን ከኤውያውያንና ከኢያቡሳውያን ጋር አብረው ኖሩ፡፡ 6 ሴት ልጆቻቸውንም ሚስት እንዲሆኗቸው ወሰዷቸው፣ የራሳቸውን ሴት ልጆችም ለወንድ ልጆቻቸው ሰጧቸው፣ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ፡፡ 7 የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ዓይን ጸያፍ የነበረውን ነገር ፈጸሙ፣ አምላካቸው እግዚአብሔርንም ረሱ፡፡ የኣልንና የአስታሮትን አማልክት አመለኩ፡፡ 8 ስለዚህም የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ ለመስጶጣምያ ንጉስ ለኩሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ የእስራኤል ሕዝብም ኩሰርሰቴን ለስምንት አመታት አገለገሉ፡፡ 9 የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር በጮሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ለመርዳት የሚመጣና ካሉበት ሁኔታም የሚያድናቸው ሰው አስነሳ፡- ይህም ሰው የካሌብ ታናሽ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ነበር፡፡ 10 የእግዚአብሔር መንፈስም አበረታው፣ እስራኤላውያን ላይም ይፈርድ ነበር፣ ወደ ውጊያም ይወጣ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በመስጶጣምያ ንጉስ በኩሰርሰቴ ላይ ድልን ሰጠው፡፡ ኩሰርሰቴንም ያሸነፈው የጎቶንያል እጅ ነበር፡፡ 11 ምድሪም ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች፡፡ የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያልም ሞተ፡፡ 12 የእስራኤልም ሕዝብ ክፉ ነገሮችን በማድረግ ደግመው እግዚአብሔርን ሳይታዘዙ ቀሩ፣ እርሱም ምን እንዳደረጉ ተመለከተ፡፡ ስለዚህ እስራኤል ክፉ ነገሮችን ስላደረጉና፣ እግዚአብሔርም ስላያቸው የሞኣብ ንጉስ ኤግሎም እስራኤልን ለመውጋት በመጣ ጊዜ እግዚአብሔር ብርታትን ሰጠው፡፡ 13 ኤግሎምም ከአሞንና ከአማሌቃውያን ጋር ተባበረ፣ እነርሱም ሄዱ እስራኤልንም አሸነፉ፣ ከዚያም የዘንባባ ከተማን ተቆጣጠሩ፡፡ 14 የእስራኤልም ሕዝብ የሞኣብን ንጉስ ኤግሎምን ለአስራ ስምንት አመታት አገለገሉ፡፡ 15 ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር በጮሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የሚረዳቸውን ሰው አስነሳ፣ ይህም ግራኝ የነበረው ብንያማዊው የጌራን ልጅ ናኦድ ነው፡፡ የእስራኤልም ሕዝብ እርሱን ወደ ሞኣብ ንጉስ ወደ ኤግሎም የሚከፍሉትን ግብር አስይዘው ላኩት፡፡ 16 ናኦድ በሁለት በኩል የተሳለ ርዝመቱ አንድ ክንድ የሆነ ሰይፍን ሰራ፤ ከልብሱም በታች በቀኝ ጭኑ አሰረው፡፡ 17 ግብሩንም ለሞኣብ ንጉስ ለኤግሎም ሰጠው፡፡ (ኤግሎም በዚያን ጊዜ እጅግ ወፍራም ሰው ነበር፡፡) 18 ናኦድም የግብሩን ክፍያ ካቀረበ በኋላ፣ ግብሩን ተሸክመው ገብተው ከነበሩ ሰዎች ጋር ወጣ፡፡ 19 ይሁን እንጂ ናኦድ በጌልጌላ አጠገብ የተቀረጹ ምስሎች ተሰርተውበት ወደነበረው ስፍራ ሲደርስ ተመልሶ ሄደና እንዲህ አለ፡- “ንጉስ ሆይ፣ ለአንተ የሚስጥር መልዕክት አለኝ፡፡” ኤግሎምም እንዲህ አለ፡- “ጸጥታ!” ስለዚህም አገልጋዮቹ ሁሉ ክፍሉን ትተው ወጡ፡፡ 20 ናኦድም ወደ እርሱ መጣ፡፡ ንጉሱም ቀዝቃዛ በሆነው ሰገነት ላይ ብቻውን ተቀምጦ ነበር፡፡ናኦድም እንዲህ አለ፣ “ለአንተ ከእግዚአብሔር የመጣ መልዕክት አለኝ፡፡” ንጉሱም ከመቀመጫው ተነሳ፡፡ 21 ናኦድም ግራ እጁን ዘረጋና ሰይፉን ከቀኝ ጭኑ አወጣ፣ ሰይፉንም በንጉሱ ሰውነት ውስጥ ሰካው፡፡ 22 የሰይፉም እጀታ ከስለቱ ጋር ወደ ሰውነቱ ገባ፣ ጫፉም በጀርባው ወጣ፣ ሞራም ስለቱን ሸፈነው፣ ናኦድም ሰይፉን ከንጉሱ ሰውነት አላወጣውም፡፡ 23 ከዚያም ናዖድ ወደ በረንዳው ወጣና የሰገነቱን በር በንጉሱ ላይ ዘግቶ ቈለፈው፡፡ 24 ናዖድም ከሄደ በኋላ፣ የንጉሱ ባሪያዎች መጡ፤ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ አዩ፣ ስለዚህ እንዲህ ሲሉ አሰቡ፣ “ምናልባት በቀዝቃዛው ሰገነት ውስጥ እየተጸዳዳ ይሆናል፡፡” 25 ንጉሱ የሰገነቱን በር ሳይከፍት በቆየም ጊዜ ስራቸውን ችላ እንዳሉ እስኪሰማቸው ድረስ ስጋት እያደረባቸው ጠበቁ፡፡ ስለዚህ ቁልፉን ወሰዱና በሮቹን ከፈቱ፣ እነሆም ጌታቸው ተጋድሞ፣ በወለሉም ላይ ወድቆ፣ ሞቶም አገኙት፡፡ 26 ባርያዎቹ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እያሰቡ ሲጠባበቁ፣ ናዖድ አመለጠ፣ የጣኦታት ምስል በተቀረጸበት ስፍራ በኩል አለፈ፣ ወደ ቤይሮታም አመለጠ፡፡ 27 በደረሰም ጊዜ፣ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ቀንደ መለከት ነፋ፡፡ ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ ከእርሱ ጋር ከኮረብታማው አገር ወረዱ፣ እርሱም ይመራቸው ነበር፡፡ 28 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ተከተሉኝ፣ እግዚአብሔር ጠላቶቻችሁን፣ ሞዓባውያንን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና፡፡” እነርሱም ተከትለውት ወረዱና የዮርዳኖስን መሻገርያ ከሞዓባውያን ቀምተው ያዙ፣ እነርሱም ማንም ሰው ወንዙን እንዳይሻገር ከለከሉ፡፡ 29 በዚያን ጊዜም ከሞዓብ አሥር ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ገደሉ፣ የተገደሉትም ሁሉ ጠንካራና ኃይለኛ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድም እንኳ አላመለጠም፡፡ 30 በዚያም ቀን ሞዓብ በእስራኤል ብርታት ድል ሆነች፡፡ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ዐረፈች፡፡ 31 ከናኦድ በኋላ የተነሳው መስፍን ስድስት መቶ የፍልስጥኤም ሰዎችን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሰሜጋር ነበር፡፡ እርሱም ደግሞ እስራኤልን ከአደጋ አዳነ፡፡
እዚህ ጋ “አሁን” የሚለው ቃል የታሪኩን አዲስ ክፍል ይጀምራል።
ይህ ተራኪው በ3፡3 የሚዘረዝራቸውን የሕዝብ ወገኖች ያመለክታል።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በከነዓን በየትኛውም ጦርነት ያልተዋጉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከዋናው የታሪክ መስመር ይነጠላል። እግዚአብሔር አንዳንድ የሕዝብ ወገኖችን ለምን በከነዓን እንዳስቀራቸው ተራኪው ዳራዊ መረጃ ይሰጣል። አ.ት፡ “ቀድሞ በጦርነት ያልተዋጉ ወጣቶችን እንዴት መዋጋት እንዳለባቸው ለማስተማር እግዚአብሔር በእስራኤላውያን መካከል ሕዝቦች እንዲቀሩ አደረገ” (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ አምስት ነገሥታት ራሳቸውንና ሕዝባቸውን ይወክላሉ። አ.ት፡ “አምስቱ ነገሥታትና ሕዝቦቻቸው”
ይህ በእስራኤል ረጅሙ ተራራ ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በሰሜናዊ የከነዓን ወሰን የሚገኝ የቦታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች በከነዓን አስቀራቸው” ወይም “እነዚህ ሕዝቦች በከነዓን መኖራቸውን እንዲቀጥሉ እግዚአብሔር ፈቀደላቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“እንደ መንገድ”
“እነርሱ” እና “የእነርሱ” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው።
“እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትዕዛዝ”
የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው የእግዚአብሔርን ፍርድ ወይም ምዘና ነው። ይህንን በመሳፍንት 2፡11 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ፍርድ ክፉ የሆነውን” ወይም “እግዚአብሔር ክፉ ያለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ረሱ” ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙ “መታዘዛቸውን አቆሙ” የሚል ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የእግዚአብሔር በጣም መቆጣት በሚቀጣጠል እሳት ተመስሎ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በጣም ተቆጣ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የእስራኤል ሕዝብ እንዲሸነፍ መፍቀዱ እግዚአብሔር ለኩስርስቴም እንደ ሸጣቸው ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “ኩስርስቴምና ሰራዊቱ ድል እንዲያደርጋቸው ፈቀደላቸው”
እዚህ ጋ “እጅ” በፈሊጣዊ አነጋገር የሚወክለው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። በተጨማሪም “ኩስርስቴም” ራሱንና ሰራዊቱን የሚወክል ተምሳሌት ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ሀገር ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር አንድ የተለየ ሥራ እንዲሠራለት አንዱን መሾሙ ከተቀመጠበት እንዳስነሣው ወይም ብድግ እንዳደረገው ተቆጥሮ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የእነዚህን ሰዎች ስም በመሳፍንት 1፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት
ይህ ማለት ታላቅ መሪ ለመሆን የሚያስፈልገው ብቃት እንዲኖረውና እንዲያጎለብተው እግዚአብሔር ጎቶንያልን ረዳው ማለት ነው።
እዚህ ጋ “ፈረደ” ማለት የእስራኤልን ሕዝብ መራቸው ማለት ነው።
በዚህ አባባል ውስጥ “እርሱ” የሚያመለክተው ጎቶንያልን ራሱንና የእስራኤልን ሰራዊት ነው። አ.ት፡ “ጎቶንያልና የእስራኤል ወታደሮች ከኩስርስቴም ሰራዊት ጋር ለመዋጋት ሄዱ”
እዚህ ጋ “ኩስርስቴም” የራሱን ሰራዊት ይወክላል። አ.ት፡ “የእስራኤል ሰራዊት የአራም ንጉሥ የኩስርስቴምን ሰራዊት ድል እንዲያደርግ እግዚአብሔር ረዳቸው”
እዚህ ጋ “እጅ” ሰራዊትን የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የጎቶንያል ሰራዊት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ምድሪቱ” ጥቅም ላይ የዋለው በምድሪቱ የሚኖሩትን ሰዎች ለማመልከት ነው። አ.ት፡ “ሕዝቡ በሰላም ኖሩ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“40 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው የእግዚአብሔርን ፍርድ ወይም ምዘና ነው። ይህንን በመሳፍንት 2፡11 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ፍርድ ክፉ የሆነውን” ወይም “እግዚአብሔር ክፉ ያለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “ብርታት” እንደ ቅጽል ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎንን አበረታው” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎን” የሚወክለው ራሱንና ሰራዊቱን ነው። አ.ት፡ “የእስራኤልን ሰራዊት በሚወጉበት ጊዜ ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎንና ለወታደሮቹ”
ይህ የንጉሥ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሌላው የኢያሪኮ ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 1፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“18 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት በሩቅ ወዳለ ወደሌላው መጣራት ወይም ከፍ ባለ ድምፅ መናገር ማለት ነው። ደግሞም አንድ ሰው፣ በተለይም እግዚአብሔር እንዲረዳ መጠየቅ ሊሆንም ይችላል።
እግዚአብሔር አንድ የተለየ ሥራ እንዲሠራለት አንዱን መሾሙ ሰውየውን ከተቀመጠበት እንዳስነሣው ወይም ብድግ እንዳደረገው ተቆጥሮ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ናዖድ በግራ እጁ በተሻለ ሁኔታ ሰይፍ መያዝ ይችል ነበር።
ዘመናዊ የርዝመት መለኪያ መጠቀም የሚያስፈልግ ከሆነ ይህንን ለማድረግ ሁለት መንገዶች አሉ። አ.ት፡ “46 ሴንቲ ሜትር” ወይም “ግማሽ ሜትር ገደማ” (ርቀት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚለውን ተመልከት)
“በቀኝ መታጠቂያው በኩል በልብሱ ስር ታጠቀው”
በወገብና በጉልበት መካከል ያለ የእግር ክፍል
እዚህ ጋ “በዚህ ጊዜ” ጥቅም ላይ የዋለው ዋናው የታሪኩ መስመር መቆሙን ምልክት ለማድረግ ነው። እዚህ ጋ ተራኪው ስለ ዔግሎን ዳራዊ መረጃ ይሰጣል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች የተቀረጹ ምስሎች ወደ ሠሩበት ወደ ጌልጌላ አቅራቢያ በደረሰ ጊዜ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከዝቅተኛው ቀጥሎ ወደ ላይ ያለ ክፍል ሲሆን ለማረፊያነትና በቀኑ ሞቃታማ ሰዓት ቀዝቀዝ ብሎአቸው የሚቆዩበት ክፍል ነው።
መቆም፣ የእርሱን መልዕክት በማድመጥ እግዚአብሔርን የማክበር ምልክት ነው።
“የሰይፉ ስለት መጨረሻ በጀርባው በኩል ወጣ”
ጣሪያው የተሸፈነና ግድግዳው አጠር ያለ ውጫዊ ክፍል
ይህ ስለሚጸዳዳ ሰው የሚነገር የትህትና አነጋገር ነው።
አንዳች ችግር ተፈጥሮ እንደሆነና የንጉሡን የግል ክፍሉን መክፈትም ቢሆን የእነርሱ ተግባር እንደሚሆን በማሰብ ሲጨነቁ ቆዩ።
“ቁልፍ ወስደው በሮቹን ከፈቷቸው”
ይህ የሚነግረን አገልጋዮቹ የላይኛውን ክፍል በሮች በመክፈት ንጉሡ ሞቶ ሳያገኙት በፊት የሆነውን ነገር ነው። አ.ት፡ “አገልጋዮቹ ከላይኛው ክፍል ውጪ በመጠበቅ ላይ እያሉ … ናዖድ አመለጠ”
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በይበልጥ ግልጽ መሆን ይችላል። አ.ት፡ “ወደ ሴርታይም በደረሰ ጊዜ”
እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን እንዲያሸንፉ እግዚአብሔር መርዳቱ እግዚአብሔር ከጠላቶቻቸው ጋር ተዋግቶ ድል እንደሚያደርግ ጦረኛ ተቆጥሮ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“መሻገሪያዎቹን መቆጣጠር ቻሉ”
ጥልቀት የሌለውና በቀላሉ ሊሻገሩት የሚቻል የወንዝ አካባቢ
“ማንም እንዳይሻገር ከለከሉ”
“10,000 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“የሚችሉ ሰዎች” ወይም “በሚገባ መዋጋት የሚችሉ ሰዎች”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የእስራኤል ወታደሮች ሞዓባውያንን ድል አደረጓቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ጉልበት” የሚወክለው የእስራኤልን ሰራዊት ነው።
እዚህ ጋ “ምድር” የሚወክለው ሕዝብን ነው። አ.ት፡ “እስራኤላውያን በሰላም ኖሩ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“80 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እስራኤላውያን ነገሥታት ሳይኖሯቸው በፊት፣ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላ፣ በችግራቸው ጊዜ እንዲመሯቸው እግዚአብሔር መሳፍንትን ሾመላቸው። መሳፍንት አብዛኛውን ጊዜ እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው ይታደጓቸው ነበር።
የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ስድስት መቶ ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
በበሬ የሚያርሱ ገበሬዎች በሬዎቹ ወደ ፊት እንዲሄዱላቸው ለመምታት ሹልነት ያለው በትር ይጠቀሙ ነበር። አ.ት፡ “በሬዎቹን ለመንዳት የሚጠቀሙበት በትር” ወይም “በሬዎችን መምሪያ በትር”
“አደጋ” የሚለው ቃል የእስራኤልን ሕዝብ ለመጉዳት የሞከሩ ጠላቶቻቸውን ያመለክታል። አ.ት፡ “እርሱም ደግሞ የእስራኤልን ሕዝብ ከጠላቶቻቸው አዳናቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 ናዖድም ከሞተ በኋላ፣ የእስራኤል ሕዝብ ክፉ ነገሮችን በመስራት እንደገና እግዚአብሔርን አልታዘዙም፣ እርሱም ምን እንዳደረጉ ተመለከተ፡፡ 2 እግዚአብሔርም በሐጾር ሆኖ ይገዛ በነበረው፣ በከነዓን ንጉሥ በኢያቢስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ የሠራዊቱም አለቃ ሲሣራ ተብሎ ይጠራ ነበር፣ እርሱም የአሕዛብ በሆነችው በአሪሶት ኖረ፡፡ 3 የእስራኤልም ሕዝብ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፣ ምክንያቱም ሲሳራ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩት፣ እርሱም የእስራኤልን ሕዝብ ለሀያ ዓመት በኃይል አስጨንቆ ገዛቸው፡፡ 4 በዚያ ጊዜ ነቢይቱ የለፊዶት ሚስት ዲቦራ፣ በእስራኤል ላይ ዋነኛ ፈራጅ ነበረች፡፡ 5 እርስዋም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤቴል መካከል ካለው የዲቦራ ዘንባባ ዛፍ ስር ትቀመጥ ነበር፣ የእስራኤልም ሕዝብ ለክርክራቸው መፍትሔ ለማግኘት ወደ እርስዋ ይመጡ ነበር፡፡ 6 እርስዋም በንፍታሌም ውስጥ ካለው ከቃዴስ የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን ጠራች፡፡ እንዲህም አለችው፣ “የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይልሃል፣ ‘ወደ ታቦር ተራራ ሂድ፣ ከንፍታሌምና ከዛብሎን አሥር ሺህ ሰዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፡፡ 7 እኔ የኢያቢስን ሠራዊት አዛዥ ሲሣራን በቂሶን ወንዝ አቅራቢያ ከሰረገሎቹና ከሰራዊቱ ጋር እንዲያገኝህ አስወጣዋለሁ፣ እኔም በእርሱ ላይ ድልን እሰጥሃለሁ፡፡’” 8-9 ባርቅም እንዲህ አላት፣ “አንቺ ከእኔ ጋር ከሄድሽ እኔም እሄዳለሁ፣ ነገር ግን አንቺ ከእኔ ጋር ካልሄድሽ እኔም አልሄድም፡፡” እርስዋም እንዲህ አለች፣ “በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፡፡ ይሁን እንጂ፣ አንተ የምትሄድበት መንገድ ወደ ክብር አያደርስህም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሲሣራን በጥንካሬዋ ድል ታደርገው ዘንድ ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና፡፡” ከዚያም ዲቦራ ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች፡፡ 10 ባርቅም የዛብሎንና የንፍታሌም ሰዎች በአንድነት ወደ ቃዴስ እንዲመጡ ጠራቸው፡፡ አሥር ሺህም ሰዎች ተከተሉት፣ ዲቦራም ከእርሱ ጋር ሄደች፡፡ 11 ቄናዊው ሔቤርም ከቄናውያን ራሱን ለየ፣ እነርሱም የሙሴ አማት የኦባብ ልጆች ነበሩ፣ እርሱም በቃዴስ አጠገብ በጻዕናይም በነበረው በበሉጥ ዛፍ ጥግ ድንኳኑን ተከለ፡፡ 12 ለሲሳራም የአቢኔኤም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደወጣ በነገሩት ጊዜ፣ 13 ሲሣራም ሰረገሎቹን ሁሉ፣ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ወታደሮቹን ሁሉ፣ የአሕዛብ ከሆነችው ከአሪሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበሰባቸው፡፡ 14 ዲቦራም ባርቅን እንዲህ አለችው፣ “ሂድ! ዛሬ እግዚአብሔር በሲሣራ ላይ ድል እንድታደርግ በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ነውና፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ከፊትህ አልወጣምን?” ስለዚህ ባርቅ ከታቦር ተራራ አብረውት ከነበሩት አስር ሺህ ሰዎች ጋር ወረደ፡፡ 15 እግዚአብሔርም የሲሣራን ሰራዊት ግራ አጋባ፣ ሰረገሎቹንም ሁሉ፣ ሠራዊቱንም ሁሉ፣ የባርቅም ሰዎች የሲሳራን ሰዎች አጠቋቸው፣ ሲሳራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ፡፡ 16 ባርቅ ግን ሰረገሎችንና ሠራዊቱን እስከ አሪሶት ድረስ አባረራቸው፣ የሲሣራም ሠራዊት ሁሉ በሰይፍ ስለት ተገደሉ፣ አንድ ሰው እንኳ አልቀረም፡፡ 17 ሲሳራ ግን በእግሩ ወደ ቄናዊው ሔቤር ሚስት፣ ወደ ኢያዔል ድንኳን ሸሸ፣ ምክንያቱም በሐሶር ንጉስ በኢያቢስና፣ በቄናዊው በሔቤር ቤት መካከል ሰላም ስለነበር ነው፡፡ 18 ኢያዔልም ሲሣራን ለመገናኘት ወጣች እንዲህም አለችው፣ “ግባ፣ ጌታዬ ሆይ፤ ወደ እኔ ግባ አትፍራም፡፡” እርሱም ወደ እርስዋ ወደ ድንኳንዋ ገባ፣ በብርድ ልብስም ሸፈነችው፡፡ 19 እርሱም እንዲህ አላት፣ “ጠምቶኛልና፣ እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጭኝ፡፡” እርስዋም ከቆዳ የተሰራ የወተቱን ማስቀመጫ ከፍታ የሚጠጣ ሰጠችው፣ ከዚያም እንደገና ሸፈነችው፡፡ 20 እርሱም አላት፣ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፡፡ ሰውም ቢመጣና ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠይቅሽ ‘የለም’ በይ፡፡” 21 ከዚያም የሔቤር ሚስት ኢያዔል የድንኳን ካስማ ወሰደች በእጅዋም መዶሻ ያዘች በቀስታ ወደ እርሱ ሄደች፣ እርሱም በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር፣ እርስዋም ካስማውን በጆሮ ግንዱ ላይ ሰካችው፣ ካስማውም ሰውነቱን ወግቶ አለፈና ወደ መሬት ጠለቀ፡፡ እርሱም ሞተ፡፡ 22 ባርቅም ሲሣራን ሲያባርር፣ ኢያዔል ልታገኘው ወጣችና እንዲህ አለችው፣ “ና፣ የምትፈልገውንም ሰው አሳይሃለሁ፡፡” እርሱም ወደ ውስጥ ከእርስዋ ጋር ገባ፣ እነሆም በዚያ ሲሣራ ሞቶ ተጋድሞ ነበር፣ ካስማውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ተሰክቶ አገኘው፡፡” 23 ስለዚህ በዚያ ቀን እግዚአብሔር የከነዓንን ንገሥ ኢያቢስን በእስራኤል ሕዝብ ፊት አሸነፈው፡፡ 24 የእስራኤል ሕዝብ ጉልበት የከነዓን ንጉሥ ኢያቢስን እስከሚያጠፉ ድረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ መጣ፡፡
የዚህን ሰው ስም በመሳፍንት 3፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው የእግዚአብሔርን ፍርድ ወይም ምዘና ነው። ይህንን በመሳፍንት 2፡11 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ፍርድ ክፉ የሆነውን” ወይም “እግዚአብሔር ክፉ ያለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው በእስራኤል ላይ የበረታውን የኢያቢስን ኃይል ነው። እግዚአብሔር ለኢያቢስ ኃይል ለመስጠት መወሰኑ እርሱ ሕዝቡን ለኢያቢስ እንደሸጣቸው ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በከነዓን ንጉሥ በኢያቢስ ኃይል እንዲሸነፉ ፈቀደ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የወንዶቹ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የከተሞች ወይም የቦታ ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“900 የብረት ሠረገላዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“20 ዓመት”
ይህ ቃል ዋነኛውን የታሪክ መስመር ለማቆም ምልክት ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል። እዚህ ጋ ተራኪው ስለ ዲቦራ ዳራዊ መረጃ ይናገራል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ሴት ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በመከራቸው ጊዜ የሚመሯቸው መሳፍንትን ሾመላቸው። አብዛኛውን ጊዜ መሳፍንቱ ከጠላቶቻቸው ያድኗቸው ነበር።
ይህ ዛፍ በዲቦራ ስም ተጠርቷል።
እነዚህ የወንዶቹ ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ተራራ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“10,000 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እኔ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል።
እዚህ ጋ “ሲሣራ” ራሱንና ሰራዊቱን ይወክላል። አ.ት፡ “ሲሣራንና ሰራዊቱን አወጣለሁ”
ሰዎች ከምቹ ስፍራቸው ወጥተው እንዲመጡ ማድረግ
የእነዚህን ወንዶች ስም በመሳፍንት 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት
ይህ የወንዝ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የዚህን ሰውዬ ስም በመሳፍንት 4፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት
ባርቅ የሚያደርገው ምርጫ የሚጓዝበትን መንገድ እንደ መምረጥ ተቆጥሯል። “ክብር”ም ለአንድ ተጓዥ እንደ መዳረሻ ተቆጥሮለታል። አ.ት፡ “በምታደርገው ነገር ማንም አያከብርህም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው እርሱን ለመግደል ያላትን ኃይል ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሲሣራን ሴት እንድታሸንፈው ያደርጋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የዚህን ሰውዬ ስም በመሳፍንት 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የዚህችን ሴት ስም በመሳፍንት 4፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ቃል ዋነኛውን የታሪክ መስመር ለማቆም ምልክት ሆኖ ጥቅም ላይ ውሏል። እዚህ ጋ ተራኪው ስለ ቄናዊው ሔቤር ዳራዊ መረጃ ይናገራል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህንን በመሳፍንት 1፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት
“የሙሴ የሚስቱ አባት”
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እነርሱ” የሚለው ቃል በተለየ ሁኔታ ማንንም አይገልጽም። አ.ት፡ “አንድ ሰው ለሲሣራ ሲነግረው”
የዚህን ሰውዬ ስም በመሳፍንት 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 4፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
እዚህ ጋ “ሠረገላዎች” የሚወክሉት ሠረገላዎቹን የሚነዱ ወታደሮችን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“900 የብረት ሠረገላዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
የዚህችን ከተማ ስም በመሳፍንት 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህንን በመሳፍንት 4፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ዲቦራ ስለ ድሉ እርግጠኛ ስለ ነበረች ባርቅ አስቀድሞ ጦርነቱን እንዳሸነፈ አድርጋ ትናገራለች። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ድልን ይሰጥሃል”
የሚዋጉት ከእግዚአብሔር ጋር ወግነው መሆኑን ባርቅን ለማስታወስ ዲቦራ ይህንን ጥያቄ ትጠይቃለች። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንደሚመራህ አስታውስ” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“ከ10,000 ጋር” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“እግዚአብሔር፣ ሲሣራን፣ ሠረገላዎቹንና ሰራዊቱን ሁሉ በአግባቡ ማሰብ እንዳይችሉ አደረጋቸው” ወይም “እግዚአብሔር፣ ሲሣራ፣ ሠረገላዎቹና ሰራዊቱ ሁሉ እንዲደነግጡ አደረጋቸው”
እዚህ ጋ “ሠረገላዎቹ” የሚለው ቃል ሠረገላዎቹን የሚነዱትን ወታደሮች የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ሠረገላዎቹን የሚነዱት ሰዎች ሁሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ባርቅ” የሚወክለው ራሱንና ሰራዊቱን ነው። አ.ት፡ “ባርቅና ወታደሮቹ አሳደዱ”
ይህንን በመሳፍንት 4፡2 ላይ በተረጎምክበት በዚያው መልክ ተርጉመው።
እዚህ ጋ “ሰይፍ” የሚወክለው ወታደሮች በጦርነት ላይ የሚጠቀሙባቸውን ሰይፍና ሌሎች የጦር መሣሪያዎች ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ባርቅና ወታደሮቹ የሲሣራን ወታደሮች በሙሉ በሰይፍ ገደሏቸው”
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
በፈረስ ወይም በሠረገላ ከመጋለብ ይልቅ በእግሩ መሮጡ ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ሴት ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የዚህን ሰውዬ ስም በመሳፍንት 4፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህንን በመሳፍንት 1፡16 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ማለት ከሚደረገው ጉዞ ለማረፍ የሚደረግ የመንገድ ለውጥ ነው። አ.ት፡ “ወዲህ ና”
ከሱፍ ወይም ከእንስሳት ቆዳ የሚሠራና በመኝታ ጊዜ ሙቀት እንዲሰጥ የሚለበስ ሰፊ የአካል መሸፈኛ ነው።
“ሲሣራ ለኢያኤል ተናገራት”
የድንኳኑን ማዕዘን ከምድር ጋር እንዲያያይዝ እንደ ትልቅ መንጠቆ በመዶሻ የሚመታ የሾለ እንጨት ወይም ብረት
የድንኳኑን ካስማ ወደ መሬት ለማጥለቅ ክብደት ካለው እንጨት የሚሠራ መምቻ
አንድ ሰው ጥልቀት ካለው ጉድጓድ ውስጥ በቀላሉ መውጣት እንደማይችል ሁሉ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ያለ ሰውም በቀላሉ አይነቃም። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ባርቅ ያባርረው ነበር” ወይም “ባርቅ ይከተለው ነበር”
እግዚአብሔር እስራኤላውያኑ ኢያቢስንና ሰራዊቱን እንዲያሸንፏቸው ማድረጉ የእስራኤል ሕዝብ እያዩ እግዚአብሔር ራሱ ኢያቢስን ድል እንዳደረጋቸው ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ወታደራዊ ኃይል”
እዚህ ጋ “እርሱ” የሚያመለክተው ራሱንና ሰራዊቱን የሚወክለውን ኢያቢስን ነው። አ.ት፡ “ኢያቢስንና ሰራዊቱን ደመሰሱ”
1 በዚያም ቀን ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህንን መዝሙር ዘመሩ፡- 2 “በእስራኤል ውስጥ መሪዎች የመሪነት ስፍራውን ሲይዙ፣ ሕዝቡም በደስታና በፈቃዳቸው ለጦርነት ሲወጡ፣ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን! 3 ስሙ፣ እናንተ ነገሥታት! አድምጡ፣ እናንተም መኳንንት! እኔ፣ እኔ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋናን እዘምራለሁ፡፡ 4 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ ከኤዶምያስም በተነሳህ ጊዜ፣ ምድር ተናወጠች፣ ሰማያት ደግሞ ተንቀጠቀጡ፤ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠባጠቡ፡፡ 5 ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት ተንቀጠቀጡ፤ ሲና ተራራም እንኳ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተንቀጠቀጠ፡፡ 6 በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣ በኢያዔል ዘመን፣ መንገዶች ተተዉ፣ መንገደኞችም በጠመዝማዛ መንገድ ብቻ ይጠቀሙ ነበር፡፡ 7 እኔ ዲቦራ አለቃ እስከሆንሁበት ጊዜ ድረስ፣ ለእስራኤል እናት ሆኜ አለቅነትን እስከወሰድሁበት ጊዜ ድረስ፣ በእስራኤል ውስጥ ገበሬዎች አልነበሩም፡፡ 8 አዲስ አማልክትን መረጡ፣ በከተማዋ ደጆች ጦርነት ነበረ፤ በእስራኤል ውስጥ በአርባ ሺህ መካከል ጋሻ ወይም ጦር አልታየም፡፡ 9 ልቤ ወደ እስራኤል አለቆች ሄደ፣ በሕዝቡ መካከል ራሳቸውን በደስታ ስለ ሰጡትም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ 10 እናንተ በነጫጭ አህዮች ላይ ትንሽ የምንጣፍ ኮርቻ ላይ ተቀምጣችሁ የምትጓዙ፣ በመንገድም የምትሄዱ እናንተ ስለዚህ ነገር አስቡ፡፡ 11 በማጠጫው ስፍራ መካከል ሆነው በጎችን የሚከፋፍሉትን ሰዎች ድምጽ ስሙ፡፡ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ድርጊትና ተዋጊዎቹ በእስራኤል ውስጥ የሰሩትን የጽድቅ ተግባር በዚያ እንደገና እየተናገሩ ነው፡፡ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ ከተማው በሮች ወረዱ፡፡ 12 ንቂ፣ ንቂ፣ ዲቦራ ሆይ! ንቂ፣ ንቂ፣ መዝሙርን ዘምሪ! ባርቅ ሆይ፣ ተነሣ፣ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፣ ምርኮኞችህን ማርከህ ውሰድ፡፡ 13 የዚያን ጊዜ የተረፉት ወደ ኃያላኑ መጡ፣ ከተዋጊዎቹም መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ እኔ መጡ፡፡ 14 መሰረታቸው ከአማሌቅ ወገን የሆኑ ከኤፍሬም መጡ፤ የብንያም ሕዝብም ተከተሉህ፡፡ ከማኪርም አዛዦች ወረዱ፣ የስልጣን በትር የያዙ ከዛብሎን ወረዱ፡፡ 15 የይሳኮርም መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤ ይሳኮርም ከባርቅ ጋር በትዕዛዙ መሰረት ከኋላው እየተከተለ ወደ ሸለቆው ሄደ፡፡ በሮቤል ጎሳ መካከል ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ፡፡ 16 የበጎች እረኞች ለመንጎቻቸው በፉጨት ሲጫወቱ እያዳመጥህ በእሳት ማንደጃ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ጎሳ መካከል ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ፡፡ 17 ገለዓድ በዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤ ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ቀረ? አሴርም በባሕሩ ዳርቻ ቀረ፣ በወንዞቹም ዳርቻ ኖረ፡፡ 18 ዛብሎን ነፍሱን ወደ ሞት አሳልፎ የሚሰጥ ሕዝብ ነው፣ ንፍታሌምም በውጊያ ሜዳ ላይ ነው፡፡ 19 ነገሥታት መጡ ተዋጉም፣ የዚያን ጊዜ የከነዓን ነገስታትም በመጊዶ ውኆች አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፡፡ ምንም የብር ምርኮ አልወሰዱም፡፡ 20 ከሰማይ ከዋክብት ተዋጉ፣ በሰማያት ላይ በአካሄዳቸውም ሲሣራን ተዋጉት፡፡ 21 ከዱሮ ጀምሮ የታወቀው፣ የቂሶን ወንዝም፣ ጠርጎ ወሰዳቸው፡፡ ነፍሴ ሆይ ገስግሺ፣ በርቺ! 22 የፈረሶች የግልብያ ኮቴዎች ድምጽ፣ የኃያላኑ ግልቢያ ድምጽም፡፡ 23 የእግዚአብሔር መልአክ “ሜሮዝን እርገሙ!” ይላል፡፡ ‘ነዋሪዎቿን ፈጽማችሁ እርገሙ! ምክንያቱም እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡም፣ ከኃያላን ጦረኞች ጋር በተደረገው ውጊያ እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡምና፡፡' 24 የቄናዊው የሔቤር ሚስት፣ ኢያዔል፣ ከሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ናት፣ በድንኳን ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ ይልቅ የተባረከች ናት፡፡ 25 ሰውየው ውኃ ለመናት፣ እርስዋም ወተት ሰጠችው፤ ለመሳፍንት በሚሆን በተከበረ ሳህን ቅቤ አመጣችለት፡፡ 26 እጅዋን ወደ ድንኳን ካስማ፣ ቀኝ እጅዋንም ወደ ሠራተኛ መዶሻ አደረገች፤ በመዶሻውም ሲሣራን መታች፣ ራሱንም ቀጠቀጠች፡፡ ጆሮ ግንዱን በወጋችው ጊዜ ጭንቅላቱንም ፈረከሰችው፡፡ 27 በእግሮችዋ መካከል ተደፋ፣ ወደቀ ተኛም፡፡ በእግሮችዋ አጠገብ ተሰብሮ ወደቀ፡፡ የተደፋበት ስፍራ በክፉ ሁኔታ የሞተበት ነው፡፡ 28 ከመስኮት ሆና ወደ ውጭ ተመለከተች፣ የሲሣራ እናት በርብራብ በኩል በኃዘን ወደ ውጭ ጮኸች፣ ‘ወደዚህ ለመምጣት ሰረገላው ረዥም ጊዜ ለምን ወሰደበት? ለምንስ ሰረገላዎቹን የሚጎትቱት የፈረሶቹ ኮቴዎች ዘገየ?’ 29 ብልሃተኞች ልዕልቶቿም መለሱላት፣ ለራስዋም ተመሳሳይ መልስ መለሰች፡- 30 ምርኮውን አግኝተው ተካፍለው የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረድ፤ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ቀለም ያለው ልብስ፣ የተጠለፈ ባለቀለም ጨርቅ ምርኮ፣ ለማረኩ ሰዎች ለአንገታቸው የሚሆን በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ባለቀለም ጨርቆች ምርኮን አላገኙምን?’ 31 ስለዚህ፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ! ነገር ግን እርሱን የሚወዱት በኃይል እንደሚወጣ ጸሐይ ይሁኑ፡፡” ምድሪቱም ለአርባ ዓመት ያህል ዐረፈች፡፡
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “እስራኤላውያን የንጉሥ ኢያቢስን ሰራዊት ድል ባደረጉበት ቀን”
ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 4፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
“ሰዎቹ ለመዋጋት በተስማሙ ጊዜ”
ዲቦራና ባርቅ፣ ነገሥታትና መሪዎች እዚያ ተገኝተው መዝሙሩን ይሰሙ ይመስል ይናገራሉ።
ይህ የሚያመለክተው በጥቅሉ ነገሥታትንና መሪዎችን እንጂ የተለዩ ነገሥታትን ወይም መሪዎችን አይደለም።
ይህ እስራኤላውያን በከነዓን የሚኖሩትን ድል ለማድረግ ኤዶምን ትተው የተነሡበትን ጊዜ ያመለክታል። እግዚአብሔር፣ ሕዝቡ የከነዓንን ሰዎች ድል እንዲያደርጓቸው ማብቃቱ እርሱ የእስራኤልን ሰራዊት እንደሚመራቸው ጦረኛ ተደርጎ እንዲነገርለት ሆኗል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሴይር በእስራኤልና በኤዶም ምድር ድንበር ላይ የሚገኝ ተራራ ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ የምድር መናወጥንና ማዕበልን እንደሚፈጥር በመግለጽ ለእግዚአብሔር ኃይል አጽንዖት የሚሰጥ ሥነ ግጥማዊ ቋንቋ ነው ወይም 2) እስራኤላውያኑ በሚወጓቸው ጊዜ የከነዓን ሰዎች መፍራታቸው ሰማይና ምድር እንደተንቀጠቀጡ ተደርጎ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ እግዚአብሔርን በጣም በመፍራታቸው ተራሮች መንቀጥቀጣቸውን ለማሳየት፣ ምናልባት የምድር መናወጥን ያመለክት ይሆናል። አ.ት፡ “ተራሮች በፍርሃት ተርበደበዱ”
እዚህ ጋ “ፊት” የእግዚአብሔርን ሀልዎት ያመለክታል። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ሀልዎት ፊት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሙሴና እስራኤል በሲና ተራራ በነበሩ ጊዜ ተንቀጥቅጦ ነበር። አ.ት፡ “ከዓመታት በፊት የሲና ተራራ እንኳን ተንቀጥቅጧል”
“በ… የሕይወት ዘመን”
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው። ሰሜጋርና ዓናትን በመሳፍንት 3፡31 ላይ እንዲሁም ኢያዔልን በመሳፍንት 4፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ሰሜጋርንና የኖረበትን ዘመን መለየት እንዲቻል ለመርዳት የሰሜጋር አባት ተጠቅሷል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር የሚችል ሲሆን መንገዶቹ የተተዉበትን ምክንያት ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “የእስራኤልን ጠላቶች ስለ ፈሩ ሰዎች አውራ ጎዳናዎቹን መጠቀም አቆሙ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ፣ የሚለውን ተመልከት)
ዲቦራ ለትናንሽ ልጆች እንክብካቤ እንደምታደርግ እናት በእስራኤል ላይ መሪ ስለ መሆኗ ትናገራለች። አ.ት፡ “እኔ ዲቦራ መምራት ጀምሬአለሁ - እናት ልጆችዋን እንደምትንከባከብ እስራኤላውያንን እንከባከባለሁ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ መቻል አለበት። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ አዳዲስ አማልክትን አመለኩ”
እዚህ ጋ “በሮች” መላውን ከተማውን ይወክላሉ። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉሙ በበለጠ ግልጽ መደረግ መቻል አለበት። አ.ት፡ “በእስራኤል ከተሞች ውስጥ ጠላት ሕዝቡን አጠቃ”
ይህ መግለጫ ምናልባት እስራኤላውያን ስለ ነበራቸው ጥቂት የጦር መሣሪያ በግነት የቀረበ ይሆናል። አ.ት፡ “በእስራኤል ለጦርነት የቀረው ጥቂት የጦር መሣሪያ ነው” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
“40,000 በእስራኤል” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ልብ” የሚለው ቃል የአንድን ሰው ስሜት ይወክላል። “ልቤ ይሄዳል” የሚለው ሐረግ ዲቦራ ያላትን አድናቆት ወይም ምስጋና የማመልከቻ መንገድ ነው። አ.ት፡ “የእስራኤልን አዛዦች አደንቃለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ንጽጽር የሚያመለክተው ምናልባት ባለጸጎችንና ድኾችን ይሆናል። አ.ት፡ “እናንት በነጫጭ አህዮች የምትቀመጡ ባለጸጎች … እናንት በመንገዱ ላይ የምትሄዱ ድኾች”
እነዚህ ስጋጃዎች ምናልባት ጋላቢው በይበልጥ እንዲመቸው በአህያው ጀርባ ላይ ለኮርቻነት የሚጠቀምባቸው ሳይሆኑ አይቀሩም።
እዚህ ጋ “ድምፆች” የሚዘምሩትን ሰዎች ይወክላል። አ.ት፡ “ስሟቸው”
እዚህ ጋ “በሮች” መላውን ከተማ ይወክላሉ። አ.ት፡ “ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ”
ተናጋሪዎች ሊሆኑ የሚችሉት 1) የእስራኤል ሕዝብ ወይም 2) ለራሷ የምትናገረው ዲቦራ ወይም 3) መዝሙሩን የጻፈው ገጣሚ ነው።
ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 4፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
“እኔ” የሚለው ቃል ዲቦራን ያመለክታል።
የኤፍሬም ሰዎች የሚኖሩበት ምድር በመጀመሪያ የአማሌቅ ተወላጆች ይኖሩበት ስለ ነበረ የኤፍሬም ሰዎች በምድሪቱ እንደ ተተከሉና ስር እንደ ሰደዱ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “በአንድ ወቅት የአማሌቅ ተወላጆች ይኖሩ ከነበሩበት ከኤፍሬም ምድር” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ተከተሉህ” የሚያመለክተው የኤፍሬምን ሕዝብ ነው። በሦስተኛ መደብ ሊነገር ይቻላል። አ.ት፡ “ተከተሏቸው” (የአንተ ቅርጾች እና አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የማኪር ተወላጆች ይኖሩ የነበሩበት ስፍራ ነው። ማኪር የምናሴ ልጅና የዮሴፍ የልጅ ልጅ ነበር። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ወታደራዊ አመራሮች የስልጣናቸው ምልክት በሆነው በትራቸው ይገለጻሉ። አ.ት፡ “የዛብሎን ወታደራዊ መሪዎች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የእኔ” የሚያመለክተው ዲቦራን ነው። ይህ መግለጫ በአጠቃላይ በአንደኛ መደብ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በይሳኮር የሚገኙት መስፍኖቼ ከእኔ ጋር ነበሩ” (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)
ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡4 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት
እዚህ ጋ “ይሳኮር” የይሳኮርን ነገድ ያመለክታል። አ.ት፡ “የይሳኮር ነገድ ከባርቅ ጋር ነበር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡6 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“መመሪያውን በመታዘዝና ወደ ሸለቆው ከበስተኋላው በመሮጥ”
“ከኋላው በመከተል” ወይም “ከኋላው በመሮጥ”
እዚህ ጋ “ልብ” አሳብን ይወክላል። የሰዎቹ እርስ በእርስ መነጋገርና ምን ማድረግ እንዳለባቸው መወሰን አለመቻላቸው ልባቸውን እንደመረመሩ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ምን ማድረግ እንዳለባቸው ብዙ ውይይት ነበር” (ፈሊጣዊ እና ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ወደ ጦርነቱ በመምጣት ለመዋጋት አልወሰኑም ነበርና ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የሮቤልን ሰዎች ለመውቀስ ነው። ይህ እንደ መግለጫ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በቤት ቀርታችሁ እረኞች ለመንጋዎቻቸው የሚጫወቱትን ዋሽንት ከምትሰሙ ይልቅ ስንዋጋ ልትረዱን ይገባ ነበር” (መልስ የማይሻ ጥያቄ እና የሚለውን ተመልከት)
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕትሞች “የበጎች ጉረኖ” ወይም “የበግ ማሳደሪያ” ይሉታል
እዚህ ጋ “ገለዓድ” የሚያመለክተው በጦርነቱ ላይ ለመዋጋት መሄድ የነበረባቸውን የገለዓድ ወንዶች ነው። አ.ት፡ “የገለዓድ ሰዎች ተቀምጠዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የዮርዳኖስን ምስራቅ ያመለክታል።
የዳን ነገድ ሰዎች ለእስራኤል ስላልተዋጉ ይህ ጥያቄ የተጠየቀው ቁጣን ለመግለጽ ነው። አ.ት፡ “የዳን ሰዎች በመርከቦቻቸው ውስጥ መቆየት አልነበረባቸውም” ወይም “በጦርነቱ የዳን ነገድ ሰዎች አልረዱንም። ይልቁንም በመርከቦቻቸው ውስጥ ሆነው ወዲያና ወዲህ ይቅበዘበዙ ነበር!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዳን” ጦርነቱን ለመዋጋት መሄድ የነበረባቸውን የዳን ሰዎች ይወክላል። አ.ት፡ “ለምንድነው የዳን ሰዎች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የዳን ነገድ የሚገኘው በሜዴትራንያን ባህር አጠገብ ነበር። በንግድና ዓሳ በማስገር ገንዘብ ለማግኘት በባህሩ ላይ በመርከብ ይጓዙ ነበር።
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉሙ በይበልጥ ሊብራራ ይችላል። አ.ት፡ “የአሴር ነገድ ሰዎችም ደግሞ ሳይረዱን ቀሩ። በወደቦቻቸው አቅራቢያ ብቻ ተቀመጡ”
እዚህ ጋ “አሴር” ጦርነቱን ለመዋጋት መሄድ የነበረባቸውን የአሴር ሰዎች ይወክላል። አ.ት፡ “የአሴር ሰዎች ተቀመጡ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ጥልቅ ውሃ ያለባቸውና መርከቦች የሚቆሙባቸው የባህር ዳርቻ አካባቢዎች
የሚታወቀውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ንፍታሌምም ደግሞ ነፍሳቸውን እስከ ሞት ድረስ አሳልፈው ከሰጡት ነገዶች አንዱ ነበር”
ራሱንና የሚያዛቸውን ሰራዊት ለማመልከት የአንድ ሕዝብ ወገን ንጉሥ የሚለው ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “ነገሥታትና ሰራዊቶቻቸው መጥተው ተዋጉ - የከነዓን ነገሥታትና ሰራዊቶቻቸው ተዋጉ”
“እኛ” የሚለው ቃል የሚታወቅ ነው። አ.ት፡ “ወጉን - ወጉን”
የእነዚህን ቦታዎች ስም በመሳፍንት 1፡27 እንዳደረግኸው ተርጉማቸው።
እዚህ ጋ “ብር” በጥቅሉ የትኛውንም ዓይነት ገንዘብ ይወክላል። አ.ት፡ “የሚበዘብዙት ብር ወይም ሌላ ሀብት አልነበረም”
አብዛኛውን ጊዜ በጦርነት ወይም በሌቦች አማካይነት በማስገደድ የሚወሰዱ ነገሮች
እግዚአብሔር፣ እስራኤላውያን ሲሣራንና ሰራዊቱን ድል እንዲያደርጓቸው መርዳቱ ከዋክብት ራሳቸው ሲሣራንና ሰራዊቱን እንደተዋጓቸው ተደርጎ ተነግሯል። ይህ እግዚአብሔር ሲሣራን ድል ለማድረግ ተፈጥሮአዊ ግብዓቶችን በተለይም ነጎድጓድን መጠቀሙን ያመለክት ይሆናል። (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ሲሣራ” የሚወክለው ራሱንና መላውን ሰራዊቱን ነው። አ.ት፡ “ሲሣራና ሰራዊቱ”
ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
በከባድ ዝናብ ምክንያት ወንዙ በፍጥነት ስለሞላ ሠረገላዎቹ በጭቃ ተይዘው ስለነበር ብዙ ወታደሮች ሰመጡ። አ.ት፡ “የቂሶን ወንዝ ጎረፈና የሲሣራን ወታደሮች ጠራርጎ ወሰዳቸው”
ይህንን በመሳፍንት 4፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እዚህ ጋ “ነፍስ” የሰውን ሁለንተና ያመለክታል። “የእኔ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ዲቦራን ነው። አ.ት፡ “እንድበረታና እንድሰለፍ ለራሴ እነግራለሁ”
ይህ የሚገልጸው ከጦርነት የሚሸሹ የብዙ ፈረሶችን ድምፅ ነው። አ.ት፡ “ከዚያም በሽሽት ላይ ያሉ የፈረሶችን ድምፅ ሰማሁ። ብርቱዎቹ የሲሣራ ፈረሶች እየሸሹ ነበር”
በፍጥነት መሮጥ
እዚህ ጋ “ሜሮዝ” የምትወክለው በዚያ የኖሩትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “የሜሮዝን ሰዎች እርገሙ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
በአንድ ስፍራ የሚኖሩ ሰዎች
ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህንን ስም በመሳፍንት 4፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የዚህን የሕዝብ ወገን ስም በመሳፍንት 1፡16 ላይ እንዳደረግኸው ተርጉመው።
እዚህ ጋ “ቅቤ” የሚያመለክተው የረጋውን ወተት ነው። ይህ በኢያዔል ሰዎች መካከል የተመረጠ ወተትና ተወዳጅ መጠጥ ነበር። አ.ት፡ “እርጎ አመጣችለት” ወይም “የረጋ ወተት አመጣችለት”
ለልዑላን ምርጥ የሆነው ነገር ይቀርብ ስለነበር ይህ ሐረግ የሚለው ማዕዱ እጅግ ምርጥ መሆኑን ነው።
“ኢያዔል በግራ እጇ የድንኳኑን ካስማ ያዘች”
ይህ ድንኳኑን ከመሬት ጋር አገናኝቶ እንዲይዝ በመዶሻ የሚመታ እንደ ትልቅ ሚስማር የሾለ እንጨት ወይም ብረት ነው። ይህንን በመሳፍንት 4፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ሙሉ ዐረፍተ ነገር ሆኖ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “በቀኝ እጇ መዶሻ ያዘች”
የድንኳኑን ካስማ ወደ መሬት ለማጥለቅ ክብደት ካለው እንጨት የሚሠራ መምቻ ነው። ይህንን በመሳፍንት 4፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የዚህን ሰውዬ ስም በመሳፍንት 4፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡
ዐቅም ማጣት ወይም መንቀሳቀስ አለመቻል
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ገደለችው” ወይም “ሞተ”(አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በመስቀልዮሽ እንጨት የተሠራ የመስኮቱ መደገፊያ ነው።
ሁለቱም ጥያቄዎች የሚሉት አንድ ነገር ነው። እነዚህ ሁለቱም መግለጫዎች መጣመር ይችላሉ። አ.ት፡ “ሲሣራ ወደ ቤት ሳይመለስ የቆየው ለምንድነው?”
ሁለቱም አነጋገሮች የሚወክሉት ሲሣራን ነው። አ.ት፡ “ሲሣራን የወሰዱት. . . እርሱ ለምን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ልዕልት” የንጉሥ ልጅ ናት፣ ነገር ግን “ልዕልቶች” ማለት ደግሞ ምናልባት የንጉሡን ቤተሰቦች የሚያማክሩ ሴት አማካሪዎች ማለት ሊሆን ይችላል። አ.ት፡ “ጠቢብ ሴቶች”
“ያንኑ ነገር ለራሷ ተናገረች”
ሴቶቹ በእርግጥ የሆነው ይኸው ነው ብለው ስላመኑበት ጉዳይ አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማሉ። አ.ት፡ “ለመከፋፈል ጊዜ የፈጀባቸው ብዙ ምርኮ እግኝተው መሆን አለበት” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ሴቶቹ በእርግጥ የሆነው ይኸው ነው ብለው ስላመኑበት ጉዳይ አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠቀማሉ። አ.ት፡ “ከበዘበዟቸው ላይ ለእያንዳንዱ ወንድ አንድ ማህፀን፣ ሁለት ማህፀን ደርሷቸው መሆን አለበት” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ማህፀን” የሚያመለክተው ሴትን ነው። የሲሣራ ሰዎች ብዙ ሴቶችን እንደማረኩ የሲሣራ እናት ታምናለች። አ.ት፡ “እያንዳንዱ ወታደር አንድ ወይም ሁለት ሴት ይደርሰዋል”
“ልዩ ልዩ ቀለም ያለው ልብስ” ወይም “ልዩ ልዩ ቀለም ያላቸው ልብሶች”
ልዩ ልዩ ቀለማት ካላቸው ክሮች የተሠሩ ንድፎች
እዚህ ጋ “አንገታቸው” የሚወክለው የሲሣራን ወታደሮች ነው። አ.ት፡ “የበዘበዙት ወታደሮች ሊለብሱት”
የየትኛውም ሀገር ሰራዊት የፀሐይን መውጣት ማስቆም ስለማይችል የእስራኤል ሕዝብ እንደ ማለዳ ፀሐይ ለመሆን ይመኛሉ።
እዚህ ጋ “ምድሪቱ” የሚወክለው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “የእስራኤልም ሕዝብ በሰላም ኖሩ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ለ40 ዓመታት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
1 የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ሥራ ሠሩ፤ እርሱም በምድያም ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ለሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ 2 የምድያምም ኃይል በእስራኤል ላይ በረታ፡፡ ከምድያምም የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ በኮረብታዎች ላይ ጕድጓድ፣ ዋሻና ምሽግም ለራሳቸው መሸሸጊያ አበጁ። 3 እንዲህም ሆነ፣ እስራኤል ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና ከምሥራቅም የመጡ ሰዎች እስራኤላውያንን ያጠቁ ነበር፡፡ 4 ሰራዊታቸውን በምድሪቱ ላይ ያሰፍሩና እስከ ጋዛ ድረስ ያለውን ሰብል ያጠፉ ነበር፡፡ በእስራኤልም ምንም መብል፣ በጎች፣ ከብቶችና አህያዎች አይተዉም ነበር፡፡ 5 እነርሱ እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ እንደ አንበጣ መንጋ ሆነው ይመጡ ነበር፤ እነርሱንና ግመሎቻቸውንም መቁጠር አይቻልም ነበር፡፡ ምድሪቱንም ያጠፉ ዘንድ ይወርሩአት ነበር፡፡ 6 ምድያም እስራኤልን ክፉኛ ከማዳከማቸው የተነሣ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡ 7 የእስራኤል ሕዝብ በምድያም ምክንያት ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ፣ 8 እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ልጆች ነቢይ ላከ፡፡ ነቢዩም እንዲህ አለ፡- “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ‘እኔ ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤ ከባርነትም ቤት አወጣኋችሁ፡፡ 9 ከግብፃውያንም እጅ እንደዚሁም ይጨቁኑአችሁ ከነበሩ ኃይላት ሁሉ አዳንኋችሁ፡፡ ከፊታችሁም አሳድጄ አወጣኋቸው፣ ምድራቸውንም ሰጠኋችሁ፡፡ 10 ለእናንተንም እንዲህ አልኋችሁ፣ “እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን፣ የአሞራያውያንን አማልክት እንዳታመልኩ አዘዝኋችሁ፡፡ ነገር ግን እናንተ ድምጼን አልታዘዛችሁም፡፡ 11 የእግዚአብሔርም መልአክ መጣና በዖፍራ ባለችው ለአቢዔዝራዊው ለኢዮአስ በነበረችው ከበሉጥ ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ የኢዮአስም ልጅ ጌዴዎን ከምድያማውያን ለመሸሸግ በወይን መጥመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር፡፡ 12 የእግዚአብሔርም መልአክ ለእርሱ ተገልጠለትና እንዲህ አለው፣ “አንተ ብርቱ ተዋጊ ሰው፣ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው አለው!” 13 ጌዴዎንም ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ፣ ይህ ነገር ሁሉ ለምን በእኛ ላይ ደረሰብን? አባቶቻችንስ የነገሩን እርሱ የሰራቸው አስደናቂ ነገሮች ወዴት አሉ፣ እንዲህ ብለው የነገሩን፣ ‘እግዚአብሔር ከግብፅ አላወጣንምን?’ አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፣ ለምድያማውያንም ብርታት አሳልፎ ሰጥቶናል፡፡ 14 እግዚአብሔርም ወደ እርሱ ተመለከተና እንዲህ አለው፣ “በዚህ ባለህ ብርታት ሂድ፡፡ እስራኤልንም ከምድያም ኃይል አድን፤ እነሆ እኔ አልላክሁህምን?” 15 ጌዴዎንም እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ እባክህ፣ እኔ እስራኤልን እንዴት ማዳን እችላለሁ? ተመልከት፣ የእኔ ቤተሰብ ከምናሴ ነገድ ከሁሉ ይልቅ ደካማ ነው፣ እኔም በአባቴ ቤት ውስጥ የመጨረሻ ነኝ፡፡ 16 እግዚአብሔርም፣ “እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፣ አንተም የምድያምን ሰራዊት በሙሉ ታሸንፋለህ” አለው፡፡ 17 ጌዴዎንም እንዲህ አለው፣ “በእኔ ደስተኛ ከሆንህ፣ የምትናገረኝ አንተ እንደሆንህ እርግጠኛ እሆን ዘንድ ምልከትን ስጠኝ፡፡ 18 ወደ አንተ እስክመጣና መስዋእቴን አምጥቼ በፊትህ እስካቀርብ ድረስ እባክህ ከዚህ አትሂድ፡፡” እግዚአብሔርም “እስክትመለስ ድረስ እቆያለሁ” አለ፡፡ 19 ጌዴዎን ሄደ የፍየሉንም ጠቦት አረደ፣ የኢፍ መስፈሪያም ዱቄት ወስዶ ያልቦካ ቂጣ አዘጋጀ፡፡ ሥጋውን በቅርጫት አኖረ፣ መረቁንም በምንቸት ውስጥ አኖረ፣ ሁሉንም ይዞ በበሉጥ ዛፍ በታች አቀረበለት፡፡ 20 የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ አለው፣ “ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ ውሰድና በዚህ ድንጋይ ላይ አኑረው፣ መረቁንም በላዩ ላይ አፍስሰው፡፡” ጌዴዎንም እንዲሁ አደረገ፡፡ 21 የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ የያዘውን የበትሩን ጫፍ ወደዚያ ዘረጋ፡፡ በበትሩም ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ ነካው፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥቶ ሥጋውንና ያልቦካውን ቂጣ በላ፡፡ የእግዚአብሔርም መልአክ ሄደ፣ ጌዴዎንም ሊያየው አልቻለም፡፡ 22 ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አወቀ፡፡ ጌዴዎንም፣ “አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮልኝ! የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና” አለ፡፡ 23 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፣ “ሰላም ለአንተ ይሁን! አትፍራ፣ አትሞትም፡፡” 24 ስለዚህ ጌዴዎን በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፡፡ ስሙንም፣ እግዚአብሔር ሰላም ብሎ ጠራው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ በአቢዔዝራውያን ጎሳ በምትሆነው በዖፍራ አለ፡፡ 25 እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት እንዲህ አለው፣ “የአባትህን በሬ፣ ሰባት ዓመት የሆነውን ሁለተኛውንም በሬ ውሰድ፣ የአባትህ የሆነውን የበኣል መሠዊያ አፍርስና በአጠገቡ ያለውን አሼራን ሰባብረው፡፡ 26 በዚህ መሸሸጊያ ስፍራ ጫፍ ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ፣ በትክክለኛው መንገድም ስራው፡፡ ከአሼራ ሰባብረህ በጣልኸው እንጨት ሁለተኛውን በሬ የሚቃጠል መስዋእት አድርገህ አቅርበው፡፡” 27 ስለዚህ ጌዴዎን ከባሪያዎቹ አሥር ሰዎችን ወሰደና እግዚአብሔር እንደነገረው አደረገ፡፡ ነገር ግን በቀን ለማድረግ የአባቱን ቤተ ሰቦችና የከተማውንም ሰዎች እጅግ በጣም ስለፈራ፣ በሌሊት አደረገው፡፡ 28 በማለዳ የከተማው ሰዎች በተነሱ ጊዜ፣ የበኣል መሠዊያ ፈርሶ ነበር፣ በአጠገቡ የነበረውም አሼራ ተሰባብሮ ነበር፣ ሁለተኛውም በሬ አዲስ በተሰራው መሠዊያ ላይ ተሠውቶ ነበር፡፡ 29 የከተማውም ሰዎች እርስ በርሳቸው፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ተባባሉ፡፡ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩና መልስ ሲፈልጉ ሳሉ፣ “ይህን ያደረገው የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ነው” አሉ፡፡ 30 የዚያን ጊዜ የከተማው ሰዎች ኢዮአስን እንዲህ አሉት፣ “የበኣልን መሠዊያ አፍርሶአልና፣ በአጠገቡ የነበረውንም አሼራ ሰባብሮታልና እንዲሞት ልጅህን አውጣ፡፡” 31 ኢዮአስም ለተቃወሙት በሙሉ እንዲህ አላቸው፣ “ለበኣል ትምዋገቱለታላችሁን? እርሱን ታድኑታላችሁን? ለእርሱ የሚምዋገትለት ሁሉ እስከ ነገ ጠዋት ይገደል፡፡ በኣል አምላክ ከሆነ፣ መሠዊያውን ሲያፈርሱበት ራሱን ይከላከል፡፡ 32 ስለዚህም በዚያ ቀን ጌዴዎን “ይሩበኣል” የሚል ስም ተሰጠው፣ ምክንያቱም እርሱ “በኣል ራሱን ይከላከል” ብሏልና፣ ጌዴዎን መሠዊያውን አፍርሶአልና፡፡ 33 ምድያማውያንና አማሌቃውያን ሁሉ፣ የምሥራቅም ሰዎች አንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ ዮርዳኖስን ተሻግረው በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ ሰፈሩ፡፡ 34 ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ጌዴዎንን ሊረዳው በእርሱ ላይ ወረደ፡፡ ጌዴዎንም ቀንደ መለከት ነፋ፣ የአቢዔዝር ጎሳ ሰዎች ይከተሉት ዘንድ ጠራቸው፡፡ 35 እርሱም ወደ ምናሴ ነገድ ሁሉ መልክተኞችን ሰደደ፣ እነርሱም ደግሞ እንዲከተሉት ተጠርተው ነበር፡፡ መልክተኞችንም ወደ አሴር፣ ዛብሎንና ንፍታሌምም ላከ፣ እነርሱም እርሱን ሊየገኙት ሄዱ፡፡ 36 ጌዴዎንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፣ “እንደ ተናገርኸው እስራኤልን ለማዳን እኔን የምትጠቀምብኝ ከሆነ 37 ተመልከት፣ በአውድማው ላይ የበግ ጠጕር ባዘቶ አኖራለሁ፡፡ በጠጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆንና በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፣ የዚያን ጊዜ እንደተናገርኸው አንተ እስራኤልን ለማዳን እንደምትጠቀምብኝ አውቃለሁ፡፡” 38 እንዲሁም ሆነ፣ ጌዴዎን በነጋው ማልዶ ተነሣ፣ ጠጕሩንም በአንድ ላይ ጨመቀው፣ ከጠጕሩም የተጨመቀው ጠል አንድ ቆሬ ለመሙላት በቂ ሆነ፡፡ 39 ጌዴዎንም እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፣ “አትቈጣኝ፣ አንድ ጊዜ እንደገና እናገራለሁ፡፡ እባክህ፣ የጠጉሩ ባዘቶ በመጠቀም አንድ ተጨማሪ ሙከራ እንዳደርግ ፍቀድልኝ፡፡ በዚህ ጊዜ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ይሁን፣ በምድሩና በዙርያውም ሁሉ ላይ ደግሞ ጠል ይሁን፡፡” 40 እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት የጠየቀውን አደረገ፡፡ ጠጕሩ ደረቅ ነበረ፣ በምድሩም ሁሉ ላይ ጠል ነበረ፡፡
የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው ፍርዱን ወይም ምዘናውን ነው። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ፍርድ ክፉ የሆነውን” ወይም “እግዚአብሔር ክፉ ነው ያለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድያማውያን” የሚወክለው የምድያምን ሰዎች ነው። በተጨማሪም፣ “እጅ” መቆጣጠርን ይወክላል። አ.ት፡ “የምድያም ሰዎች መቆጣጠራቸው” ወይም “የምድያማውያን መቆጣጠር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የምድያም ኃይል” የሚያመለክተው የምድያም ሰዎችን ነው። አ.ት፡ “የምድያም ሰዎች ከእስራኤል ሰዎች ይልቅ እጅግ በርትተው ስለነበር አስጨነቋቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሊያስጠልል የሚችል በዐለታማ ሸንተረር ላይ የሚገኝ ስፍራ
“ሰራዊቱ ይሰፍር ነበር” ወይም “ሰራዊቱ ድንኳኑን ይተክል ነበር”
የምድያም ምድር በቀይ ባህር አቅራቢያ ከእስራኤል ምድር በስተደቡብ ነበር። ከምድያም ወደ እስራኤል የሚደረግ ጉዞ በሚነገርበት ጊዜ “ወጥተው በሚመጡበት” የሚለውን ሐረግ መጠቀም የተለመደ ነበር። አ.ት፡ “ምድያማውያን ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ወደ እስራኤል ምድር በሚያመጡበት ጊዜ ሁሉ”
ምድያማውያን እጅግ ብዙ ሆነው ይመጡ ስለነበርና ከብቶቻቸው የሚበቅለውን ነገር ሁሉ ይበሉት ስለነበር ከአንበጣ መንጋ ጋር ተነጻጽረዋል።
ይህ ቁጥሩ በጣም ብዙ መሆኑን ለማሳየት የቀረበ ግነት ነው። (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድያም” የሚወክለው የምድያምን ሕዝብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንዲረዳቸው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድያም” የሚወክለው የምድያምን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “በምድያማውያን ምክንያት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ከግብፅ መርቼ አወጣዃችሁ”
ሙሴ ስለ ግብፅ ሲናገር ሰዎች ባሪያዎችን እንደሚያቆዩበት ቤት ይቆጥረዋል። አ.ት፡ “ባሪያዎች የነበራችሁበት ስፍራ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
በዚህ ሐረግ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም ቁጥጥርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ድምፄን” የሚወክለው እግዚአብሔር ያዘዘውን ትዕዛዝ ነው። አ.ት፡ “ትዕዛዜን አልጠበቁም” ወይም “አልታዘዙኝም”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የታሪኩ መስመር የተገታበትን ለማመልከት ነው። ተራኪው እዚህ ጋ የታሪኩን አዲስ ክፍል መናገር ይጀምራል።
ይህ የከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በቀድሞ አባታቸው በአቢዔዝር ስም የሚጠሩ የሕዝብ ወገን ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የ “መውቃት” ሂደት ነው። ጌዴዎን የስንዴውን ምርት ከገለባው ለመለየት ወለሉ ላይ ይወቃ ነበር”
“ወደ እርሱ ሄደ”
ጌዴዎን “ጌታዬ” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው እንግዳ የሆነን ሰው በትህትና ሰላምታ ለመስጠት ነው። እርሱ የሚናገረው በመልአክ ወይም በሰው መልክ ከታየው ከእግዚአብሔር ጋር እንደሆነ አልተገነዘበም።
እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ የነገረውን እንግዳ ለመገዳደር ጌዴዎን ጥያቄ ያቀርብለታል። ደግሞም፣ በቀጥታ የተጠቀሰው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ ባልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር አባቶቻችንን ከግብፅ ባወጣቸው ጊዜ ስላደረገላቸው የነገሩንን ዓይነት ተአምር አንድም አላየንም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ፣ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
“በ… ሰጥቶናል” የሚለው ሐረግ እስራኤላውያን እንዲሸነፉ እግዚአብሔር ፈቅዷል ማለት ነው። አ.ት፡ “ምድያማውያን እንዲያሸንፉን ፈቅዷል”
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም ቁጥጥርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድያም” የሚወክለው የምድያምን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “በምድያማውያን”(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እግዚአብሔር ወደ ጌዴዎን ተመልክቶ”
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም ቁጥጥርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድያም” የሚወክለው የምድያምን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “በምድያማውያን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንደ ላከው ለማስረገጥ በጥያቄ መልክ ይጠቀማል። እዚህ ጋ “መላክ” ማለት እግዚአብሔር ጌዴዎንን ለአንድ ግልጽ ለሆነ ሥራ ሾሞታል ማለት ነው። አ.ት፡ “የምልክህ እኔ እግዚአብሔር ነኝ!” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
አሁን ጌዴዎን ሰውየውን በመሳፍንት 6፡13 ላይ እንዳደረገው “ጌታዬ” ከማለት ይልቅ “ጌታው” ብሎ ይጠራዋል። እዚህ ጋ ጌዴዎን እየተነጋገረ ያለው ከእግዚአብሔር ጋር መሆኑን ያወቀ ወይም የጠረጠረ ይመስላል።
ጌዴዎን እስራኤላውያንን መታደግ እንደሚችል እንደማያስብ አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ያቀርባል። አ.ት፡ “እስራኤላውያንን በፍጹም ልታደጋቸው አልችልም!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“እኔንና ቤተሰቤን ተመልከትና ትክክል መሆኔን ታያለህ”
“ከምናሴ ነገድ ውስጥ”
እዚህ ጋ “ቤት” የሚወክለው ቤተሰብን ነው። አ.ት፡ “በአባቴ ቤተሰብ ውስጥ“ ወይም “በቤተሰቤ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ከአንተ ጋር” የሚለው ሐረግ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን እግዚአብሔር ጌዴዎንን ይረዳዋል፣ ይባርከዋልም ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሙሉውን ትርጉም በይበልጥ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “ከአንድ ሰው ጋር የምትዋጋውን ያህል በቀላሉ”
“በፊት ለፊትህ አድርገው”
ዘመናዊ መስፈሪያ መጠቀም ካስፈለገ ይህን ማድረግ የሚቻልበት አንድ መንገድ አለ። አ.ት፡ “ከ22 ሊትር ዱቄት ጋር”
እንደ ሥጋ ያለ የተቀቀለ ምግብ ያለበት ውሃ።
“ለእግዚአብሔር መልአክ አቀረበለት”
ይህ ከእግዚአብሔር መልአክ ጋር አንድ ነው። አ.ት፡ “በመልአክ መልክ የተገለጠ አግዚአብሔር” ወይም “እግዚአብሔር”
በ6፡11-24 እግዚአብሔር በመልአክ መልክ ለጌዴዎን ተገልጦለታል። ይህንን በመሳፍንት 6፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ተሰወረበት”
በ6፡11-24 እግዚአብሔር በመልአክ መልክ ለጌዴዎን ተገልጦለታል። ይህንን በመሳፍንት 6፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እዚህ ጋ “ሆይ” የሚለው ቃል ጌዴዎን እጅግ መፍራቱን ያሳያል።
ይህ ሐረግ ለእርስ በእርሳቸው ቅርበት ያላቸውን ሁለት ሰዎች ያመለክታል። አ.ት፡ “በእርግጥ የእግዚአብሔርን መልአክ አይቻለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ጌዴዎንን ከሰማይ ተናገረው።
ይህ ማለት መጽሐፈ መሳፍንት የተጻፈበት ጊዜ ማለት ነው።
የዚህን ከተማ ስም በመሳፍንት 6፡11 እንዳደረግከው በተመሳሳይ ተርጉመው።
የዚህን የሕዝብ ወገን ስም በመሳፍንት 6፡11 እንዳደረግከው ተርጉመው።
“ሁለተኛው” የሚለው ቃል የመቁጠሪያ ቁጥር “ሁለት” ነው። አ.ት፡ “ሌላ ወይፈን”
“በበኣል መሠዊያ አጠገብ ያለውን”
የዖፍራ ከተማ በኮረብታ አናት ላይ ነበረች። እስራኤላውያን ከምድያማውያን ለመደበቅ ወደዚያ ሸሹ።
“ድንጋዮቹን ሥርዓት ባለው መልኩ አስቀምጣቸው” ወይም “በአግባቡ አነባብረው”
ይህ እግዚአብሔር በመሳፍንት 6፡25-26 ላይ የሰጠውን ትዕዛዝ ያመለክታል።
“ከአልጋው ተነሣ” ወይም “ነቃ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው የበኣልን መሠዊያ እንዳፈረሰ፣ በአጠገቡ የነበረውን የአሼራን ምስል እንደሰባበረውና መሠዊያ ሠርቶ በእርሱ ላይ ሁለተኛውን ወይፈን እንደ ሠዋ አስተዋሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በሞት ልንቀጣው ይገባናል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ኢዮአስ ሰው ለአምላክ ጠበቃ መሆን እንደማይኖርበት አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ያቀርብላቸዋል። አ.ት፡ “ለበኣል ጠበቃ ልትሆኑት አይገባም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“ትከላከሉለታላችሁ” ወይም “ሰበብ ትሰጡለታላችሁ”
ኢዮአስ ሰው አምላክን መታደግ እንደማይኖርበት አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ያቀርብላቸዋል። አ.ት፡ “በኣልን ማዳን የለባችሁም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ትርጉሙም፣ “በኣል ራሱን ይከላከል” የሚል ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ኢዮአስ ብሏልና”
ይህ ቃል እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው የታሪኩ መስመር መገታቱን ለማመልከት ነው። እዚህ ጋ ተራኪው የታሪኩን አዲስ ክፍል መናገር ይጀምራል።
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉሙ በይበልጥ መብራራት ይችላል። አ.ት፡ “እንደ ሰራዊት በአንድ ላይ ተሰበሰቡ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ጌዴዎንን ተቆጣጠሩት” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የዚህን የሕዝብ ወገን ስም በመሳፍንት 6፡11 ላይ በተረጎምከው መልኩ ተርጉመው።
“ወደ ጦርነት” የሚሉት ቃላት ግልጽ ናቸው። አ.ት፡ “ወደ ጦርነት እንዲከተሉት”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እንዲከተሉት ይጠራቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁሉ የእያንዳንዱን ጎሳ ሕዝብ ይወክላሉ። አ.ት፡ “ወደ አሴር፣ ዛብሎንና ንፍታሌም ጎሳ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሱፍነት ያለው የበግ ጠጉር
ሌሊት ላይ እጽዋት ላይ የሚቆይ ውሃ
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉሙ በይበልጥ መብራራት ይችላል። አ.ት፡ “ይህ ከአንተ ዘንድ ምልክት ይሆናል፣ ከዚያም እንደምታድን ዐውቃለሁ”
“ጌዴዎን ከአልጋው ተነሣ”
ውሃው እንዲወጣለት አንድን ነገር ጠምዝዞ መጭመቅ
1 ከዚያም ጌዴዎን የተባለው ይሩበኣልና ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ በጠዋት ተነሡ፣ በሐሮድ ምንጭ አጠገብም ሰፈሩ፡፡ የምድያምም ሰፈር ከእነርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ፡፡ 2 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ምድያማውያንን እንድታሸንፍ የሚያደርጉህ እጅግ በጣም ብዙ ወታደሮች አሉኝ፡፡ ‘የራሳችን ኃይል አዳነን’ ብለው እስራኤል እንዳይታበዩብኝ እርግጠኛ ሁን፡፡ 3 ስለዚህም አሁን፣ በሕዝቡ ጆሮዎች እንዲህ ብለህ ተናገር፣ “ማንም የፈራ ቢኖር፣ ማንም የደነገጠ ቢኖር፣ የገለዓድን ተራራ ትቶ ይመለስ፡፡” ስለዚህ 22, 000 ሰዎች ተመለሱ፣ 10, 000 ሰዎችም ቀሩ፡፡ 4 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ሕዝቡ አሁንም ገና ብዙ ነው፡፡ ሕዝቡን ወደ ውኃ ውሰዳቸው፣ በዚያም ቁጥራቸውን ጥቂት አደርግልሃለሁ፡፡ እኔ ‘ይህ ከአንተ ጋር ይሄዳል’ ካልሁህ እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል፤ ነገር ግን እኔ ‘ይህ ከአንተ ጋር አይሄድም’ ካልሁህ እርሱ ከአንተ ጋር አይሄድም፡፡” 5 ስለዚህ ጌዴዎን ሕዝቡን ወደ ውኃ ወሰዳቸው፣ እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ውሻ እንደሚጠጣ ውኃ የሚጠጣውን ሁሉ፣ ውኃ ለመጠጣት በጕልበታቸው ከሚንበረከኩት ሰዎች መካከል ለይ፡፡” 6 ሦስት መቶ ሰዎች ውኃ እንደ ውሻ ጠጡ፡፡ የቀሩት ሰዎች ግን ውኃ ለጠጡ በጉልበታቸው ተንበረከኩ፡፡ 7 እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፣ “ውኃን እንደ ውሻ በጠጡት በሦስት መቶ ሰዎች ከምድያማውያን አድንሃለሁ፣ በእነርሱም ላይ ድል እሰጥሃለሁ፡፡ ሌሎቹ ሰዎች በሙሉ ወደ ስፍራቸው ይመለሱ፡፡” 8 ስለዚህ የተመረጡት ሰዎች ስንቃቸውንና ቀንደ መለከታቸውን ወሰዱ፡፡ ጌዴዎን የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ፣ እያንዳንዱን ሰው ወደ ድንኳናቸው ሰደዳቸው፣ ነገር ግን ሦስቱን መቶ ሰዎች በእርሱ ዘንድ አቆያቸው፡፡ የምድያምም ሰፈር ከእርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበረ፡፡ 9 በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ተነስ! ሰፈራቸውን ምታ፣ በእነርሱ ላይ እኔ ድል እሰጥሃለሁና፡፡ 10 ነገር ግን አንተ ወደ ለመውረድ ከፈራህ፣ ከአገልጋይህ ከፉራ ጋር ወደ ሰፈሩ ውረድ፣ 11 የሚናገሩትንም አድምጥ፣ ከዚያም በኋላ ሰፈሩን ለመውጋት ድፍረት ታገኛለህ፡፡” ስለዚህ ጌዴዎን ከአገልጋዩ ከፉራ ጋር በሰፈሩ ወደ ነበሩት ጠባቂዎች ወረዱ፡፡ 12 ብዛታቸውም እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና የምሥራቅም ሰዎች ሁሉ በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፡፡ የግመሎቻቸውም ብዛት መቁጠር አይቻልም ነበር፤ ቁጥራቸው በባህር ዳርቻ ካለው አሸዋ ይልቅ የሚበልጥ ነበር፡፡ 13 ጌዴዎን በዚያ በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕልምን ለጓደኛው ሲነግረው ነበር፡፡ ሰውየውም እንዲህ አለ፣ “ተመልከት! ሕልም አለምሁ፣ አንዲት ክብ የገብስ ቂጣ ወደ ምድያም ሰፈር ተንከባልላ ስትወርድ አየሁ፡፡ ወደ ድንኳኑም ደረሰች፣ እስኪወድቅ ድረስም በጣም መታችው ከዚህ የተነሳ ወደቀ፣ ደግሞም ተገለበጠ፣ ስለዚህም ድንኳኑ ተጋደመ፡፡” 14 ሌላኛውም ሰው እንዲህ አለ፣ “ይህ ነገር ከእስራኤል ሰው ከኢዮአስ ልጅ ከጌዴዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በምድያምና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ ድል ሰጥቶታል፡፡” 15 ጌዴዎን የሕልሙን ዝርዝርና ትርጓሜውን በሰማ ጊዜ በጸሎት ተደፍቶ ሰገደ፡፡ እርሱም ወደ እስራኤል ሰፈር ሄደና እንዲህ አለ፣ “ተነሱ! እግዚአብሔር በምድያም ሠራዊት ላይ ድል ሰጥተአችኋል፡፡” 16 እርሱም ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፈላቸው፣ ለሁሉም ሰዎች ቀንደ መለከትና ባዶ ማሰሮ፣ በማሰሮውም ውስጥ ችቦ ሰጣቸው፡፡ 17 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “እኔን ተመልከቱ፣ የማደርገውንም አድርጉ፡፡ አስተውሉ! ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በመጣሁ ጊዜ፣ እኔ የማደርገውን እናንተም ታደርጋላችሁ፡፡ 18 እኔና ከእኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከት ስንነፋ፣ እናንተ ደግሞ በሰፈሩ በሁሉም አቅጣጫ ቀንደ መለከታችሁን ንፉና “ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን” ብላችሁ ጩኹ፡፡ 19 ስለዚህ ጌዴዎንና ከእርሱ ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች የመካከለኛው የጥበቃ ሰዓት በተጀመረ ጊዜ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፡፡ ምድያማውያን የጥበቃ ሰዎችን በሚቀይሩበት ጊዜ፣ ቀንደ መለከቶቹን ነፉ፣ በእጃቸውም የነበሩትንም ማሰሮች ሰባበሩ፡፡ 20 ሦስቱም ቡድኖች ቀንደ መለከቶቹን ነፉ፣ ማሰሮችንም ሰበሩ፡፡ በግራ እጃቸው ችቦችን ያዙ፣ በቀኝ እጃቸው ደግሞ ቀንደ መለከቶችን ይዘው ለመንፋት ተዘጋጁ፡፡ እነርሱም “የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰይፍ” ብለው ጮኹ፡፡ 21 ሁሉም ሰው በሰፈሩ ዙሪያ በየቦታው ቆመ፣ የምድያማውያን ሠራዊት ሁሉ ሮጡ፡፡ እነርሱም ጮኹና ሸሹ፡፡ 22 ሦስት መቶውንም ቀንደ መለከቶች በነፉ ጊዜ፣ እግዚአብሔር የእያንዳንዱን ምድያማዊ ሰው ሰይፍ በጓደኛውና በራሳቸው ሰራዊት ሁሉ ላይ አዘጋጀ፡፡ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሺጣ፣ በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ፡፡ 23 የእስራኤል ሰዎች ከንፍታሌም፣ ከአሴርና ከምናሴም ሁሉ ተሰብስበው ምድያምን ከኋላ እየተከተሉ አሳደዱ፡፡ 24 ጌዴዎን መልክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ኮረብታማ አገር ሁሉ በመስደድ እንዲህ አለ፣ “ምድያምን ለመዋጋት ውረዱና እነርሱን ለማስቆም የዮርዳኖስን ወንዝ እስከ ቤትባራም ድረስ ተቆጣጠሩ፡፡” ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰብስበው እስከ ቤትባራና ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ውኃውን ተቆጣጠሩ፡፡ 25 የምድያምን ሁለቱን መሪዎች ሔሬብንና ዜብን ያዙ፡፡ ሔሬብንም በሔሬብ ዓለት ገደሉት፣ ዜብንም በዜብ ወይን መጥመቂያ ላይ ገደሉት፡፡ ምድያማውያንንም አሳደዱ፣ የሔሬብንና የዜብንም ራስ ይዘው በዮርዳኖስ ማዶ ወደነበረው ወደ ጌዴዎን አመጡ፡፡
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ስሙን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“የጦር ሰፈራቸውን አዘጋጁ”
እነዚህ የቦታዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድያም” የሚወክለው የምድያማውያኑን ሰራዊት ነው። አ.ት፡ “የምድያማውያን ሰራዊት የጦር ሰፈራቸውን ከእስራኤላውያን ሰራዊት በስተሰሜን ባለ ስፍራ አደረጉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ድል” የሚለው ቃል የነገር ስም ሲሆን እንደ ግሥ ወይም ቅጽል ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ምድያማውያንን ታሸንፋቸው ዘንድ እንድፈቅድልህ” ወይም “በምድያማውያን ላይ ባለ ድል ላደርግህ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት”
እዚህ ጋ “ኃይል” የሚወክለው ሕዝቡን ራሳቸውን ነው። አ.ት፡ “ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ራሳችንን አድነናል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ “በዚህ ሰዓት” ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ትኩረትን ወደሚቀጥለው አስፈላጊ ጉዳይ ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል።
እዚህ ጋ “ጆሮ” የሰውን ሁለንተና ያመለክታል። አ.ት፡ “ለሕዝቡ ዐውጅ”
ሁለቱም ሐረጎች ያላቸው ትርጉም አንድ ነው። (ተመሳሳይነት የሚለውን ተመልከት)
ይህ ቃል የሚገልጸው አንድ ሰው ከፍርሐት የተነሣ ሊቆጣጠረው በማይችለው ሁኔታ መንቀጥቀጡን ነው። አ.ት፡ “በፍርሐት የሚንቀጠቀጥ”
ወዴት እንደሚሄድ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “ወደ ቤቱ ይመለስ”
ይህ በገለዓድ አውራጃ የሚገኝ ተራራ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“22,000” (ቁጥሮችን ተመልከት)
በውስጠ ታዋቂነት “ሰዎች” ወይም “ወንዶች” የሚል ቃል መኖሩን ይረዷል። አ.ት፡ “10,000 ሰዎች ቀሩ” ወይም “10,000 ወንዶች ቀሩ”
x
እዚህ ጋ “ቁጥር” ሰራዊትን ይወክላል። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በበለጠ ግልጽ መሆን ይችላል። አ.ት፡ “በዚያ የሰራዊቱ ቁጥር እንዲቀንስ ማንን ወደ ቤቱ እንደምትመልሰው አሳይሃለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የሚለውን ተመልከት)
“አመጣ” የሚለው ቃል “ወሰደ” ወይም “መራ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። (ሂድ እና ና የሚለውን ቃል ተመልከት)
በምላስ በመላስ መጠጣት
“300 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“300 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አንተ” ብዙ ቁጥር ሲሆን ጌዴዎንና እስራኤላውያንን ያመለክታል።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ስለዚህ እነዚያ እግዚአብሔር የመረጣቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እነርሱ” የሚያመለክተው ሰራዊቱን ትተው የሚመለሱትን የእስራኤል ወታደሮች ነው።
ይህ ቃል እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው የታሪኩ መስመር ለአፍታ ቆም ማለቱን ለማመልከት ነው። እዚህ ጋ ተራኪው የታሪኩን አዲስ ክፍል መናገር ይጀምራል።
እዚህ ጋ “የጦር ሰፈር” የሚያመለክተው የምድያማውያንን ሰራዊት በሙሉ ነው። “ድል” የሚለው ቃል የነገር ስም ሲሆን እንደ ግሥ ወይም ቅጽል ሆኖ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እንድታሸንፋቸው ልረዳህ ስለሆነ ምድያማውያንን በጦር ሰፈራቸው አጥቃቸው” ወይም “በእነርሱ ላይ ድል አድራጊ እንድትሆን ስለማደርግ ምድያማውያንን በጦር ሰፈራቸው አጥቃቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
የታወቀውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ወርዶ ለማጥቃት ፈራ”
ይህ የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የምትሰማው ያበረታሃል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ወታደሮች የጠላትን ሰራዊት ለመቆጣጠር የሚቆሙበት አካባቢ ዳርቻ
እዚህ ጋ “ደመና” ማለት መንጋ ነው። ደራሲው ምን ያህል ወታደሮች እንደነበሩ አጽንዖት ለመስጠት የአንበጣ መንጋ በማለት ስለ ሰራዊቱ ይናገራል።
ደራሲው በጣም ብዙ ግመሎች መኖራቸውን በአጽንዖት ሲገልጽ ግነትን ይጠቀማል። ( ግነትና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ግመሎቻቸው ማንም ሊቆጥራቸው ከሚችለው በላይ ነበሩ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የጌዴዎን ሰይፍ” የሚያመለክተው አጥቂውን የጌዴዎንን ሰራዊት ነው። አ.ት፡ “በሕልምህ ያየኸው የገብስ እንጎቻ የጌዴዎን ሰራዊት መሆን አለበት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ወደፊታዊ ሁነት እንደ አላፊ ሁነት ሆኖ ተነግሯል። ይህ በእርግጠኝነት የሚፈጸም ስለመሆኑ አጽንዖት ይሰጣል። አ.ት፡ “በእርግጥ እስራኤላውያን ምድያማውያንን እንዲያሸንፉ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል”
“300 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
በውስጠ ታዋቂነት “እንዋጋለን” ማለት ነው። አ.ት፡ “ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን እንዋጋለን!”
“100 ሰዎች” (ቁጥሮችን ተመልከት)
የእኩለ ሌሊት ጅማሬ ከምሽቱ 4 ሰዓት ገደማ ይሆናል።
እዚህ ጋ “ሰይፍ” የሚያመለክተው ውጊያቸውን ነው። አ.ት፡ “ለእግዚአብሔርና ለጌዴዎን እንዋጋለን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“300 መለከቶች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ሰይፍ” የሚያመለክተው ሰይፍ በመጠቀም ማጥቃታቸውን ነው። አ.ት፡ “እያንዳንዱ ምድያማዊ ሰው ባልንጀራው ከሆነው ወታደር ጋር እንዲዋጋ እግዚአብሔር አደረገ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የመንደሮችና የከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ጌዴዎን እስራኤላውያንን ከንፍታሌም፣ አሴርና ከምናሴ ነገድ ሁሉ ጠራ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የእነስተኛ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“የዮርዳኖስን ወንዝ አካባቢ እስከ ቤት ባራ ደቡብ ድረስ ተቆጣጠሩ”
እስራኤላውያን ሔሬብና ዜብን በዚያ ከገደሉ በኋላ አካባቢዎቹ እነዚህ ስሞች ተሰጥተዋቸው ነበር።
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
1 የኤፍሬም ሰዎች ለጌዴዎን እንዲህ አሉት፣ “ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ምንድር ነው? ምድያምን ለመዋጋት በሄድህ ጊዜ እኛን አልጠራኸንም?” ከእርሱም ጋር በኃይል ተጣሉ። 2 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ከእናንተ ጋር ሲነጻጸር አሁን እኔ ያደረግት ምንድን ነው? ከኤፍሬም የወይን ቃርሚያ ይልቅ የአቢዔዝር ሙሉ የወይን መከር አይሻልምን? 3 እግዚአብሔር በምድያም መሪዎች በሔሬብና በዜብ ላይ ድልን ሰጥቶአችኋል! ከእናንተ ጋር ሲነጻጸር እኑ ምን ፈጸምሁ?” ይህን በተናገረ ጊዜ ቍጣቸው በረደ። 4 ጌዴዎን ከእርሱ ጋር ከነበሩት ከሦስቱ መቶ ሰዎች ጋር ወደ ዮርዳኖስ መጣና ተሻገረ፡፡ እጅግ በጣም ደክመው ነበር፣ ይሁን እንጂ ያሳድዱ ነበር። 5 እርሱም ለሱኮት ሰዎች እንዲህ አላቸው፣ “ደክመዋልና እባካችሁ ለተከተሉኝ ሰዎች እንጀራ ስጡአቸው፣ እኔም የምድያምን ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን እያሳደድሁ ነው፡፡” 6 የሱኮትም መሪዎች እንዲህ አሉ፣ “ዛብሄልንና ስልማናን በጉልበትህ አሸነፍኃቸውን?” እኛ ለሠራዊትህ እንጀራ ለምን እንደምንሰጥ አናውቅም? 7 ጌዴዎንም እንዲህ አለ፣ “እግዚአብሔር በዛብሄልና በስልማና ላይ ድል በሰጠኝ ጊዜ፣ እኔ በምድረ በዳ እሾህና በኵርንችት ሥጋችሁን እቦጫጭቀዋለሁ፡፡” 8 ከዚያም ወደ ጵኒኤል ወጣና በተመሳሳይ መንገድ በዚያ ለሚገኙ ሰዎች ተናገራቸው፣ ነገር ግን የጵንኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለሱለት። 9 እርሱም የጵኒኤልን ሰዎች ደግሞ እንዲህ አላቸው፣ “በሰላም በተመለስሁ ጊዜ፣ ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ፡፡ 10 ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር፣ ከምሥራቅም ሰዎች ሠራዊት ሁሉ የቀሩ 15, 000 ያህል ሰዎች በቀርቀር ነበሩ፡፡ በሰይፍ ለመዋጋት ስልጠና የወሰዱ መቶ ሀያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና፡፡ 11 ጌዴዎንም ዘላኖች ባሉበት መንገድ በኖባህና በዮግብሃ አልፎ ወደ ጠላት ሰፈር ሄደ፡፡ እርሱም የጠላትን ሰራዊት አሸነፈ፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነት አደጋ ይገጥመናል ብለው አላሰቡም ነበርና፡፡ 12 ዛብሄልና ስልማናም ሸሹ፣ ጌዴዎንም ባሳደዳቸው ጊዜ ሁለቱንም የምድያም ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ያዛቸው፣ ሠራዊታቸውንም ሁሉ ድንጋጤ ላይ ጣላቸው፡፡ 13 የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎንም በሔሬስ ዳገት በኩል በማለፍ ከጦርነት ተመለሰ፡፡ 14 እርሱም ከሱኮት ሰዎች አንድ ወጣት ይዞ ጠየቀውና ከእርሱ ምክር ፈለገ፡፡ ወጣቱም የሱኮትን መሪዎችና ሽማግሌዎች ሰባ ሰባት ሰዎች እነማን እንደሆኑ ገለጸለት። 15 ጌዴዎንም ወደ ሱኮት ሰዎች መጣና እንዲህ አላቸው፣ “‘ዛብሄልንና ስልማናን በጉልበትህ አሸነፍኃቸውን? እኛ ለሠራዊትህ እንጀራ መስጠት እንዳለብን አናውቅም?’ ብላችሁ ያላገጣችሁብኝ ዛብሄልና ስልማና ተመልከቱአቸው፡፡” 16 ጌዴዎንም የከተማይቱን ሽማግሌዎች ያዛቸው፣ የሱኮትንም ሰዎች በምድረ በዳ እሾህና በኵርንችት ገረፋቸው፡፡ 17 የጵኒኤልንም ግንብ አፈረሰ፣ የዚያችን ከተማ ሰዎችን ገደለ፡፡ 18 ጌዴዎንም ለዛብሄልና ለስልማና እንዲህ አላቸው፣ “በታቦር የገደላችኋቸው ሰዎች ምን ዓይነት ሰዎች ነበሩ?” እነርሱም፣ “እንደ አንተ ያሉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዳቸው የንጉሥ ልጅ ይመስላሉ” አሉት፡፡ 19 ጌዴዎንም “እነርሱ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ነበሩ፡፡ በሕይወት እንዲኖሩ አድናችኋቸው ቢሆን ኖሮ፣ ሕያው እግዚአብሔርን፣ እኔ አልገድላችሁም ነበር” አለ፡፡ 20 ለበኵር ልጁ ለዬቴር እንዲህ አለው፣ “ተነሳና ግደላቸው!” ነገር ግን ወጣቱ ልጅ ስለፈራ ሰይፉን አልመዘዘም፣ ምክንያቱም ገና ወጣት ልጅ ነበረና፡፡ 21 የዚያን ጊዜ ዛብሄልና ስልማና እንዲህ አሉ፣ “አንተ ተነሳና ግደለን! የሰው ኃይሉ እንደ ሰውነቱ ነውና፡፡” ጌዴዎንም ተነሥቶ ዛብሄልንና ስልማናን ገደላቸው፡፡ በግመሎቻቸውም አንገት ላይ የነበሩትን ጌጦች ወሰደ፡፡ 22 የእስራኤልም ሰዎች ጌዴዎንን “አንተ ግዛን፣ አንተ፣ የአንተ ልጅና የልጅ ልጆችህ ግዙን፣ ምክንያቱም አንተ ከምድያም ብርታት አድነኸናልና፡፡” 23 ጌዴዎንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “እኔ በእናንተ ላይ አልገዛም፣ ልጄም በእናንተ ላይ አይገዛም፣ እግዚአብሔር ይገዛችኋል አላቸው፡፡ 24 ጌዴዎን ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፡- እያንዳንዳችሁ ከምርኮአችሁ ጕትቻችሁን እንድትሰጡኝ እለምናችኋለሁ፡፡” (ምድያማውያን የወርቅ ጕትቻ ነበራቸው ምክንያቱም እነርሱ እስማኤላውያንም ነበሩና፡፡) 25 እነርሱም፣ “ለአንተ ልንሰጥህ ደስተኞች ነን” አሉት፡፡ እነርሱም ልብስ አነጠፉና ሁሉም ሰው የምርኮውን ጕትቻ በዚያ ላይ ጣለ፡፡ 26 እርሱ የጠየቀው የወርቅ ጕትቻ ክብደት 1, 700 ሰቅል ወርቅ ነበር፡፡ ይህም ምርኮ ከጌጣ ጌጦቹ ሌላ የአንገት ጌጥ፣ የምድያምም ነገሥታት ከሚለብሱት ሐምራዊ ልብስ፣ እንደዚሁም በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ጌጦች ሌላ ነበረ፡፡ 27 ጌዴዎንም ከጉትቻዎቹ ባገኘው ወርቅ ኤፉድ ሠራና በከተማው፣ በዖፍራ አኖረው፣ እስራኤልም ሁሉ እርሱን በማምለክ አመነዘረበት፡፡ ለጌዴዎንና በቤቱም ላሉት ወጥመድ ሆነባቸው፡፡ 28 ስለዚህም ምድያም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ተዋረደ፣ ራሳቸውንም እንደገና አላነሡም፡፡ በጌዴዎንም ዘመን ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም ሆነች። 29 የኢዮአስም ልጅ ይሩበኣል ሄደና በራሱ ቤት ተቀመጠ። 30 ጌዴዎንም ብዙ ሚስቶች ነበሩትና ሰባ ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡ 31 በሴኬም የነበረችው ቁባቱም ወንድ ልጅ ወለደችለት፣ ጌዴዎንም ስሙን አቤሜሌክ ብሎ ጠራው፡፡ 32 የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን በመልካም የሽምግልና ዕድሜ ሞተ፣ በአቢዔዝራውያን ጎሳ በሆነው በዖፍራ በነበረው በአባቱ በኢዮአስ መቃብር ተቀበረ፡፡ 33 ጌዴዎን ከሞተ በኋላ ብዙ ሳይቆይ እንዲህ ሆነ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንደገና ተመለሱ፣ የበኣልን አማልክት በማምለክ አመነዘሩ፡፡ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ፡፡ 34 የእስራኤልም ሕዝብ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከነበሩት ከጠላቶቻቸው ኃይል ያዳናቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን አላሰቡትም፡፡ 35 እነርሱም ለእስራኤል ስላደረገው በጎ ነገር አስበው ለይሩበኣል (የጌዴዎን ሌላኛው ስም ነው) ውለታ ለመመለስ ቃል ኪዳናቸውን አልጠበቁም፡፡
የኤፍሬም ነገድ ሰዎች በሰራዊቱ ውስጥ እነርሱን ባለማካተቱ በዚህ ምላሽ በማይፈልግ ጥያቄ ጌዴዎንን ሲወቅሱት ነበር። ይህ እንደ መግለጫ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “በአግባቡ አላየኸንም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድያም” የሚወክለው የምድያማውያንን ሰራዊት ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ከእርሱ ጋር በቁጣ ተከራከሩ” ወይም “ክፉኛ ወቀሱት”
ጌዴዎን ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው የኤፍሬምን ሰዎች ለማክበር ነው። አ.ት፡ “እናንተ ካደረጋችሁት ጋር ሲነጻጸር እኔ ያደረግሁት በጣም ጥቂት ነው” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ጌዴዎን በዚህ ምላሽ በማያስፈልገው ጥያቄ አማካይነት የኤፍሬምን ሰዎች ያበርዳቸው ነበር። አ.ት፡ “እኛ የአቢዔዝር ተወላጆች ከሰበሰብነው ምርት በሙሉ ያለ ምንም ጥርጥር እናንተ የኤፍሬም ሰዎች የለቀማችሁት ወይን የተሻለ ነው!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
የጌዴዎንና የሰራዊቱ ምድያማውያንን ማሸነፍ የወይን ምርት እንደመሰብሰብ ተቆጥሮ ተነግሯል። የኤፍሬም ሰዎች በጦርነቱ መጨረሻ ሔሬብና ዜብን መግደላቸው ከመከር በኋላ የወይን ቃርሚያን እንደ ለቀሙ ተቆጥሮ ተነግሮላቸዋል። አ.ት፡ “እኛ የአቢዔዝር ተወላጆች በመጀመሪያ ካደረግነው ይልቅ እናንተ የኤፍሬም ሰዎች በጦርነቱ መጨረሻ ላይ ያደረጋችሁት ይበልጥ ታላቅ ነው” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከጌዴዎን ቅድም አያቶች የአንዱ ስም ነው። ጌዴዎን ስሙን ያገኘው ከአቢዔዝር ተወላጆችና ከምድራቸው ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 7፡25 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ጌዴዎን ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው የኤፍሬምን ሰዎች ለማክበር ነው። ይህ እንደ መግለጫ ሊገለጽ ይችላል። አ.ት፡ “እኔ ካደረግሁት ይልቅ እናንተ ያደረጋችሁት ይበልጥ ታላቅ ነው” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“ቀነሰ”
“300 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ማሳደድ” የሚለው ቃል የነገር ስም ሲሆን እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ጠላቶቻቸውን ማባረራቸውን ቀጠሉ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
መሪዎቹ ጥያቄ የሚያቀርቡት እስራኤላውያኑ ዛብሄልንና ስልማናን ገና ያለመማረካቸውን አጽንዖት ለመስጠት ነው። አ.ት፡ “እስካሁን ዛብሄልና ስልማናን አልማረክኻቸውም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጆች” የሚያመለክተው ሙሉ ሰውነትን ነው።
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
መሪዎቹ የሚጠይቁት ለእስራኤላውያኑ እንጀራ የሚሰጡበት ምንም ምክንያት እንደሌለ አጽንዖት ለመስጠት ነው። አ.ት፡ “ለሰራዊትህ እንጀራ የምንሰጥበትን አንዳች ምክንያት አላገኘንም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ መብራራት ይችላል። አ.ት፡ “በበረሃ እሾህና አሜከላ ጅራፍ በመሥራት እገርፋችኋለሁ፣ እቆራርጣችኋለሁ”
ስል፣ በሐረግ ወይም ዛፍ ቅርንጫፍ ላይ ጫፉ የሾለና ሰውና እንስሳን ለመቁረጥ የሚችል
እዚህ ጋ በውስጠ ታዋቂነት የሚገኘው “እርሱ” የሚያመለክተው ጌዴዎንን ነው። ጌዴዎን የሚወክለው ራሱንና የሚከተሉትን ወታደሮች ነው። አ.ት፡ “ያንን ስፍራ ተዉ” ወይም “ጌዴዎንና 300 ሰዎቹ ያንን ስፍራ ተዉ”
የቦታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
በውስጠ ታዋቂነት ያለውን መረጃ ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “እዚያም በተመሳሳይ መንገድ ምግብ እንዲሰጡት ጠየቀ” ወይም “እርሱም ደግሞ ምግብ እንዲሰጡት ጠየቃቸው”
ይህ ጠላቶቹን ስለማሸነፉ የሚያመለክት የትህትና አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የምድያማውያንን ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ካሸነፍኩኝ በኋላ”
እዚህ ጋ “እኔ” ጌዴዎንን የሚያመለክት ሲሆን ራሱንና ሰራዊቱን ይወክላል። አ.ት፡ “እኔና የእኔ ሰዎች ይህንን ግምብ እናፈርሰዋለን”
ይህ ቃል እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው የታሪኩ መስመር ለአፍታ ቆም ማለቱን ለማመልከት ነው። እዚህ ጋ ተራኪው የታሪኩን አዲስ ክፍል መናገር ይጀምራል።
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 8፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ይህ የአንድ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“15,000 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በጦርነት የሞቱትን ሰዎች በትህትና የማመላከት መንገድ ነው። አ.ት፡ “ተገድለው ነበር” ወይም “በጦርነት ሞተው ነበር”
“አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ሰይፍ መምዘዝ የሚወክለው በጦርነት ውስጥ በሰይፍ መጠቀምን ነው። ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ ሐረግ የሚያመለክተው በጦርነት ውስጥ በሰይፍ የሚጠቀሙ ወታደሮችን ነው። አ.ት፡ “ሰይፍ የታጠቁ ሰዎች” ወይም “በሰይፍ የሚዋጉ ሰዎች” ወይም 2) ይህ ሐረግ የትኛውንም ወታደር ያመለክታል። አ.ት፡ “ወታደሮች” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ጌዴዎን” የሚወክለው ራሱንና ወታደሮቹን ሁሉ ነው። አ.ት፡ “ጌዴዎንና ወታደሮቹ ወጥተው ሄዱ”
እዚህ ጋ በውስጠ ታዋቂነት ያለው “እርሱ” የሚያመለክተው ጌዴዎንን ራሱንና ወታደሮቹን ሁሉ ነው። አ.ት፡ “ጌዴዎንና ወታደሮቹ አሸነፉ”
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 8፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
አንድ ሰው ማሰብ እንዳይችል ወይም በአግባቡ እንዳይሠራ የሚያስደርገው ታላቅ ፍርሃት ወይም ጭንቀት
ይህ በሁለት ተራራዎች መካከል የሚያልፍ መንገድ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ጌዴዎን ታዳጊውን ወጣት የጠየቀው ጥያቄ በግልጽ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “በከተማው ውስጥ ያሉትን መሪዎች በሙሉ ስማቸውን እንዲነግረው ጠየቀው”
“77 አለቆች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 8፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ጌዴዎን የሱኮት ሰዎች ሊሳለቁበት የጠየቁትን አባባል ይጠቅሳል። አ.ት፡ “ዛብሄልንና ስልማናን ገና ድል አላደረግሃቸውም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ጌዴዎን” የሚወክለው ራሱንና ወታደሮቹን ነው። አ.ት፡ “ጌዴዎንና ወታደሮቹ ወሰዱ - ገረፏቸው - አፈረሱት
ስል፣ በሐረግ ወይም ዛፍ ቅርንጫፍ ላይ የሚገኝ፣ ጫፉ የሾለና ሰውና እንስሳን ለመቁረጥ የሚችል። ይህንን በመሳፍንት 8፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የከተማይቱን ስም በመሳፍንት 8፡8 ላይ በተረጎምከው መልኩ ተርጉመው።
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 8፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
የዚህችን ከተማ ስም በመሳፍንት 4፡6 ላይ በተረጎምክበት መልክ ተርጉመው
“ልክ አንተን ይመስሉ ነበር”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሀይማኖታዊ መሓላ ሲሆን የሚናገረው እውነት መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “ቃል እገባላችኋለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የጌዴዎን ልጅ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “አንድ ሰው ሊያደርገው የሚገባው ሥራው ነው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሁለት ጫፍ ያለው ግማሽ ክብ ቅርጽ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ይህ ቅርጽ የሚሆነው ጨረቃ በጥላ ስትጋረድ ነው።
ማስዋቢያዎች
ይህ የሚያሳየው እርሱ ከሞተ በኋላ የጌዴዎን ተወላጆች እንዲገዟቸው ነው። አ.ት፡ “አንተና አንተ ከሞትክ በኋላም ተወላጆችህ”
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው በእስራኤል ላይ የሆነውን የምድያም ኃይል ነው። አ.ት፡ “ከምድያም ኃይል” ወይም “ከምድያም” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድያም” የሚወክለው የምድያምን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “ከምድያማውያን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ጌዴዎን ለእስራኤል ሰዎች አላቸው”
በጆሮ ላይ የሚደረግ ጌጥ
በማስገደድ የተቀሙ ወይም በጦርነት ከተገደሉ ሰዎች የተወሰዱ ነገሮች
እዚህ ጋ ተራኪው ስለ ምድያማውያን ዳራዊ መረጃ ይናገራል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
ረዘም ካለ ክር የሚሠራና እንደ ኮት በትከሻ ላይ የሚለበስ ልብስ
“አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅል ወርቅ”። ዘመናዊውን የመጠን መለኪያ መጠቀም የሚያስፈልግ ከሆነ ይህንን ማድረግ የሚያስችሉ ሁለት መንገዶች አሉ። አ.ት፡ “18.7 ኪ.ግ ወርቅ” ወይም “ወደ 20 ኪ.ግ የሚጠጋ ወርቅ” (ቁጥሮች እና የመጽሐፍ ቅዱስ ክብደት መለኪያ የሚሉትን ተመልከት)
ይህንን በመሳፍንት 8፡21 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት
በአንገት ሀብል ወይም ክር ላይ የሚንጠለጠሉ ትናንሽ ጌጣጌጦች
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የምድያም ነገሥታት የለበሱት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ጌዴዎን የወርቅ ጉትቻዎቹን ኤፉድ ለመስሪያነት ተጠቀመበት”
የከተማይቱን ስም በመሳፍንት 6፡11 እንዳደረግኸው ተርጉመው።
ይህ አመንዝራነትን በሚመስል መልክ ሐሰተኛ አምላክን ስለ ማምለካቸው ይናገራል። አ.ት፡ “እስራኤላውያን በዚያ ኤፉዱን በማምለካቸው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ሠሩ” ( ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “በሙሉ” በጣም ብዙዎቹ ልብሱን ማምለካቸውን አጽንዖት ለመስጠት የተደረገ ግነት ነው። አ.ት፡ “በእስራኤል በጣም ብዙ ሰዎች ልብሱን አመለኩት” (ግነትና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
ይህ አደን የሚያድን ሰው የሚያጠምደው ወጥመድ ይመስል ጌዴዎንና ቤተሰቡ ኤፉዱን ሊያመልኩት እንደተፈተኑ ያሳያል። አ.ት፡ “ለጌዴዎንና ለቤተሰቡ ፈተና ሆነባቸው” ወይም “ጌዴዎንና ቤተሰቡ እርሱን በማምለክ ኃጢአትን ሠሩ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “በቤቱ” የሚወክለው የጌዴዎንን ቤተሰብ ነው። አ.ት፡ “ለቤተሰቡ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰለዚህ እግዚአብሔር ምድያማውያን በእስራኤል ሕዝብ ፊት እንዲገዙ አደረጋቸው” ወይም “ስለዚህ እስራኤላውያን ምድያማውያንን እንዲያሸንፉ እረዳቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንደገና እስራኤልን አላጠቁም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ምድሪቱ” የሚወክለው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “ስለዚህ እስራኤላውያን በሰላም ኖሩ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
x
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ስሙን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“70 ወንዶች ልጆች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “በጣም በሸመገለ ጊዜ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ቀበሩት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የዚህችን ከተማ ስም በመሳፍንት 6፡11 እንዳደረግኸው ተርጉመው።
የዚህን የሕዝብ ወገን ስም በመሳፍንት 6፡11 እንዳደረግኸው ተርጉመው።
ይህ ሐረግ ጥቅም ላይ የዋለው የታሪኩ አዲስ ክፍል መጀመሩን ለማመልከት ነው። በቋንቋህ ይህንን ማድረግ የሚያስችል መንገድ ካለ ልትጠቀምበት ትችላለህ።
ሕዝቡ እግዚአብሔርን መተዋቸው በአካል ከእርሱ እንደተለዩ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን ማምለካቸውን አቆሙ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሐሰተኛ አማልክትን ማምለካቸው እንደ አመንዝራነት ተቆጥሮ ተነግሯል። አ.ት፡ “በኣልን በማምለክ በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ሠሩ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሐሰተኛ አምላክ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። አ.ት፡ “ከጠላቶቻቸው ኃይል ሁሉ” ወይም “ከጠላቶቻቸው ሁሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“የከበቧቸውን “
እዚህ ጋ “የ…ቤት” የሚወክለው የአንድን ሰው ቤተሰብ ነው። አ.ት፡ “የይሩበአል ቤተሰብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ይህንን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
1 የይሩበኣል ልጅ አቤሜሌክ ወደ እናቱ ዘመዶች ወደ ሴኬም ሄደና ለእነርሱና ለእናቱ ቤተሰብ ጎሳ በሙሉ እንዲህ አላቸው፣ 2 “በሴኬም የሚገኙ መሪዎች በሙሉ ይሰሙ ዘንድ ይህን ተናገሩ፣ ‘ለእናንተ የሚሻለው የትኛው ነው? የይሩበኣል ሰባ ልጆች ሁሉ ቢገዙአችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ?’ እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ የሥጋችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ፡፡” 3 የእናቱም ዘመዶች ስለ እርሱ ለሴኬም መሪዎች ተናገሩ፣ እነርሱም አቤሜሌክን ለመከተል ተስማሙ፣ “እርሱ ወንድማችን ነው” ብለዋልና፡፡ 4 እነርሱም ከበኣልብሪትም ቤት ሰባ ብር ሰጡት፣ አቤሜሌክም እርሱን የተከተሉትን ስርዓት አልበኞችንና ወሮበሎችን ለመቅጠር ተጠቀበመት፡፡ 5 እርሱም ወደ አባቱ ቤት ወደ ዖፍራ ሄደ፣ የይሩበኣልን ልጆች ሰባ ወንድሞቹን በአንድ ድንጋይ ላይ አረዳቸው፡፡ ትንሹ የይሩበኣል ልጅ ኢዮአታም ግን ተሸሽጎ ስለነበር እርሱ ብቻ ተረፈ፡፡ 6 የሴኬምና የቤትሚሎ መሪዎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፣ እነርሱም ሄደው በሴኬም በዓምዱ አጠገብ ባለው በበሉጥ ዛፍ ስር አቤሜሌክን አነገሡት፡፡ 7 ለኢዮአታም ይህን ነገር በነገሩት ጊዜ፣ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ሄደና ቆመ፡፡ ድምፁንም ከፍ አድርጎ ጮኸና እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ የሴኬም መሪዎች፣ እግዚአብሔርም እናንተን ይሰማ ዘንድ፣ እኔን ስሙኝ፡፡ 8 አንድ ጊዜ ዛፎች በእነርሱ ላይ የሚያነግሱት ለመቀባት ሄዱ፡፡ እነርሱም ለወይራ ዛፍ ‘በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡ 9 የወይራ ዛፍ ግን ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ ‘እግዚአብሔርና ሰዎችን ለማክበር የሚጠቅመውን ቅባቴን ትቼ ተመልሼ በሌሎች ዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን?’ 10 ዛፎቹም ለበለስ ዛፍ እንዲህ አሉት፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ፡፡’ 11 ነገር ግን የበለሱ ዛፍ፣ ጣፋጭነቴንና መልካሙን ፍሬዬን ትቼ ተመልሼ በሌሎች ዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን?’ አላቸው፡፡ 12 ዛፎችም ለወይኑ፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡ 13 ወይኑም፣ እግዚአብሔርንና ሰውን ደስ የሚያሰኘውን አዲስ የወይን ጠጄን ትቼ ተመልሼ በዛፎች ላይ ለመወዛወዝ ልሂድን? አላቸው፡፡ 14 ከዚያም ዛፎች ሁሉ የእሾህ ቁጥቋጦን፣ ‘መጥተህ በእኛ ላይ ንገሥ’ አሉት፡፡ 15 የእሾህ ቁጥቋጦውም ዛፎቹን፣ ‘በእውነት እኔን በእናንተ ላይ እንድነግስ ልትቀቡኝ የምትፈልጉ ከሆነ፣ ኑና በጥላዬ ስር ተጠለሉ፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን እሳት ከእሾህ ቁጥቋጦ ይውጣና የሊባኖስንም ዝግባ ያቃጥል’ አላቸው፡፡ 16 አሁን እንግዲህ፣ አቤሜሌክን ባነገሳችሁት ጊዜ በእውነትና በቅንነት አድርጋችሁ ከሆነ፣ ለይሩበኣልና ለቤቱም በጎነት አስባችሁ አድርጋችሁ ከሆነ፣ እንዳደረገውም መጠን ለእርሱ የተገባውን ቀጥታችሁት ከሆነ 17 አባቴ ስለ እናንተ ተዋግቶ እንደነበር፣ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠት፣ ከምድያምም እጅ እናንተን እንዳዳናችሁ አሰባችሁ ማለት ነው 18 ነገር ግን ዛሬ እናንተ በአባቴ ቤት ላይ ተነሥታችኋል፣ በአንድ ድንጋይ ላይ ልጆቹን፣ ሰባ ሰዎችን፣ አረዳችኋቸው፡፡ ከዚያም የሴት አገልጋዩን ልጅ አቤሜሌክን ዘመዳችሁ ስለ ሆነ በሴኬም መሪዎች ላይ እንዲነግስ አደረጋችሁት፡፡ 19 ያንጊዜ ለይሩበኣልና ለቤቱ በእውነትና በቅንነትን አድርጋችሁ ከሆነ፣ እንግዲያው እናንተ በአቤሜሌክ ደስ ሊላችሁ ይገባል፣ እርሱም በእናንተ ደስ ይበለው፡፡ 20 ነገር ግን እንዲህ ባይሆን፣ ከአቤሜሌክ እሳት ይውጣና የሴኬምንም ሰዎችና የቤትሚሎን ቤት ያቃጥል፡፡ ከሴኬምም ሰዎችና ከቤትሚሎ እሳት ይውጣና አቤሜሌክን ያቃጥል፡፡ 21 ኢዮአታምም ሸሽቶ አመለጠ፣ ከዚያም ወደ ብኤር ሄደ፡፡ እርሱም በዚያ ተቀመጠ ምክንያቱም ከአቤሜሌክ ከወንድሙ በጣም ሩቅ ነበረ፡፡ 22 አቤሜሌክም በእስራኤል ላይ ለሦስት ዓመት ገዛ፡፡ 23 እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም መሪዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ፡፡ የሴኬም መሪዎችም በአቤሜሌክ ላይ የነበራቸውን እምነት ጥለው ከዱት፡፡ 24 እግዚአብሔር ይህንን ያደረገው በሰባዎቹ የይሩበኣል ልጆች ላይ የተደረገውን ዓመፅ ለመበቀል ነው፣ ወንድማቸው አቤሜሌክም እነርሱን በመግደሉ ተጠያቂ እንዲሆን ለማድረግ ነው፤ የሴኬም ሰዎችም እርሱ ወንድሞቹን እንዲገድላቸው ስለተባበሩት ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው፡፡ 25 ስለዚህ የሴኬም መሪዎች በኮረብቶች ራስ ላይ እርሱን አድፍጠው የሚጠብቁ ሰዎች መደቡ፣ እነርሱም በዚያ መንገድ በአጠገባቸው ያለፉትን ሰዎች በሙሉ ዘረፉ፡፡ ይህም ወሬ ለአቤሜሌክ ደረሰው፡፡ 26 የአቤድም ልጅ ገዓል ከዘመዶቹ ጋር መጣና ወደ ሴኬም ሄዱ፡፡ የሴኬም መሪዎች በእርሱ ተማመኑበት፡፡ 27 እነርሱም ወደ እርሻው ወጥተው ሄዱና ከወይን አትክልት ቦታ ወይን ለቅመው ጨመቁት፡፡ በአምላካቸው ቤት የደስታ በዓል አደረጉ፣ በሉም ጠጡም፣ አቤሜሌክንም ሰደቡ፡፡ 28 የአቤድም ልጅ ገዓል እንዲህ አለ፣ “እናገለግለው ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ሴኬምስ ማን ነው? እርሱ የይሩብኣል ልጅ አይደለምን? ዜቡልስ የእርሱ ሹም አይደለምን? ለኤሞር ሰዎች፣ ለሴኬም አባት አገልግሉ! ለምን እርሱን እናገለግላለን? 29 ይህ ሕዝብ በእኔ አዛዥነት ስር ቢሆን እመኝ ነበር! የዚያን ጊዜ አቤሜሌክን አስወግደው ነበር፡፡ ለአቤሜሌክም ‘ሠራዊትህን ሁሉ ጥራ’ እለው ነበር፡፡” 30 የከተማይቱ ሹም፣ ዜቡል የአቤድን ልጅ የገዓልን ቃል በሰማ ጊዜ ቁጣው ነደደ፡፡ 31 ወደ አቤሜሌክም ያታልለው ዘንድ እንዲህ ብሎ መልክተኞች ላከ፣ “ተመልከት፣ የአቤድ ልጅ ገዓልና ዘመዶቹ ወደ ሴኬም እየመጡ ነው፣ ከተማይቱን በአንተ ላይ እንድትሸፍት አነሳስተዋል፡፡ 32 አሁንም አንተና ከአንተ ጋር ያሉት ወታደሮች በሌሊት ተነሡ፣ ሜዳውም ላይ አድፍጡ፡፡ 33 ከዚያም በጠዋት ፀሐይ በወጣች ጊዜ ማልደህ ተነሣና በከተማይቱ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽምባት፡፡ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉት ሕዝብ በአንተ ላይ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ላይ ልታደርግ የምትችለውን ማንኛውንም ነገር አድርግባቸው፡፡” 34 ስለዚህ አቤሜሌክ በሌሊት ተነሳ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በሙሉ፣ በአራት ወገን ተከፋፍለው በሴኬም ላይ አደፈጡ፡፡ 35 የአቤድ ልጅ ገዓል ወጥቶ በከተማይቱ በር መግቢያ ቆመ፡፡ አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎችም ከተደበቁበት ስፍራ ወጥተው መጡ፡፡ 36 ገዓልም ሰዎቹን ባየ ጊዜ ዜቡልን፣ “ተመልከት፣ ሰዎች ከኮረብቶች ራስ ወርደው እየመጡ ነው!” አለው፡፡ ዜቡልም እንዲህ አለው፣ “አንተ የምታየው ሰዎች የሚመስለውን የኮረብቶች ጥላ ነው፡፡” 37 ገዓልም እንደገና እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “ተመልከት፣ በምድር መካከል ሰዎች ወርደው እየመጡ ነው፣ አንድም ወገን በቃላተኞች የበሉጥ ዛፍ መንገድ እየመጣ ነው፡፡ 38 የዚያን ጊዜ ዜቡል እንዲህ አለው፣ “‘እናገለግለው ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው?’ ብለህ የተናገርሃቸው እነዚያ የትዕቢት ቃላቶችህ አሁን የት አሉ? እነዚህ ሰዎች አንተ የናቅሃቸው አይደሉምን? አሁን ውጣና ከእነርሱ ጋር ተዋጋ፡፡” 39 ገዓል ወጣና የሴኬም ሰዎችን ይመራ ነበር፣ ከአቤሜሌክም ጋር ተዋጋ፡፡ 40 አቤሜሌክም አሳደደው፣ ገዓልም በፊቱ ሸሸ፡፡ ብዙዎቹም በከተማይቱ በር መግቢያ ፊት ለፊት በከባድ ሁኔታ ቆስለው ወደቁ፡፡ 41 አቤሜሌክም በአሩማ ተቀመጠ፡፡ ዜቡልም ገዓልንና ዘመዶቹን ከሴኬም እንዲወጡ አስገደዳቸው፡፡ 42 በሚቀጥለው ቀን የሴኬም ሕዝብ ወደ እርሻ ሄዱ፣ ይህም ወሬ ለአቤሜሌክ ደረሰው፡፡ 43 ሕዝቡንም ወሰደ፣ በሦስት ወገንም ከፈላቸውና በእርሻዎቹ ውስጥ አደፈጡ፡፡ እርሱም ተመለከተ፣ ሕዝቡ ከከተማ ወጥተው ሲመጡ አየ፡፡ እርሱም ተዋጋቸውና ገደላቸው፡፡ 44 አቤሜሌክና ከእርሱም ጋር የነበሩት ወገኖች ተዋጉና የከተማይቱን በር መግቢያ ዘጉ፡፡ ሌሎቹ ሁለት ወገኖች ደግሞ በእርሻው ውስጥ የነበሩትን ሁሉ ወጓቸውና ገደሉአቸው፡፡ 45 አቤሜሌክም ቀኑን ሙሉ ከከተማይቱ ጋር ተዋጋ፡፡ ከተማይቱንም ተቆጣጠረና በውስጧ የነበሩትን ሕዝብ ገደላቸው፡፡ የከተማይቱንም ቅጥር አፈራረሰው፣ በላይዋም ጨው በተነባት፡፡ 46 የሴኬም ግንብ መሪዎች በሙሉ ይህንን ወሬ በሰሙ ጊዜ፣ ወደ ኤልብሪት ቤት ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡ 47 አቤሜሌክም መሪዎቹ በሙሉ በሴኬም ግንብ ውስጥ በአንድ ላይ እንደተሰበሰቡ ተነገረው፡፡ 48 አቤሜሌክ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጣ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፡፡አቤሜሌክም በእጁ መጥረቢያ ወሰደና የዛፉን ቅርንጫፎች ቆረጠ፡፡ እርሱም አንሥቶ በትከሻው ላይ አደረገውና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፣ “እኔ ሳደርግ ያያችሁትን፣ ፈጥናችሁ እኔ እንዳደረግሁ አድርጉ፡፡” 49 ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው የዛፉን ቅርንጫፎች ቈረጠና አቤሜሌክን ተከተሉት፡፡ እነርሱም ቅርንጫፎቹን በምሽጉ ላይ ከመሩአቸው፣ በላዩም ላይ እሳት አቀጣጠሉበት፣ ከዚህ የተነሳ የሴኬም ግንብ ሰዎች ሁሉ፣ አንድ ሺህ የሚያህሉ ወንድና ሴት ሞቱ፡፡ 50 ከዚያ በኋላ አቤሜሌክ ወደ ቴቤስ ሄደ፣ ቴቤስንም ከበባትና ተቆጣጠራት፡፡ 51 ነገር ግን በከተማይቱ ጠንካራ ግንብ ነበረ፣ የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ፣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ፣ የከተማይቱም መሪዎች ሁሉ ወደዚያ ሸሹና በውስጥ ሆነው ደጁን ዘጉት፡፡ ከዚያም እስከ ግንቡ ሰገነት ድረስ ወደ ላይ ወጡ፡፡ 52 አቤሜሌክም ወደ ግንቡ መጣና ተዋጋ፣ በእሳትም ሊያቃጥለው ወደ ግንቡ በር አጠገብ መጣ፡፡ 53 ነገር ግን አንዲት ሴት በአቤሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ ጣለችበት፣ መጁም ጭንቅላቱን ሰባበረው፡፡ 54 ከዚያም እርሱ በአስቸኳይ ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፣ “አንድም ሰው እኔን ‘ሴት ገደለችው’ እንዳይል ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው፡፡ ስለዚህ ወጣቱ ሰው ወጋውና ሞተ፡፡ 55 የእስራኤልም ሰዎች አቤሜሌክ እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ 56 እግዚአብሔርም ሰባ ወንድሞቹን በመግደል አቤሜሌክ በአባቱ ላይ ያደረገውን ክፋት ተበቀለው፡፡ 57 እግዚአብሔርም የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው፣ የይሩበኣልም ልጅ የኢዮአታም እርግማን በእነርሱ ላይ መጣባቸው፡፡
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ይህንን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ ያለ ትዕምርተ ጥቅስ ነው። ቀጥተኛው ትዕምርተ ጥቅስ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ሆኖ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እባካችሁ፣ የይሩበዓል ሰባ ልጆች ሁሉ እንዲገዟቸው ይፈልጉ እንደሆን ወይም ከልጆቹ አንዱ ብቻ እንዲገዛቸው ይፈልጉ እንደሆን የሴኬምን መሪዎች ጠይቋቸው” (በትዕምርተ ጥቅስ ውስጥ የሚገኝ ትዕምርተ ጥቅስ እና ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ የሚለውን ተመልከት)
“70” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አጥንታችሁና ሥጋችሁ” የሚወክለው የአንድ ሰው ዘመድ መሆንን ነው። አ.ት፡ “እኔ የቤተሰባችሁ አባል ነኝ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት የአቤሜሌክ የእናቱ ዘመዶች አቤሜሌክን ንጉሣቸው እንዲያደርጉት አሳብ በማቅረብ ለመሪዎቹ ተናገሩ።
“አቤሜሌክ መሪያቸው እንዲሆን ተስማሙ”
እዚህ ጋ “ቤት” የሚወክለው መቅደስን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ሰባ ሰቅል ብር ነው። አንድ ሰቅል 11 ግራም ይመዝናል። ይህንን ወደ ዘመናዊ መለኪያ መተርጎም አስፈላጊ ከሆነ እንደዚህ አድርገህ ልትተረጉመው ትችላለህ። አ.ት፡ “አንድ ኪሎ የሚያህል ጥሬ ብር” (ገንዘብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚለውን ተመልከት)
“70” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሐሰተኛ አምላክ ስም ነው። እርሱን በመሳፍንት 8፡33 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ቁጡና ሞኞች”
በመሳፍንት 6፡11 ላይ እንዳደረግኸው የዚህችን ከተማ ስም ተርጉመው።
“1 ድንጋይ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“70” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ይህንን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የቦታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አቤሜሌክ ወንድሞቹን መግደሉን ኢዮአታም በሰማ ጊዜ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ተራራ ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ኢዮአታም ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች በዛፎች በመመሰል ያብራራል። (ምሳሌዎች እና ሰውኛ የሚሉትን ተመልከት)
እዚህ ጋ በዘይት መቀባት አንድን ሰው ንጉሥ እንዲሆን መሾምን የሚወክል ምሳሌአዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “በሁላቸውም ላይ እንዲገዛ ንጉሥ ለመሾም”
“ንጉሣችን ሁን”
ኢዮአታም ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች በዛፎች ምሳሌ አድርጎ ያብራራል። (ምሳሌዎች እና ሰውኛ የሚሉትን ተመልከት)
የወይራው ዛፍ ንጉሥ መሆንን እምቢ ለማለት ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “በሌሎች ዛፎች ላይ … ዘይት መስጠቴን አላቆምም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“መወዛወዝ” ማለት በንፋስ ምክንያት ወደ ፊትና ወደ ኋላ ማለት ነው። ዛፉ ይህንን ሐረግ የሚጠቀመው “መግዛት” ለማለት ነው።
የበለስ ዛፉ ንጉሥ መሆንን እምቢ ለማለት ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “በሌሎች ዛፎች ላይ … ጣፋጭነቴን አላቆምም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“ጣፋጭነት” የሚለው ቃል የነገር ስም ነው። በዛፉ ላይ የሚበቅለውን ፍሬ ለመግለጽ እንደ ቅጽል ሆኖ ሊነገር ይችላል። (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
በዚህ ምሳሌ ኢዮአታም ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች ዛፎቹና የወይን ተክል እንደሚያደርጉት አድርጎ ያብራራል። (ምሳሌዎች እና ሰውኛ የሚሉትን ተመልከት)
የወይን ተክሉ ንጉሥ መሆንን እምቢ ለማለት ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “በሌሎች ዛፎች ላይ … አዲሱን ወይኔን አላቆምም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እሾህ የሚጎዳ የሾለ መውጊያ አለው። ይህ ቁጥቋጦ በየቅርንጫፎቹ ላይ በርካታ ሹል መውጊያዎች አሉት።
በዚህ ምሳሌ ኢዮአታም የቁጥቋጦው እሾህና ዛፎቹ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ነገሮች እንደሚያደርጉ ያብራራል። (ምሳሌዎች እና ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
አንድን ሰው በዘይት መቀባት ንጉሥ እንዲሆን የመሾም ምሳሌአዊ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “ንጉሣችሁ አድርጋችሁ ልትቀቡኝ” (ምሳሌአዊ ድርጊት የሚለውን ተመልከት)
“ደህንነት” የሚለው ቃል የነገር ስም ሲሆን እንደ ቅጽል ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ተጠበቁ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ዝግባዎቹን ለማቃጠል የእሾህ ቁጥቋጦው ይነዳል።
የእሾህ ቁጥቋጦው ራሱን እንደ “እሾህ ቁጥቋጦ” ያመለክታል። አ.ት፡ “ከዚያም እሳት ከእኔው ከእሾህ ቁጥቋጦው ይውጣ” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)
ይህ “በዚህ ሰዓት” ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ትኩረትን ወደሚቀጥለው አስፈላጊ ጉዳይ ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል።
ኢዮአታም ያደረጉት መልካም ይሆን እንደሆነ ምርጫውን ያቀርብላቸዋል፤ ይሁን እንጂ ያደረጉት በመሠረቱ መልካም እንደሆነ ኢዮአታም አያምንም። አ.ት፡ “መልካም የሆነውን አድርጋችሁ ከሆነና ልጆቹን ሁሉ ትገድሉበት ዘንድ ለይሩበአል የሚገባው ከሆነ”
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ይህንን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተምልከት።
እዚህ ጋ “ቤት” የጌዴዎንን ቤተሰብ ይወክላል። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ጌዴዎን የሴኬምን ሰዎች ለማዳን ከተዋጋ በኋላ የሴኬም ሰዎች ለጌዴዎንና ለቤተሰቡ በክፋት መመለሳቸውን ኢዮአታም ማመን እንደማይችል ይገልጻል።
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። አ.ት፡ “ከምድያማውያን ኃይል” ወይም “ከምድያማውያን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ተቃወማችሁ” ወይም “በእርሱ ላይ አምጻችኋል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ቤት” የሚወክለው ቤተሰብን ነው። አ.ት፡ “የአባቴ ቤተሰብ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“70” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“1 ድንጋይ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “የእርሱ” የሚያመለክተው ጌዴዎንን ነው።
ኢዮአታም ያደረጉት መልካም ይሆን እንደሆነ ምርጫውን ያቀርብላቸዋል፣ ይሁን እንጂ ያደረጉት በመሠረቱ መልካም እንደሆነ ኢዮአታም አያምንም። አ.ት፡ “ለይሩበአልና ለቤተሰቡ ሊደረግላቸው የሚገባቸውን አድርጋችሁላቸው ከሆነ”
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። እንዲህ ማለትም፣ “በኣል ለራሱ ይሟገት” ማለት ነው። ይህንን በ6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እዚህ ጋ “ቤት” የሚያመለክተው ቤተሰብን ነው። አ.ት፡ “ቤተሰቡን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ኢዮአታም ያደረጉት ክፉ መሆኑን እና እርግማን እንደሚሆንባቸው ተቃራኒውን አማራጭ ያቀርብላቸዋል። ኢዮአታም ያደረጉት ክፉ መሆኑን ያምናል። አ.ት፡ “ለይሩበአልና ለቤተሰቡ ሊደረግ የማይገባቸውን አድርጋችሁ ከሆነ ግን”
ኢዮአታም የሚናገረው እርግማንን ነው። አቤሜሌክ በእሳት ያቃጥላቸው ይመስል የሴኬምን ሰዎች እንደሚያጠፋቸው ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ኢዮአታም የሚናገረው እርግማንን ነው። የሴኬምና የቤትሚሎ ሰዎች በእሳት ያቃጥሉት ይመስል አቤሜሌክን እንደሚያጠፉት ይናገራል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የቦታ ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 9፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ኢዮአታም በአቤሜሌክና በሴኬም መሪዎች መካከል አለመግባባትንና ጠላትነትን እንዲፈጥር ክፉ መንፈስን በመላክ ያደረገውን እርግማን እግዚአብሔር ተግባራዊ አድርጎታል ማለት ነው።
ተደራጊ ድምፅ ያላቸውን ሐረጎች በአድራጊ ድምፅ መናገር ይቻላል። አ.ት፡ “አቤሜሌክ ስለገደላቸው ሰባ ልጆችና የሴኬም ሰዎች በግድያው ስለረዱት እግዚአብሔር ለመበቀል ይህንን አደረገ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“70” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ይህንን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“ሰዎች በኮረብታው ጫፍ እንዲደበቁና አቤሜሌክን ለመግደል እንዲጠባበቁ ላካቸው”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች ሊያጠቁት እየተጠባበቁ እንዳሉ አንድ ሰው ለአቤሜሌክ ነገረው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“መተማመን” የሚለው ቃል የነገር ስም ሲሆን “መታመን” በሚል ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ታመኑበት” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እነርሱ” የሚያመለክተው ገዓልን፣ ዘመዶቹንና የሴኬምን ሰዎች ነው።
ይህንን ያደረጉት የወይን ጭማቂ ለማዘጋጀት ነው።
“ሰባበሩ” ወይም “ጨፈለቁ”
እዚህ ጋ “ቤት” የሚወክለው መቅደስን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 9፡26 ላይ እንዴት እንደተርጎምከው ተመልከት።
ገዓል የሰኬም ሰዎች አቤሜሌክን ማገልገል እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “አቤሜሌክን ማገልገል የለብንም!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁለቱም ጥያቄዎች አንድ ናቸው። የአቤሜሌክ እናት ከሴኬም በመሆኗ ምክንያት ገዓል አቤሜሌክን ለማመልከት “ሴኬም” ይላል። አ.ት፡ “አቤሜሌክን ማገልገል የለብንም፣ እርሱም ሴኬም ነው!” ( እና ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ገዓል የሰኬም ሰዎች አቤሜሌክን ማገልገል እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “እርሱ የይሩበአል ልጅ ብቻ ነው፣ ዜቡልም የእርሱ ሹም ብቻ ነው” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ይህንን በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ገዓል የሚለው፣ የሴኬም ሰዎች ማገልገል ያለባቸው እውነተኛ ከነዓናውያን የሆኑትን ከኤሞር የተወለዱትን እንጂ እስራኤላዊ አባት ያለውን ሰው ማገልገል የለባቸውም።
ገዓል የሰኬም ሰዎች አቤሜሌክን ማገልገል እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ጥያቄ ይጠይቃል። አ.ት፡ “አቤሜሌክን ማገልገል የለብንም!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“የሴኬምን ሰዎች ባስተዳድር እመኛለሁ”
ይህንን ስም በመሳፍንት 9፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት
“የኤቤድ ልጅ ገዓል የተናገረውን ሰሙ”
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 9፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
መቆጣቱ እንደ እሳት መንደድ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “በጣም ተቆጣ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ዜቡል ገዓልንና የሴኬምን ሰዎች እያታለላቸው ነው። አ.ት፡ “በምስጢር”
ይህ የከተማው ሰዎች በድስት ውስጥ እንዳለ ፈሳሽ መንተክተካቸውን ያሳያል። አ.ት፡ “የከተማይቱ ሰዎች በአንተ ላይ እንዲያምጹ እያነሣሧቸው ነው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ከተማ” የሚወክለው በከተማይቱ የሚኖሩትን ሰዎች ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ “በዚህ ሰዓት” ማለት አይደለም፣ ነገር ግን ትኩረትን ወደሚቀጥለው አስፈላጊ ጉዳይ ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል።
“ተደብቆ እነርሱን በድንገት ማጥቃት”
ይህ ማለት የገዓልን ተከታዮች ለማጥፋት የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ።
“አቤሜሌክን የተከተሉ ሰዎች ሁሉ” ወይም “ለአቤሜሌክ ይዋጉ የነበሩ ሰዎች ሁሉ”
እዚህ ጋ “ሴኬም” የሚወክለው የሴኬምን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “የሴኬምን ሰዎች በድንገት ለማጥቃት ተደበቁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በ4 ቡድኖች ለያይቶ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እነዚህን ስሞች በመሳፍንት 9፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ይህ የሰው ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 9፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የሰው ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 9፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ዜቡል ገዓልን እያደናገረውና ለጦርነት እንዳይዘጋጅ እያዘገየው ነው። አ.ት፡ “ያ ሰዎች ሳይሆኑ በኮረብቶቹ ላይ ጥላዎች ብቻ ናቸው”
“1 ቡድን” ወይም “1 ጓድ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
በመሳፍንት 9፡28 ላይ ይህንን ስም እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ዜቡል በዚህ ምላሽ በማይፈልግ ጥያቄ በገዓል ላይ እየተሳለቀበት ነው። አ.ት፡ “አሁን በትዕቢት አትናገርም” ወይም “አሁን አትታበይም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ዜቡል የገዓልን የኩራት ንግግር መልሶ እየጠቀሰለት ነው። ይህ እንደ መግለጫና ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አቤሜሌክን ማገልገል የለብንም ብለህ የነበርከው አንተ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ትዕምርተ ጥቅሶች የሚለውን ተመልከት)
ዜቡል በዚህ ምላሽ በማይፈልግ ጥያቄ ገዓልን እየተገዳደረው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “የናቅኻቸው ሰዎች እኝውልህ” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እጅግ ያልተወደዱ ወይም የተጠሉ
ይህንን ስም በመሳፍንት 9፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ብዙ ሰዎች ቆስለው ሞቱ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሰው ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 9፡28 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የሰው ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 9፡26 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ይህንን ለአቤሜሌክ ነገረው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“በ3 ቡድኖች ለያያቸው” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
x
“የወታደሮቹ ቡድኖች”
“ሌሎች 2” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አቤሜሌክ” የሚወክለው ራሱንና ወታደሮቹን ነው። አ.ት፡ “አቤሜሌክና ወታደሮቹ ተዋጉ … አጠፉ”
እዚህ ጋ “ከተማ” የሚወክለው ሰዎችን ነው። አ.ት፡ “በሴኬም ሰዎች ላይ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አወደሙ”
“በምድሪቱ ላይ ጨው ዘራ”። በምድር ላይ ጨው መዝራት በዚያ ቦታ ምንም ነገር እንዳይበቅል ያደርጋል።
እዚህ ጋ ይህ የሚወክለው መቅደስን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ኤል” የሚለው ቃል ትርጉም “አምላክ” ማለት ነው። ይህ በመሳፍንት 8፡33 እንዳለው “በኣል በሪት” ሁሉ ያው ሐሰተኛ አምላክ ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ለአቤሜሌክ ነገረው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የተራራ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ቅርንጫፎቹን በብዙ መጠን እንደ ክምር መከመር ነው።
“1,000 ያህል ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ከቴመስ ከተማ ውጪ ሰፈረ”
“አጠቃት”
ሁለት ትላልቅና ጠፍጣፋ ድንጋዮች ጥራጥሬ ለመፍጨት ያገለግሉ ነበር። በታችኛው ላይ በመንከባለል በመሐል ያለውን ጥራጥሬ የሚፈጨው ከላይ የሚሆነው መጅ ነው።
ይህ የአቤሜሌክን የጦር መሣሪያ የሚሸከመው ሰው ነው።
ይህ ማለት ወጣቱ አቤሜሌክን በሰይፍ ወጋው።
“70” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ክፋት በራሳቸው ላይ ተመለሰ” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ስላደረጉት ክፋት ሁሉ የሴኬምን ሰዎች ቀጣቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “የይሩበአል ልጅ የኢዮአታም እርግማን መጣባቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የጌዴዎን ሌላው ስሙ ነው። ይህንን ስም በመሳፍንት 6፡32 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
1 ከአቤሜሌክ በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነውና በኮረብታማውም በኤፍሬም አገር ባለችው በሳምር ይኖር የነበረው የዱዲ ልጅ የፎሖ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፡፡ 2 እርሱም በእስራኤል ላይ ሀያ ሦስት ዓመት ፈረደ፡፡ እርሱም ሞተ፣ በሳምርም ተቀበረ፡፡ 3 ከእርሱም በኋላ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፡፡ በእስራኤልም ላይ ሀያ ሁለት ዓመት ፈረደ፡፡ 4 በሠላሳ አህያዎች የሚጋልቡ ሠላሳ ልጆች ነበሩት፣ እነርሱም በገለዓድ ምድር ያሉ እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው፡፡ 5 ኢያዕርም ሞተ፣ በቃሞንም ተቀበረ፡፡ 6 የእስራኤል ሕዝብ ከዚህ በፊት ከሰሩት በላይ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ስራ ጨምረው ሠሩ፣ በኣልን፣ አስታሮትን፣ እንደዚሁም የሶርያን አማልክት፣ የሲዶናን አማልክት፣ የሞዓብን አማልክት፣ የአሞንን ሕዝብ አማልክት፣ የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፡፡እግዚአብሔርን ተዉ፣ እርሱንም አላመለኩትም፡፡ 7 የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፣ እርሱም ፍልስጥኤማውያንና አሞናውያን ያሸንፉአቸው ዘንድ ለእነርሱ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ 8 እነርሱም በዚያን ዓመት የእስራኤልን ሕዝብ አደቀቋቸው፣ አስጨነቋቸው፣ ለአሥራ ስምንት ዓመት በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን ምድር በገለዓድ ውስጥ የነበሩትን የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ አስጨነቋቸው፡፡ 9 የአሞንም ሰዎች ከይሁዳ፣ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ለመዋጋት ዮርዳኖስን ተሻገሩ፣ ከዚህ የተነሳ እስራኤል እጅግ በጣም ተጨነቁ፡፡ 10 የዚያን ጊዜ የእስራኤልም ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮሁ፣ እንዲህ በማለት፣ “በአንተ ላይ በድለናል፣ ምክንያቱም አምላካችንን ትተን የበኣል አማልክትን አምልከናልና፡፡” 11 እግዚአብሔርም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ አላቸው፣ “ከግብፃውያን፣ ከአሞራውያንም፣ ከአሞናውያን፣ ከፍልስጤማውያንና 12 ከሲዶናውያን አላዳንኋችሁምን? አማሌቃውያንና ማዖናውያን አስጨነቋችሁ፤ ወደ እኔም ጮኻችሁ፣ እኔም ከእነርሱ ኃይል አዳንኋችሁ፡፡ 13 ይሁን እንጂ እናንተ እንደገና ተዋችሁኝና ሌሎችን አማልክት አመለካችሁ፡፡ ስለዚህ፣ እኔም ከእንግዲህ ወዲህ አላድናችሁም፡፡ 14 ሂዱና ወደምታመልኳቸው አማልክት ጩኹ፡፡ በመከራችሁ ጊዜ እነርሱ ያድኑአችሁ፡፡ 15 የእስራኤልም ሕዝብ እግዚአብሔርን እንዲህ አሉት፣ “እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፡፡ ለአንተ ደስ የሚያሰኝህን ማንኛውንም ነገር በእኛ ላይ አድርግብን፡፡ እባክህ፣ የዛሬን ብቻ አድነን፡፡” 16 እነርሱም በመካከላቸው ካሉት ባዕዳን አማልክት ዘወር አሉ፣ እግዚአብሔርንም አመለኩ፡፡እርሱም የእስራኤልን ጕስቍልና ሊታገሰው የማይቻለው ሆነ፡፡ 17 ከዚያም አሞናውያን በአንድ ላይ ተሰበሰቡና በገለዓድ ሰፈሩ፡፡ እስራኤላውያንም በአንድ ላይ ተሰበሰቡና ሰፈራቸውን በምጽጳ ላይ አደረጉ፡፡ 18 የገለዓድ ሕዝብ መሪዎችም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “አሞናውያንን ለመዋጋት የሚጀምር ሰው ማን ነው? እርሱ በገለዓድ በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ መሪ ይሆናል፡፡”
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የቦታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“እስራኤልን ለማዳን መጣ” ወይም “እስራኤልን ለማዳን መሪ ሆነ”
እዚህ ጋ “እስራኤል” የሚወክለው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ፈረደ” ማለት የእስራኤልን ሕዝብ መራ ማለት ነው።
“23 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ቀበሩት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከቶላ በኋላ ገለዓዳዊው ኢያዕር መሪ ነበር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ኢያዕር ከገለዓድ ነገድ ነበር
እዚህ ጋ “ፈረደ” ማለት የእስራኤልን ሕዝብ መራ ማለት ነው።
እዚህ ጋ “እስራኤል” የሚወክለው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“22 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“30 ወንዶች ልጆች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአንድ ሰው ስም የሚጠራ የአውራጃ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት መጽሐፈ መሳፍንት እስከሚጻፍበት ጊዜ ድረስ ማለት ነው።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ቀበሩት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የቦታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
አንድ ሰው እየጨመረበት እንደሚያተልቀው አንዳች ነገር ይህ የተነገረው ስለ ክፋት ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ክፉ ነው ያለውን ማድረጋቸውን ቀጠሉ”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የእግዚአብሔር ፊት የሚወክለው የእርሱን ፍርድ ወይም ምዘና ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንደሚለው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአስታሮት ብዙ ቁጥር ሲሆን በተለያየ ቅርጽ የምትመለክ እንስት አምላክ ነበረች። ይህንን በመሳፍንት 2፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
በመሠረቱ ደራሲው ሁለት ጊዜ የተናገረው ስለ አንድ ነገር አጽንዖት ለመስጠት ነው። እነዚህ ሊጣመሩ የሚችሉ ናቸው። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን ማምለካቸውን ሙሉ በሙሉ አቆሙ”
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን አለማምለካቸውና አለመታዘዛቸው ሰዎቹ እግዚአብሔርን ትተው ወደ አንድ የሆነ ቦታ እንደሄዱ ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ቁጣ የሚነድ እሳት ይመስል እግዚአብሔር እንደ ተቆጣ ተነግሯል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በጣም ተቆጣ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር ፍልስጥኤማያንና አሞናውያን እስራኤላውያንን እንዲያሸንፉ መፍቀዱ እስራኤላውያንን ለእነርሱ እንደሸጠላቸው ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁለት ቃላት የሚሉት በመሠረቱ ስለ አንድ ነገር ሲሆን እስራኤላውያን ምን ያህል እንደተሰቃዩ አጽንዖት ለመስጠት ነው። አ.ት፡ “በከፋ ሁኔታ አስጨነቋቸው”
“18 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ ማለት ነው።
“ይህ አውራጃም ደግሞ ገለዓድ ተብሎ ተጠርቷል”
“ይሁዳ” እና “ብንያም” የእነዚያን ነገዶች ሕዝቦች ያመለክታል። አ.ት፡ “የይሁዳ ነገድ ሕዝቦች … የብንያም ነገድ ሕዝቦች”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ቤት” የሚያመለክተው የኤፍሬምን ነገድ ሕዝቦች ነው። አ.ት፡ “የኤፍሬም ነገድ ሕዝቦች”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እስራኤል” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “በመሆኑም የእስራኤል ሕዝብ በጣም ተሰቃየ”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በፍጹም ልባቸው ጠየቁት።
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን አለማምለካቸውና አለመታዘዛቸው ሰዎቹ እግዚአብሔርን ትተው ወደ አንድ የሆነ ቦታ እንደሄዱ ሆኖ ተነግሯል። ( ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሕዝቡ የሚናገሩት ስለ እግዚአብሔር ሲሆን “አምላካችን” ብለው ይጠሩታል። ይህ በሁለተኛ መደብ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አምላካችን ሆይ፣ አንተን ትተንሃል” (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)
ሌሎች አማልክትን ስለማምለካቸው እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ይገስጻቸዋል። ይህ መልስ የማይሻ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከሲዶናውያን … ያዳንኋችሁ እኔ ነኝ” (መልስ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ከማዖን ቤተሰብ ወይም ጎሳ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ኃይል” የሚወክለው አማሌቃውያንን እና ማዖናውያንን ነው። አ.ት፡ “ከእነርሱ”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን አለማምለካቸውና አለመታዘዛቸው ሰዎቹ እግዚአብሔርን ትተው ወደ አንድ የሆነ ቦታ እንደሄዱ ሆኖ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ከእንግዲህ ወዲህ” የሚለው ሐረግ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙም አንድ ነገር በማድረግ መቀጠል ማለት ነው። በእግዚአብሔር አነጋገር ውስጥ ግልጽ ያልሆነውን ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “በተደጋጋሚ እናንተን ማዳኔን አልቀጥልም” ወይም “እናንተን ማዳን ማቆሜን እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ”
የዚህን መግለጫ ግልጽ ያልሆነ ትርጉም ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “የወረሷቸውን የእንግዶች አማልክት ምስሎች”
እዚህ ጋ እስራኤል የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል ሕዝብ ከእንግዲህ ወዲያ እንዲሰቃይ አልፈለገም”።(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አሞናውያንን ለመዋጋት ሰራዊታችንን የሚመራው ማን ነው?”
1 ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ኃያል ተዋጊ ነበር፣ ነገር ግን የጋለሞታ ሴት ልጅ ነበረ፡፡ አባቱም ገለዓድ ነበረ፡፡ 2 የገለዓድም ሚስት ደግሞ ሌሎች ወንዶች ልጆችን ወለደችለት፡፡ የሚስቱ ልጆች ባደጉ ጊዜ፣ ዮፍታሔን ቤቱን ለቅቆ እንዲወጣ አስገደዱት፣ እንዲህም አሉት፡- “አንተ ከቤተሰባችን ምንም ነገር አትወርስም፡፡ አንተ የሌላ ሴት ልጅ ነህ፡፡” 3 ስለዚህ ዮፍታሔ ከወንድሞቹ ፊት ሸሸና በጦብ ምድር ተቀመጠ፡፡ ስርዓት አልበኛ ሰዎችም ተከተሉት፣ ተሰብስበውም ከእርሱ ጋር ሄዱ፡፡ 4 ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ የአሞን ሰዎች ከእስራኤል ጋር ውጊያ አደረጉ፡፡ 5 የአሞንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር ውጊያ ባደረጉ ጊዜ፣ የገለዓድ ሽማግሌዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር ለማምጣት ሄዱ፡፡ 6 ዮፍታሔንም፣ “ና፣ ከአሞን ሰዎች ጋር እንድንዋጋ አለቃችን ሁን” አሉት፡፡ 7 ዮፍታሔም ለገለዓድ ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ ጠልታችሁኛል፣ የአባቴንም ቤት ትቼ እንድሄድ አስገድዳችሁኛል፡፡ አሁን በተቸገራችሁ ጊዜ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ?” 8 የገለዓድም ሽማግሌዎችም ለዮፍታሔ፣ “አሁን ወደ አንተ የተመለስነው ለዚህ ነው፤ ከእኛ ጋር ና፣ ከአሞንም ሰዎች ጋር ተዋጋ፣ ከዚያም በኋላ በገለዓድ በሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ላይ መሪ ትሆናለህ” አሉት፡፡ 9 ዮፍታሔም ለገለዓድ ሽማግሌዎች፣ “ከአሞን ሰዎች ጋር እንድዋጋ እንደገና ወደ ቤቴ ከመለሳችሁኝ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ከሰጠን መሪያችሁ እሆናለሁ” አላቸው፡፡ 10 የገለዓድ ሽማግሌዎችም ለዮፍታሔ፣ “እንደተናገርነው የማናደርግ ከሆነ እግዚአብሔር በእኛ መካከል ምስክር ይሁን” አሉት፡፡ 11 ስለዚህ ዮፍታሔ ከገለዓድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፣ ሕዝቡም በላያቸው ላይ መሪና የጦር አዛዥ አደረጉት፡፡ እርሱ በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት በነበረ ጊዜ፣ ዮፍታሔ የገባውን ቃል ኪዳን ሁሉ ደገመው፡፡ 12 ዮፍታሔም ወደ አሞን ሰዎች ንጉሥ እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላከ፡- “በእኛ መካከል ያለው ጠብ ምንድን ነው? ምድራችንን ለመውሰድ በጦር ለምን መጣህ?” 13 የአሞንም ሰዎች ንጉሥም ለዮፍታሔ መልክተኞች “እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ወስደዋል፡፡ አሁን እነዚህን መሬቶች በሰላም መልሱልኝ” ብሎ መለሰላቸው፡፡ 14 ዮፍታሔም ወደ አሞን ሰዎች ንጉሥ መልክተኞችን እንደ ገና ላከ፣ 15 እንዲህም አለው፣ “ዮፍታሔ የሚለው ይህንን ነው፡- እስራኤል የሞዓብን ምድር የአሞንንም ሰዎች ምድር አልወሰደም፣ 16 ነገር ግን ከግብፅ በወጡ ጊዜ፣ እስራኤል በምድረ በዳ በኩል ወደ ቀይ ባሕር ከዚያም ወደ ቃዴስ ሄዱ፣ 17 እስራኤል ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፣ ‘በምድርህ እንድናልፍ እባክህ ፍቀድልን፣’ ነገር ግን የኤዶምያስ ንጉሥ አልሰማም፡፡ እንዲሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ መልእክተኞች ላኩ፣ እርሱም አልፈቀደም፡፡ ስለዚህ እስራኤል በቃዴስ ተቀመጠ፡፡ 18 እነርሱም በምድረ በዳ በኩል ሄዱና ከኤዶምያስና ከሞዓብ ምድር ተመለሱ፣ በሞዓብም ምድር በምሥራቅ በኩል ሄዱ፣ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፡፡ ነገር ግን ወደ ሞዓብ ክልል ውስጥ አልገቡም፣ አርኖን የሞዓብ ድንበር ነበረና፡፡ 19 እስራኤልም በሐሴቦን ውስጥ ገዥ ወደነበረው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም ‘እባክህ፣ በምድርህ በኩል ወደ ስፍራችን እንድናልፍ ፍቀድልን’ አለው፡፡ 20 ነገር ግን ሴዎን እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ አላመነውም፡፡ ስለዚህ ሴዎን ሰራዊቱን ሁሉ ሰበሰበና ወደ ያሀጽ ተንቀሳቀሰ፣ በዚያም ከእስራኤል ጋር ተዋጋ፡፡ 21 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርም ለእስራኤል በሴዎን ላይ ድል ሰጠውና ሕዝቡን ሁሉ በቁጥጥራቸው ስር እንዲሆኑ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ስለዚህም እስራኤል በዚያች አገር ተቀምጠው የነበሩትን የአሞራውያንን አገር ሁሉ ወሰዱ፡፡ 22 በአሞራውያን ክልል ውስጥ የነበረውን ሁሉንም ነገር ወሰዱ፣ ከአርኖንም እስከ ያቦቅ ድረስ፣ ከምድረ በዳውም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ፡፡ 23 ያንጊዜ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አሞራውያንን ከሕዝቡ ከእስራኤል ፊት አስወጣቸው፣ ታዲያ አንተ አሁን ምድራቸውን ልትወስድ ይገባልን? 24 አምላክህ ካሞሽ የሚሰጥህን ምድር አትወስድምን? ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችን የሰጠንን ምድር ሁሉ እንወስዳለን፡፡ 25 አሁን አንተ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ በእውነት ትሻላለህን? እርሱ ከእስራኤል ጋር ከቶ ክርክር ነበረውን? ከእነርሱ ጋር ጦርነት አካሂዷልን? 26 እስራኤል በሐሴቦንና በቀበሌዎችዋ፣ በአሮዔርና በቀበሌዎችዋ፣ በአርኖንም ዳርቻ ባሉት ከተሞች ሁሉ ለሦስት መቶ ዓመት ሲኖር በነበረበት ጊዜ፣ ለምን ታዲያ በዚያን ጊዜ መልሳችሁ አልወሰዳችኋቸውም ነበር? 27 እኔ አልበደልሁህም ነገር ግን አንተ እኔን በመውጋት እየበደልከኝ ነው፡፡ ፈራጅ የሆነው እግዚአብሔር በእስራኤል ሰዎችና በአሞን ሰዎች መካከል ዛሬ ይፈርዳል፡፡ 28 ነገር ግን የአሞን ሰዎች ንጉሥ ዮፍታሔ የላከበትን ማስጠንቀቂያ አልተቀበለም፡፡ 29 ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፣ እርሱም በገለዓድና በምናሴ አለፈ፣ በገለዓድ ባለው ምጽጳም አለፈ፣ ከዚያም በገለዓድ ካለው ምጽጳ ወደ አሞን ሰዎች አለፈ፡፡ 30 ዮፍታሔም ለእግዚብሔር እንዲህ ሲል ስእለት ተሳለ፡- “በአሞንን ሰዎች ላይ ድልን ብትሰጠኝ፣ 31 ከአሞን ሰዎች በሰላም በተመለስሁ ጊዜ እኔን ሊያገኘኝ ከቤቴ በር የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል፣ እርሱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀርበዋለሁ፡፡ 32 ስለዚህ ዮፍታሔ እነርሱን ለመውጋት ወደ አሞን ሰዎች አለፈ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ሰጠው፡፡ 33 እርሱም ከአሮዔርም እስከ ሚኒት፣ እንደዚሁም እስከ አቤልክራሚም ድረስ ያሉ ሀያ ከተሞችን ወጋቸው፣ ታላቅ እልቂትም አደረሰባቸው፡፡ ስለዚህ የአሞን ሰዎች በእስራኤል ሰዎች ቁጥጥር ስር ሆኑ፡፡ 34 ዮፍታሄ ምጽጳ ወዳለው ቤቱ መጣ፣ በዚያም የእርሱ ልጅ ከበሮ ይዛ እያሸበሸበች ልታገኘው ወጣች፡፡ እርስዋም ብቸኛ ልጁ ነበረች፣ ከእርስዋ ሌላ ወንድ ልጅም ይሁን ሴት ልጅ አልነበረውም፡፡ 35 እርስዋንም ባየ ጊዜ፣ ልብሱን ቀደደ እንዲህም አለ፡- “ወይኔ! ልጄ ሆይ! በኀዘን አደቀቅሽኝ፣ በእኔ ላይ ጭንቅ ያመጣብኝ ሰው ሆንሽብኝ! ለእግዚአብሔር ስእለት ተስያለሁና፣ ቃሌን ማጠፍ በፍጹም አልችልም፡፡” 36 እርስዋም እንዲህ አለችው፡- “አባቴ ሆይ፣ ለእግዚአብሔር ስእለት ተስለሃል፣ ቃል የገባኸውን ሁሉ በእኔ ላይ አድርግብኝ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላቶችህ በአሞናውያን ላይ ተበቅሎልሃልና፡፡” 37 አርስዋም ለአባትዋ እንዲህ አለች፡- “ይህ ቃል ለእኔ ይደረግልኝ፡፡ ይህንን አካባቢ እንድለቅና ወደ ታች ወደ ኮረብታዎቹ እንድወርድ፣ ከጓደኞቼም ጋር ስለ ድንግልናየ እንዳለቅስ ለሁለት ወራቶች ያህል ብቻየን እንድሆን ፍቀድልኝ፡፡ 38 እርሱም፣ “ሂጂ” አለ፡፡ ለሁለት ወራትም አሰናበታት፡፡ እርስዋም ትታው ሄደች፣ ከባልንጀሮችዋም ጋር ስለ ድንግልናዋ በኮረብታዎቹ ላይ አለቀሱ፡፡ 39 በሁለት ወር መጨረሻ ላይ ወደ አባትዋ ተመለሰች፣ እርሱም ቃል እንደገባው እንደ ስእለቱ አደረገባት፡፡ እርስዋም ከወንድ ጋር ተኝታ አታውቅም፣ ይህም በእስራኤል ዘንድ ልማድ ሆነ፣ 40 የእስራኤል ሴቶች ልጆች በየዓመቱ፣ ለአራት ቀናት፣ የገለዓዳዊውን የዮፍታሔን ሴት ልጅ ታሪክ እየተናገሩ ያስቡአታል፡፡
ይህ ከገለዓድ አውራጃ የሆነ ግለሰብ ነው። የእርሱም አባት ስም ገለዓድ መሆኑ የአጋጣሚ ጉዳይ ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“የገለዓድ ሚስት የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች በጎለመሱ ጊዜ”
ጦብ የአውራጃ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ተከተሉት” ወይም “አብረው በየስፍራው ሄዱ”
“ከጥቂት ጊዜ በኋላ”
“ተዋጉ” የሚለው ቃል የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙም እስራኤልን ወጉ፣ በጦርነቱም ከእነርሱ ጋር ነበሩ። እዚህ ጋ “እስራኤል” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። (የአነጋገር ዘይቤ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ከ -- ጋር መዋጋት እንድንችል”
እዚህ ጋ “ቤት” የሚያመለክተው በቤቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “ቤተሰቦቼ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ለዚህ ነው” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው ዮፍታሔ በችግር ውስጥ ስለመሆናቸው የተናገረውን ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉሙ ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “አሁን ወደ አንተ የመጣነው በችግር ውስጥ ስለሆንን ነው”።
“የአሞንን ሰዎች ውጋቸው”
እነዚህ ሁለት ቃላት መሰረታዊ ትርጉማቸው አንድ ሆኖ ሳለ የዮፍታሔን አስፈላጊነት አጽንዖት ለመስጠት ተደግመዋል። ሁለቱን ቃላት ልታጣምራቸው ትችላለህ። አ.ት፡ “አዛዥ”።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። እዚህ ጋ “በእግዚአብሔር ፊት” የሚለው ሐረግ የተናገረውን ቃል በአግዚአብሔር ፊት እንደ መሓላ ደገመው ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው መሪያቸው ለመሆን ለገለዓድ መሪዎች የተናገረውን ቃል ነው።
“በመካከላችን ለምን ጸብ ይሆናል?” ዮፍታሔ ንጉሡ በእስራኤል ላይ ለምን እንደ ተቆጣ ይጠይቃል።
“አንተ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የአሞንን ንጉሥ ሲሆን ራሱንና ወታደሮቹን ይወክላል። አ.ት፡ “ወታደሮችህ መሬታችንን ለመያዝ ለምን ይመጣሉ”
“በጉልበት ለመውሰድ የመጡት”
እነዚህ የሁለት ወንዞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ከዮርዳኖስ ወንዝ በወዲያ በኩል”
“በሰላማዊ መንገድ” ወይም “ልትከላከላቸው እንዳትሞክር”
እዚህ ጋ “እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለንጉሡ የሚናገረውን መልዕክተኛ ነው። ይህ ምናልባት በቡድን የሆኑትን መልዕክተኞች በሚያመለክተውና በተከፈተው ተለዋዋጭ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንዳለው “እነርሱ” ተብሎ መጻፍ ይኖርበት ይሆናል። አ.ት፡ “መልዕክተኞቹ እንዲህ እንዲሉ ዮፍታሔ ነገራቸው” ወይም “እንዲህ አሉ”።
ሰዎች ወደ ተስፋይቱ ምድር በሚጓዙበት ጊዜ ሁሉ ወደ ተስፋይቱ ምድር “ወደ ላይ” እንደ ሄዱ ይነገርላቸዋል። እስራኤላውያን ግብፅን ለቀው በወጡ ጊዜ ወደ ተስፋይቱ ምድር በመጓዝ ላይ ነበሩ። አ.ት፡ “ግብፅን ለቀው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
መልዕክተኞቹ የተላኩት በእስራኤል መሪዎች ናበር። አ.ት፡ “የእስራኤል መሪዎች መልዕክተኞችን በላኩ ጊዜ”
“በመሐል ሲሄዱ” ወይም “ማቋረጥ”
ይህ ቃል ዘይቤአዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙም “እምቢ” ማለት ነው። አ.ት፡ “እምቢ አለ” ወይም “ጥያቄአቸውን አልተቀበለም” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እስራኤል ወደ ሞዓብ ንጉሥ መልዕክተኞችን የላኩበት ምክንያት ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ደግሞም ወደ ሞዓብ ንጉሥ ተመሳሳዩን ጥያቄ የሚያቀርቡ መልዕክተኞችን ላኩ”
እስራኤል በሞዓብ መካከል ለማለፍ ያቀረበውን ጥያቄ የሞዓብ ንጉሥ አልተቀበለውም። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በበለጠ ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “እርሱም ደግሞ እምቢ አለ፣ በሞዓብ ምድር መካከል እንዲያልፉም አልፈቀደላቸውም”።
ይህ የወንዝ ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 11፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
መልዕክተኞቹ የተላኩት በእስራኤል መሪዎች ነው። አ.ት፡ “የእስራኤል መሪዎች መልዕክተኞችን በላኩ ጊዜ”
ይህ የሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ሴዎን በምድሩ በሰላም ያልፋል ብሎ እስራኤልን አላመነም። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ይሁን እንጂ ሴዎን የእስራኤል ሕዝብ በግዛቱ በኩል በሰላም ያልፋል ብሎ አላመነም”።
“እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሴዎንን ሲሆን ይህም ራሱንና ሰራዊቱን ይወክላል። አ.ት፡ “በዚያ ተዋጉ” ወይም “በዚያ ሰራዊቱ ተዋጋ”
የዚህን ሰው ስም በመሳፍንት 11፡19 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው በጦርነት የማሸነፍ ኃይልን ነው። አ.ት፡ “በሴዎንና በሕዝቡ ሁሉ ላይ ለእስራኤል ኃይልን ሰጠው”። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የእነዚህን ወንዞች ስም በመሳፍንት 11፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
ዮፍታሔ ምላሽ በማይፈልግ በዚህ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ ይገስጸዋል። “የእነርሱ” የሚለው ቃል እስራኤልን ያመለክታል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በመሆኑም፣ መሬታቸውን የራስህ አድርገህ መውሰድ አይኖርብህም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አምላክህ ካሞሽ የሚሰጥህን ምድር ብቻ መውሰድ ይኖርብሃል”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙ አንድን ነገር በቁጥጥር ስር ማድረግ ማለት ነው። አ.ት፡ “በቁጥጥርህ ስር አድርግ” ወይም “የራስህ አድርግ”። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሐሰተኛ አምላክ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “አንተ የሞዓብ ንጉሥ ከነበረው ከሴፎር ልጅ ከባላቅ አትሻልም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የሰዎች ስምች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ይሁን እንጂ ከእስራኤል ጋር ለመከራከር አልደፈረም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከቶ በእነርሱ ላይ ጦርነትን አላወጀም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“300 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
በመሳፍንት 11፡19 ላይ በተረጎምክበት መልኩ የዚህችን ከተማ ስም ተርጉም።
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
በመሳፍንት 11፡13 ላይ በተረጎምክበት መልኩ የዚህችን ከተማ ስም ተርጉም።
ዮፍታሔ ምላሽ በማይሻ ጥያቄ የአሞናውያንን ንጉሥ እየገሰጸው ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “በዚያን ጊዜ ማስመለስ ነበረብህ” ወይም “ከአመታት በፊት ልታስመልሳቸው ይገባህ ነበር፤ አሁን ግን በጣም ዘግይተሃል” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ዮፍታሔ የሚናገረው ሴዎንን ነው። እዚህ ጋ፣ ዮፍታሔ፣ ራሱን እንደ እስራኤላውያን፣ ንጉሣቸውን ሴዎንን እንደ አሞናውያን አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እስራኤላውያን ሕዝብህን አልበደሉም፣ ይሁን እንጂ ሕዝብህ እየወጉን በድለውናል”።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አንድን ሰው መበደል ማለት እነርሱን መበደል ነው። አ.ት፡ “የማይገባውን አላደረግሁብህም … የማይገባውን አድርገህብኛል” ወይም “ኢፍትሐዊ አልሆንኩብህም … ኢፍትሐዊ ሆነህብኛል”። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙም በዮፍታሔ ውሳኔዎች ላይ መንፈስ ቅዱስ ተጽዕኖ አሳድሯል ማለት ነው። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር መንፈስ ዮፍታሔን ተቆጣጠረው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ዮፍታሔ በእነዚህ አካባቢዎች ከአሞን ሰዎች ጋር ለሚያደርገው ውጊያ ሰዎችን በሰራዊቱ ውስጥ ለማካተት እየመዘገባቸው አለፈ። የዚህ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከምጽጳ ገለዓድ … ሰዎችን ወደ ሰራዊቱ እየሰበሰበ በገለዓድና ምናሴ መካከል አለፈ”።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙ አንድን ነገር መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብ ማለት ነው። አ.ት፡ “እርሱን እሠዋልሃለሁ” ወይም “መሥዋዕት አድርጌ አቀርብልሃለሁ”። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ዮፍታሔ የሰራዊቱ መሪ በመሆኑ፣ እርሱና ሰራዊቱ በተደጋጋሚ ዮፍታሔን ራሱን ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ስለዚህ ዮፍታሔና ሰራዊቱ አለፉ -- ተዋጉ -- እግዚአብሔር ድልን ሰጣቸው”
የዚህችን ከተማ ስም በመሳፍንት 11፡26 ላይ በተረጎምክበት መልኩ ተርጉም።
እነዚህ የከተሞች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“20 ከተሞችን ጨምሮ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እንደ ከበሮ የሚመታበት አናት ያለው፣ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ድምፅ እንዲያሰማ በዙሪያው ቁርጥራጭ ብረቶች የሚደረጉለት የሙዚቃ መሣሪያ።
ይህ ለቅሶን ወይም ታላቅ ሐዘንን የሚያሳይ ድርጊት ነው። አ.ት፡ “ልብሱን በሐዘን ቀደደ” (ምሳሌአዊ ድርጊት የሚለውን ተመልከት)
ዮፍታሔ አንዱን አሳብ ሁለት ጊዜ መናገሩ እጅግ ስለ ማዘኑ አጽንዖት ለመስጠት ነው።
እዚህ ጋ፣ ዮፍታሔ ጥልቅ ሐዘኑን እንደሚሰባብረው አንደ አንዳች ነገር ቆጥሮ ይናገራል። አ.ት፡ “ጥልቅ ሐዘን ላይ ጥለሽኛል” ወይም “በሐዘን እንድሞላ አደረግሽኝ”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ዮፍታሔ የሚናገረው ጥልቅ ሐዘኑና ሥቃዩ እንደ ሕመም እንደሆነበት ነው። አ.ት፡ “አንቺ ሥቃይ እንደሚያመጣብኝ ዓይነት ሰው ሆነሻል” ወይም “ለጥልቅ ሐዘን ዳርገሽኛል”። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ቃልን ማጠፍ ማለት ልታደርገው ቃል የገባህበትን ጉዳይ መተው ነው። አ.ት፡ “ቃል የገባሁበትን ጉዳይ መፈጸም አለብኝ” ወይም “ቃሌን ለማጠፍ አልችልም”። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ጠላቶቹን በማሸነፍ እግዚአብሔር ተበቅሎለታል። የዚህ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በጠላቶችህ በአሞናውያን ላይ ተበቅሎልሃል”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስለ እኔ ይህንን ቃል ኪዳን ጠብቅ” ወይም “እኔን በሚመለከት ይህንን ቃል ኪዳን ጠብቅ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ድንግል በመሆኔ ምክንያት ላልቅስ” ወይም “ከእንግዲህ ስለማላገባ ላልቅስ”
ይህ አንድን ከገለዓድ የሆነን ሰው ያመለክታል። ይህንን በመሳፍንት 10፡3 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
1 ወደ ኤፍሬም ሰዎችም ጥሪ ደረሰ፤ በጻፎን በኩል ተሻግረው ዮፍታሔን፣ “ከአሞን ሕዝብ ጋር ለመዋጋት ስታልፍ ከአንተ ጋር እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምድን ነው? ቤትህን በአንተ ላይ እናቃጥለዋለን” አሉት፡፡ 2 ዮፍታሔም እንዲህ አላቸው፣ “እኔና ሕዝቤ ከአሞን ሕዝብ ጋር በታላቅ ጦርነት ውስጥ ነበርን፡፡ በጠራኋችሁም ጊዜ ከእነርሱ አላዳናችሁኝም፡፡ 3 እናንተም እንዳላዳናችሁኝ ባየሁ ጊዜ፣ ሕይወቴን በራሴ ብርታት አስቀምጬ በአሞን ሕዝብ ላይ ለመዋጋት አለፍሁ፣ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ድል ሰጠኝ፡፡ ዛሬ እኔን ለመውጋት ለምን መጣችሁ? 4 ዮፍታሔም የገለዓድን ሰዎች ሁሉ ሰበሰበና ከኤፍሬምም ጋር ተዋጋ፡፡ የገለዓድም ሰዎች የኤፍሬምን ሰዎች ወጓቸው ምክንቱም፣ “እናንተ ገለዓዳውያን በኤፍሬም ውስጥ ሸሽታችሁ የተጠጋችሁ፣ በኤፍሬምና በምናሴ ውስጥ ጥገኞች የሆናችሁ ናችሁ” ይሏቸው ነበርና፡፡ 5 ገለዓዳውያንም ወደ ኤፍሬም የሚወስደውን የዮርዳኖስን መሻገሪያ ያዙባቸው፡፡ አምልጦ የሚሸሽ የኤፍሬም ሰው፣ “ወንዙን ተሻግሬ ልለፍ” ባለ ጊዜ፣ የገለዓድ ሰዎች ደግሞ እንዲህ ይሉታል፣ “አንተ ኤፍሬማዊ ነህን?” እርሱም፣ “አይደለሁም” ቢል፣ 6 እነርሱም “ሺቦሌት በል” ይሉታል፡፡ እርሱም “ሲቦሌት” ብሎ ከተናገረ (ምክንያቱም እርሱ ቃሉን አጥርቶ መናገር አይችልምና) ፣ ገለዓዳውያን እርሱን ይዘው በዮርዳኖስ መሻገሪያ ላይ ይገድሉታል፡፡ በዚያም ጊዜ አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ፡፡ 7 ዮፍታሔም በእስራኤል ላይ ለስድስት ዓመት እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ ከዚያም ገለዓዳዊውም ዮፍታሔ ሞተ፣ ከገለዓድ ከተሞችም በአንዱ ተቀበረ። 8 ከእርሱም በኋላ የቤተ ልሔሙ ኢብጻን በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ 9 እርሱም ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፡፡ ሠላሳ ሴቶች ልጆችንም ወደ ውጭ በትዳር ለሌሎች ሰጠ፣ ሠላሳ ሴቶች ልጆችን ደግሞ ከሌሎች ሰዎች በትዳር ለወንድ ልጆቹ አመጣ። በእስራኤልም ላይ ለሰባት ዓመት ፈረደ። 10 ኢብጻንም ሞተ፣ በቤተ ልሔምም ተቀበረ፡፡ 11 ከእርሱም በኋላ ዛብሎናዊው ኤሎም በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ እርሱም በእስራኤል ላይ ለአሥር ዓመት ፈረደ፡፡ 12 ዛብሎናዊውም ኤሎም ሞተ፣ በዛብሎንም ምድር ባለችው በኤሎም ተቀበረ፡፡ 13 ከእርሱም በኋላ የጲርዓቶናዊው የሂሌል ልጅ ዓብዶን በእስራኤል ላይ እንደ ፈራጅ አገለገለ፡፡ 14 እርሱም አርባ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ወንዶች የልጅ ልጆች ነበሩት፡፡ በሰባ አህያዎች ላይ ይጋልቡ ነበር፣ እርሱም በእስራኤል ላይ ለስምንት ዓመት ፈረደ፡፡ 15 የጲርዓቶናዊውም የሂሌል ልጅ ዓብዶን ሞተ፣ በተራራማውም በአማሌቃውያን አገር በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ውስጥ ባለችው በጲርዓቶን ውስጥ ተቀበረ፡፡
እዚህ ጋ “ጥሪ” የሚለው የነገር ስም እንደ ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የኤፍሬም ሰዎች በአንድ ላይ ተጠሩ” ወይም “የኤፍሬም ሰዎች ወታደሮቻቸውን በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው”። (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“መንገዳቸውን … አልፈው ሄዱ” ወይም “ጉዞአቸውን … አልፈው ተጓዙ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ የሚያመለክተው ቤቱን በውስጡ ካሉት ሰዎች ጋር ስለ ማቃጠል ነው። አ.ት፡ “ቤትህን በውስጡ እንዳለህ እናቃጥለዋለን”። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው የኤፍሬምን ሰዎች ነው።
ዮፍታሔ “እኔ” የሚለውን ቃል የሚጠቀመው ራሱንና የገለዓድን ሰዎች በሙሉ ለማመልከት ነው። አ.ት፡ “አታድኑን”
“እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን የኤፍሬምን ሰዎች ያመለክታል። ዮፍታሔ “እኔ” በሚልበት ጊዜ የሚያመለክተው ራሱን ጨምሮ የገለዓድን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “አላዳናችሁንም”።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ በራስ ጉልበት በመደገፍ ራስን ለአደጋ መስጠት ማለት ነው። ዮፍታሔ የገለዓድን ሰዎች እንደ ራሱ አድርጎ ማመልከቱን ይቀጥላል። አ.ት፡ “በራሳችን በመተማመን ሕይወታችንን ለአደጋ ሰጥተናል”። (የአነጋገር ዘይቤ እና የሚለውን ተመልከት)
በአሞናውያን ላይ እግዚአብሔር ለገለዓድ ሰዎች ድልን እንደ ሰጣቸው ዮፍታሔ ያመላክታል። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ መብራራት ይችላል። አ.ት፡ “በእነርሱ ላይ እግዚአብሔር ድልን ሰጥቶናል” ወይም “በጦርነት እንድናሸንፋቸው እግዚአብሔር ፈቅዶልናል”
“እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ዮፍታሔንና የገለዓድን ተዋጊዎች ሁሉ ነው። አ.ት፡ “ከኤፍሬም ጋር ተዋጉ”
“እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው የኤፍሬምን ሰዎች ነው። ዮፍታሔ “እኔ” በሚልበት ጊዜ የሚያመለክተው ራሱን ጨምሮ የገለዓድን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “እኛን ልትወጉን ለምን መጣችሁ”
የዚህን ስድብ ትርጉም ግልጽ ልታደርገው ትችላለህ። አ.ት፡ “ይህ ቦታ ለእናንተ ለገለዓዳውያን አይገባችሁም። እናንተ በዚህ ለመኖር የመጣችሁ ሰዎች ብቻ ናችሁ”
ይህ ማለት በአሞን በኩል ሲያልፉ ከአሞናውያን ጋር ተዋጉ። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በግዛታቸው በኩል ስናልፍ ክአሞን ሰዎች ጋር ተዋጋን”
የገለዓድ ሰዎች
“በኤፍሬምና በምናሴ አውራጃዎች” ወይም “በኤፍሬምና በምናሴ ምድር”። እዚህ ጋ “ኤፍሬም” እና “ምናሴ” የሚያመለክቱት አውራጃዎችን ሲሆን በዚያ በሚኖሩ ነገዶች ስም ተሰይመዋል።
“ለኤፍሬም ምድር”
“ገለዓዳውያን ተቆጣጠሩት” ወይም “ገለዓዳውያን ያዙት”
እነዚህ ውሃው ጥልቀት የሌለው በመሆኑ በእግር ልታቋርጥ የምትችለው ወንዝ ያሉባቸው አካባቢዎች ናቸው።
ከኤፍሬም ነገድ የሆነ ሰው
እነዚህ ቃላት ምንም ትርጉም የላቸውም። እነዚህን ቃላት ወደ ራስህ ቋንቋ ቅዳቸውና በቃላቱ መጀመሪያ ላይ “ሺ” እና “ሲ” የሚሉ ፊደላት ለየብቻ መተርጎማቸውን እርግጠኛ ሁን። (ቃላትን መቅዳት ወይም መዋስ የሚለውን ተመልከት)
“የቃላቱን ድምፅ ማውጣት”
“42,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያንን ገደሉ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ገለዓዳዊው ዮፍታሔ ሞተና ቀበሩት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከቤተ ልሔም የሆነ የአንድ ሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ዳረ” የሚለው ቃል የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ልጆቹ እንዲያገቡ ፈቅዷል ማለት ነው። አ.ት፡ “ሠላሳ ሴቶች ልጆች ነበሩትና እያንዳንዳቸው እንዲያገቡ ቅድመ ዝግጅት አደረገላቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ከውጭ አመጣላቸው” የሚለው የአነጋገር ዘይቤ ትርጉሙ ከሌላ ጎሳ የሆኑት ሴቶች ከወንዶች ልጆቹ ጋር ተጋቡ ማለት ነው። አ.ት፡ “ከራሱ ጎሳ ውጭ ካሉ ሰዎች ሠላሳ ሴቶች ልጆች የእርሱን ወንዶች ልጆች እንዲያገቡ አደረገ”። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በቤተ ልሔም ቀበሩት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ከዛብሎን ነገድ የሆነ አንድ ሰው
የዚህን ቦታ ስም በመሳፍንት 1፡35 ላይ እንደተረጎምከው ተርጉመው።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በኢያሎን ቀበሩት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ጲርዓቶን የቦታ ስም ሲሆን ከዚያ አካባቢ የሆነ ሰው ደግሞ ጲርዓቶናዊ ይባላል። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሰዎች የሚቀመጡባቸውን ሰባ አህዮች የራሳቸው ማድረግ ችለዋል። እዚህ ጋ “መቀመጥ” የሚለው ቃል “የራስ ማድረግ” ከሚለው ይልቅ ጥቅም ላይ ውሏል። አ.ት፡ “ሰባ አህዮች ነበሯቸው” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“40 ወንዶች ልጆች -- 30 የልጅ ልጆች -- 70 አህዮች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
1 የእስራኤልም ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ስራ እንደ ገና ሠሩ፣ እርሱም ፍልስጥኤማውያን በእነርሱ ላይ ለአርባ ዓመት እንዲገዙ ፈቀደላቸው፡፡ 2 ከዳን ቤተሰብ የሆነ ስሙም ማኑሄ የሚባል አንድ የጾርዓ ሰው ነበረ፡፡ ሚስቱም መካን ስለነበረች ልጅ አልወለደችም፡፡ 3 የእግዚአብሔርም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፣ “ተመልከቺ፣ አንቺ መካን ነበርሽ፣ ልጅም አልወለድሽም፣ ነገር ግን ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ 4 አሁንም የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ጠንካራ መጠጥ እንዳትጠጪ ተጠንቀቂ፣ ሕጉ ርኩስ እንደሆነ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብዪ፡፡ 5 ተመልከቺ፣ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ልጁ ከአንቺ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፡፡ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን ጉልበት ማዳን ይጀምራል፡፡ 6 የዚያን ጊዜ ሴቲቱ ወደ ባልዋ መጥታ እንዲህ ብላ ነገረችው፣ “አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፣ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ የሚመስል ነበረ፣ በጣምም አስደነገጠኝ፡፡ ከወዴት እንደ መጣ አልጠየቅሁትም፣ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፡፡ 7 እርሱም እንዲህ አለኝ፣ ‘ተመልከቺ! ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ስለዚህ ልጁ ከአንቺ ማኅፀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ስለሚሆን የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ጠንካራ መጠጥ እንዳትጠጪ፣ ሕጉ ርኩስ እንደሆነ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብዪ፡፡’” 8 ከዚያም ማኑሄ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፣ “ጌታ ሆይ፣ አሁን በቅርቡ ለሚወለደው ልጅ ምን ማድረግ እንዳለብን እንዲያስተምረን እባክህ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና ወደ እኛ ይምጣ፡፡” 9 እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት መለሰ፣ የእግዚአብሔርም መልአክ እንደ ገና ወደ ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች መጣ፡፡ ነገር ግን ባልዋ ማኑሄ ከእርስዋ ጋር አልነበረም፡፡ 10 ስለዚህ ሴቲቱም ፈጥና ሮጠችና ለባልዋ ነገረችው፣ “ተመልከት! በሌላኛው ቀን ወደ እኔ የመጣው ሰው እንደገና ተገለጠልኝ፡፡” 11 ማኑሄም ተነሳና ሚስቱን ተከተላት፡፡ ወደ ሰውዮውም በመጣ ጊዜ እንዲህ አለው፣ “ከሚስቴ ጋር የተነጋገርህ ሰው አንተ ነህን?” ሰውየውም፣ “እኔ ነኝ” አለው፡፡ 12 ስለዚህ ማኑሄ እንዲህ አለ፣ “አሁንም ቃሎችህ እውነት ይሁኑ፡፡ ነገር ግን ልጁ የሚመራው በምንድን ነው፣ እኛስ ለእርሱ የምንሰራው ምንድን ነው?” 13 የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄ እንዲህ አለው፣ “እርስዋ የነገርኋትን ነገር ሁሉ በጥንቃቄ ማድረግ አለባት፡፡ 14 ከወይን ከሚወጣው ማንኛውንም ነገር አትብላ፣ የወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር ሌላ ጠንካራ መጠጥ አትጠጣ፤ ሕጉ ርኩስ ነው ብሎ የገለጸውን ማንኛውንም ምግብ አትብላ፡፡ እኔ እንድታደርገው ያዘዝኋትን ማንኛውንም ነገር መታዘዝ አለባት፡፡ 15 ማኑሄም ለእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “ለአንተ የፍየል ጠቦት ለማዘጋጀት ጊዜ እናገኝ ዘንድ፣ እባክህ ለአጭር ጊዜ ቆይ፡፡” 16 የእግዚአብሔርም መልአክ ለማኑሄ እንዲህ አለው፣ “ብቆይም እንኳ፣ መብልህን አልበላም፡፡ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ፣ ያንን ለእግዚአብሔር አቅርበው፡፡” ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር፡፡ 17 ማኑሄም ለእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “የተናገርሃቸው ቃሎች እውነት በሆኑ ጊዜ እናከብርህ ዘንድ ስምህ ማን ነው?” 18 የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ አለው፣ “ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? ስሜ ድንቅ ነው!” 19 ስለዚህ ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቍርባን ጋር ወሰደና በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው፡፡ ማኑሄና ሚስቱ እያዩ እርሱ አስደናቂ ነገር አደረገ፡፡ 20 ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ላይ ዐረገ፡፡ ማኑሄና ሚስቱም ይህን ተመለከቱና በግምባራቸው ምድር ላይ ተደፉ፡፡ 21 የእግዚአብሔርም መልአክ ላማኑሄ ወይም ለሚስቱ እንደገና አልተገለጠም፡፡ ያን ጊዜም ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ፡፡ 22 ማኑሄም ለሚስቱ እንዲህ አላት፣ “እግዚአብሔርን ስላየን በእርግጠኝነት እንሞታለን፡፡” 23 ነገር ግን ሚስቱ እንዲህ አለችው፣ “እግዚአብሔር ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፣ ለእርሱ ያቀረብነውን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባልተቀበለን ነበር፡፡ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን ነበር፣ በዚህ ጊዜ እንዲህ ያሉ ነገሮችንም እንድንሰማ ባላደረገን ነበር፡፡” 24 ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሴቲቱ ወንድ ልጅ ወለደች፣ ስሙንም ሳምሶን ብላ ጠራችው፡፡ ልጁም አደገ እግዚአብሔርም ባረከው፡፡ 25 የእግዚአብሔርም መንፈስ እርሱን በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ያነቃቃው ጀመር፡፡
የእግዚአብሔር ፊት የእርሱን ፍርድ ወይም ምዘና ይወክላል። ይህንን በመሳፍንት 2፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “በእግዚአብሔር ፍርድ ክፉ የሆነውን” ወይም “እግዚአብሔር ክፉ ነው ያለውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” የሚወክለው በጦርነት ድል ማድረጊያ ኃይልን ነው። አ.ት፡ “ፍልስጥኤማውያን እንዲያሸንፏቸው ፈቀደ” ወይም “በፍልስጥኤማውያን እንዲጨቆኑ ፈቀደ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“40 ዓመት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በእስራኤል የነበረ ከተማ ስም ነው። እርሱ በዳን ድንበር አቅራቢያ በይሁዳ አውራጃ ነበር። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የዳን ነገድ ሰዎች
ይህ የሰው ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሕፃን ልጅን መወለድ ያመለክታል። አ.ት፡ “ወንድ ልጅ መውለድ” ወይም “ወንድ ሕፃን ልጅ ይኖርሻል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር መበላት የለበትም ያለው ነገር በአካላዊነቱም ንጹሕ እንዳይደለ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“አስተውይ” ወይም “አድምጪ”
እዚህ ጋ “ራስ” የሚያመለክተው ጸጉሩን ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ማንም ጸጉሩን እንዳይቆርጠው”(አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ጸጉርን ከቆዳ አጠገብ አድርሶ ለመቁረጥ የሚያገለግል ስል ቢለዋ ነው
ይህ ማለት እንደ ናዝራዊ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል ማለት ነው። አ.ት፡ “ለእግዚአብሔር የተሰጠ ናዝራዊ” ወይም “እንደ ናዝራዊ ለእግዚአብሔር የተሰጠ”
እዚህ ጋ “ማህፀን” የሚያመለክተው ሕፃን ከመወለዱ በፊት ያለውን ጊዜ ነው። አ.ት፡ “ከመወለዱ በፊት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እጅ” መቆጣጠር ማለት ነው። አ.ት፡ “ከፍልስጥኤማውያን ቁጥጥር” ወይም “በፍልስጥኤማውያን ቁጥጥር ስር ከመሆን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ሰውየው የተላከው በእግዚአብሔር ነው። ይህ ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር የላከው አንድ ሰው”
እዚህ ጋ “በጣም የሚያስፈራ” ማለት “አስደንጋጭ” ማለት ነው። አ.ት፡ “የእግዚአብሔርን መልአክ ይመስል ስለ ነበረ በጣም ፈርቼ ነበር”
“አስተውል” ወይም “አድምጥ”
ይህ የሕፃን ልጅ መወለድን ያመለክታል። አ.ት፡ “ወንድ ልጅ ትወልዳለች” ወይም “ወንድ ሕፃን ልጅ ይኖራታል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር መበላት የለበትም ያለው ነገር በአካላዊነቱም ንጹሕ እንዳይደለ ተነግሯል። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት እንደ ናዝራዊ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል። ይህንን በመሳፍንት 3፡5 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ለእግዚአብሔር የተሰጠ ናዝራዊ” ወይም “እንደ ናዝራዊ ለእግዚአብሔር የተሰጠ”
ይህ አጽንዖት የሚሰጠው በሕይወት ዘመኑ ሁሉ መሆን እንዳለበት ነው። አ.ት፡ “ሕይወቱን ሙሉ”
የዚህን ሰውዬ ስም በመሳፍንት 13፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ግልጽ ያልሆኑትን የዳራውን ቃላት ግልጽ ልታደርጋቸው ትችላለህ። አ.ት፡ “ወደ ማኑሄ ሚስት መጣ”
“ስማ” ወይም “የምነግርህን ልብ በል”
ይህ በመሳፍንት 13፡3 የእግዚአብሔርን መልአክ ያመለክታል። ይህ ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር ሰው”
“የተናገርከው ቃል”
እዚህ ጋ መልአኩ ከወይን “የሚወጣ” ሲል የትኛውንም ከወይን የሚገኘውን ምግብ እንደሆነ ያመላክታል። አ.ት፡ “በወይን ላይ የሚበቅል ማንኛውም ነገር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
እግዚአብሔር መበላት የለበትም ያለው ነገር በአካላዊነቱም ንጹሕ እንዳይደለ ተነግሯል። ይህንን ሐረግ በመሳፍንት 13፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ግልጽ ያልሆነውን የማኑሄን መግለጫ ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “እንድትበላው የፍየል ጠቦት እናብስልልህ”
“የተናገርከው ሲፈጸም”
መልአኩ በተግሳጽ መልክ ይህንን ጥያቄ ይጠይቃል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስሜ ማን መሆኑን መጠየቅ የለብህም” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ስሙን ለምን መጠየቅ እንደማይኖርባቸው በይበልጥ ግልጽ ማድረጉ ይጠቅም ይሆናል። አ.ት፡ “ለመረዳት እጅግ ያስቸግራችሁ ይሆናል”
ይህ ሕግ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ የእህል ቁርባን እንዲቀርብ ያዛል። አ.ት፡ “ከእርሱም ጋር የታዘዘውን የእህል ቁርባን” ወይም “አብሮት እንዲሆን የእህል ቁርባን”
“በመሠዊያው ላይ”። ማኑሄ መሥዋዕቱን ያቀረበበት መሠዊያ ዐለት ነበር።
“መልአኩ አንድ ነገር አደረገ”
“የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ተመልሶ ወደ ሰማይ ሄደ”
“በግምባራቸው ተደፉ” ይህ የአድናቆትና የአክብሮት ምልክት ነው፣ ሆኖም እግዚአብሔርን መፍራታቸውንም ያሳያል። (ምሳሌአዊ ድርጊት የሚለውን ተመልከት)
“እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ማኑሄና ሚስቱ ያዩትን ሰው ነው።
እግዚአብሔር እንደሚገድላቸው ማሰባቸውን ያሳያል። ይህ ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ስላየነው ይገድለናል”
የማኑሄ ሚስት ስለ አንዱ ነገር ሁለት ጊዜ የምትናገረው አጽንዖት ለመስጠት ነው። እነዚህ ሁለት መግለጫዎች መጣመር ይችላሉ። አ.ት፡ “እንድናደርግ የፈለገውን አይነግረንም ነበር”
“የማኑሄ ሚስት”
ይህ የልጅ መወለድን ያመለክታል። አ.ት፡ “ወንድ ልጅ ወለደች” ወይም “ወንድ ልጅ አገኘች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ዐዋቂ ሆነ” ወይም “ጎለመሰ”
እዚህ ጋ የእግዚአብሔር መንፈስ ሳምሶንን ማነቃቃቱ በማሰሮ ውስጥ ያለ ምግብ ከሚማሰልበት መንገድ ጋር ተነጻጽሯል። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር መንፈስ በሳምሶን ላይ ተጽዕኖ ማድረግ ጀመረ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ማህነህ ዳን ለዘለቄታቸው የሚኖሩበትን በሚፈልጉበት ወቅት የዳን ነገድ በጊዜያዊነት የሰፈሩበት ቦታ ስም ነው። ኤሽታኦል የከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የዚህን ከተማ ስም በመሳፍንት 13፡2 በተረጎምክበት መልኩ ተርጉመው
1 ሳምሶንም ወደ ተምና ወረደ፣ በዚያም ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች አንዲት ሴት አየ፡፡ 2 ከዚያ በተመለሰ ጊዜ፣ ለአባቱና ለእናቱ እንዲህ ሲል ነገራቸው፣ “በተምና ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች መካከል አንዲት ሴት አየሁ፡፡ ሚስቴ እንድትሆነኝ አሁን እርስዋን አምጡልኝና አጋቡኝ፡፡ 3 ነገር ግን እንዲህ አሉት፣ “ከዘመዶችህ ሴቶች ልጆች ወይም ከሕዝባችን ሁሉ መካከል ሴት የለምን? ካልተገረዙት ከፍልስጥኤማውያን ሚስት ለመውሰድ ትሄሄዳለህን?” ሳምሶንም ለአባቱ እንዲህ አለው፣ “እርስዋን አምጣልኝ፣ እርስዋን ባየኋት ጊዜ ደስ አሰኝታኛለችና፡፡” 4 ነገር ግን አባቱና እናቱ ይህ ነገር የመጣው ከእግዚአብሔር እንደሆነ አላወቁም፣ እርሱ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ግጭት ለመፍጠር ይፈልግ ነበርና፡፡ በዚያን ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ይገዙ ነበርና፡፡ 5 ከዚያም ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ተምና ወረዱ፣ እነርሱም በተምና ወዳለው ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ መጡ፡፡ ከዚያም ከአንበሳ ደቦሎች መካከል አንዱ ተነስቶ መጣና በእርሱ ላይ አገሳበት፡፡ 6 የእግዚአብሔር መንፈስ በድንገት በእርሱ ላይ ወረደ፣ ትንሽ የፍየል ጠቦት እንደሚቆራርጥ እንዲሁ አንበሳውን በቀላሉ ቈራረጠው፣ በእጁም ምንም ነገር አልያዘም ነበር፡፡ ነገር ግን ያደረገውን ነገር ለአባቱ ወይም ለእናቱ አልነገራቸውም፡፡ 7 እርሱም ሄደና ከሴቲቱ ጋር ተነጋገረ፣ እርስዋንም ባያት ጊዜ ሳምሶንን ደስ አሰኘችው፡፡ 8 ከጥቂትም ቀን በኋላ ሊያገባት ተመለሰ፣ የአንበሳውንም በድን ያይ ዘንድ ከመንገድ ዘወር አለ፡፡ በአንበሳ በድን ትራፊ ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮበት ነበር፣ ማርም ነበረበት፡፡ 9 ማሩንም በእጁ ወስዶ መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፡፡ ወደ አባቱና ወደ እናቱ በመጣ ጊዜ፣ ለእነርሱም ሰጣቸውና እነርሱም በሉ፡፡ ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን ትራፊ ውስጥ እንደ ሆነ አልነገራቸውም፡፡ 10 የሳምሶን አባትም ሴቲቱ ወደ ነበረችበት ወረደ፣ ሳምሶንም በዚያ ግብዣ አደረገ፣ ይህን ማድረግ የወጣት ወንዶች ወግ ነበርና፡፡ 11 የእርስዋ ዘመዶች ባዩት ጊዜ፣ ከእርሱ ጋር ይሆኑ ዘንድ ሌሎች ሠላሳ ጓደኞች አመጡለት፡፡ 12 ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “አሁን እንቆቅልሽ ልንገራችሁ፡፡ ከእናንተ ውስጥ አንዱ ሰው እንቆቅልሹን ማግኘት ቢችልና በሰባቱ የግብዣ ቀኖች ውስጥ መልሱን ቢነግረኝ፣ ሠላሳ የቀጭን በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ እሰጠዋለሁ፡፡ 13 ነገር ግን እናንተ መልሱን ልትነግሩኝ ካልቻላችሁ፣ ሠላሳ የቀጭን በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ ትሰጡኛላችሁ፡፡” እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “እንሰማው ዘንድ እንቆቅልሽህን ንገረን፡፡” 14 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ከበላተኛው ውስጥ መብል ወጣ፤ ከብርቱም ውስጥ ጣፋጭ ወጣ፡፡” ነገር ግን የእርሱ እንግዶች በሦስት ቀን ውስጥ መልሱን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ 15 በአራተኛውም ቀን ለሳምሶን ሚስት እንዲህ አሏት፣ “የእንቈቅልሹን መልስ እንዲነግረን ባልሽን አግባቢልን፣ አለዚያ ግን እንቺንና የአባትሽን ቤት በእሳት እናቃጥላለን፡፡ ወደዚህ የጠራችሁን ድሃ ልታደርጉን ነውን፡፡” 16 የሳምሶን ሚስት በፊቱ ማልቀስ ጀመረች፤ እንዲህም አለችው፣ “ይህን ሁሉ ያደረግኸው እኔን ስለምትጠላኝ ነው! አንተ አትወደኝም፡፡ ከሕዝቤ ውስጥ ለአንዳንዶቹ እንቈቅልሽ ነግረሃቸዋል፣ ነገር ግን መልሱን ለእኔ አልነገርኸኝም፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “ወደዚህ ተመልከቺ፣ ለአባቴና ለእናቴ ካልነገርኋቸው፣ ለአንቺ ልነግርሽ ይገባልን?” 17 ግብዣቸው በሚቆይበት በሰባቱም ቀናት ውስጥ በፊቱ አለቀሰች፡፡ መልሱንም በሰባተኛው ቀን ነገራት ምክንቱም እጅግ በጣም አጥብቃ ስለነዘነዘችው ነው፡፡ መልሱንም ለሕዝቧ ዘመዶች ነገረቻቸው፡፡ 18 በሰባተኛው ቀን ፀሐይ ከመግባትዋ በፊት የከተማይቱ ሰዎች እንዲህ አሉት፣ “ከማር የበለጠ የሚጣፍጥ ምንድን ነው? ከአንበሳስ የበለጠ የሚበረታ ምንድን ነው?” ሳምሶንም እንዲህ አላቸው፣ “በጊደሬ ባታርሱ ኖሮ፣ ለእንቈቅልሼ መልስ ባላገኛችሁ ነበር፡፡” 19 በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በድንገት በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደ፡፡ ሳምሶንም ወደ አስቀሎና ወረደና ከሕዝቡ መካከል ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፡፡ እርሱም የለበሱትን ሁሉ ከገፈፈ በኋላ ልብሳቸውን በሙሉ ወስዶ እንቈቅልሹን ለመለሱለት ሰዎች ሰጣቸው፡፡ እርሱም በጣም ተናደደና ወደ አባቱ ቤት ወጣ፡፡ 20 የሳምሶን ሚስት ግን በጣም ቅርብ ለሆነው ጓደኛው ተሰጠች፡፡
“ወረደ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የአባቱ ቤት ካለበት ተምና ዝቅ ባለ ስፍራ ስለሚገኝ ነው። ተምና በሶሬቅ ሸለቆ የሚገኝ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ሴት ልጅ” የሚለው ቃል ያላገባችን ወጣት ሴት የሚያመለክት የትህትና አገላለጽ ነው። አ.ት፡ “በፍልስጥኤም ሰዎች መካከል አንዲት ያላገባች ሴት” ወይም “ፍልስጥኤማዊት ልጃገረድ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ሳምሶን ወላጆቹ የፍስጥኤማዊቷ ሴት ወላጆችን ለጋብቻ እንዲጠይቁለት ግድ እያላቸው ነው። አ.ት፡ “ሚስት እንድትሆነኝ አሁን አጋቡኝ” ወይም “እርሷን እንዳገባት ቅድመ ዝግጅት አድርጉልኝ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህንን ጥያቄ ሳምሶንን የሚጠይቁት ከገዛ ሕዝባቸው መካከል ሚስት ሊያገኙለት እንደሚችሉ አሳብ ለመስጠት ነው። ይህ ጥያቄ በመግለጫነት ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “በርግጥ ማግባት እንድትችል በሕዝብህ መካከል ሴቶች አሉ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“ሴት ልጅ” የሚለው ቃል ያላገባችን ወጣት ሴት የሚያመለክት የትህትና አገላለጽ ነው። አ.ት፡ “በዘመዶችህ መካከል ካላገቡት ሴቶች አንዷን”
ይህ ጥያቄ የተጠየቀው ሳምሶንን ለመገሰጽ ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል። ወላጆቹ ፍልስጥኤማዊት እንዲያገባ ያልፈለጉበትን ምክንያት ግልጽ ማድረግ ትችላለህ። አ.ት፡ “የፍልስጥኤም ሰዎች እግዚአብሔርን ስለማያመልኩ በእርግጠኝነት ፍልስጥኤማዊት ማግባት አይኖርብህም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። ሳምሶን ስለ ጋብቻው የፍልስጥኤማዊቷን ሴት ወላጆች እንዲያነጋግሩለት ወላጆቹን ግድ እያላቸው ነበር። አ.ት፡ “አሁን ሚስት እንድትሆነኝ አዘጋጁልኝ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ሴቲቱ ቆንጆ እንደ ሆነች ሳምሶን ያስባል። “ቆንጆ በመሆኗ ደስ ብሎኛል” ወይም “እርሷ ቆንጆ ናት”
ይህ የሚያመለክተው ፍልስጥኤማዊቱን ሴት ለማግባት ሳምሶን ያቀረበውን ጥያቄ ነው።
“እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው።
“ወረደ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የአባቱ ቤት ካለበት ተምና ዝቅ ባለ ስፍራ ስለሚገኝ ነው። ተምና በሶሬቅ ሸለቆ የሚገኝ ከተማ ነበር። የዚህን ከተማ ስም በመሳፍንት 14፡1 እንዳደረግኸው በተመሳሳይ መንገድ ተርጉመው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እነሆ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የአንባቢዎችን ትኩረት በታሪኩ ውስጥ ወደሚመጣው አስደናቂ ሁነት ለመሳብ ነው። “መጣበት” የሚለው ቃል ትርጉሙ አንበሳው ወደ እርሱ ቀርቧል ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“አስፈራራው”። ይህ አንበሳ አንድን እንስሳ ለማጥቃት በሚያስፈራራበት ጊዜ የሚያሰማው ዓይነት ድምፅ ነው።
“መጣበት” የሚለው ቃል ትርጉሙ የእግዚአብሔር መንፈስ ሳምሶን ላይ ተጽዕኖ አሳደረበት ማለት ነው። በዚህ ጉዳይ፣ በኃይል አበረታው። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል አበረታው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ለሁለት ቆራረጠው
እዚህ ጋ፣ በእጁ ምንም ነገር ሳይኖር የሚለው መግለጫ የጦር መሣሪያ አልያዘም ነበር ለሚለው አጽንዖት ለመስጠት ነው። አ.ት፡ “የጦር መሣሪያ አልነበረውም”
ይህ ማለት በጣም ቆንጆ እንደሆነች አስቧል። አ.ት፡ “በቁንጅናዋ ተደስቷል” ወይም “በጣም ቆንጆ እንደ ነበረች አስቧል”
ይህ ማለት፣ አንድ ነገር ለማድረግ መንገዱን ትቶ ወጣ አለ። አ.ት፡ “መንገዱን ትቶ ወጣ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የሞተ አካል
እዚህ ጋ “እነሆ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የአንባቢዎችን ትኩረት በታሪኩ ውስጥ ወደሚመጣው አስደናቂ ሁነት ለመሳብ ነው። አ.ት፡ “ንቦች ወረዉት አገኘው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እጅግ የበዙ ነፍሳት
“ሰብስቦ”
“ወረደ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የሳምሶን አባት ከሚኖርበት ተምና ዝቅ ባለ ስፍራ የሚገኝ መሆኑን ለመግለጽ ነው። አ.ት፡ “የሳምሶን አባት ሴቲቱ ወደምትኖርበት ሄደ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የጋብቻ ልማድ እንደ ነበረ መግለጹ ጠቃሚ ይሆን ይሆናል። አ.ት፡ “የሚያገቡ ወጣቶች ልማድ”
“30 ጓደኞቻቸው” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ተጫዋቾቹ ለአስቸጋሪው ጥያቄ መልስ ማግኘት የሚኖርባቸው ውድድር
ይህ ማለት የዕንቆቅልሹን ትርጉም መንገር የሚችል ማለት ነው። አ.ት፡ “ትርጉሙን መንገር የሚችል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“30 የላይነን ቀሚሶችንና 30 ሙሉ ልብስ” (ቁጥሮችን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እናንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው በግብዣው ላይ የነበሩትን እንግዶች ነው።
የልብስ ዓይነት
“ከበላተኛው ውስጥ የሚበላ ነገር ተገኘ” ወይም “አንድ የሚበላ ነገር ከአንድ ከሚበላ ነገር ውስጥ ወጣ”
“በላተኛው” የሚለው ስም ወደ ግሣዊ ሐረግ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሚባላው ነገር”
“ከብርቱው ውስጥ የሚጣፍጥ ነገር ወጣ” ወይም “ብርቱ ከሆነው ነገር ውስጥ ጣፋጭ የሆነ ነገር ወጣ”
ይህ የሚያመለክተው ብርቱ የሆነን ነገር ነው። አ.ት፡ “ብርቱው ነገር”
“በግብዣው ላይ የነበሩት ሰዎች”
እዚህ ጋ፣ የዕንቆቅልሹን መልስ መንገር እንደ አንዳች የተደበቀና እንግዶቹ ፈልገው ሊያገኙት እንደሚያስፈልጋቸው ነገር ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “መልሱን መንገር አልቻሉም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ቀን 4”
እነርሱ ሊያደርጉት የማይፈልጉትን ነገር እንዲያደርግ አንድን ሰው ማሳሳት ወይም ማሞኘት
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ ትክክለኛውን ቤት ያመለክታል። አ.ት፡ “አባትሽና ቤተሰቡ የሚኖሩበትን ቤት” ወይም 2) “ቤት” የሚያመለክተው በውስጡ የሚኖሩትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “ቤተሰብሽ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“እናቃጥለዋለን” የሚለው ቃል ትርጉም አንድን ነገር ሙሉ በሙሉ ማቃጠል ማለት ነው። አንድ ሰው “ከተቃጠለ” ያ ሰው ተቃጥሎ ሞቷል ማለት ነው።
ክፉ ስለማድረጓ ለመክሰስ ይህንን ይጠይቋታል። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “እዚህ የጠራሽን ድኻ ልታደርጊን ነው!”
ዕንቆቅልሹን ካልፈቱና አዲስ ልብሶች ከገዙለት ድኻ ይሆናሉ። አ.ት፡ “አዲስ ልብሶች እንድንገዛለት በማስገደድ ድኻ ልታደርጊን ነው”
የሳምሶን ሚስት አጽንዖት ለመስጠት ያህል ሁለት ጊዜ የምትናገረው በመሠረቱ አንድ ነው። አ.ት፡ “በእውነት ፈጽሞ አትወደኝም”
ተጫዋቾቹ ለአስቸጋሪው ጥያቄ መልስ ማግኘት የሚኖርባቸው ውድድር
ይህ ጥቅም ላይ የዋለው የአንድን ሰው ትኩረት ለማግኘት ነው። እዚህ ጋ “ተመልከቱ” ማለት “አድምጡ” ማለት ነው። አ.ት፡ “አድምጡኝ” ወይም “የምናገረውን ልብ በሉ”
መልሱን እንዲነግራት ግድ ስላለችው ሳምሶን እየገሰጻት ነበር። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሆኖ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “ለአባቴ ወይም ለእናቴ እንኳን አልነገርኳቸውም፤ አልነግርሽም” ወይም “ከአንቺ ይልቅ ቅርቤ ለሆኑት ለወላጆቼ እንኳን አልነገርኳቸውምና እንድነግርሽ ግድ ልትዪኝ አይገባም”
ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች 1) “በግብዣቸው በሰባቱ ቀናት” ወይም 2) “ከሰባቱ የግብዣቸው ቀናት በቀሩት”
“ቀን 7”
እዚህ ጋ “ነዘነዘችው” የሚለው ቃል ትርጉም “ግድ አለችው” የሚል ይሆናል። አ.ት፡ “እንዲነግራት መጨቅጨቋን ቀጠለች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው የሳምሶን ሚስት ዘመዶችን ነው። ይህ በግልጽ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “ወጣቶቹ” ወይም “ዘመዶቿ”
“ቀን 7”
ይህ የዕንቆቅልሹ መልስ ነው። በጥያቄ ፈንታ እንደ መግለጫ ሆኖ መጻፍ ይኖርበት ይሆናል። አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ መረጃ በማከል ይህ ከዕንቆቅልሹ ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ግልጽ ማድረግ ይቻላል። አ.ት፡ “ማር ጣፋጭ ነው፣ አንበሳም ብርቱ ነው” ወይም “ማር ጣፋጭ ነው፣ እርሱም ከአንበሳ ውስጥ ወጣ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና የሚለውን ተመልከት)
ሳምሶን መልሱን ለማግኘት ሚስቱን መጠቀማቸውን አንድ ሰው የራሱን እርሻ ለማረስ የሌላውን ሰው ጥጃ ከመጠቀሙ ጋር ያነጻጽራል። አ.ት፡ “በሚስቴ ባትጠቀሙ ኖሮ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ማረስ ማለት ዐፈሩን ለዘር ለማዘጋጀት እንስሳን በመጠቀም ስለታማውን ብረት ዐፈር ውስጥ አስገብቶ መሳብ ነው።
“መጣበት” የሚለው ቃል ትርጉሙ የእግዚአብሔር መንፈስ ሳምሶን ላይ ተጽዕኖ አሳደረበት ማለት ነው። በዚህ ጉዳይ፣ በኃይል አበረታው። አ.ት፡ “የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል አበረታው” ወይም “ሳምሶንን በጣም ኃይለኛ አደረገው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ከሰዎቻቸው 30 ገደለ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች”
አብዛኛውን ጊዜ ከውጊያ ወይም ከጦርነት በኋላ በኃይል የሚወሰዱ ነገሮች
እነዚህ ከአስቀሎና የወሰዳቸው ብዝበዛዎቹ ነበሩ። አ.ት፡ “የወሰዳቸውን ሙሉ ልብሶች”
“በጣም ተናዶ”
እዚህ ጋ የአባቱ ቤት ከሚገኝበት አካባቢ ሳምሶን የነበረበት ተምና የመሬት አቀማመጡ ዝቅ ያለ ስለነበረ “ወጣ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሚስቱ አባት እርሷን ለቅርብ ጓደኛው ሰጣት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ከሌላው የቀረበ ጓደኛ”
1 ከጥቂት ቀናትም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ፣ ሳምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደ፡፡ ለራሱም እንዲህ አለ፣ “ወደ ሚስቴ ወደ ጫጉላው ቤት ልግባ፡፡” ነገር ግን አባትዋ ወደ ውስጥ እንዳይገባ ከለከለው፡፡ 2 አባትዋም እንዲህ አለ፣ “እኔ በእርግጠኝነት የጠላሃት መሰለኝ፣ ስለዚህም ለጓደኛህ ሰጠኋት፡፡የእርስዋ ታናሽ እኅት ከርስዋ የበለጠች ቆንጆ ናት፣ አይደለችም እንዴ? በእርስዋ ፋንታ ታናሽዋን ውሰዳት፡፡” 3 ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ጉዳት ባደረስሁባቸው ጊዜ እኔ ንጹሕ ነኝ፡፡” 4 ሳምሶንም ሄደና ሦስት መቶ ቀበሮዎች ያዘ፣ ሁለት ሁለቱንም ቀበሮዎች በአንድ ላይ በጅራታቸው አሰራቸው፡፡ ከዚያም ችቦዎችን ወስዶ በእያንዳንዱ ጥንድ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አሰራቸው፡፡ 5 ችቦውንም በእሳት ባቀጣጠለው ጊዜ፣ ቀበሮዎቹን በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል እንዲሄዱ አደረጋቸው፣ የእህሉን ነዶና በእርሻ ውስጥ የቆመውንም እህል፣ ከወይኑ አትክልት ስፍራና ከወይራውም ተክል ጋር አቃጠሉት፡፡ 6 ፍልስጥኤማውያንም እንዲህ በማለት ጠየቁ፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” እነርሱም “ይህን ያደረገው የተምናዊው አማች ሳምሶን ነው፣ ምክንያቱም ተምናዊው የሳምሶንን ሚስት ወስዶ ለጓደኛው ሰጥቶአታልና” አሉ፡፡ ፍልስጥኤማያንም ሄደው እርስዋንና አባትዋን በእሳት አቃጠሉ፡፡ 7 ሳምሶንም “እናንተ ይህንን ካደረጋችሁ፣ እኔ እበቀላችኋለሁ፣ እኔ የማርፈው ይህን ካደረግሁ በኋላ ነው” አላቸው፡፡ 8 እርሱም ዳሌአቸውንና ጭናቸውን ቆራረጣቸውና በታላቅ አገዳደል ገደላቸው፡፡ ከዚያም ወርዶ በኤጣም ዓለት ባለው ዋሻ ውስጥ ተቀመጠ፡፡ 9 የዚያን ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ወጡና በይሁዳ ጦርነት ለማካሄድ ተዘጋጁ፣ ሰራዊታቸውንም በሌሒ ውስጥ አሰፈሩ፡፡ 10 የይሁዳም ሰዎች እንዲህ አሉ፣ “እኛን ለመውጋት የመጣችሁት ለምንድን ነው?” እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “የምንወጋችሁ ሳምሶንን ለመያዝ ነው፣ እርሱ በእኛ ላይ እንዳደረገው እኛም በእርሱ ላይ ልናደርግበት ነው፡፡” 11 ሦስት ሺህ የይሁዳ ሰዎችም በኤጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወረዱና፣ ለሳምሶን እንዲህ አሉት፣ “ፍልስጥኤማውያን በእኛ ላይ ገዢዎች እንደሆኑ አታውቅምን? ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሳምሶንም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “እነርሱ በእኔ ላይ አደረጉብኝ፣ እኔም በእነርሱ ላይ አደረግሁባቸው፡፡” 12 እነርሱም ለሳምሶን እንዲህ አሉት፣ “አንተን አስረን ለፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ ራሳችሁ እንደማትገድሉኝ ማሉልኝ፡፡” 13 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “አንገድልህም፣ በገመድ አስረን ብቻ ለእነርሱ አሳልፈን እንሰጥሃለን፡፡ እንደማንገድልህ ቃል እንገባልሃለን፡፡” ከዚያም በሁለት አዲስ ገመዶች አሰሩትና ከዓለቱ ውስጥ አወጡት፡፡ 14 ወደ ሌሒ በመጣ ጊዜ፣ ፍልስጥኤማውያን እየጮሁ መጡ፣ አገኙትም፡፡ የዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል ወረደበት፡፡ ክንዶቹ የታሰሩበት ገመዶችም በእሳት እንደ ተቃጠለ የተልባ እግር ፈትል ከእጆቹ ላይ ወደቁ፡፡ 15 ሳምሶንም አዲስ የአህያ መንጋጋ አገኘ፣ እጁንም ዘርግቶ አነሳውና በእርሱ አንድ ሺህ ሰዎች ገደለ፡፡ 16 ሳምሶንም እንዲህ አለ፣ “በአህያ መንጋጋ ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፣ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰዎች ገድያለሁ፡፡” 17 ሳምሶንም መናገሩን በፈጸመ ጊዜ፣ የአህያ መንጋጋውን ከእጁ ጣለው፣ ያም ስፍራ ራማትሌሒ ተብሎ ተጠራ፡፡ 18 ሳምሶን በጣም ተጠምቶ ነበርና ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጮኸ፣ “አንተ ይህን ታላቅ ድል ለአገልጋይህ ሰጥተሃል፣ ነገር ግን አሁን በጥም እሞታለሁ፣ ባልተገረዙትም ሰዎች እጅ እወድቃለሁ፡፡” 19 እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን ክፍት ስፍራ ሰንጥቆ ከፈተው፣ ከእርሱም ውኃ ወጣ፡፡እርሱም በጠጣ ጊዜ፣ ብርታቱ ተመለሰና ተጠናከረ፡፡ ስለዚህ የዚያ ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ተብሎ ተጠራ፣ እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ ይገኛል፡፡ 20 ሳምሶን በፍልስጥኤማውያን ዘመን በእስራኤል ላይ ለሀያ ዓመት ፈረደ፡፡
ይህ ማሰብን ያመለክታል። አ.ት፡ “በራሱ አሰበ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሳምሶን ከሚስቱ ጋር ለመተኛት አስቦ ነበር። ይህ በግልፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አብረን እንድንተኛ ወደ ሚስቴ ክፍል አሄዳለሁ”
ሳምሶን ለራሱ ከተናገረው ውስጥ “የእርሷ ክፍል” የሚለውን ሐረግ መረዳት ይቻላል። ይህ እዚህ ጋር መደገም ይችላል። አ.ት፡ “ወደ ክፍሏ እንዲገባ አልፈቀደለትም”
ይህ ማለት ሚስት እንድትሆነው ለጓደኛው ሰጣት ማለት ነው። ይህ በግልፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከእርሱ ጋር እንድትጋባ ለጓደኛህ ሰጠኋት”
ይህን ጥያቄ የሚጠይቀው ሳምሶን ከእርሱ ጋር ሊስማማ እንደሚገባ ለማመልከት ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “እንደምትስማማ ተስፋ አደርጋለው”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ሳምሶን እንደ ሚስቱ እንዲወስዳት አስተያየት እየሰጠ ነው። ይህ በግልፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በእርሷ ምትክ ሚስት እንድትሆንህ ውሰዳት”
ሳምሶን፣ ፍልስጤማውያን ስለበደሉት ቢያጠቃቸው ንጹሕ እንደሚሆን ያስባል። ይህ በግልፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስለበደሉኝ ፍልስጤማውያንን ብጎዳቸው ንጹሕ እሆናለሁ”
“300 ቀበርዎች”
ቀበሮዎች እንደ ውሻ ያሉ ረጃጅም ጭራ ያላቸው፣ በጎጆ የሚኖሩ ወፎችንና ሌሎች ትናንሽ እንስሶችን የሚመገቡ እንስሶች ናቸው።
ጥንድ ማለት የትኛውም ነገር ሁለት ሆኖ ሲገኝ ነው፤ እንደ ሁለት ቀበርዎች ወይም ሁለት ጭራዎች።
“በጭራዎቻቸው”
ችቦ በአንደኛው ጫፉ ተቀጣጣይ ነገር የተደረገበት የእንጨት ጭራሮ ነው፤ ችቦ በአብዛኛው ሊሎች ነገሮችን ለመለኮስ ወይም ብርሃን እንዲሰጥ የሚያዝ ነው።
በእርሻ ውስጥ ገና በአገዳው ላይ እያደገ ያለ እህል
ከታጨደ በኋላ ተሰብስበው የተከመሩ የእህል ነዶዎች
የፍራፍሬ ዛፎች የሚበቅሉበት ቦታ ነው።
የአንድ ሰው የሴት ልጁ ባል ለሰውየው “አማች” ነው።
ይህ ከተምናህ የሆነ ሰው ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የሳምሶን ሚስት አባት እርሷን የሳምሶን ጓደኛ እንዲያገባት ሰጠው። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሳምሶንን ሚስት ወስዶ የሳምሶንን ጓደኛ እንድታገባው ፈቀደላት”
“ፈፅመው አቃጠሏቸው” የሚለው ሐረግ አንድን ነገር ጨርሶ ማቃጠል ማለት ነው። አንድ ሰው “ፈፅሞ ተቃጠለ” ማለት ያ ሰው ተቃጥሎ ሞተ ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ፍልስጤማውያኑን አላቸው”
“ይህንን ስላደረጋችሁ”
እዚህ ጋ “ሽንጥና ታፋ” ሙሉ ሰውነትን ያመለክታል። ይህ ሳምሶን ፍልስጥኤማውያንን እንዴት እንደገደላቸው የሚያሳይ ጉልህ ገለጻ ነው። አ.ት፡ “ሰውነታቸውን ቆራረጠው”።
እዚህ ጋ “ወደታች ወረደ” የሚለው ሐረግ ከከፍታ መውረዱን ማመልከቱ ላይሆን ይችላል፤ እንዲያውም አንድ ሰው ወደ ሌላ ቦታ መጓዙን መግለጫ መንገድ ነው። አ.ት፡ “ሄደ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
በኮረብታ ወይም ተራራ ውስጥ ያለ ክፍት ቦታ
ከፍ ያለ ዐለታማ ኮረብታ ወይም የተራራ ጎን
ይህ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ያለ የዐለታማ ኮረብታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ወደ ላይ ወጡ” የሚለው ሐረግ ጥቅም ላይ የዋለው ፍልስጥኤማውያኑ እነርሱ ይጓዙበት ከነበሩበት ቦታ በከፍታ ወደሚበልጠው ይሁዳ ስለመጡ ነው።
“ራሳቸውን ለጦርነት አዘጋጅተው”
ይህ በይሁዳ ያለ ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ፍልስጥኤማውያኑ ሳምሶን ብዙዎቹን ፍልስጥኤማውያን እንደገደለ እንዴት እንደሚገሉት እያነጻጸሩ ነው። አ.ት፡ “ብዙ ሰዎቻችንን እንደገደለ ግደሉት”
“3000 የይሁዳ ወንዶች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህንን ሐረግ በመሳፍንት 15፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የይሁዳ ሰዎች እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠይቁት ሳምሶንን ለመገሰጽ ነው። እነዚህ ጥያቄዎች እንደ መግለጫ ሊጻፉ ይችሉ ይሆናል። አ.ት፡ “ፍልስጤማውያን በኛ ላይ ገዢዎች እንደሆኑ ታውቃለህ ነገር ግን አንተ የምታደርገው እንዳልሆኑ ያህል ነው። ያደረከው ነገር ከባድ ጉዳት አምጥቶብናል።” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ሳምሶን ሚስቱን እንዴት እንደገደሉበትና እርሱ በበቀል እንዴት እንደገደላቸው እያመለከተ ነው። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሚስቴን ገድለዋታል፤ ስለዚህ እኔም ገደልኳቸው።”
እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው ኃይልን ነው። አ.ት፡ “የፍልስጥኤማውያኑ መቆጣጠር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት አንድን ሰው በሌላ ሰው ቁጥጥር ስር እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው። አ.ት፡ “ለፍልስጥኤማውያኑ ልንሰጥህ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሳምሶን በመሳፍንት 15፡8 ላይ ሄዶበት የነበረውን በኢታም ገደል የሚገኘውን ዋሻ ያመለክታል። እዚህ ጋ “ወደ ላይ” የሚለው ቃል ከዋሻው አውጥተው አምጥተውታል ማለት ነው። አ.ት፡ “በትልቁ ዐለት ውስጥ ካለው ዋሻ አውጥተው”።
ሳምሶን ብቻውን እልተጓዘም፤ በገመድ ባሰሩት ሰዎች እየተመራ ነበር። አ.ት፡ “በመጡ ጊዜ”
ይህ በይሁዳ የሚገኝ ከተማ ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 15፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“በላዩ ላይ መጣበት” የሚለው ሐረግ የእግዚአብሔር መንፈስ ሳምሶን ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል ማለት ነው። በዚህ ቦታ፤ በጣም ብርቱ አድርጎታል። አ.ት፡ “ሳምሶንን በጣም ብርቱ አደረገው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሳምሶን እጁ የታሰረበትን ገመድ በቀላሉ በጣጥሶታል። ደራሲው ገመዱን እንዴት በቀላሉ እንደበጣጠሰው ለመግለጽ እንደተቃጠለ ፈትል ይለዋል። አ.ት፡ ”በክንዱ ላይ ያሉትን ገመዶች ፈትል በቀላሉ እንደሚቃጠል በጣጠሳቸው”
ከተልባ ተክል የሚገኝ ቃጫና ክር ጨርቅ ለመስራት ይጠቅማል።
ይህ ማለት አህያው በቅርብ የሞተና አጥንቶቹም ገና መበስበስ ያልጀመሩ ናቸው ማለት ነው። መንጋጋ የታችኛዎቹን ጥርሶች የሚይዝ አጥንት ነው።
“1000 ወንዶች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“የአህያ መንጋጋ”
ይህ ሐረግ ሳምሶን ምን ያህል ሰዎችን እንደገደለ ይገልጻል። ትልቅ የሬሳ ክምር ለመሥራት የሚበቃ ሬሳ ነበር። አ.ት፡ “ሬሳዎች ከምሬአለሁ”
ይህ የቦታ ስም ነው። ስሙም “የመንጋጋ ኮረብታ” ማለት ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ውሃ መጠጣት በጣም አስፈለገው”
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሳምሶን በጣም ከመጠማቱ የተነሳ የምር ሊሞት እንደሆነ። አ.ት፡ “ነገር ግን አሁን በጥም እሞታለሁ፣ ሰውነቴም ባልተገረዙት … ይወድቃል”። ወይም 2) ሳምሶን በጥም ይሞት እንደሆነ በመጠየቅ ምን ያህል እንደተጠማ ያጋንናል። አ.ት፡ “ነገር ግን አሁን በጥሜ ምክንያት እንድደክም፤ ባልተገረዙትም … እንድወድቅ ትፈቅዳለህ?” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት በቂ ውሃ ባለመጠጣትህ ምክንያት በሰውነትህ ውስጥ በቂ ውሃ አጥተህ መሞት ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“በእጃቸው መውደቅ” የሚለው ሐረግ መማረክ ማለት ነው። “እነዚያ ያልተገረዙ” የሚለው ፍልስጤማውያንን ሲሆን “ያልተገረዘ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን የማያመልኩ ስለመሆናቸው አጽንዖት የሚሰጥ ቃል ነው። አ.ት፡ “እግዚአብሔርን በማያውቁ ፍልስጥኤማውያን መማረክ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“መሬት ላይ ቀዳዳ ተከፈተ” ወይም “ዝቅ ያለው ስፍራ ተከፈተ”። ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ምንጭ እንዲፈልቅ ያደረገበትን ዝቅ ያለ ስፍራ ነው።
ይህንን በመስፍንት 15፡9 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት
እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ የሚናገሩት ስለ አንድ ነገር ሲሆን ሳምሶን እንደገና ስለ መበርታቱ አጽንዖት የሚሰጡ ናቸው። እነዚህ ሁለት መግለጫዎች መጣመር ይችላሉ። አ.ት፡ “እንደገና በረታ” ወይም “ተነቃቃ”
ይህ የውሃ ምንጭ ስም ነው። ስሙ “የጸለየው የእርሱ ምንጭ” ማለት ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ምንጩ ሳይደርቅ ቆይቷል ማለት ነው። “እስካሁን ድረስ” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው የ”አሁን ጊዜ”ን ነው። አ.ት፡ ዛሬም እንኳን ምንጩ በሌሒ ይገኛል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ፍልስጥኤማውያን የእስራኤልን ምድር ይቆጣጠሩ የነበረበትን ወቅት ያመለክታል። አ.ት፡ “ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ይገዙ በነበረበት ጊዜ”
“ለ 20 ዓመታት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
1 ሳምሶን ወደ ጋዛ ሄደና በዚያ ዝሙት አዳሪ ሴት አየ፣ ከእርስዋም ጋር ወደ አልጋ ሄደ፡፡ 2 የጋዛ ሰዎችም “ሳምሶን ወደዚህ መጥቶአል” የሚል ወሬ ሰሙ፡፡ የጋዛ ሰዎች ስፍራውን ከበቡትና ሌሊቱን ሁሉ ተደብቀው በከተማይቱ በር ጠበቁት፡፡ ሌሊቱን ሁሉ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፡፡ እንዲህ ብለዋልና፣ “እስኪነጋ ድረስ እንጠብቀው፣ ከዚያም እንገድለዋለን፡፡” 3 ሳምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በአልጋ ላይ ተኛ፡፡ እኩለ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ተነሳና የከተማይቱን በር መዝጊያና ሁለቱን መቃኖች ያዘ፡፡ እነርሱንም ከመወርወሪያው ጋር ከመሬት ነቀላቸው፣ በትከሻውም ላይ አደረጋቸው፣ በኬብሮንም ፊት ለፊት ወዳለው ኮረብታ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ፡፡ 4 ከዚህ በኋላ ሳምሶን በሶሬቅ ሸለቆ የምትኖር አንዲት ሴት ወደደ፡፡ ስምዋም ደሊላ ይባል ነበር፡፡ 5 የፍልስጥኤማውያንም አለቆች ወደ እርስዋ መጡና እንዲህ አሏት፣ “እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ በእርሱ ያለው ታላቅ ኃይል የት እንደሆነና በምን መንገድ እርሱን ማሸነፍ እንደምንችል እንዲያሳይሽ ሳምሶንን አባብዪው፡፡ ይህንን አድርጊልን፣ እኛም እያንዳንዳችን 1, 100 ብር እንሰጥሻለን፡፡ 6 ደሊላም ለሳምሶን እንዲህ አለችው፣ “እባክህ፣ እንዲህ በጣም ብርቱ የሆንከው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፣ በቁጥጥር ስር መዋል እንድትችል ሰው ሊያስርህ የሚችለው እንዴት ነው? 7 ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “ባልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች ቢያስሩኝ፣ እደክማለሁ፣ እንደ ማንኛውም ሰውም እሆናለሁ፡፡” 8 የፍልስጥኤማውያን አለቆችም ያልደረቁ ሰባት እርጥብ ጠፍሮች አመጡላት፣ እርስዋም ሳምሶንን በእነርሱ አሰረችው፡፡ 9 በዚህን ጊዜ በጓዳዋ ውስጥ ሰዎች በምስጢር ተደብቀው ይጠብቁ ነበር፡፡ እርስዋም፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው፡፡ ነገር ግን የተልባ እግር ፈትል እሳት በነካው ጊዜ እንደሚበጣጠስ ጠፍሩን በጣጠሰው፡፡ እነርሱም የብርታቱ ምስጢር ምን እንደሆነ አላወቁም፡፡ 10 ከዚያም ደሊላ ሳምሶንን እንዲህ አለችው፣ “አንተ እኔን እንዴት እንዳታለልኸኝ ግልጽ ሆኗል፣ ሐሰትንም ነገርኸኝ፡፡ እባክህ፣ እንዴት እንደምትታሰር ንገረኝ፡፡” 11 እርሱም እንዲህ አላት፣ “ለሥራ ጥቅም ላይ ፈጽሞ ባልዋሉ በአዲስ ገመዶች ቢያስሩኝ፣ እደክማለሁ፣ እንደ ማንኛውም ሰው እሆናለሁ፡፡” 12 ስለዚህ ደሊላ አዲስ ገመዶች ወሰደችና በእነርሱ አሰረችው፣ እንዲህም አለችው፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ፡፡” ተደብቀው ሲጠብቁ የነበሩት ሰዎች በጓዳዋ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሳምሶን ገመዶቹን እንደ ፈትል ክር ከክንዶቹ በጣጠሰው፡፡ 13 ደሊላም ሳምሶንን እንዲህ አለችው፣ “እስከ አሁን ድረስ አታልለኸኛልና የነገርኸኝም ውሸት ነው፡፡ አንተን ማሰር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ንገረኝ፡፡” ሳምሶንም እንዲህ አላት፣ “የራሴን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድር ጋር ጎንጉነሽ በችካል ብትቸክዪው፣ እንደ ሌላ ሰው እሆናለሁ፡፡” 14 እርሱም በተኛ ጊዜ፣ ደሊላ የራሱን ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድሩ ጋር ጐነጐነችው፣ በችካልም ቸከለችውና፣ እንዲህ አለችው፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” እርሱም ከእንቅልፉ ነቃና ችካሉን ከነቆንዳላውና ከነድሩ ነቀለው፡፡ 15 እርስዋም እንዲህ አለችው፣ “ምስጢርህን ለእኔ ሳትነግረኝ ‘እወድሻለሁ’ ልትለኝ እንዴት ትችላለህ? ሦስት ጊዜ ቀለድህብኝ፣ እንዲህ ዓይነቱን ታላቅ ኃይል እንዴት ሊኖርህ እንደቻለ አልነገርኸኝም፡፡” 16 ሞት እስኪመኝ ድረስ ዕለት ዕለት በቃሎችዋ እጅግ በጣም ጨቀጨቀችው፣ ከመጠን በላይም ጫና አደረገችበት፡፡ 17 ስለዚህ ሳምሶን ሁሉንም ነገር ነገራትና እንዲህ አላት፣ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ሆኜ ስለተለየሁ በራሴ ላይ ምላጭ ደርሶና ጸጉሬን ተላጭቼ አላውቅም፡፡ የራሴን ጸጕር ብላጭ ኃይሌ ከእኔ ይሄዳል፣ እደክማለሁም እንደ ማንኛውም ሰው እሆናለሁ፡፡” 18 ደሊላም ስለ ሁሉ ነገር እውነቱን እንደነገራት ባየች ጊዜ፣ ሰዎች ላከችና የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ጠራች፣ እንዲህም አለቻቸው፣ “ሁሉንም ነገር ነግሮኛልና እንደገና ኑ፡፡” የዚያን ጊዜ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርስዋ ሄዱ፡፡ 19 እርስዋም በጭኗ ላይ እንዲተኛ አደረገችው፡፡ ሰባቱን የራሱን ጕንጕን እንዲላጨው አንድ ሰው ጠራች፣ ኃይሉ ስለተለየው እርስዋ በቁጥጥሯ ስር ልታደርገው ጀመረች፡፡ 20 እርስዋም፣ “ሳምሶን፣ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” አለችው፡፡ እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ እንዲህ አለ፣ “እንደ ሌላው ጊዜ እወጣለሁ፣ ራሴንም ነጻ አወጣለሁ፡፡” ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ተወው አላወቀም፡፡ 21 ፍልስጥኤማውያንም ያዙትና ዓይኖቹን አወጡት፡፡ ወደ ጋዛም ወሰዱትና በናስ ሰንሰለት አሰሩት፡፡ በእስር ቤትም ውስጥ ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር፡፡ 22 ነገር ግን ከተላጨ በኋላ የራሱ ጠጕር እንደገና ያድግ ጀመር፡፡ 23 የፍልስጥኤማውያንም አለቆች ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ፣ ደስም ይላቸው ዘንድ በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ እነርሱ “አምላካችን ጠላታችንን ሳምሶንን አሸንፏል፣ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል” ብለዋልና፡፡ 24 ሕዝቡም እርሱን ባዩት ጊዜ አምላካቸውን አመሰገኑ፣ እንዲህ ብለዋልና፣ “አገራችንን ያጠፋውን፣ ከእኛም ብዙ ሰው የገደለውን ጠላታችንን አምላካችን አሸነፈው፣ በእጃችንም አሳልፎ ሰጠው፡፡” 25 እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፣ እንዲህ አሉ፣ “እንዲያስቀን ሳምሶንን ጥሩት፡፡” ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠሩትና እንዲስቁ አደረጋቸው፡፡ በምሰሶና በምሰሶ መካከል እንዲቆም አደረጉት፡፡ 26 ሳምሶንም እጁን የያዘውን ልጅ፣ “እደገፍባቸው ዘንድ ሕንጻውን የደገፉትን ምሰሶዎች እንድነካቸው አስጠጋኝ” አለው፡፡ 27 በዚያን ጊዜ ቤቱ በወንዶችና በሴቶች ተሞልቶ ነበር፡፡ የፍልስጥኤም አለቆች ሁሉ በዚያ ነበሩ፡፡ ሳምሶን እነርሱን ሲያዝናናቸው ይመለከቱ የነበሩ ሦስት ሺህ የሚያህሉ ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ፡፡ 28 ሳምሶንም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጮኸ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደገና አስበኝ! አምላኬ ሆይ፣ ሁለት ዓይኖቼን ስላወጡ ፍልስጥኤማውያንን አሁን በአንድ ምት እንድበቀል፣ እባክህ፣ ይህን አንድ ጊዜ ብቻ አበርታኝ፡፡” 29 ሳምሶንም ሕንጻው ተደግፎባቸው የነበሩትን ሁለቱን መካከለኞች ምሰሶዎች ጠምጥሞ ያዘ፣ አንዱን ምሰሶ በቀኝ እጁ ሌላውን ደግሞ በግራ እጁ ይዞ በእነርሱ ላይ ተደገፈ፡፡ 30 ሳምሶንም እንዲህ አለ፣ “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ልሙት!” በሙሉ ኃይሉ ገፋው፣ ሕንጻውም በውስጡ በነበሩት አለቆችና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፡፡ ስለዚህ እርሱ በሞተ ጊዜ የገደላቸው ሰዎች በሕይወት ሳለ ከገደላቸው ይልቅ የበለጡ ነበሩ፡፡ 31 የዚያን ጊዜ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተ ሰቦች በሙሉ ወረዱ፣ እርሱንም ይዘው ወሰዱት፣ መልሰው አመጡትና በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በአባቱ በማኑሄ መቃብር ውስጥ ቀበሩት፡፡ ሳምሶን በእስራኤል ላይ ለሀያ ዓመት ፈረደ፡፡
“ወደ አልጋ ሄዱ” የሚለው ሐረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግን የሚያመለክት የጨዋ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ከእርሷ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ” ወይም “ከእርሷ ጋር ተኛ”
“የጋዛ ሰዎች” የሚለው ሐረግ ከጋዛ የሆኑትን ሰዎች ያመለክታል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የሆነ ሰው ለጋዛ ሰዎች ነግሯቸዋል” (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው አንዳንድ የጋዛ ሰዎች ሳምሶን ያረፈበትን ቦታ መክበባቸውንና ሌሎቹ ደግሞ እንዳያመልጥ የከተማውን በር መጠበቃቸውን ነው።
ትርጓሜዎች ሊሆኑ የሚችሉት 1) “ሌሊቱን ሙሉ ምንም ዓይነት ድምፅ አላሰሙም” ወይም 2) “ሌሊቱን ሙሉ እርሱን ለማጥቃት ምንም ዓይነት ሙከራ አላደረጉም”።
“እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ድረስ”
እነዚህ ለከተማው በር ድጋፎች ናቸው። እነዚህ መቃኖች ምናልባትም ከዛፍ ግንድ የተሰሩና በምድር ውስጥ በጥልቀት የተቀበሩ ናቸው። የከተማው በር መዝጊያዎች ከነዚህ መቃኖች ጋር የተያያዙ ነበሩ።
ቋሚው ብረት በሮቹን ከመቃኑ ጋር ያያዙ ከባድ የብረት ቋሚዎች ሳይሆኑ አይቀሩም። የከተማይቱ በር መዝጊያዎች ምናልባትም ከከባድ እንጨት ወይም የብረት ቋሚዎች የተሠሩ ይሆናሉ።
ክንድንና አንገትን ከሰውነት ጋር የሚያያይዘው የሰውነት ክፍል
ይህ የከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በሳምሶን ቤት አቅራብያ የሚገኝ ሸለቆ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
እነርሱ ሊያደርጉት የማይፈልጉትን ነገር ሌላው ሰው እንዲያደርገው ማሳሳት ወይም ማታለል
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን አንድን ነገር መማር ማለት ነው። አ.ት፡ “መረዳት” ወይም “መማር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ኃይሉ ከየት እንደሚመጣ የሚያመለክት ነው። አ.ት፡ “በጣም ጠንካራ እንዲሆን የሚያደርገው ምንድነው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“እንዴት እናሸንፈው እንደሆን”
“አንድ ሺህ አንድ መቶ የብር ሰቅል”። (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በቁጥጥር ስር እንድትሆን ለማሰር” ወይም “አስሮ ለመግታት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
አብዛኛውን ጊዜ ጠፍር የሚዘጋጀው ከእንስሳ ቆዳ፤ በተለይም ከጅማት ይሠራል። “አዲስ ጠፍር” የሚሉት ቃላት በቅርብ ከታረደ እንስሳ የመጣና ያልደረቀ መሆኑን ያመለክታል።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እስካሁን ያልደረቁ” ወይም “ገና ያልደረቁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እስካሁን ያልደረቁ” ወይም “ገና ያልደረቁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“ደሊላ ሳምሶንን በአዲሶቹ ጠፍሮች አሰረችው”
ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ዋናው የትረካ መስመር ለአፍታ መገታቱን ለማሳየት ነው። እዚህ ጋ ደራሲው ደሊላ ሳምሶንን እንዲማርኩ ስለምታስጠብቃቸው ፍልስጥኤማውያን ዳራዊ መረጃ ይናገራል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
“ባንተ ላይ” የሚለው ሐረግ ሊይዙት ተዘጋጅተዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “ፍልስጥኤማውያኑ ሊይዙህ እዚህ ናቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ደራሲው የሱፍ ክር ሲቃጠል እንደሚቀልጥ የሳምሶንን በቀላሉ ጠፍሮቹን መበጣጠስ እያነጻጸረ ያብራራል። አ.ት፡ “የሱፍ ክርን እንደሚያቃጥል ጠፍሮቹን በቀላሉ በጣጠሳቸው” ወይም “ከስስ የሱፍ ክር የተሠሩ ይመስል በቀላሉ ጠፍሮቹን በጣጠሳቸው”
ማታለልና መዋሸት ተመሳሳይ ሲሆኑ ደሊላ ምን ያህል እንደተናደደች አጽንዖት ለመስጠት ተነግረዋል። አ.ት፡ “እጅግ አታልለኸኛል!”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች ሊያሸንፉህ የሚችሉት”
“ባንተ ላይ” የሚለው ሐረግ ሊይዙት ተዘጋጅተዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “ፍልስጥኤማውያኑ ሊይዙህ እዚህ ናቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ተደብቀው ለማጥቃት ትክክለኛውን ጊዜ እየጠበቁ ነበር ማለት ነው። አ.ት፡ “ሊያጠቁት እየጠበቁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ደራሲው ሳምሶን ክርን እንደሚበጣጥስ በቀላሉ ገመዶቹን እንደበጣጠሰ በማነጻጸር ያብራራል። አ.ት፡ “የክር ቁራጭ የሆኑ ያህል በቀላሉ”
ማታለልና መዋሸት ተመሳሳይ ሲሆኑ ደሊላ ምን ያህል እንደተናደደች አጽንዖት ለመስጠት ተነግረዋል። አ.ት፡ “እጅግ አታለኸኛል”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች ሊያሸንፉህ የሚችሉት” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የቁሳቁሶችን ቁርጥራጭ በማሰባጠር እርስ በእርስ እንዲያያዙ ማድረግ።
ትናንሽ የፀጉር ስብስቦች
ቁሳቁሶችን በመሸመን የሚሰራ ልብስ
የተለያዩ የክር ዓይነቶችን ልብስ አድርጎ ለማያያዝ የሚጠቅም መሳርያ። (የማይታወቁትን መተርጎም የሚለውን ተመልከት)
“ጨርቁን ከሸማኔው ዕቃ ጋር ቸንክሪው”
የሆነን ነገር በቦታው ለመያዝ በመዶሻ ሚስማር መምታት
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “እንደ ማንኛውም ሰው ደካማ እሆናለሁ”
“ባንተ ላይ” የሚለው ሐረግ ሊይዙት ተዘጋጅተዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “ፍልስጥኤማውያኑ ሊይዙህ እዚህ ናቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሳምሶን ፀጉሩን ከሸማኔው ዕቃ ላይ ሲጎትተው ከነፈትሉ ነቀለው። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ፀጉሩን ከሸማኔ ዕቃ፣ ከችካሉና ከፈትሉ ጋር ጎተተው”
ፈትሉን ከሸማኔው ዕቃ ጋር የሚያያይዘው ከእንጨት የተሰራ ችንካር ወይም ችካል ነው።
ሳምሶን በርግጥ የሚወዳት ቢሆን ኖሩ ምስጢሩን ይነግራት እንደነበር ለመናገር ደሊላ ይህንን ጥያቄ ትጠይቃለች። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “ምስጢርህን አታካፍለኝምና ‘እወድሻለሁ’ በምትልበት ጊዜ እየዋሸህ ነው” (ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ደራሲው ደሊላ ለማወቅ ምትፈልገውን ነገር ሳምሶን እንዲነግራት ለማሳመን ግፊት ያደረገችበት ይመስል ሳምሶንን ለማግባባት እንዴት እንደምትሞክር ይናገራል። አ.ት፡ “ልታግባባው በጣም ሞከረች … ለማግባባት መሞከሯን ቀጠለች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“እርሱን በምትናገረው ንግግር”
ደራሲው እዚህ ጋ ሳምሶን ምን ያህል ምሬት እንደተሰማው አጽንዖት ለመስጠት ግነትን ይጠቀማል። አ.ት፡ “ፈፅሞ እንደመረረው” ወይም “እጅግ እንዳዘነ” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
ስለ ብርታቱ ምንጭ ሁሉንም ነገር ነገራት። ይህ በግልጽ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “የብርታቱን ምንጭ ነገራት” ወይም “እውነቱን ነገራት”
ከሰው ቆዳ ድረስ ተጠግቶ ፀጉር ለመቁረጥ የሚያገለግል ስለታም መቁረጫ
ይህ ማለት እንደ ናዝራዊ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ነበር ማለት ነው። በመሳፍንት 13፡15 ያለውን ተመሳሳይ ሐረግ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ለእግዚአብሔር የተሰጠ ናዝራዊ” ወይም “እንደ ናዝራዊ ለእግዚአብሔር የተሰጠ”
እዚህ ጋ “ከእናቴ ማህፀን” የሚያመለክተው የተወለደበትን ጊዜ ነው። ይህ ማለት ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ናዝራዊ ነበር ማለት ነው። አ.ት፡ “ሕይወቴን በሙሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ፀጉሬን ቢላጨኝ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ወደ ቆዳ አስጠግቶ ፀጉርን በምላጭ መቁረጥ
ሳምሶን ስለ ብርታቱ ትቶት ሊሄድ እንደሚችል ሰው አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “ከእንግዲህ ወዲህ ብርቱ አልሆንም” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ተመለከተች” የሚለው ቃል የሆነን ነገር መገንዘብ የሚል የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ደሊላ ተገነዘበች” ወይም “ደሊላ ዐወቀች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ሁሉም ነገር” የሚለው ቃል ስለ ሳምሶን ጥንካሬ ሁሉንም ነገር የሚያመለክት ነው። አ.ት፡ “ብርቱ ስለሆነበት እውነታ”
ደሊላ ገዢዎቹን እንደገና ወደ መኖያዋ እንዲመጡ እየነገረቻቸው ነው። የእርሷ ቤት ገዢዎቹ ከሚጓዙበት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሳይሆን አይቀርም።
ይህ ሳምሶንን ለመያዝ ከረዳቻቸው ሊሰጧት ቃል የገቡላትን ብር ወደ እርሷ አምጥተዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “ሊሰጧት ቃል የገቡላትን ብር በመያዝ”
“እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገችው”
ይህ ማለት ጭንቅላቱን ጭኗ ላይ አድርጎ ተኝቷል ማለት ነው። ይህ በግልጽ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “ጭንቅላቱ በጭኗ ላይ ሆኖ”
ጭን ሰው ሲቀመጥ ደልደል የሚለው የላይኛው እግር ክፍል ነው።
ሳምሶን በራሱ ላይ ሰባት የፀጉር ጉንጉኖች ነበሩት። ጉንጉኖች ትናንሽ የፀጉር ክምችቶች ናቸው። እዚህ ጋር ሰባቱ የፀጉሩ ጉንጉኖች “የእርሱ” መባላቸው የጭንቅላቱ ንብረቶች እንደሆኑ ተደርገው ተገልጸዋል። አ.ት፡ “በራሱ ላይ የነበሩት ሰባቱ የፀጉር ጉንጉኖች” (ንብረት የሚለውን ተመልከት)
“በቁጥጥር ስር አዋሉት”
እዚህ ጋ የሳምሶን ብርታት ትቶት ሊሄድ እንደሚችል ሰው ተደርጎ ተገልጿል። አ.ት፡ “ብርታቱ ሄዶ ነበር” ወይም “ከእንግዲህ ብርቱ አልሆነም” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ዐይኖቹን ከጭንቅላቱ አውጥተዉታል ማለት ነው። “ዐይኖቹን አጠፏቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ወደ ታች” የሚለው ሐረግ እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው ሳምሶንን ከያዙበት ከቤቱ በከፍታው ዝቅ ወዳለው ወደ ጋዛ ስለ ወሰዱት ነው።
“ከነሐስ የእግር ብረት ጋር አሰሩት” ወይም “የነሐስ የእግር ብረት በመጠቀም አሰሩት”
በሰንሰለት መጨረሻ ላይ ያለ የእስረኛውን እግር ወይም እጅ ወይም ሁለቱንም ለማሰር የሚጠቅም መቆለፊያ ያለው
“የድንጋይ ወፍጮውን በክብ ይጎትት ነበር”
ይህ በጣም ትልቅ፣ ከባድና ክብ ድንጋይ ነው። ተለቅ ያለ እንስሳ የድንጋይ ወፍጮውን በክብ ዓይነት እየሳበ እህል መፍጨቱ የተለመደ ነበር። እዚህ ጋ ፍልስጥኤማውያን ሳምሶን እንዲጎትተው በማድረግ እያዋረዱት ነው።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ፍልስጥኤማውያን ከላጩት በኋላ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ከፍልስጥኤማውያን ሐሰተኛ አማልክት ዋነኛው (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ስላሸነፈልን”
እዚህ ጋ ደራሲው በገዢዎቹ ቁጥጥር ስር ስለሆነው ሳምሶን በእጃቸው ጥብቅ ተደርጎ እንደተያዘ አንዳች ነገር አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “በቁጥጥራችን ስር አድርጎታል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው ሳምሶንን ነው። “አጥፊ” የሚለው ቃል “አጠፋ” በሚለው ግሥ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሀገራችንን ያጠፋው ሰው”
እዚህ ጋ “እኛ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ፍልስጥኤማውያንን ነው። ተናጋሪዎቹ ሳሞሶን ከገደላቸው ሰዎች መካከል ራሳቸውን እየቆጠሩ አይደለም። አ.ት፡ “ከእኛ ሰዎች ብዙዎቹን የገደለ”
ሳምሶን እስረኛ ስለነበር በቀጥታ መጠራት አይችልም ነበር፤ ነገር ግን ሰዎቹ የእስር ቤቱን ኃላፊዎች ሳምሶንን ወደ እነርሱ እንዲያመጡላቸው እየጠየቁ ነበር። አ.ት፡ “ሳምሶንን እንዲያመጡላቸው ጠየቋቸው ሳምሶንን አመጡት”
“ታዳጊው ልጅ” ይህ ትንሽ ልጅ አልነበረም፣ ይልቁንም ወጣት ነው።
“ሕንጻውን ደግፈው የያዙትን ቋሚዎች እንድነካ ፍቀድልኝ”
ይህ ቃል እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው ደራሲው ስለ ዳራዊ መረጃ ሊናገር ከዋናው ታሪክ ለአፍታ መውጣቱን ለማመልከት ነው። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
“3,000 ወንዶችና ሴቶች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“እያዩ”
ሳምሶን እነርሱን ለማዝናናት ምን እንዳደረገ ግልጽ አይደለም። ፍልስጥኤማውያን እንዲቀልዱበት፣ ሊያዋርዱት የሚችሉ ነገሮችን ያስደረጉት ይመስላል።
“ወደ እግዚአብሔር ጸለየ”
ይህ ማለት እርሱንና ያለበትን ሁኔታ እንዲያስታውስ ማለት ነው። አ.ት፡ “አስታውሰኝ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“አንድ ጊዜ ብቻ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ፣ ፍልስጥኤማዊያን ስላደረጉበት ነገር ፈጽሞ ለመበቀል በእነርሱ ላይ አንድ ጊዜ የኃይል ድርጊት ለመፈጸም ይፈልጋል ማለት ነው። አ.ት፡ “በፍልስጥኤማውያን ላይ በአንድ ምት” ወይም “በፍልስጥኤማውያን ላይ በአንድ ኃይለኛ ድርጊት” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ሕንጻውን ባቆመው”
ሳምሶን ክንዶቹን ሲዘረጋ የሕንጻውን ምሰሶዎች ገፍቶ ጣላቸው። አ.ት፡ “ምሰሶዎቹን ለመጣል ብርታቱን ተጠቀመ” ወይም “ምሰሶዎቹን ለመግፋት ኃይሉን ተጠቀመ”
ይህ የሞቱትን ሰዎች ያመለክታል። “የሞቱት ሰዎች”
“በቁጥር ብዙ ነበሩ”
እዚህ ጋ “ቤት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእርሱን ቤተሰብ ነው። አ.ት፡ “የአባቱ ቤተሰቦች በሙሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ወረዱ” የሚለው ቃል እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው የሳምሶን ቤተሰብ የተጓዘበት ቦታ ከጋዛ በከፍታ የሚበልጥ ስለነበረ ነው።
የእነዚህን ቦታዎች ስም በመሳፍንት 13፡2 እና በመሳፍንት 13፡25 እንዴት እንደተረጎምካቸው ተመልከት።
“አባቱ ማኑሔህ በተቀበረበት ስፍራ”
የዚህን ሰውዬ ስም በመሳፍንት 13፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ዐረፍተ ነገር ራሱ በመሳፍንት 15፡20 ላይ አለ። እዚህ ጋ የተደገመው ለምን ያህል ጊዜ በእስራኤል ላይ እንደፈረደ አንባቢዎችን ለማስታወስ ነው። አ.ት፡ “ሳምሶን ከመሞቱ በፊት በእስራኤል ላይ ለሃያ ዓመታት ፈርዷል”
“20 አመታት” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
1 በኮረብታማውም በኤፍሬም አገር አንድ ሰው ነበር፣ ስሙም ሚካ ይባላል፡፡ 2 ለእናቱም እንዲህ አላት፣ “ከአንቺ ዘንድ ተወስዶ የነበረው 1, 100 ብር፣ የእርግማን ንግግር የተናገርሽበትና እኔም የሰማሁት እነሆ እዚህ አለ! ብሩ በእኔ ዘንድ አለ፡፡ እኔ ሰርቄዋለሁ!” እናቱም እንዲህ አለች፣ “ልጄ ሆይ፣ እግዚአብሔር ይባርክህ!” 3 እርሱም 1, 100 ብር ለእናቱ መለሰላት፣ እናቱም እንዲህ አለችው፣ “ስለ ልጄ የተቀረጸ የእንጨት ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል ለማድረግ ይህን ብር ለእግዚአብሔር ለይቼዋለሁ፡፡ ስለዚህ አሁን፣ ለአንተ መልሼዋለሁ፡፡” 4 ለእናቱም ገንዘቡን በመለሰላት ጊዜ፣ እናቱ ሁለቱን መቶ ብር ወሰደችና የተቀረጸ የእንጨት ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል አድርጎ ለሰራው ለብረት ሰራተኛ ሰጠችው፡፡ ያም በሚካ ቤት ተቀመጠ፡፡ 5 ሚካ የተባለውም ሰው የጣዖታት አምልኮ ቤት ነበረውና አንድ ኤፉድና ተራፊም ሰራ፣ ከልጆቹም አንዱ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለው አደረገ፡፡ 6 በዚያን ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም፣ ሰውም ሁሉ በዓይኖቹ ፊት ትክክል መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር፡፡ 7 አሁን በቤተ ልሔም ይሁዳ ከይሁዳ ወገን የሆነ አንድ ሌዋዊ ወጣት ሰው ነበረ፡፡ እርሱም ተግባሩን ለመፈጸም በዚያም ይቀመጥ ነበር፡፡ 8 ይህ ሰው የሚቀመጥበትን ስፍራ ለመፈለግ ቤተ ልሔም ይሁዳን ለቅቆ ሄደ፡፡ ሲጓዝም ወደ ኮረብታማው የኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጣ፡፡ 9 ሚካም ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “ከወዴት መጣህ?” እርሱም እንዲህ አለው፣ “እኔ ከቤተ ልሔም ይሁዳ የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፣ የምኖርበትን ስፍራ ለማግኘት እየተጓዝሁ ነው፡፡” 10 ሚካም እንዲህ አለው፣ “ከእኔ ጋር ተቀመጥ፣ ለእኔም አማካሪና ካህን ሁነኝ፡፡ እኔም በየዓመቱ አሥር ብር፣ እንደዚሁም ልብሶችንና ምግብህን እሰጥሃለሁ፡፡” ስለዚህ ሌዋዊው ወደ ቤቱ ገባ፡፡ 11 ሌዋዊውም ከሰውዮው ጋር ለመቀመጥ ፈቃደኛ ሆነ፣ ወጣቱም ሰው ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት፡፡ 12 ሚካም ሌዋዊውን ለተቀደሰ ሃላፊነት ቀደሰው፣ ወጣቱም ሰው ካህኑ ሆነለት፣ በሚካም ቤት ነበረ፡፡ 13 ከዚያም ሚካ እንዲህ አለ፣ “አሁን እግዚአብሔር ለእኔ መልካም እንደሚሰራልኝ አውቄአለሁ፣ ምክንያቱም ይህ ሌዋዊ ካህን ሆኖልኛል፡፡”
ይህ በታሪክ ፍሰቱ ላይ አዲስን ሰው የማስተዋወቂያ መንገድ ነው። (አዲስና ነባር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቂያ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ሰው ስም ነው። ይህ የሚክያስን መጽሐፍ የጻፈው ሰው አይደለም። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው የሰረቀብሽ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
“እኔ ነኝ የወሰድኩት”
“አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰቅል” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት አንድን ነገር ለተለየ አላማ መስጠት ማለት ነው። አ.ት፡ “ተሰጠ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የተለየ ቅርጽ ለማውጣት በቅርጽ ማውጫ ውስጥ ቀልጦ የሚጨመር ብረት
“ላንተ መልሼ እሰጥሃለሁ”
“200 ሰቅል ብር” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“እነርሱ” የሚለው ቃል የብረት ቅርጾቹን ያመለክታል። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሚካ በቤቱ አስቀምጧቸው ነበር” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በግልጽ ጣዖታት የሚመለኩበትን ቤት ያመለክታል። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ጣዖታትን የማምለኪያ ቤት”
ዐይን ዕይታን ይወክላል፤ ማየትም አሳብን ወይም ውሳኔን ይወክላል። አ.ት፡ “እያንዳንዱ ሰው ልክ ነው ብሎ የወሰነውን ያደርግ ነበር” ወይም “እያንዳንዱ ሰው ልክ ነው ብሎ የፈረደውን ያደርግ ነበር” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ከቤተልሔም”
ይህ ማለት በይሁዳ ቤተሰቦች ይኸውም በይሁዳ ነገድ መካከል ይኖር ነበር ማለት ነው። አ.ት፡ “በይሁዳ ነገድ መካከል ይኖር የነበረ”
“በዚያ ይኖርና ይሠራ ነበር”
“ሌላ የመኖርያ ቦታ ለመፈለግ”
የሚኖርበትንና የሚሠራበትን ቦታ እየፈለገ እንደሆነ ያመለክታል። አ.ት፡ “የምኖርበትና የምሠራበትን ስፍራ”
“አባት” የሚለው ቃል እዚህ ጋ አማካሪ ለማለት ጥቅም ላይ ውሏል እንጂ እውነተኛ አባትነትን አያመለክትም። አ.ት፡ “አማካሪና ካህን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በየዓመቱ አሥር ጥሬ ብር እሰጥሃለሁ”
“የልብሶች ስብስብ”
ሌዋዊው የሚካን አሳብ መቀበሉንና ወደ ሚካ ቤት መግባቱን ያመለክታል። አ.ት፡ “ስለዚህ ሌዋዊው ግብዣውን ተቀብሎ ወደ ቤቱ ገባ”
በሌዋዊውና በሚካ መካከል ያለው ግንኙነት እንደ አባትና ልጅ የጠበቀ ሆነ። አ.ት፡ “ወጣቱ ከሚካ ጋር በጣም ከመቀራረቡ የተነሣ ከወንዶች ልጆቹ እንደ አንዱ ሆነ”
እዚህ ጋ “ለየው” ማለት ሚካ “ቀደሰው” ወይም “ሾመው” ማለት ነው። አ.ት፡ “ሚካ ሌዋዊውን ቀደሰው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ በሚካ ቤት መኖሩ በቤቱ “እንደሆነ” ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “በሚካ ቤት ኖረ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 በዚያን ዘመን በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ አልነበረም፡፡ የዳን ነገድ ተወላጆች የሚቀመጡበትን ርስት ይፈልጉ ነበር፣ እስከዚያ ቀን ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልተቀበሉም ነበርና፡፡ 2 የዳን ሰዎች ከአጠቃላይ ወገናቸው በሙሉ ከጾርዓ ጀምሮ እስከ ኤሽታኦል ድረስ በጦርነት ልምድ ያላቸውን አምስት ሰዎች በእግራቸው ሄደው ምድሪቱን እንዲሰልሉና እንዲያዩ ላኩ፡፡ ለእነርሱም እንዲህ አሉአቸው፣ “ሂዱና ምድሪቱን ሰልሉ፡፡” እነርሱም ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር ወደ ሚካ ቤት መጡና ሌሊቱን በዚያ አሳለፉ፡፡ 3 በሚካ ቤት አጠገብ በነበሩ ጊዜ፣ የአንድ ወጣት ሌዋዊ ንግግር አወቁ፡፡ ስለዚህ አስቆሙትና እንዲህ ብለው ጠየቁት፣ “ወደዚህ ማን አመጣህ? በዚህ ስፍራ ምን ታደርጋለህ? ለምን ወደዚህ መጣህ?” 4 እርሱም እንዲህ አላቸው፣ “ሚካ ለእኔ ያደረገው ነገር ይህ ነው፡- የእርሱ ካህን እንድሆን ቀጠረኝ፡፡” 5 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “የምንሄድበት መንገድ መቃናቱን ወይም አለመቃናቱን እናውቅ ዘንድ፣ እባክህ፣ የእግዚአብሔርን ምክር ጠይቅልን፡፡” 6 ካህኑም ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “በሰላም ሂዱ፡፡ ልትሄዱ በሚገባችሁ መንገድ እግዚአብሔር ይመራችኋል፡፡” 7 የዚያን ጊዜ አምስቱ ሰዎች ሄዱና ወደ ላይሽ መጡ፣ ሲዶናውያን በጸጥታ ያለስጋት ይኖሩ እንደነበረ ሁሉ፣ በዚያም ተዘልለው ይኖሩ የነበሩትን ሕዝብ አዩ፡፡ በምድሪቱም በየትኛውም መልኩ የገዛቸው፣ ወይም ያስቸገራቸው አልነበረም፡፡ ከሲዶናውያን በጣም ርቀው ይኖሩ ነበር፣ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡ 8 በጾርዓና በኤሽታኦል ውስጥ ወደነበሩት ወንድሞቻቸው ተመለሱ፡፡ ዘመዶቻቸውም እንዲህ ብለው ጠየቁአቸው፣ “ምን ወሬ ይዛችኋል?” 9 እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ኑ! እንውጋቸው! ምድሪቱን አይተናታል፣ በጣም ጥሩ ናት፡፡ እናንተ ዝም ትላላችሁን? ምድሪቱን ከመውጋትና ከመውረስ አትዘግዩ፡፡ 10 በሄዳችሁ ጊዜ፣ ያለ ስጋት እንደሚኖሩ ወደሚያስቡ ሕዝብ ትደርሳላችሁ፣ ምድሪቱም ሰፊ ናት! እግዚአብሔርም ለእናንተ ሰጥቶአችኋል፣ በምድር ካለው ነገር ሁሉ አንዳች የማይጎድልባት ስፍራ ናት፡፡ 11 ከዳን ወገን የሆኑና የጦር መሳርያ የታጠቁ ስድስት መቶ ሰዎች ከጾርዓና ከኤሽታኦል ተነሥተው ሄዱ፡፡ 12 እነርሱም ሄዱና በይሁዳ ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዳን ሰፈር ብለው የሚጠሩት ለዚህ ነው፤ እርሱም ከቂርያትይዓሪም በምዕራብ በኩል ነው፡፡ 13 እነርሱም ከዚያ ተነስተው ወደ ኮረብታማው የኤፍሬም አገር አልፈው ሄዱ፣ ወደ ሚካም ቤት መጡ፡፡ 14 ከዚያም የላይሽን አገር ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ለዘመዶቻቸው እንዲህ አሉአቸው፣ “በእነዚህ ቤቶች ውስጥ ኤፉድና ተራፊም፣ የተቀረጸ ምስልና ቀልጦ የተሠራ ምስል እንዳሉ ታውቃላችሁን? ምን እንደምታደርጉ አሁን ወስኑ፡፡” 15 ስለዚህ ከዚያ ዘወር አሉና ወጣቱ ሌዋዊ ይኖርበት ወደነበረው ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላምታም አቀረቡለት፡፡ 16 በዚያን ጊዜ የጦር መሳርያ የታጠቁት ስድስት መቶ ዳናውያን በበሩ መግቢያ ቆሙ፡፡ 17 ካህኑ የጦር መሳርያ ከታጠቁት ከስድስት መቶ ሰዎች ጋር በበሩ አካባቢ ቆሞ በነበረበት ጊዜ፣ ምድሪቱንም ሊሰልሉ ሄደው የነበሩት አምስቱ ሰዎች ወደዚያ ሄዱና የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል ወሰዱ፡፡ 18 እነዚህ ወደ ሚካ ቤት ገብተው የተቀረጸውን ምስል፣ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል በወሰዱ ጊዜ፣ ካህኑ ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ምን ታደርጋላችሁ?” 19 እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “ዝም በል! እጅህን በአፍህ ላይ ጫንና ከእኛ ጋር ና፣ ለእኛም አባትና ካህን ሁንልን፡፡ ለአንተስ ለአንድ ሰው ቤት ካህን መሆን ወይስ በእስራኤል ውስጥ ላለው ነገድና ወገን ሁሉ ካህን መሆን ይሻልሃል?” 20 የካህኑም ልብ ደስ አለው፡፡ ኤፉዱን፣ ተራፊሙንና የተቀረጸውንም ምስል ወሰደና ከሕዝቡ ጋር ሄደ፡፡ 21 ስለዚህ እነርሱ ዞሩና ሄዱ፡፡ ሕፃናቶችን፣ ከብቶችንና ንብረታቸውን በፊታቸው አስቀደሙ፡፡ 22 ከሚካም ቤት ጥቂት በራቁ ጊዜ፣ በሚካ ቤት አጠገብ በነበሩት ቤቶች ውስጥ የነበሩ ሰዎች ተጠራርተው ተሰበሰቡ፣ የዳን ሰዎችንም ተከትለው ደረሱባቸው፡፡ 23 ወደ ዳንም ሰዎች ጮኹ፣ ዘወር ብለው ለሚካም እንዲህ አሉት፣ “ተሰብስባችሁ በአንድ ላይ የመጣችሁት ለምንድን ነው?” 24 እርሱም፣ “የሠራኋቸውን አማልክቴን ሰረቃችሁ፣ ካህኔንም ይዛችሁ ሄዳችሁ፡፡ ሌላ ምን የቀረኝ ነገር አለ? ‘ያስጨነቀህ ምንድን ነው?’ ብላችሁ እንዴት ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ፡፡” 25 የዳን ሰዎችም እንዲህ አሉት፣ “ምንም ዓይነት ንግግር ስትናገር እንድንሰማ አታድርገን፣ አለዚያ አንዳንድ የተቈጡ ሰዎች ይጎዱሃል፣ አንተና ቤተሰቦችህም ትሞታላችሁ፡፡” 26 የዚያን ጊዜ የዳን ሰዎች መንገዳቸውን ሄዱ፡፡ ሚካ ከእርሱ ይልቅ እነርሱ እጅግ በጣም የበረቱ እንደሆኑ ባየ ጊዜ፣ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ 27 የዳን ሰዎችም ሚካ የሠራውን ጣዖትና ካህኑን ወሰዱና ወደ ላይሽ መጡ፣ በሰላምና ያለ ስጋት ተዘልሎም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ መጥተው በሰይፍ ስለት ገደሉአቸው፣ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሉአት፡፡ 28 እነርሱን የሚያድን አንድም ሰው አልነበረም ምክንያቱም ከተማይቱ ከሲዶና በጣም ራቅ ያለች ነበረች፣ እነርሱም ከሌሎች ሰዎች ጋር ምንም ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡ እርስዋም በቤትሮዖብ አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ነበረች፡፡ የዳን ሰዎችም ከተማይቱን እንደገና ሠሩና ተቀመጡባት፡፡ 29 ከተማይቱንም ከእስራኤል ወንዶች ልጆች አንዱ በሆነው በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ የከተማይቱ ስም ላይሽ ነበረ፡፡ 30 የዳን ሰዎችም ለራሳቸው የተቀረጸ ምስል አቆሙ፣ የሙሴ ልጅ የጌርሳም ልጅ ዮናታን፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹ ምድሪቱ እስከምትያዝበት ቀን ድረስ ለዳን ሰዎች ካህናት ነበሩ፡፡ 31 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤት በሴሎ በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ ሚካ የሰራውን የተቀረጸ ምስል አመለኩ፡፡
ይህ ሐረግ በታሪኩ ፍሰት ላይ ሌላ አዲስ የሁነት ጅማሬን ያስተዋውቃል። (አዲስ ሁነትን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ስለ እስራኤልና ስለዳን ነገድ ሕዝቦች ዳራዊ መረጃ ነው። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በግልጽ የሚኖሩበትን መሬት እንዳልወረሱ ያመለክታል። አ.ት፡ “የመሬት ርስት አልተቀበልንም”
“በሙሉ” የሚለው ቃል በነገዱ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ያመለክታል። አ.ት፡ “በየነገዱ መካከል ካሉት ሰዎች ሁሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ልምድ ያላቸው ተዋጊዎች”
የዚህን ከተማ ስም በመስፍንት 13፡2 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የዚህን ከተማ ስም በመሳፍንት 13፡25 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“በእግር” የሚለው ሐረግ መራመድ ማለት ነው። አ.ት፡ “በእርሱ ላይ በመራመድ መሰለል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የዚህን ሰው ስም በመሳፍንት 17፡1 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት
ሰውየውን በሚናገርበት ድምፁ ለይተው ዐወቁት። እዚህ ጋ “ንግግር” የሚጠቁመው “ድምፁን” ነው። አ.ት፡ “ወጣቱ ሌዋዊ ሲናገር ሰሙትና ድምፁን ዐወቁ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“ድል አድርገዋቸው በምድራቸው የተቀመጡ ጠላቶች አልነበሩም”
“በውጪ ከሚኖሩ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራቸውም”፤ ይህ ማለት ከሌሎች ከተሞች ርቀውና ከሌሎች ሰዎች ተገልለው ይኖሩ ነበር ማለት ነው።
የዚህችን ከተማ ስም በመሳፍንት 13፡2 ላይ እንደተረጎምከው አድርገህ ተርጉም።
የዚህችን ከተማ ስም በመሳፍንት 13፡25 ላይ እንደተረጎምከው አድርገህ ተርጉም።
ይህ ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የተጠየቀው በአሽሙር ሲሆን ትርጉሙም ተቃራኒውን ማድረግ ነበረባቸው የሚል ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “አሁን የሆነ ነገር ማድረግ አለባችሁ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ “አትሁኑ” እና “አትዘግዩ” የሚሉት አሉታዊ ቃላቶች በአንድ ላይ በቶሎ እንዲያጠቁ አዎንታዊ አሳብ ላይ አጽንዖት የሰጣሉ። “ፍጠኑ! አጥቁ” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)
“ምድሪቱ ታላቅ ናት” ይህ የምድሩን መጠን ይገልጻል።
ሰዎቹ ለመኖር በጣም ተመራጭ ቦታ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ግነትን ተጠቅመዋል። አ.ት፡ “በዚያ የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ይኖረናል” (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
ሁለቱ አሉታዊ ቃላት በአንድነት አዎንታዊ አሳብ ላይ አጽንዖት ይሰጣሉ። አ.ት፡ “ሁሉም ነገር ያለው” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)
“600 ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የዚህን ስፍራ ስም በመሳፍንት 13፡25 ላይ እንደተረጎምከው አድርገህ ተርጉመው።
ይህ ማለት የሆነ ነገር እስካሁን እንደዚያው አለ ማለት ነው። “የአሁንን ” ጊዜ ያመለክታል። አ.ት፡ “እስካሁን ስሙ እንደዚያው ነው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
የዚህን ከተማ ስም በመሳፍንት 18፡7 ላይ እንደተረጎምከው አድርገህ ተርጉመው።
አምስቱ ሰዎች ይህንን ጥያቄ የጠየቁት ሰዎቹ ጣዖታቱን እንዲሰርቁ አሳብ ለመስጠትና ለማደፋፈር ነው። ይህ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል፤ አመልካች የመረጃ ሐረግም በቅንፍ ውስጥ ሊሰጥ ይቻላል። አ.ት፡ “እነዚህ ቤቶች የብረት ምስል የሆነውን ኤፉድ ይዘዋል (ሰዎቹ እንዚህን ነገሮች እንዲሰርቁ አሳብ እየሰጡ ነበር።) እናደርጋለን … ወስኑ” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ እና የሚለውን ተመልከት)
“ከእነዚህ ቤቶች በአንዱ ውስጥ አለ” ወይም “በእነዚህ ቤቶች መካከል አለ”
“ገቡ”
“እርሱን” የሚለው ቃል ሌዋዊውን ያመለክታል።
“600 የዳን ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“600 ወንዶች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህንን ጥያቄ መልስ በማይሻ መልኩ የሚጠይቁት የነገሩን እውነትነት ለማመልከት ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “ለአንድ ሰው ካህን ከመሆን ይልቅ በእስራኤል ላለ ነገድ እና ጎሳ ካህን መሆን ይሻልሃል” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ካህኑ በተሰማው ስሜት ላይ አጽንዖት ለመስጠት ”ልቡ” ተብሏል። አ.ት፡ “ካህኑ ተደስቶ ነበር”
በዚህ መልኩ የሚጓዙት ልጆቹን ለመጠበቅ ነው። ሚካና ሰዎቹ ቢያጠቋቸው መጀመሪያ የሚያገኙት ጦረኞቹን እንጂ ልጆቹን አይሆንም። አ.ት፡ “ትንንሾቹን ልጆች ለመጠበቅ ከፊት ለፊታቸው አደረጓቸው”
“ጥቂት ርቀት”፣ ይህ ለመለካት የሚበቃውን ርዝመት አጭር ርቀት ይለዋል። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በቤቱ አቅራቢያ ባሉ ቤቶች ውስጥ የነበሩትን ሰዎች አንድ ላይ ጠራቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ከኋላ ተከትለዋቸው እንደሮጡ ያመለክታል። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል፝። አ.ት፡ “ከዳን ሰዎች ኋላ በመሮጥ ደረሱባቸው”
“የዳን ሰዎች የሆኑት ወደ ኋላቸው ዞሩ”
ይህ የወቀሳ ጥያቄ ነው። እንደ መግለጫ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኛን ለማሳደድ ሰዎችህን ጠርተህ መሰብሰብ አልነበረብህም”። (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እነዚህን ሰዎች አንድ ላይ ጠሯቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሚካ አማልክቶቹን አልሠራቸውም፤ የሠራቸው ባለ ሙያ የሆነ ሰው ነው። አ.ት፡ “ለራሴ ያሠራኋቸውን አማልክት” ወይም “ባለ ሙያ የሠራልኝን አማልክት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሚካ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ለእርሱ አስፈላጊ የሆኑት ነገርች አሁን እንደሌሉት አጽንዖት ለመስጠት ነው። አ.ት፡ “ምንም የቀረኝ ነገር የለም” ወይም “ለእኔ አስፈላጊ የሆነውን ነገር በሙሉ ወስዳችሁብኛል” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ሚካ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው የዳን ሰዎች የሆኑት በእርግጥ ምን እንዳሳሰበው እንደሚያውቁ አጽንዖት ለመስጠት ነው። አ.ት፡ “እጅግ እንዳዘንኩ ታውቃላችሁ!” ወይም “በእኔ ላይ ባደረጋችሁት ነገር ምን ያህል እንደተቸገርኩ ታውቃላችሁ!” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
“ስትናገር እንዳንሰማህ” የሚለው ሐረግ የዳን ሰዎች ሚካ ስለሆነው ነገር የሚያወራውን መስማታቸውን ያመለክታል፤ ነገር ግን ሚካ ስለተፈጠረው ነገር ማውራቱን ከሌሎች ሰዎች መስማታቸውንም ይጨምራል። አ.ት፡ “ምን እንደተናገርክ ማወቅ እንፈልጋለን” ወይም “ስለዚህ ጉዳይ የፈለግኸውን ተናገር” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ምንም ዓይነት ነገር” የሚለው ሐረግ የዳን ሰዎች ወደ ሚካ ቤት መጥተው ጣዖቶቹን መስረቃቸውን የሚጠቁም የትኛውንም መረጃ ያመለክታል። ይህ በግልጽ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስለዚህ ጉዳይ ምንም ነገር ስትናገር እንዳንሰማህ” ወይም “ስለሆነው ነገር እንዳች ስትናገር እንዳንሰማህ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንተንና ቤተሰብህን እንገላለን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ጉዟቸውን ቀጠሉ ማለት ነው። አ.ት፡ “ጉዟቸውን ቀጠሉ” ወይም “መጓዛቸውን ቀጠሉ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚያመለክተው ሚካና ሰዎቹ እንዳይዋጓቸው የዳን ሰዎች እጅግ ብርቱ መሆናቸውን ነው። አ.ት፡ “እርሱና ከእርሱ ያሉት ሰዎች እንዳይዋጓቸው እጅግ ብርቱዎች ነበሩ”
ሚካ አማልክቶቹን አልሠራቸውም፤ ይልቁን የሠራለት ባለ ሙያ ነበር። ደግሞም ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ለሚካ የተሠሩለት ነገሮች” ወይም “የሚካ ነገሮች” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህንን በመሳፍንት 18፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
“በሰይፎቻቸው”። እዚህ ጋ “ሰይፉ” ወታደሮቹ በጦርነት የተጠቀሙባቸውን ሰይፍና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ይወክላል።
“በውጪ ከሚኖሩ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አልነበራቸውም”፤ ይህ ማለት ከሌሎች ከተሞች ርቀውና ከሌሎች ሰዎች ተገልለው ይኖሩ ነበር ማለት ነው። ይህንን ሐረግ በመሳፍንት 18፡7 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ሚካን በካህንነት ያገለግለው የነበረው የወጣቱ ሌዋዊ ስም ነው። ይህ ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የወጣት ሌዋዊው ስም የሙሴ ልጅ የጌርሳም ልጅ ዮናታን ነበር” ( እና ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የዳን ሰዎች በጠላቶቻቸው የሚያዙበትን የወደፊት ጊዜ የሚያመለክት ነው። እዚህ ጋ የምድሪቱ መያዝ በጠላት እንደተማረከ እስረኛ ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ጠላቶቻቸው ምድራቸውን እስከያዙበት ቀን ድረስ” ወይም “ጠላቶቻቸው ማርከው እስከወሰዷቸው ቀን ድረስ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሚካ አማልክቶቹን አልሠራቸውም፤ ይልቁንም ባለ ሙያ ነበር የሠራለት። አ.ት፡ “ተሠርተዉለት የነበሩት” ወይም “የእርሱ ባለ ሙያ የሠራለት” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 በዚያም ዘመን፣ በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ ባልነበረበት ጊዜ፣ በኮረብታማው የኤፍሬም አገር እጅግ በጣም ሩቅ በሆነ አካባቢ ለአጭር ጊዜ የኖረ አንድ ሌዋዊ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም አንዲትን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት፡፡ 2 ነገር ግን ቁባቱ ለእርሱ ታማኝ አልነበረችም፤ እርሱን ተወችውና ተመልሳ ወደ አባትዋ ቤት ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄደች፡፡ እርስዋም በዚያ አራት ወር ቆየች፡፡ 3 የዚያን ጊዜ ባልዋ ተነሣና ተመልሳ ወደ እርሱ እንድትመጣ ለማባበል ተከትሏት ሄደ፡፡ የእርሱ አገልጋይና ሁለት አህዮች ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ እርስዋም ወደ አባትዋ ቤት አስገባችው፡፡የልጅቱ አባት ባየው ጊዜ ደስ አለው፡፡ 4 የልጂቱ አባት፣ አማቱም በቤቱ ለሦስት ቀን እንዲቆይ ለመነው፡፡ እነርሱም በሉ፣ ጠጡ፣ ሌሊቱንም በዚያ አሳለፉ፡፡ 5 በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፣ እርሱም ለመሄድ ተዘጋጀ፣ ነገር ግን የልጂቱ አባት አማቹን እንዲህ አለው፣ “እንድትበረታ እንጀራ ብላ፣ ከዚያ መሄድ ትችላለህ፡፡” 6 ስለዚህ ሁለቱም በአንድ ላይ ለመብላትና ለመጠጣት ተቀመጡ፡፡ ከዚያም የልጂቱ አባት እንዲህ አለ፣ “እባክህ ሌሊቱን ደግሞ እዚህ ለማሳለፍ ፈቃደኛ ሁን፣ መልካም ጊዜም ይሁንልህ፡፡” 7 ሌዋዊው ለመሄድ በማለዳ በተነሳ ጊዜ፣ የወጣቷ ሴት አባት እንዲቆይ ለመነው፣ ከዚህ የተነሳ እቅዱን ለወጠና ሌሊቱን በዚያ አሳለፈ፡፡ 8 በአምስተኛው ቀን ለመሄድ ማልዶ ተነሣ፣ ነገር ግን የልጂቱ አባት እንዲህ አለ፣ “ሰውነትህን አበርታ፣ እስከ ማምሻ ድረስ ቆይ አለው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም አብረው በሉ፡፡ 9 ሌዋዊው፣ ቁባቱና አገልጋዮቹ ለመሄድ በተነሱ ጊዜ፣ የልጂቱ አባት አማቱ እንዲህ አለው፣ “ተመልከት፣ አሁን ቀኑ እየመሸ ነው፡፡ እባክህ ሌላ ሌሊት በዚህ ቆዩ፣ መልካም ጊዜም ይሁንልህ፡፡ ነገ በማለዳ ተነስታችሁ ወደ ቤታችሁ ተመልሳችሁ መሄድ ትችላላችሁ፡፡” 10 ነገር ግን ሌዋዊው ሌሊቱን በዚያ ለማሳለፍ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ተነሳና ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለችው ወደ ኢያቡስ ሄደ፡፡ ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩት፣ ቁባቱም ከእርሱ ጋር ነበረች፡፡ 11 ወደ ኢያቡስም በቀረቡ ጊዜ መሸባቸው፣ አገልጋዩም ለጌታው እንዲህ አለው፣ “ና፣ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ እንሂድና ሌሊቱን በዚያ እናሳልፍ፡፡” 12 ጌታውም፣ “የእስራኤል ሕዝብ ወገን ወዳልሆነ ወደ እንግዳ ሕዝብ ከተማ ውስጥ አንገባም፡፡ እኛ ወደ ጊብዓ እንሄዳለን፡፡” 13 ሌዋዊውም ለወጣቱ ሰው እንዲህ አለው፣ “ና፣ ከእነዚህ ስፍራዎች ወደ አንዱ እንሂድ፣ ሌሊቱንም በጊብዓ ወይም በራማ እናሳልፍ፡፡” 14 ስለዚህ መንገዳቸውን ቀጠሉ፣ የብንያም ነገድ ወደምትሆነው ወደ ጊብዓ ግዛት ሲቀርቡ ፀሐይ ገባችባቸው፡፡ 15 እነርሱም ሌሊቱን በጊብዓ ለማሳለፍ ወደዚያ አቀኑ፡፡ እርሱም ወደ ውስጥ ገባና በከተማው አደባባይ ተቀመጠ፣ ሌሊቱን በዚያ ያሳልፉ ዘንድ ወደ ቤቱ የወሰዳቸው ማንም ሰው አልነበረምና፡፡ 16 ነገር ግን በዚያን ጊዜ አንድ ሽማግሌ ሰው ከእርሻ ሥራው በምሽት እየመጣ ነበር፡፡ እርሱም ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር ነበረ፣ እርሱም በጊብዓ በእንግድነት ተቀምጦ ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያ ስፍራ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ብንያማውያን ነበሩ፡፡ 17 እርሱም ዓይኑን አነሳና መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየው፡፡ ሽማግሌውም እንዲህ አለ፣ “ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ?” 18 ሌዋዊውም እንዲህ አለው፣ “እኛ ከቤተ ልሔም ይሁዳ በጣም ሩቅ ወደሆነው ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር እንሄዳለን፣ እኔም የመጣሁት ከዚያ ነው፡፡ ወደ ቤተ ልሔም ይሁዳ ሄጄ ነበር፣ አሁን ወደ እግዚአብሔር ቤት እየሄድሁ ነው፣ ነገር ግን ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ማንም ሰው የለም፡፡ 19 ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፣ ለእኔና እዚህ ላለችው ለሴት አገልጋይህ፣ ከአገልጋዮችህም ጋር ላለው ለዚህ ወጣት ሰው እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፡፡ አንዳችም አላጣንም፡፡” 20 ሽማግሌውም ሰላምታ አቀረበላቸው፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን! የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ እኔ እሰጣችኋለሁ፡፡ በአደባባይ ግን ሌሊቱን አትደሩ” አለው፡፡ 21 ስለዚህም ሰውየው ሌዋዊውን ወደ ቤቱ ወሰደው፣ ለአህዮቹም ገፈራ ሰጣቸው፡፡ እግራቸውን ታጠቡ፣ በሉም ጠጡም፡፡ 22 እነርሱም መልካም ጊዜ ነበራቸው፣ ክፉ የሆኑ የከተማይቱ ሰዎች ያደሩበትን ቤት ከበቡ፣ በሩንም ይደበድቡ ነበር፡፡ የቤቱ ባለቤት ለሆነው ለሽማግሌው እንዲህ አሉት፣ “ከእርሱ ጋር መተኛት እንድንችል ወደ ቤትህ የገባውን ሰው አምጣው፡፡” 23 ሰውየውም፣ የቤቱ ባለቤት፣ ወደ እነርሱ ሄደና እንዲህ አላቸው፣ “አይሆንም፣ ወንድሞቼ ሆይ፣ ይህን ክፉ ነገር እባካችሁ አታድርጉ! ይህ ሰው ወደ ቤቴ የገባ እንግዳ ስለሆነ፣ ይህን ክፉ ነገር አትሥሩ፡፡ 24 ተመልከቱ፣ ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት እዚህ አሉ፡፡ አሁን ሄጄ ላምጣቸው፡፡ አስነውሩአቸው፣ የፈለጋችሁትንም አድርጉባቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ክፉ ነገር አታድርጉበት!” 25 ነገር ግን ሰዎቹ እርሱን አልሰሙትም፣ ስለዚህ ሰውዮው ቁባቱን ያዛትና ወደ ውጭ አወጣላቸው፡፡ እነርሱም ያዟትና ከእርሷ ጋር ተኙ፣ ሌሊቱን በሙሉ አመነዘሩባት፣ ጎህም ሲቀድ ለቀቁአት፡፡ 26 ሴቲቱም በማለዳ መጣችና ጌታዋ ባለበት በሰውዮው ቤት በር ወደቀች፣ ጸሐይ እስኪወጣ ድረስ እዚያው ተዘረረች፡፡ 27 ጌታዋም በማለዳ ተነሣና የቤቱን በር ከፈተ፣ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፡፡ እርሱም ቁባቱ እጅዋን በመድረኩ ላይ ዘርግታ በበሩ ተዘርራ አያት፡፡ 28 ሌዋዊውም እንዲህ አላት፣ “ተነሺ፡፡ እንሂድ፡፡” ነገር ግን ምንም መልስ አልነበረም፡፡ እርሱም በአህያው ላይ ጫናት፣ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ 29 ሌዋዊውም ወደ ቤቱ በመጣ ጊዜ፣ ቢላዋ ወሰደ፣ ቁባቱንም ይዞ ቆራረጣት፣ ብልት በብልት ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ቁራጮቹን ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ላከው፡፡ 30 ይህንን ያየ ሁሉ እንዲህ አለ፣ “የእስራኤል ሕዝብ ከግብፅ ምድር ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልተደረገም ወይም አልታየም፡፡ ስለ ነገሩ አስቡበት! ምክር ስጡን! ምን ማድረግ እንዳለብን ንገሩን!”
ይህ ሐረግ በታሪክ ፍሰቱ ላይ የሌላ ሁነትን ጅማሬ ያስተዋውቃል። (አዲስ ሁነትን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)
አብዛኞቹ ሰዎች ከሚኖሩበት የራቀ
ይህ ማለት እርሷ ለግንኙነታቸው ታማኝ አልነበረችምና ከሌሎች ወንዶች ጋር መተኛት ጀምራለች ማለት ነው። አስፈላጊ ከሆነ ይህ በግልጽ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “ከሌሎች ወንዶች ጋር መተኛት ጀመረች”
“ከእርሱ ጋር አገልጋዩንና ሁለት አህዮችን ወሰደ”
“ዐማቱ፣ ይኸውም የልጅቱ አባት አግባባው” ወይም “የልጅቱ አባት አግባባው”
“ስለተናገረው ለመቆየት ወሰነ”
ሌዋዊው አዘጋጀ
እዚህ ጋ “እንጀራ” “ምግብ”ን ያመለክታል። አ.ት፡ “ለመጓዝ እንድትበረታ ጥቂት ምግብ ብላ”
“እባክህ ደግመህ እደር”
አማቱ በመብላት ራሱን እንዲያበረታ አሳብ እየሰጠው ነው። ለመሄድ እስከ ከሰዓት እንዲቆይም እየጠየቀው ነው። ይህ በግልጽ መነገር ይችላል። አ.ት፡ “ለመጓዝ እንድትበረታ ጥቂት ምግብ ብላ፤ እስከ ከሰዓት ቆይና ትሄዳለህ” (ፈሊጣዊ አነጋገር እና የሚለውን ተመልከት)
“ቀኑ እየተገባደደ ነው” ወይም “ምሽት ሊሆን ነው”
“ከጊዜ በኋላ ኢየሩሳሌም ተብላ ተጠርታለች”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በሁለቱ አህዮቹ ላይ ኮርቻዎችን ጫነባቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ አሳብ ለመስጠት የሚጠቅም የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ብንሄድ ይሻላል” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ጉዟቸውን በመግታት የሆነ ቦታ ላይ እንዲያርፉ ማለት ነው። አ.ት፡ “እዚህ ጋ እንቆይ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ጉዟቸውን በመግታት የሆነ ቦታ ላይ እንዲያርፉ ማለት ነው። ተመሳሳዩን ሐረግ በመሳፍንት 19፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “እዚህ ጋር እንረፍ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ አሳብ ለመስጠት ጥቅም ላይ የዋለ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “እንድ… አሳብ አቀርባለሁ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት ጉዟቸውን በመግታት የሆነ ቦታ ላይ እንዲያርፉ ማለት ነው። ተመሳሳዩን ሐረግ በመሳፍንት 19፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት። አ.ት፡ “ቆሙ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሰዎች ቀን ላይ የሚሰባሰቡበት የገበያ ስፍራ
የዚህ ሐረግ ትርጉም አንድ ሰው በቤቱ እንዲያድሩ ጋበዛቸው ማለት ነው። አ.ት፡ “ያንን ሌሊት በቤታቸው እንዲያሳልፉ ጋበዟቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ብንያማዊ ሰው የብንያም ተወላጅ ነበር። ይህንን የሕዝብ ወገን ስም በመሳፍንት 3፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ሰውየው ቀና አለና በዙሪያው ያለውን ተመለከተ። አ.ት፡ “ቀና አለ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ሰዎች ቀን ላይ የሚሰባሰቡበት የገበያ ስፍራ። ይህንን በመሳፍንት 19፡14 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ሐረግ የሚያመለክተው ሌሊቱን በዚያ እንዲያሳልፍ ሌላውን ሰው ወደ ቤቱ የሚጋብዝን ሰው ነው። አ.ት፡ “በቤቱ እንዳድር የጋበዘኝ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ሌዋዊው “እኔ” ይላል፣ ነገር ግን እርሱ እያመለከተ ያለው ራሱን፣ አገልጋዩንና ቁባቱን ጭምር ነው። አ.ት፡ “የሚወስደን”
ወደ አድራጊ ድምፅ ቀይረው። አ.ት፡ “ብዙ እንጀራና ወይን አለን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ሌዋዊው አክብሮቱን ለማሳየት ራሱንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሌሎቹንም በሦስተኛ መደብ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እኔ፣ ቁባቴና አገልጋዬ” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)
ይህ አዎንታዊ መግለጫ ሆኖ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “የሚያስፈልገን ሁሉ አለን”
“አትደሩ”። “ብቻ” የሚለው ቃል እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው ሌዋዊው እንዲያደርግ ስላልፈለገው ጉዳይ አጽንዖት ለመስጠት ነው።
ይህ የከተማይቱን አደባባይ ያመለክታል። ይህንን በመሳፍንት 19፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ ማለት ሌዋዊው በቤቱ እንዲያድር ጋበዘው ማለት ነው። ሌዋዊውን በመጋበዙ ቁባቱንና አገልጋዩንም ደግሞ ጋብዟቸዋል። አ.ት፡ “ሌዋዊውንና አገልጋዮቹን በቤቱ እንዲያድሩ ጋበዛቸው” (የአነጋገር ዘይቤ እና የሚለውን ተመልከት)
“ልባቸውን ያሰደስቱ” የሚለው ሐረግ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ከአንድ ሰው ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ማለት ነው። አ.ት፡ “በአንድ ላይ ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ ነበር” ወይም “ራሳቸውን ያስደስቱ ነበር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
አንዳንድ ሰዎች በቤቱ ዙሪያ ቆሙ
ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የሰዎቹን ትኩረት ለማግኘት ነው። አ.ት፡ “አድምጡ”
እዚህ ጋ ደራሲው “መስማት” በማለት የሚናገረው ስለ “መስማማት” ነው። አ.ት፡ “ሰዎቹ ግብዣውን አለተቀበሉትም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የሰውየው ማንነት አሻሚ ነው። አ.ት፡ “ሌዋዊው ቁባቱን ይዞ”
“ፀሐይ በምትወጣበት ጊዜ” ወይም “ንጋት ሲሆን” ይህ ፀሐይ መውጣት የጀመረችበትን ጊዜ ያመለክታል።
ይህ ውጪው ብርሃን የሆነበትን ጠዋት ያመለክታል። አ.ት፡ “ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ወጥታ ነበር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ሴቲቱ ሞታ ስለነበር ምላሽ አልሰጠችም። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ይሁን እንጂ ሞታ ስለነበር አልመለሰችለትም”
“በክፍል በክፍል”። ደራሲው ይህንን ሥዕላዊ መግለጫ የሚጠቀመው ሌዋዊው አካሏን በተለየ አኳኋን በመቆራረጥ ስላደረገው ነገር አጽንዖት ለመስጠት ነው። “የተቆራረጠ አካል” የአንድን ሰው እጅና እግር ያመለክታል። በቋንቋህ ተመሳሳይ ሐረግ ከሌለ ይህ አገላለጽ ከትርጉምህ ውስጥ መቅረት ይኖርበት ይሆናል። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“12 ቁርጥራጭ” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ ማለት የተለያዩ ቁርጥራጮቹን ወደ አሥራ ሁለት የእስራኤል አካባቢዎች ልኳል ማለት ነው። አ.ት፡ “እያንዳንዱን ቁራጭ ወደ ተለያዩ የእስራኤል ክፍሎች ልኳል”
1 የዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፣ የገለዓድ አገር ሰዎችንም ጨምሮ፣ በእግዚአብሔር ፊት በምጽጳ ተሰበሰቡ፡፡ 2 የሕዝቡም ሁሉ መሪዎች፣ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ፣ እግረኞች ሆነው በሰይፍ የሚዋጉ 400, 000 ሰዎች በእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ ውስጥ ስፍራቸውን ያዙ፡፡ 3 በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ እስከ ምጽጳ ድረስ እንደ ሄዱ የብንያም ሕዝብ ሰሙ፡፡ የእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “ይህ ክፉ ነገር እንዴት እንደ ተደረገ ንገሩን?” 4 ሌዋዊውም፣ የተገደለችው ሴት ባል፣ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ “እኔና ቁባቴ ሌሊቱን በዚያ ለማሳለፍ የብንያም ግዛት ወደሆነችው ወደ ጊብዓ መጣን፡፡ 5 በዚያ ሌሊት የጊብዓ ሰዎች በእኔ ላይ ተነሱ፣ ሊገድሉኝም አስበው ቤቱን ከበቡት፡፡ ቁባቴንም ያዙና ከእርስዋ ጋር ተኙ፣ እርስዋም ሞተች፡፡ 6 እኔም ቁባቴን ወሰድሁና ሰውነቷን ቆራረኋጥኋት፣ ቁርጥራጩንም በእስራኤል ርስት ወደሚገኝ ወደ እያንዳንዱ ክልል ላክሁት፣ ምክንያቱም እንዲህ ዓይነቱን ክፋትና መአት በእስራኤል ላይ ፈጽመዋልና፡፡ 7 አሁንም፣ እናንተ እስራኤላውያን ሁላችሁም ተነጋገሩ፣ ምክራችሁንም ስጡ፣ ለዚህ ነገርም ፍርዳችሁን ስጡ!” 8 ሕዝቡም ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው በአንድ ላይ ተነሱ፣ እንዲህም አሉ፣ “ከእኛ ዘንድ ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ አይሄድም፣ ማንም ሰው ወደ ቤቱ አይመለስም! 9 ነገር ግን አሁንም በጊብዓ ላይ ማድረግ ያለብን ነገር ይህ ነው፡- ዕጣው እንደሚመራን እንወጋታለን፡፡ 10 ከእስራኤል ነገዶች በሙሉ ለሕዝቡ ስንቅ እንዲይዙ ከመቶው አስር ሰው፣ ከሺህ መቶ ሰው፣ ከአስር ሺህ አንድ ሺህ ሰው እንወስዳለን፣ ይህም ሕዝቡ ወደ ብንያም ጊብዓ በሚመጣበት ጊዜ እነርሱ በእስራኤል ላይ ለፈጸሙት ክፋት ይቀጧቸው ዘንድ ነው፡፡” 11 ስለዚህም የእስራኤል ወታደሮች በሙሉ በአንድ ዓላማ በመስማማት በከተማይቱ ላይ ለመዝመት ተሰበሰቡ፡፡ 12 የእስራኤልም ነገዶች ወደ ብንያም ነገድ ሁሉ እንዲህ ብለው ሰዎችን ላኩ፣ “በእናንተ መካከል የተደረገው ይህ ክፉ ነገር ምንድር ነው? 13 ስለዚህ እንድንገድላቸውና ይህንን ክፋት ከእስራኤል ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ በጊብዓ ውስጥ ያሉትን እነዚህን ክፉ ሰዎች አውጥታችሁ ስጡን፡፡” ነገር ግን ብንያማውያን የወንድሞቻቸውን የእስራኤልን ሕዝብ ቃል አልሰሙም፡፡ 14 የዚያን ጊዜ የብንያም ሕዝብ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ለመዋጋት ዝግጅት ያደርጉ ዘንድ ከየከተማው ወጥተው ወደ ጊብዓ ተሰበሰቡ፡፡ 15 የብንያም ሕዝብ ከየከተማው በአንድ ላይ ለመዋጋት መጡ፣ በዚያም ቀን በሰይፍ ስለት ለመዋጋት የሰለጠኑ 26, 000 ወታደሮች ነበሩ፤ ከዚህ በተጨማሪ ከጊብዓ ነዋሪዎች ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ፡፡ 16 ከእነዚህ ወታደሮች መካከል ሰባት መቶ የተመረጡ ግራኝ ሰዎች ነበሩ፤ እያንዳንዳቸውም ድንጋይ ወንጭፈው አንዲት ጠጕርስ እንኳ አይስቱም፡፡ 17 የእስራኤል ወታደሮች፣ ከብንያም ወገን የሆኑትን ሳይጨምር፣ በሰይፍ ስለት ለመዋጋት የሰለጠኑ አራት መቶ ሺህ ሰዎች ተቆጠሩ፡፡ እነዚህ በሙሉ የጦር ሰዎች ነበሩ፡፡ 18 የእስራኤልም ሕዝብ ተነሱ፣ ወደ ቤቴል ወጡ፣ ከእግዚአብሔርም ምክር ጠየቁ፡፡ እንዲህም ብለው ጠየቁ፣ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት ለእኛ መጀመርያ ማን ይውጣልን?” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ “ይሁዳ በመጀመርያ ይዋጋል፡፡” 19 የእስራኤልም ሕዝብ በማለዳ ተነሱና በጊብዓ ፊት ለውጊያ ተዘጋጁ፡፡ 20 የእስራኤልም ወታደሮች ከብንያም ጋር ለመዋጋት ወጡ፡፡ እነርሱም በጊብዓ ከእነርሱ ጋር ለመዋጋት ቦታ ቦታቸውን ይዘው ተሰለፉ፡፡ 21 የብንያም ወታደሮች ከጊብዓ ወጥተው መጡ፣ በዚያም ቀን ከእስራኤላውያን ሰራዊት 22, 000 ሰዎች ገደሉ፡፡ 22 ነገር ግን የእስራኤል ወታደሮች ራሳቸውን አበረቱ፣ በመጀመርያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደገና ቦታ ቦታቸውን በመያዝ የውጊያውን መስመር አዘጋጁ፡፡ 23 የእስራኤልም ሕዝብ ወደ ላይ ወጡና እስከ ማታ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሱ፡፡ከእግዚአብሔርም ምሪትን ፈለጉ እንዲህም ብለው ጠየቁ፣ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ሕዝብ ጋር ለመዋጋት እንደገና ወደዚያ መቅረብ ይገባናልን?” እግዚአብሔርም “በእነርሱ ላይ ውጡና ግጠሟቸው” አለ፡፡ 24 ስለዚህም በሁለተኛው ቀን የእስራኤል ወታደሮች የብንያምን ወታደሮች ለመዋጋት ሄዱ፡፡ 25 በሁለተኛው ቀን የብንያም ወታደሮች ከጊብዓ እነርሱን ሊወጉ ወጡና ከእስራኤል ወታደሮች 18, 000 ሰዎች ገደሉ፡፡ እነዚህም ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ለመዋጋት የሰለጠኑ ነበሩ፡፡ 26 የዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡና አለቀሱ፣ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጡ፣ እነርሱም በዚያ ቀን እስከ ምሽት ድረስ ጾሙ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት አቀረቡ፡፡ 27 የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን ጠየቁ፣ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በዚያ ነበረ፣ 28 በእነዚህ ጊዜያቶች የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በታቦቱ ፊት ያገለግል ነበር፣ “ከወንድሞቻችን ከብንያም ሕዝብ ጋር አንድ ጊዜ ለመዋጋት እንደገና እንሂድ ወይስ እንቅር?” እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ “ጥቃት ፈጽሙባቸው፣ ነገ እነርሱን እንድታሸንፉ እረዳችኋለሁና፡፡” 29 ስለዚህ እስራኤል በጊብዓ ዙሪያ በምስጢራዊ ስፍራዎች የተደበቁ ሰዎች አኖሩ፡፡ 30 የእስራኤል ወታደሮች ከብንያም ወታደሮች ጋር ለሦስተኛ ቀን ተዋጉ፣ ከዚህ በፊት እንዳደረጉት በጊብዓ ላይ የውጊያ መስመራቸውን ዘርግተው ተሰለፉ፡፡ 31 የብንያምም ሕዝብ ሄዱና ሕዝቡን ተዋጉ፣ ከከተማይቱም እንዲወጡ ተደረጉ፡፡ ከሕዝቡም አንዳንዶቹን መግደል ጀመሩ፡፡ ከእስራኤልም ወገን የሞቱ ሠላሳ የሚያህሉ ሰዎች በእርሻዎቹና በመንገዶቹ ነበሩ፣ ከመንገዶቹ አንዱ ወደ ቤቴል የሚወስድ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ ወደ ጊብዓ የሚወስድ ነው፡፡ 32 የዚን ጊዜ የብንያምም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “እንደ በፊቱ ተሸንፈዋል፣ ከእኛ እየሸሹ ነው፡፡” ነገር ግን የእስራኤል ወታደሮች እንዲህ አሉ፣ “እንሽሽ፣ ከከተማይቱ እንዲወጡና ወደ መንገዶቹ እንዲሄዱ እናድርጋቸው፡፡” 33 የእስራኤልም ወታደሮች በሙሉ ከስፍራቸው ተነሱና በበኣልታማር ለውጊያ ራሳቸውን አዘጋጅተው ተሰለፉ፡፡ በምስጢራዊ ስፍራ ተደብቀው የነበሩት የእስራኤል ወታደሮችም ከነበሩበት ስፍራ ከጊብዓ ወጥተው ሮጡ፡፡ 34 ከእስራኤልም ሁሉ 10, 000 የተመረጡ ሰዎች በጊብዓ ላይ መጡ፣ ጦርነቱም በርትቶ ነበር፣ ነገር ግን ብንያማውያን ጥፋት ወደ እነርሱ ቀርቦ እንደነበር አላወቁም፡፡ 35 እግዚአብሔርም ብንያምን በእስራኤል ፊት ድል አደረገ፡፡ በዚያም ቀን የእስራኤል ወታደሮች 25, 100 የብንያም ሰዎችን ገደሉ፡፡ የሞቱት ሰዎች በሙሉ በሰይፍ ለመዋጋት ስልጠና የወሰዱ ነበሩ፡፡ 36 ስለዚህ የብንያም ወታደሮች እንደ ተሸነፉ አዩ፡፡ የእስራኤልም ሰዎች ለብንያም ስፍራ ለቀቁላቸው፣ ምክንያቱም ከጊብዓ ውጭ በድብቅ ስፍራዎች ባስቀመጡአቸው ሰዎች ላይ ተማምነው ነበርና፡፡ 37 የዚያን ጊዜ ተደብቀው የነበሩት ሰዎች ተነሱና ፈጥነው ወደ ጊብዓ ሮጡ፣ በከተማይቱም ውስጥ የሚኖረውን ሰው በሙሉ በሰይፋቸው ገደሉ፡፡ 38 በእስራኤል ወታደሮችና በምስጢር በተደበቁት ሰዎች መካከል ከከተማው የታላቅ ጢስ ደመና በምልክትነት እንዲያስነሡ ስምምነት ተደርጎ ነበር፡፡ 39 የእስራኤልም ወታደሮች በውጊያው ጊዜ ከጦርነቱ ርቀው እንዲያፈገፍጉ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ ብንያማውያን ማጥቃት ጀመሩ ሠላሳ የእስራኤልንም ሰዎች ገደሉ፣ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “እንደ መጀመርያው የጦርነት ጊዜ በእኛ ፊት መሸነፋቸው እርግጠኛ ነው፡፡” 40 ነገር ግን የጢሱ ዓምድ ከከተማው ወደ ላይ መውጣት በጀመረ ጊዜ፣ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ሲመለከቱ ጢሱ ከከተማዋ በሙሉ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፡፡ 41 የዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች ዞረው አጠቋቸው፡፡ የብንያም ሰዎችም ደነገጡ፣ በእነርሱ ላይ ጥፋት እንደመጣባቸው አይተዋልና፡፡ 42 ስለዚህ ከእስራኤል ወታደሮች ተመልሰው ወደ ምድረ በዳው መንገድ ሸሹ፡፡ ነገር ግን ውጊያው ተከታትሎ ደረሰባቸው፡፡ የእስራኤልም ወታደሮች ከከተማዎቹ ወጡና በቆሙበት ስፍራ ገደሉአቸው፡፡ 43 እነርሱም ብንያማውያንን ከበቡና ተከትለዋቸው ሄዱ፤ በመኑሔም አሸነፉአቸው፣ ከጊብዓ በስተ ምሥራቅ በኩል እስካለው ስፍራ ድረስ አሳደዱአቸው፡፡ 44 ከብንያም ነገድም 18, 000 ወታደሮች ሞቱ፣ እነዚህ ሰዎች በሙሉ በጦርነት ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ፡፡ 45 እነርሱም ተመልሰው በምድረ በዳ ወዳለው ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፡፡ እስራኤላውያንም ከእነርሱ ተጨማሪ አምስት ሺህ ሰዎችን በየመንገዱ ገደሉ፡፡ እነርሱም ተከታተሉአቸው፣ ወደ ጊድአምም በቅርብ እየተከታተሉአቸው ተጨማሪ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደሉ፡፡ 46 በዚያ ቀን የሞቱት የቢኒያም ወታደሮች በሙሉ 25, 000 በሰይፍ ለመዋጋት ልዩ ስልጠና የወሰዱ ሰዎች ነበሩ፤ እነዚህ በሙሉ በጦርነት ምርጥ ተዋጊዎች ነበሩ፡፡ 47 ነገር ግን ስድስት መቶ ሰዎች ተመልሰው በምድረ በዳ ወዳለው ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፡፡ ለአራት ወራት ያህል በሬሞን ዓለት ተቀመጡ፡፡ 48 የእስራኤልም ወታደሮች በብንያም ሕዝብ ላይ እንደገና ተመለሱ፣ ሞላውን ከተማ፣ ከብቶችንና ያገኙትንም ሁሉ አጠቁ ደግሞም ገደሉ፡፡ በመንገዳቸው ያገኙትን ማንኛውንም ከተማ ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፡፡
ይህ ንጽጽር የሚናገረው አንድ ቡድን እንደ አንድ ሰው መንቀሳቀሱን ነው። ይህ የሚያመለክተው በቡድን የሆኑ ሰዎች በተመሳሳይ መንገድ ሁሉንም ነገር በጋራ የሚያደርጉ መሆናቸውን ነው። አ.ት፡ “አንድ ሰው የሆኑ ያህል” (ንጽጽር የሚለውን ተመልከት)
ይህ በጥቅሉ ምድሪቱን ያመለክታል። አ.ት፡ “ከአሥራ አንዱ ነገዶች በሙሉ”
“እግዚአብሔርና በተጨማሪም 400,000 መደበኛ ወታደሮች መጡ”
“ወደ ጦርነት ለመሄድ ብቁ የሆኑ”። የሚሄዱት እርስ በእርስ ለመዋጋት አልነበረም።
ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ዋናው የትረካ መስመር ለአፍታ መገታቱን ለማሳየት ነው። እዚህ ጋ የመጽሐፉ ደራሲ የብንያም ሰዎች ስለሚያውቁት ነገር ዳራዊ መረጃ ይናገራል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
ምጽጳ የምትገኘው ከፍ ባሉት ተራራዎች ላይ ነበር።
“ለሌሊቱ” ወይም “አንድ ሌሊት ለማደር”
“የጭካኔ ተግባር” የሚለው ቃል “ክፋት”ን ያብራራዋል። አ.ት፡ “አሰቃቂ ክፋት”
ይህ ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የሌዋዊውን ንግግር መደምደሚያ ለማስተዋወቅ ነው።
“አስተያየት” እና “ምክር” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት አንድን ነገር ሲሆን አጽንዖት ለመስጠት ተደግመዋል። ሁለቱ ሊጣመሩ ይችላሉ። አ.ት፡ “ስለዚህ ጉዳይ ምን ማድረግ እንደሚኖርብን ወስኑ”
ይህ ንጽጽር የሚናገረው እንደ አንድ ሰው ስለሚንቀሳቀስ ቡድን ነው። ሁሉም በተመሳሳይ መንገድ በአንድ ላይ ተንቀሳቀሱ። አ.ት፡ “አንድ ሰው የሆኑ ያህል” (ንጽጽር የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ሁለት አንቀጾች ስለ አንድ ነገር ሁለቴ መናገራቸው በመሠረቱ አጽንዖት ለመስጠት ነው። ሊጣመሩ ይችላሉ። “ማንም . . . አይሄድም” እና “ማንም . . . አይመለስም” የሚሉት ቃላት ሰዎቹ በዚያ መቆየታቸውን እንዴት እንደሚቀጥሉ አጽንዖት ይሰጣል። በአዎንታዊ ድምፅ ሊነገሩ ይችላሉ። አ.ት፡ “ሁላችንም እዚሁ እንቆያለን”
እነዚህ ቃላት ሰዎቹ ከመጀመሪያው ጩኸት በኋላ የተናገሩትን ዐቢይ ጉዳይ ያስተዋውቃሉ።
እግዚአብሔር የሚፈልገውን ለማወቅ ምልክት የተደረገባቸውን ጠጠሮች መወርወርን ወይም ማንከባለልን ያካትታል።
“ከ100 ሰው 10፣ ከ1,000 ሰው 100፣ ከ10,000 ሰው 1,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ሰዎቹ የሚያስፈልጋቸው ምግብና ሌሎች ነገሮች
“ከተማይቱን ለመውጋት በአንድ ላይ ተሰበሰቡ”
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ነው። አ.ት፡ “ግደሏቸው” ወይም “አስወግዷቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “ድምፅ” የሚያመለክተው የተናገሩትን መልዕክታቸውን ነው። አ.ት፡ “ወንድሞቻቸው የተናገሩትን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“26,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“700” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ግራኝ የሆነ ሰው ከቀኝ እጃቸው ይልቅ በግራ እጃቸው የበለጠ መሥራት ከሚችሉ ሰዎች አንዱ ነው።
ይህ የሚያመለክተው በሚያስደንቅ ሁኔታ ዒላማቸውን የሚመቱ መሆናቸውን ነው። ይህ በአዎንታዊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በጸጉር ላይ እንኳን ድንጋይ ወርውረው መምታት ይችላሉ” ወይም “እንደ ጸጉር በቀጠነ ነገር ላይ ድንጋይ ወርውረው መምታት ይችላሉ”
“ሳይጨመሩ”
“አራት መቶ ሺህ ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“ምን ማድረግ እንዳለባቸው እግዚአብሔርን ጠየቁ” ወይም “እንዴት መቀጠል እንዳለባቸው እግዚአብሔርን ጠየቁ”
ስለ ዕብራይስጡ ጽሑፍ ትርጓሜ አንዳንድ ጥያቄዎች አሉ። ሠፈራቸውን በጊብዓ አቅራቢያ አደረጉ ከሚለው ትርጉም ይልቅ ሰራዊቱ ተጉዞ በጊብዓ ትይዩ ለጦርነት ተዘጋጅተው ቆሙ ማለት ይሆናል።
“22,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “አበረታቱ” የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን እርስ በእርሳቸው ተበረታቱ ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ ምናልባት እስራኤላውያኑ በመሰለፍ ለቀጣዩ ቀን ጦርነት ተዘጋጅተዋል ማለት ሊሆን ይችላል። አ.ት፡ “በቀጣዩ ቀን ለመዋጋት ተዘጋጁ”
እንዴት ባለ መንገድ እንደ ፈለጉ አልተገለጸም። ምናልባት ካህኑ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ዕጣ ጥሎ ይሆናል።
“18,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“በእግዚአብሔር ሀልዎት” ወይም “ለእግዚአብሔር”
ይህ አንባቢው፣ ሕዝቡ እግዚአብሔር ምላሽ እንዲሰጣቸው እንዴት እንደጠየቁ መገንዘብ እንዲችል ለመርዳት ደራሲው የጨመረው ዳራዊ መረጃ ነው። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
“በእነዚያ ቀናት በቤቴል ነበር”
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በታቦቱ ፊት በክህነት ያገለግል ነበር”
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የብንያምን ሰራዊት አጥቁ”
እዚህ ጋ “እስራኤል” የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው። አ.ት፡ “ እስራኤላውያን” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“በደፈጣ”
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከእስራኤል ሰዎች ጋር ተዋጉ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የእስራኤል ሰዎች ከከተማይቱ ስበው አወጧቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “የብንያም ሰዎች ከእስራኤል ሰዎች ጥቂቶቹን መግደል ጀመሩ”
“ልክ እንደ ቀድሞው” ወይም “ልክ እንደ መጀመሪያዎቹ ሁለት ጊዜያት”
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ቦታ ስም ነው። ሌሎች ትርጉሞች ምናልባት “የጊብዓ ሜዳዎች” ወይም “ከጊብዓ በስተምዕራብ” ወይም “ማሬህ ጌባ” (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“10,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን እነዚህ በተለየ ሁኔታ ጥሩ ወታደሮች ነበሩ ማለት ነው። አ.ት፡ “በሚገባ የሰለጠኑ ወታደሮች” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ የጥፋት መቅረብ አጠገባቸው እንደ ቆመ ያህል ተደርጎ ተነግሯል። አ.ት፡ “ወዲያውኑ ፈጽሞ ሊሸነፉ ነው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“ሃያ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሰዎች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ከዚህ ዐረፍተ ነገር እስከ ቁጥር 41 መጨረሻ ድረስ ያለው የደፈጣ ተዋጊዎቹ ብንያማውያንን እንዴት እንዳሸነፏቸው ጸሐፊው ለአንባቢያን ለማብራራት የጨመረው ዳራዊ መረጃ ነው።
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ሆን ብለው ወደ ኋላ ተመልሰዋል ማለት ነው። አ.ት፡ “ብንያማውያን ወደ ፊት እንዲመጡ ፈቅደውላቸው ነበር” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን በሰዎቻቸው ታምነዋል ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
“ከጦርነቱ የሚያፈገፍጉ”
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አሸንፈናቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ታላቅ ጉዳት፣ መከራ፣ ስቃይ
ይህ የአነጋገር ዘይቤ ደረሰባቸው ማለት ነው። አ.ት፡ “ደረሰባቸው” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
ይህ አንድ ሰው ሌላውን በሚይዝበት መልኩ የተነገረው ስለ ጦርነት ነው። አ.ት፡ “ነገር ግን የእስራኤል ወታደሮች ያዟቸው” ወይም “ነገር ግን ከጦርነቱ ለማምለጥ አልቻሉም” (ሰውኛ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ የቦታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
የብንያማውያን መደምሰስ እስራኤላውያን በሬሳዎቻቸው ላይ እንደተረማመዱ ሆኖ ተነግሯል። አ.ት፡ “ሙሉ በሙሉ ደመሰሷቸው” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
“18,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“በጦርነት ውስጥ በጀግንነት የተዋጉ ነበሩ”
“የቀሩት ብንያማውያን ተመልሰው ሸሹ”
“5,000 … 2,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንድ ቦታ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“25,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
“600” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
እነዚህ ወደ ሬሞን ዐለት የሸሹት የብንያም ሰዎች ወታደሮች ሳይሆኑ ገና በከተማው ውስጥ የነበሩት ናቸው።
እዚህ ጋ “ከተማው” የሚያመለክተው በዚያ ከተማ የሚኖሩትን ሰዎች ነው። አ.ት፡ “በከተማው የነበረው ሁሉ” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአነጋገር ዘይቤ የሚያመለክተው ወደ ከተማይቱ በሚሄዱበት ጊዜ ያገኙትን ነገር ሁሉ ነው። አ.ት፡ “ወደ … መጡ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)
1 በዚያን ጊዜ የእስራኤል ወታደሮች በምጽጳ “ከእኛ ማንም ሰው ሴት ልጁን በጋብቻ ለብንያማውያን መዳር የለበትም” በማለት ቃል ገብተው ነበር፡፡ 2 ከዚያም ሕዝቡ ወደ ቤቴል ሄዱና በዚያ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ምሽቱ ድረስ ተቀመጡ፣ ድምፃቸውንም ከፍ በማድረግ አምርረው አለቀሱ፡፡ 3 እነርሱም እንዲህ ሲሉ ጮኹ፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህ በእስራኤል ለምን ሆነ? ዛሬ ከእኛ አንዱ ነገድ መታጣቱ ለምንድን ነው?” 4 በሚቀጥለውም ቀን ሕዝቡ በጠዋት ተነሡና በዚያ መሠዊያ ሠሩ፣ የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትንም አቀረቡ፡፡ 5 የእስራኤልም ሕዝብ እንዲህ አሉ፣ “ከእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ያልመጣ የትኛው ነው?” በምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ፊት ስላልመጣ ማንም ሰው በጣም ወሳኝ የሆነ ቃል ኪዳን አድርገው ነበርና፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “እርሱ ፈጽሞ ሊገደል ይገባዋል፡፡” 6 የእስራኤልም ሕዝብ ስለ ወንድማቸው ስለ ብንያም አዘኑ፡፡ አነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ዛሬ ከእስራኤል ነገድ አንዱ ተቆርጧል፡፡ 7 ሴቶች ልጆቻችንን ከእነርሱ ለአንዳቸውም ቢሆን በጋብቻ ላንሰጥ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለገባን ለተረፉት ሚስቶችን የሚሰጣቸው ማን ነው?” 8 እነርሱም አሉ፣ “ከእስራኤል ነገድ በምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ያልመጣ የትኛው ነው?” ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ጉባኤው አንድም ሰው አለመምጣቱን አወቁ፡፡ 9 ሕዝቡም በቅደም ተከተል ተሰልፈው እንዲቆጠሩ በተደረገ ጊዜ፣ እነሆ፣ ከኢያቢስ ገለዓድ ነዋሪዎች ማንም ሰው በዚያ አልነበረም፡፡ 10 ጉባኤውም 12, 000 ኃያላን ሰዎችን ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ልከው በዚያ ያሉትን ሰዎች ሴቶችንና ሕፃናትንም ጭምር ጥቃት እንዲያደርሱባቸውና እንዲገድሏቸው አዘዙአቸው፡፡ 11 “እንግዲህ የምታደርጉት ይህ ነው፡- ወንዱን በሙሉ እንዲሁም ከወንድ ጋር የተኛችውንም ሴት በሙሉ ግደሉ፡፡” 12 ሰዎቹም በኢያቢስ ገለዓድ ከሚኖሩት መካከል ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ አራት መቶ ወጣት ሴቶች አገኙ፣ እነርሱንም በከነዓን ወዳለው በሴሎ ወደሚገኘው ሰፈር ወሰዷቸው፡፡ 13 ጉባኤውም በሙሉ መልክት ላኩ፣ በሬሞን ዓለት ለነበሩት ለብንያም ሕዝብ የሰላም ጥሪ እንዳቀረቡላቸውም ነገሩአቸው፡፡ 14 ሲለዚህ በዚያን ጊዜ ብንያማውያን ተመለሱ፣ የኢያቢስ ገለዓድንም ሴቶች ሰጧቸው፡፡ ነገር ግን ለሁሉም የሚበቁ ሴቶች አልነበሩም፡፡ 15 ሕዝቡም በብንያም ላይ በሆነው ገር አዘኑ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በእስራኤል ነገዶች መካከል ስብራት አድርጓልና፡፡ 16 የዚያን ጊዜ የጉባኤው መሪዎች እንዲህ አሉ፣ “የብንያም ሴቶች ተገድለዋልና፣ ለተረፉት ብንያማውያን ሚስቶችን እንዴት እናግኝላቸው?” 17 እንዲህም አሉ፣ “ከእስራኤል አንድ ነገድ እንዳይጠፋ ከብንያም አሁን በሕይወት ላሉት ሰዎች ርስት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ 18 ከሴቶች ልጆቻችን ሚስቶች ልንሰጣቸው አንችልም፡፡ የእስራኤል ሕዝብ፣ ‘ለብንያም ሚስት የሚሰጥ ርጉም ይሁን’ የሚል ቃል ኪዳን ገብተው ነበርና፡፡” 19 ስለዚህ እንዲህ አሉ፣ “በቤቴል በሰሜን በኩል፣ ከቤቴልም ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ በምሥራቅ በኩል፣ በለቦና በደቡብ በኩል ባለችው በሴሎ በየዓመቱ የእግዚአብሔር በዓል እንዳለ ታውቃላችሁ፡፡” 20 እነርሱም ለብንያም ሰዎች እንዲህ ብለው አዘዙአቸው፣ “ሂዱና በምስጢር ተሸሸጉ፣ በወይኑ ስፍራም ተደበቁ፡፡ 21 የሴሎ ልጃገረዶች ለመጨፈር የሚወጡበትን ጊዜ ተመለክቱ፣ የዚያን ጊዜ ከወይኑ ስፍራ ፈጥናችሁ ውጡና እያንዳንዳችሁ ከሴሎ ልጃገረዶች ለየራሳችሁ ሚስት ውሰዱ፣ ከዚያም ወደ ብንያም ምድር ተመለሱ፡፡ 22 አባቶቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ሊጣሉን በመጡ ጊዜ፣ እንዲህ እንላቸዋለን፣ ‘ምህረት አድርጉልን! ባልና ሚስት ሆነው ይጽኑ ምክንያቱም በጦርነቱ ጊዜ እኛ ለያንዳንዳቸው ሚስት አላገኘንላቸውም፡፡ እናተ ደግሞ ሴቶች ልጆቻችሁን ለእነርሱ ስላልሰጣችሁ፣ ቃል ኪዳኑን በተመለከተ በደለኞች አይደላችሁም፡፡’” 23 የብንያምም ሕዝብ እንዲሁ አደረጉ፣ በቍጥራቸው መጠን የሚያስፈልጋቸውን ያህል ሚስቶች ይጨፍሩ ከነበሩት ልጃገረዶች ወሰዱ፣ ሚስትም ይሆኗቸው ዘንድ ይዘዋቸው ሄዱ፡፡ እነርሱም ወደ ርስታቸው ስፍራ ተመልሰው ሄዱ፤ ከተሞችንም እንደገና ሠሩ፣ በውስጣቸውም ኖሩ፡፡ 24 በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ያን ስፍራ ለቀቁና ወደ ቤታቸው ሄዱ፣ እያንዳንዱም ወደ ነገዱና ወደ ወገኑ ሄደ፣ እያንዳንዱም ወደ ርስቱ ተመለሰ፡፡ 25 በዚያም ዘመን በእስራኤል ውስጥ ንጉሥ አልነበረም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በዓይኖቹ ፊት መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር፡፡
ይህ ዳራዊ መረጃ እስራኤላውያን ከብንያማውያን ጋር ከመዋጋታቸው በፊት ስላደረጉት ቃል ኪዳን ለአንባቢው ይናገራል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የብንያም ተወላጆች ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 3፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
የእስራኤል ሰዎች ይህንን ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የተጠቀሙት ጥልቅ ሐዘናቸውን ለመግለጽ ነው። ይህ ጥያቄ እንደ መግለጫ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ሆይ፣ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ ሙሉ በሙሉ በመጥፋቱ በጣም አዝነናል” (ምላሽ የማይሻ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)
ሰዎቹ ብንያማውያንን ከመውጋታቸው በፊት በምጽጳ እያሉ የእስራኤላውያኑ ጉባዔ የተናገሩትን ያመለክታል።
ይህ እስራኤላውያኑ ብንያማውያኑን ከመውጋታቸው በፊት በምጽጳ ስላደረጉት መሐላ ለአንባቢው ለማብራራት የቀረበ ዳራዊ መረጃ ነው። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ “እርሱ” የሚያመለክተው ወደ ምጽጳ ያልሄደውን ማንኛውንም ሰው ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “በእርግጥ ያንን ሰው እንገድለዋለን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የሚናገረው ስለ ብንያም ነገድ ሲሆን ለነገዱ ያላቸውን ቅርበት ለማሳየት እንደ እስራኤል ወንድም ታይቷል። አ.ት፡ “የተረፉት ብንያማውያን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
የብንያም ነገድ መጥፋት ከእስራኤል በቢላዋ የተቆረጠ ያህል ተነግሯል። ይህ ግነት ነው፣ ምክንያቱም 600 ሰዎች ገና ቀርተው ነበር። ይሁን እንጂ ብንያማውያን ሴቶች ተገድለው ስለ ነበር የነገዱ የወደፊት ዕጣ ፈንታው በጥያቄ ውስጥ ነበር። አ.ት፡ “አንድ ነገድ ተደምስሷል” (ዘይቤአዊ አነጋገር፣ ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
እስራኤላውያኑ ለተረፉት ጥቂት ብንያማውያን ሚስቶችን ለማቅረብ ፈልገዋል፣ ነገር ግን በምጽጳ ያደረጉት መሐላ ይህንን ከማድረግ አግዷቸዋል።
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
“በምጽጳ የተሰበሰቡት ሰዎች ተጠያቂነት ነበረባቸው”
ይህ የሚያመለክተው ቀደም ሲል በምጽጳ የተደረገውን ጉባዔ ነው። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከኢያቢስ ገለዓድ ተወላጆች አንድም ሰው በምጽጳ አልተገኘም ነበር”
“12,000” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
በዚህ ጥቅል መመሪያ ላይ የሚቀጥለው ቁጥር የማይመለከተው ማንን እንደሆነ ይጨምራል።
“በሰይፎቻችሁ ግደሏቸው”
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 21፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ለማመልከት በጨዋነት የተነገረ አነጋገር ነው።
“400 ወጣት ሴቶች” (ቁጥሮች የሚለውን ተመልከት)
የነገር ስም የሆነው “ሰላም” በግሣዊ ሐረግ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ከእነርሱ ጋር መዋጋታቸውን ለማቆም ፈለጉ” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። ይህንን በመሳፍንት 21፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ከኢያቢስ ገለዓድ የተገኙት አራት መቶ ሴቶች ብቻ ሲሆኑ ብንያማውያኑ ስድስት መቶ ሰዎች ነበሩ።
“የእስራኤል ነገዶች አንድ እንዳይሆኑ አደረጋቸው”
ይህ የሚያመለክተው የብንያምን ተወላጆች ነው። ይህንን በመሳፍንት 3፡15 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ብንያማውያን ሴቶችን በሙሉ ገደልናቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)
እስራኤላውያኑ እያጋነኑ ነው። ቀደም ሲል ለአራት መቶ ብንያማውያን ሚስቶችን ሰጥተዋቸዋል፣ በመሆኑም፣ ነገዱ ሙሉ በሙሉ አይጠፋም። (ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)
እዚህ ጋ ብንያም የሚያመለክተው የብንያም ተወላጅ የሆኑትን ወንዶች ነው። አ.ት፡ “ለብንያማውያን ወንዶች ሚስት”
ይህ የሴሎ ከተማ የሚገኝበትን አካባቢ ለአንባቢው ለማብራራት የተሰጠ ዳራዊ መረጃ ነው። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)
ይህ የአንዲት ከተማ ስም ነው። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)
ብንያማውያኑ እነዚህን ሴቶች ይዘው ወደ ገዛ ምድራቸው ተመልሰው እንደሚሄዱ ይታወቃል። የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “እያንዳንዳችሁ ከሴሎ ልጃገረዶች አንዷን መያዝና ሚስት እንድትሆናችሁ ከእናንተ ጋር ወደ ብንያም ምድር መውሰድ ይኖርባችኋል”
የነገር ስም የሆነው “ምህረት” እንደ ድርጊት ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ደግነትን አድርጉልን” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)
የዚህ መግለጫ ሙሉ ትርጉም ግልጽ መደረግ ይችላል። አ.ት፡ “ከኢያቢስ ገለዓድ ጋር በተዋጋን ጊዜ ለእያንዳንዳቸው ሚስት ስላላገኘን”
ይህ የሚያመለክተው የሴሎን ሰዎች ነው። እነርሱ ሴቶች ልጆቻቸውን ለብንያማውያን በፈቃደኝነት አልሰጡም፣ በመሆኑም ይህንን ላለማድረግ የገቡትን መሐላ አላፈረሱም።
ይህ የሚያመለክተው ከኢያቢስ ገለዓድ ሚስቶችን ላላገኙ ሁለት መቶ ብንያማውያን ለእያንዳንዳቸው አንዲት ሚስት ነው። (መሳፍንት 21፡14ን ተመልከት)።
“እስራኤል ገና ንጉሥ አልነበራትም”
ዐይን ማየትን፣ ማየትም አሳብን ወይም ፍርድን ይወክላል። አ.ት፡ “ልክ ነው ብሎ የሚፈርደውን” ወይም “ልክ ነው ብሎ የሚያስበውን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)
1 መሳፍንት ይገዙ በነበረበት ዘመን በምድሪቱ ላይ ራብ ነበረ። አንድ ከበተልሔም ይሁዳ የሆነ ሰው ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር ወደ ሞአብ አገር ሄደ፡፡ 2 የሰውዮው ስም አቤሜሌክ ይባል ነበር፣ የሚስቱም ስም ኑኃሚን ይባላል፡፡ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን፣ የይሁዳ ቤተልሔም ኤፍራታውያን ነበሩ፡፡ እነርሱም ወደ ሞዓብም አገር ደረሱና በዚያ ተቀመጡ፡፡ 3 የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ ሞተ እርስዋም ከሁለቱ ወንዶች ልጆችዋ ጋር ቀረች፡፡ 4 እነዚህ ወንዶች ልጆች ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስቶችን ወሰዱ፤ የአንዷ ስም ዖርፋ ነበር፣ የሌላኛዋ ስም ደግሞ ሩት ነበረ። በዚያም ለአሥር ዓመታት ያህል ተቀመጡ፡፡ 5 ከዚያም መሐሎንና ኬሌዎን ሁለቱም ሞቱ፣ ኑኃሚንም ያለ ባልዋና ያለ ሁለቱ ልጆችዋ ብቻዋን ተለይታ ቀረች፡፡ 6 በዚያን ጊዜ ኑኃሚን ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ሞአብን ለመልቀቅና ወደ ይሁዳ ለመመለስ ወሰነች፡፡ እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር የተቸገሩትን ሕዝቡን እንደረዳቸውና መብልን እንደ ሰጣቸው ሰማች፡፡ 7 ስለዚህ እርስዋ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከነበረችበት ስፍራ ለቀቀች፣ ከዚያም ወደ ይሁዳ ምድር ለመመለስ መንገዱን ይዘው ወደታች ሄዱ፡፡ 8 ኑኃሚን ለምራቶችዋ “ሂዱ፣ እያንዳንዳችሁ ወደ እናታችሁ ቤት ተመለሱ፡፡ ለሞቱትና ለእኔ ታማኝነት እንዳሳያችሁን ሁሉ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ታማኝነቱን ያሳያችሁ፡፡ 9 ጌታ እያንዳንዳችሁን በሌላ ባል ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ” አለቻቸው፡፡ ከዚያም ሳመቻቸው፣ እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፡፡ 10 እነርሱም “አይሆንም! ከአንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን” አሉአት፡፡ 11 ኑኃሚን ግን “ልጆቼ ሆይ፣ ተመለሱ! ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ባሎቻችሁ ይሆኑ ዘንድ ለእናንተ የሚሆኑ ወንዶች ልጆች በማሕጸኔ አሁን አሉን? 12 ልጆቼ ሆይ፣ ተመለሱ፣ በራሳችሁ መንገድ ሂዱ፤ ባል ለማግባት በጣም አርጅቻለሁና፡፡ ዛሬ ማታ ባል አገኛለሁ ብየ እንኳ ተስፋ ባደርግና ወንዶች ልጆችን ብወልድ፣ 13 እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትጠብቃላችሁን? እየጠበቃችሁ አሁን ባል ሳታገቡ ትቀራላችሁን? አይሆንም፣ ልጆቼ ሆይ! ከእናንተ ይልቅ ሁኔታው እኔን እጅግ በጣም ያስመርረኛል፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ወጥቶአልና፡፡ 14 በዚያን ጊዜ ምራቶችዋ ድምፃቸውንም ከፍ አደረጉና እንደገና አለቀሱ፡፡ ዖርፋም አማትዋን ሳመቻትና ተሰናበተቻት፣ ሩት ግን ተጠግታ ያዘቻት፡፡ 15 ኑኃሚንም “አድምጪኝ፣ እነሆ የባልሽ ወንድም ሚስት ወደ ሕዝብዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፡፡ ከባልሽ ወንድም ሚስት ጋር አንቺም ተመለሽ” አለቻት፡፡ 16 ነገር ግን ሩት “ከአንቺ ርቄ እንድሄድ አታድርጊኝ፣ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፤ በምትቆይበትም እቆያለሁና፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ ይሆናል፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፡፡ 17 በምትሞችበትም እሞታለሁ፣ በዚያም እቀበራለሁ፡፡ ከሞት በቀር እኛን አንድም ነገር ቢለየን እግዚአብሔር ይቅጣኝ፣ ከዚህም በላይ ያድርግብኝ” አለቻት፡፡ 18 ኑኃሚን ሩት ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ወሰነች ባየች ጊዜ፣ ከእርስዋ ጋር መከራከር አቆመች፡፡ 19 ስለዚህ ሁለቱም ወደ ቤተ ልሔም ከተማ እስኪመጡ ድረስ ተጓዙ፡፡ ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ፣ ከተማው በሙሉ ስለ እነርሱ እጅግ በጣም ተደነቁ፡፡ ሴቶችም “ይህች ኑኃሚን ናትን?” አሉ፡፡ 20 እርስዋ ግን “ኑኃሚን ብላችሁ አትጥሩኝ፡፡ ሁሉን የሚችል አምላክ ሕይወቴን መራራ አድርጎታልና፣ ማራ በሉኝ” አለቻቸው፡፡ 21 በሙላት ሄድሁ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ ቤቴ ባዶዬን እንደገና መለሰኝ፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር አዋርዶኝ፣ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስጨንቆኝ እያያችሁ ለምን ኑኃሚን ትሉኛላችሁ?” አለቻቸው፡፡ 22 ስለዚህ ኑኃሚንና ምራትዋ ሞአባዊት ሩት ከሞዓብ አገር ተመለሱ፡፡ እነርሱ የገብስ መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ፡፡
“እንዲህም ሆነ” ይሄ የተለመደ የታሪካዊ ተረካ አጀማመር ነው።
“መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ገዜ”
ይሄ የሚያመላክተው የእስራኤልን ምድር ነው። “በአገሩ”
“አንድ ሰው” ይሄ አንድን ገፀባህሪ ወደ ትረካው ማስገቢያ (ማስተዋወቅያ)ተልምዷዊ መንገድ ነው።
ከኤፍሬም ጎሳ(ነገድ)የሆኑ፤ በይሁዳ ክልል በሆነው በቤተልሄም የሰፈሩ ሰዎች ነበሩ።
“ኑኃሚንም ከሁለት ልጆቿ ጋር በቻዋን ቀረች“
”ሴቶች ሚስት አገቡ (ወሰዱ)“ ይሄ ሚስት ማግባትን ያመላክታል
የኑኃሚን ወንድ ልጆች ከሞዓብ ጎሳ (ነገድ)የሆኑ ሴቶች። ሞዓባውያን ሌሎች አማልክትን ያመልኩ ነበር።
“. . . የተባሉ የሞዓብ ሴቶች“
አቤሜሌክ እና ኑኃሚን ወደ ሞዓብ ከመጡ ከአስር ዓመት በኋላ፤ ልጆቻቸው መሓሎን እና ኬሌዎን ሞቱ።
ኑኋሚን መበለት ሆነች።
“እርሷም በሞአብ ሳለች”። ዜናው የመጣው ከእስራኤል አገር እንደሆነ ያመላክታል። እግዚአብሄር እስራኤልን እንደጎበኘ በሞአብ ምድር ሳለች ሰማች።
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ለህዝቡ የተገለጠበት ስም ነው። (የእግዛብሔርን ስም ስለመተርጎም በቃላት አተረጓጎም መምሪያ ገፁ ላይ ተመልከቱ)
ሕዝቡን እንደጎበኘ እንጀራም እንደሰጣቸው
ምራቶችዋ፤ ወንድ ልጆቿን ያገቡት ሴቶች
“የሚመልሳቸውን መንገድ ይዘው።” መንገድ ይዘው የሚለው በአንድ መንገድ መሄድን የሚያመላክት አባባል ነው።
የወንድ ልጆች ሚስቶች ወይንም የወንድ ልጆቿ መበለቶች
ኑኃሚን የምታዋራው ሁለት ሰዎችን ነበር፤ ከዚህ በመቀጠልም እናንተ ብላ ስትናገር ሁለቱን በማስመልከት ነው።
“ወደ እናቶቻችሁ ቤትም”
“ቸርነትን እንዳደረጋችሁ”
“ቸርነት” የ ፍቅር፣ የበጎነት፣ እና ታማኝነትን ያመላክታል።
“ለሞቱት ባሎቻችሁ” ን ኡኃሚን በዚህ የሞቱትን ልጆችዋን ማመላከት ነው የፈለገችው።
“እንደዚሁ ያድርግላችሁ” ወይንም “እንዲደረግላችሁ ይፍቀድ”
እዚህ ጋር “ያሳርፋችሁ” የሚለው በትዳርም የሚገኘውን ደህንነትን ያጠቃልላል።
ከአዳዲስ ባሎቻችሁ፣ ከሌላ ሰው ባል ጋር አይደለም። ይሄ የሚያመላክተው በባልየው ቤት ውስጥ እና ከባልየው የሃፍረት ከለላ ስር ማለት ነው።
ድምፅን ከፍ ማድረግ ለጮክ በሎ ማውራትን የሚያመላክት አባባል ነው። ምራቶቷም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወይንም አምርረው አለቀሱ።
“እንመለሳለን” ዓርፋ እና ሩት “እኛ” ብለው ሲናገሩ ስለራሳቸው እንጂ ስለ ሩት አንነበረም የሚናገሩት።
እዚህ ጋር “አንቺ” የሚለው የሚያመላክተው ኑኃሚንን ነው።
ይህ ምላሽ የሚሰጥለት ጥያቄ አይነት አይደለም። “ከእኔ ጋር መሄዱ ትርጉም አይሰጥም።” ወይንም “ከእኔ ጋር መሄድ የለባችሁም።”
ኑኃሚን በዚህ ጥያቄዋ ለእነርሱ የሚሆኑ ወንድ ልጆች ከዚህ ወድያ ልትወልድላቸው እንደማትችል ትናገራለች። “መቼስ ለእናንተ ባል መሆን የሚችሉ ሌሎች ወንድ ልጆች ከዚህ በኋላ መውለድ አልችልም።”
ባል የማግባቱ ምክንያት በግልፅ ተጠቅሷል። “ሌሎች ወንድ ልጆች እንዳልወልድ”
“መፀነስ” ወይንም “ወንድ ልጆች መውለድ”
እነኚህ ምላሽ የሚሰጥላቸው ጥያቄዎች አይነት አይደሉም። “ታገብዋቸው ዘንድ እስኪያድጉ አትጠብቋቸውም። አሁን ማግባትን ትመርጣላችሁ”
መራራነት የሃዘን እና የሰቆቃ መገለጫ ነው፤ በዚህም የሃዘንዋ መንሳኤ ምን እንደሆነ ማወቁ አያዳግትም። “የእናንተ ባል አለመኖር እኔን ያሳዝነኛል።
“እጅ” የሚለው የእግዚአበሔርን ኃይል ወይንም ተፃዕኖ ያሳያል። “የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ወጥቶአልና።”
ይህ የሚያመላክተው አምርረው እንዳለቀሱ እና ጮክ ብለው እንደተጣሩ ነው።
“ልብ በይ፤ ምክኛቱም አሁን የምልሽ ነገር እውነትና ጠቃሚ ነው፤ ባልንጀራሽ።”
“ሩት ኝ ተጠጋቻት።” “ሩት ልትለያት አልወደደችም።” ወይንም “ ሩት አልለያትም አለች።”
“ባልንጀራሽ”
ዓርፋ እና ሩት ልጆችዋን ከማግባትዋ በፊት የሞአባውያንን አማልክት ያመልኩ ነበር። በትዳራቸዋም ውስጥ ሳሉ የኑኃሚንን አምላክ ማምለክ ጀምረው ነበር።
“ወደ ምትኖሪበት”
ሩት በዚህ የምታመላክተው የኑኃሚንን ህዝቦች ነው፤ እስራኤላውያንን። “የአገርሽን ሕዝቦች እንደ እራሴ ሕዝቦች እቆጥራለሁ።” ወይንም “ዘመዶችሽን እንደ ዘመዶቼ እቆጥራለሁ።”
ይህ ሩት እስከ ዕድሜዋ ፍፃሜ ከኑኃሚን ጋር በአንድ ቦታ እና ከተማ የመሆን ፍላጎቷን ያሳያል።
ይህ የሚያመላክተው ሩት አደርጋለሁ ያለችውን ባታደርግ፤ እግዚአብሔር እንዲቀጣት እየጠየቀች እንደሆነ ነው። “እግዚአብሔር አይፍቀድ እንደማለት ነው።”
“ኑኃሚን ሩትን መጐትጐቷን ተወች”
“እንዲህ ሆነ።” ይህ የታሪኩ አዲስ ምዕራፍ መነሻ አመላካች ነው።
“ከተማው” የሚለው በዛ የሚኖሩ ሰዎችን በሙሉ ያመላክታል። “የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ።”
ኑኃሚን በቤተልሔም ከኖረች በዙ ዓመታትን አስቆጥሯል በሎም ባሏ እና ወንድ ልጆቿ አብረዋ አልነበሩም፤ እናም በዛ የነበሩት ሴቶች ኑኃሚን ስለመሆኗ መጠራጠራቸውን የሚያመናክት እባባል ነው። እንደ እውነተኛ ጥያቄ ቁጠሩት።
“ኑኃሚን” የሚለው ስም “የእኔ ደስታ” የሚል ትርጉም ነው ያለው። ኑኃሚንም ባሏን እና ልጆቿን ስላጣች፤ ስሟ ሕይወቷን እንደሚመጥን አይሰማትም።
መራራ፤ የስሙ ትርጉም ሲሆን፤ ብዙውን ግዜ ይህ ስም ሲተረጎም እንደሚያወጣው ስም “ማራ” ተበሎ ይተረጎማል።
ኑኃሚን ከቤተልሔም ስትወጣ በልዋ እና ሁለት ወንዶች ልጆችዋ በሕይወት ነበሩ፤ ደስተኛም ነበረጭ ኑኃሚን ለባልዋ እና ሁለት ልጆችዋ ሞት ተጠያቂ የምታደርገው እግዚአብሔርን ነው። ወደ እስራኤልም ብቻዋን እንድትመለስ ያደረገው እርሱ ነው።
“ፍርድን አሳልፎብኛል።”
መከራ አምጥቶብኛል
“ኑኃሚንም” የሚለው ቃል መደምደምያ የሆነውን መጨረሻ ላይ የሆነውን ነገር ጠቋሚ አያያዥ ቃል ያሳያል። በእናንተ ቋንቋ ይህንን ሊተካ የሚችን ቃል ተጠቀሙ።
“የገብስ አዝመራ” የሚለውን ስንኝ ሊተካ በሚችል ቅል ሊተረጎም ይችላል። “የገብስ አዝመራ በሚሰበሰብበት ወቅት”
1 የኑኃሚን ባል አቤሜሌክ፣ በጣም ባለጠጋና ኃያል ሰው የሆነ ቦዔዝ የሚባል ዘመድ ነበረው፡፡ 2 ሞዓባዊቱ ሩት ኑኃሚንን “አሁን ልሂድና ወደ እርሻዎች ገብቼ እህል ልቃርም፡፡ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ሰው እከተላለሁ” አለቻት፡፡ ኑኃሚንም “ልጄ ሆይ፣ ሂጂ” አለቻት፡፡ 3 ሩት ሄደችና ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፡፡ እርስዋም የአቤሜሌክ ዘመድ ወደሆነው ወደ ቦዔዝ እርሻ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ደረሰች። 4 እነሆም፣ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣና ለአጫጆቹ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው፡፡ እነርሱም “እግዚአብሔር ይባርክህ” ብለው መለሱለት፡፡ 5 ከዚያም ቦዔዝ በአጫጆቹ ላይ ተቆጣጣሪ የነበረውን አገልጋዩን “ይህች ወጣት ሴት የማን ናት?” አለው፡፡ 6 አጫጆቹንም የሚቆጣጠረው አገልጋይ “ይህች ወጣት ሞዓባዊት ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ናት” አለው፡፡ 7 እርስዋም ‘ከአጫጆቹ በኋላ እየተከተልሁ የእህል ቃርሚያ እንድቃርምና እንድለቅም እባክህ ፍቀድልኝ አለች’ አለው፡፡ ስለዚህ እርስዋም ወደዚህ መጣች፣ በቤት ጥቂት ከማረፍዋ በስተቀር፣ ከጠዋት ጀምራ እስከ አሁን ድረስ መቃረም ቀጥላለች፡፡” 8 የዚያን ጊዜ ቦዔዝ ሩትን “ልጄ ሆይ፣ እኔን እያዳመጥሽኝ ነውን? ወደ ሌላ እርሻ ሄደሽ አትቃርሚ፤ ከእርሻየ አትሂጂ፣ ይልቁንም በዚህ ቆዪና ከወጠት ሴቶች ሰራተኞቼ ጋር አብረሽ ስሪ፡፡ 9 ዓይኖችሽ ሰዎቹ ወደሚያጭዱበት ስፍራ ብቻ ይመልከቱ፣ ሌሎቹንም ሴቶች ተከተያቸው፡፡ ሰዎቹን እንዳይነኩሽ አላዘዝኋቸውምን? ሲጠማሽ ወደ ውኃ ማሰሮዎቹ ሄደሽ ወንዶቹ ከቀዱት ውኃ መጠጣት ትችያለሽ” አላት፡፡ 10 ከዚያም በግንባርዋ መሬቱን በመንካት በቦዔዝ ፊት ሰገደች፡፡ እርስዋም “እኔ እንግዳ የሆንሁት ታስበኝ ዘንድ በአንተ ፊት ሞገስ ያገኘሁት ለምንድን ነው?” አለችው፡፡ 11 ቦዔዝም ለእርስዋ “ባልሽ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ የሰራሽው ስራ ሁሉ ለእኔ ተነግሮኛል፡፡ አማትሽን ለመከተልና ወደ ማታውቂው ሕዝብ ለመምጣት አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሻል፡፡ 12 ስለ ስራሽ እግዚአብሔር ይክፈልሽ፡፡ ከክንፉ በታች መጠጊያ ካገኘሽበት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ሙሉ ደመወዝሽን ተቀበይ” አላት፡፡ 13 እርስዋም “ጌታዬ ሆይ፣ ምንም እንኳ እኔ ከሴት አገልጋዮችህ እንደ አንዲቱ ባልሆንም አጽናንተኸኛልና፣ እኔን በደግነት አናግረኸኛልና በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለቸው፡፡ 14 በምሳም ጊዜ ቦዔዝ ለሩት እንዲህ አላት፡- “ወደዚህ ነይ፣ እንጀራም ብዪ፣ ጉርሻሽንም በሆምጣጤው ወይን አጥቅሺው፡፡” በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች፣ እርሱም የተጠበሰ እህል ሰጣት፣ እርስዋም እስክትጠግብ ድረስ በላች፣ የቀረውንም አተረፈች፡፡ 15 ለመቃረም ስትነሳ፣ ቦዔዝ ወጣት አገልጋዮቹን “በነዶው መካከልም እንድትቃርም ፍቀዱላት፣ ምንም መጥፎ ነገር ለእርስዋ አትናገሩአት፡፡ 16 ደግሞም ከነዶው ዘለላዎች አስቀርታችሁ በእርግጠኝነት ልተተዉላት ይገባል፣ እንድትቃርም ለእርስዋ ተዉላት፡፡ እርስዋንም አትውቀሱአት” ብሎ አዘዛቸው፡፡ 17 ስለዚህ በእርሻው ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፡፡ ከዚያም የቃረመችውን እህል ወቃችው፣ የወቃችውም እህል አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህል ገብስ ሆነ፡፡ 18 እርስዋም ተሸክማው ወደ ከተማ ሄደች፡፡ አማትዋም የቃረመችውን አየች፡፡ ሩትም በልታ ከጠገበች በኋላ የተረፋትን የተጠበሰ እህል አውጥታ ለእርስዋ ሰጠቻት፡፡ 19 አማትዋም ለእርስዋ እንዲህ አለቻት፡-“ዛሬ የቃረምሽው ወዴት ነው? ለመስራትስ ወዴት ሄድሽ? የረዳሽ ሰው የተባረከ ይሁን፡፡” ከዚያም ሩት ለአማትዋ የቃረመችበት እርሻ ባለቤት ስለሆነው ሰው ነገረቻት፡፡ እርስዋም “ዛሬ ቃርሚያ የቃረምሁበት እርሻ ባለቤት ስሙ ቦዔዝ ይባላል” አለቻት፡፡ 20 ኑኃሚንም ለምራትዋ “ታማኝነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ ባልተወው በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን” አለቻት፡፡ ኑኃሚንም ደግሞ “ይህ ሰው ለእኛ የቅርብ ዘመዳችን ነው፣ ከሚቤዡን አንዱ ነው” አለቻት፡፡ 21 ሞዓባዊቱ ሩትም “በእርግጥም፣ እንዲህ አለኝ፣ ‘መከሬን ሁሉ እስኪጨርሱ ድረስ ከወጣት ወንዶች ሰራተኞቼ አትራቂ፡፡’” 22 ኑኃሚንም ለምራትዋ ለሩት “ልጄ ሆይ፣ ከወጣት ሴቶች ሰራተኞቹ ጋር ብትወጪ መልካም ነው፣ በሌላ በየትኛውም እርሻ ጉዳት እንዳያገኝሽ” አለቻት፡፡ 23 ስለዚህም እርስዋ እስከ ገብሱና ስንዴው መከር መጨረሻ ድረስ ልትቃርም ወደ ቦዔዝ ሴቶች ሰራተኞች ተጠግታ ቆየች፡፡ እርስዋም ከአማትዋ ጋር ትኖር ነበር፡፡
ይህ ስንኝ ትረካው ከመቀጠሉ በፊት አዲስ መረጃን ያስተዋውቃል። በእናንተ ቋንቋ አዲስ መረጃን ወደ ምንባብ ለማስተዋወቅ የምትጠቀሙበት መንገድ ካለ እርሱን ተጠቀሙ።
“ባለጸጋ” ይህ የሚያሳየው ቦኤዝ ባለጸጋ እና በማህበረሰቡ በመልካም ዝና የታወቀ ሰው ነበረ።
እዚህ ጋር ትረካው ይቀጥላል። በቋንቋችሁም ታሪክ ከተቋረጠ በኋላ እንዴት እንደሚቀጥል ልብ በሉ።
ሴቲቱ ከሞዓብ ስለመሆኗ መጠቆምያ ሌላኛው መንገድ ነው።
“ከእህሉ ዘለላ እንድቃርም” ወይንም “አጨዳ ላይ ከኋላ የተተወ የእህል ዘለላ ለማንሳት”
“ዕራሱ” ወይንም “ክምችቱ” የእህሉን ዋና ፍሬ የያዘ “ዘለላ”።
“በፊቱ ሞገስ ማግኘት” የሚለው አባባል በሰው ዘንድ ተቀባይነት ማግኘትን ያመላክታል። ሩት ፈቃድ ማግኘትን በአንድ ሰው ፊት ሞገስን እንደማግኘት አድርጋ ትናገራለች። በፊቱ፤ የሚለው አገላለፅ በመታየት፣ በአስተሳሰብ እና በአወሳሰን ተቀባይነት ማግኘትን ያመላክታል።
ሩት ኑኃሚንን እንደ እናቷ ነበር የምትንከባከባት። ብትርጉም ቋንቋው ልጅን የሚተካ ቃል መጠቀም ከተቻለ እርሱን መጠቀም ይቻላል።
ሩት ስትቃርምበት የነበረው እርሻ የኑኃሚን ዘመድ የሁነው ቦኤዝ እርሻ መሆኑን አታውቅም ነበር።
“እነሆም” የሚለው ቃል የቦኤዝ መምጣት በታሪኩ ላይ የሚጫወተውን ትልቅ ሚና አመላካች ነው። የዚህ ዓይነት ሚና የሚጫወት ቃል በቋንቋችሁ ካለ እርሱን መጠቀም አስፈላጊ ነው።
እርሻው ከቤተልሔም ያልታወቀ ዕርቀት ላይ ይገኛል።
“መልካምን ነገር ይስጥህ” ወይንም “ደስተኛ ያርግህ”
ቦኤዝ እዚህ ጋር እየጠየቀ ያለው 1) ስለ ሩት ባል ወይንም 2) ስለሩት ወላጆች ውይንም ጠባቂዎች ነው።
“ኃላፊነት ላይ ያለው” ወይንም “እየተቆጣጠረ ያለው”
“በጎጆ” ወይንም “በመጠለያ” ይሄ በእርሻ መሃከል ከፀሃይ ጊዜያዊ መጠለያ ወይንም የመናፈሻ ጎጆ ነበር።
የሄ እንደ ትዕዛዝ ቃል ልንመለከተው እንችላለን። “ስሚኝ ልጄ” ወይንም የምለውን ነገር ልብ በይ ልጄ።”
ይሄ በዕድሜ የሚያንስ ሰወን የመናገርያ መንገድ ነው። ሩት የቦኤዝ ልጅ አይደለችም። ይህ ቃል ሲተረጎም ልጅን ለማለት ተፈልጎ አለመሆኑን ልብ የበሉ።
መመልከት አንደን ነገር ማየትን እና አትክሁሮት መስጠትን ያመለክታል። “እርሻውን ብቻ ተመልከቺ” ወይንም “ለእርሻው ብቻ አትክሁሮት ስጪ።”
“አላዘዝኩምን?” የሚል ጥያቄ አዘል፤ ንግግሩ ማስረገጫ ቃል። “ጉበዛዚቱን አዝዣለሁ።”
“ወጣት ወንድ ሰራተኞች . . . ወጣት ሴት ሰራተኞች።” ወንዶሽ የሚለው ቃል በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ይውላል። ወይንም ጎበዛዚቱ ይለዋል፤ ይሄ በእርሻው ላይ በአጨዳ ላይ ያሉ ሰራተኞችን ያመላክታል።
ለማለት የተፈለገው፤ 1) ወንዶቹ እንዳይጎዱሽ። 2) በዚህ እርሻ ከመቃረም እንዳይከለክሉሽ።
ከቀዱት ማለት ከውሃ ገድጓድ ካወጡት ወይንም ውሃ ከማጠራቀምያው ማድጋ ካወጡጥ
ይሄ የአክብሮት የፍርሃት ማሳያ ነው። ስላደረገላት ነገር በማመስገን ለቦኤዝ አክብሮትን እያሳየች ነው። የትህትናም ማሳያ ነው።
ሩት ከልብዋ ትክክለኛ ጥያቂአን እየጠየቀች ነው።
ሩት በግልዋ ለእስራኤል አምላክ ተሰጥታለች፤ ነገር ግን በውጪው የምትታወቀው እንደ “ሞዓባዊቷ” ነው።
“ሰምቻለሁ” ይሄ በቀጥተኛ መልኩ፤ “ሰዎች ነግረውኛል” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
ቦኤዝ መጠቆም የፈለገው ሩት በማታውቀው የኑኃሚን መንደር፣ አገር እና ኃይማኖት መሃከል ለመኖር መምጣቷን ነው።
“ይስጥሽ” ወይንም “መልሶ ይክፈልሽ”
“ለሰራሽ” ለታማኝነትሽ፤ ከኑኃሚን ጋር በቤተልሄም ለመኖር ስለመምረጥሽ እና የኑኃሚንን አምላክ ስላመንሽ።
ይሄ ቅኔአዊ አገላለፅ ሲሆን፤ ከዚህ በፊት ካለው ዓረፍተ ነገር ጋር ይመሳሰላል። “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ብድራትሽን አትረፍርፎ ይመልስልሽ”
ቦኤዝ እግዚአብሔር የሚተማመኑበትን እንዴት አድርጎ እንደሚከልል ለመግለፅ የሚጠቀመው ንፅፅር፤ ወፎች ጫጩቶቿን በክንፏ ጥላ ስር የምታደርግላቸውን እንክብካቤ ነው። “
“ሞገስ ላግኝ” የሚለው ተቀባይነት ማግኘትን ወይንም በእርስዋ ደስተኛ መሆንን ያመላክታል። “በዓይኖችህ” የሚለው ምልከታን የሚያሳይ ሲሆን፤ ምልከታም የእርሱን ግምገማ ለማሳየት የሚጠቅም ዘይቤአዊ አገላለፅ ነው።
ይህ ቃል ሊኖረው የሚችለው ትርጉም 1) ሩት ከቦኤዝ አገልጋዮች መሃከል አንዷ አልነበረችም። 2) ሩት ከ ኑኃሚን ልጆች መሃከል አንዱን ማግባቷ በቤተልሔም ምንም ዓይነት ጥቅም እንደምያስገኝላት አላሰበችም።
ይህ የሚያሳየው በዕኩለ ቀን መሆኑን ነው።
ይህ በዕርሻ የሚበላ ቀላል ምግብ ነው። ሰዎች መሬት ላይ የተነጠፈ ምንጣፍ ላይ ይቀመጣሉ፤ በመሓከልም የወይን ሆምጣጥጤ ይቀመጥና በተቆረሰ እንጀራ እያጠቀሱም ይመገባሉ።
በእንጀራ እየተጠቀሰ የሚበላ። እስራኤላውያን ይህንን ወይን ይበልጥ ሆምጣጤ እንዲሆን ያፈሉት ነበር።
በዚህ ትዕዛዝ ዐውድ ውስጥ፣ ቦኤዝ ይህንን መመርያ ሲሰጥ ሩት ልጸማ በማትችልበት ዕርቀት ላይ እንደነበረ እንረዳለን።
“ስትቆምም”
“እንኳ” የሚለው ቃል የሚያመላክተው “ከተለመደው በላይ እና ባሻገር” መሆኑን ነው። ቦኤዝ ሩት ከነዶው ዙርያ እንድትቃርም ይፈቅዱ ዘንድ ለሰራተኞቹ ተዕዛዝ ይሰጣል። ብዙውን ግዜ የሚቃርሙ ሰዎች ወደ ነዶው እንዲጠጉ አይፈቀድም።
“ከነዶው አስቀርታችሁ ተዉላት” ወይንም “ከነዶው ላይ የ እህሉን ዘለላ ወስዳችሁ ተዉላት”
“አታሳፍሯት” ወይንም “አታዋርዷት”
የሚበላውን የእህሉን ክፍል ከገለባው ለየችው።
ይሄ የሚሰበሰበወሀል የሚበላው ፍሬ ክፍል ለው
አንድ የኢፍ መስፈሪያ 22 ሊትር ያክላል። “22 ሊትር የሚያህል ገብስ”
ሩት እህሉን ተሸክማ ወደቤቷ እንደሂአደች ያመላክታል።
“ኑኃሚን”
ኑኃሚን የጠየቀችው ጥያቄ ተመሳሳይ ሲሆን፤ ሩት ስላሳለፈችው ቀን ለማወቅ እጅግ ጓጉታ እንደሆነ ያስታውቃል።
እግዚአብሔር ቦኤዝ ለሩት እና ለኑኃሚን ስላሳያቸው ቸርነት እንዲባርካቸው እየጠየቀች ነው።
“ታማኝነቱን ያልተወ” ትርጉሙ ሊሆን የሚችለው 1) ቦኤዝ እንደቤተሰብ ለኑኃሚን ያለበትን ኃላፊነት አስታውሷል። 2)ኑኃሚን በቦኤዝ ውስጥ ስራን እየሰራ ያለውን እግዚአብሔር ማለቷ ነው። 3) እግዚአብሔር ለሕያዋን እና ለሙታን ታማኝነቱን መጠበቁን ላማመልከት ነው።
“በሕይወት ላሉ ሰዎች ሁሉ።” ኑኃሚን እና ሩት “ሕያዋን” ነበሩ።
የኑኃሚን ባል እና ልጆች “ሞተው” ነበር። “ሙታን” የሚለውን ቃል ሊተካ የሚችል ሌላ ተተኪ ቃል ካለ እርሱን መጠቀም ይቻላል።
የሁለተኛው ስንኝ መጀመርያውን የደግመዋል ያሰፋዋልም። በዕብራውያን ይህ አትክሁሮት የመስጫ መንገድ ነው።
የሚቤዥ ዘመድ ማለት አንዲት መበለት የገንዘብ እና ሌላ ችግር ውስጥ እንዳትገባ አግብቶ አንድ ልጆች አብሯት ወልዶ የሚያድናት ማለት ነው።
“ደግሞ . . . አለኝ።” ይህ የሚያመላክተው ከዚህ በኋላ ቦኤዝ አለኝ የምትለው ነገር ጠቃሚ እንደሆነ ነው።
ቦኤዝ ሰራተኞቹ ሊሲጧት የሚችሉትን ጥበቃ ያመላክታል።
“መሄድ ስሻልሻል።”
ለማለት ተፈልጎ የሚሆነው 1)ሌሎች ሰራኞች ሩትን ሊጎዷት ይችላሉ እጇንም ይዘው ሊደፍሯት ይችላሉ። 2)በሌሎች እርሻ የእርሻው ባለቤተስከ መኧር መጨረሻ ድረስ እንዳትቃርም ልትከለከል ትችላለጭ
ሩትም እስከቀኑ መጨረሻ ድረስ በቦኤዝ እርሻ ስትሰራ ዋለች፤ ደንነቷም ተጠበቀ።
ሩት ማታ ላይ ለመተኛት ወደ ኑኃሚን ቤት ትሄድ ነበር።
1 አማትዋም ኑኃሚን ለእርስዋ “ልጄ ሆይ፣ ታርፊ ዘንድ፣ ነገሮችም ለአንቺ መልካም ይሆኑልሽ ዘንድ፣ የምታርፊበትን ስፍራ አልፈግልሽምን?” አለቻት፡፡ 2 አሁንም ቦዔዝ፣ ከወጣት ሴቶች ሰራተኞቹ ጋር የነበርሽበት ሰው፣ ዘመዳችን አይደለምን? ተመልከቺ፣ እርሱ ዛሬ ማታ በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል፡፡ 3 ስለዚህ፣ ታጠቢ፣ ሽቶሽን ተቀቢ፣ ልብስሽን ቀይሪ፣ ወደ አውድማውም ውረጂ፡፡ ነገር ግን መብላትና መጠጣት እስኪጨርስ ድረስ ለሰውዮው አትታወቂ፡፡ 4 በተኛም ጊዜ፣ ወደ እርሱ መሄድ እንድትችይ እርሱ የተኛበትን ስፍራ ማስታወስሽን እርግጠኛ ሁኚ፣ እግሩን ግለጪ፣ በዚያም ተጋደሚ፡፡ ከዚያም የምታደርጊውን እርሱ ይነግርሻል፡፡ 5 ሩትም ለኑኃሚን “የተናገርሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አለቻት፡፡ 6 ስለዚህ ወደ አውድማውም ወረደች፣ እርስዋም አማትዋ የሰጠቻትን ትዕዛዝ ተከተለች፡፡ 7 ቦዔዝም በበላና በጠጣ ጊዜ፣ ልቡም ደስ ባለው ጊዜ፣ በእህሉ ክምር ጫፍ ሊተኛ ሄደ፡፡ ከዚያም ሩት በቀስታ መጣች፣ እግሩንም ገለጠች፣ ተኛችም፡፡ 8 እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፡፡ እርሱም ዘወር አለ፣ አንዲትም ሴት እዚያው እግርጌው ተኝታ ነበረች፡፡ 9 እርሱም “ማን ነሽ? አለ፡፡ እርስዋም “እኔ ሴት አገልጋይህ ሩት ነኝ” አለችው፡፡ አንተ የቅርብ ዘመዴ ነህና ልብስህን በሴት አገልጋይህ ላይ ዘርጋ አለችው፡፡ 10 ቦዔዝም፣ “ልጄ ሆይ፣ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፡፡ ከመጀመርያው ይልቅ በመጨረሻ ብዙ ደግነት አሳይተሻል፣ ምክንያቱም ድሃም ይሁን ባለጠጋ ከወጣት ወንዶች ከአንዳቸውም ጋር አልሄድሽምና” አላት፡፡ 11 አሁንም፣ ልጄ ሆይ፣ አትፍሪ! ያልሽውን ሁሉ አደርግልሻለሁ፣ ምክንያቱም በከተማየ ያሉ ሕዝብ ሁሉ ምግባረ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ ያውቃሉ፡፡ 12 አሁን እኔ የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፤ ይሁን እንጂ ከእኔ የበለጠ የሚቀርብ ዘመድ አለ፡፡ 13 ዛሬ ሌሊት እዚህ ቆዪ፣ ነገም ጠዋት የዋርሳነትን ግዴታ እርሱ የሚፈጽም ከሆነ፣ መልካም ነው፣ የዋርሳነትን ግዴታ ይፈጽም፡፡ ነገር ግን እርሱ ለአንቺ የዋርሳነትን ግዴታ ባይፈጽም፣ ሕያው እግዚአብሔርን እኔ አደርገዋለሁ፡፡ እስከ ማለዳ ድረስ ተኚ፡፡ 14 ስለዚህ እስከ ማለዳ ድረስ በእግርጌው ተኛች፡፡ ነገር ግን አንዱ ሌላውን ማወቅ ከመቻሉ በፊት ተነሳች፡፡ ቦዔዝ “ሴት ወደ አውድማው መምጣትዋን ማንም እንዳያውቅ” ብሎ ነበርና፡፡ 15 ከዚያም ቦኤዝ “የለበስሽውን ልብስ አምጭና ያዢው” አላት፡፡ በያዘችም ጊዜ ስድስት ትልቅ መስፈሪያ ገብስ በልብሷ ላይ ሰፍሮ አሸከማት፡፡ የዚያን ጊዜ እርሱ ወደ ከተማ ሄደ፡፡ 16 ሩት ወደ አማትዋ በመጣች ጊዜ “ልጄ ሆይ፣ እንዴት ነሽ?” አለቻት፡፡ ሩትም ሰውዮው ለእርስዋ ያደረገውን ሁሉ ነገረቻት፡፡ 17 እርስዋም “እነዚህ ስድስት መስፈሪያ ገብስ እርሱ የሰጠኝ ናቸው፣ ‘ወደ አማትሽ ባዶ እጅሽን አትሂጂ’” ብሏልና፡፡ 18 ኑኃሚንም “ልጄ ሆይ፣ ይህ ጉዳይ እንዴት እንደሚሆን እስከምታውቂ ድረስ በዚህ ቆዪ፣ ሰውዮው ይህን ነገር ዛሬ እስኪጨርስ ድረስ አያርፍምና” አለች፡፡
ኑኃሚን የሩት ሟች ባል እናት ናት
ሩት የኑኃኒንን ልጅ በማግባት ብሎም አብራት ወደ ቤተልሔም በመመለስ የኑኃሚን ልጅ ሆናለች።
“መልካም እንዲሆንልሽ እረፍት አልፈልግልሽም?” ኑኃሚን ይሄንን ጥያቄ በመጠየቅ ያቀደችላትን ለመናገር ትጠቀምበታለች። “እረፍት የመታረጊበትን ቦታ ልፈልግልሽ ይገባኛል” ወይንም “ የሚንከባከብሽ ባል ልፈልግልሽ ይገባኛል።”
ትርጉሙ ሊሆን የሚችለው፤ 1) በቀጥታ የምትኖርበትን ቤት ማግኘት ወይንም 2) በማስጠጋት ረገድ የሚንከባከባት ባል ስለመፈለግ። ኑኃሚን ሁለቱንም ማለት ፈልጋ ሊሆንም ይችላል።
የዚህ ግልፅ ትርጉም ከሴቶቹ ጋር እየሰራች እንደነበረ ሊያሳይ ይገባል። “ከገረዶቹ ጋር የለበርሽበት።”
ኑኅሚን ከዚህ በፊት ለሩት የነገረቻትን ነገር እያስታወሰቻት ነው የሚሆነው። “እርሱ ዘመዳችን ነው።”
“ልብ በይ።” ከዚህ በኋላ የምትላትን ነገር እንድታስተውል እያመለከቻት ነው።
“በመንሽ ይበትናል” ይህ በንፍስ ድጋፍ ሰብሉን ከገለባው የመለየት ሂደት ነው።
ይህ መልካም ማዓዛ ያለው ጣሳጭ ሻታ ያለው ዘይት ሊሆን ይችላል። በሁን ግዜ ሽቶ የሚባለው ማለት ነው።
ይህ የሚያሳየው ከከተማው ወጥቶ ወደሚወቃበት ቦታ ምሄድን ነው።
ይህ የሚያመላክተው የለበሰውን መደረብያ እግሩ ጋር መግለጥ እና እግሮቹ እንዲበርዳቸው ማድረግ የሚለውን ነው።
“ከእግሩ ሳር ተኚ”
እዚህ ጋር ያለው የባህል ልማድ በእርግጥ ባይታወቅም፤ በባህላሸው የሚታወቅ እና ተቀባይነት ያለው ሴት ልጅ አንድ ወንድ እንዲያገባት ፈቃደኛ እንደሆነች የምታስታውቅበት መንገድ ነው። ቦኤዝም ልማዱ ገብቶት መቀበልም መተውም ይሽላል።
“ሲነሳም፣ እርሱ እራሱ።”
ይህ በልቡ የሆነ ነገርን ያሳያል። ሰክሮ ነበር ማለት አይደለም። “ሰውነቱም ደስ ከተሰኘ” ወይንም “ከረካ በኋላ”
“በድብቅ” “ድምጽ ሳታሰማ ማንም ሰው ሳይሰማ”
“መደረብያውን ከእግሩ ላይ ገልጣ”
“ከእግሩ ስር ተኛች”
በትረካው ውስጥ የሆነን አንደ ክስተት ለማስታወቅ የሚጠቅም ስንኝ ነው። በቋንቋችሁ ይህንን የሚያደርግ ቃል ካለ እርሱን መጠቀምን አስቡ።
“መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ግዜ”
“አንዳች ነገር አስደነገጠው”
“ዘወርም አለ”
ሲቲቱ ሩት ነበረች፤ ቦኤዝ ግን ጨልሞ ስለነበር ሊያውቃት/ሊለያት አልቻለም።
ሩት ለቦኤዝ ምላሽ የሰጠችው በትህትና ነበር
ይህ ጋብቻን የሚያመላክት አባባል ነው።
ለዘመዶቹ ኃላፊነት ያለበት ልዩ ዘመድ
ቦኤዝ ይህንን የተጠቀመው ታናሹ እንዳሆነች ሴት ለሩት ያለውን አክበሮት ነው።
“ከበፊተኛው ይልቅ በመጨረሻው ግዜ ቸርነት አድርገሻል።”
ይህ ሩት ቦኤዝ እንዲያገባት ስለመጠየቁ ነው። የኑኃሚንን ዘመድ በማግባት ሩት ለኑኃሚን የሚያስፈልጋትን ነገር ማቅረብ ትችላለች በዚህም ቸርነትን ታደርጋለች።
ይህ የሚያሳየው ሩት ከዚህ በፊትም ለአማቷ እየቃረመች እንደተንከባከበቻት እና አብራት በለቆየት ያደረገችውን ነው።
“አልተከተልሽምና” ሩት ኑኃሚንን ዘንግታ ከኑኃሚን ዘመዶች ውጪ ለማግባት ባል መፈለግ ስትችል ይህንን አላደረገችም።
መበለቲቷን መርዳት ቅርብ የሆነው ወንድ ዘመድ ኃላፊነት ነው።
ቦኤዝ እየተናገረ ያለው ቅርብ ከሆነ ከሞተው የሩት ባል የስጋ ዘመድ የሚጠበቀውን ሩትን የማግባት እና የቤተሰቡን ስም የዞ የመቀጠል ሃላፊነት ነው።
“ሕያው እግዚአብሔርን” ይህ በዕብራይስጥ የተለመደ መሃላ ነው።
ሩት ከቦኤዝ እግር ስር ተኛች። ቦኤዝ አላወቃትም፣ ምንም አላደረጉም።
ይህን አገላለፅ ከበርሃን ጋር አያይዞ መግለፅ ይቻላል። “ገና ጨለማ ሳለ”
በትከሻ ላይ የመደረብ ልብስ
ክብደቱ በውል ባይገለፅም። ቸር የሆነ ልገሳ እንደሆነ ይገመታል፣ ነገር ግን ሩት ልትሸከመው የምትችለው ያህል።
የገብሱ መጠን ሩት በራስዋ ልታነሳው የምትችለው ያክል አልነበረም።
“ወደ ከተማ ተመለሰች” አንዳንድ ቅጂዎች “ተመለሰ” ሲሉ ሌሎች ደግሞ “ተመለሰች” ይሉታል።
ኑኃሚን በዚህ ጥያቄ ማለት የፈለገችውን በሌላ ቃል ግልጽ ማድረግ ይቻላል። “ልጄ ምን ሆነ?” ወይንም “ቦኤዝ ምን ዓይነት ምላሽ ሰጠሽ?”
“ቦኤዝ ያደረገላትን ሁሉ”
“ባዶ እጅሽን አትሂጂ” ወይንም “ምንም ሳትይዢ እንዳትሄጂ” ወይንም “የሆነ ነገር የመሄድሽን እርገት፣ እኛ ሁኚ
ይህ ማን የኑኃሚንን ንብረት እንደሚገዛ እና ሩትን እንደሚያገባ የሚወሰነውን ውሳኔ ያመላክታል።
“የከተማይቱ በር” ወይንም “የቤተልሔም በር” ይህ ቅጥር ወዳላት የቤተልሔም ከተማ ዋና መግቢያ በር ነው። የማህበረሰባዊ ጉዳዪች ላይ ውይይት የሚደረግበትም ክፍት ቦታ በበሩ አቅራብያ ነበር።
በሕይወት ያላ ቅርቡ የአቤሜሌክ ዘመድ
“የከተማይቱ መሪዎች”
1 ቦዔዝም ወደ ከተማይቱ በር ሄደና በዚያ ተቀመጠ፡፡ ወዲያውኑ ቦዔዝ ሲናገርለት የነበረው የቅርብ ዘመድ መጣ፡፡ ቦዔዝም ለእርሱ “ወዳጄ ሆይ፣ ና በዚህም ተቀመጥ” አለው፡፡ ሰውየውም መጣና ተቀመጠ፡፡ 2 ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች አሥር ሰዎች ወሰደ፣ “በዚህ ተቀመጡ” አላቸው፡፡ እነርሱም ተቀመጡ፡፡ 3 ቦዔዝም የቅርብ ዘመድ ለሆነው፣ “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቤሜሌክን ቁራሽ መሬት ትሸጣለች፡፡ 4 እኔም ለአንተ አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ እንዲህም አልሁ፡- ‘ይህንን መሬት በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት ግዛው፡፡’ መቤዠት ብትፈልግ ተቤዠው፡፡ ነገር ግን መቤዠት የማትፈልግ ከሆነ ግን ከአንተ በቀር ሌላ የሚቤዥ የለምና፣ እኔም ከእአንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ” አለው፡፡ የዚያን ጊዜ ሌላኛው ሰው “እቤዠዋለሁ” አለው፡፡ 5 ቦዔዝም “ከኑኃሚን እጅ እርሻውን በምትገዛበት ቀን፣ የሞተውን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንድታስነሣለት የምዋቹን ሰው ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ደግሞ መውሰድ አለብህ” አለ፡፡ 6 የቅርብ ዘመድ የሆነውም “የራሴን ርስት ሳልጎዳ እርሻውን ለራሴ መቤዠት አልችልም፡፡ እኔ ልቤዠው አልችልምና የእኔን የመቤዠት መብት ለራስህ ውሰድ” አለ፡፡ 7 በጥንት ዘመን መቤዠትና የሸቀጦች መለዋወጥ በተመለከተ በእስራኤል ዘንድ አንድ ልማድ ነበረ፡፡ ሁሉንም ነገር ለማጽናት ሰው ጫማውን ያወልቅና ለባልንጀራው ይሰጠዋል፤ በእስራኤል ውስጥ ሕጋዊ ስምምነት የሚኖረው በዚህ ሁኔታ ነበር፡፡ 8 ስለዚህ የቅርብ ዘመዱ ቦዔዝ፣ “አንተ ለራስህ ግዛው” አለው፡፡ እርሱም ጫማውን አወለቀ፡፡ 9 ቦዔዝም ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ፣ “ለአቤሜሌክ የነበረውን ሁሉ እንደዚሁም ለኬሌዎንና ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እኔ መግዛቴን እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ፡፡ 10 ከዚህም በላይ ስለ መሐሎን ሚስት ስለ ሞዓባዊቷ ሩት፡- የምዋቹን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ፣ ስሙ ከወንድሞቹ መካከልና ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፣ እኔ ደግሞ እርስዋ ሚስቴ እንድትሆን ወስጃታለሁ፡፡ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው፡፡ 11 በበሩ የነበሩ ሕዝብ ሁሉና ሽማግሌዎቹም እንዲህ አሉ፡- “እኛ ምስክሮች ነን፡፡ እግዚአብሔር ወደ ቤትህ የመጣችውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ገነቡት እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና ልያ ያድርጋት፡፡ አንተም በኤፍራታ ባለጠጋ ሁን፣ በቤተ ልሔምም እንደገና የታወቅህ ሁን፡፡ 12 ቤትህ እግዚአብሔር ከዚህች ወጣት ሴት በሚሰጥህ ዘር በኩል ትዕማር ለይሁዳ እንደወለደችለት እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን” አሉት፡፡ 13 ስለዚህ ቦዔዝ ሩትን ወሰደ፣ ሚስቱም ሆነች፡፡ እርሱም ከእርስዋ ጋር ተኛ፣ እግዚአብሔርም ልጅ እንድትፀንስ ፈቀደላት፣ እርዋም ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ 14 ሴቶችም ለኑኃሚን፣ “ዛሬ የሚቤዥ የቅርብ ዘመድ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ይህ ሕጻን ስሙ በእስራኤል ውስጥ የገነነ ይሁን፡፡ 15 ይህ ልጅ ለአንቺ ሕይወትሽን የሚያድስ እርጅናሽንም የሚመግብ ይሁን፣ የምትወድሽ፣ ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ የምትሻል፣ ምራትሽ ይህን ልጅ ወልዳለችና፡፡ 16 ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደችው፣ በእቅፍዋም አስቀመጠችው፣ እርሱንም ተንከባከበችው፡፡ 17 ጎረቤቶቿ የሆኑት ሴቶችም “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት” እያሉ ስም ሰጡት፡፡እነርሱም ስሙን ኢዮቤድ ብለው ጠሩት፡፡ እርሱም የዳዊት አባት የሆነው፣ የእሴይ አባት ሆነ፡፡ 18 አሁንም እነዚህ የፋሬስ ትውልድ ነበሩ፡- ፋሬስ የኤስሮም አባት ሆነ፣ 19 ኤስሮምም የአራም አባት ሆነ፣ አራምም የአሚናዳብ አባት ሆነ፣ 20 አሚናዳብም የነአሶን አባት ሆነ፣ ነአሶንም የሰልሞን አባት ሆነ፣ 21 ሰልሞንም የቦዔዝ አባት ሆነ፣ ቦዔዝም የኢዮቤድ አባት ሆነ፣ 22 ኢዮቤድ የእሴይ አባት ሆነ፣ እሴይም የዳዊት አባት ሆነ፡፡
ለቅርብ ዘመድ፤ የቤተዘመዱን መሬት የመግዛት እና ቤተሰቡን የመንከባከብ ኃላፊነት አለበት። አሁን ደግሞ ይህ ሰው የኑኃሚንን መሬት መግዛት፤ ሩትን ማግባት እና ኑኃሚንን መንከባከብ ይኖርበታል።
ይህ የሚደረገውን ስምምነት ህጋዊ እና ፍፁም ያደርገዋል።
ይህ ማለት መሬቱን መግዛት እና በቤተሰቡ ውስጥ እንዲቆይ ማድረግ ማለት ነው።
ቦኤዝ በቀጣይነት መሬቱን ሊቤዥ የሚችለው ዘመድ እርሲ ነበር።
በዚህ የቦኤዝ አነጋገር ለሰውዬው መሬቱን ከመግዛት ጋር አብሮ ያለውን ኃላኢነት ይነግረዋል።
“ከኑኃሚን እጀ” ይህ የሚያመለክተው መሬቱ የኑኃሚን መሆኑን ነው።
“ሩትንም ማግባት”
“ሩት የአቤሜሌክ ልጅ መበለት”
“ንብረቱን የሚወርስ ወንድ ልጅ እንዲኖራት እና የሞተውን ባሏን ስም እንዲያስቀጠል።”
ሩት ለምትወልድለት ልጆች ደግሞ የራሱን ሃብት ማካፈል ስለሚኖርበት
“አንተው እራስህ ተቤዠው” ወይንም “በእኔ ፈንታ አንተ ተቤዠው።”
ጸሃፊው ሩት በነበረችበት ዘመን በልውውጥ ግዜ የሚደረገውን ነገር እያብራራ ነው።
“በጥንት ዘመን።” ይህ የሚያመላክተው መጸሓፉ በተጻፈበት እና ታሪኩ በተፈፀመበት ግዜ ልማዱ እንደተለወጠ ነው።
“ነጠላ ጫማውን።”
ይህ የሚያመላክተው ከእርሱ ጋር ስምምነት እያደረገ ያለውን ሰው ነው። በዚህ ግዜ ቅርብ የስጋ ዘመድ የተባለው ሰው ለቦኤዝ እንደማለት ነው።
ይህ ማለት በስብሰባቸው ላይ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ማለት እንጂ በከተማው ያሉ ሰዎች ሁሉ ማለት አይደለም።
ይህ የሚያመላክተው የኑኃሚን ሟች ባል እና ልጆች ሃብት በሙላ ማለት ነው።
“ከኑኃሚን እጅ” ለንብረቱ ሁላ ኃላፉ የነበረችው እና የምትሰጠው ኑኃሚን ለመሆኗ ማሳያ ነው።
ሩት የምትወልደው የመጀመርያ ልጅ ህጋዊ የመሓሎን ልጅ ተደርጎ ይቆጠራል። ቦኤዝም ከኑኃሚን የገዛውን መሬት ይወርሳል። “የሞተውን ሰውዬ መሬት የሚወርስ ወንድ ልጅ እንድሰጣት።”
መረሳት የሚታየው ቀድሞ ይኖሩ ከነበሩ ሰዎሽ ስም ዝርዝር እንደመቆረጥ ነው። “በወንደሞቹ ትውልድ ዘንድ እና በከተማው እንዳይረሳ።”
ይህ የሚያመላክተው የከተማውን ደጅ ሲሆን፤ በዚህም ቦታ የመሬት ባለቤትነትን በተመለከተ ውሳኔ የሚሰጥበት ቦታ ነው።
“ሌሎች በበር አቅራብያ ይሰበሰቡ የነበሩ ሁሉ።”
ይህ ምሳሌያዊም ቀጥተኛም ትርጉም አለው። ሩት ቦኤዝን ስታገባው ወደቤቱ ትገባለጭ ቤት መግባት ማለት ደግሞ ቤተሰቡን መቀላቀልንም ያመላክታል።
እነኚህ የያዕቆብ ሁለት ሚስቶች ሲሆኑ ስማቸውም ወደ እስራኤል ተቀይሯል።
“ብዙ ልጆችን ወልደው የእስራኤል ሐዝብ ያደረጉ።”
ኤፍራታ ቦኤዝ በቤተንሔም የሚነኝበት ነገድ ነው።
እግዚአብሔር ይሁዳን በልጁ በፋሬስ እጅጉን ባርኮት ነበር፤ ሰዎቹም በተመሳሳይ መንገድ ቦኤዝን በሩት ልጆች እንዲባርከው እግዚአብሔርን ጠየቁጥ
ተዕማር መበለት ነበረች። ይሁዳም ከእርሷ ወንድ ልጅ ወለደ፤ የቤተሰቡም ስም በዛ ቀጠለ።
እግዚአብሔር በሩት በኩል ልጅ እንደሚሰጠው
“ቦኤዝ ሩትን አገባት” ወይንም “ቦኤዝ ሩትን እንደ ሚስት ወሰዳት”
ቦኤዝ ሩትን እንዳወቃት የሚያሳይ ነው። “ቦኤዝ ሩትን ደረሰባት”
አዎንታዊ ትርጉም ሊሰጠው ይችላል። “ዛሬ የቅርብ ዘመድ የሰጠሽ”
ይሄ የሚያመላክተው የኑኃሚንን የልጅ ልጅ ዝና እና ባህርይ ነው።
ኑኃሚን በልጅ ልጇ ምክኛት እንዴት በድጋሚ ደስታን እና ተስፋን እንደምትለማመድ ሊያሳይ ይችላል። “ድስታን በድጋሚ ወደ አንቺ የሚያመጣ” ወይንም “በድጋሚ እንደ ወጣት የሚያበረታሽ።”
“ባረጀሽ ግዜ የሚንከባከብሽ።”
በእስራኤላውያን “ሰባት” የፍፁምነት ቁጥር ነው። የኑኃሚን ወንድ ልጆች ሳይወልዱላት ሞቱ፤ ሩት ግን ከቦኤዝ የልጅ ልጅ ወለደችላት። “ከምንም ዓይነት ልጅ የምትሻል።”
ሉጁን እንደያዘችው እንጁ ከሩት እንደወሰደችባት መታየት የለበትም።
“ከደረቷ አስጠግታ ያዘችው።”የሄ የፍቅር እና መውደድ ማሳያ ነው።”
“ልጁ ለኑኃሚን እንደልጇ ነው።” ኑኃሚን ልጁን ባትወልደውም የእርሷ የልጅ ልጅ እንደሆነ የታወቀ ነበር።
“የንጉስ ዳዊት አባት።” ንጉስ የሚለው ያልተጠቀሰው የመጀመርያዎቹ አንባብያን ዳዊት ንጉስ እንደነበረ ስለሚረዱ ነው።
“ከእርሱ የወጡት ትውልዶች።” ከፋሬስ የተለሳበት ምክንያት ከዚህ በፊት ፋሬስ የይሁዳ ልጅ መሆኑ ስለተገለጠ ነው፤ ከእርሱም ቀጥሎ የቤተሰቡን ዝርዝር መናገር የቀጥላል።
1 በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማ መሴፋ የሚኖር አንድ ሰው ነበር፤ ስሙ ሕልቃና ይባላል፥ እርሱም የኤፍሬማዊው የናሲብ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የኤሊዮ ልጅ፥ የኢያርምኤል ልጅ ነበር። 2 እርሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ስማቸውም የአንደኛዋ ሐና፥ የሁለተኛዋም ፍናና ነበር። ፍናና ልጆች ነበሯት፣ ሐና ግን አንድም ልጅ አልነበራትም። 3 ይህም ሰው በየዓመቱ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ለመስገድና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ሴሎ ይሄድ ነበር። የእግዚአብሔር ካህናት የሆኑት ሁለቱ የኤሊ ወንዶች ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በዚያ ነበሩ። 4 በየዓመቱ ሕልቃና የሚሠዋበት ጊዜ ሲደርስ፥ ለሚስቱ ፍናና፥ ለወንዶችና ሴቶች ልጆችዋ በሙሉ ሁልጊዜ ከመሥዋዕቱ ሥጋ ድርሻቸውን ይሰጣቸው ነበር። 5 ነገር ግን ሐናን ይወዳት ስለነበር ሁልጊዜም ድርሻዋን ሁለት ዕጥፍ አድርጎ ይሰጣት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶት ነበር። 6 እግዚአብሔር ማኅፀንዋን ዘግቶት ስለነበር ጣውንቷ እርስዋን ለማስመረር ክፉኛ ታስቆጣት ነበር። 7 ስለዚህ በየዓመቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ከቤተሰብዋ ጋር በምትወጣበት ጊዜ ጣውንቷ ሁልጊዜ ታበሳጫት ነበር። በዚህ ምክንያት ታለቅስ ነበር፤ ምግብም አትበላም ነበር። 8 ባሏ ሕልቃና ሁልጊዜ "ሐና ሆይ፥ ለምንድነው የምታለቅሽው? ምግብስ የማትበዪው ለምንድነው? ልብሽ የሚያዝነውስ ለምንድነው? ከዐሥር ወንዶች ልጆች ይልቅ ላንቺ እኔ አልሻልም?" ይላት ነበር። 9 ከእነዚህ ወቅቶች በአንዱ፥ በሴሎ መብላታቸውንና መጠጣታቸውን ከጨረሱ በኋላ ሐና ተነሣች። ካህኑ ዔሊ በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በራፍ በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር። 10 እርሷም እጅግ አዝና ነበር፤ ወደ እግዚአብሔር ጸለየች፥ አምርራም አለቀሰች። 11 እንዲህ ስትልም ስዕለት ተሳለች፣ "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ የአገልጋይህን ጉስቁልና ብትመለከትና ብታስበኝ፥ አገልጋይህን ባትረሳኝ፥ ነገር ግን ወንድ ልጅን ብትሰጠኝ፥ እኔም የሕይወት ዘመኑን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ መቼም ቢሆን ጸጉሩ አይላጭም"። 12 በእግዚአሔር ፊት ጸሎቷን ቀጥላ እያለች ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር። 13 ሐና በልቧ ትናገር ነበር። ከንፈሮችዋ ይንቀሳቀሱ ነበር፥ ድምፅዋ ግን አይሰማም ነበር። ስለዚህ ዔሊ ሰክራለች ብሎ አሰበ። 14 ዔሊም "ስካርሽ የሚቆየው እስከ መቼ ነው? ወይንሽን ከአንቺ አርቂው" አላት። 15 ሐናም፣ "ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፥ እኔ ልቤ በሐዘን የተጎዳብኝ ሴት ነኝ። ወይን ወይም የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም፥ ነገር ግን ነፍሴን በእግዚአብሔር ፊት እያፈሰስኩ ነው። 16 አገልጋይህን እንደ ኃፍረተ ቢስ ሴት አትቁጠረኝ፤ ይህን ያህል ጊዜ የተናገርኩት እጅግ ከበዛው ሐዘኔና ጭንቀቴ የተነሣ ነው" በማለት መለሰችለት። 17 ከዚያም ዔሊ፣ "በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ልመና ይስጥሽ" ብሎ መለሰላት። 18 እርሷም፣ "አገልጋይህ በዐይንህ ፊት ሞገስን ላግኝ" አለችው። ከዚያም መንገዷን ሄደች፥ በላችም፤ ከዚያም በኋላ ፊቷ ሐዘንተኛ አልሆነም። 19 እነርሱም ማልደው ተነሥተው በእግዚአብሔር ፊት ሰገዱ፥ ከዚያም ወደ መኖሪያቸው ወደ አርማቴም ተመለሱ። ሕልቃና ከሚስቱ ከሐና ጋር ተኛ፥ እግዚአብሔርም አሰባት። 20 ጊዜው ሲደርስም ሐና አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደች። "ከእግዚአብሔር ስለ እርሱ ለምኜ ነበር" ስትል ስሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው። 21 ሕልቃናና ቤተ ሰቡ በሙሉ ለእግዚአብሔር ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብና ስዕለታቸውን ለመፈጸም ዳግመኛ ወደ ሴሎ ወጡ። 22 ሐና ባሏን "ልጁ ጡት መጥባት እስኪያቆም እኔ አልሄድም፤ ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት እንዲታይና ለዘላለም በዚያ እንዲኖር አመጣዋለሁ" ብላው ስለነበረ አልሄደችም። 23 ባሏም ሕልቃና፥ "መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ። ጡት መጥባቱን እስኪያቆም ቆዪ፥ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽና" አላት። ስለዚህ ልጇ ጡት መጥባቱን እስኪያቆም ድረስ በቤት በመቆየት ተንከባከበችው። 24 ጡት መጥባቱን ባስቆመችው ጊዜ፥ እርሱን ከሦስት አመት ወይፈን፥ አንድ ኢፍ ዱቄትና አንድ ጠርሙስ ወይን ጋር በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው። ልጁ ገና ሕፃን ነበር። 25 ወይፈኑን አረዱት፤ ልጁንም ወደ ዔሊ አመጡት። 26 እርሷም፥ "ጌታዬ ሆይ፥ ሕያው እንደመሆንህ፥ እዚህ አጠገብህ ቆማ ወደ እግዚአብሔር የጸለየችው ሴት እኔ ነኝ። 27 ስለዚህ ልጅ ጸለይኩኝ፥ እግዚአብሔርም የለመንኩትን ልመና ሰጥቶኛል። 28 ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል"። እነርሱም በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
ይህ የአንዲት ትንሽ መንደር ስም ሲሆን ከኢየሩሳሌም በሰሜን ምዕራብ ስምንት ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ የምትገኝ ሳትሆን አትቀርም፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ፡- ተመልከት)
ይህ የመሴፍ ትውልድ የሆኑ የሰዎች ስብስብ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ፡- ተመልከት)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ፡- ተመልከት)
ይህ የአንዲት ሴት ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ፡- ተመልከት)
"ያም ሰው' የሚለው ሕልቃናን ያመለክታል፡፡
ይህ እርሱ በብሉይ ኪዳን ለሕዝቡ የገለጠው የእግዚአብሔር ስም ነው፡፡ ያህዌን በሚመለከት እንዴት እንዴት እንደሚተረጎም የትርጉም ቃላት ገጽን ተመልከት፡፡
እንዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ፡- ተመልከት)
ይህ የአንዲት ሴት ስም ነው፡፡ ይህንን በ1 ሳሙኤል 1፡2 እንዴት እንደምትተረጉም ተመልክት፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት፡፡)
"መካን አድርጓት ነበር' ወይም "ወደ እርግዝና እንዳትመጣ አግዷት ነበር'
ሌላኛዋ ሚስት (ጣውንትዋ) ሐናን ብዙ ጊዜ ታሳዝናትና ታዋርዳት ነበር
የሕልቃና ሌላኛዋ ሚስት ፍናና ነች፡፡ ተፎካካሪ ማለት ሌላውን ሰው በመቃወም የሚወዳዳር ሰው ማለት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ሕልቃና አብልጦ እንዲወዳት ፍናና ሐናን በመቃወም ትወዳደራት ነበር፡፡
አስፈላጊ ከሆነ አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች በገላጭ አባባል ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አት፡- "ሐና ማልቀስ የለብሽም፡፡ እኔ ለአንቺ ከአሥር ልጆች ይልቅ ስለምሻልሽ ልትበይና ልብሽም ደስ ሊለው ይገባል፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች ተመልከት)
ሐና ምን ያህል ለእርሱ አስፈላጊ እንደሆነች አጽንዖት ለመስጠት ሕልቃና አጋኖ እየተናገረ ነው፡፡ አት፡- "ማንኛውም ልጅ ሊሆነው ከሚችለው በላይ' (ግነትና ማጠቃለያ ተመልከት)
ሐና ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ጀመረች ዔሊም ተመለከታት፡፡
ግልጽ ያልሆነ መረጃ በዚህ ስፍራ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ ወይ የሐና ድንኳን ከመገናኛው ድንኳን ቀጥሎ ነበር ወይም ለመጸለይ ከድንኳንዋ ወደ መገናኛው ድንኳን ሄዳ ነበር፡፡ አት፡- "በኋላም ሐና ተነሣች ለመጸለይም ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄደች፡፡' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ይልተደረገ መረጃ ተመልከት)
"ም' የሚለው ቃል እየተተረከ የዋናው ታሪክ ፍሰት መቋረጡን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህ ስፍራ ጸሐፊው በታሪኩ ስለሌላ አንድ ሰው ይነግረናል፡፡ ይህም ሰው ካህኑ ዔሊ ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ፡- ተመልከት)
"መቅደሱ' በእርግጥ ድነኳን ነበር ነገር ግን ሕዝቡ ያመልክበት የነበረ ስፍራ ስለ ነበር፣ በዚህ ስፍራ መቅደስ ብሎ መተረጎም ይበልጥ የተመረጠ ነው፡፡
ምንም ልጆች ስለሌላትና የባሏ ሌላኛዋ ሚስቱ ፍናና ያለማቋረጥ ታዋርዳት ስለነበር ሐና እጅግ ትታወክና ታዝን ነበር፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትንና ያልተገለጸ መረጃን ተመልከት)
ሐና ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ጸሎት ቀጠለ፡፡
መከራ የሚለው የነገር ስም በማሰሪያ አንቀጽ ሐረግነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ ይህ የሚከተሉትን ሊያመለክት ይችላል፡- 1) የሐናን ማርገዝ አለመቻል፡፡ አት፡- "ማርገዝ ካለመቻሌ የተነሣ ምን ያህል መከራ እየተቀልኩ ነው' ወይም 2) ፍናን እርሷን ሁል ጊዜ የምታዋርድበትን መንገድ፡፡ አት፡- "ያቺ ሴት ምን ያህል መከራ እያሳየችኝ አንደሆነ' (የነገር ስሞች ተመልከት)
እግዚአብሔር ስለ ሐና እርምጃ እንዲወስድ የቀረበ የተለየ ልመና ነው፡፡ ሐና ላይ ምን እየሆነባት እንዳለ እግዚአብሔረ ያውቃል፣ አልረሳም፡፡
ይህ ሐረግ የሚለው ነገር "አስበኝ' ከሚለው ጋር ተመሣሣይ ነው ማለት ይቻላል፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
ዔሊ ሊቀ ካህናት ነበር፣ በመሆኑም በእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን ነበረ በእርሷም ኃላፊነት ነበረበት፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ፡- ተመልከት)
"እኔ እጅግ ያዘንኩ ሴት ነኝ፡፡'
ይህ "ጥልቅ የሆነ ስሜቴን ለእግዚአብሔር እየነገርኩ ነኝ' የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ሐና ትህትናዋን ለማሳየት ስለ ራሷ በሁለተኛ መደብ ተውላጠ ስም ትናገራለች፡፡ በአንደኛ መደብ ተውላጠ ስም ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "ባርያህን እንደ … አትቁጠረኝ' ወይም "አትቁጠረኝ' (አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦሥተኛ መደብ ተመልከት)
እንደ 1፡15፣ ሐዘንተኛ ልብ እንዳላት የተነገረ ሌላ የአባባል መንገድ ነው፡፡ ብዛት፣ ጭንቀት እና ብስጭት የሚሉት የነገር ስሞች በቅጽልነት እና በማሰሪያ አንቀጽነት ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አት፡- "እስካሁን የተናገርኩት በጣም ስላዘንኩና ተፎካካሪዬ እጅግ ስላበሳጨችኝ ነው፡፡' (የነገር ስም ተመልከት)
እነዚህ ሁለቱም ቃላት ተፎካካሪዋ ታበሳጫት ስለነበር ሐና ታዝንና ትናደድ ነበር የሚል ትርጉም አላቸው፡፡ (የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት ተመልከት)
ፍናና ታስቆጣትና ታናድዳት ነበር፡፡
ፍናና ክፉ ስለሆነችባት ሐና ይሰማት የነበረውን የሐዘንና የውርደት ስሜት እያመለከተች ነው፡፡
ዔሊ በማደሪያው ድንኳን የሚኖር ሊቀ ካህናት ነበር፡፡
ለሊቀ ካህናቱ ለዔሊ ያላትን አክብሮት ለማሳየት ሐና ራስዋን በሁለተኛ መደብ ተውላጠ ስም ትተራለች፡፡ ይህ በአንደኛ መደብ ተውላጠ ስም ሊተረጎም ይችላል፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦሥተኛ መደብ ተመልከት)
በዚህ ስፍራ "ሞገስ ላግኝ' ማለት ተቀባይነት ማግኘት ወይም የእርሱ በእርሷ መደሰት የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ዓይን ማየትን የሚያመለክት ስም ሆኖ ጥቅም ላየ ውሏል፣ ማየት ደግሞ የአንድን ነገር ዋጋ መበየንን ወይም መወሰንን ይወክላል፡፡ (ምትክ ስምና ስዕላዊ ንግግርን ተመልከት)
በዚህ ስፍራ ፊትዋ የሚወክለው ራሷን ሐናን ነው፡፡ አስፈላጊ ከሆነ ይህን የተለያየ ዐረፍተ ነገር ማድረግ ትችላለህ፡፡ አት፡- "በላች፡፡ እርሷ ነበረች' ወይም "በላች፡፡ እርሷ እንደ ነበረች ሰዎች ማየት ቻሉ፡፡' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)
ሐና ይገጥማት የነበረውን ነገር እግዚአብሔር ያውቅ ነበር፣ አልዘነጋትም፡፡ በ1 ሳሙኤል 1፡11 የሚገኙትን ተመሣሣይ ቃላት እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ሐና አረገዘች
ቤት የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውል የነበር ስዕላዊ ስም ነው፡፡ አት፡- "ቤተሰቡ' (ምትክ ስም ተመልከት)
ወተት መጠጣት ማቆምና ጠንካራ ምግብ ብቻ መመገብ መጀመር
ሳሙኤል ከዔሊ ጋር በቤተ መቅደስ እንዲኖርና እንዲያገለግል እንደምታደርግ ሐና ለእግዚአብሔር ቃል ገብታ ነበር (1ሳሙ 1፡11)፡፡
"ለልጅዋ ወተት ሰጠች'
አንድ ኢፍ 22 ሊትር ደረቀ ነገር ያህል ነው፡፡
ወይን የሚቀመጠው ከእንስሳት ቆዳ በተሰራ እቃ ነው (አቁማዳ)፣ በብርጭቆ ጠርሙስ አልነበረም፡፡
በዚህ ስፍራ "በሕያው ነፍስህ' የሚለው ፈሊጣዊ ንግግር ሐና ታማኝና እውነተኛ እንደሆነች ያሳያል፡፡ አት፡- "ጌታዬ ሆይ፣ የምነግርህ ፈጽሞ እውነት ነው፡፡' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
"ልመና' የሚለው ስም አንድ ነገር እንዲያደርግ ለሌላ ሰው የቀረበን ይፋ ጥያቄ ያመለክታል፡፡ በማሰሪያ አንቀጽነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ልመናን መስጠት' የሚለው ፈሊጣዊ ንግግር ሰውዬው የጠየቀውን ማድረግ ማለት ነው፡፡ አት፡- "እንዲያደርግ አጥብቄ የጠየቅሁትን ለማድረግ ተስማማ' (የነገር ስምና ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) እርሱ የሚለው ሕልቃናን ሊያመለክት ይችላል ወይም 2) እርሱ የሚለው ሁለቱንም ሕልቃናንና ቤተ ሰቡን የሚያመለክት ተለዋጭ ስም ነው፡፡ (ተለዋጭ ስም ተመልከት)
1 ሐናም እንዲህ በማለት ጸለየች፥ “ልቤ በእግዚአሔር በደስታ ተሞላ። ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ አለ። በማዳንህ ደስ ብሎኛልና አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ። 2 አንተን የሚመስልህ የለምና፥ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለም ዐለት የለም። 3 ከእንግዲህ አትታበዩ፤ አንዳች የዕብሪት ንግግር ከአፋችሁ አይውጣ። እግዚአብሔር ዐዋቂ አምላክ ነውና፤ ሥራዎች ሁሉ በእርሱ ይመዘናሉ። 4 የኃያላን ሰዎች ቀስት ተሰብሯል፥ የተሰናከሉት ግን ኃይልን ታጥቀዋል። 5 ጠግበው የነበሩት እንጀራ ለማግኘት ሲሉ ለሥራ ተቀጠሩ፤ ተርበው የነበሩት ረሃብተኝነታቸው አብቅቷል። መካኒቱ እንኳን ሰባት ወልዳለች፥ ብዙ ልጆች የነበሯት ሴት ግን ጠውልጋለች። 6 እግዚአብሔር ይገድላል፥ ያድናልም። ወደ ሲዖል ያወርዳል፥ ያነሣልም። 7 እግዚአብሔር ድሃ ያደርጋል፥ ባለጸጋም ያደርጋል። እርሱ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ያደርጋል። 8 እርሱ ድሃውን ከመሬት ያነሣዋል። ምስኪኖችን ከልዑላን ጋር ሊያስቀምጣቸውና የክብርን ወንበር ሊያወርሳቸው ከአመድ ክምር ላይ ብድግ ያደርጋቸዋል። የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጓል። 9 የታመኑ ሰዎችን እግር ይጠብቃል፥ ማንም በኃይሉ አያሸንፍም፤ ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ወዳለው ጸጥታ ይጣላሉ። 10 እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፤ እርሱ ከሰማይ ያንጎደጉድባቸዋል። እግዚአብሔር በምድር ዳርቻዎች ላይ ይፈርዳል፤ የእርሱ ለሆነው ንጉሥ ኃይልን ይሰጠዋል፥ ለቀባውም ቀንዱን ከፍ ያደርግለታል።” 11 ከዚያም ሕልቃና በራማ ወደሚገኘው ቤቱ ሄደ። ልጁም በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። 12 የዔሊ ወንዶች ልጆች ምንም የማይረቡ ነበሩ። እግዚአብሔርን አያውቁም ነበር። 13 የካህናቱ ልማድ ከሕዝቡ ጋር እንደዚያ ነበርና፥ ማንኛውም ሰው መሥዋዕት ሲያቀርብ፥ ሥጋው እየተቀቀለ እያለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ይዞ ይመጣ ነበር። 14 እርሱም ወደ ድስቱ፥ ወይም ወደ አፍላሉ፥ ወይም ወደ ምንቸቱ ውስጥ ያጠልቀው ነበር። ሜንጦው ያወጣውንም ሁሉ ካህኑ ለራሱ ይወስደው ነበር። ይህንን ወደዚያ ወደ ሴሎ በሚመጡት እስራኤላውያን ሁሉ ላይ ያደርጉ ነበር። 15 ይልቁንም ስቡን ከማቃጠላቸው በፊት የካህኑ አገልጋይ ይመጣና የሚሠዋውን ሰው፥ “ጥሬውን ብቻ እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይቀበልምና ለካህኑ እንድጠብስለት ሥጋ ስጠኝ" ይለው ነበር። 16 ሰውየው፥ "መጀመሪያ ስቡን ማቃጠል አለባቸው፥ ከዚያም የፈለከውን ያህል መውሰድ ትችላለህ" ካለው ያ ሰው መልሶ፥ "አይደለም፥ አሁኑኑ ስጠኝ፤ እምቢ ካልክም በግድ እወስደዋለሁ" ይለው ነበር። 17 የእግዚአብሔርን መስዋዕት ንቀዋልና የእነዚህ ወጣቶች ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበር። 18 ትንሹ ልጅ ሳሙኤል ግን ከተልባ እግር ጨርቅ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። 19 እናቱም ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብ ከባሏ ጋር በምትመጣበት ጊዜ በየዓመቱ አነስተኛ መደረቢያ ልብስ እየሠራች ታመጣለት ነበር። 20 ዔሊም ሕልቃናን እና ሚስቱን እንዲህ በማለት ባረካቸው፥”ከእግዚአብሔር በለመነችው ልመና ምክንያት እግዚአብሔር ከዚህች ሴት ተጨማሪ ልጆችን ይስጥህ።“ ከዚያም ወደ ራሳቸው መኖሪያ ተመለሱ። 21 እግዚአብሔር እንደገና ሐናን ረዳት፥ እንደገናም አረገዘች። እርሷም ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴት ልጆችን ወለደች። እንዲሁም ትንሹ ልጅ ሳሙኤል በእግዚአብሔር ፊት አደገ። 22 ዔሊ በጣም አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹ በእስራኤላውያን ሁሉ ላይ እያደረጉ ያሉትን በሙሉ እና በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደ ተኙ ሰማ። 23 እርሱም እንዲህ አላቸው፥”ስለ ክፉ ሥራችሁ ከዚህ ሕዝብ ሁሉ ሰምቻለሁና እንደዚህ ያሉትን ነገሮች የምትፈጽሙት ለምንድነው? 24 ልጆቼ ሆይ፥ የምሰማው መልካም ወሬ አይደለምና ልክ አይደላችሁም። የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲያምጽ ታደርጉታላችሁ። 25 አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል፥ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ይፈርዳል፤ አንድ ሰው ግን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ቢሠራ ስለ እርሱ የሚናገር ማን ነው?" እነርሱ ግን እግዚአሔር ሊገድላቸው ፈልጓልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም። 26 ትንሹም ልጅ ሳሙኤል አደገ፥ በእግዚአብሔርና በሰዎችም ፊት ደግሞ በሞገስ እያደገ ሄደ። 27 አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'በግብፅ አገር፥ በፈርዖን ቤት ባሪያዎች በነበሩ ጊዜ ለአባትህ ቤት ራሴን ገለጥኩኝ፤ 28 ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ካህን እንዲሆነኝ፥ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፥ ዕጣን እንዲያጥንልኝ፥ በፊቴም ኤፉድ እንዲለብስ መረጥኩት። የእስራኤል ሕዝብ በእሳት የሚያቀርበውን መባ ሁሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ። 29 ታዲያ በማደሪያዬ ያዘዝኩትን መሥዋዕትና መባ የምትንቁት ለምንድነው? በሕዝቤ በእስራኤል ከሚቀርበው መስዋዕት ሁሉ በተመረጠው እየወፈራችሁ ልጆችህን ከእኔ በላይ ያከበርከው ለምንድነው?' 30 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'ቤትህና የአባትህ ቤት ለዘላለም በፊቴ እንዲመላለስ ተስፋ ሰጥቼ ነበር'። አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'ይህንን ማድረግ ከእኔ ይራቅ፥ የሚያከብሩኝን አከብራለሁና የሚንቁኝ ግን ፈጽሞ ይናቃሉ። 31 ተመልከት፥ ከእንግዲህ በቤትህ ሽማግሌ የሚሆን አንድም ሰው እንዳይኖር ያንተን ኃይልና የአባትህን ቤት ኃይል የምቆርጥበት ቀን ቀርቧል። 32 በማድርበት ስፍራም መከራን ታያለህ። ለእስራኤል መልካም ነገር ቢሰጥም ከእንግዲህ በቤትህ ሽማግሌ የሚሆን አንድ ሰው አይኖርም። 33 ያንተ የሆኑትና ከመሠዊያዬ የማልቆርጣቸው ማናቸውም ዐይኖችህን እንዲያፈዝዙና ሕይወትህን በሐዘን እንዲሞሉት አደርጋቸዋለሁ። በቤተ ሰብህ ውስጥ የተወለዱ ወንዶች ሁሉ ይሞታሉ። 34 በሁለቱ ወንዶች ልጆችህ በአፍኒን እና በፊንሐስ የሚደርስባቸው ምልክት ይሆንሃል፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ። 35 በልቤና በነፍሴ ውስጥ ያለውን የሚፈጽም ታማኝ ካህን ለራሴ አስነሣለሁ። የማያጠራጥር ቤት እሠራለታለሁ፤ ለዘላለምም በቀባሁት ንጉሥ ፊት ይሄዳል። 36 ከቤተ ሰብህ የተረፈ ሁሉ ጥቂት ጥሬ ብርና ቁራሽ እንጀራ እንዲሰጠው ለመለመን በዚያ ሰው ፊት መጥቶ ይሰግዳል፥ 'ቁራሽ እንጀራ መብላት እንድችል እባክህ ከካህናቱ ኃላፊነቶች በአንዱ ስፍራ መድበኝ'" ይለዋል።
ሐና ለእግዚአብሔር መዝሙር ዘመረች፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
"ታላቅ ደስታ አለኝ'
"ከእግዚአብሔር ማንነት የተነሣ' ወይም "እግዚአብሔር እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ'
ቀንድ የብርታት ምልክት ነው፡፡ አት፡- "አሁን ብርቱ ነኝ' (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)
ሐና ለእግዚአብሔር መዘመሯን ቀጥላለች፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
ይህ እግዚአብሔር ብርቱና የታመነ ነው የሚለው ሌላኛው አባባል ነው፡፡ (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)
ይህ ዓለት ከበስተኋላው ለመደበቅ ወይም በላዩ ላይ ለመቆም እና አንድ ሰው ከጠላቶቹ በላይ እጅግ ከፍ ለማለት በቂ የሆነ ዓለት ነው፡፡
ሐና ለእግዚአብሔር መዘመሯን ቀጥላለች፡፡ ሌሎች ሰዎች እየሰሟት እንዳሉ አድርጋ ትናገራለች፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
"በትዕቢት አትናገሩ'
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት እርሱ የሰዎችን ሥራዎች ይመዝናል ወይም ሰዎች የሚያደርጉትን ለምን እንደሚያደርጉ ያውቃል (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡፡ 1) ቀስቶቹ ራሳቸው ተሰብረዋል ወይም 2) ቀስት የያዙ ሰዎች ከማድረግ ተከለከሉ፡፡ አት፡- "ኃያላን ቀስተኞች ሰዎች ከማድረግ ተከለከሉ'
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር የኃያላን ሰዎችን ቀስት ይሰብራል' ወይም "እግዚአብሔር ኃያላን ሰዎችን እንኳን ደካሞች ያደርጋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ይህ ዘይቤአዊ ንግግር ከእንግዲህ ወዲህ አይሰናከሉም ነገር ግን ኃይላቸው እንደ መታጠቂያ ጠብቆ አብሯቸው ይኖራል ማለት ነው፡፡ አት፡- "የሚሰናከሉትን ብርቱዎች ያደርጋቸዋል' (˜ይቤአዊ ንግግር ተመልከት)
ይህ ለሥራ ለመዘጋጀት አንድን ነገር በወገብ ዙሪያ ስለማሰረ ጥቅም ላይ የሚውል አጠቃላይ ቃል ነው፡፡
ሐና ለእግዚአብሔር መዘመሯን ቀጥላለች፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
"ሰባት ልጆች ወልዳለች'
ደካማ፣ ሐዘንተኛና ብቸኛ መሆን
ሐና ለእግዚአብሔር መዘመሯን ቀጥላለች፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
እግዚአብሔር ሁሉን ይቆጣጠራል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
ሐና ለእግዚአብሔር መዘመሯን ቀጥላለች፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
በማኅበረ ሰቡ ውስጥ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ጥቅም ላይ የሚውል ዘይቤአዊ ንግግር ነው፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)
የሚያስፈልጓቸው ነገሮች የሌሏቸው፡፡
ሐና ለእግዚአብሔር መዘመሯን ቀጥላለች፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
በዚህ ስፍራ "እግር' የሚለው ስም አንድ ሰው ለሚሄድበት መንገድ ጥቅም ላይ የሚውል ስዕላዊ ንግግር ነው፣ በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው ሕይወቱን ለመኖር የወሰነበትን መንገድ የሚያመለክት ዘይቤአዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "የተሳሳተ ውሳኔ እንዳይወስኑ ታማኞቹን ይጠብቃል' ወይም "ታማኞቹን ሰዎች ተገቢ ውሳኔ እንዲወስኑ ያስችላቸዋል፡፡' (ስዕላዊና ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)
በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ እግዚአብሔር ኃጢአተኛውን ይገድላል በሚል ሊገለጽ የሚችለው የተነገረበት የአክብሮት መንገድ ነው፡፡ አት "እግዚአብሔር ኃጢአተኛውን በጨለማ ዝምታ ውስጥ ያስቀምጣል' ወይም "እግዚአብሔር ኃጢአተኛውን በጨለማና በሙታን የዝምታ ዓለም ውስጥ ያስቀምጣል' (የማያስደስትን ቃል በሌላ ቃል መጠቀም ተመልከት)
"በዝምታ እንዲቀመጡ ይደረጋሉ' የሚሉት ቃላት "ዝም እንዲሉ ይደረጋሉ' ለሚለው ፈሊጣዊ ንግግር ናቸው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር እና አድራጊና ተደረጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
"ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ'
ሐና ለእግዚአብሔር መዘመሯን ቀጥላለች፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር እርሱን የሚቃወሙትን ያደቅቃቸዋል፡፡' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ይህ ፈሊጣዊ ንግግር "ያሸንፋቸዋል' ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
በሁሉ ስፍራ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ምድር ሁሉ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ቀንድ የጥንካሬ ምልክት ነው፡፡ ተመሣሣይ ቃላትን በ1ሳሙኤል 2፡1 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ አት፡- "የመረጠውን መሪ ከጠላቶቹ በላይ ብርቱ ያደርገዋል' (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)
ይህ እግዘአብሔር ሰውዬውን በዘይት እንደቀባው አድርጎ የሚናገረው እግዚብሔር ለዓላማው ስለ መረጠውና ሥልጣን ስለ ሰጠው ነው፡፡ አት፡- "የቀባው' ወይም "የመረጠው' (ዘይቤአዊ ንግግርና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽን ተመልከት)
ሰዎች እንስሳትን በመሥዋዕትነት ሲያቀርቡ በመጀመሪያ የእንስሳውን ስብ ማቃጠል፣ ሥጋውን መቀቀልና መብላት አለባቸው፡፡
"እግዚአብሔርን አይሰሙም ነበር' ወይም "እግዚአብሔርን አይታዘዙም ነበር'
ልማድ ሰዎች በቋሚነት የሚያከናውኑት ተግባር ነው፡፡
እነዚህ ምግብ የሚበስልባቸው ዕቃዎች ናቸው፡፡ ቋንቋህ ለእነዚህ ዕቃዎች የተለያዩ ቃላት ከሌለው በአጠቃላይ መልኩ ሊገለጹ ይችላላል፡፡አት፡- "በማናቸውም ሰዎች ሥጋ በሚያበስሉባቸው ውስጥ'
ከሸክላ የተሠራ ማብሰያ
የሸክላ ድስት
ተለቅ ያለ ማብሰያ ድስት
አነስተኛ ማብረጃ
ሰዎች እንስሳትን በመሥዋዕትነት ሲያቀርቡ በመጀመሪያ የእንስሳውን ስብ ማቃጠል፣ ሥጋውን መቀቀልና መብላት አለባቸው፡፡
"ከዚያም እንኳን የባሰ ያደርጉ ነበር፡፡ በፊት'
በተጨባጭ የሚያቃጥለውን ሰው ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አት፡- "መሥዋዕት ያቀርብ የነበረው ሰው መስዋዕቱን ወደ ካህናቱ ያመጣዋል፣ ካህናቱም ያቃጥሉታል፡፡' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትንና ያልተገለጸ መረጃን ተመልከት)
"እንዲጠብሰው ለካህኑ እሰጠው ዘንድ ሥጋ ስጠኝ'
እሳት ላይ ማብሰል
በፈላ ውኃ ማብሰል
ያልበሰለ
እግዚአብሔር ቁርባንን በሚመለከት የሰጠውን መመሪያ ወጣቶቹ አይወዱም ትኩረትም አይሰጡትም ነበር፡፡
ሐና እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጣት ለመነችው፣ በመቅደስም እንዲያገልገል ልጁን ለመስጠት ቃል ገባች፡፡
ይህም እግዚአብሔር እርሱን በሚያይበትና ሳሙኤል ስለ እግዚአብሔር ሊማር በሚችልበት ቦታ ማለት ነው፡፡
ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ በገላጭ አባባል ይችላል፡፡ አት፡- "እንዲህ ዓይነት ነገር ማድረጋችሁ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ በገላጭ አባባል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "በእርግጥ ስለ እርሱ የሚናገር ማንም የለም፡፡'(አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
"ምሕረት እንዲያደርገለት እግዚአብሔርን የሚለምንለት'
በዚህ ስፍራ የአባት ድምጽ አባታን ይወክላል፡፡ አት፡- "አባታቸው' ወይም "አባታቸው ያላቸውን' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)
ብዙ ጊዜ ይህ ሃረግ የእግዚአብሔር ነቢይ ማለት ነው፡፡ አት "ከእግዚአብሔር ቃላት የሚሰማና የሚናገር ሰው'
ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ እንደሚከተለው ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት "ቤት … ራሴን እንደገለጥሁ ልታውቅ ይገባሃል፡፡'
"ቤት' የሚለው ስም በቤቱ ውስጥ ላሉ ሰዎች ምትክ ስም ነው፡፡ አት ፡- "የአባትህ ቤተሰብ' (ምትክ ስም ተመልከት)
አሮን
ይህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረብን ያመለክታል፡፡
"ኤፉድ መልበስ' የሚሉት ቃላት ኤፉድ ለሚለብሱት ካህናት ሥራ ምትክ ስም ነው፡፡ አት፡- "ካህናት ያደርጉ ዘንድ ያዘዝኩትን ያደርግ ዘንድ፡፡' (ምትክ ስም ተመልከት)
የእግዚአብሔር ሰው ለዔል መናገሩን ቀጠለ
ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ የሚገሥጽ ነው፡፡ በገላጭ አባባልነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት "በማደሪያዬ … መሥዋዕቴን ልትንቁ አይገባችሁም፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
"ሕዝቤ ቁርባን ለእኔ የሚያቀርቡበት ቦታ'
ከቁርባኑ የተሻለው ክፍል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሆኖ መቃጠል ነበረበት፣ ካህናቱ ግን፡ ይበሉት ነበር፡፡
"ቤት' የሚለው ስም በቤቱ ውስጥ ላሉ ሰዎች ምትክ ስም ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 2፡27 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ አት ፡- "የአባትህ ቤተሰብ' (ምትክ ስም ተመልከት)
ይህ "ለእኔ በመታዘዝ ኑር' የሚል ትርጉም ያለው ዘይቤአዊ አነጋገር ነው፡፡ (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)
"በእርግጥ ቤተሰብህ እኔን ለዘላለም እንዲያገለግለኝ አልፈቅድም'
"በጥቂቱ ይከበራሉ' የሚሉት ቃላት "እጅግ ይዋረዳሉ' ለሚለው የማያስደስት ቃል በምጸት የተተካ ቃል ነው፡፡ ይህ በአድራጊ አንቀጽ እንደሚከተለው ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የሚንቁኝን በጥቂቱ አከብራለሁ' ወይም "የሚንቁኝን በእጅጉ አዋርዳለሁ' (ምጸት፣የማያስደስትን ቃል በሌላ ቃል መጠቀም እና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
"የምናገረውን በጥንቃቄ አድምጥ' ወይም "የምናገረው ነገር በጣም አስፈላጊ ነው'
"… ብርታት እቆርጣለሁ' የሚለው የብርቱዎችንና የወጣቶችን ሞት በማይከብድ ቃል ለመተካት ጥቅም ላይ የዋለ ሳይሆን አይቀርም፡፡ "የአባትህ ቤት' የሚሉት ቃላት "ቤተሰብህ' ለሚለው ምትክ ናቸው፡፡ (የማያስደስትን ቃል በሌላ ቃል መጠቀም እና ምትክ ቃል ተመልከት)
"ማንኛውም ሽማግሌ ቢሆን' ወይም "ያረጀ ማንኛውም ሰው ቢሆን'
"እይታህን እንድታጣ ያደርጋል' ወይም "ዓይነ ስውር እንድትሆን ያደርጋል'
ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "አንድ ሰው ካህን አደርጋለሁ፡፡' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "እንዲያገለግለኝ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
"እንዲያደርግ የምፈልገውንና እንዲያደርግ የምነግረውን'
በዚህ ስፍራ "ቤት' የሚለው "ትውልድን' የሚመለክት ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ሁሌም ሊቀ ካህን ሆኖ የሚያገለግል ትውልድ እንደሚኖረው ቃል እገባለሁ፡፡'(ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
እግዚአብሔር የሚያስነሳው የታመነ ካህን
በዚህ ስፍራ "ቁራሽ እንጀራ' የሚለው "ምግብን' ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ነው፡፡ አት፡- "አንዳች የምበላው ነገር እንዲኖረኝ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)
1 ትንሹ ልጅ ሳሙኤል በዔሊ ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር። 2 በእነዚያ ቀናት የእግዚአብሔር ቃል እምብዛም አይገኝም ነበር፤ ትንቢታዊ ራዕይም አይዘወተርም ነበር። በዚያን ጊዜ፥ ዔሊ ዐይኖቹ ከመፍዘዛቸው የተነሣ አጥርቶ ማየት ባቃተው ጊዜ፥ በአልጋው ላይ ተኝቶ እያለ፥ 3 የእግዚአብሔር መብራት ገና አልጠፋም ነበር፥ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተኝቶ ነበር። 4 እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው፥ እርሱም፥ “አቤት!” አለው። 5 ሳሙኤል ወደ ዔሊ ሮጠና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው፤ ዔሊም፥ “እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው። ስለዚህ ሳሙኤል ሄደና ተኛ። 6 እግዚአብሔር እንደገና፥ “ሳሙኤል” ብሎ ተጣራ። ሳሙኤልም እንደገና ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም፥ "ልጄ ሆይ፥ እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ" ብሎ መለሰለት። 7 ሳሙኤል እግዚአብሔርን ገና አላወቀም ነበር፥ ከእግዚአብሔር ምንም ዓይነት መልዕክት ገና አልተገለጠለትም ነበር። 8 እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው። ሳሙኤልም እንደገና ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው። ከዚያም ልጁን እግዚአብሔር እንደ ጠራው ዔሊ አስተዋለ። 9 ዔሊም ሳሙኤልን፥ "ሂድና ተመልሰህ ተኛ፤ ደግሞ ከጠራህም፥ 'እግዚአብሔር ሆይ፥ አገልጋይህ እየሰማህ ነውና ተናገር' ማለት አለብህ" አለው። ስለዚህ ሳሙኤል እንደገና ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ። 10 እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፤ እንደ ቀድሞው ሁሉ፥ "ሳሙኤል፥ ሳሙኤል" ብሎ ጠራው። ከዚያም ሳሙኤል፥ "አገልጋይህ እየሰማህ ነውና ተናገር" አለው። 11 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፥ "ተመልከት፥ የሚሰማውን ሁሉ ጆሮውን ጭው የሚያደርግ አንድ ነገር በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ። 12 በዚያም ቀን፥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ስለ ቤቱ የተናገርኩትን ሁሉ በዔሊ ላይ አመጣበታለሁ። 13 ልጆቹ በራሳቸው ላይ እርግማንን ስላመጡና እርሱም ስላልከለከላቸው፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እርሱ ስለሚያውቀው ኃጢአት በቤቱ ላይ እንደምፈርድ ነግሬዋለሁ። 14 በዚህ ምክንያት የቤቱ ኃጢአት በመሥዋዕት ወይም በመባ ይቅር እንዳይባል ለዔሊ ቤት ምያለሁ።" 15 ሳሙኤል እስኪነጋ ተኛ፤ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ። ሳሙኤል ግን ስላየው ራዕይ ለዔሊ ለመንገር ፈራ። 16 ከዚያም ዔሊ ሳሙኤልን ጠርቶ፥ "ልጄ ሳሙኤል ሆይ" አለው። ሳሙኤልም፥ "አቤት!" ብሎ መለሰለት። 17 እርሱም፥ "የነገረህ ቃል ምንድነው? እባክህ አትደብቀኝ። ከነገረህ ቃል ሁሉ አንዱን ብትደብቀኝ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብህ፤ ከዚያም የባሰውን ጨምሮ ያድርግብህ" አለው። 18 ሳሙኤል ሁሉንም ነገር ነገረው፤ ከእርሱም ምንም አልደበቀም። ዔሊም፥ "እርሱ እግዚአብሔር ነው። መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ" አለ። 19 ሳሙኤል አደገ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበር፥ ከትንቢታዊ ቃሉ ሳይፈጸም የቀረ አንድም አልነበረም። 20 ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉት እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ነቢይ እንዲሆን መመረጡን ዐወቁ። 21 እግዚአብሔር እንደገና በሴሎ ተገለጠ፥ እርሱም በቃሉ አማካይነት በሴሎ ራሱን ለሳሙኤል ገለጠለት።
እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ለሕዝብ አይናገርም ነበር
ይህ በመገናኛው ድንኳን ቅዱስ ስፍራ በሁሉም ቀን እና ባዶ እስኪሆን ድረስ ሌሊቱን ሁሉ የሚነደው ሰባት መቅረዝ ያለው መብራት ነው፡፡
"መቅደሱ' በእርግጥ ድነኳን ነበር ነገር ግን ሕዝቡ ያመልክበት የነበረ ስፍራ ስለ ነበር፣ በዚህ ስፍራ መቅደስ ብሎ መተረጎም ይበልጥ የተመረጠ ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 1፡9 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ዔሊ የሳሙኤል እውነተኛ አባት አልነበረም፡፡ ዔሊ የሳሙኤል አባት እንደሆነ አድርጎ መናገሩ እንዳልተበሳጨ ነገር ግን ሳሙኤል ሊሰማው እንደሚገባ ለሳሙኤል ለማሳየት ነው፡፡ (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ምንም መልእከት መቼም አልገለጠለትም ነበር' ወይም "እግዚአብሔር ምንም መልእክት ፈጽሞ አልገለጠለትም ነበር፡፡' (አድጊራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመለከት)
ሳሙኤል ለእግዚአብሔር አክበሮትን ለማሳየት ራሱን እንደ ሌላ ሰው አድርጎ ሳሙኤል ለእግዚአብሔር እንዲናገር ዔሊ ነገረው፡፡ አት፡- 'እኔ ነኝ' (ተውላጠ ስም ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1)እግዚአብሔር በተጨባጭ ተገልጦአል በሳሙኤልም ፊት ቆሞአል 2)እግዚአብሔር መገኘቱን ለሳሙኤል እንዲታወቅ አድርጓል
ሳሙኤል ለእግዚአብሔር አክበሮትን ለማሳየት ራሱን እንደ ሌላ ሰው አድርጎ ለእግዚአብሔር ተናገረ፡፡ አት፡- 'እኔ ነኝ' (ተውላጠ ስም ተመልከት)
በዚህ ስፍራ "ጆሮች ጭው የሚያደርግ' የሚለው ስለ ሰሙት ነገር እያንዳንዳቸው ይደነግጣሉ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "የሚሰማውን እያንዳንዱን ያስደነግጣል' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
በተለምዶ ከቅዝቃዜ የተነሳ ወይም ያንን የሰወነት ክፍል ሰዎች በእጃቸው ከመምታቸው የተነሳ አንድ ሰው በትንሽ የተሳለ ነገር በቀላሉ ሲወጋ የሚሰማው የመወጋት ስሜት ዓይነት ነው፡፡
ይህ ሙሉነትን የሚያሳይ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ፈጽሞ ሁሉን ነገር' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
"የሚያደርጓቸውን እነዚያን ሰዎች እቀጣለሁ ብሎ እግዚአብሔር የተናገረባቸውን እነዚያን ነገሮች አደረጉ'
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "የቤቱን ኃጢአት ሊያስተሰርይ የሚችል ማንም ሊያቀርበው የሚችል መስዋዕት ወይም ቁርባን የለም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
በቤተሰቡ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች የፈጸሙት ኃጢአት ነው
"ቤት' የተባለው በተጨባጭ "ድንኳን' ነበር፣ ነገር ግን በዚህ ስፍራ "ቤት' ብሎ መተርጎሙ እጅግ የተሻለ ነው፡፡
ዔሊ የሳሙኤል እውነተኛ አባት አልነበረም፡፡ ዔሊ የሳሙኤል አባት እንደሆነ አድርጎ መናገሩ እንዳልተበሳጨ ነገር ግን ሳሙኤል ሊመልስለት እንደሚገባ ለሳሙኤል ለማሳየት ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 3፡6 እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡ (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)
"እግዚአብሔር የሰጠው መልእክት'
ይህ ዔሊ ምን ያህል የምሩን እንደሆነ አጽንዖት የሚሰጥ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር እኔን እንደሚቀጣ በተናገረበት ተመሳሳይ መንገድ ይቅጣህ፣ ከዚያም በላይ እንኳን ይጨምርብህ፡፡' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
በዚህ ስፍራ ያልተፈጸሙ መልእክቶች መሬት ላይ እንደወደቁ ተገልጸዋል፡፡ ይህ አዎንታዊ በሆነ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የተነበያቸው ነገሮች ሁሉ ይፈጸሙ ነበር' (ዘይቤአዊ ንግግርና ሁኔታን በማንበብ ላይ የተመሠረተ ትንቢት ተመልከት)
"በእስራኤል ያሉ ሰዎች ሁሉ'
"በምድሪቱ ክፍል ሁሉ' የሚልን አሳብ የሚያመለክት ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ከምድሪቱ አንደኛው ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ' ወይም "ከሰሜን ጥግ ከዳን እስከ ደቡብ ጥግ እስከ ቤርሳብህ'
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይቻላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ሳሙኤልን ሾመ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
1 የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤላውያን ሁሉ መጣ። በዚህ ወቅት እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ጋር ለመዋጋት ሄዱ። የጦር ሰፈራቸውንም በአቤንኤዘር አደረጉ፥ ፍልስጥኤማውያንም የጦር ሰፈራቸውን በአፌቅ አደረጉ። 2 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት ተሰለፉ። ውጊያው በተፋፋመ ጊዜ እስራኤላውያን አራት ሺህ ሰዎቻቸው በውጊያው ሜዳ በመገደላቸው በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ። 3 ሕዝቡ ወደ ጦር ሰፈሩ በመጣ ጊዜ፥ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ "እግዚአብሔር ዛሬ በፍልስጥኤማውያን ፊት እንድንሸነፍ ያደርገን ለምንድነው? ከእኛ ጋር እንዲሆንና ከጠላቶቻችን ኃይል እንዲያድነን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ እናምጣው" አሉ። 4 ስለዚህ ሕዝቡ ወደ ሴሎ ሰዎችን ላኩ። ከዚያ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠውን የሠራዊቱን ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ። ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ። 5 የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ጦር ሰፈሩ በመጣ ጊዜ፥ የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ በታላቅ ዕልልታ ጮኹ፥ ምድሪቱም አስተጋባች። 6 ፍልስጥኤማውያን የዕልልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “ይህ በዕብራውያኑ የጦር ሰፈር የሚሰማው የዕልልታ ድምፅ ምን ማለት ይሆን? አሉ። ከዚያም የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ጦር ሰፈሩ እንደ መጣ ተገነዘቡ። 7 ፍልስጥኤማውያኑ ፈሩ፤ እነርሱም፥”እግዚአብሔር ወደ ጦር ሰፈሩ መጥቷል" አሉ። 8 እነርሱም፥ "ወዮልን! እንደዚህ ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልሆነም! ወዮልን! ከዚህ ኃያል አምላክ ክንድ ማን ያድነናል? ይህ በምድረ በዳ ግብፃውያንን በልዩ ልዩ ዓይነት መቅሠፍት የመታቸው አምላክ ነው። 9 እናንተ ፍልስጥኤማውያን በርቱ፥ ወንድነታችሁንም አሳዩ፥ ካልሆነ እነርሱ ባሪያዎቻችሁ እንደነበሩ ባሪያዎቻቸው ትሆናላችሁ። ወንድነታችሁ ይታይ፥ ተዋጉም" አሏቸው። 10 ፍልስጥኤማውያኑ ተዋጉ፥ እስራኤላውያንም ተሸነፉ። እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሸሸ፥ የተገደሉትም እጅግ ብዙ ነበሩ፤ ከእስራኤል ሠላሳ ሺህ እግረኛ ወታደር ወደቀ። 11 የእግዚአብሔር ታቦት ተወሰደ፥ ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስም ሞቱ። 12 በዚያው ቀን አንድ ብንያማዊ ከውጊያው መስመር ወደ ሴሎ በሩጫ መጣ፥ በደረሰ ጊዜ ልብሱን ቀድዶና በራሱ ላይ አፈር ነስንሶ ነበር። 13 እርሱ በደረሰ ጊዜ፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት በመስጋት ልቡ ታውኮበት ስለነበረ በመንገዱ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር። ሰውየው ወደ ከተማ ገብቶ ወሬውን በነገራቸው ጊዜ፥ ከተማው በሙሉ አለቀሱ። 14 ዔሊ የልቅሶውን ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “የዚህ ሁካታ ትርጉሙ ምንድነው?” አለ። ሰውየው ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው። 15 በዚህ ጊዜ ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ ዓይኖቹ አጥርተው አያዩም ነበር፥ ማየትም አይችልም ነበር። 16 ሰውየውም ዔሊን፥ “ከውጊያው መስመር የመጣሁት እኔ ነኝ። ዛሬ ከውጊያው ሸሽቼ መጣሁ” አለው። ዔሊም፥ “ልጄ ሆይ፥ ነገሩ እንዴት እየሆነ ነው?” አለው። 17 ወሬውን ያመጣው ያ ሰው መልሶ፥ “እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ። ደግሞም በሕዝቡ መካከል ታላቅ ዕልቂት ሆኗል። ሁለቱ ወንዶች ልጆችህ፥ አፍኒን እና ፊንሐስ ሞተዋል፥ የእግዚአብሔር ታቦትም ተወስዷል” አለው። 18 እርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ጠቅሶ በተናገረ ጊዜ፥ ዔሊ በመግቢያው በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ወደ ኋላው ወደቀ። ስላረጀና ውፍረት ስለነበረው አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤላውያን ላይ ለአርባ ዓመታት ፈርዶ ነበር። 19 በዚህ ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት አርግዛ የመውለጃ ሰዓቷ ደርሶ ነበር። የእግዚአብሔር ታቦት መማረኩን፥ ዐማቷና ባሏ መሞታቸውን በሰማች ጊዜ ተንበርክካ ወለደች፥ ነገር ግን ምጡ አስጨነቃት። 20 ለመሞት በምታጣጥርበት ጊዜ ያዋልዷት የነበሩ ሴቶች፥ "ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ“ አሏት። እርሷ ግን አልመለሰችላቸውም ወይም የነገሯትን በልቧ አላኖረችውም። 21 እርሷም የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከና ስለ ዐማቷና ስለ ባልዋ "ክብር ከእስራኤል ተለየ!" ስትል ልጁን ኤካቦድ ብላ ጠራችው። 22 እርሷም፥”የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከ ክብር ከእስራኤል ተለየ!" አለች።
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ፡- ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን አሸነፉ ገደሏቸውም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
በዚህ ስፍራ አራት ሺህ የሚለው ቁጥር የሚጠጋጋ ቁጥር ነው፡፡ ከዚያ ቁጥር በጥቂት ከፍም ዝቅም ሊል ይችላል፡፡ የሚያህሉ የሚለው ቁርጥ ያለ ቁጥር እንዳልሆነ አመላካች ነው፡፡ አት፡- "አራት ሺህ የሚያህሉ ሰዎች' (ቀጥሮች ተመልከት)
ጦርነቱን ይዋጉ የነበሩ ወታደሮች
ሽማግሌዎቹ በእርግጥ እግዚአብሔር ለምን እንደመታቸው አላወቁም ነበር፣ ነገር ግን ከእነርሱ ጋር እንዲሆን የቃል ኪዳኑን ታቦታ በማምጣት እንዴት በእርግጠኛነት ሁለተኛ እንዳይደገም እደሚያደርጉ እንደሚያውቁ በስህተት አሰቡ፡፡
ኪሩቤል በቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ ላይ የሚገኙ እንደሆኑ ግልጽ ማድረግ ያስፈልግሃል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በዙፋኑ እንደተቀመጠ ሁሉ የቃልኪዳኑ ታቦት አግዚአብሔር እግሩን የሚያኖርበት የእግሩ መረገጫ እንደሆነ በአብዘኛው ይናገራሉ፡፡ አት፡- "በቃል ኪዳኑ ታቦት ከኪሩቤል በላይ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ይልተደረገ መረጃ ተመልከት)
በሴሎ ነበሩ
"ሕዝቡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር ባመጡ ጊዜ' ትርጉሙን ግልጽ ለማድረግ ለመረዳት ምቹ የሆነ መረጃን ለመጨመር ጥቂት መግለጫዎች አስፈላጊ ናቸው፡፡ አት፡- "ሕዘቡ ከአፍኒንና ከፊንሐስ ጋር የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸከሙ ወደ ሰፈርም አመጡት፡፡' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
"ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ሰፈር አመጡት'
"ለራሳቸው አሉ … ለእርስ በእርሳቸው አሉ' ወይም "ለእርስ በእርሳቸው አሉ … ለእርስ በእርሳቸው አሉ'ሁለተኛው ሐረግ ፍልስጥኤማውያን ለርስ በርሳቸው ያሉትን በግልጽ ያመለክታል፡፡ የመጀመሪያው ሐረግ ግን ወይ ያሰበቱን ወይም ለእርስ በእርሳቸው ያሉትን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ከተቻለ ለማን እንደተነገረ አታመልክት፡፡
ፍልስጥኤማውያን በብዙ አማልክት ያመልካሉ፣ ስለዚህ ከእነዚያ አማልክት መካከል አንዱ ወይም የማያመልኩት አንዱ ወደ ሰፈር እንደመጣ አምነዋል፡፡ ሌላኛው ሊሆን የሚችለው ትርጉም "ያህዌ መጥቶአል' ሲሉ የእስራኤልን አምላክ መደበኛ ስም እየጠሩ ነበር የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም 4፡8 ስለ "አማልክት' ይናገራል፣ አንዳንድ ትርጉሞች "እግዚአብሔሮች መጥተዋል' ይላሉ፣ ይኄውም፣ "አማልክት መጥተዋል' ማለት ነው፡፡ (ተውላጠ ስሞች ተመልከት)
ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ ጥልቅ ፍርሃት መግለጫ ነው፡፡ በገላጭ አባባል ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "ከእነዚአህ ኃያላን አማልክት እጅ ሊያድነን የሚችል ማንም የለም፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች ተመልከት)
ምክንያቱም በቁጥር 7 አምላክ (ወይም እግዚአብሔር) የሚለው ቃል በነጠላ ቁጥር ነው፣ ሊሆኑ ከሚችሉ ብዙ አማልክት መካከል አንዳቸውን ወይም የእስራኤልን አምላክ መደበኛ ስም በመጠቀም "ይህ ኃያል እግዚአብሔር … የመታ እግዚአብሔር' በሚያመለክት መልኩ በርካታ ትርጉሞች "ይህ ኃያል አምላክ … የመታ አምላክ' ይላሉ፡፡ (ተውላጠ ስሞች ተመልከት)
ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ብርቱዎች ሁኑ ተዋጉ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እስራኤል' የሚለው የእስራኤልን ሠራዊት ያመለክታል፡፡ አት፡- "የእስራኤልን ሠራዊት አሸነፉ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ እና ተለዋጭ ስም ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርንም ታቦት ወሰዱ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ይህ በእስራኤል ባሕል ጥልቅ ሐዘን መግለጫ መንገድ ነው፡፡
ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ሲሆን በጣም ፈርቶ ወይም ስለ አንድ ነገር ታውኮ ነበር ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ይህ በከተማይቱ ያሉ ሰዎች ሁሉ ለሚለው ምትክ ቃል ነው፡፡ (ምትክ ቃል ተመልከት)
"የብንያም ሰው'
ዔሊ የሌላኛው ሰው እውነተኛ አባት አልነበረም፡፡ ዔሊ የሰውዬው አባት እንደሆነ አድርጎ መናገሩ እንዳልተበሳጨ ነገር ግን ሊመልስለት እንደሚገባ ለሰውዬው ለማሳየት ነው፡፡ (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)
ይህ ስለሆነው ነገር አጠቃላይ መግለጫ ነው፡፡ የቀሩት የሰውዬው ንግግሮች ዝርዝሩን ያቀርባሉ፡፡
"አሁን አንድ የባሰ ነገር እነግርሃለሁ … አሁን አንድ የባሰ ነገር እነግርሃለሁ' ወይም "ሕዝቡ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ሁለቱ ልጆችህም'
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ብንያማዊው ሰው በጠቀሰ ጊዜ
"በተናገረ'
ይህ በአድራጊ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ስለወደቀ አንገቱ ተሰበረ' ወይም "ሲወድቅ አንገቱን ሰበረ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
የዔሊ ምራት
ይህ በአድራጊ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት ማረኩ (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
"ላሉት ምንም ትኩረት አልሰጠችም' ወይም "የተሻለ እንዲሰማት ፈቀደች'
ስሙ ሐረግ ሲሆን ክብር የለም ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የአንድ ሰው ስም ስለ ግለሰቡ፣ ስለ ቦታ ወይም ስለ ሚያመለክተው ነገር መረጃ ይሰጣል፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ፡- ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት ስለማረኩ … ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት ከመማረካቸው የተነሣ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
1 ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት በመማረክ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ አመጡት። 2 እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ማርከው ወደ ዳጎን ቤት ወስደው በዳጎን አጠገብ አቆሙት። 3 የአሽዶድ ሰዎች በቀጣዩ ቀን ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። ስለዚህ ዳጎንን አንሥተው በስፍራው መልሰው አቆሙት። 4 ነገር ግን በማግስቱ ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። በደጁ መግቢያ ውስጥ የዳጎን ራሱና እጆቹ ተሰብረው ወድቀው ነበር። የቀረው የዳጎን ሌላው የአካል ክፍሉ ብቻ ነበር። 5 ለዚህ ነው እስካሁን እንኳን የዳጎን ካህናትና ሌላ ማንኛውም ሰው በአሽዶድ ወደሚገኘው ወደ ዳጎን ቤት በሚመጣበት ጊዜ የዳጎንን ደጅ መግቢያ ሳይረግጥ የሚያልፈው። 6 የእግዚአብሔር እጅ በአሽዶድ ሰዎች ላይ ከብዶ ነበር። በአሽዶድና በዙሪያው ባሉት ላይ ጥፋትን በማምጣት በእባጭ መታቸው። 7 የአሽዶድ ሰዎች የሆነባቸውን ባስተዋሉ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ከብዳለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ጋር መቆየት የለበትም” አሉ። 8 ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ልከው በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ "በእስራኤል አምላክ ታቦት ላይ ምን እናድርግ?" አሏቸው። እነርሱም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይምጣ” ብለው መለሱላቸው። የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደዚያ ወሰዱት። 9 ነገር ግን ወደዚያ ካመጡት በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፥ ታላቅ መደናገርንም አደረገባቸው። ልጅና ዐዋቂውን፥ የከተማውን ሰዎች አስጨነቀ፤ ሰውነታቸውም በእባጭ ተወረረ። 10 ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ አቃሮን ላኩት። ነገር ግን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቃሮን እንደ መጣ፥ አቃሮናውያን፥ "እኛንና ሕዝባችንን እንዲገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ እኛ አምጥተዋል" በማለት ጮኹ። 11 ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች በመላክ ሁሉንም በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ “እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ላኩት፥ ወደ ስፍራውም ይመለስ" አሏቸው። በዚያ የእግዚአብሔር እጅ እጅግ ስለበረታባቸው በከተማው ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበረ። 12 ከሞት የተረፉት ሰዎች በእባጮቹ ይሠቃዩ ስለነበር የከተማዪቱ ጩኸት ወደ ሰማያት ወጣ።
ቃሉ የታሪኩ አዲስ ክፍል መጀመሩን ያሳያል፡፡ ቋንቋህ ተመሳሳይ ትርጉም የሚሰጥ ቃል ወይም ሐረግ ካለ በዚህ ስፍራ ልትጠቀም ትችላለህ፡፡
ይህንን በ1ሳሙኤል 3፡3 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ ይህ በ1ሳሙኤል 4፡3-4 "የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት' ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
ይህ የፍልስጥኤማውያንን አምላክ የዳጎንን ቤተ ጣዖት የሚያመለክት ነው፡፡
"ዳጎንን ለማየት እጅግ በአድናቆት ነበሩ'
እግዚአብሔር በሌሊት ሐውልቱ በግምባሩ እንዲወድቅ እንዳደረገ አንባቢው ማስተዋል አለበት፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
እግዚአብሔር ዳጎንን እንዲወድቅ እንዳደረገ አንባባዊ ማስተዋል አለበት፡፡
እግዚአብሔር ጠላቱን እንዳሸነፈና የጠላቱን ራስና እጆች እንደቆረጠ ወታደር ዓይነት ነበር፡፡
ጸሐፊው ከዋናው ታሪክ ወጣ ያለ ጥቂት የመነሻ ታሪክ መረጃ እየሰጠ ነው፡፡ (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ተመልከት)
በዚህ ስፍራ "ዛሬ' የሚለው ቃል የሚያመለከትው ጸሐፊው መጽሐፉን እስከሚጽፈበት ድረስ የነበረውን ጊዜ ነው፡፡
ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ "እግዚአብሔር በጽኑ ፈረደባቸው' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት
የከተማይቱ ስም በከተማይቱ ለሚኖሩ ሰዎች ምትክ ስም ነው፡፡ "በአዛጦን የሚኖሩ ሰዎችና በአዛጦን ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች' (ምትክ ቃል ተመልከት)
"የአዛጦን ሰዎች አስተዋሉ'
ይህንን በ1ሳሙኤል 3፡3 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ ይህ በ1ሳሙኤል 4፡3-4 "የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት' ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ቀጣቸው' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) እድሜን የሚያሳይ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "በሁሉ እድሜ የሚገኙ ሰዎች' ወይም 2) ማኅበራዊ መደብን የሚያሳይ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ከድሆችና ደካሞች አንስቶ እሰከ ባለጸጎቹና ብርቱዎቹ ሰዎች' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡
ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
ይህንን በ1ሳሙኤል 3፡3 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ ይህ በ1ሳሙኤል 4፡3-4 "የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት' ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) የእስራኤልን አምላክ መደበኛ ስም እየጠሩ ነበር ወይም 2) "የእስራኤል አምላክ'፣ እስራኤል ከብዙ አማልክት መካከል አንዱን ያመልኩ እንደነበር ያምኑ ነበር፡፡ 1ሳሙኤል 5፡7 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
"ሊሞቱ ስለሆነ የከተማይቱ ሰዎች ሁሉ ፈርተው ነበር'
እጁ የእግዚብሔር ሰዎችን ስለ መቅጣተ ምትክ ቃል ነው፡፡ "እግዚአብሔር በዚያ ሰዎችን እጅግ እየቀጣ ነበር' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ይህ በተጨባጭ ብዙ ሰዎች እንደሞቱ ያመላክታል፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡
ከተማ የሚለው ቃል ለከተማው ሕዝብ ምትክ ቃል ነው፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) "ወደ ሰማያት ወጣ' የሚለው ቃል "ታላቅ ነበር' ለሚለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "የከተማይቱ ሰዎች ድምፃቸውን በጣም ከፍ አድርገው ጮኹ' ወይም 2) "ሰማያት' የሚለው ቃል ለሕዝቡ አማልክት ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "የከተማይቱ ሕዝብ ወደ አማልክቶቻቸው ጮኹ' (ምትክ ቃልና ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
1 የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን አገር ከተቀመጠ ሰባት ወር ሆነው። 2 ከዚያም የፍልስጥኤም ሰዎች ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የእግዚአብሔርን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ አገሩ እንዴት አድርገን መመለስ እንዳለብን ንገሩን” አሉአቸው። 3 ካህናቱና ጠንቋዮቹም፥ "የእስራኤልን አምላክ ታቦት መልሳችሁ የምትልኩ ከሆነ ያለስጦታ አትላኩት፤ በተቻለ መጠን የበደል መስዋዕትም ላኩለት። ከዚያም ትፈወሳላችሁ፥ እናንተም እስካሁን ድረስ እጁን ከላያችሁ ላይ ያላነሣው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ"። 4 ሕዝቡም፥ “የምንመልሰው የበደል መስዋዕት ምን መሆን አለበት?”አሏቸው። እነርሱም እንዲህ በማለት መለሱላቸው፥ "አምስት የወርቅ እባጮችንና አምስት የወርቅ አይጦችን፥ በቁጥር አምስት መሆኑም የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች ቁጥር የሚወክል ነው። እናንተንና ገዢዎቻችሁን የመታው ተመሳሳይ መቅሰፍት ነውና። 5 ስለዚህ ምድራችንን ባጠፋው በእባጮቻችሁና በአይጦቻችሁ አምሳል ማድረግ አለባችሁ፥ ለእስራኤል አምላክም ክብርን ስጡ። ምናልባት እጁን ከእናንተ፥ ከአማልክቶቻችሁና ከምድሪቱ ላይ ያነሣ ይሆናል። 6 ግብፃውያንና ፈርዖን ልባቸውን እንዳደነደኑ ለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? ያን ጊዜ ነበር የእስራኤል አምላክ ክፉን ያደረገባቸው፤ ታዲያ ግብፃውያኑ ሕዝቡን አልለቀቋቸውም?እነርሱስ ከዚያ አልወጡም? 7 እንግዲህ አዲስ ሠረገላና እስካሁን ቀንበር ያልተጫነባቸውን ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፥ እምቦሳዎቻቸውን ግን ከእነርሱ ለይታችሁ በቤት አስቀሩአቸው። 8 ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩት። የበደል መስዋዕት አድርጋችሁ የምትመልሱለትን የወርቁን አምሳያዎች በሳጥን ውስጥ አድርጋችሁ በአንደኛው ጎኑ አስቀምጡ። ከዚያም ልቀቁትና በራሱ መንገድ እንዲሄድ ተዉት። 9 ከዚያም ተመልከቱ፥ ወደ ራሱ ምድር፥ ወደ ቤት ሳሚስ በመንገዱ ከሄደ፥ ይህንን ታላቅ ጥፋት ያመጣው እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ካልሆነ ግን፥ ይህ በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን"። 10 ሰዎቹም እንደተነገራቸው አደረጉ፤ ሁለት የሚያጠቡ ላሞችን ወሰዱና በሠረገላው ጠመዷቸው፥ እምቦሳዎቻቸውንም ከቤት እንዳይወጡ አደረጉ። 11 የወርቁን አይጥና የእባጮቻቸው ምሳሌ የሆነውን ከያዘው ሳጥን ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት በሠረገላው ላይ አደረጉት። 12 ላሞቹም በቤት ሳሚስ አቅጣጫ ቀጥ ብለው ሄዱ። እነርሱም በዚያው ጎዳና፥ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳይሉ ቁልቁል ሄዱ። የፍልስጥኤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤት ሳሚስ ዳርቻ ድረስ ከበስተኋላቸው ተከተሏቸው። 13 በዚህ ጊዜ የቤት ሳሚስ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን በማጨድ ላይ ነበሩ። ቀና ብለው ባዩ ጊዜ ታቦቱን ተመለከቱ፥ ደስም አላቸው። 14 ሠረገላው የቤት ሳሚስ ሰው ወደሆነው ወደ ኢያሱ እርሻ መጥቶ በዚያ ቆመ። በዚያም ትልቅ ቋጥኝ ነበር፥ የሠረገላውን እንጨት በመፍለጥ ላሞቹን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ። 15 ሌዋውያኑ የእግዚአብሔርን ታቦትና አብሮት የነበረውን፥ የወርቁ ምስሎች የነበሩበትን ሳጥን፥ ከሠረገላው አውርደው በትልቁ ቋጥኝ ላይ አስቀመጡት። በዚያው ቀን የቤት ሳሚስ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቀርቡ፥ መሥዋዕቶችንም ሠዉ። 16 አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ይህንን ባዩ ጊዜ በዚያው ቀን ወደ አቃሮን ተመለሱ። 17 የፍልስጥኤም ሰዎች ለእግዚአብሔር የበደል መስዋዕት አድርገው የመለሷቸው የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት እና አንዱ ስለ አቃሮን ነበር። 18 የወርቁ አይጥ አምስቱ ገዢዎች ከሚገዟቸው የተመሸጉ የፍልስጥኤማውያን ከተሞችና መንደሮች ቁጥር ሁሉ ጋር ቁጥሩ ተመሳሳይ ነበር። የእግዚአብሔርን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ታላቅ ቋጥኝ በቤት ሳሚስ በኢያሱ እርሻ ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ምስክር ሆኖ ይኖራል። 19 ወደ ታቦቱ ውስጥ ተመልክተዋልና እግዚአብሔር ከቤት ሳሚስ ሰዎች ጥቂቶቹን መታቸው። እርሱም ሰባ ሰዎችን ገደለ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ክፉኛ ስለመታቸው ሕዝቡ አለቀሱ። 20 የቤት ሳሚስ ሰዎችም፥ “በዚህ ቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚችል ማነው? ከእኛስ ወደ ማን ይሄዳል?” አሉ። 21 በቂርያትይዓሪም ወደሚኖሩት መልዕክተኞች ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰዋል፤ ወደዚህ ውረዱና ውሰዱት” አሏቸው።
እነዚህ ዳጎንን የሚያመልኩ የአሕዛብ ካህናትና ጠንቋዮች ናቸው፡፡
ፍልስጥኤማውያን ከዚህ ወዲያ እግዚአብሔርን ሳያሰቆጡ ታቦቱን እንዴት እንደሚያስወግዱት ማወቅ ፈለጉ፡፡
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) የእስራኤልን አምላክ መደበኛ ስም እየጠሩ ነበር ወይም 2) "የእስራኤል አምላክ'፣ እስራኤል ከብዙ አማልክት መካከል አንዱን ያመልኩ እንደነበር ያምኑ ነበር፡፡ 1ሳሙኤል 5፡7 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ባዶውን አትስደዱት የሚሉት ቃላት አንድን ነገር አጠንክሮ መናገሪያ መንገድ ናቸው፡፡ አት፡- "የበደል መሥዋዕት መስደድ አለባችሁ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
"ከእንግዲህ ወዲህ አትታመሙ'
እናንተ የሚለው ተውላጠ ስም የብዙ ቁጥር እንደመሆኑ ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያመለክታል፡፡ (አንተ/እናንተ ተመልከት)
በዚህ ስፍራ "እጅ' የሚለው ቃል እግዚአብሔር መከራን ለማምጣትና ለመቅጣት ያለውን ኃይል ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "መከራችሁን ለምን አላቀለላችሁም' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡
ከአንድ በላይ አይጥ
ምሳሌ እውነተኛው ነገር የሚመስል ነገር ነው፡፡
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡
"የሚያጠፉ'
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) የእስራኤልን አምላክ መደበኛ ስም እየጠሩ ነበር ወይም 2) "የእስራኤል አምላክ'፣ እስራኤል ከብዙ አማልክት መካከል አንዱን ያመልኩ እንደነበር ያምኑ ነበር፡፡ 1ሳሙኤል 5፡7 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
በዚህ ስፍራ "እጅ' የሚለው ቃል እግዚአብሔር መከራን ለማምጣትና ለመቅጣት ያለውን ኃይል ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "እናንተን፣ አማልክቶቻችሁንና ምድራችሁን መቅጣት ያቆማል' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ካህናቱና ጠንቋዮቹ አሳብ ገላጭ ጥያቄ በመጠቀም፣ እግዚአብሔርን መታዘዝ እምቢ ካሉ ምን ሊሆን እንደሚችል ትኩረት ሰጥተው እንዲያስቡ ፍልስጥኤማውያንን አጥብቀው እያስገነዘቡ ነው፡፡ (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
ይህ ግትር መሆንና ለእግዚብሔር ፈቃድ አለመታዘዝ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ይህ እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ መከራ ማምጣቱን እንዲያቆም በስተመጨረሻ ግብጻውያን እንዴት እስራኤላውያን ከግብጽ እንዲወጡ እንዳደረጉ ፍልስጥኤማውያንን ለማሳሳብ የተጠቀሙበት አሳብ ገላጭ ጥያቄ ነው፡፡ (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
እስከ አሁን ወተት የሚጠጡ ጥጆች ያሉአቸው ሁለት ላሞች
እንደተለመደው ሁለቱ ላሞች ወደ ጥጆቻቸው ወደ ቤት መመለስ ይኖርባቸው ነበር፡፡
ላሞቹ ጥጆቻቸው በስተኋላ በፍልስጥኤማውያን ሰፈር እያሉ ወደ ቤትሳሚስ ለመንከራተት ይመርጣሉ ብሎ ማሰብ የማይመስል ነው፡፡
እስከ አሁን ወተት የሚጠጡ ጥጆች ያሉአቸው ሁለት ላሞች፡፡ 1ሳሙኤል 6፡7ን እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ይህን በ1ሳሙኤል 6፡4 እንዳለው ተርጉም፡፡
"የእባጮቻቸውን ምሳሌዎች'
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡
በአብዛኛው የሚያጠቡ ላሞች ወደ ጥጆቻቸው ይመለሳሉ፣ ነገር ግን እነዚህ ላሞች ወደ ቤትሳሚስ ሄዱ፡፡
እምቧ ማለት ላሞች በድምጻቸው የሚፈጥሩት ጩኸት ነው፡፡
"ከአውራ ጎዳናው አልወጡም፡፡' ይህ በአዎንታ እንደሚከተለው ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "በአውራው ጎዳና ዘለቁ' ወይም "ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይሄዱ ነበር'
ቃሉ የታሪኩ አዲስ ክፍል መጀመሩን ያሳያል፡፡ ቋንቋህ ተመሳሳይ ትርጉም የሚሰጥ ቃል ወይም ሐረግ ካለ በዚህ ስፍራ ልትጠቀም ትችላለህ፡፡
እስራኤላውያን ነበሩ፡፡
ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "አሻቅበው አዩ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ሰዎች ላሞቻቸውን ሲሰው ይህን ድንጋይ እንደ መሠዊያ ይጠቀሙበት ነበር፡፡
ይህ የሆነው ላሞቹን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ሰረገላውን ለማንደንድ ከመፍለጣቸው በፊት ነው፡፡
ሳጥኑ የአይጥና የእባጭ የወርቅ ምሳሌዎች ይዟል
"የፍልስጥኤማውያን አምስቱ ነገሥታት'
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡
ይህን በ1ሳሙኤል 6፡4 እንዳለው ተርጉም፡፡
በውስጥ ያለውን ሕዝብ ከጠላቶቻቸው ጥቃት ለመጠበቅ በዙሪያቸው ትላልቅ ቅጥች የተገነቡላቸው ከተሞች ናቸው፡፡
ድንጋዩ ማየት እንደሚችል እንደ አንድ ግለሰብ ተጠቅሷል፡፡ አት፡- "ታላቁ ድንጋይ … እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ አለ፣ሰዎችም በላዩ ላይ የተፈጸመውን ያስታውሳሉ፡፡' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየትን ተመልከት)
የሰው ስም (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ይህ ከቤትሳሚስ የሆነ ሰው የሚጠራበት ነው፡፡ አት፡- "ከቤትሳሚስ' (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ጸሐፊው መጽሐፉን እስከጻፈበት ጊዜ ድረስ
ታቦቱ እጅግ ቅዱስ ስለ ነበር ማንም ወደ ውስጥ እንዲመለከት አልተፈቀደለትም፡፡ ታቦቱን እንኳን ለማየት የተፈቀደላቸው ካህናት ብቻ ናቸው፡፡
"አምሳ ሺህ እና ሰባ ሰዎች' (ቁጥሮች ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) ሕዝቡ ስለ እግዚብሔር ያደረበትን ፍርሃት ለመግለጽ አሳብ ገላጭ ጥያቄ ነው፡፡ አት፡- "ቅዱስ ስለሆነ እግዚአብሔርን መቋቋም የሚችል ማንም የለም!' ወይም 2) መረጃ ለማግኘት የቀረበ ጥያቄ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚለው ሐረግ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናትን የሚያመለክት ነው፡፡ ሕዝቡ እግዚአብሔር ታቦቱን እንዲይዝ የፈቀደለትን ካህን እፈለገ መሆኑን ያመላክታል፡፡ አት፡- "በመካከላችን ይህን ቅዱስ አምላክ፣ ያህዌን ማገልገልና ታቦቱን ማስተዳደር የሚችል ካህን አለን?' (አሳብ ገላጭ ጥያቄዎችንና እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
መረጃ ለማግኘት የቀረበ ጥያቄ ነው፡፡ ሁለተኛ እንዳይቀጣቸው እግዚአብሔርና ታቦቱ ወደ አንድ ቦታ እንዲሄዱ ሕዝቡ እንደፈለገ ይጠቁማል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ሁለተኛ እንዳይቀጣን ይህን ታቦት ወዴት መስደድ እንችላለን?' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
1 የቂርያትይዓሪም ሰዎች መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ፥ በኮረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አስገቡት። የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ለዚህ አገልግሎት ለዩት። 2 ታቦቱ በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠ ብዙ ዓመት አለፈው፥ ሃያ ዓመትም ሆነው። የእስራኤል ቤት ሁሉ አዘኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስም ፈለጉ። 3 ሳሙኤል የእስራኤልን ሕዝብ በሙሉ እንዲህ አላቸው፥ "በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱ ከሆነ እንግዶቹን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፥ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር መልሱ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩት፥ ያን ጊዜ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል"። 4 ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ በኣልንና አስታሮትን አስወገዱ፥ እግዚአብሔርን ብቻም አመለኩ። 5 ከዚያም ሳሙኤል፥ "እስራኤልን በሙሉ ምጽጳ ላይ ሰብስቡ፥ እኔም ስለ እናንተ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ“ አላቸው። 6 እነርሱም በምጽጳ ተሰበሰቡ፥ ውሃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ። በዚያም ቀን ጾሙ፥”በእግዚአብሔር ላይም ኃጢአትን አድርገናል“ አሉ። ሳሙኤል በእስራኤል ሕዝብ ላይ የፈረደውና ሕዝቡን የመራው በዚያ ነበር። 7 የእስራኤል ሕዝብ በምጽጳ መሰብሰባቸውን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፥ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች እስራኤልን ለማጥቃት መጡ። የእስራኤል ሰዎች ይህንን በሰሙ ጊዜ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ። 8 ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ ሳሙኤልን፥”ከፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲያድነን፥ ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር መጣራትህን አታቁም“ አሉት። 9 ሳሙኤል የሚጠባ ግልገል ወስዶ ለእግዚአብሔር ሙሉውን የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ሠዋው። ከዚያም ሳሙኤል ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም መለሰለት። 10 ሳሙኤል የሚቃጠለውን መስዋዕት በማቅረብ ላይ እያለ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለማጥቃት ቀረቡ። ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ በታላቅ ድምፅ አንጎደጎደባቸው፥ አሸበራቸውም፥ በእስራኤልም ፊት ተሸንፈው ሸሹ። 11 የእስራኤል ሰዎችም ከምጽጳ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን አሳደዱ፥ ከቤትካር በታች እስካለው ቦታ ድረስ ተከትለው ገደሏቸው። 12 ከዚያም ሳሙኤል አንድ ድንጋይ አንሥቶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው።”እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል“ በማለት አቤንኤዘር ብሎ ጠራው። 13 ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፥ የእስራኤልን ድንበርም አልፈው አልገቡም። በሳሙኤል የሕይወት ዘመን ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር። 14 ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከአቃሮን እስከ ጌት ያሉ መንደሮች ለእስራኤል ተመለሱላቸው፤ እስራኤላውያን ድንበሮቻቸውን ከፍልስጥኤማውያን አስመለሱ። በዚያን ጊዜ በእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከል ሰላም ነበረ። 15 ሳሙኤል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በእስራኤል ላይ ፈረደ። 16 በየዓመቱ ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌልገላና ወደ ምጽጳ ይዘዋወር ነበር። በእነዚህ ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤላውያን መካከል ባሉ አለመግባባቶች ላይ ይፈርድ ነበር። 17 ከዚያም መኖሪያው በዚያ ነበርና ወደ ራማ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ደግሞ በእስራኤላውያን አለመግባባት ላይ ይፈርድ ነበር። በዚያም ደግሞ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ።
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
20 ዓመታት (ቁጥሮች ተመልከት)
"ቤት' የሚለው ቃል በቤት ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎችና ትውልዳቸውን የሚያመለክት ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "የእስራኤል ትውልድ' ሁሉ ወይም "የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ' (ምትክ ቃል ተመልከት)
በዚህ ስፍራ "በሙሉ ልብ' የሚለው ለአንድ ነገር ፈጽሞ መሰጠት የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "እግዚአብሔርን ብቻ ለማምለክና ለመታዘዝ ፈጽማችሁ የተሰጣችሁ ሁኑ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመለክት)
"የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ' ወይም "እስራኤላውያን ሁሉ'
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ሕዝቡ የጾም ክፍል አድርገው የራሳቸውን ወኃ አልተጠቀሙም ወይም 2) ከምንጭ ወይም ከጉድጓድ ውኃ አገኙ፣ በኃጢታቸውም ለመጸጸታቸው እንደ ውጪያዊ ምልክት በምድር ላይ አፈሰሱት፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
በእስራኤል ላይ ጥቃት ያደረሱት ሠራዊቶቹ እንጂ አለቆቹ ራሳቸው እንዳልሆኑ በግልጽ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ አት፡- "የፍልስጥኤማውየን አለቆች ሠራዊታቸውን እየመሩ በእስራኤል ላይ ጥቃት አደረሱ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
እጅ የሰውዬውን ኃይል የሚያሳይ ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "ከፍልስጥኤማውያን ሠረዊት አድነን' ወይም "የፍልስጥኤማውያን ሠራዊት እንዳይጎዱን አድርግ' (ምትክ ቃል ተመልከት)
እስካሁን ድረስ የእናቱን ወተት የሚጠጣ ጠቦት
"ለእርዳታ ጮኸ'
"እንዲያደርግ ሳሙኤል የጠየቀውን እግዚአብሔር አደረገ'
ይህ ጸሐፊው "እግዚአብሔር መለሰለት' ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ያብራራል (1ሳሙኤል 7፡9)
"ግራ መጋባት' የሚለው ቃል በዚህ ስፍራ ጥቅም ላየ የዋለው ፍልስጥኤማውያን በግልጽ ማሰብ አልቻሉም ለማለት ነው፡፡ አት፡- "በግልጽ ማሰብ እንዳይችሉ አደረጋቸው' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር በእስራኤል ፊት ድል መታቸው ወይም 2) እስራኤል ድል መታቸው (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ሰዎችን ድል መምታት ማለት ምንም ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት ማሸነፍ ነው፡፡
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
በዚያ ምድር እስራኤላውያንን ሌሎች ሕዝቦች አስፈላጊ ነገሮች ሲሆኑ ለእግዚአብሔር እርዳታ ማስታወሻ እንዲሆን ትልቅ ድንጋይ ያኖራሉ፡፡
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ጸሐፊው እንዴት ፍልስጥኤማውያን እንዴት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ መናገሩን ፈጸመ፡፡ ቋንቋህ ትረካን የሚደመድምበት መንገድ ካለው እዚህ ጋ መጠቀም ትችላለህ፡፡
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚብሔርን ፍልስጥኤማውያንን አስገዛቸው' ወይም "እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንን ጉዳት ከማድረስ አገዳቸው' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ፍልስጥኤማውያን ሊያጠቁአቸው ወደ እስራኤል ድንበር አይገቡም ነበር፡፡
እጅ የሚለው ቃል ለኃይል ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ኃይሉን ይጠቀም ነበር' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) በዚህ ስፍራ "እስራኤል' የሚለው ቃል የሚያመለከትው የእስራኤልን "ምድር' ነው፡፡ ከእስራኤል … እግዚአብሔር ከተሞችን ለእስራኤል ምድር መለሰ ወይም 2) "እስራኤል' የሚለው ቃል በዚያ ለሚኖረው ሕዝብ ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "ከእስራኤል … የእስራኤል ሕዝብ ከተሞቹን የኔ ናቸው ማለት ቻለ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽና ምትክ ቃል ተመልከት)
በአስቸጋሪ ዙር ከቦታ ቦታ ይጓዝ ነበር
ሙግት ማለት ክርክር ወይም በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች መካከል የሚፈጠር አለመስማማት ነው፡፡
1 ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ላይ ፈራጆች አድርጎ ሾማቸው። 2 የመጀመሪያ ልጁ ስም ኢዮኤል፥ የሁለተኛው ስም አብያ ነበር። እነርሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ። 3 ነገር ግን ልጆቹ ነውረኛ ጥቅም ፈላጊዎች ሆኑ እንጂ በእርሱ መንገድ አልሄዱም። ጉቦ እየተቀበሉ ፍትሕን አዛቡ። 4 ከዚያም የእስራኤል ሽማግሌዎች በአንድነት ተሰብስበው በራማ ወደሚኖረው ወደ ሳሙኤል መጡ። 5 እነርሱም፥ "ተመልከት፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም። እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ እንዲፈርድልን ንጉሥ አንግሥልን" አሉት። 6 ነገር ግን፥ “እንዲፈርድልን ንጉሥ ስጠን” ባሉት ጊዜ ነገሩ ሳሙኤልን ቅር አሰኘው። ስለዚህ ሳሙኤል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። 7 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፥ “በላያቸው ላይ ንጉሥ እንዳልሆን የተቃወሙት እኔን እንጂ አንተን አይደለምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ታዘዝ። 8 ከግብፅ ካወጣዃቸው ጊዜ ጀምሮ እኔን ትተው ሌሎች አማልክቶችን በማምለክ ሲያደርጉት የነበረውን ያንኑ አሁን እያደረጉ ነው፤ በአንተም ላይ የሚያደርጉት እንደዚሁ ነው። 9 አሁንም የሚሉህን ስማቸው፤ ነገር ግን በላያቸው የሚገዛው ንጉሥ የሚያደርግባቸውን እንዲያውቁ አጥብቀህ አስጠንቅቃቸው"። 10 ስለዚህ ሳሙኤል ንጉሥ ለጠየቀው ሕዝብ የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ነገራቸው። 11 እርሱም እንዲህ አላቸው፥ "ንጉሡ በላያችሁ ላይ የሚገዛው እንዲህ ነው። ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ፈረሰኞች እንዲሆኑና በሠረገላዎቹ ፊት እንዲሮጡ በሠረገላዎቹ ላይ ይሾማቸዋል። 12 እርሱም ለራሱ ሻለቃዎችንና ሃምሳ አለቃዎችን ይሾማል። አንዳንዶቹ መሬቱን እንዲያርሱ፥ ሌሎቹም እህሉን እንዲያጭዱ፥ አንዳንዶቹ የጦር መሳሪያዎችንና ሌሎቹም የሠረገላ ዕቃዎችን እንዲሠሩለት ያደርጋቸዋል። 13 ሴቶች ልጆቻችሁን ደግሞ ሽቶ ቀማሚዎች፥ ወጥ ሠሪዎችና እንጀራ ጋጋሪዎች እንዲሆኑ ይወስዳቸዋል። 14 በጣም ምርጥ የሆነውን መሬታችሁን፥ የወይን ቦታችሁንና የወይራ ዛፋችሁን ወስዶ ለአገልጋዮቹ ይሰጣቸዋል። 15 ከእህላችሁና ከወይናችሁ አንድ ዐሥረኛውን ወስዶ ለሹማምንቱና ለአገልጋዮቹ ይሰጣቸዋል። 16 ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁን፥ ከወጣት ልጆቻችሁና ከአህዮቻችሁ የተመረጡትን ይወስዳል፤ ሁሉንም ለእርሱ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል። 17 ከበግና ከፍየል መንጋዎቻችሁ አንድ ዐሥረኛውን ይወስዳል፥ እናንተም አገልጋዮቹ ትሆናላችሁ። 18 በዚያም ቀን ለራሳችሁ ስለመረጣችሁት ንጉሥ ታለቅሳላችሁ፤ ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር አይመልስላችሁም”። 19 ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን ለመስማት እምቢ አሉ፤ 20 ሳሙኤልንም፥ “አይሆንም፥ ንጉሣችን እንዲፈርድልን፥ በፊታችን እንዲሄድና ጦርነቶቻችንን እንዲዋጋልን፥ እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ለእኛም ንጉሥ ሊሆንልን ይገባል” አሉት። 21 ሳሙኤል የሕዝቡን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ እርሱም በእግዚአብሔር ጆሮ ደግሞ ተናገረው። 22 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “ቃላቸውን ታዘዝና ንጉሥ አድርግላቸው” አለው። ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤልን ሰዎች፥ “እያንዳንዱ ወደገዛ ከተማው ይሂድ” አላቸው።
ጸሐፊው ሰው ወይም እንስሳ ከሳሙኤል ልጆች አምልጠው ይሮጡ የነበር ይመስል፣ የሳሙኤልም ልጆች ሰውና እንስሳ በተጨባጭ ያሳድዱ የነበሩ ይመስል፣ ሕዝቡ ለሳሙኤል ልጆች ስለሚሰጠው ገንዘብ ይናገራል፡፡ (ምትክ ቃል ተመልከት)
ክፉ ለሚያደርጉ በማድላት ይፈርዳሉ
አንድ ሰው የሚኖርበት መንገድ እንደ ጎዳና ተገልጾአል፡፡ አት፡- አንተ የምታደርጋቸውን ነገሮች አያደርጉም ወይም አንተ ታደርገው እንደ ነበር ጽድቅ የሆነውን ነገር አያደርጉም ነበር፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችል ትርጉሞች፣ 1) "እንዲፈርድልን የሕዝቦችን ሁሉ ነገሥታት የሚመስል ንጉሥ ሹምልን' ወይም 2) "የሕዝቦች ነገሥታት በሚፈርዱላቸው መንግድ የሚፈርድልን ንጉሥ ሹምልን'
አለቆቹ በስህተት ንጉሡና ከእርሱም በኋላ ልጆቹ በጽድቅ ይገዛሉ ብለው አመኑ፡፡
ሕዘቡ ምግባረ ብልሹ የሆኑ ልጆቹን አስውግዶ ሌሎች የታመኑ ፈራጆችን እንዲሾምላቸው ሳይሆን ሌሎች አገራት እንዳላቸው ዓይነት በላያቸው ላይ የሚገዛ ንጉሥ በመፈለጋቸው ሳሙኤል ደስተኛ አልሆነም፡፡
ቢዘህ ስፍራ "ቃል' የሕዝቡን ፈቃድና ፍላጎት የሚያመልክት ምትክ ቃል ነው፡፡ (ምትክ ቃል ተመልከት)
ሕዝቡ የተቃወሙት ምግባረ ብልሹ የሆኑትን ፈራጆች ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር ንጉሣቸው እንዳይሆን እየተቃወሙት እንደ ነበር እግዚአብሔር ያውቅ ነበር፡፡
ይህ ከብዙ ዓመታት በፊት እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት ነጻ ማውጣቱን ያመለክታል፡፡
"አሁን እንድታደርግ የሚጠይቁህን አድርግ'
ስታስጠነቅቃቸው የምር አድርገው
የንጉሥ ወግ መውሰድ ይሆናል፡፡ ይህ የሚወስዳቸውን ነገሮች ዝርዝር ይጀምራል፡፡
ወግ የሚለው የነገር ስም በማሰሪያ አንቀጽነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "በላያችሁ የሚነግሠው ንጉሥ የሚያደርገው እንዲህ ነው' ወይም "በላያችሁ የሚነግሠው ንግሥ የሚሠራው እንዲህ ነው' (የነገር ስም ተመልከት)
ወደ ጦርነት ሰረጋላ ያስነዳቸዋል
ወደ ጦርነት ፈረሶችን ይጋልባሉ
ሳሙኤል ንጉሥ የሚስዳቸውን ነገሮች መናገሩን ቀጠለ፡፡
ሰውነቱን የሚቀባው መልካም ሽታ ያለው ዘይት መሥራት
የወይራ ዛፍ ማሳ
እህላቸውን በአሥር እኩል ቦታ መክፈልና ከእነዚያ ክፍሎች አንዱን ለንጉሥ አለቆችና አገልጋዮች መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ (ክፍልፋይ ተመልከት)
በወይን እርሻቸው ያመረቱትን በአሥር እኩል ቦታ መክፈልና ከእነዚያ ክፍሎች አንዱን ለንጉሥ አለቆችና አገልጋዮች መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ (ክፍልፋይ ተመልከት)
እነዚህ የንጉሡ ሠራዊት አዛዦች ናቸው፡፡
ሳሙኤል ንጉሥ የሚስዳቸውን ነገሮች መናገሩን ቀጠለ፡፡
መንጋቸውን በአሥር እኩል ቦታ መክፈልና ከእነዚያ ክፍሎች አንዱን ለንጉሥ አለቆችና አገልጋዮች መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ አንድ አሥረኛን በ1ሳሙኤል 8፡15 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት (ክፍልፋዮች ተመልከት)
"ባሮቹ እንደሆናችሁ ይሰማችኋል'
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡-1)ከንጉሡ እንዲያድናቸው ሕዝቡ እግዚአብሔርን ይጠይቃሉ 2)የከፋ አገዛዙን አንዲያቆም ሕዝቡ ንጉሡን ይጠይቃሉ
በዚህ ስፍራ የእግዚአብሔር ጆሮች የሚለው እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ ሕዝቡ ያሉትን ሁሉ በመድገም ሳሙኤል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ አት፡- ለእግዚአብሔር ደገማቸወ (ተለዋጭ ስም ተመልከት)
"ቃላቸውን' የሚለው ምትክ ቃል የሕዝቡን ፈቃድ ያመለክታል፡፡ አት፡- "ሕዝቡን ታዘዝ' (ምትክ ቃል ተመልከት)
አንድን ሰው በላያቸው ላይ አንግሥላቸው፡፡ አንድን ሰው ንጉሥ ማድረግን በሚመለከት የተለመደ ቃል በቋንቋህ ካለ ተጠቀም፡፡
"ወደ ቤት'
1 ከብንያም ወገን ጽኑ ኃያል የሆነ አንድ ሰው ነበር። ስሙ ቂስ ሲሆን እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጽሮር ልጅ፥ የብኮራት ልጅ፥ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ ነበር። 2 እርሱም ሳኦል የሚባል መልከ መልካም ወጣት ልጅ ነበረው። ከእርሱ የሚበልጥ መልከ መልካም ሰው በእስራኤል ሕዝብ መካከል አልነበረም። ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ ቁመቱ ረጅም ነበር። 3 የሳኦል አባት የቂስ ሴት አህዮች ጠፍተው ነበር። ስለዚህ ቂስ ልጁን ሳኦልን፥ “ከአገልጋዮቻችን አንዱን ውሰድ፤ ተነሥናም አህዮቹን ፈልግ” አለው። 4 ስለዚህ ሳኦል በኮረብታማው በኤፍሬም አገር በኩል አልፎ ወደ ሻሊሻ ምድር ሄደ፥ ነገር ግን አላገኟቸውም። ከዚያም በሻዕሊም ምድር በኩል አለፉ፥ ነገር ግን በዚያ አልነበሩም። ከዚያም በብንያማውያን ምድር በኩል አለፉ፥ ነገር ግን አላገኟቸውም። 5 ወደ ጹፍ ምድር በመጡ ጊዜ፥ ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን አገልጋዩን፥ "ና እንመለስ፥ አለበለዚያ አባቴ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ ይጀምራል" አለው። 6 ነገር ግን አገልጋዩ እንዲህ አለው፥ “ስማኝ፥ በዚህ ከተማ ውስጥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ። እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረው ነገር ሁሉ ይፈጸማል። ወደዚያ እንሂድ፤ በየትኛው አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን ሊነግረን ይችል ይሆናል"። 7 ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን፥ "ታዲያ ወደ እርሱ የምንሄድ ከሆነ ለዚያ ሰው ምን ልንሰጠው እንችላለን? እንጀራው ከከረጢታችን አልቋል፥ ለእግዚአብሔር ሰው የምናቀርበው ምንም ስጦታ የለንም። ምን አለን?"አለው። 8 አገልጋዩም ለሳኦል፥ "ይኸውና፥ የሰቅል ጥሬ ብር አንድ አራተኛው አለኝ፥ በየትኛው አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ" ሲል መለሰለት። 9 (ቀደም ሲል በእስራኤል ውስጥ፥ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ በሚሄድበት ጊዜ፥ "ኑ፥ ወደ ባለ ራዕዩ እንሂድ" ይል ነበር። የዛሬው ነቢይ ቀደም ሲል ባለ ራዕይ ተብሎ ይጠራ 10 ነበር።)ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን፥”መልካም ብለሃል። ና፥ እንሂድ“ አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወደነበረበት ከተማ ሄዱ። 11 ኮረብታው ላይ ወዳለው ከተማ በመውጣት ላይ እያሉ ወጣት ሴቶች ውሃ ለመቅዳት ሲወጡ አገኟቸው፤ ሳኦልና አገልጋዩም፥”ባለ ራዕዩ በዚህ አለ? “ በማለት ጠየቋቸው። 12 እነርሱም እንዲህ በማለት መለሱላቸው፥ "አዎን፤ ተመልከቱ፥ እንዲያውም ከፊታችሁ እየቀደመ ነው። ዛሬ ሕዝቡ በኮረብታው ራስ ላይ ስለሚሠዉ ወደ ከተማው ይመጣልና ፍጠኑ። 13 ወደ ከተማው እንደገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ራስ ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን የሚባርከው እርሱ ስለሆነ፥ እርሱ ከመምጣቱ በፊት ሕዝቡ አይበሉም፤ ከዚያ በኋላም የተጋበዙት ይበላሉ። ወዲያውኑ ታገኙታላችሁና አሁን ወደ ላይ ውጡ።” 14 ስለዚህ ወደ ላይ ወደ ከተማው ወጡ። ወደ ከተማይቱ በመግባት ላይ እያሉም ሳሙኤል ወደ ኮረብታው ራስ ለመውጣት በእነርሱ አቅጣጫ ሲመጣ አዩት። 15 ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል እንዲህ ሲል ገልጦለት ነበር፥ 16 “ነገ በዚህ ሰዓት ከብንያም ምድር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፥ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መስፍን እንዲሆን ትቀባዋለህ። እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናቸዋል። እርዳታ በመፈለግ መጮኻቸው ወደ እኔ ደርሷልና ሕዝቤን በርኅራኄ ተመልክቻለሁ።” 17 ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፥”ስለ እርሱ የነገርኩህ ሰው ይህ ነው! ሕዝቤን የሚገዛው ሰው እርሱ ነው።“ 18 ከዚያም ሳኦል በበሩ አጠገብ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፥”የባለ ራዕዩ ቤት የት እንደሆነ ንገረኝ“ አለው። 19 ሳሙኤልም ለሳኦል እንዲህ በማለት መለሰለት፥”ባለ ራዕዩ እኔ ነኝ። ከእኔ በፊት ቀድማችሁ ወደ ኮረብታው ራስ ውጡ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር ትበላላችሁና። ነገ ጠዋት በአዕምሮህ ያለውን ነገር ሁሉ እነግርህና አሰናብትሃለሁ። 20 ከሦስት ቀን በፊት ጠፍተው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋልና ስለ እነርሱ አታስብ። የእስራኤል ሁሉ ምኞት የተቀመጠው በማን ላይ ነው? በአንተና በአባትህ ቤት ሁሉ ላይ አይደለም? “ 21 ሳኦልም፥ "ከእስራኤል ነገዶች ትንሹ የሆነው ብንያማዊ አይደለሁም? ጎሳዬስ ከብንያም ነገድ ጎሳዎች ሁሉ የመጨረሻው አይደለም? ታዲያ እንዲህ ባለ ሁኔታ ለምን ትናገረኛለህ?"ሲል መለሰለት። 22 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ አዳራሹ አስገብቶ ሠላሳ ከሚያህሉ ከተጋበዙት ሰዎች ከፍ ባለው ስፍራ ላይ አስቀመጣቸው። 23 ሳሙኤልም ወጥ ሠሪውን፥ "'ለብቻ አስቀምጠው' ብዬ የሰጠሁህን ድርሻ አምጣው" አለው። 24 ወጥ ሠሪውም በመሥዋዕቱ ጊዜ ያነሣውን ጭኑንና ከእርሱ ጋር ያለውን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ከዚያም ሳሙኤል፥ "የተቀመጠልህን ተመልከት! ለአንተ እስከተወሰነው ሰዓት ድረስ የቆየልህ ነውና ብላው። አሁን 'ሕዝቡን ጋብዣለሁ' ማለት ትችላለህ" አለው። ስለዚህ በዚያን ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ። 25 ከኮረብታው ራስ ወደ ከተማው በወረዱ ጊዜ፥ በቤቱ የጣሪያ ወለል ላይ ሳሙኤል ከሳኦል ጋር ተነጋገረ። 26 ከዚያም በነጋ ጊዜ ሳሙኤል በጣሪያው ወለል ላይ ሳኦልን ተጣርቶ፥ "መንገድህን እንድትሄድ አሰናብትህ ዘንድ ተነሥ" አለው። ስለዚህ ሳኦል ተነሣ፥ እርሱና ሳሙኤል ሁለቱም ወደ ጎዳናው ሄዱ። 27 ወደ ከተማው ዳርቻ በመሄድ ላይ እያሉ፥ ሳሙኤል ሳኦልን፥ "አገልጋዩ ከፊታችን ቀድሞ እንዲሄድ ንገረው፥ (እርሱም ቀድሞ ሄደ) አንተ ግን የእግዚአብሔርን መልዕክት እንዳስታውቅህ እዚህ ጥቂት መቆየት አለብህ" አለው።
በእነዚህ ቁጥሮች ጸሐፊው የሚሰጠው የታሪካዊ ዳራ መረጃ ለአንባቢ መናገር የሚቻልበት ሌላ መንገድ በቋንቋህ ካለ እዚህ ጋ መጠቀም ትችላለህ፡፡ (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ባላጠጋ ሰው ነበር 2) የመሣፍንት ዘር ነበር 3) ኃያልና ጎበዝ ሰው ነበር
እነዚህ የሳኦል የትውልድ ሐረግ ሰዎች ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ብንያማዊ ከብንያም ነገድ የሆነ ሰው ነው
ሲታይ መልካም የሆነ
በእስራኤል የነበሩ ሌሎች ረጃጅም ሰዎች ትከሻው ጋ አይደርሱም ነበር፡፡
ጸሐፊው የታሪካዊ ዳራ መረጃ መስጠቱን ጨርሶ (1ሳሙኤል 9፡1-2) የታሪኩን አዲስ ዋና ክፍል ይጀምራል፡፡
"እያደረግህ ያለውን አቁምና ሂድ'
እነዚህ ሁሉ በእስራኤል ውስጥ ያሉ አካባቢዎች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ሁሉም አህዮችን የሚያመልክቱ ናቸው፡፡
ይህ ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን የሚገኝ በእስራኤል ውስጥ ያለ አካባቢ ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ይህ ሐረግ በአብዛኛው የእግዚአብሔር ነቢይ ማለት ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 2፡27 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ አት፡- "ከእግዚአብሔር ቃል ሰምቶ የሚናገር ሰው'
"አህዮቹን ለማግኘት የትኛውን መንገድ መሄድ አለብን?'
ሥጦታ መሥጠት ለእግዚአብሔር ሰው የአክብሮት ምልክት ነው፡፡
ይህ ሐረግ በአብዛኛው የእግዚአብሔር ነቢይ ማለት ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 2፡27 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ አት፡- "ከእግዚአብሔር ቃል ሰምቶ የሚናገር ሰው'
"የሰቅል አንድ አራተኛ'፡፡ ሰቅል በብሉይ ኪዳን አገልግሎት ይሰጥ የነበረ የገንዘብ ዓይነት ነው፡፡ (የመጽሐፍ ቅዱስ ገንዘቦችና ክፍልፋዮች ተመልከት)
ይህ በዕብራዊ ጸሐፊ የተጨመረ ባሕላዊ መረጃ ነው፡፡ ይህንን መረጃ በዚህ ስፍራ ማስቀመጥ በቋንቋህ የተለመደ ካልሆነ ወደ ቁጥር 11 መጨረሻ ሊወሰድ ይችላል፡፡ (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ተመልከት)
"ባለ ራእይ የሚለው ዛሬ ነቢይ ለሚባለው የጥንት መጠሪያ ነበር፡፡'
ይህ በመገናኛው ድንኳን መከናወን ያለበት የኃጢአት መሥዋዕት ሳይሆን፣ የበዓል ወይም የበኩራት መሥዋዕቶችን የሚመለክት ይመስላል፡፡
ይህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትና ቁርባን ለማቅርብ ሕዝቡ ቅዱስ ቦታ ብለው የሰየሙት ስፍራ ነው፡፡ ጸሐፊው በከተማይቱ ዙሪያ ካለው ቅጥር ውጪ ይገኝ እንደ ነበር ይጽፋል፡፡
ጸሐፊው ታሪኩን መናገር ያቆምና አንባቢው በመቀጠል የሚሆነውን እንዲረዳ የታሪካዊ ዳራ መረጃ ይሰጣል፡፡ (ታሪካዊ ዳራ መረጃ ተመልከት)
በዚህ ስፍራ ልዑል የሚለው ቃል ንጉሥ በሚለው ፈንታ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን እግዚአብሔር የመረጠው ሰው ይህ ነው፡፡ (የማያስደስትን ቃል በሌላ ቃል መጠቀም ተመልከት)
"ከብንያም ነገድ የሆኑ ሰዎች የሚኖሩበት ምድር'
በዚህ ስፍራ እጅ የሚለው ቃል ቁጥጥር ለሚለው ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "ከፍልስጥኤማውያን ቁጥጥር' ወይም "ከእንግዲህ ወዲያ ፍልስጥኤማውያን አይቆጣጠሩአቸውም'
"ሕዝቤ መከራ እያዩ ናቸው እኔም ልረዳቸው እፈልጋለሁ'
"እግዚአብሔር ሳሙኤልን አለው'
"የእግዚአብሔር ነቢይ'
እነዚህ ጥያቄዎች ሳኦል እስራኤል የሚፈልጉት እግዚአብሔር ንጉሥ እንዲሆን የወደደው ሰው ለመሆኑ የጥልቅ መረዳት ማሳያ ናቸው፡፡ ጥያቄዎቹ በገላጭ አባባል ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አት፡- "የእስራኤል ምኞት ሁሉ ያረፈው በአንተ ላይ እንደሆነ ልታውቅ ይገባሃል፡፡ ዓይናቸውን በአንተና በአባትህ ቤት ላይ ጥለዋል፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች ተመልከት)
ብንያም በእስራኤል ትንሹ ነገድና ሌሎች እስራኤላውያን እንደማይጠቅም ነገድ የሚቆጥሩት ስለሆነ ሳኦል ግርምቱን እየገለጠ ነው፡፡ በተጨማሪም፣ ሳኦል አባል የሆነበትን ጎሳ ብንያማውያን እንደማይጠቅም ይቆጥሩት ነበር፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በገላጭ አባባል ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አት፡- እኔ ከነገዶች ሁሉ አስፈለጊነቱ የመጨረሻ ዝቅተኛ ከሆነው ከብንያም ነገድ ነኝ፡፡ ጎሳዬም በነገዳችን አስፈላጊነቱ የመጨረሻ ዝቅተኛ ጎሳ ነው፡፡ የእስራኤል ሕዝብ እኔንና ቤተሰቤን አስፈላጊ ነገር እንድናደርግ እንደሚፈለጉን ለምን እንደምትነግረኝ ልረዳ አልቻልኩም፡፡ (አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች ተመልከት)
መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ስፍራ በአቅራቢያው ሰዎች በአንድነት የሚመገቡበት ትልቅ ሕንፃ እንደነበር አንባቢው እንደሚያውቅ ጸሐፊው ይገምታል፡፡
የክብር መቀመጫ
"30 ሰዎች' (ቁጥሮች ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ሳኦል ከስጋው ጋር ሊበላው የነበረ ሌላ ምግብ ወይም 2) የወይፈኑ ሌሎች ክፍሎች
በመጀመሪያው ቋንቋ ተናጋሪው ማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ወጥ ቤቱም ለሳኦል እየተናገረ ሊሆን ይችላል፡፡ አት፡- "ወጥ ቤቱም አለ'
ይህ ለቤተሰብና ለእንግዶች ለመብላት፣ ለመጎብኘትና ለመተኛት የተለመደ ቦታ ነው፡፡ በምሽትና በሌሊት ከቤቱ ውስጠኛ ክፍል ይልቅ የመቀዝቀዝ ሁኔታ ይታይበታል፡፡
ሳኦል በሰገነቱ ላይ ያደርግ የነበረው ግልጽ ሊደረግ ይቻላል፡፡ አት፡- "ሳኦል በሰገነቱ ላይ ተኝቶ ሳለ፣ ሳሙኤል ጠራውና አለ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
እነዚህን ቃላት ሁሉ ሳሙኤል ተናግሮ ሊሆን ይችላል፡፡ አት፡- "ከፊታችን ይለፍ፣ ከፊታችንም ሲያለፍ፣ አንተ ቆይ'
1 ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ጠርሙስ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። እርሱም እንዲህ አለው፥ "በርስቱ ላይ ገዢ እንድትሆን እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ 2 ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፥ የብንያም ወሰን በሆነው በጼልጻህ፥ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፥ 'ስትፈልጋቸው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋል። አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፥ "ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?" በማለት ተጨንቋል“ ይሉሃል። 3 ከዚያ አልፈህ ትሄድና በታቦር ወደሚገኘው ወደ በሉጥ ዛፍ ትመጣለህ። ወደ ቤቴል፥ ወደ እግዚአብሔር የሚሄዱ አንደኛው ሦስት የፍየል ጠቦቶች ይዞ፥ ሌላኛው ሦስት ዳቦ ተሸክሞ፥ ሌላኛው ደግሞ ወይን ጠጅ የተሞላ አንድ አቁማዳ ተሸክሞ ሦስት ሰዎች ይገናኙሃል። 4 ሰላምታ ከሰጡህ በኋላ ሁለት ዳቦ ይሰጡሃል፥ ከእጃቸውም ትቀበላቸዋለህ። 5 ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤም የጦር ሠፈር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ። ወደ ከተማው በምትደርስበት ጊዜ፥ አንድ የነቢያት ቡድን በፊታቸው መሰንቆ፥ ከበሮ፥ እምቢልታና በገና ይዘው ከተራራው ሲወርዱ ትገናኛቸዋለህ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገራሉ። 6 የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ይመጣብሃል፥ አንተም ከእነርሱ ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰው ሆነህም ትለወጣለህ። 7 እነዚህ ምልክቶች በሚፈጸሙልህ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ ያገኘውን ሁሉ አድርግ። 8 ቀድመኸኝ ወደ ጌልገላ ውረድ። ከዚያም የሚቃጠለውን መባ ለማቅረብና የሰላሙን መባ ለመሠዋት ወደ አንተ እወርዳለሁ። ወደ አንተ እስክመጣና ልታደርገው የሚገባህን እስከማሳይህ ድረስ ሰባት ቀን ቆይ።” 9 ሳኦል ከሳሙኤል ተለይቶ ለመሄድ ፊቱን ባዞረ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ሰጠው። እነዚህ ምልክቶች ሁሉ በዚያው ቀን ተፈጸሙ። 10 እነርሱም ወደ ኮረብታው በመጡ ጊዜ፥ የነቢያት ቡድን ተገናኙት፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል መጣበት፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ተናገረ። 11 ቀድሞ ያውቁት የነበሩት ሁሉ እርሱም ከነቢያት ጋር ትንቢት ሲናገር ባዩት ጊዜ፥ እርስ በእርሳቸው፥ “የቂስን ልጅ ምን ነካው? አሁን ሳኦል ከነቢያት አንዱ መሆኑ ነው?” ተባባሉ። 12 በዚያው ስፍራ የነበረ አንድ ሰው፥ “አባታቸው ማነው?” ሲል መለሰ። በዚህ ምክንያት፥ “ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ነው?” የሚል ምሳሌአዊ አባባል የተለመደ ሆነ። 13 ትንቢት መናገሩን በጨረሰ ጊዜ ወደ ተራራው ራስ መጣ። 14 ከዚያም የሳኦል አጎት፥ እርሱንና አገልጋዩን፥ “የት ነበር የሄዳችሁት?” አላቸው። እርሱም፥ “አህዮቹን ለመፈለግ ነበር፤ ልናገኛቸው እንዳልቻልን ባየን ጊዜ ወደ ሳሙኤል ሄድን” ብሎ መለሰለት። 15 የሳኦልም አጎት፥ “ሳሙኤል የነገረህን እባክህ ንገረኝ" አለው። 16 ሳኦልም አጎቱን፥ "አህዮቹ መገኘታቸውን በግልጽ ነገረን" ብሎ መለሰለት። ሳሙኤል ነግሮት የነበረውን የንግሥና ጉዳይ ግን አልነገረውም። 17 ሳሙኤል ሕዝቡን በአንድነት በእግዚአብሔር ፊት ወደ ምጽጳ ጠራቸው። 18 እርሱም የእስራኤልን ሕዝብ እንዲህ አላቸው፥”የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፥ 'እስራኤልን ከግብፅ አወጣሁት፥ ከግብፃውያን እጅና ካስጨነቋችሁ መንግሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ'። 19 ነገር ግን ዛሬ እናንተ ከመከራና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ተቃውማችኋል፤ እርሱንም፥ 'በላያችን ላይ ንጉሥ አንግሥልን' ብላችሁታል። አሁን በየነገዳችሁና በየጎሣችሁ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ"። 20 ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ አቀረበ፥ የብንያም ነገድም ተመረጠ። 21 ከዚያም የብንያምን ነገድ በየጎሣቸው አቀረበ፤ የማጥሪ ጎሣም ተመረጠ፤ የቂስ ልጅ ሳኦልም ተመረጠ። ነገር ግን በፈለጉት ጊዜ ሊያገኙት አልቻሉም። 22 ከዚያም ሕዝቡ”ገና የሚመጣ ሌላ ሰው አለ? “ በማለት እግዚአብሔርን ተጨማሪ ጥያቄዎች ለመጠየቅ ፈለጉ። እግዚአብሔርም፥”ራሱን በዕቃዎቹ መካከል ደብቋል" በማለት መለሰላቸው። 23 ከዚያም ሮጠው ሄዱና ሳኦልን ከዚያ አመጡት። በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜ፥ ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ ቁመቱ ረጅም ነበር። 24 ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ "እግዚአብሔር የመረጠውን ይህንን ሰው ታዩታላችሁ? በሕዝቡ ሁሉ መካከል እንደ እርሱ ያለ የለም! “ አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ፥”ንጉሥ ለዘላለም ይኑር! “ በማለት ጮኹ። 25 ከዚያም ሳሙኤል የንግሥናን ደንብና ልማዶች ለሕዝቡ ነገራቸው፥ በመጽሐፍ ጽፎም በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጣቸው። ከዚያም ሳሙኤል እያንዳንዱ ወደ ገዛ መኖሪያው እንዲሄድ ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ። 26 ሳኦልም ደግሞ በጊብዓ ወደሚገኘው መኖሪያው ሄደ፥ እግዚአብሔር ልባቸውን የነካቸው አንዳንድ ኃያላን ሰዎችም ከእርሱ ጋር ሄዱ። 27 አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች ግን፥”ይህ ሰው ሊያድነን እንዴት ይችላል? “ አሉ። እነዚህ ሰዎች ሳኦልን ናቁት፥ ምንም ዓይነት ስጦታዎችንም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።
በእስራኤል ባሕል፣ አንድ ነቢይ በአንድ ሰው ራስ ላይ ዘይት ሲያፈስስ፣ ግለሰቡ ከአግዚአብሔር ዘንድ በረከት ይቀበላል፡፡
ከተጠበሰ የሸክላ አፈር የሚሠራ ትንሽ መያዣ
ሳሙኤል ለጥያቄው የሚሰጠውን መልስ ያውቃል፡፡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር እንደመረጠው ሳኦልን እያሳሰበው ነው፡፡ አት፡- "በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር በእርግጥ ቀብቶሃል፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
አሁን የሳኦል አባት ስለ ሳኦል መጨነቅ ጀመረ ሊያገኘውም ፈለገ፡፡
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
እጆች ለግለሰቦች ተለዋጭ ስም ነው፡፡ "ከእነርሱ ውሰድ' ወይም "ተቀበል' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)
የሚመታ የታምቡር ራስ የሚመስል ያለው እና ሲንቀጠቀጥ ድምጽ የሚሰጡ የብረት ቁራጮች በጎኑ ዙሪያ ያለው የሙዚቃ መሣሪያ ነው፡፡ (የማይታወቁትን መተርጎም ተመልከት)
ይወርድባሃል የሚለው ቃል የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ላይ ተጽእኖ ያድርጋል ማለት ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ሳኦልን እንዲተነብይና እንደ ሌላ ሰው እንዲከውን ያደርገዋል ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
በዚህ ስፍራ ሳሙኤል ስለ ሳኦል እጆች ነገሮችን ለማግኘት እንደሚጥር ግለሰብ አድርጎ ይናገራል፡፡ አት፡- "ለማድረግ ትክክል እንደሆነ የምታስበውን ሁሉ አድርግ' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየትን ተመልከት)
እግዚብአብሔር ሳኦልን ቀድሞ ያስብበት ከነበረበት መንገድ በተለየ መንገድ እንዲያስብ አስቻለው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ሳሙኤል የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ሳኦል እንደሚሮጥና እርሱንም ሙሉ ለሙሉ እንደሚቆጣጠር ግለሰብ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 10፡6 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ አት፡- "የእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠረው' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየትን ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ሕዝቡ መረጃ እየጠየቀ ነው 2) ሳኦል አስፈላጊ ሰው አይደለም የሚል ትርጉም ያለው አሳብ ገላጭ ጥያቄ ነው፡፡ አት፡- "ቂስ አስፈላጊ ሰው አይደለም፣ ልጁ ነቢይ ሆነ የሚለው እውነት ሊሆን አይችልም፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
"ሳኦል የቂስ ልጅ'
ይህ ሰው፣ ነቢይ መሆን የአንድ ሰው ወላጆች እነማን ከመሆናቸው ጋር የሚያያዝው ምንም ነገር እንደሌለ ሕዝቡን ለማሳሳብ አሳብ ገላጭ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ ይህ ጥያቄ በገላጭ አባባል ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የእነዚህ የሌሎቹ ነቢያት ወላጆች እነማን መሆናቸው አስፈላጊ ነገር አይደለም፡፡ ቁም ነገሩ፣ በሚያስገርም ሁኔታ፣ ሳኦል የእግዚአብሔርን መልእክት መናገሩ ነው፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች ተመልከት)
ይህ በእስራኤላውያን መካከል ምሳሌ ሆነ፡፡ አንድ ሰው ከዚያ በፊት አድርጎት የማያውቀውን ነገር ሳይታሰብ አድርጉት ሲገኝ አድናቆትን ለመግለጽ ሰዎች በግልጽ ይህን ይላሉ፡፡ አት፡- "ሰዎች አንዳንድ ዘገባዎችን ማመን ባቃታቸው ጊዜ፣ ከዚያም የተነሳ፣ ለሳኦል ስለሆነው አሰቡና እንዲህ አሉ፣ ‘በውኑ ሳኦል ከነቢያት አንዱ ነውን?'' (ምሳሌዎችንና እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
"ከዚያም የሳኦል የአባቱ ወንድም እንዲህ አለው'
"እግዚአብሔር የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን እንደሾመው ሳኦል ለአጎቱ አልነገረውም'
እስራኤል የሚለው ስም ለእስራኤል ሕዝብ ምትክ ስም ነው፡፡ አት፡- "የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ አወጣሁ' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ሳሙኤል ፀሐይ ለመጨረሻ ከጠለቀችበት አንስቶ ያለውን ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ እስራኤል እግዚአብሔርን መቃወም ከጀመሩበት አንስቶ ስላለው ጊዜ ይናገራል፡፡
እጅ የሚለው ቃል ለኃይል ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "የግብጻውያን ኃይል … የመንግሥታት ሁሉ ኃይል'
"የሚገዛንን ንጉሥ ስጠን'
"በየነገዳችሁና በየወገናችሁ በአንድ ተሰበሰቡና በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ኑ'
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ እግዚአብሔር የመረጠውን ሕዝቡ ያወቀበት መንግድ ብሎ አለመተረጎም እጅግ የተሻለ ነው፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር የብንያምን ነገደ መረጠ … እግዚአብሔር የማጥሪንን ወገን መረጠ … እግዚአብሔር የቂስን ልጅ ሳኦልን መረጠ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
በእስራኤል የነበሩ ሌሎች ረጃጅም ሰዎች ትከሻው ጋ አይደርሱም ነበር፡፡ ይህን በ1ሳሙኤል 9፡2 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ንግሥና የሚለው የነገር ስም በመጠሪያ ሐረግነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "ንጉሥ ሊከተላቸው የሚያስፈልጉ ወጎችና መመሪያዎች' (የነገር ስም ተመልከት)
የእግዚአብሔር የሰውን ልብ መንካት የእግዚአብሔር በአእምሮአቸው ውስጥ አንድን ነገር ማስቀመጥ ወይም አንድን ነገር እንዲያደርጉ ማንቀሳቀስ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር አስተሳሰባቸውን ስለቀየረ ከሳኦል ጋር ለመሄድ የፈለጉ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ይህ ማሽሟጠጥን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የሚውል አሳብ ገላጭ ጥያቄ ነው፡፡ አት፡- "ይህ ሰው ሊያድነን ኃይል የለውም፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
እጅግ አልወደዱትም ወይም ናቁት
1 አሞናዊው ናዖስ ሄዶ ኢያቢስ ገለዓድን ከበባት። የኢያቢስ ሰዎች ሁሉ ናዖስን፥ "ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እኛም እናገለግልሃለን" አሉት። 2 አሞናዊው ናዖስም፥ "የሁላችሁንም ቀኝ ዐይኖቻችሁን በማውጣት በመላው እስራኤል ላይ ኃፍረትን አመጣለሁ፥ በዚህ ቅድመ ሁኔታ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ" ብሎ መለሰላቸው። 3 የኢያቢስ ሽማግሌዎችም፥ "ወደ እስራኤል ወገኖች ሁሉ መልዕክተኞችን እንድንልክ ለሰባት ቀናት ታገሰን። ከዚያም የሚያድነን አንድም ባይኖር ለአንተ እንገዛለን" በማለት መለሱለት። 4 መልዕክተኞቹም ሳኦል ወደሚኖርበት ወደ ጊብዓ መጥተው የሆነውን ነገር ለሕዝቡ ነገሯቸው። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። 5 በዚህ ጊዜ ሳኦል ከእርሻ በሬዎቹን እየነዳ መጣ። ሳኦልም፥ "ሕዝቡ ምን ሆኖ ነው የሚያለቅሰው?" አለ። እነርሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሉትን ለሳኦል ነገሩት። 6 ሳኦል የነገሩትን በሰማ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል መጣበት፥ እጅግም ተቆጣ። 7 የበሬዎቹን ቀንበር ወስዶ ፈለጣቸውና ወደ እስራኤል ወሰኖች ሁሉ በመልዕክተኞች እጅ ላከው። እርሱም፥ "ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ በማይመጣው ሁሉ በበሬዎቹ ላይ እንዲህ ይደረግበታል" አለ። ከዚያም ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍርሃት በሕዝቡ ላይ ወደቀ፥ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰብስበው መጡ። 8 ቤዜቅ በተባለ ስፍራ በሰበሰባቸው ጊዜ፥ የእስራኤል ሰዎች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይሁዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ። 9 እነርሱም ለመጡት መልዕክተኞች፥ "ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፥ 'ነገ ፀሐይ ሞቅ በሚልበት ሰዓት እንታደጋችኋለን' ብላችሁ ንገሯቸው" አሏቸው። መልዕክተኞቹ ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሯቸው፥ እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው። 10 ከዚያም የኢያቢስ ሰዎች ናዖስን፥”ነገ እንገዛልሃለን፥ አንተም ደስ የሚያሰኝህን ልታደርግብን ትችላለህ“ አሉት። 11 በቀጣዩ ቀን ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ቡድን ከፈላቸው። ሊነጋጋ ሲል ወደ ጦር ሠፈሩ መካከል መጡ፥ አሞናውያንንም አጠቁ፥ ቀኑ እስኪሞቅ ድረስም አሸነፏቸው። በሕይወት የተረፉትም ከእነርሱ ሁለቱ አንድ ላይ ሆነው እስከማይታዩ ድረስ ተበታተኑ። 12 በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ሳሙኤልን፥ "'ሳኦል በእኛ ላይ እንዴት ይነግሣል?' ያለው ማን ነበር? እንድንገድላቸው ሰዎቹ ይምጡልን" አሉት። 13 ነገር ግን ሳኦል፥ "ዛሬ እግዚአብሔር እስራኤልን ታድጎታልና በዚህ ቀን ማንም መገደል የለበትም" አላቸው። 14 ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ "ኑ፥ ወደ ጌልገላ እንሂድና በዚያ መንግሥቱን እናድስ" አላቸው። 15 ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ሳኦልን አነገሡት። በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የሰላምን መባ ሠዉ፥ ሳኦልና የእስራኤል ሰዎችም ሁሉ እጅግ ደስ አላቸው።
ይህ ሰው የአብርሃም የወንድም ወይም የእኅት ልጅ የሎጥ ትውልድ የሆነ አሞናዊ ነው፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)፡፡
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
"ቆርጬ አወጣለሁ' ወይም "ጎትቼ አወጣለሁ'
"ውርደት አለብሳችኋለሁ' ወይም "አሳፋሪ ስም አለብሳችኋለሁ'
"7 ቀናት' (ቁጥሮች ተመልከት)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ወረደበት የሚለው ቃል የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ላይ ተጽእኖ ያድርጋል ማለት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ እንደ ንጉሣቸው ሕዝቡ በፍርሃት እንዲያከብሩትና ሠራዊቱን እንዲቀላቀሉ እንዲያደርግ ሳኦልን አስችሎታል፡፡ 1ሳሙኤል 10፡6ን እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ናዖስንና አሞናውያንን ለመወጋት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንዲመጡ ሳዖል ጥሪ እያስተላለፈ ነበር፡፡
እንደ ንጉሣቸው ሳኦልን በፍርሃት እንዲያከብሩት እግዚአብሔር ሕዘቡን አስቻለ፡፡ በውጤቱም ሰዎቹ ከሳኦል ጋር በቤዜቅ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡
ይህ በኢያቢስ ገለዓድ አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
"የእስራኤል ሰዎች 300,000፣ የይሁዳም ሰዎች 30,000 ነበሩ' (ቁጥሮች ተመልከት)
"አሉአቸው' የሚለው ሳሙኤልንና ሳሙኤልን ያመለክታል፡፡
"ከቀኑ እጅግ ሞቃት ከሆነው ክፍል በፊት' ወይም "ከቀትር በፊት'
እነዚህ የቦታዎች ስሞች ናቸው፡፡ በ1ሳሙኤል 11፡1 እንዴት እንደተረጎምሃቸው ተመልከት፡፡
ይህ የንጉሥ ስም ነው፡፡ ይህንን ስም በ1ሳሙኤል 11፡1 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ይህ ከንጋት በፊት አብዛኛው ሕዝብ ገና በሰፈሩ ተኝቶ የነበረበት ጊዜ ነው፡፡
"እግዚአብሔር እያየ ሳኦልን አነገሡት'
ከአሮን ወይም ከሌዊ ቤት ባይሆንም እንኳን መሥዋዕት ማቅረብ የሳሙኤል የእግዚአብሔር አገልግሎት ክፍል ነው፡፡
1 ሳሙኤል እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አላቸው፥”የነገራችሁኝን በሙሉ ሰምቻችኋለሁ፥ ንጉሥንም በላያችሁ ላይ አንግሼላችኋለሁ። 2 አሁንም፥ በፊታችሁ የሚሄድላችሁ ንጉሥ ይኸውላችሁ፤ እኔ አርጅቻለሁ፥ ጸጉሬም ሸብቷል፤ ልጆቼም ከእናንተ ጋር ናቸው። ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በፊታችሁ ኖሬአለሁ። 3 ይኸው በፊታችሁ ነኝ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ። የማንን በሬ ወስጃለሁ? የማንንስ አህያ ወስጃለሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? ዓይኖቼን ለማሳወር ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? መስክሩብኝና እመልስላችኋለሁ።“ 4 እነርሱም፥”አላታለልከንም፥ ግፍም አልሠራህብንም ወይም ከማንም እጅ ምንም ነገር አልሰረቅህም“ አሉ። 5 እርሱም፥”በእጄ ላይ ምንም እንዳላገኛችሁ ዛሬ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ምስክር ነው፥ እርሱ የቀባውም ምስክር ነው“ አላቸው። እነርሱም፥”እግዚአብሔር ምስክር ነው“ ብለው መለሱ። 6 ሳሙኤልም ሕዝቡን፥”ሙሴንና አሮንን የመረጣቸው፥ አባቶቻችሁንም ከግብፅ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር ነው። 7 አሁን እንግዲህ፥ እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ስለ ሠራላችሁ የጽድቅ ሥራ ሁሉ እንድሟገታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን አቅርቡ። 8 ያዕቆብ ወደ ግብፅ በመጣ ጊዜ አባቶቻችሁ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔር፥ ከግብፅ ምድር እየመሩ አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲቀመጡ ያደረጓቸውን ሙሴንና አሮንን ላከ። 9 እነርሱ ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፤ እርሱም የሐጾር ሠራዊት አዛዥ በሆነው በሲሣራ እጅ፥ በፍልስጥኤማውያን እጅና በሞአብ ንጉሥ እጅ ሸጣቸው፤ እነዚህ ሁሉ አባቶቻችሁን ተዋጓቸው። 10 እነርሱም ወደ እግዚአብሔር በመጮህ፥ "እግዚአብሔርን ትተን በኣልንና አስታሮትን በማገልገላችን ኃጢአት አድርገናል። አሁን ግን ከጠላቶቻችን እጅ አድነን፥ እኛም እናገለግልሃለን' አሉት። 11 ስለዚህ እግዚአብሔር ይሩበኣልን፥ ባርቅን፥ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ በሰላም እንድትኖሩ በዙሪያችሁ ባሉ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ ድልን ሰጣችሁ። 12 እናንተም የአሞን ሕዝብ ንጉሥ ናዖስ እንደመጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሆኖ እያለ፥ 'አይሆንም፥ ይልቁን በላያችን ላይ ንጉሥ መንገሥ አለበት' አላችሁኝ። 13 አሁንም እናንተ የመረጣችሁት፥ እንዲሆንላችሁ የጠየቃችሁትና እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ንጉሥ እንዲሆን የመረጠው ንጉሥ ይኸውላችሁ። 14 እናንተም እግዚአብሔርን ብትፈሩት፥ ብታገለግሉት፥ ድምፁንም ብትታዘዙና በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ባታምጹ ያን ጊዜ እናንተና በላያችሁ የሚገዛው ንጉሣችሁ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ተከታዮች ትሆናላችሁ። 15 የእግዚአብሔርን ድምፅ ባትታዘዙ፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ብታምጹ፥ ያን ጊዜ በአባቶቻችሁ ላይ እንደነበረ የእግዚአብሔር እጅ በእናንተ ላይ ይሆናል። 16 አሁንም፥ ራሳችሁን አቅርቡና እግዚአብሔር በዓይናችሁ ፊት የሚያደርገውን ይህንን ታላቅ ነገር ተመልከቱ። 17 ዛሬ የስንዴ መከር ነው አይደል? ነጎድጓድና ዝናብን እንዲልክ እግዚአብሔርን እጠራለሁ። ከዚያም ለራሳችሁ ንጉሥ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደረጋችሁት ክፋት ታላቅ እንደሆነ ታውቃላችሁ፥ ታያላችሁም“። 18 ስለዚህ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ጠራ፤ በዚያው ቀን እግዚአብሔር ነጎድጓድንና ዝናብን ላከ። ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን በጣም ፈሩ። 19 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሳሙኤልን፥ "እንዳንሞት፥ ስለ አገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። ለራሳችን ንጉሥ በመጠየቃችን በኃጢአታችን ሁሉ ላይ ይህንን ክፋት ጨምረናልና” አሉት። 20 ሳሙኤል እንዲህ ሲል መለሰላቸው፥ “አትፍሩ። ይህንን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችሁ አገልግሉት እንጂ ከእግዚአብሔር ፊታችሁን አትመልሱ። 21 የማይጠቅሙ ናቸውና ሊረዷችሁ ወይም ሊረቧችሁ የማይችሉትን ከንቱ ነገሮች አትከተሉ። 22 እግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ስለ ወደደ፥ ስለ ታላቅ ስሙ ሲል ሕዝቡን አይጥላቸውም። 23 ስለ እናንተ መጸለይን በመተው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ማድረግ ከእኔ ይራቅ። ይልቁንም፥ መልካሙንና ትክክለኛውን መንገድ አስተምራችኋለሁ። 24 ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩት፥ በሙሉ ልባችሁም በእውነት አገልግሉት። ያደረገላችሁን ታላላቅ ነገሮች አስቡ። 25 ክፉ በማድረግ ብትጸኑ ግን እናንተና ንጉሣችሁ ትጠፋላችሁ”።
እነዚህ መግለጫዎች ሳሙኤልና ሳኦል የኖሩትን የሕይወት ዓይነት ሕዝቡ በተጨባጭ ማየት ችሏል ማለት ነው፡፡ አት፡- "የንጉሡ ሕይወት ታይቷል … የእኔ ሕይወት ታይቷል' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
በዚህ ንግግሩ ሳሙኤል አንዳች ተገቢ ያልሆነ ነገር በማንም ላይ አድርጎ ከሆነ ሕዝቡ እንዲናገር እየሞገተ ነው፡፡ አት፡- "አሁን በፊታችሁ ቆሜያለሁ፡፡ ምንም ዓይነት ተገቢ ያልሆነ ነገር አድርጌ ከሆነ በእግዚአብሔርና በቀባው በንጉሡ ፊት እንድትናገሩ እጠይቃችኋለሁ፡፡' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
እንሰሳቶቻቸውን ያልሰረቀባቸውን ሰዎች ለማሳሳብ ሳሙኤል አሳብ ገላጭ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት፡- "እኔ ውድ የሆነ እንስሳ ፈጽሞ ከማንም አልሰረቅሁም' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
ሁልጊዜ ታማኝ እንደ ነበር ለመናገር ሳሙኤል ሌላ አሳብ ገላጭ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት፡- "እኔ ማንንም አልታለልኩም ወይም ከማንም ጉቦ አልተቀበልሁም፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
"ከእነዚህ ክፉ ነገሮች ማናቸውንም አድርጌ ከሆንሁ አሁን ተናገሩ፣ የወሰድኩትንም እመለሳለሁ፡፡ ማናኛውንም ስሕተት አስተካክላለሁ፡፡'
እነዚህ ሃረጎች ግለሰቡ ምን ሃብት እንዳፈራ ወይም ከሌሎች ወሮታን ለማግኘት ምን እንዳደረገ የሚገልጽ ነው፡፡ አት፡- ይህ ምንም እንዳልሰረቀ፣ ወይም ጉቦ እንዳልሰጠና እንዳልተቀበለ የተናገረበት ጨዋ መንገድ ነው፡፡
በመልካምነትና በዓላማ ለተሞላው፣ እግዚአብሔር ለእስራኤል ላደረገው ታሪክ ትኩረት እንዲሰጡ ሳሙኤል አየተጣራ ነው፡፡
"ለሲሣራ … ለፍልስጥኤማውያን … ለሞአብ ንጉሥ ኃይል'
እነዚህ የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
ይህ ባሮቻቸው እንዲሆኑ እግዚአብሔር ለጠላቶቻቸው አሳልፎ መስጠቱን የሚገልጽ ነው፡፡
(እነርሱ) የእስራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ነው
ይህ አንዳንዴ ይሩባአል በሚል ይተረጎማል፡፡ ይህ ሐሰተኛ አማልከትን ለመዋጋት የጻድቅ የክብርና የጥንካሬ ስም ነው፡፡
ሳሙኤል ከሕዝቡ የኃጢአት ኑዛዜና የእርዳታ ጥሪ በኋላ እግዚአብሔር ምን እንዳደረገላቸው ታሪኩን ይናገራል፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
እነዚህ እግዚአብሔር ያስነሳቸወ ጥቂት የመሳፍንት ስሞች ናቸው፡፡ ሳሙኤል ራሱን በዚህ ዝርዝር ውስጥ አካቷል፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
በዚህ ስፍራ ማገልገል ሐሰተኛ አማልክትን የማምለክን ተግባር ያመለክታል፡፡ አት፡- ሐሰተኛ አማልክትና ሴት አማልክትን አመለኩ (ምትክ ቃል ተመልከት)
ይህ አረፍተ ነገር ኃይልን ለማመልከት "እጅ' የሚለውን ቃል ይጠቀማል፡፡ አት፡- "የጠላቶቻችን ኃይል ወይም የበላይነት' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ይህ አረፍተ ነገር እግዚአብሔር ትናንትና ስላዳናቸው በእግዚአብሔር ስለመታመን በነገራቸው ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ሳሙኤልን በመቃወም ስላሰዩት ብርቱ ምላሽ ይናገራል፡፡
እነዚህ ሁለት ቃላት ሕዝቡ የፈለገው ንጉሥ ይህ ነው የሚል ተመሣሣይ ትርጉምና አጽንዖት አላቸው፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
ይህ ምን ያህል አስፈላጊ እነደሆነ አጽንዖት ለመስጠት እነዚህ ተመሣሣይ ቃላት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
ይህ እጁ በእነርሱ ላይ እነደሆነች ሁሉ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚቀጣ ይናገራል፡፡ በዚህ ስፍራ "እጅ' የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ኃይልና የበላይነት ይወክላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር አባቶቻችሁን እንደቀጣ ይቀጣችኋል' (ምትክ ቃል ተመልከት)
በዚህ ስፍራ "ዓይኖች' የሚለው ቃል የእስራኤልን ሕዝብ ይወክላል፡፡ አት፡- "የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሊያይ በሚችልበት ግልጽ ስፍራ' (ተለዋጭ ቃል ተመልከት)
ሳሙኤል የመከር ጊዜ እንደሆነ ያውቃል፡፡ በአብዛኛው በዚህ ጊዜ ዝናብ እንደማይዘንብ ስለዚህ የእግዚአብሔር ፍርድ በመሆኑ ዝናቡ መከራቸውን እንደሚያጠፋ ሕዝቡ እንዲያውቅ አጽንዖት ለመስጠት አሳብ ገላጭ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት፡- "የመከር ጊዜ ነው በአብዛኛውም በዚህ ጊዜ አይዘንብም' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
ሳሙኤል በመከር ጊዜ እህሉን የሚያጠፋ ከባድ ዝናብ በመላክ ንጉስ ስለመጠየቃቸው እግዚአብሔር እሥራኤልን እንዲቀጣ ይጠይቃል፡፡
የኃጢአት የመጨረሻ ቅጣት ሞት ነው፡፡ እግዚአብሔር ይጨቁኗቸው የነበሩትን ሕዝቦቸ እንዳጠፋ የእስራኤል ሕዝብ አይቷል፡፡ እንደሌሎቹ ሕዝቦች "ለጥፋት እንዳይሰጡ' ተጨንቀው ነበር፡፡
ሕዝቡ ክፉ አደረጉ እንዳያጠፋቸውም እግዚአብሔርን ፈሩ፡፡ አት፡- "ከዚህ ኃጢአት የተነሣ እግዚአብሔር ይቆጣል ያጠፋናልም ብላችሁ አትፍሩ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
"ሐሰተኛ አማልክትን ማምለክ አትከታተሉ'
በዚህ ስፍራ ስም የእግዚአብሔርን ክብር ያመላክታል፡፡ አት፡- "ስለዚህ ሕዝቡ እግዚአብሔርን በማክበርና በመፍራት ይኖራል፡፡' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ሳሙኤል በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር ከላከው ዝናብና ነጎድጓድ የተነሣ ሕዝቡ በፍርሃት ተሞላ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሳሙኤል ጸሎቱን እነርሱን ለመጉዳት ሊጠቀምበት እንደሚችል ሳያምኑ አልቀሩም፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
1 ሳኦል መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት በነገሠ ጊዜ፥ 2 ከእስራኤል ሦስት ሺህ ሰዎች መረጠ። አንዱ ሺህ ከዮናታን ጋር በብንያም ጊብዓ ሲሆኑ ሁለቱ ሺህ በኮረብታማው አገር በቤቴልና በማክማስ ከእርሱ ጋር ነበሩ። የቀሩትን ወታደሮች ወደየቤታቸው፥ እያንዳንዱንም ወደ ድንኳኑ አሰናበታቸው። 3 ዮናታን በጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ድል አደረገ፥ ፍልስጥኤማውያንም ይህንን ሰሙ። ከዚያም ሳኦል፥ “ዕብራውያን ይስሙ” በማለት በምድሪቱ ሁሉ ላይ መለከት አስነፋ። 4 ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር እንዳሸነፈ፥ ደግሞም እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን እንደ ግም መቆጠራቸውን እስራኤላውያን በሙሉ ሰሙ። ከዚያም ወታደሮቹ በጌልገላ ሳኦልን ለመከተል በአንድ ላይ ተሰበሰቡ። 5 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፤ ሦስት ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ሠረገላ ነጂዎችና የሠራዊቱም ቁጥር በባህር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ነበሩ። እነርሱም መጥተው ከቤትአዌን በስተምሥራቅ ማክማስ ላይ ሰፈሩ። 6 የእስራኤል ሰዎች ችግር ውስጥ መግባታቸውንና ሕዝቡም መጨነቁን ባዩ ጊዜ፥ ሕዝቡ በዋሻዎች፥ በየቁጥቋጦ ሥር፥ በዐለቶች፥ በገደሎችና በጉድጓዶች ውስጥ ተደበቁ። 7 አንዳንድ ዕብራውያንም የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ጋድና ገለዓድ ምድር ሄዱ። ሳኦል ግን ገና በጌልገላ ነበር፥ የተከተለው ሕዝብ በሙሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጥ ነበር። 8 እርሱም ሳሙኤል በሰጠው ቀጠሮ መሠረት ሰባት ቀን ቆየ። ነገር ግን ሳሙኤል ወደ ጌልገላ አልመጣም ነበር፥ ሕዝቡም ከሳኦል ተለይቶ መበታተን ጀምሮ ነበር። 9 ሳኦልም፥ "የሚቃጠለውን መባና የሰላሙን መባዎች አምጡልኝ" አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መባ አቀረበ። 10 የሚቃጠለውን መባ ማቅረቡን እንደ ጨረሰ ሳሙኤል ወደዚያ ደረሰ። ሳኦልም ሊገናኘውና ሰላምታ ሊሰጠው ሄደ። 11 ከዚያም ሳሙኤል፥ "ያደረግከው ምንድነው?" አለው። ሳኦልም፥ "ሕዝቡ ትተውኝ እየሄዱ እንዳሉ፥ አንተም በቀጠሮው ሰዓት አለመምጣትህን፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን ባየሁ ጊዜ፥ 12 'አሁን ፍልስጥኤማውያን ወደ ጌልገላ በእኔ ላይ ሊወርዱብኝ ነው፥ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንኩም' ብዬ አሰብኩኝ። ስለዚህ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ ግድ ሆነብኝ“ ብሎ መለሰለት። 13 ሳሙኤልም ሳኦልን፥”ያደረግከው ስንፍና ነው። አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትዕዛዝ አልጠበቅክም። በዚህ ቀን እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ሊያጸናልህ ነበር። 14 አሁን ግን አገዛዝህ አይቀጥልም። እግዚአብሔር ያዘዘህን አልታዘዝክምና እርሱ እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው ፈልጓል፥ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ መስፍን እንዲሆን መርጦታል" አለው። 15 ከዚያም ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ ወደ ብንያም ጊብዓ ወጣ። ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ቆጠራቸው፥ ስድስት መቶ የሚያክሉ ነበሩ። 16 ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ከእነርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በብንያም ጊብዓ ቆዩ። ፍልስጥኤማውያን ግን በማክማስ ሰፍረው ነበር። 17 ከፍልስጥኤም ጦር ሰፈር ወራሪዎች በሦስት ቡድን ተከፍለው መጡ። አንደኛው ቡድን ወደ ሦጋል ምድር ወደ ዖፍራ ታጠፈ። 18 ሌላኛው ቡድን በቤትሖሮን አቅጣጫ ታጠፈ፥ ሌላኛውም ቡድን በምድረ በዳው አቅጣጫ ወደ ስቦይም ሸለቆ ቁልቁል ወደሚያሳየው ወሰን ዞረ። 19 ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ለራሳቸው ሰይፍ ወይም ጦር እንዳይሠሩ" ብለው ስለነበረ፥ በመላው እስራኤል ብረት ሠሪ አልተገኘም። 20 ነገር ግን የእስራኤል ወንዶች ሁሉ፥ እያንዳንዱ የማረሻውን ጫፍ፥ ዶማውን፥ ጠገራውንና ማጭዱን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርድ ነበር። 21 የክፍያው ዋጋ ለማረሻው ጫፍና ለዶማው የሰቅል ሁለት ሦስተኛ፥ ጠገራ ለማሳልና መውጊያውን ለማቃናት የሰቅል አንድ ሦስተኛ ነበር። 22 ስለዚህ በጦርነቱ ቀን ሰይፍና ጦር በሳኦልና በዮናታን እጅ ብቻ እንጂ ከእነርሱ ጋር ከነበሩት ወታደሮች በአንዱም እጅ ሰይፍ ወይም ጦር አልነበረም። 23 የፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጣ።
ሳሙኤል በጌልጌላ የሳኦልን መንግሥት አደሰለት ሳሙኤልም ጌታን እንዲከተሉ ሕዝቡን አሳሰበ፡፡
በጥንት ቅጂዎች የዚህ ጥቅስ ጽሑፍ የተጎዳ ይመስላል፣ ስለዚህ የዘመናችን እትሞች የተለያዩ ትርጉሞችን ይዘዋል፡፡ ሁሉም ሊሆን የሚችለውን የተሻለውን የመጀመሪያውን ጽሑፍ ትርጉም ለማቅረብ ጥረት አድርገዋል፡፡
"3,000 ሰዎች መረጠ' (ቁጥሮች ተመልከት)
"2,000 ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበር' (ቁጥሮች ተመልከት)
የከተማ ስም ነው (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ጊብዓ ከተማ ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 10፡26 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
"የቀሩትን ወታደሮች ቤት ሰደዳቸው'
"የፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር'
ይህ የፍልስጥኤም ጭፍራ የሰፈረበት የከተማ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ዮናታን ለፈጸመው ጥቃት ሳኦል ኃላፊነቱን እየወሰደ ነበር ወይም 2) ዮናታን በፈጸመው ጥቃት የተገኘውን ድል ሳኦል እየወሰደ ነበር
ፍልስጥኤማውያን ለእስራኤል ያላቸው ጥላቻ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን የሚረብሽ መጥፎ ሽታ እንደሆኑ ተደርጎ ተገለጾአል፡፡ አት፡- "ፍልስጥኤማውያን እስራኤላውያንን ጠሉአቸው' (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- ሳኦል ወታደሮቹ እንዲከተሉት በጌልጌላ እንዲሰበሰቡ ጠራቸው (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
"3000 … 6000' (ቁጥሮች ተመልከት)
ለመቁጠር እስከሚያስቸግር ድረስ የወታደሮቹ ስብስብ ታላቅ ነበር የሚል ግነት ነው፡፡ (ግነትና አጠቃላይነት ተመልከት)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመዋጋት በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡
ይህ ሐረግ የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል፡፡
"ሕዝቡ በጣም ተጨንቆ ነበር'
ሕዝቡ በጣም ፈርተው ነበር
"እንደሚመጣ ሳሙኤል በነገራቸው ጊዜ መሠረት'
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ሕዝቡ ሳኦልን ትቶ መሄድ ጀመረ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ)
የሚቃጠል መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ማቅረብ የተፈቀደው ለአሮን ወገን ብቻ ነበር
በእውነቱ ሳሙኤል እየጠየቀ ሳይሆን ሳኦልን እየገሰጸው ነበር፡፡ ትክክል ባይሆኑም እንኳን ሳኦል ለድርጊቶቹ ሊከላከል ፈለገ፡፡ (አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች ተመልከት)
ማክማስ የቦታ ስም ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 13፡2 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ሳሙኤል እስኪመጣና ለእግዚብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት እስኪሰዋ ድረስ ሳኦል መጠበቅ ነበረበት፡፡ እርሱ ራሱ መሠዋት አልነበረበትም፡፡
"መንግሥትህን አቁሞልህ ነበር' ወይም "መንግሥትህን አውቆልህ ነበር' ወይም "መንግሥትህን መርጦ ነበር'
ይህ በአዎንታዊ መንገድ የቀረበ ምፀት ነው፡፡ አት፡- "መንግሥትህ በቅርቡ ያከትማል' (ምፀት ተመልከት)
በዚህ ስፍራ ልብ የእግዚአብሔርን ፍላጎትና ፈቃድ ይወክላል፡፡ "እንደ ልቡ የሆነ ሰው' የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር የሚፈልገውን የሚያደርግ ሰው የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "ይፈልገው የነበረ ዓይነት ሰው' ወይም "የሚታዘዘው ሰው' (ምትክ ቃልና ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
"ሳሙኤል ትቶ ሄደ' ለሚለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ጌልጌላ ከተማ ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 7፡15 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ጊብዓ ከተማ ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 10፡26 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
"600 ሰዎች' (ቁጥሮች ተመልከት)
ጊብዓ ከተማ ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 13፡03 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ማክማስ የቦታ ስም ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 13፡02 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
አደጋ ጣዮች በአብዛኛው ለምግባቸውና ሌሎች ቁሳ ቁሶች በጠላት መንደር ላይ ጥቃት የሚያደርሱ የጦር ሰዎች ናቸው፡፡
እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ታሪኩ ይቀጥላል፡፡
ይህ ለምን የሳኦል ሠራዊት እንደፈሩ በከፊል ያሳያል፡፡
1 አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣቱን ጋሻ ጃግሬውን፥”ና፥ በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ላይ በሌላ አቅጣጫ እንሂድባቸው“ አለው። ለአባቱ ግን አልነገረውም። 2 ሳኦል መጌዶን በሚባል በጊብዓ ዳርቻ በሮማኑ ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር። 3 እርሱም በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ የሆነው፥ ኤፉድ ይለብስ የነበረውን አኪያን ጨምሮ ስድስት መቶ ያህል ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ። ዮናታን መሄዱን ሕዝቡ አላወቀም ነበር። 4 ዮናታን ወደ ፍልስጥኤማውያኑ ጦር ሰፈር አቋርጦ ለመሄድ ባሰበባቸው በመተላለፊያዎቹ መካከል በግራና በቀኙ በኩል ሾጣጣ ድንጋዮች ነበሩ። የአንደኛው ሾጣጣ ድንጋይ ስም ቦጼጽ ሲሆን የሁለተኛው ስም ሴኔ ነበር። 5 አንደኛው ቀጥ ያለው ድንጋይ የቆመው በስተሰሜን በሚክማስ ፊት ለፊት ሲሆን ሌላኛው በጊብዓ ፊት ለፊት በስተደቡብ ነበር። 6 ዮናታንም ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ "ና፥ ወደእነዚህ ወዳልተገረዙት ጦር ሰፈር እንሻገር። እግዚአብሔር በብዙ ወይም በጥቂት ሰዎች ከማዳን ሊከለክለው የሚችል ነገር የለምና፥ ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል" አለው። 7 ጋሻ ጃግሬውም፥ "በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ። ወደፊት ቀጥል፥ ተመልከት፥ የምታዝዘኝን ሁሉ ለመፈጸም ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ መለሰለት። 8 ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው፥ "ወደ እነርሱ ተሻግረን እንታያቸዋለን። 9 እነርሱም፥ 'ወደ እናንተ እስክንመጣ እዚያው ቆዩ' ካሉን በስፍራችን እንቆያለን፥ ወደ እነርሱም አንሻገርም። 10 ነገር ግን፥ 'ወደ እኛ ውጡ' ብለው ቢመልሱልን እግዚአብሔር በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናልና ወደ እነርሱ እንሻገራለን።” 11 ስለዚህ ሁለቱም ራሳቸውን ለፍልስጥኤማውያን ጦር ገለጡ። ፍልስጥኤማውያኑም፥ “ተመልከቱ፥ ዕብራውያኑ ከተደበቁባቸው ጉድጓዶች ወጥተው እየመጡ ነው" ተባባሉ። 12 ከዚያም የጦር ሰፈሩ ሰዎች ወደ ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በመጣራት፥”ወደ እኛ ውጡ፥ አንድ ነገርም እናሳያችኋለን" አሏቸው። ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “እግዚአብሔር በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና ተከተለኝ" አለው። 13 ዮናታን በእጁና በእግሩ ተንጠላጥሎ ወጣ፥ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው ተከተለው። ፍልስጥኤማውያኑ በዮናታን ተገደሉ፥ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው ተከትሎ ጥቂቶቹን ገደለ። 14 ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በፈጸሙት በዚያ የመጀመሪያ ጥቃት አንድ ጥማድ በሬ ሊያርሰው በሚችለው የመሬት ስፋት ላይ ሃያ ያህል ሰዎችን ገደሉ። 15 በጦር ሰፈሩ፥ በእርሻውና በሕዝቡ መካከል ሽብር ሆነ። የጦር ሰፈሩና ወራሪዎቹም እንኳን ተሸበሩ። ምድሪቱ ተንቀጠቀጠች፥ ታላቅ ሽብርም ሆነ። 16 በብንያም ጊብዓ የነበሩ የሳኦል ጠባቂዎች፥ የፍልስጥኤም ወታደሮች ሲበተኑና ወዲያና ወዲህ ሲራወጡ ተመለከቱ። 17 ከዚያም ሳኦል ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሰዎች፥”ቁጠሩና ከእኛ የጎደለ ማን እንደሆነ ዕወቁ“ አላቸው። በቆጠሩ ጊዜም ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው ታጡ። 18 ሳኦልም አኪያን፥ "የእግዚአብሔርን ኤፉድ ወደዚህ አምጣው" አለው። በዚያ ቀን አኪያ ኤፉድ ለብሶ ከእስራኤል ወታደሮች ጋር ነበር። 19 ሳኦል ከካህኑ ጋር በመነጋገር ላይ እያለ በፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር የነበረው ሁከት መጨመሩን ቀጠለ። ሳኦልም ካህኑን፥ "እጅህን መልስ" አለው። 20 ሳኦልና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በሩጫ ወደ ጦርነቱ ሄዱ። የእያንዳንዱ ፍልስጥኤማዊ ሰይፍ በራሱ ዜጋ ላይ ነበር፥ ታላቅ ግራ መጋባት ውስጥ ነበሩ። 21 ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበሩና አብረዋቸው ወደ ጦር ሰፈሩ የገቡት ዕብራውያን እነርሱም እንኳን አሁን ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ከነበሩት እስራኤላውያን ጋር ተባበሩ። 22 በኤፍሬም አቅራቢያ በኮረብታዎቹ ውስጥ የተደበቁ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን መሸሻቸውን በሰሙ ጊዜ እነርሱም እንኳን ለውጊያ በኋላቸው አሳደዷቸው። 23 ስለዚህ እግዚአብሔር በዚያን ቀን እስራኤልን አዳነ፥ ውጊያውም ቤትአዌንን አልፎ ሄደ። 24 ሳኦል፥”ጠላቶቼን እስከምበቀልበት እስከ ምሽት ድረስ የትኛውንም ዓይነት መብል የሚበላ ቢኖር የተረገመ ይሁን“ ብሎ ሕዝቡን አምሎ ስለነበረ በዚያን ቀን የእስራኤል ሰዎች ተጨነቁ። ስለዚህ ከሠራዊቱ አንዱም ምግብ አልቀመሰም። 25 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጫካ ውስጥ ገባ፥ ማርም በምድሩ ላይ ነበር። 26 ሕዝቡ ወደ ጫካ በገባ ጊዜ ማሩ ይፈስስ ነበር፥ ነገር ግን ሕዝቡ መሓላውን ስለፈራ በእጁ ጠቅሶ ወደ አፉ ያደረገ አንድም አልነበረም። 27 ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን በመሓላ ማሰሩን አልሰማም ነበር። በእጁ ላይ የነበረውን በትር ጫፉን በማሩ እንጀራ ውስጥ አጠቀሰው። እጁን አንሥቶ ወደ አፉ አደረገው፥ ዐይኖቹም በሩለት። 28 ከዚያም ከሰዎቹ አንዱ፥”ሕዝቡ በረሃብ ቢደክምም እንኳን አባትህ፥ 'በዚህ ቀን ምግብ የሚበላ የተረገመ ይሁን' ብሎ ሕዝቡን ከመሓላ ጋር አጥብቆ አዝዞአል" ብሎ መለሰለት። 29 ከዚያም ዮናታን፥ "አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል። ከዚህ ማር ጥቂት በመቅመሴ ዐይኖቼ እንዴት እንደበሩ ተመልከቱ። 30 ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው ከበዘበዙት ላይ ዛሬ በነጻነት በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ በተሻለ ነበር? ምክንያቱም አሁን በፍልስጥኤማውያን መካከል የተገደሉት ያን ያህል ብዙ አይደሉም“ አለ። 31 እነርሱም በዚያን ቀን ፍልስጥኤማውያንን ከሚክማስ ጀምሮ እስከ ኤሎን ድረስ መቱአቸው። ሕዝቡም እጅግ ደከሙ። 32 ሕዝቡም ተስገብግበው ወደ ብዝበዛው ተጣደፉ፥ በጎችን፥ በሬዎችንና ጥጆችንም በመሬት ላይ አረዱ። ሕዝቡም ከነደሙ በሉ። 33 ከዚያም ለሳኦል፥ "ተመልከት፥ ሕዝቡ ከነደሙ በመብላታቸው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት በመሥራት ላይ ናቸው" አሉት። ሳኦልም፥ "ተላልፋችኋል፥ አሁንም ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አምጡልኝ“ አለ። 34 በመቀጠልም፥ "ወደ ሕዝቡ ሂዱና፥ 'እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን እዚህ አምጥቶ በማረድ ይብላ። ከነደሙ በመብላት በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን አታድርጉ' ብላችሁ ንገሯቸው" አለ። ስለዚህ በዚያ ምሽት እያንዳንዱ በሬውን እያመጣ በዚያ ዐረደው። 35 ሳኦል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ ይኸውም ለእግዚአብሔር የሠራው የመጀመሪያው መሠዊያ ነበር። 36 ከዚያም ሳኦል፥ "ሌሊቱን ፍልስጥኤማውያንን እናሳድ፥ እስኪነጋም ድረስ ሀብታቸውን እንበዝብዝ፤ ከእነርሱም አንድ በሕይወት አናስቀር“ አለ። እነርሱም፥”መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ“ ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፥”እዚሁ እግዚአብሔርን እንጠይቅ“ አለ። 37 ሳኦልም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀ፥”ፍልስጥኤማውያንን ላሳድዳቸው? በእስራኤል እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ? “። ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር አልመለሰለትም። 38 ከዚያም ሳኦል፥”የሕዝቡ አለቆች የሆናችሁ ሁሉ ወደዚህ ቅረቡ፤ ዛሬ ይህ ኃጢአት እንዴት እንደመጣብን መርምሩና ዕወቁ። 39 እስራኤልን ያዳነ ሕያው እግዚአብሔርን! ልጄ ዮናታን ቢሆን እንኳን በእርግጥ እርሱ ይሞታል" አለ። ነገር ግን ከሕዝቡ ሁሉ አንዱም እንኳን አልመለሰለትም። 40 እርሱም እስራኤልን በሙሉ፥ “እናንተ በአንድ በኩል ቁሙ፥ እኔና ልጄ ዮናታን በሌላው በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት። 41 ስለዚህ ሳኦል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን፥ “በቱሚም አሳየኝ” አለው። ዮናታንና ሳኦል በዕጣ ተያዙ፥ ሕዝቡ ግን የተመረጠ ሆነና አመለጠ። 42 ከዚያም ሳኦል፥ “በእኔና በልጄ በዮናታን መክከል ዕጣ ጣሉ” አለ። ዮናታንም በዕጣ ተያዘ። 43 ሳኦልም ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በእጄ በነበረው በትር ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ። ይኸው ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለ። 44 ሳኦልም፥ “ዮናታን ሆይ፥ ባትሞት እግዚአብሔር በእኔ ላይ እንዲሁ ያድርግ፥ ይጨምርም” አለ። 45 ሕዝቡም ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህንን ታላቅ ድል ያመጣ ዮናታን መሞት ይገባዋል? ይህ ከእርሱ ይራቅ! እርሱ ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር ሠርቷልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራስ ጸጉሩ አንድ በምድር ላይ አይወድቅም" አሉት። ስለዚህ ሕዝቡ ዮናታንን ከመሞት አዳነው። 46 ከዚያም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ማሳደዱን አቆመ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ስፍራቸው ሄዱ። 47 ሳኦል እስራኤልን መግዛት በጀመረ ጊዜ፥ በየአቅጣጫው ከነበሩ ጠላቶቹ ሁሉ ጋር ተዋጋ። እርሱም ከሞዓብ፥ ከአሞን ሰዎች፥ ከኤዶም፥ ከሱባ ነገሥታትና ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ። በደረሰበት ሁሉ በቅጣት ያሰቃያቸው ነበር። 48 ከአማሌቃውያን ጋር በጀግንነት ተዋግቶ ድል አደረጋቸው። እስራኤላውያንንም ከዘራፊዎቻቸው እጅ አዳናቸው። 49 የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ የሱዊና ሜልኪሳ ነበሩ። የሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ስም፥ የመጀመሪያ ልጁ ሜሮብና ታናሿ ሜልኮል ይባሉ ነበሩ። 50 የሳኦል ሚስት ስም አኪናሆም ነበር፥ እርሷም የአኪማአስ ልጅ ነበረች። የሠራዊቱ አዛዥ ስም፥ የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አበኔር ነበር። 51 ቂስ የሳኦል አባት ነበር፤ የአበኔር አባት ኔርም የአቢኤል ልጅ ነበር። 52 በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ከባድ ጦርነት ይካሄድ ነበር። ሳኦል ኃያል ወይም ብርቱ የሆነ ሰው ባየ ጊዜ ሁሉ ያንን ወደ ራሱ ይሰበስብ ነበር።
ዮናታን በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ላይ ሁለተኛ ጥቃቱን ጀመረ፡፡
የጌታውን የጦር መሣሪያዎች የመሸከም ኃላፊነት ያለበት ከአሥራ ሦሥት እስከ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ባለ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ልጅ
ይህ የፍልስጥኤማውያን ሠራዊት የሰፈረበት የጦር ሰፈር ነው፡፡
ይህ ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን የሚገኝ የኮረብታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ፍሬው ወፍራም ሽፋን ያለው፣ ክብ፣ ቀይና የሚበሉ ብዙ ዘር የያዘ ዛፍ ነው
መጊዶን ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን የሚገኝ የቦታ ስም ነው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
"600 ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ' (ቁጥሮች ተመልከት)
"አኪጦብ' እና "ኢካቦድ' የሰዎች ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ፊንሐስ ከካህናት አንዱ ነበር፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 1፡03 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ይህ የሌላኛው ሾጣጣ ድንጋይ ስም ነበር፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን የሚገኙ ከተሞች (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
የጌታውን የጦር መሣሪያዎች የመሸከም ኃላፊነት ያለበት ከአሥራ ሦሥት እስከ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ባለ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ልጅ፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 14፡1 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
ይህ አይሁድ ላልሆኑ ወንዶች ጥቅም ላይ የሚውል ክበረ ነክ ቃል ነው፡፡
"እኛን ለመደገፍ ይሠራ' ወይም "ይረዳን'
ይህ ድርብ አሉታዊ አሳብ በአዎንታዊ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ማዳን ይችላል' (ድርብ አሉታዊ ተመልከት)
እነዚህ ጥጎች በመካከል ያሉትን ነገሮች ሁሉ ያካትታሉ፡፡ አት፡- "በማንኛውም የሰው ቁጥር' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
በዚህ ስፍራ ልብ የዮናታንን ፍልጎቶች ያመላክታል፡፡ አት፡- "ማድረግ የምትፈልገውን የትኛውንም ነገር' (ምትክ ቃል ተመልከት)
"ፍልስጥኤማውያን ወደ ሚገኙበት ወደ ሌላኛው የሸለቆ አቅጣጫ አንሄድም፡፡'
በዚህ ስፍራ እጅ እነርሱን ለማሸነፍ የሆነውን ኃይል ያመለክታል፡፡ አት፡- እነርሱን ለማሸነፍ ያስችለናል (ምትክ ቃል ተመልከት)
"ይህ ጌታ ከእኛ ጋር እንደሆነ ያረጋግጥልናል'
"የፍልስጥኤማውያን ወታደሮች እንዲያዩአቸው ፈቀዱ'
የሠራዊት ከምፕ
ዕብራውያን እንደ እንሰሳ በጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው እንደ ነበር ፍልሰጥኤማውያን አመልከቱ፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)
ይህ አንድ ትምህርት አስተምራችኋለሁ የሚል ትርጉም ያለው ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
በዚህ ስፍራ እጅ የሚለው የሚያመለክተው ፍልስጥኤማውያንን ለማሸነፍ የሆነውን ኃይል ነው፡፡ አትለ- እስራኤላውያን እንዲያሸንፉ አስቻላቸው፡፡ (ምትክ ቃል ተመልከት)
ይህን ያደረገው በጣም ከፍ ያለ ስለ ነበረ ነው፡፡ ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አት፡- "በጣም ከፍ ያለ ስለ ነበረ ዮናታን እጆቹንና እግሮቹን በመጠቀም ወጣ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊደረግ ይቻላል፡፡ አት፡- "ዮናታን ፍልስጥኤማውያንን ገደለ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
"የዮናታን ጋሻ ጃግሬ ተከተለው የፍልስጥኤማውያንንም ወታደሮች ገደለ'
ሽብር የሚለው የነገር ስም በማሰሪያ አንቀጽነት ወይም በቅጽልነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "በሰፈርና በእርሻ የነበሩ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮችና ከእነርሱ ጋር የነበረው ሕዝብ ሁሉ ተሸበሩ' ወይም "በሰፈርና በእርሻ የነበሩ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮችና ከእነርሱ ጋር የነበረው ሕዝብ ሁሉ በጣም ፈሩ' (የነገር ስም ተመልከት)
የእስራኤልን ከተሞች የሚዘርፉ ፍልስጥኤማውያን
ምክንያቱን መግልጽ ሊረዳ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ምድሪቱን አናወጣት' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
ይህቺ ሳኦል የተወለደባት ከተማ ነበረች፡፡ "ጊብዓ'ን በ1ሳሙኤል 10፡26 እንደተረጎምኸው ተርጉም፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
እነዚህ ሁለት ሃረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ይጋራሉ ወታደሮቹም በሁሉም አቅጣጫዎች ይሮጡ የነበረ በመሆኑ ላይ አጽንዖት ያደርጋሉ፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)
ጥቂት ትርጉሞች በዚህ ስፍራ "የእግዚአብሔር ታቦት' በሚለው ምትክ "ኤፉድ' ይላሉ፡፡ (ልዩ ልዩ ትርጉሞች ተመልከት)
ትልቅ ድምጽና ትርምስምስ
ይህ "እያደረግህ ያለውን አቁም' የሚል ፈሊጣዊ ንግግር ይመስላል፡፡ እግዚአብሔርን ምሪት ለመጠየቅ አኪያ ታቦቱን እንዲጠቀም ሳኦል አልፈቀደም፡፡ አት፡- "በዚህ ጊዜ የተቀደሰውን ሰንዱቅ አታምጣ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ከሳኦል ጋር የቀሩ የእስራኤል ሠራዊት ቅሬታ
ሰይፎችን በሚመለከት ልክ ሕያዋን ሰዎች እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "የፍልስጥኤም ወታደሮች እርስ በእርሳቸው በሰየፎቻቸው ተጠቃቁ' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየትን ተመልከት)
ይህ ደፈጣን እያመለከተ አይደለም፡፡ እነዚህ ወታደሮች የተሸሸጉት ፍልስጥኤማውያንን ስለፈሩ ነበር፡፡ ይህ በግልጽ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አት፡- የፈሩ የእስራኤል ወታደሮች በኮረብታዎች ተሸሽገው ነበር፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
ይህ በእስራኤል የሚገኝ ቦታ ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 13፡05 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ (የስሞች አተረጓጎም መንገድ ተመልከት)
ከሳኦል መሃላ የተነሣ ምንም መቅመስ እንዳልተፈቀደ ወታደሮቹ ተረድተው ነበር፡፡
የፍልስጥኤም ወታደሮች ወደ ጫካ ሸሽተው ነበር የእስራኤል ወታደሮችም ወደዚያ ተከትለዋቸው ነበር፡፡
በጫካ ውስጥ ምን ያህል ማር እንደነበር ለመግለጽ የተነገረ ግነት ነው፡፡ አት፡- "በሁሉ ሥፍራ በርካታ ማር ነበር' (ግነትና አጠቃላይነት ተመልከት)
በዚህ ስፍራ የአንድ ሰው እጁን በአፉ ማድረጉ መብላትን የሚያሳይ ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "ማንም ምንም አልበላም' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ሕዝቡ ይፈሩ የነበረው መሐላውን ሳይሆን መሐላውን ከመስበር ጋር የተያያዘውን ቅጣት ነበር፡፡ አት፡- "ሕዝቡ መሐላውን ከሰበሩ ሳኦል የሚያደርግባቸውን ፈሩ' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ዮናታን የአባቱን መሐላ አወቀ፡፡
በዚህ ስፍራ መሐላን የመታዘዝ ግዴታን በሚመለከት ሕዝቡ በገመድ እንደታሰረ ዓይነት ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ሕዝቡ መሐላውን እንዲያከብር አዘዘ' (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)
በዚህ ስፍራ እጁን ወደ አፉ የሚለው ለመብላት ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "ጥቂት ማር በላ' (ምትክ ቃል ተመልከት)
በረታ የሚል ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "እንደገና ብርታት አገኘ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
የእስራኤልን ሕዝብ የሚወክል ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "ለእስራኤል' (ምትክ ቃል ተመልከት)
በረታ የሚል ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "እንደገና ብርታት አገኘ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
ሕዝቡ እንዲበላ ሊፈቀድለት ይገባ እንደነበር ለመግለጽ ዮናታን ይህንን በሁኔዎች ላይ የተደገፈ ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ ይህ አሳብ ገላጭ ዐረፍተ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ አት፡- "ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው የማረኩትን ዛሪ በነፃነት በልተው ቢሆን ኖሮ ድላችን የተሻለ ይሆን ነበር፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄና ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎች ተመልከት)
ይህ ቃል ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው ጋር በነበራቸው ጦርነት የወሰዷቸውን ነገሮች ያመለክታል፡፡
በጦርነቱ ወቅቱ ወታደሮቹ ሊበሉ ስላልቻሉ፣ ቀኑ የረዘመውን ያህል እየደከሙ ሄዱ፡፡ ከዚህ የተነሣ ብዙ ፍልስጥኤማውያንን መግደል አልቻሉም፡፡
የዮናታን ቃል ሠራዊቱን ከነበረባቸው ከፍተኛ ረሃብ የተነሣ እግዚአብሔርን እንዲበድሉ አደረጋቸው፡፡
ይህ የቦታ ስም ነው፡፡ ይህንን በ1ሳሙኤል 13፡02 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
በዛብሎን እስራኤል የሚገኝ ቦታ ነው (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
እስራኤላውያንን ያመለክታል፡፡
በጣም ተርበው ስለነበር ከመብላታቸው በፊት ደሙን አላፈሰሱም ነበር፡፡ ይህ በሙሴ በኩል ለሕዝበ እሥራኤል የተሰጠውን ሕግ መተላለፍ ነበር፡፡ ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አት፡- "በሕጉ እንደታዘዘው አስቀድመው ደማቸውን ሳያፈስሱ በሏቸው' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
ይህ በሙሴ በኩል ለሕዝበ እሥራኤል የተሰጠውን ሕግ መተላለፍ ነበር፡፡ ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አት፡- "በሕጉ እንደታዘዘው አስቀድመው ደሙን ሳያፈስሱ ሥጋ በመብላታቸው'
ሁሉም ወታደር ታማኝነቱን ስላላጓደለ ሳኦል ሠራዊቱን ሁሉ በታማኝነት እንዳላደረገ መክሰሱ አጠቃላይ ፍረጃ ነው፡፡ (ግነትና አጠቃላይነት ተመልከት)
ድንጋዩ እንሰሳቱን ከፍ አድርጎ ስለሚይዝ ደማቸውን ማፍሰስን ቀላል ያደርገዋል በዚህ እረዱና ብሉ ይህ ሳኦልን ደሙ ከእንሰሳው በተገቢ ሁኔታ ተወግዶ መሆኑን ለማየት ያስችለዋል፡፡
ሕዝቡ ለማረድና ለመብላት እንሰሳቶቻቸውን ወደ ትልቁ ደንጋይ እንዲያመጡ ሳኦል ነገራቸው፡፡
ሳኦል ይህን መሠዊያ የሠራው ሕዝቡ በ1ሳሙኤል 14፡33 ወደ እርሱ ካመጡለት ትልቅ ድንጋይ ይሁን ግልጽ አይደለም፡፡
ሳኦል ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበረውን ጦርነት ለመቀጠል ፈልጓል፡፡
ለግድያው አጽንዖት ለመስጠት ይህ በአሉታዊ መንገድ ተገልጾአል፡፡ በአዎንታዊ መልኩም ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እያንዳንዳቸውን እንግደል' (ምጸት ተመልከት)
ጦርነቱን ለመቀጠል ሳኦል የሠራዊቱን ድጋፍ አግኝቶአል፡፡
በዚህ ስፍራ "ወደ እግዚአብሔር መቅረብ' እርሱን ምክር ከመጠየቅ ጋር ተያይዟል፡፡ አት፡- "ምን ማደረግ እንዳለብን እግዚአብሔርን እንጠይቅ' (ምትክ ቃል ተመልከት)
በዚህ ስፍራ "እጅ' እነርሱን ለማሸነፍ የሚሆንን ኃይል ያመለክታል፡፡ አት፡-"እንድናሸንፋቸው አስችለን' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ይህ እግዚአብሔር ሳኦልን ለመርዳት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ያመላክታል፡፡
ይህ እስራኤላውያንን ያመልከታል
"ኃጢአት የሠራውን እወቁ'
ሳኦል ዮናታን በደለኛ እንደሆነ ስላላመነ ይህንን ሊሆን እንደ ሚችል ሁኔታ አድርጎ ገለጸ፡፡ (ሊሆን የሚችል ሁኔታ ተመልከት)
አብዛኛዎቹ ዮናታን የሳኦልን መሐላ እንደሰበረ ስለሚያውቁ ዝም አሉ፡፡ ይህ በግልጽ ሊቀመጥ ይችላል፡፡ አት፡- "ሰዎቹ በደለኛው ማን እንደነበረ ያውቁ ነበር ነገር ግን ማናቸውም ለሳኦል ምንም አላሉም፡፡' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
በዚያ የነበሩት የእስራኤል ወታደሮች ብቻ ስለሆኑ ይህ አጠቃላይነት ነው፡፡ አት፡- "በዚያ ለነበሩት የእስራኤል ወታደሮች እንዲህ አለ' (ግነትና አጠቃላይነት ተመልከት)
በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር ምሪት ለመቀበል ኡሪምና ቱሚም የተባሉ የተለዩ ድንጋዮች ይጠቀሙ ነበር፡፡ አት፡- "በቱሚም አማካይነት አስታውቀን' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)
ይህ ከመጀመሪያ ቋንቋ በትውስት የተወሰደ ነው፡፡ (ቅጂ ወይም ትውስት ቃላት ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይቻላል፡፡ አት፡- ዕጣዎቹ ዮናታን ወይም ሳኦል በደለኞች እንደሆኑ ነገር ግን ሠራዊቱ በደለኛ እንዳልሆነ አመለከቱ (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- ከዚያም ዕጣው ዮናታን በደለኛ እንደሆነ አመለከተ (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
ዕጣው ዮናታን ኃጢአት እንዳደረገ አሳየ፡፡
"እንዴት ኃጢአት እንዳደረግህ ንገረኝ' ወይም "ያደረግኸው ስሕተት ምን እንደሆነ ንገረኝ'
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ለመሞት ፈቃደኛ ነኝ' ወይም 2) "ያንን ስላደረግሁ በሞት ልቀጣ ይገባኛል'
ከአንድ ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሳኦል ትርጉም የሌለው መሐላ አደረገ፡፡ አት፡- ዮናታን፣ ካልገደልኩህ እግዚአብሔር ይግደለኝ
ሠራዊቱ ከሳኦል ለዮናታን ተከላከለ ጠበቀውም፡፡
ሕዝቡ ሳኦልን ገሰፀ፡፡ ይህ አሳብ ገላጭ ጥያቄ በገላጭ አባባል ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- ዮናታን ይህን ታላቅ ድል ለእስራኤል አድርጓል፡፡ በእርግጥ ዮናታን አይሞትም፡፡ (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)
ሕዝቡ በዮናታን ላይ አንዳች ነገር እንዲሆን አንዳማየፈቅዱ ቁርጠኛነታቸውን እየገለጹ ነበር፡፡
ይህ ግነት የእስራኤል ሕዝብ እንዴት ዮናታንን እንደሚጠብቁትና ደህንነቱን እንደሚከታተሉ ያሳያል፡፡ ይህ ምፀት በአዎንታዊ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- ከየትኛውም ጉዳት እንጠብቀዋለን (ግነትና አጠቃላይነት እና ምፀት ተመልከት)
ለአጭር ጊዜ ሳኦል በታላቅ ድፍረት የእስራኤላውያንን ጠላቶች በማሸነፍ አገልግሏል፡፡
ይህ የእስራኤልን ሕዝብ የሚወክል ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "እስራኤላውያን' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ይህ የሞዓብ ሕዝብን ያመለክታል፡፡ አት፡- "ሞዓባውያን' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ይህ የዔዶም ሰዎችን ያመለክታል፡፡ አት፡- "ዔዶማውያን' (ምትክ ቃል ተመልከት)
"ሠራዊቱን በላከበት ሥፍራ ሁሉ'
እጅ የሚለው ቃል ቁጥጥርን ይወክላል፡፡ አት፡- "ከ … ቁጥጥር' (ምትክ ቃል ተመልከት)
ይህ በሳኦል ቤተሰብ ዙሪያ ታሪካዊ ዳራ ነው፡፡
እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
አነዚህ የሴቶች ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
እነዚህ የሴቶች ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
እነዚህ የወንዶች ስሞች ናቸው፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)
"በሳኦል የሕይወት ዘመን ሁሉ'
1 ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፥”እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ እንድቀባህ ላከኝ። አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። 2 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው፥ 'እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ አማሌቅ እየተቃወመ በመንገዱ ላይ ያደረገበትን አስታውሻለሁ። 3 አሁንም ሂድና አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውን ሁሉ ፈጽመህ ደምስስ። አትራራላቸው፥ ወንድና ሴቱን፥ ልጅና ሕፃኑን፥ በሬና በጉን፥ ግመልና አህያውን ግደል።" 4 ሳኦል ሕዝቡን በጥላኢም ከተማ ሰብስቦ ቆጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺህ እግረኞችና ዐሥር ሺህ የይሁዳ ሰዎች ነበሩ። 5 ከዚያም ሳኦል ወደ አማሌቅ ከተማ መጥቶ በሸለቆው ውስጥ አደፈጠ። 6 ከዚያም ሳኦል ቄናውያንን፥ "ከግብፅ በመጡ ጊዜ ለእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ደግነትን አሳይታችኋልና ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ፥ ከአማሌቃውያን መካከል ተለይታችሁ ውጡና ሂዱ" አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ። 7 ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ ከግብፅ በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው። 8 የአማሌቃውያኑን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ያዘው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። 9 ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ አጋግን፥ እንዲሁም ምርጥ የሆኑትን በጎች፥ በሬዎች፥ የሰቡትን ጥጆችና የበግ ጠቦቶች በሕይወት ተዉአቸው። መልካም የሆነውን ሁሉ አላጠፉም። የተናቀውንና ዋጋ ቢስ የሆነውን ነገር ሁሉ ግን ፈጽመው ደመሰሱ። 10 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሳሙኤል መጣ፥ 11 "እኔን ከመከተል ስለተመለሰና ያዘዝኩትንም ስላልፈጸመ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ"። ሳሙኤልም ተቆጣ፤ ሌሊቱን በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጮህ አደረ። 12 ሳሙኤልም ሳኦልን በጠዋት ለመገናኘት ማልዶ ተነሣ። ለሳሙኤልም፥ "ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ መጥቶ ለራሱ ሐውልት አቆመ፥ ከዚያም ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወረደ" ብለው ነገሩት። 13 ከዚያም ሳሙኤል ወደ ሳኦል መጣ፥ ሳኦልም፥ "አንተ በእግዚአብሔር የተባረክህ ነህ! የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ፈጽሜአለሁ" አለው። 14 ሳሙኤልም፥ "ታዲያ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ድምፅና የበሬዎች ግሣት ምንድነው?" አለው። 15 ሳኦልም፥ "ከአማሌቃውያኑ ያመጧቸው ናቸው። ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ምርጥ የሆኑትን በጎችና በሬዎች በሕይወት አስቀሯቸው። የቀሩትን ፈጽመን አጥፍተናል" ብሎ መለሰለት። 16 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልን፥ "አድምጠኝ፥ በዛሬው ሌሊት እግዚአብሔር የነገረኝን እነግርሃለሁ" አለው። ሳኦልም፥ "ተናገር!" አለው። 17 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፥ "በራስህ ግምት ታናሽ ብትሆንም በእስራኤል ነገዶች ላይ አለቃ ተደረግህ። እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ ቀባህ፤ 18 እግዚአብሔርም፥ 'ሂድና ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ተዋጋቸው' ብሎ በመንገድህ ልኮህ ነበር። 19 ታዲያ የእግዚአብሔርን ድምፅ ያልታዘዝከው ለምንድነው? ከዚያ ይልቅ ግን ከምርኮው በመውሰድ በእግዚአብሔር ፊት ክፋትን አደረግህ።" 20 ሳኦልም ሳሙኤልን፥ "የእግዚአብሔርን ድምፅ በትክክል ታዝዣለሁ፥ እግዚአብሔር በላከኝም መንገድ ሄጃለሁ። የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን ማርኬዋለሁ፥ አማሌቃውያንንም በሙሉ ፈጽሜ ደምስሻለሁ። 21 ሕዝቡ ግን ከምርኮው ላይ ጥቂት በጎችንና በሬዎችን፥ ሊጠፉም የነበሩ ምርጥ ነገሮችን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ሊሠዉአቸው ወሰዱ" አለው። 22 ሳሙኤልም፥ "የእግዚአብሔርን ድምፅ ከመታዘዝ የበለጠ በሚቃጠል መባና መሥዋዕት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛል? ከመሥዋዕት መታዘዝ ይሻላል፥ ከአውራ በግ ስብም መስማት ይሻላል። 23 እምቢተኝነት እንደ ምዋርተኝነት ኃጢአት ነው፥ እልኸኝነትም እንደ አመጸኝነትና እንደ ክፋት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እርሱም ደግሞ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል“ አለው። 24 ከዚያም ሳኦል ሳሙኤልን፥”ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ ሕዝቡን ስለፈራሁና ቃላቸውን ስለታዘዝኩ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝና የአንተን ቃል ተላልፌአለሁ። 25 አሁንም እባክህን ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፥ ለእግዚአብሔር እንድሰግድም ከእኔ ጋር ተመለስ“ አለው። 26 ሳሙኤልም ሳኦልን፥”ከአንተ ጋር አልመለስም፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና አንተም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን እግዚአብሔር ንቆሃል" አለው። 27 ሳሙኤል ለመሄድ ዘወር ባለ ጊዜ፥ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፥ እርሱም ተቀደደ። 28 ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ዛሬ የእስራኤልን መንግሥት ከአንተ ቀደደው፥ ከአንተ ለሚሻለው ለጎረቤትህም አሳልፎ ሰጠው። 29 ደግሞም የእስራኤል ኃይል አይዋሽም፥ አሳቡንም አይለውጥም፥ እርሱ አሳቡን መለወጥ ይችል ዘንድ ሰው አይደለምና“ አለው። 30 ከዚያም ሳኦል፥”ኃጢአትን አድርጌአለሁ። አሁን ግን እባክህ በሕዝቤ ሽማግሌዎችና በእስራኤል ፊት አክብረኝ። ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንድሰግድ ከእኔ ጋር ተመለስ“ አለው። 31 ስለዚህ ሳሙኤል ከሳኦል ኋላ ተመለሰ፥ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ። 32 ከዚያም ሳሙኤል፥”የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ“ አለ። አጋግ በሠንሠለት አንደታሠረ ወደ እርሱ መጣና፥”ለካስ ሞት እንዲህ መራራ ነው“ አለ። 33 ሳሙኤልም፥”ሰይፍህ እናቶችን ልጅ ዐልባ እንዳደረጋቸው አሁን እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ ዐልባ ትሆናለች“ ብሎ መለሰለት። ከዚያም ሳሙኤል አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቆራረጠው። 34 ሳሙኤል ወደ ራማ ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ሳኦል ጊብዓ ሄደ። 35 ሳሙኤል እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ሳኦልን አላየውም፥ ለሳኦልም አለቀሰለት። እግዚአብሔርም ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ አዘነ።
1 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ንጉሥ እንዳይሆን ለናቅኩት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? በወንዶች ልጆቹ መካከል ለራሴ ንጉሥ የሚሆነውን መርጫለሁና ወደ ቤተ ልሔማዊው ወደ እሴይ እልክሃለሁ። የዘይት መያዣ ቀንድህን በዘይት ሞልተህ ሂድ” አለው። 2 ሳሙኤልም፥ “እንዴት መሄድ እችላለሁ? ሳኦል ከሰማ ይገድለኛል” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፥ 'ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ' በል። 3 እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ ጥራው፥ እኔም የምታደርገውን አሳይሃለሁ። የምነግርህንም እርሱን ትቀባልኛለህ” አለው። 4 ሳሙኤልም እግዚአብሔር እንደተናገረው አደረገ፥ ወደ ቤተ ልሔምም ሄደ። የከተማይቱም ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡና፥ “በሰላም ነው የመጣኸው?” አሉት። 5 እርሱም፥ “በሰላም ነው። ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ። ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱና ከእኔ ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ”አላቸው። እሴይንና ወንዶች ልጆቹንም ቀደሳቸው፥ ወደ መሥዋዕቱም ጠራቸው። 6 እነርሱ በመጡ ጊዜም፥ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ እግዚአብሔር የሚቀባው በእርግጥ በፊቱ ቆሟል ብሎ በልቡ አሰበ። 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ሳሙኤልን፥ "እኔ ንቄዋለሁና ውጫዊ ገጽታውን ወይም የቁመቱን ዘለግታ አትመልከት። እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ አያይምና፤ ሰው ውጫዊ ገጽታን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል" አለው። 8 ከዚያም እሴይ አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገው። ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ይኸኛውንም አልመረጠውም“ አለ። 9 ከዚያም እሴይ ሳማን አሳለፈው። ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ይኸኛውንም አልመረጠውም“ አለ። 10 እሴይ ሰባቱን ወንዶች ልጆቹን በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረጋቸው። ሳሙኤልም እሴይን፥”እግዚአብሔር ከእነዚህ አንዳቸውንም አልመረጠም“ አለው። 11 ሳሙኤልም እሴይን፥”ወንዶቹ ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸው? “ አለው። እርሱም፥”የሁሉ ታናሽ የሆነው ገና ቀርቷል፥ እርሱ ግን በጎች እየጠበቀ ነው" ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም እሴይን፥ "ልከህ አስመጣው፤ እርሱ እዚህ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥምና" አለው። 12 እሴይም ልኮ አስመጣው። በመጣ ጊዜም ልጁ ቀይ፥ ዐይኖቹ የተዋቡና መልከ መልካም ገጽታ ነበረው። እግዚአብሔርም፥ "ያ ሰው እርሱ ነውና ተነሣ፤ ቀባውም" አለው። 13 ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ አንሥቶ በወንድሞቹ መካከል እርሱን ቀባው። ከዚያን ቀን ጀምሮ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል መጣበት። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ። 14 የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ተለየ፥ በምትኩም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ክፉ መንፈስ አሠቃየው። 15 የሳኦል አገልጋዮችም፥ "ተመልከት፥ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ እያሠቃየህ ነው። 16 ደህና አድርጎ በገና መደርደር የሚችል ሰው እንዲፈልጉ ጌታችን በፊቱ ያሉትን አገልጋዮቹን ይዘዝ። ከዚያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሆነብህ ጊዜ እርሱ ይጫወትልሃል፥ አንተም ደኅና ትሆናለህ" አሉት። 17 ሳኦልም አገልጋዮቹን፥ "በገና በደንብ መደርደር የሚችል ሰው ፈልጋችሁ አምጡልኝ" አላቸው። 18 ከዚያም ከወጣቶቹ አንዱ እንዲህ ሲል መለሰ፥ "ደኅና አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን፥ ጽኑ፥ ኃያል፥ ተዋጊ፥ በንግግሩ ጠንቃቃና መልከ መልካም የሆነውን የቤተ ልሔማዊውን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው።" 19 ስለዚህ ሳኦል መልዕክተኞችን ወደ እሴይ ልኮ፥ "ከበጎች ጋር ያለውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ" አለው። 20 እሴይም እንጀራና ወይን ጠጅ የተሞላ አቁማዳ የተጫነበትን አህያ፥ ከፍየል ጠቦት ጋር አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው። 21 ከዚያም ዳዊት ወደ ሳኦል መጣና አገልግሎቱን መስጠት ጀመረ። ሳኦል እጅግ ወደደው፥ ዳዊትም ጋሻ ጃግሬው ሆነ። 22 ሳኦልም፥ "በዐይኔ ፊት ሞገስን አግኝቷልና ዳዊት በፊቴ እንዲቆም ፈቃድህ ይሁን“ ብሎ ወደ እሴይ ላከ። 23 በሳኦል ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ዳዊት በገና አንሥቶ ይደረድርለት ነበር። ስለዚህ ሳኦል ይታደስና ደኅና ይሆን ነበር፥ ክፉውም መንፈስ ከእርሱ ይርቅ ነበር።
1 ፍልስጥኤማውያን ሠራዊታቸውን ለውጊያ አዘጋጁ። እነርሱም የይሁዳ በሆነችው በሰኮት ተሰበሰቡ። በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በምትገኘው በኤፌስደሚምም ሰፈሩ። 2 ሳኦልና የእስራኤል ሰዎችም ተሰብስበው በኤላ ሸለቆ ሰፈሩ፥ ፍልስጥኤማውያንን ለመግጠምም ስፍራቸውን ያዙ። 3 ፍልስጥኤማውያን በአንደኛው ወገን ተራራ ላይ ቆሙ፥ በዚህኛው ወገን ባለው ተራራ ላይ እስራኤላውያኑ ቆሙ፥ በመካከላቸውም ሸለቆ ነበር። 4 የጌት ሰው ጎልያድ የሚባል አንድ ጀግና ከፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር ወጣ፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር ነበር። 5 በራሱ ላይ ከነሐስ የተሠራ የራስ ቁር ደፍቶ፥ ጥሩርም ለብሶ ነበር። ጥሩሩም አምስት ሺህ የነሐስ ሰቅል ይመዝን ነበር። 6 በእግሮቹ ላይ የነሐስ ገምባሌዎች አድርጎ ነበር፥ በትከሻዎቹም መሓል ቀለል ያለ የነሐስ ጦር ነበር። 7 የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ወፍራም ነበር። የጦሩ ጫፍ ስድስት መቶ የብረት ሰቅል ይመዝን ነበር። ጋሻ ጃግሬው በፊቱ ሄደ። 8 እርሱም ተነሥቶ በእስራኤል ሠልፈኞች ላይ እንዲህ በማለት ጮኸ፥ “ለውጊያ የተሰለፋችሁት ለምንድነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ፥ እናንተ የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁም? ለራሳችሁ አንድ ሰው ምረጡና ወደ እኔ ይውረድ። 9 እርሱ ሊዋጋኝ ቢችልና ቢገድለኝ እኛ አገልጋዮቻችሁ እንሆናለን። ነገር ግን ባሸንፈውና ብገድለው እናንተ አገልጋዮቻችን በመሆን ታገለግሉናላችሁ።” 10 ፍልስጥኤማዊው ደገመና፥ “ዛሬ የእስራኤልን ሰልፈኞች እገዳደራቸዋለሁ። እንድንዋጋ አንድ ሰው ስጡኝ" አለ። 11 ፍልስጥኤማዊው የተናገረውን ሳኦልና እስራኤላውያን ሁሉ በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፥ ተስፋም ቆረጡ። 12 ዳዊት በይሁዳ የሚኖረው የቤተ ልሔም ኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር። እሴይ ስምንት ወንዶች ልጆች ነበሩት። በሳኦል ዘመን እሴይ በዕድሜው ያረጀና ከወንዶቹ ሁሉ በዕድሜ የገፋ ሰው ነበር። 13 የእሴይ ሦስቱ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነቱ ሄደው ነበር። ወደ ጦርነት የሄዱት የሦስቱ ወንዶች ልጆች ስም፥ የመጀመሪያው ልጅ ኤልያብ፥ ተከታዩ አሚናዳብና ሦስተኛው ሣማ ይባሉ ነበር። 14 ዳዊት የሁሉም ታናሽ ነበር። ትልልቆቹ ሦስቱ ሳኦልን ተከተሉት። 15 ዳዊት በሳኦል ሠራዊትና በቤተ ልሔም የሚገኙትን የአባቱን በጎች በመጠበቅ ተግባር ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ናበር። 16 ፍልስጥኤማዊው ኃያል ሰው ለአርባ ቀናት በየጠዋቱና በየምሽቱ ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን ለማሳየት ይቀርብ ነበር። 17 ከዚያም እሴይ ልጁን ዳዊትን እንዲህ አለው፥”ከዚህ ከተጠበሰው እሸት ዐሥር ኪሎና እነዚህን ዐሥር ዳቦዎች በጦር ሰፈሩ ውስጥ ላሉት ወንድሞችህ ፈጥነህ ውሰድላቸው። 18 በተጨማሪም እነዚህን ዐሥር የአይብ ጥፍጥፎች ለሻለቃቸው ስጠው። ወንድሞችህ ያሉበትን ሁኔታ ተመልከትና ደኅና ስለመሆናቸው ማረጋገጫ አምጣልኝ። 19 ወንድሞችህ ከሳኦልና ከእስራኤል ሰዎች ሁሉ ጋር ፍልስጥኤማውያንን እየተዋጉ በኤላ ሸለቆ ናቸው።“ 20 ዳዊት ማልዶ ተነሣና በጎቹን ለእረኛ ዐደራ ሰጠ። እርሱም እሴይ እንዳዘዘው የወንድሞቹን ስንቅ ይዞ ሄደ። ሠራዊቱ ወደ ውጊያው ግምባር እየፎከረ በመውጣት ላይ እያለ ዳዊት ወደ ጦር ሰፈሩ ደረሰ። 21 እስራኤላውያንና ፍልስጥኤማውያን፥ ሠራዊት በሠራዊት ላይ ለውጊያ ተሰለፉ። 22 ዳዊት የያዘውን ዕቃ ለስንቅ ጠባቂው ዐደራ ሰጥቶ ወደ ሠራዊቱ በመሮጥ ለወንድሞቹ ሰላምታ አቀረበ። 23 ከእነርሱ ጋር እየተነጋገረ እያለ ጎልያድ ተብሎ የሚጠራው፥ ከጌት የመጣው ፍልስጥኤማዊ ከሰልፈኞች መካከል ወጥቶ የቀድሞውን የሚመስል ቃል ተናገረ። ዳዊትም ሰማቸው። 24 የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ሰውዬውን ባዩት ጊዜ፥ ከእርሱ ሸሹ፥ እጅግም ፈርተውት ነበር። 25 የእስራኤልም ሰዎች፥ "ይህን የሚወጣውን ሰው አያችሁት? እስራኤልን ለመገዳደር ነው የመጣው። እርሱን የሚገድለውን ሰው ንጉሡ እጅግ ያበለጽገዋል፥ ልጁን ይድርለታል፥ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ውስጥ ከግብር ነጻ ያደርጋቸዋል" ይባባሉ ነበር። 26 ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ "ይህንን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድልና ከእስራኤል ኀፍረትን ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ሊንቅ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ሆነና ነው?" አላቸው። 27 ከዚያም ሰዎቹ ቀደም ሲል የተናገሩትን ደግመው፥ "ስለዚህ እርሱን ለሚገድለው የሚደረግለት ይህ ነው" አሉት። 28 ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር የሁሉ ታላቅ የሆነው ወንድምየው ኤልያብ ሰማው። ኤልያብም በዳዊት ላይ ቁጣው ነድዶ፥ "ወደዚህ የወረድከው ለምንድነው? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ውስጥ ለማን ተውካቸው? እኔ ትዕቢትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁ፤ ወደዚህ የወረድከው ውጊያውን ለማየት ነውና" አለው። 29 ዳዊትም፥ "አሁን እኔ ምን አደረኩ? እንዲያው መጠየቄ ብቻ አልነበረም?" አለው። 30 ከእርሱ ወደ ሌላው ዞር ብሎ በተመሳሳይ መንገድ ተናገረ። ሰዎቹም የቀድሞውን የሚመስል መልስ ሰጡት። 31 ዳዊት የተናገረው ቃል በተሰማ ጊዜ፥ ወታደሮች ቃሉን ለሳኦል ነገሩት፥ እርሱም ዳዊትን አስጠራው። 32 ከዚያም ዳዊት ሳኦልን፥ "በዚያ ፍልስጥኤማዊ ምክንያት የማንም ልብ አይውደቅ፤ አገልጋይህ ሄዶ ከፍልስጥኤማዊው ጋር ይዋጋል" አለው። 33 ሳኦልም ዳዊትን፥ "አንተ ከዚህ ፍልስጥኤማዊ ጋር ለመዋጋት መሄድ አትችልም፤ አንተ ገና ልጅ ነህ፥ እርሱ ደግሞ ከወጣትነቱ ጀምሮ ተዋጊ ነው" አለው። 34 ዳዊት ግን ሳኦልን፥ "አገልጋይህ የአባቴን በጎች እጠብቅ ነበር። አንበሳ ወይም ድብ መጥቶ ከመንጋው ጠቦት በሚወስድበት ጊዜ 35 በኋላው ተከትዬ እመታውና ከአፉ አስጠለው ነበር። ሊያጠቃኝ በተነሣብኝ ጊዜም ጉሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር። 36 አገልጋይህ አንበሳና ድብ ገድያለሁ። የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ስለተገዳደረ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል" አለው። 37 ዳዊትም፥ "እግዚአብሔር ከአንበሳና ከድብ መዳፍ አድኖኛል። ከዚህም ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል" አለው። 38 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ "ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን" አለው። ሳኦል የራሱን የጦር መሣሪያ ለዳዊት አስታጠቀው። በራሱ ላይ የነሐስ ቁር ደፋለት፥ ጥሩርም አለበሰው። 39 ዳዊትም ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጠቀው። ነገር ግን አልተለማመደውምና ለመራመድ አቃተው። ከዚያም ዳዊት ሳኦልን፥ "አልተለማመድኳቸውምና በእነዚህ መዋጋት አልችልም" አለው። ስለዚህ ዳዊት ከላዩ ላይ አወለቃቸው። 40 በትሩን በእጁ ያዘ፥ ከጅረቱም አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች መርጦ በእረኛ ኮሮጆው ውስጥ ጨመራቸው። ፍልስጥኤማዊውን በሚቀርብበት ጊዜ ወንጭፉን ይዞ ነበር። 41 ፍልስጥኤማዊውም በፊት ለፊቱ ከሚሄደው ጋሻ ጃግሬው ጋር መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ። 42 ፍልስጥኤማዊው ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊትን ባየው ጊዜ ቀይ፥ መልከ መልካም ገጽታ ያለው ትንሽ ልጅ ብቻ ስለነበረ ናቀው። 43 ፍልስጥኤማዊው ዳዊትን፥ "በትር ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝ?" አለው። ፍልስጥኤማዊውም በአማልክቶቹ ስም ዳዊትን ረገመው። 44 ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፥ "ወደ እኔ ና፥ እኔም ሥጋህን ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ" አለው። 45 ዳዊትም ለፍልስጥኤማዊው እንዲህ ሲል መለሰለት፥ "አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ። እኔ ግን አንተ ባቃለልከው፥ የእስራኤል ሠራዊት አምላክ በሆነው፥ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ። 46 ዛሬ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ድልን ይሰጠኛል፥ እገድልሃለሁ፥ ራስህንም ከሰውነትህ ላይ አነሣዋለሁ። ዛሬ የፍልስጥኤምን ሠራዊት ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፥ ይኸውም ምድር ሁሉ በእስራኤል አምላክ እንዳለ እንዲያውቅና 47 በዚህ የተሰበሰበው ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍ ወይም በጦር ድልን እንደማይሰጥ እንዲያውቁ ነው። ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነውና እናንተንም በእጃችን ላይ አሳልፎ ይሰጣችኋል።" 48 ፍልስጥኤማዊው ተነሥቶ ዳዊትን በቀረበው ጊዜ ዳዊት ሊገናኘው ወደ ጠላት ጦር በፍጥነት ሮጠ። 49 ዳዊት እጁን ወደ ኮሮጆው አስገብቶ አንድ ድንጋይ ከዚያ ወሰደ፥ ወነጨፈውና የፍልስጥኤማዊውን ግንባር መታው። ድንጋዩም በፍልስጥኤማዊው ግንባር ውስጥ ጠልቆ ገባ፥ እርሱም በግንባሩ በምድር ላይ ተደፋ። 50 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው። ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። በዳዊት እጅ ሰይፍ አልነበረም። 51 ከዚያም ዳዊት ሮጠና በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፥ ከእርሱም ሰይፉን ወሰደ፥ ከሰገባው አወጣና ገደለው፥ በእርሱም ራሱን ቆርጦ አነሣው። ፍልስጥኤማውያን ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ። 52 ከዚያም የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች እልል እያሉ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን እስከ ሸለቆውና እስከ ኤቅሮን መግቢያ ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያኑ ሬሳ ከሸዓራይም እስከ ጌትና ዔቅሮን ድረስ በየመንገዱ ወድቆ ነበር። 53 የእስራኤል ሰዎች ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመለሱና የጦር ሰፈራቸውን በዘበዙ። 54 ዳዊት የፍልስጥኤማዊውን ራስ ወስደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣው፥ የጦር መሣሪያውን ግን በድንኳኑ ውስጥ አኖረው። 55 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመጋጠም ሲሄድ ሳኦል ባየው ጊዜ፥ የሰራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ "አንተ አበኔር፥ ይህ ወጣት የማን ልጅ ነው?" አለው። አበኔርም፥ "ንጉሥ ሆይ፥ በሕያውነትህ እምላለሁ፥ አላውቅም" አለው። 56 ንጉሡም፥ "የማን ልጅ እንደሆነ ምናልባት ሊያውቁት የሚችሉትን ጠይቅ" አለው። 57 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ አበኔር ወሰደው፥ የፍልስጥኤማዊውን ራስ በእጁ እንደያዘ ወደ ሳኦል አመጣው። 58 ሳኦልም፥ "አንተ ወጣት፥ የማን ልጅ ነህ?" አለው። ዳዊትም፥ "እኔ የቤተ ልሔማዊው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ" ብሎ መለሰለት።
1 ለሳኦል መናገሩን በጨረሰ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፥ ዮናታንም እንደ ራሱ ነፍስ አድርጎ ወደደው። 2 በዚያ ቀን ሳኦል ዳዊትን ወደ ራሱ አገልግሎት ወሰደው፤ ወደ አባቱ ቤት እንዲመለስ አላሰናበተውም። 3 ዮናታን ዳዊትን እንደ ራሱ ነፍስ አድርጎ ስለወደደው በመካከላቸው የወዳጅነት ቃል ኪዳን አደረጉ። 4 ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከጦር ልብሱ ጋር፥ እንዲሁም ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ለዳዊት ሰጠው። 5 ዳዊት ሳኦል ወደሚልከው ቦታ ሁሉ ይሄድ ነበር፥ ይከናወንለትም ነበር። ሳኦልም በተዋጊዎቹ ላይ ሾመው። ይህም በሕዝቡ ዓይን ሁሉ ደግሞም በሳኦል አገልጋዮች ፊት ደስ የሚያሰኝ ሆነ። 6 ፍልስጥኤማውያንን ድል አድርገው ወደ መኖሪያቸው በመመለስ ላይ እያሉ ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመገናኘት፥ ሴቶች በከበሮና በሙዚቃ መሳሪያዎች በደስታ እየዘመሩና እየጨፈሩ መጡ። 7 ሴቶቹም ሲጫወቱ እየተቀባበሉ ይዘምሩ ነበር፤ እነርሱም፥ "ሳኦል ሺዎችን ገደል፥ ዳዊትም ዐሥር ሺዎችን ገደለ" እያሉ ዘመሩ። 8 ሳኦል እጅግ ተቆጣ፥ ይህም መዝሙር አስከፋው። እርሱም፥ "ለዳዊት ዐሥር ሺዎች አሉ፥ ለእኔ ግን ሺዎችን ብቻ። ታዲያ ከመንግሥት በቀር ምን ቀረው?" አለ። 9 ሳኦል ከዚያን ቀን ጀምሮ ዳዊትን በጥርጣሬ ዐይን ተመለከተው። 10 በቀጣዩ ቀን በሳኦል ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ መጣበት። እርሱም በቤት ውስጥ እንደ ዕብድ ይለፈልፍ ነበር። ስለዚህ ዳዊት በየቀኑ ያደርግ እንደነበረው በገናውን ይደረድር ነበር። ሳኦልም በእጁ ጦር ይዞ ነበር። 11 ሳኦል፥ "ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ" ብሎ በማሰብ ጦሩን ወረወረበት። ነገር ግን ዳዊት ከሳኦል ፊት ሁለት ጊዜ እንዲህ ባለ መንገድ አመለጠ። 12 እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንጂ ከእርሱ ጋር ስላልነበረ ሳኦል ዳዊትን ፈራው። 13 ስለዚህ ሳኦል ከፊቱ አራቀው፥ ሻለቃም አድርጎ ሾመው። በዚህ ሁኔታ ዳዊት በሕዝቡ ፊት ይወጣና ይገባ ነበር። 14 እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበረ ዳዊት የሚሠራው ሁሉ ይከናወንለት ነበር። 15 እንደ ተከናወነለት ሳኦል ባየ ጊዜ እጅግ ፈራው። 16 ነገር ግን በፊታቸው ይወጣና ይገባ ስለነበረ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊትን ወደዱት። 17 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ "ትልቋ ልጄ ሜሮብ ይቹት። እርሷን እድርልሃለሁ። ብቻ ጎብዝልኝ፥ የእግዚአብሔርን ጦርነቶችም ተዋጋ" አለው። ሳኦል፥ "እጄ በእርሱ ላይ አይሁን፥ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ይሁን" ብሎ አስቦአልና። 18 ዳዊትም ሳኦልን፥ "የንጉሥ አማች ለመሆን እኔ ማነኝ? ሕይወቴ ወይም የአባቴ ቤተ ሰብ በእስራኤል ውስጥ ምንድነው?" አለው። 19 ነገር ግን የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለዳዊት የምትዳርበት ጊዜ ሲደርስ ለመሓላታዊው ለኤድሪኤል ተዳረች። 20 ነገር ግን የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደችው። ለሳኦል ነገሩት፥ ይህም እርሱን ደስ አሰኘው። 21 ከዚያም ሳኦል፥ "ወጥመድ እንድትሆነውና የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ እንድትሆን እርሷን እድርለታለሁ" ብሎ አሰበ። ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን ለሁለተኛ ጊዜ፥ "አማቼ ትሆናለህ" አለው። 22 ሳኦል አገልጋዮቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፥ "ዳዊትን በምስጢር እንዲህ በሉት፥ 'አስተውል፥ ንጉሡ በአንተ ደስ ብሎታል፥ አገልጋዮቹም ሁሉ ይወዱሃል። እንግዲያው የንጉሡ አማች ሁን'" 23 ስለዚህ የሳኦል አገልጋዮች ይህንን ቃል ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ "እኔ ድሃና ብዙም የማልታወቅ ሰው ሆኜ እያለሁ የንጉሥ አማች እንድሆን ማሰባችሁ ጉዳዩ እንዴት ቀልሎ ታያችሁ?" አላቸው። 24 የሳኦል አገልጋዮችም ዳዊት የተናገረውን ቃል ነገሩት። 25 ሳኦልም፥ "ለዳዊት እንዲህ ትሉታላችሁ፥ 'የንጉሡን ጠላቶች ለመበቀል ከአንድ መቶ የፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ብቻ በቀር ንጉሡ ምንም ጥሎሽ አይፈልግም"። ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲወድቅ ለማድረግ ሳኦል አሰበ። 26 አገልጋዮቹ ይህንን ቃል ለዳዊት በነገሩት ጊዜ የንጉሡ አማች መሆን ዳዊትን ደስ አሰኘው። 27 እነዚያ ቀናት ከማብቃታቸው በፊት፥ ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሄዶ ሁለት መቶ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ። ዳዊት የንጉሡ አማች ይሆን ዘንድ ሸለፈቶቹን አመጣ፥ ለንጉሡም ሙሉውን ቁጥር አስረከቡ። ስለዚህ ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ዳረለት። 28 እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደነበረ ሳኦል አየ፥ ዐወቀም። የሳኦል ልጅ ሜልኮልም ወደደችው። 29 ሳኦልም ዳዊትን የበለጠ ፈራው። ሳኦል የዳዊት ጠላቱ እንደሆነ ቀጠለ። 30 ከዚያም የፍልስጥኤም ልዑላን ብዙ ጊዜ ያደርጉት እንደነበረው ለጦርነት መጡ፥ ዳዊት ከሳኦል አገልጋዮች ሁሉ በበለጠ ሁኔታ የተሳካለት ሆነ፥ በመሆኑም ስሙ እጅግ የተከበረ ሆነ።
1 ሳኦል ልጁን ዮናታንን እና አገልጋዮቹን በሙሉ ዳዊትን እንዲገድሉት ነገራቸው። የሳኦል ልጅ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር። 2 ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን፥ "አባቴ ሳኦል ሊገድልህ ይፈልጋል። በመሆኑም ለራስህ ጥንቃቄ አድርግ፥ በነገውም ቀን በምስጢራዊ ቦታ ተደበቅ። 3 አንተ ባለህበት አካባቢ ሄጄ በአባቴ አጠገብ እቆማለሁ፥ ስለ አንተም አነጋግረዋለሁ። አንዳች ነገር ካገኘሁኝም እነግርሃለሁ“ አለው። 4 ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል ስለ ዳዊት መልካምን ነገር ተናገረ፥ እንዲህም አለው፥”ንጉሡ በአገልጋዩ በዳዊት ላይ ክፉ ነገር አያድርግ። እርሱ ክፉ አላደረገብህም፥ እርሱ የሠራው ሥራ ለአንተ መልካም ሆኖልሃልና። 5 ነፍሱን በእጁ ላይ ጥሎ ፍልስጥኤማዊውን ገደለ። እግዚአብሔርም ለእስራኤል በሙሉ ታላቅ ድልን ሰጠ። አንተም አይተህ ደስ ብሎህ ነበር። ያለምንም ምክንያት ዳዊትን በመግደልህ በንጹህ ደም ላይ ለምን ኃጢአት ትሠራለህ?“ 6 ሳኦልም ዮናታንን ሰማው። ሳኦልም፥”ሕያው እግዚአብሔርን! ዳዊት አይገደልም“ ብሎ ማለ። 7 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን ጠራው፥ ዮናታንም ይህንን ነገር ሁሉ ነገረው። ዮናታንም ዳዊትን ወደ ሳኦል አመጣው፥ እርሱም እንደቀድሞው በፊቱ ነበረ። 8 እንደገናም ጦርነት ሆነ። ዳዊት ወጥቶ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፥ በታላቅ አገዳደልም ድል አደረጋቸው። እነርሱም ከፊቱ ሸሹ። 9 ሳኦል በእጁ ጦሩን እንደያዘ በቤቱ ተቀምጦ እያለ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሳኦል ላይ መጣበት፥ ዳዊትም በገና ይደረድር ነበር። 10 ሳኦል በጦሩ ዳዊትን ከግድግዳው ጋር ለማጣበቅ ሞከረ፥ ዳዊት ግን ከሳኦል ፊት ዘወር አለ፥ ስለዚህ የሳኦል ጦር በግድግዳው ላይ ተሰካ። በዚያ ምሽት ዳዊት ሸሽቶ አመለጠ። 11 ሳኦልም በማግስቱ ይገድለው ዘንድ ከብበው እንዲጠብቁት ወደ ዳዊት ቤት መልዕክተኞች ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮልም፥”በዚህ ሌሊት ሕይወትህን ካላዳንክ ነገ መገደልህ ነው“ አለችው። 12 ስለዚህ ሜልኮል ዳዊትን በመስኮት እንዲወርድ አደረገችው። እርሱም ሄደ፥ ሸሽቶም አመለጠ። 13 ሜልኮልም የቤተሰቡን የጣዖት ምስል ወስዳ በአልጋው ውስጥ አጋደመችው። በራስጌው ከፍየል ጸጉር የተሠራ ትራስ አስቀመጠች፥ በልብስም ሸፈነችው። 14 ሳኦል ዳዊትን የሚወስዱ መልዕክተኞች በላከ ጊዜ እርሷ፥ "አሞታል" አለቻቸው። 15 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን እንዲያዩት መልዕክተኞች ላከ፥ እርሱም፥ "እንድገድለው ከነዐልጋው አምጡልኝ" አላቸው። 16 መልዕክተኞቹ ወደ ቤት በገቡ ጊዜ፥ በዐልጋው ውስጥ የቤተሰቡ የጣዖት ምስል፥ በራስጌውም ከፍየል ጸጉር የተሠራው ትራስ ነበር። 17 ሳኦል ሜልኮልን፥ "ጠላቴ እንዲሄድና እንዲያመልጥ በማድረግ ለምን አታለልሽኝ?" አላት። ሜልኮልም ለሳኦል፥ "'ልሂድ፥ አለበለዚያ እገድልሻለሁ' ስላለኝ ነው" ብላ መለሰችለት። 18 ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፥ ሳሙኤል ወዳለበት ወደ ራማም ሄደ፥ ሳኦል ያደረገበትንም ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ሄዱ፥ በነዋትም ተቀመጡ። 19 ለሳኦልም፥ "ዕወቀው፥ ዳዊት በራማ ነዋት ነው" ተብሎ ተነገረው። 20 ሳኦልም ዳዊትን እንዲይዙት መልዕክተኞችን ላከ። እነርሱም ትንቢት የሚናገሩ የነቢያትን ጉባዔ፥ ሳሙኤልንም መሪያቸው ሆኖ ባዩ ጊዜ በሳኦል መልዕክተኞች ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ መጣባቸው፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። 21 ይህ ሁኔታ ለሳኦል በተነገረው ጊዜ፥ ሌሎች መልዕክተኞችን ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። ስለዚህ ሳኦል እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ሌሎች መልዕክተኞችን ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። 22 ከዚያም እርሱ ደግሞ ወደ አርማቴም ሄደ፥ በሤኩ ወዳለው ጥልቅ የውሃ ጉድጓድም መጣ። እርሱም፥”ሳሙኤልና ዳዊት የት ነው ያሉት? “ ብሎ ጠየቀ። አንደኛው ሰው፥”በራማ ነዋት ናቸው“ ብሎ መለሰለት። 23 ሳኦልም በራማ ወዳለው ነዋት ሄደ። የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ መጣ፥ በራማም ወደሚገኘው ወደ ነዋት እስኪደርስ ድረስ በመንገድ ላይ ትንቢት ይናገር ነበር። 24 እርሱም ደግሞ ልብሶቹን አወለቀ፥ በሳሙኤል ፊት እርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገረ፥ ያን ቀንና ሌሊቱን ሁሉ ራቁቱን ተጋደመ። እነርሱም፥”ሳኦል ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ? “ ያሉት በዚህ ምክንያት ነው።
1 ከዚያም ዳዊት በራማ ካለው ከነዋት ሸሽቶ መጣና ዮናታንን፥”ምን አድርጌአለሁ? ጥፋቴስ ምንድነው? በአባትህ ፊት ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገው? “ አለው። 2 ዮናታንም ዳዊትን፥”ይህ ከአንተ ይራቅ፥ አትሞትም። ነገሩ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሳይነግረኝ አባቴ ምንም አያደርግም። አባቴ ይህንን ነገር ለምን ይደብቀኛል? ነገሩ እንዲህ አይደለም። 3 ዳዊት ግን እንደገና ማለና፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ ያውቃል። እርሱም፥ 'ይህንን ዮናታን አይወቅ፥ ካልሆነ ያዝናል' ይላል። በሕያው እግዚአብሔር ስም፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፥ በእኔና በሞት መካከል የቀረው አንድ እርምጃ ነው" አለው። 4 ዮናታን ዳዊትን፥ "የምትጠይቀኝን ሁሉ አደርግልሃለሁ" አለው። 5 ዳዊትም ዮናታንን፥ "ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት ቀን ነው፥ ከንጉሡ ጋር ለመብላት መቀመጥ ይኖርብኛል። እስከ ሦስተኛው ቀን ምሽት ድረስ በመስኩ ውስጥ ሄጄ እንድደበቅ ፍቀድልኝ" አለው። 6 አባትህ እኔን በማጣቱ ከጠየቀህ፥ "ዳዊት፥ መላው ቤተ ሰቡ ዓመታዊ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡ ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት አጥብቆ ለመነኝ' በለው። 7 እርሱም፥ 'መልካም ነው' ካለህ ነገሩ ለአገልጋይህ ሰላም ሆኗል ማለት ነው። ነገር ግን እርሱ እጅግ ከተቆጣ ክፉ ሊያደርግብኝ እንደወሰነ በዚህ ታውቃለህ። 8 እንግዲህ አገልጋይህን በርኅራኄ ተመልከተኝ። በእግዚአብሔር ፊት ከአገልጋይህ ጋር ቃል ኪዳን አድርገሃልና። ኃጢአት ቢገኝብኝ ግን አንተው ግደለኝ፤ ለምንስ ወደ አባትህ ትወስደኛለህ?" አለው። 9 ዮናታንም፥ "ይህ ከአንተ ይራቅ! አባቴ ክፉ ሊያደርግብህ መወሰኑን ባውቅ አልነግርህም?" 10 ዳዊትም ዮናታንን፥ "አባትህ አንደ አጋጣሚ በቁጣ ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል?" አለው። 11 ዮናታንም ዳዊትን፥ "ና፥ ወደ መስኩ እንሂድ" አለው። ሁለቱም ወደ መስኩ ሄዱ። 12 ዮናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው፥ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁን። ነገ ወይም በሦስተኛው ቀን እንደዚህ ባለው ሰዓት አባቴን በምጠይቀው ጊዜ፥ ስለ ዳዊት በጎ አሳብ ካለው ልኬብህ አላሳውቅህም? 13 አባቴ በአንተ ላይ ክፉ ማድረጉ የሚያስደስተው ከሆነ በሰላም እንድትሄድ ባላሳውቅህና ባላሰናብትህ እግዚአብሔር በዮናታን ላይ ይህንን እና ከዚህም የከፋውን ያድርግበት። ከአባቴ ጋር እንደነበረ እግዚአብሔር ከአንተም ጋር ይሁን። 14 አንተስ በሕይወት በምኖርበት ዘመን እንዳልሞት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታማኝነት አታሳየኝም? 15 እግዚአብሔር የዳዊትን ጠላቶች፥ እያንዳንዳቸውን ከምድር ላይ በሚያጠፋበት ጊዜ የቃል ኪዳን ታማኝነትህን ከቤቴ አታጥፋ"። 16 ሰለዚህ ዮናታን ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገና”እግዚአብሔር ከዳዊት ጠላቶች እጅ ይጠይቀው“ አለ። 17 ዮናታን ነፍሱን እንደሚወዳት ዳዊትን ይወደው ስለነበረ፥ ለእርሱ ከነበረው ፍቅር የተነሣ ዳዊት እንደገና እንዲምልለት አደረገ። 18 ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው፥”ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት የወር መጀመሪያ ቀን ነው። ወንበርህ ባዶ ስለሚሆን ላትኖር ነው። 19 ለሦስት ቀናት ከቆየህ በኋላ፥ ፈጥነህ ውረድና በዚህ ጉዳይ ካሁን በፊት ወደተደበቅህበት ስፍራ መጥተህ በኤዜል ድንጋይ አጠገብ ቆይ። 20 በዒላማ ላይ የምወረውር መስዬ ሦስት ፍላጻዎችን ወደዚያ አቅራቢያ እወረውራለሁ። 21 ከእኔ ጋር ያለውን ታዳጊ ወጣት እልከውና፥ 'ሂድ ፍላጻዎቹን ፈልግ' እለዋለሁ። ታዳጊውን ልጅ፥ 'ተመልከት፥ ፍላጻዎቹ አጠገብህ ናቸው፤ ውሰዳቸው' ካልኩት ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ደኅንነት እንጂ ጉዳት አይሆንብህምና ትመጣለህ። 22 ነገር ግን ታዳጊውን ወጣት፥ 'ተመልከት፥ ፍላጻዎቹ ከአንተ በላይ ናቸው' ካልኩት እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። 23 እኔና አንተ ያደረግነውን ስምምነት በሚመለከት እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ለዘላለም ምስክር ነው።" 24 ስለዚህ ዳዊት በመስኩ ውስጥ ተደበቀ። አዲስ ጨረቃ በሆነ ጊዜ ንጉሡ ምግብ ለመብላት ተቀመጠ። 25 ንጉሡ እንደተለመደው በግድግዳው አጠገብ በነበረው በመቀመጫው ላይ ተቀመጠ። ዮናታን ተነሣ፥ አበኔርም በሳኦል አጠገብ ተቀምጦ ነበር። የዳዊት ቦታ ግን ባዶ ነበር። 26 በዚያን ቀን ሳኦል ገና ምንም አልተናገረም፥ ምክንያቱም፥ "አንድ ነገር ደርሶበት ይሆናል፥ ወይም በሕጉ መሰረት አልነጻም ይሆናል፤ በርግጥ ባይነጻ ነው" ብሎ ሳላሰበ ነው። 27 ነገር ግን አዲስ ጨረቃ በታየችበት ማግስት፥ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶ ነበር። ሳኦል ልጁን ዮናታንን፥ "የእሴይ ልጅ ዳዊት ትላንትም ይሁን ዛሬ ወደ ማዕድ ያልመጣው ለምንድነው?" አለው። 28 ዮናታንም ለሳኦል እንዲህ በማለት መለሰለት፥ "ዳዊት ወደ ቤተ ልሔም ለመሄድ እንድፈቅድለት አጥብቆ ለመነኝ። 29 እርሱም፥ 'እባክህን እንድሄድ ፍቀድልኝ። በዚያ ከተማ ቤተሰባችን የሚያቀርበው መሥዋዕት አለ፥ እኔም በዚያ እንድገኝ ወንድሜ አዞኛል። አሁንም በፊትህ ሞገስን ካገኘሁ፥ ወንድሞቼን አያቸው ዘንድ እንድሄድ እባክህን ፍቀድልኝ' አለኝ። ወደ ንጉሡ ማዕድ ያልመጣው በዚህ ምክንያት ነው።" 30 ከዚያም የሳኦል ቁጣ በዮናታን ላይ ነደደ፥ እርሱም እንዲህ አለው፥ "አንተ የጠማማና አመጸኛ ሴት ልጅ! ለራስህ ኃፍረትና ለእናትህ የዕርቃንነት ኃፍረት የእሴይን ልጅ እንደ መረጥክ የማላውቅ መሰለህ? 31 የእሴይ ልጅ በምድር ላይ እስካለ ድረስ አንተም ሆንክ መንግሥትህ አትጸኑም። አሁንም በእርግጥ መሞት የሚገባው ነውና ልከህ አስመጣልኝ።“ 32 ዮናታንም አባቱን ሳኦልን፥”የሚገደለው በምን ምክንያት ነው? ያደረገውስ ምንድነው? “ ሲል መለሰለት። 33 በዚያን ጊዜ ሳኦል ሊገድለው ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ አባቱ ዳዊትን ለመግደል መወሰኑን ዮናታን ተረዳ። 34 ዮናታን እጅግ ተቆጥቶ ከማዕድ ተነሣ፥ አባቱ ስላዋረደው ስለ ዳዊት አዝኖ ነበርና በወሩ በሁለተኛው ቀን ምንም ምግብ አልበላም። 35 በማግስቱ ዮናታን ከዳዊት ጋር ወደተቀጣጠሩበት መስክ ሄደ፥ አንድ ታዳጊ ወጣትም አብሮት ነበር። 36 እርሱም ታዳጊውን ወጣት፥”ሩጥ፥ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ሰብስብ“ አለው። ታዳጊው ወጣት በሚሮጥበት ጊዜ ፍላጻውን ከበላዩ ላይ ወረወረው። 37 ታዳጊው ወጣት ዮናታን የወረወረው ፍላጻ ወደ ወደቀበት ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ ዮናታን ታዳጊውን ተጣርቶ፥ "ፍላጻው ከአንተ በላይ ነው" አለው። 38 ዮናታንም ታዳጊውን፥ "ቶሎ በል፥ ፍጠን፥ አትዘግይ!" አለው። ስለዚህ የዮናታኑ ታዳጊ ወጣት ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ። 39 ታዳጊው ወጣት ግን አንዳች የሚያውቀው አልነበረም። ጉዳዩን የሚያውቁት ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነበሩ። 40 ዮናታን የጦር መሣሪያዎቹን ለታዳጊው ወጣት ሰጥቶ፥ "ሂድ፥ ወደ ከተማ ውሰዳቸው" አለው። 41 ታዳጊው ወጣት እንደ ሄደ፥ ዳዊት ከጉብታው ኋላ ተነሣ፥ ወደ ምድርም ተጎንብሶ ሦስት ጊዜ ሰገደ። እርስ በእርሳቸው ተሳሳሙ፥ ተላቀሱም፥ ዳዊትም አብዝቶ አለቀሰ። 42 ዮናታንም ዳዊትን፥”'እግዚአብሔር፥ በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም ይሁን' ተባብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናልና በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።
1 ከዚያም ዳዊት ካህኑን አቢሜሌክን ለማግኘት ወደ ኖብ መጣ። አቢሜሌክም ዳዊትን ለመገናኘት እየተንቀጠቀጠ መጣና፥ “አንድም ሰው አብሮህ ያልሆነውና ብቻህን የሆንከው ለምንደነው?” አለው። 2 ዳዊትም ካህኑን አቢሜሌክን፥ “ንጉሡ ለአንድ ጉዳይ ልኮኛል። እርሱም፥ 'ስለምልክህ ጉዳይና ያዘዝኩህን ነገር ማንም እንዳያውቅ'ብሎኛል። ወጣቶቹንም የሆነ ቦታ ላይ እንዲጠብቁኝ ነግሬአቸዋለሁ። 3 ታዲያ አሁን እጅህ ላይ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም ያለውን ነገር ስጠኝ” አለው። 4 ካህኑም ለዳዊት መልሶ፥ “ማንኛውም ሰው የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን ታዳጊ ወጣቶቹ ራሳቸውን ከሴቶች ጠብቀው ከሆነ የተቀደሰ እንጀራ አለ” አለው። 5 ዳዊትም ለካህኑ እንዲህ ሲል መለሰለት፥ “በእርግጥ በእነዚህ ሦስት ቀናት ከሴቶች ተጠብቀናል። ለተራ ተልዕኮ በሚወጡበት ጊዜ ራሳቸውን ካነጹ ለዚህ ተልዕኮማ ከእኔ ጋር ያሉት ወጣቶች ሰውነት ለእግዚአብሔር እንዴት የበለጠ የተቀደሰ አይሆንም?” 6 ስለዚህ ከተነሣ በኋላ በስፍራው ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ፊት ከተነሣው፥ ከገጸ ሕብስቱ በስተቀር ሌላ እንጀራ በዚያ አልነበረምና፥ ካህኑ ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን እንጀራ ሰጠው። 7 በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንዱ በእግዚአብሔር ፊት በእዚያ ቆይቶ ነበር፤ ስሙ ዶይቅ የሚባል ኤዶማዊ፥ የሳኦል የእረኞቹ አለቃ ነበር። 8 ዳዊት አቢሜሌክን፥ "እዚህ ጦር ወይም ሰይፍ ይኖርሃል? የንጉሡ ጉዳይ አስቸኳይ ስለነበረ ሰይፌንም ሆነ መሣሪያዬን ይዤ አልመጣሁም“ አለው። 9 ካህኑም፥”በዔላ ሸለቆ የገደልከው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ በጨርቅ ተጠቅልሎ እዚህ ከኤፉዱ ኋላ አለ። ሌላ የጦር መሣሪያ በዚህ የለምና እርሱን ልትወስደው ብትፈልግ ውሰደው።" ዳዊትም፥ "እንደ እርሱ ያለ ሌላ ሰይፍ የለም፤ እርሱን ስጠኝ" አለው። 10 በዚያን ቀን ዳዊት ተነሥቶ ከሳኦል ፊት ሸሸ፥ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አንኩስም ሄደ። 11 የአንኩስ አገልጋዮችም ንጉሡን፥ "ይህ የምድሪቱ ንጉሥ የሆነው ዳዊት አይደለም? 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ' እያሉ ስለ እርሱ በዘፈን እየተቀባበሉ ዘምረውለት አልነበረም? አሉት። 12 ዳዊት ይህንን ቃል በልቡ አኖረው፥ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው። 13 በፊታቸውም አዕምሮውን ለወጠ፥ በያዙት ጊዜም እንደ ዕብድ ሆነ፤ የቅጥሩን በር እየቧጨረም ለሃጩን በጺሙ ላይ አዝረከረከ። 14 አንኩስም አገልጋዮቹን፥ “ተመልከቱ፥ ሰውዬው ዕብድ እንደሆነ ታያላችሁ። 15 ወደ እኔ ለምን አመጣችሁት? ይህንን ሰው በፊቴ እንዲያብድ ወደ እኔ ያመጣችሁት ያበዱ ሰዎችን ስላጣሁኝ ነው? በእርግጥ እንዲህ ያለው ሰው ወደ ቤቴ ይገባል?” አላቸው።
1 ስለዚህ ዳዊት ያንን ትቶ ወደ ዓዶላም ዋሻ አመለጠ። ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰብ በሙሉ ይህንን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ወደ እርሱ ወረዱ። 2 የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። ዳዊትም አዛዣቸው ሆነ። ከእርሱም ጋር ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ። 3 ዳዊት ከዚያ በሞዓብ ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ። እርሱም የሞዓብን ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ እባክህን አባቴና እናቴ አንተጋ እንዲኖሩ ፈቃድህ ይሁን” አለው። 4 እነርሱንም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ ተዋቸው። ዳዊት በጠንካራው ምሽግ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ሁሉ አባቱና እናቱ ከንጉሡ ጋር ኖሩ። 5 ከዚያም ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፥ “በጠንካራው ምሽግ ውስጥ አትቆይ። እርሱን ትተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ያንን ትቶ ወደ ሔሬት ጫካ ሄደ። 6 ዳዊት ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሰዎች ጋር መገኘቱን ሳኦል ሰማ። ሳኦል በጊብዓ ከአጣጥ ዛፍ ስር በእጁ ጦሩን እንደያዘ ተቀምጦ ነበር፥ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር። 7 ሳኦል በዙሪያው የቆሙትን አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የብንያም ሰዎች ሆይ፥ አሁን ስሙ! የእሴይ ልጅ ለእያንዳንዳችሁ እርሻና የወይን ቦታ ይሰጣችኋል? ሁላችሁም በእኔ ላይ ስላደማችሁበት ምትክ ሻለቆችና መቶ አለቆችስ አድርጎ ይሾማችኋል? 8 ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ከእናንተ አንዱም አልነገረኝም። አንዳችሁም ስለ እኔ አላዘናችሁም። ልጄ አገልጋዬን ዳዊትን በእኔ ላይ ሲያነሣሣው ከእናንተ ማንም አልነገረኝም። ዛሬ ተደብቋል፥ እኔን ለማጥቃትም ይጠባበቃል።" 9 ከዚያም በሳኦል አገልጋዮች መካከል ቆሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ፥ "የእሴይን ልጅ ወደ ኖብ፥ ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ መጥቶ አይቼዋለሁ። 10 አቤሜሌክም እግዚአብሔር ዳዊትን እንዲረዳው ጸለየለት፥ እርሱም ስንቅና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው" አለው። 11 ንጉሡም የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቢሜሌክንና የአባቱን ቤተሰብ በሙሉ፥ እንዲሁም በኖብ ይኖሩ የነበሩትን ካህናት እንዲጠራ መልዕክተኛ ላከ። ሁሉም ወደ ንጉሡ መጡ። 12 ሳኦልም፥ "የአኪጦብ ልጅ ሆይ፥ አሁን ስማ!" አለው። እርሱም፥ "ጌታዬ ሆይ፥ ይኸው አለሁ” ብሎ መለሰለት። 13 ሳኦልም እንዲህ አለው፥ “አንተና የእሴይ ልጅ በእኔ ላይ ያሤራችሁት ለምንድነው? ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ በእኔ ላይ እንዲነሣና በምስጢራዊ ቦታ እንዲደበቅ እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፥ ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የጸለይክለት ለምንድነው?” 14 አቢሜሌክም ለንጉሡ፥ “የንጉሡ አማችና በጠባቂዎቹ ላይ የበላይ የሆነ፥ በቤትህም የተከበረ፥ በአገልጋዮችህ ሁሉ መካከል እንደ ዳዊት የታመነ ማነው? 15 እግዚአብሔር እንዲረዳው ስጸልይለት የዛሬው የመጀመሪያዬ ነውን? ይህ ከእኔ ይራቅ! ንጉሡ ምንም ነገር በአገልጋይህ ወይም በአባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያኑር። አገልጋይህ ከዚህ ሁሉ ነገር አንዱንም አላውቅምና" ብሎ መለሰለት። 16 ንጉሡም፥ "አቢሜሌክ ሆይ፥ አንተና የአባትህ ቤት በሙሉ በእርግጥ ትሞታላችሁ" ብሎ መለሰለት። 17 ንጉሡም በዙሪያው የቆሙትን ጠባቂዎች፥ "መሸሹን እያወቁ አላስታወቁኝምና፥ እጃቸውም ከዳዊት ጋር ነውና፥ ዙሩና የእግዚአብሔርን ካህናት ግደሏቸው” አላቸው። የንጉሡ አገልጋዮች ግን የእግዚአብሔርን ካህናት ለመግደል እጆቻቸውን አላነሡም። 18 ከዚያም ንጉሡ ዶይቅን፥ "ዙርና ካህናቱን ግደላቸው" አለው። ስለዚህ ኤዶማዊው ዶይቅ ዞረና መታቸው፤ በዚያም ቀን ከተልባ እግር የተሠራ ኤፉድ የለበሱ ሰማንያ አምስት ሰዎችን ገደለ። 19 እርሱም የካህናቱን ከተማ ኖብን፥ ወንዶችንና ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ በሬዎችን፥ አህዮችንና በጎችን በሰይፍ ስለት መታቸው። ሁሉንም በሰይፍ ስለት ገደላቸው። 20 ነገር ግን አብያታር የተባለው የአኪጦብ ልጅ፥ የአቢሜሌክ ልጅ አመለጠ፥ ወደ ዳዊትም ሸሸ። 21 አብያታርም ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንደ ገደለ ለዳዊት ነገረው። 22 ዳዊትም አብያታርን፥ “ኤዶማዊው ዶይቅ በዚያ በነበረ ጊዜ በእርግጥ ለሳኦል እንደሚነግረው በዚያን ቀን ዐውቄ ነበር። ለአባትህ ቤተ ሰብ ሁሉ መሞት ተጠያቂው እኔ ነኝ! ። 23 ከእኔ ጋር ተቀመጥ፥ አትፍራ። ያንተን ነፍስ የሚፈልግ የእኔንም ነፍስ የሚፈልግ ነው። ከእኔ ጋር በሰላም ትኖራለህ” አለው።
1 ለዳዊትም፥ "ፍልስጥኤማውያን ቅዒላን በመውጋት ላይ ናቸው፥ ዐውድማውንም እየዘረፉ ነው“ ብለው ነገሩት። 2 ስለዚህ ዳዊት እግዚአብሔር እንዲረዳው ጸለየ፥ እርሱም፥”እነዚህን ፍልስጥኤማውያን ሄጄ ልምታቸው? “ ብሎ ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፥”ሂድና ፍልስጥኤማውያንን ምታ፥ ቅዒላንም አድን“ አለው። 3 የዳዊት ሰዎችም፥”ተመልከት፥ እዚሁ በይሁዳ ሆነን እየፈራን ነው። በፍልስጥኤማውያን ላይ ወደ ቅዒላ ለመውጣትማ ይልቁን እንዴት አስፈሪ አይሆንብንም? “ አሉት። 4 ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔር እንዲረዳው እንደገና ጸለየ። እግዚአብሔርም፥”ተነሥ፥ ወደ ቅዒላ ውረድ። በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን እሰጥሃለሁ“ ብሎ መለሰለት። 5 ዳዊትና ሰዎቹም ሄደው ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጉ። የቀንድ ከብቶቻቸውን ወሰዱ፥ እነርሱንም በታላቅ አገዳደል መቷቸው። ስለዚህ ዳዊት የቅዒላን ነዋሪዎች አዳናቸው። 6 የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ቅዒላ ወደ ዳዊት በሸሸ ጊዜ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር። 7 ዳዊት ወደ ቅዒላ መሄዱ ለሳኦል ተነገረው። ሳኦልም፥ "በሮችና መቀርቀሪያዎች ወዳሏት ከተማ በመግባቱ በራሱ ላይ ዘግቷልና እግዚአብሔር በእጄ ላይ ጥሎታል" አለ። 8 ሳኦልም ወደ ቅዒላ ወርደው ዳዊትንና ሰዎቹን እንዲከቡ ሠራዊቱን ሁሉ ለጦርነት ጠራቸው። 9 ዳዊትም ሳኦል ክፉ ሊያደርግበት እንዳቀደ ዐወቀ። እርሱም ካህኑን አብያታርን፥ "ኤፉዱን ወደዚህ አምጣው" አለው። 10 ዳዊትም፥ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ሳኦል በእኔ ምክንያት ከተማይቱን ለማጥፋት ወደ ቅዒላ ለመምጣት እንደሚፈልግ አገልጋይህ በእርግጥ ሰምቷል። 11 አገልጋይህ እንደ ሰማው፥ ሳኦል ወደዚህ ይወርዳል? የቅዒላ ሰዎችስ በእጁ አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እባክህን ለአገልጋይህ እንድትነግረኝ እለምንሃለሁ” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አዎን፥ ወደዚህ ይወርዳል” አለው። 12 ዳዊትም፥ “የቅዒላ ሰዎች እኔንና ሰዎቼን በሳኦል እጅ አሳልፈው ይሰጡናልን?” ብሎ ጠየቀው። እግዚአብሔርም፥ “አሳልፈው ይሰጧችኋል" አለ። 13 ከዚያም ዳዊትና ወደ ስድስት መቶ የሚደርሱ ሰዎቹ ተነሡ፥ ከቅዒላም ወጥተው ሄዱ፥ ከቦታ ቦታም እየተዘዋወሩ ሄዱ። ዳዊት ከቅዒላ መሸሹ ለሳኦል ተነገረው፥ እርሱም ማሳደዱን አቆመ። 14 ዳዊትም በዚፍ ምድረ በዳ ውስጥ ባለው በኮረብታማው አገር፥ በምድረ በዳው ባለ ምሽግ ውስጥ ኖረ። ሳኦል በየቀኑ ይፈልገው ነበር፥ እግዚአብሔር ግን በእጁ ላይ አልጣለውም። 15 ዳዊት በዚፍ ምድረ በዳ ሖሬሽ በተባለ ቦታ ነበር፤ ሳኦልም የእርሱን ሕይወት ለማጥፋት እንደ ወጣ አየ። 16 ከዚያም የሳኦል ልጅ ዮናታን ተነሥቶ በሖሬሽ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት ሄደ፥ በእግዚአብሔር ስም አበረታታው። 17 እንዲህም አለው፥ "የአባቴ የሳኦል እጅ አያገኝህምና አትፍራ። አንተ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆናለህ፥ እኔም ምክትልህ እሆናለሁ። አባቴ ሳኦልም ደግሞ ይህንን ያውቃል።" 18 እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ዳዊት በሖሬሽ ቆየ፥ ዮናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ። 19 ዚፋውያንም በጊብዓ ወዳለው ወደ ሳኦል መጥተው፥ "ዳዊት ከየሴሞን በስተደቡብ በሚገኘው በኤኬላ ኮረብታ ላይ፥ በሖሬሽ ምሽጎች ውስጥ በመካከላችን ተደብቋል፤ 20 አሁንም ንጉሥ ሆይ! ወደዚህ ውረድ፥ ደስ ባለህ ጊዜ ወደዚህ ውረድ! በንጉሡ እጅ አሳልፎ የመስጠቱ ድርሻ የእኛ ይሆናል” አሉት። 21 ሳኦልም፥ “ስለ እኔ ተቆርቁራችኋልና እግዚአብሔር ይባርካችሁ። 22 ሂዱና በይበልጥ እርግጠኛ ሁኑ። የት እንደ ተደበቀና በዚያ ማን እንዳየው መርምሩና ዕወቁ። እጅግ ተንኮለኛ ስለመሆኑ ተነግሮኛል። 23 ስለዚህ ልብ በሉ፥ ራሱን የሚደብቅባቸውን ቦታዎች በሙሉ መርምሩ። የተረጋገጠ መረጃ ይዛችሁልኝ ተመለሱ፥ ከዚያ በኋላ እኔም ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ። በምድሪቱ ላይ ካለ፥ በይሁዳ ሺዎች ሁሉ መካከል እፈልገዋለሁ” አላቸው። 24 እነርሱም ተነሡ፥ ሳኦልንም ቀድመው ወደ ዚፍ ሄዱ። ዳዊትና ሰዎቹ ከየሴሞን በስተደቡብ በዓረባ በምትገኘው በማዖን ምድረ በዳ ውስጥ ነበሩ። 25 ሳኦልና ሰዎቹም እርሱን ሊፈልጉት ሄዱ። ይህም ለዳዊት ተነገረው፥ ስለዚህ ወደ ዐለታማው ኮረብታ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ውስጥ ኖረ። ሳኦል በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ አሳደደው። 26 ሳኦል በተራራው በአንዱ ወገን ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በወዲያኛው ወገን ይሄዱ ነበር። ዳዊት ከሳኦል ለማምለጥ ተቻኮለ። ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመያዝ እየከበቧቸው በነበሩበት ጊዜ 27 አንድ መልዕክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ምድሪቱን ወረዋታልና ፈጥነህ ና" አለው። 28 ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን ከማሳደድ ተመልሶ ፍልስጥኤማውያንን ለመዋጋት ሄደ። በዚህ ምክንያት ያ ስፍራ የማምለጫ ዐለት ተብሎ ተጠራ። 29 ዳዊት ከዚያ ወጥቶ በዓይንጋዲ ባሉ ምሽጎች ውስጥ ኖረ።
1 ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ በተመለሰ ጊዜ፥ "ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ ውስጥ ነው" ተብሎ ተነገረው። 2 ከዚያም ሳኦል ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ ወደ ዓይንጋዲ ሄደ። 3 እርሱም በመንገዱ በበጎች ማደሪያ አቅራቢያ ወደነበረ ዋሻ መጣ። ሳኦልም ለመጸዳዳት ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹ በዋሻው ውስጥ ከኋላ ጥጉጋ ተቀምጠው ነበር። 4 የዳዊት ሰዎችም፥ "'ደስ ያሰኘህን እንድታደርግበት ጠላትህን በእጅህ ላይ አሳልፌ እሰጥሃለሁ' ባለህ ጊዜ እግዚአብሔር የተናገረው ስለዚህ ቀን ነው” አሉት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ በጸጥታ በደረቱ እየተሳበ ወደ ፊት በመሄድ የሳኦልን የካባውን ጫፍ ቆረጠው። 5 ከዚህ በኋላ የሳኦልን የካባውን ጫፍ ስለ ቆረጠ ዳዊትን ኅሊናው ወቀሰው። 6 እርሱም ሰዎቹን፥ "እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን በማንሣት እንዲህ ያለውን ነገር ማድረግን እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው" አላቸው። 7 ስለዚህ ዳዊት የእርሱን ሰዎች በዚህ ቃል ገሰጻቸው፥ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲጥሉበት አልፈቀደላቸውም። ሳኦል ተነሥቶ ከዋሻው ወጣና መንገዱን ቀጠለ። 8 ከዚህ በኋላ ዳዊት ተነሥቶ ከዋሻው በመውጣት ሳኦልን፥ "ጌታዬ፥ ንጉሥ ሆይ!" በማለት ተጣራ። ሳኦል ወደ ኋላው ዘወር ብሎ በተመለከተ ጊዜ፥ ዳዊት በመስገድ አክብሮትን አሳየው። 9 ዳዊትም ሳኦልን፥ “ 'ዳዊት ሊጎዳህ ይፈልጋል' የሚሉህን ሰዎች ለምን ትሰማቸዋለህ? 10 በዋሻው በነበርን ጊዜ እግዚአብሔር ዛሬ እጄ ላይ ጥሎህ እንደነበረ ዓይኖችህ አይተዋል። አንዳንዶቹ እንድገድልህ ነግረውኝ ነበር፥ እኔ ግን ራራሁልህ። እኔም፥ 'በእግዚአብሔር የተቀባ ስለሆነ፥ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም' አልኩኝ። 11 አባቴ ሆይ ተመልከት፥ በእጄ ላይ ያለውን የካባህን ቁራጭ ተመልከት። የካባህን ጫፍ ቆረጥኩኝ እንጂ አልገደልኩህም፥ በመሆኑም በእጄ ላይ ክፋትና ክህደት እንደሌለ ዕወቅ፤ ምንም እንኳን ሕይወቴን ለማጥፋት ብታሳድደኝም፥ እኔ አልበደልኩህም። 12 እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፥ እግዚአብሔር ይበቀልልኝ፥ እጄ ግን ባንተ ላይ አትሆንም። 13 የጥንቱ ምሳሌ፥ 'ከክፉ ሰው ክፋት ይወጣል' ይላል። እጄ ግን ባንተ ላይ አትሆንም። 14 የእስራኤል ንጉሥ የወጣው በማን ላይ ነው? የምታሳድደው ማንን ነው? የሞተን ውሻ! ቁንጫን! 15 እግዚአብሔር ፈራጅ ይሁን፥ በእኔና በአንተ መካከል ይመልከት፥ ይፍረድም፥ ጉዳዬን ተመልክቶም ከእጅህ እንዳመልጥ ይርዳኝ።” 16 ዳዊት ይህንን ቃል ለሳኦል ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት! ይህ ድምፅህ ነው?” አለው። ሳኦልም ድምፁን አሰምቶ አለቀሰ። 17 እርሱም ዳዊትን እንዲህ አለው፥ "በክፋት ስመልስልህ በደግነት መልሰህልኛልና ከእኔ ይልቅ አንተ ጻድቅ ነህ። 18 እግዚአብሔር በእጅህ ላይ በጣለኝ ጊዜ አልገደልከኝምና በጎነትን እንዳደረግህልኝ ዛሬ አሳይተሃል። 19 አንድ ሰው ጠላቱን ቢያገኘው በሰላም ያሰናብተዋል? ዛሬ ስላደረግህልኝ ነገር እግዚአብሔር ቸርነትን ያድርግልህ። 20 አሁንም፥ በእርግጥ ንጉሥ እንደምትሆንና የእስራኤል መንግሥት በእጅህ እንደሚጸና ዐውቃለሁ። 21 ከእኔ በኋላ ዘሮቼን እንደማታጠፋና ስሜንም ከአባቴ ቤት እንደማትደመስሰው በእግዚአብሔር ማልልኝ።" 22 ስለዚህ ዳዊት ለሳኦል ማለለት። ከዚያም ሳኦል ወደ ቤቱ ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ግን ወደ አምባው ወጡ።
1 ሳሙኤል ሞተ። እስራኤላውያን ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፥ በራማም በቤቱ ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ። 2 በማዖን አንድ ሰው ነበር፥ ንብረቱም በቀርሜሎስ ይኖር ነበር። ሰውዬው እጅግ ባለጸጋ ነበር። እርሱም ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት። በቀርሜሎስም በጎቹን ይሸልት ነበር። 3 የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበር። ሴቲቱ ብልህና መልኳም የተዋበ ነበረች። ሰውየው ግን አስቸጋሪና በምግባሩ ክፉ ነበር። እርሱም የካሌብ ቤተ ሰብ ተወላጅ ነበር። 4 ዳዊት በምድረ በዳ ውስጥ ሳለ ናባል በጎቹን እንደሚሸልት ሰማ። 5 ስለዚህ ዳዊት ዐሥር ወጣቶችን ላከ። ዳዊትም ወጣቶቹን እንዲህ አላቸው፥ “ወደ ቀርሜሎስ ውጡ፥ ወደ ናባልም ሂዱና በስሜ ሰላምታ አቅርቡለት። 6 እርሱንም እንዲህ በሉት፥ 'በብልጽግና ኑር፥ ሰላም ላንተ፥ ለቤትህና ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን። 7 ሸላቾች እንዳሉህ ሰምቻለሁ። እረኞችህ ከእኛ ጋር ነበሩ፥ ምንም ጉዳት አላደረስንባቸውም፥ በቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ አንድም አላጡም። 8 ወጣቶችህን ጠይቃቸው፥ እነርሱም ይነግሩሃል። አሁንም በግብዣህ ቀን መጥተናልና ወጣቶቼ በዓይንህ ፊት ሞገስ ያግኙ። በእጅህ ያለውን ማንኛውንም ነገር ለአገልጋዮችህና ለልጅህ ለዳዊት እባክህን ስጠው።" 9 የዳዊት ወጣቶች በደረሱ ጊዜ፥ በዳዊት ስም ይህንን ሁሉ ለናባል ነገሩትና ምላሹን ጠበቁ። 10 ናባልም ለዳዊት አገልጋዮች፥ "ዳዊት ማነው? የእሴይስ ልጅ ማነው? በእነዚህ ቀናት ከጌቶቻቸው የሚኮበልሉ ብዙ አገልጋዮች አሉ። 11 ታዲያ እንጀራዬን፥ ውሃዬንና ለሸላቾቼ ያረድኩትን ሥጋ ወስጄ ከየት እንደ መጡ ለማላውቃቸው ሰዎች መስጠት ይኖርብኛል?" ሲል መለሰላቸው። 12 ስለዚህ የዳዊት ወጣቶች ዞረው በመመለስ የተባለውን ሁሉ ነገሩት። 13 ዳዊትም ሰዎቹን፥ "ሁሉም ሰው ሰይፉን ይታጠቅ" አለ። ስለዚህ ሁሉም ሰይፎቻቸውን ታጠቁ። ዳዊትም ደግሞ ሰይፉን ታጠቀ። አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ዳዊትን ተከተሉት፥ ሁለት መቶዎቹም ከስንቅና ትጥቃቸው ጋር ቆዩ። 14 ነገር ግን ከወጣቶቹ አንዱ፥ ለናባል ሚስት ለአቢግያ እንዲህ ሲል ነገራት፥”ዳዊት ከምድረ በዳ ለጌታችን ሰላምታ ለማቅረብ መልዕክተኞች ላከ፥ ጌታችን ግን ሰደባቸው። 15 ሰዎቹ ግን ለእኛ በጣም ጥሩዎች ነበሩ። በመስኩ ላይ እያለን ከእነርሱ ጋር በሄድንበት ጊዜ ሁሉ አንድም አልጎደለብንም፥ እነርሱም አልጎዱንም። 16 በጎቹን እየጠበቅን ከእነርሱ ጋር በቆየንበት ጊዜ ሁሉ ቀንና ሌሊት አጥር ሆነውልን ነበር። 17 በጌታችንና በቤተሰቡ ሁሉ ላይ ክፉ ታስቦአልና ይህንን ዕወቂ፥ ምን ማድረግ እንዳለብሽም አስቢበት። እርሱ የሚረባ ሰው አይደለምና ማንም ሊያነጋግረው አይችልም“። 18 አቢግያም ፈጥና ሁለት መቶ እንጀራ፥ ሁለት ጠርሙስ የወይን ጠጅ፥ ቀደም ብሎ የተዘጋጀ አምስት በግ፥ አምስት መስፈሪያ የተጠበሰ እሸት፥ አንድ መቶ የወይን ዘለላና ሁለት መቶ የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ ወስዳ በአህዮች ላይ ጫነች። 19 ከእርሷ ጋር የነበሩትንም ወጣቶች፥ "በፊቴ ቅደሙ፥ እኔም እከተላችኋለሁ" አለቻቸው። ለባልዋ ለናባል ግን አልነገረችውም። 20 እርሷም በአህያዋ ላይ በመቀመጥ ተራራውን ተከልላ በመውረድ ላይ እያለች ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እርሷ ወረዱ፥ እርሷም አገኘቻቸው። 21 ዳዊትም፥”የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ እንኳን እንዳይጠፋበት፥ ይህ ሰው የነበረውን ሁሉ በምድረ በዳ መጠበቄ በእርግጥም በከንቱ ነበር፥ ስላደረግሁት በጎነት ክፋትን መልሶልኛልና። 22 ነገ ጠዋት የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ ወንድ እንኳን ባስቀርለት እግዚአብሔር በእኔ በዳዊት ላይ ይህንኑ ያድርግብኝ፥ ደግሞም ይጨምርብኝ" ብሎ ነበር። 23 አቢግያ ዳዊትን ባየችው ጊዜ፥ ከአህያዋ ላይ ፈጥና ወረደች፥ በዳዊትም ፊት አጎንብሳ ወደ ምድር ሰገደች። 24 በእግሩ ላይ ወድቃም እንዲህ አለችው፥ "ጌታዬ ሆይ፥ በደሉ በእኔ ላይ ብቻ ይሁን። እባክህን አገልጋይህ እንድናገርህ ፍቀድልኝ፥ የአገልጋይህንም ቃል ስማ። 25 ጌታዬ ለዚህ ለማይረባው ናባል ትኩረት አይስጥ፥ እርሱ እንደ ስሙ ነው። ስሙ ናባል ነውና ጅልነትም ከእርሱ ጋር ነው። እኔ አገልጋይህ ግን የላካቸውን የጌታዬን ወጣቶች አላየሁም። 26 አሁንም ጌታዬ ሆይ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በራስህ እጅ ከመበቀል እግዚአብሔር አግዶሃልና፥ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ ለማድረግ የሚፈልጉ እንደ ናባል ይሁኑ። 27 አሁንም አገልጋይህ ወደ ጌታዬ ያመጣሁት ይህ ስጦታ ጌታዬን ለሚከተሉ ወጣቶች ይሰጥ። 28 እባክህን የአገልጋይህን መተላለፍ ይቅር በል፥ አንተ ጌታዬ፥ የእግዚአብሔርን ጦርነት በመዋጋት ላይ ስላለህ፥ እግዚአብሔር በርግጥ ለጌታዬ እውነተኛ የሆነን ቤት ይሠራል፥ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም። 29 ሰዎች ተነሥተው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድዱህም የጌታዬ ሕይወት በአምላክህ በእግዚአብሔር በሕያዋን አንድነት የታሰረች ትሆናለች፤ እርሱም የጠላቶችህን ሕይወት ከወንጭፍ ኪስ እንደሚወረወር፥ በወንጭፍ ይወረውራል። 30 ይህ በሆነ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠህን መልካም ነገር ሁሉ ለጌታዬ በፈጸመ ጊዜ፥ በእስራኤልም ላይ መሪ ባደረገህ ጊዜ፥ 31 ይህ ጉዳይ ሐዘን አይሆንብህም፥ ለጌታዬም የልብ ጸጸት አይሆንም፥ ያለ ምክንያት ደም ያፈሰስክ፥ በራስህም እጅ የተበቀልክ አትሆንም። እግዚአብሔር ለጌታዬ ስኬትን ባመጣልህ ጊዜ አገልጋይህን አስበኝ።" 32 ዳዊትም አቢግያን፥ "ዛሬ እንድታገኚኝ የላከሽ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን። 33 ደም በማፍሰስ ከሚሆን በደልና በራሴ እጅ ስለ ራሴ ከመበቀል ጠብቀሽኛልና ጥበብሽ የተባረከ ነው፥ አንቺም የተባረክሽ ነሽ። 34 በእውነት፥ አንቺን ከመጉዳት የጠበቀኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን፥ እኔን ለመገናኘት ፈጥነሽ ባትመጪ ኖሮ፥ ያለምንም ጥርጥር ነገ ጠዋት ለናባል አንድ ወንድ ሕፃን ልጅ አይቀርለትም ነበር“ አላት። 35 ስለዚህ ዳዊት ያመጣችለትን ከእጇ ተቀበላት፤ እርሱም፥ "ወደ ቤትሽ በሰላም ሂጂ፤ ይኸው ቃልሽን ሰማሁ፥ ተቀበልኩሽም" አላት። 36 አቢግያም ተመልሳ ወደ ናባል ሄደች፤ እርሱም የንጉሥ ግብዣን የመሰለ ግብዣ በቤቱ ያደርግ ነበር፤ ናባልም በጣም ሰከሮ፥ ልቡም ደስ ብሎት ነበር። ስለዚህ እስኪነጋ ድረስ ምንም ነገር አልነገረችውም። 37 ከነጋ በኋላ፥ የናባል ስካር በበረደ ጊዜ፥ ሚስቱ እነዚህን ነገሮች ነገረችው፤ ልቡ ቀጥ አለ፥ እርሱም እንደ ድንጋይ ሆነ። 38 ዐሥር ቀን ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ናባልን ስለመታው ሞተ። 39 ናባል መሞቱን ዳዊት በሰማ ጊዜ፥”የመሰደቤን ምክንያት ከናባል እጅ የተቀበለና አገልጋዩን ከክፉ የጠበቀ ጌታ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን። እርሱም የናባልን ክፉ ሥራ በራሱ ላይ መለሰበት“ አለ። ከዚያም ዳዊት ወደ አቢግያ መልዕክተኛ ልኮ ሚስት አድርጎ ሊወስዳት አናገራት። 40 የዳዊት አገልጋዮች ወደ ቀርሜሎስ፥ ወደ አቢግያ በመጡ ጊዜ፥ "ሚስቱ እንድትሆኚው ልንወስድሽ ዳዊት ወዳንቺ ልኮናል" አሏት። 41 እርሷም ተነሣች፥ በግምባርዋ ወደ ምድር ሰግዳ፥ "ይኸው፥ ሴት አገልጋይህ፥ የጌታዬን አገልጋዮች እግር የማጥብ አገልጋይ ነኝ" አለች። 42 አቢግያም ፈጥና ተነሣች፥ ከተከተሏት ከአምስት ሴት አገልጋዮቿ ጋር በአህያ ተቀመጠች፥ የዳዊትን መልዕክተኞች ተከትላ ሄደች፥ ሚስትም ሆነችው። 43 በተጨማሪም ዳዊት ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ሚስት እንድትሆነው ወሰዳት፥ ሁለቱም ሚስቶቹ ሆኑ። 44 ሳኦል የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን፥ በጋሊም ለሚኖረው ለሌሳ ልጅ ለፈልጢ ሰጥቶ ነበር።
1 ዚፋውያን ወደ ሳኦል ወደ ጊብዓ መጥተው፥ “ዳዊት በምድረ በዳው ፊት ለፊት በኤኬላ ኮረብታ ላይ ተደብቋል?” አሉት። 2 ከዚያም ሳኦል ተነሣ፥ ከእስራኤል የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ዳዊትን ለመፈለግ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ። 3 ሳኦልም በምድረ በዳው ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ፥ በመንገዱ ዳር ሰፈረ። ዳዊት ግን በምድረ በዳው ቆይቶ ነበር፥ ሳኦል በምድረ በዳው ከበስተኋላው እንደመጣ አየ። 4 ስለዚህ ዳዊት ሰላዮችን ላከና በርግጥም ሳኦል በመምጣት ላይ መሆኑን ዐወቀ። 5 ዳዊት ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ስፍራ ሄደ፤ ሳኦልና የሰራዊቱ አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ፤ ሳኦል በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፥ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር፥ ሁሉም እንቅልፍ ወስዷቸው ነበር። 6 ከዚያም ዳዊት ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የኢዮአብን ወንድም የጽሩያን ልጅ አቢሳን፥ "ወደ ሳኦል ወደ ጦር ሰፈሩ ውስጥ ከእኔ ጋር የሚወርድ ማነው?" አላቸው። አቢሳም፥ "እኔ ከአንተ ጋር እወርዳለሁ" አለው። 7 ስለዚህ ዳዊትና አቢሳ በሌሊት ወደ ሰራዊቱ ሄዱ። ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ፥ ጦሩም ከራስጌው በምድር ላይ ተተክሎ ነበር። አበኔርና ወታደሮቹ በዙሪያው ተኝተው ነበር። 8 አቢሳም ዳዊትን፥ "እግዚአብሔር ዛሬ ጠላትህን በእጅህ ላይ ጣለው። አሁንም፥ በአንድ ምት ብቻ በጦር ከምድር ጋር እንዳጣብቀው ፍቀድልኝ፥ ሁለተኛ መምታትም አያስፈልገኝም" አለው። 9 ዳዊትም አቢሳን እንዲህ አለው፥ "አትግደለው፤ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን ዘርግቶ ከበደል መንጻት የሚችል ማነው? 10 ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር ራሱ ይገድለዋል፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል፥ ወይም ወደ ጦርነት ሄዶ ይሞታል። 11 እርሱ በቀባው ላይ እጄን ማንሣትን እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፤ አሁን ግን፥ በራስጌው ያለውን ጦርና የውሃውን ኮዳ ይዘህ እንድንሄድ እለምንሃለሁ።" 12 ስለዚህ ዳዊት በሳኦል ራስጌ የነበረውን ጦርና የውሃ ኮዳ ወሰደና ሄዱ። ከእግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ ስለወደቀባቸው ሁሉም አንቀላፍተው ነበርና አንድም የነቃ፥ ያየ ወይም ያወቀ አልነበረም። 13 ከዚያም ዳዊት በሌላኛው ወገን ወጣ፥ በተራራው ጫፍ ላይም ርቆ ቆመ፤ በመካከላቸው ሰፊ ርቀት ነበረ። 14 ዳዊትም ወደ ኔር ልጅ ወደ አበኔርና ወደ ሕዝቡ ጮኾ፥ "አበኔር ሆይ፥ አትመልስምን?" አለው። አበኔርም፥ "በንጉሡ ላይ የምትጮኸው አንተ ማነህ?" ብሎ መለሰለት። 15 ዳዊትም አበኔርን፥ "አንተ ጀግና አይደለህም? በእስራኤልስ አንተን የሚመስልህ ማነው? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን ያልጠበቅኸው ለምንድነው? አንድ ሰው ጌታህን ንጉሡን ለመግደል መጥቶ ነበርና። 16 ይህ ያደረግኸው ነገር መልካም አይደለም። ሕያው እግዚአብሔርን! ሞት የሚገባህ ነህ፥ ምክንያቱም እግዚአብሔር የቀባውን ጌታህን አልጠበቅኸውም። አሁንም፥ የንጉሡ ጦርና በራስጌው የነበረው የውሃ ኮዳ የት እንዳለ ተመልከት" አለው። 17 ሳኦልም የዳዊት ድምፅ መሆኑን ለየና፥ "ልጄ ዳዊት፥ ይህ ድምፅህ ነው?" አለው። ዳዊትም፥ "ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ድምፄ ነው" አለው። 18 እርሱም እንዲህ አለው፥ "ጌታዬ አገልጋዩን የሚያሳድደው ለምንድነው? ምን አድርጌአለሁ? በእጄስ ያለው ክፋት ምንድነው? 19 አሁንም ጌታዬ ንጉሡ የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ። በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ከሆነ መስዋዕትን ይቀበል፤ ሰዎች ከሆኑ ግን በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ 'ሄደህ ሌሎች አማልክቶችን አምልክ' ብለው የእግዚአብሔርን ርስት አጥብቄ እንዳልይዝ ዛሬ አባረውኛልና። 20 ስለዚህ፥ አንድ ሰው በተራሮች ላይ ቆቅን እንደሚያድን፥ የእስራኤል ንጉሥ ቁንጫን ለመፈለግ መጥቷልና ደሜ ከእግዚአብሔር ፊት ርቆ በምድር ላይ እንዲፈስ አታድርግ።“ 21 ከዚያም ሳኦል፥”ኃጢአትን አድርጌአለሁ። ልጄ ዳዊት፥ ተመለስ፤ ዛሬ ሕይወቴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ አላደርግብህም። ስንፍናን አድርጌአለሁ፥ እጅግም ተሳስቻለሁ“ አለው። 22 ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰለት፥”ንጉሥ ሆይ ተመልከት! ጦርህ ያለው እዚህ ነው፥ ከወጣቶቹ አንዱ ይምጣና ይውሰድልህ። 23 ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ላይ ጥሎህ እያለ በእርሱ የተቀባውን አልመታሁትምና እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደ ጽድቁና ታማኝነቱ ይክፈለው። 24 ተመልከት፥ ዛሬ ሕይወትህ በዐይኔ ፊት እንደ ከበረች የእኔም ሕይወት በእግዚአብሔር ዐይን አብልጣ የከበረች ትሁን፥ ከመከራዬም ሁሉ ያድነኝ።“ 25 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥”ልጄ ዳዊት፥ በርግጥ ታላላቅ ነገሮችን እንድታደርግና እንዲከናወንልህ የተባረክህ ሁን“ አለው። ስለዚህ ዳዊት መንገዱን ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።
1 ዳዊትም፥”አሁንም አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ከመሸሽ የሚሻል አማራጭ የለኝም፤ ያን ጊዜ ሳኦል በእስራኤል ወሰኖች ሁሉ ውስጥ እኔን መፈለጉን ያቆማል፤ በዚህ መንገድ ከእጁ አመልጣለሁ" ብሎ በልቡ አሰበ። 2 ዳዊትም ተነሣ፥ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ ተሻገሩ። 3 ዳዊትና ሰዎቹ እያንዳንዱ ከቤተሰቡ ጋር፥ እርሱም ከሁለቱ ሚስቶቹ፥ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ ጋር በጌት ከአንኩስ ጋር ኖሩ። 4 ዳዊት ወደ ጌት መሸሹን ሳኦል ሰማ፥ ስለዚህ ከዚህ በኋላ አልፈለገውም። 5 ዳዊትም አንኩስን፥ "በዐይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፥ በዚያ እኖር ዘንድ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ስፍራ ይስጡኝ፤ አገልጋይህ በንጉሣዊ ከተማ ከአንተ ጋር ለምን ይኖራል?" አለው። 6 ስለዚህ በዚያን ቀን አንኩስ ጺቅላግን ሰጠው፤ እስከዛሬ ድረስ ጺቅላግ የይሁዳ ነገሥታት የሆነችው ለዚህ ነው። 7 ዳዊት በፍልስጥኤም ምድር የኖረበት ቀን ሲቆጠር አንድ ዓመት ከአራት ወር ሆነው። 8 ዳዊትና ሰዎቹ ጌሹራውያንን፥ ጌርዛውያንን እና አማሌቃውያንን በመውረር የተለያዩ ቦታዎችን አጠቁ፤ እነዚህ ሕዝቦች እስከ ሱርና እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። እነርሱም ከጥንት ጀምሮ በዚያ ምድር ይኖሩ ነበር። 9 ዳዊትም ምድሪቱን መታ፥ ወንዱንም ሆነ ሴቱን በሕይወት አልተወም፤ በጎችን፥ በሬዎችን፥ አህዮችን፥ ግመሎችን እና ልብሶችን ወሰደ፤ ተመልሶም እንደገና ወደ አንኩስ መጣ። 10 አንኩስ፥ "ዛሬ በማን ላይ ወረራ ፈጸማችሁ?" ብሎ ይጠይቅ ነበር፥ ዳዊትም፥ "በይሁዳ ደቡብ ላይ" ወይም "በደቡብ ይረሕምኤላውያን ላይ" ወይም "በደቡብ ቄናውያን ላይ" ብሎ ይመልስለት ነበር። 11 "ስለዚህ ስለ እኛ፥ 'ዳዊት እንዲህና እንዲህ አደረገ' ለማለት እንዳይችሉ" ብሎ ነበርና ዳዊት ወደ ጌት ይዞ ለመምጣት በማሰብ ወንድ ወይም ሴት በሕይወት አያስቀርም ነበር። በፍልስጥኤም አገር በኖረበት ጊዜ ሁሉ ያደረገው እንደዚህ ነበር። 12 አንኩስም፥ "የራሱ የሆነው የእስራኤል ሕዝብ አምርሮ እንዲጠላው አድርጓል፤ ስለዚህ ለዘላለም አገልጋዬ ይሆናል“ ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።
1 በዚያም ዘመን ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ሠራዊታቸውን ሁሉ በአንድ ላይ ሰበሰቡ። አንኩስም ዳዊትን፥ “አንተና ሰዎችህ ያለ ጥርጥር ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ እንደምትወጡ ዕወቅ” አለው። 2 ዳዊትም አንኩስን፥ “ስለዚህ አገልጋይህ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ታያለህ” አለው። አንኩስም ዳዊትን፥ “ስለዚህ እኔም በቋሚነት የግል ጠባቂዬ አደርግሃለሁ" አለው። 3 ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤል ሁሉ አልቅሰውለት በከተማው በራማም ቀብረውት ነበር። ሳኦል ከሙታንና ከመናፍስት ጋር የሚነጋገሩትን ከምድሪቱ አጥፍቶ ነበር። 4 ፍልስጥኤማውያን በአንድነት ተሰባስበው በመምጣት ሱነም ላይ ሰፈሩ፤ ሳኦልም እስራኤልን በሙሉ በአንድነት ሰብስቦ ጊልቦዓ ላይ ሰፈረ። 5 ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ባየ ጊዜ ፈራ፥ ልቡም እጅግ ተንቀጠቀጠ። 6 ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜም እግዚአብሔር በህልም፥ ወይም በኡሪም፥ ወይም በነቢያት አልመለሰለትም። 7 ከዚያም ሳኦል አገልጋዮቹን፥ "ወደ እርሷ ሄጄ ምክሯን እንድጠይቅ ከሞተ ጋር መነጋገር እችላለሁ የምትል ሴት ካለች ፈልጉልኝ" አላቸው። አገልጋዮቹም፥ "ከሞተ ጋር መነጋገር እችላለሁ የምትል ሴት በዓይንዶር አለች" አሉት። 8 ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ ራሱን ቀይሮ ከሁለት ሰዎች ጋር ሄደ፤ እነርሱም በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄዱ። እርሱም፥ "የምነግርሽን ሰው አስነሥተሽ ከሞተው ጋር በመነጋገር እንድትጠነቁይልኝ እለምንሻለሁ" አላት። 9 ሴቲቱም፥ "ሳኦል ከሙታንና ከመናፍስት ጋር የሚነጋገሩትን ከምድሪቱ በማጥፋት ያደረገውን ታውቃለህ። ታዲያ እንድሞት ለሕይወቴ ወጥመድ የምታዘጋጀው ለምንድነው?" አለችው። 10 ሳኦልም በእግዚአብሔር ስም ምሎላት፥ "ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ጉዳይ ምንም ቅጣት አይደርስብሽም” አላት። 11 ሴቲቱም፥ “ማንን ላስነሣልህ?” አለችው። ሳኦልም፥ “ ሳሙኤልን አስነሽልኝ” አላት። 12 ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኻ ሳኦልን፥ "አንተ ራስህ ሳኦል ሆንህ ሳለ ለምን አታለልከኝ?" አለችው። 13 ንጉሡም፥ "አትፍሪ፤ ምንድነው ያየሽው?" አላት። ሴቲቱም ሳኦልን፥ "አንድ መንፈስ ከምድር ሲወጣ አያለሁ" አለችው። 14 እርሱም፥ “ምን ይመስላል?” አላት። እርሷም፥ "አንድ ካባ የለበሰ ሽማግሌ እየመጣ ነው" አለችው። ሳኦልም ሳሙኤል እንደሆነ ዐወቀ፥ አክብሮቱን ለማሳየትም በምድር ላይ ሰገደለት። 15 ሳሙኤልም ሳኦልን፥ "እኔን በማስነሣት የምታስቸግረኝ ለምንድነው?" አለው። ሳኦልም፥ "በጣም ተጨንቄአለሁ፥ ፍልስጥኤማውያን ጦርነት ዐውጀውብኛል፥ እግዚአብሔር ትቶኛል፥ በሕልምም ሆነ በነቢያት አይመልስልኝም። ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንድታስታውቀኝ ለዚህ ነው የጠራሁህ" ብሎ መለሰለት። 16 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፥ "ታዲያ እግዚአብሔር ከተወህና ጠላት ከሆነህ የምትጠይቀኝ ምንድነው? 17 እግዚአብሔር አደርገዋለሁ ብሎ የነገረህን እርሱን ነው ያደረገብህ። እግዚአብሔር መንግሥትን ከእጅህ ቀዶ ለሌላ ሰው፥ ለዳዊት ሰጥቶታል። 18 የእግዚአብሔርን ድምፅ ስላልታዘዝክና ጽኑ ቁጣውን በአማሌቅ ላይ ስላልፈጸምክ ዛሬ ይህንን አድርጎብሃል። 19 በተጨማሪም እግዚአብሔር አንተንና እስራኤልን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል። አንተና ልጆችህ ነገ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ። በተጨማሪም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል።“ 20 ከዚያም ሳኦል በሳሙኤል ቃል ምክንያት እጅግ ስለፈራ ወዲያውኑ በቁመቱ ሙሉ በምድር ላይ ወደቀ። በዚያ ቀንና ሌሊት ምግብ ስላልበላ ምንም አቅም አልነበረውም። 21 ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ እጅግ መጨነቁን አየች፥ እርሷም እንዲህ አለችው፥ "እኔ አገልጋይህ ቃልህን ሰምቻለሁ፤ ሕይወቴን በእጄ ላይ ጥዬ የነገርከኝን ቃል ሰምቻለሁ። 22 አሁንም እንግዲህ አንተም ደግሞ የእኔን የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማና ጥቂት ምግብ እንዳቀርብልህ እለምንሃለሁ። መንገድህን ለመሄድ ዐቅም እንድታገኝ ብላ። 23 ሳኦል ግን፥ "አልበላም" በማለት እንቢ አለ። ነገር ግን አገልጋዮቹ ከሴቲቱ ጋር በመሆን ለመኑት፥ እርሱም ቃላቸውን ሰማ። ስለዚህ ከምድር ላይ ተነሥቶ ዐልጋ ላይ ተቀመጠ። 24 ሴቲቱም በቤቷ የደለበ ጥጃ ነበራት፤ ፈጥና አረደችው፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰችው፤ ቂጣ አድርጋም ጋገረችው። 25 እርሷም በሳኦልና በአገልጋዮቹ ፊት አቀረበችላቸው፥ እነርሱም በሉ። ከዚያም በዚያው ሌሊት ተነሥተው ሄዱ።
1 ፍልስጥኤማውያንም ሰራዊታቸውን ሁሉ አፌቅ ላይ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። 2 የፍልስጥኤማውያኑ መሳፍንት በመቶዎችና በሺዎች እየሆኑ አለፉ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋር በደጀንነት አለፉ። 3 ከዚያም የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?" አሉ። አንኩስም ለሌሎቹ የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "ይህ በእነዚህ ቀናት ሁሉ ከእኔ ጋር የነበረው፥ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ ዳዊት አይደለምን? ደግሞም በእነዚህ ዓመታት ሁሉ ወደ እኔ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁበትም” አላቸው። 4 ነገር ግን የፍልስጥኤም መሳፍንት በእርሱ ላይ ተቆጥተው፥ “ያንን ሰው ወደ ሰጠኸው ወደ ስፍራው እንዲመለስ አሰናብተው፥ በውጊያው ውስጥ ጠላት እንዳይሆንብን ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አትላከው። ይህ ሰው ከጌታው ጋር ሰላምን የሚፈጥረው በምንድነው? የሰዎቻችንን አንገት በመቁረጥ አይደለምን? 5 ይህ በዘፈን እየተቀባበሉ፥ 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ" ያሉለት ዳዊት አይደለምን?" አሉት። 6 ከዚያም አንኩስ ዳዊትን ጠርቶ፥ "ሕያው እግዚአብሔርን! አንተ ጥሩ ሰው ነህ፥ በእኔ አመለካከት በሰራዊቱ ውስጥ መውጣትህና መግባትህ መልካም ነው፤ ወደ እኔ ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬው ቀን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁብህም። ይሁን እንጂ መሳፍንቱ አልደገፉህም። 7 ስለዚህ አሁን የፍልስጥኤም መሳፍንት ቅር እንዳይሰኙ ተመለስና በሰላም ሂድ" አለው። 8 ዳዊትም አንኩስን፥ “ግን ምን አድርጌአለሁ፥ እንዳልሄድና ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ በእነዚህ በፊትህ በኖርኩባቸው ቀናት በአገልጋይህ ላይ ምን አግኝተህብኛል?” አለው። 9 አንኩስም ለዳዊት፥ “አንተ በእኔ ዕይታ ነቀፌታ እንደማይገኝበት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ ይሁንና የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ 'ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አይሄድም' ብለዋል። 10 ስለዚህ ከአንተ ጋር ከመጡት ከጌታህ አገልጋዮች ጋር ማልዳችሁ ተነሡ፤ ማልዳችሁ ተነሡና ሲነጋላችሁ ሂዱ" ብሎ መለሰለት። 11 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ በጠዋት ለመሄድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ለመመለስ ማልደው ተነሡ። ፍልስጥኤማውያን ግን ወደ ኢይዝራኤል ወጡ።
1 እንዲህም ሆነ፥ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ በመጡ ጊዜ አማሌቃውያን በኔጌቭና በጺቅላግ ላይ ወረራ ፈጽመው ነበር። እነርሱም ጺቅላግን መቱ፥ አቃጠሏትም፥ 2 ሴቶችንና በውስጧ የነበረውን ትንሽና ትልቅ ሁሉ ማረኩ። ይዘዋቸው መንገዳቸውን ሄዱ እንጂ አንዱንም አልገደሉም። 3 ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ ከተማይቱ በእሳት ተቃጥላ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ተማርከው ተወስደው ነበር። 4 ከዚያም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ለማልቀስ ኃይል እስከማይኖራቸው ድረስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። 5 ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች፥ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያ ተማርከው ነበር። 6 የሕዝቡም ሁሉ መንፈስ፥ እያንዳንዱም ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ስላዘነ በድንጋይ ሊወግሩት ይነጋገሩ ስለነበር ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አበረታ። 7 ዳዊትም የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፥ "ኤፉዱን ወደዚህ እንድታመጣልኝ እለምንሃለሁ" አለው። አብያታር ኤፉዱን ለዳዊት አመጣለት። 8 ዳዊትም ምሪት ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር፥ "ይህንን ወራሪ ብከተል እደርስበታለሁ?" ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም፥ "ተከተላቸው፥ ያለጥርጥር ትደርስባቸዋለህ፥ ሁሉንም ነገር ታስመልሳለህ" ብሎ መለሰለት። 9 ስለዚህ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ ከእነርሱ ወደ ኋላ የቀሩት ወደሚቆዩበት ወደ ባሦር ወንዝ መጡ። 10 ነገር ግን ዳዊት ከአራት መቶ ሰዎች ጋር መከታተሉን ቀጠለ፤ ሁለት መቶዎቹ በጣም ስለ ደከሙ የባሦርን ወንዝ መሻገር አልቻሉምና ወደ ኋላ ቀሩ። 11 እነርሱም በሜዳው ላይ አንድ ግብፃዊ አገኙና ወደ ዳዊት አመጡት፤ ምግብ ሰጡትና በላ፥ እንዲጠጣም ውሃ ሰጡት፤ 12 ደግሞም ከበለስ ጥፍጥፍ ቁራጭና ሁለት የወይን ዘለላ ሰጡት። ለሦስት ቀንና ሌሊት ምንም ምግብ አልበላም፥ ውሃም አልጠጣም ነበርና በበላ ጊዜ እንደገና ብርታት አገኘ። 13 ዳዊትም፥ "አንተ የማን ነህ? ከየትስ ነው የመጣኸው?" አለው። እርሱም፥ "እኔ የአማሌቃዊ አገልጋይ፥ ግብፃዊ ወጣት ነኝ፤ ከሦስት ቀናት በፊት ታምሜ ስለነበር ጌታዬ ትቶኝ ሄደ። 14 እኛም በከሊታውያን ኔጌቭ፥ የይሁዳ በሆነው ምድርና በካሌብ ኔጌቭ ላይ ወረራ ፈጸምን፥ ጺቅላግንም አቃጠልናት“ አለው። 15 ዳዊትም፥”ወደዚህ ወራሪ አካል መርተህ ልታወርደኝ ትፈቅዳለህ? “ አለው። ግብፃዊውም፥”እንዳትገድለኝ ወይም በጌታዬ እጅ ላይ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ ወደ ወራሪው አካል መርቼ አወርድሃለሁ“ አለው። 16 ግብፃዊው ዳዊትን እየመራው ወደ ታች ባወረደው ጊዜ፥ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያን ምድርና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ምርኮ ሁሉ የተነሣ እየበሉና እየጠጡ፥ እየጨፈሩም በምድሩ ሁሉ ተበትነው ነበር። 17 ዳዊትም ደንገዝገዝ ሲል ጀምሮ እስከ ማግስቱ ምሽት ድረስ መታቸው። በግመሎች ተቀምጠው ከሸሹት ከአራት መቶ ወጣቶች በስተቀር አንድም ሰው አላመለጠም። 18 ዳዊት አማሌቃውያን ወስደዋቸው የነበሩትን ሁሉ አስመለሰ፤ ሁለቱን ሚስቶቹንም አዳነ። 19 ትንሽ ይሁን ትልቅ፥ ወንዶች ልጆች ይሁኑ ሴቶች ልጆች፥ ምርኮም ይሁን ወራሪዎቹ ለራሳቸው ከወሰዱት ማንኛውም ነገር አንዱም አልጠፋም። ዳዊት ሁሉን ነገር አስመለሰ። 20 ዳዊትም ሰዎቹ ከሌሎች ከብቶች ፊት ይነዷቸው የነበሩትን የበጉን፥ የፍየሉንና የላሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ። እነርሱም፥ "ይህ የዳዊት ምርኮ ነው" አሉ። 21 ዳዊት ሊከተሉት እጅግ ደክሟቸው በባሦር ወንዝ አጠገብ እንዲቆዩ ወደተደረጉት ወደ ሁለት መቶዎቹ ሰዎች መጣ። እነዚህ ሰዎች ዳዊትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመገናኘት ወጡ። ዳዊት ወደ እነዚህ ሰዎች በመጣ ጊዜ ሰላምታ ሰጣቸው። 22 ከዚያም ከዳዊት ጋር ሄደው በነበሩት ሰዎች መካከል ክፉዎችና የማይረቡት ሁሉ፥”እያንዳንዱ ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ ከመሄድ በስተቀር እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር ስላልሄዱ፥ ካስመለስነው ምርኮ ምንም አንሰጣቸውም“ አሉ። 23 ከዚያም ዳዊት፥”ወንድሞቼ ሆይ፥ እግዚአብሔር በሰጠን ነገር እንዲህ ልታደርጉ አይገባም። እርሱ ጠበቀን፥ በእኛ ላይ የመጡትንም ወራሪዎች በእጃችን ላይ አሳልፎ ሰጠን። 24 በዚህ ጉዳይ ማን ይሰማችኋል? ወደ ጦርነት የሄደው የየትኛውም ሰው ድርሻ ስንቅና ትጥቅ ከጠበቀ ከየትኛውም ሰው ድርሻ ጋር እኩል ይሆናል፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ" አላቸው። 25 ዳዊት ለእስራኤል ደንብና ሥርዓት ስላደረገው፥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ እንደዚሁ ሆነ። 26 ዳዊት ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ፥ ከምርኮው ጥቂቱን፥ "ይህ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ካገኘነው ምርኮ ለእናንተ የተላከ ስጦታ ነው“ብሎ ለይሁዳ ሽማግሌዎችና ለወዳጆቹ ላከላቸው። 27 የላከውም፥ በቤቴል፥ በደቡብ ራሞት፥ በየቲር፥ 28 በአሮኤር፥ በሢፍሞት፥ በኤሽትሞዓ ለነበሩ ሽማግሌዎች ነበር። 29 እንዲሁም በራካል፥ በይረሕምኤላውያንና በቄናውያን ከተሞች፥ 30 በሔርማ፥ በቦራሣን፥ በዓታክ፥ 31 በኬብሮን፥ እንዲሁም ዳዊት ራሱና ሰዎቹ አዘውትረው ይሄዱባቸው በነበሩ ስፍራዎች ሁሉ ለሚኖሩ ሽማግሌዎች ላከላቸው።
1 ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ተዋጉ። የእስራኤል ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ በጊልቦዓ ተራራ ላይም ተገድለው ወደቁ። 2 ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በቅርብ ርቀት ተከተሏቸው። ፍልስጥኤማውያንም ልጆቹን ዮናታንን፥ አሚናዳብንና ሜልኪሳን ገደሏቸው። 3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታበት፥ ቀስተኞችም አገኙት። በእነርሱም ምክንያት በጽኑ ሕመም ላይ ነበር። 4 ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥”ሰይፍህን ምዘዝና ውጋኝ። አለበለዚያ፥ እነዚህ ያልተገረዙ መጥተው ይሳለቁብኛል“ አለው። 5 ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበረ እምቢ እለ። ስለዚህ ሳኦል የራሱን ሰይፍ ወስዶ በላዩ ላይ ወደቀበት። ጋሻ ጃግሬው ሳኦል መሞቱን ባየ ጊዜ እርሱም ደግሞ ሰይፉ ላይ ወድቆ አብሮት ሞተ። 6 ስለዚህ ሳኦል፥ ሦስቱ ወንዶች ልጆቹና ጋሻ ጃግሬው ሞቱ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ በአንድ ቀን ሞቱ። 7 ከሸለቆው በወዲያኛው ወገን የነበሩትና ከዮርዳኖስ በላይ የነበሩት የእስራኤል ሰዎች፥ የእስራኤል ሰዎች መሸሻቸውን፥ ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ትተው ሸሹ፥ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው። 8 በማግስቱ እንዲህ ሆነ፥ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ሰዎች ትጥቅ ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው። 9 እነርሱም ራሱን ቆረጡት፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈፉት፥ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ሁሉ ለጣዖት መቅደሶቻቸውና ለሕዝቡ ወሬውን እንዲያደርሱ መልዕክተኞችን ላኩ። 10 የጦር መሣሪያውን በአስታሮት መቅደስ ውስጥ አስቀመጡት፥ ሬሳውንም በቤትሳን ከተማ የግንብ አጥር ላይ አንጠለጠሉት። 11 የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ 12 ተዋጊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ተጉዘው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከአጥሩ ላይ ወሰዱ። ወደ ኢያቢስ ሄዱ፥ በዚያም አቃጠሏቸው። 13 ከዚያም አጥንቶቻቸውን በመውሰድ በኢያቢስ ባለው የአጣጥ ዛፍ ሥር ቀበሯቸው፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።
1 ሳዖል ከሞተ በኋላ፣ ዳዊት በአማሌቃውያን ላይ ጥቃት ከማድረስ በመመለስ በጺቅላግ ሁለት ቀን ቆየ፡፡ 2 በሦስተኛው ቀን የተቀዳደደ ልብስ የለበሰ፣ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ፡፡ ወደ ዳዊት እንደ ደረሰም ወደ መሬት ለጥ ብሎ ሰገደለት፡፡ 3 ዳዊትም “ከወዴት መጣህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “ከእስራኤላውያን ሰፈር አምልጬ የመጣሁ ነኝ” ሲል መለሰ፡፡ 4 ዳዊትም፣ “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው፡፡ እርሱም “ሰዎቹ ከጦርነት ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል ደግሞም ሞተዋል፤ ሳዖልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ፡፡ 5 ዳዊትም ለወጣቱ፤ “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት አወቅህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ 6 ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ፣ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከታትለው ደረሱበት፤ 7 ወደ ኋላውም ዞር ሲል እኔን ስላየ ጠራኝ፤ እኔም ‘እነሆኝ አለሁ’ አልኩት፡፡ 8 እርሱም፣ ‘አንተ ማን ነህ?’ ሲል ጠየቀኝ፡፡ አኔም፣ ‘አማሌቃዊ ነኝ’ ብዬ መለስሁለት፡፡ 9 እርሱም አለኝ ‘እኔ በታላቅ ስቃይ ውስጥ እገኛለሁ፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ፡፡ 10 ስለሆነም፣ ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፤ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፣ ለጌታዬ አምጥቻለሁ፡፡” አለው፡፡ 11 ከዚያም ዳዊት ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ፡፡ 12 የወደቁት በሰይፍ ነበርና ለሳኦል ለልጁ ለዮናታንና ለእግዚአብሔር ሕዝብ አዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾ፡፡ 13 ዳዊትም ወጣቱን ሰውዬ፣ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “በአገሪቱ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር አማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ፡፡ 14 ዳዊትም፣ “እግዚአብሔር የቀባውን ንጉሥ በገዛ እጅህ ስትገድል ለምን አልፈራህም?” ሲል ጠየቀው፡፡ 15 ዳዊትም ከጎልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፣ “ግደለው” አለው፤ ጎልማሳው ሰው ሄዶ መታው፣ አማሌቃዊውም ሞተ፡፡ 16 ከዚያም ዳዊት ለሞተው አማሌቃዊ፣ “‘እግዚአብሔር የቀባውን ገድያለሁ’ ስትል አፍህ መስክሮብሃልና ደምህ በራስህ ላይ ነው” አለው፡፡ 17 ከዚያም ዳዊት ለሳዖልና ለልጁ ለዮናታን የሚከተለውን የሐዘን እንጉርጉሮ አንጎራጎረ፡፡ 18 እንዲሁም የቀስት እንጉርጉሮ የተባለውን ለይሁዳ ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ ይህም በያሸር መጽሐፍ ተጽፎአል፡፡ 19 “እስራኤል ሆይ፣ ክብርህ ሞቶአል፣ በተራሮችህ ላይ ተገድሎአል! ኃያላኑ እንዴት ወደቁ! 20 የፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፣ ያልተገረዙት ሴት ልጆች ፌሽታ እንዳያደርጉ ይህን በጌት አትናገሩ፣ በአስቆሎናም መንገዶች አታውጁት፡፡ 21 እናንት የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ ጠል አያረስርሳችሁ፣ ዝናብም አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች በዚያ አይኑሩ፤ በዚያ የኃያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፣ የሳዖል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም፡፡ 22 ከሞቱት ሰዎች ደም፣ ከኃያላኑም ገላ የዮናታን ቀስት ተመልሶ አልመጣም፤ የሳዖልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰም፡፡ 23 ሳዖልና ዮናታን በሕይወት እያሉ የሚዋደዱና ግርማ ያላቸው ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ፡፡ 24 እናንተ የእስራኤል ቆነጃጅት ሆይ፤ ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ ፤ ልብሶቻችሁንም በወርቀ-ዘቦ ላስጌጠላችሁ ለሳዖል አልቅሱለት፡፡ 25 ኃያላን እንዴት እንዲህ በጦርነት መካከል ወደቁ! ዮናታን ከፍ ባሉ ስፍራዎቻችሁ ላይ ሞቶአል፡፡ 26 ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ አዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበር፤ ከሴት ፍቅርም የላቀ ነበር፡፡ 27 ኃያላን እንዴት ወደቁ፤ የጦር መሣሪዎቹስ እንዴት ከንቱ ሆኑ!”
ይህ በይሁዳ ደቡባዊ ክፍል የሚገኝ የከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"ከሶስት ቀናት በኋላ" (ተከታታይ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)
በዚህ ባህል፣ የራስን ልብስ መቅደድ እና በራስ ላይ አመድ መነስነስ የሃዘን መግለጫ ድርጊት ነበር፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ አሁን የእስራኤል ንጉሥ ለሆነው ለዳዊት ራሱን ዝቅ አድርጎ ያሳየበት መንገድ ነበር፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ብዙዎች ቆስለው ነበር ደግሞም ብዙዎች ተገድለው ነበር" ወይም 2) "ብዙዎች ቆስለው እና ተገድለው ነበር"
ይህ ሃሳብ ትኩረት የሚያደርገው ሰውየው ሳኦልን ለማገኘት እቅድ እንዳነበረው ነው
ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ሳኦል ደክሞና ጦሩን ራሱን ለመደገፊያነት ተጠቅሞበት ነበር ወይም 2) ሳኦል በራሱ ጦር ላይ በመውደቅ ራሱን ለመግደል እየሞከረ ነበር፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ቀጥተኛ ጥቅስ በርቱዕ/ቀጥተኛ ንግግር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ማን እንደሆንኩ ጠየቀኝ፣ እኔም አማሌቃዊ እንደሆንኩ ነገርኩት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ ጥቅሶች የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ህዝቦች ዳዊት በ2 ሳሙኤል 1፡1 ላይ ድል ያደረጋቸው እነዚያው ሰዎች ናቸው፡፡
የሳኦል መከራ የተገለጸው አንዳች አስጨናቂ ነገር አንቆ እንደያዘው ተደርጎ ነው፡፡ "እጅግ ተጨነቅኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ፈሊጥ ትረጉሙ እርሱ ገና በህይወት አለ ማለት ነው፡፡ "እስከ አሁን በህይወት አለሁ" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
"መሞቱ አይቀርም"
ዳዊትና የእርሱ ሰዎች በንጉሥ ሳኦል ሞት ማዘናቸውን ለመግለጽ ልብሳቸውን ቀደዱ፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)
ሁለቱ ሃሳቦች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ "ቤት" የሚለው ቃል የእስራኤልን ትውልዶች የሚወክል ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ነገር ግን፣ "ህዝብ" እና "ቤት" የሚሉት ሁለቱም ቃላት ምናልባት የእስራኤልን ወታደሮች የሚወክሉ ስኔክቲክ/የነገሩን ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ናቸው፡፡ "ለእስራኤላውያን ወታደሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እንዲሁም ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)
ይህ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ራሱን ለህዝቡ የገለጸበት ስም ነው፡፡ ይህ እንዴት እንደሚተረጎም የትርጉም ስለ ያህዌ የቃል ትርጉም ገጽን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "ወደቁ" የሚለው መገደልን በትሁት መንገድ የሚገልጽ ነው፡፡እንደዚሁም፣ "ሰይፍ" ውጊያን ይወክላል/ይገልጻል፡፡ ይህ በዚህ ስፍራ "ተገድለዋል" ማለት ነው፡፡ "በጦርነት ሞተዋል" ወይም "ጠላቶች በጦርነቱ ገድለዋቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)
በ2ሳሙኤል 1፡8 ውስጥ ሰውየው አስቀድሞውኑ አማሌቃዊ መሆኑን ገልጽዋል፡፡ ዳዊት ሰውየው ይህንን በግልጽ እንዲያረጋግጥለት ይጠይቀዋል፣ ምክንያቱ ዳዊት በሰውየው ላይ ጽኑ ፍርድ ሊፈርድበት ስለሆነ ነው፡፡
ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ያገለገለው ሰውየውን ለመገሰጽ ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እጅህ… እርሱ የቀባውን ሲገድል ያህዌን መፍራት ነበረብህ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ የሚያመለክተው ሳኦልን ነው፡፡
ይህ ሀረግ የሚገልጸው ራስህ አንድ ነገር ማድረግህን ነው፡፡ "ራስህ" ወይም "በግል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
የዚህ ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉም "ግደለው" ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልቱ)
እዚህ ስፍራ "ደም" የሚያመለክተው "ደም ማፍሰስ" የሚለውን ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን የሚያያዘውም ከሞት ጋር ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "ራስህ" የሚለው ሰውየውን እና ተጠያቂ መሆኑን የሚያመለክት ስኔክቲክ/የነገሩን ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ነው፡፡ "ለሞትህ ራስህ ተጠያቂ ነህ" ወይም "ለሞትህ ምክንያት የሆንከው ራስህ ነህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ስኔክቲክ/የነገሩን ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)
እዚህ ስፍራ "የራስህ አፍ" የሚለው የሚያመለክተው ሰውየውን ራሱን ነው፡፡ "በራስህ ላይ መስክረሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የነገሩን ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)
ዳዊት ለሳኦልና ለዮናታን የሀዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ
ይህ የእንጉርጉሮው ርእስ ነበር
ይህ ለአንባቢው ወደፊት ምን ተደርጎ እንደነበር እንዲያውቅ በዝማሬው ላይ ተጨማሪ የመረጃ ዳራ ሆኖ የተጻፈ ነው፡፡ (የመረጃ ዳራ የሚለውን ይመልከቱ) የያሻር መጽሐፍ "ያሻር" የሚለው ቃል ትርጉሙ "ቀጥተኛ/በተጠንቀቅ" ማለት ነው፡፡ "የውጊያ ውሎ" መጽሐፍ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
"የአንተ ክብር" የሚለው ሳኦልን ያመለክታል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
"ሃያል" የሚለው ሀረግ ሳኦልን እና ዮናታንን ሁለቱንም ያመለክታል፡፡ ይህ ስማዊ ቅጽል የብዙ ቁጥር ነው፤ "ሃያላኑ" ተብሎ ሊገለጽም ይችላል፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ስማዊ ቅጽል የሚሉትን ይመልከቱ)
"ወደቀ" የሚለው ቃል በዚህ ስፍራ "ሞተ" ማለት ነው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)
እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ የተደገሙትም የግጥሙ እንጉርጉሮ ክፍል ሆነው ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ጌት እና አስቀሎና ከፍልስጥኤማውያን ታላላቅ ከተሞች ሁለቱ ናቸው፡፡ ሳኦልን እና ዮናታንን የገደሉት ፍልስጥኤማውያን ናቸው፡፡
እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤የተደገሙትም የግጥሙ ክፍል ሆነው ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
ይህ ሀረግ የሚያመለክተው እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሉትን ያህዌን የማይከተሉ ህዝቦችን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
ዳዊት የእርሱን እንጉርጉሮ እንደሚሰሙት አድርጎ በቀጥታ ለ"ጊልቦዓ ተራሮች" ይናገራል፡፡ (አፖስተሮፊ የሚለውን ይመልከቱ)
ዳዊት ንጉሥ ሳኦል በጦርነት የሞተበትን ምድር ይረግማል፣ ይህ የሚያደርገው እግዚአብሔር ለቀባው ነጉሥ ካለው ታላቅ አክብሮት/ውዳሴ የተነሳ ነው
እዚህ ስፍራ "ሃያል" የሚለው የሚያመለክተው ሳኦልን ነው፡፡ ጋሻው የረከሰበት ምክንያት ምድር ላይ በመውደቁ እና የንጉሡ ደም በላዩ ስለፈሰሰበት ነበር፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለ